አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
“ስራሽ ምንድን ነው?” አለች ሴትዮዋ አቲዬን ከታች እስከ ላይ እያየቻት፡፡

“እኔ እትዬ እጥፍወርቅ ጋ እንጀራም እጋግራለሁ ያው ለሆቴሉ፣ እዚሁ ነው ስራዬ ሌላ ምን ስራ አለኝ

“እኔ የማሰራሽ ነገር የለም፡፡ ውጭ ነው የምንበላው:: ልትሄጂ ትችያለሽ፡፡” እቲዬ ደነገጠች፡፡

“ቀን ቀን ስራ ሌላ ስፍራ እየሠራሁ፣ ለማደሪያዬ እዚሁ ቢፈቅዱልኝ፡፡ መሄጃም የለኝም፣ ከነልጇ ለነፍሴ ብለው እትዬ እጥፍወርቅ አስጠግተውኝ ነው "

“ኤጭ አበሻ ሲባል የነፃ ራት ካልበላ እንቅልፍ አይወስደውም፡፡ ጤነኛ ነሽ፣ እግር እጅ አለሽ፣
ሰርተሽ ሳትሳቀቂ ቤት ተከራይተሽ መኖር ስትይይ አስጠግተውኝ ቅብርጥሶ ማለት ምን አመጣው፤
ነጮቹ ቢሆኑ…“ ደሰኮረች፡፡ እቲዬን እዛ መቆየቷ ብዙም ደስ አላላትም፡፡ ቢሆንም አንዳንድ
ሥራ ማሠራቱ እንዳለ ልቧ አውቆታል፡፡ የነፃ ጉልበት የማይፈልግ የነጭ አድናቂ ማን አለና፡፡እናም አቲዩን እንዲህ አለቻት፣ “እንግዲያው ፀባይሽን አሳምረሽ ኑሪ፣ እኔ ጫጫታ ምናምን አልወድም፡፡ ቤቱን ከፈለግኩት በማንኛውም ጊዜ ትለቂያለሽ…"

አቲዬ እኔን አዝላ ወደረሳችው መንከራተት ተመለሰች:፡ አዲሳባ ውስጥ የምታውቀው መንደር
አንድ ነው እዛም ቀለመወርቅና ዘርፌ አሉ.. አሳ ነባሪዎቹ ሦስት ዓመት ፀሐይ ሳይነካት
ብርቱካን መስላ የወጣችውን አቲዬን ሲያዩ ጥርሳቸውን እፏጩ፡፡ ቀለመወርቅ ደፋሩ ምራቁን እየዋጠ እንደገና ተመኛት፡፡ ስላማረባት መንደርተኛው በሙሉ ጠላት፡፡ ዘርፌ የክፋት ልምጯን አዘጋጅታ ነበር የተቀበለቻት።

ከከፍታ እንደመውረድ ውርደት፣ ረግጠው ወዳለፉት ነገር እንደመመለስ ታላቅ ሰቆቃ የለም፤
የራስህ ወገኖች መብረር ስትጀምር እሰይ ከማለት ይልቅ ክንፍህ ተሰባብሮ እግራቸው ስር
ወድቀህ ስትፈጠፈጥ ለማየት ይጓጓሉ፡፡ እናም ስትወድቅ ይረካሉ፡፡ 'ብዬ ነበር፣ አያችሁ
እየተባባሉ የምቀኝነት ትንቢታቸው የሰመረላቸው ምቀኛ ነብያት ይንጫጫሉ፡፡ ብሔራዊ ምቀኝነት
የተጠናወተው ሕዝብ እንደኛ ይኖር ይሆን? “ ለምን በደፈናው እንሰደባለን?” ይልሀል ምቀኛ
ስትለው የተዳፈነበት አመክንዮ እየደረደረ፣ ሁሉም አንድ አይደለም ይልሀል፤ ግን ሁሉም አንድ
ነው፡፡ ሰጥቶታል እንደ ውሃ፣ በልቶታል እንደ እንጀራኛ ጥሬ ስጋው !! ቢማርም ቢያገኝም፣
ምቀኝነቱን ያዘምናታል እንጂ ቢሞት አይጥላትም፤ ማተቡ ናት፡፡

ከነዚህ ሰኋላ የሆነውን ዝርዝር ነገር ስናገር ማንንም ሳይሆን ራሴን እጠላለሁ፡፡ አቲዩ በስጋም
በነፍስም የቀለመወርቅ መጫወቻ፣ የዘርፌ ገረድ ሆና ኖረች፡፡ ለስንት ዓመት፡፡ ዘርፌ ቤት
የመደሀኒያለም ዝክር፣ እከሊት ቤት የኪዳነምህረት ዝክር፣ አሻሮ፣ የተበላ ቂጣ፣ ድፎ ዳቦ፡፡
የእከሊት ልጅ ልታገባ ነው ወጥ ስሪ፣ ጠላ ጠማቂ፡፡ ሲወልዱ - ልደት፣ ክርስትና እሳት በላት እናቴን፡፡

ውበቷን ጤናዋን ወጣትነቷን እሳት በላው። አቲዬ እንደብረት ምጣድ እሳት ላይ ተጥዳ እኔ የምባል ጣፉጭ ኬክ በላይዋ ላይ በሰልኩ፡፡ ይሄ ሁሉ ሥራ በዚህች ሚስኪን ሴት ላይ ተጭኖ፣
ማታ ወደ ማደሪያዋ ስትመለስ የአስቴር ጨምላቃ ሴት ልጆች የውስጥ ልብስ ላይቀር በየቦታው
ተወርውሮ ይጠብቃታል፡፡ ቀን እናትና ልጆች ሲወጡ ወንድ የሚራኮትላቸው ዘናጮች፣ ሽቷቸው ከሩቅ የሚጣራ ሽቅርቅሮች፣ የቤታቸውን ጉድ ወላድ አይየው! እነዚህ በየአደባባዩ ሽቅርቅር
የሚሉ ሰዎች ቤታቸው የዝርክርክነት ጥግ የሚሆነው ለምንድን ነው ግን ? ብዙ ሰው አየሁ ብዙ ሽቅርቅር !!

ሴት ልጅ ቢያንስ የውስጥ ልብሷን የራሷን ገመና እንዴት ሌላ ሰው እንዲያጥብላት ትፈልጋለች
ለዛውም በየካፍቴሪያው ተጎልተው ሲገለፍጥ የሚውሉ ስራፈት ሴቶች፡፡ አይቻለሁ በአስቴር
ልጆች ! እናታቸውም ያው ናት፡፡ የዘር ነው መቆሸሽ፡፡ ከማን ይማራሉ? ያኔ ነው ረጅም ጫማ
አድርጎ ከመቆነን በፊት፣ ፀጉር እየነሰነሱ አገር ይየን! ከማለት በፊት፤ 'ሴት' ሲባል ፊቴ የሚደቀነው ይሄው ፅንፍ አልባ ስንፍና ነው:: የሴት ልጅ ስንፍና እንዴት ይቀፋል? መንገድ ላይ ሰበር ሰካ የሚሉ ሴቶች ሁሉ ከውስታቸው በፊት መታጠቢያ ቤታቸው ነው ዓይኔ ላይ የሚደቀነው፡፡

ድንገተኛ ፍተሻ ይደረግ ቢባል፣ ከዝርከርኩ ወንደላጤ፣ ካልሲ በየቦታው ከሚጥለው ወንድ የባሰ
ስንት ጉድ ሴቶች አሉ፥ ስንትና ስንት ወር ሙሉ ሰው ሰራሽ ፀጉር እናታቸው ላይ ጀልቶ መሬት
ኣይንካን የሚሉ፡፡ በዛ የልጅነት እድሜዬ ተላላኪነትን በተማርኩባት፣ ለመኖር ስል የመሽቆጥቆጥን እርምጃ ዳዴ ባልኩባት በህይወት ውጣ ውረዴ ነበር “ሴትነት ደራሽ ንፋስ የሚከምረው፣ ደራሽ ንፋስ የሚበትነው የምድረ በዳ የአሸዋ ክምር ነው" ብዬ በሴት ተስፋ የቆረጥኩት። የአስቴር
ልጆች፣ ሴት መስለውኝ !! መቼስ በሕይወት ውስጥ ሕይወትን አጠናግረን እንድንመዝናት
የሚያደርጉን አባይ ሚዛኖች አይጠፉ፡፡...

አላለቀም
👍34
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


ዣቬር ምልክት ሲሰጣቸው ብዙ መሣሪያ የያዙ ፖሊሶች ከክፍሉ
ውስጥ ገቡ፡፡ ሽፍቶቹን ያዝዋቸው: ክፍሉ ውስጥ በርቶ የነበረው ሻማ
አንድ ብቻ ስለነበር ክፍሉ ውስጥ ሰው ሲበዛ ጊዜ ብዙ ጥላ በማጥለሉ እየጨለመ ሄደ።

«ሁሉንም በብረት ሰንሰለት እጆቻቸውን እሰሩ» በማለት ዣቬር አዘዘ

«በሉ ወደዚህ ኑ» የሚል ቀጭን የሴት ድምፅ ተሰማ፡፡ ሚስስ
ቴናድዬ ነበረች፡፡ ባልዋ ከለበሰችው ሰፊ ካባ ስር ተሸሽጓል፡፡

ጠንቀቅ በሉ!» ስትል በመጮህ ተናገረች::

ሽፍቶቹ በሙሉ ያለማንገራገር እጆቻቸውን ሰጥተው ሲጠፈሩ
በማየትዋ «ፈሪ ሁሉ!» ስትል አጉረመረመች፡፡

ዣቬር ፈገግ አለ፡፡ ሚስስ ቴናድዬ ወደነበረችበት አመራ፡፡

«አይጠጉኝ፧ ከዚህ ቶሎ ቢወጡ ይሻላል» ስትል በማንጓጠጥ
ተናገረች::«እምቢ ካሉ ዋጋዎን ነው የምሰጥዎት::»

«ደፋር» አለ ዣቬር፡፡ «እመቤቴ እንደ ወንድ ጢም አብቅለዋል፤ እኔ
ደግሞ እንደ ሴት ጥፍር አሳድጌአለሁ» ሲል አሾፈባት።

ዣቬር እየተጠጋት መጣ፡፡ አጠገብዋ አንዳንዴ ልጆችዋ አንዳንዴም ራስዋ የምትቀመጥበት ድንጋይ ነበር፡፡ ዘልላ ሄዳ ያንን ድንጋይ አነሳችና
ዣቬርን ለመምታት ወረወረችው:: ዣቬር ጎንበስ በማለት ራሱን አዳነ፡፡ድንጋዩ ከግድግዳ ጋር ሄዶ ተላተመ:: የግድግዳው ቀለም ፈራርሶ ወለሉን ሞላው:: ድንጋዩ ሲመለስ እየተንከባለለ ከዣቬር እግር ስር ደረሰ።

ዣቬር ወደ ባልና ሚስቱ ሄደ:: በአንድ እጁ የሴትዮዋን፤ በሌላ እጁ የወንዱን ትከሻ ጨምድዶ ያዘ፡፡

«መሣሪያ አምጡ» ሲል ጮኸ፡፡

ወዲያው የብረት ማሠሪያ መጥቶ ሁለቱ ሰዎች ተቀፈደዱ። የራስዋና
የባልዋ እጆች መቀፍደዳቸውን ባየች ጊዜ «ወይኔ ልጆቼ» በማለት ከጮኸች ኋላ ከመሬት ላይ ተዘረረች፡፡

«በእድላቸው ያድጋሉ» ሲል አፌዘባት::

ሦስቱ ፊታቸውን በከሰል ያጠቆሩና ሦስቱ ፊታቸውን በጨርቅ የሸፈኑ ሽፍቶች እጃቸው ታስሮ ቆመዋል::

«ፊታችሁን እንደሽፈናችሁ ቆዩ» አለ ዣቬር፡-

እያንዳንዳቸውን በስም እየጠራ አንዱን «እንደምን አመሸህ»፣ ሌላውን ጤና ይስጥልኝ»፤ ሌላውን ደግሞ «ብርቱም አልሰነበትክ» በማለት
ሰላምታ ከሰጣቸው በኋላ ገና ከክፍሉ ሲገባ አንገቱን ደፍቶ ቆሞ
የነበረው እስረኛ ታወሰው::
«እስረኛውን ፍቱት» ሲል አዘዘ፡፡ «ከዚህ ቤት ደግሞ አንድ ሰው .
እንዳይወጣ?»
ይህን እንደተናገረ ከወንበሩ ላይ ሄዶ ቁጭ አለ፡፡ ከኪሱ ወረቀትና
ብዕር አውጥቶ ከጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ፡፡ ቀና ብሉ «እያየ እስረኛውን ወደዚህ አምጡት» አለ፡፡
ፖሊሶቹ በዓይን ፈለጉት::
«ምነው፤ ምን ያንቀረፍፋችኋል? የት አለ ሰውዬው?» ሲል
ጮኸባቸው::
እስረኛው አባባ ሸበቶ ከዚያ አልነበረም፧ ወጥቶ ሄዷል፡፡
በሩ ላይ ፖሊስ ቆሞአል፡፡ የነበሩበት ክፍል ፎቅ ቤት ነው:: ታዲያ የት ሄደ? መስኮቱ አጠገብ ፖሊስ አልነበረም:: ትርምሱ ሲበዛ ቀደም ሲል እነቴናድዬ ለማምለጫ ባዘጋጁት የገመድ መሰላል አድርጎ ሾልኮአል። የፖሊሶቹ ዓይን አርፎ የነበረው ሽፍቶቹ ላይ ነበር፡፡

«ጋኔላም!» አለ ዣቬር በጥርሶቹ መሀል፤ «ጥሩ ምስክር ይሆነን
ነበር፡፡»

በሚቀጥለው ቀን ማታ አንድ ልጅ በኃይል እያፏጨና እየዘመረ
በመንገድ ላይ ሲጓዝ ከአንድ ነገር ጋር ይጋጫል፡፡ የተጋጨው ከሴት ጋር ነበር፡፡ ለመውደቅ እንደ መንገዳገድ ይልና ወደኋላ ዞር ብሎ ይመለከታል::

«ምነው! ትልቅ ውሻ መስሎኝ ነበር፡፡»

አሮጊትዋ ገንፍላ ከተኛችበት ብድግ አለች፡፡

«የተረገምክ» አለች ፤ «ከድካም ብዛት ሰውነቴ ባይከዳኝ ምን
እንደማደርግህ አውቅ ነበር፡፡»
ልጁ ኣሁን ትንሽ ራቅ ብሎ ነበር የቆመው፡፡

«ፕስ... ፕስ...» በማለት ካሽሟጠጣት በኋላ «በካልቾ ማቅመሴ አልተሳሳትኩም ፤ አበጀሁ፤ አበጀሁ» ሲል ተናገራት፡፡
ሴትየዋ ከተቀመጠችበት ብድግ አለች፡፡ ልጁ ሮጦ ሸሽ፡፡ እርሱን ለመያዝ ስትሮጥ መብራት ከነበረበት ደረሰች፡፡ የፊትዋ መሸብሸብና የወገብዋ መጉበጥ በግልጽ ታየ:: ልጁ ራቅ ብሎ ቆሞ አጤናት።

«እኔ የምወደው መልክ የለሽም» ብሎአት እያዜመ መንገዱን ቀጠለ፡፡ የቤት ቁጥር 50-52 ስለደረሰ ቆመ፡፡ በሩ መቆለፉን ሲያይ በእርግጫ መታው
አመታቱ የልጅ ሳይሆን የአዋቂ ነበር፡፡ ለካስ መንገድ ተኝታ
ያያት ሴት ትከተለው ኖሮ ከነበረበት ደረሰች::

ምንድነው ነገሩ እባካችሁ? ያ ከበሩ ላይ የቆመው ማነው? የእግዜር ያለህ በሩን እየሰበሩት ነው፤ ሌቦች ከቤቴ ሊገቡ ነው» ስትል ጮኸች፡፡

ልጁ በር መደብደቡን ቀጠለ፡፡ ሴትዬዋ ትንፋሽ አጥሮአት መተንፈስዋ በግድ ሆነ፡፡

«የአሁነስ ዘረፋ ዓይን በዓይን ሆነ እንዴ?» ብላ ከጠየቀች በኋላ ልጁን አተኩራ ስትመለከተው ማን እንደሆነ አወቀችው፡፡

«እንዴ! ያ ርኩስ፤ ያ ሰይጣን ነው እንዴ!»

«ጉድ ፈላ! አሮጊትዋ ናትና» አለ ልጁ ወደኋላ እየሸሸ፡፡ «ዘመዶቼን
መጠየቅ መጥቼ እኮ ነው::»

«ከዚህ ማንም የለም፤ አንተ ጋኔል» አለች ሴትዬዋ ጥላቻዋን ከፊትዋ ላይ ለማሳየት እየሞከረች::

«አይ ምን ይላሉ እርስዎ ደግሞ፤ ታዲያ አባቴ የት ሄደ?»

«ላ ፎርስ ከተባለ ሥፍራ፡፡»
«እናቴስ?»
«ሳን ላዛር፡፡»
«እሺ፧ እህቶቼስ?»
«ሌ ማደለኔ ሄደዋል፡፡»
ልጁ ጆሮውን አከክ እያደረገ ሴትዮዋን ቀና ብሎ አያት:: ሴትዮዋ እነቴናድዬ ይኖሩበት የነበረው ቤት ጠባቂ ነበረች፡፡

«እንዴት ይሆናል?» ሲል ራሱን ጠየቀ።

ከዚያም ፊቱን አዙሮ ቀደም ሲል ያዜመው የነበረውን ዜማ እያዜመ
መንገዱን ቀጠለ፡

ቅዱስ ዴኒስና ከፕሎሜ
ጎዳና ያስ ቤት

ኢፓኒን

ማሪየስ ባጠመደው ወጥመድ ፍርድ ሲገለባበጥ አየ:: የፖሊሱ
አዛዥ እስረኞቹን ይዞ ወጣ፡፡ ማሪየስም ከነበረበት ክፍል ወዲያው ሄደ፡፡ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ገደማ ሆኖአል፡፡ ወደ ጓደኛው ቤት አመራ፡፡ ከጓደኛ
ው ከኩርፌይራክ ቤት እንደደረሰም ከእርሱ ጋር ለማደር እንደመጣ ገለጸለት፡፡ ኩርፌይራክም ከመሬት ላይ ፍራሽ አነጠፈለት::

በሚቀጥለው ቀን በጠዋት ከቤቱ ተመልሶ ያለበትን ቤት ኪራይ
ክፍሎ ቤቱን ለቀቀ፡፡ እቃውን በጋሪ አስጭኖ ከኩርፌይራክ ሰፈር ሄደ፡፡

ዣቬር የልጁን ስም ረስቶ ከቤቱ አገኘው እንደሆነ ብሉ ቢመጣ
አጣው:: ማሪየስን ለማግኘት ብዙ ሞከረ ፤ ግን አልተሳካለትም:: ምናልባትም ልጁ የሚደርሰውን አደጋ ላለማየት ብሎ በመፍራት ከአገር የጠፋ መሰለው::

ማሪየስ ግን ባየውና በተሰጠው ፍርድ እጅግ ተረብሾ ነበር፡፡ ሁሉም
ነገር ጨለመበት:: የሚያየው የወደፊት ተስፋ ከፊቱ ራቀ፡፡ ልቡ የተሰቀለላት ልጅና አባትዋ ድንገት እንደ ብርሃን ብልጭታ ብቅ ብለው እንደገና ተሰወሩበት:: የእርሱ የወደፊት ተስፋ እነዚህ የማይታወቁ ፍጡሮች ነበሩ፡፡
ልቡ በልጅትዋ ፍቅር ታውሮአል፡፡ «ሂድና ፈልጋት» ብሎ ስሜቱን
ቢገፋፋውም ዓይኑ ማየት ስላልቻለ እንዲያው ዝም ብሎ መረበሽ፤ መጠበብ፤
መጨነቅ ሆነ፡፡ ቀቢጸ ተስፋ ተጠናወተው:: ተስፋ የተለየው ሕይወት ጨለማ ስለሆነ ፀሐይ ወጥቶ ሳለ ምድር ጨለመችበት:: ዓይኖቹ የፍቅር ረሃብተኞች ቢሆኑም ለማየት የፈለጉትን ባለማግኘታቸው ከማየት ተቆጠቡ::ጀሮዎቹ ለመስማት የፈለጉትን ድምፅ ባለመስማታቸው ሌላ ነገር ከመስማት አፈገፈጉ፡፡ ልቡ የፈለገውን ሳያገኝ ሲቀር የፍላጎቱ መጠንና ግለት እየጎላ
👍20
ስለሚሄድና የፈለገውን ከመሻትና ከመመኘት ስለማይገታ ያንን ፍላጎቱን ለማሟላት ከመዋተት ወደኋላ እንደማይል ሁሉ የማሪየስ ልብም በምኞት ብዛት ራደ ፤ ተንሰፈሰፈ ፤ በፍላጎት ነደደ ፤ በፍቅር ጥም ተቃጠለ::
ማሪየስ ሥራውን መሥራት ስላልቻለ ሥራውን አቆመ:: የመኖር
ዋስትና ያለው ከሥራ ላይ ስለሆነ ደግሞ ሥራን ከማቆም የበለጠ አደጋ የለም:: ሥራ ለማቆም በጣም ቀላል ነው:: እንደገና ለመጀመር ግን እጅግ
ይከብዳል፡፡

ሰው በተፈጥሮው የምቾት ረሃብተኛና በቅዠት ዓለም የሚኖር
ፍጡር በመሆኑ ያንን ምቾት ለማግኘት ሲል ዘወትር በእጁ የያዘውን ይሰዋል:: ምቾት የተጠማ ሕይወት ጭንቅ አይችልም:: ክፋትና ደግነት
ይመሰቃቀሉበታል፣ ምክንያቱም ርህራሄ የሚጎዳ ሆኖ ሲታይ ክፋት ደግሞ የሚያጸድቅና ምግባረ ሠናይ ሆኖ የሚታይበት ጊዜ አለ::

ሥራ ከሌለ ምንጭ ደረቀ ማለት ነው:: የገቢ ምንጭ ከደረቀ ደግሞ ያልረኩ የእለት ፍላጎቶች ተከማችተው ያስጨንቃሉ። ይህም ወደ ወንጀል ወይም ራስን ወደማጥፋት ይገፋፋል፡፡ ማሪየስ ከዚህ ጎዳና ውስጥ ነበር
እየገባ ያለው:: በእውኑም ሆነ በሕልሙ በዓይነ ህሊናው የሚታየው አንጂ ነገር ብቻ ነበር ልጅትዋ::

ጭንቅላቱ ውስጥ የቀረውና ማር ማር የሚል አንድ አሳብ ብቻ
ተቀርጾበታል፡፡ ይኸውም «እርስዋም ትወደኛለች» የሚል ተስፋ ነበር መውደድዋን የገመተው በአመለካከትዋ ነበር፡፡ ገና ብቅ ሲል ዓይን
እንዳኰረፍዋት ፍቅረኛ ይንከራተታል፡፡ በዚህም የተነሣ የትም ትሁን የት እርሱን እንደምታሰላሰል ገምቷል፡፡ እርሱ ዘወትር በሕልሙ እንደሚያያት
ሁሉ ማን ያውቃል፤ እርስዋም በሕልምዋ ታየው ይሆናል፡፡ የሚገርመው አንዳንድ ጊዜ ያፈቀረ ከጭንቀቱና ከጥበቱ የሚወጣው በጎ ነገር በማሰብ ነው:: የእርስዋ አሳብ እኔን እንደሚያስጨንቀኝ ሁሉ እርስዋም በእኔ አሳብና ፍቅር ትጨነቃላች» እያለ ከጭንቀቱ መካከል ደስታ ይቸልስበታል።
«የእርስዎ አሳብ ምን እንደሆነ ጭንቅላቴ ውስጥ እየገባ እንደሚበጠብጠ ሁሉ የእርስዋም ጭንቅላት በእኔ አሳብ ይበጠበጣል» በማለት መንፈሱ
ያረካል፡፡

ብዙ ቀናት እያለፉ ሄዱ፡፡ ግን ምንም አዲስ ነገር አልተገኘም፡፡ ጊዜው እያለፈ ሲሄድ ፍቅረኛውን የማግኘት እድሉ እየመነመነና የተስፋ ጭላንጭ እየጠበበት ሄደ።

«እንዴት!» አለ አንድ ቀን እርስ በራሱ ሲነጋገር፤ «ሁለተኛ አላያትግል ማለት ነው?»

