አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
እ?”

"ስሞትልሽ ስሙን አትጥሪብኝ!”

“እንደዚያ ያለ ልጅ እንኳን አይመስልም። ይሁንና አሁን ግን የት ነዉ ያለዉ? ብቅ ካለ እኮ ዉሎ አደረ”

“የት አዉቄለት”

“ምንድነዉ የት አዉቄለት ብሎ ነገር? ይሁንና የቅድሟን ነገር የት
አደረግሻት? እስኪ አምጫት”

“የቷን ነገር?”

“እህእ? ቅድም እዚያ ከበዓታ ስንለያይ እቤት አኑሪልኝ ብዬም
አልሰጠሁሽ?”

“እ...” ብዬ ጎስጉሼ አኑሬበት ከነበረዉ የራሷ አልጋ ትራስጌ ሥር
አዉጥቼ ሰነዘርኩላት፡፡ አልተቀበለችኝም፡፡

“ያንቺ ነዉ” አለችኝ፣ እኛ እያለን ራሷ ወደ ጀመረችዉ የምሳ ጉድ ጉዷ እየተመለሰች፡፡ “ታዲያ አደራሽን ምንድነዉ ቅብጥርሴ እንዳትጠኝ። እኔ ምኑንም አላዉቅልሽም። ስጭ ነበር የተባልሁት፣ ይኼዉ ሰጥቼሻለሁ።
አበቃሁ” በእራፊ ጨርቅ የተጠቀለለች ትንሽ ነገር መሆኗን ቀድሞዉንም ስትሰጠኝ
ኣስተዉያለሁ፡፡ ምን እንደሆነች ለማየት ገለጥ ባደርጋትም፣ ጥቅልሉ ስለበዛ ፍሬ እቃዋን ቶሎ ልደርስበት አልቻልሁም፡፡ ስቀበላት እምነት መስላኝ ነበር። አይደለችም ማለት ነዉ? በዚያ ላይ ስንት ዙር እንደ
ተጠቀለለች! ተርትሬ ተርትሬ ስጨርስ ያገኘሁት ግን ጥፍር እንኳን የማታህል ሚሞሪ ካርድ ብቻ ነበረች፡፡ መጠቅለያ ጨርቁን ባራግፈዉም፣ ከእሷ ሌላ ምንም የለም። እመዋ ደግሞ እንዳልጠይቃት ቀድማ መንገዱን
ሁሉ ዘጋግታብኛለች፡፡ ምን ቸገረኝ ብዬ ወደ ሞባይሌ ቀፎ ከተትኋት።

ይቀጥላል
👍24
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

....ኢንጆልራስ ጎንበስ ብሎ የራሣውን ጭንቅላት ቀና ካደረገ በኋላ ግምባሩን ሳመው፡፡
መሞቱን በመርሳት በጥንቃቄ ያልያዘው እንደሆነ የሚያምመው ይመስል ቀስ ብሎ በክርኑ ደግፎ ቀና አደረገው፡፡ የሟቹን
ኮት ካወለቀ በኋላ የሚደሙትን ቀዳዳዎች ለተመልካች አሳየ።

«ይሄ ነው ባንዲራችን!»

ነጭ አንሶላ አምጥተው የመሴይ ማብዩፍን አስከሬን ሸፈኑት:: ስድስት ሰዎች ጠብመንጃዎቻቸውን ከስር አጋድመው ሬሣውን ከዚያ ላይ ካሳረፉ በኋላ ወደ ምድር ቤት በዝግታ ወስደው ከትልቅ ጠረጴዛ ላይ አጋደሙት፡፡ ሰዎቹ በሚፈጽሙት ተግባር ቅዱስነት በመዋጥ አደገኛ ሁናቴ ውስጥ
መሆናቸውን ጨርሰው ረሱ::

አስከሬኑ ከዣቬር ከታሰረበት ግንድ አጠገብ ሲያልፍ ኢንጆልራስ
ሰላዩን አናገረው::

«የምትቀጥለው አንተ ነህ::»

በዚህ ጊዜ ብቻውን የጥበቃውን ተግባር ያከናውን የነበረው ጋብሮች ሰዎች ከምሽጉ ውስጥ ሲገቡ ውልብ አለው:: በድንገት ጩኸት ተሰማ::

‹‹ተጠንቀቁ!»

የአድማው መሪዎች በሙሉ ዘልለው ወደ ውጭ ወጡ:: የሚያባክኑት ጊዜ አልነበራቸውም:: ወታደሮች ሳንጃቸውን ወድረው ከምሽጉ ሲገቡ ተመለከቱ፡፡

ያቺ ሰዓት ወሳኝ ነበረች:: ምሽጉ በንጉሡ ወታደሮች ተወረረ::
በመጀመሪያ ዘልሎ የገባው ወታደር ከውስጥ የነበረ አንድ ሰው ግምባሩን ብሎ ጣለው:: ገዳዩ ወዲያው በጠላት ወገን ወታደር ተገደለ:: አሁንም ሌላ
ወታደር ከርፌይራክን ከመሬት ስለዘረረው እንደወደቀ «እርዱኝ» እያለ ጮኸ፡፡ በዚያው ወቅት እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነ ወታደር ጋቭሮች ከነበረበት ክፍል ገባ፡፡ ጋቭሮች ጠብመንጃዋን ከዣቬር ወደ ወታደሩ አዙራ ለመተኮስ
ቶሎ ብላ ቃታውን ሳብ አደረገች:: ግን ምን ይሆናል ዣቬር ጠብመንጃውን ሲሰጥ ለካስ ጥይት አላጎረሰው ኖር ፀጥ አለ፡፡ ወታደሩ ከት ብሎ ሳቀ፡፡
ሳንጃውን ወድሮ ወደ ልጁ ሄደ::

ወታደሩ ልጁ ዘንድ ከመድረሱ በፊት ከኋላው ስለተመታ በአፍጢሙ ተደፋ:: ወዲያው ከርፌይራክን የመታው ወታደር ሲወድቅ ታየ፡፡ ሁለቱን
ሰዎች የገደላቸወ ማሪየስ ነበር፡፡
ማሪየስ የመጀመሪያውን ውጊያ በሩቁ ሆኖ ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ
ነበር ያየው:: በሁለተኛው ግን የጋብሮችን ሕይወት በመጀመሪያ ሲያድን ጓደኛውን ቀጥሎ ነው ነፃ ያወጣው፡፡ ኩርፌይራክ ከመሬት ወደቀ እንጂ አልተመታም ነበር፡፡

ወታደሮቹ ከምሽጉ ሁለት ሦስተኛ የሚሆነውን ክፍል ከቁጥጥራቸው
ሥር አውለዋል፡፡ በጣም ወደ ውስጥ ዘልቀው ለመግባት ግን አልደፈሩም:: ምናልባት አንድ ዓይነት ወጥመድ ቢኖር ብለው ተጠራጥረዋል። በዚያ !
አካባቢ ይበራ የነበረው መብራት እስከ ውስጥ ዘልቆ አያሳይም::

አንድ ወታደር ማሪየስን ለመጣል ሲያነጣጥር ድንገት ከመሀል አንድ ሰው በመግባቱ የእርሱን እጣ ሰውዬው ወሰደ:: ወዲያው በድንገት አንድ በጣም የሚጮህ ድምፅ ተሰማ::

«እጃችሁን ስጡ ፤ አለበለዚያ ምሽጉን እንዳለ እናቃጥለዋለን፡፡»

አድምኞቹ ሁሉ ድምፁ ወደ ተሰማበት አቅጣጫ ፊታቸውን አዞሩ፡፡ ማሪየስ ከየት መጣ ሳይባል ይህን ያለውን የሃምሣ አለቃ ስለጣለው ምሽጉ ከመጥፋት ዳነ፡፡

አድመኞቹ በሙሉ ማሪየስን ከበቡት:: ኩርፌይራክ ከወደቀበት ተነስቶ ከአንገቱ ላይ ተጠመጠመ
«እንዴት ያለ አጋጣሚ ነው» አለ ኮምብፌሬ::

«ጥሩ ጊዜ ደረስክ» አለ ቦስዩ ቀጠለና::

«አንተ ባትደርስ ይህን ጊዜ በሕይወት የለሁም» አለ ከርፌይራክ።

«እኔ ደግሞ ይህን ጊዜ በአፍጢሜ ተደፍቼ ነበር» አለ ጋቭሮች ቀጥሎ፡፡

ወዲያው አንድ ድርጊት በመፈጸሙ ደስታቸው በሀዘን ተለወጠ። ከመካከላቸው በጣም የሚወዱትና የሚያደንቁት አንዱ ጓደኛቸው ተሰወረ። ከቁስለኛ መካከል ፈለጉት:: ከዚያ አልነበረም:: ከሞቱት መካከል አዩት ከዚያም አልነበረም፡፡ ተማርኳል ማለት ነበር፡፡

«ወንድማችንን ወሰዱት፤ እኛ የእነርሱን መኮንን እንደያዝን ሁሉ
እነርሱም ጓደኛችንን ያዙት ማለት ነው:: በሰላዩ ላይ ስለምንወስደው
እርምጃ ወስነናል?» ሲል ኮምብፌሬ ኢንጆልራስን ጠየቀው፡፡

«አዎን» አለ ኢንጆልራስ የኮምብፌሬን ትከሻ እየነካካ፡፡ «ሆኖም የሰላዩ ደም የጓደኛችንን የዣን ጥሩቬርንን ደም አያህልም፡፡»

«እንግዲያውማ» አለ ኮምብፌራ «መሐረቤን ከጠመንጃዬ ጫፍ
አስሬ ልውጣና ሰላዩን በጓደኛችን እንዲለወጡን ልጠይቅ::»

«ስማ» ብሎ ኢንጆልራስ ሲናገር ከውጭ አንድ ድምፅ ተሰማ፡፡
የወንድ ድምፅ ነበር::

«ፈረንሣይ ለዘላለም ትኑር!»

የጓደኛቸው ድምዕ እንደሆነ አወቀ፡፡ ጥይት ተተኩሰ፡፡ ከዚያም ሁሉም ነገር እርጭ አለ::

«ጓደኛችንን ገደሉት!» አለ ኮምብፌሬ:: ኢንጆልራስ ወደ ዣቬር ዞር ብሎ «ጓደኞችህ አሁን አንተን ነው የገደሉት» አለው::

አድመኞቹ ሁሉ አሁን ከቤት ወስጥ ገብቷል:: ማሪየስም
ተከትሉኣቸው ሊገባ ሲል «መሴይ ማሪየስ» ተብሎ ስሙ ሲጠራ ሰምቶ በመደንገጥ ዞር አለ፡፡ ከሁለት ሰዓት በፊት ኮዜትን እየጠበቀ ሳለ ከአጥር ውጭ ሆኖ የጠራው ድምፅ እንደሆነ አውቋል፡፡ ማን እንደሆነ ለማወቅ
ፊቱን ቢያዞርም መለየት አልቻለም:: «እዚህ ነኝ» አለ ያው ድምፅ በጣም የደከመ በመምሰል፡፡

መሬት ለመሬት እየተንፏቀቀ የሚመጣ ሰው በሩቁ ተመለከተ፡፡
መብራት ካለበት ሲደርስ የሴት ሸሚዝ የለበሰ ሰው መሆኑን አየ:: ከስር የተቀዳደደ ሱሪ ታጥቋል፡፡ ጫማ አላጠለቀም፡፡ ይህ ፍጡር ማሪየስ ከነበረበት ሲደርስ የገረጣ ፊቱን ቀና አደረገ፡፡

«አታውቀኝም?»
«የለም»
«ኢፓኒን፡፡»
ማሪየስ ቶሎ ብሎ ወደ መሬት አጎነበሰ፡፡ እውነትም ያቺ እድለቢስ
ኢፖኒን ነበረች፡፡ እንደ ወንድ ነው የለበሰችው::
«እንዴት መጣሽ?» ከዚህ ደግሞ ምን ትሠሪያለሽ?
‹‹መሞቴ ነው» ስትል መለሰችለት::
ማሪየስ ደንግጦ «ተመትተሻል እንዴ?» ሲል ጠየቃት::
ከመሬት ብድግ ሊያደርጋት ቀኝ እጁን ከወገብዋ ስር አስገባ፡፡ ብድግ ሲያደርጋት እጅዋ ተዝለፈለፈ:: የማቃሰት ድምፅ አሰማች፡፡
«አሳመምኩሽ?»
«ትንሽ»
«ምነው እጅሽ ዛለ?» ብሎ" ሲያየው በጥይት ተመትቷል፡፡
«ቆስሎአል፧ አይደለም?»
«አዎን፡፡»
«ማን መታሽ?»
«ከጥቂት ጊዜ በፊት ጠብመንጃ ተደቅኖብህ ልትመታ ስትል አንድ
ሰው ከመሀል መግባቱ ትዝ ይልሃል?»
«አዎን፣ አስታውሳለሁ::»
የእኔ እጅ ነው ጣልቃ የገባው::
የማሪየስ ልብ ከሁለት የተሰነጠቀ መሰለው:: ነገሩ አልገባውም::
ምነው እንደዚያ አደረግሽ! ምስኪን! ብቻ ቁስሉ ለክፉ አይሰጥሽም።
ለማንኛውም ከውስጥ አስገብቼ ላስተኛሽ፡፡»
እጄ ብቻ እኮ አይደለም የተመታው:: ጥይቱ በእጄ አልፎ ከብብቴ ጥቂት ዝቅ ብሉ ወደ ወገቤ በመግባቱ ቀስፎ ይዞኛል» አለች በኃይል ለመተንፈስ እየታገለች::

«ስለዚህ ወደ ውስጥ መግባቱ ዋጋ የለውም:: አሁን ብቻ ከአጠገቤ ቁጭ ብለህ አጫውተኝ፡፡ ጨዋታህ ከሐኪም እርዳታ ይበልጥብኛል፡፡»

ትእዛዝዋን ተቀብሎ እግሩን በመዘርጋት ከአጠገብዋ ቁጭ አለ።

ጭንቅላትዋን ከጉልበቱ ላይ አሳረፈች:: ቀና ብላ ሳታየው «እፎይ ተመስገን እንዴት ይመቻል? ምን ዓይነት ደግ ሰው ነህ! በቃ! ሕመሙ ተቀነሰልኝ
ስትል ቀባጠረች፣::

ከዚያም ለጥቂት ጊዜ ፀጥ አለች:: ቀስ ብላ ፊትዋን ወደ ማሪየስ
አዙራ ቀና ብላ አየችው::

«አስቀያሚ ናት ነው ያልከው፤ አይደል? » ንግግርዋን በማቆም ጥቂት ዝም ካለች በኋላ እንደገና ቀጠለች::
👍19
«መቼስ አሁን አልቆልሃል:: ከዚህች ምሽግ ማንም በሕይወት
አይወጣም:: እኔ ነኝ፧ ከዚህ እሳት ውስጥ የጨመርኩህ:: እርግጠኛ
ነኝ አንተም ትመታለህ:: ሆኖም ሰውዬው ጠብመንጃውን እነጣጠር ሊገድልህ ሲል እጄን አፈሙዙ ላይ በማድረግ አዳንሁህ:: ይህንንም ያደረግሁት
ከአንተ በፊት ለመሞት ፈልጌ ነው፡፡ ከተመታሁ በኋላ በደረቴ እየተንፏቀቅሁ ከዚህ ስመጣ ማንም አላየኝም፡፡ ማንም ደግሞ ከወደቅሁበት አላነሳኝም::
አንተን ነበር የምጠብቀው:: ነገር ግን ከወደቅሁበት እንደማትመጣ አወቅሁ፡፡በመካከሉ እኔ በጣም ተሰቃየሁ፡፡ አሁን ግን ተሽሎኛል:: ከቤትህ መጥቼ ሰውነቴን አንተ ቤት ባለው መስታወት ያየሁበት ቀን ትዝ ይልሃል? ደግሞስ መንገድ መገናኘታችን ትዝ ይልሃል? አንተ እንኳን አንድ መቶ ሱስ
ስትሰጠኝ «ገንዘብህን አልፈልግም ብዬ እንኳን መለስኩልህ! ለመሆኑ ገንዘቡን
መሬት ስጥለው መልሰህ አነሳኸው? ሀብታም ስላልነበርክ መቼስ አትተወውም፡፡ ታዲያ መሴይ ማሪየስ ፤ ሁሉንም አስታወስክ? አቦ እንዴት
ደስ አለኝ! ሁላችንም ልንሞት ነው::
ዓይንዋ ተቅበዘበዘ፡፡ አሳብዋ ተንቀዋለለ:: እጅዋን ሊጠቀልልበት ከደረትዋ አካባቢ ሸሚዝዋን ቀደደ:: ደረትዋን ሲገልጥ ጥይት የገባበት ቦታ
በግልጽ ታየ:: ደም ይወጣው ነበር፡፡ ማሪየስ ያቺን እድለቢስ ልጅ ዝም ብሎ አፍጥጦ አያት::

«ወይኔ» ስትል በድንገት ጮኸች፡፡ «ሕመሙ እንደገና መጣ፡፡ ምነው
አፈነኝሳ!» ከለበሰችው ልብስ አንዱን ክፍል አፍዋ ውስጥ በመጉሰር ንክስ አደረገችው:: እግሮችዋ ተንቀጠቀ፡፡

«እባክህን አትሂድ» አለችው:: «አሁንማ ረጅም ጊዜ አይሆንም:: :

ብድግ ብላ ቁጭ አለች:: ድምፅዋ ግን እየሰለለ ሄዶ ውጪ ነፍስ ግቢ
ነፍስ ሆነ:: እንግዳ በሆነ ድምፅ በማቃሰት ትናገር ጀመር፡፡

«ስማ፤ ለአሞኝህ አልፈልግም:: ኪሴ ውስጥ የአንተ ደብዳቤ አለ::
ትናንትና እንድሰጥህ ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ ግን እኔ ዘንድ አቆየሁት:: ላገኝህ አልፈልግሁም ነበር:: ምናልባት ቶሉ ቶሎ ስንገናኝ ደስ አይልህ እንደሆነ ብዬ ነው:: ሆኖም ተገናኘን አይደል? ደብዳቤህን ውሰድ::»

በሚደማው እጅዋ ማሪየስን እጅ አፈፍ አደረገችው፡ የቁስሉ ሕመም
አልተሰማትም:: እጁን ይዛ ከኪስዋ ውስጥ ጨመረችው:: ኪስዋ ውስጥ የነበረውን ወረቀት በመንካቱ፡ ደብዳቤ እንዳለ ማሪየስ አመነ::

«ውሰደው » አለችው::

ማሪየስ ደብዳቤሁን አወጣ:: የደስታ ምልክት የፊትዋ አሳየችው::

«ለስቃዩ ስትል አሁን ቃል ግባልኝ::»

«ምን ብዬ?»ሲል ማሪየስ ጠየቃት::

«ቃል ግባልኝ፡፡»

«ቃሌን ሰጥቻለሁ፡፡››

«ከሞትኩ በኋላ ግምባሬን እንድትስምልኝ ቃል ግባልኝ፣ ስትስመኝ ደግሞ ይሰማኛል፡፡»

ማሪየስ ጉልበት ላይ ተደፋች፡፡ ዓይንዋን ጨፈነች፡፡ ያቺ ምስኪን
የሞተች መሰለው፡፡ ኢፓኒን ሳትነቃነቅ ዝም ብላ ቆየች፡፡ ማሪየስ «አሁንስ የዘላለም እንቅልፍ ወስዷታል ብሎ ሲያስብ ነቅነቅ አለች፡፡ ዓይንዋን ለመግለጥ ሞከረች፡ የሞት ጥላ አጥልሎባታል፡፡ ከዚያ በዝግታ ከወትሮው በተለየ ድምፅ አናገረችው፡፡»

«ማሪየስ ከአንተ ፍቅር እንደያዘኝ አምናለሁ፤ አንተ ግን ይህን ታውቅ
ኖሮአል?»

