አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የእንጀራ አባቴ

በዚያ ፀደይ ክሪስ ታመመ አፉ አካባቢ አረንጓዴ መሰለና በየደቂቃው
ያስመልሰው ጀመር። ከመታጠቢያ ቤት ወጥቶ እየተንገዳገደ አልጋ ላይ ወደቀ። የስነ አካል ጥናት ለማንበብ እየሞከረ ግን በራሱ ተናዶ ወደጎን አሽቀነጠረው። “የሆነ የበላሁት ነገር መሆን አለበት" ሲል ተነጫነጨ።

ክሪስ ብቻህን ልተውህ አልፈልግም” አልኩ ከእንጨት የተሰራውን ቁልፍ
ወደ ቁልፍ ቀዳዳው ለማስገባት እያዘጋጀሁ።

“ተመልከቺ ካቲ!” ሲል ጮኸ “በራስሽ ሁለት እግሮች መቆም የምትማሪበት ጊዜ ነው: በእያንዳንዱ ደቂቃ አጠገብሽ እንድሆን አትፈልጊ! የእናታችን ችግር
ያ ነበር። ሁልጊዜ የምትደገፍበት ሰው አጠገቧ እንዲኖር ታስባለች: በራስሽ ላይ ተደገፊ እሺ ካቲ… ሁልጊዜም!”

ፍርሀት ዘሎ ልቤ ውስጥ ገባና በአይኖቼ ፈሰሰ። አየኝና በእርጋታ “እኔ ደህና
ነኝ። እውነቴን ነው ራሴን መንከባከብ እችላለሁ: ካቲ ገንዘቡ ያስፈልገናል።
ሌላ ዕድል ላይኖረን ስለሚችል ብቻሽንም ቢሆን ሂጂ።

ወደ እሱ አልጋ ሮጩ ተመለስኩና በጉልበቴ ተንበርክኬ ፊቴን ደረቱ ላይ
አደረግኩ። በደግነት ፀጉሬን ዳሰሰኝ፡ “እውነት ካቲ፣ ደህና እሆናለሁ፤ ልታለቅሺበት የሚገባ አይደለም: ግን ሊገባሽ የሚገባው ነገር አንዳችን ላይ ምንም ነገር ቢፈጠር የቀረነው መንትዮቹን ከዚህ ማውጣት አለበት።”

“እንደዚህ አይነት ነገሮች አትናገር!” ጮህኩበት። እንደሚሞት ማሰቡ ውስጤን አሳመመኝ።
"ካቲ… አሁን እንድትሄጂ እፈልጋለሁ: ተነሺ ራስሽን አስገድጂ! እዚያ
ስትደርሺ ደግሞ ባለአንዳንድና ባለ አምስት ኖቶች ብቻ ውሰጂ እንጂ ትልልቆቹን እንዳትነኪ የእንጀራ አባታችን ኪሱ ውስጥ የሚጥላቸውን ሳንቲሞች ግን ሁሉንም ውሰጂ ከልብስ ማስቀመጫው ሳጥን ጀርባ ሳንቲሞች የሞሉበት
አንድ ቆርቆሮ ያስቀምጣሉ፡ ከእነሱ ዝገኚ”።

የገረጣና የደከመው ይመስላል። በዚያ ላይ ከስቷል: ደህና ሳይሆን ትቼው መውጣት እያስጠላኝ በፍጥነት ጉንጩን ሳም አደረግኩት። ወደተኙት መንትዮች አየት አድርጌ ከእንጨት የተሰራውን ቁልፍ ይዤ ወደ በሩ ተጣደፍኩ። “እወድሀለሁ ክሪስቶፈር” አልኩት በሩን ከመክፈቴ በፊት።

“እኔም እወድሻለሁ ካተሪን መልካም አደን” አለኝ፡
በአየር ላይ ሳምኩትና ወጥቼ በሩን ዘጋሁና ቆለፍኩት። እናቴ ክፍል ገብቶ መስረቅ አደጋ የለውም። እናታችን እሷና ባሏ ከመንገዱ በታች ያለ ጓደኛቸው ግብዣ ላይ መገኘት እንዳለባቸው የነገረችን ዛሬ ከሰአት በኋላ ነበር:

ኮሪደሩን አቋርጬ ስሄድ ለራሴ እያሰብኩ የነበረው ቢያንስ አንድ ባለ ሀያና
አንድ ባለ አስር ኖቶች መስረቅ እንዳለብኝ ነበር: የሆነ ሰው እንዳያስተውል
አደርጋለሁ። ምናልባትም ከእናታችን ጌጣጌጦች የተወሰኑ እሰርቃለሁ፡
ጌጣጌጦች አቅም ሊኖራቸው ይችላል ልክ እንደ ገንዘብ፤ ምናልባትም በተሻለ።

ሁሉም ስራ ነው፤ ሁሉም ቆራጥነት። የሽልማት ክፍሉን ለማየት ጊዜ ማባከን አልፈለግኩም ቀጥታ ወደ እናታችን መኝታ ክፍል አመራሁ። አሁን አራት
ሰዓት ነው፡ በጊዜ በሶስት ሰዓት የምትተኛውን አያትየውን እንደማላያት
አውቄያለሁ በጀግና የመተማመን ቆራጥነት ወደ ክፍሎቿ በሚያስገቡት በሮች ገባሁና በፀጥታ ዘጋኋቸው:: አንድ ደብዛዛ መብራት ብቻ በርቷል። በአብዛኛው ክፍሎቿ ውስጥ ያሉትን መብራቶች አብርታ ትተዋቸዋለች: አንዳንዴ ደግሞ
አንዱን ብቻ አብርታ እንደምትተወው ክሪስ ነግሮኛል። አሁን ለእናታችን
ገንዘብ ምኗ ነው?

እያመነታሁና እርግጠኛ ባለመሆን በሩ ጋ እንደቆምኩ ዙሪያውን ስመለከት በፍርሀት ደነዘዝኩ የእናታችን አዲስ ባል ወንበሩ ላይ ረጅም እግሮቹን ዘርግቶና ቁርጭምጭሚቱ
ጋር አጣምሮ ተዘርግቷል: ቀጥታ ፊት ለፊቱ ነኝ፡ አጭር የሚያሳይ የሌሊት ልብስና ከስር ደግሞ ከእሱ ጋር የሚመሳሰል ፓንት ለብሻለሁ፡ ማን እንደሆንኩና ሳልጠራ መኝታ ቤት ውስጥ ምን እያደረግኩ እንደሆነ ለማወቅ እስኪያጓራ ልቤ በአበደ አይነት እየመታ እጠብቃለሁ።

ግን አልተናገረም ጥቁር ቶክሲዶ ጠርዙ ላይ ወደታች ከሚወርድ ጥቁር ጌጥ ያለው ሮዝ ሸሚዝ
ጋር ለብሷል። አልጮኸም. አልጠየቀም ምክንያቱም እያንቀላፋ ነበር። ፊቴን አዙሬ ልመለስ ነበር ግን ይነቃና ያየኛል ብዬ ፈራሁ
መቼም መጓጓት ስራዬ ሆኗል በደንብ ልመለከተው ቀረብ አልኩ፡ ልነካው
እስከምችል ወንበሩ ድረስ ለመጠጋት ደፈርኩ እጄን ኪሱ ገብቼ መስረቅ
የምችልበት ቅርበት ላይ ሆንኩ ግን አላደረግኩትም፡

እንቅልፍ የወሰደው መልከመልካም ፊቱን ስመለከት፣ መስረቅ ጭንቅላቴ ውስጥ የመጣው የመጨረሻ ሀሳብ ነበር፡ አሁን የተገለጠውን በጣም የቀረብኩትን የእናቴን ተወዳጅ ባርትን በማየቴ ተደንቄያለሁ፡ የተወሰኑ ጊዜያት በሩቅ አይቼዋለሁ: በመጀመሪያ የገና ግብዣው ምሽት ሌላው ደግሞ ደረጃው አጠገብ እናታችን እጇን እንድታጠልቅ ኮት ይዞላት ማጅራቷና ጆሮዋ
ስር ሲስማትና ፈገግ እንድትል የሚያደርግ የሆነ ነገር በጆሮዋ ሲያንሾካሹክላት
እና ከበር ከመውጣታቸው በፊት ወደ ራሱ ጎትቶ ደረቱ ላይ ሲያስደግፋት
አይቼዋለሁ።

አዎ አዎ አይቼዋለሁ... እና ደግሞ ስለሱ ብዙ ሰምቼያለሁ፡ እህቶቹ የት
እንደሚኖሩ አውቃለሁ፡ የት እንደተወለደ፣ የት እንደተማረ ሁሉ አውቃለሁ።
አሁን እያየሁት ላለሁት ግን ማንም እንድዘጋጅ አላደረገኝም:

እንዴት እናቴ? ማፈር አለብሽ! ይህ ሰው በእድሜ ካንቺ ያንሳል በብዙ
አመታት ያንሳል! ግን አልነገረችንም ሚስጥር ነበር። እንደዚህ አይነት
አስፈላጊ ሚስጥር እንዴት መደበቅ እንደቻለች! ማንኛዋም ሴት የምትፈልገው አይነት ወንድ ነው፡ እና ብትወደውና ብታመልከው ምንም አይገርምም። የተለየ ግርማ ሞገስ ባለው ሁኔታ ተጋድሞ ስመለከተው ፍቅር ሲሰሩ
ኃይለኛና በስሜት የተሞላ እንደሚሆንላት ገመትኩ፡

ወንበር ላይ ተቀምጦ የሚያንቀላፋውን ይህንን ሰው መጥላት ፈለግኩ
ግን አልቻልኩም: እንቅልፍ ወስዶት እንኳን ቆንጆ ነውና ልቤ በፍጥነት እንዲመታ አደረገው። ባርትሎሚዮ ዊንስሎ ሳያውቀው በእንቅልፍ ልቡ ለእኔ የአድናቆት ምላሽ
በመስጠት አይነት ፈገግ አለ፡ እንደ ዶክተሮችና እንደ ክሪስ ሁሉንም ነገር
ከሚያውቁ ሰዎች አንዱ ነው ጠበቃ: እርግጠኛ ነኝ የሆነ በተለየ ሁኔታ ደስ የሚያሰኝ ነገር አይቶና ሞክሮ ያውቃል፡ በተከደኑ አይኖቹ ስር ያለው
ምን ይሆን? አይኖቹ ሰማያዊ ይሆኑ ወይም ቡናማ ማወቅ ፈለግኩ። ሰውነቱ ቀጭን፣ ጠንካራና ጡንቻማ ነው: ከንፈሮቹ አጠገብ ከላይ ወደታች የተሰመረ የሚመስል በእንቅልፍ ልቡ ፈገግ ሲል እየመጣ የሚመለስ ስርጉደት አለው::

ትልቅ የጋብቻ ቀለበት አጥልቋል። አይነቱን እናቴ ጣት ላይ አይቼዋለሁ:
በቀኝ እጁ አመልካች ጣት ላይ ብዙ ብርሀን በሌለበት እንኳን የሚያንፀባርቅ
የአልማዝ ቀለበት አለው ትንሽዋ ጣቱ ላይ ትምህርት ቤት ለሽልማት የሚሰጥ
የወንድማማችነት ቀለበት አድርጓል። ረጃጅም ጣቶቹ በደንብ የተፀዱና ልክ
እንደኔ ጥፍሮች የሚያንፀባርቁ አራት ማዕዘን ጥፍሮች አሏቸው
ረጅም ነው: ይህንን አስቀድሜ አውቃለሁ፡ ከሁሉ ነገር በጣም ደስ ያለኝ ስሜት የሚቀሰቅሱ ከፂሙ በታች ያሉት ማራኪ hንፈሮቹ ናቸው: በእነዚህ
ቅርፃቸው በሚያምር ማራኪ ከንፈሮቹ እናታችንን ሁሉም ቦታ ይስሟታል። ያ የወሲብ ደስታ ያለበት መፅሀፍ ትልልቅ ሰዎች እርቃናቸውን ሲሆኑ ምን ስሜት እንደሚሰጣቸው በሚገባ አስተምሮኛል።

ድንገት ያ ጥቁር ፂሙ ይኮረኩር እንደሆነ ለማየት እሱን የመሳም ግፊት
አደረብኝ:፡ በዚያውም ምንም አይነት የደም ዝምድና የሌለው እንግዳ መሳም ምን ስሜት እንደሚያሳድር ማወቅ ፈልጌያለሁ:
👍473😁2🔥1
ይኼኛው የሚከላከል አይደለም ቀስ ብሎ በቅርቡ የተላጨውን ጉንጩን
በለስላሳው መዳሰስ ኃጢአት አይደለም

እሱ እንቅልፉን ቀጥሏል።

ከበላዩ ጎንበስ ብዬ በጣም በቀስታ ከንፈሬን ከንፈሩ ጋ አነካካሁና በፍጥነት
ተመለስኩ: ልቤ ሽባ የሚያደርግ በሚመስል ፍርሃት ይደልቃል በነቃ
ብዬ ተመኘሁ: ግን ደግሞ በጣም ፈርቻለሁ: እንደ እናቴ አይነት በፍቅሩ
ያበደችለት ሴት እያለው እኔን ለመከላከል ይመጣል ብዬ ለማመን በጣም ልጅና
እርግጠኛ ያልሆንኩ ነበርኩ፡ ክንዶቹን ይዤ ነቅንቄ ብቀሰቅሰውና ታሪኬን፣
ስለ አራት በብቸኝነት ተከልለው የተቀመጡ፣ ከአመት እስከ አመት ለብቻቸው የተደረጉ፣ ትዕግስት ባጣ ሁኔታ የወንድ አያታቸውን ሞት የሚጠባበቁ ልጆች
ብነግረው ቁጭ ብሎ በእርጋታ ይሰማኝ ይሆን? ነገሩን ተረድቶ ከእኛ ጋር ያዝናል? ከዚያ እናታችን ነፃ እንድትለቀንና ያንን በርካታ ንብረት የመውረስ
ሀሳቧን እንድታቆም ያስገድዳታል?

ልክ እናታችን ግራ ስትጋባና በየትኛው መንገድ መታጠፍ እንዳለባት ማወቅ ሲሳናት እንደምታደርገው እጆቼን በጭንቀት ጉሮሮዬ ላይ አደረግኩ፡ ደመነፍሴ
በውስጤ ይጮሀል። ቀስቅሽው! ጥርጣሬዬ ደግሞ ዝም በይ፣ እንዲያውቅ አታድርጊ፣ አይፈልግሽም. የሱ ያልሆኑ አራት ልጆች መቼም አይፈልግም ይለኛል። እነዚያን ሁሉ ሀብቶችና ገንዘብ ሊገዛቸው የሚችሉ ደስታዎችን ከመውረስ ሚስቱን ስለከለከልሻት ይጠላሻል። ተመልከቺው… ወጣት ነው። ምንም እንኳን እናታችን በጣም ቆንጆና በአለም ላይ ካሉ ሀብታም ሴቶች አንዷ ለመሆን እየተጠጋች ያለች ብትሆንም ሌላ ወጣት የሆነች ማግኘት ይችላል። ማንንም አፍቅራ የማታውቅ ከሌላ ወንድ ጋር ተኝታ የማታውቅ ድንግል ማግኘት ይችላል።

ከዚያ ማወላወል አበቃ። መልሱ ቀላል ነው ሊታመን ከማይችል ሀብት ጋር
ሲወዳደሩ አራት የማይፈለጉ ልጆች ምንድናቸው?

ምንም አይደሉም እናታችን ያንን አስተምራኛለች።
ፍትሀዊ አይደለም! ስህተት ነው! እናታችን ሁሉም ነገር አላት በለፈለገችው
ጊዜ መምጣትና መሄድ፣ የፈለገችውን ያህል ገንዘብ ማውጣትና በዓለም ምርጥ
ከሆኑ ሱቆች መግዛት፣ የምትወደውና አብሯት እንዲተኛ የምትፈልገውን
ወጣት ሳይቀር ለመግዛት ገንዘብ አላት እኔና ክሪስ ምን አለን? የተሰበረ
ህልም፣ ብቸኝነትና ማለቂያ የሌለው ተስፋ መቁረጥ?

መንትዮቹስ ምን አላቸው? የአሻንጉሊት ቤትና እያደር እየቀነሰ የሚመጣ
ጤንነት?

ወደዚያ የተቆለፈ ክፍል ረዳት የለሽ፣ ተስፋ የለሽ ስሜት እንደ ድንጋይ ልቤን
ተጭኖኝና አይኖቼ በእምባ ተሞልተው ተመለስኩ: ክሪስ የስነ አካል ጥናት
መፅሀፍ ተከፍቶ ደረቱ ላይ ሆኖ እንቅልፍ ወስዶት አገኘሁት በጥንቃቄ
የሚያነበው ገፅ ላይ ምልክት አድርጌ መፅሀፉን አስቀመጥኩት ከዚያ አጠገቡ ጋደም አልኩና አቀፍኩት: እምባዬ በጉንጮቼ ወርዶ የፒጃማውን ጃኬት
አረጠበው፡ ከእንቅልፉ ነቅቶ ካቲ ምን ሆንሽ? ለምንድነው የምታለቅሽው?
የሆነ ሰው አየሽ? አለኝ፡ ሊገለፅ በማይችል ምክንያት የተጨነቁ አይኖቹን ማየት አልቻልኩም። ምን እንደተፈጠረ ልነግረው አልቻልኩም በዚያ ላይ
እንደተኛ እንደሳምኩት መንገር አልቻልኩም

“እና አንድ ሳንቲም እንኳን አላገኘሽም?” ባለማመን ጠየቀኝ።

“አንድ ሳንቲም እንኳን!” በመልሱ አንሾካሾኩ እና ፊቴን ከፊቱ ለመደበቅ
ሞከርኩ። ግን ፊቴን ዞር አድርጎ አይኖቼን በጥልቀት ለማየት አስገደደኝ..
ለምንድነው እርስ በእርሳችን በደንብ የተዋወቅነው? አይኖቼ ምንም እንዳይነበብባቸው ጥረት ባደርግም ጥቅም አልነበረውም አተኩሮ እያየኝ
ነበር። ማድረግ የቻልኩት ብቸኛው ነገር አይኖቼን ጨፍኜ ክንዶቹ ላይ ልጥፍ
ማለት ነበር። ፊቱን ፀጉሬ ላይ አጎንብሶ ጀርባዬን ቀስ እያለ እሽት እሽት
አደረገኝ። “ምንም አይደል አታልቅሺ: የት መፈለግ እንዳለብሽ የኔን ያህል
ስለማታውቂ ነው።” አለኝ።

መሄድ አለብኝ. ማምለጥ አለብኝ. ሳመልጥ ደግሞ ሁሉንም ይዤ እሄዳለሁ የትም ብሄድ ከማንም ጋር ብሆን።

“አሁን ወደ አልጋሽ መሄድ ትችያለሽ" አለ ክሪስ በጎርናና ድምፅ አያትየው
በሩን ከፍታ ልትይዘን ትችላለች”

“ክሪስ እኔ ከሄድኩ በኋላ አስመለሰህ?”

“አይ ተሽሎኛል በቃ ሂጂ ካቲ… ሂጂ”

“እውነት አሁን ተሽሎሀል?”

“ተሽሎኛል አላልኩሽም?”

“ደህና እደር ክሪስቶፈር" አልኩት ከዚያ የእሱን አልጋ ከመልቀቄ በፊት ጎንጩ ላይ ሳምኩትና አልጋዬ ላይ ወጥቼ ኬሪ ላይ ልጥፍ አልኩ፡

“ደህና እደሪ ካተሪን፡ በጣም ጥሩ እህትና ለመንትዮቹም እናት ነሽ. ግን በጣም ቀሽምና ጥሩ ያልሆንሽ ሌባ ነሽ" አለኝ።....

ይቀጥላል
👍5314👎1
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_አምስት ፡ ፡ #ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ የእንጀራ አባቴ በዚያ ፀደይ ክሪስ ታመመ አፉ አካባቢ አረንጓዴ መሰለና በየደቂቃው ያስመልሰው ጀመር። ከመታጠቢያ ቤት ወጥቶ እየተንገዳገደ አልጋ ላይ ወደቀ። የስነ አካል ጥናት ለማንበብ እየሞከረ ግን በራሱ ተናዶ ወደጎን አሽቀነጠረው። “የሆነ የበላሁት ነገር መሆን አለበት" ሲል ተነጫነጨ። ክሪስ ብቻህን ልተውህ አልፈልግም”…»
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

“ደህና እደሪ ካተሪን፡ በጣም ጥሩ እህትና ለመንትዮቹም እናት ነሽ. ግን በጣም ቀሽምና ጥሩ ያልሆንሽ ሌባ ነሽ" አለኝ።.

