አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አለ በቀዝቃዛና ጎርናና ድምፅ፡ “ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ነገር አትናገሪ
ወይም ስለ ሞት አታስቢ!” እርግጥ ነው በውስጤ የተደበቀ ጥርጣሬ አለ ግን
እስቃለሁ፤ ፈገግ እላለሁ፤ እና ራሴን እንደምንም አፅናናለሁ ምክንያቱም
በህይወት መቆየት እፈልጋለሁ፡ “በራስሽ እጅ ብትሞቺ እኔንም ይዘሽኝ ነው የምትሄጂው እና ወዲያው ደግሞ መንትዮቹም ይከተላሉ ምክንያቱም የዚያን
ጊዜ ማን እናት ይሆናቸዋል?”

አሳቀኝ ምሬት ሲሰማት የምትስቀውን የእናቴን አሳሳቅ ግልባጭ የሆነ
መራራና አስቀያሚ ሳቅ ሳቅኩ። “ለምን፣ ለምን ክሪስቶፈር? ውድ ጣፋጭና
አፍቃሪ፣ ሁልጊዜ የእኛን ፍላጎት የምታስቀድም እናት አለችን አይደል እንዴ?
እሷ መንትዮቹን ትንከባከባለች "

ክሪስ ወደ እኔ ዞረና ትከሻዬን ያዝ አደረገ: “አንዳንዴ ልክ እሷ በምትናገረው
በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ስትናገሪ ያስጠላኛል: ለኬሪና ለኮሪ ከእሷ የበለጠ
አንቺ እናታቸው እንደሆንሽ የማላውቅ ይመስልሻል? መንትዮቹ እናታቸውን
ልክ እንደ እንግዳ አፍጥጠው እንደሚያዩዋት የማላስተውል ይመስልሻል?
ካቲ እኔ እኮ እውርም ደደብም አይደለሁም: እናታችን በመጀመሪያ
የምትንከባከበው ራሷን
ቀጥሎ ግን እኛን እንደሆነ አውቃለሁ።” ጨረቃ
ወጥቶ አይኖቹ ላይ የረጋውን እምባ አሳየኝ፡ ጆሮዬ ውስጥ የገባው ድምፁ አደጋ መጋፈጥ የሚችል፣ የሚያባብልና ጥልቅ ነበር፡

ይህንን ሁሉ ሲናገር ድምፁ ውስጥ ምሬት አልነበረም ፀፀት ብቻ ነበር። ልክ
ዶክተር በሽተኛውን የመጨረሻ ደረጃ የደረሰ ህመም እንዳለበት እንደሚነግርበት አይነት ስሜት አልባ መንገድ ነበር
የዚያን ጊዜ ነበር ፀፀት እንደ መቅሰፍት ጎርፍ የመጣብኝ፡ ክሪስን እወደዋለሁ፣
ወንድሜ ነው። ሙሉ ያደርገኛል፤ ያጣሁትን ሰጥቶኛል፤ አውሬና ተናዳጅ
ስሆን መረጋጋት ሰጥቶኛል። መረጋጋት እናታችንና አያቶቻችንን መልሶ
ለማጥቃት እንዴት ያለ ጥሩ መንገድ ነው! እግዚአብሔር አያይም: ኢየሱስ መስቀል ላይ የሞተ ቀን ለሁሉም ነገሮች አይኑን ጨፍኗል። አባታችን ግን እዚያ ነው ወደ ታች እየተመለከተ… እና በእፍረት ተሸማቀቅኩ።

“ተመልከቺኝ ካቲ፣ እባክሽ ተመልከቺኝ"

“አንዱም ነገር ከልቤ አልነበረም፤ ክሪስ እውነቴን ነው ሌሎች እንደሚኖሩት
መኖር እፈልጋለሁ፤ ግን የሆነ መጥፎ ነገር የሚሆንብን ሁልጊዜ የሚዘጋብን ስለሚመስለኝ እፈራለሁ። መጥፎ ነገር የተናገርኩት ልቀሰቅሳችሁ እንድታዩ ላደርጋችሁ ፈልጌ ነው ክሪስ… ከብዙ ሰዎች ጋር መሆን፣ አዳዲስ ፊቶችና አዳዲስ ክፍሎች ማየት እጅግ ፈልጌያለሁ። ለመንትዮቹ እስከሞት ድረስ
ፈርቻለሁ፡ ሱቅ መሄድ፣ ፈረስ መጋለብና እዚህ ልናደርጋቸው የማንችላቸው
ነገሮች ሁሉ ማድረግ እፈልጋለሁ።

በጨለማ ጣሪያው ላይ በብርድ እርስ በርሳችን በስሜት ተቃቀፍን፡ እንደ
አንድ ሆነን ልቦቻችን እርስ በርሳቸው በሀይል ይደልቁ ነበር። ልቅሶም የለ ሳቅም የለ፤ ከዚህ በፊት ውቅያኖስ የሚሞላ ያህል እምባ አላፈሰስንም? መዳን አልጠበቅንም? እምባ ካልረዳና ፀሎት ካልተሰማ ታዲያ እንዴት ግን ምንም አልረዳንም በሚሊየን የሚቆጠሩ ፀሎቶችን ፀልየን የማይመጣ እግዚአብሔርን አግኝተን የሆነ ነገር እንዲያደርግልን ማድረግ እንችላለን?”

ክሪስ፣ ከዚህ በፊት ብየዋለሁ አሁንም በድጋሚ እለዋለሁ። ጅማሬውን
እኛ ማድረግ አለብን
አባታችን ሁልጊዜ የሚለው እግዚአብሔር የሚረዳው
ራሳቸውን የሚረዱትን ነው፣ አይደል?”

ጉንጩን ከጉንጬ ጋር አጣብቆ ለረጅም ጊዜ ሲመሰጥ ቆየ፡ ከዚያ
“አስብበታለሁ። ሆኖም እናታችን እንዳለችው ወደዚያ ሀብት በማናቸውም
ጊዜ ልንመጣ እችላለን።”...

ይቀጥላል
👍3215🥰5
#ሀገሬ

የድልሽ ውብ ምስል
ሰንደቅሽ ላይ ሲሳል
በልጆችሽ ገድል
የጎጥ ካብ ይፈርሳል።

🔘ኢዛና መስፍን🔘
👏228👍8
በህይወት መንገድ ላይ…
ተጋቾቹ
ምዕራፍ-8
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
///
ከህይወት መከራ ቀጥታ የሚገኝ ልምድ ከማንበብም ሆነ ከትምህርት ብሎም በፊልም ከማየት የሚገኝ አይደለም...አሁን ይታያችሁ ከመሬት በታች ተቀብራችሁ በየትኛው ደቂቃ መሬቱን ተደርምሶ እንደሚያበቃላችሁ ወይም በጥልቁ ከርሰምድር ኑዋሪ የሆነ አውሬ አንገታችሁን ፈጥርቆ በማነቅ ይዋጣችሁ .ወይንም አስፈሪ መንፈስ ድንገትአዛው አጠናግሮ ያስቀራችሁ በማታውቁበት ሁኔታ ከእነዚህ ሁሉ ስሜቶች ጋር እያታገላችሁ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ከምትወዱትና ከምታከብርቱ ጓደኛችሁ እሬሳ ጎን ለሳዕታት ቁጭ ብላችሁ…ደግሞ አንደኛዋ ጓደኛችሁ የት እንደገባች ሳታውቁ ብን ብላ ጠፍታባችሁ የሚሰማችሁን ስሜት በምን አይነት ቃላት ለሌላ ሰው ማስረዳት ትችላላችሁ…?ሰሚውስ በምን አይነት ተአምራዊ አቅሙ ሙሉ ስሜታችሁን ሳይሸራርፍ ሊረዳችሁ ይችላል?
‹‹ሰዎች ደነዘዝን እኮ…በቃ እዚሁ አብረነው ከሬሳው ጋር እሬሳ ሆነን ለመቅረት ወስነን ተስፋ ቆርጠናል ማለት ነው?››አይዳ ነች ከወትሮው በጣም ቀሰስተኛና እንክትክት ባለ ድምፅ ሀሳቧን ያቀረበችው፡፡
‹‹ምን እናድርግ ታዲያ..?ሰላምስ እሺ በራሷ ጊዜ ተሰውራ ይሁን አልያም ጠባቂ መላአኬ የምትለው በክንፉ አንጠልጥሎ ይዛት አርጎ አናውቅም ስራችን የለችም...አጠገባችን የተኛውን ጋሼ አህመድን እንዴት አደርገነው ወደ ፊት እንንቀሳቀሳለን?››
‹‹አዎ እናንተ ሁለታችሁ ሂዱ.. እኔ እዚህ ከእሱ ጋር እሆናለው››አለ በሪሁን ፡፡
‹አይ …ገና ይሳካልን አይሳካልን ለማናውቀው ነገር ተጣጥለን አንሄድም.. .እዚሁ የሚሆነውን እንጠብቃለን›አልኩ በቁርጠኝነት፡፡
‹‹አይ .አንተ አይዳን ይዘሀት ሂድ….›>በሪሁን አምርሮ ተቃወመ፡፡
‹‹ሰዎች ምን እያወራችሁ ነው ….?በአየር እጥረትና በመከራ መደራረብ የማሰብ አቅማችን እየተዳከመ ይመስለኛል…እውነታውን አምነን ተቀብለን ቢያንስ እስከቻልነው ድረስ ወደፊት መቀጠል አለብን…ሰላምም በመጨረሻ ንግግሯ ልትመክረን የሞከረችን ይሄንኑ መሰለኝ...ጋሼ አህመድ አንዴ ሞቷል…. በቃ ምንም ብናደርግ ነፍሱን መመለስ አንችልም…ግን ደግሞ ቤተሰቦች እንዳሉት አትርሱ… ቢያንስ ከመካከላችን አንዳችን እንኳን ተሳክቶልን ተርፈን ለባለቤቱና ለልጆቹ አባታቸው ወደእነሱ በህይወት ለመመለስ ምን ያህል ሲጥር እንደነበር አስረድተናቸው ልናፅናናቸው ከቻልን ቀላል ነገር አይደለም፡፡
‹‹አዎ እውነትሽን ነው…ከዚህ እንደምንም በህይወት ወጥቼ ልጆቹን መርዳት አለብኝ…አዎ እነሱን ማሳደግ ኃላፊነቱ የእኔ ነው፡፡እንደውም ሁላችንም አንዴ እጃችንም ጓደኛችን በድን ላይ እንድናኖር እፈልጋለው››
‹‹ም አልክ በሪሁን?››ገራ በመጋባትና በፍራቻ ጠየቅኩት፡፡
‹‹እጃችሁን አምጡ…››.የሶሰታችንንም እጅ በጋሽ አህመድ እሬሳ ልብ አካበባቢ አንድ ለይ አደራርበን ጫን
‹አሁን ጥለነው ከመሄዳችን በፊት ቃል ኪዳን እንገባለታለን..የምለውን ደግማችሁ ትላላችሁ.››
‹እኛ ጓደኞችህ›
‹‹እኛ ጓደኞችህ››ያለውን ደገምነው…የታደለ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሰልጣን ተሰጥቶት በተወካዬች ምርክር ቤት ፊት ቀርቦ በጠቅላይ አቃቢ ህጎ አማካይነት ቃል ይገበል እኛ እዚህ የጓደኛችንን ሬሳ አጋድመን በጨለማ ውሰጥ ሁለት ፐርሰንት በህይወት የመትረፍ እድል ይዘን ቃል እንገባለን፡፡
‹‹ከመካከላችን አንዳችን እንኳን በህይወት ከተረፍንና ወደ ኑሮችን ከተመለስን….››
‹‹በተቻለን አቅም ልጆችህን ልናስተምርና ልንረዳ ቃል እንገባለን››
‹‹ቃል አንገባለን››
የቃል ኪዳኑን ስነ-ስርዓት ካጠናቀቅን ቡኃላ እጃችንን ለቀቀና ከተቀመጠበት ተነሳ…‹‹ሞባይልህ ባትሪ አለህ አይደል አብራልኝ›አለኝ
አበራውለትና የሚያደርገውን ማየት ጀመርኩ …ሬሳውን አስተካክሎ መገነዝ ጀመረ ..ፊቱን በጨርቅ ሸፈነው…ከዛ በአቅራቢያችን የተቆለውን አፈር እየዛቀ ማልበስ ጀመረ……
ብቻ አስፈሪ የሆነና እና የተለየውን የቀብር ስነ-ስርአት በ10 ደቂቃ ውስጥ አጠናቀን ጉዞችንን ለመቀጠል ዝግጁ ሆንን…የቀረችንን ተወሰነች ሬሽንና አራት የሀይላድ ውሀ ያዝን ….በሪሁን አንድ ብስኩትና አንድ ውሀ አነሳና አፈር የተጫነበት እሬሳ ላይ አስቀመጠና ‹‹በሉ እንሂዴ.›› አለና ቀድሞና ከፊት ለፊታችን መራመድ ጀመረ
አሁን በጣም ውድ የሆነ ውሀና ምግብ ለሬሳ መስጠት ምን የሚሉት የስነልቦና ጫወታ ነው?›› ስል አሰብኩ…የጥንት ፈርኦኖች ለቀብራቸው ባሰሩት ፕሪሚዳቸው ውስጥ ሞተው ሲቀበሩ ወርቅና እንቁዋቻቸው ብቻ ሳይሆን ሚስቶቻቸውንም ጭምር አብረዋቸው ይቀበሩ እንደነበር ታሪክ ይነግረናል … .እና ያቺ የሰው ልጅ ስነ-ልቦና ከልጅ ለጅ በዲ.ኤን.ኤ እየተላለፈች መጥታ ዛሬም ይሄው እኛ ፈፀምናት…
.በሪሁን ባደረገው ነገር የተከራከረው ሰው የለም የቀረውን እቃችንን ተከፋፍለን ይዘን ጉዞ ጀመርን ..ዋሻው አንዴ ተንርቦርቅቆ ይሰፋል ..አንዴ ደግሞ ለማለፍም እስኪያስቸግር ድረስ ይጠባል..ከ45 ደቂቃ ጉዞ ቡኃላ ይመስለኛል ወደተታች አንሸራቶ የሚያስወርድ ገደል ያለበት ቦታ ገጠመን …
‹‹እንዴት ነው የምናደርገው.?››ግራ ገብቶኝ ጠየቅኩ
ሁላችንም በየራሳችን መፍትሄ ለማመንጨት ትካዜ ውስጥ ገባን …መፍትሄ ለማምጣቱ እንደተለመደው በሪሁን ቀደመን…ድንገት የሚቆፈር ነገር ካጋጠመን ብለን ከያዝነው ሁለት ብረቶች መካከል አንዱን ወደመሬት አስተካከለና በአንደኛው እየቀጠቀጠ ወደ መሬት ውስጥ መቅበር ጀመረ…
‹‹ምን እየደረክ ነው?››አይዳ ጠየቀችው
‹‹ላሳያችሁ አይደል…?›› ብሎ የለበሰውን የጅንስ ጃኬት አወለቀና በወፍራሙ በቢላዋ መተልተል ጀመረ..ከዛ እርስ በርስ ቋጠራቸውና መሬት ውስጥ ከቀበረው ብረት ላይ አጥብቆ አሰረው..
አሁን እኔን በደንብ እዩና እኔ እንደማደርገው አድርጋችሁ ትወርዳላችሁ …››አለና በጨርቁ ላይ እየተንጠለጠለ በቀላሉ ወረደ፡፡
‹‹.... አትፍሩ ..ብዙም አያስቸግር.መጀመሪያ ግን ዕቃውን በጫፍ ላይ አስራችሁ ቀስ ብችሁ ልቀቁት ›የሚል ትዕዛዝ ሰጠን…. እንዳለን አደረግን፡፡
‹ትወርዳለህ ልቅደምህ.?››አለችኝ
‹‹አይ ቅደሚ አይዞሽ.ቀስ ብለሽ.ደግሞ ጨርቁን በደንብ አጥብቀሽ ያዢው›
‹አትጨነቅ እይዘዋለው ››አለችና..ጨርቁን ይዛ እየተንሸራተተች መውረድ ጀመረች…በጣም ነበር የሰጋውት …እግዜር ይመስገን በሰላም በሪሁን ካለበት ደረሰች. . አቅፎ ተቀበላትና መሬት አሳረፋት
…ቀጥሎ የእኔ ተራ ነው …ጨርቁን በእጆቼ ሁለት ዙር ጠቅልዬ ያዝኩና በእግሬ ለመቆንጠጥ እየመከርኩ መውረድ ጀመርኩ፤.ያስፋራል.፤ወደታች ሳይ ገና ምኑን አልያዝኩትም‹‹..በርታ .በርታ › የሚለው የአይዳ ጥኡም ድምፅ ይሰማኛል..አዎ እየበረታው ነው፡፡ ግማሽ አካባቢ ደረስኩ…ከዚህ ቡኃላ ብዙም አይከብደኝም ብዬ አስቤ እንኳን ሳልጨርስ ጨርቁ መሀከል ላይ ጣ.ጣ.ጣ ብሎ ተበጠሰ ፡፡ ዥው ብዬ ወደታች ….ብዥዥ አለብኝ…ዋሻው ከስር ወደላይ እየተገለባበጠ ያለ ይመስለኛል..
‹‹እሱም እንዳይሞት ..እሱም እንዳይሞት…››የሚለው የአይዳ ጩኸት እየተሰማኝ ጭልጥ ብዬ በዛው ጠፋው..ከምን ያህል ደቂቃዎች ቡኃላ እንደሆነ አላውቅም ስነቃ አይዳ ጭን ላይ ተኝቼያለው፡፡
👍24😁42
‹‹…ምንድነው የሆንኩት..?አልሞትኩም አይደል?.››ግራ በመጋባት ዙሪያ ገባዬን በማየት ጠየቅኩ
‹‹ደህና ነህ ...›አይዳ ነች
‹‹ምን ሆኜ ነው ጭንቅላቴ ነው የተጎዳው?›
‹‹አይ ጭንቅላትህ ደህና ነው..››
‹‹እና ተርፌያለሁ ማለት ነው….ለምን እራሴን ሳትኩ ታዲያ?››
‹‹ማለቴ››ልንገረው ወይስ ይቅርብኝ እያለች ከራሷ ጋር ሙግት እንደገጠመች ገባኝ…እና ደነገጥኩ፡፡
‹‹ንገሪኝ ምንድነው የተፈጠረው?››
‹‹እግርህ..››
‹‹እግሬ ምን ሆነ…?››ብዬ ከጭኗ ላይ ተነስቼ ስመለከት በጨርቅ ተጠቅልሏል
‹‹..ወለምታ ነው.?.››ብዬ ላየው ስል ሙሉ በሙሉ እንኳን መነሳት አልቻልኩም
‹‹ተረጋጋ አጥንትህ ስለተሰበረ..መንቀሳቀስ አትችልም››በሪሁን ቁርጤን ነገረኝ፡
‹‹አጥንትህ››
‹‹አዎ ከቁርጭምጭሚትህ ከፍ ብሎ አጥንትህ ተሰብሯል››
በዚህን ጊዜ ጥዝጣዜው ጭንቅላቴን መታኝ…ለካ እስከአሁን ደንዝዤ ስለነበር ነው….ወይኔ በቃ ብሞት ይሻላል…አዎ እውነቴን ነው እንደጋሼ አህመድ ሞቼ ተገላግዬ ቢሆን ትንሽ አዝነው ጥቂት አልቅሰው ያው እንደለመዱት አፈር አለብሰውብኝ .መንገዳቸውን በመቀጠል እድላቸውን ይሞክሩ ነበር….አሁንስ ?.አሁንማ በጣም መራር የሆነ ፈታኝ ምርጫ እንዲመርጡ ተገደዋል፡፡.ተሸክመውኝ አስር ሜትርም መሄድ አይችሉም..ስለዚህ ጥሩ ሰዎች ከሆኑ ገድለውኝ ይሄዳሉ ጨካኞች ከሆኑ ደግሞ እንደሆነ ይሁን ብለው ለስቃይና ለጣረሞት ባለውበት ትተውኝ መሄድ ብቻ ነው ያላቸው ምርጫ.፡፡
.እንዲህ አይነት መከራ ውስጥ ሆኜ ከወራት በፊት መስጦኝ ያየውትን Vikings …የሚል እርዕስ ያለው . ተከታታይ ፊልምን ትዝ አለኝ፡፡
በጦርነት፤ በሽሽትነና እንዲህ እኛ እንደገጠመን አይነት መከራ ጊዜ አካል ጉዳተኝነት እንዴት እንደሚስተናገድ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡
እዚህ ፊልም ላይ ዋና ገፀ ባህሪ ራግነር መጀመሪያ ጀግና ብቻ የሆነ ደፋርና ብልህ ፤ ከዛም ቡኃም የጀግንነቱ ዝና ወደ ንግስና የወሰደው ሰው ነው፡፡እና ይሄ ንጉስ አራተኛ ልጁን ከመውለዱ በፊት በአማልዕክቱ ካህን በኩል ትንቢት ተነገረው..አሁን የምትወልደው ልጅ መራመድ አይችልም ተብሎ፡፡ኃያላን የእንግሊዝ ግዛቶችን ሲገጥም ቅንጣት ፍራቻ የማይታይበት ታላቁ ንጉስ በዚህ ዜና ሲሸማቀቅ ስንመለከተው እግር አልባ መሆን ችግሩ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ እንረዳለን፡፡
ያው ትንቢቱን 80 ፐርሰንት አምኖ ሀያ ፐርሰንት ደግሞ እየተጠራጠረ ከወይዘሮ ሚስት ጋር እንሆ በረከት አለ…ልጅ ተወለደ፡፡እንደተባለውም እግሮቹ ቆመው ለመሄድ ተስፋ አልነበራቸውም….
እናትና አባት በሀዘን ውስጣቸው ደምቶ ልጁን በተመለከተ ሲጨቃጨቁ ከሚያሳው ዲያሎግ ጥቂቱ
ዋና ገፀ ባህሪው-He will die anyway.. What is the point of pretending?ብሎ ይጠይቃል ሞት የሚጠብቀውን ጨቅላ ልጆን ታቅፋ የተቀመጠችውን እናት
-
-
‹‹It is natural.. we let such baby dye for own good …. What kind of life could he live?.
››ይላታል ለእናት እሱ ራሱ ውስጡን ማሳመን ሳይችል፡፡
I know …but I don’t care. ትላለች እናት ወደውስጧ ልጆን ጨምቃ እያቀፈች፡፡(እሱስ ታድሏል በወቅቱ እናቱ ከጎኑ ነበረች.. እኔ ግን ያው ከዚህ ጉድለቴ ሊያተርፈኝ እንዲታገል የሚያስችል ፍቅር ያለው ሰው ማንም የለም፡ይታያችሁ በዚህ አራት ቀን ያለውን አትዩ እዚህ መከራ ውስጥ ከመግባታችን በፊት በአንደኛና በሁለተኛ ደረጃ የምጠላቸው ሰዎች ናቸው አብረውኝ ያሉት)ለማኛውም ወደታሪኩ ልመለስ፡፡
በማግስቱ እናት ሳታይ ልጁን ለመግደል ወደ ጫካ ይዞ ይሄዳል ወንዝ ዳር ህፃኑን ያስቀምጣል የስንቱን ጀግና ጠንካራ አንገት በአንድ ምት አሸክርክሮ የሚቀነጥስ መጥረቢያው የገዛ ልጁ አንገት ላይ ያስቀምጣል ፡፡ሊገድለው ..ግን ማድረግ አልቻለም፡፡የሆንከውን ሁን ብሎ ልጁን እዛው ጥሎ ሳይገድለው ይሄዳል… ከኃላ ተደብቃ ስትከታተል የነበረቸው እናት ወዲያው ደርሳ በእንባ እየታጠበች ልጇን ከተጣለበት አንስታ ወደቤት ትመልሰዋለች፡፡
ያልጅ አድጎ ግን አድጎ ከሁሉም ጤነኛ ወንድሞቹ የበለጠ ብልህ ከሁሉም የበለጠ ኃይለኛ ተዋጊ፤ከሁሉም የበለጠ ታሪክ የማይረሳው ከአባቱ የበለጠ ስመ-ገናና ጀግና ለመሆን ይበቃል ‹‹ አይቨ ቦንለስ ››……አጥንት አልባው አይባ
. በእነሱ እምነት አንድ አካለ ጎዶሎ ሆኖ የተወለደሰው እንዲኖር ሊፈቀድለት አይገባም፡፡ እንደዛ አይነት ህፃን እንደተወለደ ከእናታቸው ጉያ ይነጠቅና ከመንደር ወጣ አድርገው ይገድሉታል፡፡ያንን ግዴታን መወጣት ከጉድለት ጋር የተወለደውንም ልጅ በመኖር ከሚያጋጥመው ስቃይ መገላገል እንዲሁም በአማልዕክቱ ቁጣ ያረፈበትን ህፃን በማሳደግ በማህበረሰቡ ላይ የሚመጣውን ተጨማሪ ቁጣ ለመከላከል አስፈለጊ እርምጃ አድረገው ስለሚቆጥሩት እንዲሁም በጣርነት እና ስደት ጊዜ ለማህበረሰብ ሸክም ይሆናል ብለው ሰለሚያምኑ በድርጊታቸው ቅሬታ የላቸውም፡፡እንዲህ አይነት ልማድ በግሪክ እስፓርታ ፤በአውስትራሊያ እና በእስኪሞ ይገኛል፡፡
ያ ማለት አሁንም ከቅርም አያቶቻችን አስተሳሰብ ብዙም ፈቀቅ አላልንም ማለት ነው፡፡እርግጥ አካል ጉዳተኛ የሆኑትን ህፃናት ገና እንደተወለዱ አንገታቸውን አንቀን አንገላቸውም ይሆናል፡፡ግን በሂደት ለእነሱ ምቹ ያልሆነ የማህበራዊ የኑሮ መዋቅር በመገንባት እየተንገዋለሉ በመገለልና በኑሮ ፈተናዎች በመሸነፍ ከደረጃው በታች ኖረው ከደረጃ በታች እንዲሞቱ እያደረግን ነው፡፡
አዛውንቶችንም አይ አርጅታችሆልና መኖር ይብቃችሁ ብለን ከፈረስ ጭራ ጋር አስረን ተጎትተው እንዲሞቱ አናደርግም …በዚህ ግን ከአያቶቻችን የተሻልን ነን ብለን ልንኮራ አንችልም ፡፡ምክንያም የችግር ጭራ ላይ አስረናቸው በየጎዳናው በረሀብ በእርዛት እየተጎተቱ እንዲሞቱ እያደረግን ነውና፡፡ከደሙ ንፅህ ነን ማለት አንችልም፡፡

