አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ነው የሆንኩት ? ሙናን በቀስታ ገፉ አደረግኳት። ከሆነ ከሰጠምኩበት ውኃ ውስጥ አውጥታ አየር በአፌ የምትስጠኝ እንጂ ምኑም ምኑም ስሜት የሚሰጥ ጕዳይ ሆኖ አልታይህ አለኝ።

“ምን ሆንክ?” አለችኝ።

“ምን ሆንኩ መልሼ ጠየቅኳት። ሳላስበው ኮስተር ብዬ ነበር። በቀስታ እጇን ልካ በለስለሳ መዳፏ
ጉንጬን ዳሰሰችኝ። ከአንገቴ ዘንበል በማለት እጇን ሸሸሁት። ግራ በመጋባት ስትመለከተኝ ቆየች ቅዝቅዝ ብላ በጀርባዋ ከጎኔ ተኛች። ከዛም እጅግ በጣም ከሚያስፈራ፤ ከሩቅ የሚመጣ በሚመስል ድምፅ ደስ አላልኩህም ?” አለችኝ። ዝም !አንድ የገባኝ ነገር ሙናን መጕዳት እንደሌለብኝ ነበር። ግን በዛ ቅፅበት እንኳን እሷን ላፅናናት ራሴም የሆነው ነገር ግራ ገብቶኛል። እንደምንም ብዬ፣ "ሙና ሶ…ሪ የሆነ ሐሳብ ውስጤ ገብቶ ነው ... አፈቅርሻለሁ፣ ልጎዳሽ አፈልግም። ፈራሁ
... ይህ ነገር የመጀመሪያ ነው . የሆነ ነገር እንዳትሆኝብኝ ፈራሁ…" ቀበጣጠርኩ። ሙና ቀስ ብላ ወደኔ ዞረችና፣

እኔም ነቅቼብኃለሁ” ብላ በሳቅ ፈረሰች። ሳቋ እብደት ይመስል ነበር። ከፍርሃት እና ካሰበችው መገፋት መትረፍ ደስታ የተሸከመ ሳቅ። ጠጋ አለችና አቀፈችኝ። ጡቶቿ ለብቻቸው አቀፉኝ፣ ከንፈሯ ከንፈሬ ላይ ነው። ዓይኖቼን ከድኜ፣ “ሙና ልብሶቿን አውልቃ ራቁቷን እኔ ቤት እኔ አልጋ ላይ ነን” አልኩት ራሴን፤ ምን ዋጋ አለው - ቅዝቅዝ ! ለምን ? … እንጃባቴ !! ገጣሚ ወዳጄ፡ “የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ የሚያሳቅቅ ነገር የለም…” የሚል ግጥሙ ትዝ አለኝ። እንዲህ የቀጠሩት ወንድነት ከራስ ቀጠሮ ሲቀር ሲያይ ምን ብሉ ይገጥም ይሆን ?ከሙና አብረን አደርን፤ ምንም ነገር የለም። ጠዋት ላይ ሙናን እንዲህ አልኳት፣

“ለምን ከጋብቻ በኋላ አናደርገውም ?

“አህ ሃኒ እንዳንተ ስሜቱን የሚቆጣጠር ወንድ በማግኝቴ እድለኛ ነኝ! መቼም ቢሆን በፈለግከበት ሰዓት ያንተነኝ” አይገርምም? ሙና እስካሁንም ነገሩንማድረግ የማልችል ልፍስፍስ መሆኔ አልገባትም። ጭራሽ ከዓለም ወንዶች ሁሉ አንደኛ ታጋሽ አድርጋኝ ቁጭ አለች!ግዴላችሁም ሴቶች አዕምሮ ውስጥ የተጫነው መዝገበ ቃላትና የወንዶቹ የሆነ ልዩነት አለው፡ ከሙና ጋር ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ቤት እንውልበታለን ባልናት ቅዳሜ ከተማውን ስናካለል ዋልን። የምትወዳቸውን ኬክ ቤቶች ስንጎበኝ። ሙና ከሚገባው በላይ ለእኔ ያላት ፍቅር ጨምሮ ነበር።
ታጋሽ ወንድ አግኝታ ሞታ!ጠንጋራ መገምገሚያ ፍቅርን ያጠናግረዋል እንደው መንገድ ላይ ሁሉ ብትስመኝ ደስታዋ።ጮክ ብላ የታጋሽነቴን፣ ራስ የመግዛት ብቃቴን ልክ ለሕዝቡ ብታውጅ ደስታዋ።

ከዛን ጊዜ ጀምሮ ቅዳሜና እሁድ አዳሯእኔ ቤት ሆነ - ወይ ፍንክች! ልቤና ሰውነቴ ተለያዩ። ልቤ ሙናን
በሴትነቷ ይመኛታል፤ ሳላቋርጥ ሚሊዮን ጊዜ እስማታለሁ፣ ትኩሳቴን ከመጨመር ውጭ ምን ዋጋ አለው ! ሲቆይ መሳሳሙም እያስፈራኝ መጣ፡፡ የውቦች ውብ የሆነች፣ ስንቱ የሚቋምጥላት ልጅ ቤት አልጋዬ ላይ፣ አንሶላዪ ውስጥ፣ ደረቴ ላይ ኦስቀምጬ ከምዝቀዝ በላይ ምን መርገምት አለ። ብሽቅ!ት! አልኩት ራሴን። የባሰው ነገር ሳይቆይ ተከሰተ፡ ሙና ከቀን ወደ ቀን የእኔን ጥያቄ የራሷ አደረጎችው! ትክክክክክክ ብላ ስታየኝ ከጋብቻ በኋላ.....

ይቀጥላል
👍16
#ትኩሳት


#ክፍል_አንድ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


ስብሃት ለትምህርት ወደ ፈረንሳይ በተላከበት ጊዜ ከጓደኞቹ ጋር በፓሪስ ያሳለፈውን ጊዜ የሚተርክ። በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ከኢትዮጵያ ባህልና ስርአት ወጣ ያለ ልቦለድ ነው በርግጥ ከላይ ከላይ ለሚያነበው ከወሲብ ቀስቃሽ መፅሀፍነት ላይዘል ይችላል ነገር ግን በማስተዋል ብናነበው የብዙ ነገር ትኩሳቶች ያነሳልና ስናነብ በጥሞና ይሁን ያው ሁሉንም ይመቻል ተብሎ አይጠበቅምና ከዚህ ውጪ ወደ ላይ ብዙ ድርሰቶች አሉና ያላነበባችሁ ከሆነ እስከዚያው በነሱ አሳልፉ። አሁን ወደ #ትኩሳት እንሂድ።👇
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ከውብ ሰማይ በታች

ባህራም
ከሩቅ

ይሄ ሁሉ የሆነውና የተደረገው ኤክስ ውስጥ ነበር.....
ኤክስ (ኤክስ-አን-ፕሮቫንስ) በፈረንሳይ ደቡብ ከማርሴይ አጠገብ የምትገኝ ትንሽ የዩኒቨርሲቲ ከተማ ናት፡ ህዝቧ ግማሽ በግማሽ ተማሪ ነው
የኤክስ ሰማይ አብዛኛውን ጊዜ ብሩህ ሰማያዊ ነው፡ አንዳንድ
ጊዜ ውሀ አረንጓዴ ይሆናል፣ ወደ ማታ ላይ እንደ ልጃገረዶቹ
ጉንጭ ይቀላል።

የኤክስ አየር ጠባይ የተመሰገነ በመሆኑ፣ ሀብታም በሽተኞችና
ሽማግሌዎች በሐኪም ምክር ወደ ኤክስ መጥተው ይኖራሉ፡፡ ስለዚህ
«ኩር ሚራቦ» የተባለው የኤክስ ዋና ጎዳና ላይ ሽማግሌዎች፣
አሮጊቶችና ባለሻኛዎች
እግራቸው ረዣዥም ቀጫጭን የሆነ፣የተነፋ ደረታቸው ውስጥ አንገታቸው የተቀበረ ባለሻኛ ሰዎች በቀስተኛ እርምጃቸው ሲዘዋወሩ ይታዩበታል። ባቡር መንገድ ዳር የተደረደሩት አግድም ወምበሮች ላይ የአሮጊትና የሽማግሌ መአት ቁጭ ብሎ ሹራብ እየሰራ ወይም ጋዜጣ እያነበበ ፀሀይ ይሞቃል፡
ወይም ዝም ብሎ ባዶ ብርጭቆ መሳይ ፈዛዛ አይኑን አተኩሮ (ምን
ያይ ይሆን?) ከንፈሩን ያለማቋረጥ ያንቀሳቅሳል (ምን ይል ይሆን?)

በጣም ይቀፋሉ የፈረንጅ ሽማግሌዎችና አሮጊቶች። ጨምጻዳ ቆዳቸው የተሰነጣጠቀ ደረቅ ሰም ይመስላል። ቀጥቃጣዎች::ዝምተኞች። አገጫቸው ተገንጥሎ ወደታች የወደቀ፣ ከንፈራቸው
የተንጠለጠለ፣ ጥርሳቸው የፈራረሰ ሽማግሌዎች፡፡ ጥርሳቸው አልቆ አፋቸው ወደ ውስጥ የጎደጎደ ፂማም አሮጊቶች፡፡ የመኖር ጊዜያቸው
አልፎ፤ የሞት ጊዜያቸውን ዘመናዊ ህክምና ከልክሏቸው፤ ታችኛው
ከንፈራቸውን እንደ ጡጦ እየጠቡ ሞትን ሲጠብቁ ሚውሉ
የህይወት ኦናዎች። ዝምተኞች፡፡ ለአይን ብቻ ሳይሆን ላፍንጫም
ይቀፋሉ፡፡ የልዩ ልዩ መድሀኒት፣ የእርጅና፣ የሞት ሽታ
ሳይቀበር መግማት የጀመረ ስጋ

ደሞ መብዛታቸው ከተማሪው እኩል ሳይሆኑ ይቀራሉ? ማታ
መቸስ ፀህይዋ ሙቀቷን ይዛ ስትሄድ ወደየአልጋቸው ይከተታሉ።
ቀን ግን የትም ይገኛሉ፣ ኤክስን ይወሯታል። ኩር ሚራ ግዛታቸው ነው፡ ዩኒቨርሲቲው አጠገብ ያለው መናፈሻ ቤት መንግስታቸው ነው! ካፌዎቹ ቅኝ ሀገራቸው ናቸው። ቀን ሲኒማ የገባህ እንደሆነህ በጭለማው ሳይታወቅህ፣ ሳይተኛ ከሚያንኰራፉ ሽማግሌ፣ ወይም በየሶስት ሰከንዱ አክ!» ከምትል አሮጊት አጠገብ ትቀመጣለህ. . .

ደግነቱ ይሄ ታሪክ ስለአሮጊቶችና ስለሽማግሌዎች አይደለም።
ስለኛ ስለወጣቶቹ ነው፤ ስለባህራም፣ ስለኒኮል፣ ስለሲልቪ ስለሉልሰገድ፣ ስለሌሎችም ወጣቶች ....

ጥሩ ነው ወጣት መሆን። ገንዘብ ባይኖርህም ጤና ይኖርሀል፡ መልክ ባይኖርህም አንጎል
ይኖርሀል! እውቀት ባይኖርህም ጉራ ይኖርሀል፡ ፍቅር ባይኖርህም
ተስፋ ይኖርሀል፤ ደስታ ባይኖርህም ንዴት ይኖርሀል መጨቆን ቢበዛብህ ሪቮሉሽን ታነሳለህ. .. መኖር ቢያስጠላህ ወይም ቢያቅትህ ራስህን ትገድላለህ....ሰው ባያውቀውም ቅሉ ታሪክ ይኖርሀል፤ወጣት ነህና

የኤክስ የበጋ ሙቀት እየከበደኝ አላስራ ስለሚለኝ የከሰአት
በኋላውን ተኝቼ ውልና ሌሊት ስሰራ ለማደር 'ሞክራለሁ።
አንዳንድ ሌሊት ስራው እምቢ ሲለኝ፣ ከሆቴሌ ወጥቼ በእግሬ
እዘዋወራው ደስ ይለኛል በሌሊቱ ኤክስን መዞር፡፡ ትንሽ ከተማ
ስለሆነች ሰባት ሰአት ሲደርስ ሁሉ ነገር ተዘግቷል (ከካፌ «ሰንትራ»
እና ከላ ፓሌት ናይት ክለብ በቀር) በቀን ጠባቦቹን መንገዶች
የሚያስጨንቃቸው ህዝብ በሙሉ ተኝቷል፡ እነዚያ የሚያስፈሩኝ፣ መምጫቸው የማይታወቅ እብድ ፈረንሳይ ነጂዎች
በየአልጋቸው ተከተዋል! ኤክስ-አን-ፕሮቫንስ ሰላም ነው፡፡ ቤቶቹ ሁሉ ጨልመው፣ የመንገድ መብራት በርቶ፣ በፀጥታው የጫማዬን ድምፅ ብቻ እየሰማሁ ስራመድ፣ ባዶ ከተማ ውስጥ እንዳለሁ ሆኖ ይሰማኛል። አልፎ አልፎ በየአደባባዩ የሚገኙት ሰው ሰራሽ ምንጮች ወደ ኮከቦቹ በኩል እየዘለሉ ከሌሊቱ ጋር ይንሾካሾካሉ

አንድ ሌሊት ወደ ስምንት ሰአት ላይ አንዱን መንገድ ይዤ
ስራመድ ቆይቼ ወደ ግራ በኩል ስታጠፍ፣ ከፊቴ አራት የሚታገሉ
ፈረንጆች ድንገት ብቅ አሉ። ብቅ ያልኩትስ እኔ ነበርኩ፣ ግን እነሱ
ብቅ ያሉብኝ መሰለኝ፡፡ በበጋው ሙቀት ምክንያት አራቱም በሽሚዝ ናቸው፣ ይታገላሉ። በሌሊቱ ፀጥታ ጫማዎቻቸው ከአስፋልቱ ጋር ሲፋተጉና ትንፋሻቸው ሲቆራረጥ ይሰማል። ለጊዜው ማን ከማን ጋር
እንደሚታገል ለማወቅ አልቻልኩም። ዝም ብዬ ስመለከት፣ ሶስት ግዙፍ ሰዎች አንዱን ደቃቃ ብጤ ገጥመውት ኖሮ፣ ከጥቂት ትግል በኋላ ሁለቱ በቀኝና በግራ በኩል ያዙት። ሶስተኛው ከፊቱ ቆመ::
ሁሉም ቁና ቁና ይተነፍሳሉ፡፡ ደቃቃው ሰውዬ ይፍጨረጨራል፣
ግን ድምፅ አያሰማም፡፡ ለምን ኡ ኡ እንደማይል እንጃለት

ከፊት የቆመው ግዙፍ አንዴ በጥፊ መታውና፣ ዘወር ብሎ አጠገባቸው ካለው ግድግዳ ስር አንድ ትንሽ ነገር አንስቶ መጥቶ፣ በዚህ
በጨበጠው ነገር የትንሹን ሰውዬ ግምባር ፈተገው። ትንሹ ሰውዬ
ተፋበት። ግዙፉ በሹክሹክታ እየተሳደበ ወይም እየተራገመ ከሱሪ ኪሱ መሀረብ አውጥቶ ፊቱን ጠረገና ሲያበቃ፣ ደቃቃውን አንድ ቃሪያ ጥፊ አላሰው፡፡ ጥፊው ጧ ሲል ቀሰቀሰኝ፣ ገና አሁን ከመፍዘዜ ነቃሁ። ዘወር ስል፣ አጠገቤ ለመንገድ መጠገኛ ይሁን ለቤት ማስሪያ የተከመረ ኮረት አየሁ። በፍጥነት አንድ ሰባት ከባድ ጠጠር አነሳሁና
እያነጣጠርኩ ሰዎቹ ላይ መወርወር ጀመርኩ (ስወረውር የሀበሻ ነገር!» የሚል ሀሳብ በሀይል አሳቀኝ) ከት ከት ብዬ እየሳቅኩ የወረወርኩት ድንጋይ (ሶስተኛዋ) በጥፊ ተማቺውን ሰውዬ ደረቱን ደለቀችው፣ አራተኛዋ የአንዱን ትክሻ መታች። ድንጋዩና ሳቁ አስደንግጧቸው፣ ትንሹን ሰውዬ ለቀቁትና ተፈተለኩ፡፡ ለምራቂ ያህል እጄ ውስጥ የቀሩትን ድንጋዮች ወረወርኩባቸው። በድንጋዮቼ
ሸኚነት ጥቂት እንደሮጡ ወደ ቀኝ በኩል ታጠፉ፣ ጠፉ።

ሳቄም ድንገት ጠፋ። የፍርሀት ሳቅ ኖሯል። አጠገባችን ምንጭ
ሰማሁ። ገና አሁን ሰማሁት! ለካስ «ፕላስ ዴ ካትር ዶፈን» እተባለው
አደባባይ ውስጥ ነን

ትንሹ ሰውዬ ግራ ገብቶት መንገዱ ጋር ቆሞ አኔን ያየኛል
እጄን እያራከፍኩ ወደሱ ሄድኩ።
ይህን ያህልም ደቃቃ አደለም ከኔ ትንሽ ተለቅ ይላል። ደቃቃ የመሰለኝ ጠላቶቹ በጣም ግዙፍ ስለነበሩ መሆን አለበት።

«Bon soir» አልኩት (ቦን ሷር)
«Bon soir! አንተ ነህ እንዴ? ሀለላሲ ሙት!» አለኝ እየሳቀ

ባህራም ነው፡፡ ከዚህ በፊት ከሀበሾቹ ጋር ብዙ ጊዜ
አይቼዋለሁ። ግን ያን ጊዜ ያገሬን ልጆች በብዙ ስለማልጠጋቸው፣
ይህን ባህራም ተዋውቄው ወይም አናግሬው አላውቅም ነበር።

ድምፁ ወፍራም ሆኖ ለጆሮ ደስ ይላል ፈረንሳይኛው የፈረንሳዮቹ አይደለም፣ መልኩ ግን ትንሽ የደቡብ ፈረንሳዮችን ይመስላል። ፊቱ እንደ ፈረንጅ ነጭ ሳይሆን፡ ፀጉሩ በጣም ጥቁር ነው:: «ሀለሰላሴ ሙት!» ያለኝ ሀበሻ መሆኔን ስላወቀ ነው።
አብሯቸው የሚሄድ ሀበሾች ብዙ ጊዜ ሀይለስላሴ ይሙት!» ሲሉ
ሰምቷል
👍371
«ሀበሻ መሆኔን እንዴት አወቅክ?» አልኩት

«ኧረ ስምህንም አውቀዋለሁ። ከነተመስገን ከነሉልሰገድ ጋር
ነው ምውለው:: ከፈረንሳይ ህግ ጋር ስንዳረቅ እንውላለን። ከሩቅ
ብዙ ጊዜ አይቼሀለው»

«ይሄ ምንድነው?» አልኩት። ግምባሩ ላይ በከሰል «ር»
የሚመስል ፊደል በጥቁር ተጭሮበታል። የተጫረበት ቦታ ግምባሩ በጣም ቀልቷል

«አሁን ነው የፃፉብኝ፡፡ ቆይ ስቲ» አለና ከኋላ ኪሱ ቦርሳ አውጥቶ፣ እዚያ ውስጥ ባለችው ትንሽ መስተዋት ፊቱን አየ፡፡ ሳቀ፡፡
ከኪሱ መሀረብ አውጥቶ ከሰሉን ከግምባሩ እየጠረገ «ይሄ ፊደል «C» (ሲ) ነው:: ኮሙኒስት ማለት ነው» አለኝ ፈረንሳይኛው ብዙ
የሰዋሰው ስህተት አለበት

«ኮሙኒስት ነህ ማለት ነው?» ስለው፣ መሀረቡንና ቦርሳውን
መልሶ ኪሱ እየከተተ፣

«ሀለሳሴ ሙት! ለራስህ ተመልከት» አለና ወደ ግድግዳው
ጠነቆለ። ግራጫው ግድግዳ ላይ በትልቁ (ከሩቅ እንዲታይ) በከሰል
የተፃፈ ይነበባል

Vive Ho Chi Minh!
Vive le Peuple Viet Namien!
A bas l' imperialisme Americain!
Yankee go home!
(ሆ ቺ ሚን ለዘላለም ይኑር!
የቪየትናም ህዝብ ለዘላለም ይኑር!
የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም ይውደም!
ያንኪ አገርህ ግባ!)
«ይህን ስትፅፍ አግኝተውህ ነው እነዛ ሰዎች ሊደበድቡህ
የፈለጉት?»
«ሰዎች አይደሉም፡፡ አሜሪካኖች ናቸው» አለኝ
እየሳቅኩ «በል እንሂድ ከዚህ ሳይመለሱ» አልኩት
«አትስጋ። አይመለሱም፡፡ ፈሪዎች ናቸው»
ይህን ጊዜ ከበላያችን ከሶስተኛው ፎቅ አንድ መስኮት ተከፈተና፣ ጆሮ 'ሚበሳ የሴት ድምፅ

«Laissez nous dormir non?» (እንተኛበት!)

Pardon madame on slen Va» አላት (ይቅርታ እሜቴ፣
መሄዳችን ነው)

«Si lon ne peut pas dormir chez soi, alors... » እያለች
እያጉረመረመች መስኮቷን ዘጋች («በገዛ ቤታችን ውስጥ መተኛት
ካልቻልንማ. . .»)

«ኦ! እንሂድ ከዚህ» አለኝና ወደ ኩር ሚራቦ በኩል መራመድ
ጀመርን። በጥፊ የተመታ ፊቱን እያሸ

«ፈረንሳዮችም ጨቅጫቃ ናቸው፧ አሜሪካኖችም ቂል ናቸው::
ሰው ማለት የኢትዮጵያ ሰውና የኢራን ሰው ነው!» አለኝ፡፡ ቀልደኛ
ነው።

«የኢራን ሰው ነህ ማለት ነው?» አልኩ
«ነኝ»
«የኡመር ካያም ያገር ልጅ ነህ!»
«ነኝ»
«የሱን ግጥሞች በቃል ታውቃቸዋለህ?»
««ሁሉንም አላውቃቸውም»
«የምታውቀውን በልልኝ ስቲ። እኔ ያነበብኩት በንግሊዝኛ
ተተርጉሞ ነው፡፡ እሱ ራሱ የፃፈውን በጆሮዬ መስማት ፈልጋለሁ»

አለልኝ። በጣም ደስ ይላል። ቋንቋው «ሹ» እና «ተ»
ይበዛበታል። ደሞ የሰውየው ድምፅ ወፍራምና ልዝብ ሆኖ፣ ኡመር ካያምን ራሱን የሰማሁት መሰለኝ፡፡ ድገምልኝ ኣልኩት፡፡ ደገመልኝ።ሌሎችንም በቃሉ ወጣልኝ

«ከሳዲ፣ ከሩሚ፣ ከፊርዶዜ በልልኝ ስቲ» አልኩት

«እነሱንም ታውቃቸዋለህ?» አለኝ
«የለም፣ ስማቸውን ብቻ ነው:: ባገራችሁ ከኡመር ካያም
እንደሚልቁ አውቃለሁ፣ ግን ተተርጉመው ደስ አይሉም፡፡ ስለዚህ አላነባቸውም፡፡ በልልኝ» አልኩት

አለልኝ እየተረጎመ
ኩር ሚራቦ ስንደርስ «ስለደረስክልኝ ያላመሰገንኩህ»
አቋረጥኩት «ለመሆኑ፣ ሰው እንዲደርስልህ ለምን አልጮህ
ክም?» አልኩት
«አስበው እንጂ » አለኝ «እንዴት አንድ ኢራናዊ ሶስት
አሜሪካኖች ያዙኝ ብሎ ይጮሀል?» ሁለታችንም ሳቅን «ደሞ ፈረንሳዮችን ታውቃቸዋለህ፡፡ ስለምንም ነገር «je men fous!» ነው።
ሰማዩ እስኪሰነጠቅ ብጮህም ማንም አይደርስልኝም፡፡ ለመሆኑ፣
አንተ ወዲሀ ሰፈር ምን ልታደርግ በዚህ ሰአት መጣህ?»

«የካርል ማርክስ ወይም የሌኒን መንፈስ ወዲህ መርቶኝ
ይሆናላ!» ሳቀ። ሳቁ ደስ ይላል፣ ተላላፊ ነው

«አሁን ሳስበው ጊዜ ደነገጥኩ» አለኝ
«ምኑን?»
«እነሱን ስተህ በድንጋይ እኔን አንክተኸኝ ቢሆንስ?»
«አታስብ፡፡ ሀበሻ ድንጋይ ወርውሮ አይስትም። አፍሪካውያን
እንደ መሆናችን መጠን፣ ገና ድንጋይ ዘመን ውስጥ ነው ያለነው።
ጦርነት ስንዘምትም በድንጋይ ነው»

እየሳቀ «እንደኛ ናችኋ እኛ ግን ገና ድንጋይ ዘመንም አልደረስንም»

«የት ዘመን ናችሁ?»

«ጥርስና ጥፍር ዘመን! እንደ ነብር ሀኝ!»

