አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ስኳር_መች_ይጣፍጣል?!

በዚህ እጅ ያልነካው ወዳጅ በማይገኝበት ክፉ ዘመን ሰላሳ አራት አመት እስኪሞላት ድረስ የማንም እጅ ሳይነካካት ከወር በፊት የተሞሸረች ልጃገረድ ወዳጅ አለችኝ።

‹‹ያላገባኝ አይነካኝም!›› ብላ….
‹‹ወንድ ልጅ ወተቱን በነፃ ካገኘ ላሚቱን አይገዛም›› ብላ…
ስንቱን የወንድ ፈንጂ በጥንቃቄ እንጣጥ ብላ፣ ስንቱን አማላይና አታላይ አምልጣ፣ እሷም እንደማንም ግጣሟን አገኘችና ጎጆ ወጣች። ተሰበሰበች። አገባች….ተነካች።

በቃል እና በእምነቷ መሰረት፣ ክብር እና ንፅህንናዋን ጠብቃ ኖረ ተዳረች። ከባሏ ተኛች።

በዚህ ዘመን ቀረ ብለን የምንገረምበት ወግ አጥባቂነቷ የአስናቀች ወርቁን ዘፈን ያስታውሰኝ ነበር። አስናቀች ቀኑን ሙሉ ከምታፈቅረው ልጅ ውላ ልክ ሲመሽ ሌላ እንዳያስብ ‹‹ልሂድ›› ስለምትል ወዳጄን የምትመስል ሴት ዘፍናልን ነበር።

‹‹ፍቅርዬ- ፍቅርዬ ደህና ሁን
ሊመሽ ስለሆነ መሄዴ ነው አሁን…..
…እኔ እንደምወድህ – ፍቅሬ ሆይ ውደደኝ
በህጋዊ ስርአት ማልድና ውሰደኝ…
አፍቅረኝ ላፍቅርህ ኑሯችን ባንድ ይሁን
እስከዚያው ድረስ ግን- ፍቅርዬ ደህና ሁን›› እያለች ዘፍናልን ነበር።

እናም…የ34 አመቷ ወዳጄም በህጋዊ ስርአት፣ በአማላጅና በምልጃ የፈለገችውና የፈለገችውን አገኘችና፣ ወሰዳትና አገባች። ተነካች።

ሰርጉ ተከናውኖ…
ጫጉላው አብቦ…
ከስንት ያመለጠው ብር አምባር ተሰብሮ ጥቂት ቀናት ካለፉ በኋላ አሁንስ ይበቃታል ብዬ ደወልኩላት። እንዴት ሆንሽ….አጥሚትና ገንፎ የት ይዘን እንምጣ ልል እና ላጫውታት ደወልኩላት።

ብዙ ሳይጠራ አነሳች።

(በቅቷታል ማለት ነው…)

ሰላምታችን ሲያልቅ ወደ አንገብጋቢውጉዳይ ገባሁና..
‹‹እህስ…ነገሩስ? እንደጠበቅሸው አገኘሽው ወይስ ቅር አለሽ?›› አልኳት።
‹‹ቅር አለሽ ወይ? ወይ ጉድ…አንቺ….ስኳር መች ይጣፍጣል?!›› ብላ መለሰችልኝ።

ከአንጀቴ ሳቅሁ።

እንዲህ ትላለች ብዬ ስላልጠበቅኩም፣ ያ ከአመታት በፊት የሰማሁት ታሪክ ላይ ያለችው ልጅንም አስታወሰችኝና ሳቅሁ።

(ታሪኩ እንዲህ ነው። ልጅቱ ለስኳር ያላት ፍቅር የትዬሌሌ ነው። ‹‹ከስኳር የሚጥም፣ ከስኳር የሚጣፍጥ ነገር በአለም ላይ…አንዳችም ነገር የለም›› የምትል አይነት። እጮኛዋ ‹‹ተይ ተጋብተን ፍቅር ስንሰራ ኋላ ሃሳብሽን ትለውጫለሽ›› ቢላትም እሷ ግን ወይ ፍንክች! በኋላ ጋብቻው ተከናውኖ ባልና ሚስት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅር እየሰሩ ወደ ማገባደዱ ሲደርሱ የሚስቱን ሁኔታ ያየው ባል በእጁ የጨበጠውን ስኳር በተከፈተ አፏ ውስጥ ሙጅር ያደርጋል። ይሄን ጊዜ የስኳር ነገር የማይሆንላት ሚስቱ ምን አለች? ‹‹ውይ ውዴ…! የምን አፈር ነው አፌ ውስጥ የጨመርከው?!››)

‹‹ወይ አንቺ…እና ታዲያ ይሄን ያህል ጊዜ በመቆየትሽ ትንሽ አልተቆጨሽም ታዲያ?›› አልኳት
ለመመለስ ሰከንድ አልፈጀባትም።
‹‹በጭራሽ! መቆየቴ መቼም አይቆጨኝም….ግን እንዲህ መሆኑን ግን ነገራችሁኝ አታውቁም….››
‹‹ ብንነግርሽስ ኖሮ?››
‹‹እሱስ ምንም ለውጥ አያመጣም ነበር…ያው ምናልባት ትንሽ…ይበልጥ ልጓጓ ግን እችል ነበር……..››

ወሬያችን አልቆ ስልኩን ስዘጋ በዚህ ሁሉም ሰው ሁሉንም ሰው ለመምሰል በሚሮጥበት ጊዜ፣ ለግል አቋምና እምነቷ ባላት ታማኝነት እንዳዲስ ተደነቅኩባት። ቀናሁባት።
ከዚህ ሁሉ በላይ ግን (በእኔ እና በአለም ስሌት) ዘግይታም ቢሆን አዳሜ የአለምን ምሬት የሚያጣፍጠው ፍቅርን በመስራት ስኳር መሆኑን በማወቋ ተደሰትኩላት።

🔘በሕይወት እምሻው🔘
👍5
#ማፍቀር_ወይስ_መለየት ?
:
#አጭር_ልብወለድ
:
ቅዳሜ ከሰአት በኋላ ፣ፀጥ ረጭ ብሏል፣ የቤታችን የግድግዳ ሰአት ብቻ . . .ችው . . . ችው
እያለ በዚህ ፀጥታ ውስጥ ይሰማል። ማንም የለም እኔና እኔ ብቻ። በውስጤ የብቸኝነት ስሜት ተሰማኝ። በዚህ በጠራራ ፀሐይ እቤት ውስጥ ለብቻ መቀመጥ ምን ያህል ይከብዳል እያልኩ ከራሴ ጋር አወራለው።

ዞር ብዬ ክላሲካል ሙዚቃ ሲያሰማ ወደ ነበረው ቴፕ ስመለከት መብራት ሄዶ ዝም እንዳለ ታወቀኝ። ሀሳቤን ሰበሰብኩና በእጄ ወደያዝኩት ልብ ወለድ መፅሀፍ አቀርቅሬ ማንበቤን ቀጠልኩ።

በጥሩ ተመስጦ ውስጥ እንዳለው ድንገት ከአጠገቤ የነበረው ስልክ ጮኸና ቀልቤን ገፈፈው።በጣም ደነገጥኩ። በራሴ መደንገጥ ተገረምኩና እራሴን አረጋግቼ የስልኩን እጀታ በጉጉት አነሳሁት።

<<ሃሎ>> አልኩኝ በትህትና
<<ሄሎ>> አለችኝ አንዲት ልጅ በሚያባባና በሚያምር የድምፅ ቅላፄ።
<<ማንን ፈለጉ ?>>
<<እ. . .ናሆምን ላገኘዉ እችላለሁ ?>>

በዚህን ግዜ የልብ ትርታዬ ፍጥነቱን ጨመረ።
ድምፆም አዲስና የሚማርክ ስለሆነብኝ ማን ልትሆን ትችላለች? በሚል ከራሴ ጋር ትንሽ ተሟገትኩና።

<<ነኝ. . . ማን ልበል?>>
<<. . . ሜሮን እባላለሁ >>
<<ሜሮን?.. .ይቅርታ. . . አላስታወስኩሽም፣ ሜሮን ማን ?>>
<<ሜሮን አለሙ>>

አሁንም ፈፅሞ ላስታውሳት አልቻልኩም።ሜሮን የምትባል ልጅ ፈፅሞ ማወቄን እርግጠኛ አልነበርኩም።

<<በ. .ጣም.. ይቅርታ የኔ እህት አላወኩሽም።>>
<<ይገርምሀል እኔም አላውቅህም።>>
<<የደወልሽው አንቺ መሰለሽኝ?>>
<<አልተሳሳትክም፤ ማለቴ ስልክህን የአስረኛ ክፍል ማስታወሻ ደብተሬ ላይ ከበስተጀርባው ተፅፎ ነው ያገኘሁት።ሁለት አመት እንዳለፈውና በራሴ እጅ ፅሁፍ ስለመፃፉ እርግጠኛ ነኝ ነገር ግን በምን ቀንና ሁኔታ እንደተፃፈ አላስታውሰውም
<<እና?>>
<<እናማ ብዙጊዜ ሲከነክነኝ የነበረ ስልክ ቁጥር ስለነበር ምን አልባት አንተ ካወከኝ በሚል ነበር የደወልኩት።

መልሶን ማመን አቃተኝ።ለሰኮንዶች ያህል በአይኔ የማውቃቸውን እንስቶች በአይነ ህሊናዬ እየቃኘኋቸው ድምፅን ከምስል ጋር ለማዛመድ ሞከረኩ።ሆኖም በፍፁም ልትመጣልኝ አልቻለችም ።በርግጥ ከሁለት አመት በፊት ስለተከሰተ ነገር ማስታወስ ይከብዳል።

የቀረን ነገር ቢኖር በግምት ልንተዋወቅበት የምንችልበትን ሁኔታ መመርመር ነውና ስለየግል ህይታችን መነጋገር ጀመርን።ስለ ት/ቤትና ስለመኖርያ ስፍራችን፣ ስለቤተሰብ እንዲሁም ስለ ቅርብ ጓደኞቻችን ሳይቀር በግልፅ ተወያየን።በሚገር ሁኔታ ግን አሁንም ከጥርጣሬ ያለፈ እዚህ ቦታ ይሆናል ብለን መወሰን ተቸገርን።

ለቀልድ ነው ብዬ እንኳን እንዳልጠረጥራት የምትሰጠኝ መልሶች ሁሉ ግልፅና ፈጣን ነበሩ።
በተለይ ከንግግሯ በራስ መተማመንና በሳልነቷን ለመገመት ይቻል ነበር።ሁኔታው ቢያስገርመኝም ቀስ በቀስ ምርመራውን ትተን ስለየጎል ህይወታችን ገብተነሰ መጨዋወት ጀመርን።

<<ምን አየሰራሽ ነው አሁን?>>
<<ያው አስረኛ ከጨረስኩ በኋላ የሁለት አመት አካውንቲንግ ፊልድ ተምሬ ነግል ድርጅት ውስጥ በመስራት ላይ ነኝ። አንተስ?>>
<<እኔ እንደምንም የመሰናዶ ትምህርት ተምሬ አ.አ.ዮ የአስተዳደር ትምህርት በመማር ላይ ነኝ>>
<<ኦው ጎበዝ ተማሪ ነሃ . . .!>>
<<ነኝ ብለሽ ነው . . . ለመሆኑ ግን ምን ከይነት ሰው ነሽ ማለቴ መልክሽን?>>
<<...እኔጃ ለመግለፅ ይከብዳል።>> ሳቅ እያለች።
<<ታድያ.... ለምን በአካል አንገናኝም፤ >>ምን አልባት በመልክ ልንተዋወቅ እንችላለን?
ጥያቄውን በድፍረት ነበር ያነሳሁት ፤ሆኖም በፍርሀቴ ልክ መልኳን ለማየት ጉጉቱ ነበረኝ። እርሷም በመግደርደር ይሁን አላውቅም።

<<..መገናኘቱ እንኳን የሚመች አይመስለኝም።>
<<ለምን?>>
<<እኔንጃ?>>
<<ፈራሽ እንዴ?>>
<<አይ መፍራት ሳይሆን ሰሞኑን ክፍት ሰአት ስለሌለኝ ነው።>>
ንግግሯ እንደማቅማማት አይነት ነበር ፤ እርግጠኛ አልነበረችም።

<<እሺ. . . ብዙ አላስጨንቅሽም ባይሆን ስልክሽን ስጭኝና ተደዋውለን ሌላ ግዜ እንገናኛለን።>>

ለተወሰኑ ሰኮንዶች ዝም አለች።የኔንም ግራ መጋባት ጥርጣሬ አጎላችው።

<<ምነው ዝም አልሽ?>>
<<...ስልክም አሁን ልሰጥክ አልችልም።>>
<<እህ..ያሁሉ የግል መረጃሽን በግልፅነት ስትነግሪኝ ቆይተሽ እንዴትስልክ መስጠት ከበደሽ?>>
<<በፍፁም መደበቄ አይደለም።በዚህን ሰአት እኔን የምታገኝበት ስልክ ምን አልባት ለሁለት ቀን ብቻ የሚቆይ ነው ። ሌላ ስልክ በሌላ ግዜ እንጂ አሁን ልሰጥክ አልችልም ወይም አላውቀውም።>>
<<አሀ ገባኝ፣ ቤት ልትቀይሩ ነው አይደል?>>
<<አረ አይደለም >>ሳቅ እያለች ነበር።
<<ምንድን ነው እሱ ግልፅ ሁኚ እንጂ የደበቅሽው ነገር ኦንዳለ ይሰማኛል።>>
<<በቃ ለምን ነገ ወደ ማታ አንገናኝም?>>
የአቋም ለዉጧ አስገርሞኛል፣አስደንግጦኛልም።
አሁን ለመናገር ያልፈለገችው ሚስጥሯም ከልብ አጓጓኝ።
<<ጥሩ የት እንገናኝ?>>
<<ፒያሳ ያለው ቤቲ ካፌ ይመችካል?>>
<<ደስ ይለኛል ስንት ሰአት?>>
<<አስራ ሁለት ሰአት።>>
የሰአት ምርጫዋ ወደ ማታ መሆኑ አይናፋርነቷን ቢያስገምተኝም ለኔም ጥሩ ግዜ ስለነበር ወድያው ምልክቶቻችንን መለዋወጥ ጀመርን ።
የሷን አንድ በአንድ ከሰማሁ በኋላ ፣ የኔንም እንዲሁ ነገርኳት።እንደምልክት አገላለጿ በጣም ውብ ልጅ እንደምትመስል ገምቻለው ።ነገር ግን ከዚህ በፊት ያየኋት ትሆናለች የሚል ሀሳብ አልነበረኝም።

ይቀጥላል

Like 👍 Like 👍

አስተያየት ካሎ በ @atronosebot አድርሱን
👍13
#ማፍቀር_ወይስ_መለየት(የመጨረሻ ክፍል)
:
..ሰአቴን አስር ጊዜ አያለው፤ከካፌው በረንዳ ላይ ሆኜ ሜሮን ምን ልትመስል እንደምትችል አሰላስላለው።ፍርሃቴም እንዳለ ነው።አይኔ ግራና ቀኙን ካሁን ካሁን መጣች በሚል ያለመታከት ይማትራል።ብዙ ሴቶች ሲያልፉ እያየሁ እደነግጣለው።በተለይ አንዷማ ራሷ መስላኝ ከመቀመጫዬ ብድግ ለማለት ምንም አልቀረኝ።መልሼ ደግሞ ሰአቱ እየገፋ ሲሄድ የምሞኝ መሰለኝ።
<<ቆይ እስቲ አንድ ሰው እየተጫወተብኝ ቢሆንስ?>> እያልኩ እራሴን በጥርጣሬ እሞግታለሁ ።

ብዙም አልቆየ አይኔ ሳያስበዉ ከአንድ ሰው አይን ጋር ተጋጨ።ሁሉ ነገር በሰከንድ ውስጥ ተቀያየረ።
ዞማ ፀጉር፣ጠይም መልከመልካም፣ቁመናዋ የሚማርክ በተለይ አይኗ! ምንም እንኳን በትክክል ምልክቶቿን ብታሟላም፣እርሷም ቢሆን ወደኔ እየቀረበች ቢሆንም እሷናት ብዬ ለማመን አልቻልኩም ነበር።