አሁን እኔ እንኳን በዚህ አጣብቂኝ ወቅት እንዲህ አይነት አደጋ ባያጋጥመኝ ስለአካል ጉዳተኝነት እንዲህ አምርሬ ላስብ አልችልም ነበር
‹‹በቃ እንግዲያው…እናንተ ጉዞችሁን ቀጥሉ››የደረሱኩበትን የመጨረሻ ውሳኔ ነገርኳችው፡፡
‹‹ምን..?በፍፅም በህይወት እያለህ ጥለንህ አንሄድም››አይዳ ነች፡፡
‹አይ እናንተንማ እንዲህ አይነት ፈተና ውስጥ አልከታችሁም….እሱን እኔ ራሴ አደርገዋለው..እናንተ ሂዱ››
‹‹ምኑ ነው የምትፈፅመው?››
‹‹መቼስ እንዲህ እየተሰቃየው አራት አምስት ቀን እግዜር ነፍሴን እስኪወስደው አልጠብቅም ››
‹‹እና..?››
‹‹ለማንኛውም ቢላዎ ሰጥታችሁኝ ሂዱ …››
ተንደርድራ መጣችና ከንፈሬ ላይ ተጣበቀችብኝ…እኔ ብቻ ሳልሆን በሪሁንም በጣም እንደደነገጠ ታወቆኛል፡፡ሲበቀትና ስትለቀኝ አንደምንም ትንፋሼን ሰብስቤ‹‹ምን ማለት ነው?››ጠየቅኳት…ጥያቄዬ ከግራ መጋቴ የመነጨ ነው፡፡ይህቺ ልጅ ለምድነው የሳመቺኝ…አፈቅርሀለው ለማለት ፈልጋ ይሆን?…እንዴት አንዲህ ይሆናል? እጮኛዬን እኮ በደንብ ነው የምታውቃት….እንደውም አብረን ተምረናል ሲሉ ሰምቼያለው….ግን በእውነት በህይወት ተርፌ ከዚህ ብወጣ ያቺን አለብላቢት እጮኛዬን አገባታለው….አዎ ፀባዬ ባይመቸኝም አፈቅራታለኁ…ስለዚህ እግዚያብሄር ከዚህ በተአምሩ ካወጣኝ እሷን ማጋባቴ የማይቀር ነው፡፡ግን የዚህቺኘዋ ከንፈር ልዩ ነው …ሙቀቱ የኤሌክትሪክ አይነት ንዝረት አለው…ቲ..ሽሽሽ አድርጎ የሚያቀልጥ አይነት …ስሜቱ ልቤን ምንጭቅ አድርጎ ነው ከቦታዋ ያነቃነቃት፡፡
👍22🥰5😁32
‹‹በህይወት እያለህ ጥዬህ አልሄድም…እራስህን እንዳታጠፋ አልፈቅድልህም..ከቻልን ይዘንህ እንጓዛለን ..ካልሆነም እስክታገግም አብረንህ እንጠብቅሀለን…አይደል በሪሁን?›
‹‹ትክክል ነሽ …የሆነ ነገር እንፈጥራለን...ማለቴ አብረን፤አንድ ላይ››ብሎ አብሮነቱን አረጋገጠ፡፡


ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️❤️❤️
👍174
በህይወት መንገድ ላይ……
( ታጋቾቹ)
ምዕራፍ-9
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
////

አምስት ቀን ሆነን..አምስት ቀን ሆነን ስላችሁ ጠቅላላ እዚህ መከራ ውስጥ ከገባን ማለቴ አይደለም፡፡እግሬ ከተሰበረ ቡኃላ ያለውን ቀን ቆጥሬ ነው፡፡አሁን ሁላችንም በህይወትና በሞት መካከል ተወጥራ ባለች ቀጭን ክር ላይ እንደቆምን ቁጠሩት…ክሯ መሀከል ላይ ልትበጠስ እየተከረከረች እና እየሳሳች ነው፡፡በማንኛውም ሰአት ጧ ብትል እና ቢያበቃልን ከመሀከላችን የሚገረም ሰው የለም፡፡እናንተም የምትገረሙ አይመስለኝም፡፡ካለንበት አሁናዊ ሁኔታ አንፃር መጪው ነገር ሙሉ በሙሉ ተገማች ስለሆነ ብዬ ነው፡፡
አሁን እጄ ላይ ካለው ላይተር በስተቀር ምንም አይነት ብርሀን የሚሰጥ ነገር በዙሪያችን ላይ አይገኝም…ባትሪችን፤ ሞባይላችን ጠቅላላ ቻርጅ ጨርሶ በድኗል…ምግብን በተመለከተ ሶስት ነጠላ ፍሬ ያላት አንድ ብስኩት እና ግማሽ ሊትር ውሀ ቀርቶናል፡፡ይሄንን ብስኩቱ ለአመል ያህል ቆረስ እያደረጉ በውሀ ራሰ በማድረግ በስድስት ሰዓት ልዩነት ለእኔ ያቀምሱኛል፡፡አንሱ ምንም ነገር ወደአፋቸው ካስገቡ ዛሬ ሶስተኛ ቀናቸው ነው፡፡
ሰው ግን ከህይወት ምን የሚያስፈነጥዝ ነገር ቢያገኝ ነው ነፍሱን ለማቆየት ሲል ይሄን ሁሉ መስዋዕትነት የሚከፍለው?እውነት ከኑሮችን የምንሸምተው ደስታና ፈንጠዝያ ያን ያህል አርኪ ሆኖ ይሄ ሁሉ መስዋዕትነት ይገባዋል?በውስጤ እየተመላለሰ ያስቸገረኝ ወሰኝ ጥያቄ ነው፡፡ግን ጥያቄውን ያው አዕምሮዬ እየሰራ ስለሆነ ጠየቅኩ እንጂ አይ ለህይወትማ ይሄን ያህል መስዋዕትነት መክፈል ሞኝነት ነው ብዬ ባምንና እራሴን ለማጥፋት ብወስን እራሱ ነገሮች እንዲያበቁ የሚያስችል እንጥፍጣፊ ጉልበት በውስጤ የለም…..በቃ የተሰበረ እግሬ ቆሽሾ በክቷል….በዛው ላይ ተልቶ ነፍሳቶቹ ከላዩ ላይ ሲንጠባጠብ ይታወቀኛል፡፡ከተጎዳውበት ቀን አንስቶ ለሁለት ቀናት እዛው ባለውበት የተቻላቸውን ያህል እንክብካቤና እርዳታ ሊያደርጉልኝ ሞክረው ነበር፡፡ግን ህመሜና ስቃዬ ከመባስ ውጭ ምንም ለውጥ ስላልታየብኝ እና ቀለባችን ተሞጦ በማለቁ ምክንያት በተቻለ መንገድ ወደፊት መጓዝ ወሳኝ ሆነ…እናም ልክ የኤሊን በመሰለ እርምጃ አንዳንዴ እጃቸውን አጣማረው በጋራ እየተሸከሙኝ አንዳንዴ ደግሞ በሪሁን ለብቻው እያዘለኝ ይሄው አሁን እስካንበት የመጨረሻ እስትንፋሳችን ድረስ ወደ ፊት ለመጎዝ መክረናል፡፡አሁን ግን እንኳን እኔን ሊሸከሙ እራሳቸውን መቆጣጠር አቅቶቸው ይኄው በግራና ቀኜ ተዘርረው ያንገላጅጃሉ…ብቻ ከእኔ ቀድመው አምልጠው እዳይገርመኝ፡፡
አይዳ ያቺ ዘናጯ እና ስትራመድ በአየር ላይ የምትበር የምትመስለው አይዳ….ያቺ ሳቋ ከጭፈራ ቤት ሙዚቃ በላይ ደምቆ ጆሮ ይይዝ የነበረው….ያቺ ተረቧና ቀልዷ ማብቂያ ያልነበረው አይዳ..አሁን ብታዮት ..ጸጉሯ ከመጨቅያቱም በላይ አንድ ላይ ተቋጥሮ የገሪባዎችን ጉድሮ መስሏል፤ከዚህ በፊት የጡቷን መጋለጥ እንድትሸፍንበት አልብሼት የነበረውን ጃኬት መልሳ እኔን ስላለበሰቺኝ እላዬ ላይ ያለው የተቀዳደደ ቲሸር እርባነ ቢስ ሆኗል….ለምን አውልቃ እዳልጣለቸው እርሱ ይገርመኛል…ምን አልባት ልብሱን አውልቆ ለመጣል የሚያስችል ጉልበት በውስጧ ስለሌለ ይሆናል…ቀሚሷ ሁለት ቦታ እስከላይ ከመተርተሩም በላይ ብዙ ቦታ ተቦተራርፎ አገልግሎቱን ጨርሶል….በቃ በፓንት ብቻ ነው ያለችው ማለት ይቀላል፡፡እናም ደግሞ ማንስትሬሽኗ መጥቶ እግሯ ሁሉ በደም መርጠብ ከጀመረ ሁለት ቀን ሆኗታል፡፡
የበሪሁንን ጠቅላላ ሁኔታ ብዙም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡
እንዚህ ሰዎች ልክ እንደተሰበርኩ እኔን እዛው ጥለውኝ ጉዞቸውን ቢቀጥሉ ኖሮ ዛሬ እርግጠኛ ነኝ ወይ ነፃ ይወጣሉ ካለበለዚያ ከዚህ የተሸለ ሁኔታ ላይ ይገኙ ነበር፡፡እነዛ እጠላቸውና በየሰባ አስባቡ እገፋቸው የነበረ ሁለት ሰዎች ለእኔ ህይወት የሚያስከፍል መስዋዕትነት ሲውሉልኝ…ፀፀቱ እየለበለበኝነው፡፡
እዚህ ጉዳይ ላይ ከመውደቃችን ከ15 ቀን በፊት አይዳን ከስራ አባርሬት ነበር ብያችሆለው አይደል፡፡አሁን እንዴት እንዳባርኳት ላጫውታችሁ ፡፡
ሳይት ውስጥ በምሳ ሰዓት ተሰብስበው ሲያወሩ በመሀከል የብሄር ጉዳይ ይነሳና ጭቅጭቅ ውስጥ ይገባሉ…..አንዱ ተነስቶ ሌለኛውን ‹‹የሆንክ አሸባሪ ቄሮ ነገር ነህ››ይለዋል
‹‹ነፍጠኛ ፎጤ…እቃህን ጠቅልለህ ወደሀገርህ እንድትገበ ነው የማደርግህ .አርፈህ ተቀመጥ›› ይለዋል ›..በዚህ የተነሳ ሳይት ላይ አደገኛ ግርግር ይነሳል
በዚህ በመሀከል አይዳ በተጣሉት መካከል ትገባና‹‹‹‹ …እናንተ ምንድነው ከድንጋይ መሸከም ሳትወጡ ድንጋይ በሚያክል የፖለቲካ ጥይት የምትፈነካከቱት..መጀመሪያ እስከኪ ከርሳችሁን በቅጡ ሙሉ..›እያለች በመቆጣትም በማገላገልም ነገሩ እንዲዲዘቅዝ ታደርጋለች፡፡
ሁለም ተሰብስበው እኔጋ ክስ ይመጣሉ….ሁኔታውን ሰማውና ነገ ጥዋት ውሳኔ ይሰጣችሆል አሁን ተበተኑ አልኩና ሸኘዋቸው፡፡ከዛ ቡኃላ ቀሺም ስራ ሰራው፡፡ ሁለቱን ዋና ተጣይዎች ለየብቻ አናገርኮቸውና ከስራ መባረር ካልፈለጋችሁ እኛ እርስ በርስ ስንቀላለድ በመሀከል መጥታ ‹‹ከድንጋይ ማትሻሉ ናቸሁ›› ብላ ሰደበችን …ብሄራችንንም አንቆሸሸችብን ብለው እንዲመሰክሩባት አሳመንኮቸው፡፡
በቀጠሯችን መሰረት ጥዋት የሰራተኛ አስተዳደሩን ይዤ ሶስቱን አስጠራዋቸው፡፡ እንዳኩት መሰከሩባት…ይህቺ ልጅ ፖላቲከኛ ስለሆነች አንድ ቀን ልታስጨርሰን ስልምትችል ትባረር አልኩ …ሰውዬውም ፈሪ ነገር ስለሆነ አልተቃወመኝም …ተባረሻል አልኳትና በማገስቱ ጥፋቷን ጠቅሼ እጆ ላይ ያላውን የድርጅን ንብረት አስረክቦ ስራ ለመልቀቅ ሰላሳ ቀን ብቻ እንዳላት የሚገልፅ ደብዳቤ ፅፌ ሰጠዋት …ብዙም አልተከራከረቺኝም፡፡
እና እዚህ ዋሻ ውስጥ ከገባን ቡሃላ ስለጉዳዩ እንስጬባት ነበር
‹‹ያዛን ቀን ከስራ ተባረሻል ስልሽ በጣም የምትቀውጪው መስሎኝ ነበር ….ጥፋትሽን አምነሽ ነበር ማለት ነው;?››
‹‹ምንም እንዳላጠፋውማ አንተም ታውቀወለህ››
‹‹እና ታዲያ አቤቱታ ለባለቤቷ ጭምር ማቅረብ ትቺይ ነበር››
‹‹አውቃለው….ግን ላንተ አስቤ ነው፡፡››
‹‹እንዴት ለአንተ አስቤ…?ከስራ ለሚያባርርሽ ሰው በምን ስሌት ነው የምታስቢለት?››
‹‹እኔ እንዴት አድርገህ እንድባረር እንዳቀናበርክ..ከልጆቹ ጋ የዶለትከውን ጭምር አውቃለው…..እናም ወደተቃውሞ ገብቼ አቤቱታ ባቀርብ እንዚህ ሁሉ ጉዳዬች በግልፅ ይወጡና በተቃራኒው አንተ ስራህን ታጣለህ፡፡››
እንደዛ ስትለኝ አፈርኩ..አንድን ሰው ሸውጄዋለው ብላችሁ ለረጂም ጊዜ በውስጣችሁ ስትጎርሩ ቆይችሁ በስተመጨረሻ ድንግት አንድ ቀን ከመጀመሪያው ጀምሮ ሰውዬው ሁኔታውን አውቆ ግን ደግሞ ከእናንተ በላይ በሳል ሆኖ ችላ ብሎ እንዳለፈው ስትሰሙ ብሽቀት..እፍረት…ውርድት ብዙ ብዙ ስሜት ነው የሚሰማችሁ፡፡
‹‹ታዲያ ብባረር ለአንቺ አሪፍ አይደል…?.››
‹‹አይ በፍፅም አይደለም….እኔ ስራውን ልምድ ለማግኘት ብቻ ነው የምሰራው…አንተ ደግሞ ዘላቂህ ሞያህ ነው..በምትከበርበት ቦታ ላይ አንድ ጥቂት ስህተት ሰራህ ብዬ ልፋትህን ጭላሼት ልቀው አልሞክርም››
👍222🔥1
‹‹እኔ እንደዛ እየጠላውሽ አንቺ ግን….››
‹‹እየጠላውሽ…እርግጠኛ ነህ?››አለቺኝ
‹‹እንዴ ምን ለምለት ነው?›
‹‹አይ እኔ እንደዛ አይደለም የምረዳህ…››
ተገርሜ‹‹እንዴት ነበር?››
‹‹ከእኔ የምትወዳቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ ብትቀርበኝ ወይንም ረጅም ጊዜ ዙሪያህ ብኖር ምን አልባት ፍቅር ሊይዝህ እንደሚችል ስለገመትክ …..እንደዛ ከሆነ ደግሞ እራስህን አጣብቂኝ ውስጥ እንዳታስገባ ፈርተህ ነው፡ …ለፍቅረኛህ የገባህላትን ቃል ኪዳን ለማፍረስ የሚያስገድድ ፈተና ውስጥ እገባለው ብለህ በመፍራትህ እራሱህን ይመጣብኛል ብለህ ከገመትከው ችግረር ቀድመ ጥንቃቄ የማድረጊያ መንገድህ ነው….››
‹‹እንዳዛ እንድታስቢ ያደረገሽ ምኑ ነው?፡፡››
‹‹እያዳንዱ ድርጊትህ…..እየጮክ ስትቆጣኝ እንኳን አይኖችህ በፍቅር ያባብሉኝ ነበር….ከወንዶች ጋር አፍ ለአፍ ገጥሜ ስታዬኝ እኔን ሳይሆን ወንድዬውን በግልምጫ አፍርጠህ ስትጥለው ይሉኝታ እንኳን የለህም…ምክንያት እየፈጠርክ ቢሮህ ትጠራኛለህ ..ስመጣ ደግሞ በንጭንጭና በብስጭት ትመልሰኛለህ…ስለምረዳህ ግን አንድም ቀን ተከፍቼ አላውቅም፡፡››
በፈጣሪ አሁን ወንድና ሴቶች አንድ አይነት ጭንቅላት ነው ያላቸው…?ከሴቶች ጋ ስንወዳደር እኛ ወንዶች እኮ ሰማይ ሰማዩን እያየን የምንጎዝ ግልቦች አይደለን እንዴ….?እዬት ይህቺን ሴት እያንዳንዷን በእኔና በእሷ መካከል የነበር ግንኙነት ቃላቶቻንን፤ስሜቶቻችንን በአስተውሎት መርምራ ..የሆነ ትንታኔ ሰርታ .የመጨረሻ ሳቢያና ውጤታቸውን ሁሉ ደምድማ ተቀምጣለች፡፡
‹‹ትገርeሚያለሽ..ቆይ ግን አንቺ ውሳኔውን ብትቃወሚና እኔ የሰራውብሽ ፊክ ክስ ቢጋለጥ ከስራ የምባረር ይመስልሻል?››እኔ እኮ ወሳኝ ሰው ነኝ የሚል መታበይ ያለበት ጥያቄ ጠየቅኳት
‹‹110 ፐርሰንት እርግጠኛ ነኝ..››
ሰቅኩ….ከግንዛቤ እጥረት የሰጠችው አስተያየት እንደሆነ ገምቼ ነበር መሳቄ
‹‹ምነው ሰቅክ?››
‹‹አይ ለፕሮጀክቱ ምን ያህል አስፈላጊ ሰው እንደሆንኩ በደንብ የገባሽ ስላመሰለኝ ነው፡፡››
‹‹ገብቶኛል…ለፕሮጀክቱ በጣም ወሳኙና የመጨረሻው ውሳኔ ሰጪና አስፈፃሚ እንደሆንክ አውቃለው..ባይሆን አንተ ነህ እኔ ለሪዞልቱ ባለቤት ምን ያህል ወሳኝ ሰው እንደሆንኩ ምንም ግንዛቤ የሌለህ››
‹‹አልገባኝም››
‹‹ሴትዬዋ አክስቴ ነች…አክስት ከመሆኗም በላይ በጣም ነው የምትወደኝ..ልጇ በለኝ፡፡እና እንዲህ እንዳላገጥክብኝ ብትሰማ ጥንቅር ያለው ነገር ጥንቅር ይላል እንጂ እመነኘ ታባርርሀለች….ስራ መልቀቄን ለማስረዳት ራሱ እራሱ ስንት ቀን ፈጅቶብኝ ነበር መሰለህ…ሰልችቶኝ ነው….እረፍት ፈልጌ ነው..ምናምን ብዬ አሳምኜት ነው የተረጋጋችው…እና አንደውም ይሄ መከራ ባይገጥመን በዚህ ጊዜ ከእሷ ጋር ድባይ ፈልሰስ አንድንል ፕሮግራ ይዘን ነበር፡፡
‹‹እየቀለድሽ ነው አይደል፡፡››
‹‹በፍፅም ..ምን አስቀለደኝ››
‹‹ታዲያ እንዴት እኔ እስከዛሬ ሳላውቅ….?ሌላስ ሰው ሳይነግረኝ.?››
‹‹ከበሪሁን በስተቀር ሌላ ማን አያውቅም…እንዳይታወቅ የፈለኩት እኔ ነኝ..ያው እንደምታስበኝ ጉረኛ አለመሆኔን ይህ መረጋገጫ ይሁንህ ››ብላ ፈገግ አለች
በዚህ አይነት ሁኔታ ነበር ይቅርታ የጠየቅኳት….
ዛሬ ከሁለት ቀን ቡኃላ እንዲህ ዝርር ብላ ሳያት ልቤ ፍርስርስ አለላት ..ይህቺኝ ሴት የእውነት እሷ እንዳለችው በድብቁ ስሜቴ ሳፈቅራት ነበር የኖሩኩት ብዬ እራሴን እንድጠራጠር እስገደቺኝ ፡፡
/
በሪሁን እንደምንም ከተጋደመበት ተነሳና እየተንገዳገደ በሁለት እግሮቹ ቆመ…‹‹እስቲ ወደፊት ራመድ ብዬ ሁኔታውን ልይ.. የሚበላ ቅጠላ ቅጠን ወይም ጥላትል ነገር ካገኘው ልመክር አለ ..››ቅንድቤን ከፍ ዝቅ በማድረግ ያሰበውን እንዲያደርግ መስማማቴን አሳወቅኩት.ግን ደግሞ ትላትል ሲል ከእግሬ የሚረግፉትን ትላትል አሳታወሰኝና ዝግንን አለኝ..

ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️❤️❤️
👍232
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የእናታችን ድንገተኛ ዜና

እናታችን እንደገና ልታየን ከመምጣቷ በፊት ባለፉት በእያንዳንዱ አስር ቀናት
ውስጥ፣ እኔና ክሪስ ለምን አውሮፓ ሄዳ እንደቆየችና ከሁሉም በላይ ደግሞ
ልትነግረን የነበረው ትልቅ ዜና ምን እንደሆነ ለመገመት ለሰአታት እናወራ
ነበር።

አስሩን ቀናት እንደ ሌላ ቅጣት አሰብነው ቅጣትም ነበረ: እዚህ አንድ ቤት
ውስጥ ሆነን ልክ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ያለን አይጦች እንደሆንን ሁሉ
ችላ ልትለንና ልትዘጋን ችላለች:

ስለዚህ ያን ያህል ቆይታ ስትመጣ እኔና ክሪስ በደንብ ስለተቀጣን የጥላቻ
ወይም የመውጣት ጥያቄያችንን ከደገምን ተመልሳ ላትመጣ ትችላለች ብለን በጣም በመፍራት ፀጥ ብለን እጣ ፈንታችንን ተቀበልን፡ ተመልሳ ካልመጣች ምን እናደርጋለን? መንትዮቹ ገና ጣሪያው ላይ ሲደርሱ ብርክ ከያዛቸው ከተተለተለ አንሶላ በሰራነው መሰላል ተጠቅመን ማምለጥ የማይታሰብ ነው።

ስለዚህ ለእናታችን ፈገግ አልንላት አንድም የማማረር ቃል አላሰማንም
ለወራት ጠፍታ ስለምታውቅ አስር ቀናት በመቆየት ለምን እንደቀጣችን
አልጠየቅናትም፡ ልትሰጠን የፈቀደችውን ተቀበልን፡ ከአባቷ ጋር ለመሆን
እንደተማረችው አይነት ታዛዥ የማይቃወሙ ቅን ልጆች ሆንን የሚገርመው እንዲህ መሆናችንን መውደዷ ነው: እንደገና የሷ ጣፋጭ አፍቃሪና ሚስጥራዊ “ውዶች” ሆንን።

አሁን በጣም ጥሩ፣ አስደሳች፣ ለእሷ አድናቆት ያለን፣ አክባሪና በእሷ
የምንተማመን መሆኑን ስታውቅ ጊዜውን ቦምቧን ለመጣል መረጠችው።
“ውዶቼ፣ ለእኔ ደስ ይበላችሁ! በጣም ደስ ብሎኛል!” እየሳቀች እጆቿን ደረቷ ላይ አድርጋ በክብ ተሽከረከረች: “ምን እንደተከሰተ ገምቱ ቀጥሉ… ገምቱ!” አለችን።

እኔና ክሪስ ተያየን “አያታችን ሞተ!” አለ። ልቤ ደስ የሚለውን ዜና ስትነግረን
ለመዝለልና ለመቦረቅ በመዘጋጀት በጣም እየደለቀ ነው።

“አይደለም!” አለች በድንገት ደስታዋ በጥቂቱ የደበዘዘ ይመስላል።

“ወደ ሆስፒታል ተወሰደ?” ብዬ ሁለተኛውን ምርጥ ግምት አቀረብኩ።
“አይደለም: አሁን አልጠላውም፧ ስለዚህ እናንተ ጋ መጥቼ በሞቱ መደሰቴን ልነግራችሁ አልችልም:”

“ታዲያ ለምን መልካም ዜናውን ራስሽ አትነግሪንም? ስለ ህይወትሽ ብዙም
ስለማናውቅም መገመት አልቻልንም” አልኳት።

ማለት የፈለግኩትን ችላ ብላ ቀጠለች፤ “ለረጅም ጊዜ የጠፋሁበትን ለመግለፅ አስቸጋሪ ሆኖብኝ የነበረው ምክንያት ባርት ዊንስሎ የተባለ ሰው ማግባቴ ነው። ጠበቃና በጣም ጥሩ ሰው ነው። ትወዱታላችሁ። እሱም ሁላችሁንም ይወዳችኋል። ጥቁር ፀጉር ያለው፣ በጣም መልከመልካም፣ ረጅምና የሚያምር ሰውነት ያለው ነው። ክሪስቶፈር፣ ልክ እንዳንተ የበረዶ ሸርታቴ ይወዳል፧ ቴኒስ ይጫወታል፤ ልክ እንዳንተ ጎበዝ ነው” ይህንን ስትናገር ወደ ክሪስ
እየተመለከተች ነበር።

በጣም ደስ የሚል ሰው ነው ሁሉም ይወዱታል። አባቴም ሳይቀር ይወደዋል
ወደ አውሮፓ የሄድኩት ለጫጉላ ሽርሽር ነበር። ያመጣሁላችሁ ስጦታዎች
ከእንግሊዝ፣ ከፈረንሳይ፣ ከስፔንና ከጣልያን የተገዙ ናቸው:” እኔና ክሪስ
በፀጥታ ተቀምጠን፡ ስለ አዲሱ ባሏ የምታወራውን እየሰማን ነበር።

እኔና ክሪስ ከገና በአል ግብዣ ምሽት ጀምሮ ብዙ ጊዜ ጥርጣሬዎቻችንን
አውርተናል: ልጆች ብንሆንም፣ እንደ እናታችን ያለች ወንዶች የምትፈልግ
ቆንጆ ወጣት ሴት ለረጅም ጊዜ ካለ ባል እንደማትቆይ እናውቅ ነበር። ሰርግ
ሳይደረግ ሁለት አመት ሲያልፍ ግን ያ ትልቅ ፂም ያለው መልከመልካም
ባለ ጥቁር ፀጉር ሰው ለእናታችን ብዙም አስፈላጊ ነው ብለን አላሰብንም
ነበር። በየዋሁ ልባችን እናታችን ለሞተው አባታችን አሁንም ታማኝ እንደሆነች ራሳችንን አሳምነን ነበር። ባለወርቃማ ፀጉር፣ ሰማያዊ አይኖች ያሉት አማልክትን የመሰለ የቅርብ ዝምድና እያላቸው እንኳን እሱን ለማግባት ከምክንያት ባሻገር ላፈቀረችው አባታችን ታማኝ ናት ብለን እናስብ ነበር::

የአባታችንን ቦታ ስለሚወስድ ሌላ ሰው ስትነግረን በጥላቻ የተሞላ ድምፅዋን ላለመስማት በመሞhር አይኖቼን ጨፍኜ ነበር: አሁን የሌላ ሰው ሚስት ናት ሙሉ በሙሉ የተለየ ሰው ሚስት ሆናለች: አሁን አልጋዋ ውስጥ
ይገባል፣ ከእሷ ጋር ይተኛል: እንግዲህ ከዚህ በኋላ ከምናገኛት ያነሰ ጊዜ
ነው የምትመጣው ማለት ነው: አምላኬ፣ እዚህ የምንቆየው ለምን ያህል ጊዜ ይሆን? ለምን ያህል?

ዜናዋና ድምፅዋ በደረቴ አጥንቶች ውስጥ የተያዘችና ልውጣ ልውጣ የምትል ትንሽ የፍርሀት ወፍ ፈጠረ።

“እባካችሁ…” ለመነችን፡ ፈገግታዋና ሳቋ ሀሴትና ደስታዋ እኛ ዜናውን
ባስተናገድንበት ቀፋፊና የተበላሽ አየር ላይ ለመቆየት እየታገሉ ነው::
“ለመረዳት ሞክሩና ለእኔ ደስ ይበላችሁ አባታችሁን እወደው እንደነበር
ታውቃላችሁ ግን እሱ ሞቷል። ከሞተ ረጅም ጊዜው ነው እና የምወደውና
የሚወደኝ ሰው ያስፈልገኛል።”

ክሪስ እንደሚወዳት፣ ሁላችንም እንደምንወዳት ለመናገር አፉን ከፈተ። ነገር
ግን ይህ ከልጆቿ የምታገኘው ፍቅር፣ እሷ የምታወራው አይነት ፍቅር
እንዳልሆነ ስለገባው ከንፈሮቹን ገጠመ እኔ ከአሁን በኋላ አልወዳትም።
ከዚህ በኋላ ትንሽ የመውደድ ስሜትም ለእሷ እንደሚኖረኝ እንኳን እርግጠኛ አይደለሁም: ግን መንትዮቹ በሁኔታዬ እንዳይደነግጡ መሳቅና ማስመሰል እንዲሁም ከአንገት በላይ መሆን እችላለሁ፡ “አዎ እማዬ፣ ለአንቺ ደስ ብሎኛል እንደገና የሚወድሽ ሰው ማግኘትሽ ጥሩ ነው።”

“ለረጅም ጊዜ ይወደኝ ነበር ካቲ፣” ተበረታታችና እንደገና በራስ በመተማመን
ፈገግ እያለች ቀጠለች “ወንደላጤ ሆኖ ለመቆየት ወስኖ ስለነበር ሚስት
እንደሚያስፈልገው ለማሳመን ቀላል አልነበረም: አያታችሁ ደግሞ በፊት
አባታችሁን በማግባት ለሰራሁት ኃጢአት ቅጣት እንዲሆን ሁለተኛ ጊዜ
እንዳገባ አልፈለገም ነበር። ግን ባርትን ይወደዋል፤ ብዙ ስለምነው ቆይቼ
በመጨረሻ እሺ አለኝ ባርትን ማግባትና ሀብቱንም መውረስ እንድችል
ፈቀደ” ንግግሯን ቆም አደረገችና የታችኛውን ከንፈሯን መብላት ጀመረች።
እንደገና ደግሞ በጭንቀት ተዋጠች ቀለበት ያጠለቀችበት ጣቷ ወደ ጉሮሮዋ ሄደና አንገቷ ላይ ያንጠለጠለችውን ጌጥ በጭንቀት ያፍተለትል ጀመር።“በእርግጥ አባታችሁን የምወደውን ያህል ባርትን አልወደውም” አለች።
የበራው ፊቷ አሁን ያላት ፍቅር በፊት ከምታውቀው እጅግ የበለጠ እንደሆነ
እያጋለጣት ነበር በረጅም ተነፈስኩ: ምስኪን አባቴ!

“ያመጣሽልን ስጦታዎች... ሁሉም ከአውሮፓ፣ ወይም ከእንግሊዝ ደሴቶች
አይደሉም: የስኳር ከረሜላው የመጣው ከቬርሞንት ነው: ቬርሞንትም ሄደሽ ነበር? እሱም ከዚያ ነው የመጣው?”

ልክ ቬርሞንት ብዙ ነገር የሰጣት ይመስል በደስታ ሳቀች። “አይ፣ እሱ የመጣው ከቬርሞንት አይደለም ካቲ፤ ግን እዚያ የምትኖር እህት አለችው ከአውሮፓ ከመጣን በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ ልንጠይቃት ሄደን ነበር የስኳር ከረሜላ
ምን ያህል እንደምትወጂ ስለማውቅ ከዛ ነው ያመጣሁልሽ። ደቡብ የሚኖሩ ሌሎች ሁለት እህቶችም አሉት: ደቡብ ካሮላይና ውስጥ ካለች ግሪንግሌና ግሪንግሌና ወይም እንደዚያ አይነት ስም ካላት ከተማ ነው የመጣው: ግን በኒው ኢንግላንድ ብዙ ቆይቷል: የተመረቀው ከሀርቫርድ የህግ ትምህርት
👍393😁2
ቤት ነው። በበልግ ወቅት ቬርሞንት እንዴት እንደሚያምር! ውበቱ ትንፋሽ ያሳጥራል። የጫጉላ ሽርሽር ላይ በመሆናችን ከሌሎች ሰዎች ጋር መሆን
አልፈለግንም ስለዚህ እህቱንና ቤተሰቦቿን ለአጭር ጊዜ ጎበኘናቸውና ከዚያ ባህሩ ዳርቻ ላይ ጥቂት ጊዜ አሳለፍን” አለች ከዚያ በማይመች አይነት
አይኖቿን ወደ መንትዮቹ ወርወር አደረገች

“ያመጣሁልህን ትንንሽ ጀልባዎች ወደድካቸው ኮሪ?”