እያንዳንዱ የክሪስ የእናታችንን ክፍል መጎብኘት የተደበቀውን ገንዘባችንን መጠን አሳደገው ነገር ግን ግባችን የሆነው አምስት መቶ ዶላር ላይ ለመድረስ ረጅም ጊዜ ይወስዳል አሁን እንደገና በጋ መጣ: አሁን አስራ አምስት አመት ሆኖኛል። መንትዮቹ በቅርቡ ስምንት አመት ይሆናቸዋል። በቅርቡ ነሀሴ ሲመጣ የታሰርንበት ሶስተኛ አመት ይሆናል። ሌላ ክረምት ከመግባቱ በፊት ማምለጥ አለብን፡ ኬሪን ስመለከተው ፍዝዝ ብሎ አደንጓሬዎች ይለቅማል። ምክንያቱም የመልካም ዕድል ጥራጥሬ ስለሆኑ ነበር በአዲሱ አመት መጀመሪያ ትንንሾቹ ቡናማ አይኖች ውስጡን እንዳያዩት ብሎ አይበላቸውም ነበር አሁን ግን እኔና ክሪስ እያንዳንዱ አደንጓሬ የአንድ ቀን ሙሉ ደስታ ይሰጣል ብለን ስለነገርነው ይበላል እኔና ክሪስ እንደዚህ አይነት ተረቶች እየፈጠርን እንዲበሉ እናደርጋለን፡ ወለሉ ላይ ይቀመጥና ጊታሩን አንስቶ
አይኖቹን የካርቱን ፊልም ላይ ይተክላል። ኬሪ በቻለችው መጠን ወደሱ
ተጠግታ ቲቪውን ሳይሆን የሱን ፊት እየተመለከተች ትቀመጣለች።

"ካቲ" አለች በዚያች እንደ ወፍ በመሰለች ድምፅዋ

“ኮሪ ደህና አይደለም፡”

“እንዴት አወቅሽ?”

“በቃ አወቅኩ”

“አመመኝ ብሎ ነግሮሻል?”

“ማለት የለበትም”

“እና ምን ተሰማሽ?”

“እንደ ሁልጊዜው”

“እንደ ሁልጊዜው እንዴት ነው?”

“አላውቅም”

"አዎ! መውጣት አለብን፣ በፍጥነት!

በኋላ ላይ መንትዮቹን አንድ አልጋ ላይ አደረግኳቸው: ሁለቱም እንቅልፍ
ሲወስዳቸው ኬሪን አንስቼ ወደ አልጋችን እወስዳታለሁ ለአሁን ግን ለኮሪ
እህቱ አጠገቡ ሆና መተኛት በጣም የሚመች ነው: “ሮዝ አንሶላ አልወድም።”
አለች ኬሪ ተኮሳትራ “ሁላችንም ነጭ አንሶላ ነው የምንወደው: ነጩ አንሶላ
የታለ?”

እኔና ክሪስ ነጭ ከሁሉም ቀለማት ይልቅ ተስማሚ ነው ብለን የተናገርንበት
ቀን ፀፀተኝ። ካቲ እናታችን በአብዛኛው ጥቁር ቀለም ያላቸውን ቀሚሶች
የምትወደው ለምንድነው? ጠየቀች ኬሪ ሮዙን አንሶላ አንስቼ በነጭ እስክቀይረው እየጠበቀች።

“እናታችን ፀጉሯ ቢጫና የፊቷ ቀለም ነጣ ያለ ነው፡ እና ጥቁር ቀለም ደግሞ
የበለጠ ቆንጆ ያደርጋታል።

“ጥቁር አትፈራም?”

“ጥቁር ቀለም በትልልቅ ጥርሶቹ የማይባላ መሆኑን ለማወቅ ስንት አመት
መሆን ነው ያለብሽ?”

“እንደዚህ አይነት የሞኝ ጥያቄዎችን ማወቅ የምችልበት በቂ እድሜ ሲኖረኝ::

“ግን ጣራው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ያሉት ጥቁር ጥላዎች ሁሉ የሚያበራ፣
ሹል ጥርሶች አሏቸው::” አለ ኮሪ ሮዙ አንሶላ እንዳይነካው እየሸሸ።

“አሁን ተመልከቱ” አልኩ የሆነ ዘዴ እየፈጠርኩ እንደሆነ ጠርጥሮ ክሪስ
በሚስቁ አይኖቹ እያየኝ ነው: “እናንተ ቆዳችሁ አረንጓዴ፣ አይናችሁ
ወይንጠጅ፣ ፀጉራችሁ ቀይ እንዲሁም በሁለት ጆሮዎች ፋንታ ሶስት ጆሮዎች
ከሌሏችሁ በስተቀር ጥቋቁሮቹ ጥላዎች የሚያበራ ሹል ጥርስ አያወጡም::እንደዛ ከሆነ ብቻ ነው ጥቁር የሚያስፈራው:”

ዘና አሉ‥ ከዚያ ነጭ አንሶላቸውንና ነጭ ብርድ ልብሳቸው ውስጥ ገቡና
ወዲያው እንቅልፍ ወሰዳቸው ከዚያ ገላዬንና ፀጉሬን ለመታጠብና ልብሴን ለመቀየር ጊዜ አገኘሁ: ጣራው ስር ወዳለው ክፍል ሮጥኩና መስኮቶቹን ከፋፈትኳቸው፡ ቀዝቃዛ አየር ገብቶ ክፍሉን እንዲያቀዘቅዘውና ጠውልጌ
ከምቀመጥ የመደነስ ፍላጎት እንዲሰማኝ ፈልጌያለሁ ንፋሱ ወደ ክፍሉ መግቢያ የሚያገኘው በክረምት ብቻ የሆነው ለምንድነው? ለምን አሁን በጣም በምንፈልገው ጊዜ አይመጣም?

እኔና ክሪስ ሀሳቦቻችንን፣ ተስፋዎቻችንን፣ ጥርጣሬዎቻችንንና ፍርሀቶቻችንን
አንንነጋገራለን ችግር ሲያጋጥመኝ ዶክተሬ ነው: እንደመታደል ሆኖ
የሚያጋጥሙኝ ችግሮች ከባድ አይደሉም ወር ሲመጣ የሚያጋጥመኝ
ቁርጠትና የወር አበባዬ በፕሮግራሙ መሰረት አለመምጣቱ ብቻ ነበር።
ለዚህም ዶክተሬ የሚጠበቅ እንደሆነ ይነግረኛል። እኔ በረባው ባልረባው ጥንቃቄ የማደርግ አይነት ስለሆንኩ ውስጣዊው ማሽኔም ይህንኑ ይከተላል።

ስለዚህ አሁን በመስከረም አንድ ምሽት እኔ ጣራው ስር ያለው ክፍል ውስጥ
ሆኜ ክሪስ ሊሰርቅ ሄዶ የሆነውን ነገር ልክ ክሪስ የነበረበት ቦታ እንደሆንኩ
አድርጌ መፃፍ እችላለሁ: ስለዚህ የተለየ ወደ እናታችን ክፍል የተደረገ ጉዞ
በዝርዝር ነግሮኝ ነበር።
እንደነገረኝ መሳቢው ውስጥ ያለው መፅሀፍ ሁልጊዜ ይስበው ነበር ማረከው፣በኋላ ግን አስጥሞታል። ልክ እንደኔ ለምሽቱ የፈለገውን በቂ ገንዘብ ካገኘ በኋላ ልክ በማግኔት እንደተሳበ አይነት ወደዛ ጠረጴዛ ሄደ።

እሱ እያወራልኝ እኔ ግን በአንድ እይታ እያንዳንዱ ፎቶግራፍ ለዘለአለም
ጭንቅላቴ ውስጥ ተቀርፆ እያለ ለምን እሱ ደጋግሞ ይመለከተዋል? እያልኩ
ከራሴ ጋር እያወራሁ ነበር:

“እዚያ ቆሜ በየጊዜው የተወሰኑ ገፆች ላይ የተፃፈውን እያነበብኩ ነበር” አለኝ እና ስለ ትክክልና ስህተት ስለሚባሉ ነገሮች እያሰብኩና ስለ ተፈጥሮ፣ ደስ ስለሚያሰኘው እንግዳ ጥሪዎቹ እየተገረምኩና ስለእኛ ህይወት ሁኔታዎች
እያሰላሰልኩ ነበር ስላንቺና ስለኔ እያሰብኩ ነበር፡ እነዚህ ለእኛ የማበቢያችን
አመታት መሆን ይገባቸው ነበር። በማደጌና በእኔ እድሜ ላይ ያሉ ወንዶች
ፈቃደኛ ከሆኑ ሴቶች ሊያገኟቸው የሚችሉ ነገሮችን ስለማሰብ ጥፋተኝነትና እፍረት ይሰማኛል። እና እዚያው ቆሜ ባላገኝሽ እያልኩ ስመኝ አዳራሹ ውስጥ ወደ ክፍሉ እየቀረበ የሚመጣ ድምፅ ሰማሁ። ማን እንደሆነ ታውቂያለሽ እናታችንና ባሏ እየተመለሱ ነበር። በፍጥነት መጽሀፉን ቦታው ላይ መለስኩና ቀጥሎ ትልቁ አልጋው አጠገብ ያለው የእናታችን ልብስ ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ ተደበቅኩ: ከገባች አታየኝም ብዬ አሰብኩ። ግን ልታየኝ እንደምትችልም ተጠራጥሬያለሁ። ነገር ግን ይህንን እያሰላሰልኩ
ድንገት በሩን ሳልዘጋ መርሳቴን አስታወስኩ።

የዚያን ጊዜ ነው የእናታችንን ድምፅ የሰማሁት። “የእውነት ባርት? አለች
ወደ ክፍሉ ገብታ መብራት እያበራች። “ብዙ ጊዜ የኪስ ቦርሳህን መርሳትህ
ግዴለሽነትህን ያሳያል”

“ተመሳሳይ ቦታ ስለማላስቀምጠው ነው የምረሳው:” ሲል መለሰላት።እቃዎችን ሲያንቀሳቅስ መሳቢያዎችን ሲከፍትና ሲዘጋ ይሰማኛል። ከዚያ “እዚህኛው ሱሪ ኪስ ውስጥ እንደተውኩት እርግጠኛ ነኝ ... ካለ መንጃ ፈቃዴ የትም መሄድ አልችልም::” አለ

“በአነዳድህ ላይ ቅሬታ የለኝም፧ ግን በዚህ ምክንያት እንደገና ልንዘገይ ነው ምንም ያህል በፍጥነት ብትነዳ የመጀመሪያው ክፍል ያመልጠናል” አለች
እናታችን

“ሄይ!” አለ ባሏ ድምፁ ውስጥ መደነቅ ይሰማኛል። ምን እንዳደረግኩ አስታውሼ በውስጥ አቃሰትኩ ቦርሳዬ ይኸው ኮመዲኖው ላይ: እዛ ላይ ማስቀመጤን አላስታውስም ሱሪው ውስጥ እንደነበረ መማል እችላለሁ” አለ

“መሳቢያው ውስጥ ደብቆት ነበር” ክሪስ አብራራልኝ፡ “ሸሚዞቹ ስር ተቀምጦ ጰነው ያገኘሁት: የተወሰኑ ገንዘቦች ወስጄ ከዚያ አስቀምጬው ያንን መፅሀፍ እሱ እያወራልኝ እኔ ግን በአንድ እይታ እያንዳንዱ ፎቶግራፍ ለዘለአለም ጭንቅላቴ ውስጥ ተቀርፆ እያለ ለምን እሱ ደጋግሞ ይመለከተዋል? እያልኩ
👍511
ከራሴ ጋር እያወራሁ ነበር።
“እዚያ ቆሜ በየጊዜው የተወሰኑ ገፆች ላይ የተፃፈውን እያነበብኩ ነበር” አለኝ፡ እና ስለ ትክክልና ስህተት ስለሚባሉ ነገሮች እያሰብኩና ስለ ተፈጥሮ፣ ደስ ስለሚያሰኘው እንግዳ ጥሪዎቹ እየተገረምኩና ስለእኛ ህይወት ሁኔታዎች
እያሰላሰልኩ ነበር ስላንቺና ስለኔ እያሰብኩ ነበር፡ እነዚህ ለእኛ የማበቢያችን
አመታት መሆን ይገባቸው ነበር። በማደጌና በእኔ እድሜ ላይ ያሉ ወንዶች
ፈቃደኛ ከሆኑ ሴቶች ሊያገኟቸው የሚችሉ ነገሮችን ስለማሰብ ጥፋተኝነትና
እፍረት ይሰማኛል። እና እዚያው ቆሜ ባላገኝሽ እያልኩ ስመኝ አዳራሹ
ውስጥ ወደ ክፍሉ እየቀረበ የሚመጣ ድምፅ ሰማሁ። ማን እንደሆነ ታውቂያለሽ እናታችንና ባሏ እየተመለሱ ነበር። በፍጥነት መጽሀፉን ቦታው ላይ መለስኩና ቀጥሎ ትልቁ አልጋው አጠገብ ያለው የእናታችን ልብስ ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ ተደበቅኩ: ከገባች አታየኝም ብዬ አሰብኩ። ግን ልታየኝ እንደምትችልም ተጠራጥሬያለሁ። ነገር ግን ይህንን እያሰላሰልኩ
ድንገት በሩን ሳልዘጋ መርሳቴን አስታወስኩ
የዚያን ጊዜ ነው የእናታችንን ድምፅ የሰማሁት። “የእውነት ባርት? አለች
ወደ ክፍሉ ገብታ መብራት እያበራች። “ብዙ ጊዜ የኪስ ቦርሳህን መርሳትህ
ግዴለሽነትህን ያሳያል”
“ተመሳሳይ ቦታ ስለማላስቀምጠው ነው የምረሳው:” ሲል መለሰላት።
እቃዎችን ሲያንቀሳቅስ መሳቢያዎችን ሲከፍትና ሲዘጋ ይሰማኛል። ከዚያ
“እዚህኛው ሱሪ ኪስ ውስጥ እንደተውኩት እርግጠኛ ነኝ ... ካለ መንጃ ፈቃዴ
የትም መሄድ አልችልም::” አለ።

“በአነዳድህ ላይ ቅሬታ የለኝም፧ ግን በዚህ ምክንያት እንደገና ልንዘገይ ነው ምንም ያህል በፍጥነት ብትነዳ የመጀመሪያው ክፍል ያመልጠናል” አለች
እናታችን:

“ሄይ!” አለ ባሏ ድምፁ ውስጥ መደነቅ ይሰማኛል። ምን እንዳደረግኩ አስታውሼ በውስጥ አቃሰትኩ ቦርሳዬ ይኸው ኮመዲኖው ላይ: እዛ ላይ ማስቀመጤን
አላስታውስም ሱሪው ውስጥ እንደነበረ መማል እችላለሁ” አለ

“መሳቢያው ውስጥ ደብቆት ነበር” ክሪስ አብራራልኝ፡ “ሸሚዞቹ ስር ተቀምጦ ነው ያገኘሁት: የተወሰኑ ገንዘቦች ወስጄ ከዚያ አስቀምጬው ያንን መፅሀፍ ማንበብ ቀጠልኩ ከዚያ እናታችን “እውነት ባርት?!” አለች ትዕግስት ያጣች ትመስላለች።

ከዚያ ኮሪን “ከዚህ ቦታ እንውጣ እነዚያ ሰራተኞች እየሰረቁን እንደሆነ
አምናለሁ አንቺ ገንዘብ እየጠፋሽ ነው እኔም እንደዛው፡ ለምሳሌ አራት ባለ አምስት ኖቶች እንደነበሩኝ አውቃለሁ:: አሁን ያሉኝ ሶስት ብቻ ናቸው:: አለ።

“እንደገና አቃሰትኩ፤ ያልቆጠረው ገና ብዙ እንዳለው አስባለሁ እናታችን
ቦርሳዋ ውስጥ የምትይዘውን ገንዘብ ብዛት ማወቋም አስደንጋጭ ነበር"
“አምስት ብር ምን ልዩነት ያመጣል?” ጠየቀች እናታችን፡ እሷ እንዲህ ናት
ስለገንዘብ ግድ የላትም ከአባታችን ጋር የነበረች ጊዜም እንዲሁ ነበር። ከዚያ
ሠራተኞቹ በቂ እንደማይከፈላቸውና እድል ካጋጠማቸው ቢሰርቁ መወቀስ እንደሌለባቸው ተናገረች። “እንዲሰርቁ ከተጋበዙ” አለች።

እሱ ሲመልስ “ውዷ ሚስቴ ገንዘብ ላንቺ ቀላል ሊሆን ይችላል። እኔ ግን
ገንዘብ ለማግኘት በጣም መልፋት ስለሚጠበቅብኝ አስር ሳንቲም እንዲሰረቅብኝ
አልፈልግም:: በዚያ ላይ የእናትሽን የማይፈታ ፊት በየጠዋቱ ከጠረጴዛው
ባሻገር እየተመለከትኩ ቀኔ በመልካም ተጀምሯል ማለት አልችልም:” አለ።ስለዛች ብረት ፊት አሮጊት እንደዚህ እንደሚሰማው አላሰብኩም ነበር። ልክ እንደኛ ነው የሚሰማው እና እናታችን የተናደደች መሰለችና “እንደገና ወደዚያ
አንመለስም” ድምፅዋ ጠንካራ ነበር ብታያት ካቲ እሷም አትመስል ከዚህ
በፊት እኛን ስታነጋግረን ሌላ ከሌላ ሰው ጋር ስታወራ ደግሞ ሌላ እንደሆነች
ተከስቶልኝ አያውቅም፡ ከዚያ “ታውቃለህ ይህንን ቤት መልቀቅ አልችልም ገና
ነኝ አሁን የምንሄድ ከሆነ ተነስ እንዲያውም ዘግይተናል” አለችው: የዚያን ጊዜ ነው የእንጀራ አባታችን አንድ ጊዜ የመጀመሪያው ክፍል ካመለጠው ሙሉውን ትርኢት ስለሚያበላሽበት በዚያ ላይ እዚያ ሄደው ተመልካች መሀል ከመቀመጥ እዚህ ሆነው የሆነ የሚያዝናና ነገር እንዲያደርጉ ስላሰበ
መሄድ እንደማይፈልግ የነገራት: እንደምገምተው ፍቅር ለመስራት ወደ
አልጋ መሄድ እንችላለን ማለት ነበር። ይሄ ህመም እንዲሰማኝ የሚያደርግ
ካልመሰለሽ አታውቂኝም ማለት ነው።

“ነገር ግን እናታችን በጣም ጠንካራ መሆን ትችላለች: ያ አስደንቆኛል።ከአባታችን ጋር ከነበረችው አይነት ተለውጣለች ካቲ። አሁን ልክ እንደ አለቃ ናት፡ ማንም ወንድ ምን እንደምታደርግ አይነግራትም። ከዚያ “እንዳለፈው ጊዜ? በጣም የሚያሳፍር ነው ባርት! ቦርሳህን ለመውሰድ ተመለስክ፤ በጥቂት
ደቂቃዎች ውስጥ እመለሳለሁ አልከኝና ምን አደረግክ? መጥተህ ተኛህና እዚያ ግብዣ ላይ ብቻዬን አመሸሁ:" አለችው

ተ“አሁን የእንጀራ አባታችን በአነጋገሯ የተናደደ ይመስል ነበር። በትክክል ከተረዳሁት ማለቴ ነው፡ የፊት ገፅታ እያየሽ ካልሆነ ከድምፅ ብዙ ነገር ማንበብ ይቻላል። “እንዴት ተሰቃየሽ! ሲል መለሰላት የሚያሽሟጥጥ ይመስላል። “የዚያን ጊዜ በጣም ደስ የሚል ህልም አይቼ ነበር፡ እንደሚደገም ባውቅ በየጊዜው እመጣ ነበር፡ እንቅልፍ ላይ ሳለሁ አንዲት በጣም የምታምር ረጅም ወርቃማ ጸጉር ያላት ወጣት ሴት ክፍሉ ውስጥ ተደብቃ ገብታ ሳመችኝ
በጣም ቆንጆ ናት። በናፍቆት እየተመለከተችኝ ነበር። ሆኖም አይኖቼን ስከፍት የለችም፡ እና ህልም መሆን አለባት ስል አሰብኩ” የተናገረው ነገር አስደነገጠኝ ካቲ አንቺ ነሽ አይደል? እንዴት እንደዚህ ደፋርና ስርአት የለሽ ትሆኛለሽ? ልፈነዳ የደረስኩ እስኪመስለኝ ድረስ ተናድጄብሽ ነበር።
የቆሰልሽው አንቺ ብቻ እንደሆንሽ ታስቢያለሽ አይደል? ተስፋ የቆረጥሽው
ጥርጣሬዎች የሞሉብሽ፣ በፍርሀት የተዋጥሽው አንቺ ብቻ እንደሆንሽ
ታስቢያለሽ? አምላኬ በጣም ተናድጄብሽ ነበር። ከዚህ በፊት ይህንን ያህል
ተናድጄ አላውቅም።

“ከዚያ እናታችን ባሏ “አምላኬ! ልጅቷና ስለ መሳሟ መስማት ሰልችቶኛል።
ለምንድነው ደግሜ እንድሰማው የምትነግረኝ? ከዚህ በፊት ተስመህ
አታውቅም!” ብላው እዚያው መጣላት ሊጀምሩ ነው ብዬ አስቤ ነበር። ግን
እናታችን ድምፅዋን ቀይራ ልክ ከአባታችን ጋር እንደነበረችው አይነት ጣፋጭና የፍቅር አደረገችው፡ ይሁንና ወዲያውኑ አልጋውን መጠቀም ከሚፈልገው
ፍቅረኛዋ ጋር ከመሆን ይልቅ መውጣት እንደፈለገች ያስታውቅ ነበር።

“የሆነ ነገር ከጀርባዬ ዘለለ! በበሰበሰው እንጨት ላይ ለስላሳ ርምጃ ሰማሁ!
ዘልዬ በፍርሀት ዞር አልኩ። ምን ለማየት እንደጠበቅኩ እግዚአብሔር ነው
የሚያውቀው! ከዚያ ክሪስ መሆኑን ሳውቅ በእፎይታ ተነፈስኩ ደብዛዛው
ብርሀን ውስጥ በፀጥታ ቆሞ እያፈጠጠብኝ ነው፡ ለምን? ከተለመደው በተለየ
ቆንጆ ሆኛለሁ እንዴ? በስሱ ልብሶቼ ውስጥ የሚያበራው የጨረቃ ብርሀን ነው?

