አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#ቦግ_እልም !! ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም አንዳንድ ታሪኮች አሉ፣የማያስደስቱ ግን ምን በወጣኝ ብቻዬን መሸከሜ ተብሎ ለሌሎች የሚነገሩ ልክ እንደዚህ.… አንዳንጅ ታሪኮች ደግሞ አሉ፡ እንኳን ለግጥም፣ ለእግዜር ሰላምታ አፉ የማይፈታለትን ሰው በሐዘን ኮርኩረው ገጣሚ የሚያደርጉ፣ ልክ እንደዚህ…. ብቸኝነት ማለት … ብዞዎች መካከል አንድ ሆኖ መገኘት ? ብቸኝነት ማለት … ለሕዝብ እየታዩ ደምቀው እንዳበባ፧…»
#ትኩሳት


#ክፍል_ዘጠኝ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

..ፊሬንዜ ውብ ከተማ ናት፤ የነጻንቴ የነሚኪኤል አንጀሎ ከተማ!

አንዲት ትንሽ ሬስቶራንት ውስጥ እራት ስንበላ ነበር፡፡ ሲልቪ
ምግቧን ረስታ ወደ ኋላዬ በኩል ትኩር ብላ ማየት ጀመረች።
ሳይታወቃት በግራ እጂ ፀጉሯን አስተካከለች ብቻ መስተካከል
አያስፈልገውም ነበር። ገባኝ። የምትጎመጀው ወንድ አይታ መሆን አለበት። ሹካና ቢላዋን ቁጭ አድርጋ ወይን አንስታ ፉት አለችና፣ ብርጭቆውን መልሳ እንደማስቀመጥ፣ በእጆቿ ውስጥ በዝግታ እያሽከረከረችው ወደዚያው ወደ ኋላዬ ማየቷን ቀጠለች። ቀይ ከንፈሮቿ ገርበብ፣ በወይን ረጠብ ብለው ያስጎመጃሉ

እሷ ወደዚያ ስታይ እኔ እሷን ስመለከት፣ ቆንጆ ፊቷ ቀስ ብሎ
ፈገግ አለ፤ ሰማያዊ ኣይኖቿ ስልምልም ማለት ጀመሩ። ምኞቱ
ውስጤ ሲያድግ ተሰማኝ፡፡ አይኖቿ ከአይኖቼ ጋር ተጋጠሙ፣ ፊቷ መቅላት ጀመረ፡ አይኖቿ ተርገበገቡ። ሰውየው ማን እንደሆነ ማወቅ ፈለግኩ፡ ግን ወደኋላ ከተገላመጥኩ ነገሩ ይበላሻል፣ ስለዚህ ተውኩት

«ፍሬ ይምጣልሽ?» አልኳት
«የለም በቃኝ። አንተ ብላ »
«እኔም በቅቶኛል»
«እንግዲያው እንሂድ?» አለችኝ፣ ወደ ቅድሙ በኩል እያየች
ስንወጣ እሷ ታተኩርበት ወደነበረው በኩል ተመለከትኩ፡፡
በየጠረጴዛው የተበታተኑ አንድ አምስት ወንዶች አሉ፡ የትኛው
ፍላጎቷን እንደ ቀሰቀሰ ለማወቅ አልቻልኩም፡፡ ግን ፍላጐቷ በሀይል ተቀስቅሷል። አልጋ ውስጥ ስንገባ መብራቱን አጠፋችው፣ እየተንገበገበች አቀፈችኝ፤ በመጨረሻ ላይ በእንግሊዝኛ ቃዥች

«Please, my lord! Please, have mercy!

ሌላ ሰው ሆኜ፣ ግን ማን እንደሆንኩ ሳላውቅ፣ በቅንዝርና
በቅናት እየተቃጠልኩ፣ ጥልቅ የሆነ ስጋዊ ደስታን ተደሰትኩ።
በነጋታው ቀኝ ጡቷን እያመማት ዋለ። ሳይታወቀኝ ጨፍልቄው
ኖሯል በሌላ ቀን፣ «ማን ሆኜ ነበር?» አልኳት። ስንበላ በስተኋላዬ አንድ ሰውዬ እይታ ኖሯል። «ልክ ስመ ጥሩውን ባለቅኔ ሎርድ ሳይረንን ይመስል ነበር አለችኝ እንደዚሀ ስንል፣ እሷ ደስ የሚላትን ወንድ ስታይ፤ እኔ በጭለማ እሱን እየሆንኩ ሳቅፋት እሷ ስትቃዥ፣ እኔ ስነክሳት ስጨፈልቃት፣ እንደዚህ ስንል፣ በሰማያዊ, አይኖቿ ብርሀንና በሰፊ አፏ ሳቅ እያሞቀችኝ፣ በውብ ወጣት ገላዋ እያቃጠለችኝ፡የጣልያንን ከተማዎች እያዞረችኝ «Je men fous» አያለች አያሳቀችኝ፣ እንደዚህ ስንል የበጋው እረፍት ወደ ማለቂያው ተቃረበ፡፡ ከፊሬንዜ ሮማ
ከሮማ ናፖሊ፤ ከናፖሊ ኒስ (ፈረንሳይ) ከኒስ ማርሰይ ተጓዝን።

ከማርሰይ እሷ ቤቶቿን ጥየቃ ፓሪስ ሄደች፡፡ ባቡር ጣቢያው
ሄጄ ስሸኛት ልክ የዛሬ ዘጠኝ ቀን ማክሰኞ ኤክስ እገባለሁ፤ ማታ
ቤቴ እጠብቅሀለሁ» አለችኝ
የሲልቪ ናፍቆት የሚገድለኝ መስሎኝ፤ ዘጠኝ ቀን ሙሉ
እንዴት ሊያልፍልኝ ነው? እያልኩ ስሰጋ ነበር፡፡ ግን ባቡሩ ይዟት
እንደሄደ፣ በሀዘን ፈንታ እፎይታ ተሰማኝ፡፡ ማታ አልጋ ውስጥ
ገብቼ ብቻዬን እንደ ልቤ ስገላበጥ፣ ብቸኝነት ሳይሆን ምቾት ተሰማኝ፡፡ ምቾቴ በደምብ እንዲታወቀኝ ስል በብዙ ተገላበጠኩ።ጧት ስነቃ ሲልቪ የለችም፡ ብቻዬን ነኝ፡፡ በናፍቆት ፈንታ ደስታ ተሰማኝ፡፡ ሲልቪ ሰልችታኝ ኖሯል? ወይስ ከሰው ጋር ለመኖር አልተፈጠርኩም? ሊገባኝ አልቻለም

ኤክስ ሄጄ ሲቴ (ዩኒቨርሲቲ) ውስጥ አንድ የመኝታ ክፍል
ተቀበልኩ፡ ሁለተኛው አመት ወደ መጀመሩ ነበር ጧት ስነሳ በመስኮቱ ደማቅ ሰማያዊ የሆነ ንፁህ ሰማይ ታየኝ።ደስ አለኝ። ሳይታወቀኝ የኤክስ ውብ ሰማይ ናፍቆኝ ኖሯል
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ባህራም ከቅርብ

ኤክስ እንደተመለስኩ መጀመሪያ ያገኘሁት ተካን ነበር፡፡ ያው
እንደ ልማዱ ጥፍሩን እየነከሰ፣ የት ነበርክ? ከማን ጋር ነበርክ? ምን
አደረግክ? ምን አየህ? እያለ በጥያቄ አጣደፈኝ፡፡ ግን ሳየው የጥርሱ መበለዝ የቀነሰ መሰለኝ፡፡ አፉም አልገማኝም፡፡ ጊዜው ከእራት በኋላ ነበር፤ ና ቡና ላጠጣህ ብሎ ወደ ክፍሉ ወሰደኝ፡፡ ቤቱ በጭራሽ
አይገማም!

እንግዲህ፣ የዩኒቨርሲቲው መኝታ ቤቶች ባለ ሶስት ፎቅ
ሲሆኑ፣ እያንዳንዱ ፎቅ ላይ ለሚገኙት ሰላሳ ያህል ክፍሎች የጋራ የሆኑ አንድ የገላ መታጠቢያ ክፍልና፣ አጠገቡ ደግሞ (ልክ ደረጃው መጨረሻ ላይ) አንድ የቡና ማፍያ ምድጃ ያለው ክፍል አላቸው።ተካ ቡናውን ሊጥድ ወደ ማፍያው ክፍል ሲሄድ እኔ የሱን መኝታ ክፍል ተመለከትኩ፡፡ ንፁህ ነው። ፊት መታጠቢያው ዘንድ፡ ግማሹ ያለቀ ኮልጌት የጥርስ ሳሙናና አንድ የጥርስ ብሩሽ አለ። ተካ ጥርሱን ይቦርሻል! ምን ነካው?. ምን ይነካዋል? ያው
የተለመደው መሆን አለበታ! አንድን ጎረምሳ ጥርሱን ሊያስቦርሸው የሚችል ምንድነው? ሴት አይደለችም? ግምቴ ልክ ይሆን? ልክ
መሆን አለበት። አለዚያ ምኑን ደራሲ ሆንኩት?

አንገቴን በበሩ ብቅ አድርጌ አየሁ። ጨለም ያለው ረዥም
መተላለፊያ ኮሪዶር ባዶውን ነው፡፡ ኮሪዶሩ መጨረሻ ላይ ያለው
የቡና ማፍያ ክፍል ተዘግቷል። ተካ ገና ቡናውን በመጣድ ላይ ነው
ማለት ነው። ጊዜ አለኝ፡፡ በሩን ዘጋሁ፡፡ ቶሎ ወደ አልጋው ራመድ
አልኩ፡፡ አንሶላውን ላመሉ ገለጥ ከደረግኩት። ጎምበስ ብዬ ትራሱን
አሸተተኩት፡፡ የሴት ጠረን። ያለጥርጥር። እንዴት ያለች ትሆን?
ቶሎ አልጋውን አስተካከልኩና፣ ቁጭ ብዬ ጋዜጣ እያነበብኩ
ቆየሁት ቡና ከጠጣን በኋላ ሊሎቹን ሀበሾች ፍለጋ ወጣን
ተካ «ተመስገንን ግን አታገኘውም» አለኝ «ወደ ፓሪስ
ተዛውሯል። ለምን እንደተዛወረ ታውቃለህ?»
«ለምንድነው?» አልኩት
«ነጭ ሴት ሰለቸኝ አለ።»
«ምን?
«ጥቁር ሴት ካላገኘሁ ልማር አልችልም አለ፡፡ እዚህ ኤክስ
ውስጥ ሁለት ጥቁር ሴት ብቻ ነው ያለው፡ ሁለቱም አስቀያሚ
ናቸው። ስለዚህ ፓሪስ መሄዴ ነው:: ቢሆን እግዜር ብሎ አንዲት
ሀበሻ ልጅ ታጋጥመኝ ይሆናል፡፡ ባይሆን ደሞ ሌላ ጥቁር ሴት
አላጣም፣ ብሎ ሄዴ»
ተመስገን እውነቱን ነው። ኤክስ ውስጥ ጥቁር ሴት አይገኝም
ሀበሻ ሴት ይናፍቃል። ያገራችን ሴቶች ትዝ ይሉናል፤
አነጋገራቸው፣ አሳሳቃቸው፣ መሽኮርመማቸው ይናፍቀናል፡ ጥቁር ቆዳቸው፣ ነጭ ጥርሳቸው እንቅልፍ ይነሳናል፡ በሀሳባችን
አረ ንሺ» ሲሉ ይሰማናል።

አንዳንድ ጊዜ ተሰብስበን ስለነሱ እናወራለን፡፡ ናፍቆት ሲበዛብን
እየሳቅን እየጮህን እንዘፍናለን
«አንቺ ጥቁር ድንጋይ ፍቅር አይገባሽ በሰው አገር ሆኜ ተቃጠልኩልሽ»
ሉልሰገድማ “ልጆችዬ፣ አብረን አንዲት እምስ የተቀረፀባት ሻማ ለቁልቢው እናብራለትና » አለን እምስ በፖስታ ላክልን፣
መጋረጃ እናስገባልሀለን፣ እንበለው፡፡ እውነቴን'ኮ ነው! ያገሩ ልጆች ነን፡ ይሰማናል። ኧረ እናታችሁን! ይሄ ምኑ ያስቃል?»

እኔና ተካ ሀበሾቹን ሉልሰገድ ቤት እገኘናቸው:: ባህራምና
አንድ ሌላ ኢራናዊ አብረዋቸው አሉ፡፡ ይህ ሌላ ኢራናዊ ጀምሺድ
ይባላል። ረዥም መልከ ቀና ወጣት። ጥቁር ሱፍና ነጭ ሸሚዝ
ከቢራቢሮ ክራቫት ጋር ለብሷል። ግብዣ ለመሄድ የተዘጋጀ
ይመስሳል። ረዘም ያላ ፈት፡ ቀጥ ያለ ረዥም አፍንጫ። ከሀር
መሳይ ውብ ቅንድቦቹ በታች ሰማያዊ ትንንሽ አይኖች ሁልጊዜ
ይጨፍራሉ፡፡ ብርሀን ሳቅ፣ ብልጠት የሚፈራረቅባቸው፣ ህይወት የሞላባቸው አይኖች ናቸው፡፡ በኋላ እንደተረዳሁት፣ ጀምስድ ፈረንሳይ አገር ከመጣ አመት አልፎታል። ታድያ ቢበዛ ስምንት መቶ የፈረንሳይኛ ቃላት ቢያውቅ ነው (የቋንቋ ስጦታ የለውም) ግን እነዚህ ስምንት መቶ ቃላት ለንግግር ኮርተው ይበቁታል። ምክንያቱም ቀጭን ኮሚክ ድምፁና ትንንሽ ብልጮ አይኖቹ፣ ያለ ቃላትም ቢሆን የፈለገውን ይገልፁለታል
👍131
እኔና ተካ ስንገባ ጀምሺድ አንድ ታሪክ ጀምሮላቸው ኖሮ፣
ጨብጠናው ቁጭ ካልን በኋላ እንደገና ጀምርልን አሉት፡፡
ስብርብር እንቅሽቅሽ ባለ ፈረንሳይኛ ጀመረ። ሁለት አንካሳ አረፍተ ነገር ያህል እንደተናገረ ቃል ይጠፋዋል። በፋርስ ቋንቋ ባህራምን ይጠይቃል። ባህራም ፈረንሳይኛውን ቃል ይነግረዋል። ጀምስድ ታሪኩን ይቀጥላል።

«ከአስራ ሶስት ወር በፊት አለ ጀምሺድ «እኔና ሆዚ ከኢራን
እንመጣለን፡፡ ወደ ፓሪስ፡ ሆዚ ፈረንሳይኛ አይችል። አንዳች
በፍፁም እኔ ግን 'ዊ-ዊ' ማለት እችላለሁ። ደሞ 'ሜርሲ ቦኩ'
አውቃለሁ:: ግን ሜርሲ ቦኩ አልልም 'መርሳ ባኩ እላለሁ።
እኔና ሆዚ ሀሳብ፣ ሶርቦን ዩኒቨርሲቲ ለመማር፡፡ ለመማር
መመዝገብ። ለመመዝገብ ሶርቦን መሄድ። ሶርቦን ለመሄድ ሜትሮ
መግባት። (ሜትሮ ፓሪስ ውስጥ ከምድር ስር የሚሄድ የህዝብ
ማመላለሻ ባቡር ነው)

ጧት በሁለት ሰአት ሜትሮ ገባን። ሆዚ ፈረንሳይኛ አያውቅም፡፡
እኔ ግን ፈረንሳዮቹን፣ የትኛቸው ባቡር እንሳፈረው? ብዬ ጠየቅኩ፡፡
በቃላት አይደለም፤ በእጅ፣ በራስና በድምፅ። በምልክት፡፡ ዠ ቨ ቩ
ቪ! ቫም! ቩም!! » ይለናል።
ሆዚ ዝም ይላል። ፈረንሳይኛ
አያውቅ። እኔ ግን 'ዊ ዊ! መርስ ባኩ' ይላል እላለሁ ማለቱ
ማለቴ። እኔና ሆዚ አንድ ባቡር መሳፈር ሲቆም መውረድ። ሌላ
ባቡር መሳፈር። እንደዚህ በመሳፈር የምሳ ሰአት ማለፍ። ፈረንሳዮች እንጠይቃለን። ዥ ቨ ቩ ቪ ቫም! ቪም!” ይሉናል፡፡ ሆዚ ዝም እኔ 'ዊ ዊ! መርስ ባኩ!'። መሬት ውስጥ ገብተን መምሽት።
አሁን ወደ ሆቴላችን። ሌላ ባቡር። ሌላ ባቡር። ሌላ ባቡር። ሆዚ
ድካም፣ ራብ፣ ብስጭት እምባ እኔ የሆዚ እምባ ያሳዝነኛል። እኔ
እምባ! ሁለት ጎረምሶች ሜትሮ ውስጥ እምባ!!

«አንዲት አሮጊት መምጣት። ታየናለች። ዠ ቨ ቩ ቪ?
ትለናለች። ሆዚ ፈረንሳይኛ አያውቅ። ዝም፡፡ እምባ ብቻ። አኔ 'ዊ ማዳም፣ መርስ ባኩ!! አሮጊት ሆዚን ማቀፍ፣ ማልቀስ። ሶስታችን
ተቃቅፈን ማልቀስ፡፡ በኋላ እኔ አሮጊትን 'መርስ ባኩ ማዴም' ብሎ
መሳም፡፡ እሷ ሀዚን 'አሙር ቦኩ ብላ መሳም

እኔና ሆዚ ከሜትሮ መውጣት። በታክሲ ወደ ሆቴላችን። ዋጋ
አስራ ሰባት ፍራንክ

«በነገ በንጋት ከሌላ የኢራን ልጅ ጋር ወደ ሶርቦን። በሜትሮ ባንድ አፍታ ከተፍ!»

ጀምሺድና ሆዚ ሰትት ብለው ወደ አንድ ትልቅ ቢሮ ገቡ።የፕሬዚዳንቱ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሲረግጡት ስምጥ የሚል ምንጣፍ ወለሉን በሞላ ሸፍኖታል። ከሰፊው ዴስክ በስተኋላ ተቀምጦ ፒፓ ያጨስ የነበረው መላጣ ባለትልቅ ሙስታሽ ሽማግሌ ዘሎ መጥቶ
እስኪቀመጡ እንኳ ሳይጠብቅ፣ ከጠረጴዛው ወደሰሩ፣ ከበሩ ወደ
ጨበጣቸውና፣ በእጁ መቀመጫ ሶፋ አመልክቷቸው ሲያበቃ፣
መስኮቱ፣ ከመስኮቱ ወደ ጠረጴዛው እየነጠረ መለፍለፍ ጀመረ።ይለፈልፍ ይለፈልፍና ቆም ይላል። Nest ce pas? (አይደለምን) ብሎ ፒፓውን እየማገ በመነፅሩ ሲያያቸው፣ ጀምሺድ ልክ ንግግሩኛ ቁም
ነገሩ እንደገባው ሰው ራሱን እየነቀነቀ

ዊ! ዊ!» ይለዋል

ሽማግሌው መነፅሩንና መላጣውን እያብለጨለጨ መለፍለፉንና እንደ ፈጣን ባቡር እየተዘዋወረ የፒፓውን ትምባሆ ቡልቅ ቡልቅ ማድረጉን ይቀጥላል። አልፎ ኣልፎ ቆም ይልና እያያቸው «Nest ce
pas?» ሲል፡ አሁንም ጀምሺድ ራሱን እየነቀነቀ «ዊ! ዊ!» ይለዋል፡፡አንድ እስር ደቂቃ ከተዘዋወረኛ ካለፈለፈ በኋላ፣ እሁንም «Nest ce pas?» ብሎ ፒፓውን እያቦነነ ሲያያቸው! ጀምሺድ እንደ ደምቡ
ዊ! ዊ!» አለው፡፡

«Comment oui?» («እንዴት ማለት አዎን?») ብሎ ጮኸበት
ኖ!» ማለት ነበረበት። ጄምስድ ተደናግጦ
ኖ! ዊ! ኖ! መርስ ባኩ! ዊ?» እያለ ከተቀመጠበት ተነስቶ፣
ከኪሱ የሲጋራ ፓኮ አውጥቶ ጋበዘው። ሽማግሌው በሀይል እየጮኸ ፒፓውን ከአፉ አወጣና ጀምሺድ አፍንጫ ስር ደቀነው፡፡ ጀምሺድና ሆዚ ከዚያ የሮጡ፣ ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ጊቢ ሲወጡ ቆሙ

«ሩጫችንን ጨርሰን ቆመን፡፡ ያን ጊዜ ፒፓው ገማኝ» አለ
ጀምሺድ ለካ በድንጋጤው የሽማግሌውን ፒፓ መንጭቆ ይዞ ሽሽቶ ኖሯል። ፒፓውን ሊሰጡት ቢሮው ተመልሰው ሲገቡ፣ ሽማግሌው እንደ ቡድህ እግሮቹን ከስሩ አጣጥፎ ጠረጴዛው ላይ ተቀምጧል።ፊቱ ወደ መስኮቱ በኩል ስለሆነ ሲገቡ አላያቸውም። ለጣኦት እንደሚቀርብ የሰለት ስጦታ ፒፓውን እግሮቹ አጠገብ
አስቀመጡለትና፣ እንዳይቀሰቅሱት በእግራቸው ጫፍ እየረገጡ ወጡ ሆዚ እገሩ ተመለሰ፡፡ ጀምሺድ ወደ ኤክስ መጣ ጀምሺድ ሌላ ብዙ የደረሰበትን ኮሚክ ነገር በኮሚክ ድምፁና በብልጮ ሰማያዊ አይኖቹ፣ በእጆቹና በእግሮቹ ትንሽ ትንሽ ደሞ በፈረንሳይኛው ሲያወራልን ስንስቅ ቆየን። ሶስት ሰአት ሲሆን
ኣብዛኛዎቹ ወደ ሲኒማ ሄዱ። እኔ ባህራምን ወደ ካፌ ሰንትራ
ወሰድኩት ከሰንትራ ፊት ለፊት ወዳለው «ሲኒማ ካዚኖ» ለመግባት ሰዎቹ ቲኬት ሲያስቆርጡ እያየናቸው ቀዝቃዛ ቢራ ካዘዝን በኋላ

“Alors, comment vas tu?» (ታዲያስ እንደምነህ?») አልኩት ያው እንደድሮው ቀልደኛ ነው፡ ቡናማ ትንንሽ አይኖቹ
ይስቃሉ፡፡ ግን ከስቷል፣ ጉንጮቹ ጎድጉደዋል፡ አፍንጫው ከድሮው
የባሰ ትልቅ መስሏል፡፡ በጣም ጥቁር ፀጉሩ ከጎንና ከጎኑ - አልፎ
አልፎ - አንዳንድ ሽበት ማውጣት ጀምሯል፡፡ ደህና ነኝ አለ ግን
እየለመደኝ ከሄደ በኋላና ሶስተኛ ጠርሙስ ቢራችንን ከጠጣን በኋላ
ሊነግረኝ ጀመረ

