አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ራሴው_ማበዴ_ነው
:
#ክፍል_አራት
:
ደራሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
:
....“ልትነግሪኝ የምትፈልጊው ነገር አለሽ?”
“ማለት? ስለምን?”
“እኔ እንጃ ቦስ አባትሽ እዚህ ቢሮ እግራቸው ከረገጠ ቀን ጀምሮ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ፍፁም ልክ አይደለሽም። ያዘንሽ ያዘንሽ ፣ የተከፋሽ ፣ የሆነ ነገር ያደከመሽ አይነት ነው የምትመስዪው።” ሲለኝ ለቅፅበት ያደከመኝን ሁሉ ልነግረው ዳድቶኝ ነበር።
ራሴን አውቄ ሀላፊነትን መሸከም ከቻልኩበት ጊዜ ጀምሮ ለሚያውቀኝ ሰው ወይም በምንም አጋጣሚ ቢሆን ድጋሚ ላገኘው ለምችለው ሰው ስለራሴ ተናግሬ አላውቅም። ነገር ውስጤ ተቆልሎ የሆነ ዓይነት እምቅ ሀይል ሆኖ እንደ ኒውክለር ሊፈነዳ የመሰለኝ ወቅት ላይ አንድ ሶስቴ ከዛን ቀን በኋላ ፊታቸውን አይቻቸው ለማላውቃቸው ሰዎች የተሰማኝን ዝርግፍግፍፍፍ አድርጌ ከመፈንዳት ተርፊያለሁ። አንዷ ‘ነገ አረብ ሀገር ልሄድ ነው።’ ያለችኝ ፀጉር ቤት ያገኘኋት ሴት ናት። ፀጉራችንን ተስርተን ስንወጣ ለማኪያቶ ካፌ ተቀምጠን ያወራኋት። ሁለተኛው ናዝሬት ለስራ ሄጄ ያረፍኩበት ሆቴል ብቻዬን ራት ስበላ አይቶኝ ‘እንብላ’ ባለኝ ሰበብ ያወቅኩት ጎልማሳ ነው። (ሊበላኝ(ሊያባላኝ) ባሰበ ምሽቱን የተበላው።) ሶስተኛው ከቂሊንጦ ስመለስ ሊፍት የሰጠኝ ሽማግሌ ነው። አንዳቸውንም ከዛ በፊትም ሆነ ከዛ በኋላ አይቻቸው አላውቅም። ስሜን አያውቁም ፣ ማን መሆኔን ፣ የት መሆኔን አያውቁም……… ሳወራላቸው ነገ ሲያዩኝ ምን ይሰማቸዋል? አልልም…… ሳለቅስ ወይ ስዝረከረክ ይዳኙኛል አያሰጋኝም…… በነሱ ፊት መሸነፌ ወይ ተስፋ መቁረጤ ድክመቴ አይሆንም። …… ለምንም ግድ የለኝም። ልግባቸው ላደናግራቸውም ጉዳዬ አይደለም። የተሰማኝን በሙሉ ዘርግፌ ተንፍሻለሁ።
ለሚያውቀኝ ሰው እንደዛ አላደርግም። ለሚያውቁኝ ሁሉ(ከቤተሰቦቼ ውጪ) ያቺ አልቅሳ የማታውቀው ፣ብርቱዋ ፣ ደካማ ጎኗን ማንም የማያውቅባት፣ መጠቃቷን ማንም የማያውቅላት… … የጉብዝና ምሳሌ የሆነችዋን ራሔል ነኝ።
“ፍትህ አንተ ደግሞ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ስራህን እርግፍ አድርገህ ትተህ እኔን ስራ አድርገኸኛል። am fine!! በቀን አስሬ ቢሮዬን የምትከፍተውን ነገር አቁም። please?” አልኩት። ብዙ ቀን ብዬዋለሁ ሰበብ እየፈለገ በጥያቄ ይወጥረኛል እንጂ።
“እሺ። ከፈለግሽኝ ግን አለሁ።” ብሎኝ ቆይቷል። ከቢሮዬ ግን አልወጣም። ከወንበሩም አልተንቀሳቀሰም። ሁሌም የማስበው የኖህ ታሪክ ትዝ አለኝ። ከውሃ ጥፋቱ በኋላ ኖህም ገበሬ ሆነ። ወይንም ተከለ። ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ። …… በድንኳንም ውስጥ ራቁቱን ሆነ ታናሹ ልጁ ካምም የአባቱን እርቃን ባየ ጊዜ ተሳለቀ። በአባቱ ገመና ሙድ ያዘ። ሁለቱ ልጆቹ ያፌትና ሴም ግን እርቃኑን እንኳን እንዳያዩበት አክብረውት ፎጣ በትከሻቸው አድርገው የኋሊት እየተራመዱ የአባታቸውን እርቃን ሸፈኑ… …… ኖህም ካምን ረገመው… ………… ይመስለኛል። ሲመስለኝ ሲመስለኝ……… የካም ነገድ የአክሱምን ልጅ ወለደ…… የአክሱምም ልጅ ልጆች በወንድምና ወዳጃቸው ገመናና ድክመት ሲደነቋቆሉ… … ሲሸረዳደዱ…… አንዱ የአንዱን ድክመት ሲጋለቡ ኖረው ኖረው። የእንጀራ እናቴ አባት ላይ ደረሱ። እሳቸውም ቀንደኛ ሸርዳጅ የሆነች ትውልድ አፈሩ……… ምናምን ምናምን………
የኖርኩት ዘመን የተረዳሁት አብዛኛው ሰው ከትልቁ ስኬትህ ውስጥ እንኳን ምናምኒት የምታክል ውድቀትህን ወይ እንከንህን ይፈልጋል። ካገኘብህ አለቀልህ። ሰማይ ያከለ ስኬትህን የጎመንዘር በምታክል እንከንህ ያጣፋልሃል።
“ፍትህ?”
“አቤት ቦስ?”
“ነገ ሰርጉን ትሄዳለህ እንዴ?”
“አወና!! እንዴ ቆይ ቆይ…… ትሄዳለህ ነው ትመጣለህ? ያ ማለት የእህትሽ ሰርግ ላይ አንቺ አትኖሪም ማለት ነው? ኦ……ኬ …… I think ይሄ ኬዝ ካሰብኩት በላይ ሊመስጠኝ ነው። ምንድነው እሱ?”
“ምንም big deal አይደለም። መሄድ አለመሄድህን ለማወቅ ነው። አበቃ!! የሆነ ታላቅ ግኝት ያገኘህ አታስመስለው።”
“እሄዳለሁ።” ብሎኝ ዓይኖቹን ዓይኖቼ ውስጥ ዘፍዝፎ ስሜቴን ሊጨምቅ ይታገላል።
“መልካም።” አልኩት ድምፄ ከስሜቴ ጋር አብሮ ሲወርድ እየታወቀኝ።
“በቃ?” ብሎ አፈጠጠብኝ ከተቀመጠበት መንጭቆ እየተነሳ። “በቃ ሌላ የምትዪኝ ነገር የለም?”
“እንዴ? ምን እንድልህ ነው የምትፈልገው?”
“አላውቅም!! ብቻ ከቤተሰብሽ ጋር በተያያዘ አንድ እንዳላውቅ የፈለግሽው ነገር ያለ ይመስለኛል። አላውቅም!! ንገሪኝ ማወቅ ያለብኝ ነገር ካለ ከሌላ ሰው ከምሰማው በፊት ንገሪኝ!”
“Excuse me? ከሌላ ሰው ከመስማትህ በፊት?ራስህን ምን ቦታ ላይ ነው የሰቀልከው ባክህ?” ሆኖ እንደማያውቀው እየጯጯህን ነው።
“Sorry boss! ራስን መስቀል አይደለም። እንደጓደኛ……”
“እኔና አንተ ጓደኛሞች አይደለንም! ደግሞ ቦስ አትበለኝ። አለቃህ አይደለሁም። ስም አለኝ። እኔና አንተ የስራ ባልደረቦች ብቻ ነን። የሚያገናኘንም ስራ ብቻ ነው።” ንግግራችን የማያስፈልገውን ያህል ቁጣ እየተቆጣሁ እንዳለሁ ራሴን ስሰማው አውቃለሁ። ግን ቁጣዬ ምክንያቱ ፍትህ ብቻ አልነበረምና መመጠን አልችልም።
“እሺ ጓደኛሽ አድርጊኝ? I mean not just for sayin… … real ጓደኛሽ ልሁን?።” አለኝ ሹክሹክታ በመሰለ ድምፅ እና ከኔ በተቃረነ እርጋታ። ሁኔታዬ ራሴኑ አሳፈረኝ። እሱ ላይ የምጮህበት ምንም ምክንያት የለኝም። ፀጥ አልኩ። ጠረጴዛዬ ላይ በአንድ መቀመጨው እየተቀመጠ
” I know አንቺ በጣም ጠንካራ ሴት ነሽ። ያ ማለት ግን ሰው አያስፈልግሽም ማለት አይደለም። ያንቺን ጭንቀት ማወቄ ላንቺ ያለኝን ቦታ አይቀንሰውም። በምታልፊበት ነገር ሁሉ ውስጥ አልፈሽ እዚህ መገኘትሽ ምን ያህል ጠንካራ ሴት መሆንሽን ያገዝፍብኛል እንጂ።” አለኝ የፍትህ በማይመስል እርጋታና ብስለት።
“ለምን ብለህ ምክንያቱን አትጠይቀኝ። እባክህ ሰርጉን አትሂድ?” ማለት ብቻ ነበር የመጣልኝ ሀሳብ
“እሺ።” አለ እንደዘበት። ከዛም ያልሰጠሁትን እጄን ፈልቅቆ እየማለ “ ይኸው !ቦስ ይቅርታ ራሔል ሙች! አልሄድም። ከፈለግሽ በቤተሰብሽ ኬዝም አልገባም። ያ የሚያስደስትሽ ከሆነ ምክንያትሽንም ማወቅ አልፈልግም። ራስሽ ፈልገሽ እስካልነገርሽኝ ድጋሚ አልጠይቅሽም። ግን አንድ እንድታደርጊልኝ የምፈልገው ነገር አለ!” እያለኝ ስልኬ ጠራ። ከቤት ነው። አንስቼው ስለእማዬ በሰማሁት ነገር እግሮቼ ዛሉብኝ። የብርትኳን ቢላዋ አንስታ ታፋዋ ላይ ሰክታለች። ሰራተኛዋ እየተርበተበተች ነው የነገረችኝ። ስለእማዬ በሰማሁ ቅፅበት ፍትህን ረስቼዋለሁ።
“ምንድነው እሱ? ምንድነው? እናትሽ ምን ሆነው ነው?” አፌ ቃላት መትፋት አቃተው። ምንም አላስፈቀደኝምም። አልጠየቀኝምም። ስልኬን አንስቶ መልሶ ደወለ። ልሄድ ቆሚያለሁ። ግን መንቀሳቀስ ከበደኝ። ከሰራተኛዋ ጋር እያወራ እንደሆነ አውቃለሁ። ግን አልሰማውም። ኮቴንና ቦርሳዬን ሰብስቦ እጄን መንጭቆ ይዞኝ ሲወጣ እግሬን ለመራመድ ማዘዜን ባላውቅም ተከትዬው መኪናው ጋር ደርሻለሁ። በሩን ከፍቶ መኪናው ውስጥ ሲያስገባኝ፣ ስንሄድ፣ ከሰራተኛዋ ጋር ሲደዋወል፣ እቤት ይዞኝ ሲገባ… …… ጆሮዬ ጭውውውውው ይልብኛል። ጭንቅላቴ የሆነ ከባድ ነገር እንደተጫነብኝ ለአንገቴ ከብዶታል።

🌑ይቀጥላል➡️

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ የኔ ምርጦች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ Like 👍👍 እያደረጉ

አስተያየት ካሎ በ @atronosebot አድርሱን
👍8👏1
#የወላድ_አንጀት
:
ሀገር ስታነጥስ፣
ከአንገቷ ፤ጉንብስ!
ከወገቧ -- ቅንጥስ!
ስትል ደፋ ቀና
ታፍጋ ተፋፍና፣
:
እራሱ ለኩሶ
እራሱ ነስንሶ
እራሱው አጢሶ፣
ጡት ነካሹ ልጇ
"ይማርሽ!" ሲል ደርሶ፣
:
አወይ እናትነት፣
አወይ ቅድስና
አወይ የዋህነት!
:
ጨክናም አትጨክን
ችላም አትበረታ
"ያኑርህ!" ትላለች
ባገኘችው ፋታ !!!