<<ባልሳሳት ናሆም የምትባል አንተ ነህ?>>
በካፌ ውስጥ ብዙ ወንዶች እያሉ እኔን ለይታ ማወቋ ገርሞኛል።
<<አልተሳሳትሽም . . .እራስሽ ነሽ ግን?>>
<<አይ እህቷ ነኝ!>> ስትል ቀለደችብኝ።
ፈገግታዋ ልዩ ነበር።
ለረጅም ጊዜ እንደሚተዋወቅ ሰው ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳምን።
የካፌው ሰዎች ሁሉ ወደኛ በመመልከታቸው ኩራት ኩራት አለኝ።
እንድትቀመጥ ከጋበዝኳት በኋላ አስተናጋጁን ጠራሁት።
<<. . . እሺ አስታወስከኝ ?>> በአትኩሮት እያየችኝ ነበር።
<<አረ በፍፁም!ለመሆኑ እንዳንቺ አይነት ሰው እዚህ ከተማ አለ?>>
<<እኔም እንዳተው ነኝ ግን እርገጠኛ አይደለሁም እንጂ መልክህ አዲስ አልሆነብኝም>>
<<ታድያ ስልኩ ከየት ተፃፈ ይባላል?>>
<<እኔም ደንቆኛል...ምን አልባት መንገድ ላይ ይሆን?>>
<<የምታስታውሽው አጋጣሚ አለ?>>
<<ኦው . . ይከብዳል ።>>
<<በርግጥ ልክ ነሽ . . .የእግዜር ስራ ይገርማል።>>
ለጥቂት ሰኮንዶች ዝምታ ሰፈነ።በካፌው ውስጥ ለስለስ ብሎ የኤፍሬም የድሮ ዜማ ተከፍቷል።ትንሽ እንደቆየን ፀጥታውን ሰብርን ስለየግል ህይወታችን ፣ስለመሀበራዊ ጉዳይ መጨዋወት ጀመርን።ቀስ በቀስ ፍርሀቴ ተጠራርጎ ወጣና ስለምንወደውና ትርፍ ጊዜን ስለምናሳልፍበት ሁኔታ ሳይቀር ተነጋግርን።በደቂቃ ውስጥም አንድ ስንሆን ተሰማኝ።ፍቅር እንዳይዘኝም ሰጋሁ።ግን ፈርቼም እንደማይቀርልኝ አውቃለው።ብቻ ቆይታችን በጣም ስለተመቸኝ ጊዜው እንዳይሮጥ አምላኬን ተማፀንኩት።ንግግሯም ጣፋጭ ስለነበር ፈፅሞ ፀጥታ እንዲገባ እድል አልሰጠሁም።
<<ጓደኛ አለሽ >> የሚለው ጥያቄ በውስጤ ይብሰለሰል ነበር።ነገር ግን መቸኮሉ ጥሩ እንዳልሆነ አሰብኩ።እንዲህ እንዲህ እያልን ከምሽቱ አንድ ሰአት ሲሆን ሂሳብ ከፈልኩና ከካፌው ወጥተን በእግራችን የፒያሳን ጎዳናን ማቋራጥ ጀመርን።
ምሽቱ ለኔ ውድና መቼም ልረሳው የማልችለው ትዝታን እንደጫረብኝ እርግጠኛ ነበርኩ
ለሷም ቢሆን ከዚህ የተለየ ይሆናል ብዬ አለገምትም።
<<ትላንት ለምንድን ነው ስልኩን የከለከልሽን>>
<<አልተረዳክኝም ማለት ነው>>
<<አዎ ምንም ግልፅ አልሆነኝም።>>
<<ቆይ እንግርሀለው>>
<<መቼ?>>
<<አሁን>>
<<አሁን እኮ አሁን ነው>>
<<ትንሽ ቆይቶ አሁን?>>
ምን እንደሆነ አላውቅም ልቤ ስጋት እየተሰማው እጅ ለእጅ እንደተያያዝን ከሰፈሯ ደረሰን።መለያየታችንም ግድ ነውና ካንድ ቦታ ቆም ብለን ፊት ለፊት በስስት ተያየን።
<<ልንለያይ ነው ማለት ነው?>>አልኳት በሀዘን
<< ምን ይደረግ>>
<<መቼ እንገናኛለን?>>
<<መቼም. . .።>>
<<ለምን?>>
ዝምት ሰፈነ።አምላኬን <<እባክህ ፈጣርዬ ሆይ የሰጠከኝን እድል መልሰህ እንዳትነፍገኝ>> ስል ተማፀንኩት።
<<ይቅርታ አድርግልኝ ናሆም በሰልክ ያልነገርኩክ ድምፅህ እንዲሁም ብስለትክ ሰለማረከኝ ሳላይህ አልሄድም ብዬ ነዉ።ከነገ ወድያ ለኑሮ አባቴ ጋር ወደ ካናዳ መሄዴ ነዉ።እስካሁንም ያልነገርኩህ ጫወታችን እንዳይቀዘቅዝ ሰግቼ ነው። >>
<<. . .ምን! . . . እየቀለድሽ ነው? >>
ነገሮች ሁሉ ሲገለባበጡ ተሰማኝ።የምሰማውን ማመን አቃተኝ።
የሰጋሁት ነገር እውን መሆኑን ስረዳ ተናደድኩ።ህልምም መስሎኝ ለመባነን ቃጣኝ።
<<እየቀለድኩ አደለም ናሆም፤ባንተ ውስጥ ያለው ስሜት በኔም ውስጥ እንዳለ እወቅልኝ። ስልኩን የደወልኩልህ ከስልክ ደብተሬ ላይ ያሉትን ወዳጆቼን ሁሉ ተሰናብቼ የቀረኝ ያንተ ብቻ ነበር። እኔም ቅር እያለኝ ከምሄድ ብዬ ነው የደወልኩት>>
<<ልክ አይደለሽም. . .።>> ሀሞቴ ፍስስ እንዳለ ነበር።
<<እንዴት ናሆም?>>
መልስ መስጠት ከበደኝ፤አንደበቴም ተሳሰረ።ምን እየሆነ እንዳለ፤ምን እንደማደርግ ሁሉ ግራ ገባኝ።ትንሽ እንደቆየን ከሜሮን ጋርም ምንም የቀረኝ ነገር እንደሌለ ተረዳሁ።የመጨረሻ የምትሆነኝን ቃል እንደምንም አምጬ ሰነዘርኩለት።
<<እስቲ አሁን ምን አለበት . .ሳትደውዪ ዝም ብለሽ ብትሄጂ !?. . .>>
ሳልሰናበታት ከቆመችበት ጥያት ወደ ቤቴ ማዝገሜን ቀጠልኩ።
አይኔ ላይ ብዥ ብዥ እያለብኝ ትንሽ እንደተጓዝኩ ከኋላዬ ደርሳ እጄን አጥብቃ ያዘችው።
<<እባክህን ናሆም ተረዳኝ . . .እኔ ምን አጠፋው ምንስ ማድረግ ነበረብኝ። ይሉቁንስ እግዜር ያለመክናይት አላገናኘንምና ልነደሰት ይገባናል።>>
መልስ አልሰጠኋትም።አይኖቼ አይኖቿን ሲመለከቱ ፈዝዤ ቀረሁ ።በዛ ምሽት እንደኮብ ያበራሉ።የምሰማው ድምፅዋ በደምስሬ ሰርፆ መንፈሴን ሲያድሰው ተሰማኝ ።እኔም ከፊትዋ ቆሜ አይን አይኖን እያየው አዳምጣታለው መልስ መስጠት ግን አልፈለኩም።
<<ተረዳከኝ ?ሆን ብዬ ያደረኩት አይደለም።ለምንስ ሆን ብዬ አደርጋለው።ልክ እንዳተው ሁሉ የስልክ ቁጥሩ ሚስጥር ለኔም ሚስጥር ነው። ደግሞ እግዜር በፈጠረው አጋጣሚ አትማረር፤ ሁሉም ለበጎ ነውና።. . .ተናገር እንጂ ለምን ዝም ትላለህ ? በዚ ላይ ስሜታችን አንድ እንደሆነ እገምታለሁ።>>
በረጅሙ ተነፈስኩና ለደቂቃ ሰማይ ሰማዩን ስመለከት ጨረቃን አገኘኋት።በትዝብት ተመለከትኳት።ከዛም ወደራሴ ተመለስኩና በርጋታ ማሰላሰል ጀመርኩ።ምንም እንኳን አጋጣሚው አስገራሚና አሳዛኝ እንዲሁም የማይታመን ቢሆንም፤እውነታውን ተቀብዬ በሰላም መለያየቱ ጥሩ እንደሚሆን አሰብኩ።ሜሮን ላይም ምንም ስህተት ፈልጌ አጣው።
<<ማክሰኞ ጠዋት ነው የምትሄጂው?>>
<<አዎን>>
<<ታድያ ለምን አልሸኝሽም?>>
<<አይሆንም ከቤተሰብ ጋር ስለሆንኩ እንደገና መጨነቅ የለብንም። እዛው እንደደረስኩ በደቂቃ ውስጥ እደውልልካለው >>
<<እርግጠኛ ነሽ?>>
<<አትጠራጠር ላንተ ሳይሆን ለራሴ ስል ነው የምደውለው።>>
<<እጠብቃለው።>>
<<በቃ ደህና ሁን፤በግዜ ቤትክ ግባ።>>
እቅፏ ውስጥ ስታስገባኝ ይባስ ነፍሴ ተደሰተች።ጠረንዋ ካፋንጫዬ ሲቀር ታወቀኝ።ጡቶቿ ከደረቴ ጋር ሲነካኩ ስሜቴ ጣርያ ደርሶ ተመለሰ።በረጅሙ ተነፈስኩና ዳግም የምነገናኝበትን ቀን መናፈቅ ጀመርኩ።
አንድ ነገር ተሰማኝ....አዲስ ህይወት፤አዲስ እስትንፋስ፤ዳግም ውልደት....ግን ምን ያደርጋል የወደድኳት ለት ተለየኋት.....የናፍቆቷን ኑሮ ''ሀ'' ብዬ ልጀምር ነው።

▪️▪️▪️▪️
👍82
#ዋ !
አይኔ ወደደሽ ስልሽ፣
አይኑን አጥፋው ብለሽ ገባሽ አሉ ስለት
ምኞትሽ ሰመረ
አይኖቼ ጠፉልሽ ይኸው አንደዘበት።
:
ግን መች ተውሻለው
በልቤ ብሩህ አይን ዛሬም አይሻለው።
:
ደሞ አንደዚ ስልሽ አትወጅኝምና
ልቡንም አጥፋልኝ ብለሽ ትሳይና
ፀሎት ያልቅብሻል እሞትብሽና።

🔘በረከት በላይነህ🔘
#ሆሆ

“ወንድ ሆኖ የማያመነዝር ፤ ወታደር ሆኖ እማይሰነዝር ፤ ነጋዴ ሆኖ እማይዘረዝር የለም ! “ይላል ምኡዝ።
እውነቱን ነው፤ከጥቂቶቻችን በቀር ብዙ ወንድ በህይወቱ ቢያንስ አንዴ በትዳሩ ላይ ያድጠዋል። ድርያ በአርቲስት ላይ ይጋነናል እንጂ ፊትና ጭን ከተሰጠው፤ ገበሬ ነጋዴ ፓስተር ሼህ የንስሃ አባት ሳይቀር እንደሚወሰልት እናውቃለን። መቸም የሴት ገላ ማቀፍ እንዴት እንደሚጥም የቀመሰ ያውቀዋል፤ ግን የሚያስከፍለው ዋጋ ከደስታው ጋር አይመጣጠንም፤ አንድ ጣሳ ደስታ ይሰጥህና አንድ በርሚል ጣጣ ያሸክምሃል!!

#አንድ

የሆነ ጊዜ ላይ አሜሪካ ውስጥ ባንድ ከተማ የተከሰተውን ዜና በራሴ መንገድ ስተርተው ይሄን ይመስላል፤
ሰውየው ሚስቱ ማታ ለስራ በሄደችበት ውሽማውን አምጥቶ በተቀደሰው አልጋ ላይ ይፈትጋታል፤ በፍትጊያ መሀል ኮቴ ሰምቶ ቀና ሲል ሚስቱን አያት፤ ውሽምየዋ እንደስፓይደር ውመን በመስኮት ዘልላ ነካችው፤ ባልየው ብቻውን ከሚስቱ ጋር ተፋጠጠ፤ ሚስትዮዋ ለሰይፍ ሩብ ጉዳይ የቀረው ቢላዋ ይዛለች፤ ባሉካ ለመሮጥ ተመኜ ፤ግን እግሩ ቀጤማ ሆነበት፤ በወዛደር አማርኛ እንግለፀው ከተባለ እድሩ የቡልዶዘር ጎማ ሆነበት፤ ሚስትየው ምንም አላለችም፤ አልጋው ላይ እመርር ብላ ወጣችና አገር አማን ነው ብሎ ቆሞ የሚጠብቀውን ብልቱን ጨብጣ ከስሩ መተረችው፤ ከዛ እንደ ቀይ ስር በቁንጮው አንጠልጥላው ወጣችና በቤቱ ጉዋሮ በሚገኘው ዱር ውስጥ ወርውራው ተሰወረች፤
ብዙ ሳይቆይ አምቡላንስ ስልቡን ሰውየ ይዞ ወድ ሆስፒታ መረሸ፤ ያሜሪካ ፖሊስ በቦታው ደርሶ ፤ ከሲአኤ ጋር በመተባበር አካባቢውን በብረት ለበስ መኪና አጥሮ ተቆርጦ የተጣለውን ወሸላ ፍለጋ ተሰማራ፤፤ ከላይ በሂሊኮፍተር ከታች በአነፍናፊ ውሻ የታገዘ ሰአታትን የፈጀ አሰሳ በሁዋላ የተቆረጠው ብልት የጉንዳን መንጋ ወርሶት ተገኘ፤፤ በመጨረሻ ዶክተሮች ወደ ስልቡ ባል ቀርበው፤ “የጠፋብህ ብልት ይሄ ነውን?” ብለው’ በመስቀልኛ ጥያቄ መርምረው አረጋግጠው፤ በቀዶ ጥገና ተከሉለት፤ትንሽ ከመንሻፈፉ በቀር በድሮው ቦታ ተተከለ ፤እረ እንዴውም ከዱሮው ሳይሻል አይቀርም፤ ሚስት ተብየዋን ደስ አይበላትና ሀኪሞች ፤ እንደ ክንዱ በፈለገ ጊዜ የሚዘረጋውና የሚያጥፈው አድርገው ተከሉለት፤

#ሁለት

ይሄ ደሞ ባልንጀራየ የነገረኝ ነው፤
ዲሲ ውስጥ የሚኖሩ ባልና ሚስት ኢትዮጵያውን የተጋቡበትን አስረኛ አመት በማክበር እየተዝናኑ አመሹ፤ከዚያ ሚስትዮዋ” ቤብ፤ በፍቅራችን ላይ ቅመም የሚጨምር ነገር ላሳይህ ” አለችና ከራቫቱን ፈታችለት፤ አያ ‘ቤብ ‘ ክራቫቱን እያስፈታ ፤ ከታች ስራ እንዳይፈታ፤ ቀበቶውን ፈታ፤
ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ አንድ የትራፊክ ፖሊስ መንገድ ዳር ቆሞ ቫይብሬት የሚያደርግ መኪና ስለተመለከተ ጠጋ ብሎ መስኮቱን አንኩዋኩዋ!
“is there any problem ? officer? “ አለ ባልየው ትንፋሹ እየተቆራረጠ።
“መኪና መሳረር ህገወጥ ስለሆነ ልቀጣችሁ ነው” አለና ፖሊሲ ባልየውን መቶ ዶላር ቀጣው፤ ሚስቲቱን ግን ሁለት መቶ ብር ቅጣት ጣለባት፤
ባልየው ትንሽ ቆይቶ ስለከነከነው ፖሊሱን ተከትሎ ደረሰበትና፤
“ቅጣቱስ ይሁን! ይበለኝ፤ የግሬን ነው ያገኘሁት፤ ግን በምን ምክንያት ነው እኔን መቶ ብር ቀጥተህ ሚስቴን ሁለት መቶ ቀጣሃት?’
ፖሊሱ እንዲህ መለሰ፤
“እ ሷ መኪና ውስጥ እንዲህ አይነት ነገር ስታደርግ ያገኘሁዋት ለሁለተኛ ጊዜ ነው፤ ለዝያ ነው እጥፍ ያስከፈልኩዋት”😳
ባልየው በድንጋጤ ታሞ ይሄው በጎፈንድ ሚ እያስታመምነው እንገኛለን፤

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
👍3
#ኑ_ሀገር_እንስፋ!