«ቤቶችህ ፃፉልሀ?» አልኩት
«የለም»
ታድያ የእረፍት ጊዜውን እንዴት አሳለፍከው?» አልኩት።
ሲልቪ ልብሷን ስታወልቅ ታየችኝ። በልዩ ጥንቃቄ የተቀረፁ ውብ
እግሮቿ ሀሳቤ ውስጥ ድቅን አለብኝ። ውስጤ ሙቀት ተሰማኝ::
እስክትመለስልኝ ቸኮልኩ። እንደት ያለ ግሩም የእረፍት ጊዜ
ነበር! የባህራም የእረፍት ጊዜ ግን ከዚህ በጣም የተለየ ነበር
እኔ ሲልቪን ተከትዬ በሄድኩ በሳምንቱ፣ ኒኮል ለእረፍቱ ወደ
ቤቷ ስትሄድ (ቤቶቿ ሰሜን ፈረንሳይ ለሀቭር የተባለው ወደብ
ከተማ ውስጥ ነው የሚኖሩት) ጥቂት ፍራንክ ልትተውለት ፈለገች።ግድ የለም አያስፈልገኝም፤ ቤቶቹ ካሁን ካሁን ይልኩልኝ ይሆናል፣
ሳይልኩልኝም ስራ መያዜ ነው አላት፡፡ ስራውን እስከትይዝ ምን
ትበላለህ? ቤቶችህ ባይልኩልህስ? አለችው:: እምቢ በማለቱ አፈረ።ተቀበለ፡፡ በመቀበሉ የባሰውን አፈረ

ከኒኮል ቀጥሎ ሀበሾቹ ሄዱ፡፡ ብቻውን ቀረ፡፡ ስራ ፍለጋ
ጀመረ፡፡ ኒኮል የተወችለት ፍራንክ እንዳለቀ ከሷ ደብዳቤ ደረሰው።
አንድ መቶ ፍራንክ ልላክልህ ወይ አለችው:: አትላኪልኝ፡
አያስፈልገኝም ብሎ ፃፈላት
ይርበው ጀመር። ምግብ ቤቱ ሰፈር ይዞራል፡፡ ምናልባት
በሁለት በሶስት ቀን የሚያበላው ሰው ያገኛል። (በዚያውም ሲጋራ
ይጋብዙታል) ያን ጊዜ ከምግብ ቤቱ ዳቦ በኪሱ ይዞ ይወጣል። ዳቦው በበጋው ሙቀት ቶሎ ይደርቃል። ደረቁን ዳቦ በሻይ እየነከረ ይበላል። ያለስኳር፡ ስኳሩ አልቋል፡፡ ሻይ ቅጠሉም ወደ ማለቁ ነው።ያንኑ ቅጠል አምስት ስድስት ጊዜ ያፈላል። ቅጠሉ ይቀቀልና የሻይ ቃናው ጠፍቶ ሌላ አስቀያሚ ብረት ብረት የሚል ጣእም ይሰጣል

በምግብ ሰአት ባህራም ምግብ ቤቱ አጠገብ ይዞራል። በሶስት
👍191🔥1
ቀን አንድ ጊዜ ያህል አንዱ ምሳ ወይም እራት ይጋብዘዋል። በሶስት
ቀን አንድ ሙሉ ምግብ ማግኘቱም ድንገት ተቋረጠ። የምግብ ቤቱ ሰራተኛች የአመት እረፍታቸውን እንዲያገኙ ተብሎ ምግብ ቤቱ ለአንድ ወር ተዘጋ፡፡ እንግዲህ ወዴት ይሂድ?
አንድ የዘይት ፋብሪካ ውስጥ፣ እቃ መኪና ላይ መጫንና ማውረድ፣ እና ይህን የመሳሰለ የጉልበት ስራ አለ አሉት። ግን ስራው ካ'ንድ ሳምንት በፊት አይጀመርም፡፡ እስከዚያው ምን ይብላ?
ጨነቀው፡፡ የሲጋራ ጥምም በበኩሉ የመፍዘዝ ስሜት ያሳድርበታል።ብዙ ምግብ እንዳያስፈልገው በማለት አልጋው ላይ ተጋድሞ መዋል

ደረቅ ዳቦ በጠነዛ ሻይ ከበላ ሁለት ቀን አለፈው፡፡ ራብ
ሲገድለኝ እንዴት ዝም ብዬ ልተኛ? ብሎ ከቤቱ ወጣ። በተስፋ
ሳይሆን እንደዚሁ ወጣ: ትንሽ እንደሄደ ቆሻሻ መጣያ አጠገብ
የወደቀ የሰርዲን ቆርቆሮ አገኘ፡፡ በደህና ቀን ሰርዲን በጣም ይጠ
ላል፡፡ አሁን ግን ቤቱ ወስዶ እየተንገበገበ ከፈተው። ዘይቱ አላስበላ አለው። ዳቦ ቢያገኝ ዳቦ መግዣ ፍራንክ ፍለጋ ቤቱን ይበረብር ጀመር። አልጋው ስር፣ መፃህፍቱ መካከል፣ ኪሶቹ ውስጥ፤ የተወሻሽቁ የተረሱ ሳንቲሞች አገኘ። ለዳቦ መግዣ ሶስት ሳንቲም ጎደለው: ግን ሲበረብር አንድ እንደ ድንጋይ የደረቀ ቁራጭ ዳቦ አግኝቶ ነበር። እሱን ውሀ ውስጥ ነከረው:: ሲርስ ከውሀው አውጥቶ
ከሰርዲኑ ጋር ፈተፈተው፡፡ በላው፡፡
ትንሽ ቆይቶ ሆዱን አመመው። አቅሰሽለሸው፣ አስታወከው።
ላብ አጠመቀው:: የማስታወኩ ከፍና ዝቅ ያችን የተረፈችውን
ሀይሉን ጨረሰበት ድክም አለው፡፡ አቅሙ ውሀ ሆነ፣ ወደ አልጋው
ሲራመድ ጉልበቱ ከስር ታጠፈ፣ አልወደቀም፣ ቀስ ብሎ ወደ ወለሉ
ወርዶ ተዘረጋ። አይኑን ዘጋ። ትንሽ ቆይቶ ብርድ ብርድ አለው::
እየተንፏቀቀ አልጋው ደረሰ። አንሶሳው ውስጥ ገባ። አይኑን ዘጋ። እንደማዞር አለው:: ራቡ ብቻ አይደለም፡ ሲጋራ ማጣቱም ጭምር ነው። በረደው። በዚህ በጋ ሙቀት? ትኩሳት መሆን አለበት። እናቱ ትዝ አሉት፡፡ አመመህ» ብለው ግምባሩን ሲነኩት፣ አልጋው ዳር ሲያዩት፣ ትራሱን ሲያመቻቹለት፣አስታወሰ። ድንገት ብቸኝነት ተሰማው:: ውስጡ አንድ ድምፅ ብቻዬን ነኝ፣ ማንም የለኝ ማንም አይደርስልኝ!» ብሎ ጮኸ፡፡አሰፈራው። ከውስጡ፣ የድሮ የልጅነት ድምፁ «እማማ!» ብሎ ሲጣራ ተሰማው። «ወይኔ፣ ማበዴ ይሆን እንዴ? አሜሬካኖቹን
ሳላባርር?» ብሎ አሰበ፡፡ የባሰውን ፈራ። ብርድ አንቀጠቀጠው
ጥቅልል ብሎ ተኛ። በቅዠት ህልሙ እናቱ ትልልቅ ለስላሳ ትሬሳ
ላይ አስደግፈውት ሾርባ በማንኪያ ሲያጠጡት፡ አሜሪካኖችና የሻህ
ሰዎች መጥተው ሊያርዱት ሲሉ፣ ሲሸሽ፡ በጫካ በሸለቆ ሲያባርሩትን ሲሮጥ፣ ሲሮጥ፣ ሲሮጥ፣ አልጋው ውስጥ እያቃሰተ ሲገላበጥ፣ በላብ ሲታጠብ፤ በብርድ ሲንቀጠቀጥ አደረ
ጧት በማለዳ ነቃ። ጉልበቱ ትንሽ ተመልሶለታል፡፡ ተነስቶ ወጣ። ከቤቱ ትንሽ ሄድ እንዳለ፣ የወተት መኪኛ መጣና አንድ የምግብ ሽቀጥ ሱቅ ደጃፍ ላይ ሶስት ደርዘን የወተት ጠርሙስ
ኣስቀምጦ ሄደ። ባህራም ሁለቱን ጠርሙስ አንስቶ ወደ ቤቱ
ሲመለስ፣ መንገዱ ዳር አንድ ተገምጦ የተጣለ ፖም አገኘ፡፡
የተጎመጠውን በቢላ ቀርፍ ጥሎ፤ የቀረውን ግማሽ ፖም በውሀ
አጥቦ በልቶ ወተቱን እየጠጣ ዋለ

ሲመሽ ራብ አንገበገበው:: ኩራቱን ክብሩን ረሳ፡፡ አንድ የሚያውቀው ፈረንሳይ ቤት ሄደ። በቀጥታ «በራብ ልሞት ነው። አለው። ፈረንሳዩ ቤቱ አስገባና ጭቅና ከድንች ጥብስ ጋር፣ ስፓጌቲ፣ ሰላጣ፣ ቺዝ፣ ወይን አቀረበለት። ተንገብግቦ አምስት ጉርሻ
ያህል እንደ ጐረሰ ሆዱ ተዘጋ፡፡ እስኪጠግብ ከበላ ሳምንት
አልፎታል፡፡ ራቡ ሊገድለው ነው፣ ከዛሬ በኋላ መቼ ምግብ ሊያገኝ
እንደሚችል አያውቅም፡ አሁን ታዲያ ሆዱ እምቢ አልቀበልም
አለው:: በጣም ተበሳጨ፣ እምባ ተናነቀው፣ እዚያው ራሱን ደፍቶ
ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡ ፈረንሳዩን እግዜር ይስጥልኝ፣ ይቅርታ
ያድርጉልኝ» ብሎት ወጣና ቤቱ ተመለሰ። ተኛ በማለዳ ተነስቶ ከሌላ የምግብ ሱቅ ደጃፍ ሶስት ጠርሙስ ወተት አንስቶ ወሰደ። ተጋድሞ እሱን እየጠጣ ዋለ። ሌሊት ተቅማጥ ያዘው

ሲነጋ እንደምንም እየተጐተተ ዘይት ፋብሪካው ሄደ። ስራውን
ነገ ትጀምራለክ አሉቴ አለቃው አንዲት አርጀት ያለች ሴትዮ ናት
ሲያያት ፊቷ በጣም ርህሩህ መሰለው:: ችግሩን አጫወታት።
ከደመወዝህ ትከፍለኛለህ ብላ ሃምሳ ፍራንክ አበደረችው። ምግብ ገዝቶ ቤቱ ወሰድ፡፡ ትንሽ ቀማመሰ። ለመጀመሪያ ጊዜም ሲጋራ አጨሰ። ትልቅ እፎይታ ተሰማው፡፡ ተኛ። ነቅቶ እንደገና ትንሽ በላ፣ አንድ ሲጋራ አጨሰ፡፡ ተመልሶ ተኛ። ሲነጋ ደህና ቁርስ
በልቶ፣ አንድ ሲጋራ አጭሶ ወደ ስራው ሄደ፡፡

ከባድ እቃዎችን ከመኪና ማውረድና መኪና ላይ መጫን ነበር ስራው። ለመጀመሪያ ጊዜ እንድ መጠነኛ ሳጥን ከመኪናው አንስቶ ተሽክሞ ወደ ግምጃ ቤቱ ሲወስድ፣ ጥቂት እርምጃ እንደሄደ ጉልበቱ ከስሩ ታጠፈበት። ሳጥኑን ትከሻው ላይ እንደተሸከመ ተምበረከከና! በዚያው ቀስ ብሎ ቁጭ አለ

አሮጊት ብጤ አለቃው መጥታ ሳጥኑን ከላዩ ላይ አነሳችለት።
አፍሮ ቁጭ እንዳለ ቀረ። ውሀ አምጥታ አጠጣችው:: ብርጭቆውን ሲመልስላት፣ በርህሩህ ገፅዋ እስተያየት በጣም እንዳዘነችለት ታወቀው። ለሚቀጥለው አራት ቀን፣ ማለት ጉልበቱ እስኪመለስለት ድረስ፣ ጡንቻ የማያስፈልገው ስራ ሰጠችው፡፡ በኋላ ከባድ እቃዎችን
መሽከም ጀመረ። ትከሻውን ያመዋል፤ ወዝ የሚቆረጥ ይመስለዋል፣ መዳፉ ይላላጣል፣ በበጋው ሙቀት ከባድ እቃ መሸከሙ አንዳንዴ ራሱን
ያዞረዋል። ግን ማታ እራቱን ጥስቅ አርጎ ይበላል፣ ቡና ጠጥቶ
ሲጋራ ያጨሳል። አልጋው ውስጥ ይገባል። ከመቅፅበት እንቅልፍ
ይዞት ጥርግ ይላል

ልክ አራት ሳምንት እንደሰራ ስራው አለቀ። አሰናበቱት፡፡ቅዳሜ ነበር፡፡ ባለውለታ አለቃውን አመስግኖ ሲሰናበታት እራት ጋበዘችው:: ቤቷ አመሽ፡፡ ሲያያት፣ እርጅና አፈፍ ላይ ደርሳለች። ወንድ ካገኘች ብዙ ጊዜ ሳይሆናት አይቀርም፡፡ ከእንግዲህ ማግኘቷንም እንጃ፡ ሲያስብ ጊዜ፣ እሷ ደግ ባትውልለት ኖሮ ይህን ጊዜ በራብ ሞቶ ነበር። ሆን ብሎ ብዙ ወይን ጠጣና ሰከረ። አብሯት
አደረ ስራ ከተውኩ ይኸው ዛሬ አንድ ሳምንት ሆነኝ፡፡ ግን
የተሸከምኩበት አሁንም ትከሻዬን ወገቤን ያመኛል» አለ። ከዚህ
በፊት የጉልበት ስራ ሰርቶ አያውቅም ነበር

«ይሄ ሁሉ ሲሆን ጀምሺድ የት ነበር?» አልኩት

«ሞንቴ ካርሉ»

አታውቅም እንዴ? ቁማርተኛ ነውኮ። ቅዳሜ ቅዳሜ እዚህ
ካዚኖ ነው የሚያመሽው

ከተቀመጥንበት ካፌ ሰንትራ ፊት ለፊት መንገዱን ተሻግሮ
«ሲኒማ ካዚኖ» በብዙ መብራት አሸብርቆ ይታያል። የሲኒማ ህንፃው ቀኝ ጎን ቁማር ቤት ነው። ይኸኔ እዚያ ውስጥ ጥቁር ልብስ የለበሱ ወንዶችና ክቡር ጌጣጌጥ ባንገታቸውና በእጃቸው ያሰሩ ሴቶች የመጠጥ ብርጭቆ ወይም ሲጋራ እንደያዙ አይኖቻቸውን
የሚሽከረከረው ሩሌት ላይ ተክለዋል። የጀምሺድ አይኖችም ሩሌቱ ላይ ተተክለዋል። እንደ ቅድማቸው ሳቅና ቀልድ ይጨፍርባቸው ይሆን? ወይስ ፍዝዝ ብለው ይሆን?

«ባሀራምን ብዙ ይበላል?» አልኩት

«አዎን ይበላል። ግን የበላውን ወስዶ መልሶ ያስበላል። አንድ
ቀን ሰባት ሺ ፍራንክ ሲበላ አይቼዋለሁ። ታድያ እዚያው መልሶ ተበላ።.. እውነተኛ ቁማርተኛ ነው። ማለቴ፣ የሚጫወተው አገኛለሁ ብሎ ተስፋ ለማድረግ አይደለም: ለቁማር ፍቅር ነው። ከሚያገኘው ገንዘብ የሚያጠፋው ይበልጣል። ከሁለት ወር በፊት ሲነግረኝ፣ ኤክስ ከመጣ ብቻ ሰላሳ ሰባት ሺ ፍራንክ ተበልቷል»

«ገንዘብ ከት ያመጣል?»
«ቤቶቹ በጣም ሀብታም ናቸው»
👍222👏1
ይህን ጊዜ ወደ ውጭ በኩል ስመለከት፣ ተካና አንዲት ግዙፍ
ብጤ ሴት እጅ ለእጅ ተቆላልፈው ሲሄዱ አየሁ። ባህራምን
«ተካ አገኘ እንዴ?» አልኩት
ሳቁን ለመቋጠር እየሞከረ «አዎ። ጀርመን» አለኝ
«እንዴት ያለች ናት?» አልኩት። ቡናማ አይኖቹ ያስቃሉ፣ ግን
ጥርሶቹን አንደምንም ከድኗል
«ከንፈሮቿ በጣም ውብ ናቸው:: እንደ ፅጌሬዳ ናቸው» አለ
«እና?»
አሁንስ ሳቁ እያመለጠው እና ከከንፈሯ በላይ ምን የመሰለ
ጥቁር ሙስታሽ አላት። ለምን እንደማትላጨው አይገባኝም አለ።
መሳቅ ጀመርኩ፡፡ ከኪሱ አንድ ወረቀት አውጥቶ አቀበለኝ፡፡
«ሉልሰገድ ነው ባማርኛ የፃፈልኝ፡፡ የናንተ አገር ምሳሌ ነው:: ጮክ
ብለህ አንብብልኝማ፡፡ ልሰማው እፈልጋለሁ» አለኝ፡፡ አነበብኩለት

«ለአፈ ግም አፍንጫ ድፍን ያዝለታል»

እየሳቀ «ምን ማለት ነው? በደምብ አስረዳኝማ» አለኝ፡፡ሳስረዳው የባሰውን ሳቀ:: በመጨረሻ

«ምንድነው የሚያስቅህ?» አልኩት፡፡ እየተንከተከተ

«ምሳሌው ነው የሚያስቀኝ» አለ «በፊት ተካ አፉ ይሽትህ ነበር?»

«አዎን፡፡ ታድያ ይሄ ምኑ ያስቃል?» አልኩት

«ባለሙስታሿ ጀርመን ልጅ አፍንጫዋ አያሽትም!-- ድፍን
ነው!» አለኝ፡፡ ሁለታችንም በሳቅ ተንፈራፈርን፡፡

«እውነትክን ነው ግን?» አልኩት

«ሀለላሴ ሙት!»

ከዚያ እንግዲህ የኩምክና ወሬ መጣ፡፡ አብረን ስንስቅ አመሸን።

💫ይቀጥላል💫
👍151
#ሊሆን_ይችላል !!
:
:
#በአሌክስ_አብርሃም


ለሚስቴ ያለኝ ፍቅር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ነው የሚሄደው። ችግሩ ፍቅሩ የሚጨምረው
ብቻውን አልነበረም፤ እግር እጅ ከሌለው ቅናት ጋር እንጂ። በእኔ ልብ ውስጥ ፍቅርና ቅናት
እንደመንትያ ልጆች እኩል ነበር የሚያድጉት። እየቆየ ግን የፍቅር አቅም እየኮሰመነ፣ የቅናቴ ጡንቻ
እየፈረጠመ ሄደና ቅናቴ እንደ ምርቃት ቆብ ከነመነሳንሱ በፍቅሬ አናት ላይ በኩራት ጉብ አለ።

አያድርስ ነው! ርኩሳዊ ቅናት የሰይጣን አንዱ ሥራ ሳይሆን ሰይጣን ራሱ ሳይሆን አይቀርም። ሚስቴ መዓዛ ጨዋነቷን አገር ይመሰክርላታል። ግን ምን ዋጋ አለው። የእኔ የባሏ ሆድ ግልፅ ባልሆነ ምከንያት ሻክሯል።

“ምን ስታደርግ አይተሀት ቀናህ?” ብባል መልስ የለኝም። ግን እቀናለሁ። ስቀና እስሳጭባታለሁ።
አንዳንዴ እንደውም ከመሬት ተነስቼ ሁለት-ሦስት ቀን አኮርፋታለሁ፤ ግራ ይገባታል። የምትይዝ የምትጨብጠውን ታጣለች። አንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ እየኖርን ስዘጋት የምታደርገውን ነገር ታጣለች። ..ደስ ይለኛል፡፡ ጭንቀቷ ነፍሴን ያረካታል፡፡ አንዳች የመበቀል እርካታ ይሰማኛል። ከንፈሯ እየተንቀጠቀጠና ቀይ ጉንጯ በርበሬ መስሎ ግራ ተጋብታ ስመለከታት በኩራት ኩፍስ ብዬ በስቃይዋ
እዝናናለሁ!

ብዙ ጊዜ፣ በተለይ ወንዶች በፍቅረኝነት እያሉ ቅናት ያጠቃቸዋል። ያፈቀሯትን ሲያገቡ ግን በቁጥጥራቸው የዋለች መስሎ ስለሚሰማቸው አይቀኑም ሲባል ነበር የሰማሁት። የእኔ ቅናት ግን የተገላቢጦሽ ነው። በፍቅረኝነት እንደነበርንም ይሁን የተጋባን ሰምን አልቀናም ነበር። ለዛም ሳይሆን አይቀርም መዓዛን ብዙም ትኩረት ሰጥቼ የት ገባች፣ የት ወጣች የማልለው። የኋላ ኋላ ግን ቅናት ከነ የልጅ ልጁ ሰፈረብኝ።

የቅናት ትልቁ ችግር የሚቀናበት ሰው እንደሚያስቡት መሆን አለቀመሆኑ ላይ አይደለም። የሚቀናውን ሰው ራሱን በበታችነት ስሜት አጥለቅልቆ ያልሆነውን ማድረጉ እንጂ። መዓዛ ፊልም እየተመለከተች አንዱን የፊልም ተዋናይ ካደነቀች የጨጓራ ሕመሜ ይነሳል። በቃ ስለምቀና፣ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀውን ጎበዝ የፊልም ተዋናይ ማጣጣል እጀምራለሁ። መዓዛ ከተከራከረችኝማ በቃ ሰውነቴ ሁሉ
በብስጭት ይንገበገባል፤ እቀናለሁ !

