✍✍የጠንቋዩ ዋሻ✍✍
♣♣ክፍል ሦስት♣♣
♦♦♦♦°♦♦♦♦°♦♦♦♦°
ለለሦስቱም አብሮ አደግ ጓደኛማቾች ፡ ነገሩ ሁሉ አንደዘበት ፡የሚያዩት የነበረው ፡ የወረር ፊልም ፡በሁኑ ዓለም ፡የተከሰተባቸው ፡እስኪመስላቸው ፡ድረስ ፡ በፍርሃት የሚገቡበት ፡ጠፍቷቸዋል ፡ ጠንቋዩ ለደቂቃ አይኖቹን ፡ሲያጉረጠርጥባቸው ፡ቆይቶ ፡ ኤዛ ብሎ ፡የጠራት ፡ ቆንጅዬና ፡ማራኪ የሆነች ዋ ወጣት ፡ ያዘዛትን ፡የፈላ ውሃ ፡ይዛ ፊቱ ጎንበስ ፡ብላ ስትቀርብ ፡ በሌባ ጣቱ እረጅም ፡ሉጫ ፀጉሯ ፡ያረፈበትን ፡ አናቷን ፡ነካ ነካ አደረጋት ፡ እሱ በነካት ቁጥር ፡ከጭንቅላቷ ፡ዝቅ ፡ስትል ፡ መስፍን ፡የተባለው ፡ጎረምሳ ፡ ለጓደኛው ፡ ዳንኤል ፡ ' የሴጣን አለቃ ሳይሆን አይቀርም ፡ መዳንያለም ከዚብቻ በታምሩ ያውጣን 'አለው ፡በማንሾካሾክ ፡ ዳንኤል ማለት የሚፈልገው ፡ነገር ፡ቢኖርም ፡ ከንፈሮቹ በፍርሃት ፡አልላቀቅ አሉት ፡ ሦስተኛው ፡ጓደኛቸው ፡ መሳይ ፡ ቀጣዩን ፡የጠንቋዩን ፡እርምጃ ፡አይኑ ቁልጭልጭ ፡እያለ ይጠብቃል ፡ ፍርሃቱ ከሁለቱም ፡ጓደኞቹ ይብሳል ፡ አስተዳደጉም ፡ ፍቅርና ፡ማባበል ፡የበዛበት ፡ስለሆነ ፡ እንዲ አይነቱን ፡አስጨናቂ ሁኔታ ለመቋቋም ፡ አቅም አቷል ፡ ጠንቋዩ ፡በጣም ፡ቢጮህበት እንኳ ፡የሚሞት ነው የሚመስለው ፡ ከሁሉም በላይ ደሞ ፡ እነዛ ቀያይ የለበሱ ቀንጆ ሴቶች ፡ ድንገት ፡ ወደ ሴጣንነት ፡ተቀይረው ፡የሚያጠቋቸው ፡ነው የመሰለው ፡ የቫንባዬር ፊልም ታወሰው ፡ እናም ፡እነዚንም ፡ሴቶች ፡አላመናቸውም ፡ እዚ ጥቅጥቅ ፡ጫካውስጥ ፡ የሚያስፈራ ዋሻ ፡ውስጥ ፡ ከሚያስፈራራ ግዙፍ በለነጭ ፂም ሰውዬ ጋር ፡ምን ፡ሊያስደብቃቸው ፡የችላል የተለየ ነገር ከሌላቸው በቀር ፡ ,,,, ጠንቋዩ ፡ ኤዛ የተባለችው ልጅ በሰአን ያቀረበችው ፡የፈላ ውሃ ውስጥ ፡ ከጉያው ፡ውስጥ አንዲት ትንሽዬ ብልቃጥ ፡በማውጣት ፡ ከፈታትና ፡ ሦስት ጊዜ ፡ ቀይ ጠብታ ነገር ፡ወደውሃው ፡ጨመረ ፡ ቀጥሎ ፡ ሌላኛዋ ልጅ ፡በትንሽዬ ፡ ሙዳይ ፡አንዳች ነገር ይዛ መጣች ፡እናም አጠገቡ ስትደርስ ፡ጎንበስ ፡ብላ ጠይኖቹን ፡ሳታይ ፡ሙዳዩን ከፍታ አቀረበች ፡ጠንቋዩ በእጁ ቆንጠር አድርጎ ወደፈላውሃ ጨመረ ፡ከዛም በሌባ ጣቱ ቀላቀለው ፡ በነጩ ሰአን የነበረው ፡ውሃ ሙሉ በሙሉ ወፈር ያለ ቀይ ፈሳሽ ፡ሆነ ፡ ከዛም ፡ ሴቶቹን ፡" ውርንጭሎቼ እረፍት አድርጉ ፡ ወደጨለማው ፡ ክፍል ፡ሄዳቹ ተኙ አቢያራ ይጠብቃችዋል ፡ ከኔ አይጎልባችሁም "አላቸው ፡ በዋሻው ፡ክፍል ውስጥ የነበሩት አራት ቆነጃጂት ሴቶች ፡ በተራ በተራ ፡የጠንቋዩ አቢያራን ፡ እጅ ፡እየሳሙ አመሰገኑ ፡ ፡አቢያር ፡ በተራ እጁን እየሰጣቸው ፡ ስማቸውን ፡ እየጠራ ፡መረቃቸው " ኤዛ ያቢያራ መንፈስ ፡ይውረድብሽ ፡"አላት ጎንበስ ብላ
"ጌታዬ ምስጋና ይድረስህ "አለች
"ኤፍራ ፡የአቢያራ መንፈስ ካንቺ ይሁን "
"ምስጋና ላንተ "አለች ኤፍራ ብሎ የጠራት ሴት
"ኤልያታ ፡አቢያራ ካንቺ ይሁን"
"ሁሉ ባንተ ይሁን "አለች
" ኤፊ አቢያራ በሁሉ ነገርሽ ይግባ "
"ሁሌም ላንተ ነኝ አባቴ " አለች ፡ ነገሩ ግራ የገባቸው ፡ የታፈኑት ሦስቱ ጎረምሶች ፡ በየራሳቸው ፡ውስጥ የት ነው ያለነው ይሄ ነገር ህልም ነው እንዴ ፡ ይህ አስፈሪ ሰው ፡እራሱን እንዴት ነው እንደ አምላክ የቆጠረው ፡ እነዚንስ ፡ቀያይና ቆንጆ አማሪኛ የሚናገሩ የሌላ አገር ፡ሰው የሚመስሉ ሴቶች ፡ከወዴት ፡አመጣቸው ፡ ደሞስ ፡የስም አጠራራቸው ፡ የመጀመሪያ ፊደል መመሳሰል ፡ እንዴት ቻለ ፡ ነው ፡ለራሱ እንዲመቸው ፡አድርጎ ፡ሰይሟቸው ፡ነው ፡ የሆነስ ፡ሆነና ፡ ምንድነው ፡አላማው ፡ የሚያምኑትን ሰዎች ፡ማብዛት ፡ነው ፡ወይስ ፡ በተረት እንደሚነገረው ፡የሰው ፡ደም የሚጠጣ ጭራቅ ፡ይሆን ፡ ጎረምሶቹ ከአቢያራ ፡ይልቅ ፡አይኖቻቸውን ፡ይዟቸው ፡ወደመጣው ፡ያልታወቀው ፡ሰው ፡ ተክለዋል ፡ ከዚ ሴጣን ፡ከሚመስለው ፡አቢያራ ፡ ለምኖላቸው ፡በነሱላይ ፡ሊያደርግ ካሰበው ፡ነገር ፡እንዲያወጣቸው ፡ በአይናቸው ፡ተማፀኑ ፡ ሴቶቹ በአንዲት ፡ሸለቆ ፡ውስጥ ፡ገብተው ፡ተሰወሩ ፡ እነሱ ሲሄዱ ፡ ዋሻው ፡ የሞት መንፈስ ፡የሚጮህበት ፡መሰለ ፡ 'እሽሽሽሽሽ ሿሿሿሿሿ ፂፂፂፂፂፂ ስስስስስ ,,,,,,,' የልብን ትርታ የሚጨምር ፡ዝም ያለ ጩኽት ፡
አቢያራ "ና መስፍን "ሲል መስፍን ፡ልቡ በድንጋጤ ዘለለች ፡በስሜ ይጠራኛል ፡ብሎ ፡አላሰበም ፡እና ወደሱ ለመቅረብ ፡ዘገየ ፡ያልታወቀው ፡ሰው ፡ወደመስፍን በመጠጋት ፡ አባቴን ፡አታበሳጨው ፡ሲለው ፡መስፍን ፡ተንቀሳቀሰ ፡ እናም ፡አቢያራ ፡ፊት ቆመ አቢያራ የመስፍንን አይኖች ፡አፍጥጦ ሲያየው ፡ ቆይቶ ሳቅ ፡ብሎ ፡አፉን ፡እንዲ ከፍት ፡አዘዘው ፡ መስፍን ፡በፍርሃት እንደተዋጠ አፉን ከፈተ አቢያራ ከበጠበጠው ፡ቀይ ፈሳሽ ፡በእጁ ጨልፎ የመስፍን አፍ ውስጥ ጨመረው ፡ ከዛም ወደአልታወቀው ሰው ምልክት ፡ሲሰጠው ፡ያልታወቀው ሰው ፡የመስፍንን አፍ ፈሳሹ እንዳይወጣ ግጥም አድርጎ ያዘው ፡ መሰፍን እየተንገሸገሸ ዋጠው ፡ እና አይኑን ጨፍኖ ቀጣዩን ጠበቀ ፡ ምንም አይነት ለውጥ ፡ስላላሳየ ከሞት ተርፌያለው ብሎ አስቦ ፡ ተቀመጥ በተባለበት ቦታ ሄዶ ተቀመጠ ፡ቦታው ጎድጎድ ያለ ልክ እንደ ሳፋ ያለ ድንጋይ ነገር ፡ስለሆነ ተሰበሰበ ፡ እግሩን እጥፍጥፍ አድርጎ ፡,,,,,ቀጥሎ ፡አቢያራ በሚያስገመግም ድምፁ " ዳንኤል ናወዲ "ሲል ፡የጓደኛውን ፡ምንም አለመሆን ያየው ፡ዳንኤል ፡ በርታ ብሎ ፡ቀረበ ፡ አቢያራ ፡ለሱም ፡ከፈሳሹ አጠጣው ፡ ፡ዳንኤል ፡ ፊቱን አጨፍግጎ የማይቀርለትን ተጎነጨው ፡ እሱንም ፡መጠጣቱን ካረጋገጡ በዋላ ፡ ወደ ጎድጓዳው ፡ቦታ እንዲሄድ አደረጉት ፡ ቀጥሎ ፡የመሳይ ፡ተራ ደረሰና አቢያራ "መሳይ ናወዲ "ሲለው ፡መሳይ ፡ ድንጋጤና መረበሹ ይበልጥ አይሎ ፡ በተቀመጠበት ተሰፍቶ ፡ቀረ "መሳይ ና ወዲ "መሳይ አልንቀሳቀስ አለ ፡አቢያራ ተቆጣ ፡በዚ ጊዜ ፡ ሰውዬው ፡ ወደመሳይ በመሄድ ፡"አንተ ትንሽዬ ደደብ ፡ ተንቀሳቀስ እንጂ አባቴን አታስቆጣው ፡ "አለው ፡መሳይ ፡በድን ፡ሆነ ሰውዬው ፡አቢያራ ከመናደዱ በፊት ፡ሊያስገድደው ፡ሞከረ ፡ አቢያራ "ተወው አድማስ መምጣቱ አይቀርም ፡ዞር በል ፡ካጠገቡ ፡"አለው ፡ በዚ አጋጣሚ ይዟቸው ፡የመጣው ፡ሰው ፡አድማስ ፡እንደሆነ ስሙ አወቁ ፡ አንተን ብሎ አድማስ ፡ብሎ ፡መስፍን ፡በውስጡ ሸረደደው ፡ የጓደኛው ፡ መሳይ ፡ሁኔታ ደሞ፡አስፈራው ፡ አንድነገር ፡እንዳያደርጉት በውስጡ ለአምላኩ ፀለየ ፡ ዳንኤልም መሳይን ፡እንዳይገሉት ፡ፈራ ፡ አቢያራ ድምፁ ወደ አስፈሪነት ይበልጥ ፡ተቀየረ "መ ሳ ይ ና ወደኔ አሆሆሆሆይ መሳ ይ "ጩኽቱ በፍርሃት ፡አራዳቸው ፡ መሳይ ካለበት ሳይንቀሳቀስ ፡ ወባ እንደያዘው፡ ሰው አንዘፈዘፈው ፡ አደማስ ፡ ከኪሱ የሚያብረቀርቅ ፡ ስለት አውጥቶ ፡ ለመሳይ ፡አሳየው ፡ አቢያራ ፡ ማጓራትና መጮሁን ፡ቀጠለ ፡ ንዴት ፡ቀጣ ውስጥ ፡እንደገባ በግልፅ ፡ታየ ፡ መሳይ ፡አይኖቹ ብቻ መርገብገብ ፡እና መቁለጭለጭ ሆነ ሰውነቱ ለመንቀሳቀስ አልታዘዝ አለው ፡ ደጋግሞ የፈጣሪውን ፡ስም ፡በልቡ ጠራ ,,,,,,,,,,,,
✍ ሙና መሀመድ
ይቀጥላል
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️

👍36❤1
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
ደቂቃዎች በረሩ ላራት ሰዓት ሩብ ጕዳይ አራት ተሩብ አሁንም ሪቻርድ ሔር ከእናቱ ጋር እንዳለ ነው " ሚስተር ካርላይልና ባርባራም በአትክልቱ ቦታ መኽል ባለዉ እግር መንገድ እስከዚያ ሰዓት ድረስ በትዕግሥት ይመላለሳሉ አራት ሰዓት ተሩብ ላይ ሪቻርድ ሔር ከናቱ ተሰናብቶ መጣ " ባርባራም ዕንባዋን እያወረደች ተሰናበተችው በመጣበት ለመሔድ ወደ ዐፀዱ ገባ "
“ በይ ባርባራ . . . ደኅና እደሪ " በጣም ስለመሸ ሚስዝ ሔርን አልተሰናበትኳቸውም " ሆኖም ሁሉ ነገር ደኅና በመሳካቱ የተሰማኝን ደስታ ንገሪልኝ ”ብሏት ሔደ እሱ በሰው እየተራመደ ወደ ቤቱ ሲገሠግሥ ባርባራ ብሶቷ በዕንባ እስኪወጣላት ድረስ ከበሩ ብረት ተደግፋ ማንም
ሳያቋርጣት እያነባች ዐሥር ደቂቃ ያህል ቆየች " እናቷም የራሷን የውስጥ ብሶት ስታስተነትን ፈጽማ ረስታት ኖሯል። ባርባራ ከዚያ እንደ ቆመች ፈጣን የእግር ዳና ስትሰማ በጣም ድንግጥ አለች ወዲያው ግን ሚስተር ካርላይል መሆኑን ዐወቀችው "
“ በውስጡ አንድ ብራና የያዘ ጥቅል ትቼ ነበር እባክሽ አምጭልኝ” ባርባራ
ስትበር ሔዳ አመጣችለት ሚስተር ካርላይልም ተቀበለና ባጭሩ አመስግኖ ወደ ቤቱ ገሠገሠ ። እሷም እንደ ነበረችው ከበሩ ተደግፋ በካርላይል መምጣት ተቋርጦ
የነበረውን ዕንባዋን ትለቀው ጀመር በወንድሟ ነገር አንጀቷ አሯል ይሆናል ተብሎ የተጠበቀው ካፒቴን ቶርን ሳይሆን በመቅረቱ የባሰውን በግናለች አሁንም ግና የአባቷ ዳና አልተሰማም እሷም ቁማ መጠበቋን ቀጠለች » ትንሽ ቆይታ በቁጥቋጦቹ ታኮ አንድ ስው ከሩቅ ታያት " እሷም የድንጋጤ ሀይኖቿን አፍጣ ተመለከተች " ልቧ ነጥሮ የሚወጣ እስኪመስል ይመታ ጀመር " ሪቻርድ መሆኑን ስታውቅ
ምን ጉዳይ አሳብዶ እንደ መለሰው ገረማት አሁንም ከደጅ ሲያገኛት ጊዜ ያባቱን
አለመግባት አረጋገጠና ያለ ሥጋት ተጠጋ " የሠራ አካላቱ እየተንቀጠቀጠ ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ የሚሆነው ጠፍቶታል "
“ ባርባራ ! ባርባራ !.... ” አላት በኃይል እየቃተተ “ቶርንን አየሁት !
ራሱን ቶርንን በአካል አገኘሁት ”
ባርባራ እንግዳ ነገር ሆነባትና አፍጣ ታየው ጀመር
“ልክ ከዚህ እንደ ወጣሁ ሰው ስለማይበዛበት ከዚህኛው መንገድ ይሻላል
በማለት ወደ ቢን ሌን አቋርጨ ስሔድ አንድ ሰው ከሩቅ ሲመጣ አየሁ ምንም እንኳን ሌላ ለመምሰል ብሞክርም ማንም እንዲያገኘው ስለ አልፈለግሁ ወደ ዛፎቹ
ዘወር አልኩ እሱ መኻል መንገዱን ይዞ ወዶ ዌስትሊን ሲሔድ አየሁት ግና ከአጠገቤ ሳይደርስ ዐወቅሁት "
የሠራ አካላቴን ወረረኝ " እያንዳንዷ የደሜ ጠብታ የምትሯሯጥብኝ መሰለኝ" ዘለህ እነቀው የሆሊጆን ገዳይ ነው ብለህ አስይዘው የሚል ሐሳብ መጣብኝ
ሁኔታውን ገምግሜ ቀጥቅጦ እንዳይገለኝ ፈራሁና ተውኩት አየሽ... ደሞኮ አንድ ጊዜ ነፍስ ያጠፋ ሰው ሁለተኛ ለመድገም ወደ ኋላ አይልም አላት። "
«ሪቻርድ እርግጠኛ ነህ ? ስለ ቶርን ብዙ ስለምትናገር እንዲያው በሐሳብህ
መጥቶብህ እንዳይሆን ?አለችው "
ምን ነካሽ ... ባርባራ ሐሳብ? ከዚህ ተቀርጿል አላልኩሽም ? አላት ወደ
ልቡ እያመለከተ " በየጥላው ሥር ቶርንን አየሁ የምል ሰው በለበት ሰው የሚታየኝ ሕፃን መሰልኩሽ ወይንስ ዕብድ? በአንድ እጁ ባርኔጣውን ይዞ በሌላው ፀጉሩን ከግንባሩ የኋሊት እያስተኛ አሁንም አሁንም ጸጕሩን የኋሊት የመግፋት
ልምድ አለው በጣም እየተጣደፈ ይራመድ ነበር ጸጉሩን እንደዚያ ወደ ኋላ
በሚመልስበት ጊዜ የጣቱ አልማዝ በጨረቃው ብርሃን ይፈልቅ ነበር " ምንም አትጠራጠሪ።
ባርባራ በደንብ ካዳመጠችው በኋላ እሷም እንደሱ ስሜቷ ተቀሰቀሰ ድንጋጤዉ እንቅቃጤዉ ጥድፊያዉ ጉጉቱ እንዳለ ተጋባባት ። ማሰብ ማማዘን
ቦታ ለቀቁ።
በግብታዊ ስሜት ብቻ ተነዳች " የሪቻርድ አባባል ሙሉ በሙሉ እንዳመነችቐት
ምን እንደምታደርግ በማሰብ ጊዜ ማባከን አልፈለገችም :
ምናልባት በዚያ ሰዓት ሰው ቢያገኛት ምን እንደሚላት በመዘንጋት አባቷ ከቤት ሲገባ ቢያጣት ምን እንደሚል በመርሳት ሪቻርድ ሔር ቀስ ብሎ ዙሪውን እያስተዋለ በሩቁ እየተከተላት ወደ ሚስተር ካርላይል እየሮጠች ሔዶች ገና ኢስትሊን በር ሊገባ ሲል ደረሰችበት "
“ባርባራ. . . ምን ነው በደኅናሽ ነው ?”
“ አርኪባልድ ! አርኪባልድ ! አለች ከትንፋሿ ጋር እየተናነቀች " እሱስ
ደኅና ነኝ' አንድ ጊዜ ሪቻርድን አነጋግረው ቶርንን አይቶታል ”
ሚስተር ካርላይል ምልስ አለና ወደ ቁጥቋጦች ዘወር ብለው ሪቻርድ ያየውን
ነገር ዝርዝር አድርጎ አጫወተው እሱም ምናልባት ሪቻርድን ላለማስከፋት ብሎ
እንደሆነም አይታወቅም : ልክ እንደ ባርባራ ሙሉ በሙሉ ሳይጠራጠር ያመነው መሰለ "
“ ሪቻርድ ... ዛሬ ማታ ከቢሮዬ ካየኸው ሰው በቀር በዚህ አካባቢ ቶርን የሚባል ሰው ጭራሽ የለም” አለው ካርላይል ትንሽ ካሰበ በኋላ “ የሚገርም ነገር ነው …”
“ አሁን ያገኘሁት ሰው ቶርን ለመሆኑ አልጠራጠርም ምናልባት እሱ እዚ
ያለው በሌላ ስም ሊሆን ይችላል።
አለባበሱ ምን ይመስል ነበር ? አለው ካርላይል።
እንደ ፈለገ ቢለብሰው ሰውየው አያሳስትም ” አለ ሪቻርድ “ የማታ ልብስ ለብሶ ቀጭን ካፖርት ብጤ ትከሻው ላይ ጣል አድርጎ ነበር " ለባርባራ እንደነገርኳት ጸጉሩን ከግንባሩ ወደ ኋላው በመግፋት ልምዱ ብቻ በቀላሉ ዐውቀዋለሁ
በተጨማሪ ደግሞ ለስላሳ ነጭ የሆነው እጁና የሚያንጸባርቀው የአልማዝ
ቀለበቱ ዋና ምልክቶች ናቸው ”
"በል እንግዲያው ሪቻርድ ... እኔ አሁን የምመክርህ ከዚህ አንድ
ቀን ሰንብትና ይህን ሰውዬ ፈልገው » ድንገት ያየኸው እንዪሆነ የት እንደሚገባ
ተከታተለው ከተቻለ የዚህን ሰው ማንነት ማወቅ በጣም አስፌላጊ ነው አለው
በሚስተር ካርይል
"ብገኝ የሚጠብቀኝ አደጋሳ ?”
አንተ ደግሞ በጣም ስለ ተለዋወጥክ ቀን ለቀን በአደባባይ ብትሔድ እንኳን
የሚያውቅህ አይገኝም : "
ሪቻርድ በሚስተር ካርይል አነጋገር ሊተማመን ስለ አልቻለ ስለአየው ሰውዬ
ምልክት ዝርዝር አድርጎ ከገለጸላቸው በኋላ ለማንኛውም አስፈላጊ ነገር
የሎንዶን አድራሻውን ሰጥቶ ሔደ "
“ በይ እንግዲሀ ልሸኝሽ እንጂ .. ባርባራ ” አለ ሚስተር ካርላይል "
“ በጭራሽ አይሆንም ! እንደዚህ ጊዜው መሽቶ አንተ ደክሞህ እያለህ ሁለተኛ መንገድ አላስመታህም " አሁንም ስመጣ ብቻዬን ነበርኩ " ሪቻርድም እንኳን አብሮኝ አልነበረም ።
ስትመጭ ምንም ነገር ማድረግ ባልችልም አሁን ከሌሊቱ እምስት ሰዓት
ላይ በአውራ ጐዳና ብቻሽን ስትሔጅ ዝም ብዬ አላይሽም ” አለና ክንዱን ዘረጋላት " ተያይዘው ጉዞ ጀመሩ "
“አቤት ይህን ያህል አምሽተህ ስትገባ እቤት ሳቤላ ምን ትልህ ይሆን?”
“ እስካሁን ከግብዣው የምትመለስ አይመስለኝም ደሞም አንዴ ብቻ በአንድ ምክንያት ማምሸቴ ይህን ያህልም አይደለም ”
ከበሩ አድርሷት ተመለሰ እሷ ከቤት ስትገባ አባቷ አሁንም ገና አልመጣም
ነበር "
ሚስተር ካርይል ከቤቱ ሲደርስ ሳቤላ ከመልበሻ ክፍሏ ውስጥ ተቀምጣ ስትጽፍ አገኛት " ስለ ግብዣው አንዳንድ ነገር ጠይቋት ባጭሩ ቁርጥ ቁርጥ እያደረገች
መለሰችለት " በመጨረሻም ለምን እንደማትተኛ ጠየቃት
“ እንቅልፌ አልመጣም ”
“ እኔ ግን ቶሎ መተኛት አለብኝ " ... ሳቤላ ሙትት ብዬ ደክሜአለሁ ”
" ትችላለህ ” አለችው "
ሊስማት ጐንበስ ሲል ፊቷን በዘዴ ዞር አደረገችበት ወደ ግብዣው አብሯት ባለመሔዱ የተቆጣች መሰለውና እጁን ከትከሻዋ ጣል አድርጎ ፈገግ አለ "

