#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...'መወለድ ቋንቋ ነው' ይላሉ አበው ሲተርቱ፡፡ የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ተደጋግሞ እንደታየው ሰዎች አብረው እስካልበሉና እስካልጠጡ ክፉ ደጉን በጋራ
እስካልተካፈሉ እንዲሁም እስካልተረዳዱ እስካልተደጋገፉ ድረስ የዘር ግንድና የደም ትስስርን ብቻ መሰረት በማድረግ እህቴ! ወንድሜ! አክስቴ! እቴቴ... ወዘተ መባባል ብቻ ከሆነ በርግጥም 'መወለድ' የሚለው ቃል ከቋቋነት ያለፈ ፋይዳ ሲኖረው አይታይም።
በተቃራኒው እንኳንስ መወለድ
የአንድ ወንዝ ውሃ እንኳ አብረው ሳይጠጡ ነገር ግን በአንድ ከተማ ወይም በአንድ አካባቢ አብረው በመኖራቸው ብቻ ስሜት ፍላጎታቸውና አመለካከታቸው ተገጣጥሞ ጥብቅ ቤተሰባዊ ትስስርን ሲፈጥሩ ይታያሉ ለዚህ
ደግሞ የከስቻለው፣ የበልሁ የታፈሡ የመርእድ ከልብ የመነጨ ፍቅር አይነተኛ ምስክር ነው።
ለእነዚህ የፍቅር ቤተሰቦች ትውውቅ መሰረት የሆነው የታፈሡኔ የባለቤቷ ጋብቻ ነበር፡፡ ታፈሡ በወሎ ከፍለ ሀገር በወረኢሉ አውራጃ ውስጥ
ከካቤ እስከ ጃማ ድረስ በተዘረጋው ወይናደጋማ ቦታ ላይ ከትመሰረተ ሰፊ ቤተሰብ ትወለዳለች፡፡ ባለቤቷ ደግሞ በጎጃም ክፍለ ሀገር ደጀን አካባቢ
የተወሰደ ቢሆንም አባቱ መምህር ስለነበሩ በስራ ምክንያት ብዙ በቆዩባት በመሀል ሜዳ ከተማ
ለብዙ አመታት የቆየ ነው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን
በዚያው ከተማ አጠናቆ በኋላም በተግባረእድ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት በምህንድስና ሙያ ሰልጥኖ ትምህርቱን ሲጨርስ ለስራ ተመድቦ ወደ ደሴ ነበር የሄደው።
በዚሁ ጊዜ ተይዩ ታፈሡ እንግዳሰው የአንደኛና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በወረኢሉ ልዕልት የሺመቤት ትምህርት ቤት አጠናቃ ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ደሴ በሚዋኘው ዝነኛው የወይዘሮ ስህን ትምህርት ቤት ለመማር ትሄዳለች፡፡ ሁለቱ በአንድ ሰፈር ያኖሩ ነበርና በዚያው ሰበብ ያተያያሉ፡ : በሃደት ይተዋወቃሉ፡፡ ቀስ በቀስ ይቀራረባሉ።የኋላ ኋላ ይዋደዱና በመጨረሻም ይጋባሉ።
ታፈሡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ጨርሳ አዲስ አበባ በሚገኘው የኮተቤ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ትገባለች፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ደግሞ ባለቤቷ በዝውውር ወደ ዲላ ይሄዳል፡፡ ታፈሡም የኮሌጅ ትምህርቷን ስታጠናቅት በጋብቻ ሰበብ ወደ ባለቤቷ እንድትሄድ ተደርጎ እሷም በዲላ
አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ትመደባለች፡፡
አስቻለው ተወልዶ ያደገው በመሀል ሜዳ ከተማ እንደ መሆኑ
የተማረውም እዚያው ነው፡፡ እሱ ልጅ በነበረበት ወቅት የታፈሡ ባለቤት በዚያ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሲከታተል ያውቀው ነበር፡፡ እሱ ራሱም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በነርስነት ሙያ ሰልጥኖ ሲመረቅ ለስራ ተመድቦ ወደ ዲላ ሆስፒታል ይሄዳል፡፡ ገና ዲላ ከተማ የገባ ዕለት የታፈሡን ባለቤት መንገድ ላይ ያየዋል፡፡ ፈራ ተባ እያለ ያነጋግረዋል፡፡ የትና እንዴት እንደሚያውቀው ያስረደዋል። የታፈሱ ባለቤት የአስቻለውን ለአገሩ እንግዳ መሆን በመረዳቱ ወቸ ቤቱ ይወስደዋል። ከታፈሡ ጋር ያስተዋውቀዋል ታፈሡ ለአስቻለው ትመቸዋለች። አዘውትሮ ወደ ቤቷ እንዲመጣ ታደርገዋለች። እሱም እየተመላለሰ መጠየቁን ይቀጥላል።በዚያው እየተግባቡና እየተዋደዱ ይሄዳሉ። ታፈሡ የመጀመሪያ ልጇን ስትወልድ ክርስትናውን ለአስቻለው ትሰጠዋለች፡: አበ ልጆችም ይሆናሉ፡፡
በሌላ መንገድ ደግሞ በልሁና መርዕድ ትውውቅ እየፈጠሩ ነብር
መርዕድ ወደ እጼ ዳዊት ትምህርት ቤት ከመዛወሩ በፊት ከዲላ በስተደቡ በሚገኘው በጩጩ ገብርኤል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ያስተምር
ነበር፡፡ በልሁ ደግሞ አዘውትሮ ወደ መስክ ስራ የሚሄደው በዚያ መስመር ስለነበር፣ በልሁ መርዕድ መምህር መሆኑን ስለሚያውቅ በአጋጠመው ጊዜ ሁሌ
ስለነበርና መርዕድም ብዙ ጊዜ ከዲላ ከተማ ወደ ስራው የሚሄደው በእግሩ ስለነበር
በልሁ መርእድ መምህር መሆኑን ስለሚያውቅ በአጋጠመዉ ጊዜ ሁሉ ለመስክ ስራ በሚጠቀምባት መኪና ላይ ያሳፍረዋል፡፡ በዚያው እየተግባቡ ይሄዳለ፡: መርዕድ በተፈጥሮው ተጫዋች በመሆኑ ለበልሁ በጣም እየተመችው
ይሄዳል ጫትም አብረው መቃም ይጀምራሉ።
በልሁና አስቻለው በከተማ ውስጥ በዓይን ይተዋወቁ ነበር፡፡ አንድ ቀን ደግሞ አስቻለው ከአንድ የዲላ ከተማ ነዋሪ ጋር ሆኖ በአንድ ቡና ቤት ውስጥ
ሻይ እየጠጡ ሳለ በልሁ ድንገት ይደርሳል፡፡ ያ ካአስቻለው ጋር የነበረ ሰው በልሁን በደንብ ያውቀው ኖሮ ቁጭ ብሎ" ሻይ እንዲጠጣ ይጋብዘዋል፡፡
በልሁም ቁጭ ይላል፡፡ ከአስቻለው ጋር የነበረው ሰው ለመሆኑ ሁለታችሁ ትተዋወቃላችሁ? ሲል ሁለቱንም ተራ በተራ እያየ ይጠይቃቸዋል፡፡ በዓይን ይሉታል። ሰውየው አስቻለውና በልሁን በቅደም ተከተል እየጠራ አንተ መንዜ፣ አንተ ቡልጌ፣ በትውልድ ስፍራ እኮ ጎረቤቶች ናችሁ ይላቸዋል፡፡
በልሁና አስቻለው ፈገግ ፈገግ በማለት እንደገና እየተጨባበጡ እንደ አዲስ የስም ትውውቅ ያደርጋሉ፡፡ ከዚያ በኋላ፤ መንገድ ላይ በተገናኙ ቁጥር ጠበቅ ያለ ሰላምታ መለዋወጥ ይቀጥላሉ፡፡
አንዳንዴም ሻይ ቡና መገባበዝ ይጀምራሉ::
ከወራት በኋላ ሁለቱን የበለጠ የሚያቀራርብ አጋጣሚ ተፈጠረ አንድ ምሽት ላይ በልሁ በአንድ ቡና ቤት ውስጥ በተለምዶ ባለጌ ወንበር ተብላ በምትጠራ መቀመጫ ላይ ቁጭ ብሎ ይጠጣል አንዳት የቡና ቤቱ አስተናጋጅ አጠገቡ ቆም እያለች ታጫውተዋለች። በቡና ቤቱ ውስጥ ቁጭ ብለው ይጠጡ የነበሩ አራት ጎረምሶች ልጅቷን እየፈለጉ በልሁን መተናኮል ይጀምራሉ በልሁ ግን ንቋቸው ዝም ብሎ ልጅቷን ያጫውታል ቆየት ብለው ከጎረምሶቹ መሀል መስከር የጀመረው አንዱ ልጅቷን በሀይል ጎትቶ ሊወስድ ወደ ልጅቷና በልሁ መራመድ ሲጀምር ድንገት አስቻለው ይደርሳል።
በልሁ ከተቀመጠበት ባለጌ ወንበር ላይ ወርዶ ጎረምሳውን ሊመታ ሲል አስቻለው ይይዘውና ወደ ጎረምሳው ዞሮ ብሎ 'አንተ እረፍ እንጂ' ይለዋል። ጎረመሳው ግን 'ምን አገባህ' ብሎ በአስቻለው ላይ ያፈጣል። አስቻለው ደግሞ ሲያስጠነቅቀው ያ ጎረምሳ ጭራሽ ይጠገዋል።በዚህ ጊዜ ጎረምሳው የተማመነባቸው ጓደኞቹ አስቻለውንና በልሁን ሊመቱ ግር ብለው ወደ እነሱ ይመጣሉ።ድብድብ ይጀመራል አስቻለውና በልሁ ከወንበር ወደ ወንበር ከጠረጴዛ ወደ ጠረጴዛ እየዘለሉ እነዚያን ጎረምሶች አመድ ያደርጓቸዋል ሁሉንም ይዘርሯቸዋል በድብድቡ ምክንያት የቡና ቤቱ ብርጭቆዎች እንዳሉ ይሾቃሉ ወንበሮች ይሰባበራሉ ይጮሀል ፖሊስ ይደርሳል በልሁና አስቻለው ታስረው ያድራሉ በፖሊስ። በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ሲያድሩ እንቅልፍ አልወሰዳቸውም ነበር።ሲያወሩና ሲጫወቱ ይነጋል።
ጠዋት በዋስ ሲለቀቁ ወደ አስቻሴው ቤት ነበር የሄዱት ለእንቅልፍ አረፍ ሊሉ በልሁ አስቻለው ቤት ሲገባ በቅድምያ አይኑ ያረፈው በአስቻለው አልጋ ፊት ለፊት ለጫት መቃምያ የተነጠፈች በምትመስል ፍራሽ ላይ ነበር።
ጫት ትቅማለህ እንዴ?» ሲል እስቻለውን ይጠይቀዋል፡፡
«እንደውም»
«ፍራሿ ታድያ»
«ባልቅምም ሲቃም ደስ ስለሚለኝ አንዳንዴ የስራ ባልደረቦቼ እየመጡ ይቅሙበታል።

👍8
«መርዕድ የሚባል ጓደኛ አለኝ፡፡ እኔና እሱም እንቅምበታለን፡፡»
«ትችላላችሁ»
በልሁ ብዙም ሳይቆይ መርዕድን አምጥቶ ከአስቻለው ጋር
ያስተዋውቀዋል፡፡ ከዕለቱ ጀምሮ በዚያች ፍራሽ ላይ ተቀምጠውም ይቅሙባታል ይቀጥላሉ ያዘወትራሉ። ይለምዳሉ።
አንድ ቅዳሜ ቀን በልሁና መርዕድ አስቻለውን ከጎናቸው አስቀምጠው ሞቅ ደመቅ ባለ ሁኔታ ጫት እየቃሙ በመጫወት ላይ ሳሉ ታፈሡ ወትሮም እንደምታደርገው ሁሉ ወደ አስቻለው ቤት ጎራ ትላለች። የእለቱ አለባበሷ አበጣጠሯና ፈገጎታዋ የተለየ ነበር፡፡ ነጫጭ የሀገር ልብስ ለብሳ እንቁጣጣሽ
መስላለች የሦስቱ ጓደኛሞች አቀማመጥ አስደስቷት ይበልጥ ፈገግ ብላ አየቻቸው«አቤት ደስ ስትሉ...» እያለች ወደ ውስጥ ትገባለች፡፡ ሁሉም ብድግ ብለው
ይቀበሏታል ይጨባበጣሉ አስቻለው ከበልሁና መርእድ ጋር
ያስተዋውቃታል፡፡ ለትንሽ ሰዓት ኣብራቸው ትቆያለች፡፡ ይጨዋወታሉ፡፡በልሁና መርዕድ የታፈሡን ቁንጅና፣ የአነጋገር ለዛዋንና ፈገግታዋን እያዩ ሲደነቁ ይቆያሉ።
ታፈሡ ወደ ቤቷ ልትመለስ ከቤት እንደወጣች በልሁ አስቻለውን «ይቺ ሴት ምንህ ናት?» ሲል ይጠይቀዋል?
አስቻለው የበልሁ ስሜት ገብቶት ሳቅ ፈገግ እያለ «ምነው ምን ፈለግክ?» ይለዋል።
«አቦ ቆንጆ ናት»፡፡
«የተከበረች ባለ ትዳር ናት።
«ባሏ ዕድለኛ ነው::»
«እንዴት?»
-«እንኳን ለእልጋው ለሳሎኑም ጌጥ ናት፡፡»
ይሳሳቃሉ፡፡
የታፈሡ የበልሁና የመርዕድ ግንኙነት በአስቻለው ጥግ ይቀጥላል፡፡ይግባባሉ፡፡ ይዋደዳሉ፡፡በልሁ ታፈሡን ያያት ዕለት የስሜት ህዋሳቶቹ
ተነቃንቀው የነበረ ቢሆንም
ውሎ እያደረ ግን በእህትነት እቅፏ ውስጥ ይገባል።ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ በመተው ያከብራታል፡፡ የእህትና የወንድምነት ግንኙነታቸው ይጠነክራል፡፡ በክፉ ደግ ሳይለያዩ በቤተሰባዊነት ፍቅር ይቀጥላሉ።
ይሀ የባዕድ ዝምድና መሠረት በተጣላ በሶስተኛው ዓመት ገደማ ነበር ሔዋን መጥታ ከመሀላቸው የተቀላቀለችው፡ ፡ ታፈሡ፣ በልሁና መርዕድ በአስቻለውና ሔዋን ፍቅር የተደሰቱትን ያህል ስቃያቸውንም አብረው ተሰቃይተዋል፡፡ መከራቸውንም ተካፍለዋል። ለቅሷቸውንም አብረው አልቅሰዋል፡፡ በሁሉም ነገር ዛሬም አብረው ናቸው::
የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ድንገት በመሀላቸው ተገኝቶ ስለ አስቻለው ያየውንና የሚያውቀውን ሁሉ ከነገራቸው በኋላ በተለይ በልሁ የአስቻለውን ዱካ አነፍንፎ ለማግኘት ወደ አስመራ ኤርትራ ለመሄድ ሲወስን ውሎ አላደረም፡
አንድ ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ዝግጅቱን አጠናቆ ተነሳ፡፡ አዎ፡ ወደ አስመራ በረረ፡፡
ዕለቱ አርብ ነው፣ ከቀኑ አሥር ሠዓት አካባቢ፡፡ በልሁ ከአስመራ
የአይሮፕላን ማረፊያ ክልል ወጥቶ በሩ አካባቢ ተኮልኩለው መንገደኞችን ይጠባበቁ ከነበሩ ታክሲዎች መካከል ተረኛውን
ጠየቀና ወደተጠቆመበት ታክሲ
አመራ፡፡ ኣንድ ቀጠን ያለ መልከ መልካም የታክሲ ሾፌር መኪናውን በር ከፍቶ በእጁ ጠቀሰው፡፡
«የት መሄድ ፈለጉ?» አለ ሾፌሩ በልሁን አስገብቶ በሩን ከዘጋ በኋላ::
«ሰራዬ መናፈሻ»
«መናፈሻውን ነው ወይስ አካባቢውን የሚፈልጉት?» ሲል ጠየቀው ሾፌሩ ወደ ኋላው ዞር ብሎ በልሁን እየተመለከተ፡፡
«ራሱን መናፈሻውን፡፡»
«ማረፊያ አለ ብለው ነው?»
«የለውም እንዴ?»
«መኖር ነበረው፣ ነገር ግን መናፈሻው በአሁኑ ጊዜ ዝግ ነው፡፡» ::
«ለምን ተዘጋ?» አለ በልሁ ደንግጦ።
ሾፌሩ አንገቱን ወዲያ ወዲህ መለስ ቀለስ አደረገና «ምክንያቱን እንኳ እንጃ! ከተዘጋ ግን ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡» አለው
«እና እዚያ ውስጥ ሰው ፈልጌ ማግኘት አልችልም'?» አለ በልሁ
አንገቱን ወደ ሾፌሩ ሰገግ አድርጎ፡፡
«ምን ሰው አለና!»
በልሁ ቅስሙ ስብር አለ ከሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ የተሰጠው ምልክትና አድራሻ ያ ብቻ ነበር።...
💫ይቀጥላል💫

