አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
የጠንቋዩ ዋሻ
☜☜ክፍል 6 ☞☞

መሳይ ከተጣለበት ጨለማ ውስጥ ሆኖ ድምፁን ከፍ በማድረግ ሲፀልይ ቆይቶ በጣም እየደከመው ሲመጣ እንቅልፍ ወሰደው ፡ የተኛበት መሬት ፡ምቾት ካለመኖሩ የተነሳ እያቃዠው ነበር ፡ በቅዠቱ ሁሉ የአቢያራ የሚያስፈራ ግዙፍ ሰውነት ፡ሲጫነው ሲያስፈራራው ለማምለጥ ሲታገል ነበር የሚያየው ፡ በጣም ከመድከሙ የተነሳ ግን እየባነነ መልሶ ፡ ወደ ቅዠቱ ይገባል ፡
መስፍንና ዳንኤል የአቢያራን ፡እያንዳንዷን ትህዛዝ በመቀበላቸው ፡በዋሻው፡ውስጥ ይኖራል ብለው፡ባልገመቱት ፡ያማረ መኝታ ክፍል ውስጥ የሚመች አልጋላይ ፡ መተኛት ችለዋል ፡ በዚ የአቢያራ የዋሻውስጥ ፡ያማረ በቀያይ መጋረጃ ያበደ ክፍል ሁለቱም ተደንቀዋል ፡ በየክፍሉም ፡ ደብዛዛ ቢሆንም መብራት በመኖሩ አቢያራ እውነትም ልዩ አይል እንዳለው ቆጥረውታል ፡ በርግጥ በዋሻው ውስጥ ትልቅ ጀኔረተር አለ ፡ነገርግን ለዛ ጀነሬተር ፡ነዳጅ ከየት መጥቶ ነው በሆነ ታምር ካልሆነ በስተቀር ፡ብለው ፡አስበዋል ፡አድማስ የተባለው ይዟቸው የመጣው የአቢያራ ታዛዥ ፡ ሁለቱ ጓደኛማቾች ፡ስላመኑ ደስ ብሎታል ፡ ምክንያቱም ፡ እነሱም እንደ ጓደኛቸው ፡መሳይ ፡ደረቅ ፡ቢሆኑ ኖሮ ፡ አቢያራ ፡ ምንድነው ፡ያመጣህብኝ ፡ብሎ ፡እንደሚቀጣው ፡ያውቃል ፡ መሳይንም ፡ቢሆን ፡ጊዜ ፡ወስዶ ፡ መስመሩ ውስጥ ፡እንደሚያስገባውና ፡ለአቢያራ እንደሚያሰግደው ፡ ተማምኗል ፡ ለዚህም ፡ነው ፡ መሳይን ፡ወዳስቀመጠበት ፡የዋሻው ፡ክፍል ፡ ዝር ፡ሳይል ፡ለሁለት ፡ቀን ፡የተወው ፡ ለመሳይ ፡የሚበላ ነገር እንኳ ፡አልሰጠውም ፡ ይህ ፡ኡኔታ ፡መሳይን ፡እንደሚቀይረው ፡አስቧል ፡ ,,,,,,,አቢያራ ፡ የግሌ ነው እኔ እስካልፈቀድኩ ድረስ ፡እንዳትገቡ በሚለው ፡ ሰፊ የዋሻው ፡ክፍል ፡ውስጥ ፡ ተቀምጦ ፡ የተለያዩ ድምፆች እያወጣ ሲጮህ ፡ሲያጓራ ይሰማል ፡ በዛች ክፍል ጥግ ጥጉን የአቢያራ ቀያይ የለበሱ ቀያይ ሴቶቹ ቆመው አብረው በቀስታ የሱን ቃል ይደግማሉ ፡ አድማስ ፡መስፍን እና ዳንኤልን ይዞ ፡በዋሻው ፡ውስጥ ለውስጥ እየተጓዘ ፡አካባቢውን ያስጎበኛቸዋል ፡ እነመስፍንን ያስገረማቸው ነገር ግን በዋሻው ፡በስተጀርባ ፡ያለው የአትክልት ስፍራ ነበር ፡ በጣም ፡ሰፊ በጣም ውብ ፡ ነበረ ፡ በስተቀኝ በኩል የተለያዩ ፍራፍሬዎች ያሉበት ዘፎች ፡ በስተቀኝ ፡ የሚያማምሩ ፅጌሬዳ አበባዎች ፡ አረንጓዴ ሰር እንደምንጣፍ ፡የተዘረጋበት ፡ ቦታ ፡ ከሚያስጨንቀው ፡ዋሻ ፡በስተጀርባ ፡ ማንም ሊያውቀው ፡የማይችል ፡የተለየ ስፍራ ፡ መስፍንና ዳንኤል አፋቸውን ከፍተው ፡ሲያስተውሉ ፡ አድማስ ፡ይሄን ፡ስፍራ የሚያሳያቸው ፡ለአባታችን ፡አቢያራ ፡ስለታመናቹ ነው ፡ አደራ ስእተት እንዳትሰሩ ብሎ ፡አስጠነቀቃቸው ፡ ሁለቱም ቃል ገቡ ፡ እንዲሁም ፡ ያንን የአትክልት ፡ስፍራ ሲያዩ ፡የአቢያራ ታምረኝነት ፡ ከፍ ፡አለባቸው ፡ እናም ፡ጓደኛቸው ፡ ከሚሞት ፡ለአቢያራ ፡እንዲታዘዝ ፡ሊያሳምኑት ፡ፈለጉ ፡ አድማስ ፡ግን ፡ከሱ ጋር መገናኘት ፡የሚችለው ፡እሱ ብቻ ፡መሆኑን ፡አስጠንቅቆ ፡ስለነገራቸው ፡ በቅሬታ ፡ተቀበሉት ፡ ,,,,,,, አቢያራ ፡ ብዙ የጥንቆላ ቃላቶችን ፡ሲያወራ ፡ቆይቶ ፡ በራሱመንገድ ፡የራሱን ፡እምነት አመስግኖ ፡ዝም ፡አለ ፡ ወደ ፀጥታው ፡ሲመለስ ፡ሴቶቹ ፡ አጎንብሰው ፡ ለአቢያራ ፡ክብር ከሰጡ በዋላ ፡ በየፊናቸው ፡በዋሻው ፡ውስጥ ፡ተበተኑ ፡ መስፍን ፡ሁለቱ ሴቶች ፡ወደነሱ አቅጣጫ ሲመጡ ፡ በመገረምና ፡በአድናቆት ፡ተውጦ ፡አስተዋላቸው ፡ አድማስ ፡ከሁለቱ ሴቶች ፡አንዷ ፡ኤሊያታ ናትና ፡ የመስፍን ፡አስተያየት አልተመቸውም ፡እና በማስጠንቀቅ አይነት ገላመጠው ፡መስፍን ፡አይኑን ፡ሰበር ፡አደረገ ፡ በእርግጥ ፡በዕድሜም ፡ቢሆን ፡ከነመስፍን ፡ ጋር አይገናኙም ፡ ነገርግን ልዩ ናቸው ፡ ቀያይ ፡ቀሚሳቸው ፡ ከዋሻው ፡ወጥተው ፡በአትክልቶቹ ስፍራ ሲገኙ ፡ የተለየ ቁንጅናቸውን ፡አወጣባቸው ፡ ዋሻው ፡ውስጥ ፡ግን ፡ ከቁንጅናቸው ፡ይልቅ ፡ፍርሃትን ነበር ፡የሚያጭሩት ፡ አድማስ ፡እንደነገራቸው ፡ደሞ ፡ በፍፁም ፡ከዚ አካባቢ እርቀው ፡የትም ፡ሄደው ፡አለማወቃቸውን ፡ነው ፡ እናም ፡ ሰለማያውቁት አለም አዘኑላቸው ፡ ,,,,,,, በዋሻው ፡ጨለማ ክፍል ውስጥ ፡ መሳይ በረሃብ ፡እየተሰቃየ ፡ነበር ፡ ሁለት ቀን ፡በሙሉ ፡ምግብም ፡ሆነ ውሃ የሰጠው ፡ሰው ፡የለም ፡ እናም ፡ በመጣራት ፡ ድምፁ ሰልሏል ፡ "እባካቹ እናንተ ሴጣኖች የሚበላ ስጡኝ እባካቹ ከዚ አስወጡኝ ፡ "እያለ መጣራቱን ፡ በቀጥልም ሰሚ ግን አላገኘም ፡ የመሳይን ፡ የሰለለድምፅ ፡ የሰማችው ፡ በዋሻው ፡ውስጥ ለውስጥ ፡ ስትዘዋወር ፡የነበረችው ፡ኤዛ ፡ ድንገት ቆም ፡ብላድምፁን ፡ለመስማት ፡ሞከረች ፡"እባካቹ ፡ አታሰቃዩኝ ፡ መምቴ ነው ልቀቁኝ ፡ አአአአ" ኤዛ ድምፁን ወደሰማችበት ጨለማው ክፍል ፡ ከፍታ ገባች "ማነው እባካቹ የሚበላ "አለ መሳይ
"እሽሽሽሽሽ "አለች ኤዛ
"ማነሽ እእ ባክሽ ፡ውሃ ስጪኝ ፡ "አላት
"ድምፅ አታሰማ የምትፈልገውን እሰጥሃለው ፡እሽሽሽሽ"አለች
"እሺ ቶሎ በይ " ብሎ መሳይ የማትታየውን ሴት ፡ጠየቀ ፡ እሺ ብላው ፡ወጥታ ፡ተሰወረችበት ፡ መሳይ ፡በተስፋ ጠበቀ ፡ የዛን ጠንቋይ ፡ሴቶች ፡ አላመናቸውም ፡ በመራቡ ለመነ እንጂ ፡ ቆንጆ ፡ሴጣኖች ፡እንደሰበሰበ ፡ነው ፡የሚሰማው ፡ መሳይ ፡ ከአን ፡አሁን ፡ውሃ ይዛልኝ ፡ትመጣለች ፡ብሎ ፡የሚጠብቃት ፡ሴት ፡ ቀረችበት ፡ ከቆይታ፡ በዋላ ግን ፡ ከባባድ ፡እርምጃዎች ፡ይሰሙት ፡ጀመረ ፡ ከርምጃው ፡በባሰ ፡ደግሞ ፡የሚወጣው ፡ድምፅ ፡ይረብሻል ፡ ይሄሁሉ ጋጋታ ወደሱ ፡እንደሆነ ፡ ተሰማው ፡ የቀድሞ ፡ፍርሃቱ መጣበት ፡ ጋጓጓጓጓጓጓ አሆሆሆሆ እርምጃ አስፈሪ ድምፅ ፡ መሳይ ፡ ወደጥግ ፡በመሄድ ፡ እራሱን ሰበሰበ .........

ሙና መሀመድ

ይቀጥላል...

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️
👍28🤔3
#ሳቤላ


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ታሣሥ ገብቷል » የአልፕስ ተራሮች በበረዶ ተሸፍነዋል ይህ የአየር ሁኔታ ለግሮነብል ከተማም ተረፋትና ቅዝቃዜ አመዳይና ድጥ ብቻ ሆናለች በአንዳንድ መንገዶች መኻል ለመኻል የሚያልፉት ቦዮች ያለ ወትሮአቸው ጠቁረዋል"ዐበቅዝቃዜው የተላቀቁት ሰዎች በጐዳናዎቹ ውር ውር ይላሎ " ወይዘሮ ሳቤላ ቬንን ከዚያ ብዙ መስኮቶችና በርች ካሎት ባለ ሰፊ ምድጃና ባለ ሰፊ የጢስ ማውጫ የፈረንሳይ መኝታ ቤት ወስጥ ከእሳቱ አጠገብ ተቀምጣ ትንቀጠቀጣለች ብርዱ ከየአቅጣጫው ይገባል " የበሽተኛ የራስ ቆብ ደፍታ ወፍራም የሱፍ ያንገት
ልብስ ደርባ ሰውነቷ ያለ ማቋረጥ ይንዘፈዘፋል ከእሳቱ በጣም ከመጠጋቷ የተነሳ ልብሷ በፍንጣሪው እንዳይቃጠል የፈራችው ሠራተኛዋ ከአጠገቧ ሁና ትጠብቃታች " ከሚንጣጣው ዕንጨት ፍንጣሪ ሲወረወር ብዙ ጊዜ እየዘለለች ትከለክልላት ነበር " ለሳቤላ ግን ምንም አልመሰላትም " የድንጋይ ሐውልት መስላ በአንድ አቅጣጫ እንደ ተቀመጠች አካሏ ከመንቀጥቀጡ በቀር አትነቃነቅም።

ጥቂት ሊሻላት የጀመረ ትመስላለች አንዳንድ ጊዜ ቀና እያለች መቀመጥ
ይዛለች ብዙ ቀን ታማ ሰንብታ አሁን ትኰሳቱ በረድ እያለላት ነው " ሠራተኞቿ
ግን እንደ ምንም ብላ ተነሥታ ብትንቀሳቀስ ሊሻላት እንደሚችል እርስ በርሳቸው ይንሾካሾካሉ " እሷም ከንፋሳሙ ክፍል ቁጭ ማለት ችላለች ነገር ግን ከመኝታ ቤቷ ወጣች አልወጣች ምንም ደንታ አልነበራትም ።

ዛሬ ቀን መቼም የእህል አምሮቷ ሙቷል ቀደም ብላ ራቷን ቀመሰችና ከባለ ድጋፍ ወንበርላይ ተቀምጣ ስታንጐላጅ ከውጭ የሠረገላ ድምፅ ሰምታ ነቃች።

“ ማነወ ? አለቻት ሞግዚቷን "

“ ጌቶች ናቸው .. እሜቴ! ፒየርም አብሮ አለ " እኔ እመቤቴን ብዙ ጊዜ እየመላለስኩ አይጨነቁ ጌቶች ይመጣሉ ስልዎ የነበረው አሁን እውነት ሆነ " አለመሳሳቴን ዐወቁት ? "

ወይዘሮ ሳቤላ ኮስተር ያለ ቆራጥ ገጽታ በፊቷ ተሰራጨ " ለዚህ አሁን ለመጣ ሰው በፊትም ሆነ አሁን ያልተጨነቀችለት መሆኗን የሚናገር ይመስል ነበር "ትዕግሥትና እርጋታ አይክዱኝ ! አሁን ነው እንግዲህ አለች ሳቤላ ለራሷ "

“ ጌቶች በጣም አምሮባቸዋል ”አለች ሠራተኛይቱ » በፎቅ መስኮት ቁማ ወደታች እየተመለከተች - ከሠረገላ ወረዱ እግራቸውን ከመሬት መታ መታ አደረጉ አለች

መውጣት ትችያለሽ ሱዛን” አለቻት ሳቤላ "

ሕፃኑ ቢነቃስ እመቤቴ ?

እጠራሻለሁ ”

ልጅቱ በሩን ዘግታ ወጣች ሳቤላ ተቀምጣ ሕፃኑን እየተመለከተች ትዕግሥት
እንዲሰጣትና እንዲያስችላት ራሷን በራሷ ስትመክር በሩ ብርግድ ብሎ ተhፈተ
ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ገባና ሰላም ሊላት ተጠጋት " መንፈሷ ተመርዞ ንዴቷ
ተቀጣጥሎ ድምጿን እንኳን ሳይቀር አሰለለውና ጮኻ መናገር ስላቃታት እንዳይቀርባት እጁዋን በማራገብ ከለከለችው ከፊት ለፊቷ ተቀምጦ የሚነደውን ዕንጨት
በጫማው እየገፋ ሳይመጣ የቆየው የሥራ ብዛት ከከተማ ሊያስወጣው ባለመቻሉ መሆኑን ነገራት "

አሁን ምን ልታደርግ መጣህ ?

'' ለምን መጣህ ?'' አለ የሷን አባባል ደገመውና “ እንዴ ! በዚሀ አሠቃቂ ቅዝቃዜ ይኸን ሁሉ አገር አቋርጦ ለመጣ ሰው ውለታው ይኸው ነው ማለት ነው?
እኔን በደስታ የምትቀበይኝ መስሎኝ ነበር . .ሳቤላ ”

“ ሰር ፍራንሲዝ” አለችው በሚያስደንቅ ያልተጠበቀ እርጋታ " እስከ መጨረሻው በዚሁ ዘለቀችው " የመልኳ ቶሎ ቶሎ መለዋወጥና ' የልቧን አመታት ለመቀነስ ይረዳት ይመስል አሁንም አሁንም ደረቷን በእጇ ስታስደግፍ ንዴቷን ለመቆጣጠር ከስሜቷ ጋር ምን ያህል እንደምትታገል ይታወቅባታል “ሰር ፍራንሲዝ
መምጣትህን ለአንድ ምክንያት በደስታ እቀበለዋለሁ በደንብ መግባባት አለብን ስለዚህ እዚህ በመገኘትህ በጣም ደስ ብሎኛል " ትንሽ ጠንከር ስል ልጽፍልህ ፈልጌ ነበር : ግን ያንተ መምጣት ከድካም አዳነኝ ያለ ገደብ ያለ ድብብቆሽ ያለምንም ድለላና ማታለል ግልጽልጽ አድርጌ መወያየት እፈልጋለሁ " አንተም
እንደዚሁ የኔን ምሳሌ እንድትከተል እጠይቅሃለሁ

ምን ማለትሽ ነው ?

“ግልጽ አድርጎ መነጋገር በአሁኑ ንግግራችን ግልጽ የሆነ እውነት መኖር
አለበት ”

“ አሳብሽ አልባኝም "

ምንም ሳንሸፋፍንና ሳንደባብቅ ሐቁን መነጋገር አለብን ነው የምልህ" ባለፈው ሐምሌ ስትሔድ በጋብቻችን በወቅቱ እንደምትመለስ ቃል ገብተህልኝ ነበር "
በወቅቱ ስል ምን ማለቴ እንደሆነ ታውቃለህ ነገር ግን . . .


“ በርግጥ ቃል ስገባልሽ ለመመለስ አስቤ ነበር ነገር ግን ለንደን እንደ ገባሁ
በሥራ ተዋጥኩ መምጣት አልቻልኩም አሁንም ቢሆን አጣዳፊ ሥራ ትቸ ስለ መጣሁ ከአንድ ሁለት ቀን የበለጠ አብሬሽ አልቆይም

“ እምነትህን እያፈረስክ ነው " ቃሎችህ የቅጥፈት እንጂ የእውነት ቃሎች አይደሉም ለጋብቻው በወቅቱ ለመመለስ አልፈለግህም : ከመሔድህ በፊት እንዲፈጸምም አልፈሰግህም

የምን ቅዠት ነው ከልብሽ የገባው !” አለ ፍራንሲዝ ሌቪሰን "

“ አንተ ከሔድህ ከትንሽ ጊዜ በኋላ” አለችው በረጋ አነጋገር “አንዷ ሠራተኛ ልብሶችህን ስታደራጅ ከአንዱ ኪስህ ደብዳቤ አግኝታ ሰጠችኝ ቀኑን
ሳየው ወደ ለንደን ነተነሣህ ለት ከደረሱክ ደብዳቤዎች አንዱ መሆኑን አወኩት
ደብዳቤው ፍቺው በሕግ መፈቀዱን የሚገልጽ ነበር ። ያን ጊዜ ባታታልለኝ ገና
ላልተወለደው ሕፃን ስል ብቻ የጓጓሁለት ተስፋ ከንቱ ከከንቱም የባሰ መና መሆኑን ብትነግረኝ ኖሮ ደግ ነበር ።

“እኔ በዚህ አላሰብኩትም።ያለመጠን ተናደሽ ሳይሽ ምንም ቁም ነገር ምንም ምክንያት ቢነግሩሽ በጥሞና የምታዳምጪ አልመሰለኝም
በዚህ አነጋገሩም የልቧ አመታት ጨመረ እሷ ግን እንደ ምንም ብላ ስሜቱን
ግታችው ።

“ የሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ሚስት ለመሆን መመኘቴ በቂ ምክንያት ያለው አልመሰለህም?

በዚህ ጊዜ የሚነደውን ዕንጨት በጫማው ተረከዝ እየመታ ከተቀመጠበት
ብድግ አለና ፡ “ አየሽ ሳቤላ . . .በኔ ደረጃ ላለ ትልቅ ሰው አንዲት የፈታች ሴት ማግባት ተመሳሳይ የሌለው መሥዋዕት መሆኑን ማወቅ አለብሽ

“ እኔ እኮ መሥዋዕቱን እንድትከፍል የጠበቅሁህ ወይም የተመኘሁህ ለራሴ
ብዬ እንዳልሆነ ያኔም ነግሬህ ነበር ። ነገር ግን ሳይሆን ቀረ ልጁም የኃጢአትና የውርደት ወራሽ ሆነ ። ያውልህ እዚያ ተኝቷል

ሰር ፍራንሲዝ በጣቷ ወዳመለከተችው አንገቱን ዞር አድርጎ ሲመለhት
ከአልጋው ጐን አንድ የሕፃን መኝታ አየ ሔዶ ለማየት እንኳን አልሞከረም።

“እኔ እንግዲህ የአንድ ጥንታዊ ባለማረግ ቤተሰብ ወካይ እንደ መሆኔ
መጠን ” አላት በዚያ ባለፈው የልበ ቢስ ሰው ንግግሩ ተጸጽቶ ይቅርታ የሚጠይቅ በመሰለ ድምፅ አንችን ሚስት ባደርግ ቤተሰቤን ሁሉ አስቀይማለሁ ስለዚህ ...