👍12
አንቺ የዋህ ሕፃን...አሁን በዚህ ትቆጫለሽ ?ወድጄ እንዳይመስልሽ የኔ ጥፋት አይደለም " አሁን ደክሞኛል " ሁሉንም ጧት እነግርሻለሁ አንቺም ቢበቃሽና ብትተኝ ይሻላል።
እሷ ግን ጽሕፈቷ ላይ
እንዳቀረቀረች ምንም አልመለሰችለትም "ሚስተር
ካርላይል ከመኝታ ቤቱ ገብቶ በሩን ዘጋ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሳቤላ ቀስ ብላ ወደ ጆይስ መኝታ ቤት ወጣች ጆይስ ድንገት ብንን ብላ ስትነቃ እመቤቷ ከፊቷ ቁማ አየቻት አይኗን አሻሽታ
ዙሪያውን አስተውላ ሀሳቧን
ተው " ላብን አረጋጋችኛ ከአልጋው ጠርዝ ተቀመጠች
"እሜቴ አመመዎት?"
"አዎን አሞኛል ' መሮኛል ” አለቻት ወይዘሮ ሳቤላ " እውነትም ፊቷ ወርዝቶ የታመመች ትመስል ነበር
“ጀይስ ቃል እንድትግቢልኝ እፈልጋለሁ በኔ ላይ አንድ ነገር ቢደርስ አንቺ ከልጆቼ ጋር ኢስት ሊን እንድትቀመጭ ከዚህ
በፊትም ቃል ገብተሽልኝ ነበር እንደገና ድገሚልኝ የመጣ ቢመጣ እኔ ከሌለሁ
አንቺ ከልጆቼ አንዳትለይ "
“እኔስ እሽ ከነሱ አልለይም " ግን ምን አገኘዎ ድንገተኛ በሽታ ታመሙ?
"ደኅና ሁኚ ጆይስ ” ብላት እንዳመጣጧ ቀስ ብላ ወጣች " ጆይስ ግራ እንደ
ተጋባች ለአንድ ሰዓት ስታስብ ከቆየች በኋላ እንቅልፍ ወሰዳት "
ሚስተር ካርይልም በበኩሉ ተኝቶ ቆየና ሲነቃ ሚስቱ ወደ አልጋው አለመምጣቷን አየ " ነገሩ ገረመውና ሰዓቱን ሲያይ ከሌሊቱ ዘጠኝ ተሩብ ሆኗል »
ተነሣና ወደ መልበሻ ክፍሏ ቢሔድ ጨለማ ሆነበት " ቢያዳምጥ ትንፋሽ እንኳን
አልነበረም " ስለዚህ ከዚያ ክፍል አለ መኖሯን ገመተ።
“ ሳቤላ ” ብሎ ጠራት ።
መልስ የለም " ጭልል ባለው ሌሊት የገዛ ድምፁ አያስተጋባ ነጥሮ ከመመለስ በቀር ምንም ምላሽ አጣ " ክብሪት ጭሮ ጧፍ አብሮቶ እንደ ነገሩ ለባበሰና ፍለጋ ወጣ " ታማ እንደሆነ ብሎ ሠጋ " ወይንም ደግሞ ከአንዱ ክፍል ተኝታ ይሆኖል
የሚል ሐሳብም መጣበት " ነገር ግን በየክፍሉ ፈልጎ አጣት ግራ ገባው ! የሚያደርገው ጠፋው ቢቸግረው ወደ እኅቱ መኝታ ቤት ሔዶ አንኳኳ ።
ሚስ ካርላይል ከእንቅልፋ ለመንቃት ትንሽ ምክንያት ነበር የሚበቃትና ወዟ
ዲያው ብድግ አለች "
“ ማነው ? "
“ እኔ ነኝ ...ኮርኒሊያ "”
“ አንተ ! ምን ሆንክ ? ግባ እስቲ „”
ሚስተር ካርላይል ከፍቶ ገባ " አንድ ክንድ የሚያህል የሌሊት ቆብ ደፍታ
ንቁ ዐይኖቿን እያቁለለጨች አገኛት "
“የታመመ ሰው አለ ?
" እኔ እንጃ ሳቤላ ታማለች መሰለኝ " ብፈልግ አጣኋት
“ አጣኋት ? እንዴት ?
ከመኝታዋ የለችም ? ስንት ሰዓት ነው ?” እያለች
ጮኸች "
“ አሁን ዘጠኝ ሰዓት" ከነ ጭራሹ ወደ መኝታ ቤት አልገባችም " ከክፍሎቹ
ሁሎም የለችም " ከልጆቹ ቤት ብሔድም አጣኋት "
“ እንግዲያውስ ልንገርህ አርኪባልድ የጆይስ ነገር አሳስቧት ልታያት ሔዳ ነው " ምናልባት አሁን ደግሞ አሟት ይሆናል " "
ሚስተር ካርላይል እንደ ተጠቆመው ወዶ ጆይስ ክፍል ሲንደረደር እህቱ ጠራችው
አርኪባልድ ” ጆይስ የሆነችው ነገር ካለ መጥተህ እንድትነግረኝ እኔም ሔጄ አያታለሁ " ምንም ቢሆን ልጂቱ ሚስትሀ ሳትወስዳት የኔ ገረድ ነበረች
ከጆይስ ክፍል ደረስና መብራት በርቶ ሚስቱ ከአልጋው ጐን ተቀምጋ እንደ ሚያገኛት በመተማመን በሩን ቀስ አድርጎ ከፈተው በጁ ከያዘው ጧፍ በቀር ምንም
መብራት አልበረም » የሚስቱ ምልክትም የለም ከምን ገባች ? ምናልባት ጆይስ ልትነግረው ትችል ይሆን? ቀረብ አለና ቀሰቀሳት....
💫ይቀጥላል💫

👍15🤔2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
...“እናታችንን መዝረፍ አለመቻሌ ሲገባኝ አያትየው ክፍል ሄጄ ለመስረቅ ወሰንኩ” አለኝ።
አምላኬ አይሆንም... ማድረግ አይችልም ግን ደግሞ በጣም ጥሩ በቀል ነው! ስል አሰብኩ። “ታውቂያለሽ… ጌጣጌጦች አሏት: ጣቶቿ ላይ ብዙ ቀለበቶች እና በዚያ ላይ የደንብ ልብሷ አንድ ክፍል እንደሆነ ሁሉ እድሜዋን
በሙሉ የምታደርገው የአልማዝ ጌጥ አላት እንደገናም በገና ግብዣው ላይ አድርጋቸው ያየናት እነዚያ አልማዞችም አሉ። እሷ የሚሰረቅ ብዙ ነገር እንዳላት አውቄያለሁ: በጨለማው መተላለፊያ አቋርጬ በጣቶቼ
እየተራመድኩ የአያትየው የተዘጋ ቢሮ ጋ ደረስኩ።”
ያንን ለማድረግ መድፈሩ እኔ መቼም በፍፁም . . .
“በበሩ ስር የሚታየው ቀጭን ቢጫ የብርሀን መስመር አሁንም እንቅልፍ
እንዳልተኛች እያስጠነቀቀኝ ነበር፡ ምርር አለኝ፡ መተኛት ነበረባት። ሁኔታዎቹ ያ ብርሀን እዛው እንድቆይና አሁን ካደረግኩት የባሰ አጉል ነገር እንዳላደርግ
አደረገኝ ወይም አሁን አንቺ የድርጊት ሰው ከሆንሽ በኋላ አንድ ቀን የቃልሽ ሰው ለመሆን እቅድ ስላለሽ “ድፍረት” ብለሽ ልትጠሪው ትችይ ይሆናል:"
“ክሪስ ከርዕሱ አትሽሽ! ቀጥል! ምን አይነት የእብደት ስራ እንደሰራህ ንገረኝ! አንተን ብሆን ኖሮ ፊቴን አዙሬ ቀጥታ ወደዚህ እመለስ ነበር!”
“እኔ አንቺን አይደለሁማ ካተሪን፣ እኔ እኔ ነኝ... ትንሽ ጥንቃቄ ተጠቅሜ
በቀስታ በሩን በትንሹ ከፈትኩ… በእያንዳንዷ ሰኮንድ ሲከፈት ድምፅ ያሰማል ብዬ ፈርቼ ነበር። ነገር ግን የሆነ ሰው መታጠፊያውን ዘይት አጥግቦታል:: እና እሷ ታየኛለች ብዬ ሳልፈራ በተከፈተው በር ወደ ውስጥ ተመለከትኩና ወደ ውስጥ ገባሁ:"
“እርቃኗን ሆና አየሀት?!” አቋረጥኩት።
“አይ!” ትዕግስት ባጣና በተናደደ አይነት መለሰልኝ፡ “እርቃኗን ሆና አላየኋትም እና በዚያም ደስ ብሎኛል፡ አልጋ ውስጥ ብርድ ልብሱ ስር ነበረች: እጅጌው ረጅም የምሽት ገዋን ለብሳ ተቀምጣ ነበር በትንሹ እርቃኗን ሆና አይቻታለሁ። ታውቂዋለሽ ያ የምንጠላው ብረት የሚመስለው ፀጉሯ
ጭንቅላቷ ላይ አልነበረም ሌሊት ድንገት አስቸኳይ ነገር ቢያጋጥም
አጠገቧ መሆኑን እርግጠኛ ለመሆን የፈለገች ይመስል ቅርብ ኮመዲኖ ላይ
ተቀምጧል"
“ዊግ ነው የምታደርገው?” ብዬ በመገረም ጠየቅኩት ግን ማወቅ ነበረብኝ
“አዎ ዊግ ታደርጋለች የክሪስማስ ግብዣው ዕለት ያደረገችውም ፀጉር ሳይሆን ዊግ ነበር። ጭንቅላቷ ላይ የቀረው ፀጉር የሳሳና ወደ ቢጫ የሚያደላ ነጭ ነው፡ እና ጭንቅላቷ ፀጉር የሌለባቸው ሰፋፊ ሮዝ ቦታዎች አሉት ረጅሙ አፍንጫዋ ጫፍ ላይ ጠርዝ የሌለው መነፅር ሰክታ ትልቅ ጥቁር መፅሀፍ ቅዱስ ታነባለች አሁን ከእሷ መስረቅ እንደማልችል ሳውቅ እየተመለከትኳት
መፅሀፍ ቅዱሱ ውስጥ ያቋረጠችበትን ቦታ በፖስት ካርድ ምልክት አድርጋ ኮመዲኖው ላይ አስቀመጠችና ከአልጋዋ ወርዳ ተንበረከከች ከዚያ አንገቷን አቀርቅራ እኛ እንደምናደርገው እጆቿን አገጯ ስር አደራርባ ረጅም ፀሎት ፀለየች:: ከዚያ ጮክ ብላ “ጌታ ሆይ ስለ ኃጢአቴ ይቅር በለኝ፡ ሁልጊዜ የምሰራው ጥሩ ነው ብዬ የማስበውን ነው እና ስህተቶች ከሰራሁ እባክህ ትክክል ለመስራት አስቤ እንደሆነ እመንልኝ በአንተ አይኖች ለዘለዓለም ፀጋ
ላግኝ አሜን ከተንበረከከችበት ተነስታ አልጋዋ ውስጥ ገባችና መብራቱን አጠፋች አዳራሽ ውስጥ ቆሜ ምን እንደማደርግ አሰብኩ ባዶ እጄን ወዳንቺ ተመልሼ መምጣት አልቻልኩም:: ምክንያቱም አባታችን ለእናታችን የሰጣትን ቀለበቶች እንደማንሽጣቸው ተስፋ አድርጌያለሁ "
ቀጠለ. አሁን እጆቹ ፀጉሬ ላይ ናቸው፡ ጭንቅላቴን እየዳበሱኝ ነው። “ ወደ ዋናው ክፍል ሄድኩና የወንድ አያታችንን ክፍል አገኘሁት፡ በሩን ከፍቼ ያንን እዚያ ተጋድሞ ከአመት አመት ሞቱን የሚጠብቀውን ሰው
የመጋፈጥ ድፍረት እንዳለኝ አላውቅም ነበር።
“ግን ይህ ብቸኛው እድሌ ነው: እጠቀምበታለሁ። የመጣው ይምጣ ብዬ
ልክ እንደ እውነተኛ ሌባ ድምፅ ሳላሰማ በደረጃው ወደ ታች ወረድኩ።ትልልቆቹን ውድ ክፍሎች አየሁ። በጣም ግዙፍና የሚያምሩ ነበሩ ልክ አንቺ እንደምታስቢው እኔም እንደዚህ አይነት ቤት ውስጥ ስለማደግ አሰብኩ
በብዙ ሰራተኞች ተከቦ ሁሉ ነገር በሰው ሲቀርብ ያለውን ስሜት አሰብኩ።
ኦ ካቲ፣ በጣም ቆንጆ ቤት ነው እቃዎቹ ከቤተመንግስት የመጡ መሆን አለባቸው: እናታችን ብዙ ጥያቄዎች ትጠይቂያት ስለነበር ወደ ቤተ መፃህፍት
የሚወስደውን መንገድ አውቄዋለሁ እና ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ ካቲ?
ብዙ ጥያቄዎች በመጠየቅሽ በጣም ደስ ብሎኛል ባይሆን ኖሮ ከመሀሉ ተነስተው ወደ ግራና ወደቀኝ የሚታጠፉ ብዙ አዳራሾች ስለነበሩ ይጠፉብኝ ነበር:
“ግን ወደ ቤተመፃህፍቱ መሄድ በጣም ቀላል ነበር። ረጅም፣ ጨለማማ፣ በጣም ግዙፍ ክፍል ሆኖ ልክ እንደመቃብር ስፍራ ፀጥ ያለ ነው::"
ለመስማት የምናፍቀው የነበረውን ነገር እየነገረኝ ነው: በረጅሙ ተነፈስኩ።
መሳቢያዎቹ ውስጥ ገንዘብ እንደሚደበቅ ገምቻለሁ። ስለዚህ ባትሪዬን እያበራሁ
እያንዳንዱን መሳቢያ መፈተሽ ጀመርኩ አንዳቸውም አልተቆለፉም: እና ሁሉም ባዶ፣ ሙሉ በሙሉ ባዶ በመሆናቸው አለመቆለፋቸው አይገርምም እነዚያ ሁሉ ባዶ መሳቢያዎች፣ የወረቀት መያዣዎች፣ እርሳሶች፣
እስኪሪብቶዎች፣ ማስታወሻ ደብተሮች የመሳሰሉት ነገሮችን ለማስቀመጥ
ካልተጠቀሙባቸው መሳቢያው ለምን ይጠቅማል? ወደ ሀሳቤ የመጡት ጥርጣሬዎች ምን እንደሆነ አታውቂም: የዚያን ጊዜ ነው ከቤተመፃህፍቱ
ባሻገር ያለው የወንድ አያቴ ክፍል ለመግባት የወሰንኩት በመጨረሻ ላገኘው ነው... ከምጠላው አያቴ… እንዲሁም አጎቴ ጋር ፊት ለፊት ልገናኝ ነው:
“ግንኙነታችንን በሀሳቤ ሳልኩት እሱ አልጋ ላይ ነው ታሟል። ግን አሁንም
መብራቱን አበራዋለሁ: ከዚያ ያየኛል ትንፋሽ ያጥረዋል። ይለየኛል... ማን እንደሆንኩ ማወቅ አለበት: አንድ ጊዜ ሲያየኝ ወዲያውኑ ያውቃል፡ ከዚያ
እኔ “አያቴ… እንዲወለድ ያልፈለከው የልጅ ልጅህ እኔ ነኝ. እለዋለሁ:: ፎቁ ላይ በሰሜን በኩል ባለው የመኝታ ክፍል ውስጥ የተቆለፈባቸው ሁለት እህቶች አሉኝ በአንድ ወቅት ታናሽ ወንድምም ነበረኝ፡ አሁን ግን ሟቷል እንዲገድሉት ረድተሀቸዋል” ይሄ ሁሉ አእምሮዬ ውስጥ ነበር።ግን አንዳቸውንም ስለማለቴ ተጠራጥሬያለሁ። አንቺ ብትሆኚ ግን ጮኸሽ እንደምታወጪው ጥርጣሬ የለኝም:: ልክ ኬሪ ራሷን የምትገልፅበት ቃላት
ሲኖራት እንደምታደርው አይነት ማለቴ ነው አንቺ ግን ቃላቶቹ አሉሽ ምናልባት እናገረዋለሁ፣ ሲሸማቀቅ አይቼ እደሰት ይሆናል ወይም ምናልባት ሀዘኔታ ያሳይ ይሆናል ወይም በህይወት በመኖራችን የጋለ ብስጭት ያድርበት ይሆናል፡ ይህንን አውቃለሁ ከአሁን በኋላ ግን ለተጨማሪ አንድ ደቂቃ
እንኳን እስረኛ ሆኜ ኬሪም እንደ ኮሪ ስትሞት ማየትን መቋቋም አልችልም::
ትንፋሼን ዋጥኩ። አሁንም ሞቱን በሚጠብቅበት አልጋ ላይ ተጋድሞ፣ ያ ጠንካራ የመዳብ የሬሳ ሳጥን እስኪገባበት እየጠበቀው ቢሆንም የምንጠላውን