👍13❤1🔥1
#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
....ሰሞኑን ቀለሞቹ ከደረቁለት በኋላ፣ እየተመላለሰ ሲቀባ፣ ሲያስተካክል፣ ሲያበጃጅና ሲሞሽር ቆይቶ ከአምስት ቀናት ድካምና ጥንቃቄ የተሞላው
ሥራ በኋላ፣ ሦስቱን ሥላሤ ሥሎ ጨረሰ። የመጨረሻው ቀን ራቅ
ብሎ ሥዕሉን ሲመለከት ተደነቀ። ሦስቱም በሁሉም አቅጣጫ እኩልና የተመጣጠኑ ናቸው። አንድም የተዛነፈና ከቦታው ውጭ የሆነ ነገር የለም። የፊታቸው ገፅታ ፍፁም ተመሳሳይ ነው። ፊታቸው ሙሉ ለሙሉ ይታያል። በሰማያዊ፣ በቢጫ፣ በነጭና በቀይ ቀለማት አምረዋል።
ተንበርክኮ ምስጋና አቅርቦ ወጣ።
በማግስቱ፣ አለቃ ግዕዛን ከሊቀጠበብት አዳሙ፣ ከአለቃ ተክለየሱስና ከሊቀጠበብት ያሬድ ጋር መጥተው ሥዕሉን ተመለከቱ። ጥላዬ፣ከኋላቸው ቆሞ፣ በእነዚህ ታላላቅ ሠዓሊዎችና የሥዕል መምህራን ላይ ያሳደረውን ስሜት ለማወቅ ተጠባበቀ።
መምህራኑ ፈዘው ተመለከቱ፤ የሚያዩትን ማመን አቃታቸው።
አለቃ ግዕዛን፣ “ጥላዬ፣ ይኸ የፍቅር ውጤት ነው። ፍቅር ብቻ ነው ይኸን የመሰለ ሥራ ሊያሠራ ሚችለው። እስታሁን በሥራህ ደስተኛ ነበርሁ። ዛሬ ግን ይኸን የመሰለ የላቀ ሥራ ስላሳየኸኝ አከብርሃለሁ።
ይኸን የመሰለ የጥበብ ውጤት እንዳይ ዕድሜ ለሰጡኝ ሥላሤ ምስጋናዬን ሳቀርብ፣ ላንተ ደግሞ አድናቆቴን ገልጣለሁ። አንተም ሥላሤን ብቻ ሳይሆን እኔንም ነው ያከበርኸኝ። እኔን እንዳከበርኸኝ አንተን ደሞ ሥላሤ ያክብሩህ። አንተ የሥዕል ንጉሥ ነህ። ከይኸ ቀደም ማንም አልቀደመህም፣ አሁንም ሚደርስብህ የለም ወደፊትም ሚተካህ ዠግና
ሚመጣበት ግዝየ ሩቅ ነው” አሉት፣ ደብቀውና ተጠንቅቀው የያዙትን፣ለማንም ተማሪ አድረገውት የማያውቁትን ምስጋና እያዘነቡለት።
ጥላዬ እግዚሐር ይስጥልኝ ማለት ፈልጎ፣ ልሳኑ ተዘጋበት። በዝምታ
እግራቸው ሥር ተደፋ።
“ተነስ ልዥ ። ንጉሥ እሰው እግር ሥር ኣይወድቅም” አሉት።
ሊቀጠበብት አዳሙም፣ “ውነትም የሥዕል ንጉሥ ነህ። አንተ ዛሬ
ግዕዛንን ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም ነው ያከበርኸው፣ ያኮራኸው። ውበት ማለት ይኸ እንጂ ሌላ ምን አለ? አንተ ለብዙ ተማሮች አርአያ
ትሆናለህ። ሚያሳዝነው ሥዕል እንደዝኸ ድንቅ ነገር ሁኖ ሳለ እንደ ቅኔና ዜማ በርካታ ተማሮች የሉትም። ደብረ ወርቅ እንደመጣህና ትምርት እኔጋ እንደዠመርህ፣ ውነትም የሥዕል ንጉሥ እንደምትሆን አውቄ ነበር። የናትህ ማጠን ይለምልም። ዛሬ የአለቃ ሔኖክ ነፍስም በሰማይ ቤት ትዘምራለች። ሥላሤ እጅህን ያለምልሙት” ብለው
ሊስሙት ሲጠጉት፣ ፈጠን ብሎ እግራቸውን ሳመ።
አለቃ ተክለየሱስና ሊቀጠበብት ያሬድም አድናቆትና ምስጋና
አዥጎድጎዱለት፤ ባረኩት፤ እንኳን ደስ ያለህ ብለው ሳሙት። እሱም
እግራቸውን ሳመ።
በምስክር ፊት በሥዕል ትምህርት ተመረቀ።
የመመረቂያውን አነስተኛ ድግስ እንዲቀምሱለት ሁሉንም ወደቤቱ
ይዟቸው ሄደ። እንጎች ያዘጋጀችውን ምግብ በልተው፣ አረቄ ጠጥተው አመስግነውትና መርቀውት ሊሄዱ ሲሉ፣ ሊቀጠበብት ያሬድ በድንገት
ሲቆሙ፣ ሌሎቹም ቆሙ።
ሁሉንም በተራ እየተመለከቱ፣ “በሉ ወንድሞቼ ኸመኼዳችን
በፊት አንድ ቅር ያለኝን ጉዳይ ልናገር ነው” አሉ። “ተማሪ እናታባቱ ያወጡለትን ስም እየተወ ለራሱ ስም ያወጣል። ዜማ ሲማር 'ጥዑመ ልሳን ነኝ ይላል። ቅኔ ሲማር ባሕረ ጥበብ ነኝ... ማንቴስ ነኝ ይላል።አንዳንዴም እሰበሱ ስም ይሸላለማል። ይኸ ልዣችን ግን ትሑትና የሥራ ሰው በመኾኑ ይኸው የባላገር ስሙን እንደያዘ ጥላዬ እንደተባለ
አለ። ምሥጢሩ ደግ ነው፤ ጥላ ከለላ ትኾነኛለኽ ሲሉ ማዶል አባቱ
“ጥላዬ ማለታቸው? ድንቅ ስም ነው። ግና ለእንዳንተ ያለ ጠቢብ
ዛሬ እናንተ ወንድሞቼ ኸፈቀዳችኹልኝ 'ሥሙር' ብዬዋለኹ። ደሞም አይኾንም። ሠዓሊ ተኹኖ ጥላዬ መባል ምሥጢሩ አይገጥምም። ስለዚኸ
ፊቱኑ የነበረ ወግ ነው። መምህራን ለጥበብ ልዦቻቸው ይስማማል
ያሉትን ስም ይሽልማሉ። እና ምን ትላላችኹ? ሥሙር አይዶለም
ጥላዬ?”
ሁለቱም መምህራን በአንድ ድምጽ በደስታ አደነቁት፣ “ቃለ ሕይወት ያሰማዎ ጌታዬ፤ ድንቅ ነው፤ ሥሙር ነው፤ ስሙም አሰያየሙም የተገባ ነው” ብለው አጸኑለት።”
መምህሮቹ በደስታ እያውካኩ ሲሄዱ ሸኝቷቸው እንደተመለሰ መደብ ላይ ጋደም አለ። የተዋጣለት ሥራ እንደሠራ አረጋገጠ። ሕልሙ ሁሉ
እውን ሆነ። ቋራ እያለ ወለቴን ንጉሥ ኸወሰዳት እኔ የሥዕል ንጉሥ ማልሆን? ያለውን አስታወሰ።ምኞቱ ሠመረ።
ዝናው በደብረ ወርቅ ብቻ ሳይሆን፣ አድባራቱን አልፎ መርጡለማርያም ድረስ ዘለቀ። በየደብሩ ያሉት የሥዕል መምህራን እንዲያስተምር
ገፋፉት። ዝናውን የሰሙ የአካባቢው ባላባቶች ደብራቸውን እንዲያስጌጥ ተረባረቡበት።
እሱ ግን አንዴ ለአንዱ ባላባት አድሮ መሥራት ከጀመረ ወደሌላው መሄድ ስለማይችል ለማንም አልታዘዝ አለ። በተጨማሪ፣ ሥዕል ታሪክ
ተናጋሪ፣ አስተማሪ፣ አብራሪ፣ ስሜትንና አእምሮን ቀስቃሽ እንጂ ለስም መጠሪያ ቤተክርስቲያን ማስዋቢያ ብቻ ሆኖ መወሰድ እንደሌለበት ተናገረ። በባላባቱ ዘንድ ቅሬታን አተረፈ።
ጐንደር ተመልሶ መሄድ ፈልጎ ከሀያ ዓመት በላይ በመቆየቱ
ባይተዋር የሚሆን መሰለው። ጐንደርን እንደዛ ወዶ ይህን ያህል
ርቆ መቀመጡ አልገባ አለው። ደብረ ወርቅ ብዙ አስተምራዋለች።
በርግጥም የሥዕል ንጉሥ አድርጋዋለች። ሆኖም ደብረ ወርቅ
የሕዝብ ዓይነት አይታይባትም። ደብረ ወርቅ ነዋሪዎቿን
የጐንደርን ዓይነት ታላቅነትና ግርማ ሞገስ የላትም። እንደ ጐንደር አድርጋ የመቀመጥ ባህርይ ሲኖራት፣ ጐንደር አደባባይ አውጥታ ታሟግታቸዋለች፤ የቤተክርስቲያን ምርጫ ትሰጣቸዋለች፣ ለድሆቿ
የእንፋሎት መታጠቢያ እንኳን አዘጋጅታለች።
ታዲያ ይህችን ጐንደርን እንዴት አድርጎ ለዘላለም ይተዋት? እንደ
ወለቴ የልጅነት ፍቅሩ፣ የጎልማሳ ዘመኑ ትዝታው አይደለችምን?
ጐንደር ለመሄድ ባሰበ ቁጥር፣ “እቴጌ ኸባላቸው እት ልዥ ጋር
ወዳጅነት ያዙ” የሚለውን ወሬ መርሳት ስላልቻለ ልቡ ያመነታል።
ባሏ ከሞቱ ጊዜ የቀድሞው ስሜቱ አንሰራርቶ የነበረው ዜናውን
ሲሰማ ልቡ ተሰርጉዶ ምንትዋብ ላይ ቅሬታ አድሮበታል።
በምንትዋብ ቅር መሰኘቱ ቅር የሚያሰኘው አልፎ አልፎ ደግሞ
የሚያስቀው ነገር ሆኖ አግኝቶታል ቅሬታው የመነጨው እኔ ይህን
ያህል ስለእሷ ሳስብ እሷ እንዴት ሳታስፈልገኝ ቀረች በሚል ነው።
የሚያስበው ሁሉ ተገቢ እንዳልሆነ ቢያውቅም፣ “ውነት ትወደኝ ኸነበረ እንዴት አታስፈልገኝም?” ብሎ ደግሞ በስጨት ይላል። በሌላ በኩል አፄ በካፋ ሲሞቱ ልቡ ውስጥ የተስፋ ጭላንጭል የተቀረፀበትን ጊዜ ያስብና ከት ብሎ ይስቃል። ድጋሚ ሌላ ሥዕል ሊልክላት ወሰነ።ሆኖም እንደመነኩሴው ታማኝ ሰው እንዴትና የት እንደሚያገኝ ማሰብ
አቃተው።
ቀደም ብሎ ስለአብርሃ ወሬ ይሰማ የነበረውን ያህል ባለመስማቱም በሕይወት ይኖር ይሆን እያለ መጨነቁም አልቀረም። ካንድ ሁለት
ጊዜ መልዕክት ልኮበት ሳይደርሰው ቀርቶ ይሁን ወይንም ደርሶት ዝም ብሎት እንደሆነ ለማወቅ ተቸገረ።
አንድ ቀን፣ ደብረ ወርቅ ማርያም ውስጥ የቅኔ መምህር ከሆኑት
ከመጋቤ ሥነ-ጊዮርጊስ ጋር ቤተክርስቲያኗ ግቢ ውስጥ ያለ ጥድ ስር ተቀምጠው ሲጨዋወቱ በቅርቡ ጐንደር ሄደው እንደነበር ነገሩት።
“እደብረብርሃን ሥላሤ ደርሰው ነበር?” አላቸው።
“አዎን።”
“እንዲያው መጋቤ አብርሃ ሚባል ጓደኛ ነበረኝ። መልክትም
ብልክበት አልደረሰው ሁኖ ነው መሰለኝ መልስም አልሰጠኝ።”
“አሉ። መቸም ጐንደር ኻፈራቻቸው ሊቃውንት አንዱ ናቸው ነው ሚሉ።”
ጥላዬ ደስ አለው። ጐንደር የመሄድ ፍላጎቱ ተነሳሳ።
“እንዴት ያለ ጥሩ ነገር ነገሩኝ። እኔማ ተጨንቄ ቆይቻ።”

👍10
“ጐንደርም አብባለች። እቴጌ መቸም ለካህናትና ለሊቃውንት
ያላቸው ፍቅርና አክብሮት እየብቻ ነው። ትምህርትም እንዲስፋፋ ብዙ ጣሩ፣ ብዙ አረጉ። አሁን ያየህ እንደሁ፣ ለፊደል ተማሮች እንጀራና
ወጥ፡ ለዜማ ተማሮች እንጀራና ወጥ ከጠላ ጋር፣ ለቅኔ ተማሮች
እንጀራና ወጥ ከጠጅ ጋር ይሰጣቸው ብለው እየተሰጠ ነው። ለትርጓሚ ቤት ተማሮችም እንዲሁ ቀለብና ድጎማ ያረጋሉ። ተርጓሚዎች ቁም ጸሐፊዎችና ሠዓሊዎች ባለክራሩ፣ ባለመሰንቆውና ባለበገናው
ሁሉ የዕለት ጉርስና ያመት ልብስ ተፈቅዶለታል ሥራውን ተግቶ
እንዲሠራ።”
ጥላዬ በሰማው ሁሉ ተደነቀ። እስከምን ጊዜ ድረስ ምንትዋብን
በሩቅ ሲከታተል እንደሚኖር አሰበ። ዕድሜው እየገፋ በመምጣቱ ሳያገኛት እንዳይሞት ፈራ። ዳግመኛ ምስሏን መላክ መፈለጉ ምን ትርጉም እንደሚኖረው መገመት አቃተው። ግራ ያጋባት እንደሆነም አሰብ አደረገ። የልጅነት ፍቅሩን ሳያረካ በመቋረጡ፣ ምንም እንኳ
የፍቅሩን ምዕራፍ የዘጋ ቢመስለውም፣ ምንትዋብን የአማልክት ያህል በመቁጠሩ ከልቦናው አልጠፋ ብላው እንጂ እሷን ግራ ማጋባት ፈልጎም
አይደለም።
ሥዕል ዳግመኛ የመላክ ፍላጎቱ ሲበረታበት አንድ ቀን ዕንጨት
ላይ ብራና ወጥሮ መሣል ጀመረ። ማርያም ኢየሱስን አቅፋ ምንትዋብ ነጠላ ተከናንባ፣ ማርያም እግር ስር ተንበርክካ አንገቷን ዝቅ አድርጋ ስትጸልይ ሣለ። ሥዕሉንም ወደደው። ሊልክላት ወስኖ፣ ባንድ በኩል የሚወስድለት ባለማግኘቱ፣ በሌላ በኩል መላኩ ድፍረት የሚሆንበት
ስለመሰለው ደብቆ አስቀመጠው
ከዕለታት አንድ ቀን ያልታሰበ ነገር ገጠመው። መጋቤ ሥነ-ጊዮርጊስ
ጉዳይ ገጥሟቸው ጐንደር ተመልሰው እንደሚሄዱ ነገሩት።
“እንግዲያማ እነማይ አንድ የእቴጌ ዘመድ የሆነ “ለእቴጌ ገጸበረከት አዘጋጅቼ እኔን ኸቤተመንግሥት ሚያደርሰኝ የለም እንዳው ይዞልኝ
ሚሄድ ሰው ባገኝ እያለ ይቆጫል። በቅርቡ ወደ ሸዋ ሂዷል ሲሉ
ሰምቻለሁ። ምሽቱ ስላለች ሰው ልኬ ገጸበረከቱን ባስመጣና እንደምንም ብለው ቢወስዱለት” አላቸው።
“ተሆነልኝማ ምን ገዶኝ። ለማንኛውም ሰውየው መቸ ይመለሳል?እኔ በሦስት በዐራት ቀን ውስጥ እነሳለሁ።”
“ኧረ ግድ የለም። እዝሁ እነማይ ማዶል ። ዕቃውን ሰው ልኬ
አስመጣለሁ። እቴጌ ሰብለወንጌል ኸነማይ ማዶሉ? የነሱ ዘመዶች እኮ ብዙ አሉ ኸዛ።”
“መውሰዱንስ ወሰድሁ፣ እንዴት ብየ ነው ኸቴጌ ዘንድ ማደርሰው?”
“ግዴለም፣ ለእቴጌ የተላከ ገጸበረከት ነው ብለው ታች ይቀበሉዎታል፤የተቀበልሁት ኸሥሙር ነው ቢሉም ችግር የለም። ኸዝኸ በፊትም
ኣንድ መነኩሴ ልኮ አድርሰውለታል። ግና እንዴት እንዳደረሱለት አላውቅም። መቸም ዘመድ ብለው ኸነገሯቸው እርሶን ባያስገቡ ስንኳ ዕቃውን ይቀበልዎታል” አላቸው።
በማግሥቱ፣ መጋቤ ተጠቅሎ የተሰጣቸውን መልዕክት ይዘው ጐንደር ዘለቁ።.....
✨ይቀጥላል✨

