አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስምንት ፡ ፡ #ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ በመጨሻ እኖታችን እኔና ክሪስ በግርፋቱ ቀን በመሀከላችን ስለተፈጠረው ነገር በፍፁም አላወራንም በአብዛኛው አተኩሮ ሲመለከተኝ እይዘዋለሁ፧ ግን አይኖቼ አይኖቹን ሲመለከቱ አይኖቹን ያሸሻል እኔም ሳየው ከያዘኝ አይኖቼን ወዲያው እመልሳለሁ። እኔም እሱም በየቀ እያደግን ነው፡ ጡቶቼ ሙሉ ሆነዋል። ዳሌዬ ሰፋ ብሎ ወገቤ…»
በህይወት መንገድ ላይ....
(ታጋቾቹ)
ምዕራፍ-6
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
////
አስቤዛችን ሆነ ውሀችን በናዳው ተቀብሯል።
"በትክክል ምን ይሻላል የሚለው ጥያቄ መጠየቅ ያለበት አሁን ነው?"አልኩ ከልቤ አዝኜ እና ደንግጬ…..
በሪሁን "ማን ሊመልሰው?"አለ ከፊቱ ላይ አባረውን እያራገፈ፡፡
"እንኳንም እሙሙዬ ሳትደፈን ተረፈች እንጂ ጥያቄውን እንደፈረደብኝ እኔ እመልሳለሁ … እራሳችንን እንደምንም ነፃ እንዳደረግን ሁሉ በተመሳሳይ ቢያንስ ግማሽ እቃችን ማለቴ ምግባችን፤ ውሀችንና መቆፈሪያ ብረታችንን ነፃ ማውጣት አለብን
"
ከዛስ?
"ከዛ ቀጥሎ ያለውን እናስብበታለን"
እኔ ስከራከር በሪሁንና ጋሽ አህመድ በሀሳቧ ተስማምቶ ስራ ጀምረዎል…..አረ ሰላምም እያገዘቻቸው ነው?
"ኢንጂነር ያንተ እጅ ለወርማፕ እንጂ አፈር ለመግፈት አይሆንም አይደል?"በአሽሙር
በሪሁን"ምነው የእኛ ለወርማፕ አይሆንም እያልሽ ነው?"አላት …ለእኔ የወረወረችው አሽሙር እሱን እንደነካው በሚያሳብቅ ቅላፄ
"ያው ለጫወታው ድምቀት ብዬ እንጂ እሱማ አሁን ለምሳሌ እኔን ብትጠይቁኝ ....ደልደል፤ ጠንከር ፤ሻከር ያለ መዳፍ በሰውነቴ ላይ አርፎ ሲዳብሰኝ... ሲጨምቀኝ... ሲሸረክተኝ... ሲያቆስለኝ ..ሲያደማኝ...ዋው ተው ባክህ አሁን አሁን መስሎኝ በጉጉት ሙሙዬ ረጠበች"

እሷ ብቻ አይደለችም ጋሽ አህመድን ጨምሮ ሶስታችንም ወንዶች አፍችንን ከፍተን ነበር እያዳመጥናት የነበረው...ሰላም ብቻ ነች በማይነበብ ስሜቷ አንደበቷን ቆልፋ አንገቷን አቀርቅራ ስራዎን በመስራት ላይ ያለችው....ለማንኛውም ከአንድ ሰዓት በላይ በፈጀ የጋራ ትግል መቆፈሪያና ቢላዎቻችንን ጨምሮ ግማሽ ራሽናችንን በእጃችን አስገባን
"so what now?"
"ዌል እንግዲ...አሁን ሬሽናችን እንደየአስተዋፅኦችን ይታደለንና እናገግም"
‹‹ከዛ ቡኃላስ?››
‹‹ሲደርስ እንነጋገርበታለን››
" ወደሰላም ሬሽኑ ቀረበ..እሷም በአይነትም ሆነ በመጠን ሳታዛንፍ ለሁላችንም የምንቀምሰውን አደለችን"
"አንቺ ሶሻሊስት የሆንሽ ልጅ...እንዴትና በምን ስሌት ነው በርዬና ኢንጂነሩ እኩል ድርሻ የሚደርሳቸው?"
ሰላም ፈገግ ብላ ዝም አለች...እኔም ከእሷ ጋር እንካ ሰላምታ ስላላሰኘኝ አርፌ በዝምታ የተሠጠችኝን ብስኩት በውሀ እያወራረድኩ መኮርሸሜን ቀጠልኩ....ዞር ዞር ብዬ ስመለከት ሁሉም ምግብን ጨርሷል ።ከጀርባዬ ወዳለችው አይዳ ዞሬ ..."እሺ..ከሁንስ..?››ስል እሷ የለችም።ልክ ሳባና ቢች ዳር እንዳለች ሰላማዊ ኮረዳ ለሽ ያለ እንቅልፍ ወስዷታል።
"ታድለሽ "አልኩና እኔም ባለውበት ወደኃላ ልክ እንደእሷ ጋደም አልኩ...በጣም ደክሞኝ ስለነበር ወዲያው ነው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰደኝ።
ከእንቅልፌ ስባንን ከሰላም በስተቀር ሁሉም በየቦታው ፍግም ብሎ ተኝተዋል።ሠላም ግን እደተለመደው ልክ እንደብድሀ መለኩሴ እግሮቾን አንድ ላይ አቆላልፋ ና አጣጣጥፋ እጇቾን አንድ ላይ አድርጋ ወደ ግንባሯ አድርጋ በተመስጦ ጠፍታለች።
"ነቀነቅኩና አይዳን አስነሳዎት...በዝግታ አይኖቾን ገለጠችና"ምነው ነጋ እንዴ?"አለችኝ
"ቀልደኛ ነሽ ምን መምሸትና መንጋት አለ?"
"ውይ እቤቴ ያለው መስሎኝ"
"አንቺ እቤትሽ ብትሆኚ እኔ ከጎንሽ ምን እሰራለው?"
"እኔም የገረመኝ እኮ እሱ ነው....አሁን አይኖቼን አጨንቁሬ ከፍቼ አንተን ሳይህ ከአልጋዬ ፊት ለፊት ቆመህ ሽታው የሚያውድ ምርጥ እንቁላል ፍርፍር ቁርስ ሰርተህ..‹ውዴ ተነሽ ቁርስ ደርሷል..በገዛ እጇቼ በፍቅር ያበሰልኩት ስለሆነ ልዩና ጣፋጭ ነው..እባክሽ ተነሽ ላጉርስሽ › በማለት እየለመንከኝ መስሎኝ ምን ሰይጣን አሳስቶኝ ይሄን ሰው አገባው ብዬ ስበሳጭ ነበር"
ምናወራው ሠላምን እንዳንረብሻት በለሆሳሳ ነው
"ጥሩ ታልሚያለሽ ባክሽ!!!ጭራሽ እኔን ማግባት ሲያስቆጭሽ...?በይ አሁን ንቂና ወዳለሽበት አሳዛኝና ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ቀልብሽን መልሰሽ ወንዷቹን ቀስቅሺያቸውና አንድ ነገር እናድርግ"
ከ10 ደቂቃ ብኃላ ሠላምም ፀሎቷን ጨርሳ እነበሪሁንም ከእንቅልፋቸው ተነስተው ሁላችንም ተፋፍገን ለውይይት ተቀመጥን።
"ምንድነው የምናደርገው...አሁን ከላይ ቆፍረው ያወጡናል የሚለው ተስፋችን ሞቷል....ብንተርፍም ብናልቅም በራሳችን ጥረት ነው የሚሆነው።"እኔነኝ የመወያያ ርዕስ ያቀረብኩት።
"ይሄንን ቆፍሩት"ሠላም ነች ተናጋሪዎ
"ምን? "የንግግሯ እርግጠኝነት እኔን ግራ አጋባኝ
"አዎ መውጫ መንገዳችን በዚህ እንደሆነ ጠንካራ ስሜት ተሠምቶኛል....ግዴላችሁሞ እንቆፍር"
"እንደምንተርፍ ታምኚያለሽ ማለት ነው?"
"ሁላችንም ላይሳካልን ይችላል ግን ከአምስታችን አንዳችን እንኳን ተርፈን ህይወት ሌለ እድል የምትሰጠን ከሆነ ሊሳካልን የሚችለው በዚህ መንገድ ስንጓዝ ነው።"
"በእውነት ድንቅ የሆነ ተስፋ አስቋራጭ ንግግር ነው ያደረግሽው...አሁን ሁላችንም በውስጣችን ተራፊው አንድ ሰው ከሆነ ያ ሰው እኔመሆን አለብኝ እያልን ከራስ ወዳድነታችን ጋር እንድንፋለም እያደረግሽን ነው"
"እኔ ደግሞ ተራፊው አንድ ሰው ከሆነ ያ ሰው እራሷ ነች እያልኩ በውስጤ እያሰብኩ ነበር?››አልኩ በእውነት ያሰብኩትን ነው የነገርኳቸው
"ለምን እንደዛ ልታስብ ቻልክ?"አለቺኘ ሰላም
"ያው የታወቀ ነው ከእኛ በተሻለ ከእግዜያብሄር ጋር ቀረቤታው ስላለሽ..."
"እና በዛ የተነሳ ለእኔ የተለየ ፌቨር እንደሚያደርግ ገመትክ.."
"በርግጥም እንደዛ ነው ያሠብኩት"
"ይገርመኛል.. ብዙ ሰዎች እግዚያብሄርን የሚያስብት በሰው ሚዛን ነው?እነሱ ቢሆኑ የሚያደርጉትን እሱም የሚያደርግ ይመስላቸዋል...ለማንኛውም እኔ አንድ ሰው ብቻ ይተርፋል አላልኩም...ስንት ሰው እንደሚተርፍ እርግጠኛ አይደለሁም"እርግጠኛ የሆንኩበት ሁለት ጉዳይ ግን ንገሪን ካላችሁ ልንገራችሁ››
"ንገሪን..ንገሪን"
"አንደኛ ሁላችንም ከዚህ ዋሻ በህይወት አንወጣም....ሌላው ከማይወጡት ውስጥ ደግሞ እኔ አንዷ እንደሆንኩ በእርግጠኝነት አውቃለው ።››
"ምን እያልሽ ነው? ታዲያ እንደምትሞቺ እያወቅሽ...ምን አስለፋሽ?››አይዳ ነች የእኛንም ጥያቄ የጠየቀቻት
"ከእዚህ እንደማልወጣ እርግጠኛ ነኝ አልኩ እንጂ በመሞቴ እርግጠኛ ነኝ አላልኩም።ሌላው ደግሞ በዚህ ወጥመድ ውስጥ ከመውደቃችን በፊትም እኮ ሁላችንም አንድ ቀን ሞቾች እንደሆን እያወቅን ግን ተስፋ ሳንቆርጥ የእየእለት መከራችንን ለማቃለል ከመጣር ወደ ብለን አናውቅም፡፡ስለዚህ አሁን ክርክሩን እና ጭቅጭቁን አቁመን መቆፈረ ብንጀምር የሻላል

"አምንሻለው"አለና መቆፈሪያውን በማንሳት ስንጥቁን ለመስፋት መቆፈር ጀመረ "የተከራከረ ሰው አልነበረም..ላባችን ጠብ እስኪል ድረስ ለሁለት ሰዓት ለፍን ..ከዛ ቀጠን ያለ ሠው ታኮ ማሾለክ የሚያስችል ክፍተት አገኘን...ማን ቀድሞ ይሹለክ?ከሾለክን ብኃላ ምንድነው የሚያጋጥመን...? እርግጠኛ ነኝ በሁላችንም አእምሮ እየተመላለሠ የሚያስጨንቀን ጥያቄ ነበር"
"ያው መቼስ ጉድጓድ በእኔ ልክ የቆፈራችሁት ቀድሜ እኔ እንዳልፍ ነው... ያ ዘንዶ አፍን ከፍቶ የሚጠብቀኝም ከሆነ ከወዲሁ ሰላም ሁኑ"አይዳ ነች
👍221
"አረ ተይ ስለትሽንማ ሳታደርሺ በዘንዶ መበላት የለብሽም"አላት በሪሁን
ቀሚሶን ወደላይ ሰብሰብ እንደማድረግ ብላ"እሺ ና ግባ ትንሽ ሰጥቼህ ልሂድ"አለች..ከእኔ በስተቀር ሁሉም በንግግሯ ፈገግ አሉ
"ምትሄጂ ከሆነ ጊዜ አታባክኚ ይሄው ባትሪ ሂጂና ያለውን ነገር ንገሪን"እኔ ነኝ ብስጭትጭት ብዬ የተናገርኩት
ምንጭቅ አድርጋ ባትሪውን ተቀበለችኝ..."ምን አለ ሰጥቼው ብሞት …?ቅናት ነው አይደል.? አንተ ልጅ ጭኔን ከደባበስክ ብኃላ ስለእኔ ያለህ ፍላጎት እየተቀየረ ነው...ነግሬሀላው ብኃላ ፍቅር ይዞህ እንዳትሰቃይ.. ለማንኛውም ቢላዎንም ስጡኝ "
ጋሼ አህመድ ፈጠን ብሎ አቀበላት..ሠላም ተንደርድራ አቅፋት ጉንጮን ሳመቻትና….አምላክ ካንቺ ጋር ነው እንዳትፈሪ"አለቻት
አይዳ ለመሹለክ አንገቷን ወደቆፈርነው ጉድጓድ አሰገገች... ደስ አላለኝም.."እሷ ሳትሆን ሌላ ሰው ነው ቅድሚያ መግባት ያለበት?ካልሆነ ካልሆነ እኔም ብቀድም ይሻል ነበር..አደጋ ቢያጋጥማትስ?..".በውስጤ የተርመሰመሰ የስጋት ሀሳብ ነው"ምን እየሆንኩ ነው ..?.እጠላት የለ እንዴ? ነው ወይስ እሱ ከምድር በላይ የነበረ ያለፈ ታሪክ ይሆን?እናም እሷ እንዳለችው በእሷ እየተሳብኩ ይሆን?መቼስ ከእሷ ፍቅር ከያዘኝ በራሴ አመት ነው የምስቀው…. (አምላክ የምስቅበት ተጨማሪ ጊዜ ከሰጠኝ ማለቴ ነው።) ሀሳቤን ሳልጨርስ እሷ ሾልካ ከእኛ ተለይታለች..
"እ ምን ይታይሻል..?"
"ቆይ እስኪ ትንፋሽ ልሰብስብ"አለችን...ጊዜ ልንሰጣት ሞከርን እያንዳንዷን ሰከንድ መጠበቅ ግን ጣር ነበር
"ሰዎች"
"አቤት አይዳ ሰላም ነሽ..ምንም አልገጠመሽም?"እኔ ነኝ ተስገብግቤ የጠየኳት
"ዘንዶው ውጦኝ ስላልተገላገልከኝ አዝናለው...ስለይህ እንደነበረው ሰላም ነኝ"አለች
"እሺ ምን አየሽ"
ማለቂያው የማይታወቅ ዋሻ...ወደ 50 ሜትር ሄጄ በዛው እንዳልጠፋ ፈርቼ ነው የተመለስኩት... ያለን ምርጫ እናንተም ወደእዚህ እኔ ወዳለሁበት መምጣት ነው...ባይሆን ከዛ ብኃላ አብረን እንጠፋለን።"
"እሺ መጣን...እኔ ቀድሜ ወደአንቺ እመጣለሁ እንዳትፈሪ"
"ኪ..ኪ..ኪ"ከአንድ የዋሻው ግድግዳ ወደሌላው እየተማታ የፈጠረው የገደል ማሚቱ ሳቆን አደመቀው
"ምን ያስገለፍጥሻል?"
"አትበሳጭ የእኔ ጀግና...ብቻ ፈጥነህ ናልኝ"አለቺኝ በሚያበሽቅ የደምፅ ቅላፄ
ከማፈሬ የተነሳ ላቤ ከግንባሬ ተንጠባጠበ...አጠገቤ ብትሆን በጥፊ ላቃጥላት እችል ነበር...ለማንኛውም ከሁሉም ቀድሜ እሷ ወዳለችበት የዋሻ ክፍል ለመሹለክ ዝግጅ ሆንኩ...

ይቀጥላል....


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️❤️❤️
👍9
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ሳቤላ በባሏና በባርባራ ሔር ግንኙነት የነበራት ቅናት ፍራንሲዝ ሌቪሰን
ኢስት ሊን ከገባ ወዲህ ከምን ጊዜም የበለጠ ጨምሮ ታደሰባት ባርባራ በበኩሏ ሪቻርድ ባረጋገጠው መሠረት ወንጀሉን የፈጸመው ፍሬድሪክ ቶርን መሆኑን በማመን፡ የተሰወረው ምስጢር ገሃድ ሆኖ ወንድሟ ከወደቀበት ከባድ መከራ በፍርድ ነጻ ተለቆ ለማየት ከመጓጓቷ የተነሣ ልቧን ከመሳት አፋፍ ደርሳ ነበር ።በነገሩ ብታምንበትም ምንም ለማድረግ ኃይል አልነበራትም ከእንቅልፍ ይልቅ ቅዠት የበዛበት ሌሊት ዐልፎ በነጋ ቁጥር ' ' ምነው ዛሬ አንዳች የማረጋገጫ ነጥብ ባገኘሁ! ተጠርታም
ከሔርበርት ቤት ብዙ ጊዜ ተመላልሳለች የሚስተር ሔርበርት ሴት ልጆችም ባልንጀሮቿ ስለ ነበሩ ፡ ለዕረፍት ለመጣው ወንድማቸው ልዩ ዝግጅት አድር?ው ሲጠሯት ካፒቴን ቶርንን ብዙ ጊዜ አይታዋለች
እንዶዚህ በመስሉ አጋጣሚዎች ስለ ዐለፈው ታሪኩ አንዳንድ ነር ትለቃቅምና ያገኘችውን ይዛ ወደ ሚስተር ካርላይል ትሮጣለች ከቢሮው ስትሔድ ቶርን ያያት
እንደሆነ እንዳይነቃ በመፍራት ወዶ ኢስት ሊን ሔዳ አለበለዚያ ደሞ ወደ ቢሮ ሲሔድ ወይም ከቢሮ ሲመለስ ከመንገድ ጠብቃ ነበር የምታገኘው "ነገር ግን ! ይኸን ያህል የሚጠቅም ነገር ይዛ መጥታ አታውቅም » አንድ ቀን ማታ ቶርን ዱሮ
ዌስት ሊን እንደ ነበረ ልትነግረው መጣች " በሌላ ቀን ደግሞ ለይምሰል እመቤት ሳቤላን ለመጠየቅ መጣችና ሚስተር ካርይልን ለብቻው ልታነጋግረው እንደምትፈልግ ነገረችው " ተመራርተው ወጡና ኢያወሩ እስከ መናፈሻው በር አብሯት ሲሔድ ሁሉ የሳቤላ ቀናተኛ ዐይኖች ያዩዋቸዋል " ስለ ቶርን ትነግረው " የነበሩት ነጥቦች ሁሉ ጠንካራ አይደሉም እነሱንም ሚስተር ካርላይልም ቀደም ብሎ
ያውቃቸዋል " እሱ ግን መስማቱን ሳይገልጽላት በጉጉትና በስሜት ያዳምጣታል "

ሳቤላ ባሏና ባርባራ ሲገናኙ በዐይኗ አይታ ተናደደች ቁጠዋ ተቀስቅሶ የአእምሮዋ ሰላም ደፍርሶ ትትከነከናለች " ፍራንሊዝ ሌቪሰን ደግሞ እሷ ያላየቻችውን ግንኙነቶች እየተከታተለ ይነግራት ጀመር " ሚስተር ካርላይል ለጤና ይበጃል እያለ ይበልጡን ጊዜ ከቢሮ ወደ ቤት በእግሩ ይመላለስ ነበር " በሚስተር ሔር ቤት ሲያልፍ ባርባራ እየጠበቀችም ሆነ ባጋጣሚ ስታገኘው የቶርንን ነገር በምታነጋግረው ጊዜ ካፒቴን ሌቪሰን ቁጥቋጦ ለቁጥቋጦ እንደ እባብ እየተምለገለገ ሔዶ
ይመላከታቸውና እየጨማመረና እያጋነነ ለሳቤላ ይነግራት ጀመር "

ባርባራ ግን ስለ ሳቤላ ቅናት ምንም ነገር አታውቅም እሱም ሚስቱን እንደሚወድና ለሷም አንዲት የፍቅር ፊት አሳይቷት ስለማያውቅ ሳቤላ በሷ መቅናቷን ሰው ቢነግራት እንኳን በነጋሪዋ ከመሣቅ በቀር አታምንም ነበር
ዱሮ በፍቅር ትነድለት የነበረው ሁሉ ከሁኔታው ተረድታ ትታው' አሁን ካርላይል ዘንድ የሚያመላልሳት
የወንድሟ ጉዳይ ብቻ ሆኖ ነበር "

ኣንድ ቀን ጠዋት ሚስተር ካርላይል ከልዩ ቢሮው ገብቶ ሲሠራ ዋና ጸሐፊው
ሚስተር ዲል ገብቶ ባለጉዳይ ሊያነጋግረው እንደሚፈልግ ነገረው "

አሁን ሥራ ይዣለሁ : ማንንም ማነጋገር አልችልም
" ምነው እያወቅህ ..
ዲል ? አለው።

“ እንደዚያ ብነግረው : እጠብቃለሁ " አለኝ » ያ ካፒቴን ቶርን የሚባለው
ከጆን ሔርበርት ቤት ያረፈው እኮ ነው .