👍50❤2
አያታችንን ለመጋፈጥ ድፍረቱ ገርሞኛል: ቀጥሎ የሚመጣውን ነገር ትንፋሽ አጥሮኝ እየጠበቅኩ ነው:
“ላስገርመው በማቀድ የበሩን እጄታ በጥንቃቄ አዞርኩት በድፍረት እግሬን አንስቼ በሩን በርግጫ ብዬ እከፍተዋለሁ ብዬ አስቤ ስለነበረ ያንን ባለማድረጌ እፍረት ተሰማኝ፡ ውስጡ በጣም ጨለማ ስለነበር አንድም ነገር ማየት
አልቻልኩም: ባትሪዬንም መጠቀም አልፈለግኩም: ማብሪያ ማጥፊያ ፍለጋ ግድግዳውን ብዳስስም አንድም ማግኘት አልቻልኩም: ከዚያ የያዝኩትን ባትሪ
ሳበራ የሆስፒታሉ አልጋ ነጭ እንደተቀባ ተመለከትኩት።
ዝም ብዬ አፈጠጥኩ፡ ምክንያቱም ያየሁት ያልጠበቅኩትን ስለነበረ ነው ፍራሹ ታጥፏል። ባዶ አልጋ፣ ባዶ ክፍል እንጂ እየሞተ ያለ ለመተንፈስ የሚታገል፣ በህይወት ለመቆየት የሚያግዙት ብዙ ማሽኖች የተገጠሙለት
አያት እዚያ የለም ልክ ሆድ ላይ በጣም እንደመመታት ነበር፤ ላገኘው ራሴን ሳዘጋጅ እሱን ግን እዚያ ማየት አልቻልኩም
“ከአልጋው ብዙም ሳይርቅ ጥግ ላይ ከዘራ ተቀምጧል። ከከዘራው አጠገብ ደግሞ ቁጭ ብሎበት ያየነው የሚገፋ ወንበር ተቀምጧል። ብዙ ጊዜ አልተቀመጠበትም መሰለኝ አዲስ ይመስላል። ከሁለቱ ወንበሮች በተጨማሪ አንድ ዕቃ ብቻ ነው ያለው: እሱም ባለመስተዋት ኮመዲኖ ብቻ ነው ግን
ምንም ነገር አልነበረበትም: የፀጉር ቡሩሽ የለ፣ ማበጠሪያ የለ፣ ምንም
የለ ክፍሉ ልክ እናታችን ትታው እንደሄደቸው ክፍል ባዶ ነበር። የወንድ አያትየው ታሞ የተኛበት ክፍል ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ አይመስልም አየሩ የታፈገና እምክ እምክ የሚሸት ነው: ባለመስተዋቱ ኮመዲኖ ላይ አቧራ አለ በኋላ ልንጠቀምበት የምንችለው ዋጋ ያለው ነገር ፍለጋ ተጠግቼ አየሁ። ምንም... እንደገና ምንም የለም። በንዴት ተስፋ መቁረጥ ተሞልቼ ወደ ቤተመፃህፍቱ ተመለከትኩና እናታችን የነገረችንን ግድግዳው ላይ ያለውን ሚስጥራዊ የገንዘብ ካዝና የከለለውን ልዩ የመልክአ ምድር ስዕል መፈለግ ጀመርኩ።
“በቲቪ ሌቦች ካዝናዎችን ሲከፍቱ ስንት ጊዜ እንደተመለከትን ታውቂያለሽ እና በጣም ቀላል ይመስላል። ማድረግ ያለብሽ ጆሮሽን መክፈቻው ላይ አድርገሽ ቀስ ቀስ እያሉ ማዞርና በጥንቃቄ ማዳመጥ ከዚያ ቀጭ... የሚል ድምፅ ሲያሰማ ያንን መቁጠር. አሰብኩት። ከዚያ ቁጥሮቹ ይታወቃሉ። በትክክል መደርደር እና ቀጥሎ ብራቮ! ካዝናው ይከፈታል።"
አቋረጥኩት “ወንድ አያትየው ለምንድነው አልጋው ላይ የሌለው?”
ልክ እንዳልተናገርኩ ሁሉ ዝም ብሎ ቀጠለ “እያዳመጥኩ ቀጭ የሚል
ድምፅ እየሰማሁ ነው። እድለኛ ካልሆንኩ የብረት ካዝናው ሲከፈት ባዶ ሊሆን ይችላል። ምን እንደተፈጠረ ታውቂያለሽ ካቲ? ቁጥሮቹን የሚነግረኝ
ቀጭ የሚል ድምፅ እያዳመጥኩ ነው ግን በፍጥነት መቁጠር አልቻልኩም! የካዝናው መዝጊያ አልተከፈተም… ድምፁን ብሰማም በደንብ አልገባኝም።መፃህፍት እንዴት አሪፍ ሌባ እንደሚኮን ትምህርት አይሰጡም: በተፈጥሮ
የሚመጣ መሆን አለበት ከዚያ በመቆለፊያው በኩል አስገብቼ የምከፍትበት የሆነ ጠፍጣፋና ጠንካራ ነገር መፈለግ ጀመርኩ፡ የዚያን ጊዜ ነው የእግር
ኮቴ የሰማሁት:
”ለእሱ ደነገጥኩ..
“በፍጥነት ወደ አንዱ ሶፋ ጀርባ ሄጄ በሆዴ ተኛሁ ... የዚያን ጊዜ ባትሪዬን የወንድ አያትየው ክፍል ውስጥ መርሳቴን አስታወስኩ”
“አምላኬ!”
“ተጋለጥኩ ስል አስብኩ ግን ሳልንቀሳቀስ ፀጥ ብዬ ተጋደምኩ ከዚያ የሆኑ ወንድና ሴት ወደ ቤተመፃህፍቱ ገቡ፡፡ በመጀመሪያ የተናገረችው ሴቷ ነበረች::ደስ የሚል የሴት ድምፅ አላት
“ጆን” አለች “የሌለ ነገር ሰምቼ አይደለም እምላለሁ፡ ከዚህ ክፍል ውስጥ የመጣ ድምፅ ሰምቻለሁ"
“አንቺ ሁልጊዜ የሌለ ነገር ትሰሚያለሽ” ሲል ወንዱ በከባድ ድምፅ አጉረመረመ::
ከዚያ ሁለቱም በግማሽ ልብ ቤተመፃህፍቱን ማሰስ ጀመሩ ከዚያም ባሻገር ወዳለው የመኝታ ክፍል ገቡ ከአሁን አሁን ባትሪውን አገኙት እያልኩ ትንፋሼን ዋጥ አድርጌ እየጠበቅኩ ነበር፡ ግን በሆነ ምክንያት አላገኙትም::
እንደምጠረጥረው ጆን ሴቷን እንጂ ሌላ ምንም ነገር ለማግኘት አልፈለገም::ከዚያ ተነስቼ ቤተመፃህፍቱን ለቅቄ ልወጣ ስል ተመልሰው መጡና ከጀርባው
የተደበቅኩበት ሶፋ ላይ ወደቁ!
“አየሽ…” አለ ጆን ወደ ቤተመፃህፍቱ መጥተው ሶፋ ላይ ከተቀመጡ በኋላ።“እዚህም ሆነ እዚያ ማንም እንደሌለ ነግሬሽ አልነበር?” በራሱ የተደሰተ ይመስላል፡ “እውነቴን ነው ሁልጊዜ ጭንቀታም ነሽ ያ ደግሞ ደስታችንን ያጠፋብናል” አላት።
“ግን ጆን የሆነ ነገር ሰምቼያለሁ:"
“እንደነገርኩሽ አንቺ ብዙ የሌሉ ነገሮችን ትሰሚያለሽ: የገሀነምን ደውሎች ሳይቀር ትሰሚያለሽ፡ ዛሬ ጠዋት እንኳ ጣራው ስር ስላሉት አይጦች በድጋሚ
እያወራሽ ነበር። እንዴት እንደሚጮኹ ስትናገሪ ነበር:” “ከዚያ ያ ጆን አጉረመረመ:: ያቺ ውሻ አሮጊት ጣራው ስር ያለው ክፍል ያሉትን አይጦች
ሁሉ ገደለቻቸው በሽርሽር ቅርጫት ውስጥ . . . ሁሉንም አይጦች ሊፈጅ የሚችል ምግብ ይዛላቸው ትሄዳለች ”
ክሪስ ጉሮሮውን አፀዳና ቀጠለ። ሆዴ ውስጥ እንግዳ የሆነ ስሜት ተሰማኝና ልቤ ድምፅ ማሰማት ጀመረች: ሶፋው ላይ የነበሩት ጥንዶች በእርግጠኝነት
ይሰሙታል ብዬ አሰብኩ “አዎ እሷ ክፉና ሀይለኛ አሮጊት ናት᎓ እና እውነቱን ለመናገር ሽማግሌው ይሻላል። ቢያንስ ፈገግ ማለት ያውቃል፡ እሷ ግን እንዴት ፈገግ እንደሚባል እንኳ አታውቅም: በየጊዜው እዚህ ክፍል ላፀዳ
ስመጣ ሽማግሌው ክፍል ውስጥ አገኛታለሁ ... ዝም ብላ ትቆምና ባዶው አልጋ ላይ ታፈጣለች ከዚያ እሱ በመሞቱ እሷ ደግሞ ከሱ የበለጠ ረጅም በመኖሯና አሁን ነፃ በመሆኗ እንዲሁም ጀርባዋ ላይ ተቀምጦ ይህንን አድርጊ
ያንን አታድርጊ የሚላት፣ በተናገረ ቁጥር እንድትዘል የሚጠብቅ ሰው ባለመኖሩ የተደሰተች ይመስል የተመጠነ ፈገግታ ከንፈሯ ላይ ይታያል: አምላኬ ሆይ፣ አንዳንዴ እንዴት እንደምትታገሰውና እሱም እንዴት እንደሚታገሳት
ይገርመኛል አሁን ግን ሞቷል ገንዘቡን ታገኛለች ''
“አዎ ጥቂት ገንዘብ ታገኛለች” አለ ጆን: “ግን ቤተሰቦቿ የተውላት የራሷ
ገንዘብ አላት: ሽማግሌው ማልኮም ፎክስወርዝ የተወውን ሚሊዮኖች
የምታገኘው ልጇ ናት።”
“ያቺ ጠንቋይ አሮጊት ተጨማሪ አትፈልግም ያለውን ንብረት በሙሉ ለልጁ ስለሰጠ ሽማግሌውን አትውቀሰው ከእሱ ብዙ ችግሮችን ተቀብላለች: ነርሶች የሆነ ነገር ሲሉት እሷ እዚያው እየጠበቀችው እንድታገለግለው ያደርጋት
ነበር እንደባሪያ ነበር የሚያያት፡ አሁን እሷም ነፃ ናት ያንን ቆንጆ ወጣት አግብታለች። አሁንም ወጣት፣ ቆንጆና ባለሀብት ናት። እሷን መሆን ምን ስሜት ይኖረው ይሆን? አንዳንድ ሰዎች ሁሉም እድል አላቸው: እኔ ግን
. . አንድም ኖሮኝ አያውቅም” አለች ልጅቷ።
“እኔስ ማሬ? እኔን አግኝተሻል። ቢያንስ የምትቀጥለዋ ቆንጆ እስክትመጣ ድረስ አለሁልሽ”
✨ይቀጥላል✨

👍39❤2
✍✍የጠንቀዩ ዋሻ✍✍
♣♣ክፍል 4♣♣
✆✆✆✆✆✆✂✆✆✆✆✆
"አንተ የማትረባ ፈልፈላ አባቴን እንዴት ታስቆጣዋለህ "ብሎ አድማስ መሳይን በጥፊ አጮለው ፡መሳይ ጥፊውን መቋቋም አቅቶት ወደቀ ፡ አቢያራ የለበሰውን ዝርክርክ ልብስ እየጎተተ ና የሚያስጠላ ድምፅ ፡እያወጣ ወደመሳይ ተጠጋ ፡ መሳይ ከወደቀበት ለመነሳት አቅም ስላልነበረው ፡ ባለበት ፍንግል እንዳለ አቢያራ የሚያደርገውን ጠበቀ ፡ አድማስ ፡አቢያራ ከዚ በፊት ፡ በዚመልኩ የሚያናድደው ፡ሰውም ፡ እንዲ ምርር የሚያደርግ ቁጣም ተሰምቶት ስለማያውቅ ፡ፈርቷል ፡ የፈራው ፡ደሞ መሳይ ስለሚሆነው ነገር ሳይሆን ፡ እዛ ዋሻውስጥ ለአቢያራ ተገዝተው ፡የሚኖሩት ፡ ጓደኞቹና እሱ ላይ ፡ የቁጣ በትሩ እንዳያርፍ ፡ነው ፡ በተለይ አድማስ ፡ ለኤልያታ ከሴቶቹ ሁሉ ስለሚሳሳ መጥፎ ነገር ባሰበ ቁጥር ፡የኤልያታ ፡ ጉዳት ያሳስበዋል ፡ እሱ በግልፅ ፡አይናገረው ፡እንጂ ኤልያታን ፡በፍቅር ማየት ከጀመረ ቆይቷል ፡ ሁሉንም ፡ሴቶች ፡ ከእፃንነታቸው ፡ጀምሮ ፡ያውቃቸዋል ፡ አንዲት ፡ገጠር ፡ውስጥ ፡የሚያውቃቸው ፡ አዋቂነኝ ፡ባይ ፡ሰው ፡ ስላልተሳካለት ሕይወት ፡አምርሮ ፡ሲነግራቸው ፡ህይወትህን ፡የሚቀይርልህ ፡ አንድ ፡ አባት ፡አውቃለው ፡ነገር ግን ፡አንተ ፍፁም ታማኝና ፡ሚስጢር ጠባቂ የሆንክ ፡እንደሆን ነው ፡ብለው ፡ አስጠንቅቀው ፡ ካሳሰቡት በዋላ ፡ እሱ ፍፁም ፡መስማማቱን ፡ሲነግራቸው ፡ከብዙ መፈተን በዋላ ፡ፈተናውን ፡አልፏል ብለው ፡ሲያስቡ ፡ ነው ፡ወደዚ ዋሻ ፡ ይዘውት የመጡት ፡ በዚያን ፡ጊዜ ፡ጠንቋዩ አቢያራ እንዲ አላረጀም ነበር ፡ ከየት እንዳመጣቸው ፡እራሱ ብቻ የሚያውቃቸው ፡ አራት ዕፃናት ሴት ልጆች ነበሩት ፡ አድማስ ፡ የዕፃናቱ ቀያይ ፊት እና ባለ ሉጫ ፀጉር መሆን ፡ ኢትዮጲያዊነታቸውን እንዲጠራጠር አርጎት ነበር ፡ ነገርግን አማርኛ አቀላጥፈው መናገራቸው ፡ደሞ ግራ አጋባው ፡ ቢሀንም ግን ፡ ወደ ዋሻው ፡የመሩት ሰው ፡ ስላስጠነቀቁት ምንም አይነት ጥያቄ ፡ ከመጠየቅ ተቆጠበ ፡ ይኽው እስከ ዛሬም ድረስ ፡ ስለነዚ ሴቶች ፡ ከየት መጡ የሚል ጥያቄ ሳያነሳ እነሱም ዕድሜ አቸው ጨምሮ ፡ ትላልቅና ማራኪ ለመሆን በቅተዋል ፡ሕይወታቸው ፡ደሞ ፡ ዋሻውና አቢያራ ብቻ ናቸው ፡ ዋሻውን ፡አልፈው ፡መሄድ በጭራሽ ፡አይፈቀድላቸውም ፡ እነሱም ፡ አቢያራን ፡እንደ ፈጣሪያቸው ፡ነው ፡የሚቆጥሩት ፡ ከቃሉ ቢወጡ በቁማቸው የሚፈራርሱ ይመስላቸዋል ፡ ስለዚ ዓለም ፡ ምን ትመሰል ምን የሚያውቁት ነገር የላቸውም ፡ አቢያራ ከዚ በፊት ፡ ከአድማስ ፡ቀድሞ ፡ለሱ ይታዘዝ የነበረውን ፡ሰው ፡ አድማስንም ፡ ስለዋሻው ፡አንድ በአንድ ፡እያስጎበኘ ፡ ሲያላምደውና ፡አቢያራ የሚወደውን ፡የሚጠላውን ፡ያስተምረው ፡የነበረውን ፡አገልጋይ ፡ ከረጅም ፡ጊዜ ፡በዋላ ፡ በኤዛ ፡ፍቅር ድንገት በመውደቁ ፡ አቢያራ ፡ሲያውቅ ፡ያለ አንዳች እርህራሄ ፡ አይኑ እያየ መርዝ ፡አጠጥቶ ነበር ፡የገደለው ፡ አድማስ ፡የዛኔ ፡ለኤሊያታ የነበረው ፡ፍቅር ፡ ቀቢፀተስፋ እንደሆነና ፡ሕይወቱን እንደሚያሳጣው ፡ስላወቀ ፡ ሁሌም ፡ ፍቅሩ እንዳይገነፍል ይቆጣጠረዋል ፡ ግን ፡ሁሌም ፡ይገርመዋል ፡እነዚ ሴቶች ፡አቢያራ ፡እንዳልወለዳቸው ፡ያስታውቃል ፡ ግን ከየት አመጣቸው ፡ ከግብፅ ,,ከህንድ,,,ከየመን ,,,,,,,,, ከየት ? አይታወቅም ,,,,,,,,,,,,,
,,,,,,,,,,,,,,,,,መሳይ በተገለጠው የአቢያራ ረጅም ቀሚስ ፡ውስጥ እረጃጅም ጥፍሮች ያለሉት እግር ተመለከተ ዘገነነው ፡አቢያራ በሰአን የያዘውን ፡ ፈሳሽ ፡የመሳይ አናት ላይ ፡ደፋፋው ፡ መሳይ ያቀይ ፡ፈሳሽ ፡ፊቱን ሲያዳርስው ፡ በጥይት ተመቶ በደም የተጨማለቀ ፡ነው ፡የሚመስለው ፡ በሁኔታው ፡ይበልጥ ፡በመረበሹ እዛው ፡እንዳለ ተንቀጠቀጠ ፡ አድማስ ፡የመሳይን ሁኔታ ሲያይ ፡ የአቢያራ መንፈስ ፡ነው እንዲ የሚያደርገው ፡ብሎ በማሰብ ፡ተንበርክክ ፡ለአቢያራ ሰገደ ፡ መሳይ ቴንሽን ስለሆነ ብቻ ፡ ገደኞቹም ፡ አቢያራ ልዩ እንደሆነ ፡ አሰቡ ፡እናም በጓደኛቸው ፡ሁኔታ ተረብሸው ፡ አለቀሱ ,,,,,,,,,
✍ ሙና መሀመድ
ይቀጥላል.....

👍24🤔4❤2😁2
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...ከጆይስ ክፍል ደረስና መብራት በርቶ ሚስቱ ከአልጋው ጐን ተቀምጋ እንደ ሚያገኛት በመተማመን በሩን ቀስ አድርጎ ከፈተው በጁ ከያዘው ጧፍ በቀር ምንም
መብራት አልበረም » የሚስቱ ምልክትም የለም ከምን ገባች ? ምናልባት ጆይስ ልትነግረው ትችል ይሆን? ቀረብ አለና ቀሰቀሳት
ጆይስ ዶንግጣ ብድግ አለች " ጌታዋ መሆኑን ስታውቅ ድንጋጤዋ ወደ መገረም
ተለወጠ ሳቤላ ወደሷ መጥታ እንደሆነ ጠየቃት
ጆይስ መልስ አልሰጠችውም " ለካ ሲቀሰቅሳት ስለ ሳቤላ ሕልም ስታይ ኖራለች አሁን የሱ መምጣትና መጠየቅ ከህልሟ መለየት ተስኗት ግራ ገብቷት ዝም አለች።
“ ምን አሉ ጌቶች ? እሜቴን አመማቸው ?
“ ከዚህ መጥታ እንደሆነ እኮ ነው የምጠይቅሽ ? ላገኛት አልቻልኩም "
“ እንዴ አዎ ከዚህ መጡና ቀሰቀሱኝ ልክ ስድስት ሰዓት ሲደወል " ግን ወዲያው ወጥተው ሔዱ ”
“ ቀሰቀሰችኝ ? ምን አርጋ ? ምን ልትል ከዚህ መጣች?” አላት "
ጆይስ አሳብ ያዛት ያሳብ ሥዕል ተደቀነባት የእመቤቷ የብሶት ቃሎች በአእምሮዋ ጥርቅምቅም አሉ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት እስኪሆን ወደ መኝታዋም አልገባችም ከቤት ውስጥም ተፈልጋ አልተገኘችም ! ይህ ነው የማይባል ታላቅ ይህ ነው የማይባል ታላቅ ድንጋጤ ያዛት " ዐይኖቿ ግልብጥ ብለው የወጡ እስኪመስሉ ድረስ አፈጠጠች የታመመው እግሯንና ካጠገቧ ቁሞ የነበረውን ጌታዋን ረስታ አንድ ሙቀት ያለው ለስላሳ ቀሚስ ከወንበር ላይ አፈፍ አድርጋ አንሥታ አጠለቀች ከአልጋዋ ዘላ ወረደች አሰቃቂ ፍርሃት መጣባት ሌሎች ጥቃቅን ይሉኝታዎችና ሐሳቦች እልም ብለው ጠፉ
ሞቃቱን ልብስ በአንድ እጅዋ ከሰውነቷ አጣብቃ ይዛ በሁላተኛው እጅዋ ከሚስተር ካርላይል ክንድ ላይ ጣል አደረገችው "
“ ጌቶች ጌቶች .... እሜቴ ራሳቸውን ገድለዋል ! አሁን ነገሩ ገባኝ ”
ጆይስ ! አለና አቋረጣት ።
ምንም አይጠራጠሩ ጌታዬ እሜቴ ራሳቸውን ገድለዋል በፊት ሲናገሩ አልገባኝም ነበር እንጂ! አሁንማ አነጋገራቸውን ሁሉ በደንብ ተረዳሁት " እዚህ
ድረስ መጥተው እሳቸው በማይኖሩበት ጊዜ ከልጆቻቸው እንዳልለይ ቃል እንድግባላቸው ጠየቁኝ " እኔ ደግሞ ነገሩ አልገባኝም ነበር " ታመው እንዶሆነ ብጠይቃቸው አዎን አሞኛል መሮኛል አሉኝ » ጌታዬ ከዚህ አሰቃቂ መከራስ እሱ ራሱ ይሰውርዎ …”
ሚስተር ካርላይል ግራ ገባው " የጆይስ ጤንነት አጠራጠረው " ምክንያቱም
የተናገረችው ነገር በጭራሽ የማይታመን ሆነበት "
“ ነገሩ የማይታመን ቢመስልዎትም ይኸው ነው ... ጌታዬ ?” አለችው
ጆይስ እጆቿን አያፍተለተለች እሜቴ ያለ መጠን ምርር ብለው ያዝኑ ነበር "በዚህ ምክንያት ራሳቸውን ኀድለዋል ማለት ነው”
ጆይስ ዐብደሻል ወይስ በጤናሽ ነሽ ? እንደዚህ ስትይ ምን ማለትሽ ነው።
ጆይስ መልስ ከመስጠቷ በፊት •ሚስ ካርላይል ጥቁር የግር ሹራብ አጥልቃ ያንገት ልብስ ደርባ ረጂም የሌት ቆብ ደፍታ ብቅ አለች " የጆይስ መኝታ ቤት ከሷ
መኝታ ክፍል በላይ ስለነበር ድምፅ ሰማችና የሚባለው ነግር እዳያመልጣት ነበር ቶሎ ብላ የደረሰች "
እንዴት ነው ነግሩ ! አመቤት ሳቤላ ተግኘች ?
« አልተግኙም እሳቸው እንግዲህ በአንሶላቸው ተጠቅልለው ካልሆነ በቀር
አይግኙም ” አለች ጆይስ " የነበራት ትሕትናና ሥነሥርት ከግለቷ የተነሣ ጠፍቷል።
"እማቴ...እርሶም እንኳን መጡ ከፊትዎ ለመናገር እፈልጋለሁ አሁን እመቤቲቱ ሙተው ሬሳቸው ከፊታችን ቢጋደም ምን ይጠቀማሉ ጌቶች ለሚስታቸው የሚገባቸውን አድርገዋል " እርስዎ ግን መድረሻ አሳጡዋቸው " የቁም ስቃይ አሳዮቸው።
“ ምን ትዘበዝባለች ! ” አለች ሚስ ካርላይል በቁጣ “የት ነው ያለችው?
“ ሔዶዋል ማጥፋት የማይገባቸውንም ሕይወት ለማጥፋት ተገደዋል” አለች
ጆይስ እየተንሰቀሰቀች።
“ ኢስት ሊን ከገቡ ጀምሮ በገዛ ቤታቸው የሠራተኛቹን ያህል እንኳን ነፃነት አልነበራቸውም ማዘዝ የፈለጉትን መፈጸም አይችሉም " ሲናግሩ እርስዎ አፍ አፋቸውን እያሉዋቸው አንድ ነገር ሲይዙ ጣልቃ ግብተው እየከለከሉዋቸው በእርስዎ ፍላጎትና ትእዛዝ ሥር አድረው ራሳቸውን እንደ ባርያ ቆጥረው የእርስዎን ጠባይና ጭቆና በትዕግሥት ችለው ኑረዋል እኛ ሁላችን እንወዳቸውና እናከብራቸው ነበር " በደላቸውም ይሰማን ነበር " ጌቶችም ካመት እስካመት ምን ያህል በደልና ግፍ ተሸክመው እንደኖሩ ትንሽ እንኳን ቢጠረጠሩ ኖሮ ልባቸው በኀዘን ብዛት ይደማ ነበር ።”
የሚስ ካርላይል ምላስ ከትናጋዋ ተጣበቀ "
“ ምንድነው የምትይው ጆይስ ? ነገሩ አልገባኝም ” አለ ሚስተር ካርሳይል
“ እኔ ብዙ ጊዜ ልነግርዎ እየፈለግሁ እስካሁን ኖርኩ አሁን ደግሞ ፍጻሜው
ይህ ከሆነ ሊሰሙት የሚገባ ነው " እመቤቴ ሳቤላ ሚስትዎ ሆነው እዚህ ከገቡበት ቀን ጀምሮ በኢስት ሊንና በእርስዎ ስላስከተሉት ተጨማሪ ወጭ ሲነዘነዙበትና ሲወቀሱበት ነው የኖሩ " ትንሽ ነግር ቢፈልጉ ባልሽን ከድህነት ለመጣል ነው ተብለው ይከለhሉ ነበር። ዛሬ ለነበረው ጥሪ አዲስ ቀሚስ አዘዙ " እርስዎ እኔ ነኝ የማዝ ብለው ከለከሉ ባልሽ እንደ ውሻ እየሠራ አንቺ እንደ ፈለግሽ እያጠፋሽ አከሰርሽው እያሉ ይጨቀጭቁዋቸው ነበር " ገንዘብ አባካኝና ቅንጦት
ፈላጊ እንዳልሆኑ ግን ልብዎ ያውቅ ነበር ከእርስዎ
ጭቅጭቅ ሸሽተው
መኖር ከዐቅም በላይ አንደ ከበዳቸው ደረታቸውን በሁለት እጃቸው ደግፈው ሲያለቅሱ በዐይኔ አይቻቸዋለሁ የጨዋ ልጅ
ትዕግሥተኛ ወይዘሮ ቢሆኑም የኑሮ ፈተናው
ከሚታሡት በላይ ስለሆነባቸው ይህንን አሳዛኝ የተስፋ መቁረጥ ድርጊት ለመፈጸም ተገደዱ
ጠፋት "
“ እውነት ነው ? አለ ሚስተር ካርላይል ወደ እኅቱ ምልስ ብሎ "
ምንም አልመለስችለትም ኮርኒሊያ በሕይወቷ ያን ለት ብቻ የምትናገረው ጠፋት።
“ ይቅር ይበልሽ ኮርኒሊያ ! አላትና ወጥቶ ወደ ክፍሉ ወረደ “ ሚስቱ ሕይወቷን ታጠፋለች የሚለውን ነገር የሚስተር ካርላይል ሊና አልተቀበለውም
ምናልባትም ከመመረርዋ የተነሣ ከምድረ ግቢው አንዱ ላይ ተጠግታ
ይሆናል የሚል ሐሳብ መጣበት ቤተሰቡ በሙሉ ተነሣ ሚሰተር ካርላይል ምድረ ግቢውን ለማሰስ በጅምር የተወውን መልበስ ሲያጠናቅቅ ጆይስ ከሳቤላ መልበሻ ክፍል ገባች ከዚያ አንድ ወረቀት ይዛ ጠንቀስ እያለች ወደ ሚስተር ካርላይል ዘንድ ገብታ “
ይህ ከእመቤት መልበሻ ክፍል ከመስተዋቱ ኪስ አገኘሁት ጽፈቴ የሳቸው ነው
አለችው።
ተቀበለና አድራሻውን ሲመለከተው ለአርኪባልድ ካርላይል የሚል ነበር "
ያ በቀላሉ የማይርበተበተው መንፈሱ የተደላደለ የስሜቱን መገንፈል መቈጣጠር ይችል የነበረው ልበ ሙሉ ሰውዬ የፖስታውን እሽጋት ሲከፍት ጣቶቹ ተንቀጠቀጡ "
“ ከዘመናት በኋላ ልጆቹ እናታቸው የት እንዳለችና ለምንስ ጥላቸው እንደሄደች
ቢጠይቁህ አንተው የገዛ አባታቸው ገፋፍተህ እንዳባረርካት ንገራቸው ምንነቷን ቢጠይቁህ
ፈቃድህ ቢሆን ንግራቸው " ግን አንተን አበሳጭተህ አስመርረህ አሰቃይተህ ተስፋ አስቆርጠህ ይህን አማራጭ የሌለውን የመጨረሻ ድርጊት እንድትፈጽም እንዳደረግሃትም ሳትረሳ ንገራቸው ”