ፈገግታ ለማሳየት ሞከረች፤ ግን አልቻለችም፣ ነጐደች፤ ለዘላለም
ሄደች፡፡

ማሪየስ ቃሉን አከበረ፡፡

የቀዘቀዘውን ግምባርዋን ምጥጥ አድርጎ ሳመው፡፡ ነገር ግን ኮዜትን መክዳቱ አልነበረም፡፡ ያንን የተከፋ ነፍስ ለመሰናበት የፈጸመው ተግባር ነበር፡፡

ደብዳቤው ትዝ አለው:: ለማንበብ ቸኮለ፡፡ ወዲያው ልጅትዋ እንደ
ሞተች ደብዳቤውን ገልጦ ለማየት ጓጓ:: ይኸው ነው የሰው ልጅ ጠባይ።ለእርሱ የሚሆን ምን ነገር እንዳለ ለማወቅ ይቸኩላል፡፡ ከመሬት ላይ በዝግታ አስተኝቶኣት ከዚያ ተነስቶ ሄደ::

የሻማ መብራት ወደ ነበረበት ምድር ቤት ወረደ:: በሚገባ የታሸገ አነስተኛ ደብዳቤ ሲሆን እሽጉ የሴቶች ጥንቃቄ የታከለበት ይመስላል።

በፖስታው ላይ የተጻፈው አድራሻ የራሱና የጓደኛው የከርፌይራክ ነበር። ቶሎ ብሎ ፖስታውን ቀድዶ ማንበብ ጀመረ::

«የእኔ ፍቅር፣ የሚገርምህ ነው፤ አባዬ አሁኑኑ እንድንሄድ ይፈልጋል። ዛሬ ማታ ሆም አርሜ ከተባለ ሥፍራ እንሄዳለን:: በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከእንግሊዝ አገር እንገባለን፡፡ ኮዜት፣ ሰኔ 4፡፡»

ደብዳቤውን ከሳመው በኋላ አጣጥፎ ፖስታው ውስጥ ጨመረው። የፍቅርዋን ጽናት በማረጋገጡ ደስ አለው:: ሁልጊዜም ቢሆን የሌላው ወገን
ፍቅር ብርታትና ጽናት ማወቅ ያስደስተናል፤ ለመወደዳችን ማረጋገጫ ነውና::

«መሄድዋ ነው ፤ አባትዋ ይዟት ሊሄድ ነው:: አያቴ ደግሞ እንድንጋባ አልፈቀዱም፡፡ ምንም የተለወጠ ነገር የለም» ሲል እርስ በራሱ ተነጋገረ፡፡ እንደ ማሪየስ ያለና በቅዠት ዓለም ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ የዚህ ዓይነት
ሁናቴ ሲገጥማቸው በሀዘን ተጨማልቀውና ተስፋ ቆርጠው የማይሆን መንገድ በመምረጥ ከማይሆን መደምደሚያ ላይ ይደርሳሉ፡፡ ሕይወት መሯአቸው በቶሎ መሞትን ይመርጣሉ፡፡ ይህም በመሆኑ ማሪየስ ሁለት
ነገሮችን ብቻ መፈጸም እንዳለበት ይወስናል፡፡ ይኸውም ስለመሞቱ ለኮዜት መግለጽና የመጨረሻውን የስንበት ቃል በመልእክተኛ መላክና የዚያችን የምስኪን የኢፓኒን ወንድም ማለት የሚስተር ቴናድዩ ወንድ ልጅ ከዚያ
አስከፊ አደጋ ማውጣት ነበር፡፡
የማስታወሻ ደብተሩን ከኪሱ አወጣ፡፡ አንድዋን ቅጠል ቀድዶ
የሚከተለውን ጻፈ::

«ጋብቻችን አልሆነም:: አያቴን ስጠይቃቸው እንድንጋባ አልፈቀዱም:: እኔ እንደሆነ ምንም ዓይነት ሀብት የለኝም:: አንቺም ብትሆኚ ከእኔ አትሻይም::
ወደ ቤት መጥቼ ነበር፧፧ ግን አላገኘሁሽም:: ምን ብዬ ቃል እንደገባሁልሽ
የምታውቂው ነው:: ቃሌን አከብራለሁ፤ እሞታለሁ፣ እወድሻለሁ፡፡ ይህን
ደብዳቤ ስታነቢ ነፍሴ ከአጠገብሽ ትሆናለች፤ እናም በፈገግታ ታይሻለች፡፡»
ደብዳቤውን የሚያሽግበት ፖስታ አልነበረውም፡፡ ስለዚህ ወረቀቱን
አጣጥፎ አድራሻዋን ጻፈበት:: ማስታወሻ ደብተሩን ወደ ኪሱ መለሰ፡፡ ከዚያም ጋብሮችን ጠራው:: ልጁ እየሮጠ ወደ ማሪየስ ሄደ:: «ውለታ
እንድትውልልኝ ብጠይቅህ እሺ ትለኛለህ?» ሲል ማሪየስ ልጁን ጠየቀው::
«እንዴታ» ሲል ልጁ በፈገግታ መለሰለት፡፡ «እግዚኣብሔር
በሚያውቀው ኣንተ ባትደርስልኝ ኖሮ አሁን እኮ የሞትኩ ሰው ነበርኩ፡፡»
«ይህን ደብዳቤ ታየዋለህ?»
«አዎን፡፡»
«እንካ ያዘው:: በቶሎ ከዚህ ምሽግ ውጣና ሂድ::» ጋቭሮች በመገረምና
በመረበሽ ፀጉሩን አከከ፡፡
«ነገ ጠዋት ደብዳቤውን በአድራሻው ለኮዜት ስጥልኝ::»
እስከ ነገ ምሽጋችንን ይይዙታል፡፡ ታዲያ ሲይዙት እኔ ከዚሁ ለመሆን
እፈልጋለሁ አለ ልጁ በኩራት መንፈስ፡፡
«እስኪነጋ ድረስ ሁለተኛ ምሽጋችንን አያጠቁም:: ስለዚህ ምናልባትም እስከ ነገ እኩለ ቀን ድረስ ምሽጋችን ከእጃችን አትወጣም::»

«እሺ እንግዲያውስ» ሲል ልጁ መለሰ፡፡

ልጁ በሩጫ ከዚያ ወጥቶ ሄደ:: ከዚያ ሲሄድ አንድ አሳብ ነበረው::
ግን ለማሪየስ የነገረው እንደሆነ የሚቃወመው ስለመሰለው አሳበን ሳይገልጽ ነው የሄደው:: አሳቡም ይህ ነበር፡፡

«እኩለ ሌሊት እንኳን አልሆነም:: ኮዜት ያለችበት ሰፈር ደግሞ
እስከዚህም ሩቅ አይደለም:: ደብዳቤውን አሁኑኑ እወስድላታለሁ፡፡ ከዚያም
በቶሉ እመለሳለሁ::......

💫ይቀጥላል💫
👍212
Forwarded from Eyos bot
💎 የናንተን ቴሌግራም profile 👤 ማን በብዛት እንዳየው ማወቅ ይፈልጋሉ!
profile ፎቶአቹን የሚያየውን ሰው ስም ዝርዝር ለማግኘት እነዲሁም ስንት ጊዜ እንዳየውና የቱን "save" እንዳረገው ለማወቅ ከፈለጉ 👇"START"የሚለውን ይንኩት!
👍4👎2🤔1
Forwarded from 🌹 ፍቅሬን-በ-ግጥም 🌹
🔞. መርየም ብለው ይጠሩኛል...

ወጣት እና መልከ መልካም ልጅ ነበርኩ። በዩኒቨርሲቲ ትምህርት ላይ ሳለሁ ከአንድ የሌላ አገር ወጣት ጋር ተዋወቅኩኝ። እሱም የአገሬ ልጅ ካለመሆኑም ባሻገር በሁኔታዎችም አሰገዳጅነት በብዛት እየተገናኘን አንድ ላይ በመሆን አብረን እናሳልፍ ነበር ።

ከመጀመሪያ የግንኙነት ጊዜያችን ጀምሮ በሃሳብ ደረጃ በደንብ ተግባባን ቀናቶች እያለፉ በመጡ ቁጥር ግንኙነታችን ይበልጥ እየተጠናከረ መጥቶ መለያየት ከባድ ሆነብን። ይህንን የሰሙ የሀገሬ ልጆች በኔ ላይ ሴራን ይሸርቡ ጀመር። አንድ ቀን ከዶርም በመውጣት ላይ ሳለሁ በጣም የሚዘገንን ነገር ሰሩብኝ። ያን እለት የሆንኩት አስታውሼ መናገር ይከብደኛል። እጅግ ሚሰቀጥጥ ድርጊት ነበር። ከዶርም ስወጣ …see more read
👍7👏2😁21
#ገረገራ


#ክፍል_አምስት


#በታደለ_አያሌው

.....“ያንቺ ነዉ” አለችኝ፣ እኛ እያለን ራሷ ወደ ጀመረችዉ የምሳ ጉድ ጉዷ እየተመለሰች፡፡ “ታዲያ አደራሽን ምንድነዉ ቅብጥርሴ እንዳትጠኝ። እኔ ምኑንም አላዉቅልሽም። ስጭ ነበር የተባልሁት፣ ይኼዉ ሰጥቼሻለሁ።
አበቃሁ” በእራፊ ጨርቅ የተጠቀለለች ትንሽ ነገር መሆኗን ቀድሞዉንም ስትሰጠኝ
ኣስተዉያለሁ፡፡ ምን እንደሆነች ለማየት ገለጥ ባደርጋትም፣ ጥቅልሉ ስለበዛ ፍሬ እቃዋን ቶሎ ልደርስበት አልቻልሁም፡፡ ስቀበላት እምነት መስላኝ ነበር። አይደለችም ማለት ነዉ? በዚያ ላይ ስንት ዙር እንደ
ተጠቀለለች! ተርትሬ ተርትሬ ስጨርስ ያገኘሁት ግን ጥፍር እንኳን የማታህል ሚሞሪ ካርድ ብቻ ነበረች፡፡ መጠቅለያ ጨርቁን ባራግፈዉም፣ ከእሷ ሌላ ምንም የለም። እመዋ ደግሞ እንዳልጠይቃት ቀድማ መንገዱን
ሁሉ ዘጋግታብኛለች፡፡ ምን ቸገረኝ ብዬ ወደ ሞባይሌ ቀፎ ከተትኋት።
ከዚያም በድምፅ ማጫወቻዉ ከፈትሁት፡፡ ከትንሽ የነፋስ እና የወፎች ጺዉጺዉታ በኋላ፤ ማሲንቆ የሚያስንቅ አንቺሆዬ ዓይነት ፉጨት መጣ፡፡

የት ነበር የማዉቀዉ ይኼን ድንቅ ትንፋሽ?

መቼ አጣኋቸዉ! ወይዘሮ ብርሃኔ ናቸዉ፡፡ እሳቸዉ ናቸዉ ትንፋሻቸዉን እንደ ፈለጉ የሚያሽሞነሙኑት። እንኳን በሴት በወንድ እንኳን የማላዉቀዉን፣ ማንኛዉንም ዜማ በፉጨታቸዉ ብቻ ሲያወጡት አያድርስ ነዉ። በዘለሰኛ ጨዋታቸዉ የሁሉን ነፍስ የሚገዙት፣ በሸክላ ሥራ ጥበባቸዉ ሁሉን የሚያስደንቁት፣ ፉጨት እና ሽለላዉን
የሚያዉቁበት፣ ወይዘሮ ብርሃኔ ናቸዉ። አትጠገቤዋ፣ ደርባባዋ ሰዉ! በእርግጥ መጀመሪያ ያወቅኋቸዉ በእሸቴ በኩል ነበር። የእሱ እናት ናቸዉ፡፡ እንደ ጣና ሐይቅ የተረጋጉት፣ እንደ ዥማ ወንዝ የልብ የሚያደርሱት ሴት ናቸዉ በፉጨት የመጡብኝ። ጥሎብኝ አንጎራጓሪ ሰዉ
አይሆንልኝም፡፡ እጅግ አድርጌ እወዳለሁ። በተለይ ዘለሰኛ! ዘለሰኛ ለመስማት ስል ምንም ነገር ቢሆን እተዋለሁ። አሁን አሁን እንዲህ እሸቴ የሚባል ስም በአፍንጫዬ ይውጣ ልል፣ ያኔ ልቤን ወለል አድርጌ
እንድከፍትለት ካደረገበት ብዙ ምክንያቶቹ አንዷ እናቱ ነበሩ።

ልዩ ናቸዋ!

ፉጨቱን ተከትሎ በድምፃቸዉ ደግሞ መጡብኝ። ያ ከእሕልም
ከመጠጥም የሚጣፍጠዉ ዘለሰኛቸዉ!

ኧኧኧኧኧኧ...
ሸክላ ሠሪ አርገህ ሾመኸኛል
የሸክላ ጥበብ ይገባኛል፡፡
ኧኸ

ሸክላ ማለት የእጄ ሥራ
እኔ ደግሞ የእጅህ ሥራ፤
የእጄ ተሰብሮ ብመኝም ሞት
የእጅህን ማትረፍ ግን አወቅህበት!

ኧ ኸ ኧ ኸ ኧ.....

ምንም እንኳን ቀረጻዉ ጥራት ያልሞላለት ሆኖ ሞገዱ እንደሚዋዥቅበት ሬዲዮ ወስድ መለስ ሲያደርገዉም፣ እየደጋገምሁ አጣጣምሁት። ከምኔዉ እንደሆነ እንጃልኝ ብቻ አሁን መረጋጋት ይታይብኛል። አሁን ከፋኝ ብዬ ስነፈርቅ አልነበር እንዴ? ፊቴን ዳበስሁት፤ እንባ የሚባል ጠብታዉ ሳይቀር የለም። ወደ መስታዎት ሮጬ ዓይኔን አየሁት። እንኳንስ ደም
ሊመስል! ልክ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ወደ ነባሩ ቀልቤ ተመልሻለሁ። ያውም ወደ ደስተኛዋ ዉብርስት። ጃሪም የለ፣ እሸቴ የለ፣ እርግዝና የለ
ሁሉም ደህና። ፍጹም ሰላም፡፡

“እመዋ?” አልኋት፣ እንጀራ ይዛ ወደ ሳሎን ብቅ ከማለቷ፡፡

ለወጉ ያህል ብቻ ቀና ብላልኝ፣ ወደ ማዕድ ቤት አልፋኝ ሄደች። ምን ላርግሽ፣ ይልቅ ማቀራረቡን አትረጅኝም? ማለቷ መሰለኝ። ከምኔዉ እንዲህ እንደ ተረጋጋሁ እሷንም ሳይደንቃት አልቀረም።

“ማነዉ የሰጠሽ ግን?” አልኋት፣

እግር በእግር እየተከታተልኳት።
“ማን ይመስልሻል?” አለችኝ፣ ፍርጥም ብላ።

“ብቻ እሽቴ ነዉ እንዳትዪኝ በማርያም”

“እሸቴ የሆነ እንደሆንስ? ስጦታ ሁሉ ያዉ ስጦታ አይደለም ወይ?”
“እህእ?”
ስጦታ ሁሉማ ያዉ አይደለም፡፡ ከእሸቴ ነዉ ማለት ነዉ? እንደ ፈራሁት መልሶ ከፋኝ፡፡ እንደገና ስምጥ ወደ ሆነዉ ድባቴ ዉስጥ ተወርዉሬ ወደቅሁ። መቼም ከእሱ ሌላ የእናቱን ድምፅ ቀርጾ በእናቴ በኩል የሚልክልኝ አይኖርም፡፡ ለዚያዉም ድምፁ ሌሊት ወፍ ጭጭ ሲል በድብቅ የተቀረጸ ነዉ የሚመስለዉ። ስለዚህ አብሮ የሚያድር ሰዉ ነዉ ማለት ነዉ የቀረጻቸዉ፡፡ ያም ሰዉ ከእሸቴ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ እሱ
ነዉ የላከልኝ። እጅ መንሻ መሆኑ ነዉ? የተጣላነዉ በእናቱ ይመስል፣ በዚህ ሊያባብለኝ መሞከሩ የበለጠ እልህ ዉስጥ ጨመረኝ፡፡

እናቱ ሌላ፣ እሱ ሌላ።

ራሴን ግን ታዘብሁት፡፡ ቶሎ የሚከፋኝ፣ ቶሎ የምደሰት ግልብ ሆኜ አርፌዋለሁ ማለት ነዉ በቃ? አሁን ለቅሶ፣ አሁን ሳቅ፣ እንደገና ለቅሶ?
ሰአሊ ለነ ቅድስት!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሐዘንም ሐፍረትም ቀላቅሎ ከመታኝ ይኸዉ ቀናት አለፉ፡፡ ያዉም እንደ ሙጀሌያም እየተሙጀለጀሉብኝ። በእነዚህ ቀናት ሁሉ በእመዋ ቤት ተደብቼ ራሴን አዳመጥሁት። እንደ ወትሮዬ ወደ አደባባይ ሳልወጣ፣
እንደ ድሮዉ በወዳጅ ሳልከበብ፣ እንደ ሁልጊዜዉ ወደ ሲራክ-፯ ማዕከል ሳልመላለስ ዐሥራ አንድ ረዣዥም ቀናት እያለፉኝ ሄደዋል። እንዲሁ አልፎ አልፎ ብቻ ሲልብኝ፣ ክራሬን አንስቼ ለብቻዬ እያንጎራጎርሁ በእናቴ ቤት ሰነበትሁ፡፡

በዚህ ምክንያት እመዋም ሁኔታዬን እያየች ስትብሰለሰል፣ እያሳዘነችኝ መጣች፡፡ ምናልባት ዘወር ብልላት ይቀላት እንደሆነ ብዬ፣ ሲራክ-፯ ለአንዳንድ ተልእኮዎች በማሰብ በምስጢር ቀድሞም ወደ ተከራየልኝ
ምስጢራዊዋ ቤት ደግሞ ሄድሁ። ይቺ ቤት፣ በተልእኮዬ ሂደት መሀል
እንድቀራረባቸዉ የሚያስገድዱ ሰዎች ቢኖሩ ቤቴ ብዬ የማሳያቸዉ ቤት ናት። እንደ ሁኔታዉ፣ እነዚህ ዒላማ የተደረጉ ሰዎች ረዥም ጊዜ እና የተለየ መቀራረብ የግድ የሚፈልጉ ስለሚሆን፣ የቤት ቡና የምጋብዛቸዉ በእመዋ ቤት ባለኝ ክፍል ሳይሆን፣ በዚሁ ምስጢራዊ የኪራይ ቤት ነዉ።

ወደ'ዚህ ቤት እንደመጣሁ፣ እመዋ አዘዉትራ እሸቴ ምን በደለሽ?»
ስትለኝ የሰነበተችዉ ጥያቂ ድንገት ሽዉ አለችብኝ፡፡ ገና ዛሬ፣ አሁን ገና። እንደገና አስብሁበት:: እዉነትስ ግን እሱ ምን በድሎኛል? ምንም። ምንም ወንጀል አጣሁበት። ቆይ እኔ ራሴ አይደለሁ እንዴ፣ ዓለም በቃኝ ብሎ
ከመነነበት የእናቱ ከተማ ሄጄ የተዋወቅሁት? እኔ ባልሄድበት እንኳንስ መበደል፣ ጭራሽ የት ያዉቀኝ ኖሯል? ደረስሁበት እንጂ አልደረሰብኝም እኮ፡፡ ይልቅስ ራሴ ነኝ በገዛ ሕይወቴ የተጫወትሁት። እኔን ማንም አልበደለኝም። ከተበደልሁም የተበደልሁት በራሴ ነዉ። እኔዉ ነኝ ራሴንም እግዚአብሔርንም የበደልሁት። ስለዚህ ራሴን ለካህን ማሳየት
አለብኝ።

ንስሐ ያስፈልገኛል።

ወዲያዉኑ ተስፈንጥሬ ተነሳሁና፣ ነጠላዬን እንደ ነገሩ አንገቴ ላይ ጥዬ ወደ መኪናዬ ሮጥሁ። ምስጢራዊዋ ቤቴ በአዲስ አበባ ልዩ ሰፈሩ ልደታ በሚባለዉ የምትገኝ ኮንዶሚኒየም ስለሆነች፣ ተዘግቶ እስከሚከፈት
የሚያጉላላኝ የአጥር በር የለብኝም፡፡ ይቺን መከራ ቻይ መኪናዬን ዛሬም ያለቅጥ ረግጬ አበረርኋት። የትራፊክ መብራት የሚባል ለቅጽበት አላስቆመኝም። ንስሐ አባቴ የሚያገለግሉት እዚሁ ልደታ ጎን ባለዉ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቢሆንም፣ በዚህ አመሻሽ ግን እሳቸዉ የት
እንዳሉ አላዉቅም። በቤታቸዉ ሊሆኑ እንደሚችሉ በመገመት ነበር ቀጥታ ወደ መኖሪያ ቤታቸዉ የሄድሁ። እዚያ ስደርስ ግን አጣኋቸዉ።

አቤት ጥድፊያ! ስልክ ቁጥራቸዉ አለኝ አይደል እንዴ?
ደወልሁላቸዉ።
“እዚያዉ ልደታ እኮ ጉባዔ ላይ ነበርሁ። ምናለ ከመድከምሽ ፊት ደዉለሽ ብትጠይቂኝ ኖሮ ልጄ?” አሉኝ፣ በሐዘኔታ፡፡

“ግድየለም፡፡ እዚያዉ ልምጣ ታዲያ?”