🔘በርናባስ ከበደ🔘
👍1
#ራሴው_ማበዴ_ነው
:
#ክፍል_አምስት
:
ደራሲ :-ሜሪ ፈለቀ
:
:
:
...“ራሔል ከዚህ በላይ እናትሽን እቤት ልታቆያቸው የምትችዪ አይመስለኝም። አደገኛ ነው የሚሆነው።”
“ዶክተር በፍፁም ሆስፒታል እንደማልተዋት ቃል ገብቼላታለሁ። አይሆንም!! ታውቅ የለ ምን ያህል እንደምትጠላ?”
“ራሔል እስቲ ተቀመጪ” አለኝ ወንበሩን እያሳየኝ። በእማዬ ምክንያት ከማውቀው ልምድ በዶክተሮች አባባል ‘እስኪ አረፍ በይ፣ እስኪ ተቀመጪ፣ ለመረጋጋት ሞክሪ፣ የቅርብ ዘመድ ነሽ ወይ?… ’ ዓይነት ንግግሮች ‘ ለሚከተለው አሳዛኝ ዜና ተዘጋጂ።’ የሚል አንድምታ ነው ያዘለው። ቅርፍፍፍፍፍ እያልኩ ተቀመጥኩ።
” አየሽ ራሔል በህይወት አንዳንዴ ትክክለኛው ውሳኔ ከባዱ ውሳኔ ይሆናል አሁን እናትሽ ከፍተኛ የህክምና ክትትል ያስፈልጋቸዋል። እእ… … (እንዲህ እ…እ ሲጀምር የሚነግረኝ ነገር ጨንቆታል) እ ራሔል ታውቂያለሽ እናትሽ ከአዕምሮ መታወኩ በላይ ካንሰሩ ጎድቷቸዋል። ብዙ ጊዜ የላቸውም።… ” ምን እያለ እንደሆነ ገብቶኛል። ግን ደግሞ አልገባኝም። ብዙ ምክር አክሎበት እናቴ ከግማሽ ዓመት ያለፈ ጊዜ እንደሌላት ነገረኝ። በህይወት እያለች እንዳትሰቃይ ላደርግላት የምችለው ብቸኛ ነገር አባቴ እንዲያያት ማግባባት መሆኑንም አከለልኝ። …… አልጠየቅኩም። አልመለስኩም። ቢሮውን ለቅቄ ወጣሁ። ፍትህ ውጪ እየጠበቀኝ ነበር። ከትናንት ጀምሮ እዚሁ ነበረ
“ፍትህ ምንም ነገር እንዳትጠይቀኝ።” ብዬው ነበር።
“ምንም ልጠይቅሽ አላሰብኩም።” ነበር መልሱ። እስከአሁንም ስለምንም አልጠየቀኝም። ወደ ስራው እንዲመለስ ደጋግሜ ወትውቼዋለሁ። አልሰማኝም እንጂ ከዶክተሩ ቢሮ እንደወጣሁ ፍትህ ወደነበረበት ሄጄ ወንበር ላይ ዘፍ አልኩ። አጠገቤ ያለው ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳይመቻች አቀፈኝ። ጥሩ ዜና እንዳልሰማሁ ገብቶታል።
“እማዬ መሞቻዋ ደርሷል ተዘጋጂ አለኝ።” ስለው ደንግጦ ለቀቀኝ። “ከስድስት ወር ያለፈ ጊዜ የላትም።”
“እሺ። እሺ በቃ! እሺ” የሚለኝ ከኔ በባሰ ግራ ተጋብቶ የሚለው ጠፍቶት መሆኑ ገብቶኛል። “እሺ በቃ ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን። አንድ መንገድ አናጣም።” ይለኛል።
“አሰቃየሁሽ አይደል?” አለችኝ እማዬ ገና ወደ ክፍሏ ስገባ። ሁሌም ቢሆን መጥፎ ነገር ካደረገች በኋላ ልክ ከቅዥቱ እንደባነነ ሰው ፍፁም ጤነኛ ጭንቅላት ይኖራታል።
“አንቺ ተሰቃየሽብኝ እማ።” እያልኳት ለአፍታ ሞት ለሷ ግልግል መሆኑ በጭንቅላቴ ሽው አለኝ። እንደዛ በማሰቤ ራሴን ተፀየፍኩት። ግን እንዳትሞት የምፈልገው ለሷ ነው ለራሴ? ዘመኗን ከመድሃኒት፣ ከቴራፒዎችና ከቅዥት ጋር በስቃይ እየኖረች ያለች እናቴ እንዳትሞት የምፈልገው ለሷ ስል ነው ለራሴ?
“እማ ፍትህ ይባላል። አንድ ላይ ነው የምንሰራው። ትናንት ሆስፒታል ያደረሰሽ……”
“አስታውሳለሁ። አውቄዋለሁ ልጄ…” አለችኝ ከግርጌዋ ቆሞ ወደነበረው ፍትህ እያየች። “መልካም ልጅ ነህ። በክፉ ሰዓት ባላውቅህ ደስ ይለኝ ነበር።” እያለችው። ወደ ክፍሉ አንድ ሰው ገባ። ድርብብ ያለ ጎልማሳ፤ ልብወለዶች ላይ ያለ ደግ አባት የሚመስል፤ ፀጉሩ እና ፂሙ ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት፤ ቁመቱ ረዥም፤ ቀላ ያለ ፤በለስላሳ ፂም የተሸፈነ ጉንጭ ያለው፤ ደልደል ያለ…… ሰውዬ
“ካስዬ መጣህ?” አለ ፍትህ ከቆመበት ሳይንቀሳቀስ ቀጠለና “ራሔል እሷ ናት። እሳቸው እናቷ ናቸው።” አለው።
“እንዴት ነሽ ልጄ?” ብሎ ሳብ አድርጎ በግዙፍ ሰውነቱ ውስጥ ወሸቀኝ። ፀጉሬን ደጋግሞ እየሳመ ወደ ሰውነቱ አጣብቆ አቀፈኝ።ልል የነበረው ‘ፍትህ የማላውቀውን ሰው እንዴት ይጠራብኛል? ነበር። ደረቱ ላይ በእጆቹ ተከብቤ ላስብ የቻልኩት ግን ‘ይሄን ፍቅር የት ነው የማውቀው?’ የሚለውን ብቻ ነው። ጀርባዬን አይዞሽ እንደማለት፣ አለሁልሽ እንደማለት አሸት አሸት አድርጎ ወደ እማዬ ሄደ። ወንበሩን ሳብ አድርጎ አጠገቧ እየተቀመጠ
“ሽማግሌ ነኝ አንቺን አንቱ አልልሽም። እንዴት ነሽ? እጅሽን ደግሞ እንዲህ አታድርጊው (የጉሉኮሱ መርፌ የተደረገላትን እጇን አንስቶ አስተካክሎ እያስቀመጠላት።) ያብጥብሽና ያምሻል።…………” አኳኋኑ ትናንት አብሯት የነበረ፣ ሲያስታምማት የከረመ ፣ የምታውቀው፣ የቅርብ ወዳጇ ዓይነት እንጂ ዛሬ የሚያውቃት አይመስልም።
“አባቴ ነው።” አለ ፍትህ
ለወትሮው አዲስ ፊት የሚያስደነብራት እማዬ እንኳን እንደምታውቀው ሰው ሁሉ የሚጠይቃትን ጥያቄ ደስ እያላት ትመልስለታለች። እጇን፣ ፀጉሯን የለበሰችውን ጋቢ እያስተካከለ ነው የሚያወራው። “ምግብ መውሰድ ትችያለሽ? ምግብ ከወሰድሽ ስንት ሰዓት ሆነሽ? ምን ባመጣልሽ ደስ ብሎሽ ትቀምሻለሽ? ……… ”
(አንዳንድ ሰው ገጥሟችሁ አያውቅም? ሰውየውን ገና እንዳያችሁት ላትወዱት አትችሉም። አንዳንድ ሰው ደግሞ አለላችሁ ገና እንዳያችሁት አትወዱትም። ጥሩ እያደረገላችሁ እንኳን ይከብዳችኋል።ሰውየውን የከበበው ቫይብ ነው!! ወይ ይስባችኋል አልያም ይገፈትራችኋል።)
ፍትህን ሆስፒታል ከእማዬ ጋር እንዲቆይ እና እኔ አርፌ እንድመለስ የነገረን በማስፈቀድ ዓይነት አይደለም። ትዕዛዝም አይደለም። ብቻ ‘እንቢ’ የሚሉት ዓይነት አጠያየቅ አይደለም። የገረመኝ ግን የእማዬ ከፍትህ ጋር ለመቆየት በደስታ መስማማት ነው።
“ወዴት ነው የምንሄደው?” አልኩኝ በመኪናው እቤት ሊያደርሰኝ ተስማምተን መንገድ ከጀመርን በኋላ
“ወደቤት ነዋ!”
“መንገድ ስተዋል በዚህጋ ነው ቤቴ።”
“ውይይ ………አንቱ ብለሽ አግተለተልሽኝ እኮ።(ዝግንን እያለው) የምንሄደው እኛ ቤት ነው። አሁን እቤትሽ ባደርስሽም አታርፊም። ብትፈልጊም ትናንት የተፈጠረውን ረስተሽ ምንም እንዳልተፈጠረ ልትተኚ አትችዪም።”
“ኸረ እንደውም የማላውቀው አዲስ ቤት እንቅልፍ እሺ አይለኝም። እዛው እቤቴ ይሻለኛል።” ያልኩት ከምሬ ነው። በእርግጥ ቤቴም ብሄድ ሰውነቴን ባሳርፍ እንጂ እንቅልፍ እንደማይወስደኝ አውቃለሁ።
“እስቲ ግድ የለሽም። እንድረስና መተኛት ካቃተሽ ራሴው ቤትሽ አደርስሻለሁ።” ብሎኝ መንዳቱን ቀጠለ።
ክፉ እና ደግ እንዳለየች ህፃን ልጁ እጄን ይዞ እየመራኝ ሳሎን አስገባኝ። ጎኑ ስር ሲያቅፈኝ፣ አንዴ ግንባሬን ሌላ ጊዜ ፀጉሬን ሲስመኝ ፣ እጄን ሲይዘኝ… …… ለእሱ ብዙ ዘመን ሲያደርገው እንደኖረ ሁሉ የተለመደ አይነት ነው። እኔ ያልለመድኩት ነገር ስለመሆኑ ማወቁን እንጃ! ማወቅ መፈለጉንም እንጃ!! እቤቱ እንደገባሁ መብላት መፈለጌን አልጠየቀኝም።ለሰራተኛቸው ምግብ እንድታቀርብ እና ለእንቅልፍ እንደሚረዳኝ ነግሮኝ ወተትም አፍልታ እንድታመጣ አዘዛት። መታጠብ እፈልግ እንደሆነ አይደለም የጠየቀኝ። ውሃው ሙቅ ወይስ ቀዝቃዛ ቢሆን እንደምመርጥ እንጂ። በእያንዳንዱ እንቅስቃሴው ለዘመናት አብረን የኖርን አይነት እንዲሰማኝ ያደርገኛል። ከታጠብኩ በኋላ እንድለብስ የፍትህን ቢጃማ ሱሪና ቲሸርት መታጠቢያ ቤቱ መስቀያ ላይ ሲሰቅል ይደብረኝ እንደሆነ አልጠየቀኝም። ቢሰፋኝም የሱሪውን ወገብ በማሰሪያው አጥብቤ እንድለብሰው ነገረኝ እንጂ። ምግቡን በእጄ አላስነካኝም። እያጎረሰኝ መብላት ጀመርኩ። እየሆነ ያለው ሁሉ ግራ ገባኝ።
“ለምንድነው እንዲህ ጥሩ የሆንክልኝ? ወይስ ለሁሉም ሰው እንዲህ ነህ?” አልኩት
“ለማንም ሰው ቢሆን አዎን ጥሩ ለመሆን ነው የምሞክረው። ላንቺ ግን በተለየ ጥሩ ለመሆን እየሞከርኩ ነው።”
“ለምን? ለምን በተለየ?”
አልኩት የዘረጋልኝን ጉርሻ ከመጉረሴ በፊት
“ምክንያቱም ልጄ ይወድሻል። አንቺ ትወጂዋለሽ ወይስ አትወጂውም ሌላ ነገር ነው። ይህን የማደርገውም push ላደርግሽ አይደለም።”
“ማን? ፍትህን? መውደድ ማለት? በፍቅር እያልከኝ ነው?
👍5
“ነው። እንደዛ እያልኩሽ ነው። ወተቱን ማጊበትና ይህቺን ጉረሺ።” ያጎረሰኝን አላምጬ ሳበቃ
“እስከማውቀው ድረስ ፍትህ እንደኔ አይነት ሴት ምርጫው አይደለችም። ደግሞ ይቅርታ አድርግልኝና በሴት ረገድ ልጅህ መረን ነው። በጣም ይቅርታ ግን!”
“አውቃለሁ። ስለልጄ የማላውቀው ነገር የለም። ፍትህ እናቱን ያጣው በ13 ዓመቱ ነው። እኔ ለስራ ሌላ ሀገር በሄድኩ ማታ እቤት ገብተው በዘረፉን ወንበዴዎች በሽጉጥ ነው የተገደለችው። (እስከአሁን ያላየሁበትን መከፋት ፊቱ ላይ አየሁ።) ስትመታና ስትወድቅ ስትሞትም ፍትህ እዛው ነበር። እያያት!! ለብዙ አመታት የእናቱ ሞት ሀዘን የተጫነው ምስኪን ልጅ ነበር። ተንከባክቤ አሳደግኩት ፤ ደስተኛ ያደርገዋል ብዬ ያሰብኩትን ሁሉ አደረግኩ ፤ የእናቱ መጉደል ፍፃሜውን እንዳያበላሽ ስለፈራሁ አቀበጥኩት። ነገር ግን ቆይቶ ሲገባኝ ልጄን ለድርጊቶቹ ሀላፊነት የማይወስድ ግድ የለሽ አደርጌ ነው ያሳደግኩት፤ መጎዳቱን ፍራቻ ሲያጠፋ እንኳን አምርሬ አልቆጣውም ነበር። ምንም ጎድሎበት አያውቅም።ያለው ሁሉ በጥረቱ ያገኘው አልነበረም እናም ዋጋ የሚያስከፍለው ምንም ነገር አይፈልግም። ጥሩ ትምህርት ቤት አስተምሬዋለሁ። አስጠኚ ቀጥሬ እንዲጎብዝ ጥሬያለሁ። ዩንቨርስቲ ገብቶ ተመርቆ ቢወጣም ስራ መስራት አይፈልግም። እኔን ላለማስከፋት ነው ስራ የሚሰራው። ከዛ ይልቅ ከሴትና ከመጠጥ ጋር ውሎ አዳሩ ቢሆን ደስተኛ ነው። ስለእውነት አሁንም ቢሆን ጨክኜ አምርሬ ልቆጣው ያሳሳኛል። ቁጭ አድርጌ እመክረዋለሁ። እናንተጋ መስራት ከጀመረ ቀን ጀምሮ ስለአንቺ ሳያወራልኝ አድሮ አያውቅም። ቆንጆ መሆንሽን፣ ደረቅ መሆንሽን፣ በስራሽ ጉብዝናሽን፣ ስቀሽ እንደማታውቂ…… ። ላለፋት ሁለት ሳምንት ግን ፍትህ ሌላ ሰው ነበር። በጊዜ ወደቤቱ ይገባና ሲጨቀጭቀኝ ያመሻል። ‘ምን ሆና ይሆን? አትወደኝም እኮ ቁምነገር የሌለው ዱርዬ ነው የምመስላት፣ ካስዬ ቆይ እሺ እንድታዋራኝ ከዚህ በላይ ምን ላድርግ?’ ሲለኝ ይመሻል። ትናንት ደውሎ የተፈጠረውን ነገረኝ። ልጄ በህይወቱ ስለምንም እንደዚህ ግድ ሰጥቶት አያውቅም።” የሚያወራልኝን እየሰማሁ የቀረበውን ምግብ በጉርሻ አገባድጄዋለሁ።
“በቃኝ በናትህ ብዙ በላሁ።”
“አንድ የመጨረሻ ይህቺን!”
የፍትህ መኝታ ቤት እንዳርፍ ተሰናዳልኝ። ድምፁ ዝግ ያለ ተመሳጮች ለተመስጦ የሚጠቀሙበትን የሚመስል የኮሪያ ክላሲካል ሙዚቃ ተከፍቶ ክፍሉ የሆነ የሚያባብል ድባብ አለው።
“በቃ ትንሽ አረፍ በይና እናትሽጋ እንሄዳለን። የምትፈልጊው ነገር አለ?”
“የለም። በጣም ነው የማመሰግነው።” አልኩት አልጋው ጫፍ ላይ እየተቀመጥኩ።
“እንደሱ ስትዪኝ ይከፋኛል። እቤቴ እኮ አስገባሁሽ ፤ በእጆቼ አጎረስኩሽ …… ከዚህ በላይ ቅርበት ምንድነው? እንደአባትሽ እይኝ።…… ” ይሄን ሲለኝ ከየት መጣ ያላልኩት የእንባዬ ጥርቅም በሳግ ታጅቦ ተንዠቀዠቀ።… … አጠገቤ መጥቶ በእጆቹ አጀብ ደረቱ ላይ አኖረኝ። አላባበለኝም። እንዳለቅስ ፈቀደልኝ።
“ንገሪኝ!” አለኝ ሲበርድልኝ ጠብቆ
“ምኑን?”
“ይሄ የዛሬ ወይ የትናንት ሀዘን የፈነቀለው ለቅሶ እንዳልሆነ አውቃለሁ። ንገሪኝ ሁሉንም!!”

🌑ይቀጥላል➡️

Like 👍👍 እያደራጋቹ አስተያየት እየሰጣቹ ቀዝቀዝ ማለት ነገር ይታያል የተመቸው 👍ሳያደርግ እንዳያልፍ ትዛዝ ነው😊

አስተያየት ካሎ በ @atronosebot አድርሱን
#ራሴው_ማበዴ_ነው
:
#ክፍል_ስድስት
:
ደራሴ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
...እናቴ ከመሞቷ በፊት ልውልላት የምችለው አንድ ውለታ አባቴ እንዲያገኛት ማድረግ ነው። ቢያንስ የዘመናት ፍቅሯን እጁን ዳብሳ ደስተኛ ሆና ትሞታለች። እናቴን ማጣት ማሰብ አልፈልግም። የባሰው ደግሞ ስትለየኝ ማን መሆኔን እንኳን ሳታውቅ እብደቷ ተነስቶባት መሆኑን ማሰብ ያሳብደኛል። ያ እንዲሆን አልፈልግም። የቀራትን ጊዜ ጭንቅላቷ ልክ መሆን አለበት!! ውስጤ እንዲቀር የምፈልገው የእናቴ ምስል የምትፈራኝና የምትሸሸኝ ‘አንቺ ደግሞ ማነሽ?’ የምትለኝ እብዷ እናቴ ምስል አይደለም። ያቺ በለስላሳ እጆቿ ደባብሳኝ የማትረካዋ ፣ እሷ ያልኖረችውን የስነ ምግባር ኑሮ እንድኖር የምትመክረኝ፣ በሌላት ጡት ‘በጡቴ ይዤሻለሁ በቀል ከሀሳብሽ አይኑር።’ ብላ የምትለምነኝ፣ ልጄ ስስቴ የምትለኝ፣ አገላብጣ እየሳመች ‘አሳቃየሁሽ ልጄ’ እያለች የምትለማመጠኝ፣ ለእርሷ ስል መኖሬ የሚገባት(የሚያሳስባት) እናቴ… … እሷን እናቴን ነው በልቤ ይዣት መኖር የምፈልገው።
“እንደምንም ብዬ አባቴን ማናገር አለብኝ።” አልኩት ካሳሁንን ሳለቅስ ቆይቼ። ያልኩት ግርር እንደሚለው ያሰብኩት ባይገባውም የገባው ለመምሰል ሲሞክር ሳየው ነው።
“ግን ልታናግሪው አትፈልጊም?” አለኝ።
“ላገኘውም አልፈልግም። የእሱን እርዳታ መጠየቅ ደግሞ ያሳምመኛል። ለእማዬ ስል ግን አደርግላታለሁ። ለሷ ስል አደርግላታለሁ።” አልገባውም። በጥያቄ ሊያስጨንቀኝም አልፈለገም። ከእቅፉ ወጥቼ ጋደም እንዳልኩ ከየትኛው ሃሳቤ በኋላ እንቅልፍ እንደወሰደኝ አላውቅም።… ……
በሚቀጥሉት ቀናት የካሳሁንን እና የፍትህን እማዬ አጠገብ መሆን፣ ራሴን ካሳሁን እቅፍ ውስጥ ወይም የፍትህ አልጋ ላይ አልያም የፍትህ ቢጃማ ውስጥ ማግኘት፣ የፍትህን በቡናና በቁርስ ሰበብ የቢሮዬን በር መክፈት… የተለመድኳቸው ክስተቶች ሆኑ። የሚፈጥሩብኝን ስሜት ግን በደነዘዘ ልቤ መረዳት አልቻልኩም።
ከሳምንት በኋላ አራታችንም(እኔ እና የስራ አጋሮቼ ፀሃፊያችንን ወይኗን ጨምሮ) ቢሮ ተሰበሰብን እና ለተወሰነ ጊዜ ስራ ላቆም መሆኑን ስነግራቸው በድንጋጤ አፈጠጡብኝ።
“ለምን? ቆይ እስከመቼ? ምን ተፈጥሮ ነው?” ጌትነት ነው የሚጠይቀኝ።
“እስከመቼ እንደሆነ አላውቅም ጌትሽ! ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው። መቼ እንደሆነ ባላውቅም ቃል እገባልሃለሁ ወደ ስራዬ እመለሳለሁ። እስከዛ ድረስ እጄ ላይ ያሉትን እንድትሰራልኝ ፈልጋለሁ።”
“ስራ ማቆሙ አስፈላጊ ነው? ራሁ please ፍቀጂልኝ እኔ ልርዳሽ? በምትፈልጊው ሁሉ እኔና ካስዬ ከጎንሽ ነን።” አለኝ ፍትህ ሌሎቹ ሲወጡ ጠብቆ።
“ፍትህ ልትረዳኝ ትፈልጋለህ?” አልኩት (ቁልምጫው ልቤን ቢሰርቀውም ባልሰማ አለፍኩት)
“Whatever it is.”
“መልካም! ብዙ ትግል እና ትእግስት የሚጠይቅ ስራ እጄ ላይ አለ። ሙሉ ሰዓትና አቅም ይፈልጋል።አሁን በሙሉ አቅሜ ልሰራ አልችልም። አስቸጋሪ ቢሆንም ይሄን ኬዝ አንተ እንድትይዝልኝ እፈልጋለሁ።”
” ራሁ እኔ ያንቺን ያህል ጎበዝ አይደለሁም። ……”
“ሁና! ጎበዝ ሁን! ጉብዝና ተፈጥሮ አይደለም። ጎበዝ ለመሆን ትለፋለህ እንጂ ጉብዝና ድንገት ጉብ የሚልብህ መንፈስ አይደለም። እኔን መርዳት ትፈልጋለህ? ይኸው……(መረጃ የያዘ ፍላሽ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጥኩለት)… አሁን እማዬጋ መሄዴ ነው። እየውና ስትወስን ደውልልኝ… ” ብዬው ወጣሁ።
“እሺ ላድርስሽ?”
“Am ok መንዳት እችላለሁ።”
እማዬጋ ስደርስ ካሳሁን ከእማዬ ክፍል አቅራቢያ ውጪ ተቀምጧል።
“አባትሽ ውስጥ ነው። ብቻቸውን ይሁኑ ብዬ ነው።” አለኝ ቀለል አድርጎ። ለመግባት ስፈጥን እጄን ይዞኝ። “ምንም አትሆንም እንደውም ደስተኛ ናት። ተያቸው።” አለኝ።
“ደስ የማይል ነገር ቢናገራትስ? የሆነ ነገር ብትሆን……” እጄን አስለቅቄው ገባሁ። መግባቴን ያየችው እሷ ብቻ ናት። እሱ (አባቴ) ከግርጌዋ ተንበርክኮ ሁለት እግሮቿን አቅፎ ያለቅሳል። እየሆነ ያለው ሁሉ ግርር አለኝ…… ከተቋሰሉት መቋሰል በላይ እንደምትወደው የሷን አውቃለሁ። የእሱ ግን… …
‘ገዳይሽ እኔ ነኝ ማሪኝ ፤ ያንቺን ስቃይ ለኔ ያድርገው፤ ባንቺ ቦታ ልሰቃይልሽ……’ ይላታል። ያቀፋቸውን እግሮቿን ይስማል። ‘ማሪኝ እማ እኔው ነኝ በሽታሽ። ለምን አልነገርሽኝም? ለምን ሀጢያቴን አበዛሽው?’ እንባው እግሮቿን ያርሳቸዋል። እሷን አየኋት። እንባዋ ወደጆሮዎቿ ሲወርዱ ስትጠርጋቸው አየኋት። የእኔ መኖር ምቾት የሰጣት ስላልመሰለኝ ቀስ ብዬ ወጣሁ። እኚህ ሰዎች ሙድ ነው የሚይዙብኝ? ጭንቅላቴ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች እየተርመሰመሱ ቢሆንም ደምቆ የሚያቃጭልብኝ ‘መታመሟን ማን ነገረው?’ የሚለው ነው።
“እኔ ነኝ የነገርኩት።” አለኝ ካሳሁን ያሰብኩትን ያወቀብኝ መሰለኝ። ቀጠል አድርጎ “እነርሱ እስኪጨርሱ አንድ ቦታ ደርሰን እንምጣ?” ብሎኝ ተንቀሳቀሰ። ተከትዬው መኪናው ውስጥ ገባሁ። ብዙ ከተጓዝን በኋላተጀምሮ ያላለቀ ቤት ያለበት ጊቢ ይዞኝ ገባ። እያየሁት መንፈሱ ሲቀየር አስተዋልኩኝ። ሀዘን የተጫነው ሰውዬ ሆነ። ምንም ምንም ሳይለኝ ግድግዳውን ተደግፎ የተቀመጠ መጥረጊያ አንስቶ በጅምር ከቀረ የከራረመ የሚመስለውን ቤት ግድግዳና መሬት በጥንቃቄ ማፅዳት እና ማውራት ጀመረ።
“አበባ ጎበዝ አርክቴክት ነበረች። የፍትህ እናትን ማለቴ ነው። ለወደፊት ኑሯችን ራሷ ዲዛይን ያደረገችውን ቤት መገንባት ነበር የምትፈልገው። ይሄ ነበር የወደፊት ቤቷ ( መጥረጉን ቆም አድርጎ ቤቱን አመላከተኝ) ቤቷ ተሰርቶ ሳያልቅ እሷ ሞተች። ቤቱን አሰርቶ የመጨረስ ብርታቱ አልነበረኝም። በነበረበት ቆመ። ስትናፍቀኝ ላዋራት ፈልጌ መቃብሯ ጋር ስሄድ ሀዘኔ ይበረታል። ሙት መሆኗ በድን ያደርገኛል። እዚህ ስመጣ ግን እንደዛ አይሰማኝም። እዚህ የኔ አበባ ህይወት አላት። እዚህ ህልውናዋ ይሰማኛል። እና መቃብሯጋ መሄዴን ትቼ እዚህ መምጣት አዘወተርኩ። የሆነ ቀን እንደለመድኩት ስመጣ ፍትህ ቤቱን ሲያፀዳ አገኘሁት። ሁሌ ስመጣ ቦታው ፅዱ እንደነበር አስታወስኩ። ምንም አልተባባልንም። እስከትናንት ድረስም በዚህ ጉዳይ ቃላት ተለዋውጠን አናውቅም። ለ19 ዓመታት ይሄ ቦታ ፅዱ ነበር። እንዲህ ቆሽሾ አያውቅም። ሁሌም እሁድ ጠዋት መጥቶ እንደሚያፀዳው አውቃለሁ። አልመጣበትም። ሁሌም እሁድ ከሰአት እንደምመጣ ያውቃል። አይመጣብኝም። ትናንት ከዚህ በኋላ ወደዚህ ተመልሶ እንደማይመጣ ነገረኝ። በእናቱ ትዝታና ሀዘን መደበቅ እንደሚበቃው ነገረኝ። አየሽ ሁሌም የአዲስ ነገር ጅማሬ የአሮጌው መቋጫ ነው። ከአሮጌው ቅጥያ ከሆነ ምኑን አዲስ ሆነ?”
እየሆነ ያለው፣ የሰማሁት እና የማስበው ተፐውዟል። የካሳሁንና የአበባ ታሪክ ከእናትና አባቴ ታሪክ ጋር ይደባለቅብኛል። አባቴ ለእናቴ የፃፈላት ደብዳቤ ካሳሁን ለሚስቱ የፃፈላት ይመስለኛል። ደግሞ ስለፍትህ አስባለሁ። በፍፁም ለቅፅበት እንኳን ከፍቶት የሚያውቅ የማይመስለኝ ሰው ለነዚህ ሁሉ ዓመታት ይሄን ስቃይ እሹሩሩ ሲል ነበር የኖረው? እርስ በርሱ የተከላለሰ ነገር እያሰብኩ የቤቱ ደፍ ላይ ቁጭ አልኩ። መጥረጉን ሲጨርስ አጠገቤ መጥቶ ተቀመጠ።
“ታውቃለህ ከእናቴ በቀር የሚያውቀኝ ሰው ሳለቅስ አይቶኝ አያውቅም።” ካልኩት በኋላ እሱ ካወራው ልብ የሚቦረቡር ታሪክ ወይም እሱ ካለበት ስሜት ጋር በመልክም በቅርፅም የማይገናኝ ነገር ማውራቴ አሳፈረኝ።
“አየሽ አንዳንዴ ምንም ካልሰራንበት ዘመናችን ስህተት የሰራንበት ዘመን ይሻላል። ምክንያቱም ምንም ውስጥ ምንም የለም። ስህተት ውስጥ ቢያንስ የመሳሳቻ አንዱን መንገድ አውቀሽዋል። ደግመሽ በዚያ መንገድ መንደፋደፍ
👍61
ወይም መንገድ መቀየር ያንቺ ምርጫ ይሆናል።” አለኝ። ለእኔ ያውራ ለራሱ ወይ ለሚስቱ አልገባኝም። ጭራሽ ያለውም አልገባኝም። ምን እየሆንን ነው? ጭራሽ እኔ የማወራው ነጭ እሱ የሚመልስልኝ ጥቁር!! እያበድን ነው እንዴ?… …ፀጥ ተባብለን ከቆየን በኋላ ተነሳ። ተመልሼ ሆስፒታል ስሄድ አባቴን ባላገኘው ደስ ስለሚለኝ መቆየታችንን ወድጄዋለሁ። ተከተልኩት። …… ቃል ሳንተነፍስ ሆስፒታል ደረስን።
“እኔ በቃ ወደቤት ልሂድ! ከቻልኩ በኋላ ብቅ እላለሁ።” አለኝ ከመኪናው ሳይወርድ። ተሰናብቼው ወደ እማዬ ክፍል እየሄድኩ ካሳሁንን ከጭንቅላቴ ማውጣት አልቻልኩም። መከፋት የተጫነውን ፊቱን ከሀሳቤ ማደብዘዝ አቃተኝ። እማዬና ፍትህ ከክፍሉ ውጪ የሚሰማ ሳቅ እየተሳሳቁ ደረስኩ። ሰላም ብያቸው ሳልጨርስ
“እኔ የምለው ጀብዱ ትወጃለሽኣ?” አለኝ ፍትህ የተጋነነ መገረም ባለው ድምፅ። የሰጠሁትን መረጃ አይቶት እንደሆነ ገብቶኛል።
“ማን ይጠላል?” አልኩት።
“እኔ!” አለኝ ኮስተር ብሎና አስረግጦ።
“ሃሃሃሃ ፈሪ ነህ ማለት ነዋ! ሊያውም የምትጠላው ጀብዱን አይደለም። የሚጠይቀውን ድፍረትና risk ነው። ” እያልኩት ፊቱ ላይ ስስት ያለበት ፈገግታ ተንሰራፋ…… እያወራን ካለበት ስሜት የማይገናኝ ዕይታ እያየኝ ነው። “ምንድነው?” አልኩት ግራ ሲያጋባኝ።
“ሳቅሽ!! ራሁ ድምፅ አውጥተሽ ሳቅሽ እኮ! ራስሽን ሰምተሽዋል?” እየፈነደቀ ነገር ነው ልበል? ድምፁ ውስጥ የምሰማው ነገር ምንድነው? ከመደሰት ያለፈ
“እና?”
“በፍፁም ድምፅ አውጥተሽ ስትስቂ ሰምቼሽ አላውቅማ።”
(ስቄ አላውቅም ይሆን? መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ የሳቅኩት? መቼስ ይሆን የሚያስቅ ነገር የሰማሁት? ከሁልጊዜው በላይ እንባን በሚያዘንብ ሁኔታ ተከብቤ ዛሬ ምን አሳቀኝ?)
አሳፈረኝ። ያሳፈረኝ ዕይታው ይሁን አነጋገሩ አልገባኝም። ‘ተሽኮረመመች’ ተባብለው ከእማዬ ጋር ተሳሳቁብኝ። አፍንጫዬ አላበኝ። ጉንጬ የቀላም የነደደም መሰለኝ። ምንድነው እየሆንኩ ያለሁት? መቼ ነው እንዲህ የሆንኩት?
ድሮ ድሮ ድሮ ድሮ ድሮ ድሮ… ………