👍16
የሚስቱ የእጅ ጽሕፈት በሚስተር ካርላይል ዐይኖች ፊት ተንሳፈፈበት። ከአሳፋሪው የኩብለላ ድርጊቷ በቀር ድርጊቱንም ከማን ጋር እንደ ፈጸመችው
አንድ የሚዘገንን ጥርጣሬ ይሰማው ጀመር ። ... ደብዳቤው ግልጽ አልነበረም ምን እንደ ተበደለች በጭራሽ አልጠቀሰም ። መላልሶ በዝግታ ቢያነበው የምስጢ
ሩን ፍንጭ አላገኘበትም ።
በዚህ ጊዜ የቤት ሠራተኞች ሁሉ ተነሥተው በየበሩ ያጨልቁና ይወያዩም ስለ
ነበር' ካፒቴን ሌቪሰን ከመኝታ ቤት እንዳልነበር እንዲያውም አልጋውም ተነጥፎ እንደ ዋለና እንዳልተተኛበት ሲነጋገሩ ከሚስተር ካርላይል ጆሮ ጥልቅ አለ "
ጆይስ መቆም አልቻለችም » ከአንድ ወንበር ጠርዝ ቁጭ ብላ የጌታዋን ሁኔታ
ትመለከት ጀመር " ምስጢሩ አልገባትም " ሚስተር ካርላይል የዘረጋውን ወረቀት እንደ ያዘ ወደ መዝጊያው ሔደ። እያመነታ ቀጥ ብሎ ቆመ ቀጠለና የኪስ ደብተሩን አወጣ " ወረቀቱን ከውስጡ አኖረና ወደ ኪሱ መላሰው " ይህ ሁሉ ሲሆን እጆቹም
ከንፈሮቹም ይንቀጠቀጡ ነበር ።
“ ስለዚህ ነገር ለማንም መናገር አያስፈልግሽም “ አላት ወደ ደብዳቤው እያ
መለከተ እኔን ብቻ ነው የሚመለከት ”
“ ጌታዬ" ሞቱ ነው የሚለው ?
አልሞተችም " ግን ከሞት ይብሳል ”
ምንድነው ? ማነው እሱ ? አለች ጆይስ "
የቤቱ ሰው ሁሉ ተነሥቶ ሲተራመስ ደንግጣ የተነሣችው ትንሿ ሳቤላ'ነጭ የሌሊት ልብሷን እንደ ለበሰች እነሱ ከነበሩበት ክፍል ደረሰች "
ምንድነው ነገሩ ? እማማስ የት ናት ? ”
ልጄ ብርድ ይመታሽና ትታመሚያለሽ" ሒጅና ካልጋሽ ግቢ አለቻት ጆይስ
“ እኔ እማማን እፈልጋታለሁ
ነገ ጥዋት የኔ ዓለም ” አለችና ወዘፍ አድርጋ“ ጌቶች ... ይች ልጅ ብትተኛ አይሻልም።
ሚስተር ካርላይል መልስ አልሰጣትም " ምናልባትም አልሰማትም ይሆኖል”
የሳቤላን ትከሻ ነካ አድርጎ ወደ ጆይስ እየተመለከተ'' ጆይስ ....ወደፊት ሚስ ሉሲ ብሏት ወጥቶ ሄደ ጆይስ ገርሟት ተቀምጣ ቀረች ትንሿ ሳቤላን ከእንግዲህ ሉሲ ብለን መጥራት አለብን ሔደችና ከመኝታ ቤቷ በር ቆመች ሠራተኞቹ ተስበስበው ያወራሉ " ሉሲ አጠገባቸው መኖሯን ልብ አላሏትም " ተሰብስበው የሚሉትን ከሰማች በኋላ ወደ ጆይስ እየሮጠች መጣች "
“ ጆይስ ! እውነት ነው ?
“ ምኑ ነው .. . የኔ ልጅ ?”
“ ካፒቴን ሌቪሰን እማማን ይዟት ሔዶ እያሉ ያወራሉ ”
ጆይስ ከወንበሯ እንዳለች ጮኸችና የኋሊት ድግፍ አለች "
"ለምን ወሰዳት ? ሊገድላት ነው ?
“ ልጄ ! ወደ መኝታሽ ሒጂ
“ኧረ ተይ ጆይስ ንገሪኝ ... አማማን እኮ ፈልጌ ነው " መቸ ትመለሳለች ?
ጆይስ በጣም ተጨነቀች » ጭንቀቷን ከልጂቱ ለመደበቅ ፊቷን በሁለት
እጆቿ ሸፈነች "
ወዲያው ሚስ ካርይል ቀስ ብላ መጥታ አንድ አጭር ወንበር ላይተቀመጠች
ፊቷ በኀዘን በጸጸት በድንጋጤ ልክ እንደ ጥቁር የግር ሹራቧ ከስል መሰላአለች » ቁና ተነፈሰች
“..... ለዚህ ውርደት ለደረሰበት ቤት ምሕረትህን ...!”
ሚስተር ጆስቲስ ሔር በጨዋታ አሸንፎ ትንሽ ገንዘብ በማግኘቱ ከጓዶኛው ቤት የቀረበላቸው መጠጥም ከመቸም በበለጠ ስለ ተስማማው ደስ ብሎት ነበር ያመሸው » ከሌሊቱ በስድስትና በሰባት ሰዓት መካከል እተውረገረገና እየተጀነነ ከቤቱ ደረሰ ከመኝታ ቤቱ እንደገባ አንድ በአራት ፈረሶች የሚሳብ ሠረገላ ከወደ ኢስትሊን እየበረረ መጥቶ በነሱ በር ዐልፎ ሲሔድ ማየቱን ለሚስዝ ሔር ነገራት "
በዚያ ውድቅት ሌሊት ላይ ማንን ይዞ ወዴት እየሔደ ይሆን ብሎ አሰበ "
አንድ ዓመት ያህል ዐለፈ "
እመቤት ሳበላ ካርላይል አንዳንድ ጊዜ ከወዳጅዋ ጋር ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ብቻዋን አንድ ቦታ ላይ በመቀመጥ ዓመቱን የብጤዎቿ ኮብላዮች መጠጊያ በሆነው በባሕር ማዶ አሳለፈችው ፍራንሲዝ ሌቪሰን ግማሹን ጊዜ ብቻዋን እየጣላት ሌላ እየያዘ በተለይ ወደ ፓሪስ እየሔደ የግሉን ፍላጎትና ደስታ ያሳድድ ጀመር "
እመቤት ሳቤላ ይህ ነው የማይባል ውርዶት ደረሰባት ከዚያ ቤቷን ጥላ ከኮበለለችበት ሌሊት ጀምራ የመንፈስ ጸጥታ ሰላምና ደስታ የሚባል አታውቅም "
በቅጽበታዊ ስሜት ተገፋፍታ በጭፍን ከዘለለች በኋላ ዐይኖቿን ገለጠች አሳሳቹ
ሰው ከነገራት ከጽጌረዳ አታክልት ውስጥ አለማረፋን መወጣጫ መቈናጠጫ
ከሌለበት አመልጣለሁ ተብሎ ከማይታሰብበት እልም ያለ አዘቅት ውስጥ መውረዷን አወቀችው ከኢስትሊን ከተነሣች አንድ ስዓት ሳይሞላት ከዕብደቷ ሰመመን ነቃች በሌቪሰን የተስፋ ስብከት ተሸፍኖ አልታያት ብሎ የነበረው ስሕተቷ አሁን እውነተኛና አሳፈሪ መልኩ ቁልጭ ብሎ ታያት ። ነፍሷ ዘለዓለም አዲስ በሆነ ጸጸት መታገሻ መብረጃ ማብቂያ በሌለው ጭንቀት ተወጠረች የተከበረች እመቤት ሚስት እናት የሆነች ትዳሯን ጥላ እንድትኮበልል መንፈሷ ቢፈታተናት ትንሽ ቆይታ ትነቃለች ስለዚህ በትዳር ኑሮዋ የፈለገውን ያህል ፈተናዎች ቢደቀኑባትም ሠቀቀን ባደቀቀው መንፈሷ ጐልተውና ጐልብተው ቢታይዋትና ቢገፋፋትም የሴት ልጅ ትዕግሥት የማይችላቸው ሆነው ቢከብዷትም ወደ ስሕተት የሚገፋፋትን የሐሳብ ጋኔል የሚያሸንፍ ጉልበት ትዕግሥት ለማግኘት ተንበርክካ መጸለይ ይገባታል መልካም ስሟን ንጹሕ ክብሯንና ንጹሕ ሕሊናዋን ከምታጣ እስከሞት ድረስ ብትታገሥ ይሻላታል ቸኩላ አንድ ጊዜ ከገባችበት ውጤቱ ከሞት ይከፋልና ምስኪን ሳቤላ ከዚያ ክፉ ሰው ከፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር ለመጥፋት ስትል ለሴት ልጅ ዐይነተኛ የሕይወት ትርጓሜ የሆኑትን ባሏን ልጆቿን ስሟንና ቤቷን
አጣች " የሠራችው ሥራ ገደቡን ካለፈ ከማይታረምበት ደረጃ ከደረሰ በኋላ ስሕተቷን ተረዳች ከቤቷ ወጥታ ከሔዶችበት ቀን አንሥቶ እንደ እባብ ንድፍት ጠቅ እያደረገ ያሠቃያት ጀመር " ከዚህ ሰውዬ ጋር አብራ ብትኖርም መቆሚያ በሌለው ጸጸት እየታኘከች በቁጪት እየተንገገበች እንደምትኖር አወቀችው።
አንድ ቀን ጧት ሐምሌ ወር ውስጥ ሳቤላ ወደ ቁርስ ቤት ብቅ አለች" በዚያን
ጊዜ ዓመት ሊሞላቸው ስድስት ወይም ሳምንት ብቻ ቀርቷቸው ነበር አሁን መቀመጫቸውን ግረኖብል ላይ አድርገዋል
ከስዊዝ ዘርላድ ተነስተው
በሳቦይ በኩል ሲያልፍ ግረኖብል ደረሱና ካፒቴን ሌቪሰን ከዚያ መስፈር እንዳለባቸው ወሰነ ግሪነት ከሚባለው አደባባይ አጠገብ አንድ አፓርተማ ከነዕቃው ተከራየ መዝጊያዎች መስኮቶች ጢስ መውጫዎችና ቁም ሳጥኖች በብዛት ያሉበት
ንፋሳም ቤት ነበር” ሳቤላ የኢንግላንድ ወሬ ቶሎ ቶሎ ለማግኘት ወደ ሚችሉበት ከተማ ሄደው መቀመጥ እንዳለባቸው ልትከራከረው ልታሳምነው ሞከረች
የሱ አንጂ የሷ ሐሳብና ፍላጎት ወሳኝነት አልነበረውም መልኳ ተለዋውጧል ዱሮ የሚያቃት አሁን ቢያያት
ጥላዋን እንጂ እሷን አየሁ አይልም ከሚስተር ካርላይል ጋር ወደ ባሕር ዳርቻ የሔዴፈደች ጊዜ የተመለከታትና በሽተኛ መስላ የታየችው ሰው አሁን ቢያያት ጉድ ብሎ አያበቃም። ፊቷን ከበሽታ የከፋ ኑሮ ብልሽትሽት አድርጎታል ንጣትና ግርጣት ወርሷታል እጆቿ ምንምን ብለው አልቀዋል » ዐይኖቿ ወደ ውስጥ ሠርገው በጥቁር ክበብ ተከበዋል
ያላወቀ ሰው እነዚህ ሁሉ የጤና ማጣት ምልክቶች ሊመስሉት ይችላሉ እሷ ግን በሀሳብ ብዛትና በኑሮ ምሬት መሆኑን ከማንም የተሻለ ታውቀዋለች።
አሷ ወደ ቁርስ ቤት ስትግባ የቁርስ ሰዓት ዐልፎ ነበር እሷ ግን ቀኑም እንደ
ማይመሽላት ስለምታወቅ ማለዳ መነሣቱን ጠልታዋለች እየቀፈፋት ሳትወድ እንደ ምንም ተስባ ተነሳችና ከምግብ ጠረጴዛ ወንበር ላይ እንዶ ተቀመጠች ካፒቴን ሌቪሰን ፓሪስ ሳለ የቀጠረው አንድ አሽከር ሁለት ደብዳቤዎች ይዞ ገባ።

👍18😁2
“ ጋዜጣ የለም ፒየር ? አለችው በፈረንሳይኛ "
“ ኧረ የለም እመቤቴ” አላት
ሠራተኛው ግን ጌታው ካፒቴን ሌቪሰን እሱ አስቀድሞ አይቶ ሳይፈቅድ ለወይዘሮ ሳቤላ አንድም ጋዜጣ እንዳያቀርብላት የሰጠውን ትእዛዝ ለማክበር ብሎ እንጂ የታይምስ ጋዜጣ በኪሱ ይዞ ነበር ፒየር ጋዜጣ እንዴሌለ ነግሯት ወደ ካፒቴን
ሌቪሰን ክፍል ሲገባ ሳቤላ ደብዳቤዎቹን አንሥታ በፖስታዎቹ ላይ የነበረውን
ጽሑፍ በጉጉት ተመለከተችው
ሚስተር ካርላይል ሕጋዊ ፍች እንዲፈቀድለት ማመልከቱ እንደማይቀርና የውሳኔው ማስታወቂያም በጋዜጣ እንደሚወጣ ስለምታውቅ አሽከሩ ፖስታ ይዞ በመጣ ቁጥር ፒየር ጋዜጣ የለም? እያለች በየጊዜው ትጠይቀዋለች » የፍቹ መጽደቅ ትፈልግበት የነበረው ምክንያት አንድ ጊዜ የተደላደለ ትዳሯን ጥላ ካፒቴን ሌቪሰንን ተከትላ በመኮብለል ለፈጸመችው አሳፋሪ ድርጊት ከሱ የምትጠብ አንድ ካሣ ብቻ አላት » ይኸውም ከካርላይል ጋር መፋታቷ ከተረጋገጠ በሆዷ
የያዘችው ጽንስ ከሕግ ውጭ የተወለደ ዲቃላ እንዳይባልባት ከፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር በሥርዓት ለመጋባት ነው " ይህ ራሷን የሠዋችለት ሰው የማይረባ መሆኑን አውቃዋለች » ነገር ግን ክፋቱን በሙሉ ገና አላወቀችም ከሱ የምትጠብቀውን
ካሳ ሊፈጽምላት እንደማይፈልግ አልጠጠረችም ።
ካፒቴን ሌቪሰን ሳይታጠብና ጢሙን ሳይላጭ ሌላው ቀርቶ የፒጃማ ካፖርቱን
እንኳን በወጉ አድርጎ ሳይሰበስበው እንደ ተንዘራፈፈ ወደ ቁርስ ቤት ገብቶ ዘፍ ብሎ ተቀመጠ " እነዚህ የደጅ ተሽቀርቃሪዎች አብዛኛዎቹ በቤት ውስጥ እልም ያሉ ዝርክርኮች ናቸው ሁለቱም የደንታ የለሽነት ሰላምታ ተለዋወጡ "
“ፒየር ደብዳቤዎች አሉ ይላል ” ብሎ ጀመረ “ “ አቤት ... ዛሬ እንዴት ደስ
የሚል ሞቃት ቀን ነው ! ”
“ ሁለት” አለችው ባጭሩ እሷም እንደሱ በኩርፊያ" ምን ጊዜም ይህን የመሰሉ የፍቅር ግንኙነቶች ሲጀመሩ የሚነገሩት የጋለ ፍቅር መግለጫ አባባሎች
እንደማር የሚጣፍጠው መወዳደስ መመኳሸትና መቃበጥ ዐሥር ወር አንኳን
ይቆያሉ ብሎ ማሰብ ትልቅ ስሕተት ይሆናል " ብዙ ሳይቆይ ማሩ ወደ እፊት
ጣዕሙ ወዶ ምሬት ይለወጣል "....