ፓሪስ ከተማ ውስጥ በውበቱ የሚደነቅ አንድ የአትክልትና የአበባ ሥፍራ ነበር፡፡ ከሜዳ መሃል እንደ ኩሬ ያለ ነገር ኣለው:: ወደዚህ ሥፍራ የሚወስደው መንገድ አመቺ ስላልነበረ ከሥፍራው ብዙ ሰው አይሄድም
አንድ ቀን ማሪየስ ብቸኝነት በጣም ስለተሰማው ዝም ብሎ ይጓዛል
ሳያውቀው ከዚህ ውብ ሥፍራ ሲደርስ አንድ ዓይነት አሳብ መጣበት ፍቅረኛዬ ወደ እዚህ ቦታ መምጣት አለባት» ሲል አመነ፡፡ ከዚያ ቀን ጀምሮ እርስዋን የሚያገኝ እየመሰለው በየቀኑ ተመላለሰ፡፡ ነገሩን በጥሞና
ሲያጠኑት የጀል አሳብ ይመስላል፤ ግን እርሱ ዘወትር ከመመላለስ አልቦዘነም
ዣቬር እዚች ቤት ውስጥ በፈጸመው ተግባር ድል ያደረገ ይመስላል፤ ግን አልነበረም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እነዚያ ሽፍቶች ይዘውት የነበረው እስረኛ ባለመያዙ በጣም ተናዷል፡፡ ሽፍቶቹ እንደዚያ የፈለጉት ሰው
ካብ ምናልባት የበላይ ባለልጣኖችም የሚፈልጉት ሊሆን የሚችል ይሆን ነበር ብሎ ጠርጥሮአል፡፡ ስለዚህ ማምለጥ የሌለበት ሰው አምልጦናል በሚል
ተጸጽቶአል፡፡ ይህን ሰው ለመያዝ ሌላ እድል መጠባበቅ እንዳለበት አመነ፡፡ማሪየስን ሲፈልግ ኢፓሚን ያገኛል፡፡ ኢፓኒን እህትዋ አዜልማ ከነበረች ከሌማደሎኒ ተወስዳለች፡፡

ከተያዘት ሽፍቶች መካከል ደግሞ አንዱ መንገድ ላይ ይሰወራል፡፡
ፖሊሶቹም ሆኑ የፖሊስ መኰንኖች እንዴት ሊሰወር እንደቻለ አልገባቸውም። ከእስር ቤት ሲደርሱ ብቻ ነው እስረኛው ማምለጡ የታወቀው:: ዣቬር
በዚህ ደግሞ በጣም ይበሳጫል፡፡ የማሪየስ ጉዳይ ግን ብዙም አላስጨነቀውም::
«ግን በእርግጥ ማሪየስ ጠበቃ ነው ወይስ አይደለም?» ሲል ራሱን አዘውትሮ ይጠይቃል፡፡ ለማንኛውም የታሠሩ ሰዎች ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየቱን
ቀጠለ፡፡
ማሪየስ ኣልፎ አልፎ ከመሴይ
ማብዩፍ ቤት በስተቀር ከማንም ሰው ቤት አይሄድም፡፡ ሁለቱ ሰዎች ኑሮ ስላልተሟላላቸው ሁለቱም ስሜታቸው እየቀዘቀዘና ለመኖር የነበራቸው ጉጉት እየደከመ ነበር። ሰውዬው ከማጣት ብዛት በቀን አንድ ጊዜ ብቻ እህል የሚቀምሱበት ጊዜ ነበር፡፡ ሳቅ ያበዙ የነበረው ሰውዬ ዛሬ ኩርፊያ ይቀናቸዋል፡፡ ወጣቱና ሽማግሌው ድንገት መንገድ ሲገናኙ እጅ ነስቶ ከመተላለፍ በስተቀር ቆም ብለው አይጫወቱም::ይኸው ነው፤ ችግር ሲበዛ የሚያፈቅሩት ባልንጀራ እንኳን ያስጠላል። ለዚህ ነበር ሁለቱ ጓደኛሞች በመነሳሳት የሚተላለፉት፡፡ ሁለቱም የየራሳቸው የሆነ ችግር ነበረባቸው፡፡

እኚያ የቀድሞው ጄኔራል የዛሬው የቤተክርስቲያን ሰው እድሜያቸው
ወደ ሰማንያ ቢጠጋም የሚተዳደሩት አበባ በመሸጥ ነበር፡፡ ሰሞኑን ዝናብ ጠፍቶ የአበባ ተክሎች እንደ መጠውለግ ብለዋል፡፡ ከጉድጓድ ውሃ ቀድቼ
ላጠጣ ቢሉም አቅም አነሳቸው፡፡
አንድ ቀን ማታ ከቤት ውጭ ቁጭ ብለው ሲተክዙ ወደ ሰማይ
ያንጋጥጣሉ፡፡ ምሽቱ ፀጥ ስላለ ቢያስፈራም ከዋክብት ደምቀው በመውጣቸው ልቦናን ይመስጣሉ፡፡
«ምነው ትንሽ እንኳን ቢዘንብ! ጤዛ እንኳን ይጥፋ! አትክልቴ መድረቁ ነው:: ከጉድጓድ ውሃ ቀድቶ ይህን ሁሉ ኣትክልት ማጠጣቱ የሚያደክም
ነወ» እያለ ሲያሰላስሉ ከአጠገባቸው ድምፅ ይሰማሉ፡፡
«አባታችን አትክልቱን ላጠጣልዎት?»
ቀና ቢሉ አንዲት ቀጭን መልከ መልካም ልጅ ከአጠገባቸው ቆማለች::
ልጅትዋ መልስ ሳትጠብቅ ባልዲ አንስታ ከጉድጓዱ ውሃ ማውጣት ጀመረች::
እየተመላለሰች ውሃ በመቅዳት አትክልቱን ሁሉ አጠጣችው:: ሰውዬው በጣም ደስ አላቸው:: ልጅትዋ አትክልቱን ስታጠጣ የተቀዳደው ቀሚስዋ
በውሃ ራሰ፡፡ አሳዝናቸው ብድግ ብለው ሄደው «እግዚአብሔር ይባርክሽ በማለት ግንባርዋን ሳምዋት:: ይህን ብለው አላቆሙም፡፡ «አንቺ የተባረክሽ
አበቦቼን እንዳጠጣሽ እንደ አበባ የሚያምር ነገር ይስጥሽ» በማለት መረቁዋት::

እርስዋ ግን «የለም፣ እኔ ሰይጣን እንጂ የተባረክህ ፍጡር
አይደለሁም:: ሆነም ቀረም ለእኔ ልዩነት የለውም» ስትል መለሰችላቸው::
«ምን ዓይነት እድል ነው! ምስኪን በመሆኔ ምንም ላደርግልሽ
አልችልም፡፡ ልረዳሽ ብችል ምንኛ ደስ ባለኝ!»
«ሊረዱኝ ከፈለጉ፣ ይችላሉ» አለች::
«እንዴት?»
‹ሚስተር ማሪየስ የሚኖርበትን አድራሻ ይንገሩኝ፡፡»
ሽማግሌው ስላልገባቸው «የቱ ማሪየስ?» በማለት ጠየቅዋት፡፡
«እዚህ እንኳን እርስዎ ቤት ይመላለስ የነበረው ወጣት፡፡
በዚህ ጊዜ ሽማግሌው ከቤታቸው ይመላለስ የነበረው ማሪየስ የተባለ ወጣት ማን እንደሆነ ለማስታወስ ሞከሩ፡፡
«እህ! አዎን፣ አስታወስኩት» ሲሉ ተናገሩ፡፡ «የማንን አድራሻ
እንደፈለግሽ ገባኝ:: ማሪየስ ፓንትመርሲን አይደለም የምትይው? አዎን እርሱ የሚኖረው... አይ ለካስ ከዚያ ቤት ለቅቋል:: እኔ እንጃ... አሁን የት
እንደሚኖር አላውቅም::»

ሰውዬው ከነበሩበት ሲነሱ ከኣጠገባቸው ሰው አልነበረም፡፡ ልጅትዋ ሄዳለች፡፡ ሽማግሌው ፍርሃት፣ ፍርሃት አላቸው:: ከአንድ ሰዓት በኋላ ከክፍላቸው ገብተው ተኙ::

አንድ ቀን ጠዋት ማሪየስ ከሽርሽር ሲመለስ የህሊና እረፍት አግኝቶ
ሥራ ለመሥራት የሚችል መስሎት ወደዚያ ይሄዳል:: በእለቱ ከእንቅልፉ እንደነቃ ከአልጋው ወርዶ የትርጉም ሥራ ለመሥራት ጥረት አድርጎ ሀሳቡ አልሰበሰብ ስላለው ነበር«ተነስቼ ከቤት ልውጣና ስመለስ ለመሥራት እሞክራለሁ።
👍15
ለመሄድ የተነሣው ቀደም ሲል ወደተጠቀሰው የሚያምር ግን መሄጃው መንገድ አስቸጋሪ ወደሆነው የአትክልት ሥፍራ ነበር፡፡ ከሥፍራው ሲደርስ
ልብስ አጣቢ ሴቶች ይንጫጫሉ፤ ወፎች ዝማሬያቸውን ያሰማሉ፡፡ ሴቶች ጉልበታቸውን ሲያፈሱ አእዋፍ በደስታ ያዜማሉ:: ሁለቱን ሲያነጻጽር ተገረመ።

ከወደኋላ የለመደውን ድምፅ ሰማ፡፡
«እህ! ያውና!»
ፊቱን ዞር ቢያደርግ ያቺ ያልታደለች አንድ ቀን ጠዋት ከቤቱ
የመጣችው ሴት ልጅ መሆንዋን አወቀ:: የእነሚስተር ቴናድዬ ትልቅ ልጅ ኢፓኒን ነበረች፡፡ ይህች ልጅ በይሰልጥ ብትጎሳቆልም ቁንጅናዋ በይበልጥ ጎልቶ ይታያል ፡፡ ሁለቴ ስትራመድ ብርሃን ከነበረበት ደረሰች:: ለእግርዋ
ጫማ አላደረገችም:: የተቦጫጨቀ ልብስ ነው የለበሰችው:: ከሁለት ወር
በፊት ከማሪየስ ክፍል ስትገባ የለበሰችውን ልብስ ነው የለበሰችው:: ልዩነቱ
ልብሱ አሁን በይበልጥ ተቀዳድዷል፤ በይበልጥ ቆሽሿል:: የድምፅዋ መጎርነን አልተለወጠም:: ፊትዋ በፀሐይ ብዛት ጠቋቁሮአል፡፡ አባ-ግድየለሽነትዋና የሚቅበዘበዝ ዓይንዋ ያው ነው:: ሆኖም የፍርሃት፣ የመረበሽና የሀዘን
መልክ ከበፊቱ ይበልጥ ፊትዋ ላይ ይነበባል:: ይህም ሆኖ ውበትዋ አልጠፋም:: እንደ ንጋት ኮከብ ወከትዋ ከዚያ ከተጎሳቆለ ሰውነትዋ ላይ ሲፍለቀለቅና ሲያንጸባርቅ ይታያል፡፡

ማሪየስ ከነበረበት ደርሳ ከፊቱ ቆመች:: ፊትዋን ፈካ ኣድርጋ በፈገግታ ይህን ተመለከተችው:: ልክ መናገር እንደማይችል ዱዳ ቃል ሳትተነፍስ ለአጭር ጊዜ ዝም ብላ ቆመች::

«ብመጨረሻ አገኘሁህ አይደል?» አለች፤ «አባታችን ማብዩፍ ልክ
ናቸው ማለት ነው:: ከዚህ ነዋ የተደበቅኸው፣ እንደመደበቅህ አልቀላህም::
ስንት ቀን ፈለግሁህ መሰለህ! ታውቃለህ ስንት ቦታ ዞርኩ፡፡ ለአስራ አምስት ቀን ካሠሩን በኋላ ምንም ወንጀል አለመሥሪቴን ሲደርሱበት ለቀቁኝ፡፡ እድሜዬ ደግሞ ለፍርድ የሚያስቀርብ አይደለም:: አሁን እንግዲህ
ከተለያየን ሁለት ወር መሆኑ ነው:: እንዴት ፈለግኩህ መሰለህ? ይኸው አንተን ስፈልግ ስድስት ሳምንት አለፈ:: ከድሮ ቤትህ አይደለም ያለኸው::

«የለም፧ ያንን ቤት ለቅቄአለሁ» አለ ማሪየስ:
ታዲያ አሁን የት ነው ያለኸዉ?
ማሪየስ መልስ አልሰጣትም::
«ወይ ጉድ! ሸሚዝህ ተቀዷል» ካለች በኋላ «ልስፋልህ» ስትል
ጠየቀችው::
ቀና ብላ ፊቱን አየች፡፡ ፊትዋን በማጠቋቆር ቋጠረችው::
«በእኔ መምጣት ደስ ያለህ አልመሰለኝም» አለች::
ማሪየስ አሁንም ዝም አለ፡፡ እርስዋ ለጥቂት ጊዜ ዝም አለችና በኋላ
ወሬዋን ቀጠለች::
«ግን እኮ ቢሆንልኝ አንተን ከማስደሰት ወደኋላ አልልም ነበር፡፡»
«እንዴት?» ሲል ጠየቃት አሳብዋን ለማወቅ ፈልጎ፡፡ «ምን ማለትሽ
ነው?»
«ምነው ተለወጥክ! ከዚህ ቀደም ከዚህ በተሻለ መንገድ ትህትናና
አክብሮት በታከለበት አንደበት ነበር የምታነጋግረኝ ስትል መለሰችለት::
«ግን ይሁንና ቅድም ምን ለማለት ፈልገሽ ነው እንደዚያ የተናገርሽው?»
ከንፈርዋን ነከሰች:: ለመናገር ፈልጋ አመነታች:: በውስጥዋ አንድ ዓይነት ትግል እንደሚካሄድ ያስታውቅባታል፡፡ በመጨረሻ ግን ከውሳኔ አሳብ ላይ ደረሰች::
«ምን አባቱ እንደፈለገው! ምንም ልዩነት አያመጣም» በማለት
አጉረመረመች፡፡ «የተከፋህ ትመስላለህ:: ግን እኔ ደስ ብሎህ እንዳይህ ነው የምፈልገው:: እንደምትስቅና ፈገግ እንደምትል ቃል ግባልኝና ልቀጥል፡፡
ስትስቅ ምን እንደምትመስል ማየት እፈልጋለሁ:: ጥሩ ነው ፤ እንደ እሱ
አየህ ሚስተር ማሪየስ፣ ታውቃለህ፤ የፈለግሁትን እንደምትሰጠኝ ቃል
ገብተህልኝ ነበር» ብላ ስትናገር ጣልቃ ገባ፡፡
«አዎን ብዬ ነበር፡፡ አሁን የምትፈልጊውን ንገሪኛ!»
ዓይን ዓይኑን እያየች ተናገረች::
«የምትፈልገውን አድራሻ አግኝቻለሁ፡፡»
ማሪየስ በአንድ ጊዜ ተለወጠ፡፡ የልቡ ትርታ ከፍ ሲል ፊቱ ወገግ
አለ::
«የምን አድራሻ?» ሲል ጠየቃት ያልገባው በመምሰል እየተግደረደረ፡፡
እንድፈልግልህ የጠየቅኸኝን አድራሻ ነዋ!»
«አዎን» አለ ማሪየስ በመንተባተብ፡፡
«የልጅትዋን አድራሻ እንደሆነ ገባህ አይደል?»
ማሪየስ ሳይታወቀው ከተቀመጠበት ብድግ አለ፡፡ ልጅትዋን እቅፍ አደረጋት::ኀ
«በይ ፤ ነይ እንሂድ፤ አድራሻዋን አሳዪኝ፡፡ የምትፈልጊውን ንገሪኝ፡፡
በኋላ ፈለግሽውን ነገር ጠይቂኝ፧ ይፈጸምልሻል፡፡ አድራሻዋን ብቻ አሳዪኝ ሲል ቀባጠረ::

«ተከተለኝ» ስትል መለሰችለት:: «የመንገዱን ስምና የቤቱን ቁጥር
በትክክል አላውቀውም:: ግን ቤቱን በትክክል አስታውሰዋለሁ:: መለየት አያቅተኝም:: ከዚህ ትንሽ ራቅ ይላል፡፡ ና እንሂድ አሳይሃለሁ፡፡»እጅዋን ይዞ ቆሞ ስለነበር መነጨቀችው:: የሚያይ ቢኖር እንደዚያ ስትመነጭቀው የጥል መስሉት ይደነግጥ ነበር:: ማሪየስ ግን ስሜት
አልሰጠውም::
«አቦ እንዴት ነው ደስ ያለህ!»
«ወሬውን ተይውና መንገዱን አሳዪኝ እባክሽ! »
«እሺ እንሂድ፡፡»
«አሁነኑ?»
«አዎን አሁኑኑ፡፡ ውይ እንዴት ደስ አለው!» አለች::
ጥቂት እንደተጓዙ ቆም አለች፡፡
«በነገራችን ላይ፣ አንድ ነገር ቃል እንደገባህልኝ ተስታውሳለህ?»
ማሪየስ ኪሱን ዳበስ፡፡ ያለችው አምስት ፍራንክ ብቻ ነበር፡፡ እንዳለች አውጥቶ ከኢፒኒን እጅ ውስጥ አስቀመጠው፡፡

ጣቶችዋን ዘርግታ ገንዘቡን ከመሬት ጣለችው፡፡ ቀና ብላ በማንቋሸሽ

ገንዘብህን አልፈልግም አለችው።

💫ይቀጥላል💫
👍312
አትሮኖስ pinned «#ምንዱባን ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ስድስት ፡ ፡ #ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ ዣቬር ምልክት ሲሰጣቸው ብዙ መሣሪያ የያዙ ፖሊሶች ከክፍሉ ውስጥ ገቡ፡፡ ሽፍቶቹን ያዝዋቸው: ክፍሉ ውስጥ በርቶ የነበረው ሻማ አንድ ብቻ ስለነበር ክፍሉ ውስጥ ሰው ሲበዛ ጊዜ ብዙ ጥላ በማጥለሉ እየጨለመ ሄደ። «ሁሉንም በብረት ሰንሰለት እጆቻቸውን እሰሩ» በማለት ዣቬር አዘዘ «በሉ ወደዚህ ኑ» የሚል ቀጭን የሴት ድምፅ…»
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#ስምንት

መማርን ጌታ ይባርከው ! መማር መቃጠል ነው ይላሉ ተምሮ ማቃጠል ለእኔ ዓለሜ ሆነች "
ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት አንደኛ ከፍል እስከመዘገብ የአባት ስም አልነበረኝም፡፡ አሸብር ብቻ
ነበርኩ፡፡ ልክ ትምህርት ቤት አቲዬ ወስዳኝ ስመዘገብ ጉጉት የመሰለው መዝጋቢ የእናቴ ድሪቶ ቀሚስ ለዓይኑ ቀፎት እያመናጨቃት አይቼዋለሁ፡፡ ተመዝግቤ ስንመለስ አቲዬ ከፊቱ ዞር ስትል፣ ፊቱን አጨፍግጎ መጥፎ ጠረን እንደሚያባርር ሰው በግራ እጁ አየሩን እያራገበ ሲያባርር አይቼዋለሁ፡፡

በእርግጥ አቲዩ እማማ የብርጓል ቤት እንኩሮ እያነኮረች ነበር፡፡ ምዝገባው ዛሬ ነው የሚያልቀው
ሲሏት ብድግ ብላ ነው የመጣችው፡፡ ቢሆንስ ልክ ቆሻሻ እንደሸተተው ሰው ሰው እንዲያየው አድርጎ እጁን ያራግባል እንዴ…፡፡ የእማማ የብርጓል ቁጥር አንድ የጠላ ደንበኛ እንዳልሆነ ሁሉ፡፡ ሊያስተምረን ክፍል ውስጥ ሲገባ እንደባቡር ሀዲድ የረዘመ የጠላ ትንፋግ ተከትሎት
እንደማይገባ ሁሉ ነብር አየው ያንን የውሻ ልጅ። አስተማሪውን እንደጠመድኩት ጡረታ
ወጣ !! ደግሞኮ አያፍርም መንገድ ላይ ላገኘው ሁሉ፣ እኔ ነኝ ያስተማርኩት“ እያለ በኩራት
ያወራል፡፡ በርሱ የትምህርት ዓይነት ብቻ ዶክተር የሆንኩ ይመስል!!

“ስም ?” አላት አቲዩን ድሮ፡፡

“የእኔን ነው ?” አለች እየፈራች፡፡

ፈሪ ነበረች እናቴ፡፡ ፈሪው የአዲስ አበባ ሕዝብ እንደያቅሙ ደሀ ማስፈራራትን ተክኖበታል።

“አንች ነሽ አንደኛ ክፍል የምትመዘገቢው?" አላት፡፡ አጠገባችን ያሉት ሁሉ ሳቁለት፡፡ አቲዬ ተሳቀቀች፡፡ ሰውነቷ ሽምቅቅ ሲል ቀሚሷን አንቄ ተሰምቶኛል መሸማቀቋ፡፡

የልጅሽን ሰም ንገሪኝ ሴትዮ አላት እያከላፈታት፡፡

“የእሱ አሸብር…አሸብር ነው ስሙ አለች ራሴን እያሻሸች፡፡

“የአባት ስም ?”

“እባ…ት” ብላ ዝም አለች፡፡

“የአባቱ ስም ማነው…

'ቀ' መጨረስ አልቻለችም፡፡ ቀለመወርቅ ልትል ፈልጋ እንደነበር የገባኝ ካደግኩ በኋላ ነው፡፡

የዛሬዋ ደግሞ የጉድ ናት፡፡ የልጇም አባት የሚጠፋት
እንደገና እንዲስቁለት ሰዎቹን አየ
ያልደመቀ ሳቅ ተሳቀለት፡፡

"በይ ወደዛ ሁኝ! ስታስታውሽ ትመለሻለሽ፤ ተረኛ ቀጥል!” አለ እስኪርቢቶውን እያወናጨፊ፡፡

(አልረሳትም ግማሽ ድረስ ቀለሟ ያለቀ ሰሚያዊ ቢክ እስክርቢቶ።

እናቴ ከእንቅልፉ እንደባነነ ሰው፣ “በአምላክ..በአምላክ ነው የአባቱ ስም፡፡” አለች፡፡

መዝጋቢው ራሱን ግራና ቀኝ በብስጭት እያወዛወዘ መዘገበኝ፡፡

የአባት ሰም በአምላክ (በአምላክ አባቴ አይደለም፡፡ እቲዬ ለአምላክ ሰጠችኝ፡፡) የሃምሳ ብሩ ሲገርመው፣ ለእግዜር ሰው አበደረችው አቲዬ፡፡ የእኔ እናት በሕይወት ባንክ ውስጥ ብድር
ለሚመልስ ብድር በመስጠት የተካነች ባለሙያ ነበረች ነገን የምታይ !! እግዜር የተበደረው
ትውልድ፣ ወለዱ የተባረከ ዘር ማንዘር ነው፡፡ “እስከ ሺ ትውልድ ዘርህን እባርካለሁ፡፡ ብሏል
ራሱ እግዜር

ትምህርት ቤት ገባሁ…!!