ስንስቅ ለመሆኑ ጣልያንን በምኒልክ ጊዜ ድል ያደረጋችሁት
በዱላና በድንጋይ ብቻ ነበራ?» አለኝ
«እና በመልካችን አስፈሪነት፣ እና በሽለላችን!»
«ታዲያ ትንሽ ሽለላ አታስተምሩንም? አሜሪካኖቹን
እንድናስወጣበት»

«የሚገዛችሁ የናንተው ሺህ መስሎኝ»

«ነው፤ ግን ሻህ የአሜሪካኖቹ አሽከር ነው»

«እንዴት አባህን!? የነፊርዶዚ፣ የነኡመር ካያም አጥንት
አይቆረቁራችሁም? የዛራቱስትራ መንፈስ አይቀየማችሁም?»

«እሱ ነውኮ ሚገርምህ» አለኝ፡፡ በምር ድምፅ «ግን ታያለህ።
ኢራን ንደገና የነፃነት አገር ምትሆንበት ጊዜ ይመጣል» አለኝ
«ብቻ እሱን ለጊዜው እንተወውና 'ሰንትራ' እንሂድ፣ ቢራ
ልግዛልህ»

«ጥሩ»
«ረስቼ። ስሜ ባህራም ይባላል። ባህራም አፍሻር»
«Enchante» አልኩትና ተጨባበጥን፡፡ ሳቅን፡፡ እኔም ስሜን ነገርኩት። ካፌ ሰንትራ ገብተን ቢራ እየጠጣን ትንሽ ፖለቲካ እያወራን ከሳቅን በኋላ ስንለያይ

«Vive lage de pierre!» አለኝ («የድንጋይ ዘመን ለዘላለም
ይኑር!»)
«Pour chasser les Yankees» («ያንኪዎቹን ለማባረር»)
«ሀለላሴ ሙት!» አለ
ተለይቼው ስሄድ ሳቁ ተከተለኝ

በነጋታው ማታ ተመስገንን ሲኒማ አገኘሁትና ቢራ ልጋብዝህ
ብዬ ካፌ ወሰድኩት፡፡ ግዙፍ ብጤ ጠይም ልጅ ነው፣ አይኖቹ
ትንንሽ ናቸው፡፡ ስላየነው ፊልምና ስለሌሎች ስለፈረንሳዮች፣ ስለአገራችን፣ ስለሴቶች ስናወራ ከቆየን በኋላ፣ ጨዋታውን ቀስ አድርጌ ወደ ባህራም መራሁት። እንዴት ያለ ሰው ነው? አልኩት

«ለማወቅ የማይቻል ሰው ነው» አለኝ «ያወራል፣ ይለፈልፋል።
ግን በልቡ ውስጥ ምን እንደሚያስብ በእውነት ለመገመት
አይቻልም፡፡ የሚያወራውን ወሬ ብትሰማ በጭራሽ ብልጥ
አይመስልህም፣ እንዲያውም ወደ የዋህነት ይወስደዋል። ግን ደሞ
ባንድ በኩል ስትመለከተው ብልጥ መሆን አለበት»

«እንዴት?»
የተመስገን ትንንሽ አይኖች የባሰውን አነሱና እንደማብራት
አሉ፡፡ ሳቅ ማለቱ ነው። ሲጋራውን እየኮሰተረ

«አኛ በወር ስድስት መቶ ፍራንክ እናገኛለን» አለኝ ባህራም
እስኮላርሺፕ የለውም፣ በቤተሰቦቹ ገንዘብ ነው የመጣው:: ግን ቤተሰቦቹ ሳንቲም ከላኩለት ይኸው ስድስት ወር አለፈ፡፡ ምን እንደነካቸው አይታወቅም፡፡ ታዲያ እሱ ሳንቲም ሳያገኝ፣ እኛ በወር 600 ፍራንክ እየበላን፣ ከኛ እኩል ካፌ እየገባ ይወጣል፤ ከኛ እኩል ሲኒማ ይገባል፣ ከኛ እኩል ፓርቲ እየመጣ ይደንሳል፣ ሴት ያሳድዳል።

«በፊት ያስቀመጠው ገንዘብ እንዳለው?»
«በጭራሽ ገንዘብ ማስቀመጥ : ሚችል ሰው አይደለም»
«ታዲያ ገንዘብ ከየት ያመጣል?»
ተመስገን ጠይም ፊት ላይ የማፈርና የመሳቅ ፈግታ መጥቶ
አይኖቹን ሽፈናቸው

«እኔ ያበደርኩት እስካሁን ከ200 ፍራንክ በላይ ይሆናል።
ሉልሰገድ አንድ መቶ ሃምሳ ያህል አበድሮታል። ሌሎችም ሀበሾች
እንደያቅማቸው አዋጥተዋል። ተካ ግን ከሰላሳ ፍራንክ በላይ
አልገብርም አለ»
👍23😁4
«ምነው እለ?»
«ምን መጣብኝና ለማንም አቃጣሪ አረብ እገብራለሁ? አለ»
ለምን አቃጣሪ ይለዋል?»
«ከሴቶች ጋር ያየዋል። ደሞ ቤተሰቦቹ ገንዘብ ሳይልኩለት ከኛ
እኩል ይኖራል። ስለዚህ አቃጣሪ መሆን አለበት»
«ሌላ ማስረጃ ሊኖር አይችልም?»
«ቢኖርስ? ተካን እንዴት ልታስረዳው ትችላለህ? አቃጣሪ አረብ ነው ካለ አቃጣሪ አረብ ነው ማለት ነው። በቃ፡፡ ተው አረብ
አይደለም የኢራን ሰው ነው ብንለው 'ንኳ፣ አረብ ነው ብሎ ድርቅ አለ

«አንተስ አቃጣሪ ይመስልሀል?»
«አይመስለኝም። ግን እኛ ያበደርነው እንድ አራት መቶ
ፍራንክ፣ እንኳን ለስድስት ወር ላንድ ወር አይበቃውም፡፡
ይመስለኛል፣ ሴቶቹ በብዙ ያግዙታል። ለምሳሌ የምግብ ቲኬቱን የምትችልለት ኒኮል ነች»

«ኒኮል?»

«አንዲት አጠር ያለች፣ ጥርሷ እንደ አይጥ የተዘረዘረ፣ ፀጉሯ
አቧራ የተነሰነሰበት ሚመስል አለች፣ እሷ ናት፡፡ ደሞ በወር ዘጠና
ፍራንክ የተከራየው ቤት አለው:: ባለቤትየው ስድስት ወር ሙሉ
ዝም 'ሚለው አይመስለኝም። ታድያ ኪራዩን ከየት አምጥቶ
ይከፍላል? ሴቶቹ ይከፍሉለት ይሆናል ብዬ አስባለሁ»

«ማን? ኒኮል?»

«ወይ ኒኮል፣ ወይ ሌላ። መእት ሴቶች አሉት። ምኑ እንደሆኑ
እንጃ፡፡ ብቻ ምን ልበልህ፣ ስለባህራም ለማወቅ አይቻልም።»

ሌሎቹንም ሀበሾች ስለባህራም ብጠይቃቸው በሌላ አነጋገር
ይህንኑ ደገሙልኝ

ተካ ስለባህራም ነግሮኝ ሲጨርስ፣ ጥፍሮቹን እየነከሰ «ገንዘብ እንዳታበድረው ተጠንቀቅ» አለኝ «እነሉልሰገድ የፈቀዱትን ያህል ይገብሩለት፡፡ ሉልሰገድም አባቱ ሀብታም ነጋዴ ናቸው፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ ያጭበረበሩትን ገንዘብ ጥቂቱን አንድ ምስኪን አረብ ሲጠቀምበት ምንም አይደለም፡፡ ተመስገንም አባቱ ሚኒስትር ናቸው፣
ከህዝቡ የቀሙትን ገንዘብ እንደልብ ሊልኩለት ይችላሉ። ስለዚህ ለባህራም ይስጠው። አንተ ግን የኔ ብጤ ድሀ ነህ፤ እንዳትታለል ተጠንቀቅ። ይሄ ባህራም ዋና አጭበርባሪ ነው»

ይህን ባህራምን ማወቅ ፈለግኩ። ራሴን «ለወደፊት ደራሲ
ለመሆን ካቀድክ፣ እንደ ባህራም ያለ ሰው ሲያጋጥምህ በተቻለህ
መጠን ልታውቀው መጣር አለብህ» አልኩት:: ሰውን ምናውቀው ስለራሱ የነገረን እንደሆነ ነው። ግን ከጠየቅነው አይናገርም፣ ሲናገርም እውነቷን ፍርጥ አድርጎ አይደለም። ስለዚህ መታገስ ያሻል፣ ጊዜን መጠበቅ። አንዲት ሰአት ትመጣለች፣ ሰውየው
መናገር የሚፈልግባት ሰአት፡፡ መቼ እንደምትመጣ ለማወቅ
አይቻልም፣ ግን መምጣቷ አይቀርም። ስለዚህ ዘወትር ዝግጁ መሆን ያሻል።

ዞሮ ዞሮ እኔና ባህራም መተዋወቃችን አሰንደማይቀር እርግጠኛ ስለነበርኩ ነው መሰለኝ፣ ላውቀው በጭራሽ አልቸኮልኩም፡፡ ብቻ እሱ
ስለራሱ በሚነግረኝ ጊዜ ንግግሩ በደምብ እንዲገባኝ በማለት፣ ሌሎቹ ስለሱ ምን እንደሚያስቡ እጠይቅ ነበር። በዚያውም እነሱኑ
ራሳቸውን ትንሽ ትንሽ አውቃቸው ጀመር።.....

💫ይቀጥላል💫
👍17
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#ሶስት


#በአሌክስ_አብርሃም


...ትከክክክክክ ብላ ስታየኝ እንዲህ እላታለሁ፣
“ከጋብቻ በኋላ”

በዚህ የጭንቅ ሰዓት ላይ እያለሁ ሙናን የምትሰራበት ባንክ ወደ መቀሌ ቅርንጫፍ ቀየራት። ይሄማ
የእግዜር እጅ አለበት። ደስ አለኝ። ስሸኛት አለቀሰች። ለአዲስ አበባ ሳይሆን ከእኔ በመለየቷ፤ እና ደግሞ ከብረት የጠነከረ መሻትን ድል ሰመታ ከእሳት ለተፈተነ ትዕግስቴ” (እሷ እንደዛ ነው የሚመስላት) ለእኔ ግን ጉዳዩን ለራሴ እንኳን ማመን ባልፈልግም ገብቶኛል። ስንፈተ ወሲብ !! ያውም እንደ መርዶ ለራሴም ድንገት ዱብ ብሎ የተገለጠ። ለሙና ምን ብዬ ልንገራት ? ልጅቱ ከቀን ወደ ቀን ጉዳዩን
እንድንፈፅመው አፍ አውጥታ በፅኑ መሻት ትጠይቀኛለች። እንደውም ከሌላ ሴት ጋር አንዳች ጉዳይ የጀመርኩና የገፉኋት እየመሰላት መጠራጠር ጀምራ ነበር ምነው ባደረገው..

መቀሌ እየሰራች ቢያንስ በየወሩ እርሷ ወይም እኔ እየመጣችና እየሄድኩኝ አስደሳች ጊዜ እናሳልፍ
ነበር። ግን ምን ያደርጋል ይሄ የእኔ ነገር ጥላውን አጠላብን።

“ከዚህ በላይ መታገስ አይችልም፡፡ችግር ካለብኝንገረኝ፤ ወይም ካስጠላሁህ በቃ አሳውቀኝ
ፕ…ሊስ አለችኝ አንድ ቀን የአይጥና ድመት ድብብቆሻችን አሰልችቷት። እናም ማስጠንቀቂያ ጨመረችበት፣ “ለሚቀጥለው ስመጣ ካላደረግን የእኔና ያንተ ጉዳይ አበቃ !' ሙና ታደርገዋለች። ጭካኔዋ በፍቅሯ ልክ ነው፤ ቀልድ አታውቅም። ተንቀዥቅዤ አነሳስቼ በምን ላስቁማት ? ቆይ ሰው ንብረቱ እንደሚሠራ እና እንደማይሠራ ሳያረጋግጥ እንዲህ ዓይነት እዳ ውስጥ ይዘፈቃል ?! ቢጨንቀኝ ነው እንጂ እሱማ
እንዴት ይረጋገጣል ?እንደ ደም ግፊት አይለካ ነገር።

ሳወጣና ሳወርድ አድሬ ለሃኒባል ሳማክረው ወሰንኩ። ሃኒባል አብሮ አደግ ጓደኛዬ ነው፧ የልብ ጓደኛዬ። ከሙናም ጋር በደንብ ይተዋወቃሉ። እናም ላሳውቀው ወሰንኩ። ሃኒባል ቢያንስ ለምንም
ነገር አይጨነቅም። መፍትሄም አያጣም። ከድሮውም ልጅ ሆነን እኮ ነው … በቃ ችግር በሃኒባል ፊት የቱንም ያህል ቢገዝፍ እንደ ዝንብ ነው በመፍትሄ ጭራ የሚያባርረው። ደወልኩለትና፣ና እሬሳህን ውሰድ ልለው አስቤ ተውኩት፤ እፈልግሃለሁ” ብቻ አልኩት።

ምን ጉድ ተፈጥሮ ነው እንዲህ እያግለበለብክ ያስመጣኸኝ ጃል ?" አለ ሃኒባል ያዘዘውን ቡና
አማሰለ።

"ባክህ ችግር ገጥሞኛል”

"ችግር የሚባል ነገር የለም ባክህ፤ የመፍትሄ እጥረት በለው” አለ (አላልኳችሁም ?)

"እ..እንዴት መሰለሀ ከሙናጋ የሆነ ትንሽ ችግር ... ኧረ ምን ትንሽ …. ትልቅ ችግር ውስጥ ገብተናል”
አልኩት።"

ቡና ማማሰሉን አቆመና ኮስተር ብሎ፣ “የምን ችግር…” አለኝ።

"እኔ ለካ … እንትን …. ማድረግ አልችልም አሁን ነው ያወቅኩት”

"ምን ማድረግ ?”

ኤጭ ሥሙን ቄስ ይጥራውና እንዴት እንደቀፈፈኝ፣

“ግንኙነት ማድረግ አልችልም"

“የምን ግንኙነት ?"

“የምን ግንኙነት ትለኛለህ እንዴ … ወሲብ ነዋ!" ስል አፈረጥኩት።

"እ...ንዴ ! እና እስከዛሬ ከሙና ጋር ስታድሩ ምን እየሰራችሁ ነበር የምታድሩት ?"

“በቃ ትኝት ነዋ አርፈን … ማለቴ አርፌ"

“ትኝት ትኝት .… ለሽሽ ?”

“አዎ !"

"አንተስ እሺ … ሙና እንዴት አስቻላት ?"

“ያው ላያስችል አይሰጥም”

“ኧረ ሰውዬ ተረቱን አቁምና ወደ መፍትሄው!”

"እኮ! መፍትሄው እኮ ነው የጠፋብኝ፤ ሙና ደግሞ ደበራት”

"እንዴት ነው የማይደብራት፣ ትቀልዳለህ እንዴ ?” ብሎ ተነስቶ ወጣ። አካሄዱ አስደንግጦኝ ዝም ብዬ እንደተቀመጥኩ ትንሽ ቆይቶ አንድ መፅሄት ይዞ ተመለሰ። ከነወንበሩ ጠጋ ብሎኝ የመጽሄቱ የኋላ ሽፋን ላይ በውስጥ በኩል የታተመ ማስታወቂያ ጠቆመኝ።

“ደብተራ ግዛው ደበሌ የባሕል ሕክምና አዋቂ” ይላል። ጥምጣማቸው የሚያምር አፍንጫቸው ደፍጠጥ ያለ ደብተራ ሳይሆን ቦክሰኛ የሚመስሉ ሰውዬ ባለቀለም ፎቶ ሩብ ገፁን ተቆጣጥሮ በኩራት ተገጥግጧል። የሰውየውን ኩራት ለተመለከተው መቼስ እንኳን ከበሽታ ከሞት የሚያድኑ ሳይመስለው አይቀርም። ከሥር “መፍትሔ የተገኘላቸው ሕመሞች” ዝርዝር ሰፍሯል...

ለዓይነ ጥላ

ለቡዳ

ትምህርት ለማይገባው (ከድድብና የባሰ በሽታ የለም ብለው ይሆን)

ለሽንፈተ ወሲብ

ለስንፈተ ወሲብ ….

ቢንጎ !! ግን ስንፈተና ሽንፈተ ወሲብ ልዩነታቸው ምንድን ነው ?


አድራሻ ጦር ኃይሎች! እፎይይይ ሙና ተመልሳ ልትመጣ ሰላሳ አራት ቀናት ብቻ ይቀራሉ።
“በዚህ ሰላሳ አራት ቀናት ደብተራ ግዛው ተዓምር ፈጥረው የወደቀውን እንደሚያነሱት፣ የተኛውንም እንደሚያቀኑት ተስፋ እናደርጋለን አይዞህ ወዳጄ” ሃኒባል አፅናናኝ።

እናም ታሪካዊው ጉዞ ወደ ጦር ኃይሎች። የጠፋውን ወንድነት ፍለጋ። ወንድነትን ለመፈለግ፣

መኮላሸትን እምቢ ልንል

እንኳን ጦር ኃይሎች ጦር ሜዳ እንዘምታለን።

ኧ…ረ

ጎራው…

አልዋጋም ብሎ የተኛውን አውሬ.

ቆስቁሰው ቆስቁሰው አደረጉት አውሬ ... አለ ያገሬ አሽቀራሪ - መጣንልሽ ሙና !!

“በመጪዎቹ ሰላሳ አራት ቀናት የወንድነት ሕዳሴን ለማረጋገጥ ከደብተራ ግዛው ደበሌ ጋር ወ ደ ፊ ት !!”

ይሄ ሃኒባል የሚባል ልጅ እኮ የማይቀልድበት ችግር፣ በንቀት የማይመለከተው መከራ የለም፤ እንዲህ ጨንቆኝ እንኳ በግድ ፈገግ ያስብለኛል።

ጦር ኃይሎች እስከምንደርስ ሃኒባል ቀልድ እያወራ ብሶቴን ሊያስረሳኝ ቢሞክርም በፍፁም መርሳት አልቻልኩም። “አቡቹ ጣጣ የለውም ሰውዬው አደገኛ ናቸው፤ እንደ መኪና ተረክ አድርገው ነው የሚያስነሱት” ይለኛል። አይ ተረክ ... በስንት ጉድ ግፊ፣ እንደ ነዳጅ በትኩሳት የምትነድ ልጅ አየተማፀነችው ለሽሽ ያለ 'እንትን' እንዴት ነው ተረክ ብሎ የሚነሳው ? መርሳት ብቻ ሳይሆን የሆነውን
ሁሉ ማመን አልቻልኩም። ብቻ ቶሎ ይሄ ሰውዬ የሚያደርጉትን ባደረጉና

ጦር ኃይሎች የተባለው ሰፈር ደረስን፤ ዓየር ጤና አካባቢ ነው
አሉን፤ ዓየር ጤና ሄድን - ዘነበ ወርቅ፣ ከዛ ወይራ ሰፈር ... አንዲት ጭርንቁስ በቅጠላቅጠል የታጠረች አጥር ውስጥ ያዘመመች የጭቃ ቤት። “ይሄ
ነው ቤቱ” አሉን። አሁን ማን ይሙት ይሄን ቤታቸውን በስርዓት ያላቆሙ ሰውዬ ሌላ ነገር ያቆማሉ ?
እንደዚህ እያሰብኩ አሮጌውን የቆርቆሮ በር ገፍተን ገባን።

አንድ የቆሸሸ ቱታ የለበሰ ጎልማሳ ሰው አገኘን።

“ደብተራ ግዛውማ ቦሌ ምን የመሰለ ቢላ ቤት ገዝቶ ሄደ እናትዬ፤ ዛሬ ጆሮውን ቢቆርጡት የማይሰማ ኃብታም ሁኗል። ሰው ሁሉ በባዶ እግሩ ከገጠር እየመጣ እንዲህ ባለፀጋ ይሆናል፤ እኛ ነን የአርባ ቀን እድላችን ከአፈር አትነሱ ብሎን.." እያለ ብሶቱን ይዘረግፈው ገባ።

ተመለስን።

“እንዳንከራተትሽኝ አላህ ያንከራትሽ አለ አሉ ሰውየው፤ ጨረቃን መግቢያዋን አያለሁ ብሎ ሲከተል ከርም አልሆን ቢለው እኮ ነው። ስንመለስ ሃኒባል እንዲህ አለኝ፣ “አቡቹ አየህ የዚህን አገር ነገር፡ አንተ በቀን ስምንት ሰዓት ቆመህ በየወሩ የቤት ኪራይ መክፈል የማትችል ደመወዝ ትከፈላለሁ አጅሬው እንትን ከቁሞ ቪላ ይገዛል ያውም ቦሌ”

“ተናግረህ ሞተሃል፤ እንትን ከማቆም በላይ ለአንዲት አገር ምን ትልቅ ሥራ አለ” ብዬ ገላመጥኩት:

“አብርሽ እንዲህማ አትነጫነጭ፣ ይቆማል አይዞህ”
👍282🔥1
ቦሌ የደብተራ ግዛውን ቤት (ቤተመንግሥት በሉት) ስናገኘው ሪፈራል ሆስፒታል እንጂ የአንድ ሰው ቤት አይመስልም። ሰራተኛ ትሁን ነርስ ያልገባኝ ሴት እየመራች ወደ ሰፊውና ሙሉውን ነጭ ቀለም
ወደተቀባው ውብ ሳሎኑ ወሰደችን። ኧረ ጉዴ !እኔ ጥምጣሙን አሳምሮ በጋቢው ላይ ካፖርት የደረበ የእግዜር ሰው አገኛለሁ ብዬ ... ሰውዬው ምቹ የሌዘር ሶፋው ላይ ተንጋልሎ የግድግዳውን ሩብ ክፍል
በያዘ ትልቅና ጠፍጣፋ ቴሌቪዥን ኳስ ጨዋታ ይመለከታል። የቴሌቪዥኑን ስፋትና የኳስ ሜዳው በዛው ልክ መንጣለል ስመለከት ሰውዬውን ቤት ውስጥ ሳይሆን የሆነ መስክ ዳር ጋደም ብሎ ያገኘነው መሰለኝ፡፡ ጎንና ጎኑ ላይ ኪስ ያለው የዘመኑ የጨርቅ ቁምጣ ለብሷል፣ ነጭ ካልሲ አድርጓል፣ ላይ ከላይ ፈርጣማ ጡንቻውን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ፓክ አውት ለብሷል። ገብተን ቆመን ሁሉ ከቁም
አልቀጠረንም። በስሜት ብቻውን ያወራል።

“አይ አርሴናል .. እንዲህ ተጨማልቀህ ትቀር እኛ ስንት ቦታ ትደርሳለህ ስንልህ ? ምነው ያንተ ደጋፊ ከምሆን በጽንሴ እናቴ መሀፀን በቀረሁ…” አለ እና የሌዘር ሶፋውን በብስጭት በቡጢ አቀመሰው። እኔና ሃኒባል ተገርመን እርስ በእርስ ተያየን።

ድንገት ወደኛ ዞር ብሎ፣
ተቀመጡ አለንና ወደ ቴሌቪዥኑ ተመለሰ። አነጋገሩ ተቀመጡ ሳይሆን 'ውጡ ያለን ነበር
የሚመስለው፤ አመናጨቀን ቢባል ይቀላል።

በስሜት ኳሱን ሲመለከት ቆይቶ ድንገት ወደኛ ዞረና፤

"ወጣቶት ምን እግር ጣላችሁ ?” ሲል ፈፅሞ አክብሮት በሌለበት የሚያበሳጭ ሁኔታ ጠየቀን። አገቀ አጎጌ ኳሴን ልመልከትሰት ውጡሉኝ ይመስላል።

"አይ እንትን ነበር… እ አለ ሃኒባል ድንገት ስለተጠየቅን ተደናግጦ እየተሽቆጠቆጠ።

ምን .. ስንፈተ ወሲብ ነው ”

"አዎ አዎ" አለ ሃኒባል እየተጣደፈ። እኔማ ሰውዬው አብግኖኝ እንደ ሐውልት ደርቄያለሁ። ጭራሽ
አኮ ወደኛ እይመለከትም ስው ጤፉ…

ታዲያ ምን አስፈራችሁ ? ባሁኑ ጊዜ ካዲሳባ ወንድ አስራ አንድ ነጥብ ዘጠኙ ስንፈተ ወሲብ ችግር
ያለበት ነው። ባገር የመጣ ነው፤ አይዟችሁ ! ከሆነስ ሆነ የማንኛችሁ ቆለጥ ነው አልቆምም ያለው ?”
ሲል ጠየቀ፡፡

አሁንም ዞሮ አላየንም።

“የሱ ነው” አለ ሃኒባል ወደ እኔ እየጠቆመ። ከሰውዬው ድንገተኛ አጠያየቅና ከሃኒባል አመላለስ
ድርቅና ተነስቼ የኔ አይደለም ብዬ ልክድ ነበር። ሁኔታው አሳቃቂ ነበር። የሰውዬው ድፍረትና ትዕቢት
ያበሳጫል። ከዋናው ጉዳይ በላይ የሰውዬው ንቀት አበገነኝ፡፡

ታዲያ ምን ይዘጋዋል፤ ራሱ አይናገርም … ወይስ ምላሱም ሰነፈ ? ይሄ የውሻ ልጅ ! ልናገረው
አፌን ሳሞጠሙጥ ሃኒባል ገላመጠኝ ዝም አስባለኝ፡ ሰውዬው ጋደም እንዳለ በርቀት መቆጣጠሪያው የቴሌቪዥኑን ድምፅ ለአመል ያህል ቀነስ አደረገና ከተንጋለለበት ተነስቶ ፊቱን ወደኔ አዙሮ ተቀመጠ።
አንዴ ከእግር እስከ ራሴ ፊቱን ጨፍግጎ ቃኘኝና፣

እ..ጎረምሳው መቼ ጀመረህ?” አለኝ። (በቃ ምርመራ ተጀመረ ማለት ነው ?) ሰውዬውን ትኩረት
ስመለከተው ለካስ ዓይኑ ልክ አይደለም፤ ትንሽ ሸውረር ያለ ነው። ታዲያ መጽሔት ላይ ከየት አባቱ ያመጣውን ፎቶ ነው የለጠፈው ?.....