👍12
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
....በልሁ ቅስሙ ስብር አለ ከሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ የተሰጠው ምልክትና አድራሻ ያ መናፈሻ ብቻ ነበር።ሃምሳ አለቃ እራሱ በአስመራ ከተማ ውስጥ ከዚያ መናፈሻ በስተቀር ሌላ አካባቢ ብዙም አያውቅም። የአስመራ ቆይታው አጭር ስለ ነበርጰተዘዋውሮ አላየውም።
“ምን ይሻለኛል ታዲያ የኔ ወንድም" ሲል በልሁ ጭንቅ እያለው ሹፌሩን ጠየቀው።
«እኔ እንጃ!» አለና ሾፌሩ ለአፍታ ያህል ቆየት ብሎ ወዴ በልሁ ዞር በማለት «እዚያ የሚሰራ ሰው ነበር የሚፈልጉት?» ሲል ጠየቀው
«እዚያ አዘውትሮ የሚገባ ወንድሜን ነበር፡፡»
«ታዲያ አንዱ ጋ አረፍ ብለው ያፈላልጉታ»
በልሁ ለአፍታ ያህል ፀጥ ብሎ ሲያሰላስል ቆየና እስቲ ጥሩ ማረፍያ ወደምትለው ሆቴል ውሰደኝ።አለው የበልሁ ተክለ ሰውነታዊ ገፅታና በራሱ
አንደበት 'ጥሩ ማረፊያ' በማለት በተናገረው ቃል መሰረት ጥሩ ኗሪ
እንደሆነ የገመተው ሾፈር «ወደ ኮምፒሽታቶ ያሻልዎታል» አለው፡፡
«ኮምፒሽታቶ ምንድነው?ሲል በልሁ ጠየቀው በልሁ ቃሉ የተለየ ትርጉም ካለው ብሎ በማሰብ።
መሀል ከተማ ላይ የሚገኝ ቦታ ነው ጥሩ ጥሩ ሆቴሎችም የሚገኙት በዚያው አካባቢ ነው።» አለ ሹፌሩ።
«እሺ እንሂድ!»
በእርግጥ በልሁም የገንዘብ ችግር የለበትም፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ከጥቂት ወራት በፊት ወላጅ አባቱ እስቲ ብትኖርበትም ብትሽጠውም ቦታ መያዝ ደግ ነውና ቤት ለመስራት ሞክር በማለት ከሰጡት በርካታ ገንዘብ ላይ ግማሽ ያህሉን በመንገድ ሻንጣው ውስጥ አድርጐ ይዞት ሄዷል።አስቻለውን በመፈለግ ሂደት ታሪካዊቷን የአሥመራ ከተማ ለማየት ይጓጓ የነበረው በልሁ ገና ከጅምሩ መንፈሱ በስጋት በመወጠሩ በሚጓዝበት
ጎዳና ግራና ቀኙ ያሉትን የከተማዋን ቦታዎች እንኳ ልብ ብሎ ሳያይ ያ ባለ ታክሲ ተጉዞ ተጉዞ ከአንድ ኣካባቢ ሲደርስ ዳር ይዞ በመቆምም «ኮምፒሽታቶ
ማለት ይህ ነው!» አለው፡፡
«ወደ አንዱ ሆቴል ጠጋ ብታደርገኝ
«ይቻላል» አለና ሾፌሩ ከመንታ መንገዱ ወደ ቀኝ ታጠፈና ኒያላ
ሆቴል» ከተባለ ሆቴል በር ላይ አደረሰው፡፡
በልሁ የታክሲ አገልግሎት ክፍያውን ከምስጋና ጋር ከፈልና የልብስ ሻንጣውን ትከሻው ላይ አንግቶ ወደ ሆቴሉ የእንግዳ መቀበያ ክፍል አመራ፡፡አልጋ ሲጠይቅ መኖሩ ተነገረው፡፡ አንድ አስተናጋጅ ከፊት ከፊት እየመራ
ወሰደውና ክፍሉን አሳየው፡፡ ከፍሉ ንፁህና ግሩም የሚባል አልጋ አለው በልሁ የክፍሉን በር ዘግቶ አልጋው ላይ አረፍ በማለት ስለገጠመኑ ችግር ያሰላስል ጀመር፡፡ ማሰቡ ግን መላ አላስገኘሰትም፡፡ ይልቁንም የባሰ ጭንቅ ጭንቅ ይለው ጀመር፡፡
በምሀል አንድ ነገር ትዝ አለውና ከዚያው ጋር በተያዘ ሌላም ነገር ቆጨው በመሠረቱ አስቻለው አካል ጉዳተኛ ነው፡፡ ብዙ መጓዝ ስለማይችል ቤት የሚከራየው በሚሰራበት አካባቢ ሊሆን ይችላል፡፡ ስራዬ መናፈሻ ውስጥ
የሚያዘወትር ከሆነም ቤቱም ሆነ መሥሪያ ቤቱ በዚያው አካባቢ ከመሆን እንደማያልፍ ገመተና ያንን ባለ ታክሲ በመናፈሻው አካባቢ ማረፊያ ወደዚያ አድርሰኝ ሳይለው በመቅረቱ ነበር ቁጭቱ፡፡ ሆኖም አሁንም ሳይዘገይ ጥሩ ሀሳብ እንደ መጣላት አስቦ ጭንቀቱ ከፈል ሲልለት ሀሳቡን ሰብሰብ አደረገና ወደ መታጠቢያ ክፍል ሊገባ ፈለገ፡፡ የሚለብሰውን ፒጃማ አዘጋጀና ሊታጠብ ገባ።
ታጥቦ አበጥሮ ሲያበቃ ምግብ አሰኘው፡! ወደ ሆቴሉ ሬስቶራንት ሄዶ ከበላ በኋላ በቀጥታ ከሆቴሉ ቅጥር ግቢ ወጣ፡፡ ሰዓቱ ከአስራ ሁለት እለፍ ብሏል፡፡ የመንገድ መብራቶች በርተዋል፡፡ ከሆቴሉ በስተግራ አቅጣጫ ተራመደና መንታውን መንገድ አቋርጦ ወደ ምዕራብ አቅጣፍ ደራመድ
ጀመር፡፡ የምሽት የአስመራ ውበት ማራኪ ነው፡፡ አየሩም ሞቅ ያለ፡፡
መብራቶቸ የደመቁ፡፡ የከተማዋ ከቀማመጥ ማራኪ፡፡ መንገዶች ንፁህና የተስተካከሉ፡: በልሁ በሁሉም የአስመራ ገፅታ እየተደሰተ በግምት እስከ ሶስት
መቶ ሜትር ከተጓዘ በኋላ በስተቀኙ በኩል አንድ በበረንዳው ላይ በርካታ ወንበሮች የተደረደሩበት፣ በሰው ብዛት ሞቅ ደመቅ ያለ ሆቴል አየና ጎራ
አለበት፡፡ ሰው አልባ የነበረች ጠረጴዛ አግኝቶ ቁጭ እንዳለ አንዲት ወፈር ያለች ጠይም ጎፈሬ አስተናጋጅ ቀረብ ኣለችውና፡-
«እንታይ ክዕዘዝ» አለችው፡፡
«ትግሪኛ አልችልም፡፡» አላት በልሁ ቀና ብሎ በፈገግታ እያያት
«ዋይ! ይቅርታ የኔ ወንድም!» ብላ አስተናጋጇ በፈገግታ ኣየት
ካደረገችው በኋላ «ምን ልታዘዝ ማለቴ እኮ ነው፡፡» አለችው::
በልሁ በልጅቷ ትህትናና ፈገግታ ደስ ብሎት እሱም ፈገግ በማለት
«ቢራ አምጪልኝ» አላት፡፡
አስተናጋጇ ቢራውን ይዛ መጥታ በብርጭቆ ሞላችለትና ከአጠገቡ ራቅ ብላ የግድግዳ ጥግ ደገፍ ብላ ቆመች፡፡ በልሁ ልጅቷ ያሳየችውን ትህትና አስታውሶ ሁኔታዋ ደስ ስላለው በልቡ ስላለው ጉዳይም ሊያወያያት ፈልገና ሊጠራት አሰበ፡፡ ነገር ግን በዚያች ቅጽበት ማጣደፉ ለሌላ ነገር ይመስላል በማለት ለጊዜው ተወት አረገው፡፡ የመጀመሪያውን ቢራ ጨርሶ ሁለተኛውን
ስታቀርብለት ግን እንደ ምንም ጨከነና፡-
«የኔ እህት ላነጋግርሽ እፈልግ ነበር!» ሲል ጠየቃት፡፡
«ምን?» አለችው አስተናጋጇ ጠጋ ብላ፡፡
«ቁጭ ማለት አትችይም?»
«እችላለሁ፡፡ብላው ቁጭ ልትል ወንበር ሳብ ስታደርግ በልሁ
ቀደማት:: እየጠጣሽ ነዋ»
አስተናጋጅዋ ሳቅ እያለች ወደ ውስጥ ገባችና ለራሷም ቢራ ይዛ
በመምጣት ከፊትለፊቱ ቁጭ አለች፡፡
«አስመራ፡ ከተማዋም ሰዎቹም በጣም ደስ ትላላችሁ» አላት በልሁ ፈገግ ብሎ እየተመለከታት፡፡
«አይደል?" አለች አስተናጋጇም እንደ መሽኮርመም እያደረጋት።
«በእውነት ታምራላችሁ፡፡»
«እናመሰግናለን::»
በልሁ አስተናጋጇን እያጫወተ ትንሽ ሳያሳስቃት ከቆየ በኋላ ወደ ዋና ጉዳዩ ተመለሰ፡፡ «አንድ ነገር ብጠይቅሽ ታውቂ ይሆን?» ሲል ጠረጴዛውን ደገፍ ብሎ ዓይን ዓይኗን እያየ ጠየቃት፡፡
«ምን?»
«እዚህ አስመራ ወስጥ 'ሰሪዬ መናፈሻ' የሚባል ሆቴል እንዳለ ሰምቻለ። የት አካባቢ ይሆን?»
«ያ የተዘጋው»
«ሲሉ ሰማሁ፤ ግን ለምን እንደተዘጋ ታውቂያለሽ?»
«ኧረ እኔም አላውቅም!» አለችና አስተናጋጇ በልሁን ለየት ባለ
እስተያየት ታየው ጀመር፡፡ በእርግጥ በልሁም የአስተያየቷ መለወጥ ገብቶታል።
«ምነው? መጠየቄ ቅር አለሽ እንዴ? ሲል ጠየቃት፡፡
«አይ እሱ እንኳ ብላ ንግግሯን ቆረጥ ስታደርገው በልሁ ጣልቃ ገባ።
«ቅር ካለሽ ጥያቄዬን አነሳለሁ፡፡» አለና ብርጭቆውን ብድግ አድርጎ ቢራውን ተጎነጨ
«የሸዋ ሰዎች እኮ አትታመኑም፡፡» ብላ አስተናጋጁ የቅንድቧ ስር
አሾልካ በልሁን አየት አደረገችው፡፡
«የሽዋ ሰው መሆኔን በምን አወቅሽ?» አላት በልሁ እንደመገረም ብሎ ለነገሩ አልተግባቡም፡ በልሁ የሸዋ ሰው ሰትለው የደብረ ብርሃን ተወላጅ
መሆኑን ያወቀች መስሎት ነው፡፡ እሷ ግን ቀደም ሲል ትግሪኛ አልችልም ስላላትና ለበርካታ የአስመራ ሰው ትግሪኛ የማይችል ሁሉ የሸዋ ሰው እንደያነ ተደርጎ ስለሚገመት ነው።
«ትግሪኛ አልችልም አላልከኝም?አለችው ፈገግ እያለች፡፡
«ትግሪኛ የማይችል ሁሉ የሸዋ ሰው ነው እንዴ» ሲል ጠየቃት

👍10❤3👎1
«ታዲያ ከየት ሊባል ነው?»
«ብዙ አገር አለ እኮ!
«ለእኛ ግን ትግሪኛ የማይችል ሰው የሽዋ ወይም የመሀል አገር ሰው ነው የሚባለው።
በልሁ ምስጢሩ ገባው፡፡ እንደ መሳቅ አለና «ጥሩ እሺ» ካለ በኋላ «ግን ለምን እንታመንም?» ሲል ጠየቃት፡፡
«እኔ እንጃ ግን የሸዋን ሰው አትመኑ ሲባል እሰማለሁ፡ ፡ አለች
የቢራዋን ጠርሙስ አንገት ይዛ ሸከርከር ሸከርከር እያረገች፡፡
በልሁ ስሜቷን እያተረዳ ሲሄድ ራሱንም ወዝወዝ ወዝወዝ አደረገና
ትኩር ብሎም ተመለከታት፡፡
ሆድ ሆዱንም ይቆጨው ጀመር : ከአፍታ ዝምታ በኋላ «ለነገሩ እኮ
እኛም እናንተን አናምናችሁም» አላት የምትመልሰውን ለመስማት ጓጓ ብሎ እየጠበቃት፡፡
«ደሞ እኛ ምን አደረግን?»
« ማድረጉን ምንም አላደረጋችሁም። እኛም ብንሆን ምንም አላደረግንም:: ግን ገዢዎቻችን ብዙ ሊያደራርጉን
ስለሚፈልጉ እንዳንተማመንና እርስ በእርሳችን እንድንጠራጠር ያደርጉናል፡፡ ይህ የኔና የአንቺ አለመተማመን እንኳ በመጠኑም
ቢሆን በመጠኑም ቢሆን እየተሳካላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡» ካለ በኋላ እጆቹን አቆላልፎ ጠረጴዛውን ደገፍ በማለት
«አያሳዝንም?» ሲል ጠየቃት፡፡
«እኔ እንጃ» አለችና አስተናጋጇ ቢራዋን ጎንጨት እያለች አካባቢዋን ቃኘት ቃኘት ታደርግ ጀመር፡፡
«አንድ ነገር ልንገርሽ» አላት በልሁ አሁንም ትኩር ብሎ እያያት፡፡
«ምን?»
«ያለ መተማመናችን ምስጢር ምንም ይሁን ምን፣ እንዳንተማመን ያደረጉን ወገኖች ዓላማቸው ምንም ይሁን ምን ውጤቱም የቱንም ያህል የከፋ
ይሁን ነገር ግን የአንዲት አገር ልጆች ነን፡፡ ዘመን በዘመን ተሽሮ ጊዚን ጊዜ ቢተካው ዞሮ ዞሮ አንድ መሆናችን አይቀርም፡፡» አላት፡፡
«ሊሆን ይችላል»
«አትጠራጠሪ፡ ፡» አላትና በልሁ ስለዛሬው ጉዳዩ ሊያወያያት በማሰብ
«እስቲ ለዛሬ እንኳ ታምኚኝ ከሆነ ስለ ሰራዩ መናፈሻ የጠየኩበትን
ምክንያት ዝርዝር አድርጌ ልንገርሽ፡፡» አላት፡፡
«ምንድነው እሱ?» ብላ ጓጓ አለችና ትመለከተው ጀመር፡፡
በልሁ ወዲያው ጀመረ፡፡ በቅድሚያ ለአስመራ እንግዳ መሆኑን ነገራት፡፡ ወደ አስመራ የመጣበትን ምክንያት አስከተለ፡፡ ስለ አስቻለው ሁኔታ ገለጸላት፡፡ የአስቻለውንና የመናፈሻዋን ቁርኝት አስረዳት፡፡ የመናፈሻዋ
መዘጋት ያስከተለበትን ስጋት አብራራላት፡፡
እስተናጋጇ በዕሞና ነበር ያዳመጠችው፡፡ ከልቡ እየተናገረ መሆኑን ከአጠቃላይ ገፅታው ትረዳ ነበር፡፡ በተለይ ስለ አስቻለው ሁኔታ ሲተርክላት ፊቷ በሀዘን ስሜት ይሞላ ነበር፡፡ በልሁ ነገሩን ሲያጠቃልል ራሷን ለብዙ ጊዜ
ወዘወዘች፡፡ በመጨረሻም በረጅሙ ተነፈሰችና፡-
«ያሳዝናል» አለችው:
«ፈቃደኛ ከሆንሽ እርጂኝ»
«መናፈሻው የተዘጋው ባለቤቱ የሻቢያ አባል ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡
አለችው፡፡»
«ኣ!» አላት በልሁ ይበልጥ እንድታብራራለት ፈልጎ፡፡
«ለሰበቡ አንድ የጦር ሜዳ ተዋጊ የነበረ ሰው በዓልቤርጎው ውስጥ
አርፎ ተገኘ፡፡ የጦር መሳሪያዎችም አብረውት ነበሩ፡፡ ሰውየው ግን እጅ አልሰጥም ብሎ ተዋግቶ እዛው ሞተ የመናፈሽዋ ባለቤትና ሰራተኞችም ወድያው እየደተያዙ ታሰሩ፡ ብታይ የዚያን ዕለት መላ
አስመራ ከተማ ቀውጢ ሆና ነበር የዋለችው በርካታ ወጣቶች መንገድ ላይ ተገድለዋል እየተያዙም ታስረዋል፡፡ከመናፈሻው ባለቤት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ የተጠረጠሩትን ሁሉ በቀጣይ ቀናት ሲለቀሙ ዋሉ ስለዚህ ስለዛ መናፈሻ ማውራት ራሱ ስለሚያስፈራ ነው እኔም ቅድም ችላ ያልኩህ አለችው «ደንበኞችም ሞተው ይሆን?»
«እሱን እንኳ እርግጠኛ አይዶለሁም፡ ፡»
በልሁ ጥርጣሬ ገባው መንፈሱ ተጨነቀ በረጅሙ ተነፈሰና ወደ መሬት አቀርቅሮ ብዙ ከአሰበ በኋላ እንደገና ወደ አስተናጋጁ ቀና በማለት ግን መናፈሻዋ የምትገኝበት አካባቢ የት ነው?» ሲል ጠየቃት።
አስተናጋጇ በእጇ ወደ ምዕራብያዊ አስመራ አቅጣጫ እያመለከተች በዚህ በኩል ነው' ወደ ኣባ ሻውል ሲሄዱ ወዴ ግራ ወረድ ሲሉ የሚገኝ አካባቢ አለችው
«ታከሲ ይገባዋል?»
«በእግርም ይቻላል፡፡»
«አመሰግናለሁ የኔ እመቤት አለና በልሁ ከኪሱ ገንዘብ እያወጣ
«ሂሳብ ስንት ይሆን» እያለ ጠየቃት
«ሶስት ቢራ አይደል ሦስት ብር ብቻ አለችው
በልሁ አስር ብር ሰጣትና በተረፈው አንቺ ጠጪ እኔ ግን መንገድ ላይ ደክሞኛልና ወደ ማረፊያዪ ልሂድ አላት።
በጥሩ ስሜትና ፈገግታ ተሰነባበቱ፡፡.....