“ምን ገዶኝ? ነይ በይ እዚሁ”
👍352
ከምኔዉ እንደ ደረስሁ። ከቅጽሩ ገብቼ፣ ለአርምሞ ወደሚያዘወትሩበት
ሥፍራቸዉ ስሄድ፣ የግላቸዉን የሠርክ ጸሎት ጀምረዉ አገኘኋቸዉ።ፈንጠር ብሎ በሚገኝ ለስላሳ ድንጋይ ላይ ተቀምጩ ጠበቅኋቸዉ።

“መጥተሽ ነወይ ፍቅርተማርያም? እንደምን አምሽተሻል?” አሉኝ፣
ከረዥሙ ጸሎታቸዉ መልስ።

ተመስገን!

ምኑንም ሳላስቀር ዝክዝክ አድርጌ ተናዘዝሁላቸዉ። መቼም ንስሐ ከገባሁ በኋላ እንደማገኘዉ ያለ ዕረፍት በሌላ በምንም አላገኝም፡፡ አረፍሁ። በዚያዉም ላይ፣ በክርስትና እምነት አንዴ ተጸጽቶ ንስሐ የተቀበሉበትን ኃጢአት እያወሱ ማዘን፣ ክህደት እንደሆነ አባቴ ራሳቸዉ ደጋግመዉ
ነግረዉኛል። መሐሪ ነዋ አምላካችን! የሆነዉ ሁሉ ሆኖ አልፏል በቃ። አለቀ፡፡ የተቀበልሁትን ቀኖና መፈጸም እና ስለ ይቅር ባይነቱ ማመስገን
እንጂ፣ ከእንግዲህ ማለቃቀስ አይገባኝም፡፡ አጠፋሁ ይቅርታ ለመንሁ
ይቅርታ አገኘሁ። አበቃ::

ቅልል ብሎኛል።

“ምስጢር ልንገርሽ?” አሉኝ፣ መስቀል ተሳልሜ የንስሐ አባቴን
ይፍቱኝ ብዬ ልሰናበታቸዉ ወደ ጉልበታቸዉ አፌን ሳሞጠሙጥ። ቆም ብዬ ጠበቅኋቸዉ። አፍ አፋቸዉን እያየሁ ለመስማት ብጠባበቅም፣ እሳቸዉ ግን ለማጓጓት ይመስላል፤ ምስጢር ያሉትን ለመናገር ሆነ ብለዉ
አዘገዩብኝ፡፡ እዉነትም ጓጓሁላቸዉ። ለነገሩ ምስጢር መስማት የማያጓጓዉ ማን አለ? ሰዉ በምንም ዓይነት ስሜት ዉስጥ ቢሆን እንኳን፣ ምስጢር
ከተባለ ጆሮዉ መቆሙ የማይቀር ነዉ። ያዉም ከካህን ልብ አምልጦ
የሚገኝ ምስጢር! በጣም ጓጓሁ።

“ቀድሞሻል”

“ማን?”

እሸቴ”

ኧረ በስመ አብ! የዚህን ልጅ ስም የማልሰማበት ቦታ የለም በቃ? በእርግጥ እሳቸዉን እንኳን እሸቴን እንዴት አወቁት ማለት አልችልም። እኔ ራሴ ነኝ የንስሐ አባት ይኑርህ ብዬ እሳቸዉ ዘንድ አምጥቼ እሸቴን ያስተዋወቅኋቸዉ፡፡ እኔ ለስንትና ስንት ቀናት እንደዚያ ቀኑ
ሲጨልምብኝ፣ አጅሬ እሽቴ ቀድሞኝ ንስሐ በመግባቱ አደነቅሁት። የትና የት ጥሎኝ ሄዷል፡፡ በልጦኛል፡፡ የንስሐ አባቴ ግን ጉዴን ያዉቁ ኖሯል ማለት ነዉ? ታዲያ ምነዋ ቀድመዉ ቢነግሩኝ? ቢያንስ ደዉለዉ ልጄ
ጠፋሽብኝ ሊሉኝ አይገባም ነበር? አይዞሽ ብለዉ ማጽናናት
አልነበረባቸዉም?
“አታኩርፊ” አሉኝ፣ የዉስጤን ሁሉ እንደሚያዉቁበት አዉቀዉብኝ::
“ራስሽ እንደምትመጪ ስለማምን ነበር እንዲህ ነዉ እንዲህ ነዉ ሳልል የጠበቅሁሽ። ጸጸት ከዉስጥ ሲሆን አይዶል ዋጋ የሚኖረዉ?”

አሳመኑኝ፡፡ እንኳንስ እንደኔ ላለ ትዕቢተኛ ይቅርና ማንም ቢሆን ጥፋቱን ማመን ያለበት ራሱ ጥፋተኛዉ ነዉ። ጥፋት የሆነዉንና ያልሆነዉን ለይቶ የማስተማር የካህኑ ድርሻ ሲሆን፣ ይኼን ይኼን በድያለሁ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቁኝ ብሎ ካህን ፊት መዉደቅ ግን የኔ ፋንታ ነዉ። ያለበለዚያማ ምኑን ኑዛዜ ሆነዉ? መቼስ እንደ መርማሪ ፖሊስ
አይመረምሩኝ።

እሳቸዉ ልክ ነበሩ። አበጁ!
ክብረ ንጽሕናዬን እንደ ዘበት ማጣቴን ካወቅሁባት ዕለት ጀምሮ እሽቴ በደረሰበት ላለመድረስ ያልሞከርሁት መሸሸጊያ ጭንብል የለም፡፡ እሱም እኔ ያለሁበት ቦታ እንዳይደርስ ያልሠራሁበት ተንኮል የለም። በተለይም ዕለት በዕለት ሊያገናኘን ይችል ከነበረዉ የሲራክ-፯ ማዕከል ያስወጣሁበት
ሴራ ትዝ ብሎኝ ፈገግ አልሁ።
በደንቡ እንደሚታወቀዉ፣ አንድ ሰዉ የማኅበሩ አባል ለመሆን ኹለት መሠረታዊ ቅድመ ግዴታዎች ተቀምጠዉለታል። በቅድሚያ ከጀርባዉ ምንም የቅሰጣ እከክ የሌለበት ክርስቲያን መሆን፣ ሲቀጥል ደግሞ
የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ተገንዝቦ መቀበል ይጠበቅበታል። ከዚያ በኋላ በሕዝብ ዘንድ በግላጭ ከሚታወቁት እና እጅግ ከበሬታ ካላቸዉ የማኅበሩ የአገልግሎት ማዕከላት በአንደኛዉ ገብቶ ማገልገል ይጀምራል።
ይኼ ለማኅበራችን ማኅበርተኞች ሁሉ የሚሠራ ሲሆን፣ ደንቡም
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀጥተኛ ይሁንታ አለዉ። ሕዝብም ሆነ
መንግስት ይኼንን ጠንቅቀዉ ያውቁለታል። ከማኅበሩ ማዕከላት አንዱ፣ የመረጃና ደኅንነት ጉዳይ የሚመለከተዉ ሲራክ፯ ግን እንኳንስ በሰፊዉ ሕዝብ ይቅርና በራሱ በማኅበሩ ማኅበርተኞችም አይታወቅም። በጣም ከጥቂቶች በቀር፣ ሲራክ ፯ን የሚያዉቀዉ ራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነዉ።
ስለሆነም የሲራክ ፯ አባል ለመሆን እንደ ሌሎቹ ማዕከላት በምርጫ የሚገኝ አይደለም። ይልቁንም ራሱ ማዕከሉ ነዉ አባሎቹን በሥዉር ከማኅበሩ አባላት መካከል መርጦ የሚመመለምለዉ። ምልመላዉም እጅግ ዘለግ ያለ ሂደት አለዉ። አንድ ዕጩ አባል ወደ ማዕከሉ መመልመል ሲጀመር፣ ቅድሚያ ከአፍ መፍቻ ቋንቋዉ ተጨማሪ፣ ቢያንስ ኹለት የሀገር ዉስጥ ቋንቋዎች እንዲማር ይደረጋል። በኹለተኛነት ደግሞ መደበኛ ሙያዉ ምንም ሆነ ምን ለስድስት ወራት ያህል ወደሚመደበበት
ገጠር ሄዶ በሙያዉ እንዲያገለግል ግዳጅ አለበት። በዚያም ለኗሪዎቹ የሚያበረክተዉ በጎ ሥራ ታይቶ፣ ነጥብ ይሰጠዋል። ያመጣዉ ነጥብ
ከተወደደለት ብቻ ወደ ከተማ ተመልሶ ተጨማሪ የመስክ ልምምድ ይጀምራል፡፡ በእርግጥ የተመለመለዉ ለመረጃ ሰብሳቢነት ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። ቢሆንም ባይሆንም ግን ቀጥታ ወደ ታጨበት ንኡስ
ክፍል ዘሎ መግባት የለም።

በሁሉም ምዕራፎች ደግሞ የጎንዮሽ ሥልጠናዎች እና ግዴታዎች አሉ።

ሂደቱ እንደዚህ ቢሆንም፣ እሸቴ የተመለመለዉ ግን በመደበኛዉ የሲራክ ፯ የምልመላ መንገድ አልነበረም። እሱ እንዲያዉም ከነጭራሹም የማኅበሩ አባል አልነበረም:: አባል አለመሆን ብቻም ሳይሆን፣ ማኅበሩን
ከነስሙ ይጠላዉ ነበር። ማንም ያልታደለዉን ዕዉቀቱን ለመጠቀም ሲባል ብቻ፣ በቀጥታ ነዉ የሲራክ ፯ አባል እንዲሆን የተደረገዉ፡፡ እኔም እሱን የመረጃ ማዕከሉ አባል በማድረግ ሂደቱ ላይ እንዲያ ከፍ ዝቅ እንዳላልሁ
ሁሉ፣ ማየት ባስጠላኝ ጊዜ ደግሞ ከሲራክ ፯ ላማስባረር ያልፈነቀልሁት ድንጋይ አልነበረም። በመጨረሻም ተሳካልኝ፡፡ ባልቻ የሲራክ ፯ ዋና ኃላፊ ሆኖ የተሾመ ዕለት በቡና ሰዓት ስንጨዋወት፣ የምመኘዉን ዜና አበሠረኝ፡፡

(እሸቴ ወደ ባንቱ ሊሄድ መሆኑን አዉቀሻል ወይ? አለኝ፡፡
‹ እረ በጭራሽ! የት ነዉ ደግሞ ባንቱ?)


(አሃ. ለእሱ እኮ ተነግሮታል። እንዴት አልነገረሽም?)

(የት አባቱ!) አልሁኝ በለሆሳስ፣ ዞር ብዬ ለልቤ ደስታ እያጠጣሁት።
ለይስሙላ እንደማያዉቅ ሆንሁበት እንጂ፣ ለምን ጉዳይ እና ለምን ያህል ጊዜ ባንቱ እንደሚሄድ ሳይቀር ጠንቅቄ አዉቃለሁ፡፡ እንደገና እንደ ዕጩ
አባል ተቆጥሮ የስድስት ወሩን የገጠር የግዳጅ አገልግሎት ለመወጣት፣ በደቡብ ምዕራብ በኩል በምትገኘዉ ባንቱ መመደቡን ሳዉቅ ማንም
አልቀደመኝም፡፡ ባንቱ ከአዲስ አበባ በምን ያህል ርቀት ላይ እንደምትገኝ ሳይቀር ራሴ ከተማዋ ድረስ ሄጄ ለክቼዋለሁ። ምክንያቱም ራሴ ነኛ ወደ'ዚያ እንዲልከዉ ከባልቻ በፊት የነበረዉን የሲራክ፤ ኃላፊ
የወተወትሁት። እንደ ተባለዉም ጓዙን ጠቅልሎ ሄደልኝ፡፡ ነገር ግን
ሳምንት ያህል እንኳን ሳይቆይ፣ ግዳጁን እያቋረጠ ወደ አዲስ አበባ መለስ ቀለስ አበዛ፡፡ የኋላ ኋላ እንዲያዉም ከነጭራሹ አልሄድም ብሎ መቅረቱን
ሰምቼለታለሁ። እንዲችዉ ሲቅበጠበጥ ከራርሞ አሁን ግን አይቼዉ አላዉቅም።

በእርግጥ ግዳጁን ለማቋረጥም ምክንያቱ እኔ እንደ ሆንሁ አላጣሁትም።

“እህእ” ብለዉ ጎሮሯቸዉን ሲጠራርጉ ባነንሁ። ለካንስ የንስሐ አባቴ ከፊቴ ቆመዉ ኖሯል በትዝታ እንዲህ ጭልጥ ያልሁት? ወይ እኔ!

“ሐሳብ ገባሽሳ”

“እሸቴ ሲሉኝ ጊዜ...”

“ልትነግሪኝ የምትፈልጊዉ ነገር አለ ልበል፣ ስለ እሸቴ?”

“ሰሞኑን ድምፁ ለኔም ጠፍቶብኛል። የት እንዳለ ያዉቃሉ? ነግሮዎት ከሆነ”
👍271
“አንቺም አታዉቂም ማለት ነዉ? ይኼዉ ስንት ቀኑ ስልኩንም ስሞክረዉ እምቢ ብሎኛል። ምናልባት የምታዉቂዉ ካለ ብዬ እኔም ልጠይቅሽ አልጠይቅሽ እያልሁ ነበር። አታዉቂማ?”

“ኧረ በጭራሽ። በደህናዉ ይሆን ብለዉ ነዉ?”

“ምኑን አዉቄ ልጄ፤ ምን በላብኝ ልጄን?”

“እረ እንጃልኝ”

“ይሁንና ለመጨረሻ ጊዜ መቼ ነዉ አንቺ ያገኘሽዉ?”

“የዚያዉ ዕለት። ነገሩ የተበላሸበት ጊዜ የተያየን ነን”

“በስመ አብ! ከስንት ከአምስት ወር በፊት?”

“ያዉ እሱማ፣ ያዉ አልፎ አልፎማ እየተደበቀ ያየኝ ነበር። እኔም አልፎ አልፎ እንደሱ”

“እንጂ ይቅር ለማለት አሳስቦሽ አያውቅም?”

“አልፎ አልፎ”

“አልፎ አልፎ?

አልፎ አልፎ ብሎ ጉድ! እንዲያማ ክርስቶስ አምላክ አይደለም የሚሉ ክርስቲያኖችስ የሉም ብለሽ ነወይ? አልፎ አልፎማ ልጅ
የማይወዱ እናቶች፣ የማታሞቅ ፀሐይ፣ የማይመሽ ቀናት፣ የማይቀድሱ ካህናት፣ የማይዘንብ ደመና፣ የማይሞቱ ሰዎች ይታጣሉ ብለሽ ነዉ? አረ አሉ፡፡ ከስንት አንድማ የሚዳሰስስ ሰማይ፣ የሚቀመስስ መርዝ፣ የሚለበስስ
ጨለማ፣ የሚደረስበትስ እንጦርጦስ፣ የሚገመጥስ ድንጋይ፣ የሚሽተትስ
ዉሃ አለ አይደል?”

አፌን ከፍቼ ቀረሁ። ለመሆኑ ገብቶኛል ግን? ምንድነዉ ያሉኝ? ወጣ ወረደ ስለ እሽቴ ነዉ አይደል ያወሩት?

አንዴ የእሸቴ ሐሳብ ስለሞላብኝ፣ ንስሐ አባቴ ያሉት ምንም ሆነ ምን
የገባኝ እሽቴን መፈለግ እንዳለብኝ ብቻ ነዉ። ልቤን ተወግቻለሁ። ምን አግኝቶት ይሆን? በቅጽበት ስንቱን አሰብሁት! እሸቴ ማለት ፈላጊዉ ብዙ የሆነ ባለ ልዩ አእምሮ ልጅ ነዉ። ሌላዉ ይቅርና ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት (NISS) የሚባለዉ የኢትዮጵያ የመንግሥት
የደኅንነት ተቋም በጥብቅ እንደሚፈልገዉ አዉቃለሁ። ቢቻል ቢቻል ወደር በሌለዉ አእምሮዉ ለመጠቀም፣ ያ ካልሆነ ደግሞ ማኅበሩ እንዳይጠቀምበት ሊገድለዉ ያሳድደዉ ነበር። ሁልጊዜም ቢሆን በድብቅ
ጥበቃ የሚያደርጉለት የእኛዎቹ የሲራክ አባላት እያሰናከሉባቸዉ እንጂ የመንግሥት የደኅንነት ወኪሎች ብዙ ጊዜ አንቀዉ ሊወስዱት ሞክረዋል።

አሁን እንዲህ የጠፋዉ ምናልባት በእነሱ እጅ ወድቆ ቢሆንስ?