👍13👎1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሁለት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
...“እኔስ ማሬ? እኔን አግኝተሻል። ቢያንስ የምትቀጥለዋ ቆንጆ እስክትመጣ ድረስ አለሁልሽ”
“እና እኔ ከሶፋው ጀርባ ሆኜ ይህንን ስሰማ በድንጋጤ ፈዘዝኩ። ሊያስመልሰኝ የተዘጋጀሁ መሰለኝ ግን ፀጥ ብዬ ተጋድሜ ጥንዶቹ ሶፋ ላይ ሆነው ሲያወሩ እያዳመጥኩ ነበር። ብድግ ብዬ በፍጥነት ወዳንቺና ወደኬሪ ሮጬ መምጣትና
ከመዘግየቱ በፊት ከዚህ ላስወጣችሁ ፈለግኩ።
“ግን ተይዣለሁ ብንቀሳቀስ ያዩኛል። በዛ ላይ ጆን ከሴት አያትየው ጋር
ዝምድና አለው፡ ጆን የአያትየው መተማመኛ ሳይሆን አይቀርም አለበለዚያ መኪናዎቿን እንዲጠቀም ያን ያህል ነፃነት አትሰጠውም ነበር። ካቲ፣
አይተሽው ታውቂያለሽ እኮ… የክሪስማስ ግብዣው ቀን የአገልጋዮች ልብስ ለብሶ የነበረው ?መላጣ ሰውዬ ነው” ማንን ማለቱ እንደሆነ አውቄያለሁ ግን የራሴ የመደንገጥ ድንዛዜ ተሰምቶኝ መናገር ስላቃተኝ፣ ማድረግ የቻልኩት ዝም ብዬ መጋደም ብቻ ነበር።
ክሪስ ቀጠለ። “ሶፋው ጀርባ እንደተደበቅኩ ጆንና ሰራተኛዋ መላፋት ጀመሩ። ልብሶቿን ማውለቅ ሲጀምርና እሷም የእሱን ልታወልቅ ስትጀምር እንቅስቃሴዎቻቸው ይሰማኛል።" “አንዳቸው የሌላኛቸውን ልብስ አወለቁ?” ስል ጠየቅኩት። “ልብሱን እንዲያወልቅ የምር አገዘችው?”
“እንደዛ ነው የተሰማኝ አለኝ በግድየለሽነት:
“አልጮኸችም፣ አልተቃወመችውም?”
“አልተቃወመችውም፡ እሷም ፈልጋ ነበር! አምላኬ ሆይ እና በጣም ረጅም ጊዜ ወሰደባቸው! ካቲ
የሚያወጡትን ድምፅ አታምኚም! ታቃስታለች፣ትጮሀለች አየር ያጠራት ትመስላለች፣ ታለከልካለች እና እሱ ደግሞ እንደ አሳማ ያጓራል ግን እዛ ላይ በጣም ጥሩ ሳይሆን እንደማይቀር እገምታለሁ::
ምክንያቱም በመጨረሻ ሠራተኛዋ እንዳበደ ሰው ነበር የጮኸችው። ከዚያ ሲያልቅ ጋደም ብለው ሲጋራ እያጨሱ እዚህ ቤት ስለሚደረገው ነገር እያወሩ ነበር። እመኚኝ የማያውቁት በጣም ጥቂት ነገሮችን ብቻ ነው። ከዚያ ለሁለተኛ
ጊዜ ፍቅር ሰሩ:"
“በአንድ ምሽት ሁለት ጊዜ?”
“ይቻላል።”
“ክሪስ ለምንድነው አነጋገርህ የተቀየረው?”
አመነታ፤ ትንሽ ራቅ አለና ፊቴን አጠና። “ካቲ እያዳመጥሽኝ አይደለም? ሁሉንም ነገር ልክ እንደሆነው አድርጌ ለአንቺ ለመንገር ትልቅ ህመም ውስጥ
ነኝ። አልሰማሽኝም?”
መስማት? አዎ ሰምቼያለሁ ሁሉንም:
የእናታችንን ጌጣጌጦች ለመዝረፍ ብዙ ጊዜ ጠበቀ።
እናታችንና ባሏ ሌላ ሽርሽር ሄዱ። ይሄ ምን አይነት ዜና ነው? ሁልጊዜ
ይመጣሉ… ይሄዳሉ፤ ከዚህ ቤት ለመውጣት ምንም ነገር ያደርጋሉ። እና እወቅሳቸዋለሁ ማለት አልችልም: እኛስ ተመሳሳይ ነገር ልናደርግ ተዘጋጅተን
የለ? ቅንድቦቼን ወደ ላይ ሰቅዬ ክሪስን በጥያቄ አስተያየት ተመለከትኩት ያልነገረኝ
የሆነ የሚያውቀው ነገር እንዳለ ግልፅ ነው: አሁንም እየተከላከለላት ነው። አሁንም ይወዳታል
ካቲ” ሲል ጀመረ፡ ድምፁ እየተቆራረጠ ነው
“ምንም አይደል ክሪስ፣ እየወቀስኩህ አይደለም ውዷ፣ ጣፋጯ፣ ደጓና አፍቃሪዋ እናታችን ከመልከመልካም ወጣት ባሏ ጋር ጌጣጌጣቸውን ሁሉ ይዘው ሌላ ሽርሽር ሄዳለች፡ በውጪው አለም ያለውን ጥበቃ ደህና ሁን
በለው: ግን አሁንም እሄዳለሁ! እንሰራለን ራሳችንን የምንደግፍበት መንገድ እንፈልጋለን፡ ከዚያ ኬሪ እንደገና ደህና እንድትሆን ለዶክተር እንከፍላለን፡ዠ ስለጌጣጌጦች አትጨነቅ፤ ስለ እናታችን ርህራሄ የለሽ ድርጊት አትጨነቅ።
የት እንደምትሄድ፣ መቼ እንደምትመለስ እንኳን አልነገረችንም: አሁን አስቀያሚ መጥፎ የማናስብ ቸልተኞች እንድንሆን ተትተናል፡ ታዲያ ይሄ
ሁሉ ዕንባ ለማን? ለምን?
"ካቲ!” ተቆጣ በእምባ የረጠበ ፊቱን ወደ እኔ መልሶ አይኖቼ ላይ አተኮረ:
“ለምንድነው የማታዳምጪውና የሆነ ነገር የማትይው? ጆሮሽ የት ነው? ያልኩትን ሰምተሽኛል? ወንድ አያታችን ሞቷል! ከሞተ አንድ አመት ገደማ ሆኖታል!”
ምናልባት በደንብ አልሰማሁትም፤ በጥንቃቄ አላዳመጥኩትም ማለት ነው ሀዘኑ ምንም ነገር እንዳልሰማ አድርጎኛል ማለት ነው አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ መታኝ አያትየው በእውነት ከሞተ እጅግ መልካም ዜና ነው አሁን እናታችን ውርስ ታገኛለች… ሀብታም እንሆናለን…በሩን ትከፍትልናለች… ነፃ ታደርገናለች:: አሁን ለማምለጥ መሞከር የለብንም:
ሌሎች ሀሳቦች ጎረፉ አስደንጋጭ የጥያቄ ጎርፍ መጣብኝ። እናታችን አባቷ መሞቱን አልነገረችንም:: እነዚህ አመታት ለእኛ እንዴት ረጃጅም እንደሆኑ እያወቀች፣ ለምን በጨለማ ሁልጊዜ በመጠበቅ ውስጥ አስቀመጠችን? ለምን?
ግራ ተጋባሁ። ተደናገረብኝ፤ የትኛው ስሜት እንደሚሰማኝ አላውቅኩም። ደስታ ይሁን ሀዘን ሀሳቤን አለመቁረጤን ሽባ የሚያደርግ እንግዳ ፍርሀት
አስቆመኝ።
“ካቲ…” አለኝ ክሪስ በሹክሹክታ። ለምን ማንሾካሾክ እንዳለበት አላወቅኩም ኬሪ እንደሆነች አትሰማም: የእሷ አለም ከእኛ በእጅጉ ተለይቷል ኬሪ
በህይወትና በሞት መካከል ተንጠልጥላለች: በእያንዳንዱ ቅፅበት ወደ ኮሪ እየተጠጋች ነው: ራሷን በማስራብ ያለ ግማሽ አካሏ ለመኖር መፈለጓን ትታዋለች። “እናታችን ሆን ብላ አታላናለች: ካቲ አባቷ ሞቶ ከወራት በኋላ
ኑዛዜው ተነቧል። እና ሳትነግረን ፀጥ ብላ ሞታችንን እንድንጠብቅ እዚህ ተወችን፡ ከዘጠኝ ወራት በፊት ሁላችንም በዘጠኝ ወራት ጤናማ ነበርን! አባቷ የሞተ ጊዜ ከዚህ አስወጥታን ቢሆን ወይም ኑዛዜው የተነበበ ጊዜ እንኳን ወጥተን ቢሆን ኮሪ አሁን በህይወት ይኖር ነበር፡"
ስሜቴ ተጎድቶ እናታችን ልታሰምጠን የቆፈረችው ጥልቅ የክህደት ጉድጓድ ውስጥ ወደቅኩ። ማልቀስ ጀመርኩ።
“ዕንባሽን ለበኋላ አቆይው" አለ ክሪስ ራሱም እያለቀሰ ነው። “ሁሉንም ነገር አልሰማሽም ሌላም አለ። ብዙና የከፋ”
“ብዙ?” ሌላ ምን ብዙ ነገር ሊነገረኝ ይችላል? እናታችን ከእንግዲህ
ከማትወዳቸውና ከማትፈልጋቸው ልጆቿ ጋር መካፈል የማትፈልገውን
ንብረት በማካበት ሂደት ውስጥ ኮሪን የገደለች፣ውሽታም፣ አታላይና
ወጣትነታችንን የሰረቀች ሌባ መሆኗ ተረጋግጧል። በዚያ ምሽት ደስተኛ ባለመሆናችን ትንሽዋን ንስሀችንን ስትሰጠን ምን መጠበቅ እንዳለብን እንዴት አሳምራ እንዳብራራችልን! የዚያን ጊዜ አያታችን የሰራት አይነት
ሴት እንደምትሆን ታውቅ ወይስ ትገምት ነበር ይሆን? ክሪስ ክንዶች ላይ ወደቅኩና ደረቱን ተደገፍኩ “ከዚህ በላይ አትንገረኝ! የሰማሁት ይበቃኛል ከዚህ በላይ እንድጠላት አታድርገኝ! አልኩት።
“መጥላት. ጥላቻ ምን እንደሆነ ገና ማወቅ አልጀመርሽም ግን የቀረውን
ከመናገሬ በፊት ምንም ቢሆን ይህንን ቦታ ለቀን እንደምንሄድ አስቢ።እንዳቀድነው ወደ ፍሎሪዳ እንሄዳለን በፀሀይ ብርሀን ውስጥ እንኖራለን::እና ህይወታችንን በቻልነው ሁሉ በጣም ጥሩ እናደርገዋለን። ማን በመሆናችን ወይም በስራነው ለአንዲት ሰኮንድ እንኳን ሳናፍር እንኖራለን።
በመሀከላችን የተፈጠረው ነገር እናታችን ካደረገችው ጋር ሲነፀር ምንም ማለት አይደለም ከእኔ በፊት ብትሞቺም እንኳን፣ እዚህ ጣሪያ ስር ያለው ክፍል የነበረንን ህይወት ሁልጊዜ አስታውሰዋለሁ: በወረቀት አበባዎቹ ስር ስንደንስ አንቺ በጣም ግርማ ያለሽ እኔ ደግሞ ገልጃጃ ሆኜ የአቧራውንና የበሰበሰ እንጨቱን ሽታ ልክ እንደ ጣፋጭ ሽቶ አስታውሰዋለሁ ምክንያቱም
ህይወቴ ያላንቺ በጣም ቀፋፊና ባዶ ነው የሚሆነው። ፍቅር ምን ሊሆን
እንደሚችል የመጀመሪያውን ጣዕም ሰጥተሽኛል።

👍40❤3🥰3👎2😢2
“እንለወጣለን! በውስጣችን ያለውን ቆሻሻ ነገር ጥለን ጥሩውን እናስቀራለን፡ ግን ምንም ቢመጣ ሶስታችንም አብረን እንሆናለን ሁሉም ለአንዱ አንዱ ለሁሉ። ካቲ… በአካል፣ በአእምሮና በስሜት ጭምር እናድጋለን፡ ያ ብቻ
አይደለም: ለህይወታችን ያስቀመጥናቸው ግቦች ላይ እንደርሳለን፡ አለም የሚያውቀው ምርጥ ዶክተር እሆናለሁ"
አሁንም ከተዘጋ በር ጀርባ ሆነንና ሞት ልክ እንደ ፅንስ አጠገቤ ተጠቅልሎ ተኝቶ በእንቅልፍ ልቡ ሳይቀር በትንንሽ እጆቹ እየለመነ እያለ ክሪስ ስለ ፍቅርና ወደፊት ሊሆን ስለሚችለው ነገር ሲያወራ ደከመኝ።
“ጥሩ ክሪስ መተንፈሻ ሰጥተኸኛል። ለየትኛውም ነገር ተዘጋጅቻለሁ: እና
ያንን ሁሉ ስላልhኝ፣ ስለወደድከኝ አንተም ራስህ ሳትፈቀር ወይም ሳትደነቅ ስላልቀረህ ጭምር አመሰግናለሁ።" በፍጥነት ሳም አደረግኩት።
“በእውነት ክሪስ አንድ የሆነ በጣም መጥፎ ልትነግረኝ የሚገባ ነገር እንዳለ አውቃለሁ... ስለዚህ አውጣው ስትነግረኝ ግን ይዘኸኝ መሆን አለበት።የዚያን ጊዜ የምትነግረኝን የትኛውንም ነገር መቋቋም እችላለሁ።
ምን አይነት ለመገመት የማስቸግር ደፋር ሰው ነኝ!....

👍26❤8🥰3
✍✍የጠንቋዩ ዋሻ ✍✍
♦♦ክፍል 5,,,♦
✉❀✿❀✿❀✿❀✉
አቢያራ መሳይ ላይ ቀዩን ፈሳሽ ካፈሰሰበት ፡በዋላ ወደ አድማስ በመዞር ፡ መብራቱን እንዲያጠፋው ፡አዘዘው ፡ አድማስ ፡ በፍጥነት ፡ ወደ ጀኔሬተሩ በመሄድ ፡ የዋሻውስጥ መብራት እንዲቋረጥ ፡አደረገ ፡ ያ በቀያይ መጋረጃ ያበደ ዋሻ ወደፅልመት ተቀየረ ፡ በደብዛዛው ፡ብርሃን እንኳ ፡ ልባቸው ፡የቀለጠው ፡ ሦስቱ ጓደኛሞች ፡ ይበልጥ ፡እራዱ ፡ መሳይ በላዩላይ የፈሰሰውን ፡ፈሳሽ ለመጥረግ እንኳን ፡አልተንቀሳቀሰም ፡ በፀጥታና በፍርሃት ፡ቀጥሎ የሚፈጠረውን ፡በለበት ፡እንዳለ ማዳመጥ ፡ጀመረ ፡ መስፍንና ዳንኤል በጨለማውስ ውስጥ ተፈላልገው ፡እጅለእጅ በፍርሃት ፡ተያያዙ ፡ ይሄን ሁሉ ቁጣ ያመጣባቸውን ፡ ጓደኛቸውን ፡አማረሩ ፡ በፍቃደኝነት ፈሳሹን ቢጠጣው ፡ኖሮ ፡አቢያራ ባልተቆጣ ነበር ፡ብለው ፡አሰቡ ፡ አድማስ ፡ መብራቱን ካጠፋው ፡በዋላ ፡በለመደው ፡ዋሻ ያለአንዳች ችግር በመምጣት ፡ ከአቢያራ ትይዩ ቆመ ፡ ከትንሽ ፡የትንፋሽ ፡መቆራረጥ ፡በዋላ የአቢያራ ድምፅ ፡ መጮህ ማጓራት ማፏጨት ጀመረ ፡ በዋሻው ፡ውስጥ ፡ ፍርአት እና ጭንቀት ነገሰ ፡ አድማስ ፡ጮክ ፡ብሎ ፡አባቴ ፡ ጌታዬ ፡ ይቅር ፡በለን ፡እባክህ ፡አለ ፡ የመስፍን እና የዳንኤል ፡የሳግ ድምፅ ፡ተሰማ ፡ መሳይ ፡ድምፁ ቢያሸብረውም ፡አሁንም ፡ካለበት ፡ቦታ ፡አልተንቀሳቀሰም ፡ አቢያራ ፡ ከብዙ ማጓራት ፡በዋላ ፡ዝም አለ ፡ ዝምታው ፡እንኳ ፡ ፍርሃትን ያጭራል ፡ ዳንኤል ፡ወደ መስፍን ፡ጆሮ ፡ተጠግቶ ፡"የምንሞት ፡ከሆነ እንፀልይ ፡ በልባችን ፡ "አለው
"አይ የሚገለን አይመስለኝም ፡ ግን ፡ፈጣሪ ከዚ ጉድ አውጥቶ ከቤተሰቦቻችን ጋር ፡እንዲያገናኘን እንፀልይ "ብሎ ለማፅናናት ሞከረ
"ግን መሳይስ ዝም አለ እኮ ገሎት ነው እንዴ "ብሎ ዳንኤል አንሾካሾከ
"ኧረ እኔጃ በፍርሃት እንዳይሞት ነው የፈራውት " አለ መስፍን ፡
"ማነው ማነው ፡ እዚ ያለው "አለ አቢያራ ግርማ ሞገስ ባለው ድምፅ ፡ ዳንኤልና መስፍን ፡ በዋሻው ፡ውስጥ ከአቢያራ ሌላ ሰው ያለ እንጂ አቢያራ እስከማይመስላቸው ተደነጋገሩ
"ጌታዬ ሆይ መጣህ ክብር ላንተ ይሁን ፡ "አለ አድማስ ፡
"ከማን ጋራ ነው ያለኽው ፡ አንተ ልጅ "አለው አቢያራ ፡እንደ አዲስ
"ጌታዬ ፡ እነዚ ጎረምሳ ልጆች ፡ ያለ ዕድሜ አቸው ፡አጓጓል ፡ሕይወት ውስጥ የገቡና ፡ ምንም አይነት ፡ ሰላም ፡የሌላቸው ፡ናቸው ፡ እናም ፡በየምሽቱም ፡ በከተማው ፡ ከሚገኝ ፡መሸታቤት ፡ እንደልባቸው ፡ጠጥተው ፡ አካባቢንና ቤተሰቦቻቸውን ፡የሚያውኩ ናቸው ፡ እናም ጌታዬ ፡ እንደው ፡በከንቱ የሚያሳልፉት ፡ሕይወታቸው ፡ ለአቢያራ መስዋት ይሁኑ ብዬ ነው ያመጣዋቸው ፡ " አለ አድማስ እየተንቀጠቀጠ
"ሆሆሆሆሆሆይ ማነው ያዘዘ ""
"ማንም ጌታዬ"
"ሚስጢራዊ ቤቴን ልትገልጠው ፡ነው ፡ወይ ፡ እነዚን ፡ወይፈኖች ፡ ከዋሻዬ ያስገባሃቸው ፡ "
"ይቅርታ ጌታዬ "
"አሁን ብርሃን ይሁን "አለ የአቢያራ ሌላኛው ማንነት
"እሺ ጌታዬ "አለና አድማስ በጨለማው ውስጥ ፡ፈጥኖ ፡በመሄድ ፡ጄነሬተሩን ለኮሰው ፡ ዋሻው ፡በብርሃን ፡ሲሞላ ፡ ከቀድሞው ፡ብርሃን ፡ጨምሮ ፡የመጣ መሰለ ፡
መስፍን ፡ጉልበቱን በሁለቱም እጁ አቆፎ ይዞ ፡አቢያራን ፡ተመለከተው ፡ አቢያራ ሲያጓራና ፡ሲወራጭ ፡የተበታተነው ፡እረጅም ፡ፀጉሩ ፊቱን ፡አልብሶት ፡ፍፁም ፡ሌላ ሰው ፡መስሏል ፡ አይኑን ከአቢያራ ፡አስፈሪ ገፅታ አንስቶ ፡ወደወደቀው ፡ጓደኛው ፡አየ አሁንም ባለበት እንዳለ ነው ፡አልተንቀሳቀሰም ፡ ወደ ዳንኤል ሲያይ ፡ ዳንኤል ፡አቢያራን ፡ላለማየት ይመስል ፡አቀርቅሯል ፡ የተቀመጡበት ፡ሳፋ መሰል ጎድ ጓዳ ቦታ ፡ቢቀዘቅዝም ፡ ከፍርሃታቸው ፡የተነሳ ፡ ጭንቀት አልሆነባቸውም ፡ አድማስ ፡ አቢያራ ፡ በዋሻው ፡ውስጥ ፡ገዘፍ ፡ብሎ ፡ከሚታየው ፡ምቹ መቀመጫላይ ፡ሄዶ ፡ዘፍ ፡አለ ፡ አድማስ ፡ወደነ መስፍን ፡ዞሮ ፡ተነሱ አላቸው ፡ ሁለቱም ፡ተነስተው ፡ቆሙ ፡ አድማስ ፡ወደመሳይ ፡ዞሮ ፡ተነስ ፡አለው ፡ መሳይ ዝም አለ ፡ አድማስ ፡ተናደደ ድጋሚ አቢያራን እንዳያስቆጣው ፡ሰጋ ፡ እናም፡አጠገቡ ሄዶ ፡ጭምቅ ፡አድርጎ ፡በማንሳት ፡አቆመው ፡ መሳይ ፡ፊቱ በቀዩ ፈሳሽ ፡ስለ ተጥለቀለቀ ፡ አስፈሪ ገፅታ ይዟል ፡ ሁኔታው ፡ስጋት ፡የለቀቀበት ፡መስፍን ፡እኔ ላግዘው ፡ብሎ ፡አድማስን ፡ሲጠይቀው ፡አድማስ ፡ድምፅ ፡እንዳያወጣ ፡በማስጠንቀቅ ፡ መስፍን ፡ባለበት እንዲሆን ፡አደረገው ፡ በመቀጠል ፡አቢያራ ፡የሆነ በውል የማይታወቅ ፡ግራ የሚያገቡ ቋቋዎች ፡ተናገረ ፡ ይሄኔ ፡አድማስ ፡ከወገቡ ጎብደድ ፡ብሎ ፡እነሱም ፡ለአቢያራ ፡እንዲያጎነብሱ ነገራቸው ፡ ዳንኤልና መስፍን ፡አጎነበሱ በፍርሃት ፡ መሳይ ቆሞ ፡ሁኔታውን ፡ከመከታተል ፡ውጪ ምንም አይነት ፡እንቅስቃሴ ፡ሳያሳይ ፡የአቢያራን ሁኔታ ያያል ፡
አድማስ ወደጎን እያየው "አንተ ደደብ አጎንብስ "አለው በሹክሹክታ ፡ መሳይ አንገቱን በመነቅነቅ " ለፈጣሪ ብቻ ነው የምሰግደው ፡"አለው ይሄን ሲል አቢያራ ድምፁን በመስማቱ ፡ደንገጥ ብሎ ወደ መሳይ አፈጠጠ ፡ አድማስ የሚገባበት ጠፋው ፡ እናም ፡አቢያራ ፡ከመበሳጨቱ በፊት ፡የመሳይን ፡ፀጉር ፡ጨምድዶ ፡በመያዝ ፡ወደ አቢያራ ፡አቀረበው ፡እና ፡ስለቱን ፡በማውጣት ፡"ጌታይ እንደፍቃድህ ፡አለው "አቢያራ ፡ ጥርሱን አፋጨ ፡መሳይን አይኖቹን ተመለከታቸው ፡ የመሳይ ሰውነት ቢንቀጠቀጥም ፡ አይኖቹ ውስጥ ፡ግን ፡ ምንም ፡ግልፅ ፡የሆነ ፍርሃት ፡ያየ አልመሰለውም ፡ "ተወው ልጄ ፡ የኔ ነው ፡ ይህ ወይፈን ፡ የትስ ሊሄድ ትቢቱ ፡እንዲለቀው ፡ ጨለማው ፡ቤት ለብቻው ፡አስቀምጠው ፡"አለ አቢያራ ፡ መሳይ ፡ እንደ እብድ መለፍለፍ ፡ጀመረ " እማዬ ፡ በጭራሽ ፡ ለሰይጣን አልሰግድም ፡ በጭራሽ ፡ ፈጣሪዬ ፡ አንድ ነገር አድርግ ፡ ለሴጣን ከምሰግድ ብሞት ይሻለኛል ፡ እማዬ ይቅርታ ፡ስላሳዘንኩሽ ፡ አባዬ ፡ ,,,,,"
"ዝም በል አንተ የማትረባ "ብሎ አድማስ አፉ ላይ ከደነበት ፡ መሳይ ተስለመለመ ፡ አድማስ አንከብክቦ ፡ተሸክሞ ፡በዋሻው ፡ውስጥ ፡ከተሽሎከለከ በዋላ ፡ አንዲት ፡ጨለማ ፡ ክፍል ፡መሰል ፡ውስጥ ፡አስገብቶት ፡ ዘጋበት ፡ መሳይ እራሱን ፡ባይስትም ፡ደካክሞታል ፡ፍርሃቱም ፡እንዳለ ነው ፡ ቢሆንም ፡ግን ፡ ፈጣሪውን ፡ በዚ ጠንቋይ መቀየር ልቡ አልፈቀደም ፡ ጨለማው ፡ክፍል ፡ውስጥ ፡ምን ፡ይኑር ፡ምን ፡የሚያውቀው ፡ነገር ፡ባይኖርም ፡ ተጋደመ ፡ ስለቤተሰቦቹም ፡አስቦ ፡አለቀሰ ፡ ይሄኔ ፡ስንት ፡ቦታ ፡ፈልገውታል ፡ በራሱ ተበሳጨ ፡ ፡
,,,,መስፍንና ዳንኤል ፡የጠንቋዩን እያንዳንዷን ፡ ትህዛዝ ተቀብለው ፡አድርጉ የተባሉትን አደረጉ ፡ በዚ ሁኔታም ፡አድማስም ፡አቢያራም ፡ተደሰቱ ፡ እናም ፡አቢያራ ፡ እንዲታጠቡ ካደረገና ፡የሆነ እራሱ ብቻ የሚያውቀውን ፡ቅባት መሰል ነገር ፡ከቀባባቸው ፡በዋላ ፡ ቀይ ፡ሽርጥ ፡አለበሳቸው ፡ ፀጉራቸው ፡ላይም ፡ ቀይ ሪሻን መሰል ነገር ታሰረላቸው ፡ እናም ፡ከዚ በዋላ ፡ ከአድማስ ጋር በመሆን ፡ ስለዋሻው ፡መማር ያለባቸውን ፡ነገር ፡ ጠንቅቀው ፡መማር እንደሚችሉ ፡ነገር ፡ግን ፡የማምለጥ ሙከራ ቢያደርጉ ግን ፡ሕይወታቸው ፡በአቢያራ እንደሚነጠቅ ፡ ተነገራቸው ፡ በዚ ተስማምተው ፡ የፈሩት ሞት ቀረላቸው ፡ነገርግን ፡የጓደኛቸው ፡የመሳይ ፡ነገር ፡በጣም ፡አሳስቧቸዋል ፡ ምን ፡አለበት ፡ እንደእኛ ፡ ያለውን ፡ነገር ፡ለጊዜውም ቢሆንተቀብሎ ቀን ቢያሳልፍ ፡ብለው ፡አዘኑበት ፡ አድማስ ፡ተሸክሞ ፡ወስዶ