የክፍላችን ልጆች የኑሮ ደረጃ በዳግማዊትና በእኔ መካከል የተወሰነ ነበር፡፡ ዳግማዊት የሚታዘል ባለዚፕ ቦርሳ ያላት ቆንጆ አንደኛ የሀብታም ልጅ ስትሆን፣ እኔ ከሹራብ የተሰራች ኮሮጆ የነበረኝ አንደኛ የደህ ልጅ፡፡ ይሁን እንጂ በንፅህና አልታማም፡፡ ልብሶቼ ሁልጊዜም ንፁዎች ነበሩ
ንፁህና አሮጌ፡፡ ሰኞ ሰኞ ሰልፍ ሜዳ ላይ የእጅ ጥፍሮቻችን ሲታዩ ንፁሀ ጥፍርቼን በኩራት
ነበር የምዘረጋው:: የዳግማዊትን ያህል በፈገግታ “ጎበዝ“ ባልባልም፣ ከቆሻሻና ከስንፍና የተጣላች ቆራጥ ደሀ እናት አለችኝና ስንፍናና ቆሻሻ አጠገቤ ዝር አይሉም ! (ሰው ወዶ አይደለም ለካ ዘራፍ የሚለው፡፡)

አንድ ቀን ግን በሕይወቱ ስሳቀቅበት የኖርኩበት ነገር ተፈጠረ፡፡

እንግዲህ አስቴር ከዋናው ቤት እሮጌ ፍራሽ (የሆቴሉ አልቤርጎ ውስጥ የነበሩ፡፡) እና ሌሎችም
ከፍል ውስጥ ቤት፡፡ እናም ቤታችን ውስጥ በታጨቀው ዕቃ ምከንያት ቤቱን አንደ ልብ ማፅዳት ባለመቻሉ ቁንጫ እንደጉድ ይፈነጭ ጀመረ፡፡

ጋሽ መሀሪ ኣካባቢ ሳይንስ መምህራችን ነበር፡፡ ሲያስተምር ስወደው:: የርሱን ትምህረት አስር
ካስር ነው ሁልጊዜም የምደፍነው፡፡ እኔ ስለምወደው፣ የሚወደኝ ይመስለኝ ነበር ፡፡ አንድ ቀን ግን ዘላለማዊ ጠላቴ ያደረገውን የማይረባ ነገር አደረገ።

ስለ ጓር አትክልት ጥቅም እያስተማረ ነበር፡፡ ድንገት ዳግማዊት፣ “ ዋይ” ብላ ጮኸች::
ቦርሳዋ ላይ ሁለት እሳት የመሳሰሉ ቁንጫዎች ዘለውባት ነበር፡፡ የክፍሉ ልጅ ሁሉ በድንጋጤ
ወደ ዳግማዊት ዞረ፡፡ መምህሩ ሁኔታውን ሊያጣራ ከምኔው አጠገባችን እንደደረሰ እንጃላት::

“ምንጩን ነው?”

“ቁ..ን..ጫ አለች ለቅሶ በሚመስል ሞልቃቃ ድምፅ፡፡

እኔ ከዳግማዊት ጎን ነበር የምቀመጠው፡፡ ባልገባኝ ምክንያት ተቆጣ፡፡

"እስቲ ቦርሳህ” አለኝ፡፡ በቃ እንዲህ ነው ያለኝ፡፡ ከወንበሩ ስር ከተሰራው የደብትር ማስቀመጫ፣
የሹራብ ኮሮጆዬን አወጣሁ፡፡ በዚህች ቅፅበት የተከሰተው ነገር አስደንጋጭ ነገር ነበር፡፡ በርካታ
ቁንች ከእኔ ኮሮጆ ላይ ተፈናጠሩ፡፡

መምህር ምሀሪ ፊቱን አጨፍግጎ ኮሮጆዬን አነሳና ወደፊት ወደ ጥቁር ሰሌዳው ወረወረው::
ደብተሮቼ በአየር ላይ ወረቀታቸውን እያርገበገቡ ተበታተኑ፡፡ (እስከዛሬም ደብተሮቼ በአየር ላይ እየተንሳፈፉ ይታዩኛል አላረፉም፡፡)

“ውጣ ጆሮህን ያዝ ብሎ በኩርኩም አፈለሰኝ፡፡ ወጥቼ ጆሮዬን ያዝኩ፡፡ ከኩርኩሙ በላይ
ሀፍረቱ ጠዝጥዛኝ ነበር፡፡

የታፈነ የጓደኞቼ ሳቅ፡፡ በትምህርት አልችለኝ ሲሉ እችን እንደውድቀት፣ እችን ከእነሱ እንዳነስኩባት አጋጣሚ ሊጠቀሙባት፡፡ የእፉኝት ልጆች…ስንቱን ትምህርት ስደፍን ለጭብጨባ በመከራ የሚነሳ እጃቸው፧ ዛሬ ሳቃቸውን ሊያፍን ወደ አፋቸው ተወነጨፈ።

ቡፍ.….ቡፍ...ሂሂሂ..

መምህሩ መሀሪ (ስሙን ቄስ ይጥራውና!) ስለጓሮ አትክልት የፃፈውን አጥፍቶ ጥቁር ሰሌዳው ላይ፣

“ተስቦ" ብሎ በትልቁ ፃፈና ከስሩ በድርቡ አሰመረበት፡፡ ያውም አረንጓዴ ቀለም ባለውና እንደ
ብርቅ በምናየው ጠመኔ !!

ከዛም ስለተስቦ ሙሉ ክፍለጊዜውን ሲለፈልፍ ዋለ፡፡

“አያችሁ ልክ እናንተ ወደ ትምህርት ቤት ወይም ዘመድ ለመጠየቅ በታክሲ፣ በአውቶብስ
ተሳፍራችሁ እንደምትሄዱት፣ ቁንጫዎችም በአይጦች ተሳፍረው ንፅህናው ወዳልተጠበቃ ቤት ይሄዳሉ፡፡ አሁን እሱ ደብተር መያዣ ላይ እንዳያችሁት እኔን እየጠቆመ)፣ ንፅህናው ባልተጠበቀ የልብስ ሻንጣ፣ የደብተር መያዣ፣ በሌላም ቁሳቁሶች አማካይነት እየተንጠላጠሉና እየተደበቁ
ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ፣ እንደ ዳግማዊት ዓይነት ንፁህ ልጆች በተስቦ ይያዛሉ..” በማለት
አስተማረ፡፡ ምን ያስተምራል አስተማሪ የሚባለው ነገር የጠላት ስም እንዲመስለኝ እደረገ እንጂ !
ለረዥም ጊዜ 'ተስቦ' እያሉ ጓደኞቼ ያበሽቁኝ ነበር፡፡ ከአርባው ስንፈተን ግን ስለተሳቦ ተጠይቀን
የደፈንኩት እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ ሰው ስድሱን አይረሰማ !! በተለይ እኔ ስድቤን አልረሳም !! መገፋቴን አረሳም።

ስድስና መግፋት እንደ አረግራጊ ሳንቃ ሽቅ

ብ ተኩሰው በቀል የሚባል ጨረቃ ላይ የሚያሳርፉኝ
👍36🥰32😁1😢1
ሮኬቶቼ ነበሩ፡፡ እንዲያ ካልሆነ በቀል መቼ አምሮ !! የሰደበኝን ሁሉ አልለቀውም !! ለምን
ዘላለም አይኖርም፣ አልረሳም! የአዲስ አበባ ሕዝብ ሂትለሩን እቅፍ እያሳደገ መሆኑን መች
ጠርጥሮ? ለፋሽስቱ እድገት ኩርኩምና እርግማን እያዋጣ እንደሆነ መቼ ቀልቡ ነግርት? ሬዲዮና ቴሌቪዥኑ አደንቁሮት፣ ፊልምና ድራማው አሳውሮት፣ ሽቅርቅሮቹ ልቡን አጥፍተውት፣ ሕዝቡ ምን እያሳደገ እንደሆነ ያስተውልም !! እያንዳንዱ መንደር አለ የተጎፋ ሕፃን ሂትለር - የሕዝብ
ንቀትና ጥላቻ በክፋት ያፈረጠመው፡፡ በቀጥታ ሳይሆን ሳያውቁ ለልጆቻቸው በሚያለብሱት ልብስ፤ በሚያገምጡት ኬክ እንቁልልጭ እያሉ አርፎ የተኛ ረሀቡን ቀስቅሰው ያስነከሱት
የቆሰለ አቦሸማኔ አለ። ሕዝብ ጠላቱን የሚጠብቀው ድንበሩ ላይ ወታደር አሰልፎ ነው:: አገርና
ሕዝብ ንፋስ እንደገረሰሰው ዛፍ ከስራቸው ተነቅለው የሚወድቁት ግን ውስጣቸው ባሳደጉት
ጭቆና፣ ባፈረጠሙት የጥላቻ ክንድ በተደቆሱ ግለሰቦች ነው::

ሕዝቤ ያሳረፈብኝን የጥላቻ ኩርኩም ነገ በጅምላ እልቂት እከፍለዋለሁ ብቻ ልደግ ።
ማሪያምን አልለቀውም ይሄን ሕዝብ፡፡ ደግሞ ብቻዬን አይደለሁም ይሄ ሁሉ ተገፍቶ
ጎዳና የሚንከራተት ሕፃን፣ ነገ ተንደላቀው የሚማሩትን ቆንጆ የለበሱትን ልጆችህን ሕይወት
ያመሳቅለዋል፡፡ የዘራኻትን የጥላቻ ፍሬ ታፍሳታለህ፡፡ ነገ የበደልከው፤ ያከላፈትከው፤ የረገምከው
ሕፃን እጅ ላይ ትወድቃታለህ፡፡ ያኔ በቀሉን በሁለት እጅህ ትቀበላለህ፡፡ ድፍን አገር ይስማ
ተቀምጣችሁ የሰቀላችሁትን ቆማችሁ ማውረድ የሚያቅትባችሁ ቀን ይመጣል፡፡ ቱ !! አሸብር አይደለሁማ !! እንዲህ ነበር ሁሌም የምለው፡፡

እኔ ዶከተር አሸብር የሚስኪን እናቴን በደል የምከፍልበትን የመጨረሻውን ክፉ በቀል እያሰብኩ ነው ያደኩት። ኒውክሌር ቦንብ ሲኖረኝ እያልኩ፣ ወስጄ ቀለመወርቅ ግቢ እጥለውና ቁልፉን እጫነዋለሁ፡፡ የቀለመወርቅ ባርኔጣ ከነራስ ቅሉ በርሮ ኪንያ ጠረፍ ቢገኝ ግድ አለኝ? እነዛን የአሜሪካ ላሞች እንደ ኢላማ ፊት ለፊት አቁሜ በመድፍ ነገር ሆዳቸውን ብደረማምሰው፣ ወተታቸው ወደ ሰማይ ጎኖ አዲስአበባ ላይ እንደ ነጭ ዝናብ ቢዘንብ.ዠ እችን ያህል ሊሰማኝ ነው?

በአውቶሞቢል፣ በታክሲ፣ በአውቶብስ የሚጓዘውን ሕዝብ አንዳች ኃይል ኖሮኝ አፋፍሼ ቀበና
ብከተው አይወጣልኝም፡፡ የእሳት ዲንጋይ እንዲያወርድ እግዚአበሄርን ብዙ ቀን ለምኜዋለሁ፡፡ ዝም ሲል፣ “እግዚአብሄር ለአዲስ አበባ ህዝብ እዝኖ ሳይሆን ህዝቡን ተፀይፎ፣ ለእነዚህ ማን እሳት ያባክናል? ብሎ ትቷቸው ነው እያልኩ አስባለሁ፡፡

ቢሆንም አንድ ቀራፎ አስተማሪ አፉን ከፈተብኝ ብዩ አልተዘናጋሁም፡፡ ብዙ ስዎች ጎበዝ ተማሪ ነህ ሲሉኝ ይገርመኛል፡፡ እኔ ምንም የተለየ ነገር አላደርግም፡፡ አስተማሪው ሲናገር፣ የፃፍኩትም
ሳነብ፣ ከዚህ በፊት የማወቀውን ታሪክ የምሰማ ነበር የሚመስለኝ፡፡ ፈተናዎችን ሁሉ እኔ ራሴ
ያወጣኋቸው እስኪ መስለኝ ነበር መልሶቻቸውን ጠንቅቄ የማውቀው። በትምህርት ቤታችን
ማንም ጎበዝ ነኝ የሚል ተማሪ ሲያድግ ከእኔ ጋር እኩል መሆን ይመኝ ነበር ብል ማጋነን
አይሆንም፡፡ እነሱ እስከሚያድጉ ቆሜ እጠብቃቸው ይመስል !! “የዛሬ ምናምን ዓመት አሽብር
የደረሰበት እንደርሳለን” የዛሬ ምናምን ዓመት አሸብር የኒውክሌር ቦምብ ባለቤት ይሆናል ቡምምምምምምምምምምምምምም ጥርግርግ !

እነዚህ ጉረኛ ሴቶች ሁሉ ሰው ሰራሽ ፀጉራቸው እንደችቦ አናታቸው ላይ እየነደደ በቀላ
ጫማቸውን ወርውረው በባዶ እግራቸው ለመዳን ሲሮጡ ሆዴን ይዤ እስቃለሁ፡፡

ሽማግሌዎች መሸሽ አቅቷቸው ሲንቀጠቀጡ፣ እነዛ ልጆቻቸውን በትልቅነት ያልገሰፁ ሁሉ
አላዝንላቸውም፡፡ የቀለመወርቅን ቀደል ዓይተው እንዳላዩ ያለፉ ዓይኔ አፍንጫዬ ቁርጥ
ቀለመወርቅን መምሰሉን እያዩ፣ “ብየት ቤት ብሎ! ኧረ ቀለመወርቅ ቀጭን ጌታ ነው፡፡ እዚህ
ቋቁቻም ጋር ምኑም አይመሳሰል” እያሉ ያሽቃበጡ ሁሉ አባቴ ጣረሞት ነው ብዬ እልቂት
ይዤ ፊታቸው ስቆም፥ “ቁርጥ ጣረሞትን” ይሏታል አልምራቸውም ! “ታላላቆቻችሁን
አክብሩ፣ ከወንበራችሁ ተነሱላቸው ሲሉ ይገርመኛል፡፡ ብችል ታላላቆቹን ከነከዘራቸው
እያነሳሁ ሳፈርጣቸው፣ አልያም ከወንበር መነሳት ሳይሆን ወንበር አንስቼ ጎባጣ ወገባቸው
ላይ፣ ሽበታም አናታቸው ላይ ባፈጋባቸው ደስታዬ ነው፡፡ ቅሌታም፣ አስመሳይ ሁሉ፡፡ ነገር
ከዛ ከዚህ ሲያቃሉ ስላረጁ ትልቅ የሆኑ ይመስላቸዋል፡፡ ውቤ በረሀ ሴት ሲያሳድዱና አተላ
ሰጋፉ ያረጁ አስመሳዮች፤ በአባቶቻችን ስም አድዋ የዘምቱ፣ ማይጨው ላይ እልፍ የመከቱ
መስለው ደኮፈሳሉ፡አላከብራቸውም፡፡ የአንዲትን ሴት እንባ ማበስ ያቃታቸው፣ በጠራራ
ፀሐይ እውነትን የሸመጠጡ “እንምከር" ሲሉ ያቅለሸለሹኛል፡፡..

አላለቀም
24👍17
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


ከፕሎሜ ጎዳና ላይ ያለ ቤት

ፕሎሜ ከተባለ ጎዳና ላይ ንብረትነቱ የመንግሥት ባለሥልጣን የሆነ ባለአንድ ፎቅ ቤት ነበር፡፡ ቤቱ ሁለት ክፍል ቤት ከፎቁ ላይ፣ ሁለት ክፍል
ደግሞ ከምድር ቤት ነበረው፡፡ በተጨማሪ እንደ ወጥ ቤት የሚያገለግል ተጨማሪ ክፍል ፎቁ ላይ ነበረው:: ከዋናው ጎዳና ጋር የተያያዘ ትልቅ የውጭ በር ሲኖረው በአበባ ያጌጠ ሰፊ ግቢ አለው:: ከበስተጓሮው እንደ
እቃና ማድቤቶች ሊጠቅሙ የሚችሉ ሌሎች ሦስት ክፍሎች ነበሩ:: በጓሮ በኩል ደግሞ የምሥጢር በር አለው::
ምስጢሩን ለሚያውቅ እንጂ ይህ
በር፣ በር መሆኑ በቀላሉ አይታይም:: ቤቱ ብዙ ጊዜ ሰው አይከራየውም::

በ1829 ዓ.ም አንድ በእድሜ በሰል ያለ ሰው መጥቶ ይህን ቤት
ይከራየዋል፡፡ ሰውዬው ብቻውን አልነበረም:: አንዲት ወጣት አብራው ነበረች፡፡ ይህ ሰው ዣን ቫልዣ ነው:: ወጣትዋ ልጅ ደግሞ ኮዜት ናት፡፡ ቀደም ሲል ዣን ቫልዣ ይረዳት የነበረችው አሮጊት ደግሞ አብራቸው ናት:: ስምዋ ቱሴይ ይባላል:: ዣን ቫልዣ ቤቱን የተከራየው መሴይ ፎሽለማ በሚል ስም ነው::

ዣን ቫልዣ ለረጅም ጊዜ የኖረበትን ገዳም ለቅቆ ከወጣ በኋላ ምን
ተፈጸመ ቢባል ምንም የሆነ ነገር የለም:: እንደሚታወሰው ዣን ቫልዣ ገዳሙ ውስጥ ደስ ብሎት ነበር የሚኖረው:: በየቀኑ፡ ኮዜትን ያገኛታል።በተገናኙ ቁጥር ፍቅራቸው እየጠናና የአባትነት ስሜቱ እየዳበረ ይሄዳል፡፡
ልጅትዋን ፈጣሪ የሰጠው ፀጋ እንደሆነች ከማነ ባሻገር ይህችን ልጅ ከእርሱ ማንም ሊለያት እንደማይችል ገምቷል:: እስከ ሕይወቱ መጨረሻ ከእርሱ የማትለይ ፍጡር ለመሆንዋ አልተጠራጠረም:: ይህም ደስታውን እጥፍ አደረገለት፡፡ ነገር ግን ልጅትዋን የግሉ ሀብት አድርጎ በመቀበልና የደስታው ምንጭ እንድትሆን በማድረጉ በመጠኑም ቢሆን የሕሊና ወቀሣ
ነበረበት::

ይህቺ ልጅ ገና እምቡጥ ናት:: ምንም ነገር አታውቅም:: ሕይወትዋን እንደፈቀደ የሚመራው ዣን ቫልዣ ነው:: ይህንንም ያደረገው ከክፉ ነገር
ላይ እንዳትወድቅ በማሰብ ነበር፡፡ ሆኖም ይህን ዓይነቱ አስተዳደግ የዓለምን ምንነት ለማወቅ እድል አልሰጣትም:: የራስዋን እድል ራስዋ ልትወስን አልቻለችም:: እንደ እውነቱ ከሆነ ሰውዬው ይህቺን ልጅ እንደ ቦይ ውሃ የመራት ከእርሱ እንዳትሄድ እንጂ ሙሉ በመሉ ለእርስዋ ብሎ አልነበረም፡፡
ይህ ነው የሕሊና ወቀሣ ያስከተለበት::
ከመነኩሴ ትምህርት ቤት ያስገባት እርሱ ነው:: መነኩሲት እንድትሆን የወሰነው እርሱ በመሆኑ ምናልባት ስታድግ በዚህ የተነሣ ልትጠላው ትችላለትች፡ ይህንና ይህን የመሳሰለ አሳቦች ናቸው ገዳሙን ለቅቆ እንዲወጣ
ያደረጉት:: ከዚህ ለመውጣት ከውሳኔ አሳብ ከደረሰ በኋላ አልቆየም::ግቢውን ለቅቆ ለመውጣት ጥሩ አጋጣሚ እየጠበቀ ሳለ ሽማግሌው ፎሽለማ መሞታቸው በዚሁ ሳቢያ ግቢውን ለቅቆ ወጣ፡፡

ከገዳሙ ሲወጣ ለገዳሙ አለቃ የነገራቸው ወንድሙ በመሞታቸውና እንደ እርሳቸውም መሞት የተነሣ መጠነኛ ሀብት ስለወረሰ ሌላ ቦታ ሄዶ መኖር የሚችል መሆኑን ነበር፡፡ ስለዚህ ልጁን ይዞ ያለ ብዙ ድካም ከሌላ
ቦታ ለመኖር የወሰነ መሆኑን ሲነግራቸው አልተቃወሙትም:: ልጅትዋን በማስተማር ገዳሙ ላበረከተው አስተዋጽኦ ለገዳሙ አምስት ሺህ ፍራንክ በስጦታ መልክ ሰጥቶ ነው የወጣው::

ከገዳሙ ሲወጣ የማንንም እርዳታ ሳይጠይቅና ማንንም ሳያስቸግር
ያቺን ትንሽ ሳጥን እርሱ ራሱ በእጁ ይዞ ነው የወጣው:: የሳጥንዋን ቁልፍ ዘወትር ከእርሱ አይለያትም:: ስለሳጥንዋ ኮዜት ሁልጊዜም ትገረማለች፡፡አንድ ዓይነት የተለየ ጠረን አላት:: ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሳጥንዋን ከራሱ አይለያትም:: ሁልጊዜም የሚያስቀምጣት ከራሱ ክፍል ውስጥ ነው:: ከቦታ ወደ ቦታ በተዘዋወሩ ቀጥር እርስዋን ብቻ ነው አንጠልጥሉ የሚሄደው::
ኮዜት «ይህቺን ሣጥን ቀናሁባት» እያለች አንዳንዴ ብቻዋን ትስቃለች::

ከጊዜ በኋላ ዣን ቫልዣ ወደ ከተማ በወጣ ቁጥር እየተጨነቀ እንጂ
መዝናናትን ከተወ ሰንበት ብሉአል:: ፕሎሜ ጎዳና ላይ ካለው ቤት ውስጥ ከገባ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ከቤት አይወጣም:: ከዚያ ቤት ውስጥ እያለ ስሙ የሚታወቀው ኧልቲስ ፎሽለማ በሚል ስያሜ ነው::

እዚያው ቤት ውስጥ እያለ ሌሉች ሁለት አነስተኛ ቤቶች ከተለያዩ
ሰፈር ተከራይቶ በስሙ ይይዛል:: አልፎ አልፎ ወደ እነዚህ ቤቶች ተራ በተራ አንድ ጊዜ ከአንደኛው በሌላ ጊዜ ደግሞ ከሁለተኛው እየሄደ ወርም ሁለት ወርም ኮዜትን ይዞ ይቀመጣል:: አሮጊትዋን ግን ይዟት አይሄድም፡፡ይህንንም ያደረገው ከፖሊሶች ለመሰወር ነበር፡፡

ከቤት ውስጥ ሲሆኑ ቤቱን የምትመራው ኮዜት ናት ገዳም ውስጥ እያለች ስለቤት አያያዝ ትምህርት ቀስማለች:: ብዙውን ጊዜ ዣን ቫልዣ በጓሮ በኩል ከነበሩት ቤቶች ውስጥ ሲቀመጥ ኮዜት ከትልቁ ቤት ውስጥ
ፎቅ ላይ ነው የምትቀመጠው:: በየቀኑ ዣን ቫልዣ የኮዜትን እጅ እየያዘ ከዚያ ከተንጣለለውና ስአበባ ከአጌጠው ግቢያቸው ውስጥ ይንሸራሽራሉ፡፡
ወደ ከተማ የሚወጠበት ቀን
ውሰን ነው:: እሑድ እሑድ ግን
ወደ ውጭ ወጣ ብለው ይንሸራሸራሉ በዚህ ጊዜ የኮዜትን ቁንጅና ተመልካች እየበዛ መጣ በርግጥ እርሷም ሁሌ የምታስበው ነው ለሽርሽር በወጡ ቁጥር ወንዶች ሰብሰብ ብለው አንዱን አፍጥጣ ስታይ አንድ ሰው ‹‹በእርግጥም ቆንጆ ነሽ የሚላት መሰላት::ትንሽ ተሽኮረመመች:: ያን እለት ማታ ጥሩ እንቅልፍ አልተኛችም፡፡ ከተኛች በኋላ «እውነትም ቆንጆ ነኝ፤ የወንዶች ልብ አሁን እኔን ይመኛል?»
ስትል ብዙ አሰበች:: ገዳም ውስጥ በነበረችበት ጊዜ የምታውቃቸውን ጓደኞችዋን በማስታወስ መልክዋን ከእነርሱ መልክ ጋር ማነፃፀር ጀመረች::
«እኔ እኮ ከእገሊት አላንስም፡፡ እገሊትም ብትሆን እስከዚህም የምትደነቅ ልጅ አይደለችም፡፡ ውይ እገሊት ግን በጣም ቆንጆ ናት:: እኔን ትበልጠኛለች ብቻ ምንዋ ነው ከእኔ የሚበልጠው?» እያለች ስለውበትዋ ታሰላስል
ጀመር::