ወደ መኪናዬ ሽምጥ እየሮጥሁ ሳለ ነበር፣ የንስሐ አባቴን እንኳን
እንዳልተሰናበትኋቸዉ ያወቅሁት፡፡ እንደ ልማዴ በጥድፊያ ወደ ሲራክ፯ አሽከረከርኩ....

ይቀጥላል
👍316👏3
አትሮኖስ pinned «#ገረገራ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #በታደለ_አያሌው .....“ያንቺ ነዉ” አለችኝ፣ እኛ እያለን ራሷ ወደ ጀመረችዉ የምሳ ጉድ ጉዷ እየተመለሰች፡፡ “ታዲያ አደራሽን ምንድነዉ ቅብጥርሴ እንዳትጠኝ። እኔ ምኑንም አላዉቅልሽም። ስጭ ነበር የተባልሁት፣ ይኼዉ ሰጥቼሻለሁ። አበቃሁ” በእራፊ ጨርቅ የተጠቀለለች ትንሽ ነገር መሆኗን ቀድሞዉንም ስትሰጠኝ ኣስተዉያለሁ፡፡ ምን እንደሆነች ለማየት ገለጥ ባደርጋትም፣…»
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_ሰባት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


የልጅትዋ አድራሻ

ኮዜት ቀኑን ሙሉ እህል በአፍዋ ሳይገባ ከክፍልዋ ውስጥ ተዘግታ
ዋለች፡፡ መሄጃቸው ስለተቃረበ ያንን የነበሩበትን ትልቅ ቤት ለቅቀው ሆቴል ቤት ነበር የገቡት:: ያን እለት የዣን ቫልዥ የመብላት ፍላጎት ከመቼውም ይበልጥ ስለተከፈተ እራቱን በጊዜ እንክት አድርጎ ይበላል።
ኮዜት ከማዕዱ አልቀረበችም፡፡ እራቱን እየበላ ሳለ ሠራተኛው ከአንዴም ሁለቴ፣ ከሁለቴ ሦስቴ ብቅ ጥልቅ እያለች «ኧረ እኔ አላማረኝም፤ አገሩ ተረብሿል፧ ውጊያው ተጧጡፏል አሉ» በማለት ስታናግረው መንፈሱ
ጥቂት ይሽበራል፡፡ ሆኖም እስከዚህም ስሜት አልሰጠውም:: ኮዜትን ይዞ ወደ እንግሊዝ አገር ከሄደ ከዚያ ደስ ብሎት ሊኖር እንደሚችል ያሰላስላል።
ከነበረበት ብድግ ብሎ ነበር ወደ መስኮት፧ ከመስኮት ወደ በር በአሳብ ተውጦ ሲንቆራጠጥ አንድ ነገር አየ፡፡

ተሰቅሎ ከነበረው መስታወት አጠገብ አንድ ጽሑፍ ሳይተጣጠፍ
ከመሬት ወድቆ ስለነበር በመስታወቱ አንጸባራቂነት ከውስጥ በኩል አየው፡፡
ጽሑፉም እንዲህ ይላል፡፡

የእኔ ፍቅር! የሚገርምህ ነው፤ አባዬ አሁኑኑ እንድንሄድ ይፈልጋል፡
ዛሬ ማታ ሆም አርሜ ከተባለ ሥፍራ እንሄዳለን:: በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከእንግሊዝ አገር እንገባለን፡፡ ኮዜት ሰኔ 4»

ዣን ቫልዣ ፈዝዞ ቀረ::
ኮዜት ሀዘን በዝቶባት ስለነበር ለማሪየስ የላከችውን ደብዳቤ ረቂቅ ጽሑፉን ከጻፈችበት ሥፍራ ረስታዋለች::

ዣን ቫልዣ ወደ መስታወቱ ጠጋ ብሎ ጽሑፉን እንደገና አነበበው::
ማመን አቃተው፡፡ ከኮዜት የተለየ መሰለው:: «ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?» ሲል ጭንቀት ያዘው:: ጎንበስ ብሎ ጽሑፉን አነሳው:: በጣም ተረበሸ፡፡ ዓለም ጨለመችበት:: መቼስ በሕይወት ሊደርስ ከሚችል ማንኛውም
አሲቃቂ ነገር ሁሉ የወደዱትን ከማጣት ይበልጥ የሚያንገበግብ፣ የሚያሳርር
ነገር የለም:: ዣን ቫልዣ ያንን ጽሑፍ በማንበቡ ያቺን የሚወዳትንና ብቸኝነቱን የሚረሳባትን ኮዜት ያጣ መሰለው:: ከአሁን በፊት እንደጠቀስነው ዣን ቫልዣ ኮዜትን እንደ ልጅ ብቻ ኣልነበረም የሚያያት:: ኮዜት ለእርሱ
እንደ ልጅም፣ እንደ እህትም፣ እንደ እናትም ነበረች:: ሕይወትን ጠልቶ ሳለ ሕይወትን መልሶ እንዲያፈቅር ያደረገችው ኮዚት ናት:: ዣን ቫልዣ
ፍቅረኛ ወይም ሚስት አልነበረውም:: ስለዚህ የፍቅሩ ጽናት የሰፈረው ኮዜት ላይ ነበር ለማለት ይቻላል:: በአባትነቱ እርስዋም ከልብ ትወደዋለች::
ያ ፍቅር አክትሞ በሌላ የተተካ ስለመሰለው ነበር እንደዚያ እጢው ዱብ እስኪል የደነገጠው:: ሌላ ማስረጃ የሚያሻው ነገር አይደለም፡፡ ወረቀቱ ከፊቱ ላይ ነው ያለው:: «ፍቅረኛ አላት ማለት ነው ፤ መሄድዋ ነው እንግዲህ» ሲል አጉረመረመ:: የብቸኝነት ስሜት ወረረው:: «እኔን እንደጎበያ
ድንጋይ ጎልታ ልትሄድ! » ለእኔ የሚለው የራስ ወዳድነት ስሜት
ተጠናወተው:: ልቡ የተቃውሞ ኃይል አረገዘ:: ዣን ቫልዣ ይህን እያሰላሰለ ሳለ ሠሪተኛዋ እርሱ ከነበረበት ክፍል ገባች::

«ውጊያ ይካሄዳል ያለሽው የት ሰፈር ነበር? ቦታውን አውቀሽዋል?»

ሠራተኛዋ ተገርማ «እርስዎ ከፈለጉ ምን ገድዶኝ እነግሮታለሁ» ስትል መለሰች::

«ውጊ.ያው ተጧጡፎአል ብለሽ አሁን አልነገርሽኝም እንዴ!» በማለት ቀጠለ::

«አዎን ጌታዬ!›› አለች ሠራተኛዋ ፤ ከዚያ ከማርያም ቤተ ክርስቲያን
ባሻገር ነው:: ››

ዣን ቫልዣ ከነበረበት ውጭ ወጥቶ ደንጋይ ላይ ቁጭ አለ፡፡
ጊዜው ጨልሞአል::

ውርጭ ላይ ለምን ያህል ሰዓት ተቀመጠ? እግሩን በመዘርጋትና
በማጣጠፍ ራሱን አዝናና ወይስ ኩርምት ብሎ ነው የቀረው? እንዳጎነበሰ ቀረ ወይስ ቀና አለ? አንድ ነገር ተደግፎ ነው ወይስ እንዲሁ ጉች ብሎ ነው
የተቀመጠው? ራሱ እንኳን ቢሆን ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ሊሰጥ አይችልም።

በአንድ ወቅት የኮቴ ድምፅ ስለሰማ ብቻ ቀና አለ፡፡ አንድ ልጅ ወደ እርሱ ሲመጣ ተመለከተ፡፡ ጋቭሮች መልእክቱን ለማድረስ ከቤቱ ደረሰ። ወደ ላይ እያየ የቤት ቁጥር ሲፈልግ ዣን ቫልዣ አየው:: ሆኖም ከቁጥር አላስገባውም::

«አንተ ልጅ» አለ ዣን ቫልዣ ፧

«ምን ሆነሃል?»

«የሆንኩትማ እርቦኛል» ሲል ጋቭሮች በድፍረት መለሰለት:: ምናምን ይሰጡኛል?» አለ ቀጠለና፡፡

ዣን ቫልዣ ከኪሱ አንድ መቶ ሱስ አወጣና ሰጠው::

ግን ጋቭሮች አደብ የሌለው ተቅበጥባጭ ልጅ እንደመሆኑ መጠን ገንዘቡን እንደ መቀበል ድንጋይ አነሳ፡፡ የሚሰራ የመንገድ መብራት አየ::

«አሁንም የውጭ መብራት ታበራላችሁ እንዴ?» ሲል ጋቭሮች
ጠየቀ፡፡ «በአሁኑ ጊዜ እኮ መብራት ማብራት ጥሩ አይደለም» ካለ በኋላ
ድንጋዩን ወርውሮ መብራቱን ሰበረው፡፡ አካባቢው በድንገት ጨለመ::

ዣን ቫልዣ ወደ ልጁ ተጠጋ::

«ወይ ምስኪን፣ እንዲህ የሚያስደርገው ምናልባት ረሃቡ ይሆናል። ሲል እርስ በራሱ ተነጋገረ፡፡ መቶውን ሱስ አስጨበጠው::

ጋብሮች የምንተ እፍረቱን ገንዘቡን ተቀበለ፡፡

«ሌላ መብራት እንዳልሰብር ነው» አለ እንዳቀረቀረ፡፡

«እንደ ፈለግህ ስበር፧ እኔ ምን አገባኝ» ሲል ዣን ቫልዣ መለሰለት።

«ጥሩ ሰው ነዎት!» አለ ጋቭሮች::
አምስቱን ፍራንክ ማለት አንድ መቶ ሱስ ከኪሱ ውስጥ ጨመረ።
ሰውዬውን ስለወደደው በድፍረት ጥያቄ ጠየቀው::

«የዚሁ ሰፈር ሰው ነዎት?»

«ምን ፈለግህ?»

«የቤት ቁጥር 7 የትኛው እንደሆነ ያሳዩኛል?»

«ከዚያ ምን አለህ?»

እዚህ ላይ ልጁ አመነታ:: ሰውዩውን ያስቀየመው መስለው:: ፀጉሩን በጥፍሩ ያክ ጀመር፡፡

«ብቻ» በማለት የያዘውን ደብዳቤ አሳየው::

ዣን ቫልዣ በድንገት አንድ ሀሳብ ስለመጣለት «ስጠብቀው የነበረውን ደብዳቤ አመጣህልኝ» አለው::

«ለእርስዎ?» ሲል ጋቭሮች ጠየቀ፡፡ «እርስዎ ሴት አይደሉ!»

«ደብዳቤው ለወ/ት ኮዜት ነው፤ አይደለም?»

«ኮዜት?» ሲል ጋቭሮች አጉረመረመ:: «አዎን ደብዳቤው የእርሳቸው ነው ፤ ስማቸው ግን ያስቃል፡፡»

«ይሁን ግድ የለም» አለ ዣን ቫልዣ ፤ «ደብዳቤውን እኔ እሰጣታለሁና
ለእኔ ስጠኝ፡፡»

«እንግዲያውስ ውጊያው ከሚካሄድበት ቦታ እንደመጣ እንዲነግሯት እፈልጋለሁ::»

«ጥሩ» አለ ዣን ቫልዣ::

ጋቭሮች ደብዳቤውን ከሰጠው በኋላ ለዣን ቫልዣ ወታደራዊ ሰላምታ ሰጠው::

«ደብዳቤውን በጥንቃቄ ይያዙት ፤ ከአስተዳደር ነው የመጣው::
እርስዎም ይቸኩላሉ እንዴ? ለመሆኑ ደብዳቤውን የተቀበለው ማነው እላለሁ? ስምዎን ይንገሩኛ ደብዳቤውን ለላኩት እመቤት እንድነግር» ሲል
ኩራት እየተሰማው ተናገረ፡፡
‹‹ጥያቄውን የሚያቀርቡት ቅድስት ፍንዱቄ ናቸው?» ሲል ዣን
ቫልዣ ጠየቀው::

«ቸኩያለሁ፤ ደብዳቤውን ያመጣሁት ከውጊያ ሥፍራ ነው፤ አሁንም ወደዚያው መመለሴ ነው» ብሎ መንገዱን በመቀጠል ሰፈር እንደጠፋበት ወፍ በርሮ ሄደ::

ዣን ቫልዣ ማሪየስ የጻፈውን ደብዳቤ ይዞ ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ከክፍሉ ውስጥ ገብቶ በሩን ከዘጋ በኋላ ጥምብ እንዳገኘ አሞራ በመቸኵል ደብዳቤውን
ገለጠው:: የታየሁ እንደሆነ ብሎ በመፍራት ቀና አለና ዙሪያውን ተመለከተ፡፡
ማንም የለም:: ኮዜትና ሠራተኛዋ ተኝተዋል ሲል ግምት ወሰደ::

የሚያደርገው ነገር የሌብነት ስለሆነ ሻማ ለመለኮስ ክብሪት ሲጭር እጁ ተንቀጥቅጦበት ነበር፡፡ አሁን ግን ትንሽ መንፈሱ ስለተረጋጋ ሻማውን አቀጣጠለ፡፡ ከጠረጴዛ ላይ ክርኑን አስደግፎ ደብዳቤውን ማንበብ ጀመረ::
ማሪየስ ለኮዜት ከጻፈው ደብዳቤ ውስጥ የሚከተሉትን ቃላት ብቻ
አጤነ፡፡

«እሞታለሁ፤ ይህን ደብዳቤ ስታነቢ ነፍሴ ከአጠገብሽ ይሆናል፡፡»
👍21👏21
ይህን ሲያነብ ፊደሎቹ የሚዘልለ መሰለው:: ልክ እንደ ሰከረ ሰው
እየተንገዳገደ ነበር ጽሑፉን አንብቦ የጨረሰው:: ያ በመንፈስ የጠላው ሰው ከሞት አፋፍ ቆሞ በማየቱ ውስጥ ውስጡን ደስ አለው:: አለቀ እንግዲህ፣ ያ የፈራው ነገር ተወገደለት፡፡ ከአሰበው ጊዜ አጥሮ ለፍጻሜ ደረሰለት::የወደፊት ሕይወቴን አበላሸብኝ ያለው ሰው ሕይወት መጨረሻ ተቃርቦአል::
ስለዚህ «ውስጥ ውስጡን ደስታ እንክት ያድርገኝ እንጂ» ሆነ፡፡ ለዚህ ሰው መሞት ደግሞ ዣን ቫልዣ ያደረገው አስተዋጽኦ የለም፡፡ ኮዜትን ሊጋራበት
የነበረው ሰው በፈጣሪ ኃይል ተወገደለት::

ደብዳቤውን ለኮዜት ካልሰጣት ማሪየስ የት እንደደረሰ ካዜት
አታውቅም:: ከጦርነት መካከል የገባ ሰው ሊያመልጥ አይችልም፡፡ ማሪየስም ቢሆን ይህን አውቆአል፡፡ እስከዚያች ሰዓት ካልሞተ በቅርቡ እንደሚሞት
ጥርጥር የለውም:: ጥሩ አጋጣሚ! ውብ የሆነ ደስታ!
ልቦናው ይህን ሲያሰላስል ዣን ቫልዣ ሳይታወቀው ከልቡ ውስጥ
ሀዘን ተሰማው:: ከአንድ ሰዓት በኋላ ሙሉ የሚሊቴሪ ልብስ ለብሶ ከቤቱ ወጣ፡፡ በአካባቢው የነበረ አንድ ወዝ አደር የሚፈልገውን ልብስና መሣሪያ
በቀላሉ አሟላለት:: ጠብመንጃ ሳይቀር ይዞ ዣን ቫልዣ ወደ ውጊያው ሥፍራ አመራ::

💫ይቀጥላል💫
👍16👏2
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

የቤት ውስጥ ጦርነት

ሌሊቱን ሌላ ውጊያ ስላልተካሄደ አድመኞቹ የፈራረሰውን ምሽጋቸውን ለማደስና ለማስፋት ጊዜ አገኙ፡፡ ከቁመቱ ትንሽ ጨመሩለት፡፡ ብረት መከላከያም አበጁ፡፡ ወጥ ቤቱን አጸዳድተው የቁስለኛ ማከሚያ ክፍል
አደረጉት:: የሞቱትን ሰዎች አስከሬን አንስተው ጥግ አስያዙ፡፡ በስርቆሹ በር በኩል ያለውን መግቢያና መውጫ በሚገባ ተጠቀመበት፡፡ ቡና ቤቱ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ሦስት ሴቶች ጨለማን ተገን በማድረግ በጓሮ በር በኩል ወጥተው በመሄዳቸው አድመኞቹ እፎይታን አገኙ::

ጎህ ሲቀድ ኢንጆልራስ ሁናቴውን ለመቃኘት በስርቆሹ በር በኩል
ወደ ውጭ ወጣ፡፡ አድመኞቹ «እናሸንፋለን» የሚል እምነት ነበራቸው:: ሆኖም ኢንጆልራስ ከተመለሰ በኋላ ሁኔታው በአንድ ጊዜ ተለወጠ፡፡ ኢንጆልራስ በከተማው የነበረው ጦር በሙሉ እነርሱን ሊያጠቃ መውጣቱን
ሕዝቡ ግን ባለፈው ቀን ገንፍሎ ወጣ እንጂ በእለቱ ሁሉም ከቤቱ መከተቱን ሊነግራቸው መሞቻቸው መቃረቡን ጠረጠሩ፡፡ ከመካከላቸው አንዱ «ወንድሞቼ ሕዝቡ ሪፑብሊኩን ሲከዳ እኛ ሕዝቡን አንከዳም፡፡ እኛ አሁን
ማድረግ ያለብን ምሽጋችንን አጠናክረን በአለን ኃይል መዋጋት ነው» ብሎ ተናገረ፡፡

እነዚህ ቃሎች የአድመኞቹን ሞራል ገነቡት፡፡ ይህ ቃል የማን እንደነበር
እስከዛሬ አልታወቀም:: ብቻ ቀቢጸ ተስፋ በሚገኝበት ጊዜ ዘወትር አንዱ ብቅ ብሎ ሁኔታውን እንደሚለውጥ ሁሉ ይህም ከዚህ የተለየ አልነበረም::

ያ «የሕዝብ ወገን ነኝ» የሚለው ሁሉ ተቃውሞውን ካሰማ በኋላ
«እድሜ ለሞት፧ ለዚያች ቅጽበት ሁላችንም እንቆይ!» ሲሉ ሁሉም በአንድነት ጮኹ::

«ለምን ሁላችንም?» ሲል ኢንጂልራስ ጠየቀ፡፡

«ሁላችንም! ሁላችንም!» የሚል ድምፅ አስተጋባ፡፡

«ምሽጉ ጥሩ ነው:: ለመመከት ሰላሳ ሰዎች ይበቃሉ:: ለምን አርባ
ሰዎችን እንሰዋለን» በማለት ኢንጆልራስ ተናገረ::

«ምክንያቱማ ከዚህ ለመሄድ የሚፈልግ ሰው ባለመኖሩ ነዋ!» አሉ ሁሉም በአንድነት::

ኢንጆልራስና ኮምብፌሬ ወደ ምድር ቤት ወርደው አራት የወታደር ልብስ ይዘው መጡ፡፡

«ከመካከላችን ቤተሰብ ማለት የሚጦሯቸው እናት! እህት፣ ሚስት፣ ልጆች ያልዋቸው አይጠፉም፡፡ የዚህ ዓይነት ኃላፊነት ያለባቸው ከዚህ
ይሂዱ» ሲሉ ኢንጆልራስ አሳሰበ፡፡

«እውነት ነው! አሁን እርስዎ ቤተሰብ አለዎት! እርስዎ ቢሄዱ»
በማለት አንዱ ወጣት ከአጠገቡ የነበሩ ጠና ያሉትን ሰው መከራቸው፡፡

«ይልቅስ አንተ ሁለት እህቶችህ በአንተ ላይ አይደለም ያሉት?»