ክፍፍል መችነበር፥
በእግዜሩ አሰራር፥በቅድመ አፈጣጠር
ሰው ሰው ብቻ ነበር፥ዘሩ ሳይቆጠር
ሰውነት ተንዶ፥
እንዲህ እንደዛሬ፥ሳይኖር መበታተን
የመቆጣጠር ዛር፥መቃብር ሳይከተን
አንድ እናት ነበረን፥
ቀሚሷ እንደኪዳን፥ሁላችን ምንለብሰው
ዛሬ ተለያይተን፥
ክብሯን እንደ እቃቃ፥ዳቦ ሳንቆርሰው
ሻህላ ወረሰን፥
ውስጣችን ተበላ፥
ፍቅር የጠመቅንበት፥ተሰበረ ጋኑ
ለናታችን ቀሚስ
ጥጥ የነደፍንበት፥ተጣለ ደጋኑ
ሰው ተተነተነ፥ሰው ተቆራረሰ
ዘር ስንቆጣጠር፥ሀገር ፈራረሰ
ፍቅር እንደቁና፥አርጅቶ ተጣለ
ጥላቻ ድንኳኑን፤በላያችን ጣለ
የናታችን ቀሚስ፥
ባለሶስ ቀለሙ፥
በሰማይ ዳስ ሲጥል፥ለምድር የሚያጠላው
ትውልድ ሲናጠቅ፥
በ"የኔ ነው !" "የኔ"፥የጥል እሳት በላው
ይኼው እና ዛሬ!
ያች ሙሉ እመቤት
ያቺ ሸዋ ግርድሽ፥
በክፍፍል ክናድ፥
ከፍቅር ሰገነት፥ከርማ ስትገፋ
እርቃኗን ቆማለች፥
የቃልኪዳን ልብሷን፥ቀሚሷን ተገፋ
ያ ብልህ አያቴ
ትውልድ በሽሚያ፥የቀደደው ልብሷን
ሊሰፋ ይጥራል፥የክብር ቀሚሷን
ስሩ ተቀምጬ፥
በልጅ አእምሮዬ፥ጥያቄ ይዘንባል
በቦዘዙ ዐይኖቹ፥
ክሩ ከመርፌው ጫፍ ላይገባ ይዛባል
እንዲህ ጠይቃለሁ?
ምን ነካህ አባባ፥
ይኼ ቅዳች ቀሚስ፥ዳግም ተጠግኖ
እንደቀድሞው አይጥል፥ውበቱ ጀግኖ?"
ለምን ትለፋለህ፥?ብዬ ስጠይቀው
አያቴ እንዲህ አለኝ፥እንባው እያነቀው
ልጄ ሆይ አድምጪ፥
መስፋቴ ቅኔ ነው፥እንደወርቅ እንደሰም
አላዳውር አይል፥ስንጥቅ ኖሮት ቀሰም
አስተውይ ልጄ፥
መርፌ ማለት ፍቅር፥ሰርስሮ ሚገባ
ክር ማለት ሰላም፥
ቀዳዳን ጠግኖ፥ዳግም ሚገነባ
ይለኛል አያቴ፥
ፍቅር ባለው መርፌ፥ነፍሱ እየተወጋች
ክር ላለው ሰላም፥ደጀን እየተጋች
የእናቴን ቀሚስ
ሲጠግን ስላየሁ፥
እንሆኝ አንድ ቃል!
የናት ክበር ወድቆ፥
የለምና ለክብር፥የሚሰነቅ ተስፋ
ኑ እርቃን እንሸፍን፥ኑ ሀገር እንስፋ

🔘በዳግም ህይወት🔘
👍2
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አንድ
:
ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...የዲላ ከተማ ነዋሪ የሆነችው የ45 አመቷ ወ/ሮ ምንትዋብ በህይወቷ አሥቸጋሪ ግዜ ላይ ትገኛለች።ሀዘን ውሥጧን ሠብሯታል።ስጋት ቅሥሟን ሠልቧታል።ሞራሏንም ንብረቷንም ፍቅሬ ብላ ላሥጠጋችው፤ ትዳሬ ብላ ለተቀበለችው ሰው ቀሥ በቀሥ አስረክባው ነበር። ያ ሰው ግን በዚህ ወቅት ሁሉን ነገር ይዞባት ተሰውሯል...ለንግድ ብሎ እንደወጣ የዉሀ ሽታ ሁኖ ከቀረ እነሆ ሁለት ወራት ደፍኗል...ሶስተኛው እየተጋመሰ ነው።መልዕክት የለ...ሥልክ የለ...ምንም ፍንጭ የሌለው ድፍንፍን ያለ ወጋገን አልባ ጨለማ ስጋት ዙሪያዋን ከቧታል።
ምንትዋብን እንዲህ ስጋት ላይ የጣላት የሶሶት አመት ባለቤትዋ ሁኖ አልጋዋን ሲጋራት የነበረው ወርቅ አለማው ነው።እርግጥ መጀመርያ ከቤት ሲወጣ እንደወትሮው ለተለመደ ሥራ ነበር..ያልተለመደው ሥልክ ደውሎ ያለማወቁ..ከዚያ በፊት ከሚያሳልፈው የሣምንትና የአስራ አምስት ቀን የግዜ ቆይታ ባልተጣጣመ መልኩ ከሁለት ወር በላይ መዘግየቱ ነው።ይዞ የሄደው ንብረት ወይም በእሡ እጅ ያለው ንብረት ቀላል የሚባል አይደለም።ከዛ ውሥጥ ደግሞ 80 ፐርሰንቱ የሷ የግል ንብረት ነው..እረ ምን የሷ ብቻ የአንድዬ ልጇም ንብረት ነው፤ከአባቱ በውርሥ የተላለፈለት..ከሟች ባሏ ጋር በአንድነት ያፈሩት የቤተሠቡ መተዳደርያ ጥሪት ነው..ወደድኩሽ ብሎ ለተጠጋት ባል ነኝ ብሎ እቤቷ ለአመታት ለኖረው ወርቅ አለማው አምናና አሳልፋ የሠጠችው።ወርቅ አለማው የምንትዋብ የበፊት ሟች ባል ተቀጣሪ ሰራተኛ ሁኖ ከአምሥት አመት በላይ የኖረ የ40 አመት ጎልማሳ ነው።ምንትዋብ ከእሡ ጋር የመቀራረብ እድሉ ያጋጠማት የልጇ አባት የሆኑት አዛውንት ባሏ ከሞቱ በሁዋላ በእሳቸው ይተዳደር የነበረውን ሆቴል እሷ መቆጣጠር ስትጀምር ነበር።ምክንያቱም ወርቅ አለማውም የሆቴሉ ስራ-አስኪያጅ ስለነበር በየቀኑ የመገናኘትና የመነጋገር እድል ነበራቸው።ሳያስቡት መቀራረብ ቀስ በቀስ
መሳሳብ ጀመሩ..
ትክክለኛውን ነገር ፈታተን እና ከፋፍለን እንየው ከተባለ ግን ሳያስቡት የሚለው ቃል የሚሠራው ለምንትዋብ ብቻ ነው...ወርቅ አለማው እያንዳንዷን እርምጃውን በእቅድ ነበር ያከናወናት...ቀድሞውንም በፍቅር ስም እየማለ የሚከውነው ከፍቅር ውጭ የሆነ አላማ ነበረው።በፍቅር መሠላልነት በመንጠላጠል ወደ ሀብት ማማ ላይ መንጠልጠል..አዎ ይሄን በልቡ ውስጥ በሚስጥር ቀብሮ ለማንም ትንፍሽ ሳይል በአላማ ሲንቀሳቀስ ነበር።...ያው ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር ሠው ብርቱና የአሸናፊ ሀይል በውስጡ ይዞ የሚዞር የእግዛብሔርን እስትንፋስ የተጋራ ልዩ ፍጡር ነውና ከልቡ ካቀደ..ያቀደውንም እንዲሳካለት ሳይሰለች ከጣረና ከለፋ ይሳካለታልና ይሄው ለሶስት አመት በማድባት ከሠራ በኋዋላ ዛሬ ያሳካው ይመስላል...ክፋቱ ይሄንን እግዛብሔር ከእስትንፋሱ ጋር ደባልቆ የሠጠውን የአሸናፊነት ሀይል በጎ ላልሆነ ነገር ስለተጠቀመበት(ተጠቅሞበት ከሆነ ማለቴ ነው)እንዴት ነው የሚቀጣው......? አዎ ምንትዋብ ዛሬ ነገሮች ከእጇ ሾልከው ያመለጡ ከመሠሉ በሁዋላ ነው አይኖቿ በድርበቡም ቢሆን የተከፈቱላት እና ልቦናዋም በጥርጣሬ ይታመሥ የጀመረው... ...እርግጥ አሁን ሥጋት ነው እንጂ ምንም የሚታወቅና የተረጋገጠ ነገር የለም።እውነት በውስጧ እንደጠረጠረሽው ከድቷት ይሆን ወይስ በሄደበት ሀገር አደጋ አጋጥሞት.. ...?ሌባ ዘርፎት ወይስ ሽፍታ ገድሎ አንድ ስርቻ ጥሎት? እግዜር ነው የሚያውቀው።ምንትዋብ ማለቂያ የሌላቸው ግትልትል ሀሳቦቿን በአእምሮዋ ስታመላልስ ቆይታ ድንገት እንደመባነን ብላ ወደ ቀልቧ ስትመለስ የ29 አመቱ ወጣት የፖሊስ መኮንን ልጇ ስሯ ተንበርክኮ አይን አይኗን በሀዘኔታ እያያት ትካዜዋን ሲጋራት ተመለከተች......
<<የኔ ውሻ>>አለችው እጇን ግንባሩ ላይ ጭና
<<አቤት እማ>>
<<የምሳ ሰአት ደርሶ ነው የመጣኸው? ምን አንበረከከህ ደግሞ..? ለምን አትነሳም?>>
<<አዎ 7 ሰአት ሊሆንኮ ነው...ጠዋት ትቼሽ የሄድኩበት ቦታ ሳገኝሽኮ ደነገጥኩ>> በማለት ከተንበረከከበት በመነሳት ከጎኗ ሶፋው ላይ ተቀመጠና መናገር ጀመረ
<<እማ ያንቺ ስጋት ሙሉ በሙሉ ግልፅ አልሆነልኝም..ለስራ ነው የወጣው አይደል...? ለዚያውም ጅቡቲ ድረስ...እርቀቱን አስቢው የቆየበትን ግዞኮ ያን ይህል ተስፋ የሚቆረጥበት አይደለም...ሶስት አራት ወር የሚቆይበት ጉዳይ ሊያጋጥመው ይችላል>>እናቱን ለማፅናናት ብሎ እንጂ ሰውዬው ያለምንም ነገር ድምጹን አጥፍቶ ይሄን ያህል ግዜ እንዳልቆየ የሱም ልብ ጠርጥሯል።
<<መቆየቱ አይደለም ያስጨነቀኝ።ባልተለመደ መልኩ ለአንድ ቀንም ቢሆን ያለመደወሉ...ስልኩም ጥሪ ያለመቀበሉ ነው ያሳሰበ ኝ....በቃ ውስጤ ፈርቷል ።>>አለችው ከአይኖቿ ያለፍላጎቷ የሚረግፈውን እንባ በእጆቿ እየጠራረገች
<<እርግጥ መደወል ነበረበት...ሳይመቸው ቀርቶ ይሆናል።ወይንም የሡ አለመደወል እኛን ይሄን ያህል ያስጨንቃቸዋል ብሎ ስላላሠበም ሊሆን ይችላል።>>
ምንትዋብ ከተቀመጠችበት ተነሳች...በአንድ እጇ ወገቧን ይዛ በሌላ እጆ የተንጨፈረረ ፀጉሯን ይበልጥ እንዲንጨፋረር እያፍተለተለች ንግግሯን ቀጠለች<<አዎ..እሡን እንኳን እውነትህን ነው..አጅሬ ምን ጎደለበት? እስቲ ተወኝ..ጉድ ሳያደርገኝ አልቀረም...በውስጤ እሳት እየተንቀለቀለ ነው።አሁን ትንሽ እረፍት ልውሰድ....>>ብላ እግሮቿን እየጎተተች ሳሎኑን ለቀቀችና ወደ መኝታ ቤቷ ሄደች።
ኮማንደር መሀሪ የእናቱን ወደ መኝታ ቤቷ ገብታ በራፉን ከውስጥ መቀርቀሯን ከተመለከተ በሁዋላ ከኪሱ ሞባይሉን አወጣና ደወለ...ፍቅረኛው ጋር።
የእናቱ ጭንቀት የሱም ጭንቀት ሆኗል...ከዚህ ጭንቀቱ ረገብ እንዲል ደግሞ ወደ ሥራ ከመግባት ይልቅ ፍቅረኛውን ማግኘት ይሻለዋል። ከአምስት ጥሪ በሁዋላ ስልኩ ተነሳ።ግን እሷ አልነበረችም ያነሳችው ታናሽ እህቷ ነበረች።
ሞባይሏን እቤት ጥላ እንደወጣችና እቤት እንደሌለች ነገረችው...ምንም አላላትም ስትመጣ እንድትደውልለት መልእክት አስቀምጦላት ስልኩን ዘጋው።
<<ይቺ ደግሞ ሲፈልጓት ሁሌ የማትገኝ ሰበበ ብዙ የሆነች የልብ በሽታ ነች>>ብስጭቱ ሳያስበው ድምጽ አውጥቶ እንዲነጫነጭ እስገደደው።ደግነቱ ሳሎኑ ውስጥ ለብቻው ስለሆነ የሰማው ሰው አልነበረም።
ምን ማድረግ እንዳለበት ባለማወቅና ግራ በመጋባት ክፍሉ ውስጥ መንጎራደድ ጀመረ ሁሉ ነገር አስጠላው።ይሄን ወርቅ አለማው የተባለውን አባቱ ከሞተ በሁዋላ የእናቱ ባል ሆኖ እቤታቸው ለሶስት አመት የኖረውን ሠውዬ ከመጀመርያው አንስቶ ቀልቡ ወዶትና ልቡም ተቀብሎት አያውቅም ነበር..ግን ለእናቱ ካለው ክብርና ፍቅር የተነሳ ከአንደበቱ ቃላት አውጥቶ ተቃውሞውን ገልጾ ወይም ፊቱን በማጨማደድ ያለመፈለግ ስሜቱን አሳውቆ አያውቅም ነበር...እንዴት ብሎ እናቱን<<እማዬ የእንጀራ አባቴን አልወደድኩትም..ጥሩ ባል አልመረጥሽም...ይቅርብሽ>>ሊላት ይችላል? በፍጹም እንደዛ ማድረግ አይቻለውም።አስተዳደጉም ያንን አይፈቅድለትም።በዚህ ምድር ላይ በጣም የሚያፈቅረውና በዛውም ልክ የሚፈራው ሰው ቢኖር እናቱን ነው።
ቢሆንም ግን ሁልግዜ አንድ ቀን አንድ ነገር እንደሚከሰት ይጠረጥር ነበር...አሁን ያ ጥርጣሬው በአስፈሪ መልኩ እውን ሳይሆን አልቀረም<<መሀሪ>>ከኪችን አከባቢ የመጣ የጥሪ ድምጽ ከሰመጠበት ሀሳብ ውስጥ መዞ አወጣው።መስታወት ነበረች።መስታወት የ25 አመት የጎመራች ወጣት ስትሆን በቤታቸው ከ12 አመት በላይ የኖረች ሠራተኛችው ነች...ለነገሩ እንዲሁ ስሙ ነው እንጂ ሠራተኛ ከማለት የማደጎ ልጃቸው ነች ማለት ይቀላል
👍101
<<ምነው መስ ፈለግሽኝ?>>
አላት..ከተረጋጋ በሁዋላ
<<ምሳ ላቀርብልህ ነው>>
<<በቃኝ አሁን አልበላም>>
<<እንዴ ቁርስም በቃኝ ብለህ ሄድክ ምሳም በቃኝ..?እዚህ ቤትኮ ተመጋቢው እኔ ብቻ ሆንኩ።እትዬ ምንቴም ይሄው በሶስት ቀን አንዴ ብቻ ነው ምግብ ምታሸተው...አሁን አንተም ታከልክበት..እረ ለኔ ሞራል እንኳን ስትሉ ትንሽ ቅመሱ..>>
<<አሁን መብላት ስላላሠኘኝ ነው...ትንሽ ቆይቼ እበላለሁ...ይልቅ ምሳውን ተይና ጠዋት ሰው ፈልጎኝ ነበር እንዴ?>>ውስጡን እየበላው ያለውን ጥያቄ ጠየቃት
<<ማንም አልፈለገህም>>
<<የስልክ መልእክትም የለኝም?>>
<<ማንም አልደወለም>>አሁንም ተስፋ አልቆረጠም።
<<ሮዝም አልደወለችም?>>
የሮዝን ስም ስትሰማ ፊቷ በጥላቻ ተጨማደደ
<<እሷማ ደውላ ነበር መሰለኝ>>
<<እንዴት መሰለኝ?>>ሀይሉ ጠንከር ባለ ድምጽ ጠንከር ብሎ ጠየቃት
<<ደውላለች በቃ>>
<<ምን አለች?>>
<<ማታ ከተመቸኝ እመጣለሁ ብላለች...ላንተ ግን ባትመጣ ይሻልሀል>>
<<አልገባኝም.....?>>
<<ታውረህ መች ይገባኸል....ስለማፈቅርህ ቀንቼ እንዳይመስልህ...እርግጥ ከማንም ሴት ጋር ሳይህ ቅር ይለኛል ምክንያቱም ባትወደኝም እወድሀለሁ...ባታፈቅረኝም አፈቅርሀለሁ።በዚህም የተነሣ የኔ ብትሆንና ከሌላ ሴት ጋርም ባላይህ ደስ እንደሚለኝ አልደብቅህም...ግን ከሮዝ ጋር ሳይህ ደግሞ ይበልጥ እበሳጫለሁ...እሷ ፈጽሞ ለአንተ የምትሆን ሴት አይደለችም።>>
<<ለምን ቆንጆ አይደለችም....?>>
ፈገግ እያለ ጠየቃት
<<ቆንጆማ ቆንጆ ነች..ውብ ቆንጆ።ግን ያም ቢሆን አታፈቅርህም እያስመሠለች እንጂ ላንተ ያላት ፍቅር ጥልቀት የለውም።ነገረ ስራዋ ሁሉ ከአንገት በላይ ነው።ማፍቀርያዋ የተበላሸባት ሴት ትመስለኛለች።>>
<<እሙ ስለምክርሽ አመሠግናለሁ..ግን ሮዝን አላወቅሽያትም...እርግጠኛ ነኝ ወደፊት በደንብ ስትግባቡና በደንብ ስታውቅያት፤ይሄን ሀሣብሽን ትቀይሪያለሽ።
<<እሺ ይሁንልህ እኔ ግን ተናግሬያለሁ>>ብላው ፊቷን አዞረችና ወደ ኩሽናዋ ተመለሠች።
ኮማንደር መሀሪም በሀሳብ እየተብሠለሠለ ቤቱን ትቶ..ግቢውን ለቆ ወደ ሥራ ሄደ።እራሱን ሥራ ውስጥ ለመቅበር....የምናቡን ጫጫታ ለግዜውም ቢሆን ለማስታገስ።