ሚስተር ካርላይል ቀና ብሎ ከዲል ጋር ተያዩና እሱንስ አነጋግረዋለሁ አስገባው አለው ።

የካፒቴን ጕዳይ ቀላል ነበር በየጊዜው ብዙ መኮንኖች እንደሚያደርጉት በዱቤ ዕዳ ምክንያት ክርክር ስለ ተነሣበት የሚስተር ካርላይልን የሕግ ምክር ለመጠየቅ ነበር "

ምክሩን ልሰጥህ እችላለሁ ነገር ግን የማንንም ጉዳይ ከማጥናቴ በፊት
ማንነት በደንብ ማወቅ አለብኝ " አባቴም አንድን ጉዳይ ከመቀበሉ
በፊት የባለ ጉዳዩን ትክክለኛ ሰው መሆንና የጉዳዩንም ሐቀኛ አነሣሥ ያጠና ነበር እኔም ከሱ ወርሼ በዚህ ዐይነት ነው የምሠራው "

“ ቤተሰቦቼም የታወቁ ናቸው " አለው ካፒቴን ቶርን

“ የኔ ጥያቄ የቤተሰብ ጥያቄ አይደለም » እኔ የቀን የጉልበት ሠራተኛም ሆነ
ለምኖ አዳሪ ቢመጣ ሐቀኛ ሰው መሆኑን በትክክል ካወቅሁ አነጋግረዋለሁ " ስለዚህ አሁንም ካንተ የምፈልገው ስለ ራስህና ስለ ጠባይህ ለማወቅ ነው
ታዲያ እኔ ጥሩ ሰው መሆኔን በምን ላሳምንሀ እችላለሁ ? አለው ካፒቴኑ
የጠበቃው ጥያቄ እንግዳ ቢሆንበትም በትሕትናውና በአቀራረቡ ተደፋፍሮ " አገሬን ማገልገል የጀመርኩት ካሥራ ስድስት ዓመቴ ጀምሬ ሲሆን የሥራ ጓደኞቼ በኔ ጠባይ ምንም የቅሬታ ነጥብ አግኝተውብኝ አያውቁም ከዚህ በተረፈ ጆን ሔርበርትን መጠየቅ ይቻላል ”

“ እስቲ በል ባለብኝ የሥራ ብዛት ምክንያት ጥብቅና ልቆምልህ አስቀድሜ
ቃል ልገባልህ ባልችልም ' ለጊዜው ማድረግ የምትችለውን ልነግርሀ እችላለሁ ” ካፒቴን ቶርን ችግሩን ገለጸለትና አስፈላጊውን ምክር ከሰጦው በኋላ ሌላ
ጨዋታ ያዙ " የዛሬ ዐሥር ዐመት ኢስት ሊን አልነበርክም ? አንድ ጊዜ እባቴ መጥተው ክደህ ነበር በኋላ ግን ከዚህ እንደ ነበርክ ደረስኩበት ” አለው

በርግጥ እንዲዛመት የማልፈልገው የግሌ ምክንያት ስለ ነበረኝ ነው እንጂ እሱስ ነበርኩ " አሁንም ካንተ አይለፍ እንጂ ብነግርህ ግድ የለኝም በዌስት ሊን ኣካባቢ ነበርኩ ያን ጊዜ የልጅነት ጠባይ ይዞኝ በሴት የተነሣ አንድ ነገር ተፈጠረ
ዛሬም በዚህ አካባቢ መኖሬ እንዲወራ ኣልፈልግም "

“ ገባኝ ” አለ ሚስተር ካርላይል የልቡ አመታት እየጨመረ “ ልጅቱ አፊ
ሆሊጆን የምትባል ነበረች "
“ አፊ ሆሊጆን ? እኔ እንደዚህ ያለ ስም በሕይወቴ ሰምቸ አላውቅም " "

በዚያን ዘመን አንድ አሳዛኝ ነገር መፈጸሙን አላወቅህም ? አልሰማህም ?
አሃ ! ቆይ እስቲ ያቺ አባቷ እንደ ተገደለ መጥፋቷን ቶም ሔርበርት የነገረኝ
እንደሆነች ?
“ አዎን ከገዛ ቤቱ ከልጁ ፊት የተገደለው ያባቴ ጸሐፊ ነበር ” አለው ሚስተር ካርላይል

“የገደለው ደግሞ የጀስቲስ ሔር ልጅ የዛያች ቆንጆይቱ የባርባራ ወንድም ትንሹ ሪቻርድ ሔር ነበር ይህን ነገር ብታነሳ አንድ ጊዜ ሰዎች የነገሩኝ ትዝ አለኝ
መጀመርያ ሔርበርት ቤት የመጣሁ ዕለት ማታ ጀስቲስ ሔርና ሌሎችም ትምባሆ ለማጤስ እዚያ መጥተው ነበር ያን ጊዜ ደግሞ ባባራን ካንተ ግቢ በር አይቻት ነበርና ቶም ሔርበርት ስለ ግድያው አጫወተኝ የሔርን ቤተሱብ ከባድ መከራ ነው
ያገኛቸው " ሚስ ሔርም በቂ ሀብትና ጥሩ መልክ እያላት ባል አግብታ ስሟን መለወጥ ሲገባት እስከ ዛሬ ባርባራ ሔር መባሏ በዚህ ምክንያት ይመስለኛል "

ምክንያቱ እንኳን እሱ አይደለም " ወንድሟ ነፍስ አጥፍቷል ቢባልም እሷን
ለማግባት የጠየቄ ብዙ ሰዎች እንዳሉ ዐውቃለሁ ስለዚህ ስሟን አታጉድፈው
ይኸን አባባልህን ዐርም ።

“እኔስ በዚህ አልንቃትም እንዲያውም ልጅቱ በጣም ደስ ትለኛለች " አለና ካፕቴን ቶርን ጫወታውን ቀጠለ “ እና ያቺ አፊ ከዚያ ወዲህ ወሬዋ ተሰምቶ አያውቅም ?

“ በጭራሽ ” አለ ሚስተር ካርላይል "ደህና አድርገህ ታውቃት ነበር አለው ሆነ ብሎ ።

“ እኔ ቶም ሔርበርት ስለሷ ሳይነግረኝ በፊት ስሟንም ሰምቸው አላውቅ ግን ለምንድነው የማውቃት መስዬ የታየሁህ ?

ሚስተር ካርላይል ' ሰውየው የሚናገረው እውነት ይሁን ውሸት ለማረጋገጥ በጣም ጓጓ "
👍15😁2
“ አየህ አፊ ፈገግታዋ ፡ ጨዋታዋ ግልጽነቷ ውበቷ ግድ የለሽነቷና ሽቅርቅር ባይነቷ ብዙ ወዳጆች ስበውላት ነበር የሷን የፍቅር ጮራ የመሞቅ ዕድል ከገጠማቸው ውስጥ አንዱ ካፒቴን ቶርን የተባለ መኮንን ነበር " ያ ሰው አንተ አይደለህም ?”

“ እኔስ በሷ የመወደድ ዕድል አላጋጠመኝም "

“ እንግዲያ ከዚህ አካባቢ አንድ ትልቅ ምክንያት የሆነችህ ቆንጆ እሷ አይደለችም ? አለው ሚስተር ካርላይል "
.
አይደለችም በርግጥ ያችም ሁኔታዋ ሁሉ ልክ አሁን አፊን እንደ ገለጽክልኝ ብጤ ሆኖ ባለ ትዳር ነበረች » ከጊዜ በኋላ ግን ነገሩ እየበረደ መጣና እሷም
ምንም የማያውቅ ባላገር ከነበረው ባሏ ጋር ታረቀች እኔ ግን ከዚያን ነገሩ ያሳፍረኝ ጀመር በተለይ እየበሰልኩ ኢያደግሁ ስሔድ ስፈጽመው የነበርኩት ዕብደቴን ሁሉ ሳስበው እኔ መሆኔን እንድታውቅ አልፈልግም ።

ካፒቴን ቶርን ቶሎ ወጣ ሚስተር ካርይል ሰውየውን እሱ ይሁን አይሁን ለማወቅ በጥርጣሬ እንደ ተወጠረ ተቀምጦ ቀረ " ከሱ ቀጥሎ ሚስተር ዲል ገባ።

“ ሚስተር አርኪባልድ ይህ ሰው ከአፊ ጋር ለመዳራት ከስዌንሶን በፈረስ እየጋለበ ይመጣ እንደ ነበረ አንድ ጊዜ የነገርከኝ መቶ አለቃ መሆኑን ትዝ አለህ ?

“እሱስ በደንብ ትዝ ብሎኛል” አለው ሚስተር ካርላይል 'አሁንም ቢሆን
ይህ ሰውዬ እሱ ለመሆኑ ለሚያረጋግጥልኝ አምስት መቶ ፓውንድ ከኪሴ እከፍል ነበር።

ከሔርበርት ዘንድ ከመጣ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አይቸዋለሁ ”አለ ዲል

እኔም የምንፈልገው ሰው እሱ ሳይሆን እንደማይቀር የነበረኝ ጥርጣሬ እየጠነከሪብኝ መጣ " ትናንት ዶክተር በዛንት ከስዊንሰን መጥቶ ስለነበር አብረን ስንሔድ
ካፒቴን ቶርንን አገኘውና ከሱ ጋር ሰላም ተባባሉ የት እንዳወቀው ሚስተር ፍረደሪክ እንደሚባል ነገረኝ " እኔም ቀበል አድርጌ ከፍረዶሪክ ሌላ ተጨሪ ስም አለው? ” አልኩት

“ስሙ ቶርን መሆኑን ዐቃለሁ አለኝ " ነገር ግን ከጥቂት ዓመት በፊት
ስዌንስን ሳለ 'ቶርን የሚለውን ስም ተወውና ከተማው ሁሉ ሚስተር ፍረዴሪክ ብሎ ይጠራው ነበር። እዚያ ምን ይሠራ ነበር?” ብለው ራሱን ማስደስት አንዳንድ ጊዜም
ከባድ ነገር ባይሆንም በሱ ዕድሜ ያሉት እንደሚያደርጉት ሁሉ ጠብ ማንሣት ችግር መፍጠር አለኝ ስለ ፈረሰኝነቱ ጠይቄው ከልክ ያለፈ ፈረሰኛ መሆኑን ሁልጊዜ
ብዙ እርቀት መጋለቡንም ነገረኝ ። ጊዜዉ እንዳሰብኩት ደግሞ' ያ አሳዛኝ ግድያ
በተፈጸመበት ዘመን ነበር ታዲያ ምን ይመስልሃል ሚስተር ካርላይል ?”

“እኔማ ሰውየው እሱ መሆኑን አምኘበታለሁ ” አለና ከወንበሩ ተደግፎ ከፊቱ ተዘርግቶ የነበረውን ብራና ተወት አድርጎ ሐሳብ ይዞት ጭልጥ አለ ።.....

💫ይቀጥላል💫
👍17🥰1😁1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ትርጉሜ_ሀኒም_ኤልያስ

...ልታገኝ ስለምትፈልገው ነገር ስትል ድራማ የምትሰራ አድርጌ የማስባት ለምንድነው? እኔን ችላ ብላ ክሪስን ተመለከተች።

ለሚቀጥለው ልደትህ ኢንሳይክሎፒድያ አዝዤልሀለው። ማተምያው ድረስ ራሴ ሄጄ ነው ያዘዝኩት ስምህንና ቀኑን ሰጥቺያቸዋለሁ ግን ወደዚህ በቀጥታ መላክ አይችሉም:: የሆነ ሰው ሊቀበላቸው ይገባል ልክ ሁልጊዜ ራስህን ለማስተማር ምርጡን ልሰጥህ እንደምፈልግ ሁሉ የሚያስደስትህን ስጦታ ሳስብ ሳስብ ቆይቼ ነው ያዘዝኩልህ”

ክሪስ የሚናገረውን አጣ ፊቱ ላይ የሚታየው ድብልቅልቅ ስሜት ነበር፤አይኖቹ ግራ የተጋቡና የፈዘዙ መሰሉ። አምላኬ! ካደረገችው ነገር በኋላ እንኳን ይወዳታል ማለት ነው::

ስሜቶቹ ቀጥታ ናቸው:: በቁጣ ነደድኩ እንደዚህ አይነት መፅሀፍት ከአንድ
ሺ ዶላር በላይ ይፈጃል: ምናልባትም ሁለት ወይም ሶስት ሺም ሊፈጅ ይችላል። ይህንን ገንዘብ ለምን የማምለጫ ገንዘባችን ውስጥ አትጨምረውም?
ልክ ኬሪ ስትቃወም እንደምታደርገው ልጮህ ስል ክሪስ አይኖች ላይ ያየሁት ነገር አፌን እንድዘጋ አደረገኝ፡ ሁልጊዜ እነዚያ መፃህፍት እንዲኖሩት ይፈልግ ነበር፡ በዚያ ላይ አንድ ጊዜ ታዟል: አሁን ለሷ ገንዘብ ምኗም አይደለም፧
ምናልባት እንዲያው ምናልባት አያታችን ዛሬ ወይም ነገ ሊሞት ስለሚችል አፓርታማ መከራየትም ሆነ ቤት መግዛት አያስፈልጋት ይሆናል፡

ጥርጣሬዬ ተሰምቷታል።

እናታችን ጭንቅላቷን ቀና አደረገችና ወደ በሩ ተራመደች። ስጦታዎቻችንን
ገና አልከፈትንም፤ ስንከፍት የሚኖረንን ስሜት ለመመልከትም አልቆየችም።
እየጠላኋት ለምንድነው በውስጤ የማለቅሰው? አሁን አልወዳትም አልወዳትም።

በሩጋ ደርሳ እየከፈተች “ዛሬ ስለፈጠራችሁብኝ ህመም ስታስቡና እንደገና
በፍቅርና በአክብሮት ልታስተናግዱኝ ስትችሉ ተመልሼ እመጣለሁ ከዚያ
በፊት ግን አይሆንም::” አለች።

መጣች።

ሄደች።

መጥታ ስትመለስ
ኬሪና ኮሪን አልነካቻቸውም አልሳመቻቸውም አላናገረቻቸውም ለምን እንደሆነ አውቄያለሁ፤ ሀብት ማግኘት መንትዮቹን ምን ያህል ዋጋ እንዳስከፈላቸው ማየት መቋቋም ባለመቻሏ ነበር።

ከጠረጴዛው አጠገብ ተነስተው እየሮጡ ወደ እኔ መጡና ቀሚሴን እየጎተቱ
ፊቴ ላይ አፈጠጡ ትንንሽ ፊቶቻቸው ጭንቀትና ፍርሀት አጥልቶባቸዋል።
እነሱም ደስታ እንዲሰማቸው መደሰቴን ለማየት ፊቴን እያጠኑ ነው:
ተንበርክኬ እሷ የጎዳቻቸውን በመሳምና በማቀፍ አጥለቀለቅኳቸው።
መልካችን ያስጠላል?" ጠየቀች ኬሪ በመጨነቅ፤ ትንንሽ እጆቿ እጄን
ይዘውኛል

“አይ በጭራሽ! አንቺና ኮሪ ቤት ውስጥ ብዙ በመቆየታችሁ ትንሽ የገረጣችሁ ትመስላላችሁ”

“በደንብ አድገናል?”

“አዎ፣ አዎ አድጋችኋል” እየዋሸሁ እንኳን ፈገግ ብያለሁ: በዚያ የማስመሰል
ደስታና የውሸት ፈገግታ ወለሉ ላይ ከክሪስና ከመንትዮቹ ጋር ተቀምጠን
አራታችንም ልክ እንደ ገና ቀን ስጦታዎቻችንን መክፈት ጀመርን። ሁሉም
በውድ የስጦታ ወረቀቶች በሚያምር ሁኔታ የታሸጉ ናቸው።

ወረቀቱን ቀደድን ሪቫኑን ጥለን የታሸጉበትን ካርቶኖች ገነጣጥለን ውስጡ ያለውን አወጣን... በውስጡ ለእያንዳንዳችን የሚያማምሩ ልብሶች ነበሩ:
አዳዲስ መፃህፍት፣ መጫወቻዎች፣ አንድ አይነት ቅጠል የሚስል ቅርፅ ያላቸው በትልቅ ካርቶን ውስጥ የታሸጉ የስኳር ከረሜላዎች።

እንደምታስብልን ማሳያው ይኸው! ሁላችንንም በደንብ ታውቀናለች።ከመጠኖቹ በስተቀር ፍላጎታችንን፣ ማድረግ የምንፈልገውን ሁሉ ታውቃለች።
በፈቃደኝነት ሞተን ስንቀበር ማየት ደስ በሚላት ጠንቋይ አያታችን ጥበቃ ስር የተተውንባቸውን እነዚያን ባዶና ረጃጅም ወራት በስጦታዎቹ ከፈለችን።

በዚያ ላይ እናቷ ምን አይነት እናት እንደሆነች እያወቀች... የምትሰራው ሁሉ በልቧ ትክክል እንዳልሆነ እያወቀች በመጫወቻዎቹና በአሻንጉሊቶቹ
ልትደልለንና ይቅርታ ልትጠይቀን ፈለገች
በጣፋጭ የስኳር ከረሜላ መራራውን ብቸኝነታችንን ከአፋችን፣ ከልባችንና
ከአእምሯችን ልትወስድ ተስፋ አደረገች ምንም እንኳን ክሪስ መላጨት
የሚያስፈልገው እኔም ጡት መያዣ መልበስ የሚገባን እድሜ ላይ የደረስን
ቢሆንም በእሷ አስተሳሰብ አሁንም ልጆች ነን ልክ በምታመጣው መፃህፍት
ርዕስ ትንሽ አድርጋ ለዘለዓለም ልታስቀምጠን ትፈልጋለች፡

ኬሪን አዲስ ቀይ ቀሚስ ሳለብሳትና ሀምራዊ ሪቫን ሳደርግላት ፈገግ እንዳልኩ
ነበር አሁን ሁልጊዜ እንደምትፈልገው አይነት ለብሳለች የምትወዳቸውን
ቀለማት እግሮቿ ላይ ሀምራዊ ካልሲ ከነጭ አዲስ ስኒhር ጋር አለበስኳት “በጣም ታምሪያለሽ ኬሪ” እሷም ብሩህ ቀለም ያለው ልብስ በመልበሷ ተደስታለች።

ቀጥሎ ኮሪን ቀይ አጭር ሱሪና ኪሱ ቀይ የሆነ ነጭ ካኒቴራ አለበስኩት፡

ከዚያ “አንተንም ላልብስህ ክሪስቶፈር?” ስል ቀለድኩ

“ልብሽ ከፈቀደ ቆዳዬን ገልብጠሸ ማልበስ ትችያለሽ”

“ጋጠ ወጥ አትሁን!”

