አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
የጠንቋዩ ዋሻ
**ክፍል 11**

ምሽት ላይ ነው ከዋሻው በስተጀርባ ካለው አትክልት ስፍራ አንድ ጥቁር ድንጋይ ላይ መሰይ በፀጥታና በትካዜ ተቀምጧል ፡ ነገሮች ፡በሆነታምር ፡ተቀይረው ፡አልፈው ከቤተሰቡ ጋር እንዲገናኝ ፈጣሪውን እየለመነም ጭምር ነው ፡ ይሄን አስፈሪ ና ባለማወቅ የሚፈፀም የዋሻው ውጥ ትርሂት ፡ ማብቂያ እየናፈቀ ፡ ነበር ፡ ከርቀት ጓደኞቹ ፡ ለብቻቸው ፡ተነጥለው ፡ተቀምጠው ፡ወደሱ እያዩ ሲያወሩ ፡ አልፎ አልፎ ቀና እያለ ያያቸዋል ፡ የገዛ ጓደኞቹ ወደ አስፈሪ አውሬነት የመቀየራቸው ፡ጉዳይ ፡አሳስቦታል ፡ አብሮ ፡አደገቹና በጣም ፡የሚግባቡ ፡ ነበሩ ፡ዛሬ ፡ሕይወት ባልጠበቁት ሁኔታ አምጥታ ከማያውቁት ዋሻ ፡ ጥላቸዋለች ፡ ይሁኔታ ሦስቱንም ፡ ቀያይራ ፡ ለዚ አብቅታቸዋለች ፡ መሳይ ነገሮች ሁሉ ፡ በዚመልኩ እዚጋር መድረሳቸውን ሲያስበው ፡ጩህ ጩህ ይለዋል ፡ ጓደኞቹ በሰው ደም እስከመታጠብ ፡ደርሰዋል ፡ የአቢያራ ፡አይል፡ይበልጥ ፡የጨመረ ፡ይመስላል ፡ አንዳንዴ ፡ከሁኔታው ፡አንፃር ፡ምን ፡አልባት ፡አቢያራ ፡ለየት ፡ያለ ፡የሴጣን ፡መንፈስ ፡ይኖረው ፡ይሆን ፡ብሎ ፡እንዲጠራጠር ፡ያደርገዋል ፡እዛ ዋሻውስጥ ፡ትንሽም ፡ቢሆን ፡ተስፋው ፡ኤዛ ናት፡ ፡በጣም ፡እየመሸ ሲመጣ ፡ ከአትክልቱ ስፍራ ተነስቶ ፡ወደ ዋሻው ፡ ሊገባ ተረመደ ፡ ጥቂት እንደሄደ ኤዘን አይቷት ፡ቆም አለ ያንን ቀዩን ቀሚሷን ፡እየጎተተች ፡ ደስ ፡በሚል ፡ፈገግታ ታጅባ ወደሱ ስትመጣ ፡ በመገረም ፡አያት ፡ለመጀመሪያ ጊዜ ፡ያገኛት ፡ይመስል ፡በውበቷ ፡ተደነቀ ፡ በልቡም ፡እቺ ሴት ፡ግን ፡ የሆነ የተለየ ነገር አላት ልበል አለ ፡ ደሞም ፡የሌላ አገር ደም ያላት ነው የምትመስለው ፡ ነው ፡አድማስ ፡በዛች ፡ቆሼ መኪናው ፡ በሆነታምር ፡ከአገር ፡ይዞን ፡ወጥቶ ፡ይሆን ፡ ግን ደሞ ፡አማርኛ ፡እንዴት ፡ሊያውቁ ቻሉ ፡ ወይ አምላኬ ፡ብሎ ፡ተወዛገበ......
"መሳይ ልትገባ ነው?"አለችው ፡ኤዛ ደርሳ
"አዎ "አለ ቀና ብሎ ለማየት እየከበደው
"በዚ ሰአት እንቅልፍ መተኛት ይከብዳል ጥቂት ከኔጋር አትቀይም"አለችው አገጩን ያዝ አድርጋ
"አይ አውሬ ቢኖርስ "አለ ቀና ብሎ እያያትና አገጩላይ ያሳረፈችውን እጇን ለመሸሽ እየሞከረ
"አይ እዚ አውሬ አይገባም የአቢያራ መንፈስ ይጠብቀናል ፡በዛላይ እኔ እስካለው ፡አትፍራ ፡"አለች
"ኤዛ እባክሽ ስሚኝ አቢያራ የሚባል መንፈስ የለም ፡ አትሞኚ በተሳሳተ መንገድ ላይ ነሽ ፡ አንድ አምላክ ፡ነው ፡ያለን ፡እሱም ፡በሰማይ ፡ነው ፡ቤቱ እና ደሞ ፡በእያንዳንዳችን ፡ልብ ፡ውስጥ ፡ እሱን ማመን ብቻ ነው የሚጠበቅብሽ ፡ ታጋሽ ፡ አምላክ ፡አላት ፡ለዝች ፡ምድር ፡ ብዙ ስእተቶችን ፡ብንሰራ ፡ብናጭበረብር ፡ አንድቀን ፡እንደምንመለስ ፡አስቦልን ፡በትህግስት ፡ይጠብቀናል ፡ እሱ ከኛ የሚፈልገው ፡ታማኝነትን ተስፋን ፍቅርን ፡ ይቅር ባይነትን ምስጋናን ነው ፡ አሰተኛ እና ጠንቋይ ፡ግን ሁሌም ፡ ካንቺ ይፈልጉብሻል ፡ በውሸት ፡ይገነቡሻል ፡ አይለኝነትና እንቢተኝነትን ፡ ጥሎ ማለፍን ፡ ያልደከምሽበትን ሀብት እያሳዩ ገደል መክተትን፡ክቡሩን የሰው ልጅ ደም ፡ መስዋት ማድረግን ፡እያስተማሩ ወደውቀት ነው የሚመሩሽ ፡ ስለዚ እባክሽ ፡ከዚ ሕይወት ፡እንድትወጪ ፀሎት አድርጊ ስፀልዪ ግን አምላኬ ሆይ ሰማይና ምድርን ዘረጋህ ,,,,,,,,እያልሽ እንጂ፡ አጠገብሽ ፡ቁጭብሎ እንዳንቺ የሚበላና ፡ እንደ አውሬ ፡የሰው ደም ፡ ለሚጠጣ አቢያራ ስለተባለ ጠንቋይ ብለሽ አይደለም ፡ ለዚ ጠንቋይ መፀለይም ምስጋናም ማቅረብ ፡አይጠበቅብሽም ፡!!"አላት መሳይ አይኖቿን በድፍረት፡እያስተዋለ ፡ ኤዛ በፀጥታ ስታዳምጠው ፡ቆይታ ፡አገጩን ፡በመልቀቅ ፡አፉን ፡እፍን ፡አድርጋ ፡ያዘችው ፡በጣም ፡የደነገጠች ፡ትመስላለች ፡ እናም ፡ዙሪያ ገባውን ፡አየች ፡ ማንም የለም ፡እነመስፍንም ፡ወደዋሻው ፡ገብተዋል ፡ የአቢያራን ፡መንፈስ ፡የተቆጣ እንደሆን ፡ብላ እንደምታጣራ ፡መሳይ ፡ገባው ፡ እጁን ፡ወገቧ ፡ላይ ፡በማሳረፍ ፡ትኩረቷን ፡ሳበ ፡ ኤዛ ፡ ወደሱ ተመለሰች ፡አየች ፡ በጨረቃዋ ፡ብርሃን ፡የታገዙት ፡አይኖቿ ፡አይኖቹ ውስጥ ፡አንፀባረቁ ፡ የመሳይ ፡አሳዛኝ ፡አስተያየት ፡ኤዛን ፡ፈተናት ፡ የሆነ አይል ፡ ወደሱ ጎተታት ቀረበችው ፡ ወደማታውቀው ዓለም ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ፡ ,,,,,,,,,,,,


ሙና መሀመድ

ይቀጥላል

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍37😁6😱2🤩1
የጠንቋዩ ዋሻ
ክፍል 12
°❖°❖°❖°❖°❖°❖°
መሳይ በኤዛ ቀጭን ወገብ ላይ እጆቹን ጠምጥሞ ወደራሱ እያስጠጋ ቀልቧን ይገዛው ጀመረ ፡ ኤዛ የስሜት ቁንጥጫውን ተቆጣጥራ ማስቆም እስኪሳናት ሆና በዝምታ ተከተለችው ፡ የልቧ ምት ለራሷም እስኪገርማት ሆነች ፡ መሳይ በአሳዛኝ አይኖቹ አይኖቿን ፈልጎ አተኮረባቸው ፡ ኤዛ አይኖቹን ተከትላ ወደ ከንፈሮቹ ዝቅ አለች ፡መሳይ ያቀረበችለትን እነዛን እንጆሪ የመሱሉ ከንፈሮቿን በፍጥነት ተቀበላቸው ፡ እሱ እንደተራበ ሰው ሲሆንባት እሷ በማታውቀው አዲስ ስሜት ተቀጣጠለች ፡ ይሄ ለሷ ለየት ያለ ሌላ አዲስ የሕይወት መንገድ ነው ፡ ተስሞ የማያውቀው ከንፈሯ ፡ግን ቦታውን አልሳተም ፡ እሱ የሚያደርገውን እየተከተለች ፡ በመሳይ ከንፈሮች ላይ ፈሰሰች ፡ መሳይ ጠበቅ እያደረገ ልቧን አጠፋው ፡ ፡ እንዲ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጠፍተው ሲወዛወዙ ፡ከወደዋሻው ደውል ተሰማ ፡ኤዛ ብርግግ ብላ መሳይን ገፍትራው ድንብርብር ብላ ቆመች ፡ መሳይ በድንጋጤ ቀጥሎ የምታደርገውን ጠበቀ፡ ትንሽ ስታየው ፡ቆይታ "ና ቶሎ እንግባ ፡አባት አቢያራ ነው የደወለው ፡ እኔ እንዳልገባው አውቋል ፡ ይቅር ይበለኝ አባቴ "አለች እየተርበተበተችና የመሳይን አጅ እየያዘች ፡
"እኔ ለብቻዬ ልሂዳ ፡አብረን ካየን ሊቆጣ ይችላል"አላት እጁን አይዛ ወደዋሻው እየጎተተች ስትወስደው
"አይቶናል ፡ቀጣይ የምቀጣውን ቅጣት መቀበል ብቻ ነው "አለች ትንፋሿ ቁርጥቁርጥ እያለ
"ኧረ አላየንም እዚ ማንም አልነበረም እኮ"አለ መሳይ
"አይ አይ አቢያራ በልባችን ውስጥ አለ ጌታዬ "አለች በቁጭት
"እንዲማ መቼም ሊሆን አይችልም በልባችን የሚኖረው ፈጣሪ ብቻ ነው ፡ ፈጣሪ ደሞ ብርሃን ነው ፡ እንደ አቢያራሽ ጨለምተኛ እና ሰውም አይደለም ......."ብሎ ሊቀጥል ሲል
"ዝም በል አንተ ልጅ ችግር ውስጥ አትክተተኝ ፡አፍህን ዘግተህ ወደውስጥ ግባ ነገ እንገናኛለን በ"ብላው ፡በስተግራ ካለው የዋሻው ጨለማ ክፍል ውስጥ ገብታ ተሰወረች ፡ መሳይ ቀስ እያለ ወደማደሪያው ለመግባት የዋሻውን ግድግዳ እየታከከ በጨለማው ተጓዘ ፡ የዋሻው ውስጥ ነብሳቶች ሲርርርር ማለት ጀምረዋል ፡ የተለያየ ደምፅ ሲሰማ ልቡ መምታቱን ዛሬም አላቆመም፡ ሊለምደውም አልቻለ ፡ በፍርሃት ፡ እንደተወጠረ ፡ ግድግዳውን እየታከከ ሲሄድ ፡ ለየት ያለ ድምፅ የሰማ መሰለውና ወደዋላው ለመመለስ ቃጣው ፡ እናም ባለበት ቆመ ፡ ድምፁ ደሞ እየቀረበው መጣ ፍርሃቱ ጨመረ ኦርርርር ኡኡኡኡኡ ስስስስስስ ሽሽሽሽሽሽሽ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,


ሙና መሀመድ

ይቀጥላል

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍21🤔3😢3
#ሳቤላ


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


..ወሩ ጥር ሰዓቱ ማታ ነው ከደጅ ያለው ብርድ ነፍስ ያወጣል ሚስተር ካርላይል እና እህቱ ኢስት ሊን ውስጥ ከምቹ ሳሎን ተቀምጠዋል ቤት ሙስጥ ያለው ሁኔታ ከውጭው የተለየ ነው የሚንቀለቀለው እሳት ብርሃኑ ከሚያምረው ምንጣፍ ላይ ያንጸባርቃል ። ወንበርና ጠረጴዛ የመሳሰሉ የቤት ዕቃዎች እጅግ ባማረና የቀንዲሉ ብርሃን ክፍሉን በሙሉ ቦግ አድርጎታል ይህ ሁሉ
አንድ ቦታ ላይ ሲታይ ቅንጦት ለመባል ባይበቃም የቤት ሰላም ገጽታ አለው ። በደጅ ግን በብዛት የሚወርደው በረዶ አየሩን ጥቅጥቅ አድርጎ ስላ
አጨለመው አንድ ሰው ከአንድ ሜትር የራቀ ማየት አይችልም ሚስተር ካርላይል በድንክ ፈረሶች በሚሳበው ሠረገላው ነው ወደቤት የመጣው " የተጓዘበት መንገድ አጭር ቢሆንም ከላዩ ላይ በረዶ ተቆልሎበት ስለነበር ልጁ ሉሲ ወደ ነጭነት ተለወጠ እያለች ነበር የገባው እየሣቀችበት ነበር የገባው አሁን ሰዓቱ መሽቷል
"ልጆቹ ተኝተዋል " አስተማሪያቸውም ከራሷ ሳሎን ገብታ ተቀምጣለች "
ቤቱ ጸጥ ብሏል ሚስተር ካርላይል አንድ ወርኃዊ መጽሔት በተመስጦ ያነባል
ሚስ ካርላይል ጉሮሮዋ እየታፈነ አፍንጫዋ እየተነፋነፈ ከእሳት ዳር ተቀምጣ ታጉረመርማለች "

ሚስ ካርላይል'ክብራቸውን ለበሽታ ሰጥተው ከማያውቁት ልበ ብርቱ ወይዛዝርት አንዷ ነበረች » በርግጥ ጠበቅ ያለ በሽታ ከያዛት መሸነፏ አይቀርም " በተረፈ ሌላውን ሰው ሁሉ የሚያጠቁት እንደ ራስ ምታት ከባድ ጉንፋንና የጉሮሮ መቁሰል የመሳሰሉ ጥቃቅን ሕመሞች ነክተዋት አያውቁም እንደዚህ ተከብራ የኖረች እመቤት ራስዋን ሲከብዳት ደረቷ ሲቆሳስል ድምጿ ሲዘጋ ባጭሩ በሕይወቷ
ለመጀመሪያ ጊዜ ጉንፋን ሲይዛት ምን ያህል እንደምትረበሽ ለመገመት አያዳግትም "

“ ያ ቢራ ነው”ኮ እንደዚህ ጉድ የሠራኝ ” ስትለው ሚስተር ካርላይል ከሚያነብበት ቀና ብሎ አያት "

“ አዎ ቢራው !” አለች እንደገና ኮስተር ብላ ። አርኪባልድ ... ጨረቃ
ናት ጉንፋን ያሲያዘችኝ ያልኩህ ይመስል እንደዚህ አፍጠህ አትየኛ » "

“ ታድያ አልቦሽ ሳለ በርከት አድርገሽ ባንድ ጊዜ ካልጠጣሽ ቢራ እንዴት
ጉንፋን ሊያስይዝሽ ይችላል ? ”

ዕድሜ ልክህን ሕፃን እንደ ሆንክ መቅረትህ ነው ኮ ... አርኪባልድ ብዙ ቢራ መቸ ጠጥቸ ዐውቃለሁ ? በመጨረሻ የተረፉት ሁለት በርሜሎች ያፈሳሉ መባላቸውን አልስማህም ?

"እናሳ ?

ከሠራተኞች ያገጣጠም ጉድለት መሆኑን ወዲያው ዐወቅሁት ዛሬ ጧት
ከቁርስ በኋላ ከሚሞቁት ክፍሎች ወጥቸ ወደ ቤቱ ራሴ ወርጄ ተመለከትኩ ክፍሉ በራሱ የበረዶ ቤት ይመስል ነበር ኻያ ደቂ ሙሉ ከዚያ ውስጥ ስለ ቆየሁ ጉንፋን ያዘኝ።"

ሚስተር ካርይል አልመለስላትም ፒተር የሚሰራውን የሚያውቅ ስለ
ሆነ በነሱ ሥራ ጣልቃ መግባት አልነረብሽም ቢላት ኖሮ መዓቷን ታወርድበት ነበር » አሁን እሷ ስትጨነቅበት አፍንጫዋን ሲዘጋት ጉሮሮዋን ሲፍቃት ወንበሯን ወደ አሳቱ ስታስጠጋ መልሳ ስታሸሽ እጆችዋን ስታፋትግ እግሮችዋን ስታወራጭ ሚስተር ካርላይል ዝም ብሎ ያነብ ነበር "

“ስንት ሰዓት ሆነ ? ” አለችው

ሚስተር ካርላይል ስዓቱን አይቶ ከምሽቱ ሶስት መሆኑን ነገራት

“ እንግዲያውስ እስከ ዛሬ ይህን የበሽተኞች ምግብ ደኅና ሳልቀምስ የኖርኩትን ያህል አንድ ሣህን ሾርባ ልጠጣና ልተኛ።

"ጥሩ ነው ( ይበጅሽ ይሆናል " አላትና ሚስተር ካርላይል ንባቡን ቀጠለ „
ከዚያ በኋላ አምስት ደቂቃ ያህል ተቀምጣ ወጣች እሱም ማንበቡን ቀጥሎ አንድ ሁለት ጊዜ ከገለበጠ በኋላ መጽሔቱን ከጠረጴዛው ላይ ጥሎ ብድግ ብሎ ተንጠራራ

የሳሎኑን አሳት ቆስቁሶ አቀጣጠለና ከምድጃው ዳር ትንሽ ቆም አለ " ከደጅ
በረዶው መጣሉን አላቆመ እንደሆነ ለማየት ወደ መስኮቱ ሔዶ መጋረጃውን ገለጥ አድርጎ ቢመለከት • ከመጨለሙ የተነሣ ምንም ነገር ማየት አልቻለም " የአየሩን ሁኔታ ማወቅ ስላልቻለ መስኮቱን ከፈተውና አንገቱን ወደውጭ አውጥቶ ተመለከተ"

በረዶው በኃይልና በብዛት ይወርድ ነበር " ሚስተር ካርላይል የአንድ ሰው
እጅ እጁን ሲነካው ፊቱንም ከሌላው ሰው ፊት ጋር እስኪላተም ድረስ ተጠግቶ
ድንገት ድቅን ሲልበት ክው ብሎ ደነገጠ "

“ልግባ ሚስተር ካርላይል ስለ ነፍስ ! ብቻህን መሆንህን አይቻለሁ
ሙቻለሁ ደግሞ ነገሩን አላውቅም ተሸሽጎ ያሳለፈኝ ሰው ያለም መስሎኛል "

የተናገረው ድምፅ የማን መሆኑን ቢያውቅም ለጊዜው የደመ ነፍሱን ወደ ኋላ ሸሸት አለ ። ስውየው ደግሞ ተከተለው " ያን የመሰለ ዱቄት በረዶ እየጣለ ብዙ ሰዓት በእግሩ ተጉዞ ስለ መጣ ባርኔጣው ልብሱ ቅንድቡ የውሸት ሪዙ ሳይቀር ንድፍ ጥጥ የተቆለለበት ይመስል ነበር " ገና እንደ ገባ በሩን እንዲቆልፍለት ጠየቀው
ሚስተር ካርላይል ' መስኮቱን ዘግቶ መጋረጃውን ሳበውና ከውጭ ወደ ሳሎን
የሚያስገባውን ከሳሎን ወደሚቀጥለው ክፍል የሚያሳልፈውን ሁለቱ በሮች
ቆለፈ " ሪቻርድ የደረበውን ልብስ ባርኔጣውንና የውሸት ጢሙን አውልቆ በሮዶውን አራገፈ "

“ ሪቻርድ” አለው ሚስተር ካርላይል “ በጣም አስደነገጥከኝ " ወዲህ በመ
ምጣትህ በጣም ተሳስተሃል

“ አስቸኳይ ማሳሰቢያ ደረሰኝና ” አለ ሪቻርድ ' ከቅዝቃዜው የተነሣ እየተንቀጠቀጠ ' ከለንደን እስከዚህ መንገድ እያሳበርኩ ነው የመጣሁ አሁንም ቢሆን እያሳደዱኝ ነው " ያ የተረገመ ቶርን የላካቸው ፖሊሶች አሁንም ይከተሉኛል

ሚስተር ካርላይል ወደ ቁም ሳጥኑ ምልስ ብሎ አንድ ብርጭቆ ብራንዲ ቀዳለትና
ጠጣ . . . ሪቻርድ ጠጣ ያሞቅሃል " አለው።

‹ ኧረ እኔስ በትኩስ ውሃ ቢሰጠኝ "

“ ትኩስ ወሃ እንዴት አድርጌ ላስመጣልህ እችላለሁ ? በል ይኸን ጠጣው ግን
ምነው እንደዚህ መንቀጥቀጥህ?