💫ይቀጥላል💫

እንደተለመደው Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
#ብዙ_እያሳዘኑ_ብዙ_የሚያስቁ


"የማያውቁት ሀገር
አይናፍቅም የሚል ፣ ብዙ አላዋቂ
ማያውቃትን ሀገር ፣
"እወርሳለሁ " የሚል ፣ ገነትን ናፋቂ፡፡
************************
ሁለት እግር ይዞ..
ሁለት ዛፍ መውጣት ፣ የሚያምረው ዛፍ ቆራጭ
በመንታ መንገድ ላይ...
ለመጓዝ የሚወድ ፣ ብኩን መንገድ መራጭ ።
******************************
በኮት ላይ ኮት ለብሶ...
"ሁለት ኮት ያለው ፣
አንዱን ለሌለው ይስጥ" ፣ የሚል ደቀ መዝሙር
ከመንገድ ገፍትሮህ...
"እያየህ ሒድ " የሚል ፣
ማየትን የማያውቅ ፣ ደፋር አይነ ስውር።
***********-**-***********
"ዝምታ ወርቅ ነው"
እያለ ሚያወራ ፣ ብዙ ተናጋሪ
"እድል እድል " የሚል...
እድል የከዳችው ፣ የሎተሪ አዟሪ።
*****************************
አድር ባይ ክርክር...
ለፍቅር ተሟግቶ ፣ ለገንዘብ ሚጣላ
"አንድንድ ሰው የምላ..
አንድሰው የሞላ"
እያለ የሚጮህ ፣
ራሱን እንዳንድ ሰው ፣ ማይቆጥር ወያላ ።
**----------***************
"በፆም ስጋ አልበላም "፣ የምትል ዘማዊ
አሳ እያሰገረ...
"አሳ አትብሉ " ብሎ ፣ ሚጮህ ባህታዊ።
**********************-*******
ጠዋት ጠዋት መዝሙር ፣
ማታ ማታ ዘፈን ፣ ሚያሰማ ንግድ ቤት
ምንም የማይሰራ...
"አለሁ አለሁ " የሚል ፣ የሌለ መስሪያ ቤት።
*******************************
ገብቷችኀል" የሚል ...
እራሱ ያልገባው ፣ ሰነፍ አስተማሪ
"ገብቶናል" እያለ...
ፈተናውን ዜሮ ፣ ሚደፍን ተማሪ።
ሌላም
ሌላም
ሌላም ፣
ብዙ እውነት ነገር
ብዙ ውሸት ነገር
በበዙባት ሀገር
"ዝም በል" ሚል ይበዛል ፣ ምንም ሳትናገር፡፡
ሁሉም ያስቃሉ!!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሁለት
:
ደራሲ-በዘረሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...ኩማንደር መሀሪ ቢሮው ቁጭ ብሎ ሰሞኑን በእጁ የገቡትን የክስ ፋይሎች እያገላበጠ ነው፡፡ግን አዕምሮው ተረጋቶ የነገሮችን ብልት መከፋፈል እና መመርመር አልተቻለውም፡፡የቤተሰቡ ጉዳይ በመሀል ጣልቃ እየገባበት እየረበሸው ነው፡፡ያለችው አንድ እናቱ ብቻ ስለሆነች እና አንድ አይን ያለው በእሳት አይጫወትም እንደሚባለው የእሱም እናት ሙሉ ቤተሰቡ ማለት ነች፤ የእሷ በሀሳብ መናወዝ እሱን እያናወዘው ነው፤የእሷ ያለመረጋጋት እሱንም ልቦናውን እያተረማመሰው ነው፡፡እያገላበጠ የነበረውን የክስ የወንጀል ሪፖርት ዶሴ መልሶ ከደነውና የእናቱ ጉዳይ ላይ ብቻ አተኮረ፡፡
‹‹ወይ ጉድ ምን አይነት አውሬ ሰውዬ ነው ››ሲል ስለወርቅአለማው አሰበ፡፡ወርቅ አለማው ከቤት ከወጣ ሶስተኛ ወሩን እያገመሰ ነው፡፡እናትዬው በአስቸኳይ ወርቅአለማው የሚባለውን ሰውዬ በተመለከተ የሆነ ነገር ካልሳማች በቃ ይለይላታል ፤ጨርቋን ጥላ ማበዶ የማያጠራጥር ሀቅ ነው፡፡ስለዚህ ማድረግ ስላለበት ጉዳይ ሲያሰላስል የሆነ ሀሳብ መጣለት ፡፡ሞባይሉን አወጣና ጓደኛው ጋር ደወለ..ኮማንደር ደረስ ጋር
‹‹ሄሎ››
‹‹የት ነህ?››
‹‹ከተማ ነኝ..ምነው በሰላም››
‹‹ለግል ጉዳዬ ፈልጌህ ነበር››
‹‹እ በቃ ገባኝ..››
‹‹ምኑ ነው የገባህ?››
‹‹ያው ተዘጋጅ ልትለኝ አይደል..››
‹‹ለምኑ ነው የምዘጋጀው.?.››
‹‹አንደኛ ሚዜ እንድሆንህ ነዋ ፡፡መቼስ ከእኔ የቀረበ ጓደኛ የለህም..ሮዝን ልታጋባ በመሆኑ አንደኛ ሚዜ እንድሆንህ ቀድመህ ማሳሰብ ጥሩ ነው..መቼስ በዛሬ ጊዜ ሚዜ መሆን ጣጣውም ወጪው አይጣል ነው..እስቲ እንሞክራለን ፡፡መቼስ እምቢ አይባል ነገር››አለው ኩማንደር ደረሰ፡፡
ምንም ይሁን ምንም በማንኛውም ነገር እንደቀለደ ነው፡፡ለእሱ ህይወት ዘና የሚሉባት በፈገግታ የሚስተናገዱባት ብርሀናዊ ስፍራ ነች ፡፡ከመሀሪ ጋር የጠበቀ ጓደኝነት በመሀከላቸው ቢኖርም በባህሪ ግን ምንም ሚያመሳስላቸው ነገር የለም፡፡ደረሰ ቀልድ ወዳጅ፤ ሁልጊዜ ፊቱ በፈገግታ የተሞላ ፤ለስራው ብዙ ግድ የሌለው ፤ተጨማሪ ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ እስከአልሆነ ድረስ ተረጋግቶ ሲሞላለት ብቻ የሚሰራ ሰው ነው፡፡መሀሪ ደግሞ በተቃራኒው ለዋዛ ፈዛዛ ብዙም ግድ የሌለው፤የተቋጠረ ፊት ባለቤት የሆነ፤ ስራውን አክባሪ ፤የሞያውን ስነምግባር አክብሮ የሚንቀሳቀስ ሰው ነው፡፡እንደዛም ሆኖ ጓደኛሞች ናቸው፡፡
‹‹ባክህ አትዘባርቅ ለቁም ነገር ነው የደወልኩልህ››ኮስተር አለበት፡፡
‹‹ቀጥላ ምን ያነጫንጭሀል››
‹‹ባክህ ያ በቀደም ያጫወትኩህ የእናቴን ጉዳይ እየተባባሰ ነው››
‹‹ምነው አባትህ አልደወለም እንዴ?››
‹‹አባትህ አልከኝ..››አለው በጣም የሚጠላው ሰው አባቱ ሆኖ መጠቀሱ ቅረ አሰኝቶት
‹‹ያው ነው እናቴን ያገባ ሁሉ አባቴ ነው ሲባል አልሰማህም››
‹‹ይሁንልህ ..እስከዛሬ ድረስ ምንም ድምጹ የለም ፤እሷ ደግሞ ከእለት ወደእለት በሀሳብ እያለቀች ነው…. ምግብ መመገብ ካቋመች ሰነበተች ..››
‹‹እና ምን እንድናደርግ ፈለግክ?››
‹‹የእሱ ጓደኛ ነኝ ብለህ እንድትደውልላት እና ለጊዜውም ቢሆን እንድትጽናናት ነው፡፡ የሚያረጋጋትን የሆነ ነገር እንድትነግራት ፈልጌ ነበር››
‹‹ማ እኔ?››
‹‹አዎ አንተ››
‹‹አሁን ልደውል››
‹‹አይ ያንተ ነገር… ለሁሉ ነገር መጣደፍ ትወዳህ፡፡ በደንብ አስብበትና ምን ማለት እንዳለብህ ተጠንቅቀህ ዛሬ ማታ ወይም ነገ ትደውላለህ››
‹‹እሺ እንዳልክ ››
‹‹እሺ ቻው››ተሰናብቶት ስልኩን ዘጋው፡፡
ወደተከፈቱት ዶሴዎች ሊመለስ ቢሞክርም አልተሳካለትም፡፡ ከሞባይሉ ላይ ሰዓቱን ተመለከተ፡፡10 ሰዓት ነው፡፡ በዚህን ሰዓት ከቢሮ ወጥቶ መሄድ አልፈለገም ፡፡ደግሞስ የት ይሄዳል… ?ሮዛ እንደሆነ እንኳን ያለቀጠሮ በቀጠሮም በመከራ ነው የምትገኝለት..፡፡ስለሚያፈቅራት እንጂ ይሄ ሁኔታዎ በጣም አማሮታል፡፡በዛ ላይ በከተማው ውስጥ እንኳን በሳምንት ከሁለት ወይ ከሶስት ቀን በላይ አትገኝም ፡፡ዛሬ ቦረና ሄጃለው ትለዋለች..በማግስቱ ደግሞ ሀዋሳ ትሆናለች ፡፡በዚህ ጉዳይ ብዙ ጊዜ የመረረ ጠብ ውስጥ ገብተዋል፡፡እሷ ግን ከእለት እለት እየባሰባት እንጂ ልትሻሸል አልቻለችም፡፡
አንዴ ያግባት እንጂ ይሄንን ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር ሰበብ እየሆናት ያለውን ያየር ባየር ንግድ ያስተዋትና እዛው ዲላ ከታማ ውስጥ አንድ ቡቲክ ከፍቶላት የተረጋጋ ስራ እየሰራች የተረጋጋ ኑሮ እንድትኖር ያደርጋታል..በዛ ውስጥ እሱም በደንብ ይረጋጋል..አዎ ይህ ነው ዕቅዱ ፡፡ እንደእዛ ካደረገ እንደልቡ በፈለገ ጊዜ ያገኛታል፡፡እንደዚህ አይራባትም፡፡ይሄ የእሱ ሀሳብ ነው፡፡ ሀሳብማ ከዚህም የጠከረ ነው፡፡ሮዝን ሊያገባት የሚፈልገው በኦርቶዶክስ ሀይማኖት የጋብቻ ስርአት መሰረት ነው፡፡በተክሊል፡፡ይሄም እንዲሆን የፈለገበት ምክንያት ለአስር አመት በዲቁንና ባገለገለበት ቤተክርስቲያን መዳርና ለሌሎችም ታናናሾቹ ምሳሌ መሆን ስለሚፈልግ ነው፡፡እራሱንም ማስደሰት ለፈጣሪ ያለው ክብር እና ታማኝነትም ማረጋገጥ ስለሚፈልግ ነው፡፡
ደግሞም የሟች አባቱ ምኞትም እንደዛ ነበር፡፡ለዚህም ሲል ከሮዝ ጋር ከአንድ አመት በላይ በፍቀርኝነት ቢያሳልፉም ጾታዊ ግንኙነት ግን አልፈፀሙም.. በዚህም የተነሳ እሱ ድንግል እንደሆነ ሁሉ እሷም ድንግል እንደሆነች በሙሉ ልቡ ያምናል…እርግጥ ዝም ብሎ አይደለም ያመናት ሲጠይቃት ወንድ አላውቅም ስላለችው ነው፡፡የሚያየውን እንቅስቃሴዋን እና ተግባሮን ሳይሆን አንደበቷን አመነ…ሚገርመው ግን ሮዝ ወሲብ ከጀመረች አስራ ሶስት አመታት አልፎታል፡፡ገና ደረቷ ላይ ያሉ ጡቷቾ ለአይን ሳይሞሉ..ብልቷ በስርአት ፀጉር አብቅሎ ሳይወጣለት ነው የጀመረችው፡፡እርግጥ አጀማመሮ ከእሷ ፍላጐትም ቁጥጥርም ውጭ በሆነ ሁኔታ እና አጋጣሚ ነበር..፡፡ቢሆንም የረጅም ዓመት ልምድ አላት፡፡ለዛውም የጠነከረ ልምድ፡፡በዛ ላይ መሀሪን ፈጽሞ አታፈቅረውም፡፡የቀረበችው ለጥቅም ነው፡፡ከቦረና እና ከኬኒያ ወደ መሀል ሀገር ለምታሻግራቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከለላ እንዲሆናት ፡፡እሱ በቀጥታ ባይረዳት እንኳን በእሱ አማካኝነት በምትተዋወቃቸው ሰዎችም ለመጠቀም እንጂ እሷ በምንም አይነት የአንድ ሰው ፍቅረኛ ሆና መታሰር የምትችል ሴት አይደለችም፡፡
በአሁኑ ጊዜ እንኳን ቦረና 3 ፤ሀዋሳ 2 ፤ሻሸመኔ 2 እዚሁ ዲላ እንኳን እንድ በወሲብ የምትወዳጃቸው ጓደኖች አሏት፡፡በዛ ላይ ከወንድ ጋር ባለት የየእለት ግንኙነት የትኛውንም ቀልቧን የሳበትን ወንድ ሳታገኘውና ሳትጠቀምበት ማባከን አትፈልግም፡፡የእዚህ ጉዳይ መጨረሻው ወይም የግንኙነታቸው ማገባደጃው ምን እንደሚሆን ለሚያስበው የቅርብ ሰው ሁሉ ይጨንቃል፡፡ኩማደሩ ግን ለጊዜው ስለእሷ ከሚያውቀው ይልቅ የማያውቀው በብዙ ሺ እጥፍ ስለሚበልጥ በሁኔታው እየተጨነቀ አይደለም፡፡ለምሳሌ እሱ እህቷ ነች ብሎ የሚያስባት እቤታቸው ሲሄደ የሚገኛት የ12 ዓመቷ ሄለን የእሷ የልጅነት ልጇ የአብራኮ ክፋይ እንደሆነች ምንም ፍንጭ የለውም፡፡ለጊዜው እሱን የሚያስጨንቀው ቀላሉ ነገር ነው ፡፡በፈለጋት ጊዜ እያገኛት ስላልሆነ ብቻ ያንን ማስተካከል እና እንዴት እና መቼ እንደሚያገባት ማሰብ ..በቃ፡፡
….ግን ስለእሷ ያልሰማቸውን ሲሰማ ያማያውቃአቸውን ሲያውቅ ምን ይፈጠር ይሆን..?ጊዜ የሚመልሳቸው የነገ ስጋቶች ናቸው፡፡
ሀሳቡን ከእሷም መለሰና በአይኑን ከጀርባው ወዳለው ሼልፍ ወረወረ፡፡ አንድ 10 የሚሆኑ በወንጀል እና በህግ ላይ የሚያወሩ መጽሀፎች ይገኛሉ ፡፡አንድን አንሳላና ገለጥ ገለጥ እያደረገ ማንበብ ጀመረ፡፡ከ15 ደቂቃ ቡኃላ
👍53
የቢሮ በራፍ ተንኰኰ
‹‹ይግቡ ክፍት ነው››
በራፉ ተከፍቶ ወደውስጥ የገባው ያልጠበቀው ሰው ነው‹‹እንዴ አንተው ነህ እንዴ በስርአት ምታንኳኳው.?ደግሞ አሁን ከተማ ነኝ አላልከኝም ነበር ?››
‹‹ባክህ ሚገርም ነገር ገጥሞኝ ነው ወደእዚህ የመጣውት..››እያለ ወደውስጥ ዘልቆ ገባና ወንበር ስቦ ከፊት ለፊቱ ተቀመጠ
‹‹የምን የሚገርም ነገር…?ደግሞ የምን ቦርሳ ነው የያዝከው ….?››
‹‹ባክህ አንድ ሚሊዬን ብር ነው››ብሎ በብስጭት ጠረጲዛው ላይ ወረወረለት
‹‹የምን ሚሊዬን ብር ..አንተ እኮ አታደርገም አይባልም.. ይሄን ያህል ብር ጉቦ ተቀበልኩ እንዳትለኝ››
‹‹ቢሆንማ በምን እድሌ..ደግሞ ጥሬ ብር እንዳይመስልህ ሀሽሽ ነው፡፡የሆኑ ሁለት ጐረምሶች ከሻሸመኔ ይመስለኛል ወደ ኬኒያ ሊያሻግሩ ሲሉ ነው ሲንከረፈፉ የተያዙተ››
‹‹ታዲያ እነሱ ለተያዙት አንተ ምን አበሳጨህ››
‹‹ለምን አልበሳጭ አንድ ሚሊዬን ብር እንደዋዛ እዲቃጠል ሲያደርጉ››
‹‹ለመሆኑ አንተ ነህ ያያዝካቸው?››እሱ እንዳላያዛቸው ያውቃል፡፡እንደዛ ሆኖ ቢሆን ኖሮ እዚህ አያደርሳቸውም ነበር ፡፡እዛው ተደራድሮ እዛው የድርሻው ተቀብሎ ጥፉ ከፊቴ ነበር የሚላቸው
‹‹ባክህ እኔ አይደለውም …አንድ ከርፋፋ 50 ሃለቃ ነው፡፡››
‹‹እና ታዲያ ምን ወደእኔ ቢሮ አመጣህ? ››
‹‹ይሄ ዕቃ አንተ ጋር እንዲቀመጥ ነው?››
‹‹ለምን ቢባል?››
‹‹የእኔ ሎከር አስተማማኝ አይደለም ቁልፍ የለውም ..››
‹‹እንዴ ለምን ኤግዚቢት ክፍል አታስርክበውም››
‹‹እሱንማ መች አጣውት ..ግን ሰውዬው ቆልፎ ልጄ ታሞብኛል ብሎ ወጥቷል አሉ እስከ ነገ ጥዋት አንተ ጋር ይቀመጥ፡፡››
‹‹ካልክ እሺ አለና ከመቀመጫው ተነሳና ሎከሩን ከፍቶ የሰጠውን ቦርሳ አስገባና ቆልፎበት፡፡ ቁልፉን ኪሱ ከተተና ቢሮውንም ቆልፈው ተያይዘው ወጡ፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like👍👍 በጣም እየቀነሰ ነው ምንድን ነው ታሪኩ አልተመቻችሁም ? እስቲ የቸመቻቹ 👍 Like እያደረጋቹ አስተያየት ያላችሁ እታች ባለው አድራሻ አድርሱኝ።

