አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
የምታስታውሰው ጭንቀት ጭንቀቱን ብቻ ነው ። ቀዝቃዛውን የእጓለማውታን መመገቢያ አዳራሽ ! ያ አዳራሽ ዛሬም ትዝ ባላት ቁጥር ይቀዘቅዛታል የማታውቀው ፤ያለመደቻቸው ሰዎች ጠረን ዛሬም ይሸታታል ፤ ያስፈራታል ። እንቅልፍ የወሰዳት መሰላ አልጋዋ ላይ ተኝታ ትሰማቸው የነበሩ የተለያዩ እንግዳ ድምጾች ዛሬም እንግዳ ሆነው ትሰማቸዋለች ። ዛሬም ወደ አንድ የማታውቀው ዓለም የተጣለች ብቸኛ ፍጡር የሆነች ይመስላታል በጠቅላላ ናንሲ አባቴ ወይም እናቴ የምትለው ሰው ሳይኖራት ፡ ልጄ ብሎ እቅፎ የሚስም ወላጅ ሳታይ የእናት.. አባት ፍቅር ሳታገኝ ያደገች ልጅ ናት ። ታዲያ ይህች ልጅ ምን ሆና ምንስ አድርጋ ለማይክል ሂልያርድ በቶሎ ልቧን ከፍታ ትስጠው ? የማይቻላት ነገር ነበረና ፍቅሯንም ፤ አካሏንም የሰጠችው ቀስ እያለች ነበር ።

ናንሲ ማክአሊስቶር ማይክል ሂልያርድን እሰክታገኝ በነፍሷ ውስጥ አንድ ትልቅ ክፍት ቦታ እንዳለ አዘውትራ ታስብ ነበር። ያን ክፍት ቦታ ሊሞላ የሚችል ሰው አገኛለሁ የሚል ሕልም እንኳን አልነበራትም ። ግን አገኘች ዛሬ ያንን ባዶ ማይክል ሞልቶታል ። ዛሬ ያ ባዶ የለም ። የኔ እምትለው ሰው አላት ።

የማይክልና የናንሲ ፍቅር የአንድ ሰሞን ሽር ብትን ፤የአንድ ሰሞን የስጋን ትኩሳት ለማብረድ የታለመ ተራ ፍቅር አልነበረም አይደለም ። የነዚህ የሁለቱ ፍቅር በጠንካራ ስሜት ላይ የተመሰረተ ፍቅር ነው። ይህ ፍቅር ስላለም እሷ በሱ የተሟላና የተደላደለ አስተዳደግ የበታችነት አይሰማትም፡፡ እሱ የሷን ተራ አስተዳደግ ተመልክቶ እንደ ዝቅተኛ አያያትም ። በዚህ ፈንታ አንዳቸው ካንዳቸው አስተዳደግ እየተማሩ የኖሩትንና ከዚያ ኑሮ ያገኙትን ልምድ አዋጥተው በመቀየጥ ውብና እጹብ ድንቅ የሆነ እዲስ ኑሮ ፈጠሩ ። ስለዚህ እሷ ለሱ አዲስ አይደለችም ፣እሱም ለሷ አዲስ አይደለም ።
የማይክል እናት ማሪዮን ሂልያርድ የማይክልና የናንሲን ፍቅር ስትሰማ «ለየት ካለ ሰው ጋር ፍቅር ሲይዝህ ደግ አይደለም» ስትል ለልጅዋ እንደማስጠንቀቂያም እንደምክርም አድርጋ ነግራው ነበር ። ማሪዮን ነገሯን የጀመረችው «ከሆነች ሰዓሊ ጋር ፍቅር ያዘኝ ብሎ ይንዘላዘላል ብለው ነገሩኝ» በማለት ነበር ።

ይቀጥላል...

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍21
#ሳቤላ


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ከበረዶው ማዕበል በኋላ ብራ የሆነ ጧት ተተካ ሰማዩ ፍንትው ብሎ ጠርቶ
ፀሐይ ደምቃ ስታበራ ሲጥል ያደረው በረዶ ግን ከመሬት እንደ ተቆለለ ነበር
ሚስዝ ሔር በወንበር ተቀምጣ የቀኑን ድምቀት እያየች ትደሰታለች የማስተር ካርላይልም
አጠገቧ ቆሟል ከባርባራ ጋር የመለያየቷን ነገር ስታስበው ኀዘኑ ለሷ አቻዋ የሆነ ባል በማግኘቷ ደስታው ሁለቱ ስሜቶች ተጋጭተው ሲያስጨንቋት ዐይኖቿ የኀዘንና የደስታ እንባ አቀረሩ ።

“አርኪባልድ . . . ይህች ልጅ ከኛ ጋር ሁና ደስተኛ ነበረች አንተ ዘንድም የለመደችውን ደስታ ታገኘው ይመስልሃል ?

“ እኔ በምችለው ሁሉ።"

“ ታዝንላታለህ ? ትንከባከባታለህ ?

ሚስዝ ሔር ... ደኅና አድርገው
ስለሚያውቁኝ የሚጠራጠሩኝ አይመስለኝም ነበር " አሁንም ባለኝ አቅም ሁሉ በሙሉ ልቤ እሷን ለማስደሰት እሞክራለሁ " "

“ አንተን አልጠረጥርህም ! በደንብ አምንሃለሁ ዓለም ሁሉ ከባርባራ እግር ቢወድቅ አንተን እንድትመርጥልኝ እጸልይ ነበር ግን አርኪባልድ የኮርንሊያ ነገርስ እንዴት ይሆናል ? እኔ እንኳን ባንተ ጉዳይ ወይም አንተና ባርባራ ተስማምታችሁ በምትፈጽሙት ለመግባት ሳይሆን ባልና ሚስት ብቻቸውን ቢሆኑ የማሻል መስሎኝ ነው "

"እሷ የፊተኛዋ ሚስቴ ሳለችም ብዙ ጊዜ ጣልቃ እየገባች ታስቸግራት እንደ ነበረ ለማወቅ ችያለሁ ይህን ነገር በጊዜው ብሰማ ኖሮ አንድ ቀን አላሳድራትም ነበር " አሁን ግን ይህ ነገር አይደገምም " በርግጥ ገና አልነገርኳትም እንጂ ኮርኒሊያ ከኢስት ሊን ለቃ ከቤቷ ትገባለች " በዚህ ምንም አያስቡ "

“ኧረ ለመሆኑ ባርባራ ስንቱን ሰው ስትመልስ ኖራ አንተን እንዴት እሺ አለችህ ? አለ ቀደም ሲል በነገሩ መደስቱንና ስምምነቱን የገለጸው ሚስተር ጀስቲስ ሔር "

“ ምናልባት መስተፋቅር አድርጌባት ይሆናል ” አለ ሣቅ ብሎ "
“ እንዲያውም ይኸው መጣች ” አለና አባትየው።

“ ኧረ እንዲያው ለነገሩ ካርላይልን ከሌሎች የተለየ ምን ብልጫ አየሽበት ? አላት "

ጉንጮቿ ፍም በመምሰል መልሱን ተናገሩላት “ “ አባባ .... ሚስተር ኦትዋይ ቤቴል ከደጅ ሊያነጋግርህ ይፈልጋል " ጃስፐር እንዶፈደ ነገረኝ ከሆነ ለመግባት አልፈለገም አለችው።

“ እኔም ብሆን በዚህ ብርድ አልወጣለትም " ሚስተር ኦትዌይ ... ግባ እንጂ
ምን አስፈራህ ? አለው
“ቀጠሯችሁ ከሰባት ሰዓት ወደ ስምንት ሰዓት ቢለወጥ የሚመችዎ እንደሆነ ኮሎኔል ጠይቅ ብለውኝ ነው የመጣሁት " አንድ ያልታሰበ እንግዳ ስለ መጣባቸውና እሱም ዛሬ በስምንት ሰዓቱ ባቡር ተመልሶ ስለሚሔድ ነው ” አለው "

“ እኔምን ከፋኝ ! በሰባትም ሆን በስምንት ግድ የለኝም ” አለው ሚስተር ሔር"

“እሺ! እንግዲያው ይኸንኑ ለሔርበትና ለፒነር ልንገራቸው " ለመሆኑ ሙቶ ስለ ተገኘው ሰውዬ ሰምተዋል ?

" የምን ሰው ነው ?

“ እንግዲህ አንዱ መንገድ የጠፋው ወይም ደክሞት ከበረዶው የወደቀና በዚያው እንዳለ የቀረ ይሆናል እንጂ ከሆሊጀን ቤት መዞሪያ አጠገብ ካለው ጐድጓዳ ሥፍራ ነው ከመንገዱ ዳር ሞቶ የተገኘው "
ብዙ ስዎች ወደዚያ ሲጎርፉ
አየሁና እኔም ሄጄ አየሁት" አለው።

“ ማነው እሱ ?” አለ ጀስቲስ ሔር ።

“ የሚታወቅ ሰው አልመሰለኝም ! ፊቱን አይቸ ላውቀው አልቻልኩም "
የሥራ ካፖርት ለብሷል ። በጣም ጢማም የሆነ ልጅ እግር ነው ” አለ ኦትዌይ ቤቴል »

“ ትናንት ጃንጥላውን በስተፊቱ ገትሮ እየተደናበረ ሲያልፈኝ ጃንጥላዬን
ሊሰብርብኝ የነበረው ሰው ሳይሆን አይቀርም » አንድ
የሥራ ካፖርት የደረበ ሪዙ ችምችም ያለ ልጅ እግር ነበር ሰውዬው ጤነኛ አልመሰለኝም " ተናደድኩና
ስጮህበት ጊዜ የድንጋጤውን ያህል ጮኸና እንደ ጥይት ሽው ብሎ ሔደ እና ኦትዌይ ይህ የምትለው ሰው እሱ ይሆናል ” አለ ሚስተር ሔር ።

“ ሊሆን ይችላል ጌታዬ " አለው ።

የሚስተር ሔር ገለጻ ' ከሪቻርድ ጋር የሚመሳሰል ስለ ነበር ባርባራ በበኩሏ
ሪቻርድ ይሆናል ብላ ተጨነቀች ሚስተር ካርላይልም ገባው "
ሚስተር ካርላይል ክፍሉን አቋርጦ ወደ በሩ ሲያልፍ እንደ ምንም ብሎ አንድ
ነገር በጆሮዋ ሹክ አላት "
ሔጄ አይቸ ወሬውን አመጣልሻለሁ እስከዚያው ቻይው የኔ ፍቅር"

“መሔድህ ነው አርኪባልድ ? አለችው ሚስዝ ሔር "

ይህን ቤቴል የሚለውን ሰውዬ አይቸ ለመምጣት ነው " መቸም ለወሬ መጓጓት ነው "

ሚስተር ካርላይል በአትክልቱ ቦታ አቋርጦ ወርዶ ሔደ ባርባራ በዐይኗ እስከ በሩ ተከተለችው
በጣም ተጨነቀች ካርላይል ተመልሶ ነው ወይም አይደለም የሚል መልስ እስኪሰጣት ድረስ እንዴት ትቆይ በጣም ተቸገረች ሪቻርድ ነው ብሎ አንድ ነገር እንደነገራት ተሰማት ኦትዌይ ቤቴልም ሔዶ ጀስቲስ ሔርም ሰው ሠራሽ ጸጉሩንና ኮቱን ማለፈያ ማለፊያውን መርጦ ለባበስና ተከትሎት ወጣ እሱም ሞተ የተባለውን ሰውዩ ለማየት ፈለገ ዌስት ሊንን በመሰለ ትንሽ ከተማ
ጥቃቅኑ ነገር ሁሉ እንደ ብርቅ ይታያል በትልልቅ ከተሞች ከቁም ነገር የማይገባው ሁሉ እዚህ ሲሆን በጣም ይጋነናል " ሕዝቡ ያደንቀዋል "

ባርባራ ከበረንዳ ቁማ በጭንቀት በጕጕት ስትጠባበቅ ካርላይልን ሲመለስ ከሩቅ አየችው ዶርሶ እስኪነግራት መቸኮሏን ተረድቶ ጥቂት ቀረብ አንዳለ ራሱን በመነቅነቅ የፈግታ ምልክት አሳያት ልቧ መምታቱን ባይቀንስላትም በፈገግታው ትንሽ ጠንከር አለች
«እንዲያው ነው የተደናገጥነው .... ባርባራ » አንድ መንግድ ጠፍቶት ይንከራተት የነበረ ማንም የማያውቀው መንገደኛ ነው " ሪዙ ቀይ ነው » በምኑም ሪቻርድን አይመስልም።

«ያን ለት ማታ ሚስ ካርላይል ጉንፋኗ ቀሏት ነበር " ራት ተበላና ሚስተር ካርላይል ስለ ጋብቻው ሊያጫውታት ጀመረ።

“ ኮርኒሊያ... እመቤት ሳቤላ ቬንን ሳገባ አስቀድሜ ስለአልነገርኩሽ በጣም ተቆጥተሽ ነበር "

« ማንም ሰው ድረግ እንደሚገባው አስቀድመህ ብታማክረኝ ኖሮማ
የደረሱት ነገሮች ሁሉ ሌላ መልክ ይኖራቸው ነበር " በዚህ ቤት ላይ የወረደው ውርደትና ፈተና አይደርስም ነበር ” አለችው እየተቆጣች "

“አሁንም ያለፈውን ትተን ስለ ወደፊቱ እናስብ " እንደ ከዚህ ቀደሙ በተሣሣመሳሳይ ሁኔታ ዳግመኛ ላስቀይምሽ ሐሳብ እንደሌለኝ ልነግርሽ ፊልጌ ነው " እንደ ሚመስለኝ ከልብሽ ይቅር አላልሽኝም"

“ ወደፊትም ከልቤ ይቅር አልልህም ” አለችው “እንደዚህ መናቅ አይገባኝም ነበር "

ስለዚህ እኔ ራሴ በቁርጥ እንዳወቅሁት ወዲያው ከሐቁ ጋር ላስተዋውቅሽ
እፈልጋለሁ " ኮርኒሊያ አሁን ሁለተኛ ላገባ አስቤአለሁ ”

ሚስ ካርላይል ክው ብላ ደነገጠችና ቀና ስትል መነጽሯ ከአፍንጫዋ ወደቀ
ስትሠራው የነበረውን ክር የያዘችበት ባኮ ከጉልበቷ ላይ ስለ ነበር ተንሸራትቶ ከመሬት ዐረፈ ።

ምን ምን ” አልክ ?”
“ አሁን በቅርቡ ማግባቴ ነው ”

“አንተ !?

“ አዎን እኔ ... ምነው ? ምን የሚያስገርም ነገር አገኘሽ ?”

“ በል በል አሁን ደግሞ በገዛ እጅህ ገብተህ አትጃጃል " አንድ ጊዜ ያየኸውዐአይበቃህም ? አሁን ደግሞ ዐይንህ እያየ ባንገትህ ሸምቀቆ ታስገባለህ ?

“ ኮርኒሊያ ... እኔ የምነግርሽን ሁሉ አንቺ በዚህ ዐይነት ስትቀበይው
እያየሁ እንዲህ ያሉትን ነገሮች ባልነግርሽ ሊገርምሽ ይገባል ? አንቺ እኔን ልክ እንደ ሕፃንነቴ ጊዜ ነው የምታይኝ " ይኸ ደግሞ ከፍተኛ የዋህነት ነው”
👍13🥰1
“ ትልቆችም ቢሆኑ የልጅ ሥራ ከሠሩ እንደ ልጆች መታየት አሰፈለባቸው "
ከዚህ በፊት ስታገባ ጊዜ አበድክ ብዬ ሳስብ ኖርኩ " አሁን ደግሞ ዕብደትህ በእጥፍ እንደ ጨመረ እቁጥረዋለሁ ። ”

አንቺ ለራስሽ ብቸኛና ነጠላ ሆነሽ መኖርን ስለ መረጥሽ እንዴት እንደ እኔ አድርግ ብለሽ ትፈርጅብኛለሽ ? አንቻ ብቻሽን በመሆንሽ ደስተኛ ነሽ " እኔ ደግሞ
የበለጠ ደስ የሚለኝ ከትዳር ጓደኛዬ ጋር ስሆን ነው " "

“ ልክ የፊተኛይቱ ሚስትህ እንዳደረገችው እንድታዋርድህ ነው የፈለግኽው''

' የለም " አላት ረጋ ብሎ!“በአሁኑ ምርጫዬ አንቺ የምትይው ችግር ይደርስብኛል ብዬ ምንም አልሠጋም
ኮርኒሊ እየሰራች ያለውን
ሥራዋን ሰበሰበች ካርላይል ባኮውን አነሳላት
እጆቿ ሲንቀጠቀጡ የግንባሯ ሥሮች ደግሞ ቁጥር ፈታ ይሉ ነበር" ይህ ወሬ ልክ እንደ ፊተኛው ጋብቻ የበትር ያህል ተስማት።

“ አገር ምድሩ ዐይን ዐይንህን ሲያይ ለመሆኑ ማንን ልታግባ ነው?

“ ምን ያዶርጋል ማንም ትሁን ማን አንቺ እንደሆነ ልዕልትም ትሁን የገበሬ ልጅም አንድ እንከን ለማውጣት ምክንያት አታጭላትም "

አዎን ፤ማድረግ አለብኝ ማን እንደ ሆነችም ዐውቄያታለሁ " ያቺ ትአቢተኛ ሎዊዛ ዶቢዴ ናት።

“አይደለችም እኔ ሚስት የማግባው ለደስታ ነው "ስለዛህ የምፈልገውን
ደስታ ከሷ ስለማላግኘው እኔ እሷን ለማጨት'እም እኔን ለመምረጥ ሐሳብ አልነበረንም

“ ልክ ባለፈው ጊዜ እንዳደረግኸው ” አለችው እያሽሟጠጠች »

አዎን ልክ ባለፈው እንዳደረግሁት

“ ግን ማን መሆኗን ለመናገር አትችልም ?
“ ባርባራ ሔር ናት "

“ ማን?” ብላ ጮኸችና “ አን† ከብት ነህ ” አለችው እጆንና ዐይኖቿን ሽቅብ አንሥታ በመጮህ “ስትከታተልህ ስታጠምድህ ስታደባህ ስትዞርሀ ኖራ
ኖራ በመጨረሻ በጂዋ አስገባችህ » አትረባም ከብት ነህ አርኪባልድ"

አመሰግናለሁ አላት ከፊቱም ምንም ቅሬታ ሳያሳይ እሷ ምንም አላጠመደችኝም እንደዚህ አድርጋ ቢሆን ኖሮ ሚስዝ ካርላይል ለመሆን አትችልም ነበር " እንዲያውም በዚህ በሁለተኛው ጊዜ ጋብቻዬ እሷን እንደምጠይቃት ምንም አልጠረጠረችም”

ልታይ ባይ ራስ ወዳድና ትዕቢተኛ ናት "
ሌላስ በሷ ላይ የምትሰጪው አስተያየት አለሽ ?
“ እኔ ብሆን ካገባሁ ላይቀር ጥቁር ነጥብ የሌለባትን ነበር የማገባው "

የምን ጥቁር ነጥብ ?”
“ የሪቻርድ ሔርን እኅት ስታግባ ' ላንተ ክብር መሆኑ ነው ?ፀ

" ሆነም አልሆነም ይህ የባርባራ ጥቁር ነጥብ አይደለም » ሪቻርድም ቢሆን ንጹሕነቱን የሚያረጋግጥበት ቀን ይመጣ ይሆናል »

“ አዎ እንጂ ይቀራል ? ዓሣሞችም ባየር ይበሩ ይሆናል " እስከ ዛሬ ግን ሲበሩ አላየሁም

አሁን ሌላው ነገር የመኖሪያሽ ጉዳይ ነው ከቤትሽ ተመልሰሽ መግባት
ሊኖርብሽ ነው "

ሚስ ካርላይል የገዛ ጆሮዋን ማመን አቃታት “ እኔ ከዚህ ወጥቼ ከቤት ተመልሸ ልገባ ! እንደዚያ ያለውን ነገር ጭራሽ አልሞክረውም ኢስት ሊን ለመቀመጥ ምን ያግደኛል ?”
ሚስተር ካርላይል ራሱን ነቀነቀና ( እንዶሷ ሳይጮU ዝግ ባለ ድምፅ'' ሊሆን
አይችልም አላት።

“ማነው ያለው ?

እኔ ነኝ ያን ጊዜ ሌሊት እሷ የኮበለለች ጊዜ ጆይስ የተናገረችውን ረሳሽው
ኮርነሊያ ... ጆይስ ያላችው እውነት ቢሆንም ባይሆንም ያሁኒቱ ሚስቴንም ለዚህ እድል አልዳርጋትም።

መልስ አልሰጠችም ከንፈሮቿ እንዶ መከፈት አሉና መልሰው ግጥም አሉ"የጆይስን ንግግር ሲያስታውሳት ኩምሽሽ አለች » ተሰማት

“ እኔ ስሳንቺ መጥፎ አስተያየት የለኝም አንቺ ለብዙ ዘመን የቤት አስተዳሪ
ሁነሽ ኑረሻል » አሁንም በዚያው ብትቆይ ደስ የሚልሽ ቢሆን አያስደንቅም "ግን በአንድ ቤት ሁለት እመቤቶች ኖረው እንደማያውቁ ሁሉ ወደፊትም አይኖሩም ” አለና ቁርጡን ነገራት ።

“ ታዲያ አንተስ ይህን ስታስብ መጀመሪያ ወደ ኢስት ሊን ስመጣ ለምን አትነግረኝም ነበር ?

ያን ጊዜ ይህን ሁሉ አላውቅም " በኋላ ከኑሮ ልምድ ያገኘሁት ነው
“ ቤትህን እኔ ይዠልህ ከነበረው ሁኔታ አብልጣ የምትይዝልህ አታገኝም

“ እኔም ይህን ለማድረግ አላሰብኩም " የቤትሽ ኪራይተኞች በመጋቢት አይ አይደለም የሚለቁት ? ”

“ በል እንግዲያው እኔ ከባርባራ ጋር ብቀመጥ መርዝ የማበላት መስሎ ከታየህ እለቃለሁ ግን ኢስት ሊን ለናንተ በመጠኑም በዐይነቱም በጣም ስለሚበዛባችሁ
አከራዩትና እናንተ ከኔ ቤት ግቡ እኔ ደግሞ እንዳቅሜ አነስ ያለች ቤት ፈልጌ
ልከራይ ”

“ እኔ ደግሞ ኢስትሊን በምኑም አይበዛብኝም ስለዚህ ልለቀው አልፈልግም'

“ግን ሚስተር አርኪባልድ . . . ካንተ ቤት ወጥቸ ስሔድ የራሴን ገቢ ይዤ መሔዴን ዐወቀኸዋል ?”

“እንዴታ ! ገቢሽማ ለራስሽ ነው !! ለራስሽ ጣጣ ያስፈልግሻል " እኔ ለግንዘብሽ ፍላጐትም መብትም የለኝም "

“ የኔ መጣት በገቢህ ላይ በቀላሉ የማይደፈን ቀዳዳ ያበጅብሃል ዕወቀው
አንተም ኢስት ሊንም ተያይዛችሁ እንዳትወድቁ ።

“ አንቺ እንደምትዪ ብዙ ገንዘብ ባወጣም የዚያን ያህልም ተቀማጭ አላጣም
" አንቺም ታውቂያለሽ " "

“ አየህ ወጭህን ቀነስ ብታደርገው ከዚህ የበለጠ ማስቀመጥ ትችል ነበር"
"እኔ ኮ እንደ ስስታም ወይም እንደ ባሕታዊ ለመኖር አልጸልግም ተበሳጨች “

በዚህ ጊዜ አንድ እንግዳ መምጣቱ ተነገረ ሆድ የባሳት ሚስ ካርላይል በዚወያው ተበሳጨች
ደሞ ዛሬ ሌሊት መጥቶ የሚረብሸው ማነው ?” አለች "

ወድያው አሽከሩ ፒተር ገባና “ሻለቃ ቶርን ነው ከሳሎን አስገባሁት" አለው

ሚስተር ካርላይልም ገረመው እሱ ወደ ሳሎን ሲገባ እሷ ደግሞ ጆይስ እንድ ትመጣላት ጥሪያውን ደወለች » የሚርመው ግን በወንድሟ ውሳኔ የታሰበውን
ያህል አልተቃወመችም
ሚስተር ካርላይል የግባ እንደሆነ መውጣቷ እንደማይቀር በልቧ ዐውቃውና አስባበት የተቀመች ይመስል ነበር ኤስት ሊን የሱ ነበር አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከተናገረው ቃል ፍንክች እንደማይልም ታምን ነበር "

ጆይስ...ይኽ ጌታሽ ተጃጃለ " አሁን ደግሞ ሁለተኛ ላግባ ይላል "ስለዚህ ከሱም መለየቴ ኢስት ሊንንም መልቀቄ ነው አንቺስ ከአኤ ዘንድ መጥተሽ የሠራተኞች አዛዥ ትሆኛለሽ ?”