ጥርሱን ነክሶ ዝቅ ባለ ድምፅ “እንደዚህ ተቀምጠሽ በጣም ታምሪያለሽ፡” ሲለኝ
ጥርጣሬዎቼ ሁሉ ገለል አሉ፡ ጉሮሮውን አፀዳና “የጨረቃው ብርሀን በብርማ ሰማያዊ ስሎሽ በልብስሽ ስር የሰውነትሽን ቅርፅ ማየት እችላለሁ ከዚያ ግራ በሚያጋባ አይነት ትከሻዬን በጣቶቹ አጥብቆ ያዘኝ! ያማል፡ “የተረገምሽ ካቲ! ያንን ሰውዬ ሳምሽው! ነቅቶ ሊያይሽና ማን እንደሆንሽ ለማወቅ ሊጠይቅሽ ይችል ነበር! የህልሙ አንድ ክፍል እንደሆንሽ አያስብም ነበር::”

ድርጊቱ የሚያስፈራ ነበር፡ “ምን እንዳደረግኩ በምን አወቅክ? እዛ አልነበርክም
በዚያ ምሽት ታመህ ነበር”
👍351👎1
አይኖቹን አፍጥጦ ትከሻዬን እንደያዘ አርገፈገፈኝ፡ እንደገና ሌላ ሰው
እንደመሰለ አሰብኩ “አይቶሻል ካቲ! በደንብ እንቅልፍ አልያዘውም ነበር!”

“አይቶኛል?” ባለማመን ጮህኩ። ሊሆን አይችልም!

“አዎ!” ሲል ጮኸ። ክሪስ ይሄ ነው በተለምዶ ስሜቱን የሚቆጣጠር። “እሱ
የህልሙ አንድ ክፍል እንደሆንሽ ነው ያሰበው: ግን እናታችን ሁለትና ሁለትን በመደመር ልክ እኔ እንደገመትኩት ማን እንደሆነ ልትገምት አትችልም ብለሽ
ታስቢያለሽ? አንቺና የአንቺ የፍቅር እምነት የተረገማችሁ ናችሁ! አሁን
እኛ ላይ ይሆናሉ። በፊት እንደሚያደርጉት ገንዘብ እንዲሁ አያስቀምጡም::
እየቆጠረ ነው እሷም እየቆጠረች ነው: እኛ ደግሞ ገና በቂ የለንም ... ገና
ነን!”

ከመስኮቱ አራቀኝ። በጥፊ ሊመታኝ የሚያደርስ አውሬነትና ቁጣ ይታይበታል በተለይ ልጅ ሳለሁ ሊመታኝ የሚያስችለው ብዙ ምክንያት ሰጥቼው የማውቅ ቢሆንም በህይወታችን አንድ ጊዜ እንኳ መትቶኝ አያውቅም: ነገር ግን አይኖቼ እስኪዞሩ፣ እስክደነዝዝና “አቁም እናታችን በተቆለፈ በር ውስጥ እንደምናሳልፍ አታውቅም! ብዬ እስክጮህ አርገፈገፈኝ።

ይሄ ክሪስ አይደለም
ይሄ የሆነ አይቼው የማላውቀው ሰው ነው...
ያልሰለጠነ አውሬ: “የኔ ነሽ ካቲ! የኔ! ሁልጊዜም የኔ ትሆኛለሽ! ወደፊት
ማንም ቢመጣ አንቺ ሁልጊዜ የኔ ነሽ ዛሬ ማታ. አሁን የኔ አደርግሻለሁ!
እያለ ጮኸ እኔ አላምንም ክሪስ አይደለም!

ይገባዋል እንዳልል እንኳን አእምሮው ውስጥ ያለውን ሙሉ በሙሉ አልተረዳሁትም። ያለውን ያደርጋል ብዬ ግን አስባለሁ ስሜት ግን ሰውን
የሚቆጣጠርበት መንገድ አለው ሁለታችንም ወለሉ ላይ ወደቅን ልታገለው ሞከርኩ። ታገልን፣ ተገለባበጥን፣
መንፈራገጥና መጨነቅ ያለበት የፀጥታ ትግል የእሱ ጥንካሬ ከእኔ ጋር።ፍልምያ አልነበረም..

ይቀጥላል
👍2318😱15😢3
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ስድስት ፡ ፡ #ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ “ደህና እደሪ ካተሪን፡ በጣም ጥሩ እህትና ለመንትዮቹም እናት ነሽ. ግን በጣም ቀሽምና ጥሩ ያልሆንሽ ሌባ ነሽ" አለኝ።. እያንዳንዱ የክሪስ የእናታችንን ክፍል መጎብኘት የተደበቀውን ገንዘባችንን መጠን አሳደገው ነገር ግን ግባችን የሆነው አምስት መቶ ዶላር ላይ ለመድረስ ረጅም ጊዜ ይወስዳል አሁን እንደገና በጋ መጣ:…»
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

ውድ አንባብያን #የጣሪያ_ስር_አበቦች የተሰኘው መፅሀፍ #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ድርሰት ነው ስለዚህ እውነተኛ ታሪክ ደሞ የሚቀናነስ ነገር አይኖረውም ከባህላችን ምናምን አትበሉ እኛም በየቤታችን ስንት ጉድ አለ ያልወጣ ያልታተመ...መልካም ንባብ



...ይገባዋል እንዳልል እንኳን አእምሮው ውስጥ ያለውን ሙሉ በሙሉ አልተረዳሁትም። ያለውን ያደርጋል ብዬ ግን አስባለሁ ስሜት ግን ሰውን
የሚቆጣጠርበት መንገድ አለው ሁለታችንም ወለሉ ላይ ወደቅን ልታገለው ሞከርኩ። ታገልን፣ ተገለባበጥን፣
መንፈራገጥና መጨነቅ ያለበት የፀጥታ ትግል የእሱ ጥንካሬ ከእኔ ጋር።ፍልምያ አልነበረም።

እኔ ጠንካራ የዳንሰኛ እግሮች አሉኝ፡᎓ እሱ ትልቅ ክብደትና ቁመት አለው... በዛ ላይ ከእኔ የበለጠ የሆነ የጋለ ያበጠና ጠንካራ ነገር ለመጠቀም ማስተዋሉንና
ጤንነቱን የሰረቀው ቆራጥነት ነበረው
እወደዋለሁ ያንን ያህል የሚፈልገው ከሆነ እሱ የሚፈልገውን እኔም
እፈልገዋለሁ ትክክልም ይሁን ስህተት᎓ የሆነው ሆኖ ከዚህ ምሽት በፊት
ፍቅረኞችን የማያውቀው አሮጌ፣ ቆሻሻና የሚሸት ፍራሽ ላይ አረፍን፡ እዛ
ነው የወሰደኝ እና መርካት ያለበትን ያንን ያበጠ፣ ጠንካራ የወንድ የወሲብ
አካል በግድ ያስገባው: ጥብቅና የተቋቋመውን አካሌን ቀዶትና አድምቶት
ወደ ውስጥ ገባ።

አሁን በጭራሽ አናደርገውም ብለን የማልንበትን ነገር አደረግን።

አሁን ለዘለዓለም ተፈርዶብናል። ለዘለዓለም በእሳት ልንጠበስ ተረግመናል።በማያቋርጠው የገሀነም እሳት ውስጥ እርቃናችንን ተዘቅዝቀን እንሰቀላለን
ልክ አያትየው ከረጅም ጊዜ በፊት እንደተነበየችው ሆንን ኃጢአተኞች!

አሁን መልሶች ሁሉ አሉኝ፡

አሁን ልጅ ሊኖር ይችላል፡ ለእንደኛ አይነቶቹ የተዘጋጀውን ዘለአለማዊ
የገሀነም እሳት ሳይጠብቅ በህይወት ስለኃጢአታችን የሚያስከፍለን ልጅ
ይመጣል። ተራራቅንና እርስ በርስ ተያየን: ፊቶቻችን በድንጋጤ የደነዘዙና
የገረጡ ሆነዋል። ልብሶቻችንን ስናስተካክል መነጋገር እንኳን አልቻልንም

አዝናለሁ ማለት አያስፈልገውም ሁሉ ነገሩ ላይ ይታያል... የሚንቀጠቀጥበት
መንገድ፣ ልብሶቹን ለመቆለፍ ሲሞክር እጆቹ የሚንቀጠቀጡበት መንገድ
መደንገጡን ይናገራሉ፡

ቆይቶ ወደ ጣራው ላይ ወጣን።

ረጃጅም የደመና መስመሮች የድፍኗን ጨረቃ ፊት እያቋረጡ ነው እሷም
ትደበቅና እንደገና ትወጣለች:: ጣራው ላይ ሆነን ለፍቅረኞች በተዘጋጀው ምሽት ተቃቅፈን ተላቀስን ሊያደርገው ፈልጎ አልነበረም፡ እኔም ልፈቅድለት ፈልጌ አልነበረም ከእኔ ጋር ተመሳሳይ ደም ካለው ሰው ጋር አንድ ጊዜ ባደረግነው ነገር ልጅ የመምጣቱ ፍርሀት ወደ ጉሮሮዬ መጥቶ ምላሴ ላይ ቀረ: ከገሀነም ወይም ከእግዚአብሔር ቁጣ በላይ የሆነው ከባዱ ፍርሀቴ ጭራቅ የሚመስል፣ ቅርፁ የተበላሸና ደደብ ልጅ መውለድ አስፈርቶኛል። ግን
እንዴት ስለዚህ ጉዳይ ለክሪስ መናገር እችላለሁ? በበቂ ሁኔታ እየተሰቃየ
ነው: ሆኖም ግን መንገር አለብኝ ምክንያቱም የእሱ ሀሳቦች ከእኔ በተሻለ
በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ናቸው።

“በአንድ ጊዜ መፀነስ አይኖርም:: ምንም ነገር ቢፈጠር ሌላ ጊዜ እንደማይሆን
እምልልሻለሁ፡ ይህ ነገር ከመፈጠሩ በፊት ራሴን አኮላሻለሁ! አለኝ፡ ከዚያ
ወደ እሱ ሳበኝና የጎን አጥንቶቼ የሚሰበሩ እስኪመስለኝ ድረስ አጥብቆ አቀፈኝ። “አትጥይኝ ካቲ… እባክሽ እንዳትጠይኝ፡ ልደፍርሽ ፈልጌ አልነበረም
በእግዚአብሔር እምልልሻለሁ። ብዙ ጊዜ ተፈትኜ አውቃለሁ ግን ብዙ ጊዜ ክፍሉን እለቃለሁ ወይም ወደ መታጠቢያ ቤት እገባለሁ አለዚያም ጣራው
ስር ወዳለው ክፍል እወጣለሁ ወይም እስክረጋጋ ድረስ አፍንጫዬን መፅሀፍ ውስጥ እቀብራለሁ እና ማለፍ ችዬ ነበር:”

በቻልኩት መጠን ጥብቅ አድርጌ አቀፍኩት። “አልጠላህም ክሪስ” ስል አንሾካሾኩ ጭንቅላቴን ደረቱ ላይ አድርጌያለሁ: “አልደፈርከኝም፤ የምሬን ብፈልግ ኖሮ ላስቆምህ እችል ነበር ማድረግ ያለብኝ ጉልበቴን ጥንክር አድርጌ ወደላይ ማድረግ ብቻ ነበር፡ የኔም ጥፋት ነው” አዎ የኔም ጥፋት ነው። የእናቴን
መልከመልካም ወጣት ባል ከመሳም የተሻለ ነገር ማወቅ ነበረብኝ፡ የወንድ
ጥንካሬ አካላዊ ፍላጎቶች ባሉትና ሁልጊዜ በሁሉም ነገርና በሁሉም ሰው
ተስፋ በቆረጠ ሰው ዙሪያ ወንድሜም ቢሆን እንኳን ሰውነትን የሚያሳይ ልብስ
መልበስ አልነበረብኝም: በፍላጎቶቹ እየተጫወትኩ፣ ሴትነቴን እየሞከርኩ፣
የራሴን የሚቃጠል የመርካት ፍላጎት እያየሁ ብቻ ነበር።

ይህ የተለየ አይነት ምሽት ነው፤ ልክ ዕድል ከረጅም ጊዜ በፊት ይህንን ቀን
ያቀደው ይመስላል እና ይህ ምሽት ትክክልም ይሁን ስህተት እጣ ፈንታችን
ነው:

ንፋሱና ቅጠሎቹ ዜማ አልባ ሙዚቃ ያሰማሉ: ሙዚቃው ያው ነው: ሰው የመሰለ አፍቃሪ የሆነ ፍጥረት እንዴት በዚህ ቆንጆ ምሽት አስቀያሚ ሊሆን
ይችላል?

ምናልባት ጣሪያው ላይ ብዙ ቆይተናል፡

የመስከረም መግቢያ በመሆኑ ጣሪያው ቀዝቃዛ፣ ጠንካራና ሻካራ ሆኗል።
ቅጠሎቹ መርገፍ ጀምረዋል ጣራው ስር ያለው ክፍል ልክ እንደ ገሀነም ያቃጥላል ጣራው ላይ ግን በጣም በጣም ይቀዘቅዛል
እኔና ክሪስ ለደህንነትና ለሙቀት ተቃቅፈን ተቀምጠናል። በጣም መጥፎ ወጣቶችና ኃጢአተኞች:: ያለማቋረጥ በመጠጋጋት በጣም ተወጥረው በቀጠኑ
ታሪኮች የራሳችንን ክብር አሽቀንጥረን ጥለነዋል፡ በአንድ ወቅት በራሳችን
ስሜታዊ ተፈጥሮ አብዝተን የተፈተንን ቢሆንም... በዚያ ወቅት እንኳን እሱ እኔም ስሜታዊ መሆኔን አላውቅም ነበር፡ ልቤን የሚሰውርና ሽንጤን
እንድሰብቅ የሚያደርገኝ ቆንጆ ሙዚቃ ብቻ ይመስለኝ ነበር፡ በጣም ተጨባጭ የሆነ ሌላ ነገር እንዳለ አላውቅም ነበር።

ልክ አንድ ልብ እንደምንጋራ ሁሉ በሰራነው ስራ ራስን የመቅጣት አሳዛኝ ቅኝት
እየደለቅን ነበር ቀዝቃዛው ነፋስ የረገፈ ቅጠል ወደ ጣራው አምጥቶ ድንገት
ፀጉሬ ውስጥ እንዲያዝ አደረገው:: ክሪስ ሊያነሳው ሲሞክር ደርቆና ተሰባብሮ
ወደቀ ህይወቱ ቅጠሉ በንፋስ መብረር እንዴት እንደሆነ በሚያውቀው
ሚስጥር ላይ የተመሰረተ ይመስል ክሪስ ቅጠሉን አተኩሮ እየተመለከተ
ነበር: እጆችም ክንፎችም የሉትም... ግን ሞቶም መብረር ይችላል።

“ካቲ” በሚደነቃቀፍ ደረቅ ድምፅ ጠራኝ፡ “አሁን ልክ ሶስት መቶ ዘጠና ስድስት
ዶላር ከአርባ አምስት ሳንቲም አለን በቅርቡ በረዶ መጣል ይጀምራል።
በልካችን የሆነ የክረምት ኮት ወይም ጫማዎች የሉንም፧ መንትዮቹ ደግሞ
ደካማ ስለሆኑ በቀላሉ ብርድ ሊያሳምማቸውና ከዚያ ወደ ኒሞኒያ ሊለወጥባቸው
ይችላል ሌሊት ነቅቼ ስለእነሱ እጨነቃለሁ እና አንቺንም አልጋሽ ላይ
ሆነሽ ኬሪን አተኩረሽ ስትመለከቻት አይሻለሁ፡ አንቺም ተጨንቀሽ መሆን
አለበት። አሁን ከእናታችን ክፍል ውስጥ እንደበፊቱ ገንዘብ የማግኘታችንን
ነገር እጠራጠራለሁ። ሠራተኞች ገንዘብ እየሰረቋቸው እንደሆነ ጠርጥረዋል።አሁን ምናልባት እናታችን አንቺ ልትሆኚ እንደምትችይ ትጠራጠር ይሆናል አላውቅም... እንደማይሆን ተስፋ አለኝ።

“እነሱ ምንም ቢያስቡ በሚቀጥለው ለመስረቅ ስሄድ ጌጣጌጧን ለመስረቅ
እገደዳለሁ። ትልቅ ነገር እወስድና ከዚያ እናመልጣለን ልክ ርቀን እንደሄድን በቂ ገንዘብ ስለሚኖረን መንትዮቹን ወደ ዶክተር እንወስዳቸዋለን፡” አለ፡

“ጌጣጌጦቹን ውሰድ።” እንዲወስድ ብዙ ጊዜ ለምኜው ነበር። በመጨረሻ
ሊያደርገው ነው እናታችን ልታገኘው የታገለችለትን ብዙ ገንዘብ የሚያወጣ
ጌጥ ታጣለች በዚያ ሂደት ውስጥ እኛንም ታጣለች: ግን ግድ ይኖራት
ይሆን?
👍402👏2
ወደዚህ በመጣን በመጀመሪያው ምሽት የተቀበለችን ያቺ አሮጌ ጉጉት ከሩቅ እንደ ጣረ ሞት ስትጮህ ይሰማል እኛ ደግሞ ቀጫጫ፣ ቀርፋፋ፣ በምሽቱ ድንገተኛ ቅዝቃዜ ደንዝዘን ከመሬት ላይ መነሳት የጀመረ ጭጋግ መስለን እያዳመጥናት ነው።

በግራጫና ቀዝቃዛ ደመናዎቹ ላይ በጨረቃዋ ውስጥ የእግዚአብሔር
አይን እያንፀባረቀ ነው ከመንጋቱ በፊት ነቃሁና ክሪስና ኮሪ ወደተኙበት
ተመለከትኩ። ልክ አይኖቼ ሲከፈቱና ጭንቅላቴን ዞር ሳደርግ ክሪስ እንደነቃና
ከነቃም ቆየት ያለ እንደሆነ ተሰማኝ፡ ወደ እኔ እየተመለተ ነበር ሰማያዊ
አይኖቹን ዕንባ ሸፍኗቸዋል፡ ትራሱ ላይ የሚንጠባጠቡ እምባዎቹ የምን
ዕንባዎች እንደሆኑ አውቄያለሁ እፍረት፣ ጥፋተኝነትና ወቀሳ።

“እወድሀለሁ ክሪስቶፈር፡ ማልቀስ የለብህም: እኔ መርሳት እችላለሁ አንተም
መርሳት ከቻልክ ይቅር የሚያባብል ምንም ነገር የለም።

ምንም ሳይናገር ጭንቅላቱን ነቀነቀ ግን በደንብ አውቀዋለሁ እስከ አጥንቱ ድረስ። ሀሳቦቹን፣ ስሜቶቹንና እስከ ስር ድረስ የቆሰለበትን መንገድ ሁሉ
አውቃለሁ፡ በእኔ ውስጥ እምነቱን፣ መተማመኑንና ፍቅሩን የከዳቸውን
አንዲት ሴት መልሶ እንደሚያጠቃት አውቄያለሁ ማድረግ ያለብኝ ብቸኛው
ነገር ጀርባው ላይ የስሜ የመጀመሪያ ፊደል የተቀረፀበትን የእጅ መስተዋት አንስቼ እናታችን በእኔ እድሜ ሳለች ትመስል የነበረውን ማየት ነበር።
እናም አያትየው እንደተነበየችው ይፈጠራል- የዲያብሎስ ዘር… የሰይጣን
ልጆች: በተሳሳተ መሬት ላይ የተዘራ ክፉ ዘር የአባቶችን ኃጢአት ለመድገም አዳዲስ ተክሎችን ያፈራል

የእናቶችን ጨምሮ!