“ምናባቱ ይሄ ሴታሴት ካሜራ ፊት ጀግና ይመስላል፣ ልክስክስ፣ እዚህ ካዛንችስ መጠጥ ቤት በመጠጥ ቤት፣ ጫት ቤት ለጫት ቤት ሲዞር አይደል የሚውለው!? እሱ ያልተኛቸው ሴተኛ አዳሪዎች የሉም።

“ኧረ አብርሽ በእግዚአብሔር፣ የተከበረ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነው…” ትላለች መአዚ።

“አንቺ ስለ እሱ ሕያወት ስታጣሪ ነው የምትውይው? ምን ታውቂያለሽ…”

“እኔማ ምን አውቃለሁ ራሱ ነው በቲቪ ከነሚስቱ ቀርቦ ኢንተርቪው ሲሰጥ ያየሁት።” ትላለች
ጩኸቴ አስደንግጧት።

“እና በቴሌቪዥን ቀርቦ ጠጣለሁ፣ እቅማለሁ፣ ሴት አይተርፈኝም ይበል…?” እልና ሙዓዚ ላይ
አፈጥባታለሁ። መዓዚ በግርምት እየተመለከተችኝ ዝም ትላለች። ፊልም በተከፈተ ቁጥር መዓዛ
የምታደንቀውን ሰው ስዘልፍና ሳጣጥል ፊልሙን በቅጡ ሳናየው ስለሚያልፍ መዓዘ. ቀስ በቀስ
ማድነቋን አቆመች። እኔ ግን መቅናቴን አላቆምኩም። አንዱ ወንድ ተዋናይ በተናገረው ነገር ከሳቀች ወይም በመደነቅ ራሷን ከነቀነቀች ቅናቴ ያስለፈልፈኛል፤ እነዚህ የጠላ ቤትና የጫት ቤት ቀልድ እያመጡ ይቀባጥራሉ፤…አይ የኢትዮጵያ ፊልም እንዲህ የዱርዬ መናኸሪያ ሆኖ ይቅር…! ምን የፊልም ኢንዱስትሪ ነው፣ የዱርዬ፣ የሥራ ፈት ኢንዱስትሪ ቢሉት ይሻላል።”

ይሄ ባህሪዬ ሲያስመርራት መዓዚ ከእኔ ጋር ፊልም ማየት አቆመች፡፡ በፊት ፊልምሲከፈት ተንደርድራ
መጥታ ጎኔ ትቀመጥና ራሷን ትከሻዬ ላይ ዘንበል አድርጋ ነበር የምትመለከተው። የሚያስቅ ነገር
ስትመለከት አንገቴ ሥር ገብታ ፍርፍር ብላ ትስቅ ነበር። ዕድሜ ለቅናቴ! ይሄው ፊልም ከእኔ ጋር
ማየት አቆመችና አረፈችው። ፊልም ሲከፈት ወይ ጓዳ ገብታ ትንጎዳጉዳለች፣ ወይ መኝታ ቤት ትገባና ትተኛለች፣ ወይም ታነባለች፡፡

“ፊልም አታይም እንዴ?” እላታለሁ።

"ይቼዋለሁ።”

“የት አየሽሁ?”

"ባለፈው እማዬጋ የሄድኩ ጊዜ።"

"እማዬ ቴሌቪዥናቸው ተበላሸ አላልሽም…?”

“ሌላ ገዛች።”

“ማን "ገዛላቸው?”

"ኧረ አብርሽ በእግዚአብሔር አታጨናንቃኝ” ትልና በምሬት ታየኛለች። በቃ እናቷ ቤት አይደለም ያየችው …. የሆነ ወንድ ጋር ትክሻው ላይ ራሷን ጣል አድርጋ (በየመሀሉም እየተሳሳሙም ሊሆን ይችላል)፣
በቃ እንደዛ ነው ያየችው፣ … ልክስክስ ውይ ሴቶች ! እብሰለሰላለሁ፡፡ ትከሻውን የተደገፈችው ወንድ ማን ይሆን…? ምናልባት አብረውም ተኝተው ሊሆን ይችላል፤ አብራ ፌልም ለማየት ያልተመለሰች
እሺ ለእናቷ ማን ቴሌቪዥን ገዛላቸው? ይሄው ታሪኩ ሲገጣጠም መዓዛ ሀብታም ወንድ ጋር ሄደች…፣ ቤቱ ሄደው ፊልም አብረው አዩ፣ (ሶፋ ላይ አብረው ተቀምጠው፣ ጫማዋን አውልቃ፣ የሚያማምሩ እግሮቿን ሶፋው ላይ ሰብስባ አስቀምጣ፣ ልክ እንደ ቤቷ ዘና ብላ….)፣ ከዛ አብረው መኝታ ቤት ገቡ …፣ ኧረ ሶፋውን ማን ይዞባቸው ከዛ ነፍሳቸው መለስ ሲል አወሩ፣

ፊልም ትወጂያለሽ የኔ ቆንጆ ሊላት ይችላል፣ ግን “የኔ ማር" ነው የሚላት፣

“በ.ጣ.ም!!” ትለዋለች ደረቱ ላይ ተለጥፉ! ይቺ መዥገር። ሁለቱም መዥገር ናቸው እንጂ እሷም እሱ
ላይ እሱም ትዳራ ላይ የተጣበቁ መዥገሮች!!

"እና በየቀኑ ትመለክቻለ?”

"በፊት ነበር፤ አሁን ባሌ እየተነዛዘነዘ በየት በኩል ሊያሳየኝ ብለህ።”

"ኦ..ባልሽ ግን ምናይነት ደደብ ቅል ራስ ነው ባክሽ። ሙቪ እያያችሁ ይነዛነዛል ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ አሜዚንግ !

በጣ…ም…! ምን ቅል ብቻ፡ ድንጋይ …! ባልጩት ራስ ነገር ነው እንጂ። ሲጋባ ሲዉጣ መነዛነዝ ነው።
እንዳልተሳካላት ተዋናይ ያየውን ተዋናይ ሁሉ ምዠመዝለፍ ነው ስራው” ትለዋለች::

እሷን ባፈቀርናት፣ ቤቴን ትዳሬን ባልኩ የማንም ዱርዬ ጋር ስታማኝ አያበሳጭም? (ውስጤ ይብከነክናል፤) ላብ ላብ ይለኛል! በላብ የጨቀየ መዳፌን በእልህ ጨብጬ ሶፋውን በቡጢ እነርተዋል መዓዛ በድንጋጤ ከራማዋ ተገፍፎ እያማተበች ትቀርበኝና ጭንቀት በወረረው ፊቷ ላይ እንባ በቋጠሩ ዓይኖቿ እየተመለከተቸኝ፣

“ምነው ፍቅር ምን ሆንክ? ከሰው ጋር ተጣላህ እንዴ? ላብ በላብ ሆንክ እኮ፧ አመመህ እንዴ የኔ
ፍቅር…?” ጉንጬ ላይ እጇን ልታሳርፍ ስትልክ እጇን ወደዛ አሽቀንጥሬ ተነስቼ ወደ መኝታ ቤቴ እገባና የቁም ቅዠቴን ተኝቼ እቀጥላለሁ፡ እሷም ግራ በመጋባት ወገቧን ይዛ መኝታ ቤት በር ላይ ቆማ ትቆያለች፣ “ምን እዳ ገባሁ!” እያለች።

እቀናለሁ…. እቀናለሁ ! እቀናለሁ ! አንዳንዴማ በህልሜ ሁሉ ስለምቃዥ መዓዛ ፀበል እንሂድ
ትለኛለች። ቢመቻት እብድ ነው ብላ አማኑኤል አሳሰራኝ ዓለሟን ከሌላ ወንድ ጋር ልትቀጭ
እንዳሰበች እጠረጥራለሁ… ተገኝቶ ነው ?አሁን ሌላ ወንድ ጋር ብትሄድ ሰው እያስቀምጣትም፣ እስኪ ምን አጥታ ጥጋብ ልክስክስነት እኝጂ ቱ ይሄን የመሰለ ሸበላ የጠገበ ደመውዝ የሚያበላ ባል ትታ …ወይ ጥጋብ ይላታል .. ካበድኩላት ግን እንዳሻት ትዘላለች ሰውም አይቃወማትም ምን ታድርግ
እብድ ጋር ትኑር እንዴ ታዲያ? ወጣት ናት! ቆንጆ ናት! ስንት ነገር ያምራታል! ምን አልባት…” ሊሉ
ይችላሉ። እኔ ደግሞ ለእልኳ አላብድ ሲያምራት ይቅር!!
👍45
ሌላ ቀን ደማቅ ሰማያዊ ሹራብ በቢጫ ሱሪ ለብሼ ልወጣ ስል፣ ኧረ አብርሽ አብሮ አይሄድም!
ሱሪውን ቀይረው የኔ ቆንጆ፤ ፊትህ ጥቁር ቢሆን እንኳን ያምርብህ ነበር፤ ካንተ ጋር ግን አይሄድም።”
ብላ በሳቅ ፍርስ አለች።ቆይ እሷ ስለወንድ አለባበስ እንዴት አወቀች? ይሄ ስለ ልብስ ቀለም ሳይሆን ስለእኔ ምርጫ አለማወቅ ለመናገር ሆነ ብላ የተናገረችው ነገር መሆን አለበት. እንዳልሰማ ሰው ትቻት ወጣሁ! እዛ ላስቀመጠችው ለእናቷ ቴሌቪዥን ለሚገዛው ደደብ ውሽማዋ ትንገረው … ምናልባት
ጥቁር ሊሆን ይችላል … ትቻት ወጣሁ። ለምን እንደሆነ እንጃ እንደማላከበራት ማሳየት እፈልጋለሁ።

አላለቀም
👍18👎31
#ሊሆን_ይችላል


#በአሌክስ_አብርሃም (መጨረሻው)

...ትቻት ወጣሁ። ለምን እንደሆነ እንጃ እንደማላከበራት ማሳየት እፈልጋለሁ።
በር ላይ አንድ የማልወደው ጎረቤቴ ደረቱን ገልብጦ በጠዋቱ በፓክ አውትና በቁምጣ ኮንዶሚኒየም ደረጃ ላይ እገኘሁት። እኔ ስወርድ እሱ ሲወጣ ነበር የተገናንነው፡፡ በእጁ የመዝለያ ገመድ ይዟል፤
ከስፖርት እየተመለሰ ነው።

“ሰላም አብርሽ!” አለኝ በፈገግታ።

"ሰላም ሰለሞን!” ብዬው ላልፍ ስል፣

“ምነው ይሄ አለባበስህ ትንሽ አልደመቀም…?” አለና ፈገግ አለ። ቀልዶ ምቷል ለዛ ቢስ ለካፌ ሁላ!!
እንዳልሰማሁ አለፍኩት። ጣሳ ራስ እሱ ስለኔ አለባበስ ምን አገባው!? ይሄ ቦዘኔ ጎረቤቴ ሥራው ምን እንደሆነ እንጃለት (ሥራ እንኳን ያለው አይመስለኝም) ሁልጊዜ የምንጋራው በረንዳ ላይ ወንበር
ያወጣና ዝሆኔ የያዘው የሚመስል (ፈርጣማ ይሉታል አንዳንዶች) ጠብደል ግንዲላ እግሩን ዘርግቶ
ጋዜጣ ያነባል። ኑሮው ዘና ያለ ነው።አንዳንዴ ውድ የሆነ ሙሉ ልብሱን ይለብስና ዲ ኤክስ መኪናውን አስነስቶ ይሄዳል … አፍታ ሳይቆይ ያመለሳል፡፡ ቤቱ ውስጥ የቀበረው ነገር ሳይኖር አይቀርም፤ ከቤቱ ርቆ አይሄድም፡፡ ይዞት ይሂድና! ቆይ ግን ቤት እየዋለ እንዲህ ተዝናንቶ የሚውልበትን ገንዘብ ከየት
አባቱ ነው የሚያመጣው። ሌባ ይሆን…? ወይንስ ቅጥር ነፍሰ ገዳይ …?

ድንገት አንድ ሐሳብ እእምሮዬ ውስጥ ፈነዳና ቀጥ ብዬ ቆምኩ፤ ፋጭጭጭጭጭጭጭ እንደ
መኪና አቋቋሜ ድንገተኛ ስለነበር ከኋላዬ የነበረች ልጅ ልትጋጨኝ ለትንሽ ተረፈች። ቆይ ይሄ ጎረቤቴ
ቤት ሲወል ምን እያደረገ ይውላል? መደዳውን አራት ቤቶች አሉ። ጥግ ላይ የኔ ቤት። መዓዛ ሥራ ስለሌላት ቤት ነው የምትውለው። ቀጥሎ ሁልግዜ ዝግ የሆነው እንደኔ ከርታታው ጎረቤቴ (ፊልድ ነው ሥራው)፤ ቤቱ ሁልግዜ ዝግ ነው፤ የሸረሪት ድር ሁሉ በሩ ላይ ያደራል። ቀጥሎ ይሄ ቦዘኔ አለ። ቦዘኔው
መልኩ ጥቁር ነው፡፡ ልክ እንደ ፊልም የሚስቴ ንግግር በምልሰት ታየኝ፤ “ጥቁር እንኳን ብትሆን…”
ነው ያለችው አይደል?…ቢንጎ !!!

ቦዘኔው ቤት ነው የሚውለው። ምን ቤት እኔ ቤት ልበል እንጂ ! መቼስ በአንድ ዝግ ቤት ዳርና
ዳር ቦዘኔውና ሚስቴ ብቻቸውን ሲውሉ አይነጋገሩም ማለት ዘበት ነው። እንዴ አብረውም ፊልም
ሊመለከቱ ይችላሉ እንጂ። በእኔው ቴሌቪዥን፣ በእኔው ዲቪዲ፣ እኔው ሶፋ ላይ !...
ሊሆን ይችላል !!

ተመልሼ ወደ ቤቴ ሮጥኩ!

ጉድና ጅራት አሉ ! ወይ ድፍረት……!

በቤቴ … በራሴ ቤት … በራሴ አልጋ … በራሴ ብርድ ልብስ … በራሴ እንሶላ … በራሴ ፍራሽ … በራሴ ሚስት በራሴ … ! ባፍጢሜ እስከምደፋ ታጣደፍኩ። ምን ዋጋ አለው እስካሁን ነገር የተበላሸውን !አልጋውን እንደሆነ እኔ ሚስኪኑ እኔ ራሴ እንደ መኪና አሙቄ ትቼለት ወጥቻለሁ። መዓዛንም ቢሆን ሌሊቱን ልታቅፈኝ ስትሞክር በኩርፊያ እጇን እየገፋሁ ጀርባዬን ሰፕቻት በአምሮት አቃጥያት ነው
ትቻት የወጣሁት። በስስ ፒጃማ የሞቀ አልጋ ውስጥ እሳት ሆና ትጠብቀዋለች። በቃ ምን ቸገረው
ቁምጣውን ወለቅ አድርጎ በጠዋቱ ገነት መግባት ነው !!! ጉድ ጉድ ጉድ አሟሙቄ ለሰው። ወይ ነዶ
!! ሮጥኩ! ኮቴ እንደ ክንፍ እየተውለበለበ ወደ ቤቴ … ምን ቤት አለኝ ቤቴ ፈራርሶ ! ሱናሚ አውሎ ነፉስ ከሥር መሠረቱ ቤቴን ነቅሎ የሚጥል ጎርፍ ከጎረቤት አገር !

መንገዱ ረዘመብኝ። የመዓዛ ደረት የተላለጠ ሸንኩርት መስሎ ታየኝ። ጡቶቿ ስስ ፒጃማዋን ወጥረው
ጫፋቸው ባቄላ ባቄላ መስሎ… ቀይ ከንፈሯ እየተንቀጠቀጠ ከሥር ተንጋልላ.. የሚያማምሩ እግሮቿ በጠረንገሎው ዙሪያ ተጠምጥመው ታየችኝ። እግሮቿማ ለምን አያምሩ፧ እሾህ አይወጋቸው ጋሬጣ ሎሚ መስለው እንደተቀመጡ ሳይወጡ ሳይወርዱ ቤታቸው። መኝታ ቤታቸው ድረስ ካንድ አይሉ ሁለት ባል ሲመጣላቸው …፤ ያ የገደል ስባሪ የሚያህል ቦዘኔ ጎረቤቴ ከነለቡ፣ ከነጠረኑ አልጋ
ላይ ታየኝ። ምናለ ሻወር እንኳን ቢወሰድ የሰው እልጋ መድፈሩ ካልቀረ ለወጉ ለሥርዓቱ ሰውነቱን
ለቅለቅ ብሎ ቢዳፈር ምናለ! ስራ ውዬ ደክሞኝ ነው የምገባው ለኔስ አያዝኑም? አንሶላ መጋፈፉን
ቢቀማኝ አንሳላ ለብሼ ኩርምት የምልባትን አልጋ ምናለ ቢተውልኝ? ወይ ጭካኔ ! ታየኝ ላቡ እንደማስቲሽ መዓዛ ውብ ሰውነት ላይ ታመርጎ አልለቅም ሲል። ማን ያውቃል የራሴ ሚስት በስሜት እየተስረቀረቀች የኔ ጌታ! ጠረንህ የናርዶስ ሽቶ ነው› እያለችው ይሆናል፤ ፍቅር እንኳን አፍንጫን እእምሮን ይዘጋ የለ!

ሲሆይችላል!!

ደግሞ እንደ አባወራ ቤት አለኝ ብዬ ሶፋ ላይ ተጎልቼ የማላውቀው አገር እሳተ ገሞራ ሲፈነዳ በሐዘን
ከንፈሬን እየመጠጥኩ ቢቢሲ አያለሁ…. የዋህ ኣባወራ እሳቱን ጎረቤት አስቀምጦ እሳተ ጎሞራ በዜና ያያል። እኔን ራሴን ዜና አደረጉኝ፤ ዕድሜ ለሚስቴ፣ እኔን ራሴን ዜና ! ያውም ሰበር ዜና …! ሞራሌንም ቅስሜንም የሚሰባብር የሚያነካካት ሰበር ዜና ! ሞኝ ጋዜጠኛ አለ እዚህ አገር …ቢኖርማ ካሜሬአቸውን ይዘው ከኋላዬ ተከትለውኝ በሮጡ ነበር ! ዝም ብለው ስለግድብ ያውሩ … እዚህ ስንት ሚሊዮን ሜጋ ዋት እሳት ከመኝታ ቤቴ ሲመነጭ መቼ በቁም ነገር ተመለከቱት…!!

ቤት ስደርስ ሰሩ ብርግድ ብሏል…!

እግዚኣ ድፍረት ! ያምናለ በሩን እንኳን መለስ ገርበብ ቢያደርጉት ሰው ባይፈሩ ነፉስ እንኳን አይፈሩም ወይስ የመኝታ ቤቱን በር ቆልፈው ሊሆን ይችላል !!

በተከፈተው በር ተወርውሬ ስገባ መዓዛ “አብርሽዬ ድረስ…" ብላ በእጇ የያዘችውን የዱቄት ሳሙና
በቁሟ ለቀቀችው፤ (ሳትለኝም ደርሼ ነበር እኔማ). ... ዱቄት መስሎ ሳሎኑ ምንጣፍ ላይ ተዘራ። ራቅ ብሎ ሊታጠብ የተዘጋጀ የእኔ የቆሸሸ ልብስ ተከምሯል! በዚህ ሌሊት ልብሴን ልታጥብ እየተዘጋጀች ነበር፤ መዓዛ ! የሐፍረቴን ወደ መኝታ ቤት ገብቼ ኮሜዲኖውን ከፈትኩና የረሳሁትን እቃ የወሰድኩ
መስዬ ተመልሼ ወደ ሥራዬ ሮጥኩ። ትንሽ ሐፍረት ቢሰማኝም አእምሮዬ ውስጥ ግን አንድ ሐሳብ
መጣብኝ ..

መዓዛ ልብስ አጥባ ካሰጣጥቻ በኋላ እስከሚደርቅ ምን ትሠራላች በተሰጣት ልብስ ውስጥ
ጠረንገሎ፤ ጎረቤቴ እየተሽሎከለከ ወደ ቤቴ ሲገባ … በሩ ሲዘጋ … ታየኝ !

ሊሆን ይችላል!

ከሰዓት ከምሠራበት አየር መንገድ ቢሮዬ ሆኜ ለመዓዛ ስልክ ደወልኩላት። አንዴ ጠራ …. 2 3 4
5. የደወሉላቸው ደንበኛ ስልክ አይመልስም? እባክዎ …”

ወይ እባክዎ … ምኑን ተከበርኩት … ምኑን ለአንቱታ በቃሁት… ኮት መልበስ ብቻውን አንቱ አያስብል
ቢሮ ያማረ ወንበር ላይ መጎለት አንቱ እያስብል … ጓዳዬ እየፈረሰ ቤቴ እየተገረሰሰ .… ሦስት ጉልቻ
ያልኩት ትዳሬ ስድስት ጉልቻ እየሆነ ወይ አንቱታ : ሰልኩ ያለው ሳሎን፤ ሚስቴ እሰካሁን መኝታ
ቤት ... ወይም የጠረንገሎው ጎረቤቴ ቤት ትሆናለች … ማን ያንሳው ስልኩን … ዘመድ እንደሌለው ሐዘንተኛ ብቻውን ያልቅስ አንጂ…፤ ብቻውን ስልኩ…!

ስብሰለሰል ስልኬ ጠራ …. መዓዛ ነበረች።

"የት ሄደሽ ነው ስልኩ ይሄን ያህል ሲጠራ…"
"ልብስ ሳጥብ ውዬ አሁን ገና ጨረስኩና ሻወር ገብቼ እኮ ነው…! ከነሳሙናዬ ራቁቴን ነው አሁን የቆምኩት ፍቅር ብታየኝ ሳስቅ…

"ማን አለ?”

“ማን አለ? የት አለች በግርምትና ግራ መጋባት። ያመለጠኝን ጥያቄ አልደገምኩትም፡ መዓዛም ከዛ
በኋላ አላነሳችውም።

ቅናቴ ሲጨምር ልፍስፍስና በራሴ የማልተማመን ሰው ሆንኩ። በፊት በቀላሉ የምሠራውን ነገር ሁሉ
መስራት አልቻልኩም። ቅናት አቅም ያሳጣል። አንድ የማይረባ ነገር ላይ ብቻ በማተኮር በዙሪያችን ያሉ መልካም ነገሮችን ሁሉ ይጋርድብናል።
👍27
አንድ ቀን ከመዓዛ ጋር ሻይ ቡና እንበል ብለን ውጣንና አምሽተን ስንመለስ እኔ ይዢው የነበረው
የቤት ቁልፍ ጠፋ። ውጭ ቆመን አማራጭ መፈለግ ጀመርን። እኔ ሰብረን እንግባ ስል፣ መዓዚ
ሳይመሽና ታክሲ ሳናጣ እናቷ ቤት ሄደን እንድናድር ሐሳብ አቀረበች። ልሰማት አልፈለግኩም።
ቁልፉን ለመስበር መታገል ጀመርኩ፡፡ ታች አንደኛ ፎቅ ላይ ካሉ 'ጎረታች ቤት' (ለኮንዶሚኒየም የታች ጎረቤቶች የሰጠሁት ስም ነው… ላይ ያሉትን 'ጎረላይ ቤት … ጎን ሰው የለም እንጂ ጎረቤት ይሆን ነበር…) እና ከጎረታች ቤት ቢላዋ፣ ፒንሳ፣ መፍቻ ተውሼ መጣሁና መታገል ጀመርኩ - ወይ ፍንክች በሩ ! መዓዚ ረዥም ጫማ ስላደረገችና ወክ እያደረግን ስለመባን መቆም ደክሟት፣ የለበሰችውም ቀሚስ አጭር ስለነበር ብርጅ እያንሰፈሰፋት ከጎኔ ትንቆራጠጣለች።

አንድ ሰዓት የሚሆን ታግዬ ላብ በላብ ሆኜ እና እጄ ደም አርግዞ ያተረፍኩት ነገር ቢኖር በሩ ሊከፈት
እንደማይችል ማረጋገጥ ነበር !