“አዎ እመቤቴ” ልክ እንግዳ እንደሆነች ሁሉ በጣም በጨዋነት፣ በትልልቅ
አይኖቹ አተኩሮ እየተመለከታት ነበር።
“የምወድሽ ኬሪ... ትንንሾቹን አሻንጉሊቶች ያሉሽ አሻንጉሊቶች ላይ
እንድትጨምሪያቸው ከኢንግላንድ ነው የገዛሁልሽ ሌላ የአሻንጉሊት አልጋ እንደማገኝልሽ ተስፋ አለኝ: ግን አሁን አሁን የአሻንጉሊት ቤት ውስጥ
የሚቀመጡ የአሻንጉሊት አልጋዎች መስራት የተው ይመስላል።” “ምንም
አይደል እማዬ” ኬሪ ከወለሉ ላይ አይኖቿን ሳትነቅል መለሰች: “ክሪስና ካቲ
የአሻንጉሊት አልጋ በካርቶን ሰርተውልኛል እና ወድጃቸዋለሁ”

አምላኬ! አይታያትም እንዴ?

አሁን አያውቋትም እኮ: አሁን እሷ ስትኖር ምቾት አይሰማቸውም፡

“አዲሱ ባልሽ ስለኛ ያውቃል?” ድርቅ ብዬ ጠየቅኳት። ክሪስ በመጠየቄ ተናደደብኝ፤ ድምፅ ባያወጣም እናታችን ላገባችው ሰው ጥቂቶች የዲያብሎስ
ልጆች እንደሆኑ የሚቆጥሯቸው የተደበቁ አራት ልጆች እንዳሏት ተናግራ ማታለል አትችልም እያለ እየነገረኝ ነበር።

የእናታችንን ደስታ የሚያጠቁር ጥላ መጣ። እንደገና የተሳሳተ ጥያቄ ጠየቅኩ። “ገና አላወቀም ካቲ፤ ልክ አባቴ እንደሞተ ስለ አራታችሁ እነግረዋለሁ:
እያንዳንዷን ዝርዝር ሳይቀር አብራራለታለሁ ይረዳኛል ደግና አዋቂ ሰው ስለሆነ ትወዱታላችሁ።”

ይህንን ከአንድ ጊዜ በላይ ብላዋለች: ያ ሽማግሌ ሰው እስኪሞት መጠበቅ
ያለበት ሌላ ነገር መጣ፡ “ካቲ እንደዚያ አትይኝ! ከጋብቻችን በፊት ለባርት ልነግረው አልቻልኩም የአያታችሁ ጠበቃ ነው ኑዛዜው እስኪነበብና በስሜ ገንዘብ እስኪኖረኝ ድረስ ስለ ልጆቼ እንዲያውቅ መፍቀድ አልችልም::"

አንድ ሰው ሚስቱ ከመጀመሪያ ባሏ አራት ልጆች ያሏት መሆኑን ማወቅ
ይገባዋል ለማለት ቃላት ምላሴ ጫፍ ላይ ደርሰዋል እንዴት ይህንን
መናገር ፈልጌ እንደነበር፤ ግን ክሪስ እያፈጠጠብኝ ነበር። መንትዮቹ ደግሞ ተጠጋግተውና ቁጢጥ ብለው ትላልቅ አይኖቸውን ቲቪ ላይ ሰክተዋል። እና መናገር ይኑርብኝ ወይም አይንርብኝ አላወቅኩም: ዝም ማለት ቢያንስ አዲስ
ጠላት እንዲያፈሩ አያደርግም: ምናልባት እሷ ትክክል ልትሆን ትችላለች።አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ትክክል ትሁን፤ እምነቴ ይታደስ… እንደገና ልመናት።በገፅታዋ ብቻ ሳይሆን በሁሉ ነገር ቆንጆ እንደሆነች ልመን።

እግዚአብሔር ወደታች ወርዶ ሞቃትና የእርግጠኝነት እጁን ትከሻዬ ላይ አላሳረፈም: እዚያ ተቀምጬ ጥርጣሬዎቼ በእኔና በእሷ መካከል ያለውን ገመድ በጣም ወጥረውት በጣም በጣም እንደቀጠነ አስተዋልኩ።

ፍቅር… ይህ ቃል በመፅሀፎች ውስጥ እንዴት በብዛት እንደተፃፈ! ደግሞ ደጋግሞ ተፅፏል። ሀብትና ጤና፣ ውበትና ተሰጥኦ ቢኖርህ ... ፍቅር ከሌለ ምንም የለህም: ፍቅር ተራ የሆነውን ሰው ወደ ደስተኛ፣ ኃይለኛ፣ በሀሴት ወደሰከረና ውብ ወደሆነ ሰው ይለውጠዋል።

ዝናቡ ጣሪያው ላይ ሲያርፍ በሚሰማበት የክረምቱ መግቢያ ላይ ባለ ቀን፣መንትዮቹ ወለሉ ላይ ከቲቪው ፊት ለፊት ተቀምጠዋል። እኔና ክሪስ ክረምቱ በደንብ ከመጀመሩና የጣሪያው ስር ክፍል በጣም ከመቀዝቀዙ በፊት
ልንደሰትበት ከመማሪያ ክፍሉ መስኮት አጠገብ ያለው አሮጌ ፍራሽ ላይ ጎን ለጎን ተጋድመን እናታችን ምድር ቤት ካለው ትልቁ ቤተ መፃህፍት ያመጣችውን መፅሀፍ እያነበብኩ ነው።

እኔ ሳነብ እሱ በጀርባው ጋደም ብሎ ኮርኒሱ ላይ እያፈጠጠ ነበር። የመጽሀፉ አጨራረስ ደስ አላለኝም: አስደሳች ፍፃሜ የሌለው መፅሀፍ አልወድም እያነበብኩት የነበረውን መፅሀፍ ዘግቼ ቅርብ ወዳለው ግድግዳ አሽቀነጠርኩትና ልክ እሱ እንደፃፈው ሁሉ ወደ ክሪስ ዞሬ በቁጣ “በጣም አስቀያሚና የማይረባ ታሪክ ባይሆን ኖሮ ያፈቀርኩት ሰው ማንም ይሁን ማን ይቅር ማለትና በደሉን መርሳት እንዳለብኝ እማርበት ነበር!” አልኩት: በተለየ መንገድ መፃፍ
ያልተቻለው ለምንድነው? አዋቂ ለሆኑ ሁለት ሰዎች፣ ዕጣ ፈንታ ሁልጊዜ መጥፎ ዕድል ሊያመጣ እንደሚችል ሳያስተውሉ አንገታቸውን ደመና ውስጥ
አድርገው መንሳፈፍ ይቻላቸዋል?

እኔ መቼም በጭራሽ መፅሀፉ ላይ እንዳሉት ሰዎች አልሆንም! አንዳንዴ
እንኳን ወደ ምድር መመልከት የማያውቁ ሞኞች ናቸው!”

ወንድሜ የመፅሀፉን ታሪክ በቁምነገር ወስጄ በመናደዴ የተገረመ ይመስላል።
“ፍቅረኞች ምናልባት ወደ ምድር መመልከት አይገባቸው ይሆናል እንደዚህ አይነት ታሪኮች የሚነገሩት በምሳሌ ነው። ምድር እውነታን ይወክላል፤ እውነታ ደግሞ ተስፋ መቁረጥን፣ ህመምን፣ ሞትንና እሱን የመሳሰሉ አሳዛኝ ክስተቶችን የሚወክል ይሆናል። ስለዚህ ፍቅረኞች ማየት ያለባቸው፣ ውብ
እምነቶቻቸው ወደማይበለሻሹበት ወደ ሰማይ ነው” አለ።

ወደ ክሪስ እየተመለከትኩ “እኔ ፍቅር ሲይዘኝ…” ብዬ ጀመርኩ “ሰማይን የሚነካ ተራራ እገነባለሁ። ከዚያ ፍቅረኛዬና እኔ ለሁለቱም አለም ምርጥ ነገሮች ይኖሩናል። ጭንቅላታችንን ደመና ውስጥ አድርገን የምናልመው ሳይበላሽ እውነታው በእግራችን ስር ፅኑ ሆኖ ይቆያል” አልኩት።

ሳቀ... አቀፈኝ... በደግነት እና በቀስታ ሳመኝ አይኖቹ ለስላሳና ቅን ነበሩ። “የኔ ካቲ ያንን ማድረግ ትችላለች።” አለ “ካቲ አንዳንዴ በጣም ትበዥብኛለሽ”

ይህንን ሲናገር ድምፁ ከወትሮው ጥልቀት ያለው ይመስል ነበር። ለስላሳ አስተያየቱ ቀስ እያለ ከፊቴ ወደ ከንፈሬ ከዚያ ወደ ደረቴ እያለ ስቶኪንግ ወደ ለበሱት እግሮቼ ወረደ: በስቶኪንጉ ላይ አጭር ቀሚስና ከላይ ደግሞ ሹራብ ለብሻለሁ ከዚያ አይኖቹ እንደገና ወደ ላይ ተመለሱና ከእኔ የመገረም አስተያየት ጋር ተላተመ።አፍጥጬ መመልከቴን ስቀጥል ፡አፈረና ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፊቱን አዞረ: ልቡ በፍጥነት ሲመታ የምሰማበት ርቀት ላይ ነኝ። እና ድንገት የእኔም ልብ የእሱን ልብ አመታት ተከተለ፡ በፈጣን እይታ ገረፍ አደረገኝ አይኖቻችን ሲገናኙ ግራ በመጋባት ሳቀ፤ እነዚህ ሁሉ ነገሮች የእውነት ሊሆኑ እንደማይችሉ ለማስመሰልና ለመደበቅ ሞከረ።

እያነበብን የነበረውን መፅሀፍ አስታውሶ “ለመጀመሪያ ጊዜ ትክክል ሆንሽ ካቲ የማይረባ ታሪክ ነው! ለፍቅር ብለው የሚሞቱ ያበዱ ሰዎች ብቻ ናቸው::እወራረዳለሁ ይህንን የማይረባ ታሪክ የፃፈችው ሴት መሆን አለባት”

“ወንድ ነው የሚሆነው፤ ምክንያቱም በዚያ ዘመን የስሟን የመጀመሪያ
ፊደሎች ወይም የወንድ ስም ካልተጠቀመች በስተቀር ሴት መፅሀፍ የማሳተም እድል አልነበራትም፡ ግን ሁሉም ወንዶች ሴቶች የሚፅፉትን የፍቅር ታሪክ ሁሉ የማይረባ ነው ብለው የሚያስቡት ለምንድነው? ወንዶች የፍቅር ስሜት የላቸውም? ወንዶች ፍፁም ፍቅር ለማግኘት አያልሙም?”

“ወንዶች ምን እንደሚመስሉ አትጠይቂኝ! ምርር ባለ ስሜት ተናገረ ራሱን
የሆነ አይመስልም ተቆጣ፡ “እዚህ እኛ እንደምንኖረው እየኖርኩ ወንድ መሆን ምን ስሜት እንዳለው እንዴት አውቃለሁ? እዚህ ውስጥ የፍቅር ስሜት እንዲኖረኝ አይፈቀድልኝም ይህንን አድርግ… ያንን አታድርግ
አይኖችህን ዞር አድርግ፤ አይኖችህ ፊት ያለውን አትመልከት… ያየህ
አትምሰል መባል ሰልችቶኛል። ወንድ ብሆንም፣ ወንድምሽ ስለሆንኩ ስሜት
የሌለኝ እያስመሰልኩ ነው፡”
👍302🥰1
አይኖቼ ፈጠጡ። እሱ ላይ እንደዚህ አይነት ያየሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ስለነበረ አስገረመኝ በሚነካ ሁኔታና በቁጣ ተናግሮኝ አያውቅም።

አይሆንም እኔ መልካም ፍሬዎች ባሉበት በርሜል ውስጥ የተቀመጥኩ
መራራ ሎሚ፣ የተበላሸ አፕል ነኝ፡ እየበከልኩት ነው አሁን እያደረገ ያለው እናታችን ሄዳ ብዙ የቆየች ጊዜ ያደረገው አይነት ነገር ነው እኔ እንደሆንኩት አይነት እንዲሆን በማድረጌ ክፉ ነኝ ሁልጊዜ እንደነበረው
ሆኖ መቆየት ይገባዋል ደስተኛና ሳቂታ፣ የህይወትን በጎ ጎን የሚመለከት።
ከመልከመልካምነቱና ማራኪነቱ በተጨማሪ የነበረውን ትልቁን ንብረቱን
ዘረፍኩት ይሆን?

ክንዱን ለመንካት እጄን ዘረጋሁ። “ክሪስ” እምባ እያነቀኝ በሹክሹክታ ጠራሁት
“ወንድ መሆንህ እንዲሰማህ ምን እንደሚያስፈልግህ የማውቅ ይመስለኛል።"
አልኩት።

“ኧረ? ምን ማድረግ ትችያለሽ?”...

ይቀጥላል
20👍10
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_አንድ ፡ ፡ #ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ የእናታችን ድንገተኛ ዜና እናታችን እንደገና ልታየን ከመምጣቷ በፊት ባለፉት በእያንዳንዱ አስር ቀናት ውስጥ፣ እኔና ክሪስ ለምን አውሮፓ ሄዳ እንደቆየችና ከሁሉም በላይ ደግሞ ልትነግረን የነበረው ትልቅ ዜና ምን እንደሆነ ለመገመት ለሰአታት እናወራ ነበር። አስሩን ቀናት እንደ ሌላ ቅጣት አሰብነው ቅጣትም ነበረ: እዚህ…»
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

....ክንዱን ለመንካት እጄን ዘረጋሁ። “ክሪስ” እምባ እያነቀኝ በሹክሹክታ ጠራሁት
“ወንድ መሆንህ እንዲሰማህ ምን እንደሚያስፈልግህ የማውቅ ይመስለኛል።"
አልኩት።

“ኧረ? ምን ማድረግ ትችያለሽ?”

አሁን ወደ እኔ እየተመለከተ አይደለም:: በዚያ ፋንታ ኮርኒስ ላይ እያፈጠጠ ነው ለእሱ ታመምኩ ምን እንዳስከፋው አውቄያለሁ። ሀብቱን ወረስንም አልወረስንም ህልሙን የተወው እኔን መምሰል እንዲችል ብሎ ነው: እኔን
መምሰል ደግሞ ጎምዛዛ፣ መራራ፣ ሁሉን የሚጠላና የተደበቀ ምክንያታቸውን
የሚጠራጠር መሆን ማለት ነው።

ቀስ እያልኩ ፀጉሩን ነካካሁትና “የሚያስፈልግህ አንድ ነገር ነው ፀጉር
መቆረጥ። ፀጉርህ በጣም ረጅምና የሚያምር ነው፡ ወንድነት እንዲሰማህ አጭር ፀጉር ሊኖርህ ይገባል። አሁን ግን ፀጉርህ የኔን ፀጉር ነው የሚመስለው”

እና ማነው የአንቺ ፀጉር ያምራል ያለው? ምናልባት በአንድ ወቅት ከሬንጁ
በፊት የሚያምር ፀጉር ነበረሽ” አለኝ፡

“የእውነት?” ብዙ ጊዜ አይኖቹ ፀጉሬ ከማማር በላይ እንደሆነ ነግረውኛል።
hፊት ለፊቴ ያለውን ፀጉሬን ሊቆርጥ መቀስ ሲያነሳ እየተመለከተኝ የነበረበትን
መንገድ ነግሮኛል። በጣም ሲያመነታ ላየው ህመም የማይሰማውን ፀጉር
ሳይሆን ጣቶች የሚቆርጥ ነበር የሚመስለው ከዚያ አንድ ቀን ጣሪያው
ስር ያለው ክፍል ውስጥ ፀሀይ ላይ ተቀምጦ የተቆረጠውን ጸጉሬን በእጆቹ ይዞ ሲያሸተው፣ በጉንጮቹ ሲዳስሰውና ወደ ከንፈሮቹ ሲያስጠጋቸው
አይቼዋለሁ ከዚያ ደግሞ ትራሱ ስር ለማስቀመጥ ካርቶን ውስጥ ሲደብቀው
ተመልክቻለሁ፡

ማየቴን እንዳያውቅ ሳቄን መደበቅ ቀላል አልነበረም: “ኦ ክሪስቶፈር… በጣም ውድ ሰማያዊ አይኖች አሉህ፤ ከዚህ ቦታ ነፃ ስንሆንና ወደ አለም
ስንመለስ አንተን ለሚያፈቅሩ ሴቶች ሁሉ በጣም አዝንላቸዋለሁ። በተለይ ደግሞ ከመልከመልካም ባሏ ጋር የፍቅር ግንኙነት የሚፈልጉ
በሽተኞች ያሉት ዶክተር ባል ላላት ሚስትህ አዝናለሁ። እና እኔ ሚስትህ ብሆን ከጋብቻህ ውጪ አንድ የፍቅር ግንኙነት ቢኖርህ እገድልሀለሁ! በጣም ስለማፈቅርህ እቀናለሁ ምናልባት በሰላሳ አምስት አመትህ ከህክምና
እንድትወጣ አደርግሀለሁ” ያልኩትን ሁሉ ችላ ብሎ “አንድ ጊዜም ፀጉርሽ
ያምራል ብዬ ተናግሬ አላውቅም” አለ።

በቀስታ መላጨት የሚያስፈልጋቸው ፀጉሮች ያሉበትን ጉንጩን ዳሰስ
አደረግኩት፡

ከዚያ “ባለህበት ቁጭ በል! ታውቃለህ ለረጅም ጊዜ ፀጉርህን ቆርጬህ
አላውቅም… መቀስ ላምጣ” አልኩት፡ ግን የፀጉራችን ምንም መምሰል
የህይወት ዘይቤያችን ለመለወጥ አስፈላጊ ካልሆነ የክሪስንና የኮሪን ፀጉር
ለመቁረጥ ለምን እቸገራለሁ? ከፊት ያለው ፀጉሬ ብቻ በዚያች ከብረት
የተሰራች የምትመስል ክፉ አሮጊት መሸነፋችንን ለማሳየት ከመቆረጡ
በስተቀር፤ እዚህ ከመጣን እኔና ኬሪ ፀጉራችን ጫፍ ጫፉ እንኳን ተከርክሞ
አያውቅም።

መቀሱን ላመጣ ስሄድ የእኛ ፀጉር በጣም ሲያድግ አንዳቸውም አረንጓዴ
ተክሎቻችን አለማደጋቸው እንግዳ ነገር መሆኑን አሰብኩ።

ክሪስ ወለሉ ላይ ተቀመጠ ከኋላው ተንበረከክኩ ፀጉሩ ከትከሻው በታች
የወረደ ቢሆንም ብዙ እንዲቆረጥ አልፈለገም፡ “ቀስ እያልሽ ቁረጪ" ሲል
አዘዘኝ “በአንዴ ብዙ አታሳጥሪው ድንገት በአንድ ዝናባማ ከሰአት በኋላ
ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ወንድነት ቢሰማኝ አደገኛ ሊሆን ይችላል
ብሎ ቀለደና ፈገግ አለ። ከዚያ ድርድር ያሉ ነጫጭ ጥርሶቹን እያሳየ ሳቀ:
መምሰል የሚገባውን ያህል አሳምረዋለሁ።

ዙሪያውን እየዞርኩ ፀጉሩን ስቆርጥና ስከረክም እንዴት እንደምወደው እያሰብኩ ነበር፡ ያለማቋረጥ ወደኋላ ሄድ እያልኩ ፀጉሩ በትክክል መቆረጡን አረጋግጣለሁ ጭንቅላቱ የተጣመመ እንዲመስል አልፈለግኩም።
ፀጉር አስተካካዮች ሲያደርጉ እንዳየሁት፣ ፀጉሩን በማበጠሪያ ይዤ በጥንቃቄ ቆረጥኩት። ምን መምሰል እንዳለበት እንደምፈልግ አእምሮዬ ውስጥ አሉ
የሆነ የማደንቀውን ሰው