ኮሪ ሌላ የሙዚቃ መሳሪያ መጣለት፡ እሱ የሙዚቃ መሳሪያውን እየነካካ ኬሪ
ትዘፍንለታለች።

ሁሉም ነገር ላይ ያለኝን ደስታ የሚወስዱብኝ እግዚአብሔር የሰጠኝ ክፉ
ሀላቦች ነበሩኝ: ማንም የማያያቸው ከሆነ ቆንጆ ልብሶች ምን ይጠቅማሉ?
እኔ የምፈልገው በሚያምሩ ወረቀቶች ያልተጠቀለሉ፣ በሪቫን ያልታሰሩ፣ ሱቆች ውስጥ በካርቶን ያልተቀመጡ ነገሮችን ነው፧ የምፈልገው ገንዘብ
ሊገዛቸው የማይችላቸውን ነገሮች ነው: ጸጉሬ ከፊቴ በአጭሩ መቆረጡን
አስተውላለች? እንዴት እንደሳሳ አይታለች?የገረጣና የሳሳው ቆዳችንን እያየች
ጤነኛ እንደሆንን ታስባለች?

ለእኔ የተባሉትን ቆንጆ ቆንጆ ልብሶች ተመለከትኩ፡ ሰማያዊ ቬልቬት ቀሚስ፣ ለግብዣ የሚለበስ ሮዝና ሰማያዊ የምሽት ጋዋን አብሮት ከሚሄድ ጫማ ጋር፧ እዚያ ተቀምጬ ከረሜላውን እየበላሁ የሆነ ነገር ትዝ አለኝ፡፡
“ኢንሳክሎፒዲያ!” ለዘለዓለም እዚህ ልንኖር ይሆን?

የስኳር ከረሜላ በጣም ከምወዳቸው ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ይህንን የከረሜላ
ካርቶን ያመጣችው ለኔ ነበር ለኔ፡ እኔ ግን መብላት የቻልኩት አንድ ብቻ
ነበር። ያንንም በጣም በችግር።

የከረሜላው ካርቶን መሀል ላይ ተቀምጦ ክሪስ ኮሪና ኬሪ ከበውት ተቀምጠው
በጣም በመደሰት ከረሜላዎቹን እያጣጣሙ ነበር፡ “ከረሜላዎቹን ሁሉ
መጨረስ አለባችሁ ለረጅም በጣም ለረጅም ጊዜ የማታዩት የመጨረሻ
ከረሜላችሁ ነው፡” አልኳቸው በመረረ ጥላቻ

ክሪስ አየት አደረገኝ ሰማያዊ አይኖቹ ደስተኛና የሚያበሩ ሆነዋል።
እምነቶቹና መተማመኑ ሁሉ እናታችን ለአጭር ጊዜ ባደረገችው ጉብኝት
እንደተመለሱለት ለማየት ቀላል ነበር፡ ስጦታዎቹ እሷ ከዚህ በኋላ ለእኛ ግድ የሌላት የመሆኑን ሀቅ የመደበቂያ መንገድ እንደሆነ ለምን ማየት አልቻለም? ከዚህ በፊት እንደነበርነው አሁን ለእሷ እውነት እንዳልሆንን እኔ
እንዳወቅኩት እንዴት አያውቅም? እኛ ልክ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ እንዳሉት አይጦች፣ ሰዎች ሊነጋገሩባቸው ከማይፈልጓቸው ደስ የማይሉ ርዕሶች ውስጥ ነን፡

“እዚያ ቁጭ ብለሽ የማይናገር ምሰይ” አለ፡ ክሪስ ደስታውን እኔ ላይ እያንፀባረቀ: “እኛ ሶስታችን አይጦቹ መጥተው ከመብላታቸው በፊት አምሮታችንን ስንወጣ አንቺ ከረሜላውን እምቢ በይ: አንቺ ቁጭ ብለሽ ስታለቅሺ፣ ለራስሽ
ስታዝኚና ራስን መስዋዕት በማድረግ ሁኔታችንን መለወጥ እንደምትችይ ስታስመስይ ኮሪ፣ ኬሪና እኔ በልተን ጨርሰን ጥርሶቻችንን እናፀዳለን፡ ቀጥይ
ካቲ አልቅሺ! ሰማዕት ሁኚ! ተሰቃይ! ጭንቅላትሽን ከግድግዳ አላትሚ! ጩኺ እኛ እንደሆነ ወንድ አያታችን እስኪሞት እዚህ መሆናችን የማይቀር ነው::በዚያ ላይ ከረሜላዎቹ ሁሉ ያልቃሉ! ያልቃሉ! ያልቃሉ”
👍423
እየቀለደብኝ በመሆኑ ጠላሁት! ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ራቅ ያለው ጥግ ላይ ሄድኩና ጀርባዬን ሰጥቻቸው አዳዲስ ልብሶቼን መለካት ጀመርኩ። ሶስት
የሚያማምሩ ቀሚሶች ናቸው: አንድ በአንድ ለካኋቸው እስከወገቤ ድረስ
በቀላሉ ይዘጋሉ። ነገር ግን ቀሚሱ ደረቴ ላይ ሲደርስ ከኋላ ያለው ዚፕ
አይዘጋም፡ “ለመዝጋት ስሞክር አንደኛውን ቀሚስ ቀደድኩት። የገዛችልኝ ቀሚሶች ሁሉ አላየችሽም እያሉ የሚጮሁ የልጅ ቀሚሶች ነበሩ። ሶስቱንም
ቀሚሶች ወለሉ ላይ ጥዬ ወደ ሱቅ እንዳይመለሱ አድርጌ በእግሮቼ
ረጋገጥኳቸው፡

ክሪስ ከመንትዮቹ ጋር ወለሉ ላይ ተቀምጦ እየሳቀብኝ ነው “የሚገዛልሽን ነገር
በዝርዝር ፃፊ” ሲል ቀለደብኝ፡ “የጡት መያዣ መልበሻ ጊዜሽ ነው: በባዶ ወዲህ ወዲያ አትበይ የወገብሽንም ቁጥር ፃፊ”
ደስተኛ ፊቱን በጥፊ ማጮል በቻልኩ! “ዝጋ!” ጮህኩበት። “ለምንድነው ዝርዝር ፅፌ እናታችንን ምንም ነገር የምጠይቀው? ብታየኝ ኖሮ ምን ልብስ እንዳለኝና ምን መልበስ እንደሚገባኝ ታውቅ ነበር፡ የማዘውን የጡት መያዣ
መጠን እንዴት አውቃለሁ? መቀነትም አልፈልግም! አንተ የሚያስፈልግህ ሀፍረትህን የምትሸፍንበትና ቁራጭ ጨርቅና በጭንቅላትህ ውስጥ ከመፅሀፍ
የማይገኝ ትንሽ ስሜት ነው!” የደነገጠ ገፁን ስመለከት ደስ አለኝ።

“ክሪስቶፈር” አልኩ እየጮህኩ፤ ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም አንዳንድ ጊዜ እናቴን እጠላታለሁ! ያ ብቻ አይደለም አንዳንዴ አንተንም እጠላሀለሁ አንዳንዴ ሁሉንም ሰው በተለይ ራሴን እጠላዋለሁ! አንዳንዴ በሞትኩ ብዬ
እመኛለሁ: ምክንያቱም እዚህ ቦታ በቁም ከመቀበር መሞት ይሻላል! እኛ የበሰበሰ፣ የሚራመድ፣ የሚያወራ አትክልቶች ነን!...

ይቀጥላል
17👍6
በህይወት መንገድ ላይ…
ምዕራፍ-7
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
///
የሠው ልጅ ከሌላው እንስሳ የሚለይበት አንድና አበይቱ ነገር ተስፋ በማድረግ ችሎታው ነው። የሠው ልጅ ህይወት ከተስፋ ጋር ጥብቅ የሆነ ሚስጥራዊ ቁርኝት አለው።አንድ በሬ ፊት ለፊቱ የሚፈሰው ወንዝ ጋር ደርሶ ውሀ በመጠጣት ከጥሙ እንደሚረካ ደመነፋሳዊ ተስፋ የማድረግ ችሎታ ሊኖረው ይችላል።የሠው ልጅ ተስፋ የማድረግ ችሎታው ግን በይዘትም በመጠንም እጅግ ውስብስብ በምናባዊ ትዕይንት የተገመደ ነው...ህይወት በአብዛኛው ኢተገማቾች ሲሆኑ..የሰው ልጅ ተስፋ የሚያደርገው የእለት ጉርሱንና የአመት ልብሱን ወይንም ምቾቱንና ድሎቱን በተመለከተ ብቻ አይደለም ከሞት ብኃላ ስላለው መንፈሳዊም ህይወት ጭምር የማለምና ተስፋ የማድረግ ልዩ ችሎታ አለው።እኛም ይሄው ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ሆነን እራሱ ተስፋ ማድረጋችንን ቀጥለናል፡፡
በመጀመሪያ የቀረንን ሬሽንና ውሀ ከዋሻው ወዲያማዶ ላለችው ኤደን እናቀብላት በሚለው ተስማማንና አንድ በአንድ በማቀባል አጠናቀቅን ፤አሁን ተራ በተራ እኛም ወደ እሷ ለመሸጋገር ዝግጁ ሆን፡፡
‹ሰላም አንቺ ቅደሚ››
‹‹ምነው እኔ ልቅደም ስትል አልነበረም እንዴ?››
‹‹አዎ ብዬ ነበር አሁን ግን ሀሳቤን ቀየርኩ.ለደቂቃም ቢሆን ከዚህች ሴይጣን ጋር ብቻዬን እዛ መሆን እፈራለሁ፡፡››
‹‹እና እኔ ልቅደም?››
‹‹አዎ ቅደሚ››
አዎ እሷን ገፍተን አሻገርናት…በመቀጠል እኔ ተሸገርኩ.፤ቀጥሎ ትንሽ ቢያስቸግርም በሪሁን ተሸገረ..አሁን ጋሽ አህመድ ብቻ ቀረ..ጭንቅለቱን ቀድሞ ወደእኛ አሾለከ ግዙፍ ትከሻው ግን አንቆ ያዘው ፡፡ ብንጎትተውም እሱም እራሱን ለመርዳት ቢፋተግም ንቅንቅ የሚል ነገር ጠፋ‹‹ …ምን ይሻላል?›አይዳ ጠየቀች
‹ጋሽ አህመድ ወደኃላ ተመለስና መሽሎኪያውን ትንሽ ሰፋ እናድርገው››ሀሳብ አመጣው፡፡
‹‹አዎ ወደኃላ ተመለስ›በሪሁንም በሀሳቤ ተስመማማ….አይዳ በጭንቀት እጇቾን እያፋታገች ነው...ሰላም ፀጥ ብላለች. በፊቷ ላይ .ምንም አይነት የተለየ ስሜት አይነብባትም…ዝም ብላ ብቻ ከእኛ ፈንጠር ብላ እጆቾን አጣምራ አንጋቷን ወደመሬት ቀብራ ቆማለች
ጋሽ አህመድ ምክራችንን ሰምቶ ወደኃላው ተመለሰ...ቀድመን ወደ እኛ ያሻገርነውን ብረት እኔና በሪሁን አንድ አንድ ያዝንን…እና በተቻለን አቅም በጥንቃቄ መቆፈር ጀመርን…
ግን ከጨለማው ሲኦል የተላከ መአት ሲወርድብን ሁለት ደቂቃ አልሞላም….መለከት ሳይነፋ፤፤ከበሮ ሳይመታ ድንገት ነጓድጓድ የመሰለ ደምፅ…ምፅአት የመሰለ መደርመስ ተከሰተ..ሁለችንም በደመነፍስ ወደኃላችን ተስፈንጥረን በመሸሽ ከናዳው ለማምለጥ ሞከርን….እኛ ቢሳካልንም ጋሽ አህመድ ግን ሙሉ በሙሉ አፈር ለብሷል…
‹‹ወይ ጋሽ አህመድ…ወይኔ ሞተ ወይኔ ወንድሜን…. ››አይዳ በማያቆርጥ ጩኸት ዋሻውን አናጋችው፡፡በሪሁን ወደኃላ ከሸሸበት በመመለስ አፍሩን በእጁም በብረቱም ወደኃላው መበተን ጀመረ...ስራው በማሰብ ሳይሆን በድንጋጤ ነበር የሚከውነው…ጋሽ አህመድን ለማትረፍ ከጊዜ ጋር ግብ ግብ መግጠም….እኔም እሱ እንደሚያደርገው ማድረግ ጀምርኩ...አይዳም ከጩኸትና ከለቅሶ እራሷን ሳትገታ አፈሩን በመናድ ታግዘን ጀመረ….ሰላም ግን ከቆመችበት አልተንቀሳቀሰችም….በቁሟ ተኝታ የተፈጠረውን ነገር አላወቅችም ይሆን እንዴ…?ስል አሰብኩ….ቢሆን ዋናው አጣዳፊ ነገር ስለእሷ ማሰብ ሳይሆን ጋሽ አህመድን ለማዳን የመጨራሻውን ጥረት ማደረግ ነው..
አስር ከሚሆኑ ደቂቃዎች ቡኃላ ‹‹እጁን ያዝኩት.እጁን››በማለት ጮኸች ..አይዳ...እኔና በሪሁን ወደጠቆመችኝ ቦታ ተስፈነጠርንና እጅን ይዘን ለመጎተት ሞከርን፡፡
‹‹ኸረ ይጎዳል ትገነጥሉታላችሁ››
‹ተገንጥሎም ቢሆን መትረፍ ከቻለ እድለኞች ነን ››አልኳት
ግን አሁን በህይወት ማውጣት ችለን እግሮቹ ድቅቅ ቢሉስ እንዴት ነው ከዚህ መታገት በእግሩ ቆሞ መራመድ የማይችል ሰው ይዞ መጎዝና ከዚህ ወጥምድ እራስን ማዳን የሚቻለው…?.የሚል ሀሳብ በአእምሮዬ መጣና ጭንቅ ውስጥ ከተተኝ፡፡
ጋሽ አህመድን ብዙ ጥረት ከአፈሩ አላቀን ማውጣት ቻልን .ግን በድኑን ነው ያገኘነው...ይሄ በህይወቴ ሙሉ በሰው ሞተ ምክንያት ያጋጠመኝ እጅግ መራሩ ሀዘን ነው፡አባቴ ሲሞት እንኳን ምን አልባት ልጅነት ዕድሜዬ ላይ ስለነበርኩ እንደሆነ አላውቅም እንዲህ ልቤ አንቅሽቅሽ እስኪል አላዘንኩም ነበር፡፡ልጆቹ ፊቴ ላይ መጥተው ድቅን አሉ…ከአንድ ወር በፊት እኮ ነው ሶስት ክፍል ሰርቢስ ቤት ሰርቶ የቤት ምርቃት ጠርቶኝ እቤቱ ሄጄ ልጆቹንና ሚስቱን የተዋወቅኩት….እንዴት እንደሚወዳትና እላዩ ላይ ይንጠለጠሉበት እንደነበረ ትዝ ሲለኝ አጥወለወለኝና ባለውበት ቁጭ አልኩ፡፡..እኔ ራሴ በየትኛው ደቂቃ እንደሚያልቅልኝ እርግጠኛ ባልሆንም ውስጤን ግን የጥፋተኝነት ስሜተ እየቦጫጨቀኝ ነው፡፡ጉድጓዱን ስቆፍር ከልምድ ማጣት ያልሆነ አቆፋፈር ቆፍሬ እንዲናድ ያደረኩት እኔ ልሆን እችላለሁ.?በፀፀት እሳት እየተለበለብኩ ነው፡፡
.በሪሁን ሬሳውን እያገላበጠና እያንገላታ ፍርፍር ብሎ እያለቀሰ ነው….ከእሱ ጋር እንደታላቅ ወንድምም እንደጓደኛም ስሚቀራረቡ ከሁላችንም በላይ ማዘኑ የሚጠበቅ ነው፡፡
አይዳ አሁን ዝም ብላላች…ግን ፊቷ ጥውልግልግ ብሏል…የለበሰችው ልብስ ሁሉ አቧራ ከመልበሱ በላይ ቲሸርቷ መሀል ላይ ተቦጭቆ ቀኝ ጡቷ አፈትልኮ ወጥቶ ሙሉ በሙሉ ለእይታ ተጋልጧል….እሷ ግን በሀዘን ከመደንዘዞ የተነሳ ነገሬም ያለችው አይመስለኝም.. በአጠቃላይ ያቺ ሽቅርቅሯ ልጅ ጭቃ አቡኪ መስላለች…ከተዘረፈጥኩበት እንደምንም ተነሳውና የለበስኩትን ጃኬት አውልቄ ወደእሷ ሄጄ ትከሻዋ ላይ አለበስኮት…ቀና ብላ አየችኝና መልሳ አይኗን ሰበረች…በሌላ ጊዜ ቢሆን ይሄኔ ምገባበት እስኪጠፋኝ በተረብ አጥረግርጋኝ ነበር….ወደቦታዬ ተመለሰኩና ቁጭ አልኩ..፡፡
ጃኬቱን አስተካክላ ለበሰችና ዚፑን በመቆለፍ ጡቶቾን ወደእስራታቸው መለሰቻቸውና ቀጥታ ወደሰላም ተራመደች …ተጠጋቻት‹‹ታውቂ ነበር አይይል?››አለቻት፡፡
‹‹ምኑ ነው የምተውቀው?››ግራ ገብቶኝ ጣልቃ ገባው፡፡
‹የሆነ አደጋ እንደሚከሰት ታውቅ ነበር?.››
‹‹እውነቷን ነው እንዴ?››በሪሁን አፈጠጠባት
‹አዎ.. .ወደኃላ ተመለስ ብላችሁት ሲመለስ ከዛ በህይወት መውጣት እንዳማይችል ተሰምቶኝ ነበር››
‹‹ታዲያ ለምን አላስጠነቀቅሺም?››
‹ማስጠንቂያው ለውጥ ላያመጣ ለምን ነግራችሆለው..?ቢያንስ የምትወዱትን ሰው ለማትረፍ መጣራችሁ እራሱ አንድ ነገር ነወ››
በሪሁን ከተቀመጠበት ተነሳና ‹‹.ተቀልጂያለሽ እንዴ…?ቢያንስ ወደኃላ ተመለስ አንለውም ነበር...ቀስ ብለን እየጎተትን ስበን እናወጣው ነበር››
‹‹ነገርኮችሁ እኮ….ወደፊትም ወደኃላም ቢመለስ አይተርፍም ነበር..ዛሬ የተቆረጠለት የመጨረሻ ቀኑ ነበር››
‹‹ቆይ ይሄ ትከሻዬ ነገረኝ የምትይው ነገር ምንድ ነው?›
‹‹የእምነት ጉዳይ ነው..ብነግራችሁም ወይ አትረዱኝም አልያም አታምኑኝም፡፡
‹‹ሞክሪን….ማመን ያለማመኑን ለእኛ ተይልን››
‹‹እንግዲያው ትከሻዬ የምላችሁ ጠባቂ መላኬን ማለቴ ነው፡፡እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ጠባቂ መልዐክ አለው.. ግን ሁላችንም በሚባል መልኩ ትኩረት አንሰጠውም...እንዳሉንም የምናወቅ ጥቂቶቻቸን ነን..እኔ ግን ያው እንደምታውቁት መንፈሳዊ ልምምድ ስላለኝ ያው ››
👍15👏2
‹‹እና ለማለት የፈለግሽው የሚሆነውን ነገር ሁሉ የሚነገሩሽ ጠባቂ መልአክ የምትያቸው ናቸው..?››
‹‹አዎ..ከዚህ በለይ ዝርዝሩን ልነግራሁ አልችልም›በማለት ለቀጣይ ውይይት ፍቃደኛ አለመሆኗን በሚያስገነዝብ ሁኔታ ከእኛ ፈንጠር አለችና እንደልማዷ እግሮቾን አፈናጣ ወደተመስጦዋ ገባች፡፡
ሶስታችን የጓደኛችንን እሬሳ ዙሪያ ከበን ደንዝዘን ተቀመጥን፡፡ለረዥም ሰዓት እርስ በርስ የተነጋገረ ሰው አልነበረም፡፡ምን አልባት ለሶስት ወይም ለአራት ሰዓት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ቁጭ ብለን ጭለማ ሀሳብ እያሰብን በፍርሀት ና በመንቀጥቀጥ ካሳለፍን ቡኃላ ድንገት ሰላም ማውራት ጀመረች..ዝም ብላ ከመሬት ተነስታ ነው ማውራት የጀመረችው..ሁላችንም በፀጥታ እያዳመጥናት ነው ፡፡