“በቃ አይከፈትም!” አልኳት፡፡

“ንግሬህ ነበር እኮ ፍቅር…! በቃ እማማ ጋር እንሂድ” አለችኝ እየተቻኮለች። በዚች ቅፅበት የጠረንገሎው 'ጎረቤት' በር ተከፈተ። በሩ ሲከፈት በበሩ ስፋት ልክ የብርሃን ምንጣፍ በሩ ፊት ለፊት ያለው በረንዳ ላይ ተነጠፈ፡፡ ጠረንገሎው የደረቱን እና የእጆቹን ጡንቻ አጉልቶ የሚያሳይ ጉርድ ቲ ሸርት ከቁምጤ ጋር ለብሶ ብቅ አለ።

የብርሃን ምንጣፉ ላይ ቆሞ ወደ እኛ አየት አደረገና፣

“ደህና አመሻችሁ አብርሽ፡” አለ። እሱን ሳይ እልሄ ከየት መጣ ሳልሰው ከንበል አለብኝ። ለሰላምታው መልስ ሳልሰጥ ኮቴን አውልቄ ያዥ.…. አልኳትና ቢላውን አንስቼ ቁልፉን መጎርጎር ጀመርኩ።

“ሰላም አመሸህ አቶ ሰለሞን፡፡ ቁልፍ፡ ጠፍቶብን ለመከፈት እየታገልን ነው ይሄውልህ” አለች መዓዛ።ምን አስለፈለፋት…።

እየተንጎራደደ መጥቶ አጠገባቻን ሲቆም ጥላው ከበደኝ።

አያያዜን ትንሽ ተመለከተና፣ “እስኪ መፍቻዋን ስጭኝ ...” ብሎ ከመዓዛ ተቀበለ።

እንዳቀረቀርኩ ገመትኩ ….

መፍቻውን ስትሰጠው እጆቻቸው ተነካክተዋል … ዓይኗን ዓይኑ ላይ ተከላ ፈገግ ብሳም ሊሆን
ይችላል። እጁ ሲነካት ብርድ ላይ ያመሸ ሰውነቷ በደስታ ተፍታትቶ ሙቀት በሙቀት ሆናም ሊሆን
ይችላል ... 'በዚህ ብርድ ይሄ ደፍዳፋ ባሌ ድራሹ ጠፍቶ አንተ ቤት ገብቼ እቅፍ ብታደርገኝ የሚል መልእክት በዓይኖቿ ልትነግረው ትችላለች፤ እሱም በጉርድ ቀሚስ ያልተሸፈኑትን ውብ እግሮቿን ተስገብግቦ እየተመለከተ ይሆናል ፤ እግሮቿን ሲስማቸው፦ እያለመስ እንደሆን ማን ያውቃል?

“አብርሽ አንዴ ልሞክረው እሰኪ…” አለኝ ወደ በሩ ጠጋ ብሎ።

“አይ አይከፈትም፤ ሞከርኩትኮ …፤በቃ ነገ በባለሞያ እናስከፍተዋለን። ቁልፉን ቢሮ ረስቼው ሊሆን ይችላል።" ብዬ ቀበጣጠርኩ።

ጠረንገሎው ግን እኔ ስናገር ወደ በሩ ጠጋ ብሎ ጀርባውን ሰጠኝና በሰከንዶች ዕድሜ … ምኑን
እንደነካው እንጃ ቀጭ ብሎ በሩ ተባረገደ። 'ካለበለቤቱ አይነድም እሳቱ' ባለቤት ሆኖበት የለ ቤቱን …ገና ሲነካው ተበረገደ!

ውስጤ በብስጭት፣ በመበለጥ ስሜት በቅናት ተንገበገበ፡፡

መዓዛ በሳቅ እና ደስታ በታጀበው ስርቅርቅ ድምፅ፣ “ኦ እግዚአብሔር ይስጥልን…” አለችው። ይሄ ድምጽዋ ከነፍሷ ስትደሰት ነው፦ ከውስጧ የሚወጣው። ለምሳሌ አግቢኝ ያልኳት ቀን “ኦ ማይ ጋድ ”
ብላለች፤ ከወሲብ በኋላም በጣም ስትደሰት “ኦ ማይ ጋድ ትላለች። አሁንም ይሄው ይሄ ጠረንገሎ
እኔ ያላላሁትን ስለከፈተ ደገመችው።

እባክህ ግባና ሻይ ጠጥተህ ትሄዳለህ' እያለች ትለምነው ጀመረ። ይሄ ጠረንገሎ በሩን ብቻ አይደለም፣የሚስቴንም ልብ ነው የበረገደው፤ ቀናሁ አመሰግናለሁ እንኳን ማለት አልቻልኩም። ገብቼ ወደ መኝታ ቤቴ አመራሁ። በዚህ አያያዛቸው ቀድመው መኝታ ቤቴን ሳይዙብኝ እረፍ ልበል ብዬ…

መዓዛ ሰውየዋን ሽኝታ ወደ መኝታ ቤት መጣችና ፈቷ ተቀያይሮ ፊቴ ቆመች፡፡ ያላየኋት መስዬ
ዓይኖቼን ጨፈንኩ!
“ስማ አብርሽ ! ለምን ይሄን ያህል ባለጌ ትሆናለህ። ሰው ጎረቤቱ ሲረዳው ማመስገኑ ቢቀር እንዲህ
መገላመጥ አለበት…? ለምን እኔንስ ታሳፍረኛለህ…?”

“ምንድነው የረዳን…? የሰው ቤት ቁልፍ ስለፈለቀቀ.? ወሮበላ !! ይሄ እንደውም ልምድ ያለው ቤት
ፈልቃቂ ሳይሆን እይቀርም።”

“ኧረ በእግዚአብሔር ኣብርሽ ሥርዓት ይኑርህ!"

“ሥርዓት አንቺ ነሽ የምታስተምሪኝ? መጀመሪያ ራሰሸ ሥርዓት ይኑርሽ። ሌላውን በሌለሁበት የምታደርጊውን ሁሉ ያላወቅኩ መስዬ ብችለው ጭራሽ የማንንም ቤት ሰርሳሪ እየጠራሽ ቤቴን ማሰበር ጀመርሽ…።”

መዓዛ ትክ ብላ እየተመለከተችኝ በተረጋጋና በሚያስፈራ ድምፅ፣ “ምንድነው በሌለህበት ያደረግኩት? አለችኝ

“አላውቅልሽም ! ልተኛበት !" ብዬ ልብሴን ማወላለቅ ጀመርኩ።

“ምንድነው በሌለህበት ያደረግኩት?” ብላ ከበፊቱ ጠንከር ባለ ድምፅ ጠየቀችኝ።

“ቁልፍ ሰባሪ ጓደኛሽን ሂጅና ጠይቂው” አልኳት በእልህ።

በዚህች ቅፅበት በራችን ተንኳኳ። የጎለጎታችብኝ ዓይኗን እንደታጎለጎላ በሩን ልትከፍት ሄደች።

"ረስቼው መፍቻውን ይዤባችሁ ሄድኩ!” ሲል ሰማሁት ጠረንገሎውን።

ምን ትረሳዋለህ ... በየምክንያቱ ዓይንሽን ልይ አትልም !? እላለሁ በውስጤ።

"ውይ መጥቼ እወስደው አልነበር፣ ምን አመላለሰህ?" ስትል ሰማኋት፤ ከበፊቱ ሻከር ባለ ድምፅ፡፡
ይሄን የመዓዚን ድምፅ ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ ሰምቼዋለሁ። ለሁለት ዓመት ትምህርት ሌላ አገር ልሄድ ስትሰናበተኝ እናቴ እንዳላገባት ፊቷ የነጎረችኝ ቀን። ይሄን ድምጿን እፈራዋለሁ። መኝታ ቤቴን ከውስጥ መቀርቀር ከጀለኝ። … ማንን ደስ ይበለው ብዬ!

መዓዛን ጠበቅኳት፤ ወደ መኝታ ቤት አልመጣችም። ቀስ ብዬ ወደ ሳሎን ሄድኩ። ሶፋ ላይ ቁጭ ብሳ
ባዶው ላይ አፍጥጣለች።

ተመልሼ ተኛሁ።

ሌሊት ወደ ዘጠኝ ሰዓት ከእንቅልፌ ስነቃ መዓዛ አሁንም ጎኔ የለችም።

ወደ ሳሎን ሄድኩ፤ ማታ እንዳየኋት ከነልብሷ ከነጫማዋ ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ ባዶው ላይ አፍጥጣለች።

ተመልሼ ተኛሁ።

ጠዋት ተነስቼ ወደ ሳሎን ሄድኩ። መዓዛ የተተኮሰ ልብስ ፤ ቁርስ አላዘጋጀትልኝም። እዛው ቦታ
በዛው ሁኔታ ተቀምጣ እንቅልፍ ወስዷታል።

እንደተኛች ወጣሁ።

ምን ሲያኮርፍ ፆሙን ያድራል አሉ .…ጠረንገሎው መኪና ማቆሚያው አካባቢ ገመድ ይዘላል።
ቁንጣን ያዘልለውና!

ማታ ወደ ቤት ስመለስ መዓዛ ቤቱን ትታልኝ ሄዳለች። አሁን ቅናት ሙሉ ሆነች። ማሰብ ጀመርኩ …
ሻንጣዋን ይዛ ስትሄድ የሆነ ባለ መኪና አገኛት ቆንጆ ወዴት ነው ልሸኝሽ?” ይላታል፤ ትግባለች፤ …
እያለቀሰች ታሪኳን ትነግረዋለች፣ አቅፎ ያባብላታል…።

መዓዛ ንፁህ አፍቃሪ መሆኗን ባውቅም ሁለት ሰው የሆንኩ እስኪመስለኝ አእምሮዬ የቅናት ቅዠቱን ሊያቆምልኝ አልቻለም።

ልቤ ይገስፀኛል ... ልቤን ገደል ግባ ስለው ነው ድሮም ራሴ ገደል የገባሁት።

መዓዛ አልተመለሰችም። እናቷ ቤት የለችም። ጓደኛም ከእኔ ውጭ አልነበራትምና ማን ጋር ሄጄ
ልጠይቅ …

ሌላ ሰው አግብታ ይሆን እንዴ…? ምናልባት ከእኔ ጋር እያለች ይገናኙ የነበረ ሀብታም ሊሆን ይችላል !
ከሦስት ዓመታት መለያየት በኋላ አየር መንገድ ሥራ ላይ እያለሁ ከሳኡዲ ታፍሰው ከተባረሩ
ኢትዮጵያዊያን ስም ዝርዝር መካከል የመዓዛን ስም ተመለከትኩት። ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር ጀምሬ ነበርና ከዚህ በላይ ስለ መዓዛ ማሰብ አልፈለግኩም

ግን አዲሷ ፍቅረኛዬ ዛሬ እንዴት ሳትደውል ቀረች? ….ያ በጸሐፊነዠት የሚያሰራት አስቀያሚ ሀብታም ጋር ????

ሊሆን ይችላል !!

አለቀ
👍37
#ትኩሳት


#ክፍል_አስር


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ባህራም
ምጥ


ባህራም በሰኔ ወር የወደቀውን ፈተና እንደገና ለመፈተን
ማጥናት ጀመረ። የራሱ መኝታ ቤት ያረጀና የከረከሰ ሆኖ፣ ደምበኛ ጠረጴዛና ወምበር የለውም፡፡ እዚያ ማጥናት አልቻለም፡፡የዩኒቨርሲቲው ቤተመፃህፍት እየሄደ እንዳያጠና፣ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች ውር ውር እያሉ ሀሳቡን ይሰርቁታል። ከቀኙ፣ ከግራው፣ከፊቱ፣ ከኋላው ደሞ አስር፣ አስራ አምስት ፍራንክ ያበደሩት ሰዎች ያዩታል፣ ይከብዱታል። እነሉልሰገድ ቤት ሄዶ እንዳያጠና ወሬና
ጫጫታ ይበዛል። እኔ ቤት እየመጣ ያጠና ጀመር። ከሰአት በኋላ ሲኒማ እሄድለታለሁ፣ ሲያጠና ይውላል። ማታ እፅፋለሁ ወይም አነባለሁ፣ ሲያጠና ወይም የማኦ ትዜ ቱንግን መፃህፍት ሲያነብ ያመሻል፡፡ ጧት ግን ምንም ያህል አይሰራም፡፡ ወሬ እናበዛለን።

ጧት ገና ከእንቅልፌ ሳልነቃ መጥቶ፣ በቀስታ በሩን ከፍቶ
ገብቶ፣ ጠረጴዛው ዘንድ ተቀምጦ ሲሰራ ይቆያል። ስነቃ “Bon jour
እለዋለሁ። Bon jour ብሎኝ ቡና ይጥድና ስራውን ይቀጥላል።
አልጋዬ ውስጥ እንዳለሁ ትላንት የፃፍኩትን እመለካከታለሁ፤
አርማለሁ፣ እሰርዛለሁ፣ እቀዳለሁ። ሙሉ ሰአት ሲሆን ባህራም «አንድ ጊዜ ዜና ብንሰማ ይረብሽሀል?» ይለኛል፡፡ (የፈረንሳይ ራዲዮ በየሰአቱ አጫጭር ዜና ያሰራጫል) ራስጌዬ ያለችውን ራዲዮ እከፍታታለሁ። ባህራም ያፈላውን ቡና በዱቄት ወተት እየጠጣን ስለቪየትናም ወሬ እንሰማለን። ቪየትኮንግ የደፈጣ አሜሪካኖቹን አጥቅተዋቸው እንደሆን ባህራም ደስ ይለውና ደስታው
አላስጠና ይለዋል። መናገር ይጀምራል።ቬየትኮጎቹ ድል
ማድረጋቸው አይቀርም ይላል፡፡ ንግግሩ ቀስ ብሎ ወደ ኢራን
ይወሳስደዋል።ስለኢራን ሊነግረኝ ይጀምራል። ስለኢራን፣
ስለኮሙኒዝም፣ ስለማኦ ትዜ ቱንግ፣ ስለአሜሪካን ወራሪነትና
አጥቂነት፣ ስለካፒታሊዝም ስናወራ እንቆይና፡ ሙሉ ሰአት ሲደርስ
እንደገና ራዲዮ እንከፍታለን፡፡ ዜናው ያስደስተዋል ወይም
ያበሳጨዋል። ወሬያችንን እንቀጥላለን። የምሳ ሰአት እስኪደርስ እናወራለን፣ እናወራለን ማለት፣ በአብዛኛው እሱ ሲያወራ እኔ አዳምጠዋለሁ፤ እንዳንድ ጊዜ ጥያቄ እጠይቀዋለሁ፡፡ የነገረኝን
እያንዳንዱን ማታ ልተኛ ስል አንድ ትልቅዬ ደብተር ውስጥ አሰፍረው ነበር

አሁን ያንን ደብተር ሳነበው ባህራም ይታየኛል፡፡ እኔ አልጋ
ውስጥ ትራስ ተደግፌ ቁጭ ብዬ፡ እሱ በሽተኛ ሊጠይቅ የመጣ
ይመስል አጠገቤ ወምበር ላይ ተቀምጦ፣ በብልህ ቡናማ አይኖቹ
እያየኝ፣ ፀጉራም እጆቹን በብዙ እያንቀሳቀሰ፣ በወፍራም ልዝብ
ድምፁና በተሰባበረ ፈረንሳይኛው ሲያወራልኝ፣ ቁልጭ ብሎ
ይታየኛል

ወሬው አንድ መስመር ይዞ አይሄድም። ኢራን፣ ኒኮል፣
የባህራም ቤተሰብ፣ የባህራም ጓደኞች፣ ፈረንሳዮች፣ ጥቁሮች፣
ወጣት ኮሙኒስቶች የተባለ የኢራን አገር ማህበር፣ ትምህርት
ቤት፣ ሴቶች፣ ቡሽቲዎች፣ ጋዜጠኞች ብቻ ባህራም ያየውንና
የሰማውን ነገር፣ በህይወቱ የደረሰበትን ወይም በሌሎች ላይ
የደረሰባቸውን ነገር አሳዛኝ ነገር፣ አስደሳች ነገር፣ አስቂኝ ነገር፣
የሆነ ነገር ያወራልኝ ነበር፡፡ ስንቱን ብዬ ልናገረው እችላለሁ?
ጥቂቱን ብቻ ባጭሩ ላስፍረው፣ እንደ ባህራም ካንዱ ወደ ሌላው
እየዘለልኩ. እንደሚከተለው...

አሜሪካኖቹ ይወድቃሉ (ይላል ባህራም) ታያለህ፡፡ ስንቱን ህዝብ
ጨቁነው፣ ስንቱን አገር ፈትፍተው፣ ስንቱን መንግስት ገዝተው
ይችላሉ? አንድ ቀን ይወድቃሉ። እንኳን እንደነሱ ያለ ቂል ፈረስ
ይቅርና፣ እንደ እንግሊዝ ያለ ተንኮለኛ ቀበሮም ወድቋል። ተነስቶ ሌሎች ህዝቦችን
ጨቁኖ መውደቅ የሚቀርለት የለም፡፡ “አሜሪካኖችም ይወድቃሉ፡፡ ይወድቃሉ። ታይቶ የማይታወቅ አወዳደቅ ይወድቃሉ። ያን ጊዜ የአለም ህዝቦች እልል ይላሉ።
በአሜሪካ አግር ተረግጠው ደክመው እልል ለማለት ያህል አቅም ያነሳቸው ደሞ እፎይ ይላሉ

አሜሪካኖቹን መጀመሪያ
ሆ ቺ ሚን ከቪየትናም ያባርራቸዋል::ቀጥሎ እነ ማኦ ሴቱንግ ወይም ወራሾቹ ከሩቅ ምስራቅ ያስወጡዋቸዋል፡፡ ቀጥሎ እንግዲህ ማን ከየት እንደሚያስወጣቸው አላውቅም:: ብቻ እርግጠኛ ነኝ ያስወጡዋቸዋል። ይህን የሰው አገር ደም ጠጥቶ የወፈረ ቂጣቸውን በካልቾ እየመቱ “Yanked go home!
And stay honte!' (ያንኪ ወደ አገርህ ግባ እና እዚያው ቅር!»)
እያሉ ያስወጡዋቸዋል። ከሰው እድሜ በላይ በኖርኩ! አሜሪካ
ስትወድቅ ለማየት እንድችል ብቻ

ምን ማለትህ ነው? ለምን አልጠላቸውም? አሜሪካኖችን ያልጠላሁ ማንን ልጠላ ነው የነፃነትን ዋጋ እያወቅኩ፣ የተጨቆነ ህዝቤን እየወደድኩ፣ አሜሪካኖችን ካልጠላሁማ ሰው አይደለሁም ማለት ነው። ድንጋይ ነኝ ማለት ነው አሜሪካኖች አንድ የተቀደሰ ተግባር አላቸው:: ይኸውም፣ እባብ ያንዲትን ወፍ እንቁላል መጦ ጨርሶ ቅል ብቻ እንደሚያስቀርላት፣እነሱም ያንዲትን አገር ሀብት መጠው ጨርሰው፣ አፈርና ድንጋይ
ይተዉላታል። የኔን አገር ውሰድ። ዋና ሀብቷ ነዳጅ (ፔትሮል
ነው። ነዳጁን ከመሬት መጦ የሚወስደው አሜሪካ ነው

አንድ ቀን ሞሳዴግ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ። ተነሳና የኢራን
ሀብት ለኢራን ህዝብ ነው አለ፡፡ አሜሪካኖቹ ተሳስተሀል አሉት፡፡
በቃል ሳይሆን በተግባር፣ የኢራን ሀብት ለአሚሪካ ነው፣ የኢራን
ሀብት ለኢራን ነው ካልክ ኮሙኒስት ነህ ማለት ነው አሉት።
ሲ.አይ.ኤ ልከው ገለበጡት። ሞሳዴግ ተይዞ ሞት ተፈረደበት። ግን ሽማግሌ በመሆኑ፣ የሞት ፍርዱ ወደ እስራት ተሻሻለለት። አሁንም ታስሯል፡፡ የኢራን ሀብት ለአሜሪካኖቹና ለሻህ ነው ያለ ሰው ግን ይሾማል ያሸለማል። ሻህ ማለት በነሲሩስ፣ በነዳርዩሽና በነኻሻር ያዥ ስመ ጥሩ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ኢራንን የሚጨቁን ጋንግስተር ማለት ነው:: አጋዦች አሉት። ህዝቡ ያረሰውን ለመንጠቅ የእርሻ ሚኒስትር ያግዘዋል። ህዝቡ ሲነግድ ከነጋዴው ለመቀማት የንግድ ሚኒስትር
ያግዘዋል። ለልዩ ልዩ አይነት ጭቆና ልዩ ልዩ ሚኒስትር አለው።
ህዝቡ በደስታ እንዲጨቆን፣ ማለትም ተጨቆንኩ ብሎ
እንዳያጉረምርም፣ ፀጥ የሚያሰኙ ያገር ግዛትና የፍርድ ሚኒስትሮች
አሉት

ያሻህን ሻህ ሚኒስትሮች፣ በተለይም የውጭ ጉዳይና ያገር ግዛት ሚኒስትሮቹ፣ ትእዛዛቸውን በቀጥታ ከዋሽንግተን ይቀበላሉ።
ምክንያቱም ኢራን የአሜሪካ የነዳጅ ማእድን ናት። ደሞ ኢራን
የሩሲያ ጎረቤት ስለሆነች፣ አሜሪካኖች በጣም ለኢራን
ይጠነቀቁላታል። አንድ ገበሬ ብዙ የምትታለብ ላም ብትኖረው
አይጠነቀቅላትም?