“ ቆይ” አለችና ሳይጨርስ'' ግድ የለህም የማያስፈልግ ምክንያት ለመፍጠር ራስህን አታስጨንቅ ያሁኑ አመጣጥህ እኔን ሚስት ለማድረግ ቢሆን ኖሮ
ዛሬውኑ እንድንፈጽም የምትጠይቀኝ ቢሆን ኖሮ ሥርዓት አስፈጻሚ ቄስ ይዘህ መጥተህ ብትሆን ኖሮ ከምንም ቁም ነገር አልቈጥረውም ነበር የልጁ ጉዳት አይመለስም ስለራሴ የሆነ እንደሆነ ከአንተ ጋር እንድኖር ከመገደድ የከፋ ፈተና
ያ ገኘኛል ብዬ አላስብም።”

በኔ እንደዚህ ያለ ጥላቻ ካደረብሽ ምንም ማድረግ አይቻልም " ሆኖም
እንድክስሽ አጥብቀሽ በመለመን ከፍተኛ ሁከት ያኔ ፈጥረሽብኝ ነበር ” አላት አሁን አግባኝ ስላላለችው በሆዱ እየተደሰተ።
👍14👎1😁1
ራሷን ነቀነቀች “ አንተ ባለው ዐቅምህ ሁሉ የምታደርገው ካሣ ዓለም በመላ የሚፈጥረው ማንኛውም ካሣ ቢሆን ወንጀሌን አያፀዳውም ውጤቱም
እስከ መጨረሻው ከራሴ ላይ አይወርድም ”

“ አዬ ወንጀል ! ሴቶች ስትባሉ ስለ ወንጀሉ ማሰብ የነበረባችሁ ገና ሳይሆን ነበር ።

“ አዎን ! እንደኔ ከስሕተት ሊወድቁ ለሚችሉ ሁሉ ይኸ እንዲገለጽላቸው
እመኝላቸዋለሁ”

ይህ አነጋገርሽ እኔን ለመሳዶብ ያመጣሽው ከሆነ ተሳስተሻል” አለ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ቈጣው ከቈጥጥሩ ውጭ ሲሆንበት። ንግግሩ የማንንም ስሜት ቢነካ ደንታ በሌለው ልማዱ እንደምትዪው ወደ ስህተት ተገፋፍተሽ መግባትሽ
በባልሽ ላይ ያሳደርሽው የቅናት ቁጣ የመራሽን ያህል የኔ ማባበል አልገፋፋሽም " ይኸም የተሳሳተ ፈር ተከትለሽ የፈጸምሽው ስሕተት ነው

ምን ለማለት እንደ ፈለግህ አልገባኝም " የምን የተሳሳ ፈር ነው?

ስለ ባልሽና ስለዚያች የሔር ልጅ'ያለምንም ተጨባጭ ነገር ቅናት ያዘሽ” ካርላይል ስለዚያች ልጅ ምንም ሐሳብ የነበረው አይመስለኝም " በሁለቱ መካከል አንድ የፍቐር ሳይሆን የሌላ ሥራ ምስጢር ነበር ስለዚህ ያ ሁሉ የምስጢር ግንኙነታቸው ምክራቸው በዚሁ ምክንያት ብቻ ነበር።

ፊቷ ደም መሰለ እሱ ደግሞ ዝግ ብሎ ነበር የሚናገር " ሲናደድ ይኸው
ነበር ጠባዩ ዝግታው እየጨመረ ሲሔድ የኃይለ ቃሉ አንጀት ቆራጭነትም በዚያው መንገድ እየጨመረ ይሔዳል ።

“ ግን ሰር ፍራንሲስ..ያኔ ለኔ የነገርከኝ ሌላ ታሪክ ነበር።

ሰር ፍራንሲዝ ሣቀና በፍቅርና በጦርነትጊዜ ማንኛውም ስልት ትክክለኛ ነው።

ምንም መልስ ለመስጠት አልቻለችም " ለጊዜው ዝምታ ሰፈነ"ሁለቱም ጸጥ
ብለው ቆዩ "

“ ያንን ትንሽ ነገር ማን ብለሽ ጠራሽው ለመሆኑ ?
“ ፍራንሲዝ ሌቪሰን ” አለችው
“ ስንት ቀን ሆነው ? መልኩስ እኔን ይመስላል ...ሳቤላ ?”
“ ነሐሴ ሲያልቅ ነው የተወለደው " በውነት ይህ ልጅ በአስተሳሰብ አንተን
መስሎ የሚወጣ ከሆነ ' ማሰብም መናገርም ሳይችል ቢሞት እመርጣለሁ"

“ አሁን ለመሆኑ መኝታዬ ተዘጋጅቶ ይሆን

አልተዘጋጀልህም " ይህ ቤት እኮ አሁን የኔ ነው በስሜ አዛውሬዋለሁ

ከእንግዲህ ወዲያ አንተ ከዚህ ማረፊያ ልታገኝ አትችልም " በል ይልቅ እንደ ልቤ ለመነሣት ጉልበት ስለሚያንሰኝ ፈቃድሀ ቢሆን እሱን ሻንጣ አቀብለኝ "

ሌቪሰን ተነሥቶ ዕቃውን ከነበረበት ጥግ ሔዶ አንሥቶ አመጣላት ከዚያ
ቁልፍ አውጥታ ' ሻንጣውን ከፍታ፡“የዛሬ ወር እነዚህን በፖስታ ልከሀልኝ ደርሰውኝ ነበር ” አለችው "

“ አንቺ ግን ተቀብለሽ እንኳን አታመሰግኝም ” አላት በፌዝ ድምፅ
“ዐርባ ፓውንድ አልነበረም የላክልኝ?”
እንደዚያ መሰለኝ ”
በል እንድመልስልህ ፍቀድልኝ : ቁጠራቸው !”
“ለምንድነው የምትመልሽልኝ ?

ከእንግዲህ ወዲያ ካንተ ጋር ምንም ዐይነት ግንኙነት አይኖረኝም ያንተን
ምንህንም አልፈልግም " አሁን የዘረጋሁትን ክንዴን አታሳምመኝ " እንካ
ተቀበለኝ።

“ ግንኙነታችን እንዲቋረጥ ፍላጎትሽ ከሆነ ይሁንልሽ እውነቱን ለመናገር የኔና ያንቺ ኑሮ የድመትና የውሻ ኑሮ ስለሆነ ከዚህ ከንዝንዝ ኑሮ የተሻለ ማስተዋል የተመላበት ውሳኔ ነው። ግን ያንቺ ውሳኔ እንጂ የኔ አለመሆኑን አስታውሺ "
ቢሆንም አንቺ እየተራብሽ ዝም ብዬ የምመለከት አይምሰልሽ ፤እኔና አንቺ ተስማምተን የምንወስነውን ገንዘብ በየመንፈቁ እልክልሻለሁ » ስለዚህ . .

" እባክህ ይብቃህ ዝም በል ! ኧረ ለመሆኑ እኔ ምን መሰልኩህ ?”

እንዴ ምን ማለትሽ ነው?ሀብት የለሽ ዕርዳታ ካላገኘሽ እንዴት መኖር
ትችያለሽ ?”

“ እኔ ካንተ አልቀበልም ። ዓለሙ በሙሉ ቢጥለኝ ከባዕዳን ዕርዳታ ማግኘት
ቢሳነኝ ወይም የዕለት እንጀራን እንኳን ሠርቶ ማግኘት ቢያቅተኝና በሕይወት መኖር ግን አስፈላጊ ቢመስለኝ ' ካንተ ከምረዳ ችግሬን ለባሌ ባመለክት እመርጣለሁ ይህ አባባሌ የያዝነውን ርዕስ እዚህ ላይ ማቆም እንዳለብን ሊያሳምንህ
ይግባል ” ” ለጠቅ አድርጋ
“ አዎን ፡ ለቀድሞዉ ባሌ” አለችው ለፌዙ መልስ

“ለራስሽ ባትፈልጊም ለሕፃኑ መቀበል አለብሽ " የልጁ ጉዳይ የኔ ሐሳብ ነው። ስለዚህ ጥቂት መቶ ፓውንዶችን እሰጥሻለሁ "

ሰውየውን በንግግሩ የደበደበችው ይመስል እጆቿን ታማታ ጀመር ” “አሁንም ወደፊትም አንዲት ቤሳ እንኳን አልቀበልም ። በልጁ ስም ገንዘብ ለመላክ ብትሞክር ተቀብዬ ባቅራቢያ ከሚኘው ወንዝ ውስጥ እጥለዋለሁ ።ኧረ እኔ ማን መሰልኩህ ? አለች ከተቀመጠችበት ብድግ ብላ ። አንተ በዓለም ፊት እንድዋረድ ብታደርግም ፡ አሁንም የሎርድ ማውንት እስቨሮን ልጅ ነኝ እኮ ! " አለችውና ንዴቷን ለመቈጣጠር እየተጣጣረች ተቀመጠች "

አጥብቃ ስትይዘው ጊዜ የመለሰችለትን ገንዘብ ተቀብሎ ከቦርሳው ከተተ።

“ አሁን በፈጠረህ ወደ ኢንግላንድ ስትሔድ የተውካቸውን ልብሶችህን ዛሬውኑ እንዲወስድልህ ፒየርን እዘዘው ። እንግዲህ ሰር ፍራንሲዝ .... ጨርሰናል
ብዬ አምናለሁ ፣ ይብቃን ።”

“ ከእንግዲህ ዕርቅ የማይገባን ጠላቶች ሁነን እንቀራለን ማለት ነዋ?

“እንደማንተዋወቅ እንሆናለን” ብላ አረመችውና፡ “በል ደኅና ሁን” አለችው
ባይሆን የጅ ሰላምታ እንኳ አትሰጭኝም ሳቤላ ?”
አዎን ልጨብጥሀ አልፈቅድም ”

እንዲህ ሆነው ተለያዩ ። ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ሳቤላ ከነበረችበት ክፍል ወጥቶ
ከፊቱ የነበሩትን የቤት ሠራተኛ ሁለቱንም ጠርቶ ወደ አንድ ራቅ ያለ ክፍል ወሰዳቸውና : ' እመቬቲቱን ገንዘብ ብላችሁ እንዳታስቸግሯት " ብሎ የአንድ ዓመት ቅድሚያ ደሞዝ ከፈላቸው ። ከዚያም ወደ ቤቱ ጌታ ዘንድ ሔዶ ለሱም ተመሳሳይ ቃል ነግሮ የአንድ ዓመት ቅድሚያ ኪራይ ከከፈለው በኋላ ከአንድ ሆቴል ራት
አዘዘና ከሚያበሳጨው ጭቅጭቅ በቀላሉ በመገላገሉ ዕድሉን እያመሰገነ የዚያ ዕለት ሌሊት ከፒየር ጋር ወደ ኢንግላንድ ተመለሰ

ሳቤላ ከአንድ ቦቷ ሳትነቃነቅ ከእሳቱ ተጠግታ ብቻዋን ተጎልታ አመሸች ሠራተኛዋ ወደሷ ቀርባ ይህን ያህል ማምሸት ለጤናዋ እንደማይበጃት ብትነግራት ከነምክሯ ወደ ሌላው ክፍል ዘወር እንድትልላት አዘዘቻት

ጸጸቷ እንደዚያን ዕለት ምሽት ግልጽ ሆኖ ተሰምቷት ያሁኑና የወደፊቱ
ሁኔታዋም ጭልም ብሎ አንዣብቦባት አያውቅም " አስከፊው አድራጎቷ ቁልጭ
ብሎ ታያት ። ማዕረጓንና መልካም ስሟን ጣለች ተንግዲህ ወዲያ አሷና
ጥገኞቿ ሚበሉት እንጀራ ለሚለብሱት ጨርቅ
ለሚጠለሉበት ጣራ
ሠርታ ማፍራት የሚኖርባት ወንዶች የሚያዝኑላት ሴቶች የሚሽማቀቁባት
አለሁልሽ ባይ የሌላት የተተወች የተጣለች ችግረኛ ፍጡር ሆናለች ከናቷ
ወይም ካባቷ ያኘቻቸውና ከኢስት ሊን ያመጣቻቸው ጥቂት የወርቅ ጌጦች ነበሯት ሚስተር ካርላይል ከሰጣት ውስጥ አንድም አልነካችም አሁን ጌጦቹ እስኪያልቁ ድረስ እየሽጠች ትጠቀማለች ከዚህያ የምታገኘው ገንዘብ በጥንቃቄ የተጠቀመችበት እንደሆነ ካሥራ ሁለት እስከ ዐሥራ ስምንት ወር ሊቆያት እንደሚችል አሰላችው ። ከዚያ በኋላ ላለው ግን አንድ የገቢ ምንጭ መፈለግ ሊያስፈልጋት ሆነ
ለጊዜው የታያት ሕፃኑን ከሞግዚት ጋር ትታ ስሟን ለውጣ ከአንድ ጀርመን ወይም የፈረንሣይ ቤተሰብ የልጆች አስተማሪ ሆና መቀጠር ነበር "
👍91
ከቤት ከትዳሯ በኮበለለች ጊዜ ሚስተር ካርላይልን ተበቀልኩ ብላ የፈፀመችው የዕብዶት ሥራ አሁን እዝነ ሕሊናዋን ዐይነ ልቡናዋን ከፍታ ከፍራንሲዝ ሌቪሰን እውነተኛ ጠባይ ጋር እያነጻጸረች ስታየው ለሷ ከመሰላት የባሏ በደል ጋር አመዛዘነችው በግዛ ስሜቷ ግለትና ብስጭት የሱን ጥፋት በጥልቀትና በምጥቀት በስፋትና በቁመት እያጋነነ ኩይሳውን እንደ ተራራ እያደረገ እንዳቀረበላት አሁን ገና
ማወቅ ጀመረች ገና ሰው ነውረኛ ድርጊቷን ሳይረሳው ሕጋዊ ፍችው ከጸደቀ
ብዙ ሳይቆይ ሊሆን ባይችልም ካሁኑ ተመልሳ የካርላይል ሚስት ብትሆን ተመኘች " መልካም ጠባዩ ትዝ አላት " አሁንማ የሷ መሆኑ ሲቀር ጊዜ በዕጥፍ በልጦና ጎልቶ ታያት ስለ ባራባራ ጉዳይ እያሰበች ራሷን ከማሰቃየት ሌላ ከባሏ ጋር ምን ያህል ደስተኞች እንደነበሩ ትዝታው መጣባት ለክፋቱ ደግሞ ለሱ የነበራት አክ
ብሮት አድናቆትና አፍቅሮት አሁን ሲቀር ጊዜ ትዝታው አራት ዕጥፍ ጨምሮና
ጠንክሮ ድቅን አለባት የአንዱን ነገር ሙሉ ጥቅም እስክናጣው ድረስ አናውቀውም " ጤንነትና ብልጽግና ደስታና የሕሊና ሰላም የመሳሰሉ ሁሉ የኛ እስከሆኑ ድረስ አስበንባቸው አናውቅም ዛሬ ሚስተር ካርላይልን አጥታዋለች " በገዛ እጅዋ
አሸቀንጥራ ጥላዋለች እንግዲህም ምናልባት ሕይወቷን ሙሉ ስለሱና ስለ ልጆቿ እንዳሰበች እንደ ተንገገበች ትገፋው ይሆናል

እንደዚህ በሐሳብ ጉዞ ስትንከራተት ዕኩለ ሌሊት ሆነ " ወይዘሮ ሳቤላ ለማረፍ ጋደም እንዳለች በቅርቡ እያጣችው ትቸገርበት የነበረው እንቅልፍ ሸለብ አደረጋት "

ሕልም ታያት። ወደ ኢስት ሊን ተመልሳ ይመስላታል። ከውጭ ተመልሳ ሳይሆን
እንደ ጥንቱ እንጂ ትታው የሔደች አይመስላትም ከሚስተር ካርላይል ጋር በጓሯቸው አበቦች መኻል ሲንሸራሸሩ ሦስቱ ልጆች ከግቢው ጨፌ ይፈነጥዛሉ " ክንዷን ከባሏ ክንድ ጋር አጠላልፋ አንድ ነገር ያጫውታታል ታሪኩን ኋላ ልታስታውሰ ባትችልም ከቢሮና ከሚስተር ዲል ጋር የተያያዘ ነበርና ሚስተር ካርላይል ሲያወጋ
ይሥቃል በዚህ መኻል ትንሹ አርኪባልድ አለቀሰና ወጋቸውን ያቋርጣሉ ሳቤላ
ምን እንደሆነ ለመጠየቅ ወደ ልጆቹ ዞር ስትል ነቃች ከእንቅልፎ የቀሰቀሳት ኢስትሊን የቀረው የልጅዋ የአርኪባልድ ድምፅ ሳይሆን ከአጠገቧ በልብስ ተጠቅልሎ ከሕፃን አልጋ የተኛው የዚያ ያልታደለው ልጅ የእውነት ልቅሶ ነበር ነገር ግን ላንዳፍታም ቢሆን በቅርቡ የደረሱትን ችግሮች ረሳችና ኢስት ሊን ውስጥ ከደስታ ቤቷ የኮራች እናት የተከበረች ሚስት ሁና የተቀመጠች መስሏት ነበር በአእምሮዋ ተናዳፊ ትዝታ ብልጭ ብሎ ያለችበትን በማስታወስ ጠቅ ሲያደርጋት የሥቃይ ውኸት ጮኽች ".....

💫ይቀጥላል💫
👍15🥰3
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_አርባ_ሶስት ፡ ፡ #ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ የጨሻው መጀመርያ “ምን እንደነገረቻቸው ገምቺ…” ክሪስ ቀጠለ “ክፍሉ በወሩ መጨረሻ በሚመጣው አርብ እንዳይፀዳ የፈለገችበትን ምክንያት ገምቺ። “እንዴት መገመት እችላለሁ? እኔ የእሷ አይነት አእምሮ የለኝም:" ጭንቅላቴን ነቀነቅኩ። ሠራተኞቹ ወደዚህ መምጣት ካቆሙ ብዙ ጊዜያቸው ነው እነዚያን አስፈሪ የመጀመሪያ ሳምንታት…»
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አርባ_አራት


#ትርጉሜ_ሀኒም_ኤልያስ


በፍሎሪዳ ወርቃማ የፀሀይ ብርሃን ውስጥ ደስተኛ ህይወት እንደሚኖረን ያቀድነውን እቅድ በቀስታ እየነገርኳት ነበር።

ክሪስ ልብሶቹን በደንብ ለብሶ በሚወዛወዘው ወንበር ላይ የኮሪን ጊታር እየነካካ ተቀምጧል። በቀስታ እያንጎራጎረ ነበር፡ ድምፁ መጥፎ አይደለም: ምናልባት ኬሪ ተሽሏት እንደገና እንደበፊቱ ከሆነች ሶስታችን አብረን ሙዚቀኞች እንሆን ይሆናል።

እጄ ላይ ያሰርኩት ስዊዘርላንድ ውስጥ የተሰራ ባለ ሀያ አራት ካራት የወርቅ
ሰዓት አለ። መቼም እናታችንን ብዙ ገንዘብ ሳያስወጣት አልቀረም፤ ክሪስም ሠዓት አለው ጊታር አለን፣ የክሪስ ካሜራና የውሀ ቀለሞችም አሉ… ስለዚህ እነሱን መሸጥ እንችላለን በዚያ ላይ አባታችን ለእናታችን ሰጥቷት የነበሩት
ቀለበቶችም አሉ።

ነገ ማለዳ የማምለጫ ቀናችን ሆኖ ተይዟል ግን የሆነ አስፈላጊ ነገር የረሳሁ
እንደሆነ አድርጌ የማስበው ለምንድነው?

ከዚያ ድንገት የሆነ ነገር አስተዋልኩ! እኔም ክሪስም ችላ ያልነው ነገር አያትየው የተዘጋውን በር ከፍታ እኛ ሳናያት በፀጥታ መቆም ከቻለች ሌላም ጊዜ እንደዚህ ታደርግ ይሆን? የምታደርግ ከነበረ አሁን እቅዳችንን አውቃ ሊሆን ይችላል። የእኛን ማምለጥ ለማስቆም የራሷን አቅድ አዘጋጅታ ሊሆን
ይችላል!