እኔ እድሜዬን ሙሉ ብቸኛ ሰው ነኝ…ብቸኝነት ቆፈን ነው...ጥዝጣዜው ልብን ሰርስሮ ካንሰር ይሆናል....ብቸኝነት ረሀብ ነው ስጋን አርግፎ በአጥንት ያስቀራል፡፡...ብቸኝነት ጥማት ነው ጉሮሮን አድርቆ ውስጥን በንቃቃት ይሰነጣጥቃል።

ደግሞ ብቸኝነት ፀጋ ነው..መንፈሳዊ ልምምድ የምናደርግበት ቁልፍ መሳሪያ ነው... ብቸኝነት ስክነት ነው ከራሳችን ጋር የምንወያይበት ጥልቅ የሆኑ እሳቤዎችን የምናመነዠግበት የህይወት ቡልኮ ነው

ብቸኝነታችን ከሰው አጀብ በሆነ ምክንያት በመነጠላችን ውስጣችን በእጦታችን የሚሰቃይ ከሆነ ውጤት ህመም እንጂ ፀጋ ሊሆን አይችልም።ብቸኝነታችን በሰው እጦት ሳይሆን በእውቀት(በምርጫችን)ከሆነ ወይም ያለፍላጎታችን ያጋጠመንን ብቸኝነት ለበጎ ነው ብለን አምነን ተቀብለን ከሆነ ወደአብርሆት መንደር መግቢያ በራችን ወደመንፈሳዊ ልዕልና መስፈንጠሪያ መሠላላችን ይሆናል።
ቢሆንም በብቸኝነት መቆዘም፤ በብቸኝነት መሠበር ለእንደእናንተ አይነቱ ታጋይና የተሠቀለ ተስፋ ላለው ወጣት የማይታሠብ ነው።ግን ደግሞ አንዳአንዴም ቢሆን ጥሩ ነገር ስለሆነ አስቡበት እርግጥ በአካል ፍፅም ብቸኛ ሆኖ በመንፈስ ብቻኛ ሳይሆኑ መቆየት ቀላል ነገር አይደለም። አያችሁ ስለብቸኝነት ብዙ ያወራውት እንደነገርኳችሁ እድሜዬን ሙሉ በብቸኝነት ሰላሳለፍኩና ብቸኝነትን በተመለከተ በቂ ልምድ ስላለኝ ነው፡፡

ከሁላችሁም ጋር በቅርብ ነው የተዋወቅኩት...ግን እመኑኝ በህይወቴ ረጂም የአብሮነት ግዜ ያሳለፍኩት ከእናንተ ጋር ነው ፤መክንያቱም እንደነገርኳችሁ በህይወቴ ሙሉ ብቸኛ ነበርኩ፡፡ዕድሜዬ 22 ወይም 23 ዓመት የሚሆነኝ ይመስለኛል።ይሄ ስል ዕድሜዬን ለመናገር እያንገራገርኩ አድረገጋችሁ እታስብት።ለእንደዛ አይነት ቅንጦት መች ታደልኩ።እናቴንም ሆነ አባቴን ምን እንደሚመስሉ አላውቅም፤ወንድሞችም ሆነ እህት የለኘም፡፡በአጠቀቃላይ ዘመድ የሚባል ኖሮኝ አያውቅም፡፡ማደጎ ቤት ነው ያደኩት ..ድፍን 18 ዓመት እዛ ማደጎ ቤት ውስጥ ኖሬለው ...ትምህርቴን ጀምሬ 12ተኛ ክፍል እስካጠናቅቅ ማለት ነው።እዛ እያለው አብሬ ያደኮቸው እናም እንደእህት ማያቸው በርከት ያሉ እኩዬቼ ነበሩ...የእኔ ፀባይ ምቹ ባይሆንም አስተማሪዎቼና ሞግዚቶቼም ልክ እንደወላጆችቼ ነበሩ፤በዕውቀትም በስነምግባርም በተቻላቸው አቅም አንፀው ሊያሳድጉኝና ለፍሬ ሊያበቁኝ ጥረዎል ለፍተዋል.. የስነምግባሩን አላውቅም በእውቀቱ ግን አልተሳካላቸውም.፡፡.ግማሽ መንገድ ላይ ሽብርክ አልኩ...ድልድዩን ተስፈንጥራ በተደላደለ ብቃት ታልፈዋለች ሲባል ከድልድዪ ተንሸራትቼ ወንዙ መሀከል ቦጭረቅ ብዬ ወደቅኩ።

ከዛ በማደጎ ተቋም ህግደንብ መሠረት አንድ ተረጂ ተማሪ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያላመጣ ድርጅቱን ይለቅና ለሁለት አመት አንድ ሺ ብር እየተከፈለው እራሱን ለመቻል ይጥራል። ተሳካለትም አልተሳካለትም ከሁለት አመት ብኃላ ድርጅቱ ድጋፊን ሙሉ በሙሉ ያቋርጣል።እናም እኔ ላይ የወደቀው ዕጣ ይሄ ነበር።

ከዛ ያደኩበትን ሀዋሳን ከተማ በደመነፍስ ጥዬ ወደቢሾፍቱ መጣው…ለምን ምንም ምክንያት አልነበረኝም፡፡ ምን አልባት አሁን ያለውበት ሁኔታ ከእጣ ክፍሌ ላይ ስለተፃፈ ያ እንዲፈፀም ይሆናል..እናም መጣውና ሶስት በሁለት የምትሰፋ ደሳሳ ሰርቢስ ቤት በአራት መቶ ብር ተከራየው።አስተማሪዎቼ ጓደኞቼ የሚያውቁኝም የማያውቁኝ የግቢው ማህበረሰብ አዎጥተው በሰጡኝ 2300ብር አንድ ፍራሽ ሁለት አንሶላና ብርድ ልብስ፤ማብሰያ ዕቃዎች ብረት ድስት፤ማንቆርቆሪያ..ወዘተ ገዛው።ቀጥሎ ያለው ጥያቄ ምን ሰርቼ ልኑር?የሚለው ነበር፡፡ ዝም ብዬ ምን ሰርቼ እንደምኖር በማሰብ አንድ ወር ያህል አሳለፍኩ፡

.አንድ ቀን ታዲያ ዝም ብዬ ወክ ሳደርግ እናንተ ሰይት ጋር ደረስኩ…ድንገት በሪሁን ከግቢው ሲወጣ ተገጣጠምን ፡፡እደተላካፊ የሴት ጎረምሳ መንገድ ላይ አስቁሜው እዚህ ሳይት ለእኔ የሚሆን ስራ አለ ወይ ብዬ ጠየቅኩት…በማግስቱ ደውዬ እንድጠይቀወ ስልኩን ሰጥቶኝ ተለየኝ …ከአራት ቀን ቡኃላ ደወልኩለት፡፡

…....ለረጅም ጊዜ እንደሚያውቀኝ ሰው የት ጠፋሽ…?.እንዴት እስከዛሬ ሳትደውይ ?ብሎ ተቆጣኝና በማግስቱ ሳይት እንድመጣ ነገረኝ….የቀን ስራ ያስቀጥረኛል ብዬ ነበር የጠበቅኩት…ለዛም ደስተኛና አመስጋኝ ሆኜ ነበር በማግስቱ ወደሳይ የሄድኩት፡፡ እሱ ግን ዘመዴ ነች ብሎ፤ዋስ ሆኖ በእሰቶር ኪፐርነት በ3ሺብር ደሞዝ አስቀጠረኝ.…እስከዛሬ በቅጡ እንኳን አላመሰገንኩትም. ፡በሪሁን ካሳደገኝ ማደጎ ቤት ውጭ በህይወቴ ትልቁን ውላታ የዋልክልኝ አንተ ነህ..ከዚህ በሰላም እንድትወጣ ፀልያለው….አዎ ቀና ሰው ስለሆንክ ሁለተኘ እድል ይገባሀል…ሁላችሁንም በጣም እወዳችሆለሁ….አሁን ሀዘኑን ተውትና ተኩረታችሁን ወደራሳችሁ መለሱ…እንዴት እራሳችሁን ማተትረፈፍ እንዳለባች ትኩረት አድርጉ..እግዚያብሄር የወደደውን ያድርግ …ይሄው ነው፡፡
👍21
ድንገት ፀጥ አለቸ..ከመካከላችን ማውራት የቀጠለ ሌላ ሰው አልነበረም…መልሰን ወደ ድባቴ ገባን..…ከ20 ደቂቃ ቡኃላ አንድ ሲበላኝ የነበረን ጥያቄ ሰላምን መጠየቅ ፈለኩ ‹ሰላም የነገርሽን ታሪክ ልቤን ነክቶታል….የእውነት በሪሁን ዘመድሽ ነበር የሚመስለኝ…..ብትዋሹንም ደስ ብሎኛል…ምክንያቱም አንቺ በህይወቴ ካወቅኳቸው ሴቶች ሁሉ በጣም ልዩዋ ነሽ…በህይወት ከዚህ ከወጣን ካንቺ ብዙ ነገር መማር እፈልጋለው….ማለቴ ስለዚህ መንፈሳዊ ስጦታሽ …ስለፅናትሽ ››ምንም መልስ የለም
‹ሰላም ተኛሽ እንዴ?›መልስ የለም
የሆነ ነገር ሸከከኝ.እኔም የእሷ ተጋገባበብኝ እንዴ.ማለቴ …ጠባቂ መላኬ ሹክ ይለኝ ጀመር እንዴ?
‹ባትሪው ማን ጋር ነው.አብሩት››
‹‹ድንጋይ ጨCሶል››አለቺኝ አይዳ
ኪሴ ገባውና ሞባይሌን አውጥቼ ባትሪውን አበራው… ዘሪያ ገባውን አየው…‹‹የለችም››
‹‹የለችም ማለት?››በሪሁን ነው በድንዛዜ የጠየቀኝ
ከተቀመጥኩበት ተነሳውና ወደፊት ሮጥኩ…አይዳ ከኃላዬ እየተከተለችኝ ነው.‹‹ተረጋጋ…ቀስ በል..ቆይ ጠብቀኘ››
ወደሰላሳ ሜትር ወደፊት ከሄድኩ ቡኃላ ደክሞኝ ቆምኩ..አይዳ እያለከለከች ደረሰችብኝ…‹‹የለቸም›
‹.አዎ ንግግሯ የስንብት ነበር›
‹‹ግን እንዴት እንዲህ ታደርገናለች….?ተስፋ በመቁረጥ ላይ ሌላ ተስፋ መቁረት ጨምረንበት ወደኃላችን ተመለስንን..በሪሁን አሁንም ሬሳውን ታቅፎ እንደተቀመጠ ነው….እሷንም አጣናት›ስል ጠየቀ
አዎ .አጥተናታል››
እንግዲህ ስድስት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለት ሰው ከመሀላችን አጉድለን ሶስት ቀረን ማለት ነው፡፡ጌታ ሆይ አረ በቃ በለን!!


ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️❤️❤️
👍13
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ሳምንቶች ሁለት ሦስቱ ሲያልፉ ጉዳዮች ደግሞ ከወደፊት ይልቅ የኋሊት
የሚሠግሡ መሰሉ የፍራንሲዝ ሌቪሰን ጉዳይ ፈቀቅ አልል አለ ባለ ዕዳዎቹም ፍንክች አላሉም ሰው እንዳያየው በሚስተር ካርላይል ዝግ ሠረገላ እየሆነ ሦስት ጊዜ ሌቪሰን ፖርክ ቢመላለስም ሰር ፒተርም እንደ ባለ ዕዳዎቹ ድርቅ አለ አንድ ጊዜ ለአንድ ዕዳ አንዲከፌል የሰጠውን ገንዘብ ለቪሰን ተቀብሎ ሳይከፍል ለራሱ
ማጥፋቱን ስለ ደረሰበት ፡ ሰር ፒተር በጣም ተናደደና ምንም ማድረግ እንደ ማይችል ነገረው " ሌቪሰን ወደ ነበረበት ወዶ አውሮፓ ከመመለስ በቀር ሌላ ተስፋ
እንደሌለው ተረዳ ።

ሰር ፒተርም የሱ ብጤ ከንቱዎች የተጠራቁሙበት እዚያው ስለሆነ፤ከሁሉ
ፍራንሲዝ ሌቪሰን የተሻለ የሚስማማው ወደዚያው ቢመለስ መሆኑን ነገረው
ሊሔድ ሲነሣ ሰር ፒተር የአንድ መቶ ፓውንድ ኖት አውጥቶ ወደሱ ሲመጣ ላወጣው ወጭ መተኪያ ብሎ ሰጠው ። አበሉንም እንደማያቋርጥበትም ገለጸለት ።

“ ዛሬ ከሰር ፒተር ጋር እንዴት ሆናችሁ ? አለው ሚስተር ካርላይል ማታ
ከራት ላይ እንደ ነበሩ ።

“ መቸም ምንም አይል” አለው ፍራንሲዝ ሌቪሰን ' “ ከሱ ጋር ምንም ያህል
ነገር አልፈጸምኩም " እነዚህ የዱሮ ሰዎች ጉዳዮችን ቶሎ አይቆርጡም " ጊዜ መውሰድ ደስ ይላቸዋል "

ከኢስት ሊን ለመውጣት ስለ አልፈለገና እውነቱን ቢናገር ደግሞ የማይሔድ
በት ምክንያት ስላልነበረው ያልሆነ መልስ ነገረው ።
በመሻሻል ፈንታ በፍጥነት እየባሰ የሔደው ደግሞ የሳቤላ ቅናት ነበር ። ባርባራን በየዕለቱ ከሚስተር ካርላይል ጋር ስትገናኝ ታያለች ካፒቴን ሌቪሰን ነገሩን እየተከታተለ የተመለከተውን እያጋነነ እየተነተነ ይነግራታል ። ሳቤላ በዚህ ጊዜ ራሷንና በዙሪያዋ ያሉትን ሁሉ ትጠላ ጀመር በባሏ ላይ አደገኛ የሆነ ጥላቻ ጠነሰሰች ጥንስሱም እየፈላ መጣ ካፒቴን ሌቪሰን ከሰር ፒተር ዘንድ በሔደበት
ቀን በሠረገላ ሆና በዌስት ሊን ስታልፍ ባሏና ባርባራ በጣም የጠበቀ ጫወታ እንደያዙ አገኘቻቸው " እነሱ ግን ሠረገላዋ ባጠገባቸው ዐልፎ ሲሔድ ልብ ብለው አላዩትም ።

በበነጋው ጧት የጆስቲስ ሔር ቤተሰብ ቁርስ ላይ እንደ ተቀመጡ ፖስተኛኛውን ሲመጣ አዩትና ባርባራ በመስኮቱ ዘልቃ አንድ ደብዳቤ ተቀበለችው "

“ ከማን የተላከ ነው ?” አላት አድራሻው ለሱ ባይሆንም የማንኛውንም ደብዳቤ ይዘት ለማወቅ ጉጉት የነበረው አባቷ ።

“ ከአን ነው ... አባባ” አለችው ደብዳቤውን ከጐኗ በማስቀመጥ "

“ ታዲያ ለምንና ምን ብላ እንደ ጻፈችው ከፍተሽ አታይውም ?”

“ እከፍተዋላሁ " ለእማማ ሻይ ልቀዳላት ብዬ ነው „”

ባርባራ ሻዩን ለናቷ ሰጥታ ፖስታውን ስትከፍተው፡አንዲት ትንሽ የታጠፈች
ወረቀት ከጭኗ ላይ ወደቀች : ደግነቱ ግን አባቷ ከቡናው ስኒ እንዳቀረቀረ ስለ ነበር ወረቀቲቱን አላያትም ሚስዝ ሔር ግን አይታ ነበር "

“ባርባራ አንድ ነገር ጣልሽ"

ባርባራም ወረቀቲቱን አይታ ስለ ነበር ቀስ አድርጋ ሳትታይ ያዘቻት ።
“ አንቺ የኔ ልጅ ኧረ አንድ ነገር ከጭንሽ ላይ ወይቀ ”
“አንቺ እናትሽን አትሰሚያትም እንዴ?