አንድ ቀን ከግቢው ውስጥ እየተንሸራሸረች ሳለ አሮጊትዋ ቱሴይ
«ጌታዬ ይህቺ ልጅ እንዴት እየቆነጀች እንደሄደች ልብ ብለዋል?» ብላ ስትናገር ትሰማለች:: አባትዋ ምን መልስ እንደሰጠ ግን አልሰማችም::
የቱሴይ ንግግር ግን ስሜትዋን ነካው:: እየሮጠች ወደ ክፍልዋ ሄደች::
ከመስታወት ፊት ቆማ መልክዋን አየችው:: መስታወት በማየት መልክዋ ካስደነገጣት አንድ ሦስት ወር ያህል አልፎአል፡፡ የመጀመሪያው ቀን ሰው
ሳያያት ትንሽ አልቅሳለች:: የምታየው ራስዋን ሳይሆን የሌላ ሰው መስሎአት ነበር።

በጣም ቆንጆ ለመሆንዋ ለሁለተኛ ጊዜ አረጋገጠች:: መስታወቱና
ቱሴይ ያሉት ነገር ትክክል እንደሆነ አልተጠራጠረችም:: ቅርጽዋ፣ የቆዳዋ ቀለም፣ ፀጉርዋ፣ ዓይንዋ፣ ጥርስዋ፣ አፍንጫዋ ይህ ቀረሽ የምትባል ልጅ አልነበረችም:: ውበትዋ እንደጠዋት ፀሐይ ፊትዋ ላይ በራ፤ ተንጸባረቀ፣ ደመቀ፡፡ ወደ አበባው ቦታ ተመለሰች:፡ ወፎች ስለእርስዋ የሚዘምሩ መሰላት።
ራስዋንም እንደ ንግሥት ለመቁጠር ቃጣች::

ተመልሳ ስትመጣ ዣን ቫልዣ በአያት ጊዜ ልቡ ደነገጠ፡፡ የኮዚት
👍194
ውበት በየቀኑ እየፈካ መሄዱን ቀደም ብሎ የተገነዘበው ቢሆንም ያን እለት ግን በጣም አስደነገጠው:: እርሱን እንደዚያ ያስደነገጠው ውበት የወጣቶችን
ልብ በቀላሉ ሊሰርቅ እንደሚችል አመነ፡፡
«እንዴት ቆንጆ ናት» አለ ለራሱ፡፡ «መጨረሻዋ ምን ይሆን? ማን
ይሆን ከእኔ ነጥቆ የሚወስዳት?» ሲል አሰበ:: በሚቀጥለው ቀን «እውነትም ቆንጆ ነኝ» ስትል ተናገረች:: ከዚያን ቀን ጀምሮ ስለምትለብሰው ልብስ ጥንቃቄ ታደርግ ጀመር:: ከዚያ በኋላማ
ኮዜት ከሰፈሩ ቆንጆዎች እንደ አንድዋ ከመቆጠር አልፋ ጥሩ ጥሩ ልብስም የምትለብስ ዘናጭ ልጅ በመባል በሰፈሩ እየታወቀችና ዝናዋ እየገነነ ሄደ።
አንድ ቀን ዝንጥ ብላ ለብሳ ወደ ውጭ ሊወጡ ሲሉ «አባዩ ዛሬ እንዴት ነው አለባበሴ?» ብላ ጠየቀችው::

ምኑ ይነገራል፧ በጣም አምሮብሻል» ሲል የሀዘን ስሜት እየተሰማው መለሰላት::

ይህን መልስ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ «አባዩ፣ እቤት ካንተ ጋር መቀመጡ በጣም ደስ ይለኛል» ትል የነበረችዋ ልጅ ሰበብ አስባብ እየፈጠረች «ልሂድ፣ ልሂድ » ሆነ፡፡ እውነትዋን ነው፤ ቆንጆ ሆኖ ቆንጆ ልብስ እየለበሱ ከቤት መዋል ምን ይባላል፡፡ እንዲህ አምራና ደምቃ የመስከረም አበባ በመሰለችበት
ጊዜ ነው ማሪየስ ስድስት ወር ሙሉ ከጠፋችበት በኋላ ያያት::

ልክ እንደ ማሪየስ ኮዜትም ከፍቅር ረመጥ ውስጥ ገብታ ለመቃጠል
ዝግጁ ሆነች:: ተፈጥሮ በሚደነቅ ሁኔታ እነዚህን ሁለት ወጣቶች ለማገናኘት ታጥቆ የተነሣ ይመስል ሁለቱም በየፊናቸው የሰው ያለህ የሚሉበት
ጊዜ ሲሆን ሁለቱ ቢገናኙ ማርና ወተት መሆናቸው አያጠራጥርም::
ሁለት ሰዎች በዓይን በመተያየት ብቻ ፍቅር አይዛቸውም የሚሉ
አሉ:: ግን መዘንጋት የሌለበት ፍቅር የሚጠነሰሰው በመተያየት መሆኑን ነው:: የተቀረው በኋላ ይቀጥላል፡፡ ልብን ከሁለት ከሚሰነጥቀው ከመጀመሪያው እይታም ይበልጥ የእውነተኛ ፍቅር ብልጭታ፣ ጥንስስ፣ እንቅልፍ የሚነሳና የሚያስደነግጥ የለም፡፡ ኮዜትና ማሪየስ ከአንድ የሽርሽር
ቦታ ብዙ እየተሰራረቁ መተያየታቸው የምናስታውሰው ነው::

ማሪየስ ኮዜት ከምትገኝበት ሲሄድ ምን ያህል ይፈራ፣ ይተባ፧ ምን
ያህል ይጨነቅ፤ ምን ያህል ያመነታም እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ለካስ ራቅ
ብሎ ተቀምጦ ኮዜትን በሩቁ ብቻ ሊያያት ያንገበግባት ኖሮአል:: አንድ ቀን ዣን ቫልዣን «አባባ፣ በዚህ በኩል እንሂድ እስቲ» አለችው ማሪየስ ወደ
ተቀመጠበት እያመለከተች፡፡ ይህን ያለችው ማሪየስ ወደ እርስዋ አለመምጣቱን በመገንዘብዋ ነበር፡፡ እርሱ አልመጣ ሲላት እርስዋ ወደ እርሱ ሄደች::
ያን እለት የኮዜት አስተያየት ማሪየስን አሳበደው:: የማሪየስ አመለካከት ደግሞ ኮዜትን አርበተበታት፡፡ ኮዜት እንዳፈቀረችው ማሪየስ እርግጠኛ ሆኖ ሲሄድ ኮዜትን ግን አስጨነቃት፡፡ ከዚያች ቀን ጀምሮ አንዱ ሌላውን ያመልካል፤ልባቸው በጽኑ ይፈላለጋል::
ኮዛት በመጀመሪያ የተሰማት በጭላንጭል የሚታይ የሀዘን ስሜት ነበር፡፡ የወደፊት ሕይወትዋ በጭንቀት ተሞልቶ የጨለመ መሰላት::
የወጣት ልጃገረዶች ልብ እንደ በረዶ ነው:: ልባቸው ገራገር ስለሆነ እንደ በረዶ የነጣ ሲሆን የፍቅር ፀሐይ የወጣለት በቶሎ ይሟሟል፡፡ በሕልምዋም
ሆነ በእውንዋ የሚታያት መሽኮርመም፣ መዳራትና መላፋት ይሆናል::ስለዚህ ከማሪየስ ጋር ይህን ለመፈጸም ፈለገች ፧ ጓጓች፤ ተመኘች:: በአንድ በኩል ማሪየስን በማድነቅ በሌላ በኩል መቼ ነው የማገኘው በማለት
ተጨነቀች::

ማሪየስ ማንና ምን እንደሆነ አታውቅም:: እርሱም ቢሆን ስለእርስዋ ያለው እውቀት ከዚህ የተለየ አይደለም:: ቃል አልተለዋወጠም፤ ሰላምታ
አልተሰጣጡም፤ አልተዋወቁም:: እውቀታቸው በዓይን ብቻ ሲሆን እንደ ሰማይ ከዋክብት በአካል ተራርቀዋል፡፡

በእለት ኑሮአችን ለእያንዳንዱ ሁናቴ ስሜታችን መልእክት
ያስተላልፍልናል፡፡ በዚህ ዓይነት ተፈጥሮ ማሪየስ በቤቱ አካባቢ ለመኖሩ ዣን ቫልዣን አስጠንቅቃዋለች:: ዣን ቫልዣ ያየው ወይም የሰማው ነገር
አልነበረም፡፡ ሆኖም አንድ ነገር እየዳበረ ለመምጣቱ ታውቆታል፡፡ ያቸው ተፈጥሮ ማሪየስን ከልጅትዋ አባት ጋር ፊት ለፊት አላጋለጠችውም፡፡ ነገር
ግን ፊት ለፊት ባይገጣጠሙም ማሪየስ ኮዜትን ለመፈለጉ ገብቶታል፡፡

ኮዜትን ለመጠየቅ አልደፈረም:: አንድ ቀን ግን ስሜቱን ለመደበቅ
አልቻለም:: ማሪየስን ባየው ጊዜ «ምን ዓይነት ልጅ ነው!» ብሎ በማንቋሸሽ ይናገራል::

ይህን ያለው ከአንድ ዓመት በፊት ቢሆን ኖሮ «ምነው፣ በጣም ደስ
ይላል» ትለው ነበር፡፡ አሁን ግን «ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም» እንዲሉ ይህን ብላ መናገር አልቻለችም:: ምናልባት ከኣሥር ዓመት በፊት ቢሆን ደግሞ «ልክ ነህ፣ ሁኔታው ይህን ያህል ደስ አይልም» ብላ በተናገረች፡፡
አሁን የደረሰችበት እድሜና ያደረባት የስሜት መቧጠጥ ግን ስሜትዋን ሰብሮ «የቱ፣ ያ ወጣት!» የሚል መልስ በማንቋሸሽ እንድትሰጥ ገፋፋት፡፡
ይህን መልስ የሰጠችው ልክ በሕይወትዋ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየችው አስመስላ ነው::

«እንዴት አላስብም» አለ ዣን ቫልዣ በልቡ:: በአጠገባችን ማለፉን እንኳን ልብ አላለችም፡፡ እንድታየው እኔው ራሴ ገፋፋኋት::
አይ የዋህነት! አይ ብልጠት!
ዣን ቫልዣ ልቡ ላይ አንድ ዓይነት ሕመም ተሰማው:: ኮዜት ፍቅር ሲይዛት ታየው፡፡ ይህ ደግሞ ቶሎ እንደሚሆን ተገነዘበ፡፡ ከፍቅር ማንቋሸሽ ይቀድም የለ!

ኮዜትና ማሪየስ በተያዩ ቁጥር እርሱ ያፈጣል፤ ኮዜት የፈገግታ አበባ ታስታቅፈዋለች፡፡ ዣን ቫልዣ ማሪየስን በዓይን አለንጋ ይገርፈዋል፡፡ ኮዜት እንዳታውቅበት ግን በተቻለ ሁሉ ይጠነቀቃል፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ከዚያ
ከሽርሽር ቦታ ሲሆን ከዚያ በኋላ ምን እንደተከተለ ሁላችንም የምናውቀው ነው::

ከዚያ ሥፍራ ሲቀሩ ኮዜት ጥያቄ አልጠየቀችም ፧ ተከፋሁም
አላለችም፡፡ ምክንያቱን ለማወቅ ብትጓጓም ስሜትዋን አምቃ ዝም አለች::ዣን ቫልዣ በፍቅር ሳቢያ ስለሚደርስ የውስጥ ጭንቀትና መከራ ልምድ የለውም፡፡ ስቃዩ እንደሚያስደስት፧ ስቃዩ እንደሚያስለቅስ አያውቅም::
ነገሩ «ያልተነካ ግልግል ያውቃል» ነው:: ኮዜት ስትደበር፤ ኮዜት ስትዘጋ፤ ኮዜት ስትከፋ እያየ ለማየት አልቻለም:: ማዘንዋን ግን ትንሽ ጠርጥሮአል፡፡
ነገር ግን፦ «ምን ያስከፋታል» በማለት እንደማጽናናት እርሱ ራሱ ቅር ተሰኘ፡፡

አልፎ ኣልፎ «ምን ነካሽ?» እያለ ይጠይቃታል፡፡

«ምንም» ብላ ትመልስለታለች::

አብረው ሲሆኑ ዝምታ ይሰፍን ጀመር፡፡ እርስዋ እንዳዘነችው እርሱም አዝኖአል:: ይህ በሚሆንበት ጊዜ ነው በተለይ «ምን ነካሽ?» እያለ
የሚጠይቃት::
እርስዋም ‹ምንም» ብላ አትተወውም:: ኣንዳንድ ጊዜ «አንተስ ኣባዬ ፧ ምንም አልሆንክም?» በማለት ትጠይቀዋለች::
«እኔ! ምንም፣ ምንም አልሆንኩም» ሲል ይመልሳል::
እነዚህ በፍጹም ልቦና የተዋደዱ ለረጅም ጊዜ አብረው የኖሩ ሁለት
ሰዎች አንዱ ለሌላው ስቃይ ምክንያት ሆነ:: ሆኖም «አንተ አስቀየምከኝ፣አንቺ አስቀየምሽኝ» አይባባሉም ፣ አልተቀያየሙም ፤ አልተኳረፉም:: በፈገግታ ይነጋገራሉ፡

💫ይቀጥላል💫
👍28
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#ዘጠኝ

የአስቴር ትልቋ ልጅ ዛፒ ትባላለች፡፡ ትርጉሙ ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ምናልባትም 'ሰይጣናዊ መዝገበ ቃላት የሚባል ነገር ካለ፣ ትክከለኛ ትርጕሙ እዛ ላይ ሳገኝ አይቀርም፡፡ እስከዛው
ግን በግምት “ዋጋ ቢስ' ብዬ ተርጉሜዋለሁ።

ዘር ከልጓም ይስባል እንዲሉ ቁርጥ እናቷን (ለነገሩ አባቷን የት አውቄው?)እኔ ከስምንተኛ ክፍል
ወደ ዘጠነኛ ክፍል ሳልፍ እሷ የሀያ አምሰት ወይም የሀያ ስድስት ዓመት ወጣት ነበረች፥ ተስፋ
የቆረጠች ወጣት፡፡ እናቷ አስቴርና ትንሽ እህቷ ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ ውጭ አገር ሲመለሱ
እሷ እዚሁ እኛ የነበርንበት ግቢ ውስጥ ከንድ ደስ የሚል የተረጋጋ ወጣት ጋር መኖር ጀመረች፣

ምናልባት እዚሁ የቀረችው ልጁን ስለወደደችው ይሆናል፡፡

መጀመሪያ መኪናውን ውጭ ጋር ያቆምና ተያይዘው ይሄዱ ነበር፡፡ ከመሄዳቸው በፊት ዋጋ ቢሷ ትጠራኝና አሸብር ኛ እችን መኪና ወልውል!” ትላለች፡፡

ዛፒዩ አሁን እኮ ነው ያሳጠብኳት!” ይላታል፡፡ እርሱ የዋጋ ቢሷ መልዕክት ተንቀጥቅጦ
የሚታዘዛት ሚስኪን መኖሩን ማሳየት መሆኑን መቼ አውቆ፡፡

ቆይታ እቤት እየገባ መቆየት ጀመረ፡፡

“አሽብር ና ለስላሳ ግዛ! ና ቢራ ግዛ” ብታምኑም ባታምኑም ኮንዶም ሁሉ ታስገዛኝ ነበር፡፡
መላላኬ ሳይሆን በዛ እድሜ ፋርማሲ ሂዶ ኮንዶም መግዛት ያሳቅቀኝ ነበር፡፡ ፋርማሲስቶቹ
በትዝብት ያዩኛል፣ “የተቀደደ ሱሪውን ሳይቀይር…” በሚል ግርምት…ሱሪው የተቀደደ ሰው
እንትን አያደርግም የተባለ ይመስል፡፡

ከዛ ማደር ጀመሩ፡፡ በጨለማ በዛ በኮረኮንች መንገድ ቢራ ተሽከሜ እጀን የፌስታሉ እጄታ እየከረከረኝ የተላላኩበት ጊዜ መቼም አይረሳኝም (እስከዛሬ እቃ በፌስታል መያዝ አልወድም፡፡ አቲዩ የግቢው በር ላይ ብርድ እያቆራመታት ቆማ ትጠብቀኛለች፤
ገብቼ ቢራውን ስሰጥ ዛፒ ልክ ከፍሪጅ ያወጣችው ያህል ከእጄ ላይ ትወስድና፣ እንካ ሁለት ፓኬት ሮዝማን ግዛና ና” ትላለች፡፡
በመጨረሻ ጠቅልሎ ገባና አብረው መኖር ጀመሩ፡፡ መኪና ማጠብ ቋሚ ስራዬ ሆነ፡፡ እውነቱን
ለመናገር ጥሩ ባል ነበር፡፡ ዋሲሁን ይባላል። ቤቱ የባለትዳር ቤት እንዲመስል የተቻለውን ሁሉ
ይጥር ነበረ፡፡ ዛፒ ግን የሚቋቋማት ዓይነት 'ሚስት አልነበረችም፡፡ ጉራዋ ፀጉር ያስነጫል፣ በውበቷ ስትመካ ልክ የላትም፡፡ የእናቷ ጫማ ውስጥ ዘላ የገባች ጉረኛ ! አቤት ጉረኛ ሴት እንዴት እንደምትቀፍ፡፡ ከምትናገራቸው አስር ዓረፍተ ነገሮች፣ አስራ አንዱ ስለራሷ ውበት፣ ስለቆዳዋ ጥራት፣ ስልጣቶቿ አለንጋነት፣ ስለልብስና ሽቶዎቿ ብራንድ በቀጥታ አልያም በተዘዋዋሪ ይተርካሉ ፡፡

ዘላ የተዘፈቀችበት ትዳር ከጭፈራ ቤት መዳራት በምን እንደሚለይ ገና ያልገባት አካሏ ብቻ
ህሊናዋን ጥሎ ያደገባት ከንቱ ነበረች፡፡ ዋሲሁን ውጭ መመገብ አይወድም፡፡ የታሸጉ ምግቦችን
ገና ሲመለከታቸው ያንገሸግሸዋል፡፡ እንጀራ በሽሮ ወጥ ነፍሱ ነው:፡ ዛፒ ታዲያ ቤት ውስጥ ለባለቤቷ ምግብ አብስሎ ማቅረብን በሴት ልጅ ላይ የሚፈፀም ታላቅ በደል አድርጋ ነበር የምታየው፡፡አበሻ ወንድ ጓዳለጓዳ ካልተንደፋደፈች ሚስቱ ሚስት አትመስለውም፡፡ ሴት አደባባይ መውጣቷ ያማቸዋል” የምትለው ከእናቷ የወረሰችው ዘይቤ አላት፡፡ በጓዳም በአደባባይም ምንም የማትፈይድ የወሬ ቋት፡፡ ኩኪስ አልያም ጭማቂ ነገር ከፍሪጅ ታወጣና ሶፏዋ ላይ እግሯን አጣጥፋ ቴሌቪዥን እያየች ትበላለች፣ ትጠጣለች፡፡ ስለፋሽን ሳታቋርጥ ትቀባጥራለች፤ በዓለም ላይ ስላሉ የቅንጦት ሆቴሎችና ጌጣጌጦች ዋ.….ው” እያለች ትቋምጣለች፡፡ ቤትም የለችም፡ የምትመኘውም ቦታ የለችም፡፡ የትም የሌሎች የውሀ ላይ ኩበት ነገር!!

ዋሲሁን ያደበትን የቤተሰብ ስነስርዓት፣ የኢትዮጵያዊነ ወግ ምሳ ተዘጋጅቶ፣ ቡና ተፈልቶ፣ ቤቱ
ሞቅ ብሎ እንደሚጠብቀው በማመን እንደ ኣባወራ
ምሳ ሰዓት ላይ ሲመጣ ዛፒ ጠረጴዛው ላይ እግሯን ሰቅላ ዙሪያዋን የጥፍር ቀለም ጠርሙሶች ከበዋት ቤቱ በአልኮል ሽታ ታፍኖ ስትቆነጃጅ
ያገኛታል፡፡ ማታ ሲመጣ ዛፒ ለባብሳ ኣንዲወጡ ስትጠብቀው ይደርሳል፡፡

ሀኒ ዎከ እናድርግ ትለዋለች፣ ባል ጋር መታየት እንጂ የባልን መሻት ማየት አልፈጠረባትም፣
የሆሊዉድ ተረቶች ባዶ ጭንቅላቷን ሞልተውት ነበር፡፡ ከንዱን ይዛ መንገድ ላይ ስትውረገረግ ብጤዎቿ፣ “ዋው ምናይነት ጥምረት ነው? ማች ያደርጋሉ" እያሉ ያወሩላታል፡፡
ሚስኪን ዋሲሁን ሳይወድ በግድ እግሩ እስኪቀጥን ሲዞር አምሽቶ እኩለ ሌሊት ላይ ስልችት
ብሎት ይመለሳሉ፡፡ የተሰቀለችበት ባለ ተረከዝ ጫማ ለመራመድ ስለማይመቻት ክንዱ ላይ
ተዘፍዝፋ ትወናገራለች፡፡

“ሃኒ ዲጄው ሽቶሽ ብራንዱ ምንድን ነው?' ሲለኝ ሰምተኸዋል?”