“ ጠንካራ የተባለውን ሰው ለማንቀጥቀጥ ኮ በዚያ ቀዝቃዛ በረዶ ውስጥ ጥቂት ሰዓት መቆየት ይበቃል ከአንድ አንድ ቦታማ በረዶው በጣም ተቆልሎ እግር እየዋጠ እንደ ልብ አያስኬድም ። እንደ ቀንድ አውጣ እየተጐተትክ እንድትጓዝ ያስገድድሃል አሁን እንደ መጣሁ የዛሬ ሁለት ሳምንት ዌስት ኤንድ ላይ ካላው የሠረገላ ተራ ሔጄ ካንድ ነጅ ጋር ስነጋገር ዝናብ ማካፋት ጀመረ " በዚህ ጊዜ አንድ መኮንንና አንዲት ወይዘሮ ሲያልፉ እኔ ለራሴ ልብ ብዬ አላስተዋልኳቸውም እሱ ግን ኧረ እኔስ ነገሩ ቀፈፈኝ በሠረገላ ብንሔድ ይሻላል የኔ ፍቅር '' ሲላት ሰማሁት ሳወጋው የነበረው ሠረገላ ነጂ ይህን ሲሰማ በሩን ከፈተላትና ሴትዮይቱ
ገባች መቼም ልጂቱ ስታምር ሌላ ነገር ናት " እኔ ደግሞ እሷን አይቸ ሰውየውን ልብ ብዬ ለማየት ፊቴን ሳዞር ማንን እንዳየሁ ታውቃለህ ? .... ቶርንን " '

“ እውነት ? ”

ያን ጊዜ በጨረቃ ልሳሳት እንደምችል አስበህ ነበር " በቀን ግን ልሳሳት አልችልም " ዐይኔን ሞልቸ ፊቱን ስመለከተው 0መድ ለበሰ እኔም ምናልባት እንደሱ ሁኘ ይሆናል " አልታወቀኝም " "
“ አለባበሱ ጥሩ ነበር ? '
ያለባበሱ ነገርማ ምኑ ይጠየቃል " ከዚያ በኋላ ሠረገላው ሲንቀሳቀስ በስተኋላ ተንጠላጥዩ ተሳፈርኩ ። ነጂው ልጆቹ የገቡ መሰለውና ከነአለንጋው ወደኔ
በኩል ፊቱን ሲመልስ ምልክት ሰጠሁት " ብዙ መንገድ ሳንሔድ አንድ ቦታ ላይ ሠረገላው ገና ሊቆም ሲል ወረድኩና ስመለከተው ጊዜ አሁንም ፊቱ 0መድ እንደመሰለ ነበር የሚኖረው እዚያ ሳይሆን አይቀርም በማለት የገባበትን ቤት ልብ ብዬ አስተዋልኩት ”

“ ለምንድነው ያላስያዝከው
ሪቻርድ ” አለ ሚስተር ካርላይል "
👍12
ሪቻርድ ራሱን ነቀነቀ ስለ ጥፋተኛነቱ የተጨበጠ መረጃ በእጄ ሳልይዝ
እንዴት አድርጌ . . .ሚስተር ካርላይል ? ራሱን ለማዳን ሲል ሲገድል አይቸዋለሁ ብሎ በኔ አዙሮ ሊጠመጥምብኝ ይችላል " እኔ የቶርንን ትክክለኛ ስም የማገኘው ዛሬ ነው
አልኩና ከመሸ በኋላ ወደዚያ ቀን ሲገባበት ወዳየሁት ቤት ሔጀ አንዱን አሽከር አግኝቼ አነጋገርኩት

“ ካፒቴን ቶርን እዚህ ነው የሚኖረው?ስለው' “ እኔ ካፒ
ቱን ቶርን የሚባል ሰው አላውቅም "ይህ የሚስተር
ዌስተርቢ መኖሪያ ነው አለኝ "እኔም እንግዲያውስ ትክክኛ ስሙ ይኸው ነው ብዬ አሰብኩና ቆንጆ ሚስት አለችው አለባበሷ ጥሩ የሆነ ልጅ እግር ” አልኩት "አንተ ልጅ እግር
የምትለውን አላውቅም የኔ ጌታ ስልሳ ዓመት ይሆናቸዋል " ሚስቲቱም ከሳቸው አያንሱም ” ሲለኝ መልሼ ደነገጥኩ ። ምናልባት ልጆች እንዳሉዋቸው? ብለው
ከሁለቱ በቀር ማንም እንደሌላቸው አረጋገጠልኝ " እኔም የዚያኑ ለት ቀን አንድ
ወጣት መኮንን ከነሚስቱ በኪራይ ሠረገላ መጥተው ከዚያ ቤት ሲገቡ ማየቴን ገልጬ የሰውየውን ስም ለማወቅ መፈለጌን ነገርኩት " ጌታው ከብዙ ጊዜ ሕመም በኋላ ያን ለት ገና መነሣቱ ስለነበር ብዙ ጠያቂ ሲመላለስ በመዋሉ የመጡትን ሁሉ ለይቶ ማወቅ እንደማይችል ነገረኝ

ይኸው ብቻ ነው ሪቻርድ ? ''

ይኸው ብቻ! ለኔማ በሆነል እንዴት ጥሩ ነበር ? ከዚያ በየደኅናው መንገድ ስፈልገው...."

ግን ይህ ሰው አንተ ባየኸው ሁኔታ ሎንደን የሚኖር ከሆነ ለምን አይተኸው እንደማታውቅው


ሪቻርድ ራሱን ነቀነቀ ስለ ጥፋተኛነቱ የተጨበጠ መረጃ በእጄ ሳልይዝ
እንዴት አድርጌ . . .ሚስተር ካርላይል ? ራሱን ለማዳን ሲል ሲገድል አይቸዋለሁ ብሎ በኔ አዙሮ ሊጠመጥምብኝ ይችላል " እኔ የቶርንን ትክክለኛ ስም የማገኘው ዛሬ ነው
አልኩና ከመሸ በኋላ ወደዚያ ቀን ሲገባበት ወዳየሁት ቤት ሔጀ አንዱን አሽከር አግኝቼ አነጋገርኩት

“ ካፒቴን ቶርን እዚህ ነው የሚኖረው?ስለው' “ እኔ ካፒ
ቱን ቶርን የሚባል ሰው አላውቅም "ይህ የሚስተር
ዌስተርቢ መኖሪያ ነው ' አለኝ "እኔም እንግዲያውስ ትክክኛ ስሙ ይኸው ነው ብዬ አሰብኩና ቆንጆ ሚስት አለችው አለባበሷ ጥሩ የሆነ ልጅ እግር ” አልኩት "አንተ ልጅ እግር
የምትለውን አላውቅም የኔ ጌታ ስልሳ ዓመት ይሆናቸዋል " ሚስቲቱም ከሳቸው አያንሱም ” ሲለኝ መልሼ ደነገጥኩ ። ምናልባት ልጆች እንዳሉዋቸው? ብለው
ከሁለቱ በቀር ማንም እንደሌላቸው አረጋገጠልኝ " እኔም የዚያኑ ለት ቀን አንድ
ወጣት መኮንን ከነሚስቱ በኪራይ ሠረገላ መጥተው ከዚያ ቤት ሲገቡ ማየቴን ገልጬ የሰውየውን ስም ለማወቅ መፈለጌን ነገርኩት " ጌታው ከብዙ ጊዜ ሕመም በኋላ ያን ለት ገና መነሣቱ ስለነበር ብዙ ጠያቂ ሲመላለስ በመዋሉ የመጡትን ሁሉ ለይቶ ማወቅ እንደማይችል ነገረኝ

ይኸው ብቻ ነው ሪቻርድ ? ''

ይኸው ብቻ! ለኔማ በሆነል እንዴት ጥሩ ነበር ? ከዚያ በየደኅናው መንገድ ስፈልገው...."

ግን ይህ ሰው አንተ ባየኸው ሁኔታ ሎንደን የሚኖር ከሆነ ለምን አይተኸው እንደማታውቅ ስታስበው ምን ተሰማህ?
አለው ጅምር ንግግሩን ከቋርጦ።

ምናልባት ዌስት ሊን ሳለሁ የሚያውቀኝ ሰው እንዳያገኘኝ ባልባሌ
ቦታዎችና በፈረስ ጋሬጣዎች ካልሆነ በቀር ወደ ጎዳና መንገዶች ስለማልዘልቅ ለምን
አይቸው አላውቅም ብዬ አልተደነቅሁበትም ።

“አሁን ደግሞ፡በዚያው ሳምንት ውስጥ እንደገና አገኘሁት ። ማታ ነበር ።
እሱ ከአንድ ቲያትር ቤት ሲወጣ አየሁትና ከፊቱ ሔጄ ቆምኩ ። ስውዬ ምን ትፈልጋለህ ? ከዚህ በፊትም ስትከታተለኝ አይቸሃለሁ አለኝ ። እኔም ለጊዜው ስምህን ለማወቅ ነው የምጸልገው ስለው እብድ ሆነብኝ ሁለተኛ ከአጠገቡ ቢያየኝ
በፖሊስ እንደሚያስይዘኝ ዛተብኝ። ልብ በል አለኝ ሰዎች በፖሊስ የሚያስይዙት
ሌሎችን ስለ ተመለከተ አይደለም ። አንተን ዐወቅሃለሁ ስለዚህ ለራስህ ደኅንት የምታስብ ከሆነ እኔ በምሔድበት ዞር እንዳትል ብሎኝ ከአንድ የግል ሠረገላ ተሳፈረና ሔደ”

“መቸ ነው አልከኝ እንዲህ የሆነው ?

“ የዛሬ ሳምንት ! አንድ ጊዜ ካየሁት በኋላ ስሙን ለማወቅ ብዙ ለፋሁ ።በየ
ቦታው ዞርኩ ። አሁንም አንድ ቀን አገኘሁት " ከአንድ ሌላ ሰው እጅ ለእጅ ተያይዞ በፍጥነት ይራመድ ነበር ። ከዚያም በኋላ አንድ ቦታ ላይ ከዚያው ሰው ጋር ቁሞ
ሲያወራ አገኘሁት። የዚያን ጊዜ ሲያየኝ ፡ ፍራትና ቁጣ የተደባለቀበት ይመስል ነበር። አንበሳ ሆነብኝ ትንሽ አመነታና አንድ ፖሊስ ወደሱ ጠርቶ በእጁ ወደኔ እያመለከተ አንድ ነገር ነገረው ። በዚህ ጊዜ እኔም ፈራሁ ። ከሁለት ሰዓት በኋላ ከሌላ ቦታ
ሔጄ ዞር ብዬ ወደኋላየ ባይ ፖሊስ ሲከተለኝ አየሁ። ሠረገላ እየሳቡ በሚያልፉ ፈረሶች ሥር ተወርውሬ አለፍኩና ባቋራጭ በአልባሌ መንገዶች እየተሽሎከለክሁ
ትንሽ እንዴ ሔድኩ አንድ ሠረገላ አገኘሁ " ከጐኑ አስቀምጦኝ በዶኅና ከሰፈሬ ደረስኩ ብዬ ሳስብ ወደቤቴ ከመግባቴ በፊት አሁንም ዞር ብዬ ወደ መንገድ ተመለከትኩ " አሁንም ሰውዬው ተከትሎኝ መጥቶ የኔን መኖሪያ ሲያጠና የነበረ መሰለኝ ከሩቅ ሆኖ ሲመለከት አየሁት ከቤት ስመጣ እርቦኝ የነበረውን ይህን ሁኔታ ላይ ዘጋኝ " ማሳሳቻ ልብሴን ከሳጥን ኣውጥቼ ለባበስኩና በጓሮ በር ወጥቸ ሔድኩ ዐልፎ ዐልፎ ብቻ አንዳንድ ሠረገላዎች ትንሽ መንገድ ሲረዱኝ በቀር አብዛኛውን
መንገድ የመጣሁት በእግሬ ነው።

“ ግን ሪቻርድ
ልትሸሸግባቸው ከምትችል ቦታዎች ሁሉ ዌስት ሊን
የከፋ መሆኑን ታውቃለህ ? '' ከዚህ ቀደም አራሽ መስለህ ከዚህ መምጣትህን አገር
ሰምቶታል።

“ ይኸን ደግሞ ማን ነገረብኝ ? ”

“ ማን እንዳወጣው እኔም አላወቅሁም ነገር ግን ወሬው ይፋ ሆኖ ስለ ነበር
ካባትሀ ጆሮ ሳይቀር ደርሷል አሁን ሰው በዚህ ወሬ ተቀስቅሶ የማሳሳቻ ልብስህን እነደለበስክ ሊያይህ በመጓጓት ነቅቶ ይጠብቅህ ይሆናል ።”

“ ታዲያ ምን አባቴ ልሁን ? ወደዚህ እንድመጣ ያስገደደኝ ዋነኛው ምክንያትም የገንዘብ ችግር ነው ከለንደን ለቅቄ ራቅ ወዳለ ትልቅ ከተማ ማለት ወደ ሊቨርፑል ወይም ወደ ማንቸስተር ሒጄ ሥራ እፈልግ ነበር ግን በእጄ ምንም ገንዘብ የለኝም " የመጨረሻዎቹን ሳንቲሞቼን ዛሬ ዳቦ አይብና አንድ ብርጭቆ ቢራ ገዛሁበት ከዚህ መስኮት ውጭ ከአንድ ሰዓት በላይ ቆምኩ

“ገና ዌስት ሊን ልገባ ስቃረብ ምን እንደማደርግ ማሰብ ጀመርኩ " በዚህ
ጨለማ ወደ 0ጽዱ ሔጄ ባርባራን በምልክት መጥራት ከንቱ መሆኑን ተረዳሁ ግን ዘብ ከፍዬ እንዳላድር ባዶ እጄን ሆንኩ ስለዚህ አንተን ባገኝህ ብዬ ወደዚህ መጣሁ መስኮቱ በደንብ ስለ አልተዘጋ ተለጥፌ ስመለከት ቆየሁ " ሚስ ካርላይል ወጥታ ስትሔድ አየኋት " ከዚያ ደግሞ አንተም ተነሣና መስኮቱን ከፈትከው "ያኔ
ተናገርኩ " እንግዲህ ሚስተር ካርላይል . . . . . የኔ ኑሮ እስከ መጨረሻው ይኸው መሆኑ ነው።

“ ያንተ ነገር በጣም እያሳዘነኝ ነው . . . . . ሪቻርድ ከዚህ ሥቃይ ላወጣህ ብችል በጣም ደስ ይለኝ ነበር "

ሌላ ቃል ከመናሩ በፊት መዝጊያው ለመከፈት ከተሞከረ በኋላ በቀስታ ተንኳኳ ሪቻርድ በጣም ፈራና የሚሆነውን አጣ "

"ረጋ በል አይዞህ አትሸበር
ከዚህ ማንም አይገባም አሁን ፒተር ነው ሊከፍት የሞከረው ” አለው " ነገር ግን ወዲያው "ማነው” ሲል ጆይስ መሆኗ ዐወቀ "

“ ሚስ ኮርኒሊያ ' መሐረብ ከሱ ስለረሱ እንዳመጣላቸው ልከውኝ ነው? ” አለችው።
👍103
አሁን ሥራ ስለ ያዝኩ መግባት አትችይም ” አላት በማያዳግም ድምፅ "
“ ማናት ? ” አለ ሪቻርድ አሁንም እየተንቀጠቀጠ "
ጆይስ ናት"
“ እስከ ዛሬ እዚህ አለች ? ለመሆኑ ያቺ አፊ ወሬዋ ተሰምቶ ያቃል?”

“የዛሬ ሦስት ወር ገደማ መሰለኝ እዚህ መጥታ ነበር እንደሷ አባባል ቶርን
አብሯት ስለ ነበረ ከግድያው የለበትም አንተም በዐይንህ እስካላየህ ድረስ የሷን አባባል ልታስተባብል አትችልም "

“መጀመሪያ እሱ ከነገሩ ንጹሕ ከሆነ ልቡ እስኪጠፋ አይሮጥም እንደዚያም ሆኖ አይደነግጥም ሁለተኛ ደግሞ ነገር ከሌለበት እኔን ምን አድርግ ብሎ ነው የሚያሳድደኝ? ለምንስ ባየኝ ቁጥር እንደዚያ እየሆነ ይደነግጣል ደግሞስ ይኸስ ይቅርና በግድያው ጊዜ ከቤቱ በስተጀርባ ከነበረው ጫካ ውስጥ ብቻዋን እንደ ነበረችና ስለ ግድያውም በወቅቱ ምንም እንዳላወቀች ምላ መስክራ የለ? ከሱ ከነበረች ለምን ብቻዬን ነበርኩ ብላ ምላ መስከረች ዛሬ ለአፊ የነበረኝ የጋለ ስሜት በርዷል እንከኖቿን ሁሉ ማየት ችያለሁ ...ሚስተር ካርላይል " በሙሸቷ እንኳ አትፀናም እሷ።

የነበሩበት ክፍል መዝጊያው ቤቱን ሊያፈርስ የሚችል በመሰለ ' እንደ ነጎድጎድ
በሚጮህ ድምፅ ተንኳኳ ወንጀለኛን አስሰሙ እንዲያመጡ ሕጋዊ ትእዛዝ
የያዙ የሕግ አስከባሪዎች እንኳን ከዚህ የበለጠ አስደንጋጭ ድምፅ አሰሙ ተብለው አያውቁም " ሪቻርድ ሔር ፊቱ ባንድ ጊዜ ዐመድ መሰለ » ዐይኖቹ ተጎለጎሉ......

💫ይቀጥላል💫
👍155👏3
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አራት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


...ይህንን ማሰቡ በራሱ አንቀጠቀጣት፡፡ ወደ ክፍሏ ተመለሰችና ራሷን አረጋግታ ለአባቷ የምትለውን ነገር አሰላሰለች፡፡ ረጋ ማለት አለባት፡፡ እምባ እንደማያሳዝናቸውና ቁጣ ለስድብ እንደሚጋብዛቸው ታውቃለች፡፡ ምራቁን እንደዋጠ ሰው ነው መናገር ያለባት፡፡ ተጨቃጫቂ ከሆነች ቁጣቸውን ይቀሰቅስባቸውና ፍርሃት ተሰምቷት ያሰበችውን ከመናገር ልትታቀብ ትችላለች፡.
እንዴት ብላ ትጀምር? ስለ ወደፊቱ አንድ ነገር ለመናገር መብት
አለኝ?.ትበል።

አይደለም ይሄ ጥሩ አይደለም፡፡ ለአንቺ ህይወት ሀላፊው እኔ ነኝ፧ እኔ ነኝ መወሰን ያለብኝ ይሏታል፡

ምናልባትም ስለአሜሪካ ጉዞ ላናግርህ› ብትል ይሻል ይሆን?

‹ምንም የምንነጋገረው የለም› ይሏት ይሆናል፡

አጀማመሯ ተቃውሞ የማይቀሰቅስ መሆን አለበት፡፡

‹አንድ ነገር ልጠይቅህ› ልትላቸው ወሰነች፡፡ ለዚህም እሺ› ይሏታል፡ ከዚያ በኋላስ? ቁጣቸውን ሳትቀሰቅስ እቅዷ ጋ እንዴት ትጠጋ፡፡ባለፈው ጦርነት የጦር ሰራዊቱ ውስጥ ነበርክ ትበላቸው ይሆን? ፈረንሳይ ውስጥ መዋጋታቸውን ታውቃለች፡፡ እናታችንስ ነበረችበት?› ትበል ይሆን?እናታቸው የቆሰሉ የአሜሪካ ወታደሮችን በፈቃደኝነት ለማከም ለንደን ውስጥ
አገራዊ ግዴታቸውን ተወጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ሁለታችሁም ሀገራችሁን አገልግላችኋል፧ መቼም እኔም ይህን ለማድረግ እንደምፈልግ ልትረዱት ይገባል፣› ማለት ሊኖርባት ነው።

ይህን የአገር ማገልገልን መርህ የሚቀበሉ ቢሆን እንኳን ሌላ ተቃውሟቸውን ሊቀሰቅስ የሚችለውንም ነገር አሰበች፡፡ ጦር ሰራዊቱን እስክትቀላቀል ዘመድ ጋ መቆየት ትችላለች፡ ይህም ለተወሰኑ ቀናት ነው፡፡አሁን አስራ ዘጠኝ አመቷ ነው፡ በዚህ እድሜ ላይ ያሉ ሴት ወጣቶች በቀን
ስድስት ሰዓት ይሰራሉ፡፡ መኪና ለመንዳት፣ ለትዳርም ሆነ ወህኒ ለመውረድ
እድሜዋ ይፈቅድላታል፡ እንግሊዝ ውስጥ እንዳትቆይ የማይፈቅዱበት
ምንም ምክንያት የለም፡

አሁን ያሰበችው ነገር ትክክል እንደሆነ ገመተች። የሚያስፈልጋት ድፍረት ብቻ ነው፡

አባቷ ከንግድ ድርጅታቸው ኃላፊ ጋር እየተወያዩ ነው፡፡ ማርጋሬት ከክፍሏ ወጣች፡ ደረጃውን ስትወርድ በፍርሃት እግሮቿ ራዱ፡፡
አባቷ ለሚቃወማቸው ንዴታቸው የከረረ ሲሆን ቅጣታቸውም የከፋ
ነው፡፡ በሰባት አመቷ አልጋ ላይ በመሽናቷ አሻንጉሊቷን ተነጥቃለች፡፡የአስራ አንድ አመት ልጅ ሳለች አንድ እንግዳ አንጓጣ ቀኑን ሙሉ ፊቷን ወደ ግድግዳ አዙራ እንድትቆይ አድርገዋታል፡ አንድ ጊዜ ተናደው ድመቷን
ከፎቅ በመስኮት ወርውረውባታል፡
አሁን እንግሊዝ ውስጥ
እንደምትቀርና ናዚዎችን እንደምትዋጋ ለአባቷ ብትናገር ምን ያደርጋሉ?

