🗻የጠንቋዩ ዋሻ🗻
🙈ክፍል 14🙈
💔💔💔🗾💔💔💔
ጠንቋዩ አቢያራ በዋሻው ውስጥ አስተዳድራቸዋለው ብሎ የሚያስባቸውንና እንደባሪያው የሚያዛቸውን አገልጋዮቹን ዛሬ በተለየ መልኩ ሰብስቧቸዋል ፣ ሁሉም የመሰብሰባቸው ምክንያት ስላልተገለፀላቸው እርስ በእርስ ከመተያየት በቀር ምንም መተንፈስ አልቻሉም አቢያራ ዙፋኔ ብሎ ከሚጠራው ትልቅ መቀመጫላይ ጥቁሩን አስፈሪ አልባሳቱን እንደለበሰ ቀያይ ዛጎሎች በእጁ ይዞ እያወዛወዘ አጎንብሶ በቀስታ የማይገቡ ቃላቶችን እያወጣ ነው ፣የአቢያራ ሴቶች እንዳቀረቀሩ ናቸው ፣ አልፎ አልፎ ኤዛ ብቻ ባልተለመደ ጭንቀት ተወጥራ በጨረፍታ ወደመሳይ አየት የምታደርገው ፣የሆነ ነገር ሸቷታል አቢያራ አንዳች ነገር ለማድረግ እስካላሰበ ድረስ በዚ መልኩ አይሰበስባቸውም ወይ በሷ ላይ ወይ በመሳይ ላይ አንዳች ጉዳት ሊደርስባቸው እንደው ተሰምቷታል ።።
ኤሊያታ እንዳቀረቀረች ከፊትለፊቷ ስለምትሰማው የአቢያራ ሹክሹክታ አንድ ነገር ለመረዳት ጥረት እያደረገች ነው ፣ ኤፍራም ግራ እንደገባት ነው ያለችው አድማስ አቢያራ የሚያዘውን ሁሉ ለመፈፀም ተዘጋጅቶ እየጠበቀ ነው ፣ መሳይ የአቢያራን አንገት የሚቀነጥስበት አንድ ስለት በድንገት እጁላይ እንዲያርፍ ተመኘ አነመስፍን ምን ያጠፋነው ነገር ይኖር ይሆን ብለው በራሳቸው ውስጥ በጨንቀት ጠፍተዋል ። ቤቱ እንዲ በፀጥታ ሲታመስ ቆይቶ ፣ ድንገት አቢያራ ብድግ ብሎ ሲቆም የሁሉም ልብ ቀጥ ያለ መሰለ ።አቢያራ ጥቂት ሲንጎራደድ ቆይቶ በአስፈሪ እና የተሰበረ በሚመስል ድምፅ መናገር ጀመረ "
"እእእእ ዛሬ እዚ የሰበሰብኳቹ አባቴ አንድ ነገር እንዳደርግ ስላዘዘኝ ነው እኔን በእናንተ ላይ የሾመኝ አባቴ የኔ ጌታ ከልጆቼ ውስጥ አንዷን መስዋት እንዳደርግ አዞኛል እንደምን እንቢ ማለት ይቻለኛል ፣በርግጥ ልቤ አዝኗል ግን አባቴ የኔንም ሕይወት ቢጠይቀኝ እሰጠዋለው ልጆቼ ለአባታቹ ጥያቄ መቼስ በደስታ መላሾች ናቹ እኔም ልክ እንደዛ ነው ያሳደኳቹ እናም አንድ ነገር ያጎደለች ልጅ አለች ከናንተ መካከል ለዚህም ነው አባቴ ወደሱ የጠራት "ብሎ አቢያራ ፀጥ ሲል
መሳይ በጥላቻና በፍራቻ ቀና ብሎ ተመለከተው ፣ይሄ ጠንቋይ ሴጣንነቱ ይበልጥ ጨምሯል ማለት ነው ሰውን እያጭበረበረ የደም ጥማቱን እየተወጣነው ፣በቃ ኤዛን ሊያጠፋት ነው ስለኔና ስለሷ አውቋል ማለት ነው ብሎ በማሰብ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ ።
አድማስ ኤዛን ዞር ብሎ አይቶ አቀረቀረ ኤዛ አድማስ ሲያያት ይሄ ድግስ ለሷ እንደሆነ በማሰብ በፍርሃት አድማስ በቀኝ እጁ የያዛትን የተሸፈነች ስለት ተመለከተች ፣ ኤልያታ ለጓደኛዋ በማዘን ዞራ አየቻት እናም በአንድ አይኗ እንባዋ ኮለል አለች እህታማችነታቸው ማብቂያው ደረሰ ልጅነታቸው የዋሻው ውስጥ የፀጥታ ኑሯቸው ታወሳት ግንአቢያራ ካለ አለ ነው በቃ ፣እነ መስፍን ጉዳዩ እነሱን ስለማይመለከት በግልግል መንፈስ ተንፍስ አሉ ፣ እነሱም የአቢያራ ተጠቂ የምትሆነው ኤዛ እንደሆነችና ለዚሁሉ ችግር የዳረጋት ደሞ ጓደኛቸው መሳይ እንደሆነ ተሰምቷቸዋል ። አቢያራ ከጎነ በጣም ቀረብ ብሎ ወደቆመው አድማስ እያየ ይበልጥ እንዲቀርበው ምልክት ሰጠው ። አድማስ ስለቱን እየነካካ ወደ አቢያራ ተጠጋ አቢያራ ለአድማስ በሹክሹክታ ተናገረ በዚ ጊዜ አድማስ ግራ በመጋባትና በድንጋጤ አቢያራ ላይ አፈጠጠ ፣አቢያራ መልህክቱን እንደዘበት ለአድማስ ከነገረ በዋላ ወደ ኤሊያታ አፈጠጠ እናም እረጃጅም ጥፍር አማ ጣቶቹን ወደ ኤልያታ ቀስሮ "የኔ ልጅ አንቺ የጌታዬ ምርጫ ነሽ "ብሎ በሚያስፈራ ድምፁ ኤልያታን እንድትቀርበው ጠራት ። እዛ የነበሩት ሁሉ ግራ በመጋባት አንዴ ኤልያታን አንዴ አቢያራን ተመለከቱ ኤልያታም አልገባትም ነገር ግን ወደሱ መንቀሳቀስ ስትጀምር አድማስ የሚያፈቅራትን ሴት በገዛ እጁ እንዲሰዋት በመታዘዙ ዘገነነውና አይደረግም ብሎ ሳያስበው ጮኽ ፣ በዚ ድምፁ ጠንቋዩ እራሱ ሳይደነግጥ አልቀረም ፣ መሳይ የአድማስን ቁጣ ሲያይ ደስ አለው በዚ አጋጣሚ አንድ ነገር ለመፍጠር እራሱን አዘጋጀ ........
✍ ሙና መሀመድ
ይቀጥላል
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️

👍24😱2
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...የነበሩበት ክፍል መዝጊያው ቤቱን ሊያፈርስ የሚችል በመሰለ ' እንደ ነጎድጎድ
በሚጮህ ድምፅ ተንኳኳ ወንጀለኛን አስሰሙ እንዲያመጡ ሕጋዊ ትእዛዝ
የያዙ የሕግ አስከባሪዎች እንኳን ከዚህ የበለጠ አስደንጋጭ ድምፅ አሰሙ ተብለው አያውቁም " ሪቻርድ ሔር ፊቱ ባንድ ጊዜ ዐመድ መሰለ » ዐይኖቹ ተጎለጎሉ ስሱ የራሱ ጸጉሩ ሽቅብ ቆመ የሥራ ካፖርቱን እየተርበተበተ አጥልቆ ባርኔጣውን ደፍቶ የውሸት ሪዙን አጥልቆ የሚገባበት ቁም ሳጥን ወይም የሚሾልክበት ቀዳዳ ለመፈለግ የክፍሉን ዙሪያ በዐይኑ ቃኘና ምንም ሲያጣ ወደ ሳሎኑ እሳት ሔደ።
አንድ እግሩን ከመከላከያው ብረት ላይ አሳረፈ እሳቱን እንዴት ሊያልፈው እንደሚችል ምንም ሳያስብ በጢስ መውጫው አድርጎ ሽቅብ ለመውጣት ፈለገ ከሚደበደበው በር አንድ የተቆጣ ድምፅ በቁልፉ ቀዳዳ ሲንረጨረጨር ሚስተር ካርላይል ረጋ ብሎ ትከሻውን ይዞ ወዶ ኋላ ሳበው "
ሪቻርድ ወንድ ወንድ ሽተት ይህን ፍራትህን ወዲያ ጣል "ከኔ ቤት ሆነህ ምንም አንደማይመጣብህ አልነግርኩህም ? አለው ሚስተር ካርላይል »
እኔ እኮ የለንደኑ ፖሊስ መኮንን ወታዶርች ጨምሮ መጥቶ አስከብቦኝ እንደ ሆነ ብዬ ነው።
እንዲያው ዝም ብለህ ነው " በል አሁን ዐርፈህ ተቀመጥ ኮርኒሊያ ናት " እሷ.. ደግም አንተን ከክፉ ለመጠበቅ የኔን ያህል ነው የምታስብልህ"
"ናት እንዴ ? አለ ከጫንቃው ከባድ ሽክም እንደ ወረደለት የቀለለው ሪቻርድ ግን በውጭ ልትመልሳት አትችልም ? አለው ጥርሶቹ አሁንም እየተንቀጫቀጩ
"እሷ ለመግባት ከወሰነች እኔ ልመልሳት አልችልም አንተማ ከወትሮ ታቃት የለም አንዴ ? እስከ ዛፌ ምንም አልተለወጠችም ያው ናት - -
ድርቅናዋ ከተነሣባት እሱ በውስጥ እሷ በውጭ ሆኖ በሩ እንደ ተዘጋ ማነጋገር
ዋጋ እንደሌለው ገባው " ስለዚህ ሚስተር ካርላይል በሩን ቀስ አድርጎ በጠባቡ
ከፍቶ ራሱ ወጣና መልሶ ዘጋው " በዚያ ቁመቷ ቁጣ ጨምራበት ወጋግራ መስላ
ቁማ አግኛት
,
ሚስ ካርላይል አጥሚት እንዲመጣላት አዝዛ ጉንፋኗን ይዛ ወደ መኝታ
ቤቷ ሔዳ ነበር " ወዲያውኑ ከራሷ በመጀመር የሌሊት ልብሷን መልበስ ቀጠለች የቀን ቆቧን አወለቀች
የሌሊቱን አጠለቀች " ይህ አስራሚ ቅርጽና መጠን…, ያለው ቆብ ቀደም ሲል ተገልጿል ቀጠለችና ስለ ራስ መጠምጠሚያዋ አሰበች " ሦስት ሜትር በሦስት ሜትር የሆነ ጨርቅ አመጣችና እንደ ምንም ብላ በሙሉ ሸፈነችው
የጨርቁ ዐይነት ለመጠምጠም አስቸጋሪ ስለነበር ስትጠመጥም ሲተረተርባት ስታውል እየተፈታ ሲሾልክባት ሥራው ብዙ ጊዜ ፈጀባት " የዚህ ሁሉ ልፋቷ ውጤት ግን በጣም የሚያስደንቅ ሆነ " ሥዕል ተነሥቶ በእንግሊዝ ቤተ መዘክር ቢቀመጥ የሚያሰኝ ነበር " ከጭንቅላቷ ላይ እንደ ፒራሚድ ቆመ " ጥምጥሟ ሁለት ጫፎች በግንባሯ ተንዘልዝለዋል "
ሚስ ካርላይል ከፎቅ ሆና ሻሿን ስትከብስ ፡ ስታፈርስ ስትቋጥር ስታሳምር
ወንድሟን ትታው ከመጣችበት ክፍል የንግግር ድምፅ ሰማች " በሁሉ ነገር ንቁ ብትሆንም ፡ በተለይ የመስማት ተሰጥኦ ነበራት " በመጀመሪያ ወንድሟ የሚያነብ
መሰላት ። ነገር ግን ወዲያው ሐሳቧን ለወጠች “ ማነው አብሮት ያለው ? አለች አጠገቧ መልስ ሰጭ ያለ ይመስል ድምጿን ከፍ አድርጋ ።
የራስ ጥምጥሟን አስተካክላ አበቃችና መጥሪያውን ስትደውለው ጆይስ ገባች
“ ከጌታሽ ጋር ማን አለ ?
" ማንም የለም እሜቴ ”
- መኖርማ አለ ሲነጋገርኮ እየሰማሁ ነው "
“ ኧረ እኔስ ማንም ያለ አልመሰለኝም " ደግሞ ግድግዳዎቹ በጣም ጥብቅ
ሆኑ ከሳሎን የተነገረ ነገር ከታችኛው ቤት እዚህ ድረስ መስማቱ ያስቸግራል ”
“እንማዲህ ያንቼ ዕውቀት እዚህ ድረስ ነው ከዚያ ክፍል ንግግር ካለ ቀጥታ
ድምፅ" አዚህ ይሰማል እኔ ከልምድ ዐውቀዋለሁ " ይልቁንስ ሒጅና ማን እንደ
ሆነ አይተሽ ነይ "
ሚስ ካርላይል'ጆይስን ልካ እሷ የቀን ልብሷን በሌሊት ልብስ የመተካት ሥራ
ዋን ቀጠለች » ከቀሚሷ ቀጥላ የሐር የውስጥ ልብሷን አወለቀች » ከዚያ ከሞቃቱ የውስጥ ጥብቆዋ ስትደርስ 'ጆይስ ተመልሳ መጣች "
“ እና እውነት ነው
እማማ ጌቶች ከሰው ጋር ይነጋገራሉ " ነገር ግን በሩ
ስለ ተቆለፈና ጌቶችም ሥራ ስለ ያዙ እንዳልገባ ነግረውኝ ተመልሼ መጣሁ” አለቻት
ሚስ ካርላይል ለአንጐሏ ምግብ አገኘች » በዚያ ሰዓት ማንም የውጭ እንግዳ ሊመጣ እንደማይችል በገዛ ግምቷ አረጋግጣ ከቤተሰቡ ውስጥ ማን ሊሆን እንደሚ
ችል ጥቂት አሰበች » ከሚስተር ካርላይል ጋር ቤት ዘግታ ለማውጋት የምትደፍር ያቺ የልጆች አስተማሪ ሚስ ማኒንግ ናት ብላ ደመደመች » ልጂቱ መልከኛ ስለ ነበረች
እንግዲህ የሚስ ካርላይልን መተኛት አይታ ተሠርቃ በመግባት የምትጫወት
ሚስ ካርላይል ከሚስተር ካርይል ጋር እንዳትቃረብ ትጠባበቃት ነበር ። አሁን
መሰላት በር የሚዘጋበት ምክንያት ሊኖር እንደማይችል እያውጠነጠነች
ወደ ሳሎን ወረደች "
“ከዚህ ክፍል አብሮህ ያለ ማነው ? አለችው ቆጣ ብላ
“ አንድ ለሥራ ጉዳይ የመጣ እንግዳ ነው ” አላትና ፈጥኖም " ኮርኒሊያ
መግባት አትችይም ” አላት
ሣቋ መጣባት „ “ መግባት አትችይም ? ! "
“ በውነቱ ባትገቢ ይሻላል ፤ እባክሽ ተመለሽ ፤እዚህ ቁመሽ ጉንፋንሽን ታጠነክሪዋለሽ ።
የለም በሥራህ አለማፈርህን ለማወቅ እፈልጋለሁ አንተ ያገባህ ሰው ነህ ልጆች ከቤት አሉህ አንተ እንደዚሀ ካለው ቅሌት ውስጥ ትገባለህ ብዬ አልጠረ
ጥርም ። ከራሴ ይልቅ አንተን አብልጬ አምን ነበር
ሚስተር ካርላይል ዐይኑን አፍጦ ቀረ ።
“ዘወር በልልኝ አሁን አስወጣታለሁ ከዚህ ቤት ወጥታ ደግሞ ነገ እየዞረች ትለምናለች ። ሁለት ደፋሮች እግሬ ከመውጣቱ መቸም ሔዳለች ብላችሁ ቤት
ዘግታችሁ መቀመጥ ! አሁን ወግድልኝ ዘወርበል አርኪባልድ እገባለሁ ! ”
ሚስተር ካርላይል ደግሞ እንደዚህ ሣቁ መጥቶበት አያውቅም ። እኅቴ
ደግሞ ሁኔታውን አይታ የበለጠ ስትናደድ አስተማሪይቱ ከግራጫዉ ሳሎን ወጥታ የግድግዳ ሰዓት ተመልክታ ተመልሳ ስትገባ አየቻት ።
“ እንዴ እዚያ ናትሳ ! እኔኮ ካንተ ጋር ያለች መሰለኝ ”
ሚስ ማኒንግ እኔ ዘንድ ነች ብለሽ ነው ! ? ይህ ነው በአእምሮሽ ሲመላለስብሽ
የነበረው ሐሳብ ? እውነትም ጉንፋኑ አእምሮሽን ጋርዶታል
ግድ የለም ያም ሆነ ይህ ያለውን ሰው ገብቸ አያለሁ ” አለችው
ምን ቸገረኝ ግድ ልግባ ካልሽ ግቢ » ግን ኀዘን እንጂ ደስታ እንደማታዬ
አስቀድሚ ላስጠንቅቅሽ " ከውስጥ ያለችው ሴት አይደለችም " ወንድ ነው ተፈልጎ እንዲያዝ የተበየነበት ! ካሁን አሁን ፖሊሶች ተከታትለው መጡብኝ እያለ የሚርበተበት አዳኝ እንዳሳደደው አጋዘን እየተሳደዶ በመስኮት ዘሎ የገባ ሰው ነው ከውስጥ ያለው ማን መሆኑን ዐወቅሽው ?”
አሁን ደግሞ አፍጥጦ መቆሙ የሚስ ካርይል ተራ ሆነ
ያንቺው ዘመድ ሪቻርድ ሔር ነው " በዚህ ነፍስ የሚያወጣ አስጨናቂ ሌሊት የሚጠጋበት ጣራ የሚገባበት በር የለም ዝም ብላ ስትተክዝ ቆየችና በሩን እንዲከፍት ምልክት ሰጠች
መቸም እንደዚህ ሆነሽ ለብሰሽ የምትገቢ አይመስለኝም
“ለምን በልጅነቱ ዐስር ጊዜ ስገርፈው ለነበረው ለሪቻርድ ሔር ነው ደሞ
የምጨነቅለት ? አለባበሱ እንኳን እሱም ከኔ አይሻልም እሱ ወደዚህ መምጣቱ ግን ፍጹም ዕብደት ነው