“አልሰማሁትም ይላል ትክት ብሎት፡፡

"ሃሃሃሃሃሃሃ ጠጥተህ ነበር ብዙ.ሰካራም ሃሃሃሃሃ” ትላለች እየተለፉደደች፡፡ አብሯት አይስቅም፡፡

"በናትህ ቀሚሴ ላይ ዋይን ደፋብኝ ያ ወልካፋ አስተናጋጅ" ትላለች ረዥም የራት ቀሚሷን
እያሳየችው::

“ይታጠባል.ደግሞ አንቺ ስታልፊ እኮ ነው የገጨሽው” ይላታል ስልችት ብሎት፡፡

“እዚህ አገር ምን ላውንደሪ አለ? ሰባት መቶ ዶላር የወጣበት ቀሚስ እንደቀልድ - ምን አይነት
አገር ነው? ብላ ቀሚሷ ባአደባባይ ባለመከበሩ አስራ አምስት ቀን ታወራለች፡፡ ስለ ተራ ቀሚስ
ሳይሆን ስለ ባንዲራ መደፈር የምታወራ ነው የምትመስለው::
ጧት ተነስቶ በተሳሳት መንፈስ ወደ ስራ ሲሄድ ዛፒ አትሰማም አትላማም ተኝታለች፡፡ ምሳ
ሰዓት እንደገና ጓደኞቿ ጋር እንደሄደች ትደውልለትና፣ “ምሳህን ውጭ ብላ ሃኒ" ትለዋለች፣ በዛውም አያችሁ ባሌን ሳዘው!' እያለች በከንቱ ጓደኞቿ፡፡ ምሳ፣ ራት፣ ቁርስ በአበሻ ባህል
ከምግብ የዘለለ ፋይዳ ያለው ጉዳይ መሆኑ ለዛፒ አልታያትም ነበር፡፡

የቤተሰብ እትብት ከእናት ማዕድ ጋር እንደሚያያዝ ማን ይመከራታል? ዋሲሁን ለአንድ ዓመት አብሯት ቆየና ከፉ ደግ ሳይናገር፣ አንቺ ጋር እንግዲህ በቃኝ ብሏት ሄደ...!! መሄድ ብቻ
አይደለም፡ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ድል ባለ ሰርግ ሌላ ሴት አገባ፡፡ ዛፒ መጀመሪያ፣ “ጥርግ
ይበል! ለሞላ ወንድ!" አለች፡፡ ቆይታ፣ “ይሄ ችጋራም ፒዛ እንኳን መብላት ያለማመድኩት እኔ
ነበርኩ፡ ጥጋበኛ የደሀ ልጅ” ማለት ጀመረች፡፡ በመጨረሻ ፎቶውን እያየች ማልቀስ ሆነ ስራዋ፡፡

ዛፒ ሲበዛ ቆንጆ ናት፡፡ ልብሶቿ ጌጣጌጦቿ የብዙ ሴቶች የቁም ቅዠት፡፡ ግን ዋሲሁን ከሄደ በኋላ
ወንድ የሚባል አልቀርብ አላት፡፡ ይፈሯታል፡፡ የተጋነነ ቁንጅናዋና ውድ ጌጣጌጦቿ የማትደፈር
ግዛት ስለሚያስመስሳት የሚመኛት እንጂ ድፍሮ የሚቀርባት ጠፋ፡፡

የአበሻ ወንድ ተመካከሮ ሸሸ

ዛፒ ታዲያ የለየላት ስካራም ሆነች። ማታ ማታ ሰክራ ትመጣና፣
በምን አባታችሁ ዕድላችሁ ነው እኔን የምትስሙት!? እዛ የጉራጌ ጫማ ደንቅረው የቻይና ሱሪ ውስጥ የተቆጠሩ ኋላ ቀር ሠራተኛ ሴቶቻችሁ ጋር ኑሩ! ጎ ቱ ሄል ቆሻሾች! ቦርጫሞች! ቀ'ጂም'
አጠገብ አልፋችሁ የማታውቁ” እያለች በረንዳዋ ላይ ቆማ ድፍን የአበሻን ወንድ ትሳደባለች ።

በጣም ስከር ብላ ጨርቅ ሆና ያመጣት ባሰታከሲ ግቢ ውስጥ ደግፎ አስገብቷት ሲመለስ
ትጠራኛለች፣

“አሸብር ና ጫማዩን አውልቅ!”
👍26👏1
ጫማዋን አወልቅላታለሁ፡፡ እች የውሻ ልጅ! የእግሮቿ ጣቶች የመላዕክትን ጣቶቻ ይመስላሉ፤
አረዛዘማቸው፣ ጥራታቸው፡፡
ቀስ በል እንተ ! ሶሉን ልትገነጥሰው ነው፡፡ የእናትህን ኮንጎ ጫማ አደረከው፡፡ ይሄኮ አራት መቶ ዶላር የወጣበት ነው። በዚህ ችጋራም አገር ወረቀት ሲመነዘር ስንት ይሆናል አንደኛ እይደል ከክላስ የወጣኸው” (እደግጣለሁ፡፡ ማን ነገራት? ስለመፈጠሬም የማታስታውስ ሴት ደረጃዬን አወቀችው፡፡)

እስኪ አስበዋ፣ እኔ የቻይና ሸራ ጫማ የምደነቅር መሰለህ?” እየለፈለፈች መኝታ ክፍሏ
አስገባታለሁ፡፡ አቤት ሽቶዋ! ቆም ብላ አልጋውን በጥላቻ ታየውና፣ ወደ ሳሎን ትገፋኛለች፡፡
አንዘፋዘፍኩ ሳሎን ሶፋው ላይ አስተኛታለሁ፡፡ እየለፈለፈች እንቅልፍ ይወስዳታል፡፡

ጧት ምንም እንዳልተፈጠረ አታናግረኝም፣ መኖሬም ትዝ አይላትም፡፡

ዛፒን እጠላታለሁ፡፡ጉረኛ ናት፡፡ ሰው ትንቃለች፡፡ ግን የማይደበቀው ሀቅ ከእናቷ ትሻላለች፡፡ድንገት አቲዬን ትጠራትና፣

“ያውልሽ ይሄን ውሰጅ!” ብላ ገና ያልተከፈት ውድ ሽቶ ትሰጣታለች፡፡


አቲዬ ግን እጇን የሆነ ነገር ሲቆርጣት ብቻ ቁስሉ ላይ ስትረጨው ነው የማያት፡፡

ሊላ ቀን አቲዩን ትጠሪትና፣ እስቲ ቡና አፍይ!" ትላታለች፡፡ አቲዬ ሽር ጉድ ብላ፣ እጫጭሳ ቤቱን ነፍስ ትዘራበታለች፡፡ ዛፒ ግን ቡና አትጠጣም፡፡ አቲዬም ስለምትፈራ አትጠጣም፣ አነሳሰታ ወደ ቤት ትመለሳለች፡፡

ዛፒ እዕምሮዋ ጤነኛ አለመሆኑን መጠራጠር ጀምሬ ነበር፡፡

አንድ ቀን ሰላማዊት የምትባል የሰፈራችን ልጅ አገባችና ሰፈሩ በጭፈራ ቀውጢ ሲሆን ዛፒ
ጠራችኝ

"ማናት ያገባችው?” አለችኝ፡፡

ነገርኳት፡፡

“ቆንጆ ልጅ ናት እንዴ?”

“አንድ ቀን ጋሽ ዋሲሁን ጋር ሆናችሁ አሟት በመኪና ሆስፒታል የወሰዳችኋት ልጅ ናት እኮ::

“እና እሷ ልጅ ቆንጆ ናት እንዴ
ምን ልበል፣ ጨነቀኝ፡፡ “እኔ እንጃ!” አልኩ፡፡

ዝም ስትል፣ የጨረሰች መስሎኝ ልሄድ ስል፣

“መልኳ ከእኔ ይበልጣል ?” አለችኝ፡፡

“ኧረ…" ብዬ ሳቅኩ፡፡

“ምን ያስቅኸል? ዝም ብለህ የጠየቅኩህን አትመልስም?" አለች በቁጣ--

ፈገግታዬ ፊቴ ላይ ከስም፣ “አንች ላይ ጫፍሽ ላይ አትደርስም፣ እንች እኮ በጣም ቆንጆ ነሽ
እልኳት፡፡ ከልቤ ነበር የተናገርኩት፡፡

ትኩር ብላ አየችኝና፣ ወደ መኝታ ክፍሏ ገባች፡፡ የክፍል ደረጃዬን የማታውቀው እንዳስገረመኝ
ቁንጅናዋን አይቼው የማላውቅ መስሏት ነበር መሰል፡፡
“ምን አስለፈለፈኝ” እያልኩ ወደ ቤቴ ገባሁ፡፡ ግን ያደነቅኳት ሳይሆን ልኳን የነገርኳት ያህል
ውስጤን ደስ ብሎት ነበር፡፡

እየው እንግዲህ፣ “የነገር አመጣጥ እንደ ውሀ አፈሳሰስ ነው ነው የሚለው መጣፉ፡፡ ይሄን
ነው ጠብጠብጠብ ፈስስ፣ ከለል.ጎረፍ ዥቅዥቅዠቅ፣ ከዛ ግንድ የላ ድንጋይ ይጠራርገዋል፡፡
ጠብታው መኝታ ቤቱ ነው፣ ግንዱ ሰርቪሲ.:: አስቴር አወቀ ዛቲ መኝታ ቤት ድምጽዋን ከፍ
ኢድርጋ ትዘፍናለች፡፡ ምን እያለች እኔንጃ ! ምናልባት እንዴት እንደምትጎርፍ፣ እየመከረቻት
ይሆናል፡፡ አስቴር እኮ ዘፋኝ አይደለችም መካሪ ናት፡፡ ሰንቱ መኝታ ቤት እየገባች በጆሯቸው
የሚድንም የማይሆንም ነገር ሹክ ስትል ከርማለች፡፡ አስቴር ሴረኛ ናት! የዛፒ ዓይን እንደ አንቴና መዞ ወዲያው አሳድጎኛል፣ ሳድግ የባሰ ፈሪ ሆንኩ፡፡...

አላለቀም
👍373👎1🤔1
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

መጨረሻው እንደ አጀማመሩ አልሆነም

ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ኮዜት ከሀዘንዋ እያገገመች መጣች:: የጊዜው
መርዘም፣ ወጣትነትዋ፣ የአባትዋ ፍቅርና የአካባቢዋ ማማር ቀስ በቀስ ሀዘንዋን እንድትረሳ ረዱዋት:: ቀን አልፎ ቀን ሲተካ፧ ወር አልፎ ወር ሲተካ የፍቅርዋ ሙላት በየቀኑ በጠብታዎች እየጎደለ ሄደ:: ወላፈኑ በርዶ
ወደ መጥፋት ተቃረበ፡፡ ሆኖም ረመጠ ጨርሶ ስላልጠፋ ማቃጠሉ፣ ማስጨነቁና ማሰቃየቱን ትቶአታል እንጂ ጨርሶ አልተወገደም::

አንድ ቀን በድንገት ማሪየስ ታወሳት:: «ምን!» አለች:: «ደግሞ ከየት መጣ? ረስቼው አልነበረም እንዴ!» በማሪየስ በኩል ደግሞ «ምነው ከመሞቴ በፊት አንድ ጊዜ ብቻ ባየኋት!» የሚልበት ወቅት ነበር፡፡

የማን ጥፋት ነው? የማንም::

አንዳንድ ሰው ከገባበት ወጥመድ በቀላሉ መውጣት አይችልም፡፡
ማሪየስ የዚያ ዓይነት ሰው ነው:: ከደረሰበት ሀዘን እንደ ኮዜት በቀላሉ ሊላቀቅ አልቻለም:: ሀዘን ውስጥ ገብቶ እዚያው ነው ተዘፍቆ የቀረው።

አንድ አጋጣሚ ይከተላል፡፡ በትልቁ በር በኩል ከአንድ ግቢ ውስጥ
አንድ እንደ መቀመጫ የሚያገለግል ጥርብ ድንጋይ ነበር፡፡ እንደ ሴት ጎፈሬ
የተከረከመ የዛፍ አጥር በአጠገቡ ስለነበር ማንም ሰው በመንገድ ሲያልፍ ወደ ውስጥ ማየት አይችልም፡፡ ነገር ግን ከውስጥ ያለ ሰው ከፈለገ እጁን
በአጥሩ ቀዳዳ በማበጀት አሾልኮ በውጭ የሚያልፈውን ሰው ማየትና መጨበጥ ይችላል፡፡

አንድ ቀን ማታ ዣን ቫልዣ ወደ ውጭ ወጥቶ ነበር፡፡ አየሩ ጥሩ
ስለነበር መሸት ሲል ኮሴት ከዚያ ድንጋይ ላይ ተክዛ ቁጭ ብላለች፡፡ የጥንት ትዝታዋ ተቀሰቀሰባት፡፡ ጊዜው ጨለምለም ብሏል፡፡ የእናትዋ መንፈስ ከዚያ ያለ መሰላት፡፡ ከተቀመጠችበት ብድግ ብላ ሄደች::

ቀደም ሲል ዝናብ ዘንቦ ስለነበር ሳሩ ያቀዘቅዛል፡፡ «ይህስ ጉንፋን
ያሲዛል ፧ ብቀመጥ ይሻላል» ብላ ወደ ድንጋዩ መቀመጫ ስትመለስ
መቀመጫው ላይ አንድ ነገር አየች:: አንድ እጥፍጥፍ ብላ የተጠቀለለ ነገር ከትንሽ ጠጠር ጋር ተያይዟል:: ከመቀመጫው ተነስታ ስትሄድ ከዚያ
አልነበረም::

ኮዜት ገርሞኣት «ምንድነው እሱ?» ስትል ራስዋን ጠየቀች:: መቼም ሰው ካላስቀመጠው በራሱ ኃይል ሊመጣ እንደማይችል ተረዳች:: ፍርሃት፣ፍርሃት፣ አላት፡፡ ድንጋዩን መንካት አልደፈረችም:: ወደኋላ ሳታይ ቤትዋ ሮጠች፡፡ ቤትዋ ከገባች በኋላ በርና መስኮት ዘጋጋች፡፡ መቀርቀሪያዎቹን
ሁሉ ቀረቀረች:: ከጥቂት ጊዜ እረፍት በኋላ ‹አባባ ተመልሷል እንዴ?»
ስትል ቱሴይን ጠየቀቻት::

«ኧረ አልተመለሰም» አለቻት::

ክፍሎቹ በሙሉ ተዘግተው እንደሆነና ከቤት ውስጥ ሰው እንዳለ እንድታይ ቱሴይን አዘዘቻት:: አጎንብሳ ከአልጋዋ ስር እንዲሁም ቁም ሣጥንዋን ከፍታ ሰው እንዳለና እንደሌለ አጣራች:: ከተኛች በኋላ ያ ያየችው
ጠጠር ተራራ አክሉ በውስጡ ዋሻ እንዳለበት አለመች::

ጠዋት ፀሐይ ስትወጣና ጨለማ ለብርሃን ቦታዋን ስትለቅ ማታ
እንደዚያ ያስፈራሩን ነገሮች እንደሚያስቁን ይታወቃል:: ኮዜት ስትነቃ ማታ እንደዚያ ያስፈራት ነገር ቅዠት መስሎ ታያት:: ስለምን ነበር የምቃዠው?» ስትል ራስዋን ጠየቀች::

ልብስዋን ለብሳ ወደ አትክልቱ ቦታ ሄደች:: ስትፈራኛ ስትቸር ማታ
ተቀምጣበት ወደነበረው የድንጋይ መቀመጫ ሄደች:: የተጠቀለለው ነገር ከዚያው ቁጭ ብሉአል:: በመጀመሪያ ትንሽ ፈርታ ነበር:: በኋላ ግን ፍርሃቱ ተወገደላት:: ደግሞም በጨለማ የሸሸነወ ነገር በብርሃን እንጓጓለታለንና ምን እንደሆነ ለማየት ቸኩለች፡፡

«አይ ምን አስፈራኝ፤ ፈትቼ ልየዋ» አለች ለራስዋ:: የተጠቀለለውን
ነገር አንስታ ከፈታታችው በኋላ አብሮ ታስሮ የነበረውን ድንጋይ ጣለችው::

አድራሻ ያልተጻፈበትና በውስጠ ወረቀት ያለው እንደ ደብዳቤ ያለ ነገር መሆኑን ተገነዘበች:: ወረቀቱን ከውስጡ ሳታወጣ አገላብጣ አየችው:: አሁን መፍራትዋ ቀርቶ «ከውስጡ ምን አለ» በማለት በመጓጓት ለማወቅ ፈለገች::
ፖስታውን ከፍታ ከውስጡ የነበረውን ወረቀት አወጣች:: በጥሩ የእጅ ጽሑፍ እንደ ጥቅስ ያሉ ነገሮች ተጽፎበታል፡፡ የገጹ ብዛት ከአንድ በላይ ነው:: እያንዳንዱ ገጽ ላይ ቁጥር ተጽፎበታል:: ሆኖም እያንዳንዱ ገጽ ሞልቶ የተጻፈበት ሳይሆን መሐሉ ላይ ብቻ ነው የተጻፈው:: የመጻፊያ ቦታ እያለ ወደ ሚቀጥለው ገጽ ይዞራል::

ፊርማ ወይም ስም ካለበት በሚል በችኮላ ፈለገች፤ ግን አላገኘችም::
ለማነው የተጻፈው? ለራስዋ እንደሆነ ጠረጠረች፡፡ ምክንያቱም እርስዋ ተቀምጣበት ከነበረው ሥፍራ ነው የተገኘው፡፡ ታዲያ ማነው ጸሐፊው?
ግራ ገባት:: በመገላመጥ አካባቢዋን ቃኘች፡፡ ከርግቦች በስተቀር ምንም ነገር የለም:: ወረቀቱን ማንበብዋን ቀጠለች::
ቀጥሎ የተመለከተው ነበር በወረቀቶቹ ላይ የተጻፈው::

«ዓለም ተጨብጣ አንዲት ትንሽ ነገር ስትሆን፧ አንዲት ትንሽ ነገር
ደግሞ ተነፍታ እግዚአብሔርን ስታክል ፍቅር ትባላለች፡፡ ፍቅር ነፍስን ትመስላለች፤ አፈጣጠራቸው አንድ ነው፡፡ እንደ ነፍስ የመንፈስ ቅዱስ
ብልጭታ ኣለባት፡፡ እንደ ነፍስ ግን አትገድፍም፣ አትነጣጠልም
አትጠፋም፡፡ የእሳት ረመጥ ስትሆን በውስጣችን አለች፤ ዘላለማዊ ናት..ማለቂያና መደምደሚያ የላትም፡፡ ረመጥዋ በምንም ነገር አይጠፋም::
ከአጥንታችን ውስጥ እንኳን ገብታ ስትፋጅ ይሰማናል:: እንዲሁም ከሰማየ ሰማያት ወርዳ፧ ከአካል ውስጥ ዘልቃ ትገባለች፡፡ ሆኖም ስታንፀባርቅ አካላችን ውስጥ በጉልህ እናያታለን፡፡

«ፍቅር! አድናቆት! የሁለት የሚግባቡ አእምሮዎች ፣ የሁለት
የሚወሳሰቡ ልቦች፣ የሁለት አካልን ሰነጣጥቀው የሚገቡ ዓይኖች ያላት ብርሃን! አንቺ ደስታ ወደ እኔ ትመጪያለሽ ወይስ አትመጪም! ፍቅር
ብቸኝነትን ሲያጠቃ አብሮ የሚጓዝ፤ የሚንሸራሽር! የተባረኩ ቀኖች! የሰዎችን እድል፣ የሰዎችን እጣ ፈንታ ለመካፈል መላእክት ከሰማየ ሰማያት ወርደው
በዚህች ምድር ሲኖሩ በሕልሜ ያየኋቸው ነው የመሰለኝ፡፡ አይ ፍቅር!

«ዘላለማዊ ከማድረግ በስተቀር ማንም ከሁለት ከሚዋደዱ ፍጡሮች ደስታ ላይ የሚጨምረው ነገር የለም፡፡ በእርግጥ የፍቅር ዘላለማዊነት
ከፍቅር ዘመን በኋላ የሚታከል ነው:: ግን የፍቅርን መጠን፣ የፍቅርን ግለት ለማሳደግ ከፍቅረኞቹ ከራሳቸው በስተቀር ማንም ሊያስቀረው አይቻለውም፡፡ ፍቅር የሰዎች ፍጹምነት ይታይበታል፡፡

«ከዋክብትን የምናይበት ምክንያት ሁለት ነው:: ይኸውም
ስለሚያብረቀርቁ ወይም ምንነታቸውን ስለማናውቅ! ከጎናችን ግን ከከዋክብት
ይበልጥ ምሥጢሩ ያልታወቀ የላመ፣ የለሰለሰና የሚያንፀባርቅ ፍጡር አለ... ሴት::

«ድንጋይ ከሆንክ ትልቅ ድንጋይ ሁን፤ የዛፍና የቅጠላቅጠል ዘር
ከሆንክ ስሜት፤ ሰው ከሆንክ ደግሞ ፍቅር ይኑርህ::

«ወደ ሽርሽሩ ቦታ ትመጣለች? የለም ጌታዬ! በየሳምንቱ እሑድ ወደ ቤተክርስቲያን ትመጣ የለ? የለም መምጣቱን ትታለች:: አሁን ከዚሁ ቤት ውስጥ ነው የምትኖረው? የለም ለቅቃለች፡፡ አሁን ከየት ሰፈር ገባች?
አድራሻዋ አይታወቅም፡፡ ስትሄድ አልተናገረችም? አልነገረችንም:: ምን ዓይነት የተዳፈነ ጨለማ ነው እባካችሁ የአንድን ነፍስ አድራሻ አለማወቅ!

በፍቅር ምክንያት የምትጨነቅ፣ የምትሰቃይ ነፍስ! አሁንም ውደድ፤ በይበልጥ አፍቅር፡፡ በፍቅር መሞት ማለት በፍቅር መኖር ማለት ነውና፡፡
👍17😱1
«መወደድ እንዴት ያለ ትልቅ ፀጋ ነው:: ስለዚህ መውደድ፣ ማፍቀር
በበለጠ ፀጋን መጎናጸፍ ሲሆን በፍቅር ስሜት ልብ ይደነድናል፣ ጀግና ይሆናል ፤ ይጠራል፡፡ ማረፊያው የከበረ፣ መቆሚያው ከፍ ያለ ይሆናል፡አንጎል በፍቅር ከተሞላ ተልካሻ አሳብ ከጭንቅላት ውስጥ መግባቱን ያቆማል፡፡ አንዱ ለሌላው ያለው ፍቅር ሲያከትም የፀሐይ ብርሃን አብራ በማክተም ምድር ትጨልማለች::

ኮዜት ደብዳቤውን በተመስጦ አንብባ ስትጨርስ ስሜትዋ ረካ፡፡
ጽሑፉ ጉልህ ሆኖ ነው ያገኘችው:: እያንዳንዱ መስመር ዓይንዋን በአዲስ ብርሃን የሞላው:: እያንዳንዱ ቃል ልብዋን አፈነደቀው:: ገዳም ውስጥ
የተማረችው ትምህርት ዘወትር ይመክራት የነበረው ስለነፍስዋ ነበር እንጂ በወንድና በሴት መካከል ስላለው ፍቅር አልነበረም:: ይህ ጽሑፍ ግን
በተጣጣመና በጣፈጠ ቋንቋ ስለፍቅር ዘላለማዊነት ፣ ሀዘንና ደስታ፣ መጨረሻና መጀመሪያ ገለጸላት:: አንድ ሰው የፀሐይ ጨረርን በእጁ ጨብጦ በድንገት የወረወረባት መሰላት:: በእነዚያ ጥቂት መስመሮች ውስጥ
የጋለ ስሜትን፣ ግልጽ በሆነ ተፈጥሮ የተቀደሰ በጎ ምግባርን፤ ስፍር ቁጥር የሌለው ሀዘንና ደስታን፤ የተጨቆነ ልብን፣ የመንፈስ እርካታን አየች::

ታዲያ ይህን ጽሑፍ ማን ሊጽፈው ይችላል? ማነው ወደ እርስዋ
በአጥር ኣሾልኮ የሰደደው? ጥያቄዎቹን ለመመለስ ለአንድ አፍታ እንኳን አላመነታችም:: ከአንድ ሰው ብቻ ነው ሊመጣ የሚችለው ስትል ደመደመች::

‹‹እሱ ራሰ ነው!»

የሽርሽሩ ቦታ ትዝ አላት፡: ላይ ላዩን በጣም ደስ ሲላት ውስጥ
ውስጡን ግን የፍቅር ጥማት አንገበገባት፡፡ ይህን የመሰለ ደብዳቤ የጻፈላት ሰው ያን እለት ማታ ከአጠገብዋ ነበር ማለት ነው:: እጁን በአጥር አስገብቶ
ነው ደብዳቤውን የወረወረላት፡፡ «ከዓይን የራቀ ከልብ ራቀ» እንዲሉ ካአጠገበዋ ባለመኖሩ ልትረሳው ስትል እንደገና አገኛት:: አድራሻዋን እንዴት አገኘው?

በእርግጥ ረስታው ነበር እንዴ? የለም፣ በጭራሽ! የዚህ ዓይነት አሳብ ጭንቅላትዎ ውስጥ በመግባቱ እብድ አደረጋት፡፡ ሁልጊዜም እንዳፈቀረችውና
እንዳደነቀችው ነበር እንጂ አልረሳችውም፡፡ እሳቱ ተዳፍኖ ነበር እንጂ አልጠፋም፡፡ የፍቅር አመድ ስለበዛ ፍሙ ተቀበረ እንጂ አለመጥፋቱን ታውቃለች:: አሁን አመዱ ሲነሣ ጊዜ የፍሙ ወላፈን ሁለንተናዋን አቃጠለው፤ ለበለበው:: ደብዳቤው እንደ ብልጭታ ተፈናጥሮ ከልጁ ነፍስ
ወደ እርስዋ ነፍስ ተሻገረ፡፡ ብልጭታው አካልዋ ውስጥ ሲፋፋ ተሰማት:: የጽሑፉ እያንዳንዱ ቃል የፍቅር እሳት ብልጭታም መሰላት፡፡ «አዎን፣ አሁን አስታወስኩ፤ አሁን ገና ገባኝ» አለች፡፡ «ይኼ ሁሉ ስሜት ያኔ
ዓይኖቹ ውስጥ ያየሁት አይደለም!»

