አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#አምስት


#በአሌክስ_አብርሃም



...ከሃኒባል ጋር ሆነን ያልረገጥነው የባሕል ሕክምና አዋቂ ቤት የለም፤ ደከመን። ሃኒባል ለእኔ ሲል
ያለችውን የዓመት እረፍት ጨርሶ ካለ ክፍያ አንድ ሳምንት ከሥራው ቀረ። ግን ምን ያደርጋል፣ ሁሉም
ነገር ከንቱ ልፋት ብቻ ሆነ። የሄድንባቸው ሁሉ ለእኔ ችግር መፍትሔ ማምጣት ይቅርና፣ ማፅናናት እንኳን ያልፈጠረባቸው አጋሰስ ነጋዴዎች ነበሩ። ቢጨንቀን አንድ ሁለት የልብ ጓደኞቻችንን ጨምረን
ጉዳዩን ነገርናቸው።ኣንዱ ጓደኛችን ለትምሕርት ውጭ ቆይቶ ገና መመለሱ ነበረ፤ ማይክሮባይሎጅ
ነው።

ጉዳዩን በጥሞና አዳመጠና፣ “…እስቲ እንዲት ውጭ ኣብረን የተማርን የስነልቦና ባለሞያ አውቃለሁ”አለ። ደስ የምትል የተረጋጋች ልጅ ጋር ወሰደኝ። ቢሮዋ ይገርማል፤ ሁሉም ነገር ነጭ ከእስከርብቶና ወረቀቱ ውጭ። ተነስታ ተቀበለችን። ከአንድ ሰዓት በላይ ያወራሁ ሳይመስለኝ ብዙ አስወራችኝ

“እኔ የምልህ አብርሃምም
እ ?"

ፍቅረኛህ ምናልባት ከቤተሰብህ አንድኛቸውጋ በመልከ ወይ በባሕሪ ትመሳሰል ይሆን?ፀ

"ኧረ በጭራሽ !እህቴ አፍንጫ የሚባል ነገር አልፈጠረባትም፣ ሙና'ኮ ሰልካካ ናት። እህቴ ከማጠር ብዛት ከራሷ ቦርሳ ቻፕስቲክ ለማውጣት እንኳን ወንበር ላይ ቆማ ነው፤ ሙና'ኮ መለሎ ፈገግ አለች
የሥነልቦና ባለሞያዋ። ጥርሶቿ ያማምራሉ (ልብ አይሞት አሁንም ሴት አደንቃለሁ)
እናቴም ብትሆን ቁመቷ እህቴ ነው የወጣችው። በዛ ላይ እናቴ ጠይም ሙና እኮ ዝም አልኩ!
ምናልባት የወሲብ ፊልሞችን ትመለከት ነበር እንዴ ?
“ኧረ አይቼ አላውቅም" እውነቴን ነበር።
“ቤተሰባችሁ ውስጥ የሚበዙት ሴቶች ናቸው ወንዶች ?
“ልጆቹ እኔና እህቴ ነን.… በቃ ! የሥነልቦና ባለሞያዋ የሆነ ነገር ቀይ ወረቀት ላይ በቀይ እስክርቢቶ
ስትጽፍ ቆየችና፣ (እንዴት እንደሚታያት እኔጃ
«ኃይማኖት ላይ እንዴት ነህ ?» «ታጠብቃለህ ?”
«ኧረ የለሁበትም።"
ቤተከርስቲያን የሄድኩት ራሱ ኢህአዴግ አዲስ ኣበባን ሲቆጣጠር የበቅሎ ቤቱ
ፍንዳታ ጊዜ፡ እናቴ ሚካኤል ልትደበቅ ስትሄድ እጄን ይዛኝ ነው ከዛ በኋላ ሄጄ አላውቅም

ፍቅረኛህ ሌላ ወንድ ጋር ግንኙነት አላት ብለህ ታስባለህ ?”

ማን ሙና … ኧረረረረረረረረረረ"

ከዚህ በፊት ከሌላ ሴት ጋር ወሲብ ያልፈጸምከው ለምንድን ነው ”

"እኔጃ"

"ሴን ትፈራለህ እንዴ ?

"መፍራት ሳይሆን እንዲሁ መቅረብ ብዙም አልፈልግም።” ወንበሯ ላይ ተመቻችታ ወደኔ ዘንበል አለችና (ጡቶቿ አፈጠጡብኝ)

“ለምን ?” ስትል ጠየቀችኝ፤ ቁልፉን ያገኘችው ሳይመስላት አልቀረም።

ረዥም ሰዓት በስልክ እንዳያወሩኝና ሸኘኝ እንዳይሉኝ … ! ስል መለስኩላት። እንደው ይህ ምላሽ መታበይ ይመስል ይሆናል እንጂ ማንንም እንደመሸኘትና እና በስልክ እንደማውራት የምጠላው ነገር
የለም። እኔም ሲሸኙኝ አልወድም፤ ሰውም መሸኘት ያንገሸግሽኛል። ምንድን ነው መጓተት፣ ምንድነው
ስልክ ላይ ተለጥፎ ማላዘን ? እንዴት እንደሚያስጠላኝ ! ስልከ አልወድም።

እሺ አብርሽ ጨርሰናል፣ ስልክህን ስጠኝና እደውልልሃለሁ” እርፍ!!
የሥነልቦና ባለሞያዋ እየደወለች ልትረዳኝ ብትሞከርም ነገሩ ዋጋ አልነበረውም። የበለጠ ስለጉዳዩ
ባሰብኩ ቁጥር በእግሮቼ መሃል ሳይሆን በፍርሃት መሃል ቁም ነገሩ ጠፋ። ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም !! ወዶ ነው አበሻ፣ “ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ" የሚለው። ትውልድን የሚሻገር ሕያው ድምጽ
መፈጠሪያው የት እንደሆነ ሲገባው እንጂ ! ኤዲያ!ወንድነት ደገፍ ብሎ የሚኮፈስበት ከዘራ ሸንበቆ ሲሆን አለ ከልብ የሚሰነጠር ወኔ ከተራ ብልግና የገዘፈ ሃቅ፤ ቃጭሉም ዝም ! ቤቴ ውስጥ ካሉት እቃዎች ምን አስጠላሀ ብባል አልጋዬ። የተሸነፍኩበት፣ የተማረክኩበት፣ የቆሰልኩበትና የተሰዋሁበት
ጦር ማዴ መስሎ ታየኝ። “ወኔዬን ያፈሰስኩበት አልጋ እኮ ነው ብዬ የልጅ ልጆቼ ላይ እኮፈስበት
ይሆናል። ያኔ ወኔው ያፈሰሰ ትውልድ ነፍ ነው የሚሆነው ! ወኔ ቢስነትም ክብር!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሙና ልትመጣ አስራ አንድ ቀናት ቀሩ ። አስራ አንድ የሽብር ቀናት ! “አብርሽ ፈራህ እንዴ ?ሂሂሂሂሂ
እንደ ቀልድ ትጠይቃለች። ለምን ጀግና ለመምሰል እንደምጣጣር ለራሴም አይገባኝ፤ ፈርቻለው
አይደል እንዴ ? አዎ ፈርቻለሁ ብላት ምን ነበር ? እኔ ግን ኮስተር ብዬ እንዲህ አልኳት፣ “ለምኑ ነው
የምፈራው?

“ለብር አምባሩ ነዋ አለችና ትንፋሽ እስኪያጥራት በሳቅ ፈረሰች። ሳቋ ውስጥ ሺ ጊዜ ፍራ እንጂ
አሁንማ ቁርጥ ነው የሚል ንዝረት አለ። እኔ'ኮ የሚገርመኝ “ብር አምባር” ከእንትን” ጋር ምን
አገናኘው? እውነቴን እኮ ነው … ብዙ ወንዶች ከአንዲት ሴት ጋር ወሲብ ሊፈፅሙ “ፈረሱም ሜዳውም ያውላችሁ” ሲባሉ በስሜት ስለሚሳከሩ እንኳን ቃል ሊሰነጥቁና ሊመረምሩ አልጋ ላይ ይሁኑ ዓየር ላይ የሚያውቁት ከተረጋጉ በኋላ ነው። ከዛ በፊትማ ብር ይልሰር አምባር ይሰበር ብርጭቆ ይሰበር ቅስም
ይሰበር ምን ግዳቸው "ሰማዩን ሰበረው ጀግናው” ቢባልም አይሰሙም፤ እኔ ግን የያዘ ይዞኝ ቀልቤን አሰላሳይ አድርጓታልና “ብር አምባር” ከድንግልና ጋር ምን አገናኘው ብዬ አስባለሁ -- (ሰው ወዶ ፈላስፋ አይሆንም መቼስ ይሄ ሁሉ ሚዜ እና ታዳሚ ላንቃው እስኪደርቅ በየሰርግ ቤቱ“ብር አምባር ሰበረልዎ ጀግናው ልጅዎ እያለ ይዝፈነው እንጂ “ድንግልናን ከብር አምባር ምን አገናኘው ለሚለው ጥያቄ መልስ ያለው አይመስለኝም።

እኔ ግን ዝም ብዬ ሳስሰው፣ “ብር አምባር መስበር አስገድዶ ከመድፈር ጋር “ጥብቅ ቁርኝት ያለው ጉዳይ ይመስለኛል። ልጅቱ የብር አምባር እጇ ላይ አጥልቃለች፤ ያው ሴት የብር አምባር ማድረጓ ከጥንት የተለመደ ነገር ነው) እና ባሏ ወላ ወዳጇ እጇን ይይዛታል .… (ያዝ እጆን) እንዲል ዘፈኑ ከዛ ለማምለጥ ወይም ራሷን ለማዳን እንዳቅሟ መታገሏ አይቀርም፤ መቼስ ዝም ብሎ ያውልህ አይባልም።
በሩን ይዘጋል (ዝጋ ደጇን) እንዲል ቀጣዩ የዘፈኑ ስንኝ፤ ትግሉ ከበረታ እጇን ጠምዝዞ ጉንጯን (ሳም ጉንጯን ) የሚለው ልክ መጣ። ለከንፈሯ ያሞጠሞጠው ከንፈር በልጅቱ መወራጨት ስቶ
ጉንጯ ላይ አርፎም ሊሆን ይችላል፣ ወይም አየር ላይ እንደ ርችት የከሸፈ መሳም ብትን ! ሲታገላታ እጇ ላይ ያለው አምባር ስብር ! ከሽ ! “ይሰበር የታባቱ ቅዳሜ ገበያ ስወጣ ሌላ እገዛልሻለሁ ያውም ወርቅ የመስለ” እያለ ወደ ጉዳዩ !
እንዲህ የሚያስለፈሰፈኝ ወድጄ አይደለም፤ አምባሩ እኔ እጅ ላይ ያለ እስኪመስለኝ መዘዜ ሊመዘዝ
አስራ አንድ ቀን ቢቀረኝ እንጂ። ሙና ይቅርታ አታውቅም ! በአሁኑ ጉብኝቷ ጉንጯን ስሜ ብልካት
እርሷም እንደ ይሁዳ ስማ ነው ለብቸኝነት ስቅላቴ የምትሸጠኝ። ሙናን እኮ አፈቅራታለሁ። እንደ
ቀልድ ሳጣት ነው በቃ ? እሺ አሁን የእኔ ጥፋት ምንድን ነው? የሙና ጥፋትስ ? እግዚኣብሔር ግን
ምን አደረግኩት ? እስኪ አሁን ማን ይሙት ሊቃጣኝ ፈልጎ ከሆነ ሌላ ልምጭ አጥቶ ነው !? ለምሳሌ ሰፈራችንን በጎርፍ አጥለቅልቆ እኔን ብቻ በመግደል ዜና ማድረግ አይችልም ? መንገድ ላይ ሱክ ሱክ ስል መብረቅ አውርዶ ድምጥማጤን ማጥፋት ያቅተዋል ? ምን አድርጌው ከማን የተለየ ጥፋትና በደል ሰርቼ በውርደት የምወዳትን ልጅ ዓይኔ እያየ ያስነጥቀኛል ? አባታችን አብርሃም እንኳን በዘጠና ስንት
አሙቱ ተሳክቶለት ልጅ ሲወልድ እኔን ሚስኪኑ በሃያ ሰባት አመቴ እንዲህ ጉድ ስሆን እግዜር እንዴት
ሆዱ ቻለ ?

'አብርሽ” እለኝ ሃኒባል፣

"እ"

“ግን ችግሩ ከሙና ቢሆንስ ?"

“እንዴዴዴዴዴ ምን አገናኘው ከሙና ጋር”
👍23
“አይ እንደው ካልደበረህ … ሌላ ሴት ጋር ብትሞክር ምናልባት ነገሩ ሊቀየር ይችላል”

"ምናልክ አንተ ? .. ችግር አለብህ እሺ … ሁለተኛ እንዳትደግመው”

“ሶሪ" ብሎ ዝም አለ። እሱ ዝም ይበል እንጂ አዕምሮዬ ግን ሃኒባል የለኮሳትን ችቦ አንስቶ ሩጫውን
ተያያዘው። ሌላ ሴት፣ ሌላ ሴት፣ ሌላ ሴት … ሌላ ሴት ለሙከራ የምትሆን ሴት … ሴት .. በቀላሉ
የምትገኝ ሴት .. ሰራም አልሰራም ከሙከራው በኋላ ዳግም አጠገቤ የማትደርስ ሴት .. ሴት …. ወሬ
የማታበዛ ሴት፤ በቃ ቀጥታ ወደ ገደለው ስትባል ቀሚሷን ወላ ሱሪዋን የምታወልቅ ሴት … ሴት …
ሴተኛ አዳሪ ! ምንም ! አዕምሮዬ ውስጥ ቤተሙከራውን የያዘ ሐሳብ ፈነዳ። ሴተኛ አዳሪ ጋር
መሄድ ! አዕምሮ የሰው ልጅ የገጠመውን ችግር ሁሉ መፍቻ ሐሳብ አመንጭቶ ሽቅብ እንደሚተኩስ ሁሉ የሕይወት ክርፋት ውስጥ በአናታችን የሚከት ሐሳብም እንዲህ ይዞልን ከተፍ ይላል። ሰው የራሱን አዕምሮ ካሻው መምጠቂያ ሮኬት፡ ከፈለገም መቀበርያ የአስክሬን ሳጥን ሊያደርገው ይቻላል።

ለድፍን ሳምንት ይሄ ሃሳብ ከአዕምሮዪ ሊወጣ አልቻለም

እንደውም አንድ ሌሊት በህልሜ ምን አየሁ ቡና ቤት አንዲት ከምድር ወገብ መስመር የረዘመ
ቀይ እግር ያላት ሴተ ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጣለች።እግሯ ከመርዘሙ ብዛት ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጣም መሬቱን ረግጣለች፡ እኔ ከኋላዋ ወደ እሷ እየሄድኩ ነው እየተራመድኩ ሳይሆን ልክ በካሜራ ክሎዝ አፕ እንደሚሉት ባንዴ በዓይኔ ስብያት አጠገቧ ቆምኩ፡፡ ሽቶዋ ሸተተኝ ደግም የሚገርመው ወንድነቴ ሱሪዬን የወጠረው ይመስለኛል። “ማድረግ የቻልነኩ ይመስለኛል። ልጅቱ ወደ እኔ ዞረች፣ ሙና ነበረች። ባንኮኒው ላይ ብር ከምራ እየቆጠረች። ወድያው ቡና ቤቱ ባንክ ቤት ነው።

ጓደኞቹ ሃኒባል እግዜር ይይልህ ! (የዋልከልኝን ውለታ አቀናንሶ )

ሮጠ ጊዜው ሸመጠጠ ! ሦስት ቀናት ብቻ ቀሩ ሙና ልትመጣ

ሃኒባልን “ሦስት ቀን ቀረ ምናባቴ ላድርግ?” አልኩት።

“በሦስት ቀን … ሊደረግ የሚችለው ብቸኛው ነገር መፀለይ ነው አብርሽ።

“አትቀልድ ባክህ"

እውነቴን ነው አምላኬ ሆይ ጉድ ልሆንልህ ነው፧ የሰጠኸኝ ሔዋን እንደ ሰሜን ኮከብ ያውም እንደ
ጅራታሙ እየተንቀለቀለች ሰማዩን ሰነጣጥቃ አዲስ አበባ ላይ ልታርፍ ነው … እሳቱ በረዶ ክምር
ላይ ተከስክሳ እንዳትከስም እርዳኝ በልና ድፍት ብለህ በሩ ላይ አልቅስ : እየቀለደ መስሎኝ ልበሳጭ ተዘጋጅቼ ፊቱን ሳየው ሃኒባል ከምሩ ነው!

“እና እንትኔን አቁምልኝ ብዬ ልፀልይ ? - ባለጌ ብሎ ነው እዛው የሚቀስፈኝ ብዬ ሃኒባልን
ገላመጥኩት።

“ለምን ባለጌ ይልሃል ? ለምን ይቀስፍል ? ብዙ ተባዙ ብሎ አዝዞ ሲያበቃ መባዣውን መንሳት
ከፈጣሪ አይደለም። ይሄ የሰይጣን ሥራ ነው፡ ይልቅ ያልኩህን አድርግ። ሰው እንዲራመድ እግዜር እግር ሲሰጥ፡ ሰይጣን እየዞረ ሽባነትን ያድላል፤ እግዜር ውብ ተፈጥሮን ትማለከትበት ዘንድ ዓይን ሲፈጥር፣ ሰይጣን በሰበብ አስባቡ አንዴ በትራኮማ፣ አንዴ በአደጋ ሰበብ እይታህን ይቀማሃል፣ የነፍስም ዓይንህን ይጋርደዋል፤ እግዚአብሄር የማንም አካል እንዲጎድል አይሻም። ሙሉ ስለሆነ ማንም በሙላት እንዲኖር ነው ፍላጎቱ፤ ለዛም ነው መጽሐፍ ቅዱስ በፈውስ ታሪክ የተሞላው። ሰይጣን ግን ጎዶሎ ነገር ስለሆነ
አትታሎም ይሁን አጭበርብሮ ለሰዎች ጉድለት ያድላል። ይሄ ጎዶሎ ምን ይሻለዋል እንደው? ግዴለህም አብርሽ … ሂድ ምድርን ያለካስማ ሰማይን ያለባላ ያቆመ ጌታ ያንተን እንትን ማቆም አያቅተውም። ሂድ ብያለሁ ሂድ !!” ሃኒባል እኔ ላይ በደረሰው ነገር በጣም አዝኖ ተቆጭቶ
እንደተነገረ ግንባሩ ላይ ሲበሳጭ የሚጋደመው የደም ስር ይመሰክራል። እኔ ግን በሳቅ ፍርፍር አልኩ፤ አነጋገሩ በጣም ነው ያሳቀኝ።....

ይቀጥላል
👍212
#ትኩሳት


#ክፍል_አራት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ሲልቪ
ላይ ላዩን


..ተመስገን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብዬ ስሰራ አንዳንዴ ውቢቱ ሲልቪ ትመጣና «Salut Castro noire» ትለኛለች። («ሰላም፣ ጥቁር ካስትሮ») (ፂም ስላለኝ ነው፡፡)

«Que la paix soit avec toi Scheherazade Blanche» እላታለሁ
(«ሰላም ላንቺ ይሁን፣ ፃእዳይቱ ሻህራዝድ ሆይ»)

ትስቃለች። በምስራቃውያን አነጋገር እንቀጥላለን። ቀልድ
ነው። ከሲልቪ ጋር ሁልጊዜ ቀልድ ነው:: እውነተኛ ፈረንሳዊት ናት፣ ስለምንም ነገር ቢሆን «Moi je men fous!» ነው የምትለው
(«እኔ ስለዚህ ነገር ደንታ የለኝም»)
ታድያ ደስ ትላለች። ሰፊ አፏ
ሳሙኝ ሳሙኝ ይላል፡፡ አብረሀት ስትሆን ሳቅ ቀልድ ታበዛለህ፣

«ዠማንፉቲዝሟ» ይጋባብሀል፤ ስለምንም ነገር ደንቴ አይኖርህም
አንድ ቀን ግን
«ምንድነው ሁልጊዜ ስትፅፍ የማገኝህ?» አለችና ደብተሬን
አየችው:: የምን ፅህፈት ነው ይሄ? ያገራችሁ ነው?» አለችኝ
«አዎን»
«ምኑም አይገባም»
«ቀላል ነው፡፡ ሁለት መቶ አርባ የሚሆኑ ፊደላት አሉት»
«Quel horreur! (ኧረ የጉድ ያለህ!) እንግዲያው አታስረዳኝ
ይቅርብኝ .. ምንድነው ምትፅፈው?»
«ምንም አይደለም»
«ልብወለድ ነው?»
«ብጤ ነው»
«እንዴት ማለት ብጤ?»
«እንዴት ልበልሽ? ልብወለድ ነው፣ ግን ፈጥሬው አይደለም፣
ያየሁትን የሰማሁትን ነገር ሰብስቤ ቅርጹን እለዋውጣለሁ እንጂ፣
ላንባቢ እንዲጥም»

«ቆይ ቆይ፡፡ አሁን መፃፍ አለብህ ወይስ ለጊዜው ልትተወው
ትችላለህ»
«ልተወው እችላለሁ»
«እንግዲያው ከዚህ እንሂድና ቡና ልጋብዝህ:: እና ስለድርሰት
እናውራ። ይስማማሀል?»