👍14❤1
እንድትገባ ሲያሳልፋት በሩን እንድትወጋ ነገራት ። እሱ ወደ ኋላ ቆርቶ ፒተርን ጠርቶ ለሁለት ሰው ራትና አንድ ማብረጃ ቢራ ከምግብ ቤቱ ጠረጴዛ እንዲቀርብ አዘዘ ከአንድ እንግዳ ጋር ምናልባትም ብዙ ሊያስመሽ የሚችል ሥራ ስለ አለበት ሰራተኞች ሁሉ እንዲተኙ ካልደወለ በቀር ማንም ወደሱ አካባቢ በመምጣት እንዳይረብሸው አስጠንቅቆ ወደ ነበረበት ክፍል ተመለሰ።
ሪቻርድና ሚስ ካርላይል እንደ ተፋጠጡ አገኛቸው
ሪቻርድ በርግጥ በሕይወቱ ብዙ ዐይነት አስደናቂ አለባበሶችን አይቷል ነገር
ግን እስከ ዛሬ ካሁኑ የሚስ ርላይል አለባበስ ጋር የሚስተካከል አላጋጠመውም እንዲያውም እንደሷና እንደሱ ሆነው የለበሱ ሁለት ሰዎች እንዳሁኑ ፊት ለፊት ተጋጥመው አያውቁም ። እሷ ጥቁር ጫማ ጥቁር የእግር ሹራቦች ከባቷ ድረስ የወረደ የሌሊት ኮት ፡ ይህን ይመስላል ብሎ ለመግለጽ የሚያስቸግር ያንገት ልብስና ሲያዩት የሚያስቀይም ከዚያ በፊት በዚች መሬት ተመሳሳይ ያልተኘለት የራ ጥጥም አድርጋ እሱ ደግሞ
ከመናኛ የተልባ እግር የተሠራ ፡ አዝራሮቹ በከፊል
የተበጠሱበት ልብስና ጭርምትምት ያለ ባርኔጣ ደፍቶ : ቸምቸም ያለ ሪዝ፡ በፍራት የሚንቀጠቀጡ እጆች ፡ በድንጋጤ ዱቄት መስሎ የነጣ ፊት ! በውጭ አገር ብዙ እሥቂኝ የሆኑ የፈንጠዝያ ትርዒቶች ተመልክቻለሁ ነጋር ግን ከነዚህ ሁሉቱ ጋር
የሚደርስ አላየሁም ። በኒስ ወይም በሮም የትርዒት ሰገነቶች ቢቀርቡ ማንም ሳይጠጋቸው ያሸንፉ ነበር ።
“ እባክሽን በሩን ዝጊው ኮርኒሊያ ብሎ ጀመረ ይንቀጠቀጥ የነበረው ሪቻርድ በአለባበሷ ተገርሞ ከእግር እስከ ራሷ ሲያያት ቆይቶ ካለፈለት በኋላ ።
“ መዝጊያውስ ተዘግቷል አንተ ግን ወዲህ ምን አመጣህ ... ሪቻርድ ?
ከዕብድ ትብሳለሀ ።
“ ከሎንደን የቦው ስትሪት ፖሊሶች አሳደዱኝ ” አላት ።
“ ከዚህ በፊት አለመከታተላቸውም ደጎች ቢሆኑ ነው ። አሁን ነገ በዌስት ሊን መንገዶች ጥሩንባ እየነፋህ መምጣትህን ልትለፍፍ ነው?”
“ ቢቻለኝ ማንም እንዳያየኝ ነው የምፈልገው ”
“ ዌስት ሊን ከመጣህ የመምጣትህ ወሬ መሰማቱ ስለማይቀር በመንገድ ወጥተህ ከመለፈፉ አያንስም " ከዚህ በፊት እዚህ ታይተሃል ተብሎ ስንትና ስንት ወሬ
ነበር " ይህ ወሬ እንዴት እንደ ወጣ ግን እንጃ
“ የምኖረው ኑሮ በጣም አስቸጋሪ ነው ምንም ልምድ ባይኖረኝም፡እንደ
ምንም ብዬ አንዳንድ ሥራዎች ለመሥራት እፈልግ ነበር ። ነገር ግን ተሰድጄ መብቴን ታግጀ ተዋርጀና ቀን ለቀን ተሳቅቄ ተጨንቄ ከመኖር ፈጣን ሞት ቢወስዶኝ እመርጣለሁ” አላት ሪቻርድ ።
“ አንተው በገዛ እጅህ እዚያች ኃፍረተ ቢስ ከውካዋ ቃፊ ዘንድ እየተመላለስክ
ያመጣኽው መዘዝ ነው ማንንም መውቀስ አትችልም
“ እኔን ከዚህ ሁሉ ጣጋፈጣ የከተተኝ ይህ ሳይሆን ያ ሰይጣን ሆሊጆንን ስለ ገዴፈደለው ነው
“ በውነት ገዳዩ ሌላ ሆኖ በግልጽ የይታወቅበት ምክንያት አይገባኝም "
አንድ ቶርን የተባለ ሰው የገደለው እያልክ ፊ
ታወራለህ የምትለው ሰው ግን ማንም አይቶት ወይም ስለሱ ሰምቶ አያውቅም ራስህን ንፁሕ ለማድረግ ስትል የፈጠርከው ነው”
የፈጠርከው አለ ሪቻርድ ጋል ብሎ በፖሊሶች የሚያሳድደኝኮ እሱ
ነው " በዚህ ሁለት ሳምንት ውስጥ ሦስት አራት ጊዜ አይቸዋለሁ ”
ታዲያ ለምን ነግሩን አስገልብጠህ ፖሊሶችን በሱ አታሰማራበትም?”
"እሱማ እንዳይሆን እሱ ለመግደሉ ከኔ ቃል በቀር ሌላ መረጃ ስለሌለኝ ጥሩ አይደለም እሱ ያን ጊዜ ከአፊ ጋር ተሻርኮ ነበር " አሁንም ቢሆን ከሷ ጋር
ጠንካራ ትስስር ባይኖረው ' በግድያው ጊዜ እሱ አብሯት እንደ ነበር ለሚስተር ካርላይል አትነግረውም ነበር " ነገር ግን አብሯት አልነበረም ሰውየውን የገደለው አሱ ነው " "
“ ምናለ ! ይህች ኃፍረት የለሽ የድፍረቷ ድፍረት ሰተት ብላ እዚህ ድረስ
መጣች ግን እኔ ከቤት ባለመኖሬ ዕድሏን ታመስግን አርኪባልድም ካንተ አይሻልም " አይረባም ፡ ያቺን እየተሽቀረቀረች ከማበድ በቀር ምንም ቁም ነገር የሌላት መለኮን ሰው ብሎ ሁለት ቀን ማረፊያ ሰጥቶ አስተናገዳት "
“ አፊ እኮ ከጥቂት ጊዜ በፊት ጀምሮ ቶርን ያለበትን አለማወቋን ነግራኛለች”
አለ ሚስተር ካርላይል : ካርላይል የእኅቱን ነቀፌታ እንዳልሰማ በመተው " ግን
ረጂመንቱ” ወደ አለበት ውጭ አገር የመሔዱን ወሬ ሰምታለች »
“ ስለሱ ምንም ነገር አለማወቋ እውነት ከሆነ በተለይ ለሷ ጥሩ ነው ” አለ
ሪቻርድ " እሱ ግን ኢንግላንድ ውስጥ ነው ያለው ውጭ አገር አለመሆኑን አሳምሬ
ዐውቃለሁ "
“ ኧረ ለመሆኑ ዛሬ የት ልታድር ነው ?” አለችው ሚስ ካርላይል ሌላውን
ነገር ትታ ።
“እኔ እንጃ! አለ ኩምሽሽ ባለ አነጋገር " እኔ ከበረዶው ቁልል ብተኛና በበነጋው እዛው ድርቅ ብዬ ብገኝም ምንም አይደለም "
እንደዚህ ለማድረግ አስበህ ነው የመጣኸው ? አለችው
“ እሱስ አልነበረም” አላት ልስልስ ባለ አንደበት ' “ ከዚህ ሦስት አራት ኪሎ ሜትር ያህል ራቅ ብሎ አንድ የማውቀው የማያሰጋ ቦታ አለ ስለዚህ
ሐሳቤ ከሚስተር ካርላይል ጥቂት ሽልንጐች ባገኝ እዛው ተከራይቸ ለማደር ነበር "
"ሪቻርድ አለው ሚስተር ካርላይል „ “ ይኸን በመሰለ ሌሊት ውሻን እንኳን ቢሆን ሦስት አራት ኪሎ ሜትር ይሒድ ብዬ አላስወጣም ከዚሀ ታድራለህ።
" ግን” አለች ሚስ ካርላይል የቤት ሠራተኞች የሱን መኖር ሳያውቁ
መኝታውስ እንዴት ይዘጋጅለታል ? ከተዘጋጀ በኋላስ በየት አድርጎ ገብቶ ይተኛል? አለች " ሚስ ካርላይል መቸም ጠባይዋ ነው አስቸጋሪ እንጂ የልብ ደግነት ኢያንሳትም ነበር " ስለዚህ ችግር ከወንድሟ ጋር ተወያዩና ' ቢሆንም ጆይስ ማወቅ እንዶገሚባት ከዚያ በፊት ግን ሪቻርድ ያባቷ ገዳይ ያለመሆኑን ሚስተር ካርላይል እንዲ
ያሳምናት ተነጋገሩ
ሚስተር ካርላይል • የተቆለፈውን በር ከፍቶ ወጣ" ጆይስን ጠራና አንድ ክፍል ውስጥ ይዟት ገባ " አባቷን የግደለው ሪቻርድ ስለ መሆኑ ምንም ጥርጣሬ እንዳልነበራት ያውቅ ነበር " አሁን እሱ ያን ሥር የሰዶደ እምነቷን ሊያስለውጣት ፈለገ ጆይስ አለና ጀመረ አፊ ከሪቻርድ ሔር ጋር ኮብልላ አብራው ስለመኖሯ የነበረሽን ጽኑ እምነት ትዝ ይልሻል እኔ ደሞ በጣም እጠራጠር እንደነበር ብዙ ጊዜ ነግሬሽ ነበር እንደዚ ስልሽ ነገሩ ከልቡ እንዲቆይ አስፈላጊ መስሎ ስለ አገኘሁት እንጂ ከትክክለኛ ምንጭ አሰጋግጭ ነበር አሁን ግን አብራው እንዳልነበረች አምነሽ የለ።
"አሁንማ በደንብ አምኛለሁ"
እንዲህ አየሽ ጆይስ
ድሮውንም የኔ ሐሳብ በሚገባ መሰማት የነበረበት ነው አሁን ደም ስለ ሌላ ጉዳይ ያለሽን እምነት ለማሰጣል ልሞክር ነው
ስለዚህ አንቺም በቂ ምክንያት እንዳለኝ ካረጋገጥኩልሽ ታምኛለሽ ?
እርስዎ ከውነት በቀር እንደማይናገሩ እርግጠኛ ነኝ ጌታዬ ስለዚህ የእርስዎ አስተያየት ትክክለኛ መሆኑን ዐውቀዋለሁ " አለች ጆይስ „
“ እንዲያው ሰማሽ ... አባትሽን የገለው ሪቻርድ ሔር ነው መባሉን እንደ
ማላምንበት ልንገርሽ ሪቻርድ ሔር በዚህ ጕዳይ ልክ እንዳንቺና እንደኔ ንጹህ
ነው ለዚህም በቂ ምክንያት ካገኘሁ ብዙ ዓመቴ ነው "
“ኧረ እ!... ታዲያ ማን ገደለው ? ”
“ እኔ በደንብ አንደማምነው ያ የአፊ ፍቅረኛ ነው " ያ ቶርን የተባለው አለባበስ አሳማሪ
“ እና ለዚህ እምነትዎ በቂ ምክንያት አለኝ አሉ ?
“ አዎ ደንበኛ ምክንያት አለኝ - ከተረዳሁት ብዙ ዘመኔ ነው " አንቺም እኔ እንደማምነው ብታምኚ ደስ ይለኛል "

👍10
“ ግን ጌታዬ .... እሱ ከደሙ ንጹሕ ከሆነ ላምን ሸሸ? ለምንስ እንደ ሸሸ ጠፍቶ ቀረ ?
“ አዎ Iልክ ነሽ ነገሩን ሁሉ ያበላሸውም ይኸው አድራጐቱ ነበር " እዚ!
ውሉ ያደረስው ፈሪነቱ ነው " ኋላም ለመመለስ ፈራ " ሰው በሱ ላይ ካሳዶረው የጥርጣሬ ጥላቻ የሚላቀቅ አልመሰለውም ነበር " ጆይስ ለሁሉም እሱን ብታምኚውና ታሪኩን ከራሱ ብትሰሚ ደስ ይለኛል ”
“እሱማ እንዴት ይቻላል ?እሱም እንግዲህ ደፍሮ እዚህ ግድም ብቅ አይልም'
“ እሁን እዚህ ነው ያለው "
ጆይስ በጣም ደነገጠችና ሚስተር ካርይልን ቀና ብላ አየችው "
• አዎን እዚህ ከዚህ ቤት ውስጥ " አላት ሚስተር ካርላይል “ከዚህ ተጠግቷል ስለዚህ ከዚህ ቤት ለሚቆይባቸው ጥቂት ሰዓቶች በተቻለ መጠን ደብቀንና ጠብቀን እንድስተናግደው ያስፌልጋል ይኸንንም እምነት ባንቺ ላይ መጣሉ
እንደሚሻል አመንኩበት " በይ አሁን ነይ ግቢና እይው
ገብታ ተግናኙና ስትጠይቀው ሲመልስላት ቆዬ » ሪቻርድ በጋለ ስሜት ሲናገር ጆይስ ጥያቄ በጥያቄ ስታከታትልበት የሚስ ካርላይል ምላስም የነሱን ያህል ሲንቀለቀል ድብልቅልቅ አለ " ሚስተር ካርላይል ብቻ ዝም ብሎ ያዳምጥ ጀመር በመጨረሻ ጆይስ በሪቻርድ ላይ የነበራትን ጥርጣሬ ወደ ካፒቴን ቶርን አዞረች "
ከዚያ በኋላ የሚተኛበት ክፍል ተመረጠለትና ጆይስ መኝታውን ልታዘጋጅለት ሔደች ሚስ ካርላይል ወደ መኝታዋ ገባች ሚስተር ካርላይል ለራት አብሮት ተሸምጦ ብላ እያለ በደንብ ጋበዘው " ሪቻርድ የሚያደፋፍር ጥሩ አቀባቀል
ጥሩ እሳት አንድ ብርጭቆ ትኩስ ብራንዲ በውሃ ሲገኝ ጊዜ ሰውነቱ ተፍታናፈታና
ወንበሩ ላይ እንደ ተቀመጠ እንቅልፍ ወሰደው " አምስት ደቂቃ ሳይቶmቆይ መቃዠት
ጀመረ።
“ ኧረ እኔ አይዶለሁም ! እኔን ብትወስዱኝ ምንም አይጠቅማችሁም ምክንያቱሜ እኔ አደለሁማ
ሌላ ሰው እኮ ነው። ያ እንኳ
" ሪቻርድ ! ሪቻርድ ! አለው ሚስተር ካርይል ረጋ ብሎ
ሪቻርድ ነና ይኖቹን በድንጋጤ እንዳፈጠጡ የምግብ ጠረጴዛውን እሳቱን ሚስተር ካርይልን ሲያይ ልቡ ረጋ መንፈሱ ተመለሰ ወይ ጉድ ይዘውኝ
ሲሔዱ በሕልሜ አይቼ እኮ ነው " ሕልሞች አሥቂኝ ናቸው ” አለው "
ከዚያ ጆይስ መኝታውን አዘጋጅታ ስትጨርስ መጥታ ወሰዶችውና ከሻማ ጋር
ካስገባችው በኋላ ዘግታበት ተመለሰች ".....
💫ይቀጥላል💫

👍14👎1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
...‹የሚያስቸኩልሽ ነገር የለም›› አለ ኮንስታብሉ ‹‹አባትሽ ሊወስዱሽ
እየመጡ ነው፡፡››
የማርጋሬት ልብ በድንጋጤ ቀጥ አለ፡ እንዴት ሊሆን ይችላል? አሁን
ያለችበት ቦታ አባቷ የማያውቁት ስለሆነ ደህነኛ ቦታ ነው ብላ ተማምና ነበር፡፡
አባቷን ዝቅ አድርጋ ነበር የገመተቻቸው፡ በዚህ ደቂቃ ውስጥ ሊይዟት ይመጣሉ! ሃሳቡ አንቀጠቀጣት ‹‹የት እንዳለሁ እንዴት አወቀ አባባ?›› አለች፡፡
ወጣቱ ፖሊስ በኩራት ‹‹ትናንት ማታ ስለመጥፋትሽ የቴሌግራም መልዕክት ደርሶን ነበር፡፡ ስመጣ አየሁት፡፡ በጨለማ የመጣሽ ጊዜ
አላወቅኩሽም ነበር፡፡ ስምሽን ግን አስታወስኩት፡፡ ከተገኘሽ ለጌታ ኦክሰንፎርድ
እንዲነገራቸው ቴሌግራሙ ያዛል፡፡ እዚህ እንዳመጣሁሽ ለአባትሽ ደወልኩ››
ማርጋሬት ብድግ አለች፧ ልቧ በጣም ይመታል፡፡ ‹‹እሱን አልጠብቅም
አሁን ነግቷል›› አለች፡፡
ፖሊሱ ስጋት ገባው ‹‹ትንሽ ቆይ›› አለ፡፡ ዞር አለና ‹‹ሃምሳ አለቃ እመቤት ማርጋሬት መሄዴ ነው እያለች ነው›› ብሎ ነገረው፡፡
ሄሪ ማርክስ ‹‹እዚህ ይዘው ሊያቆዩሽ አይችሉም ባንቺ እድሜ ከቤት ጠፍቶ መሄድ ወንጀል ተደርጎ አይቆጠርም፡፡ መሄድ ከፈለግሽ ቀጥ ብለሽ
ሂጂ›› አላት፡፡
ሃምሳ አለቃውም ‹‹ነገር ግን ጫማ የለሽም፤ ስቶኪንግሽ ተቀዳዷል፡፡ አባትሽ ጋ ልደውልልሽ›› አላት፡፡
ማሰብ ጀመረች፡፡ ጣቢያ እንደደረሰች ነው ለአባቷ ስልክ የተደወለው፡፡
አሁን አንድ ሰዓት አልሞላውም ማለት ነው፡፡ አባቷ ደግሞ ከዚህ በኋላ
እዚህ ለመድረስ ቢያንስ ከአንድ ሰዓት በላይ ይፈጅባቸዋል፡ ‹‹ደህና›› አለች ለደጉ ፖሊስ ‹‹አመሰግናለሁ፡፡››
ሄሪ ወደ ፖሊስ ስታዘግም አየና ‹‹ጅል›› አላት፡፡
ፖሊሱ አንድ ትንሽ ክፍል ውስጥ ወስዶ አስገባት፡፡ ወንበሮቹ ተራ ናቸው፡
አንድ አግዳሚ ወንበር ይታያታል፡፡ ከላይ ማቀፊያ የሌለው አምፑል ተንጠልጥሏል፡ መስኮቱ በብረት ፍርግርግ ተዘግቷል፡ ሃምሳ አለቃው ይህ
ክፍል ከባለጉዳይ መቀበያው ክፍል የተሻለ ነው ብሎ እንዴት እንዳሰበ
አልገባሽ አላት፡፡ ልትነግረው ዞር ስትል በሩን ፊቷ ላይ ጠረቀመው፡፡ አንድ
ክፉ ነገር እንዳለ በልቧ ጠረጠረችና ፍርሃት ገባት፡፡ ተወርውራ በሩ ጋ ሄዳ
ለመክፈት ታገለች ከዚያም ፍርሃቷም እውነት መሆኑን በሩ ሲቆለፍ አረጋገጠች፡፡ የበሩን እጄታ በሃይል ነቀነቀችው፤ ነገር ግን በሩ የሚከፈት አልሆነም በተስፋ መቁረጥ በሩ ላይ ልጥፍ አለች፡፡
ከውጭ በኩል ሳቅ ይሰማታል፤ ከዚያም ሃሪ ‹‹እናንተ እርጉሞች›› ሲል
ተሰማት ‹‹አፍክን ዝጋ›› አለው ፖሊሱ፡፡
‹ምንም መብት የላችሁም ልጅቷን ለማቆየት፤ አንተም ታውቃለህ አለው።
‹‹አባቷ የተከበሩ ሰው ስለሆኑ ነው እንደዚህ ያደረኩት›› አለ፡
ማርጋሬት ያሰበችው ባለመሳካቱ በምሬት ተንገበገበች፡ የማምለጥ
እቅዷ ውሃ በልቶታል። ይረዱኛል ብላ የገመተቻቸው ሰዎች አታለዋታል ለትንሽ ጊዜ ነፃ
ነበረች አሁን ግን ነፃነቷ አብቅቷላተል ምድር ጦር
መምሪያው መሄድ አለመቻሏ አንገበገባት
ከጦርነቱ ለመሸሽ የፓን አሜሪካ ንብረት በሆነችው አይሮፕላን ተሳፍራ ኒውዮርክ ልትሄድ ነበር። ይህን ያህል ደክማም እድሏ አልሰምር አላት፡፡
ከብዙ ቆይታ በኋላ ከበሩ ወደ መስኮቱ ሄደች። በመስኮት አጮልቃ
ስታይ ምንም ነገር የማይታይበት ጓሮና የሸክላ ግድግዳ ብቻ ነው::
በሽንፈትና በአቅመቢስነት መስኮቱ ጋር ተገትራ የአባቷን መምጣት
ከመጠባበቅ በስተቀር ምንም ምርጫ አልነበራትም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኤዲ ዲኪን ለአይሮፕላኑ የመጨረሻ ፍተሻ አደረገ እያንዳንዳቸው የ1500 የፈረስ ጉልበት ያላቸው አራቱ ሞተሮች የተቀቡት ዘይት ያብለጨልጫል፡ እያንዳንዱ ሞተር የሰው ቁመት አለው። ኤዲ እያንዳንዱን የሞተር ክፍል መርምሮ ሲጨርስ ዘጋጋና ከመሰላሉ ላይ ወረደ። አይሮፕላኑ ለበረራ ሲዘጋጅ ቱታውን ያወልቅና ሰውነቱን ታጥቦ የአየር መንገዱን የበረራ ዩኒፎርም ይለብሳል።
ከአይሮፕላን ማረፊያ ወደቡ ወጥቶ ሲሄድ ፀሀይ ገና አልጠለቀችም፡ከዚያም የስራ ባልደረቦቹ ወደሚገኙበት ሆቴል አመራ: በአይሮፕላኑና
በሚሰራው ስራ ይኮራል። አትላንቲክ አቋራጭ በረራ ከሁሉም የበረራ ስራ
የበለጠ ስለሆነ አየር መንገዱ ያሰማራው አሉ የሚላቸውን የበረራ ሰዎች
ነው።
ሆኖም ይህን ስራ በቅርቡ ለመተው አቅዷል፡ አሁን እድሜው ሰላሳ ሲሆን ትዳር ከያዘ ዓመት ሆኖታል። ሚስቱ ካሮል አን ነፍሰ ጡር ናት ይህ ስራ ለወንደላጤ ምንም አይልም እሱ ግን ከቤተሰቡ ርቆ መኖር
አይፈልግም፡ የራሱን ስራ ለመጀመር በቂ ገንዘብ አጠራቅሟል፡ አሜሪካ
ውስጥ ይህን ስራ ለመስራት የሚያስችለው አየር ማረፊያ አለ፡፡" አይሮፕላን ይጠግናል፣ ነዳጅ ይሸጣል፡ በኋላም አይሮፕላን ገዝቶ ያከራያል፡
ሆቴሉ ውስጥ ሲገባ ረዳት ኢንጂነሩን ሚኪን አገኘው፡ ሚኪ ተጫዋች ሲሆን ኤዲን በችሎታው ይወደዋል። ሚኪ ስልክ እየተነጋገረ ሳለ ኤዲንን
ሲያይ ‹‹እድለኛ ነህ አሁን መጥቷል ላገናኝህ›› አለው ለደዋዩ ‹‹አንተን ነው
የሚፈልገው›› ብሎ የስልኩን መነጋገሪያ ለኤዲ ሰጠና ብቻውን መነጋገር
እንዲችል ጥሎት ሄደ።
ኤዲም ስልኩን ተቀበለና ‹‹ሄሎ?›› አለ፡
‹‹ኤድዋርድ ዲኒኪን ነህ?›› ብሎ ጠየቀ ደዋዩ፡፡
ኤዲ ግንባሩን በግርታ ቋጠረ፡ በስልክ የሚሰማው ድምጽ አዲስ ሆነበት ከዚህ በፊትም ማንም ኤድዋርድ ብሎት አያውቅም፡፡ ‹አዎ ነኝ
ማን ልበል?›› አለ፡
‹‹ቆይ ትንሽ ጠብቀኝ ባለቤትህን ላገናኝህ አጠገቤ ነው ያለችው›› የኤዲ ልብ ተንጠለጠለ ካሮል አን ለምንድነው ከአሜሪካ የደወለችልኝ ችግር አለ ማለት ነው?› ሲል ተጨነቀ፡፡
ከአፍታ በኋላ የካሮል አን ድምጿ ተሰማ ‹‹ኤዲ›› አለች እምባ እየተናነቃት፡
‹‹እንዴት ነሽ ማርዬ ምን ሆነሻል?››
ካሮል አን የባልዋን ድምጽ ስትሰማ ለቅሶዋን ለቀቀችው።
ኤዲ በዚያች ደቂቃ ውስጥ ክፉ ነገር አዕምሮው ውስጥ አቃጨለበት፡
‹ካሮሌ ላይ ምን ደርሶባት ይሆን? ውርጃ ገጠማት ይሆን? ቤቱ ተቃጠለ?
ማን ይሆን የሞተው? የሚሉ ሃሳቦች በአንድ ላይ መጡበት፡፡
«ካሮል ተረጋጊ ደህናም አይደለሽ?››
‹‹አይ ምንም አልሆንኩም›› አለች እየተነፋረቀች፡
‹‹ታዲያ ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሺው?›› አለ ሆዱ በፍርሃት እየተንቦጫቦጨ፡
‹‹ምን ተፈጠረ ንገሪኝ የኔ ውድ?››
‹‹እነዚህ ሰዎች እቤት መጡ››
ኤዲ ይህን ሲሰማ በድንጋጤ የበረዶ ክምር ሆነ ‹‹የምን ሰዎች? ምን
አደረጉሽ?››
‹‹መኪና ውስጥ ከተው ወሰዱኝ››
‹‹ወይ አምላኬ! ማን ናቸው?›› ንዴቱ ደረቱ ላይ ውጋት ለቀቀበትና
መተንፈስ አቃተው፡
‹‹ጎድተውሻል?››
‹‹አይ ደህና ነኝ፡ ነገር ግን ኤዲ ሰዎቹ ያስፈራሉ››
ምን እንደሚል ጨነቀው፡ ብዙ ነገሮች አዕምሮው ውስጥ መጡበት፡፡"
የሆኑ ሰዎች ሚስቱን አግተዋታል፡፡ ምንድነው ነገሩ? በመጨረሻም
‹‹ለምን?›› ሲል ጠየቀ፡፡
‹‹ምክንያቱን አልነገሩኝም››
‹‹ምን አሉሽ?››
‹‹ኤዲዬ የሚሉህን በሙሉ አርግላቸው፡፡ የማውቀው ይህን ብቻ ነው››
ንዴትና ፍርሃት እየተፈራረቁበት ‹‹አንቺን ከሚያሰቃዩብኝ ያሉትን
አደርግላቸዋለሁ›› አለ፡፡
‹‹እውነት?››
‹‹አዎ የኔ ማር››
‹‹ተመስገን አምላኬ ላንተ ምን ይሳንሃል›› አለች ካሮል አን።
‹‹መቼ ነው ያገቱሽ?››
‹‹ከሁለት ሰዓት በፊት››
‹‹አሁን የት ነው ያለሽው?››
‹‹ከኛ ቤት ብዙም አይርቅም.›› ብላ ሳትጨርስ የድንጋጤ ጩኸት
አሰማች፡፡