ሁሉም በየፊናው «አንተ ሂድ፣ አንቱ ሂዱ» ሲባባል ጫጫታ ሆነ፡፡
«ወንድሞቼ! የምንዋጋው ለሪፑብሊኩ ነው ! አሁን ጭቅጭቀን ተዉና መሄድ ያለባቸው ይሂዱ» አለ ኢንጆልራስ፡፡

አምስት ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አምስት ሰዎች በኣንድ ድምፅ ተመርጠው እንዲሄዱ ተወሰነ፡፡

«አምስት ናቸው» ሲል ማሪየስ ተናገረ፡፡

የነበረው ዩኒፎርም ግን አራት ነው:: በዚህ ጊዜ ከሰማይ የወረደ
ይመስል አንድ ሌላ ዩኒፎርም ተጣለ፡፡ የአምስተኛው ሰው ሕይወት ዳነ ማለት ነው::
ማሪየስ ልብሱን ማን እንደጣለው ለማየት ቀና ብሎ ሲያይ መሴይ
ፎሽለማንን አየው:: ዣን ቫልዣ ከምሽጉ መግባቱ ነበር፡፡
በጓሮ በኩል ማንም ሳያይ በሚያስገባው መንገድ ነው የገባው:: ያንን መንገድ ቀደም ብሎ ይወቀው ወይም በአጋጣሚ ይድረስበት አይታወቅም፡፡
ከቤቱ ሲወጣ የወታደር ልብስ ለብሶ ስለወጣ ለማለፍ ብዙም አልተቸገረም::

«ይህ ሰው ማነው?» ሲል አንዱ ጠየቀ::

«እሱማ» አለ ኮምብፌሬ የሌሎችን ሕይወት የሚያድን ሰው ነው::

«እኔም አውቀዋለሁ» ሲል ማሪየስ ሀዘን እየተሰማው ተናገረ::

ከዚህ ይበልጥ ሌላ ማረጋገጫ አልተፈለገም:: ኢንጆልራስ ወደ ዣን ቫልዣ ዞረ::

«እንኳን ደህና መጡ፡፡ እንደምንሞት ያውቃሉ?»

ዣን ቫልዣ መልስ ሳይሰጥ ዩኒፎርም የጣለለትን ሰውዬ ያለብስ ጀመር

ምንም እንኳን ጊዜው ረፈድ ቢልም አንድም መስኮት አልተከፈተም።
በሩቁ ግን ሰዎች ከወዲያ ወዲህ ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ፡፡ ወሳኙ ሰዓት
እንደቀረበ ያስታውቃል፡፡

ኢንጆልራስ ከመጠጥ ቤቱ በራፍ ድንጋይ ቆልሉአል፡፡ እያንዳንዱ
ሰው ለውጊያ እንዲዘጋጅ አስጠነቀቀ፡፡ ብዙም አልጠበቁም፡፡ ከባድ ጦር
ወደነበሩት ሲመጣ ተመለከቱ፡፡ የተኩስ ድምፅ ተሰማ::

«ተኩስ» ሲል ኢንጆልራስ አዘዘ፡፡

ከዚያ በኋላ ምኑ ቅጡ፤ አገር ተቃጠለ፡፡ ሰማዩ ሁሉ በጭስ ተሸፈኑ።ፊት ለፊት የነበረውን ጣልኩ ሲባል ሌላው ከኋላ ብቅ ይላል::

«ቶሎ ቶሎ እያላችሁ ጠብመንጃችሁን አጉርሱ» ሲል ኢንጆልራስ ጮኸ፡

አድመኞቹ ከባድ መሣሪያ መተኰስ ጀመሩ፡፡ ብዙ ስው ተረፈረፈ።ሁሉም በያለበት «ብራቮ፣ ብራቮ» ሲል ጮኸ፡፡ ሁሉም ተተራመሰ፡፡ ጋቭሮች
እየሮጠ ወደፊት መጣ፡፡ ልጁን ሲያዩ ሁሉም ተበራታ::

«ጓዶች በርቱ» ሲል ጋቭሮች ተናገረ:: «በርቱና ተዋጉ፤ ከየአቅጣጫው ብዙ ጦር እየመጣ ነው።»

«ይኸው ነው፤ እስቲ ሞራል ስጥልኝ!» አለ ኢንጆልራስ፡፡ ጦሩ
ሲመጣባቸው «ጭንቅላታችሁን ዝቅ አድርጉ፤ ደግሞም ወደ ግድግዳው ጠጋ በሉ» በማለት ኢንጆልራስ ምክር ለገሠ፡፡ ከባድ መሣሪያ የያዘ ወጣት
መሣሪያውን እየገፋ ሲመጣ ያዩታል:: ኮምብፌሬ ወጣቱን ሲያየው በጣም አዘነ፡፡

«እንዴት ያሳዝናል፧ ምን ዓይነት የጭካኔ ሥራ ነው የሚፈጽሙት።
ምናልባት ንጉሦች ሲጠፉ ጦርነትም ይጠፋ ይሆናል፡፡ ኢንጆልራስ፣ ወጣቱ ላይ ነው እንዴ የምታነጣጥረው ምን ማለትህ ነው? ይህ ወጣት እኮ ገና ለጋ ነው፡፡ ቢበዛ 25 ዓመት ቢሆነው ነው:: ምናልባት የሚጦራቸው አባት ፤ እናት፣ ወንድምና እህት ይኖሩት ይሆናል፡፡ ከዚህም በላይ መልከ ቀና እንደመሆኑ የሚወዳትና የምትወደው ፍቅረኛ ትኖረው ይሆናል።
ደግሞም የእኔ ወይም የአንተ ወንድም ሊሆን ይችላል፡፡»

«እሱማ ነው» ሲል ኢንጆልራስ መለሰለት፡፡

«እንግዲያውማ እርሱን መምታትና መግደል የለብንም።»

«እባክህን ዝም በለኝ፣ ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን፡፡

ደም ከመሰለው የኢንጆልራስ ጉንጭ እምባ እንደ ጐርፍ ይወርድ
ጀመር፡፡ ወዲያው የጠመንጃውን ቃታ ሳብ አደረገና ለቀቀው:: ያ ለግላጋ ወጣት ከመሬት ተዘረረ፡፡ አየር ይበላ ይመስል አፉን ከፍቶ ከአንገቱ ቀና አለ፡፡ ይጎትተው ከነበረ ከባድ መሣሪያ ላይ ተደፍቶ ፀጥ እንዳለ ቀረ፡፡ዐከጀርባው ደም ሲፍለቀለቅ ታየ:: የወጣቱ ነፍስ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ከሥጋው ተለየች::

ውጊያው ቀጠለ፡፡ ስለውጊያው ከዚህ ይበልጥ ዝርዝር ውስጥ ለመግባት ቢፈለግ ሌላ መጽሐፍ ይወጣዋል፡፡ ሆኖም በዚያች ቀውጢ ቀን የነበረው ሁኔታ ስለጦርነቱ ትንሽ መጨመር ያስገድዳል፡፡ የንጉሡ ጦር በሚገባ ተዘጋጅቶ የመጣ ስለነበር የአድመኞቹን ጥይት ለማስጨረስ ፈልጎ ኃይሉን በመበታተን ከተለያየ አቅጣጫ ተኩስ ይከፍታል፡፡ በአንድ ወገን በከባድ መሣሪያ በመጠቀም ምሽጉን አፈራረሰው:: ያንን ለመቋቋም አድመኞቹ
ባላቸው ኃይል በመታኮስ ተከላከሉ፡፡ ይህም በመሆኑ ጊዜያዊ ድልን ተቀዳጁ፡፡
ሁሉም ደስ አላቸው:: ግን የሚያሳዝነው የነበራቸው ጥይት ተገባድዶ ያገኙታል::
👍16
«በጣም ጥሩ ነው ፤ ድል መታናቸው አይደል» ሲል ጓደኛው
ኢንጆልራስን ያሞቀዋል፡፡ ኢንጆልራስ ጭንቅላቱን በመነቅነቅ «አልመሰለኝም፤
ይህ ድል ከሩብ ሰዓት ወዲያ አይዘልቅም፤ ጥይት እያለቀብን ነው» ይለዋል፡፡ ጋቭሮች ይህን ጭውውታቸውን ይሰማል፡፡ ጥቂት ቆይቶ ኩርፌይራክ ቀና ብሎ ሲያይ መንገድ ላይ እየተንፏቀቀ የሚሄድ ነገር ያያል፡፡ ጋቭሮች
ከሞቱት የንጉሡ ወታደሮች አጠገብ የተዘሩትን ጥይቶች በያዘው ከረጢት ይለቅማል፡፡ ቦታው ምሽጉ ከነበረበት ሥፍራ ብዙ ሩቅ አልነበረም::
ልጁ ጥይት ሲለቅም እንዴት አልታየም:: በመጀመሪያ ደረጃ በጉም የተሸፈነ ዝናብ ይዘንብ ነበር፡፡ ሌላው ምሥጢር ደግሞ ቀደም ሲል ከባድ ተኩስ ተካሂዶ ስለነበርና በዚያን ዘመን የነበሩ መሣሪያዎች ሲተኮሱ ብዙ
ጭስ ይወጣቸው ስለነበር አካባቢው በጭስ ተሸፍኗል:: ውጊያው በመሀል ጋብ ያለው መሪዎቹ ጭሱ በንኖ እስኪጠፋ እየጠበቁ ሊሆን ይችላል፡፡ ልጁ
ደግሞ ጥይቱን የሚለቅመው በደረቱ እየተንፏቀቀ ሲሆን የከረጢቱን ጫፍ በጥርሱ ይዞ ነበር የሚጐትተው:: በዚህ ዓይነት ጥቂት ጥይቶችን ሰብስቦ
አመላለሰ፡፡

ግን አሳዛኝ ልጁ ብዙም አልቆየ፤ ተደፋ፡፡ እርሱ ከወደቁት ሰዎች
ጥይት ሲለቅም እዚያው ከሞቱት ጋር ተደባልቆ ቀረ፡፡ የልጅ ነገር ወዲያው ብድግ ብሎ እኔስ ወድቄአለሁ፣ ግን የእነ ቮልቴር፣ የእነ ሩሶ አገር አትወድቅም» እያለ ሲጮህ ደግሞ ተመታ:: ከአፈሩ ላይ ተደፋ :: ሁለተኛም አልተነቃነቀም:: ነፍሱ ከሥጋው ተለየች::

ልጁ ሲወድቅ ማሪየስ ከምሽጉ ሮጦ ወጣ፡፡ ኮምብሬ ተከተለው፡፡
ግን አልደረሰበትም:: ጋቭሮች ሞቷል:: ኮምብፌሬ ከረጢቱን፣
ማሪየስ ይዘው ተመለሱ።

ማርየስ የልጁን ሬሣ ታቅፎ ሲመጣ እርሱም ፊት እንደ ልጁ በደም ተጨማልቆ ነበር፡፡ ለካስ ጋቭሮችን ለማንሳት ጎንበስ ሲል ግምባሩ ላይ በጨረፍታ ተመትቶ ነበር፡፡ ግን አልታወቀውም:: ኩርፌይራክ እራፊ ጨርቅ ቀድዶ ቁስሉን አሰረለት::

የጋቭሮችን አስከሬን ከማብዩፍ አስከሬን አጠገብ ጠረጴዛ ላይ አስተኙት፡፡ ሁለቱንም ሬሣ በጨርቅ መሳይ ነገር ሸፈንዋቸው:: ዣን ቫልዣ ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ አልተነቃነቀም:: ኮምብፌሬ ጥይት ሲሰጠው ራሱን ነቀነቀ።

«ምን ማለቱ ነው፧ አሁን ከዚህ ገብቶ አልዋጋም ለማለት ነው» ሲል ኮምብፌሬ አጉረመረመ::

ኮምብፌሬ ወገቡ ላይ ጨርቅ አስሮ ቁስለኞችን ያክማል፡፡ ሁለት
ጓደኞቹ ደግሞ ጋቭሮች ከሞቱት ሰዎች አጠገብ የለቃቀማቸውን ጥይት ያጎርሳሉ፡፡ ኩርፌይራክ ጠመንጃውና ሽጉጦቹ መጉረሳቸውንና ጐራዴው
በትክክል ቦታ መቀመጡን አረጋገጠ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁሉም በየፊናው ማድረግ ያለበትን ሲሰራ ዣን ቫልዣ ጥግ ይዞ ይመለከታቸዋል፡፡ ከዚያ ከነበሩ አንዳንድ ሰዎች የቡና ቤቱን ጠረጴዛ ኪሶች ሳብ ሲያደርጉ የደረቁና አንዳንዶቹም የሻገቱ ዳቦዎችን ያገኛሉ፡፡ ያንን ሲቆረጣጥሙ ማሪየስ የአባቱ መንፈስ ምን እንደሚለው ያሰላስላል፡፡

ኢንጆልራስ ወደ ዣቬር ዞር ብሎ «አንተን አልረሳሁህም፧ ከዚህች
ክፍል በሕይወት የሚወጣው የመጨረሻው ሰው ግምባርህን ብሎ ነው የሚወጣው» አለው ሽጉጡን ጠረጴዛ ላይ እያስቀመጠ፡፡

ዣን ቫልዣ ወደ ኢንጆልራስ ጠጋ አለ፡፡
«አንተ ነህ አዛዡ!»
«አዎን ነኝ:: »
«በሪፑብሊኩ ስም አንድ ነገር ልለምንህ::»
«ምንድነው የምትፈልገው?»
«የዚህን ሰው ጭንቅላት እኔ ላፍርሰው?»
ዣቬር ቀና ብሎ ሲመለከት ዣን ቫልዣን አየው:: የኢንጆልራስን
ዓይን እያየ «ይገባዋል» አለው::

ኢንጆልራስ «ግድ የለኝም» ካለ በኋላ ወደ ዣን ቫልዣ ዞር ብሎ
ስላዩን ከዚህ ዞር አድርግና በለው» ሲል ትእዛዙን ሰጠው::

ዣን ቫልዣ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ የነበረውን ሽጉጥ አነሳ:: በዚያች
ቅጽበት የመለከት ድምፅ ተሰማ፡፡

«ጥግ ያዙ» ሲል ማሪየስ ፎቅ ላይ ሆኖ ጮኸ፡፡

ዣቬር ብዙም ድምፅ ሳያሰማ ሳቀ፡፡ ከዚያ የነበሩትን እያየ «የእናንተም እድል ከእኔ ብዙም አይሻል» ሲል ተናገረ::

«ሁላችሁም ውጡ!» ሲል ኢንጆልራስ አዘዘ፡፡ሁለቱ ተፋላሚዎች ብቻቸውን ቀሩ፡፡ ሰላዩ ከግንድ ጋር የታሠረበትን
ገመድ ዣን ቫልዣ አላቀቀ፡፡ ዣቬር የፍጥኝ እንደታሰረ እየጎተተ ከክፍሉ ይዞት ወጣ፡፡ እግሩም ታስሮ ስለነበር ሰላዩ በአጭሩ ነው የሚራመደው፡ ዣን ቫልዣ ሽጉጡን ከኪሱ አወጣ፡፡ አድመኞቹ ከባድ ውጊያ ላይ ስለነበሩ ዣን ቫልዣና ሰላዩ ከክፍል ወጥተው ወደ ጓሮ ሲሄዱ ልብ አላልዋቸውም:: ማሪየስ ግን አይቶአቸዋል፡፡
በስርቆሽ በር በኩል ወጥተው ከመንገድ ደረሱ፡፡ የሞቱት ሰዎች አስከሬን ከመውጫው ላይ ተቆልሎ ስለነበር በችግር ነው ያለፉት:: የሰው ሬሣ እንደ
ድንጋይ ተቆልሎ ማየቱም በጣም አሰቃቂ ነበር፡፡....

💫ይቀጥላል💫
👍11
#ገረገራ


#ክፍል_ስድስት


#በታደለ_አያሌው

...ወደ መኪናዬ ሽምጥ እየሮጥሁ ሳለ ነበር፣ የንስሐ አባቴን እንኳን
እንዳልተሰናበትኋቸዉ ያወቅሁት፡፡ እንደ ልማዴ በጥድፊያ ወደ ሲራክ፯ አሽከረከርኩ። መቼም ከባልቻ የተደበቀ ነገር የለም፡፡ እሱን አግኝቼ እስከማማክረዉ ድረስ ትንፋሼን እንኳን ወደ ዉስጥ መሳብ አልሆነልኝም፡፡ ቸኩያለሁ። አይደርሱት የለም ደረስሁና ቢሮዉን በርግጄ ስገባ፣ ባልቻ በወንበሩ ላይ ለጠጥ ብሎ እንቅልፍ አሸልቦት አገኘሁት።
በተለይም የሲራክ ፯ ዋና ኃላፊ ከሆነ በኋላ የግል መኖሪያ ቤቱን አይቶት የሚያዉቅ አይመስለኝም። ዉሎዉም አዳሩም እዚሁ ሆኗል። እዚሁ ምግብ ያስመጣል፣ እዚሁ ወንበሩ ላይ ትንሽ ዕረፍት ያደርጋል። ከስንት አንድ ወደ ዉጪ ቢወጣ እንኳን ምክንያቱ ለዚሁ ለሲራክ ጉዳይ ብቻ
ነዉ፡፡

“ባልቻ!” ብዬ ስጮህበት፣ ብርግግ ብሎ ብድግ አለልኝ።
“ዉብርስት?” አለ ተጨናብሶ፣ እጁን ለሰላምታ እየዘረጋልኝ፡፡
“እሰይ! ‹ዉብርስት?” አልሁት፣ ልጃለሜ የሚለዉ ቁልምጫዉ
መቅረቱ ከንክኖኝ፡፡ እኔ ደግሞ ከእሱ ብቻ ሳይሆን ከማንም ቁልምጫ የለመድሁ ሰዉ ነኝ። ቁልምጫዉን ሳይቀር እንደገና በሚያቆላምጥ ቤተሰብ መሀል ነዉ ያደግሁት። ያዉም ዉብዬዋ፣ ‹ዉቤዋ፣ የኔ ዉብ፣ ዓለሜዋ፣ ‹ልጃለሜ› እየተባልሁ። ባልቻ እንዲሁ እንደ ወረደ በስሜ ጠርቶኝ ካለማወቁ የተነሳ፣ ስሜን ሁሉ የሚያዉቀዉ አይመስለኝም
ነበር። ትዝ ሲለኝ እኔ ራሴ ባልቻ ብዬ ነዉ የጠራሁት ለካ። «አባታለም» የሚለዉ ቁልምጫዬስ? የት ተዉሁት?

“ይኸዉ መጣሽ። በስንት ጊዜሽ? ስደዉል ሳታነሺ፣ ሳስጠራሽ ሳትመጪ፣ ስፈልግሽ ሳትገኘ፤ ዛሬ ምን አመጣሽ በይ?”