👍22😱8😁3
፡የትኛው ፡ጨለማ ፡ዋሻ ውስጥ ፡እንደጣለው ፡አያውቁም ፡እና ሊረዱትም ፡አይችሉም ፡ አቢያራ ፡ ሁለቱን ፡ጎረምሶች ፡ ወደ አላማው ፡ካስገባ ፡በዋላ ፡ እርካታ ፡ቢሰማውም ፡በአንደኛው ፡የትቢት ፡አይኖች ፡ግን መረበሹ ፡አልቀረም ፡ከዚ በፊት ፡እንዲ ተዳፍሮ ፡አይኖቹን ፡ያየው የለም ፡ እና አሳስቦታል ፡ ይህ ልጅ ፡ማመን ፡አለበት ፡በኔስር ፡እስኪሆን ፡እንቅልፍ ፡ያለኝም ፡አለ ለራሱ ,,,,,,,,,,
✍ ሙና መሀመድ
ይቀጥላል.....
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️
✍ ሙና መሀመድ
ይቀጥላል.....
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️
😢8👍5
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አርባ
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
....“ፒየር ደብዳቤዎች አሉ ይላል ” ብሎ ጀመረ “ “ አቤት ... ዛሬ እንዴት ደስ
የሚል ሞቃት ቀን ነው ! ”
“ ሁለት” አለችው ባጭሩ እሷም እንደሱ በኩርፊያ" ምን ጊዜም ይህን የመሰሉ የፍቅር ግንኙነቶች ሲጀመሩ የሚነገሩት የጋለ ፍቅር መግለጫ አባባሎች
እንደማር የሚጣፍጠው መወዳደስ መመኳሸትና መቃበጥ ዐሥር ወር አንኳን
ይቆያሉ ብሎ ማሰብ ትልቅ ስሕተት ይሆናል " ብዙ ሳይቆይ ማሩ ወደ እፊት
ጣዕሙ ወዶ ምሬት ይለወጣል "
“ ሁለት ይብቤዎች” አለችው በመቀጠል ሁለቱ በአንድ ዐይነት የእጅ ጽሑፍ የተጻፉ ናቸው ከነገረ ፈጅህ የተላከ ይመስለኛል
ደብቤዎቹን ያዘና ራቅ ወዳለው መስኮት ሔዶ አንዱን ከፍቶ እነበበው ።
ክቡር ሆይ ጒዳዩን ተከታትለን ባስቸኳይ እንድናስታውቅዎ ጠይቀውን በነበረው መሠረት ካርላይል የከፈተው የሥራ ፋይል ፍቼው ያለ ምንም ተቃዉሞ
ጸድቆ የተዘጋ መሆኑን በትሕትና እንገልጻለን "
ታማኞችዎ
ሞስና ግራብ
“ ፍራንሲዝ ሌቪሰን ኢስኳየር ‥
እንግዲህ አበቃለት እመቤት ሳቤላ ካርላይል ከሚለው ስም ምንም ግኑኝነት እንደማይኖራት በህግ ጸደቀ። ጋብቻው ፈረሰ! !
ካፒቴን ሴቪሰን ደብዳቤውን በጥንቃቄ አጥፎ ከውስጠኛው ኪስ ከተተው።
“ ምን ወሬ አለ ? አለችው "
ወሬ ?
“ አዎን ' ስለፍቺዉ ወሬ ማለቴ ነው ”
“ ኤዲያ ! ” አለ የፍቼ ነገር ገና ብዙ ጊዜ የሚጠይቅ መሆኑን ለመግለጽ የፈለገ መስሎ » ከዚያ ሌላ መልስ ሳይሰጥ ሁለተኛዉን ደብዳቤ መክፈት ጀመረ "
“ ክቡር ሆይ ዛሬ አንድ ደብዳቤ ከጻፍንልዎ በኋላ ያጎትዎ የሰር ፒተር
ሌቨሰንን ዕረፍት ሰማን የሕክምና እርዳታ ለማግኘት ወደ ከተማ በሔዱበት ዛሬ ከቀትር በኋላ ዐርፈዋል " የማዕረጋቸውና የሀብታቸው ወራሽ ለመሆን በመብቃትዎ እንኳን ደስ ያለዎ ብለን ደስታችን እየገለጽን ምናልባት ባሁኑ ጊዜ ወደ ኢንግላንድ ለመምጣት የማይመችዎ ቢሆን መመሪያ ይላኩልንና እርስዎን መስለን አስፈላጊውን ለመፈጸም የምንችል መሆናችንን እንገልጻለን " ምንጊዜም የእርስዎ ታማኞች ፡
“ ሞስና ግራብ ”
“ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ባርት ”
በውጪ አድራሻ ግን ይኸኛውም ደብዳቤ እንደ መጀመሪያው “ ፍራንሲዝ
ሴቪሰን › እስኳየር” የሚል ተጽፎበት ነበር " እንደዚያ የተደረገበት ምክንያት በቀላሉ እንዲደርሰው ተብሎ የታሰበ ለመሆኑ አያጠራጥርም "
“ አቤት አቤት ! ብሎ ብሎ ተፈጸመ እኒህ አሳሞች ! ኧረ እግዜር ይስጣቸው” አለና ደብዳቤውን አንደ ተከፈተ ከቁርስ ጠረጴዛው ላይ ጣል አደረገው ።
ፍቹ ጸደቀ እንዴ ?” አለችው ሳቤላ በጉጉት "
ምንም መልስ ሳይሰጣት ቁርሱን ሊበላ ተቀመጠ "
ይኸንስ ላንበው ?
ታዲያ ለምን ከፊትሽ አኖርኩት ?
“በቀደም እንደዚሁ» ከጠረጴዛው የጣልከውን ደብዳቤ ባነብ አልተቆጣኸኝም ካፒቴን ሌቪሰን ?”
" ይኸን ለብዙ ጊዜ ተለጥፎብኝ የኖረውን አስቀያሚ ማዕረግ ተይው '
ሳቤላ " አሁን ከሱ የተሻለ አግኝቻለሁ " ደብዳቤውን እይው ...
ሳቤላ ደብዳቤውን አንሥታ አነበበችው ሰር ፍራንሲዝ ቡናውን ጭልጥ አድርጎ መጥሪያውን ደወለውና ፒየር መጣ "
“ ቅያሬ ልብስ አዘጋጅልኝ አለው በፈረንሳይኛ
ከአንድ ስዓት በኋላ ወደ ኢንግላንድ እነሣለሁ” ሲለው ፒተር እጅ ነሥቶ ወጣ » ሳቤላ ፒየር እስኪወጣ ዝም ብላ ቆየችና “ከልብህ ነው የምትናገረው? እንደዚህ ሁኘ እያየህ ያለ አንዳች
ውል ጥለኸኝ ልትሔድ ?
“ ምንም ማድረግ አልችልም አሁን ሥልጣን ላይ ስለ ወጣሁ ተራራ የሚያህል ሥራ ተቆልሎ ይጠብቀኛል ”
“ ሞስና ግራብ አንተን መስለው ሊሠሩልህ እንደሚችሉ ጽፈውልሃል "ያንተ መሔድ ቢያስፈልግ ኖሮ እንደዚህ ብለው መቸ ይጽፉልህ ነበር ?
“ አዎን እነሱማ ይላሉ በኔ ሀብት ኪሳቸውን ለመሙላት ቋምጠዋል ወደ ኢንግላንድ መሔድ በግድ አስፈላጊ ነው " ከዚህም ሌላ የሽማግሌው ቀብር እኔ በሌለሁበት እንዲፈጸም አልፈልግም ”
“ እንግዲያው እኔም አብሬህ መምጣት አለብኝ ”
“ እኔስ የማይረባ ነገር ስትናገሪ ባልሰማሽ ሳቤላ " አንቺ ቀንና ሌሊት እንደ ተጓዝሽ ለመኖር ነው የምትፈልጊው ደሞስ አሁን ወደ ኢንግላንድ መሔድ
ላንቺ ደግ ነው ?
“ ወደ እንግላንድ ከሔድh በወቅቱ ላትመለስ ትችላለህ
ለምኑ ?
" እንዴት እንዲህ ብለህ ትጠይቀኛለህ ? በደንብ ታውቀዋለህ " ፍቹ ሕጋዊ
ሆኖ ይፋ እንደ ወጣ በውል እንድንጋባ በጊዜው እንድትመለስ ነዋ።
“ብችል እደርሳለሁ አሁን ግን አልቀርም
"ብችል? ለገዛ ልጅህ ሕጋዊነት? ከሁሉ በፊት ይኸን ማረጋግጥ አለብሀ።
“ ራስሽን አታቃጥይ ሳቤላ " ስለዚህ ነገር ስንት ጊዜ ነው የምለምንሽ? አይጠቅምሽም " በድንገት ወደ ኢንግላንድ መጠራቴ የኔ ጥፋት ነው ?
ለልጅህ አታዝንም ? ዐይንህ እያየ አንድ ጊዜ ለጉዳት ከዳረግኽው ምንም
ነገር አይጠግነውም " ዕድሜ ልኩን የማንም መተረቻ ሆኖ ይቀራል ”
“ ፍቺውን እንዲያጸድቀው ለፍርድ ቤቱ መጻፍ ነበረብሽ” አላት " “ ስለ
መዘግቱ እኔ ምንም ማድረግ አልችልም ”
" ኧረ ተው አይዘገይም እንደማይዘግይ ዐውቃለሁ " አሁንም በሰዓት በሚቆጠር ጊዜ ውስጥ ይደርሳል ይሆናል "
“ ዝም ብለሽ እኮ ነው የምትጨነቂ ሳቤላ ‥.. " እኔ በጊዜው እመለሳለሁ”
ብሏት ወጣ" ሐውልት መስላ ፈዛ እንደ ተቀመጠች አንድ ሰዓት ያህል ዐለፈ ብትን ያለው ሐሳቧ ሲሰበሰብላት የቁርሱ ዕቃ አለመነሳቱን አየች አሽከር መጥቶ እንዲያነሳው ስትደውል አንዲት ሴት ሠራተኛ ገባች "
“ ፒየርሳ የት ነው ?
ፒየርማ ጌቶችን ተከትሎ ወደ ኢንግላንድ ለመሔድ እየተሰናዳ ነው ብላት ዕቃውን አንሥታ ስትወጣ በሩን ከመዝጋቷ ሌቪሰን የጉዞ ልብሱን ለብሶ
ብቅ አለ ያለ ምንም ሐተታና ዙሪያ ጥምጥም ንግግር “ ደኅና ሁኝ . .. ሳቤላ ” አላት።
ሳቤላ ራሷን መቁጣጠር እስኪያቅታት ድረስ ተሸበረች መዝጊያውን ቀርቅራ ተደገፈችውና እግሩ ላይ ተንበርክካ እጆቿን አንሥታ እያርበገበች ትለምነው ጀመር "
“ ፍራንሲዝ ... ስለኔ ምንም ግድ የለህም ? ትንሽ እንኳን አታዝንልኝም ?
“ እንዴት እንይዚህ ታስቢያለሽ ... ሳቤላ ? በደንብ አስብልሻለሁ እንጂ
እንዴት አታስብልኝም ትይኛለሽ ?” አላት አዘኔታ ባለው አነጋገር ከእንብርክኳ
ለማከነሣት እጁን እየዘረጋ ።
“ የለም እኔ አልነሣም ። አንድ ወይም ሁለት ቀን ከዚህ እንደምትቆይ ካልነገርከኝ አልነሣም የፍቹ መጽደቅ እንደ ተረጋገጠ ቄሱ ሊያጋቡን ዝግጁ መሆኖቸውን ታውቃለህ " አሁንም ካሰብክልኝ ትቆያለህ እንጂ ጥለኸኝ አትሔድም '''
“ ተይ የማይሆን ነገር አትጠይቂኝ ምንም ቢደረግ መቆየት አልችልም "
ይልቅ በከንቱ አታስቸግሪኝ
“ አልሔድም በለኝ : ”
“ደስ ይበልሽ አልሔድም፤ ግን እንደ ልጅ አትሁኚ እኔ ጊዜን ጠብቄ እመለሳለሁ ።
“ ኧረ ተው ለራሴ ስል የምለምንህ አይምሰልህ " ለራሴ እንዳልሆነ ታውቃለህ በራሴ የመጣ ቢመጣብኝ ግድ የለኝም ስማኝ ሳትሰማኝ አትወጣም "
ፍራንሲዝ አንተን ብዬ አንተን አምኘ ባበላሸሁት ዕድሌ በጣልሁት ክብሬ
ባፈረስኩት ትዳሬ እለምንሃለሁ " ሳለ ....
“ ተነሽ ... ሳቤላ ” አለና አቋረጣት "

👍14🔥1
“ ለሚወለደው ልጅ ስትል ! ዕድሜ ልኩን ኃፍረት ተሸክሞ አንገቱን ደፍቶ
እየተሳቀቀና እየተሸማቀቀ ለሚኖረው ሕፃን ስትል ተለመነኝ » ከባልንጀሮቹ እኩል የማይናገር ማንም እየተነሣ በኃጢአት የተወለደ ዲቃላ እያለ የሚስድበው ሕፃን
እናት አታድርገኝ ፍራንሲዝ ! ፍራንሲዝ ለኔ ማዘኑን ብትተወው ለየዋሁ
ሕፃን እዘንለት ” አንድ ' ሁለት ቀን ቆይ የፍቺው ጋዜጣ ይድረስ " የጋብቻችን
ውል ይፈጸም "የተረገዘው ልጅ በስምህ ይጠራ”
“ የለም እኔስ ማበድሽ መሰለኝ ! ገና አንድ ወር አለን " እኔ ከአንድ ሳምንት በላይ ለንደን የሚያስቆየኝ ሥራ የለኝም " ስለዚህ ጊዜው ገና ሳይጋመስ
እመለሳለሁ " በዚሀ ቃል እገባልሻለሁ " ስለዚህ አሳልፊኝ "
እሷ ግን ንቅንቅ አላለችም " ከነበረችበት ቆመችና እጆቿን በልመና ወደ
ላይ ዘረጋች " እሱም ትዕግሥቱ አለቀ " ቀስ አለና በሩን በመላ ሲከፍተው ክንዱን ግጥም አድርጋ ያዘችው "
ለራሴ እኮ አይደለም ” አለችው ትንፋሽ እያጠራት • የደረቁት ከንፈሮቿ ዐመድ እንደ መሰሉ ።
ወይ ጉድ ምን ያለችው ናት!እኔ!ኮ የገባሁልሽን ቃል አክብሬ የምመጣው ላንቺ ስል ነው " አሁን ግን መሔድ አለብኝ" በይ. . ደኅና ሁኝ " ራስሽን
ጠብቂ ” አላትና ገፍቷት ፒተርን አስከትሎ ወጣ " ያልታደለችው ሴትዮ እንደዚያ ተርገብግባ እየለመነችው ረግጧት ሲወጣ እንደገና እንደማታየውና እሷ ለምትፈልገውም ጉዳይም የማይደርስላት መሆኑን ልቧ ዐወቀው።
እውነቷን ነበር ሳምንቶችና ወሮች ዐለፉ ። እሱ ግን የውሃ ሽታ ሆነ "

👍13
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሶስት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
የጨሻው መጀመርያ
“ምን እንደነገረቻቸው ገምቺ…” ክሪስ ቀጠለ “ክፍሉ በወሩ መጨረሻ
በሚመጣው አርብ እንዳይፀዳ የፈለገችበትን ምክንያት ገምቺ።
“እንዴት መገመት እችላለሁ? እኔ የእሷ አይነት አእምሮ የለኝም:" ጭንቅላቴን ነቀነቅኩ። ሠራተኞቹ ወደዚህ መምጣት ካቆሙ ብዙ ጊዜያቸው ነው እነዚያን
አስፈሪ የመጀመሪያ ሳምንታት ረስቻቸው ነበር፡
“አይጦች ካቲ...” አለ ክሪስ ሰማያዊ አይኖቹ ቀዝቃዛና ጠንካራ ሆነዋል
“አይጦች አያትየው የፈጠረቻቸው ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ የሚገኙ በመቶ የሚቆጠሩ አይጦች ከሁለተኛ ፎቅ በደረጃ ወደታች የሚወርዱ
ትናንሽ ብልጥ አይጦች፣ አርሰኒክ የተደረገበት ምግብ ትታላቸው በሩን
ቆልፋባቸው ልትሄድ የምትገደድባቸው ትንንሽ ጨካኝ አይጦች”
ሠራተኞቹ እዚህ አካባቢ እንዳይደርሱ ግሩምና ድንቅ ታሪክ እንደሆነ አሰብኩ ጣራው ስር ያለው ክፍል በአይጥ ተሞልቷል። አይጦቹ በደረጃውም
ይወርዳሉ።
“አርስኒክ ነጭ ነው ካቲ፣ ከተፈጨ ስኳር ጋር ሲቀላቀል ምሬቱ አያስታውቅም
ጭንቅላቴ ተሽከረከረ! በየቀኑ በሚመጣልን አራት ዶናት ላይ ያለው የተፈጨ
ስኳር! ለእያንዳንዳችን አንድ አንድ: አሁን ግን ቅርጫቱ ውስጥ ሶስት ብቻ ነው: “ግን ክሪስ ታሪክህ ምንም ስሜት አይሰጥም አያትየው በአንድ ጊዜ ብዙ መርዝ ሰጥታ ልትገድለን ስትችል ለምን ቀስ በቀስ ትመርዘናለች? ለምን
በአንዴ አትገላግለንም?”
ጭንቅላቴ በመዳፎቹ መሀከል ሆኖ በረጃጅም ጣቶቹ ፀጉሬን እየዳበሰኝ ነበር።ቀስ ባለ ድምፅ ተናገረ “በቲቪ ያየነው የሆነ ያረጀ ፊልም አስታውሺ
አስታውሺ ለሽማግሌው ለሀብታሙ ሰውዬ ቤት የምትጠብቅለትን ያቺን ትንሽ ሴት ካመኗት፣ ከወደዷትና ኑዛዜያቸው ውስጥ ካስገቧት በኋላ
በየቀኑ ትንሽ ትንሽ አርሰኒክ ትመግባቸው አልነበር? በየቀኑ ትንሽ ትንሽ
አርሰኒክ ሲወሰድ ቀስ በቀስ ወደ ሰውነታችን ይሰርግና በየቀኑ ተጠቂው ትንሽ ትንሽ እያመመው ይመጣል፤ በጣም ብዙ ግን አይታመምም ትንንሽ
የራስ ምታቶች የአንጀት መቆጣት እና የመሳሰሉት በቀላሉ መገለፅ የሚችሉ
ህመሞች ያጋጥሙታል ተጠቂው ሲሞት፣ ለምሳሌ ሆስፒታል ውስጥ ሲሆን
መጀመሪያውኑ ከስቶ፣ ደም ማነስ ይዞትና ረጅም የህመም ታሪክ፣ የጉንፋን
አይነት ትኩሳት፣ ብርድና የመሳሰሉት ይታዩበታል እና ተጠቂው የሳምባ ምች ምልክቶችን ሁሉ ቢያሳይም ልክ እዛ ፊልም ላይ እንዳየነው ዶክተሮቹ
መመረዝ መሆኑን አይጠራጠሩም:”
ኮሪ!” ትንፋሽ አጠረኝ: “ኮሪ የሞተው በአርሰኒክ ተመርዞ ነው? እናታችን የገደለው የሳምባ ምች ነው ብላን ነበር”
“የምትፈልገውን ልትነግረን አትችልም? እውነቱ መናገሯን በምን
እናውቃለን? ምናልባት ሆስፒታል ወስዳውም ላይሆን ይችላል። ወስዳውም ከሆነ ዶክተሮቹ ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ሞት መሆኑን አልጠረጠሩም ማለት ነው። እንደዛ ባይሆን ኖሮ አሁን እስር ቤት ትሆን ነበር”
“ግን ክሪስ” ተቃወምኩ። “እናታችን አያትየው መርዝ እንድታበላን አትፈቅድም! ያንን ገንዘብ እንደምትፈልገው አውቃለሁ፤ በፊት የምትወደንን ያህል እንደማትወደንም ይገባኛል፤ ግን አሁንም ልትገለን አትፈልግም”
ክሪስ ጭንቅላቱን ወደጎን ዘምበል አደረገ፡ “እሺ አንድ ሙከራ እናድርግ፤ ለኮሪ ጓደኛ አይጥ ትንሽ የተፈጨ ስኳር ያለበት ዶናት እንስጠው”
“አይሆንም! በሚወደንና በሚያምነን ላይ እንደዚህ ማድረግ አንችልም ኮሪ
ያንን ግራጫ አይጥ ይወደው ነበር። ክሪስ፣ ሌላ አይጥ እንይዛለን” ካቲ አይጡ አርጅቷል፡ በዚያ ላይ እግሩ ሽባ ነው፡፡ አይጥን ከነህይወቱ መያዝ ደግሞ ከባድ እንደሆነ ታውቂያለሽ፡ ከዚህ ስንሄድ ነፃ ስንለቀው አሁን የቤት እንስሳ ስለሆነ መኖር አይችልም በእኛ ላይ ጥገኛ ሆኗል።"
ከእኛ ጋር ይዘነው እንድንሄድ አስቤ ነበር
“በዚህ መንገድ ተመልከቺው ካቲ። ኮሪ ሞቷል፣ ገና መኖር እንኳን አልጀመረም ነበር። ዶናቶቹ መርዝ ከሌለባቸው አይጡ በህይወት ይቆያል፡ ከዚያ ይዘነው መሄድ እንችላለን፡ የግድ ካልሽ ማለቴ ነው: አንድ ነገር እርግጥ ነው፣ማወቅ አለብን፡ ለኬሪ ስንል እርግጠኛ መሆን አለብን: ተመልከቻት፡ እሷም
"እየሞተች እንደሆነ አይታይሽም? ከቀን ቀን ጤና እያጣች ነው። እኛም እንደዚያው
ተጠግቶ እኛን፣ ያ ትንሽ ፍጥረት በሶስቱ ጤናማ እግሮቹ እያነከስ ወደ እኛ መጣ። ወደ ክሪስ ጣቶች ተጠግቶ እኛን፣ ጌቶቹን፣ ወላጆቹን፣ ጓደኞቹን አምኖ ቁንጥር አድርጎ በላ፡፡ ያንን ማየቱ ራሱ ያሳምማል።
አልሞተም! ወዲያውኑ አልሞተም፡ ቀርፋፋ፣ ፈዛዛ፣ ፍላጎት ያጣ ሆነ። በኋላ እንዲያቃስት ያደረገው ትንሽ ህመም ተሰማው፡ በጥቂት ስዓታት ውስጥ ድርቅ ብሎና ቀዝቅዞ በጀርባው ተጋደመ: ሮዝ ጣቶቹ ተቆለመሙ፤ ትናንሽ ጥቁር አይኖቹ ጎደጎዱ። አሁን አወቅን... በእርግጠኝነት ኮሪን የወሰደው
እግዚአብሔር አይደለም!
“አይጡንና የቀሩትን ሁለት ዶናቶች በኪስ ወረቀት ውስጥ አድርገን ወደ
ፖሊስ እንወስደዋለን" አለ ክሪስ በሚያስተማምን አይነት አይኖቹን ከእኔ ዞር እያደረገ፡“አያትየውን እስር ቤት ያስገቧታል” አልኩት
“አዎ” አለና ጀርባውን አዞረ:
“ክሪስ፣ የሆነ ነገር ደብቀኸኛል፡ ምንድነው?”
“በኋላ... ከሄድን በኋላ፡ አሁን ማለት የምችለውን ሁሉ ሳያስመልሰኝ
ተናግሬያለሁ። ነገ በማለዳ ከዚህ እንሄዳለን፡” አለ ምንም አልተናገርኩም እጆቼን በሁለት እጆቹ ይዞ ጭምቅ አደረጋቸውና “በተቻለ ፍጥነት ኬሪን ወደ
ዶክተር መውሰድ አለብን ራሳችንንም ጭምር” አለ ቀኑ በጣም ረጅም ሆነብን፡ ሁሉንም ነገር አዘጋጅተን ስለጨረስን ለመጨረሻ ጊዜ ቲቪው ላይ ከማፍጠጥ በስተቀር ምንም የምንሰራው አልነበረንም ኬሪ
ጥጉ ላይ እንደተቀመጠች ሁለታችን ደግሞ በተለያየ አልጋ ላይ ጋደም ብለን የምንወደውን ተከታታይ የቴሌቭዥን ፊልም እያየን ነው: ሲያልቅ ክሪስ እዚህ ፊልም ውስጥ ያሉት ሰዎች ልክ እንደኛ ናቸው: እምብዛም ወደ ውጪ
አይወጡም ሊወጡም መውጣታቸውን እንሰማለን እንጂ አናይም ሳሎንና መኝታ ቤት ውስጥ ሲንጎራደዱ፣ ወጥ ቤት ቁጭ ብለው ቡና ሲጠጡ ወይም
ቆመው ብራንዲያቸውን ሲጠጡ ነው የምናያቸው: ግን በፍፁም ውጪ ወጥተው አይተናቸው አናውቅም፡ የሆነ ጥሩ ነገር ተፈጥሮ በመጨረሻ ደስተኛ እንደሚሆን ባሰቡ ቁጥር የሆነ መቅሰፍት ይመጣና ተስፋቸውን ሁሉ ያጠፋዋል” አልኩት ድንገት የሆነ ሰው ክፍሉ ውስጥ እንዳለ ተሰማኝ፡ ትንፋሽ አጥሮኝ ዞር ስል
አያትየው ቆማለች: አቋቋሟና ከጨካኝና ንቀት የሚያሳዩ አይኖቿ ለሆነ ጊዜ ያህል እዚያው እንደነበረች ነገሩኝ።
በቀዝቃዛው ድምጽዋ ተናገረች “ከአለም ተነጥላችሁም እያላችሁ ሁለታችሁም እንዴት ሰልጥናችኋል! ህይወት እንዴት እንደሆነ በቀልድ መልክ እያጋነናችሁ ነበር በትክክል ነው የገመታችሁት ምንም ነገር እናንተ በምታስቡት መንገድ
አይሰራም: በመጨረሻ ሁልጊዜም ታዝናላችሁ” አለች:
እኔና ክሪስ አተኩረን ተመለከትናት: ሁለታችንም ፈርተናል። ፀሀዩዋ
አፍንጫዋን ወደ ምሽቱ ውስጥ እየደበቀች ነው:: የምትፈልገውን ተናግራለች: ስለዚህ ወጣችና በሩን ቆለፈች: አልጋዎቻችን ላይ ተቀመጥን፡ ኬሪም ጥጉ
ላይ ተቀምጣለች።
ካቲ፣ የተሸነፍሽ አትምሰይ! እንደገና ተስፋ ልታስቆርጠን እየሞከረች ብቻ
ነው። ምናልባት ምንም ነገር በትክክል አልሄደላት ይሆናል። ያ ማለት ግን እኛ እንሞታለን ማለት አይደለም ምንም ፍፁም የሆነ ነገር እናገኛለን ብለን ሳንጠብቅ እንሂድ። ትንሽ ደስታ እንደሚኖረን ብቻ እንጠብቅ። ተስፋ አንቆርጥም:”