ይቀጥላል
😢3618👍18😁2🥰1👏1
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ሰባት ፡ ፡ #ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ ውድ አንባብያን #የጣሪያ_ስር_አበቦች የተሰኘው መፅሀፍ #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ድርሰት ነው ስለዚህ እውነተኛ ታሪክ ደሞ የሚቀናነስ ነገር አይኖረውም ከባህላችን ምናምን አትበሉ እኛም በየቤታችን ስንት ጉድ አለ ያልወጣ ያልታተመ...መልካም ንባብ ...ይገባዋል እንዳልል እንኳን አእምሮው ውስጥ ያለውን ሙሉ በሙሉ…»
✍️✍️የጠንቋዩ ዋሻ✍️✍️
❀❀ክፍል 1 ❀✈️✈️✈️
☜☜☜☞☞☞☞☞
በድቅድቅ ጨለማ የተዋጠው ዋሻ ከማስፈራት አልፎ ያስጨንቃል ፡ ልብይስባል ፡ ፀጥታው ደሞ ይብስ ፡ሞትን ያስመኛል ፡ በዛ አስፈሪ ጎሬ ውስጥ ፡ በማያውቁት ፡ሰው በድንገት ታፍነው የመጡት ሦስት ፡ የደረሱ ጎረምሶች ፡ አይኖቻቸውን ፡በቀይ ጨርቅ ፡ቢሸፈኑም ፡ የገቡበት ፡ ጎሬ ፡አንዳች ብርሃን እንደሌለ ተውቋቸዋል ፡ ሦስቱም ፡በአካልም ሆነ በዕድሜ ተቀራራ ቢ ናቸው ፡ ገና በመፈርጠም ላይ ያለው ፡ ታዳጊ ሰውነታቸው ፡ የገቡበትን ፡ድንገተኛ ፡ወጥመድ ፡እንዴት ፡መቋቋም ፡እንደሚችል ፡ ምንም አልገባቸው ፡ ብቻ ከነሱ በገዘፈ ክንድ ውስጥ ፡በቁጥጥር ፡እንደዋሉ ካወቁ ሰአታት ተቆጥሯል ፡ ለወትሮው ፡ የሰፈር ውስጥ አይለኝነታቸውና የጎረምሳ ቲቢታቸው ፡ ልዩ ነበር ፡ ተወልደው ካደጉባት ፡ከተማ ፡አዲስ አበባ ፡ ወጥተው አያውቁም ፡ የነሱ ግዛት ፡ ከአብነት ፡እስከ ሜክሲኮ ፡ሲያልፍ ፡እስቴዴዬም ፡ድረስ ፡ብቻ ነው ፡ ዛሬን ፡ግን ፡ ከመጠን ፡ባለፈ ፡ ስካር ፡ውስጥ ፡ገብተው ፡ የሜክሲኮን ፡መንገድ ፡ይዘው በመምጣት ፡ሳሉ ፡ ባልታወቀ ፡ሰው ፡ ተጠልፈው ፡ ወደማያውቁትና ወዳልገባቸው ፡ስፍራ ፡እየተወሰዱ ነው ፡ * በመጀመሪያ ያፈርጣማ ና አስፈሪ ሰው ፡ በሚኒ ባስ ፡መኪናው ፡ከፊታቸው ፡ሲቆም ፡ በስካር ፡መንፈስ ፡ውስጥ ፡ሆነው ፡ ዕድላቸውን ፡በማመስገን ፡ቶሎ ፡ወደቤታቸው ፡እንዲያደርሳቸው ፡ ሰውየውን፡በጩኽትና ፡ በማስጠንቅቅ ፡እያደነቆሩት ፡ነበር ፡ ከቆይታ በዋላ ግን ፡ ያልታወቀው ፡ሰው ፡ በስካር ፡እብድ ፡ብለው ፡የሚለፈልፉትን ፡ ሦስቱን ጎረምሶች ፡አፋቸውን እንዲዘጉ በቁጣ ፡ሲጮህባቸው ፡ ከሱ የበለጠ በመናደድ ፡ መልሰው ፡ጮሁበት ፡ ያልታወቀው ፡ሰው መኪናውን ፡አቁሞ ፡በመውረድ ፡ ከዋላ የጫናቸውን ፡ጎረምሶች ፡አንድ ፡በአንድ ፡ከመኪናው ፡አውርዶ ፡ በፈርጣማ እጆቹ ፡ ደና አድርጎ ፡እየነረተ ፡መልሶ ፡ወደውስጥ ፡አስገባቸው ፡ እነሱም ፡በዚ ጊዜ ነበር ፡በተሳሳተ መስመር ላይ እንደሆኑ ያወቁት ፡ እናም ፡ሰውዬውን ፡ለመጀመሪያ ጊዜ ከስካር መንፈሳቸው ፡ተላቀው ፡ልብ ብለው ፡ አዩት በጣም ፡ከማስጠላቱም በላይ ፡ግዝፈቱ አነጋጋሪ የሚባል አይነት ፡ነው ፡ አንድ ፡አይኑ በጥቁር ፡ ጨርቅ መሰል ነገር ተሸፍኗል ፡ በዛ ሰፊና ፡አስጠሊ ፊቱ ላይ ፡ጉርጥርጥ የምትለ ብቸኛ እና ፡ቅልት ያለች ፡አይኑ ፡የበለጠ የልብን ፡ምት ታፈጥናለች ፡ ሦስቱም ፡እርስ ፡በእርስ ፡ተያይተው ፡አንድ ፡ዘዴ ፡ለማመንጨት ፡እና ፡ይህ ፡ሰው ፡በዚ ፍጥነቱ ፡ ሲሆል ፡ሳያደርሳቸው ፡በፊት ፡ለማምለጥ ፡አሰቡ ፡ ነገር ግን ያሰቡትን ፡ያወቀ ይመስል ፡ አንድ ፡ጨለማ ቦታ ሲደርስ ፡ መኪናውን ፡በማቆም ፡ ወደ እነሡው ፡መጥቶ ፡ ከአንድ ፡ ጥቁር ቦርሳ ውስጥ ፡ቀያይ ፡ጨርቅ ፡አውጥቶ ፡የሦስቱንም ፡አይን ፡አሰራቸው ፡ ቢፈራገጡም ምንም ፡ማድረግ ፡ሳይችሉ ቀሩ ምን እንዳስነካቸው ፡ሳያውቁ ፡ከቆይታ በዋላ ፡እራሳቸውን ፡ዝልፍልፍ ፡ አደረጋቸው ፡ ከዛ በዋላ ፡ያልታወቀው ፡ሰው ፡እረዥም ፡ሰአት ፡ነዳ ፡እነሱ ግን ፡ ወዴት ፡በየት ፡እንደሚነዳው ፡በጭራሽ ፡አላወቁም ፡ድንዝዝ ፡እንዳሉ ፡ነበር ፡ ከብዙ መደናዘዝ ፡በዋላ ነበር ፡የነቁት ፡ሲነቁ ፡በድቅ ድቅ ፡ጨለማ ፡በተዋጠ ጫካ ውስጥ ፡ተዘርረው ፡ነበር ፡ከመኪናው ፡ውስጥ ፡እንኳ ፡እንዴት ፡ብለው እንደወጡ የሚያስታውሱት ፡ነገር የለም ፡ እዛ ጨለማውስጥ ፡በትህግስት ፡እንዲነቁ ሲጠብቃቸው ፡የነበረው ፡ያልታወቀው ፡ሰው ድንገት ፡መንቀሳቀሳቸውን ፡ሲያውቅ ፡
"ተነሱ እናንተ ይበቃቹሃል ፡ አቢያራ ይጠብቃቹሃል " አላቸው ፡በሚያስፈራ ድምፅ ፡ ሦስቱም ፡ የሰሙትን ፡ስም ፡ ከዚ በፊት የትም ፡ቦታ ሰምተው ፡ስለማያውቁ ፡ግራ ተጋቡ ፡ ማነው ፡አቢያራ ፡ ምንድነው፡ከኛ የሚፈልገው ፡ ሁሉም ፡በየራሳቸው ፡አሰቡ ፡ መጠየቅ ፡እንዳይችሉ ግን ፡የሆነ ነገር ፡አንቆ ፡እንደያዛቸው፡አይነት ፡ሆኑ ፡ እናም ፡ያለምንም ፡ጥያቄ ፡ በፀጥታ እየተንቀጠቀጡ እና እየተደነቃቀፉ ፡ ያልታወቀውን ፡አስፈሪሰው ፡ተከተሉት ፡ እሱ መንገድ እየመራ ፡ወደግራ ታጠፉ ፡ደሞ ፡ወደቀኝ ፡እያለ ፡በድምፁ ሲመራቸው ፡እና፡አንዳንዴም ፡ሲገፈትራቸው ፡ ዕንባና ሳግ እየተናነቃቸው ፡ ስለማይጨክኑባቸው ፡ውድ ፡ቤተሰቦቻቸው ፡እያሰቡ ፡ሰውየውን ፡ተከትለው ፡ወደዋሻው ፡ገቡ ፡ ዋሻው ፡ውስጥ አይናቸው ፡ታስሮ ፡ምንም ፡ነገር ፡ለማየት ፡ ባይቻላቸውም ፡ግን ፡ አልፎ ፡አልፎ ፡ጪጪጪ የሚል ፡ልብ ፡የሚያሸብር ፡ድምፅ ፡ከተሰማ ፡በዋላ ፡ጭንቅላታቸውን ፡ገጭቷቸው ፡የሚያልፍ ፡ ወፍ ፡ይሁን ፡በውል ፡ያላወቁት ፡ነገር ፡አለ ፡የሰውዬው ፡ድምፅ ፡ የቁጣ መሆኑ ቀርቶ ፡በለሰለሰ ፡ድምፅ ፡"አባቴ ፡መጥቻለው ፡ክብር ፡ላንተ ይሁን ፡ ጌታዬ ፡በሰላም ፡ጠብቀህ ፡እዚ ላደረስከኝ፡ክብር ፡ላንተ ይገባል ፡ይላል" ጎረምሶቹ፡ይሰው ፡ የአንድ ፡አይለኛሰው ፡ ታዛዥ እንደ ሆነ ተሰምቷቸዋል ፡ ለማን አሳልፎ ፡እንደሚሰጣቸው ፡ ገና ያወቁት ነገር ባይኖርም ፡ ግን ያ እየጠበቃቸው ፡ያለው ፡ሰው ፡ቀላል ፡እንዳልሆነ ገብቷቸዋል ፡ በተሸፈኑት ፡ጨርቅ ላይ ፡የእንባ ፡ዘለላዎች ፡እየወረዱ ፡ ነበር ፡
"ደርሰናል ያአቢያራ ባሪያዎች "አለ ሰውዬው
"ምም ንድን ነው " አለ ከሦስቱ ጎረምሶች አንዱ ፡የሚያስፈራና ፡ እንደንፋስ አይነት ፡ሽውሽውታ ፡በአይል ፡ሲያዳምጥ ፡በፍርሃት ተውጦ ፡
"ድምፅ አታሰማ ተናገር ሳትባል ከአሁን በዋላ ፡እንዳትናገር ፡ ስትተነፍስ እንኳን ፡ መቆጠብ አለብህ ፡ ያአቢያራን ታስቆጣለህ "አለው በሹክሹክታ ፡ ሦስቱም ፡ተንቀጠቀጡ ፡ ሌላ ድምፅ ፡ሲያስገመግም ፡ተሰማ ፡ "አሆ አሆ አሆራራራራራ ያያአቢሃራራራ አሆያ አሆያ ሆሆሆሆሆ "የጩኽቱ መጠን ፡ልክ ፡የለውም የሚያጓራ ድምፅ አስጨናቂ ድምፅ ፡ በዛ ጨለማ ፡የሦስቱ ነብሶች ፡ ተስፋ ያበቃለት መሰለ

✍️✍️✍️ይቀጥላል,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,


ሙና መሐመድ

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️
👍57😱11👎6👏51
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


ቀኖቹን ሁላ ሰማያዊ ስትቀባ አንዱን ለጥቁር ተወው።

በማንኛውም ቀን ልንሄድ ነው፡፡ እናታችን በምሽት ወጣ እላለሁ እንዳለች፣
መጓጓዝ የሚችሉ ውድ ንብረቶቿም ከእሷ ይወጣሉ። ወደ ግላድስተን
አንመለስም እዚያ አሁን ክረምት ገብቷል። ገና እስከ ግንቦት ይቆያል።ሰርከስ የሚሰሩ ሰዎች ወደሚኖሩበት ወደ ሳራሶታ እንሄዳለን፡ እዚያ ያሉ
ሰዎች ለየት ያለ የኋላ ታሪክ ላላቸው ሰዎች ደግነት በማሳየት የሚታወቁ
ናቸው ክሪስና እኔ ከፍ ያለ ቦታ ማለትም ጣራ ላይ ስለኖርን ምሰሶዎቹ
ላይ ብዙ ገመዶች የታሰሩበት በመሆኑ ለክሪስ “የዥዋዥዌ ትርኢት የምንሰራ እንሆናለን” አልኩት እየተፍለቀለቅኩ። በመጀመሪያ የሞኝ ሀሳብ እንደሆነ አስቦ ፈገግ አለ፤ ቀጥሎ ግን መንፈስን የሚቀሰቅስ ሀሳብ ብሎ ጠራው።

ኮሪ ጭንቅላቱን ቀና አደረገ፡፡ ሰማያዊ አይኖቹ በፍርሀት ፈጥጠዋል።

“አይሆንም!” አለች ኬሪ “እቅዳችሁን አልወደድነውም እንድትወድቁ አንፈልግም::”

“አንወድቅም” አለ ክሪስ፡ “እኔና ካቲ የማንቻል ቡድን ነን፡" አሻግሬ ወደ እሱ
እየተመለከትኩ መማሪያ ክፍሉ ውስጥ ከዚያም ጣሪያው ላይ ሆነን “ከአንቺ
በስተቀር ማንንም አላፈቅርም፣ ካቲ አውቀዋለሁ... እንደዚያ አይነት ስሜት ነው ያለኝ... ሁልጊዜ እኛ ብቻ:" ያለኝን አስታወስኩና በተለየ ሁኔታ ሳቅኩ። “ሞኝ አትሁን፣ በዚያ መንገድ እንደማትወደኝ ታውቃለህ፡ እና ጥፋተኝነት
ሊሰማህ ወይም ልታፍር አይገባም: የእኔም ጥፋት ነው: እንዳልተፈጠረ
ማስመሰልና በድጋሚ እንዳይፈጠር እርግጠኛ መሆን ነው ያለብን፡"

"ግን ካቲ....."

“አንቺና እኔ ሌሎች ሰዎች ሲኖሩን፣ በፍፁም… በፍፁም እርስ በርሳችን በዚህ መንገድ እንዲሰማን አይሆንም''

“እኔ ግን ስላንተ በዚህ መንገድ እንዲሰማኝ ነው የምፈልገው። እና ለእኔ ሌላ
ሰው ለማመንና ለመውደድ በጣም ዘግይቷል።”

ክሪስን መመልከት… ከዚያ መንትዮቹን. ለሁላችንም እቅድ ሳወጣና እንዴት
እንደምንሄድ ሳወራ ትልቅ የሆንኩ አይነት ስሜት ፈጠረብኝ፡ ለመኖር
የትኛውንም ነገር ለመስራት እንደምንገደድ ባውቅም እንኳን መንትዮቹ ሰላም
እንዲሰማቸው መፅናኛ ነገሮች አወራቸዋለሁ።

መስከረም አልፎ ጥቅምት ተተካ። በቅርቡ በረዶ መጣል ይጀምራል:
“ዛሬ ማታ” አለ ክሪስ፡ እናታችን በሩጋ ቆም ብላ ዞራ እንኳን ሳታየን
በግዴለሽነት ደህና ሁኑ ብላን ሄደች:: አሁን እኛን መመልከት እንኳን
መቋቋም አቅቷታል። አንዱን የትራስ ልብስ ሌላኛው ላይ ደርበን ጠንhር እንዲል አደረግን፡ በዚያ ትራስ ጨርቅ ውስጥ ክሪስ የእናታችንን ውድ
ጌጣጌጦች ሁሉ ከትቶ ያመጣል፡ እኔም ሁለት ሻንጣዎችን አሽጌ እናታችን
አሁን ወደዚያ ስለማትሄድ ጣራው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ደብቄያለሁ።

ቀኑ መምሸት ሲጀምር ኮሪ ማስመለስ ጀመረ። እየደጋገመ ያስመልሰው
ጀመር። በመድኃኒት ማስቀመጫው ውስጥ ለሆድ የሚሆን መድኃኒት ነበረን የገረጣውን፣ የሚያንቀጠቅጠውን፣ የሚያስለቅሰውን አሰቃቂ ማስመለስ ያደረግነው ጥረት ሁሉ ሊያስቆመው አልቻለም ከዚያ ክንዶቹን በአንገቴ ዙሪያ ጠምጥሞ “እማዬ ደህና አይደለሁም::” ሲል አንሾካሾከ።

“እንዲሻልህ ምን ላድርግልህ ኮሪ?” ስል በጣም ልጅ መሆኔና ልምድ የሌለኝ መሆኔ እየተሰማኝ ጠየቅኩ።

“ሚኪ” አለ ያላመደውንና ጓደኛ ያደረገውን አይጥ በደካማ ድምፅ እየተጣራ
“ሚኪ እኔ ጋር እንዲተኛ እፈልጋለሁ”

“ግን ስትገለበጥ ላዩ ላይ ትተኛበትና ይሞትብሀል፡ እንዲሞትብህ አትፈልግም
አይደል?”