ይቀጥላል
👍131
#ትኩሳት


#ክፍል_ሁለት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

#እንደወረደ_ነውና_ለአንባቢ
#የማይመቹ_እኛ_ፀያፍ_የምንላቸው
#ቃላቶች_አሉትና_አሁንም
#በድጋሚ_እንደምናገረው
#የማይመቸው_እንዳታነቡት
#እመክራለሁ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አማንዳ
ለጥቂት ጊዜ


ያን ሰሞን አንዲት ቆንጆ አሜሪካዊት ነበረችኝ፣ አይኗ
ሰማያዊ፣ ፀጉሯ በጣም ንፁህ ቡና አይነት፡፡ እጅግ ደስ ትላለች፣
አልጋ ውስጥ ልብ ታጠፋለች ግን በማልፈልጋት ሰአት ሆቴሌ
እየመጣች አላሰራ ስላለችኝ፤ ቤተ መፃህፍት እየሄድኩ መስራት ግድ
ሆነብኝ፡፡ ሆቴሌ ስታጣኝ ወደ ቤተ መፃህፍቱ መምጣት ጀመረች።

እሷን ለመሸሽና በዚያውም ባህራምን ለማወቅ ስል ሀበሾቹን
እጠጋቸው ጀመር ምግብ ቤት አብሬያቸው እገባለሁ፣ ካፌ
ዶርቢቴል አብሬያቸው ካርታ እጫወታለሁ ከባህራም ጋር ግን ላይ ላዩን እየቀለዱ ለመሳቅ እንጂ፣ የልብ ለመጫወት አጋጣሚ ለጊዜው አላገኘሁም። ይልቅስ ከሀበሾቹ ጋር ግንኙነት በማድረጌ «ሚስቶቻቸውን» በመጠኑ እያወቅኳቸው ሄድኩ፡፡

የነበርንበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሴቶች ከወንዶቹ በጣም ይበዛሉ፡፡
ስለዚህ ለሁሉ ሴት 'ሚዳረስ ወንድ የለም....አሉ ሶስት፣ አራት፣
አምስት 'የሆኑ ወንድ 'ሚያድኑ ልጃገረዶች። ታድያ ወንዱን ቆንጆ
ቆንጆዎቹ ይዘውታል፣ ተጠምጥመውበታል። ነፃ የሆነ ወንድ አይገኝም፣ ቢገኝም ወይ የደስ ደስ የለውም፣ ወይ ጥቁር ነው። ጥቁር ደሞ ምን ቢወዱት አገሩ መመለሱ አይቀርም፡፡ ብልጥ ወይም ውብ ወይም እድለኛ ካልሆኑ፣ ፈረንሳይ ወንድ ማግኘት አይቻልም። ሳያገቡ የማርጀት ፍርሀት በወራቱ ዋሻ ሰአመታቱ ጫካ አድፍጦ
ይጠብቃል.

ጥቁሮቹ ወንዶች ገና እንደመጡ፣ በንግድነት ምክንያት ቆንጆ
ሴት ማጥመዱን ለጊዜው ስለማያውቁበት፣ የተገኘችውን እሺ ብለው ይቀበላሉ። የምትገኘው ደሞ ቆንጆ ያልሆነች ናት፣ ስለዚህ ማቆያ
ናት...

«የሀበሾቹ ሚስቶች» ጎደሎ ብጤዎች ነበሩ፡- እዚህ ቅርፅ
ይጎድሳል፣ እዚያ ድምፅ ይጎድላል፣ እዚያ ጠባይ ይጎድሳል። ብቻ፣ሉልሰገድ እንዳለኝ ሁሉም ያ ነገር ኣላቸው ለጊዜው ሀበሾቹ የፈለጉት እሱን ነው:: መልኩ፣ የደስደሱ፣ ደማምነቱ፣ ጠባዩ፣ በኋላ
ዝግ ተብሉ ይፈለጋል ከሁሉም አስቀያሚ አማንዳ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ድብልብል
አሜሪካዊት ናት፡፡ ወፍራም አንገቷ ዙርያ ስጋው ተጣጥፏል፣ ሽንጥ
ሚሉት የላትም፣ ስትራመድ የሚንቀጠቀጠው ባቷ ረዥም ቂጥ ይመስላል። በጭራሽ ስሜት አትቀሰቅስም። ሉልሰገድ ለምን
እንደያዛት ለጊዜው ሊገባኝ አልቻለም፡፡ የቸገረው እርጉዝ ያገባል ይባላል፣ እሱ ግን አቅፏት ይዞራል። ወገቧ ዙርያ እጁ ስለማይደርስ ትከሻዋን አቅፎ እሷ ወገቡን አቅፋ ሲሄዱ አያቸዋለሁ። የአማንዳ ፈገግታ ደግና ንፁህ ነው፣ ትንንሽ አይኖቿ ንፁሀ ሰማያዊ ናቸው፣ ረዥም ፀጉሯ በጣም ንፁህ ነጭ ሆኖ፣ ጨረቃ ውስጥ ተነክሮ የወጣ ይመስላል። ግን ይህን ሁሉ ውበት ጮማዋ አፍኖ ይዞ እንደሌለ አድርጎታል። ስታያት ውፋሬዋ ነው 'ሚታይህ፣ ስታስታውሳት ጮማዋ ነው ትዝ ሚልህ

ሲልቪ ግን በጣም ቆንጆ ናት። «እጥር ምጥን» ያለች ፈረንሳዊት ሆና፣ ቡናማ ጉልህ አይኖቿ ውስጥና ውብ ሰፊ አፏ
ዙርያ እንደ ነበልባል የሚውለበለበው ፈገግታዋ ልብ ያሞቃል። ወደ ኋላ የተለቀቀው ንፁህ ጥቁር ፀጉሯ ያብለጨልጫል፣ ስትራመድ
ረዥም አንገቷን እያወዛወዘች ስለሆነ፣ ይሄ ጥቁር ሀር ፀጉሯ ዥው ዥው ይጫወታል። ከታች ደሞ አበጥ ያለው ዳሌዋ ያንኑ ያህል ይወዛወዛል። እግሯ በብዙ ጥንቃቄ የተቀረፀ ውብ ፍጥረት ነው::ፍቅርም ምኞትም የምትቀሰቅስ ወጣት ትመስላለች። ተመስገንን በጣም ትወደዋለች ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ይሄ ተመስገን ፈረንሳይ አገር የተስማማው ይመስላል።

ዩኒቨርሲቲውን «ሲቴ» ይሉታል። ሲቴ ውስጥ መኝታ ቤት
ያላቸው ሀበሾች ተመስገን፣ ሉልሰገድ፣ ተካ፣ ሀይለየሱስ ናቸው፡፡
ሌሉቹ እንደኔው የሆቴል ክፍል ወይም የከተማ ቤት ተከራይተው
ይኖራሉ ቆንጆዋን አሜሪካዊት እንዳላገኝ ስፈልግ ከሉልሰገድ ወይም ከተመስገን ቁልፍ ለምኜ መኝታ ቤታቸው ቁጭ ብዬ ሰራለሁ::ሀይለየሱስ ቤት እንዳልሰራ ሰውየውን አልወደውም። ተካ ቤት
እንዳልሰራ ደሞ የተካ ቤት ይገማል። አይ ተካ! እግዜር ይይለት አንዳንዴ እንኳ እግሩን ቢታጠብና እግር ሹራቡን ቢያጥብ ምን ቸገረው ነበር? ዝም ብሎ ብቻ ጥፍሩን እየነከሰ መነጫነጭ ምን ያረግለታል?

ሉልሰገድ ወይም ተመስገን ቤት ቁጭ ብዬ ስስራ አንዳንዴ
ባህራም ይመጣል፡፡ ትንሽ እናወራና ፂሙን ተላጭቶ መልካም ስራ ብሉኝ ይወጣል። ፀጉራም ነው። እጆቹን፣ ደረቱን፣ አንገቱን፣ ፊቱን ፀጉር ወሮታል። ፂሙን ሲላጭ አይኑ፣ አፍንጫውና ጆሮው ብቻ ናቸው መላጨት የሌለባቸው:: ቢሆንም ፀጉሩ አያስቀይምም፡፡ በጣም
ንፁህ ሰው ነው።

አንዳንዴ ደሞ ቁጭ ብዬ ስሰራ ድቡልቡሏ አማንዳ ወይም
ውቢቷ ሲልቪ ይመጣሉ ወዳጃቸውን ፍለጋ፡፡ ቀስ በቀስ እነዚህን ሁለት ልጃገረዶች» እያወቅኳቸው፣ እየወደድኳቸው ሄድኩ፡፡ እነሱም ሊወዱኝ እንደጀመሩ ታወቀኝ። ስለራሳቸው ኑሮ በመጠኑ ይነግሩኝ ጀመር ..

አንዳንድ ቅዳሜ ማታ ሀበሾቹና ጓደኞቻቸው «ሱርፕሪዝ ፓርቲ»
ያደርጋሉ። «ሰርፕሪዝ ፓርቲ» ድንገተኛ ብጤ ነው። ታስቦ የታቀደ
ፓርቲ ሳይሆን፣ ጓደኛሞች ሲገናኙ «ዛሬ ምን እናርግ? ሲኒማ
እንግባ ወይስ ምን ይሻላል?» ይባባሉና ለምን ሰርፕሪዝ ፓርቲ
አናረግም?» ይላሉ፡፡ ያን እለት ማታ ፓርቲው ይደረጋል። የተገኙ
ሰዎች ይጠራሉ፣ የራሳቸውን መጠጥ ይዘው እንደሚመጡ የታወቀ ነው:: አንዱ ቤት ፓርቲው ይደረጋል። ለዚህ ጉዳይ ሀበሾቹን
ባህራም ያገለግላቸዋል
ይጀምራል፤ ወንዶቹን ይጠራል፣ ሴቶቹን ይጋብዛል፣ እዚህ ትእዛዝ
እንደ አውሎ ነፋስ በፍጥነት መዘዋወር ይጀምራል ወንዶቹን ይጠራል ሴቶቹን ይጋብዛል እዚህ ትእዛዝ እዚያ ምክር ይሰጣል፣ ከዚህ ዲስክ ከዚያ ሴት ይዋሳል፣ ፓርቲው ይጀመራል። ተሳታፊዎቹ ወንዶች ኣብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያንና ኢራናውያን ናቸው፣ የሁለቱ አገሮች ማህበር ይመስላል።

እንዲህ አይነት ፓርቲ ውስጥ ነበር ሉልሰገድ አማንዳን ያገኛት። ፓርቲው ውስጥ ጥቂት ሴቶች ብቻ ነበሩ፣ እነሱም ተይዘዋል፡፡ ያልተያዙ አንዲት በጣም ደቃቃ የሆነች የሩቅ ምስራቅ
ልጅና እንዲት አስቀያሚ ድቡልቡል ኣሜሪካዊት ብቻ ናቸው::ምስራቃዊቷ በጣም ደስ ትላለች፣ ግን ሉልሰገድ እሷን ይዞ አልጋ ውስጥ ሲገባ ሊታየው አልቻለም። «ዎ! ብትሞትብኝስ?» ብሎ አሰበ፡፡ ተዋት። ድቡልቡሏ አሜሪካዊት ፈፅማ ደስ አትልም፣ ግን ሙዚቃውና መጠጡ እየገፋፉ ወደሷ ወሰዱት። ተዋወቃት። ስሜ
አማንዳ ነው አለችው፣ አብረው ይደንሱ ጀመር፡፡ በእንግሊዝኛ
እያወሩ ሁለቱም በብሉይ ጠጡ፣ ሞቅ አላቸው:: ስታቅፈው
ስታናግረው በጣም ደስ እያለችው ሄደች ይስማት ጀመር

«ተው እዚህ አትሳመኝ» አለችው

«ምናለበት?» አላት ጆሮዋን እየሳመ አልችልም፡፡ ስሜቴ በጣም ይቀሰቀሳል» አለችው:: ድምፅዋ
በጣም አቆመበት።

ታድያ ምናለበት?» አለ እየተሻሻት

"ያኔ መሳም ብቻ አይበቃኝም» ብላ በሀይል ተጠጋችው::

ሉልሰገድ ቀስ ብሎ ወደ አንዱ መኝታ ክፍል ገብቶ እዚያ
ይሳሳሙ የነበሩትን ሁለት ፈረንሳዮች አስወጣቸው። (መኝታው የማን እንደሆነ እንጃ መብራቱን አጠፋ። ተመልሶ መጥቶ አማንዳን ወደዚህ ጭለማ መኝታ ቤት ወሰዳት፡፡ በሩን ቆለፈ። አልጋው ላይ አጋድሞ ይስማት ጀመር። እየሳመ፣ እያሻሽ ሙታንታዋን አስወለቃት። ጭለማ በመሆኑ አስቀያሚ መልኳ ስለማይታየውና፣አሳሳም ከማወቁም በላይ ወፍራም ገላዋ ምቹ ስለሆነ፣ እጅግ በጣም ተደሰተባት ጠግቦ ከላይዋ ሊነሳ ሲል፣ እቅፍ አደረገችውና እንዳይነሳ ከለከለችው
👍231
“እባክህን ትንሽ ቆይልኝ» አለችው። አንድ የማይታወቅ ሀዘን
ከድምፅዋ በኩል መጥቶ ልቡ ውስጥ ገባ። ዝም ብለው ቆዩ::

«ይሰማሀል ዘፈኑ?» አለችው

እዚያኛው ክፍል ውስጥ፣ ዝግ ያለ ያዘነ የአለን ባርዬር ዘፈን
ይሰማል።

"Elle était si jolie
Je noublierai jamais..."

(እጅግ የተዋበች ነበረች፡- እስከመቸም አልረሳትም. .)

በፈረንሳይኛ «አንተ ግን አሁን ትረሳኛለህ» አለችውና እቅፍ
አደረገችው:: እንባዋ ጉንጩን ነካው:: የሚያደርገውን አጣ፣
የሚናገረውን አጣ፡፡ ዝም ብሎ አቀፋትና በእንግሊዝኛ
«አልረሳሽም፤ ለምን እረሳሻለሁ?» አላት
«ርካሽ ሴት መስዬ እታይሀለኋ»
«በጭራሽ ርካሽ አትመስይኝም»
«ርካሽ እመስላችኋለሁ፣ ግን ርካሽ አይደለሁም፡፡ ነገሩ ሌላ ኘው።»
«እኔ ርካሽ ሆነሽ አትታይኝም»
«እውነትክን ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ»
«እውነቴን ነው:: ለምንድነው ምታለቅሺው?»
«እንዲሁ»
«ንገሪኝ» አላት፣ በእጁ እንባዋን እየጠረገ
«ሌላ ቀን እነግርሀለሁ. .. የተገናኘን እንደሆነ»
«ለምን አንገናኝም?»
«ትሽሽኛለህ፡፡ ይታወቀኛል»
«ለምን?»
«እጣዬ እንደሱ ነው»
«ተሳስተሻል»
«እስቲ እናያለን ስማ. . .»
የአለን ባርዬር ዘፈን ተደግሟል፡-

"Aujourd'hui cest l'automne
Et je pleure souvent
Aujourd hui c est l automne
Qu'il est loin le printemps..."

(ዛሬ በልግ ነው
ዘወትር አለቅሳለሁ
ዛሬ በልግ ነው
ፀደዩ ምንኛ ይርቃል!. . )
ሲያባብላት ትንሽ ከቆየ በኋላ ተነስተው ወደ መደነሻው ክፍል
ገቡ። በብርሀን አያት:: ከነጭ ፀጉሯ ሌላ መልክ የላትም፡፡ ዙሪያ
ፊት፣ ጮማ ውስጥ የተቀበሩ አይኖች፣ ካገጯ በታች ትርፍ
አገጭ፡- እስቀያሚ ነች፡፡ ግን ስታሳዝን! ሉልሰገድ ሊለያት
አልፈለገም። ሲያስደንሳት ሲያጫውታት አመሽ
ሌሊት ቤቷ ሲያደርሳት «መቼ አገኝሀለሁ?» አለችው:: በምሳ
ሰአት ምግብ ቤቱ በር እንዲገናኙ ተቃጠሩ።
ተካ ብሽቅ ነው እንጂ መጥፎ ልጅ አይደለም። እንዲያውም
ልቡ በጣም ሰፊ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ቀን ስናወራ
«እኔ ሰው አውቆ ክፉ ይስራል የሚባለውን አልቀበልም» አለኝ
«ማንም ሰው በጣም ክፉ የትባለው እንኳ ቢሆን፣ ክፉ የሚሰራው ደግ የሰራ እየመሰለው ነው። ባለማወቅ ነው»
«ሚስትህን ወይም እጮኛህን ቢያማግጥብህስ?» አልኩት
«አንተን ለመጉዳት አይደለም፣ ሴትዮዋን ሊደሰትባት ፈልጎ
ነው እንጂ»
«አሳብቆ ሲያጣላህስ?»

«ለክፋት ያለው አይደለም፡፡ ወይም ስብቀቱ ትልቅ ደስታ ስለ
ሚሰጠው ነው፣ ወይም ስትጣሉ እሱ የተጠቀመ እየመሰለው ነው::
ለክፋት ብሎ ክፋት አይሰራም፡፡ ባለማወቅ፣ ባለማመዛዘን ነው»

«አሁን አንዱ ቢጎዳህ አትቀየመውም?»

ለጊዜው እቀየመዋለሁ። ግን ንዴቱ ሲበርድልኝ፣ ለክፋት ብሎ
እንዳልጎዳኝ ይገባኛል፡፡ ስለዚህ እሸሽዋለሁ እንጂ አልጠላውም»

«ባንተ ቤት የሰው ልጅ ጥሩ ነው?»

«አዎን። ጥሩ ባይሆንም ክፉ አይደለም። የሚያበላሸው
አለማወቅ ብቻ ነው:: ብታስብበት፣ አንድ ነገር በእውነት መጥፎ
መሆኑን ካየ፣ ሊያደርገው አይችልም :

ተካ በልቡ ጥሩ ልጅ ነው:: ግን አቤት ሲያበሽቀኝ ጥፍሩን
መንከሱ፣ ሰውነቱን አለመታጠቡና ጥርሱን አለመቦረሹ የራሱ ጉዳይ
ነው፡፡ ግን ባገኘኝ ቁጥር ከየት ነው የምትመጣው?» ብሎ ይጠይቀኛል። መመለስ አለብኝ፡፡ ምን ትሰራ ነበር?» ይለኛል። እመልሳለሁ። ቀጥሎ «ወዴት ነው የምትሄደው?» ይለኛል። እነግረዋለሁ።ምን ልታረግ ነው እዛ " ምትሄደው?» ይለኛል። እነግረዋለሁ

ባገኘሁት ቁጥር እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ይሰለቸኛል። ግን እርር ቅጥል የሚያረገኝ ምንድነው? ከየትም ብመጣ፣ ወዴትም ብሂድ፣ ምንም ብስራ፣ በጭራሽ ደንታ የለውም! እንዲሁ ነው የሚጠይቀኝ፡፡ ያለ አንዳች ምክንያት! ልማድ ስለሆነበት ብቻ

ሌሎቹን ሀበሾች ይሄ የተካ ጥያቄ ማብዛት አያናድዳቸውም፣ በመጠኑ ያስቃቸዋል እንጂ። እነሱን የሚያናድዳቸው (እና እኔን የሚያስቀኝ ሌላ አመል አለው። እርር ቅጥል የሚያረጋቸው! አንዲት ልጅ ደስ ብላቸው ሊያበስሏት የፈለጉ እንደሆነ «እባክህን ለኔ ተውልኝ ልቤን ወስዳዋለች። ልሞክራትና
እምቢ ያለችኝ ንደሆነ አንተ ትሞክራለህ» ይላቸዋል
እንግዲህ እነሱ ለጊዜው ሌላ ሴት ስላላቸውና እሱ ሴት
ስለሌለው እስበውለት ይተዉለታል። ታድያ ምንም አይሰራም።ሞክሮ ሲያቅተው እንኳ ያዝኑለት ነበር፡፡ በጭራሽ ሊያነጋግራትም አይሞክርም እንጂ። እንዲያው ብቻ «ዛሬ እንዲህ ብላ አየችኝ ዛሬ እንዲህ እንዲህ እያለች ባጠገቤ አለፈች» ይላቸዋል። በመሀሉ አንዱ ፈረንሳይ ይቀልባታል። ጓጉተው ይቀራሉ

ሀበሾቹ በተካ ምክንያት ከዚህ የባሰ የሚበሳጩበት ጊዜም አለ።
ፓርቲ ላይ አንዲቱን አብስለው ሰብከው አሰሰደስተው እሺ ሊያሰኟት ትንሽ ይቀራቸዋል። በዝግተኛ ሙዚቃ አቅፈዋት
እየተወዛወዙ በጆሮዋ አስደሳች ምናምን እያንሾካሾኩላት «ዛሬ
አብረን ብናድር እንዴት ጥሩ ነበር! የሚቻልሽ ይመስልሻል?»
ይሉዋታል። «አይመስለኝም» . ትላቸዋለች። የምሯን ይሁን ወይስ
መግደርደሯ ይሁን አያስታውቅም፡፡ ስለዚህ የበለጠ እያስጠጉዋትና
እየተሻሹዋት እረ ባክሽን አስቢልኝ፡፡ ተሰቃየሁ'ኮ» ይሏታል። ዝም ትላለች። «ታድያስ የኔ ቆንጆ፣ እሺ ትይኛለሽ?» ይሏታል
ይህን ጊዜ ተካ ከተፍ ይልና አንድ ጊዜ እንደንስ?» ብሎ ልጅቷን ይወስዳታል፡፡ እዚህ ላይ ያለ ንዴት! ታድያ ምንም አያረጋትምኮ። እንዲሁ ነው።

ይኸው ካዲስ አበባ ከመጣን ሰባት ወር ያልፋል። ተካ እስካሁን
እንዲት ሴት እሺ አሰኝቶ አያውቅም፡፡ ሴት ሲያምረው ማርሰይ ይወርድና ሽርሙጣ ተኝቶ ይመለሳል፡፡ ለዚህ ነው አንድ ቀን
ስለአማንዳ የነገረኝን በሙሉ ላምነው ያልፈለግኩት
ከምሳ በኋላ ነበር። ሲቴ የዩኒቨርሲቲው) አጠገብ ያለው
መናፈሻ ውስጥ እኔና ተካ ቁጭ ብለን ፀሐይ ስንሞቅ፣ አማንዳ
መጣችና “ሉን አላያችሁትም ወይ?» አለችን። (ሉልሰገድን ሉ ነው ምትለው) «አላየነውም አልናት። እየተድበለበለች ሄደች። ውብ ነጭ ፀጉሯ ወደ ኋላዋ ተለቆ ፀሀይ ውስጥ ይብለጨለጫል፣ የረጋ የጨረቃ ብርሀን ይመስላል። ተካ ጥፍሩን እየነከሰና የጥፍሩን
ብጥስጣሽ «ጵ» እያለ እየተፋ

«እቺ ቂንጥራም! አሁን' ኮ ቁላ አምሯት ነው» አለ። አበሸቀኝ።

«ለሌላ ጉዳይ ሊሆን አይችልም?» አልኩት»

«አዎ! ቁላ ፍለጋ ነው እያልኩህ!»