«በደምብ ነዋ! ቆንጆ ሴት ቡና ስትጋብዘኝ ሁልጊዜ
ይስማማኛል»
«Malin Castro noir va!» («ሂድ ወድያ! ፎሌ ጥቁር ካስትሮ!»)
Deux Chevaux መኪናዋ ውስጥ ከገባን በኋላ
«ኤክስ ውስጥ የምወደው ካፌ የለኝም፡፡ ማርሰይ እንሂድ?»
አለችኝ
እየቀለድን እየሳቅን ደጋግማ «Moi, u sais je m en fous!»
እያለች፣ በሆዴ ውበቷን እያደነቅኩ፣ ማርሰይ ደረስን፡፡ የንግድ ሳይሆን የግል የመደሰቻ ልዩ ልዩ አይነት ጀልባዎች ከተደረደሩበት ወደብ አጠገብ አንድ ካፌ ገብተን ቢራ ካዘዝን በኋላ፣ ጉልህ ሰማያዊ
አይኖቿ በፈገግታ እያዩኝ
«ንገረኛ ስለምትፅፈው» አለችኝ
«ምን ልንገርሽ?»
«ስለሰዎቹ፣ ስለጊዜው፣ ስለግንኙነታቸው፣ ማን ማንን እንደ
ሚወድ፣ ማንስ ማንን እንደሚጠላ፣ መፅሀፍህ አንዴት እንደ ሚጀመር፣ አሁን የት እንደደረሰ፣ በኋላ እንዴት እንደሚያልቅ፣
ምን ምን ነገር እንደሚያስቸግርህ፣ መፅሀፍህ ምን እንዲል እንደ
ምትፈልገው፣ ሁሉን ንገረኝ
ቆንጆ ስለሆነች ይሁን፣ አጠያየቁን ስላወቀችበት ይሁን ወይ ሌላ ያልተገለፀልኝ ምክንያት ይኑር እንጃ፣ ስለመፅሀፌ ሁሉን
ነገርኳት። ለማንም ነግሬ የማላውቀውን ለሷ አጫወትኳት፡፡ ችግሩን ደስታውን፣ ብስጭቱን፣ የድል አድራጊነት ስሜቱን፣ ምንም
ሳልደብቅ አዋየኋት። ፈረንሳይኛው ሲያስቸግረኝ ልክ ልናገረው
የፈለግኩትን ቃላት ታቀብለኛለች፣ ምክንያቱም ሀሳቤ ቃላቱን
ቀድሞ ደርሷት ይቆያል። አንዳንድ ቦታ አንድ ሀሳብ ተናግሬ
ጨርሼ ሌላ ሀሳብ አልመጣልህ ሲለኝ አንድ ጥያቄ ትጠይቀኛለች
እሱን ጥያቄ ስመልስ፣ ሌላ ሀሳብ ይመጣልኝና እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ ብዙ ካወራሁ በኋላ

«ይገርምሻል፣ ይህን ለማንም ነግሬ አላውቅም» አልኳት
«Jen suis lattee» አለችኝ (ክብር ይሰማኛል።)
«እኔ እውነቴን ነው»
«እኔም እውነቴን ነው»
«አሁን ተራሽን አውሪልኝ
«ቆይ» አለችና ከያዘችው የመፃህፍት ቦርሳ አንድ አስር የሚሆኑ ባንድ በኩል ብቻ በታይፕ የተፃፈባቸው ነጠላ ወረቀቶች ሰጠችኝ።
አንብበው አለችኝ፡፡ አነበብኩት፡፡ አጭር ልብ ወለድ ታሪክ ነው።
ስጨርስ ምን ይመስልሀል?» አለችኝ
«አንቺ ነሽ የፃፍሽው?» አልኳት
«አዎን» አለችኝ
«አዝናለሁ። ጥሩ ታሪክ አይደለም»
«ምንድነው የጎደለው?»
«እርግጠኛ አይደለሁም። አየሽ፣ አንድ ሰው የሚወዳትን ሴት
ሊገድል ይችል ይሆናል፡፡ ግን ባስር ገፅ ውስጥ ይህን መናገር
የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ሁለት መቶ ገፅ
ያስፈልገዋል»
«ይህንንም አንብብ እስቲብላ ሌላ አስራ ሶስት ገፅ ሰጠችኝ።
አነበብኩት። ግሩም ታሪክ ነበር፡፡
«ይህንንም አንቺ ነሽ የፃፍሽው?»
«አዎን»
«ታሪክ ይሉሻል ይሄ ነው! ይህን ጊ ደ ሞፓሳን ራሱ ነው የፃፈው ቢሉኝ አምናለሁ» አልኳት
ጉልህ ሰማያዊ አይኖቿ ልዩ አስተያየት ሰጡኝ፣ እንደማቀፍ ያለ
አስተያየት፣ ሙቀት ያለው አስተያየት

«Merci»አለችኝ

«Je ten prie (ኧረ ምንም አይደለም) ይህን የመሰለ ለመፃፍ
ስትችዪ፣ እንዴት አርገሽ የቅድሙን ፃፍሽው?» አልኳት
መሳቅ ጀመረች (ጥርሶቿ ትክክል ሆነው ነጫጭ ናቸው። ነጭ
የፈረንጅ ጥርስ ብዙ እይታይም) «እኔ እንጃ አለችኝ «በምፅፍበት
ሰአት ሁሉም እኩል ጥሩ ሆኖ ይሰማኛል። ካንድ ሁለት ወር በኋላ
ሳነበው ነው እውነተኛው ዋጋው የሚታየኝ»
«ይሄ መጥፎው መቼ ነው የተፃፈው?»
«ካንድ አመት ተኩል በፊት
«እንግዲያው መጥፎ መሆኑ
ድሮ ገብቶሻል። ለምን
እስነበብሽኝ?»
«ላውቅህ ስለፈለግኩ። ማንም ሰው ቢሆን፣ እንደምፅፍ ካወቀ
ወይም እንዲያውቅ ከፈለግኩ፣ መጀመሪያ መጥፎ ታሪኬን
አስነብሰዋለሁ። አንብቦት ጥሩ ነው ካለ በቃው። ሁለተኛ እኔ
የፃፍኩትን አያነብም። እስካሁን ለአንድ ስምንት ሰው አስነብቤያለሁ።
አንተና አንድ የፓሪስ ጓደኛዬ ብቻ ናችሁ መጥፎውን መጥፎ
ያላችሁት። ስለዚህ ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ ጥሩውን ያነሰሳችሁ»
«ሌላ የፃፍሽው አለ?»
«ሃያ ሶስት አለኝ፡፡ አስራ አንዱ ጥሩ ይመስሉኛል። ሰባቱ
በጣም መጥፎ ነው:: አምስቱ ግን ጥሩም አይደል፣ መጥፎም
ኣይደል እንደኔ እስተያየት። ስለዚህ አንተ እነዚህን አምስት
አንብበህ ምን እንደሚመስልህ ብትነግረኝ፣ ተስፋ የሌለውን
እጥለውና ተስፋ ያለውን እየመከርከኝ አሻሽለዋለሁ»

«ክብር ይሰማኛል፣ ግን ልመክርሽ መቻሌን እንጂ
«ትችላለህ። ታግዘኛለህ? »
«ከቻልኩማ በደስታ! አሁን ስለራስሽ ንገሪኝ፡፡ ቅድም እኔ
እንደነገርኩሽ»
ነገረችኝ፡፡ የምንፅፍበት ቋንቋ ተለያየ 'ንጂ ሙከራችን፤
ችግራችን፣ አስተያየታችን በጣም ይመሳሰላል፡፡ ስንወያይ መሸ፡፡
«እማውቃት ጥሩ ርካሽ ምግብ ቤት አለች» ብላ ሳን ሻርል
ባቡር ጣቢያ አጠገብ ወስዳ እራት ጋበዘችኝ። በፈረንሳይ ደምብ ከምግቡ ጋር አንድ ጠርሙስ ወይን ጠጣን፡፡ ሲኒማ ላስገባሽ አልኳት፡፡ ሁለታችንም እንደዚህ ልንጨዋወት የምንችልበት ጊዜ
መቼ ተመልሶ እንደሚመጣ አይታወቅም አለችኝ፡፡ እውነትሽን ነው አልኳት
ወደ ወደቡ ተመልሰን በእግር እየተዘዋወርን ወሬያችንን ቀጠልን። በተርታ የቆሙ ጀልባዎች የሚወዛወዙበት ውሀ ውስጥ የማርሰይ መብራት ይጫወታል። የባህር ሽታ ይዞ ከባህር በኩል የሚመጣው ነፋስ ቅዝቅዝ ያለ ሆኖ ይለሰልሳል። እንደኛው እያወሩ
የሚዘዋወሩ ሰዎች አሉ፤ አብዛኛዎቹ ተቃቅፈዋል፡፡ መንሽራሽር ሲበቃን አንድ ካፌ ገብተን ቁጭ ብለን ቢራ አዘዝን
👍271👏1
«ስለ ኑሮ ምን ታስባለህ?» አለችኝ
«ኑሮ በጣም አጭርና በጣም ጣፋጭ ናት እላለሁ። አንቺስ ምን
ይመስልሻል?»
እኔም በጣም አጭር ናት እላለሁ፡፡ ስለዚህ ለመኖር
መሽቀዳደም፣ መጣደፍ አለብን»
«በተቻለን መጠን ኑሮአችን ውስጥ ሀሴትን መጠቅጠቅ አለብን
«ሀሴት» ስል bonheur የሚለውን ቃል ነበር የተጠቀምኩት
«Il n'y a pas de bonheur, tu sais ha «Il n'y a que du
plaisir,» (ሀሴት የሚሉት የለም'ኮ፡፡ የስሜት ደስታ ብቻ ነው
ያለው»)
እና አንቺ ምን አይነት የስሜት ደስታ ትወጂያለሽ?»
ሳቅ እያለች «ከምግባባው ሰው ጋር እንደዚህ ማውራት፣
«ከማምነው ሰው ጋር ማታ ባህር ዳር መንሽርሽር»
«ሌላስ?»
«ውብ ሙዚቃ መስማት፣ ጥሩ ትያትር ማየት፣ ጥሩ መፅሀፍ
ማንበብ፣ እስክጠግብ ከበላሁ በኋላ ወይን እየጠጣሁ ማውራት. . .»
«ሌላስ?»
ልንገርህ?»
«ንገሪኝ»
«አትደነግጥም?»
«ሞክሪኝ»
አመነታች። «ለሰው ተናግሬው አላውቅማ»
እየሳቅኩ «እኔና አንቺ'ኮ ከሰው በላይ ነን፡፡ ደራሲያን ነን፣
ፈጣሪዎች ነን» አልኳት
ሳቀች። ሳቋ ጉሮሮዋ ውስጥ ይሰማል፣ በጣም ደስ ይላል፡፡
ሁለመናዋ ደስ ይላል
«እንግድያው ልንገርህ»
«ንገሪኝ
«J'aime faire l'amour,» («ከወንድ ጋር መተኛት እወዳለሁ»)
አየሁዋት። እስካሁን የተመስገን «ሚስት» በመሆኗ ስለሷ
እንዲገለፅልኝ ያልፈቀድኩለት ስሜት አሁን የአእምሮዬን በር
በርግዶ ገባ። ሲልቪን በጣም ተመኘኋት!
«ኦ! ላ-ላ! እንደሱ አትየኝ!» አለችኝ፡፡ አፍራለች፣ ጉንጮቿ ደም
መልበስ ጀምረዋል፣ አይኖቿ ይርገበገባሉ። የባሰውን አማረችኝ፡፡
«ምናለበት ባይሽ?» አልኳት
«Tu me fais rougir» («ፊቴ እንዲቀላ ታደርገኛለህ»)
«በጣም ታምሪኛለሽ ፊትሽ ሲቀላ» አልኩና ጉንጮቿን በሁለት
እጄ ይዤ አፏ ላይ ሳምኳት። አፏ ይሞቃል።
«እንሂድ ከዚህ?» አልኩዋት። Deux Chevaux መኪናዋ ውስጥ እንደገባን
«እኔም ከሴት ጋር መተኛት በጣም በጣም እወዳለሁ» አልኳት
«አውቃለሁ» አለችኝ
«እንዴት ታውቂያለሽ?»
«ምስጢር ነው:: Secret professionnel» («የባለሞያተኞች ምስጢር»)
«Mais nous sommes de la meme profession» («ታድያ
የሁለታችንም ሞያ አንድ ነው)
እውነትክን ነው»
«ንገሪኛ። ሴት መውደዴን እንዴት ታውቂያለሽ?»
«አንደኛ አስተያየትህ አይንህ ቆንጆ ሴት ላይ ሲያርፍ
ሴትዮዋን በሙቀት ያጎናፅፋታል፡፡ ደሞ ቆንጆ ሴት አይንህን ጣል
ሳታረግባት አታልፍም፡፡ ሁለተኛ ድምፅህ፡፡ ከወንዶች ጋር ስትነጋገር ሰምቼሀለሁ። ከሴት ጋር ስትነጋገር ግን ድምፅህ ልስልስ ይላል፣
ሙቀት ይሞላዋል፡፡ እንዴት ያለች ሴት ነው 'ምትመርጠው?»
«እንዳንቺ ያለች»
«የምሬን ነው 'ምጠይቅህ»
«እኔም የምሬን ነው «ምመልስልሽ»
«እንዴት ነው እንደኔ ያለች ሴት «ማለት?»
«አእምሮዋን ላከብረው ስችል፣ ጠባይዋን ልወደው ስችል
ገላዋን ልመኘው ስችል፣ በዚህ በሶስት በኩል በቂ ሆና ሳገኛት፣
ሴትዮዋ እንዳንቺ ያለች ናት ማለት ነው» ብዬ እንደገና ሳምኳት።
መሳሙን በጣም ትችልበታለች፣ ሰፊ አፏ ይመቻል
«ተመስገን ጓደኛህ ነው?» አለችኝ
«ጓደኛ የለኝም» አልኳት። ሳመችኝ፡፡ ሙቅ እርጥብ አሳሳም
ሳመችኝ
«ስለተመስገን እንዴት እናድርግ?» አለችኝ
«እንግደለው»
እየሳቀች «እውነቴን ነው!»
አንቺ እንደፈለግሽ። ብትፈልጊ ተይውና እኔጋ ነይ፡፡
ብትፈልጊ ሳትነግሪው በድብቅ እንገናኝ፡፡ ብትፈልጊም የሚገባው
ከመሰለሽ' ነገሩን አስረጂው:: እንደመሰለሽ አርጊ”
«ላንተ እንዴት ይሻልሀል?»
«ለኔ ሁለም ያው ነው:: እናንተ ፈረንሳዮች እንደምትሉት “Je
m'en fous! ብቻ አንቺን ላግኝሽ
አትቀናም?»
«አልቀናም፡፡ ምን ያስቀናኛል? በማገኝሽ ጊዜ የተቻለሽን ያህል
የስሜት ደስታ ስጪኝ እንጂ፣ ከኔ ጋር ባልሆንሽበት ጊዜ ምንስ
ብታረጊ ላንቺ ከተስማማሽ ምን ይጎዳኛል?»
«እውነትህን ነው?»
“አዎና!»
«Mon Dieux! እንዴት ያለኸው ሰውዬ ነህ!» (ወይ አንተ
አምላክ!)
«ምነው?»
መልሷ መሳም ነበር
ወደ ኤክስ እንመለስ?» አለችኝ
ምናልባት አሜሪካኗ ሆቴሌ ትጠብቀኝ ይሆናል በማለት
«ለምን እዚህ አናድርም?» አልኳት
«ነገ በጧቱ ክፍል አለብኝ»
«ቅሪ ከክፍል»
«ትምህርቱስ?»
«ስሚኝ። ዛሬ ከኔ ጋር ነው ምታድሪው፡፡ ሌሊቱን ችዬ
እንቅልፍ እላስወስድሽም፡፡ ስለዚህ፣ ነገ ጧት ብትገቢም እንቅልፍ ኣጥቶ ማደሩና ድካሙ በደምብ አያሰሩሽም፡፡ ስለዚህ አንደኛውን ብትቀሪ አይሻልም? ቅሪ እባክሽን! ደሞ ጧት ልለይሽ አልችልም»
ብዬ እቅፍ አድርጌ ሳምኳት። እሺ አለች፡፡ ሳን ሻርል አጠገብ አንድ
ትንሽ ሆቴል ውስጥ አንድ ክፍል ተከራየን፡፡
እጅ ለእጅ ተያይዘን ፎቁን ወጣን። የክፍላችንን በር ከፈትኩላት፡፡ ገባን። መብራቱን አበራችው:: አነስ ያለ ንፁህ ከፍል ልብስ የተዘረጋበት ሰፊ አልጋ ይጠብቀናል፡፡
መሀል አልጋ ሁለታችንም ለአልጋው ቸኩለናል፣ ሁለታችንም አልጋውን ፈርተነዋል

በሩ አጠገብ እንደቆምን ወደኔ ሳብኳት፣ ተጠጋች፡፡ ቀጭን
ወገቧን አቅፌ፣ ደረቷ እየገፋኝ፣ ጭኖቿ እየተሻሹኝ አንገቷን
ጉንጫን ስስም፣ ሰፊ አፏ ተከፍቶ ከጎን ታየኝ፡ አይኔ አጠገብ
ከንፈሮቿ በጣም ወፍረው ቀይ እርጥብ ሆነው ታዩኝ እየተንገበገብኩ
ጎረስኩዋቸው:: እሷም ጎረሰችኝ በሰፊ አፏ፡ በእርጥብ ከንፈሮቿን
በፈጣን ምላሷ፤ በትኩስ ትንፋሿ፣ በሚያዳልጡ ጥርሶቿ ታክኝ
ታላምጠኝ ጀመር አፎቻችን እንደተቆላለፉ ልብሶቻችንን በሙሉ አወለቅኳቸው፣
በለስላሳው ሌሊት ራቁት ለራቁት ተቃቅፈን ቆመን መተሻሸት
መሳሳሙን ቀጠልን። ጡቶቿ ደረቴን ሲገፉ ልዩ ስሜት ተሰማኝ፣
ትንሽ ራቅ አደረግኳትና አየኋቸው፣ ኮረዳነት የገተራቸው የውበት
ክምሮች የምኞት ህውልቶች ይመስላሉ። እጆቿን ዘርግታ ራሲን ወደ ደረቷ ሳበች፣ አንዱን አበባ ጡት አፌ ውስጥ ከተተችው፣ ራሴን አቀፈችኝ። ሽቶና ኮረዳነት የተደባለቁበትን ጠረኗን ወደ ውስጥ ተነፈስኩት

በኋላ ቀስ አርጋ ገፋችኝ፣ ለብቻዋ ቆመች። እየተያየን ብዙ ጊዜ
ቆየን። ሳኝካቸው የነበረ ጡቶቿ ቆመዋል፣ ከረዥም ቀጭን ሽንጧ
በታች ሰፊ ዳሌዋ ወደ ረዣዥም ጭኖቿ፣ በልዩ ጥንቃቄ ወደ
ተቀረፁ እግሮቿ ይወርዳል።
“እንዴት ቆንጆ ነሽ!» አልኳት
ሰበሰበችና ወስዳ ወምበር ላይ ከመረቻቸው። ጎንበስ ስትል ቀና
ፈገግታ እልሰጠችኝም፡፡ ዙሪያችን የተንጠባጠቡትን ልብሶች
ስትል፣ ስትራመድ፣ የገላዋ ቅርፅ የዳሌዋ መወዛወዝ አቅበጠበጠኝ፡፡
ቶሎ ሄጄ አቀፍኳት፡ አልጋው ላይ አጋደምኳት። እጇን ወደ ራስጌ
ዘርግታ መብራቱን አጠፋች። በጭለማው እጆቿንም፣ እግሮቿንም፣ ከንፈሮቿንም ከፈተችልኝ፣ እቅፏ ውስጥ አፏ ውስጥ ሴትነቷ ውስጥ
እስገባችኝ ትኩሳት እየተቀቀልን በስጋ ርጥበት ተጠበስን
የጉርምስና ስሜት ውስጥ እንደ ሀረግ ተገማምደን፣ በምኞት
በተቃቀፉ ገላዎቻችን መቅደስ ውስጥ፣ ዘለኣለማዊውን ጭለማ
ለተጎናፀፈ፣ ጥንታዊ ለሆነ፤ ዘወትር አዲስ ለሆነ፣ ቅዱስ ለሆነ
ህይወት በጠረናችን ከርቤ በወጣት ልባችን ከበሮ፣ በማቃሰታችን መዝሙር ምስጋናችንን አቀረብንለት
👍171🤔1
በኋላ፣ አንሶላው ውስጥ ገባንና ክንዴን አንተርሻት
«አውሪልኝ» አልኳት
ምን ላውራልህ?»
«ያሰኘሽን»
«ተደሰትክ?»
«እንዲህ ተደስቼ አላውቅም»
«እኔም፡፡ አልጋ ውስጥ አርቲስት ነህ፡፡ እንዳንተ ማንም
አስደስቶኝ አያውቅም»
በጭራሽ? እውነት ተናጋሪ»
«አንድ ብቻ ነበር። እሱም ያንተን ግማሽ ያህል አይችልበትም»
ታድያ እንዴት አስደሰተሽ?»
«የመጀመሪያዬ ነበር። ፍቅር ይዞኝ ነበር»
«እሱስ?»
«እሱም በጣም ይወደኝ ነበር። ግን ፍቅር አልያዘውም ነበር፡፡
ፍቅር ሊይዘው አይችልም፡፡ ፍቅሩን በሙሉ ለነፃነት ሰጥቷል።
አንድሬ ማልሮን አንብበሀል? La Condition Humaine የሚባለው ልቦለዱ ውስጥ ያሉትን ጀግኖች ተስታውሳቸዋለህ?»

«ቻይና ሄደው ለሬቮሉሽኑ እውቀታቸውንና ህይወታቸውንም
ጭምር ይሰጣሉ፡፡»
«አዎን! እንደነሱ አይነት ነው እሱም፡፡ ፖል ይባላል፡፡ መልኩ
ይህን ያህልም ኣይደለም፡፡ ደቃቃ ብጤ ነው:: ግን የአስር ሰው
ድፍረት ተሰጥቶታል። አይኑ ውስጥ ደሞ 'ነፃነት' ባለ ቁጥር ቦግ የሚል ነበልባል አለ። ያባቱን ሀብት ወርሶ ነበር። ግን እሱን ለታናሽ እህቱ ትቶላት ሄደ»
ወዴት ሄደ?»
«ወደ ኩባ፡፡ እነካስትሮን ለማገዝ»
«አሁንም እዚያው ነው?»
«አይ! እነካስትሮ አሸንፈው የለም”ንዴ?»
«እንግዲያው የት ነው?»
ቪየትናም፡፡ ቪየትኮንጎቹን ያግዛል»
«ኮሙኒስት ነው?»
«አይደለም፡፡ የነፃነት ነብይ ነው። የነፃነት አርበኛ ነው። ያን
ጊዜ በ56 ዓ.ም. ሀንጋሪ ውስጥ ብጥብጥ አልተነሳም? ለሀንጋርያኖች ነፃነት ለመዋጋት ቀዩን ጦር ሰራዊት (የሶቭዬት ህብረት ጦር) ከሀን ጋሪ ለማስወጣት እዋጋለሁ ብሎ ሀንጋሪ ሊሄድ ተነስቶ ነበር፡፡ በስንት መከራ አባቱ አስቀሩት። ያን ጊዜ ሀያ አንድ አመቱ ነበር፡፡»
«እንዴት ያለ ሰው ቢሆን ነው?» አልኳት
«የአርነት ሰው ነው:: የጭቆናን ቀምበር በያለበት እየዞርኩ
መስበር አለብኝ ይላል»
«ይፅፍልሻል?»
«ብስድስት በሰባት ወር አንዴ ይፅፍልኛል። አሁን ስለሱ
አናውራ 'ባክህን። አለዚያ ማዘን እጀምራለሁ። ዛሬ ማታ በጭራሽ
ማዘን ኣልፈልግም።
ወሬውን ተውነው፤ ግን ሌሊቱን እልተኛንም። የወጣትነት
ትኩሳት እያቃጠለን፣ በህይወት ርጥበት ውስጥ ተነክረን አደርን
ሊነጋጋ አቅራቢያ እንቅልፍ ወሰደን። እስከማታ አልነቃንም
ሲልቪ አጠገቤ በመሆኗ ትልቅ ፍስሀ ተሰማኝ፡፡ እቅፍ እያደረግኳት
ከእንቅልፌ ስነቃ ሰውነቴ ታድሷል፣ አስተያየቴ ተለውጧል።
«ስለተመስገን ጉዳይ እንዴት ልታረጊ ነው?» አልኳት
«እንዴት ላድርግ?» አለች
«ተይው!»
«ምን?»
«ለብቻዬ ነው 'ምፈልግሽ»
«ትላንት ስናወራ ከኔ ጋር ባልሆንሽበት ጊዜ ምንም ብትሰሪ
የራስሽ ጉዳይ ነው አላልከኝም ነበር?»
«ትላንት ፍቅር አልያዘኝም ነበራ!»
በሀይል እቅፍ አደረገችኝ.....