እኔ ከእርስዎ ጋር ለመሔድ እፈልግ ነበር ነገር ግን እመቤት ሳቤላ አንድ ጊዜ ታመው በደከሙ ጊዜ የሚሞቱ ስለ መሰላቸው ከልጆቻቸው እንዳልለይ አስምለውኛል " በርግጥ ያኔ በሞት ባይለዩዋቸውም ዙሮ ዙሮ መጨረሻው ልጆቹ እናታቸውን አላገኙም ? "

“ግን በቤቱ ሌላ እመቤት ስትመጣበት ከዚህ እንድትቀመጭ ይፈቅድልሻል?”
አለቻት እንደ ማሾፍ እያለች

ጆይስ ትንሽ አሰበችና አስተማማኝ መልስ ስታጣ ( “ይታገሡኝና አስቤ እነግርዎታለሁ " አለቻት "

“ እንዲህ ያለ መንገድ ! አለው ሻለቃ ቶርን ደግሞ ለሚስተር ካርላይል
“ መንገድ ስወጣ ዕድሌ ሆኖ መጥፎ አየር አያጣኝም ዝናብ የበረዶ ጠጠር ነጎድጓድ የሚያቃጥል ሙቀት አንድም አይቀርም " እኔ ከወጣሁ በረዶው ሐዲዱ
ላይ ተቆልሏል ። ከአንድ ጣቢያ ላይ ሁለት ሰዓት ሙሉ ቆምን ።
“ ዌስት ሊን ለመሰንበት ሐሳብ አለህ እንዴ ?”

“ ነገ እሔዳለሁ የዛሬው ፈቃዴን ከእናቴ ጋር ላሳልፈው ነው ያቀድኩት
ቢሆንም ለዌስት ሊንም ሳምንት ያህል እሰጠው ይሆናል " አሁን እንኳን ወደዚህ ያመጣችኝ አንዲት ሴት ናት ካርላይል ” አለው "

“ እውነት ? እንዴት ነው? ”

“ ከባርባራ ሔር ጋር ፍቅር ይዞኛል = እሷ ግን አይሆንም ብላ ደብዳቤ ጻፈችልኝ " አሁን ሔርበርትም በግንባር ቀርቤ አጥብቄ እንድጠይቃት ስለ መከረኝ
ለዚሁ ስል መጣሁ።
👍9😁2
ሚስተር ካርላይል ነገሩን በሐሳቡ አውጥቶ አውርዶ አሰበ » ባርባራ ለሁለተኛ
ጊዜ እምቢ ብላ ከምትመልሰውና ነገሩን ከሌላ ሰው ከሚስማው እውነቱን ገልጾ ሊነግረው ወሰነ ።

“ ሻላቃ ባርባራን እንግዲህ ደግመህ መጠየቅ ምንም ፋይዳ የሌለው ልፋት
መሆኑን ብነግርህ አይከፋህም "

“ መቸም አልተያዘችም ' አይደለም ? አለ ሻለቃ ቶርን ፈጠን ብሎ "

“ ማግባት አላግባችም " ግን በቅርቡ ታገባለች "

ይኸማ የዕድሌ መጥመም ነው " እንዴት ያለ ዕድለኛ ስው አገኛት በል ?

ስሙን ብገልጽልU ላትጮህብኝ ቃል ግባልኝ "

"" ካርላይል ! አንተን አንዳይሆን አንጂ ?

" አንተው ተናገርከው " "

ትንሽ ጸጥ ብለው ከቆዩ በኋላ “ቶርን . . መቸም ይኸ ወዳጅነታችንን ሊቀንሰው አይገባም አለው "

ሻለቃው እጁን ዘርግቶ የሚስተር ካርይልን እጅ ያዘና “ በምንም አይነት አይቀንሰውም ሁሉም የዕድል ጉዳይ ነው ለኔ ካልሆነች ከሌላ ዘንድ ከማያት ያንተ ሁና ባያት ው የምመርጠው ገና በፊት ጠይቄያት የነበረ ጋዜም አጭተሃት ነበር ? ”

" የለም አሁን በቅርቡ ነው የተጨነው " "
"ግን እኔ ጠይቄያት እንደ ነበረ ነገረችህ ?

በጭራሽ !አባቷ ናቸው አንድ ቀን ተናደዱና ነግሩን ያወጡት „

" ልጃቸውን ለማግባት ስለ ጠየቅሁ ነው የተናደዱት ? ”

የለም ጥያቄህን ባለመቀበሏ እንጂ አንተን ብቻ ሳይሆ የጠየቋትን ሁሉ
መመለስ ልማድ ስለ አደረገችው ነበር የተናደዱት

“ አንተስ አይሆንም ብላህ ነበር ?

“ የለም ” አለ ካርላይል ሣቅ ብሎ“ ስጠይቃት ተቀበለችኝ

“ምን ይደረግ ዕድል ያስፈልጋል " መቸም ልጂቱ ለጥሩነቷ ጓዶኛ አይገኝላትም " ባገኛት ኖሮ ጥሩ ነበር "

“ አንዱን ለቆ ሌላውን አይሁንብኝና ቶርን ... ሁለተኛ ብንግናኝ እጠይቅሃለሁ ብዬ ሳሰላስለው የኖርኩት አንድ ጥያቄ ነበረኝ አንተ ስዌንስ መጥተህ የተቀመጥከው መቼ ነበር ?

ሻለቃ ቶርን ጊዜውን ሲያስታውስ ሆሊጆን በሞተበት ዘመን ሆነ "
“ ታዲያ በዚያን ጊዜ ቶርን የሚባል ሌላ የስም ሞክሸህ የነበረ ሰው ታስታ
ሳለህ ?

አንድ ሰው ያየሁ ይመስለኛል » አንድ ቀን ብቻ ስላየሁት አላውቀውም እንያውም በከተማው ነዋሪ አይመስለኝም ከከተማ ውስጥ አይቸው አላው
ቅም "

“ ታዲያ የት አየኸው ?”

“ ከስዌንስን ሁለት ማይል ያህል ወጣ ይላል " አንድ የመንገድ ዳር መጠጥ
ቤት ነበር ያየሁት " አንድ ቀን በፈረስ ስሔድ በጣም የሚያስፈራ ነፋስ የቀላቀለ
ዝናብ ያዘኝና ከዚያ መጠጥ ቤት ተጠለልኩ " ወዲያው አንድ አለባበስ መልካም
የትልቅ ሰው ወገን የመሰለ ረጂም ፈረሰኛ ተከትሎኝ ገባ " ዝናቡ ሲያባራ ቀድሞ
ወጣና ሔደ። ማን መሆኑን ጠየቅኩ " ሰዎች ሁልጊዜ በፈረስ እየሆነ ሲያልፍ ቢያዩትም ስሙን እንደማያውቁት ነገሩኝ » አንድ ሲጠጣ የነበረ ሰው ብቻ ካፕቴን ቶርን እንደሚባልና ከወደ ዌስት ሊን እንደሚመጣ የነገረኝን አስታውሳለሁ" ሆኖም
ሰውዬው የካፕቴን ቶርንን ስም ከማወቅ በቀር ሌላ የሚያውቀው ዝርዝር አልነበረም

ብታየው የምታውቀው ይመስልሃል ?” አለው ሚስተር ካርላይል "

“ አዎን ይመስለኛል መልኩ አንድ የሆነ ልዩ ገጽታ ስለነበረው ዛሬም በደንብ ትዝ ይለኛል ”

ምናልባት ባጋጣሚ ብታየው እኔም እንዳውቀው ለማድረግ ትረዳኛለህ
ቶርን የውሸት ስሙ ሳይሆን አይቀርም እኔ ትክክለኛ ስሙን ለማወቅ እፈልግ ነበር”
"ያለሁበት ቦታ ከሌሎች ረጅመንቶች የተለየ እሩቅ በመሆኑ ለዚህ አጋጣሚ
አይመችም እጂ ካጋጠመኝ በደስታ እፈጽማለሁ "

ሻለቃ ቶርንን ከሸኘ በኋላ ፡ እኅቱን ወደ ተወበት ከፍል ሊመለስ ሲል ጆይስ
"ጌታዬ ” አለችው “ ኢስት ሊን ውስጥ አንድ ለውጥ እንደሚኖር ሚስ ካርላይል ነገሩኝ እኔም አብሬአቸው ለመሐድ እፈልግ እንደሆነ ጠይቀውኛል"እርስዎን እስካማክር እንዲታገሠኝ ነርኩዋቸው "

“ አናስ ?”

እኔማ ሟቺቷ እመቤቴ አንድ ጊዜ ታመው የደከሙ ጊዜ ያኔውኑ የሚሞቱ
መስሏቸው እንደ ኑዛዜ አድርው ከልጆቻቸው እንዳልለይ አደራ ብለውኝ ነበር » እኔም ለመኖር እስከ ተፈቀደልኝ ድረስ እንደማልለይ ቃል
ገባሁላቸው" ስለዚህ
የሚደረገሙ ለውጥ የኔንም ኢስት ሊን ውስጥ የመቆየቴን ነገር የሚነካ እንዴሆነ ልጠይቅዎ ፈልጌ ነው ።

“ የለም ጆይስ . . . እኔም ከልጆቼ ጋር እንድትቆይ እፈልጋለሁ ” አላት።

ጥሩ ነው ጌታዬ ” አለችውና ፊቷ በደስታ ተሞልቶ ከሳሎን ወጥታ ሔዶች።...

💫ይቀጥላል💫
👍144😁1
😘😘 #ቃል 😘😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሁለት (2)


የማይክል እናት ማሪዮን ሂልያርድ የማይክልና የናንሲን ፍቅር ስትሰማ «ለየት ካለ ሰው ጋር ፍቅር ሲይዝህ ደግ እይደለም» ስትል ለልጅዋ እንደማስጠንቀቂያም እንደምክርም.-አድርጋ 'ነግራው ነበር ።* ማሪዮን ነገሯን የጀመረችው «ከሆነች ሰዓሊ ጋር ፍቅር ያዘኝ ብሎ ይንዘላዘላል ብለው ነገሩኝ» በማለት ነበር ።

ማሪዮን ያለችውን ትበል እንጂ ማይክል ናንሲን ያውቃታል ። ናንሲን ከማፍቀር የበለጠ ነገር እንደሌለ ያውቃል ። ናንሲ አፈቀረችው መባል ደግሞ ራሱን የቻለ ጽድቅ እንደሆነ ያምናል።
ማይከል ልጅም ጅልም ስላይደለ መጥፎና ጥሩን ለራሱ አሳምሮ ያውቃል ። እናቱ ልዩ ስላለችውም ቢሆን ናንሲ ከሰው የተለየች ፍጡር አይደለችም ። ልዩ የሚያደርጋት ነገር ግን አታጣም ። አንደኛው ናንሲ እንደሌሎች በሷ እድሜ እንዳሉ ልሻገረዶች ገና ተማሪ ፣ ገና እምትሆነውን ያልመረጠች ልጅ አይደለችም ሙያዋን መርጣለች ። ሰአሊ ናት ። ናንሲ እምትወደውን ሰው ለመምረጥ አንድ ቀን አንዱን ፤ በሌላ ቀን ሌላውን እየቆያየረች በመፈተንና በመፈታተን ላይ ያለች ልጅ አይደለችም ። የምትወደውን ወንድ ለማግኘትም በመባዘን ላይ አይደለችም ፤ መርጣለች ። ከምታፈቅረው ወንድ ጋር መኖር ጀምራለች ፤ ችኖራለች ። ዛሬ ለናንሲ ከማይክል ሌላ ወንድ አይታያትም። ናንሲ የተለየች ሴት ከተባለች ጠንካራ ፍጡር ፤ ንጹህ ልጅ በመሆኗ ብቻ እንደሆነ ይገባዋል ። ይህ ደግሞ ጉድለት አይደለም ። እንዲያውም ማይክል ምንም እንኳ ዛሬ ዛሬ የሚወደው ሙሉ እሷነቷን እንደሆነ ቢታወቅ በመጀመሪያ የወደዳት በዚህ ልዩ በሚያደርጋት ባህሪዋ እንደሆነ ያስባል ።

ማይክል ናንሲን ይወዳታል ። ናንሲም ማይክልን ታፈቅረዋለች ። የሁለቱ ፍቅር ሚዛኑ የተስተካከለ ነው። ከተገናኙ ሁለች ዓመት ሞላቸው ። ይህን ያህል ጊዜ አብረው ሲኖሩ መሰልቸት የሚሉት ስሜት አይታበት አታውቅም ። ዛሬማ ተዋውቀዋል ።

የልጅነት አጉል ምኞቱን ፤ የልጅ ሸረኝነቱን ፤ አስቂኝ ምስጢሮቹን፤ መሰረት የለሽ ስጋቱንና ፍርሃቱን ይህንን ሁሉ አካፍሏታል። የሷንም አካፍላዋለች ። ዛሬ ደግሞ ምኞታቸውም ፤ ስጋታቸውም፤ ደስታቸውም ፤ ሐዘናቸውም የጋራ ነው። ማይክል የሚባል አዲስ ሰው የለም ። ርግጥ ነው ከእናቱ ጋር አላስተዋወቃትም ። ቤተሰቤ የሚለውን ነገር በዓይኗ አላየችውም ። ግን ደግሞ እናቱም ሆነ ቤተሰቡን ቁልጭ አድርጋ ታውቃችዋለች፡፡ ያን ቤተሰብ በሚገባ ከማወቋ የትነሳ በታላቅነታቸው ታከብራቸዋለች ። ስለሷ ያላትን አስተያየት እያወቀች ማሪዮንን ሳይቀር ታከብራታች።

ማሪዮን ሂልያርድ በመላው የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ውስጥ ታዋቂነትንና ዝናን ያተረፈው «ኮተር ሂልያርድ የሕንፃ ንድፍ ጥበብ (አርክቴክቸር) ሥራ ተቋራጭ ድርጅት » ዋና ሥራ አስኪያጅ ናት ። ማይክል «ኮተር ሂልያርድን» ለመምራት ብቁ ሲሆን «ዙፋኑን» ይረከባል ። ሥራውን በሚገባ እንዲያካሂድ « ኮተር ሂልያርድን» በይበልጥ እንዲያገዝፍ እየተኮተኮተ ነው ያደገው ።የተማረውም ድርጅቱ የሚፈልገውን ዓቢይ ሙያ ነው… የሕንፃ ንድፍ ጥበብ ። በቅርቡ ከታወቀው የሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ በዚሁ ሙያ የዶክሬት ዲግሪውን በመቀበል ይመረቃል ።

ታዲያ የማይክል ስጋት «ለዚህ ታላቅ ኃላፊነት ብቁ ሆኘ አልገኝ ይሆን ?» የሚል ነው። ናንሲ ግን ያላንዳች ጥርጥር ታውቃለች ። ማይክል «ኮተር ሂልያርድን» በሚገባ ሲመራ ይችላል ። ያም ብቻ ሳይሆን «ኮተር ሂልያርድ» በማይክ «ዘመነ መንግሥት» እጅግ ይበለፅጋል ። ማይክ ጠንካራ ሰው ነው። ግትርም አይደለምና ሁሉን ልፍጀው ባይ አይደለም ለአመራሩ ከማይክ የተሻለ ሰው ከየት ሊመጣ ትላለች ።

ማይክም ቢሆን ይስጋ እንጂ ... ያለውን ኃይል ሁሉ በሚገባ ከተጠቀመ አደራውን የማይወጣበት ምክንያት እንደማይኖር ያምናል ። ሆኖም ገና አልገባበትምና… ሰው ደግሞ የማያውቀው ፤ ያልገባበት ነገር ያስፈራዋልና ይፈራል ፤ ይገነግናል ።
ምክንያቱ ? በቂ ምክንያት አለው ።

« ኮተር ሂልያርድ » ባንድ ትውልድ የተገነባ ድርጅት አይደለም ። ማይክል ሦስተኛው ትውልድ ነው ። በዛሬ ስሙ ሳይሆን «በኮተር» ብቻ ይህን ድርጅት የጠነሰሰው የማይክል አያት የማሪዮን አባት ሪቻርድ ኮተር ነበር ። ሪቻርድ ኮተር የሕንፃ ንድፍ ጠቢብ (አርክቴክት) ነበርና ድርጅቱን መሠረተ ። ይህ ከሆነና ድርጅቱ እያደገ በመሄድ ላይ እንዳለ የማይክል አባትና እናት ተዋወቁ; ተፋቀሩ ። ሊጋቡ ወሰኑ። የኮተርና የሂልያርድ ቤተሰብ በጋብቻ ተሳሰሩ ። የእነዚህ የሁለቱ መጋባት የዛሬውን ታዋቂ ድርጅት ፈጠረ… “ኮተር ሂልያርድን”። የማይክል አባት ሚስተር ሂልያርድም እንደ አማቱ እንደ ሪቻርድ ኮተር የሕንፃ ንድፍ ጠቢብ ነበረ። የሂልያርድ ቤተሰብ የታወቀ ሀብታም ቤተሰብም ስለነበረ ድርጅቱ የደለበ ገንዘብ በገፍ አገኘ ።ትልቅ ስሙን ተከለ ።

እንግዲህ ይህን በሁለት ታላላቅ ቤተሰቦች ኃይልና ጥረት የተመሠረተ ግዙፍ « መንግሥት» መቀበል በቸልታ የሚታይ አልነበረም ።

ከላይ እንዳልነው ናንሲ ሙሉ በሙሉ ትተማመንበታለች ይህንንም ትነግረዋለች ። እሱም ያምናታል ። እሱም በበኩሉ በሷ ይተማመናል ። ምንም እንኳ አስተዳደጓ አመቺ ባይሆን ናንሲ ብዙ ትረዳኛለች ይላል በልቡ ። ይህን በልቡ የሚያደርገውን ጭውውት በመቀጠል… ባንድ በኩል በጣም ታላቅ ሰዓሊ ስለሆነች «ኮተር ሂልያርድ» ደግሞ ሰዓሊዎች ስለሚያስፈልጉት በሙያዋ ታግዘኛለች ። በሌላ በኩል ደሞ ንቁና አስተዋይ ናትና ቤቴን በሚገባ ትመራልኛለች ። አስተዳደጓ? ያ! ለናንሲ ምንም አይደለም ይላል ። ተገናኝተው ከተካፈሏቸው ሐሳቦች ብቻ በመነሳት ስለበለጸገ ቤተሰብ አኗኗርና አስተዳደር ያላት አስተያየት ዛሬ እንኳ የሚያኮራ እንደሆነ ተገንዝቧል ።

ናንሲ ፊት ፊት እየጋለበች ማይክልም ቢስክሌቱን በፍጥነት እያሽከረከረ ፣በየፊናቸው ሐሳባቸውን እያውጠነጠኑ መንገዱን ተጋትረውታል ። ስለ ናንሲ አእምሮ ክፍትነት እያሰበ በኩራት ተሞልቶ ሲያያት ፤ ዞር ብላ አገጩን በትከሻዋ ላይ አሾልዳ አየችውና «በል ድረስብኝ» በሚል መልክ ስቃ የቢስክሌቱን መርገጫ በኃይል ትመታ ጀመር ። በፍጥነት ሊነዳና ሊደርስባት ከጀለ ። ሆኖም በርቀት ሲያያት የተስተካከለ ቅርጽ ፤ ፈጣን ውብ እግሮቿ ልዩ የሆነ ስሜት አሳደሩበት ። ዞራ ፈገግ ስትል ደስታው ከመጠን እለፈ ። ሰውነቱን ወረረው ሂድ ... ሂድ ድረስባት የሚል ጉትጐታ ተሰማው ። ከደረሰባት በኋላ … ከዚያ በኋላ ብስክሌቷን ይዞ ከብስክሌቱ ላይ ወርዶ ከብስክሌቷ ላይ ያወርዳትና እመስኩ ላይ… እዚያ ደስ እሚል አረንጓዴ ምንጣፍ ላይ . . . እዚያ ላይ ይጥላትና ከዚያ በኋላ ልክ እንደትናንት ማታ !.... እንደ ማታው ! ልክ እንደ...

ይህን ሐሳብ በግድ አስወጣው ፤ ከአእምሮው ውሰጥ ። ሐሳቡ ሊመለስ ሲታገለው ፤ ብስክሌቱን በኃይል እየነዳ በጥሪ ድምፅ እንዲህ አለ፤ «የኛ ሐሳበ ቢስ … ይህን ያህል… ›› አለ ዞራ ሳቀችና ፍጥነት ጨመረች። እሱም ፍጥነት እየጨመረ… ‹‹ጠብቂኝ እንጂ! ጅል» አለ ። ብዙ ጊዜ ሳይፈጅ ደረሰባት ። ሁለቱም በጣም ደክመው ነበረና መነጋገር አልቻሉም ። ስለዚህም ፍጥነት ቀንሰው ፤ ጸጥ ብለው ጎን ለጎን በመሆን ጉዟቸውን ቀጠሉ ። በዚህ ሁኔታ ሲጓዙ ሳለ ድንገት ተያዩ ። እጁን ዘረጋላት እጅዋን ዘርግታ ጣቱን ነካ አድርጋ ለቀቀችው ። ትኩር ብሎ እያያት የደስታና የአድናቆት ሲቃ በተሞላ ድምፅ
👍262
«ናንሲ» አላት
«ናንሲ ዛሬ ደሞ እንዴት ቆንጅዬ ልጅ የሆንሽ መሰለሽ?» አላት ።

ድምጹ ነፋሻውን የመጸው ወራት እየር እየሰነጠቀ ሲደርሳት የሰራ አካላቷ ተፍነከነከ ። በአካባቢያቸው ያለው አለም ምንም ነገር ያልበከለው ፤ ንጹህ ወላንሳ በመሆን ደስታዋን ፤ ደስታውን ፤ ደስታቸውን አደመቀው ።

«ናንሲ !» አላት በዚያው ድምፅ «ናንሲ ! ምን ያህል እንደምወድሽ ብታውቂ !» «እይጠፋኝም !፤ አይጠፋኝም ሚስተር ሂልያርድ» አለች ናንሲ በውሸት ጠብ ድምፅ ፤ ማይክል በማለት ፋንታ እንደ ሩቅ ሰው ሚስተር ሂልያርድ እያለችው ።

«አይጠፋኝም ! ግን ፍቅርህ የእኔን ፍቅር ከፊሉን እንኳ አይሆንም» አለች ። የውሸት ብሽቀት በሽቆ፣ «ባትናገሪ ይሻልሽ ነበር ። ስትናገሪ ነገር የማይገባሽ መሆንሽ ቁልጭ ብሎ ይታያል» ሲል ተናገረ። ይህን የብሽሽቅ ጨዋታ በመሻት ነበር ያን መልስ የሰጠችው እንጂ እንደሚወዳትማ ታውቃለች ። ምን ያህል እንደሚወዳት ያወቀችው ፤ ወደኋላ ስታስበው ፤ በመጀመሪያ የተገናኙ እለት ነበር።. . . ያን ለት «ወይ ለኤግዚብሽን ያቀረብሻቸውን ስዕሎች ሁሉ ሽጭልኝ ፤ እምቢ እምትይኝ ከሆነ ዶግሞ የለበስኩትን ልብስ ሁሉ አውልቄ ጥየ ባደባባይ በጸሐይ ራቁቴን እሄዳለሁ» ሲል ኩስተር ብሎ የዛተው ትዝ አላት ። እንዲያ ያላት እለት ነበር እንደሚወዳት የተረዳችው ።
«ብስል ሰው ብትሆኚ ፍቅሬ ያንችን ሰባት እጥፍ እንደሆነ ይገባሽ ነበር» አለ ።
«ሰባት እጥፍ ? »
«አዎ!»
«አትዋሽ ! በጭራሽ የሌለ ነገር !»
«ያንችን...»