👍47🥰5👏1
ክሪስን ትንሽ የደስታ ኮረብታ የምታረካው ከሆነ ለሱ ጥሩ ነው። ነገር ግን ከነዚህ ሁሉ አመታት ጥረት፣ ተስፋ ማድረግ፣ ማለምና መናፈቅ በኋላ ኮረብታ አይበቃም! እንደ ተራራ የገዘፈ ደስታ ነው የምፈልገው! ከዚህ ቀን ጀምሮ ህይወቴን የምቆጣጠረው እኔ እንጂ እጣ ፈንታ ወይም እግዚአብሔር አይደለም ብዬ ለራሴ ማልኩ። ከዚህ በኋላ ክሪስ እንኳን ምን ማድረግ እንዳለብኝ አይነግረኝም ወይም በማናቸውም መንገድ ተፅዕኖ አያሳድርብኝም።
ከዚህ ቀናት ጀምሮ የምፈልገውን በምፈልገው ጊዜ የምወስድና ለራሴ ብቻ መልስ የምሰጥ የራሴ ሰው ነኝ፡ በስግብግብነት ምርኮ ተይዤ እስረኛ ተደርጌያለሁ: ተከድቻለሁ፣ ተታልያለሁ፣ ተዋሽቻለሁ፣ ተጠቅመውብኛል፣
ተመርዤያለሁ. ግን አሁን ሁሉም ነገር ያበቃል።
እናታችን ጥቅጥቅ ባለ ጫካ መሀል በኮከብ በደመቀ ጨረቃማ ምሽት እየመራች ስታመጣን... ሙሉ ሴት ለመሆን የደረስኩ የአስራ ሁለት አመት ገደማ እድሜ ያለኝ ልጅ ነበርኩ: እና በእነዚህ ሶስት አመት ከአምስት ወራት ጊዜ መብሰል ደረጃ ላይ ደርሻለሁ: ውጪ ካሉት ተራራዎች እድሜ እበልጣለሁ
ጣራው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ጥበብ በአጥንቴ ውስጥ ነው ከአእምሮዬ ውስጥ ተቀርፆ የስጋዬ አካል ሆኗል።
በአንድ በማላስታውሰው ቀን ክሪስ ሲጠቅሰው እንደሰማሁት መፅሀፍ
ቅዱስ. . . “ለሁሉም ጊዜ አለው” ይላል። የደስታ ጊዜዬ ወደፊት መሆኑን አውቄያለሁ እየጠበቀኝ ነው:
ያቺ በቀላሉ ተሰባሪ የሆነችው ባለ ወርቃማ ፀጉር የድሬስደን አሻንጉሊት የት ሄደች? ጠፍታለች ልክ ሽክላ ወደ ብረት እንደተቀየረ አይነት፣ መንገዷ ላይ ማንም ወይም ምንም ቢቆምና ምንም ነገር ቢፈጠር ሁልጊዜ የምትፈልገውን
ወደምታገኝ ወደ ሌላ ሰው ተለውጣለች። የተለወጠውን አስተያየቴን ወደ ኬሪ መለስኩ። አንገቷን ደፍታ ፀጉሯ ፊቷን ከልሎት ጥጉ ላይ ተቀምጣለች:
ዕድሜዋ ስምንት አመት ተኩል ሆኗል። ግን እንዳረጀ ሰው እየተንቀራፈፈች ነው የምትሄደው፡ አትበላም፣ አትናገርም: በአሻንጉሊቱ ቤት ውስጥ ካለችው ቆንጅዬ ትንሽ አሻንጉሊት ጋር አትጫወትም ከነዚያ አሻንጉሊቶች መሀከል የተወሰኑትን መውሰድ ትፈልግ እንደሆነ ስጠይቃት አቀርቅራ
አልመለሰችልኝም:
አሁን ኬሪ በዚያ ግትርነቷ እንኳን አታሸንፈኝም: አሁን ያለኝን የመንፈስ
ጥንካሬ እንኳን የስምንት አመት ልጅ ማንም የትም ቦታ ሊቋቋመው
አይችልም።
ወደ እሷ ተራምጄ አነሳኋት። እንደደከማትም ብትሆን ታገለችኝ። ራሷን ከእኔ ነፃ ለማድረግ ያደረገችው ጥረት ፍሬ አልባ ነበር። ጠረጴዛው አጠገብ
ተቀመጥኩና አፏ ውስጥ በግድ ምግብ ከተትኩና መትፋት ብትፈልግም እንኳን እንድትውጥ አስገደድኳት። ወተት በብርጭቆ አድርጌ ወደ ከንፈሮቿ
ሳስጠጋ ከንፈሮቿን ገጥማ እምቢ ብትለኝም በግድ ፈልቅቄ ወተቱንም
እንድትጠጣ አደረግኳት። ክፉ እንደሆንኩ እየጮኸች በመናገር አለቀስች።ወደ መታጠቢያ ቤቱ ተሸክሜ ወስጄ ብትቃወምም እንኳን የመፀዳጃ ወረቀት
ተጠቅሜ እንድትፀዳዳ አደረግኳት።
ገንዳው ውስጥ አስገብቼ ፀጉሯን አጠብኩ: ከዚያ ልክ እኔ እንደለበስኩት የሚሞቁ ልብሶች ደራርቤ አለበስኳት። ፀጉሯ ሲደርቅ በፊት እንደነበረው እስኪያብረቀርቅ ድረስ አበጠርኩት- በጣም የሳሳና ውበቱ ከበፊቱ ያነሰ
ቢሆንም:
በምንጠብቅበት ረጃጅም ሰዓታት ውስጥ ኬሪን አቅፌ እኔና ክሪስ ወደፊት በፍሎሪዳ ወርቃማ የፀሀይ ብርሃን ውስጥ ደስተኛ ህይወት እንደሚኖረን ያቀድነውን እቅድ በቀስታ እየነገርኳት ነበር።....
ዋው #የጣሪያ_ስር_አበቦች ሊያልቅብን አንድ ወይም ሁለት ክፍል ቀረው ሲያልቅ አስተያየታችሁን ትሰጣላችሁ እስቲ ከማለቁ በፊት እስካሁን ባለው ክፍል አስተያየታችሁን እፈልጋለው ስለ ልጆቹ ስለ እናትየው አያትየው ስለ አባታቸው ሁሉንም እያነሳቹ አስተያየት መስጠት ይቻላል መልካም ምሽት

👍66😢27❤1
✍✍የጠንቋዩ ዋሻ ✍✍
☜☜ክፍል 6 ☞☞
♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦
መሳይ ከተጣለበት ጨለማ ውስጥ ሆኖ ድምፁን ከፍ በማድረግ ሲፀልይ ቆይቶ በጣም እየደከመው ሲመጣ እንቅልፍ ወሰደው ፡ የተኛበት መሬት ፡ምቾት ካለመኖሩ የተነሳ እያቃዠው ነበር ፡ በቅዠቱ ሁሉ የአቢያራ የሚያስፈራ ግዙፍ ሰውነት ፡ሲጫነው ሲያስፈራራው ለማምለጥ ሲታገል ነበር የሚያየው ፡ በጣም ከመድከሙ የተነሳ ግን እየባነነ መልሶ ፡ ወደ ቅዠቱ ይገባል ፡
መስፍንና ዳንኤል የአቢያራን ፡እያንዳንዷን ትህዛዝ በመቀበላቸው ፡በዋሻው፡ውስጥ ይኖራል ብለው፡ባልገመቱት ፡ያማረ መኝታ ክፍል ውስጥ የሚመች አልጋላይ ፡ መተኛት ችለዋል ፡ በዚ የአቢያራ የዋሻውስጥ ፡ያማረ በቀያይ መጋረጃ ያበደ ክፍል ሁለቱም ተደንቀዋል ፡ በየክፍሉም ፡ ደብዛዛ ቢሆንም መብራት በመኖሩ አቢያራ እውነትም ልዩ አይል እንዳለው ቆጥረውታል ፡ በርግጥ በዋሻው ውስጥ ትልቅ ጀኔረተር አለ ፡ነገርግን ለዛ ጀነሬተር ፡ነዳጅ ከየት መጥቶ ነው በሆነ ታምር ካልሆነ በስተቀር ፡ብለው ፡አስበዋል ፡አድማስ የተባለው ይዟቸው የመጣው የአቢያራ ታዛዥ ፡ ሁለቱ ጓደኛማቾች ፡ስላመኑ ደስ ብሎታል ፡ ምክንያቱም ፡ እነሱም እንደ ጓደኛቸው ፡መሳይ ፡ደረቅ ፡ቢሆኑ ኖሮ ፡ አቢያራ ፡ ምንድነው ፡ያመጣህብኝ ፡ብሎ ፡እንደሚቀጣው ፡ያውቃል ፡ መሳይንም ፡ቢሆን ፡ጊዜ ፡ወስዶ ፡ መስመሩ ውስጥ ፡እንደሚያስገባውና ፡ለአቢያራ እንደሚያሰግደው ፡ ተማምኗል ፡ ለዚህም ፡ነው ፡ መሳይን ፡ወዳስቀመጠበት ፡የዋሻው ፡ክፍል ፡ ዝር ፡ሳይል ፡ለሁለት ፡ቀን ፡የተወው ፡ ለመሳይ ፡የሚበላ ነገር እንኳ ፡አልሰጠውም ፡ ይህ ፡ኡኔታ ፡መሳይን ፡እንደሚቀይረው ፡አስቧል ፡ ,,,,,,,አቢያራ ፡ የግሌ ነው እኔ እስካልፈቀድኩ ድረስ ፡እንዳትገቡ በሚለው ፡ ሰፊ የዋሻው ፡ክፍል ፡ውስጥ ፡ ተቀምጦ ፡ የተለያዩ ድምፆች እያወጣ ሲጮህ ፡ሲያጓራ ይሰማል ፡ በዛች ክፍል ጥግ ጥጉን የአቢያራ ቀያይ የለበሱ ቀያይ ሴቶቹ ቆመው አብረው በቀስታ የሱን ቃል ይደግማሉ ፡ አድማስ ፡መስፍን እና ዳንኤልን ይዞ ፡በዋሻው ፡ውስጥ ለውስጥ እየተጓዘ ፡አካባቢውን ያስጎበኛቸዋል ፡ እነመስፍንን ያስገረማቸው ነገር ግን በዋሻው ፡በስተጀርባ ፡ያለው የአትክልት ስፍራ ነበር ፡ በጣም ፡ሰፊ በጣም ውብ ፡ ነበረ ፡ በስተቀኝ በኩል የተለያዩ ፍራፍሬዎች ያሉበት ዘፎች ፡ በስተቀኝ ፡ የሚያማምሩ ፅጌሬዳ አበባዎች ፡ አረንጓዴ ሰር እንደምንጣፍ ፡የተዘረጋበት ፡ ቦታ ፡ ከሚያስጨንቀው ፡ዋሻ ፡በስተጀርባ ፡ ማንም ሊያውቀው ፡የማይችል ፡የተለየ ስፍራ ፡ መስፍንና ዳንኤል አፋቸውን ከፍተው ፡ሲያስተውሉ ፡ አድማስ ፡ይሄን ፡ስፍራ የሚያሳያቸው ፡ለአባታችን ፡አቢያራ ፡ስለታመናቹ ነው ፡ አደራ ስእተት እንዳትሰሩ ብሎ ፡አስጠነቀቃቸው ፡ ሁለቱም ቃል ገቡ ፡ እንዲሁም ፡ ያንን የአትክልት ፡ስፍራ ሲያዩ ፡የአቢያራ ታምረኝነት ፡ ከፍ ፡አለባቸው ፡ እናም ፡ጓደኛቸው ፡ ከሚሞት ፡ለአቢያራ ፡እንዲታዘዝ ፡ሊያሳምኑት ፡ፈለጉ ፡ አድማስ ፡ግን ፡ከሱ ጋር መገናኘት ፡የሚችለው ፡እሱ ብቻ ፡መሆኑን ፡አስጠንቅቆ ፡ስለነገራቸው ፡ በቅሬታ ፡ተቀበሉት ፡ ,,,,,,, አቢያራ ፡ ብዙ የጥንቆላ ቃላቶችን ፡ሲያወራ ፡ቆይቶ ፡ በራሱመንገድ ፡የራሱን ፡እምነት አመስግኖ ፡ዝም ፡አለ ፡ ወደ ፀጥታው ፡ሲመለስ ፡ሴቶቹ ፡ አጎንብሰው ፡ ለአቢያራ ፡ክብር ከሰጡ በዋላ ፡ በየፊናቸው ፡በዋሻው ፡ውስጥ ፡ተበተኑ ፡ መስፍን ፡ሁለቱ ሴቶች ፡ወደነሱ አቅጣጫ ሲመጡ ፡ በመገረምና ፡በአድናቆት ፡ተውጦ ፡አስተዋላቸው ፡ አድማስ ፡ከሁለቱ ሴቶች ፡አንዷ ፡ኤሊያታ ናትና ፡ የመስፍን ፡አስተያየት አልተመቸውም ፡እና በማስጠንቀቅ አይነት ገላመጠው ፡መስፍን ፡አይኑን ፡ሰበር ፡አደረገ ፡ በእርግጥ ፡በዕድሜም ፡ቢሆን ፡ከነመስፍን ፡ ጋር አይገናኙም ፡ ነገርግን ልዩ ናቸው ፡ ቀያይ ፡ቀሚሳቸው ፡ ከዋሻው ፡ወጥተው ፡በአትክልቶቹ ስፍራ ሲገኙ ፡ የተለየ ቁንጅናቸውን ፡አወጣባቸው ፡ ዋሻው ፡ውስጥ ፡ግን ፡ ከቁንጅናቸው ፡ይልቅ ፡ፍርሃትን ነበር ፡የሚያጭሩት ፡ አድማስ ፡እንደነገራቸው ፡ደሞ ፡ በፍፁም ፡ከዚ አካባቢ እርቀው ፡የትም ፡ሄደው ፡አለማወቃቸውን ፡ነው ፡ እናም ፡ ሰለማያውቁት አለም አዘኑላቸው ፡ ,,,,,,, በዋሻው ፡ጨለማ ክፍል ውስጥ ፡ መሳይ በረሃብ ፡እየተሰቃየ ፡ነበር ፡ ሁለት ቀን ፡በሙሉ ፡ምግብም ፡ሆነ ውሃ የሰጠው ፡ሰው ፡የለም ፡ እናም ፡ በመጣራት ፡ ድምፁ ሰልሏል ፡ "እባካቹ እናንተ ሴጣኖች የሚበላ ስጡኝ እባካቹ ከዚ አስወጡኝ ፡ "እያለ መጣራቱን ፡ በቀጥልም ሰሚ ግን አላገኘም ፡ የመሳይን ፡ የሰለለድምፅ ፡ የሰማችው ፡ በዋሻው ፡ውስጥ ለውስጥ ፡ ስትዘዋወር ፡የነበረችው ፡ኤዛ ፡ ድንገት ቆም ፡ብላድምፁን ፡ለመስማት ፡ሞከረች ፡"እባካቹ ፡ አታሰቃዩኝ ፡ መምቴ ነው ልቀቁኝ ፡ አአአአ" ኤዛ ድምፁን ወደሰማችበት ጨለማው ክፍል ፡ ከፍታ ገባች "ማነው እባካቹ የሚበላ "አለ መሳይ
"እሽሽሽሽሽ "አለች ኤዛ
"ማነሽ እእ ባክሽ ፡ውሃ ስጪኝ ፡ "አላት
"ድምፅ አታሰማ የምትፈልገውን እሰጥሃለው ፡እሽሽሽሽ"አለች
"እሺ ቶሎ በይ " ብሎ መሳይ የማትታየውን ሴት ፡ጠየቀ ፡ እሺ ብላው ፡ወጥታ ፡ተሰወረችበት ፡ መሳይ ፡በተስፋ ጠበቀ ፡ የዛን ጠንቋይ ፡ሴቶች ፡ አላመናቸውም ፡ በመራቡ ለመነ እንጂ ፡ ቆንጆ ፡ሴጣኖች ፡እንደሰበሰበ ፡ነው ፡የሚሰማው ፡ መሳይ ፡ ከአን ፡አሁን ፡ውሃ ይዛልኝ ፡ትመጣለች ፡ብሎ ፡የሚጠብቃት ፡ሴት ፡ ቀረችበት ፡ ከቆይታ፡ በዋላ ግን ፡ ከባባድ ፡እርምጃዎች ፡ይሰሙት ፡ጀመረ ፡ ከርምጃው ፡በባሰ ፡ደግሞ ፡የሚወጣው ፡ድምፅ ፡ይረብሻል ፡ ይሄሁሉ ጋጋታ ወደሱ ፡እንደሆነ ፡ ተሰማው ፡ የቀድሞ ፡ፍርሃቱ መጣበት ፡ ጋጓጓጓጓጓጓ አሆሆሆሆ እርምጃ አስፈሪ ድምፅ ፡ መሳይ ፡ ወደጥግ ፡በመሄድ ፡ እራሱን ሰበሰበ .........
✍ ሙና መሀመድ
ይቀጥላል...