“አልፈልግም” አለ ሀሳቡ ራሱ ያስደነገጠው መሰለ፡ ከዚያ ያ አሰቃቂ መጓጠጥ
እንደገና ጀመረውና ክንዶቼ ላይ እንደያዝኩት እየቀዘቀዘ መጣ፡ በላብ የረጠበ
ፀጉሩ ግንባሩ ላይ ተለጥፏል ሰማያዊ አይኖቹ ፊቴ ላይ ተተክለው እየደጋገመ እናቱን ይጣራል። “እማዬ፣ እማዬ፣ አጥንቶቼን አሞኛል” “አይዞህ” አልኩት።
የተበላሸውን ፒጃማውን ለመቀየር ተሸክሜ ወደ አልጋው እየወሰድኩት ነው።
ሆዱ ውስጥ የቀረ ምንም ነገር ሳይኖር እንዴት ሊያስመልሰው ይችላል?
ክሪስ ይረዳሻል አትጨነቂ!” ሲለኝ ከጎኑ ጋደም ብዬ ደካማና የሚንቀጠቀጥ
ሰውነቱን በክንዶቼ አቀፍኩት::

ክሪስ ጠረጴዛው ጋ ተቀምጦ የኮሪ የህመም ምልክቶች የሚያሳየውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያንዳንችንን ሊያጠቃን የሚችለውን ሚስጥራዊ በሽታ ለማወቅ
የሀክምና መፅሀፍ ላይ ተደፍቷል አሁን አስራ ስምንት አመት እየሆነው
ነው እኔንና ኬሪን ትታችሁን አትሂዱ! ሲል ለመነኝ፡ ጮክ ባለ ድምፅ “ክሪስ አትሂድ እዚህ ቆይ!” አለ።

ምን ማለቱ ነው? እንድናመልጥ አይፈልግም? ወይስ ለመስረቅ እንደገና
ወደ እናታችን ክፍል አትሂድ ማለቱ ይሆን? እኔና ክሪስ መንትዮቹ የምናደርጋቸውን ነገሮች በመረዳት ይመለከታሉ ብለን ያመንነው ለምንድነው?
በእርግጠኝነት እሱና ኬሪ ትተናቸው እንደማንሄድ ያውቃሉ ያንን ከማድረግ
ብንሞት ይሻለናል።

ኬሪ ነጭ ልብስ የለበሰች ትንሽ ጥላ መስላ ወደ አልጋው መጣችና በረጠቡት ትላልቅ ሰማያዊ አይኖቿ መንትያ ወንድሟን አተኩራ እየተመለከተች
ቆመች: ትንሽ ናት። በጨለማ ክፍል ውስጥ መንምና በአጭር ቀርታ ያደገች ትንሽዬ ተክል ናት።

“ከኮሪ ጋ መተኛት እችላለሁ? ምንም መጥፎ ወይም ክፉ ወይም ቅዱስ
ያልሆነ ነገር አንሰራም: እሱ አጠገብ መሆን ስለፈለግኩ ብቻ ነው” አለች።

አያትየው ትምጣና መጥፎ የምትለውን ነገር ታድርግ! ኬሪን ከኮሪ ጋር አስተኛኋት። ከዚያ እኔና ክሪስ ከትልቁ አልጋ ግራና ቀኝ ቆመን በሀዘን ተሞልተን ኮሪ ረፍት ባጣ ሁኔታ ሲቅበጠበጥና ለመተንፈስ ሲታገል እንዲሁም በቅዠት ሲጣራ እየተመለከትን ነው
እናቱንና አባቱን፣ ክሪስንና እኔን ይፈልጋል እምባዬ በሌሊት ልብሴ ኮሌታ
ላይ እየወረደ ነው ክሪስንም ስመለከተው ጉንጮቹ በእምባዬ ረጥበዋል። “ኬሪ
ኬሪ... ኬሪ የታለች?" ሲል በመደጋገም ጠየቀ እንቅልፍ ከወሰዳት ትንሽ
ቆይታለች: ፊቶቻቸው ተጠጋግተው ነበር። ቀጥታ ወደ እሷ እየተመለተ
ቢሆንም እያያት አይደለም

ቅጣት እንደሆነ አሰብኩ፡፡ እግዚአብሔር እኔና ክሪስ ስለሰራነው ነገር እየቀጣን
ነው አያትየው አስጠንቅቃን ነበር. እስክተገረፍንበት ቀን ድረስ በየቀኑ
ታስጠነቅቀን ነበር ሌሊቱን ሙሉ እኔ ክፍሉ ውስጥ ስንጎራደድ፣ ክሪስ ደግሞ ከአንዱ የህክምና መፅሀፍ ወደ ሌላው እየሄደ ሲያነብ ነበር።

በመጨረሻ ደም የመሰሉ አይኖቹን ቀና አድርጎ “የምግብ መመረዝ ነው::
ወተቱ ተበላሽቷል ማለት ነው” አለ።

“ስቀምሰውም፣ ሳሸተውም ደህና ነበር” ስል መለስኩለት ሁልጊዜ የትኛውንም ምግብ ለክሪስና ለመንትዮቹ ከማቅረቤ በፊት በጥንቃቄ አሽትቼና ቀምሼ ነበር። በሆነ ምክንያት ሁሉንም ነገር ከሚወደውና ምንም ነገር ከሚበላው
ክሪስ የተሻለ የመቅመስ ችሎታ እንዳለኝ አስባለሁ።

“ሀምበርገሩ ይሆናል፡ ለየት ያለ ጣዕም ነበረው”

“አረ ጣዕሙ ለእኔ ደህና ነበር” አልኩት ለእሱም ደህና የነበረ ይመስለኛል::
ምክንያቱም ቀኑን ሙሉ ኮሪ ምንም መብላት ስላልፈለገ የኬሪን ግማሽ ሀምበርገር ጨምሮ የኮሪንም ፋንታ ነበር የበላው ኮሪ ቀኑን ሙሉ ምንም መብላት አልፈለገም ነበር።

“ካቲ አንቺም ቀኑን ሙሉ ምንም እንዳልበላሽ አስተውያለሁ አንቺም እንደ
መንትዮቹ ያህል ከስተሻል፡ የምታመጣልን ምግብ በቂ ነው ራስሽን መበደል
አይጠበቅብሽም” አለኝ፡
👍343🥰1
“ኮሪ የሚወደው ዶናቶቹን ነው፡ እኔም መብላት የምፈልገው እነሱን ብቻ
ነው እኔ ከምፈልጋቸው በላይ ለእሱ ያስፈልጉታል።”
ምሽቱ ቀጠለ፡፡ ክሪስ የህክምና መፃህፍቱን ማንበብ ቀጠለ፡ ለኮሪ የሚጠጣው ውሀ ስሰጠው ወዲያው አስመለሰው: ፊቱን ከደርዘን ጊዜ በላይ አጠብኩት ፒጃማውን ሶስት ጊዜ ቀየርኩለት᎓ ኬሪ መተኛቷን እንደቀጠለች ነው።

ነጋ።

ፀሐይዋ ወጣች፡ አያትየው የሽርሽር ቅርጫቱን ይዛ ስትገባ አሁንም ኮሪን
ዘግታ ቆለፈችና ቁልፉን ኪሷ ከታ ወደ ጠረጴዛው ተመለከተች። ከቅርጫቱ
ያሳመመው ምን እንደሆነ ለማወቅ እየሞከርን ነበር ቃል ሳትናገር በሩን
ውስጥ ወተት የያዘ ትልቅ ፔርሙዝ፣ ሾርባ ያለበት አነስ ያለ ፔርሙዝ፣
ሳንድዊቾች የያዘ የተጠቀለለ ወረቀት እና ሌሎቹንም አስቀመጠችና ለመውጣት ፊቷን አዞረች:

“አያቴ” አልኳት እያመነታሁ። ወደ ኮሪ አልተመለከተችም- አላየችውም:

“አላነጋገርኩሽም” አለች በቀዝቃዛ አነጋገር፡

“እስካነጋግርሽ ጠብቂ”
“መጠበቅ አልችልም” አልኩ ከተቀመጥኩበት የኮሪ አልጋ ጠርዝ ላይ
እየተነሳሁ እየተናደድኩ ነው “ኮሪ ታሟል! ሌሊቱን ሙሉ ሲያስመልሰው ነው ያደረው: ትናንትና ቀኑን ሙሉም እንደዚያው ዶክተርና እናቱን
ይፈልጋል።"

ወደ እኔም ሆነ ወደ ኮሪ አልተመለከተችም ከበሩ ወጣችና በሩን ቆለፈችው፡
ምንም አይነት የማፅናኛ ቃል አልተናገረችም: ለእናታችን እንደምትነግራትም
አልገለፀችም
በሩን ከፍቼ እናታችንን እፈልጋታለሁ:" አለ ክሪስ ትናንትና የለበሰውን
ልብስ እንደለበሰ ነበር። ስላልተኛ ልብሱን አልቀየረም

“ቁልፉ እንዳለን ያውቁብናል”

“ይወቁ!”

ልክ የዚህን ጊዜ በሩ ተከፍቶ እናታችን ገባች: አያትየው ከጀርባ አጅባት
ነበር። አብረው ወደ ኮሪ ተጠጉና የገረጣውን ቀዝቃዛ ፊቱን ዳስሰው አይን
ለአይን ተያዩ። ጥግ ላይ ሄደው በሹክሹክታ እየተነጋገሩ አሁንም አሁንም
ፀጥ ብሎ ወደተኛው የሞት አፋፍ ላይ ወዳለው ኮሪ ይመለከታሉ። ደረቱ
ብቻ ከፍና ዝቅ ይላል። ከጉሮሮው አየር ያጠረውና የታፈነ አይነት ድምፅ
ያወጣል ከቅንድቡ ላይ ላቡን ጠረግኩለት እንደዚያ ሰውነቱ ቀዝቅዞ እያዩ
ምን እንደሚያስቡ ይገርማል።

ኮሪ በፍጥነት ወደ ውስጥ፣ ወደውጪ… ወደ ውስጥ፣ ወደውጪ ይተነፍሳል።

እናታችን እዚህ አለች ግን ምንም አታደርግም መወሰን አልቻለችም! መኖር
የሌለባቸው ስለሆኑ አሁንም የሆነ ሰው ልጅ እንዳላት እንዳያውቅ ፈርታለች።

“ለምንድነው እዚያ ቆማችሁ የምትንሾካሾኩት?” ብዬ ጮህኩ። “ኮሪን ወደ
ሆስፒታል ወስዳችሁ የተገኘው ዶክተር ጋር ከማድረስ ሌላ ምን ምርጫ
አላችሁ?"

ሁለቱም አፈጠጡብኝ በተኮሳተረና በገረጣ ፊት እናታችን ሰማያዊ አይኖቿን
እኔ ላይ ተከለች፡ ከዚያ በሽብር ወደ ኮሪ አማተረች። አልጋው ላይ ያየችው
ነገር ከንፈሮቿ እንዲቀጠቀጡ፣ እጆቿ እንዲርበተበቱና ጡንቻዎቿ በሙሉ እንዲዝሉ አደረጋቸው እምባዋ እንዳይወርድ በሚመስል አይነት አይኖቿን
በተደጋጋሚ ታርገበግባለች:
እያንዳንዳቸውን የክህደት ምልክት የሆኑ በስሌት የተሰሩ ሀሳቦቿን በጠባቡ
ተመለከትኩ በኮሪ ልጇ መሆን መገለጥና ምድር ቤት ያለው ሽማግሌ አንድ
ቀን ሲሞት የምታጣው ውርስ መካከል እየመዘነች ነው መቼም አንድ ቀን
መሞቱ አይቀርም አይደል? ለዘለአለም አይኖርም:

ጮህኩኝ። “ምን ሆነሻል እማዬ? ትንሹ ልጅሽ እዚያ ተጋድሞ እየሞተ
አንቺ እዚያ ቆመሽ ስለራስሽና ስለምትወጂው ገንዘብ ታስቢያለሽ? ልትረጅው ይገባል! እሱ ላይ የሆነው ግድ አይሰጥሽም? እናቱ መሆንሽን ረስተሻል?
ካልረሳሽው እንደ እናት ሁኚ! ማመንታትሽን አቁሚና ትኩረት ስጪው! ነገ
ሳይሆን ዛሬ ያውም አሁኑኑ ትኩረት ያስፈልገዋል!”

የጭካኔ ቀለም ፊቷን አለበሰው አይኖቿን ወደ እኔ ዞር አደረገች። “አንቺ!”
ተናደደች። “ሁልጊዜም አንቺ ነሽ አለችና ቀለበት የተደረገበትን እጇን አንስታ
በሀይል በጥፊ አጮለችኝ! እንደገናም መታችኝ። በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ
ለዚያውም በእንደዚህ አይነት ምክንያት በጥፊ መታችኝ! በጣም ተናድጄ
ምንም ሳላስብ እኔም በጥፊ መታኋት... በኃይል!
አያትየው ቆማ እየተመለከተች ነው: በአስቀያሚው ስስ ከንፈሯ ላይ ግብዝ እርካታ ታየ። እናታችንን እንደገና ከመምታቴ በፊት ክሪስ ፈጥኖ እጄን ያዘኝ፡
ካቲ በዚህ አይነት ኮሪን አትረጂውም። ረጋ በይ: እናታችን ትክክለኛውን
ነገር ታደርጋለች” አለኝ።

የአባታችን ፊት አይኔ ላይ መጣ፡ ኮስተር ብሎ ለወለደችሽ ሴት ሁልጊዜ
ክብር ይኑርሽ ሲል በፀጥታ ነገረኝ፡ እንደዚያ እንደሚሰማው አውቃለሁ።
እንድመታት አይፈልግም
“ገሀነም ግቢ ኮሪን ፎክስወርዝ" እስከ መጨረሻው ጮህኩ። “ልጅሽን ሀኪም ቤት ካልወሰድሽ ገሀነም ግቢ! እኛ ላይ የምትፈልጊውን ነገር ማድረግ
እንደምትችይና ማንም እንደማያውቅ ታስቢያለሽ? ያንን የሚስጥር ብርድ
ልብስ መወርወር ትችያለሽ ግን የመበቀያ መንገድ አገኛለሁ አሁን የኮሪን
ህይወት ለማዳን ምንም ነገር ካላደረግሽ ህይወቴን በሙሉ ቢወስድብኝም እንኳን አስከፍልሻለሁ! በደንብ ትከፍያለሽ! ቀጥይ አይንሽን አፍጥጪብኝ አልቅሺ ለምኚ ስለገንዘብና ገንዘብ ስለሚገዛው ነገር ንገሪኝ ግን የምትይው ገንዘብ አንድ ጊዜ የሞተን ልጅ መልሶ መግዛት እንደማይችል እወቂ፡ አሁን አንድ ነገር ማድረግ ካልቻልሽ ወደ ባልሽ ሄጄ መጫወቻ ቦታቸው ጣሪያው ስር ያለው ክፍል የሆነ ለአመታት በተቆለፈ ክፍል ውስጥ ደብቀሽ ያስቀመጥሻቸው
አራት ልጆች እንዳሉሽ የምነግርበት መንገድ እንደማላገኝ ታስቢያለሽ? የዚያን ጊዜ ይወድሽ እንደሆነ ታያለሽ! የዚያን ጊዜ ፊቱን አይተሽ ለአንቺ ምን ያህል አክብሮትና አድናቆት እንደሚኖረው ጠብቂ: ተሸማቀቀች አይኖቿ ግን በሚገድል አይነት አስተያየት እየተመለከቱኝ ነው፡ “በተጨማሪ… ወደ ወንድ
አያትየው ሄጄ ለእሱም እነግረዋለሁ” የበለጠ ጮህኩ። “እና ሰባራ ሳንቲም አያወርስሽም:: ያ ሲሆን ደግሞ በጣም በጣም በጣም ደስ ይለኛል!”

ልትገለኝ ብትችል ደስ እንደሚላት ፊቷ ላይ ይታየኛል በሚገርም ሁኔታ
ያቺ የማትረባ አሮጊት ግን ረጋ ባለ መንገድ ተናገረች: “ልጅቷ ልክ ናት ኮሪን… ልጁ ሆስፒታል መሄድ አለበት!”

በዚያ ምሽት ተመልሰው መጡ፡ ሁለቱም ሠራተኞቹ ክፍላቸው ውስጥ ከተኙ
በኋላ መጡ አየሩ ድንገት ስለቀዘቀዘ በወፋፍራም ኮት ተጠቅልለዋል። የምሽቱ
ሰማይ ግራጫ ሆኗል። የክረምቱ መግቢያ ስለሆነ ይበርዳል በዛ ላይ በረዶ
ሊጥል ይመስላል። ሁለቱም ኮሪን ከእኔ ክንዶች ላይ ወስደው በአረንጓዴ
ብርድ ልብስ ጠቀለሉት። ያነሳችው እናታችን ነበረች። ኬሪ የጭንቀት ጩኸት
አሰማች። “ኮሪን አትውሰዱብኝ!" አለች። “አትውሰዱት… አትው...” አንድ ጊዜ እንኳን ተለይታው የማታውቀውን መንትያዋን ከመውሰድ እንዳስጥልላት
ራሷን ክንዶቼ ላይ ጥላ አምርራ አለቀሰች:

በዕንባ የራስ የገረጣ ፊቷ ላይ አተኩሬ “ኮሪ መሄዱ ጥሩ ነው" አልኳት።
ከእናታችን አይን ጋር ተጋጨን። “እኔም እሄዳለሁ ኮሪ ሆስፒታል ውስጥ
ሲሆን አብሬው እሆናለሁ። እኔ ካለሁ አይፈራም ነርሶቹ እሱን ለመጠበቅ ስራ ከበዛባቸው እኔ እዚያ እሆናለሁ። ያ ቶሎ እንዲሻለው ያደርገዋል። ኮሪ
እኔ ከእርሱ ጋር እንዳለሁ ሲያውቅ ጥሩ ይሰማዋል” አልኳት የተናገርኩት
እውነቴን ነበር፡ አሁን እሷን አይወዳትም፧ የሚፈልገው እኔን ነው: ልጆች
በተፈጥሮ አስተዋይ ናቸው: ማን በጣም እንደሚወዳቸውና ማን እያስመሰለ እንደሆነ ያውቃሉ።
👍19👏6😱1
'ካቲ ትክክል ናት እማዬ” አለ ክሪስ ያለምንም ስሜት ቀጥታ አይኖቹን
እየተመለከተ። “ኮሪ ካቲ ላይ ጥገኛ ነው: እባክሽ እንድትሄድ ፍቀጂ
እንዳለችው የሷ ከዛ መገኘት ቶሎ እንዲሻለው ያደርጋል በዚያ ላይ ከአንቺ
በተሻለ የበሽታውን ምልክቶች ለዶክተሩ በደንብ መግለፅ ትችላለች፡"
የእናታችን ባዶ ፍጥጫ ወደ እሱ ዞረ:: ልክ ምን ማለት እንደፈለገ ለመያዝ


የምትታገል ይመስል ነበር፡ የተምታታባት ትመስላለች… አይኖቿ ከኔ ወደ ክሪስ ከዚያ ወደ እናቷ ከዚያ ወደ ኬሪ ዘለሉና ተመልሰው ወደ ኮሪ መጡ።.....

ይቀጥላል
26👍18
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ስምንት ፡ ፡ #ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ ቀኖቹን ሁላ ሰማያዊ ስትቀባ አንዱን ለጥቁር ተወው። በማንኛውም ቀን ልንሄድ ነው፡፡ እናታችን በምሽት ወጣ እላለሁ እንዳለች፣ መጓጓዝ የሚችሉ ውድ ንብረቶቿም ከእሷ ይወጣሉ። ወደ ግላድስተን አንመለስም እዚያ አሁን ክረምት ገብቷል። ገና እስከ ግንቦት ይቆያል።ሰርከስ የሚሰሩ ሰዎች ወደሚኖሩበት ወደ ሳራሶታ እንሄዳለን፡…»
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

...የእናታችን ባዶ ፍጥጫ ወደ እሱ ዞረ:: ልክ ምን ማለት እንደፈለገ ለመያዝ የምትታገል ይመስል ነበር፡ የተምታታባት ትመስላለች… አይኖቿ ከኔ ወደ ክሪስ ከዚያ ወደ እናቷ ከዚያ ወደ ኬሪ ዘለሉና ተመልሰው ወደ ኮሪ መጡ።

“እማዬ” አለ ክሪስ ጥንክር አድርጎ፡ ካቲ አብራሽ ትሂድ ለኬሪ እኔ አለሁ
ምናልባት ያስጨነቀሽ ያ ከሆነ።"

እንድሄድ አልፈቀዱልኝም።

እናታችን ኮሪን ይዛ ወደ አዳራሹ ወጡ አያትየው ባገኘሁት ድል የጭካኔ
ፈገግታ ሰጥታኝ በሩን ቆለፈችው ኬሪ ወንድሟን በማጣቷ እየጮኸችና እምባዋ እየወረደ ትተዋት ሄዱ። ትንንሽ ደካማ ቡጢዎቿ ጥፋተኛዋ እኔ የሆንኩ ይመስል እኔ ላይ አረፉ፡ ካቲ እኔም
መሄድ እፈልጋለሁ! እንድሄድ እንዲፈቅዱልኝ አድርጊ! ኮሪ እኔ የማልሄድበት ቦታ መሄድ አይፈልግም... ጊታሩን ደግሞ ረስቶታል” አለች።

ከዚያ ቁጣዋ ሁሉ ሲበርድላት፣ ክንዶቼ ላይ ሆና ተንሰቀሰቀች: “ለምን ካቲ? ለምን?”

“ለምን?”