ነገሩን ሳይጨርስ ፍጥነት ጨምራ ፈትለክ አለችና ዞራ ከሳቀች በኋላ ኮስተር በማለት «ማይክል ! ያንተ ፍቅር መጠን አለው ። የኔ ግን መጠን ስለሌለው ፤ ሰባት ጊዜ ፤ መቶ ጊዜ፣ተብሎ አይለካም» አለች ። «እንዴት አወቅሽ ? » አላት ፤ እሱም ቢስክሌቱን በኃይል እየነዳ … ሊደርስባት እየተቃረበ ። ዞራ አየችውና…
«ዛር ነገረኝ |» ብላው እንደገና ፍጥነት ጨምራ ራቀችው” ርቀታቸው ሳይቀንስም ሳይጨምርም ፊትና ኋላ ሆነው ጉዞ ጀመሩ ። በመካከላቸው ያለው ርቀት አካሏን ለሁለተኛ ጊዜ እንዲማትር አደረገው ። እንደገና ሰውነቱ በደስታ ተሞላ ሆኖም አሁን እመስኩ ላይ ሊጥላትና . . . አላሰበም ። ለዘለአለም የሱ እንድትሆን ግን ተመኘ ። የኔ ማድረግ አለብኝ አለ… ይህ ሐሳብ ወደ ዛሬ ጧት ውሳኔው መራው ።

ፍጥነቱን ጨመረና ደረሰባት ። ቢስኪሌቶቻቸው ተጠጋግተው መንገዱን ተያያዙት ። እንደደረሰባት ስታውቅ ፍጥነቷን ጨምራ ልታመልጠው ከመርገጫው ጋር መታገል ጀመረች። እግሮቿ እንደመቂናጥ ብቅ ጥልቅ ይላሉ ። ጥረት ላይ ነበረችና ዞር ብላ አላየችውም ። እሱም ወደ ኋላ ላለመቅረት ፍጥነቱን ጨመረ ። በዚህ ሁኔታ ሲጓዙ ከቆዩ በኋላ መንገዱ ተጠመዘዘ ። መጠምዘዣውን እንዳዩ ፍጥነት ቀነሱ ። መጠማዘዣውን እንደጨረሱ ገና ፍጥነትም ሳትጨምር መሪውን ባንደኛው እጅ ብቻ ይዞ በሌላኛው እጅ ጀርባዋን መታ መታ እያደረገ
«ሚስዝ ሂልያርድ !» አላት «ሚስዝ ሂልያርድ እንዴ ይቅርታ አድርጊልኝ»

እንዲህ ሲላት እፍረት ቢጤ ተሰማት ። የምንተ እፍረቷን ፈገግ አለች ። መልስ አልሰጠችውም ። እየቆየ የምንተ እፍረት ፈገግታዋ ወደ ተስፋ ፈገግታ እየተለወጠ ሔደና ፊቷ በራ ። ምክንያቱም እሱ ማይክል ሂልርድ ሲሆን ፤ እሷን ሚስዝ ሂልያርድ ብሎ መጥራት ማለት ባልና ሚስት ሆነናል ፤ ተጋብተናል ማለት ነው ። ዞራ አየችው ።
« ምነው አየሽኝ ? ያልኩትን አልሰማሽም እንዴ ሚስዝ ሂልያርድ? »
«ልጅ ሳይወለድ ለልጁ ስም ማውጣቱ አጉል ችኮላ አይመስልህም ማይክ ?» አለች ። ፍቅራቸውን አትጠራጠርም ። ግን ደግሞ ስጋት አለባት ። ስጋቷ የማይክል እናት ማሪዮን ሂልያርድ ናት ። «ማሪዮን እንድንጋባ ትፈቅድልን ይሆን ?» የሚለው ጥያቄ ሁልጊዜም በናንሲ ማክአሊስተር አእምሮ ውስጥ እንዳለ ነው ። «ምንም ያቻኮልኩት ነገር ያለ አይመስለኝም» አለ ማይክል። ዝም አለች ። «ልጅ አይደለሁም ። እልቸኮልኩም ። ውሳኔ ላይ የደረስኩት ነገሩን አውጥቼ አውርጄ ነው » አለ ፤ነገሩን በመቀጠል ። የለም የለም ከመወሰኑ በፊት ቢያንስ ቢያንስ ከእናቱ ጋር መመካከር አለበት አለች በሐሳቧ።

«እሰብኩበት ። ወሰንኩ ። ናንሲ በጣም ታስፈልጊኛለሽ » አለ ። ማይክል ይህን ቢል አዲስ ነገር አልተናገረም ። ሁለቱማ እንደሚጋቡ ከወሰኑ ቆይተዋል ። የሰርጉን እቅድ ሁሉ አውጥተዋል ። ይህ የታወቀ ነገር ነው ። የናንሲ ሐሳብ ቀጠለ ። « የስርጋችን ቀንም» አለ ማይክል « የዛሬ አስራአምስት ቀን እንዲሆን ወስኛለሁ ። ያም ማለት ዲግሪየን የምቀበልበት ቀን መሆኑ ነው

እሷ ቤተሰብ ስለሌላት ድግሱ የአንድ ወገን ብቻ እንደሚሆን ካሰበበት በኋላ የሱ ድግስም ቻቻታ የሌለበት ፤ የልብ ጓደኞቹ ብቻ የሚገኙበት እጥር ምጥን ያለ ሰርግ እንደሚሆን ነገራት
«ለምን ማይክ ?» አለችው ።
«ምክንያቱም በጫጫታ የምናሳልፈው ጊዜ የለንም ። ብቻችንን መሆን ያስፈልገናል » ብሎ መለሰላት ። ሁለቱም ዝም አሉ። «ዛሬ ጧት አንድ ነገር እነግርሻለሁ ብዬ ረሳሁትና እስካሁን ሳልነግርሽ ቆየሁ።... ኒው ዮርክ ልሄድ አስቤአለሁ ። ከማሪዮን ጋር ስለሰርጋችን ለመመካከር » አለ ፤ ድንገት ። ናንሲ ዝም አለች ። «ዛሬውኑ ልሄድ ነው የወሰንኩት
«ዛሬውኑ! »
« አዎ !... ዛሬ ማታ ። እደርሳለሁ »
ይህን ሲል የብስክሌቷን ፍሬን ያዘች ። በአላምንህም አስተያየት እያየችው
«ዛሬ?... ዛሬ ማታ ፤ ዛሬ ማታ ?» አለች ። ራሱን በአዎንታ ነቀነቀ። ሁለቱም ቆሙ።
«ማሪዮን እምትስማማ . . . ይመስልሃል ?» አለች በመጠራጠር… መልሱን ለመስማት በመፍራት።
«አትጠራጠሪ ። ትስማማለች ።» አለ። በጥርጣሬ አይን አየችው።የተናገረውን እሱም እራሱ ያመነበት
አልመሰላትም ።
«ጋብቻውን ላትፈቅደው ትችላለች ።ግን ደሞ ሚስት ልምረጥልህ ለማለትም አትደፍርም ። ይህን ያህል አውቃታለሁ ። ስለዚህ አታስቢ ።»
ነገሩ እንኳ እሷን ብቻ አይደለም ራሱን ማይክልንም ያሳስበዋል ። ሴትዮዋ ማሪዮን ሂልያርድ ናታ ! ማሪዮን የማይክልንና የናንሲን ጋብቻ ካልፈቀደችው እንዳይጋቡ ከመከልከል አትመለስም ። ምክንያቱም ለማሪዮን ከራሷ እምነት ውጪ ምንም ነገር የለም። ይህንን ደግሞ ከናንሲ ይበልጥ የሚያውቀው ማይክል ነው ። ማሪዮን ሲጀመር ጀምሮ የሁለቱን በፍቅር መተሳሰር አልወደደችውም ።

ለረጅም ጊዜ ማሪዮን ያችን ሰአሊ ካልተውክ እረግምሃለሁ ፤ እክድሃለሁ ፤ ውርስህን አፈርሳለሁ ስትልና ስታስፈራራው፤ ማይክል የመጣው ፤ይምጣ የቻልሽውን ሁሉ አድርጊ ናንሲን ግን አልተውም ፤ ሲል ደብዳቤም መፃፍ፡ ስልክም መደወል ሲያቆም ፤ ጠርታ ስታባብለው ፤ የተለያዩ ምርጫዎች ስታቀርብለት ፤ቆንጆ ከሚባሉት የደህና ቤተሰብ ሴቶች ልጆች ጋር ስታስተዋውቀው ማይክል ግን ሁሉን ችላ ብሎ ወደናንሲ ሲመለስ ፤ ናንሲን እንደሚወድ ደጋግሞ ሲነግራት ስታስፈራራው ዛሬ ፤ ዛሬ ያ ሁሉ የለም … ዛሬ፤ ዛሬ ማሪዮን ፤ ናንሲን ተቀብያለሁ አስተዋውቀኝም አትል ፤ ናንሲን ካልተውክ ! ብላም እታስፈራራው ፤ ያለፈው ስህተትም አይነሳ ፤ የዛሬው ሁኔታም አይወጋ፣ ዝም ዝም ሆኗል።
👍23😱21
ይህ ደግም ናንሲን ያናድዳታል ። የማሪዮን ዝምታ ናንሲ የለችም የማለት ያህል የገነነ ነበርና ። እያሉ እንደሌሉ መቆጠርን ያህል ደግሞ የሚያናድድ ነገር የለም ። ግን መቼም ቢሆን ፤ምንም ዓይነት ሀኔታ ቢፈጠር፤ የሰው ልጅ አንድ ቀዳዳ ፈልጐ ተስፋ ማየት ይወዳልና ናንሲ አንዳንዴ ተስፋ ታደርጋለች ። የማሪዮንን ዝምታ ፤ መቀበል ነው ብላ ታስባለች ። መቀበሏን እንዳትገልፅ ባለፈው የፈፀመችውን ድርጊት እያስታወሰች ስለምታፍር ነው ትላለች ። ይህ ሃሳብ ሲመጣ ክፉ ነገርን ሁሉ በመጣስ መልካም ራእይ ታያለች።. … ማሪዮንና እሷ ተስማምተው ፤ ማይክል ሲደሰት ፤ ማይክል የሚፈልገውን ሁሉ እየተማከሩ ሲያደርጉለት… የሚወደውን ልብስ ሲገዙለት ፤ የሚወደውን ምግብ ሲያበስሉለት... ይታያታል ። ሃሳብ በዚህ በኩል ወደውስጣዊ ቁስሏ ይመራታል ። ያለ እናት ማደጓን ታስታውሳለች ። ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር ከተስማሙ ግን ችግሩ ሁሉ አይኖርም ። ማሪዮን የማይክል ብቻ ሳይሆን የናንሲም እናት ትሆናለች ። ተፈጥሮ ናንሲን የነፈገቻችን የእናት ፍቅር ማሪዮን ትሰጣታለች ።

ወዲያው ጨለማ ሃሳብ. . . እንደ ልጅ መፈቀር ቀርቶብኝ እንደሰው ባስታወሰችኝ ! ማይክል ግን የማሪዮንን ዝምታ እንደመቀበል ነው የቆጠረው። ከዚህ በፊት ይህንኑ ለናንሲ ነግሯት ነበር ። «ታዳያ ለምን ተቀብያለሁ እትልም» ብላው ነበር ናንሲ ። «አፍራ ነው... አየሽ ስንጀምር ባደረገችው ነገር አፍራለች ። ስለዚህ ይቅርታ ከመጠየቅ የጋብቻ ፈቃድ ሲጠይቁ ፈቅጃለሁ ማለት ይቀለኛል ብላ ነው ፀጥ ያለችው» ሲል መለሰላት ።
«እኔም አንዳንዴ እንደሱ ይመስለኛል» አለች ናንሲ « ግን አላምንም ››
« አልፈቅድም ብላ ምን ትፈይዳለች ? » አላት ማይክ እያቋረጣት ።
« ካልፈቀደች ልንጋባ አንችልማ !»
«ለምን ? ልትነግሪኝ ትችያለሽ ? ለምን ?»
«ካልፈቀደች !? . . .» ብላ ምን ማድረግ ይቻላልን ትከሻዋን ነቀነቅ በማድረግ ገለፀችለት ። «ሞኝ አትሁኝ ናንሲ» አላት ። « እኔም አንችም ለአካለ መጠን ደርሰናል ። ሕጋዊ የሆነ ነገር ሁሉ በፈቃዳችን ልንፈጽም መብት ያለን ሰዎች ነን ። ስለዚህ አይሆንም ካለች መኪናችን ውስጥ ገብተን ወደ አንድ ፍርድ ቤት መጓዝ ነው። በሕግ እንጋባለን አየሽ » ያንለት ያነጋገሩን ገራገርነት በማጤን ብቻ ሳቀች። ይህ እንዲህ ቀላል አድርጐ ያቀረበው ሃሳብ ግን ከማንኛውም ሰው ይበልጥ አስቸጋሪ ሆኖ የሚታየው ለሱ ለራሱ ለማይክል ነበር። ለማይክል ግማሽ ሕይወቱ « ኮተር ሂልያርድ » አይደለምን ።

እጅዋን ያዝ ሲያደርጋት ክሐሳቧ ተመለሰች ። «እንዴት ቆንጆ ነሽ!» አላት አይን አይኗን እየተመለክተ። ደካማ ፈገግታ አሳየችው ። «በጣም እወድሻለሁ!.. . የኔ እመቤት !» አለ። «ማይክ . .. በጣም እወድሀለሁ» አለችው ። ከብስክሌቷ ወርዳ ቆመች ። እሱም ወረደ ። ገጽታዋም ፤ አይኗም ጥያቄ ይታይባቸዋል ። ጭንቀት ይነበብባቸዋል ። አቅፎ ሳማት ። የገፅታዋና የዓይኖቿ ጥያቄ ተሰረዘ ። በሁለቱም ልብ ውስጥ የሰፈረው ጥያቄና ጭንቀትም በልባቸው ውስጥ ተዳፈነ ። ያን ጥያቄ ሊያጠፋ የሚችል የለም… ካላንድ ሰው ፤ ካለማሪዮን ሂልያርድ ። ያች ሴት ካልራራች የሁለቱም ልብ በተዳፈነው ጥያቄ ይግላል ። ከብስክሌቷ ወርዳ ብስክሌቷን ለቅቃ እቅፉ ላይ አረፈች ።

‹‹ ማይክል የማሪዮንን ሆድ ቢያራራልን … ቢረዳን » አለች ። «አይዞሽ ! ይረዳናል ። ሁሉ ነገር ቀላል ሆኖ ነው የምናገኘው እመኝኝ» አላት ። ይህን ብሎ በቀልድ ቁጣ ፤ «ምንድነው ነገሩ ፤ አሁን ጉዞ እንቀጥላለን ፤ ወይስ እዚህ ቆመን ማደር ሊኖርብን ነው ? » አለ ። ገዟቸውን ሲቀጥሉ ማሪዮን ሂልያርድን የረሷት ይመስላሉ ። ሆኖም ማሪዮን ከነፍሳቸው አልተሰረዘችም ። ማሪዮን አንድ ሰው ብትሆንም ትልቅ ተቋምም ናት ። በቀላሉ አትሰረዝም ። ማሪዮን በማይክል ሕይወት ውስጥ የቆመች ትልቅ ምሶሶ ናት ። ዛሬ ዛሬ ደግሞ በናንሲ ሕይወት ውስጥም ጎልታ መታየት ጀመረች ።

በብስክሌታቸው ላይ ሆነው ለሙን መሬት እያቋረጡ እሽቅድምድሙን ተያያዙት ። አንዴ ስትቀድመው ወዲያው ሲደርስባት ጎን ለጎን ሲጓዙ እንደገና ስትቅቀድመው ዞራ ስታሾፍበት ሊደርስባት ሲያባርራት ። እንደለቆ ጥጃ ሲፈነጥዙ … » በሌላ ጊዜ ፀጥ ብለው ጎን ለጎን ሲጓዙ . . . እነሱም ገሰገሱ ፤ ፀሐይም የሰማዩን ዳገት እየተንፏቀቀች ወጣች ። ወደ ሪቨር ቢች ሲቃረቡ ተሲያት ተቃርቦ ነበር ። ከፊት ለፊታቸው የመጣው መኪና ፍጥነቱን ሲቀንስ ቤን አቭሪ መሆኑን ተመለከቱ ።
‹‹ ታዲያስ?» አለ ቤን ።
«ሃይ ቤን ! » አለች ናንሊ። ሰላምታ ተለዋወጡ። ከቤን አቭሪ ጎን አንዲት ልጅ ተቀምጣለች-። ናንሲም ሆነች ማይክል ይህችኛዋን ልጅ አይተዋት አያውቁም ። ግን ከየት አገኛት ? ብለው አልተደነቁም ። ቤን አቭሪ ዛሬ አብሯት ከወጣት ልጅ ጋር ነገ ተመልሶ አይወጣም ። ይህን ባህሪውን ናንሲም ማይክልም ያውቃሉ ።
«ወዴት ነው?ወደ ባዛሩ የምትሔዱ ይመስላል» አለ ቤን። ሁለቱም ዝም አሉ ። ሀሳባቸው እልጅቷ ላይ ነበር ። ይህን የተገነዘበው ቤን ቶሎ ብሎ አስተዋወቃቸው ፡፡
«ጃኒት ትባላለች … ናንሲና ማይክል ይባላሉ » አለ።
‹‹ ባዛሩ እንዴት ነው ? » አለ ማይክል ከትውውቁ በኋላ። እንግዲህ እንደየሰዉ ነው ። ግን » አለና እባዛሩ ውስጥ ያለውን ነገር ይዘረዝርሳቸው ጀመር “ በጫወታ አሸንፈው ያመጧቸውን ዕቃዎች ፣ የገዟቸውን ምግቦችና መጦችም ነገራቸው … ገለጻውን ሳይጨርስ … «በቃ በቃ … እንሔዳለን ። በቂ አድርገህ እንድንሔድ ገፋፍተኽናል » አለ ማይክል ። ከዚያም ወደ ናንሲ ዞሮ « ምን ይመስልሻል ደረስ ብለን ብንመለስ ›› ሲል ጥያቄ እቀረበላት ።

«በጣም ደስ ይለኛል » አለች ናንሲ ። « እናንተስ አብራችሁን አትመለሱም ቤን? » እንደጠየቀች መልሱን አገኘች ። ቤን አቭሪ ጎምዥቷል ። ጃኒትም ብትሆን ረሀቡን ለማርካት የጓጓች ትመስላለች ። የሁለቱን ሰዎች በሥጋ የመፈላለግ ችኮላ ስትገነዘብ ናንሲ ማክአሊስተር እንደመሳቅ ቃጣት ። ቢሆንም ሳቋ አካሏን ዘልቆ ሳይታይ አፍና አስቀረችው ።
«እኛ እንኳ አረፈድንበት » አለ ቤን « እሁን ወደ ቤት፤ደክመናል ። በስንት ሰዓት የወጣን መሰላችሁ … ጧት ፤ በአሥራ ሁለት ሰዓት » ይህን ብሎ ፤ .
« ግን ማታ ፒዛ መብላት የሚፈልግ ካለ ቤት ድረስ ብቅ ማለት ይችላል › ሲል ጨመረ ። ማይክልና ቤን ጎረቤት ናቸው።
«ለመሆኑ እራት የምትበሉት የት ነው ዛሬ?» ቤን ይህን ሲጠይቅ ናንሲ
‹‹ ሲኛር ፤ ዛፊ እራት የምንበላው የት ነው? » ስትል ማይክልን ጠየቀች ። ማይክል ራሱን በአሉታ ነቀነቀና ፡… «ጉዳይ አለኝ . . - እራት ላይ አንገናኝም» ሲል በደፈናው መልስ ሰጠ ። «ሆኖም» አለ ቀጠለና « በሌላ ቀን ለፒዛው ፕሮግራም ልንይዝ እንችላለን »
ጉዳይ አለኝ ? ቆርጦ ማሪዮንን ሊያነጋግራት አስቧል ማለት ነው ።

‹‹ እሺ እንግዲያ. . . እንዲያ ከሆነ በቸር ይግጠመን ›› አለ ቤን። ጂኒትና ቤን ለስንብት እጃቸውን አወዛወዙ ። ከሄዱ በኋላ ፤ «እውነት ዛሬ ማታ ልትሔድ እስበሀል ? » አለች ናንሲ። «እንዲህ , አይነት ፌዝ የምሞክር ይመስልሻል ባንች ላይ?» አላት ጥያቄዋን በጥያቄ እየመለሰ። ፤ «አይመስለኝም፤ ሆኖም … ››
👍20🎉1
«የኔ እመቤት ምንም የሚያ ስጨንቅሽ ነገር የለም ። እርግጠኛ ነኝ ማሪዮን ትስማማለች። እርግጠኛ ነኝ ሁሉ ነገር እንዳሰብነው ይሆናል» አለና ድምጹን ወደ ደስታ ቅኝት ለውጦ « በነገራችን ላይ ማሪዮን ቤንን ልትቀበለው ነው፣፤ ስራ ለመግባት አመልክቶ እንደነበር ነግሬሻለሁ አደል ?» !
‹‹ ነግረኸኛል።»

«በጣም ጥሩ ሆነ አየሽ። ስራውን የምንጀምረወም ባንድ ቀን ነው። የምንሰራበት ቦታ ግን ይለያያል» ማይክ ይሀን ለናንሲ ሲነግር ጉዳዩ ለራሱ እንጂ ለእንድ ሌላ ሰው የተፈፀመለት አይመስልም ነበር። ቤንና ማይክ የተዋወቁት እዚሁ ሀርቫርድ ውስጥ ነበር … የመጀመሪያ አመት ተማሪ ሆነው ። የኮሌጅ ትምህርታቸውን አብረው ጨረሱ፡፡ ለድህረ ምረቃ ፕሮግራም ሁለቱም ቀጠሉ ። በነዚህ ዓመታት ውስጥ ባህሪ ለባህሪ ተዋውቀዋል ። ዛሬ እንደወንድማማች እንጂ እንደጓደኛ አይደሉም ።

ቤንጃሚን (ቤን) አቭሪን ከማሪዮን ጋር ካስተዋወቀው ቆይቷል ትምህርቱን ጨርሶ ሲመረቅ ቤን ለማሪዮን ማመልከቻ እንዲያስገባ ነገረው። ቤን እንደተባለው አደረገ ። ማይክ ስለቤን ጉብዝና ለእናቱ ተናገረ ። በመጨረሻ ማሪዮን ቤንን እንደተቀበለችው ለማይክል አስታወቀች።
«ቤን ስራውን እንዳገኘ አውቋል አለች ናንሲ። ማይክ በአሉታ ራሱን ነቀነቀና… «ከአሁኑ ቢያውቅ ደስታው ይበላሽበታል ብዩ አልነገርኩትም ። በድንገት ነግሬ ላስፈነድቀው አስቤአለሁ» ናንሲ ገረማት ።
«ምን አይነት ሰው ነህ ማይክ? በጣም ደግ ነህ ። አንተን ስለወደድኩ ምን ያህል የታደልኩ ሰው ነኝ እላለሁ» «አመሰግኖለሁ ሚስዝ ሂልያርድ›› «እባክህ እንዲያ ብለህ አትጥራኝ ማይክ?» «ለምንድነው እንዲያ ብዬ የማልጠራሽ? ምክንያቱን ልትነግሪኝ ትችያለሽ ? ይልቅስ ካሁኑ ተላመጅው ። አዲስ ስም በቀላሉ አይለመድም››
«ሁሉም ነገር ቢሆን ይለመዳል ። ሲሆን የማይለመድ ነገር የለም» አለች ። ቀጥላም «ለጊዜው ግን ናንሲ ማክአሊስተር ነኝ። ሚስ ማክአሊስተር ብትለኝ በቂ ነው» ስትል ጨመረች። « ጊዜ የለንምኮ የኔ እመቤት ። ለአሥራ አምስት ቀን እድሜ ማክአሊስተር ብልሽ ግፍ አይሆንም !» ይሆን ብሎ ድምጹን ወደ ጨዋታ ቅኝት ቀየረና…
«አሁን ወንድና ሴቱ ይለይ!...ባዛሩ በር ድረስ እሽቅድምድም እንገጥማለን። ይለይ!›› አለ ።
«ይለይ!» አለች።

ትንፋሽ እስከሚያጥራቸው ድረስ በፍጥነት መንዳት ጀመሩ ። «ለረጂም ጊዜ ማንም አልቀደመም ። በመጨረሻ ማይክል ከናንሲ ግማሽ ደቂቃ ቀድሞ ደረሰ « ሁለቱም ከላይ የተነጋገሩትን ረስተው ድንገት በተፈጠረው ደስታ ታጥበው ፣ ፀድተው ነበር ። ቢስክሌታቸውን ዛፍ አስደግፈው ወደ ባዛሩ ቅጥር አመሩ ። በዚህ ጭር ባለ ገጠር ማንም ቢስክሴት እንደዶማይሰርቅ እርግጠኛ ነበሩ።
ይህ ሁሉ ከሆነ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ኮርን (ከነቆረቆንዳው ተቀቅሎ በቅቤ የተዘፈዘፈ በቆሎ) ይዘው መጋጥ ጅመሩ ። ቅቤው እጃቸውን አረስርሶ ሲንጠባጠብ ይታይ ነበር ። በቆሎ ቅቅል በቅቤአቸውን ካስገቡ በኋላ « ሆት ዶግ» በብዛት ጎስጎሱ። በላዩ ላይም ቀዝቃዛ ቢራ ቸለሱበት ። ናንሲ በዚህ አላበቃችም ። ጣፍጭ የሆነና እንደ ጀላቲ መያዣ እንጨት ያለው ግን ጠንከር ያለ ሳይሆን ጥጥ የሚመስል ካንዲ ፍሎስ የሚሉት ጣፍጭ ነገርሩ መብላት ቀጠለች፡፡ ካንዲ ፍሎሱን ስትልስ ፊቷና ጉንጯ ፤ ከንፈሯና አፍንጫዋ ተቀባብተው ነበር ።

«ልጅ መሆንሽ ነው?!... አይቀፍሽም› እላት ማይክል «ይጣፍጠኛል እንጂ ለምን ይቀፈኛል ! ትንሽ ብትቀምስ አስሩን ትረሽነው ነበር» አለች ካንዲ ፍሎሱን አፏ ውስጥ እንደያዘች። ስለዚህም ቃላቷ ሁሉ የህፃን ልጅ ይመስሉ ነበር። ሁኔታዋም የህፃን ልጅ ነበር «ምን አይነት ፍጡር እንደሆንሽ አይገባኝም ! ባየሁሽ ቁጥር የበለጠ ቆንጆ የምትሆኝው ለምንድነው" አለ፡፡ ሰፊ ፈገግታ ለገሰችው፡፡ ፊቷ በካንዲ ፍሎሱ ተበካክሏል። መሀረብ አወጣና ጉንጯን ጠረገላት ።፡ ከዚያም ፤ «ፊትሽ እንዲህ ባይበካከልኮ ፎቶ እንነሳ ነበር› አላት ።
‹‹ፎቶ!›› አለች እንደአምስት ዓመት ህፃን እየፈነጠዘች «የት የት ነው እምንነሳዉ›› ይህን እያለች ሌላ ካንዲ ፍሎስ አነሳች ። አንስታ ስትልስ ጥጥ መሰሉ ጣፍጭ ነገር ፊቷን ሸፈናት ። ‹‹ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ለምን አይበቃሺም ይኸ ነገር››
‹‹የት ነው ፎቶ እምንነሳው!? የት ነው?››
‹‹ እዚያ ጋ››