«ለምን እንዲህ ትሆናለህ? የት ታውቃታለህና ነው ኢንደዚህ
ስሟን የምታጠፋው?»
«ይልቅ አንተ የት ታውቃታለህና ነው እንዲህ የምትከራከርላት?»
«እኔማ አላውቃትም»
«እንግዲያው ለምን ትከራከርሳታለህ? አንዲት ቂንጥራም አሜሪካን ናት፣ በቃ»

አብዛኛውን ጊዜ ተካ ምንም አይነት መራራ ነገር ቢናገር
ያሳዝነኛል እንጂ አልናደድም፡፡ ዛሬ ግን ምን እንደነካኝ እንጃ፡
ለአማንዳ ተቆረቆርኩላት። ተናድጄ
የት ታውቃታለህ? አንዳንተ ያለ የት ያውቃታል?» አልኩት
«እኔ አውቃታለሁ አላልኩም'ኮ»
«እንግዲያው አታውቃትማ»
«አላውቃትም»
«ጥሩ፣ እንግዲያው ስሟን አታጥፋ።»
አጭር ዝምታ፡፡ ከኛ ራቅ ብለው የፈረንሳይ ህፃናት አሸዋ
👍30
እየሰፈሩ ይጫወታሉ ይንጫጫሉ። አግድም ወንበሮቹን አሮጊቶችና
ሽማግሌዎች ሰፍረውባቸዋል
«አላውቃትም። ግን አሁን ቁላ ፈልጋ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ
አለ ተካ ከመናደዴ የተነሳ ወደሱ በኩል ተንጠራርቼ ፊቴን ወደ ፊቱ
አስጠግቼ እንዴት እንደዚህ እርግጠኛ ሊሆኑ ቻሉ፣ እባክዎትን?» አልኩት
በጭራሽ ሳይናደድ፣ እንዲያውም ያልተጠረገ ጥርሱን ብጫ
ብጤ ፈገግታ እያሳየኝ፣ ዝቅ ባለ ሰላማዊ ድምፅ
«በድቻታለኋ!» አለኝ፡፡ (ትንፋሹ!)
እየሳቅኩ ወደ ቀድሞ ቦታዬ ተመለስኩ
«እውነቴን ነው» አለ «ያለፈው ቅዳሜ ሳምንት ኢራንያኖቹ
ቤት ሱርፕሪዝ ፓርቲ ነበር። ሉልሰገድ አልነበረም፡፡ እሷ ስክራ
ነበር። ትንሽ ተጠጋኋትና ስተሻሻት ጊዜ ቆመባት፣ እቺ ቂንጥራም!»
«ቂንጥራም አትበላት! ካልሰደብካት ማውራት አትችልም
«እንዴ?»
«ፓርቪስ መኝታ ቤት አስገባኋትና በጭለማው እየደነስን እጄን
ልብሷ ውስጥ ከትቼ ወፍራም ቂጧንና እምሷን አሻሽሁላት። እምሷ ረጠበ፣ ጨቀየ፣ ጣቴን ከተትኩባት። ማቃሰት ጀመረች፡፡
ሙታንቲዋን ላወልቅ ስል
«ሉን እንዳትነግረው ቃልህን ስጠኝ» አለችኝ
«ቃሌን ሰጠኋት። ሞላኋት። ከጨረስኩ በኋላ «አንዴ
እንድገም?» አለችኝ

«ምን አልካት?» ብዬ ጠየቅኩት

«Go to hel!» አልኳት («ገደል ግቢ»)

«ለምን?»

«አስጠላችኛ! ብተፋባት አልጠላም ነበር» ዝም አልኩት»

«ሱሪዪን ስታጠቅ 'ሉ እንዳያውቅ ቃልህን ሰጥተኸኛል' አለችኝ»

«Shut up!» አልኳት («ዝም በይ!»)

«ከዚያ በኋላ ሌላ ጊዜ ተኝተሀት ታውቃለህ?» አልኩት

«የለም»

«እምቢ አለችህ?»

«የለም፡፡ በነጋታው ለሉልሰገድ ነገርኩት»

«ለምን? ለምን ነገርከው? ምን ይጠቅመኛል ብለህ ነገርከው?
ምን ጥቅም አገኘህበት?»

«እውነቱን ይወቅ ብዬ ነዋ!»

«ልጅትዋስ? አትቆጠርም?፦
የሰጠሀት ቃልስ? ዋጋ የለውም?»

«ላንዲት ቂንጥራም አሜሪካን ብዬ ከእውነቱ ልራቅ እንዴ?»

«ቂንጥራም አትብላት አልኩህ!»

«እሺ»

«ለምን መጀመሪያውኑ ቃልህን ሰጠሀት?»

«እንድትሰጠኝ ብዬ ነዋ!»

«ሉልሰገድ ምን አለ የነገርከው ጊዜ?»
«ምንም አላለም፡፡ ይቅርታ አርግልኝ ቆሞብኝ ስለነበረ ነው
አልኩት»

«ምን አለህ?»
«ምንም ይቅርታ አያስፈልግ፤ እርሳው» አለኝ
«ሌላ ምንም አላለህ?»
«እንደነገርከኝ አማንዳ እንዳታውቅ፡፡ ያወቀች እንደሆነ
ትጣላኛለህ፣ አለኝ»
«ስለዚህ ጉዳይ ሌላ 'ምትነግረኝ አለ?» አልኩት ተካን
«የለም» አለኝ
ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ
«የት ልትሄድ ነው?» አለኝ፡፡
«የትም፡፡ ካንተ መሸሼ ነው»
«ምነው? ምን ኣረግኩህ?»
«አናደድከኝ»
«ለምን?»
«በልጅቷ ምክንያት»
«ምን የሚያናድድ አለው? አንተ ጉዳዩ ውስጥ የለህበት»
«አሁን ዝም በለኝ!» ብዬው ሄድኩ
ታድያ ለእራት አገኘኝና፣ ልክ ምንም እንዳልተባባልን ያህል
አነጋገረኝ። ተካ ቂም አይይዝም። በዚህ በኩል ልቡ ንፁህ ነው
ይህን የተካንና የአማንዳን ታሪክ ላምነው አልፈለግኩም፡፡ ግን
ተካ ከመሬት ተነስቶ የሚዋሽ ዓይነት አይደለም። ቢሆንም. . .
ምናልባት ግማሹ እውነት ሊሆን ይችላል። ግን ከጨረሱ በኋላ
«አንዴ እንድገም?» ያለችው ውሽት መሆን አለበት
ለመሆኑም ለምን ይህን ታሪክ ነገረኝ? ሴት ማግኘት መቻሉን
ለማሳወቅ ያለው ይሆን? ምስኪን ተካ! ....

💫ይቀጥላል💫
👍321
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#አራት


#በአሌክስ_አብርሃም


..."እ..ጎረምሳው መቼ ጀመረህ?” አለኝ። (በቃ ምርመራ ተጀመረ ማለት ነው ?) ሰውዬውን ትኩረት
ስመለከተው ለካስ ዓይኑ ልክ አይደለም፤ ትንሽ ሸውረር ያለ ነው። ታዲያ መጽሔት ላይ ከየት አባቱ ያመጣውን ፎቶ ነው የለጠፈው ?..

“መቼ እንደ ጀመረኝ አላወቅኩም ድንገት ከፍቅረኛዬ ጋር…"

"እ … ድንገት ከፍቅረኛህ ጋር ዓለምሆን ልትቀጭ … ሱሪህን አውልቀህ .… ቡታንታህን አውልቀህ በልስትለው…. ባባቴም የለ ብሎ ድፍት፣ ቅዝቅዝ አለብህ … እ? አዋራጅ እኮ ነው!አዋራጅ! ስንቱ በዚህ ዓይነት አጉል ጊዜ በሴት ፊት መዋረዱ አሸማቅቆት ገመዱን ቋጥሮ ራሱን ሲጥ አድርጓል መሰለህ ! እኔ እንኳን ሁለት ምን የመሳሰሉ ልጆች በዚሁ ጠንቅ ታንቀው የሞቱ አውቃለሁ አንዱ እንኳን መርዝ ጠጥቶ ነው … ያው ነው!ቀላል ነገር እንዳይመስላችሁ፡ ሴቶቹ ደሞ ይችን ወሬ ካገኙ እየዞሩ ለሁሉ
ነው የሚያወሩት“ አለ ከአፌ ላይ ነጥቆ። ይሄ ሰውዬ እንዴት ነው የሚቀባጥረው በእግዚአብሔር
በአንድ ጊዜ መንፈሴንም አኮላሸው እኮ።

እና.እንዴት ነው ትንሽም አይላወስ፣ ወይስ ጀማምሮ መሃል ላይ ወገቤን ነው የሚለው ሲል
ጠየቀኝ።

"ምኑ ?” ብዬ ጠየቅኩት።

"ቆ..ህ ነዋ" ብሎ ቃሉን እንደተፈጠረ አፈረጠው! ስድ !

“አይ ምንም የለም” አልኩ እየተሸማቀቅኩ።

"ከዚህ በፊት ሌላ ሴት ጋር እንዴት ነው …አልጀማመርክም ?”

"ሌላ ሴት ጋር ሄጄ አላውቅም
“ተው ተው ! ለኃኪምና ለንስኃ አባት ሚስጥር አይደበቅም … ሃሃሃ እስቲ አንተኛው ወደ ውጭ
ውጣ¨ አለና ሃኒባልን እዘዘው። ሃኒባል ሹክክ ብሎ ወጣ (ይሄ ደግሞ ምን ያሽቆጠቁጠዋል)

ሃኒባል እስኪወጣ ጠበቀና፣
"እ… ጓደኛህ እንዴት ናት ”

“እንዴት ናት ማለት ?” አልኩት ጥያቄው ግራ አጋብቶኝ።

እንደው መልኳ፣ ጸባይዋ ማለቴ ነው። አንዳንዷ ሴት እኮ ትዘጋለች። እውነቴን ነው ዛላዋ አምሮህ፡፡
መልኳ ስብሆ ስትቀርባት አንዳንዷ ሴት እንኳን መተቃቀፍ ምግብ ትዘጋለች

"እ … ፀባይማ እናት ናት መልኳም ቢሆን" አልኩና ዋሌቴን አውጥቼ ፎቶዋን ሰጠሁት። መነፅሩን ፈልጎ ዓይኑ ላይ ሰካና ፎቶውን በትኩረት ወደ ዓይኑ ቀረብ ራቅ እያደረገ ተመልከቶ፣

"ኧረግ… ኧረግ ... ኧረግ ወንድሜን ! እውነትም ተይዘሃል። ይችን የመሰለች ልጅማ ካመለጠችህማ ሰውም አትሆን…” ብሎ አፉን ጠረገ። ዝም ብዩ አየዋለሁ፡፡ የሙናን ፈቶ እስኪበቃው ተመለከተውና
ጉሮሮውን ገርገጭ አድርጎ ምራቁን ከዋጠ በኋላ
እንደው ትንሽም አልሞከራችሁ ?” ሲል ጠየቀኝ።

"ኧረ ምንም የለም" ፎቶዋን እንደገና ተመለከተው።

"ምናምን አዙራብህ እንዳይሆን” አለኝ።

"ምንድነው ምናምን ?”

"የዛሬ ሰው አይታመንም። አንዳንድ ሴቶች ሌላ ሴት ጋር እንዳትሄድባቸው ሌላ ሌላ ነገር እንዳታደርግ ያሰሩብህና፣ ሲቆይ ለነሱም ይተርፋል ጠንቁ። እንደው አቋም ብቻ ሆንክ እንጂ አንተም ብትሆን ሸበላ አንዷ እንዳትቀማት አዙራብህ ቢሆን ማን ያውቃል"

"አረ እሷ" ሰለቸኝ ሰውዬው። እውነቱን ለመናገር ራሱን ቁልል ያደረገ ዘላባጅ ነገር ነው። ለስጋዬ
ፈውስ ብመጣ ጭራሽ ነፍሴንም ያቆስላታል እንዴ ?!

"ቀላል ነው አይዘህ !! የሰው እጅም ሆነ ሌላ መፍትሄው በእጃችን ነው' ሲለኝ ብስጭቴ ብን ብሎ ጠፍቶ ጆርዬ ቆመ።
አውርቶም ተሳድቦም ብቻ ያቁምልኝ፤ ሌላው ትርፍ ነው።

"እውነትዎትን ነው ቀላል ነው ” አልኩት በጉጉት።

"አዎ ! ይች ምንአላት ?” አለ ልክ ወደ ብልቴ አቅጣጫ በእጁ እየጠቆመና ቀማጣጣል ዓይነት ከንፈሩን ወደ ታች ጣል እያደረገ። እንኳን ይችን ስቱን አቁምነዋል!ይሄ ወዲህ ስትመጡ መታጠፊያው ጋ ያለውን ቀልቀሎ ሆቴል ታቀው የለም?”

"አዎ አውቀዋለሁ" አልኩ በጉጉት። ደግሞ አንድ የሆቴል ሕንፃ ከእኔ ጕዳይ ጋር ምን አገኘው ብዬ።

“ይሄውልህ የሱ ሕንፃ ባለቤት እንዲህ እንዳተ ፀሐይ የመሰለች ሚስት አለችው። መቼስ ብር አለን
ብነሆ ጉዳያቸውን ሳይፈትሹ ነው ትዳር ውስጥ የሚዘፈቁት። እቅፎ ቢለው ቢሰራው ወንድነት ከየት
ይምጣ ? ጭራሽ አጅሪት ውጭ ውጭ ታይ ጀመረልሃ ... ይሄን ሲሰማ ሊያብድ ሆነ። በኋላ እኔ ጋ
በሰው በሰው መጣና እንደሚሆን አድርጌ ላኩት። ይሄው ዛሬ እንኳን ለሚስቱ ለውሽሞቹም ተርፏል።
ሚስቱ እንዴት እንደምትንሰፈሰፍለት አገር የሚያውቀው ነው” የተቸገረ ሰው ሞኝ ነው፤ ዝም ብዬ
ሰውዬውን እሰማዋለሁ። አወራሩ ድራማ የሚሰራ ነው የሚመስለው።

“አንተ እሱን ትላለህ ! ይሄ በየቀኑ ቴሌቪዥን ሳይ 'እንትን' ፕሮግራም ላያ የሚቀርበው አውግቸው
” … በቴሌቪዥን ሲናገር ድምጹ ሲያስገመግም አንሰሳ ገዳይ አይመስልም ነበር ? ሃሃሃሃ ማታ ማታ ሚስቱ እያንከላፈተችው ስንት ዓመት አልቅሷል መሰለህ፡፡ እንደውም ይሄ ትልቁ ልጁ የሱ አይደለም እየተባለ ይታማልኮ። አሃ ምን ታርግ ታዲያ ያችን የመሰለች ቆንጆ በአምሮት ትሙት እንዴ ! የሱ እንኳን ሽንፈተ ወሲብ ነው”

“ሸንፈተ ወሲብ ምንድን ነው ?”
አልኩ መጽሔቱ ላይ አይቼው ያልገባኝ ነገር ትዝ ብሎኝ።

“እሱማ እንግዲህ … አገር አማን ብለህ ልትተቃቀፍ ገና ሴቷ ሰላም ብላ እጅህን ስትጨብጥህ አንተ
ጥንቅቅ ብለህ በቁምህ ጨራርሰሃል !! ሲበዛ እስከመሳሳም ብትዘልቅ ነው፡፡ አንዳንዱማ የተሞናደለ ዳሌ፣ ሎሚ የመሰለ ተረከዝ ሲመለከትም በቁሙ ሱሪው ላይ ይለቀዋል። ባንድ ፊቱ እንዲህ እንዳተ መዳፈን ይሻላል እንጂ፣ ሴቶች ሽንፈተ ወሲብ ያለበት ወንድ ላይናቸው ነው የሚቀፋቸው … ላይናቸው ወይ አይተወው ወይ አያደርገው … አጉል ነካክቶ የሰው አምሮት መቀስቀስና ሥም ነው ትርፉ ከፉ ችግር ነው። ያንተ በስንት ጣዕሙ፡ ያንተማ ምናላት ቢሆንልህ እሰየው ባይሆንም ሴት ቀረ አትሞት"

“ላይሳካ ይችላል እንዴ ?” ስል የነበረችኝ ተስፋ ኩስምን ብላ ጠየቅኩ።

“ምሳሌውን ማለቴ ነው እንጂ .. አንተማ ታሰታውቃልህ፤ የአገር ሴት አይመልስህም ቱ ግዛው ምናለ
ቀለኝ። ከዚህ ቤት እግርህ ሳይወጣ ነው እንደ ሚዳቋ ቀንድ ቀጥ ብሎ የሚቆመው። ወዮላት ለዛች ሚስኪን” አለና የሙናን ፎቶ እንደገና ወደ ዓያኑ እስጠግቶ ተመለከተው። ተስፋዬ መለስ አለልኝ።

“እግዲህ ሁለት ዓይነት አሰራር አለ፤ አንዱ .. ይሄ እንኳን ላንተ አይሆንም” አለ መልሶ።

“ለምንድነው ለኔ የማይሆነው ?”
“ውድነዋ ! ውድ ነው ... ዋጋውን ብትሰማ ከወንድነትህ በፊት ትንፋሸህ ነው እዚሁ የሚቆመው

"ወዳጄ"

"ግዴለም ይንገሩኝ ?"

"አይ ይቅርብህ። አሁን ጓጉተህ ነው፣ በኋላ ፍቅሩም አምሮቱም ሲወጣልሀ የከፈልከው ገንዘብ ትዝ ባለህ ቁጥር እንኳን እንትንህ ነፍስህም ጭምር ነው የሚሸማቀቀው። እንደውስ ተመልሰህ መጥተህ ብሬን መለስልኝ ልትል ነው ? ቅቅቅቅ' ሳቁ ይቀፋል። የሆነ ነገር ሲቧጠጥ የሚወጣው ዓይነት ድምጽ ነው።

"እሺ ሁለተኛውስ ?"

"ባይሆን እሷ ትሻላለች አንድ ሐያ ሺ ታስከፍልሃለች እንጂ ፍቱን ናት”

"ሐያ ሺ …?”

"አዎ! ምነው?”

"አልተወደደም ?”

"እኮ ! የመጀመሪያውን ብትሰማ ያልኩህ ለዚህ እኮ ነው ! ቢሆንም ዓይንን ባይን ለማየት ሒያ ሺ ምን
አላት ? እንኳን ለማቆም የቆመበት ልክስክስ ሁሉ እዚህ እኛ አካባቢ ላሉ ሴተኛ አዳሪዎች ሐያ ሺ
ይከፍል የለም እንዴ ?! ያውም ላንድ ሌሊት። መቼስ ሐያ ሺ ብር ሳይኖርህ ይችን የመሰለች ቆንጆ ላይ አትንጠለጠልም፤ እንግዲህ ምርጫው ያንተ ነው።” ብሎ ፎቶውን መለሰልኝ ወደ ቴሌቪዥኑ ዞሮ በሪሞት መቆጣጠሪያው ድምጹን ከፍ አደረገው፡፡
👍272🔥2
የሙናን ፎቶ ሳየው እንባዬ መጣ። ሐያሺ ብር ፣ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ሐያሺ ብር ኖሮኝ አያውቅም።
ያው በዛም አለ በዚህ፣ ፍቅርን ብር አይገዛውም ይሉት ዲስኩር ካፈር ተቀላቀለ ? ሙናን ላጣት
አልፈልግም፡ አፈቅራታለሁ። በሐሳብ ተውጬ መሬት መሬት ስመለከት የሰውዬው ድምጵ አባነነኝ…

"ይችን የመሰለች ቆንጆ አንዴ ወንድ ከቀመሰች አበቃ ! አጠገብህ አትደርስም። ወዳጀ አፈላልግና ይሰራልህ አለኝ፡፡ ይሄ ደነዝ አቤት ቃሉ እንዴት እንደሚያም!ጕዳዩ የወሲብ አይደለም፣ ጉዳዩ የሴትና
የወንድ ጣጣ ብቻ አይደለም፣ ጉዳዩ የሙሉ ሰውነት ጉዳይ ነው። ፍቅር ጢም ብሎ የሞላ እኔነት
እንደተነደለ በርሜል ቀስ በቀስ ፍቅሩን ማንጠባጠብ ሳይሆን እንደፈረሰ ግድብ ሙልጭ ብሎ ውስጡ ያለው የፍቅር ሙላት ፈስሶ ባዶ መሆን፤ ባዶ የመሆን አፋፍ ላይ ነኝ።

“ሴት ልጅ አንዴ የወንድ ጠረን ቀምሳ ትመለሳለች ብለህ እንዳታስብ ?! ይለፈልፋል ደብተራ ግዛው ድከም ባለ እርምጃ ከተንጣለለው ቪላ እግሬን እየጎተትኩ ወጣሁ። ከኋላዬ የሰውዬው ድምፅ ተከተለኝ፣ “ሴት አንዴ … ከቀመሰች… " ከዚህ በላይ ብቆይ ይሄን ሰውዬ አፍንጫው ላይ ሳላቀምሰው አልቀርም ነበር።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ቀጥ ብሎ ቆመ!!

አዎ የነበረኝ ተስፉ ቀጥ ብሎ ቆመ !

ሙና ደወለች። ሰው ማታ ይደውላል፣ እሷ በደረቅ ሌሊት ስምንት ሰዓት ላይ ! ምን ሆነች ብዬ ደነገጥኩ።

“ተኝተህ ነው አብርሽ ” አለችኝ ስልል ባለ ድምጽ። ያ የምወደው ድምጽዎ የጦር ክተት አዋጅ
ከሆነብኝ ሰንብቷል። ወሬዋ ሁሉ ሄዶ ሄዶ እንትን እየሆነብኝ ተቸግሬያለሁ። እስቲ በዚህ ሰዓት
"ተኝተህ ነው ?" ማለት ምን ማለት ነው ? እና ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ምን እሰራለሁ? እንኳን ብቻ
እሷም ከጎኔ ኖራ በዚህ ሰዓት ድብን ያለ እንቅልፍ ላይ ነው የምሆነው ! አንዳንድ ሴቶች ፍቅረኛቸውን እንቅልፍ የመንሳት መብት ያላቸው መስሎ ይሰማቸዋል !ድምፃቸው
ፍራሽ፣ ሹክሹክታቸው አንሶላ፣ ሳቃቸው እንቅልፍ ሆኖ እረፍት እንደሚሰጥ ዓይነት፤ የምንሰለቻቸው አይመስላቸውም። ከተፈጥሮ በላይ የመሆን አቅም ያላቸው ይመስላቸዋል ? ልካቸውን አያውቁትም!! ደግሞ የሆነ ጊዜ አለ፣ ሴቶች እንቅልፍ የሚያጡበት። እውነቴን ነው፤ ምከንያቱን ራሳቸውም
አያውቁትም። ሌሊት ተነስተው ቁልጭ ቁልጭ ይላሉ። ቀን የጠጧትን ማከያቶ፣ መንገድ ላይ .
የፎገራቸውን ወንዶች እያስታወሱ ካለ እንቅልፍ የሚያሳልፏቸው ሌሊቶች አሉ። በሐሳብ
የሚዛብሩሳቸው ! ነጭናጫ ሆኛለሁ።

“ናፍቄሃለሁ አብርሽዬ”

"እስካሁን ኤልተኛሽም?"

ተኝቼ ነበር፤ ድንገት ቀሰቀሰኝ"

“ማነው የቀሰቀሰሽ ?”

"ፍ…ቅ…ር…ህ" አለች ሞልቍቅ ብላ። ሙና ቆንጆ ናት። ድምጽዋም ያምረኛል፤ ግን መሞላቀቅ አያምርባትም ! መሞላቀቅ የሚያምርባት ሴት አለች፣ መሳቅ የሚያምርባት አለች፣ መኮሳተር ውበቱን
የሚደፋባትም አለች፣ መሞላቀቅ ግን የሙና መክሊት አይደለም። ሙና የሚያምርባት የጣውላ
መሰንጠቂያ ማሽን ሰሚመስል የጠዋት ድምጽ፣ “ሂድ ወደዚያ" ስትል ነው።

"ምነው ዝም አልክ ?”

"ኧረ አላልኩም !”

“ምነው ኮስተር አልክ ”

"ኧረ አላልኩም”

"አልናፈከኝም?” ማውራት ፈልጋለች። ማውራት አልፈለግኩም። ማውራት አልፈለግኩም ማለት
ሙናን አልፈልጋትም ማለት አይደለም። ይሄ ፆታዊ ሰካራም ሒሳብ ቅፅበትን እንደዘላለም እየደመረ የተናገረ ድምሩን በሰው ሕሊና ይቆልላል፡ ነገ ሥራ እገባለሁ መተኛት አለብኝ። ሙና ሕይወት አይደለችም፤ የሕይወት አንድ ክፍል ናት። ሕይወት አገር ቢሆን … ፍቅረኛ፣ ሥራ ዕውቀት፡
መዝናናት፣ ሐዘን፣ ደስታ፣ ቤተሰብ ብሔር ብሔረሰቦች ናቸው።

አገርን ለማቆም እኩል ድርሻ፣ እኩል አስተዋፅኦ ያላቸው የአገር ክፍሎች፡ እና እንቅልፍም አንድ ብሔር ነው። ሙና የምትባል ብሔር እንቅልፍ ለሚባል ብሔር ከብር ልትሰጥ ይገባል። ዝም ብላ ስምንት ሰዓት ደውላ የእንቅልፍ ብሔርን ከአልጋ ክልሉ እንድታቀርር ማን መብት ሰጣት ? ቀን አንስቷት ስለተፈቀረች ብቻ፣ ቀን በኪነጥበቡ ልቤ ዙፋን ላይ ስላስቀመጣት ብቻ፡ ያሻትን ማባረር፣ ያሻትን መግፋት ምን የሚሉት አንባገነንነት ነው ? የድሃ ርስቱ እንቅልፍ ነው፤ ደሃ ሶደሬ አይዝናና ዱባይ፣እንቅልፉ ነው ስጋና ነፍሱን የሚያሳርፈው በህልሙ ነው ቅቤ እየጠባ የሚወዘው። ነጭናጫ ሁኛለሁ።

“ተኝቼ በህልሜ አየሁህ (ኤጭ ! ሰሞኑን ህልም አብዝታለች) ሰው ለካ አንዱን ህልሙን መፍታት
ሲያቅተው ነው ብዙ ህልም የሚያንጋጋው።

“ኧረ…አየሸኝ ? መቼም ያንን የምትወጂውን ኬክ እየጋበዝኩሽ መሆን አለበት ያየሽኝ ... አንቺና ኬክ : ብዬ አዎ እንድትለኝ ምላኬን ተማፀንኩ።

“አ...ይ….ይ..ሌም ! እንደገና ሞክር እደግመዋለሁ ሙና
"መሞላቀት ያምርባትም!