💫ይቀጥላል💫
👍19
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#ስድስት


#በአሌክስ_አብርሃም


...ወደ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ቤተክርስቲያን ሄድኩ። እንደ እብድ ብቻዬን ማውራት ጀምሬ ነበር። ቀጥ ብዬ ዋናውን በር አልፌ ገባሁ። ትዝ ሲለኝ አልተሳለምኩም፤ ተመልሼ ግራ ቀኝ በሩን ተሳለምኩ። ዘው
አይባልም ዘሎ፤ ፈጣሪ የተጎዳ ልቤን ቢመለከትም ቅሉ እዚህ ድረስ ልብ ውልቅ መሆኔ ለኔም ደግ አይደል ወደ ውስጥ ስገባ የቤተክርስቲያኑ ድባብ፣ የቤተመቅደሱ ወፋፍራም የጣውላ ከፈፎች ላይ የሰፈሩት ዋነሶች፣ እድሜ ጠገቦቹ ዛፎች፣ ከምንም በላይ ደግሞ ዝምታው ከውስጥ ብሶቴ ተዳምሮ አጃዬን አመጣው። ከምርም የሰው ልጅ ምናምኒት አቅም እንደሌለው የሚያውቅበት የሆነ ጭብጦ ነገር መሆኑን የሚረዳበት ቦታ ሲኖር ቤተክርስቲያን ይመስለኛል።

ፈጣሪን ምን ማለት እንዳለብኝ ግራ ገባኝ። ታቆምልኛለህ ወይስ አታቆምልኝም…” ከይባል ነገር። ቆይ ግን ከዘፍጥረት ጀምሮ በዚህ ጕዳይ እግዜር ፊት ቆሞ የፀለየ ሰው ይኖር ይሆን ? በሐሳቤ ስቀላምድ ቆየሁና ዞር ዞር ብዬ አካባቢዩን ቃኘሁ። ከእኔ ወደ ግራ ሲል ቢጫ ልብስ የለበሱ መነኩሴ ተቀምጠዋል።ምን እንደገፋኝ እንጃ ወደሳቸው ገሰገስኩ፤ ምናልባት እዛው እንደ ደንቡ እግዜርን በሚያዝንበት ቋንቋ
ቢያናግሩልኝ ብዬም እንደሆን እንጃ ! አጠገባቸው ስደርስ፣

“አባ " አልኳቸው።

"አቤት የኔ ልጅ፣ እንደምን ዋልክ” አሃ !ለካ ሰላምታም ነበር።

"ጓደኛዬ ልትመጣ ሦስት ቀን ቀራት፤ ከመቀሌ ከሦስት ቀን በኋላ ትመጣለች፤ ሙና ነው ስሟ
ሦስት ቀን ብቻ ቀና ብለው በእርጋታ አዩኝና ከጎናቸው ያለውን ግንድ መቁጠሪያ በያዘ እጃቸው
እያመሰከቱኝ፣

"ና እስቲ እዚህ አረፍ በል የኔ ልጅ” አሉኝ።

“አይ እሄዳለሁ" ብያቸው ያመለከቱብኝ ቦታ ላይ ተቀመጥኩ። (ሁለት ሰው የሆንኩ መሰለኝ፤)
የምናገረው ሌላ የማደርገው ሌላ

“ምን ሆነህ ነው የምታለቅስ ልጄ” ቢሉኝ እጄ ወደ ዓይኔ ሄደ አይገርምም ? እየተነፋረቅኩ ነበረ
ለካ፡ እንባዩን በእጄ ሞዥቄ አባን የሆነውን ሁሉ ነገርኳቸው። አቤት መስማት ሲችሉበት

በጥሞና ሲሰሙኝ ቆይተው፣ "የኔ ልጅ እግዲህ ዋናው ነገር … እግዜር የጊዜ አምላክ ነው፤ የሰውና የአግዜር አሰራር ልዩነቱ ይሄ ነው። ሰው የቻላትን ባሰኘው ጊዜ ያደርጋል፥ እግዜር ግን ሁሉን ይችላል የሚያደርገው ግን ለልጆቹ በሚጠቅመው ጊዜ በሚጠቅመው ልክ ነው። ካለጊዜው እንዲህ ያለው ነገር
ውስጥ እንዳትገባ ሊያስተምረህ ወድዶ ይሆናል አንድም ደሞ የምድር ጠቢባን ያቃታቸውን ሁሉ
የሚችል መሆኑን ሊገልጥልህ ሲወድ እንደሆነ ምኑ ይታወቃል ልጄ.."

"እና ምን ላርግ አባ፤ ሶስት ቀን ብቻ ቀራት እኮ"

“መምጣቷ መልካም ነው ! ታዲያ መውደድ ሲሞላ ብቻ አይደለም፣ ሲጎድልም እንጂ፤ መሳቅህን
ብቻ እያሳየህ በወዳጅህ ፊት ትልቅ አትምሰል ልጄ፡ ሰው ነህ ድከመት አለብህ፣ ድክመትህን ለራሷ ንገራት፤ እውነቱን ተናገር። የውሸትና ማስመሰል ዙፋን ከእንቧይ ገንብተህ ንገሽ ብትላት እሷንም ተንዶ ጉድ ይሰራታል፣ ላንተም ፀፀት ነው። የውሸት እና ማስመሰል ካባ ከነፍስ ከረምት፣ ከመንፈስም ቁር አያስጥልም፤ አትድከም! ግራ ቀኝም አትበል፤ እሷን ሸፋፍነህ ብታሳምናት ከራስህ ልብ የገባህው
አተካራ አያባራም። እውነቱን ንገራት፣ ከእውነት የበለጠ ፈውስ የለም የኔ ልጀ።”

"ከዛስ እባ ፤"

ከዛማ እውነት ከተናገርከ ሰውም ምክርም አያሻህ፤ እውነት ራሱ መንገዱን ይምራሄል።"ብለው ወደ
መቁጠሪያቸው አቀረቀሩ። ደህና ዋሉ ልበላቸው አልሰላቸው እንጃ ወደ ቤቴ ተመልሼ ጥቅልል ብዬ
ተኛሁ። እውነት መንገዱን ይመራሃል፤ እውነት ዋጋ ያስከፍላል ያውም ከነወለዱ። ከሆንስ ሆነና እውነት ዋጋው ስንት ነው?
እውነት ዋጋው ስንት ነው?
እውነት ዋጋው ስንት ነው?
እውነት ዋጋው ስንት ነው?
የቱንም ያህል ዋጋው ቢወደድ፣ በቃ ለሙና እውነቱን እነግራታለሁ። ወሰንኩ !
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የቁርጥ ቀን!

እነሆ የተንኳኳ በሬን ከፈትኩ፤ ልብ የሚያቀልጥ የሙና ውበት ከወትሮው ሰባት እጅ ደምቆ በሬ ላይ ቆሟል። ሙናን አፈቅራታለሁ፤ ልለያት አልፈልግም። ሳያት ልክ ብርሃን ጨለማ ክፍልን ድንገት ቦግ ብሎ እንደሚሞላው ውስጤን የሚሞላው አንዳች ነገር አላት፤ እንደ ባዶ ፊኛ የሟሸሽ መንፈሴ ሙናን ሳያት በዓየር እንደተሞላ ባሉን በፍቅርና በደስታ ሕዋ ላይ ይንሳፈፋል። ይሄው የእውነት ዋጋው በሬ ላይ። እውነት ዋጋው ይሄን ያህል ውድ ነው። እቅጩን ተናግሬ የነፍሴን ግማድ ሙናን መክፈል፤አልያም ሰቆቃዬ ላይ ስሳቀቅ በየዕለቱ በማስመሰልና በሽሽት ሚስማር የፍርሃት ጉልላቴ ላይ መቸንከር።

በሐሴት የሚንሳፈፍ የነፍሴን ባሉን፣ ክፉ እሾህ ጠቅ አድርጎ ሊያተነፍሰው ወደኔ ሲወነጨፍም
እከላከልበት ዘንድ በእጄ ያለው መሳሪያ አባ ያስታጠቁኝ ጋሻ ብቻ ነው እውነት !! እውነቱን ተናግሬ
የመሸበት አድራለሁ። እስከመቼ የነገር አንጆ ሳመነዥክ ልኑር ? በቃኝ !!

ምን እንዳረጋጋኝ እንጃ በውስጤ "ሙና ብትሄድ ሺ ሙናዎች ይተካሉ” ስል ረጋ ብዬ ፎከርኩ። ላንዲት ሙና ያልሆንኩ እኔ ለሺ ሙና ስፎክር የሰማ ራሴ ቢታዘበኝም ግድ አልሰጠኝም። ፉከራ ከጀግንነት ብቻ ሳይሆን ጥልቅ ከሆነ ፍርሃትም እንደሚመነጭ የገባኝ ያኔ ነው።
ሙና በእቅፏ ሙሉ አፍሳኝ በሞቃት ከንፈሯ በናፍቆት ግጥም አድርጋ ስትስመኝ ነፍሴ ከተወዘፈችበት ኩርፊያ ተመንጥቃ ልትወጣ ተጣጣረች፤ ቢሆንም እንቅ አድርጌ ነፍሴን ያዝኳት። መቆጣት አለብኝ መኮሳተር አለብኝ። ሙና የሆነ ነገር ሆኗል ዛሬ ልለፈው" እንድትል የሆነ ነገር የሆንኩ መምሰል አለብኝ። ተሸከማ የመጣችውን እሳት በቁጣ ውኃ በር ላይ ማጥፋት፡ መደርገም አለብኝ። ቦርሳዋን
ጠረጴዛ ላይ ወርወር አደረገችና በናፍቆት አንዴ ቤቱን ከእግር እስከ ራሱ ዙሪያውን ቃኝታ በረዥሙ
ተነፈሰችና ለሞላ ቦታ መጥታ ጉልበቴ ላይ ተቀመጠች። ደረቷ ላይ አስጠግታ አቀፈችኝ ለሞላ
የሰውነት ክፍል ፀጉሬን ሳመችኝ።

“ፀጉርህ አድጓል” ብላ በጣቷ መንጨር መንጨርጨ አደረገችኝ። ወይ ነዶ ልጅቱማ የፍቅር ሰው
ነበረች፤ ካለቦታው ተከሰተች እንጂ። ተነስታ ወደ ውስጥ ገባችና የእኔን ቁምጣ ለበሰች፤ ቁምጣ የተሰራው የሙና ዓይነት እግር ላላቸው ሰዎች ይመስለኛል። የእኔን ቲሸርት ለበሰች፤ ቲሸርት
የተፈጠረው የሙና ዓይነት ጡት ላላቸው ሴቶች ብቻ ይመስለኛል። ከዛም ወደ ኪችን። ዝም ብዬ
አያታለሁ፤ ፊቷ ላይ ምንም ነገር የለም፤ ረጋ ያለ ለስላሳ ፊት፤ ትረጋጋ እንጂ እሷ ምን አለባት
የመጣው ቢመጣ ሁሉ በጇ፣ በአንድ እይታ ብቻ ወደ እሳት ነበልባልነት የሚለወጥ አረር ሰውነት ምን አስጨነቃት።

እያጠናኋት ነበር፤ መለያየታችን እንደማይቀር አንድ ነገር ሹክ ስሳለኝ እድሜ ልኬን እንዳልረሳ
እያጠናኋት ነበር። ሙናን መቼም ቢሆን መርሳት አልፈልግም፣ ፍቅረኛዬ ስለሆነች አይደለም
በሕይወት ውስጥ የመሰላል እርካን ሆነው አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርጉን ሰዎች አሉ፣ ሙና እንደዚ ናት ለእኔ። ምን ያህል ልትናፍቀኝ እንደምትችል አሁን ላይ ሆኜ አውቀዋለሁ። ዝም ብዪ አያታለሁ ድንገት ዞር ስትል ዓይናችን ተገጣጠመ ሳቀች። ፍፁም ገራገር እና ንፁህ ፊት። እኔ ግን ደነገጥኩ፡ ወይ ጉድ፡ ሰው በሰላም አገር እንደ ሌባ ደንጋጭ ሆኖ ይቀራል ?!
👍36🥰21
በዓለም ላይ ሁለት ሰዎች እሉ፣ ሙና እና አብርሃም የሚባሉ። ወደፊት ሰዎች ሲመረቁ፡ “ጋብቻችን ወላ ፍቅራችሁ የአብርሃምና የሙና እንዳይሆንባችሁ” የሚሉ ይመስለኛል። ይብሉ ! ሰዎች ግን ማለት ሲወዱ፡ ማለት… ማለት እፉፉፉ… ሙና ቤቴ ውስጥ ጉድ ጉድ ስትል፣ ድንገት ድብርቴ ድራሹ ጠፍቶ መሳሳቅ ማውራት ጀመርን። ግዴላችሁም ሴቶች የሆን ድግምት ነገር አለባቸው፣ ምቾት ያሰቃየው
ሶፋ ገዝታችሁ፡ ቡፌ እዛጋ ገትራችሁ፣ ባለምናምን ኢኝች ቲቪ ገጥግጣችሁ፣ ኳስ ሜዳ የሚያክል አልጋ፣ መስክ የሚመስል ምንጣፍ አጭቃችሁበት ጭር ያለ ቤታችሁ አንዲት ሴት ምንም ሳትሰራ
ቤታችሁ ወሰጥ በመገኘቷ ብቻ የሆነ ነገር ይቀየራል፡ ድምቅምቅምቅምቅ ይላል፤
ይፍለቀለቃል ቤቱ። ወዙ ግጥም ይላል ቤቱ፣ ይስቃል ቤቱ። አመዳም ቤት፤ እስከዛሬ ዳቦውን
የነጠቁት ሕፃን መስሎ ለንቦጩን ጥሎ የከረመ ቤት፣ እንደተወረረ ከተማ በዝምታው በጭርታው
ሲያስፈራኝ የከረም ቤት፣ ልክ እንደ ድግስ ኣሳላፊ አደግድጎ አሸሸውን አስነካው። ይሄው ቤት ቤት ብለን እንድንሞት የሚያደርገን አንዱ ነገር!...
ሙና ቀጥ ብላ መጣችና የሆነ የጓዳ ጣጣ በነካካው መዳፏ እንዳትነካኝ ተጠንቅቃ በእጆቿ
ተጠመጠመችብኝ። ጡቶቿ መሃል ተቀበርኩ። እዚሁ ብቀር ደስታዬ፤ ጨለማው ጠረኑ እና ምቾቱ።
ቀና ብላ አየችኝና ከእግርቼ መሄል ቁጢጥ ብላ ተቀምጣ (ማነሽ በሱጋ ማለፍ ክልል ነው ! እንኳን
እንቺ ባለቤቱም ማለፍ አቅቶታል) ወደ ላይ ቀና ብላ እያየችኝ፣ “ዛሬ ምን ሆነሻል አቡቹ ፍዝዝ አልሽ”
አለች። በጣም ስትቀርበኝ አንቺ ነው የምትለኝ። እጣን እጣን ትሽታለች፣ ታምራለች እና ታሳሳለች
የኔ ሰው። ምን ዋጋ አለው፤ የሆነ በእዳ ተይዛ ልትወሰድ ቀጠሮ የተያዘላት መሰለችኝ፡፡ መልሴን
አልጠበቀችም ጉንጬን ስማኝ ወደ ሥራዋ ተወለሰች።

ከደቂቃዎች በኋላ ቤቱ በእጣን ደመና ተውጦ፣ ቡና ፈልቶ፣ የሙና እጅ የሚያስቆረጥም ዓይነት ብዙ
ምሳ ቀራረበ። ለሙና የተለመደው የፍቅር ውሎ፣ ለእኔ የሽኝት ፕሮግራም የመሰለ ሰመመናም ምሳ

ቡናው እንዳለቀ የተቀመጥኩበት መጥታ ተቀመጠች፣ እጄን አንስታ ሳመችኝ (እየው ነገር ሲጀመር…)

“ለምን እንደምወድህ ታውቃለህ ?” ጠየቀች ሙና።

በደንብ ነዋ !” መለስኩ ኮራ ብዬ። ሳቋን አዘጋጅታ ጠየቀችኝ፣

"እሺ ንገረኝ"

የድሮ ፍቅረኛሽን ስለምመስል” ቤቱ ውስጥ ያለው ትራስ ሁሉ ተወረወረብኝ፡፡ ድብድባችን ጀመረ፤ ሞቅ ካለ ሳቅ ጋር። ሆነ ብላ ሰውነታችን እንዲነካካ ታደርጋለች፤ ጡቶቿ ደረቴ ላይ ይጨፈለቃሉ፤ እና ተጫንከኝ” ትላለች። ይታያችሁ ሳይንስ ሲገለበጥ፣ እሷ እኮ ከላይ ናት እና ተጫንከኝ (ገብቶናል)።
አንድ የገረመኝ ነገር፣ ሙና የማትወደው ነገር ቢኖር ልፊያና ድብድብ ነበር። ጫፏን እንኳን ለቀልድ ሲነኳት ታብዳለች። በቃ ሰውነቷ የፈንጂ ቀጠና ነበር። ይሄው እኔ ጋር እኔ ፈንጂ አምካኙ፣ የራሴንም ስሜት የሰውም ባሕሪ አምከኜ ስላፉት።

መሽ ! ቀኑ ጨለመብኝ ያሉት አበው እንደዚህ ዓይነቱን ቀን ሳይሆን አይቀርም። ስናወራ፣ ስናወራ (ምን ስናወራ እንደነበር እኔጃ ብቻ የመኝታቤት ሰዓታችንን ለማሳጠር ብዙ ሳልለፈልፍ አልቀረሁም፡፡

“አብርሽ እንቅልፌ መጣ” አለች ትልልቅ ውብ ዓይኖቿን እያንከባለለች (አሄሄ እንቅልፍ ሲመጣ እንደዚህ ነው እንዴ ?
ይህቺ አይነቷ መስለምለም የሌላ ጉዳይ ናት)......

ይቀጥላል
👍131
#ትኩሳት


#ክፍል_አምስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

...ካንድ ስምንት ቀን በኋላ፣ ማታ ተመስገን ክፍል ቁጭ ብዬ
ስስራ፣ ተመስገን መጣና አልጋው ላይ ዘጭ ብሉ ተጋደመ፡፡ እፎይ!
ብሎ ተነፈሰ
«ሲኒማ የገባችሁ መስሉኝ» አልኩት
«ሌሎቹ ገቡ፣ እኔ ግን ተውኩት»
«ለምን ተውከው?» አልኩት። ድምፄ «አንተ ተንኮለኛ!»
እንደሚል አይነት ነበር
«ደስ አላለኝማ!» አለኝ፡፡ ትንንሽ አይኖቹ ሊደበቁ ጀምረዋል፣
ግን ጥርሶቹ ገና መታየት አልጀመሩም
«ውሸታም! ቀጠሮ ቢኖርህ ነው እንጂ» አልኩት
«ከማን ጋር?»
«እኔ አውቃለሁ እንዴ ያንተን ተንኮል? ወይ ካንዷ ብሎንድ
(ፀጉሯ ብጫ ወይም ነጭ ብጤ) ጋር፣ ወይ ከሲልቪ ጋር»
«ሲልቪ!? አላወቅክምና!»
«ምን?»
«ቀርቶ!»
«ምነዋ?»
«ምን እባክህ የሴት ነገር» አለ «አገር ጤና ብዬ እንደ ሁልጊዜያችን ወዲህ አመጣሁዋት፡፡ ከሰአት በኋላ ነበር። የከሰአት በኋላው እንዴት እንደሚጣፍጥ ታውቅ የለ? ልብሷን አወላለቀችና
አልጋው ውስጥ ገባች። እየተንገበገብኩ ተከትያት ልገባ ስል፣
ከትራሱ ላይ ኣንዲት ፀጉር እንስታ አቀበለችኝ። ረዥም የፈረንጅ
ፀጉር ነው፤ ግን ጥቁር አይደለም፣ ቡና አይነት ነው»
«ይሄ የኔ ፀጉር እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ አለችኝ»
«ዝም ኣልኩ። አልገባኝም አየህ
«ተናገር እንጂ» አለችኝ። እግዜር ያሳይህ፡፡ በመጀመሪያ
አልጋው ውስጥ ልገባ ጎምበስ እንዳልኩ ኣሁንም አለሁ፡፡ ይታይሀል? ራቁቴን አልጋው ላይ ባራት እግሬ ቆሜ? እንደሚድህ ልጅ:: ልብሷን ስታወልቅ እያየሁና የሚጠብቀኝን ደስታ እያሰብኩ ግትር አድርጎ ቅንዝር ወጥሮኛል፡፡»

የተመስገን አይኖች ጨርሰው ጠፉ፣ ጥርሶቹ ተገለጡ፣ ይሰቅ
ጀመር፡፡ ከት ብሎ እየሳቀ፣ ሳቅ በሚቆራርጠው ንግግር
ገና አሁን ታየኝ ሀ! ሀ! ሀ! እንዴት እንዴት - ሀ! ሀ! U! እንዴት እንደነበርኩ ሁ! ሁ! ሁ! አንዲህ ነበርኩ» አለና በጀርባው ከተጋደመበት ተነስቶ ዞሮ በጉልበቱና በእጁ ተንበረከከ፡፡
ከስሩ ትራሱን አስተካከለና፣ ሌባ ጣቱን እያነጣጠረበት

«እኔ እንዲሀ ነኝ፣ ሂሂ!!» ትራሱን «እቺ ሲልቪ ናት።
ያቀበለችኝን ፀጉር ባንድ እጄ እንደዚህ ይዣለሁ። እንዳትበጠስ
ወይም ወድቃ እንዳትጠፋ እየተጠነቀቅኩ፣ ያቺን ነጃሳ ፀጉር እንዲህ ይዣለሁ። ቁላዬ ደሞ እዚህ ጋ ቆሞ ሲልቪን ቁልቁል ያያታል።አይ የኔ ቁላ! ቂል ነውኮ፡፡ ያንተም ቂል ነው?» እንደገና ሳቅ
አሸነፈው። አልጋው ላይ ተንከባለለ። ሳቁ ሲያልፍለት