ፎቶግራፍ ተነሱ ። ፎቶግራፍ አንሺዎቹ የተለያዩ ልብሶች ይሰጣሉ ። ማይክና ናንሲ የርሄት በትለርን የስካርለት ኦ ሀራን አለባበስ መረጡ ። ( ርሄት በትለርና ስካርለት ኦ ሀራን (gone with the wind) በሚል ርእስ አሜሪካዊቷ ማርግሬት ሚቸል በፃፈችው ዝነኛ ልብወለድ መፅሐፍ ውስጥ ዋናዎቹ ገፀ ባህርያት ናቸው።) እንደ ርሄት በትለርና እንደ ስካርለት ኦ ሀራን ለብሰው የተንሱትን ፎቶግራፍ ሲያዬ ተገረሙ ። ናንሲ የደቡባዊ ዩናይትድ ስቴትስን ቆነጃጅት ልብስ ስትለብስ ውባቷ ጎላ። ማይክልም ኮስታራ ወንድ ሆኖ ቁጭ አለ። ይህን ያየው ፎቶግራፍ አንሺ ሳይቶር ገንዘቡን ተቀብሎ ፎቶግራፉን ሲሰጣቸው
«ይህን ፎቶ መስጠት አልነበረብኝም ። አንድ የተለየ ደስ የሚል ነገር አላችሁ ። ይህን ካየሁ ደግሞ ቆየሁ። ስለዚህ ቢያንስ ፎቶግራፋችሁን እያየሁ ዶስ እንዲለኝ ማስቀረት ነበረብኝ» አላቸው። ናንሲ ይህን ስትሰማ ደስ አላት ። ማይክልም ፈገግ አለ ያን ያህል ግን አልተደሰተም፡፡ ምክንያቱም አይቶ እማያደንቃት እንደሌለ ያውቃል። ግን የሱ ናት ።ሙሉ በሙሉ የሱ ትሆናለች። ሁለት ሳምንት . . . የናንሲ ጉትጎታ ከሃሣብ መለሰው።

«ተመልከት. . . እዚያ ጋ… ቀለበት በጠርሙስ አንገት ማስገባት ጨዋታ አለ» አለች። ይህን ጨዋታ ለመጫወት ከልጅነቷ ጀምሮ ትልቅ ጉጉት ነበራት ። ሆኖም እድሉ አጋጥሟት አያውቅም ። ከእጓለማውታን ማሳደጊያው ውስጥ የነበሩ መነኩሴ ሞግዚቶቿን ስትጠይቅ ከፍተኛ ገንዘብን የሚያባክን ጥቅም የሌለው ጨዋታ ስለሆነ አይቻልም ይሏት ነበር።

«መጫወት እንችላለን ? » አለች ገንዘብ ይባክናል እንዳይላት እየፈራች ። «ከፈለግን ደግሞ ማን ይከለክለናል ? ያውም አንች ብለሽ አለና በትያትር ደንብ ለጥ ብሎ እጅ ነሳት ። ከዚያም ክንዱን በክንዷ ታስገባ ዘንድ አዘጋጀላት ። ጅንን እያለ ለመሄድ ሞከረ ። ናንሲ ግን በዚያ የመጀነን ጉዞ ተካፋይ ልትሆን አልተቻላትም። ልክ እንደ እንቦሳ መፈንጠዝ ጀምራ ነበርና ። ይህ ፈንጠዚያ ደግሞ ይበልጥ ደስ አሰኘው።
«አሁኑኑ መጫወት እንችላለን!››
«አሳምረን ነዋ ፍቅሬ» አንድ ዶላር አወጣና ለአጫዋቹ ሰጠ። አጫዋቹም ከተለመደው አራት እጥፍ የሆነ ቁጥር ያላቸው ቀለበቶች ሰጣት ። ሩቡ በቂ ነበር።እሷ ግን ልምድ ስለሌላት ያን ሁሉ ቀለበት ተቀብላ ወደ ጠርሙሶቹ ብትወረውርም ጉዳዩ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ነበር ።ማይክል ደስ ብሎት ሲያስተውላት ከቆየ በኋላ፣
«ምን ማግኘት ነው እምትፈልጊው?» ሲል ጠየቃት ።
«ያንገት ጌጦቹን ፣ መቁጠሪያ መሰል ጌጦችን» አለች።

በጣም እንደጓጓች ድምጺም አይኗም ጠቅላላ አካላቷም ይናገር ነበር «እንደዚያ አይነት ውብ ጌጥ አጥልቄ አላውቅም» አለች። በህፃንነቷ የምትመኘው አንዱ ትልቅ ነገር ይኽ የአንገት ጌጥ ነበር ። የሚያብረቀርቅ ፤ የሚያምር ጌጥ ስታይ እንደጓጓች ነበር ያደገችው ።
👍19
«የምትፈልጊው ነገር ቀለል ያለውን ነውና ውዴ ። ሌላ ፤ ለምሳሌ ጃኒት የያዘችውን አይነት አትፈልጊም ?» አላት ። አንገቷን በአሉታ ነቀነቀች። «እሺ ተይው። የፈለግሽውን ለማድረግ ታዛዥሽ ነኝ» አለና ወረወረ። ሶስቱም ኢላማቸውን መቱ ። የአንገት ጌጡን ተቀብሎ ለናንሲ አጠለቀላት ። «ይኸው ወጣቷ እመቤት። የፈለግሽውን አምጥቻለሁ። ያንችው ነው። ኢንሹራንስ ልንገባለት ይገባል ብለሽ ትገምቻለሽ»

«አይ ፣ እንግዲህ በአንገት ጌጤ ላይ ማሾፍሀን አቁም ።ደስ አይልም?» ቀስ ብላ ነካ ነካ አደረገቻቸው ። እያንዳንዳቸውን ነቅነቅ ነቅነቅ… ሲያንፀባርቄ ለማየት ። «ጌጡ ሳይሆን ውብና ደስ እምትይ አንቺ ብቻ ነሽ። ስለዚህ ሌላ ልብሽ የሚሻው ነገር ቢኖር ታዛዥሽ እሆናለሁ» የደስደስ የተሞላ ፈገግታዋን አሳየችውና ፣ «ሌላ ካንዲ ፍሎስ ግዛልኝ» አለችው ገዛላት ። ከባዛሩ ወጡ። ቢስክሌቶቻቸውን ወዳቆሙበት ቦታ ሲያመሩ ማይክል… እንዴት ነው፤፣ ደክሞሻል?» ሲል ጠየቃት ።
«በጣምም አልደከመኝም » «ወደ ቤታችን እንመለስ ወይስ ወደ ፊት እንቀጥል ?» «ምን ያሀል እንቀጥል ?» «ቅርብ ነው ፤ ላሳይሽ የምፈልገው ቦታ አለ ። እባህሩ ዳር አካባቢ አንድ ደስ እምትለኝ ቦታ አለች» «ደስ ይለኛል እንሂዳ»
ቀስ ብለው፣ፀጥ ብለው ጉዟቸውን ቀጠሉ ። ድንገት ሁለቱም በየግል ሀሳባቸው ተዋጡ የቅድሙ መቃበጥና መቧረቅ ጥሏቸው የሸሸ ይመስል ነበር ። ወደ ባህሩ ዳር ሲደርሱ ገና ይህ ነው ሳይላት ሊያሳያት የፈለገውን ቦታ አወቀችው። በትላልቅ ዛፎች የተከበበ ለመፋቀርና ትዝታን ለዘላለም አጥምዶ ለማስቀረት ተብሎ የተሰራ የመሰለ ቦታ ነበረ ። ይህን ቦታ እንዳየች ናንሲ እየፈነደቀች ‹‹ እንዴት ደስ ይላል ! እንኳን መጣን» አለች።

‹‹በጣም ደስ ይላል ፤አይደለም ፣» አለ ፤ደስ ሲላት ስላዬ እየተደሰተ ። «በጣም በጣም» አለች እየፈነጠዘች ። « ብዙ ጊዜ እስባለሁ ፤ ላሳይሽ››
«ዛሬ እንኳን ይዘኽኝ መጣህ ። እንኳን አላመለጠኝ» እጅ ለጅ ተያይዘው በጸጥታ ተቀመጡ ። ለተወሰነ ጊዜ በዚህ ሁኔታ ቆዩ። ከዚያም ናንሲ ድንገት ብድግ አለች ። «ምነው?... ሰለቸሽ ?» አለ ማይክል ።
«አይ . - -. አልሰለቸኝም »
«ታዲያ የት መሄድ ፈለግሽ››
«አንድ ጉዳይ አለኝ. . .»
«ነው? ቀላል ነው። ወደጥሻው ገባ ብለሽ...»
«ግን እኔ ያሰብኩት ሌላ ነው » ይህን ብላ ጥላው ሮጠች። ቀስ እያለ ተከተላት ። በልቡ ምን ይሆን ደግሞ አሁን ያሰበችው? የሚል ጥያቄ እየጠየቀ ። ጐንበስ ብላ አንድ ትልቅ ድንጋይ ለመፈንቀል ትታገል ጀመር። ድንጋዩ ግን ንቅንቅም አላለ ።
« ቂል ‹ከድንጋይ ጋር ትታገላለች?» አለ የቀልድ እየናቃት። ቀና አላለችም ። ትግሏን ቀጠለች .።

«በቃ በቃ ። ይህን ያህል ካስፈለገሽ አንዴ ዞር በይልኝ ልሞክረው» አለ። ደካክማ ቀና አለች ። «ግን ለምንድነው የፈለግሽው !? » አላት ፤ ድካሟን በፊቷ ላይ ሲየይ ግራ ተጋብቶ « «ለሆነ ጉዳይ. . . ትንሽ ብቻ ብድግ ካለ ይበቃል» አለች ። ማይክ ሲሞክረው ድንጋዩ በመጠኑ ተነሳ ።
«በቃ | እንደሱ ያዘው » አለች ናንሲ ።
ከዚያም እባዛሩ ላይ ማይክል ተጫውቶ በማሸነፍ የሸለማትን የጌጥ መቁጠሪያ አውልቃ እድንጋዬ ሥር ከተተችው። ይህን ካደረገች በኋላ ፤
«አሁን ልቀቀው » አለች ።
«ምን ? የአንገት ጌጥሽን መቅበር ፈለግሽ »
«አዎ | ልቀቀው » ድንጋዩ ወደ ቦታው ተመለሰ። መቁጠሪያ መሰሉ ጌጥ ተቀበረ። ከዚያም መቁጠሪያው የተቀበረበትን ቦታ እየተመለከተች ፤ «ይህ የአንገት ጌጥ በቃል ኪዳን የመተሳሰራችን ቋሚ ምስክር ነው።ይህ ምስክርም ይህ ድንጋይ ፤ ይህ ወደብና እነዚህ አድባር መሳይ ዛፎች በዚህ ቦታ ላይ ፤እስከ ኖሩ ድረስ ይኖራል ። ትስማማለህ ? » አለች ። «እስማማለሁ ግን...» አለ ፈገግ እያስ « ግን ፍቅራችን የጀማሪ ፍቅር አልሆነም ? »

«ምን ነውር አለበት ? ...ከፍቅር ሁሉ የጀማሪ ፍቅር ንጹህ ፍቅር መሆኑን አታውቅም ? ስለዚህ እንዲያ አይነት ፍቅር ሲያጋጥምህ በደንብ መያዝ ፤ መንከባከብ ፣ መጠለያ ማበጀት አለብህ » አለች ።
«ልክ ነሽ ። በጣም ልክ ነሽ ፍቅሬ ። አሁን ፍቅራችን እዚህ ቦታ ላይ መጠለያ ይኖረዋል» አለ ማይክል"ደስ እያለው።
«አሁን በዚህ ቋሚ ምስክር ፊት እኔ ላንተ፤አንተ ለኔቃል ኪዳን እንገባለን ። እኔ ናንሲ ማክአሊስተር እዚህ ኦማይሞት ድንጋይ ስር ካረፉት መካከል እያንዳንዷን መቁጠሪያ በህይወቴ እያለሁ ላልረሳ ቃል እገባለሁ። እነዚህ መቁጠሪያዎች የፍቅራችን ፤ የመተሳሰራችን ምልክት እንደሆኑ ላልረሳ ቃል እገባለሁ » አለችና ቀና ብላ «አሁን ደሞ ያንተ ተራ ነው» አለች።

«እኔም. . . እኔ ማይክል ሂልያርድም የመጣው ቢመጣ የሆነው ቢሆን ፤ እነዚህን መቁጠሪያዎች ምስክር በማድረግ ካንቺ ሌላ ላላስብ ቃል እገባለሁ። ቃል ኪዳን ነው » አለ ። በቃል ኪዳን ተሳሰሩ ። በደስታ ፈንደቁ ። የደስታ ሳቅ ሳቁ ። ያን ያህል የሚያስቅ ፤ የሚያስፈነድቅ ምን ነገር አጋጠማቸው ? ወጣት ናቸው ፤ ፍቅር የያዛቸው አፍላ ወጣት መሆናቸው ውብ ፍቅርን መላበሳቸው ደስታ ለኮሰባቸው ። ይህ ደስታ አሳቃቸው ፤ አስፈነደቃቸው። ያን ለት በዚህ ሁኔታ ቀኑን በደስታ አሳለፉት ፤ ሲወዳደሩ ሲደናነቁ ፤ ሲፈነጥዙ ። በመጨረሻ አንዳቸው አንዳቸውን ላይዘነጉ? ሌላ ላያስቡ በቃል ኪዳን ተሳሰሩ ። ቃል ኪዳናቸውን በደስታ ሳቅ አሳረጉ። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ማይክል «አሁን ወደቤታችን እንድንመለስ ትፈልጊያለሽ ? » ሲል ጠየቃት። ራሷን በአወንታ ነቀነቀች ። ቀስ እያሉ ብስክሌቶቻቸውን ወዳቆሙበት ቦታ አመሩ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍233
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ድፍን የዌስት ሊን ሕዝብ ደስ በሚለው የሰኔ ማለዳ አየር ወዲያና ወዲህ ይተ
ራመሳል ሕዝቡ ምንጊዜም በጧት ወጥቶ በመንገድ ሲተላለፍ በብዛት መታየቱ
የተለመዶ ቢሆንም እንደዚያን ዕለት ሆኖ ወጥቶ አያውቅም ዕለቱ ሚስተር ካርይል ከባርባራ ሔር ጋር በጋብቻ የሚተሳሰሩበት ቀን ስለ ነበር ሕዝቡ ንቅል ብሎ ወጥቶ ሥነ ሥርዓቱ ወደ ሚፈጸምበት ቦታ ይጐርፋል
ሚስ ካርላይል ከዚያ ሁሉ ድብልቅልቅ አልገባችበትም " ትልቅ 'ደማቅ የጋብቻ በዓል አይወድልኝም ቢፈልጉ እሷ ሳትኖር በገዛ እጃቸው ግጥም ብለው
መታሰር ይችላሉ ” ብላ አልተጠጋቻቸውም " የካርላይል ልጆች የሁለተኛዋን እናት መምጣት በጸጋ እንዳይቀበሉ በማሰብ አስተማሪያቸውንና ጆይስን ጭምር ከበቷ ጠርታ ወስዳቸዋለች " የቤት ሠራተኞቿን ይዛ ከሚስተር ካርላይል ቢሮ ቀጥሎ ከሚገኘው ቤቷ ለዘለቄታ ከገባች ሰንብታለች ፒተር ብቻ ከኢስት ሊን
ለመውጣት ባለ መፈለጉ ከሷ ተለይቶ ቀረና አስቀየማት "

ሚስተር ዲልም ስለ ጋብቻዉ አከባበር በጣም አሰበበት " እንዳያያዙ ከሆነ
በሚስተር ካርላይል የመጀመሪያ ጋብቻ ጊዜ እንዳደረገችው ሁሉ ዛሬም ኮርነሊያ! አንግቱን ይዛ ሳትንጠው በመቅረቱ ዕድለኛ ነበር " በአራት ሰዓት ገደማ ከሚስ ካርላይል ቤት መጣ " ነባር ሰው በመሆኑ የጥንቱን ባህላዊ ሥነ ምግባር በሚገባ ያውቃል " ስለዚሀ እሷ ዘንድም ጐራ ብሎ ደስታውን ቢገልጽላት እሱን ከመሰለ ሽማግሌና ጨዋ ሰው የሚጠበቅ መልካም ሥራ ነው ብሎ ሔደ ።

ሚስ ካርላይል እጆቿን አጣጥፋ ከምግብ ቤት ውስጥ ተቀምጣለች ያለ ምንም ሥራ እንዳሁኑ ዝም ብላ ተቀምጣ ታይታ አታውቅም ሚስተር ዲል ሲገባ ዞር ብላ አየችው ።

“ ዛሬ ምን አግኝተሃል?” አለችው እሱ ሳይናገር አስቀድማ ' “ ወጣት መስለሀል ሽቅርቅር ብለሃል
“ ወደ ሠርጉ መሔዴ ነው ሚስ ኮርኒሊያ አንቺስ አልሰማሺም እንዴ |
ሚስዝ ሔር ለቁርስ ጠርተውኛል " ሚስተር አርኪባልድ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንድገኝ አጥብቆ ነግሮኛል" ይህን ያህል ከልክ በላይ አጊጫለሁ እንዴ ? አይመስለኝም" "
ምስኪኑ ሚስተር ዲል ' “ ሽቅርቅር ብለሃል ” የተባለው ' አንድ ባለ ወርቅ
ቁልፍ ነጭ ሰደርያና ደረቱ ላይ የተጠለፈ ሸሚዝ በመልበሱ ነበር " ሚስ ኮርኒሊያ ግን እሱን ለማሽሟጠጥና ለማብሸቅ ተመቻት "

"ማማር ?” ብላ ጮኸችበትና “ ምን እንደምትለው አላውቅም " እኔ መቸም ወርቅ በቁና ቢሰፈርልኝ እንደዚያ መሣቂያ ሁኘ አልወጣም " ከመንገዱ ባፈር የሚ
ፀጫወቱት ሕፃናት አንተን ሙሽራ አድርገው "ሆ” እያሉ ይከተሉሀል ይኸው ነበር የጎደለህ « በዚህ ዕድሜህ በተጠለፈ ሸሚዝ ስታጌጥ አለማፈርህ " በኮትህ ጠርዝ ያበባ ጌጥ ብትጨምርበት ደግሞ የበለጠ ባማረብህ ነበር እንዴ ኮቴን ኮ በምንም ነገር አላስጌጥኩትም ' ሚስ ኮርኒሊያ "

"አላስጌኩትም ? ” አለች ካፉ ነጥቃ ምናልባት ከዙሪያ ያበባ ጉንጉን ልትዘመዝምበት ባንገትያው የነጭ የባሕር አምራ ለስላሳ ላባና ቀይ አበባ ልታስጠልፍበት አምሮህ ይሆን ? ከሱ ሸሚዝህና ሰደርያህ ጋር ይስማማ ነበር !”

“በሰርግ ቀን ኮ ከአዘቦቱ ለየት ያለ ልብስ መልበስ የሚገባ ነው....ሚስ ኮርኒሊያ አንድ ሰው ተጠርቶ ከሔዶ እንደዚህ ለብሶ መሔድ ጠሪዎችን ማክበር ነው ”

“ እኔ እኮ ሰዎች ወደ ሠርግ ቤት ኬሻ ለብሰው ይሒዱ ኘልወጣኝም " ብቻ ለሁሉም ነገር መጠን አለው ። እስቲ አንተ አሁን ዕድሜህን ታውቀለህ ?

“ ልክ ስልሳኛዬን መያዜ ነው

ታዲያ አንድ የስልሳ ዓመት ሰው አንተ አሁን እንደ ተሸለምከው ሆኖ ማጌጥ
የሚገባው ነገር ነው ? የሰበካው ሕዝብ መሣቂያ ነው የሚያደርግህ " ብቻ ልጆች የቆርቆሮ ማንቆርቆሪያ ከልብስህ ጋር ቋጥረው እንዳያንጠሰጥሉብህ ተጠንቀቅ "

ሚስተር ዲል ለኮርኒሊያ የመሰላትን ያህል እንደማይሣቅበት ያውቃል እሷ ለምታቀርብለት ሐሳብ ሁሉ ጥሩ አክብሮት ስላለው ያጠለቃቸውን ነጫጭ የጅ ሹራቧን ሳታየው አውልቆ ከኪሱ ከተተና ገባ ።

አሁን እንኳን የመጣሁት በዚህ ታላቅ ቀን ደስታዬን ልገልጽልሽ ነው ያለኝ ተስፋ ሚስተር አርኪባልድ ሚስቱና አንቺም...."

“ በል በቃህ አትልፋ ” አለችው አቋርጣ " ዛሬ ጥናቱን ይስጣችሁ የምን
ባልበት ቀን ነው " አርኪባልድን ወስደው ሲያንጠለጥሉት ባይ በጣም ደስ ይለኝ ነበር .

ምነው ኮርኒሊያ !

“ አዎን ሁንም ደስ ይለኝ ነበር። አንተም ጉሮሮህን እንደ ተያዝክ አታፍጥጥብኝ እስኪ አሁን እንደገና በገዛ እጁ ከሚስት ጋር በሰንሰለት መታሰርን ምን አመጣው ? ያለፈው አይበቃም ነበር ? እኔማ ጭንቅላቱ ዶኅና አይደለም ማለት ከጀመርኩ
ቆይቻለሁ

ያለፈው ዐለፈ " ሁላችንም ልናወሳው አይገባንም " ጋብቻ ያስደስታል ያስከብራል ። እሱም ቢሆን ነገሩ ከመበላሸቱ በፊት ጥቂት የደስታ ዓመታት አሳልፎበታል " አሁንም ቢሆን ካዲሷ ሚስቱ የበፊቱን የሚያስረሳ እንደሚያገኝ ተስፋ አለኝ " ከሷ የበለጠች ቆንጆ ማግኘት አይችልም " ሚስተር ካርላይል እሷን በማግኘቱ በበኩሌ የተሰማኝ ደስታ ይህ ነው አይባልም "

“ እንዴ ከምን ያገኛል ? እሷን የመሰለች ሥራ ፈት • ስድ ባለጌ ' አውደልዳይ :
አሻንጉት ስለሚመስለው ፊቷና ስለ አርኪባልድ ካልሆነ በቀር ምንም ሐሳብ የሌላት ከንቱ ' የትም አትገኝም ” ብላ ደነፋች "

“ አይ ሚስ ኮርኒሊያ ...
መልከኛ ወጣት ሲቶች ቁንጅናቸውን ያውቃሉ "
ስለ ውበታቸው መታየት ' መሽቀርቀር መወደዳቸውንም ማንም ሊወስድባቸው አይችልም " ነገር ግን እሷ ጥሩ ሚስት እንደምትሆንለት አልጠራጠርም " ያች ያል
ታደለች ከንቱ እንዶ በደለችው አትበድለውም

“ እኔ እሷም እንደዛችኛይቱ እንደምታዋርደው ብሠጋ ኖሮ አሁኑኑ ሥነ ሥርዓቱ ከሚካሔድበት ሔጄ ጋብቻውን እከለክል ነበር " እምቢ ብትል እንኳን
እዚያ እንዳለች አንቃት ነበር
" አለችና ደነፋች "
እያት ደሞ ያቺ ከውካዋ ዐይን አውጣ ! አለች ትንሽ በረድ ብላ ወደ መንገዱ እያየች " ሚስ ካርላይል ከወንበሯ ተንደርድራ ወደ መስኮቱ ሔደች ሚስተር
ዲልም ወደዚያው ዞር ብሎ ተመለከተ።

ራስ ወዳድና ትዕቢተኛዋ አፊ ሆሊጆን ሽቅርቅር ብላ ለብሳ ስታልፍ ሚስተር
ዲልን አየችውና የሰላምታ ምልክት ሰጠችው ። ትሕትና የተሞላው ሽማግሌም
አጸፋውን መለሰላት " ሚስ ካርላይል አሁንም ጮኽችበት "

“ ደግሞ ለሷ ሰላምታ የምትሰጣት ምን መሆንህ ነው? ”
“ አይ ሚስ ኮርኒሊያ ሰላምታ ስትሰጠኝ አንቺም አይተሻታል "

አይቻታለሁ !እሷም አይታኛለች " ግን የብልግናዋ ብልግና አንተን እጅ ነሣችህ አንተም እኔ እያለሁ ቡጢህን ጨብጠሀ ልትነቀንቅባት ሲገባህ አጻፍውን መለስክላት።

“ ሚስ ኮርኒሊያ ያለፈው ዐለፈ ። በርግጥ እሷ አትረባም " ሆኖም ሪቻርድ ሔር ጋ ያለ መሔዷ ተረጋግጧል አሁንም ስክን ብላ ረግታ ተቀምጣለች " ታዲያ ሰላም ብላት ምናለበት ።

“ አንተማ ምናለ! ሰይጣኑ ራሱ ቀንዱን ገትሮ ጅራቱን ቀስሮ ቁሞ ብታየውም ይቅርታ የሚያስደርግ ምክንያት ሳትፈልግለት አትቀርም " አንተም እንደዚያ እንደ አርኪባልድ ነህ " አትረባም ! እስኪ አፊ ሆሊጆንን ልብ ብለህ ተመልከታት " እስኪ የማን ገረድ እንደዚህ ለባብሳ አደባባይ ወጥታ ታውቃለች ? ያደረገችው ዐይነ ርግብ እንዳንተ ሸሚዝ ጥልፍ ያሳፍራል ።

አፊ እኮ የእመቤቷ ደንገጡር ናት እንጂ የቤት ሠራተኛ ልትባል አትችልም"
የወይዛዝርት ደንገጡሮች ኮ በደንብ ነው የሚለብሱት " ለአባቷ ትልቅ አክብሮት ነበረኝ " ከሱ የተሻለ ጸሐፊ ከቢሮአችን አይተን አናውቅም ።
👍142
“ ምናልባት እሷንም አከብራታለሁ እንዳትለኝ ብቻ ! እኔስ ነገሩ ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆነብኝ " ዱሮ አመቤቶች ገረዶቻቸውን በሥራ ይጠምዱዋቸው ነበር " ዛሬ ግን ለአጫዋችነት ነው የሚያስቀምጧቸው " ተራ የጥጥ ቀሚሷን አጥልቃ የሥራ ሽርጧን ታጥቃ ከቤት አልጋዎችን ማሰናዳትዋን ትታ ከሰርጉ ሥነ ሥርዓት ተገኝታ ለማፍጠጥ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየሔዶች ነው » ደግሞ ያ የምን ሠረገላ ነው?” አለች ሚስ ካርላይል አንድ ሠረገላ ወደ ቢሮ ጠጋ ብሎ ሲቆም አይታ "

“ ሠረገላ ? አለ ዲል መላጣ ራሱን ወደፊት በማሰገግ እንዲመጣልኝያዘ ያዘዝኩት ይሆናል " በይ ደኅና ዋይ ሚስ ኮርኒ ።

“ ሠረገላ ላንተ?” አለችና ጮኸች!“ ምነው? ቤተክርስቲያን በእግርህ የማትሔደው ሪህ አለብህ እንዴ ?