"ምንድነው የጣልሽው? አላት አባቷ"

ባርባራ ፊቷ በድንጋጤ እንደ ቀላ ከተቀመጠችበት ተነሣችና ልብሷን አራገፈች “ምንም ነገር የለም... አባባ ” አለችው " ከዚያ ከቦታዋ ተመልሳ ከተቀመጠች በኋላ እናቷን ዝም እንድትል በዐይኗ ገረመመቻት "

ባርባራ የእኅቷን ደብዳቤ አንብባ ማየት የሚፈልግ እንዲያየው ጠረጴዛው
ላይ አኖረችው ።

አባትየው ቶሎ አነሣና ከተመለከተው በኋላ እያልጐመጐመ ከጠረጴዛው ላይ
ጣለው "

“ ዱሮውንም ከአን ደብዳቤ ምንም አይገኝም ። እስኪ አንድ ስኒ ቡና ጨምሪልኝ ' ባርባራ ። ”

በመጨረሻ ዳኛው ቁርሱን በልቶ ካበቃ በኋላ ወደ አትክልቱ ቦታ ለመንሸራሸር ወጣ ። ሚስዝ ሔር ባርባራን ቀና ብላ አየቻት "

“ ልጄ ... ምን አድርጌሽ ነው እንደዚያ ተቆጥተሽ ያየሺኝ ? ከጭንሽ ላይ
የወደቀውስ ምን ነበር ? እኔማ ከአን ደብዳቤ የወደቀ መስሎኝ ነው ።

“ እሱስ ነው ፤ከአን ፖስታ ነው የወደቀው ። አባባ ግን ሁሉን ነገር እኔ ልየው እያለ መጠየቅ ይወዳል አን ለማንም ሳይሆን ለኔ ብቻ በተለየ ወረቀት አብራ ትጽፍልኛለች " ምናልባት ከዚህ አብራ ከአንድ ፖስታ ከምትልካቸው ትናንሽ ደብዳ
ቤዎች አንዱ ሊሆን ይችላል

“ ባርባራ አባትሽ ላንቺ የሚጻፉትን ደብዳቤዎች ማየት አይችልም የምት
ይው ደስ አይለኝም ።”

“ የምትይው እውነት ነው ... እማማ ። እሱ ግን ትንሽ ልብ ቢኖረው እኔና አንም ስለየግላችን የመጻጻፍ ነጻነት ሊኖረን እንደሚገባ ማወቅ አለበት " እሱ በሆነው ባልሆነው ጥልቅ ማለት አያስፈልገውም ነበር

ባርባራ ወድቃ የነበረችውን ወረቀት አውጥታ “እማማ ... ስለ ሪቻርድ
ነው” አለቻትና አነበበችላት
“ ከሪቻርድ ቀንም ስምም የሌለው ማስታወሻ ደረሰኝ እኔም በጽሑፉ ነው ያወቅሁት አሁን የተወለደችው ጨረቃ ስትደምቅ ስለሚመጣ ከአፅዱ እንድትጠብቂው ሲመጣ ምልክት ያሳይሻል” ይላል የአን ወረቀት "

ሚስዝ ሔር ፊቷን ለጥቂት ደቂቃዎች ሸፍና ቆየች።

ግን እኮ ... እማማ ለመምጣት ሙከራው ለሱ አደገኛ ነው'' አለቻት

“ በሕይወት መኖሩን ማወቅሳ ! ስለ አደጋው እስካሁን የጠበቀው አምላክ
ይጠብቀዋል ይልቅስ ልጄ
እሷን ወረቀት አጥፊያት ''

« በፊት አርኪባልድ ካርላይል ያንብበወና ኋላ አጠፋታለሁ "

“ እንግዲያውስ ዛሬ ፌልግሽ አሳይው።እሱን ካላጠፋሽ ልቤ አያርፍልም"

ባርባራ ሚስተር ካርላይልን ፍለጋ ወደ ዌስትሊን ብትዘልቅ ወደ ሊንበራ መጓዙን ሚስተር ዲል ነግራት ከዚያ ወደ ቤቷ ተመልሳ ሲያልፍ እንድታገኘው ከበር
ስትጠብቅ አመሸች " ሲቀር ጊዜ በሌላ በኩል አድርጐ ወደ ቤት ዐልፎ ይሆናል
በማለት ወደ ኢስት ሊን ሔደች " እዚያ ስትደርስ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተደወለ

ሚስተር ካርላይል አሁን ነጻ ነው ወይስ ሥራ ይዟል ?

«ሚስተር ካርላይል
አልገቡም እሜቴ ና ሚስ ካርላይልም ራት እየጠበቋቸው ነው ” አለና በሩን የከፈተው አሽከር እንድትገባ ጠየቃት " እሷ ግን ገብታ ለማነጋገር አላሰኛትም ነበርና ተመልሳ ሔደች "

በመስኮት ቁማ የባሏን መምጣት ስትጠብቅ የነበረችው ሳቤላ ባርባራን ወደ ቤት ስትመጣና ተመልሳ ስትወጣ አየቻት ወዲያው ደግሞ በሩን የከፈተላት አሽከር ሳቤላ ወደ ነበረችበት ክፍል ገባ
“ ያቺ ሚስ ሔር አይደለችም እንዴ ? አለችው " ናት . .
እመቤቴ ጌቶችን ነበር የፈለገች " እኔ እንኳን የእርስዎን መኖር ነግሬአት ነበር ግን ለመግባት አልፈለገችም :

ሳቤላ ምንም ሳትመልስ ዝም አለች " ፍራንሲዝ ሌቪሰን በአስተዛዛኝነት
መልኩ ሲያያት አየችው " እጆቿን እስኪያማት ድረስ እያፋተገች ወደ መስኮቱ ተመለሰች "

ባርባራ እያዘገመች ቁልቁል ስትወርድ ሚስተር ካርላይል ቶሎ ቶሎ እየተራመደ! አሻቅቦ ወደ ቤቱ ሲመጣ ተገናኙና ሲጨባበጡ ሳቤላ አየቻቸው "

“ ከቢሮህ መጥቸ አጣሁህ ፤ ይኸውልህ ይህ ወረቀት ከሪቻርድ ደረሰኝ "ብላ ያችን ቁራጭ ወረቀት ሰጠችው "

ሚስተር ካርላይል ወረቀቲቱን ተቀብሎ ሲያነብ ባርባራ ተጠግታ ስትመለከተው እነሱን ደግሞ በቅናት የተንገገበችው ሳቤላና በተንኮል የተመረዘው ካፕቴን ሌቪሰን በመስኮት ዘልቀው ከሩቅ ይመለከቷቸው ነበር ኮርኒሊያ ካርላይል
አየቻቸው
👍18
“ አየሀ አርኪባልድ
እኔስ አምላክ ነው ወደዚህ የሚልከው መሰለኝ "
እንግዲህ ስለ ቶርን ያለን ጥርጣሬ ያበቃል " አሁን ሪቻርድ እንዲያየው አንድ መላ መፍጠር አለብህ !” አለችው።

“ለመሆኑ እንደሚመጣ ሚስዝ ሔር ስምተዋል ? ” አላት "አዎን ሰምታለች " የአን ደብዳቤ ሲደርሰኝ የሪቻርድ ነገር ይኖርበታል
ብዩ ሳልጠራጠር ከፊቷ ከፈትኩት ። እሱ እዚህ እስኪደርስ ድረስ ባልነግራት
ጥሩ ነበር " አሁን ደግሞ መጥቶ እስክታየው ድረስ በመጓጓት ልቧ ይሰቀልና በሽታዋ እንዳይቀሰቀስባት ፈራሁ ። እዚሀ ከደረሰ በኋላም በደኅና ተመልሶ መሔዱ እስኪረጋገጥ ድረስ የመንፈስ ሰላም አላገኝም " አዬ ሪቻርድ ! አዬ ያልታደልከው ከርታታ ባልሠራኸው ነገር ይህን ሁሉ ፈተና ትቀበላለህ ! " አለች "

አድራጎቱ ሁሉ እኮ ልክ ወንጀሉን እንደ ፈጸመ ሰው ነበር . .አፈጻጸሙ ራሱ የወንጀለኛን ያህል መዘዝ ያስከትላል „”

“ አንተ ግን ወንጀለኝነቱን አታምንም ?
“አላምንም ቶርን ወንጀሉን ስለ መሥራቱ እኮ ምንም አልጠራጠርም ''
“ አዬ ! ምነው በሆነለት ! አሁን ሪቻርድ ሲመጣ እንዴት ተደርጎ ነው ቶርንንን ሊያየው የሚችለው ?

እንጃ እስኪ ላስብበት ፤ አንቺ ግን እንደ ደረሰ እንድትነግሪኝ ምናልባት
ገንዘብ የሚፈልግ ከሆነም ሚስዝ ሔር በቀላሉ ሊያገኙለት ስለማይችሉ እንዶዚያን ጊዜው እኔ ልሰጠው እችላለሁ " በይ ደኅና ሁኝ” አላትና ወደ ቤቱ ሔደ "

“ አመሰግናለሁ አርኪባልድ!እማማም አንተኑን ነው የተማመነችው ”

ከሊንበራ እንደ ተመለሰ አንዳንድ ትእዛዝ ለመስጠት ወደ ቢሮው ሔዶ እንደ
ነበር ገልጾ ስለ አስጠበቃቸው ይቅርታ ጠየቃቸው " ሳቤላ ከንፈሯን ገጥማ ዝም አለች " ሚስተር ካርላይል ግን አላስተዋላትም " ተቆጥታለች ብሎም አልጠረጠረም "

“ ኧረ ያቺ ባርባራ ሔር ካንተ ጋር ምን ነገር አላት ? አለችው እኅቱ ።

“ ስለ አንድ ጉዳይ ልታነጋግረኝ ፈልጋ ነው” አላት መልሳ እንድትጠይቀው
በማያደፋፍር አነጋገር ።
“ ከሷ ጋር ስታነበው የነበረው ምን ነበር ?”

ቀጠለች የማትሰለቸውና ከጀመረች የማትለቀው ኮርኒሊያ "
“ ይኽም በዛ ፤ ቆነጃጂት የፍቅር ደብዳቤዎቻቸው ምስጢረኛ ሲያደርጉኝ
ምስጢራቸውን ማውጣት አልችልም ” አላት እንዲያ ቀላልዶ ርዕስ ለመለወጥ ስለ ፈለገ
“ ነገሩን ምስጢር ሳታደርግ መግለጽ ስትችል ትቀልዳለህ " እሷ አሁንም
አሁንም በጣም ነው የምትፈልግህ ለምን እሷ የምትፈልገውን አትነግረንም ?”
ሚስተር ካርላይል እኅቱን ዝም እንድትል በሚያስጠነቅቅ አመለካከት አያት እሷ ደግሞ ልትፈራውና ካሰበችው ልትመለስ ቀርቶ ባሰች "
“ አርኪባልድ! አርኪባልድ!” አለችው ደጋግማ “ ያለፈው ነገር የሚዶገም እንዳይመስልሀ ”
ያለፈ ነገር ስትል ለሚስተር ካርላይል እንደ ገባው የሪቻርድ ሔር ጉዳይ ማለቷ
ነበር ሳቤላ ደግሞ ያለፈ ነገር " ማለት የባሏንና የባርባራን የዱሮ ፍቅር መሰላት

ምነው ዝም ብለሽ ራትሽን ብትበይ ኮርኒሊያ አላት ኮስተር ብሎ "ከዚያ እንደገና ፈታ ብሎ በሙያዬ ሚስጢር ብላ የነገረችኝን እንድናገር አትጠይቂኝ
አላደርገውም " አንተስ ምን ትላለህ ካፒቴን ሌቪሰን?”

ካፒቱን ሌቪሰን ፈገግ ብሎ እጅ ሲነሣ ለሳቤላ ግን ምን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነበር " ሚስ ኮርኒ ካርላይልም ጸጥ ብላ ወደ ራቷ አተኮረች
የዚያኑ ዕለት ማታ ሳቤላ ከባሏ ጋር ብቻዋን ዐመፀኛው ልቧ እንድተናገር አስገደዳት " " ያች ባርባራ ሔር ይህን ያህል የምትፌልህ ለምንድ'ው ?

የግል ጉዳይ ነው . . ሳቤላ ከናቷ መልእክት ታመጣልኛላች "

"ጉዳዩ ከኔ መደበቅ አለበት?

ልንገራት አልንገራት እያለ ለጥቂት ጊዜ ዝም ብሎ ቆየ " ነገር ግን ካፒቴን ቶርን መጠርጠሩን መናገር ተግቢ ያልሆነ ስሕተት ነው የሪቻርድ ሔር በምስጢር መምጣት እንኳን አስድዳ ያናገረችው ሚስ ኮርኒሊያ ናት ያውም እሷ ለሌላ ትናገራች ብሎ ስለማይጠረጥራት ነው እንጂ ለማንም ሊተነፍሰው አልፈለገም ነበር።


ማወቅ አያስደስትሽም ሳቤላ የሔርን ቤተሰብ የሚመለከት አንድ
ከባድ ምስጢር መኖሩን ታውቂያለሽ የኔና የሷ ንግግር ከዚያ ምስጢር ጋር በተያያዘ ጉዳይ ነው

ከነገራት መልስ አንዷን ቃል እንኳን አላመነችም ሚስቱ እንደ መሆኗ መጠን እውነቱን የነገራት እንደሆነ ትቆጣለች ብሎ የፈራ መሰላት ስለዚህም የባሰውን ተናደዶች አሁንም ሚስተር ካርይል ይከፋታል ብሎ አልጠረጠረም የቅናት ነገር ገና ዱሮ ከልቧ ያስወጣውና አሁን ያለን ምንም መጠራጠር የምታምነው ይመስለው ነበር "

በበነጋው ጠዋት መንፈሷ ተረብሾ ሚስተር ካርላይል ወደ ቢሮው ሲሔድ እንደ
ወትሮው አልሸኘችውም ብስጭትጭት ብላ ተቀምጣ ቀረች ካፒቴን ሌቪሰንና ሚስተር ካርላይል ከውጪ በር ድረስ እየተጫወቱ አብረው ሔዱ" የግቢውን በር ከወጡ በኋላ ተለያዩ ከዚያ ሌቪሰን ቁጥቋጦ ለቁጥቋጦ እየተሹለከከ ከሩቅ
ተከትሎት ሔዶ ። ባርባራ ካርላይልን ከበሯ ቁማ ስትጠብቀው ኖሮ አገኛት በጣም ምክክር ሲማከሩ እንዳያቸው ሌቪስን ተመልሶ መጥቶ ለሳቤላ ነገራት " እሷም
የሰማችውን መርዶ አያሰላሰለች እንደ ተቀመጠች አንድ ማስታወሻ ደረሳት ገልጣ ስታየው በተከታዩ ማክሰኛ ማታ ለሚስተርና ለሚስዝ ካርላይል እንዲሁም
ለሚስ ካርላይል የራት ግብዣ ጥሪ መሆኑን አየች » ለሚስ ካርላይል እንድታየው
ሰጥታ እሷ መልስ ለመጻፍ ትዘጋጅ ጀመር ።

ትሔጃለሽ ?'' አለቻት ሚስ ካርላይል "

“ አዎን ሚስተር ካርላይልና እኔ ሁለታችንም ለውጥ እንፈልጋለን ስለዚህ
ምንም እንኳን ለአንድ ምሽት ቢሆንም እንቀበለዋለን " አለቻት ሳቤላ " ይህ አሳዛኝ ቅናት ይህ የባሏን አለማመን የእመቤት ሳቤላን ጠባይ የለዋወጠው መሰለ "

“ ካፒቴን ሌቪሰን ለብቻው ይቅር ? አለቻት ሚስ ካርላይል "
ሳቤላ ምንም ሳትመልስ ከጠረጴዛው አቀርቅራ መልስ ለመጻፍ ልትጀምር
ስትል “ ካፕቴን ሌቪሰን እኮ ነው የምልሽ '' አለች ሚስ ካርላይል "

“እሱማ ከዚህ ቆይቶ ራቱን ብቻውን ሊበላ ይችላል እርስዎስ ግብዣውን
ተቀብለዋል ብዬ ልጻፍ ? አለቻት "

“ አይ .... እኔ አልሔድም
አለች ሚስ ኮርኒሊያ ካርላይል "
“ይኸማ ከሆነ ስለ ካፒቴን ሌቪሰን ምንም ችግር አይኖርም” አለች ሳቤላ"

“ እኔ እሱን ሰውዬ አልቀርበውሞ ውቃቢዬ አይወደውም ” ብላ ጮኸች
ሚስ ካርላይል “ እንዲያውም ከሚስዝ ጀፈርሰን ጥሪ እገኝ ነበር! ግን አዲስ ቀሚስ ያስፈልገኛል

“ እሱስ ቀላል ነው እኔም ለራሴ አንድ እፈልጋለሁ " ስለዚህ እንገዛለን”
አለች ሳቤላ

ምን ?. አዲስ ቀሚስ ትፈልጊያለሽ ? ለምን ? በደርዘን የሚቈጠር እያለሽ !!

ሁሉ ተጠቃሎ አንድ ደርዘን መሙላቱንም እንጃ” አለች ሁልጊዜ የሷን ሐሳብ ለማጨናገፍ በምታደርገው ሙከራ የተመረረችው ሳቤላ በኮርነሊያ ንግግር
በመበሳጨት "

ሳቤላ ስለ ጥሪው የጻፈችውን መልስ አጥፋና አሽጋ ደወለችና አሽከር ገባ
ደብዳቤውን እንዲያደርስ ሰጥታው ሲወጣ ዊልስንን እንዲልካት ነገረችው " ዊል
ሰን ገባች

“ ለዛሬ ነበርኮ ዊልሰን ልብስ ሰፊው የልጂቱን የሚስ ሳቤላን ቀሚስ ለመለካት ሊመጣ የነበረው? ” አለች ሳቤላ "
ዊልሰን አመነታች ከእመቤቷ ወደ ሚስ ካርላይል እየተመለከተች ስታጕተመትም ሚስ ካርላይል ከሥራዋ ቀና ብላ ተመለከተች "

“ሳቢላ አዲስ ቀሚስ ስለማያስፈልጋት ልብስ ሰፊውም እንዳይመጣ አድርጌአለሁ” አላቻት

“ስለማያስፈልጋት ? መለሰች እመቤት ሳቤላ ከዚያ በፊት ለሚስ ካርይል
አሳይታት በማታውቀ ከፍተኛ የቁጣ ገጽታ “ለልጆቼ ስለሚያስፈልጋቸው ነገር
እኮ እኔ ነኝ የማውቅ !
👍15
ብዙ ቀሚሶች አሉዋት " ያ ባለመሥመሩ የሐር ቀሚሷም ተገልብጦ ቢሰፋ
ጥሩ ልብስ ይወጣዋል።”
ሳቤላ የጠረጴዛዋን ኪስ ሳበችና አጭር ማስታወሻ ጽፋ ልብስ ሰፊው ባስቸኳይ ኢስት ሊን ድረስ እንዲመጣ ላከችበት "

ሚስ ካርላይል በቁጣ አጉራራች „ “ ተይ ! ባልሽ ሀብቱን ሁሉ ጨርሶ ሲደኸይ የኔን ምክር ባለ መስማትሽ ይቆረቁርሻል እንደ መጋዣ እየሠራ ግን ወጭውን መቀነስ አልቻለም

ይሀን አባባል ሚስተር ካርላይልን ካገባች ጀምሮ ስትሰማው የኖረችው ነው "
በርግጥ ወጪያቸው ከባድ መሆኑንም ታውቅ ነበር ስለዚህ ራሷም ሆነ ለልጆቿ
ለትንሿ ሳቤላ ያሰበችውን ቀሚስ መልሳ ተወችው " በዚህ ምክንያት ኀዘኗ በረታ
መንፈሷ ድቅቅ አለ " የምትሆነው አጣች " ልቧ ፍስስ አለ " በዚህ ሁኔታ ጥቂት ቀኖች ዐለፉ .....

💫ይቀጥላል💫
👍146
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ



...“ክሪስቶፈር” አልኩ እየጮህኩ፤ ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም አንዳንድ ጊዜ እናቴን እጠላታለሁ! ያ ብቻ አይደለም አንዳንዴ አንተንም እጠላሀለሁ አንዳንዴ ሁሉንም ሰው በተለይ ራሴን እጠላዋለሁ! አንዳንዴ በሞትኩ ብዬ እመኛለሁ:
ምክንያቱም እዚህ ቦታ በቁም ከመቀበር መሞት ይሻላል! እኛ የበሰበሰ፣ የሚራመድ፣ የሚያወራ አትክልቶች ነን!...