በህይወታችን ትልቁ ጥያቄ ነው።

በህይወታችን ከነበሩት አስቀያሚውና ረጅሙ ቀን ነበር። ኃጢአት ሰርተናል
እና እግዚአብሔር እንዴት በዚህ ፍጥነት ቅጣት ላከብን? ፈጠነም ዘገየም
አያትየው እንዳወቀችው ሁሉ ራሳችን ዋጋ ቢስ መሆናችንን እንደምናረጋግጥ
ያወቀ ይመስል፣ አይኖቹ እኛ ላይ ነበሩ ማለት ነው።

ቲቪ መጥቶ የቀኖቻችንን የተሻለ ክፍል ከመውሰዱ በፊት እንደነበረው እንደ
መጀመሪያው ቀን ቀኑን ሙሉ ቴሌቪዥን እንኳን ሳንከፍት በፀጥታ ቁጭ
ብለን ኮሪ እንዴት እንደሆነ ለመስማት እየጠበቅን ነው።

ክሪስ በሚወዛወዘው ወንበር ላይ ተቀምጦ እኔና ኬሪ ጭኖቹ ላይ ተቀምጠን
በቀስታ ወደፊት ወደኋላ፣ ወደፊት ወደኋላ እየተወዛወዝን ነው።

ለረጅም ጊዜ ጭኖቹ ላይ ስንቀመጥበት የክሪስ እግሮች ለምን እንደማይደነዝዙ
አላውቅም ምግባችንን ለማሰናዳት ተነሳሁ። ጭራሽ አልነካነውም: የቀኑ
የመጨረሻ ምግብ ሲያበቃና ሳህኖቹ ታጥበው ከተቀመጡ በኋላ እኛም ገላችንን ተጣጥበን ለመተኛት ተዘጋጀን፡ ኮሪ አልጋ አጠገብ በመደዳ ተንበርክከን ፀሎታችንን አቀረብን “እባክህ፣ እባክህ ኮሪ እንዲሻለውና ወደ እኛ እንዲመለስ አድርግ አልን ሌላ ነገር ፀልየንም ከነበረ ምን እንደነበረ አላስታውስም ተኛን ወይም ለመተኛት ሞከርን ኬሪን በእኔና በክሪስ መካከል አድርገን ሶስታችንም አንድ አልጋ ላይ ተኛን በሁለታችን መካከል ድጋሚ ምንም
ነገር አይፈጠርም መቼም... መቼም እንደገና አይፈጠርም እግዚአብሔር
እኔና ክሪስን ለመጉዳት ብለህ ኮሪን አትቅጣው አስቀድመን ተጎድተናል
ልናደርገው ፈልገን አልነበረም ጌታ ሆይ አልነበረም በአጋጣሚ ነው
የሆነው ለዚያውም አንድ ጊዜ ብቻ በዚያ ላይ ምንም ደስታ አልነበረበትም።

እግዚአብሔር ሆይ በእውነት በእውነት ደስታ አልነበረበትም
አዲስ ቀን ነጋ ከመጋረጃዎቹ ጀርባ ውጪ ለሚኖሩት በእኛ ለማይታዩት
ህይወት ተጀመረ። ራሳችንን ዘና ለማድረግ፣ ሰዓታችንን ለመሙላትና ለመብላት ሞከርን ክሪስ እየረዳኝ የፍራሹን ልብስ ቀየርኩ ምክንያቱም በጣም ከባባድ በመሆናቸው ብቻዬን ላገባቸው አልችልም፡ በዚያ ላይ ኮሪ በአብዛኛው ሽንቱን ስለሚሸና በየጊዜው መቀየር ነበረበት፡ ክሪስና እኔ አልጋውን አንጥፈን ክፍሉን አፀዳድተን ጨርሰን ኬሪ የሚወዛወዘው ወንበር
ላይ ብቻዋን ተቀምጣ ባዶ አየር ላይ አፍጥጣለች።

አራት ስዓት ገደማ የምንሰራውን ሁሉ ጨርሰን ወደ አዳራሹ ቀረብ ወደሚለው አልጋ ላይ ተቀምጠን በሩ እጀታ ላይ አይኖቻችንን ተክለን ዜናውን ይዛልን የምትመጣልንን እናታችንን እንዲያስገባ እየጠበቅን ነው።

ጥቂት ቆይቶ እናታችን ከማልቀስ ብዛት አይኖቿ ቀልተው መጣች። ከእሷ
ጋር ባለብረት አይኗ አያታችን ረጅም፣ ድርቅ ያለችና እምባ የሌላት ሆና ተከትላታለች።

እናታችን እግሮቿ መቆም አቅቷቸው ወለሉ ላይ እንዳይጥሏት የፈራች
ይመስል በሩን ተደገፈች እኔና ክሪስ ከተቀመጥንበት ዘለን ተነስተን ቆምን፡
ኬሪ ግን እናታችን ባዶ አይን ላይ እንዳፈጠጠች ነው: “ኮሪን በመኪና ወደ
ሆስፒታል እየወሰድኩት ነበር ቅርብ ወዳለው ሆስፒታል ነበር በእውነት"
አለች እናታችን ውጥረት በተሞላበት ሻካራና አሁንም አሁንም እንቅ እንቅ
በሚል ድምፅ፡ “እና የወንድሜ ልጅ ነው ብዬ በውሸት አስመዘገብኩት"

“ውሸት! እማዬ ሁልጊዜ ውሸት እንዴት ነው?” ትዕግስት ባጣ ሁኔታ ጠየቅኳት። ሰማያዊ አይኖቿ ወደ እኛ ዞሩ፡፡ ባዶ ነገር ላይ ያፈጠጡ፣ የጠፋ፣የሆነ ለዘለአለም የጠፋ ነገር የሚፈልጉ አይኖች ሰብአዊነቷ እየፈለጉ
እንደሆነ ገምቻለሁ። “ኮሪ የያዘው የሳምባ ምች ነበር። ዶክተሮቹ የቻሉትን ሁሉ
አድርገው ነበር . . .ግን በጣም በጣም . . . በጣም ዘግይቶ ነበር”

“የሳምባ ምች ነበር?"

“የሚችሉትን አድርገው ነበር?”

“ዘግይቶ ነበር?”

“ነበር… ነበር!

ኮሪ ሞቷል እንደገና አናየውም!

ዜናው ክሪስን ልክ ወንድነቱ ላይ የተመታ አይነት ስሜት ነበር የፈጠረበት
እንደተረገጠ አይነት፡ ወደ ኋላ ተንጋሎና ፊቱን ለመደበቅ ዞሮ ትከሻዎቹ
እየተርገፈገፉ ሲንሰቀሰቅ አይቼዋለሁ።

በመጀመሪያ አላመንኳትም ነበር። ቆምኩ፣ አፈጠጥኩ፣ ተጠራጠርኩ፣ ፊቷ አሳመነኝ እና ልቤ ውስጥ የሆነ ትልቅና ባዶ ቦታ ሲሰፋ ተሰማኝ። ደንዝዤና
ሽባ ሆኜ አልጋው ላይ ወደቅኩ። ልብሶቼ ረጥበው እስክመለከት ድረስ
እያለቀስኩ እንደነበረ አላወቅኩም ነበር
ቁጭ ብዬ እያለቀስኩ ቢሆንም ኮሪ ከህይወታችን ወጥቶ መሄዱን ማመን
አልፈለግኩም ደግሞ ኬሪ፣ ምስኪን ኬሪ ጭንቅላቷን ቀና አደረገች። ወደ
ኋላ ወረወረችና አፏን ከፍታ እሪ... አለች።

ድምፅዋ ተዘግቶ መጮህ እስከማትችል ድረስ ጮኸች: ኮሪ ጊታሩን
ወደሚያስቀምጥበትና ትንንሽ ያለቁ የቴኒስ ጫማዎቹን ወደደረደረችበት
ጥግ ሄደች። መቀመጥ የፈለገችው እዚያ ከጫማዎቹና ከሙዚቃ መሳሪያው ጋር ነበር እና ከዚያች ቅፅበት ጀምሮ አንዲት ቃል እንኳን ከከንፈሮቿ አልወጣም::

“ወደቀብሩ እንሄዳለን?” ክሪስ ጀርባውን እንዳዞረ ጠየቀ።

“ተቀብሯል” አለች እናታችን፡ “በመቃብሩ ላይ የውሸት ስም አፅፌያለሁ"አለችና ከጥያቄዎቻችንና ከክፍሉ ለማምለጥ በጣም በፍጥነት ወጣች
አያትየውም ተከተለቻት፡

በፈሩት አይኖቻችን ፊት ኬሪ በእያንዳንዱ ቀን የበለጠ እየጠወለገች ነው
እግዚአብሔር ኬሪንም ሊወስዳት እንደሚችል እና ሩቅ ቦታ ባለ የመቃብር
ስፍራ በሀሰት ስም ከኮሪ አጠገብ በቅርብ ርቀት የተቀበረ አባት እንኳን
በሌለበት እንደምትቀበር ተሰማኝ።

ማንኛችንም ብዙ መብላት አልቻልንም:: ፈዛዛና የደከመን ሁልጊዜ የደከመን
ሆነናል፡ ምንም ነገር ፍላጎታችንን አያነሳሳውም: ዕንባ ብቻ። ክሪስና እኔ
ውቅያኖስ የሚሞላ ያህል አለቀስን ወቀሳውን ሁሉ የእኛ አደረግነው: ከብዙ
ጊዜያት በፊት ማምለጥ ይገባን ነበር፡ ያንን የእንጨት ቁልፍ ተጠቅመን
ወጥተን እርዳታ መፈለግ እንችል ነበር። ኮሪ እንዲሞት አድርገናል: የእኛ
ሀላፊነት ነበር! ትንሹ ባለ ብዙ ተሰጥኦውና ፀጥተኛው ውድ ልጃችን እንዲሞት አደረግን አሁን ደግሞ ጥግ ላይ ተኮራምታ የምትቀመጥ በየቀኑ እየደከመች የምትሄድ ታናሽ እህት አለችን፡

ክሪስ ኬሪ እንዳትሰማ
ቀስ ባለ ድምፅ “ማምለጥ አለብን ካቲ! በፍጥነት።
አለዚያ ሁላችንም እንደ ኮሪ እንሞታለን፡ ሁላችንም የሆነ ነገር ሆነናል።ለረጅም ጊዜ ተዘግቶብናል፡ የምንኖረው ትክክለኛ ያልሆነ ህይወት ነው፡ ልክ ጀርሞች በሌሉበት አየር አልባ ቦታ እንደመኖር ነው።
👍46😢63👎1🥰1
“በተለምዶ ልጆች የሚይዛቸው አይነት ኢንፌክሽኖች የሌሉበት ነው
የምንኖረው ስለዚህ እኛ ለኢንፌክሽን ምንም መከላከያ የሌለን ነን፡” አለ፡

“አልገባኝም” አልኩ።

“ማለቴ” አለ አንድ ወንበር ላይ እንደተቀመጥን በሹክሹክታ። “ልክ 'የአለማት ጦርነት' የሚለው መፅሀፍ ውስጥ እንዳሉት ከማርስ የመጡ ፍጡራን በአንድ የብርድ ጀርም ምክንያት ሁላችንም ልንሞት እንችላለን፡”

በፍርሃት እሱ ላይ ማፍጠጥ ብቻ ነው የቻልኩት እኔ ከማውቀው በላይ
ብዙ ነገሮች ያውቃል፡ እይታዬን ጥግ ላይ ወደ ተቀመጠችው ኬሪ መለስኩ።በሚያምር የልጅነት ፊቷ ላይ አይኖቿ ትላልቅ ሆነውና ከስራቸው ጠቁረው ባዶ ነገር ላይ አፍጥጣለች: ኮሪ ያለበት ዘለአለም ላይ ያተኮረ የራሷ እይታ እንዳላት አውቃለሁ ለኮሪ የሰጠሁትን ፍቅር ሁሉ አሁን ኬሪ ውስጥ
አድርጌያለሁ... ለሷ ፈርቼላታለሁ አካሏ ትንሽዬ አጥንት ብቻ ነው አንገቷ
ጭንቅላቷን መሸከም የሚችል አይመስልም የሁላችንም መጨረሻ በዚህ
መንገድ ይሆን?

ክሪስ. የምንሞት ቢሆንም እንኳን በወጥመድ እንደተያዘ አይጥ ሆነን
መሞት የለብንም: ጀርሞች ሊገድሉን ከቻሉ ይግደሉን ስለዚህ ዛሬ ማታ ትሰርቃለህ። ዋጋ ያለውና ልንይዘው የምንችለውን የትኛውንም ነገር ውሰድ!
ይዘን የምንሄደው ምሳ እቋጥራለሁ ከሻንጣው ውስጥ የኮሪን ልብሶች ስናወጣ በቂ ቦታ ይኖረናል ከመንጋቱ በፊት እንሄዳለን፡” አልኩት “አይሆንም!” አለ
በቀስታ: “ገንዘቡን ሁሉ ወስደን መሄድ የምንችለው ጌጣጌጦቹንም የምናገኘው
እናታችንና ባሏ ምሽቱን ከወጡ ብቻ ነው: በጣም የምንፈልጋቸውን ነገሮች
ብቻ ነው የምንወስደው ምንም አይነት አሻንጉሊት፣ መጫወቻ አንይዝም:
ችግሩ ግን ካቲ እናታችን ዛሬ አትወጣም ይሆናል በእርግጠኝነት በሀዘኗ
ወቅት የትኛውም ግብዣ ላይ አትገኝም:"

ባሏን ሁልጊዜ ጭለማ ውስጥ አስቀምጣ እንዴት ልታዝን ትችላለች? ምን
እንደተፈጠረ ለእኛ ለመንገር ከአያትየው በስተቀር ማንም አልመጣም: እኛን ለማነጋገርም ሆነ ለማየት አትፈልግም:: በጭንቅላቴ ውስጥ መንገድ ጀምረናል እና እሷን የማያት የድሮ ህይወታችን አንድ ክፍል እንደነበረች ብቻ አድርጌ ነው: የመለያያ ጊዜያችን በጣም ስለቀረበ ፍርሀት ተሰማኝ::ውጪው በጣም ትልቅ ነው: በራሳችን ነው የምንሆነው… አሁን አለም ስለኛ ምን ያስባል?

በፊት እንደነበርነው ያህል ቆንጆ አይደለንም: ረጅም ወደ ቢጫ የሚወስደው
ቀለም ያለው ፀጉር ያለን የጣራ ስር አይጦች… ውድ ግን በልካችን ያልሆኑ
ልብሶች ለብሰን እግሮቻችን ላይም ስኒከሮች አጥልቀናል።

እኔና ክሪስ ብዙ መፃህፍት በማንበብ ራሳችንን አስተምረናል። ነገር ግን እውነታውን ለመጋፈጥ የሚያስችል ጠቃሚና ተግባራዊ ነገር አልሰጠንም።

መዳን፡፡ ቴሌቭዥን ምንም የማያውቁ ልጆችን የሚያስተምራቸው ይህንን
ነው፡ ስለራሳቸው ብቻ እንጂ ስለማንም ሳይጨነቁ አንዳንዴ ስለራሳቸውም
ሳይጨነቁ አለም ላይ እንዴት እንደሚኖሩ ያስተምራል።

ገንዘብ፡፡ በእስር ዘመናችን የተማርነው አንድ ነገር ቢኖር ገንዘብ መጀመሪያ
ላይ የሚመጣና ሌሎች ነገሮች ሁሉ ከእሱ በኋላ መሆናቸውን ነው᎓ እናታችን
ከብዙ ጊዜያት በፊት ተናግራው ነበር “አለምን የሚያሽከረክራት ገንዘብ እንጅ ፍቅር አይደለም”
የኮሪን ትንንሽ ልብሶች፣ በሁለተኛ ደረጃ የሚወደው ጫማውን፣ሁለት ጥንድ ፒጃማዎችን ከሻንጣው ውስጥ አወጣሁ፡ እናም ሁሉንም ጊዜ
እምባዬ እየረገፈና አፍንጫዬም እየረጠበ ነበር በሻንጣው የጎን ኪስ ውስጥ ያስቀመጠውን ሙዚቃ የተፃፈበት ወረቀት አገኘሁ። ማስመሪያ በመጠቀም ያሰመራቸውን መስመሮች፣ የፃፋቸውን ትናንሽ ጥቋቁር የሙዚቃ ኖቶች,ማየት በጣም ያሳዝናል።

ኮሪን በአእምሮዬ ውስጥ እንደያዝኩ ወደ መኝታ ሄድኩ። እንደ ሁልጊዜው
በጣም ስጨነቅ ህልም አየሁ በዚህ ጊዜ ግን እኔ ብቻ ነበርኩ፡ ራሴን ንፋስ
በበዛበት ዳርና ዳሩ የዱር አበቦች በበቀሉበትና በቀኝ በኩል ደግሞ ቢጫና
ነጭ የፈኩ አበቦች በለስላሳና ሞቃት የፀደይ ንፋስ ሲወዛወዙ ያሉበት ሰፊ
መንገድ ላይ አገኘሁት በእጄ ትንሽ ልጅ ይዣለሁ፡ ኬሪን ለማየት በመጠበቅ
አጎንብሼ ስመለከት ኮሪ ነው።

ሳቂታና ደስተኛ ነበር ከጎኔ ዘለል ዘለል እያለ በትንንሽ እግሮቹ ከእኔ ጋር እኩል ለመራመድ እየሞከረ ነበር፡ በእጁ እቅፍ አበቦች ይዟል ወደ እኔ እያየ ፈገግ አለና ሊናገር ሲል በጣም ብዙ ብሩህ ቀለማት ያላቸው ወፎች ከፊት ባሉ የጥላ ዛፎች ላይ ሆነው ሲንጫጩ ሰማን።

ወርቃማ ፀጉር ያለው፣ ቆዳው በፀሀይ የጠየመ፣ ነጭ የቴኒስ ልብሶች የለበሰ
ረጅም ቀጭን ሰውዬ ብዙ ዛፎች እንዲሁም የተለያዩ ቀለማት ያላቸውን
ፅጌረዳዎች ጨምሮ የሚያማምሩ አበቦች ካሉበት ባለ ግርማ የአትክልት ስፍራ
ወጥቶ በቀጥታ መጣ፡ ከእኛ ራቅ ብሎ ቆመና ለኮሪ ክንዶቹን ዘረጋለት።

ልቤ በህልሜ እንኳን በአድናቆትና በሀሴት ይደልቅ ነበር! አባታችን ነበር! ኮሪ የቀረውን መንገድ ብቻውን እንዳይሄድ አባታችን ሊያገኘው መጣ የኮሪን ትንሽዬ ሞቃት እጅ መልቀቅ እንደሚገባኝ ባውቅም ለዘለአለም ከእኔ ጋር ልይዘው ፈለግኩ።

አባታችን ወደኔ ተመለከተ በሀዘን ወይም በወቀሳ ሳይሆን በኩራትና
በአድናቆት ነበር። ከዚያ የኮሪን እጅ ለቅቄ በደስታ እየቦረቀ ወደ አባታችን
እቅፍ ሲገባ ቆሜ በደስታ ተመለከትኩት በአንድ ወቅት ሲይዙኝ አለም ሁሉ
በጣም ድንቅ እንደሆነ እንዲሰማኝ የሚያደርጉ ወደ ነበሩት ጠንካራ ክንዶች
ገባ፡ እኔም ወደ መንገዱ ገብቼ እነዚያን ክንዶች በድጋሚ አገኘኋቸውና አባቴ
የፈለገበት እንዲወስደኝ ፈቀድኩለት።

“ካቲ፣ ተነሺ!” አለኝ፡ ክሪስ አልጋው ላይ ተቀምጦ እየነቀነቀኝ ነው: “በእንቅልፍ
ልብሽ እያወራሽ ነበር፡ ትስቂያለሽ… ታለቅሺያለሽ ሰላም ትያለሽ ደህና ሁኑ
ትያለሽ ለምንድነው በጣም ህልም የምታይው?" እየፈጠንኩ ስናገር ቃላቶቼ
ተዛቡ ክሪስ ለማዳመጥ እንደነቃችው ኬሪ ተቀምጦ በትኩረት ይመለከተኝ
ነበር አባታችንን ለመጨረሻ ጊዜ ካየሁት ቆይቼ ነበር፡ ፊቱ ከአእምሮዬ
ውስጥ ደብዝዞ ነበር ክሪስን ስመለከተው ግን ግራ ተጋባሁ ወጣት ከመሆኑ
በስተቀር እጅግ በጣም አባታችንን ይመስላል።

ያ ህልም በቀን ብዙ ጊዜ ከሀሳቤ ውስጥ ተመላለሰ ደስ በሚል አይነት። ሰላም
ሰጠኝ፡ ከዚህ በፊት ያልነበረኝን እውቀት ሰጠኝ፡ ሰዎች ለካ አይሞቱም::
የሚወዷቸው ሰዎች መጥተው እስኪያገኟቸው ለጥቂት ጊዜ ሊጠብቁ ወደተሻለ ቦታ ነው የሚሄዱት ከዚያ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጡበት በተመሳሳይ መንገድ እንደገና ተመልሰው ወደ አለም ይመጣሉ፡....