ደረጃውን በፍጥነት ወረደች፤ ነገር ግን የንባብ ክፍላቸው ጋ ስትደርስ
ፍርሃት ዋጣት፡፡ ሲናደዱ፣ ፊታቸው ሲቀላና አይናቸው ሲጎለጎል ታያት፤ጉልበቶቿ ተብረከረኩ፡፡ ራሷን ለማረጋጋት ሞከረች፡፡
አባቷ ያሉበት ክፍል በር ላይ ስትደርስ ቤት ጠባቂዋ ሚስስ አለን አዳራሹን አቋርጣ መጣች፡ ሚስስ አለን የቤት ሰራተኞች አለቃ ስትሆ በስሯ ያሉትን ሰራተኞች አሽቆጥቁጣ ነው የምታስተዳድረው፡፡ ቤተሰቡን በሙሉ ስለምትወድ አገር ለቀው መሄዳቸው በጣም አሳዝኗታል“ የእንጀራ ገመድ ተበጠሰ ማለት ነው፡፡ ለማርጋሬት ያሳየችው ፈገግታ በእምባ የታጀበ ነበር፡፡

ማርጋሬትም ሚስስ አለንን ስታይ ልቧ ተነካ፡፡ ወዲያውኑም የመጥፋት
ዕቅዷ በአዕምሮዋ ውስጥ ቅርፅ እየያዘ መጣ፡፡ ከሚስስ አለን ገንዘብ ትበደርና ቤቱን አሁኑኑ ለቃ የአስር ሰዓት ከሃምሳ ደቂቃውን ባቡር ተሳፍራ ወደ ለንደን ትሄዳለች፧ በአክስቷ በካትሪን ቤት ሌሊቱን ታሳልፍና በጧት የምድር ጦር መምሪያን ትቀላቀላለች፡፡ አባቷ ሲደርሱ እሷ ሰራዊቱን ስለምትቀላቀል ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡
‹እቅዱ በጣም አደገኛና ድፍረት የሚጠይቅ በመሆኑ ሊሳካ አይችልም ብላ ሃሳቧን ከመለወጧ በፊት ‹‹ኦ ሚስስ አለን ትንሽ ገንዘብ ትስጪኛለሽ?
አንድ ነገር ገበያ ሄጄ ልገዛ አስቤ ነበር፤ አባባን ደግሞ መረበሽ አልፈለኩም በስራ ተጠምዷል፣›› አለቻት፡

ሚስስ አለን ሳታመነታ ‹‹እሺ እመቤቴ ምን ያህል ነው የሚፈልጉት? ማርጋሬት ወደ ለንደን ለመጓዝ የባቡሩን ዋጋ አታውቀውም፡፡ ትኬት
ገዝታ አታውቅም፡፡

እንዲያው በግምት ‹‹አንድ ፓውንድ ይበቃኛል›› አለቸ
ወዲያው በሃሳቧ ላደርገው ነው?› አለች፡፡
ሚስስ አለን ከቦርሳዋ ውስጥ ሁለት የአስር ሽልንግ ኖቶት አወጣች
ብትጠይቃት ዕድሜዋን ሙሉ ያጠራቀመችውን ገንዘብ ትሰጣት ነበር፡
ማርጋሬት ገንዘቡን እየተንቀጠቀጠች ተቀበለች፡፡ ይሄ የነፃነቴ ትኬት ይሆን ይሆናል› ስትል አሰበች፡፡ ፍርሃት ልቧን ቢያርደውም እንደ እሳ
የሚንቀለቀል ተስፋ ልቧ ውስጥ ተጫረ፡፡

ሚስስ አለን አገር ለቀው መሄዳቸው አሳዝኗት የማርጋሬትን እጅ
ጭምቅ አደረገች፡፡
‹‹ክፉ ቀን ነው የመጣብን እመቤት ማርጋሬት ለሁላችንም›› አለችና
ሽበት የወረረውን ጭንቅላቷን በሃዘን እየወዘወዘች ወደ ማድቤቷ ሮጠች።

ማርጋሬት በመረበሽ ዙሪያውን ቃኘች፤ አንድም ሰው አይታይም፡፡ ልቧ
ይደልቃል፧ ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል፡፡ከተጠራጠረች እቅዷ አፈር ድሜ መብላቱ ነው፡፡ ኮቷን ለመልበስ ጊዜ ሳታጠፋ ገንዘቧን በእጇ ጨብጣ በፊት ለፊቱ በር ወጥታ ሄደች፡፡

የባቡር ጣቢያው ከቤታቸው ሁለት ኪሎ ሜትር ያህል ይርቃል፡፡በመንገድ ላይ የአባቷ ሮልስ ሮይስ መኪና ከኋላ የሚመጣ እየመሰላት
ትደነብራለች፡፡ ምን እንዳደረገች እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ? መጥፋቷ ቢያንስ ከራት ሰዓት በፊት ሊታወቅ አይችልም፡፡ ሚስስ አለን ገበያ መሄዷን ትነግራቸዋለች፡፡

ባቡር ጣቢያ ቶሎ ደረሰች ቲኬት ገዝታ ብዙ ገንዘብ ተርፏታል፡ የሴቶች መቆያ ክፍል ገብታ የግርግዳ ሰዓቱን አየች፡
ባቡሩ ዘግይቷል፡
አስር ሰዓት ከሃምሳ አምስት ሆነ ከዚያም አስራ አንድ እያለ አስራ አንድ ከአምስት ሆነ፡ በዚህ ጊዜ ማርጋሬት ከመፍራቷ የተነሳ እቅዷን ሰርዛ ወደ ቤቷ በመመለስ ጭንቀቷን ማስወገድ እንደሚሻል ተሰማት፡፡

ባቡሩ አስራ አንድ ሰዓት ከአስራ አራት ደቂቃ ላይ መጣ፡፡ አባቷ በአካባቢው አይታዩም፡፡

ማርጋሬት ልቧ በጉሮሮዋ ተወትፎ ባቡር ላይ ተሳፈረችና መስኮቱ ጋ
ቆማ ‹አባቴ በመጨረሻው ደቂቃ ላይ መጥቶ ይወስደኛል› ስትል ተጨነቀች፡፡

በመጨረሻም ባቡሩ ተንቀሳቀሰ፡፡

ማምለጧን ማመን አቃታት፡፡
ባቡሩ ፍጥነቱን ሲጨምር የመጀመሪያው የደስታ ፍንጣቂ በልቧ ተጫረ፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ባቡሩ ጣቢያውን ለቆ ተጓዘ፡፡ ማርጋሬት
መንደሩ ወደ ኋላ ሲጓዝ ስትመለከት ልቧ በድል አድራጊነት ሲግል
ተሰማት፤ አደረገችው፤ አመለጠች፡፡

ወዲያው ጉልበቷ በድካም ተብረከረከ፡፡ መቀመጫ
ዙሪያውን ሲማትር ባቡሩ ሙሉ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ተገነዘበች፡:ሁሉም ወንበሮች ተይዘዋል፤ አንደኛ ማዕረግም ቢሆን፡፡
ወለሉ ላይም የተቀመጡ ወታደሮች ነበሩ፡፡ እሷ ግን እንደቆመች ቀረች፡ ጉዞዋ ቅዠት ቢመስልም በልቧ የሚሰማት ደስታ አልቀነሰም፡፡

በየጣቢያው ባቡሩ ውስጥ ሰዎች ይጠቀጠቃሉ፡ ሪዲንግ ከተማ ላይ
ባቡሩ ሶስት ሰዓት ተገተረና አረፈው፡፡
👍21👎2
ከአየር ቦምብ ዱብዳ ለመዳን ሲባል መብራት እንዳይበራ በመከልከሉ
የባቡሩ አምፑሎች ተነቅለዋል፡ በመሆኑም አንዳንድ ጊዜ የጥበቃ አባሉ
ህዝብ በተቀመጠበትና በተጋደመበት ወለል ላይ ሲያልፍና ሲያገድም
ባትሪውን ከሚያበራው በስተቀር ምሽቱን በፍፁም ጭለማ ነበር የሚጓዙት፡፡
ማርጋሬት ይሄ ምንም አይደለም› በማለት ራሷን አሳመነች፡ ቀሚሷ
በመረጋገጡና ወለሉ ላይ በመቀመጧ ቢቆሽሽም ነገ ወታደራዊ ዩኒፎርም
ትለብሳለች፡፡ አገሪቱ ጦርነት ላይ ነች፡፡

ማርጋሬት አባቷ መጥፋቷን አውቀው ባቡር ተሳፍራ ይሆናል ብለው
በመገመት ከለንደን በከፍተኛ ፍጥነት በመብረር ፓዲንግተን ጣቢያ ላይ
ያቆሙኝ ይሆን? ብላ ገመተች፡፡ የመሆን ዕድሉ ጠባብ ቢሆንም ባቡሩ
ጣቢያው ላይ ሲደርስ ልቧ በሀይል ደለቀ፡፡
ከባቡሩ ስትወርድ አባቷ አሁንም በጣቢያው አይታዩም ሌላ ድል ተሰማት፡ እሳቸው ሁሉን ማድረግ የሚችሉ አምላክ አይደሉም::

ድንግዝግዝ ባለው ጣቢያ ታክሲ አገኘች፡፡ ታክሲው የጎን መብራቱ ብቻ አብርቶ ወደ ባይስ ዎተር ወሰዳት፡፡ ታክሲ ነጂው ካትሪን የምትኖርበት ህንፃ ጋር ሲደርስ ባትሪውን አብርቶ
ወደ ህንፃው መራት።

የህንፃው መስኮቶች በሙሉ መብራት አይታይባቸውም፡፡ ኮሪደሩ ውስጥ ንግንባር መብራት በርቷል፡፡ ጥበቃው ስራውን ጨርሶ ወደ ቤቱ ሄዷል፡ እኩለ ለሊት ሊሆን
ምንም አልቀረው ማርጋሬት
የካትሪን አፓርታማ
የሚገኝበትን ታውቃለች፡ ደውሉን ተጫነች፡፡

ምንም መልስ የለም፡፡

ልቧ ስንጥቅ አለ፡፡

እንደገና ደውሉን ተጫነች ሆኖም ዋጋ እንደሌለው ተረዳች የአፓርታማው የደወል ድምፅ ጆሮ ይሰነጥቃል፡፡ ስለዚህ ካትሪን የለችም

ካትሪን የምትኖረው ኬንት ውስጥ ከወላጆቿ ጋር ነው: ይህ አፓርታማ የምትጠቀመው አንዳንዴ መዝናናት ሲያምራት ለማረፊያነ ነው:: የለንደን ማህበራዊ ህይወት ቆሟል እየላላ በመምጣቱ ካትሪን እዚ የምትቆይበት ምንም ምክንያት አልታይሽ ብሏት ይሆናል፡ ማርጋሬት
አስቀድማ ይህን አላሰበችበትም ነበር፡፡
ሀዘን ተሰማት፣ ከካትሪን ጋር ቁጭ ብላ ኮኮዋ እየጠጡ የሰራችውን ጅብድ ልታካፍላት ጓጉታ ነበር፡
ቀጥሎ የምታደርገውን አሰበች፡፡ ለንደን ውስጥ ብዙ ዘመዶች አሏት።
ነገር ግን እነሱ ጋር ብትሄድ አባቷ ጋ ስልክ ከመደወል ወደኋላ አይሉም
ካትሪን ግን የእሷ አጋር ትሆን ነበር፡፡ ሌሎቹን ዘመዶቿን አታምናቸውም:
ሌላም ነገር አስታወሰች፡ አክስቷ ማርታ፡ ወዲያው ስልክ እንደሌላቸው
ትዝ አላት አክስቷ በትንሹ በትልቁ የሚቆጡ የሰባ አመት ቆሞ ቀር ባልቴት ናቸው፡ የሚኖሩት ማርጋሬት አሁን ካለችበት አንድ ኪሎ ሜትር ያህል ርቀው ነው፡፡ ይኼኔ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ላይ ይሆናሉ፡፡ እናም
ቢቀሰቀሱ ይናደዳሉ፡፡

ማርጋሬት ተመልሳ ደረጃውን ወርዳ መንገድ ላይ ስትወጣ ድቅድቅ ያለ
ጨለማ ገጠማት፡፡

ጨለማው ያስፈራል፡፡ ዓይኗን በልጥጣ ዙሪያውን ተመለከተች ነገር
ግን ዓይን ቢወጉ አይታይም፡ ሆዷ ታወከ፤ የመደንዘዝ ስሜትም ተሰማት፡፡

አሁንም አይኗን ገለጠች ነገር ግን ምንም አይታያትም፡፡
ጨለማው አንጎል ያደርጋል፡ ራሷን አረጋጋችና ወደ አክስቷ ቤት የሚወስደውን መንገድ በዓይነ ህሊናዋ ቃኘች፡
የምስራቅን አቅጣጫ ይዤ እሄድና በሁለተኛው መጠምዘዣ መንገድ
ላይ በግራ በኩል እሄዳለሁ የአክስቴ ቤት እመጨረሻው ህንፃ ላይ ነው በጨለማም ቢሆን ቀላል ነው አለች በሆዷ

አንዳች ከዚህ ማጥ የሚያወጣ ነገር ተመኘች መብራት የሚያበራ
ታክሲ፣ሙሉ ጨረቃ ወይም ፖሊስ፡፡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ፀሎቷ ተሰማላት፡፡
አንዲት በጥቅጥቅ
መኪና ጭለማ ውስጥ አይኗን እንደምታቁለጨልጭ ድመት የጎን መብራቷን ጭልጭል እያደረገች በዝግታ መጣች፣ በዚህ ጊዜ እስከ መንገዱ መጠምዘዣ ድረስ የመንገዱን ጠርዝ
ማየት ቻለች።

መራመድ ጀመረች፡፡

መኪናዋ ቀይ መብራቷን በርቀት እያብለጨለጨች ከአይን ተሰወረች፡፡
ማርጋሬት መጠምዘዣው ጋር ለመድረስ ሶስት ወይም አራት እርምጃ
እንደቀራት የመንገዱ ጠርዝ አደናቀፋት፡፡ መንገዱን አቋረጠችና እግረኛ
መንገዱ ላይ ያለምንም ችግር ወጣች፡፡ ይህም ድፍረቷን ጨመረላትና
ያለስጋት መራመድ ቀጠለች፡፡

ድንገት ፊቷን የገጫት ነገር ከፍተኛ ህመም ለቀቀባት፡፡

በስቃይና በፍርሃት አንዴ ጩኸቷን አስነካችው፡፡ በመሸበሯ ሩጭ ሩጭ
አላት፡፡

እራሷን እንደምንም አረጋጋችና ህመሙ የሚሰማትን ጉንጯን መዳበስ ጀመረች፡፡

‹መንገዱ መሐል የሰው ቁመት ያለው ምን ነገር ነው ፊቷን የመታት?› በሁለቱም እጆቿ የመታትን ነገር ደባበሰች፡፡ አንድ ነገር በእጆቿ ነካችና በድንጋጤ እጇን ሰበሰበች፡፡ ጥርሷ በፍርሃት እየተንቀጫቀጨ እንደገና እጇን ሰደደች፡ አንድ የሚቀዘቅዝ፣ ጠንካራና ክብ የሆነ ነገር ነካች፡ እጇን በደንብ ዘርግታ ደባበሰች ፊቷ ላይ ህመም ቢሰማትም ምን እንደሆነ
ስታውቅ ከት ብላ ሳቀች፡፡ ፊቷን የገጫት የመንገድ ዳር ፖስታ መክተቻ
ሳጥን ነው፡፡

ዙሪያውን ዞረችና እጆቿን ዘርግታ ርምጃዋን ቀጠለች፡፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደገና ሌላ የመንገድ ጠርዝ አደናቀፋት፡፡ ሚዛኗን
እንደምንም መጠበቅ ስትችል ልቧ ምልስ አለ፡፡ የአክስቷ ቤት ያለበት
መንገድ ላይ ደረሰችና ወደ ግራ ታጠፈች::

አክስቷ የበሩን የደወል ድምፅ ይሰሙ ይሆናል ብላ ገምታለች፡፡ብቻቸውን ስለሚኖሩ ካለሳቸው በር የሚከፍት የለም፡፡ ካልሰሙ ግን ወደ ካትሪን ቤት ተመልሳ ትሄድና ኮሪደሩ ውስጥ ትተኛለች፡፡ መቼም ወለሉ ላይ መተኛቱን ትችለዋለች፡፡ ነገር ግን እንደገና ጨለማ ውስጥ መግባት ፈራች፡፡

ምናልባትም አክስቷ በር ላይ ጥቅልል ብላ ተኝታ እስኪነጋ መጠበቁ ሳይሻል
አይቀርም፡ የአክስቷ ቤት በህንፃው ዳር ነው የሚገኘው፡ ማርጋሬት ቀስ
እያለች ተራመደች።

መንገዱ ፀጥ ያለ ቢሆንም በአካባቢው ከየቦታው የሚያፈተልክ ድምፅ
ይሰማል፡ ከርቀት የመኪና ድምፅ አልፎ አልፎ
ይሰማል። ውሾች በበራቸው ስታልፍ ይጮሃሉ፤ ድመቶችም ስትቀርባቸው እንዲሁ፡ የጭፈራ ቤት ሙዚቃና የሰዎች ጭቅጭቅ ከሩቅ ይሰማታል፡ መብራት፣ ለብርዱ የምድጃ እሳት፣ ለቆፈኑ ደግሞ የጀበና ሻይ ፈለገች፡፡

ህንፃው ካሰበችው በላይ ወደ ጎን ረዘመባት፡፡ መንገድ የሳተች አልመሰላትም፡ በሁለተኛው ማቋረጫ ወደ ግራ ታጥፋለች፡ ሰዓቱ ስንት
እንደሆነ አታውቅም፡
በአካባቢው ቤቶች ይኑሩ አይኑሩ እርግጠኛ
አልሆነችም: ምናልባትም መናፈሻ ውስጥ ገብታ እየተደናበረች ይሆናል፡

ማሰብ ጀመረች፡ የት ጋ ነው የተሳሳተችው? በአሁኑ ጊዜ ተሳስታ ከአንድ ኪ.ሜ በላይ ሳትሄድ አትቀርም::

ባቡሩ ላይ የተሰማትን የድል አድራጊነት የደስታ ስሜት ለማስታወስ ሞከረች: አሁን ግን ያ ሁሉ የለም፡ አሁን ብቸኝነትና ፍርሃት ነግሶባታል። ጉዞዋን አቁማ መገተር አለብኝ ብላ ወሰነች፡ በዚህ አይነት ምንም ጉዳት አይደርስባትም
እንደቆመች ረጅም ጊዜ ቆየች፡ አሁንም ቢሆን መንቀሳቀሱን ፈራች:
ፍርሃት ጠፍንጓታል፡ እስከምትወድቅ ወይም እስከሚነጋ ድረስ እቆማለሁ
ስትል አሰበች፡

ከዚያም መኪና መጣ፡፡

የመኪናዋ የጎን መብራቶች ትንሽ ብርሃን ሲፈነጥቁ ቀድሞ ከነበረው ድቅድቅ ጨለማ ጋር ሲነጻጸር ጸሃይ የወጣ ያህል መሰለ፡፡ የመኪና መብራቱ መንገዱ መሐል መሆኗን ስላሳወቃት ሮጣ መንገዱ ዳር ወጣች፡ አንድ የምታውቀው አደባባይ ታያት፡

መኪናው አለፋትና በኩርባው ሲጠመዘዝ የሆነ የሚታወቅ ነገር አገኛለሁ ብላ መኪናውን ተከትላ ሮጠች፡፡ እንዳሰበችው የምታውቀው ቦታ
አየችና በደስታ አነባች
👍18
ከደቂቃዎች በኋላ አንድ ሆቴል በር ላይ ደረሰች፡፡ ህንፃው መብራት
ባይኖረውም በሩን አገኘችው፡ ለቤርጎ ኪራይ የሚበቃ ገንዘብ እንደሌላት
አውቃለች፤ ነገር ግን ተከራዮች ሆቴሉን ለቀው እስኪወጡ ድረስ ክፍያ
እንደማይጠየቁ አሰበች፡

ለሁለት ቀን ቤርጎ ትከራይና በሚቀጥለው ቀን ትወጣለች ምድር ጦር
መምሪያ ተመዝግባ ለሆቱሉ በመደወል የሆቴል ኪራዩን ደረሰኝ ለአባቷ ጠበቃ እንዲላክ ታደርጋለች፡
በረጅሙ ተነፈሰችና በሩን ከፍታ ገባች፡፡....