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍31
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሶስት
:
ደራሲ-በዘረሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...አየሩ ቀዝቃዛ ሲሆን ለሊቱ ደግሞ ፀጥታ ያረበበበት ነው፡፡ምንትዋብ አልጋዋ ላይ ተዘርራ አይኖን ጣሪያ ላይ ሰክታ ታስባለች፡፡ምሽቱም ገፍቶ 7 ሰዓት ማለፉን ግድግዳው ላይ የተንጠጠለውን የወርቅ ቅብ የግድግዳ ሰዓት ይናገራል፡፡እንደ ድሮ ቢሆን ለምንትዋብ ይሄ ጥሩ የእንቅልፍ ሰዓት ነበር ፡፡አሁን ግን ታሪክ ተቀይሯል፡፡ እንቅልፍ ከምንተዋብ መኝታ ቤት ከተሰደደ ሰነባብቷል፡፡
ከመኝታዋ ተነሳች፡፡ ከመኝታ ክፍሏ በመውጠት ከጐኗ ያለውን የልጇን መኝታ ክፍል ተመለከተች እና ስለእሱ አሰበች
‹‹ልጄ ንብረትህን ለበላተኛ አስረከብኩብህ ፡፡ ባክህ ማረኝ፡፡በድዬሀለው ይቅር በለኝ››ስትል ብቸዋን አጉተመተመች፡፡እንባዋን በዓይኖቾ ግጥም አለባት፡፡ከተገተረችበት ተንቀሳቀሰችና እርምጃዋን ቀጠለች፡፡የመስታወት መኝታ ክፍል ገርበብ ብሎል፡፡ በተከፈተው በር አንገቷን አስግጋ ተመለከችና ለደቂቃዎች በገረሜታ አስተዋለቻት..፡፡በሚገርምና በተረጋጋ ሁኔታ ተዘረጋግታ ጭልጥ ባለ ዕንቅልፈ ውስጥ ተውጣለች
‹‹የታደልሽ …ምነው ፈጣሪ ለእኔም ለአንድ ለሊት እንኳን እፎይታ ሰጥተኝ የሰላም እቅልፍ መተኛት በቻልኩ››በማለት ተመኘች፡፡
ለካ አንድ ነገር ሲያጡት ነው ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ መረዳት የሚችሉት..፡፡በሰላም ተኝቶ..አሪፍ ህልም አልሞ…ታድሶ መነሳት ቀላል እና ተራ ነገር ቢመስልም በዋጋ ሊተመን የማይችል ትልቅ ፀጋ ነው ፡፡ክፋቱ ግን እንዲህ አይነት የሰላም እንቅልፍ እና ጥሩ ህልም በብዙ ሺ ብር የማይገዛ ለሰላማዊ ህይወት የምግብን ያህል አስፈላጊ ነገር መሆኑን ለመረዳት እንዲህ እንደምትዋብ አጥተውት ካዩት ቡኃላ ነው የምር የሚገባው፡፡
ፊቷን አዙራ ወደ ሳሎን በረንዳ ወጣች፡፡ጨላማው ደማቅ ቢሆንም ጨረቃዋ ግን ሙሉ ነበረች፡፡ሙሉነቷ እንደሰዓሊዎች አላስጐመዣትም ፤እንደከዋክብት ተመራማሪዎች አልሳባትም፤በአጠቃላይ ጥሩ ስሜት እንዲፈጠርባት አላደረጋትም ፤እንደውም በተቃራኒው ውስጧ እርብሽብሽ አለባት…መከፋቷ ጠንክሮ የውስጧ ብሶት ከገደቡ አልፎ መንጠባጠብ ጀመረባት..፡፡
‹‹ግን ምን ሀጥያት ሰርቼ ይሆን ..?››ይሄንን ጥያቄ እራሷን ብትጠይቅም መልሱን ግን ከውስጦ ማግኘት አልቻለችም ፡፡ባል ሲሞት ሌላ ባል ማግባት በእሷ አልተጀመረ፡፡እንደማንኛውም ባሎ የሞተባት ሴት የሟች ባሏን አርባ አስቆርባ ፤ሰማንያ ደግሳ አብልታ፤ የሙት አመቱን መታሰቢያ ካከበረች ቡኃላ ነው ለሀዘን ስትለብስ የከረመችውን ጥቁር ልብስ አውልቃ ለሌላ ፍቅር ለሌላ ግንኙነት ዓይኗን የከፈተችው..አጋጣሚ ሆኖ የተከፈተው አይኖ በቅርቧ ያለውን ወርቅ አለማውን ላይ አረፈላት፡፡ አፈቀረችው… አገባችው..፡፡ታዲያ እዚህ ሁሉ ውስጥ የእሷ ጥፋት፤ የእሷ ሀጥያት ምኑላይ ነው …?
በረንዳ ላይ ምን ያህል ጊዜ እንዳሳለፈች ትዝ አይላትም ብቻ ከሀሳቧ ያባነናት ከውስጥ የሰማችው የበራፍ መከፈት እና መዘጋት ድምጽ ነው፡፡
‹‹ማነው? ››በማለት ተንቀሳቀሳ የሳሎኑን በራፉ ከፈተችና ወደ ውስጥ ገባች..ምንም አይነት እንቅስቀቃሴ አይታያትም፡፡የራሷን ጆሮ ተጠራጠረች..‹‹‹እያበድኩ ይሆን እንዴ?››እራሷን ጠየቀች፡፡በዝግታ እርምጃ ወደ መስታወት መኝታ ክፍል አመራች፡፡ክፍሏ እንደቅድሙ ገርበብ እንዳለ ነው፡፡ወደውጥ አንገቷን አስግጋ ተመለከተች …ከእንደ ቅድሙ የተዘረጋጋ የመስታወት አካል ግን አልጋው ላይ አይታይም ..የተዘበራረቀ ብርድ ልብስና አንሶላ እለዩ ላይ የተከመረት ባዶ አልጋ ብቻ….
‹‹ድምጽ መስማቴ ቅዠት አልነበረም ማለት ነው..መቼስ ፊኛዋ አይቋጥር.. ወደሽንት ቤት ሄዳ ይሆናል›› ስትል አሰበች፡፡ወደበረንዳዋ ልትመለሰ ፊቷን ስታዞር አሁንም ጆሮዋ ውስጥ የሆነ በዚህ ሰዓት መሰማት የሌለበት ድምጽ ጥልቅ አለባት፡፡ የሰው ድምፅ..ንግግር የመሰለ ድምጽ..ትኩረቷን ወደእዛ ላከች..ድምጹ ከልጇ መኝተ ክፍል አካባቢ የሚበተን መስላት፡፡..በመገረም ወደእዛው አመራች፡፡በደንብ ተጠጋችና ጆሮዋን ግድግዳው ላይ ለጥፋ ማድመጥ ጀመረች፡፡የወንድ እና የሴት ንግግር ነው፡፡
‹‹ለምን አትሰሚኝም ጥያቄሽን ልቀበል አይቻለኝም››
የልጇ ድምጽ ነው፡፡‹‹ወይ ጉድ በዚህን ሰዓት የምን ጥያቄ ይሆን…?››ምንትዋብ በውስጧ አብሰለሰለች፡፡ ከውስጥ የሚሰማው ንግግር ቀጥሏል
‹‹አውቃለው ብዙ ጊዜ ነግረኸኛል››
‹‹እናስ?››
‹‹እናማ የምትለው አይገባኝም….የቤታችሁ ሰራተኛ ብሆንም አንተን ከማፍቀር እራሴን ማቀብ አልተቻለኝም››
‹‹መስታወት አሁን ተረጋጊና ወደክፍልሽ ተመለሺ…ባይሆን ነገ በቀኑ እንነጋገራበታለን››
‹‹እንደዚህ ብለህ እኮ መአት ቀን አታለኸኛል፡፡››
‹‹ወድጄ አይደለም እኮ ታውቂያለሽ በጣም የምወዳት ፍቅረኛ አለቺኝ ፡፡ፈጽሞ እሷን ማጣት ስለማልፈልግ ከሌላ ከማንኛውም ሰው ጋር በፍቅር መነካካት አልፈልግም››
‹‹ያነው ትክክለኛ ምክንያትህ ወይስ የቤት ሰረተኛ በመሆኔ ደበርኩህ?››
‹‹መስታወት እኔ እኮ አንቺን እንደ እህቴ እንጂ እንደቤት ሰራተኛ አይቼሽ አላውቅም፤ እዚህ ቤት እንደ እህት እና ወንድም አብረን ነው ያደግነው..ሰራተኛ መሆንሽን አንቺ ስትነግሪኝ ብቻ ነው ትዝ የሚለኝ ..››
‹‹ውሳኔህ ግን ፍትሀዊ አይደለም››
‹‹እንዴት… ?ፍትህና ፍቅርን ደግሞ ምን አገናኛቸው…በፍቅር ውስጥ ፍትህ ቦታ የለውም…አንቺ የጫማሽ ሶል ተሰንጥቆ ውሀ እያስገባ ለምትወጂው ሰው ግን ተበድረሽ ጃኬት ገዝተሸ ልትሰጪው ትቺያለሽ?...ፍቅረኛሽ በሆነ አሸባሪ እጅ ገብቶ እጁ ከሚቆረጥ አንቺ አንገትሽን ሰጥተሸ መሞትን ትመርጪያለሽ…..ወይም የምትወጂው ሰው በሽታ ተይዞ ሆስፒታል ቢገባ እና እሱን የምታሳክሚበት ገንዘብ ብታጪ ወይም ሌላ አማራጭ ባይኖርሽ ሸርሙጠሸም ሆነ ብር ከሚሰጥሽ ወንድ ጋር ተኝተሸ የእሱን ህክምና በመክፈል ልታሳክሚውና ልታድኚው ትችያለሽ..ታዲያ እነዚህ በምሳሌ ከጠቀስኩልሽ ክስተቶች መካከል የትኛው ነው ፍትሀዊ የሚባለው… ?አየሽ በፍቅር ውስጥ ፍትህ ታናሽ ነች…ለዚህ ነው በፍቅር እና ጦርነት ውስጥ ሁሉ ነገር ትክክል ነው የሚባለው… ስለዚህ እኔም በሮዝ ላይ ያለኝ አቋም በፍቅር የተቃኘ ስለሆነ ትክክል አይደለህም ልትይኝ አትቺይም›
‹‹ቢሆንም…ለማታፈቅርህ.. ለአንተ ቅንጣት ደነታ ለሌላት ሴት ስትል የምታፈቅርህን ሴት መግፋት..ቢያንስ እሺ አታግባኝ ..ወይንም እንደፍቅረኛህ አትቁጠረኝ..ግን ቢያንስ በድብቅም ቢሆን ከፍቅርህ እንድቋደስና እቅፍህ ውስጥ እንድገባ ብትፈቅድልኝ ነፍሴ ትደሰት ነበር ..ማምሻም እኮ ዕድሜ ነው..››
‹‹አይ መስታወት ፍቅር ፍቅር ነው…አብሬሽ ምተኛው ሳቅርሽና ስታፈቅሪኝ ብቻ ነው››
‹‹ባክህ ዝም በል፤ይሄ ህግ እኔ ላይ ሲሆን ብቻ ነው የሚሰራው..ከማታፈቅርህ ጋር ትኖር የለ..››አንቧረቀችበት፡፡
ምንትዋብ ከዚህ በላይ መታገስ አልቻለችም..በራፍን በርግዳ ወደ ልጇ ክፍል ዘው ብላ ገባች፡፡መሀሪ ከተቀመጠበት የአልጋ ጠርዝ መስታወት ከተቀመጠችበት ወንበር ሁለቱም ተስፈንጥረው ተነሱና ቆሙ፡፡ ያልጠበቁት ስለሆነ ሁለቱም በእፍረት አንገታቸውን ወደምድር አቀረቀሩ ምንትዋብም ሁለቱንም እያፈራረቀች ለደቂቃ ያህል በፅሞና ከተመለከተቻቸው ቡኃላ
‹‹መኝታ ቤት መጋራት ከጀመራችሁ ቆየ እንዴ?››የአሽሙር ንግግሯን ተናገረች መልስ ሚሰጣት ስታጣ ቀጠለች
‹‹አንቺ ለካ ስራ ብዙ ነሽ ቀን በጉልበት ስራ ስትባክኚ ትውያለሽ ለሊት ደግሞ እዚ……አሁን ጨርሰሻል ወይስ እዚሁ ነው የምታድሪው?››መስታወት ምንም ሳትናገር ሹክክ ብላ ክፍሉን ለቃ ወደራሷ ክፍል አመራች፡፡መሀሪ ግን እንደተገተረ ነው ምንም እንኳን እራሱን የቻለ ለአቅመ
2👍2
አዳም ከደረሰ አመታተን ያስቆጠረ ቢሆንም በዚህ ጉዳይ እናቱን ብዙም አይደፋራትም፡፡ምንዋብም በቆመችበት በልጇ ላይ ብታፈጥበትም ምን መናገር እንደለባት ግራ ገባት…ደግሞ ልጇን አጥፍተሀል ብሎ ለመቆጣት ምን የሞራል ብቃት አላት ?
‹‹በል ድህና እደር ››ብላ ከክፍሉ ለመውጣት ፈቷን አዙር ስትንቀሳቀስ ሳሎን ያለው ስልክ ተንጫረረ..ፍጥነቷን ጨምራ ወደ እዛው አመራች..
ኩማንደር መሀሪም ግራ ተጋባና ሰዓቱን ተመለከተ 7፤45 ይላል ፡፡‹‹በዚህ ሰዓት ማነው የሚደውለው?ያ ዕብድ ደረሰ እንዳይሆን ብቻ..?መቼስ እሱ ከሆነ በእዚህ ሰዓት ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ መሆን አለበት..››ተጨነቀ
‹‹በስካር መንፈስ ዘባርቆ ጭራሽ ነገሮችን እንዳያባብስ ሰጋት ቀስፎ ያዘው ..እናቱን ተከትሎ ወደሳሎን ተንቀሰቀሰ ፡፡
//////
እናቱ ስልኩን አንስታ ማናገር ጀምራች
‹‹ለመሆኑ ነፍስህ አለ?››
‹‹መኖር ከተባለ?››
‹‹እንዴት ምን አጋጠመህ...?ለመሆኑ የት ነው ያለኸው ....?ደግሞ ሰው ያስባል አትልም እንዴ?››ግትልትል ጥያቄዎችን በአንዴ ደረደረችለት፡፡
ቀለም ወርቅ በተረጋጋ እና ለስለስ ባለ ድምጸት ከዛኛው የስልክ ጫፍ የሚያወራው ይሰማዋል‹‹ቀስ በይ እንጂ..እዬዬም ሲዳላ ነው ሲባል አልሰማሽም..ያልሻቸውን ነገረች ሁሉ ለማድረግ እኮ ማድረግ የምችልበት ሁኔታ ላይ መሆን አለብኝ››
በምንትዋብ አዕምሮ ውስጥ ለወራት የዘለቀው ስጋት እውን መሆኚያው ደቂቃ መቅረብን ሰውነቷ ነገራት…
‹‹የሆንከውን ልትነግረኝ ትችላለህ?››አለችው ተስፋ በመቁረጥ ጫፍ ላይ ባለ ስሜት
‹‹ መደወሌ እኮ የሆንኩትን ልነግርሽ ነው….››የምንትዋብ ሰውነት ሲንቀጠቀጥን የስልኩን እጄታ መያዝ አቅቷት ስትቸገር ከዛ እልፎ ለመውደቅ ስትንገዳገድ ልጇ መሀሪ በቅርብ እርቀት ሆኖ እየተመለከተ ነው፡፡እንደጠረጠረው ሰልኩን የደወለው ጓዳኛው ደረሰ ሳይሆን ያልጠቀው ቀለመወርቅ መሆኑ አስገርሞታል … አስፈርቶታልም፡፡
‹‹እሺ ንገረኝ..እያዳመጥኩህ ነው››
‹‹በደንብ አድምጪኝ አሁን ያለውት ሱዳን ነው፡፡በድንገት ቆንጇ ስራ አለ ብለውኝ ደላሎች አጭበርብረውኝ የንግድ ዕቃ ጭኜ ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ ነበር ያመረውት..፡፡እንደተባለውም ይዤ የሄኩትን ዕቃ እጥፍ በሆነ ትርፍ መሸጥ ችዬ ነበር፤ ግን ምን ዋጋ አለው ብሩን በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ብድኖች ድንገት ወረሩንና ደብድበውና ቀጥቅጠው ዘረፍኝ ..አሁን ባዶዬን አስቀርተውኛል፡፡ኤፍ.ኤስ.አር መኪናችንንም አቃጠሏት፡፡ ባዶዬን ቀርቼያለው..ይሄውልሽ…››
/////
የስልኩ እጄታ ከእጆ ተንሸራቶ ወደ መሬት ተምዘገዘገ ፡፡እሷም በአንድ ወገን ዘንበል ብላ ልትገነደስ ስትል ሁኔውን በተጠንቀቅ ቆሞ ሲከታተል የነበረው ልጇ ፈጠን ብሎ ደረሰላተትና ደጋግፎ ወደመኝታ ክፍሏ ወሰዳት፡፡
በዚህ ሰዓት በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ የወሬውን ዝርዝር ሊጠይቃት አልፈለገም፡፡ ያንን ማድረግ ይበልጥ እንድትጨነቅ እና እንዳትረጋጋ ማድረግ ነው ብሎ ስላሰበ ተወው፡ከእዛ ይልቅ እንቅልፍ እንዲወስዳት አመቻችቶ አስተኛትና ክፍሉን መለስ አድርጐላት ወደ መኝታ ክፍሉ ተመለሶ ትካዜ ውስጥ ገባ፡፡እስከአሁን በቤቱ ነግሶ ከነበረው ጭንቀት ይልቅ በቀጣቹ ቀኖች የሚከሰተው ሁኔታ ጨለማ እንደሚሆን ሲታሰበው በሰውነቱን ቅጽበታዊ ቅዝቃዜ ተሰራጨ….ልቡ ድረስ የተሰማው ኩምትርትር የሚያደርግ ቅዝቃዜ….