ሻህ ማለት ውሻ ነው፡፡ አሜሪካኖቹ ኢራንን አርደው ብልቷን ሲያወጡ እፉ ምራቅ እየሞላ በአይኑ ይከተላቸዋል፣ ሳምባ ወይም
ሌላ ቁራጭ ስጋ ጣል ያረጉለታል። እሱ ደሞ ህዝቡን ጨቁኖ
ይይዝላቸዋል። አየህ፣ ህዝቡ ተጨቁኖ ካልተያዘ፣ እንደ ሞሳዴግ
ተነስቶ የኢራን ሀብት ለኢራን ሰዎች ይላል። ስለዚህ አሜሪካኖቹ
ለህዝቡ የማይቆረቆር፣ ጥቂት ሚልዮን ብር ቢሰጡት የሚበቃው፣ ህዝቡን ጨቁኖ የሚይዝላቸው ገዥ ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህ ነው ዙፋኑን
የሚጠብቁለት በሞሳዴግ ጊዜ ረብሻ ተነሳ፡፡ ሽህ ሽሽቶ ከአገር ወጣ።አሚሪካኖች መጥተወ «የኢራን ሀብት ለኢራን ሰዎች» የሚሉትን የሞሳዴግ ተከታዮች ፈጅተው፣ በዚያውም ያለ የሌለውን ኮሙኒስት አርደው ጨርሰው፣ አገሩን ጸት ካደረጉ በኋላ፣ ና ወደ ዙፋንህ
ተመለስ አሉት፡፡ ወደ ዙፋኑ ተመለሰ
👍22
ሻህ መሸሽ ልማዱ ነው:: ቴህራን ከተማ ውስጥ አራት ቤት
መንግስት አለው። እና ሁለቱ ውስጥ ለመብረር ዘወትር ዝግጁ የሆኑ ሁለት ኤሮፕላኖች አሉት፡፡ ትንሽ ረብሻ የተነሳ እንደሆነ፣ ወድያው ኤሮፕላኑ ውስጥ ይገባና ካገር ይጠፋል፡፡ ብቻ እሱ ያምልጥ እንጂ፣ ስዊስ፣ አሜሪካ፣ እና ምናልባት ኢንግላንድ ባንኮች ውስጥ ብዙ ሚልዮን ብር ስላለው፣ እንዴት እኖራለሁ ብሎ አይሰጋም እንግዲህ ፡ ይሽሻል። ረብሻው አልፎ ሰላም ሲመለስ፣ ወደ ውድ አገሩ ይመለሳል፣ ለውድ ህዝቡ ንግግር ያደርጋል
አንድ ቀን ግን የሚያስደንቅ ስራ ሰራ። ማለቴ፣ ረብሻ ሲነሳ
አልሸሽም፡፡ አይገርምም? አንተማ ምን ይገርምሀል? ሀለሳሴ ረብሻ
ሲነሳ ወደሀገሩ ይገሰግሳል እንጂ አይሸሽም። የሆነ ሆኖ ያን ጊዜ
ሻ ሳይሽሽ የቀረ ጊዜ ለህዝቡ በሬዲዮ “ህዝቤ ሆይ! ዛሬም
እረኛችን ትቶን ይሄድ ይሆን? ብለህ አትስጋ:: ዛሬስ እዚችው
እሞታታለሁ እንጂ አልሄድም!» አለ

እዚህ አለም ላይ እንደ ኢራን ተራ ወታደር የመሰለ ጀግና አታገኝም። በጭራሽ አታገኝም። አየህ፣ ጦርነት የተፋፋመ ጊዜ ፣ የኢራን ተራ ወታደር ማንንም ኣይታዘዘ፡፡ በገዛ ራሱ እንዳሰኘው ይዋጋል፡፡ ጄኔራሉንም ሻለቃውም
አይታዘዝ። ምክንያቱም ጄኔራሉም የለ፣ ሻለቃውም የለ። በጦርነት
ጊዜ፣ የኢራን ሰራዊት ተራ ወታደር ብቻ ነው ሚዋጋው የኢራንን ጄኔራሎች የሚመስል የለም::

ከነመለዮዋቸው፤
ከነሊሻናቸው፣ ከነሙስታቸው፣ ከነአስተያየታቸው፣ አቤት ደስ
ማለታቸው! አረማመዳቸው ሲያኮራ! ግርማቸው ሲያስፈራ! እነሱም ይህን ያውቃሉ። መለዮዋቸውንና ሊሻናቸውን በሰላም ጊዜ ፈፅሞ
አያወልቁም፡፡ ጦርነት ሲመጣ
መለዮና ሊሻናቸ አውልቀው፣ የወታደር ሳይሆን የሰላማዊ ሰው ልብስ ይለብሳሉ። ይሄ
እንግዲህ የሴት ልብስ ያጡ እንደሆነ ነው:: የሴት ልብስ ካገኙ ግን፣ እሷን ይለብሱና እልም! ይጠፋሉ፣ በቃ፡፡ ተራው ወታደር ያለ አለቆቹ ይዋጋል ጦርነቱ አልቆ የሰላም ውል ከተፈረመ በኋላ፣ ጄኔራሎቹ መለዮአቸውን ለብሰው፣ ሊሻናቸውን ደርድረው፣ አንድ በአንድ ከተፍ ይላሉ፡፡ በየመፅሄቱ ስለጦርነቱ ይፅፋሉ፡፡ አንዳንዶቹም ሙሉ መፅሀፍ ይደርሳሉ፡፡ ጦርነቱ ላይ እንዴት እንደተዋጉ፣ እንዴት
እንደተከበቡ፣ እንዴት
በጣጥሰው እንደወጡ፣
ወታደራቸው ሁሉ አልቆ እንደተማረኩ፡ እንደታሰሩ፣ ስቃይ አንዳዩ ምናምን ይዘበዝባሉ። ሽህ ውሽታቸውን እንደሆነ ያውቃል። ግን የበለጠ ማእረግና ሊሻን ይሽልማቸዋል:: ሲሞቱ ብሄራዊ የቀብር ስርአት ያውጅላቸዋል፡፡ ይሄ ሁሉ ለምንድነው? ንጉሳቸው ሲሸሽ አርአያውን ተከትለው ስለሸሹ ነው

ግን ያልሸሹ፣ በጀግንነት ተዋግተው፣ ብዙ ተጋድሎን
አድርገው፣ ድልን ያስገኙ አንድ አራት ጀኔራሎች ይኖራሉ። እነሱ
ማእረግም፣ ክብርም፣ ሊሻንም አይጨመርላቸውም፡፡ ስማቸውም
አይጠራም፡፡ ስእላቸው በየጋዜጣው አይወጣም። ወደ ቤተመንግስትም አይጋበዙም። ምክንያቱም ሻ እነሱ እንደሚበልጡት ስለሚገነዘብ፣
እሱ ጋንግስተር ሆኖ እነሱ ግን እውነተኛ ኢራናውያን መሆናቸው
በጣም ስለሚከብደው፣ ሊያያቸው አይፈልግም እንግዲህ ሰላም መጣ፤ አይደለም? ጄኔራሉቹ መለዮዋቸውን ለብሰው፣ ሊሻናቸውን ደርድረውእንደ ውሀ በሚፈስ የአሜሪካን መኪና እየተዘዋወሩ ለህዝቡ ይታያሉ፡፡ ቀን ቀን። ሌሊት ሌሊት
ደሞ ሲበዱ ያድራሉ፡፡ የራሳቸውን ሚስቶች አብዛኛውን ጊዜ ሌላ
ሰው ነው የሚበዳቸው። እነሱ ሚበዱት የሌላ ሰው ሚስት ነው
እኛ ከተማ ውስጥ አንድ ጀኔራል ነበር። ከዋናው ፖሊስ አዛዥ
ጋር ሽርክ ነው:: ታድያ አንድ ግብዣ ላይ ደስ የምትለው ሴት
ሲያይ፣ ለፖሊስ አዛዡ ይነግረዋል፡፡ ፖሊስ አዛዡ የሴትዮዋን ባል ለምርመራ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይወስደውና፣ ባልየው ሲመረመር ያድራል። ጄኔራሉ ሂዶ ያችን ሴትዮ ሲበዳት ያድራል። ታዲያ አየህ ከቆሻሻነታቸው የተነሳ ሴትዮዋን እንኳ ወደ ጀኔራሉ ቤት
ወይም ወደ ሌላ ቦታ አይወስዷትም፡፡ እዚያው የባልየው አልጋ ላይ ጄኔራሉ ሲበዳት ያድራል። ምን ይሄ ብቻ? እዚያ ቤት የጄኔራሉ ዘብ ይቆማል። የጀኔራሉ ደስታ የሰው ሚስት በጉልበት መብዳት ብቻ ሳይሆን፣ የባልየውንም ክብር ማዋረድ ነው። ሰውየው ልጆች ይኖሩታል፤ ሽማግሌ ወላጆች ይኖሩታል፣ ከጄኔራል ጋር ለመጋጨት
ያህል ሀይል አይኖረውም። ውርደቱን ውጦ ዝም ይላል

አቤት ኢራን ውስጥ ስንት ሰው አለ ውርደቱን ውጦ ዝም ያለ!
ሞሳድግ እንደ ወደቁ የኢራን ፖሊስ ሰራዊት በሲ.አይ.ኤ ትእዛዝና እርዳታ ኮሚኒስቶችን መፍጀት ጀመረ። ዘዴው እንደዚህ ነበር

የጠረጠሩትን ሰው ይይዙና ፖሊስ ጣቢያ ወስደው ኮሙኒስት
ነህ?» ይሉታል። አይደለሁም ይላል፡፡ ያሰቃዩታል፡፡ ውስጥ እግሩን በማስመሪያ ይጠፈጥፉታል፡ ጥፍሮቹን አንድ በአንድ ከስር ይነቅሉለታል። ቂጡ ውስጥ እንቁላል ይከቱበታል። ስቃዩ ሲበዛበት ኮሙኒስት ባይሆንም «አዎን፣ ኮሙኒስት ነኝ ይላል። በል አሁን የኮሙኒስት ጓዶችህን ስም ንገረን ይሉታል፡፡ ያሰቃዩታል። እንደ በረዶ የቀዘቀዘ ውሀ ውስጥ ይነከሩትና በአለንጋ ይገርፉታል። እጁን ጠምዝዘው ይሰብሩታል።ጥርሱን ቀጥቅጠው ያወላልቁታል።በመጨረሻ ስቃዩን አይችለውም። ስለዚህ ስም ይሰጣቸዋል።
ኮሙኒስት ከሆነ አውነተኛ ስም ሊነግራቸው ይችላል፡፡ ኮሙኒስት
ካልሆነ ግን የሆነ ስም ይነግራቸዋል፡፡ እነዚያ ስሞች መሀል ያንተ ስም ይገኛል፡፡ ትያዛለህ፡፡ ይሄኔ አንተ ኮሙኒስት አይደለህም እንዲያውም ኮሙኒስት ትጠላለህ። ግን ወስደው «ኮሙኒስት
እስከትል ያሰቃዩሀል። በኋላ፣ ስቃዩ ስለሚበዛብህ አንተም የመጣልህን ስም ትናገራለህ። በዚህ አኳኋን ኮሙኒስቶቹ አለቁ። ኮሙኒስት ያልሆኑም ብዙ ብዙ ታሰሩ፣ ተሰቃዩ፣ በስቃይ ላይ ሞቱ.
መንገድ ላይ አንዱ ሊላውን እየደበደበ «አንተ ውሻ ኮሙኒስት!
አንተ ነህ እኛን ፡ የምትሰድብ? ይለዋል። ሲደበደብ የነበረው
ፖሊስ ጣቢያ ይወሰዳል። ኮሙኒስት ነኝ እስኪል የተለመደውን ስቃይ ይቀበላል

ግን ይሄ ሁሉ ስቃይ የሚደርስህ ገንዘብ ከሌለህ ብቻ ነው።
ገንዘብ ካለህ ኮሙኒስት ብትሆንም ትድናለህ። እንደታሰርክ አባትህ ወይም ወንድምህ ሄደው ጉቦ ይሰጡልሀል። ፋይልህ ላይ «በስህተት የተያቀ» ተብሎ ይፃፍና አንተ ነፃ ትለቀቃለህ፡፡ መጥፎነቱ፡
አብዛኛዎቹ ኮሙኒስቶች ድሀ ነበሩ
ታስረው ከተፈቱት ጥቂቶች ኣንዱ የደረሰበትን ነገረኝ።

መጀመሪያ ደበደቡት፣ ገረፉት:: ኮሙኒስት ነኝ አለ። በኋላ የሌሎች
ኮሙኒስቶች ስም ተናገር፣ አሉት፡፡ እምቢ አለ። ቀዝቃዛ ውሀ ውስጥ
ነክረው በእለንጋ ገረፉት፡፡ እምቢ አለ። ቂጡ ውስጥ እንቁላል
ጨመሩበት። እምቢ አለ፡፡ ልብሱን በሙሉ አስወለቁና ሁለት እጁን
በገመድ አስረው፣ እግሩ መሬት እንደማይነካ እድርገው ሰቀሉት።
ተንጠለጠለ። ሩብ ኪሎ ብረት አምጥተው ብረቱን በሲባጉ አስረው ከቆለጡ ላይ አንጠለጠሉት። ብረቱ በየደቂቃው ክብደት እየጨመረ
የሚሄድ ይመስል ስቃዩ እያደገ ሄደ። ሀሳቡን ለግማሽ ሰከንድ እንኳ ከቆለጡ ህመም ለማራቅ አልቻለም፡፡ ህይወቱ በሙሉ ቆለጡ ውስጥ ያለ መሰለው። ከግማሽ ሰአት በኋላ ተናገር» አሉት። ዝም አለ ክብደቱ ላይ አስር ግራም ብረት ጨመሩለት። ቀስ እያሉ አምስት አምስት ግራም እየጨመሩ፣ ስቃዩ እየበዛ ጩኸት የእብድ ሰው ይመስል እየቀጠለ፤ እስር ኩዊንታል ብረት ከቆለጡ የተንጠለጠለ እየመሰለው ሲጮህ፣ እነሱ ትንሽ በትንሽ ክብደቱ ላይ እየጨመሩ
👍19
«ተናገር» እያሉት፣ እሱ «አምቢ» ብሎ እየጮኸ፣ ድንገት ህመሙ
ተወው፣ ጭለማ ዋጠው።
ልቡ ሲመለስለት፣ እሱ አሁንም ተሰቅሏል፣ ግን ብሪቱን
ክቆለጡ ላይ አንስተውለታል። ትንሽ ቆየ። መጡ። «
ተናገር» አሉት፡፡ እምቢ አለ። በሲባጎ የታሰሩትን ብረቶች አመጡዋቸው።
ብረቶቹን በአይኑ ሲያይ ብቻ በሀይል ቆለጡን አመመውና ጮኸ «አታሳዩኝ! እናገራለሁ!» አለ፡፡ ፈትተው አወረዱትና ልብሱን
አልብሰው ወደ አለቃቸው በር ወሰዱት። አንጠልጥለው ወሰዱት።
ምክንያቱም ሲራመድ ቆለጡ ትንሽ ሲወዛወዝ ሊገድለው ሆነ። ቢሮ ሲደርስ ለመናገር ዝግጁ ነህ ወይ? ተባለ፡፡ አይደለሁም አለ። ምነው እናገራለሁ ብለህ? አሉት። ስቃዩን ፈርቼ ነው እንጂ፣ የማላውቀውን ከየት አምጥቼ ልናገር? አላቸው

ይህን ጊዜ አንድ ጓደኛው መጣ፡፡ የታሸገ ደብዳቢ ለፖሊስ
አለቃው ሰጠው። አለቅየው ደብዳቤውን አነበበ፡፡ ጓደኝየውን ወደ ልዩ ቢሮ ወሰደው። ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ተመለሱ። የፖሊሱ
አለቃ፣ እስረኛውን ወደ ስቃዩ ቦታ ሳይሆን፣ መኝታ ወዳለበት
ክፍል አስወሰደው:: በነጋታው ጓደኛው መጥቶ ወደ ቤት ወሰደው::ፋይሉ ውስጥ እንግዲህ በስህተት የታሰረ ወይም «
ተመርምሮ የተጣራ ኮምኒስት ኣይደለም» ተብሎ ተፅፏል፣ ማለት ነው ልጁ እንዴት ሊፈታ እንደቻለ ገርሞታል። ጓደኛው ድሀ ነው፣
ዘመዶቹ በሙሉ ድሀ ናቸ። ጉቦ ከየት ተገኘ?. . . ታድያ ልጁ
ድሀ ይሁን ኢንጂ፣ የከተማችን ኮሙኒስቶች ሶስተኛ አለቃ ነው።
ኮሙኒስት የሆንን ሁላችን አዋጥተን ነው ጉቦውን የከፈልንለት። ብቻ ካለቆቻችን አንዱን ለማስፈታት ገንዘብ አዋጡ ተባልን እንጂ፣ ማን እንደሆነ አናውቅም (እኔም ከብዙ አመታት በኋላ ነው ያወቅኩት)
አየህ፣ ኮሙኒዝም እንደ ወንጀል የሚቆጠርበት አገር ውስጥ፣
አለቆቻችንን እኛ ሌሎቹ ኮሙኒስቶች አናውቃቸውም፡፡

ሳስረዳህ ኮሙኒስት ፓርቲ በፍራ (cell) ነው ሚሰራው:: ከሁሉ በላይ አንድ «ፍሬ» አለ። ስድስት አባላት አሉት፡፡ ስድስቱ ሰዎች
እያንዳንዳቸው የአንድ ሌላ «ፍሬም አለቃ ናቸው:: የዚህ የሁለተኛው ፍሬ አምስቱም ሌሎች አባላት እያንዳንዳቸው የአንድ ፍሬ
አለቃ ናቸው:: እነዚያ ደሞ ተራቸውን አንዳንድ ፍሬ አላቸው።
አንተ የምታውቀው እንግዲህ ሁለት ፍሬ ብቻ ነው:: የአንድ ፍሬ
አባል ነህ፣ የፍሬው አለቃ ያንተ አለቃ ነው። ሌላው ፍሬ ደሞ
ኣለቃው አንተ ነህ:: አንተ አለቃቸው የሆንክ ሰዎች፣ እያንዳንዳቸው ካንተ በታች የአንድ ፍሬ አለቃ ናቸው። እንዲህ እያለ ይቀጥላል::ገባህ?

ደሞ ኮሙኒስቶቹ ሁሉም የኮድ ስም አላቸው። እርስ በራሳቸው
የሚጠራሩት በኮድ ስማቸው ብቻ ነው:: የእውነት ስማቸው ማን
እንደሆነ አይተዋወቁም። እንዲህ የሆነ እንደሆነ፣ አንተ ብትያዝ፣
እና ፈሪ ብትሆን፣ እና ስቃዩን ፈርተህ መናገር ብትፈልግ፣
ለፖሊሶቹ የምትነግራቸው የኮሙኒስቶቹን የኮድ ስም ብቻ ነው፡፡ምክንያቱም የእውነት ስማቸውን አታውቅም፡፡ ይህም ሲሆን፣ የአንድ «ፍሬ»። አባሎች አንድ ሁለቱ ያንድ ሰፈር ወይም ያንድ ትምህርት ቤት ልጆች ስለሚሆኑ፣ የእውነት ስማቸውን ይተዋወቃሉ። ይህም
ፖሊሶቹን ይረዳቸዋል።

ኮሙኒስት ፓርቲ አንድ ነገር ለማድረግ ሲወስን፣ ውሳኔው
ከላይ ወደ ታች፣ ከፍሬ ወደ ፍሬ ይተሳለፋል። አንድ ሀሳብ ታች
ሲፈጠር፣ ከታች ወደ ላይ ከፍሬ ወደ ፍሬ ይተላለፋል

የኔ የፍሬ አለቃ ኣንድ ቀጭን፣ መነፅር የሚያደርግ ማኑ
የምንለው ልጅ ነበር። አምስታችንም የፍሬ አባሎች እንወደው ነበር። እኔ ግን በጣም በጣም ነበር የምወደው:: አደንቀው ነበር። አቤት
ሲፅፍ ስለሀገራችን አስተዳደር ጉድለት፣ ስለጭቦው፣ ስለከይሲነቱ ይፅፋል። ታድያ ሲፅፍ ልዩ አይነት ነው።
የፃፈውን ስታነበው ፡ ፍሬ ነገሩ በጣም እያናደደህ፣ አፃፃፉ በጣም
ያስቅሀል። በሳምንት በሳምንት አንድ ሙሉ ገፅ ይፅፋል
አንድ በከተማው የታወቀ፣ የማይጠረጠር ሀኪም አለ፡፡ ትልቅ
ቤት አለው:: ቤቱ ውስጥ ከመሰረቱ ስር የሚገኝ አንድ ክፍል አለ። እዚያ ውስጥ በስቴንስል የሚያባዛዐመኪና ኣለ። የከተማችን ኮሙኒስቶች ፅሁፋቸውን ሁሉ የሚያባዙት እዚያ ነው፡፡ ብዙ ሰው ለመታከም ስለሚመላለስ፣ ለመጠርጠር ያስቸግራል። እኔና ማኑ ያችን የፃፋትን ገፅ እናትማለን። ሁለት ሺ ኮፒ እናትምና፡ በየቡና ቤቱ፣ በየመንገዱ፣ በየአደባባዩ፣ ብቻ ምን ልበልሀ፣ ሰው ሊያያቸው
በሚችልበት ቦታ እንነዛቸዋለን:: በስርቆሽ፡፡ ሌሊት እየዞርን
በየግድግዳው እንለጥፋቸዋለን
አንድ ሌሊት በጭለማ እንደዚህ ስንለጥፍ፣ ሳናስበው ሁለት
ፖሊሶች ከተፍ አይሉም?! ደንግጨ ልሮጥ ስል' በወድያ በኩልም የመጡ መሰለኝ። ግን ጨለማ ነው፣ በደምብ አይታይም። ማኑ ድንገት አቀፈኝና በሹክሹክታ «ለጊዜው ማምለጫ የለም፡፡ እቀፈኝ!» አለኝ፡፡ ሁልጊዜ ስለሚያዘኝ በልማድ ታዘዝኩት እንጂ ነገሩ አልገባኝም፡፡ ተቃቀፍን። ፖሊሶቹ አጠገባችን ሲደርሱ፣ ማኑ በቀጭን
ድምፅ «እኔ ፈራሁ፣ ቤት ውሰደኝ አለኝ «አይዞሽ ምንም
አይደለም። ፖሊሶች ናቸው» አልኩት፡፡ «ዝም በል! እፈራለሁ!» አለ
«አይዞሽ እይዞሽ» እያልኩ ሳባብለው፣ ፖሊሶቹ ትንሽ ተለያይተው ቆመው ሲመለከቱን፣ ማኑ የሴት ድምፁን ትቶ በእውነት ድምፁ

«በለው!» አለኝ

ሁለታችንም ተወረወርን፡፡ በኔ በኩል ያለውን ፖሊስ በጭንቅላቴ
ሆዱን መታሁትና፣ ሲወድቅ ትቼው ተፈተለክኩ። ትንሽ እንደሮጥኩ
ማኑ እጠገቤ እንደሌለ ታወቀኝ፡፡ በሩጫ ተመልሼ አጠገቡ ስደርስ
«ሂድ መጣሁ» አለኝ፡፡ ፖሊሶቹ ተጋድመዋል፣ ግን በጭለማው
በደምብ ኣይታዩኝም፡፡ በቀስታ ስራመድ ማኑ በፍጥነት እርምጃ
ደረሰብኝ፡፡ ይስቃል
«ምነው ቆየህ?» አልኩት
«ቀበቶና ቁልፋቸውን ስበጥስ» አለኝ እየሳቀ። ብርሀን ጋ
ስንደርስ ከኪሱ ገንዘብ አወጣና ቆጠረ። ስምንት መቶ ቱማን (ብር
250.00):
«ከማን ነጥቀውት ይሆን?» አለ «ስምንት መቶ ቱማን።
የማተሚያ ቤታችን ወረቀት ወደማለቁ ተዳርሷል። ነገ ወረቀት
እንገዛለን የታተሙትን ወረቀቶች አሰራጭተን ከጨረስን በኋላ፣ የደስ ደስ ካፌ ገብተን ቡና ስንጠጣ ሳቅ እያለ፣
«ለመሆኑ የትናንቱን ፖሊስ ፍንግል አርገኸው ነበር ለካ
የሮጥከው» አለኝ
«አዎን» አልኩት
«ተነስቶ ቢከተልህስ? እና ካንተ የፈጠነ ሯጭ ቢሆንስ? ወይም
ስትሮጥ ውጋትቢይዝህስ? ወይም ቢተኩስብህስ? ወይ ፊሽካ ቢነፋና
ሌሎች ፖሊሶች ከያለበት ወዳንተ ቢሮጡስ?»