“እ እ እ ስፕሪስ እየጠጣን ?” ስፕሪስ ትወዳለች ... ይሄ ድምጽ ግን የስፕሪስ እንዳልሆነ አውቀዋለሁ።

"ሃድ ! በ….ቃ መብላትና መጠጣት ብቻ ነው እንዴ የምታውቀው ? እስኪ ሌላ ፍቅረኞች የሚሰሩት
ነገር ገምት ?"

“ፍቅረኞች የሚሰሩት ? ... ዎክ እያደረግን ይሆናላ መለስኩ።

“ኡፍፍፍፍፍ ... ቤት ውስጥ … መኝታ ቤት ውስጥ… ቆጣ ብላ ጠየቀችኝ (ህልሟን እኔ ያየሁ መሰላት እንዴ፡ የፈለግኩትን ብገሃምት ምን አነጫነጫት) ሰው ለካ ከመሻቱ ሲፈጠር፡ ከምኞቱ አብራከ እንደገና ሲወለድ ሕፃን ይሆናል። ሙና ሕፃን ሆነች !

“መኝታ ቤት ፍቅረኞች የሚሰሩትን ነገር ገምት” አታበሳጭም ? በሷ ቤት በአፈ ከተናገርኩት፡ በልቤ
የማምንበት ሃቅ የሚሆን መስሏታል ! ደግሞስ ለእንትን ወኔው ካለ ማነው መኝታ ቤት ብቻ ይደረጋል ያለው ?

"እኔ የምልሽ …. የጠየቅሽውን የሥራ ዝውውር እምቢ አሉሽ በቃ ”
“አሁን ማን ስለሱ አወራ ተበሳጨች። እኔ ደግሞ ሰለቸችኝ።

“አሁን ምን እያደረግሽ ነው ?

“አሁን ልብሴን ውልቅልቅ.. አድርጌ፣ ብርድ ልብሴ ውስጥ፣ አንሶላዪ ውስጥ፡ በቃ አንተን እያሰብኩ፡ ትራሴን እቅፍፍፍፍፍ እድርጌ እገላበጣለሁ አላሳዝንህም ? (ምነው ይች ልጅ እሳት አደረጋት እስክንጋባ ምናምን ሰትል አልነበረ እንዴ ?) ሕይወት እንዲህ ናት እንግዲህ፣ በተሸነፍንበት ነገር ላይ
ደነዙን ስሜት ሁሉ ውኃ ውስጥ እንደገባ ውሻ ድንዛዜውን አርገፍግፎ እንዲነሳብን ታደርጋለች።ድምጽዋ ውስጥ እኔ አለሁ፡ ማድረግ የማልችለውን ምኞት እያደረግኩ። አኔ … ከትራስ የማልሻል አንዳንዴ የሙና ችግር የምታፈቅረው ሰው ማውራት የማይፈልገው ነገር ላይ መሟዘዝ መውደዷ ላይ ነው !ሙዝዝዝ !ምን ያህል ለእኔ ስቃይ እንደሆነ አይገባትም ! በቃ ማውራት የምትፈልገው ስትመጣ
ማድረግ የምትፈልገውን ብቻ ነው፡፡ እኔ ደግሞ ማውራት የምፈልገው ምንም ማድረግ አለመቻሌን ነው። “ሙና ካንቺ በላይ ችግሬን የሚረዳ ሰው በምድር ላይ የለኝም፣ ችግር አለብኝ ወሲብ ማድረግ
አልችልም” ልላትና ጭንቄን ልገላገል እፈልጋለሁ፤ ግን የፍላጎቷ ቀዝፈት ግልፅነቴን ደፈጠጠው ! ዝም!!

“ምነው ዝም አልክ ?”

ኡፍፍፍፍፍፍፍፍ!እድሜ ልኬን ዝምብል፣ ሰፈራችን እንዳለው ከተወለድኩ ጀምሮ እንደማውቀው
👍251🔥1
ድንጋይ ዝም ብል ብዬ ተመኘሁ። “ሴት አሳዳጅ ይላል ሞኝ ሰው፤ በራሱ ችግር መሽሻ አጥቶ አንዲት
ሴት ያውም የምታፈቅረው የሚያፈቅራት ሴት የምታሳድደው ሚስኪን እዚህ ያላየ ሁሉ። ስማይ ዝም ያለው ምድር ፍቅሩን ሽታ ቀን ከሌት ስለነተረከችው መሰለኝ። ተራሮች ዝም ያሉት ሴት ተራሮች
ሕልማቸውን እያወሩባቸው ፍቺው ሲጠፋባቸው መሰለኝ፡፡ ሰዎች የሚጮኹት መሻታቸውን ከማይሻ
ሕይወት ስለተላተሙ መሰለኝ። እውነተኛው ሕይወት ከሽፎ አሻንጉሊት ኑሮ አቅፈው እዬዬ እያሉ።

ሙና ጆሮ ላይ ስልኬን ዘጋሁባት።

ለመጀመሪያ ጊዜ ሙና ላይ ስልክ ዘጋሁባት። ነፍሴ የሚራሰውን ድምጽ ቋቅ ብሎ ተፋው: "ኔትወርክ ተቋርጦ ነው” አልኩት ለራሴ። ራሴ የሙና ጠበቃ ሆና እንዳይሞግተኝ ፊት ስነሳው መሆኑ ነው። ከራስ የተረፈንን ነው መቼስ ለሌሎች የምንዋሸው።

ጠዋት ሙና ደውላ ምንም እንዳልተፈጠረ፣ “ይሄ ኔትወርክ ምቀኛ እኮ ነው፤ ሶሪ ጆሮህ ላይ ተዘጋ የኔ ቆንጆ" ስትለኝ ልቤ ተፈራገጠችብኝ። ከመኝታዬ መነሳት አልቻልኩም። ስንት ነፍስ አለ ግራ ቀኝ የማያይ፣ በተቆፈረለት የፍቅር ቦይ ኮለል ብሎ የሚፈስ ቢሻን ! አመመኝ ! ስንት እርግብ ነፍስ አለ
በእግዚአብሔር !! እንደ ውሸት ትልቅ ጉልበት የሚጠይቅ ጕዳይ ምን አለ ?....

ይቀጥላል
👍11
#ትኩሳት


#ክፍል_ሶስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

...በካፌ ዶርቢቴል በኩል ሳልፍ ሉልሰገድ ከዚያ ወጣ። ቀይ ፊቱ
ደም ለብሷል። ጉልህ ዓይኖቹ ጉድጓዳቸው ውስጥ ይገላበጣሉ። በጣም ተናዷል።

“ምን ሆንክ?» አልኩት
"ይህን ተካ አስታግስልኝ፣ አለዛ አንድ ቀን እገድለዋለሁ» አለኝ
“ምነው?»
"ባገኘኝ ቁጥር ያበሽቀኛል። ላብድ ነው»
«ለምን ሁለተኛ እንዳታናግረኝ አትለውም?»
የተዘረዘሩ ጥቃቅን ጥርሶቹን በተሸነፈ የንዴት ሳቅ እያሳየኝ
ቢያንስ አስር ጊዜ ብየዋለሁ» አለ ሁለተኛ ያናገርከኝ እንደሆነ፣ ወይ ለፖሊስ እነግራለሁ ወይ እገድልሀለሁ ብዬዋለሁ።
ደጋግሜ ደጋግሜ ነግሬዋለሁ፡፡ ሰድቤዋለሁ»

«ታድያስ?»
በሚቀጥለው ጊዜ ሲያገኘኝ ያነጋግረኛል። ትንሽ ካናገረኝ በኋላ
ያበሽቀኛል»
«አታኮርፈውም?»
«አይገባውማ!»
«አሁን ምን ይሻላል?»
«እኔ 'ንጃ፡፡ ይህን ከተማ ለቅቄ ልሂድ መሰለኝ
እየሳቅኩ «እስከዚያው ና ምን የመሰለ ቢራ ላጠጣህ» አልኩና
ባቡር ጣብያው አጠገብ አንዲት ስም የሌላት ካፌ አለች፣ እዚያ
ወሰድኩት። አንድ ቡና አይነት ቢራ አለ፣ ከስኮትላንድ የሚያስመጡት፡፡ ፀሀይ ላይ ቁጭ እንዳልን እሱን ቀመሰና
«ይህን እንዴት አገኘኸው ባክህን? እኔ ሁለተኛ ሌላ ቢራ
አልቀምስም» አለ። ንዴቱን መርሳት ጀምሯል፡፡ ራሱን እየነቀነቀ
«የተካ ዋና ፕሮብሌሙ ምን መሰለህ?» አለኝ «ጥሩ ልጅ ነው::
ከሰው ጋር ተስማምቶ መኖር ይፈልጋል። ግን በሄደበት ሰውን
እንዳበሸቀ ነው:: ወዶ አይደለም። ፍጥረቱ ነው»

«አውቃለሁ። ረስቼ አማንዳ ስትፈልግህ ነበር»
ዝም አለ። ገባኝ
"የፈረንጅ ሴቶች ሲሰለቹ!» አልኩት
«ያንተም ሰልችታሀለች?» አለኝ
«ፈረንጅ አይደለች?»
«አንተስ አትረባም» አለኝ
«ለምን?»
«ያችን የመሰለች ቆንጆ ምኗ ይሰለቻል? ድምፅዋ ብቻ
ይበቃል። በዛ ሰማያዊ አይኗ እያየችህ ያን ፈገግታ ስትሰጥህ
አንድ ፈገግታ እንደሱ ብታጠጣኝ ችዬ ከሷ አልለይም ነበር። በዚያ
ወፍራም ድምፅዋ ሉ ሃኒ ሉ' ብትለኝ ለዘለዓለም እታሰራለሁ»

«ፈገግታውንም ቁልምጫውንም ትሰጥሀለች ከፈለግክ»
«እንዲህም ብልህ'ኮ፣ ፈገግታውና ቁልምጫው ብቻ አይበቃም»
«አንተ ከፈለግክ ሌላውንም ትሰጥሃለች»
«እሱን ተወው! ካንተ ጋር ፍቅር እንደያዛት ያስታውቃል»
« ይመስልሀል» አልኩት
«ትወድሀለች ስልህ!»
«እሺ ይሁን፡፡ ግን አንዳንዴ ስላንተ ጣል የምታረገው ንግግር
አንተም ጠጋ ብትላት እንደማትሸሽህ ያሳያል»
«አዬ? ምን አለች?»
«አይ፣ እሱን አልነግርህም፡፡ ጠጋ ብትላት ራሷ ትነግርሀለች»
«እውነት እንድወስድልህ ትፈልጋለህ?» አለኝ
«አዎን፡፡ ግን ለሀበሾቹ እንዳትነግር»
«ግድ የለህም። እኔ ምልህ የኔን ሸክም ደሞ እንተ ትንሽ
ብትሸከምልኝ። አውቃለሁ አስቀያሚ ነች። ግን ጠጋ ስትላት የደስ ደስ አላት። ደሞ ከዛች ከቆንጆ ጋር ሰንብትህ ወደዚችኛዋ ስትመጣ
ጥሩ ለውጥ ሳይሆን አይቀርም። ሞክር እስቲ»
“አንተ ሞክር"
Shake on It! (ጨብጠኝ)» አለኝ፡፡ ተጨባበጥን
ትንሽ ቆይቶ፣ ራሱን እየነቀነቀ
«አባቶቻችን አሁን የተባባልነውን ቢሰሙ ምንኛ በናቁን!» አለ
እኔና ሉልሰገድ ሚስቶቻችንን እየያዝን አብረን ሲኒማ ገባን፣
አብረን ናይት ክለብ ሄድን። ለመለዋወጥ ሞከርን። አልቻልንም።
እነሱም ጓደኝነት ተያያዙ፡፡ እንደተሸነፍን ገባን

«ገና የፈረንጆቹን ያህል አልሰለጠንንም ባክህ» አለኝ

«እስከመቸም አንሰለጥንም» አልኩት

ሚስት መለዋወጥ ሲያቅተን ጊዜ ታሪክ ተለዋወጥን፡፡ የኔን
እንዴት እንዳገኘኋት ነገርኩት። እሱም ተራውን ነገረኝ። ታሪኩን
ሲጨርስ፣

“እንድ ቀን ምን ሆንኩ መሰለህ?» አለ «ከእራት በኋላ እቤቴ
እንድንገናኝ ተቃጠርን። የቀጠሮው ሰአት ሲደርስ ቤቴ መሄድ
በጣም አስጠላኝ፡፡ ሴት አጥተው ብቻቸውን የሚያድሩትን ጎረምሶች
በጣም ቀናሁባቸው። ቡና ጠጥተህ' ሲኒማ አምሽተህ ቤትህ
መመለስ፣ ፒጃማህን ለብሰህ ጥቅልል ብለህ ብቻህን መተኛት፤ ይሄ በጣም ትልቅ እድል መስሎ ታየኝ! ገደል ትግባ! አልኩና ሲኒማ
ገባሁ። የጀምስ ቦንድ ፊልም ነበር ያየሁት። ሰለላውን፣ ተኩሱን፣
ቦክሱን፣ ድፍረቱን ከምንም አልቆጠርኩለት። ትልቅ ጉብዝና ሆኖ የታየኝ ምን መሰለህ? ይሄ ጄምስ ቦንድ ያሰኘችውን ሴት ተኝቶ፣ ሲበቃው ዘወር ማለት ነው፤ አለቀ በቃ፡፡ እኔ ግን ከአንዲት ሴት
ዘወር ማለት አቅቶኝ እየቀጠርኳት ሲኒማ እገባለሁ፡፡ ራሴን እንዴት
ናቅኩት!

ስለጀምስ ቦንድ እያሰብኩ ወደ ሊቴ ሄድኩ። አኩርፋ
ኣንደምትቆየኝ ስላወቅኩ፣ የምነግራትን ውሸት እያሰላሰልኩ መኝታዬ ገባሁ:: መብራቱን አበራሁ። እንቅልፍ ተኝታለች። መስኮቱ ላይና ወንበሩ ላይ ሸሚዞቼ፣ ካናቴራዎቼ ሙታንታዎቼ፣ እግር ሹራቦቼ
ታጥበው ተሰጥተዋል። የተሰማኝን ልገልፅልህ አልችልም። እፍረት
ነው ይመስለኛል። ድቅቅ አልኩ፡፡ ተሸነፍኩ ልብሴን አውልቄ አልጋ ውስጥ ስገባ ነቃች። የት ቆየህ
አላለችኝም። ዝም ብላ አቀፈችኝ፡፡ አቤት እንዴት ነው ያሳዘነችኝ
ሳለቅስ ምንም ያህል አልቀረኝም

« በነጋታው ከሷ ጋር ዋልኩ፡፡
ስለሷ ማወቅ ፈለግኩ::
ጠያየቅኳት። ነገረችኝ። ያልደረሰባት ግፍ ያለ አይመስለኝም ማለቴ በወንድና በሴት መካከል የሚደረግ ግፍ፡፡ ባሜሪካን አገር የሚደረገው ነገር አንዳንዴ ከኛ አገር ይብሳል። ባስራ ሁለት ኣመቷ ሶስት ጎረምሶች በግድ ያዟትና ጭኗን ከፍተው ሻማ ጨመሩባት።ይህን ምን ትለዋለህ? እስቲ እንደ ሴት ቢበዷት ምን ቸገራቸው ነበር? ባስራ ሰባት አመቷ ደሞ የታላቅ እህቷ ባል በጉልበት ተኛት፡፡
ይህንንስ ስትነግረኝ አለቀሰች። 'ቆንጆንኳ ብሆን ደስ ብየው ነው፣
አላስችል ብሎት ነው ይባላል። ግን ቆንጆ አይደለሁም። ምኔም ደስ አይልም። እንግዲያው ለምን አዋረደኝ? ክፋትንና ጭቆናን የሚስብ አብሮኝ የተፈጠረ አንድ ነገር አለ መሰለኝ አለች

«እውነት ይህን ምን ትለዋለህ» አለ ሉልሰገድ አንድ ሰካራም
አጎት አላት፡፡ እሱ ደሞ አንድ ቀን በግድ ሊተኛት ሞከረ። ታግላ
አመለጠችው:: ግን መሞከሩ እጅግ ጎዳት፡፡ ምን ትለዋለህ ይህን
አይነት እድል? ከዚህ ሁሉ በኋላ ወንዶችን ጨርሳ መሸሽ ነበረባት።
አሷ ግን ተቃራኒ አደረገች፡፡ ለለመናት ሁሉ መስጠት ጀመረች።
እኔ ለዚህ ማስረጃ ላገኝለት አልችልም፡፡ ግን ምናልባት ለሁሉም መስጠት ያው ለማንም እንዳለመስጠት ይቆጠር እንደሆን?

ብቻ ምን ልበልህ? በጭራሽ አምላክ ያጠቃት ልጅ ናት።
ካወቀኝ ወንዶች ሁሉ አንተ ብቻ ነህ እሰካሁን እንደ ሰው የቆጠርከኝ አለችኝና እንደገና ኣለቀሰች፡፡ አልጋው ግርጌ ተንበረከከችና ጉልበቴን አቅፋ
"if you only knew what it means to me i will never be able to repay you never!” never እያለች እንባዋን አወረደችው።«ለኔ ምን ማለት እንደሆነ ባወቅክ! እስከመቸም ውለታህን ልከፍል አልችልም፣ እስከመቸም!»)
ራቁቷን ተንበርክካ ሳለ፣ ነጭ ገላዋ እንዴት ድቡልቡልና
አስቀያሚ እንደሆነ ታየኝ። በጣም አሳዘነችኝ፡፡ እንደዛ እዝኜ
አላውቅም፡፡ አብሪያት አለቀስኩ»
«ምነው አለቀስክ ? ትወደኛለህ እንዴ?' አለችኝ»
«ምንም ምርጫ አልነበረኝም
«አዎን እወድሻለሁ' አልኳት»
«'ምንም ወፍራም ብሆን?»
«'ምንም ወፍራም ብትሆኚ' »
ምንም ርካሽ ብሆን?»
«ምንም ርካሽ ብትሆኚ። ደሞ ርካሽ አይደለሽም፡፡ ተጠቃሽ
ተበደልሽ እንጂ አንቺ ያጠፋሽው ጥፋት የለም። You are a victim
(«ጥቃት የደረሰብሽ ነሽ»)
👍26😢2🤔1
"Yes I am a victim. God, I am a vicitim with no one to defend me” አለችና የባሰውን ስቅስቅ ብላ አለቀሰች
(«አዎን ተጠቂ። ማንም ተከላካይ የሌለኝ ተጠቂ ነኝ»)
«ሳባብላት ብዙ ጊዜ ወሰደብኝ
«እና ይኸውልህ፣ አገሯ እስክትገባ ድረስ እንድወዳት ከራሴ
ጋር ግዴታ ገብቻለሁ»
«መቼ ነው 'ምትሄደው?» አልኩት፣ ውስጥ ውስጡን እያደነቅኩት
«ካንድ ወር ተኩል በኋላ
«አይ! አጭር ጊዜ ነዋ»
«በኔ ቦታ ብትሆን አጭር ጊዜ አይመስልህም ነበር። ያንተስ
መቼ ነው 'ምትሄድልህ?»
«የኔ እንጃ መሄዷን። ግን እጮኛዋ ካንድ ሁለት ወር በኋላ
ይመጣልን»
«እጮኛ አላት?! ትወደዋለች ይመስልሀል? ፍቅር ማለቴ ነው»
«አዎን»
«ታድያ ካንተ ጋር. . .»
«ከኔ ጋር ያ ነገር ብቻ ነው:: አየህ፣ አገሯ ሳለች ከጥቁር ጋር
መተኛት በጣም ያምራታል። ግን አትደፍርም፡፡ ስለዚህ፣ ፍራንስ
የነፃነት አገር እንደመሆኑ መጠን
ትከሻዪን አንቀሳቀስኩ
«እጮኛዋስ ምን ይላል?» አለኝ ሉልሰገድ
«እንዴት ያውቃል?»
«አይ ሴቶች! እኛም'ኮ ስናምናቸው እንደዚህ ይጫወቱብናል»
«ምን አለበት? እኛስ እንጫወትባቸው የለ?»
«ቢሆንም አንድ አይደለም»
«ለምን አንድ አይደለም?»
«እነሱ ሴቶች ናቸዋ!»
በዚህ ስንስቅ «እኔ ምልህ» አለኝ በዚያ በሰማያዊ አይኗ
ስታይህ ፍቅር የያዛት ይመስለኝ ነበር፡፡ ለካስ ጥቁር ወንድ
ስለሚያምራት ኖሯል?»
«አዎን»
እንዲህ ከሆነማ ብሞክር ሳይቀናኝ አይቀርማ»
«እርግጠኛ ነኝ ይቀናህል። በጣም ደስ ትላታለህ ስልህ!»
እንደማፈር ብሉ፣ ግን ጉልህ አይኖቹ እየሳቁ
«ምኔ ነው ደስ የሚላት?» አለኝ
«ምን ልበልህ፤ ብዙ ነገር ነው:: አይኖችህ፣ ቅላትህ፣
አረማመድህ፡፡ ከሁሉ ይበልጥ ደስ የሚላት ግን ምን መሰለህ?»
«ምንድነው?» አለኝ
«ሌላ ቢራ እዘዝልኝና እነግርሀለሁ» አልኩት፡፡ አዘዘልኝ
ለምኔ ነው ከሁሉ ደስ የሚላት?» አለኝ
«ቆይ ቢራው ይምጣ» አልኩት። በሽቀ፡፡ ጠረጴዛው ላይ በጣቶቹ
ታምቡር እየመታ እኔ እያየሁት እየሳቅኩ ቆየን። ቢራዬ መጥቶ
አንዴ እንደተጎነጨሁለት፣
«ተናገር እንጂ!» አለኝ
«ከሁሉ ደስ የሚላት ፈገግታህ ነው»
«ሙት? ቆይ ' ስቲ» አለና ከኪሱ አንድ ትንሽ መስተዋት
አውጥቶ መስተዋቱን እያየ ፈገግ አለ። ራሱን እየነቀነቀ «እቺ ልጅ
አልተሳሳተችም፡፡ እነዚህ ጥርሶቼ እንደ አይጥ ጥርስ ቢዘረዘሩም፣
ፈገግታዬ ልብ ያጠፋል። ፈገግታዬ ልብህን እያጠፋውም?»
«እናትክን! ይልቅ ምን እንዳለች ልንገርህ» አልኩት
«ንገረኝ»
«ፈገግታው በሀይል ደስ ይለኛል፡፡ ጥርሶቹን ሳያቸው ጭኖቼ
መሀል ትኩሳት ሲቆሰቆስ ይሰማኛል» አለች
«እውነትክን ነው? ጥርሶቼ ይህን ያህል sex-appeal (ማራኪነት)
አላቸው? እቺ ልጅ በጣም እስተዋይ መሆን አለባት»
«እንዲህ አይምሰልህ፡ ሌላ ምን አለች መሰለህ?»
«ምን አለች? »
«እዚህ አለም ላይ ምን ያምርሻል ብትለኝ» አለች «ሉልሰገድ
ጭንና ጭኔን ክፍት ቢያደርገኝና» አቋረጥኩ
«እና?» አለ። ተንገብግቧል
እና ብልቅጥ ሲልለት፣ ሉልሰገድ ይህን እምሴን በጥቃቅን
ቆንጆ ጥርሶቹ ጋጥ ጋጥ! ጉርስ! እኝክ! ሲያደርግልኝ ያምረኛል»
አለች
«በሽቃጣ! አንት እርኩስ!»
«እኔ ምን አጠፋሁ? የፈለገችህ እሷ» አልኩት
ሁለታችንም መሳቅ ጀመርን፡፡ ሌላ ቢራ አዘዝን። ብዙ ሌላ ወሬ
አወራን። ስለባህራም ጠየቅኩት። እንዲህ አለኝ
«በእውነቱ አውቀዋለሁ ልልህ አልችልም፡፡ የሚታወቅ ኣይነት
ሰው ኣይደለም፡፡ ስምንት ወር ሙሉ ገንዘብ ሳታገኝ መኖር፣ ግን
ገንዘብ ከሚያገኙ ሰዎች እኩል መኖር፣ ቀልድ አይደለም፡፡
ኮሙኒስት መሆኑን ታውቅ የለ? አንዳንዴ ከሀበሾቹ ወይም
ከኢራኖቹ ጋር ሳይሆን ከፈረንሳይ ጓደኞቹ ጋር ማታ ማርሰይ ሄዶ
ኣምሽቶ ወይም አድሮ ይመለሳል፡፡ የኮሙኒስቶች ስብሰባ ነበረን
ይላል፡፡ ግን አንዳንዴ ምን ብዬ አስባለሁ ይመስልሀል? በእውነት
ኮሙኒስቶች ስብሰባ ይሄዳል? ወይስ ማርሰይ ጋንግስተሮች ጋ
ይሄዳል? እንደሱ ከሆነ ለገንዘቡ እንቆቅልሽ ፍች ይገኝለታል፣ አየህ
በፈት በይሩት ነበርኩ ይላል። ሁለተኛ አመት ኮሌጅ ጨርሼ
ሶስተኛ አመት ስገባ በያስሚን ፍቅር ምክንያት ወዲህ መጣሁ
ይላል። ያስሚን ይወዳት የነበረ የሊባኖስ ልጅ ናት። ግን ባንዲት
ልጅ ፍቅር ምክንያት ትምህርትህን አጋምሰህ አይንህን ጨፍነህ
ትሽሻለህ? ደሞ፡ በይሩት ሳለሁ ቤተሰቦቼ ብዙ ገንዘብ ይልኩልኝ ነበር፣እዚህ ስመጣ ጊዜ ግን ድንገት ድምፃቸው 'ንኳ ጠፋ ይላል፡፡ ለምን? ሌላ
ነገር ደሞ በይሩት የመካከለኛው ምስራቅ ሰላዮችና ጋንግስተሮች ዋና ከተማቸው ነው ሲባል ሰምቻለሁ። ባህራም
የሚለው ሁሉ እውነት ሊሆን ይችላል። ግን አይመስልም

"ይህንም ስልህ፣ እንዲሁ የሚመስለኝ ነው፣ እንጂ፣ ለምን
እንዲህ ይመስልሀል ብትለኝ በቂ ምክንያት ልሰጥህ አልችልም

«እኔ የበኩሌ ጋንግስተር ሆነ ኮሙኒስት ሆነ ግድ የለኝም: ልጁ
እንደተካ ብሽቅና ነጃሳ ሳይሆን፣ ተወዳጅና አብረኸው ስትሆን
የሚያስቅህ የሚያስደስት ነው። ስለዚህ ባላውቀውም እወደዋለሁ።ሲቸግረው አንዳንዴ ጥቂት ፍራንክ እፀድቅበታለሁ»

“አቃጣሪ ሊሆን ይችላል?