👍21❤2
«ካሮልዬ ምን አደረጉሽ? ደህናም አይደለሽ?›› ሲል ጠየቀ፤ ሆኖም መልስ አላገኘም፡፡ ኤዲ በሽብር ተውጦ መዳፉ ደም እስኪያግት ድረስ የስልኩን እጀታ ጨምድዶ ይዞ መልስ ጠበቀ፡፡ ከዚያም የመጀመሪያው
የወንድ ድምፅ ተመልሶ መጣና ‹‹ልብ ብለህ አድምጠኝ ኤድዋርድ››
‹‹አንተ ራስህ አድምጠኝ›› አለ ኤዲ በንዴት ‹‹ጫፏን ትነካና የገባህበት ገብቼ እገልሃለሁ፧ ህይወቴ እስካለች ድረስ፤ አምላክ ምስክሬ ነው አልለቅህም!! ያገኘሁህ ጊዜ አንተ ዱርዬ በእጄ ነው አንገትህን ጠምዝዤ የምቀነጥሰው ገባህ?›› አለው፡
ስልክ የደወለው ሰው እንደዚህ አይነት የስድብ ናዳ ያልጠበቀ በመሆኑ ዝም ብሎ ቆይቶ ‹‹እንደዚህ አትሁን፤ ሩቅ ነው ያለኸው›› አለው፡
ሰውዬው እውነቱን ነው፡፡ ኤዲ ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ‹‹ፀጥ ብለህ አድምጠኝ›› አለ ሰውዬው፡፡
ኤዲ ምላሱን እንደምንም ብሎ ሰብስቦ ማዳመጥ ጀመረ፡
‹‹አይሮፕላኑ ላይ የተሳፈረ ቶም ሉተር የተባለ ሰው መመሪያ ይሰጥሃል››
‹‹ምን እንዳደርግላችሁ ነው የምትፈልጉት?››
‹‹አፍህን ዝጋ! ሁሉንም ነገር ሉተር ይነግርሃል፤ ሚስትህን በህይወት ማግኘት ከፈለግህ! የሚሻልህ የእሱን ትዕዛዝ መቀበል ብቻ ነው››
‹‹እንዴት ነው እሱን የምለየው?››
‹‹አንድ ሌላ መመሪያ፤ ለፖሊስ እንዳትጠቁም፡ ምንም አይጠቅምህም፤
ከጠቆምክ ሚስትህን የማደርገውን አውቃለሁ››
‹‹አንተ ወንበዴ አገኝሃለሁ!. . .
ስልኩ ኤዲ ጆሮ ላይ ተዘጋ፡፡
✨ይቀጥላል✨

👍14❤2
👉የጠንቋዩ ዋሻ👉
🗾ክፍል 15🗾
⚡⚡⚡⚡⚡
አቢያራ የአድማስን ያልተለመደ ተቋውሞ ሲሰማ ያልጠበቀው ነገር ነውና ለመጀመሪያ ጊዜ ደንገጥ ብሎ አድማስ ላይ አይኑን ተከለ ፣ ኤልያታ በአቢያራና በአድማስ መካከል እንደቆመች ናት ግራ ገብቷታል ምን እንዳጎደለች እራሷን ደጋግማ ብጠይቅም ምንም አይነት ጥፋት ማስታወስ ሳትችል ቀረች ፣ አድማስ ፈርጠም እንዳለ ነው ሁኔታው ሁሉ ሴት የላከው ሞት አይፈራም እንዲሉ 'አይነት ነው ፣ እነመስፍን የአቢያራንና የአድማስን ፍጥጫ በፍርአትና ከአሁን አሁን ምን ሊከሰት ነው በሚል እየጠበቁ ነው ፣ መሳይ አንዳች ግርግር እስኪነሳ እና አቢያራን ማጥቃት የሚችልበትን አጋጣሚ እየጠበቀ በመቁነጥነጥ ላይ ነው ፣ ኤዛም አይኖቿን አድማስ ላይ ብትተክልም ለአቢያራ የሚከላከል አንዳች ምልክት አላሳየችም ሌሎቹም ሴቶች ባሉበት ሆነው ከመተያየት ውጪ አልተንቀሳቀሱም ።
"አድማስ የኔ ታላቁ ፈረስ ምን እያልክ ነው ?" ብሎ አቢያራ አስፈሪ ጣቶቹን ወደ አድማስ ቀሰረ
"ጌታዬ እኔ ኤሊያታ እንድትሞት አልፈቅድም "አለ ድምፁ እየተርገበገበ
"አድማስ ልጄ አንተን ማን ፈቃጅ አደረገ ? እኔ ይሁን ካልኩ ከመታዘዝ ውጪ ምን ምርጫ አለህና ነው ? ይልቅ ኤልያታን ወደመሰዊያው ውሰዳትና እረፍት ስጣት ፣ እኔና አንተ ደሞ ቀሪውን በደንብ እንነጋገርበታለን መቼም ለዛሬው ያልተገባ እንቢተኝነትህ የምትከፍለው መስዋትነት ይኖራል እኔ ይቅር ብልህ ታላቁ አባቴ ይቅር አይልህም "ብሎ አቢያራ ማጓራት ጀመረ
አድማስ ከቆመበት አልተንቀሳቀሰም እንዴት ነው በሚያፈቅራት ልጅ ላይ ስለት የሚያነሳው ግራ ገባው ልቡ እሺ አላለውም ፣ አቢያራ ማጓራቱ ባሰ ዋሻው በጣም ተረበሸ ሴቶቹ ጥግ ጥጉን ይዘው ማነብነብ ጀመሩ ኤዛ ወደ መሳይ ስትመለከት ጠቀስ አደረጋት የሚለውን ባትረዳም አንገቷን ነቀነቀች ፣ ኤሊያታ አድማስ እንዲገላት ለመነችው አቢያራ ከሚከፋ አሷ መስዋት መሆኗን መረጠች አቢያራ ያለው እንዲፈፀም የጥንቆላ ጩኽቱን እየጮኽ ግፊት አደረገ ፣ በዚ አጋጣሚ መሳይ ወደ አድማስ በፍጥነት ተጠጋ ሁሉም በየራሱ ፍርሃት ውስጥ ስለሰመጡ እንዳቀረቀሩ ናቸው ስለዚ ልብ አላሉትም ፣ መሳይ የሚያጓራውን አቢያራን ወደጎን እያየ አድማስ ጋር ደረሰ ፣ልክ አድማስ አጠገብ እንደደረሰ በፍጥነት አድማስ የያዘውን ስለት ተቀበለው.........

👍47❤3
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
እንደ ሄሪ ማርክስ አይነት እድለኛ ሰው የለም፡፡
እና ሁል ጊዜ እድለኛ እንደሆነ ይነግሩት ነበር፡ ምንም እንኳን አባቱን በአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ያጣ ቢሆንም ደከመኝ ሰለቸኝ በማይሉ ብርቱ እናቱ እጅ በማደጉ እድለኛ ነው፡፡ እናቱ የፅዳት ሰራተኛ ናቸው አገሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ በገባችበት በዚያ ቀውጢ ወቅት እንኳን ስራቸውን አላጡም ነበር፡፡ የሚኖሩት እዚህ ግባ በማይባል ኮንዶሚኒየም
ውስጥ ቢሆንም በችግር ጊዜ የሚረዳዱ ጥሩ ጎረቤቶች አሏቸው: ሄሪ ከችግር የማምለጥ እድልና ክህሎት ነበረው፡፡ እሱና የትምህርት ቤት ጓደኞቹ
ረብሸው ሲገረፉ የአስተማሪው አርጩሜ እሱጋ ሲደርስ ይሰበር ነበር፡ ሄሪ ከፈረስ ወይም ከጋሪ ላይ ሲወድቅ ፈረሶቹ ሳይረግጡት በስልት ያሳልፋቸዋል፡፡
ለውድ ጌጣጌጥ ፍቅር ስላለው ነው ሌባ የሆነው፡፡
በጉርምስናው ወቅት በየወርቅ ቤቱ እየተዘዋወረ ዕንቁዎችን መመልከት
ይወድ ነበር፡ እነዚህ እንቁዎች የሚመስጡት ስለሚያምሩ ብቻ ሳይሆን በመጻሕፍት ላይ እንደሚያነበው የሀብታም ምልክት ስለሆኑም ጭምር ነው፡
አንድ ቦታ ረግቶ መስራት ስለማይወድ አንድ ወርቅ ሰሪ ጋ በተቀጠረ በስድስት ወሩ ስራውን ለቀቀ፡፡ ሰዓት መጠገንና የጋብቻ ቀለበቶች ማስፋት ስራም እንዲሁ አስጠላው፡ ነገር ግን የተለያዩ የከበሩ ድንጋዮችን ለይቶ
የማወቅ ችሎታ አዳብሯል፡፡
ሬቤካ ሞግሃም ፍሊንትን የተዋወቃት በፈረስ እሽቅድድም ቦታ ላይ ሲሆን የአንዱ ተወዳዳሪ ደጋፊ ነው ብላ አስባለች ሬቤካ ቀውላላ፣አፍንጫዋ አለቅጥ የረዘመ መልከ ጥፉ ሴት ናት፡ ራሷ ላይ በደፋችው ቆብ ላይ ላባ ሰክታለች፡፡ አጠገቧ ያሉት ወጣት ወንዶች ከምንም ሳይቆጥሯት ሄሪ
ስላናገራት በጣም ነው በሆዷ ያመሰገነችው::
እሷን ለመተዋወቅ የጓጓ እንዳይመስል መግባባቱን በዚያው ቀን ማድረግ አልፈለገም፡፡ በሌላ ቀን ስዕል አዳራሽ ስታገኘው ደስ ብሏት ከዚህ ቀደም በደምብ እንደምታውቀው ሁሉ ሰላምታ ሰጠችውና ወስዳ ከእናቷ ጋር
አስተዋወቀችው፡፡
እንደ ሬቤካ ያሉ እመቤቶች ሲኒማ ወይም ምግብ ቤት ያለ አጃቢ
አይሄዱም፡፡ ብቻቸውን የሚሄዱ የደሃ ልጆች ናቸው፡፡ የሬቤካ እናትና አባት የሄሪን የቤተሰብ ሁኔታ ማጣራት አልደፈሩም፡፡ ቤተሰቦቹ ዮርክሻየር ውስጥ የገጠር ቤት፣ ስኮትላንድ ውስጥ የትግል ትምህርት ቤት እንዳላቸው፣ አካል
ጉዳተኛ እናቱ ደቡብ ፈረንሳይ ውስጥ እንደሚኖሩና በንጉሠ ነገሥቱ አየር ኃይል ውስጥ ለሹመት መታጨቱን ሲነግራቸው እውነት ነው ብለው ተቀብለውታል።
ሄሪ በከፍተኛው መደብ ህብረተሰብ ዘንድ ውሸት ማውራት እንደሚብስ አውቋል።
በዚህ አይነት ሄሪ ከሬቤካ ጋር ጓደኝነት ከመሰረተ ሶስት ሳምንት
ሞላው፡፡ አንድ ቀን አንድ ፓርቲ ይዛው ሄደች፡፡ እዚያም ክሪኬት ሲጫወት ዋለና ከተጋበዘበት ቤት ገንዘብ ሰረቀ፡ ጋባዦቹም እንግዶቻቸውን ማሳጣት
ስላልፈለጉ ለፖሊስ ሳያሳውቁ ቀሩ፡፡ በሌላ ቀን ደግሞ አንድ ዳንስ ምሽት ላይ ወስዳው ኪስ ሲያወልቅና የሴቶችን ቦርሳ እየከፈተ ሲበረብር አመሸ፡፡ ሬቤካ
ቤተሰቦቿን ልታስተዋውቀው የወሰደችው ጊዜ እንኳን ገንዘብ፣ ከብር የተሰሩ ቢላዎችንና ከወርቅ የተሰሩ የቀሚስ ማያያዣዎችን መንትፏል፡
በሱ አመለካከት ከሀብታሞች መስረቅ እንደ ጥፋት አይቆጠርም፡
እነዚህ ሃብታሞች የሰበሰቡት ሃብት አይገባቸውም ባይ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ህይወታቸውን በሙሉ የአንድ ቀን ስራ እንኳን ሰርተው አያውቁም፡፡ ከነዚ ሰዎች ገንዘብ መስረቅ ናዚዎችን እንደመግደል ይቆጠራል እንደወንጀል
ሳይሆን ለህዝብ እንደሚሰጥ አገልግሎት።
ይህን የስርቆት ተግባር ከጀመረ ሁለት አመት ያህል ሆኖታል፡ ነገር
ግን በዚህ ከቀጠለ አንድ ቀን መያዙ እንደማይቀር ተገንዝቦ ሌላ ስራ
መፈለግ ሲያስብ ጦርነቱ ከተፍ አለለት፡
ምንም ቢሆን በመደበኛ ወታደርነት መቀጠር አይፈልግም፡፡ አሸር ባሽር
ምግብ፣ ዩኒፎርምና ወታደራዊ ስነ-ስርዓት የእሱ ዕጣ ክፍሎች አይደሉም ሆኖም የአየር ኃይል ዩኒፎርም ይማርከዋል፡፡ አይሮፕላን አብራሪ መሆን ይፈልጋል፡፡ እንዴት እንደሚፈፅመው ባያውቅም ያደርገዋል፡፡ እሱ እንደሆነ
እድለኛ ነው፡፡
ሬቤካን ርግፍ አድርጎ ከመተዉ በፊት እሷን ተጠቅሞ አንድ ሁለት
የሀብታም ቤት መዝረፍ ፈልጓል፡፡
ሰር ሲሞን ሞንክፎርድ የተባሉ ሀብታም የመጽሐፍ አሳታሚ ቤት
ለግብዣ ተጠርተው ሄዱ፡ ሄሪ ክብርት ሊዲያ ሞስ ከተባለች እመቤት ጋር ወሬ ጀመረ፡፡ እመቤቲቷ ብቻዋን ስለነበረች ለአንድ ሃያ ደቂቃ ያህል
አጫወታትና ወደ ሬቤካ ዞረ፡ ከዚያም ጊዜው አሁን ነው ብሎ በመገመት ተንቀሳቀሰ፡፡
ሁለቱን ወይዛዝርት ይቅርታ ጠየቀና ከዳንሱ አዳራሽ ወጣ
የሚቀጥለው ፎቅ ላይ ወጣና ኮሪደሩን ይዞ ሄደ፡፡ ኮሪደሩ መጨረሻ አንድ ትልቅ መኝታ ክፍል አገኘ፡፡ ወደ ውስጥ ሊገባ ሲል አንድ ሰው ‹‹ምን ነበር?›› አለው፡፡
‹‹እዚህ ነው?›› ብሎ ጠየቀው
‹‹ምኑ?››
‹‹መፀዳጃ ቤቱ?››
ወጣቱ ሰው ከቁጣው መለስ አለና ‹‹አሃ ገባኝ፤ መፀዳጃ ቤቱ ኮሪደሩ
ጥግ ነው የሚገኘው›› አለው፡፡
‹‹በጣም አመሰግናለሁ፡››
‹‹ምንም አይደል››
ሄሪ ወደ መፀዳጃ ቤቱ እየሄደ ‹‹በጣም የሚያምር ቤት ነው›› አለው ወጣቱን፡፡
‹‹አዎ›› አለና በደረጃው ወርዶ ሄደ ወጣቱ፡
ሄሪ በእፎይታ ፈገግ አለ፡፡ ወጣቱ ሰው መሄዱን አረጋገጠና ወደ
መኝታ ቤቱ ተመልሶ ሄደ፡
መኝታ ቤቱ የእመቤት ሞንክፎርድ ሲሆን የመልበሻ ክፍልም እንዳለው
ሄሪ ተመለከተ፡ ቀጥሎ ደግሞ የወንድ መልበሻ ክፍል አለ፡፡ ሀብታም ባልና ሚስቶች የየራሳቸው መኝታ ክፍል አላቸው፡፡ ይህም የሆነው ከሰራተኛው
መደብ ያነሰ ወሲባዊ ፍላጎት ስላላቸው ይሆን?› ሲል አሰበ፡፡
ሄሪ የሰር ሲሞን መልበሻ ክፍል ገባና የኮሞዲኖውን መሳቢያ ከፈተው፡፡መሳቢያው ውስጥ በተለያዩ ጌጣጌጦችና አምባሮች የተሞላ ከቆዳ የተሰራ
የጌጣጌጥ ማስቀመጫ ሳጥን አገኘ፡፡ ብዙዎቹ ጌጣጌጦች ተራ ቢሆኑም ከነዚያ ውስጥ ግን ከወርቅ የተሰሩ የእጅ አምባሮች ላይ አይኑ አረፈ፡ አምባሮቹን
ኪሱ ጨመራቸው፡፡ ከጌጣጌጥ ሳጥኑ ቀጥሎ ውስጡ ሃምሳ ፓውንድ የያዘ የቆዳ የኪስ ቦርሳ አገኘ፡፡ ከቦርሳው ውስጥ ሃምሳ ፓውንድ ወሰደ፡፡ ብዙ ሰዎች ሃያ ፓውንድ ለማግኘት ከሁለት ወር ያላነሰ ከባድ የፋብሪካ ስራ
መስራት ያስፈልጋቸዋል፡፡
በየሄደበት ያገኘውን ሁሉ አይሰርቅም፡፡ የተወሰነ ዕቃ ብቻ መስረቅ ጥርጣሬ ይፈጥራል። ሰዎች ዕቃ ጎድሎ ሲያዩ ጌጣጌጡን ሌላ ቦታ እንዳስቀ
መጡት ወይም ቦርሳ ውስጥ ምን ያህል ገንዘብ እንደነበራቸው ማስታወስ ስለሚያቅታቸው ስርቆት ተፈፅሟል ብለው ለፖሊስ ሪፖርት አያደርጉም፡፡
መሳቢያውን ዘጋና እመቤት ሞንክፎርድ መኝታ ክፍል ዘው አለ፡፡
የያዘውን ይዞ ለመውጣት ቢመኝም ትንሽ ደቂቃዎች እመቤቲቱ ክፍል
ቢያጠፋ ወደደ፡፡ ሴቶች ከባሎቻቸው የተሻለ ጌጣጌጥ ይኖራቸዋል፡፡ እመቤት
ሞንክፎርድ ደግሞ ዕንቁ ሳይኖራቸው አይቀርም፡፡ ሄሪ ደግሞ ዕንቁ ነፍሱ ነው፡፡
የምሽቱ አየር ምቹ በመሆኑ መስኮቶቹ በሙሉ ተከፍተዋል፡ በቀጥታ መልበሻ ክፍል ውስጥ ገባና ጌጣጌጡ ያለበት ኮሞዲኖጋ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ሁሉንም መሳቢያዎች ሲከፋፍት የተለያዩ የጌጣጌጥ ሳጥኖች እና ትሪ ሙሉ
ጌጣጌጥ አገኘ፡፡ የበር መከፈት ድምፅ ለመስማት ጆሮውን ቀስሮ እያንዳንዱን የጌጣጌጥ ሳጥን ፈተሸ፡፡