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
1👍1
#እናቴ_ትሙት_አንላቀቅም !

1⃣

“ሰማህ የኔ ውድ . . .
ሳፈቅርህ ከልቤ ባንተ ተረትቼ
ስላንተው ስባክን አቅሌን ነፍሴን
ስቼ
በክንድህ እያሟሟህ ባፍህ
እያቀለጥከኝ
ከማያውቁት ዓለም ወስደህ
እየከተትከኝ
ነፍሴን አስክረሃት በሀሴት ዳንኪራ
እንዳልቆም እንዳልሄድ ያላንተ
እንዳልሰራ
አድርገህ ጠንርፍህ እንዲህ አሳስረኸኝ
እሄዳለሁ ብትል ከመንገድ ጥለኸኝ
እናቴ ትሙት አንላቀቅም
እኔ በፍቅር ቀልድ አላውቅም!”
ስትይኝ ፈራለሁ
አንዳንዴም ኮራለሁ
አንዴ ደስ ይለኛል
አንዳንዴ ይጨንቀኛል።
👇
👍2
#እናቴ_ትሙት_አንላቀቅም

2⃣

“እየውልህ ውዴ . . .
እኔማ ስወድህ ሁኚ ያልከኝን ሆኜ
የኔን ዓለም ትቼ ባንተ ዓለም
መንኜ
ጠቅልዬ ግብቼ ከገዳምህ ዋሻ
በስምህ ፀልዬ ሃጢያቴን ማስረሻ
እንደሆነ መቼም አንተም
ታውቀዋለህ
ከቶ ያልሰጠውህ ኧረ እንደው ምን
አለህ
ታዲያ ሁሉን ወስደህ ባዶዬን ቀርቼ
ኑሮዬን በሞላ አንተው ላይ ገንብቼ
ስታውቀው እንዳልኖር አንተን
ተለይቼ
እሄዳለሁ ብትል ድንገት አንቺን ትቼ
እናቴ ትሙት አንላቀቅም
እኔ በህወት ቀልድ አላውቅም!”
ስትይኝ ፈራለሁ
አንዳንዴም ኮራለሁ
አንዴ ደስ ይለኛል
አንዳንዴ ይጨንቀኛል።
👇
#እናቴ_ትሙት_አንላቀቅም

3⃣

ሰማሽ የኔ እመቤት . . .
እውነት አንቺን ርቄ
እምነትሽን ፍቄ
በፍቅርሽ ቀልጄ
ሌላ ሴት ለምጄ
ምኖር ይመስልሻል ?!
እውነት እውነት እውነት
በእውነት ተሳስተሻል !
ደግሞ ፉከራሽን ዛቻሽን ፈርቼ
እንዳይመስልሽ ውዴ እኔስ ተረትቼ!
ይልቅ እኔም አልኩሽ . . .
እናቴ ትሙት አንላቀቅም
ካንቺስ ወዲያ ሴት አላውቅም።

🔘አብዲ ሰዒድ🔘
👍1
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አራት
:
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...ቁርስ መብላት ትቶ እየቆነጠረ ሲተክዝ ታዝባው ግራ በመጋባት‹‹ቁርስህን በልተህ ወደስራ አትሄድም እንዴ ?እየረፈደብህ እኮ ነው››አለችው መስታወት
‹‹ምኑን ሄድኩት ››አላት ከትካዜው ::
‹‹እንዴት? ምነው የማታው ነገር አሳሰበህ እንዴ?አይዞህ እንኳን አንተ እኔም አልተጨነቅኩ፡፡እርምጃ ቢወሰድም እኔ ላይ ነው፡፡ ከቤቱ ብባረርም እኔው ነኝ..ያ ከሆነ ደግሞ ላንተ ይበልጥ ጥሩ ይሆናል …ከእኔ የዘወትር ጭቅጭቅ ትገላገላለህ››
‹‹አይ… ዶሮ ብታልም ጥሬዋን….መች ይሄ አሰሰበኝ ብለሽ ነው››አላት..እውነቱን ነወ..ውስጡ የፍርሀት ቆፈን ጨረማምቶታል…ከመቼውም በላይ ነገን እየፈራ ነው….የእናቱ ጤንነት ስጋት አሳስቦታል..
‹‹ታዲያ ምን አዲስ ነገር ተከስቶ ነው እንዲህ ፊትህን የሆረር ፊልም አክተር ያስመሰልከው?››
‹‹ባክሽ ሊሊት ሰውዬው ደውሎ ነበር››
‹‹የቱ ሰውዬ?››
‹‹ወርቅአለማው ነዋ.. ሌላ ምን ሰውዬ አለ?››
‹‹ ….ምን ሆኜ ጠፋው አለ?››
‹‹ባክሽ ያለውን ነገር አላውቅም፡፡ ግን ጥሩ ዜና ያበሰራት አልመሰለኝ፡፡ ፍጽም ተስፋ ቆርጣ ና አቅመ ቢስ ሆን ነበር ለሊት ወደ መኝታዋ ያመራችው..››
‹‹ታዲያ እንዴት እንዳደረች አላየሀትም?››
‹‹አይ አላየዋትም፡፡ ሰሞኑን ያጣችውን እንቅልፍ ምን አልባት ዛሬ አግኝታ ከሆነ እንዳልረብሻት ስለፈራው ነው››
መስታወት በለበሰችው ቀለም የበዛበት ቀሚስ ላይ ደርባ ያገለደምችውን ነጭ ሽርጥ ላይ እጇን እየጠራረገች‹‹ቆይ እስቲ ቀስ ብዬ አይቼት ልምጣ ››ብላ ወደ ምንትዋብ መኝታ ቤት በመንሾከክ ሄደች…. ቀስ ብላ በራፉን ገፋ አደረገች ፡፡ከውስጥ ስላልተቀረቀረ በቀላሉ ተከፈተላት፡፡የማታው ትዕይንት በአዕምሮዋ መጣባትና ፈራች
‹‹…ያንን አስታውሳ ትቆጣኝ ይሆን? እንደፍጥርጥሯ ፡፡መጋፈጥ እንጂ ሸሽቼ ማመልጠው ጉዳይ አይደለም ›› በማለት እራሷን አበረታታችና ወደውስጥ ገብታ አይኖቾን ወደአልጋው ወረወረች፡፡ምንትዋብ ዝርግትግት ብላ አልጋው ላይ ተዘርራ ትታያለች፡፡እንቅልፋ አልወሰዳትም፡፡ አይኖቾ ይንከባለላሉ፡፡
‹‹ምንቴ ደህና አደርሽ?››
ፈራ ተባ እያለች ጠየቀች፡፡መልስ አልሰጠቻትም፡፡‹‹በለሊቱ ድርጊቴ ተቀይማኛለች ማለት ነው…›› ስትል አሰበች፡፡በዚህም በውስጧ ሲጉላላ የነበረው ስጋቷ ናረባት…
‹‹ምንቴ በማታው ጉዳይ ተቀይመሺኝ ከሆነ ይቅርታ ሁለተኛ አይደገምም..››አሁንም መልስ የለም ..ግን ከሁለቱም አይኖቾ እንባ መንጭቶ መንኳለል ጀምሯል፡፡
መስታወት ይበልጥ ደነገጠችና በጣም ተጠግታት አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለች‹‹ ምንቴ አረ ተረጋጊ ..ነገሮች እኮ እንዲህ እንደተበለሻሹ አይቆዩም… በሂደት ይስተካከላሉ››
‹‹ምንቴ ኸረ በፈጣሪ አታልቅሺ እጆን ወደ ጉንጮ ላከችና አንባዋን ታብስላት ጀመር፡፡ ከምንትዋብ በኩል ግን ለውጥ አልነበረም፡፡
መስታወት ግራ ተጋባች‹‹ምንቴ…››መልስ የለም››ብርድልብሱን ገለጠች፡፡ቢጃማ ለብሳለች እጆን ያዘችው እንደተንከረፈፈ ነው..በአየር ላይ እንዳለ ስትለቀው እንደተዘረጋጋ ወደቦታ በራሱ ተመለሰ..እግሯንም ብድግ እንደማድረግ አለችና ስትለቀው ተመሳሳይ ነው ፡፡ምንትዋብ ሰውነቷን በአዕምሮዋ ማዘዝ አትችልም፡፡መስታወት ድንገት ሳታስበው ጩኸቷን ለቀቀችው…በሰከንድ ውስጥ መሀሪ የመኝታ ቤቱን በራፍ በርግዶ ገባ
‹‹ምንድነው? ምንሆንሽ?››
‹‹አትናገርም..እጅና እግሯንም ማዘዝ አትችልም››በተረዳችው መጠን ልታስረዳው ሞከረች፡፡
‹‹እንዴት ሆኖ ..?እማ ..እማዬ ምን ሆንሽ?››እጁን በአንገቷ ዙሪያ ሰቅስቆ በመክተት እየነቀነቃት ቢጠይቃትም አሁንም እንባ ከማፍሰስ ውጭ ምንም ልትለው አልቻለችም››
‹‹ወይኔ እናቴ !! ወይኔ ጉድ ሆንኩ!!››ብር እየተርበተበተ መልሶ አስተኛትና ስልኩን አውጥቶ ደወለ፡፡ ባለመኪና የሆነ ጐረቤቱ ጋር ነው የደወለው ..መኪና ይዞ እንዲመጣለት
‹‹በይ እስኪመጣ ልብስ አምጪ እንቀይርላት፡፡››መስታወት እየተርበተበተች ወደ ቁም ሳጥኑ ሄደች፡፡ ልብስ መርጣ አመጣችና በመከራ እየተጋገዙ የለበሰችውን ልብስ አወለቁላትና ሌላ ልብስ አለበሶት፡፡ አዕምሮዋ ሙሉ በሙሉ አካሏን የማዘዝ ስልጣኑን ሙሉ በሙሉ ተነጥቆል፡፡
መሀሪ የእናቱ የሰሞኑ ሁኔታዋ በጣም ሲያሳስበው የቆየ ቢሆንም እዚህ ደረጃ ደርሶ በጤናዋ ላይ አደጋ ያመጣባታል ብሎ ፈጽሞ ተጠራጥሮ አያውቅም ነበር፡፡ይሄ የሚያሳየው ደግሞ የቀለም ወርቅ ጉዳይ ምን ያህል የእናቱን ልብ እንደሰባበረው ነው፡፡
አሁን ደግሞ የእሱም ልብ መቃጠል ጀምሯል፡፡ውስጡ በንዴት እየተንበለበለ ነው፡፡እንዴት አድርጐ አግኝቶ በእንዴት አይነት ሁኔታ ሊበቀለው እንደሚችል ለጊዜው ባይገለጽለትም ግን እንደዛ ማድረጉ እደማይቀር እርግጠኛ ነው፡፡
የተደወለለት ሰውዬ መኪናውን ይዞ መጣና አፋፍሰው ተሸክመው አስገብተዋት ወደ ሆሰፒታል ይዘዋት ሄዱ ፡፡እንደ ደረሱ ከመኪናው ወደ እስትሬቸሩ አሸጋገሯት እና ወደ ምርመራ ክፍል ይዘዋት ሲገቡ መስታወት ደግሞ ስልኳን አውጥታ መደወል ጀመረች
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
‹‹ሄሎ..መስታወት ››የመዝናናት ስሜት የተጫነው ሞዛዛ ድምጽ
‹‹ሄሎ ሮዛ አሁኑኑ ሆስፒታል ድረስ መምጣት ትቺያለሽ ?››
‹‹ታሾፊያለሽ..ምን ተፈጠረ?››
‹‹ባክሽ አትቀልጂ መሀሪ ችግር ላይ ነው ››
‹‹የምን ችግር..?ወንጀለኛ ተኩሶ አቆሰለው እንዴ…?ሞተ ማለት ነው?››
መስታወት ምነው ባልደወልኩላት ብላ ተፀፀተች..‹‹ቢሞትም በቃ እንዲህ ነው ተንቀባራ የምትሰማኝ…ይህቺን ታህል ብቻ ነው ድንጋጤዋ….ምን አይነት ልበ ደንዳናነት ነው…ስትል ገረሜታዎን በውስጦ አብሰለሰለች፡፡
‹‹ባክሽ እናቱ በጣም ታማ ነው ከቻልሽ ለኩማደር ጓደኛውም ደውለሽ ንገሪው..››
‹‹ወይኔ አማቼ በቃ ሰርጌን ልታሰናክል ነው እንዴ!! ››አሾፈች
‹እንግዲህ ትመጪ እደሆን ነይ ካለበለዚ የራስሽ ጉዳይ››አለቻትና ሞባይሉን ጆሮዋ ላይ ጠረቀመችባት፡፡
መስታወት በሁኔታዋ በጣም ተበሳጭታለች‹‹አሁን ሰው ይህቺ ፍቀረኛዬ ነች ብሎ አብሮ ይኖራል..?የታባቱ ይበለው››አለችና ሆስፒታሉ ኮሪደር ላይ ባለው አግዳሚ ላይ ተቀመጠች፡፡መሀሪ በቅርብ ርቀት ወዲህ ወዲያ እያለ በጭንቀት ሲሰቃይ እየተመለከተችው ነው፡፡ ያም ጨክና እንድትጨክንበት ሊያደርጋት አልቻለም….ውስጦ ተንሰፈሰፈበት……
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ለመሀሪ ይህ ወቅት በህይወቱ በጣም መራሩ ወቅት ሆኖበታል፡፡ወላጅ እናት ስትከፋ ማየት ውስጥን ያሳዝናል..ወላጅ እናት ታማ አልጋ ላይ ወድቃ ማየት ደግሞ ውስጥን ያሳምማል፡፡ስለዚህ የእሱ ውስጥም በዚህ ሰዓት በጣም ታሟል፡፡በልጅነቱ ‹‹እሹሩሩ…ማሙሽ እሹሩሩ..
ማሙሽ እሹሩሩ
ልጄ እሹሩሩ…
ስወቅጥም አዝዬ ..
ስፈጭም አዝዬ…
ወገቤን አመመኝ ና ውረድ ማሙዬ…
ብለው ሲያባብሉት፤አባብለውም ሲያስተኙት የነበረው የእናቱ አንደበት ተቆልፎል፡፡ሰውነቱን በፍቅር እየዳበሱ ያሳደጉት የእናቱ አለንጋ ጣቶች ዛሬ አቅም አንሷቸው ዝርግትግት ብለዋል…ከእዚህ እዛ እየኳተኑ ..ከቦታ ቦታ እየባከኑ ሚያስፈልገውን ነገር ያቀርቡለት የነበሩት የእናቱ እግሮች ዛሬ ድንገት አቅም አልባ ሆነው አልጋው ላይ ተዘረጋግተዋል..ታዲያ ለአንድ ሰው ከዚህ በላይ የሚያም .. ከዚህ በላይ የሚከብድ መከራ ከየት ይመጣል ……ፈራ ..ነገን በጣም ፈራ፡፡ጥልቅ ድረስ እስኪሰማው እና እስኪንቀጠቀጥ ድረስ ፈራ…..
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ሮዝ የመሀሪ እናት ሆስፒታል መግባቷን መስታወት በስልክ ደውላ ስትነግራት አልጋዋ ውስጥ ነበረች፡፡