ሚስጥራዊ ሀሳቦቼ በሙሉ ይፋ ወጡ፤ ልክ እንደ ቆሻሻ ተዘርግፈው ሁለቱንም
ወንድሞቼን አስደነገጣቸው፡ ትንሸዋ እህቴ ደግሞ መንቀጥቀጥ ጀምራ የበለጠ ትንሽ መሰለች እነዚያ ጨካኝ ቃላት ከአፌ እንደወጡ ወዲያውኑ እንዲመለሱ ፈለግኩ በእፍረት ሰመጥኩ፣ ይቅርታ መጠየቅና መመለስ አልቻልኩም።ዞርኩና እየሮጥኩ ወደ ልብስ ማስቀመጫው ከዚያ ወደ ደረጃዎቹ ከዚያ ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ሄድኩ። ስጎዳ፣ ብዙ ጊዜም እጎዳለሁ ሙዚቃ ፈለግኩ፤ የዳንስ ልብሴን ለበስኩና ችግሮቼን ሁሉ ለመርሳት መደነስ ጀመርኩ።
እስኪደክመኝ ድረስ መደነስ ቀጠልኩ፡ ከዚያ ድንገት ሙዚቃው ሲያልቅ
ቀኝ እግሬ ታጠፈና ወለሉ ላይ ወደቅኩ። ለመነሳት ብታገልም መራመድ
አልቻልኩም: ጉልበቴን በጣም አሞኛል: ሌላ አይነት እምባ ወደ አይኖቼ
መጣ እየተጎተትኩ ወደ መማሪያው ክፍል ሄድኩኝ፡ ጉልበቴ ለዘለዓለም
ባይሰራም ግድ አልነበረኝም መስኮቱን በሰፊው ከፈትኩና ወደ ጥቁሩ ጣራ ወጣሁ። እያመመኝ መታጠፊያው ጫፍ ደረስኩና በውሀ መውረጃው አሸንዳ
ጠርዝ ላይ ስደርስ ቆምኩ። ታች ያለው መሬቱ ነው። ፊቴ ለራሱ የማዘን እምባና ህመም ምልክት አወጣ፣ እምባዬ እይታዬንም ብዥ አደረገው አይኖቼን ጨፍኜ ሚዛኔን ሳልጠብቅ መወዛወዝ ጀመርኩ፡ በደቂቃዎች ውስጥ
ሁሉም ያበቃል። እሾሀማ የፅጌረዳ ተክሎቹ ውስጥ እወድቃለሁ።

አያትየውና እናቴ አንዲት የማትታወቅ ደደብ ልጅ ጣሪያው ላይ ወጥታ
ድንገት ወደቀች ሊሉ ይችላሉ። እናቴ ሞቼና ተሰብሬ የሬሳ ሳጥን ውስጥ
ተጋድሜ ስትመለከት ታለቅስ ይሆናል። ከዚያ ያደረገችውን ታስታውስና
ክሪስንና መንትዮቹን ነፃ ለማድረግ በሩን ከፍታ እንደገና እውነተኛ ኑሮ
እንዲኖሩ ታደርግ ይሆናል።

ያ ራሴን የመግደሌ ወርቃማ ጎን ነበር።

ሌላኛውን ጎን ማየት አለብኝ: ካልሞትኩስ? ብወድቅና አወዳደቄ የሚገል ሳይሆን ቀርቶ ህይወቴን ሙሉ አካለ ጉዳተኛ ወይም ጠባሳ ቢያደርገኝስ? ከዚያ እንደገና ምናልባት ብሞትና እናታችን ባታለቅስ ወይም ባታዝን ወይም ባትፀፀትስ? እንዲያውም እንደኔ አይነቷን ተባይ በማስወገዷ ደስ
ቢላትስ? ክሪስና መንትዮቹ ያለ እኔ እንዴት ይሆናሉ? ማን ይንከባከባቸዋል?
ለመንትዮቹ ማን እናት ይሆናቸዋል?

ክሪስ ምናልባት አይፈልገኝ ይሆናል፤ የሚገዛለት ትልቁ ውዱ መፅሀፍ የኔን
ቦታ ይተካለት ይሆናል ከስሙ በፊት ዶክተር የሚለውን ማዕረግ ሲያገኝ
ህይወቱን ሙሉ ለመርካት በቂ ይሆንለት ይሆናል ግን ዶክተር ቢሆንም በቂ እንደማይሆን፣ እኔ ከሌለሁ በጭራሽ በቂ እንደማይሆን አውቃለሁ።ሁለቱንም ገፅ ለማየት ባለኝ ችሎታ ከሞት ተረፍኩ፡

ህፃንነትና ሞኝነት እየተሰማኝ ከጣሪያው ጠርዝ ስርቅ አሁንም እያለቅስኩ ነበር ጉልበቴ በጣም ስላመመኝ የጭስ መውጫው ጀርባ ጋ እስክደርስ ድረስ ጣሪያው ላይ ዳዴ እያልኩ እየሄድኩ ነበር። ሁለት ጣራዎች ተገናኝተው ምቹ ጥግ የፈጠሩበት ቦታ ነው: በጀርባዬ ተጋድሜ የማይታየውና ግድ
የሌለው ሰማይ ላይ አፈጠጥኩ። እግዚአብሔርም ሆነ መንግስተ ሰማያት
እዚያ መኖራቸውን ተጠራጠርኩ።

እግዚአብሔርና መንግስተ ሰማያት እዚሁ ምድር ላይ በአትክልት ስፍራዎቹ፣
በጫካዎቹ፣ በመናፈሻዎቹ፣ በባህር ዳርቻዎቹ፣ በሀይቆቹና በአውራ ጎዳናዎቹ ውስጥ ናቸው።

ሲኦልም እዚሁ ነው… እኔ ያለሁበት ያለማቋረጥ የከበበኝ ወደ እሱ ሊወስደኝ
የሚሞክርና አያትየው እንደምታስበው የሰይጣን ዘር ሊያደርገኝ የሚጥር
ነው።

ጨለማ እስኪሆን ድረስ እዚያ ጠንካራና ቀዝቃዛ ጣራ ላይ ተጋደምኩ።
ጨረቃ ወጣች፣ ኮከቦቹም ምን እንደሆንኩ እንደሚያውቁ ሁሉ በቁጣ እኔ ላይ አበሩ የለበስኩት የዳንስ ልብስ ብቻ ነበር ከብርዱ የተነሳ ክንዶቼ ላይ ሽፍ አለብኝ አሁንም በቀሌን እያቀድኩ ነው፡ ከመልካም ወደ ክፉ የለወጡኝንና
ከዚህ ቀን ጀምሮ የምሆነውን አይነት ሰው ያደረጉኝን እበቀላለሁ። አያቴና እናቴ በመዳፌ ስር የሚሆኑበት ቀን እንደሚመጣ ራሴን አሳመንኩት አለንጋ
እይዛለሁ፣ ሬንጁንም እይዛለሁ፣ የምግብ አሰጣጥም እቆጣጠራለሁ።

ምን እንደማደርጋቸው ለማሰብ እየሞከርኩ ነው:: ትክክለኛው ቅጣት
ምንድነው? ሁለቱንም ቆልፌባቸው ቁልፉን መወርወር? እኛ እንደተራብነው ማስራብ?

ለስላሳ ድምፅ ምሽቱንና የተጠላለፉ ሀሳቦቼን አቋረጠ። ክሪስ እያመነታ
ስሜን እየጠራ ነው: ምንም አልተናገረም ስሜን ብቻ ይጠራል: መልስ
አልሰጠሁትም አልፈልገውም፣ አሳፍሮኛል ማንንም አልፈልግም ባለ መረዳቱ አልፈልገውም።
የሆነው ሆኖ መጣና አጠገቤ ጋደም አለ። ምንም ቃል ሳይናገር ይዞት
የመጣውን ሞቃት የሱፍ ጃኬት ደረበልኝ፡ ልክ እንደ እኔ ወደ ቀዝቃዛውና
የተከለለው ሰማይ ላይ አፍጥጧል በመከላችን አስፈሪና ረጅም ፀጥታ
ነገሰ። ስለ ክሪስ የምጠላው ወይም የማልወደው ምንም ነገር የለም ወደ እሱ ዞሬ ይህንን ልነግረውና የሚሞቅ ጃኬት ስላመጣልኝ ላመሰግነው በጣም
ፈልጌያለሁ። ነገር ግን አንዲት ቃል መናገር አልቻልኩም: የሚሰማኝን
እሱና መንትዮቹ ላይ ስለተወጣሁት እንደተፀፀትኩ እንዲያውቅ ፈልጌ ነበር።ማንኛችንም ሌላ ጠላት እንደማያስፈልገን እግዚአብሔር ያውቃል በጃኬቱ ውስጥ ሆነው የሚንቀጠቀጡት ክንዶቼ አቅፈው ሊያፅናኑት ናፍቀዋል ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ከቅዠቴ ስባንን የሚያባብለኝ እሱ ነው ነገር ግን ማድረግ የቻልኩት ብቸኛው ነገር፣ እዚያው ጋደም ብዬ በብዙ ነገሮች የተያዝኩ መሆኔን እንዲረዳ ተስፋ ማድረግ ብቻ ነበር።

ሁልጊዜ አስቀድሞ ነጭ ባንዲራ የሚያውለበልበው እሱ ነው፡ ለዚህም
ለዘለአለም አመስጋኝ ነኝ። እንግዳ በሆነ ጎርናና እና ውጥረት በሚሰማበት
ከሩቅ የሚመጣ በሚመስል ድምፅ፤ እሱና መንትዮቹ ራታቸውን እንደበሉና
ለእኔ ድርሻዬን እንዳስቀመጠልኝ ነገረኝ፡ “እና ከረሜላዎቹን ሁሉ በላናቸው ያልነው እያስመሰልን ነው ካቲ ለአንቺ ብዙ ተቀምጦልሻል” አለኝ።

ከረሜላ? ስለ ከረሜላ ያወራል፤ አሁንም ከረሜላ የእምባ ማበሻ በሆነበት
የልጆች አለም ውስጥ ነው? እኔ አድጌ ለልጆች መደሰቻ ጉጉት አጥቼያለሁ።
የምፈልገው ሌሎች በእኔ እድሜ ያሉ ልጆች የሚፈልጉትን ነው፤ የምፈልገው ወደ ሙሉ ሴትነት ማደግ የምችልበትን ነፃነት ነው፤ ህይወቴን በሙሉ የምቆጣጠርበትን ነፃነት ነው፡፡ ይህንን ልነግረው ስሞክር ድምፄ ልክ እንደ እምባዬ ደረቀብኝ
ካቲ ያልሺው ነገር... ሁለተኛ አስቀያሚና እንደዚያ አይነት ተስፋ ቢስ ነገሮች አትናገሪ” አለኝ፡

“ለምን?” ተናነቀኝ “የተናገርኩት እያንዳንዱ ቃል እውነት ነው፡ የተናገርኩት በውስጤ የሚሰማኝን ነው ያወጣሁት አንተ በውስጥህ የቀበርከውን ነው
ከራስህ መደበቅህን ቀጥልበት እነዚያ እውነታዎች ወደ አሲድነት ተቀይረው ውስጥህን ሲበሉት ታገኛቸዋለህ!” “አንድ ጊዜም መሞት ተመኝቼ አላውቅም”
👍46🥰31
አለ በቀዝቃዛና ጎርናና ድምፅ፡ “ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ነገር አትናገሪ
ወይም ስለ ሞት አታስቢ!” እርግጥ ነው በውስጤ የተደበቀ ጥርጣሬ አለ ግን
እስቃለሁ፤ ፈገግ እላለሁ፤ እና ራሴን እንደምንም አፅናናለሁ ምክንያቱም
በህይወት መቆየት እፈልጋለሁ፡ “በራስሽ እጅ ብትሞቺ እኔንም ይዘሽኝ ነው የምትሄጂው እና ወዲያው ደግሞ መንትዮቹም ይከተላሉ ምክንያቱም የዚያን
ጊዜ ማን እናት ይሆናቸዋል?”

አሳቀኝ ምሬት ሲሰማት የምትስቀውን የእናቴን አሳሳቅ ግልባጭ የሆነ
መራራና አስቀያሚ ሳቅ ሳቅኩ። “ለምን፣ ለምን ክሪስቶፈር? ውድ ጣፋጭና
አፍቃሪ፣ ሁልጊዜ የእኛን ፍላጎት የምታስቀድም እናት አለችን አይደል እንዴ?
እሷ መንትዮቹን ትንከባከባለች "

ክሪስ ወደ እኔ ዞረና ትከሻዬን ያዝ አደረገ: “አንዳንዴ ልክ እሷ በምትናገረው
በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ስትናገሪ ያስጠላኛል: ለኬሪና ለኮሪ ከእሷ የበለጠ
አንቺ እናታቸው እንደሆንሽ የማላውቅ ይመስልሻል? መንትዮቹ እናታቸውን
ልክ እንደ እንግዳ አፍጥጠው እንደሚያዩዋት የማላስተውል ይመስልሻል?
ካቲ እኔ እኮ እውርም ደደብም አይደለሁም: እናታችን በመጀመሪያ
የምትንከባከበው ራሷን
ቀጥሎ ግን እኛን እንደሆነ አውቃለሁ።” ጨረቃ
ወጥቶ አይኖቹ ላይ የረጋውን እምባ አሳየኝ፡ ጆሮዬ ውስጥ የገባው ድምፁ አደጋ መጋፈጥ የሚችል፣ የሚያባብልና ጥልቅ ነበር፡

ይህንን ሁሉ ሲናገር ድምፁ ውስጥ ምሬት አልነበረም ፀፀት ብቻ ነበር። ልክ
ዶክተር በሽተኛውን የመጨረሻ ደረጃ የደረሰ ህመም እንዳለበት እንደሚነግርበት አይነት ስሜት አልባ መንገድ ነበር
የዚያን ጊዜ ነበር ፀፀት እንደ መቅሰፍት ጎርፍ የመጣብኝ፡ ክሪስን እወደዋለሁ፣
ወንድሜ ነው። ሙሉ ያደርገኛል፤ ያጣሁትን ሰጥቶኛል፤ አውሬና ተናዳጅ
ስሆን መረጋጋት ሰጥቶኛል። መረጋጋት እናታችንና አያቶቻችንን መልሶ
ለማጥቃት እንዴት ያለ ጥሩ መንገድ ነው! እግዚአብሔር አያይም: ኢየሱስ መስቀል ላይ የሞተ ቀን ለሁሉም ነገሮች አይኑን ጨፍኗል። አባታችን ግን እዚያ ነው ወደ ታች እየተመለከተ… እና በእፍረት ተሸማቀቅኩ።

“ተመልከቺኝ ካቲ፣ እባክሽ ተመልከቺኝ"

“አንዱም ነገር ከልቤ አልነበረም፤ ክሪስ እውነቴን ነው ሌሎች እንደሚኖሩት
መኖር እፈልጋለሁ፤ ግን የሆነ መጥፎ ነገር የሚሆንብን ሁልጊዜ የሚዘጋብን ስለሚመስለኝ እፈራለሁ። መጥፎ ነገር የተናገርኩት ልቀሰቅሳችሁ እንድታዩ ላደርጋችሁ ፈልጌ ነው ክሪስ… ከብዙ ሰዎች ጋር መሆን፣ አዳዲስ ፊቶችና አዳዲስ ክፍሎች ማየት እጅግ ፈልጌያለሁ። ለመንትዮቹ እስከሞት ድረስ
ፈርቻለሁ፡ ሱቅ መሄድ፣ ፈረስ መጋለብና እዚህ ልናደርጋቸው የማንችላቸው
ነገሮች ሁሉ ማድረግ እፈልጋለሁ።

በጨለማ ጣሪያው ላይ በብርድ እርስ በርሳችን በስሜት ተቃቀፍን፡ እንደ
አንድ ሆነን ልቦቻችን እርስ በርሳቸው በሀይል ይደልቁ ነበር። ልቅሶም የለ ሳቅም የለ፤ ከዚህ በፊት ውቅያኖስ የሚሞላ ያህል እምባ አላፈሰስንም? መዳን አልጠበቅንም? እምባ ካልረዳና ፀሎት ካልተሰማ ታዲያ እንዴት ግን ምንም አልረዳንም በሚሊየን የሚቆጠሩ ፀሎቶችን ፀልየን የማይመጣ እግዚአብሔርን አግኝተን የሆነ ነገር እንዲያደርግልን ማድረግ እንችላለን?”

ክሪስ፣ ከዚህ በፊት ብየዋለሁ አሁንም በድጋሚ እለዋለሁ። ጅማሬውን
እኛ ማድረግ አለብን
አባታችን ሁልጊዜ የሚለው እግዚአብሔር የሚረዳው
ራሳቸውን የሚረዱትን ነው፣ አይደል?”

ጉንጩን ከጉንጬ ጋር አጣብቆ ለረጅም ጊዜ ሲመሰጥ ቆየ፡ ከዚያ
“አስብበታለሁ። ሆኖም እናታችን እንዳለችው ወደዚያ ሀብት በማናቸውም
ጊዜ ልንመጣ እችላለን።”...