👍28🤔3
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
ታሣሥ ገብቷል » የአልፕስ ተራሮች በበረዶ ተሸፍነዋል ይህ የአየር ሁኔታ ለግሮነብል ከተማም ተረፋትና ቅዝቃዜ አመዳይና ድጥ ብቻ ሆናለች በአንዳንድ መንገዶች መኻል ለመኻል የሚያልፉት ቦዮች ያለ ወትሮአቸው ጠቁረዋል"ዐበቅዝቃዜው የተላቀቁት ሰዎች በጐዳናዎቹ ውር ውር ይላሎ " ወይዘሮ ሳቤላ ቬንን ከዚያ ብዙ መስኮቶችና በርች ካሎት ባለ ሰፊ ምድጃና ባለ ሰፊ የጢስ ማውጫ የፈረንሳይ መኝታ ቤት ወስጥ ከእሳቱ አጠገብ ተቀምጣ ትንቀጠቀጣለች ብርዱ ከየአቅጣጫው ይገባል " የበሽተኛ የራስ ቆብ ደፍታ ወፍራም የሱፍ ያንገት
ልብስ ደርባ ሰውነቷ ያለ ማቋረጥ ይንዘፈዘፋል ከእሳቱ በጣም ከመጠጋቷ የተነሳ ልብሷ በፍንጣሪው እንዳይቃጠል የፈራችው ሠራተኛዋ ከአጠገቧ ሁና ትጠብቃታች " ከሚንጣጣው ዕንጨት ፍንጣሪ ሲወረወር ብዙ ጊዜ እየዘለለች ትከለክልላት ነበር " ለሳቤላ ግን ምንም አልመሰላትም " የድንጋይ ሐውልት መስላ በአንድ አቅጣጫ እንደ ተቀመጠች አካሏ ከመንቀጥቀጡ በቀር አትነቃነቅም።
ጥቂት ሊሻላት የጀመረ ትመስላለች አንዳንድ ጊዜ ቀና እያለች መቀመጥ
ይዛለች ብዙ ቀን ታማ ሰንብታ አሁን ትኰሳቱ በረድ እያለላት ነው " ሠራተኞቿ
ግን እንደ ምንም ብላ ተነሥታ ብትንቀሳቀስ ሊሻላት እንደሚችል እርስ በርሳቸው ይንሾካሾካሉ " እሷም ከንፋሳሙ ክፍል ቁጭ ማለት ችላለች ነገር ግን ከመኝታ ቤቷ ወጣች አልወጣች ምንም ደንታ አልነበራትም ።
ዛሬ ቀን መቼም የእህል አምሮቷ ሙቷል ቀደም ብላ ራቷን ቀመሰችና ከባለ ድጋፍ ወንበርላይ ተቀምጣ ስታንጐላጅ ከውጭ የሠረገላ ድምፅ ሰምታ ነቃች።
“ ማነወ ? አለቻት ሞግዚቷን "
“ ጌቶች ናቸው .. እሜቴ! ፒየርም አብሮ አለ " እኔ እመቤቴን ብዙ ጊዜ እየመላለስኩ አይጨነቁ ጌቶች ይመጣሉ ስልዎ የነበረው አሁን እውነት ሆነ " አለመሳሳቴን ዐወቁት ? "
ወይዘሮ ሳቤላ ኮስተር ያለ ቆራጥ ገጽታ በፊቷ ተሰራጨ " ለዚህ አሁን ለመጣ ሰው በፊትም ሆነ አሁን ያልተጨነቀችለት መሆኗን የሚናገር ይመስል ነበር "ትዕግሥትና እርጋታ አይክዱኝ ! አሁን ነው እንግዲህ አለች ሳቤላ ለራሷ "
“ ጌቶች በጣም አምሮባቸዋል ”አለች ሠራተኛይቱ » በፎቅ መስኮት ቁማ ወደታች እየተመለከተች - ከሠረገላ ወረዱ እግራቸውን ከመሬት መታ መታ አደረጉ አለች
መውጣት ትችያለሽ ሱዛን” አለቻት ሳቤላ "
ሕፃኑ ቢነቃስ እመቤቴ ?
እጠራሻለሁ ”
ልጅቱ በሩን ዘግታ ወጣች ሳቤላ ተቀምጣ ሕፃኑን እየተመለከተች ትዕግሥት
እንዲሰጣትና እንዲያስችላት ራሷን በራሷ ስትመክር በሩ ብርግድ ብሎ ተhፈተ
ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ገባና ሰላም ሊላት ተጠጋት " መንፈሷ ተመርዞ ንዴቷ
ተቀጣጥሎ ድምጿን እንኳን ሳይቀር አሰለለውና ጮኻ መናገር ስላቃታት እንዳይቀርባት እጁዋን በማራገብ ከለከለችው ከፊት ለፊቷ ተቀምጦ የሚነደውን ዕንጨት
በጫማው እየገፋ ሳይመጣ የቆየው የሥራ ብዛት ከከተማ ሊያስወጣው ባለመቻሉ መሆኑን ነገራት "
አሁን ምን ልታደርግ መጣህ ?
'' ለምን መጣህ ?'' አለ የሷን አባባል ደገመውና “ እንዴ ! በዚሀ አሠቃቂ ቅዝቃዜ ይኸን ሁሉ አገር አቋርጦ ለመጣ ሰው ውለታው ይኸው ነው ማለት ነው?
እኔን በደስታ የምትቀበይኝ መስሎኝ ነበር . .ሳቤላ ”
“ ሰር ፍራንሲዝ” አለችው በሚያስደንቅ ያልተጠበቀ እርጋታ " እስከ መጨረሻው በዚሁ ዘለቀችው " የመልኳ ቶሎ ቶሎ መለዋወጥና ' የልቧን አመታት ለመቀነስ ይረዳት ይመስል አሁንም አሁንም ደረቷን በእጇ ስታስደግፍ ንዴቷን ለመቆጣጠር ከስሜቷ ጋር ምን ያህል እንደምትታገል ይታወቅባታል “ሰር ፍራንሲዝ
መምጣትህን ለአንድ ምክንያት በደስታ እቀበለዋለሁ በደንብ መግባባት አለብን ስለዚህ እዚህ በመገኘትህ በጣም ደስ ብሎኛል " ትንሽ ጠንከር ስል ልጽፍልህ ፈልጌ ነበር : ግን ያንተ መምጣት ከድካም አዳነኝ ያለ ገደብ ያለ ድብብቆሽ ያለምንም ድለላና ማታለል ግልጽልጽ አድርጌ መወያየት እፈልጋለሁ " አንተም
እንደዚሁ የኔን ምሳሌ እንድትከተል እጠይቅሃለሁ
ምን ማለትሽ ነው ?
“ግልጽ አድርጎ መነጋገር በአሁኑ ንግግራችን ግልጽ የሆነ እውነት መኖር
አለበት ”
“ አሳብሽ አልባኝም "
ምንም ሳንሸፋፍንና ሳንደባብቅ ሐቁን መነጋገር አለብን ነው የምልህ" ባለፈው ሐምሌ ስትሔድ በጋብቻችን በወቅቱ እንደምትመለስ ቃል ገብተህልኝ ነበር "
በወቅቱ ስል ምን ማለቴ እንደሆነ ታውቃለህ ነገር ግን . . .
“ በርግጥ ቃል ስገባልሽ ለመመለስ አስቤ ነበር ነገር ግን ለንደን እንደ ገባሁ
በሥራ ተዋጥኩ መምጣት አልቻልኩም አሁንም ቢሆን አጣዳፊ ሥራ ትቸ ስለ መጣሁ ከአንድ ሁለት ቀን የበለጠ አብሬሽ አልቆይም
“ እምነትህን እያፈረስክ ነው " ቃሎችህ የቅጥፈት እንጂ የእውነት ቃሎች አይደሉም ለጋብቻው በወቅቱ ለመመለስ አልፈለግህም : ከመሔድህ በፊት እንዲፈጸምም አልፈሰግህም
የምን ቅዠት ነው ከልብሽ የገባው !” አለ ፍራንሲዝ ሌቪሰን "
“ አንተ ከሔድህ ከትንሽ ጊዜ በኋላ” አለችው በረጋ አነጋገር “አንዷ ሠራተኛ ልብሶችህን ስታደራጅ ከአንዱ ኪስህ ደብዳቤ አግኝታ ሰጠችኝ ቀኑን
ሳየው ወደ ለንደን ነተነሣህ ለት ከደረሱክ ደብዳቤዎች አንዱ መሆኑን አወኩት
ደብዳቤው ፍቺው በሕግ መፈቀዱን የሚገልጽ ነበር ። ያን ጊዜ ባታታልለኝ ገና
ላልተወለደው ሕፃን ስል ብቻ የጓጓሁለት ተስፋ ከንቱ ከከንቱም የባሰ መና መሆኑን ብትነግረኝ ኖሮ ደግ ነበር ።
“እኔ በዚህ አላሰብኩትም።ያለመጠን ተናደሽ ሳይሽ ምንም ቁም ነገር ምንም ምክንያት ቢነግሩሽ በጥሞና የምታዳምጪ አልመሰለኝም
በዚህ አነጋገሩም የልቧ አመታት ጨመረ እሷ ግን እንደ ምንም ብላ ስሜቱን
ግታችው ።
“ የሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ሚስት ለመሆን መመኘቴ በቂ ምክንያት ያለው አልመሰለህም?
በዚህ ጊዜ የሚነደውን ዕንጨት በጫማው ተረከዝ እየመታ ከተቀመጠበት
ብድግ አለና ፡ “ አየሽ ሳቤላ . . .በኔ ደረጃ ላለ ትልቅ ሰው አንዲት የፈታች ሴት ማግባት ተመሳሳይ የሌለው መሥዋዕት መሆኑን ማወቅ አለብሽ
“ እኔ እኮ መሥዋዕቱን እንድትከፍል የጠበቅሁህ ወይም የተመኘሁህ ለራሴ
ብዬ እንዳልሆነ ያኔም ነግሬህ ነበር ። ነገር ግን ሳይሆን ቀረ ልጁም የኃጢአትና የውርደት ወራሽ ሆነ ። ያውልህ እዚያ ተኝቷል
ሰር ፍራንሲዝ በጣቷ ወዳመለከተችው አንገቱን ዞር አድርጎ ሲመለhት
ከአልጋው ጐን አንድ የሕፃን መኝታ አየ ሔዶ ለማየት እንኳን አልሞከረም።
“እኔ እንግዲህ የአንድ ጥንታዊ ባለማረግ ቤተሰብ ወካይ እንደ መሆኔ
መጠን ” አላት በዚያ ባለፈው የልበ ቢስ ሰው ንግግሩ ተጸጽቶ ይቅርታ የሚጠይቅ በመሰለ ድምፅ አንችን ሚስት ባደርግ ቤተሰቤን ሁሉ አስቀይማለሁ ስለዚህ ...
“ ቆይ” አለችና ሳይጨርስ'' ግድ የለህም የማያስፈልግ ምክንያት ለመፍጠር ራስህን አታስጨንቅ ያሁኑ አመጣጥህ እኔን ሚስት ለማድረግ ቢሆን ኖሮ
ዛሬውኑ እንድንፈጽም የምትጠይቀኝ ቢሆን ኖሮ ሥርዓት አስፈጻሚ ቄስ ይዘህ መጥተህ ብትሆን ኖሮ ከምንም ቁም ነገር አልቈጥረውም ነበር የልጁ ጉዳት አይመለስም ስለራሴ የሆነ እንደሆነ ከአንተ ጋር እንድኖር ከመገደድ የከፋ ፈተና
ያ ገኘኛል ብዬ አላስብም።”
በኔ እንደዚህ ያለ ጥላቻ ካደረብሽ ምንም ማድረግ አይቻልም " ሆኖም
እንድክስሽ አጥብቀሽ በመለመን ከፍተኛ ሁከት ያኔ ፈጥረሽብኝ ነበር ” አላት አሁን አግባኝ ስላላለችው በሆዱ እየተደሰተ።

👍14👎1😁1
ራሷን ነቀነቀች “ አንተ ባለው ዐቅምህ ሁሉ የምታደርገው ካሣ ዓለም በመላ የሚፈጥረው ማንኛውም ካሣ ቢሆን ወንጀሌን አያፀዳውም ውጤቱም
እስከ መጨረሻው ከራሴ ላይ አይወርድም ”
“ አዬ ወንጀል ! ሴቶች ስትባሉ ስለ ወንጀሉ ማሰብ የነበረባችሁ ገና ሳይሆን ነበር ።
“ አዎን ! እንደኔ ከስሕተት ሊወድቁ ለሚችሉ ሁሉ ይኸ እንዲገለጽላቸው
እመኝላቸዋለሁ”
ይህ አነጋገርሽ እኔን ለመሳዶብ ያመጣሽው ከሆነ ተሳስተሻል” አለ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ቈጣው ከቈጥጥሩ ውጭ ሲሆንበት። ንግግሩ የማንንም ስሜት ቢነካ ደንታ በሌለው ልማዱ እንደምትዪው ወደ ስህተት ተገፋፍተሽ መግባትሽ
በባልሽ ላይ ያሳደርሽው የቅናት ቁጣ የመራሽን ያህል የኔ ማባበል አልገፋፋሽም " ይኸም የተሳሳተ ፈር ተከትለሽ የፈጸምሽው ስሕተት ነው
ምን ለማለት እንደ ፈለግህ አልገባኝም " የምን የተሳሳ ፈር ነው?
ስለ ባልሽና ስለዚያች የሔር ልጅ'ያለምንም ተጨባጭ ነገር ቅናት ያዘሽ” ካርላይል ስለዚያች ልጅ ምንም ሐሳብ የነበረው አይመስለኝም " በሁለቱ መካከል አንድ የፍቐር ሳይሆን የሌላ ሥራ ምስጢር ነበር ስለዚህ ያ ሁሉ የምስጢር ግንኙነታቸው ምክራቸው በዚሁ ምክንያት ብቻ ነበር።
ፊቷ ደም መሰለ እሱ ደግሞ ዝግ ብሎ ነበር የሚናገር " ሲናደድ ይኸው
ነበር ጠባዩ ዝግታው እየጨመረ ሲሔድ የኃይለ ቃሉ አንጀት ቆራጭነትም በዚያው መንገድ እየጨመረ ይሔዳል ።
“ ግን ሰር ፍራንሲስ..ያኔ ለኔ የነገርከኝ ሌላ ታሪክ ነበር።
ሰር ፍራንሲዝ ሣቀና በፍቅርና በጦርነትጊዜ ማንኛውም ስልት ትክክለኛ ነው።
ምንም መልስ ለመስጠት አልቻለችም " ለጊዜው ዝምታ ሰፈነ"ሁለቱም ጸጥ
ብለው ቆዩ "
“ ያንን ትንሽ ነገር ማን ብለሽ ጠራሽው ለመሆኑ ?
“ ፍራንሲዝ ሌቪሰን ” አለችው
“ ስንት ቀን ሆነው ? መልኩስ እኔን ይመስላል ...ሳቤላ ?”
“ ነሐሴ ሲያልቅ ነው የተወለደው " በውነት ይህ ልጅ በአስተሳሰብ አንተን
መስሎ የሚወጣ ከሆነ ' ማሰብም መናገርም ሳይችል ቢሞት እመርጣለሁ"
“ አሁን ለመሆኑ መኝታዬ ተዘጋጅቶ ይሆን
አልተዘጋጀልህም " ይህ ቤት እኮ አሁን የኔ ነው በስሜ አዛውሬዋለሁ
ከእንግዲህ ወዲያ አንተ ከዚህ ማረፊያ ልታገኝ አትችልም " በል ይልቅ እንደ ልቤ ለመነሣት ጉልበት ስለሚያንሰኝ ፈቃድሀ ቢሆን እሱን ሻንጣ አቀብለኝ "
ሌቪሰን ተነሥቶ ዕቃውን ከነበረበት ጥግ ሔዶ አንሥቶ አመጣላት ከዚያ
ቁልፍ አውጥታ ' ሻንጣውን ከፍታ፡“የዛሬ ወር እነዚህን በፖስታ ልከሀልኝ ደርሰውኝ ነበር ” አለችው "
“ አንቺ ግን ተቀብለሽ እንኳን አታመሰግኝም ” አላት በፌዝ ድምፅ
“ዐርባ ፓውንድ አልነበረም የላክልኝ?”
እንደዚያ መሰለኝ ”
በል እንድመልስልህ ፍቀድልኝ : ቁጠራቸው !”
“ለምንድነው የምትመልሽልኝ ?
ከእንግዲህ ወዲያ ካንተ ጋር ምንም ዐይነት ግንኙነት አይኖረኝም ያንተን
ምንህንም አልፈልግም " አሁን የዘረጋሁትን ክንዴን አታሳምመኝ " እንካ
ተቀበለኝ።
“ ግንኙነታችን እንዲቋረጥ ፍላጎትሽ ከሆነ ይሁንልሽ እውነቱን ለመናገር የኔና ያንቺ ኑሮ የድመትና የውሻ ኑሮ ስለሆነ ከዚህ ከንዝንዝ ኑሮ የተሻለ ማስተዋል የተመላበት ውሳኔ ነው። ግን ያንቺ ውሳኔ እንጂ የኔ አለመሆኑን አስታውሺ "
ቢሆንም አንቺ እየተራብሽ ዝም ብዬ የምመለከት አይምሰልሽ ፤እኔና አንቺ ተስማምተን የምንወስነውን ገንዘብ በየመንፈቁ እልክልሻለሁ » ስለዚህ . .
" እባክህ ይብቃህ ዝም በል ! ኧረ ለመሆኑ እኔ ምን መሰልኩህ ?”
እንዴ ምን ማለትሽ ነው?ሀብት የለሽ ዕርዳታ ካላገኘሽ እንዴት መኖር
ትችያለሽ ?”
“ እኔ ካንተ አልቀበልም ። ዓለሙ በሙሉ ቢጥለኝ ከባዕዳን ዕርዳታ ማግኘት
ቢሳነኝ ወይም የዕለት እንጀራን እንኳን ሠርቶ ማግኘት ቢያቅተኝና በሕይወት መኖር ግን አስፈላጊ ቢመስለኝ ' ካንተ ከምረዳ ችግሬን ለባሌ ባመለክት እመርጣለሁ ይህ አባባሌ የያዝነውን ርዕስ እዚህ ላይ ማቆም እንዳለብን ሊያሳምንህ
ይግባል ” ” ለጠቅ አድርጋ
“ አዎን ፡ ለቀድሞዉ ባሌ” አለችው ለፌዙ መልስ
“ለራስሽ ባትፈልጊም ለሕፃኑ መቀበል አለብሽ " የልጁ ጉዳይ የኔ ሐሳብ ነው። ስለዚህ ጥቂት መቶ ፓውንዶችን እሰጥሻለሁ "
ሰውየውን በንግግሩ የደበደበችው ይመስል እጆቿን ታማታ ጀመር ” “አሁንም ወደፊትም አንዲት ቤሳ እንኳን አልቀበልም ። በልጁ ስም ገንዘብ ለመላክ ብትሞክር ተቀብዬ ባቅራቢያ ከሚኘው ወንዝ ውስጥ እጥለዋለሁ ።ኧረ እኔ ማን መሰልኩህ ? አለች ከተቀመጠችበት ብድግ ብላ ። አንተ በዓለም ፊት እንድዋረድ ብታደርግም ፡ አሁንም የሎርድ ማውንት እስቨሮን ልጅ ነኝ እኮ ! " አለችውና ንዴቷን ለመቈጣጠር እየተጣጣረች ተቀመጠች "
አጥብቃ ስትይዘው ጊዜ የመለሰችለትን ገንዘብ ተቀብሎ ከቦርሳው ከተተ።
“ አሁን በፈጠረህ ወደ ኢንግላንድ ስትሔድ የተውካቸውን ልብሶችህን ዛሬውኑ እንዲወስድልህ ፒየርን እዘዘው ። እንግዲህ ሰር ፍራንሲዝ .... ጨርሰናል
ብዬ አምናለሁ ፣ ይብቃን ።”
“ ከእንግዲህ ዕርቅ የማይገባን ጠላቶች ሁነን እንቀራለን ማለት ነዋ?
“እንደማንተዋወቅ እንሆናለን” ብላ አረመችውና፡ “በል ደኅና ሁን” አለችው
ባይሆን የጅ ሰላምታ እንኳ አትሰጭኝም ሳቤላ ?”
አዎን ልጨብጥሀ አልፈቅድም ”
እንዲህ ሆነው ተለያዩ ። ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ሳቤላ ከነበረችበት ክፍል ወጥቶ
ከፊቱ የነበሩትን የቤት ሠራተኛ ሁለቱንም ጠርቶ ወደ አንድ ራቅ ያለ ክፍል ወሰዳቸውና : ' እመቬቲቱን ገንዘብ ብላችሁ እንዳታስቸግሯት " ብሎ የአንድ ዓመት ቅድሚያ ደሞዝ ከፈላቸው ። ከዚያም ወደ ቤቱ ጌታ ዘንድ ሔዶ ለሱም ተመሳሳይ ቃል ነግሮ የአንድ ዓመት ቅድሚያ ኪራይ ከከፈለው በኋላ ከአንድ ሆቴል ራት
አዘዘና ከሚያበሳጨው ጭቅጭቅ በቀላሉ በመገላገሉ ዕድሉን እያመሰገነ የዚያ ዕለት ሌሊት ከፒየር ጋር ወደ ኢንግላንድ ተመለሰ
ሳቤላ ከአንድ ቦቷ ሳትነቃነቅ ከእሳቱ ተጠግታ ብቻዋን ተጎልታ አመሸች ሠራተኛዋ ወደሷ ቀርባ ይህን ያህል ማምሸት ለጤናዋ እንደማይበጃት ብትነግራት ከነምክሯ ወደ ሌላው ክፍል ዘወር እንድትልላት አዘዘቻት
ጸጸቷ እንደዚያን ዕለት ምሽት ግልጽ ሆኖ ተሰምቷት ያሁኑና የወደፊቱ
ሁኔታዋም ጭልም ብሎ አንዣብቦባት አያውቅም " አስከፊው አድራጎቷ ቁልጭ
ብሎ ታያት ። ማዕረጓንና መልካም ስሟን ጣለች ተንግዲህ ወዲያ አሷና
ጥገኞቿ ሚበሉት እንጀራ ለሚለብሱት ጨርቅ
ለሚጠለሉበት ጣራ
ሠርታ ማፍራት የሚኖርባት ወንዶች የሚያዝኑላት ሴቶች የሚሽማቀቁባት
አለሁልሽ ባይ የሌላት የተተወች የተጣለች ችግረኛ ፍጡር ሆናለች ከናቷ
ወይም ካባቷ ያኘቻቸውና ከኢስት ሊን ያመጣቻቸው ጥቂት የወርቅ ጌጦች ነበሯት ሚስተር ካርላይል ከሰጣት ውስጥ አንድም አልነካችም አሁን ጌጦቹ እስኪያልቁ ድረስ እየሽጠች ትጠቀማለች ከዚህያ የምታገኘው ገንዘብ በጥንቃቄ የተጠቀመችበት እንደሆነ ካሥራ ሁለት እስከ ዐሥራ ስምንት ወር ሊቆያት እንደሚችል አሰላችው ። ከዚያ በኋላ ላለው ግን አንድ የገቢ ምንጭ መፈለግ ሊያስፈልጋት ሆነ
ለጊዜው የታያት ሕፃኑን ከሞግዚት ጋር ትታ ስሟን ለውጣ ከአንድ ጀርመን ወይም የፈረንሣይ ቤተሰብ የልጆች አስተማሪ ሆና መቀጠር ነበር "

👍9❤1