ይቀጥላል
👍29😢215🥰2
የጠንቋዩ ዋሻ
ክፍል 2
❖✿❖✿❖✿❖✿❖✿
☞☞☞
"አባቴ ሆይ መጥቻለው ፡ ባሪያህ ሁሉ ባንተ ፍቃድ "አለ ያልታወቀው ሰው ፡ ከዋሻው ፡ውስጥ ፡ከምትገኘው ፡ እንደቤት ፡ተስተካክላ የተሰራች ፡ አንዲት ክፍል ፡ ጋር ፡ ከወገቡ እንደ ማጎንበስ ፡ብሎ ፡ ከጥቂት ፡ ማጓራት በዋላ ፀጥታ ሰፈነ ፡ ያልታወቀው ፡ሰው ፡ ወደሦስቱ ጎረምሶች ፡በመዞር ፡ማስጠንቀቃያ ሰጣቸው ፡ እዚ ዋሻ ውስጥ ፡ አቢያራ ፡ካልፈቀደ በስተቀር ፡ማንም፡ ድምፅ አያወጣም ፡አለበለዚያ ትቀሰፋላቹ ፡ አላቸው ፡ በሹክሹክታ ፡ ሦስቱም ፡ፍርሃታቸው ፡ጨመረ ፡ ነገርግን ፡ሦስቱም ፡በልባቸው ፡የፈጣሪያቸውን ፡ስም ፡ደጋግመው መጥራታቸውን ፡አልተውም ፡ አይናቸውን ፡እንደታሰሩ በመሆናቸው ፡ አካባቢውን ፡እስካሁን ፡አላዩትም ፡ሲገምቱ ግን ፡አስፈሪ መሆኑን ፡አውቀዋል ፡ ከቆይታ በዋላ ፡ ሲጢጢጢ የሚል ድምፅ ሰሙ ፡ እናም ፡ከውስጥ በኩል ፡የሚያስገመግምና ውፍረቱ ደሚከብድ ፡ድምፅ ፡" ግቡ ግልገሎቼ የጨለማው ፡ጌታ የቀዩ ቤት ፡አይል ፡ በናንተ ዙሪያ ነው "አለ ፡
"አሚን አባቴ ጠባቂዬ "አለ ያልታወቀው ፡ሰው ፡፡ ሦስቱም ፡ ፈጣሪያችን ፡ሆይ ፡ከዚ ጉድ ፡አውጣን ፡ እባክህ ፡ አሉ ፡
" ግለጣቸው ፡አይኖቻቸው ፡ውስጥ ፡ማየት ፡እፈልጋለው ፡ ኤዛ በሰአን ውሃ አፍልተሽ ይዘሽ ፡ነይ "አለ አስፈሪው ፡ድምፅ
"እሺ ጌታዬ "አለቺ አንዲት ሴት ፡ ያልታወቀው ፡ሰው ፡ጠጋብሎ ፡አይኖቻቸውን ፡ያሰረበትን ቀይ፡ጨርቅ ፡ ከሦስቱም ጎረምሶች ላይ ተራ በተራ ፈታ ፡ ጎረምሶቹ በዙሪያቸው ፡ባዩት ፡ነገር ፡ተርበተበቱ ፡ ሳያስቡት ፡በፍርሃት ፡ተጠጋጉ ፡ በመጀመሪያ ፡አይናቸው ፡ያረፈው ፡የፊቱ ገፅታ ሙሉ በሙሉ የማይታይ ፡ አንድ አንድ አስፈሪ ሰው ላይ ፡ነው ፡ እረጅም ፡ሰፊና ዝርክርክ ፡ያለ ጥቁር ፡ቀሚስ ፡ለብሷል ፡ በእጁ ቀይ ፡የተቀባ ፡ከዘራ ይዛል ፡ እረዘም ፡ያለው ፡ፀጉሩ ፡ሙሉ በሙሉ ሸብቷል ፡ የሚያስፈራ ፡ ግርማ ሞገስ ፡ነው ፡ያለው ፡ በክፍሉ ውስጥ ፡ ፀጥታ ቢሰፍንም ፡ ሰዎች ግን ፡ነበሩ ፡ አንዲት ሴት ፡በትልቅ ፡ረኮቦት ፡ብዙ ሲኒዎች ፡ደርድራ ፡ ትልቅ ፡ጀበና ፡ ይዛ ፡ ቡና እየቀዳች ፡ነበር ፡ በጣም ፡ታዳጊ የምትባል አይነት ፡ናት ፡ የለበሰችው ፡ቀይ ፡ቀሚስ ፡ ለእይታ ይከብዳል ፡ ሌሎች ፡ ሁለት ሴቶችም ፡ነበሩ አንድ ፡ጥግ ይዘው ፡ የተቀመጡ ፡ ቆንጆናቸው ፡ ረዘም ፡እረዘ ያሉ መሆናቸው ያስታውቃል ፡ እነሱም ፡ ቀይ የበዛበት ፡ልብስ ፡ለብሰዋል ፡ ዋሻው ፡ደሞ ፡በቀያይ ፡ጨርቅ ፡ዳበደ ነው ፡ አንድ ፡ጥግ ላይ ትልቅ ፡መጋረጃ ይታያል ፡ ቀይ፡ ነው ፡እሱም ፡ ያልታወቀው ፡ሰው ፡ አንድኛውን ጎረምሳ በመግፋት ፡ከጠንቋዩ አቢያራ አጠገብ ፡ አቆመው ፡ ልጁ ተንቀጠቀጠ፡ እዚ በቀይ ፡ጨርቅ ፡ያበደ ዋሻውስጥ ፡ቀይ ደሙ መሬቱን ሲያርሰው ፡ታየው ፡በቃ መስዋት ልንሆን ፡ነው ብሎ ፡አሰበ፡
" እራስህን አስተዋውቅ ፡ በርግጥ ፡ማነትህን ፡ጠንቅቄ አውቀዋለው ፡ ነገርግን ካንተም መስማት እፈልጋለው ፡ አንተ ውርንጭላ ኦሆሆሆይ አቢያራ "ብሎ ጮህ አለ ጠንቋዩ
"መመስፍን መስፍን ደስታ ፡ የእናቴ ስም ስምረት ፡የምኖረው ፡አብነት አዲሳባ ፡ አንዲት ታናሽ ፡እህት ፡አለችኝ ፡ሜሮን ፡ትባላለች ፡ የየ አስረኛ ክፍል ተተማሪ ነኝ ፡ ውጤት ፡ስላልመጣልኝ ፡ሰፈር ፡ነው ፡የምውለው ፡ እናቴ በምትሰጠኝ ፡ገንዘብ ፡አልፎ ፡አልፎ ፡ከገደኞቼ ጋር ፡እየወጣው ፡እዝ ,,,,,,,"
"በቃ ትርኪምርኪ ወሬህን ፡መስማት አልፈልግም ፡ እዛ መደብ ላይ ተቀመጥ ፡"አለ ጠንቋዩ ፡ የተሰላቸ ነው የሚመስለው ፡
"ቀጥል አንተ ቶሎ በል "አለ ያልታወቀው ፡ሰው
"እኔ ዳንኤል አሰፋ እና እእ,,,,,,"ብሎ ሁለተኛው ፡ጎረምሳ ሊቀጥል ሲል፡ እንዲቀመጥ ፡ምልክት ፡ተሰጠው ፡ሄዶ ፡ከጓደኛው ፡መስፍን ፡አጠገብ ፡ጥምልምል ፡ብሎ ፡ተቀመጠ
"አንተ ቶሎ ፡ስምህን ፡ተናገር "አለው ያልታወቀው ሰው
"መሳይ አበራ ፡ከ ,,,,,,,,"
"ቁጭ በል ፡ "ተባለ ፡ ያልታወቀው ፡ሰው ፡ምን ላድርጋቸው ፡በሚል ፡አስተያየት ፡ጠንቋዩን ፡ተመለከተው ፡ ጠንቋዩ ፡ ጸደ ቡናው ፡አየ ፡ የሆነ ነገር እያሰበ ይመስላል ,,,,, ,,


ሙና መሀመድ

ይቀጥላል....


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️
👍36
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...ቀኑ ሰኞ ማታ ነው አየሩ ለሰስ ብሏል " ጨረቃ ፍንትው ብላ ወጥታለች "
እንዳይታይ ሠግቶ አንገቱን ደፍቶ ተገን እየመረጠ በእግሩ ከሚጓዘው ብቸኛ የሩቅ መንገደኛ ላይ የሚያበሩት ከዋክብትም ጥርት ብለው ደምቀዋል " ሰውየው የሥራ ካፖርቱን ለብሶ ሶሉ ምስማር የተጠቀጠቀበት ጫማ አድርጎ የጉልበት ሠራተኛ
ይመስላል " ረጅምና ጥቁር ሪዙ ታችኛውን ፊቱን ሲሸፍነው ክፈፈ ሰፊው ባርኔጣው ደግሞ ግንባሩን ዐልፎ ወርዷል " ወደ ሚስተር ሔር ቤት ተጠግቶ ግራና ቀኙን ደኅና አድርጎ ተመልክቶ በአጥር ተንጠልጥሎ ገብቶ ወደ አትክልቱ ቦታ መጣና ዛፎቹ መኻል ተጠግቶ ቆመ።

ሚስተር ሔር እቤት እንግዶች ካልመጡበት በቀር በዓመት ሁለት ቀን
እንኳን አድርጎት የማያውቅውን የዚያን ቀን ከቤቱ አምሽቷል ባርባራ የወንድሟን መምጣት በጉጉት ስትጠባበቅ ፡ በሌላ በኩል ደግሞ የአባቷ ከቤት ማምሸት በጣም አስጨንቋታል ካሁን አሁን በመጣ እያለች ስትመኝ እሱ ወንበሩን ወደ መስኮቱ አስጠግቶ ረጂም ፒፓውን ካፉ ሰክቶ ሰው ሠራሽ ጸጉሩን ወደ አንድ በኩል
ገደድ አድርጎ በአትክልት ቦታውና በዐፀዱ ሙሉ ትይዩ ተቀምጦ ይመለከታል

“ ዛሬ አትወጣም እንዴ . . . ሪቻርድ '' አለችው ሚስዝ ሔር ፈራ ተባ እያለች

አልወጣም "
“ እማማ . . .የመስኮቱን መከለያዎች ላስዘጋቸው ? አለች ባርባራ "

“ ይዘጉ ?” ብሎ አጉረመረመ " “ ማነው ይህች ጨረቃ እያለች የሚዘጋው የኛ ቆንጆ ብትፈልጊ ፋኖሱ ከዚያ ጥግ አለልሽ ከዚያው ሔዶሽ ተቀመጭ ”

አባትው እንደዚያ በሚመለከትበት ጊዜ ሪቻርድ በድኑንም ይዘልቅና ያየው እንደሆን ብላ በጣም ሠጋች እንደ ፈራችው ምልክቱ መጣ ሲንቀሳቀስ ታያት "ባርባራ ተጨነቀች ነጭ ዐመዷ ቡን አለ » ከንፈሯ ደረቀ ።
አቤት በጣም ምቀኝ ! እኔስ በአትልቱ ቦታ ትንሽ ነፋስ ተቀብዬ ልምጣ መሰለኝ " አለች የመውጫ ምክንያት ፈልጋ "

ጠቆር ባለው የሐር ቀሚሷ ላይ ጠቆር ያለ መደረቢያ ጣል አድርጋ ሹልክ ብላ ወጣችና አባቷ አስተውሎ እንዳይመለከታት እየተጠነቀቀች ሪቻርድን ወዳየችበት ቦታ ሔዳ ተግናኙ ፊቱ ነጥቶ ከስቶ ስታየው በጣም አዘነች " ጸጉሩም እንዳለ
ሸበት መሆኑን ነገራት "

ሪቻርድ አሁን አላነጋግርህም " ዛሬ አባባ ያለ ወትሮው ከቤት አምሽቷል ስለዚሀ ነገ ማታ ተመለስ ”

ለሁለተኛ ምሽት ወደዚህ መምጣት ደስ አይለኝም ... ባርባራ የዚ አካባቢ ምድር በእያንዳንዱ ስንዝር ርቀት አደጋ አለበት

“መቆየትማ አለብህ ...
ሪቻርድ ! ያ ይህን ሁሉ ተንኮል የፈጸመው ቶርን
ዌስት ሊን መጥቷል” እሱ ሆነም አልሆነም ቶርን የሚባል ሰው እዚህ ይገኛል
እኔና ሚስተር ካርላይል
እሱ መሆኑን አምነንበታል
አንተም እንድታየው
እንፈልጋለን እንዴት አይተህ ልታረጋግጥ እንደምትችል ግን ሚስተር ካርላይል
ይነግረናል" ምንም እንኳን ሰውየው አንተ የምትለው ቶርን መሆኑ ስለ ተረጋገጠ
ብቻ አንተን ነፃ ለማድረግ በችኮላ የሚፈጸም ባይሆንም አንድ ትልቅ ነጥብ አጣርቶ መጠበቅም ቀላል ነገር አይደለም ግን አትረሳውም ? እንደምታውቀው እርግጠኛ ነኝ ትጠራጠራለህ?"

“አባቴን አላውቀውማ ! አንቺ አሁን ትጠፊኛለሻ ! አሱንም እንደዚሁ
እይው i ግን እንዴትና መቸ ነው ላየው የምችል ... ባርባራ ?

ሚስተር ካርላይልን እስክጠይቀው ድረስ ልነግርህ አልችልም አንተ ነገ
ማታ በጣም ሳይመሽብሀ እንደ ተመቸህ እዚሀ ድረስ እንድትመጣ " አባባም ከቤት አይኖርም ምናልባት.."

ነጎድጓድ የመሰለው የጀስቲስ ሔር ድምፅ በመስኮቱ አስተጋባ „ “
ባርባራ ብርድ እንዲመታሽ ነው እዚያ የምትንከለከይው አሁን ነይ ግቢ ነው የምልሽ.

“አዝናለሁ ሪቻርድ? . . . ልለይህ ነው” አለችውና በጆሮው “ ነገ ግን
አባባ ከቤት እንደማያመሽ አትጠራጠር ቢሞት አከታትሎ ሁለት ቀን ከቤት
አያመሽም " ደህና እደር ።

አሁን እንግዲህ መጣደፍ አስፈላጊ ሆነባት " የማንንም ሐሜትና ትችት ሳትፈራ ጧት ከሚስተር ካርላይል ቢሮ ደረሰች " እንደዚያ እየተጣደፈች ?ስትደርስ ሚስተር ካርላይል አልገባም ። ጸሐፊዎቹም የሚገባበትን ሰዓት አላወቁም ።

"ሚስተር ዲል” አለች ባርባራ ሰውየው ሰላም ሊላት ወደሷ ሲመጣ“ ሚስተር ካርላይልን ማግኘት አለብኝ " በጣም እፈልገዋለሁ ”

“ ከሰዓት በኋላ ያውም ቆየት ብሎ ነው የሚገባው ከዚያ በፊት አይመጣም "
እኔ ልረዳሽ የምችለው ጉዳይ ነው?”
“ አይደለም ፣ አይደለም " አለችው በረጅሙ ተነፈሰችና

ሁለቱ ቁመው ሲነጋገሩ ሳቤላ ልጅዋን ትንሿ ሳቤላን ይዛ በሠረገላ ስታልፍ አየቻቸውና ለባርባራ ጅንን ብላ በንቀት እጅ ስትነሣት ለሚስተር ዲል ደግሞ ደመቅ ባለ ፈገግታ ሰላም አለችው "

ባርባራ ሚስተር ካርላይልን በዐሥር ሰዓት ላይ አገኘችውና የሪቻርድን መምጣት ነገረችው

ሚስተር ካርላይል ማንኛውንም ማታለልና ማጭበርበር በጣም ይጠላ ነበር አሁን ግን ቶርን በነበረበት ችግር አመካኝቶ ከቢሮው ማስጠራት እሱ ሳያውቅ ሪቻርድ እንዲያየው ማድረግ አማራጭ ያልነበረው ተገቢ ሥራ መሆኑን አመነበት"ስለዚህ ሪቻርድን በቀጠረችው ሰዓት ሲመጣ ወደሱ እንድትልከው ነገራት » እሱም በበኩሉ ጀፈርሰን ቤት የነበረበትን የራት ጥሪ ሰርዞ ካፔቴን ቶርን አማክሮት ስለ ነበረው ጉዳይ ማታ በሁለት ሰዓት ከቢሮው ድረስ እንዲመጣ ላከበት ” እንዳጋጣሚ ሆኖ ደግሞ ቀኑን ከቢሮ ባለመዋሉ አልላከበትም እንጂ ስለሱ ጉዳይ ጧቱን
አግባብ ካላቸው ጋር ተነጋግሮ መፍትሔ አግኝቶለት ነበር።

የሚስተር ካርላይልን አስቸኳይ ውሳኔ የሚጠይብቅ ብዙ ጉዳዮች ከቢሮ ይጠብቁት ነበር። ስለዚህ ወደ ቤቱ ከመሄዱ በፊት አስራ አንድ ሰአት ሆነ ከራት ጥሪው መገኘት አለመቻሉን ገና ለሚስቱ አልነገራትም " ስለዚህ ከቢሮው የነበረውን ውዝፍ ሥራ ሳይጨርስ ወደ ቤቱ መሔድ ግድ ሆነበት "

ሚስተር ካርላይል የግል ደስታውን ለወዳጅነትም ሆነ ለሥራ ለመሠዋት የማያወላውል ሰው ነበር ።

ከሰረገላው ተዘጋጅቶ ከበሩ ቁሞ ሳቤላም ልብሷን ለብሳ ከመልበሻ ክፍሏ ተቀምጣ ስትጠብቀው መጣ “ ጀፈርሰን ቤት ራት የሚጀመረው ባሥራ ሁለት ሰዓት መሆኑን ረሳኸው ? አለችው በሰላምታ ፈንታ

“ አልረሳሁትም. . .ሳቤላ ግን ከዚህ ቀድሜ መድረስ አልቻልኩም " አሁንም ቀደም ብዬ የደረስኩት አብሬሽ ለመሔድ ስለ አልተመቸኝ ሚስዝ ጀፈርሰንን ይቅርታ እንድትጠይቂልኝ ልነግርሽ ነው " ዛሬ ማታ ሌላ ሰው ሊሠራልኝ የማይችል ሥራ ስለ አጋጠመኝ አሁን ራት እንደ በላሁ ተመልሼ ወደ ቢሮ እሔዳለሁ " ሳቤላ
ሲላት ሳቤላ ፊቷ ተለዋወጠ " እሷን ወዝውዞ ሊገድላት የሆነው ልዩ ልዩ ሰበብ እየፈጠረ ጊዜውን ከባርባራ ሔር ጋር ለማሳለፍ ስለሚፈልግ ነው የሚለው እምነቷ ነበር "

“ አትቆጭ . . . ሳቤላ እውነቴን ነው ወድጄ አይደለም ። ለሌላ ቀን የማይተላለፍ ዲልም ሊፈጽመው የማይችል ብርቱ ጉዳይ አጋጥሞኝ ነው በዚህ አጉል ሰዓት እንደዚህ ያለ ነገር በመፈጠሩ በጣም ነው የማዝነው።

"አለ ዛሬ ከመሸ በኋላ ወደ ቢሮ ተመልሰህ ገብተህ አታውቅም ”

“ እውነትሽን ነው " ምክንያቱም ማታ ወደ ቢሮ የሚያስገባ ነገር ቢፈጠርም
ዲል ሊሠራው የሚችል ነበር " የዛሬው ግን እኔ ራሴ መሥራት ያለብኝ ጉዳይ ስለ
ሆነ ነው ' '

ባይሆን ስትሠራ ቆይተህ ስትጨርስ አዛው ድረስ አትመጣም ?

በውነቱ የምደርስ አይመስለኝም ”
👍18👎1
ቀለል ያለ የአንገት ልብሷን ትከሻዋ ላይ ጣል አደረገችና ደረጃዎቹን ስትወርድ
ሚስተር ካርላይል ደግፎ ከሠረገላው ሊያስገባት ተከተላት አስገብቷት ሲያበቃ ደኅና አምሺ ” ሲላት ምንም ሳትመልስለት እንደ ሐውልት ፍዝዝ ብላ ወደ ውጭ ትመለከት ጀመር "

"በስንት ልመለስ እሜቴ ” አለ ሠረገላ ነጂው ሚስዝ ጀፈርሰን ቤት አድርሷት ከሠረገላው እንደ ወረደች

ቀደም ብለህ ና በሦስት ሰዓት ኩል ”

ሪቻርድ ሔር አሳሳች ልብሱን ለብሶ የውሸት ጢሙን አድርጎ ከሁለት ሰዓት
ቀደም ብሎ ከሚስተር ካርላይል ቢሮ ሲደርስ ብቻውን ስለ ነበር ወዲያው ከፈተለትና እጁን ይዞ አስገባው

“ ከመንገድ ላይ ብዙ የምታውቃቸው ሰዎች አገኘህ እንዴ ?