👍19👎2❤1
እመቤት ሞንክፎርድ ጥሩ ጌጣጌጥ አያውቁም፡፡ እመቤቲቱ ወዘና ያላቸው ሴት ቢሆኑም ጌጣጌጦቻቸው ተራ ናቸው፡ ሄሪ በምርጫቸው ተበሳጨ፡፡
ሄሪ አንድ ጌጣጌጥ አይኑን ሳበው፡፡ ጠጋ ብሎ ሊያይ ሲል የመኝታ ቤቱ
በር ሲከፈት ሰማና በድንጋጤ ደርቆ ቀረ። ሆኖም ማሰቡን አላቆመም::
የመልበሻ ክፍሉ በር ወደ መኝታ ቤቱ የሚያስገባ ብቸኛው በር ነው፡ ክፍሉ ውስጥ አንድ መስኮት ቢኖርም በጥብቅ የተዘጋ ስለሆነ ድምጽ ሳያሰማ ለመክፈት እንደማይቻል ተረዳ፡፡ በቁም ሳጥኑ ውስጥ መደበቅ እችል
ይሆን?› ሲል አሰበ፡፡
ካለበት ቦታ ሆኖ የመኝታ ቤቱን በር ማየት አይችልም፡፡ ጠጋ ብሎ
ሲያዳምጥ እመቤት ሞንክፎርድ እየመጡ ነው፡፡ የከፋፈታቸውን መሳቢያዎች ለመዝጋት ጊዜ አላገኘም፡
ሄሪ ጫን ጫን ይተነፍሳል፡ ድንጋጤ ቢወረውም ከዚህ በፊትም
እንዲህ አይነት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ያውቃል፡፡ ከዚያም ራሱን አረጋግቶ ተንቀሳቀሰ፡፡ ተነሳስቶ በበሩ በኩል አለፈና መኝታ ቤቱ ውስጥ ገብቶ ድምጹን
አሰማ፡፡
እመቤት ሞንክፎርድ ደነገጡ፡፡
‹‹በመኝታ ቤትዎ መስኮት አንድ ሰው ሲዘል አየሁ›› አላቸው፡፡
እመቤቲቱ ከድንጋጤያቸው መለስ አሉና ‹‹ምን እያልክ ነው የኔ
ልጅ?›› አሉ፡ ‹‹መኝታ ቤቴ ውስጥ ምን ልታደርግ ገባህ?››
ወደ መስኮቱ ሄደና ወደ ውጭ አይቶ ‹‹አሁንማ ሄደ›› አላቸው፡፡
‹‹አንተ ለመሆኑ ማነህ?››
እመቤት ሞንክፎርድ እድሜያቸው አርባ ውስጥ ይገመታል፡ ካወቀበት
ወይዘሮዋን መሸወድ አያቅተውም፡
‹‹እኔ ኮሪደሩ ውስጥ እየሄድኩ አንድ ሰው እዚህ ክፍል በር ላይ ሆኖ
አጮልቆ ሲመለከት ዓይን ለዓይን ግጥም ስንል ተመልሶ መኝታ ቤት ገባ፡፡
ይህን ቤት መጸዳጃ ቤት ስፈልግ ነው ያየሁት፡፡ ይሄ ሰው ምን እንደሚፈልግ አላወቅሁም፡፡ ሳየው የቤት አሽከር አይመስልም፡፡ ተጋባዥ እንግዳም አይመስልም፡፡ ሁኔታው ስላጠራጠረኝ ልጠይቀው ወደ እሱ ስሄድ በመስኮት
ዘሎ ሄደ፡፡ የተከፈቱትንም መሳቢያዎች ሳይ ሰውየው ጌጣጌጥ ፈልጎ እንደመጣ ተረዳሁ››
እመቤት ሞንክፎርድም ‹‹ምን አይነት ነገር ነው›› አሉ፡፡
ወንበር ሳበና ‹‹አረፍ ይበሉ›› አላቸው፡፡
‹‹ሳስበው አንተ ባታባርረው ኖሮ›› አሉ ሴትዮዋ ‹‹እዚህ ስገባ ባገኘው በድንጋጤ ራሴን እስት ነበር›› አሉና የሄሪን እጅ ለቀም አድርገው በመያዝ
‹‹አመሰግናለሁ›› አሉት፡፡
ሄሪ ፈገግ አለ፡፡ አሁን አምልጧል፡፡ ትንሽ አሰብ አደረገ፡፡ ሰው
እንዲጠሩ አልፈለገም፡፡ ያዩትን ሁሉ በሚስጥር መያዝ ይሻላቸዋል፡
‹‹ለሬቤካ የሆነውን ነገር አይንገሯት፡ አይሻልም? የአዕምሮ ችግር
ስላለባት እንደዚህ አይነት ነገር ስትሰማ ትረበሻለች››
‹‹እኔም እንደዛው ነኝ›› አሉ እመቤት ሞንክፎርድ ‹‹ሳምንት ያህል
ያመኛል፡››
‹‹ምናልባትምፖሊስ መጥራት ያስፈልግዎት ይሆናል፡ ነገር ግን
ያዘጋጁት ፓርቲ ይታመስብዎታል››
‹‹እሱም ጥሩ አይደለም›› አሉ እመቤቲቱ፡
‹‹ደህና›› አለ ሄሪ በውስጡ እርካታ ተሰምቶት፡ ‹‹ፖሊስ የሚጠራው
እኮ ሰውየው የወሰደው ዕቃ ካለ ነው፡፡ እስቲ መሳቢያውን ይፈታትሹ››
አላቸው
‹‹ወይኔ የኔ ነገር! እስቲ ልፈትሽ›› አሉ፡፡
ሄሪ እጃቸውን ያዝ አደረገና እንዲነሱ አገዛቸው፡፡ ወደ መልበሻ ክፍሉ ውስጥ ገቡና መሳቢያው ሁሉ ተከፍቶ ሲያዩ በድንጋጤ አፋቸውን ያዙ፡፡ ሄሪ
ወንበር አቀረበላቸው፤ ቁጭ ብለው ጌጣጌጦቻቸውን ፈታተሹና ‹‹አይ ብዙም
የወሰደ አይመስለኝም›› አሉ፡፡
‹‹ምናልባትም ገና ሲጀምር ይሆናል የመጣሁበት›› አለ ሄሪ ወይዘሮዋ እያንዳንዱን ጌጣጌጥ በዓይነት በዓይነቱ ደርድረው ፈታተሹና
‹‹ደርሰህበታል›› አሉ፡፡ ‹‹አንተን እግዚአብሔር ባይጥልልኝ ኖሮ ምን
ይውጠኝ ነበር!›› አሉ።
‹‹ምንም ጌጥ ካልጠፋብዎት ለሰው መንገር አያስፈልግም››
‹‹ከጌታ ሲሞን በስተቀር ለማንም አልነግርም›› አሉ፡
‹‹አዎ ልክ ነው›› አለ ሄሪ ለጌታ ሲሞን እንዳይነግሯቸው ቢፈልግም፡፡
‹‹ፓርቲው ካለቀ በኋላ ይንገሯቸው፧ እንደዚያ ይሻላል፤››
‹‹ጥሩ ሃሳብ ነው›› አሉ ሴትዮዋ በእፎይታ፡፡
ሄሪ ልቡ አረፍ አለ፡፡ ‹‹እኔም እንግዲህ ትቼዎት እታች ልሄድ ነው››አለና ጎንበስ ብሎ ጉንጫቸው ላይ ሳም አደረጋቸው፡፡ ድንገት በመሆኑ አፈር ቢሉም ወይዘሮዋ አልከፋቸውም፡፡
‹‹እርስዎ ጎበዝ ሴት ነዎት›› አለና በተቀመጡበት ትቷቸው ሄደ፡፡
ጎልማሳ ሴቶች ከወጣቶቹ ቀለል ይላሉ፡፡ ኮሪደሩ ላይ ባገኘው መስታወት ቁመናውን አየና ክራቫቱን አስተካከለ፡፡ ‹‹አንተ ሰይጣን›› አለ ራሱን፡፡
ፓርቲው እያበቃ ነው፤ ሄሪ ዳንሱ አዳራሽ ሲገባ ሬቤካ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ አገኛት፡፡
‹‹የት ነው የጠፋኸው?›› አለችና ጠየቀችው በቁጣ፡
ከጋባዦቻችን ጋር እያወራሁ ነበር›› ሲል መለሰላትና ‹‹ይቅርታ እንሂድ›› አላት፡
ከግብዣው ቤት ሲወጣ የእጅ አምባሩና ሃያ ፓውንዱ ኪሱ ውስጥ ናቸው፡፡
ታክሲ ያዙና ወደ መሃል ከተማ የሚገኝ ምግብ ቤት ገቡ። ሄሪ ጥሩ ጥሩ ምግብ ቤቶች ደስ ይሉታል፡ የዕቃዎቹ ጥራት የፈረንሳይ ምግቦች ዝርዝርና ከተፎዎቹ አሳላፊዎች ይማርኩታል፡ አባቱ እንደዚህ አይነት ምግብ ቤቶች ውስጥ ለመግባት አልታደሉም፡፡ እናቱ ምናልባት ለጽዳት ስራ
ገብተው ይሆናል፡ ሜኑው ላይ የሰፈረውን የምግብ ዝርዝር አየና ውድ
ያልሆነ ምግብና ወይን ጠጅ አዘዘ፡
ከዚህ ቀደም ወጣት ሴቶችን ለመጋበዝ ምግብ ቤት ገብቶ ብዙ ጊዜ
ስህተት ይፈጽም ነበር፡ ነገር ግን ፈጣን አዕምሮ ያለው በመሆኑ ከስህተቱ
ይማራል ከልምዱ እንደተረዳውም ብዙዎቹ የእንግሊዝ ሃብታሞች
የፈረንሳይ ምግብ ስለማያውቁ ይጠይቃሉ፡፡ እሱ ግን አንድ ምግብ ለመመገብ ሲገባ ስለሌላው ምግብ ይጠይቃል፡ እንዲህ እንዲህ እያለ ነው የፈረንሳይ
ምግብ ያወቀው። ስለሆነም ከብዙዎቹ ሃብታም የእድሜ እኩዮቹ ይልቅ የፈረንሳይ ምግብ ዝርዝር ያውቃል። ወይን ጠጅ ላይ ግን ችግር የለበትም አስተናጋጆች ደግሞ የትኛው ወይን ጠጅ ጥሩ እንደሆነ ሲጠየቁ ደስ
ይላቸዋል፡ ምክንያቱም ብዙ ወጣቶች የተለያየ ወይን ጠጅ ያውቃሉ ተብሎ
አይጠበቅም፡፡ ስለዚህ ምግብ ቤት ሲገቡ ዋናው ነገር የሚያውቁ መስሎ ረጋ
ብሎ መታየት ነው፡
ሻምፓኙ ጥሩ ቢሆንም ምሽቱ ድብር ብሎታል፡ ለዚህም ምክንያቱ
ሬቤካ እንደሆነች ተገንዝቧል እዚህ ቦታ ደስ የምትል ልጅ አምጥቶ ቢሆን
ኖሮ ምን ያህል ደስ እንደሚለው አሰበ፡፡ ብዙ ጊዜ ይዞ የሚመጣው
አስቀያሚ፣ ወፍራም፣ ፊታቸው ላይ ማዲያት ያለባቸውና ጅላጅል ሀብታም ሴቶችን ነው፡፡ እነሱን መተዋወቅ በጣም
ከተማረኩለት በኋላ እንዳይተዋቸው ስለሚሰጉ ያላቸውን መቀበል ብቻ ነው
ቀላል ነው፡ አንድ ጊዜ
ምርጫቸው፡፡ ስለዚህ ሀብታም ቤት ውስጥ ለመግባት ተመራጩ መንገድ ይሄ ነው፡፡ ታዲያ ከማይፈልጋቸው ሴቶች ጋር ነው ጊዜውን የሚያጠፋው፡፡
ሬቤካ ዛሬ አኩርፋለች አንድ ነገር ሆዷን በልቶታል፧ ከተዋወቁ ጀምሮ ለሶስት ሳምንት በየቀኑ ሊጋብዛት ይዟት ሲወጣ አንድ ቀን እንኳን ሰውነቷን
ለመደባበስ ለምን እንዳልሞከረ አልገባትም፡፡ ለወሲብ እንዳልፈለጋት
ገብቷታል፡
ከዚህ በፊት ድንግልናዋን ልትሰጠው ዝግጁ ከነበረች አንዲት ቀጫጫ ልጅ ጋር ለወሲብ መታገል ሲሞክር ገላው አልታዘዝልህ ብሎት እንደተቸገረ ሲታሰበው በእፍረት ይሽማቀቃል፡ እሱ ወሲብ የለመደው ከእሱ መደብ ሴቶች ጋር ነው፡ ታዲያ ከእነሱ ጋር የነበረው ግንኙነት ብዙም አይቆይም፡

👍17
አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚያረካ የፍቅር ግንኙነት የነበረው፡ የአስራ ስምንት
ዓመት ልጅ እያለ አንዲት ባሏ የሰለቻት ጠና ያለች ጠበቃ ከመንገድ ላይ
ተዋውቃው ለሁለት ዓመት ያህል በወዳጅነት ይዛው ነበር፡ ከእሷ ብዙ ነገር
ተምሯል እሷም በሙሉ ፈቃደኝነት አስተምራዋለች፡ አልጋ ላይ ሆነው
ከዚያ ግጥም ታነብለት ነበር፡ ሄሪ ለእሷ ጥልቅ ፍቅር ነበረው፡፡ ባሏ ውሽማ
መያዟን መስማቱን ስታውቅ ሄሪን በጭካኔ ጣል ጣል አደረገችው በኋላ ወዳጁን ከባሏ ጋር ብዙ ጊዜ አይቷቸዋል፡ መንገድ ላይም ከዚህ በፊት እንደማታውቀው ሁሉ ዝም ብላው ታልፈዋለች፡፡ ሄሪም ይከፋው ነበር፡፡ እሷ
ሁሉም ነገሩ ነበረች፡
ጣፋጩ ምግብና ሻምፓኙ የእሱንና የሬቤካን መንፈስ አላነቃቃ አለ፡፡ከእሷ ጋር ቁጭ ብሎ አዕምሮው እረፍት አጣ፡፡ ዛሬ ማታ እርግፍ አድርጎ ሊተዋት ቢያቅድም ምሽቱን እንኳን ከእሷ ጋር ለማሳለፍ ትዕግስት አጣ፡፡እሷን ራት ለመጋበዝ የሚያወጣው ወጪ ቆጨው፡ ላባ ከተሰካበት ኮፍያ
ስር ያለውን ሜክአፕ ያልተቀባ አስቀያሚ ፊቷን ሲያይ ጥላቻው ተቀሰቀሰበት።
ያዘዙትን ምግብ በልተው እንደጨረሱ ቡና አዘዘና ወደ መጸዳጃ ቤት ሄደ። ከዚያም በጓሮ በኩል ሾልኮ ወጣ፡
የምሽቱ አየር ጥሩ ነው፡ በጦርነቱ ምክንያት ለጠላት ዒላማ እንዳይሆን መብራት የጠፋ በመሆኑ ጨለም ቢልም ሄሪ ቦታውን በደምብ
ያውቀዋል፡ በተጨማሪም የትራፊክ መብራቶችና ከየመኪናው የሚወጣው
መብራት መንገዱን ወለል አድርገው ያሳዩታል፡ ከትምህርት ቤት የተለቀቀ
ተማሪ የሆነ ያህል ተሰማው፡ ሬቤካን ምግብ ቤት ውስጥ ጥሏት ስለሄደ
አንድ ስምንት ፓውንድ ያህል አድኗል፡

👍18
🗾👉👉የጠንቋዩ ዋሻ👉👉👉🗾
🙈🙈🙈ክፍል 16🙈🙈🙈🙈
👉👉👉👉⚡
የመሳይን ፈጣን እንቅስቃሴ መቋቋም ያልቻለው አድማስ የተቀበለውን አብረቅራቂ ስለት መሳይ እጅላይ ሲያየው በድንጋጤ አፉን ከፍቶ ቀረ ፣ኤልዬታ ግራበመጋባትና በፍርሃት ፈጣ ተመለከተችው ሕይወቷ በመሳይ እጅ ሊያልፍ መሆኑን አስባ ባለማመን ፣ ኤዛ መሳይ አጉል ነገር ሞክሮ ችግር ውስጥ እንዳ ይገባ በመፍራት እንዲያቆም እጆቿን እያንጨፈረረች አስጠነቀቀችው እነ መስፍን የጓደኛቸውን ድፍረት አይተው ተደናግጠው አቢያራ የሚያደርስበትን የጭካኔ በትር ለማሰብ ከበዳቸው .......... መሳይ በኦጁ የገባውን ስለት ያለ አንዳች ማመንታት ወደ አቢያራ ደረት ሰቀሰቀው ያ አልበቃ ብሎት ከአቢያራ በባሰ እየጮኽ የአቢያራን ሰውነት ሰርስሮ የገባውን ስለት በጭካኔ አሽከረከረው " አንተ ...መጥፎ ጠንቋይ እስኪ አሁን እምነትህ ያድንህ .....እስኪ የታለ የጨለማው ንጉስ አባትህ .....አንተ አረመኔ ጨካኝ የስንት ሰው ደም አፍሰህ ነበር ፣ እስኪ ያንተም ይፍሰስ ፣ አንተ ሴይጣን ....በላ አሁን አጓራ ....እኔ አልፈራህም ....እኔ ያንተ ባሪያ አይደለውም .... ፈጣሪዬን የማቅ ሰው ነኝ ..... ፈጣሪ አዛኝ ነው ፈጣሪ ፍቅር ነው ፈጣሪ ሕውነት ነው ፈጣሪ ታጋሽ ነው ፈጣሪ ሰብሳቢ ነው ፈጣሪ ብርሃን ነው !! እሺ አንተ ደም የጠማህ ውሸታም ሴጣን ከነ ጨለማህ ገደል ግባ ........."መሳይ እንደ እብድ እየጮኽና እየተሳደበ የአቢያራን ሰውነት በሳሳው ። ያቢያራ ደም በዋሻው ውስጥ ኮለል አለ .....አቢያራ አይኖቹ በድንጋጤ ፈጠው ሰውነቱ ተደጋግሞ በፍጥነት በሚገባበት ስለት እየተሰቃየ ወዲወዲያ ተወዘወዘ ፣እግሮቹ ተብረከረኩበት ፣በጭራሽ ሊሆን ይችላል ብሎ ባልጠበቀው ተራ ብሎ ባሰበው ጎረምሳ እጅ መውደቁ ሳያስገርመው አይቀርም ቡዝዝ ባሉት አይኖቹ የመሳይን ደማቅ አይኖች በልመና አይነት አያቸው ደግሞ ስለቱን እንዳያስገባበት ተማፀነ ፣ መሳይ ግዳይ እንደጣለ አውሬ ከወዲ ወዲያ እያለ ለሁሉም አቢያራ ተራ እና ደም የጠማው የሴጣን ቁራጭ መሆኑን ተናገረ ፣ ምንም አይነት ተሃምር እንደማይፈጥር ይልቅ ይሄን ሴይጣን አብረን እንቅበረው ፣ ደም ባፈሰሰበት ዋሻውስጥ ቀብሩን እንፈፅምለት ዘላለሙን ለአጢያቱ ሲከፍል ይኖራታል ነብሱ መቼስ እዚው ዋሻውስጥ ትንቀለቀላታለች እንጂ አምላኬ ለሱ የሚሆን ቤት የለውም ወደገሃነም ያውርድህ ፣ አንት ጨካኝ ፣
አድማስ ከቆመበት ተንቀሳቀሰ እና ወደ አቢያራ በግርምት ተጠጋ ምንም አይነት ታምር ስላጣበት ግራ ገባው አቢያራ ሁሉንም ነገር ማድረግ የሚችል ጌታ መስሎት የነበረበትን ዘመን እና እሱን ተከትሎ ትህዛዞቹን የፈፀመበትን ሁኔታ አስቦ ተንዘፈዘፈ ፣ እሱም የሰይጣን መልህክተኝነቱን የአጭበርባሪው አቢያራ ስራ አስፈፃሚነቱ አሳፈረው እናም ከመሳይ በበለጠ ጮኽ ፣የፀፀት በሚመስል ሁኔታ ፣ ይሄን ጊዜ ኤዛ ተደናግጣ እሮጣ በመሄድ መሳይን ከለለችው ፣ አድማስ እየጮኽ ወዲ ወዲያ ካለ በዋላ እየተንገዳገደ መሳይን ሲለምን የነበረውን አቢያራን ተወርውሮ አንገቱን አንቆ ይዞት መሬት ወደቀ ...... በዚህን ጊዜ መስፍንና ዳንኤል በፍጥነት ከዋሻው ለማምለጥ እሮጡ ፣ መሳይን ፈርተውታል ፣ ጓደኝነታቸውን ወደጎን በመተው ያደረሱበትን በደል አስበው መሳይ ለነሱም እንደማይመለስ ተሰምቷቸው ነበር ፣ እነሱ ሲሮጡ በማየትም የአቢያራ ሁለቱ ሴቶች ተከተሏቸው ወዴት እንደሚሄዱ ባያውቁምጨበጌታቸው ድንገት መውደቅ ጨለማው የባስ ጨልሞባቸዋል ፣ በደመ ነፍስ ግን እነመስፍንን ተከትለው እሮጡ ........
.✍ ሙና መሀመድ