«ታድያ እንዴት ማድረግ ነበረብኝ?» አልኩት
«አታውቅምን ?»
«አላውቅም»
«እንግዲያው ነገ ጧት በአስራ አንድ ተኩል ቤቴ ና....

💫ይቀጥላል💫
👍34🥰1
#አላሐምዱሊላሒ_ደህና_ናት!


#በአሌክስ_አብርሃም


ልክ ከ8ኛ ክፍል ወደ 9ኛ ክፍል ሳልፍ ደስታ የሚያደርገኝን አሳጣኝ። አበድኩ፤ ልቤ በደስታ ጧልትል ደረሰች። የባሰ ደስታዬን ጣራ ያስነካው ጉዳይ ደግሞ ወደ 9ኛ ክፍል ማለፌ ብቻ ሳይሆን 9ኛ ክፍል እንድማርበት የተመደብኩበት ትምሕርት ቤት ነበር። ታሪካዊውና ታላቁ ወይዘሮ ስኂን ትምህርት ቤት። እውነቱን ለመናገር ያኔ ዩኒቨርስቲ መግባት ራሱ ወይዘሮ ሲኂን እንደ መግባት አያኮራም ነበር።ሰማያዊ ዩኒፎርሙ፥ ምርጥ መምሕራኖቹ፣ የቀለም ቢባል የሙያ…። እንደውም ከዛ በፊት የራሱ የሆነ
ትልቅ የሙዚቃ ትምሕርት ክፍል እና ኦርኬስትራ ቡድን ሁሉ ነበረው።

ረዥምና ግርማ ሞገስ የተላበሰው ቢጫ ፎቁ ከሩቅ ተጋድሞ ሲታይ ቤተ መንግሥት እንጂ
ትምሕርት ቤት አይመስልም። እንዲያውም ይኼን ሁሉ ዓመት የተማርኩበት ትምሕርት ቤት አሁን
ከተመደብኩበት ጋ ሳወዳድረው አመዳም ሆነብኝ፤ ኮሰሰብኝ። የሆነ ከላሶቹን ሳያቸው የዶሮ ቤት
ወስለው ታዩኝ።

ሞት ይርሳኝ! እንዲህ በደስታ ሰከሬ ጓደኛዬን፣ አብሮ አደጌን አልአሚንን ረሳሁት። የት ሄደ? ፍለጋ ጀመርኩ። አል አሚን ጓደኛዬ ነው፤ አብሮ አደጌ። ዝምተኛ ልጅ ነው። ድፍን ተማሪው በዝምታውና
በጉብዝናው ነበር የማያውቀው። ትምህርት ቤቱን አካልዬ ሳጣው በትምሕርት ቤታችን የኋላ በር
ወጥቼ ሁልጊዜ ወደምንቀመጥባት ትንሽ ጫካ ሄድኩ፡፡ ብቻውን ተክዞ ተቀምጧል።አቤት አቀማመጡ
ሲያሳዝን። ያ ረዥም ቁመቱ እንደሳንቡሳ ጥቅልል ብሎ ውስጡ የሐዘን ምስር ተሞልቶበት… ግራ ገባኝ። በዚህ ልዩ ቀን እንኳን አል አሚን ማንም ያዝናል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ምን አስተከዘው ግን? ካርዱን በዓይኔ አይቼዋለሁ፤ 99ነጥብ ምናምን ነቅንቆት ነው ያለፈው። ያውም ከትምህርት ቤት
አንደኛ ወጥቶ ።

“ምን ሆንክ?” አልኩት፤

“ምንም?”

“ታዲያ ምን እዚህ ጎልተህ?”

አፍራ እኮ ወደቀች።” አለኝ እንባ ተናንቆት። ሚ.ስ……ኪ….………….ን !! እኔም እንደሳንቡሳ
እጥፍጥፍ ብዩ አላአሚን ጎን ተቀመጥኩ፤ ጠጋ አለልኝ። በቃ ሁሰታችንም የሚኒስትሪ ካርዳችንን አንክርፍን በትካዜ ቁጭ አልን። ከሩቅ ለሚመለከተን ሰው ካርዱ ወደ 9ኛ ክፍል በጥሩ ውጤት ያለፍንበት መረጃ ሳይሆን ተከፍሎ የማያልቅ እዳ እንድንክፍል ከፍርድ ቤት የተሰጠን ትዕዛዝ ወረቀት .
ይመስል ነበር። ሰናሳዝን!! ደሴ ዕውቀት ጮራ ትምሕርት ቤት ጀርባ፣ ጦሳ ተራራ ሥር እኔና አላሚን በትካዜ ተቀምጠን ቀረን።

እስካሁን እንደአፍራህ ትልልቅ ዓይኖችና እንደቲማቲም የቀላ ከንፈር ያላት ሴት ዓይቼ አላውቅም።ለነገሩ እኔን ትዝ የሚሉኝ ዓይኖቿና ከንፈሮቿ ናቸው እንጂ አፍራህ “ውብ” የሚለው ቃል የማይገልጻት ጉድ ነበረች። ቁመቷ ምዝዝ ብሎ የወጣ፣ ፀጉሯ ለስፖርት ፔሬድ' ጠቅልላ ካሠረችበት ስትፈታው
መቀመጫዋ ላይ የሚደርስ፤ በዚያ ላይ ጥቁረቱ!በዚያ ላይ ብዛቱ!“ጥቁር ፏፏቴ !” (“ጥቁር አባይ ሲባል የአፍራህ ፀጉር ይመስለኝ ነበር።) እጆቿ፣ እግሯ፣ ኧ………….ረ የአፍራህ ቁንጅና ! በመቶ ዓመት አንዴ የሚከሰት ዓይነት ነገር ነው። ወሎ የቆንጆ አገር ሲባል እፍራህ ትዝ ትለኝና “ሃቅነው!” እላለሁ። እንዲያውም ወሎ አፍራህን ብቻ ይዞ ከድፍን ኢትዮጵያ ጋር በቁንጅና ቢወዳደር አጠገቡ የሚደርስ ያለ አይመስለኝም፡፡

ታዲያ ይህን ሁሉ ቁንጅና ይዛው 7ኛ እና 8ኛ ከፍል እኛ ከፍል ነው የተማረችው። ይሄን ጉድ ችለን መኖራችን ተዓምር አይደል ? በዛ አፍላ ዕድሜ ኤርታሌ ላይ ጥደው ነው እኮ ያስተማሩን።
ዳኛቸው የሚባል ሌላ ክላስ የሚማር ጓደኛችን ታዲያ ልክ የእረፍት ሰዓት ደውል ሲደወል እንቅፋት እስኪደፋው እየሮጠ እኛ ከፍል ይመጣና አፍራህን እያየ እንዲህ ይለናል፣ “አፍራህ ያለችበት ክላስ አንድ ቀን ብማር አንጎሌ ይከፈት ነበር፣ ከመቶው መቶ ነበር የማመጣው፤ መናፈሻ ውስጥ እኮ ነው የምትማሩት፣ ብርቅዬ ድንቅዬ ፍጥረት እየጎበኛችሁ፣ ቱሪስት ናችህኮ ቱሪስት፤ በኢትዮጵያ ብቻ፣
ደሴ ብቻ፣ በዕውቀት ጮራ ትምሕርት ቤት ብቻ፣ሰባተኛ ሲ ክፍል ብቻ የምትገኝ ብርቅዬ ፍጥረት እየጎበኛችሁ።”
እውነት አለው። አፍራህ እነዚያን ዓይኖቿን አንዴ ስታሳርፍብን ልባችን ከቅቤ የተሠራች ይመስል
ቅ…ልጥ! ደግሞ ዓይኖቿን ጨፍና የምትስቀው ነገር አላት፤ አቤት ሲያምርባት! “አፍራህ! አፍራህ!
አፍራህ!” ይላል ሳር ቅጠሉ። ታዲያ እሷ ጋር ለማውራት ለመቀራረብ የማይጥር ማነው?

አፍራህ፣ ወይንሸትና ሰዓዳ አንድ ወንበር ላይ ነበር የሚቀመጡት። እውነቱን ለመናገር አፍራህን ዓይቼ
ዳርና ዳር የተቀመጡትን ወይንሸትና ሰዓዳን ስመለከት ሰው አይመስሉኝም።ይቅር ይበለኝ!…አፍራህን ዙሪያዋን ለመጠበቅ የተገነቡ ግንቦች መስለው ነው የሚታዩኝ። ለነገሩ ሁላችንም የከላሱ ልጆች የኾንን ዙሪያዋን የበቀልን አረም ነገሮች ነበር የምንመስለው። አፍራህ የምትባል ጉድ እንድታጣላን መሃላችን
ጥሎብን ምን እናድርግ።7ኛ “ሲ” ክፍል ማን አለ ቢባል አፍራህ ብቻ። ሒሳብ አስተማሪያችን ራሳቸው ሰባት ጥያቄ ከጠየቁ አምስቱ ለትፍራህ ነው። በእርግጥ አፍራህ አምስቱንም አትመልስም፤ ግን ፈገግ ይሉላታል። ግንኮ እኛ ሐበሾች ብዙዎቻችን እናስመስሳለን እንጂ ሴት አናከብርም፤ የምናከብረው
ቆንጆ ሴትን ነው።

ሚስኪን ጓደኛዬ አል አሚን ታዲያ ከዚች ተዓምረኛ ልጅ ፍቅር ያዘው። ያውም የማያፈናፍን፣ ትንፋሽ የማይሰጥ ፍቅር። አል አሚን አባቱ ሞተዋል። እናቱም አቅመ ደካማ ነበሩ፤ እማማ ከድጃ።
(ለጀነት ይበላቸው! ዛሬ በሕይወት የሉም።) ከትምሕርት ቤት መልስ በሶላት ሰዓት መስጊድ ሲሰግዱ
የሚገቡ ሰዎችን ጫማ በመጠበቅና በመጥረግ ነበር ራሱንም እናቱንም የሚያስተዳድረው። አፍራህን
እንዳፈቀራት የነገረኝ በሐሳብ መንምኖ ሳር ካከለ በኋላ ነው።
ሲጀመር አል አሚን ዝምተኛ ልጅ ነው። አይናገር ! አይጋገር ! አንድ ቀን ታዲያ እኛ ቤት ሄደን ሳለ
(እናቴ ባጣም ነው አል አሚንን የምትወደው…)

“አላሚን!” አለችው፤ ስትጠራው እንደዚህ ነው።

“አቤት” አለ፤

“ትምርት ከበደህ እንዴ?” አለችው በሐዘን እያየችው።

“አይ!”

“ታዲያ ምነው ጭው አልክ? እስቲ አቡቹ ጋር ይችን ብሉ” ብላ እንጀራ እየጋገረች ስለነበር ትኩስ
እንጀራ ላይ በርስሬ ነስንሳ ቅቤ ለቅልቃ ሰጠችን። እኔ ላጥ ላጥ ሳደርገው አል አሚን የእንጀራውን
ዓይኖች የሚቆጥር እስኪመስለኝ እንጀራውን በትኩረት እያየ በሐሳብ ጭልጥ አለ። አል አሚንን
በትኩረት ያየሁት ከዚህ ቀን በኋላ ነበር። እውነትም ጭንቅላቱ ብቻ ቀርቶ ነበር::

“አንተ ምን ኹነህ ነው? ወስፌ መሰልክ እኮ” አልኩት፤ እውነቴን ነው ገርሞኝ ነበር። ሰው ሲከሳ አናቱ እንዲህ ቋጥኝ ያክላል እንዴ!? በስማም!!!
“አቡቹ ለማንም አትናገርም የሆነ ሚስጥር ልንገርህ ?”
“አልናገርም”
“ማሪያምን በል”
“ማሪያምን! …ሂድ ወደዛ ! እኔ ሚስጥራችንን ለሰው ተናግሬ አውቃለሁ?” ተቆጣሁ።
“እሱማ አታውቅም፤ ይሄ ግን ሚስጥር አይደለም”
“እና ምንድን ነው?”
“እ…ሚስጥር ነው” አለኝ እየፈራ። ሚስኪን!
“ምን መሰለህ ! እ.አፍራህን እያት እያት ይለኛል…እ…ማታ ማታ ዝም ብላ ትዝ ትለኛለች…አርብ
👍136
ሲመጣ በጣም ነው የሚጨንቀኝ፤…ቅዳሜ ሰፈሯ እሄዳለሁ፣ ግን አላያትም፡፡ እ..ቅዳሜና እሑድ ግን የት ነው የምትቀመጠው? የሆነ ሌላ ዓለም ላይ የምትኖር ነው የሚመስለኝ። ሰፈሯን ማየት ደስ
ይለኛል። ቅዳሜ ከነአፍራህ ቤት ፊት ለፊት ያለው ከረንቦላ የሚጫወቱበት ቤት ገብቼ እቆምና ከሩቅ ቤታቸውን አየዋለሁ። አንዳንዴ አባቷ ቀስስስ እያሉ እየተራመዱ በር ላይ ይንጎራደዳሉ። አባቷን ሳያቸው ዘመዴ ይመስሉኛል። አፍራህ ግን ትናፍቀኛለች። እስከ ማታ እዛው ቆሜ እጠብቃታለሁ። ሌላ ቤት አላቸው መሰለኝ አትወጣም። ቁርስም ምሳም አልበላም፤ እዛው እውላለሁ።.እሑድ ከረንቦላ ቤቱ ስለሚዘጋ የምቆምበት ግራ ይገባኛል። ድንገት ብትወጣና ብታየኝስ ብዬ እፈራለሁ።
በቃ ዝም ብዬ በመንገዱ እመላለሳለሁ፣.ግን አላያትም። ትናፍቀኛለች.." ሲናገር ድምፁ በፍርሃትና ጭንቀት ይርገበገባል።

"ፍቅር ይዞህ እንዳይሆን"

"ፍቅር አይደለም ባክህ"

"እና ምንድን ነው?”

“እኔ…ጃ! ፍቅር ነው መሰለኝ"

በቃ ከዛን ቀን ጀምሮ ወሬው ሁሉ አፍራህ ሆነች።

''አቡቹ ቅድም 'ማትስ' ስንማር አፍራህ ያንን ከባድ ጥያቄ ስትመልሰው አልገረመህም?” ይለኛል።

“አልመለሰችውም እኮ…ተሳስታለች"

"ባክህ ቲቸር ራሳቸው ናቸው የተሳሳቱት” ይለኛል ኮስተር ብሎ። አፍራህ የማትስ ሊቅ፣ አፍራህ
የውበት ጥግ (የውበቱ እንኳን እውነት ነው)። አፍራህ ስታድግ ሳይንቲስት እንደምትሆን ሁሉ አል
አሚን ይተነብይልኛል። ወይኔ ፍቅር!

በተደጋጋሚ ስለአፍራህ ከመስማቴ ብዛት አፍራህን እኔም ላፈቅራት ምንም አልቀረኝም። እውነቱን ለመናገር የዛን ጊዜ ክላስ ውስጥ ነበርነው ሠላሳ ምናምን ወንዶች አስራ ምናምኑ በአፍራህ ፍቅር የተለከፉ ነበር፤ ሒሳብ አስተማሪያችን ጭምር። መቼም ሒሳብ አስተማሪያችን እያካፈሉም፣ እየደመሩም፣ እየቀነሱም፣ እያባዙም ሳያስቧት አይቀሩም፡፡ አንዳንዴ ቡዝዝ ብለው መላጣቸው ላይ ላብ ፊጭ ፊጭ እያለ ሲመለከቷት ያሳዝኑኝ ነበር። “ወይኔ ምነው ያችን አመዳም አግብቼ አምስት ልጅ ባልወለድኩ ኖሮ" እያሉ በሚስታቸው የሚቆጩ ነው የሚመስለኝ።

አላለቀም
9👍7
አትሮኖስ pinned «#አላሐምዱሊላሒ_ደህና_ናት! ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ልክ ከ8ኛ ክፍል ወደ 9ኛ ክፍል ሳልፍ ደስታ የሚያደርገኝን አሳጣኝ። አበድኩ፤ ልቤ በደስታ ጧልትል ደረሰች። የባሰ ደስታዬን ጣራ ያስነካው ጉዳይ ደግሞ ወደ 9ኛ ክፍል ማለፌ ብቻ ሳይሆን 9ኛ ክፍል እንድማርበት የተመደብኩበት ትምሕርት ቤት ነበር። ታሪካዊውና ታላቁ ወይዘሮ ስኂን ትምህርት ቤት። እውነቱን ለመናገር ያኔ ዩኒቨርስቲ መግባት ራሱ ወይዘሮ…»
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


...«ለመሆኑ የትናንቱን ፖሊስ ፍንግል አርገኸው ነበር ለካ
የሮጥከው» አለኝ
«አዎን» አልኩት
«ተነስቶ ቢከተልህስ? እና ካንተ የፈጠነ ሯጭ ቢሆንስ? ወይም
ስትሮጥ ውጋትቢይዝህስ? ወይም ቢተኩስብህስ? ወይ ፊሽካ ቢነፋና
ሌሎች ፖሊሶች ከያለበት ወዳንተ ቢሮጡስ?»

«ታድያ እንዴት ማድረግ ነበረብኝ?» አልኩት
«አታውቅምን ?»
«አላውቅም»
«እንግዲያው ነገ ጧት በአስራ አንድ ተኩል ቤቴ ና....
ከዚያ በኋላ አራት ወር ሙሉ ጧት ጧት ካስራ አንድ ተኩል እስከ
አንድ ተኩል ድረስ የሚያውቀውን ሁሉ አስተማረኝ፡፡ ከሱ እኩል
ከሆንኩ በኋላ፣ አንድ ሌሊት ማጅራት መቺዎች የሚበዙበት
ሰፈር ወሰደኝና እኔ እንግዲህ አላግዝህም፣ ዝም ብዬ ማየት ነው።ይሄ የመጨረሻ ፈተናህ ነው አለኝ

አንድ ቦታ ስድስት ዱርዬዎች ከበቡና ማኑ «ወዲህ በኩል
ያሉት ሁለቱ የኔ ናቹው፣ አራቱን ውሰድ አለኝ በእንግሊዝኛ።
የኔን ሶስቱን አጋደምኳቸው፣ አንዱ ሸሸ። ፈተናዬን አለፍኩ

ግን አንድ ሌሊት አክስ ውስጥ ብቻዬን ስዘዋወር፣ ሶስት
አሜሪካኖች ግድግዳ ላይ ሲፅፍ ይዘውት፣ ሊደበድቡት እንደ ጀመሩ
ድንጋይ በመወርወር አስጥዬዋለሁ። ይህን የአምባጓሮ ችሎታውን ለምን ከነሱ ለማምለጥ አልተጠቀመበትም? ማወቅ ፈለግኩ፣ ግን አልጠየቅኩትም። ከፈለገ እሱ ራሱ እንደሚነግረኝ አውቃለሁ)

ማኑ አንድ ሊላ ነገር አስተኖሮኛል (አለ ባህራም) አየህ፣ ድሮ ሻህ ግርማ ሞገስ ያለው፣ ከነሲሩስ ከነዳርዮሽ የሚስተካከል ንጉስ
መስሎኝ ነበር። እና እየጠላሁትም አከብረው እፈራው ነበር። በማኑ
ቀልድ እየሳቅኩ በማኑ አይን ሳየው ግን ሽህ ምንም ግርማ ሞገስ የለውም። በነዳርዮሽ ዙፋን ላይ ተቀመጠ እንጂ፣ የነዳርዮሽ ደም ወይም ክብር ወይም ጀግንነት የለውም፡፡ የአንበሳ ቆዳ የለበሰ ውሻ ነው

ብኝ እሱን ተወው

አንድ ጊዜ የኮረምሻህር ወደብ ከተማ የሰራተኞች ማርበር
ሰላማዊ ሰልፍና ንግግር ለማድረግ በህግ ተፈቀደለት። የኛ ፓርቲ ላያግዛቸው ወስኖ፣ እኔና ማኑ በባቡር ሄድን፡፡ ስነ ስርአቱ
የሚካሄደው በታጠረ ኳስ ሜዳ ውስጥ ነበር። ቦታ ቦታችንን ይዘን
ንግግሩ የሚደረግበት ሰአት ጥቂት ደቂቃ ሲቀረው፣ ብዙ ብዙ
ፖሊሶች በትልቁ በር ሲገቡ አየሁ። እንደገቡ ፊታቸው ያገኙትን
በዱላ መጨፍጨፍ ጀመሩ
ማኑን «እንሂድ?» አልኩት
«አንተ ሂድ አለኝ
«አንተስ?» አልኩት
«እኔ ደህና ቦታ እንድይዝና ካለቆቻችን ትእዛዝ ካልመጣ
በስተቀር እንዳልለቅ ታዝዣለሁ»
ይህን ጊዜ ሜዳውን ጩኸትና ትርምስምስ ሞልቶታል
“አለቆቻችን የተፈቀደላቸው መስሏቸው ነበር፡፡ ግን ፈቃዱ
ወጥመድ ነው፡፡ ስለዚህ አሁን እዚህ መቆም ምንም ጥቅም የለውም፡፡
«ና እንሂድ» አልኩት
«አልሄድም፡፡ ኮሙኒስት ነኝ። አለቆቼ ሽሽ ካላሉኝ ልሸሽ
አልችልም» አለኝ
«እዚህ መቆምህ ጥቅም የለውማ!» አልኩት
“ምን ታውቃለህ? ይልቅ ሂድ ፖሊሶቹ እዚህ ሊደርሱ ነው።
በወዲያ በኩል ዝለልና አምልጥ» አለኝ
«አንተ ካልሄድክ አልሄድም» አልኩት
«እኔ አለቆቼን እታዘዛለሁ። አንተም አለቃህን ታዘዝ፡፡ አለቃህ
እኔ ነኝ፡፡ በል አሁን ሂድ። ሂድ!» አለኝ ሄድኩ። አጥሩን ልዘል ስል ዘወር ብዬ አየሁት። ዙሪያውን
ፖሊሱና ሰዉ ሲተራመስ ሲከታከት፣ እሱ ሁለት እጆቹን ደረቱ ላይ አጣምሮ እንደ ሀውልት ቆሟል። በአጥሩ ዘለልኩ
ማኑ ፖሊሶቹ ደብድበውት ሶስት ሳምንት ሙሉ ሀኪም ቤት ተኛ
መሀል ጣቱ ተሰብሮ ቀረ። አሁን ሊያጥፈው ኣይችልም
ማኑ እንዴት ኮሙኒስት እንደሆነ ልንገርህ?
አንድ የትምህርት ቤት ጓደኛ ነበረው። ጓደኝየው በጣም ጥሩ
ልጅ ነው:: ቆንጆ ቆንጆ ግጥሞችን ይደርሳል። ግን ድሀ ብጤ ነው።
ከዚህም በላይ እጅግ የተዋበ!