በመንገድ የማገኛቸውን ሰዎች ቀና ብዬ ከተመለከትኳቸው እነሱም አስተውለው ያዩኛል ብዬ ስለ ፈራሁ ፊት ፊቴን ብቻ እያየሁ ነው ቀጥ ብዬ የመጣሁት ቦታው ግን ብዙ ተለዋውጧል " ዱሮ የሽማግሌው የሞርጋን ሱቅ የነበረበት ቦታ አዲስ ሸክላ ቤት ተሠርቶበታል "

“እሱ አዲሱ ፖሊስ ጣቢያ ነው። ዌስትሊን እኮ በታላላቅ ሕንፃዎች ከፍተኛ
ዕድገት እየታየባት ነው ታዲያስ . . . ሪቻርድ ? እንደ ምን ነህ ? ኑሮህ እንደት ነው?

“ የኑሮማ ነገር በበሽታና በችጋር እንገላታለሁ ” አለው ሪቻርድ ሌላ ምን ዕድል አለኝና. . . ሚስተር ካርላይል?በተላከከብኝ የሐሰት ክስ እንደ ባሪያ
እየለፋሁ ኑሮዬን እገፋለሁ"

“ ይህን መልክ አጥፊ ባርኔጣህን አኑረው እዚህ ከሁለታችን በቀር ማንም
የለም" አለው ሚስተር ካርላይል ። ነገሩን በመቀጠል ፡ “ የፊቱ በር ተሰግቷል! ቢሮው አሁን ባዶ ነው ። እንግዲሀ ማንም ሊመጣ አይችልም ። ”

“ እኔ ኮ” አለ ሪቻርድ ባርኔጣውን አንሥቶ እያስቀመጠ "እንደምታውቀው የታየሁ እንደሆነ አሳደው ይዘው ይሰቅሉኛል ብዬ ነው " አሁን እውነት ቶርን እዚህ ድረስ ሊመጣ ነው ? ባርባራ ነገረችኝ …”
“አዎን የሆሊጆን አጥፊ መቶ አለቃ ቶርን ምን እንደሚመስል ከሰጠኸኝ ገለጻ ጋር ስናገናዝበው ' ይህ አሁን ያለው ቶርን እሱ ይሆናል ብለን ገምተናል” አለ ሚስተር ካርላይል “ መልኩ ቁርጥ አንተ እንዳልከው ነው። በተጨማሪም ከጥቂት ዓመት በፊት በስዌንሰን እንደ ነበርና አንድ አምባጓሮ †ፈጥሮበት እንዶ ነበረም አረጋግጫለሁ ። ክፍሉ ከጆ ሔርበት ረጂመንት ስለሆነ አሁን ለዕረፍት የመጣው ከሱ ጋር ነው "

“ ግን እንደዚያ ደፍሮ እዚህ ድረስ ከመጣ በውነቱ ከብት ነው በዚህ ሰፊ ዓለም ለሱ የሚሆን መሸሽጊያ ያጣል ?”

“እሱ ባለመታወቁ ይተማመናል እኔ እንደ ደረስኩበት እሱን በዚህ አካባቢ ካንተና ከእኔ በቀር የሚያውቀው የለም ። እንግዲህ ከሚስተር ዲል ቢሮ ካስገባሁህ በኋላ በትንሿ መስኮት በኩል ወደኔ ታያለህ " እኔ ደግሞ እሱ ገና ከቢሮዬ ሲገባ
ፊት ለፊት እንደምታየው አድርጌ አስቀምጠዋለሁ " አንተ ግን ሰውየውን ካየኸው ብዙ ጊዜ ስለሆነ አሁን ለይተህ ታውቀው ይመስልሃል ? አለው "

“ ከሃምሳ ዓመት በኋላም ቢሆንም አይጠፋኝም " እንደኔ መልኩን ለውጦ
አልባሌ ልብስ ለብሶ ሌላ ለመምሰል ሞክሮ ቢመጣም ለይቸ ዐውቀዋለሁ "

“ አሁን ወደ ዌስት ሊን እንደገና የመጣኸው ለምንድነው? ያጋጠመህ የተለየ ነገር አለ ?”

“ በርግጥ በተለይ ከታመምኩ ወዲህ እናቴና ባርባራ ናፍቀውኛል ነገር
ግን በአእምሮዬ ውስጥ ተንሰራፍቶ አልለቅም ያለኝ አጉል ተስፋ ነው ሒድሒድ
እያለ አላሳርፍ ያለኝ " ስለዚህ ለአንድ ቀን ብቅ ብዬ ለመመለስ ነው የመጣሁት ።

“ እኔ ዶግሞ እንደ በፊቱ ምናልባት የገንዘብ እርዳታ ፈልገህ መስሎኝ ነው"

ብዙ አይደለም እንጂ ገንዘብም እፈልጋለሁ ። በበሽታዬ ምክንያት እዳ
ገብቻለሁ » ስለዚህ እናቴ ትንሽ ገንዘብ ብታገኝልኝ በጣም ደስ ይለኛል ።”

“ ይስጡሃል ዛሬ ማታ ከኔ ትቀበላለህ ግን ምን ሆነህ ኖሯል ?”

መጀመሪያ ፈረስ ረግጦኝ "ስድስት ሳምንት ተኛሁ ። ከዚያ በጎ ሁኘ ሥራ
ስጀምር እንደገና ሰውነቴን አተኮሰኝና ታመምኩ ተመልሼ ሌላ ስድስት ሳምንት ተኛሁ ። ከዚያ ወዲህ ጤንነት አይሰማኝም

“ ታዲያ ምን ሆነህ ነው ያልጻፍክልኝ ወይም አድራሻህን ያልላክልኝ ''

“ ፈራሁ አንተን ሳይሆን ሚስተር ካርላይል ወረቀቱ
ከሌሎች እጅ እንዳይገባና
እንዳይታወቅ ፈራሁ።

ቶርን በቀጠሮው መጥቶ ሲደውል ሪቻርድ ከተነገረው ክፍል ገብቶ ተደበቀ
ሚስተር ካርላይል ቶርንን አስገብቶ ሪቻርድ ተጠግቶ ከተቀመጠበት ትንሽ መስኮት ፊት ለፊት ቁመው ትንሽ ከተነጋገሩ በኋላ አስቀመጠው "

“ ይቅርታ አድርግልኝ .. ሚስተር ካርላይል ከነገርከኝ ሰዓት ሠላሳ ደቂቃ አሳልፌአለሁ ከሔርበርት ቤት ለራት የተጠሩ ሦስት ያህል እንግዶች ስለ ነበሩ
ትቻቸው መነሣት አልቻልኩም " መቸም ዛሬ ማታ ለኔ ብቻ ስትል ከቢሮ እንዳልገባህ ተስፋ አደርጋለሁ ”

“ በሥራ ዋዛ የለም አለው እንደ ቀልድ አድርጎ። “ዛሬ ቀኑን ሙሉ ቢሮ አልገባሁም ነበር። ስለ አንተ ጉዳይ ዛሬ ጧት ከለንደን አንድ መልእክት ደርሶኛል ነገሩ
ደስ አይልም ። ለማቆየት አልፈለኩም ”

“ ግን በፍትህ ከሆነ የሚያስጠይቀኝ አይደለም .. ሚስተር ካርላይል ።

“ የምተነግረኝ እውነት ከሆነ አያስጠይቅህም " ግን አንዳንድ ጊዜ ሕግና
ፍትሕም እርስ በርሳቸው ይቃረናሉ . . . ካፒቴን ቶርን

ግን አሁን የሚይዙኝ ይመስልሃል ?

ያለ ጥርጥር ይይዙህ ነበር። ነገር ግን ማንኛውም የኃይል እርምጃ ከመወሰዱ
በፊት መልስ እንዲላክ የሚል ደብዳቤ ጽፌአለሁ " መልሱ ከነገ ወዲያ ይመጣል ”

“ ታዲያ እኔ አሁን ምን ላድርግ ?”

“ የምትከራከርበት መንገድ እንኳን ሊኖር የሚችል ይመስለኛል ነገር ግን
ከዚህ በፊት የነገርኩህን የምታስታውስ እንደሆነ እኔ ይህን ጉዳይ ለመከታተል የምችል አይመስለኝም”

“ እኔ ደግሞ እምነቴም ተስፋዬም ባንተ ነው ”

እንደ ነገርኩህ ቃል ልገባልህ አልችልም "ለማንኛውም ምናልባት እኔ ባልችል ሌላ እንደኔ አድርጎ ሊረዳህ ወደሚችል እመራህ ይሆናል ፤ነገ እንድትመጣ” ብሎት ተሰነባበቱና እሱ እንደ ወጣ ሪቻርድን ከተዘጋበት ክፍል አስወጣው።

“ ታዲያስ ሪቻርድ . . . እሱ ነው ?”

“ ኧረ በጭራሽ ! በምንም አይመሳሰሉም ። ጥቂት በቁመትና በጸጉር ቀለም
ይቀራረባሉ ። ፊታቸውና አቋማቸው ግን የብርሃንና ጨለማ ያህል ነው ልዩነታቸው " ያኛው መልከ መልካም ሆኖ ሳለ ልዩ የሆነ ገጽታ አለው ”

ሚስተር ካርላይል ስለ ካፒቴን ቶርን ልዩ የሆነ እፎይታ ተሰማው " የስው
የውን ሁኔታ እንደ ገመገመው በነፍስ ግዳይ የሚጠረጠር ዐይነት አልመስል ብሎት ነበር " አሁን እንግዲህ ላለበት የሕግ ጥያቄም ሊከራከርለት ወሰነ "

አየህ ሚስተር ካርላይል. . . ያ ሆሊጆንን የገደለው እዚህ ላይ ልዩ የሆነ አመለካከት አለው።ሪቻርድ ጣቱን ወደፊቱ እያመለከተ "

ከምኑ ላይ ?”

ከምኑ ላይ እንደሆነ እንኳን በትክክል መናገር አልችልም ከቅንድቡ ይሁን ወይም ከዐይኑ ውስጥ ይሁን
ብቻ ከሁለቱ ባንደኛው ላይ ነበር ” እኔ እኮ የቶርን እዚህ መታየት ባርባራ ስትነግረኝ በጣም ገርሞኝ ነበር " ማመን አልቻልኩም ምክንያቱም ካላበዶ በቀር ወደዚህ ብቅ አይልም

በል እንግዲያው አሁን ወደ ዐፀዱ ሒድ » እናትህ ሊያዬህ በጣም ስለጓጉ በመዘግየትህ ይጨነቃሉ
ምን ያህል ገንዘብ ትፈልጋለህ?።

ኻያ አምስትም ፓውንድ ባገኝ ይበቃኛል " በርግጥ ሠላሳ ፓውንድ ባገኝ ችግሬን የበለጠ ያቀልልኛል።

« ደኅና ሠላሳ እሰጥሃለሁ " አሁን ከኔ ጋር ወይስ ብቻህን ብትሔድ ይሻልሃል?
👍14
ሚስተር ካርላይልን በመንገድ ያገኘው ሁሉ ስለሚያነጋግረው ሪቻርድ ፈራና ብቻውን መሔድ መረጠ " ከዚያ ሁለቱም ምንም ነገር ሳይገጥማቸው ከሚስተር ጀስቲስ ሔር ቤት ደረሱ " ያኔ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ዐልፎ ነበር "

በጣም አመሰግናለው ሚስተር ካርላይል " ውለታህን ለመመለስ ያብቃኝ ” አለው ሪቻርድ ከግቢው ደርሰው በእግሩ መንጀድ አብረው እየሔዱ "

“ ምነው ይህን እንቆቅልሽ መፍታት በቻልኩና ከዚህ የበለጠ : በረሁዳሁህ "
ለመሆኑ ባርባራ እየጠበቀች ነው ብለህ ? አዎን ያውና በሩ ቀስ ብሎ እየተከፈተ
ነው ” አለ ሚስተር ካርላይል የራሱን ጥያቄ በመመለስ "

ሪቻርድ ሹልክ ብሎ ወደናቱ ገባ ባርባራ የካፒቴን ቶርንን ውጤት ለማወቅ
ከበረንዳው ቁማ ሚስተር ካርላይልን ትጠብቅ ነበር " መልሱን ለማወቅ
ስለ ነበር ድምጿም ተንቀጠቀጠ ።

“ እንዴት ነው ? ያው እኛ የምንፈልገው ቶርን ነው ? ” አለችው "

“ በሪቻርድ አባባል ምንም አይመሳሰሉም ። እንግዲህ የካፒቴን ቶርን ነገር በዚህ ያበቃል " እኛም ትኩረታችንን ሁሉ በዚህ ሰው ላይ ብቻ ስለ አደረግን ሌላ ፍለጋ አልሞከርንም ።

ሚስተር ካርላይልና ባርባራ ሲገቡ እናትና ልጅ ተጠማጥመው ሲላቀሱ አገኙዋቸው " ሚስዝ ሔር ወዲያው ሪቻርድን ለቀቀችና የካርላይልን እጅ ይዛ “ አንተ
ባትኖር ኖሮ ምን እሆን እንደ ነበር አላውቅም። የዋልክልኝ ውለታ ልክ የለውም "አሁን ደግሞ ደግነትህን በተጨማሪ ልጠቀምበት ፈልጌ ነበር " ነገሩን ባርባራ አንሥታልህ ነበር ?”

“ አሽከሮች እንዳይሰሙ ፈርቸ ከኮሪደሩ ልነግረው አልፈለግሁም ...እማማ”
ሚስተር ሔር ዛሬ ወደ በክስ ሔድ ሲሔድ አሞኛል ሲል ስለ ነበር ምናልባት እንደ ወትሮው እስከ አራት ሰዓት ማምሸት ካቃተው ቀደም ብሎ ይመጣ ይሆናል
ብዬ ፈራሁ " ስለዚህ ከሪቻርድ ጋር ያለሥጋት እንድጫወት ከባርባራ ጋር ሆናችሁ በአትክልቱ ውስጥ አየር እየተቀበላችሁ ጠብቁት " ምናልባት ከአራት ሰዓት በፊት
ከመጣ አንተ ከዚያው ቆም አድርገህ እስክታነጋግረው ድረስ ባርባራ መጥታ ልታስ
ጠነቅቀን ትችላለች " ከዚያ ሪቻርድ ከኮሪደሩ ካለው ቁም ሳጥን ገብቶ ካሳለፈው
በኋላ በደኅና ወጥቶ ሊሔድ ይችላል " ይኸን ለማድረግ ይመችሃል ... አርኪባልድ ? ” አለችው ሚስዝ ሔር

“ ምናለ ግድ የለም ” አለ ሚስተር ካርላይል "

“ አየህ አርኪባልድ” አለችው ሔር እጁን በምስጋና ጫን አድርጋ ይዛ “ ግድ ካልሆነብኝ በቀር ከአራት ሰዓት በፊት ከሱ ጋር ለመለያየት አልፈልግም
ሰባት ዓመት ሙሉ ጠፍቶ የኖረውን ልጅ ለአንድ ሰዓት ማነጋገር ማለት ምን
ማለት እንዶሆነ ላታውቀው ትችላለህ · · · በአራት ሰዓት እንሰነባበታለን “በሚስዝ ሔር ጥያቄ መሠረት ሚስተር ካርላይልና ባርባራ በበሩ አካባቢ ወዲያና ወዲህ እያሉ ይጠባበቁ ጀመር " ሚስተር ካርላይል ለአክብሮት ሲል ክንዱን
ሰጣት እሷም ተቀብላ ተያያዙና መጠበቅ ቀጠሉ » ጀስቲስ ሔር ግን ብቅ አላለም "

ልክ በሦስት ሰዓት ተኩል የወይዘሮ ሳቤላ ካርላይል ሠረግላ ሚስዝ ጀፈርስን
ቤት ሲደርስ ራስ ምታት አመካኝታ ወዲያውኑ ወጣች » ኢስትሊን በአቋራጭ መንገድ ሁለት ማይል ያህል ብቻ ይርቅ ስለነበር ለመድረስ ብዙ አያቆይም ሠረገላው
በጉዞ ላይ እንዳለ አንድ ሰው ለነጅው እጁን ሲያወዛውዝለት ቆመ " ሌላ ሰው ያስመሰለው ቆብ ደፍቶ ስለነበር ምንም እንኳን ደማቅ ጨረቃ ብትኖርም በደንብ እስኪጠጋ ድረስ ሳቤላ ሌቪሰን መሆኑን አላወቀችም ነበር " እሱ መሆኑን ስታውቅ መስ
ኮቱን ከፈተችለት "

“ ያንቺ ሠረገላ ይሆናል ብዬ አሰብኩ ምነው ቶሎ ተመለስሽ ? ሰለቸሽ?”

“ እመቤቴ በስንት ሰዓት እንደሚመለሱ ጠይቆኝ ዐውቆት ነበር አለ ሠረገላ ነጅው ለራሱ '' እኔስ ይኸ ሰው አታላይ መሰለኝ "

“ ነፋስ ልቀበል ብዬ ወጣሁና አሁን ድክም አለኝ ” አለና ነገሩን በመቀጠል
“አብሬሽ ልመጣ መቀመጫ ትፈቅጅልኛለሽ ?

ፈቀደችለትና ፍራንሲዝ ሌቪስን ከወይዘሮ ሳቤላ ጐን ተቀመጠ “ዋናውን
መንገድ ይዘህ ሒድ” አለ አንገቱን ወደ ነጂው አውጥቶ " ነጂውም በእሽታ ባርኔጣውን ነካ አደረገ " ዋናው መንገድ የሚወስደው በጀስቲስ ሔር በኩል ነበር "

“አላወቅሁህም ነበር እኮ” አለችው ራሷን መግዛትና ሐሳቧን መሰብሰብ ስትችል "የምን አሳሳች አስቀያሚ ቆብ ነው የደፋኸው ? ላለመታወቅ የፈለግህ ትመስላለህ ?”

ኧረ የለም : ለምን ብዬ ? በዚህ አካባቢ ባለ ዕዳዎች የሉኝም

“ ሚስተር ካርላይል ከቤት አለ ?

“ የለም”ብሎ ጥቂት ዝም ብሎ ቆየና ' “ እሱ ደኅና ደስ በሚል ሥራ የተያዛ መሰለኝ

በምን ሥራ ነው የተያዘው ?”

“ አሁን በጀስቲስ ሔር ደጅ ሳልፍ አንድ ጎበዝና አንዲት ቆንጆ በፍቅር ተጠማጥመው አፍ ላፍ ገጥመው ሲያወሩ በጨረቃው ብርሃን አየኋቸው እነሱም
ያንቺ ባልና ሚስ ሔር ነበሩ
ሳቤላ ጥርሶቿን ልታፋጭ ምንም አልቀራትም ማምሻውን ሁሉ ሆድ ሆዷን ሲያቃጥሏት ያመሹ የቅናት ጥርጣሬዎች ተረጋገጡ " ያ እንዲህ ያናደዳትና የጠላችው ሰውዬ አብሯት ወደ ተጠሩበት ግብዣ እንዳይሔድ አሳፋሪ ውሸት ደርድሮላት የቀረው!ጊዜውን ባርባራ ሔር ጋር ለማሳለፍ እንደነበር ተረዳች ከሠረገላው ውስጥ
ብቻዋን ብትሆን ኖሮ የብሶቷን ያህል ትጮኸ ነበር "

ከጀስቲስ ሔር ቤት ፊት ለፊት ሲደርሱ ሥራዬ ብላ ወደ ውስጥ ስትመለከት
በጠራው ጨረቃ ክንድ ለክንድ ተያይዘው ቀስ እያሉ ሲንጓራደዱ አየቻቸው
ልትቈጣጠረው ልትደብቀው ባልቻለችው የታፈነ እንቅስቃሴ እመቤት ሳቤላ
የኋሊት መቀመዋ መደገፊያ ላይ ተላትማ ቁጭ አለች "

ባለቤቷ ፍቅሩን ሲነፍጋት ደፋሩና ክፉሙ ሰው የሱ ፍቅር ያለላት መሆኑን
እያንሾካሾከ በክንዱ እቅፍ አድርጎ ወደሱ ጠጋ አደረጋት

የቀናች ሴት ዕብድ ናት የተናደደች ደግሞ እጥፍ ዕብድ ናትና ሳቤላም በባልና ሚስት መካከል ሊኖር በሚገባው ክቡር ስሜት ላይ ሚስተር ካርላይል
ክህደት የፈጸመ መሰላት

“ይህን እምነተ ቢስ ተበቀው ወትሮም አቻሽ አልነበረም !አሁንም የመከራ ኑሮሽን ትተሽ ወደ ደስታ ነይ ” እያለ ፍራንሲዝ ሊቪሰን ጣፋጭና አደገኛ በሆኑ ቃላት ያባብላት ጀመር.....

💫ይቀጥላል💫
👍171