"አሁን እንኳን ወደ እዚያ ሳይሆን ወደ ዐጸዱ ነው የምሔደው ። ይሁን
እንጂ በሠረገላ መሔዱ ለጠሪዎች ክብር መስጠት ስለ መሰለኝ ነው "

'አይጠረጠርም እንደዚያ ሺክ ብለህ መሔድ ያስፈልግሃል ብቻ ለምን የዳንስ ጫማና በጥልፍ ያጌጠ የግር ሹራብ አታክልበትም ?”

ወዲያው ጥሏት ቢወጣ ይወድ ነበር ፤ነገር ግን በንግግሯ ያለመቀየሙን ለመግለጥ መልካም ቃል ተናግሮ ቢለያት መሻሉን አሰበ “ ወደ እዚያ የሚጐርፈውን ሕዝብ ተመልከቺውማ ! መቸም ቤተ ክርስቲያኑ ግጥም ብሎ መሙላቱ ነው ” አላት
“ እኔም መሰለኝ !ምክንያቱም አንድ ሞኝ ብዙ ሕዝብ ይሰበስባል … ”

"ሚስ ኮርኒሊያ ያሁኑን ጋብቻ ከፊተኛው የተሻለ የወደደችው አልመሰለኝም
አለ ሚስተር ዲል ለራሱ “ በሌሎች ነግርች አስተዋይ ሰው ናት » ሚስተር አርኪባልድ በማግባቱ እንደዚህ መቆጣቷ ግን ልክ አይደለችም ኧረ ለመሆኑ
አለ ሐሳቡን በመለወጥ ይህ ሸሚዝ እሷ እንደምትለው አስጠልቶብኝ ይሆን እንዴ !
አኔ ደግሞ ለሚስተር አርኪባልድና ለሚስ ባርባራ አክብሮቴን ለመግለጽ እንጂ
ሌላ ለምን ብዬ ነው ኻያ አምስት ሽልንግ ያወጣሁት ምናልባት በጧቱ እንደዚህ
መልበሱ ከሥነ ሥርዓት ውጭ ይሆን ? ቢሆንም እንግዲህ ወደ ቤት ተመልሼ ለመለወጥ ጊዜ የለኝም ምንም ማድረግ አልችልም "

ቤተክርስቲያኑ ግጥም ብሎ በሕዝብ ሞላ " ከውስጥ ሊገቡ ያልቻሉ ከግቢውና
ከዚያም ተርፈው በመንዱ ቆሙ " የዚያን ቀን የመቃብር ሐውልቶችም አልተከበሩም ደንታ ቢስ እግሮች ብዙዎቹን ደቀደቋቸው ቢንስ አምሳ የሚሆኑ ልጆች እርስ በርሳቸው ተያይዘው
ከሎርድ ማውንት እስቨርን መቃብር ማገሮች ላይ ወጥተው ነበር " ከቀኑ አምስት ሰዓት ሆነ፤ሙሽሮች ግን ገና ብቅ አላሉም " ከደጅ አብርቆ ለብሶ የቆመው ሕዝብም ሆነ ከውስጥ ጥቅጥቅ ብሎ የተቀመጠው ዕድምተኛ ትዕግሥቱ አለቀ አንዳንዶቹ ከሁለት ሰዓት በላይ ጠብቀዋል " በመጨረሻ የሠረገላ ድምፅ ተሰማ" ሕዝቡም ከመቅደሱ አካባቢ ገለል እንዲል ተደረገ "

ወይዛዝርቱ መኳንንቱ አበባ መስለው አምረው ዘለቁ። ከሁሉ በፊት ሚስተር
ካርላይል ረጋ ብሎ ስሜቱን ገዝቶና ተዝናንቶ ወደ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ገባ "
የሙሽራይቱ ወላጆችና እኅቷ አን ከሌሎች እንግዶች ጋር ገቡ ሚስዝ ሔር ስር ጆን ዶቢዴ ክንዷን ይዞ ደግፎ ሲያስገባት የሚያምረው ፊቷ ከመቸም ይበልጥ ግር
ጥት ብሎ ያዩ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እየተጠቃቀሱ አዬ ጉድ ! አሁንም የዚያ የተረገመ ልጂዋ ክፉ ሥራ እየመጣባት እኮ ነው” ይባባሉ ነበር " ሚስተር ጀስቲስ ሔር የተዘናፈለ ሰው ሠራሽ ጸጉር አጥልቆ በኮቱ የአዝራር ማስግቢያ ቀዳዳ ነጭ ጽጌረዳ ሰክቶ ፊቱን ኮስተር አድርጎ እየተጀነነ ሲራመድ ሰው ሁሉ እሱን ለማየት አንገቱን ወደ ፊት አሠገገ ።

ባርባራ ለስላሳ ነጭ ሐር ቀሚስ ለብሳ ወለል የሚል ዐይነ ርግብ አድርጋ” በሚዜዎቸ ታጅባ ገባች።

ሚስተር ካርላይል ቀደም ብሎ ከመቅዶዘደሱ ዳር ቦታውን ያዘ " ባርባራ ወደ እሱ ስትጠጋ ' ወደሷ ቀርቦ አጂዋን ያዘና በግራው በኩል አቆማት " የተለመደ ነገር አይመስልም ነገር ግን በፊት ስለገባ ማወቅ ነበረበት " ሌሎችን የሚቆሙበትን ጸሐፊው አመለከታቸው " ከዚያ ሥርዓተ ጸሎቱ ተጀመረ።

ባርባራ ስሜቷ በኃይል እንደሚተናነቃት ባያጠራጥርም ቀጥ አድርጋ መለሰች "ይህን ሰው ቅዱስ በሆነ ጋብቻ አብረሽው ለመኖር ባል ብለሽ ተቀብለሽዋልን ?”
አለ ቄስ ሊትል " ሁለታችሁም በሕይወት
አስካላችሁ ድረስ
በጤናም ሆነ በሕመም ጊዜ በታዛዥነት በአገልጋይነት በፍቅር ትይዥዋለሽን ?

“አዎን ” የባርባራ አነጋገር ግልጽና የማያወላውል ነበር

ሥነ ሥርዓቱ ቶሎ አበቃ " ባርባራ በጣቷ የጋብቻ ቀለበቷን አጥልቃ በክንዷ
የሚስተር ካርላይልን ክንድ ይዛ እየተመራች ዛሬ የሷም ጭምር ወደ ሆነው ሠረገላ
ገባች " የተሰበሰበው ሕዝብ የሙሽራይቱን የደስ ደስ ያለው ፊት ሲያይ ጭብጨባውን አቀለጠው
የሙሽሮቹ ሠረገላ እየመራ አጃቢ ሠረገሎች እየተከተሉ ለቁርስ ወደ 0ፀዱ አመሩ።

" ባርባራ ... " አላት ሚስተር ካርላይል “ ለቄሱ የገባሽልኝን ቃል .
ታከብሪያለሽ ?

እንደ ማፈር አለች " የጠራ ሰማይ የመሰሉት ዐይኖቿን በፍቅር እንደ ተመሉ ወደሱ 0ይኖች ቀና ስታደርጋቸው ከልብ የፈለቀ አውነተኛ ስሜት በእንባ ክድን አደረገቻው።

ሁልጊዜ ! ቃሉንም መንፈሱንም ሞት እስኪጠራኝ ድረስ ! ” አለች....

💫ይቀጥላል💫
👍15
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስር


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርክ አልደር በመጀመሪያ ዳያና ላቭሴይንን ያያት ጊዜ ‹‹የአምላክ ያለህ! እንዳንቺ የምታምር ሴት አይቼ አላውቅም›› አላት፡፡

ያገኛት ሁሉ እንዲህ ይላታል፡፡ ዲያና ያለጥርጥር ውብ ሴት ስትሆን ጥሩ ጥሩ ልብስ መልበስም ትወዳለች፡፡ የዚያን ቀን እጀ ጉርድ ቅልጥሟ ጋ የሚደርስ ቀሚስ ለብሳ ነበር፡፡ እንዳማረባትም አውቃለች።

ማንቼስተር ከተማ ሚድላንድ ሆቴል ውስጥ ራት ግብዣ ተጠርታለች
በግብዣው ላይ ከነበሩት ከባሏ የንግድ ሸሪኮች ጋር በሙሉ ስትደንስ አመሸች ታዲያ ሁሉም አብረዋት የደነሱት ወንዶች ደረታቸው ላይ ይለጥፏታል ወይም እግሯ ላይ ይቆማሉ ሚስቶቻቸው ደግሞ በጥላቻ ዐይን አፈር ድሜ ያስግጧታል፡ ወንዶች ቆንጆ ሴት አይተው ሲቅበጠበጡ
ሚስቶች ለምን ባሎቻቸውን ትተው ሴቷ ላይ በቁጣ እንደሚያፈጡ ሁልጊዜ
ይገርማታል፡፡ እሷ እንደሆነ እነዚህን ጉረኛና በዊስኪ የደነበዙ ባሎቻቸውን
አትፈልግም፡፡

አንድ ጊዜማ የከተማውን ምክትል ከንቲባ በሰው ፊት በማዋረዷ ባሏን አሳፍራው ነበር፡ በኋላም ትንሽ እረፍት አገኝ ብላ ሲጋራ የምትገዛ መስላ ከሆቴሉ ወጥታ ሄደች፡

ኮኛኩን እየተጎነጨ ብቻውን ተቀምጧል። ልክ በክፍሉ ውስጥ የፀሃይ ብርሃን የፈነጠቀች ይመስል ስትገባ ዓይኑን ተከለባት፡ ሰውዬው አጠር ያለና እንደ ህፃን ፍልቅልቅ ያለ ፈገግታ የተላበሰ ሲሆን አሜሪካዊ መሆኑ ሁኔታው ያሳብቅበታል፡፡ ገና እንዳያት አድናቆቱን የገለፀላት ሲሆን ሰውዬው የደስ ደስ ያለው በመሆኑ ፈገግ ብትልለትም አላናገረችውም፡፡ ሲጋራዋን
ገዝታ ቀዝቃዛ ውሃ በጉሮሮዋ ለቀቀችና ወደ ዳንሱ አዳራሽ ተመለሰች፡

ሰውዬው ማን እንደሆነች ከቡና ቤቱ አስተናጋጅ ጠየቀና አድራሻዋን
እንደምንም አግኝቶ የፍቅር ግጥም ፅፎ ላከላት፡፡ ግጥሙን ስታነብ አነባች፡፡
ያስለቀሳት ብዙ ነገር ተመኝታ ሁሉንም ነገር ባለማግኘቷ ነው፡፡ ያለቀሰችው በዚች ደስታ በራቃት ከተማ የዓመት እረፍት መውጣት ከሚጠላ ባሏ ጋር ተጣብቃ በመቅረቷ ነው፡፡ ያለቀሰችው ከአምስት ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ
ጊዜ የፍቅር ግጥም በመስማቷ ነው: ያለቀሰችው ለመርቪን ያላት ፍቅር የተሟጠጠ በመሆኑ ነው፡፡

በነጋታው እሁድ ስለነበር ዳያና ቤቷ ውስጥ መሸገች፡፡ ሰኞ ዕለት ወደ
ከተማው መጽሐፍ ቤት ሄዳ ከዚህ ቀደም የተዋሰችውን መጽሐፍ መለሰችና ፊልም ቤት ገባች፡፡ ከዚያም ለእህቷ ልጆች ስጦታ ስትገዛ ዋለች፡፡ በኋላም
እራት መስሪያ የሚሆኑ ቁሳቁሶች ገዛችና ከከተማ ወጣ ወዳለው መኖሪያዋ
በጊዜ ለመድረስ ባቡር ላይ ተሳፈረች፡፡ ከተማ ውስጥ ስትዟዟርና ቡና ስትጠጣ የአሜሪካዊ አነጋገር ቅላፄ ያለውን ሰው ሳታገኘው በመመለሷ ተከፋች፡፡

ነገር ግን ነገሩን ስታስበው ጅልነት ሆነባት፡፡ ሰውዬውን ያየችው ለአፍታ ጊዜ ሲሆን በወቅቱም አላነጋገረችውም፡፡ ሆኖም ይህ ሰው ለዓመታት ያጣችውን ፍቅር የሚቀሰቅስባት ሆነባት፡ ታዲያ ይህ ሰውዬ ደግማ ብታገኘው ወይ ባለጌ ይሆናል፣ ወይ ወፈፌ ይሆናል፣ ወይ በሽተኛ
ይሆናል፣ ወይ ደግሞ ገላው የሚቀረና ይሆናል ብላ አሰበች

ከባቡሩ ወርዳ የቤቷን መንገድ ይዛ ስትሄድ ባልጠበቀችው ሁኔታ
ሰውዬው ወደ እሷ ሲመጣ በማየቷ ክው ከማለቷም በላይ ተርበተበተች፡፡
ፊቷ ቲማቲም መሰለ፧ልቧም መቶ ሜትር ሸመጠጠ፡፡ እሱም ሲያያት መደንገጡ ባይቀርም ሊያናግራት ቆም አለ፡፡ እሷ ግን እርምጃዋን ቀጠለች።

አልፋው ስትሄድ ‹‹ነገ ጠዋት ማዕከላዊ መጻሕፍት ቤት ጠብቀኝ›› አለችው
መልስ ይሰጠኛል ብላ ባትጠብቅም ሰውዬው ፈጣን አዕምሮ ያለው መሆኑን በኋላ ተረድታለች፡፡ ወዲያው ‹‹የትኛው ክፍል?›› አላት።

አፏ እንዳመጣላት ‹‹ባዮሎጂ ክፍል›› በማለቷ ሳቅ አለ፡፡

ቤቷ የደረሰችው በደስታ ተሞልታ ነው፡

ቤቱ ውስጥ ሰው የለም፡፡ የፅዳት ሰራተኛዋ ስራዋን ጨራርሳ የሄደች ስትሆን
መርቪን ገና አልገባም፡፡

በማግስቱ ቀጠሯቸው ቦታ መጻሕፍት ቤት ከላይ ‹‹ፀጥታ›› የሚል
ፅሁፍ የተንጠለጠለበት ቦታ ተቀምጦ አገኘችውና ‹‹ሰላም›› ስትለው ሌባ ጣቱን ከንፈሩ ላይ አድርጎ ዝም እንድትልና እንድትቀመጥ አመለከታት
ከዚያ ብጣሽ ወረቀት ላይ አንድ ነገር ፅፎ አቀበላት፡፡ ‹‹ኮፍያሽ ያምራል» የሚል ነበር፡፡ ኮፍያዋን በአንድ በኩል ገደድ አድርጋ ራሷ ላይ የደፋች በመሆኗ የግራ አይኗን ከልሎታል፡፡ ይህ ኮፍያ አደራረግ ፋሽን ሲሆን ይህን ፋሽን ለመከተል የሚደፍሩት ወኔ ያላቸው ጥቂት ሴቶች ብቻ ናቸው።

እስክርቢቶ ከቦርሳዋ አወጣችና ‹‹ኮፍያው ላንተ አይሆንም› ብላ ፅፋ
አሳየችው:፡ እሱም ‹‹የግቢዬን አበባ አስቀምጥበታለሁ›› ብሎ ሲፅፍላት በሳቅ ተንከተከተች፡፡ ‹‹ሽሽሽሽ›› አላት ዝም እንድትል፡

ዳያና ይሄ ሰውዬ ወፈፌ ነው አስቂኝ አለች በሆዷ፡፡ ከዚያ
‹‹ግጥሞችህን ወድጃቸዋለሁ›› ብላ ፃፈችለት፡፡

‹‹እኔም አንቺን ወድጄሻለሁ› ብሎ መለሰላት በፅሁፍ፡፡

‹እብድ› ስትል አሰበች፡፡ ሆኖም እምባዋ በዓይኗ ተንቆረዘዘ፡፡

‹‹ስምህን እንኳን አላውቀውም› ብላ ፃፈችለት።

ቢዝነስ ካርድ አወጣና ሰጣት፡፡ ስሙ ማርክ አልደር ሲሆን የሚኖረው ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ነው፡፡
የምሳ ሰዓት ሲደርስ ምሳ ለመብላት ወደ ምግብ ቤት ሄዱ፡ ይህን ሰዓት የመረጠችው ባሏ እንዳያገኛት ነው መቼም በዚህ ሰዓት ባሏ
አይመጣም ብላ፡፡

ከምሳ በኋላ የሙዚቃ ድግስ ለማየት ቴያትር ቤት ገቡ፡፡

ያን ቀን ማርክ የሬዲዮ ኮሜዲ ደራሲ መሆኑን፣ ለታዋቂ ኮሜዲያኖች
እንደሚደርስ፣ እንዲሁም የሬዲዮ ጣቢያ ባለቤት መሆኑን አጫወታት
እንግሊዝ አገር የመጣው ትውልዳቸው ከሊቨርፑል
ውስጥ የሚሳብ የትውልድ ዘር ሐረጎችን ለማፈላለግ መሆኑን ነገራት፡፡

ማርክ አልደር ቁመቱ አጠር ያለ ሲሆን ከዳያና አይበልጥም፧ በእሜም እኩያዋ ነው፡፡ ፊቱ ሁል ጊዜ ፈገግታ አይለየውም፡፡ በአእምሮ የበሰለ አስቂኝና ተጫዋች ሲሆን ባህሪው ልስልስ ያለ በአለባበሱ ሸጋና ፅዱ ነው የሞዛርትን ሙዚቃ የሚወድ ሲሆን ከሁሉም በላይ ግን ዳያናን ወዷታል።
እስካሁን የምታውቃቸው ወንዶች ገላዋን መተሻሸት የሚወዱ፣ ባሏ መርቪን ጀርባውን ማዞሩን አይተው እንተኛ የሚሏት፣ በመጠጥ የደነበዙና ካንቺ ፍቅር ይዞናል እያሉ የሚቀባጥሩ ዓይነት ናቸው፡:

መቼም እሷን ሳይሆን ገላዋን እንደሚፈልጉ ታውቃለች፡፡ ንግግራቸው
የማይጥም ፍሬፈርስኪ ሲሆን እሷ የምትለውን ለመስማት አይፈልጉም፡፡
ስለእሷም ማወቅ ችግራቸው አይደለም:: ማርክ ግን ከነሱ ለየት ያለ ሰው መሆኑን ከቀን ወደ ቀን ማወቅ ችላለች፡፡

መጻሕፍት ቤት በተገናኙ ማግስት መኪና ተከራየና ባህሩ ዳርቻ ወስዶ
አዝናናት፤ ሳንድዊች ጋበዛትና ከለል ያለ ቦታ ፈልገው ተሳሳሙ፡፡

ማርክ ሚድላንድ ሆቴል አልጋ የያዘ ቢሆንም ዳያና እዚያ በጣም ታዋቂ በመሆኗ ከሱ ጋር መግባት አትችልም፡፡ ከምሳ በኋላ እዚያ ከወንድ ጋር ስትገባ ብትታይ በመክሰስ ሰዓት ወሬው በከተማው በሙሉ ይዳረሳል፡በመሆኑም የማርክ ፈጣን አዕምሮ አንድ ነገር ዘየደ፡፡ ሌላ የባህር ዳርቻ ላይ የሚገኝ ከተማ በመኪና ሄደው ሻንጣ አንጠልጥለው ሆቴል ደረሱና አቶ እና ወይዘሮ አልደር ብለው ተመዝግበው አልጋ ያዙ፡፡ ከዚያም ምሳ በሉና አልጋ ላይ ወጡ፡፡

ማርክ በፀጥታ ልብሱን ማወላለቅ ጀመረ፡፡ እሷ ደግሞ እፍረት ስለያዛት
ልብሷን ያወላለቀችው በሳቅ እየተንከተከተች ነው፡፡

ይወደኝ ይሆን ብላ አልተጨነቀችም፡፡ ከመውደድም እንደሚያመልካት
አውቃለች፡፡ እሱም ጥሩ ሰው በመሆኑ አልተረበሸችም
👍16
ከሰዓት በኋላውን በሙሉ አልጋ ውስጥ ገላቸውን ሲያስደስቱ ውለው
ሆቴል ማደር እንደሌለባቸው ሃሳባቸውን የለወጡ መሆኑን በመግለጽ የአዳር ሂሳብ ከፍለው ከሆቴሉ ወጥተው ሄዱ፡ ከዚያም ከቤቷ አንድ ፌርማታ ሲቀራት ከመኪና ወረደችና ባቡር ተሳፍራ በመሄድ ልክ ማንቼስተር የዋለች ይመስል ቀጥ ብላ ቤቷ ገባች፡፡

ማርክ ማንቼስተር በቆየበት ጊዜ ሁሉ በዚህ ሁኔታ አሳለፉ፡፡

መድረስ አይቀርምና የማርክ ወደ አሜሪካ መመለሻ ቀን ደረሰ፡፡
ዳያናና ማርክ ጊዜው ሮጦባቸዋል፡፡ ዳያና ስለወደፊቱ ማሰብ
አስፈርቷታል፡፡ ማርክ አንድ ቀን ጥሏት ይሄዳል፡፡ ሆኖም ነገ እዚህ ነው ያለው ብላ ራሷን አፅናናች፡ አሁን ማሰብ ያለባት ስለዚህ ቀን ብቻ ነው፡፡ልክ እንደ ጦርነት፡፡ ጦርነት አስከፊ መሆኑን ሁሉም ያውቃል፤ መቼ እንደሚጀመር ግን ቅንጣት ታህል አያውቅም፧ እስኪጀምር ግን ሁሉም
የዕለት ተዕለት ስራውን ይሰራል፡፡ ጊዜውንም በደስታ ለማሳለፍ ይሞክራል፡፡

ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ግን አልደር ሊሄድ እንደሆነ ነገራት፡፡

ጡቷን አንገፍጥጣ አልጋ ላይ ተቀምጣለች ማርክ እንደዚህ ስትቀመጥ ደስ ትለዋለች፡ እሱ ጡትሽ ያምራል ቢላትም እሷ ግን ጡቶቼ ትላልቅ ናቸው ብላ ታስባለች፡፡አሁን ስለ ጦርነቱ መወያየት ጀምረዋል፡፡ እንግሊዝ በጀርመን ላይ
ጦርነት አውጃለች በአፍላ ፍቅር ላይ ያሉ ፍቅረኛሞች እንኳን ስለጦርነቱ ማውራት ጀምረዋል።

ዳያና በሁሉም ሰው አዕምሮ ውስጥ የሚጉላላውን ጥያቄ ለማርክ አቀረበችለት።

‹‹ጦርነቱ ምን ሊያስከትል ይችላል?›› ስትል

‹‹ጦርነቱ አስከፊ መሆኑ አይቀርም›› አላት ኮስተር ብሎ፡ ‹‹አውሮፓ
ድምጥማጧ ይጠፋል ብዬ እገምታለሁ ምናልባት እንግሊዝ ከአውሮፓ
በባህር በመለየቷ ብዙ ጉዳት ላይደርስባት ይችላል።››

‹‹ወይ አምላኬ›› አለች ዳያና፣ ፍርሃት እየጨመደዳት

እንግሊዞች እንዲህ አይደሉም፡ ጋዜጣው በሙሉ የሚያትተው
ጦርነት ነው፡፡ መርቪን ጦርነቱን በአዎንታዊነቱ ነው የሚያየው መርቪን ያለው ነገር ትዝ አላት፡ ‹‹አሜሪካ ወደደችም ጠላችም በቅርቡ ጦርነት ውስጥ ትዘፈቃለች፡፡››