“እሸቴ ጠፍቷል”

“ጠፋ? ማን እፍ ብሎት ይሆን በናትሽ? ቀድሞስ በርቶ ኖሯል እንዴi” ሲል አላገጠብኝ፡፡

“ማላገጥህ ነዉ?”

“ራስሽ ከመሀል ጀመርሽዋ! እኔና አንቺ እኮ ገና እንደገና መተዋወቅ
አለብን። ቆይ የት አዉቅሻለሁ? አንቺ ታዉቂኛለሽ?”

“በማርያም አባታለም? ፈርቻለሁ። እሽቴ በመንግሥት ደኅንነቶች እጅ
ወድቆ እንዳይሆን ልቤ ሰግቷል”

“እና ምናገባኝ እኔን?”

“ኧረ ባዛኝቱ? እንዴት ነዉ የማያገባህ፤ እሽቴ እኮ ነዉ!”

"የሆነስ እንደሆነ!”

“አዉቃለሁ አሳዝኜሃለሁ። ለዚያም እንዴ ት ይቅርታ መጠየቅ እንዳለብኝ አላዉቅም። ቢሆንም ግን በዚህ መሀል እሸቴ በጨካኞች እጅ ወድቆ
ከሆነ አያሳዝንህም?”

“ያሳዝነኛል”

“እኮ አንድ ነገር አድርጋ”

“ምን ላድርግ?”

“የማታስፈልገዉ?”

“እሺ። አስፈልጌ ሳገኘዉስ?”

“ያንተን አላዉቅም። እኔ ግን ተንበርክኬ ይቅርታ እለምነዋለሁ”

“ለምን?”

“ስለሚገባዉ”

“እሺ። መጀመሪያ ግን እንስማማ”

“ንገረኝ በምን?”

“ተንበርክከሽ የምትጠብቀዉ ከሆነና፣ ተሳክቶልኝ ካገኘሁት ደግሞ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ቃል ከገባሽልኝ.…”

“ይኼዉ!” ብዬ ጉልበቴ ግዉ እስከሚል ድረስ ወድቄ ተንበረከክሁ፡፡
“ብቻ አንተ እሺ በለኝ። እገባለሁ። እሄዳለሁ፤ አሁኑኑ ፈልግልኝ!”

“ዉዉዉ-ዉቤ?” የሚል ድምፅ ከኋላዬ ሰማሁ። ማን በተብታባ ድምፁ እንደ ጠራኝ ለማጣራት ዞሬ ማየት ያስፈልገኝ ኖሯል? ኧረ በጭራሽ በጠረኑ ብቻ አዉቀዋለሁ፡፡ እሸቴ ነዉ፡፡ ወይ ባልቻ! ምን ዓይነት ልብ
ነዉ የታደለዉ ግን? መቼም ጨክኖ ማኩረፉን አያውቅበት! ሆነ ብሎ ኖሯል ለካ እሸቴን ከሁላችንም እይታ እንዲጠፋ ያደረገዉ፡፡ እኔ እንደሆነ
እንዳልሞተ ሰዉ የማራክስዉ ነገር የለኝም፡፡ ጊዜ እንኳን ዉድ
የሚሆንብኝ ካለፈ በኋላ ዞሬ ሳየዉ ብቻ ነዉ። እቃም ቢሆን ከእጅ አምልጦ ካልተሰበረ ወይ ደግሞ ካልተሰረቀ በቀር ዉድነቱ አይታወቀኝም።እሸቴንም ባላጣዉ ኖሮ አልፈልገዉም ነበር። ለዚህ ይመስለኛል ባልቻም
እሸቴን ከዓይኔ እንዲጠፋ ያደረገብኝ። የእሽቴን ዉድነት እንዳምን፣ ከዓይኔ ሠወረብኝ፡፡ እንኳንም ሠወረብኝ፣ እንኳንም ናፈቅሁት፣ እንኳንም
አገኘሁት። ተሳክቶለታል።

ባልቻን በስስትም በኩራትም እያየሁት ሳለ፣ እሸቴ ከፊት ለፊቴ መጥቶ እንደኔዉ በጉልበቱ ወደቀ። ጥዉልግ ብሏል። ከንፈሩ ሳይቀር ኩችር ብሎ ደርቆ ታየኝ፡፡

“እሽቴ?”

“ጨጨጨ ጨከንሽብኝ እኮ
ዉቤ”

“ኹለተኛ አላደርገዉም”

“አአአ አአ አለሽልኝ ግን?”

“አለሁልህ። አለህልኝ?”

የባልቻን መኖር ሁሉ ረስተን፣ አንገት ለአንገት ተቆላልፈን ቆየን፡፡
እንደዚሁ እንዳለን፣ ልክ እሸቴን እንዳገኘልኝ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ የገባሁት ቃል ትዝ አለኝ። እስከሚነጋ ቸኮልሁ።

ከአምስት ወር በላይ በሆዴ ፅንስ ይዤ፣ ያዉም እኔ ራሴ የሕክምና
ባለሙያ ሆኜ ፤ እስከ አሁን ግን የሕክምና ክትትል አለመጀመሬ ለግድ የለሽነቱ ወደር የማይገኝልኝ ሴት መሆኔን መስክሮብኛል፡፡ ይኼንን ማንም ሳይነግረኝ አዉቄዋለሁ። ሲሆን ሲሆን እርግዝና ከመፈጠሩ ከዓመት ወይ
ከወራት ቀደም ሲል ጀምሬ ዝግጅት ማድረግ ነበረብኝ፡፡ እንደኔ እንኳን እርግዝናዉ በድንገት ለተፈጠረበትም ቢሆን፣ ከመጀመሪያዉ ጀምሮ
ሙሉ ምርመራ እና ክትትል ማድረግ የግድ ነዉ። እኔ ግን ቢያንስ ቅሪት መሆኔን ያወቅሁት ቶሎ ቢሆንም፣ ይኼዉ 22ኛ ሳምንቴን ጭልጥ አድርጌ ነዉ ገና ነገርዮዉን እንኳን በበጎነቱ የተቀበልሁት።

ዛሬ ነዉ ወደ ሆስፒታል ለመምጣት የወሰንሁት። ዛሬ ገና።

ዛሬ ግን ቆርጬ መጥቻለሁ።

በእናቶች እና ሕጻናት ሕክምና ዝነኛ ወደ ሆነዉ ሐሚያሉ ሆስፒታል ገብቼ ካርድ አወጣሁና ወደ ተጠቆምሁት የዶክተር ክፍል አመራሁ። ብዙም ሳልቆይ ወረፋዬ ደረሰኝና፣ መለስ ያለዉን በር ገፍቼ ወደ ዉስጥ ገባሁ። ሆስፒታሉን በበጎ ስሙ መረጥሁት እንጂ፣ የተለየ የሐኪም ምርጫ አላደረግሁም ነበር። ሆኖም ከዉስጥ የጠበቀችኝን ሐኪም ካየሁ በኋላ፤ ሕይወት የአጋጣሚዎች ጋን መሆኗን አመንሁ።

ሐኪሟ ስንቱን አብራኝ ያሳለፈች፣ የቀድሞ ጓደኛዬ ሆና እርፍ!

“ሸዊት!” አልኋት፣ ለረዥም ደቂቃ እጄን አፌ ላይ ጭኜ ስደነቅ ከቆየሁ በኋላ።

"የፈጣሪ ያለህ! ዉብዬ ?” አለች እሷም፣ አሁንም አሁንም ዓይኖቿን
ጨፍና እየገለጠቻቸዉ። ከመልኬ እኩል በሆዴ ያለዉን አስተዉላለች፡፡ ከነጭራሹ የምንገናኝ፣ ያዉም እንዲህ ሆኜ፣ አልጠበቀችኝም ነበር። ለነገሩማ እኔስ እንዴት ብዬ እጠብቃለሁ? በጎንደር ዩኒቨርስቲ የሕክምና
ዶክትሬት ዲግሪያችንን አብረን በተማርንበት ወቅት የነበረንን ጓደኝነት አይቶ ትንሽ ትልቁ እንደዚያ ከዓይን ያዉጣችሁ እንዳላለን ሁሉ፣ እንደዚህ በአንድ ከተማ መኖራችንን እንኳን እስካለመተዋወቅ ድረስ
መራራቃችን ዋዛ ነዉ፡፡ ምን ሆነን ነዉ ግን? ምንም፡፡ ለነገሩ ዩኒቨርስቲ ካስተዋወቀኝ ወዳጆቼ ማንን አግኝቼ አዉቃለሁ? ከስንት አንድ በአጋጣሚ ካልሆነ በቀር፣ አብዛኞቹ የት እንዳሉ እንኳን አላዉቅም፡፡

“ዋዉ!” አለችኝ፣ እንደ ታቦት እየዞረችኝ፡፡

“እሩ እስኪ ሰላም በዪኝ መጀመሪያ”

“እንኳን ለዚህ አበቃሽ ዉብዬ” ብላ መጥታ አንገቴ ሥር ሰረገች፡፡
እንደገና ሆድ ሆዴን ትኩር ብላ አየችኝና፣ ጭምጭም አድርጋ ሳመችኝ፡፡የምር ደስ ብሏታል። እንባዋ ሳይቀር ጠይም ጉንጮቿን እያራሰ በብርቅዬ አንገቷ በኩል ፈሰሰ።

ሀገር ዉስጥ ነዉ የምትኖሪዉ? ጭራሽ እዚሁ አዲስ አበባ?” አልኋት፣

ደስታዋ እንዲጋባብኝ ልቤን እየደቃሁት።

“አይ፤ ቅርብ ጊዜ ነዉ የመጣሁት። ጀርመን ነበርሁ፣ ትምህርት ላይ”

“ተዪ እንጂ? ጀርመን፤ ምን ስፔሻላይዝ አደረግሽ ታዲያ?”

“ይኸዉ እያየሽኝ? ለእር ግዝና ክትትል አይደል እንዴ እኔ ጋ
የመጣሽዉ?”

“አይ አጅሪት! እንዲያ ነዉ እንጂ የኔ እህት! ደግሞ ጥሩ ምርጫ ነዉ”

“አንቺስ ምን አጠናሽ?”
👍481
“አይ እኔን እንኳን ተዪኝ። እዚያዉ እንዳስቀመጥሽኝ ነኝ። ሰዉ ሁሉ
እንዳንቺ ቁም ነገረኛ መስሎሻል ኣ?”

“ኧረ ሾርኔ! ... ከትዳር እና ከልጅ የሚበልጥ ቁም ነገር አለና ነዉ? ቁም ነገረኛስ አንቺ!” አለችኝ፣ ሆዴን እንደገና እያየች፡፡

ትዳር የሚለዉን ቃል ስሰማ ድንገት ሆዴን ወጋኝ፡፡ እንደገና ወደ ኋላ ተመልሼ ወደዚያ የድባቴ ስሜት እንዳልዘፈቅ ፈራሁ፡፡

“ሰዉዬሽን አዉቀዋለሁ? ከዚያ ከጥብርያዶስ ጋር ተጋባሁ እንዳትዪኝ ብቻ! ግቢ እያለን እኮ የብቻ ለብቻ መንገድ ኣብዝታችሁ ነበር። እሱን ነዉ ያገባሽዉ?”

“ጥብርያዶስ? ጭራሽ እኔና እሱን በሌላ ትጠረጥሪን ኖሯል እንዴ?”

“እንክት!”

“እንደዚያ የሚያደርግ እንደዚያ ያወራል የሚለዉን አስታወስሽኝ። ካነሳሽዉማ፣ ባንቺ አይብስም ነበር?”

“እርፍ! ወዴት ወዴት?”

“ምነዉ አንቺ ዉሸታም! ነግሬሽ አላውቅምና ነዉ?”

“አረ ዉቤ ተዩ። እሺ አሁን የት እንዳለ ታዉቂያለሽ? በእናትሽ ንገሪኝ”

ከፊቷ የቆመ ይመስል ጥምልል ብላ ተሽኮረመመች። ምስኪን! ፍርስ ብዬ ሳቅሁባት፡፡ ቀድሞዉንም ከእሱ ጋር እንቀላለድ ስለነበር ልታዉጣጣኝ
ስሙን አነሳችብኝ እንጂ፣ ከእሷ በላይ ጥብርያዶስን በሌላ የሚመኝ ኖሮ አይመስለኝም። በእርግጥ እንዳለችዉም ከእሷ ባልተናነሰ ከጥብርያዶስም
ጋር ጥሩ ቀረቤታ ነበረን። ነገር ግን በስሕተት እንኳን እሷ በምትለዉ
ዓይን አይቼዉ አላዉቅም፡፡ ሲጀመር ካልመነኮስሁ ብዬ ገጭ እጓ የምልበት ጊዜ አልነበረ? በዚያን ጊዜ ልቤ ላይ እንዲህ ያለ ምኞት ደርሶብኝ መቼ ያዉቅና! እሷ ግን ትወደዉ ነበር፡፡ በዚያም ላይ ባል ያስፈልገኛል ብላ ያመነችበት ዕድሜዋ ላይ የደረሰች ትመስላለች፡፡ ብዙ ዶክተሮች ሥራና ትምህርታቸዉን ብቻ እያዩ ዕድሜያቸዉን ይፈጁና፣ ያመለጣቸዉ የሕይወት ምዕራፍ እንዳለ ሲያስተዉሱ ይዋከባሉ ተብለዉ ይታማሉ። ትምህርቱ በራሱ ረዥም በመሆኑ፣ ሐሜቱ ዉሸት ነዉ ማለት ከይቻልም፡፡ ምናልባት ጓደኛዬም የጎደላት ያለ መስሎ ይሰማት ይሆን?
ልጠይቃት ስል፣ ሆነ ብላ ወሬ ለወጠችብኝ፡፡

እንግዲያዉ ሰዉዬሽ ማነዉ፤ አዉቀዋለሁ?”.....

“አይ”

“እኮ ንገሪኛ ልወቀዉ”

"እሸቴ ይባላል”

“እሽቴ?”

“አዎ””

“መቼም መልካም ሰዉ መሆን አለበት። ደሞ ጥንታዊት፣ ታሪካዊት ...ሃሃሃ ... ጓደኛዬን ለዚህ ቁም ነገር ያበቃትን ሰዉማ መተዋወቅ ይኖርብኛል። እንኳንም አንዴ አጋጣሚዉ መልሶ አገናኘን እንጂ፣ በዐሥር ዓይነት ቅመም ያበደ ሻይም ቢሆን አፍልቼ እቤቴ እጠራችኋለሁ”

“እሺ” አልኋት፣ ጓደኝነታችን እንዲቀጥል እኔም ከልብ እየፈለግሁ።ፈገግ ብላ አየችኝ። ፈገግታዋ እየጎላ፣ ደስታዋ እያየለ መሆኑን አስተዉያለሁ። ድሮዉንም ልበ ቀና ናት። ለስንተኛ ጊዜ እንደሆነ እንጃ፣ ሆዴን እንደገና በስስት አየችዉ። ሳመችዉ። ጨመጨመችዉ።

“በይ እስኪ ንገሪኝ፤ ምን ያህል ጊዜ ሆነዉ?”

“ሃያ ሶስት ሳምንት ይመስለኛል”

“አዉቀሽ!” አለችኝ፣ ለመሳቅ ጥርሶቿን በብርሃን እየለኮሰች።
ይመስለኛል ማለቴ ሳይሆን አይቀርም ለሳቅ ኩሎ የዳራት።

“በናትሽ እንዳትስቂብኝ። ገና ክትትል ልጀመር ነዉ አመጣጤ።
አዉቃለሁ፣ እጅግ አርፍጃለሁ። ምክንያቴን ብቻ ጠይቂኝ። ያን ያልሽኝን ባለቅመም ሻይ የምትጋብዥኝ ከሆነ አጫዉትሻለሁ ጉዴን”

ጨክና እንዳትስቅብኝም፣ እንዳትቆጣኝም ሆነች። በዚሁ ስሜቷ ፍጥጥ ብላብኝ ቆየችና የሚያስፈልጉ ምርመራዎችን ሁሉ ከዜሮ ጀምራ ዘርዝራ ጻፈችልኝ፡፡ ያኮረፈችኝም መሰለኝ፡፡ በአንዴ ከጓደኝነት ወርዳ፣
ከማንኛዉም ታካሚ በታች ፈጠፈጠችኝ፡፡

“በይ ሌላ ሌላዉን ጨርቪና ነይ። ባይሆን ወደ አልትራሳዉንድ ክፍል
አብሬሽ ልገባ እችላለሁ። እስከዚያዉ ሌሎች ታካሚዎች ካሉ እያስተናገድሁ ልጠብቅሽ። ይሻላል ኣ?”

እሺ። ከገዛ ጓደኛ እጅ ሕክምና ማግኘት እንደምን ያለ መታደል እንደሆነ ባየሽልኝ!”

“በይ እሺ፡፡ በይ ደርሰሽ ነይ”....