👍16❤1
#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
“ደብረ ወርቅ ማርያም የሥዕል ንጉሥ አለ።”
የአስራ ስምንት ዓመቱ ብርሃን ሰገድ ኢያሱ በትምህርት የበሰለ፣
በአስተሳሰቡ የበለፀገ፣ በመልኩና በአቋሙ ያማረ ሆነላት ምንትዋብ።ፈረስ ላይ ተቀምጦ፣ ነጭ ሻሹን ሹሩባው ላይ አስሮ፣ በወርቅ ያጌጠ ካባውን ደርቦ፣ የወርቅ በትረ መንግሥቱን ጨብጦ፣ ቀይ ድባብ ተይዞለት፣ ባልደራስ አጅቦት ከግቢ ሲወጣ፣ ሕዝቡ፣ “አቤት አበቃቀሉ!
አቤት የፊቱ አወራረድ!” እያለ አደነቀው: ወደደው፤ አከበረው፤
ሰገደለት፤ “ቋረኛው ኢያሱ” የሚል ቅጽል ስምም አወጣለት።
አደን አፍቃሪው ኢያሱ እንደ በፊቱ ሰስና ድኩላን ሳይሆን፣ ዝሆን፣
አውራሪስና ጎሽ እየገደለ መምጣት ጀምረ። ምንትዋብና እናቷ ግን ለአደን በወጣ ቁጥር ወገባቸውን በገመድ እየታጠቁ፣ መሬት እየተኙ፣ እየጸሙና እንቅልፍ እያጡ ይሰነብታሉ።
ኢያሱ በድፍረቱና በጀግንነቱ ተወዳዳሪ አጣ። ስለሃገር ጉዳይም መከታተል፣ ውሳኔ መስጠትና እርምጃ መውሰድ ያዘ። ከእናቱ መዳፍ ሥር ወጥቶ የራሱ ሰው ሆነ። አክሱም ጽዮን ሄደ። የእናቱን የትውልድ
ቦታ ለማየትም ቋራ ደርሶ መጣ። አንድ ጊዜ የግዛት ማስፋፋት ፍላጎቱ አድጎ ሰቆጣ ሄዶ ተሸንፎ ቢመጣ፣ በቁጭት ወኔውን ሞልቶ ሱዳን ጠረፍ ሄደ፡፡
የገጠመውን ጦር አሸንፎ በሰላም ተመለሰ።
በሰላም ይመለስ እንጂ ከእናቱ ጋር አተካራና ቅያሜ ውስጥ ገባ።
በግራዝማች ኢያሱና በእናቱ መሃል ያለው የፍቅር ግንኙነት ይከነክነው
ገባ። ምንትዋብም ወለተእስራኤል ያለቻትን ሦስተኛ ልጇን ከወለደች
ቆይታለች።
ኢያሱ እናቱ ላይ ቅሬታና ምሬት አደረበት። ምንም እንኳ እናቱን
ቢያከብርና ቢፈራ፣ ከግራዝማች ኢያሱ ጋር ያላትን ግንኙነት ችላ
የማይለው ጉዳይ ሆነበት።
ፀሐይ መግቢያ ላይ ነው። እናትና ልጅ ቤተመንግሥት እንግዳ
መቀበያው ክፍል ተቀምጠዋል። ኢያሱ ነገር ሲገባው ታውቃለች
ምንትዋብ። ገና፣ “ኸያሱ ጋር..” ሲልና ሲጠጣበት የነበረውን የወርቅ ዋንጫ ሲያስቀምጥ፣ የንግግራቸው አቅጣጫ ወዴት እንደሆነ ገባት።
“ኸያሱ ጋር ባለሽ ግንኙነት ሰው ሁሉ ያማሻል። ቀደም ብየ ብሰማም ዕድሜየም ገና ስለነበር ፈርቸ እስተዛሬ በዝምታ ቆየሁ” አላት።
“ኢያሱ አባትህኮ ሲሞቱ ዕድሜዬ ገና ነበር። ብቸኛም ነበርሁ።
ልችም መውለድ ፈልግ ነበር። ደሞስ እንዲህ ያለው በኔ ተዠመረ?” አለችና፣ ለራሷ ዛዲያ እንዴት ልሁን ሰው መሆኔ ቀረ? እቴጌ ያሉኝ እንደሁ ሰው ማይደለሁ እንዴ? ሰው መሆን ዛዲያ ትርጉሙ ምኑ ላይ ነው? ስትል መናገር ሲጀምር ቀና አለች።
“የመዠመርና ያለመዠመር ጉዳይ ማዶል” አለ፣ እናቱ ላይ አድርጎ
በማያውቀው መንገድ ፊቱን አኮማትሮ።
ከእሷ ስሜት በላይ ክብር የሚባል ነገር አለ።
መልስ አልሰጠችውም። ስሜቱ እንደተጎዳ አውቃለች። እባክህ
አምላኬ ኸልዤ ጋር እንዳልጣላ ትግስት ስጠኝ አለች።
“ኢያሱ አንደኛ ያክስቴ ልዥ ነው” ሲል ቀጠለ። “ያባቴ እት...
የወለተስራኤል ልዥ እኮ ነው። ያባቴ ክብርስ ቢሆን፣ ስለምን ይነካል? ላንቺም ቢሆን ነውር ነው። ስለምንስ ስማችን በዝኸ ይነሳል? መልካም ስምሽንስ ስለምን ታጎድፊያለሽ? ግራማች ብትይውም ሰዉ አሁንም
ምልምል ኢያሱ ነው ሚለው። ኸዝኸ ወዲያ ውርደት ምን አለ?”
ንግግሩ ጎመዘዛት። ከንፈሯን በጥርሷ ነከስ ኣድርጋ በግራ ሌባ ጣቷ መታ መታ አደረገችው። ቁጣ ሰውነቷ ውስጥ ሲቀሰቀስ ተሰማት።
“ተው እንጂ ኢያሱ! እኔን እናትህን እንዲህ አትናገር። ምወድህ
እናትህ እንጂ ሌላ ነኝ?”
“ሰዉ ያማሻል እኮ!” ግንባሩ ኩምትር ብሏል።
“አምተው በቅቷቸዋል። ኢያሱ ... ኸግራማች ጋር ተዋልደናል እኮ!
እህቶችህ የማን ይመስሉሃል? እኔ ያባትህን ስም ለማጉደፍ ሳይሆን፣
ብቸኝነት ስላጠቃኝ ነው። ተረዳኝ እንጂ!”
“ኸዝኽ ወዲያ ውርደት ምን አለ?” የሚሉት ቃላቶቹ ረበሿት። ትክ ብላ አየችው። ፊቱ ላይ ቅያሜ አየች። ዛዲያ ዕድሜዬን እንዲሁ
ላሳልፍ ኑሯል እንዴ? አለች።
ለእሱ የክብር ጉዳይ እንደሆነ አላጣችውም። እንኳንስ የባሏን
የእህት ልጅ ባሏ የሞተባት ንግሥት ጨርሶ ሌላ ማግባት እንደሌለባት ታውቃለች።
ግን ደግሞ ውጣ ውረድ ከበዛበት የቤተመንግሥት ሕይወት ዘወር ብላ የምትዝናናበትና ሐሳቧን የምትከፍልበት ነገር ባለመኖሩ፣
አንድ ቀን ከልጇ ጋር የሚያቃቅራትና አልፎም ሊያጣላት የሚችል ነገር እንደሆነ ብታውቅም አድርጋዋለች።
ከልጇ ጋር ይህን ያህል ጠንከር ያለ ንግግር ተለዋውጠው ስለማያውቁ ቅር ብትሰኝም፣ የምትወደውንና የምትሳሳለትን ገራሙን ልጇን መቀየም
አልሆነላትም። ቅሬታና ቅይሜ በሆዷ አምቃ መሄድ አልፈለገችም።
የአባቱ ብቻ ሳይሆን የእሱ፣ ብሎም የእሷ ክብር እንደተነካበት ስላወቀች ትችቱን ተቀብላ ዋጥ ማድረግን ፈለገች።
በራሷ አምሳል ቀርጻ ያወጣችው ቢመስላትም፣ እየተመካከረች፣
ሲሻትም እየተጫነችው ያሳደገችው ልጇ ብሩህ አእምሮ ያለውና በራሱ አስተሳሰብ የሚመራ መሆኑን በመገንዘብ ልቧ ላይ ሊሰርፅ የቃጣውን
ቅሬታ ለመግታት ታገለች።
ለብቻው ለመግዛት ዕድሜው ቢፈቅድለትም፣ ለእሷ ካለው ፍቅር፣አክብሮትና ፍራቻ ጭምር የእሷን የበላይነት ተቀብሎ መኖር እንደቻለ ተገነዘበች። እሱም ቢሆን ከሥልጣኗ ለማውረድ የሚያስችለው በቂ
ምክንያት የለውም።
እንዲያውም የእሱ መንግሥት በእሷ ብርታት፣ ጥበብና ዘዴ የተሞላው አመራር መደላደሉን፣ አንዳንድ መኳንንት ቋረኞች ላይ ያላቸውን ጥላቻ አርግባ ተስማምታና አስማምታ መቆየቷን፣ ከአንዴም ሁለት
ጊዜ የተቃጣባቸውን ዓመጽ ድል መቀዳጀታቸውን፣ ሌሎችን ደግሞ
በሰላማዊ ድርድር እየፈታች ሰላም እንዲሰፍን ማድረጓን ይገነዘብ
እንደሆነ ራሷን ጠየቀች። ይህን ልታስታውሰው ግን አልፈለገችም፤
ዝም ብላ ተቀመጠች። ተነስቶ ሲወጣ በተለመደው የእናትና የልጅ ፍቅር አልተሰነባበቱም።
ከሄደ በኋላ፣ የተነጋገሩትን ሁሉ በጭንቅላቷ ከለሰችው። መቸም
እኔስ ብሆን በነገሩ ሳልጨነቅ ቀርቸ ነው? አልሆንልኝ ብሎ ነው እንጂ።ብቸኝነት አጥቅቶኝ ነው ኸኢያሱ ጋር እዚህ ሁሉ ውስጥ የገባሁት።እሱም ቢሆን እነአስቴርን የመሳሰሉ ልዦች ሰጥቶኛል። ኸንግዲህ
ምን አረጋለሁ። የአብራኬ ክፋይ እንዲህ ሲለኝ መስማት ለእኔ ደግ
ማዶል። መቸስ የክብር ጉዳይ ሆኖበት ነው። በዝኸ አልቀየመውም። እነሱ እንዳይጣሉብኝ እንጂ። ለግራማች ኢያሱ ነግረዋለሁ እያለች አሰላሰለች።
ግራዝማች ኢያሱ፡ “ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ተለውጦብኛል” ማለት
ሲያዘወትር፣ እንዳይጣሉባት ሰጋች፤ በሐሳብ ባከነች። እየቆየም በሁለቱ መሃል ነገሮች እየከረሩ፣ ግንኙነታቸው ወደ ፀብ መቀየሩ እንቅልፍ አሳጣት። አስታራቂ ሽማግሌዎች ላከች።
ይህ ሳያንሳት በመጋቤ ሥነ-ጊዮርጊስ አማካኝነት ሁለተኛው የጥላዬ ሥዕል መጣላት። የሥዕሉ ውበትና የያዘው ጥልቅ ሐሳብ
ቢያስደስታትም፣ ሁለቱም ሥዕሎች ከአንድ ሥሙር ከሚባል ሰው መምጣታቸውን በሥራው አረጋገጠች፤ ለወራት ተረበሸች።
እነዚህን ሥዕሎች የሚልከው ሰው ምን አስቦ እንደሆነ ለማወቅ
ቸገራት። እኼ ሰው ስለምን ማንነታቸው ስንኳ በማይታወቅ ሰዎች ይልካል? ይኸ ከበጎ አሳብ የመጣ ነው ወይንስ እኔን ሰላም ለመንሳት ሚደረግ እኔ ለራሴ ኸልዤ ጋር ችግር ውስጥ በገባሁበት ግዝየ ስለምን
እንደዝኸ ያለ ነገር ይገጥመኛል? አንቺ ምወድሽ ቁስቋም የዝኸን ሰው ማንነት አንቺው ግለጭልኝ እያለች ማርያምን ተለማመነች። ለሌላ ሰው የማታዋየው ምሥጢር ሆኖባት ሥዕሉን በመጣበት ጨርቅ መልሳ ጠቅልላ ከበፊተኛው ሥዕል ጋር ደብቃ አስቀመጠችው።

👍14
የዚህን ግራ የሚያጋባ ነገር ግን ከልጇ ጋር ሽማግሌዎች ባደረጉት
መማጸን ዕርቅ በመውረዱና፣ ዳግማዊ ኢያሱና ግራዝማች ኢያሱም በመታረቃቸው ችላ አለቸው፤ እስከነአካቴውም ረሳችው።
ዳግማዊ ኢያሱም ከዕርቁ በኋላ አገር ጉዳይ ላይ ማተኮሩን ያዘ።
ሽፍታ የጐንደርን ሕዝብ ሆነ ከስናር የሚመጣውን ሲራራ ነጋዴ
እየዘረፈ ቢያስቸግር፣ እንደ ቀደምት ነገሥታት ቅሚያ ላይ የተሰማሩትን ለመቅጣት የሰላም ዘበኞች አቋቋመ። የሰላም ዘበኞቹ ሽፍታና ቀማኛን ኣጥፍተው ነጋዴው ያለ ስጋት የንግድ መስመሩን ተከትሎ ንግዱን
እንዲያቀላጥፍ አደረገ።
ጐንደርም ዘና ብላ እንድትተኛ አስቻላት።
የቁስቋም ግንባታ ካለቀና ከልጇ ከኢያሱ ጋር ዕርቅ ካወረደች በኋላ፣ምንትዋብ ልታስገነባ ያሰበቻቸውን ሁሉ ማስገንቢያ ሰዐቱ አሁን ነው ከለች። እሷና ዳግማዊ ኢያሱ የግንባታ ሥራውን እንዲቆጣጠሩ ከሾሟቸው ከእነአዛዥ ማሞ ጋር ምክክርና ዝግጅት አደረጉ። አፄ ፋሲለደስ ቤተመንግሥት ቅጥር ግቢ ውስጥ የእሷ ቤተመንግሥት
እንደተደረገው ሁሉ፣ ከዳባት የመጣ ኖራ ተቃጥሎ፣ ከቅባታማ እህሎች፣ አጃ ከመሰሉ ጥሬዎች፣ ቅንጭብና ቁልቋል ከመሳሰሉት ፈሳሾች ጋር ተቦክቶ እንዲብላላ ለወራት ተቀመጠ።
ለግንባታ መሣሪያዎች ማስቀመጫ ህንፃ ተሠራ። አንድ ሺህ ግንበ ገፊዎች፣ አምስት መቶ ባንድ ቀን፣ ሌሎች አምስት መቶ በሚቀጥለው ቀን እንዲሠሩ ሆኖ ግንባታው በፍጥነት ተጀመረ። አካባቢው በግንበኛው፣
በኖራ አንጣሪው፣ በዕንጨት ቀራጩ፣ በለሳኙና በሌሎችም ተጣበበ።ሁሉም በየሥራው በታላቅ ትጋትና ቅልጥፍና ተሰማራ።
ሳንቃ መሥሪያና የግንቦች መወጠሪያ ጠንካራና ግዙፍ የሆኑ
ግማርዳ፣ ጥድ፣ ዝግባ፣ ወይራና ድንበቃ ዓይነት ዕንጨቶች ከአርማጨሆ፣ከወልቃይትና ከመሳሰሉት ቦታዎች እየመጡ፣ ምንትዋብም ከአናጢዎቹ
ጋር አብራ ጥሩውን እየመረጠች የግንባታ ዝግጅት ተጀመረ።
እናትና ልጅ በየቀኑ እየተከታተሉ፣ ገላ መታጠቢያና መጸዳጃ ክፍል
ያለው፣ መግቢያው ላይ ሁለት ክብ የድንጋይ ቅርጾች የቆሙለት፣
ከጎኑ የተለያዩ ክፍሎች ያሉት ባለ ሁለት ፎቁ የእሷ ቤተመንግሥት
ተገንብቶ አለቀ።
ዳግማዊ ኢያሱ እዛው የነበረበት ፋሲለደስ ቤተመንግሥት ቅጥር
ግቢ እናቱ ባሠራችው ቤተመንግሥት ውስጥ ሲቀር ምንትዋብ ወደ ቁስቋም ተዛወረች።
ከቤተመንግሥቷ ትይዩ፣ የጥሞና ቦታና የሴትነት ግዴታዋ ላይ
በምትሆንባቸው ቀናት የምትጠቀምበት ፎቅና ምድር ያለው ክቡ ጸሎት ቤቷም ተሠራ። ቤቱ የጎደለ ነገር እንዳለው ሲሰማት አንድ ጠዋት ረፋዱ ላይ መልአከ ፀሐይ ሮብዓምን እልፍኟ አስጠራችው።እሷ በወርቅ የተለበጠው ወንበሯ ላይ ተቀምጣለች። እጅ ነስቶ ሲቀመጥ
ወርቀ ዘቦ ለብሶ የተቀመጠው ጠረጴዛ ላይ ጠጅ ቀረበለት።
“መላከ ጠሐይ የፈለግህዎት እንዳው ለዝኸ ለጸሎት ቤቴ ሥዕሎች ስለሚያስፈልጉ ሠዓሊ ፈልጌ ነው።”
ሮብዓም ዝናው ጐንደር ድረስ የተጓዘውን ሥሙርን አሰበ፡፡
“ደብረ ወርቅ ማርያም የሥዕል ንጉሥ አለ። ማንም አይደርስበት
አሉ። ሊቀጠበብትነት ኋላም አለቅነት ማዕረግ እንዳገኘ ሰምቻለሁ” አላት።
“ዛዲያማ ስለምን አናስጠራውም? ስሙስ ማን ይባላል?”
“ሥሙር ይሉታል። የሥዕል ንጉሥም ይሉታል። ባስቸኳይ
እንዲመጣ ግን ሰው ልካለሁ።”
“እኔም ይኸን ሥሙር ሚባል ስም ሰምቻለሁ፤ እንዲያው ኸሰዎች
አፍ ላይ። ጥሩ ባለሙያ ባይሆን እንዲህ ስሙ ባልገነነ ነበር። ኸተገኘ እሱ ቢመጣ ደሕና ነበር” አለች ምንትዋብ፤ ስለተላከላት አሳሳቢ ሥዕል ትንፍሽ ሳትል።
ቀጠል አድርጋም፣ “ያው እንደሌሎቹ ማደሪያው እሚኾን በቂ ድርጎ ይሰጠዋል። መላከ ጠሐይ እኔ መቸም ልክ እንደ ቅኔ ለሥዕል ይኸ ነው ማይባል ፍቅር አለኝ። ያሉትን ሠዓሊ ተሎ አስመጡልኝ” አለችው።
“እቴጌ ለሥዕል ያለዎትን ፍቅር አውቃለሁ” አላትና እጅ ነስቶ
ወጣ።ለሳምንታት ምንትዋብ የሥዕል ንጉሥ የተባለውን ሠዓሊ መምጣት አለመምጣት ሮብዓምን አጥብቃ ትጠይቃለች። ሮብዓም፣ ጥላዬ ሊያቆየኝ የማይችል ሥራ ላይ በመሆኔ ልመጣ አልችልም ማለቱ አስጨንቆታል። ስለ ድፍረቱ ተደንቋል፤ ከጥጋብ ቆጥሮበታል። ይህ ዓይነቱ ድፍረት ከየትና እንዴት ሊመጣ እንደቻለ ገርሞታል ።
ምንትዋብ ስትጠይቀው የሚመልሰው መልስ እያጣ ተቸገረ።በመጨረሻም “ሠዓሊው አልተገኘም። ወደ ሸዋ ሂዷል አሉኝ ሲል መለሰላት።
ሌሎች ሠዓሊዎች ሥራውን እንዲሠሩ ተደረገ።
የቁስቋም ግቢ ግብር አዳራሽም ሥራ በተቀላጠፈ መንገድ ተያያዘ።
አዳራሹ ውስጡ ከላይም ከታችም ለምንትዋብና ለኢያሱ መቀመጫ
የሚሆን ገባ ያለ ቦታ ተሠራለት። በስተቀኝ በኩል ስድስት፣ በስተግራ ደግሞ አምስት ማሾ ማስቀመጪያ ሸክላዎች የሚይዙ ድፍን መስኮቶች ተደረጉለት።....