ወደ ቤትዋ ተመለሰች:: የክፍልዋን በር ዘግታ እንደገና ደግማ ደጋግማ አነበበችው ፤ በቃልዋ አጠናችው:: በደምብ ከያዘችው በኋላ ወረቀቱን ሳመችው:: እንደ ሕፃን ልጅ ከጡትዋ መካከል አስገብታ ታቀፈችው:: አሁን
አለቀ፡፡ ኮዜት ማለቂያና መጨረሻ ከሌለው የፍቅር ማጥ ውስጥ ተዘፈቀች፡፡በሩ ወለል ብሎ እንደገና ተከፈተ::

ያን እለት ቀኑን ሙሉ ደብሮአት ዋለ:: ማሰብ እንኳን አልቻለችም።
አሳብዋ ሁሉ እንደ ጢስ ተነነ እንደ ጉም ፎለለ፡፡ የምትይዘውንና
የምትጨብጠውን ስላጣች ያን እለት ነገሩ ሁሉ እንዲያው ጭንቅ፣ እንዲያው ጥብብ፣ ያዝ ለቀቅ ሆነ፡፡ ልብዋ እየመታና ሰውነትዋ እየተንቀጠቀጠ አንድ
ነገር ተስፋ አደረገች:: ምን? ለማወቅ አይቻልም፤ ምክንያቱም የተጨበጠ ነገር አይደለምና፡፡ ለራስዋ ቃል ለመግባት አልደፈረችም፡፡ ሆኖም ምንም
ነገር ብትጠየቅ እምቢ ለማለት አልደፈረችም:: ነገር ሁሉ አዛንተዘ ሆነ፡፡ ታዲያ ፍቅር አዛንተዘ አይደለም እንዴ? እኔ አንጃ ፍርዱን ለአንባብያን፡፡

ፊትዋ መከፋቱን፤ ስርዋ መሸማቀቁን፤ ጉሮሮዋ መጠማቱን ከሁሉም በላይ አንጀትዋ መንሰፍሰፉ መሸሸግ አልቻለችም።
አዲስ ዓለም ውስጥ
መግባትዋን እየታወቃት እውነት ነው እንዴ ስትል ራስዋን ጠየቀች፡፡
በዚህ ጊዜ ከጡቶችዋ መሀል በመወሸቅ የታቀፈችው ደብዳቤ ትዝ አላት። ጫን በማለት ከልብዋ ጋር አጣበቀችው:: የወረቀቱ ጫፍ ገላዋን ሲቧጭረው
ተሰማት፡፡ በዚያን ሰዓት ዣን ቫልዣ ቢያያት እንዴት በደነገጠ፡፡ ከዚያ በፊት ያላየው የደስታ ወላፈን ከዓይኖችዋ እንደዚያ ሲፍለቀለቅ ቢያይ በእርግጥ ይደነግጣል:: ልብዋ ምን ያህል እንደተጨነቀ ግን ልብዋ ውስጥ ግን ልቧው ውስጥ ገብቶ ማየት አይችልም::

«ወይ ጉድ!» አለች፣ «በእርግጥ እርሱ ነው! እርሱ ለእኔ የላከው
ነው? መላእክት ከሰማየ ሰማያት ወርደው አማልደውኛላ! እነርሱ ጣልቃ ገብተው መልሰው አመጡልኛ! እንዴት ያለ እድል ነው» ስትል አሰበች፡፡

ማታ መሸት ሲል ዣን ቫልዣ እንደ ልማዱ ወጣ አለ:: ኮዚት ጥሩውን ቀሚስ መርጣ ለበሰች:: ፀጉርዋን ወርቅ አድርጋ አበጠረችው፡
የለበሰችው ቀሚስ ከወደ ደረትዋ መቀስ የጎዳው ነበር:: ከወደ አንገትዋ መቀሱ አላርፍ ብሎ ስለሸረከተወ፡ ወደ ጡትዋ በጣም ዝቅ ብሏል፡፡ ዓይን በቀላሉ ያርፍበታል ነገር ካልፈለጉ በስተቀር፣ አደባባይ የሚወጣበት ዓይነት ልብስ አደለም አለ አይደል፣ አንዳንድ ወጣት ልጃገረዶች «ኧረ ትንሽ ያስፈራል» የሚሉት አይነት ቀሚሱ ግን የሚያሳፍር ሳይሆን ልብን
ስቅል፣ የሚያሳምር፣ ፉንጋ ቢሆኑ እንኳን ቆንጆ የሚያደርግ ዓይነት ነበር በጣም አቆነጃት ለምንድነው እንዲህ እንደማለዳ ፀሐይ ያጌጥሽው?» ብላ ብትጠየቅ መልስ የላትም፡፡ ያጌጠችውና ምርጥ ልብስ የለበሰችውም
ይታወቃት ነው::

ወደ ውጭ ለመውጣት ፈልጋ ነው? አይደለም:: ከቤት የሚመጣ ሰው አለ? የለም::
ወደ ግቢው የአትክልት ቦታ ሄደች:: ቱሌይ ማድቤት ውስጥ ሥራ ላይ ነች:: በመስኮት ወደ ውጭ ማየት ትችላለች:: ከግቢው ውስጥ መንሸራሸር ጀመረች:: የዛፎችን ቅርንጫፍ ትነካካለች፡፡ አንዱን ለቅቃ ሌላውን ትይዛለች:: በቁመትዋ ልክ የተንዠረገጉ ዛፎች በብዛት ነበሩ:: በትናንትናው ምሽት ተቀምጣበት ከነበረው መቀመጫ ደረሰች፡፡ ከደብዳቤው ጋር
የተወረወረው ድንጋይ እዚያው እንዳለ ነው::

ቁጭ አለች:: ልክ ፍቅረኛዋን የምትደባብስ ይመስል በለስላሳ እጆችዋ ድንጋዩን በማሻሸት አመሰገነችው:: «ምነው ተጫጫነኝ፣ ማን አለ ከአጠገቤ»
እንደሚባለው ሁሉ ምንም እንኳን በዓይንዋ ባታየውም ከአጠገብዋ ሰው እንደቆመ ከበዳት:: ይህ እንዴት ሆነ ቢባል በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡
ፊትዋን አዙራ ከተመለከተች በኋላ ብድግ አለች::

💫ይቀጥላል💫
👍35
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስር

....ጥቁር አምበሳ፣ ኮከብ ፅባህ፣ ምኒሊክ፣ መነን፣ አዲስ ከተማ፣ ድልበር፣ ቦሌ ከሚማሩ የአስረኛ
ክፍል ተማሪዎች ሁሉ፣ “አንደኛ ጎበዝ አንተ ነህ” አሉና የምስክር ወረቀት ሸለሙኝ፡፡ እኔ ግን ጥቁር አምባሳ፣ ኮከበ ፅባህ፣ ምኒሊክ፣ መነን፣ አዲስ ከተማ፣ ድልበር፣ ቦሌ ከሚማሩ ሴት ተማሪዎች ሁሉ አንደኛ ቆንጆ የሆነችው ዮርዳኖስ የት ተቀምጣ ይሆን እያልኩ በዓይኔ ከተሰበሰቡት ሰዎች መሀል እየፈለግኳት ነበር፡፡

ዮርዳኖስ ማለት ማንም አይደለችም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመሬት ተነስታ ጉንጬን የሳመችኝ ልጅ ናት፡፡ ጉንጬን ሳይሆን በቀኝ በኩል ከከንፈሬ ጥግ ሁለት….አረ አንድ ተኩል ሴንቲ ሜትር ርቀት ላይ ነው የሳመችኝ (ለሞላ ጉንጭ፡፡)

ዮርዳኖስ ቀይ ልጅ ናት፡፡ ለነገሩ ቀይ ሳትሆን ጠየም ያለች ግን ቀይ ዳማ እንደሚሉት ሳትሆን
አትቀርም፡፡ አቦ የራሷ ጉዳይ ገደል ትግባ ብትፈልግ ኤጭጭጭ!! ይሄው ስንት ጊዜ ሌትም ቀንም
ዮርዳኖስ ቀይ ናት ቀይ ዳማ እያልኩ ስዛብር ማደር ከጀመርኩ፡፡ እንኳን ሴት ልጅ፣ ቆንጆ ወጣት ሴት ልጅ፣ ነፍስ ካወቅኩ ጀምሮ ሰው ሲስመኝ የመጀመሪያዬ ስለነበር ዮርዳኖስ ጉንጬን
ሳይሆን ልቤ ላይ እንደሳመችኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ማስረጃ ብባል፣ ከዛን ጊዜ ጀምሮ አተነፋፈሴ ልክ አይደለም፤ ሳያት የሆነ ነገር ያፍነኛል፡፡ ሳላያት እንደ ነብር አዳኝ ትንፋሼን ውጬ በጉጉት በዓይኔ እፈልጋታለሁ፡፡ ሳላያት ታፍኜ ሳያትም ታፍኜ ልሞት ሆነ፡፡

"አንቺ ዮርዳኖስ የምትባይ፤ ምን ቆርጦሽ ነው ኧረ ከከንፈሬ አንድ ተኩል ሴንቲሜትር ርቀት
ላይ በሚሞቅና በሚለሰልስ እርጥብ ከንፈርሽ የሳምሽኝ?” ብላት ደስታዬ፡፡ ግን ታፍኛለሁ!!

አርብ ቀን ከትምህርት ቤት ወጥቼ ወደ ቤቴ እሄዳለሁ፡፡ ምንም እያሰብኩ አልነበረም፡፡ ዝም
ብዬ እየተራመድኩና በግዴለሽነት ሁሉንም ከፊቴ ያለውን ነገር እየተመለከትኩ እራመዳለሁ፡፡

“አሸብር፣” አለችኝ ከኋላዬ፡፡

ስሜ ሲጠራ የምደነግጠውን ያህል የሰይጣን ስም ቢጠራ እንኳን አልደነግጥም፡፡ ሰዎች ስሜን ሲጠሩኝ ከዝምታዬ ባሕር በምላሳቸው መንጠቆ ጠልፈው ያወጡኝ ይመስለኛል፡፡

ጭራሽ ጠሪዎ ዮርዳኖስ ስትሆን ደግሞ፣ በመንጠቆው ላይ መረብ ተተበተብኩ !! ከእኔ ጋር
ብዙ ሰዎች ወደኋላ አብረው ዞሩ፡፡ ሰዉ ሁሉ ሳይጠራ ሲዞር፣ ጠሪዋን ተመልከቶ ደሰ ካሰችው
ስሙን አሸብር ሊያስብል ያሰበ ይመስል እኔ ለተጠራሁት መዓት ሰው ዞረ፡፡

ዮርዳኖስን ዞሬ አየኋት፡፡ ጉርድ ቀሚሷ በደንብ አላራምዳት ስላለ በእጇ ሰብሰብ አድርጋ ወደ
እኔ ትጣደፋለች፡፡ እግሯ ቀይ ነው፡፡ ባቷ ፍርጥም ያለ ከእድሜዋ በላይ ትልቅ የሚያስመስላት
ነው፡፡ ባቷ ብቻውን አስራሁለተኛ ክፍል ይመስለኛል። ጡቶቿ ደግም እዛና እዚህ ይላጋሉ:: ስትጣደፍ፣ በሁለት እጆቿ ክንዶች ገፋ አድርጋ ታረጋጋቸዋለች፡፡ ፀጉርዋ አጭር ነው፡፡ ግንባሯ ትንሽ ወጣ ያለ፡ ቀረበችኝ ፈገግ አለች፡፡ ዓይኖቿ እንዴት ያምራሉ፡፡

ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍ አሁን ስትጠራኝ መኪና እየነዳሁ ቢሆን ኖሮ ከዓይኖቿ ለማምለጥ ስል
ፊት ለፊት የሚያላዝነው ቦት መኪና ጋር እላተም ነበር፡፡ የያዘው ነዳጅ ይዘረገፍና ከዮርዳኖስ
ፈገግታ እሳት ለኩሶ ጭሱ ፀሐይን ጥቁር ጉልቻ እስከትመስል የሚያጥን፡፡ ሰማይ የሚነካ እሳት
ይነሳ ነበር፡፡ በቁሜ ቅዥት ስጀምር ታወቀኝ፡፡

“እንዴት ነው የምትርጠው ወተት ጥደሄል ቤትህ ?” ቀለደች።

አልሳቅኩላትም፡፡ ስላልሳቅኵላት ግን ራሷ ከመሳቅ አልታቀበችም፡፡ እየሳቀች ወሬዋን ቀጠለች፡፡

"ቤትህ በዚህ በኩል ነው እንዴ ?”

“እዎ"

“እኔ ግን አይቼሀ አላውቅም"

ዝም አልኩ፡፡ ካላየችኝ ምን ይሁን፣ ወሬዋን ቀጠለች፡፡
አዎ

አዎ

አዎ

“አዎ ብቻ ነው እንዴ የምታውቀው ?
“አይ” እላታለሁ፡፡ አነጋገሬ ሴት የመፍራት ሳይሆን ሰው የመሰልቸት ነበር፡፡ እንዳንዴ የሰዎች ንግግር ይረዝምብኛል፡፡
"ሰላም ሲሉኝ ይረዝምብኛል፡፡ ሰላም፤ እጃቸውን አንስተው፣ ግንባራቸውን ነቅንቀው፣ ፈገግ
ብለው፡፡ አንዳንዴም እጃቸውን ለሰላምታ ዘርግተው፣ ይሄን ሁሉ አድርገው፣ “ሰላም” ብቻ "

ዝም አለች፡፡ አብረን ሄድን ሄድንና የሆነ መገንጠያ ላይ ስንደርስ ክንዴን ይዛ አቆመችኝና ተንጠራርታ ሳመችኝ፡፡ ምንም አላማ የሌለው፣ ምክንያት የሌለው ወይም “ደፋር ነኝ አየህ" የሚል ምናልባትም፣ “ዘመናዊ ነኝ መንገድ ላይ የወንድ ጉንጭ መሳም አልፈራም” አሳሳሟ
የሆነ ድምፅ አለው፣ የሚያፏጭ ዓይነት ድምፅ፡፡ የመምጠጥ አይነት ድምፅ፡፡ የበዛ ግለኝነቴን
ምጥጥ አድርጋ የሐሳብ ሀይቄን አደረቀችው፡፡ የሰው አለማያ ሆንኩ !! ባደረቀችው የብቸኝነት
ኩሬ ራሷን ሞላችው፡፡እዚህ ዮርዳኖስ የምትባል ውሃ የሞላችው ባህር ውስጥ ልቤ አምልጦኝ ገባ፡፡ ይሄው አስባታላሁ፣ የተረገመች ዮርዳኖስ ! እየጠበቀችኝ ይሁን እየተገጣጠምን ብቻ ከዛን ጊዜ በኋላ በየቀኑ እንገኛኝ ጀመረ፡፡ ሲቆይ ግን ጉዳዩ የነፍስ ቀጠሮ ሆነ፡፡ ጠበቅኩሽ ላለማለት በቀስታ እየተራመድኩ እጓዛለሁ፣ ከየትኛውም ርቀት ላይ አውቃታለሁ፡፡

ፊት ለፊት ሳላያት መንፈሷ እዛ አካባቢ ካረበበ ትካሻዬ ሹክ ይለኛል፡፡ ትከብደኛለች፣ “ሃይ አሹ” የሚል ድምጽ እጠብቃለሁ፡፡ ሀይ አሹ ትለኛለች ውስጣችን ያውቃል እንደምንጠባበቅ፡፡ ከዛም ታወራኛለች።

"ዛሬ ይበርዳል!”

"አዎ"

"ሆም ወርክ ሰራህ ?”

"አዎ"
.
.
.
“አዎ ብቻ ነው የምታውቀው፡፡”

"አይይ"። አሁን ግን ምን ማውራት እንዳለብኝ እያሰብኩ ነው ችግሩ፣ አስቤ ሳልጨርስ እንደርሳለን፡፡

ስንመለስም እንገናኛለን፡፡ ስንመለስ መለያያችን ላይ ትስመኛለች፣ “ቻው” ከሚል ስርቅርቅ ያለ መለያየቱ ያስከፋው ድምፅ ጋር ከንፈሯ ጆሮዬ ላይ ያፏጫል፡፡

አንዴ መሀል ጉንጩ ላይ፣ አንዴ ዝቅ አንዴ ከፍ እያለች ትስመኛለች፡፡ በየቀኑ ትስመኛለች፡፡ ዝም ብዬ አሳማለሁ፡፡ ከንፈሯ ክብ ነው፤ በሃሳቤ ስትስመኝ ከብ ቅርፅ ጉንጩ ላይ የታተመ ይመስለኛል፥
የሳምንቱ ክቦች ተቆላልፈው፤ ቅዳሜ የኦሎምቲካ አርማ ጉንጩ ላይ ታትሞ በጉልህ ይታየኛል፡፡
እንዱ ከብ እንደ ደቡብ ኦሞ ሴቶች፣ ከንፈሬን ተልትሎ ከንፈሬ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁት በህልሜ!

አንድ ቀን ግጥም ጻፍኩ፡፡ በህይወት ዘመኔ የጻፍኩት ብቸኛ ግጥም ነበር፡፡ ወደፊትም ግጥም
አልጽፍም " ግጥም ያስጠላኛል፡፡ ሰው ዝም ማለት እያለለት፣ ለማውራት ቃል መጠምዘዝ
መድከም ምን ያደርግለታል? ቢፅፍ ላይጠቀም፣ ባይፅፍ ላይጎዳ ባይ ነኝ፡፡ ደግሞ አዲስ
ግጥም ሰምቼ አላውቅም፡፡ ግጥሞች ሁሉ አንድ ናቸው፤ ደራሲያቸው ይለያይ እንጂ ባይ ነኝ::

እኔን የገረመኝ (ርእሱ)

እኔን የገረመኝ፣
እኔ የጠላሁትን፣
እኔነት ሳትጠላ፤
ልጅቱ ስትስመኝ !!

በቃ !! ይሄው ነው ግጥሙ።

ግጥም ማለት ቤት የሚመታ፣ ቀለሙ፣ ስንኙ የሚሉ ሰዎችን ተዋቸውና ግጥም ማለት እስክርቢቶ ሳትጨብጥ ወረቀት ፊትህ ሳይነጠፍ አንደ አፍ ወለምታ ከከንፈርህም፣ ከነፍስሀም፣ ከአዕምሮህም
የሚያመልጥ እውነት ነው፡፡ ለምሳሌ በዚች ዓለም ላይ ከሰማኋቸው ግጥሞች አሳዛኙ የአቲዬ ግጥም ነው፡፡ ርእሱ፣ “እሺ፤ ግጥሙም፣ “እሺ” አበቃ፡፡

ማንም ለጀመረው የትዕዛዝ ስንኝ፣ አቲዩ 'እሺ' የሚል ግጣም እየሰራችለት፣ የማንም ቤት
እንዲቆም አድርጋለች። የእኔ እናት ገጣሚ ናት፡፡

“ቤት ጥረጊ!”
“እሺ!"
“ልብስ እጠቢ”
“እሺ”
“ሂጂና ሳሙና ግዢ!
"እሺ"
“እንጀራ ጋግሪ”
"እሺ
“ደመወዝሽን ሌላ ቀን ውሰጂ!”
"እሺ"
ግጥም ይሄ ነው !! ከትዕዛዘ እኩል ይሁንታው ዜማ ሲፈጥር፡፡ እናም ያሉትን ሲሆኑ፡፡
👍39
ቤት መምታት ይሄ ነው፡፡ መጥፎ ቃል የደሀ ስጋ ለብሶ አዛዥ ቤት ሲያድር፣ በዓመቱ አይኑ
በምኞት የሚባብር 'ገጣሚ' “ውዴ ዘላለም ልፈጥፈጥልሽ፣ ልቆራመትልሽ” ሲል አይገባኝም፡፡
ግጥም ከቃል ሲሰረሰር ሳይሆን፣ ከነፍስ ሲምዘዝ ከሕይወት ሲቀመም ነው ቤት የሚመታው፡፡
ቢሆንም ግጥም ገጠምኩ፡፡ አላሰብኩም፣ አልደለዝኩም፣ አልቆረብኩም፡፡ አንድ ደብተሬ ጀርባ ላይ በቀጥታ ጻፍኩት፡፡ ያውም ኬሚስትሪ የሚባል ትምህርት እየተማርን ልክ ስልክ ቁጥር እንደሚጽፍ ሰው ሳላስብ ግጥም ጻፍኩ፡፡ ከብዙ ዓመት በኋላ ይሄን ግጥም ያሳየሁት ገጣሚ፣
“ጭብጡ የላላ ወደታች የተጻፈ ስድ ፅሁፍ ነው የሚመስለው” አለኝ፡፡ ጉዳዬ አልነበረም፡፡ ድሮስ
መቼ ግጥም መጻፈ ገረመኝ፡፡ በልጅቱ ጉንጬን፣ ያውም አንድ ተኩል ሳንቲሜትር ለከንፈሬ
የቀረበ ቦታ ላይ መሳሜ እንጂ !!

ዮርዳኖስ አንድ ቀን ጠራችኝ፣ “አሹ” ብላ !!

"አሹ” ማለት ለካ አሸብር ማለት አይደለም፤ በጭራሽ አሹ ማለት ከአሸብር ጋር የሚገናኘው
ሁለቱም አጠራር ስለሚያስደነግጡኝ ብቻ ነው እንጂ አሸብር "አሹ” አይደለም፡፡ ከየት አመጣቸው ግን እች ዮርዳኖስ !! ደግሞ “አሹ" ከአሸብር ይረዝማል፡፡ አሹ፣ ሙሉ ቀን ጆሮ ላይ ያቃጭላል
አይገርምም ?

ከተማሪዎች ሁሉ አንደኛ ወጥቼ የተሸለምኩ ቀን ሌሊት ከእንቅልፌ ነቃሁ፡፡ ምን እንዳነቃኝ
እኔንጃ፡፡ ፀጥታው የነቃ ያስተኛል እንኳን የተኛ ሊቀሰቅሰ፡፡ ግን ነቃሁ፡፡ ነቃሁና ልክ ዓይኔን
ስከፍት፣ ዮርዳኖስ ያንኳኳችወን በር የከፈትኩ ይመስል ምስሏ ፊት ለፊቴ ተደቀነ፡፡ ልትስመኝ
ስታሞጠሙጥ፣ ስትስቅና “አሹ" ስትለኝ፣ “ፍቅር ይዞኛል” የሚል የማልፈልገው ዓረፍተ ነገር
ከምኔ እንዳመለጠ ሳላውቅ ፈነዳ ቡምምምምምምምምምምምምምም ፍቅር እርፍ !

ልክ እንደ ግጥሙ ያልፈለኩት እንባ ጉንጬ ላይ ተንኳለላ፡፡ በምድር ላይ አለኝ ከምለው አንድ
የሆነ እምነት የተካድኩ መሰለኝ፡፡ ለነብስ ጉዳይ የተበደርኩት ብር ከኪሴ የጠፉ ያህል ተሰማኝ፡፡
እንባዬን ጠረግኩና መብራቱን አበራሁት። ፊት ለፊት ያለው ግድግዳ ላይ በፌስታል የተሰቀለ የአቲዬ ልቃቂት፡፡ ራቅ ብሎ ትንሽ መጋረጃ እንደ ዕቃ ቤት የምንጠቀምባትን ቦታ የከለለች፣ ከመጋረጃዋ ፊት ልፊት አቲዬ ፍራሽ ላይ አሮጌ ብርድ ልብስ ለብላ ኩርምት ብላ ተኝታለች፡፡ ቤታችን አስጠላኝ፡፡ራሴ አስጠላኝ፡፡ አስረኛ ከፍል አስጠላኝ፡፡ ከአሁን በኋላ ስንት ዓመት ተምሬ ነው ስራ የምይዘው?