ይህንን መናገር ይገባኝ እንደሆን እያሰብኩ ወደ ክሪስ ተመለከትኩ አሁን
በማመንታት እንድንቆይ ምክንያት አልፈልግም: ስለዚህ ጥርጣሬዬን
ነገርኩት። ምንም ሳይረበሽ ጊታሩን መነካካቱን ቀጠለ “እሷን ባየሁበት ደቂቃ
ያ ሀሳብ አእምሮዬ ውስጥ ብልጭ ብሎ ነበር።” አለኝ: “ያንን ጆን የተባለ
ሠራተኛ ልትተማመንበት እንደምትችል አውቃለሁ። እንዳናመልጥ በማሰብ
ደረጃው ላይ እንዲጠብቀን ልታደርግ ትችል ይሆናል። ተይው ይሞክር! ምንም ነገር ሆነ ማንም ነገ ጠዋት ከመሄድ አያቆመንም!”
የአያትየውና የሰራተኛው ደረጃው ስር የመጠበቅ ሀሳብ ሰላም ሊሰጠኝ
አልቻለም። ኬሪ አልጋው ላይ እንደተኛች ክሪስም የሚወዛወዘው ወንበር ላይ
ተቀምጦ ጊታሩን እየነካካ ትቻቸው ለመሰናበት ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ወጣሁ።

በሚወዛወዘው አምፑል ስር ቆሜ ዙሪያውን ተመለከትኩ፡ ሀሳቤ ወደዚህ ወደመጣንበት የመጀመሪያ ቀን ተጓዘ... እኛን... አራታችንን. እጅ ለእጅ
እንደተያያዝን ግዙፉን የጣሪያ ስር ክፍልና ውስጡ ያሉትን ጣዕረሞት
የሚመሳስሉ እቃዎቹን በመገረም ዙሪያውን ስንመለከት፣ ክሪስ ለመንትዮቹ ዥዋዥዌ ለመስራት ራሱን አደጋ ላይ ሊጥል የነበረበትን ሁኔታ በሀሳቤ ተመለከትኩ ከዚያ ወደ መማሪያው ክፍል ገብቼ መንትዮቹን አስቀምጠን
የነበረውን በሀሳቤ እየተመለከትኩ ሳለ ክሪስ በደረጃው በኩል ተጣራ ካቲ
መሄጃችን ደርሷል።"


ማንበብና መፃፍ ያስተማርንባቸውን መቀመጫዎች አየሁ። ብቻዬን ስደንስ

ፈጠን ብዬ ወደ መማሪያ ክፍሉ ተመለስኩና በጥቁር ሰሌዳው ላይ በጠመኔ
በትልልቁ እንዲህ ብዬ ጻፍኩ…

ጣራው ስራ ባለው ክፍል እንኖር ነበር።

እኔ፣ ክሪስቶፈር፣ ኮሪና ኬሪ።

አሁን ሶስት ብቻ ነን።

ከዚያ ስሜንና ቀኑን ፃፍኩ። በልቤ የአራታችን መንፈስ ከዚህ ጣራው ስር
ያለው መማሪያ ክፍል ውስጥ ተዘግቶባቸው የነበሩ የሌሎች ልጆችን መንፈስ እንደሚበልጥ አውቃለሁ የሆነ ሰው ወደፊት እንዲፈታው አንድ እንቆቅልሽ ትቻለሁ።

የሞተውን አይጥ ከሁለቱ የተመረዙ ዶናቶች ጋር ኪስ ወረቀት ውስጥ ከትተን ክሪስ በኪሱ እንዲይዘው ተደረገ፡ ከእንጨት በተሰራው ቁልፍ የእስር
ቤታችንን በር ለመጨረሻ ጊዜ ከፈተ። አያትየውና ሠራተኛው ታች እየጠበቁን
ከሆነ እስከሞት እንታገላለን ክሪስ ልብሶቻችንና ዕቃዎቻችን የተሞሉባቸውን
ሁለት ሻንጣዎች ያዘ ትከሻው ላይ ደግሞ የኮሪን ጊታር አንጠለጠለ፡ ጨለም
ባለው አዳራሽ ውስጥ እየመራ በጀርባ ወዳለው ደረጃ ወሰደን። ኬሪ በከፊል
እንደተኛች አቅፌያታለሁ ትንሽ ከበድ ትላለች። ነገር ግን ከሶስት አመታት
በፊት በእነዚህ ደረጃዎች ላይ ተሸክሜያት ስወጣ ከነበራት ክብደት ምንም
ያህል አልጨመረችም። ወንድሜ የያዛቸው ሁለቱ ሻንጣዎች ልጆች ሳለን
በጣም አፍቃሪና ሰውን የምናምን በነበረበት ወቅት፣ ከረጅም ጊዜ በፊት በዚያ
ቀፋፊ ምሽት እናታችን ያሸከመችን ሻንጣዎች ነበሩ።

በልብሶቻችን ስር በሁለት ትንንሽ ቦርሳዎች ከእናታችን የሰረቅናቸውን ገንዘቦች
እኩል ለእኩል ተከፋፍለን ይዘናል የተካፈልናቸው ምናልባት የሆነ ነገር
ተፈጥሮ እኔና ክሪስ ብንለያይ አንዳችን ባዶ እጃችንን እንዳንቀር ለማድረግ ነበር። ኬሪ ደግሞ በእርግጠኝነት ከአንዳችን ጋር ትሆናለች በሁለቱ ሻንጣዎች
ውስጥም እንደዚሁ ሳንቲሞቹን እኩል ቦታ ከፍለን በሁለት ቦርሳዎች ውስጥ አድርገናል

እኔና ክሪስ ሁለታችንም ውጪ ምን እንደሚጠብቀን አውቀናል። ረጅም ጊዜ ቴሌቭዥን ማየታችን የዋህና ምንም ለማያውቁ ሰዎች የአለም ጨካኝ
ውሸቶች እንደሚጠብቋቸው አስተምሮናል። ልጆች፣ ተጠቂዎች፣ ደካሞችና
በከፊል የታመምን ነን ነገር ግን ከአሁን በኋላ የዋህ ወይም ምንም የማናውቅ
አይደለንም።

ክሪስ የጀርባውን በር እስኪከፍት ስጠብቅ የሆነ ሰው ሊያስቆመን እየመሰለኝ በእያንዳንዷ ሰኮንድ በፍርሀት ልቤ ቀጥ ብላ ነበር። ወደ እኔ ዞር ብሎ ፈገግ እያለ ወደ ውጪ ወጣ:

ውጪው ይበርዳል። መሬቱ ላይ እየቀለጠ ያለ በረዶ ይታያል: ግራጫው
ሰማይ በረዶ እንደገና ሊጥል እንደሆነ ይጠቁማል ቢሆንም ግን ጣራው ስር
ካለው ክፍል በላይ አይቀዘቅዝም፡ መሬቱ ከእግራችን ስር ያሙለጨልጫል።
ለብዙ አመታት ጠንካራና የተስተካከለ የእንጨት ወለል ብቻ ረግጠን
የምናውቅ በመሆኑ፣ መሬት ላይ መራመድ እንግዳ ስሜት አሳድሮብናል።
ደህንነት አልተሰማኝም: ምክንያቱም ጆን ሊከተለንና ሊመልሰን ይችላል
ወይም ይሞክራል ብዬ ፈርቻለሁ።

ንፁሁንና ጠንካራውን የተራራ አየር ለመሳብ ጭንቅላቴን ቀና አደረግኩ።
ትንሽ እስክንሄድ ድረስ ኮሪን አቅፌያት ነበር። ከዚያ በእግሮቿ አቆምኳት።
እርግጠኛ ባለመሆን እየተንገዳገደች ዙሪያውን አማተረች: ግራ የተጋባችና
የተገረመች ትመስላለች።
ትንሽና ቆንጆ ቅርፅ ያላትን የቀላች አፍንጫዋን ጠረገች። አምላኬ! ብርድ
ያማት ይሆን? ካቲ…” ሲል ክሪስ ተጣራ። “ሁለታችሁ መፍጠን አለባችሁ!
ገና ረጅም መንገድ ከፊታችን ስላለ ኬሪ ከደከማት እቀፊያት” አለ፡ ትንሽዬ እጇን ይዤ እጎትታት ጀመር። “ኬሪ ጥልቅና ረጅም ትንፋሽ ውሰጂ!
ሳታውቂው ንፁህ አየር፣ ጥሩ ምግብና የፀሀይ ብርሃን እንደገና ጠንካራና
ደህና ያደርግሻል:” አልኳት

ትንሽዋን የገረጣችውን ፊቷን ወደ እኔ ቀና አደረገች: በመጨረሻ ያቺ ተስፋ
አይኖቿ ውስጥ አንፀባረቀች: “ኮሪን ልናገኘው ነው?"

የኮሪን መሞት ካወቅንበት አሳዛኝ ቀን በኋላ የጠየቀችው የመጀመሪያ ጥያቄ ነው። የውስጥ ፍላጎቷ ኮሪ መሆኑን ስለማውቅ አተኩሬ ተመለከትኳት የተስፋ ብልጭታዋን ላጠፋባት ስላልፈለግኩ አይደለም ማለት አልቻልኩም
ኮሪ ከዚህ በጣም በጣም ሩቅ ቦታ ነው ያለው: አባታችንን የሚያምር
የአትክልት ቦታ ውስጥ አየሁት ብዬ ሳወራ አልሰማሽኝም? አባታችን ኮሪ እንዳቀፈውና አሁን እሱ እየተንከባከበው እንደሆነ ስናገር አልሰማሽም እነሱ እዚያ እየጠበቁን ነው: አንድ ቀን እንደገና እናገኛቸዋለን፡፡ ግን በቅርብ አይደለም" አልኳት።
👍43😢13🥰61🔥1
“ግን ካቲ፣ እኔ እዚያ ከሌለሁ ኮሪ የአትክልት ስፍራውን አይወደውም። እና ሊፈልገን ከመጣ የት እንዳለን አያውቅም” እንደዚህ ያለ ቅንነት እምባዬን አመጣው: ብድግ አድርጌ ልይዛት ሞከርኩ። ግን እግሯን እየጎተተች ወደ
ኋላ ለመመለስና ነፃ ለመሆን ታገለችኝ ከዚያ ለቀነው የምንሄደውን ግዙፍ
ቤት በትኩረት ለማየት በግማሽ ወደ ኋላ ዞረች።

“ነይ ኬሪ፣ ፈጥነሽ ተራመጂ! ኮሪ እየተመለከተን ነው: ከዚህ እንድናመልጥ ይፈልጋል! አያትየው የሆነ ሰው ልካ መልሳ ወስዳ ከመቆለፏ በፊት ከዚህ እንድንርቅ ተንበርክኮ እየፀለየ ነው: አልኳት ፈጠን ፈጠን እያለ የሚሄደውን ክሪስን እየተከተልን ነው: ልክ የሚያደርገውን
እንደሚያውቅ ወደዚህ ስንመጣ ወደወረድንባት ትንሽዋ የባቡር ጣቢያ
እየመራን ነበር።

የማለዳዋ ፀሀይ የማለዳውን ጭጋግ እያባረረች በተራራው ጫፍ ላይ ብቅ አለች ወደ ባቡር ጣቢያው ስንጠጋ ሰማዩ ቀላ ያለ ሆኖ ነበር።

“ፍጠኚ ካቲ!” አለኝ ክሪስ። “ይሄ ባቡር ካመለጠን እስከ አስር ሰዓት መጠበቅ
ይኖርብናል።” አምላኬ! ይሄ ባቡር ሊያመልጠን አይገባም! ካመለጠን አያትየው እኛን ለመያዝ
በቂ ጊዜ ታገኛለች። ፖስታ የሚያመጣው መኪና አጠገብ የቆመ ረጅም ሰውዬ ተመለከትን፡፡ ኮፍያውን አወለቀና ወደ እኛ አቅጣጫ እያየ ፈገግ አለ “እናንተ ሰዎች እውነትም በጠዋት ተነስታችኋል” ሲል በፈገግታ አወራን። “ወደ
ቻርለትስቪል እየሄዳችሁ ነው?” አለ፡ “አዎ! ወደ ቻርለትስቪል እየሄድን
ነው:: መለሰ ክሪስ፡ ከዚያ በእፎይታ በሚመስል አይነት ሻንጣዎቹን መሬት
አስቀመጠ፡

“ቆንጅዬ ልጅ ይዘሻል” አለ ረጅሙ ፖስተኛ በፍርሀት ቀሚሴን ጥብቅ አድርጋ የያዘችውን ኬሪን በአሳዛኝ አይን እየተመለከተ። “ይህንን ስናገር ቅር
ካላላችሁ ትንሽ ያመማት ትመስላለች።”

“አሟት ነበር” ክሪስ አረጋገጠለት፡ “ግን አሁን ይሻላታል” አለው። ፖስተኛው ጭንቅላቱን ነቀነቀ፤ የነገርነውን ያመነ ይመስላል።

“ትኬት ይዛችኋል?”....

ይቀጥላል
👍31😢16
የጠንቋዩ ዋሻ
"★★ክፍል 7★★★★

መሳይ ዳግም ያንን ጠንቋይ ባያየው ደስ ይለው ነበር ፡ነገር ግን ኤዛ አንዳች የሚቀመስ ታመጣለች ብሎ ሲጠብቅ አቢያራንና ጓደኞቹን እንዲሁም አድማስን አስከተል በመምጣት በሩን ገፋ አድርገው ሲገቡ በተከፈተው በር መሰል ነገር በትንሽዬ ብርሃን አያቸው ፡ መሳይ በሕይወቱ እንደዚያ ተገርሞ አያውቅም ፡ የገዛ ጓደኞቹ በሁለት ቀናቶች ውስጥ ፡ፍፁም ተቀይረው ፡ሌላ ሰው መስለዋል የለበሱት ቀያይ ሽርጥ ፡እና አናታቸው፡ላይ ያሰሩት እሪቫን ፡ ወደ አስፈሪ ነት ቀይሯቸዋል ፡ አቢያራ ከመሃላቸው ገዘፍብሎ ይታያል ፡ የለበሰው እንደተለመደው ጥቁር ፡ነው አድማስ በእጁ በያዛት ፡ባትሪ ወደ መሳይ ፡አበራ ፡ መሳ ፍፁም ተጎሳቅሎ ፡እና ከንፈሮቹ ድርቅ ብለው ፡ለሚያየው ፡አሳዛኝ ሁኔታውስጥ ነበረ ፡ ኤዛ ከአቢያራ ትህዛዝ ውጪ መውጣት እርግማን የመጣል ብላ ስላሰበች እንጂ፡ለመጀመሪያ ጊዜ ልቧ እንደመራራት ብሎ ነበር ፡ ይህ ልጅ አይኖቹ ውስጥ የሆነ የሚያሳዝን ፡ነገር ፡አለው ብላ አስባለች ፡ ምን ደፋር መስሎ ቢታይም ፡ አኖቹ ትኩር ብሎ ለሚያየው ውስጡ አንዳች መልክት ያስነብባል ፡ ኤዛ ከዚ በፊት እዚ ዋሻ ውስጥ ፡የተለያየሰው ፡መስዋት ሲሆን አይታለች ፡ነገርግን ፡ለአቢያራ ደስታ ስትል፡እራሷንም ፡አሳልፋ ለመስጠት ፡የምትሰስት አይደለችም ፡ ይህ ልጅ ግን አንዳች ነገር እንድታዝንለት እየገፋፋት ፡ነው ግራ ገብቷታል አቢያራ መስዋት እንዳያደርገው በልተለመደ ሁኔታ ፈርታለች ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
,,,,,አድማስ በጣም ተጠግቶት ባትሪውን ሲያበራበት ፡መሳይ የውስጡን ፍርሃት እየታገለ ፡"ምን ታየኛለህ አይበቃም እኔ እንደው አልፈራህም "አለው ድምፁ እየተንቀጠቀጠ
"ዝም በል አንተ በአባቴ ፊት እንዲ በድፍረት አታውራ ደምህን ነው የምጠጣው "አለ ወደ ጆሮው ተጠግቶ
"ምንም ብትል ለናንተ ሴጣን አልሰግድም ፡ከፈለክ የፈለከውን አድርገኝ"አለ መሳይ ፡አድማስ ወደ መስፍን ትግስት በማጣት ዞረ
"መሳይ እባክህ እሺ ብለህ እኛን ተቀላቀል ፡ይኽው ሁሉም ነገር ሰላም ነው ፡አባታችን ፡ቤተሰቦቻችንን ማየት እና ፡እንዳስፈለገን መሆን እንደምንችል ፈቅዶልናል ፡ ስለዚ ፡ምንም የሚቀየር ነገር የለም ፡አንተ ብቻ እሺ ብለህ ፡የአባተችንን የህይወት ዘይት ጠጣ "አለ መስፍን ወደመሳይ ተጠግቶ በማባበል
"ቱ ....አንተ ውሻ በቀላሉ ትሸወዳለህ እነሱ እኮ ሴጣኖች ናቸው ለምን አይገባህም የፈጠረንን እንድንክድ ሊያደርጉን ነው ፡የሞትክ "አለው መሳይ መስፍን ላይ በመትፋት ፡መስፍን ፊቱን ጠራርጎ ሲያበቃ ፡በንዴት ጦፎ ፡የመሳይን ጉንጭ በጥፊ አላሰው ፡ መሳይ ደነገጠ ጓደኛው እንዲ በፍጥነት ተቀይሮ ፡ይሰነዝርብኛል ብሎ አላሰበም፡ ጉንጩን እንደያዘ አይኖቹን አቁለጨለጨ ፡ሰውነቱ መንቀጥቀጡን አባሰበት ፡ አቢያራ ፡ተቆጥቶ ፡መስፍንና ዳንኤል እንዲወጡ አዘዘ ፡
አድማስ ፡ ከአቢያራ ትህዛዝ ውጪ መስፍን መሳይን በመማታቱ ፡ደነገጠ፡ለራሱ እንዲ አለ ፡ምነው እነዚን ፡ሰካራም ልጆች ፡ወደአባቴ ይዤ ፡ባልመጣው ፡እኔ ፡ለጥሩ ነበር ፡ያሰብኩት ፡ከዋሻው ፡ውጪ ያለውን ፡ዓለም ፡እንዲያገናኙንና ፡ሁሉንም ፡ነገር ፡እንዲፈፅሙልን ፡ነገርግን ፡የመረጥኳቸው ልጆች ፡ስህተቶቼ ናቸው ፡ ይባስ አባቴን በኔ ላይ እንዳያስነሱብኝ "
"አንተ ልጅ የኔ ፈረስ "አለ አቢያራ በሚያስገመግም ድምፅ
"አቤት አባቴ "አለ አድማስ በማጎንበስ
"ና ወደኔ "አለው፡፡ አድማስ ወደ ጠንቋዩ ተጠጋ ፡ አቢያራ በሚያስፈራ ሹክሹክታ
" ይሄንን ወይፈን እፈልገዋለው ፡ማንም እንደይነካው ፡ለየት ያለ ወይፈን ነው ፡ በቀላሉ ያመነበትን ፡ነገር የሚቀይር ፡አይደለም፡ ስለዚ እምነቱን ቀስበቀስ ፡ከውስጡ ሸርሽሬ ነው የማስወጣው ፡ ከዛ ግን የኔ ልዩ ታማኝ ፡አደርገዋለው ፡ እንዲ አይነቱን ፡ፈረስ ቀልቤ ይወደዋል ፡ የኔ ባሪያ ነው የኔ የኔ ,,,,,"አለው አይኖቹ በፍላጎት እያንፀባረቁ ፡ አድማስ የሚፈራውን ፡የጠንቋዩን አይን ፡ሲያይ ፡ልቡ ተረበሸበት ፡እናም ትህዛዙን እንደሚያከብር ደጋግሞ በማጎንበስ ቃል ገባ
"በል አሁኑኑ አስወጥተህ ፡በአትክልቱ ስፍራ እንደሚፈልገው አድርግለት ፡በጭራሽ እንዳትነኩት ይታጠብ ፡ ነጭ ልብስ አልብሰው እንዳሸነፈ ሆኖ እንዲሰማው ፡አድርግ ፡ በቁጣ ሳይሆን ፡በሰላም አናግረው ፡ "አለ ጠንቋዩ፡፡አድማስ ግራ ገባው ፡ስለምንድነው ለዚ ልጅ ክብር የሚሰጠው፡ ለምን ካል ተቀበለን ፡እንደ ሁል ጊዜው ለመስዋት ፡አይቀርብም ፡ ምን አዲስ ነገር አለ እሱ ላይ ፡ ብሎ አስቦ ፡መልሶ አቢያራ የውስጡን እንዳይሰማበት ፈራ እና ይቅር በለኝ አባቴ አለ ፡ አቢያራ ልክ የአድማስን ፡አሳብ ያወቀ ይመስል ፡ "ችግር የለም የልኩህን አድርግ "ብሎት ፡ ወደ መሳይ ተጠግቶ ጥቁር ጓንት የለበሰ ሰፊ እጁን አናቱ ላይ ጫነው ፡መሳይ ፡ለማምለጥ ፡ጭንቅላቱን አንቀሳቀሰ ፡አቢያራ ፡ የትህቢቱን መጠን በመገረም ፡አስተውሎ ፡ሲያበቃ ፡እጁን ፡ሰብስቦ ፡ረጅም ፡ጥቁር ፡ቀሚሱን ፡እየነሰነሰ ፡ ወደ ራሱ ዋሻ ሄደ ፡ አድማስ ፡ያለምንም ፡ንግግርና እንቅስቃሴ ፡ጥጓን ፡ይዛ ወደቆመችው ፡ኤዛ ፡በመዞር ፡ ምልክት ሰጣት ፡ጠጋ ብላው ቆመች "አባታችን ፡ይሄን ልጅ ፡ እንድንታዘዘውና ፡በአትክልት ቦታው ካለው ፡ክፍል ፡እንድናስቀምጠው ነገሮናል ፡ስለዚ ፡ወደ መታጠቢያው ፡ውሰጂው፡ እናም ፡ነፃ ያለ ልብስ ፡ስጪው ፡ ለሱ ለየት ያለ የእንግድነት ጊዜ እንድንሰጠው ፡ ከአባታችን መልህክት እንደተላለፈልን ንገሪ "አላት ፡ ኤዛ ፊቷ ፡ፈገግ ያለ መሰለውና አድማስ ልብ ብሎ አያት ፡ እናም ፡ መልሶ ፡አሰበ ፡ትህዛዙን ጥሳ ፡ ቆራርጣ እንዳትጥለው ፡ "አባት አቢያራ ነው ያዘዘው ኤዛ አንዳች ነገር እንዳታደርጊው ፡"አላት ጭንቅላቷን ፡ብቻ ፡አወዛወዘች ፡ አድማስ ፡የአራቱንም ፡ሴቶች ፡ባህሪ የሚያመሳስልበት ፡አጋጣሚ እንግዲ ፡ ካልፈለጉ ለረጅም ሰአት ፡ አለማውራታቸውን ፡ነው ፡ በፀጥታ ፡ለሚታዘዙት ነገር ፡አንገታቸውን ፡እንደነቀነቁ የሚውሉበት ፡ጊዜ አለ ፡ ቆንጆ እና ማራኪ ባይሆኑ አስፈሪ እነታቸው ፡ከዝምታቸው ጋር ፡በበዛ ነበር ,,,,,,,,,,,,ኤዛ የመሳይን እጅ ይዛ እንዲነሳ ስትረዳው ፡ መሳይ ሊገሉት እንደሆነ በማሰብ ፡ለፈጣሪው ፡ አንድ ነገር ፡እንዲያደርግለት እየፀለየ ተከተላት ፡ ኤዛ ፡ጨብጣ የያዘችው ፡የመሳይ እጅ ፡ አንዳች ደስ የሚል ስሜት ሲያሰማት ፡በመገረም ፡ደጋግማ ዞራ እያየችው ፡ነበር ፡የምትሄደው ፡ ዋሻውን ፡ እንደልቧ ፡እጥፍ ፡እጥፍ ፡እያለች ፡ስትሄድ ፡መሳይም ፡መገረሙ አልቀረም ፡እንዴት ፡በጨለማውስጥ ፡ያለምንም ፡እንከን ፡መጓዝ ፡ቻለች ፡ብሎ ፡ በመጨረሻ አንድ ክፍል ስትደርስ ፡ወደውስጥ ፡ገብቶ ፡እንዲታጠብ ፡ነግራው ፡ ቆመች ፡ መሳ በመገረም ፡አያት ፡ ንግግር አቁማ ምልክት ሰጠችው ፡ ፈራት እውስጥ ስገባ እንደ ቫንባየር ተቀይራ ልትቦጫጭቀኝ ነው እንዴ አምላኬ ድረስልኝ ፡አለ ለራሱ ፡ትህዛዟ ጠንከር ሲልበት ፡ወደውስጥ ፡ገባ ፡ ከውስጥ ፡የመታጠቢያ ገንዳ የመሰለ ነገርና በባሊ ውሃ ተቀምጦ አየ ፡ ጥቂት ግራ በመጋባት ከቆመ በዋላ ፡ ወደ ገንዳው ሄዶ ፡ልብሱን ፡ አወላለቀ እና ገንዳ ውስጥ ፡ገባ ፡ ,,,,,,,,,,,

ሙና መሀመድ

ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍44🥰2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አርባ_አምስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

“ቆንጅዬ ልጅ ይዘሻል” አለ ረጅሙ ፖስተኛ በፍርሀት ቀሚሴን ጥብቅ አድርጋ የያዘችውን ኬሪን በአሳዛኝ አይን እየተመለከተ። “ይህንን ስናገር ቅር
ካላላችሁ ትንሽ ያመማት ትመስላለች።”

“አሟት ነበር” ክሪስ አረጋገጠለት፡ “ግን አሁን ይሻላታል” አለው። ፖስተኛው ጭንቅላቱን ነቀነቀ፤ የነገርነውን ያመነ ይመስላል።

“ትኬት ይዛችኋል?”