ይቀጥላል
👍132
የጠንቋዩ ዋሻ
★፠፠ክፍል 13፠፠★

መሳይ የድምፁ አሰቀያሚነት እና የኮሽታው ሁኔታ ልቡን እርብሽ አደረገበት ፡እዛ ዋሻውስጥ ካመጡት ጀመሮ ምንም ሰላም ባይሰማውም ፡በዚ ሁለት ቀን ግን የበለጠ ነገሮች አስፈሪነታቸው ፡እየጨመረበት መጥቷል ፡ በዚጊዜ ደሞ ፡ ጓደኞቹም ተጨማሪ ፍርሃቶቹ ሆነዋል ፡ አስተያየታቸውንም እየወደደው አይደለም ፡
ድምፁ እየቀረበው ሲመጣ የዋሻውን ግድግዳ ተደግፎ ፡በመቆም ፡ ፈጣሪውን መለመን ጀመረ ፡'አምላኬ ሆይ ፡ከመጣው ነገር ሁሉ ከልለህ ከዚጉድ አውጣኝ እስካሁንም በጥበብህ ጠብቀኽኛል አሁንም አንተ ሸፍነኝ እኔ ይሄን ሁሉ የምችልበት አቅም የለኝም እባክህ'ብሎ ተማፀነ ከፍርሃቱ የተነሳ ዕንባው እየወረደ ነበር በቃ ዛሬ ሊያልቅልኝ ነው መሰለኝ እነዚ እብዶች ጉድ ሊያደርጉኝ ነው እዚ ጨለማ ዋሻ ውስጥ ,,,,,,,,,,,,,, የሚያስፈራራው ድምፅ አጠገቡ ሲደርስ ቀመ፡ የሱም ልብ ቀጥ አለ ለአፍታ
" የጨለማው ጌታ የዓለም ሁሉ አይል በጄ ይረፍፍፍፍፍ ሁሉንም የሚቆጣጠር አይል ስጠኝኝኝኝኝኝ ማንም ከቃሌ አይውጣጣጣጣ የጨለማው ሰላም ይጠበቅቅቅቅቅ ፈረሶቼን በአረቱም አቅጣጫ እንድጋልባቸው አይሉን በኔላይ አውርድድድድ አይሉ የኔ ይሁንንን ጨለማው ይንገስስስስስ ብርታቱ ሁሉ በኔላይ ይደርርርርር አሆሆሆይ አቢያራራራ,,,,,,,,,' የሚያስጨንቅ እና የሚያስፈራራው የአቢያራ ድምፅ ነበረ መሳይ ጭንቀቱ የበለጠጨምሮ እግሩ ተብረከረከበት ፡ ከአሁን አሁን ያዘኝ ብሎ በጣም ፈራ ፡ ነገርግን አቢያራ ጥቂት መሳይ ባለበት ቦታ ከቆመ በዋላ ያንን የጥንቆላ ጩኽቱን እያሰማ በዋሻው ውስጥ ያለምንም ብርሃን እየተዟዟራ ቀጠለ ፡መሳይ አልፎት ሲሄድ አላመነም ፡ እንደምንም ብሎ የሚንቀጠቀጥ እግሩን እየጎተተ ወደ ማደሪያው ሄደ ፡የሚያድርባ ትንሽዬ የዋሻው ክፍል ጋር ሲደርስ በግልግል ተነፈሰ ፡ ወደውስጥ ፡በመግባት ፡መኝታው ላይ ተዘረጋ ፡መልሶ በመነሳት መዝጊያውን በጥንቃቄ ዘጋውና እዛው መዝጋውን ተደግፎ ቆመ፡ እናም አይኑን ጨፍኖ ፡ እስከመቼ በዚ መልኩ እንደተሳቀቀ እንደሚኖር ፡እራሱን ጠየቀ ፡ እንዴት ነው ፡ከዚ ጉድ ማምለጥ የሚችለው በሆነ ዘዴ ከሁሉም ጋር መጋፈጥ አለበት በቃ፡ መሞቴ ካልቀረ ሞክሬ ብሞት አይሸለም ፡ አዎ ይሄንን የጭካኔና ያለማወቅ ሰንሰለት መበጣጠስና ማምለጥ አለብኝ !!! አይኑን ገለፀና የዋሻው ግድግዳላይ አሳረፈ አንዳች ብርሃን ያየ መሰለው ፡ተንበርክኮ ለፈጣሪው ከልቡ ፀሎቱን አደረሰ ፡ ከዚ በዋላ ለሚያደርገው ነገር ሁሉ ይቅርታንም ጠየቀ ፡ እናም አልጋውላይ ተንጋሎ ፡እቅድ ማውጣት ጀመረ ፡ ይሄንን የሴጣን ጎሬ መበታተን እና ነፃ መውጣት ፡ያለበት በራሱ ጥንካሬ ነው ፍርሃትና መረበሽ መጨረሻው ሞት ነው ፡ ስለዚ እነዚህን ሰዎች አንድ በአንድ ለመጋፈጥ ወሰነ ,,,,,,,,

¥አድማስ በጠዋት መጥቶ የተዘጋውን የመሳይን በር ሲያንኳኳ መሳይ በድንጋጤ ተነስቶ ቆመ
"ማነው እእ"
"እኔነኝ አንተጩጬ ክፈት በሩን "አለው ቆጣ ብሎ
"ለምን"አለ መሳይ እንደዛ ምስኪን ሰውዬ ሊያርዱኝ ነው እንዴ ሊቀድሙኝ እንዳይሆን
"ክፈት እንጂ ለምን ይላል እንዴ!"አለ ቁጣው ሰይበርድ
"ባልከፍትስ "አለ መሳይ ፍርሃቱ ሳይለቀው ፡እናም በዙሪያው አንዳች ስለት ነገር እየፈለገ ፡ነገር ግን ያለሰአን ምንም የለም
"አንተ የማትረባ ፈልፈላ ጌታ አቢያራ ቢፈቅድልኝ ፡አንድ ቀን አላሳድርህም ነበር አንገትህን አንቄ ለዘንዶ ነበር የምሰጥህ "አለው በጩኽት ፡ ይሄን ጩኽት ሰምታይሆን አይታወቅም ፡ ኤልያታ የተባለችው ፡ የአቢያራ ሴት ፡ድምጿን አሰማች
"አድማስ ምንድነው "ስትል፡አድማስ ተርበተበተ ኤልያታን በጣም ስለሚወዳት ፡ የሷን ድምፅ ሲሰማ የሌለ ይለሰልሳል
"አይ ሰላም ነው መሳይ አልወጣም ሲለኝ ተናድጄ ነው"
"መሳይ መተኛት ከፈለገ ተወው ለምን ፈለከው"
"አይ ለሱ አንድ ማስጠንቀቂያ ነበረኝ ለዛ ነው"አለ አድማስ ፡መሳይ ማስጠንቀቂያ አለኝ ብሎ ለኤልያታ ሲነግራት ፡ተጨነቀ በቃ ትላንት ከኤዛ ጋር አይቶኛል ብሎ
"እሺ ማስጠንቀቂያውን በዋላ ሲነሳ ትነግረዋለህ እንቅልፉን ይጨርስ ይደርሳል ፡"አለች በትህዛዝ አይነት ፡
"እሺ ካልሽ ፡ግን እኔ ወደከተማ ልወጣ ነው የጀኔተሮቹ ነዳጅ ስላለቀ ማምጣት አለብኝ"አለ ቅር እያለው
"ከሆነ ማስጠንቀቂያህን ልትነግረኝ ትችላለህ እኔ አናግረዋለው "አለች ኤልያታ ፡ መሳይ የአቢያራ ሴቶች እረጅም ወሬ ሲያወሩ ሰምቶ አያውቅም ኤዛም ትንሽ ስለቀረበችው እንጂ ፡የኤልያታ የሚያምርና የሚስረቀረቅ አይነት ድምፅ እየገረመው ፡የማስጠንቀቂያው ጉዳይ እያሳሰበው ፡ ጆሮውን ጣል አድርጎ ሰማቸው
"እእሺ ግን ላንቺ ,,,,,"
"ለማንም ተናገርከው ለውጥ አየመጣም ተራ ነገር ከሆነ አትንገረኝ ወደስራህ መሄድ ትችላለህ "አለችው ፡ አድማስ በሚያፈቅራት ሴት እንደተራ መታየት ስላልፈለገ"ኤልያታ ምን መሰለሽ ፡መሳይ እእእ ማለቴ ኤዛን እያታለላት ነው ፡ ማለቴ ወደሱ እንድትሳብ ፡በማድረግ ችግር ውስጥ እየከተታት ነው ፡ እና ይሄን ደሞ ጌታዬ ከሰማ ታውቂያለሽ ፡ከዚ በፊት እንደተፈጠረው ያልጅ ፡በኤዛ ምክንያት የተገደለው፡እንደዛ ነው የሚፈጠረው"ብሎ ዝም አለ
"እና አንተን ምን አሳሰበህ እና ነው ማስጠንቀቂያ የምትሰጠው ፡ አባታችን ያውቅ ይሆናል ፡ደሞ ከሱ ምንም አይሸሸግም ብታስጠነቅቀውም አባታችን ቀድሞ ፡አውቆት ይሆናል ዝም ያለው ፡ ነው ይሄንን ልጅ መርዳት ፈልገሃል "ብላ አፋጠጠችው
"ኧረ እኔ እንደዛ አላሰብኩም "አለ ጭንቅ እያለው
"በቃ ወደ ምትሄድበት ሂድ "ብላው እስኪሄድ ጠብቃ እሷም መሳይን ምንም ሳትለው ሄደች ፡መሳይ በግልግል ተነፈሰ ፡ በቃ ከኤዛ ጋር ያለው ነገር ሁሉንም የሚያሳስብ ከሆነ ጉድ ነው የሚፈላው ምክንያቱም ኤዛ እንደወደደችው ገብቶታል ፡ ምን አልባትም ፡እሱን አንድ ነገር እንዲያደርጉት አትፈቅድ ይሆናል ፡ ወይም ደሞ ፡እራሷንም ፡ይገሏት ፡ይሆናል ፡ እንግዲ የሁለቱን ግንኙነት አድማስና ኤልያታ ሰምተዋል ፡በቀጣይ ፡ደሞ ፡ሌሎቹ ጋር መድረሱ አይቀርም ይሄ ከመሆኑ በፊት እና ሁለቱም ፡ከሚ ጠፉ ቀድሞ አቢያራ የተባለውን ፡ሴጣን፡እሱ እራሱ ቀርቦ ማጥፋት እንዳለበት አመነ ግን እንዴት ?,,,,,,,,,,

ሙና መሀመድ

ይቀጥላል

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍532
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አምስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


...ለሁለት ቀን ቤርጎ ትከራይና በሚቀጥለው ቀን ትወጣለች ምድር ጦር
መምሪያ ተመዝግባ ለሆቱሉ በመደወል የሆቴል ኪራዩን ደረሰኝ ለአባቷ ጠበቃ እንዲላክ ታደርጋለች፡
በረጅሙ ተነፈሰችና በሩን ከፍታ ገባች፡፡

ማርጋሬት በቀጥታ ወደ እንግዳ ተቀባዩ አመራች ከፍተኛ እረፍት ተሰማት። ፍርሃትና ቅዠቱ አብቅቷል።
አንድ ወጣት እንግዳ ተቀባይ ባንኮኒ ተደግፎ ያንጎላጃል። ማርጋሬት
‹‹እህምም›› ብላ ጉሮሮዋን ስትጠራርግ ወጣቱ ነቃ ድንጋጤ እና መደናገር
ፊቱ ላይ ይታያል።

‹‹ቤርጎ አላችሁ?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹በዚህ ሰዓት?›› ሲል መለሰ።
‹‹ጨለማው አላስኬድ አለኝና እቤት መሄድ አልቻልኩም››
ወጣቱ ራሱን ገዛና ‹‹ሻንጣሽ የታለ?›› ሲል ጠየቃት።
<<የለኝም›› አለች ማርጋሬት በማፈር፧ ከዚያም አሰብ አደረገችና
‹‹የለኝም ጨለማው አያስኬደኝም ብዬ አላሰብኩም ነበር›› አለች
ወጣቱ ሁለመናዋን አስተዋለ። ፊቱን ደባበሰና መዝገቡን የሚያይ
መሰለ። ሰውዬው ምን ነካው? ስትል አሰበች።

‹‹ቦታ የለንም›› አላት።
‹‹አላችሁ››
‹‹ከአባትሽ ጋር ተጣልተሽ ነው አይደለም?›› አላት እየጠቀሳት።
‹‹አይደለም፣ እቤት መሄድ ስላልቻልኩ ነው›› ስትል ደገመች።
‹‹ታዲያ ምን ላድርግ ሂትለርን ጠይቂ››
ልጅነቱን አየችና ‹‹አለቃህ የት ነው?›› አለችው፡
የተሰደበ መሰለው ‹‹እስከ ጧቱ 12፡00 ሰዓት እኔ ነኝ ኃላፊው›› አላት
ማርጋሬት ዙሪያውን አየችና ‹‹እስኪነጋ እዚሁ እቀመጣለሁ›› አለች
በመሰላቸት፡
‹‹አይቻልም!›› አለ ወጣቱ ፈርቶ ሻንጣ ያልያዘች ኮረዳ እንግዳ መቀበያ
ክፍል ልታድር?› ሲል አሰበና ‹ቀዚህ ምክንያት ከስራ እባረራለሁ›› አላት።
‹‹እኔ ኮረዳ አይደለሁም›› አለች ብልጭ ብሎባት፤‹‹እኔ እመቤት ኦክሰንፎርድ ነኝ›› ማዕረጓን መጠቀም አልፈለገችም ነበር፤ ምን ታድርግ፡
ይህን ብትልም ምንም አልጠቀማትም፡ እንግዳ ተቀባዩ ገላመጣትና
‹‹ትቀልጃለሽ!›› አላት በማሽሟጠጥ።ማርጋሬትም ልትጮህበት አሰበችና መልኳን በመስታወት ስታይ ዓይኗ እንደጠቆረ ተገነዘበች ከዚያም በላይ እጇ ቆሽሿል፤ ቀሚሷም ተቀዳል፡
እንግዳ ተቀባዩ ቦታ የለንም ማለቱ አያስደንቅም: በተስፋ መቁረጥ ‹‹መቼም
ጨለማ ውስጥ ሂጂ አትለኝም!›› አለችው:
‹‹ከዚህ ሌላ የምልሽ የለም›› አላት።

ማርጋሬት ዝም ብዬ ብቀመጥና ከዚህ አልነቃነቅም ብል እንግዴ
ተቀባዩ ምን ይለኝ ይሆን? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ ይኸው ነው ማለት የፈለገችው ምክንያቱም በጣም ደክሟታል፤ ሰውነቷም ዝሏል ለጠብ
የሚሆን ጉልበት የላትም፡፡ ከዚህም በላይ ውድቅት በመሆኑ ወጣቱ ምን
እንደሚያደርጋት አይታወቅም፡፡

ሰውነቷ እንደዛለ ጀርባዋን ሰጥታው እንደከፋት ወጥታ ጨለማ ውስጥ ገባች፡፡ እየሄደችም ከእንግዳ ተቀባዩ ጋር ልጣላ ይሆን?› ስትል ነገር ስታስብ ይበልጥ ኃይል ያላት የሚመስላት? አሁን እጅ ከሰጠች በኋላ
አሰበች፡፡ ግን ለምንድ ነው ከምታደርገው ይልቅ ማድረግ የምትፈልገው
ይበልጥ መናደዷ ገረማት፡፡ እንደ ንዴቷ ከሆነ ከእንግዳ ተቀባዩ ጋር ትጣላ ነበር፡፡ ተመልሳ ለመሄድ ፈለገች፡ ሆኖም ወደፊት መራመዷን ቀጠለች:: አዎን መሄዱ ነው የሚሻለው፡፡

ዳሩ ምንም መሄጃ የላትም፡፡ ከእንግዲህ የካትሪንን ቤት ማግኘት አትችልም፡፡ የአክስቷ ቤት ጠፍቶባታል፡ ሌሎች ዘመዶቿን አታምናቸውም ሰውነቷ ስለቆሸሽም ቤርጎ ማግኘት አልቻለችም፡

እስኪነጋ መዞር ትችላለች፡፡ አየሩ ጥሩ ነው፡፡ ዝናብ ስለሌለም ብዙም
አይበርድም፡፡ ያለማቋረጥ ከተራመደችም አይበርዳትም አሁን ያለችበት መንገድ ላይ ብዙ የትራፊክ መብራት ስላለ የምትሄድበትን መንገድ ማየት ትችላለች በየደቂቃው መኪና ይተላለፋል፡፡ ከየምሽት ክበቡ ሙዚቃና ሁካታ ይሰማታል፡፡ በየመንገዱ ሽክ ያሉ ሴቶችና በየፓርቲው ያመሹ ሱፍ ግጥም አድርገው የለበሱ ወንዶች በሾፌር በሚነዱ መኪኖች ሲሄዱ ታያለች፡፡ አለፍ እንዳለች ሶስት ብቸኛ ሴቶች አየች፣ አንዷ በር ላይ ሌላዋ ደግሞ ስልክ እንጨት ተደግፋ ቆማለች፣ ሶስተኛዋ መኪና ውስጥ ቁጭ ብላለች፡፡ በአንድ ወቅት እናቷ ኑሮ የጨለመባቸው ሴቶች ያሏት እነዚህን ሳይሆን አይቀርም፡
ድካም ተሰማት ጫማዋ ከቤት እንደወጣች ያደረገችው ነጠላ ጫማ
ነው: ያገኘችው ደጃፍ ላይ ቁጭ አለችና ጫማዋን አውልቃ እግሯን
አከከች።

ቀና ስትል ከመንገዱ ባሻገር ያለው ህንፃ ቅርፅ በመጠኑ ታያት፡፡ እየነጋ ይሆን? በጧት የሚከፈት ሻይ ቤት ታገኝ ይሆናል። ለቁርስ የምድር ጦር መምሪያው የምግብ ክፍል እስኪከፈት ትቆያለች፡፡ ምግብ ከበላች ረጅም ጊዜ በመቆጠሩ የአሳማ ስጋና እንቁላል ትዝ ሲላት በአፏ ምራቋ ሞላ፡፡

ድንገት ቁልቁል የሚያያት አመድ የመሰለ ፊት ድቅን አለባት በድንጋጤ ጮኸች፡፡ ሰውዬው ወጣት ነው፡ ታዲያስ ቆንጂት›› አላት፡

እመር ብላ ተነሳች፡፡ ሰካራም አትወድም፡፡ እነሱ ክብራቸውን የሸጡ ናቸው፡፡ ‹‹ሂድ ጥፋ ከዚህ!›› አለች ቆጣ ብላ፤ ድምጿ ግን ይንቀጠቀጣል፡ቀስ እያለ ተጠጋት ‹‹ታዲያ ሳሚኛ›› አላት፡፡
‹‹አላደርገውም!›› አለች በንዴት ከእሱ ለመሸሽ ወደኋላዋ ስትሄድ ጫማዋ ወለቀባት፡፡ ዞር ብላ ጫማዋን ፍለጋ ስታጎነብስ ወጣቱ አስካካና እጁን ጭኖቿ መሀል ሰዶ ጎነታተላት፡፡ ጫማዋን ይዛ በፍጥነት ቀጥ ብላ
ቆመችና ‹‹ሂድ ከአጠገቤ›› ብላ ጮኸች፡፡

እንደገና ሳቀባትና ‹‹ልክ ነሽ፤ ሴቶች እምቢ ሲሉኝ ደስ ይለኛል›› አለና
የጠጣውን አልኮል ሲተነፍስባት አቅለሸለሻት፡፡ አንቆ አፏን ግጥም አድርጎ
ሳማት፡፡

ሁኔታው ሁሉ የሚያስጠላ ነው፤ ሆዷ ታወከ፡፡ አጥብቆ ስለያዛት ለመታገል ቀርቶ ለመተንፈስ አቃታት፡፡ ለማምለጥ ሙከራ ብታደርግም ለሀጩን እያዝረበረበ ይስማታል፡፡ ከዚያም አንድ እጁን ወደ ጡቷ ሰደደና በእጁ ሲጨመድደው ላንቃዋ እስኪላቀቅ ጩኸቷን ለቀቀችው፡፡

‹‹ደህና፧ ልጎዳሽ አይደለም፧ አታምርሪ›› አላት፡፡ እሷ ግን ጩኸቷን ቀጠለች፡ ሰዎች ከየቦታው ብቅ ብቅ አሉ፡ ሰካራሙ ሰው መምጣቱን ሲያይ ጨለማው ውስጥ ገብቶ ተሰወረ፡ ማርጋሬትም ጩኸቷን አቁማ ለቅሶዋን
ተያያዘችው፡:

አንድ ፖሊስ ባትሪውን እያበራ መጣና ፊቷ ላይ አበራባት፡፡ ከተሰበሰቡት ሰዎች መሀል አንዲት ሴተኛ አዳሪ ‹‹እቺ ልጅ ሽሌ አይደለችም›› አለችው ፖሊሱን፡፡
ፖሊሱ ‹‹ስምሽ ማነው ልጅት?›› አላት
‹‹ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ››
‹‹እመቤት ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ ነሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡
ማርጋሬት ንፍጧን ወደ ውስጥ ሳበችና ራሷን ነቀነቀች በአዎንታ
‹‹ነግሬሃለሁ አይደል! ሸሌ አይደለችም›› አለችው ሴተኛ አዳሪዋ፡፡
‹‹ነይ እንሂድ የኔ እመቤት፣ አይዞሽ›› አላት በማጽናናት፡፡
ማርጋሬት በእጅጌዋ ፊቷን ጠርጋ ተነሳች፡:
ፖሊሱ ባትሪውን እያበራ አብረው ሄዱ፡በፍርሃት እየተርገፈገፈች ‹‹ሰውዬው እንዴት ያስፈራል!›› አለች፡፡
‹‹ሀዘኔታ የጎደለው ነው እሱ ምን ይፈረድበታል›› አለ ፖሊሱ ሳቅ እያለ፡፡ ‹‹ይህ ቦታ ከለንደን መንገዶች ሁሉ አደገኛው ነው፡፡ በዚህ ሰዓት
የምትጓዝ ሴት የምሽቱ እመቤት የሆነች ሴት ብቻ ናት፡››

ማርጋሬት ፖሊሱ ያለው ትክክል ነው አለች በሆዷ፡
‹‹ትኩስ ሻይ እንሰጥሽና ብርዱ ለቀቅ ያደርግሻል›› አላት ወደ ጣቢያው ገቡ፡፡ ከባንኮኒው ኋላ ሁለት ፖሊሶች ይታያሉ፡ አንዱ
ጎልማሳና ወደል ሲሆን ሌላው ደግሞ ወጣትና ከሲታ ነው፡፡ ክፍሉ ከጥግ
እስከ ጥግ በእንጨት ባንኮኒ ተገጥግጧል፡፡ ጣቢያው ውስጥ አንዲተ ሴት ትታያለች፡፡

‹‹እዚህ ቁጭ በይ›› አላት ፖሊሱ፡፡ማርጋሬት ተቀመጠች
👍28👎2
ከባንኮኒው ኋላ ላለው ሰውም ‹‹ሳጅን ይቺ ሴት እመቤት ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ ናት፡፡
አንድ ሰካራም አንገላቷታል›› ሲል ነገረው

በዚህ ሁኔታ ምድር ጦር መምሪያ ምዝገባ ክፍል መሄድ አልታይሽ
አላት፡፡

ይሄ ሁሉ መከራ ከደረሰባት በኋላ መምሪያው አልቀበልሽም ቢላት
መቼም ልቧ ይሰበራል፡ ነገር ግን የት ሄዳ ነው የምትታጠበው? ሲነጋ
የአክስቷ ቤትም እንኳን ያሰጋል፡፡ አባቷ እዚያ ሊፈልጓት መጥተው
ይሆናል፡

ጫማና ንፁህ ልብስ ስለሌላት ያቀድኩት ሁሉ መና ሊሆን ነው ስትል
በምሬት አሰበች፡፡

መንገድ ላይ ያገኛት ፖሊስ ሻይ በማቅረቢያ ይዞላት መጣ፡ቀዝቃዛና ስኳር ያነሰው ቢሆንም ጠጣችው፡፡ ሻዩን እንደጨረሰች ትሄዳለች::
ሳልባጅ ልብስ ሄዳ ትገዛለች፡፡ ጥቂት ገንዘብ ቀርቷታል፡ ቀሚስ፣ ሰንደል
ጫማና ፓንት ትገዛበታለች፡፡ የህዝብ ገላ መታጠቢያ ቤት ሄዳ ትታጠብና
ልብሷን ለውጣ ለምዝገባ ዝግጁ ትሆናለች፡፡

ይህን በአዕምሮዋ ስታውጠነጥን ውጭ ጫጫታ ሰማች፡ የሆኑ
ወጣቶች በሩን በርግደው ገቡ፡፡ ወጣቶቹ አለባበሳቸው ያማረ ሲሆን አንድ ሰው እየጎተቱና እየገፈታተሩ ይዘው መጡ፡፡ አንደኛው ወጣት ከባንኮኒው
ጀርባ ባለው ሃምሳ አለቃ ላይ ይጮሃል፡፡