🌑ይቀጥላል➡️

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ ምርጦች

አስተያየት ካሎ በ @atronosebot አድርሱን
👍5
#ራሴው_ማበዴ_ነው
:
#ክፍል_ሰባት
:
ደራሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
....“ይሄ ኬዝ እንዲህ ቀልብሽን የሳበው የትኛው
ነጥብ ነው? ግልፅ ማስረጃ ነው የተያዘባት። ራሷም ድርጊቱን መፈፀሟን አምናለች።”
“ፍትህ ሰዎቹን ፈራሃቸው እንዴ?”
“በፍፁም ፈርቼ አይደለም። ከእነሱ ጋር ስለመያያዙም ገና መላምት ነው ያለሽ።”
ከፍትህ ጋር ሻይ እየጠጣን እየተነጋገርን ያለነው ስለትዝታ ነው። ትዝታ የ23 ዓመት ልጅ ናት። የአጎቷን ‘ፍቅረኛ’ በአጎቷ ሽጉጥ አራት ጊዜ ተኩሳ መግደሏን አምናለች። ለፖሊስ እጇን የሰጠችው ራሷ ናት። ለመግደል አበቃኝ ያለችው ምክንያት ለጥፊም የሚጋብዝ አይደለም። አጎት በአዲሳባችን ካሉ ባለሀብት አንዱ ነው። በተጨማሪም የሚንስቴር ወንድም ነው። ትዝታ አባቷ በ7 አመቷ ስለሞተ ያሳደጋት አጎቷ ነው። በ16 አመቷ ከጋብቻ ውጪ የወደቻትን ልጇንም እያሳደገላት ነው።
“ሰውየው ምንም ነገር የማድረግ አቅሙ ያለው ሆኖ ሳለ ጠበቃ እንኳን የቀጠሩላት የእናቷ ዘመዶች ናቸው። አስበው ትዝታ ልጁ ማለት ናት። ሌላው የሟች ጉዳይ ነው። ሟች የናጠጠ ሀብታም ሰውዬ ፍቅረኛ ሆና እናትና አባቷ ግን ከልጃቸው እጅ ስባሪ ሳንቲም ያልተለገሳቸው እና ለእለት ምግብ የሚቸግራቸው ሰዎች መሆናቸው ሲደመር ፍቅረኛ እንዳላትም አለማወቃቸው የሚጎረብጥ ነገር አለው። ትዝታ የሆነን ሰው እየተከላከለች እንደሆነ ነው የሚሰማኝ።”
“ማንን?”
“እሱን ማወቅ ያንተ ድርሻ ነው። እ? ገብተህበታል?”
“እሺ። ገብቼበታለሁ” ይበለኝ እንጂ እንዳላመነበት ያስታውቅበታል።
“ፍትህ በህይወትህ ያልተለመደ ዓይነት ስኬት ላይ መድረስ ከፈለግክ ያልተለመደ ዓይነት ድፍረት ሊኖርህ ይገባል ከተራ መንገድ ለመውጣት ማፈንገጥ አለብህ ለእኔ ብለህ ብቻ እንድታደርገው አልፈልግም አንዲት እርምጃ ከመራመድህ በፊት አንተ እንድታምንበት እፈልጋለሁ።” አልኩት
“እስቲ መጀመሪያ ከትዝታ ጋር የምገናኝበትን መንገድ አመቻቺልኝ”
“ሌላው ችግር ይሄ ነው ጉዳዩን ውስብስብ እና አዳጋች የሚያደርገው ትዝታ ምንም አይነት መረጃ አትሰጥህም። መታሰር ነው የምትፈልገው። ጠበቃ እንዲኖራትም አትፈልግም። አንድ ሺህ ጊዜ ብትጠይቃት አንድ ሺህ ጊዜ የምትመልስልህ አንድ ዓይነት መልስ ነው ለማንኛውም ግን ነገ ቀጠሮ አለኝ እናገኛታለን።”
በዚህ ጉዳይ ላይ እርግጠኛ ባልሆንኩበት ምክንያት ፍትህ ጥሩ ሰርቶ ማየት እፈልጋለሁ። እንድኮራበት እፈልጋለሁ። አባቱ እንዲኮራበት እፈልጋለሁ እሱም ራሱ በራሱ እንዲኮራ እፈልጋለሁ።
“ፍትህ አባትህ ዛሬ ደብሮታል። አንተ ወደ ቤት ሂድ። እኔ እማዬጋ ልመለስ።”
“ህምም እናቴጋ ሄዶ ነበር?”
“አዎን” አልኩት ሂሳብ እንዲቀበሉን አስተናጋጅ ለመጥራት እጄን እያነሳሁ። እጄን ለቀም አድርጎ ያዘኝ። ደንግጬ አየዋለሁ
“ይቅርታ ራሁ አስደነገጥኩሽ። ትንሽ አብረሽኝ ቆዪ?” አለኝ ያያዘውን እጄን አጥብቆ እየያዘው። በጭንቅላቴ እሺ አልኩት። ዓይኖቹን ሳያርገበግብ ስላፈጠጠብኝ ተጨነቅኩ። ዓይኔን ከዓይኑ ብነቅልም እንዳፈጠጠብኝ ይታወቀኛል። ምራቄን ስውጥ ጉሮሮዬ ያስተጋባል። ያልያዘውን እጄን ጣቶች ከጠረጴዛው ስር አፍተለትላለሁ።
“ዓይኖቼን እንድታያቸው የግድ ስለስራ ነው ማውራት ያለብን?” ድምፁ ወፍራም ግን ለስላሳ ዓይነት ሆነ። የሰውነቴ ቆዳ ላይ እንደሆነ ሞገድ ሽው ሲል ይታወቀኛል
“እያሳፈርከኝ ነው ፍትህ!” አልኩት። ባላየውም ፈገግ ማለቱን አውቄያለሁ። ባይናገርም አንደኛውን እጁን ዘርግቶ የጠየቀኝ ሌላኛውን እጄን መሆኑን ስላወቅኩ አቀበልኩት። እጆቼን ዘርግቶ ጣቶቼን እያያቸው ቀና ይላል።
“ጣቶችሽ ያምራሉ።” ባለኝ ቅፅበት ተራ በተራ ሁለቱንም እጆቼን ጣቶቼጋ ሳማቸው። ሆነ ብሎ ከንፈሮቹን ጣቶቼ ላይ አቆይቶ የተሰማኝን ለማወቅ ዓይኖቼን ይፈልጋልበርግጌ ተነስቼ ልቆም ትንሽ ነበር የቀረኝ። ‘አገኘሁሽ’ አይነት ፈገግታ ፈገግ አለ።
“ፍትህ ሰው እያየንኮ ነው?”
“እና እኔ ምንአገባኝ? ዓይኑን የሚያሳርፍበት ቆንጆ ጎኑ ባይኖር ነው።” ብሎኝ የእጆቼን መዳፍ ተራ በተራ ሳማቸው። አይኔን ጨፈንኩ ልበል?
“ስለአንቺ የማላውቀውን አንድ ነገር ንገሪኝ?” አለኝ ወደእኔ እየሰገገ ተጠግቶኝ።
“ምንም አታውቅምኮ። ስለምንድነው ማወቅ የፈለግከው?”
“አሁን እኔ ማወቅ ስለሚገባኝ ነገር” ድምፁ ልክ የሆነ ስሜት አይሰጥም። እንኳን ቃላት ሰካክቼ በስርዓቱ ላወራ የማስበውን እንኳን ይበትንብኛል።
“ማለት?”
“አሁን መስማትም ማወቅም የምፈልገው እነዚህን እጆች የሚጨብጣቸው ሰው አለመኖሩን ነው።(እጆቹ እጆቼ ላይ አስማታዊ መርመስመሳቸውን አያቆሙም።) ፤ ፀጉርሽ ውስጥ ጣቶቹን ሰክቶ የአንገትሽን ጠረን የሚምግ፣ ከንፈሮችሽን ጎርሶ በትንፋሽሽ እድሜውን የሚቀጥል፣ (ዓይኖቹ የሚጠራቸው የሰውነት አካሌ ላይ በስድ እይታ ያርፋሉ። እኔን ግን ምን እየነካኝ ነው? የምሰማው ድርጊት እየሆነ ያለ ያህል ይሞቀኛል።) በአይኖችሽ መስለምለም ቀኖቹን የሚያደምቅ፣ የሸሚዞችሽን ቁልፍ ከፍቶ… ”
“እረፍ ፍትህ! እረፍ በቃህ! ማንም የለም!” አስቤ የተናገርኩት አልነበረም። አሁንም የቅድሙን ፈገግታ ደገመልኝ። እጆቼን ስለለቀቀልኝ ተነፈስኩ። ሆስፒታል ሸኝቶኝ ተመለሰ። ካፌ ተቀምጠን ያደረገውን እንዳላደረገ በቅጡ እንኳን ሳይጨብጠኝ ነው የሄደው። ተናደድኩ ልበል? ምን እየሆንኩ ነው? ምን እንዲያደርግ ነበር የፈለግኩት? ምናልባት የሚያደርገው ሁሉ ለብዙ ሌሎች ሴቶች ያደረገው ለእርሱ ምኑም ያልሆነ ይሆን? ምንዓይነቷ ቀሽም ነኝ?
እማዬ አስር ጊዜ “ምን ሆነሻል?” ስትለኝ ራሴን ገስፃለሁ። እየሆንኩ ያለሁት በግሳፄ ማቆም የምችለው ጉዳይ ግን አልሆነም።
“አባትሽ ስለመጣ ተናደሻል?” እማዬ ስትጠይቀኝ በራሴ በሸቅኩ። ምንም የኑሮ ማገር እንዳላፈነገጠብኝ ስለፍትህ በዚህ ጥልቀት ማሰቤ አናደደኝ።
“ኸረ እማዬ… … ለምን እናደዳለሁ? አንቺ ደስ ካለሽ የኔ ደስታ ያ ነው።”
“እንደምትጠዪው አውቃለሁ። አንቺን ደስ ካላለሽ ድጋሚ እንዳይመጣ እነግረዋለሁ።”
“እማዬ አንደኛ አልጠላውም። አልወደውም ማለት እጠላዋለሁ ማለት አይደለም። ከመጥላትና ከመውደድ ፅንፍ መሃል ምንም ስሜት ማጣት አለ። እንደዛ ነው ለሱ ያለኝ ስሜት። ሁለተኛ የአንቺ ፈቃድ ይሁን እንጂ በተመቸው ሰዓት መጥቶ ሊያይሽ ይችላል።”
የአባቴን ጉዳይ በጤነኛ ጭንቅላቷ ስትሆን ደፍራ አታወራኝም። በዚህ ሁሉ ስቃይዋ እሱን ማፍቀሯ እኔን መበደል የሚመስላት ይመስለኛል። ለእኔ አንዳችም የአባት ርህራሄ ያላሳየኝን ሰው ጭንቅላቷ እስኪዛባ ማፍቀሯ እኔ ለእርሷ ያደረግኩትን መልካምነት መደለዝ ይመስላታል መሰለኝ። ስለእውነቱ ሰውየውን አልወደውም። እሷ ስለምታፈቅረው ግን አልናደድባትም። ያንን ደግሞ ያስተማረችኝ ራሷ ናት። ‘ኩታ በየፈርጁ ይለበሳል።’ ትለኛለች። ለእሱ ያላት ፍቅርና ለእኔ ያላት ቦታ የሚጋጭም ፣አንዱ ሲጨምር ሌላው የሚቀንስም ፣ የሚወዳደርም አይደለም ስለዚህ እኔንና እሱን ለምርጫ አላቀርብላትም ሁለታችንንም በልቧ መያዝ ትችላለች
“እማዬ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ? ካልፈለግሽ አለመመለስ ትችያለሽ። ”
“ጠይቂኝ!”
“የእውነትሽን ያደረገሽን ነገር ረስተሽለት ነው? ይቅር ብለሽው ነው?”
“በእርግጥ ይቅር ብዬው ነው። ያ ማለት ያደረገኝን ረስቼው ነው ማለት አይደለም አየሽ ሚሚሾ በደንብ ስሚኝ ከመስከረም እስከ ነሃሴ በፍቅሩ ከልሎ ፣ በርህራሄው ከብቦሽ፣ በሀዘንሽ አልቅሶ፣ በደስታሽ ፈንጥዞ ፣ በጉያው አሙቆ…ያከረመሽ ሰው ጳጉሜ 5 ላይ ቢበድልሽ የቱን ትቆጥሪበታለሽ? ብዙ ፍቅሩን ወይስ አንዲት በደሉን? ሰዎች ስሪታችን ሆኖ ከፍቅር ይልቅ በደል በደማችን ቶሎ ይሰርፃል
👍71
እኔ የመረጥኩት ብዙ ፍቅሩን ነው። ፍቅሩ በደሉን ይከድንብኛል። ለነፍሴም ሰላም የሚሰጠኝ ያ ነው።” አለችኝ በጣም በተረጋጋ መንፈስ። በልቤ ይዣት መኖር የምፈልገው ይህቺን እናቴን ነው። በብዙ ምክሯና ፍቅሯ በማይነቃነቅ የሞራል አለት ላይ የተከለችኝ እናቴን።
“እሺ!” ከማለት ውጪ እሷ ላለችበት የፍቅር ልእልና መልስ አልነበረኝም።
“ደግሞም ልጄ የተበደልነው ህመም ከበደልነው በላይ የሚጠዘጥዝ እንደሆነ ስለሚሰማን የተደረገብን እንጂ ያደረግነው የሚፈጥረው ቁስል አያመንም እንጂ አባትሽን ከበደለኝ በላይ በድዬዋለሁ። ምናልባትም እኔ ካለፍኩት ስቃይ ያለፈ ተሰቃይቷል።” አለችኝ ቀጥላ። ‘አንቺ በየሆስፒታሉ ስትሰቃዪ እሱ ሚስት አግብቶ ወልዷል። የወለዳትን ልጅ ድሯል። እንዴት ተሰቃየ?’ ልላት ነበር ያሰብኩት። እንደ እማዬ ፍቅርና ቅንነት የሞላበት ሀሳብ ባልታደልም ይሄን ማለት ቅን ሀሳቧን በክፋት የመበረዝ ሀጢያት ስለመሰለኝ ዝምታን መረጥኩ።
በሰዎች የእለት ተዕለት ኑሮ ውስጥ የማይቀየር አንድ ህግ አለ። የሰዎች ድርጊት የሀሳባቸው ልጅ ነው። ልምዳቸው ደግሞ የሀሳባቸው የልጅ ልጅ ነው። ታስባለህ– ታደርጋለህ– ልምድህ ይሆናል። ድርጊትህ ወይም የየዕለት ልምድህ በሀሳብህ ያረገዝከውን አንኳር ይመስላል።
በሚቀጥለው ቀን አባቴ እናቴን ሊያያት ሲመጣ እኔና ፍትህ ትዝታን ልናያት ሄድን።
“እኔ የማንም እርዳታ አያስፈልገኝም። አንቺንም እሱንም አልፈልግም።” አለችኝ ትዝታ ከዛሬ በኋላ ጠበቃዋ ፍትህ መሆኑን ስነግራት። ከብዙ ልመና ቀረሽ ንግግር በኋላ ፍትህ ጠበቃ እንዲሆን በ‘ምንቸገረኝ’ ተስማማች። ትቻቸው ልወጣ ስል
“ጠበቃ ልጅ አለሽ?” አለችኝ።
“የለኝም። ምነው ጠየቅሽኝ? ትዝታ በልጅሽ እያስፈራራሽ ያለ ሰው አለ? ንገሪኝ? ማንም ቢሆን ከህግ አያመልጥም። በእኔ ልትተማመኚብኝ ትችያለሽ እባክሽ ንገሪኝ።” ከዚህ በኋላ ምንም ቃል አልተናገረችም። ትቻቸው ወጥቼ እንኳን የኔ ጭንቅላት ግን በሀሳብ እዚህና እዚያ መርገጡን አላቆመም።
ከዚህ ቀን በኋላ አባቴ በየቀኑ እናቴጋ ይመጣል፣ ፍትህ በትዝታ ጉዳይ አዲስ ነገር ለማግኘት ቀን ሲሯሯጥ ይውላል… … አመሻሹን እማዬጋ መጥቶ አይቶን ወደቤቱ ይሄዳል ወይ ያድራል ፣ ካሳሁን በተመቸው ሰዓት ሁሉ ከእኔና ከእማዬ ጎን ይሆናል… ፤ እኔ የፍትህ ክፍል ማደሬን ትቼ ፍትህ ሆስፒታል የሚያድር ቀን እቤቴ አድራለሁ። ሌላውን ቀን ከእማዬጋር። ……
በአንዱ ቀን አባቴ በትንሽዬ ካርቶን ያለ ነገር ሰጥቶኝ ሄደ። እቤቴ ገብቼ አየሁት። ደብዳቤዎች ናቸው። እማዬጋ የሌሉ እሱ የፃፈላት ደብዳቤዎች። አንብቤያቸው ስጨርስ አንድ ነገር ገባኝ። እማዬጋ ያሉት በሙሉ የፍቅር ደብዳቤዎች ናቸው። እሱጋ ያሉት ግን ቅሬታና በደል የተፃፈባቸው ናቸው። እንደ እማዬ አባባል እሱ አንዲትን በደል መርጧል። እሷ ለዘመናት የፍቅር ደብዳቤዎቹን ስታነብ እሱ ለዘመናት በደሉን እያነበበ ቂም ሲደምር ኖሯል። …… እሷ ከመስከረም እስከ ነሃሴ ላይ ናት። እሱ ግን ጳጉሜ 5 ላይ ነው። በሬ ሲንኳኳ ነው የባነንኩት
“ፍትህ? እማዬ ምን ሆነች?”
“ኸረ ምንም አልሆነችም። አባትሽ እሷጋ ሊያድር ነው። ወደቤት ከመግባቴ በፊት ስለትዝታ አንዳንድ ነገር ላውራሽ ብዬ ነው የመጣሁት።”
“ነገ መድረስ የማይችል ጉዳይ ነው?”
“ወሬው ይደርሳል። ……” ብሎኝ እጆቹን በአንገቴ ስር አሳልፎ ፀጉሬ መሀከል ጣቶቹን ሰክቶ ወደራሱ አስጠጋኝ። አንገቴ ስር ስሞኝ በሹክሹክታ “… ይሄ ግን ለነገ ማደር አይችልም ነበር።” አለኝ።