“ገንዘብ ይዘናል፤ ለትኬቱ ክፍያ የሚበቃ ገንዘብ ይዘናል” አለ

“ስጠኝ ልጄ፤ የአስራ አንድ ሰአት ከአርባ አምስት ደቂቃው ባቡር መጥቷል”
አለው በዚያ ማለዳ ወደ ቻርለትስቪል በሚወስደው ባቡር ስንጓዝ የፎክስወርዝ ግዙፍ ቤት በኮረብቶቹ ላይ ከፍ ብሎ እያየነው ነበር። እኔና ክሪስ አይኖቻችንን
ከእሱ ላይ መንቀል አልቻልንም: እስር ቤታችን ከአይናችን እስኪሰወር ድረስ ውጪ እየተመለከትነው ነበር በተለይ በጥቁር መጋረጃ የተዘጉትን የጣሪያ
ስር ክፍል መስኮቶች እያየናቸው ነበር

ከዚያ ትኩረቴ በሰሜን አቅጣጫ ባለው የሁለተኛው ፎቅ የመጨረሻ ክፍል ሄደ ከባዱ መጋረጃ ተከፍቶና ጥላ የሚመስል ከሩቅ የሚታይ የግዙፍ
አሮጊት ሴት ምስል ወጥቶ ሲፈልገንና… ከዚያ ሲጠፋ ታይቶኝ ክሪስን ጎነተልኩት።

እርግጥ ነው ባቡሩን ማየት ትችላለች: ግን እዚያ ሆነን መንገዶቹን ማየት
እንደማንችለው ሁሉ እሷም እንደማታየን አውቀናል። ቢሆንም ግን እኔና
ክሪስ መቀመጫችን ላይ እንዳለን ወደ ታች ሸርተት አልን፡

“በዚህ ጠዋት ምን ትሰራ ይሆን?” ስል ክሪስን በሹክሹክታ ጠየቅኩት።
“በተለምዶ እስከ አስራ ሁለት ሰአት ተኩል ድረስ ምግባችንን ይዛ አትመጣም”

ሳቀ። የምሬት ሳቅ ይመስላል። “ምናልባት የሆነ ኃጢአት ወይም የተhለከለ ነገር ስንሰራ ለመያዝ ጥረት እያደረገች ይሆናል” አለ። ይሆን ይሆናል። ግን እዚያ ክፍል ውስጥ ገብታ ባዶ ሆኖ ስታገኘውና ልብሶቻችንም ማስቀመጫው ውስጥ ያለመኖሩን ስታይ፣ ከዚያ ስትጣራ፣ ምንም አይነት ድምፅም ሆነ ሮጦ
የሚመጣ የእግር ኮቴ ሳትሰማ ስትቀር የምታስበውንና የሚሰማትን ባውቅ ደስ ይለኝ ነበር።

ቻርለትስቪል ስንደርስ ወደ ሳሪሶታ የሚያደርሰንን የአውቶቢስ ቲኬት ስንገዛ
ወደ ደቡብ የሚሄደውን አውቶቢስ ለመያዝ ሁለት ሰአት መጠበቅ እንዳለብን
ተነገረን።

በሁለት ሰአት ውስጥ ጆን ጥቁሩን ሊሞዝን ይዞ ቀርፋፋውን ባቡር
ይቀድመዋል!” አልኩ
“አታስቢ” አለ ክሪስ፡ “ስለ እኛ ለእሱ የምትነግረው ሞኝ አይደለችም ምናልባት
በራሱ መንገድ ካላወቀ በስተቀር" እንዲከተለን ከተላከም እንዳያገኘን ምርጡ መንገድ አለመቆም እንደሆነ አሰብን ዕቃ ማስቀመጫ ተከራይተን ሁለቱን ሻንጣዎቻችንንና ጊታሩን አስቀመጥን ኬሪን መሀከል አድርገን እጅ ለእጅ ተያይዘን ዋና ዋና መንገዶች
ተከትለን የፎክስወርዝ ሰራተኞች በእረፍት ቀናቸው ዘመድ ለመጠየቅ ዕቃ ለመግዛትና ሲኒማ ለመግባት ወይም በሌሎች መንገዶች ራሳቸውን ለማስደሰት የሚመርጡትን ከተማ በደንብ አየነው። ሀሙስ ቢሆን ኖሮ በጣም
ያስፈራ ነበር። ግን እሁድ ነው።

በልካችን ያልሆኑ ልብሶቻችን፣ ጫማዎቻችን፣ ያልተስተካከለው የፀጉር
ቁርጣችንና የገረጣው ፊታችን ከሌላ አለም የመጡ ጎብኚዎች መስሎኝ ነበር። ግን እንደፈራሁት ማንም አላፈጠጠብንም ልክ የሰው ዘር እንደሆንን ነው የተቀበሉን እንግዳ ፍጡር አልመሰልናቸውም ብዙ ሰዎች ወዳሉበት ቦታ መመለሳችን በጣም ጥሩ ነበር: የተለያዩ ፊቶች ያሉበት ቦታ መሆን።

“ሁሉም እየፈጠነ ወዴት እንደሚሄድ አይገርምም?” ስል ክሪስን ጠየቅኩት:
መወሰን አቅቶን ጥግ ላይ ቆምን፡ ኮሪ የተቀበረው ከዚህ ብዙም ሳይርቅ
እንደሆነ ገመትኩ። መቃብሩን ፈልጌ አበባ ማስቀመጥ በጣም ፈለግኩ።በሌላ ቀን ቢጫ አበቦች ይዘን ተመልሰን እንመጣና ይጥቀምም አይጥቀም ተንበርክከን ፀሎት እናደርስለታለን፡ ለአሁኑ ግን ኬሪን ከአደጋ ለመጠበቅ ወደ ዶክተር ከመውሰዳችን በፊት . . . ከቨርጂኒያ ርቀን በጣም ርቀን መሄድ አለብን

የዚያን ጊዜ ነው ክሪስ በኪስ ወረቀት የያዘውን የአይጥ ሬሳና ስኳር
የተነሰነሰባቸውን ዶናቶች ከጃኬት ኪሱ ያወጣው ኮስታራ አይኖቹ ከአይኖቼ
ጋር ተገናኙ ኪስ ወረቀቱን ፊት ለፊቴ ይዞ ፊቴን እያጠና በአይኖቹ “አይን ላጠፋ አይን?” እያለ ጠየቀኝ፡

“ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደን ታሪካችንን መናገር እንችላለን" አለ ክሪስቶፈር
አይኖቹን ከእኔ እያሸሸ፡ “መንግስት ለአንቺና ለኬሪ ማደጎ ቤት ይፈልግላችኋል።
ስለዚህ መኮብለል አይጠበቅባችሁም: ለእኔ ደግሞ አላውቅም . . .
ክሪስ የሆነ ነገር ካልደበቀኝ በስተቀር አይኖቼን ሳያይ አያወራም: ያ የተለየ ነገር ከፎክስወርዝ አዳራሽ እስክንወጣ መቆየት የነበረበት ነገር መሆን አለበት።“እሺ ክሪስ አሁን አምልጠናል ምንድነው የደበቅከኝ ተናገር!

ኬሪ ብዙ መኪናዎች ወዲያ ወዲህ ሲሉና አንዳንድ ሰዎች ፈገግ እያሉላት
እየፈጠኑ ሲያልፉ አይኖቿ በአድናቆት ፈጥጠው ወደ እኔ ተጠግታ ቀሚሴን
ስትይዝ ክሪስ አንገቱን ደፋ አደረገ።

እናታችን ናት” አለ ዝቅ ባለ ድምፅ:: ከአባቷ ለመውረስ እንድትችል እሽታውን ለማግኘት ምንም ነገር እንደምታደርግ ስትናገር ታስታውሻለሽ? ምን ቃል እንዳስገባት አላውቅም ካቲ፣ ግን ሠራተኞቹ ሲያወሩ ሰምቻለሁ።
ወንድ አያታችን ከመሞቱ ጥቂት ቀናት በፊት፣ ኑዛዜው ውስጥ ተጨማሪ ቃል ገብቷል። ያስገባው ቃል የሚለው እናታችን ከመጀመሪያው ባሏ ልጆች እንዳሏት ከተረጋገጠ የወረሰችውን ንብረት በሙሉ በቅጣት መልክ ትመልሳለች
በገንዘቡ የገዛቻቸውን ነገሮች ሁሉ፣ ልብሶቿን ጌጣጌጦቿንና ዋጋ የሚያወጡ ነገሮችን በሙሉ ትመልሳለች። ያ ብቻ አይደለም: ያፃፈው
ኑዛዜ ውስጥ ከሁለተኛ ትዳሯ ከወለደችም ሁሉንም ነገር ታጣለች: እና
እናታችን ይቅር እንዳላት ታስባለች። ይቅር አላላትም፣ አልረሳምም፣ መቃብር
ውስጥ ሆኖ እንኳን እየቀጣት ነው::”

ነገሮችን ሳገጣጥም አይኖቼ በድንጋጤ ፈጠጡ። “ማለት እናታችን . . . ?
እናታችን ናት አያትየው አልነበረችም?”

ሊሰማው እንደሚችል ባውቅም ግን ልክ ግድ እንደሌለው ሁሉ ትከሻውን
ሰበቀ: “ያቺ አሮጊት አልጋዋ አጠገብ ሆና ስትፀልይ ሰምቻታለሁ። ክፉ ናት፣ ግን ዶናቶቹ ላይ መርዝ መጨመሯን እጠራጠራለሁ።ወደ እኛ
ይዛቸው ትመጣለች... እንደምንበላቸውም ታውቃለች ግን እንዳንበላቸው ታስጠነቅቀን ነበር።"

“ግን ክሪስ፣ እናታችን ልትሆን አትችልም ዶናቶቹ በየቀኑ መምጣት ሲጀምሩ
እሷ የጫጉላ ሽርሽር ላይ ነበረች”

ፈገግታው የመምረርና የመጠየፍ ነበር “አዎ ግን ከዘጠኝ ወር በፊት ኑዛዜው
ተነቦ ነበር፤ ከዘጠነኛ ወር በፊት እናታችን ተመልሳ ነበር። ከወንድ አያታችን
ኑዛዜ የምትጠቀመው እናታችን ብቻ ናት ሴት አያታችን አይደለችም እሷ
የራሷ ገንዘብ አላት፡ የእሷ ስራ በየቀኑ ቅርጫቱን ማምጣት ብቻ ነበር።"

መጠየቅ የምፈልጋቸው ብዙ ጥያቄዎች ነበሩኝ፡ ግን ኬሪ ነበረች: ቀሚሴን
ይዛ አተኩራ እያየችኝ ነበር ኬሪ በተፈጥሮ ሞት መሞቱን እንጂ ሌላ ምንም
ነገር እንድታውቅ አልፈለግኩም: የዚያን ጊዜ ነው ክሪስ ማስረጃ የሆነውን
👍501👎1🔥1
ኪስ ወረቀት እጄ ላይ ያስቀመጠው "አንቺ ነሽ መወሰን ያለብሽ አንቺና
ደመነፍስሽ ሁልጊዜ ትክክል ናችሁ፤ በፊት ሰምቼሽ ቢሆን ኮሪ ዛሬ በህይወት
ይኖር ነበር:”
ፍቅር ከወለደው መከዳት በላይ ጥላቻ የለም እና አእምሮዬ ለበቀል እየጮኸ ነው። አዎ፣ እናቴና ሴት አያቴ እስር ቤት ውስጥ እንዲቆለፍባቸው፣
እንዲፈረድባቸው፣ ታስቦበት ስለተደረገ ነፍስ ግድያ ማሰባቸው ሁሉ ተቆጥሮ
እንዲጠየቁ እፈልጋለሁ። ልክ ወጥመድ ውስጥ እንዳሉ አይጦች እንዲሆኑ እፈልጋለው። ከእኛ የሚለዩት የሀሺሽ ሱሰኞች፣ ሴተኛ አዳሪዎችና እንደ እነሱ ነፍሰ ገዳይ የሆኑ ሰዎች መሀል ሲታሰሩ ብቻ ነው: ልብሶቻቸው የእስር ቤት የደንብ ልብስ ይሆናል፡ እናታችን ደግሞ በሳምንት ሁለት ጊዜ የውበት ሳሎን
መሄድ፣ ሜካፕ መቀባት፣ በባለሙያዎች ጥፍሮቿን መሰራት አትችልም
በሳምንት አንድ ጊዜ መታጠብ ብቻ! እንዳይታዩ የምትፈልጋቸው የሰውነት
ክፍሎቿን ያለ ማሳየት መብቷን ሁሉ ታጣለች:: ትልቁ አልጋዋ ላይ አብሯት
የሚተኛ አፍቃሪ የሆነ መልከመልካም ባል አይኖርም::”

እግዚአብሔር ሊኖርበት ይችላል ወደሚባልበት ሰማይ ቀና አልኩ። በራሱ
መንገድ እንዲዳኘው ሚዛኑን እንዲያመጣጥንና ፍትህ የመስጠቱን ሸክም
ከእኔ ላይ እንዲወስድልኝ ልፈቅድለት እችላለሁ?

ክሪስ ውሳኔ የመስጠቱን ሸክም ትከሻዬ ላይ ማድረጉ ጭካኔና ፍትህ አልባነት
ነው ብዬ አሰብኩ። ለምን?
ለሁሉም ነገር… ለኮሪ መሞትና እኛን ለመግደል ላደረገችው ጥረት ሁሉ
ይቅር ሊላት ፈልጎ ነው? እንደ እሷ አይነት ወላጆች እንደዚህ አይነት ነገሮች
ነፍስ ግድያም ቢሆን እንድታደርግ ገፋፍተዋት ነው ብሎ ምክንያት ሊሰጥ
ነው? አራት ልጆቼን እንድገድል የሚያደርግ በአለም ላይ በቂ የሆነ ገንዘብ ይኖራል?

አእምሮዬ ውስጥ አባቴ ከመሞቱ በፊት ወዳሉት ቀናት የሚመልሱኝ ምስሉ
ብልጭ አሉብኝ፡ ከጓሮ ያለው የአትክልቱ ቦታ ውስጥ፣ ሁላችንም ስንስቅና
ስንደሰት አያለሁ በባህሩ ዳርቻ ላይ በጀልባ ስንቀዝፍ፣ ስንዋኝ ወይም
ተራሮቹ ያሉበት ጋ የበረዶ ላይ ሸርታቴ ስንጫወት አያለሁ እናታችን ወጥ
ቤት ውስጥ ሆና እኛን ለማስደሰት ምርጥ ምግብ ስትሰራልን ይታየኛል።

ክሪስ እኔ እንደማስበው እያሰበ ይሆን? ማለቴ፣ ወደ ፖሊስ ሄደን ታሪካችንን
ብንናገር ፎቷችን ሀገሪቱ ውስጥ ባሉት ጋዜጦች የፊት ገፅ ላይ ይወጣል
የነገሩን አደባባይ መውጣትስ ያጣነውን ያካክስልናል? የግል ህይወታችንን፣አብረን የመቆየት ፍላጎታችንን ያሟላልናል? ሁሉንም ለማግኘት ብለን እርስ
በርስ መተጣጣት እንችላለን?

እንደገና ወደ ሰማይ ቀና አልኩ።

እግዚአብሔር እዚህ ታች ላለነው ትንንሽ ደካማ ተዋንያን ይህንን ድርሰት
አልፃፈም በምንኖረው በእያንዳንዱ ቀን፣ በምንናገረው እያንዳንዱ ቃል፣ አእምሯችን ላይ በተቀረፀው እያንዳንዱ ሀሳብ ድርሰቱን የፃፍነው ራሳችን ነን እናታችንም የራሷን ድርሰት ፅፋለች ታሪክ የሆነ!

አንድ ጊዜ በሁሉም ነገር ፍፁም ናቸው የምትላቸው አራት ልጆች ነበሯት።
አሁን ምንም የላትም! አንድ ጊዜ የሚወዷትና በሁሉም ነገር ፍፁም አድርገው
የሚቆጥሯት አራት ልጆች ነበሯት አሁን አንድም ልጅ የላትም! ሌላም
ልጆች እንዲኖሯት ብትፈልግም አታገኝም ገንዘብ ሊገዛቸው ለሚችላቸው ነገሮች ያላት ፍቅር፣ በአባቷ ኑዛዜ ላይ ለተጨመረው ጨካኝ ቃል ለዘለዓለም ታማኝ እንድትሆን አድርጓታል።

እናታችን ማርጀቷ አይቀርም ባሏ ደግሞ ከእሷ በአመታት ያንሳል።ብቸኝነትን የምትጋፈጥበት ጊዜ ይመጣል። የዚያን ጊዜ በተለየ መንገድ
ባደረግኩት ኖሮ ብላ መመኘቷ አይቀርም።

በእርግጠኝነት አንድ ቀን ክንዶቿ የእኛ የሆኑ ልጆች ለመያዝ ይፈልጋሉ።
ራሳችንን ሰው ለማድረግ ከዚህ ከተማ በአውቶቡስ ተሳፍረን ወደ ደቡብ
እንሄዳለን። እንደገና እናታችንን ካየናት በእርግጠኝነት እጣ ፈንታ በዚያ መንገድ ያመቻችልናል፧ የዚያን ጊዜ በቀጥታ አይኖቿን እየተመለከትን ጀርባችንን እናዞራለን፡፡

ኪስ ወረቀቱን ቅርብ ባለው የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ጣልኩት።

“ካቲ ነይ!” ክሪስ እጆቹን ዘርግቶ ተጣራ፡ “የሆነው ሆኗል፡ ያለፈውን ተሰናበቺና
የወደፊቱን ሰላም በይ: ጊዜ አባክነናል፡ በጣም ብዙ ጊዜ አጥፍተናል። አሁን ሁሉም ነገር ከፊታችን አለ፡ እየጠበቀን ነው" አለኝ።

እውነትም ህያውና ነፃ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ያደረጉና የበቀል ሀሳቦችን
ለመርሳት ነፃ የሚያደርጉ ትክክለኛ ቃላት ነበሩ። ሳቅኩና ዞሬ እጄን እጁ
ውስጥ ወደማደርግበት ተዘርግቶ ወደተዘጋጀውና ወደሚጠብቀኝ እጁ ሮጥኩ
ነፃ በሆነው እጁ ኬሪን ብድግ አድርጎ አስጠግቶ አቀፋትና ጉንጯን ሳማት።
“ኬሪ ሁሉንም ነገር ሰምተሻል? አበቦች አመቱን ሙሉ ወደሚያብቡበት
ወደዚያ እየሄድን ነው፡ ያ ፈገግ እንድትይ አያደርግሽም?” አላት
ፈገግ ማለት እንዴት እንደሆነ የረሳች ይመስል ትንሽዬ ፈገግታ የገረጡ
ከንፈሮቿ ላይ ብልጭ ብሎ ጠፋ: ያ ለአሁን በቂ ነው!