ስጨርስ ትከሻው ላይ የወደቁትን የተቆራረጡ ፀጉሮች አራገፍኩና ወደኋላ
ራቅ ብዬ በማየት ቆንጆ እንዳደረግኩት አረጋገጥኩ።

“ያው!” አልኩ በድል አድራጊነት ከባድ ጥበብ የሚመስለውን ስራ ባልተጠበቀ ጉብዝና በማጠናቀቄ ደስ ብሎኛል። “የተለየህ መልከመልካም ብቻ ሳይሆን በጣም ወንዳወንድ ሆነሀል! ሁልጊዜም ወንዳወንድ ነበርክ። አለማወቅህ
ያሳዝናል” አልኩት።

ብራማ ጀርባ ያለው የስሜ የመጀመሪያ ፊደል የተቀረፀበትን መስተዋት እጁ ላይ አስቀመጥኩለት፡ ይህ መስተዋት እናታችን ለመጨረሻ ልደቴ ከሰጠችኝ
ስጦታዎች አንዱ ነበር። ብሩሽ፣ ማበጠሪያና መስተዋት አያትየው ሶስቱ
ውድና ኩራት የሚያመጡ እቃዎች እንዳሉኝ እንዳታውቅ የሚቀመጡት
ተደብቀው ነው።

ክሪስ በመስተዋቱ ላይ ለረጅም ደቂቃዎች አፈጠጠ ለቅፅበት ደስ ያላለውና ያልወሰነ ሲመስለኝ ልቤ ደነገጠ፡ ከዚያ ቀስ በቀስ ደማቅ ፈገግታ ፊቱን አበራው።

አምላኬ! ልዑል አስመሰልሽኝ! በመጀመሪያ አልወደድኩትም ነበር። አሁን ግን ሳየው የፀጉሬን ሁኔታ ስለቀየርሽው ፊቴን አሳምሮታል። አመሰግናለሁ
ካተሪን ፀጉር መቁረጥ ላይ እንደዚህ አይነት ችሎታ እንዳለሽ አላውቅም ነበር" አለኝ።

አንተ የማታውቃቸው ብዙ ችሎታዎች አሉኝ፡”

"እኔም መጠርጠር ጀምሬያለሁ”

“እና ልዑሉ መልከመልካም፣ ወንዳወንድና ባለወርቃማ ፀጉሩን ወንድሜን በመምሰሉ እድለኛ ነው” ስል ቀለድኩ። የጥበብ ስራዬን አለማድነቅ
አልቻልኩም። ኦ አምላኬ! አንድ ቀን ልብ የሚሰብር ቆንጆ ነው የሚሆነው።

አሁንም መስተዋቱን እንደያዘ ነበር ከዚያ ቀስ ብሎ ወደጎን አስቀመጠውና
ምን ሊያደርግ እንደሆነ ከማወቄ በፊት እንደ ድመት እመር ብሎ ተነሳ ታገለኝ፤ ወደ ወለሉ እያስጎነበሰኝ መቀሱን ያዘ! ከእጄ ላይ መነጨቀኝና ፀጉሬን በእጁ ያዘ አሁን የኔ ቆንጆ እስቲ እኔም እንዳንቺ ማድረግ እችል እንደሆነ እንመልከት:"

በፍርሀት ገፈተርኩት

ስገፈትረው በጀርባው ወደቀ ከዚያ ተነሳ። ማንም የጸጉሬን ጫፉን እንኳን
አይነካም! ምናልባት አሁን በጣም ስስ ሆኖ ይሆናል። ግን ያለኝ ፀጉር ይኸው
ነው! አሁንም ከብዙ ሴቶች ፀጉር በተሻለ የሚያምር ነው እንዳይዘኝ ሮጥኩ።
ከመማሪያው ክፍል ወጥቼ ሻንጣዎቹን እየዘለልኩ በትልልቆቹ ጠረጴዛዎች
ስር እየሾለኩ ሮጥኩ። እሱም እያሯሯጠኝ ነው፡

ምንም ያህል በፍጥነት ብሮጥና በፍጥነት ብሽሎከለክም ላመልጠው
አልቻልኩም፡ በትከሻዬ በኩል ዞር ብዬ ስመለከተው ፊቱን እንኳን መለየት
አልቻልኩም ያ ደግሞ የበለጠ አስፈራኝ፡ ከጀርባዬ የተበተነውን ረጅሙን
8ጉሬን ለመያዝ ጥረት አደረገ። ፀጉሬን ቆርጦ ለመጣል የወሰነ ይመስላል

አሁን ጠልቶኛል ማለት ነው? ፀጉሬን ለማትረፍ አንድ ቀን ሙሉ በትጋት እንዳልለፋ ሁሉ… አሁን ደስ ስላለው ብቻ ሊቆርጠው ነው?

ተመልሼ ወደ መማሪያው ክፍል ሮጥኩ። ከዚያ ውስጥ ገብቼ በሩን እቆልፍና ወደ ራሱ ተመልሶ ሲረጋጋና ስህተት መሆኑ ሲገባው ተመልሼ እወጣለሁ::

ምናልባት ያሰብኩት ገብቶት ሳይሆን አይቀርም ረጃጅም ቅልጥሞቹ ላይ ፍጥነት ጨመረና ደርሶብኝ ረጅሙን ፀጉሬን ሲይዘውና ወደፊት ስወድቅ ጮህኩ!

እኔ ብቻ ሳልሆን እሱም ወደቀ ቀጥታ ላዬ ላይ! ጎኔ ላይ ድንገተኛ ህመም
ሲሰማኝ እንደገና በፍርሀት ሳይሆን በድንጋጤ ጮህኩ።

እላዬ ላይ ነው። በእጆቼ መሬቱን ተደግፎ ፊቴን አተኩሮ ይመለከታል። ፊቱ
ነጭ ሆኖ የፈራ ይመስላል። “ተጎዳሽ? ወይኔ አምላኬ! ካቲ ደህና ነሽ?” አለኝ።
👍401
ደህና ነኝ እንዴ? ደህና ነኝ? ጭንቅላቴን ቀና አድርጌ ሹራቤን በፍጥነት
ያረጠበውን በከባድ የሚፈስ ደሜ ላይ አፈጠጥኩ ክሪስም አየው። ሰማያዊ አይኖቹ በድንጋጤ ፈጠጡ: በሚንቀጠቀጡ ጣቶቹ የሹራቤን ቁልፎች
መፍታት ጀመረ፧ ከዚያ ገለጠና ቁስሉን ተመለከተ።

“ወይኔ አምላኬ!...” ትንፋሹን ሳበ፡ ከዚያ በእፎይታ ወደ ውጪ ተነፈሰ።
“ተመስገን አምላኬ ጥልቀት ያለው ከባድ ቁስል መስሎኝ ነበር። ከላይ መቆረጥ ብቻ ነው ካቲ። ብዙ ደም እየፈሰሰሽ ስለሆነ ምንም ሳትንቀሳቀሺ ያለሽበት ቦታ ቆይ… መታጠቢያ ቤት ሄጄ መድኃኒትና ፋሻ አመጣለሁ”

ጉንጬ ላይ ሳመኝና ጊዜ ለመቆጠብ ከእሱ ጋር ብሄድ እያልኩ ሳስብ እሱ
በኃይለኛ ፍጥነት እንዳበደ ሰው ወደ ደረጃዎቹ ሮጠ። በዚህ ሁኔታ እያለሁ
ወደታች ብወርድ መንትዮቹ እዚያ ስለሆኑ ደሙን ያዩታል። ገና ደሙን
እንዳዩ ደግሞ ደንግጠው ይጮሃሉ።

ክሪስ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የህክምና ዕቃዎቹን ይዞ በፍጥነት ተመለሰ።
እጆቹ በውሀ ስለረጠቡ አጠገቤ ተንበርክኮ ለማድረቅ እየተጣደፈ ነው፡
የሚያደርገውን የሚያውቅ መሆኑን ስመለከት ተገረምኩ። በመጀመሪያ
ፎጣውን አጣጥፎ የተቆረጥኩበት ቦታ ላይ ጫን አድርጎ ያዘው ከዚዬ
በየሰከንዱ ደሙ መቆም አለመቆሙን እየተመለከተ ነበር፡ ከዚያ ከቁስሉ
የበለጠ የሚያሳምመውን የባክቴሪያ መከላከያ አፈሰሰበት።

“እንደሚያቃጥል አውቃለሁ ካቲ. ግን ኢንፌክሽን እንዳፈጠር የግድ ይህን
ማድረግ ስላለብኝ ነው ሰውነትሽ ላይ የመጀመሪያውን ጠባሳ የፈጠርኩብሽ እኔ በመሆኔ አዝናለሁ: ግን በእኔ ምክንያት መቀሱ በአጉል አይነት ተሰክቶብሽ ብትሞቺ ኖሮ እኔም እሞት ነበር” አለኝ።

እላዬ ላይ ተጋድሞ ፊቱ ለፊቴ ቅርብ ሆኖ ነበር፡ አይኖቹ የተጨነቁና
ውጥረት ያለባቸው ይመስሉ ነበር፡ ያ የማውቀው የነበረው ልጅ የት ነው
እያልኩ እያሰብኩ ነበር። ወንድሜ የታለ? ይሄ ወርቃማ ሪዝ ያለው አተኩሮ
አይኖቼን የሚመለከተው ወጣት ማነው?

አስተያየቱ ባሪያ አደረገኝ፡ የሚሰማኝ ነገር ከዚህ በፊት ከተሰማኝ ከየትኛውም
ህመም ወይም መጎዳት የበለጠ ነበር ህመሙ የመጣብኝ የተሰቃዩ የቀስተ ደመና ቀለማትና ብርቅርቅታ የሚመስሉ ነገሮች ከሚታይባቸው አይኖቹ ውስጥ በተመለከትኩት ስቃይ መሰለኝ።

ክሪስ እንደዚህ አትሁን… ያንተ ጥፋት አይደለም አልኩትና ፊቱን በመዳፎቼ
መሀል ይዤ ልክ እናታችን ስታደርግ እንዳየሁት ጭንቅላቱን ወደ ጡቶቼ
አስጠጋሁት። “ትንሽ ጭረት ነው ብዙም አያምም እና ደግሞ ሆነ ብለህ
እንዳላደረግከው አውቃለሁ።”

ድምፁ እንደጎረነነ “ለምን ሮጥሽ? ስለሮጥሽ ነው ያባረርኩሽ፡ እየቀለድኩ
ነበር። ከጭንቅላትሽ አንድ ዘለላ ፀጉር እንኳ አልቆርጥም: ዝም ብሎ
ለመደሰት ያህል ያደረግኩት ነው። ፀጉርሽ የሚያምር መሆኑን እንደማስብ
ስትነግሪኝ ተሳስተሸ ነበር። ከማማር በላይ ነው: ጭንቅላትሽ ላይ የበቀለው
በአለም ላይ ካሉት ፀጉሮች ሁሉ እጅግ የሚያምረው ነው" አለኝ ፀጉሬ ተበትኖ እርቃን የሆኑ ጡቶቼን ሲሸፍንና ክሪስ ጭንቅላቱን ከደረቴ ላይ ሲያነሳ ትንሽ ቢላዋ ልቤ ላይ የተሰካብኝ መሰለኝ ጠረኔን ወደ ውስጥ
ሲምግ ይሰማኛል። የክረምቱ ዝናብ ጣሪያውን ሲደበድብ እያዳመጥን በፀጥታ ተጋድመናል። ዙሪያው ሁሉ ፀጥ ብሏል አሁንም አሁንም የፀጉሩን ዘለላ በጣቴ እያፍተለተልኩ ፊቱ ያልሸፈነውን አንዱን ጡቴን በጥንቃቄ የሚነካኩትን እጆቹን ያላስተዋልኩ እያስመሰልኩ ነው: መነካካቱን ስላልተቃወምኩ፣
የጡቴን ጫፍ ለመሳም ድፍረት አገኘ ዘለልኩ ይህ ነገር ለምን እንግዳ
ስሜት እንዲሰማኝ እንዳደረገ ገረመኝ፤ የሚያሸብር አስደናቂ ሁኔታ ነበር። “ያነበብነው መፅሀፍ ላይ ሰውየው ሴትዮዋን አንተ የሳምከኝ ቦታ ላይ ነበር የሳማት” ትንፋሽ እያጠረኝ ቀጠልኩ መሳሙን እንዲያቆምም… እንዳያቆምም
ፈልጌያለሁ: “ግን ቀጥሎ የሚመጣውን ሲያደርጉ ማሰብ አልችልም አልኩ፡

ጭንቅላቱን ቀና የሚያደርጉ ቃላት! እንደገና አይኖቹ እንግዳ በሆነ በሚያንፀባርቅ ብርሃን ተሞልተው እንዲመለከቱኝ የሚያደርጉ ትክክለኛ ቃላት ነበሩ “ካቲ…ቀጥሎ የሚመጣው ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?”

እፍረት ፊቴን አጋለው “አዎ የማውቅ ይመስለኛል አንተስ ታውቃለህ?”
ሳቀና “በደንብ አውቃለሁ። ትምህርት ቤት በመጀመሪያ ቀን በወንዶች መፀዳጃ
ቤት ውስጥ ትልልቆቹ ወንዶች የሚያወሩት ሁሉ ይህንን ነበር የማይገባኝን
ባለ አራት ፊደል ቃል በግድግዳዎቹ ላይ ይፅፉ ነበር: ግን ወዲያው በዝርዝር ተብራራልኝ፡ የሚያወሩት የነበረው ስለሴቶች፣ ስለቤዝቦል፣ ስለሴቶች፣ስለቅርጫት ኳስ፣ ስለሴቶች፣ ሴቶች፣ ሴቶችና ከእኛ ስለሚለዩባቸውን
መንገዶች ብቻ ነበር ለብዙ ወንዶች ደስ የሚል ርዕስ ይመስለኛል”

“ግን ለአንተስ ደስ የሚልህ አልነበረም?”

“እኔ ስለሴቶችም ሆነ ወይም ስለ ወሲብ አላስብም፧ እግዚአብሔር እንደዚህ የምታምሪ ባያደርግሽ ኖሮ ብዬ ግን እመኛለሁ። ሁልጊዜ ቅርብና የምትገኚ ባትሆኚ ደግሞ ጥሩ ነበር።”

“ስለኔ ታስባለህ? ቆንጆ እንደሆንኩ ታስባለህ?”

ማቃሰት የሚመስል ድምፅ ከከንፈሩ አመለጠ፡ ቀጥ ብሎ ለመቀመጥ ብድግ
አለና የተከፈተው ሹራቤ ያጋለጠው ነገር ላይ አተኮረ።

በሚንቀጠቀጡ ጣቶቹ የሹራቤን ቁልፎች ሲቆልፍ አይኖቹን ከአይኖቼ እያሸሽ
ነበር።

“ይህንን ነገር ወደ አእምሮሽ አስገቢ ካቲ። እርግጥ ነው ቆንጆ ነሽ፤ ግን ወንድሞች እህቶቻቸውን በዚያ አይነት አያስቧቸውም ከወንድምነት ፍቅርና ከመተጋገዝ አንዳንዴም ከመጣላት ሌላ ምንም አይነት ስሜት ሊሰማቸው አይገባም:”

“አንተ ከጠላኸኝ በዚች ሰከንድ እግአብሔር ቢገድለኝ እመርጣለሁ
ክሪስቶፈር”

በእጆቹ ፊቱን ደበቀ፡ ከተደበቀበት ሲወጣ ፈገግ እያለና እየተደሰተ ነበር
ጉሮሮውን አፀዳና፡-

“ተነሽ ልጆቹ ቲቪ ላይ ብዙ ከማፍጠጣቸው የተነሳ አይናቸው ሳይጠፋ
ወደታች እንሂድ” አለኝ...