🌑ይቀጥላል➡️

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ 👍👍 ተሳትፎ አሪፍ ነው

አስተያየት ካሎ በ @atronosebot አድርሱን
👍6
#ራሴው_ማበዴ_ነው
:
#ክፍል_ስምንት
:
ደራሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
:
...በሰላሳ አንድ ዓመቴ ማንም ወንድ ነክቷት የማታውቅ ድንግል ሴት መሆን የሚያኮራ ነገር ይሁን የሚያሳፍር አላውቅም (‘ድንግል’ የሚለውን ቃል እጠላዋለሁ ቃሉን እንጂ ነገርየውን አይደለም። በእርግጥ ነገርየውንም ልውደደው ልጥላው እርግጠኛ አይደለሁም። ቃሉ ግን የሆነ አፍ ላይ ሲባል ራሱ ድንግል፣ ደናግል፣ ድንጉላ……… ድንዝና አለበት።) እውነታው እግሮቼ መሃል ካለ ነገር ድፍንነት ወይ ጠባብነት በላይ ዓይኖቼን የማያስነቅሉ የኔን ትኩረት የሚሹ አሳሳቢ የዕለት ተዕለት ጉዳዮች የከበቡኝ ሴት ሆኜ በመኖሬ ትርጉሙም ጣዕሙም አይገባኝም። ድንገት እንኳን በሀሳቤ ሽው ካለ የማልም የነበረው አቅፎኝ የሚያድር የሆነ የማላውቀው ፈርጣማ ወንድ ሰውነት ነው። ማቀፍ ብቻ!! ሌላውን ‘ፓኬጅ’ አላስበውም። እኔ እና እማዬ ብቻችን መኖር የጀመርን ዓመት እማዬ ሲነሳባት ለሊቶቹ ይረዝሙብኛል። ምን እንደምፈራ አላውቅም ግን ስለምፈራ ዓይኔን አልከድንም። ጨለማው፣ ኮሽታው፣ ፀጥታው…… ሁሉም ያስፈራኛል። እጅግ ጥልቅ ፍርሃት እፈራለሁ። ድፍረት የፍርሃት ተቃራኒ አይደለም። የፍርሃት ሌላ ተቃራኒ ሊኖረው ይገባል። ምክንያቱም ድፍረት አለመፍራት አይደለማ። ይልቁንስ ድፍረት ፍርሃትን መጋፈጥ ነው። ድፍረት ፍርሃት እንዳያስቆምህ እየተንቀጠቀጥክም ሆነ እየዳህክ በፍርሃትህ ጫካ ውስጥ ሰንጥቀህ ማለፍ ነው።
እማዬ እና አባቴ ከተለያዩ በኋላ ከታላቅ እህቷ (ከአክስቴ) ጋር ነበር የምንኖረው። የአስራ ሁለተኛ ክፍል ትምህርቴን ጨርሼ ውጤት እየጠበቅኩ በነበረበት ክረምት አክስቴ ትኖር የነበረበትን ትልቅነቱ እና ፀጥታው የሚያስፈራ ቤቷንና ቢያንስ በዓመት ሶስቴ እብደቷ የሚነሳባት እህቷን (እናቴን) አስተዳድሪ ብላኝ አውስትራሊያ ከሄዱ ከእኔ እድሜ በላይ ያስቆጠሩ ቤተሰቦቻቸውን ተቀላቀለች። ከእርሷ በቀር ሀገር ውስጥ የቀረ የቅርብ ዘመድ ያልነበራት እናቴ ብዙም ሳትቆይ የበረራ ቁጥሯን መቁጠር ጀመረች። እንኳን እሷን ላረጋጋት እኔ ከርሷ ብሼ እጅና እግሬ እየተንቀጠቀጠ አለቅሳለሁ። መድሃኒቷን በስቃይ ወስዳ ስታንቀላፋልኝ። እያንዳንዱ የቆዳዬ ነጠብጣብ ቀዳዳ ፍርሃትን እየማገ ወደሰውነቴ ሲነዛው እየተሰማኝ ተስፋ ላለመቁረጥ እና ላለመውደቅ እታገላለሁ። ለፍርሃት እጅ ላለመስጠት!! ያ ነው ድፍረት ማለት። መታገል!! በነዚህ ጊዜያት ነበር በእቅፉ የሚከልለኝ ሰውነት የምመኘው!! ሰውነቱን እንጂ ሰውየውን አልሜ አላውቅም። ሰፊ ትከሻ፣ ሰፊ ደረት፣ ፈርጣማ ጡንቻ፣ ረዥም ቁመት…… ለውበት ሳይሆን ከፍርሃቴ ለመከለያ፤ ለስሜት ሳይሆን ለመደበቂያ፤ ለመፈንጠዣ ሳይሆን ለመወሸቂያ… …ከአንገቱ በላይ ባይኖረውም አልያም ምንም ቢመስልም አስቤው አላውቅም።
“ራሁ? እየሰማሽኝ እኮ አይደለም። ምን ሆነሻል? ከቅድም ጀምሮ ላጫውትሽ እሞክራለሁ። ከእኔ ጋር አይደለሽም።”
“ይቅርታ ፍትህ ትንሽ ራሴን አሞኛል።”
“ምን ላድርግልሽ? ሀኪም ቤት ልውሰድሽ? (እጁን ግንባሬ ላይ አድርጎ ማተኮሴን ያረጋግጣል። በጭንቅላቴ ንቅናቄ መሄድ ያለመፈለጌን ነገርኩት።) እሺ በቃ ነገ ይደርሳል ነገ አወራሻለሁ።እረፍት አድርጊ!” ብሎኝ ተነሳ። ምን አስቤ እንደሆነ እንኳን ለመረዳት ከራሴ ተማክሬ ያላደረግኩትን ድርጊት ተስፈንጥሬ እጁን ይዤ አሰቆምኩት። ቀጥዬ ለምን እንዳስቆምኩት የምሰጠው ምክንያት አልነበረኝም።
“ወዬ? ምን ላድርግልሽ? እንዲህ አድርግልኝ በይኝ። እ ራሁ? (ተመልሶ ተቀምጦ ይዞ ያስቀረውን እጄን እያሻሸ ፣ዓይን ዓይኔን እያየ እና ሁሉም የስሜት ህዋሳቶቼ በሚገባቸው ድምፅ ተንሾካሾከ።) ልታወሪልኝ የምትፈልጊው ነገር አለ? እ? እሺ እንዳድርልሽ ትፈልጊያለሽ?”
“አይይይ አልፈልግም።” አልኩት። አጠገቤ እንዲሆን እኮ እፈልጋለሁ። ሲነካኝ ግን እበረግጋለሁ። እጆቼን ሲያሻሽ ፣ ቅድም እንዳደረገው አንገቴ ስር ሲስመኝ ፣ ዓይኖቼን በሚለማመጡ ዓይኖቹ ሲያያቸው…… መሸሽ እፈልጋለሁ። እንዲህ ሲያደርግ የሚሰማኝን ስሜት ስለምጠላው አይደለም። ስለምወደው እንጂ። ነገር ግን ደስ የሚለኝ አዲስ ስሜት ያስፈራኛል። ሁሌም ቢሆን ያልተለማመድነው አዲስ ነገር፣ አዲስ ሀሳብ፣ አዲስ ስሜት……… ብቻ አዲስ ልምድ መጠኑ ቢለያይም ፍርሃት ያጅበዋል። ምክንያቱ ደግሞ ውጤቱ ከግምት ያለፈ ማረጋገጫ የለውም። ለዚህ ይመስለኛል የብዙ ሰዎች ኑሮ የተለመደ እና የተደጋገመ የሚሆነው። ከአዲስ ነገር ጋር አብሮ ብልጭ የሚለውን ፍርሃት መጋፈጥ የቻሉ ጥቂት ደፋሮች ለአለማችን አዳዲስ ሀሳቦች እና ፈጠራዎች አበርክተዋል።
“እሺ እኛ ቤት እንሂድ? ከካስዬ ጋር ስትጫወቺ ይለቅሻል። እንሂድ?”
“አይ… … ስለትዝታ የደረስኩበት ነገር አለኝ አላልክም ነበር? እሱን እንድትነግረኝ ነው።” የሚል ምክንያት ነበር የመጣልኝ
“ስለትዝታ ልትጠይቂኝ ነው እጅሽ የሚያልብሽ?( ያላበው መዳፌን በእጁ እየጠረገ ያደርቃል። ይሄኔ እኮ ድምፅ ከጆሮ ውጪ በሌላ የስሜት ህዋስ እንዴት ይተረጎማል? ብሎ የሚጠይቅ አላዋቂ አይጠፋም። አሁን ፍትህ እያወራ ያለበት ባለጣዕም ድምፅ ቀላል ይጣፍጣል?) ስለትዝታ ልትጠይቂኝ ነው ዓይንሽ የሚሸሸኝ? (ይሄን ያለበት ድምፅስ ቀላል የሚያውድ መዓዛ አለው?) ስለትዝታ ልትጠይቂኝ ነው ጉንጭሽ የቀላው? (ይሄኛው ቀለማት አሉት። ዓይን የሚይዝ የቀለም ስብጥር) ስለትዝታ ልትጠይቂኝ ነው ቃላት ለማውጣት ያማጥሽው?( ይሄኛው እንደሚያባብል የውሃ ዳር ንፋስ በቆዳዬ ላይ ሽውውውው እያለ ይዳብሰኛል።)” ጭራሽ የማወራው ጠፋብኝ። በዛው ድምፅ ቀጠለ
“ስለስራ ስታወሪ ዓይኖችሽ ዓይኖቼን ያሳድዳሉ ፣ አንገትሽን ቀና አድርገሽ የምትናገሪው ተፅፎ የተሰጠሽ አይነት ‘articulated’ ነው፣ በጥያቄሽ ብዛት እኔን ያልበኛል። …… ንገሪኝ ምን ልትዪኝ ነበር እጄን የያዝሽኝ?” (ይሄንን ድምፅ ጥፍሬ እና ፀጉሮቼ እንኳን ላይሰሙት አይችሉም።)
“ምንም!! ምንም የምልህ ነገር ኖሮኝ አይደለም። …… በቃ እንድትቆይ ብቻ ፈልጌ ነው።”
“እሺ (ያልከለለውን ፀጉሬን ወደኋላ እያደረገ) እሺ እንድቆይልሽ እስከምትፈልጊው ጊዜ ሙሉ የእድሜዬን ቁጥርም ቢሆን እቆይልሻለሁ። ምን እያደረግኩልሽ እንድቆይ ነው የምትፈልጊው?”
“አላውቅም!! ፍትህ የተሰማኝን ስለነገርኩህ እንዳፍር እያደረግከኝ ነው።” ስለው ፈገግ ማለቱን ሳላየው በምን አወቅኩ? ምራቄን እየደጋገምኩ በሚያስተጋባ ጉሮሮዬ የምውጠው ምን ሆኜ ነው? አፍንጫዬ ሳይቀር የሚያልበኝስ?
“እሺ!!” ብሎኝ እጄን ለቀቀኝ። ከሶፋው ላይ ትንሽዬዋን ትራስ አንስቶ እኔ ከተቀመጥኩበት በተቃራኒ ጥግ ተቀመጠ።ትራሷን ጭኑ ላይ ካስቀመጠ በኋላ በእጁ እየመታ ጠቆመኝ። ጀርባዬን ሰጥቼው እግሬን ሰቅዬ እሱን ተንተርሼ ተጋደምኩ።
“ፊትሽን አትከልዪኝ። ወደዚህ ዙሪና ከፈለግሽ ዓይንሽን ጨፍኚ።” አለኝ ቀጠለና። እንዳለኝ አደረግኩ። ዓይኔን ግን አልጨፈንኩም። ፀጉሬን በጣቱ እያበጠረ ለደቂቃዎች ካለምንም የቃላት ልውውጥ ከቆየን በኋላ።
“እንቅልፍሽ ከመጣ መተኛት ትችያለሽ።” አለኝ
“ከዛስ? አንተስ?”
“ያላደለው ጨለማ ላይ አፍጥጦ ያድር የለ? አንቺን የመሰለ ውበት ላይ አፍጥጦ ማደር ተገኝቶ ነው? ውብ’ኮ ነሽ ካስዬ ይሙት! (እጄን የማስቀምጥበት አጥቼ አቅበዘበዝኩት።) እፍረትሽ መጣ?” ብሎኝ ሳቅ ሲል በጨረፍታ አየሁት።
” አንዳንድ ነገር ሳጣራ ነበር። ምን ያህል እንደሚጠቅመኝ ባላውቅም አንዳንድ መረጃዎች ……”
“እስኪ ንገረኝ።”
“የሟች ታሪክ ትዝታ ካለችው የራቀ ነው። ሟች የሰውየው ፍቅረኛ አልነበረችም። ከዚያ ቀን በፊትም ተያይተው አያውቁም። የምትማርበት
👍9
ትምህርት ቤት ጓደኞቿ የሞተች ዕለት መጥቶ ከትምህርት ቤቷ ወሰዳት ያሉትን ሰው አገኘሁት።”
“እና?” ከተጋደምኩበት ቀና ብዬ ለመልሱ አቆበቆብኩ። ፈገግ አለ። ‘ስለስራ ሲሆንማ እንዲህ ነው የምትሆኚው’ የሚል ትዝብት ያለበት ዓይነት ፈገግታ።
“ወንጀሉን መሸፈኛ ስራው ትዳር ፈላጊ አገናኝ ነው። ዋነኛ ስራው ተማሪ ህፃናትና ወጣት ሴቶችን ለከተማችን ዋልጌ ሀብታም ሽማግሌዎች ማቅረብ ነው። ‘ሀብታም የሆነ ባል ፈልጋለሁ ስላለችኝ ነው ያገናኘኋት።’ ባይ ነው። ትዝታ ለመጀመሪያ ጊዜ እቤታቸው የመጣችን ሴት ‘ልጄን በጥፊ ስለመታቻት’ በሚል ቀሽም ምክንያት ትገድላታለች ብሎ ማመን ይከብዳል። ካልሆነስ ማንን እየተከላከለች ነው? ሰውየውን? እሱስ ቢሆን ከዚያን ቀን በፊት አይቷት የማያውቃትን ሴት ለመግደል ምን በቂ ምክንያት ይኖረዋል?”
“አንድ የሆነ ነገር ግን አለ። ልጅ አለሽ ወይ ብላ የጠየቀችኝ ቀን በደንብ አስተውለሃታል? አነጋገሯ ለልጇ ብላ እየከፈለች ያለችው መስዋዕትነት እንደሆነ ነገር ነው።”
“ሌላው ነገር… …ማንም የሚያውቀው ሰው ክፉ ስለማያወራለት አጎቷ አንድ ትኩረቴን የሳበ መረጃ ሰማሁ። የትዝታ ፍቅረኛ ፣ የልጇ አባት ትዝታ እርጉዝ በነበረችበት ወቅት እቤታቸው ድረስ መጥቶ አጎትየውን ደብድቦት ሄደ። ከዚያ ቀን በኋላ ልጁን አየሁት የሚል ሰው የለም። ትዝታም ምንም ልትነግረኝ ፈቃደኛ አይደለችም። አጎትየው በሁለቱ ግንኙነት ደስተኛ ካልነበረ ጥቃት ሊያደርስ የሚገባው እሱ ሆኖ የተገላቢጦሽ እንዴት ሆነ?”
“እሱን እያሰብኩ ነበር። ጎብዘኻል ግን ደስ ብሎኛል።” አልኩት ለጊዜውም ቢሆን ያ የሚያሽኮረምመኝ ፍትህ ተዘንግቶኝ ዓይን ዓይኑን እያየሁ።
“በልብሽ ደምቄ ለመፃፍ የሚያስከፍለኝ ጉብዝናን ከሆነ እተጋለሁዋ ምን አማራጭ አለኝ?” አለኝ እሽኩርምሚቴን በሚያመጣው ድምፁ። ተመልሼ እንደመጀመሪያው እላዩ ላይ ተጋደምኩ እና ዓይኔን ጨፈንኩ። ፀጉሬን በጣቶቹ እያበጠረ መነሻም ማረፊያም የሌለው ወሬ እያወራኝ ለምን ያህል ደቂቃ እንደቆየ አላውቅም። እንቅልፍ ወስዶኝ የነቃሁት ለሊት ዘጠኝ ሰዓት ነው። የሶፋውን መደገፊያ ተደግፎ በተቀመጠበት እንቅልፍ ወስዶታል። ጣቶቹ ከፀጉሬ መሃል አልወጡም። በሁለት የሶፋ ትራስ እግሬን ሸፍኖ ከብርድ ከልሎልኛል። ሆስፒታል ለማደር አስቦ ስለነበር የወጣው ቱታ ሱሪና ጃኬት ነበር የለበሰው። ጃኬቱን አውልቆት እጄን አልብሶኝ በ‘ፓክ አውት’ ነበር። ቀሰቀስኩት።
” ፍትህ ተነስ በስርዓቱ ተኛ አንገትህን ያምሃል። ተነስ እኔ መኝታ ቤት ተኛ። እኔ እማዬ ክፍል እተኛለሁ።” ይሄን የሚለው በምክንያትና በእውቀት ካላመንኩ የሚለው ጭንቅላቴ ነው። ልቤ ግን ከአጠገቡ መራቅን አልፈለገም።
“ከአንቺጋ እንድተኛ ካልፈቀድሽልኝ እዚሁ ሶፋ ላይ የምለብሰው ስጪኝና እተኛለሁ።” አለኝ አይኑን እንኳን አስተካክሎ ሳይገልጥ። ግራ ገባኝ ምን እንደምለው። ያንን እሱም ያወቀ መሰለኝ
“አብረን ተኝተን ነበር እኮ! አልጋ ላይ ሲሆን ምኑ ይለያል? ራሁ ስወድሽ አታወሳስቢው።”
“እሺ!” እያልኩት ወደመኝታዬ ገባሁ። ተከትሎኝ ገብቶ ጫማውን ብቻ አውልቆ ቀድሞኝ አልጋ ልብሶቹ ውስጥ ገብቶ በጀርባው ተኛ። አይኑን ጨፍኖ እጁን ለማቀፍ ዘረጋልኝ። አለማወሳሰብ ይሔ መሆኑን እየገመትኩ እቅፉ ውስጥ ገባሁ። በሁለቱም እጆቹ ደረቱ ላይ አጣብቆ አቅፎኝ ተኛ።… … አፌን እየሞላ እና ጉሮሮዬ ውስጥ የገደል ማሚቶ እየሰራ የሚያልፈውን ምራቄን እየዋጥኩ፤ ድው ድውታው ለእርሱ የሚሰማውን ልቤን ለመቆጣጠር እየታገልኩ የሚቀጥለውን እንቅስቃሴ ጠበቅኩ።… … ጠበቅኩ። …… ጠበቅኩ። …ተኝቷል። …… እንቅልፍ ወስዶታል። ካለፍርሃት ተኛሁ።