አቲዬ ድንገት ባነነችና፣ “አሸብር ምነው አመመህ እንዴ?” አለችኝ፣ ከወገቧ ቀና ብላ፡፡ ዝም
ብዬ አየኋት፡፡ አቲዩ እያረጀች ነው፡፡ ደረቷ ክስት ብሏል፡፡ ፊቷ ላይ ማዲያት ነገር አለ፡፡ ግንባሯ ላይ ብዙ መስመሮች ተጋድመዋል፡፡ አንገቷ ስር ያለው ቆዳዋ ተሸብሽቧል፡፡ እስከዛሬ
አላየኋትም ወይስ “እውር ያደርጋል" የሚሉት ፍቅር የእኔን ዓይን ገለጠው ገመናዬን አሳይቶ፣
ልክህን እወቅ! ሲለኝ፡፡ አቲዬን ስራ እስከምይዝ በምን ላፅናናት?

“አቲ ደስ ብሎኝ ነው አልኳት ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ።

"እሰይ፣ አረ ደስ ይበልልኝ" ከለች ከእኔ የበለጠ ፈገገ ብላ፡፡ ምኑንም ሳትሰማ፣ ምን ተገኘ? እንኳን አላለችኝም፡፡ በቃ ደስ ካለኝ ደስ ይላታል፡፡

“ከአዲስ አበባ ተማሪዎች ሁሉ አንደኛ ወጥቼ ሰልፍ ሜዳ ተማሪዎች ፊት ተሸለምኩ” አልኳት፡ አዲስ አበባ ያልኩት ሆን ብዬ ነበረ፡፡ 'የገፋሽ ሕዝብ ሰነፍ ነው፣ ያንከራተተሽ ሕዝብ ልጆች
በአንቺ በተንከራታቿ፡ በአንቺ ልጅ አፈር ድሜ ግጧል፡፡ ተበልጠዋል፡፡ በእጅ አዙር በልጠሻቸዋል ለማለት፣ ሌላም ለማለት

አቲዬ ፊቷ በፍርሀት ተወረረ፣ “ልጄን የሰው ዓይን ውስጥ ሊያስገቡብኝ” አለች።

“አቲዩ ደግሞ፣ ሁልጊዜ እንታያይ የለ" አልኳት፡፡ ዓይን ውስጥ ግን ጎብቻለሁ ልክ ነው፡፡
ዮርዳኖስ የምትባል ቡዳ በልታኛለች በከንፈሯ !!

"በል ጧት ሂድና ማለፍህን ንገራት!" አለችኝ በኣገጪ ወደ ዛፒ ቤት እየጠቆመች፡፡ አቲዬ
ከሚገርመኝ ባህሪዋ ማንንም በስም አትጠራም፡፡ ተመልከቱ ምን ያህል እንደተበደለች እች
ሴት፡፡ የሰውን ስም መጥራት በራሱ መናቅ እንዳይመስልባት ትፈራለች ትፈራለች ! እናም
ለዛፒ ምን ብዬ እንደምነግራት አሰብኩ፡፡

'ዛፒ አንደኛ ወጣሁ ዛፒ አለፍኩ..ዛፒ ሰካራም..ዛፒ ጠብራራ ዮርዳኖስን አፈቀርኳት…
ኡፍፍፍፍፍፍ ላብድ መሰለኝ፡፡ መብራቱን አጠፋሁት፡፡ ጨለማው ውስጥ ዮርዳኖስ ገጭ አለች እች ግንባራም ! እግሯ ቀይ ነው፡፡ ጡቶቿ ትልልቅ ናቸው:: ስትራመድ ይነቃነቃሉ። ግን ጡት ሴቶችን ይከብዳቸዋል…አይከብዳቸውም? ታዲያ 'ዮርዲ ለምንድን ነው ስትራመድ ጎበጥ የምትለው፡፡

ዮርዲ” ነው ያልኩት ? ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ከአቲዬ ቀጥሎ በዚች ምድር ያቆላመጥኩት ስም እነሆ..

አላለቀም
👍225
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


....ልክ ፍቅረኛዋን የምትደባብስ ይመስል በለስላሳ እጆችዋ ድንጋዩን በማሻሸት አመሰገነችው:: «ምነው ተጫጫነኝ፣ ማን አለ ከአጠገቤ»
እንደሚባለው ሁሉ ምንም እንኳን በዓይንዋ ባታየውም ከአጠገብዋ ሰው እንደቆመ ከበዳት:: ይህ እንዴት ሆነ ቢባል በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡
ፊትዋን አዙራ ከተመለከተች በኋላ ብድግ አለች:: እሱው ነበር:: ቆብ
ወይም ኮፍያ አላጠለቀም:: ሰውነቱ ገርጥቶአል፡፡ ትንሽ ከሳ ያለ ሰውነት ያለው ሲሆን የለበሰው ልብስ ጠቆር ያለ ነው፡፡ ፊቱ ጎልቶ ይታይ እንጂ አፍንጫው ሰልከክ ያለ ለመሆኑ ይታያል::

ኮዜት ብትደነግጥም የጩኸት ድምፅ ለማሰማት አልደፈረችም::
አንድ ነገር ወደፊት የሳባት ስለመሰላት ወደኋላ ሸሸት አለች:: ልጁ ከነበረበት አልተነቃነቀም:: ዐይኑን ለማየት ባትችልም በሀዘን መሞላቱን ገመተች::

ኮዜት ወደኋላ ስትሸሽ ከግንድ ጋር ስለተላተመች ያንኑ ግንድ ተደግፋ
ቀረች:: ዛፉን ተደግፋ ባትቆም ኖሮ እጅ እግርዋ ስለዛለባት ትወድቅ ነበር፡፡ዛፉን ተደግፋ እንደቆመች ድምፁን ሰማች:: ያን ድምፅ ከዚያ በፊት ሰምታው አታውቅም:: በጣም ዝግ ብሎ ነበር የሚናገረው::

«ይቅርታሽን፣ እዚህ ነው ያለሁት፡፡ ልቤ ሊፈነዳ ነው:: መኖር እየተሳነኝ ነው ከዚህ የመጣሁት፡፡ ከመቀመጫው ላይ የወረወርኩትን ፅሑፍ አንብበሽዋል? ለመሆኑ ማን እንደሆንኩ አውቀሽኛል? አትፍሪኝ::ጊዜው በጣም
ቆይቷል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የተያየንበት ቀን ታስታውሺዋለሽ?
ዘወትር ትሄጅበት የነበረው የሽርሽር ቦታ! በአጠገቤ ያለፍሽበት ቀንስ ቀኖቹ ሰኔ 16 እና ሐምሌ 2 ነበሩ፡፡ አሁንማ ዓመት ሊሞላው ምን ቀረው።
ዓይንሽን እንኳን ሳላይ ብዙ ጊዜ አለፈ፡፡ ማታ ማታ ከዚህ እመጣለሁ አትፍሪ፣ ግድ የለሽም፣ ከዚህ ማንም የለም:: ከዚህ የምመጣው የመኝታ ክፍልሽን መስኮት በሩቁ ለማየት ነው:: ከዚህ አካባቢ በምመጣበት ጊዜ
ደግሞ ድንገት በአካባቢው ካለሽ እንዳትደነግጪ እያልኩ ስራመድ
በዝግታ ነበር፡፡ አንድ ቀን ስትዘምሪ ሰምቼሽ በጣም ደስ አለኝ፡፡ ከክፍልኝ ውስጥ ሆነሽ ስትዘምሪ መስማቴ ያስከፋሻል? ጉዳት ያለው አይመስለኝም። አየሽ፣ አንቺ እኮ ለእኔ መልአኬ ነሽ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እስቲ ከዚህ እንድቀመጥ
ፍቀጂልኝ፡፡ በቅርቡ እንደምሞት አውቃለሁ፡፡ ይህን ብታውቂ! እኔ እኮ እንደ አምላክ ነው የማመልክሽ! ይቅርታ አድርጊልኝ፤ ንግግር አላውቅም
ከአንቺ ጋር ማውራቴን ረስቼአለሁ፡፡ ምናልባት ሳላውቀው አናድጄሽ ወይ አበሳጭቼሽ ይሆናል፡፡ አዘንሽብኝ?

«ወይ እማዬ!» አለች፡፡ ልክ እንደሚሞት ሰው ተዝለፈለፈች፡፡

ከነበረበት ወደ እርስዋ ሮጠ፡፡ ከወደቀችበት እቅፍ አድርጎ አነሳት!
ምን እንደሚያደርግ ሳይታወቀው በጣም በመጭመቅ አቀፋት:: እየተንገዳገደ ወደ ላይ ብድግ አደረጋት፡፡ አካሉ በጭስ የተሞላ ይመስል ሰውነቱ ውስሳ
እየተነነ የሚሄድ ነገር እንዳለ ተሰማው:: መንፈሳዊ ተግባርም የሚያከናው መሰለው፡፡ ምንም እንኳን ከልቡ አስጠግቶ ቢያቅፋትም የፍቶተ ስሜት ጨርሶ አልተሰማውም፤ እውነተኛ ፍቅር የፍቶተ ሥጋ መርካት አይደለምና፡ ልጁ ከእውነተኛ ፍቅር ወጥመድ ውስጥ ለመግባቱ ምልክት
ነበር፡፡

እጁን ይዛ ወደ ልብዋ አስጠጋችው:: ወረቀት ከጡቶችዋ መኖሩን ተገነዘበ፡፡ ዝግ ባለ ድምፅ ተናገረ::

«እንግዲያውማ ትወጂኛለሽ ማለት ነዋ!»
ጆሮን በኃይል ካላቀኑ በማይሰማ በጣም ዝቅ ባለ ድምፅ መልስ
ሰጠችው::

«እስቲ ዝም በል፤ እሱንማ የምታውቀው ነው::»

በሀፍረት የቀላው ፊትዋን ላለማሳየት ኩራት በተሰማውና በፍቅር በሰከረው ወጣት ብብት ስር ራስዋን ደበቀች::

ከድንጋዩ መቀመጫ ላይ ቁጭ ሲል እርሱዋም ከአጠገቡ
አለች:: ዝምታ ሰፈነ፡፡ ከዋክብት ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል:: እንዴት ነው ከንፈሮቻቸው የተገናኙት? እንዴት ነው አእዋፍ በዚህ ሰዓት ማዜም
የጀመሩት? እንዴትስ አበቦች ሊፈኩ ቻሉ?
አለቀ! በቃ ! ሥሮቻቸው የተነቀሉ እስኪመስላቸው ተሳሳሙ::

የሁለቱም ሰውነት ነፋስ እንዳወዛወዘው ቅጠል ተንቀጠቀጠ፡፡ በጨለማ
የሁለቱም ዓይኖች ቦግ ስላሉ ተፋጠጡ፡፡ ብርዱ አልተሰማቸውም፤ ድንጋዩ
አልቆረቆራቸውም፤ መሬቱና ሳሩ አልቀዘቀዛቸውም:: አሁንም በመፋጠጥ እየተያዩ ነው፡፡ ልባቸው በአሳብ ተሞልቷል፡፡ ሳይታወቃቸው እጅ ለእጅ
ተጨባብጠዋል፡፡

ለማንኛውም እንዴት አድርጎ ከአጥር ግቢው ውስጥ እንደገባ
አልጠየቀችውም፤ ለመጠየቅም አልፈለገችም፡፡ የእርሱ ከዚያ መገኘት እንግዳ ነገር
አልሆነባትም::

አልፎ አልፎ የማሪየስ ጉልበት የኮዜትን ጉልበት ሲነካ ሁለቱም
በደስታ ይፈካሉ፡፡ ቆይታ ኮዜት አንዳንድ ቃል ትወረውራለች፡፡ ስትናገር ነፍስዋ ከከንፈርዋ ጫፍ ላይ እንደሆነች ከከንፈርዋ ጋር አብሮ ተንቀጠቀጠ ለማለት ይቻላል፡፡

ቀስ በቀስ ዝምታው ተወግዶ ማውራት ጀመሩ፡፡ እንደገና የፍቅር
ስበታቸው ሞልቶ ስለፈሰሰ ዝም ተባባሉ፡፡ ምድርም ዝም አለች፡፡ ነፋስ እንኳን «ዝም በል» ብለው ያዘዙት ይመስል ፀጥ አለ፡፡ እንደገና ጨዋታ ጀመሩት፡፡ እነዚህ ሁለት እንደ ጥቅምት ውሃ የጠሩ ፍጡሮች ስለነበሩ ስላለፈው ምኞታቸው፣ ወፈፍ አድርጎአቸው ስለፈጸሙት ተግባር፣ ስለደስታ
ዘመናቸውን ፣ ስለተከፉበት ጊዜ እንዲሁም አንዱ ሌላውን ምን ያህል ይመኝ እንደነበር አንድም ነገር ሳይደባበቁ ተጫወቱ፡፡ አንዱ ስለሌላው ስለነበረው
ምኞትና አድናቆትም ተነጋገሩ፡: ሳይተያዩ ሲቀሩ ሁለቱም ምን ያህል ተስፋ ቆረጠው እንደነበር ተገላለጹ፡፡ ከሁለቱም ልብ ውስጥ የነበረው ሁሉ እንደ ውሃ ፈሰሰ፣ ተንቆረቆረ:: ስለዚህ ከአንድ ሰዓት በኋላ ወጣቱ የወጣትዋ፣
ወጣትዋ የወጣቱ ሕይወት ማለት እርሱ እርስዋን፣ እርስዋ እርሱን ሆኑ፡፡አንዱ ሌላው ልብ ወስጥ ዘልቆ ገባ፡፡ አንዱ የሌላው ጌታ ሆነ፡፡ አንዱ በሌላው ረካ፤ ፈካ፤ ተደሰተ፡፡

ልባቸው ውስጥ የነበረው ነገር ተሟጥጦ ሲያልቅ ጭንቅላትዋን
ከትከሻው ላይ አሳርፋ ጥያቄ ጠየቀችው::

«ስምህ ማነው?»

«ስሜ ማሪየስ ይባላል» አለ::

«የአንቺስ?»

«ኮዜት እባላለሁ፡፡››
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ማምለጥ

ምንም እንኳን ቴናድዬ የታሠረው ከተለየ ክፍል ውስጥ ቢሆንም
እርሱና ሌሎች ሦስት ሽፍቶች የማምለጥ አድማ ይመታሉ፡፡ ሁለቱ ሽፍቶች ከምድር ቤት ውስጥ ሲሆኑ ቴናድዬ ብቻውን ፎቅ ላይ ነበር፡፡ ከአደሙ
መካከል አንደኛው አደገኛነቱ ታውቆ እንዲሁ ለብቻው ነበር የታስረው::

በምን ተአምር ጠርሙስ ቪኖ እንዴት ሊያስገባ እንደቻለ ባይታወቅም መጠጡ ቴናድዬ ክፍል ውስጥ ተገኝቷል ይህ መጠጥ በውስጡ ሱስ
የሚያሲዝ እንደ ሐሺሽ ያለ ቅመም እንደነበረበት ይነገራል

መቼስ በእያንዳንዱ እስር ቤት ውስጥ እስረኞች እንዲያመልጡ
የሚተባበሩና እምነታቸውንና መሐላቸውን ለገንዘብ የሚሰጡ ጉበኞች ወይም ሌቦች ወይም ቀጣፊዎች አይታጡም: እንደነዚህ ያሉ ሰዎች ከደመወዛቸው
በላይ ገቢ አላቸው::

ሁለቱ ሽፍቶች አንድ ቀን ጠዋት ማምለጣቸውና ከመንገድ
የሚጠብቋቸው ለመሆኑ የሚያወቁ ሌሎች ሁለት ሽፍቶች ከውስጥ ይቀራሉ እነርሱም ለማምለጥ ዘዴ ይፈጥራሉ በአጋጣሚ በእለቱ በረዶ የተቀላቀለበት ከባድ ዝናብ ይጥል ስለነበር በዚህ አጋጣሚ በመጠቀምና ጨለማን ተገን
በማድረግ እነዚያ ሁለት ሽፍቶች በፈጠሩት ዘዴ ተጠቅመው ለማምለጥ ችለዋል::
👍21👏21😁1
ከእስር ቤቱ እንዳመለጡ ቀደም ሲል አምልጠው የነበሩትን ሁለት
ጓደኞቻቸውን አገኙ ሰዎቹ ከተለያዩ አካባቢዎች ቢታሰሩም እንዴት
አድርገው አቅድ እንዳወጡና እንደተመካከሩ አይታወቅም፡ ለምሳሌ ባመለጡበት ሌሊት ቴናድዬ ሳይተኛ ድምፅ እስኪሰማና ምልክት እስኪሰጥ
እስከ ሌሊቱ ሰባት ሰዓት ድረስ አፍጥጦ ጠብቋል እንደ ነፍሰ ገዳይ ተቆጥሮ እጅግ በጣም ይጠበቅ የነበረው ይኸው ሰው ማምለጡ ግራ የሚያጋባ ነው፡ ከነበረበት ክፍል ጠመንጃ የያዘ ዘብ ይቆም ነበር በከባድ የብረት ሰንሰለት ታስሮአል በየእለቱ በአሥር ሰዓት ፈታሽ እየገባ
ያየዋል: እግር ብረቱን ይመረምራል ይኸው መርማሪ ማታ ማታ እየመጣ በዓይነ ቁራኛ ይጠብቀዋል ለእስረኛው የተፈቀደለት ነገር ቢኖር የሚሰጠው ደረቅ ዳቦ አይጥ እንዳይበላበት ሰክቶ ከግድግዳ ላይ እንዲያንጠለጥልበ አንድ ሾል ያለ ብረት ነበር አንድ ቀን ከጠባቂዎቹ አንዱ የቴናድዬ
አደገኛነት በመገንዘብ ከብረት ይልቅ የሾለ እንጨት እንዲሰጠው
አሳስቦ ነበር።

ከሌሊቱ በስምንት ሰዓት የጠባቂ ለውጥ ተደረገ: መርማሪው
ክፍሎቹን ጎበኘ፡፡ አዲስ ነገር አላየም አስር ሰዓት ላይ የጠባቂ ለውጥ ለማድረግ ሲመጡ ቀደም ሲል የተቀየረወ ጠባቂ ቴናድዬ ተኝቶበት ከነበረው ክፍል ውስጥ ለጥ ብሎ ተገኘ: ወደ ውስጥ ቢገባ ቴናድዬ አልነበረም:: እግሩ የታሰረበት ወደ 25 ኪሎ የሚመዝን የእግር ብረት
ወለሉ ላይ ወድቋል እርሱ የነበረበት ክፍል ጣራ ቆርቆሮ ተነቅሏል፡፡ከክፍሉ ውስጥ የተከፈተ ግማሽ ጠርሙስ ቪኖ ተቀምጧል:፡ ጠባቂው
እንቅልፍ የወሰደው ያንን ስለጠጣ እንደሆነ በኋላ ተደርሶበታል፡ የጠባቂው ጠመንጃ ከእጁ ላይ የለም።

ቴናድዬ የታሰረበት ክፍል ሦስተኛ ፎቅ ላይ ስለነበር ከዚያ እወርዳለሁ ብሎ ሲታገል አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል ብለው ጠባቂዎቹ ጠረጠሩ ወደ
ጣራ ወጥተው ሲመለከቱ አንድ የተንጠለጠለ ገመድ አዩ ሆኖም ገመዱ አጭር ስለነበር ከመሬት የሚያደርሰው አልነበረም:: ነገር ግን ጣራ ለጣራ ጥቂት ከተራመዱ በኋላ ከእስር ቤቱ አጥር ውጭ አንድ የፈራረሰ ረጅም
አጥር ያለው ቤት አዩ ምናልባት ከጣራ ወደዚያ አጥር ዘልሎ ለመውጣት ይቻላል የሚል አሳብ ተቀረጸባቸው:: ግን ያም ቢሆን አደገኛ ነበር ቴናድዬ ከብዙ ትግልና ጥረት በኋላ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን በዚህ
ቤት በኩል ነበር ከመንገድ አጠገብ የደረሰው፡ ከዚህ ይበልጥ ዝርዝር ውስጥ ባንገባ ይሻላል እንጂ የደረሰበት ውጣ ውረድ ቀላል አልነበረም: ግን
ዝርዝሩን እንግለጽ ቢባልም ትክክለኛውን ለማወቅ አይቻልም:: ሆነም ቀረም ከነበረበት ለመድረስ ሰውነቱ በላብና በዝናብ መራሱ፣ ሰውነቱ መጋጋጡና መድማቱ፤ ልብሱ መቀዳደዱና መቦጫጨቁ የማይካድ ሐቅ ነው፡፡

የያዘው ገመድ አጭር ነው፡፡ ለመዝለልም ፈራ፡፡ ከዘለለ ሞት
የሚጠብቀው መሰለው፡፡ ንጋት ስለተቃረበ ቶሎ ከዚያ ካልወጣ እንደሚያዝ ያውቃል፡፡ እንዲሁ ሲያመነታ አሥር ሰዓት ሆነ
ጠባቂዎቹ የቴናድዬ መጥፋት በደረሱበት ጊዜ ብዙ ድምፅ አሰሙ ቴናድዬ በፍርሃት ተዋጠ፣ ሰውነቱ ተርበተበተ፡፡ ከወደኋላ በር እየተከፈተ ሲዘጋና የእጅ መብራት ብርሃን ላይ ታች ሲል ከሩቁ አየ መብራቱ ጠባቂዎቹ ካደረጉት ቆብ ላይ አርፎ ንቅናቄያቸውን አመላከተው እርሱን
ፍለጋ እንደሆነ ታወቀው:
አሁንም ቴናድዬ ያለው ከሦስተኛ ፎቅ ጣራ ላይ ነው ቢዘል ሞት
እንደሚጠብቀው፣ ቢቆይ እንደሚያዝ በሚገባ ያውቃል ታዲያ እንዴት ይሁን?
አሁንም ጊዜው እንደጨለመ ነው ሆኖም ሰዎች ከየጎራው ሲወጡ
ለመለየት ይቻላል አራት ሰዎች ከተለያየ አቅጣጫ መጥተው በሩቁ በመንገዱ ሲያልፉ ተመለከተ ግን እነማን እንደሆኑ ለመለየት አልተቻለውም:፡ ሰዎቹ ተሰባስበው እርሱ ወደነበረበት አመሩ፡፡ እየቀረቡ ስለሄዱ ጨዋታቸውን አዳመጠ፡፡ ድምፃቸውንና የሚጠቀሙባቸውን ቃላት በሰማ ጊዜ ጓደኞቹ እንደሆኑ አወቀ: የሚነጋገሩት በዱር አዳሪ ቋንቋ ነው ልቡ በተስፋ ተሞላ ሰዎቹ ንግግራቸውን ቀጠሉ
«እንሂድ፣ ከዚህ ምን እናደርጋለን» አለ አንዱ
«ዝናቡ ሳይቆም ከዚህ እንጥፋ: ይኸው እንደምታዩት ፖሊሶቹ
እየተንቀሳቀሱ ነው፡»

«ምን ማለታችሁ ነው፣ ከዚህ ደርሰው እንዲይዙን ነው እንዴ
የምንጠብቀው» አለ ሌላው::

«ምን ያስቸኩላችኋል፣ ጊዜው እንደሆነ ገና ነው: ትንሽ እንቆይ::
የእኛ እርዳታ አለመፈለጉን እንዴት እናውቃለን?» አለ ሦስተኛው:

አራቱም ሰዎች ሽፍቶች ጓደኞቹ እንደሆኑ ቴናድዬ አረጋገጠ:
ለመጣራት አልደፈረም:: ቢጣራ ድምፁ ይሰማል በእጁ የያዘውን የገመድ ቁራጭ ጠቅልሎ ወደ መንገዱ ወረወረው ገመዱ ከሰዎቹ እግር ስር
ወደቀ

‹‹የምን ገመድ ነው?» ሲል ባቤ የተባለ ሽፍታ

«ይሄማ እኔ እስር ቤት ሆኜ የገመድከት ነው» ሲል ብሩዦ የተባለው መለሰ::

‹‹የሆቴሉ ጌታ ከዚህ አካባቢ ነው ያለው ማለት ነው» አለ ሞንትፐርናሴ የተባለው ሽፍታ፡፡

ዓይኖቻቸውን ቀና አደረጉ፡፡ ቴናድዬ ተነቃነቀ

«በሉ ፍጠኑ» አለ ሞንትTርናሴ:: «ብሩዦ ገመድ ይዘሃል?»
«አዎን ይዤአለሁ:
«ሁለቱን ጫፎች ደህና አድርገህ ቋጥራቸወ:: ገመዱን
እንወረውርለታለን ከግምቡ ጫፍ ጋር አያይዞ መውረድ ይችላል፡»

«እንዴት አድርጎ?»