ይቀጥላል
👍2819
በህይወት መንገድ ላይ……
( ታጋቾቹ)
ምዕራፍ-10
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
በሪሁን የሚቀመስ ነገር ልፈልግ ብሎ በድካም የዛሉ እግሮቹን እየጎተተ ሲሄድ ውስጤ የተሰማኝ ሀዘን ጥልቅ ነበር ፡፡ ሰው ጦርነትን ይፈራል አዎ ጦርነት በጣም አስፈሪና አውዳሚ ነገር ነው፤ ረሀብ ግን 666 ጥፈር ያለው አውሬ ነው፡፡በቀናት ውስጥ ስጋን ከላያችን ላይ ቦጫጭቆ በማርገፍ በአፅም ያስቀርና በአጥንት ብቻ እንድንቀበር ያደርገናለል፡፡
በወታደራዊ ሳይንስ ለስፔሻል ፎርሶች የሚሰጥ ሰርቫይቫል ኮርስ ወይም እራስን ከሞት የማትረፍ ጥበብ የሚባል ስልጠና አለ፡፡ ይሄ ኮርስ በጠላት ተከበህ መውጫ ስታጣና ለቀናት ታግተህ የመቆየት ግዴታ ውስጥ ስትገባ ወይንም እንደዚህ እንደኛ አይነት ተአምራዊ ቅርቃር ውስጥ ሲገባ ጫናዎችን ተቆቁሞ በራሀብና በውሀ ጥም ሳይረቱ እንዴት ህይወትን ማቆየት እንደሚቻል በተግባር የሚሰለጥኑበት አንድ ወሳኝ የስልጠና አይነት ነው፡፡በዛ ኮርስ አንድ ወታደር አካባቢውን በጥልቀት በማስተዋል ዙሪያው ካሉ ነገሮች ምግቡን የማግኘት ችሎታ እንዲኖረው በበቂ ሁኔታ በተግባር በረሀ ፤በተራራ እና በሸንተር ምንም የምግብና የውሀ ስንቅ ሳየቋጠርለት ለሳምንታት በመጓዝ ተግባራዊ ስልጠና ይሰለጥናል፡፡
እኛ ግን ወታደር ስላልሆን እንዲህ አይነት ስልጠና አልወሰድንም፡፡ግነ ደግሞ ይሄ ወታደራዊ ስልጠና በተለይ በአሁኑ ጊዜ እንደህዝብም መሰጠት ያለበት ስልጠና ነው፡፡
በሀገራችች ብዙ የስነ-ምግብ ባለሞያዎች እንዳሉ እገምታለው…ግን ሁሉም ማለት በሚቻልበት ደረጃ የተለመዱትን የምገብ አይነቶች የትኛው ከየትኛው ጋር እንደሚዋሀድ በማጥናት.አዲስ አይነት የምግብ ውህደት በመፍጠር ላይ ብቻ የተወሰኑ ናቸው፡፡
.እንደእኔ እንደእኔ ግን ቢያንስ አሁን በዚህ ወቅተ እይታቸውን አስተካክለው አካሄዳቸውን መቀየር አለባቸወ ብዬ አስባለው፡፡በተለይ እንደኢትየጵያ አይንት ባዬ-ዳይቨረሲቲ ኖሯት ግን ደግሞ ሚሊዬዬን ዜገቾ በየአመቱ በረሀብ በሚገርረግፍበት ሀገር አዲስ የምግብ አይንት ወደ ምግብ ዝርዝራችን ለማካተት መጣር መቻል አለባቸው….አንድ ቅጠላ ቅጠል ወይም አዝዕርት እንዲሁም የእንስሳት ተዋፅኦ ለምገብ ለመዋል ምን አይነት መስፈርት ማሞላት አለበት…ምን ያህሉ የኢትዬጵያ ጥቅጥቅ ጫካዎች ውስጥ የሚበቅሉ ቅጠላ ቅጠሎች ፍራፍሬዎች እንዲሁም እንስሳቶች ለምግብነት እንደሚውሉና እንዳማይወለ ተጠንጥተዋለ?፡፡ካልተጠኑስ መቼ ነው መጠናት የሚጀምሩት? በዙሪያችን ያሉት አጥሮቻቸንን የከለሉት ቅጠላቅጠሎችና ሀገረጎች፤በየሜዳው በዘፈቀደ ያለእንክብካቤ አሻፈረኝ ብለወ የሚበቅሉት ዛፎችና ቁጥቀጦዎች ሁሉም መርዝ ናቸው..?ወይንስ ምንም ንጥረነገር የሌለባቸው እርባነቢስ ናቸው…?
ለምሳሌ ሞሪንጋ ወይም ሽፈራው የተባለው የዛፍ ቅጥል እጅግ መራር ነው..ግን ደቡቦች በተለይ አርባምንጭ አካባቢ ምሬቱን እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል ማንኛዋም ባለሞያ ሴት ታውቃለች እናም በአካባቢው የጎመንን ያህል በጣም የተለመደ ምግብ ነው…ለሰውነት ጤና የሚሰጠው ጥቅም ደግሞ ተዘርዝሮ አያልቅም..ይህ ዛፍ በሚበቅልባቸው አብዛኞቹ የሀገራችን ክፍል ግን እንደማንኛውም ዛፍ ዝም ብሎ ተፈጥሮን ሚዛን ለመጠበቅ ብቻ የሚውል ዛፍ ነው፡፡እናም እንደሞሪንጋ አይነት በጣም ጠቃሚ ዛፎች ግን ደግሞ ያልሞከርናቸው የማያናውቃቸው ስንት አሉ…?ለምሳሌ ያህል በአለም ላይ 3000 የእባብ ዝርያዎች ሲኖሩ ከአነዚህ መካከል 90 ፐርሰንቱ መርዝነት የሌላቸው እና ለምግብነት የሚሆን ናቸው፡፡ይሄን መስማት መቼስ ያስደንቃል?፡፡
በሀገራችን ከሶስት ወይም ከአራት አመተ በፊት በዜና የተነገረ ነገር ነው፡አዲስአባ ውስጥ አንድ ምግብ ቤት ነበር…እዛ ምግብ ቤት ዱለት በወረፋ ነው የሚበላው..ታክሲ ሹፌሩ፤ ወያላው ሌላው ሌለው እየተራመሰ ሚመገብበት የታወቀ ቤት ነበር…ከአመታት ቡኃላ ግን ያ እንደዛ ሰው ይጋደልበት የነበረው ምግብ ቤት ድለቱ ከአይጥ ስጋ እንደሚሰራ ተደረሰበት……አይጦቹም ሚመረቱበት የነበረ ሙሉ መጋዘን ቤት በጥቆማ በቁጥጥር ስር ዋለ.፡፡ሀገር ጉድ አለ …ሰዎቹ መሰቀል አለባቸው ሁሉ ያለ ቀላል ሰው አይደለም.አሁንም ይሄንን ከሚያነቡት መካከል አዎ መሰቀል አለባቸወ የሚል እንደሚኖር የታወቀ ነው…ነገሩ ቀላል አይደለም፡፡
አዎ ነገሩን በጥንቃቄ ካስተዋልነው ችገሩ የአየጥ ስጋ ምግብ መሆን ስለመይችል ፤ስለማይጣፍጥ፤መርዝነት ስላለው ወይንም ከምንመገበው የዶሮ ወይም የጠቦት ስጋ ያነሰ የምግብ ይዘት ስላለው ፍፅም አይደለም፡፡ስላለመድነው እና የባህላችን ጋር ስለሚጋጭ ነው፡፡እንዲህ እኛ እንዳለንንት አጣብቂኝ ሁኔታ ማንም ቢገባ ግን ሁኔታው የተለየ ይሆናል፡፡አዎ አሁን እውነቱን ንገረን ካላችሁ በሪሁን ከሄደበት አንድ አይጥ ገድሎ ይዞ ቢመጣ ወይም ነፍሱ የወጣ እባብ በእጁ ላይ ጠቅልሎ ቢመጣ እስኪጠበሱ እራሱ የምጠብቅ አይመስለኝም፡፡ቶሎ ተቀብዬው አንድ ሁለቴ ነጭቼ ሳላኝክ ምውጠው ነው የሚመስለኝ፡አዎ ተገኝቶ ነው፡፡
እና በመጨረሻ የሕይወት ማብቂያ ቀኔ ላየ ሆኜ ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር ቢኖር አደጋ ላይ ከወደቅንና ብዙ መስዋዕትነት ከከፈልን ብሃላ በግዳጅ በፊት ማናደርጋቸውን ነገሮች በድንገት ለማድረግ ከምንገደድ ቢያንስ በሰላሙ ጊዜ በከፋ ሁኔታ ከባህላችን ጋር የማይጋጩትን በጥናትና በምርም በማረጋገጥ ቀስ በቀስ ወደምግብ ዝርዝራችን ማካተት ብንችል ብዙ ይደግፈናል ብዬ አስባለው፡፡
1.5 ቢሊዬን ህዝብ ያላት ቻይና ህዝቦን ከረሀብ ስጋት ማላቅ ከቻልቸባቸው መንገዶች አንዱ የሚበሉ ምግብ ዝርዝሮችን በጣም በማስፋት ነው፡ውሻ ፤ጦጣ፤.ትላትል ፤ ቅጠላ ቅጠልማ ምኑ ተነግሮ . ፡፡
ሰው ሊሞት ሲል እንዲህ ቁም ነገር በቁም ነገር ይሆናል እንዲ? በጣም ነዘነዝኳችሁ አይደል…?
.አሁን አይዳ ከእንቅልፎ ባነነችና እንደምንም ከተጋደመችበት ተነስታ ቁጭ አለች…አይኖቾን እያሻሸች.‹በሪሁንስ የት ሄደ?›ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹የሚቀመስ ነገር ልፈልግ ብሎ ወደፊት ሄደ…››
‹‹ለምን ሳትቀሰቅሰኝ...ብቻን አንድ ነገር ቢሆንስ?››
‹‹አንቺ ግን ደህና ነሽ…እስቲ እንቺ ከዚህች ውሀ ጉሮሮሽን አርጥቢ››አልኳት በእጄ ባለቸው ሀይላንድ ውስጥ ያለችውነ ጭላጭ ውሀ ፡፡
‹‹አይ አያሰፈለግም. እኔ ደህና ነኝ..››ብላ ተነስታ ቆመችና ወደእኔ ተጠጋች በርክ አለችና ግንባሬን በፍቅር እያሻሸች በሀሰቧ ፍዝዝ አለች፡፡
መናገር ጀመረች ‹‹አንድ ቀን ድል ባለ ሰርግ የምወደውን ጉብል የማግባትና ሶስት የሚያማምሩ ልጆች የመውለድ እቅድ ነበረኝ..አዎ ጥሩ ቤት፤ጥሩ መኪና እና በፍቅር የተሞላ ትዳረር ህልሞቼ ነበሩ..››
‹‹አይዞሽ ...እግዚያብሄረ ይረዳናል ህልምሽም ይሳካል፡፡››አልኳት…እንዲሁ በአንደበቴ ስለመጣ ነው እንጂ በተናገርኩት ነገር ከልቤ አምኜበት አይደል
‹‹ለመልከም ምቾትህ አመሰግናለው.”አለችና ለሁለተኛ ቀን ጎንበስ ብላ ከንፈሬን መጠጠችልኝ፡፡
‹‹ታውቃለህ አይደል የከንፈሬን ድንግልና የወሰድከው አንተ ነው››
‹‹እየቀለድሽ ነው አይደል?.ለዛውም ከንፈርሽን ..እንኳን የከንፈርሽን የዋናውን እራሱ በአስራ ሁለት አመትሽ ሳታስረክቢ ትቀሪያለሽ;?›› የተናረኩት እውነቴን ነው ..ስለእሷ ለረጅም ጊዜ ማስበው እንደዛ ነው፡፡
👍28🥰2
‹‹በንግግርህ ብዙም አልበሳጭም ብዙ ሰዎች እንደዛ ነው የሚያስብኝ…ውሎዬ ከወንደች ጋር ነው….ወሬዬ ከወሲብ የተለወሰ ነው… ስለዚህ ማንም እንደዛ ቢያስብ አይገርምም››
‹‹እና እውነትሽን እንዳለ ነው?››
‹‹ልስጥህ ሞክረህ ታረጋግጣለህ እንዴ?››አለቺኝ ፈገግ እያለች
‹‹አይ ሽባ ሆኖ መንቀሳቀስ አይችልም.. ብሰጠውም ከማየት ውጭ ምንም ማድረግ አይችልም ብለሽ ነው አይደል?
‹‹የእውነት ግን ባታገባኝ እንኳን ላንተ ብሰጥ ደስ ይለኛል፡››
‹‹ለምን?››
‹‹ስለማፈቅርህ ..ከበፊቱም ሴትዬዋ ባትቀድመኝ አንተን የማግባት እቅድ ነበረኝ..ያው አሁን ከደቂቃዎች ቡኃላ ምን እንደሚፈጠር ስስማላውቅ ነው እውነት እውነቱን የምናዝልህ፡፡››
‹‹አንድ ነገር ልንገርሻ…››
‹‹ምን?››
‹‹እኔም ከደቂቃዎች ቡኃላ ምን እንደሚፈጠር ስለማላውቅ ልናዘዝ››
‹‹እየሰማውህ ነው››
‹‹አፍቅሬሻለው…እና በህይወት ከዚህ ተያየዘን ከወጣን እጅግ በጣም ችግር ላይ መውደቄ ከአሁኑ ይታየኛል፡፡››
‹‹እንዴት ማለት?››
ያው እንደምታውቂው ከሰናይት ጋር ቀለበት አስረን አሁን በቅርብ ለመጋባት ዝግጅት ላይ እያለን ነው ይሄ ነገር የተከሰተው…..ስለእኔና እሷ ፍቅር ምንም ልልሽ አልችልም…ግን አንድ ነገር ልነግርሽ የምችለው ከአንቺና ከእሷ አንዳችሁን ለመምረጥ ከባድ ፈተና ውስጥ እንደምገባ ነው፡››
‹‹አይዞኝ…››አለችኝ ..ተስተካክላ በእኔ ትከክል ከአጠገቤ ተኛች…እግሬን እንዳትነካ እየተጠነቀቀች ተጠጋችኝ.. እንደምንም አልኩና እጄን ዘርግቼ በአንገቶ ዙሪያ አሻግሬ አቀፍኳት… .ደረቴ ላየ ልጥፍ አለች፡፡.ፈራው፡፡ በቃ እንዲሁ ተቃቅፈን እስከመጨረሻው ሊያበቃልን ይሆን እንዴ …?በሪሁንም ቆየ….እግሬን ደግሞ ለጉድ እየበላኝ ነው፡፡ወይንም ትሎቹ ቁስሌን እየቦጫጨቁ ሲበሉት ለእኔ እየተሰማኝም ይሆናል….አዎ እግሬ ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ ሰውነቴ እየፈረሰ በመውደቅ ላይ ያለ መስሎ ነው እየተሰማኝ ያለው.. .ፈርሶ ፈርሶ ሲያልቅ ያው ነፍሴ ብቻዋን እርቃኗን ትቀራለች፡፡መሞቴን አረጋግጥና ስጋዬን በሀዘን ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብቼ ከነፍሴ ጋር ጉዞዬን ቀጥላለው፡፡እናም ምን አልባት አይዳም እንደኔው እየፈረሰች ሊሆን ይችላል ፡በስጋ ባይሳካልንም በነፍስ ተቃቅፈን ወደምንሄድበት አብረን ጉዞችንን የመቀጠል እድል ሊኖረን ይችላል…ሀሳቤን ሳላጠቃልል ድንገት እየፈረሰቸ ነው ያልኳት አይዳ በከፍተኛ ንቃት ምንጭቅ ብላ ከስሬ ተነሳች ..ተንበረከች‹‹..ወይኔ ጉዴ…ወይኔ ጉዴ ››ማት ጀመረች
‹‹ምን ሆንሽ ?ምን ተፈጠረ…?››በደነጋጤ ቀዝቅዤ ጠየቅኳት
ዩሆነ እበብ ነገር ሰውነቷ ላይ የተጠመጠመባት ነበር የመሰለኝ..አንገቴን ያዘችና ወደፊት ላፊት የዋሻወ ሽንቁር አዞረችው.
‹‹ምንድነው ታአምሩ?››
‹‹በሪሁን ይሆን እንዴ?››
እንዴ ቁጠሪ 1.2..3 አምስት መብራት
አዎ በቅርብ አርቀት ወደእኛ እየተንቀሳቀሱ የሚመጡ 5 የጣፍ የሚመስል መብራቶች በግልፅ ይታያሉ ‹አምላኬ ልንተርፍ ይሆን እንዴ?››
መብራቱ ወደእኛ እየቀረበ ሲመጣ የሰዎችም ንግግርና ወደ ጆሮችን ገባ ጥላቸውንም በተሰባበረ መልኩም ቢሆን በእየታችን ገባ።

ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️❤️❤️
👍369
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

...“ተነሽ ልጆቹ ቲቪ ላይ ብዙ ከማፍጠጣቸው የተነሳ አይናቸው ሳይጠፋ
ወደታች እንሂድ” አለኝ...

ስነሳ ስላመመኝ አገዘኝ በክንዶቹ ውስጥ አስጠግቶ ስለያዘኝ ጉንጬ ደረቱ
ላይ ነበር ከእሱ በፍጥነት ቢያላቅቀኝም እኔ ግን ጥብቅ አድርጌ ይዤው
ነበር። “ክሪስ አሁን ያደረግነው ኃጢአት ነው?
እንደገና ጉሮሮውን አፀዳና

“ነው ብለሽ ካሰብሽ ነው:"

ምን አይነት መልስ ነው? የኃጢአት ሀሳብ ካልገባባቸው እነዚያ ወለሉ ላይ ተኝተን በምትሀታዊ ጣቶቹና ከንፈሮቹ ሲነካካኝ የነበረባቸው ጊዜያት እዚህ
አስጠሊታ ቤት ልንኖር ከመጣንበት ጊዜ ጀምሮ አጋጥመውኝ የማያውቁ
ጣፋጭ ጊዜያት ናቸው ምን እንደሚያስብ ለማየት ቀና ብዬ ሳየው አይኖቹ ውስጥ እንግዳ የሆነ አስተያየት ተመለከትኩ፡ እርስ በእርሱ በሚጋጭ አይነት
ደስተኛ፣ ያዘነ፣ ያረጀ፣ ወጣት የሆነ፣ ብልህ፣ ሞኝ ... ይመስል ነበር። ወይም አሁን እንደ ትልቅ ወንድ እየተሰማው ይሆን? እንደዚያ ከሆነ ኃጢአት
ይሁንም አይሁንም ደስ ብሎኛል።

እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ መንትዮቹ ለመሄድ ደረጃውን መውረድ ጀመርን።ኮሪ የሙዚቃ መሳሪያ እየተጫወተና ኬሪ ደግሞ እየዘፈነች ነው:

ከኮሪ አጠገብ ወለሉ ላይ ተቀመጥኩና ጊታሩን ተቀብዬ ለመጫወት ሞከርኩ።

ሁላችንንም አስተምሮናል በጣም የሚወደውን ዘፈን ዘፈንኩለት፡ ስጨርስ
“የኔን ዘፈን አልወደድሽውም ካቲ?” አለኝ።

“በጣም ወድጄዋለሁ ኮሪ ግን በጣም ያሳዝናል።
ለምን ደስ የሚሉ ግጥሞች
አንጨምርበትም?” አልኩት።

“ታውቂያለሽ ካቲ… እናታችን ስለመጫወቻዬ ምንም አላለችም" አለኝ፡

“አላየችውም እኮ ኮሪ።''

“ለምን አላየችውም?”

እንወዳት የነበረች እንግዳ ሴት ከመሆኗ በስተቀር ከአሁን በኋላ እናታችን
ማንና ምን እንደሆነች ባለማወቄ በከባዱ ተነፈስኩ፡ አንዳንዴ የምንወዳቸውን ሰዎች ከእኛ ነጥሎ የሚወስዳቸው ሞት ብቻ አይደለም: አሁን ይህንን አውቄያለሁ።

“እናታችን አዲስ ባል አግኝታለች:” አለ ክሪስ “እና ሰው ፍቅር ሲይዘው ደግሞ ከራሱ ደስታ በስተቀር የሌሎችን ደስታ አያይም"

ኬሪ ሹራቤን አተኩራ እየተመለከተች፣ ካቲ፣ ሹራብሽ ላይ ያለው ምንድነው?” አለችኝ። “ቀለም” አልኩ ያለምንም ማመንታት። “ክሪስ ስዕል
መሳል ሊያስተምረኝ እየሞከረ ነበር። ከዚያ የኔ ስዕል ከእሱ ስዕል ይበልጥ
እንደሚያምር ሲመለከት ቀይ ቀለም የነበረበትን ዕቃ አንስቶ ወደ እኔ ወረወረው"

ትልቁ ወንድሜ አተኩሮ እያየኝ ነበር። “ክሪስ፣ ካቲ ከአንተ የተሻለ መሳል
ትችላለች?”

“እችላለሁ ካለች መቻል አለባት”

“ስዕሉ የታለ?”

“ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ።”

“ማየት እፈልጋለሁ”
“እኔ ደክሞኛል አንቺ ሂጂና አምጪው ካቲ ራት እስክታዘጋጅ ቲቪ ማየት
እፈልጋለሁ፡" ብሎ አየት አደረገኝ፡፡ “ውድ እህቴ ጨዋ ለመሆን ብለሽ
ተቀምጠን ራት ከመብላታችን በፊት ንፁህ ሹራብ ብትለብሽ ቅር ይልሻል? ስለዛ ቀይ ቀለም ጥፋተኝነት እንዲሰማኝ የሚያደርግ የሆነ ነገር አለ:”

“ደም ይመስላል” አለ ኮሪ። “አጥበሽ ካላስለቀቅሽው እንደ ደም ይሆንብሻል።"
በዚያ ምሽት የማይመች ስሜት ተሰምቶኝ እረፍት የለሽ ሆንኩ ሀሳቤ ክሪስ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ይመለከተኝ ወደነበረበት ሁኔታ
ይመላለሳል።

ለረጅም ጊዜ ስፈልገው የነበረው ሚስጠር ምን እንደሆነ አወቅኩ ያ የሚስጥር ቁልፍ ፍቅርን አካላዊና ወሲባዊ ፍላጎትን የሚገልጥ ነበር። እርቃን
ሰውነቶችን ማየት አይደለም ምክንያቱም ለረጅም ጊዜ ኮሪን ሳጥብ ነበርና።
ክሪስም እርቃኑን ሆኖ አይቼው አውቃለሁ: ነገር ግን እሱና ኮሪ ያላቸው
ነገር እኔና ኬሪ ካለን ነገር የተለየ መሆኑ ምንም አይነት የወሲብ መነሳሳት
ፈጥሮብኝ አያውቅም: እርቃን መሆን አይደለም

አይኖቹ ናቸው: የፍቅር ሚስጥር አይን ውስጥ ነው። አንድ ሰው ሌላኛውን
የሚመለከትበት መንገድ፣ ከንፈሮች ሳይነቃነቁ አይኖች የሚገናኙበትና
የሚያወሩበት መንገድ ነው: የክሪስ አይኖች ከአስር ሺህ ቃላት በላይ ተናግረዋል።

እኔን የነካበት መንገድም አይደለም… ቀስ እያለ በደግነት ማድረጉም አይደለም ሲነካኝ ወደኔ የሚመለከትበት መንገድ ነው እና ለዚያ ነው ማለት ነው አያትየው ሌላኛውን ፆታ መመልከት እንደማይገባ ህግ ያወጣችው:: ያቺ
ጠንቋይ አሮጊት የፍቅርን ሚስጥር ታውቃለች ብሎ ማሰብ ከባድ ነው መቼም ተፈቅራ ልታውቅ አትችልም አይሆንም እሷ ባለ ብረት ልብ፣ ባለ ብረት አጥንት ናት... አይኖቿም ለስላሳ ሆነው አያውቁም:

ከዚያ ርዕሱን በጥልቀት ስመረምር ከአይኖች በላይ ነው: ከአይኖች ኋላ
አእምሮ ውስጥ ነው፧ ሊያስደስትህ የሚፈልግ፣ ደስ የሚያሰኝህ፣ ሀሴት
የሚሰጥህና እንዲረዱህ በምትፈልግበት መንገድ የሚረዳህ፣ ማንም ሳይረዳህ ሲቀር ደግሞ ብቸኝነትህን የሚወስድልህ ነው። ኃጢአት በፍቅር ጉዳይ ምንም አያገባውም

ፊቴን ስመልስ ክሪስም እንደነቃ ተመለከትኩ። በጎኑ ተኝቶ ወደ እኔ
እየተመለከተ ነው። በጣም ደስ የሚል ፈገግታ ነው ያለው።እናታችን በዚያን ቀን ልታየን አልመጣችም: ከዚያ ቀን በፊትም ብቅ አላለችም
እኛ ግን የኮሪን የሙዚቃ መሳሪያ በመጫወትና በመዝፈን ራሳችንን የማስደሰቻ መንገድ አግኝተናል: እናታችን በጣም ግድ የለሽ እየሆነች የመጣች ቢሆንም
በዚያ ምሽት ሁላችንም የተኛነው በተስፋ ተሞልተን ነው፡ ለረጅም ሰዓት የደስታ ዘፈኖች መዝፈናችን፣ ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ የወረሰው ጫካ ውስጥ የነበረን ጉዞ እያለቀ መሆኑንና ፀሀይ፣ ፍቅር፣ ሐሴትና ደስታ መታጠፊያው ላይ እየጠበቁን መሆናቸውን እንድናምን አድርጎናል።

በብሩህ ህልሜ ውስጥ የሆነ ጨለማና የሚያስፈራ ነገር ይመጣብኛል።
በየቀኑ ቅርፁ የጭራቅ አይነት ይሆንብኛል። አይኖቼን ስጨፍን አያትየው ሳትታይ መኝታ ክፍላችን ገብታ እንቅልፍ እንደወሰደኝ አስባ ፀጉሬን በሙሉ ስትላጨኝ አያለሁ። እጮሀለሁ አትሰማኝም ማንም አይሰማኝም፡ ከዚያ ትልቅ የሚያንፀባርቅ ቢላዋ ታወጣና ሁለቱንም ጡቶቼን ቆርጣ ክሪስ አፍ ውስጥ ትጨምረዋለች: እና ሌላም ሌላም… ከዚያ እወራጫለሁ። ክሪስን የሚያነቃ የጩኸት ድምፅ አሰማለሁ። መንትዮቹ ልክ ሞቶ እንደተቀበሩ ልጆች ተኝተዋል። ክሪስ እንቅልፉ ሳይለቀው አልጋው ላይ ቁጭ ብሎ እጄን
ለመያዝ እየፈለገ “ሌላ ቅዠት ነው?” ሲል ጠየቀኝ።

አይይ! ... ተራ ቅዠት አይደለም ቀድሞ ማወቅና በተፈጥሮ መረዳት መቻል ነው:: የሆነ መጥፎ ነገር እንደሚፈጠር በአጥን መቅኒ ሳይቀር ተሰምቶኛል።
ድክም ብዬና እየተንቀጠቀጥኩ አያትየው ያደረገችኝን ለክሪስ ነገርኩት። “ያ ብቻ አይደለም መጥታ ልቤን ቆርጣ ያወጣችው እናታችን ነበረች: ሁሉ ነገሯ
በአልማዝ ያብረቀርቅ ነበር” አልኩት

ካቲ ህልም እኮ ምንም ትርጉም የለውም::”

“አለው!”

ሌሎች ህልሞችና ሌሎች ቅዠቶች ለወንድሜ እነግረዋለሁ። ያዳምጠኝና ይስቃል ከዚያ ሌሊቱን ልክ ፊልም ቤት እንዳሉ አይነት ሆኖ ማሳለፍ አሪፍ እንደሆነ ያለውን እምነት ይገልፅልኛል። ግን በፍፁም እንደዛ አልነበረም::ፊልም የሆነ ሰው የፃፈው መሆኑን እያወቅህ ቁጭ ብለህ ትልቁን ስክሪን
ትመለከታለህ እኔ ግን በህልሜ ውስጥ ተሳታፊ ነኝ፡ ህልም ውስጥ
እየተሰማኝ… እየተጎዳሁ እየተሰቃየሁና ይህንን ስል እያዘንኩ ነው አልፎ አልፎም በጣም እየተደሰትኩ ነው።

ክሪስ፣ እሱ ከእኔና ከእንግዳ መንገዶቼ ውስጥ የሌለ ሆኖ ሳለ ይህ ህልም ከሌሎች ይልቅ እሱን ይጎዳው ይመስል ለምን ፀጥ ብሎ እንደ ሀውልት ተቀመጠ? እሱም ህልም አይቶ ይሆን?
👍44👏21
ካቲ፣ ከዚህ ቤት እንደምናመልጥ የክብር ቃሌን እሰጥሻለሁ! በደንብ
ስላሳመንሽኝ አራታችንም እናመልጣለን፡ ህልምሽ የሆነ ነገር እየነገረሽ መሆን አለበት ባይሆን ኖሮ አንድ ህልም ደጋግመሽ አታይም ነበር። ሴቶች ከወንዶች በበለጠ ሊመጣ ያለ ነገር እንደሚሰማችው የተረጋገጠ ነው።
ድብቁ የአእምሯችን ክፍል ሌሊት በስራ ላይ ይሆናል። እናታችን ከማይሞተው፣ መኖሩን እየቀጠለ ካለው ወንድ አያታችን ውርስ እስክታገኝ አንጠብቅም:
እኔና አንቺ ሆነን መንገድ እንፈልጋለን፡፡ ከዚህ ሰከንድ ጀምሮ በህይወቴ እምልልሻለሁ። የምንተማመነው በራሳችንና በህልሞችሽ ይሆናል።” አለኝ።

ከአነጋገሩ እየቀለደ፣ እያሾፈ እንዳልሆነ አውቄያለሁ። ያለውን ያደርጋል።እፎይታ ስለተሰማኝ ልጮትህ እችል ነበር። ይህ ቤት መኖሪያችን አይሆንም!

እንሄዳለን! ከትልልቅ ጥላዎቹ የተነሳ ደብዛዛ ብርሃን ባለበት በዚህ ክፍል ውስጥ አይኖቼን ትክ ብሎ እያየ ነበር፡ ምናልባት እኔ እንዳየሁት እያየኝ ይሆናል ከህይወት የገዘፈ ከህልም የለሰለሰ፡ በዝግታ ጭንቅላቱ ወደኔ ዘምበል አለና
ልክ ቃሉን በጠንካራና ትርጉም ባለው መንገድ እያቆመ በሚመስል አይነት ከንፈሮቼን ጥብቅ አድርጎ ሳመኝ። አስቀድሜ ጋደም ያልኩ ቢሆንም ወደታች እየወደቅኩ... እየወደቅኩ. እየወደቅኩ የምሄድ የሚመስል ስሜት የፈጠረብኝ
ረጅም መሳም ነበር።
በጣም የሚያስፈልገን ነገር የመኝታ ክፍላችን ቁልፍ ነው: እዚህ ቤት ላሉ
ክፍሎች ሁሉ ወሳኝ ቁልፍ እንደሆነ እናውቃለን በተተለተለ አንሶላ የሰራነውን መሰላል በመንትዮቹ ምክንያት ልንጠቀምበት አንችልም: አያትየው ቁልፉን በግዴለሽነት እንደማታስቀምጠው ገብቶናል። እንደዚያ አታደርግም: በሩን
እንደከፈተች ወዲያውኑ ኪሷ ውስጥ ትከተዋለች ሁልጊዜም አስቀያሚዎቹ ግራጫ ቀሚሶቿ ኪስ አላቸው::

እናታችን ደግሞ ግድ የለሽ፣ ዝንጉና ምንም የማይመስላት ናት። ልብሶቿ ላይ ኪስ ሲኖር አትወድም: ስለዚህ በእሷ መተማመን እንችላለን፡

ምናችንን ትፈራለች? ደካሞች፣ ዝምተኞች፣ የዋሆች. የእሷ ሚስጥራዊ ትንንሽ ምርኮኛ “ውዶች” መቼም ቢሆን አድገው አደጋ የማይሆኑ! በዚያ ላይ ደስተኛና ፍቅር የያዛት ናት: ያም አብዝታ እንድትስቅና አይኖቿ እንዲያንፀባርቁ አድርጓታል። በጣም ትኩረት የሌላት ከመሆኗ የተነሳ
እንድታይ ለማድረግ መጮህ ሁሉ ያስፈልግ ነበር። መንትዮቹ በጣም
ዝምተኛና የታመሙ መስለው እንዳሉ እንድታይ መጮህ ያስፈልጋል።

በወር ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ ትመጣለች: በመጣች ቁጥር ለእሷ መፅናኛ
ለእኛ ግን ምንም ያልሆኑ ስጦታዎች ተሸክማ ትመጣለች። ለጥቂት ደቂቃዎች ለመቀመጥ በጌጣጌጦች የተዋቡ ውድና ቆንጆ ልብሶቿን ለብሳ ትመጣለች:

እንደንግስት ዙፋኗ ላይ ትቀመጥና ለክሪስ የስዕል ዕቃዎች፣ የዳንስ ጫማዎች
ለእኔ. እና ደግሞ ለእያንዳንዳችን በጣም የሚያማምሩ ጣሪያው ስር ላለው ክፍል በደንብ የሚመጥኑ ልብሶች ይዛ ትመጣለች። ልብሶቹ አንዳንዴ ብቻ ልክ
ሲሆኑ በአብዛኛው ግን ወይም በጣም ሰፊ፣ ወይም በጣም ጠባብ መሆናቸው
ችግር አልነበረም: ጫማዎቻችን አንዳንዴ ይመቻሉ፣ አንዳንዴ አይመቹም።እና ቃል እየገባች ሁልጊዜ የምትረሳውን የጡት መያዣ አሁንም እየጠበቅኩ ነው።

በደርዘን የሚቆጠሩ አመጣልሻለሁ" አለችኝ በደስተኛ ፈገግታ “ሁሉንም
መጠኖች፣ ሁሉንም ቀለማት እና ሁሉንም ዲዛይን ትሞክሪያቸውና
የወደድሻቸውንና የሚሆኑሽን ትወስጃለሽ፡ የማትፈልጊያቸውን ለሠራተኞቹ እሰጣቸዋለሁ።” ደግማ ደጋግማ በደስታ ትነግረኛለች፡ ሁልጊዜ ለውሸት ገፅታዋ
እውነተኛ ናት። አሁንም በእሷ ህይወት ውስጥ ቦታ እንዳለን ታስመስላለች።

አይኖቼን እሷ ላይ ተክዬ መንትዮቹ እንዴት እንደሆኑ እስክትጠይቀኝ
እየጠበቅኩ ነው ኮሪ ሁልጊዜ አፍንጫው ፈሳሽ እንዲያመነጭ የሚያደርግ
ጉንፋን እንዳለበትና አንዳንዴ የአፍንጫው ቀዳዳዎች ስለሚታፈኑ በአፍንጫው
መተንፈስ እንደማይችልና በአፉ ብቻ እንደሚተነፍስ ረስታዋለች? በወር አንድ
ጊዜ ለአለርጂ የሚሆን መርፌ መወጋት እንዳለበትና የመጨረሻውን ከተወጋ አመታት እንዳለፉት ታውቃለች: ኮሪና ኬሪ እኔ የወለድኳቸው ይመስል እኔ
ላይ ሲንጠለጠሉ ስታይ አይጎዳትም? የሆነ ነገር ወጥቶ የሆነ ችግር እንዳለ
ይንገራት?

ቢነግራትም እንኳን ደህና ያለመሆናችንን እንዳላየ ነው የምታልፈው ከጊዜ ወደ
ጊዜ ራሳችንን እንደሚያመን፣ ሆዳችንን እንደሚቆርጠን፣ እንደሚያስመልሰንና
አንዳንዴም ኃይል የምናጣ መሆናችንን ብታውቅም ማለት ነው።

“ምግባችሁን ቅዝቃዜ ባለበት ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ አስቀምጡት::አለች ፍንክች ሳትል።

ከዚያ ይልቅ ለእኛ ከእሷ ባርት ጋር ወደ ግብዣዎች፣ ኮንሰርቶች፣ ቲያትሮች፣
ፊልሞችና ዳንስ ቦታዎች ስለመሄድ የምታወራበት ወኔ አላት። “ባርትና እኔ
ለንግድ ትርኢት ኒውዮርክ ልንሄድ ነው፡

እንዳመጣላችሁ የምትፈልጉትን ነገር ንገሩኝ። ዝርዝሩን ፃፉት” አለችን።

“እማዬ ኒውዮርክ ውስጥ ካለው የገና ግብይት በኋላ ወዴት ነው የምትሄዱት?”
ጠየቅኳት የመልበሻው አናት ላይ ወዳስቀመጠችው ቁልፍ ላለመመልከት
ጥንቃቄ እያደረግኩ። ሳቀች። ጥያቄዬ ደስ ብሏታል። እጆቿን አጨበጨበች።ከበአሉ በኋላ ላሉት ቀናት ያላትን ዕቅድ መዘርዘር ጀመረች። “ወደ ደቡብ እንሄዳለን፤ ምናልባት አንድ ወር ወይም ከዚያ በላይ ፍሎሪዳ ውስጥ እንሆን ይሆናል እና አያታችሁ ልትንከባከባችሁ እዚህ ትሆናለች:”

እሷ እያወራች ክሪስ ቁልፉን ሰርቆ ሱሪው ኪስ ውስጥ ከተተው: ከዚያ ይቅርታ ጠይቆ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባ፡ መጨነቅ አልነበረበትም። መሄዱን
ልብም አላለችው በእሷ ቤት ስራዋን እየሰራች ነው ልጆቿን እየጎበኘች።
እና ለመቀመጥ ትክክለኛውን ወንበር ስለመረጠች እግዚአብሔር ይመስገን፡ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ክሪስ ቁልፉን ሳሙና ላይ እያተመ እንደነበረ እርግጠኛ ነኝ: ማለቂያ ለሌላቸው ሰዓታት የምናፈጥበት ቴሌቪዥን ካስተማሩን ነገሮች
አንዱ ይህ ነበር።

እናታችን ከሄደች በኋላ ክሪስ እንጨት አምጥቶ ወዲያውኑ ከእንጨቱ ቁልፍ
መቅረፅ ጀመረ፡ በአሮጌ ሻንጣዎች መቀርቀሪያ ላይ ብረት የምናገኝ ቢሆንም
እሱን የምንቆርጥበትና ቅርፅ የምናስይዝበት ጠንካራ ነገር አልነበረንም። ክሪስ ያንን ቁልፍ ለመስራት ለሰዓታት ደከመ። ሆነ ብለን ጠንካራ እንጨት ነበር
የመረጥነው: ምክንያቱም እንጨቱ ለስላሳ ከሆነ ቁልፍ ማስገቢያው ውስጥ
ይሰበርብንና የማምለጫ እቅዳችን ይከሽፋል: የሚሰራ ቁልፍ እስኪያገኝ ድረስ የሶስት ቀን ስራ ጠይቆታል:

ፍንደቃ የእኛ ሆነች! ተቃቅፈን እየሳቅን፣ እየተሳሳምን፣ እያለቀስን በክፍሉ ዙሪያ ደነስን መንትዮቹ በአንድ በትንሽ ቁልፍ ምክንያት መደሰታችንን በግርምት ይመለከታሉ።

አሁን ቁልፍ አለን፡ የእስር ቤታችንን በር መክፈት እንችላለን፡ ሆኖም በሚገርም ሁኔታ ከሚከፈተው በር ባሻገር ያለውን የወደፊታችንን አላቀድንም።

“ገንዘብ፣ ገንዘብ ሊኖረን ይገባል” አለ ክሪስ ድል የምናከብርበትን ዳንስ
አቋርጦ

ብዙ ገንዘብ ካለን በሮች ሁሉ ክፍት ናቸው መንገዶች ሁሉ ልንሄድባቸው
የእኛ ናቸው:"

ገንዘብ ከየት ማግኘት እንችላለን?” ስል ጠየቅኩት: አሁን ተከፍቻለሁ።ለመቆየት ሌላ ምክንያት ስለተገኘ:

“ከእናታችን፣ ከባሏና ከአያትየው ከመስረቅ በስተቀር ሌላ አማራጭ የለንም” ሲናገር ሌብነትን ልክ የጥንትና የተከበረ ሙያ አስመስሎት ነበር። በጣም
አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ምናልባት የተከበረ ሙያ ይሆን ይሆናል… ወይም ነው።
👍34🥰4
ከተያዝን ሁላችንም እንገረፋለን፤ መንትዮቹም እንኳን” አልኩ አይኖቼን
የፈሩ ገፆቻቸው ላይ ተክዬ: “እና እናታችን ከባሏ ጋር ጉዞ ስትሄድ እንደገና
ልታስርበን ትችላለች ሌላ ምን ልታደርግ እንደምትችል ደግሞ እግዚአብሔር
ነው የሚያውቀው”

ክሪስ ከመልበሻ ጠረጴዛው ፊት ያለ ወንበር ላይ ተቀመጠ፡ አገጩን በእጁ
ደግፎ ለደቂቃዎች እያሰበ ቆየ: “በአንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ። አንቺም ሆንሽ መንትዮቹ ስትቀጡ ማየት አልፈልግም ስለዚህ ወጥቼ የምሰርቀው እኔ
ነኝ። ድንገት ከተያዝኩ ጥፋተኛው እኔ ብቻ እሆናለሁ: ግን አልያዝም።
ከዚያች አሮጊት መስረቅ አደገኛ ነው በጣም ተጠራጣሪ ናት፡ ቦርሳ ውስጥ ያለውን ገንዘብ መጠን ሳንቲሙን ሳይቀር እንደምታውቅ ጥርጥር የለውም እናታችን ግን ገንዘቧን ቆጥራ አታውቅም: አባታችን እንዴት ይወቅሳት
እንደነበረ ታስታውሳለህ?” በማረጋገጥ ፈገግ አለልኝ፡ “ልክ እንደ ሮቢን ሁድ....