ይቀጥላል
👍341
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

....የሞቱት ሰዎች አስከሬን
ከመውጫው ላይ ተቆልሎ ስለነበር በችግር ነው ያለፉት:: የሰው ሬሣ እንደ ድንጋይ ተቆልሎ ማየቱም በጣም አሰቃቂ ነበር፡፡
ቁና ዣቬር በረጋ መንፈስ «ይህችን ልጅ አውቃት ነበር» ሲል ድምፁን ዝቅ አድርጎ የኢፖኒን የተገላለጠ ጡትና ገላ እያየ ይናገራል፡፡ ከዚያም ወደ
ዣን ቫልዣ ዞር አለ፡፡"

ዣን ቫልዣ ቃል ሳይናገር ዝም ብሎ በማፍጠጥ አየው:: ደግሞ
መናገርም አያስፈልግም ነበር፡፡ አስተያየቱ ብቻ ዣቬር እኔው ነኝ!» ለማለቱ ግልጽ ነበር፡፡

ዣቬር ንግግሩን ቀጠለ፡፡

«አሁን ልትበቀለኝ ትችላለህ::»
ዣን ቫልዣ ሽጉጡን ከኪሱ ከከተተ በኋላ ሰንጢውን አወጣ፡፡ ሰንጢውን ዘረጋው፡፡

«ወይ ጉድ!» አለ ዣቬር፡፡ «ልክ ነህ፣ እሱ ይሻልሃል»

«ፊትህን አዙር» ሲል ዣቬርን አዘዘው:: ዣቬርም ፊቱን ወደ
ግድግዳው አዞረ:: ከዚያም ዣን ቫልዣ ጠላቱ የፍጥኝ የታሠረበትን ገመድ ይቆርጥ ጀመር፡፡ እጁንና እግሩን አላቀቀለት:: እግሮቹ የታሠሩባቸውን ገመድ ቆርጦ እንደጨረሰ እዚያው ከመሬት ሆኖ ዣቬርን ቀና ብሎ አያየ

«መሄድ ትችላለህ» አለው::

ዣቬር ግራ ተጋብቶ አፉን እንደከፈተ ቀረ:: ዣን ቫልዣ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

«እኔ ግን ከዚሁ ማለት ከምሽጉ ውስጥ እቆያለሁ፡፡ ምናልባት በአጋጣሚ በሕይወት ከወጣሁ አድራሻዬን ልስጥህ» ብሎ የቤቱን አድራሻ ሰጠው።ዣቬር በመገረም እያየውና ከንፈሩን በግድ አላቅቆ «ራስህን ጠብቅ» ሲል መከረው::

«ለማንኛውም ሂድ ብያለሁ፤ ቶሎ ብለህ ከዚህ ጥፋ» ሲል ዣን
ቫልዣ በተራው መከረው::

ዣቬር አድራሻውን ለማረጋገጥ «ሆም አርሚ ጐዳና የቤት ቁጥር
ሰባት ነው ያልከኝ?» ሲል ጠየቀው::

«በደምብ ይዘኸዋል» ሲል ዣን ቫልዣ መለሰለት::

ዣቬር ልብሱን አስተካክሎና በአንድ እጁ ጉንጩን ይዞ መንገዱን ቀጠለ፡፡ ዣን ቫልዣ ከዚያው እንደቆመ በዓይኑ ተከተለው:: ዣቬር ጥቂት
ከተጓዘ በኋላ ወደ ኋላ መለስ ብሎ «አናደድከኝ፣ ለምን አልገደልከኝም ነበር»ሲል ተናገረው:: «ሂድ ብያለሁ፤ ሂድ» ሲል ዣን ቫልዣ መለሰለት።

ዣቬር በዝግታ እየተራመደ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ኩርባ ላይ ሲደርስ ወደ ግራ ታጠፈ::ዣቬር ከዓይኑ ሲሰወር ዣን ቫልዣ ሁለት ጊዜ ወደ ሰማይ ተኩሰ፡፡ ከዚያም ወደ ምሽጉ ተመልሶ «እርምጃው ተወስዷል» ሲል ሪፖርቱን አቀረበ።

«አጥቃ» የሚለው የከበሮ ምልክት እንደገና በኃይል ተመታ፡፡ ማጥቃቱ እርምጃ ከማዕበል የከፋ ነበር፡፡ እግረኛው ጦር ጠመንጃን ወድሮ በቀጥታ ወደ ምሽጉ ገሠገሠ፡፡ መለከቱና ከበሮው ተንጣጣ፡፡ የእግረኛው እርምጃ መሬቱን አነቃነቀው::

ከምሽጉ ውስጥ በሕይወት የቀሩት አድመኞች ጠመንጃቸውን
አንጣጡት:: ኢንጆልራስ በአንድ ፊት ማሪየስ በሌላ በኩል አጋሮቻቸውን ለማነቃቃት ይጮሃሉ፡፡ ጦሩ እየቀረባቸው መጣ፡፡ ከአጠገባቸው የደረሰው
እየተንገዳገደ ከእግራቸው ስር ይወድቃል:: ኃይለኛ የመከላከያ ምሽግን ተገን አድርጎ በቀዳዳ የሚዋጋን ጦር ቶሎ ለመጣል ያዳግታል። ሆኖም ! የነበረው
ምንም እንኳን የምሽጉ አቀማመጥ ቢረዳቸውም በመጨረሻ ለመቋቋም አልቻሉም።

እህል ከቀመሱና የእንቅልፍ ዓይን ካዩ ሃያ አራት ሰዓታት ኣልፈዋል።
ቁጥራቸው አንድ ስልሣ ይሆናል:: የነበራቸው ጥይት እየተሟጠጠ ነው።ከመካከላቸው ያልቆሰለ ቢኖር በጣም ጥቂት ነው፡፡ የመንግሥት ጦር ከምሽጉ ለመግባት አሥር ጊዜ ያህል ሞክሮአል፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉ ደረት
ለደረት በጠብመንጃና በጎራዴ በመከላከል በሙሉ ልብ ተዋጉ፡፡ በዚህ ውጊያ እነኩርፌይራክ፣ ቦሌይና ሌሎችም ሲሞቱ ኮምብፌሬ በሳንጃ ደረቱ ላይ
ከሦስት ቦታ ተወግቷል፡፡ እሱም ቢሆን ከተወጋ በኋላ ብዙ አልቆየም፧ ሕይወቱ አለፈች፡፡ ማሪየስ እስከመጨረሻው ቢዋጋም ቆስሉ ስለነበር እየደከመ
ሄደ፡፡ ኢንጆልራስ ብቻ ነበር ያልተነካው::

በየአቅጣጫው ጥግ ይዞ ይዋጋ የነበረው ሰው ቀስ በቀስ አንዱ
ከሌላው ቀጥሎ ስለተመታና ስለወደቀ ወደ ምሽጉ የሚያስገባ ቀዳዳ እየሰፋ ሄደ፡፡ የመንግሥት ጦርም ከምሽጉ መሃል ለመግባት ቻለ፡፡ ሰው ሲያልቅ የምሽጉ የውጭ ግምብም በመሣሪያ ኃይል ተናደ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር በሕይወት የቆዩት እጅግ ጥቂት አድመኞች የመጨረሻውን መንፈራገጥ ያሳዩት።በዚህች የመጨረሻ ደቂቃ ነው የሰው ልጅ የመኖር ፍላጎቱ የሚያይልበትና
የእንስሳ ባሕርዩ የሚጎላው:: ያቺን ሰዓት ለማለፍ የማያስበው ዘዴና
የማያልመው መላ አይኖርም፡፡ ወደ ፎቅ የሚሮጠውን የተዘጋ በር ለመክፈት የሚታገለው፤ ተከፍቶ የነበረውን በር ላመቀርቀር የሚሽቀዳደመው ሲታይ
በጣም አሳዛኝ ትርዒት ነበር::
በዚያች ቀውጢ ሰዓት በድንጋጤ መንፈሱ ተረብሾ ወደ ስርቆቱ በር
የሚወስደውን መንገድ በጉልህ ያስታወሰ ኢንጆልራስ ብቻ ነበር፡፡ በአንድ እጁ ጠመንጃውን በሌላው ጎራዴ ይዞ ከፊት ለፊት የሚመጣውን ጦር እየተከላከለ በሕይወት የቀሩትን ሰዎች ወደ ውስጥ እንዳስገባ ወታደሮች
ደርሰው የብረቱን በር ለመግፋት ይታገላሉ:: አድመኞቹ ከውስጥ ወታደሮች ከውጭ ሆነው በሩን ሲገፉ አንድ ወታደር ጣቱ በበሩ በመቀርጠፉ ይጮሃል፡፡
ማሪየስ በመመታቱ በበሩ አላለፈም:: እንዲያውም ከነአካቴው ሕሊናውን ስቶ ይወድቃል፡፡ ልክ ሲወድቅ አንድ ሰው መጥቶ ሲይዘው
ይታወቀው እንጂ ከዚያ በኋላ የሆነውን አያውቅም:: ከዚያ ጥቂት ቀደም ብሎ እንደ ተመታ ኮዜት ትዝ ብላው «ስለቆሰልኩ እማረካለሁ፤ ከዚያም
በጥይት ተደብድቤ እሞታለሁ» ሲል ያስባል፡፡ ልክ ኮዜት አጠገቡ እንዳለች ቆጥሮ ነበር ታሪኩን የሚነግራት::

እነ ኢንጂልራስ ከውስጥ ወታደሮች ከውጭ ሆነው ከአንደኛ ፎቅ ላይ የነበረውን ክፍል በር በጥይት አጋዩት:: በዚያች ሰዓት የነበረው ጩኸት ! የነበረው ዋይታና የስቃይ እንጉርጉር በቃላት ለመግለጽ እጅግ በጣም
ስለሚያዳግት እንዲያው ዝም ይሻላል፡፡

በመጨረሻ በሩ ተበርግዶ ሲከፈት በሕይወት የቆየው ኢንጂልራስ
ብቻ ነበር፡፡ ኢንጆልራስ ጥይት አልቀበት ሰውነቱ በደም ተበክሎና ልብሱ ተቦጫጭቆ ጥግ ይዞ ቆሞአል፡፡ ጠመንጃውን ግን በእጁ እንደያዘ ነው።አንድ ሰው ገና ሲያየው በኃይል እየጮኸ ይናገራል::

«መሪው እሱ ነው፡፡ ያንን መልከ መልካም ወጣት የገደለ እርሱ
ነው:: እዚህቹ ከቆመበት በሉት::»

«ግደሉኝ» አለ ኢንጆልራስ ረጋ ብሎ ደረቱን እየገለበጠ፡፡

አሥራ ሁለት ወታደሮች ኢንጆልራስ ላይ ለመተኰስ ጥግ ይዘው
ጠመንጃቸውን አቀኑ።

የሃምሣ አለቃ «ለመተኩስ ተዘጋጁ» ሲል ትእዛዝ ሰጠ::

የሃምሳ አለቃው ጩኸት ግራናትዬን ከእንቅልፉ ቀሰቀሰው:: ግራናትዬ ከሰካራሞቹ አንዱ ነው:: ከመጠጥ ቤቱ ተኝቶ እንቅልፍ የወሰደው ከአንድ ቀን በፊት ነበር::

እንደሚታወቀው ሰካራም አንዴ እንቅልፍ ከወሰደው እንቅልፉን
ካልጨረሰ በቀር ምንም ዓይነት ድምፅ አይቀሰቅሰውም፡፡ ከእንቅልፉ እንደነቃ በእንቅልፍ ልቡ «ሪፑብሊኩ ለዘላለም ይኑር፤ እኔም የዚያው አባል ነኝ
በማለት ጮክ ብሉ ሲናገር ወታደሮቹ ደንግጠው ወደ ግራናትዬ ፊታቸውን
አዞሩ፡፡

ሰካራሙ ከተኛበት ብድግ ይላል:: ሁለም አፍጥጦ ያየዋል፡፡
የሚያናግረው ግን የለም::
«ሪፑብሊኩ ለዘላለም ይኑር» ይላል በድጋሚ፡፡ በቀጥታ ወደ ኢንጆልራስ ሄዶ ከአጠገቡ ቆመ::

«በአንድ ጥይት ሁለት ሰው» ይላል:: ከዚያም ወደ ኢንጆልራስ ዞር ብሎ ረጋ ባለ መንፈስ «አብሬህ ብሞት ትፈቅድልኛህ?» ሲል ጠየቀው።
👍182
ኢንጀልራስ ፈገግታ እያሳየ እጁን ይይዘዋል፡፡ ሆኖም ፈገግታውን
ሳይገታ ኢንጆልራስ በስምንት ጥይት ተመትቶ ጥይቱ ከግድግዳው ጋር
ያጣበቀው ይመስል ቆሞ ቀረ:: አንገቱን ግን ደፍቶአል:: በትከሻው ግድግዳውን ተደግፎ ነው የቆመው:: ግራናትዬ ግን ጥምልምል ብሎ ከመሬት ወደቀ።
ከዚያም ወታደሮቹ ቤቱን መፈተሽ ጀመሩ፡፡ ጣራ ላይ አንድ ወታደርና
አንድ ተቃዋሚ አንገት ለአንገት ተያይዘው ሲተናነቁ ሁለቱም ተያይዘው በመውደቃቸው ሕይወታቸው አለፈ:: አንዱ የሴት ቀሚስ ለብሶ በሕይወት
ስለተገኘ ሆዱን በሳንጃ ተርትረው ገደሉት:: ከዚያ በኋላ ምሽጉ ሙሉ
በሙሉ በመንግሥት ወታደሮች ቁጥጥር ስር ሆነ፡፡

ማሪየስ እውነትም ከተመታ በኋላ እንዳለው እስረኛ ሆኖ ቀረ፡፡
ያሠረው ግን ዣን ቫልዣ ነበር፡፡ ከተመታ በኋላ ነፍሱን ስቶ ሲወድቅ ከኋላ መጥቶ የያዘው የዣን ቫልዣ እጅ ነበር::ዣን ቫልዣ ማሪየስን ፍለጋ የመጣው ውጊያው እየተፋፋመ ሲሄድ
አልነበረም፡፡ እውነታው ከዚያው ማሪየስ አጠገብ ሆኖ በውጊያው ሳይሳተፍ ማሪየስን በዓይነ ቁራኛ ሲጠብቅ ነው የቆየው:: ልክ ማርየስ ሲመታ ነብር ፍየልን ከመቅጽበት ከመቼው ደርሶ አፈፍ እንደሚያደርገው ሁሉ ዣን
ቫልዣም ማሪየስ ወድቆ መሬት ሳይከስከስ ዘልሎ በፍጥነት ያዘው:: ከዚያም ተሸክሞት ሄደ::

ልክ ጦርነቱ ተፋፍሞ ወታደሮቹና እነኢንጆልራስ በር ለመዝጋትና
ለመክፈት ሲታገሉ ዣን ቫልዣ ማንም ልብ ሳይለው ማሪየስን ተሸክሞ ይወጣል፡፡ ማሪየስ በዚህን ጊዜ ሕሊናውን ስቶ ስለነበር ነፍሱን አያውቅም::
ዣን ቫልዣ ማሪየስን እንደተሸከመ ከዚያው አካባቢ ወደ አንድ ሰወር ወዳለ ሥፍራ ስለደረሰ ማሪየስን ከመሬት አስቀመጠው: አካባቢውን ቃኘ:: ማምለጫ ቀዳዳ የለውም፡: በጓሮ በኩል የሚያስወጣውን የስርቆሽ በር
እንዳለ ግን ያውቃል፡፡ በዚያች ሾልኮ እንዳይሄድ በዚያች ሰዓት ወታደሮች ምሽጉን ጥሰው ገብተው ከቤቱ ጣራ ላይ ስለወጡ ያዩታል:: እጅግ በጣም አስጨናቂ ቅጽበት ነበር፡፡

በጓሮ በኩል ብቅ ብሉ ቢታይ ሞት እንደሚጠብቀው ያውቃል::
እንዳይመለስ ከበስተኋላው ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው:: ታዲያ የት
ይሂድ? ወፍ አይደል አይበር! መሬቱ ተከፍቶ «ና ከዚህ ተደበቅ» ይለው ይመስል መሬቱን ዝም ብሎ ተመለከተው:: የሰው ዓይን በማየት ብዛት ቀዳዳ የማውጣት ችሎታ ቢኖረው ሁለት ቦታ በሰነጠቀው::

ከቆመበት ጥቂት እርምጃዎች ራቅ ብሉ ከግምብ አጥር ስር ብረት ነገር አለ፡፡ ክብ ነገር ነው:: ዓይኑ እዚያ ላይ ተሰባስቦ ቀረ:: ሰፋ ያለ ነገር ሲሆን የመሬቱን ወለል ነው የያዘው:: ጥቂት ወደፊት ተራምዶ ብረቱን አየው:: የቆሻሻ መውረጃ ትልቅ ቱቦ ክዳን ነበር፡፡ አሳብ ብልጭ አለለት::
ያንን የብረት ክዳን ከፍቶና እንደ ሬሣ የሚከብደውን ማሪየስን ተሸክሞ ከዚያ ውስጥ መግባት::

ያንን የብረት ክዳን ማንሳት ቀላል ባይሆንም ቀደም ብለን እንደገለጽነው ዣን ቫልዣ ጉልበተኛ በመሆኑ አነሳው:: ማሪየስን ተሸክሞ ከዚያ የቆሻሻ
መውረጃ ቱቦ ውስጥ ከገባ ሰኋላ ማሪየስን እንደ ግድግዳ ካለ ነገር ላይ አጋደመው:: እርሱ ተመልሶ ሄዶ በመንጠላጠል ያንን ክብ የብረት መዝጊያ ከውስጥ ሆኖ ከቦታው መለሰው:: ያም ብዙ ልፋት ነበረበት፧ ዝርዝር
ውስጥ አንገባም:: እዚህ ላይ የቱቦውን ሁኔታ መግለጽ ያስፈልጋል፡፡ እኛ የቆሻሻ
መውረጃ ሲባል የሚታየን አንድ ከሲሚንቶ የተሠራ ሰፊ ክብ ነገር ነው:: የፓሪስ ከተማ የቆሻሻ መውረጃ ቱቦ ግን ከዚህ የተለየ ነው:: የፓሪስ ከተማ የቆሻሻ መውረጃ ቱቦ የመሬት ውስጥ ግምብ ነው:: መሬቱ በጥልቀት
ከተቆፈረ በኋላ በድንጋይ ንጣፍ ይለጠፍና ከግራ ተቀኝ ይገነባል፡፡ ከዚያም ሁለቱን ግምብ በማገናኘት ተደፍኖ ከላዩ ላይ መንገድ ይሠራበታል፡፡ ከላዩ
ላይ አጥር ወይም ቤት የተሠራበትም አይጠፋም::
ዣን ቫልዣ የገባው ከዚህ ውስጥ ነው:: ከዚያ ውስጥ ለመግባት
ደግሞ ዘልለው የሚወርዱበት ሳይሆን ከግምቡ ጋር ተጣብቆ የተሠራ የብረት መሰላል ስላለ በዚያ ነው የሚወረደው:: ይህም ማለት ሰው ከዚያ ከገባ የሚሄደው በደረቱ ተንፏቆ ሳይሆን ቆሞ ነው:: ነገር ግን የሚራመደው
በውሃ ከላቆጠ ዓይነ ምድርና ሽንት ላይ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ጥልቀቱ.
ከወገብ በላይ ሊደርስ ይችላል፡፡ እንኳን ሊሄዱበት ሲገልጹትም ይሸታል::

የሚሄደው ውሃ ድምፅ አይሰማም፡፡ ድርግም ያለ ጨለማ ነው:: ዣን ቫልዣ ከወታደሮች ለማምለጥ በግምብ ተንጠላጥሎና ኮዜትን ተሸክሞ
ከገዳም ውስጥ የገባበትን ጊዜ አስታወሰ፡፡ ልዩነቱ አሁን የተሸከመው ኮዜትን ሳይሆን የኮዜትን ፍቅረኛ ነው:: ያን ጊዜ ከመሬት በላይ ሲሆን
አሁን ከመሬት በታች ነው:: ውጊያው ከተካሄደበት ቡና ቤት የነበረው ትርምስ በጭላንጭል እንጂ በውል አይሰማውም::....

💫ይቀጥላል💫
👍202
#እንዴት?

የአለሜን ስፋት
የህልሜን ፍቺ ወሰን
የብርሀኔን ልክ
አንቺን በልቤ የዤ፤
ከጎጆዬ
ከሰማዬ . . .ጣራ፣
የብቸኝነት
ግት
በበረዶ እንገሩ ያቀዘቅዘኛል?
ለእምነቱ የቀረበ
ለእውነቱ የቆረበ
ሞጋች
ወትዋች . . . ልቤ
ስለ ፍቅርሽ ሲሆን፣ እሽሩሩ ይለኛል?

የትኛው ነው እውነት?
የትኛው ነው እምነት?
ከባዶው ሶፋ ላይ ያንቀላፋች ድመት!
የቀረበው ስኒ፣ ቡና ያልተቀዳበት!
የካፌው በረንዳ፣ አንቺ የሌለሽበት!
የማለዳው ጸሀይ፣ አንቺ ያልደመቅሽበት!
. . . . . . . ............የማየው የሚያየኝ?
ወይስ . . .
ትዝታሽ
ጠረንሽ
የሽንቁሬ ውታፍ፣ አሳጥሮ ያሰረኝ?
.........................አትዋጋ ሚለኝ?