👍14❤2
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
....በልሁ አስር ብር ሰጣትና በተረፈው አንቺ ጠጪ እኔ ግን መንገድ ላይ ደክሞኛልና ወደ ማረፊያዪ ልሂድ አላት።
በጥሩ ስሜትና ፈገግታ ተሰነባበቱ
የበልሁ የማግስቱ የመጀመሪያ ስራ አስተናጋጇ በጠቆመችው
አቅጣጫ ሄዶ ያቺን መናፈሻ ማግኘት ነበር።ብዙ ሳይቸገር
አጎኛት፡፡ ሲያዩዋት ደስ የምትል መናፈሻ የነበረች ትመስላለች፡፡ ግቢዋ በልዩ ልዩ ተክል ያሸበረቀ ነው፡፡ ዋናው ቡና ቤት መሀል ላይ ይገኛሉ፡፡ በአራት ማእዘን ቅርፅ ጥርብ ድንጋይ የተሰራ ነው:: በየአትከልቱ መሀል አልፎ አልፎ
የፈራረሱ መዝናኛ ጎጆዎች ይታያሉ። ከአንዱ ወደ ሌላው መተላለፍያ መንገድ በሲሚንቶ የተሰራ ነው፡፡ አሁን ግን የዛፎቹ ቅርንጫፍ ስለማይከረከም እየተዘጉ ያሉ ይመስላሉ፡፡ በዚያ ላይ የወፎች ኩስ ተንጠባጥቦባቸው
ተዥጎርጉረዋል፡፡
የግቢው ዙሪያ አጥር ከታች አንድ ሚትር ያህል በግንብ፡ ከላይ ደግሞ የዚያኑ ያህል በብረት
ፍርግርግ የታጠረ ነው፡፡ ዋና መግቢያው በር በብረት መዝጊያ ተከርችሟል፡፡ አንድ ሰው ብቻ ይጠብቀዋል፡፡
በልሁ የዚያች መናፈሻ የቀድሞ ገፅታ በአይነ ልቦናው ታየውና እንባ እንባ አለው፡፡ አስቻለውን በዚያ ውስጥ አስታወሰው፡፡ አስቻለው አሁን እዚያ ውስጥ እያለ ነገር ግን ቢጠራው አልሰማ፣ እጁን ቢዘረጋ አልደርስበት ያለው
ይመስል ሆዱ ባባ፡፡ እንባውም ፈሰሰ፡፡ መሀረቡን አውጥቶ አይኑን ጠረግ ሲያደርግ ድንገት ድምፅ ሰማ፡፡ ከመናፈሻዋ በር ጠባቂ በኩል ነበር፡፡
“ምን አሉኝ ጌታዬ?» ሲል በልሁ ወደ ሰውየው እያየ ጠየቀው፡፡
ሰውየው አሁንም ተናገሩ።ነገር ግን በትግርኛ ስለነበር ለበልሁ አልገባውም።
ሰውየው ከስልሳ አለፍ የሚላቸው ይመስላሉ የሰማያዊ ካኪ ቱታ ለብሰው ራሳቸው ላይ የዘበኛ ቆብ
አድርገዋል። እሳቸውም አማርኛ በደንብ አይችሉ ኖሮ በእጃቸው እያመለከቱ « ወዲያ ወዲያ..»
አሉት በልሁም ከዚህ አካባቢ ሂድ ማለታቸው እንደሆነ ገብቶት ከቦታው መራቅ ጀመረ፡፡
ከአባ ሻውል በስተደቡብ አቅጣጫ በሚወስደው አቧራማ መንገድ ላይ ዝም ብሎ ይራመድ ጀመር፡፡ ያ አካባቢ ከሌላው የአስመራ አካል ጋር ሲነጻጸር
ደከም ያሉ ናቸው:: ሞቅ ደመቅ ያሉ ቡና ቤቶች አይታዩበትም ትንንሽ ግሮሰሪዎች ጠላና እንዲሁም አረቄ ቤቶች ይበዙበታል።
በልሁ ድንገት በል በል አለውና ከከንድ ጠላ ቤት ውስጥ ገባ ሰዓቱ ገና ከአራት ብዙም አላለፈም፡፡ ነገር ግን በርካታ ጠጪዎች ቤቱ ውስጥ አሉ፡፡ ባለ ጠላ ቤቷ ሳይሆኑ የማይቀሩ
ወደ ሃምሳ የሚጠጋቸው ቀይ ረጅም ዘንካታ የሆኑ ሴት ወይዘሮ ወንበር ላይ ጉብ ብለው በየመደቡ ላይ ተቀምጠው ከሚጠጡ ሰዎች ጋር ይጫወታሉ። ቋንቋቸው ትግረኛ ነው።
በልሁ ገብቶ ሲቀመጥ ምን ልታዘዝ የሚል አስተናጋጅ ከፊቱ
አልቀረበም፡፡ ጠላ ቤት ነውና መስተንግዶው የታወቀ ነው፡፡ አንዲት በኑሮዋ ጎስቆል ያለች ልጅ እግር ሴት በጣሳ ጠላ ይዛለት ቀረበች፡፡ በእጁ ሰጠችው፡፡በልሁ ጠላውን ቀመስ ሳያደርግ ወለሉ ላይ ቁጭ አደረገው።
እኒያ ነጫጭ የሀገር ልብስ ለብሰው ወንበር ላይ ቁጭ ያሉት ቀይ መልከ መልካም ሴት በልሁን
አየት አደረጉና «ብርጭቆ ክህቦም» አሉት በትግርኛ። «ምናሉኝ እማማ!» አለና በልሁ «ትግርኛ አልችልም» አላቸው
«ዋይ!» አሉና ሴትዮዋ «ብርጭቆ ይሰጥህ ወይ ማለቴ እኮ ነው፡፡» አሉት «አያስፈልግም እማማ! አመሰግናለሁ!» አለና ጣሳውን አንስቶ ፉት አለ።
«የሸዋ ሰው ነህ?» ሲሉ ጠየቁት ሴትየዋ ፈገግ እያሉ፡፡
«አዎ» አላቸው፡፡ በልሁ ያቺን የማታዋን አስተናጋጅ አስታወሳት፡፡
«አይዞህ የኔ ልጅ! በል ጠጣ!» አሉትና ሴትዮዋ ወደ ሌለች ጠጪዎች ዞር በማለት ጨዋታቸውን ቀጠሉ፡፡
በልሁ አልፎ አልፎ ጠላውን ፉት እያለ የሚያወሩት ነገር ባይገባውም የጠጪዎችን ወሬ ሲያዳምጥ ብዙ ቆየ፡፡ በየመሀሉ ግን ልቡን ዳዳ የሚያረገው
ነገር አለ፡፡ ሊናገር አሁን አሁን ሲል ድንገት ሴትዮዋ ቀድመው አናገሩት:
«ተጫወት የኔ ልጅ!፡፡» አሉት በልሁን ፈገግ ብለው እያዩ፡፡ በልሁ
ጣሳውን እያነሳ ሳለ ሴትዮዋ ቀጠሉ፡፡ «ቋንቋችንን አታውቀው፣ እንዴት እናርግህ?» አሉት እጆቻቸውን በጡቶቻቸው ስር አጣምረው ፊት ለፊት
እየተመለከቱት፡፡
«አረ ይሁን ምንም አይደል» ብሎ በልሁ ወዲያው ደግሞ በዚህ
አካባቢ የሚያውቁት የሚሲዮኖች ሀኪም ቤት ይኖር ይሆን እማማ?» ሲል ጠነቃቸው።
ሴትዮዋ ትንሽ አሰብ አደረጉና «እነዚያ ጥልያኖቹ?» ሲሉ ጠየቁት፡፡ «ይሆናሉ በእርግጥ ፈረንጆች ናቸው»
«ከዚህ ወደታች በኩል ነበሩ፡፡ ነገር ግን አሁን እኮ ከዚያ ቦታ «ለቀዋል?» በልሁ አሁንም ደንገጥ እያለ
«ምን ያህል ጊዜ ሆናቸው?
«ቆዩ እኮ!»
«ምን ያህል ጊዜ ሆናቸው?»
ሴትዮዋ በቀጥታ ለበልሁ ምላሽ ሳይሰጡ ወደ ጠጪዎቹ ዞር በማለት በትግሪኛ ያነጋግሯቸው ጀመር፡፡ ደግመው ደጋግመው ከተመላለሱ በኋላ ሴትዮዋ ፈታቸውን ወደ በልሁ መለስ አድርገው «ከዓመት በላይ ይሆናቸዋል ነው የሚሉኝ» አሉት።
በልሁ እንደገና ወሽመጡ ቁርጥ አለ ፡፡ አጋጣሚዎች ለምን
እንደሚደጋገሙበት ግራ ገባው፡፡ እዝን ባለ ፊት ትክዝ ባለ አነጋገር «በቃ ይተውት እማማ!» እላቸውና ጣሳውን አንስቶ ፉት ካለለት በኋላ መልሶ አስቀመጠው፡፡ ወደ መሬት እጎንብሶ ራሱን ደጋግሞ ወዘወዘው፡፡
«ልትታከም ኖሯል?» ሲሉ ሲትዮዋ ጠየቁት፡፡
«አይደለም፡፡ እነሱ ጋር ይሰራ የነበረ ሰው እፈልግ ነበር፡፡» አላቸውና አሁንም ጎንበስ አለ።
«አየየ... ለቀዋላ!» ብለውት ሲትዮዋ ወደ ጨዋታቸው ተመለሱ፡፡
በልሁ ከዚያ በኋላ ብዙ መቆየት አልፈለገም፡፡ ውስጡም ተናደደ፡፡
እስከ አሁን ባገኘው መረጃ የአስቻለው ዱካ በቀላሉ እንደማይገኝ፡ ምናልባትም
ጭራሽ ላይገኝም እንደሚችል ፈራ፡፡ ተስፋው እየጨለመ ሄደ፡፡
ወዲያው አንድ ነገር ታየው፡፡ ወደ አረፈበት ሆቴል መብረር፡፡ አዎ
ሄደ፡፡ በጠራራ ፀሐይ በአንሶላና ብርድ ልብስ ጥቅልል ብሎ ተኛ አስቻለውን እንዳያገኝ ከጋረደው የጭንቅ ጉም ያመለጠ መስሎት፡፡
የሰው ልጅ የቱንም ያህል ቢያሰብ፡ ቢጨነቅ ወይም ቢናደድ፡ ቢበሳጭ አልያም ቢፈራ በአጠቃላይ በየትኛውም ስሜት ውስጥ ቢሆን በህይወት
ለመሰንበት የግድ የሚያስፈልገው አንድ ነገር አለ፡ ምግብ፡፡ በልሁ በአንሶላና በብርድ ልብስ ውስጥ ቢደበቅም አላመለጠውም፡ አጅሬ ርሀብ ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ የሚነሳ እሳት ነውና አንጀቱን ይሞረሙረው ጀመር፡፡ ከአንድ ጣሳ ጠላ ሌላ የቀመሰው ነገር ባለመኖሩ ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት አካባቢ ከተኛበት ሰቅስቆ
አስነሳው:: ምግ አይሉት ራት አደባልቆ ሊበላው ወደ ሆቴሉ ራስቶራንት ወረደ፡፡ ሚሲዮኖቹ ሀኪሞች ይሰሩ ከነበሩበት አካባቢ በመልቀቅ ዜና ተበሳጭቶ
ሳይበላ ሳይጠጣ በመዋሉ መንፈሱ ድክምክም ብሎበት የነበረው በልሁ ምሳ በልቶ ቀዝቀዝ ያለ ለስላሳ ከውሃ ጋር እየቀላቀለ ሲጠጣ በዚያው ልክ ተነቃቃ፡፡
ረጋ ብሎ ማሰብ ጀመረ።
አንድ ነገር ታየው ሚሲዮኖቹ
ሀኪሞች እንደ መሆናቸው መጠን
ከክፍለ ሀገሩ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ጋር በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችል ታሰበው ምናልባትም የስራ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል " ያ ከሆነ ደግሞ ወቅታዊ ሪፖርቶች ይጠበቅባቸው ይሆናል፡፡ በዚያው መጠን በሁለቱ አካላት መካከል መቀራረብና የአድራሻ ልውውጥ ሊኖር ይችላል “ሚሲዬኖቹ እዚያው አስመራ ካሉም እዚያው

👍13❤1
ሊፈልጋቸው ወደ ሌላ ክፍለ ሀገርም ተዛውረው ከሆነ በአለበት ቦታ መሄድ እንዲችል በቅድሚያ ወደ ክፍለ ሀገሩ ዜና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ሄዶ አድራሻቸውን ሊጠይቅ ወሰነ፡፡ በእርግጥም ጥሩ ሀሳብ የመጣለት መሆኑ
ተሰማውና ልቡን ደስ አለው።
ማግስቱ እሁድ ስለሆነ የመንግስት መስሪያ ቤት አይከፈትም ዕለቷን ግን በከንቱ ማሳለፍ አልፈለገም፡፡ ወዲያው ትዝ ያለው ያንኑ የተዘጋ የሚሲዮኖች የቀድሞ መስሪያ ቤት መፈለግና በዚያው ዙሪያ የእስቻለውን ዱካ ማነፍነፍ ነበርና ትናንት ወደ ሰራየ መናፈሻ የሄደበትን መንገድ ይዞ ተጓዘ፡፡
ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት አለፍ ብሏል ጠላ የጠጣባትን ቤት ሳይቸግር አገኛት ሴትዮዋ የጠቆሙትን አቅጣጫ በመያዝ ቁልቁል ወደ አስመራ ከተማ ደቡባዊ
ምስራቅ አቅጣጫ ተጓዘ፡፡ በየመንገዱ የሚጠይቃቸው ሰዎች እያመላከቱት ትክክለኛውን አቅጣጫ ይዞ እንዲጓዝ ረዱት
በግምት ከቀኑ አራት ሰዓት አካባቢ ያን ቀድሞ የሚሲዮኖች መስሪያ ቤት አገኘው ዙሪያው በረጅም ግንብ የታጠረ ሰፊ ግቢ ነው፡፡ ቤቱ በርካታ ክፍሎች ያሉት ባለ አንድ ፎቅ ነው፡፡ በሩ ግን የመደበኛ ወታደር መለዮ በለበሰ ሰው ይጠበቃል፡፡ በልሁ ለመጠጋት ፈራ፡፡ በዓይኑ ሰረቅ እያረገ እያየው ፊትለፊት ባለው መንገድ ላይ ሲዘዋወር ከቆየ በኋላ አንድ ብቻውን የሚሄድ
ወጣት ቢጢ አገኘና «የኔ ወንድም!» አለው በአጠገቡ አለፍ ሊል ሲል::
«አቤት»
«ይሄ ቤት ቀደም ሲል ሃኪሞች ይሰሩበት እንደነበር አውቃለሁ፡፡ አሁን ግን በሩ ላይ ወታደር ሳይ ጊዜ ለመግባት ፈራሁ፡፡ ሌላ መስሪያ ቤት ሆኖ ይሆን? ሲል ጠየቀው
«የአንድ የጦር ጄኔራል መኖሪያ ሆኗላ!» አለው ወጣቱ በልሁን አየት እያረገ፡፡
«ከመቼ ጀምሮ?»
«ዓመት ያልፈዋል፡፡»
«ሃኪሞቹ የት ሄደው?» አለ በልሁ
ትናንት ተናድዶ ሳይጠይቅ
የቀረውን ጥያቄ ማንሳት ፈልጎ፡
«አላውቅም፡፡ » ብሎት ወጣቱ ርምጃውን ሊቀጥል ሲል፡፡ «ሰፈርህ እዚሁ ነው የኔ ወንድም?» ሲል ጠየቀው ወጣቱ ሳይሄድበት ፈጠን ብሎ::
«አዎ»
«ይህ ቤት ሃኪም ቤት በነበረበት ወቅት ከሰራተኞቹ መሀል ለየት ያለ
ሰው ታውቅ ነበር?» ሲል ጠየቀው ፈራ ተባ እያለ።
«በምን የሚለይ?»
«አካል ጉዳተኛ የሆነ።»
«ብዙ አካል ጉዳተኞች ነበሩ፡፡ ግን የማናቸውንም ስም አላቅም፡፡
ሲወጡ ሲገባ ብቻ ነበር የማያቸው፡፡ " አለው ወጣቱ አሁንም ርምጃውን ሊቀጥል ዳዳ እያረገው፡፡
«እግሩ ተቆርጦ ሰው ሰራሽ እግር የተተካለት ታውቅ ነበር?» አለው
በልሁ አሁንም'ዠ ፈጠን ፈጠን ባለ አነጋገር
«አዎ፡፡ ስሙን ግን አላውቀውም፡፡»
«ፊቱም ላይ ጠባሳ ነበረው፡፡»
«ያውም እስከ ጆሮው ድረስ » አለው ወጣቱ የበለጠ ገፋ አድርጎ
«የት አካባቢ ይኖር እንደነበር የምታውቀው ነገር ካለ የኔ ወንድም?»
«ብዙ ጊዜ ሰራተኞች በመኪና ስለሚገቡና ስለሚመጡ መኖሪያቸው ራቅ ሳይል አይቀርም፡፡ » ካለ በኋላ ወጣቱ "ግን ለምንድን ነው ይኸን ያህል
የምትመረምረኝ?» ሲል ኮስተር ብሎ በልሁን ጠየቀው፡፡
በልሁ ዛሬም ያቺን የመጀመሪያ ያነጋገራትን የቡና ቤት አስተናጋጅ
አስታወሰ፡፡ ከእሷ ይበልጥ ይኼኛው ወጣት ብዙ እንደታገሰው ተረዳና
«ይቅርታ የኔ ወንድም» ብሎ ጉዳዩን አጠር እድርጎ እስረዳው፡፡
ወጣቱ ርምጃውን ቀጠለ፡፡ በልሁ ግን እዚያው ባለበት አቀርቅሮ
ቆመ ወጣቱ አስቻለውን በዓይን እንደሚያውቀው ተረድቷል ፡፡ ነገር ግን የሰራተኞች በመኪና መግባትና መውጣት ጉዳይ መኖሪያቸው የግድ በዚያ
አካባቢ ላይሆን እንደሚችል አመሰከተው፡፡ በዚያው ልክ በልሁ ተስፋ ቆረጠ፡፡በነገው ዕቅዱ ላይ ብቻ አተኮረ፡፡ ሲያስብበት ውሉ ሲያስብበትም አደረ፡፡.....