ጥያቄዬ አሳቀው; በጉልህ ውብ አይኖቹ ብቻ ሳይሆን በጥቃቅን
ዝርዝር ጥርሶቹ ጭምር ሳቀብኝ

«ይህን ሀሳብ ያሳደረብህ ተካ መሆን አለበት» አለኝ
«አዎን»
“አይ ተካ ብሽቁ! ለምን ደግ ሲውሉለት አይገባውም? ስለሱ
ልንገርህ፡፡ አንድ ቀን ማታ ሱርፕሪዝ ፓርቲ አድርገን ሁላችንም
ስንደንስ ሴት ስናባስል፡ ተካ አንድ ማአዘን ጋ አንድ ወንምበር ላይ
ቁጭ ብሎ ነጭ ወይን እየጠጣ ሲጋራ ያጨሳል፣ ጥፍሩን ይነክሳል።ባህራም እንዲሀ አለኝ 'ይሄ ተካ ብቻውን ቁጭ ብሎ አሳዘነኝ፡፡ ያቺ ልጅ አልተያዘችም ቀስ አርገን እናያይዛቸው:: እኔ መቸም ተካን አቀዋለሁ፣ እምቢ አልኩ፡፡ ባህራም ተቆጣኝ 'ኣትረባም አለኝ፡፡ ሄዶ
ተመስገንን ኣግዘኝ አለው። ተመስገንም እምቢ አለ። ባህራም አናን ሀበሾች በጣም ጥሩ ሰዎች ትመስሉኝ ነበር፤ ለካስ አትረቡም።
ለራሳችሁ ደስታን ካገኛችሁ፣ ሌላው ቢቀና ቢበሳጭ ግድ የላችሁም፡፡
በሉ ተውት! ብቻዬን እሞክራለሁ አለ። ተው ይቅርብህ አልነው፡፡
እምቢ አለ፡፡ ተካንና ያችን ልጅ ሊያያይዛቸው ሞከረ
«ለመልካም ሙከራው ተካ ሲያመሰግነው ሰምተህል
«እነተካ ነጃሳ ያሉትን ቢሉ፣ ባህራም የሚወደድና የሚከበር
እንጂ የሚናቅ አይደለም» አለኝ
ይሄ ሉልሰገድ ራሱ የሚወደድና የሚከበር ልጅ ነው፣
ያስታውቃል

አንድ ቅዳሜ ከሰአት በኋላ ሉልሰገድ ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ
ስሰራ አማንዳ ቁና ቁና እየተነፈሰች ገባች (ሶስተኛ ፎቅ ነው ቤቱ)
«ፈረንሳዮቹ ለምን ኤለቬተር አይሰሩም?» አለችና አልጋው ላይ
በጀርባዋ ተከመረች:: ስራዬን ትቼ ወንበሬን ከመፃፊያው ጠረጴዛ
ወደ አልጋው በኩል ኣርኩት
«ስራህን አላቋርጥህ» አለችኝ
«ምንም ኣይደለም» አልኳት
ወሬ ጀመርን፡፡ ሞርሞን ነኝ አለችኝ። ስለሞርሞን ሀይማኖት
ብዙ ስለማላውቅ ጠያየቅኳት፡፡ ስለጆዜፍ ስሚዝና ስለወንጌሉ፣
እንዴት ሁለቱ የጠፉ የእስራኤል ነገዶች» ውቅያኖስ አቋርጠው
እሜሪካ እንደደረሱ፣ እንዴት በሀጢአታቸው ምክንያት ነጮቹና
👍272🔥1
ቀዮቹ እንደዋጡዋቸው፣ ምናምን ዝብርቅርቅ ታሪክ ዘበዘበችልኝ፡፡
አሁን ኣብዛኛውን ረስቼዋለሁ፡፡ ግን ስለራሷ የነገረችኝን አስታውሳለሁ
«እኔ የሞርሞንን ሀይማኖት በሙሉ ልቤ እቀበለዋለሁ» አለች
«የሞርሞን ሀይማኖት ደሞ የጥቁሮች ፍጥረት ከነጮች ፍጥረት በታች ስለሆነ፣ ነጮች ከጥቁሮች ጋር አይጋቡ ይላል። እኔ ግን ቢቻለኝ ከሱ ጋር ልጋባ እፈልግ ነበር። ሉን ምን ያህል
እንደምወደው ይታይህ»
«ለመሆኑ ሉልሰገድ የት ሄደ?» አልኳት
“ብመኪናዬ ኒስ ሄደ። ማታ ይመለሳል»
«መኪና አለሽ እንዴ?»
«አዎን፣ ስፖርት ጃጉዋር፡፡ ካራት ቀን በፊት ከኢንግላንድ
መጣልኝ»
«ጃጉንዋር?»
«አዎን። አባቴ ሀብታም ነው:: ከሁለት ወር በፊት ነበር
መኪናው ይደርስሻል ያለኝ፤ ገና ዛሬ ደረሰኝ። ስለዘገየብኝ ተበሳጭቼ ነበር፣ አሁን ግን እንኳን ዘገየ እላለሁ»
«ለምን?»
«ያን ጊዜ መጥቶልኝ ቢሆን ኖሮ ከሉ ጋር ከመተዋወቄ በፊት
ይሆን ነበር፡፡ እና ሉ የተጠጋኝ ለራሴ ሲል ይሁን ወይስ ለጃጉዋር
መኪናዬ ሲል ይሁን ለማወቅ አልችልም ነበር። እንዲያውም
ለመኪናዬ ሲል ነው ማለቴ አይቀርም ነበር እርግጠኛ ነኝ። አሁን እንደዛ አይነት ሰው እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ ግን ከመተዋወቃችን በፊት ጃጉዋር ቢኖረኝ ኖሮ እንዴት ላውቅ እችል ነበር? የፈረንሳይ
ቆንጆዎች እንደ ልቡ ሊያማርጥ ሲችል ለምን እኔን ይጠጋኛል?
'ለጃጉዋሬ ሲል ብዬ ማሰቤ አይቀርም ነበር፡፡ እና ይህ ሁሉ ደስታ ይቀርብኝ ነበር»
«ደስታ ይሰጥሻል?»
«እንዲህ አይምሰልህ። እሱን ከማግኘቴ በፊት ደስታ ምን
እንደሆነ አላውቅም ነበር። አሁን ግን. . .»
«ፍቅር ይዞሻል»
«ያውም ውብ የሆነ፡ የቀስተ ደመና ቀለማት የለበሰ ፍቅር
ነዋ!» ወፍራም ክብ ፊቷ ላይ የልጅ መሳይ ፈገግታ ይጫወታል፤
ቆንጆ ነጭ ፀጉሯ ትራሱ ላይ ተበትኗል
«ቅድም ጓደኞቼ ማርሰይ እንሂድ ብለውኝ ነበር» አለች የራሴ
አልጋ ደሞ ከዚህ ይበልጥ ይመቻል. . . ግን እዚህ መምጣት
ፈለግኩ። ሉ ባይኖርም የሉ ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ ወይም የሱ
አልጋ ላይ ተጋድሜ፣ በሱ እቃዎች ተከብቤ መቆየት ኣንድ እይነት
ጥሩ ስሜት ይሰጠኛል .. ፍቅር ይዞህ ያውቃል?»
«አዎን»
«እንግድያው ምን ማለቴ እንደሆነ ይገባሀል»
«በደምብ ይገባኛል፡፡ ታድለሻል»
«እኔም ታድያለሁ እላለሁ-- ምንም እንኳ ላጭር ጊዜ ብቻ
ቢሆን»
ዝም አልኩ፡፡ ፊቷ ላይ ሀዘኑን እንዳላይባት መሬት መሬቱን
አየሁ፡፡

«ቴኒሰንን አንብበህ ታውቃለህ?» አለችኝ

«አዎን»

«ይህንን ጥቅስ ታስታውሳለህ?

«I hold it true, what'er befall,
I feel it when I sorrow most
ተቀበልኳት
"'Tis better to have loved and lost
Than never to have loved at all"

ሳቅ እያለች
« Wow, man!» አለችኝ

ቴኒሰን አቀራረበን

«ቡና ላፍላልህ?» አለችኝ

«አብረሽኝ ትጠጪ እንደሆነ» አልኳት

ቡናውን ከቀዳችልን በኋላ ተመልሳ አልጋው ላይ ተከመረችና
ወሬያችንን ቀጠልን። ስለሞርሞን ሀይማኖት፣ ስለአሜሪካ፣
ስለኮሙኒዝም ስናወራ ቆይተን፣ ወሬው ወደ ሉልሰገድ ወሰደን፡፡
እንዲህ አለችኝ

«ሉን ከማግኘቴ በፊት ርካሽ የርካሽ መጨረሻ ነበርኩ። እሱ
እንኳ ሱርፕሪዝ ፓርቲ አግኝቶኝ፣ ያኔውኑ ወደ አንድ ክፍል
ኣስገብቶ ተኛኝ። ያን ጊዜ በሉ ቦታ ማንም ወንድ ቢለምነኝ ኖሮ
እሺ እል ነበር። ይተኛኛል፣ ሌላ ጊዜ አንገናኝም፤ በቃ፡፡ ሉ ሲተኛኝ
ግን ሌላ አይነት ስሜት ተሰማኝ፡፡ እንዳይተወኝ ፈራሁ፡፡ አለቀስኩ።
ቢሆንም ገና የእውነት ፍቅር አልያዘኝም ነበር። ይህን 'ምልበት
ምክንያት ኣለኝ። በሳምንቱ እዚያው ቤት ሌላ ፓርቲ ነበር፡፡ ሉ
ኣልነበረም፡፡ ተካ እዚያ ነበር፡፡ ተዋወቀኝ፡ አስደነሰኝ፣ ሊተኛኝ ፈለገ፡፡
እኔ 'ንኳ አልፈለግኩትም ነበር። ግን ከሉ ጋር ፍቅር እንዳይዘኝ
ፈርቼ ስለነበረ፣ ዝም ብዬ እንደ ድሮዬ መሆን ይሻለኛል በማለት
ተካን እሺ አልኩት፡፡ በኋላ በጣም ቆጨኝ»
«ለምን ቆጨሽ?»
ምክንያቱም፣ ከሉ ጋር ስተኛ ንፁህ እንደሆንኩ መስሎ ተሰምቶኝ ነበር። ተካ ተኝቶኝ ሲነሳ ግን ቁሽሽ ያልኩ ቆሻሻ እርኩስ እንደሆንኩ ተሰማኝ። ትቶኝ ሲሄድ እዚያ ጭለማ ውስጥ ብቻዬን
ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ»

ሁለታችንም ዝም አልን፡፡ ትንሽ ቆይታ ቀጠለች

«አሁን በቅርቡ ሉን ስለተካ ነገርኩት። ማንም ወንድ ቢሆን፣
ሸርሙጣ ነሽ ብሎ ይሰድበኝ ወይም ይመታኝ ነበር፤ ወይም
እስከነጭራሹኑ ይተወኝ ነበር፡፡ ሉ ግን ምን እንዳለ ልንገርህ? ምንም
አይደለም። የበፊት መጥፎ ልማድሽ ባንዳፍታ ሊለቅሽ አይችልም መቸስ። ደሞ አትደግሚውም፡፡ የምትደግሚው ቢሆን ኖሮ አትነግሪኝም ነበር። ስለዚህ አልፏል ማለት ነው? እንርሳው' አለኝ

«ጥልቅ ፍስህ ስለተሰማኝ አለቀስኩ፡፡ ከዚህ በፊት ማንም
አስቦልኝ አያውቅም፤ አየህ፡፡ ሉ ሊያሻሽለኝ ይሞክራል፣ ርካሽነቴን
ሊያስተወኝ ከልቡ ይጥራል
ርካሽነትን ካልተውሽ ራስሽን ለማክበር አትችይም። ራስሽን
ካላከበርሽ ደሞ ሰው ሊያከብርሽ አይችልም፡፡ ሰው ካላከበረሽ ደስታን ልታገኚ አትችይም ይለኛል፡፡ እንዲያ እያሰበልኝ እንዴት ላልወደው እችላለሁ?» የፊቷ ጮማ ያፈናቸው ንፁሀ ሰማያዊ አይኖቿ እምባ አቀረሩ
«እኔ ላለቅስ ነው፣ ወሬ እንለውጥ» አለችኝ
«እሺ፡ ስለምን እናውራ?» አልኳት
«ስላንተ፡፡ ፍቅር ከማን ጋር ነው የያዘህ?»
«አንዲት ያገሬ ልጅ አለች
ቆንጆ ናት እርግጠኛ ነኝ
«እንዴት እርግጠኛ ሆንሽ?»
«ሉ ነገረኝ»
«ምን አለሽ?»
«እንደሷ ቆንጆ አይቼ አላውቅም አለኝ፡፡ ደሞ--»
በር ተንኳኳ። ወንድ መኝታ ቤት ሴት ማስገባት ክልክል ስለሆነ
ፈራን፡፡ እንደገና ተንኳኳ
«ማነው?» አልኩ በፈረንሳይኛ
«እኔ ነኝ፡፡ ክፈት» አለኝ
«ሉ ነው!» አለችና ካልጋው ዘላ ተነስታ በሩን ከፈተች
«ከግማሽ መንገድ ተመለስኩ» አለ ሉልሰገድ
«ምነው? መኪናዋ ተበላሸች?» አለችው
«የለም፣ ሳስብበት ጊዜ፣ ለምን ከኔ ጋር አትመጪም?» አላት
«እንድመጣ ትፈልገኛለህ?» አለችው
«አለዚያ ለምን እመለስ ነበር?» አላት
ሲወጡ ከበሩ ጋ መለስ አለችና፣ እሱ እንዳይሰማ
«እኔስ ምን አልኩህ?» አለችኝ። በጣም ደስ ብሏታል
ይሄ ሉልሰገድ ተራ ሰው አይደለም። ከአማንዳ ጋር ባደረገው ግንኙነት የታየኝ ጠባዩ የሀበሻ ጠባይ አይመስልም፡፡ አስቀያሚ ሴት መተኛቱስ የሀበሻ ደምብ ነው ሰው ሁሉ እያየው አቅፏት መዘር ግን! አምራው ቢተኛት ያባት ነው እየሰለቸችው
እየታከተው እወድሻለሁ ማለቱ ግን! ልጅቱ አስቀያሚ በመሆኗ
አይወዳትምና፣ ተካ ተኛኋት ብሎ ሲነግረው ከተካ ጋር አለመጣላቱስ እሺ እሷ ራሷ
ተካ ተኝቶኛል ብላ ስትናዘዝ ሰበብ
አገኘሁ ብሎ እሷን አለማባረሩ ግን!. . . ይህ ጠባዩ በጭራሽ የሀበሻ አይመስልም፡፡ በልጅነቱ ሚሲዮን ነበር የሚማረው። ለዚህ ይሆን?....

💫ይቀጥላል💫
👍24🔥4
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#አምስት


#በአሌክስ_አብርሃም



...ከሃኒባል ጋር ሆነን ያልረገጥነው የባሕል ሕክምና አዋቂ ቤት የለም፤ ደከመን። ሃኒባል ለእኔ ሲል
ያለችውን የዓመት እረፍት ጨርሶ ካለ ክፍያ አንድ ሳምንት ከሥራው ቀረ። ግን ምን ያደርጋል፣ ሁሉም
ነገር ከንቱ ልፋት ብቻ ሆነ። የሄድንባቸው ሁሉ ለእኔ ችግር መፍትሔ ማምጣት ይቅርና፣ ማፅናናት እንኳን ያልፈጠረባቸው አጋሰስ ነጋዴዎች ነበሩ። ቢጨንቀን አንድ ሁለት የልብ ጓደኞቻችንን ጨምረን
ጉዳዩን ነገርናቸው።ኣንዱ ጓደኛችን ለትምሕርት ውጭ ቆይቶ ገና መመለሱ ነበረ፤ ማይክሮባይሎጅ
ነው።

ጉዳዩን በጥሞና አዳመጠና፣ “…እስቲ እንዲት ውጭ ኣብረን የተማርን የስነልቦና ባለሞያ አውቃለሁ”አለ። ደስ የምትል የተረጋጋች ልጅ ጋር ወሰደኝ። ቢሮዋ ይገርማል፤ ሁሉም ነገር ነጭ ከእስከርብቶና ወረቀቱ ውጭ። ተነስታ ተቀበለችን። ከአንድ ሰዓት በላይ ያወራሁ ሳይመስለኝ ብዙ አስወራችኝ

“እኔ የምልህ አብርሃምም
እ ?"

ፍቅረኛህ ምናልባት ከቤተሰብህ አንድኛቸውጋ በመልከ ወይ በባሕሪ ትመሳሰል ይሆን?ፀ

"ኧረ በጭራሽ !እህቴ አፍንጫ የሚባል ነገር አልፈጠረባትም፣ ሙና'ኮ ሰልካካ ናት። እህቴ ከማጠር ብዛት ከራሷ ቦርሳ ቻፕስቲክ ለማውጣት እንኳን ወንበር ላይ ቆማ ነው፤ ሙና'ኮ መለሎ ፈገግ አለች
የሥነልቦና ባለሞያዋ። ጥርሶቿ ያማምራሉ (ልብ አይሞት አሁንም ሴት አደንቃለሁ)
እናቴም ብትሆን ቁመቷ እህቴ ነው የወጣችው። በዛ ላይ እናቴ ጠይም ሙና እኮ ዝም አልኩ!
ምናልባት የወሲብ ፊልሞችን ትመለከት ነበር እንዴ ?
“ኧረ አይቼ አላውቅም" እውነቴን ነበር።
“ቤተሰባችሁ ውስጥ የሚበዙት ሴቶች ናቸው ወንዶች ?
“ልጆቹ እኔና እህቴ ነን.… በቃ ! የሥነልቦና ባለሞያዋ የሆነ ነገር ቀይ ወረቀት ላይ በቀይ እስክርቢቶ
ስትጽፍ ቆየችና፣ (እንዴት እንደሚታያት እኔጃ
«ኃይማኖት ላይ እንዴት ነህ ?» «ታጠብቃለህ ?”
«ኧረ የለሁበትም።"
ቤተከርስቲያን የሄድኩት ራሱ ኢህአዴግ አዲስ ኣበባን ሲቆጣጠር የበቅሎ ቤቱ
ፍንዳታ ጊዜ፡ እናቴ ሚካኤል ልትደበቅ ስትሄድ እጄን ይዛኝ ነው ከዛ በኋላ ሄጄ አላውቅም

ፍቅረኛህ ሌላ ወንድ ጋር ግንኙነት አላት ብለህ ታስባለህ ?”

ማን ሙና … ኧረረረረረረረረረረ"

ከዚህ በፊት ከሌላ ሴት ጋር ወሲብ ያልፈጸምከው ለምንድን ነው ”

"እኔጃ"

"ሴን ትፈራለህ እንዴ ?

"መፍራት ሳይሆን እንዲሁ መቅረብ ብዙም አልፈልግም።” ወንበሯ ላይ ተመቻችታ ወደኔ ዘንበል አለችና (ጡቶቿ አፈጠጡብኝ)

“ለምን ?” ስትል ጠየቀችኝ፤ ቁልፉን ያገኘችው ሳይመስላት አልቀረም።

ረዥም ሰዓት በስልክ እንዳያወሩኝና ሸኘኝ እንዳይሉኝ … ! ስል መለስኩላት። እንደው ይህ ምላሽ መታበይ ይመስል ይሆናል እንጂ ማንንም እንደመሸኘትና እና በስልክ እንደማውራት የምጠላው ነገር
የለም። እኔም ሲሸኙኝ አልወድም፤ ሰውም መሸኘት ያንገሸግሽኛል። ምንድን ነው መጓተት፣ ምንድነው
ስልክ ላይ ተለጥፎ ማላዘን ? እንዴት እንደሚያስጠላኝ ! ስልከ አልወድም።

እሺ አብርሽ ጨርሰናል፣ ስልክህን ስጠኝና እደውልልሃለሁ” እርፍ!!
የሥነልቦና ባለሞያዋ እየደወለች ልትረዳኝ ብትሞከርም ነገሩ ዋጋ አልነበረውም። የበለጠ ስለጉዳዩ
ባሰብኩ ቁጥር በእግሮቼ መሃል ሳይሆን በፍርሃት መሃል ቁም ነገሩ ጠፋ። ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም !! ወዶ ነው አበሻ፣ “ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ" የሚለው። ትውልድን የሚሻገር ሕያው ድምጽ
መፈጠሪያው የት እንደሆነ ሲገባው እንጂ ! ኤዲያ!ወንድነት ደገፍ ብሎ የሚኮፈስበት ከዘራ ሸንበቆ ሲሆን አለ ከልብ የሚሰነጠር ወኔ ከተራ ብልግና የገዘፈ ሃቅ፤ ቃጭሉም ዝም ! ቤቴ ውስጥ ካሉት እቃዎች ምን አስጠላሀ ብባል አልጋዬ። የተሸነፍኩበት፣ የተማረክኩበት፣ የቆሰልኩበትና የተሰዋሁበት
ጦር ማዴ መስሎ ታየኝ። “ወኔዬን ያፈሰስኩበት አልጋ እኮ ነው ብዬ የልጅ ልጆቼ ላይ እኮፈስበት
ይሆናል። ያኔ ወኔው ያፈሰሰ ትውልድ ነፍ ነው የሚሆነው ! ወኔ ቢስነትም ክብር!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሙና ልትመጣ አስራ አንድ ቀናት ቀሩ ። አስራ አንድ የሽብር ቀናት ! “አብርሽ ፈራህ እንዴ ?ሂሂሂሂሂ
እንደ ቀልድ ትጠይቃለች። ለምን ጀግና ለመምሰል እንደምጣጣር ለራሴም አይገባኝ፤ ፈርቻለው
አይደል እንዴ ? አዎ ፈርቻለሁ ብላት ምን ነበር ? እኔ ግን ኮስተር ብዬ እንዲህ አልኳት፣ “ለምኑ ነው
የምፈራው?