ይቀጥላል
👍2312
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ሶስት ፡ ፡ #ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ ...“ተነሽ ልጆቹ ቲቪ ላይ ብዙ ከማፍጠጣቸው የተነሳ አይናቸው ሳይጠፋ ወደታች እንሂድ” አለኝ... ስነሳ ስላመመኝ አገዘኝ በክንዶቹ ውስጥ አስጠግቶ ስለያዘኝ ጉንጬ ደረቱ ላይ ነበር ከእሱ በፍጥነት ቢያላቅቀኝም እኔ ግን ጥብቅ አድርጌ ይዤው ነበር። “ክሪስ አሁን ያደረግነው ኃጢአት ነው? እንደገና ጉሮሮውን አፀዳና …»
በህይወት መንገድ ላይ……(የመጨረሻ ክፍል)
ምዕራፍ-11
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
//
ከሩቅ መዳረሻ ስባክንና ስዳክር ከርሜ በስንት መቧጣጥ ከገባውበት ጥልቀት ፀጥታ ተመንጭቄ በመውጣት አይኖቼን ስገልጥ እራሴን ያገኘውት አንድ ሆስፒታል አልጋ ላይ እንደተገነዘ እሬሳ ተዘርግቼ በአፍንጫዬ እና በእጆቼ ላስቴኮችና ቱቦዎች ተሰካክተውልኝ ነበር፡፡ተአምር ነው ከዛ ግዙፍ መቃብር በሰላም ወጥቼያለው እንዴ.?አዎ ክፍል ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ በግልፅ ይታየኛል፡፡ አንገቴን አንቀሳቅሼ ዙሪያዬን ሰቃኝ ከአምስት ሰዎች በላይ በክፍል ውስጥ ከእኔ ራቅ ባለ አግዳሚ ወንበር ላይ ተደርድረው ይታዩኛል፡፡መንቀሰቀሴን ሲያዩ ሁሉም ከተቀመጡበት በደስታ በርግገው ተነሱ፡፡
እህቴ ‹‹ዶክተር.. ነቀቷል..ወንድሜ ነቅቷል.. ›› .እያለቸች በፍንጠዛ ወደውጭ ሮጣ ሄደች....እናቴ በእርጋታ ወደእኔ እየተራመደቸ እንባዋ በጉንጮቾ ስታረግፍ ተመለከትኳት…መቼስ የደስታ አንባ ነው እያነባች የለችው….አይ የእናት ነገር ችግር ላይ ስንወድቅ በሀዘን ምክንያት አልቅሳ ከችግር ስንወጣ በደስታ አልቅሳ ፡፡
ሁለት ወንድሞቼ በቆሙበት በስስት እያዩኝ ፈገግ አሉልኝ…ፈግታቸው ብሩህና አንፀባራቂ አይደለም..ከጀርባው የሆነ ጥቁር ሀዘን የተደበቀበት መፈገግ ነው፡፡አዎ እንደዛ ነው የተሰማኝ፡፡ ከእነሱ ጎን ያለች አንድ ሴት በርከክ ብላ የሆስፒታሉን ለመርገጥ እንኳን የሚቀፍ ቆሻሻ ወለል ሳመች.፡፡እኔን ለማረኝ አምላክ ምስጋና ማቅረቧ እንደሆነ ገባኝ ..ማነች ይሀቺ ሴት..? አዎ እጮኛዬ ሰናይትን ነበር ትሆናለች ብዬ የጠበቅኩት ...ከተንበረከከችበት ተነስታ ስትቆም ግን እሷ አለመሆኗን በደንብ አጠርቼ አየዋት..የመከራ ጊዜ ጓዴ የጭነቀት ቀን መደገፊያዬ የነበረችው አይዳ ነበረች…፡፡እሷ በቆመችበት ቦታ ፈቅረኛዬ ሰናይትን ማየት ሲገባኝ እሷን በማየቴ አልከፋኝም እንደውም በተቃራኒው በጣም ደስ ነው ያለኝ…አዎ በዚህ ህይወት ሁለተኛ እድል ተሰጥቶኘ አይኖቼን በገለጥኩበት ቅፅበት እናቴንና አይዳን ፊት ለፊት በማየቴ ደስታዬ ሙሉ ሆነ፡፡
እህቴ ዶክተሩን አስከትላ መጣች
‹‹‹ምንድነው እንዲህ የከበባችሁት? አንዴ ወደውጭ›አለ ኮስተር ብሎ፡፡ዶክተሩን ተከትላ የመጣችው ነርስም ሁሉንም እንደማዘዝም እንደመግፋትም እያደረገች ከክፍሉ ውጭ አስወጣቻቸውና ክፍሉ ዘጋች፡
ዶክተሩ በነፃነት አገላብጦ መረመረኝ….
‹‹ኢንጂነር አሁን በጥሩ ጤንነት ላይ ትኛለህ..እንግዲህ በአእምሮም ጠንከር ማለት ነው ሚጠበቅብህ..በዚሁ ከቀጠልክ በሳምንት ውስጥ ሙሉ በሙሉ አገግመህ ወደቤትህ ትገባለህ››አለኝ እና አፌ ውስጥ ያሉትን ቱቦዎች በመነቃቀል እጄ ላይ ያሉትን ባሉበት ትቶ ነርሷን አስከትሎ ወጣ..
እነሱ ከወጡ ከደቂቃዎች ቡኃላ እናቴ ብቻዋን መጣች…አሁንም የሚፈሰው እንባዋ እልነጠፈም…
‹‹ብችዬ የእኔ ጌታ…..››ግንባሬን ፤ጉንጬን እጆቼን እያገላበጠች ሳመቺኝ
እንደምንም አንደበቴን አለቀቅኩና‹‹..እማ አሁን እኮ የመከራው ጊዜ ሁሉ አልፎል..አይኝ እስኪ አሁን ፍፅም ጤነኛ ነኝ ..ድካም ነው እንጂ ድኛለወ..ዶክተሩም በቀናቶች ውስጥ ወደቤት እንደሚሄድ ነገሮኛል፡
‹‹አዎ ልጄ…የእኔ ጠንካራ ልጅ..ምንም እንዳታስብ …እኔ እናተህ በሀይወት እያለው እንባ በአይኖችህ ላይ አይፈሱም….ልክ እንደልጅነትህ እኔ ጠብቅሀለው..ልክ እንደልጅነትህ እኔ እንከባከብሀለው…አለም ሁሉ ጀርባዋን ብትሰጥህ እራሱ አኔ እናትህ ግን ሁሌ ከጎንህ ነኝ.››
‹‹እንዴ እማ!! እንዳለቅስ እያደረግሺኝ ነው እኮ….ለመሆኑ አሁን የት ነው ያለነው?፡፡››
‹‹አዲሰአባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ነው››
‹‹እ..ቆየን እንዴ?››
‹‹አይ ብዙም አልቆየንም ..ዛሬ 11 ኛ ቀንህ ነው፡፡››
‹‹11 ቀን ሙሉ እራሴን ስቼ ነበር…?አይ አማ ልጅሽን ጠንካራ አድርገሽ አላሳደግሺውም ማለት ነው፡››
‹‹ትቀልዳለህ .ሶስታችሁም ነበር እኮ እራሳችሁን የሳታችሁት…ወዲያው ከዋሻው መውጣት እንደቻላችሁ በአንቡላንስ ወደእዚህ ነበር ይዘናችሁ የመጣነው..ወንድዬው በሶስተኛወ ቀን ድኖ ወደቤቱ ተመለሰ .ሴቲቱ ለመንቃት አመስት ቀን ፈጀባተት.ግን ቡኃላ ብትድንም እሱ ሳይነቃ ወደቤቴ አልገባም ብላ ይሄው ከእኛ ጋር ሆስፒታል በረንዳ እያደረቸ እስከዛሬ አለች…ቤተሰቦቾ ቢለሙናት፤ ቢቆጦት አልሰማችሁም አለቻቸው››
ፈገግ አልኩ ፤ይህንን በመስማቴ ደስማ አለኝ‹‹አይዳ .በጣም ጥሩ ልጅ ነች…ሰላም መሆኗን በማየቴ ደስ ብሎኛል›
ነግግሬን እናቴ ደገፈች ‹‹ኸረ ከጥሩም በላይ ነች….ያቺ ቀበጥ እጮኛህ ከአንድ ቀን በላይ መች እዚህ እግሯ ዝር አለ…አረ ተውኝ እስኪ ልጄ ...ብቻ ዋናው ያንተ መትረፍ ነው…አሁን በል ሌሎቹም ሊያዩህ ስለሚፈልጉ ወረፋ ልልቀቅላቸው.ዶክትሩ በየተራ ግብ ብሎ አስጠንቅቆናል›አለችና ግንባሬን ስማ ወደበሩ እርምጃ ስትጀምር
‹‹እማ›› ስል ጠራዋት
‹‹አቤት ቡቻዬ››
‹‹ቅድሚያ አይዳ ትግባ››
እማዬ የነገር ፈገግታ ፈገግ አለችና ‹‹እሺ …እንደዛ አደረጋለው››ብላ ወጥታ ሄደች
አይዳ እስትገባ አተራረፋችንን በምልስት ማስታወስ ጀማርኩ...በወቅቱ እዛ ጨለማና የታፈነ ዋሻ ውስጥ እኔና አይዳ በሚቦን አቧራና በሚቆረቁር አለት መሬት ላይ ጎን ለጎን ተቃቅፈን ተኘተን ፍቅር ፍቅር ስንጨወት ነበር አምስት የሚሆኑ የጧፍ የመሰሉ መብረቶች ወደእኛ ሲቀርብ ያየነው.ከዛ ድምጽ ሰማን…ከድምጾቹ መካከል የበሪሁን ለየነው›
‹‹አይዳ አላችሁ….?አይዳ ይሰማል?››
‹‹በሬ አለን...ሰው አገኘህ እንዴ?››እያየች እራሱ ባለማመን ጠየቀችው፡፡
‹‹አይ እንሱ ናቸው ያገኙኝ ››በዚህ ጊዜ ስራችን ደርሰው ነበር ፤ከእሱ ሌላ አራት ሰዎች ይታዩኛል…አራቱም የመነኩሴ አደፍ ያለ ባለ ቢጫ ቀለም ረጅም ቀሚስ የለበሱና በጭንቀቅላታቸው ድፍን ቆብ የደፉ ናቸው፡፡
‹‹የተጎዳው እሱ ነው? ›ሲሉ ጠየቁ አንደኛው አዛውንት ወደእኔ አጨንቁረው እየተመለከቱ፡፡
‹‹አዎ አባቴ እሱ ነው››በሪሁን አንጀት በሚበላ ለስላሳ ደድፅ መለሰላቸው
‹‹ምኑ ላይ ነው?››
‹‹ይሄው ይሄን እግሩን ነው››በሆነ ተአምር ነካ ነካ አድርገው ያድኑኘ ይመስል በጉጉት በጣቷ ቦታውን እየጠቆመች አሳየቻቸው፡
.በርከክ አሉና ጨርቁን ገለጥ አድርገው ሊያዩት ሞከሩ….ዝግንን አላቸውና መልሰው ሸፉኑት…..በሉ ይህቺን እንደምንም መክሩ ብለው ዳቤና(ገዳማዊያን የሚጠቀሙት የምግብ አይነት) በኮዳ ውሀ አደሉን
‹‹…ውሀውን ጉሮሮችሁን ብቻ ለማርጠብ ተጠቀሙበት …ካለበለዚያ ያማችሆል›› ብለው አስጠነቀቁን..፡፡ሁላችንም ድስ አለን፡፡ደስታችን ግን ስሜታችንን አውጠተን መግለፅ አልቻልንም...ሁኔታው ድንገተኛ እና ከግምታችን ውጭ ስለሆነ ህልም ውስጥ ያለን ነው የመሰለን፡፡አንዳሉን ውሀውን ብቻ ሳይሆን የሰጡንን ምግብ እራሱ ከመቅመስ ያለፈ እንደግምታችን መብላት አልቻልንም..ጥርሳችን ማኘክ፤ምላሳችን ማላመጥ ፤ጉሮሮችንም መዋጥ እረስቷል፡፡
‹‹ግን እንዴት አገኛችሁን ?››እኔ ነኝ የጠየቅኩት፡፡
አንድ ወጣት ሴት ነች …ጎደኛቼ በሞትና በህይወት መካከል እያሉ ነው ጥያቸው የመጣውት›› ብላ የነገረችን›
👍161
‹‹ሰላም ነች..አዎ በህይወት አለች ማለት ነው››
ይህንን በመስማታችን ሁለችንም ፈነጠዝን፡፡
‹‹አሁን እሷ ወጥታለች?››ተየኳቸው
‹አናውቅም ልጄ …ያገኘችን ዋሻ ውስጥ ነው...ሁኔታውን ነግራን እንደጨረሰች ተሰወረችብን…አውሬ ይተናኳለት ወይም በራሷ ጉዞ ትቀጥል አናውቅም፡፡››
‹‹አይ ተወት እሷ እንደዛ ነች..ለማንኛውም ነፍስችንን አዳነችልን…እና አሁን ቶሎ ከዚህ ዋሻ እንወጣለን ማለት ነው አይደል?፡፡ለመሆኑ በየት በኩል ነው የምንወጣው.?..አይዳ ጠየቀች፡፡
‹ልጄ ከመውጫው የአንድ ቀን መንገድ ተጉዘን ነው እዚህ የደረስነው..የምንወጣው በየረር ተራራ ባለ የዋሻ መውጫ ነው..አሁን ስንመለሰ እናንተ ሰለደከማችሁና እሱም የተጎዳ ስለሆነ ምን አልባት እስከሁለት ቀን ሊወስድብን ይችላል፡ቢሆን አይዞችሁ ቢዘገይም ከእግዚያብሄር ጋር እናድናችሆለን›፡››አሉን ብሩህ ተስፋ ሰጡንና ለጉዞ መዘጋጀት ጀመሩ..ይዘውት ከመጡት ጓዝ መካከል አንድ የሻራ ቃሬዛ አወጡና በመዘርጋ እኔን በጥንቃቄ ተረዳተው በማንሳት እላዩ ላይ አስቀመጡኝ ..ከፊትና ከኃላ ተሸክመውኝ ጉዞ ጀመርን..ብዙም ሳይቆይ ብዥ እያለብኝና እያጥወለወለኝ መጣ ..ከዛ ቀስ በቀስ እየጠፋው እየጠፋው እራሴን የሳትኩ ይመስለኛል…በዚህ ምክንያት እንዴት እንደተጓዝን ?ከዋሻው ለመውጣት ስንት ቀን እንደፈጀብን? ምንም ማውቀው ነገር የለም..ደግሞም እንኳንም አላወቅኩ፡፡
የአይዳ ወደውስጥ መግባት ነው ሀሳቤን አንዳቆርጥ ያስገደደኝ….አዎ አሁንም ሙሉ በሙሉ አገግማለች ባይባልም ግን ለመጨረሻ ቀን ካየዋት ጋር ሳነፃፅር 12 ክንፎች ያሏት መላአክ መስላለች ማለት ይቻላል…በፅዳት የተያዘ እና ተበጥሮ ትከሻዋ ላይ የተኛ ፀጉሯ…በእንባና በአቧራ ያልተበከለ ንፅህ ፊት….ማራኪና ከሰውነቷ የሚስማማ ብራንድ ቀሚስ..
ተንደርድራ መጥታ ደረቴ ላይ ተለጠፈችብኝ ..‹‹ፈርቼ ነበር..የማጣህ ተሆነ ምን ይውጠኛል ብዬ ስጨነቅ ነበር…ደህና ስለሆንክ በጣም እድለኛ ነኝ…በጣም ነው የናፈቅከኝ››አለቺኝ
‹‹እኔም በጣም ነፍቀሽኛል .ግን ካንቺ በላይ እነዛ ከተቀዳደደው ቲሸርትሽ ሾልከው ሲደንሱ የነበሩ ጡቶችሽ ናቸው የናፈቁኝ››አልኩና ቀለድኩባት፡፡
ሳቀች …ከተኛችበት ተነሳችን ቆመች….ወደ በራፉ ሄደችና ክፍሉን ከውስጥ ቆለፈችው.‹‹.ልጅቷ ምን ልታደርግ ነው.?.ግራ አጋባችኝ…እጆቾን ወደኃላ ጠምዝዛ አዞረችና የቀሚሶን የኃላ ዚፕ ፈታች…ከዛ ቀሚሶን በግማሽ ወደታች አወለቀቸችና የጡት ማስያዣዋን ፈታች..
‹‹አዎ ንጽትና ጥርት ያሉ እንደሚዳቆ ገልገል መንታና ድድር ጠቶቾ ፊት ለፊቴ ተጋረጡ ››
‹‹አሁን ነፍሴ መለስ አለች….ጡቶቾሽ ናፍቄያቸው መሰለኝ እየተንቀጠቀጡ ነው ›አልኩ
‹‹አዎ በደንብ›› አለችና ያወለቀችውን መልሳ ላበሰች
‹‹የእኔ ፍቅር ..ማንም ከጎንህ ባይኖር ምንም አትጨነቅ..እኔ በማንኛውም ነገር ከጎንህ ነኝ..ሚስትም ከፈለክ ፤ውሽማም ካሰኘህ ሳትሳቀቅ ጠይቀኝ...የፈለከውን ሆንልሀለው››
‹‹እሺ ጠይቅሻለው… ግን ምንድነው እንቺም እማዬም ንግግራችሁ የፉክክር ይመስላል.. በዛ ላይ ክርር ያለ ነው?››
‹‹አረ ከእናትህ ጋርማ አልፎካከርም..ከእሳቸው መልስ ማለቴ ነው…በሆነው ነገር ሁሉ እንዲች እንዳይሰማህ..ዋናው በህይወት መትረፍህ ነው፡፡ትንሽ ቀን የህይወትህን አቅጣጫ እስከታስተካከል ድረስ ቢከብድህ ነው፡፡ከዛ ነገሮች እንደውም የተሻሉ ሊሆኑ ይችላሉ…በማንኛውም ነገር እስከመጨረሻው ከጎንህ መሆኔን እወቅ››አለችኝ …ንግግሯ አስፈራኝ .ምሬት እና ቁጭት ያለበት ኮስታራ ንግግር ነው..፡:፡
‹‹ምነው? የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ?››
‹‹ኸረ ከእግርህ ውጭ ሁሉ ነገር ሰላም ነው››
‹‹ከእግርህ ውጭ…?እግሬ ምን ሆነ? ምኔን እንደታመምኩ እራሱ እስከአሁን ዘንግቼው ነበር…ከወደታች ምንም ህመም እየተሰማኝ አይደለም…ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ..?ያ ሁሉ ጥዝጣዜ የት ሄዴ…?እነዛ ሁሉ ትሎች የቦጫጨቁት ቆዳዬ እንዴት እንዲህ ሰላማዊ ሆነ ? …ውስጤ ፈራ ‹‹…ቆይ ከመሄድሽ በፊት ደግፈሽ አንሺኝ››
ፈራ ተባ እያለች‹ለምን ምን ፈለክ?››
‹‹ዝም ብለሽ እንሺና አስቀምጪኝ››
ከጀርባዬ ሆና ደገፈቺኝ… እንደምንም ብዬ ቁጭ አልኩ…ነጸ የሆነውን ግራ እጄን በዝግታ ወደታች ሰደድኩ..ቀኝ እግሬ..ከግልበቴ ትንሽ ወረድ ብሎ ተጎምዷል…እነዛ የምወዳቸው የእግር እጣቶቼ የሉም..ከአሁን ቡኃላ መሮጥ አልችልም...ከአሁን ቡኃላ በጅምር ህንፃ ላይ በእንጨት በተሰራ መወጣጫ ከአንዱ ፎቅ ወደሌላው ፎቆ እየተስፈነጠርኩ ስራ መስራት አልችልም፤
ምንም አልባት የቢሮ መሀንዲስ ልሆን እችል ይሆናል ፤ግን በምንም መልኩ ህይወቴ ቀላል አይሆንም..ሁሉ ነገር ግልፅ ሆነልኝ.የእናቴ እርብትብት ንግግር፤ የአይዳ መንሰፍሰፍ…የወንድሞቼ የቅድም አስተያየት.. የዛች እጮኛ ተብዬ ብን ብሎ በዛው መቅረት..አዎ ለእሷ በክራንች ሚራመድ ሙሽራ ከጎኖ አድርጋ በእድምተኞች ፊት ከምትታይ ሞት ይሸለታል…እሷን እንኳን .ተገላገልኳት፡፡
‹‹ደነገጥክ እንዴ..?ምንም የሚከብድ ነገር የለም ፤ዋናውን እግርህን ልመልስልህ ባልችልም በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ አለ የተባለ አርቴፊሻል እግር አስተክለልሀለው..እውነቴን ነው..እናም ደግሞ ከዛ በላይ ከጎንህ ሆኜ አንከባከብሀለው››
ፈገግ አልኩ‹‹አይዳ››
‹‹አቤት››
‹‹ለሁሉ ነገር አመሰግናለሁ ...አሁን ደክሞኛል ልተኛ››አልኳት
‹‹እሺ ተኛ ›› አለችና ወደቦታዬ መለሰቺኝ፡፡
‹‹ስትወጪ ዝጊው ...ሌሎቹን ቡኃላ አነጋግራቸዋለው…አሁን እንቅልፌ መጣ›› እልኩና አይኖቼን ጨፈንኩ..የእውነት እንቅልፌ መቶ ሳይሆን አይኖቼን ገልጬ ዙሪያዬን ማየት እራሱ ስለፈረው ነው፡፡በመትረፌ ምክንያት በውስጤ ተፈጥሮ የነበረው ፈንጠዝያ አሁን እንደጉም በመብነን ወደ ሰማይ እያረገ ነው፡
ተፈፀመ

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️❤️❤️
👍305😢3