«በኋላስ?» አልኩት

«በኋላማ ምን ልበልህ ልጄ? ቃል ሳትናገር ተነስታ ልብሷን
መልሳ ለበሰች፡፡ ረጋ ባለ ድምፅ 'የኔና ያንተ ነገር በዚሁ አለቀ”
ብላኝ ልትወጣ ስትል፣ እኔ እዚች ጋ ራቁቴን እንደቆምኩ
«ምን ነካሽ?» አልኳት፡፡ ሲያቀብጠኝ'ኮ ነው:: እስቲ ዝም ብላትስ?
«ዘወር አለችና፣ እሱ ጠረጴዛ ላይ ያለውን መፃህፍትና ደብተር
በአጇ አንዴ ገፍታ መሬት ላይ አዝረከረከችው:: እና ጠረጴዛውን
በተጨበጠ እጇ ደጋግማ እየመታች

«እኔ የእስላም ሀሪም ሴት - አይደለሁም!» ብላኝ ስታበቃ፣ ወጥታ በሩን በሀይል ጓ! አርጋው ሄደች። ልብሴን ልለብስ
ካናቴራዬን ሳነሳ በሩ ብርግድ ብሎ ተከፈተ። ማን ገባ መሰለህ?»
አለኝ

«ማን?» አልኩት

«ሲልቪ ራሷ ነቻ! የሴት ነገር! ከመቼው ሀሳቧን ለወጠች?!
እያልኩ ልገረም ስጀምር፣ ኣጠገቤ መጣች። አቅፋ ልትስመኝ
እንደሆነ ገባኝ፡፡ ትንሽ ልኮራባት አሰብኩ። ታድያ እሷ ምን አረገች
መሰለህ? እወቅ : ስቲ።»
«በጥፊ መታችህ?»
«ብጭራሽ!»
«አቅፋ ሳመችህ?»
«ትቀልዳለህ?»
«እንግዲያው ምን አረገች?» አልኩት
«ጫማዋን አረገች»
«ምን?»
«በንዴት ጫማዋን ረስታው ሄዳ ነበር፡፡ ተመልሳ አረገችውና
ወጣች። እኔ ራቁቴን ቆሜ ቀረሁ፡፡ ቁላዬ እስካሁን ተኝቷል፡፡ ከዚያ
በኋላ አናግራኝ አታውቅም»
«ጥፋቱ ያንተ ነው» አልኩት
«እንዴት?» አለኝ
«ያመጣሀቸው ሴቶች ሊሄዱ ሲሉ «ፀጉሮችሽን ሁሉ ይዘሻል?
ቁጠሪ እስቲ ለምን አትላቸውም?» አልኩት
«መቼ ሴት አመጣሁና?» አለኝ
«እ-ህ? ቡናማው ፀጉርሳ?»
«ከየት እንደመጣ እንጃለት:: ምናልባት ቤት የምትጠርገው
አልጋ የምታነጥፈው አሮጊት ያን እለት ታማ ኖሮ፣ በሷ ምትክ
ባለቡናማ ፀጉር ሴት አልጋዬን አንጥፋልኝ ይሆናል»
«ምስኪን ተመስገን!» አልኩት
ምስኪን ትላለህ ምስኪን። ይኸው እስከዛሬ ዖም ላይ እገኛለሁ
«ዛሬ ማታ ግን ለመግደፍ ያሰብክ ትመስላለህ»
«ነበር እባክህን። ፀጉሯን እንደ ወንድ ነው 'ምትቆርጠው፣
ቢሆንም ምንም አትል። ብቻ »
«ብቻ ምን?»
«የት እንደምወስዳት ጨንቆኛል»
ሲመሽ ፈረንሳዮች concierge
የሚሉት ዘበኛ ይመጣና' ወደመኝታ ቤቶቹ የሚያስገባው በር አጠገብ አንዲት ቢሮ አለችው፣ እዚያች ቁጭ ብሉ ወጪ ገቢውን ሁሉ ይመለከታል። ወንዶች መኝታ ቤት ሴት ማስገባት ክልክል ነው፡፡)

«የኔ ሆቴል አለልህ አይደለም እንዴ?» አልኩት
«አትጠቀምበትም?»
«እዚህ ልተኛ እችላለሁ»
እሱማ ጥሩ ነበር»
“ብቻ እንዳታስጮሀት አደራ፡፡ ካስጮህካትም ፎጣ አጉርሳት።
ብዬ የሆቴሌን ቁልፍ ሰጠሁት
ተመስገን ወደ ቀጠሮው ከሄደ በኋላ ተመልሼ ልስራ
በጠበጠኝ። ተነስቼ አሜሪካዊቷ ቤት ሄድኩ፡፡ ጉዳዬን አስረዳኋት።
አልቻልኩም፡፡ ሲልቪ ለኔ ስትል እንደተወችው ገባኝ፡፡ ይህ ሀሳብ
ከዚህ በፊት አገሬ እጮኛ አለችኝ ብያት ነበር፡፡ አሁን፣ እጮኛዬ
ካንቺ ጋር ያለኝን ግንኙነት አወቀች፡፡ ማን እንደነገራት እንጃ፡
ወረቀት ፃፈችልኝ። በአንድ ሳምንት ውስጥ ኣሜሪካንህን ትተሀታል
የሚል ወሬ ካልደረሰኝ ሌላ እኛ ፈልግ አለችኝ፣ ብዬ ነገርኳት።
«i derstand የዚህ መጥፎ ዜና ምክንያት በመሆኔ በጣም
አዝናለሁ» አለችኝ። ያቀድኩት ይህን ነግሬያት ደህና እደሪ ብያት
ሲልቪን ፍለጋ ለመሄድ ነበር። ግን ልጅቱ ጥቁር ስስ የሌሊት ልብስ
ለብሳ ስትራመድ በጣም ታስጎመጃለች፣ ገላዋን ታጥባ ቆዳዋን በታልከም ዱቄት አሻሽታው፣ ሽታው ይማርካል፡፡ ከሷ ጋር አደርኩ
«ራሷን በጣም ታዘብኩት። በጣም ፀፀት ተሰማኝ፣ ሲልቪን
የበደልኳት መሰለኝ»
በነጋታው ሲልቪን ከምግብ ቤት ስትወጣ ጠብቄ ኣገኘኋት።
ቡና ልጋብዝሽ አልኳት። ኤክስ ውስጥ የምወደው ካፌ የለኝም
አልኩህ? አለችኝ፣ እሺ ማርሰይ ልውሰድሽ አልኳት። መኪናዬ
ጋራዥ ናት አለችኝ፡፡ በኦቶቡስ ልውሰድሽ አልኳት። አልፈልግም
አለችኝ። እንግዲያው ምን እናርግ? አልኳት፡፡ እኔ ቡና ላጠጣህ፣ራሴ አፍልቼ፣ አለችኝ፡፡ ቤቷ ወሰደችኝ፣ ከኤክስ ትንሽ ወጣ ብሎ ባላገሩ ውስጥ ነው

«የሴዛን የነበረው ቤት በዚህ በኩል ነው። መሄድ ትፈልጋለህ?»
አለችኝ
«አልፈልግም» አልኳት
«እኔም ሄጀ አላውቅም» አለችኝ
እየሳቅኩ «Tut'en fous, ch?» አልኳት («ደንታ የለሽም፣ እ?»)
እየሳቀች፣ «Je m'en fous eperdument!» አለችኝ («እቺን ያህል እንኳ ደንታ የለኝም»)
ቤቷ ገባን። ሁለት ክፍል (አንድ መኝታ፣ አንድ ሳሎን) ወጥ
ቤት፣ መታጠቢያ ክፍል። በየግድግዳው የልዩ ልዩ አቢይ ስእሎች እትም ተለጥፏል። የቤት እቃው ዘመናዊ ነው፣ ሰማያዊና ወይን ጠጅ ቀለማት ይበዙበታል
👍25
«ግሩም ቤት አለሽ» አልኳት
«ከርስዎ በፊት ሌላ ወንድ ገብቶበት እንደማያውቅ ስገልፅልዎት
በትህትና ነው» አለችኝ፡፡ አመንኳት። እጅ እየነሳኋት
«ሻህራዛድ የኔ ፍቅር፣ የቀኔ ጨረቃ፣ የሌሊቴ ፀሀይ! ክብር
ይሰማኛል» አልኩና፣ እንደ ፈረንሳዮቹ እጇን ሳምኳት፡፡ ደስ የሚለኝ
ሳቋን እየሳቀች
«ቁጭ በል ቡና ላፍላልህ» አለችኝና ወጥ ቤት ገባች
አንዱን ግድግዳ በሙሉ ያያዘ ባለአምስት ተርታ የሆነ
የመፃህፍት መደርደሪያ አለ፡፡ በፈረንሳይኛና በእንግሊዝኛ የተፃፈ
መአት መፅሀፍ ተደርድሮበታል። ባንዱ ተርታ የአርት መፃህፍት
ባንዱ የፊሎዞፊና የታሪክ የሶሲዮሎጂ መፃህፍት፣ በሶስተኛው ልዩ
ልዩ አይነት መፃህፍት፣ በተቀሩት ሁለት ተርታዎች ደሞ ልብወለድ
መፃህፍት። መደርደርያው አጠገብ መፅሄቶችና ጋዜጦች የተሸከመ
ሰፊ ጠረጴዛ አለ። ወድያኛው ግድግዳ ጥግ ትልቅ ራዲዮ-ግራማፎን፣
አጠገቡ እንደ መፃህፍቱ የተደረደሩ ሸክላዎች ይህን ቆሜ ሳደንቅ መጣችና
«ቁጭ በል እንጂ» ብላ ከሰማያዊዎቹ ሶፋዎች አንዱ ውስጥ አስቀምጣኝ «ምን አይነት ሙዚቃ ትፈልጋለህ?» አለችኝ
«የላቲን አሜሪካ አለሽ?»
«እንዴታ!»
ሙዚቃው ሲጫወት አጠገቤ ቁጭ ብላ እጄን ያዘችኝ። ዝም
ብለን ስንሰማ ከወጥ ቤቱ ቀጭን የባቡር መሳይ ፉጨት ጮኸ። ዘላ
ተነሳች
«ቡና ደርሷል። ከወተት ጋር ነው ምትፈልገው?» አለችኝ
«አዎን፣ ውድ ሻህራዛድ ሆይ» አልኳት
ቡናውን ስንጠጣ «ተመስገን ቤት መሄድ መተውሽን ለምን
አልነገርሽኝም?» አልኳት፡፡ ጉልህ ሰማያዊ አይኖቿ በመልካም
ብርሀናቸው አዩኝ፣ ውብ ሰፊ አፏ በፈገግታ ተከፈተ
ኩራት እንዳይሰማህ ብዬ ነዋ» አለችኝ
ጥቁር ፀጉሯን ወደታች እየዳሰስኩ
ጉንጮቿ መቅላት ጀመሩ፣ ወደታች አየች
«ስሰማ እንዴት ደስ እንዳለኝ ልነግርሽ አልችልም» አልኳት።
«እንደሱ አትየኝ!» አለችኝ
አገጯን በግድ ወደላይ አንስቼ፣ አይን አይኗን እያየሁ
«ምናለበት ባይሽ?» አልኳትና ግምባሯን ሳምኳት
ዝም ብለን ቡና በወተታችንን ፉት እያልን ሙዚቃውን
እየሰማን ትንሽ ከቆየን በኋላ
«ለመሆኑ፣ ተመስገን ትራስ ላይ ቡና አይነት ፀጉር እንዴት
እገኘሽ?» አልኳት
እየሳቀች «እኔው ራሴ ነኝ ይዤው የሄድኩት» አለችኝ
አንዲት ቡናማ ፀጉር ያላት ጓደኛ አለችኝ። ቤቷ ሄጄ ከፀጉር
ብሩሿ ፀጉሮች ለቅሜ ይዤ ሄድኩ»
እኔም እየሳቅኩ «ጫማሽን ሳታረጊ ወጥተሽ ነበር። ረስተሽ
ነው?» አልኳት
«ረስቼ አይደለም»
“ታዲያስ?»
የእውነቴን የተናደድኩ እንዲመስለው ብዬ ነው:: ምናልባት
"ቡና አይነት ፀጉር እዚህ ሊገኝ በጭራሽ አይችልም ብሎ ያሰበ
እንደሆነ፣ ቀጥሎ 'እሷ ራሷ አምጥታው እንደሆነ ነው እንጂ ብሎ ሊያስብ ይችላል፡፡ ያን ጊዜ ራሷ አምጥታው ቢሆን ኖሮ፣ በንዴት መፅሀፎቼንም ከጠረጴዛው አትበትንም ነበር፥ ጫማዋንም ማድረግ አትረሳም ነበር ብሎ ማሰቡ አይቀርም»
በአድናቆት ራሴን ነቀነቅኩ


💫ይቀጥላል💫
👍10🔥4
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#ሰባት


#በአሌክስ_አብርሃም


....“አብርሽ እንቅልፌ መጣ” አለች ትልልቅ ውብ ዓይኖቿን እያንከባለለች (አሄሄ እንቅልፍ ሲመጣ እንደዚህ ነው እንዴ ?
ይህቺ አይነቷ መስለምለም የሌላ ጉዳይ ናት)

“ትንሽ እናውራ ናፍቀሽኛል”

“ከመቼ ጀምሮ ነው ወሬ የወደድከው ግን ?" አለችኝ። ትዝ ሲለኝ ለካ ለሙና ዝምተኛ ልጅ ነበርኩ
(ስምንተኛው ሺ አሉ እኚያ ሰውዬ)። እጄን ይዛ እየጎተተች ወሰደችኝ። መኝታ ቤት እንደገባን መሀል ሜዳው ላይ ቆማ ልብሷን በቁሟ ብትጥለው ማታ እኔ መኝታ ቤት ፀሐይ ፏ ብሎ ወጣ። ፀሐይ
ከምስራቅም ከምዕራብም ሳይሆን፣ በቃ ከልብስ ውስጥ ፍንትው ብሎ ወጣ። እስቲ አሁን እዚህ ፀሐይ ላይ ቆሞ የማይፍታታ ወንድ የት አባቱ ሄዶ ሊፍታታ ነው ? ሲጀመርስ ምናባቱ ሊሰራ ወደዚች ምድር መጣ ? ቀስ ብዬ ልብሴን ማወላለቅ ጀመርኩ። አወላለቄ ከመንቀርፈፉና ከፍርሃቴ ብዛት፣
“ልብስህን አውልቅና አርባ ጅራፍ ትሞሸለቃለህ” የተባልኩ እንጂ ውብ ፍቅረኛዬ ጋር ልተኛ የምዘጋጅ አልመስልም ነበር። የአልጋ ልብሱን ወደታች ገፈፍኩት፣ ብርድ ልብሱን፣ አንሶላውን፣ መቃብሬን የምቆፍር ነበር የመሰለኝ።
ቀስ ብዬ አንሶላዬ ውስጥ ገባሁና (ሙና ገና ከመግባቴ እንደ መዥገር ተለጠፈችብኝ ምን አስቸኮላት ለመርዶ) አንሶላና ብርድልብሱን ወደላይ ስቤ ስደርብ የመቃብር አፈር በላዬ ላይ የመለስኩ መሰለኝ።

“ውይ አፈንከኝ የተሸፋፈንበትን ብርድ ልብስ ገለጠችው፡፡ ገብቶኛል በነዛ ዓይኖቿ እየተስለመለመች የፈራሁትን አጀንዳ ልትከፍት ነው። ተንጠራርቼ መብራቱን አጠፋሁት፤ ትልቅ ስህተት ! ሙና መብራት ሲጠፋ በብርሃን የፈራሁትን በጨለማ ልዘምትበት መስሏት የበለጠ ተጠጋችኝ፡፡ ሰውነቴ ላይ
ከመጠበቋ ብዛት ሁለት ሰውም እንድ ሰውም ሳይሆን ግማሽ ሰው መሰልን። አንድ እግሯን ታፋዬ
ላይ ደርባ ተጠመጠመችብኝ። አሁን እንግዲህ .. አርማጌዶን !!

እና ለምን እንደምወድህ ሳልነግርህ አረሳሳኸኝ ሙና በጨለማው ውስጥ አንሾካሾከች።
“ለምንድን ነው ?"
እርጋታህ ! ማንም ወንድ እዚህ ድረስ ይታገሳል ብዬ አስቤ አላውቅም። ሰምቼም አላውቅ። ልዩ እኮ ነህ አብርሽ … እሟ” (ምኔን እንደሳመችኝ እኔጃ) እኔኮ ግራ የሚገባኝ ካለሥማችን ስም እየሰጡ ለምን ጨዋ ያደርጉናል ?! ኧረ የቸጎረቸግሮን ነው ቀዝቀዝ ያልነው(እስካሁን አገር ሰላም ቢሆን በሩጫ ሞያሌ
ደርሰን ነበር አሉ ጋሽ ምትኩ)። ስለጋሽ ምትኩማሰብ ጀመርኩ። ጋሽ ምትኩ በሕፃንነታችን ሰፈራችን ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የድሮ ወታደር ናቸው። ቆይ ግን ጋሽ ምትኩ የፂማቸው አበቃቀል አይገርምም? ልክ እንደ ፍየል ፂም ሹገጥ ያለች ሆና ደረታቸውን ትነካለች። ጋሽ ምትኩ እኮ በሕፃንነቴ ከእማማ ሊባኖስ ፅድ ላይ ወድቄ የግራ ክንዴን ተሰብሬ አሽተው አድነውኛል፡፡ የግራ ከንዴ ስል ትዝ አለኝና ላነሳው ስሞክር ሙና ተኝታበታለች። ሙና ትዝ አለችኝ። አሁንም እንገቴን እየሳመችኝ ነው። ሙቀቱ
ውቀት አይደለም፡፡ እሳት ተነስቷል እዚህ ብርድ ልብስ ውስጥ፡፡ (ደመዟን የሚከፍሏት እሳት ነው
እንዴ፤ አጠራቅማ ይዛው መጥታ ይሆን…)

ቆይ ግን የዓለም ሙቀት መጨመር ... ብዬ ሌላ ሐሳብ ውስጥ ልገባ ስል ድክ…ም ባለ ድምፅ የሆነ መካከለኛው አፍሪካ አካባቢ ቆማ ስሜን የጠራችው እስኪመስለኝ በራቀ ድምፅ…

“አ..ብርሽ” አለችኝ።

“አብርሽ የለም ! አሁን ወጣ” ማለት አምሮኝ ነበር።

“እወድሃለሁ" ውይ !ይሄ ሁሉ ጥሪ ለዚች ነው ? ብዬ መውደዷን ለመንኳስስ ብሞከር አልተሳካልኝም።
እኔም እንደ ራሴ ነው የምወድሽ ሙና” ብዬ ዓየር እስኪያጥራት ከንፈሯን ሳምኳት። እግሯ ተንቀሳቀሰ (ወዴት ነው…ባለህበት ቁም ብያለሁ የሙና ግራ እግር !) እንግዲህ ፊት ሲሰጧቸው…
በእንግሊዝኛ እንዲህ አለችኝ፣
'አር ዩ ሬዲ ?” እንደው አማርኛችን ወሲብ ላይ ሐሞቷ የሚፈስሰው ለምንድን ነው ? ወሲብ ነክ
ላይ እንግሊዝኛ ይቀለናል። “ሴክስ” “ኪሲንግ" ቋንቋችን መከበር አለበት !በራሳችን ቋንቋ የራሳችንን ጉድ ማውራት አለብን ! የራሱ ጉዳይ ... ! አሁን በዚህ ሰዓት አማርኛ ፤ ምንኛ ላይ
ምርምር ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው ?ቁም ነገሩ በአማርኛ ይሁን በእንግሊዝኛ ይሁን በጀርመንኛ ወላ በእብራይስጥ ትናገረው እኔ እንደሆንኩ እንትን ላይ የለሁበትም !!
እንግዲህ ሙና ከመጠጋቷ ብዛት እልፉኝ ሙሄድ ቀራት፣ እኔ ዝም!
ሳመችኝ
ዝም
ነካካችኝ
ዝም
አፍ አውጥታ “በቃ እናድርግ" አለች
ዝም!
በመጨረሻ ሰውነቷን ከሰውነቴ ቀስ እድርጋ አላቀቀች። ሰውነታችን ሲላቅቅ ፕላስተር ከሆነ ነገር ላይ
ሲላጥ የሚያሰማውን ዓይነት ድምፅ አሰማ። በላባችን አጣብቆን ነበር፡፡ ምንም ላልተፈጠረ ቅጡ ይሄ
ሁሉ ላብ በከንቱ። ሙና ተንጠራርታ መብራቱን አበራችውና ቀጥ ብላ ፊቴን ተመለከተችኝ አቤት ስታስፈራ፡ አቤት ስታምር..

ምንድን ነው የሆንከው ስለኔ የሰማኸው መጥፎ ነገር አለ ?አለችኝ በሚንቀለቀል ቁጣ። ዝም ብዬ አየኋት። ዝም ብላ አየችኝ። ፊቷ ላይ ግራ መጋባት ያሁን ፍርሃት ያልገባኝ ስሜት ያንዣብባል።

ሌላ ሴት ጋር ጀምረኸል አይደል ግልፁን ንገረኝ ?” ቁጣዋ ተንቀለቀለ። እኔ ደግሞ እፌ ተያያዘ ዝም፡
ብርድ ልብሱን በንዴት ገፍፋ ወደዛ ጣለችውና ቤቱን በሚያደበላልቅ ጩኸት፣

“ምንድን ነው ችግርህ፣ ለምን ትዘጋኛለህ … ላንተ እንዲህ መሆኔ ለሁሉም ወንድ እንደዚህ የምሆን
ልክስክስ እንድመስልህ አድርጎህ ነው ወይስ … ለምን ትገፋኛለህ፣ ለምን ዝቅ አድርገህ ታየኛለህ
አንድ ቀን እንደ ሰው፣ እንደ ፍቅረኛ አይተኸኝ አታውቅም። ሁልጊዜም ሴትነቴን፣ ከብሬን ዝቅ አድርጌ ላንተ ነው የኖርኩት። ስንት እና ስንት ርቀት ተሰቃይቼ የምመጣው አንተን ብዬ ምንድነው ችግርህ ንገረኝ፣ አስጠላሁህ ? ያስቀየምኩህ ነገር አለ ? ለምንድነው እንደዚህ ቅዝቅዝ
የምትለው ? ችግር ካለ ንገረኝ። ልርቅህ አልፈልግም፡ አፈቅርሃለሁ … አፈቅርሃለሁ ... አፈቅርሃለዉ
እንባዋ ተዘረገፈ። ከወገቤ በላይ ራቁቴን እንደሆንኩ አልጋው ላይ ተቀመጥኩ። ሙና ሁሉም ሰውነታ
ተራቁቶ ነበር። የአልጋ ልብሱን ላለብሳት ስምከር ከነእጄ ወደዛ ወረወረችው፤ ፈራኋት። ተፋጠጥን!