ማርክም ‹‹አይመስለኝም: ይሄ የአውሮፓውያን ችግር በመሆኑ እኛን
አይመለከተንም፡ እንግሊዝ በጀርመን ላይ ጦርነት ማወጇ እሺ ነገር ግን
አሜሪካኖች ፖላንድን ለመከላከል ሲሉ የሚሞቱበት ምክንያት አይገባኝም በማለት የተናገረው ዳያናን በእጅጉ አሸማቋታል፡ አነጋገሩ አበሳጭቷታል፡ ሃሳቡ ግን ትክክል ነው ብላ ተቀብላለች፡፡

‹‹እውነት አሜሪካኖች ለፖላንድ ሲሉ አንገታቸውን ለካራ ይዳርጋሉ።
ለአውሮፓስ ቢሆን››

‹‹እኔስ?›› ስትል ድንገተኛ ጥያቄ ሰነዘረች፡፡ ‹‹እስከ ጉልበት የሚደርስ
የተወለወለ ቦት ጫማ በሚያደርጉ ጀርመኖች ብደፈር መቼም አትፈልግም? ትፈልጋለህ?›› አለችው፡

ከዚያም አንድ ኤንቨሎፕ ከሻንጣው አወጣና ሰጣት፡
ከኤንቨሎፑ ውስጥ ትኬት አወጣችና ‹‹ልትሄድ ነው?›› ብላ ጮኸች

የዓለም መጨረሻ የሆነ መሰላት፡ እሱም ፈርጠም ብሎ ‹‹ቲኬቶ ሁለት ናቸው›› አላት፡፡

‹‹ሁለት ቲኬቶች›› አለች ግራ በመጋባት፡፡

አልጋው ላይ ተመቻችቶ ተቀመጠና እጇን ያዝ አደረገ፡፡

ቀጥሎ የሚለውን በመገመቷ በአንድ በኩል ስትደሰት በሌላ በኩል
ፍርሃት ጨመደዳት፡፡

‹‹አገሬ ይዤሽ እሄዳለሁ ዳያና›› አላት ከኔ ጋር ኒውዮርክ በአይሮፕላን እንሄዳለን፡፡ ከዚያ በኋላ ባልሽን ትፈቺና ካሊፎርኒያ ሄደን እንጋባለን፤ እወድሻለሁ››
በአይሮፕላን መሄድ! አትላንቲክ ውቅያኖስን በአየር ማቋረጥ፡፡ እንደዚህ
አይነት ነገር በተረት ነው የምታውቀው፡

ወደ ኒውዮርክ! ኒውዮርክ የታላላቅ ህንፃዎች፣ የምሽት ክበቦች፣ የማፊያ፣ የሚሊየነሮች፣ የፋሽን ንግስቶች እና የምቹ መኪኖች ከተማ፡፡

ፍቺ መፈፀምና ከመርቪን መላቀቅ፡፡

ካሊፎርኒያ እንሄዳለን ፊልሞች የሚሰሩበት፣ ብርቱካን እንደ ልብ
የሚበቅልበትና ከአመት እስከ አመት ፀሃይ የሚፈነጥቅበት አገር፡ ከማርክ ጋር ጋብቻ መፈፀም፣ ማርክን ለዘላለም የራስ ማድረግ፤ ነጋ ጠባ፡፡ መናገር
አቃታት፡

ማርክም ‹‹ልጆች እንወልዳለን›› አላት፡
ሳታውቀው በደስታ ሲቃ ጮኸች

‹‹እንደገና ጠይቀኝ›› አለችው በለሆሳስ፡፡

‹‹እወድሻለሁ፤ የትዳር አጋሬ ትሆኛለሽ? የልጆቼ እናት ትሆኚኛለሽ?››

‹‹አዎ በደስታ›› አለችው ‹‹አዎ፣ አዎ፣ አዎ!!!››
ማታውኑ ለመርቪን መንገር ሊኖርባት ነው፡፡
ቀኑ ሰኞ ነው፡፡ ማክሰኞ እለት ከማርክ ጋር ሳውዝ ሃምፕተን መሄድ አለባት፡ አይሮፕላኑ ሮብ እለት በ8፡00 ሰዓት ይበራል፡፡ ሰኞ እለት ከሰዓት በኋላ እቤቷ እስክትደርስ በደስታ ስትንሳፈፍ ነበር፡፡ እቤቷ ስትደርስ ግን ያ ሁሉ ደስታ ተነነ፡፡

ለባሏ እንዴት ብላ ልትነግረው እንደሆነ ቸገራት፡፡

ቤቷ ጥሩ ነው፡ ትልቅ፣ አዲስ፣ ባለ አራት መኝታ ቤት፡ ሶስቱ ክፍሎች ግን ሰው ተኝቶባቸው አያውቅም፡፡ ቤቱ ዘመናዊ ባኞ ቤት እና ዘመኑ ባመጣቸው ቁሳቁሶች የተሞላ ኩሽና አለው፡፡ አሁን ግን ትታው ልትሄድ በመሆኑ በስስትና በፍቅር እየተዘዋወረች አየችው፡:
ይሄ ቤት ለአምስት አመት ያህል የኖረችበት ቤቷ ነው፡፡
የባሏን እራት ራሷ ነች የሰራችው፡፡ የፅዳት ሰራተኛዋ ቤት ወልውላለች፤ ልብሱንም አጥባለች፡፡ ዳያና ከእራት በስተቀር ሌላ ምንም የምትሰራው
ነገር የለም፡፡ ባሏ ደግሞ ደስ የሚለው ሚስቱ ራቱን ሰራርታ ጠረጴዛ ላይ
አድርጋ ስትጠብቀው ነው፡፡ ባሏ ምንም አይነት ምግብ ቢዘጋጅለትም ምግቡን
መልካም ነው የሚለው፤ ለሱ ምግብ ማለት ሆቴል ሄዶ የሚበላውን ነው፡

ዛሬ መርቪን ራቱ የበሬ ስጋ ሲሆን ሽርጧን አገልድማ ድንች መላጥ ጀመረች፡፡ ጥላው መሄዷን ስትነግረው እንዴት እንደሚቆጣ ስታስበው እጇ
ተንቀጠቀጠና ቢላው ቆረጣት፡፡

የደማውን እጇን በውሃ አጣጥባ በፎጣ አድርቃ በፋሻ አሰረችው:፡
ለምንድነው የፈራሁት? ስትል ራሷን ጠየቀች አይገድለኝ፤ ሊከለክለኝም
አይችልም፤ እድሜዬ ከ21 አመት በላይ ነው! ይህም አገር ነፃ አገር ነው! በማለት ራሷን ለማሳመን ሞከረች፡፡
ይህም ሆኖ ግን ልትረጋጋ አልቻለችም፡፡

ይቀጥላል
👍15👏1
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_አስር ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ማርክ አልደር በመጀመሪያ ዳያና ላቭሴይንን ያያት ጊዜ ‹‹የአምላክ ያለህ! እንዳንቺ የምታምር ሴት አይቼ አላውቅም›› አላት፡፡ ያገኛት ሁሉ እንዲህ ይላታል፡፡ ዲያና ያለጥርጥር ውብ ሴት ስትሆን ጥሩ ጥሩ ልብስ መልበስም ትወዳለች፡፡ የዚያን ቀን እጀ ጉርድ ቅልጥሟ ጋ የሚደርስ ቀሚስ ለብሳ ነበር፡፡ እንዳማረባትም አውቃለች።…»
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሶስት (3)



ቃል ኪዳናቸውን በደስታ ሳቅ አሳረጉ። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ማይክል «አሁን ወደቤታችን እንድንመለስ ትፈልጊያለሽ ? » ሲል ጠየቃት። ራሷን በአወንታ ነቀነቀች ። ቀስ እያሉ ብስክሌቶቻቸውን ወዳቆሙበት ቦታ አመሩ። በቀጥታ ወደ ቦስተን ፤‹ወደ ናንሲ መኖሪያ ቤት አመሩ፡፡ እዚያ እንደገቡ ማይክል የደስታ ስሜት ተሰማው ። ለማይክል ሌላው ሁሉ ዝም ብሎ ቤት ነው። ይህቺ የናንሲ መኖሪያ ግን ማረፊያው ነች። የናንሲ መኖሪያ ምቹ በሆኑ የቤት ዕቃዎች የተደራጀች በመሆኗ አይደለም እጅግ ሰፊ ሆና እንደልብ ስታዝናናው በመቻሏም አይደለም። ናንሲ ሰፊ መኖሪያ ቤትም ፤ ምቹ የቤት ዕቃ ሊኖራት አይችልም ። ሆኖም ሰላም በዕቃ ዓይነት ወይም በቤት ስፋት አይገኝም ። ሰላም በዚህ ሁኔታ ቢገኝ ኖሮ እጅግ ሰፊ የሆነው የእናቱ መኖሪያ ይሆን ነበር ለማይክል ሰላምና ዕረፍትን የሚሰጠው ። ያ ያደገበት ቤት ለሱ ምኑም አልነበረም ።

የናንሲ ጠባብ ቤትና በውሶጧ ያሉት ትናንሽ ፅቃዎች ግን ከላይ እንደተገለጠው ሰላምና ዕረፍት ይሰጡታል ። ናንሲ ሰዓሊ ናትና ውበትን የሚያደንቅ ዓይን አላት ። ይህ ስለሆነ ከሰፋፊና ግዙፍ ውድ የእናቱ መኖሪያ ቤት ዕቃዎች ይልቅ የናንሲ የቤት ዕቃዎች ያስደስቱታል ። ግድግዳው የተቀባው ቀለም ፤ የወለሉ ምንጣፎች ለማይክ ደስታ ይሰጡታል ። በዚህ ሁሉ ላይ ናንሲ በሕይወት ተከብባ የምትኖር ፍጡር ናት ። የተጀመሩም ሆኑ ያለቁ ሥዕሎቿ ለሱ ሕያው ናቸው። በመጀመሪያ በኤግዚብሽኑ አዳራሽ ውስጥ ሲያያቸው ያየባቸው ሕያውነት ይበልጥ እውን እየሆነ ሄዶ ነበር ።

በዚህ ሁሉ ላይ በናቱ ግዙፍ አዳራሾችም ውስጥ ሆነ የትም ቦታ የማያገኘው ፤ እንደልቡ ሆኖ እየተዝናና የሚያጣጥመው ያ የቀለም ሽታ ለሱ የሱስ ያህል ነበር። « እዚህ ቤት ስሆን ምን ያህል ደስ እንደሚለኝ ታውቂያለሽ ናንሲ ?» አለ ማይክል ።
« አዎ ... አውቃለሁ » አለችና ዞር ብላ በናፍቆት ተመለከተችው ። ከዚያም ቤቷን በፍቅር እየቃኘች «እኔም እንደዚች ቤት ደስ የሚለኝ ቦታ የለም ። ለመሆኑ ከተጋባን በኋላ እንዴት ነው እምናደርገው !
«ቀላል ነው። እነዚህን ውብ ነገሮች ጥርግ አድርገን እንወስዳለን ። ኒውዮርክ ውስጥ ሽክ ያለ አፓርታማ እንከራያለን ። እቃዎቹ ሲገቡ ቤቱ እንደዚሁ ደስ ይለናል ። አይመስልሽም ?» አለ ።
እንዲህ እያለ በቤቱ ውስጥ ያሉትን ውብ ነገሮች ሲቃኝ ድንገት ዓይኑ አንድ ነገር ሳይ አረፈ፤ « እንዴ ! ያ ምንድን ነው ?» አለ ወደ ሸራ መወጠሪያ አትሮኖሷ እያመለከተ « አዲስ ሥዕል ነው ?» ብድግ ብሎ ወዶ አትሮኑሱ እየሄደ ፤« መቼ ነው የሠራሽው ? የጀመርሽው ? » አለ። ሥዕሉ ገና ጅምር ቢሆንም የመሳብ ምስጢራዊ ኃይሉ እሚከሰትበት ደረጃ ላይ ደርሷል ። ሥዕሉ የገጸ ምድርን ምስል የያዘ ሲሆን የተፈጠረው ገጸ ምስልም ዛፎች የሚገኙበት አንድ ሜዳን ያሳያል ።

ማይክል ወደ ሥዕሉ ተጠጋ ። በዚህ ጊዜ ሌላ ነገር አጋጠመው ። በሥዕሉ ውስጥ ከሚገኙት ዛፎች ባንደኛው ላይ የተደበቀ ልጅ አየ ። የልጁ እግሮች ተንጠልጥለው እሱም ላለመውደቅ ሽምቅቅ ብሎ ታየው። ሥዕሉን በተመስጦ ሲመለከት ከቆየ በኋላ ወደ ልጁ እያመለከተ ፤
« ሥዕሉ ተስሎ ሲያበቃ ልጁ እንዲህ እንዳለ ይታያል ? ማለት የዛፍ ቅጠልም ሆነ ቅርንጫፍ አይሸፍነውም ?» ሲል ጠየቃት ። «እንዲህ እንዳለ ማለት አይቻልም ። ሆኖም' በሆነ መንገድ ልጁ መኖሩ አይቀርም » አለችው ። ቀጥላም « እንዴት ነው? ወደድከው?» ስትል ጠየቀችው።
ጠየቀችው እንጂ እንደወደደው ፣ እንዳደነቀው ከፊቱ ላይ አንብባለች ። ሥዕሎቿን እንደሱ የሚወዳቸው ሰው አጋጥሟት አያውቅም ። ሐሳቧን እንደሱ የሚረዳላት ሰው የለም ። « ወደድከው ወይ?! አፈቀርኩት እንጂ !» አላት። '
«ነው?»
« አትጠራጠሪ »
« እንግዲያስ ይህ ሥዕል የግልህ ነው ። ለሠርግህ ዕለት የማበረክትልህ ስጦታ ነው » አለች ። «ተስማምቻለሁ ። የሠርግ ወሬ ብታነሺ» አለና ሰዓቱን አዬ ፤ «አሁን መሄድ አለብኝ››
«ምንድነው እሱ?ግድ ዛሬ መሔድ አለብህ ማለት ነው?»
«አዎ መሄድ አለብኝ ። ከምሽቱ አንድ ሰዓት ኒውዮርክ ብደርስ ፤ እንደበረራው ትራፊክ ሁኔታ እቤት አንድ ሰዓት ተኩል ብደርስ ፡፤ ማሪዮንን አነጋግሬ የሠርጋችንን ጉዳይ አዘጋጅቼ ከጨረስኩ በኋላ ወደዚህ ለመመለስ ቢያንስ የመጨረሻዋን አውሮፕላን አገኛለሁ። ተመልሼ እዚሁ ነው እማድረው ። ገቢቶ »
«ገቢቶ » አለች ። ሆኖም ለምን እንደሆነ አትወቅ እንጂ የዚያን ዕለት አካሄዱ በምንም መንገድ ደስ አላላትም ። የሆነ ነገር ቅር ይላታል ። ባይሔድ . . . ባይሔድ የሚል ሐሳብ ይሰማታል።
«ሁሉም ነገር እንዲሳካ እመኛለሁ » አለች ።
«አትጠራጠሪ ፤* ይሳካል » አላት። ሆኖም ራሱ የተናገረውን እንደሚይተማመንበት ሁለቱም ያውቃሉ ። ማሪዮንን ያውቋታላ ። ተቃቅፈው ለረጅም ጊዜ ቆዩ ። ከዚያም ተሰናብቷት ሊወጣ ሲዘጋጅ ፤ «እንግዲህ ይቅናህ አለችው›› «ናንሲ በጣም እወድሻለሁ » ሲል መለሰላት ። ሔደ።

ለረጅም ጊዜ ብቻዋን ቁጭ ብላ እባዛሩ ላይ የተነሱትን ፎቶግራፍ ተመለከተች ። ማይክል ሂልያርድና ናንሲ ማክአሊስተር አይደለም ፤ ርሄት በትለርና ስካርለት ኦሀራ… እነዚህ ሁለቱ ዘለአለም በፍቅር ሲነሱ ይኖራሉ ። ማይክና ናንሲ የርሄትንና የስካርለትን ልብስ ለብሰው ሲታዩ የዚያ አለባበስ ዘመኑ አልፏልና ትንሽ ሞኝ አስመስሏቸዋል ። ሆኖም ደስ ብሏቸዋል። ዋናው ደስታ ነው ።

አዎ ፍቅር ደስታ ነው ። ምነው ማሪዮን ሂልያርድ ይህን መገንዘብ ብትችል ! ሞኝነትና ዶስታ እንደሚለያዩ ብታውቅ! የተለያየ ሰው ነው እንጂ ሞኝ እንደሌለ ቢገባት ። ደስታ ግን ደስታ ነው ። ምነው ማሪዮን በሐሳብና በኑሮ መካከል ያለውን ልዩነት ብታውቅ !፣
ናኒስ ብቻዋን በሐሳብ...
👍18
የመመገቢያ ቤቱ ጠረጴዛ እንደ አንድ ፀጥተኛ ሃይቅ ተንጣሏል ፤ ያብረቀርቃል ። ከዳር እስከዳር ያብረቀርቃል እንዳንል ከወደ አንድ ወገን የሆነ ነገር አርፎበታል፡፡ ይለያል ማለት እንጂ ውበቱን ይቀንሳል ማለት አይደለም ። እጅግ ውብ በሆነ የኪነጥበብ ሥራ የተጌጠው የጠረጴዛ ልብስ ፤በሱ ላይ ያረፈው በሰማያዊና በወርቅማ ቀለም ያጌጠ ሳህንና ባጠገቡ የተቀመጠው የቡና ዕቃዎችን የያዘ ሰርቪስ… ሁሉም ውበት ናቸው ። ከነዚህ አጠገብ የመጥሪያ ደወል ይታያል ። ይህም ደወል ከንጹህ ብር የተሠራ ነው::

ማሪዮን ሂልያርድ ብቻዋን ተቀምጣለች ። ሲጋራዋን ለኩሳ ጭሱን ስባ ወደ ውጭ ካስወጣች በኋላ በረጅሙ ተነፈሰች ። በጣም እንደደከማት ይታወቅባታል ። እሁድ ቢባል ሁል ጊዜም ቢሆን ለሷ አድካሚ ቀን ነው ። አንዳንድ ገዜ ከሥራ ቀኖች ይልቅ እሁድ ሥራ ይበዛብኛል ብላ ታስባለች ። እውነት ነው። እሁድ ለሷ ሥራ የበዛበት አድካሚ ቀን ነው። ለሚደርሷቸ ደብዳቤዎች መልስ መስጠት አለባት ። የቤተሰቡን አስተዳደር የምትከታተለውም እራሷ ናት ። ለቅመም ስንት ወጣ? ምን ያህል ሥጋ ተገዛ? የቤት መወልወያ ሰም… ወዘተ… ሁሉን መቆጣጠር አለባት ። ይህን ደግሞ በሌላ ቀን ልታከናውነው አትችልም ። ማሪዮን የኮተር ሂልያርድ ሥራ አስኪያጅ ናት ። ኮተር ሂልያርድ ዶግሞ ከአንድ መንግሥት የሚስተካከል ግዙፍ የኤርክቴክቸር ድርጅት ነው ።

የቤቱን አያያዝ እሁድ እሁድ ነው የምትቆጣጠረው ። ሥራው አሰልቺና አድካሚ ነው ። እንኳን ዛሬ ባለቤቷ ሞቶ የሱን ሥራ ደርባ በምትሠራበት ጊዜ ያኔም ሥራዋ ይኸው የቤት አስተዳደር በነበረበት ጊዜም ቢሆን የቤት ለቤት ሥራ ለማሪዮን አሰልቺ ነበረ። ሆኖም ሥራ ሥራ ነው ። ኃላፊነት ኃላፈነት ነው ። ስለዚህም ማሪዮን ሥራዋን ትሰራለች ። ዛሬም ያኔም። ብቻ ያኔ ማሪዮን አንድ ደስታ ነበራት ። ያኔ ማንም ማን ሳይሻማት ማይክልን ታቅፈው ታጫውተው ነበር ። ማንም ማን ሳይሻማት ማይክልን ይዛ ሽርሽር ትሔድ ነበር…
ከማይክል ጋር ታሳልፍ የነበረውን ጊዜ ስታስታውስ ትዝታ ውስጥ ተነክራ ሳታስበው አይኗን እንቅልፍ እንደያዛት አድርጋ ጨፈነች።ያ ደስ የሚል ጊዜ ነበር። እነዚያ እሁዶች ልዩ ነበሩ። ያለፈ ጊዜ ትመልሶ የማይመጣ ። ዛሬም ማይክልን ትወደዋለች ። ዛሬም ሁሉን ነገር የምታስበው ለማይክል ነው ። የወንዱንም የሴቱንም ሥራ አጣምራ የምትስራው፤ከሰኞ እስከ ሰኞ ያለ እረፍት የምትደክመው ለማይክል ነው ። ደግሞም ልፋቷ ከንቱ አይደለም ። ይኸውና ይህን ግዙፍ ድርጅት እንደሰፋ እንደተንሰራፋ እንዲደርሰው አድርጋለች ። ከዚህ የበለጠ ቅርስ ፤ ከዚህ የላቀ ውርስ ከየት ሊመጣ ይችሳል ?

ድንገት ትዝ አላት ፤ በሁለት አመቱ ድክ ድክ ሲል፤ያ ሪጅም ዘመን ። ማይክል ታያት። ሀፃኑ ማይክል! ውስጧ በትዝታው በራ
«እንዴት ውብ ሆነሻል ፤አምረሻል እማዬ!»
" ይህን ድምፅ ስትሰማ በቅጽበት አይኗን ገለጠች ። ስታስበው የነበረው ማይክል ልጅዋን ፤ ባላሰበችው ጊዜ እፊቷ ቆሞ ስታየው እይኗን ማመን አቃታት ። ሆኖም እውነት ነውና ነገሩ አስደነቃት ። ተነስታ ልክ እንደሀፃንነቱ አቅፋ ልትስመው ፈለገች ፤ ግን አስፈላጊ አይደለም ። የዚያ አይነቱ ስሜታዊ ነገር አጉል ልቡን ያለሰልሰዋል ስትል አሰበች ። ስለዚሀም ስሜቷን አምቃ ቀዝቀዝ ባለ አነጋገር…


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍15
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_አንድ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ከአንድ ዓመት በላይ ዐለፈ።

የጀርመን ያባሕር ዳርቻ መዝናኛዎች በመከሩ ወራት ጀመሪ ላይ በሕዝብ
ተጨናንቀዋል " እነዚህ ቦታዎች በዚሀ ወራት በብዛት እየጉረፉ በሚመጡ እንግሊዞች መሞላታቸው የተለመደ ነው ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደገና ወደ አገራቸው ይመለሳሉ " ስታልከንበርግ በተለይ በዚያ ዓመት በእንግዶች ጢም ብላ ተሞልታለች
ከተማይቱ ስሟን ዝናዋን ሌላም የሷ የሆነ ነገር ሁሉ ያገኘችው ከባላባቱ ከባሮን ቮን እስታልከንበርግ ነው ባርኑ ትክለ ቁመናው ግዙፍና ጠንካራ ጢሙና የራስ ጸጉሩ ሽበት የቀላቀለ ከዕድሜውም ገፋ ያለ በሥን ምግባሩ በአደን
ከሚገድላቸው ከርከሮዎች ያልተሻለ ስድ ነበር በግዝፈት ባባታቸው መጠን የወጡ አራት ወንዶች ልጆች ነበሩት » የመጀመሪያ ልጁ አብዛኛውን ጊዜ ትንሹ ባሮን
ሲባል ሶስቱ ግን የስታልከን በርግ ካውንቶች በሚል የማዕረግ ስም ይጠራሉ » ስለዚህ አንዱን ከሌላው መለየት የሚቻለው በክርስትና ስማቸው ነው ሁለቱ ወታደሮች ሆነው ሔደዋል የመጀመሪያውና የመጨረሻው ልጆች ግን ከአባታቸው ጋር እስታልከን በርግ ግምብ ውስጥ ይኖራሉ ይህ የወላለቀ አሮጌ ግምብ የሚገኘው
ከእስታልከንበርግ ከተማ አንድ ማይል ያህል ወጣ ብሎ ነው " ወጣቱ ባሮን ለማግባት ነፃ ነበር » ሦስቱ ግን ራሷንና ባለቤቷን ማስተዳዶር የሚያስችል ሀብት ያላት ሚስት ካላገኙ በቀር ትዳር ለመያዝ አልፈለጉም ።

እስታልከንበርግ መሰሎቿ ከሆኑት ሌሎች የመዝናኛ ሥፍራዎች የምትለይበት የላትም የሚያምሩ ዛፎች ደስ የሚል ጠቅላላ ትዕይንት የዳንስ የሙዚቃ
ትዕይንት በትእዛዝ የሚዘጋጅ ምግብ ሕዝብ የሚራኮትባቸው የቁማር ጠረጴዛዎች የእግር መንሸራሸሪያ ቦታዎችና የመታጠቢያ ጸበሎች አሏት በተለይ ጸበሎቹ በብዛት ከታጠቡባቸው ማንኛውም ዐይነት በሕሊና የታሰበ በአካል የደረሰ በሽታ ሁሉ ማለት ከሚጥል ሕመም እስከ ፍቅር ትኰሳት ድረስ ይፈውሳሉ እየተባለ በሰፊው ይነገርላቸዋል ይታመንባቸዋል " ለብዙዎቹም እንደ እምነታቸው ተሳክቶላቸዋል