‹‹ሲደብር ይህቺ ደባሪ አሮጊት ደግሞ ካልጠፋ ቀን በዛሬ ቀን ትታመማለች እንዴ›
👍6
ስትል ተማረረች፡፡ዛሬ ቀጠሮ ነበረባት ፡፡ሶስት ጓደኛሞች የሆኑ ወጣቶች ሊያዝናኖት ከ7 ሰዓት ጀመሮ ፕሮግራም አስይዘዋት ነበር፡፡እነዚህ ልጆች ከዚህ በፊትም ሶስት አራት ጊዜ በተመሳሳይ ሁኔታ አዝናንተዋት ያውቃሉ፡፡ከእነሱ ጋር ስትውል ነፍሷ ሀሴት ነው ምታደርገው፡፡ እስክትግል ድረስ ያስቅሟታል..እስክትንገዳገድ ያጠጧታል..ከዛ ይዘዋት ያድራሉ….፡፡‹‹ለስንት ?››እንዳትሉ፡፡እነዚህን ልጆች የምትወዳቸው አንደኛው በአንደኛው ሳይቀና ..ተሳስበውና ተግባብተው አብረው ስለሚቋደሷት ነው፡፡ ብትንትን እስክትል ተጋግዘው ስለሚያስደስቷት ነው፡፡የግሩፕ ወሲብ ላይ መሳተፍ ..ወይም በግሩፕ የተደራጁ ወንዶችን በወሲብ ማስተናገድ ለሮዝ አዲስ ነገር አይደለም ከ17ዓመቷ ጀመሮ ደገጋግማ ያደረገችውና በጣም የምትደሰትበት ነገር ነው፡፡ለዚህ ነው አሁን የተበሳጨችው፡፡ ይህን የመሰለ አስደሳች ነገር ችላ ብላ ሆስፒታል ከበሽተኛ ጋር ማሳለፉን ስታስበው ነው የደበራት፡፡እንደምንም ተነስታ ፊቷን ታጥባ ልብሷን ለባብሳ፤ ተኮኩላ ና ተቀባብታ ከቤቷ እስክትወጣ 35 ደቂቃዎች ፈጅቶባታል፡፡የኩማደሩ ስልክ እምቢ ስላላት ቀጥታ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ነው ያመራችው፡፡
አለባበሷን ያስተዋለችው ከቤቷ ወጥታ ታክሲ ተሳፍራ ስትቀመጥ ከጐኗ የነበረው አንድ ጐረምሳ ከሰጣት አስተያየት በመነሳት ነው፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
‹‹ኸረ አሁንስ ለእናንተ ስንል ወዴት እንሂድ?››ነበር ያላት
‹‹አቤት››ኮስተርተር አለችበት፡፡
‹‹እንዲህ እያማራችሁ በዛ ላይ ግምሽ ዕርቃን ሆናችሁ ሚስጥራዊ አካላችሁን ሳይቀር ለእይታ እያጋለጣችሁ .. እኛ እንዴት እንሁን..?ለፍቅረኞቻችንስ እንዴት እንታመን….?››
‹‹ይህቺ ጠጋ ጠጋ ዕቃ ለማንሳት እንዳይሆን?››
‹‹ፊት ለፊት ያለ ዕቃ ቢነሳ ምን ያስደንቃል?››
‹‹እየተሳደብክ ነው እንዴ?››
‹‹በፍጹም አይደለም… ደግሞ ለምንድነው ፓንት ያላደረግሺው?››አመዷ ቡን አለ፡፡ቆንጣላ ጉርድ ቀሚሷን ወደ ታች ለመጐተት ጥረት ብታደርግም አልተሳካላትም
‹‹አይ…!!!ልትሸፍኚው እየሞከርሽ ነው?›› ብሎ ጭራሽ አሳፈራት፡፡
‹‹ዝም ብለህ በግምት ባትናገር ጥሩ ነው …መስሎህ ነው እንጂ አድርጌያለው››አለችው በሹክሹክታ ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ፡፡
‹‹ማድረግማ አድርገሻል፡፡ ሮዝ ቀለም ያለው አይደል.. የገረመኝ ግን ቀሚስሽም ብጣቂ ..ፓንትሽም ብጣቂ መሆኑ ነው››
‹‹የሆንክ ቡዳ ነገር ነህ …ለመሆን ፓንቴን እንዴት አድርገህ አየኸው?››
‹‹ታክሲ ውስጥ እንደገባሽ ለመስተካከል እግርሽን ወዲህ ወዲያ ስታደጊው ጓዲያሽ ውስጥ ያሉት ነገሮችሽ ሳላስበው አይኔ ውስጥ ገቡ…››አላት ፈገግ እያለ፡፡
ንግግሩም እይታውም ሰውነቷ እንዲግል አደረጋት፡፡በተቀመጠችበት ተቁነጠነጠች፡፡
‹‹‹ምነው ዝም አልሽ?››
‹‹ምን ልበልህ? ፈራውህ እኮ››
‹‹አይዞሽ ያንቺን ያህል አስፈሪ አይደለውም..በነገራችን ላይ ዳንኤል እባላለው፡፡››
‹‹እኔ ደግሞ ሮዛ››
‹‹ስምን መላአክ ያወጣዋል ማለት እንዲህ ነው..መልክሽን ሲያስተውሉት ከዓይን ሞልቶ ይፈሳል..ስምሽንም ሲጠሩት አንደበት ውስጥ ይደምቃል››
‹‹አመሰግናለው››አለችው ያለወትሮዋ እየተሸኮረመመች፡፡
‹‹ምስጋናው ቀርቶብኝ …ሞባይል ቁጥርሽን ብታውሺኝ››
አልተግደረደረችም፡፡ መውረጃው ቦታ ስለደረሰች በፍጥነት ነገረችውና ተሰናብታው ታክሲውን አስቁማ ወረደች፡፡እሱም በዓይኖቹ ሸኛት፡፡ከኋላዋ እያያት እንደሆነ ገብቶታል፡፡ይሄ ልዩ ተሰጥኦዋ ነው፡፡ ምን ግዜም ከኃላዋ የወንድ ዓይን ከተሰካባት ጀርባዋን ይሞቃታል..፡፡ይሄ ሁኔታ ሁሌ ይገርማታል…….
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ፖሊስ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ገባችና ወደ ኮማንደር ደረሰ ቢሮ አመራች፡፡ስታንኳኳ
‹‹ይግቡ›› የሚል ድምጽ ከውስጥ ስለሰማች በሩን ገፋ አድረጋ እግሯን አስቀድማ ገባች
‹‹የተከበሩ ኩማንደር እንደምን አደሩ?››
‹‹አንቺው ነሽ እንዴ እንዲህ መላአክ መስለሽ በጥዋት የምታስደነግጪኝ?››ሲላት ታክሲው ውስጥ ባገኘችው ወጣት ቀስቃሽነት ይዛ የመጣችው ሙቀት ይበልጥ በመላ ሰውነቷ ተሰራጭቶ አቅነዘነዛት፡፡
‹‹እኔ በመሆኔ ከፋህ እንዴ?››
‹‹ባይከፋኝም አልዋሽሽም… የጓደኛዬ ሚስት ባትሆኚ ይሻለኝ ነበር?››
‹‹ባልሆን ምን ታደርገኝ ነበር…?››ጠየቀችው..በመንሰፍሰፍ፡፡
‹‹ያው በዚህ ብርሀናማ ጥዋት ከአንድ አማላይ ወጣት ሴት ጋር ምን ማድረግ የምፈልግ ይመስልሻል?››
‹‹ልገምት?››
‹‹ገምቺ››
‹‹ወደ ኃላዋ ተመለሰች እና የቢሮውን በራፍ ከውጥ ቀረቀረችውና ..ልብሷን ከላይ ጀምራ እያወለቀች ወደ እሱ መሳብ ጀመረች፡፡ ኩማንደሩ ደነገጠ፡፡ ግራ ተጋባ ፡፡ማሰቢያ ጊዜ ግን አላገኘም….የጓደኛው እጮኛ የሆነችው ይህቺ አማላይ ሰይጣን ዕርቃኖን ጠረጴዛው ላይ ወጥታ የእሱን ልብስ ለማውለቅ ትረዳው ጀመራለች፡፡እሱም በፍጥነት ተባበራት..፡፡አዎ አሁን የሚደረገውን አድርጐ ቡኃላ ቢያስብበት ይሻለዋል፡፡ በቅጽበት አውሬ ሆነችበት….ተጠመጠመችበት..ሳመችው… ነከሰችው… ቧጨረችው፡፡ ነፍሱ ጥፍት አለችበት፡፡ ቢሮ በደቂቃ ውስጥ ተተረማመሰ ፡፡በህይወቱ አይቷት የማያውቀው የወሲብ አለም ውስጥ ከታ አሳሩን አበላችው፡፡ የመጨረሻ ጡዘት ላይ እኩል ደርሰው እኩል ነው የረገቡት..፡፡
ነገሮች ከተጠናቀቁ ቡኃላ ግን የሮዝ የሚያስደነግጥ ተንሰቅሳቂ ለቅሶ ነበር የተከተለው፡፡ኩማንደሩ በጣም ደነገጠ..፡፡በሁኔታዋ ግራ ገባው፡፡ ልብሱን እንደነገሩ በፍጥነት ለበሰና ወደእሷ ተጠጋ‹‹እንዴ ምን ያስለቅስሻል? አስገድጄሽ እኮ አይደለም? ሁለታችንም በፍቃደኝነት ፈልገነው ነው ያደረግነው፡፡››
ልብሷን ከተበታነበት ወለል እየለቃቀመች በማንሳት ተራ በተራ አራግፋ እየለበሰች ‹‹አልገባህም …ልታስቆመኝ ይገባ ነበር ፡፡እኔ የማረባ ሰው ነኝ…ደደብ ነኝ››አለች ከለቅሶዋ ሳትወጣ፡፡
‹‹አልገባኝም…እንዴ ምን ነካሽ? ወንድ እኮ ነኝ፡፡ ይሄንን የመሰለ አማለይ ዕርቃን ገላ እያየው እንዴት አልፈልግም ልልሽ እችላለው? ደግሞስ እንደዛ ብዬሽ ቢሆን ኖሮ ላንቺስ ሞራል ጥሩ ነበር እንዴ?››
ለቅሶዋን ቀጠለች….
‹‹ መቼስ አልጐዳውሽም.. እንደውም እኔ ነኝ የተጐዳውት… ጀርባዬን እንዳለ በጥፍርሽ ተልትለሺኛል እኮ!!!››
‹‹ይቅርታ ››አለቺው በስተመጨረሻ ጫማዋን እየተጫማች
‹‹አይ ይቅርታ እንድተጠይቂኝ እኮ አይደለም..ባደረግነው ነገር ሁሉ ደስተኛ ነኝ..ያንቺ ለቅሶ ነው የረበሸኝ››
‹‹ባክህ የማረባ በሽተኛ ነገር ነኝ፡፡ አሁን ተነስ ፈጠን በልና እንሂድ..››
‹‹የት ነው የምንሄደው?››
‹‹ሆስፒታል››
‹‹ብቻ እንመርመር እንዳትይኝና እንዳታስቂኝ፡፡››
‹‹ምንድነው የምንመረመረው…የመሀሪ እናት በድንገት ሽባ ሆና ሆስፒታል ገብታለች እሱን ልነግርህ ነበር አመጣጤ ፡፡ትመጣ እንደሆነ ተከተለኝ›› ብላው እየተመናቀረች ቀድማ ቢሮውን ለቃ ወጣች፡፡
ኰማንደሩም በታላቃ መደነቅ እና የልጅቷን ጤንነት እወነትም እንዳለችው እብድ ሳትሆን አትቀርም ብሎ በመጠራጠር ቢሮውን ለቆ ተከትሏት ወጣ …ወደ ሆስፒታል ለመሄድ፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እየተረሳ ነው 👍እየተጫናቹ እስቲ የናተ Like👍 ለኛ ደሞዛችን ነው