ቅጣይ

ቀሪውን ህይወታችንን መሰረት ስላደረግንባቸው የመጀመሪያ አመታት መናገር የጨረስኩት በእፎይታ ነው።

ከፎክስወርዝ አዳራሽ ካመለጥን በኋላ የራሳችንን መንገድ ጀመርን... እናም
ሁልጊዜ ወደ ግቦቻችን ለመድረስ መጣር እንደሚገባን አውቀናል።

ህይወታችን ሁልጊዜም ውሽንፍር የበዛበት ነበር። ግን እኔና ክሪስ ከሞት
የተረፍን መሆናችንን አስተምሮናል፡ ለኬሪ ግን በጽጌረዳዎች ተከባ የምትኖርም ቢሆን እንኳን ከዚህ የተለየ ነው፡ ቢሆንም እንኳን ኮሪ የሌለበትን ህይወት እንድትመራ እንድትፈልግ፣ መኖሩንም እንድታምን መደረግ ነበረባት።

ለኬሪ ግን ከዚህ የተለየ ነው በጽጌረዳዎች ተከባ የምትኖር ቢሆንም እንኳን
ኮሪ የሌለበት ህይወት እንዳለ እንድታምን መደረግ ይኖርበታል።

አሁን ግን ጥያቄው እንዴት ነው መኖር የምንችለው? የሚለው ነው ያ ደግሞ ሌላ መፅሐፍ የሚወጣው ታሪክ ነው።

ተፈፀመ
👍79😢16👏1312🥰7😁2
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_አርባ_አምስት ፡ ፡ #ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ “ቆንጅዬ ልጅ ይዘሻል” አለ ረጅሙ ፖስተኛ በፍርሀት ቀሚሴን ጥብቅ አድርጋ የያዘችውን ኬሪን በአሳዛኝ አይን እየተመለከተ። “ይህንን ስናገር ቅር ካላላችሁ ትንሽ ያመማት ትመስላለች።” “አሟት ነበር” ክሪስ አረጋገጠለት፡ “ግን አሁን ይሻላታል” አለው። ፖስተኛው ጭንቅላቱን ነቀነቀ፤ የነገርነውን ያመነ ይመስላል። “ትኬት…»
የጠንቋዩ ዋሻ
፠★፠ክፍል 8፠★

የውሃው ቅዝቃዜ ጩሁ ጩሁ ያሰኛል ፡ መሳይ በመጥለቂያው እየቀዳ ሰውነቱ ላይ ባፈሰሰ ቁጥር ፡ ድምፅ ያወጣ ነበር እና ፡ ኤዛ ባለችበት እንዳለች መቆየት ተሳነት ፡ እናም ምን እየሆነ ነው ብላ በማሰብ ፡ በቀስታ የከለላቸውን ወፍራምና ቀይ መገረጃ ገልፃ ገባች ፡ ስትገባ ፡የመሳይና ፡እርቃን በማየቷ ፡ ባለችበት ደንዝዛ ቀረች ፡ መሳይ የኤዛ መግባት ስላስደነገጠው ፡ በመጥለቂያው ፡የያዘውን ውሃ እንዳንከረፈፈ ፡ በፍርሃት ፡አይኖቿን አያት ፡ ቀጥሎ ፡ኤዛ ወደ ሚያስፈራ አውሬነት ፡መቀየሯ አይቀርም ፡ብሎ ፡ተጠባበቀ ፡ የለበሰችው ቀይ ቀሚስ ረጅም ሉጫ ፀጉሯ ፡ትላልቅ አንፀባራቂ አይኖቿ ሳሟት ሳሟት የሚያሰኙት ወፈር ያለው ልብ ቅርፅ ከንፈሯ ውብና ማራኪ ቁመናዋ ፡ በመሳይ አይኖች ውስጥ ቦታ አልነበራቸውም ፡ ለመሳይ የሚሰማው ፡ የሴጣን መልህክተኛነቷ ፡ብቻ ነው ፡ ኤዛ ፡ ለሰከንዶች ፡ተከፍቶ ፡በአድናቆት የቀረውን ፡ አፏን ፡ዘጋችው ፡እና ወደመሳይ ቀረበች ፡ መሳይ ገንዳ ውስጥ ፡ አንቃ ስታስቀረው ተሰምቶት ፡ ሰውነቱ ተሸማቀቀ ፡ኤዛ መናገር ጀመረች ፡" እእእ የተለየ ነገር ነው የሚታየኝ ፡ "ብላ አንድ ነገር ላይ እንዳተኮረች ሲገባው ፡ መጥለቂያውን ለቆ እጆቹን በፍጥነት ፡ ከለለ መጥለቂያው እየተንኳኳ ሲወድቅ ፡ ኤዛ ግራ በመጋባት ፡እና በልተረዳስው ሁኔታ ፡አስተዋለችው ፡ እና ሊሸሸጋት በመሞከሩ ፡ ፊቷ ላይ ቁጣ ታየ ፡
"ወንድ ልጅ ምምን እንደሚመስል አታውቂም እንዴዴዴ "አላት እየተጠጋችው እንደሆነ ሲያውቅ የሞት ሞቱን ፡ ድንገት ፡ፊቷ ቀልቶ ፡ቆጣ ስትል ደሞ ፡ በጥፍሮቿ ፡ዘልዝላ ልተበጣጥሰው ያሰበች ነው የመሰለው
" አይቼ አውቃለው ፡ ጌታ አቢያራን ፡ በሳምንት ፡አንዴ ፡አየዋለው ፡ አጥበዋለው ፡ ሁላችንም ፡ለጌታችን ያለንን ፡ክብር ፡ በዚ መልኩ እየተፈራረቅ እንገልፅለታለን ፡ እእእ ነገር ግን የሱ ሰውነት ካንተ ጋር የተለያየ ነው ፡ እንዳንተ በጭራሽ ፡አይደለም ፡ "ብላ ትኩረቷን ሳትቀንስ ፡አየችው ፡ በውስጧ ፡ደሞ ፡የአቢያራ መንፈስ፡ስለምትናገረው ፡ነገር ፡ይቅር ፡እንዲላት ፡ለመነችው
"ይሄ ጠንቋይ እያንዳንዳችሁን ይጫወትባችዋላ ማለት ነው ፡" ሲላት ፡ ኤዛ በፍጥነት አንገቱን ፡አንቋ ፡በመያዝ "ዳግም ጌታዬን በዚ ስም እንዳትጠራው ፡እሱ የኛ ጠባቂ ነው ፡እሺ ፡አንተ ሚዳቆ "ብላ ጮኽችበት ፡ መሳይ ፡ ልቡ እየፈራ ምላሱ ለምን ቀደም ቀደም እንደሚል ለራሱም ፡ይገርመዋል ፡ በኤዛ እጆች ውስጥ ሲገባ ፡ እንደገመተው ፡ ሞቱ የቀረበ መሰለው፡ እና አይኑን ጨፈነ ፡ ቤተሰቦቹን አሰበ እናቱን አባቱን ፡ አንድ ልጃቸውነውና ፡እሱን ፍለጋ የማይደርሱበት ፡ቦታ እንደሌለ ፡ ያውቃል ፡ስቃያቸውን ፡ተሰቃየ ፡ በተለይ ወደባሻ እናቱን ፡አሰባት ፡ አሳዘነችው ፡ ምን ፡ቢያስቸግራት ፡ ሁሉንም ፡ችላ ዝም ብላ ፡ፍቅሯን ፡ብቻ ታሳየው የነበረች ፡እናቱ እሱን ፍለጋ ስትንከራተት ተያው ፡ እዚ ምንነታቸው ፡ግራ በሚያጋቡ ፍጡሮች ፡ አንገቱን ተቀንጥሶ ፡እንደዋዛ ፡ሊጣል ፡ነው ፡
ኤዛ በእጆቿ ፡የመሳይን ፡አንገት ፡ይዛ ፡በይ በይ ፡ከሚላት ፡ክፉ መንፈስ ፡ጋር ታገለች ፡ ግደይ ፡ግደይ ፡የሚል ስሜቷን ፡ለመቆጣጠር ፡ ዘገየች ፡ እናም ፡መሳይ ፡ ሸብረክ ፡ሲል ፡ ከክፉ መንፈሷ ፡ነቃችና ፡ አየችው ፡ መሳይ እጇ ፡ለስለስ ፡ሲልለት ፡ አልቃሻ አይኖቹን ገልፆ አያት ፡ ኤዛ አይኑን ፡ሲገልፅ ፡ስታየው ፡የቀድሞ ፡አዛኝ ፡ልቧ ፡ተመለሰ ፡ እናም ፡አንገቱን ፡ለቃ ፀጉሩን ፡ መዳበስ ፡ጀመረች ፡ እንዲ አይነት ነገር አድርጋ አታውቅም ፡እና እጆቿ ፡በራሳቸው ፡መንገድ ፡ሲንቀሳቀሱ ለራሷም ፡ገረማት ፡ መሳይ ፡በፀጉሩውስጥ ፡የሚንሸራሸረውን ፡የኤዛን ፡ጣቶች ፡ እየፈራ ሰአል ቢጤ እያሰማ ነበር ፡ ኤዛ ፡በነካችው ቁጥር ፡ ይበልጥ ፡ተጠጊው ፡የሚል ስሜቷ ፡ይገፋፋት ፡ጀመር እናም ስትጠጋው ፡መሳይ ፡ሲሸሽ የገንዳው ጫፍ ላይ ደርሶ ሊወድቅ ፡ሆነ ፡ ኤዛ እንደመወራጨት ሲል ፡ ከድርጊቷ ፡በፍጥነት ፡ታቀበች ፡ እናም ፡መሳይን ፡ ለቃ ፊቷን ፡ወደመጋረጃው ፡አዙራ ተንበረከከች ፡"ይቅር በለኝ ፡ ጌታ አቢያራ ይቅር በለኝ "እያለች ስትማፀን ፡መሳይ የታነቀበትን ቦታ እያሻሸ ፡በመገረም ፡ተመለከታት ፡ በልቡ ምን አልባትም ፡እዚ አካባቢ ያለው ፡ሴይጣን ፡አቢያራ ፡ብቻ ነው ፡ ሌሎቹ እንደኔ ጓደኞች ፡ በአቢያራ ፡ ስነ ልቦናቸውን ፡የተነጠቁ ይሆናሉ አለ ፡ ኤዛ ከተንበረከከችበት ተነስታ ፡ ወደ መሳይ በመቅረብ ፡
"በፍጥነት ታጠብና እዛች ጋር ነጭ ሽርጥ አለልህ ፡ ለብሰ ውጣ ከደጅ እጠብቅሃለው ፡"ብላ ዞራ ሳታየው ፡ የልቧን ፡እረብሻ እየታዘበች ፡ወጣች ፡

ሙና መሀመድ

ይቀጥላል.....


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍29🥰5
#ሳቤላ


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

በተከታዩ መጋቢት አንድ መንገደኛ ወደ ግረኖብል መጣ በጣም ንፋሳም ቀን ነበር ሰውየው እንግሊዛዊ ነበርና አንዱን ዕቃ ተሸካሚ ጥሩ ሆቴል የት እንደሚገኝ እንደ ነገሩ በሚችለው በእንግሊዛዊ ፈረንሳይኛ ጠየቀው "
ሰውየው አሰብ አደርገና በእርጋታና በትሕትና አንድ አካባቢ ላይ ሁለት
ጥሩ ሆቴሎች አሉ ትርዋ ዶፏ እና አምባሳዶሮች ከሁለቱም እኩል አገልግሎት ሊያገኙ ይችላሉ
እንግዳው ሰው ባጋጣሚ አምባሳደሮችን መረጠና ሔደ
ትንሽ ዐረፍ እንዳለ ወደ ግረኖብል አደባባይ የሚወስደውን መንገድ ጠየቀ እሱ እንኳን መሪ ተሰጥቶት
ነበር ግን ብቻውን መሔድ ፈለገ ከቦታው ደርሶ ወይዘሮ ሳቤላ ቬን ወደምትኖርበት ቤት ታጠፈ "

ሳቤላ አሁንም ሙቀቱን የእሳቱን ፍንጣሪ ጭምር ደጅ እየጠናች ልክ ባለፈው ታኅሣሥ ከነበረችበት ቦታና ሁኔታ እሳቷን አቅፋ ተቀምጣለች" እሳቱን ምን ያህል እንደ ተጠጋችው ለተመለከተ በነበልባሉ ልብሷ አለመያያዙ ያስገርመዋል " ክፍሉን
ቀና ብሎ ለሚያይ ሁሉም ነገር ሳይነካካ ስለ ነበር ባለፈው ታኅሣሥ ሳይሆን በትናንቱ ዕለት ያየው ይመስለው ነበር " በአልጋው አጐበር በከፊል የተጋረደውና
ሕፃኑ ተጠቅልሎ የተኛበት የልጅ አልጋ እንኳን ከነበረበት አልተለወጠም።

ወይዘሮ ሳቤላ አካላቸውንና አእምሮአቸውን በታመሙ ሰዎች ላይ እንደሚደርሰው ሁሉ የሷም ጤንነት ቶሎ አልመለስ አለ ከላይ በተባለው ዐይነት እንደ
ተቀመጠች ሱዛን ገብታ አንድ እንግሊዛዊ መኮንን መምጣቱን ነገረቻት "

ሳቤላ ደነገጠች እሷን የሚጠይቅ እንግሊዛዊ መኮንን ማን ይሆን ብላ ተጠራጠረች

“ መቸም እንግሊዛዊ ነው ” አለች ሱዛን ፈረንሳይኛውን ለመረዳት ተቸግራ ስለ ነበር" “ ረጅም መልከኛ ረጋ ያለ መስፍን የመሰለ ከባድ ሰው ነው ” ብላ
አብራራችላት "

ወይዘሮ ሳቤላ ይባሱን ደነገጠች ልቧ ጐኗን ሰንጥቆ ለመውጣት የፈለገ ይመስል እየዘለለ ይመታ ጀመር " የሱዛን ገለጻ የሚስተር ካርላይልን መልክ አመጣባት
ከተቀመጠችበት ተነሥታ ወደ ምድር ቤት ወርዳ መቀበል ተንገዳገደች " ሁኔታዋን ስታይ ጊዜ ሱዛንም ምላሷን ፈታች

“ እመቤት አበዱ ወይስ በጤናዎ ነው ” አለቻት " የፎቁን ደረጃ ስትወርድ እንደምትወድቅና ምናልባት ሆስፒታል ካልሔዶች በቀር ሰው እንደማትሆን በመገንዘብ „ “ሰውዬውም ሽበት የቀላቀለ ያምሳ ዓመት ሰው የሚሆን ነው.” ወጣት እንኳን አይዶለም • ስለዚሀ እርስዎ ከመኝታ ቤትዎ እንዳሉ እንግዳውን ወዲህ ባመጣው ምን ያስከፋል ? ”
አሁን ስለ እንግዳው የበለጠ ስታብራራላት ሚስተር ካርላይል አለመሆኑን ዐወቀችና ልቧ ረጋ " እንዲያውም እሱ ይሆናል ብላ በማሰቧም በራሷ የዋህነት
ሳቀች " ቀጠለችና ምናልባት ፍራንሲዝ ሌቪሰን ገንዘብ እንድትቀበል የሚያግባባ
ሰው ልኮባት ሳይሆን እንደማይቀር በመገመት ላለማነጋገር ቆረጠች »

ሱዛን .. በይ እንግዲያው ውረጅና የሰውዬውን ማንነትና የመጣበትን ቦታ ጠይቂው ” አለቻት

ሱዛን ወዲያው ወጥታ እንዲገባ ትጥራው ወይም ራሱን ይጋብዝ
አይታወቅም ሰውዬውን አስከትላ ብቅ አለች ሳቤላ ገና ስታየው እጆቿን ዘርግታ አራገበችና በኃፍረት የሚቃጠሉት ሁለቱን ጉንጮን እፍን አድርጋ ያዘች እንግዳው ሎርድ ማውንት እስቨርን ነበር !!

" ያለሁበትን በምን ዐውቀህ መጣህ ? "

በቅርቡ በተመለከትኳቸው አንዳንድ ነገሮች መለያየታችሁን የሚጠቁም ሁኔታዎች ስላየሁባቸው አንቺን ከምን እንዳደረሰሽ መጠየቅ አስፈላጊ ሆኖ አገኘሁትና ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ዘንድ ሔጄ አድራሻሽን ጠየቅሁት ”

“ ካለፈው ሐምሌ ጀምረን ተለያየን " በታኅሣሥ መጥቶ ነበር” ለአንድ ሰዓት በነገር ስንናቆር ቆይተን ተመልሶ ሔደ "

“ ስለሱ በቅርቡ ምን ሰምተሻል ? ”

“ ምንም ነገር አልሰማሁም » አሁን እኮ በአገራችን የሚደረገውን ነገር ምንም አላውቅም " ጋዜጣ የለኝም " ከማንም ጋር አልጻጻፍም " እሱም ቢሆን እስከዚህ ደፍሮ አይጽፍልኝም ”
“ እንግዲያውስ ስለሱ የሰማሁትን አንዳንድ ወሬ ብነግርሽ አላስደነግጥሽም ። ''

“ እኔ በጣም ልደነግጥና ሊዘገንነኝ የሚችለው እሱን ለማየት የምገደድ መሆኔን የሰማሁ እንደሆነ ብቻ ነው

“ እየውልሽ . . . በቅርቡ አገባ "
“ እሱን ያገባች ያልታደለች ናት ” አለችው እመቤት ሳቤላ ።
“ አሊስ ሻሎነርን ነው እኮ ያገባ ”

ራሷን ቀና አደረገችና እንደ መገረም ብላ“አሊስን? ብላንሽን አይደለም?” ብላ
ጠየቀችው ።

“ብላንሽን አታለላት እየተባለ ይወራል " እሷን እንደሚያገባት ተስፋ እየሰጠ ቆየና ሳታስብ ታናሽ እኅቷን ለማጨት ጠየቀ " እኔ ለራሌ ዝርዝር ነገሩን አላውቀውም ነበር " በቀደምለት ከክበብ ሳለን ሥርዓተ ተክሊሉን በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚፈጽም መሆኑን አንድ ጽሑፍ አየሁ " እኔም ከሱ ቀድሜ ቤተክርስቲያን ደረስኩና ምን እንዳደረገሽ የት እንዳለሽ አጥብቄ ስጠይቀው ይኸን አድራሻ
ሰጠኝ ከታኅሣሥ ወዲህ ተንቀሳቅስሽ እንደሆነ ግን የማያውቅ መሆኑን ነገረኝ

ረጂም ጸጥታ ሆነ " ኧርሉ ክፍሉን በዐይኑ እየቃኘ ነገር የሚያሰላስል ይመስል ነበር " ሳቤላ አንገቷን ደፍታ ተቀመጠች "

“ለምን ልትፈልገኝ መጣህ ? አሁን እኔ ምኔ ይፈለጋል ስምህን በአሳፋሪ ሥራዬ አሰነሣሁት እኔ አን† ልትፈልገኝ የሚገባኝ ሰው አይደለሁም "

የምትይው እውነት ነው ! የኔን ስም ብቻ ሳይሆን የባልሽንና የልጆችሽን ስም ጭምር ነው ያዋረድሽው አላት ነገር የማለባበስ ጠባይ ያልነበረው ሎርድ ማውንት እስቨርን" "ቢሆንም” አለ ነገሩን በመቀጠል, “አሁን እንደገና ብቸኛ ስትሆኝ ከባሰ ችግር እንዳትወድቂ የሚያስብልሽ ከኔ የቀረበ ዘመድ ስለሌለሽ አንቺን የመጠየቅና በምችለው ሁሉ የመደገፍ ኃላፊነት አለብኝ » አንድ ሺልንግ እንኳን የለሽም አሁን እንዴት ሆነሽ ለመኖር ታስቢያለሽ ? ”

እስካሁን እንኳን ጥቂት ገንዘብ አለኝ : በኋላም . .
የሱ ገንዘብ ” ብሎ አቋረጣት ቁጣና ኩራት በተሞላበት አነጋር "
የለም ! አለችው እሷም በንዴት " ያሉኝን ጌጦች እየሽጥኩ ነው እነሱ
ከማለቃቸው በፊት ግን በሆነ መንግድ ሠርቼ ለመተዳዶር እሞክራለሁ " ምናልባትም ሕፃናትን በማስተማር "

ጌጦች?” አለ ሎርድ ማውንት እስቨርን “ ከኢስት ሊን አንድም ነገር እንዳልወሰድሽ ሚስተር ካርላይል ነግሮኛል "

" እሱ ከሰጠኝ ውስጥ አንድም አላነሳሁም እነዚህ እሱን ሳላግባ የነበሩኝ
ናቸው " ሚስተር ካርላይልን አይተኸዋል?” አለችው እጅዋን ያዝ እንዳደረጋት
“ እንዴ ምን ማለትሽ ነው ? አንድ ዘመዴ የሆነ ሰው ላይ ይህን የመሰለ ከባድ
በደል ሲደርስበት ኢስትሊን ድረስ ሔጄ ኀዘኔን መግለጽ ይብዛብኝ? ሌላው ደግሞ
ከዚህ ሁሉ ለመድረስ የበቃሽበትን ምክንያት ለማወቅ እፈልግ ነበር " ይህ አሳዛኝ ወሬ ሲደርሰኝ ካላበድሽ በቀር እንደማታደርጊው ተከራከርኩ " አንቺን
አምንብሽ ነበረ ሔጄም ያወቅሁት ነገር የለም " ካርላይልም ቢሆን ነገሩ አልገባውም እንዲያው ምን ብትሆኝ ነው እንደዚህ ጉድ ያደረግሽው ?