👍19❤2
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
....«ይቅርታ የኔ ወንድም» ብሎ ጉዳዩን አጠር እድርጎ እስረዳው፡፡
ወጣቱ ርምጃውን ቀጠለ፡፡ በልሁ ግን እዚያው ባለበት አቀርቅሮ
ቆመ ወጣቱ አስቻለውን በዓይን እንደሚያውቀው ተረድቷል ፡፡ ነገር ግን የሰራተኞች በመኪና መግባትና መውጣት ጉዳይ መኖሪያቸው የግድ በዚያ
አካባቢ ላይሆን እንደሚችል አመሰከተው፡፡ በዚያው ልክ በልሁ ተስፋ ቆረጠ፡፡በነገው ዕቅዱ ላይ ብቻ አተኮረ፡፡ ሲያስብበት ውሉ ሲያስብበትም አደረ፡፡
ሰኞ ዕለት ጠዋት ከረፋፍዶ ከመኝታው ተነሳ፡፡ አለባበሱንም ለየት አደረገው፡፡ ዲላ ውስጥ ለሰርግ ወይም ለየት ባለ ድግስ ካልሆነ በቀር አዘውትሮ
የማይለብሰውን ደብዘዝ ያለ ሰማያዊ ሙሉ ልብስ ለብሶ የጥቁርና የነጭ ቡራቡሬ ክራባት አሰረ፡፡ ጥሩ ቁርስ በላ፡፡ ትናንት ቦታውን አጥንቶት ወደነበረው የክፍለ ሀገሩ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አመራ ከጠዋቱ ሶስት
ሰዓት አካባቢ ከቅጥር ግቢው ውስጥ ገባ፡፡ የአስተዳደር ምክትል ሰራ አስኪያጅ የሚል ጽሁፍ ወዳለበት ቢሮ ልቡ አደላ፣ በፀሐፊዋ በኩል ከመራና በር ላይ ቆሞ
«ጤና ይስጥልኝ» አላት፡፡
«አብሮ ይስጠን» አለችና ፀሃፊዋ ከመቀመጫዋ ብድግ አለች፡፡ አጠር ብላ ወፈር የምትል፡ የቀይ መልከ መልካም የሆነች ዕድሜዋ ወደ አርባ የሚጠጋት ሴት ወይዘሮ ናት፡፡ አጠር ያለ ፀጉሯን ጆንትራ አበጥራለች፡፡
«ሃላፊውን ማነጋገር እችላለሁ?»
«ስለምን ጉዳይ?»
በልሁ የልቡን መዘርዘር አልፈለገም ያን ጉዳይ ካነሳ ይህ አይመለከታቸውም ልትለው እንደምትችል አሰባና «የግል ጉዳይ ነው፡» አላት።
በኋላ፡ የምታዝንለት መስሎት «የመጣሁትም ከሲዳሞ ነው» ሲል ገለጸላት፡፡
ፀሐፊዋ ወንበር እያሳየችው ይቀመጡ» ብላ ወደ አለቃዋ ቢሮ
ገባች፡፡ ብዙ ፡ ሳትቆይ ወዲያው ተመለሰችና "ይግቡ አለችው "
የሃላፊው ቢሮ ለየት ያለ ነው፡፡ መጠነ ሰፊ ወለሉ በአረንጓዴ ቀለም ምንጣፍ የተሸፈነ መስኮቱ በነጭ ስስ እና ቀይ ወፍራም መጋረጃ የተከለለ ከስድስት የማያንሱ ወንበሮች ያሉት ትልቅ የእንግዳ ጠረጴዛ የተንጣለለበት
ግድግዳው ሹሯማ ቀለም የተቀባና ደስ የሚያሰኝ ገፅታ ያለው ነው፡፡
ሃላፊው አቶ ካህሳይ ገብሩም መልካ መልካም ነው፡፡ ድምቅ ብሎ ቀይ ጥቁር ሰማያዊ ሙሉ ልብስ በነጭ ሸሚዝና ጥቁሩ በዛ ያለበት ቡራቡሬ ካራባት ያደረገ፣ አፍንጫው ሰልከክ ዓይኖቹ ጎላ ያሉና ዕድሜው ከአርባ አምስት
ዓመት የማያንሰው ጎልማሳ ነው።
«ጤና ይስጥልኝ አለ በልሁ ወደ ውስጥ ገብቶ ሃላፊውን እጅ እየነሳ
«አብሮ ይስጠን» ብሎ ካህሳይ ከወንበሩ ብድግ ብሎ ተቀበለው፡፡
ስማቸውን በመለዋወጥ እጅ ለእጅ ተጨባበጡና በካህሳይ ግብዣ በልሁ ከእንግዳ መቀበያ ወንበር ላይ ተቀመጠ።
«ምን ልርዳዎት አቶ በልሁ?» ሲል ካህሳይ በልሁን ጠየቀው፡፡
«ችግር ገጥሞኝ ነው አቶ ካህሳይ»
«ምን ዓይነት ችግር?
በልሁ የመጣበትን አገርና ለምን ወደ አስመራ እንደመጣ በአጭሩ
ከአስረዳ በኋላ «ወንድሜ በሚሲዮኖች ክሊኒክ ውስጥ ይሰራ እንደነበር ተጠቁሜ ነበር ።
የሚሰኒዮቹን የስራ ቦታ አጠያይቄ ባገኘውም ነገር ግን ከአንድ ዓመት በፊት ከዛ ቦታ እንደለቀቁ ሰማሁ፡፡ ምናልባት ከሙያ አንጻርና
የምታውቸው ከሆነና አሁን የሚገኙበትን ቦታ ትጠቁሙኝ ከሆነ ብዩ ነበር፡፡» አለና በልሁ ካህሳይን ቀና ብሎ ተመለከተው፡፡
«የት አካባቢ የነበሩት ናቸው?» ሲል ካህሳይ በልሁን ጠየቀው::
«ቀበሌውን በትክክል አላወኩትም፡፡ ነገር ግን አባ ሻውል ከሚባለው ቦታ ወረድ ብሎ በምዕራባዊ የከተማዋ ዳርቻ የሚገኝ ክሊኒክ እንደ ነበር ማወቅ ችያለሁ።
ካህሳይ ሚሲዮኖቹን ያወቃቸው ይመስላል፡፡ አንገቱን ነቅነቅ ነቅነቅ ካደረገ በኋላ «ታዲያ እኮ እነሱ አስመራ ውስጥ አይደሉም ቦታ የቀየሩት ጠቅላላ ከሀገር ተባርረዋል አለውደ
«ተባርረዋል?» ሲል ጠየቀ በልሁ፡፡ ዓይኖቹ ፍጥጥ ብለው
በካህሳይ ላይ ተተከሉ፡፡
«ከዓመት በላይ ሆናቸው»
«በምን ምክንንያት ተባረሩ አቶ ካህሳይ? ምናልባት ወንድሜም አብሮ ተባሮ ይሆን?» ሲል በስጋት ስሜት ውስጥ ሆና ጠየቀው፡፡
ወንድምክ እንኳ ከብሮ ሊባረር የሚችልበት ሁኔታ የለም፡፡ እነሱ የተባረሩት በሀገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገቡ ተብሎ ነው፡፡»
«በፖለቲካ?»
«በመሆኑ ነዋ ለነገሩ እነርሱም አያርፉ ነገሮች ሁሉ እንደራሳቸው
ሀገር እየመሰላቸው የኛ መንግስት አካሄድ ሳይጥማቸው ሲቀር በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ወጋ ማድረግ ይወዳሉ፡፡ አለ ካህሳይ ፈገግ ብሎ የበላሁን ምላሽ እየጠበቀ።
በልሁ ፈጥኖ ለካህሳይ መልስ መስጠት አልፈለገም ወይም አልቻለም ዓይኑን ብቻ ትክል አድርጎ ካህሳይን ያየው ጀመር፡፡ እንዲያውም ቀስ በቀስ ዓይኖቹ በእንባ ይሞሉ ጀመር፡፡
«ምነው አቶ በልሁ?» ሲል ካህሳይ የበልሁ ስሜት መለዋወጥ አስገርሞት ጠየቀው፡፡
በልሁ አሁንም መልስ ከመስጠት ይልቅ ፊቱን በካህሳይ ላይ መልሶ
ወደ ጠረጴዛው በማጎንበስ በእንባ የሞላውን ዓይኑን በመሀረብ ይጠርግ ጀመር፡፡
«አቶ በልሁ» አለ ካህሳይ ይበልጥ እየደነገጠ፡፡
«ሆዴ አዘነ አቶ ካህሳይ!»
«ምነው? ወንድምህ አብሮ የተባረረ መሰሎህ?
«አይደለም አቶ ካህሳይ የዕድሉ ነገር እሳዝኖኝ ነው ፡፡" አለና ንግግሩን በማራዘም «አዩ አቶ ካህሳያ፣ ወንድሜ የጤና ባለሙያ እንጂ ፖለቲከኛ አልነበረም፡፡ ነገር ግን በሄደበት ቦታ ሁሉ የፖለቲካ መዘዝ አልለቀው አለው
አሁንም የዓይኖቹን እንባ እየጠራረገ፡፡
«ማለት?»
«ወንድሜ ገና ልጅ ሳለ የሚረዳው ወንድሙ በፖለቲከኞች ተገደለበት
በችግር ተማረ፡፡ በስንት ስቃይ ትምህርቱን ጨርሶ ስራ ከያዘም በኋላ አሁንም ፖለቲከኞች ሰላም ነስተው ሲያዋከቡት ኖሩ፡፡ የኋላ ኋላም በግፍና በተፀዕኖ ወደዚህ ክፍለ ሀገር በ እናት ሀገር ጥሪ ሽፋን እስገድደው ላኩት፡፡ በእነሱ ጦስ አካሉን አጣ፡፡ እዚሁ ከተማ ውስጥ እየተውትሮ ያርፍባት የነበረችው ሰራዩ መናፈሻ ደግሞ ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ መዘጋቷን ሰማሁ፡፡ እነሆ አሁን ደግሞ
እርስዎም አሰሪዎቹ በፖለቲካ ጉዳይ ከሀገር መባረራቸውን እየነገሩኝ ነው፡፡ ይህ የፖለቲካ ጉዳይ እኔም እንዳላገኘው ምክንያት ሊሆን ነው፡፡ ታዲያ ይሄ
አያሳዝንም እቶ ካህሳይ?» ሲል በልሁ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ለካህሳይ ገለፀለት::
ካህሳይ ገብሩ በሰማው ታሪክ፣ በበልሁ አለቃቀስና የነገሮች አገላለፅ የእሱም ልብ ነካ፡፡ በልሁን ያህል ግርማ ሞገሱ ግጥም ያለ የወጣት ጠንበለል ከፊቱ ቁጭ ብሎ እንባውን እያፈሰሰ ብሶቱን ሲገልጽላት የእሱም አንጀት
ተላወሰ፡፡ ወንድ ልጅ ሲከፋው እንባው ምን ያህል ቅርብ እንደሆነ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሲረዳ ሆዱ ተንቦጫቦጨ በሀዘን ሰሜት ራሱን ደጋግሞ ወዘወዘና በልሁን ትኩር ብሎም ተመለከተው። በልሁ አሁንም ንግግሩን ቀጠለ
«በቃ እኮ አቶ ካህሳይ ከእንግዲህ ወንድሜን ላላገኘው ነው።አለው እንባው በአይኖቹ ላይ ተቋጥሮ ሰማይ እየመሰለ።
ካህሳይ ገብሩ አሁንም ላፍታ ያህል በሀዘን ዓይን ከተመለከተው በኋላ ራሱን ለረጅም ግዜ ወዝውዞ በረጅሙ ተነፈሰና «ለመሆኑ የወንድምህ ስም ማን ይባላል?» ሲል ጠየቀው።