አሁን ነው ጊዜው!እውነት እርቃኗን አልጋ ላይ ይቻት ይህ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ወሳኝ ጊዜ ነው። አለ አይደል ላይመለሱ በስደት ከአገር ሊወጡ ዞር ብለው ተራራ ሸንተረሩን፣ ያደጉበትን ሰፈር የሚመለከቱባት ቅፅበት። ሙና ለእኔ ሰፈሬ ናት፤ ፍቅር እየተራጨሁ ፍቅር ያደግኩባት። አለ አይደል የደከመች እናት በመጨረሻ እስትንፋሷ ከአልጋ ላይ ሽቅብ ልጇን ተመልክታ በተስፋ መቁረጥ ዓይኖቿን የምትጨፍንበት፣ አለ አይደል አብሮን የተፈጠረ አብሮን ያደገና የኖረ እግር፣ እጅ በሆነ በሽታ ምክንያት ሊቆረጥ የመጨረሻው ማደንዘዣ ሲሰጥ … ይሄ ጊዜ ያ ሁሉ ነው። በዚህች ቅፅበት ሴት
ብትሄድ ሴት ትተካለች አይባልም። ሙና ሴት ብቻ አይደለችም። ማንም ሴት ላፈቀራት ወንድ መልዓክ ምትሆንባት ነጥብ አላት። “ማንም ሴት በአካል የማይደገም ግልባጯን ልብ ላይ የምታትምበት ቅፅበት አለ፡ ጣጣ የለኝም የሚለውና የምትለው ሰዎች ሁሉ ጣጣ የሚኖርባቸው፡ ውጋት የሚለቅ ቅፅበት አለ ይሄው ያ ቅፅበት።.

ሙናን ወደኔ ስቤ ከንፈሯን ሳምኳት። የሆነ በቀል የሚመስል አሳሳም። ልቧ ሳይፈራ አልቀረም።
በፍርሃት አየችኝ። ፊቴ ላይ ምን እንዳየች እንጃ።

"ሙና"

"ወዬ አብርሽ” ፈርታለች። ለምን እንደፈራች አላወቅም። ብቻ እንድ ነገር መኖሩን የጠረጠረች
ይመስለኛል።
👍42
“ስንፈተ ወሲብ የሚባል ነገር አለብኝ፤ ሴክስ ማድረግ አልችልም፡፡ በጣም ብዙ ቦታ
በዘመናዊም በባሕልም ሕክምና ለማድረግ ሞከሬ ነበር፤ ግን አልቻልኩም። ልለይሽ ኤልፈልግም፤ አፈቅርሻለሁ።
አንቺን ብለይሽ ምን እንደምሠራ፣ ምን እንደማደርግ አላውቅም። የማውቀው ሥራ ነው፤ ከሥራ ሌላ
አንቺን። በቃ ! ያልነገርኩሽ እንዳትለይኝ ስለፈራሁ ነበር። አሁን ግን አማራጭ የለኝም። በዚህ ወር ከመምጣትሽ በፊት የተቻለኝን ሁሉ ሞክሬያለሁ። ምንም ለውጥ የለውም፡፡ እውነቱ ይሄው ነው ስል ነገርኳት። የሪሴ ድምጽ ለራሴ እንኳን አስፈርቶኝ ነበር። ይሄው እውነቱን ተናገርኩ !እንግዲህ “መንገድ ይመራሃል” የተባለው እውነት ይሄውለት መንገደኛው !

ሙና ዝም ብላ በግርምት ስታዳምጠኝ ቆየች ድክም ባለ ድምፅ አብርሽ አለችኝ። አብርሽ ብቻ፡ እንዲሁ ስሜን ማረጋገጥ እንደፈለገች ዓይነት፡ ዓይኗ ውስጥ ግን ምንድነው የማየው … ደንግጣለች ? ፈርታለች ? ወይንስ ምንድነው ይሄ ወልጣቀኝ እይታ ?

ሁልጊዜም እንደ ሩቅ ሰው አጠገቤ ሆነሽ ትናፍቂኛለሽ። ሰውነትሽ ይናፍቀኛል። ግን ምንም ማድረግ አልቻልኩም። እኔ ታጋሽ አይደለሁም ሙና፧ ስላልቻልኩ ነው። እኔ ምንም ትዕግስት የለኝም። ስላልቻልኩ ነው። አፈቅርሻለሁ፥ እንዲህ ሞራሌ ተንኮታኩቶ ተሸማቅቄም አፈቅርሻለሁ።" ሙና ፀጥ ብላ በግርምት ይሁን በሐዘን ስታየኝ ቆየች። አንዴ ወደዛ አንዴ ወደዚህ ዓይኖቿ ቃበዙ። ተደነጋገረች። ዓይኖቿ እንባ ተሞሉ። እንባዋ ሲዘረገፍ ነው ብዬ ስጠብቅ፤ ዓይኗን የሞላው እንባ ድራሹ ጠፋ። ተጨነቀች። ተናግራ እንዳታሳዝነኝ ፈርታ፣ ዝም ብትል ይሄ እንደ ጥቁር ጭስ የሚያፍን
መርዶ ቃላትን ከአንደበቷ እንደ ሳል አስፈንጥረሽ አውጭ እያላት፣ ሙና የኔ ፍቅር ተጨነቀች ስቃይ
ፈቷ ላይ አረበበ። የማደርገው ጠፋኝ። ጉንጮቿ እሳት መስለው ቀሉ። ብዙ ጊዜ ስታፍር ነበር እንዲ
የሚቀሉት።

“ቆይ አብርሸ ምንድን ነው … ማለቴ…ተወው በቃ” ግራ ተጋባች። እናም እንዲህ አለችኝ፣ ችግር የለውም እንዳታስብ፣ ምንም ነገር እንዳታስብ !” ስትናገር ዓይኔን ማየት ፈርታ ነበር።እጆቿ እነዛ ቆንጆ
ጣቶቿ በሆነ ፍርሃት ሲንቀጠቀጡ ይታዩኛል። ብርድ ልብሱን ከጎኔ ገልባ ሸርተት ብላ ገባች።
ወዲያው ተመልሳ ተነሳችና የሌሊት ልብሷን ከትራስጌ በኩል አንስታ ለበሰች፤ ተመልሳ ተኛች። ድንብርብሯ ወጥቶ ነበር። በብርድ ልብስ በታፈነ ድምፅ ችግር የለውም” አለች እንደገና።..

ይቀጥላል
👍25👏42
#ትኩሳት


#ክፍል_ስድስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


ይሄ ሁሉ ሲሆን ባህራምን አልረሳሁትም ነበር ከምሳ በኋላ Le Monde የተባለውን ስመጥሩ የፈረንሳይ ጋዜጣ እገዛና፣ ካፌ ዶርቢቴል ገብቼ petit creme (ቡና በወተት በሲኒ)
አዝዤ ሀበሾቹ አጠገብ ቁጭ ብዬ ጋዜጣዬን ማንበብ እጀምራለሁ።
ጩኸት፣ ሳቅ፣ ወሬ፣ የሲጋራ ጪስ፣ የሴት ሽቶ ካፌውን
ይሞላዋል። በበጋው ሙቀት ምክንያት መስኮት ሁሉ ይከፈታል፡፡
ሰማያዊ ካኪ የስራ ልብስ የለበሱ የፋብሪካ ሰራተኞች የቡና ማፍያው መኪና የተቀመጠበትን ረዥም ባንኮኒ በክንዳቸው ተደግፈው በተርታ ቆመው ፓስቲስ (ነጭ አረቄ) እየጠጡ፣ የፋብሪካ ዘይት ምናምን ያቆሽሽውን ቀያይ ፀጉራም እጃቸውን በብዙ እያንቀሳቀሱ፣
በአስቂኝ የደቡብ ፈረንሳይኛቸው ያወራሉ። ከባንኮኒው ዳር፣ ከመስተዋት የተሰራው በር አጠገብ፣ የካፌው ባለቤት መስዬ ፖል የቂል ሳቁን እየሳቀ “Merc Bien morosiuro (እግዜር ይስጥልኝ ጌታዬ» እያለ የሚከፍሉትን ገንዘብ ይቀበላል፤ ቴምብርና ሲጋራ ይሸጣል

ከባንኮኒው ኋላ ቆንጆዋ የመስየ ፖል ሚስት ባጭሩ የተቆረጠ
ብጫ ብጤ ቀለም የተቀባ ፀጉሯ እያብለጨለጨ ለሰዎቹ ቡና ወይም ፓስቲስ እያቀበለች፣ ከወጣቶቹ ጋር ፈገግታና ቃላት ትቀባበላለች፣ ትሽኮረመማለች፣ በማርሰይ ዜማ ታወራለች። ሸርሞጥሞጥ የምትል ሴት ናት። ድምፅዋ፣ አስተያየቷ፣ አረማመዷ፣ ሁለመናዋ ወንድ ይጣራል። መስዬ ፖል በብስጭት ነው የሚኖረው ሲባል እሰማለሁ፡፡
ግን ተማሪ ውሽማ ያላትም ይላሉ። ተማሪዎቹ መስዬ ፖልን
ይወዱታል፣ ሚስቱን ሊነኩበት አይፈለጉም፡፡ እሷም ተማሪ
የምትፈልግ አትመስልም፡፡ ውሽሞቿ ጎረምሶችና የፋብሪካ ወይም የኩባ ሰራተኞች ናቸው በበጋው ሙቀት ኮታቸውን አውልቀው የሸሚዛቸውን ቁልፍ በሙሉ ፈተው፣ የደረታቸውን ፀጉርና ጡንቻ እያሳዩና እጅጌያቸውን ሰብስበው ጡንቸኛ ፀጉራም እጃቸውን እያወዛወዙ ካፌ ዶርቢቴል የሚመጡ ጎረምሶች

እጠረጴዛዎቹ መሀል ሁለቱ ሴት ቦዮች ቡና፣ መጠጥ፣ ሲጋራ እየያዙ ይዘዋወራሉ

ሀበሾቹና ባህራም ካንድ ሁለት አፍሪካውያን ወይም ፈረንሳዮች
ጋር ካርታ ሲጫወቱ፣ አጠገባቸው ቁጭ ብዬ ጋዜጣዬን አነባለሁ።
በካርታ የተሸነፉት ሁለት ልጆች፣ ሌሎች ሁለት ተሽንፈውሳቸው
ተራቸውን ለመጫወት እስኪችሉ ድረስ መጥተው ከኔ ጋር ያወራሉ
ተካ ይመጣና ጋዜጣዬን ሳነብ «የማታነበውን ገፅ ልመልከተው
ስቲ» ብሎ ጋዜጣዬን ነጥሎ ግማሹን ይወስድብኛል። የማነበውን ጨርሼ ወደሌላ ገፅ መሄዴ ሲሆን፣ ተካ «ቆይ እቺን ልጨርስና እሰጥሃለሁ» ይለኛል። «አምጣ እንጂ» ስለው «ጋዜጣው ካንተ ጋር ይውላል፣ ትንሽ ባነብ ምናለበት?» ይለኛል። ብሽቅ ብዬ አየዋለሁ፡፡
ጥፍሩን እየነከሰ ያነባል።ጋዜጣው ውስጥ ያሳቀውን ወይም
ያስገረመውን ነገር ያሳየኛል፤ በጭራሽ አያስቅም፣ አያስገርምም።አይ ተካ ብሽቁ! ግን ጥሩ ልጅ ነው፡፡ እሱ ራሱ ጋዜጣ ገዝቶ ያነብ እንደሆነ ጋዜጣውን ይሰጠኝና «የማታነበውን ገፅ ስጠኝ። ሌላውን ካንተ በኋላ ቀስ ብዪ አነበዋለሁ» ይለኛል
አንዳንዴ ሀበሾቹ ተሰብስበው ካርታ ሲጫወቱ ወዳጆቻቸው
ሴቶች አንድ ጠረጴዛ ይዘው እያወሩ ይጠብቁዋቸዋል፡፡ ሲያሰኘኝ ከነሱ ጋር ትንሽ አወራለሁ ከኒኮል ጋር ማውራት እሞክራለሁ፣ ያቅተኛል። በጣም
ታፍራለች፤ ያልለመደችውን ሰው ማናገር አይሆንላትም። ለጊዜው
በጭራሽ ላውቃት አልቻልኩም። ስለዚህ ባሀራም ምን አይቶባት
ይሆን? ለሚለው ጥያቄ የመልስ ጫፍ እንኳ አላገኘሁለትም፡፡
መልኳን አይቶ እንዳልሆነ ግን ግልፅ ነበር፡፡ ውሀ አረንጓዴ አይኖች፣ የተዘረዘሩ ጥቃቅን ጥርሶች፣ ትኩሳት እንደያዛቸው አይነት ቆዳቸው የደረቀ ከናፍር። ድምፅዋ ደስ ይላል። ባህራም ምን አይቶባት ይሆን? እውነት ለገንዘቧ ሲል ይሆን?
ከአማንዳ ጋር ግን ብዙ እናወራለን። ሀበሾቹ አማንዳ ዱቤ ነው የሚሏት፡፡ ሉልሰገድ ይዟት ሊሄድ ሲል ተካ «እንግዲህ ሂድና
ዱባህን አገላብጥ!» ይለዋል። ሉልሰገድ «አንተ ደሞ ከዱባ የተሻለች እስክታገላብጥ ድረስ ስለዱባ ባታወራ ጥሩ ነው!» ብሎት አማንዳን እቅፎ ይሄዳል፡፡ አማንዳ በእንግሊዝኛ «ምንድነው "ሚለው?»
ትለዋለች፡፡ «ተይው ዝም ብሎ ነው» ይላታል።

ጋዜጣዬን እንብቤ፣ ሰዉን አይቼ፣ ባህራምን ተመልክቼ፣ ስለራሱ ለማውራት ዝግጁ እንዳልሆነ ከተገነዘብኩ በኋላ፣ ከካፌው
ወጥቼ ወደ ኩር ሚራቦ በኩል ትንሽ እራመዳለሁ። ወደኋላ ዞሬ፣
ማንም ሀበሻ እንዳልተከተለኝ ካረጋገጥኩ በኋላ፣ እታጠፍና ወደ
ሲልቪ ቤት አመራለሁ

"አንድ ቀን ባህራምን ያዘክው?» አለችኝ
"የለም" አልኳት
"የምትይዘው ይመስልሀል?»
"እርግጠኛ ነኝ»
«የምስራቅ ሰው እንደሆንክ ያስታውቃል፡፡ ጊዜ የሚያመጣውን
ጊዜ እስኪያመጣው ትጠብቃለህ እንጂ ጊዜን ልታጣድፈው
አትሞክርም፡፡ የምእራብ ሰው ብትሆን ግን ባህራምን ሄደህ በብልሀት ታዋራው ታወጣጣው ነበር»
«እንደሱ ካረግኩማ እሱን ራሱን ላውቀው አልችልም፡፡ የማሰብና
የሰዋስው ችሎታውን ብቻ ነው ላውቅ የምችለው»
«ምን የሚል ይመስልሀል?»
«ምን እንደሚልማ ማወቅ ቀላል ነው»
«አንግዲያው ምንድነው የምትጠብቀው?»
«ያ ያልኩሽ ጊዜ ሲመጣ፣ ተጠንቅቄ ምሰማው ቃላቱን
አይደለም ኮ»
«ታድያስ?»
ድምፁን ነው:: ዜማውን፡፡ እጁ እንዴት እንደሚንቀሳቀስ። ምን
ሲል ድምፁ እንደሚለሰልስ፣ ምን ሲናገር ግምባሩ እንደሚቋጠር።
አንዳንድ ጊዜ እኛ ሳናውቅ ፊታችን ላይ ፈገግታ ወይም ህዘን በገዛ
ራሱ ይጫወት የለ? ያንን ነው ምጠብቀው:: አንድን ሰው
የምናውቀው በሚናገረው ቃላት አይደለም፣ ያን ቃላት ሲናገር
በሚያሳየው ገፅ፣ በሚያሰማው ድምፅ ነው:: እሱን እሱን ለማየት
ነው ባህራምን አድፍጬ የምጠብቀው

ከሰአት በኋላውን ከሷ ጋር አሳልፈዋለሁ፡፡ እንቅልፍ ከወሰደን ወደ አስራ አንድ ላይ እንነቃለን። ወይ እናወራለን፣ ወይ እናነባለን!
ወይ ሙዚቃ እንሰማለን። ሰኞና አርብ በአስር ሰአት ላይ ክፍል
አለባት። አንዳንዴ ተኝቼ ትታኝ ሄዳ ስትመለስ ትቀሰቅሰኛለች።
አንዳንዴ ነቅቼ እንደ ሌላ ቀን ከአርት መፃህፍት አንዱን
እየተመለከትኩ፣ ወይም እያነበብኩ፣ ወይም ሙዚቃ እየሰማሁ አቆያታለሁ

ሲመሽ ተለይቻት እሄዳለሁ። A ጠdemain cheri» («እስከ ነገ
ደህና ሁንልኝ») ምግብ ቤት ሄጄ እራቴን በልቼ፣ ከዚያ ወጥቼ
የቴሌቪዥን ዜና አይቼ ሳበቃ፣ ሆቴሌ ሄጄ ስራ እጀምራለሁ።
(አሜሪካዊቷ መምጣት ትታለች) ወይም ሲኒማ እገባለሁ። ከሲኒማ
በኋላ ለመስራት እሞክራለሁ፡፡ እምቢ ካለኝ፣ የሌሊት ፀጥታ
የዋጣቸውን የኤክስን ጠባብ መንገዶች እዘዋወርባቸዋለሁ፡፡ ንጉሳቸው ነኝ

ጧት ተነስቼ፣ ቁርሴን ሁለት croissant በልቼ፣ ቡና በወተት
ጠጥቼ፣ ወደ ቤተመፃህፍት ሄጄ እስከምሳ ሰአት እሰራለሁ። (ክፍል
መግባት ከተውኩ መቸስ ዘመን የለኝም)
ከምሳ በኋላ ካፌ ዶርቢቴልን ጎብኝቼ ወደ ሲልቪ እሄዳለሁ፡፡
በሰፊ አፏ እየሳቀች ትቀበለኛለች
አያሌ ቀናት ካለፉ በኋላ፣ ተመስገንን እየሳቅኩ
«ሲልቪ እንደወጣች ቀረች?» አልኩት
«ቀረች!» አለኝ «አሁንማ ብትመለስም አልፈልጋት»
«ምነው?»
👍201
«አንጎሏ ምላጭ የሆነ ሴት መቶ በመቶ ሴት አትመስለኝም፡፡
አሁን አንዲት ጅል ብጤ ፈረንሳይ ይዣለሁ:: በጣም ተስማምታ
ኛለች፡፡ እጄን ሰደድ ሳረግ መክፈት ነው። ዝብዝብ የለም፡፡
ፖለቲካ፣ ሊትሬቸር፣ ምናምን የለም። ያቺ ግን! ስለኢትዮጵያ
የምትጠይቀኝን ጥያቄ ለመመለስ ብቻ ስንትና ስንት አስፕሮ መዋጥ
ያስፈልገኝ ነበር፡፡ ያውም አብዛኛውን ለመመለስ አልችልም ነበር»
«እኔ ግን በጣም ደስ ትለኛለች ልጄ» አልኩት «እውነት
በጭራሽ አትፈልጋትም?»
«በጭራሽ። አንተ 'ምትወዳት አይነት ሴት ናት፡፡ ሞክራት»
«ብኋላ ይቆጭሀና መልስልኝ ትለኛለህ ልባርግ» አልኩት
«እርም ይሁንብኝ!»
«ተው!»
«ኦዎ! ይልቅ አንዱ ጭልፊት ፈረንሳይ ሳይሞጨልፋት ቶሉ
አብስላት»
«ታድያ አንተ የተጠቀምክበትን ዘዴ ንገረኛ፡ እንዲረዳኝ ያህል»
አልኩት
ነገረኝ መከረኝ፣ አብረን ፕላን አወጣን፡፡ በመጨረሻ
«አንድ ምክርና አንድ ማስጠንቀቅያ ልስጥህ መሰለኝ» አለኝ
«ምክሩ ይኸውና፣ ልጅቱን እንደፈለግካት ጌታው ተካ
እንዳያውቅብህ»
በዚህ ስቀን ስንጨርስ
«ማስጠንቀቂያውስ?» አልኩት
እቺ ሲልቪ አንዳንዴ ሌላ ሰው ትሆንብኛለች፡፡ አልጋ ውስጥ
ያለልማዷ እንደማበድ ትላለች፣ ወፈፍ ያረጋታል። እና በደስታ
ታሳብድሀለች፣ ታድያ--»
«ታድያ?»
ታድያ ነገሩ ካለቀ በኋላ ታኮርፋለች፡፡ ወደዚያ ፈንጠር ብላ
ራሷን እጂ ውስጥ ትደፋለች። አንዳንዴም ታለቅሳለች»
«ምን ሆንሽ ስትላትስ?»
«አትነግርህም፡፡ እና ግራ ያገባሀል። አውቀህ ብትገባበት ይሻላል ብዬ ነው»
«ይገባኛል» አልኩት
ተመስገን እንዳልዋሸ አውቄያለሁ። ግን ሳቂታዋ ሲልቪ አኩርፋ
ወይም ስታለቅስ - በጭራሽ ሊታየኝ አልቻለም
ካንድ ሳምንት በኋላ እኔና ሲልቪ በይፋ አብረን እንወጣ ጀመር፡፡ ሀበሾቹ «አልጋ ወራሽ» አሉኝ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አልጋ
ወራሽነቴን ረሱት፤ ሰነሱ አይን ሲልቪ የኔ ሆነች
ተመስገን «የነገርኩህ ብልሀት ስራ መሰለኝ» አለኝ፡፡ የደስ ደስ
ቢራ ጋበዝኩትና ሲኒማ አስገባሁት። የያዛትን «ጅል ብጤ» ፈረንሳይ አስተዋወቀኝ። ብሎንድ ነጭ ፀጉራኝ እንደ ወንድ ተቆርጣለች።
በጣም ቆንጆ ናት። ይሄ ተመስገን ሴት አመራረጥ ያውቃል፡፡

ደሞ ሴቶች የሚወዱት ይመስላል። ታድያ የሚገርመኝ ነገር አለ፡፡ አዲስ አበባ በነበርንበት ጊዜ የምትጠጋው ሴት አልነበረችም.....