“ለብር አምባሩ ነዋ አለችና ትንፋሽ እስኪያጥራት በሳቅ ፈረሰች። ሳቋ ውስጥ ሺ ጊዜ ፍራ እንጂ
አሁንማ ቁርጥ ነው የሚል ንዝረት አለ። እኔ'ኮ የሚገርመኝ “ብር አምባር” ከእንትን” ጋር ምን
አገናኘው? እውነቴን እኮ ነው … ብዙ ወንዶች ከአንዲት ሴት ጋር ወሲብ ሊፈፅሙ “ፈረሱም ሜዳውም ያውላችሁ” ሲባሉ በስሜት ስለሚሳከሩ እንኳን ቃል ሊሰነጥቁና ሊመረምሩ አልጋ ላይ ይሁኑ ዓየር ላይ የሚያውቁት ከተረጋጉ በኋላ ነው። ከዛ በፊትማ ብር ይልሰር አምባር ይሰበር ብርጭቆ ይሰበር ቅስም
ይሰበር ምን ግዳቸው "ሰማዩን ሰበረው ጀግናው” ቢባልም አይሰሙም፤ እኔ ግን የያዘ ይዞኝ ቀልቤን አሰላሳይ አድርጓታልና “ብር አምባር” ከድንግልና ጋር ምን አገናኘው ብዬ አስባለሁ -- (ሰው ወዶ ፈላስፋ አይሆንም መቼስ ይሄ ሁሉ ሚዜ እና ታዳሚ ላንቃው እስኪደርቅ በየሰርግ ቤቱ“ብር አምባር ሰበረልዎ ጀግናው ልጅዎ እያለ ይዝፈነው እንጂ “ድንግልናን ከብር አምባር ምን አገናኘው ለሚለው ጥያቄ መልስ ያለው አይመስለኝም።

እኔ ግን ዝም ብዬ ሳስሰው፣ “ብር አምባር መስበር አስገድዶ ከመድፈር ጋር “ጥብቅ ቁርኝት ያለው ጉዳይ ይመስለኛል። ልጅቱ የብር አምባር እጇ ላይ አጥልቃለች፤ ያው ሴት የብር አምባር ማድረጓ ከጥንት የተለመደ ነገር ነው) እና ባሏ ወላ ወዳጇ እጇን ይይዛታል .… (ያዝ እጆን) እንዲል ዘፈኑ ከዛ ለማምለጥ ወይም ራሷን ለማዳን እንዳቅሟ መታገሏ አይቀርም፤ መቼስ ዝም ብሎ ያውልህ አይባልም።
በሩን ይዘጋል (ዝጋ ደጇን) እንዲል ቀጣዩ የዘፈኑ ስንኝ፤ ትግሉ ከበረታ እጇን ጠምዝዞ ጉንጯን (ሳም ጉንጯን ) የሚለው ልክ መጣ። ለከንፈሯ ያሞጠሞጠው ከንፈር በልጅቱ መወራጨት ስቶ
ጉንጯ ላይ አርፎም ሊሆን ይችላል፣ ወይም አየር ላይ እንደ ርችት የከሸፈ መሳም ብትን ! ሲታገላታ እጇ ላይ ያለው አምባር ስብር ! ከሽ ! “ይሰበር የታባቱ ቅዳሜ ገበያ ስወጣ ሌላ እገዛልሻለሁ ያውም ወርቅ የመስለ” እያለ ወደ ጉዳዩ !
እንዲህ የሚያስለፈሰፈኝ ወድጄ አይደለም፤ አምባሩ እኔ እጅ ላይ ያለ እስኪመስለኝ መዘዜ ሊመዘዝ
አስራ አንድ ቀን ቢቀረኝ እንጂ። ሙና ይቅርታ አታውቅም ! በአሁኑ ጉብኝቷ ጉንጯን ስሜ ብልካት
እርሷም እንደ ይሁዳ ስማ ነው ለብቸኝነት ስቅላቴ የምትሸጠኝ። ሙናን እኮ አፈቅራታለሁ። እንደ
ቀልድ ሳጣት ነው በቃ ? እሺ አሁን የእኔ ጥፋት ምንድን ነው? የሙና ጥፋትስ ? እግዚኣብሔር ግን
ምን አደረግኩት ? እስኪ አሁን ማን ይሙት ሊቃጣኝ ፈልጎ ከሆነ ሌላ ልምጭ አጥቶ ነው !? ለምሳሌ ሰፈራችንን በጎርፍ አጥለቅልቆ እኔን ብቻ በመግደል ዜና ማድረግ አይችልም ? መንገድ ላይ ሱክ ሱክ ስል መብረቅ አውርዶ ድምጥማጤን ማጥፋት ያቅተዋል ? ምን አድርጌው ከማን የተለየ ጥፋትና በደል ሰርቼ በውርደት የምወዳትን ልጅ ዓይኔ እያየ ያስነጥቀኛል ? አባታችን አብርሃም እንኳን በዘጠና ስንት
አሙቱ ተሳክቶለት ልጅ ሲወልድ እኔን ሚስኪኑ በሃያ ሰባት አመቴ እንዲህ ጉድ ስሆን እግዜር እንዴት
ሆዱ ቻለ ?

'አብርሽ” እለኝ ሃኒባል፣

"እ"

“ግን ችግሩ ከሙና ቢሆንስ ?"

“እንዴዴዴዴዴ ምን አገናኘው ከሙና ጋር”
👍23
“አይ እንደው ካልደበረህ … ሌላ ሴት ጋር ብትሞክር ምናልባት ነገሩ ሊቀየር ይችላል”

"ምናልክ አንተ ? .. ችግር አለብህ እሺ … ሁለተኛ እንዳትደግመው”

“ሶሪ" ብሎ ዝም አለ። እሱ ዝም ይበል እንጂ አዕምሮዬ ግን ሃኒባል የለኮሳትን ችቦ አንስቶ ሩጫውን
ተያያዘው። ሌላ ሴት፣ ሌላ ሴት፣ ሌላ ሴት … ሌላ ሴት ለሙከራ የምትሆን ሴት … ሴት .. በቀላሉ
የምትገኝ ሴት .. ሰራም አልሰራም ከሙከራው በኋላ ዳግም አጠገቤ የማትደርስ ሴት .. ሴት …. ወሬ
የማታበዛ ሴት፤ በቃ ቀጥታ ወደ ገደለው ስትባል ቀሚሷን ወላ ሱሪዋን የምታወልቅ ሴት … ሴት …
ሴተኛ አዳሪ ! ምንም ! አዕምሮዬ ውስጥ ቤተሙከራውን የያዘ ሐሳብ ፈነዳ። ሴተኛ አዳሪ ጋር
መሄድ ! አዕምሮ የሰው ልጅ የገጠመውን ችግር ሁሉ መፍቻ ሐሳብ አመንጭቶ ሽቅብ እንደሚተኩስ ሁሉ የሕይወት ክርፋት ውስጥ በአናታችን የሚከት ሐሳብም እንዲህ ይዞልን ከተፍ ይላል። ሰው የራሱን አዕምሮ ካሻው መምጠቂያ ሮኬት፡ ከፈለገም መቀበርያ የአስክሬን ሳጥን ሊያደርገው ይቻላል።

ለድፍን ሳምንት ይሄ ሃሳብ ከአዕምሮዪ ሊወጣ አልቻለም

እንደውም አንድ ሌሊት በህልሜ ምን አየሁ ቡና ቤት አንዲት ከምድር ወገብ መስመር የረዘመ
ቀይ እግር ያላት ሴተ ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጣለች።እግሯ ከመርዘሙ ብዛት ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጣም መሬቱን ረግጣለች፡ እኔ ከኋላዋ ወደ እሷ እየሄድኩ ነው እየተራመድኩ ሳይሆን ልክ በካሜራ ክሎዝ አፕ እንደሚሉት ባንዴ በዓይኔ ስብያት አጠገቧ ቆምኩ፡፡ ሽቶዋ ሸተተኝ ደግም የሚገርመው ወንድነቴ ሱሪዬን የወጠረው ይመስለኛል። “ማድረግ የቻልነኩ ይመስለኛል። ልጅቱ ወደ እኔ ዞረች፣ ሙና ነበረች። ባንኮኒው ላይ ብር ከምራ እየቆጠረች። ወድያው ቡና ቤቱ ባንክ ቤት ነው።

ጓደኞቹ ሃኒባል እግዜር ይይልህ ! (የዋልከልኝን ውለታ አቀናንሶ )

ሮጠ ጊዜው ሸመጠጠ ! ሦስት ቀናት ብቻ ቀሩ ሙና ልትመጣ

ሃኒባልን “ሦስት ቀን ቀረ ምናባቴ ላድርግ?” አልኩት።

“በሦስት ቀን … ሊደረግ የሚችለው ብቸኛው ነገር መፀለይ ነው አብርሽ።

“አትቀልድ ባክህ"

እውነቴን ነው አምላኬ ሆይ ጉድ ልሆንልህ ነው፧ የሰጠኸኝ ሔዋን እንደ ሰሜን ኮከብ ያውም እንደ
ጅራታሙ እየተንቀለቀለች ሰማዩን ሰነጣጥቃ አዲስ አበባ ላይ ልታርፍ ነው … እሳቱ በረዶ ክምር
ላይ ተከስክሳ እንዳትከስም እርዳኝ በልና ድፍት ብለህ በሩ ላይ አልቅስ : እየቀለደ መስሎኝ ልበሳጭ ተዘጋጅቼ ፊቱን ሳየው ሃኒባል ከምሩ ነው!

“እና እንትኔን አቁምልኝ ብዬ ልፀልይ ? - ባለጌ ብሎ ነው እዛው የሚቀስፈኝ ብዬ ሃኒባልን
ገላመጥኩት።

“ለምን ባለጌ ይልሃል ? ለምን ይቀስፍል ? ብዙ ተባዙ ብሎ አዝዞ ሲያበቃ መባዣውን መንሳት
ከፈጣሪ አይደለም። ይሄ የሰይጣን ሥራ ነው፡ ይልቅ ያልኩህን አድርግ። ሰው እንዲራመድ እግዜር እግር ሲሰጥ፡ ሰይጣን እየዞረ ሽባነትን ያድላል፤ እግዜር ውብ ተፈጥሮን ትማለከትበት ዘንድ ዓይን ሲፈጥር፣ ሰይጣን በሰበብ አስባቡ አንዴ በትራኮማ፣ አንዴ በአደጋ ሰበብ እይታህን ይቀማሃል፣ የነፍስም ዓይንህን ይጋርደዋል፤ እግዚአብሄር የማንም አካል እንዲጎድል አይሻም። ሙሉ ስለሆነ ማንም በሙላት እንዲኖር ነው ፍላጎቱ፤ ለዛም ነው መጽሐፍ ቅዱስ በፈውስ ታሪክ የተሞላው። ሰይጣን ግን ጎዶሎ ነገር ስለሆነ
አትታሎም ይሁን አጭበርብሮ ለሰዎች ጉድለት ያድላል። ይሄ ጎዶሎ ምን ይሻለዋል እንደው? ግዴለህም አብርሽ … ሂድ ምድርን ያለካስማ ሰማይን ያለባላ ያቆመ ጌታ ያንተን እንትን ማቆም አያቅተውም። ሂድ ብያለሁ ሂድ !!” ሃኒባል እኔ ላይ በደረሰው ነገር በጣም አዝኖ ተቆጭቶ
እንደተነገረ ግንባሩ ላይ ሲበሳጭ የሚጋደመው የደም ስር ይመሰክራል። እኔ ግን በሳቅ ፍርፍር አልኩ፤ አነጋገሩ በጣም ነው ያሳቀኝ።....

ይቀጥላል
👍212
#ትኩሳት


#ክፍል_አራት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ሲልቪ
ላይ ላዩን


..ተመስገን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብዬ ስሰራ አንዳንዴ ውቢቱ ሲልቪ ትመጣና «Salut Castro noire» ትለኛለች። («ሰላም፣ ጥቁር ካስትሮ») (ፂም ስላለኝ ነው፡፡)

«Que la paix soit avec toi Scheherazade Blanche» እላታለሁ
(«ሰላም ላንቺ ይሁን፣ ፃእዳይቱ ሻህራዝድ ሆይ»)

ትስቃለች። በምስራቃውያን አነጋገር እንቀጥላለን። ቀልድ
ነው። ከሲልቪ ጋር ሁልጊዜ ቀልድ ነው:: እውነተኛ ፈረንሳዊት ናት፣ ስለምንም ነገር ቢሆን «Moi je men fous!» ነው የምትለው
(«እኔ ስለዚህ ነገር ደንታ የለኝም»)
ታድያ ደስ ትላለች። ሰፊ አፏ
ሳሙኝ ሳሙኝ ይላል፡፡ አብረሀት ስትሆን ሳቅ ቀልድ ታበዛለህ፣

«ዠማንፉቲዝሟ» ይጋባብሀል፤ ስለምንም ነገር ደንቴ አይኖርህም
አንድ ቀን ግን
«ምንድነው ሁልጊዜ ስትፅፍ የማገኝህ?» አለችና ደብተሬን
አየችው:: የምን ፅህፈት ነው ይሄ? ያገራችሁ ነው?» አለችኝ
«አዎን»
«ምኑም አይገባም»
«ቀላል ነው፡፡ ሁለት መቶ አርባ የሚሆኑ ፊደላት አሉት»
«Quel horreur! (ኧረ የጉድ ያለህ!) እንግዲያው አታስረዳኝ
ይቅርብኝ .. ምንድነው ምትፅፈው?»
«ምንም አይደለም»
«ልብወለድ ነው?»
«ብጤ ነው»
«እንዴት ማለት ብጤ?»
«እንዴት ልበልሽ? ልብወለድ ነው፣ ግን ፈጥሬው አይደለም፣
ያየሁትን የሰማሁትን ነገር ሰብስቤ ቅርጹን እለዋውጣለሁ እንጂ፣
ላንባቢ እንዲጥም»

«ቆይ ቆይ፡፡ አሁን መፃፍ አለብህ ወይስ ለጊዜው ልትተወው
ትችላለህ»
«ልተወው እችላለሁ»
«እንግዲያው ከዚህ እንሂድና ቡና ልጋብዝህ:: እና ስለድርሰት
እናውራ። ይስማማሀል?»

«በደምብ ነዋ! ቆንጆ ሴት ቡና ስትጋብዘኝ ሁልጊዜ
ይስማማኛል»
«Malin Castro noir va!» («ሂድ ወድያ! ፎሌ ጥቁር ካስትሮ!»)
Deux Chevaux መኪናዋ ውስጥ ከገባን በኋላ
«ኤክስ ውስጥ የምወደው ካፌ የለኝም፡፡ ማርሰይ እንሂድ?»
አለችኝ
እየቀለድን እየሳቅን ደጋግማ «Moi, u sais je m en fous!»
እያለች፣ በሆዴ ውበቷን እያደነቅኩ፣ ማርሰይ ደረስን፡፡ የንግድ ሳይሆን የግል የመደሰቻ ልዩ ልዩ አይነት ጀልባዎች ከተደረደሩበት ወደብ አጠገብ አንድ ካፌ ገብተን ቢራ ካዘዝን በኋላ፣ ጉልህ ሰማያዊ
አይኖቿ በፈገግታ እያዩኝ
«ንገረኛ ስለምትፅፈው» አለችኝ
«ምን ልንገርሽ?»
«ስለሰዎቹ፣ ስለጊዜው፣ ስለግንኙነታቸው፣ ማን ማንን እንደ
ሚወድ፣ ማንስ ማንን እንደሚጠላ፣ መፅሀፍህ አንዴት እንደ ሚጀመር፣ አሁን የት እንደደረሰ፣ በኋላ እንዴት እንደሚያልቅ፣
ምን ምን ነገር እንደሚያስቸግርህ፣ መፅሀፍህ ምን እንዲል እንደ
ምትፈልገው፣ ሁሉን ንገረኝ
ቆንጆ ስለሆነች ይሁን፣ አጠያየቁን ስላወቀችበት ይሁን ወይ ሌላ ያልተገለፀልኝ ምክንያት ይኑር እንጃ፣ ስለመፅሀፌ ሁሉን
ነገርኳት። ለማንም ነግሬ የማላውቀውን ለሷ አጫወትኳት፡፡ ችግሩን ደስታውን፣ ብስጭቱን፣ የድል አድራጊነት ስሜቱን፣ ምንም
ሳልደብቅ አዋየኋት። ፈረንሳይኛው ሲያስቸግረኝ ልክ ልናገረው
የፈለግኩትን ቃላት ታቀብለኛለች፣ ምክንያቱም ሀሳቤ ቃላቱን
ቀድሞ ደርሷት ይቆያል። አንዳንድ ቦታ አንድ ሀሳብ ተናግሬ
ጨርሼ ሌላ ሀሳብ አልመጣልህ ሲለኝ አንድ ጥያቄ ትጠይቀኛለች
እሱን ጥያቄ ስመልስ፣ ሌላ ሀሳብ ይመጣልኝና እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ ብዙ ካወራሁ በኋላ

«ይገርምሻል፣ ይህን ለማንም ነግሬ አላውቅም» አልኳት
«Jen suis lattee» አለችኝ (ክብር ይሰማኛል።)
«እኔ እውነቴን ነው»
«እኔም እውነቴን ነው»
«አሁን ተራሽን አውሪልኝ
«ቆይ» አለችና ከያዘችው የመፃህፍት ቦርሳ አንድ አስር የሚሆኑ ባንድ በኩል ብቻ በታይፕ የተፃፈባቸው ነጠላ ወረቀቶች ሰጠችኝ።
አንብበው አለችኝ፡፡ አነበብኩት፡፡ አጭር ልብ ወለድ ታሪክ ነው።
ስጨርስ ምን ይመስልሀል?» አለችኝ
«አንቺ ነሽ የፃፍሽው?» አልኳት
«አዎን» አለችኝ
«አዝናለሁ። ጥሩ ታሪክ አይደለም»
«ምንድነው የጎደለው?»
«እርግጠኛ አይደለሁም። አየሽ፣ አንድ ሰው የሚወዳትን ሴት
ሊገድል ይችል ይሆናል፡፡ ግን ባስር ገፅ ውስጥ ይህን መናገር
የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ሁለት መቶ ገፅ
ያስፈልገዋል»
«ይህንንም አንብብ እስቲብላ ሌላ አስራ ሶስት ገፅ ሰጠችኝ።
አነበብኩት። ግሩም ታሪክ ነበር፡፡
«ይህንንም አንቺ ነሽ የፃፍሽው?»
«አዎን»
«ታሪክ ይሉሻል ይሄ ነው! ይህን ጊ ደ ሞፓሳን ራሱ ነው የፃፈው ቢሉኝ አምናለሁ» አልኳት
ጉልህ ሰማያዊ አይኖቿ ልዩ አስተያየት ሰጡኝ፣ እንደማቀፍ ያለ
አስተያየት፣ ሙቀት ያለው አስተያየት

«Merci»አለችኝ

«Je ten prie (ኧረ ምንም አይደለም) ይህን የመሰለ ለመፃፍ
ስትችዪ፣ እንዴት አርገሽ የቅድሙን ፃፍሽው?» አልኳት
መሳቅ ጀመረች (ጥርሶቿ ትክክል ሆነው ነጫጭ ናቸው። ነጭ
የፈረንጅ ጥርስ ብዙ እይታይም) «እኔ እንጃ አለችኝ «በምፅፍበት
ሰአት ሁሉም እኩል ጥሩ ሆኖ ይሰማኛል። ካንድ ሁለት ወር በኋላ
ሳነበው ነው እውነተኛው ዋጋው የሚታየኝ»
«ይሄ መጥፎው መቼ ነው የተፃፈው?»
«ካንድ አመት ተኩል በፊት
«እንግዲያው መጥፎ መሆኑ
ድሮ ገብቶሻል። ለምን
እስነበብሽኝ?»
«ላውቅህ ስለፈለግኩ። ማንም ሰው ቢሆን፣ እንደምፅፍ ካወቀ
ወይም እንዲያውቅ ከፈለግኩ፣ መጀመሪያ መጥፎ ታሪኬን
አስነብሰዋለሁ። አንብቦት ጥሩ ነው ካለ በቃው። ሁለተኛ እኔ
የፃፍኩትን አያነብም። እስካሁን ለአንድ ስምንት ሰው አስነብቤያለሁ።
አንተና አንድ የፓሪስ ጓደኛዬ ብቻ ናችሁ መጥፎውን መጥፎ
ያላችሁት። ስለዚህ ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ ጥሩውን ያነሰሳችሁ»
«ሌላ የፃፍሽው አለ?»
«ሃያ ሶስት አለኝ፡፡ አስራ አንዱ ጥሩ ይመስሉኛል። ሰባቱ
በጣም መጥፎ ነው:: አምስቱ ግን ጥሩም አይደል፣ መጥፎም
ኣይደል እንደኔ እስተያየት። ስለዚህ አንተ እነዚህን አምስት
አንብበህ ምን እንደሚመስልህ ብትነግረኝ፣ ተስፋ የሌለውን
እጥለውና ተስፋ ያለውን እየመከርከኝ አሻሽለዋለሁ»

«ክብር ይሰማኛል፣ ግን ልመክርሽ መቻሌን እንጂ
«ትችላለህ። ታግዘኛለህ? »
«ከቻልኩማ በደስታ! አሁን ስለራስሽ ንገሪኝ፡፡ ቅድም እኔ
እንደነገርኩሽ»
ነገረችኝ፡፡ የምንፅፍበት ቋንቋ ተለያየ 'ንጂ ሙከራችን፤
ችግራችን፣ አስተያየታችን በጣም ይመሳሰላል፡፡ ስንወያይ መሸ፡፡
«እማውቃት ጥሩ ርካሽ ምግብ ቤት አለች» ብላ ሳን ሻርል
ባቡር ጣቢያ አጠገብ ወስዳ እራት ጋበዘችኝ። በፈረንሳይ ደምብ ከምግቡ ጋር አንድ ጠርሙስ ወይን ጠጣን፡፡ ሲኒማ ላስገባሽ አልኳት፡፡ ሁለታችንም እንደዚህ ልንጨዋወት የምንችልበት ጊዜ
መቼ ተመልሶ እንደሚመጣ አይታወቅም አለችኝ፡፡ እውነትሽን ነው አልኳት
ወደ ወደቡ ተመልሰን በእግር እየተዘዋወርን ወሬያችንን ቀጠልን። በተርታ የቆሙ ጀልባዎች የሚወዛወዙበት ውሀ ውስጥ የማርሰይ መብራት ይጫወታል። የባህር ሽታ ይዞ ከባህር በኩል የሚመጣው ነፋስ ቅዝቅዝ ያለ ሆኖ ይለሰልሳል። እንደኛው እያወሩ
የሚዘዋወሩ ሰዎች አሉ፤ አብዛኛዎቹ ተቃቅፈዋል፡፡ መንሽራሽር ሲበቃን አንድ ካፌ ገብተን ቁጭ ብለን ቢራ አዘዝን
👍271👏1
«ስለ ኑሮ ምን ታስባለህ?» አለችኝ
«ኑሮ በጣም አጭርና በጣም ጣፋጭ ናት እላለሁ። አንቺስ ምን
ይመስልሻል?»
እኔም በጣም አጭር ናት እላለሁ፡፡ ስለዚህ ለመኖር
መሽቀዳደም፣ መጣደፍ አለብን»
«በተቻለን መጠን ኑሮአችን ውስጥ ሀሴትን መጠቅጠቅ አለብን
«ሀሴት» ስል bonheur የሚለውን ቃል ነበር የተጠቀምኩት
«Il n'y a pas de bonheur, tu sais ha «Il n'y a que du
plaisir,» (ሀሴት የሚሉት የለም'ኮ፡፡ የስሜት ደስታ ብቻ ነው
ያለው»)
እና አንቺ ምን አይነት የስሜት ደስታ ትወጂያለሽ?»
ሳቅ እያለች «ከምግባባው ሰው ጋር እንደዚህ ማውራት፣
«ከማምነው ሰው ጋር ማታ ባህር ዳር መንሽርሽር»
«ሌላስ?»
«ውብ ሙዚቃ መስማት፣ ጥሩ ትያትር ማየት፣ ጥሩ መፅሀፍ
ማንበብ፣ እስክጠግብ ከበላሁ በኋላ ወይን እየጠጣሁ ማውራት. . .»
«ሌላስ?»
ልንገርህ?»
«ንገሪኝ»
«አትደነግጥም?»
«ሞክሪኝ»
አመነታች። «ለሰው ተናግሬው አላውቅማ»
እየሳቅኩ «እኔና አንቺ'ኮ ከሰው በላይ ነን፡፡ ደራሲያን ነን፣
ፈጣሪዎች ነን» አልኳት
ሳቀች። ሳቋ ጉሮሮዋ ውስጥ ይሰማል፣ በጣም ደስ ይላል፡፡
ሁለመናዋ ደስ ይላል
«እንግድያው ልንገርህ»
«ንገሪኝ
«J'aime faire l'amour,» («ከወንድ ጋር መተኛት እወዳለሁ»)
አየሁዋት። እስካሁን የተመስገን «ሚስት» በመሆኗ ስለሷ
እንዲገለፅልኝ ያልፈቀድኩለት ስሜት አሁን የአእምሮዬን በር
በርግዶ ገባ። ሲልቪን በጣም ተመኘኋት!
«ኦ! ላ-ላ! እንደሱ አትየኝ!» አለችኝ፡፡ አፍራለች፣ ጉንጮቿ ደም
መልበስ ጀምረዋል፣ አይኖቿ ይርገበገባሉ። የባሰውን አማረችኝ፡፡
«ምናለበት ባይሽ?» አልኳት
«Tu me fais rougir» («ፊቴ እንዲቀላ ታደርገኛለህ»)
«በጣም ታምሪኛለሽ ፊትሽ ሲቀላ» አልኩና ጉንጮቿን በሁለት
እጄ ይዤ አፏ ላይ ሳምኳት። አፏ ይሞቃል።
«እንሂድ ከዚህ?» አልኩዋት። Deux Chevaux መኪናዋ ውስጥ እንደገባን
«እኔም ከሴት ጋር መተኛት በጣም በጣም እወዳለሁ» አልኳት
«አውቃለሁ» አለችኝ
«እንዴት ታውቂያለሽ?»
«ምስጢር ነው:: Secret professionnel» («የባለሞያተኞች ምስጢር»)
«Mais nous sommes de la meme profession» («ታድያ
የሁለታችንም ሞያ አንድ ነው)
እውነትክን ነው»
«ንገሪኛ። ሴት መውደዴን እንዴት ታውቂያለሽ?»
«አንደኛ አስተያየትህ አይንህ ቆንጆ ሴት ላይ ሲያርፍ
ሴትዮዋን በሙቀት ያጎናፅፋታል፡፡ ደሞ ቆንጆ ሴት አይንህን ጣል
ሳታረግባት አታልፍም፡፡ ሁለተኛ ድምፅህ፡፡ ከወንዶች ጋር ስትነጋገር ሰምቼሀለሁ። ከሴት ጋር ስትነጋገር ግን ድምፅህ ልስልስ ይላል፣
ሙቀት ይሞላዋል፡፡ እንዴት ያለች ሴት ነው 'ምትመርጠው?»
«እንዳንቺ ያለች»
«የምሬን ነው 'ምጠይቅህ»
«እኔም የምሬን ነው «ምመልስልሽ»
«እንዴት ነው እንደኔ ያለች ሴት «ማለት?»
«አእምሮዋን ላከብረው ስችል፣ ጠባይዋን ልወደው ስችል
ገላዋን ልመኘው ስችል፣ በዚህ በሶስት በኩል በቂ ሆና ሳገኛት፣
ሴትዮዋ እንዳንቺ ያለች ናት ማለት ነው» ብዬ እንደገና ሳምኳት።
መሳሙን በጣም ትችልበታለች፣ ሰፊ አፏ ይመቻል
«ተመስገን ጓደኛህ ነው?» አለችኝ
«ጓደኛ የለኝም» አልኳት። ሳመችኝ፡፡ ሙቅ እርጥብ አሳሳም
ሳመችኝ
«ስለተመስገን እንዴት እናድርግ?» አለችኝ
«እንግደለው»
እየሳቀች «እውነቴን ነው!»
አንቺ እንደፈለግሽ። ብትፈልጊ ተይውና እኔጋ ነይ፡፡
ብትፈልጊ ሳትነግሪው በድብቅ እንገናኝ፡፡ ብትፈልጊም የሚገባው
ከመሰለሽ' ነገሩን አስረጂው:: እንደመሰለሽ አርጊ”
«ላንተ እንዴት ይሻልሀል?»
«ለኔ ሁለም ያው ነው:: እናንተ ፈረንሳዮች እንደምትሉት “Je
m'en fous! ብቻ አንቺን ላግኝሽ
አትቀናም?»
«አልቀናም፡፡ ምን ያስቀናኛል? በማገኝሽ ጊዜ የተቻለሽን ያህል
የስሜት ደስታ ስጪኝ እንጂ፣ ከኔ ጋር ባልሆንሽበት ጊዜ ምንስ
ብታረጊ ላንቺ ከተስማማሽ ምን ይጎዳኛል?»
«እውነትህን ነው?»
“አዎና!»
«Mon Dieux! እንዴት ያለኸው ሰውዬ ነህ!» (ወይ አንተ
አምላክ!)
«ምነው?»
መልሷ መሳም ነበር
ወደ ኤክስ እንመለስ?» አለችኝ
ምናልባት አሜሪካኗ ሆቴሌ ትጠብቀኝ ይሆናል በማለት
«ለምን እዚህ አናድርም?» አልኳት
«ነገ በጧቱ ክፍል አለብኝ»
«ቅሪ ከክፍል»
«ትምህርቱስ?»
«ስሚኝ። ዛሬ ከኔ ጋር ነው ምታድሪው፡፡ ሌሊቱን ችዬ
እንቅልፍ እላስወስድሽም፡፡ ስለዚህ፣ ነገ ጧት ብትገቢም እንቅልፍ ኣጥቶ ማደሩና ድካሙ በደምብ አያሰሩሽም፡፡ ስለዚህ አንደኛውን ብትቀሪ አይሻልም? ቅሪ እባክሽን! ደሞ ጧት ልለይሽ አልችልም»
ብዬ እቅፍ አድርጌ ሳምኳት። እሺ አለች፡፡ ሳን ሻርል አጠገብ አንድ
ትንሽ ሆቴል ውስጥ አንድ ክፍል ተከራየን፡፡
እጅ ለእጅ ተያይዘን ፎቁን ወጣን። የክፍላችንን በር ከፈትኩላት፡፡ ገባን። መብራቱን አበራችው:: አነስ ያለ ንፁህ ከፍል ልብስ የተዘረጋበት ሰፊ አልጋ ይጠብቀናል፡፡
መሀል አልጋ ሁለታችንም ለአልጋው ቸኩለናል፣ ሁለታችንም አልጋውን ፈርተነዋል