«እባክህ አንተ ብቻ የገመዱን ሁለት ጫፎች ደህና አድርገ
ቋጥራቸው»

«አልችልም»

«አንደኛችን እርሱ ካለበት እንውጣ» አለ ሞንትፐርናሴ፡፡

«ሦስት ፎቅ ነው የምንወጣው!» አለ ብሩዦ

ከእስር ቤቱ አጠገብ ከሚገኘው ፍርስራሽ ቤት የወደቀና ወደ እስር
ቤቱ ግድግዳ የተጋደመ አሮጌ የጭስ መውጫ ቱቦ ነበር፡፡ የጭስ መውጫው ቱቦ በጣም ረጅም ስለነበር ከሦስተኛው ፎቅ ወለል ለመድረስ ምንም ያህል
አይቀረውም፡፡ ይህ ከሲሚንቶ የተሠራው ቱቦ ቅጥልጥል የበዛበት ሲሆን አልፎ አልፎ ተሰነጣጥቋል ደግሞም የውስጡ ስፋት ጠባብ ነው፡

«በዚያች ቱቦ አማካይነት ልንወጣ እንችላለን» አለ ሞንትፐርናሴ፡

«በዚያች ቱቦ!» በማለት ባቤ አሽሟጠጠው፡፡ ‹‹በውስጡ ሰው ሊያልፍ! ጭራሽ አይደረግም: እንኳን ትልቅ ሰው ሕፃንም አያልፍ፡»

«ትንሽ ልጅ ብቻ ነው ከዚያ ቱቦ ውስጥ ሊያልፍ የሚችለው» አለ
ብሩዦ ::

«ታዲያ ልጅ ከየት ይገኛል?» ሲል ግዩለሜ ጠየቀ፡

«ቆዩ» አለ ሞንትፐርናሴ፣ ዘዴ አላጣም፡፡››

የዚያን የፈራረሰ ቤት የውጭ በር ቀስ ብሎ ከፍቶ ወደ ውጭ ወጣ:
ሰው አለመኖሩን ግራና ቀኝ ተመልክቶ በሩን መልሶ ዘጋው ከዚያም በሩጫ ፈረጠጠ፡፡

ሰባት ወይም ስምንት ደቂቃ አለፈ፡፡ ለቴናድዬ እንደ ስምንት ሺህ ዓመት ረዘመበት ባቤ፣ ብሩዦና ግዩለሜ ጥርሳቸውን ነክሰው ተገትረው ቀሩ በመጨረሻ በሩ እንደገና ተከፈተ ሞንትፐርናሴ ትንፋሽ አጥሮት ከጋቭሮች ጋር ብቅ አለ፡ አሁንም በኃይል ይዘንብ ስለነበር ማንም ደፍሮ
መንገድ ላይ አልወጣም፡፡
ትንሹ ጋቭሮች ከቱቦው ሥር ሆኖ ወደ ላይ ተመለከተ ሲያይ ውሃ
ጭንቅላቱ ላይ ተንጠባጠበ፡፡
«እንዴት ነው አንተ ልጅ! የአባትህ ልጅ ነህ ወይስ የእናትህ» ሲል
ግዩለሜ ልጁን ጠየቀው

«እንዴ እኔ ያለውማ የአባቱ ልጅ ነው፤ እንደእናንተ ያለው ነው
እንጂ የእናቱ ልጅ» ሲል ልጁ ትከሻውን እየነቀነቀ ተናገረ
እንዴት ያለ የሾለ ምላስ ነው ያለው?» አለ ባቤ እየተገረመ
ፓሪሱ ወጣት ከገለባ የተሠራ ይመስላችኋል» በማለት በአገሩ የአራዳ ቋንቋ ባቤ ተናገረ::

«ምንድነው የምትፈልጉት?» ሲል ልጁ ጠየቀ፡፡

«በቱቦው አድርገህ ከሦስተኛ ፎቅ ጣራ ላይ እንድትወጣ ነው
የምንፈልገው» ሲል ሞንትፐርናሴ መለሰለት::

«ይህቺን ገመድ ይዘህ ነው የምትወጣው» አለ ባቤ::
👍22
ልጁ ገመዱን አገላብጦ አየው፡፡ የጭስ መውጫ ቱቦውንና ግድግዳውን አጤነ፡፡ ከዚያም «ለምንድነው የምወጣው?» ሲል ጠየቀ::

«ከሦስተኛው ፎቅ ጣራ ላይ አንድ ሰው አለ፡፡ የምትወጣው የእርሱን
ሕይወት ለማዳን ነው» ሲል ሞንትፐርናሴ መለሰለት::

«ትወጣለህ?» ሲል ብሩገር በጉጉት ጠየቀው::

«ይቻላል» አለ ልጁ የተጠየቀውን ጥያቄ በማቃለል፡፡

ግዩለሜ ልጁን ተሸክሞ ከፈራረሰው ቤት ጣራ ላይ ወረወረው::

የበሰበሰው ጣራ ተንቋቋ፡፡፡ ብሩና ሁለቱን ጫፍ ከቋጠረ በኋላ ይዞት
የነበረውንም ገመድ ወረወረለት:: ልጁ ወደ ጭስ መውጫው አመራ፡፡ ልጁ እየተንፏቀቀ መውጣት እንደ ጀመረ ቴናድዬ አየው፡፡ ቴናድዩ ዝናብ እየዘነበበት ሳለ ውስጥ ውስጡን ከፍርሃት ብዛት እንዳላበው ታውቆታል።

ልጁ ገና ሲያየው ማን እንደሆነ አወቀው፡፡

«ቆዩ እስቲ! ይሄማ አባቴ ነው» ሲል ተናገረ፡፡ «ብቻ ይህም ቢሆን
ከመውጣት አያግደኝም» ብሎ ገመዱን በጥርሱ እንደያዘ ጉዞውን ቀጠለ፡፡

ልጁ እንዴት እንደወጣ በቃላት ለመግለጽ ያዳግታል፡፡ ዱር አዳሪ
ልጆች የሚሠሩት ሥራ ተአምር ነው ብሎ ከማለፍ በስተቀር ሌላ ለመናገር አይቻልም፡፡ ልጁ ቴናድዬ ከነበረበት ደርሶ ገመዱን በማጠላለፍ ረድቶት
በአጭር ጊዜ ውስጥ ከዚያ አምልጠው ወረዱ፡፡ ልክ እነርሱ ከዚያ ወርደው መንገድ ሲጀምሩ ጎሕ እንደ መቅደድ አለ፡፡ ልጁ ምናልባት አባቱ ወደ እርሱ
ፍጡር መጥቶ ያነጋግረው እንደሆነ ጠበቀ፡፡ የጠበቀውን አላገኘም:: መንገድ ዳር
ከነበረው ድንጋይ ላይ ቁጭ አለ፡፡ ከዚያም የተቀደደ ጫማውን ካጠለቀ በኋላ «አልቋል አይደል? ከአሁን በኋላ አትፈልገኝም? ችግራችሁ ተወግዶላችኋል፤ እንግዲህ እኔ ልሂድ?» ሲል ጠየቀ::

ይህን እንደተናገረ መንገዱን ቀጠለ፡፡ አምስቱ ሰዎች ግን ተራ በተራ ከፈራረሰው ቤት ወጥተው ሄዱ፡፡ ልጁ ራቅ ብለው እንደሄደ ባቤ ወደ ቴናድዬ ዞር ብሉ «ልጁን አየኸው?» ሲል ጠየቀው::

‹‹የምን ልጅ?››

«ገመዱን ከነበርክበት ያመጣልህ ልጅ ነዋ!»

«ልብም ብዬ አላየሁት::»

«ብቻ... እኔ እንጃ፣ ልጅህ ነው መሰለኝ::»

«ወይድ እባክህ» አለ ቴናድዬ ፣

«ይመስልሃል?»....

💫ይቀጥላል💫
👍28😁2
አትሮኖስ pinned «#ምንዱባን ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ ፡ ፡ #ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ ....ልክ ፍቅረኛዋን የምትደባብስ ይመስል በለስላሳ እጆችዋ ድንጋዩን በማሻሸት አመሰገነችው:: «ምነው ተጫጫነኝ፣ ማን አለ ከአጠገቤ» እንደሚባለው ሁሉ ምንም እንኳን በዓይንዋ ባታየውም ከአጠገብዋ ሰው እንደቆመ ከበዳት:: ይህ እንዴት ሆነ ቢባል በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡ ፊትዋን አዙራ ከተመለከተች በኋላ ብድግ አለች:: እሱው…»
#ሰው (አጭር ልቦለድ)


#በበእውቀቱ_ስዩም

ጢም ማቀምቀም በጀመርኩበት ዘመን በከተማችን አንድ ተአምረኛ ባህታዊ ብቅ አለ፤ 'ጥቁር ኢየሱስ ብለው ሊጠሩት የደፈሩ ሰዎች ሁሉ ነበሩ ፤ ባህታዊው እውር ያበራል፤ ጎባጣ ያቀናል፤ ባንድ ጊዜ የከተማው ሆስፒታሎች ሁሉ ባዶ ሆኑ፤ የሆነ ጊዜ ላይ እንዲያውም ሙት ማስነሳት ሁሉ ጀምሮ ነበር፤ የከተማችን አስተዳዳሪ ግን “ ለተነሺዎች ማቋቋሚያ የሚሆን በጀት የለንም ብሎ ከለከለው፤

ባህታዊው ባንድ ወቅት ከተማውን አቋርጦ ሲያልፍ ወልደ ሰንበት ከተባለ የከተማው ነዋሪ ጋራ ተገናኘ፤ ወልደ ሰንበት በራዛ ዘመቻ ጊዜ ፈንጅ ብልቱን ቆርጦበታል፤ በጥሮታ ከተገለለ በሁዋላ ‘መራባት የተሳናቸው ወንዶች ማህበር’ ፕሬዚዳንት ሆኖ ያገልግላል፤

ወልደሰንበት ባህታዊውን ሲያየው “ አባት ሆይ፥ አገሬን አገሬን ብየ ስዋትት ዘሬን ሳልተካ ላልፍ ነው፤ ፈውሰኝ “ ሲል እግሩ ላይ ወድቆ ተማጠነው።

ባህታዊው ወደ ሰማይ አንጋጦ ትንሽ ከጸልዩ ሲያበቃ ወልሰንበትን አስወልቆ ጉያውን ዳበስ አደረገው ፥ መቸም አታምኑኝም ፤ ግን ሀቅ ከከመመስከር አልታገድም፤ የሰውየው ጉምድ ብልት ወዲያውኑ አቆጠቆጠ። ተአምረኛውን ሰውየ ያጀቡ ወንዶች አፋቸውን በጋቢያቸውና በኮሌታቸው ጫኑ !የሴቶች እልልታማ ፤እስከመተማ ፤ ተሰማ፥

ባህታዊው ይህንን ተአምራዊ የብልት- ተከላ ፈጽሞ ትንሽ አለፍ እንዳለ ወልደ ሰንበት እያለከለከ ደረሰበትና እግሩ ስር ተደፋ፤

“ አሁን ደግሞ ምን ፈለግህ?” አለው ባህታዊ፥ በታከተ ሰው ድምጽ ፥
ወልዴ እንዲህ ሲል መለሰ፥

“አባት ሆይ ! በነካ እጅህ ትንሽ ተለቅ ልታረግልኝ ትችላለህ?”🙄
😁29👍18
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስራ_አንድ

...ዮርዲ” ነው ያልኩት ? ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ከአቲዬ ቀጥሎ በዚች ምድር ያቆላመጥኩት ስም እነሆ..

ጠዋት ዩኒፎርሚን ለብሼ ደብተሮቼን አዘጋጀሁና እየቀፈፈኝ ወደ ትልቁ ቤት ሄጀ አንኳኳሁ፡፡

“ማነው?” አለችኝ ዛፒ፡፡ ደነገጠኩ፡

እኔ ነኝ አልኩ እየፈራሁ፡፡

«ግባ ክፍት ነው»፡፡ ገፋ ሳደርገው የሚያብረቀርቀው የጣውላ ሰር ድምፅ ሳያሰማ ተከፈተ ክፍቱን ነው ያደረው ማለት ነው::
ዝርከርክ ያለው ሳሎን ጋር ተፋጠጥኩ፡፡ ዛፒ ሶፋው ላይ
የአልጋ ልብስ ጣል አድርጋ ተኝታለች፡፡ ፊቷ የተቀመጠው ጠረጴዛ ላይ የሻይ ብርጭቆ፣ የውሃ ጠርሙስ፡ ሩቡ ብቻ የተበላ ሰላጣ፣ ምንም ያልተነካ ዳቦ ዝርክርክ ብሏል፡፡ ብዙ ምግብ
ማቅረብና ምንም አለመብላት ልማዷ ነው ይገርመኛል፡፡

“ምንድነው በጠዋቱ“ አለች እየተነጫነጨች፡፡ ድምጿ የወንድ ይመስላል ጎርንኗል፡፡

"እ..ትምህርት ቤት ከሁሉም ትምህርት ቤቶች እንደኛ ወጣሁና ልንገርሽ ብዬ ነው"
ድምጼ ተንቀጠቀጠብኝ፡፡

ቀጥ ብላ ግራ በገባው ፊት እየችኝ፡፡ የሌሊት ልብሷን ትከሻዋና ትከሻዎ አካባቢ ይዛ አስተካከለች!
አቤት ደረቷ ቅላቱ ይንቦገቦጋል፡፡ ከኋላው ቢጫ መብራት የበራበት መስተዋት ይመስላል፡፡

"እኔ ምናገባኝ ታዲያ?!" የምትል መስሎኝ ነበር፡፡ ድንገት የሆነ ነገር ትዝ እንዳለው ሰው ፈገግ ብላ፤

"እና ሳመኛ! እንደዚህ ነው እንዴ የምስራች የሚነገረው? መርዶ አስመሰልከው እኮ!” አለችኝና
ሁለት እጆቿን እንደ ክንፍ ዘረጋቻቸው፤ ያውም በፈገግታ፡፡ ሁለት ጡቶቿ አፈጠጡብኝ፡፡

ግራ ገብቶኝ እንደቆምኩ፣ ና እንጂ ሳመኝ!” ብላ ጮኸትብኝ፡፡

በደመነፍስ እየተደነቃቀፍኩ ሄጄሄጄ ሄጄ ሄጄሄጀ.ሄጀ እጆቿ ሲጠመጠሙብኝ ሁሉ እርምጃዬን
ያቆምኩ አልመሰለኝም፡፡ ጥብቅ አድርጋ እቅፉኝ፣ “ጎበዝ የኔ ወንድም እኮራብሀለሁ!” አለችኝ፤
በለው ! ከሽ አለ የሻዩ ብርጭቆ ከጠረጴዛው ላይ ወድቆ፡፡ “ይሰበር ተወው!” አለቸኝና ጉንጬን
ስማ ለቀቀችኝ፡፡ ይሄ ቤት ለካ የወይዘሮ እጥፍወርቅ ቤት ነው !!

ከዛፒ ጋር እንደወጣሁ በደስታ ሰከሬ መንገዱን ሁሉ፣ ሰውን ሁሉ አየሁት፡፡ መቼ ነው ይሄ ትልቅ
የመኪና ኪራይ ማስታወቂያ ነዳጅ ማደያው ፊትለፊት የተሰቀለው ? መቼ ነው ይሄንኛው ሕንፃ
ተሰርቶ ያለቀው? ወቸ ጉድ አዲስአበባ እንዴት ተለውጣላች? ከሆነ አገር የመጣሁ መሰለኝ፡፡
ደግም ደስ የሚል ነገር ይሸተኛል፡፡ አፍንጫዬም ዛሬ ገና የተከፈተ ይመስል።

ዮርዳኖስ ጋር ስንገናኝ፣ “ምነው?” አለችኝ፡፡

"እ" አልኳት፡፡

"አይ ቆመህ ሳገኝህ ነዋ” አለችኝ፡፡ ለካስ ዮርዳኖስን ቆሜ አልነበረም የምጠብቃት። ያልጠበቅኳት
መስዬ ነበር መጠበቅ የነበረብኝ፡፡ ሳመችኝ ጉንጬን፡፡ ዛፒና ዮርዳኖስ እኔ በምባል ኳስ
በከንፈራቸው እየተቀባበሉ ቮሊ ቦል የሚጫወቱ መሰለኝ፡፡ "ተስመህ ትወጣለህ፣ ሰመው
ይቀባሉሀል የሚል ትንቢት ከሰማይ የታወጀም መሰለኝ፡፡ ድፍን አዲስ አበባ እንደ ዳቦ፡ እንደ
ዘይት፣ እንደታክሲ እኔን ለመሳም የተሰለፈ መስሎ ተሰማኝ፡፡(ቀስ ትደርሳላችሁ አትጋፉ ሂሂሂሂ)

ዮርዳኖስ ፈገግ ብላ አፍንጫዋን በመቀሰር ጠጋ አለችኝና፣ ደሞ አሪፍ ሽቶ ፣ እፉፉፉፉፉፉ
ያደረጉብ ማነው?" አለችኝ:: አፈርኩ፡፡ ለካ የዛፒ ሽቶ ነው ሲከተለኝ የነበረው፡፡ የዛቲ ሽፋ
የዋዛ አልነበረም፡፡ ከዚች ቀን ጀምሮ እድሜ ልኬን ሲከተለኝ ነው የኖረው፡፡ ሲያሳድደኝ ሳይሆን
ሲከታለኝ፡፡ የሆነ ዙሪያዬን ከብቦ እንደ እናት አቅፎኝ፡፡

ሰው ወደ ውስጥ የሚስበው አየር እክስጅን፥ ወደ ውጭ የማያስወጣው ካርቦንዳይ ኦክሳይድ እያሉ ያስተማሩን ቅኔ ነበር ሳይንሳዊ ቅኔ !! አሁን አሸብር ወደ ውስጥ የሚስበው ፍቅር፣ መፈቀር፣ መከበር፣ መፈለግን ነው፡፡ ወደ ውጭ የሚተነፍሰው እርካታ፡፡ የአየር ብክለት ማለት ሌላ ትርጉም የለውም እኮ የተገፉ፣ የተገለሉ፣ የተናቁ፣ ሕዝቦች ጥላቻን ወደ ውስጣቸው ሰበው መልሰው ጥላቻን ወደ መላው ዓለም መተንፈሳቸው ነው:: መፍትሄው የፍቅር ችግኝ በልባቸው
መትከል ነው:: እነሆ ዮርዳኖስ የተከለችውን ዝግባ ዛፒ የምትባል ዝናብ ስታረሰርሰው ዘርፈፍ
ብሎ በቀለ፡፡ ሕያውነት ከስሩ አረፍ የሚልበት ጥላ ሆነ፡፡

እኔማ ዛፒ ጥቁር ደመና አዝላ እያጉረመረመች ሰማይ ላይ ተንጠልጥላ ሳያት፣ መሽቆጥቆጥና ጥላቻዬን እንደ ዥንጥላ ስዘረጋ ነበር የኖርኩት፡፡ ክፉትም ጉልበት የሚኖረው እንደክፋት ልንቀበለው በተዘጋጀነው መጠን ነው::

“አንተ ሴት ነህ እንዴ?” ብላ ዛፒ ሳቀችብኝ፡፡ አፈርኩ፡፡ አንደኛ መውጣቴን ምክንያት በማድረግ
ዛፒ ልብስ ልትገዛልኝ ወሰደችኝና ምረጥ! ስትላኝ መጀመሪያ እጄ አንድ ቀሚስ ላይ አረፈ፡፡
ለእቲዬ ልኳ የሚሆን ቀሚስ ነበረ፡፡ ለዛ ነበር የሳቃችው::ልብስና ጫማ ገዛችልኝ፡፡ የሱሪዬን ቁጥር ስጠየቅ አላውቅም ነበር፡፡ ሱሪ ገዝቼ አላውቅማ፤ የጫማ
ቁጥርም አላውቅም፡፡ የሀብታም ልጆች ልብስና ጫማቸው ከሱቅ የተገባ ሳይሆን አብሯቸው
የሚወለድ ይመስለኝ ነበረ፡፡
ሃሃሃ… ግን ይሄው ሁሉ ነገር ሱቅ ውስጥ አለ ሸቀጥ ነው፡፡ ያው እዛጋ ቶማስ የሚባለው
ሁልጊዜ በሴት የሚከስሰው የክፍላችን ልጅ ጫማ ይሄው የራሄል ቦርሳ ኧረ ጉድ የቲቸር
ተስፋ የጥቁር ባለ ብዙ ኪስ ጃኬትም ያውና፡፡ ትንሽ ብቆይ እነዛ ውድ ነን የሚሉ ልጆች
እዚህ ተደርድረው ሲሸጡ አገኛቸው ይሆናል፡፡
ሲገርም ሁለት ሱሪ፣ አንድ ጫማ፣ ሁሉት ሸሚዝና አንድ ሹራብ ነፍስ ካወቅኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ ልብስ ከሱቅ ገዛሁ፡፡ ለካሁት፡፡ መስተዋቱ ፊት ስቆም ደነገጥኩ፡፡ ልብስ ማለት ተራ ድሪቶ ነው ምናምን የሚሱ ሰዎች እንዴት ጅሎች ናቸው እባካችሁ! ራሴን በመስተዋት ሳየው ታላቅ ፍንዳታ እዕምሮዬ ውስጥ ተፈጠረ፡፡

እወራረዳለሁ ጥቁር አምበሳ፣ ኮከበ ፅባህ፣ ምኒሊክ፣ መነን፣ አዲሰ ከተማ፣ ድልበር፣ ቦሌ ከሚማሩ ተማሪዎች ሁሉ አንደኛ ቆንጆና ወንዳወንድ አቋም ያለኝ ልጅ እኔ ነኝ !! እፎይ! ከቤተክርስቲያን ሃጢያቱን ተናዞ እንደወጣ ሰው ሸክሜ ቀለለኝ አደግኩ ደግሞ !! የክፍሌን ልጆች በየቤታቸው እየሄድኩ እጄን ኪስና ኪሴ እስገብቼ “ሃይ!” ማለት አማረኝ፡፡

ዛፒ የለበስኩት አዲስ ሹራቡ ላይ የነበረውን ወረቀት ከኋላ ክሩን በጥርሷ በጥሳ አላቀቀችልኝና፣
አንተ ልጅ ቆንጆ እኮ ነህ አለችኝ፡፡ በሙቅ ውሃ በተሞላ ገንዳ ውስጥ የመግባት ያህል ቓሏ ይሞቅ ነበር፡፡ ቆንጆ መሆን ማለት የአፍንጫ መሰልከከ፣ የዓይን መንከባለል፤ የጥርስ መደርደርና
ንጣት ማለት አልነበረም፡፡ ለኔ ቆንጆ ማለት በሰው ዓይን መሙላት ማለት ሆነልኝ፡፡

ዝም ብላችሁ የሕይወት መንገዳችሁኝ ዙሩና ተመልከቱ! አለቀ ያላችሁበት ቦታ ላይ የነበረውን የሚመጣውን የሚያያይዝ ድልድይ ይኖራል፡፡ ይሄን ድልድይ የሚያምኑ ፈጣሪ ነው ይሉታል የማያምኑ 'የስነሕይወት መርህ ነው' ይሉታል፡፡ ለእምነቱም ለሳይንሱም ግድ የማይሰጣቸው እድል ይሉታል፡፡ እኔ ግን ይሄ አንዴ በዛ አንዴ በዚህ የሕይወቴን ተራዳ አየደገፈ የሚያቆመው
ከአቲዬ ድፍን ሃምሳ ብር የተበደረው እግዚያብሔር ነው እላለሁ፡፡
👍3316