ሃምሳ አለቃውም ‹‹ዝም በል!›› አለ ቆጣ ብሎ ‹‹አሁን ያላችሁት ኳስ
ሜዳ አይደለም ይሄ ፖሊስ ጣቢያ ነው፡፡››

አሁንም መረበሻቸውን ስላላቆሙ ሀምሳ አለቃው ‹‹አደብ የማትገዙ
ከሆነ ሁልሽንም ሰብስቤ ወህኒ አጉርሻለሁ: አሁን አፋችሁን ዝጉ! አላቸው::

ወጣቶቹ የፖሊሱን ትዕዛዝ በማክበር ዝም አሉና የያዙትን ሰው ለቀቁት፡፡ ፖሊሱ ‹‹አንተ ምን እንደሆናችሁ ንገረኝ›› ሲል አንዱን ወጣት ጠየቀው፡፡
ወጣቱም ወዳመጡት ሰው እያመለከተ ‹‹ይሄ ሰውዬ እህቴን ምግብ ቤት ጋበዛትና የበሉበትን ሳይከፍል በጓሮ በር ሾልኮ ጠፋ›› አለ፡፡

አነጋገሩ የደህና ቤተሰብ የሚመስለውን ጎትተው ያመጡትን ሰው ማርጋሬት ስታየው የምታውቀው መስሏታል፡ ወጣቱ እንዳያውቃት ተመኘች፡፡
ሌላው ሱፍ የለበሰ ወጣት ‹‹ሄሪ ማርክስ ይባላል መታሰር አለበት››
አለ፡፡

ማርጋሬት ሄሪ ማርክስ እድሜው ሃያ አንድ ወይም ሃያ ሁለት ዓመት
ይሆናል ብላ ገመተች፡፡ መልከ መልካም ነው፡፡ ልብሶቹ የተጨማደዱ
ቢሆኑም አለባበሱ ያማረ ነው፡፡ ዙሪያውን በትዕቢት ቃኘና ‹‹እነዚህ ልጆች
ጠምብዘዋል›› አለ፡፡

አንደኛው ወጣት ‹‹እኛ ጠጥተን ሊሆን ይችላል፡፡ እሱ ግን ሌባ ነው፡፡
እኪሱ ውስጥ ምን እንዳገኘን ተመልከት›› አለና ባንኮኒው ላይ አንድ ነገር
ወረወረ።

‹‹እነዚህን የወርቅ እጅ አምባሮች ከጌታ ሲሞን ሞንክፎርድ ነው
የመነተፋቸው››

‹‹ደህና›› አለ ሃምሳ አለቃው የማይገባ ጥቅም በማጭበርበር ለማግኘት
በሚል ነው ማለት ነው የምትከሱት ማለትም የምግብ ቤት ክፍያውን
አልከፈለም፣ ዕቃ ሰርቋል በሚል፡፡ ሌላስ?››
አንደኛው ልጅ ‹‹ይሄ አይበቃም?›› አለው፡፡
ፖሊሱ ልጁ ላይ በእርሳስ እየጠቆመ ‹‹አንተ ልጅ የት እንዳለህ አስታውስ፡ የሀብታም ልጅ ልትሆን ትችላለህ፣ ነገር ግን ይህ ፖሊስ ጣቢያ ነው፣ በትህትና የማትናገር ከሆነ ሌሊቱን እስር ቤት ልታሳልፍ ትችላለህ›› አለው፡

ልጁ መልስ አልሰጠም፡፡
ሃምሳ አለቃው ወደ መጀመሪያ ተናገሪው ወጣት ፊቱን አዞረና
‹‹ስለክሱ ዝርዝሩን ልትነግረኝ ትችላለህ? የምግብ ቤቱን ስምና አድራሻ፣ የእህትህን ስምና አድራሻ፣ በተጨማሪ የወርቅ አምባሩ ባለቤት ስምና
አድራሻ፡፡››

‹‹አዎ ሁሉንም ልሰጥህ እችላለሁ›› አለና መረጃውን ሰጠው፡፡

‹‹ጥሩ አንተ እዚህ ቆይ›› አለው ሄሪ ማርክስን፤ ሌሎቹን ደግሞ ‹‹ወደ
ቤት መሄድ ትችላላችሁ›› አላቸው ወጣቶቹ ግራ ገባቸው፡፡ እንኳን ሊሄዱ አልተንቀሳቀሱም:
ሃምሳ አለቃውም ‹‹ሂዱ ጥፉ ከዚህ! ሁላችሁም!›› አላቸው፡፡

ወጣቶቹ እያልጎመጎሙ ተንቀሳቀሱ፡፡ አንደኛው ወጣት ‹‹ሌባ ይዘህ ጣቢያ ስትመጣ እንዴት እንደ ወንጀለኛ ትስተናገዳለህ!›› እያለ ወጥቶ ሄደ ሃምሳ አለቃው የተከሳሹን ወጣት ቃል ተቀበለ፡፡ ሄሪ ማርክስ ለትንሽ ጊዜ ቆመና በትዕግስት ማጣት ዞረ፡፡
በዚህ ጊዜ ማርጋሬትን
አያትና እንደ ፀሀይ የሚያበራ ፈገግታ አሳይቶ ጎኗ ቁጭ አለ፡፡ ‹‹እሺ ልጅት? በዚህ ምሽት
እዚህ ምን ታደርጊያለሽ?›› አላት፡፡

ማርጋሬት ድንግርግር አላት፡፡ ሄሪ ተለወጠባት፡፡ ያ ትዕቢቱና የጨዋ አነጋገሩ የለም ልክ ፖሊሱ በሚናገርበት ዓይነት የንግግር ቅላፄ ነው
የተናገራት፡፡
ልክ ሮጦ ማምለጥ እንደሚፈልግ ሰው የበሩን አቅጣጫ መልከት
አደረገና ድምጹን አጥፍቶ በዓይነ ቁራኛ ወደሚከታተለውና እስካሁን ምንም ወዳልተናገረው ወጣት ፖሊስ ተመለከተ፡ የመጥፋት ሃሳቡ እንደማያዋጣው ሲረዳ ተወው፡፡ ወደ ማርጋሬት ዞረና ‹‹አይንሽን ማነው እንዲህ ያደረገሽ አባትሽ ናቸው ?" አላት።

‹‹ጨለማው ውስጥ መንገዱ ጠፋኝና ከፖስታ ማከማቻ ሳጥን ጋር ተጋጨሁ።

አሁን መደነቅ የእሱ ተራ ሆነ፡፡ እንደ ሰርቶ አዳሪ ሴት አድርጎ ነው የገመታት፡፡ የአነጋገር ቅላፄዋን ሲሰማ እንደተሳሳተ አወቀ፡፡ ከዚያም በጨዋ ሰዎች የአነጋገር ቅላፄ ‹‹ምን አይነት ክፉ አጋጣሚ ነው›› አላት።

ማርጋሬት ተገረመች፡፡ የቱ ነው የእሱ ትክክለኛ ባህሪው? አልኮል ጠጥቷል ፀጉሩ በሚገባ ተከርክሟል፡፡ ጥሩ ልብስ ለብሷል፡፡ ያደረገው ጌጣጌጥ ሌላ ነው፡፡ የሸሚዙ ቁልፎች አልማዝ ሲሆኑ ከዚሁ ጋር የሚሄድ የወርቅ አምባር አድርጓል: ከአዞ ቆዳ የተሰራ ማሰሪያ ያለው የወርቅ ሰዓት፣ በግራ እጁ ጣት የወርቅ ቀለበት ሰክቷል ጥፍሮቹም ንፁህ ናቸው::
ድምጿን ዝቅ አድርጋ ‹‹ከምግብ ቤቱ እውነት ሳትከፍል ወጥተሃል?›› ስትል ጠየቀችው።

አየት አደረጋትና ‹‹በእርግጥ አዎ›› አላት፡፡

‹‹ለምን?››

‹‹ምክንያቱም ሬቤካ ስለፈረሶቿ ስትናገር ከአንድ ደቂቃ በላይ የምሰማት
ከሆነ ጉሮሮዋን ለማነቅ የሚታገለኝን ኃይል መቋቋም ስላልቻልኩ››
ማርጋሬት በሳቅ ተንከተከተች፡፡ ሬቤካን ታውቃታለች፡፡ ግዙፍና
አስቀያሚ ናት፡ አባቷ ጄነራል ናቸው፡ የአባቷን ጯሂና
የወታደር ድምፅ ነው
የያዘችው፡፡

‹‹ይገባኛል›› አለች፡፡ ለመልከ መልካሙ ለሚስተር ማርክስ ተስማሚ
የግብዣ ጓደኛ ልትሆነው እንደማትችል ገመተች ማርጋሬት።

ኮንስታብል ስቲቭ ባዶውን የሻይ ሲኒ አነሳና ‹‹አሁን ይሻላል እመቤት ማርጋሬት?›› አላት፡፡

ፖሊሱ እመቤት ብሎ በማዕረግ ስሟን ሲጠራት በዓይኗ ቂጥ ሄሪ ማርክስ ምን ስሜት ሊሰማው እንደሚችል አየችና ‹‹አሁን ይሻላል አመሰግናለሁ›› አለች፡፡

ለትንሽ ጊዜ ከሄሪ ጋር ስታወራ የደረሰባትን ችግር ረስታ ነበር፡፡ አሁን
ግን ማድረግ የሚገባትን ነገር አስታወሰችና ‹‹ላደርጋችሁልኝ ነገር አመሰግናለሁ›› በማለት ቀጠለች ‹‹አሁን አንድ የምሰራው ነገር ስላለኝ ልሄድ ነው››

‹የሚያስቸኩልሽ ነገር የለም›› አለ ኮንስታብሉ ‹‹አባትሽ ሊወስዱሽ
እየመጡ ነው፡፡››.....

ይቀጥላል
👍23👎2
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ ...ለሁለት ቀን ቤርጎ ትከራይና በሚቀጥለው ቀን ትወጣለች ምድር ጦር መምሪያ ተመዝግባ ለሆቱሉ በመደወል የሆቴል ኪራዩን ደረሰኝ ለአባቷ ጠበቃ እንዲላክ ታደርጋለች፡ በረጅሙ ተነፈሰችና በሩን ከፍታ ገባች፡፡ ማርጋሬት በቀጥታ ወደ እንግዳ ተቀባዩ አመራች ከፍተኛ እረፍት ተሰማት። ፍርሃትና ቅዠቱ አብቅቷል። አንድ…»
🗻የጠንቋዩ ዋሻ🗻
🙈ክፍል 14🙈
💔💔💔🗾💔💔💔
ጠንቋዩ አቢያራ በዋሻው ውስጥ አስተዳድራቸዋለው ብሎ የሚያስባቸውንና እንደባሪያው የሚያዛቸውን አገልጋዮቹን ዛሬ በተለየ መልኩ ሰብስቧቸዋል ፣ ሁሉም የመሰብሰባቸው ምክንያት ስላልተገለፀላቸው እርስ በእርስ ከመተያየት በቀር ምንም መተንፈስ አልቻሉም አቢያራ ዙፋኔ ብሎ ከሚጠራው ትልቅ መቀመጫላይ ጥቁሩን አስፈሪ አልባሳቱን እንደለበሰ ቀያይ ዛጎሎች በእጁ ይዞ እያወዛወዘ አጎንብሶ በቀስታ የማይገቡ ቃላቶችን እያወጣ ነው ፣የአቢያራ ሴቶች እንዳቀረቀሩ ናቸው ፣ አልፎ አልፎ ኤዛ ብቻ ባልተለመደ ጭንቀት ተወጥራ በጨረፍታ ወደመሳይ አየት የምታደርገው ፣የሆነ ነገር ሸቷታል አቢያራ አንዳች ነገር ለማድረግ እስካላሰበ ድረስ በዚ መልኩ አይሰበስባቸውም ወይ በሷ ላይ ወይ በመሳይ ላይ አንዳች ጉዳት ሊደርስባቸው እንደው ተሰምቷታል ።።
ኤሊያታ እንዳቀረቀረች ከፊትለፊቷ ስለምትሰማው የአቢያራ ሹክሹክታ አንድ ነገር ለመረዳት ጥረት እያደረገች ነው ፣ ኤፍራም ግራ እንደገባት ነው ያለችው አድማስ አቢያራ የሚያዘውን ሁሉ ለመፈፀም ተዘጋጅቶ እየጠበቀ ነው ፣ መሳይ የአቢያራን አንገት የሚቀነጥስበት አንድ ስለት በድንገት እጁላይ እንዲያርፍ ተመኘ አነመስፍን ምን ያጠፋነው ነገር ይኖር ይሆን ብለው በራሳቸው ውስጥ በጨንቀት ጠፍተዋል ። ቤቱ እንዲ በፀጥታ ሲታመስ ቆይቶ ፣ ድንገት አቢያራ ብድግ ብሎ ሲቆም የሁሉም ልብ ቀጥ ያለ መሰለ ።አቢያራ ጥቂት ሲንጎራደድ ቆይቶ በአስፈሪ እና የተሰበረ በሚመስል ድምፅ መናገር ጀመረ "
"እእእእ ዛሬ እዚ የሰበሰብኳቹ አባቴ አንድ ነገር እንዳደርግ ስላዘዘኝ ነው እኔን በእናንተ ላይ የሾመኝ አባቴ የኔ ጌታ ከልጆቼ ውስጥ አንዷን መስዋት እንዳደርግ አዞኛል እንደምን እንቢ ማለት ይቻለኛል ፣በርግጥ ልቤ አዝኗል ግን አባቴ የኔንም ሕይወት ቢጠይቀኝ እሰጠዋለው ልጆቼ ለአባታቹ ጥያቄ መቼስ በደስታ መላሾች ናቹ እኔም ልክ እንደዛ ነው ያሳደኳቹ እናም አንድ ነገር ያጎደለች ልጅ አለች ከናንተ መካከል ለዚህም ነው አባቴ ወደሱ የጠራት "ብሎ አቢያራ ፀጥ ሲል
መሳይ በጥላቻና በፍራቻ ቀና ብሎ ተመለከተው ፣ይሄ ጠንቋይ ሴጣንነቱ ይበልጥ ጨምሯል ማለት ነው ሰውን እያጭበረበረ የደም ጥማቱን እየተወጣነው ፣በቃ ኤዛን ሊያጠፋት ነው ስለኔና ስለሷ አውቋል ማለት ነው ብሎ በማሰብ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ ።
አድማስ ኤዛን ዞር ብሎ አይቶ አቀረቀረ ኤዛ አድማስ ሲያያት ይሄ ድግስ ለሷ እንደሆነ በማሰብ በፍርሃት አድማስ በቀኝ እጁ የያዛትን የተሸፈነች ስለት ተመለከተች ፣ ኤልያታ ለጓደኛዋ በማዘን ዞራ አየቻት እናም በአንድ አይኗ እንባዋ ኮለል አለች እህታማችነታቸው ማብቂያው ደረሰ ልጅነታቸው የዋሻው ውስጥ የፀጥታ ኑሯቸው ታወሳት ግንአቢያራ ካለ አለ ነው በቃ ፣እነ መስፍን ጉዳዩ እነሱን ስለማይመለከት በግልግል መንፈስ ተንፍስ አሉ ፣ እነሱም የአቢያራ ተጠቂ የምትሆነው ኤዛ እንደሆነችና ለዚሁሉ ችግር የዳረጋት ደሞ ጓደኛቸው መሳይ እንደሆነ ተሰምቷቸዋል ። አቢያራ ከጎነ በጣም ቀረብ ብሎ ወደቆመው አድማስ እያየ ይበልጥ እንዲቀርበው ምልክት ሰጠው ። አድማስ ስለቱን እየነካካ ወደ አቢያራ ተጠጋ አቢያራ ለአድማስ በሹክሹክታ ተናገረ በዚ ጊዜ አድማስ ግራ በመጋባትና በድንጋጤ አቢያራ ላይ አፈጠጠ ፣አቢያራ መልህክቱን እንደዘበት ለአድማስ ከነገረ በዋላ ወደ ኤሊያታ አፈጠጠ እናም እረጃጅም ጥፍር አማ ጣቶቹን ወደ ኤልያታ ቀስሮ "የኔ ልጅ አንቺ የጌታዬ ምርጫ ነሽ "ብሎ በሚያስፈራ ድምፁ ኤልያታን እንድትቀርበው ጠራት ። እዛ የነበሩት ሁሉ ግራ በመጋባት አንዴ ኤልያታን አንዴ አቢያራን ተመለከቱ ኤልያታም አልገባትም ነገር ግን ወደሱ መንቀሳቀስ ስትጀምር አድማስ የሚያፈቅራትን ሴት በገዛ እጁ እንዲሰዋት በመታዘዙ ዘገነነውና አይደረግም ብሎ ሳያስበው ጮኽ ፣ በዚ ድምፁ ጠንቋዩ እራሱ ሳይደነግጥ አልቀረም ፣ መሳይ የአድማስን ቁጣ ሲያይ ደስ አለው በዚ አጋጣሚ አንድ ነገር ለመፍጠር እራሱን አዘጋጀ ........

ሙና መሀመድ

ይቀጥላል

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍24😱2
#ሳቤላ


#ክፍል_አርባ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...የነበሩበት ክፍል መዝጊያው ቤቱን ሊያፈርስ የሚችል በመሰለ ' እንደ ነጎድጎድ
በሚጮህ ድምፅ ተንኳኳ ወንጀለኛን አስሰሙ እንዲያመጡ ሕጋዊ ትእዛዝ
የያዙ የሕግ አስከባሪዎች እንኳን ከዚህ የበለጠ አስደንጋጭ ድምፅ አሰሙ ተብለው አያውቁም " ሪቻርድ ሔር ፊቱ ባንድ ጊዜ ዐመድ መሰለ » ዐይኖቹ ተጎለጎሉ ስሱ የራሱ ጸጉሩ ሽቅብ ቆመ የሥራ ካፖርቱን እየተርበተበተ አጥልቆ ባርኔጣውን ደፍቶ የውሸት ሪዙን አጥልቆ የሚገባበት ቁም ሳጥን ወይም የሚሾልክበት ቀዳዳ ለመፈለግ የክፍሉን ዙሪያ በዐይኑ ቃኘና ምንም ሲያጣ ወደ ሳሎኑ እሳት ሔደ።
አንድ እግሩን ከመከላከያው ብረት ላይ አሳረፈ እሳቱን እንዴት ሊያልፈው እንደሚችል ምንም ሳያስብ በጢስ መውጫው አድርጎ ሽቅብ ለመውጣት ፈለገ ከሚደበደበው በር አንድ የተቆጣ ድምፅ በቁልፉ ቀዳዳ ሲንረጨረጨር ሚስተር ካርላይል ረጋ ብሎ ትከሻውን ይዞ ወዶ ኋላ ሳበው "

ሪቻርድ ወንድ ወንድ ሽተት ይህን ፍራትህን ወዲያ ጣል "ከኔ ቤት ሆነህ ምንም አንደማይመጣብህ አልነግርኩህም ? አለው ሚስተር ካርላይል »

እኔ እኮ የለንደኑ ፖሊስ መኮንን ወታዶርች ጨምሮ መጥቶ አስከብቦኝ እንደ ሆነ ብዬ ነው።

እንዲያው ዝም ብለህ ነው " በል አሁን ዐርፈህ ተቀመጥ ኮርኒሊያ ናት " እሷ.. ደግም አንተን ከክፉ ለመጠበቅ የኔን ያህል ነው የምታስብልህ"

"ናት እንዴ ? አለ ከጫንቃው ከባድ ሽክም እንደ ወረደለት የቀለለው ሪቻርድ ግን በውጭ ልትመልሳት አትችልም ? አለው ጥርሶቹ አሁንም እየተንቀጫቀጩ

"እሷ ለመግባት ከወሰነች እኔ ልመልሳት አልችልም አንተማ ከወትሮ ታቃት የለም አንዴ ? እስከ ዛፌ ምንም አልተለወጠችም ያው ናት - -

ድርቅናዋ ከተነሣባት እሱ በውስጥ እሷ በውጭ ሆኖ በሩ እንደ ተዘጋ ማነጋገር
ዋጋ እንደሌለው ገባው " ስለዚህ ሚስተር ካርላይል በሩን ቀስ አድርጎ በጠባቡ
ከፍቶ ራሱ ወጣና መልሶ ዘጋው " በዚያ ቁመቷ ቁጣ ጨምራበት ወጋግራ መስላ
ቁማ አግኛት
,
ሚስ ካርላይል አጥሚት እንዲመጣላት አዝዛ ጉንፋኗን ይዛ ወደ መኝታ
ቤቷ ሔዳ ነበር " ወዲያውኑ ከራሷ በመጀመር የሌሊት ልብሷን መልበስ ቀጠለች የቀን ቆቧን አወለቀች
የሌሊቱን አጠለቀች " ይህ አስራሚ ቅርጽና መጠን…, ያለው ቆብ ቀደም ሲል ተገልጿል ቀጠለችና ስለ ራስ መጠምጠሚያዋ አሰበች " ሦስት ሜትር በሦስት ሜትር የሆነ ጨርቅ አመጣችና እንደ ምንም ብላ በሙሉ ሸፈነችው
የጨርቁ ዐይነት ለመጠምጠም አስቸጋሪ ስለነበር ስትጠመጥም ሲተረተርባት ስታውል እየተፈታ ሲሾልክባት ሥራው ብዙ ጊዜ ፈጀባት " የዚህ ሁሉ ልፋቷ ውጤት ግን በጣም የሚያስደንቅ ሆነ " ሥዕል ተነሥቶ በእንግሊዝ ቤተ መዘክር ቢቀመጥ የሚያሰኝ ነበር " ከጭንቅላቷ ላይ እንደ ፒራሚድ ቆመ " ጥምጥሟ ሁለት ጫፎች በግንባሯ ተንዘልዝለዋል "

ሚስ ካርላይል ከፎቅ ሆና ሻሿን ስትከብስ ፡ ስታፈርስ ስትቋጥር ስታሳምር
ወንድሟን ትታው ከመጣችበት ክፍል የንግግር ድምፅ ሰማች " በሁሉ ነገር ንቁ ብትሆንም ፡ በተለይ የመስማት ተሰጥኦ ነበራት " በመጀመሪያ ወንድሟ የሚያነብ
መሰላት ። ነገር ግን ወዲያው ሐሳቧን ለወጠች “ ማነው አብሮት ያለው ? አለች አጠገቧ መልስ ሰጭ ያለ ይመስል ድምጿን ከፍ አድርጋ ።