🌑ይቀጥላል➡️

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ Like Like👍

አስተያየት ካሎ በ @atronosebot አድርሱን
👍8
#ራሴው_ማበዴ_ነው
:
#ክፍል_ዘጠኝ
:
ደራሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
:
...“አገኘሁት! ራሁ አገኘሁት!” ይለኛል የሆስፒታሉ ኮሪደር መሃል እየደነሰ
“ምኑን? እስኪ አንዴ ዳንስህን አቁመህ ንገረኝ!”
“የትዝታን ፍቅረኛ አገኘሁት!”
“በጣም ጥሩ! የሚጠቅም መረጃ አገኘህ?”
“ገና ነው። ደቡብ አፍሪካ ነው ያለው። ከሀገር እንዲወጣ ያደረገው ማን እንደሆን ገምቺ? የትዝታ አጎት! አስፈራርተውት ነው ከሀገር እንዲወጣ ያደረጉት።”
“ለምን?”
“ትዝታን ለሌላ ለተከበረ ሰው ሊድሯት እንደሆነና ከሷ ህይወት እንዲወጣ እንዳስፈራሩት ጓደኛው ነው መረጃ የሰጠኝ። የሚደውልለትን ስልክ ሰጥቶኝ ደውዬለት ነበር።”
“እና?”
” በዚህ ርቀት ሆኖ እንኳን ይፈራቸዋል። ገና ስለትዝታ ሳነሳበት ‘ሰውየው አረመኔ ነው። አታውቁትም። ትንፍሽ ብል ይገድለኛል።’ አለኝ። ትዝታ ያለችበትን ሁኔታ አስረዳሁት። ልጁ ያለእናትና አባት መቅረቷ መሆኑን ስነግረው ስራ ቦታ መሆኑን እና መልሶ እንደሚደውልልኝ ነግሮኝ ስልኩን ዘጋው።”
“በቃ?”
“ለጊዜው አዎን በቃ!”
“እና የሚያስደንስህ ይሄ ነው? ገና የመፅሃፉን ሽፋን እየገለጥክ እንደሆነ አልገባህም ልበል? ገና ገፅ አንድን እንኳን አላነበብክም እኮ!”
“ራሁዬ ገፅ አንድ ላይ ነኝ ማለት ታዲያ ቢያንስ ትክክለኛውን ትራክ አጊንቻለሁ ማለት አይደል? የተሳሳተ መፅሃፍ ካልገለጥኩ am good ማለት ነው። ሌላው የውልሽ ትዝታን አናገርኳት። ‘ተወኝ’ ከሚል ቃል ውጪ ትንፍሽ ብላ የማታውቅ ልጅ። የልጇን አባት እንዳገኘሁት ስነግራት ከመቀመጫዋ ዘላ ተነስታ ‘በህይወት አለ?’ ብላ ነበር የጠየቀችኝ። ደስ ያላት ትመስላለች። ሞቷል ብላ አስባ ነበር ማለት ነው። ከዚህ ተጨማሪ ነገር ልትናገር አልፈለገችም። ይልቅ ያሰብሽውን ንገሪኝ።”
“የማስበውማ እንዴትም ብለህ ድጋሚ ልታናግረው ይገባል! ስለሰውየው የሚያውቀው ነገር የሚያስገድለው ወይም ከሀገር የሚያሰድደው ከሆነ ሰውየው እንዴት ያለ ወንጀል ውስጥ የዘቀጠ ቢሆን ነው? ስለሰውየው ተጨማሪ መረጃዎች መሰብሰብ አለብህ። የማስበው ዜሮ ላይ እንዳለን ነው።”
በእርግጥ ለእርሱ ይሄን ልበለው እንጂ በትዝታ ጉዳይ የሚገኙት መረጃዎች ብጥቅጣቂና ለማስረጃነት የማይበቁ ምስክርነቶች መሆናቸው ተስፋ አስቆራጭ ሆኖ እንኳን በየቀኑ መረጃ ለማግኘት የሚያደርገው ጥረት እያስገረመኝ ነው። ካሳሁን በሁኔታው መደሰቱን እያመሰገነኝ ነግሮኛል።
“እሺ እማዬን ተሰናብቻት ልውጣ!” ብሎኝ አልፎኝ ወደ ውስጥ ገባ። እማዬ ዛሬ ጠዋት እንዲህ ብላኝ ነበር።
“ሚሚሾ ወጣትነትሽን ለእኔ ብለሽ ገብረሻል። ለራስሽ መኖር ያለብሽ ጊዜ የደረሰ ይመስለኛል። ፍትህ መልካም ሰው ነው። ይወድሻል። አትግፊው።”
“በምን አወቅሽ?” ስላት ሳቀችብኝ። …… ፍትህን እንደወደደችው አውቃለሁ። ከእርሱም ጋር ሆነ ከካሳሁን ጋር ስትጫወት ያለስስት ነው። እነሱ አጠገቧ ሲኖሩ ደስተኛ ናት።…… ካሳሁን ሲኖር ፍትህን ያበሽቀዋል። እኔና እማዬ እንስቅበታለን። እሱ ሳይኖር እማዬና ፍትህ በእኔ ሙድ እየያዙ ይስቃሉ። …… ሆስፒታል ያለን አይመስልም… …… ወደሞት እየተንደረደረች ያለች እማዬን የከበብን አንመስልም። አዲስ ህፃን ወደቤተሰቡ የቀላቀለች እናት ከበን የምንደሰት ነው የምንመስለው። አባቴም በየቀኑ መምጣቱን አላቆመም። እሱ ሲመጣ እኔ እወጣለሁ። ላናግረው እንደማልፈልግ እርሱም ያውቃል። አይሞክርም። ከእኔ ይልቅ ከፍትህ ጋር ያወራሉ። እንዲህ እየሆነ እማዬ ሆስፒታል ከገባች አንድ ወር አልፏታል።
” ፍቅር ብርሃን ነው ሚሚሾ አይደበቅም። በምንም ልትከልዪው ብትሞክሪ የብርሃን ፍንጣቂዎቹ ቀዳዳ እየፈለጉ ያበራሉ። እንደሚወድሽ ትጠራጠሪያለሽ?” አለችኝ።
“አላውቅም እማ! ገና አጭር ጊዜ ነው ካወቅኩት እንኳን። አላውቀውም!” ከማለት ውጪ ግራ ስለሚያጋባኝ ድርጊቱ ለሷ ማውራት አልችልም። አንዴ በፍቅር አክናፍ አፈናጦኝ አርያም የደረስኩ እንዲሰማኝ ያደርገኝና መልሶ ለቀናት በመሃከላችን ከጓደኝነት የዘለለ ነገር እንደሌለ ያስመስላል። ባለፈው ለት አቅፎኝ አድሮ ጠዋት ስነቃ አጠገቤ ካለመኖሩ በላይ ሳገኘው ማታ እቅፉ ውስጥ እንዳልነበርኩ ያስመስላል። አላውቅም! እንዴትስ ማወቅ እችላለሁ? አዝኖልኝ ይሆን ወዶኝ ራሱ ካልነገረኝ በምን አውቃለሁ?
“ሚሚሾዬ የምትፈልጊውን ነገር ለማግኘት ምቹ ጊዜ እስኪመጣ ወይም ጊዜው የምትፈልጊውን ይዞ እስኪመጣ ቁጭ ብለሽ ለመጠበቅ ህይወት በጣም አጭር ናት። በእጅሽ ያለውን ጊዜ ምቹ አድርጊው።” አለችኝ የተዘጋጀ ምግብ እንደመጉረስ ቀላል ነገር የተናገረች ይመስል ልዝብ ብላ።
በቆምኩበት ሀሳብ ሳመነዥክ ፍትህ ተመልሶ መጣ።
“ባለፈው እማዬ ራሷን የጎዳች ቀን ስናወራ የእህቴን ሰርግ ላለመሄድ እና ለአባቴ ጥብቅና ላለመቆም በምላሹ አንድ ነገር እንዳደርግልህ ጠይቀኸኝ ነበር። ታስታውሳለህ? ምን ነበር?” አልኩት ለመሄድ እየተጣደፈ ስለነበረ ላቆየው ፈልግያለሁ።
“እኔ እንጃ! ብዬሽ ነበር? ትዝ አይለኝም።” አለኝ ጥድፈቱን ሳያቆም ትከሻዬን ጨበጥ አድርጎኝ በቆምኩበት ትቶኝ ሄደ። ከፋኝ። የሚናገረውንና የሚያደርገውን ነገር በፍቅር የምተረጉመው ብቻዬን እንደሆነ ተሰማኝ።ለእርሱ ከቀን ተቀን የተለመደ ድርጊትና ንግግር በላይ ዋጋ ያለው ነገር አልነበረም ማለት ነው። እግሬን እየጎተትኩ እማዬጋ ተመለስኩ። እማዬ እየደጋገመች ምን እንደሆንኩ ትጠይቀኛለች። እየደጋገምኩ የሆንኩት ያለመኖሩን እመልስላታለሁ። ሲመሻሽ ካሳሁን ቢመጣም እንደሌላው ቀን መደሰት አልቻልኩም። አንድ የሰውነቴ አካል የከዳኝ መሰለኝ። በሩ በተከፈተ ቁጥር እሱ እየመሰለኝ አፈጣለሁ። አባቴ ሊያድር ስለመጣ እኔና ካሳሁን ወደየቤታችን ሄድን። ጭራሽ ያለወትሮው ስልክም ሳይደውልልኝ አደረ። በሚቀጥለው ቀን ምሽት ሆስፒታል እማዬጋ ቁጭ ብዬ ደውሎልኝ ሊያገኘኝ እንደሚፈልግ ነገረኝ።
“ታዲዎስ ተገድሏል!” አለኝ የተቀጣጠርንበት ካፌ ደርሼ ገና ሳልቀመጥ። ያለኝ ገብቶኝ ሳያልቅ ቀጠለ “ያልታወቁ ሰዎች በጩቤ ወግተውት መንገድ ላይ ወድቆ ነው የተገኘው።” ተስፋ የቆረጠ፣ የተናደደ፣ ያዘነ… ብዙ ዓይነት ስሜት ነው የሚፈራረቅበት። “…… ጓደኛው ነው ደውሎ የነገረኝ። ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ? ‘በሰላም ይኖር የነበረውን ልጅ አስገደልከው። አንተ ነህ ያስገደልከው።’ አለኝ።” የተፈጠረው ነገር በጣም ስሜታዊ ስላደረገው ቅደም ተከተሉን ያልጠበቀ ወሬ ነው የሚያወራኝ።
የትዝታ ፍቅረኛ ታዲዎስ ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ ለቤተሰቡ መርዶ ተረድቷቸው አስክሬን እየጠበቁ ነው። ፍትህ በተደጋጋሚ ደውሎለት ስልኩ እንቢ ብሎት ነበር። የትዝታ አባት ትንፍሽ ቢል እንደሚገድለው ለፍትህ በተናገረ ማግስት ሞቶ መገኘቱ አጋጣሚ ሊሆን አይችልም። ግን ማስረጃ የለም። አጋጣሚ ግጥምጥሞሽም ሊሆን ይችላል። የሟች ጓደኛ ሞቱ ከፍትህ ጋር ከማውራቱ ጋር የተያያዘ መሆኑን በምን እርግጠኛ ሊሆን ቻለ?
“ትዝታ አንቺን ማግኘት ትፈልጋለች።” አለኝ በጎርናና ድምፅ “ምናልባት የምትነግርሽ ነገር ሳይኖር አይቀርም። የታዲዎስን አሟሟት ስነግራት ኩርምት ብላ ነበር የተንሰቀሰቀችው። እሷም ‘አስገደልከው’ አለችኝ። ማን? ለምን? ለሚለው ጥያቄዬ ግን መልሷ ዝምታ ነበር።” ሀዘናቸው ተጋብቶበታል። እሱም አስክሬን የሚጠብቅ ለቀስተኛ መስሏል።
“እሺ! አንተ ተረጋጋ እና ወዴት እንደሚወስደን እናስብ።”
“አይታይሽም? ወዴትም መሄጃ የለም።”
“ገና ከአሁኑ ተስፋ ቆርጫለሁ እንዳትለኝ? ገና ሳትጀምረው ይሄ ጉዳይ የተወሳሰበ ሊሆን እንደሚችል ነግሬህ ነበር። ገና ከመጀመርህ እጅ መስጠትህ ነው?” ስለው በቃል አልመለሰልኝም። ሁኔታው ግን
👍8
የመሸነፍ ነው። ላፅናናው አልሞከርኩም። ምን እያሰበ እንደሆነ አላውቅም። እኔም በሀሳብ ተጠምጃለሁ። …… ሆስፒታል ማደር የእርሱ ተራ ነበረ።
“ወደቤት ሄደህ እረፍ! እማዬጋ እኔ እሆናለሁ።” አልኩት። ሄደ። እስከ ሶስት ቀን አልተመለሰም። ስልኩም ዝግ ነበር።
“ምን ሆኖ ነው? አስቀየምሽው እንዴ? ንገሪኝ ምን ተፈጥሮ ነው?” እማዬ ሶስት ቀን ስላላያት በጥያቄ ልትደፋኝ ነው። በስራ ምክንያት መሆኑን ብነግራትም አላመነችኝም። ካሳሁን ሲመጣም ተመሳሳይ መልስ ቢሰጣትም አላመነችም። አባቴ እንኳን ‘ምነው ጠፋ?’ ብሎ ጠየቀኝ።
ትዝታን ላገኛት ቀጠሮ አስይዤ አገኘኋት። አልቅሳ የሷን ጉዳይ እንድንተወው ለመነችኝ።
“ነገር መቆፈራችሁን ካልተዋችሁ ሌላ ተጨማሪ ሰው ይጎዳል።” አለችኝ ቃል በቃል።
“ተጨማሪ ማለት ከታዲዎስ ሌላ ማለትሽ ነው? ማነው የሚጎዳው? ልጅሽ? አጎትሽ? ሌላ ማን?” ከዚህ በኋላ ለጠየቅኳት ብዙ ጥያቄ መልስ አልሰጠችኝም።
“የልጅሽ አባት በሰው ነው የተገደለው። በእርግጠኝነት የምታውቂው ነገር አለ። መናገር ግን አትፈልጊም። ማንን ነው እየተከላከልሽ ያለሽው? ለልጅሽ ስታድግ ምን ምላሽ ይኖርሻል? አባቴስ ስትልሽ ምንድነው የምትያት? የአባቷን ገዳይ በነፃነት እንዲኖር የፈቀድሽበትን ምክንያት ታስረጃታለሽ? አባቷን በግፍ ላጣች ልጅ በቂ ምክንያትስ ይመስልሻል? ወይስ የአባቷን አሟሟት ትዋሻታለሽ? እስከመቼ? እውነት ቢረፍድም አንድ ቀን መውጣቷኮ አይቀርም።……… ” ምንም ቢሆን እናት ናትና ደካማ ጎኗ ልጇ ናት። ትዝታ ግን አልተሸነፈችም። ልወጣ ቦርሳዬን ሳነሳ
“የሱ ልጅ አይደለችም። አባቷ አይደለም።” አለችኝ። ከዛ በላይ ግን ልትነግረኝ አልፈለገችም። እየወጣሁ ለፍትህ ደወልኩለት እና ተገናኘን። ከትዝታ ጋር ያወራሁትን ነገርኩት። ሞቶ የነበረው መነቃቃቱ አንሰራርቶ መላምቶቹን ይነግረኝ ጀመር።
“የልጇ አባት እሱ ያለመሆኑን የተናገረችው እውነት ከሆነ ትዝታ ከሌላ ሰው ጋር ግንኙነት ነበራት። ምናልባትም አጎቷ ልድራት ነው ካለው ሰውጋ… … አንዱ ባለስልጣን ወይም አንዱ ሀብታም ይሆናል። ምናልባት ሟች በሆነ መንገድ ከዚህ ሰው ጋር ተያያዥነት ሊኖራት ይችላል። …… ምናልባት…… በስመአብ ወ ወልድ… … እኔ ያሰብኩትን አስበሃል?”
“በትክክል!!…… እያሰብኩ ያለሁት እንደሱ ነው!” አለኝ

🌑ይቀጥላል➡️

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ የኔ ምርጦች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ በ Like Like እያጀረጉ