👍20🔥2👎1🤔1
🍷የጠንቋዩ ዋሻ🍷
🙈ክፍል 17🙈
👉👉👉👉👉👉👉
አድማስ ከአቢያራ ላይ ሲነሳ በዋሻው ውስጥ ግራ በመጋባትና በጭንቀት ቆመው መጨረሻውን ሲከታተሉት የነበሩት ኤዛና ኤሊያታ አጎንብሰው የአቢያራን በድን ተመለከቱ ፣ ከልጅነታቸው ጀምሮ እንደ ታምረኛ አባት ሲቆጥሩት የነበረው አቢያራ በደም ተጨማልቆ ፀጥ ብሏል ፣ኤልያታ አንዴ አድማስን አንዴ የወደቀውን አቢያራን ስታስተውል ቆይታ ምን እናድርግ በሚል እይታ ወደ ኤዛ ዞረች ፣ኤዛ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳታደርግ ባለችበት ቆማለች ፣ መሳይ ደሞ ሴቶቹ በቀል ይፈልጉ አይፈልጉ ማረጋገጥ ስላልቻለ በለበት ሆኖ በጥንቃቄና ስለቷን አጠብቆ በመያዝ ይከታተላቸዋል
"ኤዛ አባታችን ሞቷል በቃ እንደማንኛውም ሰው ሞቷል "አለች ኤልያታ ግራ ተጋብታ ፣ ድንገት በታምር እንደሚነሳ ጠበቀች
" ኤላ በቃ አባታችን እንደኛ ሰው ነበር ስለዚህ ነው የሞተው ።መሳይ ይነግረኝ የነበረው ነገር ሁሉ እውነት መሆኑን ነው እያየው ያለሁት እናም የኛ ፈጣሪ ሌላ ነው አቢያራ እና የአቢያራ አምላክ ብሎ ነገር የለም ፣ ኤላ መበርታት አለብን ፣"አለች ኤዛ ወደ መሳይ እየተጠጋች መሳይ በደስታ ወደኤዛ ቀረበ
"ይሄንን ስለት በቃ ጣለው መሳይ ማንም ባንተ ላይ ጉዳት አያደርስም እኔ እስካለው ፣ ሁልም አብረን ነን እንዳልከው ከዚ ጨለማ እንወጣለን ፣ ብርሃንንም ታሳየኛለህ ፣ በአንተ ዓለም ውስጥ በደስታ ለመኖር ዝግጁ ነኝ "አለች ኤዛ የመሳይን እጅ እየያዘች ። አድማስ አንዳች ሳይናገር ብዙ መስዋት ሲከፍልለትና ሲያስከፍልለት ይኖር ለነበረው የአቢያራ በድን ላይ እንዳፈጠጠ ነው ፣ ኤሊያታ ሁሉንም ስታይ ቆይታ " በፍፁም አይሆንም ኤዛ ይሄ ክህደት ነው የሞተው እኮ አባታችን ነው ፣ እኛ ደሞ በውጪ እንዳሉት እንደማንኛውም ሰዎች አደለንም ፣ እደጅ ስላለው ነገር ምንም የምናውቀው የለም ፣ ይሄ ልጅ ጌታችንን አሳዳጊያችንን ደሙን አፍስሶታል ፣ ጨካኝ ነው አድማስም አንቆ ገድሎታል ፣ እህቶቻችንን መስፍንና ዳንኤል ይዘውብን እሮጠዋል ፣ አይታይሽም ኤዛ ውጪ ያሉት ሰዎች ምን ያክል ጨካኝ እንደሚሆኑብን ፣ በጭራሽ እኔና አንቺ እነዚህን ሰዎች አምነን ከዋሻው መውጣት የለብንም ፣ አይታይሽም ሊያጠፉን እንደሚችሉ ፣ አባታችንን እኮ ነው የገደሉት ኤዛ ንቂ ለኛም አይመለሱም ፣ "አለች ኤልያታ ወደዋላዋ እየተራመደች ፣ አድማስ በእጁ ምልክት እየሰጠ በጭራሽ እነሱ ላይ ጉዳት እንደማያደርስ ሊያስረዳት ሞከረ እናም በፍቅር እያስተዋላት ተጠጋት ፣ ኤልያታ ይበልጥ በመሸሽ ከአንድ ትልቅ በርሜል ጋር ደረሰች ፣ አድማስ ባለበት ቆም ብሎ ለመናት እንድታምነው እንደሚወዳትም ጭምር እየነገረ ይሄ ሁሉ ለሳ ካለፍቅር የተነሳ እንደተፈጠረ እና አቢያራ በሷ ባይመጣበት ትህዛዞቹን ሁሉ ይፈፅም እንደነበረ ለፈለፈ ፣ ኤልያታ ከበላይዋ በዋሻው ውስጥ የተሰካው እንደችቦ የሚንቦገቦገውን ለብርሃን የሚጠቀሙበትን ዱላመሰል ነገርላይ ያለውን እሳት ለአፍታ ተመልክታ ስታበቃ ፣ አድማስን ለመሸሽ በሚያስመስል ሁኔታ ከበርሜሉ ዋላ ዞረች እና በርሜሊን ክዳኑን ከፈተችው በመቀጠል በውስጡ ያለውን ፈሳሽ ገፍታ አፈሰሰችው በርሜሉ በኤልያታ አቅም ተበግሮ ከመሬት ሲከነበል በውስጡ ያለ ፈሳሽ እየተንደቀደቀ በዋሻው ውስጥ መፈላሰስ ጀመረ ፣ "ኤልያታ ምን እያደረግሽ ነው ጋዙን ....ቤዚሉን......እንዴ ለምን እንዲ ታደርጊያለሽ " እያለ የቀረውን ለማትረፍ ሲጣጣር እሱም ተዘፈቀበት ፣ ያለከልካይ የሚወርደው ፈሳሽ አቢያራንም በድኑን አራሰው ፣ መሳይ ደመነፍሱ አንዳች ነገር ያስተጋባለት ይመስል ፣ በቅፅበት ወደ ኤዛ ተመለከተ ፣ አየችው እጇን ለቀም አድርጎ በመያዝ ወደ ውጪ የሚያስወጣ ፣መንገድ ፍለጋ እሮጠ ፣ በዛው ቅስበት ፣ኤልያታ ፣ከበላይዋ የተሰቀለውን ፣ለብርሃን የሚጠቀሙበትን እሳት መሬት ላይ በመጣል ፣" የትም መሄድ አንችልም እዚው ነው መኖሪያችን በቃ ከአባታችን ጎን ነው መሆን ያለብን ""አለች እሳቱ ከፈሰሰው ቤንዚል ጋር ሲዋሃድ ለጥፋት ጊዜ አልፈጀበትም አድማስ በቤንዚል የረጠበ ልብሱ ወዲያው ተያያዘ ፣ ኤልያታ የተቀሩትን ፈሳሾች እየገለበጠች ፣ እራሷንም በእሳት ነክራ በቃጠሎ ወደሚጮኽው አድማስ ሄዳ ተጣበቀችበት አድማስ እቅፏ ውስጥ ተንገበገበ ፣ አቢያራ በድኑ በእሳት ተያያዘ ..... ኤዛ ከመሳይ ጋር በምታውቀው ዋሻውስጥ መውጫ ፍለጋ ተሯሯጠች ፣ እየተንቦገቦገ የሚመጣው እሳት እንዳይደርስባቸው በመስጋት መሳይ በፍርሃት ወደዋላው እየዞረ እያየ ኤዛ መውጫውን በትክክ እንድታገኘው ተማፀነ ፣ ኤዛ እሳቱ እነ ኤልያታ ካሉበት በኩል በፍንዳታ አይነት ጭምር ሲያይል ጓደኛዋን አስባ ብርክ ያዛት ፣እንደመቆም ስትል ፣ መሳ እጇን ይዞ ጎተታት ፣ ኤዛ ዕንባዋ ዱብ ዱብ እያለ ስለ ጓደኛዋ ፣ መሳይን ተከትላ ተንቀሳቀሰች ፣ እናም የሚከተላቸውን አሳት እየተወለካከፉ ፣ በማምለጥ ፣ ከዋሻው በመከራ ወጡ ፣ ከወጡ በዋላ ፣ ሳምባቸው ውስጥ የገባው ጨስ ሰአል ፈጠረባቸው ፣እናም ከዋሻው እስኪርቁ እያሳሉ ሮጡ ፣ እናም ወደ አንድ ዛፍ ስር ተጠግተው ተቀመጡ ፣ከርቀት ዋሻው ሲነድና በጭስ ሲትጎለጎል ተመለከቱ ኤዛ ዕንባዋን ማቆም አልቻለችም ፣ እዛ ዋሻውስጥ ከእፃንነቷ ጀምሮ ያሳለፈችው ሕይወት የውሸት እንደነበረ ለማሰብ ከብዷታል ጓደኞቿን እህቶቿን አጣች ብቸኝነት ተሰማት ፣ ወደፊት የሚጠብቃት ሕይወት አሳሰባት ፣ መሳይ ሲያቅፋት የእጆቹ ጥንካሬ ተሰምቷት ወደሱ ዞረች ፣ ፊቱ ጥላት ተቀብቷል ግን ፍፁም ደስተኛ ነበረ ፣ ድል አድራጊነት ይነበብበታል ፣ ስታየው ቆይታ ፈገግ ለማለት ሞከረች ፣ ጠጋ ብሎ በአለሁልሽ መንፈስ ፣ከንፈራን አጥብቆ ሳማት ፣ በደከሙ እጆቿ ተጠመጠመችበት.....

👍31🥰7😱2❤1
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...ሌሊቴ ነጋ» አየሩ አሁንም እንደ ማታው እንደ ጠገነነው ነው በረዶውም ያለ መጠን መውረዱን ቀጥሏል " ሚስ ካርይል እንኳን አድርጋው የማታውቀውን ቁርሷን ካልጋው ሳትወረድ በላች
ሪቻርድም ከልጋው ቢነሳም
ከመኝታ ክፍሉ ሳይወጣ
ቁርሱን ጆይስ አቀረበችለትና ሲበላ ሚስተር ካርላይል ገብቶ እንዴት እንዳደረ ጠየቀው "
በጣም ድክም ብሎኝ ስለ ነበር በደንብ ተኛሁ እንግዲህ ግን ቶሎ ብዬ
ከዚህ ብጠፋ ይሻለኛል "
የመሔድ ነገር ከማታ በፊት አይሞከርም ቢሆንም አሽከሮች መኖርህን
ሳይሰሙ መሔድ ስለ አለብህ ብዙ አትቆይም። አሁን ሊቨርፑል ወይም ማንቸስተር ነው እሔዳለሁ የምትለው ?
“ወደ ማንኛውም ትልቅ ከተማ ብሄድ ግድ የለኝም መቸም እንደኔ በመሳደድ ላይ ላለ ሰው ሰፊ ከተማ ነው የሚሻለው "
«ለአኔ እንደሚመስለኝ ሪቻርድ ይህ ቶርን የምትለው ሰውዬ ሊያስፈራራህ ብቻ ነው የፈለግው በርግጥ ጥፋተኛ ከሆነ አሱ የሚበጀው ሀርፎ መቀመጥ ነበር አሁንም ቢሆን እሱ መጥፎ ነገር የሚያገኘው አንተ የተያዝክ እንደሆነ ነው ” አለው
ሚስተር ካርላይል "
“ ታዲያ ለምን ያስቸግረኛል ? ለምንድነው ፖሊስ ልኮ እንዲከታተለኝ የሚያደርገው ?
አንተም እንድታስቸግረው ስላልፈለገ በፍራት ሊያባርርህ ይፈልጋል " የፖሊሱ ፍላጎት አንተን ለመያዝ ቢሆን ኖሮ አስካሁን አያቆይህም » ከቦታ ቦታ እየተንከራተተ አይከተልሀም " የምስጢር ሠራተኛ ቢሆን ኖሮ ደግሞ እንደዚህ ሰው
በየደረስክበት ብቅ እያለ ሳይሇን አንተ እንዳታየው እየተጠነቀቀ ነበር የሚከታተልህ "
“ ነገሩ አንተ የምትለው እውነት ነው ” አለ ሪቻርድ ' ' ምክንያቱም እሱ በከፍተኛ ማዕረግ ያለ ሰው ስለሆነ በዚህ ወንጀል መጠርጠሩ ብቻ በአኩያዎቹ ዘንድ
የተናቀ የተዋረደ ያይርገዋል።
"አኔ ግን ሪቻርድ. . . ሰውየው አንተ እንደምትለው ትልቅ ሰው መሆኑን ማመን ይቸግረኛል
በዚህስ ምንም ጥርጥር የለበትም ሚስተር ካርላይል
ስሙን ብጠራልህ ደስ አይልህም ብዬ ነው እንጂ ትናንት ማታ ከማን ጋር ሲሔድ እንዲያውም እንዳየሁት ብነግርህ ይቸግርሃል ?”
“ ተናገር ራቻርድ ንገረኝ ግድ የለም"
"ከሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር ሁለት ጊዜ አየሁት " አንድ ጊዜ በቁማር ከሚወራሪድባቸው ክፍሎች በር ቁመው ሲያወሩ ሁለተኛ ጊዜ ደግሞ ክንድ ለክንድ ተያይዘው ሲሔዱ አገኘኋቸው " ለሚያያቸው በጣም የሚግባቡ ይመስላሉ … ”
በዚህ ጊዜ አንድ የተቆጣ ድምፅ በበረንዳው በኩል ሽቅብ እየጮኸ ሲጣራ ተሰማና ሪቻርድ ሔር ልክ በጥይት የተመታ ያህል ከተቀመጠበት ዘለለ ይጣራ የነበረው የሚስተር ጀስቲስ ሔር ድምፅ ነበር ።
" ካርላይል የት ነህ ? የማይሰማ ጉድ የለ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገር
ይደረጋል " ና እስ ውረድ !”
ሚስተር ካርላይል የሚሆነው ቅጡ ጠፋው በሕይወቱ እንደዚያ ተጨንቆ አያውቅም " ያንን ድምፅ ሲሰማ እሱም ፈጥኖ ብድግ አለ " ሪቻርድ በበኩሉ ወዲያው ባርኔጣውን አንሥቶ የውሸት ሪዙን አጥልቆ ከአልጋው ሥርና ከቁም
ሳጥኑ ውስጥ መሸሸጊያ ያማርጥ ጀመር "
“ እባክህ አትሸበር ሪቻርድ
ምንም አይመጣብህም " እኔ እዛው እሸኛቸዋለሁ ” አለው ሚስተር ካርላይል በጆሮው ሹክ ብሎ "
ሚስተር ሔር ከደጅ ሲጮህ ለካ ሚስስ ካርላይል ልብሷን በመልበስ
ላይ ኖራለች " ሌላውን ሁሉ አብቅታ የሌት ቆቧን ገና ሳታወልቀው አቋርጣ ወጣች ያንን አስገራሚ የሌሊት ቆብ ያየ ቢያየው እሷ ግድ አልነበራትም " ወጥታ ከበረንጀፈዳው ገረገራ ተደገፈች "
“በዚህ ውርጭ የሚያስመጣ ምን ነገር ገጠመህ ?” አለችው በድንጋጤ ድምፅ
“ሚስተር ካርላይልን ለማነጋገር እፈልጋለሁ ። ጥሩ ወሬ ሰምቻለሁ
“ ስለ ምን ? ስለ አን ወይም ስለ ቤተሰቧ የሆነ ነገር አለ ?
የማን አን ? " አለ በሆነ ምክንያት የተበሳጨዉ ዳኛ ያ ልጄ ብዬ እንድጠራው የተገደድኩት ወመኔ ልጅ እዚህ ነው ያለ ይሉኛል " የሱ
ጉዳይ ነው የበጠበጠኝ "
ሚስተር ካርላይል ከፎቅ ደረጃዎቹን አራት አራቱን ባንዴ እየተራመደ ወረደና ሚስተር ጆስቲስ ሔርን ክንዱን ይዞ ወደ ሳሎን አስገባው ።
እንደ ምን አደሩ ? በዚህ በረዶ እንዴት ችለው መጡ?ምነው ደኅናም አይደሉ ? ሲቃ የያዘው ይመስላሉሳ ? ”
“ሲቃ!” ብሎ በጩኸት ተቀብሎ ደገመና የጋለ ጡብ እንደ ረገጠች ድመት እግሮቹን በተራ እየሰቀለ በክፍሉ ውስጥ እየተንጎራዶደ አንተም ሕይወትህ በተረገመ ልጅ ቢበጠበጥ ኖሮ እንደኔ ሲቃ ይይዝህ ነበር " እንዲያው ሰዎች ጭንቅላታቸውን በራሳቸው ጕዳይ ቢበጠብጡና የራሴን ጉዳይ ለራሌ ቢተዉልኝ ምን አለ ?
ግን ከዚህ ሁሉ ተሰቅሎልኝ ቢሆን ኖሮ መቸ ይህ ሁሉ ይመጣብኝ ነበር "
“ ምነው ምን ነገር መጣ ? አለ ሚስተር ካርላይል "
"የመጣው ነገር ይኸውልህ አለና አንድ ደብዳቤ ከጠረጴዛው ላይ ወረወረለት " " ይኽንን አሁን ፖስተኛው አመጣልኝ " እንደዚህ የሚስደስት ወሬይዞልኝ መጣ "
ሚስተር ካርላይል ወረቀቱን አንሥቶ አነበበው " ሁኔታው ከተቆርቋሪ ዘመድ የተላከ ይመስል ነበር መልእክቱ ወንጀለኛዉ ልጅ እስካሁን ዌስት ሊን ያልደረሰ
ከሆነ በሚመጡት አንድ ሁለት ቀን ውስጥ ሊደርስ ይችላል "ዌስትሊን መግባቱ ከተሰማ ደግሞ ወዲያው ሊያዝ ስለሚችል አባትየው ተጠባብቆ መዲያሙኑ መልሶ
አስወጥቶ እንዲሰደው የሚምክር ነበር "
ይኽ ዴብዳቤ የሐኀፊው ስም አልተጻፈበትም አለ ሚስተር ካርላይል
" አዎ የለውም !እና ቢሆንሳ ? አለ ጀስቲስ ሔር ።
" እኔ ስም ላልተፃፈበት ደብዳቤ የማደርገው ጥንቃቄ ከእሳት መጨመር ብቻ " አለው ሚስተር ካርይል።
“ ግን ማን ጻፈው ? አለ ጀስቲስ ሔር “ ሪቻርድስ አሁን ዌስት ሊን ላይ ነዎይ ነው ዋናው ጥያቄው
“ አሁን ሲያስቡት ወደ ዌስት ሊን የሚመጣ ይመስለዎታል እንዲያው ግልጽ ያለ አስተያየቴን ብሰጠዎ ይቀየሙኛል ? ”
“ የት አባቱ ይኸ ዕብድ ደሞ ዌስት ሊን ላይ ሊታይ?ሰተት ብሎ ሮጦ ከሞት መንጋጋ ሊገባ ? አዬ ምነው እጀጄ ላይ በጣለውና በሕግ ሥር አውዬ ባረፍኩት ”
“ እኔ ልነግርዎ የፈለግሁትይህን ሁሉ ንዴት በራስዎ ላይ የሚያመጡት በገዛ እጅዎ መሆኑን ነው”
“ ለምን እንዲህ ትለኛለህ .... ሚስተር ካርላይል? ሆሊጀንን የገደልኩ እኔ ነኝ ? ከሕግ የሸሸሁት እኔ ነኝ ? የት እንደሆነ ቤልዘቡብ ይወቀው እንጂ ' የተደበቅሁት እኔ ነኝ ? አባቴ በሰላም እንዳይኖርበት የአራሽ ቡቲቶ ለብሼ ወደ ተወለድኩበት መንደር እየመጣሁ ያባቴን ስም የማስነሣው እኔ ነኝ? ስም ያልተጻፈባቸው ደብዳቤዎች እጽፋለሁ ? እስቲ በል ንገረኝ ሚስተር ካርላይል እንዴት አድርጌ
ነው በራሴ ላይ ንዴት የማመጣው ?
“ ይስሙኝማ አንድ ጊዜ ስለ ተናደዱ የልጅዎ ስም በፈለገው ምክንያት ቢነሳም ይበሳጫሉ " እንደኔ ደግሞ ይህን የመሰለ ደብዳቤ የሚጽፍልዎ እርስዎን ለማናደድ ታጥቆ የተነሣ ሰው ነው ምናልባትም ዌስት ሊን ውስጥ አብሮን የሚኖረው ሰው ሊሆን ይችላል ”
“ ይሀ ጭራሽ የማይመስል ነገር ነው "
“ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ማን ስለመሆኑ ምንም ፍንጭ እንደማይሰጥ ማወቅ አለብዎ እኔ ብሆን ደብዳቤውን እሳት ውስጥ እከትና ስለሱ ማሰቤን አቆም ነበር
አሁን እርስዎ በዚህ በረዶ እየዳከሩ ሲመጡ ተንኮለኞች ከዚህ ከኛው አካባቢ ከሆኑ ደብዳቤውን ይዘው እኔን ለማማከር እንደሚመጡ ስለሚያውቁ ይህን ጊዜ አሻግረው
እያዩዎ ይሣሣቁ ይሆናል "