አንድ ቀን የዚህ ልጅ አባት ታሰሩ። በሽተኛ ሚስት፣ ስድስት
ትንንሽ ልጆች ኣሏቸው። እሱ የመጀመሪያ ልጃቸው ነው። አባትየው ታስረው ልጆቹ ምን ይብሉ? ልጁ ጨነቀው። ያባትየውን ጉዳይ የሚከታተለው የፖሊስ ሹም ቢሮ ሄደና እያለቀሰ የቤቱን ችግር ነገረው። ፖሊሱ ደግ ነበር። የልጁ ችግር ገባው። ጉዳዩ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ፣ አባትህን ዝም ብዬ ነፃ ብለቃቸው፣ የበላይ ሹማምንት ይቀጡኛል፡፡ ብቻ ለማንኛውም ዛሬ ማታ ለእራት ቤቴ ብቅ በልና እንመካከርበታለን» አለው
ሲመሽ ልጁ ፖሊሱ ቤት ሄደ፡፡ እራት ከበሉ በኋላ ፖሊሱ
ልጁን ያሻሽው ጀመር። ልጁ በመጀመሪያ ደነገጠ፤ በኋላ ተቆጣ::ይኸኔ የፖሊሱ ፊት ተለወጠ። ደግ የነበረው በሀይል ክፉ ሆነ፡፡ ረጋ ባለ ድምፅ ልጁን እንዲህ እላው
«አባትህ በኔ እጅ ነው:: ላስገድለውም እችላለሁ፣ ላሳስረውም እችላለሁ፣ ላስፈታውም እችላለሁ፡፡ ስለዚህ አባትህ ባንተ እጅ ነው
ማለት ነው:: እዚህ ከኔ ጋር ካደርክና ካስደሰትከኝ፣ ነገ አባትህ
ለምሳ ቤቱ ይመጣል፣ ተነገ ወዲያ መስሪያ ቤቱ ይሄዳል፣ በስህተት
መያዙን አስመሰክርለታለሁ፡ ቤቶችህ የሚበሉትን ያገኛሉ። እኔን
እምቢ ካልከኝ ግን አባትህ ወየውለት! ትንንሽ ወንድሞችህና
እህቶችህም ምን እንደሚውጣቸው አላውቅም፡፡ ባንተ አጅ ናቸው።
ሁሉም ባንተ እጅ ነው»
ልጁ እሺ እርስዎ እንዳሉኝ አደርጋለሁ አለ። አባትየው ተፈታ።
መስሪያ ቤቱም ተቀበሉት
ልጅየው ውርደቱን ተሸክሞ መጣና የተፈፀመበትን ግፍ
እያለቀሰ ለማኑ አጫወተው። ምን ባደርግ ይሻለኛል? አለው
አየሀ፣ ሲለያዩ ፖሊሱ ምን ብሎታል «እኔ የተገደልኩ ወይም
የተጎዳሁ እንደሆነ፣ ሁለት ሌሎች የፖሊስ ሹማምንት አሉ፤ ጓደኞቼ
ናቸው፡ ኣንተ እንደጎዳኸኝ ያውቃሉ፤
ስለዚህ አባትህን እነሱ
መልሰው ያሳስሩታል። ያን ጊዜስ አባትህን አያርገኝ፣ ቤቶችህን
አያርገኝ! ስለዚህ በኔ ላይ የበቀል ሀሳብ ባታስብ ጥሩ ነው።
ብሉታል። ልጁ ምን ይሁን? የተዋረደ ክብሩን ሊበቀል አልቻለም።
ግን ውርደቱ ሊረሳ የሚችል አይነት አይደለም። ልጁ አልቻለም።
በዛበት፡፡ ከሚችለው በላይ በዛበት፡ አበደ። አበደ በቃ! እብድ ሆነ።
ቤቶቹ በድህነታቸው ላይ ሀዘን ተጨመረጣቸው:: ደግሞስ ማን
ያውቃል? ኢራንም አንድ ታላቅ ደራሲ ባጭሩ ተቀጨባት ማለት
ይሆናል'ኮ
አይ ኢራን! ስንቱን ጉድ ትችያለሽ! ኢራን ውቢቱ! እንዴት
መሰለችህ! አቤት ህዝቡን ብታውቀው! ቋንቋውን ብትሰማው! አይ ህዝብ! እንደ ምንም ብዬ ከሻህና ከጋንግስተሮቹ ነፃ ባወጣው'ኮ የኢራን ህዝብ በደስታ ሊኖር የሚችል ህዝብ ነው። ክብሩን ልመልስለት ብችል፡ ማንንም ሳይፈራ ሰርቶ ለመብላት ቢችል፤ ህግ ካልጣስ ማንም ሊያስረው እንደማይችል እርግጠኛ ለመሆን ቢችል!
ሻህና አሜሪካኖቹ ሀብቱን ባይነጥቁት! ብቻዬን እንዳልመስልህ! በጭራሽ ብቻዬን አይደለሁም፡፡ እኔ ያየሁትን ያዩ፣ እንደኔ የሚቆረቆሩ፣ እንደኔ የተናደዱ፣ እንደኔ ደም ለማፍሰስ ዝግጁ የሆኑ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ኢራናውያን አሉ። አሉ! አሉ!
የሚመራቸውን ይጠብቃሉ! (አለ ባህራም)
ባህራምና እኔ ከተዋወቅን ጀምሮ እስከተለያየን ድረስ ስለኢራን
ያወራልኝ ነበር። ኢራን፣ ኢራን፣ ኢራን። አልሰለቸኝም ግን ይበዛብኝ ነበር። ይልቁንም የአገሩ መበስበስ ያንገሸግሸኝ ነበር፡፡ ሁሉ ነገር በጉቦ ነው። ፖሊሱ፣ ጃኛው፣ አስተማሪው ሳይቀር ጉቦ ይበላል።
👍17🔥2
ልጅህ ፈተናውን የሚያልፈው ለአስተማሪው ጉቦ ከሰጠኸው ነው። ወዘተርፈ... የመጥፎውን ያህል ብዙ ጥሩ ነገር ይነግረኝ ነበር፡፡ ብቻ አብዛኛው ጥሩ ነገር በናፍቆት ቀለማት ያጌጠ በመሆኑ
የመጥፎውን ነገር ያህል እምነቴን አይማርከም ነበር ለምን ስለኢራን ይህን ያህል እንደሚለፈልፍ ቀስ በቀስ እየገባኝ ሄደ። ካገሩ የወጣ ብዙ ጊዜው ነው። አገሩና እዚያ የሚደረገው ነገር አልተረሳውም ግን ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ እንደ ህልም እየሆነበት ሄዷል። ጊዜ ሊያሸንፈው ሆነ። ስለዚህ ስለ አገሩ ብዙ ማውራት አለበት፡፡ ቃላቱ የጊዜ ወንዝ ዳር የተተከሉ ሳሮች ናቸው:: ወንዙ
እንዳይወስደው ሳሮቹን እየተቆናጠጠ ይከራከራል. . . እስከ መቼ ድረስ?

አንዳንድ ጊዜ ተስፋ ይቆርጣል። እዚህ ቁጭ ብዬ ምን
እስራለሁ? ወይ አገሬ ገብቼ ሬቮሉሽን ኣልቆሰቆስኩ፡ ወይ ጠበንጃ አንጠልጥዬ ሄጄ ቪያት ኮንጐችን አላገዝኩ። ታድያስ? ቁጭ ብዬ እዳ አከማቻለሁ፡ ጊዚዬን አሳልፋለሁ እድሜዬን እገፋለሁ፣ ይላል::
ያ የማይበገር መንፈሱ ለጊዜው ይሸነፋል

ያን ጊዜ እኔ አወራለታለሁ፡፡ ስለሌኒን፣ ስለማኦ፣ ስለ
ሆ ቺሚን፣ ስለ ካስትሮ እነግረዋለሁ። በጊዜያቸው ከሱ የባሰ ብቸኝነት እንዳጠቃቸው፣ ከሱ የከፋ ጭንቀት እንዳፈናቸው፣ ከሱ ለረዘመ ጊዜ ስራ ፈትተው መቀመጥ ግድ እንደሆነባቸው፣ ከዚያ በኋላም ያን ሁሉ ችግር ጥሰው፣ ያን ሁሉ ተስፋ መቁረጥ ዘልቀው፣በድል አድራጊነት ብቅ እንዳሉ፣ ብቅ ብለውም አለምን እንዳናወጡ፣ ጠላታቸውን አፈር እንዳስጋጡ፣ ለተጠቃ ህዝባቸው እንጀራና ክብር እንደሰጡ፣ አልሸነፍ ባይ ተስፋ አልቆርጥ ባይ በመሆናቸው ታሪክ ውስጥ ስማቸውን በደምና በእሳት እንደፈረሙ፣ ይህን ሁሉ
ደጋግሜ እነግረዋለሁ

እሱ ራሱ ከኔ ይበልጥ የሚያውቀውን ከኔ አፍ ሲሰማው
ይፅናናል

«ለሁሉ ጊዜ አለው» እለዋለሁ «የልብን ለማድረስም ጊዜ
አለው፣ ያ ጊዜ እስኪመጣ ቁጭ ብሎ ለመታገስም ጊዜ አለው።
አሁን አንተ ልታረግ የምትችለው አንድ ነገር ብቻ ነው:: እጅህን
አጣምረህ ጊዜህን ጠብቅ። ተዘጋጅ። የሬቮሉሽን ጊዜ፣ ቆሻሻ ደም የማፍሰስ ጊዜ፣ ለተጠቃ ህዝብህ ነፃነትን በገፍ የማደል ጊዜ ይመጣል። ስለዚህ ያ የተባረከ ጊዜ ሲመጣ ተገቢውን ዝግጅት ሳታደርግ ይደርስብህና ወየውልህ!»
ምን ዝግጅት ለማረግ እችላለሁ?»
ውስጣዊ ዝግጅት። ዋናው ዝግጅት እሱ ነው:: ለነማኦ
ለነካስትሮ የወጣው ቀይ የንጋት ኮከብ ላንተም ይወጣልሀል»
ዝም ይላል፡፡ ዝም ሲል የኢራንን ሻህ ይመስላል
አንድ ቀን የኢራን ሰው ብትሆን እንዴት ጥሩ ነበር!» አለኝ
«ለምን?» ስለው
ታስፈልገኛለህ» አለኝ በጣም ታስፈልገኛለህ፡፡ እኔ መፃፍ
አላውቅም፡፡ ማድረግ ብቻ ነው:: ግን ለሬቮሉሽን ማድረግ
አይደለም። ማድረግ ግማሹ ነው፡፡ ሌላው ግማሽ መፃፍ ነው።
አዋቂዎቹን ለማሳመን ሀቁን መፃፍ፤ ተራውን ህዝብ ለማሳመን
ፕሮፓጋንዳ መፃፍ፡፡ ይህን እኔ የማላውቅበትን ግማሽ አንተ
ትሰራልኝ ነበር። እኔ ደሞ የማድረጉን ግማሽ እሰራልህ ነበር፡፡ለሁለት ግሩም ገድል እንጀምር ነበር፡፡ እንደኛ ያሉ ስድስት ሰባት ሌሎች እንፈልግና በቃ ነገሩ ተጀመረ ማለት ነበር፡፡ ያን ጊዜ ማን ያቆመን ነበር!?
«በፊት ከማኑና ከሌሎቹ ጋር ነበርኩ። ብዙ እቅድ ብዙ ተስፋ
ነበረን፡፡ አሁን ግን የት እንደደረሱ ወይም ምን እንደዋጣቸው እንጃ፡፡
ማኑ ለንደን ነበር። ጠፋ። ሞተ ሲ.አይ.ኤ ገደለው? እንጃ፡፡
ብቻዬን ነኝ በቃ። እዚህ ያሉት ያገሬ ልጆች እንደሆኑ ጀግንነታቸው
እምስ ማደን ብቻ ነው፡፡ አገሬ ገብቼ እንዳንተ አይነት ሰዎች
እንዳልፈልግ እንዴት እገባለሁ? ብገባስ የት አገኛቸዋለሁ? የሉም'ኮ እንዳንተ አይነት ሰዎች፡ ይገባሀል? የለም፡፡ ኢራን ውስጥ አሁን የሉም፡፡ ጥቂት ነበሩ፣ የሲ.አይ.ኤ ሰዎች ከሻህ ጋር ሆነው አረዷቸው:: አሁን የቀሩት መሪ ካገኙ የሚከተሉ ናቸው፣ እንጂ ራሳቸው ለመነሳት የሚችሉ አይደሉም
«እንዴት ነው የደከመችው ኢራን! እንዴት ነው የቆሽሸችው
አገሬ መለወጥ አለባት፡፡ ኢራን መለወጥ አለባት፡፡ ጋንግስተሮች
እየገዝዋት መኖር አትችልም። መለወጥ አለባት። ህዝቡ ዘለአለም ተጨቁኖ መኖር አይችልም፡፡ ዘለአለም በፍርሀት እየተርበተበተ መኖር አይችልም። ዘለአለም እንገቱን አቀርቅሮ መሄድ አይችልም።
ገዢዎቹ ተወግደው መሪዎች መምጣት አለባቸው። ህዝቡ ቀና ብሎ የመሪዎቹን አይን በማይፈራ አይን ለማየት የሚችልበት ቀን
መምጣት አለበት
"ይህ ቀን ይመጣ ዘንድ ስንቶቹ ህይወታቸውን ሰውተዋል!
አቤት ስንቶቻችን በተጨማሪ መሰዋት ይኖርብናል!
“ደም መፍሰስ አለበት። ብዙ ቆሻሻ የተመረዘ ደም መፍሰስ
ይኖርበታል! ሳስበው ያሳዝነኛል፡ ያስፈራኛል ..
ግን አንተ በጣም ታስፈልገኝ ነበር» አለ ወደፊተኛው ሀሳቡ
እየተመለሰ
«እኔኮ በሬቮሉሽን ኣላምንም» አልኩት
«ኢራን ተወልደሀ ኢራን አድገህ! የኢራንን መበስበስ አይተህ
ቢሆን ኖሮ በሬቮሉሽን ማመንህ አይቀርም ነበር። ሌላ ምርጫ
አይኖርህማ!»
«በጭራሽ!» አልኩት
ሬቮሉሽን የምትፈልገው፣ በሰው ልጅ ጥሩነት የፀና እምነት ስላለህ ነው:: የሰው ልጅ ካልተጨቆነና ካልተጠቃ ሰርቶ ይበላል፣ ብጤውን ይወዳል፣ ብለህ ታምናለህ፡፡ እኔ ግን የሰው ልጅ በተፈጥሮ መጥፎ፣ ግም
መሆኑን አርግጠኛ ነኝ፡፡ ሻህና አሽከሮቹ ቢሻሩ፣ የሚከተሉት
ገዢዎች ያው ተመልሰው ህዝቡን ይጨቁናሉ

«ፖሊሱንና ጥቃቅኑን ዳኛ ውሰድ፡፡ በሁሉ ነገር ተራ ሰው ናቸው። ግን ትንሽ ስልጣን ስለተሰጣቸው፣ በዚያች በትንሽ
ስልጣናቸው ህዝባቸውን ያጠቃሉ፣ ይጨቁናሉ፡፡ ይህ ያስቆጣሀል። ግደላቸው ይልሀል፡፡ ግን ልብ አድርግ፡፡ የሚጨቆነው ተራው ሰው፣ የነሱ ስልጣን ለሱ ቢሰጠው፣ ልክ እነሱ የሚስሩትን ግፍ ይስራል። ጭቦና ጭቆና ሊቀር የማይችል የሰው ልጆች እጣ ነው። እንግዲህ ጥያቄው ማን ይጨቁን፣ ማንስ ይጨቆን?' ነው እንጂ እንዴት አድርገን ጭቆናን እናጥፋ?' አይደለም። ሰው ከስረ መሠረቱ አስቀያሚ፣ መጥፎ፣ ክፉ ነው። ስለዚህ፣ ለሰው ልጆች ብዬ እንኳን
ህይወቴን ልሰዋ ይቅርና፣ ያንድ ቀን እንቅልፌን አልሰጥም፡

«ውሸትክን ነው» አለኝ «ውሸትክን ነው እንዲህ የምትለው።
የፈረንሳዮቹ ፍቅር የለሽነት በመጠኑ ተላልፎብ ነው። ከልብህ ሰው እንዲህ ክፉ ከመሰለህ፣ ለምን እኔን ትመግበኛለህ? ለምን ተሰፋ ስቆርጥ ታፅናናኛለህ? ሀብታም አይደለህም። ግን፣ እንደማልከፍልህ እያወቅክ፣ ካቅምህ በላይ የሆነ ገንዘብ ለኔ ታወጣለህ። ለምን?»

«አንተማ አንድ ሰው ነህ፡፡ የሰው ልጆች በጠቅላላው አይደለህም። አንተን ብቻህን ሳይህ ጎበዝና ብርቱ ሆነህ ትታየኛለህ፡፡ በሚልየን ውስጥ እንዳንተ ያለ አንድ እንደማይገኝ ይሰማኛል። ደሞ ላንት ስል አይደለም፡፡ ካንተ ጋር ስሆን ደስ ስለሚለኝ ለራሴ ስል ነው፡

«አይምሰልህ። አይምሰልህ። እንግዲያው ትፈልጋለህ? እውነቱን ንገረኝ ስቲ፡፡»

«መፃፍ ደስ ይለኛል፡፡»

«ለምን? እውነትን በምታየው አኳኋን ለመግለጽ ስለምትፈልግ
አይደለም?»

«አዎን»

«ለምን? እውነትን ካወቅካት አይበቃህም? ውበትን ካየሃት
አይበቃህም? ለምን እነዚህን ለመግለፅ ጊዜህን ታጠፋለህ?»

«እኔ እንጃ»
👍141
«ለሌሎች ማጋራት ፈልገህ ነው:: እውነትን ላላወቁ ለማሳወቅ፣
ውበትን ላላዩዋት ለማሳየት፣ ሰለህይወት የሚሰማህን አድናቆት
ለሌሎች ለማካፈል። ለዚህ ነው የምትፅፈው። ምክንያቱም
ወገኖችህን ትወዳቸዋለህ፡፡ ሰውን ትወዳለህ፡፡ ባትወድ ኖሮ እንደዚህ
አትሆንም ነበር፡፡ ለኔ የተሰጠኝ እድል ለሰዉ ሁሉ ቢሰጠው ኖሮ
እንደኔ ይሆን ነበር፡፡ ሰው ሁሉ እንደኔ ቢሆን ሀያ ሚልዮን እንደኔ
ያሉ ሰዎች በባርነት በጭቆና ሲኖሩ ብታይ ሬቮሉሽን
ልትቆሰቁስላቸው አትሞክርም ነበር?

«አየህ ሰው በመሰረቱ ጥሩ ነው:: የትም አገር ሄደህ መንገድ ይጥፋህ። ያገኘኸው ሰው ሁሉ ሊመራህ ዝግጁ ነው፡፡ እኔ እንደ
ፈረንሳዮች ለሰው ግድ የሌለው ህዝብ አይቼም ሰምቼም አላውቅም፡፡ግን የፈለግከውን ፈረንሳዊ ተማሪ፣ ትምህርት እምቢ አለኝ፤ እንዴት ላድርግ በለው። ከልቡ ሊረዳህ ይሞክራል። ያስተማሪዎቹን ፀባይ
ይገልፅልሀል፤ ምን
ምን መፅሀፍ ማንበብ እንደሚጠቅምህ ያስረዳሀል፣ የራሱን መፃህፍትና ደብተሮች ያውስሀል። ሰው መጥፎ የሚሆነው ጥቅሙን የነካህበት እንደሆነ ብቻ ነው ወይም ገዢዎቹ መጥፎነቱን ለማረም እንደመጣር፣ ክፋቱንና ጭካኔውን በብልሀት እየኮተኮቱ ያሳደጉት እንደሆነ ነው።»

«እሱን ተወውና፡ ስለካስትሮ የማታውቃት አንዲት ትንሽ
ታሪክ አለች። ልነግርህ?» አልኩት
«ንገረኝ...አየህ፣ ካስትሮ የአብዮቱ መልካም ሂደት በአለም
እንዳይታወቅ በአሜሪካ mass media ስለታፈነበት፣ ሚዛናዊና
በህዝባቸው ተደማጭ የሆኑ ምእራባውያን ጋዜጠኞችንና ደራስያንን በአክብሮት ጋብዞ መጥተውለት፣ ኩባን እያዞረ በሚያስጎበኝበት ጊዜ
በጂፕ ሲሄዱ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ እንደደረሱ፣ ድንገት አንድ ትልቅ
ደንደሳም ጡንቸኛ ጥቁር ሰውዬ ከየት መጣ ሳይባል መንገዳቸው
ላይ ቆመ መትረየስ እያነጣጠረባቸው፣ ካስትሮን
«የት ነው የምትሄደው?» አለው
ካስትሮ «እንግዶች ይዣለሁ፣ ለማስጎብኘት ነው» አለው
ሰውየው «በዚህ በኩል መሄድ አትችልም» አለው
«ለምን»
«አደገኛ ነው:: እንግዶችህ ቢፈልጉ በዚህ ሊሄዱ ይችላሉ፡፡
አንተ ግን በወዲያ በኩል ዞረህ መሄድ አለብህ።»
ካስትሮ ቀዚያ በኩል መሄድ ብዙ ብዙ ሰአት ያጠፋብናል።
ስለዚህ በዚህ መሄድ አለብን» አለው።
ሰውዬው በጣም ተቆጣ፡፡ «አደገኛ ነው እያልኩህ እንዴት በዚህ
ልሂድ ትላለህ? ለኛ አታስብም እንዴ? አንተን አደጋ የደረሰብህ
እንደሆነ፣ እኛ ምን እንሆናለን? የት እንገባለን? ምን ይውጠናል?
አይገባህም?» አለው
ካስትሮና እንግዶቹ በዙሪያ መንገድ መሄድ ግድ ሆነባቸው፡፡»
የባህራም ቡናማ አይኖች በልዩ ብርሀን ተሞሉ ብርሀን አይደለም፤ እምባ ነው የሀዘን እምባ አይደለም፤ ሌላ አይነት እምባ ነው፡፡ ከዚህ በፊት አንድ ጊዜ እንዲህ ኣይነት እምባ አይኖቹ
ውስጥ አይቼ ነበር በነጭ መሀረብ አይኖቹን እያዳበሰ
«እንደዚህ ውብ ታሪክ ሰምቼ አላውቅም» አለኝ. ..