አንገቷን ይበልጥ አቀረቀረች " ኃፍረቷ ትኩሳትና ክሳት በመጠጠው ፊቷ ታየባት በባሏ ላይ የፈጸመችው በደል ምሬቱና ግለቱ ተሰማት ሎርድ ማውንት እስቨርንም መጸጸቷን ከገጽታዋ ላይ አነበበው "

“ሳቤላ ” አላት ከበፊቱ ኃይለኛ አነጋገሩ በረድ ባለ ድምፅ " በዚህ ስሟ
ሲጠራት የመጀመሪያ ጊዜ ነበር "
👍19
“ አሁን እንደማይሽ የሥራሽን ፍሬ እየሰበሰብሽ ነው እስቲ እንዴት እንደሆነ
ንገሪኝ . . እንዲያው ምኑ ጋኔል ነው ራስሽን ለዚያ ክፉ ሰው ለመሸጥ የገፋፋሽ ? ''

“ መጥፎ ሰው ነው " አለችው ክፉ ጨካኝ ' መጥፎ ስው " ! ”

ገና በጋብቻሽ መጀመሪያ ጊዜ ካጠገብሽ እንድታርቂው ከሱ ጋር ምንም ግንኙነት እንዳይኖርሽ ከቤትሽ እንዳታስቢው አስጠንቅቄሽ ነበር "

“ ወደ ኢስት ሊን የመጣው በሚስተር ካርላይል ጠሪነት እንጂ በኔ አልነበረም "

“ እሱ እንደ ጠራው ዐውቃለሁ" ጥርጣሬ ባልነበረው እምነቱ ሚስቱን የሱ ብቻ እንደምትሆን በማመኑ ነበር የጠራው

“ጥሩ ባል አላት የተባለች አንዲት ሴት ካለች አንቺ ነበርሽ።ሚስተር ካርላይል
ባልነቱ ምንም የሚጐድለው አልነበረም : እንዴት እንደዚህ ያለ ውለታ
ትመልሽለታለሽ ? ለባልሽ የተውሽለትን ማስታወሻ አነበብኩት » በጭራሽ ሊገባው አልቻለም " ለኔም ያው ነበር እኅቱ ሰላም ነሥታሽ እንደነበረ አንቺ ከሔድሽ በኋላ ጉዳዩ ተነሥቷል“ ይህም ቢሆን ባልሽን አምነሽ ችግርሽን ብትገልጭለት ኖሮ በጊዜው ሊያስተካክለው ይችል ነበር " ይህን ባለማድረግሽ እጅግ አዝኖብሻል " ይህ የራስሽን ዕድል ለማበላሸትና ሁላችንን ለማዋረድ በቂ ምክንያት ሊሆንሽ አይችልም

“ ስለነዚህ ነገሮች ይቅር አናንሣው » ያለፈውን ለመመለስ አይቻልም ''
የለም መናገር አለብኝ " ስለነሱ ለመነጋግር ነው እኮ የመጣሁት " በአንዲት
ሴት ሕይወት እንደነዚህ ያሉ ምክንያት የማይገኝላቸው ድርጊቶች ሲደርሱ ዓላማቸውን መነሻቸውንና ድርጊታቸውን መከታተል ያባት ተግባር ነው አባትሽ
ዐልፏል " በቦታው የተተካሁት እኔ ነኝ » ሌላ ማንም የለም "

እንባዋ መውረድ ጀመረ እሷ ቃል ሳትተነፍስ ለቀቀችው » ኧርሱም ንግግሩን ቀጠለ „

ያንን አስገራሚ ደብዳቤሽን ባላይ በዚያ በኩቲ በሌቪስን የዕብደት ፍቅር
ተገፋፍተሽ የፈጸምሽው ይመስለኝ ነበር " ይዘቱን ሳየው ነገሩ የተለየ ሆነብኝ
ይህን ነገር እንድትፈጽሚ የባልሽ ግፊት መሆኑን የገለጽሽው ምን ማለትሽ ነበር?

“ እሱ ያውቀዋል ”አለች ድምፅዋን ለመስማት እስኪያስቸግር ድረስ ዝቅ
አድርጋ ።

"አላወቀውም ” አለ ኧርሉ ኮስተር ብሎ "ከካርላይል የተሻለ ትክክለኛ ሰው በገጸ ምድር አይገኝም በደልሽ ምን እንደነበር ቢያስብ ' ቢያስብ አንድም የሚጠረጥረው ምክንያት ማጣቱን ነግሮኛል " ለእነተኛነቱ የተፈለገውን ያህል ተወራርጄ ባስያዝኩ ለወደፊቱም ያው ነኝ " "

" ፍቅሩን ነፍጐኛል እኔን በሌላ ለውጦ ከድቶኛል ብዬ በማመን ነበር "

“ ከድቶኛል ስትይ ምን ማለትሽ ነው ? ከአንቺ ጋር ነበር "

የልብ ክደትም እኮ አለ "

“የቅዠት ክደት! ” አለ ኧርሉ እኔና ካርላይልም በቅናት ተገፋፍተሽ መሆኑን ገምተናል " ነገር ግን ትሰሚኛለሽ ሳቤላ? ፍንጭ አሳይቶሽ እንደሆነ
ብጠይቀው እሱ ላንቺ በሐሳብ በንግግርና በተግባር ፍጹም ታማኝ እንደ ነበርና አንቺን ካገባበት ሰዓት ጀምሮ ማንንም ሴት በፍትወት ዐይን ቀና ብሎ አይቶ አንደማያውቅ ሐሳቡ ሁሉ ስላንቺ እንደ ነበር ነግሮኛል "

የልቧ ምት ጨመረ የኧርሉ ንግግር እውነተኛነት የዕውር ቅናቷ ስሕተት ግልጽ እየሆነባት መጣ ስሕተቷ ያስከተለው ጸጸት ከአእምሮዋ ገባ "

“ እኔም ከዚያ በኋላ ደብዳቤሽ ዓላማሽን ለመሸፈን ብለሽ ያቀረብሽው ሐቅን ያልያዘ ' እፍረተ ቢስ ምከንያት ነው ብዬ ነው የፈታሁት " ባንቺና በቤታችሁ በሰፈረው ውሻ መካከል አንዳች ምስጢራዊ ግንኙነት መኖሩን እንዴት
እንዳልጠረጠረ እንኳን ጠይቄው ነበር " የዚያን ዐይነት ጥርጣሬ ጨርሶ እንዳላሰበው ' በተለይ ደግሞ አንቺን ራሱ ከቤት እያለ ቀርቶ በሌለበትም ቢሆን ከዚህ ሰው ጋርም ሆነ ከማንም ወንድ ሆነሽ ዓለምን ብትዞሪ እንደማይጠረጥርሽና ያለ
ምንም ገደብ ያምንሽ እንደ ነበረ ዘርዝሮ አጫውቶኛል "

አጆቿን አጠላልፋ አስኪያማት ድረስ ታፋትጋቸው ጀመር ሆኖም የነሱ መፋተግ የልቧን ሕመም አልከፈለላትም "

ሎርድ ማውንት እስቨን ትችቱን በመቀጠል“ ሰውየው ከቤታችሁ ዐርፎ
በነበረበት ጊዜ ከምንጊዜውም የበለጠ ሥራ በዝቶበት እንደ ነበረ አንድ ባንድ ዘርዝሮ አስረድቶኛል” አላትና ከዚህ አያይዞ ከመደበኛ የቢሮ
ሥራ ሌላ በሪቻርድ ሔር ጉዳይ ከፍተኛ መሯሯጥ እንደ ነበረበት በተለይም
አሳዛኙ የኩብለላ ድራማ የተፈጸመ ጊዜ ራት ተጠርቶ ወደ ነበረበት ቤት እንኳን ለዚህ ክትትል ሲል አብሯት ሊሔድ ያለ መቻሉንና እንዲያውም ሪቻርድ ክእናቱ
ጋር ሲጫወት ካርላይልና ባርባራ ከአጥሩ በር ሲጠባበቁ ማምሽታቸውን ገለጸላት "

“ግን እኮ እሱን ሁልጊዜ ከባርባራ ሔር ጋር አየው ነበር "

ለወንድሟ ጉዳይ ስትል በናቷ ስም ሁልጊዜ ከካርላይል ጋር መነጋር ነበረባት " እናቲቱ እንደልቧ እንዳታነጋግር አባትዬው እንዲሰማ አይፈልግም " እንቺ ግን ለሥራ ጉዳይ ያደርጉት የነበረውን ግንኙነት የፍቅር ቀጠሮ መሰለሽ እኔ አንቺን ዐዋቂ ሰው አደርግሽ ነበር " ግን የዚያ ቀጣፊ ሰውዬ ስብከት ነው ከዚህ ሁሉ መዘዝ የከተተሽ እንጂ ያንቺ ምክንያት እውነት በቂ ሆኖ አልነበረም

" አሁንማ ሆነ አይደል ” አለችው "

“ ካርላይል ላንቺ ላንቺ ብቻ ታማኝ ነበር ያንቺን የመሰለ ባል ለማግኘት የታደሉ ሴቶች ቢገኙ በጣት የሚቆጠሩ ናቸው " ቀጥተኛና ጥሩ ሰው ነው
እንግላንድ እንኳን እሱን የመሰለውን ሰው በማፍራቷ ልትኮራ ይገባታል እኔማ
ባየሀት ቁጥር ለሱ ያለኝ አድናቆትና አክብሮት እየጨመረ ይሔዳል " ስለ ጉዳት ካሳው ምን እንዳደረገ ሰምተሻል ? ”

ራሷን በአሎታ ቀነቀች "

“ መጀመሪያው በካሳው ሊሟገት አልፈለገም ፍርድ ቤቱ ግን ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፈለው በየነለት። ሰውዬውም ወደ ባሮንነት አድጎ ስለ ነበር ከፈለው
ካርላይል ግን ' ገንዘብ የሚስትን ውርደት አያስለቅቅም የሚለውን የጥንት ሐሳብ በመከተል ተቀብሎ ወዲያውኑ ለአንድ ሆስፒታል ሰጠው ”

“ ይህን ጨዋታ እዚሀ እናቁመው " አለች ምስኪኒቱ በሽተኛ “ የክፋቴንና
የእብደቴን ውጤት እስከ ዘለዓለም ተሸክሜው እኖራለሁ ። ከዚህ በላይ ምንም ለማለት አልችልም በቃኝ ።

“ የወደፊት መኖሪያሽን የት ለማድረግ ታስቢያለሽ"

“ እንጃ ' አሁን መናገር አልችልም " በጐ ሆኘ ለመንቀሳቀስ ስችል ከዚህ
ከተማ እለቃለሁ

“ እውነት ነው ' ከከተማው
ነዋሪዎች ጋር መኖር ላንቺ ደስ አይልሽም ። እዚህ
አብረሽው ነበርሽ አይደል ?

“ አዎን ለስዎች ሚስቱ እመስላቸዋለሁ ። ለሠራተኞቹም ሳይቀር ሚስቱ እመስላቸዋለሁ : ”

·ግድ የለም ጥሩ ነው ” ስንት ሠራተኞች አሉሽ ? ”
“ ሁለት ጉልበቴም አልጸናም ስለዚህ እኔ ብዙ መሥራት ስለማልችል
ሁለት ሠራተኞች መቅጠር ግድ ሆነብኝ። ሕፃኑ አድጎ ቁሞ ከሔደልኝ በኋላ ግን
አንድ ብቻ ትበቃኛለች "

ኧርሉ ግራ ገባው“ ሕፃኑ !” አለ በመደነቅ “ እንዴ !... ሕፃንም አለ? አላወቅሁም ኮ ! ክፉ ሰው ጨካኝ ተንኮለኛ " ከመውለድሽ በፊት ሊያገባሽ ይገባው ነበር ... ፍቺው የጸናው ቀደም ብሎ ነበር ? ”

“ አዎን "

“ ቀጣፊ ሌባ ! የመልካም ሰዎች መውደድ ይንሣው በሰዎች ዘንድ ሞገስ ይጣ ! አንቺን የኧርሉን ልጅ እንዲህ ያድርግሽ ! አዬ ሳቤላ | እንዲህ አድርገሽ ዕድልሽን ሰበርሽ ! ”

ሳቤላ ከተቀመጠችበት ብድግ አለችና የልመና እጆቿን ወደሱ ዘርግታ እየተርበተበተች ተንቀሳቀሰች “ እባክህን ተወኝ ! ኧረ ተወኝ ይብቃህ ከገባህ ጀምሮ እስካሁን ኮ ልቤን እያዘለዘልከው ነው ስውነት ያለኝ መሰለህ ? አልቄአለሁ ደክሜአለሁ : አልችለውም ተወኝ ይብቃኝ
👍12
እርሉም ካስበው በላይ መናገሩን ተሰማው "

“ተይው ቁጭ በይ ወደ መጣሁበት ዋናው ጉዳይ ልመለስ " ለመኖር ምን
ያህል ገንዘብ ይበቃሻል ? "

“ እኔ ምንም አልቀበልም " ለኑሮ የሚሆነኝን ገንዘብ ሠርቼ አፈራለሁ "

ሲነግሩሽ ስሚ ከስሕተቶችሽ ቐላይ ሌላ የዋህነት አታክይባቸው በርግጥ ሠርተሽ ኑሪ እኔም ለመኖር የሚበቃሽን ያህል እሰጥሻለሁ " አትግደርደሪ እኔ ይህን ሁሉ የማስበው አባትሽን ተክቼ ነው አባትሽ በሕይወት ቢኖር ኖሮ እየተ
ራብሽ ሠርተሽ ኑሪ ብሎ ይተውሽ ነበር ? ''

“ እኔማ እያስተማርኩ እተዳደራለሁ ብዬ ነው የማስበው ” አለች የኧርሉ
ንግግር ሆድን የሚያባብስ ትውስታ ስላመጣባት እንባዋ እንደ ውሃ ይወርዳል

“በማስተማር ምን ያህል ማግኘት የምትችይ ይመስልሻል?”

“ እስከዚህም አይሆንም | ሙዚቃና መዝሙር በደንብ እችላለሁ " ምናልባት አንድ መቶ ፓውንድ ባመት ለመኖር ያህል ይበቃል "

“ እንዲህ ያለም ገቢም የለ! በይ ይህን ያህል ገንዘብ እኔ በየሦስት ወሩ እሰጥሻለሁ ” አላት "

“ የለም አይሆንም! መረዳት አይገባኝም » አልቀበለውም ማንኛውንም የእርዳታ መብቴን አበላሽቼዋለሁ "

“ ያበላሸሺው የኔን እርዳታ አይደለም እኔ የወሰንኩ ስለሆነ አትከራከሪኝ "
የግዴታ ተግባሬ ስለሆነ አሁን እንደ ተመለስኩ አራት መቶ ፓውንድ ስለምልክልሽ
በየሦስት ወሩ ማውጣት ትችያለሽ "

“ እንግዲያስ ግማሹ ይብቃኝ " በዓመት ሁለት መቶ ፓውንድ እኮ ብዙ ግን
ገንዘብ ነው "

“ ስለ መጠኑ አንድ ጊዜ ወስኘዋለሁና አልቀንሰውም" በየሦስት ወሩ አንድ መቶ ፓውንድ እልክልሻለሁ . እሱን አይጨምርም " አለና የወረቀት ገንዘብ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠላት “ ከዚሀ በተረፈ ለማንኛውም ነገር እንድትገልጭልኝ እንጂ ምንም ቢሆን ዕዳ እንዳትገቢ "

“ ለመሆኑ አገር ስለኔ ምን ይላል ? ” አለችው " ሁልጊዜ በአእምሮዋ ሲጉላላ የነበረ ጥያቄ ነበርና

ልክ አንቺ ያደረግሽውን ነገር ሌላ ሰው ቢያደርገው ኖሮ ልትይው አንዶ ነበር ነዋ ? ሌላ ምን የሚል ይመስልሻል ? ”

ፊቷ በኃፍረት ተለዋወጠ " ልቧ በኃይል እየመታ ከፊቱ እንደ ቆመች ኧርሎ እጇን በስንብት መልክ ከጨበጠ በኋላ ወጥቶ ወደ ሆቴሉ ሔደ ራቱንም ከዚያ
በልቶና አድሮ ሲነጋለት ወደ ኢንግላንድ ተመለሰ " ሳቤላም ከመኝታ ቤቷ ብቻዋን ቀረች "....

💫ይቀጥላል💫
👍22
የጠንቋዩ ዋሻ

★★★*★★★*★★★

ክፍል 9
ቀናቶች እየነጎዱ ነው ፡ አስፈሪው ዋሻ ፡ ከነጨለማው ፡ በአስፈሪነቱ ቀጥሏል ፡ ይሄ፡ ጭንቀትና ፍርአት ፡ግን በአንድ ሰው ላይ ብቻ ነበር ፡ተፅኖውን ያሳረፈው ፡ እሱም የአቢያራን እምነት አልቀበል ብሎ ፡ባቋሙ የፀናው ፡ መሳይ ላይ ፡ ፡ ሌሎቹ በፍርሃት ለተገዙለት ፡ጠንቋይ ፡ የቀኝ እጅ ሆነዋል ፡በዚህም ፡ምክንያት ፡ የፈለጉበት ቦታ ደርሰው ፡ ለመምጣት ፡አሳውቀው ፡ መውጣት ተፈቅዶላቸዋል ፡ ከሴቶቹ ፡ በስተቀር ፡ መሳይ በጓደኞቹ መለወጥ ፡እንደተገረመ ነው ፡ እለት በህለት ፡ ፍፁም ወደ አውሬነት ፡ እያዘነበሉ ፡ ጭራሽ ፡ከአድማስ ፡ ጋር መፎካከርም ጀምረዋል ፡ ለአቢያራ ያላቸው ፡እምነት ፡ ከሚገመተው ፡በላይ ፡ጨምሮ ፡ከስርስሩ እንደ አባታቸው ፡መከተል ፡ጀምረዋል ፡ አቢያራም ፡በፍጥነት ፡ በነሱ ተስቦ ፡አድማስን ችላ ማለት ፡እና አሳቡን ፡ሁሉ ፡ለነ መስፍን ፡ እያካፈለ ፡ ትህዛዙን ፡አስፈፃሚ አድርጓቸዋል ፡ ሁለቱም ስለ ቤተሰባቸው ትተዋል ፡ አንድም ቀን ፡አንስተው አያውቁም ፡ እንደልባቸው ፡በሚያገኙት ፡ገንዘብ ፡ ከተማ ወጥተው ፡የፈለጉትን አድርገው ፡ መምጣት ፡ጀምረዋል ፡ ሁኔታቸው ፡ሁሉ ፡ ለረጅም አመታት ፡ከአቢያራ ጋር እንደኖሩ ነው ፡የሚያስመስላቸው ፡ አድማስ ፡ወደከተማ ይዟቸው ፡በመኪናው ፡ይወስዳቸዋል ፡ በአንዲት ፡ትንሽዬ የገጠር ከተማ ውስጥ ፡ በፍጥነት ፡ ተወቁባት የልጅ አብታም የሚል ስያሜ ተሰጣቸው ፡ እራሳቸውን ፡ ከአዲሳባ ድረስ ፡ለስራ የመጡ የቱጃር ልጆች ፡አድርገው ፡አስተዋውቀዋል ፡ በአካባቢው ፡የሚያዩ አቸው ፡ሰዎች ፡ሁሉ እሱን ፡አምነው ፡ተቀብለው ፡ ከፍ ከፍ ያደርጓቸው ፡ጀምሯል ፡ ይሄን ሁኔታም ፡በመጠቀም ፡ከተለያዩ የከተማው ፡ሴቶች ፡ጋር ፡በፈለጉት ሰአት እንዳሰኛቸው ፡ይወጣሉ ፡ ይህ ፡ሁኔታቸው ፡ለአድማስ ፡አልተዋጠለትም ፡ ድንገት ፡ አንድ ፡ቀን ፡ነገር ፡አበላሽተው ፡ሚስጢር ፡እንዳያወጡ ና ፡አባት ፡አቢያራን ፡ ችግር ፡ውስጥ ፡እንዳይከቱትና ፡ቁጣው ፡እንዳይነሳ ይፈራል ፡ በተለይ ፡ደሞ ፡ አቢያራ ፡የሰጣቸውን ፡ የማደንዘዣ ምትሃተኛ አመድ ፡ በወጡ ቁጥር ፡በብልቃጥ ፡ይዘው ፡መውጣታቸውንና ፡ ባልተፈቀደላቸው ፡ ሰዎች ፡ላይ ፡እየበተኑ ፡ አፍዝዘው ፡ ገንዘብ ፡መሰብሰብ ፡መጀመራቸው ፡አሳስቦታል ፡ ይሄን ፡አይነት ፡ድርጊት ፡ አቢያራ ፡ ጌታዬ ፡በጭራሽ ፡አይፈቅድም ፡ አባቴ ለምን ፡ አያስቆማቸውም ፡እያለ አድማስ መጨነቅ ፡ጀምሯል ፡ ነገር ግን መስፍንም ፡ሆነ ዳንኤል ፡ከተማ ወጥተው ፡በመምጣታቸው ፡ቁጥር ፡ ለአቢያራ ፡ የተለያየ ስጦታ እያመጡ ቀልቡን ፡ ስለገዙት ፡ የአድማስ ፡ ፍራቻ ቦታ አጥቷል ፡ ፡ መሳይ ፡የጓደኞቹ በሱ ላይ የመለወጥ ፡ምክንያት ፡የጠጡት ፡የአቢያራ ፡የጠንቋይ ፡ፈሳሽ ፡ይሆናል ፡ብሎም ፡አስቧል ፡ምናልባትም ፡እሱ የዛን ፡እለት ፡ ጠጣ የተባለውን ፡ፈሳሽ ፡ቢጠጣ ኖሮ ፡ እንደነሱ እንዲ እንደሚሆን ፡ገመተ ፡ አሁን ፡ላይ ፡ ፈፅሞ ፡ ጓደኞቹን እንዳጣ እና ፡ ብቸኛ ፡ሰው ፡መሆኑ እየተሰማው ፡ነው ፡ ለብቻው ፡ነው ፡እራቅ ፡ብሎ ፡የሚቀመጠው ፡ ከጀርባ በኩል ፡ካለው ፡ውብ መናፈሻ አልፎ ፡አልፎ ፡እንዲወጣ ቢደረግም ፡ ጥግላይ ፡ተቀምጥ ፡ማየት ፡እንጂ ወደየትም ፡እንዲንቀሳቀስ ፡አይፈቀድለትም ፡ ቀረብ ፡ብላ የሚፈልገውን ፡የምትጠይቀው ፡ኤዛ ፡ብቻናት ፡እሷም ፡ብትሆን ፡ ብዙ አትናገርም ፡ ከማውራት ፡ይልቅ ፡ በአይኖቿ ፡ መከታተሉን ታበዛዋለች ፡ አይኖቿ ፡ ደሞ ፡ልቡን ፡ሞቅ ፡ማድረግ ፡ጀምሮል ፡ በሕይወት ፡እንዳለ የሚሰማው ፡እሷ ፡አጠገቡ መጥታ ለረጅም ሰአት ፡በዝምታ ስታስተውለው ፡ነው ፡ ኤዛ እንደዛ ስትሆን ፡ የአቢያራ ሳይኮ ፡እሷላይ ሙሉ በሙሉ አላረፈ ይሆናል ፡ ብሎ ፡ለማመን ይዳዳል ፡ ግን ስልችት ፡ብሎታል ፡ ተስፋ ቢስነትም ይሰማዋል ፡ቤተሰቦቹም ፡ናፍቀውታል ፡ በየጊዜው ፡አድማስም ፡ጓደኞቹም ፡ በቁጣና ፡በዘለፋ ስሜት ፡አቢያራን ፡ተቀበል ፡ቢሉትም ፡ በእምነቱ ጠንክሯል ፡ ፈጣሪዬን ፡ አልክድም ፡ነው ፡የሁሌም ፡መልሱ ',,,,,,,,,,,,,,,
!
ሙና መሀመድ

ይቀጥላል.....