👍16❤1
መቸም እንዳልከው የዚያ ቀጣፊ መምጣት ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ! ነገር ግን ለሁሉም ፖሊስ ጣቢያ ልሒድና ነቅተው እንዲጠባበቁት ልንገራቸው"
እንደዚህ ያለውንስ በምንም አያደርጉትም ... ጀስቲስ መጀመሪያ ነገር ሪቻርድ ወደ ዌስት ሊን ብቅ አይልም ግን ድንገት ቢመጣስ?እርስዎ የገዛ ወላጅ አባቱ ሆነው ውሃ ይብላህ ብለው ጎርፍ ላይ ይለቁታል እርስዎ ይህን ከፈጸሙ
ሕዝበ አዳም እንዳለ ዐይንህን ላፈርይል ይልዎታል ሌሎች ሰዎች ሐቁን ለመንገር ቢያፈገፍጉ
እኔ አልደብቀዎትም • ልጁ ከጅዎ ቢገባ አሳልፈው እንደሚሰጡት የሚናገሩትን ዛቻ ማንም ሰው ይፌጽሙታል ብሎ አያምነዎትም" ቢያርርጐ ግን ወዳጆችዎን ሁሉ ባንድ ጊዜ ያጣሉ » ከዚያ ወዲያም አንድም ሰው እንደማይጠጋዎ ማወቅ አለብዎ።
"እኔ የማልኩበት ጉዳይ ስለሆነ አልተወውም "
“ እንደዚሀ ያለ የማይረባ ወረቀት ቢደርስዎ ልጄ ወደዚህ መጥቷል የሚል ወሬ አግኝቻለሁና ተከታተሉት ብለው ለፖሊስ ለመንገር አልማሉም እንዴ ምን መሆንዎ ነው ፖሊስ ከፈለገ ራሱ ይከታተል እንጂ እርስም ኢያሠማርዋቸው "
“ይህን ደብዳቤ ለሚስዝ ሔር አሳይተዋቸዋል ወይንም ስለሱ አንሥተውላቸዋል ?
"አላሳየኋትም እንዲያውም ወዳንተ ልመጣ ካፖርቴንና ጥላዬን ይዠ ስወጣ አይታ ወዴት ለመሔድ እንደምቸኩል ብትጠይቀኝ እንኳን መልስ አልሰጠኋትም'
“ በጣም ጥሩ አድርገዋል እንደዚህ ያለ ወሬ ሚስዝ ሔርን ሊጐዳቸው ስለሚችል'ምንም ነር እንዳይተነፍሱ እስከ ዛሬ የተሠቃዩትን እንኳን ቢያስቡት የትናየት ነው ።
“ በከፊል”ኮ የራስዋ ጥፋት ነው ይኽን እርጉም ልጅዋን ለምን ከጭንቅላቷ አታወጣውም?
“ እሳቸው እንደዚህ ማድረግ ከቻሉ'ከሰው ተፈጥሮ ውጭ የሆነ ሥራ ሠሩ ማለት ነው " እርስዎም ቢሆኑ በሁሉ መልኩ ያልተመለከቱት ጥያቄ አለ " ልጅዎን ይዘው ለሕግ እንደሚያስረክቡት ብዙ ጊዜ ይናገራሉ " ነገር ግን የባለቤትዎንም ሕይወት አሳልፈው መስጠትዎ መሆኑን ልብ ብለውት ያውቃሉ ? ''
“ ኤዲያ ወሬ ነው ! ” አለ ጀስቲስ ሔር "
“ በእርስዎ ጥረትም ሆነ ወይም በሌላ መንግድ ሪቻርድ ?ተይዞ ለፍርድ ከቀረበ

“ በእርስዎ ጥረትም ሆነ ወይም በሌላ መንግድ ሪቻርድ ?ተይዞ ለፍርድ ከቀረበ ባለቤቶ እንደሚሞቱ ሳይታለም የተፈታ ነው ያን ጊዜ አሁን የምነግሮ ነገር ወሬ አለመሆኑን ይገነዘባሉ።
ሚስቶር ሔር ከጠረጴዛው ተዘርግቶ የተጣለውን ደብዳቤ አንሥቶ አጠፈና ወደ አንቬሎፑ መልሶ እስገባው “ ጽሕፈቱንም የምታውቀው አልመሰለኝም "
አለው ሚስተር ካርላይልን "
እኔ እንደዚህ ያለ ጽሕፈት ማየቴን አላስታውስም " ወደ ቤት መመለሰዎ ነው ?
“ የልም ቦሻ ዘንድ ሔጀ አሳየውና የሚለውን እሰማዋለሁ " ብዙም ሩቅ አይደለም "
“ ቦሻ በሪቻርድ ነገር ሁልጊዜ ስለሜያዝኑ ቢያሳዩዋቸውም ግድ የለም » ከፈለጉም በግልፅ ይጠይቁዋቸው " አስተያየታቸውን ይገልፅልዎታል » ግን ለሌላ
እንዳይናገሩ ያሳስቧቸው "
"አከራካሪ ጥያቄ ነው አጥጋቢ መልስ ማግኘት ያስቸግራል "
ጀስቲስ ሔር ወጣና ጃንጥላውን ዘርግቶ መንገዱን ይዞ ዘቅዝቆ ሲሔድ ካርላይል በዐይኑ ሸኘው ከዚያ ተመልሶ ከሪቻርድ ክፍል ገብቶ ተቀምጦ ካባትየው ጋር የተነጋሩትን ባጭሩ ገጸለት ሪቻርድም ምንም ሳያመነታ ደብዳቤዉ የቶርን ሥራ መሆኑን ነገረው … ለመሆኑ ዛሬስ እናቴን ላያት እችላለሁ ? " አለው
የለም አሁን እንኳን እዚህ መምጣትህም ባይነገራቸው በጣም የተሻለ ነው.
አንዳንድ እያሉ ብዙ ነገ መጠየቃቸው ስለማይቀር ክትትል እንደሚደረግብህ ከሰሙ የመንፈስ ሰላም ያጣሉ " የዛሬውን ይቅርብህ አትያቸው "
"ባርባራንሳ ?"
“ እሷንስ ዛሬ ጧት መቸም አየሩ በጣም ቀዝቃዛ ስለሆነ ለመምጣት ትቸገር ይሆናል እንጂ እዚህ መጥታ አብራህ ልትውል ትችላለች "
"እሷ እኔን ለማየት በበረዶ ተራራ ተንኳትታ ፡ ሸርተቴ መሬት ተንፋቅቃ
ብትመጣ የሚደርስባትን ችግር ከችግር አትቆጥረውም " አለ ሪቻርድ "
ዐውቃለሁ አለ ሚስተር ካርላይል “ ዛሬ ለሚስዝ ሔር ኮርኒሊያ ስለ አመማት ባርባራ መጥታ ታነጋግራት ብዬ እነግራቸዋለሁ ምን ይመስልሻል ኮርኒሊያ
“ብትፈልግ ሙታለች በላት ።"
ሚስተር ካርላይል ሠረገላውን አስጭኖ ጆን እየነዳ ወደ ጀስቲስ ሔር ቤት ሔዶ " ሚስዝ ሔርና ባርባራ አብረው ተቀምጠው አገኛቸው። በማለዳው በመምጣቱ
ደነገጡ ጀስቲስ ሔርን ፈልጎ እንደሆነ ብለው የቀረበለትን ቁርስ እንኳን ሳይቀምስ ገና ማለዳ ወጥቶ መሔዱን ነገሩት ። እሱ ግን ኮርኒሊያን ኃይለኛ ጉንፋን ስለ ያዛት
ባርባራ ስታጫውታት እንድትውል ብሎ ሊወስዳት መምጣቱን ገለጸላቸው "
ዛሬስ እማማም ስለ አመማትና ያለኔ ደግሞ ቀኑ ቶሎ ስለማይመሽላት ትቻት መውጣት አልችልም ”
ኧረ እኔም አልሰዳትም . . . . አርኪባልድ ፤ዛሬ ባርባራ የምትወጣበት ቀን አይደለም አለችው እናቲቱ "
ሚስተር ካርላይል ምስጢሩን ለባርባራ እንዴት እንደሚገልጽላት እየተጨነቀ ሳለ አንዷ ሠራተኛ በሳሎን በር ዘለቀች "
የዓሣ ሻጩ ሠራተኛ መጥቷል ፡ እሜቴ ። ዛሬ ዓሣ ሊኖር እንደማይችል እንዲነግር ጌታው ልኮት ነው " በዚህ አየር ባቡሮቹ በሰዓቱ መድረስ አልቻሉም ”

👍7
ሚስዝ ሔር ከተቀመጠችበት ተነሥታ ሠራተኛይቱን ለማነጋገር ወደ በሩ ሔደች « ሚስተር ካርላይል በዚህ አጋጣሚ ተጠቅሞ ከባርባራ ጋር ወግ ጀመሪ
ባርባራ ተይ እንጂ እምቢ አትበይ " አንቺን የፈለግሁበት እውነተኛ
ምክንያት ስለ ሪቻርድ ጉዳይ ነው " ሚስዝ ሔር ወደ ውስጥ ተመልሳ፡ አቤት አቤት : የዛሬውስ ቀን እንዴት ያለ ቀን ነው : አለች በብርድ እየተንቀጠቀጠች መቸም ኮርኒሊያ ባርባራን በዚህ ዐይነት ቀን ለምን አልመጣችም ብላ አታማትም""
"
“ እሷማ ትመጣለች ብላ ትጠብቃታለች እንጂ " ወደ ቢሮዬ ከመሔዴ በፊት እንዳዶርሳት ሠረገላዬ ከደጅ እየጠበቀ ነው " አንዲት ቅንጣት በረዶ እንኳን አይነ
ካትም " በይ ባርባራ ይልቅ እንሒድ ” አላት "
ግን እማማ ... አንቺ ብቻሽን መቅረቱን የማይከፋሽ ከሆነ ብሔድ እወድ ነበር።
“ ኋላ ብርድ ቢመታሽ አንቺ ታውቂያለሽ "
“ አይ ' አይነካኝም በደምብ ደራርቤ እለብሳለሁ "
ከዚያ ወዲያው ተሳፈሩና ወደ ኢስት ሊን ተመለሱ ከመንግድ እንዳያውጉ ጆን ከኋላቸው ተቀምጦ ስለ ነበር ፡ ምስጢር እንዳይወጣ ፈርተው እሷ ለመጠየቅ እሱ ደሞ ለመናገር እንደ ጓጉ ኢስት ሊን ደረሱ ። ሚስተር ካርላይል ክንዱን ሰጣትና ይዟት ወደ ምግብ ቤት ገባ
“ እንግዲህ ላስደነግጥሽ ስለሆነ ተጠንቀቂ ... ባርባራ ” አላት "
ልቧ ተንጠለጠ ብርክ ያዛት ፊቷ በፍራት ዐመድ መሰለ “ የሚያስደነግጥስ አይደለም ሪቻርድ አንድ ነገር አጋጥሞት ነበር ”አላት "
ከዚያ ቀጠለና ማታ እንዴት እንዶ መጣ ጀምሮ እስከ ጀስቲስ ሔር ኢስት ሊን መጥቶ እስከ ተመለሰበት ድረስ የሆነውን ነገራት ከዚያም ሚስ ካርላይልና ሪቻርድ
ወደ ነበሩበት ክፍል አስገብቷትና ትንሽ ተጨዋውቶ ወደ ሥራው ሔዶ ባርባራ ሪቻርድ ከቶርን ጋር ስለ መገናኘቱና በተለይም ከሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር እጅ
ለእጅ ተያይዘው ሲነጋገሩ እንዳያቸው ሌላም ሌላም ሲያጫውታት እሷም አንዱን
አንዱን ስትጠይቀው አብራቸው የነበረችው ሚስ ካርላይልም አንዳንድ ቃል ከጨዋታቸው ደብለቅ ስታደርግ ዋሉ ።
" ግን ” አለችው “ ከሰር ፍራንሲዝ ጋር አልከኝ?ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን
ታውቀዋለህ እንዴ ? ”
“ እንዴ በደንብ ነዋ ! እንዲያውም በከተማዉ ውስጥ በደንብ የማውቀው ሰው እሱ ብቻ ነው ለማለት እደፍራለሁ " "
ባርባራ የሐሳብ ሰመመን ይዟት ጭልጥ አለ " ከዚያ ለቀቅ ሲያዶርጋት ፡ “ እና ሁለቱ ይመሳሰላሉ ? " አለችው "
ሁለቱም በመጥፎነታቸው በጣም ሳይመሳሰሉ አይቀሩም "
“እኔ ያልኩህ በመልካቸው ነው ። "
ሁለቱም ረጃጂሞች ከመሆናቸው በቀር ምንም አይመሳሰሉም ” አላት
ባርባራ አሁንም በሐሳብ ባሕር ሰመጠች " የሪቻርድ ንግግር አስገረማት እንዲሁ ልቧ በሐሳብ እንደ ተዋጠ ቆይታ ከሚቀጥለው ክፍል የልጅ ድምፅ ሰምታ ነቃች
ትንሹ አርኪባልድ ካርላይል ነበር ጆይስ ምግብ ለማቅረብ ወደ ምግብ ቤት ስትሔድ ሕፃኑ ኋላ ኋላዋ ይሮጥ ነበር ባርባራ ወደ ልጆች ቤት ለመውሰድ አንሥታ
አቀፈችውና
አንተ ወደል !” ስትለው ሕፃኑ ተፍነከነከ "
“ እባክሽን ጆይስ.... ሚስ ካርሳይል አሟታልና ዛሬ የልጆቹን ረብሻ
አትችለውም " ስለዚህ ከክፍሉ እንዳይወጣ ተቆጣጠሪው ” ብላት ገባች
ሰዓቱ መሸ የሪቻርድ መሔጃ ደረስ ቀኑ ላይ ብራ ሆኖ ነበር :አሁን ደግሞ በረዶው በጣም መጣል ጀመረ " ለጊዜው የሚቢቃው ገንዘብ ተሰጠው " ሔዶ የሚ
ያርፍበትን ሲያውቅ አድራሻውን ቶሎ እንዲልክ ሚስተር ካርላይል ነገረው ሪቻርድ እንባዋን መቈጣጠር እንደ ተሳናት እንደ ባርባራ ተነቀነቀ ሚስ ካርላይልም
“ሞኝ አትሁን ልጄ ... ሁለተኛ ከምንም ጠብ እንዳትገጥም ” ብላው ተሰናብቷት ወጣ" ከእኅቱ ጋርም በእንባ ተለያዩ በመጨረሻም ሚስተር ካርላይል ከበሩ ድረስ
ሸኘው .
ባርባራ እየተንሰቀሰቀች ሪቻርድ ወደ ነበረበት ክፍል ገባች " ጆይስ ቀድማ ገብታ ነበርና እዚያው አı
ገኘቻት "
“ በውነቱ ጥፋቱ ካልሆነ ከባድ መከራ ላይ ነው የገባው " አለች ጆይስ በባርባራ ለቅሶ አመካኝታ
" እንዴ !” አለች ባርባራ እንባ የሚያወርዱትን 0ይኖችዋን ቀና አድርጋ “ ደሞ ጥፋተኛ ያለ መሆኑን ትጠረጥሪያለሽ ? ''
አሁን እንኳን ሁኔታውን ሳየው ንጹሕ መሆን እያመንኩለት ነው " ተንግዲህ ዋናው ነገር ያን ካፕቴን ቶርንን ማግኘት ነው .
“ ጆይስ አለች ባርባራ እጂዋን ግጥም አድርጋ ይዛ እኔስ ያገኘሁት መሰለኝ " በኔ ሐሳብ ማን መሆኑን ዐውቄዋለሁ ብዬ አምኛለሁ እስከ ዛሬ ለማንም ያልተናርኩት ቢሆንም አሁን ላንቺ ብነግርሽም ግድ የለኝም " ዛሬ ማታ ነገሩን አላውቅም ተናገሪ የሚለኝ ሐሳብ መጣብኝ እና እንደኔ ይህ ቶርን የተባለው ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ነው "
ጆይስ ያላሰበችው ነገር ስለሆነባት ደነገጠች ዐይኖቿን አፍጣ ' “ ሚስ ባርባራ ! " አለች "
“ እኔ መቸም እሱን ጠረጠርኩ "እመቤት ሳቤላን ይዞ ከፋበት ቀን ጀምሮ ነበር የጠረጠርኩት " ያን ጊዜ ሪቻርድ ለጥቂት ሰዓት መጥቶ ነበር " ቶርንን ቢንሌን አገኘው " የማታ ልብስ መልበሱን ጸጉሩን ከግንባሩ ወደ ኋላ የመግፋት ልማዱን በጨረቃ ብርሃን ጐልቶ የታየው ነጭ እጁንና የአልማዝ ቀለበቱን ሁሉ ሲገልጽልኝ ካፕቴን ሌቪሰን ጋር ተመሳሰለብኝ " እና ከዛች ሰዓት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ
ሪቻርድ ያየው ሰው ካፒቴን ሌቪሰን መሆን አለበት ስል ኖርኩ " ዛሬ ሪቻርድ ቶርንን ከፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር እንዳየውና ሁለቱም የቅርብ ግንኙነት እንዳላቸው አጫወተኝ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ላነሣለት ስላልፈለግሁ ለሚስተር ካርላይል አልነገርኩትም
ባርባራ ወደሚስተር ካርላይል ዘንድ ወርዳ “አሁን አንድ ሰዓት ተኩል ሆነ! እማማ ታስባለች ስለዚህ ወደ ቢቴ ልሒድ” አለችው " ሰዓቱ ከባድ በረዶ የሚወርድበት ስለ ነበር ራሱ በሽፍን ሠረገላው ይዟት ሔደ አሁንም የወንድሟን ነገር እያሰበች በለሆሳስ ስታለቅስ ሚስተር ካርላይል ዝም ብሎ ይመለከታት ጀመር በመጨረሻ ወደ ዐጸዱ ሲቃረቡ እንደ ተቀመጠ ወደፊቱ ደገፍ አለና እጂዋን ያዛት "
“ አትዘኝ ፡ ምናልባት ለሱም አንድ ቀን ያልፍለት ይሆናል ” አላት "ሠረግላው ደረሰና ቆመ
“ ተመለሱ ” አለችው ተከትለውት የመጡትን አሽከሮች እኔ ቀስ ብዬ
በእግሪ አመለሳለሁ "
ዛሬስ እኛ ጋር ልታመሽ ነው መሰለኝ እቤት እማማ በጣም ነው ደስ የሚላት " እሷም ደስ እንዳላት በድምጿ ይታወቅባት ነበር - ሚስተር ካርላይል እጂዋን
ሳብ አድርጎ ተያይዘው ወደ ቤት ማዝገም ጀመሩ "
ባርባራ ከቤት ስትግባ እናቷ ተኝታ ነበር አባቷም ወደ ውጭ እንደ ሔዶ ገና አልግባም " ስለዚ ሚስተር ካርላይልን የማስተናገዱ ሥራ በሷ ላይ ብቻ ወደቀ ከሚንቀለቀለው እሳት አጠገብ አብረው ቆሙ ባርባራ ስለ ዕለቱ አዋዋሏ ታስብ
ነበር • ሚስተር ካርላይል ግን'ስለ ምን ያስበ እንዶ ነበር ከራሱ በስተቀር ያወቀ የለም " ዐይኖቹን ሰበር አድርጎ ወደ ባርባራ ሲያይ ጸጥታ ሆነ " ሁለቱም ዝም አሉ"
ኋላ ወደ እሷ እንደሚመለከት ተሰማትና እሷም ቀና ብላ አየችው "
« ባርባራ የትዳር ጓዶኛዬ ለመሆን ፈቃድሽ ይሁን ? አላት
መልኳ እንዴት በአንድ ጊዜ ልውጥውጥ አለ ! የልብ እርካታ ብርሃን የስሜት ፍላትና የደስታ ቅላት በአንድ ጊዜ ፊቷ ላይ ቦግ ሲሉ ታዬና ወዲያው ድብዝዝ ' ጭልም አሉ !
ባርባራ ራሷን በአምቢታ ነቅንቃ “ ቢሆንም ስለ ጠየቅኸኝ እመሰግንሃለሁ አለችው
ምን የሚያግደን ነር አለ ?”
ወዲያው እንባዋን ዱብ ዱብ አደረገችው "
“ ከዚህ በፊት ሌላ አግብቸ ስለ ነበር ነው ?