አስተያየት ካሎ በ @atronosebot አድርሱን
👍3
#ራሴው_ማበዴ_ነው
:
#ክፍል_አስር
:
ደራሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
:
...የገዛ ሚስትህ በአደባባይ አብረሃት እየሄድክ ጡቶቿን የከለላቸውን ጨርቆች ገፋ ሳምልኝ ብትልህ ብልግና ይሆንብሃል። በሷ ድርጊት አንተ ትሸማቀቃለህ። መኝታ ቤታችሁ ውስጥ ራቁቷን ሆና ያንኑ ነገር ብትልህ ለቦታው የሚገባ ቅድስና አድርገህ ልትቆጥረው ትችላለህ። ምናልባትም ከዛ በላይ ‘ስድ’ ብትሆንልህ ያምርሃል።
በመንፈሳዊው ዓለም የመጀመሪያው ለሰው ልጆች የተሰጠ የተፃፈ ህግ አስርቱ ትዕዛዛት ናቸው። አትግደል የሚል ህግ ፅፎ ሰጥቷቸዋል። ጠላት በተነሳባቸው ጊዜ ግን አሳልፌ ሰጥቻችኋለሁና ዝመቱባቸው ብሎ እልፎች ያስገድላል።
በምድረኛው ህግም መግደል ወንጀል ነው ይልሃል። አንዳንድ ወንጀሎች ግን በዛው ህግ በሞት ያስቀጣሉ። እናም ፍትህ ነው ይልሃል። በተመሳሳይ በቀል ሀጢያት ነው ይሉሃል። የበደለህን ሰው አስጠፍንገህ ወህኒ ማስወርወር ግን በቀል ሳይሆን ፍትህ ነው ትባላለህ። ምናልባት አንተም ከዛ በላይ የምታደርገው ላይኖር ይችል ይሆናል እኮ!
አየህ በዚህኛው አለም ስትኖር ሀጢያት ወይ ፅድቅ፣ ልክ ወይ ስህተት፣ መልካም ወይም ክፉ፣ ብልግና ወይ ጨዋነት… እነዚህ አንዱ ከሌላኛው ተቃራኒ ዋልታ የሚገኝ መቼም የማይስማሙ ሊመስል ይችላል። አይደለም! እንደውም አንዱ በአንደኛው የሚተካካበት ቦታ አለ። በመሃከላቸው የተሰመረ የሚመስልህን ቀይ መስመር ስታልፍ ከአንደኛው ክልል ወደሌላኛው አልተሻገርክም። ጊዜ፣ ቦታና ሁኔታ…… ምናልባትም ሌላ ተጨማሪ ገቢር ትርጉማቸውን ያፋልሰዋል።
የሆነውን ለመረዳት(ለመዳኘት አላልኩም) ከነዚህ ሁለት ተቃራኒ ፅንፍ ከሚመስሉ ሀሳቦች መሃከል በሀሳባችን በምናሰምረው መሃል መስመር ላይ እንቁም! ወደየትኛውም እቅፍ ተጠግተን አንሙቅ።
እናማ የሆነው እንዲህ ነው…………
አንድ
የውብ ዳር አባቴን እና እናቴን ለያይታ አባቴን ያገባችው ስላፈቀረችው አልነበረም። ለበቀል እንጂ! የውብዳርና እማዬ ከልጅነት ጀምሮ ጓደኛሞች ነበሩ። የውብዳር ወንድም ያፈቀራትን እናቴን ማግባት የነፍስም የስጋም ፍፃሜያዊ ትልሙ ነበር። እና እናቴ ከአባቴ ጋር ፍቅር ስትጀምር ለምናልባቱ ያስቀመጡት የባይሆን ጭላንጭል የሌላቸው ስጋና ነፍሱ አድመው በዚህ ዓለም ዓለመኖርን መረጡ። የውብዳር ለብቸኛ ታላቅ ወንድሟ መርዝ ጠጥቶ መሞት ተጠያቂዋ ጓደኛዋ መሆኗን ብታምንም በራሷ እጅ ፍትህን ካላደረገች በቀር በየትኛውም ህግ እንደማትዳኝ ታውቃለች። (እዚህጋ የእማዬን ሚና በትክክል አላውቅም። ‘ከዳችው’ የሚለውን የየውብዳርን ቃል ወይም ‘ምንም አልነበረንም’ የሚለውን የእማዬን ቃል የትኛውን እንደማምን አላውቅም።) የሆነው ሆነና እናትና አባቴ ሲጋቡ የእናቴ ሚዜዋ የውብዳር ነበረች። በዓል ሆኖ እኛ ቤት ያልመጣችበት ቀን የለም።(እናቴ ስራ የሆነችባቸውን በዓላት የእመቤትነት ስርዓቱን የምትከውነው እሷ ነበረች።) እኔ ወይ አባዬ ታመን እማዬ ከሌለች እያደረች የምታስተዳድረን እሷ ነበረች። ልደቴ ሲከበር የሚያጓጓኝ የእርሷ ስጦታ ነበር። በቤታችን የፎቶ አልበም ውስጥ እሷ የሌለችበት ፎቶ ውስን እንደሆነው ሁሉ በኑሯችን ውስጥም እሷ የሌለችበት ገፅ ውስን ነበር።
ዘጠኝ ዓመት እስኪሆነኝ ድረስ አባትና እናቴ ሲሳሳሙ ወይ ሲላፍ ደርሼባቸው በሀፍረት ጉንጫቸው ቀልቶ አስደንግጫቸው ይሆናል እንጂ ተጣልተው ሲጨቃጨቁ ከእንቅልፌ ነቅቼ ያውም እናቴ አባቴን በጥፊ ስትለው አይቼ በመጮሄ አስደንግጫቸው አላውቅም። በሰዓቱ የፀቡ መንስኤ እማዬ ፓንት መኝታ ቤት ማግኘቷ መሆኑን ብሰማም አባዬ ከየውብዳር ጋር መማገጡን እሱ ከሰጠኝ ደብዳቤዎች ነው የተረዳሁት። (በደብዳቤው ላይ ጠጥቶ እንደነበር እና ስህተት እንደሆነ ፅፎ ይቅርታ ይለምናታል። የውብዳር ፓንቷን መኝታ ቤት ጥላ መሄዷ ያሰበችበት ተንኮል ነበረ።) ከዚህ በኋላ በብዙ ላብና እድሜ የከመሩትን ጡብ በአንድ ቀን እንደማፍረስ ሁሉ ቤታችን የፈረሰው ተምዘግዝጎ ነበር። እማዬ የበለጠ የጎዳት ከሌላ ሴት ጋር መተኛቱ አይደለም። ከምትወዳት ጓደኛዋ ጋር መተኛቱ እንጂ…… የየውዳር በቀል የገባት ሲቆይ ነው።
እዚህ ተረክ ውስጥ ማናቸውም ጥሩ አይደሉም። ማናቸውም ክፉ አይደሉም። እንደማንኛውም ሰው ባበዙት ይጠሩበታል። ቤታችን በየእለቱ ጭቅጭቅ ሆነ። እማዬ አባቴን ጥላ ከእኔጋ ማደር ጀመረች። በነዚህ ሁሉ ጊዜያት የይቅርታ ደብዳቤ ፅፎላታል። ብዙም ሳይቆይ የውብዳር ማርገዟ ታወቀ። እናቴ ከልጁና ከእሷ እንዲመርጥ ነገረችው። ይሄን ከሰማች በኋላ እማዬ አንድ ቀን ከስራ ውጪ ሌላ ቦታ አደረች። ከሌላ ሰው ጋር… … አባቴ አወቀ። …… የአባቴ በደል ወይስ የራሷ ፀፀት አላውቅም ብዙ ሳይቆይ በአዕምሮ መታወክ ስራዋን አጣች። እህቷ ፀበል ይዛት ትኳትን ጀመር። አባቴ መምረጥ ነበረበት። እብድ ሚስቱን ወይም በፍቅርህ ሞትኩ የምትለውን የውብዳርን፤ በደሏን በራሱ በደል አጣፍቶ ይቅር ማለት እና ከእናቴ ጋር መኖር (ይሄ ያልተወለደች ልጁን ችላ ማለትን ያካትታል።) ወይም አዲስ ህይወት መጀመር።
አየህ ክልል ብሎ ፍልስፍና እንደሌለ? ያበደች ሚስቱን ትቶ ገና ተወልዳ ያላያትን ልጁን መምረጥ ልክ አይደለም። ለፍቅሩና ለሚስቱ አድልቶ በእነርሱ በደል ምንም የማታውቀውን ልጁን ቤተሰብ መንሳትም ልክ አይሆንም። ግድ ሲሆን ግን ከሁለት ስህተት አንዱን ስህተት መምረጥ ልክ ይሆናላ!
ትልቅ የሚባል ስኬት ፣ ፍፁም የሚባል ፍቅር ፣ ግዙፍ የሚባል እምነት ፣ የማይረታ የሚባል አንድነት…… ለመውደቅ ‘ትልቅ ምክንያት’ ሊያንገዳግደው ግድ አይደለም። ብዙ ትንሽ ምክንያቶች ከስሩ መንግለው ይደፉታል።
ሁለት
ቤተሰቦቼ በራሳቸው ጡዘት ሲጦዙ ዕጣ ፈንታዬ ምን እንደሚሆን አርቀው ያላሰቡልኝ እኔ እነርሱ በበሉት የተበላሸ ምግብ እኔ ስቀዝን ኖርኩ። እነርሱ በበሉት የተበላሸ ፍሬ የእኔ ጥርስ በለዘ። እናቴ በከፊል ጤነኛ በሆነ ጭንቅላቷ በከፊል በእህቷ ጭንቅላት ከአባቴ ጋር ላለመኖር ወሰነች። አባቴ የውብዳርን አገባ። ከአባቴ እና ከእንጀራ እናቴጋ ሁለት ዓመት ኖርኩ። ያጣሁት እናቴን ብቻ አልነበረም። አባቴም በዝምታና በድባቴ የተከበበ እኔ ከማውቀው ሳቅና ፍቅር ከሞላው አባቴ የተለየ ሌላ ሰው ሆነ። አብዛኛውን ምሽት አምሽቶ ጠጥቶ ስለሚገባ አላገኘውም። የቤቱ አዛዥ ሚስቱ ናት! እሱ ደግሞ ለሚሆነው ሁሉ መልሱ ዝምታ ነው። አክስቴ ስትወስደኝ ሚስቱ ምን ያህል እንደምትከፋብኝ ስለሚያውቅ አባቴ አልተቃወመም።
እዚህጋ ስህተትም ልክም ፅድቅም ሀጢያትም… … መልካምነትም ክፋትም… … ሁሉም ቦታ የላቸውም። ምክንያቱም ለእነዚህ ሁሉ ክስተቶች አንዲት ጥሬ ዘር ያላበረከትኩ እኔ ጎተራ ሙሉ መራራ ፍሬ ሳጭድ በየትኛው ሚዛን ተዳኝቶ ከአንዳቸው ይመደባል?
“ብትጠይኝ አልፈርድብሽም። በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ የተጎዳሽው አንቺ ነሽ።” አለኝ አባቴ ከዘመናት በኋላ ዛሬ ላይ
“ስለእውነት እንደክህደትህ ብጠላህ ደስ ይለኛል። ከቤትህ አውጥተህ እንደጣልከው ቆሻሻ ስለረሳኸኝ አስከፍልህ ነበር። እድሜ ለእናቴ በል በሷ ልብ ውስጥ ስላነገሰችው ማንነትህ ስል እንደማንኛውም በህይወቴ ትርጉም እንደሌለው ሰው ቆጥሬሃለሁ።”
“ምንም ብልሽ ላንቺ በቂ የሚሆን ምክንያት ልሰጥሽ አልችልም ግን አልከዳሁሽም አንድም ቀን ረስቼሽም አላውቅም አንቺንም ሆነ እናትሽን እንዳላያችሁ አክስትሽ በህግ አስከልክላኛለች። አንቺን ከእናትሽ መንጠቁ ደግሞ
እናትሽን እንደመግደል ነበር።”
አያችሁ…ትልቅ ምክንያት አያስፈልግም። አባት ልጁን ለመተው እንኳን ቢሆን ትንንሽ ብዙ ምክንያቶች ሀያል ጉልበት አላቸው እናቴን በማጣቱ መጎዳቱ፣ሌላኛዋንም ልጁን
👍8
እንደእኔ የተመሳቀለ ህይወት እንዳይኖራት ለመከላከል፣ የአክስቴ ሀይለኛነት፣ የእኔ እማዬጋ ለመኖር መፈለግ፣ የእንጀራ እናቴ ክፋት……… አንዳቸው ለብቻቸው ምንም የማይሆኑ ሲደማመሩ በኔና በሱ መሀከል ያለውን ትስስር መበጠስ የቻሉ ምክንያቶች ናቸው። አሁን ደግሞ ሚስቱን ሊፈታት ነው። ምክንያቱ ልጁ ስላገባች ከየውዳር ጋር የሚያኖር ምክንያት እንደሌለው ስለሚያስብ።
“ይቅርታ ልጄ! አሁን ይቅርታዬ ያለፍሽበትን ነገር እንደማይሽር አውቃለሁ። አስቤሽ ሁሌም እንደምታመም ግን እወቂ።”
“አሁን ዋናው ነገር የእማዬ ደስታ ነው። በቀራት ጊዜ ደስተኛ እንድትሆንልኝ እፈልጋለሁ።” አልኩት አንድ ቀን መጥቶ ይጠይቀኛል ብዬ የጠበቅኳቸው ቀናት እንዳልነበሩ፣ ከእኔና ከእናቴ የውዳርንና እህቴን በመምረጡ በእህቴ እንዳልቀናሁ፣ እነርሱን ትቶ ከእኛጋር እንዲኖር ልለምነው አስቤ እንደማላውቅ…………
ሶስት
ፍትህ ፍርዱ ልክ እንዳልሆነ እያወቀ ትዝታ 25 ዓመት ሲፈረድባት እጅ ሰጥቶ መቀመጥን መረጠ። ምክንያቱ ደግሞ የነበረው ምርጫ ማሸነፍ ወይ መሸነፍ አልነበረም። ይሄ ቀሽም የአንደኛ ደረጃ መምህር ያዘጋጀው ዓይነት ምርጫ ቀላል በሆነለት ነበር። ሁለት የማይመረጡ ምርጫዎች ነበሩት። ትዝታን ማዳን ወይ ቤተሰቡን ማዳን!! ትዝታን መርጦ ከሚወዳቸው አንዳችንን ማጣት ለእርሱ በምንም ስሌት ልክ አይሆንም። የሚወዳቸውን መርጦ ትዝታን መክዳትም በሂሳብም በሳይንስም ልክ አይሆንም። አየህ ድንበር ብሎ ፈሊጥ እንደሌለ? ግድ ሲሆን ከሁለት ስህተት አንዱን ስህተት መምረጥ ልክ የሚሆንበት አጋጣሚ ይፈጠራል። ቆይ ቆይ…… እንዲህ ቀላልና ምክንያታዊ ውሳኔ አልነበረም። ሁላችንንም ዋጋ ያስከፈ እንጂ……
እንደውም ትዝታን ማዳን የሚለው ምርጫ አይደለም። ትዝታ መዳን አትፈልግም። ደፍሯታል ወይም አታሏታል…… ልጅን ያህል ነገር ወልዳለች። ለምን ለዚህ ሰው ትከላከልለታለች? የልጇ አባት አጎቷ መሆኑን ፍትህ ሲጠይቃት ድንጋጤዋ እውነቱን ቢያሳብቅባትም ካደች።
“በቅቶኛል። ራሁ ይህቺ ልጅ ምንም መስዋዕትነት የሚገባት አይደለችም።” አለኝ ፍትህ።
“ፍትህ ለእርሷ ብለህ ነው ወይስ ለሙያህ? ለእውነት? ለፍትህ?”
“የሆነ ሰው አርፌ ካልተቀመጥኩ አንቺን፣ ካስዬን ወይ እማዬን እንደሚያስከፍለኝ አስጠንቅቆኛል። ማስፈራሪያ ብቻ አይደለም።” አለኝ በሰጋ ልብ። እሱ ይሄን ከማለቱ ከአንድ ሰዓት በፊት የማላውቀው ሰው ሆስፒታሉ መግቢያ ጋር አስቁሞኝ ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ ለእኔም ሰጥቶኛል።

🌑ይቀጥላል➡️

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ ያበረታናልና 👍
Like👍 እያደረጋቹ

አስተያየት ካሎ በ @atronosebot አድርሱን
👍3🥰1
#ራሴው_ማበዴ_ነው (የመጨረሻ ክፍል)
:
#ክፍል_አስራ_አንድ
:
ደራሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
:
...አልነገርኩትም። የማላውቀው ሰው የሆስፒታሉ መግቢያ በርጋ ጠብቆኝ የትዝታን ጉዳይ ማነፍነፍ ካላቆምኩ ከምወዳቸው ሰዎች አንዳቸውን እንደማጣ እንዳስጠነቀቀኝ አልነገርኩትም። ብዙ ነገር አልነገርኩትም። እንዲያውም ምንም አልነገርኩትም። እማዬ ከዚህ በኋላ ህክምና የሚፈይድላት ነገር ስለሌለ ወደቤቷ ወስደናት ዓይን ዓይኗን እያየሁ የምትሞትበትን ቀን መጠበቅ ትኩስ ቁስል ላይ ሚጥሚጣ እንደመበተን እየለበለበኝ እንደሆነ አልነገርኩትም። እቅፉ ውስጥ ሆኜ እዬዬ ብዬ ማልቀስ እንደምፈልግም። ከሰሞኑ አባቴን ሆስፒታል በማድረስ ሰበብ አዘውትረው ሲመጡ እህቴና ባሏን ማየት ልቤን በደም ፈንታ ቅናት እንደሚያስረጨው አልነገርኩትም። በእኔና በእርሱ መሃል ምንም ነገር እንደሌለ የሚሆነው መሆን እየከፋኝ አልቅሺ አልቅሺ እንደሚለኝ አልነገርኩትም። በዚህ ሁሉ ማጥ ውስጥ አቅፎኝ ያደረ ቀን የማግኩት ጠረኑን እርሱ አጠገቤ ሳይኖር እንኳን ካለበት ንፋሱ እያንጓለለ ለአፍንጫዬ እንደሚያቀብለው አልነገርኩትም። አጠገቤ ሆኖ ስለስራ እያወራኝ ልነካው እንደምፈልግ፣ ልስመው እንደምጎመዥ፣ እርሱ የኔ ቢሆንና በፈለግኩት ቁልምጫ ልጠራው እንደምመኝ… … አልነገርኩትም።]
“ማንናቸው?” አለኝ ዓይኔን ተከትሎ መኪና ውስጥ ያሉትን እህቴንና ባሏን እያያቸው
“እህምም…… እህቴ ናት! ባሏ ነው። አባቴን ወደቤት ሊያደርሱት እየጠበቁት ነው።” አልኩት አንገቴን ሰብሬ
“ታዲያ ምን?” አለኝ ዓይኔን እየፈለገ
“ምን?”
“ለምንድነው ስታያቸው በነበረው እይታ የምታያቸው? ምንድነው እሱ?”
“ኸረ ምንም አይደለም። በቃ ከእህቴ ጋር ስለማንነጋገር ነው።”
“አይደለም ራሁ። እያየሁሽ እኮ ነው። ቆይ ምንባደርግ ነው የተሰማሽን ልትነግሪኝ የምታምኚኝ? የበለጠ የቀረብኩሽ በመሰለኝ ቁጥር ለአካልሽ እንጂ ለልብሽ አልቀርብሽም። አብሬሽ ውዬ ባድር ቅርበቴ አይሰማሽም።…”
“ፍቅረኛዬ ነበረ። እህቴ ያገባችው ሰው…” ወቀሳውን እንዲያቆምልኝ ይሆን ለልቤ መቅረቡን እንዲያውቅልኝ አላውቅም። ነገርኩት!!
[ ዘጠነኛ ክፍል ስገባ አንድ ወንበር ላይ ከተቀመጥን ጀምሮ ብቸኛ ጓደኛዬ ዓለማየሁ እንደነበረ ግን አልነገርኩትም። የአስረኛ ክፍል ፈተና ተፈትነን ከተማሪዎች ጋር ከከተማ የወጣን ጊዜ ከንፈሬን ሲስመኝ ከርሱ ውጪ ያለውን ዓለም እንደረሳሁ አልነገርኩትም። በመከራ ከተከበበው ኑሮዬ የተረፈኝን ሰዓት ከርሱ ጋር ማሳለፌ በነገ ተስፋ እንዳልቆርጥ መፅናኛዬ ሆኖ በጥሩ ውጤት አብረን ዩንቨርስቲ እንደገባን አልነገርኩትም። ብዙ ጊዜ ‘ድብቅ ነሽ አላውቅሽም’ እያለ ቢነጫነጭም ይተወኛል ብዬ ለአፍታ አስቤ ባለማወቄ ሲተወኝ ከእማዬጋ አብሬ ማበድ ዳድቶኝ እንደነበረም አልነገርኩትም። የባሰው ደግሞ ከዓመታት በኋላ እሱ ዩንቨርስቲ አስተማሪ ሆኖ ተማሪው ከሆነችው እህቴ ጋር በአጋጣሚ ይሁን አስቦበት እስከአሁንም በማይገባኝ ሁናቴ ግንኙነት መጀመራቸውን ሆነ ብሎ ደውሎ የነገረኝ ማታ ራሴን ልስት እንደነበረ አልነገርኩትም። እህቴ ከዩንቨርስቲ በተባረረች በወራት ውስጥ የሰርጋቸው ጥሪ ካርድ ሲደርሰኝ ራሴን ባለመፈለግ ስሜት ውስጥ አዝቅጬው መብሰክሰኬን አልነገርኩትም። ከዓለማየሁ በፊትም በኋላም ሌላ ፍቅር እንደማላውቅም አልነገርኩትም።]
“እና አሁንም ድረስ ትወጂዋለሽ? እየቀናሽ ነው?” አለኝ
“አይይይ ለሱ ምንም ስሜት የለኝም። በሱ አልቀናም።”
“በሷ?” እያለኝ በጣም ተጠጋኝ። ትንፋሹ ጉንጮቼ ላይ እያቃጠለኝ አስቤ የተሰደሩ ቃላት መናገር አልችልም ነበር። በጭንቅላቴ ንቅናቄ ‘አዎን’ አልኩት። አልበቃውም እንድቀጥልለት ይጠብቃል። ምራቄ እያነቀኝ ነው።
“አባቴ ከእኔ እሷን ነበር የመረጠው። ፍቅረኛዬም… …” አላስጨረሰኝም ከንፈሬን በከንፈሩ ከደነው። መሳሙ ቀለምም ነበረው፣ ሽታም ነበረው፣ ጣዕምም ነበረው……
“በሚፈጠሩ ክስተቶች ውስጥ ራስሽን እየከተትሽ አትስፈሪ። ሁኔታዎች ሁሉ አንቺን ሚዛን ላይ አስቀምጠው አይለኩም።” አለኝ ለምን ያህል ደቂቃ እንደሆነ ስሞኝ ሲያበቃ… … ሰምቼዋለሁ? ገብቶኛልስ? መሳሙን እያጣጣምኩ ነበር።
“ተያቸው! እርሻቸው!” አለኝ ወደእነእህቴ እያየ። እያየኋቸው ነበር። የልጅ ስሜት ቢመስልም አዎን ሲስመኝ ማየታቸውን ለማረጋገጥ ነበር የማያቸው። አለ አይደለ እኔም ሰው አለኝ አይነት! አልጎዳችሁኝም አይነት! እንዳዩኝ በማወቄም በከፊል የታባታችሁ አይነት ስሜት……
በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ብዙ ነገር ተቀየረ። እንደውም ሁሉም ነገር!! እማዬ ወደቤት መጣች። ካስዬና አባቴ እቤታችን እየመጡ እናቴን መጠየቅ ጀመሩ። እኔና ፍትህ ቤተሰቦቻችን እስኪያውቁ እንደፍቅረኛሞች ገብተን መውጣት ጀመርን። ፍትህ የትዝታን ጉዳይ ተለዋጭ ቀጠሮ ሊጠይቅ በተዘጋጀበት ወቅት እጅ ያሰጠው ሁናቴ ተፈጠረ። አባቴ ሞቶ ተገኘ።
ቆይ ቆይ ፍትህ በትዝታ ጉዳይ ተስፋ መቁረጡ እና 25 ዓመት ሲፈረድባት መዋጡ ቀላል አልነበረም። ቤተሰቡን በሙሉ ያስከፈለ መስዋዕትነት እንጂ… …… ካልንበት እንቀጥል። አባቴ ተገደለ! ይቅርታ እንዳደርግለት ሲለማመጠኝ የነበረው አባቴ አንድስ እንኳን በጎ ቃል ሳልነግረው ሞተ። በራሴው ጉዳይ እርሱ አንዲት ጠጠር ባላበረከተበት የነገር ካብ ህይወቱን አጣ!! ለፍትህ ይሄ የመጀመሪያው መሆኑ እና ካላረፈ ሌሎቻችንም ተራ ጠባቂዎች መሆናችን እና ቀጣይዋ እኔ መሆኔ ማስጠንቀቂያ ደረሰው። ይሄኔ ነው እጅ የሰጠው! ከእኔ በላይ ሁሉ የተጎዳ መሰለኝ።
“በፍፁም አንቺን ለምርጫ ማቅረብ አልችልም። አንቺን ማጣት አልችልም።” ይለኛል እየደጋገመ። ለማን እንዳለቀሰ ያልገባኝን ለቅሶ በአባቴ ቀብር ላይ ምርር ብሎ አለቀሰ። ግራ የገባው ስሜት ውስጥ ጠለቅኩ። አንዱ አካሌ ሽባ የሆነ ነገር ይመስለኛል። ከሬሳው ጋር የቀበርኩት ነገር ያለ ይመስል የሆነ ስሜቴ ወደአባቴ መቃብር ይጎትተኛል።
የባሰው ነገር ለእናቴ የፍቅሯን ሞት ማርዳት ነበር። በየቀኑ እየመጣ ሲያያት የከረመውን ሰው በምንም ሰበብ ቀረ ልንላት አንችልም። እንደገና እንደተዋት በምንም ምክንያት ሰንገን ብንነግራት ጤነኛ አትሆንም። መሞቱንም ብታውቅ ጤነኛ አትሆንም። ቢያንስ ግን ከመከዳት ስሜት ፍቅረኛዋ እያፈቀራት መሞቱን ማወቋ ይሻላል በሚል ተስማምተን የተሻለ ሁኔታ ላይ ያለው ካስዬ ነገራት። ዝም አለች። ለሁለት ሰዓታት ዝም አለች። እኔን የምታይበትን መንገድ አልወደድኩትም። ያንቺ ጦስ ነው ፍቅሬን ያሳጣኝ አይነት መልዕክት አለው። ድንገት ከየት ባመጣችው ጉልበት እንደሆነ እንጃ ተስፈንጥራ ተነስታ ቀብሩን እሄዳለሁ ብላ አመሰችን። ካስሽ ይዟት ሄደ። ካስሽ ደግፏት ፍቅሯ አፈር ሲገባ አነባች። አለቃቀሷ ግጥምም ቃልም ሳይኖረው ዜማ አለው። እያየኋት ለአባቴ ይሁን ለእርሷ ብቻ አነባሁ! ስለእውነት የውብዳር እንኳን ስታለቅስ አሳዘነችኝ። በየመሃሉ ለሞቱ ተጠያቂ መሆኔን ልትነግረኝ አንዳንድ ሀረግ ትመዛለች። እህቴ አፈሩ ላይ ተልሞሰሞሰች። ትንፋሽ አጥሮኝ ደረቴ ላይ ሲያፍነኝ ነው ቀብሩ ያበቃው እና ወደቤታችን የተመለስነው።
እቤት ከመግባታችን እማዬ “ይሄ የበረራ ቁጥር… …” ማለት ጀመረች። መሬቷ ያንሳፈፈችኝ አይነት ስሜት ተሰማኝ። ግራቪቲ የከዳኝ! ያልበላሁት ምግብ ወደ ላይ ወደላይ አለኝ። እሪሪሪ ብዬ ማልቀስ እፈልጋለሁ። ግን ጉሮሮዬም ደረቴም የታፈነ ይመስለኛል።
“እኔ አለሁ አንቺ እረፊ!” አለኝ ካስዬ። እንዳለውም ከዚያን ቀን በኋላ ኖረ። ምክንያቱም በሚቀጥሉት ቀናት እናቴ ማነሽ? ማለት ጀመረች። ፍትህንም ስታይ መበርገግ ጀመረች። የሚገርመው ካስዬን በባሏ ስም አንድዬ
👍81😁1
እያለች መጥራት ጀመረች። ከእርሱ ውጪ ማንንም አታስጠጋም። (ሀኪሟ እሷ እንኳን ሳታውቀው ለካስዬ የሆነ የተለየ ስሜት እንደነበራት እና ሲያማት ከፍቅሯ ጋር እንደተማታባት ሳይኮሎጂ ጠቅሶ መላ ምት መታ።) ፍትህ በኔ ልመናና ጭቅጨቃ ይግባኝ በመጠየቁ ስጋቱ ሊያሳብደው ደርሶ ራቅ ያለ ቦታ አዲስ ቤት ተከራይተን አብረን መኖር ጀመርን።
” 20 ዓመት ሙሉ ያላየሁት አባቴ ለወራት ካጠገቤ ነበረ። ይቅር በይኝ እያለኝ ፣ እንደምጠላው እያሰበ… አልጠላህም ሳልለው፣ ስናፍቅህ ነው የኖርኩት ሳልለው፣ ይቅር ብዬሃለሁ ሳልለው ነው የገደሉት……” እንባዬን ማስቆም ተስኖኝ በመሃከላችን ባለው ርቀት እንዲሰማት ጮክ እያልኩ ለትዝታ ነው የምነግራት። አትመልስልኝም። የአባቴ መሞትም የእኔ እንባም ስሜት የሰጣት አትመስልም።
“እናቴ ልትሞትብኝ ነው። በሰዎችሽ ጦስ አዕምሮዋ ተቃውሶ እኔን ልጇን እንኳን አታውቀኝም። ያ ምን ማለት እንደሆነ ታውቂያለሽ? ማን እንደሆንኩ ሳታውቅ ሳትሰናበተኝ እማዬ ትሞትብኛለች ማለት ነው።” ብዙ የሀሳብ ድሮች ያደሩበት በሚመስል ጠባብ እይታ ታየኛለች እንጂ አትመልስልኝም።
“ፍቅረኛሽን አስገድለውታል። አንቺንም ለማይሆን ህይወት ዳርገውሻል። ሀያ አምስት ዓመት ወህኒ እንድትበሰብሺ አጨብጭበው ሸኝተውሻል።ልጅሽም ነገ እጣዋ ምን እንደሆነ አይታወቅም። እና አሁንም ለእነርሱ ትከራከሪያለሽ! ምንድነው ችግርሽ? አሁን ካለሽበት የባሰ ምን እንዳይመጣ ነው?…… ” ለፍልፌ ሳበቃ
“እወደዋለሁ።” አለችኝ
“ማንን?” የማስበው እውነት ባይሆንና ብንንን ብሎ ቢጠፋ እየተመኘሁ
“ሰለሞንን!”(አጎቷ ነው) ደነዘዝኩ። ከሁለት አንዳችን ጤነኛ ባንሆን ነው። ለተከታዮቹ ደቂቃዎች እሷ ተናጋሪ እኔ በድን ሰሚ ሆንን። ትቻት ስወጣም በድኔን እየጎተትኩ ነበር። ጭንቅላቴ ውስጥ የሀሳብ መዘውር ያለ ይመስለኛል። አንዱ ሀሳብ ሌላውን እያስከተለ በመዘውሩ የሚፈጭ…… ርርርርር የሚል የሞተር ድምፅ ያለው መዘውር።
ሰውየው አስገድዷት አይደለም። ገና ከ12 አመቷ ጀምሮ እያባበለ ያስለመዳት የስድ ጨዋታ ነው። ለምዳዋለች። ልምዱን አልጠላችውም። እንደውም ስታወራኝ እንኳን ከሚወዱት ፍቅረኛ ጋር እንዳሳለፉት ጣፋጭ ጊዜ የፊቷ ፀዳል እየበራ ነው። በመጀመሪያ ፊልሞች ያሳያታል። እያንገላቱ፣ እያሰቃዩና እየገረፉ የሚረኩ ወንዶች ፊልም… … በስቃዩ ውስጥ የተሳመች ያህል በማቃሰት የምታብድ… … እንዲያሰቃያት የምትለምን ሴት ያለችበት ፊልም… … ቀስ በቀስ አለማመዳት። ጤነኛ ሰው ሊወደው የማይችለውን sex torture እንደ ሱስ ለመደችው። ደስ ብሏትና ፈልጋ የምታደርገው ቅውሰት ሆነ። አጎትየውን ከሴት ጋር ስላገኘችው በእልህ ታዲዎስን ፍቅረኛዋ አደረገችው። ሰላማዊው ታዲዎስ አጎቷ የሚነዳትን የእብደት ቁልቁለት ሊያንቆለቁላት አይችልምና ሱስ እንዳባዘተው ወመኔ በሱስ ጥም አዛጋች። ከሁለቱም ጋር ሆነች። በዚህ መሃል የአጎቷን ልጅ አረገዘች። ታዲዎስ የእኔ ልጅ ነው ብሎ ቁምስቅሏን ሲያሳያት ነው እውነቱን የነገረችውና የዘመኑ ቁጥር በአጎቷ በጎ ፈቃደኝነት እንዲወሰን የፈረደችበት። ከዛ የቫንፓየር ወይ የማርስ ፍጡሮች ተረት እንጂ ሰውነት የማይመስል አኗኗር ሰውየው ከወንድሙ ልጅጋር እንደባልና ሚስት ኖሩ።… … የዛን ዕለት ምሽት ሴት ይዞ እቤት መጣ! በቅናት የነደደ አካሏ ያዘዛትን አደረገች። ምንም የማታውቅ ንፁህ ነፍስ ጠፋች።
“ልጄ ከአጎቴ እንደወለድኳት እንድታውቅ አልፈልግም። ሶልም ይሄ ነገሩ ቢታወቅ ስሙ ይጠፋል፣ ይታሰራል። የወንድሙም ስም አብሮ ይነሳል(ባለስልጣን ወንድሙን ማለቷ ነው።) ሶልን እወደዋለሁ። መጥፎ ነገር እንዲደርስበት አልፈልግም።” አለችኝ የሆነ ልክ የሆነ ነገር እንደነገረችኝ ሁሉ ሀፍረት ሳይሰማት። ዘገነነችኝ። በእርግጥ አሳዘነችኝም። የሆነ አይነት በሽታ እንደሚሆን አሰብኩ። የገዛ ሰውነቴ እየሸከከኝ ወጣሁ። ጭንቅላቴ ውስጥ ያለው መዘውር አልቆመም።
የኑሯችን መዘውር የሚዞረው በሚገጥሙን ክስተቶች ግብዓትነት አይደለም እያልኩ አስባለሁ። ይልቅስ በገጠሙን ክስተቶች ላይ በወሰንነው ውሳኔና በዘረጋነው እርምጃ እንጂ…… ኑሯችን የውሳኔያችን ውጤት እንጂ ያጋጠሙን መከራና ፍሰሃ ውጤት አይደለም። ……
“ literally she is sick, serious ህክምና ያስፈልጋታል።” አለኝ ፍትህ ነገሩን ስነግረው እየሰቀጠጠው።
“ከአሁን በኋላ የትዝታ ኬዝ አይደለም። አባቷን በስድ ግፈኞች የተቀማች ልጅ ኬዝ ነው። የራሴ ጉዳይ ነው።” አልኩኝ ከመናገሬ በፊት ያሰብኩት ያልመሰለኝን ንግግር!