ወጣቱ ባሮን ካባቱ ጋር በማስተያየት ወጣት ተባለ እንጂ ዐርባ አንድ ዓመት
ሞልቶታል በመልኩና በአውሬ አዳኝነቱ ስመ ጥር ሰው ነው " በተለይ የከርከሮና የተኩላ ፀር መሆኑ በስፋት ይነገርለታል ከወንድሙ በዐሥራ አንድ ዓመት ያንስ የነበረው ካውንት ኦቶፎን እስታልክንበርግ ሪዙን በማፍተልተል በመብላትና
በመጠጣት ልማድ ካልሆነ በቀር ሌላ የሚታወቅበት ሙያ የለውም ሽማግሌው
ባሮንም ሆነ ወራሹና የመጀመሪያ ልጁ ወጣቱ ባሮን ስለ መዝናናትና ስለ ቅንጦት ተጨንቀው አያውቁም " የእስታልክንበርግ ግንብ ምግብ እምብዛም
እንደነበር ይነገርለታል ስለዚህ ካውንት ኦቶ ጋባዥ ባገኘ ቁጥር ከሆቴሉ እየሔደ ለመመገብ
ዐይኑን አያሽም ካውንት ኦቶ እስቶልከንበርግ ሙሉ ባለቤትና አስተዳዳሪ በመሆኑ በራሱ ከባድ ማዕረግና ባባቱ ሙሉ ባለሥልጣንነት በመጠቀም በየጊዜው እየተጋበዘ ከሆቴሉ ይመጣል ።

በቦታው የሚገኘው የታወቀው ሆቴል ሉድቢግባድ ይባላል " ሚስተር ክሮ ሰቢ የተባለ ሰው ሚስቱንና ተከታይ የሌላት አንዲት ልጁን የሷን አስተማሪና ሁለት ወይም ሦስት የቤት ሠራተኞችን ይዞ ከዚሁ ሆቴል ዐርፋል
ኢንግላንድ ውስጥ የሰራው
ነገር ወይም የደረሰበት በደል አይታወቅም እሱ ግን ወደ ትውልድ አገሩ ሊመለስ ቀርቶ አስቦት አያውቅም » በውጭ አግር ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ መኖር ከጀመረ ብዙ ዘመን ሆኖታል

ሚስዝ ክሮስቢይ የደስ ደስ ያላት ተጫዋች ሴት ስትሆን ልጂዋ ሑሌና ክሮስቢም
ደስ የምትል ያሥራ ሰባት ዓመት ቆንጆ ናት ልጂቱ በመልኳም በጠባይዋም ሆነ በአካሏ መዳበር የትልቅ ሰው ሁኔታ ስለሚታይባት ላላወቃት ሰው በዕድሜዋም የበሰለች ትመስላለች » ከዚህም በላይ አንድ አጎቷ ሲሞት ባመት ሠላሳ ሺህ ፓውንድ የሚያስገኝ ውርስ ትቶላታል እናቷ ስትሞት ደግሞ የዐሥር ሺህ ፓውንድ
ያመት ገቢ ውርስ ትጠብቃለች » ካውንት
ኦቶ ፎን እስታልከንበርግ ስለ ሠላላ ሺህ ፓውንድ ውርስ ሲሰማ ፊቱን ወደ ሚስ ሔሌና መለሰ "

“ እንዴ ሠላሳ ሺ ፓውንድና ቆንጆ ልጅ ! ታዲያ እኔስ ከዚህ ሌላ ምን ስጠብቅ ኑሬአለሁ ! አለ ለራሱ "

ስለ ሀብቷ የሰማው ወሬ ትክክለኛ መሆኑን አረጋገጠ " ከዚያ ወዲህ ከክሮስቢ
ቤተሰብ ጋር መቃረብ ጀመረ የዘወትር ጠያቂያቸው ሆነ እሱ ከነሱ ባይለይ ደስ እንደሚለው እነሱም የሱን ቀረቤታ ወደዱት ሌሎች የእስታልከንበርግ እንግዶች ቀኑበት እነሱም ያችን መሳይ ቆንጆ ካለችበት ቤተሰብ ጋር መወዳጀትን ተመኙ " ሚስተር ክሮስቢ ግን ወጣቱን ካውንት ልጁና ሚስቱ ባዩት ዐይን አይቶት
እንደሆነ አይታወቅም " በትሕትና ሲቀርበው እሱም በደስታ ይቀበለዋል "

አንድ ቀን ሽማግሌዉ የእስታልንከንበርግ ባሮን በሠረገላ መጣ " መቸም የሠረገላው ቅርጽና የብር ጌጦች ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ታይቶ አይታወቅም " የአያቶቹ ኩራትና ቅርስ ሆኖ በክብር ተቀምጧል ኑሮ ኑሮ አንዳንድ ጊዜ ካልሆነ በቀር
ከተቀመጠበት አይነቃነቅም በብር ያጌጠ አረንጓዴ ልብስ የለበሱ ምርጥ አሽከሮች አጅበውት ከሎድቪግ ባድ ሆቴል በራፍ ተጠግቶ ቆመ የሆቴሉ ኗሪ በየመስኮቱ
ሆኖ ለማየት ግልብጥ ብሎ አሰፈሰፈ " ሽማግሌዉ መኮንን የመጣው ሚስተር ክሮስቢ ዘንድ ስለሆነ እሱም በታላቅ አክብሮት ተቀብሎ ወደ ሳሎን አስገባው “ ኃያሉ ባሮን ከዚያ ወይም ከዚ Oረፍ ይበሉ ! አለው …

“ ኃያሉ ባሮን የመጣው ክሮስቢን ከሚስቱና ከልጁ ጋር ግብዣ ሊጠራው
ነው " በባሮኑ ቤተ ግምብ ከዚያ በፊት ያልታየ ታላቅ ድግስ ካለፈ ጥቂት ቀኖች
ቆይቶ ካውንት ኦቶፎን እስታልከንበርግ ልጂቱን ሔሌናን ለሚስትነት ለመነ "
ጥያቄውም ተቀባይነት አላጣም ።"

“ ገና ልጅ ናትኮ ” አለ ሚስተር ክሮስቢ በቅሬታ ሁለት ዓመት ብቻ ቢጠብቁ ስለ ጥያቄዎቹ ምንም ተቃውሞ አይኖረኝም ነበር

“ እንዴ እንዴ ! ሁለት ዓመት ይጠብቅ ብለን ሌሎች ይውሰዱብን ብለህ ነው
አይሆንም ተው እነዚህ የእስታልከንበርግ ካውንቶች እኮ አይታመኑም ” አለችው ሚስቱ።

ታድያ ቢሆንሳ ! እሱ በማዕረጉና በሐረጉ ቢመካ ሔሌና ደግሞ በገንዘቧ ትመካለች።

እንግዲያ በደንብ ተመጣጥነዋል ማለት ነው " እኔ ደግሞ እሱን አላሰብኩትም ካውንቴስ ፎን እስታልከንበርግ ሲል ብቻ ለጆሮ ደስ ሲል አዳምጠውማ !

“ ያን ቀፋፊ ሪዙን ወዲያ ቢጥለው ደስ ባለኝ ” አለ ሚስተር ክሮስቢ "

“አንተ ደሞ የማያሳስበው ጥቃቅኑ ነገር ሁሉ ያሳስብሀል ሔሌና እንደ
ሆነች በጣም ወዳለታለች » አሁን የቸገረን ያስተማሪዋ ነገር ነው።

"የሷ ደግሞ ምንድነው ችግሯ ?

እኔ የቀጠርኳት እስከ ገና ስለሆነ ሌላ ስራ ካላገኘሁላት እስከዚያ ድራስ
ደሞዝ መክፈል ሊኖርብኝ ነው "

“እንደ እኔስ ሄሊና አሁን ከምታገባ ከአስተማሪዋ ጋር ብትቆይ ይሻል ነበር"
ሴቶች ልጆች በትንሽነታቸው ሲያገቡ ደስ አይለኝም " አሁን እዚህ ያሉ እንግሊዞች
ምን እንደሚሉ አላውቅም ።

አንተ ካልተናገርክ በቀር ስለ ዕድሜዋ ማንም አያውቅም ዛሬ እሷ ለራሷ ሙሉ ሴት እንጂ ልጅ አትመስልም እንግሊዞችማ እንደዚያ ያለ ዕድል ለነሱ ስላልገጠማቸው በቅናት ከመብሰልሰል በቀር ሌላ ምን ሊሉ ኖረዋል?

ሚስተር ክሮስቢ ተቃውሞው ሁሉ እየከሸፈ ሲያስቸግረው ዝም አለ "
በዚህ መነታረኩ ዋጋ እንደሌለው ዐወቀው "

ሔሌና ክሮስቢ ደሞ በበኩሏ ወደ አስተማሪዋ እየሮጠች ሒዳ ! ማዳም ማዳም ባል ላገባ እኮ ነው ! " አለቻት "

ማዳም ጥውልግ ያለውን ፊቷን ቀና አድርጋ አየቻትና እውነት !” አለቻት
👍152
“ ትምህርቴንም ከዛሬ ጀምሮ ይበቃሻል ብላኛለች እናቴ "

“ ግን ለማግባት ገና ልጅ ነሽ ኮ ሔሌና አለቻት አስተማሪቱ ።

“አንቺም አባባን ይመስል እንዲህ አትበይ «እሱም እየደጋግመ እንደዚህ
ይለኛል "

ካውንት ኦቶን ነው?” አለቻት አስተማሪቱ ምንም እንኳን ሔሌና 'ማዳም ” እያለች ብትጠራትም ሴትየዋ የጠራ የእንግሊዝኛ ድምፅ አወራረድ እንዳላት በግልጽ ይታወቅ ነበር ።
አዎን ካውንት ኦቶን እንጂ ሌላ ላገባ ኖሯል!”

አስተማሪዩቱ ሌላ ሳትሆን ወይዘሮ ሳቤላ ቬን ናት " አይሆኑ ሁና ልውጥውጥ
ብላለች " ብዙ የለዋወጣት የባቡር አደጋ ሲሆን ከሱ የተረፈውን ኀዘንና ጸጸት አስተካክሎታል " ስትራመድ ትንሽ ታነክሳለች « ከትከሻዋ ስግደድ ማለቷም ከቁመቷ ቀንሶባታል " ከላይ አገጯ ጀምሮ የተዘረጋው ጠባሳዋ በታች በኩል የፊቷን ፈጽሞ ሌላ አስመስሏታል "
ጥርሶቿም ጥቂቸቹ ስለ ወለቁ ስትናገር ተኮላተፋለች
የሸበተው ጸጉሯን ጥቅልል አድርጋ ጥብቅ ቆብ ደፍታበታለች እሷም ራሷ የመታወቅ ሥጋትን ለማጥፋት መነጽር ሰክታ አንድ ሰፊ አረንጓዴ ሻሽ እስከ ቅንድቧ ዝቅ አድርጋ ጠምጥማለች " ይኸም መልካም ቅርጿንና መልኳን ለማጥፋት ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል " ወፍራም ዐይነ ርግብ ሳታደርግ ከቤት አትወጣም ሚስዝ ዱሲ እና ሴቶች ልጆቿ እስታልከንበር ውስጥ ሲሰነብቱ በጭራሽ አላወቋትም " ስለዚህ እንጻትታመቅ የነበራት ሥጋት መወገዱን ተገነዘበች በመልከ መልካሟ ወይዘሮ በዱሮይቱ ሳቤላ ቬንና በዛሬይቱ ማዳም ቬን መካከል ምንም ግንኙነት አይታይም " ሚስተር ካርላይል ራሱ እንኳን ቢያያት ሊያውቃት አይችልም " ይሁንና
ይህ ሁሉ ለውጥ ቢደርስባትም መልኳ አሁንም ይስባል እርጋታዋና የደስ ደስ ያለው ግጽታዋም አልጠፋም ሰዎች ያን በመሰለ የወጣት መልክ የሽበት ጸጉር ማየታቸው ይገረሙ ነበር።

በባቡሩ አደጋ ከደረሰባት ጕዳት ካገገመች በኋላ በዚያ አካባቢ ወደ ነበረ አንድ ከተማ ሔደች የክሮስቢ ቤተሰቦች እዚያ ከተማ ውስጥ ይቀመጡ ስለ ነበር የሔለና ተመላላሽ አስተማሪ አድርገው ቀጥረዋት ከነሱ ጋር ሁለት ዓመት ያህል ተቀመጠች።

ለክሮስቢ ቤተስቦች እንግሊዛዊት መሆኗን ፈረንሳዊ ባሏ እንደ ሞተባት ነገረቻቸው ስለ ራሷ የበለጠ እንድታብራራ ብትጠየቅም ብዙ ልትነግራቸው አልፈቀደችም
ሔሌናን እየተመላለሰች ስታስተምር ከፍተኛ ግምት
አሳደረችባቸው ተመላላሽነቷ ቀርቶ ከቤት ጠቅልላ እንድትባ አደረጉ " ስዎቹ እንግሊዞች ወደሚያዘወትሩት የባሕር ዳርቻ መናፈሻ እንደሚሔዱ ብትጠረጥር ኖሮ ቅጥሩንም ለመቀበል ታመነታ ነበር ኋላ ግን ጠቀማት ሚስዝ ዱሲ ሳቤላን እስታል ከንበርግ ላይ ስታገኛት አላወቀቻትም " በዚህ ጊዜ ማንም ድሮ የሚያውቃት ሰው ቢያያት እንደማይለያት ተማመነች"ብዙ መለወጧን አረጋገጠች ተንግዲህ ያለ ምንም ሥጋት የትም መሄድ እንደምትችል ተረዳች።

አሁን አንጀት አንጀቷን እየበላት የመንፈስ ዕረፍት ያስጨነቃት የልጆቿ ናፍቆት ሆነ " እስኪ አንዲት እናት ማንም ትሁን ምን ለትንሽ ጊዜ ከልጆቿ ተለይታ ትዋል ትደርና ናፍቆቱ እንዴት እንደሚያደርጋት እሷው ትናገር የመዝናናት ጉዞ ለማድረግ በመሔድ ለጥቂት ሳምንቶች ብትለያቸው እንኳን
ትንንሽ ፊታቸውን ማየቱ የሚንተባተቡት ምላሶቻቸውን መስማቱ ለስላሳ ጉንጮቻቸውን መሳሙ ! ሌላው ቀርቶ እማማ ደኅና ነሽ ወይ የሚለውን መልእክታቸውን መቀበሎ ምን ያህል
እንደሚያስጨንቅ : ከሁሉ
የበለጠ የሚሰማት ፡ እሷ ናት " ልጆቿን የማየት ፍላጐቷ ከቁጥጥሯ ውጭ ይሆንባታል እነሱ ወዳሉበት በረሽ ሒጂ የሚል ይመጣባታል " የመለየቷ ጊዜ በረዘመ ቁጥር የናፍቆቷ ብሶት ይጠናባታል ታዲያ የዚህ ዐይነቱን ናፍቆት ለብዙ ዓመት በወላድ አንጀቷ እያጠራቀመች ችላው ለኖረችው ለሳቤላ ቬን ምን ያህል ይከብዳት ልጇቿን ስፍስፍ ብላ ትወዳቸው ነበር " ስለ ደኅንነታቸ ስለ አስተዳደጋቸው ከልክ
ያለፈ ትጠበብላቸው ነበር ዛሬ እንዲህ ችላው ልትኖር!ልጆን ከባዕድ እጅ ለመጣል ! ባዕድ ሰው ሥነ ሥርዓት እንዲያስተምራቸው ሐሳብ አልነበራትም "
ይኸን ሁሉ ቁጭ ብላ ታስበውና እጆቿን ዐይኖቿ ላይ ዘርግታ ታቃስታለች "...

ናፍቆቷ እያደር እየጠናባት ሔዶ ትኩሳት ሆነባት አእምሮዋንና ሰውነቷን
ባንድ ጊዜ አጣምሮ የሚለክፍ ትኩሳት የገረጡት ከንፈሮቿ በየጊዜው እየደረቁ
የገዛ ጭንቀቷ በፈጠረው እሳት እየተጠበሱ ከስውነት ወጣች ከሦስት ዓመት
በፊት ሎርድ ማውንት እስቨርን ግሮኖብል ላይ ከጠየቃት ወዲህ ከኤስትሊን ምንም
ነገር ሰምታ አታውቅም " ልጆቿን ለአንድ ቀን ቀርቶ ለአንድ ስዓት እንኳን ቢሆን
አይናቸውን አይታ ከንፈሮቻቸውን ስማ እፎይ ብትል በጣም ትመኝ ነበር "
አሁንም ቢሆን ይህን ካላደረገች ለመኖር የምትችል አልመስላት አለ።

በመጨረሻ እንዲህ ሆነ " ሚስዢ ላቲመር የምትባል የዌስትሊን ነዋሪ የሆነች
ወይዘሮ እንደ ገረድና አነጋጋሪም እንድትሆናት አፊ ሆሊጆንን አስከትላ ወደ
እስታልክንበርግ መጣች አፊ ከመቤቲቱ ጋር አብራ ትቀመጣለች ወይም ትበላለች ማለት ሳይሆን ከብዙ እመቤቶች ደንገጡሮች የተሻለ የመቅረብ ዕድል ነበራት እሷ ደግሞ ይህንን ጫፍ በመያዝ ጓደኛዋ እንደ ሆነች አድርጋ ታወራ ነበር » ሚስዝ ላቲመር ደግ ሰው ነበረች አፊም አባቷ በተገደለበት ጊዜ በነበረው
ሁኔታ የራሷን ታሪክ እያሠማመረች ለመቤቲቱ ታጫውታት ስለ ነበር በጣም ወደደቻት የሚስዝ ላቲመር ክፍል ከሚስዝ ክሮስቢ ቀጥሎ ስለ ነበር ' ሁለቱ ሴቶች ከመተዋወቅ ዐልፈው ባልንጀሮች ሆኑ " የመጀመሪያዋ ሎድዊግ ከገባች ሳምንት ሳይሆናት ምናልባት ሁለቱም ከሌሎች ጋር ብዙ ጊዜ እንዳደረጉት
ለዘለዓለም እትማማችነት ቃል ተጋቡ ".....

💫ይቀጥላል💫
👍83
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


የደማውን እጇን በውሃ አጣጥባ በፎጣ አድርቃ በፋሻ አሰረችው:፡
ለምንድነው የፈራሁት? ስትል ራሷን ጠየቀች አይገድለኝ፤ ሊከለክለኝም
አይችልም፤ እድሜዬ ከ21 አመት በላይ ነው! ይህም አገር ነፃ አገር ነው! በማለት ራሷን ለማሳመን ሞከረች፡፡

ይህም ሆኖ ግን ልትረጋጋ አልቻለችም፡

ጠረጴዛው ላይ የገበታ እቃዎች ደረደረችና ሰላጣ አጠበች፡፡ መርቪን ስራ ወዳድ ቢሆንም እቤቱ የሚመጣው በሰዓቱ ነው፡፡ በሙያው ኢንጂነር ሲሆን ከአይሮፕላን ሞተር መዘውሮች ጀምሮ እስከ ማቀዝቀዣ ሲስተሞችና የመርከብ መፍቻዎች ድረስ ያሉትን ዕቃዎች የሚያመርት ፋብሪካ ባለቤትና ጥሩ የቢዝነስ ሰው ነው፡፡ መርቪን የአይሮፕላን ሞተሮች መስራት ከጀመረ
ጀምሮ ነው ገንዘብ በሻንጣ መቁጠር የጀመረው፡፡ የመዝናኛ አይሮፕላን ማብረር የጊዜ ማሳለፊያው ሲሆን ለዚህም ሲል ትንሽ አይሮፕላን ገዝቷል።
መንግስት አየር ኃይል ሲያቋቁም የአይሮፕላን ሞተር መስራት ከሚችሉት ጥቂት ሰዎች ውስጥ መርቪን አንዱ ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህማ መርቪን ያለ
እረፍት ይሰራል፡፡

ዳያና ሁለተኛ ሚስቱ ስትሆን የመጀመሪያ ሚስቱ ሁለቱን ልጆቹን ይዛ ሌላ ሰው አግብታ ከሄደች ሰባት ዓመት ሆኗታል፡ መርቪንም ፊርማውን ቶሎ ቀደደና ዳያናን ላግባሽ ብሎ ጠየቃት፡፡ መርቪን ፈርጠም ያለና ኪሱ ረብጣ ገንዘብ ያለው ከመሆኑም በላይ ዳያናን ከማፍቀርም አልፎ ያመልካት
ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የጋብቻ ስጦታ ብሎ ያበረከተላት የአልማዝ ሀብል ነበር፡፡

የአምስት ዓመት የጋብቻ በዓላቸውን ሲያከብሩ ግን ስጦታ ብሎ
ያበረከተላት የልብስ ስፌት መኪና ነው፡፡ የስፌት መኪናውን ሲሰጣት ትዳሯ እንዳበቃለት ተገነዘበች፡፡ መኪና መንዳት ስለምትችል የራሷ መኪና እንዲኖራት ትመኝ ነበር፤ መርቪን ደግሞ የመግዛት አቅም አለው፡፡ አምስት ዓመት ሙሉ አብረው ሲኖሩ ልብስ ሰፍታ እንደማታውቅ እንኳን
አልተገነዘበም፡፡

ባሏ እንደሚወዳት ብታውቅም እሱ ግን ከሚስትነቷ ውጭ ትኩረት
አይሰጣትም፡፡ እቤት ውስጥ ሚስት የምትባል ሴት እንዳለች፣ ቆንጆ
እንደሆነች፣ በሴትነቷ የሚጠበቅባትን ማህበራዊ ህይወት የማታጓድል፣ምግቡን ሰራርታ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ የምትጠብቅ፣ አልጋም ላይ ፈቃደኛ
የሆነች ሴት አለችው ታዲያ ሚስት ከዚህ በላይ ምን ይጠበቅባታል በእሱ አስተሳሰብ፡፡ ስለምንም ነገር አማክሯት አያውቅም እሷ የቢዝነስ ሰው ወይም ኢንጂነር ባለመሆኗ በሱ ቤት አንጎል የላትም፡፡ ከሷ ይልቅ ፋብሪካው ውስጥ ካሉት ሰዎች ጋር ብዙ ጠቃሚ ሃሳቦችን ይለዋወጣል፡ በሱ አመለካከት መኪና ለወንዶች፣ የስፌት መኪና ደግሞ ለሴቶች ነው፡፡

መርቪን ከልጅነቱም ጮሌ ነበር፡ አባቱ የማሽን ኦፕሬተር ነበሩ¨
መርቪን በማንቼስተር ዩኒቨርስቲ ፊዚክስ ያጠና ሲሆን ለማስተርስ ዲግሪው እንዲያጠና በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ዕድል ቢያገኝም እሱ ግን የትምህርት ሳይሆን የተግባር ሰው በመሆኑ በአንድ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ውስጥ የዲዛይን መምሪያ ውስጥ ተቀጠረ፡፡ በዓለም ላይ በፊዚክስ መስክ የሚደረጉትን
ግስጋሴዎች የሚከታተል ሲሆን ከአባቱ ጋርም ስለነዚህ ነገሮች ይወያይ ነበር፡ ከዳያና ጋር ግን እንደዚህ አይነት ነገር መነጋገር ሲያልፍም አይነካካውም::

እንደ ዕድል ሆኖ ዳያና ፊዚክስ ባለበት ድርሽ ብላ አታውቅም፡፡
አይገባትም፡፡ እሷን የሚጥማት ሙዚቃ፣ ስነጽሑፍ ከፍ ካለም ታሪክ ብቻ ነው:፡ መርቪን ደግሞ ከፊልምና ከዳንስ በስተቀር ሌላው አይጥመውም፡፡ስለዚህ እነሱን የሚያነጋግር ነገር የለም ማለት ነው:

ልጅ ቢኖራቸው ኖሮ ነገሮች ይለዋወጡ ነበር፡፡ መርቪን ከመጀመሪያ ሚስቱ ሁለት ልጅ ስለወለደ ሌላ ልጅ አይፈልግም፡፡ ዕድሉን ቢሰጣት ልጆቹን ማቅረብ ትፈልግ ነበር፤ በየት በኩል? የልጆቹ እናት ከአባታቸው ጋር የነበራት ጋብቻ ያፈረሰው በዳያና ምክንያት መሆኑን በመናገር የልጆቹን
አዕምሮ ስለመረዘች ደመኛ አድርገዋታል፡፡ ታዲያ የእናትነት ፍላጎቷን የምትወጣው ሊቨርፑል ውስጥ በምትኖረው እህቷ መንታ ልጆች ነው፡፡

ክፋቱ አሜሪካ ከሄደች ልጆቹ እንደሚናፍቋት ጥርጥር የለውም፡፡

መርቪን ከከተማው ነጋዴዎችና ባለስልጣናት ጋር ስለመሰረተ በፊት በፊት እቤት በጋበዛቸው ቁጥር እነሱን ማስተናገድ
ያስደስታታል፡ ለጥሩ ልብስ ያላት ፍቅር ከፍተኛ ሲሆን ልብስም
ያምርባታል፡ ነገር ግን ህይወት ማለት ከመልበስም በላይ መሆኑን
ትረዳለች፡