👍9
«አስቻለው ፍስሃ»
«እዚያ አልከኝ ቦታ ላይ ይሰሩ ከነበሩ ሚሲዮኖች ጋር ይሰራ እንደነበረ እርግጠኛ ነህ?
«በቂ የሆኑ አመልካች ምልክቶችን አግንቻለሁ በአመዛኙ እርግጠኛ ሆኛለሁ፡፡»
ካህሳይ ገብሩ በልሁን እየተመለከተ ትንሽ ከቆየ በኋላ ፈጠን ባለ ሁኔታ የስልክ እጀታ አነሳ፡፡ ቁጥሮች፣ አዙር ያዳምጥም ጀመር፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ መናገር ጀመር በስልክ።
«ሄሎ አቶ ሀይለአብ የእነዚያ ባለፈው ዓመት ከሀገር የተባረሩ
የጣሊያን ሚሲዮኖች ፋይል በቅርብ ይገኝልሀል... እስቲ ያቀርቡት በነበረው ዓመታዊ የስራ ሪፖርት ላይ በሰው ሀይል ዝርዝራቸው ውስጥ የስራ ማዕረጉ ነርስ የሆነ አስቻለው ፍስሃ የሚባል ሰው ተመዝግቦ ከሆነ አይተህ ብትነግረኝ...ጎሽ የኔ ወንድም ደውልልኝ እጠብቅሀለሁ።» አለና ስልኩን ዘጋው። ወዲያው ወደ በልሁ ዞር ብሎ ሲመለከት በረጅሙ ሲተነፍስ አየው
«ሰማህ አቶ በልሁ!» ሲል ጀመረ ካህሳይ ገብሩ በሁለት ክንዶች ጠረጴዛ ተደግፎ ፊት ለፊት በልሁን እየተመለኩት፡፡
«አቤት አቶ ካህሳይ»
«ስሜትህ ሁሉ ገብቶኛል፡፡ እሳዝኖኛልም፡፡ ግን
እንድትረዳልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ትቀበለኝ ይሆን?»"
«ምን ይሆን አቶ ካህሳይ?»
«የወንድምህ በፖለቲካ መዘዝ መሰቃየት የዕድሉ ወይም የዕድለ ቢስነቱ ውጤት አይደለም፣ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ብቻ የሚጠብቀው እሳት ነው፡፡ ይህ
ደግሞ ምናልባት ልክ እንዳንተ ወንድም ጠባሳው ጎልቶ አይታይብን እንደሆነ እንጂ እኔም አንተም በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በፖለቲካ እሳት ነደን ነደን እንዳናልቅ ስጋትና ፍራት ያለብን ዜጎች ነን፡፡ » ካለ በኋላ የተቃጠልንና በመቃጠል ላይ የምንገኝ አሳዛኝ ፍጡራን ነን፡፡
እንዲያውም ነደን ነደን እናዳናልቅ መስጋትና መፍራት ያለብን ዜጎች ነን።» ካለ በኋላ
ካህሳይ ምራቁን ዋጥ አድርጎ ለአፍታ ያህል ካሰላሰለ በኋላ ንግግሩን ቀጠለ፡፡
«አየህ እቶ በልሁ! ለዚህ ደግሞ ምክንያቷ ሀገራችን ኢትዮጵያ
አይደለችም፡፡ ምናልባት እኛ ዜጎቿና ይበልጥ ግን ፖለቲከኞቻችን ናቸው
የሀገራችን ፖለቲከኞች የሚመሩበትና የሚያራምዱት የፖለቲካ አስተሳሰብ ከራሳቸው ጥቅም ባለፈ ለሀገርና ለወገናቸው ምንም እንደማይጠቅም ራሳቸው
ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ ይህም ስለሆነ ሕዝባችን ተቀብሎናል
ብለው ስለማያምኑ እንኳንስ የእያንዳንዱ ግሰሰብ ወይም ማህብረሰብ የተቃውሞም ኮሽታ
ዝምታው ራሱ ያስፈራቸዋል፡፡ ኮሽታውን ለማምከን በሃያል ይመቱታል የዝምታውንም
ትኩሳት ለማዳመጥ ሆን ብለው ራሳቸው ይቆሰቁሱታል፡፡በአጠቃላይ ስለሚፈሩ ሕዝባቸውን ማሳረፍ አይፈልጉም፡፡ ለዚህም ሲባል የማይገቡበት የእንቅስቃሴ ዘርፍ የለም ከግለሰብ ህይወት ጀምሮ በዕድሩ በእርሻው በንግዱ በእምነት በሃይማኖት ወዘተ፡፡ ከዚያም ባለፈ የእያንዳንዱን ግለሰብ የየዕለት እንቅስቃሴ ካልተከታተሉ አይሆንላቸውም
ፈሪዎች ናቸውና ማስፈራራት የወገብ ቀበቷቸው ነው በዚህ መሀል ተጎጂው እያንዳንዱ ግለሰብ ነው፡፡ እያንዳንዱ ማህበረሰብ ነው ፡፡ የዚህ ሁሉ ጠቅላላ ድምር ውጤት ደግሞ የመላ የሀገራችን ሕዝብ ጉዳትና ስቃይ ነው፡፡ ካለ በኋላ
ካህሳይ ገብሩ ንግግሩን ጠበቅ በማድረግ ታዲያ በእንዲህ ያለ መከራ ውስጥ ማህበረሰብ ውስጥ የተዘፈቀ ማህበረሰብ ውስጥ የተወለደው የአንተ ወንድም የፖለቲካና
የፖለቲካኞች ሰለባ ቢሆን ምን ያስደንቃል?» ሲል ጠየቀና ወደ ኋላ ወንበሩን ደገፍ በማለት የበልሁን ምላሽ ይጠባበቅ ጀመር፡፡
በልሁ ፍዝዝ ብሎ ካህሳይን እየተመለከቱ በፅሞና ያዳምጥ ነበርና ካህሳይ ንግግሩን ለጊዜው ቆም ሲያደርግ እስካ አሁን አምቆ ይዞት የነበረውን ትንፋሽ«እሁሁ...» በማለት በረጅሙ ተንፍሶ አወጣው፡፡ በካሀሳይ አነጋገር
ተደንቆም ለረጅም ጊዜ ራሱን ወዘወዘ
«ተሳሳትኩ አቶ በልሁ?» ሲል ጠየቀው ካህሳይ የበልሁን አኳኋን ፊት ለፊት እየተመለከተ፡፡ በልሁ ግን ለካህሳይ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ ከመስጠት ይልቅ ሀሳቡ በትክክል የገባው መሆኑን በሚገልጽ አነጋገር
«የመጨረሻው ነግር አያስፈራም አቶ ካህሳይ? ሲል ጠየቀው፡፡
ካህሳይ አሁንም በሁለት ክንዶች ጠረጴዛናውን ተደግፈና «ያስጨንቃል!»
ሲል ቀጠለ፡፡ እንደምታውቀው ሀገሪቱ ዳር እስከዳር በጦርነት እየታመሰች ነው፡፡ ሁሌም እየደማች ነው፡፡ በየቀኑ እየቆሰለች ነው፡፡ ከተፋላሚ ወገኖች
የሚሰማው ሁሉ የጀግንት ወሬ እንጂ የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ወይም የተለየ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፍልስፍና አይደለም፡፡ በተቃውሞ ወገን የተሰለፈው ቡድን አሸንፎ ስልጣን ቢይዝ እንኳ የሀገራችንና የህዝቦቿ ዕጣ
ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል በግልጽ አይታወቅም ፡ ምናልባት ሰዎች በሰዎች ተለውጠው የጭቆና አገዛዙ መልክና ባህሪ ይለወጥ እንደሆነ እንጂ! እንዴት
ብትለኝ ድሉ የጠመንጃ እንጂ የአዲስ ሀሳብና አመለካክት ስለማይሆን፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ከዚህ ጦርነት በኋላ ሌላ ጦርነት ላለመነሳቱ አንዳች ዋስትና ሊኖር
አይችልም፣ ሌላ የተከፋ ቡድን መሽመቁ እይቀርምና፡፡» ካለ በኋላ ካህሳይ ንግግሩን በባሰ እልህና ስሜት ቀጠለ፡፡
ያ ከሆነ የባሰ ችግር ሊያስከትል ይችላል አቶ በልሁ፡፡ አየህ፤ ኣንድ
ጦርነት ወደ ሌላ ጦርነት እየተሸጋገረ የሕዝብ ስቃይና መከራ በተራዘመ ቁጥር
ሕዝብም ከሕዝብ እየተለየና እየተከፋፈለ ይሄዳል፥ በዘር፣ በሃይማኖት፣በቋንቋ፣ በጎሳ…ወዘተ፡፡ ምናልባት ገዢዎች በስልጣን ላይ የመቆያ ዘዴ
ይሆናቸው ዘንድ ይህን የሕዝብ የመከፋፈል አዝማሚያ ለራሳቸው ሲሉ ያበረታቱትም ይሆናል፡፡ በህዝብ መካከል ጠብና ጥላቻ፡ ጥርጣሪና ፍርሀት በማስፈን እነሱ ከሌሉ አደጋ ሊፈጠር እንደሚችል እስመስለው ለማውራት ይችሉ ዘንድ የክፋ ውጥረትን ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ ያም ሆና የተወጠረ ነገር
ውሎ አድሮ መበጠሱ አይቀርምና
የከፋ አደጋ የሚፈጠረውም ያኔ ነው
«ይታይህ! አቶ በልሁ ሁለት የፖለቲካ ቡድኖች ተፋልመው አንዱ ሌላወን አሸንፎ ስልጣን ሲይዝ ቢያንስ እንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ሊሲሰፍን ይችላል
ነገር ግን በዘር፣ በሃይማኖት፣ በጎሳና በቋንቋ ተከፋፍሎ የተፋጠጠ ሕዝብ ባለበት እገር
ድንገት አንድ ቀን የሽብር ፊሽካ የተነፋች እንደሆነ ማነው ያንን እሳት የሚያጠፋው? ማነው ያን የመከራ ሌሊት የሚያነገው? ማን ነው ያን ጨለማ የሚገፈው ? ካለ በኋላ ካህሳይ ፊቱን ላብ ላብ እያለው የአፍንጫው ቀዳዳዎች ሳብ ገተር ያሉና ዓይኑንም ፍጥጥ አድርጎ በልሁን እየተመለከተ በኔ እምነት ፈንድቶ ፈንድቶ የማያልቅ የበቀል ቦንብና መግሎ መግሎ የማይጠግግ የሀገር ቁስል ወርዶ ወርዶ የማይቆም የህዝብ እንባ ያስከትላል ብዬ እፈራለሁ
ኢትዮጵያውያን እርስ በእርሳችን እየተረጋገምን በራሳችን ላይ የምናመጣው ምፅአት!!» አለና ዓይኖቹን በበልሁ ላይ ተከላቸው
በልሁ ተገኔ በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈራ፡፡ በተፈጥሮው ጀግና ነበር በግሉ እንኳን አንድ ሰው አስር ሆነው ቢከቡት ጭራሽ የማይደነግጥ ልበ ሙሉ፣ ቢሰነዝር ከመሬት የሚደባልቅ፣ ቢሰነዘርበት በአስተማማኝ የሚመክት:: ዛሬ ግን ጉዳዩ የሀገርና ሕዝብ ሆነበትና ልቡ ራደ፡፡ መላ
ሰውነቱን የቀውስና የሽብር ሹክሹክታ ተሰራጨበት፡፡ ብቻ በረጅሙ ተነፈሰና በወቅቱም ያቺን መጀመሪያ አስመራ ከተማ የገባ ዕለት ያነጋገራትን የቡና ቤት

👍13
አስተናጋጅ ስሜት አስታውሶ።
«እንዲያውም እኮ ያ ጊዜ የደረሰ መሰለኝ አቶ ካህሳይ?» አለው
በጣም ተቃርቧል፡፡ በመገሰግስ ላይ ነው፡፡ ይቆም ዘንድ መላ
ካልተበጀለት በቀር!! በአጠቃላይ እኛ ዜጎቿ፡ በተለይ በተለይ ገዥዎች ሆድና አደጋው የከፋና አሰቃቂ ነው፡፡ " ያ እደጋ ከተከሰተ ደግሞ የኔ ስጋት ምን እንደሆነ ታውቃለህ?» አለና በልሁን አከታትሉ ተመለከተው፡፡
"እ" አለ በልሁ ካህሳይ ቀጥሎ ለሚናገረው ነገር በጣም እየጓጓ፡:
«ወደፊት የዚች ሀገር ታሪክ ሲጻፍ 'ኢትዮጵያ የምትባል አንድ ሀገር
ነበረች ተብሎ እንዳይጀመር!»
ከዚህ ቀኋላ ቀልሁና ካህሳይ አንዱ የሌላውን ውስጣዊ ስሜት የበለጠ ለመረዳት በመናበብ ላይ ያሉ በሚመስል ሁኔታ እርስ በእርስ በመተያየት ላይ ሳሉ ድንገት ስልክ ጮኸ፡፡ ካህሳይ ስልኩን አነሳና በጆሮው ላይ ለትሞ ሄሎ..
አቶ ሀይለአብ፡ እህ ካምን ደረስክ?... ተገኘ? .... አመሰግናለሁ የኔ ወንድም
ኣለና ስልኩን ዘግቶ ወደ በልሁ እየተመለከተ «በእርግጥም የወንድምህን አድራሻ በትክክል ደርሰህበት ኖሯል፡፡» አለው::
አዎ አቶ ካህሳይ፡ እኔም አልተጠራጠርኩ ነበር፡፡ አለና በልሁ ስለ መፍትሄው ምክር የፈለገ በሚመስል ዓይነት «ታዲያ እንግዲህ ምን ባደርግ የሚሻል ይመስሎታል?» ሲል ካህሳይን ጠየቀው።
«በኔ በኩል አንድ ነገር ላደርግልህ የምችል ይመስለኛል፡፡»
"ምን ይሆን አቶ ካህሳይ?» አለ ባልሁ ቀልቡ ጓጓ እያለ፡፡
«እነዚህ ሚሲዮን የሚባሉ ነገሮች እኛ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ወይም በተለምዶ ኤን ጂ ኦ የምንላቸው ናቸው፡፡ አስራ
አንድ ያህል ድርጅቶች አሁን በአስመራ ከተማ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ብዙ ጊዜ በአንድ ኤንጂኦ ያገለገለ ሰራተኛ ያ ድርጅት ሲፈርስ
ወይም ሲዘጋ አሊያም በሌላ ሁኔታ ስራ ሲያቆም ሰራተኛው ያለውን የስራ ልምድ በመጠቀም ወደ ሌላው ሄዶ የመቅጠር ልምድ አለ፡፡ የአንተም ወንድም ከዚያ ከተባረሩት ሚሲዮናዊ ድርጅት ውስጥ እንደ ወጣ ምናልባት በሌላ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ከሆነ ልክ ዛሬ አቶ ሀይለአብ እንዳደረገው ሁሉ እኔም ከእሱ ጋር
በመተባበር የሌሉቹን ድርጅቶች ሪፖርቶች በመመርመር
የወንድምህ ስም ከተገኘ ውጤቱን በአንድና በሁለት ቀን ውስጥ ልንገልጽልህ እንችላለን» አለው።
«አመሰግናለሁ አቶ ካህሳይ!» አለ በልሁ በአክብሮትና በትህትና እጅ እየነሳ።
«የት ነው ያረፍከው?» ሲል ጠየቀው ካህሳይ፡፡
«ኒያላ ሆቴል ሃያ አራት ቁጥር፡፡»
ጥሩ አቶ በልሁ በተረፈ እግዚኣብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፡፡» ብሎ በልሁን በሰላምታ ለመሸኘት ከወንበሩ ላይ ብድግ አለ፡፡ በልሁም ብድግ አለና ለሁለተኛ ጊዜ የከበረ ምስጋናውን አቅርቦ ተጨባብጠው ተሰነባበቱ፡፡....

👍7👏1
#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
....የቁስቋም ግቢ ግብር አዳራሽም ሥራ በተቀላጠፈ መንገድ ተያያዘ።አዳራሹ ውስጡ ከላይም ከታችም ለምንትዋብና ለኢያሱ መቀመጫ የሚሆን ገባ ያለ ቦታ ተሠራለት። በስተቀኝ በኩል ስድስት፣ በስተግራ
ደግሞ አምስት ማሾ ማስቀመጪያ ሸክላዎች የሚይዙ ድፍን መስኮቶች ተደረጉለት።
ሠራተኛው ከፊሉ ድንጋይ ሲያግዝ፣ ሌላው ዕንጨት ሲያቀርብ፣የቀረው ሲለስን፣ ኖራ ሲቀባ፣ አነዋሪው ተቀምጦ ወይም ቆሞ እየተዟዟረ ሲያነውር፣ የተበላሸውን ሲጠቁም፣ በትክክል ያልተለሰነ ወይንም በትክክል ያልገባ ዕንጨት ወይንም ድንጋይ ሲያይ ሲጠቁም ኢያሱ
ከሠራተኛ ጋር ሲሠራ፣ እናትና ልጅ እርስ በእርስ፣ ከሙያተኞችና
ከሠራተኞች ጋር ሲወያዩ፣ ሐሳብ ሲሰሙና ሲሰጡ ይቆያሉ።
“እስቲ በሉ የተበላሸ ያያችሁትን ተናገሩ” ትላቸዋለች ምንትዋብ፣
ሠራተኞቹን።
“እቴጌ ኸግማርዳ ጥዱ አይሻልም ኑሯል?” ይላታል አንዱ ግንበኛ።
“ግማርዳ ነው እንጂ ለንድህ ያለው” ይላል ሌላው።
“ሁሉም ለመጡበት ጉዳይ ያገልግላሉ” ይላሉ እናትና ልጅ።
ሠራተኞቹ ነገሥታቱ ከእነሱ ጎን ሆነው መሥራታቸው፣ የእነሱን ሐሳብ መስማታቸው አስደነቃቸው። እንደ ሰማይ ከዋክብት ሩቅ የመሰሏቸው፣ ብሎም እንደነሱ ከስጋና ከደም የተሰሩ የማይመስሏቸው የነበሩት ነገሥታት ሰው ሆነው አገኟቸው። በተለይም ደግሞ ኢያሱ ራሱ ሥራው ላይ ተሰማርቶ ከእነሱ እኩል ሲቀባና ሲሠራ አይተው
ተደመሙ።
ወትሮውንም ማንም ፍርድ ፈላጊ ሰተት ብሎ ቤተመንግሥት ገብቶ
እንዲዳኝ ስላደረገ፣ ፍትሕ ለጎደለበት ፍትሕ ስለሰጠና ለድኃ ስለቸረ ይወዱትና ይሳሱለት ነበረና እንደዚህ በቅርብ ከነሱ ጋር ሲሠራ ሲያዩት ይበልጥ ወደዱት።
አንድ ጠዋት ሠራተኞቹ በግብር አዳራሹ አንድ ወገን ላይ እየተሠራ
ስላለው ረጅም የእንቁላል ቅርጽ ያለው ግንብ ድምጻቸውን ዝቅ
አድርገው ያወራሉ። ምንትዋብና ኢያሱ ጎን ለጎን ቆመው የተሠራውን ሥራ ይመለከታሉ።
“አላየህም እንዴ ኸዛ ላይ ሁነህ? ቀሀ እኮ ወለል ብሎ ይታያል” አለ፣
አንዱ ግንበኛ።
“ቀሀ ትላለህ? ጣና ይታይ የለ? ቀሀማ ኸዝሁ ነው።” ከት ብሎ ሳቀ ሌላው።
“ጣና ይታያል ነው ምትሉት?” አለች ምንትዋብ፣ በመገረም።
“አዎ እቴጌ ሲያልቅ ያዩታል። እንዲያው ጣና ወለል ብሎ ነው
ሚታይ” ኣላት፣ አንደኛው ግንበኛ።
“እስቲያልቅ ምን አቆየን፣ አሁን አናየውም?” አላት ኢያሱ።
እናትና ልጅ ፎቁ ላይ ወጡ።
“ውነት ነው ኢያሱ። ያውልህ ... ያ ሚታየው ጣና እኮ ነው። ይኸማ
ለጥበቃ አይሆንም። ለኔ ነው ሚሆን” አለችው።
“ውነትም ወለል ብሎ ይታያል። ቀሀም ይኸው። ውነትሽ ነው።
ላንቺ ይሆናል። ዐጥሩ ተሠርቶ ሲያልቅ ቁስቋም ፊት ለፊት እንደ
ተደረገው የጥበቃ ሰቀላዎቹ ዙርያውን ይሠራሉ።”
ምንትዋብ ደስ አላት። እንዴት እሰተ ዛሬ አላሰብሁትም ብላ
ተገረመች። የተመረጡ እንደ ግራዝማች ኢያሱ፣ ሮብዓምና ሌሎችም እንግዶች መቀበያና ለራሷም መዝናኛ እንደምታደርገው ወሰነች።
አንድ ቀን፣ ምንትዋብ አፄ ፋሲለደስ ቤተመንግሥት ልጇ ኢያሱጋ ለመሄድ፣ በልዩ ልዩ ጌጣ ጌጥ የተሸለመችው በቅሎዋ ላይ ተቀምጣ፣የእሷና የኢያሱ መግቢያና መውጫ ብቻ በሆነው በር ከዐጀቧ ጋር እንደ ሁልጊዜው ባለ ወርቀ ዘቦ ድባብ ተይዞላት ከግቢ ወጣች።
ቤተመንግሥት ስትገባ እንደወትሮው ሁሉም ሰገዱላት። ወደ ኢያሱ መኖሪያ አመራች። ኢያሱ ወጥቶ በደስታ ተቀበላትና ውስጥ ገብተው ጨዋታ ጀመሩ። ኢያሱ ልትነግረው የምትፈልገው ነገር ሲኖር ያውቃል። ምን ልትነግረው፣ ወይንም ምን ልትጠይቀው እንደፈለገች
በጉጉት መጠበቅ ለምዷል።
“ኢያሱ ዛሬ የመጣሁት” አለችው፣ በመጨረሻ። “አንድም አንተን
ለማየት ሌላም ቀደም ብሎ እንደተነጋገርነው ቃሮዳና ዙርያውን
የተተከለው ወይን እንዴት እንዳፈራ ልነግርህ ነው። ትናንት ይዘው
መጡ፤ መቸስ ጉድ ትላለህ። እንዳው ማማሩን ብታይ ጉድ ትላለህ።”
“እንዴት እንደዝኸ ተሎ ደረሰ?”
“ደረሰ። ይገርምሀል። እና አሁን የግብር ቤቱም ሥራ እያለቀ ነው።
ለሊቃውንቱና ለካህናቱ ግብሩን በሰፊው እናርግላቸው።የስተዛሬው እንዳው በቂ ከልነበረም።”
“እናርግላቸው እንጂ አሁንማ። ምን እንጠብቃለን?”
“ወይኑ መጠመቅ እንዲጀምር ትዛዝ ሰጥቻለሁ።”
“መልካም ነው።”
ጥቂት ስለቤተመንግሥት ጉዳይ ከተወያዩ በኋላ ተነስታ ወጣች።
ከወራት በኋላ፣ አንድ ቅዳሜ ዳግማዊ ኢያሱ ማለዳ ላይ ቁስቋም መጣ።ሰማዩ ጥርት ብሏል። ፀሐይዋ ደምቃለች። ምንትዋብ ከቤተመንግሥቷ
በደረጃ ወጥታ ተቀበለችው። እያወሩ ቁልቁል ሲወርዱ ተሰርቶ
ያለቀውን የግብር አዳራሽ አይታ ንግግሯን አቋርጣ፣ “ኢያሱ እይልኝ!ጉድ በልልኝ! እይልኝ እንዴት እንደሚያምር!” አለችው። በደስታ እንደ ልጅ በጨፈረች ደስ ባላት፣ የቤተመንግሥት ሥርዐትና ዕድሜ አልፈቅድ ብለዋት እንጂ።
“ውነትሽ ነው ያምራል! ሁለዜ ስለምናየው እስታሁን እንደዝኸ
እንደዛሬው ማማሩን አላወቅነም እኮ።”
ምንትዋብ ቀልቧ ግንቡ ላይ ነው። አልሰማችውም።
በተጠጋች ቁጥር የግንቡ ግርማ ሞገስ አስደነቃት። የአሠራሩ ጥራት፣የልስኑ ማማርና መርቀቅ፣ የቀለሙ ውበት ከገመተችው በላይ ሆነባት።
ኣጠገቡ ሲቆሙ ስሜቷ አሽነፋትና እንባዋ ዱብ ዱብ አለ።
ከኋላቸው የቆሙት የቤተመንግሥት ባለሟሎች፣ ሠዓሊዎች፣ሮብዓም፣ ካህናትና ሊቃውንት አዳራሹን በአድናቆት ተመለከቱ።
ሁሉም በአንድ ላይ ምንትዋብንና ኢያሱን፣ “እዝጊሃር ያክብራችሁ።
የናንተ ሥራ ነው” እያሉ አመሰገኗቸው።ምንትዋብ መናገር ተስኗት የለም የለም የሁሉም ነው። ሰው ተረባርቦ ነው ይኸን መሳይ ታላቅ ሥራ የሠራው። ሁሉም ይመሰገናል። የሠሩትን
ሁሉ ትናንትም አመስግኛቸዋለሁ። ያለኝን ሁሉ ሰጥቻለሁ። እዝጊሃር
ያክብራቸው አለች፣ ለራሷ። ራሴን ማመስገን አይሁንብኝና ልክ
እንዳልሁት፣ ልክ በሰጠሁት አሳብ መሠረት እኮ ነው የተሠራ አለች።
ባልስን፣ በቀለም ምርጫና በአጠቃላይ ላይ አሻራዋን የጣለችበትን ግንብ እያየች።
በስተቀኝ በኩል ወደ ላይ የወጣውን እንቁላል ግንብ አይታ፣ እሱስ ቢሆን እንዴት አምራል? ኸ'ያሱ ጋር እንደልብ ቁጭ ብሎ ለማውራት ይመቻል አለች፣ በአደባባይ እንደልብ መገናኘት ሰለማይችሉት ስለ
ግራዝማች ኢያሱ አስባ። ኸመላከ ጠሐይ ሮብዓምም ጋር ጥሩ ወግ
መያዝ እችላለሁ ኸዝያ አለች።
ፊቷን ወደ ልጇ መልሳ፣ “ኢያሱ ኸላይ እግንቡ ላይ በግራ በኩል
ያሉትን የመስቀል ቅርጦች አየኻቸው? ቀጥሎ ያለውንስ ዘውድ?”
“ሁሉም ቁልጭ ብለው ይታያሉ። አየሽው ከጎኑ ያለውን በጉን
ሲገድል ሚታየው አንበሳ? ኸጎኑ አንበሳ ላይ የተቀመጠውስ ንጉሥ ያገራችን ምልክት! እንዴት ጥሩ ወጥቷል። ቀጥሎ ያሉት ዝሆንና
አንበሳስ እንዴት እንዳማሩ አየሽ?”
“አዎ ልክ አንተ እንዳልኸው ነው የተሠሩት። የጣድቁ የአባ
ሳሙኤልና የአቡነ ዮሐንስ ምስሎችስ ቢሆኑ እንዴት እንዳማሩ” አለች፣
የዋልድባውን መነኩሴ የአባ ሳሙኤልንና የዐዲሱን አቡን የዮሐንስን ምስል እየተመለከተች።
ራሷን አረጋግታ ዙርያውን ቃኘች። አስቀድማ ያሰበችው ሐሳብ
ሥራ ላይ የሚውልበት ሰዐት
ተቃርቧል።ወደ ኢያሱ ዞረች።
“ኢያሱ ኸዝኸ ኻዳራሹ በስተግራ በኩል ኻሰብሁት በላይ በቂ መሬትአለ። የሴቶች ሙያ ተማሪ ቤት ማሳነጽ ፈልጋለሁ ብዬ ማልነበር? ያውልህ ኸጠሎት ቤቱ ዠርባ ዋርካው አጠገብ ደሞ ሌላ ሰፊ መሬት።እሱም ቢሆን እንዳሰብሁት...”
“ምን አስበሽለት ነበር ለቦታው?”