ይቀጥላል
👍3215🥰5
#ሀገሬ

የድልሽ ውብ ምስል
ሰንደቅሽ ላይ ሲሳል
በልጆችሽ ገድል
የጎጥ ካብ ይፈርሳል።

🔘ኢዛና መስፍን🔘
👏228👍8
በህይወት መንገድ ላይ…
ተጋቾቹ
ምዕራፍ-8
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
///
ከህይወት መከራ ቀጥታ የሚገኝ ልምድ ከማንበብም ሆነ ከትምህርት ብሎም በፊልም ከማየት የሚገኝ አይደለም...አሁን ይታያችሁ ከመሬት በታች ተቀብራችሁ በየትኛው ደቂቃ መሬቱን ተደርምሶ እንደሚያበቃላችሁ ወይም በጥልቁ ከርሰምድር ኑዋሪ የሆነ አውሬ አንገታችሁን ፈጥርቆ በማነቅ ይዋጣችሁ .ወይንም አስፈሪ መንፈስ ድንገትአዛው አጠናግሮ ያስቀራችሁ በማታውቁበት ሁኔታ ከእነዚህ ሁሉ ስሜቶች ጋር እያታገላችሁ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ከምትወዱትና ከምታከብርቱ ጓደኛችሁ እሬሳ ጎን ለሳዕታት ቁጭ ብላችሁ…ደግሞ አንደኛዋ ጓደኛችሁ የት እንደገባች ሳታውቁ ብን ብላ ጠፍታባችሁ የሚሰማችሁን ስሜት በምን አይነት ቃላት ለሌላ ሰው ማስረዳት ትችላላችሁ…?ሰሚውስ በምን አይነት ተአምራዊ አቅሙ ሙሉ ስሜታችሁን ሳይሸራርፍ ሊረዳችሁ ይችላል?
‹‹ሰዎች ደነዘዝን እኮ…በቃ እዚሁ አብረነው ከሬሳው ጋር እሬሳ ሆነን ለመቅረት ወስነን ተስፋ ቆርጠናል ማለት ነው?››አይዳ ነች ከወትሮው በጣም ቀሰስተኛና እንክትክት ባለ ድምፅ ሀሳቧን ያቀረበችው፡፡
‹‹ምን እናድርግ ታዲያ..?ሰላምስ እሺ በራሷ ጊዜ ተሰውራ ይሁን አልያም ጠባቂ መላአኬ የምትለው በክንፉ አንጠልጥሎ ይዛት አርጎ አናውቅም ስራችን የለችም...አጠገባችን የተኛውን ጋሼ አህመድን እንዴት አደርገነው ወደ ፊት እንንቀሳቀሳለን?››
‹‹አዎ እናንተ ሁለታችሁ ሂዱ.. እኔ እዚህ ከእሱ ጋር እሆናለው››አለ በሪሁን ፡፡
‹አይ …ገና ይሳካልን አይሳካልን ለማናውቀው ነገር ተጣጥለን አንሄድም.. .እዚሁ የሚሆነውን እንጠብቃለን›አልኩ በቁርጠኝነት፡፡
‹‹አይ .አንተ አይዳን ይዘሀት ሂድ….›>በሪሁን አምርሮ ተቃወመ፡፡
‹‹ሰዎች ምን እያወራችሁ ነው ….?በአየር እጥረትና በመከራ መደራረብ የማሰብ አቅማችን እየተዳከመ ይመስለኛል…እውነታውን አምነን ተቀብለን ቢያንስ እስከቻልነው ድረስ ወደፊት መቀጠል አለብን…ሰላምም በመጨረሻ ንግግሯ ልትመክረን የሞከረችን ይሄንኑ መሰለኝ...ጋሼ አህመድ አንዴ ሞቷል…. በቃ ምንም ብናደርግ ነፍሱን መመለስ አንችልም…ግን ደግሞ ቤተሰቦች እንዳሉት አትርሱ… ቢያንስ ከመካከላችን አንዳችን እንኳን ተሳክቶልን ተርፈን ለባለቤቱና ለልጆቹ አባታቸው ወደእነሱ በህይወት ለመመለስ ምን ያህል ሲጥር እንደነበር አስረድተናቸው ልናፅናናቸው ከቻልን ቀላል ነገር አይደለም፡፡
‹‹አዎ እውነትሽን ነው…ከዚህ እንደምንም በህይወት ወጥቼ ልጆቹን መርዳት አለብኝ…አዎ እነሱን ማሳደግ ኃላፊነቱ የእኔ ነው፡፡እንደውም ሁላችንም አንዴ እጃችንም ጓደኛችን በድን ላይ እንድናኖር እፈልጋለው››
‹‹ም አልክ በሪሁን?››ገራ በመጋባትና በፍራቻ ጠየቅኩት፡፡
‹‹እጃችሁን አምጡ…››.የሶሰታችንንም እጅ በጋሽ አህመድ እሬሳ ልብ አካበባቢ አንድ ለይ አደራርበን ጫን
‹አሁን ጥለነው ከመሄዳችን በፊት ቃል ኪዳን እንገባለታለን..የምለውን ደግማችሁ ትላላችሁ.››
‹እኛ ጓደኞችህ›
‹‹እኛ ጓደኞችህ››ያለውን ደገምነው…የታደለ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሰልጣን ተሰጥቶት በተወካዬች ምርክር ቤት ፊት ቀርቦ በጠቅላይ አቃቢ ህጎ አማካይነት ቃል ይገበል እኛ እዚህ የጓደኛችንን ሬሳ አጋድመን በጨለማ ውሰጥ ሁለት ፐርሰንት በህይወት የመትረፍ እድል ይዘን ቃል እንገባለን፡፡
‹‹ከመካከላችን አንዳችን እንኳን በህይወት ከተረፍንና ወደ ኑሮችን ከተመለስን….››
‹‹በተቻለን አቅም ልጆችህን ልናስተምርና ልንረዳ ቃል እንገባለን››
‹‹ቃል አንገባለን››
የቃል ኪዳኑን ስነ-ስርዓት ካጠናቀቅን ቡኃላ እጃችንን ለቀቀና ከተቀመጠበት ተነሳ…‹‹ሞባይልህ ባትሪ አለህ አይደል አብራልኝ›አለኝ
አበራውለትና የሚያደርገውን ማየት ጀመርኩ …ሬሳውን አስተካክሎ መገነዝ ጀመረ ..ፊቱን በጨርቅ ሸፈነው…ከዛ በአቅራቢያችን የተቆለውን አፈር እየዛቀ ማልበስ ጀመረ……
ብቻ አስፈሪ የሆነና እና የተለየውን የቀብር ስነ-ስርአት በ10 ደቂቃ ውስጥ አጠናቀን ጉዞችንን ለመቀጠል ዝግጁ ሆንን…የቀረችንን ተወሰነች ሬሽንና አራት የሀይላድ ውሀ ያዝን ….በሪሁን አንድ ብስኩትና አንድ ውሀ አነሳና አፈር የተጫነበት እሬሳ ላይ አስቀመጠና ‹‹በሉ እንሂዴ.›› አለና ቀድሞና ከፊት ለፊታችን መራመድ ጀመረ
አሁን በጣም ውድ የሆነ ውሀና ምግብ ለሬሳ መስጠት ምን የሚሉት የስነልቦና ጫወታ ነው?›› ስል አሰብኩ…የጥንት ፈርኦኖች ለቀብራቸው ባሰሩት ፕሪሚዳቸው ውስጥ ሞተው ሲቀበሩ ወርቅና እንቁዋቻቸው ብቻ ሳይሆን ሚስቶቻቸውንም ጭምር አብረዋቸው ይቀበሩ እንደነበር ታሪክ ይነግረናል … .እና ያቺ የሰው ልጅ ስነ-ልቦና ከልጅ ለጅ በዲ.ኤን.ኤ እየተላለፈች መጥታ ዛሬም ይሄው እኛ ፈፀምናት…
.በሪሁን ባደረገው ነገር የተከራከረው ሰው የለም የቀረውን እቃችንን ተከፋፍለን ይዘን ጉዞ ጀመርን ..ዋሻው አንዴ ተንርቦርቅቆ ይሰፋል ..አንዴ ደግሞ ለማለፍም እስኪያስቸግር ድረስ ይጠባል..ከ45 ደቂቃ ጉዞ ቡኃላ ይመስለኛል ወደተታች አንሸራቶ የሚያስወርድ ገደል ያለበት ቦታ ገጠመን …
‹‹እንዴት ነው የምናደርገው.?››ግራ ገብቶኝ ጠየቅኩ
ሁላችንም በየራሳችን መፍትሄ ለማመንጨት ትካዜ ውስጥ ገባን …መፍትሄ ለማምጣቱ እንደተለመደው በሪሁን ቀደመን…ድንገት የሚቆፈር ነገር ካጋጠመን ብለን ከያዝነው ሁለት ብረቶች መካከል አንዱን ወደመሬት አስተካከለና በአንደኛው እየቀጠቀጠ ወደ መሬት ውስጥ መቅበር ጀመረ…
‹‹ምን እየደረክ ነው?››አይዳ ጠየቀችው
‹‹ላሳያችሁ አይደል…?›› ብሎ የለበሰውን የጅንስ ጃኬት አወለቀና በወፍራሙ በቢላዋ መተልተል ጀመረ..ከዛ እርስ በርስ ቋጠራቸውና መሬት ውስጥ ከቀበረው ብረት ላይ አጥብቆ አሰረው..
አሁን እኔን በደንብ እዩና እኔ እንደማደርገው አድርጋችሁ ትወርዳላችሁ …››አለና በጨርቁ ላይ እየተንጠለጠለ በቀላሉ ወረደ፡፡
‹‹.... አትፍሩ ..ብዙም አያስቸግር.መጀመሪያ ግን ዕቃውን በጫፍ ላይ አስራችሁ ቀስ ብችሁ ልቀቁት ›የሚል ትዕዛዝ ሰጠን…. እንዳለን አደረግን፡፡
‹ትወርዳለህ ልቅደምህ.?››አለችኝ
‹‹አይ ቅደሚ አይዞሽ.ቀስ ብለሽ.ደግሞ ጨርቁን በደንብ አጥብቀሽ ያዢው›
‹አትጨነቅ እይዘዋለው ››አለችና..ጨርቁን ይዛ እየተንሸራተተች መውረድ ጀመረች…በጣም ነበር የሰጋውት …እግዜር ይመስገን በሰላም በሪሁን ካለበት ደረሰች. . አቅፎ ተቀበላትና መሬት አሳረፋት
…ቀጥሎ የእኔ ተራ ነው …ጨርቁን በእጆቼ ሁለት ዙር ጠቅልዬ ያዝኩና በእግሬ ለመቆንጠጥ እየመከርኩ መውረድ ጀመርኩ፤.ያስፋራል.፤ወደታች ሳይ ገና ምኑን አልያዝኩትም‹‹..በርታ .በርታ › የሚለው የአይዳ ጥኡም ድምፅ ይሰማኛል..አዎ እየበረታው ነው፡፡ ግማሽ አካባቢ ደረስኩ…ከዚህ ቡኃላ ብዙም አይከብደኝም ብዬ አስቤ እንኳን ሳልጨርስ ጨርቁ መሀከል ላይ ጣ.ጣ.ጣ ብሎ ተበጠሰ ፡፡ ዥው ብዬ ወደታች ….ብዥዥ አለብኝ…ዋሻው ከስር ወደላይ እየተገለባበጠ ያለ ይመስለኛል..
‹‹እሱም እንዳይሞት ..እሱም እንዳይሞት…››የሚለው የአይዳ ጩኸት እየተሰማኝ ጭልጥ ብዬ በዛው ጠፋው..ከምን ያህል ደቂቃዎች ቡኃላ እንደሆነ አላውቅም ስነቃ አይዳ ጭን ላይ ተኝቼያለው፡፡
👍24😁42
‹‹…ምንድነው የሆንኩት..?አልሞትኩም አይደል?.››ግራ በመጋባት ዙሪያ ገባዬን በማየት ጠየቅኩ
‹‹ደህና ነህ ...›አይዳ ነች
‹‹ምን ሆኜ ነው ጭንቅላቴ ነው የተጎዳው?›
‹‹አይ ጭንቅላትህ ደህና ነው..››
‹‹እና ተርፌያለሁ ማለት ነው….ለምን እራሴን ሳትኩ ታዲያ?››
‹‹ማለቴ››ልንገረው ወይስ ይቅርብኝ እያለች ከራሷ ጋር ሙግት እንደገጠመች ገባኝ…እና ደነገጥኩ፡፡
‹‹ንገሪኝ ምንድነው የተፈጠረው?››
‹‹እግርህ..››
‹‹እግሬ ምን ሆነ…?››ብዬ ከጭኗ ላይ ተነስቼ ስመለከት በጨርቅ ተጠቅልሏል
‹‹..ወለምታ ነው.?.››ብዬ ላየው ስል ሙሉ በሙሉ እንኳን መነሳት አልቻልኩም
‹‹ተረጋጋ አጥንትህ ስለተሰበረ..መንቀሳቀስ አትችልም››በሪሁን ቁርጤን ነገረኝ፡
‹‹አጥንትህ››
‹‹አዎ ከቁርጭምጭሚትህ ከፍ ብሎ አጥንትህ ተሰብሯል››
በዚህን ጊዜ ጥዝጣዜው ጭንቅላቴን መታኝ…ለካ እስከአሁን ደንዝዤ ስለነበር ነው….ወይኔ በቃ ብሞት ይሻላል…አዎ እውነቴን ነው እንደጋሼ አህመድ ሞቼ ተገላግዬ ቢሆን ትንሽ አዝነው ጥቂት አልቅሰው ያው እንደለመዱት አፈር አለብሰውብኝ .መንገዳቸውን በመቀጠል እድላቸውን ይሞክሩ ነበር….አሁንስ ?.አሁንማ በጣም መራር የሆነ ፈታኝ ምርጫ እንዲመርጡ ተገደዋል፡፡.ተሸክመውኝ አስር ሜትርም መሄድ አይችሉም..ስለዚህ ጥሩ ሰዎች ከሆኑ ገድለውኝ ይሄዳሉ ጨካኞች ከሆኑ ደግሞ እንደሆነ ይሁን ብለው ለስቃይና ለጣረሞት ባለውበት ትተውኝ መሄድ ብቻ ነው ያላቸው ምርጫ.፡፡
.እንዲህ አይነት መከራ ውስጥ ሆኜ ከወራት በፊት መስጦኝ ያየውትን Vikings …የሚል እርዕስ ያለው . ተከታታይ ፊልምን ትዝ አለኝ፡፡
በጦርነት፤ በሽሽትነና እንዲህ እኛ እንደገጠመን አይነት መከራ ጊዜ አካል ጉዳተኝነት እንዴት እንደሚስተናገድ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡
እዚህ ፊልም ላይ ዋና ገፀ ባህሪ ራግነር መጀመሪያ ጀግና ብቻ የሆነ ደፋርና ብልህ ፤ ከዛም ቡኃም የጀግንነቱ ዝና ወደ ንግስና የወሰደው ሰው ነው፡፡እና ይሄ ንጉስ አራተኛ ልጁን ከመውለዱ በፊት በአማልዕክቱ ካህን በኩል ትንቢት ተነገረው..አሁን የምትወልደው ልጅ መራመድ አይችልም ተብሎ፡፡ኃያላን የእንግሊዝ ግዛቶችን ሲገጥም ቅንጣት ፍራቻ የማይታይበት ታላቁ ንጉስ በዚህ ዜና ሲሸማቀቅ ስንመለከተው እግር አልባ መሆን ችግሩ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ እንረዳለን፡፡
ያው ትንቢቱን 80 ፐርሰንት አምኖ ሀያ ፐርሰንት ደግሞ እየተጠራጠረ ከወይዘሮ ሚስት ጋር እንሆ በረከት አለ…ልጅ ተወለደ፡፡እንደተባለውም እግሮቹ ቆመው ለመሄድ ተስፋ አልነበራቸውም….
እናትና አባት በሀዘን ውስጣቸው ደምቶ ልጁን በተመለከተ ሲጨቃጨቁ ከሚያሳው ዲያሎግ ጥቂቱ
ዋና ገፀ ባህሪው-He will die anyway.. What is the point of pretending?ብሎ ይጠይቃል ሞት የሚጠብቀውን ጨቅላ ልጆን ታቅፋ የተቀመጠችውን እናት
-
-
‹‹It is natural.. we let such baby dye for own good …. What kind of life could he live?.
››ይላታል ለእናት እሱ ራሱ ውስጡን ማሳመን ሳይችል፡፡
I know …but I don’t care. ትላለች እናት ወደውስጧ ልጆን ጨምቃ እያቀፈች፡፡(እሱስ ታድሏል በወቅቱ እናቱ ከጎኑ ነበረች.. እኔ ግን ያው ከዚህ ጉድለቴ ሊያተርፈኝ እንዲታገል የሚያስችል ፍቅር ያለው ሰው ማንም የለም፡ይታያችሁ በዚህ አራት ቀን ያለውን አትዩ እዚህ መከራ ውስጥ ከመግባታችን በፊት በአንደኛና በሁለተኛ ደረጃ የምጠላቸው ሰዎች ናቸው አብረውኝ ያሉት)ለማኛውም ወደታሪኩ ልመለስ፡፡
በማግስቱ እናት ሳታይ ልጁን ለመግደል ወደ ጫካ ይዞ ይሄዳል ወንዝ ዳር ህፃኑን ያስቀምጣል የስንቱን ጀግና ጠንካራ አንገት በአንድ ምት አሸክርክሮ የሚቀነጥስ መጥረቢያው የገዛ ልጁ አንገት ላይ ያስቀምጣል ፡፡ሊገድለው ..ግን ማድረግ አልቻለም፡፡የሆንከውን ሁን ብሎ ልጁን እዛው ጥሎ ሳይገድለው ይሄዳል… ከኃላ ተደብቃ ስትከታተል የነበረቸው እናት ወዲያው ደርሳ በእንባ እየታጠበች ልጇን ከተጣለበት አንስታ ወደቤት ትመልሰዋለች፡፡
ያልጅ አድጎ ግን አድጎ ከሁሉም ጤነኛ ወንድሞቹ የበለጠ ብልህ ከሁሉም የበለጠ ኃይለኛ ተዋጊ፤ከሁሉም የበለጠ ታሪክ የማይረሳው ከአባቱ የበለጠ ስመ-ገናና ጀግና ለመሆን ይበቃል ‹‹ አይቨ ቦንለስ ››……አጥንት አልባው አይባ
. በእነሱ እምነት አንድ አካለ ጎዶሎ ሆኖ የተወለደሰው እንዲኖር ሊፈቀድለት አይገባም፡፡ እንደዛ አይነት ህፃን እንደተወለደ ከእናታቸው ጉያ ይነጠቅና ከመንደር ወጣ አድርገው ይገድሉታል፡፡ያንን ግዴታን መወጣት ከጉድለት ጋር የተወለደውንም ልጅ በመኖር ከሚያጋጥመው ስቃይ መገላገል እንዲሁም በአማልዕክቱ ቁጣ ያረፈበትን ህፃን በማሳደግ በማህበረሰቡ ላይ የሚመጣውን ተጨማሪ ቁጣ ለመከላከል አስፈለጊ እርምጃ አድረገው ስለሚቆጥሩት እንዲሁም በጣርነት እና ስደት ጊዜ ለማህበረሰብ ሸክም ይሆናል ብለው ሰለሚያምኑ በድርጊታቸው ቅሬታ የላቸውም፡፡እንዲህ አይነት ልማድ በግሪክ እስፓርታ ፤በአውስትራሊያ እና በእስኪሞ ይገኛል፡፡
ያ ማለት አሁንም ከቅርም አያቶቻችን አስተሳሰብ ብዙም ፈቀቅ አላልንም ማለት ነው፡፡እርግጥ አካል ጉዳተኛ የሆኑትን ህፃናት ገና እንደተወለዱ አንገታቸውን አንቀን አንገላቸውም ይሆናል፡፡ግን በሂደት ለእነሱ ምቹ ያልሆነ የማህበራዊ የኑሮ መዋቅር በመገንባት እየተንገዋለሉ በመገለልና በኑሮ ፈተናዎች በመሸነፍ ከደረጃው በታች ኖረው ከደረጃ በታች እንዲሞቱ እያደረግን ነው፡፡
አዛውንቶችንም አይ አርጅታችሆልና መኖር ይብቃችሁ ብለን ከፈረስ ጭራ ጋር አስረን ተጎትተው እንዲሞቱ አናደርግም …በዚህ ግን ከአያቶቻችን የተሻልን ነን ብለን ልንኮራ አንችልም ፡፡ምክንያም የችግር ጭራ ላይ አስረናቸው በየጎዳናው በረሀብ በእርዛት እየተጎተቱ እንዲሞቱ እያደረግን ነውና፡፡ከደሙ ንፅህ ነን ማለት አንችልም፡፡

አሁን እኔ እንኳን በዚህ አጣብቂኝ ወቅት እንዲህ አይነት አደጋ ባያጋጥመኝ ስለአካል ጉዳተኝነት እንዲህ አምርሬ ላስብ አልችልም ነበር
‹‹በቃ እንግዲያው…እናንተ ጉዞችሁን ቀጥሉ››የደረሱኩበትን የመጨረሻ ውሳኔ ነገርኳችው፡፡
‹‹ምን..?በፍፅም በህይወት እያለህ ጥለንህ አንሄድም››አይዳ ነች፡፡
‹አይ እናንተንማ እንዲህ አይነት ፈተና ውስጥ አልከታችሁም….እሱን እኔ ራሴ አደርገዋለው..እናንተ ሂዱ››
‹‹ምኑ ነው የምትፈፅመው?››
‹‹መቼስ እንዲህ እየተሰቃየው አራት አምስት ቀን እግዜር ነፍሴን እስኪወስደው አልጠብቅም ››
‹‹እና..?››
‹‹ለማንኛውም ቢላዎ ሰጥታችሁኝ ሂዱ …››
ተንደርድራ መጣችና ከንፈሬ ላይ ተጣበቀችብኝ…እኔ ብቻ ሳልሆን በሪሁንም በጣም እንደደነገጠ ታወቆኛል፡፡ሲበቀትና ስትለቀኝ አንደምንም ትንፋሼን ሰብስቤ‹‹ምን ማለት ነው?››ጠየቅኳት…ጥያቄዬ ከግራ መጋቴ የመነጨ ነው፡፡ይህቺ ልጅ ለምድነው የሳመቺኝ…አፈቅርሀለው ለማለት ፈልጋ ይሆን?…እንዴት አንዲህ ይሆናል? እጮኛዬን እኮ በደንብ ነው የምታውቃት….እንደውም አብረን ተምረናል ሲሉ ሰምቼያለው….ግን በእውነት በህይወት ተርፌ ከዚህ ብወጣ ያቺን አለብላቢት እጮኛዬን አገባታለው….አዎ ፀባዬ ባይመቸኝም አፈቅራታለኁ…ስለዚህ እግዚያብሄር ከዚህ በተአምሩ ካወጣኝ እሷን ማጋባቴ የማይቀር ነው፡፡ግን የዚህቺኘዋ ከንፈር ልዩ ነው …ሙቀቱ የኤሌክትሪክ አይነት ንዝረት አለው…ቲ..ሽሽሽ አድርጎ የሚያቀልጥ አይነት …ስሜቱ ልቤን ምንጭቅ አድርጎ ነው ከቦታዋ ያነቃነቃት፡፡
👍22🥰5😁32
‹‹በህይወት እያለህ ጥዬህ አልሄድም…እራስህን እንዳታጠፋ አልፈቅድልህም..ከቻልን ይዘንህ እንጓዛለን ..ካልሆነም እስክታገግም አብረንህ እንጠብቅሀለን…አይደል በሪሁን?›
‹‹ትክክል ነሽ …የሆነ ነገር እንፈጥራለን...ማለቴ አብረን፤አንድ ላይ››ብሎ አብሮነቱን አረጋገጠ፡፡


ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️❤️❤️
👍174
በህይወት መንገድ ላይ……
( ታጋቾቹ)
ምዕራፍ-9
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
////

አምስት ቀን ሆነን..አምስት ቀን ሆነን ስላችሁ ጠቅላላ እዚህ መከራ ውስጥ ከገባን ማለቴ አይደለም፡፡እግሬ ከተሰበረ ቡኃላ ያለውን ቀን ቆጥሬ ነው፡፡አሁን ሁላችንም በህይወትና በሞት መካከል ተወጥራ ባለች ቀጭን ክር ላይ እንደቆምን ቁጠሩት…ክሯ መሀከል ላይ ልትበጠስ እየተከረከረች እና እየሳሳች ነው፡፡በማንኛውም ሰአት ጧ ብትል እና ቢያበቃልን ከመሀከላችን የሚገረም ሰው የለም፡፡እናንተም የምትገረሙ አይመስለኝም፡፡ካለንበት አሁናዊ ሁኔታ አንፃር መጪው ነገር ሙሉ በሙሉ ተገማች ስለሆነ ብዬ ነው፡፡
አሁን እጄ ላይ ካለው ላይተር በስተቀር ምንም አይነት ብርሀን የሚሰጥ ነገር በዙሪያችን ላይ አይገኝም…ባትሪችን፤ ሞባይላችን ጠቅላላ ቻርጅ ጨርሶ በድኗል…ምግብን በተመለከተ ሶስት ነጠላ ፍሬ ያላት አንድ ብስኩት እና ግማሽ ሊትር ውሀ ቀርቶናል፡፡ይሄንን ብስኩቱ ለአመል ያህል ቆረስ እያደረጉ በውሀ ራሰ በማድረግ በስድስት ሰዓት ልዩነት ለእኔ ያቀምሱኛል፡፡አንሱ ምንም ነገር ወደአፋቸው ካስገቡ ዛሬ ሶስተኛ ቀናቸው ነው፡፡
ሰው ግን ከህይወት ምን የሚያስፈነጥዝ ነገር ቢያገኝ ነው ነፍሱን ለማቆየት ሲል ይሄን ሁሉ መስዋዕትነት የሚከፍለው?እውነት ከኑሮችን የምንሸምተው ደስታና ፈንጠዝያ ያን ያህል አርኪ ሆኖ ይሄ ሁሉ መስዋዕትነት ይገባዋል?በውስጤ እየተመላለሰ ያስቸገረኝ ወሰኝ ጥያቄ ነው፡፡ግን ጥያቄውን ያው አዕምሮዬ እየሰራ ስለሆነ ጠየቅኩ እንጂ አይ ለህይወትማ ይሄን ያህል መስዋዕትነት መክፈል ሞኝነት ነው ብዬ ባምንና እራሴን ለማጥፋት ብወስን እራሱ ነገሮች እንዲያበቁ የሚያስችል እንጥፍጣፊ ጉልበት በውስጤ የለም…..በቃ የተሰበረ እግሬ ቆሽሾ በክቷል….በዛው ላይ ተልቶ ነፍሳቶቹ ከላዩ ላይ ሲንጠባጠብ ይታወቀኛል፡፡ከተጎዳውበት ቀን አንስቶ ለሁለት ቀናት እዛው ባለውበት የተቻላቸውን ያህል እንክብካቤና እርዳታ ሊያደርጉልኝ ሞክረው ነበር፡፡ግን ህመሜና ስቃዬ ከመባስ ውጭ ምንም ለውጥ ስላልታየብኝ እና ቀለባችን ተሞጦ በማለቁ ምክንያት በተቻለ መንገድ ወደፊት መጓዝ ወሳኝ ሆነ…እናም ልክ የኤሊን በመሰለ እርምጃ አንዳንዴ እጃቸውን አጣማረው በጋራ እየተሸከሙኝ አንዳንዴ ደግሞ በሪሁን ለብቻው እያዘለኝ ይሄው አሁን እስካንበት የመጨረሻ እስትንፋሳችን ድረስ ወደ ፊት ለመጎዝ መክረናል፡፡አሁን ግን እንኳን እኔን ሊሸከሙ እራሳቸውን መቆጣጠር አቅቶቸው ይኄው በግራና ቀኜ ተዘርረው ያንገላጅጃሉ…ብቻ ከእኔ ቀድመው አምልጠው እዳይገርመኝ፡፡
አይዳ ያቺ ዘናጯ እና ስትራመድ በአየር ላይ የምትበር የምትመስለው አይዳ….ያቺ ሳቋ ከጭፈራ ቤት ሙዚቃ በላይ ደምቆ ጆሮ ይይዝ የነበረው….ያቺ ተረቧና ቀልዷ ማብቂያ ያልነበረው አይዳ..አሁን ብታዮት ..ጸጉሯ ከመጨቅያቱም በላይ አንድ ላይ ተቋጥሮ የገሪባዎችን ጉድሮ መስሏል፤ከዚህ በፊት የጡቷን መጋለጥ እንድትሸፍንበት አልብሼት የነበረውን ጃኬት መልሳ እኔን ስላለበሰቺኝ እላዬ ላይ ያለው የተቀዳደደ ቲሸር እርባነ ቢስ ሆኗል….ለምን አውልቃ እዳልጣለቸው እርሱ ይገርመኛል…ምን አልባት ልብሱን አውልቆ ለመጣል የሚያስችል ጉልበት በውስጧ ስለሌለ ይሆናል…ቀሚሷ ሁለት ቦታ እስከላይ ከመተርተሩም በላይ ብዙ ቦታ ተቦተራርፎ አገልግሎቱን ጨርሶል….በቃ በፓንት ብቻ ነው ያለችው ማለት ይቀላል፡፡እናም ደግሞ ማንስትሬሽኗ መጥቶ እግሯ ሁሉ በደም መርጠብ ከጀመረ ሁለት ቀን ሆኗታል፡፡
የበሪሁንን ጠቅላላ ሁኔታ ብዙም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡
እንዚህ ሰዎች ልክ እንደተሰበርኩ እኔን እዛው ጥለውኝ ጉዞቸውን ቢቀጥሉ ኖሮ ዛሬ እርግጠኛ ነኝ ወይ ነፃ ይወጣሉ ካለበለዚያ ከዚህ የተሸለ ሁኔታ ላይ ይገኙ ነበር፡፡እነዛ እጠላቸውና በየሰባ አስባቡ እገፋቸው የነበረ ሁለት ሰዎች ለእኔ ህይወት የሚያስከፍል መስዋዕትነት ሲውሉልኝ…ፀፀቱ እየለበለበኝነው፡፡
እዚህ ጉዳይ ላይ ከመውደቃችን ከ15 ቀን በፊት አይዳን ከስራ አባርሬት ነበር ብያችሆለው አይደል፡፡አሁን እንዴት እንዳባርኳት ላጫውታችሁ ፡፡
ሳይት ውስጥ በምሳ ሰዓት ተሰብስበው ሲያወሩ በመሀከል የብሄር ጉዳይ ይነሳና ጭቅጭቅ ውስጥ ይገባሉ…..አንዱ ተነስቶ ሌለኛውን ‹‹የሆንክ አሸባሪ ቄሮ ነገር ነህ››ይለዋል
‹‹ነፍጠኛ ፎጤ…እቃህን ጠቅልለህ ወደሀገርህ እንድትገበ ነው የማደርግህ .አርፈህ ተቀመጥ›› ይለዋል ›..በዚህ የተነሳ ሳይት ላይ አደገኛ ግርግር ይነሳል
በዚህ በመሀከል አይዳ በተጣሉት መካከል ትገባና‹‹‹‹ …እናንተ ምንድነው ከድንጋይ መሸከም ሳትወጡ ድንጋይ በሚያክል የፖለቲካ ጥይት የምትፈነካከቱት..መጀመሪያ እስከኪ ከርሳችሁን በቅጡ ሙሉ..›እያለች በመቆጣትም በማገላገልም ነገሩ እንዲዲዘቅዝ ታደርጋለች፡፡
ሁለም ተሰብስበው እኔጋ ክስ ይመጣሉ….ሁኔታውን ሰማውና ነገ ጥዋት ውሳኔ ይሰጣችሆል አሁን ተበተኑ አልኩና ሸኘዋቸው፡፡ከዛ ቡኃላ ቀሺም ስራ ሰራው፡፡ ሁለቱን ዋና ተጣይዎች ለየብቻ አናገርኮቸውና ከስራ መባረር ካልፈለጋችሁ እኛ እርስ በርስ ስንቀላለድ በመሀከል መጥታ ‹‹ከድንጋይ ማትሻሉ ናቸሁ›› ብላ ሰደበችን …ብሄራችንንም አንቆሸሸችብን ብለው እንዲመሰክሩባት አሳመንኮቸው፡፡
በቀጠሯችን መሰረት ጥዋት የሰራተኛ አስተዳደሩን ይዤ ሶስቱን አስጠራዋቸው፡፡ እንዳኩት መሰከሩባት…ይህቺ ልጅ ፖላቲከኛ ስለሆነች አንድ ቀን ልታስጨርሰን ስልምትችል ትባረር አልኩ …ሰውዬውም ፈሪ ነገር ስለሆነ አልተቃወመኝም …ተባረሻል አልኳትና በማገስቱ ጥፋቷን ጠቅሼ እጆ ላይ ያላውን የድርጅን ንብረት አስረክቦ ስራ ለመልቀቅ ሰላሳ ቀን ብቻ እንዳላት የሚገልፅ ደብዳቤ ፅፌ ሰጠዋት …ብዙም አልተከራከረቺኝም፡፡
እና እዚህ ዋሻ ውስጥ ከገባን ቡሃላ ስለጉዳዩ እንስጬባት ነበር
‹‹ያዛን ቀን ከስራ ተባረሻል ስልሽ በጣም የምትቀውጪው መስሎኝ ነበር ….ጥፋትሽን አምነሽ ነበር ማለት ነው;?››
‹‹ምንም እንዳላጠፋውማ አንተም ታውቀወለህ››
‹‹እና ታዲያ አቤቱታ ለባለቤቷ ጭምር ማቅረብ ትቺይ ነበር››
‹‹አውቃለው….ግን ላንተ አስቤ ነው፡፡››
‹‹እንዴት ለአንተ አስቤ…?ከስራ ለሚያባርርሽ ሰው በምን ስሌት ነው የምታስቢለት?››
‹‹እኔ እንዴት አድርገህ እንድባረር እንዳቀናበርክ..ከልጆቹ ጋ የዶለትከውን ጭምር አውቃለው…..እናም ወደተቃውሞ ገብቼ አቤቱታ ባቀርብ እንዚህ ሁሉ ጉዳዬች በግልፅ ይወጡና በተቃራኒው አንተ ስራህን ታጣለህ፡፡››
እንደዛ ስትለኝ አፈርኩ..አንድን ሰው ሸውጄዋለው ብላችሁ ለረጂም ጊዜ በውስጣችሁ ስትጎርሩ ቆይችሁ በስተመጨረሻ ድንግት አንድ ቀን ከመጀመሪያው ጀምሮ ሰውዬው ሁኔታውን አውቆ ግን ደግሞ ከእናንተ በላይ በሳል ሆኖ ችላ ብሎ እንዳለፈው ስትሰሙ ብሽቀት..እፍረት…ውርድት ብዙ ብዙ ስሜት ነው የሚሰማችሁ፡፡
‹‹ታዲያ ብባረር ለአንቺ አሪፍ አይደል…?.››
‹‹አይ በፍፅም አይደለም….እኔ ስራውን ልምድ ለማግኘት ብቻ ነው የምሰራው…አንተ ደግሞ ዘላቂህ ሞያህ ነው..በምትከበርበት ቦታ ላይ አንድ ጥቂት ስህተት ሰራህ ብዬ ልፋትህን ጭላሼት ልቀው አልሞክርም››
👍222🔥1
‹‹እኔ እንደዛ እየጠላውሽ አንቺ ግን….››
‹‹እየጠላውሽ…እርግጠኛ ነህ?››አለቺኝ
‹‹እንዴ ምን ለምለት ነው?›
‹‹አይ እኔ እንደዛ አይደለም የምረዳህ…››
ተገርሜ‹‹እንዴት ነበር?››
‹‹ከእኔ የምትወዳቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ ብትቀርበኝ ወይንም ረጅም ጊዜ ዙሪያህ ብኖር ምን አልባት ፍቅር ሊይዝህ እንደሚችል ስለገመትክ …..እንደዛ ከሆነ ደግሞ እራስህን አጣብቂኝ ውስጥ እንዳታስገባ ፈርተህ ነው፡ …ለፍቅረኛህ የገባህላትን ቃል ኪዳን ለማፍረስ የሚያስገድድ ፈተና ውስጥ እገባለው ብለህ በመፍራትህ እራሱህን ይመጣብኛል ብለህ ከገመትከው ችግረር ቀድመ ጥንቃቄ የማድረጊያ መንገድህ ነው….››
‹‹እንዳዛ እንድታስቢ ያደረገሽ ምኑ ነው?፡፡››
‹‹እያዳንዱ ድርጊትህ…..እየጮክ ስትቆጣኝ እንኳን አይኖችህ በፍቅር ያባብሉኝ ነበር….ከወንዶች ጋር አፍ ለአፍ ገጥሜ ስታዬኝ እኔን ሳይሆን ወንድዬውን በግልምጫ አፍርጠህ ስትጥለው ይሉኝታ እንኳን የለህም…ምክንያት እየፈጠርክ ቢሮህ ትጠራኛለህ ..ስመጣ ደግሞ በንጭንጭና በብስጭት ትመልሰኛለህ…ስለምረዳህ ግን አንድም ቀን ተከፍቼ አላውቅም፡፡››
በፈጣሪ አሁን ወንድና ሴቶች አንድ አይነት ጭንቅላት ነው ያላቸው…?ከሴቶች ጋ ስንወዳደር እኛ ወንዶች እኮ ሰማይ ሰማዩን እያየን የምንጎዝ ግልቦች አይደለን እንዴ….?እዬት ይህቺን ሴት እያንዳንዷን በእኔና በእሷ መካከል የነበር ግንኙነት ቃላቶቻንን፤ስሜቶቻችንን በአስተውሎት መርምራ ..የሆነ ትንታኔ ሰርታ .የመጨረሻ ሳቢያና ውጤታቸውን ሁሉ ደምድማ ተቀምጣለች፡፡
‹‹ትገርeሚያለሽ..ቆይ ግን አንቺ ውሳኔውን ብትቃወሚና እኔ የሰራውብሽ ፊክ ክስ ቢጋለጥ ከስራ የምባረር ይመስልሻል?››እኔ እኮ ወሳኝ ሰው ነኝ የሚል መታበይ ያለበት ጥያቄ ጠየቅኳት
‹‹110 ፐርሰንት እርግጠኛ ነኝ..››
ሰቅኩ….ከግንዛቤ እጥረት የሰጠችው አስተያየት እንደሆነ ገምቼ ነበር መሳቄ
‹‹ምነው ሰቅክ?››
‹‹አይ ለፕሮጀክቱ ምን ያህል አስፈላጊ ሰው እንደሆንኩ በደንብ የገባሽ ስላመሰለኝ ነው፡፡››
‹‹ገብቶኛል…ለፕሮጀክቱ በጣም ወሳኙና የመጨረሻው ውሳኔ ሰጪና አስፈፃሚ እንደሆንክ አውቃለው..ባይሆን አንተ ነህ እኔ ለሪዞልቱ ባለቤት ምን ያህል ወሳኝ ሰው እንደሆንኩ ምንም ግንዛቤ የሌለህ››
‹‹አልገባኝም››
‹‹ሴትዬዋ አክስቴ ነች…አክስት ከመሆኗም በላይ በጣም ነው የምትወደኝ..ልጇ በለኝ፡፡እና እንዲህ እንዳላገጥክብኝ ብትሰማ ጥንቅር ያለው ነገር ጥንቅር ይላል እንጂ እመነኘ ታባርርሀለች….ስራ መልቀቄን ለማስረዳት ራሱ እራሱ ስንት ቀን ፈጅቶብኝ ነበር መሰለህ…ሰልችቶኝ ነው….እረፍት ፈልጌ ነው..ምናምን ብዬ አሳምኜት ነው የተረጋጋችው…እና አንደውም ይሄ መከራ ባይገጥመን በዚህ ጊዜ ከእሷ ጋር ድባይ ፈልሰስ አንድንል ፕሮግራ ይዘን ነበር፡፡
‹‹እየቀለድሽ ነው አይደል፡፡››
‹‹በፍፅም ..ምን አስቀለደኝ››
‹‹ታዲያ እንዴት እኔ እስከዛሬ ሳላውቅ….?ሌላስ ሰው ሳይነግረኝ.?››
‹‹ከበሪሁን በስተቀር ሌላ ማን አያውቅም…እንዳይታወቅ የፈለኩት እኔ ነኝ..ያው እንደምታስበኝ ጉረኛ አለመሆኔን ይህ መረጋገጫ ይሁንህ ››ብላ ፈገግ አለች
በዚህ አይነት ሁኔታ ነበር ይቅርታ የጠየቅኳት….
ዛሬ ከሁለት ቀን ቡኃላ እንዲህ ዝርር ብላ ሳያት ልቤ ፍርስርስ አለላት ..ይህቺኝ ሴት የእውነት እሷ እንዳለችው በድብቁ ስሜቴ ሳፈቅራት ነበር የኖሩኩት ብዬ እራሴን እንድጠራጠር እስገደቺኝ ፡፡
/
በሪሁን እንደምንም ከተጋደመበት ተነሳና እየተንገዳገደ በሁለት እግሮቹ ቆመ…‹‹እስቲ ወደፊት ራመድ ብዬ ሁኔታውን ልይ.. የሚበላ ቅጠላ ቅጠን ወይም ጥላትል ነገር ካገኘው ልመክር አለ ..››ቅንድቤን ከፍ ዝቅ በማድረግ ያሰበውን እንዲያደርግ መስማማቴን አሳወቅኩት.ግን ደግሞ ትላትል ሲል ከእግሬ የሚረግፉትን ትላትል አሳታወሰኝና ዝግንን አለኝ..

ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️❤️❤️
👍232