የሚያውቋት ሴቶች መጠጥ የማያበዛ፣ ታማኝ፣ ደግ ባልና ጥሩ
መኖሪያ ቤት ስላላት ዕድለኛ ናት ብለው ያምናሉ፡ ሆኖም እሷ ደስተኛ
አይደለችም፡፡ የማታ የማታ ግን ማርክ የተዘጋ ልቧን ከፈተው፡፡
የመርቪን መኪና ግቢ ሲገባ ሰማች፡፡ የመኪናው ድምጽ የለመደችው ቢሆንም ዛሬ ግን የአውሬ ድምጽ መሰላት፡፡

መጥበሻውን ምድጃው ላይ ስትጥድ እጇ ተንቀጠቀጠ፡፡ መርቪን ወደ ማድ ቤት ገባ፡ ባሏ ነፍስ የሚያስት ቁመና ያለው ሲሆን በጥቁር ፀጉሩ ላይ ጣል ጣል ያደረገበት ሽበቱ የተለየ ግርማ ሞገስ ሰጥቶታል፡፡ ቁመቱ ሎጋ
ሲሆን እንደ ጓደኞቹ ቀፈታም አይደለም፡፡ ኩራተኛም ባይሆን ዳያና በጥሩ ልብስ ሰፊ የተሰፋ ሱፍ ልብስና ውድ ሸሚዞች እንዲለብስ አድርጋዋለች፡፡

ዳያና መጨነቋን ከፊቷ ላይ አንብቦ ምንድን ነው ነገሩ ብሎ
ይጠይቀኛል ብላ ሰግታለች።

መጥቶ ከንፈሯን ሲስማት ሀፍረቷን ውጣ እሷም ሳመችው፡፡ አንዳንድ
ጊዜ እቅፍ አድርጎ በእጁ የቂጧን ፍንካች ሲደባብስ ይሟሟቁና ወደ መኝታ ቤት ሲሮጡ ምድጃው ላይ ያለው ምግብ አርሮ ይጠብቃቸዋል አሁን አሁን ግን እንዲህ አይነት ነገር እምብዛም አያደርጉም፡፡ ዛሬም ከወትሮው የተለየ አይደለም፡፡ እንደ ነገሩ ሳም አደረጋትና ዞር አለ፡፡
ኮቱን፣ ሰደርያውንና ክራቫቱን አውልቆ የሸሚዙን እጀታ ጠቀለለና ፊት መታጠቢያው ላይ ፊቱንና እጁን ታጠበ፡፡ የትከሻው መስፋትና የክንዱ መፈርጠም ለጉድ ነው፡
አሁን አልነግረውም አለች በልቧ፡
ጋዜጣ እያነበበ ስለሆነ ከቁብም አልቆጠራት፡፡

ድንቹ ምድጃው ላይ ሲንጨረጨር ሻይ ጥዳ ዳቦውን ማርጋሪን ቀባች:
የእጇን መንቀጥቀጥ ባሏ እንዳያውቅባት ለመደበቅ እየሞከረች ነው መርቪን
‹‹ስራ ቦታ ውስጥ አንድ በጥባጭ ሲበጠብጠኝ ዋለ›› አላት ሰሃኑን ፊቱ ስታስቀምጥ።

‹እኔ ምን ቸገረኝ ታዲያ አለች በሆዷ እኔ እንደሆነ ከዚህ በኋላ
በቅተኸኛል፡፡› ለምን ሻይህን አፈላውልህ?›

‹‹ደሞዝ እንድጨምርለት ጠየቀኝ፣ እኔ ደግሞ ለመጨመር ዝግጁ
አይደለሁም›› አላት፡፡

ዳያና ፍርሃቷን ዋጥ አድርጋ ‹‹አንድ የምነግርህ ነገር አለ›› አለች:
የተናገረችውን ነገር መልሳ ብትውጥ ወደደች፤ ግን አንዴ አምልጧታል፡

‹‹ጣትሽ ምን ሆነ?›› ሲል ጠየቃት በፋሻ የታሰረውን ጣቷን አይቶ፡

ይህ ጥያቄ ትንሽ ከጭንቀቷ መለስ አደረጋት ‹‹ምንም›› አለች ወንበሩ
ላይ ዘፍ እያለች ‹‹ድንች ስቆርጥ ቢላ ቆረጠኝ›› ብላ ሹካና ማንኪያዋን አነሳች፡:

መርቪን ምግቡን ስልቅጥ አድርጎ በላና ‹‹ከዚህ በኋላ ሰው ስቀጥር
መጠንቀቅ አለብኝ: ችግሩ ጥሩ ባለሙያዎችን ማግኘት በአሁን ጊዜ
አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ ነው፡››

ስለ ስራው ሲናገር አስተያየት እንድትሰጥ አትጠበቅም፡፡ ሀሳብ የሰጠች እንደሆን ይገላምጣታል፡፡ እሷ እንደሆን ለእሱ ለማዳመጥ ብቻ የተፈጠረች ፍጡር ናት፡፡
👍23🥰1👏1
እሱ ስለአዲሱ ሰራተኛ ሲያነበንብ እሷ የሰርጓ ቀን በሃሳቧ መጣባት።
የተጋቡት ማንቺስተር ውስጥ ሲሆን በሚድላንድ ሆቴል ድል ያለ ድግስ
ተደግሶ ነበር፡ መርቪን የሙሽራ ልብሱን ለብሶ በመላው ኢንግላንድ ካሉ ወንዶች ሁሉ አይን የሚማርክ ሆኖ ነበር የዋለው፡ ዳያና በዛን ጊዜ እንዲህ እንደሆነ ይቀጥላል ብላ ገምታ ነበር፡፡ ጋብቻቸው እንዲህ ባጭሩ ይቀጫል ብላ አስባም አታውቅም፡፡ ይህ ሁሉ በሃሳቧ መጥቶ አልቅሽ አልቅሽ አላት።

መርቪን ጥላው ስትሄድ አእምሮው እንደሚበጠበጥ ታውቋታል”
በአዕምሮዋ ምን እንደሚመላለስ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ የመጀመሪያ ሚስቱ በዚህ ሁኔታ ጥላው ስለሄደች በዳያና መሄድ ኑሮው ምስቅልቅሉ መውጣቱ አይቀርም፡፡

የሥጋ ጥብሱን በቢላ እየቆረጠ በሹካ እየወጋ ከበላ በኋላ ሻይ ደገመ፡፡

‹‹ብዙም አልበላሽ›› አላት፡፡ እውነትም እራቷን አልነካችውም፡:
‹‹ምሳዬን ጥርቅም አድርጌ ስለበላሁ አልራበኝም›› አለች
‹‹የት ሄደሽ ነበር?››

እንደ ቀልድ የጣለው ጥያቄ አስበረገጋት፡፡ ከማርክ ጋር አልጋ ላይ ሆነው ሳንድዊች በልተዋል፡፡ ሊታመን የሚችል ውሸት ብታስብ አልመጣላት አላት፡ ማንቺስተር ውስጥ ያሉት ጥሩ ጥሩ ምግብ ቤቶች በአዕምሮዋ መጡ፤ ነገር ግን አንዳቸውጋ መርቪን ምሳ መብላቱ አይቀርም፡፡ ትንሽ
አስጨናቂ ደቂቃዎች ቆየችና ‹‹ዋልዶርፍ ካፌ›› አለች፡፡ በርካሽ ዋጋ ስጋና ድንች ጥብስ የሚሸጡ ዋልዶርፍ ካፌዎች በከተማዋ ውስጥ እዚህም እዚያም
አሉ፡፡ መርቪን ግን የትኛውጋ እንደበላች አልጠየቃትም፡:

ሰሃኑን ሰብስባ ብድግ ስትል ጉልበቷ ሲብረከረክባት የምትወድቅ መሰላት፡ ሰሃን ማጠቢያው ድረስ እንደ ምንም ሄደችና ‹‹ጣፋጭ ትፈልጋለህ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎን›› አላት

ወተትና ኬክ አመጣችለት፡ ልትነግረው ትልና ልቧ በፍርሃት ይርዳል፡፡
በኋላ ግን ልትነግረው አቅም ማጣቷ ታወቃት፡፡

መርቪን ማንኪያውን ስኒ ማስቀመጫው ላይ አኖረና ሰዓቱን
ተመለከተ፡ ‹‹አንድ ሰዓት ተኩል ሆኗል፡ እስቲ ሬዲዮ ክፈቺና ዜና
እንስማ›› አላት፡

‹‹አልችልም›› አለች ከሃሳቧ ጋር እየተሟገተች፡፡

‹‹ምን አልሽ?››

‹‹አልችልም›› አለች ሳይታወቃት እንደገና ውጥኗን ልትሰርዘው ነው፡፡
ማርክጋ ሄዳ ሃሳቧን የለወጠች መሆኑን ልትነግረው ነው
እንደማትሄድ ልታረዳው፡፡

ዳያና ባሏ ላይ አፈጠጠችበት፡፡ እውነቱን ፍርጥ ልታደርግለት ዳዳት
ነገር ግን ወኔ አጥታለች፡፡

‹‹መሄድ አለብኝ›› አለችው አንድ የሆነ ማስመሰያ ነገር ወዲያው
አውጠንጥና ‹‹ዶሪስ ዊልያምስ ታማ ሆስፒታል ተኝታለች፤ ሄጄ ልጠይቃት ነው››
‹‹ማናት ዶሪስ ዊልያምስ ለመሆኑ?››

እንደዚህ አይነት ሰው የለም፡፡
‹‹ከዚህ በፊት እኮ ታውቃታለህ, አለች ዳያና አፏ እንዳመጣላት፧
‹‹ኦፕሬሽን ተደርጋለች››

‹‹አላስታውሳትም›› አለ፡፡ ይህን ሲል ግን የጠረጠረው ነገር የለም፡፡
ለነገሩ ብዙም የማያውቀውን ሰው የሚያስታውስ አዕምሮ የለውም፡፡

ዳያናም በድፍረት ‹‹ታደርሰኛለህ?›› ብላ ጠየቀችው:

‹‹ኧረ እኔ አልሄድም›› አላት፡፡

‹‹እንግዲያው ራሴ በመኪና እሄዳለሁ›› አለች፡

‹‹በጨለማ በፍጥነት አትንጂ፡፡›› ከመቀመጫው ተነሳና ሬዲዮ ሊከፍት ሄደ።

ዳያና ከኋላው ባሏን እያየችው ትቼው መሄዴን መቼም ቢሆን
አያውቅም› ስትል በሀዘኔታ አሰበች፡፡

ኮፍያዋን ራሷ ላይ ደፋችና ኮቷን ክንዷ ላይ አድርጋ ወጣች፡ እግዜር
ይስጠውና የመኪናው ሞተር ባንዴ ተረክ ብሎ ተነሳ፡፡ መኪናዋን እየነዳች ከግቢ ወጣችና የማንቺስተርን አቅጣጫ ይዛ ተፈተለከችበጣም ብትቸኩልም የመኪናዋ የፊት መብራት በጦርነቱ ምክንያት ብርሃኑ እንዲቀንስ በመጋረዱ በደንብ ስለማይታያት የኤሊ ጉዞ ለመጓዝ ተገደደች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እምባዋ እየተንዠቀዠቀ በመሆኑ በከፊል
እይታዋን ጋርዶባታል፡ መንገዱን ባታውቀው ኖሮ መጋጨቷ የማይቀር ነበር፡፡

ከቤቷ እስከምትሄድበት ቦታ ድረስ አስር ኪ.ሜ ያህል ቢሆንም ጉዞው
አንድ ሰዓት ያህል ፈጀባት፡፡
ሚድላንድ ሆቴል ደርሳ ስታቆም ሙሉ በሙሉ ሰውነቷ ዝሎ ነበር፡
ራሷን ለማረጋጋት አንድ ደቂቃ ያህል ቆየችና አልቅሳ የነበረች መሆኗ
እንዳይታወቅባት ፊቷን በፓውደር ደባበሰች።

ማርክ አብራው እንደማትጠፋ ስትነግረው ልቡ እንደሚሰበር ጥርጥር ባይኖርም መቻል አለበት፡፡ የአምስት አመት ጋብቻ ከሚፈርስ መቼም የሚጥም አጭር የፍቅር አለም ቢቋረጥ ይሻላል፡ መቼም የተዋወቁባትን ዓመት ባስታወሱ ቁጥር እሷና ማርክ ከንፈራቸውን መምጠጣቸው አይቀርም፡፡

እንደገና ለቅሶዋን ለቀቀችው:

እዚህ ቁጭ ብሎ ማሰቡ ዋጋ የለውም፤ ቀጥታ ማርክ ያለበት ሆቴል ሄዳ ሁሉም ነገር እንዳበቃለት ትነግረዋለች ፊቷን በሜካፕ አሰማመረችና ከመኪናዋ ወጣች፡፡

የሆቴሉን መተላለፊያ አቋርጣ በቀጥታ ወደ ማርክ ክፍል አመራች፡
የማርክን አልቤርጎ ቁጥር ታውቃለች፡፡ ምንም እንኳን ሴት ልጅ ወንድ ልጅ አልቤርጎ ብቻዋን መሄዷ አሳፋሪ ቢሆንም አይኗን በጨው አጥባ ለመሄድ ወስናለች፡፡ ሌላው አማራጭ ማርክን የሆቴሉ እንግዳ መቀበያ ጋ ወይም ቡና ቤቱ ውስጥ ጠርታ መንገር ነው፡፡ ነገር ግን እንዲህ ያለውን ዱብ ዕዳ ሰው
ፊት ልትነግረው አልፈለገችም፡፡ አካባቢውን ዞራ ባለማየቷ ሰው ይያት አይያት የምታውቀው ነገር የለም፡፡
በሩን ቆረቆረች፡፡ ክፍሉ ውስጥ ባላጣው› ስትል ተመኘች፡፡ ምግብ
ለመብላት ወይም ሲኒማ ለመግባት
ሄዶ ከሆነስ? መልስ ስታጣ እንደገና
በደንብ አንኳኳች፡ እንዴት በዚህ ጊዜ ይሄዳል?

ከአፍታ በኋላ ‹‹ማነው?›› የሚል ድምፅ ሰማች፡፡

‹‹እኔ ነኝ!›› አለች፡፡

ፈጠን ያለ የኮቴ ድምፅ ሰማች፡፡ በሩ ወለል ብሎ ተከፈተና ማርክ
በግርታ አያት፡፡ ከዚያም ፊቱ በደስታ እያበራ ወደ ውስጥ ጎትቶ በሩን ዘጋና እቅፉ ውስጥ ጣላት፡፡

ወዲያው መርቪን ላይ የፈፀመችው የክህደት ዓይነት ስሜት በማርክ
ላይ መፈጸሟ ተሰማት፡፡ በፀፀት ከንፈሩን ስትጨመጭመው የደስታ ሙቀት በደም ስሯ ሲሰራጭ ተሰማት፡፡ ብዙም ሳይቆይ ግን ‹‹ካንተ ጋር አልሄድም›› አለችው፡፡

ማርክ ፊቱ በድንጋጤ አመድ መሰለ፡፡ ‹‹ተይ እንጂ እንዲህ አትበይ›› ክፍሉን እየተዘዋወረች ስትቃኝ ዕቃ እየሸካከፈ መሆኑን አወቀች፡፡ ቁም ሳጥኑና መሳቢያዎቹ በሙሉ ተከፋፍተዋል፡፡ የተከፈቱ ሻንጣዎች ወለሉ ላይ
ይታያሉ፡፡ የታጠፉ ሸሚዞች፣ የውስጥ ሱሪዎችና ካናቴራዎች እንዲሁም ጫማዎች በየቦርሳው ውስጥ ተሸጉጠዋል፡፡ መቼም ጽዳቱን ሲጠብቅ ለጉድ ነው፡፡

‹‹አብሬህ አልሄድም›› አለችው፡፡
እጇን ሳብ አደረገና ወደ መኝታ ክፍሉ ይዟት ገባ፡፡ አልጋው ላይ
አስቀመጣትና ‹‹ከልብሽ ነው?›› ሲል ጠየቃት እየተርበተበተ፡፡

‹‹መርቪን ይወደኛል፡፡ የአምስት ዓመት ባሌ ስለሆነ እንዲህ ያለ ግፍ
በሱ ላይ መፈጸም የለብኝም››

‹‹እኔስ?›› ሲል ጠየቃት

ዳያና ከላይ እስከታች አለባበሱን ስታይ ማርክ አምሮበታል፡፡ ልብ
ይሰርቃል፡፡ ‹‹ሁለታችሁም እንደምትወዱኝ አውቃለሁ›› አለች ‹‹እሱ ግን ባሌ ነው፡፡››
‹‹እሱ ይወድሻል፡፡ እኔ ግን አፈቅርሻለሁ›› አላት ማርክ፡፡
‹‹እሱስ የማያፈቅረኝ ይመስልሃል?››

‹‹ከነመኖርሽ ረስቶሻል፤ አድምጪኝ!
ዕድሜዬ ሰላሳ አምስት ቢሆንም
ካንቺ በፊት ፍቅር አውቃለሁ፡ አንድ ወቅት ላይ እንደውም ስድስት ዓመት የዘለቀ ፍቅር አሳልፌያለሁ፡ ከዚህ በፊት ትዳር መስርቼ ባላውቅም አሁን ወደዚያው እያመራሁ ነው፡፡ አሁን አሁን በእውነት ትዳር ትዳር እያለኝ
ነው፡፡ አንቺ ደግሞ እዚህ ቀረሽ የማትባይ ቆንጆ ነሽ፤ እንደኔም ተጫዋችና ሳቂታ ነሽ፡፡ ስለዚህ አሁኑኑ አልጋ ላይ እንድንወጣ እፈልጋለሁ›› አላት፡፡
👍17👏1
‹‹አይሆንም›› አለች ከልቧ እንዳልሆነ እየታወቃት፡፡

ሳብ ሲያደርጋት እሷም ተሳበችለትና ተማጠጡ፡፡

‹‹አንቺ ለኔ እኔ ላንቺ የተፈጠርን
መሆኑ ይሰማኛል›› ሲል አጉተመተመ:: ‹‹እዚያ ላይብረሪ ውስጥ ሆነን በወረቀት እየተጻጻፍን
የተለዋወጥነውን መልእክት ታስታውሻለሽ? አንቺ እኮ የጨዋታው ህግ ወዲያው ነው የገባሽ፡፡ ሌሎች ሴቶች ቢሆኑ ጨርቁን ጥሏል እንዴ ነበር የሚሉኝ አንቺም በዚህ ሁኔታዬ ነው የወደድሺኝ፡:››

እውነት ነው› አለች በልቧ፡ ፒፓ ብታጨስ ወይም ያለፓንት ቤት
ውስጥ መንጎራደድ ያለ እንግዳ ነገር ብታደርግ ባሏ በንዴት የሚንጨረጨር ሲሆን ማርክ ቢሆን ግን በሳቅ ልቡ ይፈርሳል

ደጸጉሯን ማፍተልተል ጉንጮቿን መደባበስ ጀመረ፡፡ ቀስ በቀስ ፍርሃቷ ለቀቃትና ሰውነቷ መፍታታት ጀመረ፡፡ ራሷን ትከሻው ላይ ደፋችና በከንፈሯ አንገቱን መዳሰሱን ተያያዘችው፡፡ እጁን በቀሚሷ ስር ሰዶ ከስቶኪንጓ በላይ
ያለውን ጭኗን ቀስ እያለ ሲደባብስ የእጁ ሙቀት ተሰማት፡ ይህ ይሆናል ብላ ስላልጠበቀች እግሮቿ ገላዋን መሸከም አቃታቸው፡

አልጋው ላይ ገፍተር አድርጎ ሲጥላት ኮፍያዋ ተሽቀነጠረ

‹‹ተው ይቅርብን›› አለች በደከመ ድምፅ፡፡ በከንፈሩ እያንዳንዱን
ከንፈሯን እየቆነጣጠረ መጠጣቸው፡: ጣቶቹን ከሃር በተሰራው ፓንቷ ውስጥ
ጨምሮ ሲያርመሰምሳቸው በወሲብ ባህር ውስጥ ሰጠመች፡፡

ሁሉን ነገር ጨርሰው ሲተቃቀፉ ሰውነቷ ይንቀጠቀጥ ነበር፡ ከእቅፏ
ውስጥ እንዲወጣ አልፈለገችም::
ጥላው እንደምትሄድ ለባሏ አትነግረውም፡፡ መልሳ መላልሳ የማርክ ፈጣን አዕምሮ ያፈለቀላትን መፍትሄ በአዕምሮዋ እያጠናች ወደ ቤቷ አመራች፡፡

መርቪን ፒጃማውን ለብሶ ሲጋራውን እያቦነነ ሬዲዮ ሲያዳምጥ
አገኘችው፡፡ ‹‹በጣም ቆየሽ›› አለ ብዙም ሳይቆጣ፡፡

ዳያናም ዘና ብላ ‹‹ቀስ እያልኩ ነው የነዳሁት›› አለችና ትንፋሿን ዋጥ
አድርጋ ‹‹ነገ መሄዴ ነው›› አለችው፡፡ ‹‹እህቴንና ልጆቹን ሄጄ አያቸዋለሁ
ናፍቀውኛል፡፡ ባቡር እንደበፊቱ ሁል ጊዜ ስለማይገኝ ይህን እድል አላገኝም፡
የነዳጅ ራሽንም የሚቀጥለው ሳምንት ይጀምራል እየተባለ ነው›› አለችው።

በስምምነት ራሱን ነቀነቀ፡፡ ‹‹ልክ ነሽ ከሄድሽ አሁኑኑ ሂጂ››
‹‹አሁኑኑ ሻንጣዬን ልቀረቅብ ነው፡፡››
‹‹ለኔም ሻንጣዬን አሳስሪልኝ›› አላት፡፡
እንዲህ ሲል ከኔ ጋር ሊሄድ ፈለገ እንዴ?› ስትል አሰበች፡፡ ‹‹ለምን?››
ስትል ጠየቀችው፣ በድንጋጤ፡
‹‹ባዶ ቤት አልተኛም›› አላት ‹‹ክለብ ሄጄ አሳልፋለሁ፤ ረቡዕ መቼም
ትመለሻለሽ፡፡››
‹‹አዎ ረቡዕ እመለሳለሁ›› ስትል ዋሸች፡፡
‹‹ደህና››

ፎቅ ላይ የሚገኘው መኝታ ቤታቸው ሄደችና የውስጥ ሱሪዎቹንና
ካልሲዎቹን ሻንጣ ውስጥ ስትከት ይህን የማደርገው ለመጨረሻ ጊዜ ነው ስትል በልቧ አሰበች፡ የነገረችውን የፈጠራ ታሪክ መቀበሉ እረፍት ሰጣት ነገር ግን የሆነ ነገር የረሳች እየመሰላት መበርገጓ አልቀረም፡፡ እሱን አተካራ
መግጠሙን ብትፈራም ለምን ትታው እንደምትሄድ ልትነግረው ከጅሏታል እድሜ ልኳን ሲጨቁናት መኖሩንና አዕምሮ ቢስ መሆኑን እንዲሁም እንደቀድሞው የማያቀማጥላት
ልትነግረው የማትችል መሆኑን መንገር አሰኝቷት ነበር፡፡ ይህን
አስቆጭቷታል፡፡

ሻንጣዎቹን ዘጋጋችና
የሜክ አፕ እቃዎቿን ቦርሳ ውስጥ
ጨመረቻቸው: የአምስት አመት ጋብቻ በዚህ አይነት ማለቁ አስቂኝ
ሆኖባታል፡

ትንሽ ቆይቶ መርቪን መጣ፡፡ ሻንጣ ማሳሰሩን አጠናቃ መስታወት ፊት
ቁጭ ብላ ሜክ አፕ እየተቀባች ነው፡፡ ከኋላዋ መጣና ጡቶቿን ጨበጥ አደረጋቸው፡:

ተው አይሆንም፧ ዛሬስ ይቅር! አለች በልቧ፡

ምንም እንኳን ሰውነቷ ለወሲብ ቢነሳሳም በማርክ ላይ የሄደች መስሏት ድርጊቱ አሳፈራት፡፡ መርቪን የጡቷን ጫፎች ሲያፍተለትላቸው በወሲብ ደስታ ጫን ጫን መተንፈስ ጀመረች፡፡ እጇን ያዝ አድርጎ ከመቀመጫዋ አስነሳትና ወደ አልጋው ሲወስዳት በእሺታ ተከተለችው፡፡ መብራቱን አጠፋና
በጨለማ ውስጥ እቅፍቅፍ ብለው ተኙ፡፡ ልክ ትታው እንደምትሄድ ያወቀ ይመስል እላይዋ ላይ ወጥቶ በሙሉ ሃይሉ ወሲብ ይፈፅምባት ጀመር፡፡

ሰውነቷም አሳጣትና እፍረቷን ውጣ በወሲብ ደስታ መናጧን ተያያዘችው፡: በሁለት ሰዓት ጊዜ ውስጥ ከሁለት የተለያዩ ስዎች ጋር ወሲብ ፈፅማ የወሲብ እርካታ ላይ መድረሷ አሳፈራትና ስሜቷን ልታምቅ ብትሞክርም
አልሆነላትም፡ የመጨረሻ ወሲባዊ እርካታ ስታገኝ ጮኸች፡፡ መርቪን ግን ይህንም አላስተዋለም፡፡...

ይቀጥላል
👍24