የራስ ጥምጥሟን አስተካክላ አበቃችና መጥሪያውን ስትደውለው ጆይስ ገባች

“ ከጌታሽ ጋር ማን አለ ?
" ማንም የለም እሜቴ ”
- መኖርማ አለ ሲነጋገርኮ እየሰማሁ ነው "

“ ኧረ እኔስ ማንም ያለ አልመሰለኝም " ደግሞ ግድግዳዎቹ በጣም ጥብቅ
ሆኑ ከሳሎን የተነገረ ነገር ከታችኛው ቤት እዚህ ድረስ መስማቱ ያስቸግራል ”
“እንማዲህ ያንቼ ዕውቀት እዚህ ድረስ ነው ከዚያ ክፍል ንግግር ካለ ቀጥታ
ድምፅ" አዚህ ይሰማል እኔ ከልምድ ዐውቀዋለሁ " ይልቁንስ ሒጅና ማን እንደ
ሆነ አይተሽ ነይ "

ሚስ ካርላይል'ጆይስን ልካ እሷ የቀን ልብሷን በሌሊት ልብስ የመተካት ሥራ
ዋን ቀጠለች » ከቀሚሷ ቀጥላ የሐር የውስጥ ልብሷን አወለቀች » ከዚያ ከሞቃቱ የውስጥ ጥብቆዋ ስትደርስ 'ጆይስ ተመልሳ መጣች "

“ እና እውነት ነው
እማማ ጌቶች ከሰው ጋር ይነጋገራሉ " ነገር ግን በሩ
ስለ ተቆለፈና ጌቶችም ሥራ ስለ ያዙ እንዳልገባ ነግረውኝ ተመልሼ መጣሁ” አለቻት
ሚስ ካርላይል ለአንጐሏ ምግብ አገኘች » በዚያ ሰዓት ማንም የውጭ እንግዳ ሊመጣ እንደማይችል በገዛ ግምቷ አረጋግጣ ከቤተሰቡ ውስጥ ማን ሊሆን እንደሚ
ችል ጥቂት አሰበች » ከሚስተር ካርላይል ጋር ቤት ዘግታ ለማውጋት የምትደፍር ያቺ የልጆች አስተማሪ ሚስ ማኒንግ ናት ብላ ደመደመች » ልጂቱ መልከኛ ስለ ነበረች
እንግዲህ የሚስ ካርላይልን መተኛት አይታ ተሠርቃ በመግባት የምትጫወት
ሚስ ካርላይል ከሚስተር ካርይል ጋር እንዳትቃረብ ትጠባበቃት ነበር ። አሁን
መሰላት በር የሚዘጋበት ምክንያት ሊኖር እንደማይችል እያውጠነጠነች
ወደ ሳሎን ወረደች "

“ከዚህ ክፍል አብሮህ ያለ ማነው ? አለችው ቆጣ ብላ

“ አንድ ለሥራ ጉዳይ የመጣ እንግዳ ነው ” አላትና ፈጥኖም " ኮርኒሊያ
መግባት አትችይም ” አላት

ሣቋ መጣባት „ “ መግባት አትችይም ? ! "

“ በውነቱ ባትገቢ ይሻላል ፤ እባክሽ ተመለሽ ፤እዚህ ቁመሽ ጉንፋንሽን ታጠነክሪዋለሽ ።

የለም በሥራህ አለማፈርህን ለማወቅ እፈልጋለሁ አንተ ያገባህ ሰው ነህ ልጆች ከቤት አሉህ አንተ እንደዚሀ ካለው ቅሌት ውስጥ ትገባለህ ብዬ አልጠረ
ጥርም ። ከራሴ ይልቅ አንተን አብልጬ አምን ነበር

ሚስተር ካርላይል ዐይኑን አፍጦ ቀረ ።

“ዘወር በልልኝ አሁን አስወጣታለሁ ከዚህ ቤት ወጥታ ደግሞ ነገ እየዞረች ትለምናለች ። ሁለት ደፋሮች እግሬ ከመውጣቱ መቸም ሔዳለች ብላችሁ ቤት
ዘግታችሁ መቀመጥ ! አሁን ወግድልኝ ዘወርበል አርኪባልድ እገባለሁ ! ”

ሚስተር ካርላይል ደግሞ እንደዚህ ሣቁ መጥቶበት አያውቅም ። እኅቴ
ደግሞ ሁኔታውን አይታ የበለጠ ስትናደድ አስተማሪይቱ ከግራጫዉ ሳሎን ወጥታ የግድግዳ ሰዓት ተመልክታ ተመልሳ ስትገባ አየቻት ።

“ እንዴ እዚያ ናትሳ ! እኔኮ ካንተ ጋር ያለች መሰለኝ ”
ሚስ ማኒንግ እኔ ዘንድ ነች ብለሽ ነው ! ? ይህ ነው በአእምሮሽ ሲመላለስብሽ
የነበረው ሐሳብ ? እውነትም ጉንፋኑ አእምሮሽን ጋርዶታል
ግድ የለም ያም ሆነ ይህ ያለውን ሰው ገብቸ አያለሁ ” አለችው

ምን ቸገረኝ ግድ ልግባ ካልሽ ግቢ » ግን ኀዘን እንጂ ደስታ እንደማታዬ
አስቀድሚ ላስጠንቅቅሽ " ከውስጥ ያለችው ሴት አይደለችም " ወንድ ነው ተፈልጎ እንዲያዝ የተበየነበት ! ካሁን አሁን ፖሊሶች ተከታትለው መጡብኝ እያለ የሚርበተበት አዳኝ እንዳሳደደው አጋዘን እየተሳደዶ በመስኮት ዘሎ የገባ ሰው ነው ከውስጥ ያለው ማን መሆኑን ዐወቅሽው ?”

አሁን ደግሞ አፍጥጦ መቆሙ የሚስ ካርይል ተራ ሆነ

ያንቺው ዘመድ ሪቻርድ ሔር ነው " በዚህ ነፍስ የሚያወጣ አስጨናቂ ሌሊት የሚጠጋበት ጣራ የሚገባበት በር የለም ዝም ብላ ስትተክዝ ቆየችና በሩን እንዲከፍት ምልክት ሰጠች

መቸም እንደዚህ ሆነሽ ለብሰሽ የምትገቢ አይመስለኝም

“ለምን በልጅነቱ ዐስር ጊዜ ስገርፈው ለነበረው ለሪቻርድ ሔር ነው ደሞ
የምጨነቅለት ? አለባበሱ እንኳን እሱም ከኔ አይሻልም እሱ ወደዚህ መምጣቱ ግን ፍጹም ዕብደት ነው
👍141
እንድትገባ ሲያሳልፋት በሩን እንድትወጋ ነገራት ። እሱ ወደ ኋላ ቆርቶ ፒተርን ጠርቶ ለሁለት ሰው ራትና አንድ ማብረጃ ቢራ ከምግብ ቤቱ ጠረጴዛ እንዲቀርብ አዘዘ ከአንድ እንግዳ ጋር ምናልባትም ብዙ ሊያስመሽ የሚችል ሥራ ስለ አለበት ሰራተኞች ሁሉ እንዲተኙ ካልደወለ በቀር ማንም ወደሱ አካባቢ በመምጣት እንዳይረብሸው አስጠንቅቆ ወደ ነበረበት ክፍል ተመለሰ።

ሪቻርድና ሚስ ካርላይል እንደ ተፋጠጡ አገኛቸው
ሪቻርድ በርግጥ በሕይወቱ ብዙ ዐይነት አስደናቂ አለባበሶችን አይቷል ነገር
ግን እስከ ዛሬ ካሁኑ የሚስ ርላይል አለባበስ ጋር የሚስተካከል አላጋጠመውም እንዲያውም እንደሷና እንደሱ ሆነው የለበሱ ሁለት ሰዎች እንዳሁኑ ፊት ለፊት ተጋጥመው አያውቁም ። እሷ ጥቁር ጫማ ጥቁር የእግር ሹራቦች ከባቷ ድረስ የወረደ የሌሊት ኮት ፡ ይህን ይመስላል ብሎ ለመግለጽ የሚያስቸግር ያንገት ልብስና ሲያዩት የሚያስቀይም ከዚያ በፊት በዚች መሬት ተመሳሳይ ያልተኘለት የራ ጥጥም አድርጋ እሱ ደግሞ
ከመናኛ የተልባ እግር የተሠራ ፡ አዝራሮቹ በከፊል
የተበጠሱበት ልብስና ጭርምትምት ያለ ባርኔጣ ደፍቶ : ቸምቸም ያለ ሪዝ፡ በፍራት የሚንቀጠቀጡ እጆች ፡ በድንጋጤ ዱቄት መስሎ የነጣ ፊት ! በውጭ አገር ብዙ እሥቂኝ የሆኑ የፈንጠዝያ ትርዒቶች ተመልክቻለሁ ነጋር ግን ከነዚህ ሁሉቱ ጋር
የሚደርስ አላየሁም ። በኒስ ወይም በሮም የትርዒት ሰገነቶች ቢቀርቡ ማንም ሳይጠጋቸው ያሸንፉ ነበር ።

“ እባክሽን በሩን ዝጊው ኮርኒሊያ ብሎ ጀመረ ይንቀጠቀጥ የነበረው ሪቻርድ በአለባበሷ ተገርሞ ከእግር እስከ ራሷ ሲያያት ቆይቶ ካለፈለት በኋላ ።

“ መዝጊያውስ ተዘግቷል አንተ ግን ወዲህ ምን አመጣህ ... ሪቻርድ ?
ከዕብድ ትብሳለሀ ።

“ ከሎንደን የቦው ስትሪት ፖሊሶች አሳደዱኝ ” አላት ።

“ ከዚህ በፊት አለመከታተላቸውም ደጎች ቢሆኑ ነው ። አሁን ነገ በዌስት ሊን መንገዶች ጥሩንባ እየነፋህ መምጣትህን ልትለፍፍ ነው?”

“ ቢቻለኝ ማንም እንዳያየኝ ነው የምፈልገው ”

“ ዌስት ሊን ከመጣህ የመምጣትህ ወሬ መሰማቱ ስለማይቀር በመንገድ ወጥተህ ከመለፈፉ አያንስም " ከዚህ በፊት እዚህ ታይተሃል ተብሎ ስንትና ስንት ወሬ
ነበር " ይህ ወሬ እንዴት እንደ ወጣ ግን እንጃ

“ የምኖረው ኑሮ በጣም አስቸጋሪ ነው ምንም ልምድ ባይኖረኝም፡እንደ
ምንም ብዬ አንዳንድ ሥራዎች ለመሥራት እፈልግ ነበር ። ነገር ግን ተሰድጄ መብቴን ታግጀ ተዋርጀና ቀን ለቀን ተሳቅቄ ተጨንቄ ከመኖር ፈጣን ሞት ቢወስዶኝ እመርጣለሁ” አላት ሪቻርድ ።

“ አንተው በገዛ እጅህ እዚያች ኃፍረተ ቢስ ከውካዋ ቃፊ ዘንድ እየተመላለስክ
ያመጣኽው መዘዝ ነው ማንንም መውቀስ አትችልም

“ እኔን ከዚህ ሁሉ ጣጋፈጣ የከተተኝ ይህ ሳይሆን ያ ሰይጣን ሆሊጆንን ስለ ገዴፈደለው ነው

“ በውነት ገዳዩ ሌላ ሆኖ በግልጽ የይታወቅበት ምክንያት አይገባኝም "
አንድ ቶርን የተባለ ሰው የገደለው እያልክ ፊ
ታወራለህ የምትለው ሰው ግን ማንም አይቶት ወይም ስለሱ ሰምቶ አያውቅም ራስህን ንፁሕ ለማድረግ ስትል የፈጠርከው ነው”

የፈጠርከው አለ ሪቻርድ ጋል ብሎ በፖሊሶች የሚያሳድደኝኮ እሱ
ነው " በዚህ ሁለት ሳምንት ውስጥ ሦስት አራት ጊዜ አይቸዋለሁ ”

ታዲያ ለምን ነግሩን አስገልብጠህ ፖሊሶችን በሱ አታሰማራበትም?”

"እሱማ እንዳይሆን እሱ ለመግደሉ ከኔ ቃል በቀር ሌላ መረጃ ስለሌለኝ ጥሩ አይደለም እሱ ያን ጊዜ ከአፊ ጋር ተሻርኮ ነበር " አሁንም ቢሆን ከሷ ጋር
ጠንካራ ትስስር ባይኖረው ' በግድያው ጊዜ እሱ አብሯት እንደ ነበር ለሚስተር ካርላይል አትነግረውም ነበር " ነገር ግን አብሯት አልነበረም ሰውየውን የገደለው አሱ ነው " "

“ ምናለ ! ይህች ኃፍረት የለሽ የድፍረቷ ድፍረት ሰተት ብላ እዚህ ድረስ
መጣች ግን እኔ ከቤት ባለመኖሬ ዕድሏን ታመስግን አርኪባልድም ካንተ አይሻልም " አይረባም ፡ ያቺን እየተሽቀረቀረች ከማበድ በቀር ምንም ቁም ነገር የሌላት መለኮን ሰው ብሎ ሁለት ቀን ማረፊያ ሰጥቶ አስተናገዳት "

“ አፊ እኮ ከጥቂት ጊዜ በፊት ጀምሮ ቶርን ያለበትን አለማወቋን ነግራኛለች”
አለ ሚስተር ካርላይል : ካርላይል የእኅቱን ነቀፌታ እንዳልሰማ በመተው " ግን
ረጂመንቱ” ወደ አለበት ውጭ አገር የመሔዱን ወሬ ሰምታለች »

“ ስለሱ ምንም ነገር አለማወቋ እውነት ከሆነ በተለይ ለሷ ጥሩ ነው ” አለ
ሪቻርድ " እሱ ግን ኢንግላንድ ውስጥ ነው ያለው ውጭ አገር አለመሆኑን አሳምሬ
ዐውቃለሁ "

“ ኧረ ለመሆኑ ዛሬ የት ልታድር ነው ?” አለችው ሚስ ካርላይል ሌላውን
ነገር ትታ ።

“እኔ እንጃ! አለ ኩምሽሽ ባለ አነጋገር " እኔ ከበረዶው ቁልል ብተኛና በበነጋው እዛው ድርቅ ብዬ ብገኝም ምንም አይደለም "

እንደዚህ ለማድረግ አስበህ ነው የመጣኸው ? አለችው

“ እሱስ አልነበረም” አላት ልስልስ ባለ አንደበት ' “ ከዚህ ሦስት አራት ኪሎ ሜትር ያህል ራቅ ብሎ አንድ የማውቀው የማያሰጋ ቦታ አለ ስለዚህ
ሐሳቤ ከሚስተር ካርላይል ጥቂት ሽልንጐች ባገኝ እዛው ተከራይቸ ለማደር ነበር "

"ሪቻርድ አለው ሚስተር ካርላይል „ “ ይኸን በመሰለ ሌሊት ውሻን እንኳን ቢሆን ሦስት አራት ኪሎ ሜትር ይሒድ ብዬ አላስወጣም ከዚሀ ታድራለህ።

" ግን” አለች ሚስ ካርላይል የቤት ሠራተኞች የሱን መኖር ሳያውቁ
መኝታውስ እንዴት ይዘጋጅለታል ? ከተዘጋጀ በኋላስ በየት አድርጎ ገብቶ ይተኛል? አለች " ሚስ ካርላይል መቸም ጠባይዋ ነው አስቸጋሪ እንጂ የልብ ደግነት ኢያንሳትም ነበር " ስለዚህ ችግር ከወንድሟ ጋር ተወያዩና ' ቢሆንም ጆይስ ማወቅ እንዶገሚባት ከዚያ በፊት ግን ሪቻርድ ያባቷ ገዳይ ያለመሆኑን ሚስተር ካርላይል እንዲ
ያሳምናት ተነጋገሩ

ሚስተር ካርላይል • የተቆለፈውን በር ከፍቶ ወጣ" ጆይስን ጠራና አንድ ክፍል ውስጥ ይዟት ገባ " አባቷን የግደለው ሪቻርድ ስለ መሆኑ ምንም ጥርጣሬ እንዳልነበራት ያውቅ ነበር " አሁን እሱ ያን ሥር የሰዶደ እምነቷን ሊያስለውጣት ፈለገ ጆይስ አለና ጀመረ አፊ ከሪቻርድ ሔር ጋር ኮብልላ አብራው ስለመኖሯ የነበረሽን ጽኑ እምነት ትዝ ይልሻል እኔ ደሞ በጣም እጠራጠር እንደነበር ብዙ ጊዜ ነግሬሽ ነበር እንደዚ ስልሽ ነገሩ ከልቡ እንዲቆይ አስፈላጊ መስሎ ስለ አገኘሁት እንጂ ከትክክለኛ ምንጭ አሰጋግጭ ነበር አሁን ግን አብራው እንዳልነበረች አምነሽ የለ።

"አሁንማ በደንብ አምኛለሁ"

እንዲህ አየሽ ጆይስ
ድሮውንም የኔ ሐሳብ በሚገባ መሰማት የነበረበት ነው አሁን ደም ስለ ሌላ ጉዳይ ያለሽን እምነት ለማሰጣል ልሞክር ነው
ስለዚህ አንቺም በቂ ምክንያት እንዳለኝ ካረጋገጥኩልሽ ታምኛለሽ ?

እርስዎ ከውነት በቀር እንደማይናገሩ እርግጠኛ ነኝ ጌታዬ ስለዚህ የእርስዎ አስተያየት ትክክለኛ መሆኑን ዐውቀዋለሁ " አለች ጆይስ „

“ እንዲያው ሰማሽ ... አባትሽን የገለው ሪቻርድ ሔር ነው መባሉን እንደ
ማላምንበት ልንገርሽ ሪቻርድ ሔር በዚህ ጕዳይ ልክ እንዳንቺና እንደኔ ንጹህ
ነው ለዚህም በቂ ምክንያት ካገኘሁ ብዙ ዓመቴ ነው "

“ኧረ እ!... ታዲያ ማን ገደለው ? ”

“ እኔ በደንብ አንደማምነው ያ የአፊ ፍቅረኛ ነው " ያ ቶርን የተባለው አለባበስ አሳማሪ


“ እና ለዚህ እምነትዎ በቂ ምክንያት አለኝ አሉ ?

“ አዎ ደንበኛ ምክንያት አለኝ - ከተረዳሁት ብዙ ዘመኔ ነው " አንቺም እኔ እንደማምነው ብታምኚ ደስ ይለኛል "
👍10
“ ግን ጌታዬ .... እሱ ከደሙ ንጹሕ ከሆነ ላምን ሸሸ? ለምንስ እንደ ሸሸ ጠፍቶ ቀረ ?

“ አዎ Iልክ ነሽ ነገሩን ሁሉ ያበላሸውም ይኸው አድራጐቱ ነበር " እዚ!
ውሉ ያደረስው ፈሪነቱ ነው " ኋላም ለመመለስ ፈራ " ሰው በሱ ላይ ካሳዶረው የጥርጣሬ ጥላቻ የሚላቀቅ አልመሰለውም ነበር " ጆይስ ለሁሉም እሱን ብታምኚውና ታሪኩን ከራሱ ብትሰሚ ደስ ይለኛል ”

“እሱማ እንዴት ይቻላል ?እሱም እንግዲህ ደፍሮ እዚህ ግድም ብቅ አይልም'

“ እሁን እዚህ ነው ያለው "

ጆይስ በጣም ደነገጠችና ሚስተር ካርይልን ቀና ብላ አየችው "

• አዎን እዚህ ከዚህ ቤት ውስጥ " አላት ሚስተር ካርላይል “ከዚህ ተጠግቷል ስለዚህ ከዚህ ቤት ለሚቆይባቸው ጥቂት ሰዓቶች በተቻለ መጠን ደብቀንና ጠብቀን እንድስተናግደው ያስፌልጋል ይኸንንም እምነት ባንቺ ላይ መጣሉ
እንደሚሻል አመንኩበት " በይ አሁን ነይ ግቢና እይው

ገብታ ተግናኙና ስትጠይቀው ሲመልስላት ቆዬ » ሪቻርድ በጋለ ስሜት ሲናገር ጆይስ ጥያቄ በጥያቄ ስታከታትልበት የሚስ ካርላይል ምላስም የነሱን ያህል ሲንቀለቀል ድብልቅልቅ አለ " ሚስተር ካርላይል ብቻ ዝም ብሎ ያዳምጥ ጀመር በመጨረሻ ጆይስ በሪቻርድ ላይ የነበራትን ጥርጣሬ ወደ ካፒቴን ቶርን አዞረች "

ከዚያ በኋላ የሚተኛበት ክፍል ተመረጠለትና ጆይስ መኝታውን ልታዘጋጅለት ሔደች ሚስ ካርላይል ወደ መኝታዋ ገባች ሚስተር ካርላይል ለራት አብሮት ተሸምጦ ብላ እያለ በደንብ ጋበዘው " ሪቻርድ የሚያደፋፍር ጥሩ አቀባቀል
ጥሩ እሳት አንድ ብርጭቆ ትኩስ ብራንዲ በውሃ ሲገኝ ጊዜ ሰውነቱ ተፍታናፈታና
ወንበሩ ላይ እንደ ተቀመጠ እንቅልፍ ወሰደው " አምስት ደቂቃ ሳይቶmቆይ መቃዠት
ጀመረ።

“ ኧረ እኔ አይዶለሁም ! እኔን ብትወስዱኝ ምንም አይጠቅማችሁም ምክንያቱሜ እኔ አደለሁማ
ሌላ ሰው እኮ ነው። ያ እንኳ

" ሪቻርድ ! ሪቻርድ ! አለው ሚስተር ካርይል ረጋ ብሎ
ሪቻርድ ነና ይኖቹን በድንጋጤ እንዳፈጠጡ የምግብ ጠረጴዛውን እሳቱን ሚስተር ካርይልን ሲያይ ልቡ ረጋ መንፈሱ ተመለሰ ወይ ጉድ ይዘውኝ
ሲሔዱ በሕልሜ አይቼ እኮ ነው " ሕልሞች አሥቂኝ ናቸው ” አለው "

ከዚያ ጆይስ መኝታውን አዘጋጅታ ስትጨርስ መጥታ ወሰዶችውና ከሻማ ጋር
ካስገባችው በኋላ ዘግታበት ተመለሰች ".....