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍30
#ሳቤላ


#ክፍል_አርባ_ሶስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


አንድ ቀን ጀንበሯ ለመጥለቅ በምትሽለቆለቅበት አመሻሽ ላይ ሚስተርና ሚስዝ ሔር ከባርባራ ጋር ምግብ ላይ እንደ ተቀመጡ አባትየው እየተሳደበ ያስለቅሳታል ።

እናቲቱ ደግሞ ምንም እንኳን በልቧ ለባርባራ ብታደላም ጀስቲን ሔር
ባርባራን ከቤት ዘግተን እናቃጥላት ቢላትም መቃወም የሚባል ስለማይቃጣት አሁንም ከባሏ ሐሳብ ጋር ተስማምታና ተደርባ አብራ ትቆጣት ነበር "

ባርባራ ጥሩ እጮኛ እየመጣላት እምቢ ብላ በመመለስ አባቷን ደጋግማ አስቀይማዋለች » እሱ ደግሞ ለምን እንዲህ ይደረጋል ብሎ እብድ ይሆንባታል " ሴቶች
ልጆቹ ሳይዳሩ ጠውልገውና መንምነው ቢያረጁ ወይም ተድረውና ተኩለው የቤት
እመቤቶች ቢሆኑ ለሚስተር ጀስቲስ ሔር ስሜት አይሰጠውም " እንዲያውም "ባርባራ ከቤት በመኖሯ ልትከብደው ቀርቶ ከነጭራሹም እንድትርቀው አይፈልግም ነበር " የሀብት ፍላጎትም አይደለም " ባርባራ ብታገባም ባታግባም የሚበቃ ሀብት
አላት " ባርባራ ለጋብቻ ስትጠየቅ ባለ መቀበሏ አባቷ የሚቆጣት ምክንያት
እነዚህን ከመሰሉ ተራ ነገሮች የተለየ ነበር
የዊስትሊን ሰው በማያገባው ነገር ሁሉ በየሰዉ የግል ሕይወትና ኑሮ እየገባ አሉባልታ ሳያናፍስ መኖር አይሆንለትም ባርባራ ሔር አግብታ በባሏ ስም ሚስዝ
እገሌ መባል ሲገባት ስሟን ሳትለውጥ ባርባራ ሔር ሁና በመቅረቷ ሁሉም በይፋ
ስሟን አነሣው በውበቷ በመልካሙ ጠባይዋና በሀብቷ ከሆነ ካገሩ ቆነጃጅት ሁሉ የሚወዳዶራት አልነበረም እሷ ሳትያዝ ሌላ ልጃገረድ ትታጫለች ብሎ ለማመን
የሚያስቸግር ይመስል ነበር " ነገር ግን እስከ ዛሬ ይኸው ባርባራ ሔር እንደሆነች አለች » አሁን አሉባልተኞች ምክንያቱን ለማወቅ አንገት ላንገት ገጥመው ሲያቶኮትኩ በመጨረሻ ቆማ የቀረችበት ብቸኛው ምክንያት ወንድሟ የፈጸመሡ አሳዛኝ ወንጀል ነው እየተባለ ተወራ " ይህ አጉል መሬ በተወራበት አልቀረም ሲል ሲል
ጀስቲስ ሔር ጆሮ ዶረሰ ጀስቲስ ሔር ደግሞ ምርር ብሎ የሚጠላው ነገር ቢኖር ያን ጥቁር ነጥብ የተወበት አሲቃቂ ድርጊት ነው እሱ የሚጠላው ያው ፍጡር አለ ከተባለ ደግሞ ያን ዕድለ ቢሱ ልጁን ነው " ባርባራ ጠያቂ አጥታ የቀሪችው በወንድሟ ወንጀል ነው የሚለው ወሬ ለጀስቲስ ሔር እንዶ ሐሞት መሪሪው መንፈሱን እንደ
ቅንቅን ቦረቦረው » ከብሽቀቱ የተነሣ በቅርብ ከሚገኘው ኩሬ አሽቀንጥሮ ቢጥለው ወይም ሪቻርድን አግቶ አንገቱን አንቆ ለፍርድ ቢያቀርበው ወይም የሚነፍሰወን አሎባልታ ለማስቀረት ባርባራን ወዲያው ድሮ ቢያርፍ ደስታውን አይችለውም ነበር " አሷ ግን የሚመጡላትን ባሎች ሁሉ በእምቢታ ስትመልስ አራተኛ ጊዜዋ ስለሆነ አባቷን በጣም አበሳጨችው
“ አንቺ እኮ ይህን የምታደርጊው ሆን ብለሽ 'እኔን ለማበሳጨት ነው ” ብሎ እንደ መብረቅ ጮኸባትና ጠረጴዛወን በቡጢ ሲመታው ፍንጃሎቹ ተንቀቀጫቀጩ

“ ኧረ አይዶለም ... አባባ ” አለችው ባርባራ እየተንሰቀሰቀች
ታዲያ ለምን እንደዚህ አደረግሽ ?
ባርባራ ዝም አለች።
“ድሮውንስ ምን ልትይ ኖሯል የምታቀርቢው ምክንያት የለሽማ ! እስኪ አሁን
ለሻለቃ ቶርን ምን ሊወጣለት ነው ? በይ እስቲ ተናገሪ "

“ አልወደውም
ብላ ተንተባተበች »

“ እሱን ተይው ! ትወጅዋለሽ « እዚህ በመጣ ቁጥር ትወጂው ነበር " ለምን

" እንደ ማንም ዕውቂያ እንጂ ለባልነት አልወደውም

“ ለባልነት አልወደውም ?

ወይ አንተ ! ግድ የላችሁም ልጅቱ ማበዷ ነው" አሁንስ ቢሆን ገና ሳታግቢው ማን ውደጅው ብሎ ጠየቀሽ?እስኪ ማን ይሙት
አንዲት ልጃገረድ ባሏ የሚሆነውን ሰው ሳታገባ መውደድ አለባት ሲባል ሰምተሽ ታውቂያለሽ ? ”

"ባርባራ ግራ ገባት "

ይኸውና አገር ምድሩ ማግባት አትችልም በዚያ እርጉም ስሙን እኮ
ስጠራው ዘገነነኝ ወንጀል የተነሣ ማንም አይፈልጋትም እያለ ያወራል " ታዲያ ይኸ ራሱ ከባድ ውርደት አይደለም ? ''

“ ግን እኮ ውሸት ነው ፤ ሰዎች ይጠይቁኛል ”

“ ታዲያ አንቺ እምቢ እያልሽ ከመለስሻቸው ምን ያደርጋል ? ሰዎች እንደ
ጠይቁሽ የምታሳውቂው እንዲህ በመናገር ነው ? አንቺ እኮ የሚነገርሺን የማትሰሚ እንደ ልቧ አዳሪ ዐመፀኛ ነሽ " ደግሞ እንደዚህ ሆነሽ መቅረትሽን
ዕወቂው "

የባርባራ እንባ እንደ ውሃ ወረደ" ጀስቲስ ሔር የሻይ ዕቃውን ከጠረጴዛው
እንዲያነሡት ጠርቶ ለማዘዝ የደወሉን እጅታ በቡጢ መታው" ዕቃዎቹ ከተነሡ
በኋላ ነገሩ እንደገና ተቀሰቀሰ " የባርባራ ለቅሶም ባሰ " የጀስቲስ ሔር አንዱ መጥፎ ጠባዩ ይኸው ነበር " ደግነቱ ሁልጊዜ ከልቡ አይበሳጭም እንጂ አንድ ጊዜ ባንድ ነገር ቅሬታ ከተሰማው ንዝንዙ ማቆሚያ የለውም » በባርባራ ላይ የቁጣውን መዓት ሲያወርድበት ሚስተር ካርላይል ገባ "

ያለፉት ኻያ አንድ ወሮች በግራና ቀኝ የራስ ጸጉሩን ላይ ሽበት ጣል ጣል
እንዲልበት ከማድረጋቸው በቀር እምብዛም ለውጥ አላደረሱበትም ባርባራ
ልትወጣ ተነሣች
አትሔጅም '' አለ ጀስቲስ ሔር በሷና በመዝጊያው መኻል ተገድግዶ።“እኔ
በቁም ነገር እያነጋገርኩሽ አንቺ ጥለሽኝ ተነሻለሽ " መሔድ የለም " ቁጭ በይ"
ድንገት ጥቂት ብታፍሪ ጉድሽን ሁሉ ከሚስተር ካርላይል ፊት ነው የምነግርሽ "

ባርባራ ተመልሳ ተቀመጠኛ " ሚስተር ካርላይል ምን እንዳገኛት ለማወቅ
እየፈለገ ተቀመጠ "

" በኛ ላይ የወረደውን አስደንጋጭ መከራ አሳፋሪ ውርደት አንተ ታውቃለህ
ሚስተር ካርላይል " ሕዝቡ ደግሞ ስለዚህ ጉዳይ የሚያወራው ቢያጣ ወደ ባርባራ ዞረና አንድም ባል ልሁን ብሎ የሚጠይቃት ያጣችው ወንድሟ የፈጠረው ኃፍረትና ውርደት በሷም ስለ አንጸባረቀ ነው " እያለ ማውራት ጀመረልህ " ይህን እየሰማች ይህን መጥፎ ስም ይዛ ለአሎባልተኞች ወሬ ተመቻችታ ተቀመጠች
የቤተክርስቲያን ተላላኪም ቢሆን ማግባት አለባት በሚባልበት ጊዜ እንዴት እንዴት ያሉ ዶኅና ደኅና ሰዎች ሊቀርቡ አሻፈረኝ እያለች መለሰቻቸው " አሁን ዛሬም ከሻለቃ ቶርን የቀረበላትን ጥያቄ እናት አባቴ ያውቃሉ ማለት ሲገባት እኛን ሳታማክር በሥልጣኗ እምቢ” ብላ መለሰችሙ » አሁን እስቲ
ምን ይባላል ? አንተስ ምን ትላለህ? ”
«ምናልባት የቤት እመቤትነት ላባርባራ ደስ ይላት ይሆናል ” አለ ሚስተር ካርላይል እንደ መሣቅ ብሎ "

“ እሷ መጀሪያ ምን ደስ የሚላት አለና ? ነግሯ ሁሎ የተግላቢጦሽ ነው ኧረ
የሆነስ ሆነና ” አለ ጀስቲስ ሔር አንድ ሐሳብ በአእምሮው ብልጭ ስላለበት ይዞት የነበረውን ጭቅጭቅ ተወት በማድረግ “ትናንት በክስ ሔድ ሁኜ ስምህን ከጋብቻ ጋር ሲያግናኙት ሰማሁ አለው ወደ ሰርጀን ዶቢድ የምትመላለሰው ለልጃቸው
ሚስ ዶባድን ስትል ነው ይላሉ „ ”

“ በክስ ሔድ በዚህ ሲሥቅ አምሽቷላ? በርግጥ ግን ሚስ ዶቢድ ስለምታገባ
የውል ሰነድ እያረቀቅሁ ነው

"የለም የለም እሷንስ ሰመርሴትን እንደምታገባ ሁሉ ዐውቆታል " ሌላይቱን ነው እንጂ ሎዊዛ ነው የምልህ መቸም ቆንጆ ልጅ ናት... ካርላይል ...

“ በጣም ” አለና ሚስተር ካርላይል ዝም አለ ጃስቲስ ሔር ከቤት መቀመጥ
👍14👏1
ሰልቸት ስላለው ምናልባት ከሚስተር ካርላይል ምንም ነገር ማወጣጣት ባለመቻሉ
ጭምር ይሆናል ከተቀመጠበት ተነሥቶ ሰው ሠራሽ ጸጉሩን በመስተዋት እያየ አስተካክሎ ሁል ጊዜ ወደሚያመሽበት ወደ በክስ ሔድ አመራ። ባርባራ አቆልቁላ ትመለከተው ስለ ነበር ልክ ከአጥሩ ሥር ሲደርስ ከአንድ ሰው ጋር ተገናኝቶ ሲነጋገር
አየችው " ማን መሆኑን ለመለየት ስትቸገር ከቆየች በኋላ ስዎቹ ቁመው ሲያወጉ አቋቋማቸውን ለወጡ። ልክ በዚህ ጊዜ ስለ ሆሊጆን መገደል በወንድሟ ዋና ምስክር
ሆኖ ቀርቦ የነበረው ሎክስሌይ የተባለ ሰው መሆኑን ዐወቀችው

“ አባባ ምን ሆነ ? አለች ባርባራ'“ሎክስሌይ የሚያስቆጣ ነገር ነግሮታል"
በጣም ተበሳጭቶ እጆቹን እያወናጨፈ ወደ ቤት ተመለሰ ... እማማ ።

ገባና መዝጊያውን ዘግቶ ከክፍሉ መኻል ቁሞ አንድ ጊዜ ወደ ባርባራ አንድ
ጊዜ ወደ ሚስዝ ሔር እያለዋወጠ ይመለከት ጀምር

“እንዴት ያለ ወሬ ነው በዚህ አካባቢ በሹክሹክታ የሚነፍሰው ? ”

ሚስዝ ሔር መናገር አልቻለችም ባርባራም ቀደም ሲል ሲጨቃጨቅ በት የነበረውን ጉዳይ የሚያነሣባት መስሏት አደፈጠች " በዚህ ጊዜ “ ምን ወሬ አለ? ካርላይል "

“የጉልበት ሠራተኛ መስሎ ኋላ ሊሰቀል ወደሚመጣበት ወደዚህ ቦታ ዘልቆ ነበር አሎሳ ? ”

ሚስዝ ሔር ፊቷ ባንዴ ደም መሰለ ። ሚስተር ካርላይል እንደዚያ ሆና በአንዴ
መለዋወጧን ባሏ እንዳያይ ብሎ ተነሣና ከፊቷ ቆመ " ባርባራ እጆቿን አቆላልፋ
ወደ መስኮቱ ዞረች።

“ስለ ማን ነው የሚናገሩት?” አለ ሚስተር ካርላይል ስለ ማን እንደ ተናገረ በደንብ ቢገባውም ለሚስዝ ሔር ሲል ለማዘናጋት በመፈለግ

“ ስለዚያ ከውካዋ ዲቃላ ነው እንጂ ስለ ማን እናገራለሁ ? ”

“ ሪቻርድ ! ” አለች ሚስዝ ሔር ባሏን። “ እባክህን ራራለት " ልጃችን ኮ ነው "

አይደለም እሱ የሔር ልጅ አይደለም እሱ የጭካኔ የመዓት የፍራት እውነተኛ ልጅ ነው ወደ ኢስት ሊን ብቅ ለማለት ከደፈረ የኢንግላንድ ፖሊሶች የትም አድነው እንዲያመጡት በየቦታው አሠማራቸዋለሁ " እኔ በውነቱ ሎክስሌይ አሁን ሲነግረኝ ውሸት ነው ብዬ ልመታው ነበር " እዚህ አካባቢ ስለ መምጣቱ የምታውቂው አለ ? " አላት ሚስቱን "

ሚስዝ ሔር የጥያቄ ዱብ ዕዳ ሲወርድባት ተጨንቃ ሳለ ሚስተር ካርላይል ወደሱ ተጠጋና '“ምነው ጌታ ሚስዝ ሔርን እኮ አስደነገጧቸው መጀመሪያ
ነገሩ ሲነሣ እንኳን ያን ያህል ፊታቸው እንደ ተለዋወጠና በሽታቸውን ሊቀሰቅስባ
ቸው እንደ ጀመረ አይመለከቱም? ግን እስቲ ለመጠየቅ ይፈቀድልኝና ሎክስሌይ ምን ብሎ ነው የነገረዎት ? "

“ እየውልህ ብሎ ጀመረ ።
እኔ ስወጣ እሱ ሲያልፍ ተገናኘንና “ኧረ እንኳን አገኘሁዎ ሪቻርድ በዚህ አካባቢ ታይቷል” እየተባለ ይወራል " ይህ ጉዳይ
ደኅና የተረሳውን እንደገና የፖሊስን ክትትል የሚቀሰቅስ ስለሆነ · እኔ እርስዎን ብሆን ነገሩ ጭራሽ የማይወሳበትን መንገድ እፈልግ ነበር አይለኝም መስለህ! እኔ ደግሞ የመንደሩን ተራ ሐሜት እንደገና እሱ በመድገሙ አናደደኝና እዛው ላጋጨው ካሰብኩ በኋላ መልሸ ትቸው የሰማውን እንዲያብራራልኝ ጠየቅሁት "

“ ሰውየው የዛፊ ዓመት አካባቢ የጉልበት ሠራተኛ መስሎ ዘልቆ ነበር ይላሉ "
አውነት አድርጎት ከሆነ አብዷል ማለት ነው "

“ በርግጥ ዕብደቱ ነው " ነገር ግን እንዲህ ያለውን ነገር አያደርገውም "
ድፍን ዌስት ሊን የፈለገውን ቢያወራ አይቀበሉት እኔ ብሆን አልቀበለውም "
ምስኪኑ ሪቻርድ ደግሞ የትም ይሁን የት "

እኔ ፊት ሲታዘንለት ለመስማት አልፈልግም! “ምስኪን ሪቻርድ?“ሌባው”
ሪቻርድ በለው "

“ ብቻ በአሜሪካ ጫካዎች ይግባ ወይም ካሊፎርኒያ ወርቅ ቁፋሮ ይጀምር
ወይም ኢንግላንድ ውስጥ አገር ላገር ይንከራተት ከተወሰረበት ቦታ ወጥቶ ዌስት ሊንን ይረግጣል ተብሎ አይታሰብም " እኔስ እርስዎን ብሆን ሎክስሌይን በንግግሩ እሥቅበት ነበር "

ታዲያ ዌስት ሊን ለምን እንደዚህ ያለውን ውሸት ይፈጥራል ? ”

“ ይኸ አስቸጋሪ ነው። ዌስት ሊን ደግሞ ይህን ገንዘብ ቢከፍለው እንኳን ለምን
እንደዚህ ብሎ እንደሚያወራ ሊነግረዎ አይችልም ግን መሠረት የሌለው ነው " ካዩት ለምን ያምናውን
ያወራሉ? አምና ያዩትን ለምን አስከ ዛሬ አልተናገሩም ? ለምን ዛሬ ወይም ትናንት አየነው አይሉም እኔ ብሆን እንደዚህ ያለ ወሬ ብሰማ ከቁም ነገር አልቆጥረውም " ንቄው ዝም እላለሁ "

ሚስተር ጃስቲስ ሔር እንኳን ንቆ ዝም ከማለት ይልቅ ሰምቶ መደንፋት ነበር
የሚቀናው ነገር ግን፡ሚስተር ካርላይልን በጣም ያከብረው ስለ ነበር በሱ አባባል መስማማቱን ለመግለጽ አጕረመረመና ወደሚያመሽበት ለመሔድ እንደገና ወጣ

“ አርኪባልድ!” አለች ሚስዝ ሔር ባሏ ራቅ ብሎ ከሔደ በኋላ “ዛሬ እዚህ በመገኘትህ ከጉድ አወጣኸኝ " እውነቱን ተናግሬ ዐርፈው ነበር

ግን ሎክስሌይ ለምን ተናገረ ? ” አለች ባርባራ ከቆመችበት መስኰት ፊቷን
መልሳ "

ሎክስሌይ መቸም የሪቻርድ ጠላት አይደለም " ስለዚህ ሚስተር ሔር የሰሙ
እንደሆነ አሉባልታውን ያስቆሙታል መስሎት በቅንነት ተነሥቶ ይመስለኛል ወሬውን ኮ እኔም ሰምቸዋለሁ " "

“ እንዴት ሊታወቅ ቻለ ? '
“ እኔም ገርሞኛል " ትናንት ቶም ሔርበትርን አገኘሁትና ሪቻርድ ሔር ገበሬ መስሎ ዌስት ሊን ላይ ስለ መታየቱ መወራቱን ነገረኝ ስሰማ ሣቅሁ እሱም ቢሆን ይህን ወሬ ብሎ እንዳያወራ ሊሆን እንደማይችል እንዲንቀው እደረግሁት " ወሬው እሱ እዚህ በነበረበት ጊዜ ቢሆን ኖሮ እንኳን ዴስ አይልም ነበር " አሁን ግን ሁለት
ዓመት ሊያልፈው ነው " ስለዚህ ምንም የሚያሠጋ ነገር የለም " አለ ሚስተር ካርላይል።

ሚስዝ ሔር በረጅሙ ተነፈሰችና †ነሥታ ወዶ መኝታ ቤቷ ስትሔድ ካርላይልና ባርባራ ቀሩ "

“ አዬ ምነው እውነተኛዉ ወንጀለኛ ቢገኝ በዚህ ዐይነት እማማ ከጥቂት
ጊዜ በኋላ ሰው አትሆንም!"