ባህራም ስለኢራን ሲያወራልኝ አርፍዶ፣ በየሙሉው ስአት
ስለቪየትናም ወሬ ስንስማ አርፍደን፣ የምሳ ሰአት ሲደርስ ወደ
ዩኒቨርሲቲው ምግብ ቤት እንሄዳለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ ባጋጣሚ ከአሜሪካን ተማሪዎች ጋር ስንቀመጥ፣ ወሬ መጀመሩ አይቀርም። አብዛኛውን ጊዜ እየሳቀና እነሱንም እያሳቀ፣ እንደማይረቡና ተስፋ እንደሌላቸው ይነግራቸዋል። ሳይንሳችሁ የሚራመደው በጀርመኖች እውቀት ነው፣ በሲኒማ አሰራር ጣልያኖንና ስዊድን ይበልጧችኋል
ይላቸዋል በስነፅሁፍና በፖለቲካ እንግሊዞች ያስከነዷችኋል፤ በአርትና በአእምሮ ስልጣኔ ፈረንሳዮች ያጥፏችኋል ይላቸዋል።

ስለምንም ቢያወራ ዞሮ ዞሮ ወደ ኩባና ቪየትናም ይመጣና
«በጦርነት ኩባን ለመውረር ስትሞክሩ፣ ካስትሮ በኩርኩም ብሎ መለሳችሁ “Bay of Pigs" ውጊያ ላይ ሽንፈትን፣ ውርደትንና
እፍረትን አከናነባችሁ፡፡ የ
«Bay of Pigs ቅሌት!» አለ ነፃው አለም ሲሳለቅባችሁ። እናንተ ግን ጉድ እንደተሰራችሁ እንኳ አልተገነዘባችሁም፡፡ ከስህተታችሁ የመማር ፀጋ አልተሰጣችሁማ! “The bigger they
come the harder they fall” በምትሉ ጊዜ እንኳ ስለገዛ ራሳችሁ መተንበያችሁ አይታያችሁም፡፡ አሁን ደሞ ቪየትናምን ለመውረርና
ለመግዛት ትሞክራላችሁ፣ ግን ጀግናው ሆ ቺ ሚኒ ገትሮ ይዟችኋል» ይላቸዋል

ንግግሩን ሁልጊዜ በኢራን ይደመድማል «እኔ ደሞ ትምህርት
ጨርሼ አገሬ ስመሰስ፣ ከኢራን እየነዳሁ አስወጥቼ፣ ህንድ ውቅያና ውስጥ እጨምራችኋለሁ። ምን አለ በሉኝ!»

ይስቃሉ

ይህን ሁሉ ሲልና ከአሜሪካኖቹ ጋር ሲከራከር፣ እኔ ዝም ብዬ
እሰማለሁ። ....

💫ይቀጥላል💫
👍13
#አልሐምዱሉላሒ_ደህና_ናት


#ሁለት(መጨረሻ)


#በአሌክስ_አብርሃም


...በተደጋጋሚ ስለአፍራህ ከመስማቴ ብዛት አፍራህን እኔም ላፈቅራት ምንም አልቀረኝም። እውነቱን ለመናገር የዛን ጊዜ ክላስ ውስጥ ከነበርነው ሠላሳ ምናምን ወንዶች አስራ ምናምኑ በአፍራህ ፍቅር የተለከፈ ነበር፤ ሒሳብ አስተማሪያችን ጭምር። መቼም ሒሳብ አስተማሪያችን እያካፈሉም፣ እየደመሩም፣ እየቀነሱም፣ እያባዙም ሳያስቧት አይቀሩም፡፡ አንዳንዴ ቡዝዝ ብለው መላጣቸው ላይ ላብ ፊጭ ፊጭ እያለ ሲመለከቷት ያሳዝኑኝ ነበር። “ወይኔ ምነው ያችን አመዳም አግብቼ አምስት ልጅ
ባልወለድኩ ኖሮ" እያሉ በሚስታቸው የሚቆጩ ነው የሚመስለኝ።

እኔና አል አሚን ወደ ቤት ስንሄድ አፍራህና ጓደኞቿን ከሩቅ በቀስታ ተከትለን ነው። አንድ ቀን
ታዲያ አፍራህ ማስቲካ ገዝታ (ባናና ማስቲካ) ልጣጩን ጥላው ወደ ጓደኞቿ ተቀላቀለች። እኛ
የማስቲካውን ልጣጭ የጣለችበት ቦታ ስንደርስ አል አሚን ተስገብግቦ ቢጫውን የማስቲካ መሸፈኛ ወረቀት አነሳው፡፡ የሆነ ከባድ ቅርስ ወድቆ ያገኘ ነበር የሚመስለው። ለራሴ ማመን እስከሚያቅተኝ ለሁለት ዓመት አካባቢ የማስቲካውን ልጣጭ በክብር፣ በታላቅ ክብር አስቀምጦት ነበር። ለእርሱ ብቻ
በሚታይ ስውር ቀለም የአፍራህ ምስል የታተመበት እሰኪመስለኝ።
አል አሚን እንዲሁ ሲሰቃይ ክረምት ገባ። እፍራህን ለሁለት ወራት መለየት ለአል አሚን የቁም ሞት ነበር። ሱስ ሆናበታለች፡፡ አፍራህ ዓለሙን ሁላ አጨላልማ በነፍሱ ሰማይ ብቻዋን የደመቀች ኮከብ ነበረች። ቢሆንም እንደለመደው በዝናብ ሳይቀር ከረንቦላ ቤት እየሄደ እዛው ቆሞ አፍራህን ስትወጣ ለማየት ይጣጣር ነበር። ለአስራ አምስት ቀናት ጠብቆ ኣላያትም፤ ሊያብድ ሆነ።

ታዲያ በመሀሉ በጣም የምንወዳቸው ሼህ ያሲን የሚባሉ ሰውዬ መንገድ ላይ አገኙኝ። የአል አሚን ቁርአን አስቀሪ ናቸው።

“አቡቹ ደህና ዋልክ?”

“ደህና ዋሉ ሸሃችን "

"አልሃምዱሊላሂ…. እስቲ ወዲህ የማወጋህ ጕዳይ አለኝ” አሉና ከመንገዱ ወደ ዳር ወስደው እንዲህ አሉኝ፣ “ ጓደኛህ አል አሚን ምን ነክቶት ነው ልጄ? ከቀልቡም አይደለም፤ ቁርአን ቤትም መምጣት ካቆመ ስንት ጊዜው! …ተበላሽቷል ይሄ ልጅ ጭራሽ ዛሬ እዛ ቁማር የሚጫወቱበት ቤት ቁሞ አየሁት። ጓደኛው ነህ፤ አትመክረውም? ኧረ ቀልቡ ደረቀ…።” ብለው ነገሩኝ። በአል አሚን አዘንኩ።ማን ያውቃል የልጁን ጉዳት። የዋልንበት ቦታ ሁሉ ያለን እየመሰላቸው ስንቶች በዋልንበት ፈረጁኝ…

አል አሚን አንድ ቀን እየተጣደፈ ቤት መጣ። ከመቸኮሉ ብዛት ድመታችንን በሩ ሥር እንደተኛት
ጀራቷን ረግጦ ካቅሟ በላይ እስጮኻት፤

"አቡቹ…! አቡቹ! አይገርምም የነአፍራህ ቤት ለካ በሩ እኔ ከምቆምበት በኩል አይደለም፤ …
ከኋላ በኩል በዘይት ቤቱ ጋ ነው፤ በዛ በኩል ነው የምትወጣው… ሂሂሂ ተሸውጄ " አለኝ፤ ሲያወራ
በደስታ ፊቱ በርቶ ነበር። “…ዛሬ ባጋጣሚ በታች በኩል ስሄድ ከእናቷ ጋር ሆና ፌ…ት ለፊት፣
እንደዚህና እንደዛ …በቃ ተያየን፣ ወ…ላሂ አቡቹ ግጥምጥም ነው ያልነው፣ አኡዙቢላሂ …ልሮጥ ነበር ሂሂሂሂሂሂሂ አለና ፍርፍር ብሎ ሳቀ። ድንገት ተነስቶ ቆመና ደግሞ “እስኪ እየኝ፣ እንዲህ ሆኜ እኮ ነው ያየችኝ፤ እደብራለሁ እንዴ …?” አለኝ። ሁለት እጆቹን ግራና ቀኝ እንደ ከንፍ ዘርግቶ አንዴ እኔን
እንዴ ራሱን ቁልቁል እየተመለከተ። አሳዘነኝ። የአፍራህን ቅንጡ አለባበስ እና የአላሚንን የተንሻፈፈ
ሸራ ጫማ፣ ያረጀች እና የወየበች ቪ ቅርፅ ቲሸርት በውጤ እያሰብኩ፣

ኧረ እይደብርም!" አልኩት።

እንደ ሕፃን እየተፍነከነከ መጥቶ አጠገቤ ኩርምት ብሎ ተቀመጠ። “…አይገርምም ከእናቷ ጋር ሆና
በቃ እንደዚህ እና እንደዛ ፊት ለፊት…! እንዴት አምሮባታል አቡቹ ብታያት…ወላሂ ያች የምታውቃት
አፍራህ አይደለችም! በቃ እንደዚህና እንደዛ እኮ ነው…" እጆቹ ይንቀጠቀጣሉ፤ ዓይኖቹ የደስታ! የሐዘን፣ የሐፍረት፣ የምኞት ብርሃን ይረጫሉ። ፊቱ ላይ ደስታ እንደረበበት ልሸኘው ውጣሁ።
ልንለያይ ስንል፣ “..አቡቹ ሁለት ብር አለህ እንዴ?” አለኝ እየፈራ። አል አሚን እንኳን ደፍሮ ብር
መጠየቅ፣ ያዋሰውን ደብተሩን እንኳን መልሱልኝ ለማለት የሚፈራ ልጅ ነበር፡፡ ብር ስላልያዝኩ…ወደ
ቤት ተመልሰን ከእናቴ ተቀብዬ ሰጠሁት። ደስ ብሎት ሄደ።

ቆይቼ ስሰማ በአዲሱ የእነአፍራህ በር በኩል አንድ ሻይ ቤት አለች! ሻይ ሃምሳ ሳንቲም ነው!
በሰጠሁት ብር ሻይ እያዘዘ ቁጭ ብሎ አፍራሀን ሲጠብቅ ነበር፤ አራቱንም ቀን ግን አላያትም።
እናም ከረንቦላ ቤት አካባቢ ያገኘውን የእነእፍራህን ሰፈር ልጅ ጠይቆ አፍራህ አዲስ ኣበባ ለእረፍት እንደሄደችና ትምሕርት ሲያልቅ እንደምትመጣ አረዳው፡ ቅስሙ ተሰበረ። ቢሆንም እነአፍራህ ሰፈር መሄድ አላቆመም። በየቀኑ ያንን ሰፈር ሳይረግጥ አይውልም። ሸርፍ ተራ ትርምሱ፣ ግርግሩ፣ ጫት
ተራው፣ መኪናው፣ የደሴ አንደኛ “ቀውጢ" ሰፈር… ይሄ ሁሉ ግርግር ግን ከአፍራህ አይበልጥም። አፍራህ ብቻዋን የአንድ ትምሕርት ቤት ወንዶች ነፍስ የተደረደረባት ገበያ አይደለች እንዴ ።

“እሷ ከሌለች ለምን ትሄዳለህ?” እለዋለሁ፤

“እኔንጃ” ነው መልሱ፤ ያሳዝነኛል !!

አንድቀን ደግሞ ቤት መጣና አቡቹ ሥራ ልጀምር ነው" አለኝ፣ በደስታ ፍንክንክ ብሎ።

“የምን ሥራ አልኩት፤

“አይሱዙ መኪና ላይ ረዳትነት”

“ትቀልዳለህ !?"

“ወላሂ እውነቴን ነው። ካአዲስ አበባ ደሴ የሚምሳለስ አይሱዙ ላይ ሥራ ልጀምር ነው። እናቴንም
ነግሬያት ኣሳምኛታለሁ። መኪናው ቅዳሜ ወደ አዲስ አበባ ይወጣል። አብሬው እሄዳለሁ። ብታይ ቀላል እኮ ነው ሥራው።” ፊቱ ላይ ተስፋ ይንቀለቀላል። በቀጫጭን እጆቹ ሸራ ሲጎትት፡ የጎማ ብሎን ሲያጠብቅ አሰብኩት፤ አል አሚን ትንታጉ ተማሪ። ይሄ ፍቅር የሚሉት ነገር ግን ምናይነት ልክፍት ነው
በእግዚእብሔር!!

አልአሚን ገና በመጀመሪያ ጉዞው ከመኪና ላይ ሲወርድ ወድቆ ግንባሩ ተፈንከቶና ከንዱ ተላልጦ
መጣ። ሰው ሁሉ እንኳን አላህ አተረፈህ!” እያለ አዘነለት። እንዲህ ካልተላላጡና ካልተፈነከቱ የልብን
ስብራት፣ የመንፈስን መድቀቅ ዓይቶ የሚያስታምም የለም መቼም። እንዲህ አለኝ፣ አሮጌ ፍራሹ ላይ እንደተኛ “አንተ … አፍራህ ያንን ሁሉ መንገድ አልፋ ነው አዲስ አበባ የሄደችው…? እነዛን ተራራዎች ዓይታቸዋለች…፣ ያንን ገደል እያየች ፈርታለች ፣ ደብረሲና ምሳ በልታለች፤ ቆሎም ገዝታ ሊሆን ይችላል….እዛ ጨለማ ዋሻ ውስጥ ስትገባ በፍርሃት ተንቀጥቃጣም ይሆናልኮ። ኡፍፍፍፍ አንጀቴን
በላው፡፡ ከላይ እንደእቃ ተጭኖ አፍራህ ባረፈችበት መንገድ በማለፉ ምናባዊ ዳናዋን ተከትሎ ሲነጉድ ታየኝ። ሚስኪን አልአሚን !

ቀስ በቀስ አልአሚን ነገሮች ሁሉ ተቀላቀሉበት። አንድ ቀን ትምሕርት ቤት ሄደና ጭርር ያለው በር ላይ ያገኛቸውን የትምሕርት ቤታችን ጥበቃ ጋሽ ደምሴን፣ “ትምሕርት መቼ ነው የሚጀመረው?” አላቸው፤

“ምን አውቄ ብለህ ልጄ” አሉት። ቀጠል አድረገውም…የኔ ልጅ ኳስ ሰራገጥ ይውላል፣ አንተ ትምርት
ናፍቆህ.የወለዱህ ኣባትና እናት ምንኛ ይኮሩ!! እሰይ!! እሰይ!”

ትቷቸው ወደ ቤት ተመለሰ፤ በቃ መረጋጋት አቃተው ተወዛገበ።
8ኛ ክፍል በተመሳሳይ ለአፍራህ ፍቅሩን ሳይነግራት በየቀኑ እያያት በዓይኖቹ ተስፋ ነፍሱን አፋፍቶ
ኖረ። አንድ ቀን ለአፍራህ ስጦታ ልሰጣት አሰብኩ" አለኝ። ገረመኝ ! ወይኔ ፍቅር ጉድለት አይገባው፣ ድህነት እያልኩ ሳስብ አልአሚን አንድ የሃምሳ ብርና ሦስት አስር አስር ብሮች ከኪሱ አውጥቶ አሳየኝ።

“ከየት አመጣኸው?"
👍28👎1
“ለረመዳን መስገድ ጫማ ጠርጌ ያጠራቀምኩት ነው"

እና ለአፍራህ ስጦታ ለመገዛት በድፍን ደሴ ስጦታ መሽጫ ቤት ዞርን። ለአፍራህ የሚሆን ስጦታ
ጠፋ። ለነገሩ ስጦታው ብቻ አይደለም የጠፋው፤ ስጦታ መስጫ ወኔም ነጠፈ። አሁንማ አፍራህን እኔም እንደ አልሚን ሆነኮ የምፈራት። ይሄው ወደ 9ኛ ክፍል ስናልፍ አፍራህ ወደቀች፡ አል አሚን ደግሞ እሷን ጥሎ ማለፉን ጠላት አድርጎ ጠመደው።

ወይዘሮ ሲኂን ገባን ። ያንን ሰማያዊ ዩኒፎርም ለብሰን የፒያሳ ደረጃ ላይ ተጀነንበት፤ ተኮፍሰንበት። በተለይ ያኔ ሌላኛው ሃይ ስኩል' (ሆጤ ይባላል) እዛ ይማሩ የነበሩ ልጆች በእኛ ይቀኑ እንደነበረ ትዝ ይለኛል። ሃሃሃ…በእርግጥ ከዛ ቀይ ሹራባቸው እና አረንጓዴ ካሽመሪ ሱሪያቸው ጋር ሲተያይ እኛ የሲኂን ተማሪዎች አምባሳደር ነበር የምንመስለው፣ የዛሬን አያርገውና። ስንኮፈስ ታዲያ ደረጃችንን እንደ ዶላር እንመነዝረዋለን። "የወይዘሮ ስኂን 9ኛ ክፍል የሆጤ 12ኛ ክፍል ጋር ሒሳሱ እኩል ነው።"እያልን ሃሃሃሃ እንደ ሹራባቸው ፊታቸው በብስጭት ይቀላል። ቢሆንም ምርጥ ጓደኞቻቸን ነበሩ።

እኔ ልክ ወደ 10ኛ ክፍል ሳልፍ ደሴን ለቀቅኩ፤ ውድ ጓደኛዬን ከነኑሮ ድቅስቃሱ ብቻውን ትቼው።
በቃ ከአል አሚን ጋር በዛው ተለያየን። ሁልጊዜም ትዝ ይለኝና ምን ሰይጣን እጄን እንደሚይዘው እንጃ ስልክ እንኳን አልደውልለትም ። በቃ ተለያይተን ቀረን። ሲቆይ ትዝታውም እራሱም ደበዘዘ። በራሴ የሕይወት አዙሪት፣ በራሴ ጓደኞች ተከብቤ አልአሚን ምርጡን ጓደኛዬን ከነመኖሩም ረሳሁት። ሰው ወረተኛ ነው።

ወደ ደሴ የተመለስኩት ከአስር ዓመት በኋላ ነበር። የጓደኝነት መንፈሱ ከተማው መግቢያ በር ላይ ቆሞ የጠበቀኝ ይመስል ገና ሸዋ በር ስደርስ አልአሚን ከነናፍቆቱ አእምሮዬን ሞላው። በቀጣዩ ቀን እነ አልአሚን ቤት ስሄድ እናቱ እንደሞቱ፣ አል አሚንም የአይሱዙ ረዳት እንደሆነና ሸርፍ ተራ አካባቢ
እንደማይጠፋ አንዲት ልጅ ነገረችኝ፤ የት ነው የማውቀው ብላ በትኩረት እየተመለከተችኝ። ድሮ
አውቃታለሁ፤ የነአልአሚን ጎረቤት ነበረች።

ሽርፍ ተራ ሄድኩ። ትርምሱ ብሶበታል። አዳዲስ ሕንጻዎች ወረውታል። ጣሊያን በሠራው ጅብሩክ በሚባለው የገበያ አዳራሽ ውስጥ ለውስጥ ብዙ አይሱዙ መኪናዎች የተደረደሩበት መንገድ ላይ አንዲት ትንሽ ሻይ
ቤት በረንዳ ስደርስ ብዙ ወጣቶች ተሰብስበው ጫት እየቃሙ ሞቅ ያለ ወግ ይዘዋል። ጠጋ ብዪ አንዱን አልአሚን የሚባል ልጅ ያውቅ እንደሆነ ጠየቅኩት። ፊት ለፊት ያለ ሌላ ሻይ ቤት ጠቆመኝና ወደዛው አቀናሁ፡፡

አልአሚንን አየሁት። ጫቱን በግራ እጁ እንደያዘ በጩኸት ተቀበለኝ።

"እ......ኔ አላምንም!! እኔ አላምንም.!! አቡቹ እንዳትሆን..እኔ አላምንም!! የአ...ላህ!!”
ተቃቀፍን። አል አሚን እንደዛው ክስት እንዳለ ነው፤ ጥርሱ በጫት በልዟል፣ ሲያየኝ ትንሽ ተሳቀቀ።
ትከሻና ትከሻዬን ይዞ ራቅ አድርጎ ያየኝና፣ “የ…አላህ!!" ብሎ አንደገና አቅፎ ይስመኛል። ተያይዘን
እዛው ጅብሩክ ፎቅ ላይ ወዳለ ካፌ ገባን።

“እንዴት ነህ አሚ?” ስጠራው እንደዛ ነበር።

ከልሃምዱሊላ.!! ደህና ነህ አቡቹ ..? ማሻ አላህ!! አምሮብሃል!” አለኝ ትከሻዬን በቀኙ ቸብ ቸብ እያደረገ። እኔ ስላማረብኝ ብቻ አቤት ፊቱ ላይ የነበረው ደስታ!! እኔም እንደዛው ሳልሆን አልቀረሁም የእኔ ግን ስላገኘሁት ነበር። ምሳ እየበላን የባጥ የቆጡን አወራን።

አልአሚን ትምህርቱን ከአስረኛ ከፍል አቋርጧል። እናቱን ለማስታመም ነበር ያቋረጠው። እናቱ አልተረፉም። ከዛ በኋላ መቀጠል አልፈለገም። እዛው ሽርፍ ተራ የድለላ ሥራ እየሠራ፣ ረዳትነትም እየሞከረ ቀልጦ ቀረ። ያ ፈጣኑ አስገራሚ አእምሮ የነበረው አልአሚን በቃ ይኼው ሆነ እጣ ፋንታው…።

እየፈራሁ የማይቀረውን ጥያቄ አስከተልኩ፤

“እኔ የምልህ "አ..አፍራህስ አለች?”

ዝምምምምምሃምም አለ አልአሚን። እናም ቅሬታ የተቀሳቀለ ፈግታውን እያሳየኝ “ኤልሃምዱሊላሂ ሁለት ቆንጆ ልጆች ወልዳለች። እንዴት ያማምራሉ መሰለህ!” አለኝ። ግራ ገባኝ! ግራ መጋባቴን አይቶ
ካለንበት ፎቅ ላይ አሻግሮ ጫፉ የሚታይ ፎቅ በእጁ በያዛት የጫት እንጨት እየጠቆመኝ፣ “…የነሱ
ነው…አንድ ሃብታም አግብታ ይሄን ፎቅ ሠርተው እየኖሩ ነው። ከስር ያለው ትልቅ ሱቅ የእሷ ነው
ሁልጊዜ አያታለሁ፤ ወላሂ አምሮባታል…" አለኝ።

ከነቅሬታ ፈገግታው አቀረቀረ። ከረዥም ዝምታ በኋላ የምግብ ጠረጴዛው ላስቲክ ላይ እንባው ጠብ ሲል አየሁት። አቅፌ ወደ ራሴ አስጠጋሁት፤ ከልቤ አዝኜ ነበር። እናም በእቅፌ እያለ ድምፁን ቀንሶ እንዲህ አለ፣
“አልሐምዱሊላሂ! አፍራህ ደህና ናት። አያታለሁ ዛሬም።

አለቀ
👍15😢86
አትሮኖስ pinned «#አልሐምዱሉላሒ_ደህና_ናት ፡ ፡ #ሁለት(መጨረሻ) ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ...በተደጋጋሚ ስለአፍራህ ከመስማቴ ብዛት አፍራህን እኔም ላፈቅራት ምንም አልቀረኝም። እውነቱን ለመናገር የዛን ጊዜ ክላስ ውስጥ ከነበርነው ሠላሳ ምናምን ወንዶች አስራ ምናምኑ በአፍራህ ፍቅር የተለከፈ ነበር፤ ሒሳብ አስተማሪያችን ጭምር። መቼም ሒሳብ አስተማሪያችን እያካፈሉም፣ እየደመሩም፣ እየቀነሱም፣ እያባዙም ሳያስቧት…»