🌑አለቀ🌑

ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁን በሙሉ እናመሰግናለን🙏

አስተያየት ካሎ በ @atronosebot አድርሱን
አስተያየት መስጠት ላልተመቻችሁ Like👍 በማድረግ አብሮነታችሁን አሳዩን።
👍11
#ስኳር_መች_ይጣፍጣል?!

በዚህ እጅ ያልነካው ወዳጅ በማይገኝበት ክፉ ዘመን ሰላሳ አራት አመት እስኪሞላት ድረስ የማንም እጅ ሳይነካካት ከወር በፊት የተሞሸረች ልጃገረድ ወዳጅ አለችኝ።

‹‹ያላገባኝ አይነካኝም!›› ብላ….
‹‹ወንድ ልጅ ወተቱን በነፃ ካገኘ ላሚቱን አይገዛም›› ብላ…
ስንቱን የወንድ ፈንጂ በጥንቃቄ እንጣጥ ብላ፣ ስንቱን አማላይና አታላይ አምልጣ፣ እሷም እንደማንም ግጣሟን አገኘችና ጎጆ ወጣች። ተሰበሰበች። አገባች….ተነካች።

በቃል እና በእምነቷ መሰረት፣ ክብር እና ንፅህንናዋን ጠብቃ ኖረ ተዳረች። ከባሏ ተኛች።

በዚህ ዘመን ቀረ ብለን የምንገረምበት ወግ አጥባቂነቷ የአስናቀች ወርቁን ዘፈን ያስታውሰኝ ነበር። አስናቀች ቀኑን ሙሉ ከምታፈቅረው ልጅ ውላ ልክ ሲመሽ ሌላ እንዳያስብ ‹‹ልሂድ›› ስለምትል ወዳጄን የምትመስል ሴት ዘፍናልን ነበር።

‹‹ፍቅርዬ- ፍቅርዬ ደህና ሁን
ሊመሽ ስለሆነ መሄዴ ነው አሁን…..
…እኔ እንደምወድህ – ፍቅሬ ሆይ ውደደኝ
በህጋዊ ስርአት ማልድና ውሰደኝ…
አፍቅረኝ ላፍቅርህ ኑሯችን ባንድ ይሁን
እስከዚያው ድረስ ግን- ፍቅርዬ ደህና ሁን›› እያለች ዘፍናልን ነበር።

እናም…የ34 አመቷ ወዳጄም በህጋዊ ስርአት፣ በአማላጅና በምልጃ የፈለገችውና የፈለገችውን አገኘችና፣ ወሰዳትና አገባች። ተነካች።

ሰርጉ ተከናውኖ…
ጫጉላው አብቦ…
ከስንት ያመለጠው ብር አምባር ተሰብሮ ጥቂት ቀናት ካለፉ በኋላ አሁንስ ይበቃታል ብዬ ደወልኩላት። እንዴት ሆንሽ….አጥሚትና ገንፎ የት ይዘን እንምጣ ልል እና ላጫውታት ደወልኩላት።

ብዙ ሳይጠራ አነሳች።

(በቅቷታል ማለት ነው…)

ሰላምታችን ሲያልቅ ወደ አንገብጋቢውጉዳይ ገባሁና..
‹‹እህስ…ነገሩስ? እንደጠበቅሸው አገኘሽው ወይስ ቅር አለሽ?›› አልኳት።
‹‹ቅር አለሽ ወይ? ወይ ጉድ…አንቺ….ስኳር መች ይጣፍጣል?!›› ብላ መለሰችልኝ።

ከአንጀቴ ሳቅሁ።

እንዲህ ትላለች ብዬ ስላልጠበቅኩም፣ ያ ከአመታት በፊት የሰማሁት ታሪክ ላይ ያለችው ልጅንም አስታወሰችኝና ሳቅሁ።

(ታሪኩ እንዲህ ነው። ልጅቱ ለስኳር ያላት ፍቅር የትዬሌሌ ነው። ‹‹ከስኳር የሚጥም፣ ከስኳር የሚጣፍጥ ነገር በአለም ላይ…አንዳችም ነገር የለም›› የምትል አይነት። እጮኛዋ ‹‹ተይ ተጋብተን ፍቅር ስንሰራ ኋላ ሃሳብሽን ትለውጫለሽ›› ቢላትም እሷ ግን ወይ ፍንክች! በኋላ ጋብቻው ተከናውኖ ባልና ሚስት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅር እየሰሩ ወደ ማገባደዱ ሲደርሱ የሚስቱን ሁኔታ ያየው ባል በእጁ የጨበጠውን ስኳር በተከፈተ አፏ ውስጥ ሙጅር ያደርጋል። ይሄን ጊዜ የስኳር ነገር የማይሆንላት ሚስቱ ምን አለች? ‹‹ውይ ውዴ…! የምን አፈር ነው አፌ ውስጥ የጨመርከው?!››)

‹‹ወይ አንቺ…እና ታዲያ ይሄን ያህል ጊዜ በመቆየትሽ ትንሽ አልተቆጨሽም ታዲያ?›› አልኳት
ለመመለስ ሰከንድ አልፈጀባትም።
‹‹በጭራሽ! መቆየቴ መቼም አይቆጨኝም….ግን እንዲህ መሆኑን ግን ነገራችሁኝ አታውቁም….››
‹‹ ብንነግርሽስ ኖሮ?››
‹‹እሱስ ምንም ለውጥ አያመጣም ነበር…ያው ምናልባት ትንሽ…ይበልጥ ልጓጓ ግን እችል ነበር……..››

ወሬያችን አልቆ ስልኩን ስዘጋ በዚህ ሁሉም ሰው ሁሉንም ሰው ለመምሰል በሚሮጥበት ጊዜ፣ ለግል አቋምና እምነቷ ባላት ታማኝነት እንዳዲስ ተደነቅኩባት። ቀናሁባት።
ከዚህ ሁሉ በላይ ግን (በእኔ እና በአለም ስሌት) ዘግይታም ቢሆን አዳሜ የአለምን ምሬት የሚያጣፍጠው ፍቅርን በመስራት ስኳር መሆኑን በማወቋ ተደሰትኩላት።

🔘በሕይወት እምሻው🔘
👍5
#ማፍቀር_ወይስ_መለየት ?
:
#አጭር_ልብወለድ
:
ቅዳሜ ከሰአት በኋላ ፣ፀጥ ረጭ ብሏል፣ የቤታችን የግድግዳ ሰአት ብቻ . . .ችው . . . ችው
እያለ በዚህ ፀጥታ ውስጥ ይሰማል። ማንም የለም እኔና እኔ ብቻ። በውስጤ የብቸኝነት ስሜት ተሰማኝ። በዚህ በጠራራ ፀሐይ እቤት ውስጥ ለብቻ መቀመጥ ምን ያህል ይከብዳል እያልኩ ከራሴ ጋር አወራለው።

ዞር ብዬ ክላሲካል ሙዚቃ ሲያሰማ ወደ ነበረው ቴፕ ስመለከት መብራት ሄዶ ዝም እንዳለ ታወቀኝ። ሀሳቤን ሰበሰብኩና በእጄ ወደያዝኩት ልብ ወለድ መፅሀፍ አቀርቅሬ ማንበቤን ቀጠልኩ።

በጥሩ ተመስጦ ውስጥ እንዳለው ድንገት ከአጠገቤ የነበረው ስልክ ጮኸና ቀልቤን ገፈፈው።በጣም ደነገጥኩ። በራሴ መደንገጥ ተገረምኩና እራሴን አረጋግቼ የስልኩን እጀታ በጉጉት አነሳሁት።

<<ሃሎ>> አልኩኝ በትህትና
<<ሄሎ>> አለችኝ አንዲት ልጅ በሚያባባና በሚያምር የድምፅ ቅላፄ።
<<ማንን ፈለጉ ?>>
<<እ. . .ናሆምን ላገኘዉ እችላለሁ ?>>

በዚህን ግዜ የልብ ትርታዬ ፍጥነቱን ጨመረ።
ድምፆም አዲስና የሚማርክ ስለሆነብኝ ማን ልትሆን ትችላለች? በሚል ከራሴ ጋር ትንሽ ተሟገትኩና።

<<ነኝ. . . ማን ልበል?>>
<<. . . ሜሮን እባላለሁ >>
<<ሜሮን?.. .ይቅርታ. . . አላስታወስኩሽም፣ ሜሮን ማን ?>>
<<ሜሮን አለሙ>>

አሁንም ፈፅሞ ላስታውሳት አልቻልኩም።ሜሮን የምትባል ልጅ ፈፅሞ ማወቄን እርግጠኛ አልነበርኩም።

<<በ. .ጣም.. ይቅርታ የኔ እህት አላወኩሽም።>>
<<ይገርምሀል እኔም አላውቅህም።>>
<<የደወልሽው አንቺ መሰለሽኝ?>>
<<አልተሳሳትክም፤ ማለቴ ስልክህን የአስረኛ ክፍል ማስታወሻ ደብተሬ ላይ ከበስተጀርባው ተፅፎ ነው ያገኘሁት።ሁለት አመት እንዳለፈውና በራሴ እጅ ፅሁፍ ስለመፃፉ እርግጠኛ ነኝ ነገር ግን በምን ቀንና ሁኔታ እንደተፃፈ አላስታውሰውም
<<እና?>>
<<እናማ ብዙጊዜ ሲከነክነኝ የነበረ ስልክ ቁጥር ስለነበር ምን አልባት አንተ ካወከኝ በሚል ነበር የደወልኩት።

መልሶን ማመን አቃተኝ።ለሰኮንዶች ያህል በአይኔ የማውቃቸውን እንስቶች በአይነ ህሊናዬ እየቃኘኋቸው ድምፅን ከምስል ጋር ለማዛመድ ሞከረኩ።ሆኖም በፍፁም ልትመጣልኝ አልቻለችም ።በርግጥ ከሁለት አመት በፊት ስለተከሰተ ነገር ማስታወስ ይከብዳል።

የቀረን ነገር ቢኖር በግምት ልንተዋወቅበት የምንችልበትን ሁኔታ መመርመር ነውና ስለየግል ህይታችን መነጋገር ጀመርን።ስለ ት/ቤትና ስለመኖርያ ስፍራችን፣ ስለቤተሰብ እንዲሁም ስለ ቅርብ ጓደኞቻችን ሳይቀር በግልፅ ተወያየን።በሚገር ሁኔታ ግን አሁንም ከጥርጣሬ ያለፈ እዚህ ቦታ ይሆናል ብለን መወሰን ተቸገርን።

ለቀልድ ነው ብዬ እንኳን እንዳልጠረጥራት የምትሰጠኝ መልሶች ሁሉ ግልፅና ፈጣን ነበሩ።
በተለይ ከንግግሯ በራስ መተማመንና በሳልነቷን ለመገመት ይቻል ነበር።ሁኔታው ቢያስገርመኝም ቀስ በቀስ ምርመራውን ትተን ስለየጎል ህይወታችን ገብተነሰ መጨዋወት ጀመርን።

<<ምን አየሰራሽ ነው አሁን?>>
<<ያው አስረኛ ከጨረስኩ በኋላ የሁለት አመት አካውንቲንግ ፊልድ ተምሬ ነግል ድርጅት ውስጥ በመስራት ላይ ነኝ። አንተስ?>>
<<እኔ እንደምንም የመሰናዶ ትምህርት ተምሬ አ.አ.ዮ የአስተዳደር ትምህርት በመማር ላይ ነኝ>>
<<ኦው ጎበዝ ተማሪ ነሃ . . .!>>
<<ነኝ ብለሽ ነው . . . ለመሆኑ ግን ምን ከይነት ሰው ነሽ ማለቴ መልክሽን?>>
<<...እኔጃ ለመግለፅ ይከብዳል።>> ሳቅ እያለች።
<<ታድያ.... ለምን በአካል አንገናኝም፤ >>ምን አልባት በመልክ ልንተዋወቅ እንችላለን?
ጥያቄውን በድፍረት ነበር ያነሳሁት ፤ሆኖም በፍርሀቴ ልክ መልኳን ለማየት ጉጉቱ ነበረኝ። እርሷም በመግደርደር ይሁን አላውቅም።