💫ይቀጥላል💫
👍19
#ትኩሳት


#ክፍል_ሰባት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ባህራም
ከቅርብ


ማክሰኞ ነበር አስታውሳለሁ፡፡ ከምሳ በኋላ Le Monde ጋዜጣዬን ገዝቼ ካፌ ዶርቢቴል ገብቼ እንደ ልማዴ petit creme አዝዤ ካርታ የሚጫወቱት ሀበሾች አጠገብ ቁጭ አልኩ። ትንሽ ቆይቶ ባህራም መጣ፡፡ ሳየው የተለወጠ መሰለኝ፡፡ ልማዱ በፍጥነት እርምጃው ከተፍ ብሎ ሲያበቃ፣ ሀበሾቹን «እናትክን! ሀለላሴ ሙት! Je veux jouer
aux cartes.» («ካርታ አጫውቱኝ») ብሎ ቁጭ ማለት ነበር፡፡ ዛሬ ግን በቀስታ እርምጃ መጣ። እንደ ድሮው አልቀለደም፡፡ እንደ አጋጣሚ ለካርታ ጨዋታው አንድ ሰው ጎድሏቸው ስለነበረ «ባህራም! ና ካርታ እንጫወት አሉት

«ካርታ ጨዋታ አላሰኘኝም» አለና ዝም ብሎ ቁጭ አለ።

የተበሳጨ ይመስላል
«ምን ሆነሀል?» አለው ሉልሰገድ
«በፈተና ወደቅኩ» አለ
ሁሉም የሚሉትን አጡ
እንግዲህ በፈረንሳይ ዩኒቨርሲቲዎች ደምብ፣ አንድ ተማሪ የሰኔ ወር ፈተናውን የወደቀ እንደሆነ በእረፍት ጊዜው ሲያጠና
ይከርምና፣ በጥቅምት (ትምህርት ቤት ሲከፈት) እንደገና
ይፈተናል። ስለዚህ ተመስገን
«አይዞህ በጥቅምት ፈተና ታልፋለህ» አለው ባህራም አልተፅናናም፡፡ ሁሉም ዝም አሉ። ካርታ ጨዋታቸውን ቀጠሉ።

ባህራም «ዘላለም ካርታ ጨዋታ ምን ያረጋል? እንውጣ ትንሽ
እንንሽርሽር» አለ። ማንም መልስ አልሰጠውም፡፡አብረውት
መውጣት ፈርተዋል። ካርታ ጨዋታቸውን ቀጠሉ ለጨዋታው
ብቻ ሳይሆን ከባህራም ብስጭት ለማምለጥም ጭምር። ገባው::
ተነስቶ ብቻውን ወጣ፡፡ ተከትዬው ወጣሁ። ወደ መናፈሻው በኩል
እያመለከትኩ
«ወደዚያ እንሂድ?» አልኩት፡፡ መልስ ሳይሰጠኝ ወደዚያው
አመራ። ትንሽ እንደተራመድን
«ያውና ተካ። ወደኛ በኩል ይመጣል» አለኝ «አደራህን አብሮን እንዳይመጣ። ዛሬ እሱ ሁለት ቃላት ቢያናግረኝ አብዳለሁ»
«አትስጋ» አልኩት
ተካ አቆመንና በፈረንሳይኛ
«ከየት ነው የምትመጡት?» አለን
«አሁን ከየትም ብንመጣ ደንታ የለህ። ለምንድነው የምትጠ
ይቀን?» አልኩት በአማርኛ
«ከዶርቢቴል ነው የምትመጡት?» አለኝ ባማርኛ
«አዎን» አልኩት ባህራም እጁን ኪሱ ከቶ ወደዚያ ይመለከታል
«ወዴት ነው የምትሄዱት?» አለኝ ተካ
«ወዴትም፡፡ ምን ያረግልሀል?»
«ወደ ሲቴ ነው የምትሄዱት?»
«ምነው? ከኛ ጋር ሲቴ መሄድ አማረህ?»
«አይ! እኔ ለራሴ ከዛ መምጣቴ ነው። ቡና አምሮኛል»
«እንግዲያው ሂድና ቡናህን ጠጣ»
«ጋዜጣህን አሁን አታነበው እንደሆነ ስጠኝ»
ጋዜጣዬን ሰጠሁትና መንገዳችንን ልንቀጥል ስንል
«ይሄ አቃጣሪ ገንዘብ እንዳያጭበረብርህ ተጠንቀቅ» አለኝ
«ሂድ ቡናህን ጠጣ» እልኩት። ሄደ
እኔና ባህራም አንድ ቃል ሳንነጋገር መናፈሻው ደረስን፡፡ ዛፎች
ጥላ ስር አንድ አግድም ወምበር ላይ ቁጭ አልን ፈተና መውደቅ የተለመደ ነገር ነው:: በጥቅምት ታልፋለህ» አልኩት
በተገማመደ ፈረንሳይኛው፣ በወፍራም ልዝብ ድምፁ መናገር
ጀመረ መውደቄ አይደለም የሚያበሳጨኝ፣ አወዳደቄ ነው።
ትምህርቱን በደምብ ይዤዋለሁ። በምን እንደጣሉኝ ታውቃለህ?
በፈረንሳይኛዬ ጉድለት: አያስቅህም? ፈተናውን የወደቅኩት እኔ ራሴ ባልሆን ያስቀኝ ነበር
«እኔንና ፈረንሳዮቹን የክፍሌን ልጆች አስተያየን እስቲ፡፡
ትምህርቱን እኩል እናጠናቀው። ፈተና እንግባና ጥያቄው ይሰጠን።
መልሱን እኔም እነሱም እኩል እንወቀው። እነሱ ምን ያረጋሉ?
መልሱን በፍጥነት ይፅፋሉ፡ አሰካኩንና አገባቡን ያማርጣሉ፡፡
ጥቃቅኗን ነገር ጭምር ያስገቧታል፡፡ ሀያ ሀያ አንድ ገፅ ፅፈው ይወጣሉ፡፡ ያልፋሉ፡፡ እኔም መልሱን ከነሱ እኩል አውቀዋለሁ፡፡
ታድያ ፈረንሳይኛው ከየት ይምጣ? ከሱ ጋር ስታገል የጊዜዬን
ግማሽ አጠፋለሁ:: ለዚያውም አምጩ የማመጣው ፈረንሳይኛ አንካሳ ሽባ ስለሆነ፣ በደምብ የማውቀውን መልስ ልክ እንደማላውቀውና
በግምት ወይም በነሲብ እንዳገኘሁት ያስመስልብኛል። ዘጠኝ አስር ገፅ ፅፌ እወጣለሁ፣ በመጥፎ ፈረንሳይኛ፡፡ ትምህርቱን እያወቅኩት ፈተናውን እወድቃለሁ

«ፈረንሳዮች ደሞ ታውቃቸዋለህ። በቋንቋቸው የመጣ በጣም
አንጎለ ጠባብ ናቸው። ለምሳሌ አስተውለህ እንደሆነ በፍጥነትና ያለ ስህተት ያነጋገርካቸው እንደሆነ ያከብሩሀል፣ «Intelligentይሉሀል።
እየተንተባተብክ ያነጋገርካቸው እንደሆነ ግን ምንም ቁም ነገር
ብትናገር መሃይም ነህ ማለት ነው። በቋንቋህ ብታናግራቸው እንደ ቂል አፋቸውን ከፍተው እንደሚቀሩና፣ የነሱም ቋንቋ ላንተ ያንን ያህል እንግዳ እንደነበረ፣ የሚሉት ሁሉ «ዠቨሹቪ» ይመስልህ እንደነበረ፣ በስንት ልፋት በመጠኑ ልታውቀው እንደቻልክ፣ በቋንቋቸው መንተባተብ ስለቻልክም ሊያመሰግኑህ እንጂ ሊንቁህ
እንደማይገባቸው፣ ይህን ለመገመት ያህል ሰፊ አንጎል የላቸውም።ተራውስ ሰው እንዲህ ቢሆን አልፈርድበትም፡፡ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮቹ እንዲህ ሲሆኑ ግን በጭራሽ አይገባኝም፡፡ እንግዲያውኑ የነሱ ትምህርት የታል? እቺን ያህል ቀላል ነገር ማመዛዘን ካልቻሉ አንጎላቸውስ ትምህርታቸውስ ምን ትርጉም ይኖረዋል?

«እማናውቀው አገር መጥተን፣ በማናውቀው ቋንቋ
የማናውቀውን ህዝብ ባህልና ታሪክ ለመማር ስንታገል፣ ለምን
አስተያየት አያደርጉልንም?»

“ምን አይነት አስተያየት ሊያደርጉልን ይችላሉ?» አልኩት

«ፈረንሳይኛችን ትንሽ የተጣመመ እንደሆነ፣ የቋንቋውን መጣመም ችላ ብለው የፍሬ ነገሩን እዚያ መገኘት ለምን አያስቡልንም? አገራችን ስንመለስ በራሳችን ቋንቋ ነው የምንmቅመው፣ ስለዚህ ፈረንሳይኛውን አንደነሱ ቻልነው በመጠኑ ተንተባተብንበትስ ምን ያህል ልዩነት ያመጣል? እንግዳ ስንሆን፣ ፈረንሳይኛውን በሀያ ሶስት፣ በሀያ አራት፣ በሀያ አምስት
አመታችን ስንጀምረው፣ እንዴት ከናታቸው ጡት ጋር ሲጠቡት
ካደጉ ሰዎች እኩል ካልሆነ ተብለን እንቀጣበታለን? ቅጣት መሆኑ
ይታይሀል? ፍሬ ነገሩን እንደማውቀው ግልፅ ሳለ፣ የተጠቀምኩበት ፈረንሳይኛ የተቀመመ ፈረንሳይኛ ባለመሆኑ ፈተናዬን ስወድቅ፣አንድ አመት ሙሉ የለፋሁበትን ስከለከል፣ ይሄ ቅጣት ነው እንጂ ምንድነው? ፍትህ የሌለው ቅጣት

«አንድ አመት ምን ያህል እንደሆነ ይገባሀል? አስበው፡፡ የዘጠኝ
የአስር አመት ልጆች ሳለን ክፍል በመድገም አንድ አመት ብናጠፉ
ምንም አይደለም፡፡ በህያ ስድስት፣ በሀያ ሰባት አመታችን አንድ
አመት ማጥፋት ግን ሌላ ነገር ነው:: ምክንያቱም እነዚህ አመታት
ከሀያ አምስት እስከ ሰላሳ አምስት ሰፈር ያሉት አመታት የሌሎቹን አመታት ሶስት አራት እጥፍ ዋጋ አላቸው። አሁን ነው ህይወታችንን ለመጨረሻ የምንቀርፀው:: አሁን ነው ያለ የሌለንን ለሀገራችን ልናበረክትላት የሚገባን። አሁን ነው የኑሮ ስራችንን የምንመርጥበት የምንጀምርበት ጊዜ። አሁን ነው የኑሮ ጓደኛችንን
የምንመርጥበት፣ ትዳራችንን የምንቆረቁርበት ጊዜ፡፡ አሁን ነው።
አሁን! አሁን! አሁን ነው ልጅነትም የማያታልለን፣ እርጅናም የማይ
ጫጫነን፡፡ አሁን ነው ፍሬ ለመስጠት ዋጋ ለማስገኘት የምንችለው» ረጋ ባለ ድምፅ

«አሁን ነው ፈረንሳዮች "ለምን ቋንቋችንን ከኛ እኩል
አልቻላችሁም?' ብለው ወርቅማ አመታችንን የሚያጠፉብን
👍175😁1
«ጠፋች በቃ እቺ አመት:: እኔም፣ ቤቶቼም፣ አገሬም አንድ ወርቃማ አመት ተነጠቅን። ታድያ የነጠቁን ሰዎች አልተጠቀሙበትም፡፡ እንደነጠቁንም ኣላወቁም፡፡ በጫካ ስታልፍ አንድ ትል ብትጨፈልቅ አይታወቅህም፣ የትሉ ሚስት ግን አለም ይጨልምባታል፡፡ ፈረንሳዮቹ አመቴን አጠፉብኝ። አንድ አመት ሙሉ!»
«ፈተናውን ባታልፍበትም እውቀቱን አግኝተህበታል» አልኩት
«እኛ አገር ምስክር ወረቀት የሌለው እውቀት ከእውቀት
አይቆጠርም፡፡ ስለዚህ ያገኘሁት እውቀት በምንም ሊጠቅመኝ
አይችልም። የህግ ትምህርት እንደ ፍልስፍና ወይም እንደ ስነ-ጽሁፍ
ትምህርት አይደለም። ጥቅሙ በስራ ሳይ ልታውለው ከቻልክ ብቻ
ነው። በስራ ላይ እንድታውለው ደሞ የምስክር ወረቀት
ያስፈልግሀል። የምስክር ወረቀት ለማግኘት የፈረንሳይኛ ቋንቋን
እንደ ፈረንሳዮቹ ማወቅ አለብህ:: በፈረንሳይኛ እርሳስ ተባእታይ
ፆታ ነው፣ ብእር ግን አንስታይ ፆታ ነው። ለምን? ምክንያት የለውም። መኪና፣ አውቶብስ፣ መፅሀፍ፣ ደብተር፣ ሰማይ፣ መሬት፣
ፀሀይ፣ ኮከብ፣ ደመና፣ ነፋስ እነዚህ ተባእታይ ይሁኑ እንስታይ
ፈረንሳይ ያልሆነ ሰው ቢያሳስት ይህን አሳሳትክ ተብሎ ፈተናውን
ይወድቃል? ይሄ የሚገባ ነገር ነው?»

እውነቱን ስለሆነ ምንም ልለው እልቻልኩም

«አይዞህ በጥቅምት ወር ተፈትነህ ታልፋለህ» አልኩት

«እንዴት አድርጌ?» አለኝ

«ትምህርቱ ቢሆን ያቃተኝ፣ ሌት
ተቀን አጥንቼ እፈተን ነበር። ፈረንሳይኛውን ግን በሶስት ወር ውስጥ ከምን ላደርሰው እችላለሁ? ከእንግዲህ ልጅ አይደለሁም፡፡ ሀያ አምስት አመቴ አልፏል፡፡ እስከ መቼስ ቢሆን ፈረንሳይኛውን ከነሱ እኩል ላውቀው እችላለሁ እንዴ?
“ጠፋች እቺ አመት። እንደ ሌሎቹ አመታት ጠፋች፣ ተከተለቻቸው»
«ሌሎቹ አመታት?» አልኩት
«በይሩት ነበር የምማረው፡፡ በህክምና ትምህርት ሁለተኛ
አመት እንደጨረስኩ ነው ወዲህ የመጣሁት»

(«ለምን መጣህ? መጥተህስ በህክምና ትምህርት እንደመቀጠል እንደገና ሀ ብለህ ህግን ለመማር ለምን ቆረጥክ?” ልለው ፈለግኩ፤ግን አሁን የመጠየቅ ጊዜ አልነበረም፡ ዝም ብሎ የመስማት ጊዜ ነበር)

ዝም ሲል ጊዜ ንግግራችን እንዲቀጥል ለመቆስቆስ ያህል
“አይዞህ በርታ፣ ሁሉም ሰው ችግር ያጋጥመዋል» አልኩት
ሳቅ አለ። አስተያየቱ በምቾት ቁጭ ብለህ በችግር
የሚፍጨረጨረውን ሰው 'አይዞህ፡ ረጋ በል ማለት ምንኛ ቀላል
ነው!» የሚል ይመስላል

ችግሩ ይህን ያህልም ከባድ አይደለም» አለ እንዲህ
የሚያስለፈልፈኝ ከሌላ ችግር ጋር ተጋግዞ ስለሚያጠቃኝ ነው።
በፈተና ስለወደቀ ያለቅሳል ብለህ እንዳትታዘበኝ

«ሌላ ችግር አለብህ?»

ቤቶቼ ናቸው ሌላው ችግር፡ አየህ፣ አባቴና ከሁሉ ታላቅ ወንድሜ ነጋዴዎች ናቸው:: አንዴ ገንዘብ ይተርፋቸዋል፣ አንዴ
ደሞ የተገዛው እቃ መሽጥ እስኪጀምር ጥሬ ገንዘብ ከእጃቸው ያጣሉ፡፡ በዚህ ምክንያት፣ በይሩት ስማር ሳለሁ በሶስት በአራት ወር ነበር ገንዘብ ሚልኩልኝ። ላኩልኝ ስላቸው ከጓደኞችሀ ተበደር በኋላ እንከፍላለን ይለኛል ..

እንግዲህ በይሩት ውስጥ መአት ሰው ያውቀዋል። ይበደራል። እሰከ ስድስት ሺ ፍራንክ ድረስ (3,000 ብር) ይበደር ነበር፡፡ ቤቶቹ ሲመቻቸው አንድ ስምንት ሺ ፍራንክ ይልኩለታል።
እዳውን ከፍሎ ሲጨርስ ሁለት ሺም ያህል ይተርፈዋል። እሷ
እስከታልቅ ካላኩለት እንደገና ሌላ ይበደራል፡፡ እንደዚህ ነብር
የሚኖረው

እዚህ ኤክስ እንደመጣ አድራሻውን ላከላቸው እንግዳ አገር ስለሆነብኝና የማውቃቸው ሰዎች ስለሌሉ እንድትልኩልኝ አደራ አላቸው፡፡ «እንደተመቸን እንልክልሀለን አሉት። መበደር ጀመረ፡፡ እንደገና ደብዳቤ ፃፈ። በቀን በቀን ደብዳቤ መጥቶልኝ እንደሆነ እያለ እየተንገበገበ ይጠብቃል። አራት ወር ሙሉ ምንም መልስ ሳይልኩለት ቆዩ። ብድሩ እየበዛ ሄደ።
ቴሌግራም ላከ «ምን ሆናችኋል? ሰግቻለሁ፣ እዳ ተጠራቅሞብኛል፣
ረሀብም አጥቅቶኛል» አላቸው:: መልስ ይጠብቅ ጀመር
ማታ ሲተኛ ስለነሱ ያስባል። ነገ ደብዳቢ ይደርሰኛል ይላል።
ጧት ሲነሳ ስለነሱ ያስባል። ዛሬስ ደብዳቤ አገኛለሁ ይላል። ደብዳቤ
ሳይደርሰው ቀኑ ሲመሽ ይገርመዋል። ይሰጋል፡፡ ምን ሆነው ይሆን? ይፈራል፡፡ ነገ ደብዳቤ ይደርሰኛል ይላል።

እዳው እየከበደው ሂደ

እንግዲህ የኤክስ ፖስታ በቀን ሁለቴ ነው የሚታደለው። የጧቱ
ባምስት ሰእት ሰፈር ይመጣል። ባህራም ከክፍል ወጥቶ ሲጣደፍ
ቤቱ ይሄዳል። ምንም ደብዳቤ አይጠብቀውም፡፡ ኩም ይላል። በአስር ተኩል ላይ ይመጣልኝ ይሆናል ይላል። እስከ አስር ተኩል ይጠብቃል። በአስር ተኩል ምንም ደብዳቤ አይመጣለትም፡፡ እነዚህን
ሰአቶች ይፈራቸው ጀመር። ተስፋ ልቡ ውስጥ እየተጠራቀመ
ይቆይና፣ ምንም ደብዳቤ እንዳልመጣለት ሲያይ፣ ነብሱ በኩምታ ሽምቅቅ ትላለች። በዛበት፡፡ ስለዚህ፣ ሁለቴ ኩም ከማለት ብሎ ከቤቱ ጧት የወጣ እስከ ማታ አይመለስም። ማታ ወደቤቱ ሲራመድ ጧት ደብዳቤ መጥቶልኝ ይሆናል፣ ወይም ከሰአት በኋላ መጥቶልኝ
ይሆናል፣ ከሁለቱ በአንዱ ሳይመጣልኝ አይቀርም» እያለ ያሰላስላል፡፡ታድያ ደብዳቤ የሚሏት የለችም። ተስፋና መንገብገቡ ድንገት አፈር
ይሆናል። ራሱን ማመን ያቅተዋል። እንዲህ ሊሆን አይችልም፣
ደብዳሲ ሳይኖረኝ አይችልም!» ይላል። «ነገ ይላል። እስከ ነገ በብዙ ይሰጋል። ቤቶቼን ምን ነክቷቸው ይሆን? አባቴና ወንድሜ ከስረው ይሆን? ግን ቢከስሩ ፅፈው አይነግሩኝም? መፃፍ አልቻሉ ይሆን?
ታስረው ይሆን? ሞተው ይሆን? ምን አግኝቷቸው ይሆን?»

ይሄ ሁሉ ሲሆን እዳው እየተካሃቸ ሄደ

«ከማውቃቸው ሰዎች ከአብዛኛዎቹ አምስት አስር፣ ሀያ ፍራንክ ተበድርያለሁ ይመስለኛል፡፡ አሁንማ ስንት ፍራንክ ከስንት ሰው
እንደተበደርኩ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ሰዎቹን በቀን በቀን
ኣገኛቸዋለ፡፡ በቅርቡ እመልስልሀለሁ እያልኩ ነበር የተበደርኳቸው::እና ሳያቸው አፍራለሁ። ሲያሳፍር የሰው አይን! አይተውህ ሲያልፉና፣ ካለፉህ በኋላ አይናቸው ውስጥ ያየኸውን ንቀት ስታስታውሰው ማሳፈሩ!»