“ትክከለኛው ሰው ቢገኝ የኔም ምኞቴ ነበር ! ነገር ግን ያለው ተስፋ በጣም
ሩቅ ነው ” አላት ' ሚስተር ካርይል "

ባርባራ ተቀምጣ ነገር ታሰላስል ጀመር ለሚስተር ካርይል ልትገልጽት የፈለገችው ነገር አላት " ነገር ግን እንዳትናገር ያገዳት ምክንያት ያላት ትመስላለች በመጨረሻ ድምጿን ዝቅ አድርጋ ፍራት ፍራት ያላት ተነፈሰችው "

“ያን ጊዜ ሪቻርድ ቶርንን አገኘሁት ሲለን ሰውየው ምን እንደሚመስል ?
የሰጠን ምልክት ትዝ ይልሃል ? ”

"አዎን ”

“ ታዲያ በዚያ ገለፃ ማንን እንደሚመስል ያሰብከው ነገር የለም ? ''

የሱ አባባልማ ከቶርን ጋር ይስማማል "

“ሪቻርድ ሰውዬው ጸጉሩን ወደ ኋላው ሲመልስ ስለሚያደርገው ልዩ
እንቅስቃሴ ሁሉ ነግሮን ነበር " ታዲያ ያንን እንቅስቃሌ ከነጭ እጀና ከአልማዝ ቀለበት ጋር አገናዝበህ በሌላ ሰው አላየኸውም ? ”

“ ጸጉራቸውን ወደኋላ የመመለስ ልማድ ያላቸው ብዙ ናቸው " እኔም አንዳንድ ጊዜ አደርጋለሁ " ምነው ጠየቅሽኝ ?የምትጠራጠሪው ሰው አለ ? ”

“ አንተ የጠረጠርከው የለህም ወይ ? ”

“ እኔ የምጠረጥረው የለኝም " ካፒቴን ቶርን እሱ ያለመሆኑን ካወቅን ወዲህ
ማንንም ጠርጥሬ አላውቅም ” አላት "
👍12
ባርባራ ይሀን ስትሰማ አፋን ይዛ ዝም አለች " እሷ ግን የጠረጠረችው ነበራት"
አንዳንድ ግልጽ ያልሆኑ ጥርጣሬዎች በሐሳቧ እየመጡ ራሷንም በጣም ያስገርማታል ታድያ ለእሷ የታይዋት ነገሮች ለሚስተር ካርላይልም በሐሳቡ ሳይመጡበት አይቀሩም የሚል ግምት ነበራት " አሁን ግን ምንም እንዳልመጡለት ተረዳች " ሪቻርድ ሔር ቶርንን አየሁት ብሎ በተናገረ ጊዜ ሌሊቱን በሚስተር ካርላይል ትዳር ላይ አስዶንጋጭ አደጋ ደረሰ " ይህ ድንገተኛ ነገር ባርባራ ስለ ተሰማት ጥርጣሪ ከሚስስተር ካርላይል ጋር እንድትነጋገርበት ምክንያት ሆኖ አገዳት " ከዚያ ወዲህም አንሥታበት አታውቅም " ሪቻርድም ወሬው ጠፋ " የሱ ጉዳይም ቀዘቀዘ "

እኔስ የወንጀለኛው መገኘት ተስፋ እያስቆረጠኝ ሔዷል" አሁን የሪቻርድ ነገር መጨረሻው ምንድነው ?”

ቶርን ተፈላጊው ቶርን ያለመሆኑን ካወቅን ወዲህ እኮ ፍንጬ ጠፋን " ፍለጋችን ቆመ ”

ሪቻርድ የሱን “ቶርን ባያየው ኖሮ እንዳልከው በዚህ ይቆም ነበር "

“ የሪቻርድ አእምሮ በቶርን ሐሳብና ምስል የተያዘ ስለሆነ ' ማንም መንገደኛ
እሱ መስሎ ሊታየው ይችላል ።

“ ይኸ እንኳን በጭራሽ ሊሆን አይችልም " እኔ ምንም አልጠራጠርም
አንተም ራስህን ያን ጊዜ አምነኸው ነበር።

አዎን ቅን አነጋሩ አሳመነኝ " በነገሩ ለማሰብ ጊዜ አጣሁ " ከሪቻርድ አገላለጽ ጋር የሚስማማ ሰው ደግሞ ከካፒቴን ቶርን በቀር ዌስት ሊን ውስጥ ማንም
አልነበረም " ስለዚህ ጊዜ እስኪገልጠው ድረስ ከመጠበቅ በቀር ሌላ ምንም ማድረግ አንችልም "

“ ግን መጠበቁ እኮ ያስጨንቃል መጠበቅ

“ ከአባትሽ ጋር የሚያጣላሽ ምንድነው ? '' አላት ፈታ ብሎ ። ፊቷ ፍም መሰለ “ እሷም ፈግግ ብላ አየችውና ዝም አለች "

“ አባትሽ ያነሡት “ሻለቃ ቶርን” ያ እኛ የምናውቀው መሰለኝ?” ሲላት ራሷን
በአዎንታ ነቀነቀች "

እሱ ከሆነ የደስ ደስ ያለው ብዙ ሴቶች ባላቸው ቢሆን የሚኮሩበት ሰው ነው።

“ አዎን ደስ የሚል ሰው ነው ” ብላ ንግግር ዘጋች "

ካፒቴን ቶርን አንድ ቀን ሔርበርት ቤት እንግድነት በሔደበት ነበር ባርባራን
ገና ሲያያት ልቡ የደነገጠላት " ያን ጊዜ ሁኔታዎች ቢመቻቹለት ኖሮ ለጋብቻ ይጠይቃት ነበር አሁን በቅርቡ ሀብት ከመውረሱም በላይ በሙያውም አንድ ደረጃ
ከፍ ብሏል ስለዚህ እሷንና አባቷን በደብዳቤ ቢጠይቅ ወዲያው አይሆንም አለ
ችው » አባቷ ደግሞ ለጊዜው እሷ እንዳትሰማ ብሎ ደብቆ ይዞት ነበር ።

“ይኸን ስለ ሪቻርድ የሚነፍሰውን ወሬ ለማስቆም የምትችለውን ሁሉ ታደርጋለህ አይደለም ?

“ አታስቢ " የሪቻርድ ስም ዌስት ሊን ላይ ባይነሣ የተሻለ ነው ግን አሁንም
እንዴት ሊወራ እንደቻለ እየገረመኝ ነው ”

ከዚያም ሁለቱም ዝም ብለው ከቆዩ በኋላ ' “ ሌላው ወሬስ” አለችው ወደሚስተር ካርላይል ሳታይ ' “ እውነት ነው ? ”

“ የምን ሌላ ወሬ? ”
ሉዊዝ ዶቢድን ልታገባ ነው መባሉ ? ”
አይደለም " እኔ ማንንም ለማግባት ሐሳብ የለኝም " እንዳለሁ እቆያለሁ "
ባርባራ በመግረም ቀና ብላ ተመለከተችው "

“ ምነው ገረመሽ ... ባርባራ ? አየሽ ያቺ ሚስቴ የነበረችው እኮ በሕይወት
አለች " ”

እና ምናለበት ?”

ለጊዜው ዝም ብሎ ቆየና ባርባራ አጠገብ ቆሞ ቁልቁል ወዶ እሷ እያየ ዝግ ባለ ድምፅ “ ማንም ሰው ሚስቱን ሰዶ ሌላይቱን ካገባ አመነዘረ ” አላትና መልስ
ለመስጠት ከመቻሏ በፊት
ምናልባት የምትሰጠው መልስ ቢኖራት ወይም
ከድንጋጤዋ ከመመለሷ በፊት ባርኔጣውን አንሥቶ ሔደ ....

💫ይቀጥላል💫
👍13🥰51👏1
#ጠላፊዎቹ የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ታሪክ በተለመደው ሰአት በቅርቡ እጀምራለው እንደተለመደው በመከታተልና አስተያየት በመስጠት አብራችሁኝ ሁኑ።
👍57
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አንድ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


ጦርነቱ የፈነዳው በአንዱ ፀሐያማ እሁድ ቀን ነበር፡
አይሮፕላኑ እስካሁን ከተሰሩት ሁሉ የተለየ ነው፡፡ ጦርነቱ የታወጀ ቀን ስድስት ሰዓት ከሰላሳ ላይ አይሮፕላኑ ብቅ ይል ይሆን እያለ ቶም ሉተር ልቡ ተሰቅሎ ወደ ሰማይ አንጋጦ እየጠበቀ ነው።

ቶም ወሬ ለማየት ባሰፈሰፉ ሰዎች ተከቧል፡ የፓን አሜሪካን ኩባንያ ንብረት የሆነው ባህር ላይ ማረፍና መነሳት የሚችለው አይሮፕላን ሳውዝ ሃምፕተን ወደብ ላይ ሲያርፍ ይህ ዘጠነኛው ጊዜ ቢሆንም አሁንም ማራኪነቱ አልደበዘዘም፡፡ ይህ አይሮፕላን አስደናቂ በመሆኑ አገሪቱ ጦርነት
ባወጀችበት ቀን እንኳን ሰዎች እሱን ለማየት ወደሚያርፍበት ቦታ
እየተንጋጉ ነው፡፡ በዚሁ ወደብ ዳርቻ አንዳች የሚያካክሉ ሁለት መርከቦች መልህቃቸውን ጥለው ቢቆሙም እነሱን ነገሬ ያለ የለም፡፡

ታዲያ አይሮፕላኑን እየጠበቁም ቢሆን ሰዎች የሚያወሩት ስለጦርነቱ
ነው ወንዶቹ ስለታንክና መድፎች ሲያወሩ ሴቶቹ በአርምሞ ይመለከታሉ፤
ከፍቷቸዋል። ሉተር አሜሪካዊ እንደመሆኑ ፍላጎቱ ሀገሩ በጦርነቱ እጇን እንዳታስገባ ነው፡፡ ጦርነቱ የእሷ ጉዳይ አይደለም፡፡ ከዚህም በላይ ናዚዎች በኮሚኒስቶች መጨከናቸው ተገቢ ነው፡፡

ሉተር በንግድ ሥራ የሚተዳደር ሲሆን የልብስ ስፌት ፋብሪው ውስጥ የሚሰሩት ኮሚኒስቶች አንድ ወቅት ላይ ችግር ፈጥረውበት ሊያጠፉት ሁሉ ምንም አልቀራቸውም ነበር፡፡ ትዝ ሲለው በንዴት
ይንቀጠቀጣል፡፡ የአባቱ የልብስ መሸጫ መደብር በይሁዳውያን ተቀናቃኞች
አፈር ድሜ ሊበላ ነበር፡፡ ሉተር ሬይ ፓትሪያርካን በጡት አባትነት ሲይዝ
ግን ህይወቱ ባንድ ጊዜ ተለወጠ የፓትሪያርካ ሰዎች እዚህም እዚያም
አደጋ በመፍጠር ኮሚኒስቶችን ልክ ማስገባት ያውቃሉ አንዱ ከውካዋ
ኮሚኒስት እጁ በማዳወሪያ ማሽን ውስጥ ተወትፎ እንዲቀር ተደረገ፡፡ የሰራተኛ ማህበር ቀስቃሽ አባል በመኪና ተገጭቶ ህይወቱ አለፈ፡ በፋብሪካ ውስጥ ስላለው የደህንነት ደምብ መጣስ ቅሬታ ያቀረቡ ሁለት ሰዎች ቡና ቤት ውስጥ በተፈጠረ ጠብ ቆስለው የአልጋ ቁራኛ ሆኑ፡ አንዷ ችግር ፈጣሪ ቤቷ በእሳት እንዲጋይ በመደረጉ በኩባንያው ላይ ያቀረበችውን ክስ ለማንሳት
ተገደደች፡፡ ከዚህ በኋላ ሰላም ሰፈነ፡፡ ፓትሪያርካ ሂትለር የሚያውቀውን
ያውቃል፡፡ ኮሚኒስቶችን ልክ ለማስገባት እንደ በረሮ መንጋ መደምሰስ ነው::

ሉተር ይህን እያሰላሰለ እግሩን ወለሉ ላይ ይጠበጥባል፡፡ አንዲት ጀልባ
አይሮፕላኑ የሚያርፍበት የባህር ክፍል አካባቢ ለማረፍ ችግር የሚፈጥርበት
አንዳች የተንሳፈፈ ነገር እንዳለ ለማየት ወደ ቦታው በረረች፡፡ የተሰበሰበው
ሰው ይህን ሲያይ በጉጉት አጉተመተመ አይሮፕላኑ እየመጣ ነው ማለት
ነው፡፡

አይሮፕላኑን ቀድሞ ያየው አንድ ትንሽ ልጅ ነው፡፡ አጉልቶ የሚያሳይ
መነጽር ባይዝም ‹‹ያውላችሁ!›› ሲል ጮኸ፡፡ ‹‹ባህር ላይ የሚያርፈው
አይሮፕላን መጣ!›› በማለት ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሲያመለክት ሁሉም
ዓይኑን ወደዚያው ወረወረ፡፡ ሉተር በመጀመሪያ አሞራ የመሰለ ነገር ደብዘዝ
ብሎ ታየው፡፡ በኋላ እየጎላ መጣ ‹‹ልጁ እውነቱን ነው! እውነቱን ነው!››በማለት የተሰበሰበው ህዝብ አውካካ፡፡

ፓን አሜሪካን አየር መንገድ ሰዎችን በምቾት አሳፍሮ አትላንቲክ ውቅያኖስን ማቋረጥ የሚችል ቦይንግ B 134 የተሰኘ አይሮፕላን በቦይንግ ኩባንያ አሰርቷል፤ ግዙፍ፣ ማራኪና ጉልበቱ ከፍተኛ የሆነ የአየር ላይ ቤተ መንግስት፡፡ አየር መንገዱ ስድስት አይሮፕላኖችን ያስመጣ ሲሆን ሌሎች ስድስት ደግሞ እንዲሰሩለት አዟል። በምቾትና በማራኪነት በወደቡ ላይ ከቆሙት የመንገደኛ መርከቦቹ አይተናነሱም፡፡ ነገር ግን መርከቦቹ አትላንቲክን ለማቋረጥ አራት ወይም አምስት ቀን ሲወስድባቸው ይህ ባህር ላይ ማረፍና ከባህር ላይ መነሳት የሚችል አይሮፕላን ግን ይህን ጉዞ በሃያ አራት ወይም በሰላሳ ሰዓት ያጠናቅቀዋል፡፡

ልክ ክንፍ ያለው ዓሳ ነባሪ ይመስላል› አለ ሉተር በሆዱ አይሮፕላኑ እየቀረበ ሲመጣ፡፡ ከወደ ፊቱ ሾል ያለ ግዙፍ ነው፡፡ ክንፎቹ ውስጥ ኃይለኛ
ሞተሮች ተሰክተዋል፡ አይሮፕላኑ ውሃ ላይ ሲያርፍ ሚዛኑን እንዲጠብቅ
የሚያስችሉት ከክንፎቹ በታች አጠር ወፈር ያሉ ትናንሽ ክንፎች
ተገጥመውለታል፡፡ የአይሮፕላኑ የታችኛው ክፍል እንደ ፈጣን ጀልባ
ውሃውን መሰንጠቅ እንዲያስችለው ጫፉ እንደ ቢላ የሰላ ነው፡፡

አይሮፕላኑ ፎቅና ምድር አለው፡ ሉተር ባለፈው ሳምንት ስለመጣበት
የአይሮፕላኑን ውስጣዊና ውጫዊ ገጽታ በሚገባ ያውቀዋል፡ የላይኛው ፎቅ
ፓይለቶቹንና የዕቃ ማስቀመጫ ክፍሎችን የያዘ ሲሆን የታችኛው ክፍል
ተሳፋሪዎች የሚቀመጡበት ነው፡፡ ተሳፋሪዎች የሚቀመጡባቸው ክፍሎች
በመደዳ በተደረደሩ የእንግዳ ማረፊያ ሶፋዎች የተሞሉ ናቸው፡፡ በመብል ጊዜ እነዚህ ክፍሎች ወደ መብል ቤትነት የሚለወጡ ሲሆን በመኝታ ጊዜ ደግሞ
ሶፋዎቹ እንደ አልጋ ይዘረጋሉ፡

ተሳፋሪዎቹን ከሙቀትና ከብርድ ለመጠበቅ አይሮፕላኑ ውስጡ
ተለብጧል፡ ወለሉ ወፋፍራም ምንጣፍ የተነጠፈበት ሲሆን ክፍሉ ዓይን የማይወጉ መብራቶች ተገጥመውለታል፡፡ በሃር ጨርቅ የተሸፈኑ ሶፋዎቹ
ድሎታቸው ልክ የለውም፡ የአይሮፕላኑ ግድግዳ ላይ የተገጠመው ድምጽ
ማፈኛ የሞተሮቹን ድምጽ ይውጣል፡ የአይሮፕላኑ ካፒቴን የአዛዥነት ባህሪ
የተላበሰ ሲሆን ባልደረቦቹ ደግሞ ጸዳ ያለና ማራኪ የፓን አሜሪካን አየር
መንገድ ዩኒፎርም ለብሰዋል፡፡ አስተናጋጆቹ የተሳፋሪዎቹን ፍላጎት ለማርካት ተፍ ተፍ ይላሉ፡ ምግብና መጠጥ ያለማቋረጥ ይጋዛል፡፡ ተሳፋሪዎች የጠየቁት ነገር በሙሉ ልክ በአስማት የሚመጣ እንደሆነ ሁሉ እፊታቸው ዱብ ይላል፡ እንዲህ አይነት ድሎት በቀላል ዋጋ አይገኝም፡ ተሳፋሪዎቹ አብዛኛውን ጊዜ የንጉሣውያን ቤተሰቦች፣ የፊልም ተዋናዮች፣ የትላልቅ ኮርፖሬሽኖች ኃላፊዎች እና የአገር መሪዎች ናቸው፡፡ ቶም ሉተር ከእንደነዚህ አይነት ሰዎች ጋር የሚመደብ አይደለም፡ ሀብታም ቢሆንም እዚህ ደረጃ ለመድረስ ብዙ የለፋ በመሆኑ ለድሎት ሲል ብቻ ገንዘቡን አይረጭም: ቢሆንም ራሱን ከአይሮፕላኑ ጋራ ለማለማመድ ፈልጓል፡፡
አንድ ኃያል ሰው በጣም ኃያል የሆነ አንድ አደገኛ ተግባር እንዲፈጽምለት
ውለታ ጠይቆታል፤ ለዚህ ስራው ሉተር የሚከፈለው ነገር የለም፡ ነገር ግን
ለዚህ ሰው ውለታ መዋል ከገንዘብ ይልቃል፡

ይሄ ዕቅድ ምናልባት ይሰረዝ ይሆናል፡ ሉተር ‹‹ስራውን ቀጥል››
የሚለውን የመጨረሻውን ትዕዛዝ እየጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ግን አዕምሮው
ዕቅዱን ቶሎ ለመፈጸም በመጓጓትና ምነው ባልሰራሁት! ብሎ በመመኘት መካከል ይዋልልበታል፡

አይሮፕላኑ ከአፍንጫው ከፍ ከጭራው ዝቅ እያለ ወደ መሬት እየወረደ
ነው፡፡ አሁን ለማረፍ ተቃርቧል፡ ሉተር በአይሮፕላኑ እንደአዲስ ተደንቋል፡፡

ለአፍታ ያህል አይሮፕላኑ እየተንሳፈፈ ይሆን እየወደቀ ሳይለይ አንዳንዴ ደግሞ ወደ ላይ ከፍ እያለ በመጨረሻም ባህር ላይ እንደተወረወረ ዝይ እዚህም እዚያም እየነጠረና ውሃውን ሁለት ቦታ እየከፈለ ፍጥነቱን በመቀነስ ውሃው ላይ አረፈና እንደ ጀልባ ይሄድ ጀመር፡

ሉተር ትንፋሹን ውጦ ቆይቶ ስለነበር በእፎይታ ለቀቀው፡ አይሮፕላኑ ወደ መቆሚያው ተጠግቶ ቆመ፡ ሉተር ከሳምንት በፊት እዚህ ቦታ ላይ ነው ከአይሮፕላኑ የወረደው:፡ ከአፍታ በኋላ አይሮፕላኑ ከፊትና ከኋላ
በገመድ ከወደቡ ምሰሶ ጋር ይታሰራል፡
👍593👎1🔥1