<<..መገናኘቱ እንኳን የሚመች አይመስለኝም።>
<<ለምን?>>
<<እኔንጃ?>>
<<ፈራሽ እንዴ?>>
<<አይ መፍራት ሳይሆን ሰሞኑን ክፍት ሰአት ስለሌለኝ ነው።>>
ንግግሯ እንደማቅማማት አይነት ነበር ፤ እርግጠኛ አልነበረችም።

<<እሺ. . . ብዙ አላስጨንቅሽም ባይሆን ስልክሽን ስጭኝና ተደዋውለን ሌላ ግዜ እንገናኛለን።>>

ለተወሰኑ ሰኮንዶች ዝም አለች።የኔንም ግራ መጋባት ጥርጣሬ አጎላችው።

<<ምነው ዝም አልሽ?>>
<<...ስልክም አሁን ልሰጥክ አልችልም።>>
<<እህ..ያሁሉ የግል መረጃሽን በግልፅነት ስትነግሪኝ ቆይተሽ እንዴትስልክ መስጠት ከበደሽ?>>
<<በፍፁም መደበቄ አይደለም።በዚህን ሰአት እኔን የምታገኝበት ስልክ ምን አልባት ለሁለት ቀን ብቻ የሚቆይ ነው ። ሌላ ስልክ በሌላ ግዜ እንጂ አሁን ልሰጥክ አልችልም ወይም አላውቀውም።>>
<<አሀ ገባኝ፣ ቤት ልትቀይሩ ነው አይደል?>>
<<አረ አይደለም >>ሳቅ እያለች ነበር።
<<ምንድን ነው እሱ ግልፅ ሁኚ እንጂ የደበቅሽው ነገር ኦንዳለ ይሰማኛል።>>
<<በቃ ለምን ነገ ወደ ማታ አንገናኝም?>>
የአቋም ለዉጧ አስገርሞኛል፣አስደንግጦኛልም።
አሁን ለመናገር ያልፈለገችው ሚስጥሯም ከልብ አጓጓኝ።
<<ጥሩ የት እንገናኝ?>>
<<ፒያሳ ያለው ቤቲ ካፌ ይመችካል?>>
<<ደስ ይለኛል ስንት ሰአት?>>
<<አስራ ሁለት ሰአት።>>
የሰአት ምርጫዋ ወደ ማታ መሆኑ አይናፋርነቷን ቢያስገምተኝም ለኔም ጥሩ ግዜ ስለነበር ወድያው ምልክቶቻችንን መለዋወጥ ጀመርን ።
የሷን አንድ በአንድ ከሰማሁ በኋላ ፣ የኔንም እንዲሁ ነገርኳት።እንደምልክት አገላለጿ በጣም ውብ ልጅ እንደምትመስል ገምቻለው ።ነገር ግን ከዚህ በፊት ያየኋት ትሆናለች የሚል ሀሳብ አልነበረኝም።

ይቀጥላል

Like 👍 Like 👍

አስተያየት ካሎ በ @atronosebot አድርሱን
👍13
#ማፍቀር_ወይስ_መለየት(የመጨረሻ ክፍል)
:
..ሰአቴን አስር ጊዜ አያለው፤ከካፌው በረንዳ ላይ ሆኜ ሜሮን ምን ልትመስል እንደምትችል አሰላስላለው።ፍርሃቴም እንዳለ ነው።አይኔ ግራና ቀኙን ካሁን ካሁን መጣች በሚል ያለመታከት ይማትራል።ብዙ ሴቶች ሲያልፉ እያየሁ እደነግጣለው።በተለይ አንዷማ ራሷ መስላኝ ከመቀመጫዬ ብድግ ለማለት ምንም አልቀረኝ።መልሼ ደግሞ ሰአቱ እየገፋ ሲሄድ የምሞኝ መሰለኝ።
<<ቆይ እስቲ አንድ ሰው እየተጫወተብኝ ቢሆንስ?>> እያልኩ እራሴን በጥርጣሬ እሞግታለሁ ።

ብዙም አልቆየ አይኔ ሳያስበዉ ከአንድ ሰው አይን ጋር ተጋጨ።ሁሉ ነገር በሰከንድ ውስጥ ተቀያየረ።
ዞማ ፀጉር፣ጠይም መልከመልካም፣ቁመናዋ የሚማርክ በተለይ አይኗ! ምንም እንኳን በትክክል ምልክቶቿን ብታሟላም፣እርሷም ቢሆን ወደኔ እየቀረበች ቢሆንም እሷናት ብዬ ለማመን አልቻልኩም ነበር።

<<ባልሳሳት ናሆም የምትባል አንተ ነህ?>>
በካፌ ውስጥ ብዙ ወንዶች እያሉ እኔን ለይታ ማወቋ ገርሞኛል።
<<አልተሳሳትሽም . . .እራስሽ ነሽ ግን?>>
<<አይ እህቷ ነኝ!>> ስትል ቀለደችብኝ።
ፈገግታዋ ልዩ ነበር።
ለረጅም ጊዜ እንደሚተዋወቅ ሰው ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳምን።
የካፌው ሰዎች ሁሉ ወደኛ በመመልከታቸው ኩራት ኩራት አለኝ።
እንድትቀመጥ ከጋበዝኳት በኋላ አስተናጋጁን ጠራሁት።
<<. . . እሺ አስታወስከኝ ?>> በአትኩሮት እያየችኝ ነበር።
<<አረ በፍፁም!ለመሆኑ እንዳንቺ አይነት ሰው እዚህ ከተማ አለ?>>
<<እኔም እንዳተው ነኝ ግን እርገጠኛ አይደለሁም እንጂ መልክህ አዲስ አልሆነብኝም>>
<<ታድያ ስልኩ ከየት ተፃፈ ይባላል?>>
<<እኔም ደንቆኛል...ምን አልባት መንገድ ላይ ይሆን?>>
<<የምታስታውሽው አጋጣሚ አለ?>>
<<ኦው . . ይከብዳል ።>>
<<በርግጥ ልክ ነሽ . . .የእግዜር ስራ ይገርማል።>>
ለጥቂት ሰኮንዶች ዝምታ ሰፈነ።በካፌው ውስጥ ለስለስ ብሎ የኤፍሬም የድሮ ዜማ ተከፍቷል።ትንሽ እንደቆየን ፀጥታውን ሰብርን ስለየግል ህይወታችን ፣ስለመሀበራዊ ጉዳይ መጨዋወት ጀመርን።ቀስ በቀስ ፍርሀቴ ተጠራርጎ ወጣና ስለምንወደውና ትርፍ ጊዜን ስለምናሳልፍበት ሁኔታ ሳይቀር ተነጋግርን።በደቂቃ ውስጥም አንድ ስንሆን ተሰማኝ።ፍቅር እንዳይዘኝም ሰጋሁ።ግን ፈርቼም እንደማይቀርልኝ አውቃለው።ብቻ ቆይታችን በጣም ስለተመቸኝ ጊዜው እንዳይሮጥ አምላኬን ተማፀንኩት።ንግግሯም ጣፋጭ ስለነበር ፈፅሞ ፀጥታ እንዲገባ እድል አልሰጠሁም።
<<ጓደኛ አለሽ >> የሚለው ጥያቄ በውስጤ ይብሰለሰል ነበር።ነገር ግን መቸኮሉ ጥሩ እንዳልሆነ አሰብኩ።እንዲህ እንዲህ እያልን ከምሽቱ አንድ ሰአት ሲሆን ሂሳብ ከፈልኩና ከካፌው ወጥተን በእግራችን የፒያሳን ጎዳናን ማቋራጥ ጀመርን።
ምሽቱ ለኔ ውድና መቼም ልረሳው የማልችለው ትዝታን እንደጫረብኝ እርግጠኛ ነበርኩ
ለሷም ቢሆን ከዚህ የተለየ ይሆናል ብዬ አለገምትም።
<<ትላንት ለምንድን ነው ስልኩን የከለከልሽን>>
<<አልተረዳክኝም ማለት ነው>>
<<አዎ ምንም ግልፅ አልሆነኝም።>>
<<ቆይ እንግርሀለው>>
<<መቼ?>>
<<አሁን>>
<<አሁን እኮ አሁን ነው>>
<<ትንሽ ቆይቶ አሁን?>>
ምን እንደሆነ አላውቅም ልቤ ስጋት እየተሰማው እጅ ለእጅ እንደተያያዝን ከሰፈሯ ደረሰን።መለያየታችንም ግድ ነውና ካንድ ቦታ ቆም ብለን ፊት ለፊት በስስት ተያየን።
<<ልንለያይ ነው ማለት ነው?>>አልኳት በሀዘን
<< ምን ይደረግ>>
<<መቼ እንገናኛለን?>>
<<መቼም. . .።>>
<<ለምን?>>
ዝምት ሰፈነ።አምላኬን <<እባክህ ፈጣርዬ ሆይ የሰጠከኝን እድል መልሰህ እንዳትነፍገኝ>> ስል ተማፀንኩት።
<<ይቅርታ አድርግልኝ ናሆም በሰልክ ያልነገርኩክ ድምፅህ እንዲሁም ብስለትክ ሰለማረከኝ ሳላይህ አልሄድም ብዬ ነዉ።ከነገ ወድያ ለኑሮ አባቴ ጋር ወደ ካናዳ መሄዴ ነዉ።እስካሁንም ያልነገርኩህ ጫወታችን እንዳይቀዘቅዝ ሰግቼ ነው። >>
<<. . .ምን! . . . እየቀለድሽ ነው? >>
ነገሮች ሁሉ ሲገለባበጡ ተሰማኝ።የምሰማውን ማመን አቃተኝ።
የሰጋሁት ነገር እውን መሆኑን ስረዳ ተናደድኩ።ህልምም መስሎኝ ለመባነን ቃጣኝ።
<<እየቀለድኩ አደለም ናሆም፤ባንተ ውስጥ ያለው ስሜት በኔም ውስጥ እንዳለ እወቅልኝ። ስልኩን የደወልኩልህ ከስልክ ደብተሬ ላይ ያሉትን ወዳጆቼን ሁሉ ተሰናብቼ የቀረኝ ያንተ ብቻ ነበር። እኔም ቅር እያለኝ ከምሄድ ብዬ ነው የደወልኩት>>
<<ልክ አይደለሽም. . .።>> ሀሞቴ ፍስስ እንዳለ ነበር።
<<እንዴት ናሆም?>>
መልስ መስጠት ከበደኝ፤አንደበቴም ተሳሰረ።ምን እየሆነ እንዳለ፤ምን እንደማደርግ ሁሉ ግራ ገባኝ።ትንሽ እንደቆየን ከሜሮን ጋርም ምንም የቀረኝ ነገር እንደሌለ ተረዳሁ።የመጨረሻ የምትሆነኝን ቃል እንደምንም አምጬ ሰነዘርኩለት።
<<እስቲ አሁን ምን አለበት . .ሳትደውዪ ዝም ብለሽ ብትሄጂ !?. . .>>
ሳልሰናበታት ከቆመችበት ጥያት ወደ ቤቴ ማዝገሜን ቀጠልኩ።
አይኔ ላይ ብዥ ብዥ እያለብኝ ትንሽ እንደተጓዝኩ ከኋላዬ ደርሳ እጄን አጥብቃ ያዘችው።
<<እባክህን ናሆም ተረዳኝ . . .እኔ ምን አጠፋው ምንስ ማድረግ ነበረብኝ። ይሉቁንስ እግዜር ያለመክናይት አላገናኘንምና ልነደሰት ይገባናል።>>
መልስ አልሰጠኋትም።አይኖቼ አይኖቿን ሲመለከቱ ፈዝዤ ቀረሁ ።በዛ ምሽት እንደኮብ ያበራሉ።የምሰማው ድምፅዋ በደምስሬ ሰርፆ መንፈሴን ሲያድሰው ተሰማኝ ።እኔም ከፊትዋ ቆሜ አይን አይኖን እያየው አዳምጣታለው መልስ መስጠት ግን አልፈለኩም።
<<ተረዳከኝ ?ሆን ብዬ ያደረኩት አይደለም።ለምንስ ሆን ብዬ አደርጋለው።ልክ እንዳተው ሁሉ የስልክ ቁጥሩ ሚስጥር ለኔም ሚስጥር ነው። ደግሞ እግዜር በፈጠረው አጋጣሚ አትማረር፤ ሁሉም ለበጎ ነውና።. . .ተናገር እንጂ ለምን ዝም ትላለህ ? በዚ ላይ ስሜታችን አንድ እንደሆነ እገምታለሁ።>>
በረጅሙ ተነፈስኩና ለደቂቃ ሰማይ ሰማዩን ስመለከት ጨረቃን አገኘኋት።በትዝብት ተመለከትኳት።ከዛም ወደራሴ ተመለስኩና በርጋታ ማሰላሰል ጀመርኩ።ምንም እንኳን አጋጣሚው አስገራሚና አሳዛኝ እንዲሁም የማይታመን ቢሆንም፤እውነታውን ተቀብዬ በሰላም መለያየቱ ጥሩ እንደሚሆን አሰብኩ።ሜሮን ላይም ምንም ስህተት ፈልጌ አጣው።
<<ማክሰኞ ጠዋት ነው የምትሄጂው?>>
<<አዎን>>
<<ታድያ ለምን አልሸኝሽም?>>
<<አይሆንም ከቤተሰብ ጋር ስለሆንኩ እንደገና መጨነቅ የለብንም። እዛው እንደደረስኩ በደቂቃ ውስጥ እደውልልካለው >>
<<እርግጠኛ ነሽ?>>
<<አትጠራጠር ላንተ ሳይሆን ለራሴ ስል ነው የምደውለው።>>
<<እጠብቃለው።>>
<<በቃ ደህና ሁን፤በግዜ ቤትክ ግባ።>>
እቅፏ ውስጥ ስታስገባኝ ይባስ ነፍሴ ተደሰተች።ጠረንዋ ካፋንጫዬ ሲቀር ታወቀኝ።ጡቶቿ ከደረቴ ጋር ሲነካኩ ስሜቴ ጣርያ ደርሶ ተመለሰ።በረጅሙ ተነፈስኩና ዳግም የምነገናኝበትን ቀን መናፈቅ ጀመርኩ።
አንድ ነገር ተሰማኝ....አዲስ ህይወት፤አዲስ እስትንፋስ፤ዳግም ውልደት....ግን ምን ያደርጋል የወደድኳት ለት ተለየኋት.....የናፍቆቷን ኑሮ ''ሀ'' ብዬ ልጀምር ነው።

▪️▪️▪️▪️
👍82
#ዋ !
አይኔ ወደደሽ ስልሽ፣
አይኑን አጥፋው ብለሽ ገባሽ አሉ ስለት
ምኞትሽ ሰመረ
አይኖቼ ጠፉልሽ ይኸው አንደዘበት።
:
ግን መች ተውሻለው
በልቤ ብሩህ አይን ዛሬም አይሻለው።
:
ደሞ አንደዚ ስልሽ አትወጅኝምና
ልቡንም አጥፋልኝ ብለሽ ትሳይና
ፀሎት ያልቅብሻል እሞትብሽና።

🔘በረከት በላይነህ🔘
#ሆሆ

“ወንድ ሆኖ የማያመነዝር ፤ ወታደር ሆኖ እማይሰነዝር ፤ ነጋዴ ሆኖ እማይዘረዝር የለም ! “ይላል ምኡዝ።
እውነቱን ነው፤ከጥቂቶቻችን በቀር ብዙ ወንድ በህይወቱ ቢያንስ አንዴ በትዳሩ ላይ ያድጠዋል። ድርያ በአርቲስት ላይ ይጋነናል እንጂ ፊትና ጭን ከተሰጠው፤ ገበሬ ነጋዴ ፓስተር ሼህ የንስሃ አባት ሳይቀር እንደሚወሰልት እናውቃለን። መቸም የሴት ገላ ማቀፍ እንዴት እንደሚጥም የቀመሰ ያውቀዋል፤ ግን የሚያስከፍለው ዋጋ ከደስታው ጋር አይመጣጠንም፤ አንድ ጣሳ ደስታ ይሰጥህና አንድ በርሚል ጣጣ ያሸክምሃል!!

#አንድ

የሆነ ጊዜ ላይ አሜሪካ ውስጥ ባንድ ከተማ የተከሰተውን ዜና በራሴ መንገድ ስተርተው ይሄን ይመስላል፤
ሰውየው ሚስቱ ማታ ለስራ በሄደችበት ውሽማውን አምጥቶ በተቀደሰው አልጋ ላይ ይፈትጋታል፤ በፍትጊያ መሀል ኮቴ ሰምቶ ቀና ሲል ሚስቱን አያት፤ ውሽምየዋ እንደስፓይደር ውመን በመስኮት ዘልላ ነካችው፤ ባልየው ብቻውን ከሚስቱ ጋር ተፋጠጠ፤ ሚስትዮዋ ለሰይፍ ሩብ ጉዳይ የቀረው ቢላዋ ይዛለች፤ ባሉካ ለመሮጥ ተመኜ ፤ግን እግሩ ቀጤማ ሆነበት፤ በወዛደር አማርኛ እንግለፀው ከተባለ እድሩ የቡልዶዘር ጎማ ሆነበት፤ ሚስትየው ምንም አላለችም፤ አልጋው ላይ እመርር ብላ ወጣችና አገር አማን ነው ብሎ ቆሞ የሚጠብቀውን ብልቱን ጨብጣ ከስሩ መተረችው፤ ከዛ እንደ ቀይ ስር በቁንጮው አንጠልጥላው ወጣችና በቤቱ ጉዋሮ በሚገኘው ዱር ውስጥ ወርውራው ተሰወረች፤
ብዙ ሳይቆይ አምቡላንስ ስልቡን ሰውየ ይዞ ወድ ሆስፒታ መረሸ፤ ያሜሪካ ፖሊስ በቦታው ደርሶ ፤ ከሲአኤ ጋር በመተባበር አካባቢውን በብረት ለበስ መኪና አጥሮ ተቆርጦ የተጣለውን ወሸላ ፍለጋ ተሰማራ፤፤ ከላይ በሂሊኮፍተር ከታች በአነፍናፊ ውሻ የታገዘ ሰአታትን የፈጀ አሰሳ በሁዋላ የተቆረጠው ብልት የጉንዳን መንጋ ወርሶት ተገኘ፤፤ በመጨረሻ ዶክተሮች ወደ ስልቡ ባል ቀርበው፤ “የጠፋብህ ብልት ይሄ ነውን?” ብለው’ በመስቀልኛ ጥያቄ መርምረው አረጋግጠው፤ በቀዶ ጥገና ተከሉለት፤ትንሽ ከመንሻፈፉ በቀር በድሮው ቦታ ተተከለ ፤እረ እንዴውም ከዱሮው ሳይሻል አይቀርም፤ ሚስት ተብየዋን ደስ አይበላትና ሀኪሞች ፤ እንደ ክንዱ በፈለገ ጊዜ የሚዘረጋውና የሚያጥፈው አድርገው ተከሉለት፤

#ሁለት

ይሄ ደሞ ባልንጀራየ የነገረኝ ነው፤
ዲሲ ውስጥ የሚኖሩ ባልና ሚስት ኢትዮጵያውን የተጋቡበትን አስረኛ አመት በማክበር እየተዝናኑ አመሹ፤ከዚያ ሚስትዮዋ” ቤብ፤ በፍቅራችን ላይ ቅመም የሚጨምር ነገር ላሳይህ ” አለችና ከራቫቱን ፈታችለት፤ አያ ‘ቤብ ‘ ክራቫቱን እያስፈታ ፤ ከታች ስራ እንዳይፈታ፤ ቀበቶውን ፈታ፤
ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ አንድ የትራፊክ ፖሊስ መንገድ ዳር ቆሞ ቫይብሬት የሚያደርግ መኪና ስለተመለከተ ጠጋ ብሎ መስኮቱን አንኩዋኩዋ!
“is there any problem ? officer? “ አለ ባልየው ትንፋሹ እየተቆራረጠ።
“መኪና መሳረር ህገወጥ ስለሆነ ልቀጣችሁ ነው” አለና ፖሊሲ ባልየውን መቶ ዶላር ቀጣው፤ ሚስቲቱን ግን ሁለት መቶ ብር ቅጣት ጣለባት፤
ባልየው ትንሽ ቆይቶ ስለከነከነው ፖሊሱን ተከትሎ ደረሰበትና፤
“ቅጣቱስ ይሁን! ይበለኝ፤ የግሬን ነው ያገኘሁት፤ ግን በምን ምክንያት ነው እኔን መቶ ብር ቀጥተህ ሚስቴን ሁለት መቶ ቀጣሃት?’
ፖሊሱ እንዲህ መለሰ፤
“እ ሷ መኪና ውስጥ እንዲህ አይነት ነገር ስታደርግ ያገኘሁዋት ለሁለተኛ ጊዜ ነው፤ ለዝያ ነው እጥፍ ያስከፈልኩዋት”😳
ባልየው በድንጋጤ ታሞ ይሄው በጎፈንድ ሚ እያስታመምነው እንገኛለን፤

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
👍3