💫ይቀጥላል💫
👍14👎1
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ስድስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

...‹የሚያስቸኩልሽ ነገር የለም›› አለ ኮንስታብሉ ‹‹አባትሽ ሊወስዱሽ
እየመጡ ነው፡፡››

የማርጋሬት ልብ በድንጋጤ ቀጥ አለ፡ እንዴት ሊሆን ይችላል? አሁን
ያለችበት ቦታ አባቷ የማያውቁት ስለሆነ ደህነኛ ቦታ ነው ብላ ተማምና ነበር፡፡

አባቷን ዝቅ አድርጋ ነበር የገመተቻቸው፡ በዚህ ደቂቃ ውስጥ ሊይዟት ይመጣሉ! ሃሳቡ አንቀጠቀጣት ‹‹የት እንዳለሁ እንዴት አወቀ አባባ?›› አለች፡፡

ወጣቱ ፖሊስ በኩራት ‹‹ትናንት ማታ ስለመጥፋትሽ የቴሌግራም መልዕክት ደርሶን ነበር፡፡ ስመጣ አየሁት፡፡ በጨለማ የመጣሽ ጊዜ
አላወቅኩሽም ነበር፡፡ ስምሽን ግን አስታወስኩት፡፡ ከተገኘሽ ለጌታ ኦክሰንፎርድ
እንዲነገራቸው ቴሌግራሙ ያዛል፡፡ እዚህ እንዳመጣሁሽ ለአባትሽ ደወልኩ››

ማርጋሬት ብድግ አለች፧ ልቧ በጣም ይመታል፡፡ ‹‹እሱን አልጠብቅም
አሁን ነግቷል›› አለች፡፡

ፖሊሱ ስጋት ገባው ‹‹ትንሽ ቆይ›› አለ፡፡ ዞር አለና ‹‹ሃምሳ አለቃ እመቤት ማርጋሬት መሄዴ ነው እያለች ነው›› ብሎ ነገረው፡፡
ሄሪ ማርክስ ‹‹እዚህ ይዘው ሊያቆዩሽ አይችሉም ባንቺ እድሜ ከቤት ጠፍቶ መሄድ ወንጀል ተደርጎ አይቆጠርም፡፡ መሄድ ከፈለግሽ ቀጥ ብለሽ
ሂጂ›› አላት፡፡

ሃምሳ አለቃውም ‹‹ነገር ግን ጫማ የለሽም፤ ስቶኪንግሽ ተቀዳዷል፡፡ አባትሽ ጋ ልደውልልሽ›› አላት፡፡
ማሰብ ጀመረች፡፡ ጣቢያ እንደደረሰች ነው ለአባቷ ስልክ የተደወለው፡፡
አሁን አንድ ሰዓት አልሞላውም ማለት ነው፡፡ አባቷ ደግሞ ከዚህ በኋላ
እዚህ ለመድረስ ቢያንስ ከአንድ ሰዓት በላይ ይፈጅባቸዋል፡ ‹‹ደህና›› አለች ለደጉ ፖሊስ ‹‹አመሰግናለሁ፡፡››

ሄሪ ወደ ፖሊስ ስታዘግም አየና ‹‹ጅል›› አላት፡፡
ፖሊሱ አንድ ትንሽ ክፍል ውስጥ ወስዶ አስገባት፡፡ ወንበሮቹ ተራ ናቸው፡
አንድ አግዳሚ ወንበር ይታያታል፡፡ ከላይ ማቀፊያ የሌለው አምፑል ተንጠልጥሏል፡ መስኮቱ በብረት ፍርግርግ ተዘግቷል፡ ሃምሳ አለቃው ይህ
ክፍል ከባለጉዳይ መቀበያው ክፍል የተሻለ ነው ብሎ እንዴት እንዳሰበ
አልገባሽ አላት፡፡ ልትነግረው ዞር ስትል በሩን ፊቷ ላይ ጠረቀመው፡፡ አንድ
ክፉ ነገር እንዳለ በልቧ ጠረጠረችና ፍርሃት ገባት፡፡ ተወርውራ በሩ ጋ ሄዳ
ለመክፈት ታገለች ከዚያም ፍርሃቷም እውነት መሆኑን በሩ ሲቆለፍ አረጋገጠች፡፡ የበሩን እጄታ በሃይል ነቀነቀችው፤ ነገር ግን በሩ የሚከፈት አልሆነም በተስፋ መቁረጥ በሩ ላይ ልጥፍ አለች፡፡

ከውጭ በኩል ሳቅ ይሰማታል፤ ከዚያም ሃሪ ‹‹እናንተ እርጉሞች›› ሲል
ተሰማት ‹‹አፍክን ዝጋ›› አለው ፖሊሱ፡፡

‹ምንም መብት የላችሁም ልጅቷን ለማቆየት፤ አንተም ታውቃለህ አለው።

‹‹አባቷ የተከበሩ ሰው ስለሆኑ ነው እንደዚህ ያደረኩት›› አለ፡

ማርጋሬት ያሰበችው ባለመሳካቱ በምሬት ተንገበገበች፡ የማምለጥ
እቅዷ ውሃ በልቶታል። ይረዱኛል ብላ የገመተቻቸው ሰዎች አታለዋታል ለትንሽ ጊዜ ነፃ
ነበረች አሁን ግን ነፃነቷ አብቅቷላተል ምድር ጦር
መምሪያው መሄድ አለመቻሏ አንገበገባት
ከጦርነቱ ለመሸሽ የፓን አሜሪካ ንብረት በሆነችው አይሮፕላን ተሳፍራ ኒውዮርክ ልትሄድ ነበር። ይህን ያህል ደክማም እድሏ አልሰምር አላት፡፡

ከብዙ ቆይታ በኋላ ከበሩ ወደ መስኮቱ ሄደች። በመስኮት አጮልቃ
ስታይ ምንም ነገር የማይታይበት ጓሮና የሸክላ ግድግዳ ብቻ ነው::
በሽንፈትና በአቅመቢስነት መስኮቱ ጋር ተገትራ የአባቷን መምጣት
ከመጠባበቅ በስተቀር ምንም ምርጫ አልነበራትም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኤዲ ዲኪን ለአይሮፕላኑ የመጨረሻ ፍተሻ አደረገ እያንዳንዳቸው የ1500 የፈረስ ጉልበት ያላቸው አራቱ ሞተሮች የተቀቡት ዘይት ያብለጨልጫል፡ እያንዳንዱ ሞተር የሰው ቁመት አለው። ኤዲ እያንዳንዱን የሞተር ክፍል መርምሮ ሲጨርስ ዘጋጋና ከመሰላሉ ላይ ወረደ። አይሮፕላኑ ለበረራ ሲዘጋጅ ቱታውን ያወልቅና ሰውነቱን ታጥቦ የአየር መንገዱን የበረራ ዩኒፎርም ይለብሳል።

ከአይሮፕላን ማረፊያ ወደቡ ወጥቶ ሲሄድ ፀሀይ ገና አልጠለቀችም፡ከዚያም የስራ ባልደረቦቹ ወደሚገኙበት ሆቴል አመራ: በአይሮፕላኑና
በሚሰራው ስራ ይኮራል። አትላንቲክ አቋራጭ በረራ ከሁሉም የበረራ ስራ
የበለጠ ስለሆነ አየር መንገዱ ያሰማራው አሉ የሚላቸውን የበረራ ሰዎች
ነው።

ሆኖም ይህን ስራ በቅርቡ ለመተው አቅዷል፡ አሁን እድሜው ሰላሳ ሲሆን ትዳር ከያዘ ዓመት ሆኖታል። ሚስቱ ካሮል አን ነፍሰ ጡር ናት ይህ ስራ ለወንደላጤ ምንም አይልም እሱ ግን ከቤተሰቡ ርቆ መኖር
አይፈልግም፡ የራሱን ስራ ለመጀመር በቂ ገንዘብ አጠራቅሟል፡ አሜሪካ
ውስጥ ይህን ስራ ለመስራት የሚያስችለው አየር ማረፊያ አለ፡፡" አይሮፕላን ይጠግናል፣ ነዳጅ ይሸጣል፡ በኋላም አይሮፕላን ገዝቶ ያከራያል፡

ሆቴሉ ውስጥ ሲገባ ረዳት ኢንጂነሩን ሚኪን አገኘው፡ ሚኪ ተጫዋች ሲሆን ኤዲን በችሎታው ይወደዋል። ሚኪ ስልክ እየተነጋገረ ሳለ ኤዲንን
ሲያይ ‹‹እድለኛ ነህ አሁን መጥቷል ላገናኝህ›› አለው ለደዋዩ ‹‹አንተን ነው
የሚፈልገው›› ብሎ የስልኩን መነጋገሪያ ለኤዲ ሰጠና ብቻውን መነጋገር
እንዲችል ጥሎት ሄደ።
ኤዲም ስልኩን ተቀበለና ‹‹ሄሎ?›› አለ፡

‹‹ኤድዋርድ ዲኒኪን ነህ?›› ብሎ ጠየቀ ደዋዩ፡፡

ኤዲ ግንባሩን በግርታ ቋጠረ፡ በስልክ የሚሰማው ድምጽ አዲስ ሆነበት ከዚህ በፊትም ማንም ኤድዋርድ ብሎት አያውቅም፡፡ ‹አዎ ነኝ
ማን ልበል?›› አለ፡

‹‹ቆይ ትንሽ ጠብቀኝ ባለቤትህን ላገናኝህ አጠገቤ ነው ያለችው›› የኤዲ ልብ ተንጠለጠለ ካሮል አን ለምንድነው ከአሜሪካ የደወለችልኝ ችግር አለ ማለት ነው?› ሲል ተጨነቀ፡፡

ከአፍታ በኋላ የካሮል አን ድምጿ ተሰማ ‹‹ኤዲ›› አለች እምባ እየተናነቃት፡

‹‹እንዴት ነሽ ማርዬ ምን ሆነሻል?››

ካሮል አን የባልዋን ድምጽ ስትሰማ ለቅሶዋን ለቀቀችው።

ኤዲ በዚያች ደቂቃ ውስጥ ክፉ ነገር አዕምሮው ውስጥ አቃጨለበት፡
‹ካሮሌ ላይ ምን ደርሶባት ይሆን? ውርጃ ገጠማት ይሆን? ቤቱ ተቃጠለ?
ማን ይሆን የሞተው? የሚሉ ሃሳቦች በአንድ ላይ መጡበት፡፡

«ካሮል ተረጋጊ ደህናም አይደለሽ?››

‹‹አይ ምንም አልሆንኩም›› አለች እየተነፋረቀች፡

‹‹ታዲያ ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሺው?›› አለ ሆዱ በፍርሃት እየተንቦጫቦጨ፡

‹‹ምን ተፈጠረ ንገሪኝ የኔ ውድ?››

‹‹እነዚህ ሰዎች እቤት መጡ››

ኤዲ ይህን ሲሰማ በድንጋጤ የበረዶ ክምር ሆነ ‹‹የምን ሰዎች? ምን
አደረጉሽ?››

‹‹መኪና ውስጥ ከተው ወሰዱኝ››

‹‹ወይ አምላኬ! ማን ናቸው?›› ንዴቱ ደረቱ ላይ ውጋት ለቀቀበትና
መተንፈስ አቃተው፡

‹‹ጎድተውሻል?››

‹‹አይ ደህና ነኝ፡ ነገር ግን ኤዲ ሰዎቹ ያስፈራሉ››
ምን እንደሚል ጨነቀው፡ ብዙ ነገሮች አዕምሮው ውስጥ መጡበት፡፡"
የሆኑ ሰዎች ሚስቱን አግተዋታል፡፡ ምንድነው ነገሩ? በመጨረሻም
‹‹ለምን?›› ሲል ጠየቀ፡፡

‹‹ምክንያቱን አልነገሩኝም››

‹‹ምን አሉሽ?››

‹‹ኤዲዬ የሚሉህን በሙሉ አርግላቸው፡፡ የማውቀው ይህን ብቻ ነው››

ንዴትና ፍርሃት እየተፈራረቁበት ‹‹አንቺን ከሚያሰቃዩብኝ ያሉትን
አደርግላቸዋለሁ›› አለ፡፡

‹‹እውነት?››

‹‹አዎ የኔ ማር››

‹‹ተመስገን አምላኬ ላንተ ምን ይሳንሃል›› አለች ካሮል አን።

‹‹መቼ ነው ያገቱሽ?››

‹‹ከሁለት ሰዓት በፊት››

‹‹አሁን የት ነው ያለሽው?››

‹‹ከኛ ቤት ብዙም አይርቅም.›› ብላ ሳትጨርስ የድንጋጤ ጩኸት
አሰማች፡፡
👍212
«ካሮልዬ ምን አደረጉሽ? ደህናም አይደለሽ?›› ሲል ጠየቀ፤ ሆኖም መልስ አላገኘም፡፡ ኤዲ በሽብር ተውጦ መዳፉ ደም እስኪያግት ድረስ የስልኩን እጀታ ጨምድዶ ይዞ መልስ ጠበቀ፡፡ ከዚያም የመጀመሪያው
የወንድ ድምፅ ተመልሶ መጣና ‹‹ልብ ብለህ አድምጠኝ ኤድዋርድ››

‹‹አንተ ራስህ አድምጠኝ›› አለ ኤዲ በንዴት ‹‹ጫፏን ትነካና የገባህበት ገብቼ እገልሃለሁ፧ ህይወቴ እስካለች ድረስ፤ አምላክ ምስክሬ ነው አልለቅህም!! ያገኘሁህ ጊዜ አንተ ዱርዬ በእጄ ነው አንገትህን ጠምዝዤ የምቀነጥሰው ገባህ?›› አለው፡

ስልክ የደወለው ሰው እንደዚህ አይነት የስድብ ናዳ ያልጠበቀ በመሆኑ ዝም ብሎ ቆይቶ ‹‹እንደዚህ አትሁን፤ ሩቅ ነው ያለኸው›› አለው፡

ሰውዬው እውነቱን ነው፡፡ ኤዲ ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ‹‹ፀጥ ብለህ አድምጠኝ›› አለ ሰውዬው፡፡

ኤዲ ምላሱን እንደምንም ብሎ ሰብስቦ ማዳመጥ ጀመረ፡

‹‹አይሮፕላኑ ላይ የተሳፈረ ቶም ሉተር የተባለ ሰው መመሪያ ይሰጥሃል››

‹‹ምን እንዳደርግላችሁ ነው የምትፈልጉት?››

‹‹አፍህን ዝጋ! ሁሉንም ነገር ሉተር ይነግርሃል፤ ሚስትህን በህይወት ማግኘት ከፈለግህ! የሚሻልህ የእሱን ትዕዛዝ መቀበል ብቻ ነው››

‹‹እንዴት ነው እሱን የምለየው?››

‹‹አንድ ሌላ መመሪያ፤ ለፖሊስ እንዳትጠቁም፡ ምንም አይጠቅምህም፤
ከጠቆምክ ሚስትህን የማደርገውን አውቃለሁ››

‹‹አንተ ወንበዴ አገኝሃለሁ!. . .

ስልኩ ኤዲ ጆሮ ላይ ተዘጋ፡፡


ይቀጥላል
👍142
👉የጠንቋዩ ዋሻ👉
🗾ክፍል 15🗾

አቢያራ የአድማስን ያልተለመደ ተቋውሞ ሲሰማ ያልጠበቀው ነገር ነውና ለመጀመሪያ ጊዜ ደንገጥ ብሎ አድማስ ላይ አይኑን ተከለ ፣ ኤልያታ በአቢያራና በአድማስ መካከል እንደቆመች ናት ግራ ገብቷታል ምን እንዳጎደለች እራሷን ደጋግማ ብጠይቅም ምንም አይነት ጥፋት ማስታወስ ሳትችል ቀረች ፣ አድማስ ፈርጠም እንዳለ ነው ሁኔታው ሁሉ ሴት የላከው ሞት አይፈራም እንዲሉ 'አይነት ነው ፣ እነመስፍን የአቢያራንና የአድማስን ፍጥጫ በፍርአትና ከአሁን አሁን ምን ሊከሰት ነው በሚል እየጠበቁ ነው ፣ መሳይ አንዳች ግርግር እስኪነሳ እና አቢያራን ማጥቃት የሚችልበትን አጋጣሚ እየጠበቀ በመቁነጥነጥ ላይ ነው ፣ ኤዛም አይኖቿን አድማስ ላይ ብትተክልም ለአቢያራ የሚከላከል አንዳች ምልክት አላሳየችም ሌሎቹም ሴቶች ባሉበት ሆነው ከመተያየት ውጪ አልተንቀሳቀሱም ።
"አድማስ የኔ ታላቁ ፈረስ ምን እያልክ ነው ?" ብሎ አቢያራ አስፈሪ ጣቶቹን ወደ አድማስ ቀሰረ
"ጌታዬ እኔ ኤሊያታ እንድትሞት አልፈቅድም "አለ ድምፁ እየተርገበገበ
"አድማስ ልጄ አንተን ማን ፈቃጅ አደረገ ? እኔ ይሁን ካልኩ ከመታዘዝ ውጪ ምን ምርጫ አለህና ነው ? ይልቅ ኤልያታን ወደመሰዊያው ውሰዳትና እረፍት ስጣት ፣ እኔና አንተ ደሞ ቀሪውን በደንብ እንነጋገርበታለን መቼም ለዛሬው ያልተገባ እንቢተኝነትህ የምትከፍለው መስዋትነት ይኖራል እኔ ይቅር ብልህ ታላቁ አባቴ ይቅር አይልህም "ብሎ አቢያራ ማጓራት ጀመረ
አድማስ ከቆመበት አልተንቀሳቀሰም እንዴት ነው በሚያፈቅራት ልጅ ላይ ስለት የሚያነሳው ግራ ገባው ልቡ እሺ አላለውም ፣ አቢያራ ማጓራቱ ባሰ ዋሻው በጣም ተረበሸ ሴቶቹ ጥግ ጥጉን ይዘው ማነብነብ ጀመሩ ኤዛ ወደ መሳይ ስትመለከት ጠቀስ አደረጋት የሚለውን ባትረዳም አንገቷን ነቀነቀች ፣ ኤሊያታ አድማስ እንዲገላት ለመነችው አቢያራ ከሚከፋ አሷ መስዋት መሆኗን መረጠች አቢያራ ያለው እንዲፈፀም የጥንቆላ ጩኽቱን እየጮኽ ግፊት አደረገ ፣ በዚ አጋጣሚ መሳይ ወደ አድማስ በፍጥነት ተጠጋ ሁሉም በየራሱ ፍርሃት ውስጥ ስለሰመጡ እንዳቀረቀሩ ናቸው ስለዚ ልብ አላሉትም ፣ መሳይ የሚያጓራውን አቢያራን ወደጎን እያየ አድማስ ጋር ደረሰ ፣ልክ አድማስ አጠገብ እንደደረሰ በፍጥነት አድማስ የያዘውን ስለት ተቀበለው.........