"የለም : አይደለም ! የዚያን ጊዜ ማታ ትዝታ ነው መቸም ልትረሳው አትችልም በኔም አእምሮ ውስጥ በእሳት ፊደሎች ተጽፋል " ራሴን እንደዚያ አጋልጬ እሰጣለሁ ብዬ አስቤው አላውቅም " አንተም ያን ጊዜ በተፈጸመው ሁኔታ እንኳን
ዛሬ ልትጠይቀኝ አይገባህም ነበር "
ባርርባራ ቀና ብላ አየችውና ያነጋገሩ ቃና በሠራ አካላቷ ሠርጾ ገባ "
“ እንደምወድሽ ታውቂያለሽ ? ካንቺ በቀር ሌላ ማግባት ፍላጎትም ምርጫም እንደ ሌለኝ ታውቂያለሽ ?
አይሆንም : ደስታ በጃችን ሲገባልን በስሜት አንሥተን አንጣለው ! " ክንዱን ተደገፈችና እንባዋን ለቀቅ አደረገችው “ ደስታ? ላንተ
ደስታ ይሰጥሃል ?”
እጅግ በጣም ጥልቅ የሆነ ደስታ ይስጠኛል " "
ሐቅ ገጽታው ላይ አነበበችው " ፀሕይ በመሰለው ፊቷ ልብን ወከክ የሚያደርግ ፈገግታ ፈካበት ።
“ እንደ ዱሮው ታፈቅሪኛለሽ ... ባርባራ ? ”
“ ከዱሮው በበለጠ ' በጣም በበለጠ ” ስትል በሹክሹhታ
እቅፍ አድርጎ ሲይዛት ' ፊቷን ሳብ አድርጎ ወደሱ ሲያስጠጋው
በመጮረሻ እፎይታ አገኘ "
ሪቻርድ ሔር ጠርማሳ ባርኔጣውን ሳይሆን ፊቱን ከታዛቢ ዓይኖች እንዲከልለት ሚስዝ ካርላይል የሰጠችውን ጥላ ዘርግቶ በበረዶው መኻል ጃንጥላው ከሌላ ሰው ጋር ተጋጨ ከሱ ጋር የተጋጠመው ጥላ ጨርቁ መኳንንት ብቻ ሊያገኙት የሚችል ልዩ ሐር ሆኖ እጀታው ደግሞ እንዳለ የማይቈጠር ነበር "
የሁቱም ጥላዎች ተገፋፍተው ወደ ጐን ሲገፋተሩ ሁለቱ ተላላፊዎች ተፋጠጡ "
“ እንዴት እንደዚህ ትደፍራለህ ... ሰውዬ ? ለመሆኑ መንገድህን አይተህ መሔድ አትችልም ? ሲለው ሪቻርድ ተዝለፍልፎ የሚወድቅ መሰለው " ከሱ ጋር የተፋጠጠው ሰውዬ አባቱ መሆኑን ሲያይ በኪሱ ያለውን ግፈገንዘብ ሁሉ በስጠና
መሬት ተከፍታ በዋጠችው ደስ ይለው ነበር "
ሪቻርድ ሳይታወቀው የድንጋጤ ጩኸት አመለጠውና እንደ ቀስት ተወርውሮ በረረ » ጀስቲስ ሔር በዚያ ሪዙ ቸምቸም ያለው ሁኔታው ሁሉ ልዩ የሆነ ሰውዬ ተገርሞ ፡ የእግሩ ዳና ከርቀቱ የተነ ለጆሮ እስኪጠፋ ድረስ ቆሞ ተመለከተው

👍14🥰2❤1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
ጀርመን በእንግሊዝ ላይ የምታወርደው የቦምብ ናዳ እስኪቆም ድረስ መንግስት ትያትር ቤቶችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ዳንስ ቤቶችን ቢዘጋም ዳንስ ቤቶች ግን ህጉን ተጋፍተው የሌሊት ስራቸውን እየሰሩ ነው፡፡ ሄሪም በአንድ ዳንስ ቤት ውስጥ ተወሽቆ የአሜሪካን ሙዚቃ በጆሮው እየተንቆረቆረ ውስኪውን ይጨልጣል፡ ሬቤካን እንዴት ሸውዶ ጥሏት እንደሄደ እያሰበ እያለ ወንድሟ ድንገት ከች አለበት፡፡
እዳውን ሳይከፍል ከምግብ ቤቱ በመውጣቱ የጅል ስራ ሰርቷል ሬቤካ ደግሞ ክብሯን ሽጣ ገንዘብ የምትከፍል ዓይነት ሴት አይደለችም፡ ትንሽ
ስታስቸግር የምግብ ቤቱ ኃላፊ ፖሊስ ጠራ፡ ቤተሰቦቿም ፖሊስ ጣቢያ
ተጎተቱ፡፡ እንዲህ አይነቱን ችግር ሄሪ ዘወትር ሲሸሽ ነው የኖረው፡፡ ዛሬ ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ ሰላሳ ያህል እስረኞች ጋር ጣቢያ ተዘግቶበታል፡፡ ክፍሉ
መስኮት የሚባል ነገር የሌለው ከመሆኑም በላይ በሲጋራ ጢስ ታፍኗል፡
ሬቤካ ሄሪ የቀረበበት ክስና ማስረጃ የሚያከራክር አይደለም፡፡ ለመሰረተችበት ክስ የምግብ ቤቱ ኃላፊ ምስክር ሆኖ የሚቀርብ ሲሆን ጌታ ሞንክፎርድም የጠፋውን የሸሚዝ ማያያዣ በተመለከተ ከሰውታል፡ ከዚህም የከፋ ነገር አለ፡ በወንጀል ምርመራ መምሪያ ሲመረመር ነው የዋለው
ከሁለት ወይም ከሶስት ዓመት ወዲህ ጌጣጌጥ ጠፍቶብናል የሚሉት
አመልካቾች በርክተዋል፡ አመልካቾቹ ጌጣጌጦቹ ተሰርቀዋል የሚል ግምት
የላቸውም ምክንያቱም ለመውሰድ ዕድሉ ያላቸው እንግዶቻቸው ብቻ ናቸው ለፖሊስ የሚያመለክቱትም እንዲያው ከተገኙ በማለት ነው፡፡
በምርመራው ወቅት ሄሪ አይናገር አይጋገር መልስ ለመስጠት አሻፈረ ብሏል፡፡ ሆዱ ግን ታምሷል፡፡ እስካሁን የፈጸመው ስርቆት እንዳልታወቀበት እርግጠኛ ቢሆንም በተቃራኒው የሰማው ነገር ፍርሃት ለቆበታል፡
መርማሪው አንድ የጠበደለ ዶሴ አውጥቶ እስካሁን ጠፉ የተባሉትን
ጌጣጌጦች ዘረዘረና ‹‹ይሄ ሰው ከፍተኛ የጌጣጌጥ ፍቅር የተጠናወተው ብቻ
ሳይሆን ጌጣጌጥም ያውቃል አለ። ፋይሉ እሱ በተለያዩ ጊዜያት የመነተፋቸውን ጌጣጌጦች ጉዳይ የያዘ ሳይሆን አይቀርም ሲል ገመተ።
ስርቆቶቹ በተፈጸሙበት ጊዜ ሄሪ በነዚህ ቦታዎች ላይ እንደነበር የሚመሰክ
ምስክሮችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ቤቱም በፖሊስ
መበርበሩ አይቀርም:
አብዛኛዎቹን ጌጣጌጦች ቢሸጣቸውም ጥቂቶቹን አስቀምጧቸዋል፡ የሽሚዝ
ማያያዣውን የሰረቀው አንድ ፓርቲ ላይ ሰክሮ ከሚያንቀላፋ ሰው ላይ ነው: እናቱ ያደረጉትን የአንገት ጌጥ ደግሞ የወሰደው አንድ ሰርግ ላይ ከአንዲት ሀብታም ሴት ላይ ነው፡፡ በተጨማሪም ስራህ ምንድነው ብለው ቢጠይቁት ምን ብሎ ሊመልስ ነው?
ለረጅም ጊዜ እስር ቤት ይወረወር ይሆናል፡፡ እስሩን አጠናቆ ሲወጣ ደግሞ ውትድርና ውስጥ ይከቱታል፡፡ ይሄ ደግሞ ከእስር ቤት አይሻልም።
ይህን ሲያስበው ብርድ ብርድ አለው።
መርማሪው የሸሚዙን ኮሌታ ጨምድዶ ከግድግዳ ጋር ቢያላጋውም ትንፍሽ አልል አለ፡፡ ዝምታው ግን የትም አያደርሰውም፡፡ሄሪ ነጻ
ለመውጣት ያለው አንድ እድል ብቻ ነው፤ ደኛው በዋስ እንደለቁት
ማድረግና ከአገር መጥፋት፡፡ ልክ በሰዓታት
ዳኛው በዋስ እንዲለቁት
ለዓመታት እንደታሰረ ሰው ያህል ነጻነቱን ተመኘ፡፡
ሀብታሞችን እየዘረፈ አኗኗራቸውን እየተላመደው መጥቷል፡፡ ጧት ዘግይቶ ከእንቅልፉ ይነሳል፤ የሚያማምሩ ልብሶች ይለብሳል፡፡ አንዳንድ ጊዜ
ደግሞ እንደ መሰሎቹ አነስተኛ ቡና ቤት ሄዶ ወይም እናቱን ይዞ
መዝናናቱንም አልተወም፡፡ ነገር ግን የእስር ቤት ኑሮ ለጠላቱ አይስጠው ቆሻሻ ልብስ፣ አሸር ባሽር ምግብ፣ መተፋፈጉ ከሁሉም በላይ ደግሞ ትርጉም የሌለው ኑሮ፡፡
በዋስ እንዴት ሊወጣ እንደሚችል ማሰብ ጀመረ፡፡ ፖሊስ የዋስ መብቱ እንዲከበርለት ባይፈልግም ዳኞቹ መወሰን አለባቸው፡፡ ሄሪ እስር ቤት ገብቶ
ባያውቅም ከየስዉ አፍ እንደሰማው የዋስ መብት የሚከለከለው ለግድያ
ወንጀል ብቻ ነው፡ ይሄን ደግሞ ሁሉም ሰው ያውቀዋል፡፡ ባብዛኛው ዳኞች ፖሊስ የጠየቀውን ነው የሚያደርጉት፡ ሁልጊዜም ባይሆን ተከሳሾች አሳዝነው ከነገሯቸው ሆዳቸው ሊራራ የሚችልበት አጋጣሚ ይኗራል አንዳንዴ ደግሞ ጋጠወጥ ፖሊስ ሲገጥማቸው የበላይነታቸውን ለማሳየት
ሲሉ ዋስ የሚፈቅዱበት ጊዜም አለ፡፡ የዋስ መብቱን ለማስከበር የሚያሲዘው
ገንዘብ አያጣም፡፡ ለዚህ ችግር የለበትም፡፡ ረብጣ ገንዘብ አለው፡፡ ስልክ
እንዲደውል ስለተፈቀደለት እናቱ ጋ ደውሎ ‹‹የዋስ መብቴን ሊያከብሩልኝ
ነው እማማ›› አለ ሄሪ
‹‹አውቃለሁ የኔ ልጅ›› አሉ ‹‹እናቱ አንተ ሁልጊዜ ዕድለኛ ነህ››
ብዙ ጊዜ ከችግር አምልጫለሁ አሁን ግን እንጃልኝ ሲል አሰበ፡፡
የእስር ቤት ዘበኛው ‹‹ማርክስ›› ሲል ተጣራ
ሄሪ ተነስቶ ቆመ ዳኞቹ ሲጠይቁት ምን እንደሚል ያቀደው ነገር የለም፡ እንደመጣለት የመናገር ችሎታ ያለው ቢሆንም ለዚህ ጊዜ ግን ተዘጋጅቶ ቢሆን በወደደ፡፡ ክራቫቱን አጠባብቆ ኮቱን ቆላለፈ፡ አገጩን አሻሽና ጢሙን እንዲላጭ ቢፈቅዱለት ተመኘ፡፡ በመጨረሻ አንድ ሃሳብ ብልጭ አለለትና የሸሚዙን ማያያዣ አምባር ከክንዱ ላይ አንስቶ ኪሱ ከተተው፡፡
ችሎቱ ውስጥ ሲገባ ፊት ለፊት የዳኞቹ መንበር ጉብ ብሏል፡ ህዝብ የተቀመጠበትን ቦታ ሲያማትር እናቱ የክት ልብሳቸውን ለብሰው ራሳቸው ላይ ቆብ ደፍተው ተቀምጠዋል፡ የዋስ ገንዘብ እንዳለ ለማመልከት ይመስላል አስር ጊዜ ደረታቸውን ይደባብሳሉ፡ ከአንዷ ሀብታም ላይ የመነተፈውን የኮት ማያያዣ ጌጥ አድርገውት ሲያይ ፍርሃት ጨመደደው፡፡ እጁ
እንዳይንቀጠቀጥበት የተከሳሽ መቀመጫውን ፍርግርግ ለቀም አድርጎ ያዘ፡፡
አፍንጫው አለቅጥ የረዘመው አቃቤ ህግ ‹‹ክቡር ፍርድ ቤት፣ ተከሳሹ
የሎርድ ሞንክፎርድ የሆነ ሃያ ፓውንድ ጥሬ ገንዘብና ጥንድ ከወርቅ የተሰሩ የሸሚዝ ማያያዣዎች ስርቆትና አንድ ምግብ ቤት ውስጥ ተመግቦ ሳይከፍሉ የመውጣት ጥፋት በመፈጸም ተከሷል፡ ፖሊስ የበርካታ ገንዘብ ስርቆት ጉዳይ እየመረመረ ስለሆነ ይህ ተከሳሽ በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ይጠይቃል›› አለ፡፡
ሄሪ ዳኞቹን ሲመለከት ሁለቱም በንቀት ያዩታል፡ እነሱም ፊታቸው የቀረበ ሁሉ ጥፋተኛ ነው የሚሉ ይመስላሉ፡ ፍርሃት ፍርሃት አለው፡፡እንግዲህ የመሃል ዳኛው ናቸው ወሳኙ፡፡ ሰውዬው ሪዛቸው የሸበተ ሲሆን ገፅታቸውን ላነበበ በስራ ዘመናቸው በርካታ የክስ ጉዳይ ሲዳኙ የኖሩ
መሆኑን ያሳያል፡፡ እሳቸውን ነው መጠንቀቅ ሲል አሰበ ሄሪ፡፡
የመሃል ዳኛውም ‹‹የዋስ መብት ትጠይቃለህ?›› አሉት
ሄሪ ግር አለው ‹‹ወይ አምላኬ፤ አዎ ጌታዬ›› አለ፡፡
የትልቅ ሰው ንግግሩን ሶስቱም ዳኞች አስተዋሉ፡
ሄሪም ይህን ተገንዝቧል፡፡ የሰዎችን ግምት ማስለወጥ በመቻሉ ይኮራል፡ የዳኞቹ ሁኔታ ስላበረታታው አሞኛቸዋለሁ ሲል አሰበ፡፡
‹‹ምን ትላለህ?›› ሲሉ ጠየቁት።
‹‹አንድ ችግር ሳይፈጠር አይቀርም ጌታዬ›› ሲል ጀመረ፡ በዚህ ጊዜ ዳኞቹ ለመስማት በማቆብቆብ ወንበሮቻቸው ላይ ሲቁነጠነጡ ታዩ፡፡
‹‹እውነቱን ለመናገር በዚያ ምሽት ካርልተን ቡና ቤት
አንዳንዶቹ ሰዎች በጣም ጠጥተው ነበር›› አለና ዳኞቹን አማተረ፡
‹ካርልተን ክለብ ነው ያልከው?››
ሄሪ ከሚገባው በላይ የሄደ መሰለው፡፡ ምናልባትም የዚህ ክለብ አባል ነኝ ማለቱን ሊያምኑ ይችላሉ፡፡
ከዚያም ፈጠን ብሎ ‹‹በእውነት በጣም ያሳፍራል፡፡ ነገር ግን አሁኑኑ
እቦታው ድረስ ሄጄ ሁሉንም ሰዎች ይቅርታ እጠይቃለሁ›› ልክ የምሽት
ልብስ መልበሱን ድንገት እንዳስታወሰ ለመምሰል ‹‹ይህን የለበስኩትን ልብስ
ለውጬ›› አለ።

‹‹ሃያ ፓውንድና የእጅ አምባር አልሰረቅሁም እያልክ ነው?›› ዳኛው
ድምፃቸው ለስለስ ያለ ሆንዋል፡፡ ሆኖም ጥያቄ መጠየቅ መጀመራቸው ጥሩ ጅምር ነው፡፡ የፈጠረውን ታሪክ አልጣሉበትም ማለት ነው፡፡ ያለውን ካልተቀበሉት ዝርዝሩን ለመጠየቅ አይቸገሩም ነበር፡፡ ልቡ ተስፋ አቆጠቆጠ፡
ምናልባትም ፍርድ ቤቱ ይለቀው ይሆናል፡፡
‹‹የሸሚዝ ማያያዣዎቹን እንኳን ተውሼ ነው እንጂ አልሰረቅሁም የኔን እቤት ትቼ ነበር የወጣሁት።›› በኮቱ እጅጌ ስር ብቅ ያሉትን በሸሚዝ
ማያያዣ ያልተያያዙትን የሸሚዙን እጅጌዎች ከፍ አደረጋቸው፡፡ የራሱን
የሸሚዝ ማያያዣዎች ኪሱ ከቷቸዋል፡፡
‹‹ሃያ ፓውንዱስ?›› አሉ ሽማግሌው ዳኛ፡፡
ከባድ ጥያቄ መጣበት፡፡ መልስ አልመጣለት አለው፡ ‹‹የሸሚዝ ማያያዣህን ረስተህ ብትመጣ ከሰው መዋስ አንድ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን የሰው ገንዘብ ከወሰድክ እንደ ሰረቅክ ነው የሚቆጠረው፡፡››
‹‹ከመጀመሪያውም ጌታ ሲሞን ቦርሳቸው ምን ያህል ገንዘብ እንዳላቸው
የሚያውቁ አይመስለኝም›› ፍርድ ቤቱ ውስጥ ያሉ ተራ ሰዎች ቀጥሎ የሚለውን እንዳይሰሙ የፈለገ ይመስል ድምጹን ዝቅ አደረገ፡፡ ‹‹ጌታዬ
እሳቸው ሀብታቸው የተትረፈረፈ ባለፀጋ ናቸው››
መሃል ዳኛው ‹‹ምን ያህል ገንዘብ እንዳላቸው በመርሳት መቼም
ሀብታም አልሆኑም ጌታ ሲሞን›› አሉ፡፡ ሰዉ በሳቅ አውካካ፡፡ ቀልድ ጣል
መደረጉ አበረታች ቢሆንም መሀል ዳኛው ፈገግም አላሉም፧ፊታቸው ቅጭም እንዳለ ነው፡፡ ‹በምግብ ቤቱስ ሂሳብህን ሳትከፍል ለምን ወጣህ? ሲሉ ጠየቁት፡፡
‹‹ለዚህ በጣም አዝኛለሁ፡፡ ከራት ተጓዳኜ ጋር ብርቱ ጥል ተጣልቼ ነበር፡፡›› ሄሪ ከማን ጋር እራት እንደበላ መግለፁን ሆን ብሎ ተወው፡ የሴት ጓደኛውን ስም ሰው ፊት መግለፅ ተገቢ አይደለም፡፡ ዳኞቹም ይህን
ያውቃሉ፡ ‹‹ስለ ክፍያው ሳላስብ እብስ ብዬ ከምግብ ቤቱ ወጣሁ፡››
መሃል ዳኛው አፈጠጡበት፡፡ ሄሪ አንድ የማይገባ ነገር እንደተናገረ
ተሰማው፡፡ ልቡ በድንጋጤ ዘለለች፡፡ ምን ብሎ ይሆን? ዕዳውን (ሂሳቡን)
አለመክፈሉን እንደ ቀላል ነው ያየው፡፡ ይህ ደግሞ በትልቅ ሰዎች ዘንድ
ብዙም ትኩረት የሚሰጠው ነገር አይደለም፡፡ በአባባል ስህተት የገነባው ውሽት ሁሉ የሚናድ መሰለውና ሰውነቱን ፍርሃት ወረረው፡፡ ወዲያው ‹‹ጌታዬ፣ በእውነት ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው የፈፀምኩት፡፡ ምሳ ሰዓት አካባቢ ሄጄ እዳዬን እከፍላለሁ፤ የሚለቁኝ ከሆነ›› አለ፡፡
መሃል ዳኛው ጥያቄውን ይቀበሉ አይቀበሉ እርግጠኛ አልሆነም፡
‹‹ይህን በማለትህ ባንተ ላይ የቀረበው ክስ ሁሉ ውድቅ የሚደረግ መሰለህ?›› አሉት፡፡
አንተ ጉረኛ ሽማግሌ ዳኛ› ሲል ሄሪ በሆዱ ተሳደበ፡፡ ዳኞቹ ብዙ የሚሰድቡት ከሆነ ወህኒ የማውረዳቸው ዕድል ያነሰ ነው፡፡
‹‹ሌላ የምትለው አለህ?›› ሲሉ ዳኛው ጠየቁት፡
ሄሪ ደከም ባለ ድምፅ ‹‹ያደረኩት ነገር አንገቴን አስደፍቶኛል፡››
‹‹ህም›› መሃል ዳኛው በጥርጣሬ አጉተመተሙ፡ ሆኖም በመቀበል
ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡
ሶስቱ ዳኞች እርስ በእርስ አንሾሾኩ፡፡ ሄሪም ትንፋሹን ውጦ ቆይቶ በረጅሙ ለቀቀው፡፡ የወደፊት እጣ ፈንታው በእነዚህ ደደብ ዳኞች እጅ መውደቁ አበሳጨው፡፡ ፈጥነው ተስማምተው ውሳኔያቸውን እንዲያሳውቁት ተመኘ፡ ነገር ግን ወዲያው በአንድነት ራሳቸውን ሲነቀንቁ ሲያይ
ውሳኔያቸውን ለሌላ ጊዜ እንዲያሰሙ ፍላጎት አደረበት፡፡
መሃል ዳኛው ‹‹አንድ ሌሊት እስር ቤት ማደርህ ከጥፋትህ እንድትማር
ያደረገህ ይመስለኛል›› አሉ፡፡
ኦ አምላኬ ዳኛው ሊለቁኝ ነው ሲል አሰበ፡፡ ምራቁን ዋጥ አደረገና
‹‹እርግጥ ነው ጌታዬ እዚያ መመለስ አልፈልግም›› አለ፡፡
‹‹ለወደፊቱ ተጠንቀቅ››
ዳኛው ወደ ተሰበሰበው ህዝብ እየተመለከቱ ‹‹የሰማነውን በሙሉ
አምነን ተቀብለናል ማለት አይደለም›› አሉ፡፡
ሄሪ በእፎይታ ጉልበቶቹ ሲብረከረኩ ተሰማው፡፡
መሃል ዳኛው ‹ብዋስ ተለቀሃል፡ የሃምሳ ፓውንድ ዋስ አቅርብ›› አሉ፡፡
ከእስር ቤት እንደወጣ ለተወሰኑ ስዓቶች ሳይሆን ልክ አንድ አመት የታሰረ ያህል መንገዱ ሁሉ አዲስ ሆነበት፡ ለንደን ለጦርነት ተፍ ተፍ እያለች ነው፡፡