በሩ አጠገብ እንደቆምን ወደኔ ሳብኳት፣ ተጠጋች፡፡ ቀጭን
ወገቧን አቅፌ፣ ደረቷ እየገፋኝ፣ ጭኖቿ እየተሻሹኝ አንገቷን
ጉንጫን ስስም፣ ሰፊ አፏ ተከፍቶ ከጎን ታየኝ፡ አይኔ አጠገብ
ከንፈሮቿ በጣም ወፍረው ቀይ እርጥብ ሆነው ታዩኝ እየተንገበገብኩ
ጎረስኩዋቸው:: እሷም ጎረሰችኝ በሰፊ አፏ፡ በእርጥብ ከንፈሮቿን
በፈጣን ምላሷ፤ በትኩስ ትንፋሿ፣ በሚያዳልጡ ጥርሶቿ ታክኝ
ታላምጠኝ ጀመር አፎቻችን እንደተቆላለፉ ልብሶቻችንን በሙሉ አወለቅኳቸው፣
በለስላሳው ሌሊት ራቁት ለራቁት ተቃቅፈን ቆመን መተሻሸት
መሳሳሙን ቀጠልን። ጡቶቿ ደረቴን ሲገፉ ልዩ ስሜት ተሰማኝ፣
ትንሽ ራቅ አደረግኳትና አየኋቸው፣ ኮረዳነት የገተራቸው የውበት
ክምሮች የምኞት ህውልቶች ይመስላሉ። እጆቿን ዘርግታ ራሲን ወደ ደረቷ ሳበች፣ አንዱን አበባ ጡት አፌ ውስጥ ከተተችው፣ ራሴን አቀፈችኝ። ሽቶና ኮረዳነት የተደባለቁበትን ጠረኗን ወደ ውስጥ ተነፈስኩት

በኋላ ቀስ አርጋ ገፋችኝ፣ ለብቻዋ ቆመች። እየተያየን ብዙ ጊዜ
ቆየን። ሳኝካቸው የነበረ ጡቶቿ ቆመዋል፣ ከረዥም ቀጭን ሽንጧ
በታች ሰፊ ዳሌዋ ወደ ረዣዥም ጭኖቿ፣ በልዩ ጥንቃቄ ወደ
ተቀረፁ እግሮቿ ይወርዳል።
“እንዴት ቆንጆ ነሽ!» አልኳት
ሰበሰበችና ወስዳ ወምበር ላይ ከመረቻቸው። ጎንበስ ስትል ቀና
ፈገግታ እልሰጠችኝም፡፡ ዙሪያችን የተንጠባጠቡትን ልብሶች
ስትል፣ ስትራመድ፣ የገላዋ ቅርፅ የዳሌዋ መወዛወዝ አቅበጠበጠኝ፡፡
ቶሎ ሄጄ አቀፍኳት፡ አልጋው ላይ አጋደምኳት። እጇን ወደ ራስጌ
ዘርግታ መብራቱን አጠፋች። በጭለማው እጆቿንም፣ እግሮቿንም፣ ከንፈሮቿንም ከፈተችልኝ፣ እቅፏ ውስጥ አፏ ውስጥ ሴትነቷ ውስጥ
እስገባችኝ ትኩሳት እየተቀቀልን በስጋ ርጥበት ተጠበስን
የጉርምስና ስሜት ውስጥ እንደ ሀረግ ተገማምደን፣ በምኞት
በተቃቀፉ ገላዎቻችን መቅደስ ውስጥ፣ ዘለኣለማዊውን ጭለማ
ለተጎናፀፈ፣ ጥንታዊ ለሆነ፤ ዘወትር አዲስ ለሆነ፣ ቅዱስ ለሆነ
ህይወት በጠረናችን ከርቤ በወጣት ልባችን ከበሮ፣ በማቃሰታችን መዝሙር ምስጋናችንን አቀረብንለት
👍171🤔1
በኋላ፣ አንሶላው ውስጥ ገባንና ክንዴን አንተርሻት
«አውሪልኝ» አልኳት
ምን ላውራልህ?»
«ያሰኘሽን»
«ተደሰትክ?»
«እንዲህ ተደስቼ አላውቅም»
«እኔም፡፡ አልጋ ውስጥ አርቲስት ነህ፡፡ እንዳንተ ማንም
አስደስቶኝ አያውቅም»
በጭራሽ? እውነት ተናጋሪ»
«አንድ ብቻ ነበር። እሱም ያንተን ግማሽ ያህል አይችልበትም»
ታድያ እንዴት አስደሰተሽ?»
«የመጀመሪያዬ ነበር። ፍቅር ይዞኝ ነበር»
«እሱስ?»
«እሱም በጣም ይወደኝ ነበር። ግን ፍቅር አልያዘውም ነበር፡፡
ፍቅር ሊይዘው አይችልም፡፡ ፍቅሩን በሙሉ ለነፃነት ሰጥቷል።
አንድሬ ማልሮን አንብበሀል? La Condition Humaine የሚባለው ልቦለዱ ውስጥ ያሉትን ጀግኖች ተስታውሳቸዋለህ?»

«ቻይና ሄደው ለሬቮሉሽኑ እውቀታቸውንና ህይወታቸውንም
ጭምር ይሰጣሉ፡፡»
«አዎን! እንደነሱ አይነት ነው እሱም፡፡ ፖል ይባላል፡፡ መልኩ
ይህን ያህልም ኣይደለም፡፡ ደቃቃ ብጤ ነው:: ግን የአስር ሰው
ድፍረት ተሰጥቶታል። አይኑ ውስጥ ደሞ 'ነፃነት' ባለ ቁጥር ቦግ የሚል ነበልባል አለ። ያባቱን ሀብት ወርሶ ነበር። ግን እሱን ለታናሽ እህቱ ትቶላት ሄደ»
ወዴት ሄደ?»
«ወደ ኩባ፡፡ እነካስትሮን ለማገዝ»
«አሁንም እዚያው ነው?»
«አይ! እነካስትሮ አሸንፈው የለም”ንዴ?»
«እንግዲያው የት ነው?»
ቪየትናም፡፡ ቪየትኮንጎቹን ያግዛል»
«ኮሙኒስት ነው?»
«አይደለም፡፡ የነፃነት ነብይ ነው። የነፃነት አርበኛ ነው። ያን
ጊዜ በ56 ዓ.ም. ሀንጋሪ ውስጥ ብጥብጥ አልተነሳም? ለሀንጋርያኖች ነፃነት ለመዋጋት ቀዩን ጦር ሰራዊት (የሶቭዬት ህብረት ጦር) ከሀን ጋሪ ለማስወጣት እዋጋለሁ ብሎ ሀንጋሪ ሊሄድ ተነስቶ ነበር፡፡ በስንት መከራ አባቱ አስቀሩት። ያን ጊዜ ሀያ አንድ አመቱ ነበር፡፡»
«እንዴት ያለ ሰው ቢሆን ነው?» አልኳት
«የአርነት ሰው ነው:: የጭቆናን ቀምበር በያለበት እየዞርኩ
መስበር አለብኝ ይላል»
«ይፅፍልሻል?»
«ብስድስት በሰባት ወር አንዴ ይፅፍልኛል። አሁን ስለሱ
አናውራ 'ባክህን። አለዚያ ማዘን እጀምራለሁ። ዛሬ ማታ በጭራሽ
ማዘን ኣልፈልግም።
ወሬውን ተውነው፤ ግን ሌሊቱን እልተኛንም። የወጣትነት
ትኩሳት እያቃጠለን፣ በህይወት ርጥበት ውስጥ ተነክረን አደርን
ሊነጋጋ አቅራቢያ እንቅልፍ ወሰደን። እስከማታ አልነቃንም
ሲልቪ አጠገቤ በመሆኗ ትልቅ ፍስሀ ተሰማኝ፡፡ እቅፍ እያደረግኳት
ከእንቅልፌ ስነቃ ሰውነቴ ታድሷል፣ አስተያየቴ ተለውጧል።
«ስለተመስገን ጉዳይ እንዴት ልታረጊ ነው?» አልኳት
«እንዴት ላድርግ?» አለች
«ተይው!»
«ምን?»
«ለብቻዬ ነው 'ምፈልግሽ»
«ትላንት ስናወራ ከኔ ጋር ባልሆንሽበት ጊዜ ምንም ብትሰሪ
የራስሽ ጉዳይ ነው አላልከኝም ነበር?»
«ትላንት ፍቅር አልያዘኝም ነበራ!»
በሀይል እቅፍ አደረገችኝ.....


💫ይቀጥላል💫
👍19
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#ስድስት


#በአሌክስ_አብርሃም


...ወደ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ቤተክርስቲያን ሄድኩ። እንደ እብድ ብቻዬን ማውራት ጀምሬ ነበር። ቀጥ ብዬ ዋናውን በር አልፌ ገባሁ። ትዝ ሲለኝ አልተሳለምኩም፤ ተመልሼ ግራ ቀኝ በሩን ተሳለምኩ። ዘው
አይባልም ዘሎ፤ ፈጣሪ የተጎዳ ልቤን ቢመለከትም ቅሉ እዚህ ድረስ ልብ ውልቅ መሆኔ ለኔም ደግ አይደል ወደ ውስጥ ስገባ የቤተክርስቲያኑ ድባብ፣ የቤተመቅደሱ ወፋፍራም የጣውላ ከፈፎች ላይ የሰፈሩት ዋነሶች፣ እድሜ ጠገቦቹ ዛፎች፣ ከምንም በላይ ደግሞ ዝምታው ከውስጥ ብሶቴ ተዳምሮ አጃዬን አመጣው። ከምርም የሰው ልጅ ምናምኒት አቅም እንደሌለው የሚያውቅበት የሆነ ጭብጦ ነገር መሆኑን የሚረዳበት ቦታ ሲኖር ቤተክርስቲያን ይመስለኛል።

ፈጣሪን ምን ማለት እንዳለብኝ ግራ ገባኝ። ታቆምልኛለህ ወይስ አታቆምልኝም…” ከይባል ነገር። ቆይ ግን ከዘፍጥረት ጀምሮ በዚህ ጕዳይ እግዜር ፊት ቆሞ የፀለየ ሰው ይኖር ይሆን ? በሐሳቤ ስቀላምድ ቆየሁና ዞር ዞር ብዬ አካባቢዩን ቃኘሁ። ከእኔ ወደ ግራ ሲል ቢጫ ልብስ የለበሱ መነኩሴ ተቀምጠዋል።ምን እንደገፋኝ እንጃ ወደሳቸው ገሰገስኩ፤ ምናልባት እዛው እንደ ደንቡ እግዜርን በሚያዝንበት ቋንቋ
ቢያናግሩልኝ ብዬም እንደሆን እንጃ ! አጠገባቸው ስደርስ፣

“አባ " አልኳቸው።

"አቤት የኔ ልጅ፣ እንደምን ዋልክ” አሃ !ለካ ሰላምታም ነበር።

"ጓደኛዬ ልትመጣ ሦስት ቀን ቀራት፤ ከመቀሌ ከሦስት ቀን በኋላ ትመጣለች፤ ሙና ነው ስሟ
ሦስት ቀን ብቻ ቀና ብለው በእርጋታ አዩኝና ከጎናቸው ያለውን ግንድ መቁጠሪያ በያዘ እጃቸው
እያመሰከቱኝ፣

"ና እስቲ እዚህ አረፍ በል የኔ ልጅ” አሉኝ።

“አይ እሄዳለሁ" ብያቸው ያመለከቱብኝ ቦታ ላይ ተቀመጥኩ። (ሁለት ሰው የሆንኩ መሰለኝ፤)
የምናገረው ሌላ የማደርገው ሌላ

“ምን ሆነህ ነው የምታለቅስ ልጄ” ቢሉኝ እጄ ወደ ዓይኔ ሄደ አይገርምም ? እየተነፋረቅኩ ነበረ
ለካ፡ እንባዩን በእጄ ሞዥቄ አባን የሆነውን ሁሉ ነገርኳቸው። አቤት መስማት ሲችሉበት

በጥሞና ሲሰሙኝ ቆይተው፣ "የኔ ልጅ እግዲህ ዋናው ነገር … እግዜር የጊዜ አምላክ ነው፤ የሰውና የአግዜር አሰራር ልዩነቱ ይሄ ነው። ሰው የቻላትን ባሰኘው ጊዜ ያደርጋል፥ እግዜር ግን ሁሉን ይችላል የሚያደርገው ግን ለልጆቹ በሚጠቅመው ጊዜ በሚጠቅመው ልክ ነው። ካለጊዜው እንዲህ ያለው ነገር
ውስጥ እንዳትገባ ሊያስተምረህ ወድዶ ይሆናል አንድም ደሞ የምድር ጠቢባን ያቃታቸውን ሁሉ
የሚችል መሆኑን ሊገልጥልህ ሲወድ እንደሆነ ምኑ ይታወቃል ልጄ.."

"እና ምን ላርግ አባ፤ ሶስት ቀን ብቻ ቀራት እኮ"

“መምጣቷ መልካም ነው ! ታዲያ መውደድ ሲሞላ ብቻ አይደለም፣ ሲጎድልም እንጂ፤ መሳቅህን
ብቻ እያሳየህ በወዳጅህ ፊት ትልቅ አትምሰል ልጄ፡ ሰው ነህ ድከመት አለብህ፣ ድክመትህን ለራሷ ንገራት፤ እውነቱን ተናገር። የውሸትና ማስመሰል ዙፋን ከእንቧይ ገንብተህ ንገሽ ብትላት እሷንም ተንዶ ጉድ ይሰራታል፣ ላንተም ፀፀት ነው። የውሸት እና ማስመሰል ካባ ከነፍስ ከረምት፣ ከመንፈስም ቁር አያስጥልም፤ አትድከም! ግራ ቀኝም አትበል፤ እሷን ሸፋፍነህ ብታሳምናት ከራስህ ልብ የገባህው
አተካራ አያባራም። እውነቱን ንገራት፣ ከእውነት የበለጠ ፈውስ የለም የኔ ልጀ።”

"ከዛስ እባ ፤"

ከዛማ እውነት ከተናገርከ ሰውም ምክርም አያሻህ፤ እውነት ራሱ መንገዱን ይምራሄል።"ብለው ወደ
መቁጠሪያቸው አቀረቀሩ። ደህና ዋሉ ልበላቸው አልሰላቸው እንጃ ወደ ቤቴ ተመልሼ ጥቅልል ብዬ
ተኛሁ። እውነት መንገዱን ይመራሃል፤ እውነት ዋጋ ያስከፍላል ያውም ከነወለዱ። ከሆንስ ሆነና እውነት ዋጋው ስንት ነው?
እውነት ዋጋው ስንት ነው?
እውነት ዋጋው ስንት ነው?
እውነት ዋጋው ስንት ነው?
የቱንም ያህል ዋጋው ቢወደድ፣ በቃ ለሙና እውነቱን እነግራታለሁ። ወሰንኩ !
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የቁርጥ ቀን!

እነሆ የተንኳኳ በሬን ከፈትኩ፤ ልብ የሚያቀልጥ የሙና ውበት ከወትሮው ሰባት እጅ ደምቆ በሬ ላይ ቆሟል። ሙናን አፈቅራታለሁ፤ ልለያት አልፈልግም። ሳያት ልክ ብርሃን ጨለማ ክፍልን ድንገት ቦግ ብሎ እንደሚሞላው ውስጤን የሚሞላው አንዳች ነገር አላት፤ እንደ ባዶ ፊኛ የሟሸሽ መንፈሴ ሙናን ሳያት በዓየር እንደተሞላ ባሉን በፍቅርና በደስታ ሕዋ ላይ ይንሳፈፋል። ይሄው የእውነት ዋጋው በሬ ላይ። እውነት ዋጋው ይሄን ያህል ውድ ነው። እቅጩን ተናግሬ የነፍሴን ግማድ ሙናን መክፈል፤አልያም ሰቆቃዬ ላይ ስሳቀቅ በየዕለቱ በማስመሰልና በሽሽት ሚስማር የፍርሃት ጉልላቴ ላይ መቸንከር።

በሐሴት የሚንሳፈፍ የነፍሴን ባሉን፣ ክፉ እሾህ ጠቅ አድርጎ ሊያተነፍሰው ወደኔ ሲወነጨፍም
እከላከልበት ዘንድ በእጄ ያለው መሳሪያ አባ ያስታጠቁኝ ጋሻ ብቻ ነው እውነት !! እውነቱን ተናግሬ
የመሸበት አድራለሁ። እስከመቼ የነገር አንጆ ሳመነዥክ ልኑር ? በቃኝ !!

ምን እንዳረጋጋኝ እንጃ በውስጤ "ሙና ብትሄድ ሺ ሙናዎች ይተካሉ” ስል ረጋ ብዬ ፎከርኩ። ላንዲት ሙና ያልሆንኩ እኔ ለሺ ሙና ስፎክር የሰማ ራሴ ቢታዘበኝም ግድ አልሰጠኝም። ፉከራ ከጀግንነት ብቻ ሳይሆን ጥልቅ ከሆነ ፍርሃትም እንደሚመነጭ የገባኝ ያኔ ነው።
ሙና በእቅፏ ሙሉ አፍሳኝ በሞቃት ከንፈሯ በናፍቆት ግጥም አድርጋ ስትስመኝ ነፍሴ ከተወዘፈችበት ኩርፊያ ተመንጥቃ ልትወጣ ተጣጣረች፤ ቢሆንም እንቅ አድርጌ ነፍሴን ያዝኳት። መቆጣት አለብኝ መኮሳተር አለብኝ። ሙና የሆነ ነገር ሆኗል ዛሬ ልለፈው" እንድትል የሆነ ነገር የሆንኩ መምሰል አለብኝ። ተሸከማ የመጣችውን እሳት በቁጣ ውኃ በር ላይ ማጥፋት፡ መደርገም አለብኝ። ቦርሳዋን
ጠረጴዛ ላይ ወርወር አደረገችና በናፍቆት አንዴ ቤቱን ከእግር እስከ ራሱ ዙሪያውን ቃኝታ በረዥሙ
ተነፈሰችና ለሞላ ቦታ መጥታ ጉልበቴ ላይ ተቀመጠች። ደረቷ ላይ አስጠግታ አቀፈችኝ ለሞላ
የሰውነት ክፍል ፀጉሬን ሳመችኝ።

“ፀጉርህ አድጓል” ብላ በጣቷ መንጨር መንጨርጨ አደረገችኝ። ወይ ነዶ ልጅቱማ የፍቅር ሰው
ነበረች፤ ካለቦታው ተከሰተች እንጂ። ተነስታ ወደ ውስጥ ገባችና የእኔን ቁምጣ ለበሰች፤ ቁምጣ የተሰራው የሙና ዓይነት እግር ላላቸው ሰዎች ይመስለኛል። የእኔን ቲሸርት ለበሰች፤ ቲሸርት
የተፈጠረው የሙና ዓይነት ጡት ላላቸው ሴቶች ብቻ ይመስለኛል። ከዛም ወደ ኪችን። ዝም ብዬ
አያታለሁ፤ ፊቷ ላይ ምንም ነገር የለም፤ ረጋ ያለ ለስላሳ ፊት፤ ትረጋጋ እንጂ እሷ ምን አለባት
የመጣው ቢመጣ ሁሉ በጇ፣ በአንድ እይታ ብቻ ወደ እሳት ነበልባልነት የሚለወጥ አረር ሰውነት ምን አስጨነቃት።

እያጠናኋት ነበር፤ መለያየታችን እንደማይቀር አንድ ነገር ሹክ ስሳለኝ እድሜ ልኬን እንዳልረሳ
እያጠናኋት ነበር። ሙናን መቼም ቢሆን መርሳት አልፈልግም፣ ፍቅረኛዬ ስለሆነች አይደለም
በሕይወት ውስጥ የመሰላል እርካን ሆነው አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርጉን ሰዎች አሉ፣ ሙና እንደዚ ናት ለእኔ። ምን ያህል ልትናፍቀኝ እንደምትችል አሁን ላይ ሆኜ አውቀዋለሁ። ዝም ብዪ አያታለሁ ድንገት ዞር ስትል ዓይናችን ተገጣጠመ ሳቀች። ፍፁም ገራገር እና ንፁህ ፊት። እኔ ግን ደነገጥኩ፡ ወይ ጉድ፡ ሰው በሰላም አገር እንደ ሌባ ደንጋጭ ሆኖ ይቀራል ?!
👍36🥰21