ሙና መሀመድ

ይቀጥላል

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍473
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰባት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

እንደ ሄሪ ማርክስ አይነት እድለኛ ሰው የለም፡፡

እና ሁል ጊዜ እድለኛ እንደሆነ ይነግሩት ነበር፡ ምንም እንኳን አባቱን በአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ያጣ ቢሆንም ደከመኝ ሰለቸኝ በማይሉ ብርቱ እናቱ እጅ በማደጉ እድለኛ ነው፡፡ እናቱ የፅዳት ሰራተኛ ናቸው አገሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ በገባችበት በዚያ ቀውጢ ወቅት እንኳን ስራቸውን አላጡም ነበር፡፡ የሚኖሩት እዚህ ግባ በማይባል ኮንዶሚኒየም
ውስጥ ቢሆንም በችግር ጊዜ የሚረዳዱ ጥሩ ጎረቤቶች አሏቸው: ሄሪ ከችግር የማምለጥ እድልና ክህሎት ነበረው፡፡ እሱና የትምህርት ቤት ጓደኞቹ
ረብሸው ሲገረፉ የአስተማሪው አርጩሜ እሱጋ ሲደርስ ይሰበር ነበር፡ ሄሪ ከፈረስ ወይም ከጋሪ ላይ ሲወድቅ ፈረሶቹ ሳይረግጡት በስልት ያሳልፋቸዋል፡፡

ለውድ ጌጣጌጥ ፍቅር ስላለው ነው ሌባ የሆነው፡፡

በጉርምስናው ወቅት በየወርቅ ቤቱ እየተዘዋወረ ዕንቁዎችን መመልከት
ይወድ ነበር፡ እነዚህ እንቁዎች የሚመስጡት ስለሚያምሩ ብቻ ሳይሆን በመጻሕፍት ላይ እንደሚያነበው የሀብታም ምልክት ስለሆኑም ጭምር ነው፡
አንድ ቦታ ረግቶ መስራት ስለማይወድ አንድ ወርቅ ሰሪ ጋ በተቀጠረ በስድስት ወሩ ስራውን ለቀቀ፡፡ ሰዓት መጠገንና የጋብቻ ቀለበቶች ማስፋት ስራም እንዲሁ አስጠላው፡ ነገር ግን የተለያዩ የከበሩ ድንጋዮችን ለይቶ
የማወቅ ችሎታ አዳብሯል፡፡

ሬቤካ ሞግሃም ፍሊንትን የተዋወቃት በፈረስ እሽቅድድም ቦታ ላይ ሲሆን የአንዱ ተወዳዳሪ ደጋፊ ነው ብላ አስባለች ሬቤካ ቀውላላ፣አፍንጫዋ አለቅጥ የረዘመ መልከ ጥፉ ሴት ናት፡ ራሷ ላይ በደፋችው ቆብ ላይ ላባ ሰክታለች፡፡ አጠገቧ ያሉት ወጣት ወንዶች ከምንም ሳይቆጥሯት ሄሪ
ስላናገራት በጣም ነው በሆዷ ያመሰገነችው::

እሷን ለመተዋወቅ የጓጓ እንዳይመስል መግባባቱን በዚያው ቀን ማድረግ አልፈለገም፡፡ በሌላ ቀን ስዕል አዳራሽ ስታገኘው ደስ ብሏት ከዚህ ቀደም በደምብ እንደምታውቀው ሁሉ ሰላምታ ሰጠችውና ወስዳ ከእናቷ ጋር
አስተዋወቀችው፡፡

እንደ ሬቤካ ያሉ እመቤቶች ሲኒማ ወይም ምግብ ቤት ያለ አጃቢ
አይሄዱም፡፡ ብቻቸውን የሚሄዱ የደሃ ልጆች ናቸው፡፡ የሬቤካ እናትና አባት የሄሪን የቤተሰብ ሁኔታ ማጣራት አልደፈሩም፡፡ ቤተሰቦቹ ዮርክሻየር ውስጥ የገጠር ቤት፣ ስኮትላንድ ውስጥ የትግል ትምህርት ቤት እንዳላቸው፣ አካል
ጉዳተኛ እናቱ ደቡብ ፈረንሳይ ውስጥ እንደሚኖሩና በንጉሠ ነገሥቱ አየር ኃይል ውስጥ ለሹመት መታጨቱን ሲነግራቸው እውነት ነው ብለው ተቀብለውታል።
ሄሪ በከፍተኛው መደብ ህብረተሰብ ዘንድ ውሸት ማውራት እንደሚብስ አውቋል።

በዚህ አይነት ሄሪ ከሬቤካ ጋር ጓደኝነት ከመሰረተ ሶስት ሳምንት
ሞላው፡፡ አንድ ቀን አንድ ፓርቲ ይዛው ሄደች፡፡ እዚያም ክሪኬት ሲጫወት ዋለና ከተጋበዘበት ቤት ገንዘብ ሰረቀ፡ ጋባዦቹም እንግዶቻቸውን ማሳጣት
ስላልፈለጉ ለፖሊስ ሳያሳውቁ ቀሩ፡፡ በሌላ ቀን ደግሞ አንድ ዳንስ ምሽት ላይ ወስዳው ኪስ ሲያወልቅና የሴቶችን ቦርሳ እየከፈተ ሲበረብር አመሸ፡፡ ሬቤካ
ቤተሰቦቿን ልታስተዋውቀው የወሰደችው ጊዜ እንኳን ገንዘብ፣ ከብር የተሰሩ ቢላዎችንና ከወርቅ የተሰሩ የቀሚስ ማያያዣዎችን መንትፏል፡

በሱ አመለካከት ከሀብታሞች መስረቅ እንደ ጥፋት አይቆጠርም፡
እነዚህ ሃብታሞች የሰበሰቡት ሃብት አይገባቸውም ባይ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ህይወታቸውን በሙሉ የአንድ ቀን ስራ እንኳን ሰርተው አያውቁም፡፡ ከነዚ ሰዎች ገንዘብ መስረቅ ናዚዎችን እንደመግደል ይቆጠራል እንደወንጀል
ሳይሆን ለህዝብ እንደሚሰጥ አገልግሎት።

ይህን የስርቆት ተግባር ከጀመረ ሁለት አመት ያህል ሆኖታል፡ ነገር
ግን በዚህ ከቀጠለ አንድ ቀን መያዙ እንደማይቀር ተገንዝቦ ሌላ ስራ
መፈለግ ሲያስብ ጦርነቱ ከተፍ አለለት፡

ምንም ቢሆን በመደበኛ ወታደርነት መቀጠር አይፈልግም፡፡ አሸር ባሽር
ምግብ፣ ዩኒፎርምና ወታደራዊ ስነ-ስርዓት የእሱ ዕጣ ክፍሎች አይደሉም ሆኖም የአየር ኃይል ዩኒፎርም ይማርከዋል፡፡ አይሮፕላን አብራሪ መሆን ይፈልጋል፡፡ እንዴት እንደሚፈፅመው ባያውቅም ያደርገዋል፡፡ እሱ እንደሆነ
እድለኛ ነው፡፡

ሬቤካን ርግፍ አድርጎ ከመተዉ በፊት እሷን ተጠቅሞ አንድ ሁለት
የሀብታም ቤት መዝረፍ ፈልጓል፡፡
ሰር ሲሞን ሞንክፎርድ የተባሉ ሀብታም የመጽሐፍ አሳታሚ ቤት
ለግብዣ ተጠርተው ሄዱ፡ ሄሪ ክብርት ሊዲያ ሞስ ከተባለች እመቤት ጋር ወሬ ጀመረ፡፡ እመቤቲቷ ብቻዋን ስለነበረች ለአንድ ሃያ ደቂቃ ያህል
አጫወታትና ወደ ሬቤካ ዞረ፡ ከዚያም ጊዜው አሁን ነው ብሎ በመገመት ተንቀሳቀሰ፡፡

ሁለቱን ወይዛዝርት ይቅርታ ጠየቀና ከዳንሱ አዳራሽ ወጣ
የሚቀጥለው ፎቅ ላይ ወጣና ኮሪደሩን ይዞ ሄደ፡፡ ኮሪደሩ መጨረሻ አንድ ትልቅ መኝታ ክፍል አገኘ፡፡ ወደ ውስጥ ሊገባ ሲል አንድ ሰው ‹‹ምን ነበር?›› አለው፡፡
‹‹እዚህ ነው?›› ብሎ ጠየቀው
‹‹ምኑ?››
‹‹መፀዳጃ ቤቱ?››
ወጣቱ ሰው ከቁጣው መለስ አለና ‹‹አሃ ገባኝ፤ መፀዳጃ ቤቱ ኮሪደሩ
ጥግ ነው የሚገኘው›› አለው፡፡
‹‹በጣም አመሰግናለሁ፡››
‹‹ምንም አይደል››
ሄሪ ወደ መፀዳጃ ቤቱ እየሄደ ‹‹በጣም የሚያምር ቤት ነው›› አለው ወጣቱን፡፡

‹‹አዎ›› አለና በደረጃው ወርዶ ሄደ ወጣቱ፡

ሄሪ በእፎይታ ፈገግ አለ፡፡ ወጣቱ ሰው መሄዱን አረጋገጠና ወደ
መኝታ ቤቱ ተመልሶ ሄደ፡
መኝታ ቤቱ የእመቤት ሞንክፎርድ ሲሆን የመልበሻ ክፍልም እንዳለው
ሄሪ ተመለከተ፡ ቀጥሎ ደግሞ የወንድ መልበሻ ክፍል አለ፡፡ ሀብታም ባልና ሚስቶች የየራሳቸው መኝታ ክፍል አላቸው፡፡ ይህም የሆነው ከሰራተኛው
መደብ ያነሰ ወሲባዊ ፍላጎት ስላላቸው ይሆን?› ሲል አሰበ፡፡

ሄሪ የሰር ሲሞን መልበሻ ክፍል ገባና የኮሞዲኖውን መሳቢያ ከፈተው፡፡መሳቢያው ውስጥ በተለያዩ ጌጣጌጦችና አምባሮች የተሞላ ከቆዳ የተሰራ
የጌጣጌጥ ማስቀመጫ ሳጥን አገኘ፡፡ ብዙዎቹ ጌጣጌጦች ተራ ቢሆኑም ከነዚያ ውስጥ ግን ከወርቅ የተሰሩ የእጅ አምባሮች ላይ አይኑ አረፈ፡ አምባሮቹን
ኪሱ ጨመራቸው፡፡ ከጌጣጌጥ ሳጥኑ ቀጥሎ ውስጡ ሃምሳ ፓውንድ የያዘ የቆዳ የኪስ ቦርሳ አገኘ፡፡ ከቦርሳው ውስጥ ሃምሳ ፓውንድ ወሰደ፡፡ ብዙ ሰዎች ሃያ ፓውንድ ለማግኘት ከሁለት ወር ያላነሰ ከባድ የፋብሪካ ስራ
መስራት ያስፈልጋቸዋል፡፡

በየሄደበት ያገኘውን ሁሉ አይሰርቅም፡፡ የተወሰነ ዕቃ ብቻ መስረቅ ጥርጣሬ ይፈጥራል። ሰዎች ዕቃ ጎድሎ ሲያዩ ጌጣጌጡን ሌላ ቦታ እንዳስቀ
መጡት ወይም ቦርሳ ውስጥ ምን ያህል ገንዘብ እንደነበራቸው ማስታወስ ስለሚያቅታቸው ስርቆት ተፈፅሟል ብለው ለፖሊስ ሪፖርት አያደርጉም፡፡

መሳቢያውን ዘጋና እመቤት ሞንክፎርድ መኝታ ክፍል ዘው አለ፡፡
የያዘውን ይዞ ለመውጣት ቢመኝም ትንሽ ደቂቃዎች እመቤቲቱ ክፍል
ቢያጠፋ ወደደ፡፡ ሴቶች ከባሎቻቸው የተሻለ ጌጣጌጥ ይኖራቸዋል፡፡ እመቤት
ሞንክፎርድ ደግሞ ዕንቁ ሳይኖራቸው አይቀርም፡፡ ሄሪ ደግሞ ዕንቁ ነፍሱ ነው፡፡

የምሽቱ አየር ምቹ በመሆኑ መስኮቶቹ በሙሉ ተከፍተዋል፡ በቀጥታ መልበሻ ክፍል ውስጥ ገባና ጌጣጌጡ ያለበት ኮሞዲኖጋ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ሁሉንም መሳቢያዎች ሲከፋፍት የተለያዩ የጌጣጌጥ ሳጥኖች እና ትሪ ሙሉ
ጌጣጌጥ አገኘ፡፡ የበር መከፈት ድምፅ ለመስማት ጆሮውን ቀስሮ እያንዳንዱን የጌጣጌጥ ሳጥን ፈተሸ፡፡
👍19👎21
እመቤት ሞንክፎርድ ጥሩ ጌጣጌጥ አያውቁም፡፡ እመቤቲቱ ወዘና ያላቸው ሴት ቢሆኑም ጌጣጌጦቻቸው ተራ ናቸው፡ ሄሪ በምርጫቸው ተበሳጨ፡፡
ሄሪ አንድ ጌጣጌጥ አይኑን ሳበው፡፡ ጠጋ ብሎ ሊያይ ሲል የመኝታ ቤቱ
በር ሲከፈት ሰማና በድንጋጤ ደርቆ ቀረ። ሆኖም ማሰቡን አላቆመም::
የመልበሻ ክፍሉ በር ወደ መኝታ ቤቱ የሚያስገባ ብቸኛው በር ነው፡ ክፍሉ ውስጥ አንድ መስኮት ቢኖርም በጥብቅ የተዘጋ ስለሆነ ድምጽ ሳያሰማ ለመክፈት እንደማይቻል ተረዳ፡፡ በቁም ሳጥኑ ውስጥ መደበቅ እችል
ይሆን?› ሲል አሰበ፡፡
ካለበት ቦታ ሆኖ የመኝታ ቤቱን በር ማየት አይችልም፡፡ ጠጋ ብሎ
ሲያዳምጥ እመቤት ሞንክፎርድ እየመጡ ነው፡፡ የከፋፈታቸውን መሳቢያዎች ለመዝጋት ጊዜ አላገኘም፡

ሄሪ ጫን ጫን ይተነፍሳል፡ ድንጋጤ ቢወረውም ከዚህ በፊትም
እንዲህ አይነት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ያውቃል፡፡ ከዚያም ራሱን አረጋግቶ ተንቀሳቀሰ፡፡ ተነሳስቶ በበሩ በኩል አለፈና መኝታ ቤቱ ውስጥ ገብቶ ድምጹን
አሰማ፡፡

እመቤት ሞንክፎርድ ደነገጡ፡፡

‹‹በመኝታ ቤትዎ መስኮት አንድ ሰው ሲዘል አየሁ›› አላቸው፡፡

እመቤቲቱ ከድንጋጤያቸው መለስ አሉና ‹‹ምን እያልክ ነው የኔ
ልጅ?›› አሉ፡ ‹‹መኝታ ቤቴ ውስጥ ምን ልታደርግ ገባህ?››

ወደ መስኮቱ ሄደና ወደ ውጭ አይቶ ‹‹አሁንማ ሄደ›› አላቸው፡፡

‹‹አንተ ለመሆኑ ማነህ?››
እመቤት ሞንክፎርድ እድሜያቸው አርባ ውስጥ ይገመታል፡ ካወቀበት
ወይዘሮዋን መሸወድ አያቅተውም፡
‹‹እኔ ኮሪደሩ ውስጥ እየሄድኩ አንድ ሰው እዚህ ክፍል በር ላይ ሆኖ
አጮልቆ ሲመለከት ዓይን ለዓይን ግጥም ስንል ተመልሶ መኝታ ቤት ገባ፡፡

ይህን ቤት መጸዳጃ ቤት ስፈልግ ነው ያየሁት፡፡ ይሄ ሰው ምን እንደሚፈልግ አላወቅሁም፡፡ ሳየው የቤት አሽከር አይመስልም፡፡ ተጋባዥ እንግዳም አይመስልም፡፡ ሁኔታው ስላጠራጠረኝ ልጠይቀው ወደ እሱ ስሄድ በመስኮት
ዘሎ ሄደ፡፡ የተከፈቱትንም መሳቢያዎች ሳይ ሰውየው ጌጣጌጥ ፈልጎ እንደመጣ ተረዳሁ››

እመቤት ሞንክፎርድም ‹‹ምን አይነት ነገር ነው›› አሉ፡፡
ወንበር ሳበና ‹‹አረፍ ይበሉ›› አላቸው፡፡

‹‹ሳስበው አንተ ባታባርረው ኖሮ›› አሉ ሴትዮዋ ‹‹እዚህ ስገባ ባገኘው በድንጋጤ ራሴን እስት ነበር›› አሉና የሄሪን እጅ ለቀም አድርገው በመያዝ
‹‹አመሰግናለሁ›› አሉት፡፡
ሄሪ ፈገግ አለ፡፡ አሁን አምልጧል፡፡ ትንሽ አሰብ አደረገ፡፡ ሰው
እንዲጠሩ አልፈለገም፡፡ ያዩትን ሁሉ በሚስጥር መያዝ ይሻላቸዋል፡
‹‹ለሬቤካ የሆነውን ነገር አይንገሯት፡ አይሻልም? የአዕምሮ ችግር
ስላለባት እንደዚህ አይነት ነገር ስትሰማ ትረበሻለች››
‹‹እኔም እንደዛው ነኝ›› አሉ እመቤት ሞንክፎርድ ‹‹ሳምንት ያህል
ያመኛል፡››
‹‹ምናልባትምፖሊስ መጥራት ያስፈልግዎት ይሆናል፡ ነገር ግን
ያዘጋጁት ፓርቲ ይታመስብዎታል››
‹‹እሱም ጥሩ አይደለም›› አሉ እመቤቲቱ፡
‹‹ደህና›› አለ ሄሪ በውስጡ እርካታ ተሰምቶት፡ ‹‹ፖሊስ የሚጠራው
እኮ ሰውየው የወሰደው ዕቃ ካለ ነው፡፡ እስቲ መሳቢያውን ይፈታትሹ››
አላቸው

‹‹ወይኔ የኔ ነገር! እስቲ ልፈትሽ›› አሉ፡፡

ሄሪ እጃቸውን ያዝ አደረገና እንዲነሱ አገዛቸው፡፡ ወደ መልበሻ ክፍሉ ውስጥ ገቡና መሳቢያው ሁሉ ተከፍቶ ሲያዩ በድንጋጤ አፋቸውን ያዙ፡፡ ሄሪ
ወንበር አቀረበላቸው፤ ቁጭ ብለው ጌጣጌጦቻቸውን ፈታተሹና ‹‹አይ ብዙም
የወሰደ አይመስለኝም›› አሉ፡፡

‹‹ምናልባትም ገና ሲጀምር ይሆናል የመጣሁበት›› አለ ሄሪ ወይዘሮዋ እያንዳንዱን ጌጣጌጥ በዓይነት በዓይነቱ ደርድረው ፈታተሹና
‹‹ደርሰህበታል›› አሉ፡፡ ‹‹አንተን እግዚአብሔር ባይጥልልኝ ኖሮ ምን
ይውጠኝ ነበር!›› አሉ።

‹‹ምንም ጌጥ ካልጠፋብዎት ለሰው መንገር አያስፈልግም››

‹‹ከጌታ ሲሞን በስተቀር ለማንም አልነግርም›› አሉ፡
‹‹አዎ ልክ ነው›› አለ ሄሪ ለጌታ ሲሞን እንዳይነግሯቸው ቢፈልግም፡፡

‹‹ፓርቲው ካለቀ በኋላ ይንገሯቸው፧ እንደዚያ ይሻላል፤››

‹‹ጥሩ ሃሳብ ነው›› አሉ ሴትዮዋ በእፎይታ፡፡

ሄሪ ልቡ አረፍ አለ፡፡ ‹‹እኔም እንግዲህ ትቼዎት እታች ልሄድ ነው››አለና ጎንበስ ብሎ ጉንጫቸው ላይ ሳም አደረጋቸው፡፡ ድንገት በመሆኑ አፈር ቢሉም ወይዘሮዋ አልከፋቸውም፡፡

‹‹እርስዎ ጎበዝ ሴት ነዎት›› አለና በተቀመጡበት ትቷቸው ሄደ፡፡

ጎልማሳ ሴቶች ከወጣቶቹ ቀለል ይላሉ፡፡ ኮሪደሩ ላይ ባገኘው መስታወት ቁመናውን አየና ክራቫቱን አስተካከለ፡፡ ‹‹አንተ ሰይጣን›› አለ ራሱን፡፡

ፓርቲው እያበቃ ነው፤ ሄሪ ዳንሱ አዳራሽ ሲገባ ሬቤካ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ አገኛት፡፡

‹‹የት ነው የጠፋኸው?›› አለችና ጠየቀችው በቁጣ፡

ከጋባዦቻችን ጋር እያወራሁ ነበር›› ሲል መለሰላትና ‹‹ይቅርታ እንሂድ›› አላት፡

ከግብዣው ቤት ሲወጣ የእጅ አምባሩና ሃያ ፓውንዱ ኪሱ ውስጥ ናቸው፡፡

ታክሲ ያዙና ወደ መሃል ከተማ የሚገኝ ምግብ ቤት ገቡ። ሄሪ ጥሩ ጥሩ ምግብ ቤቶች ደስ ይሉታል፡ የዕቃዎቹ ጥራት የፈረንሳይ ምግቦች ዝርዝርና ከተፎዎቹ አሳላፊዎች ይማርኩታል፡ አባቱ እንደዚህ አይነት ምግብ ቤቶች ውስጥ ለመግባት አልታደሉም፡፡ እናቱ ምናልባት ለጽዳት ስራ
ገብተው ይሆናል፡ ሜኑው ላይ የሰፈረውን የምግብ ዝርዝር አየና ውድ
ያልሆነ ምግብና ወይን ጠጅ አዘዘ፡

ከዚህ ቀደም ወጣት ሴቶችን ለመጋበዝ ምግብ ቤት ገብቶ ብዙ ጊዜ
ስህተት ይፈጽም ነበር፡ ነገር ግን ፈጣን አዕምሮ ያለው በመሆኑ ከስህተቱ
ይማራል ከልምዱ እንደተረዳውም ብዙዎቹ የእንግሊዝ ሃብታሞች
የፈረንሳይ ምግብ ስለማያውቁ ይጠይቃሉ፡፡ እሱ ግን አንድ ምግብ ለመመገብ ሲገባ ስለሌላው ምግብ ይጠይቃል፡ እንዲህ እንዲህ እያለ ነው የፈረንሳይ
ምግብ ያወቀው። ስለሆነም ከብዙዎቹ ሃብታም የእድሜ እኩዮቹ ይልቅ የፈረንሳይ ምግብ ዝርዝር ያውቃል። ወይን ጠጅ ላይ ግን ችግር የለበትም አስተናጋጆች ደግሞ የትኛው ወይን ጠጅ ጥሩ እንደሆነ ሲጠየቁ ደስ
ይላቸዋል፡ ምክንያቱም ብዙ ወጣቶች የተለያየ ወይን ጠጅ ያውቃሉ ተብሎ
አይጠበቅም፡፡ ስለዚህ ምግብ ቤት ሲገቡ ዋናው ነገር የሚያውቁ መስሎ ረጋ
ብሎ መታየት ነው፡

ሻምፓኙ ጥሩ ቢሆንም ምሽቱ ድብር ብሎታል፡ ለዚህም ምክንያቱ
ሬቤካ እንደሆነች ተገንዝቧል እዚህ ቦታ ደስ የምትል ልጅ አምጥቶ ቢሆን
ኖሮ ምን ያህል ደስ እንደሚለው አሰበ፡፡ ብዙ ጊዜ ይዞ የሚመጣው
አስቀያሚ፣ ወፍራም፣ ፊታቸው ላይ ማዲያት ያለባቸውና ጅላጅል ሀብታም ሴቶችን ነው፡፡ እነሱን መተዋወቅ በጣም
ከተማረኩለት በኋላ እንዳይተዋቸው ስለሚሰጉ ያላቸውን መቀበል ብቻ ነው
ቀላል ነው፡ አንድ ጊዜ
ምርጫቸው፡፡ ስለዚህ ሀብታም ቤት ውስጥ ለመግባት ተመራጩ መንገድ ይሄ ነው፡፡ ታዲያ ከማይፈልጋቸው ሴቶች ጋር ነው ጊዜውን የሚያጠፋው፡፡

ሬቤካ ዛሬ አኩርፋለች አንድ ነገር ሆዷን በልቶታል፧ ከተዋወቁ ጀምሮ ለሶስት ሳምንት በየቀኑ ሊጋብዛት ይዟት ሲወጣ አንድ ቀን እንኳን ሰውነቷን
ለመደባበስ ለምን እንዳልሞከረ አልገባትም፡፡ ለወሲብ እንዳልፈለጋት
ገብቷታል፡

ከዚህ በፊት ድንግልናዋን ልትሰጠው ዝግጁ ከነበረች አንዲት ቀጫጫ ልጅ ጋር ለወሲብ መታገል ሲሞክር ገላው አልታዘዝልህ ብሎት እንደተቸገረ ሲታሰበው በእፍረት ይሽማቀቃል፡ እሱ ወሲብ የለመደው ከእሱ መደብ ሴቶች ጋር ነው፡ ታዲያ ከእነሱ ጋር የነበረው ግንኙነት ብዙም አይቆይም፡
👍17