የሚገባበት ይጨንቀዋል፡፡ ግን ምን ለማድረግ ይችላል?
እፍረቱና ስጋቱ ሲፈራረቁበት እያየ «ይሄ ሁሉ መጨረሻው ምን
ይሆን?» ማለት ብቻ ነበር
ከሁሉ የሚጎዳው ስለቤቶቹ ማሰብ ነበር። ማታ እንቅልፍ እምቢ እያለው ስለነሱ ሲያስብ፣ አንጎሉ እንደ ወሬኛ የመንደር ሴት ክፉ ክፉ ሀሳቦችን እየለቃቀመ የጭካኔ የጭቆና ትርኢቶችን ያሳየው ነበር ለጊዜው አንተን ችግር አያጥቃህ እንጂ፣ ቤቶችህስ ምንም አይሆኑም አይዞህ» አልኩት

«አንተ የኛን አገር አታውቀውም። ስንት ጭቦ እንደሚሰራ፣
ስንት በደል እንደሚፈፀም፤ እንኳን ልትገምት ልትጠረጥር
ኣትችልም»

ሌሊት ሲሆን የሚመጡብህ ሀሳቦች አሉ፡፡ ህልም አይደሉም፣ ምክንያቱም እንቅልፍ አይወስድህም። ግን ጤነኛ ሀሳቦች አይደሉም፧ የሌሊቱን ጭለማ ይለብሱና እንደ ጉንዳን ይወሩሀል ያስፈራሩሀል ቀን ቢመጡብህ ትስቅባቸዋለህ፤ እነሱም በቀን ደፍረው አይመጡብህም፡፡ ሌሊት ግን እውነት ይመስሉሀል። ብቻህን
በጭለማ በረሀ ውስጥ ስትፈራ እንደምታየው ቁጥቋጦ ናቸው።
በመጥፎ ህልምና በውን መካከል አንድ የሀሳባችን ጫካ አለ። ብቻህን ነህ፣ ጭለማ ውጦህል፣ የቁጥቋጦ መአት ከቦሀል.መሰረት
የሌለው ሀሳብ ሁሉ የመጨረሻ እውነት መስሎ ይመጣብሀል
እና በዚሀ ጊዜ ባህራም ስለቤቶቹ ሲያስብ፤ አንዴ ቤታቸው
ተቃጥሎ ሁለም ሞተው ይታየዋል፡ “አንዴ አባቱና ወንድሙ
ከስረው በእዳ ተይዘው ታስረው፣ ወንድሞቹና እህቶቹ መጠጊያ
አጥተው ሲጨነቁ ይታየዋል
👍22
በተለይ ከሁሉም አብልጦ
የሚወዳት እህት አለችው
የመጨረሻ ልጅ ናት። ቤቶቹ ሁሉም እሷን ነው የሚወዷት፡፡ ታድያ እሷ አልጋዋን ነው ምትወደው። ስታጠና አልጋዋ ላይ ሆና፤ ስትጫወት፣ ስታዝን፣ ስትደሰት የሚያገኙዋት፡፡ ይህን አልጋ ገረዶቹ እንዲያነጥፉት አይፈቀድላቸውም፤ ልጅቱ ራሷ ናት የምታነጥፈው በቀን ኣራት አምስት ጊዜ ይነጠፋል
«እህቴን ያመማት እንደሆነ እማማ ብቻ ናት እንድታነጥፈው
የሚፈቀድላት። ይሄ አልጋ በአመት ስድስት ሰባት አልጋ ልብስ
ይገዛለታል። ብቻ ምን ልበልህ፣ እህቴ ያለአልጋዋ መኖር
አትችልም፡፡ ታድያ በሀሳቤ ቤታችን ከነዕቃው ሲወረስ፣ የእህቴ
አልጋ በሀራጅ ሲሽጥና፣ እሷ ይህን ስትመለከት ይታየኛል። አይኖቿ ይታዩኛል። ሆዴን ያመኛል»

አንዳንዴ ደሞ አባቱ በፖለቲካ ምክንያት ተይዘው ወታደሮች
እያዳፉ ሲወስዷቸውና ሌሎቹ ወታደሮች ደሞ እህቶቹን
ሲደፍሩዋቸው፣ ወንድሞቹን በሰደፍ ራሳቸውን ሲፈነካክቷቸው
ይታየዋል። . «ይሄ ሁሉ እኛ አገር በየቀኑ የሚደረግ ስለሆነ፣
እነዚህ የሌሊት ሀሳቦች በጣም ያስፈሩኛል፣ ያስጨንቁኛል»
አንዳንዴ ስጋቱ ከመጠን በላይ ይበዛበትና፣ ተነስቼ አገሬ ልግባ
ይላል። ግን እንዴት ለመሄድ ይችላል? ባንድ በኩል ተስፋ የሚሉት አለ

«ይሄኔኮ ይህን ሁሉ ዝምታ የሚያስረዳ ደብዳቤና እዳዬን
በሙሉ ለመክፈል የሚያስችለኝ ገንዘብ መንገድ ላይ ይሆናል፣ ነገ
ወይ ተነገ ወድያ ይደርሰኝ ይሆናል» ይላል። በሌላ በኩል ለመሄድ ብቆርጥስ በምን እሄዳለሁ?» ብሎ ሲያስብ፣ በአሮፕላን፣ በመርከብ፣
በባቡር ወይም በአውቶብስ እንዳይሄድ፣ ምን ከፍሎ? በእግሩ እንዳይሂድ፣ አመት ወይም ሁለት አመት ይፈጅበታል፤ ለዚያውስ ስንቅ ከየት ይመጣል? ሲመሽስ የት ይተኛል? በሌላ በኩል ደሞ፣ የመሄጃ ዘዴ ቢያገኝስ እዳውን ሳይከፍል እንዴት አድርጎ ለመሄድ ይችላል?

እስረኛ ነኝ በቃ። በእዳና በተስፋ ታስሬ፣ በእፍረትና በስጋት
የምገረፍ እስረኛ ነኝ»

«እንዴት ጎበዝ ነህ!» አልኩት

እንዴት?» ለማለት ያህል አየኝ፡፡

ከቅንድቦቹ ጥቁር ጫካ ጥላ
ስር ቡናማ ትንንሽ አይኖቹ ያዩኛል፣ ሀዘን ሞልቷቸዋል፣ ግን ተስፋ
አልከዳቸውም፣ እንዲያውም ሳቁን የረሱ አይመስሉም

«እኔ አንተን ብሆን ድሮ ተስፋ ቆርጫለሁ» አልኩት።

አፍንጫው ትልቅና ሸካራ መሆኑን ገና አሁን አስተዋልኩ
በይሩት ሳለሁ እንዲህ አይነት ኑሮ የሚኖር ሰው አለ ቢሉኝ
ኖሮ፣ እኔም 'እንዴት ተስፋ አይቆርጥም!?' ብዬ ይገርመኝ ነበር።ስትገባበት ግን ሌላ ነው። አየህ፣ የሰው ልጅ በጣም ጠንካራ ነው፤ምንም ያህል መከራ ቢናድበት አይሸነፍም፣ መቸም ቢሆን ተስፋ አይቆርጥም

ዝም አልን። አፍንጫው ምን ያክላል!

«እኔ ተስፋ እንዳልቆርጥ የደገፈኝ ምን መሰለህ?» አለኝ

«ምን?»

«ሉልሰገድ፣ ተመስገንና፣ ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን። እንደዚህ
ያሉ ሰዎች አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ ፈረንሳዮችን ታውቃቸዋለህ
እግራቸው ስር ወድቀህ እየተንፈራገጥክ በራብ ሞትኩ ብትላቸው፣እጃቸውን ብድግ አርገው ትካሻቸውን እንቀሳቅሰው 'ኧእ! መስዬ፣ታድያ ይህ የኔ ጥፋት ነው? ለምን ወደ ኤምባሲዎ አያመለክቱም?ብለውህ መንገዳቸውን ይቀጥላሉ። ኤክስ ውስጥ ተበድሬ ተበድሬ፣
የማውቃቸውን ሰዎች ጨረስኩ። የቀረኝ ጥቅልል ብሎ በረሀብ
መሞት ነበር። ተመስገንና ሉልሰገድ አበሉኝ። ያገሬ ልጆች ማጣቴን አይተው ፊት በነሱኝ ሰአት፣ እንግዳ የሆኑ ሰዎች፣ ቋንቋቸውን ባህላቸውን የማላውቀው ሰዎች፣ ቆዳቸውና ፀጉራቸው ሳይቀር ከኔ
የተለየ ሰዎች ጠርተው አበሉኝ፡፡ በሀበሾች ጓደኞቼ ምክንያት፣ በሰው ልጅ ላይ ያልነበረኝ መተማመን አደረብኝ:: ምግብ ብቻ አይደለም የሰጡኝ። ስሙን እኔ እማላውቀው፣ ከምግብ የበለጠ ነገር ነው የሰጡኝ። ሌላ ሰው ሰጥቶኝ እማያውቀው ነገር ነው የሰጡኝ»

አይኖቹ ብርሀን ሙሉ
ብርህን አይደለም፣ እንባ ነው -
የሀዘን አምባ አይደለም፣ ሌላ አይነት እምባ ነው:: ወደዚያ አየ፡፡
እኔም ወደ ሌላ በኩል አየሁ
ሀበሾቹ እንደዚህ ጥሩ ሰዎች መስለው የታዩት ምንኛ የዋህ
ቢሆን ነው? ብዬ አሰብኩ
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ችግሬን ትከሻ ላይ ጫንኩብህ፣ ይቅርታ አርግልኝ አለኝ ዘወር ብዬ አየሁት። አይኖቹ ውስጥ እንባ የለም

«አታምነኝም ይሆናል» አልኩት «ግን ችግርህን ስላዋየህኝ ክብር
ይሰማኛል። ደሞ አይቼው የማላውቅ ጉብዝና ዛሬ አየሁ።
ሳቅ አለ

«አንድ ነገር ልንገርህ» አለኝ «ይሄ ስጋት፣ ፍርሀትና በእዳ ተይዞ ማፈር እየከበደኝ እያስጨነቀኝ ሲሄድ ጊዜ፤ ብቻዬን አልችለውም በማለት ለሰው ልናገረው ሞክሬ ነበር። ደጋግሜ ሞክሬ ነበር። ግን ልናገረው አልቻልኩም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሰሚ አጣለሁ፡፡
የሚሰማኝ ሳገኝ ደሞ ልናገር እንደጀመርኩ እፍረት ይይዘኛል፡፡
መናገሩን እተወዋለሁ። ላንተ መናገር ግን በፍፁም አያሳፍርም፡፡
የማዳመጥ ስጦታ አለህ። ቄስ ለመሆን አስበህ ታውቃለህ?»

እፍረት ተሰማኝና ሳቅ ስል፣ እሱም ሳቅ እያለ

«ህለላሴ ሙት!» ብሎኝ ተነሳ። እኔም ተነሳሁ
«Vive l amitié frar Ethiopienne!» አለኝ:: ይስቃል።
(የኢራንና የኢትዮጵያ ጓደኝነት ለዘለአለም ይኑር») አሁን አሁን
ያን ሁሉ ችግሩን ሲያወራልኝ እንደነበረ ለማመን አመነታሁ

«Vive!» አልኩት « A bas les Yankees!» («ይኑር!
ያንኪዎች ይውደሙ!»)
«A bas!» አለኝ፡፡ (“ይውደሙ!»)
ወደ ካፌ ዶርቢቴል በኩል ስንራመድ መንገዳችን ላይ ምናምን ሲለቃቅሙ ከነበሩት ወፋፍራም እርግቦች አንዷን በእግሬ ቃጣሁባት:: አልበረረችም። እንዲያውም አልዘለለችም፡፡ እንደ ሞጃ
ወይዘሮ ደበልበል እያለች ከመንገዳችን ወጣ አለች። ባህራም

«የከይ ኮስሮ እርግብ ብትሆን ይህን ጊዜ በራ ጠፍታ ነበር»
አለ።

«ከይ ኮስሮ?»

«የጥንት የኢራን ሻህ፡፡ አየህ ከይ ኮስሮ በሰረገላ መሄድ ሰለቸው:: በአየር መሄድ አማረው:: የሌላ አገር ንጉስ ቢሆን መብረር
እንዳማረው ይቀር ነበር። ከይ ኮስሮ ግን የኢራን ሻህ-ን-ሻህ ነው::
መብረር ካሰኘው መብረሩ አይቀርም፡፡ ስለዚህ አንድ አምስት መቶ ወፎች ሰበሰበና ከአልጋው ጋር አስሯቸው ሲያበቃ፣ በማእረግ
አልጋው ላይ ወጥቶ ተጋደመና፣ አንዴ ጅራፉን ሲያስጮህባቸው
ጊዜ ተነስተው በረሩ። ከይ ኮስሮ አልጋው ላይ እንደ ተቀመጠ
ወደላይ ወጣ፣ ግን የልጓሙን ጉዳይ ሳያስብበት ቀርቶ ኖሮ፣ ወፎቹ ወደ ልዩ ልዩ ኣቅጣጫ መብረር ስለሞከሩ፣ ሩቅ ሳይሄዱ አልጋው ወደታች መዝኗቸው ወደቁ፡፡ ከይ ኮስሮ እግሩን
ተሰበረ። ከሚኒስትሮቹ አንድ አምስቱን አስገደለ»

«ለምን?»

«መጀመርያውኑ ተው እንዳትሰበር ብለው ስላልመከሩት። ግን
መጀመርያውኑ ተው እንዳትሰበር ቢሉት ኖሮ ደግሞ ያስገድላቸው
ነበር»

«ምክንያቱስ?»

መብረር ሲያምረኝ፣ ለምናባታችሁ ነጃሳ ቃል ትናገሩኛላችሁ? ብሎ ነዋ!»

«ግሩም ንጉስ ኖሯል!»

«እንዴታ! ተራ ንጉስ መስሎህ ኖሯል እንዴ? የኢራን ኻህ ን.
ሻህ ነው' ኮ።

እና ከዛስ?»

«ከዛ እግሩ ሲድንለት ለራዊቱን አስከተተና ወደ ህንድ ዘመተ።
«ከህንድ ጋር ጠብ ኖሯችኋል?»
«የምን ጠብ? ህንድ መቼ ጠብ ያውቃል?»
👍15
«እህ! እንግዲያው ከይ ኮስሮ ለምን ወደ ህንድ ዘመተ?»
«የደምቡን ለማድረስ ነዋ»
«በጭራሽ አልገባኝም»
ላስረዳህ፡፡ በዚያን ዘመን ማንም የኢራን ንጉስ ገንዘብ
ሲያስፈልገው ወይም ጉልበቱን ማሳየት ሲያምረው፣ ትንሽ ሰራዊት
ይሰበስብና ወደ ህንድ ብቅ ይላል፡፡ እንግዲህ ህንዶች ለቡድሀ ወይም ለሺቫ ይሁን፣ ለሌላ አምላክ ይሁን፤ ያለ የሌላቸውን አልማዝ፣ ወርቅ፣ ብር፣ ሉል፣ ምናምን ቤተ መቅደስ ውስጥ ያከማቻሉ።የኢራን ሰራዊት ይመጣና ለደምቡ ያህል ማለት ጦርነት አርገናል ለማለት ያህል ጥቂት የህንድ ወታደሮች ገድሎ፣ ሌሎቹን አባሮ
ሴቶቹን ትንሽ ተደስቶባቸው ሲያበቃ፣ ቤተ መቅደሱ ውስጥ
የተከማቸለትን ሀብት ተሸክሞ ወደ አገሩ በሰላም ይመለሳል

«ማንም ሻህ.ን.ሻህ በዘመነ መንግስቱ አንድ ጥያቄ ይገጥመዋል።ይኸውም፣ የኢራንን ህዝብ አዲስ ግብር ማስከፈል ይቀላል፣ ወይስ አንድ ሁለት ሺ ወታደር አስከትሎ ህንድ አገር ደርሶ መመለስ ይቀላል? የሚል ጥያቄ ነው፡፡ አንዳንድ ነገስታት አሉ፤ የኢራን ታሪክ የሚያስታውሳቸው ህንድ አገር ባለመዝመታቸው ነው»

እንደዚህ እየቀለደ ካፌ ዶርቤቴል ደረስን። ሀበሾቹ አሁንም
ካርታ ጨዋታቸውን ይዘዋል፡፡ ባህራም እንደልማዱ

«አስቀያሚ! ሸርሙጣ! ሀሳለሴ ሙት! Je veix jouer aux cartes!»
እያለ መሀላቸው ቁጭ አለ። (ካርታ አጫውቱኝ)

እንደ ወጣት ረዥም ባህር ዛፍ ሆኖ ታየኝ . የመከራ ነፋስ
ይነፍሳል፣ ባህራም ይታጠፋል፤ መሬት እስኪነካ ይታጠፋል፤ ግን
አይሰበርም፣ ተመልሶ ቀጥ ይላል፤ እስከሚቀጥለው ነፋስ ድረስ ..

በስንት ጭቅጭቅ ጋዜጣዬን ከተካ ተቀብዬ ወደ ሲልቪ
ቤት ሄድኩ ባህራም የነገረኝን ሁሉ አጫወትኳት፡፡ ለረዥም ጊዜ ዝም ብላ ከቆየች በኋላ
«ይገርምሀል፡፡ እኔ' ኮ gigolo ይመስለኝ ነበር» አለችኝ
«ዢጐሎ? ምንድነው እሱ?» አልኳት
«ዢጐሎ አታውቅም? ገና አልሰለጠንክማ!»
«እኮ ምንድነው እሱ?»
«ሴቶችን እያስደሰተ ገንዘብ የሚቀበል ወንድ ነው»
«ታድያ ባህራም ምኑ ያምራልና ዢጊሎ ይሆናል?» አልኳት
«አያምርም። ግን ከሚያምሩ ወንዶች ይበልጥ ደስ ይላል»
«አይ! እንግዲህ ወሬ እንለውጥ»
“እሺ። ግን እሱ የነገረህን ሁሉ ባታምን ይሻላል»
«ለምን?»
«ሰውዬው አሪፍ ውሸታም እንደሆነስ?»
«ይመስልሻል?»
«ይመስለኛል»
«እኔ ግን አይመስለኝም።
«እስቲ እናያለን» አለችኝ
እንዲህ በማለቷ በሸቅኩ፡፡ ግን መብሸቄን አላሳየኋትም፡፡...

ይቀጥላል
👍11
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#ስምንት (የመጨረሻ)


#በአሌክስ_አብርሃም

...“ቆይ አብርሸ ምንድን ነው … ማለቴ…ተወው በቃ” ግራ ተጋባች። እናም እንዲህ አለችኝ፣ ችግር የለውም እንዳታስብ፣ ምንም ነገር እንዳታስብ !” ስትናገር ዓይኔን ማየት ፈርታ ነበር።እጆቿ እነዛ ቆንጆ
ጣቶቿ በሆነ ፍርሃት ሲንቀጠቀጡ ይታዩኛል። ብርድ ልብሱን ከጎኔ ገልባ ሸርተት ብላ ገባች።
ወዲያው ተመልሳ ተነሳችና የሌሊት ልብሷን ከትራስጌ በኩል አንስታ ለበሰች፤ ተመልሳ ተኛች። ድንብርብሯ ወጥቶ ነበር። በብርድ ልብነስ በታፈነ ድምፅ ችግር የለውም” እለች እንደገና።..

“ሙና” አልኳት ጀርባዋን ሰጥታኝ ነበር የተኛችው። ልክ ሰይጣን የጠራት ይመስል ድንግጥ ብላ፣

“እ” አለችኝ። ድንጋጤዋ እኔንም አስደነገጠኝ።

“ይቅርታ እስካሁን ስላልነገርኩሽ"

“ችግር የለውም ! ይሄ ማንንም ሊያጋጥም የሚችል ነገር ነው እንተኛ።” አነጋገሯ ምንም ለዛ የሌለው የሽሽት ይመስል ነበር፤ ዝም ላለማለት ያህል። ተኛች፤ እንቅልፍ የወሰዳት መሰለኝ። ልነካት ፈራሁ።የሆነ አተኛኘቷ ራሱ ትንሽ ከሰውነቴ ራቅ የማለት ነገር ነበረበት። ይሰማኛል እባብ የሆነ ነፋስ በመሐላችን በተፈጠረ ሰርጥ መለያየት ሲሳብ …

ተነስቼ ከአልጋዬ አጠገብ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጥኩ። ከፊቴ ትንሽ ጠረጴዛ አለች፤ መፃፍ ሲያምረኝ ከምኝታዬ ተነስቼ የምፅፍባት። ለምን ያህል ጊዜ እንደተቀመጥኩ እኔጃ፤ ሙና በእንቅልፉ ስትንቀሳቀስ ብርድ ልብሱ ተንሸራትቶ ግማሽ አካሏ .ተራቆተ። ህልም የሚመስል ቀይ ሰውነት፣ ከውስጡ ብርሃን የሚያመነጭ ሙልት ያለ ሰውነት፤ ውብ ሰውነት። በዚህች ቅፅበት ውስጤ በቅናት አረረ። የማላየው የወንድ እጅ እዚህ ሰውነት ላይ ሲያርፍ አሰብኩ። የሙና ሰውነት የደረቀ መሬት መስሎ ተሰማኝ። ውሃ የናፈቀ፡ የተቃጠለ፣ ማንም መቼም ሲዘንብበት ምጥጥ የሚያደርግ ምድረበዳ።

ዝም ብዬ አያታለሁ። ልቤ ታፍኗል። መረረኝ፣ ሕይውት አስጠላኝ። ሙና ስዕል ብትሆን ብዬ ተመኘሁ። የትም የማትሄድ፣ ለዘላለሙ እዚህ ተቀምጬ የማያት ስዕል፣ የምትታይ ብቻ። የስዕል፣የግጥም፣ የዘፈን የሁሉም ጥበብ መነሻ አለመቻል መሆኑ የገባኝ እዚህች ነጥብ ላይ ነው። ሰው አለመቻሉን ሲገልፅ መግለጫው መንገድ ላይ ይጠበብና ጥበበኛ ይባላል። ሰው በአካል ያልደረሰበትን ጥግ
ነው በጥበብ እጆቹ ተንጠራርቶ ለመንካት የሚፍገመገመው።

ሙና ተንቀሳቀሰች። ብርድ ልብሱ ሙሉ ለሙሉ ወደ እንድ ጎን ተሰበሰበ። በስስ የሌሊት ልብስ፣
ሰውነቷ ፍም መስሎ ቀልቷል። እዛጋ ሆና እዚህ ያለሁ እኔን ወላፈኗ ፈጀኝ። እንቁልልጭ የምታጣትን ልጅ ተመልከት.. እንዴት ውብ እንደሆነች እይ” የሚለኝ ሰይጣን ጭንቅላቴ ውስጥ የተቀመጠ መሰለኝ።

እየኋት …. ትክክከከ ብዬ አየኋት። ሕሊናዬ ትልቅ ሸራ ሆኖ መንፈሴ በማይጠፋ ቀለም ሙናን እየሳለ
ነበር። ልቤ ትልቅ ብራና ሆኖ ሙናን እየፃፋት ነበር። ከወንበሬ ተነስቼ የሙናን የእግር ጣቶች ተራ
በታራ ሳምኳቸው፤ አስሩንም። የተለኮሰ የሲጋራ ጫፍ የሳምኩ ይመስል የእግሮቿ ጣቶች ከንፈሬ ላይ ረመጥ ሙቀታቸውን አተሙት። ደግሞ የእግሯ ልስላሴ ! ወደ ቦታዩ ተመለስኩ። ብርድ ልብሱን አላለበስኳትም፤ ላያት ፈልጌያለሁ።

ወንበሬ ላይ ቁጭ ብዬ ሙናን ስመለከታት የገጣሚ ኤፍሬም ስዩም ግጥም ልክ ጎረቤት እንደተከፈተ ዓይነት ከነድምፁ ጥርት ብሎ እንደ ጅረት ውኃ አዕምሮዬ ውስጥ ይፈስስ ጀመረ። ያውም በዓይኖቼ ሞልቶ በሚፈሰስ እንባዬ ታጅቦ። #ሶልያና የእኔ ኑዛዜ - የግጥም አልፋና ኦሜጋዬ … እያንዳንዱ ግጥም የኑሮ ዝባዝንኬ ድንጋዩን ቢጭንበትም አለ ጊዜ እንደ ከርሰ ምድር ውኃ የሚፈነዳበት። ገጣሚው እዚህ ተቀምጦ ሙናን እየተመለከተ የፃፈው እስኪመስለኝ፣ ሶሊያና የሙና የቤት ስሟ፣ የመኝታ ቤት
ስሟ እስኪመስለኝ … ገጣሚው የእኔን ሙሾ በደረቀ ሌሊት አወረደው ….