👍15
“እንዴ ኸዝኸ በፊት እኒህን የጃንሆይን ሆነ የሌላ ነጋሢ ዘሮች..የኔንም ዘመዶች ጭምር
ሚይዝ ማደሪያና ተማሪ ቤት ማሠራት ፈልጋለሁ ብየህ ማልነበር?”
“ርግጥ ነው ብለሽኛል። አንቺ እናቴ እንዳልሽው ይሁን። የተባረከ
አሳብ ነው።”
የተባረክኸውስ አንተ። ያባቶችህ በረከት አይለይህ።”
ተመልሰው እሷ ቤተመንግሥት ውስጥ ወደተዘጋጀው ምሳ ሄዱ።
በነጋታው እሑድ ምንትዋብ ግንቡን ማስመረቂያ ትልቅ ግብር አግብታለች። ምግቡ በዓይነት፣ በቅርብ በቅርብ የተጠመቀው
ወይን ጠጅ፣ አረቄና ጠጅ በገፍ ተዘጋጅቷል። ከቅዳሴ በኋላ መኳንንት፣ወይዛዝርት፤ ከየደብሩና ከየገዳማቱ የመጡ ካህናት፣ ሊቃውንት፣ሠዓሊዎች፣ ባለክራርና ባለመሰንቆዎች ከቅዳሴ በኋላ ግብር ሊታደሙ እንደየደረጃቸው በተመደበላቸው በር በኩል ገብተዋል።
ምንትዋብ በዕውቀት ለበለፀጉት፣ በሰዋሰው፣ በሕግና በታሪክ
ዕውቀታቸው ለተደነቁት ሊቃውንት ታላቅ አድናቆትና ክብር ስላላት
ከእሷ ሳይርቁ እንዲቀመጡ አድርጋለች። በየዓይነቱ ምግብና ጥሬ ስጋ ቀረበ። ጠጅ፣ አረቄና ወይን ጠጅ ታች ካሉት ማቀዝቀዣ ክፍሎች እየተቀዳ፣ እላይ ለተቀመጡ እንግዶች በላይ በር፣ እታች ለተቀመጡት ደግሞ በታች በር ገባላቸው።
ምንትዋብና ብርሃን ሰገድ ኢያሱ በወርቅ የተለበጡ ወንበሮች ላይ
ተቀምጠው ቅኔ ከወይን ጠጅ ጋር ሲያወራርዱ ካህናቱና ሊቃውንቱ
ለእሷ ውበት፣ ብልሐት፣ ለዕውቀት ፈላጊነትና ለጨዋታዋ ቅኔ ሲቀኙ፣
ሲናጠቁና ሲዛረፉ አገር መግዛት ምነው እንዲህ በሆነ አሰኛት።
ኢያሱንም ለቁመናው፣ ለለጋስነቱ፡ ለአስተዋይነቱና ለብሩህ አእምሮው ውዳሴና ሙገሳ አዘነቡለት።
ምንትዋብና ኢያሱ እንደፈለጉት ይህ ዓይነቱ ግብር የዘወትር የእሑድ ተግባር ሆነ። በሌላ በኩል ግን በካህናቱ ዘንድ፣ “እቴጌ እኛን አይወዱም፤ለሊቃውንቱ ያደላሉ” የሚል ቅሬታ ተፀንሶ አደገ።
ምንትዋብ፣ ሐሜቱ ሲበዛባት አንድ እሑድ ግብር እንዳበቃ፣
ለካህናቱ ያላትን አክብሮት ከገለጸች በኋላ፣ “እኔ...” አለቻቸው። “እኔ ለሊቃውንቱ ባደላ እነሱ ሊቆች፣ ያነን ሁሉ መጻሕፍት የጻፉ ናቸው ብየ ነው። እናንተ ኸነሱ የተካከለ ችሎታ አላችሁን? እስቲ ልፈትናችሁ”ብላቸው ወደ ውጭ ይዛቸው ወጣች። ፈተናው ምን እንደሆነ ያላወቁት ካህናትና ሊቃውንት በጉጉት ውጭውን ቃኙ።
ቀደም ብላ ያስቆፈረችው ጉድጓድ ውስጥ ቅል እንዲጨመር ትዕዛዝ
አስተላለፈች። ምን አስባ እንደሆነ ያልገባቸው ካህናትና ሊቃውንት
በአንክሮ ተመለከቱ፣ እርስ በርስ ተያዩ። በመጨረሻም ምንትዋብ ወደ ካህናቱ ዞራ፣ “በሉ እስቲ ይኸን ቅል ሳትሰብሩ ኸጉድጓዱ አውጡ አለቻቸው።
ከካህናቱ መሃል ዘዴኛ የተባሉት በየተራ ቀረቡ። አንዴ በእጃቸው
ደግሞም በመቋሚያቸው ቅሉን ለማውጣት ታገሉ። የጉድጓዱ ጥበት ቅሉን ሳይሰብሩ እንዲያወጡ አላስችል አላቸው።
ምንትዋብ ሊቃውንቱን ደግሞ ቅሉን ሳይሰብሩ እንዲያወጡ
ጠየቀቻቸው። ምን ጊዜም ቢሆን ዕውቀታቸው፣ ሚዛናዊነታቸውና
አስተዋይነታቸው የሚያስደንቃት፣ ልክ እንደ መልአከ ፀሐይ ሮብዓም
ከእሳቸውም ጋር ተቀምጣ ማውራት የሚያስደስታት የቅኔ ሊቅ የሆኑት መምህር አእምሮ ወደ ፊት ቀረብ ብለው፣ “እስቲ ውሃ አምጡልኝ አሉ።
ውሃው ሲመጣላቸው ተቀብለው
ጉድጓዱ ውስጥ ጨመሩት።
ቅሉ ተንሳፈፈ። በቀላሉ አወጡት። ሁሉ በብልሐታቸው ተገረመ።
ምንትዋብ ወደ ካህናቱ ፊቷን መልሳ፣ “አያችሁ ለምን ለነሱ የላቀ ቦታ እንደምሰጥ?” አለቻቸው።
ተሳስቀው ወደ አዳራሹ ተመለሱ።
የተዋሕዶ ካህናት ግን “እቴጌ ቅባት ናቸው” የሚለው ስጋት ውስጣቸው በመኖሩ፣ በተለይም ደግሞ የደብረብርሃን ሥላሤ ተዋሕዶዎችና የቁስቋም
ቅባቶች እርስ በርስ በመናቆራቸው፣ ካህናቱ በጥርጣሬ መተያየታቸው
አልቀረም። ምንትዋብ ምንም እንኳ ሁለቱን ለማስማማት ጥረት
ብታደርግም፣ ቅባት የቤተመንግሥቱ ዋነኛ እምነት በመሆኑ የተዋሕዶ ካህናት በተለይ በጉዳዩ ከእሷ ጋር መከራከራቸውን አልተዉም።
አንድ ቀን እንደዚሁ ሲከራከሩ አንደኛው ካህን፣ “እቴጌ ንጉሥ
የደገፈው ማዶለም እንዴ ያገሪቱ ሃይማኖት ሚሆነው? የጃንሆይ
አንድም በነበሩት በአጤ ተክለሃይማኖት ግዝየ ለምሳሌ ክርክር ተደርጎ ቅባት ቢያሽንፍ ንጉሡ ስንት የአዘዞን ተዋሕዶ መነኮሳት አስፈጁ” አሉ፣ ታስፈጀናለች የሚል ስጋት ባይኖራቸውም ቅባትነቷን ለማስታወስ ያህል።
“በሣልሳዊ ዳዊት ግዝየስ የሞተው?” አሉ፣ ሌላው።
“አይ እሳቸው እኮ በሰው ተታለው ነው” ሌላው አከሉ።
“ዘፋኝ ዳዊት! ዘፈን አለቅጥ ወደዱ። በገና ይጫወቱ ማልነበር? የንጉሥ ወጉ ማዶለም” አሉ፣ ሌላው ካህን።
ምትዋብ ተቆጣች፣ “ዘፈን የወደዱ እንደሆነስ? ማንን ጎዱ? ምነው
አጤ ዳዊት የሠሩትን በጎ በጎውንም ብታወሩ? ኸባላገር ሚገባውን ግብርና ኸሌላ ሚመጣውን እጅ መንሻ አልነካም ብለው ብራና እየደጎሱ
ማልነበር ሚተደደሩ? ልክ አያታቸው ጣድቁ ዮሐንስም እንደዝሁ ኸባላገር ሚመጣ ግብር አልበላም ብለው ሰሌን እየሠሩ በሚያገኙት ነበር ሚተዳደሩ።
እ... እንደ አጤ ዳዊትስ ለድኻ ማን ሰጠ? ተዉ እንጂ ምስጋና ማንን ገደለ? ክፉ ክፉውን ብቻ ማውራት ምን ዋጋ አለው? አጤ ዮሐንስስ በደግነታቸውና በሃይማኖተኝነታቸው የታወቁ
ስለነበሩ፣
የደጉ ዮሐንስ የዕውቀት ቃል ቢነሳ፤
ባህር ዘሎ ገባ የተጠበሰ ዓሳ።
ተብሎ ቢዘፈንላቸው ሴትየይቱ፣
ልጆቸ አልቀውብኝ ትንሹ ትልቁ፤
የልጆቼን ማለቅ ንጉሥ ቢጠይቁ፤
ኸሞቱ በኋላ ልጆቸ ኻለቁ፣
ያስነሱልኝ ነበር ዮሐንስ ጣድቁ።
ብላ አልገጠመችም? ጣድቁ ዮሐንስ ኸርህሩህነታቸው የተነሳ
ሰው ሲያጠፋ ቤተክሲያን ገብቶ ኸደወለ ይማራል፣ የቆሰለች አህያ
እንዳትጫንና ዶሮም ተዘቅዝቃ እንዳትያዝ ሚለውን ደንብ ሁሉ
ያቆሙ እሳቸው ማልነበሩ?”
እንደዚህ ስትቆጣ ስለሚፈሩ ሁሉም በዝምታ ተያዩ። እሷም ብትሆን የሃይማኖት ልዩነት እንዴት በቀላሉ ወደ ፓለቲካ ልዩነት ሊቀየርና የመንግሥትን መረጋጋት እንዴት ሊያደፈርስ እንደሚችል፣ ካህናቱ ሆኑ ሊቃውንቱ የተጠናከሩ መሆናቸውን፣ አንዱን ነጋሢ ዘር፣ “ክርስቶስ በተዋሕዶ ከበረ አስብልልን እናነግሥኻለን” ወይንም፣ “ክርስቶስ በቅባት
ከበረ አስብልልን እናነግሥኻለን” እያሉ፣ ብዙ ውዝግብ እንዳስከተሉና አሁንም ያን ከማድረግ እንደማይመለሱ የምታውቀው ምንትዋብ
አንዳንዴም እየተቆጣች፣ ሌላ ጊዜ እየተቸች በአመዛኙ ግን ጉልትና
መሬት፣ ይበልጡንም ደግሞ የእሷ ቅባትነት ለሚያሰጋቸው የተዋሕዶ
ካህናት በገፍ እየሰጠች፣ በፍቅርና በዘዴ ይዛቸዋለች።
መኳንንቱንም ቢሆን ሊያነሳሱና ሊከፋፍሉ ስለሚችሉ፣ ጉዳዩ በተነሳ ቁጥር “ሁሉም እንደ ሃይማኖቱ ይሁን” በማለት የመጡበትን አቅጣጫ
በብልሓት ትቀይስባቸዋለች።
ቢያንስ ልዩነታቸውን ለራሳቸው ይዘው አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ
እንዳይገቡ በማድረግ፣ ሌላው ቀርቶ የእሷን ቅባት ተከታይነት
ተቀብለው መኖር እንዲችሉ በዘዴ ይዛ የሃይማኖት ሰላም አወረደች። እነሱም ቢሆኑ ቃሏ ልስልስ፣ አንደበቷ ርቱዕ፣ ጨዋታ ወዳድና ደጓሚያቸው በመሆኗ በቀላሉ ተረቱ
በመቋሚያ የሚፈላለጉት ሊቃውንትና ካህናት ምንም እንኳን በቅኔ ቢወራረፉም መቻቻልን ተምረው አንድ ማዕድ ተቋደሱ። እሷም ብዙ ጊዜ ከእነሱ ጋር ስለምታጠፋ፣ ስለብዙ ጉዳዮች አብራቸው ስለምትወያይ፣
ስለምታከብራቸውና ስለምታደንቃቸው ወደዷት፣ በእሷና በልጇ መንግሥት ላይ ሊነሱ የሚችሉበት ምክንያት አጡ።

👍18❤1