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍91
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አምስት
:
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...ምንትዋብ ሆስፒታል በገባችበት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ባገኘችው የህክምና እርዳታ የተወሰነ መሻሻል አሳይታለች ፡፡በሽታዋ ከበፊቱም እንዳለባት የሚታወቀው የስኳር በሽታ አሁን ከተከሰተባት ድንገተኛ የደም ግፊት በሽታ ጋር አንድ ላይ ተዳብሎ የፈጠረባት የጤና መቃወስ ነው፡፡ይህ በሽታዋ በፍጥነት ሊያሽመደምዳት የቻለው ግን በቀለመወርቅ ክህደት ምክንያት የተፈጠረባት ብስጭት ቤንዚል ሆኖ ስላቀጣጠለባት ነው፡፡
አሁን ግን ሙሉ በሙሉ ፓራራይዝድ ሆኖ የነበረው አካሏ አሁን ወደ ግማሽ ጐን ተቀይሯል፡፡ ግራ እጆን እና ግራ እግሯን በመጠኑም ቢሆን ማንቀሳቀስ ችላለች፡፡በተደረገላት ጠንካራ ህክምና ሌላም ለውጥ ታይቶባታል፡፡ተቆልፎ የነበረው አንደበቷ ተላቋል፡፡ይሄ ማለት ግን እንደ ድሮዋ ቃላትን ሰካክታ አረፍተ ነገር መስርታ ለደቂቃዎች በማንበልበል ሀሳቧን ሙሉ በሙሉ መግለጽ ትችላለች ማለት አይደለም፤ግን የቤተሰቦቹን ቋንቋ ለመለማለድ እንደሚጥር የሁለት አመት ህጻን የተሰባበሩና የተወለካከፉ ቃላቶችን ከአንደበቷ ማሾለክ ችላለች፡፡ይሄ ደግሞ ለእሷም ለልጆም ትልቅ ተስፋ ነው፡፡አይ ለእሷ እንኳን ምንም ተስፋ አይደለም ..ከተስፋ ጋር ተፋታለች… አሁን የምትፈልገው ትንሽ አቅም ማግኘት ብቻ ነው፡፡ እራሷን በመጠኑ ማንቀሳቀስ የሚያስችላት ብጣቂ አቅም..ከዛ ያቺን ያገኘቻትን አቅም እራሷን ለማጥፋት ትጠቀምበታለች፡፡አዎ ፍጹም በዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ሆና በህይወት ለመቆየት አትፈቅድም፡፡አዎ ልጇን ደጋግማ አትበድለውም…የድህነት ማጥ ውስጥ ከታው በተጨማሪ የእሱ ሸክም በመሆን ህይወቱን ጨለማ ልታደርግበት ፈፅሞ አትፈልግም፡፡ ..ይሄ በፍፁም አይሆንም ፡፡አሁን ፈጣሪዋን የምትለምነው አንድ ነገር ብቻ ነው ..እራሷን ለማጥፋት እንድትችል የሚረዳትን ትንሽ አቅም..በቃ ጥቂት የመንቀሳቀስም ባይሆን የመንፎቀቅ አቅም ማግኘት፡፡ከዛ ያሰበችውን ታደርገዋለች፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
መሀሪ ከሳምንታት የሆስፒታል ተከታተይ ቆይታ ቡኃላ አሁን ወደቤት እያመራ ነው፡፡ወደ ቤት መሄድ የፈለገው ለሁለት ጉዳይ ነው ፡፡አንድም የገዛ ሰውነቱን ለራሱ ስለሸተተው ሊታጠብ እና ልብሱን ሊቀይር ነው፡፡ሁለተኛው ሮዛን የሚያነጋግራት ነገር ስላለው እና ቤት ሰለቀጠራት ነው፡፡ከዛ ቡኃላ ወደ እናቱ ይመለሳል፡፡ቤቱ ደርሶ የሳሎኑን በራፍ አልፎ ወደ ውስጥ እንደገባ መስታወት በሀዘኔታ እና በፍቅር ነው የተቀበለችው
‹‹ውይ..መጣህ?››
‹‹አዎ መጣው››
‹‹እኔ እኮ ምሳ ይዤ ልመጣ ነበር››
‹‹ባክሽ ሰውነቴን ልታጠብ ፈልጌ ነው የመጣሁት››
‹‹አይ ደግ አደረግክ..ጉስቁል ብለሀል እኮ.. ይሄንን ጺምህንም ብትላጨው ጥሩ ነው..በቃ ወደ ሻወር ቤት ሂድ ፤ሳሙና እዛው አለልህ..እኔ የምትቀይረውን ልብስ መርጬ አመጣልሀለው፡፡››አለችውና እሱ ወደ ሻወር ሲያመራ እሷ ወደ እሱ መኝታ ቤት አመራች፡፡ በስርዓት አጥባ ተኩሳና አጣጥፋ ካስቀመጠቻቸው ልብሶች መካከል ፓንትም ጭምር መረጠችለት እና ይዛለት ወደ ሻወሩ አመራች፡፡ሻውር ቤቱ አልተዘጋም፡፡የያዘቻቸውን ልብሶች በራፉ አካባቢ ባለ ወንበር ላይ አስቀመጠችና ወደ ውስጥ ገባች፡፡
መሀሪ ፊቱን በተቃራኒው አቅጣጫ አዙሮ ጀርባውን ለበራፉ ሰጥቶ ተገትሮ ቆሟል… ከላይ ከቧንቧው እየተስፈነጠረ ከግንሩ ላይ በመላተም ወደ ጠቅላላ ሰውነቱ እየተንቆረቆረ በሚወርደው ውሃ ሰውነቱን እያቀዘቀዘው ነው፡፡መስታወት በአንድ ሜትር ርቀት ቆማ እርቃን ሰውነቱን በፍዘት እና በተመስጦ እያስተዋለች ነው፡፡መሀሪ ከምታውቃቸው ከአብዛኞቹ የኢትዮጵያ ፖሊሶች ይለይበታል፡፡ብዙዎቹ ፖሊስ ሳይሆን አንዳንድ የከባድ መኪና ሹፌሮችን ነው የሚመስሉት…. ከመቀመጫቸው ሰፋ፤ ከሆዳቸው ገፋ ያሉ ወጣ ገባ የሰውነት ቅርጽ ያላቸው ናቸው፡፡መሀሪ ግን የሰውነቱ ቅርጽ የአትሌቶችን አይነት ነው፡፡ቁመናው የተስተካለ ፤ጡንቻው የፈረጠመ፡፡ይህን ቅርጹን ደግሞ ከልብስ ውጭ እንዲህ እርቃኑን ሆኖ ለዛውም እንዲህ እንደመስታወት በፍቅር አይን ከተመለከቱት የሚያደነዝዝ መሆኑ ብዙም አያስገርምም፡፡
ከተገተረችበት እንደመባን አለችና ተንቀሳቀሰች፡፡ከሳሙና ማስቀመጫው ሳሙናውን አነሳችና ከኃላ ተጠጋችው …ሳሙና የያዘ እጆን ጀርባው ላይ አሳርፋ አካባቢውን ማዳረስ ጀመረች፡፡መሀሪ በመመሰጥ ውስጥ ካለበት ስሜት ወጣና ፊቱን አዙሮ በትኩረት ተመለከታ…ገረመው፤ሊቃወማት አልፈለገም…ዝም አላት፤ከእሷ ጋር አታካራ ለመግጠም በዚህ ሰዓት ወኔ የለውም፡፡ የአምስት አመት ህጻን ልጆን ሰውነት እንደምታጥብ እንስፍስፍ እናት ከፀጉሩ አንስታ እስከ እግር ጥፍሮቹ ድረስ እሽት አድርጋ አጠበችው፡፡እሱ እንዳደረገችው ነው የሆነላት… ሰውነቱንም መንፈሱም በመጠኑም ቢሆን ነቃ አለለት፡፡
መስታወትም ይሄንን ዕድል በማግኘቷ እያንዳንዱን የሰውነት ክፍሉን መዳሰስ ስለቻለች እሱን ማገዝ..እሱን መንከባከብ ስለቻለች …ከእሱ ጋር ፍቅር የመስራን ያህል ስሜት ሰጥቶታል፡፡ግን ከዚህ አልፋ ድንበሩን ለማለፍ አልሞከረችም፤ለዛሬ ይሄ ይበቃታል ..ነገ ተነገ ወዲያ ደግሞ ሌሎች ከእሱ ጋር የሚያቆራኟትን አጋጣሚዎች ሊፈጠሩላት ይችላሉ..ደግሞም ይፈጠራሉ እርግጠኛ ነች፡፡ስለዚህ ‹የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል ›ተብሎ እንዲተረትባት አልፈለገችም፡፡
‹‹በቃ ተለቃለቅ እና ልብስህን ለብሰህ ና… እስከዛ ምሳ ላቀራርብልህ››አለችው በደስታ እንደተዋጠች፡፡
‹‹ምሳውን ትንሽ አዘግይው››
‹‹ምነው..ለምን?››
‹‹ሮዝ እየመጣች ነው..ትንሽ ልጠብቃት እና ከእሷ ጋር እበላለው››
ብሩህ የነበረው የመስታወት ፊት በአንዴ ሲጨልም..ፈክቶ የነበረው የውስጥ ደስታዋ በአንዴ ሲከስም ለራሷም ታወቃት.. ቢሆንም ግን በዚህ መሰበር ላይ እያለ ልትከራከረው አልፈለገችም‹‹እሺ እንዳልክ››ብላው ሻወር ቤቱን ለቃ ወደ ክፍሏ ገባች፡፡በውሀ የራሰ ልብሷን ቀየረችና ያንን ጨምቃ ውጭ በመውሰድ ካሰጣች ቡሃላ ወደ ማድ ቤቷ ገባች፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ሮዝ ጭንቅ ውስጥ ገብታለች፡፡ያስጨነቃት የኩማንደሩ መሀሪን ጥያቄ መመለስ አለመቻሎ ነው፡፡አሁን እቤቱ ድረስ እፍልግሻለው ብሎ የጠራት ለምን እንደሆነ ጠርጥራለች ..ያው የፈረደበትን የጋብቻ ጥያቄ ሊጠይቃት እንደሆነ ለእርግጠኝነት የቀረበ ጥርጣሬ በውስጦ እየተጉላላ ነው፡፡እሷ ጋብቻ አትፈልግም፡፡ፍፅሞ የትዳር ሴት እንዳልሆነች ታምናለች፡፡ዋና ችግሯ በአንድ ሰው መወሰን ነው..እንደዛ ማድረግ ለእሷ የማይታሰብ ነው፡፡..አገባች ማለት ደግሞ ታሰረች ማለት ነው…በዛ ላይ በእሷ እና በእሱ መካከል የተቀበሩ ብዙ ሚስጥሮች አሉ …ከነዚህም ውስጥ ዋና የልጅ እናት መሆኗ ነው ..ይሄንን እንዴት እንደምትወጣው ጨንቆታል…ያላት ምርጫ ሀገር ጥሎ መሰደድ ነው፡፡..እርግጥ መሀሪ የእሷን ልጅ በአካል ያቃታል …ግን የሚያቃት እህቷ እንደሆነች እንጂ ልጆ እንደሆነች አይደለም፡፡ለእሱ ሮዛ ድንግል ነች ሮዝ ሄለን የተባችውን የ10 ዓመት ልጆን የወለደችው አዲስ አበባ አጐቷ ጋር ሆና በምትማርበት ጊዜ ነው፡፡ገና 15 ዓመት ሳይሞላት፤የሃይስኩል ትምርቷን እንኳን ሳትጨርስ ነው ያረገዘችው፡፡ያረገዘችው ካፈቀረችው ሰው አይደለም፡፡አስገድዷ ከደፈራት ሰው ነው፡፡አስጠሊታው ነገር በጮርቃነቷ ማርገዞ አይደለም…አስቀያሚው ነገር ከደፈራት ሰውም ማርገዞ አይደለም፡፡አስቃያሚው ነገር ሰውዬው አጐቷ መሆኑ ነው፡፡አስቀያሚው ነገር በወላጅ እናቷ እሰከመመለክ የሚወደደው የገዛ አጐቷዋ የእናቷ ወንድም ከወንድምም አልፎ መንታ ወንድም መሆኑ ነው፡፡

ገና በዘጠኝ አመቷ ነበር እናትዬውን አባብሎ
3👍2
…የተሸለ ኑሮ ትኑር ብሎ….የተሻለ ትምህርት ትማር ብሎ ከዲላ ወደ አደዲስ አበባ የወሰዳት፡፡እርግጥ እንደለው ነበር ያደረገው፡፡ሀብት ስለነበረው ቅምጥል ህይወት ውስጥ ነበር የከተታት፡፡ በወር አንድ ሺ ብር እየተከፈለ የሚማሩበት የግል ትምህርት ቤት አስገባት፡፡አፈር አይንካሽ፤ ዓይን አይይሽ አላት፡፡እሷ አመነችው…አጐቷን ከእናቷ እኩል ወደደችው፡፡ ሰውነቷም ካለጊዜው ፋፋ…ካለወቅቱ መጐምራት ጀመረ..ጐረምሶች በእሷ መደመምና ዙሪያዋን መሽከርከር ጀመሩ..እሷም እያጐጠጐጡ የነበሩ ጡቷቾን ያስደምሟት፤ብልቷ አካባቢ እየበቀለ ያለው ፀጉሯ እያስፈነጠዛት ባለበት ወቅት አጐቷ ልጅነቷን ጨፈለቀባት፤ወጣትነቷን አጠቆረባት..፡፡ድንግል ነኝ ብላ ሳትጨርስ ሴት ሁኚ አላት፡፡ከዛም አልፎ ፀነሰች ፡፡
ትምህርቷን አቋርጣ …በሆዷ ጽንሷን ተሸክማ …በእፍረት አንገቷን ደፍታ …ሚስጥሯን በውስጧ ቀብራ…ከአዲስ አባባ ወደ ዲላ ተመለሰች፡፡እናቷ መቼም እናት ነችና ተቀበለቻት፡፡ሸሽጋት እንድትወልድ አደረገች፡፡የተወለደችው ልጅም ሄለን ተባለች፡፡ሄለን ግርማይ፡፡ግርማይ ማለት የሮዝ አባት ናቸው፡፡በዚህም የተነሳ ሚስጥሩን ከሚያውቁ በጣም ጥቂት ሰዎች በስተቀር ሮዝ እና ሄለን እናት እና ልጅ ሳይሆን እህትአማቾች እንደሆኑ ነው የሚታሰበው፡፡የሄለን አባት ማንነት ከራሷ ከሮዝ እና ከአጐቷ በስተቀር እስከዘሬ ድረስ የሚያውቅ ሰው የለም፡፡
ከዛ ቡኃላ ሌላ ሮዝ ተፈጠረች፡፡የዛሬዋ ሮዝ….ለሰው ግድ የሌላት…ለፍቅር ግድ የሌላት ሮዝ፡፡ላዬ በውበት የሚያብረቀርቅ አማላይ… ውስጧ ስብርብር ያለ ጨለማ ….፡፡የመንታ ማንነት ባለቤት ሆነች፡፡ውስጧ ካለው ብርሀን ይልቅ ጨለማው ይሰፋል፡፡ለልጇ እና ለእናቷ ካላት ፍቅር ይልቅ አጐቷ ላይ ያሳደረችው ጥላቻ በብዙ እጥፍ ይበልጣል፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
አሁን መሀሪ ጋር እየሄደች ነው፡፡ምን እንደምትለው አልተዘጋጀችበትም፡፡ገና ግራ እንደተጋባች ነው ፡፡‹‹እኔ አግብቼ ልቀመጥ ለዛውም በተክሊል .? ›› ስታስበው እራሱ አንገሸገሻት፡፡
‹‹ ግን ድንግል ነኝ ስለው እንዴት አመነኝ..?አሁን እኔ ምኔ ድንግል ይመስላል?››እራሷን ጠየቀች …መልስ ባታገኝም፡፡የኩማንደር መሀሪ ቤት ደርሳ ወደ ውስጥ ለመግባት የግቢውን በራፍ ልታንኳኳ ስትል ስልኳ ጠራ ..አወጣችና አነሳችው፡፡ኩማንደር ደረሰ ነው የደወለላት
‹‹ሄሎ ኩማንደር››
‹‹ሄሎ ልዕልት››
‹‹ልዕልት አልከኝ ደግሞ?››
‹‹ሲያንስሽ ነው..››
‹‹እሺ አመሰግናለው…››
‹‹የት ነሽ?››
‹‹ጓደኛህ እፈልግሻለው ብሎኝ እሱ ጋር እየሄድኩ ነው››
‹‹ትቆያለሽ እንዴ?››
‹‹ብዙም አልቀይ››
‹‹በጣም ለጥብቅ ጉዳይ ፈልጌሽ ነበር… እንደጨረሽ ትደውይልኛለሽ?››
‹‹በሚገባ››
‹‹ደህና ቆይልኝ …የእኔ ጣፋጭ››ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡እሷም ስለኩማደሩ እያሰላሰለች ወደውስጥ ዘልቃ ገባች፡፡መሀሪን ሳሎን ቁጭ ብሎ ሲተክዝ ነበር ያገኘችው፡፡ሲመለከታ የተቋጠረ ፊቱን ፈታ.. የተከደነ ከንፈሩን ገለጥ አድርጐ ተቀበላት፡፡
‹‹ምነው በሰላም…?የሆነ ከቦረና የተላከልኝ ዕቃ እኮ ልቀበል ልወጣ ስል ነው ሞቼ እገኛለው ስትል እሰቲ አናግሬህ ልሂድ ብዬ በዚሁ ጎራ ያልኩት››አለችው፡፡ቶሎ እንዲለቃት የፈጠረችው ዘዴ ነው …ቀልቧ ያለው ኩማንደር ደረሰ እፈልግሻለወ ያላት ጉዳይ ላይ ነው፡፡ከዚህኛው ለጊዜው ንዝንዝ እንጂ ምንም አታተርፍም፡፡
‹‹ምሳ እኮ እየጠበኩሽ ነው እንብላና እንጫወታለን››
‹‹እየነገርኩህ በጣም ቸኩላለው..››
‹‹ካልሽ እሺ .ያው ስለሰርጋችን እንድንነጋገር ነው››
‹‹እንዲ አስቸኳይ ብለህ የጠራሀኝ ለዛ ነው?››
‹‹እንዴ !!! ከዛ በላይ ምን ጠቃሚ ጉዳይ አለ?››
‹‹እንዴ ጊዜ አለን ብዬ ነዋ… የእናትህ ጉዳይ….. ››
‹‹ማለቴ..››
‹‹ግድ የለም አትጨነቅ ይገባኛል..እሳቸው እስኪደኑ አመት ሁለት አመት ቢሆንም መቆየት እችላለው ፡፡ ቅር አይለኝም.. ዋናው እሳቸው ብቻ ይዳኑ››
‹‹ባክሽ እኔ እንዲፈጥን ነው የምፈልገው..በቅርብ እንድንጋባ››
‹‹እንደዛማ አታደርገውም ..እናትህ አልጋ ይዛ እንዴት ነው ስለሰርግ የምታሰብው ?ሰውስ ምን ይለናል?››
‹‹እርግጥ መጀመሪያ እንዳቀድኩት ድል ያለ ድግስ አልደግስም …በመጠነኛ ድግስ መጋባት እንችላለን ዋናው የቤተክርስቲያኑ ዝግጅት ነው፡፡ቅድስ ጋብቻ በተቀደሰ ስፍራ ነው የሚመሰረተው፡፡ዋናው ድግሱ ሳይሆን ጋብቻችንን በህገ-እግዚያብሄር … በቅዱስ ታቦቱ ፊት ማስባረካችን ነው..ይሄ ደግሞ እናቴን ያስደስታታ እንጂ አያስከፋም..በጋራ ሆነን እንንከባከባታለን…እናስታምማታለን››
ንግግሩ መረራት..የሆነ እንጨት እንጨት አላት‹‹ላስብበት››
‹‹ምንድ ነው የምታስቢበት?››
‹‹ቤተሰቦቼን ላማክር ማለቴ ነው››
‹‹ምን ማማከር ያስፈልጋል? የሚቀጥለው እሁድ እኮ ሽማግሌ ልልክ ነው››
‹‹የት ነው የምትልከው?››
‹‹እናትሽ ጋር ነዋ››
‹‹በቃ አሁን ልሂደ …ሰዎቹ ዕቃውን ይዘውብኝ ይመለሳሉ… ነገ መጥቼ እናወራበታለን›› ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳች፡፡እሱም ተከተላትና በር ድረስ ሸኛት፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
2👍2
#የተስፋይቱ_ምድር_ልጆች_ነን


በእጦት ስንኖር - አግኝተን ባናውቅም
በድህነት ሳለን...
የምድር እድሜያችን - ዘመናችን ቢያልቅም
በሰማይ ተስፋ አለን - ተስፋችን አይጠልቅም
ባለ ሀብት የሆነ...
ለእግዜር መርፌ ሽንቁር
እንደኛ ክር ሆኖ - በመንግስቱ አይፀድቅም።
እንላለን!
በተስፋ ተስፋ የማንቆርጥ...
የተስፋይቱ ልጆች ነን።
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
እርስ በርስ እየተናከስን
እርስ በርስ እየተጫረስን
አንድ ለመሆን ቢያቅተን
ላብሮነታችን ትንሳኤ - ብንታይ አንድ ላይ
ሞተን
እንድነታችን አይነጥፍም!
አንድ ነው አንድ ቢበተን።
እንላለን!
በተስፋ ተስፋ የማንቆርጥ....
የተስፋይቱ ልጆች ነን!
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ከዓለም በፊት ሰልጥነን - ከዓለም ኃላ
ብንቀርም
የተጉዋዝንበት እድሜ እንጂ - የደረስንበት
ባይኖርም
የየልባችን እግር ግን...
በመሄድ አያውቅም ዝሎ
ጥቅጥቅ ብርሐን ይገኛል...
ድቅድቅ ጨለማን ቀጥሎ።
እንላለን!
በተስፋ ተስፋ የማንቆርጥ...
የተስፋይቱ ልጆች ነን።
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ተስፋ በኛ ተስፋ ቆርጦ - ትቶን ካልሄደ
በስተቀር
ከኖርነው ጨለማ ይልቅ...
የማናውቀውን ብርሐን
በተስፋ እየሰበከች - ለምታሳየን ውብ ሀገር
የተስፋ ልጆች ነንና.....በተስፋ ተስፋ አንቆርጥም
በምንም አይነት ባህር ውስጥ ፣ አንድነታችን አይሰምጥም
በምንም አይነት መከራ
በምንም አይነት መማረር
አለት ተስፋችን አይቀልጥም።
የኖርነው ጨለማ ዘመን....
በተስፋ ከምንጠብቀው - ካልኖርነው ብርሀን
አይበልጥም!!!


ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ከተስፋዋ ጋራ!!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