👍20👏1😱1
👉👉👉የጠንቆዩ ዋሻ👉👉👉
🗾🗾ክፍል 18🗾🗾🗾
⚡⚡⚡
መሳይ የኤዛ ያልተገደበ ስሜት ከበደው የዚች ሴት ሕይወት በሱ እጅ ያለች ያህል ተሰማው ትንሽ ጭንቅ አለው እሱ ወደትክክለኛ ኑሮው ሲመለስ ኤዛን መንከባከብ ይችል እንደሆነ እርግጠኛ መሆን አቃተው ፣ እውነት ለሷ የተገባው ሰው እሆን ይሆን ፣ በመካከላችን ያለው የዕድሜ ልዩነትስ የውጭውን ሕይወት ስታየው ቢሰማትስ እኔስ ብሆን ይሄ የጉርምስና ስሜቴን በምን መጠን መገደብ እችላለው ፣ ....በኤዛ እቅፍ ውስጥ ያለውን ሰውነቱን ደካማነት እየታዘበ ፣ በችግርና በጭንቀት የከረመውን አይምሮውን ሰብሰብ አድርጎ
"ኤዛ ውዴ ? የኔ ቆንጆ በቃ ተነሽ ፡ከዚ አካባቢ እንሽሽ ቃጠሎውን አይተው በአካባቢው ሰውም ካለ ወዲ መምጣቱ አይቀርም እኔና አንቺ ደግሞ ድንገት ብንታይ ጥሩ አይሆንም እሺ ፍቅር " ብሎ ረጅም ፀጉሯን በጣቶቹ እንደማበጠር አደረገላት ፣ ኤዛ መሳይን ከእቅፏ በማውጣት ትላልቅ አይኖቿን አይኖቹ ውስጥ በፍቅር አንከራተተቻቸው ፣ መሳይ የጎረምሳ ልቡ ፍርፍር እያለበት ፣ ተቸገረ የኤዛ እይታ ደሞ ያስተላለፈለት 'በዚች ምድር ላይ ካላንተ ማንም ሰው የለኝምና እባክህ ጠብቀኝ 'የሚል ለዛ ያለው መሰለው
"የኔ ቆንጆ ፈራሽ እንዴ አይዞሽ ፣ ቤተሰቦቼ ጋር ነው የምወስድሽ አንቺ ከሞት እንዳተረፍሽኝ ከነገርኳቸው በጣም ነው የሚወዱሽ በተለይ እናቴ "ብሎ በማባበል ከንፈራን በማበረታታት ሳማት ፣ መለሱን ሰጠችው ፣ እናም እቅፍ አድርጎ አነሳትና ልብሷን አስተካከለላት ፣ እሷም የለበሰውን ልብስ ስታራግፍለት ፈገግ አለ ፣ ምክንያቱም እሱ የሚራገፍ ነገር አልነበረበትም ፣ ከፍቅሯ የተነሳ እየተንከባከበችው እንደሆነ ገብቶታል ፣
እጇን ይዞ አካባቢውን በጥንቃቄ እያስተዋለ ተጓዘ ፣ መንገድ ለማግኘት ብዙ አስቸጋሪ ነበር በትላልቅ ዛፎች የተከበበ ስፍራ ነው በግልፅ መውጫ እንዳለው እንኳ አያስታውቅም ፣ ድክክም እስኪላቸው ነው ለመውጣት የተሽከረከሩት አመሻሹ ላይ ግን አንድ መንገድ አገኙና በግልግል ተነፈሱ ፣ ስለ አስባልት መንገዱ ኤዛ የምታውቀው ነገር ባይኖርም በመሳይ ደስታ ጥሩ ነገር እንደሆነ አስባ ተደሰተች ፣ በቀጭኑ አስባልት ላይ እየተጓዙ ሳለ ትላልቅ መኪኖች አልፈዋቸው ሲሄዱ ለኤዛ አዲስ ነገር ነውና ፈንጠዝ ስትል መሳይ እየሳቀ ያረጋጋታል ፣አልፎ አልፎም ከርቀት ሰዎችን እያየችም በመገረም ለመሳይ ትጠቁመዋለች ፣ መሳይ ከዚ የበለጠ በሰዎች የተሞላ ከተማ ሊሄዱ እንደሆነ እየነገረ ለዛ እንድትዘጋጅ ነገራት ፣ ኤዛ ለሁሉም ነገር እሱ አጠገቧ እስካለድረስ ፍራቻ እንደሌለባት ነገረችው እቅፍ አድርጓት በልበ ሙሉነት ተጓዘ ....በነፃነት በጀግንነት በፈቅር በብርሃን መንፈስ ታጅቦ ቆንጆና ማራኪ ልጅ ይዞ ወደ አዲስ አበባ ወደ እናቱ ቤት ፣ የአቢያራን የጥንቆላ እርኩሰት ድራሹን አጥፍቶ ፣ ጓደኞቹን ምን ያክል በእምነት በፅናት በአላማ እንሚበልጣቸው ጥግ ድረስ አሳይቷቸው ፣ አፍረው እንዲሸሹት አድርጎ ፣ .......
መሳይ ከኤዛ ጋር ከአንድ የጭነት መኪናላይ ለምኖ በመውጣት ወደ አዲስ አበባ ተጓዘ ፣ የኤዛ ውበት ከብዙ ሰዎ ጋር እንደሚያታግለው እያሰበ ግን ለማንም አሳልፎ እንደማይሰጣት ፣እንደሚጠብቃት ከልቡ ቃል እየገባ ፣ ወደራሱ አስጠግቶ ፣እቅፍቅፍ እንዳደረጋት ወደፊት አየ፣ የጭነት መኪናው ፣ ይዟቸው ከነፈ................................
ተ ፈ ፀ መ ።

👍39👎8❤7🥰5🤔5😁3
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
የጀርመንን ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች ለማሳሳት በርካታ ትላልቅ ብርማ
ቀለም ፊኛዎች ሰማዩ ላይ ያንዣብባሉ፡ ሱቆችና የመንግስት ህንፃዎች
ከቦምብ ናዳ ለመጠበቅ በአሸዋ በተሞሉ ጆንያዎች ዙሪያቸውን ተከበዋል፡
በየመናፈሻው የቦምብ
መከላከያ የተዘጋጀ ሲሆን ሁሉም ሰው በእጁ የጋዝ
ጭስ መከላከያ ጭምብል አንጠልጥሏል ሰዎች በማንኛውም ደቂቃ በቦምብ
ናዳ እንደሚያልቁ ያስባሉ፡፡
ሄሪ ስለ አንደኛው የአለም ጦርነት ምንም ትዝታ የለውም፡ ጦርነቱ
ሲያልቅ የሁለት አመት እምቦቃቅላ ነበር፡፡ ነፍስ እያወቀ ሲመጣ ጦርነት
ምን ያህል አሰቃቂ እንደሆነ አወቀ፡፡ በኋላም ፋሺስቶች በለንደን መንገዶች
ያደረጉትን ወታደራዊ ሰልፍ አዛውንት ይሁዳውያን በፍርሃት ሲመለከቱ
ሲያይ የጦርነትን አስፈላጊነት ተረዳ፡ሆኖም ሂትለር ሶቭየት ህብረትን
ይደመስስልኛል ብሎ የአንግሊዝ መንግስት የሆነውን ሁሉ እንዳላየ ሲያልፍ ጥላቻው ነገሰ፡፡
ሄሪ ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ ቤቱ መሄድ እንደሌለበት ወስኗል።
ፖሊሶች በዋስ በመለቀቁ ስለተበሳጩ በማንኛውም አጋጣሚ ሊያስሩት
አቆብቁበዋል፡፡ ለትንሽ ጊዜ መደበቅ ያዋጣዋል፡፡ ተመልሶ እስር ቤት መግባት
አይፈልግም፡፡ ታዲያ ስንት ጊዜ ፖሊስ መጣ እያለ ሲበረግግ ሊኖር ነው?
ሁልጊዜስ ፖሊስን መሽወድ ይቻላል? ካልሆነስ ምን ማድረግ ይኖርበታል?
እናቱ በሃዘን ፊታቸው ጠቁሯል፡ ገንዘብ እንዴት እንደሚያገኝ ቢያውቁም አንስተውበት አያውቁም፡፡ ‹‹በእናትነቴ ምንም አድርጌልህ አላውቅም›› አሉት ‹‹እማማ ያለሽን አድርገሽልኛል›› ሲል መለሰላቸው፡፡
‹ሃሰት፤ ምንም አላደረኩልህም፤ ለዚህ አይደለም መስረቅህ››
ሄሪ ለዚህ መልስ አጣ፡፡
ከአውቶብስ እንደወረዱ ጋዜጣ ሻጩ በርኒን እናቱን በስልክ ስለጠራለት
እንደውለታ ቆጥሮት ጋዜጣ ገዛው፡፡ የጋዜጣው የፊት ሽፋን ጀርመን ፖላንድን በቦምብ ደበደበች ይላል፡ ወዲያውም አንድ ፖሊስ በብስክሌት ሲመጣ ተመልክቶ በደመነፍስ ተርበተበተ፡፡ እግሬ አውጪኝ ሊል ሲያስብ ሰው ለማሰር ሁለት ሆነው የሚመጡ መሆኑን ሲያውቅ አደብ ገዛ፡፡
እንደዚህ እየሰጋሁማ እንዴት እኖራለሁ› ሲል አስበ፡፡
እቤት ሲገባ እናቱ ሻይ ጥደው ‹‹ሰማያዊ ሱፍ ልብስህን ተኩሼልሃለሁ፤ መለወጥ ትችላለህ›› አሉት
እስካሁንም ልብሱን የሚያጥቡለትና የሚያዘገጃጁለት ካልሲውንም የሚሰፉለት እናቱ ናቸው፡፡ ሄሪ መኝታ ቤት ገባና ከአልጋው ስር ሻንጣውንዐአውጥቶ ገንዘቡን ቆጠረ፡፡ ሁለት ዓመት በስርቆት ተሰማርቶ ሁለት መቶ አርባ ሰባት ፓውንድ አጠራቅሟል፡፡ የአሜሪካ ፓስፖርት እጁ ገብቷል በሃሳብ ተውጦ ፓስፖርቱን እያገላበጠ ተመለከተው፡፡ ከአንድ አሜሪካዊ ላይ እንደመነተፈው አስታወሰ፡ የሰውየው ስም ሃሮልድ መሆኑን ሰውየውም
እሱን እንደሚመስል ተገነዘበና ኪሱ ከተተው፡
የአሜሪካውያንን የአነጋገር
ቅላጼ ይችላል፡፡ በአሜሪካ ውስጥ የእንግሊዛውያን የአነጋገር ቅላጼ ካለህ የከበርቴ መደብ አባል እንደሆንክ ተደርጎ ይቆጠራል፡ አሜሪካ ውስጥ በርካታ በፍቅር ልታሳብዳቸው የምትችላቸው ኮረዶች አሉ፡፡
እንግሊዝ ውስጥ የሚቀርበት እስር ቤትና ውትድርና ብቻ ነው፡፡
አሁን ፓስፖርትና ኪሱ ሙሉ ገንዘብ አለው፡ እናቱ ቁም ሳጥን ውስጥ ንፁህ ሱፍ ልብስ ያለው ሲሆን አንድ ሁለት ሸሚዝ መግዛት ይችላል።
ከሳውዝ ሃምፕተን 75 ማይል ነው የሚርቀው
ዛሬውኑ መሄድ ይችላል።
ሁሉም ነገር እንደ ህልም መሰስ ይላል።
እናቱ ‹‹ሄሪ ሳንድዊች ትፈልጋለህ?›› ሲሉ ጠየቁት
‹‹እሺ እማ››
ኩሽና ሄዶ ተቀመጠ፤ እናቱ ሳንድዊቹን ፊቱ ቢያደርጉለትም ንክች
አላደረገውም፡፡‹‹እማ አሜሪካ እንሂድ›› አላቸው
እናቱ በሳቅ ፈነዱ ‹‹እኔ አሜሪካ?!››
‹‹እውነቴን ነው፡ እኔ ልሄድ ነው፡››
አሁን ፈገግታቸው ጠፋ ‹‹ለኔ አይሆንም ልጄ፡፡ በዚህ እድሜዬ ስደት
ለኔ አይሆንም››
‹‹እዚህ እኮ ጦርነት ሊጀመር ነው፡፡››
‹‹አንድ ጦርነት፣ የስራ ማቆም አድማና የኢኮኖሚ መዳሸቅ አሳልፌያለሁ፡››
ጠባብዋን ማድቤት አማተሩና ‹‹የኔ ዓለም ይሄ ነው›› አሉ።
ሄሪ እናቱ በዚህ እንደማይስማሙ ቢያውቅም ቁርጡን ሲነግሩት ተስፋው ተሟጠጠ፡፡
በዚህ አለም ላይ ያሉት እናቱ ብቻ ናቸው፡፡
‹‹እዚያስ ምን ልትሰራ አስበሃል?›› ሲሉ ጠየቁት፡፡
‹‹የሌብነት ስራዬ ያሳስብሻል?››
‹‹ሌብነት የትም አያደርስም፡ በሌብነት ያለፈለት ሰው አላውቅም›› አሉት፡፡
‹‹እዚያ አየር ኃይል ገብቼ አብራሪ መሆን እፈልጋለሁ፡ አሜሪካ ውስጥ ጭንቅላት ካለሽ የሰራተኛው መደብ ብትሆኝም ግድ የላቸውም።››
እናቱ በመጠኑ ፈገግ አሉ፡ እሳቸው ሻይ ሲጠጡ እሱ ሳንድዊቹን ይገምጣል።
በልቶ እንደጨረሰ ገንዘቡን ከኪሱ አወጣና ሃምሳ ፓውንድ ቆጥሮ ለየ
‹‹ይሄ ለምንድን ነው?›› ሲሉ ጠየቁ፡፡ ይህ ገንዘብ ሁለት አመት ልብስ አጥበው የሚከፈላቸውን ገንዘብ ያክላል
‹‹ይጠቅምሻል እማ ውሰጂው›› አለ፡፡
እናቱ ገንዘቡን ተቀበሉና
‹‹እውነት ልትሄድ ነው?›› ሲሉ ጠየቁት።
‹‹ወደ ሳውዝ ሃምፕተን በሞተር ሳይክል እሄድና መርከብ ላይ እሳፈራለሁ»
እጃቸውን ሰደዱና የልጃቸውን እጅ ለቀም አደረጉ፡፡ ‹‹ልጄ መልካም
ዕድል ይግጠምህ፡››
እሱም የእናቱን እጅ ጨበጥ አደረገና ‹‹ከአሜሪካ ገንዘብ እልክልሻለሁ አለ።
‹‹አያስፈልግም፡፡ ከዚያ ደብዳቤ ቶሎ ቶሎ ስደድልኝና ጤንነትህን
ልወቅ፡፡››
‹‹እሺ እፅፍልሻለሁ፡››
አይናቸው በእንባ ተቆረዘዘ ‹‹አንድ ቀን ናና አሮጊት እናትህን እያት››
እጃቸውን ጨበጥ አደረገ፡፡ ‹‹እመጣለሁ እንጂ እማ፡፡ እመለሳለሁ፡››
ሄሪ በመስታወት ከላይ እስከ ታች ራሱን አየ፡፡
ሰማያዊው ሱፍ ልብስ ያማረበት ሲሆን ከሰማያዊው የአይኑ ቀለም ጋ ሄዷል፡፡
ሸሚዙ የአሜሪካ ሽሚዝ ይመስላል፡ ፁጉር አስተካካዩ የባለ ሁለት
ደረት ኪስ ኮቱን ትከሻ በቡሩሽ ሲጠርግለት ሄሪ ጉርሻ ሰጠውና ወጣ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሳውዝ ሃምፕተን ወደብ በሰው ተጥለቅልቋል። ከዚህ ቦታ ነው የአትላንቲክ አቋራጭ ጉዞ የሚነሳው፡፡ በመሆኑም በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች
ከእንግሊዝ ለመውጣት ይተራመሳሉ፡፡
ሄሪ መርከብ ለማግኘት ሲጠያይቅ የሁሉም መርከቦች ቦታ ለመጪዎቹ
ሳምንታት ጉዞ አስቀድመው እንደተያዙ አወቀ፡ አንዳንዶቹ የመርከብ ትራንስፖርት ድርጅቶች ባዶ ቢሮ ታቅፈው ለሰራተኛ ደመወዝ ከመክፈል በራቸውን ዘግተዋል፡ ለተወሰነ ጊዜ ምንም ቦታ የማይገኝ መሰለው።
በመርከብ መሄዱን ትቶ ሌላ አማራጭ መጓጓዣ ሲያፈላልግ አንድ የጉዞ ወኪል ባህር ላይ የሚያርፍና ከባህር ላይ የሚነሳ የፓን አሜሪካን
አውሮፕላንን እንዳለ
አበሰረው፡፡ ስለዚህ አይሮፕላን በየጋዜጣው ላይ
አንብቧል፡ መርከብ ወደ ኒውዮርክ ከተማ ለመሄድ አራትና አምስት ቀን
የሚፈጅበት ሲሆን አይሮፕላኑ ከ30 ሰዓት ባነሰ ይደርሳል፡ ታዲያ የአንድ
ጊዜ ጉዞ ትኬት ዋጋ 90 ፓውንድ አዲስ መኪና ይገዛል።
ሄሪ በርካታ ገንዘብ አባክኗል፡፡ እብደት ነው፡፡ ታዲያ ከአገር ለመውጣት
ሲል የፈለገውን ያህል ዋጋም ቢሆን ለመክፈል ወስኗል፡፡ አይሮፕላኑ ምቾቱ
ያጓጓል፡ ኒውዮርክ እስክትደርስ ድረስ ሻምፓኝ መጨለጥ ነው፡፡ እንዲህ
አይነት ቅንጦት ደግሞ ለሄሪ ነፍሱ ነው፡፡
ፖሊስ ባየ ቁጥር መደንበሩ ሊቀር ነው፡፡ ሳውዝ ሃምፕተን ውስጥ
ደግሞ ስለ እሱ ሌብነት የሚያውቅ ፖሊስ የለም፡፡ ከዚህ ቀደም በአይሮፕላን
በርሮ ስለማያውቅ ግን አዕምሮው ተረብሿል፡፡
ሰዓቱን አየ፤ከቤተመንግሥት አንጋች ላይ የመነተፈው ነው፡፡

👍30