ዳሩ በዚህ ቅዠት፣
ዳሩ በዚህ መንፈስ፣
ጨርቁን በጣለ አለም፤
ቋሚ ስፍር የለም
ገፍፈው የሚጥሉት፣
ስልባቦት ነው እምነት፤
ብጣሪ ነው እውነት፡፡

🔘በድሉ ዋቅጅራ)🔘
👍121
#ገረገራ


#ክፍል_ሰባት


#በታደለ_አያሌው


...“በይ እሺ፡፡ በይ ደርሰሽ ነይ”

የምርመራ ማዘዣዎችን ተቀብያት ስወጣ፣ ለአልትራሳውንድ ምርመራዉ ጨመር ያለ ዉሃ መጠጣቱ እንደሚጠቅመኝ ስለማዉቅ፣ ወደ ሆስፒታል
ስመጣ ጀምሬዉ ያጋመስሁትን ኹለት ሊትር ዉሃ እየተጎነጨሁለት
ወደ ቤተ ሙከራዉ ተመለስሁ። እንደ ፈራሁት ስዓቱ ሰዉ የማይበዛበት ሰዓት ሆኖ ይመስለኛል፣ የሚያማርር ወረፋ አልገጠመኝም። በመሆኑም፣
ደሜን ጨምሮ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ናሙናዎችን ሰጥቼ በግማሽ ሰዓት ዉስጥ ዉጤት ደረስልኝ። ዉጤቴን ይዤ እንደገና ወደ ቀድሞዋ የልቤ ሰዉ፣ የአሁኗ ደግሞ ሐኪሜ ቢሮ ወጥሮ የያዘኝን ሽንቴን እንደ
ቆነጠጥሁ ተመለስሁ። ገለጥ አድርጌ እንኳን ወረቀቱን የማየት ሐሳብ ብልጭ አላለልኝም።

ሆስፒታላችሁ ብርሃናዊ አይደል እንዴ አንቺ፣ ፍጥነቱ!”

“ዉጤቱ ደረሰልን?”

“ይኼዉ” አልኋት፣ ጠረጴዛዋ ላይ እንደ ከባድ እቃ በኹለት እጄ
እያስቀመጥሁላት።

“ደፈንሽዉ ኣ?” አለችኝ፣ ትኩረቷን አድርጋበት ከነበረዉ ኮምፒዉተሯ
ወደ ዉጤት ወረቀቴ እያመጣችዉ።

“እረ እኔ ምኑንም አላየሁት”

ለመጨረሻ ጊዜ ሆዴን ሰረቅ አድርጋ አየችዉና ወረቀቱን ገለጠችዉ፡፡ድንገት ፊቷ እብጥ አለብኝ። ዉጤቱ ላይ ደስ የማይል ነገር እንዳገኘች ጠረጠርሁ። ቢሆንም ግን ራሷ እስከምትነግረኝ ድረስ ብጠብቅ ይሻላል ብዬ ያላየኋት መሰልሁ። እሷም ያልደነገጠች ለመምሰል የሆነ ያልሆነዉን ቀበጣጠረች፡፡ እንደገና በሚያደናግር ትኩረት አስተዋለችዉና ወደ አልትራሳዉንድ ክፍሉ እንድከተላት ነገረችኝ፡፡ ስንገባ ያገኘነዉን ራዲዮሎጂስት እንኳን በቅጡ ሰላም አላለችዉም። ቶሎ ብዬ ሆዴን ገልጬ አልጋዉ ላይ እንድንጋለል አዘዘችኝ፡፡ ለወትሮዉ በልዩነት የተማረዉ ባለሙያ ያለበትን አልትራሳዉንድ ይቅርና ተራ ነገርም ቢሆን
ሐኪም ያለሙያዉ ገብቶ አይፈተፍትም፡፡ እሷ ግን እጅግ ከመቻኮሏ የተነሳ እሱን ጨምራ በጥድፊያ ከፍ ዝቅ አደረገችዉ። የእዉር ድንብሯ ወጥቷል። ሌላዉ ቀርቶ ገና በመመርመሪያዉ (ultrasound probe)
እንኳን ሳይዳብሰኝ ነበር ዓይኖቿን ወደ ምስል መከሰቻዉ የተከለቻቸዉ።

ችኮላዋን በበጎ የተረዳት የክፍሉ ባለሙያ፣ ሳይቀየማት የሚደረገዉን ሁሉ አድርጎ የፅንሱን ጥላማ ገጽ ፊት ለፊታችን ባለዉ ዝርግ መከሰቻ አመጣልን። ይኼ ሁሉ ሲሆን የእሷን አድራጎት ብቻ ነበር የምከታተለዉ።
እስኪበቃት ድረስ እያጎላች እና እያሳነሰች ስትመለከተዉ ቆየች። እኔንም እንዳየዉ ጋበዘችኝ፡፡

አየሁት።

ችግር አለ። ከባድ ችግር!
“አይ፤ ያን ያህል እንኳን አንገት የሚያስደፋ አይደለም” አለችኝ፣
ከአልጋዉ ላይ እንድነሳ እየደገፈችኝ። ድንገት ሰዉነቴ እየከዳኝ፣ የበለጠ ድጋፍ እየፈለግሁ መጣሁ። ደግነቷ፣ እጇን አልከለከለችኝም።
“በእርግጥ የማልደብቅሽ ነገር ቢኖር፤ እኔም ልክ የላብራቶሪ ዉጤትሽን ሳየዉ ደንግጫለሁ። በዚያም ላይ ከእኔ ባልተናነስ ስለ ሁኔታዉ ልታወቂ እንደምትችይ ስለማዉቅ በማይመስልሽ ቃል አንቺን አልሸነግልሽም።እንኳንስ የሕክምና ሥነ ምግባር ለማገባት ላንቺ ለጓደኛዬ ይቅርና፣
ለታካሚዎቼ ሁሉ የሆነዉን በግልጽነት የማስረዳት ኃላፊነት አለብኝ። የምልሽ ይገባሻል መቼስ”

ጓደኛዬም ሐኪሜም በሆነችዋ ሸዊት ፊት፣ ግብኔ ብቻ ያልቀረ ለመምሰል ተጣጣርሁ። ጠንካራ ለመምሰል እየሞከርሁ የዉጤት ወረቀቱን እንድትመልስልኝ እና የሆነዉን ሁሉ በራሴ ዓይን እንዳየዉ እጄን ዘረጋሁላት። ሐኪሜ ለምን እንደዚያ እንደሆነች ገባኝ፡፡ ምክንያቱም የፎሊክ አሲድ መጠኑ ከሚጠበቀዉ መጠን እጅግ የወረደ ኖሯል።
እንደዚህ ሲሆን ደግሞ በፅንሱ ላይ የነርቭ ክፍተት የማስከተል ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን እንኳንስ ሥራዬ ብላ ያጠናችዉ እሷ ትቅርና፣ እኔ ዉብርስትም አዉቀዋለሁ። የፎሊክ አሲድ እጥረት ከተከሰተ፣ የነርቭ
ዘንግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ በወቅቱ እንዳይዘጋ ያደርገዋል። በመሆኑም፣ የፎሊክ አሲድ እጥረት እንዳያጋጥም፣ እርግዝና ከመፈጠሩ አስቀድሞ ወይ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ከተመረጡ ምግቦች፣ ወይ ደግሞ ሰዉ ሰራሽ እንክብሎችን መዉሰድ ያስፈልጋል። ያለበለዚያ ይኼዉ በእኔ የምርመራ ዉጤት ላይ እንደ ታየዉ፣ ልክ ያልሆነ ነገር በፅንሱ ላይ ይፈጠራል።

ምን ዋጋ አለኝ? አርፍጃለኋ!

“በእርግጥ ሌሎችም መነሻዎች ስላሉት፣ የፎሊክ አሲድ እጥረቱ ነዉ ይኼን ያመጣዉ ብሎ አፍን ሞልቶ መደምደም አይቻልም። ሆኖም እኔን ደጋግመዉ ከገጠሙኝ ዐሥር የፎሊክ አሲድ እጥረት ያየሁባቸዉ ነፍሰ
ጡሮች፣ ቢያንስ የስድስቱ ወደ ነርቭ ክፍተት ያደርሳል። የነርቭ ክፍተት ስልሽ የተለመዱትን፣ በተለይም ስፓይናቢፊዳ(አከርካሪው ላይ ያለው ነርቭ ወደ ውጭ መውጣት) ማለቴ ነዉ። ይኼ ደግሞ ያልሰለጠነ ሀገር በሽታ እየሆነ መጥቷል። ምክንያቱም የበለጸጉት ሀገራት ምግባቸዉን በጠቅላላ በፎሊክ እንዲበለጽግ ስላደረጉት፣ ብዙም አያጋጥማቸዉም። የእኛን ሀገር ግን አታንሺዉ”

“በናትሽ መፍትሔ አለዉ በዪኝ”

“ደግሞ በኛ ዘመን መፍትሔ የሌለዉ ነገር ምናለና ዉቤ”

“እኮ ምን?”

“በተአምር ታምኛለሽ?”

የጭንቅ ዝልዝል የተንጠለጠለበትን ፊቴን መለስሁላት።

“ተአምር?”

“አሁን አንዴ ፅንሱ ቅርጽ ይዟል። ተአምር ካልተፈጠረ በቀር፣ ሕጻኗ... በነገራችን ላይ ጾታዋን አልነገርሁሽም አይደል ቅድም? ሴት ናት። እና፤ከላብራቶሪም ሆነ ከአልትራሳዉንድ ባገኘነዉ ዉጤት መሠረት፣ በወሊድ ጊዜ ሊገጥሙን የሚችሉ የነርቭ ዘንግ ክፍተቶች ይኖራሉ፡፡ በተለይ
ስፓ ይናባይፊዳ የሚባለዉ ለብቻዉ ወይም ደግሞ ሀይድሮሴፋለስ(ጭንቅላት ውስጥ ውሃ መቋጠር) ጭምር
ሊሆኑ ይችላሉ። ግን እንዳልሁሽ ነዉ፤ ተወልዳ በዓይናችን እስከምናያት ድረስ መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን አንችልም”

“እንዲያዉ አይበልብኝና ይኼ ነገር እዉነት የሚሆን ከሆነ ምንድነዉ
የሚሆነዉ ግን?”

“እንደምታዉቂዉ፤ ለሐቅ የቀረበ ግምት እንጂ ፍጹም የሚባል ያለቀ
የደቀቀ ሐቅ የለም በሳይንስ፡፡ አንቺም ሐሳቤን የምትጋሪዉ ይመስለኛል።ሆኖም አብዛኛዎቹ የዚህ ክፍተት ተጠቂዎች የታወቁ ጉዳቶች ይገጥሟቸዋል። ለምሳሌ ሽንትና ሰገራ ያለመቆጣጠር፣ የእግርና የእጅ ሽባነት፣ የዓይን መንሸዋረር ወይ መጥፋት እና ሌሎችም ጭምር።እንዲያዉም አልፎ አልፎ የከፋዉ ሲመጣ፣ እነዚህ ያልሁሽ ሁሉም አንድ
ላይ የሚከሰቱበት አጋጣሚ ሁሉ አለ። ታዲያ እንዳልሁሽ፣ በኛ ዘመን
መፍትሔ የሌለዉ ችግር የለም። ቢፈጠርም እንኳን ሕክምና አለዉ”

“አለዉ?” አልሁኝ፣ ለእፎይታ ራሴን እያመቻቸሁ። አንደኛዬን ግልብ
ሆኜ የለ አሁንማ? አሁን መሳቅ አሁን ማልቀስ፣ አሁን ማመን አሁን
መካድ። ስስ ሆኛለሁ።

“አዎ። ቀዶ ጥገናም እኮ አለዉ። አንቺን መምከር ሳይገባኝም፣ ከዚህ በላይ መጨነቅ ግን አይኖርብሽም። ጭንቀት ራሱ ሌላ ጣጣ ስላለዉ፣ እዉነታዉን የምነግርሽ እንድትጨነቂበት ሳይሆን ለግልጽነት ብዬ ነዉ።
በዚያ ላይ አንቺ ጠንካራ ሰዉ መሆንሽን ለእኔ ለጓደኛሽ እንዲነግሩኝ አልጠብቅም። አዉቅሻለኋ!”

ቀዝቃዛ ትንፋሽ ተነፈስሁ። ገና ዛሬ፣ አሁን ገና የእግዚአብሔርን ይቅር ባይነት ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠራጠርሁት። ወይ ስለ ንስሐ ምንም አላዉቅም፣ ወይ ደግሞ እግዚአብሔር ቂመኛ ነዉ
ስል አሰብሁ። እኔ የተማርሁት ሰዉ ፍጹም ተጸጽቶ ንስሐ ከገባ
ኃጢአቱ ሁሉ ፍጹም ይሰረይለታል የሚለዉን ነበር። ከእግዚአብሔር
ጋር የሚያደረገዉም እርቅ ፍጹም ይሆንለታል ሲባል አዉቃለሁ። ታዲያ እኔ ፍጹም የሆነ ጸጸት ተጸጽቼ ንስሐ አልገባሁም? ቀኖናዬንስ በሚገባ ወይስ እግዚአብሔር ፍጹም አምላክ መሆኑን አላመንሁም?
👍391
አንድ ተረት ትዝ አለኝ። ተረት አልሁት እንጂ ነገሩስ እዉነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ በደጉ ጊዜ ነዉ አሉ፡፡ በደጉ ነዉ በድሮዉ የሚባለዉ? እሺ በድሮዉ ጊዜ ነዉ አሉ፤ ትኩስ የማር እንጀራ ለመሸጥ አንድ ሽማግሌ
ወደ ገበያ ከቤት ሲወጡ፣ መዉጫቸዉ ላይ ጦጣን ተዝለፍልፋ ወድቃ አገኟት። ሽማግሌዉ ደግሞ ለአራዊቱም ለትላትሉም ሳይቀር አዛኝ
ኖረዋልና፣ ጦጣን ከወደቀችበት በሐዘኔታ አነሷት፡፡ ከዚያ ምክንያቷን ሲጠይቋት፣ ወደ ገበያ ለመድረስ ከሩቅ መነሳቷን እና እዚህ ስትደርስ እንደ ደከማት የማስመሰል እያቃሰተች ነገረቻቸዉ። እንዳለችዉ ግን
ደክሟት ሳይሆን፣ ሽማግሌዉ ባለ ማር መሆናቸዉን እያወቀች ለብልጠቷ ኖሯል የመዉጫቸዉን ሰዓት ጠብቃ መዝለፍለፏ። ቀጥላ አንድ የማታለያ ሐሳብ አመጣች። እሷ ማሩን ልትሸከም፣ እሳቸዉ ደግሞ እሷን ሊሸከሟት። ገና ሽማግሌዉ እሺም እምቢም ሳይሏት፣ ማሩን ነጥቃቸዉ
በራሷ ተሸከመችና ትከሻቸዉ ላይ ጉብ አለች፡፡ ሽማግሌዉም እንደ ፈለግሽ ብለዉ ጦጣዋን ከትከሻቸዉ ሳያስወርዱ መንገዳቸዉን ቀጠሉ። ይኸኔ
በራሷ ላይ ወደ ተሸከመችዉ ማር እጁን ሰደድ አድርጋ ያንን የማር
እንጀራ እየቆረሰች ማምሽክ ጀመረች። እዚህ ላይ ነዉ ጉዷ የፈላዉ እንግዲህ። ለካንስ በዚያ ትኩስ የማር እንጀራ ዓይኖች ላይ አልፎ አልፎ ንቦች አድፍጠዉበት ኖሯል። ጦጣ ሆዬ ብልጥ ሆና ሞታ፣ እንደ ለመደችዉ እጇን ደግማ ወደ ማር እንጀራዉ ስትሰድ ንብ ሆዬ እጇን ንድፍ! ይኼ ብቻዉን ነፍሷን ሊያንሰፈስፈዉ፣ ሌሎች ንቦችም ህዉ ብለዉ
ወጥተዉ ኹለቱንም ዓይኖቿን ድርግም!

ይኸኔ ጥፋቷ ተገለጠላት፡፡ ተጸጸተች፡፡ በእርግጥ ዘግይታለች። ቢሆንም ግን ጸጸቷ ከልብ ነዉ፡፡ እንደ ተጸጸተች ይቅር ይበሉኝ ብላ ሽማግሌዉ እግር ሥር ወደቀች፡፡ ይኼን ስታደርግ፣ ቢያንስ ቢያንስ ሽማግሌዉ ብርሃኗን እንደሚመልሱላት ማመኗን ያሳያል። የቅጥፈቴን ሀገሬ ሩቅ
ነዉ ብዬ ዋሸሁ እንጂ፣ እኔስ ደን በሚያስንቀዉ የጓሮዎ ጥቅጥቅ የወይራ ዛፎች ላይ ነዉ የምኖረዉ:: ወደ ዛፎችዎ በየለቱ እየመጡ ስለሚ ጎበኙን ያዉቁኝ ይሆን ብዬ ሰግቼ ነበር እንዲያዉም። አላወቁኝም እዉነት? ደንቆኛል። እባክዎ ስላታለልሁዎ ይማሩኝ” ብላ ተማጸነቻቸዉ::
ሽማግሌዉም አላሳፈሯትም! ይቅር ብለዉ ሸኟት። ዓይኗ ግን እንደ ጠፋ ቀረ አሉ።

ይኼን ተረት እንደ ሰማሁ በሽማግሌዉ ነበር ያዘንሁባቸዉ። ጦጣዋ ተወልዳ ያደገችዉ በጓሯቸዉ መሆኑን እያወቁ፤ ምናለበት እስኪ ገና
የመጀመሪያዋን ዉሽት ስትዋሽ ቢያስቆሟት ኖሮ? ሲጀመር ተናዳፊ ንቦች በማሩ ላይ ሲቀሩ ለምን ዝም አሉ? እሱም ይቅር፤ ምናለበት በማር እንጀራዉ ላይ ንቦች እንዳሉበት ቢነግሯት? እሺ እሱም ይቅር፤ ምናለበት
ይቅርታ ከጠየቀች እና ከእሳቸዉ ጋር ፍጹም የሆነ እርቅ ከታረቁ በኋላ ዓይኗን ቢያክሙላት? ዓይን አልባ ሆና ስትቀር አታሳዝናቸዉም? ቂመኛ
ቢሆኑ ነዉ ስል አሰብሁ። ሆነ ብለዉ መበቀላቸዉ ነዉ። ተበቅለዋታል።

ምንም እንኳን እግዚአብሔር በዚህ ሽማግሌ ይቅርና፣ በሰማይ በምድር ባለ በምንም የማይመሰል አምላክ መሆኑን ባምንም፣ እኔና ጦጣዋ ግን
አንድና ያዉ ነን። አይደለንም ወይ?

ሎቱ ስብሐት! ምኑን ከምን ነዉ የሚያሳስበኝ? ምን ዓይነት ፍርጃ ነዉ የፈረድሁት? ቆይ ከመቼ ወዲህ ነዉ ግን ለእንዲህ ያለ ክፉ መንፈስ ገረድ ሆኜ ያረፍሁት?...

ይቀጥላል
👍291😁1
አትሮኖስ pinned «#ገረገራ ፡ ፡ #ክፍል_ሰባት ፡ ፡ #በታደለ_አያሌው ...“በይ እሺ፡፡ በይ ደርሰሽ ነይ” የምርመራ ማዘዣዎችን ተቀብያት ስወጣ፣ ለአልትራሳውንድ ምርመራዉ ጨመር ያለ ዉሃ መጠጣቱ እንደሚጠቅመኝ ስለማዉቅ፣ ወደ ሆስፒታል ስመጣ ጀምሬዉ ያጋመስሁትን ኹለት ሊትር ዉሃ እየተጎነጨሁለት ወደ ቤተ ሙከራዉ ተመለስሁ። እንደ ፈራሁት ስዓቱ ሰዉ የማይበዛበት ሰዓት ሆኖ ይመስለኛል፣ የሚያማርር ወረፋ አልገጠመኝም።…»