ሶ ሊ ያ ና

እኔን ከወንበር ላይ፤
ቀን ያየሁት እንባ
ቀን ያየሁት ደባ
እንቅልፍ አሳጥቶኝ፣
ወረቀት ላይ ወስዶኝ ….
እርሷን ካልጋችን ላይ፣
እንቅልፍ አሽኮርምሟት፣
ቀን ያየችው ሁሉ በቅዠት አልፎላት፣
እኔ ከቃላት ጋር ጦርነት ገጥሜ፣
በሰው ልጆች ጭንቀት እጅግ ተዳክሜ፣
በሌሊት ጭንቀቴ የቀን ስቃይ ላበርድ፣
ከደጋው ሐሳቤ በረሃ ስሰደድ፣
እንባን በፊደላት፣
ፊደልን በቃላት፣
ቃላትን በሐሳብ፣
ወረቀት ላይ ልወልድ፣
ወረቀት ላይ ፅፌ ወረቀቱን ስቀድ
እንዲህ እየፃፍኩኝ እያሰብኩኝ ሳለሁ፣
"የኔ ነሽ” የምላት ያንተ ነኝ የምትል፣
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ መሃል
“ተመልከት ወዳጀ እኔም ካልጋዬ ላይ፣
አንተን መናፈቅ በስሜት ስሰቃይ"
ቀና ብዬ ሳያት እውነት አለው ቃሏ፣
ፍም መስሏል አካሏ፣
ከሌሊት ልብሶቿ ጡቷ ሾልኮ ወጥቷል፣
እጇ ተዘርግቶ እግሯ ተከፋፍቷል፣
እኔን በመጓጓት ደሟ ተቆጥቶ፣
ፍቅሯ ተሰውቶ፣
ስሜቷ ተጎድቶ፣
አንዳች ነገር አይቶ እንደፈራ ሕፃን፣
ፊቷ ሲሸማቀቅ ፀጉሯ ሲበታተን፣
ካልጋው ላይ ተፅፎ አየሁት እውነቷን፣
ፍ ቅ ሬ ሶሊያና አወራችኝ መሰል በቅዠቷ መሃል …
አስተውል ወንድሜ…
ባንተ የቀለም ቅብ በድርሰት ዓለም፣
የሰዎች ጥላ እንጂ አካላቸው የለም !
ባንተ ከንቱ ድርሰት በወረቀትህ ላይ፣
የሰው እንባ ሳይሆን ያንተው ነው የሚታይ፧
ሌሊት ትጋትህ በድርሰት በግጥም በቀለም ሸራህ ላይ፣
እኔ ውበቱ ነኝ ለፍቅርህ ስሰቃይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም፣
ይህ ሁሉ ቢሆንም... ወዲህ እንዳትመጣ፣
በሌሊት ትጋትህ ሐዘን ሳይቀጣ፣
በኔ ያልጋ ድርሰት ቅፅበታቶች አሉ፣
ከየሰዉ ዓለም የሚመሳለሉ፣
ባንተ ቀለም ሸራ በድርሰትህ ፅሁፍ፣
ዘመን ይታየኛል እኔን የሚያሳልፉ፣
ይህ ሁሉ ቢሆንም
የሰዎችን እንባ
አትፃፍ ግዴለም፡
የፍጥረትን ሐዘን ስለህ አትዘልቅም፣
እውነት እለው ብለህ ሐዘንን አታልም፣
((ያለቀሱም ሰዎች ሐቀኞች እይደሉም}
ይልቅ የኔን ስሜት፤
ያንተንም እንባዎች ሁለቱን አሳየኝ፣
በድርሰት
በግጥም
በቀለም ሸራህ ላይ እኔን ብቻ ሳለኝ ! እኔን ብቻ ፃፈኝ !
“ያልተደሰተች ሴት” በሚል መጽሐፍህ
ዘ ላ ለ ም አሻግረኝ፣
ዘ ላ ለ ም ውሰደኝ፣
ዘ ላ ለ ም አኑረኝ !!”
“የኔ ነሽ” የምላት፣ “ያንተ ነኝ የምትል፣
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ መሃል።


ቁጭ ያልኩበት ወንበር ላይ እንቅልፍ ወሰደኝ…

ሊነጋጋ ሲል….
“አብርሽ” የሙና ድምጽ እንደ ህልም ተሰማኝ። ዓይኖቼን ስገልጥ ፊቴ ቆማ ነበር። ልብሷን ለባብሳ፣አንድ እርምጃ የሚሆን ከእኔ ራቅ ብላ ቆማ ነበር። ሙና ስትቀሰቅሰኝ እንዲህ አልነበረም፡፡ ከተኛሁበት የምትቀሰቅሰኝ በከንፈሯ ነበር። በተኛሁበት ስትስመኝ ነበር የምነቃው። እና እዛጋ ምን አቆማት ፣
ሁሉን እንቅልፍ ባስረሳው በደበዘዘ አዕምሮ አያታለሁ።
“ተነስ ቁርስ ሰርቼልሃለሁ”
በዝምታ እንቁላል ፍርፍር በላን፣ ሻይ ጠጣን፤ (በዝምታ) ዕቃዎቹን አነሳስታ አጣጠበች እና መጥታ
ጎኔ ተቀመጠች። ሁለታችንም በአስፈሪ ዝምታ ውስጥ በዝምታ እንደተቀመጥን ድንገት የሙና እንባ ተዘረገፈ፤ እናም አቀፈችኝ። ከሙና እንዲህ ዓይነት ጉልበት ያለው አስተቃቀፍ አልጠበቅኩም ነበር።
👍251🥰1
ጥብቅ አድርጋ አቀፈችኝ። ጥብቅ ! አውቄያለሁ ሙና እየተለየችኝ ነው። ተነሳች .. ቦርሳዋን አነሳች ..
ቆም ብላ አይታኝ ወደ በሩ አመራች፤ ከፍታ ስትወጣ አላየኋትም።
እስከ ምሳ ሰዓት ከተቀመጥኩበት ሳልንቀሳቀስ ቁጭ ብዬ፣ ምንም ሳላስብ፣ ምንም ሳላይ ምንም ሆኜ ቆየሁ። የሆነ የመሬት ስበት የሌለበት ሕዋ ላይ እንደመንሳፈፍ ዓይነት ስሜት።
“ቻው ሙና” አልኩ ቁርስ ሰዓት ላይ የወጣችውን ልጅ ምሳ ሰዓት ላይ …. ቻው !
በሕዋ ላይ እየተንሳፈፍኩ ሥራ እሄዳለሁ፣ እመጣለሁ፤ እሄዳለሁ፣ እመጣለሁ … ከሙና ጋር ከተለያየን
2.3.45.67...
ወራት! “ግን ምክንያቱ ያለያይ ነበር እንዴ ?” እላለሁ አንዳንዴ። ሙና ቢያንስ የእኔ ችግር አለመሆኑን አውቃ፣ “እንዴት ሆንክ አይዞህ” አትለኝም እንዴ ? እላለሁ። ቅዳሜ ሁልጊዜ
የምትመጣ ይመስለኛል። ሁልጊዜ ከመኝታ ቤት ስወጣ ሳሎን ተቀምጣ የማገኛት ይመስለኛል። ሙና አለመደወሏ ይገርመኛል። ለድፍን ሰባት ወራት ስልኬ ሲጮህ ሙና እንደምትሆን እርግጠኛ ሆኜ አነሳው ነበር። ሙና ግን ተወችኝ !! (ተወችኝ ቃሉ እንዴት ያማል) ስልኳን ከሄደች ከሳምንቱ ጀምሮ እሞክር ነበር፤ አይሰራም ቁጥር ቀይራ ይሆናል።

ከሙና ጋር ከተለያየን ከዓመት ከምናምን በኋላ ሃኒባል እንዲህ አለኝ፣ “አብርሽ ከሌላ ሰው ሰምተህ ከምታዝን ራሴ ልንገርህ ብዬ ነው”

“ምንድን ነው”

ሙና ልታገባ ነው። ነገ እሁድ ነው ሰርጓ። አልደነገጥኩ፣ አልተከፋሁ፣ አልተደሰትኩ፣ አላዘንኩ !!
ድንዙዝ !!
እና ይሄ ምኑ ያሳዝናል” አልኩት ሃኒባልን።
( እ ? ሙና እኮ ነው ያልኩህ” አለ በግርምት እያየኝ።
“አይገርምም” ደገምኩለት ! የፍቅረኛ ሌላ ሰው ማግባት የመጨረሻው ጭካኔ የሚመስላቸው የመጨረሻ የዋህ ሰዎች አሉ። በፍቅር ውስጥ የመጨረሻው ህቅታ .. ጀርባን መስጠት ነው። ሙና ጀርባዋን ሰጥታኛለች። በእርግጥ እውነት አላት፤ ሙሉ ለሙሉ እኔ ችግር ውስጥ ነኝ። ሙና ደግሞ
ሰው ናት። ስለዚህ መሟዘዙ እድሜንም ስሜትንም ማባከን ነው፤ ደግ ሄደች ! እንኳንም ለቁም ነገር አበቃት። በቃ! ሙና ድል ባለ ሰርግ አገባች። የሰርጓ ቀን እዚህ ብሔራዊ መናፈሻ ውስጥ ተቀምጬ ዝም ብዬ ያንን የድንጋይ አንበሳ ሳየው ዋልኩ። “አንበሳው አንበሳ ባይመስልም የበላው ብር አንበሳ
ያስመስለዋል” አሉ አሉ ንጉሡ። ወንድነታችን ወንድ ባይሆንም ወንድ ለመምሰል ያቃጠልነው
ጊዜ ወንድ ያስመስለናል። ማሕበረሰቡ የከፈለልን የሞራልና የባሕል ዋጋ ወንድ ያደርገናል ... ቱ ! ቀፋፊ ቀን !! በሕይወት ውስጥ እንዲህ አፈር ድቤ በሚያስበላ ሽንፈት ያለህን ሁሉ ተነጥቀህ ባዶህን ሐውልት ሆነህ ሐውልት ፊት የምትቀመጥበት ጊዜ አለ። ያው ሐውልቱም የራሱ ታሪክ አለው፤ አገር የሚያውቀው። አንተም ታሪክ አለህ ማንም የማያውቀው፤ ብቻህን የሚያንገበግብህ። የእኔና የዚህ
የአንበሳ ሐውልት አንድነታችን ሁለታችንም የምንመስለውን አለመሆናችን ነው። እሱም አንበሳ፣ እኔም ወንድ አይደለሁም፤ መምሰል ብቻ።

አንዲት የሙና ጓደኛ አለች ሔዋን የምትባል። ከጥቁረቷ ብዛት የሙና ጥላ የምትመስል። ጀበና ሔዋን ጎን ቢቀመጥ ጠይም ይባላል። ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ የመሰለች። ድሮ እንኳን ብዙም አልቀርባትም ነበር፤ ከሙና ጋር ከተለያየን ጀምሮ ግን ሙና ስትናፍቀኝ አገኛታለሁ። እንዲሁ የጋራ ጉዳያችን ሙና ሆና።

“ሙና ደህና ነች ?” እላታለሁ።

“ደህና ነች”

“ፀሐይ ሲመታት ራሷን ያማት ነበር፤ አሁን እንዴት ነች ?”

“ደህና ናት ! ባሏ መኪና ገዝቶላታል፤ ፀሐይ የት ያገኛታል ብለህ ሃሃሃሃሃሃ

“ማንስትሬሽን ላይ ስትሆን በጣም ነበር የሚያማት አሁን እንዴት ሆና ይሆን ?”
አይ አብርሽ ! እሱማ ያው በየወሩ ነው አይቀየር ነገር፤ ስትወልድ ይተዋል ይባላል ባይ ዘ ዌይ
ሙና እርጉዝ ናት !” ልቤ ላይ የሆነ ነገር ሲሰካ ይሰማኛል። አገባች ሲባል ምንም ያልተሰማኝን፣ ልከ
እርምህን አውጣ ዓይነት መርዶ ይመስል ይሄንኛው አመመኝ፤ በጣም አመመኝ።

ከመቀሌ ወደዚህ ለመምጣት ቅያሬ ጠይቃ ነበር ተሳክቶላት ይሆን ?”

“ጠይቃ ነበር እንዴ ? እኔ ይሄንን አላወቅኩም ... አሁን ግን ሥራ አቁማለችኮ” አለችኝ በግርምት
(ምን አስገረማት)። በቃ ስለሙና ጥግብ እስከምል እጠይቃታለሁ፤ ሳትሰለች ታወራኛለች። መተንፈሻዬ
ሔዋን። በጣም ተቀራረብን፤ ቤቷ ሁሉ ወስዳኝ ቡና ታፈላልኛለች። መቼም መድረሻ ቢስ ሆኛለሁ።
ሙና ከሄደች በኋላ ለጎተተኝ የምጎተት ከርታታ ዘባተሎ ነገር ... የት ነበርክ ብባል እዚህ የማልል
የቱንም ያህል ጥብርር ያላችሁ ብትሆኑ፣ ሰው ለዓይኑ የሚናፍቃችሁ እንኳን ብትሆኑ፣ የሆነ ጊዜ አለ
እንደምናምንቴ የትም የምትገኙበት፣ ምነው በዛህ የምትባሉበት ...

አንድ ቀን ታዲያ ሔዋን ቤት ሄደን ከተደረደሩት ሲዲዎች አንዱ ላይ ዓይኔ አረፈ። የሙና የሰርግ
ቪዲዮ ! እንድትከፍትልኝ ሔዋንን ጠየቅኳት። አንገራግራ ተለምና በመከራ ከፈተችልኝ። ሙናዬ የኔ
ቆንጆ እንዴት ነው ያማረችው በእግዚአብሔር ! ባሏም ቆንጆ ኃብታም ነው። እንደኔ ኮሳሳ ሳይሆን የሆነ ግርማ ሞገስ ያለው፤ በጣም ነው የሚመጣጠኑት ! ቀናሁ፣ አደገኛ የበታችነት ስሜት ደቆሰኝ።
ቪዲዮውን እያየሁ ነው፤ ባሏ ለቤተዘመዱ ዲስኩር እያሰማ ሙና ከጎኑ ቆማ በእፍረት ትሽኮረመማለች
(ስትሽኮረመም ስታምር !)

እና የሙና ባል በኩራት እንዲህ አለ፣ (እጁን የሙና ትከሻ ላይ ጣል አድርጎ ... የእኔ ትከሻ ላይ እጁ
ያረፈ ያህል ከበደኝ)

ከሙና ጋር የዛሬ (ሦስት ዓመት) ፍቅር ስንጀምር፣ ለእኔ የከፈለችውን መስዋትነት ባትከፍል ኑሮ ለዚህቀን ባልበቃን ነበር። እኔ መቀሌ፣ እሷ አዲስ አበባ ሆነን((((ለእኔ ስትል ቅያሬ ጠይቃ መቀሌ ድረስ መጣች))))። የፍቅር ጀግና ናት ሙንዬ” ... ታዳሚው አጨበጨበ ቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿ
ቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿቿ

ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ አብርሾ ሞኙ ሰው አማኙ..እንደ እብድ ነው የሳቅኩት።
አስታወስኩ…አንድ ጊዜ መቀሌ ሄጄ የሙና ቤት አከራይ፣ “ደህና ዋልክ አክሊሉ” አሉኝ። ወደ እርሳቸው ስዞር፣ “የኔ ነገር ያንዱን ስም ከአንዱ ማጋጨት” ብለው ሳቁ። የሙና ባል አክሊሉ ነው ሥሙ!

ተቀበል አዝማሪ ...

ኧረ ሙና ሙና ሙና አቀበቲቱ፣
ስቃ ገደለችው ወንዱን ልጅ ሴቲቱ!
አሁን ሰሜን ደቡብ ምን ያሰኘዋል ሰው፣
አሁን ቆላ ደጋ ምን ያሰኘዋል ሰው፣
እንዴት ዞሮ ማያ አንገቱን ያጣል ሰው፣
እንዴት ማስተዋያ ዓይኑንስ ያጣል ሰው፣
ያጣል ሰው

ያጣል ሰው ሚሊየን ጊዜ እስከ ምፅዓት ድገመው!

አንድ ሰው አራት የሚሆንበት ምናይነት ዘመን መጣ ?! ይሄ የሰርግ ቪዲዮ አይደለም። ስምንተኛው ሺ በራችንን እያንኳኳ መሆኑን የሚያረዳ “ዶክመንተሪ” እንጂ !! ቱ ! አፈርኩ እግዚአብሔርን - አፈርኩ! ሐፍረቱ አሸማቀቀኝ። ቅናት ሳይሆን ሐፍረት ! የዛሬ ሦስት አመት ማለት እኮ ከሙና ጋር በፍቅር
ያበድንበት ጊዜ ነበር። አንዲት የባንክ ሰራተኛ ከመቀሌ አዲስ አበባ በአውሮፕላን ስትመላለስ ብሩ ከየት መጣ እንዴት አላልኩም ... ! አፈርኩ በራሴ ! አንዲት የባንክ ሰራተኛ የወርቅ ሃብል ገዝታ ስትሰጠኝ እንዴት ብሩ ከየት መጣ አልልም፣ ይሄው አንገቴ ላይ የለማዳ ውሻ ሰንሰለት መስሎ- ቱ! አንዲት የባንክ
ሰራተኛ ከአዲስ አበባ መቀሌ ተቀይራ ስትሄድ፣ “ምንም እቃ አላንዘፋዝፍም እዛው የሚያስፈልገኝን እገዛለሁ” ስትል፣ ቤቷ በውድ ዕቃዎች ተሞልቶ ስመለከት እንዴት?' አላልኩም ...
👍303😁2
ቱ! እኔ ደግሞ፣ “እንዳንተ የሚታገስ ወንድ አይቼ አላውቅም” ስትለኝ ካየችው ማወዳደሯን በምን አባቴ
ጠርጥሬ። ሰው ትንሽ እንኳን ምልክት ሳይታይበት ጣናን የሚያህል የፍቅር ሐይቅ ፍቅረኛው አፍንጫ
ስር ተደብቆ ይገድባል ? ኧረ ገረመኝ፤ ከምር ገረመኝ ! የሆነ ፀሐይ ወርዳ እዚህ አራት ኪሎ ላይ የተከሰከሰች ነገር መሰለኝ። ሙና የኔ ፍቅር ምንድነው ያደረግኳት .. እርሷኮ ነፍሴ ነበረች። አንድ ነፍስ
ለሁለት ወንድ ይካፈላል እንዴ። እሺ እኔ ያጎደልኩባት ነገር እንዲህ የበቀል ብትር የሚያሰነዝር ነበር ?
በቀል ይሁን ምናባቴ አውቃለሁ ? እንደው ምን እንደምለው ቸግሮኝ እንጂ ..

ሔዋን ቀስ ብላ መጥታ ጎኔ ተቀመጠች - ሔዋን የሙና ጓደኛ። እናም ትካሻዬ ላይ እጄን ጣል አድርጋ
እንዲህ አለች፣

አብርሽ በናትህ እንደሱ አትሁን” ዓይኗን አንከባለለችው። ያላት ውበት እሱ ብቻ ነው መቼም።

አንቺ ታውቂ ነበር ሙና ከእኔ ጋር ሆና ሌላ ወንድ ጋር ፍቅር እንደ ጀመረች ?”

በእውነት አላውቅም!እኔም ቪዲዮውን ሳየው ገርሞኛል”
ዓይኖቿ ተስለመለሙ። ሔዋን እጇ ትከሻዬ ላይ ነው። በጣም ተጠግታኛለች። እና ዝምታችን የሆነ ድባብ አለው። ሔዋን በጣም ተጠግታኛለች።
እንደውም አንዲት የቆመች ፀጉሯ በስሱ ጆሮዬን ስትነካኝ ተሰማኝ።
ምን ተፈጠረ ? ሔዋንን እያየኋት ወንድነቴ ነፍስ ሲዘራ ተሰማኝ። ማመን አልቻልኩም፤ ሱሪዬን
አውልቄ በዓይኔ ላየው ዳድቶኝ ነበር።ሔዋን ጎኔ ናት፤ እጄን አንስቼ ትከሻዋ ላይ አሳረፍኩት፤ ጠጋ
አለች እና እንዳቅፋት ተመቻቸችልኝ። እንደውም ራሷን ትከሻዬ ላይ ዘንበል አደረገችው። ወንድነቴ ዘራፍ ማለቱ እውን ሆነ።

ለሃኒባል ደውሉና ቆመ በሉልኝ !! አብሮኝ ተንከራትቷል። ቋሚ ይቆም ዘንድ አብሮኝ በችግሬ ለቆመ ቁም ነገረኛ ወዳጄ እመብርሃን በችግርህ ከጎንህ ትቁም በሉልኝ!ሙና ግን መንፈሷ የተኮላሸ ሴት ናት።
ልከስክስ !! መቶ ዓመት ለማይኖርባት ምድር ረክሶ ተልከስክሶ እና አስመስሎ መኖር ክብር መስሏት ቆይ ዘላለም ላይ እንገናኝ የለ!
፡፡፡፡፡፡፡፡።፡
የሔዋን መኝታ ቤት እንዴት ሰፊ ነው ? ሔዋን ደረቴ ላይ በእርካታ ተኝታ እንዲህ አለችኝ፣ “አንተ
የሚወራው ሁሉ ውሸት ነው ማለት ነው ...ውይ የሰው ወሬ"

"ምን ተወራ"

" እንትን አይችልም እየተባለ ነዋ የሚወራው”

“ማነው ያለው” አልኩ ታሪኬን ሐሰት ልል እየተንደረደርኩ።"

“የድሮ ሚስትህ ነቻ” ሙንዬ፣ ሙኒት፣ ሙንሻ የምትላት ጓደኛዋን “የድሮ ሚስትህ” ስትል አይቀፋትም ?

“ባክሽ እሷን ተያት” እቅፍ እቅፍቅፍ … እቅፍፍቅፍቅፍ !! ያልታቀፈበት ዘመናችንን ቀይ የሙና ገላ በጥቁር የሔዋን ገላ መቀያየሩ አልጋ ላይ የተዘረፈ ቅኔ ነገር ነው ... ይነጋል ይመሻል እንደማለት !

“አንተ አፈ ን ከ ኝ ሂሂሂ” ሔዋን የሙናን ፍቅረኛ በፍቅር አሸንፋ ራሷን የድል ማማ ላይ አስቀምጣ
ተፍነሽንሻለች። የሙና ባል እኔን አሸንፎ፣ሙናም እኔን አታልላ በብልጠት አልፋኝ እንደሄደች ሳይሰማት አልቀረም። እኔም ደስ አላለኝ አልከፋኝ፤ እንደው ደርበብ ባለ አብሮነት ዝምታን መረጥኩ። ለምን ደስ ይለኛል? ማፍቀር ተኮላሽቶ ወንድነት ስለቆመ? እንዲህ ዓይነቱን ደነዝ ወንድ የሚያመርተው፣ ደነዝ ክህደት ... ለሙና ሆነ!! መቼም ቢሆን አፉ አልላትም፤ ምክንያቱም አፈቅራታለሁ።


አለቀ
👍33👏3👎2
አትሮኖስ pinned «#ቀስ_ብሎ_ይቆማል ፡ ፡ #ስምንት (የመጨረሻ) ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ...“ቆይ አብርሸ ምንድን ነው … ማለቴ…ተወው በቃ” ግራ ተጋባች። እናም እንዲህ አለችኝ፣ ችግር የለውም እንዳታስብ፣ ምንም ነገር እንዳታስብ !” ስትናገር ዓይኔን ማየት ፈርታ ነበር።እጆቿ እነዛ ቆንጆ ጣቶቿ በሆነ ፍርሃት ሲንቀጠቀጡ ይታዩኛል። ብርድ ልብሱን ከጎኔ ገልባ ሸርተት ብላ ገባች። ወዲያው ተመልሳ ተነሳችና የሌሊት…»