አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ሲዳሞ ሲመለስ በተነሳበት ወቅት በአስመራ ከተማ ለጥቂት ቀናት ቆይቶ ነበር:: በእነዚያ ቀናት ውስጥ አንድ ቀደም ብሎ
ከሚያውቀው የአስመራ ነዋሪ ከሆነ ሰው ጋር 'ሳራዬ መናፈሻ ተብላ በምትታወቅ ቡና ቤት ቀጠሮ ይይዛል በቀጠሮ ቀን የሀምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ ከቀጠሮው ቦታ ቀድሞ ይደርሳል። ጓዳኛውን ለመጠበቅ እዚያው ቡና ቤት ውስጥ ብቻውን ይቀመጣል።
እሱ በተቀመጠበት ጠረጴዛ ማዶ ብቻውን የተቀመጠ ሰው ከዓይኑ ይገባል፡፡ያ ስው የአካል ጉዳተኛ ነው፡፡ የግራ እግሩ ተቆርጦ ሰው ሰራሽ እግር ተተክቶለታል። ቀኝ እጁም እንዲሁ ከአምባር መዋያው በታች ተቆርጦ በፕላስቲክ
ጣቶች የተተካ ነው፡፡ ከአጠገቡ ደግሞ ክራንች ግድግዳ ተደግፎ ቆሟል፡፡ የሰውዬው ግራ ፊት በእሳት የተለበለበ ይመስላል። ግራ ዓይነም የጠፋች ያህል ሆናለች፡፡ ግራ ጆሮው በጉዳት ምክንያት የተለጠፈች ስጋ እንጂ በእርግጥ ጆሮ አትመስልም፡፡
በዚሁ ላይ ውስጡም ሰላም ያለው አይመስልም፡፡ የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ አትኩሮ ሲመለከተው ያ ሰው ያሚያስቦ የሚተክዝ ይመስለዋል። ፊቱ ቶሎ ቶሎ ይለዋወጣል፡፡ ብቻውን እንደሚያወራ ሁሉ ከንፈሮቹን ያነቃንቃል።
የሀምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ ያን ሰወዬ አከታትሎ እያየው ሳለ ያ
የቀጠረው ሰው ድንገት ይመጣል፡፡ ያ አካል ጉዳተኛ ከበሩ ፊትለፊት ተቀምጦ ነበርና የሀምሣ አለቃው ጓደኛ ቡና ቤቱ ውስጥ እንደገባ በቀጥታ ወደ ጉዳተኛው
ሰው በመሄድ ሰላም ይለዋል፡፡ ትንሽ ከተጠያየቁ በኋላ አዲስ መጪው ሰውየ ወደ ሀምሣ አለቃው ይመለሳል። እነሱም ሰላምታ ተለዋውጠው አብረው ቁጭ ይላሉ፡፡
መጠጥ አዝዘው መጠጣት ይጀምራሉ፡፡ በመሀል ሀምሣ አለቃው ስለዚያ አካል
ጉዳተኛ ሰው ጓደኛውን ይጠይቀዋል፡፡
«ያ ሰውየ ምን ሆኖ ነው? ከአካሉ መጎዳት በተጨማሪ ውስጡም ሰላም ያለው አይመስልም፡፡» ሲል ጓደኛውን ይጠይቀዋል፡፡
«እንደውም እኮ የአገርህ ሰው ነው፡፡»
የሲዳሞ?»
«አዎ፣ እንዳተው ለዘመቻ ተልኮ ነው የመጣው፡፡ በሙያው ሀኪም ነው። ጉዳት የደረሰበት ደግሞ በፈንጂ ነው፣ በአንድ ወቅት ያውም አስመራ ገብቶ ወር
እንኳ ሳይሞላው በተንቀሳቃሽ ክሊኒክ ወደ አንድ የጦር ግንባር ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቹ ጋር ሲሄድ፡፡»
«ማን ይባላል?
«ነርስ አስቻለው ፍስህ ይባላል።»
የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ ከንፈሩን መጠጠና «ላነጋግረው ይሆን?»
«በእናትህ እስቲ አነጋግረው፡፡»
የሆሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ አላመነታም ብድግ ብሉ ወደ አስቻለው ሄደ፡፡ እጁን ለሰላምታ እየዘረጋ የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ እባላለሁ፡
«አስቻለው ፍስሃ » በማለት አስቻለውም ጨበጠው። የሃምሣ አለቃው ከአስቻለው አጠገብ ቁጭ እያለ
“ይቅርታ እስቻለው! የሀገሬ ልጅ መሆንህን ሰምቼ ላነጋግርህ ፈልጌ ነው፡፡» አለው
«የት አገር»
«የሲዳሞ ልጅ እያደለህም?»
አስቻለው ትንሽ ፈገግ ብሎ መሬት መሬት ካየ በኋላ፡ «በእርግጥ ሲዳማ ውስጥ እልወለድም:: ነገር ግን ወደዚህ የመጣሁት ለሥራ ከሄድኩበት ከዲላ ሆስፒታል ነው» ካለ በኋላ የሃምሳ አለቃውን ቀና ብሎ እያየ«አንተ ሲዳሞ የት
ላይ ነህ?» ሲል ጠየቀው::
«ውልደቴም ዕድገቴም በሀገረ ማሪያም ከተማ ነው፡፡»
«እእእ» አለና አስቻለው «በእርግጥም ዲላና ሀገረ ማርያም ቅርብ ለቅርብ
ናቸው::» እለው።
“ወዲህ ከመጣህ ቆየህ?» ሲል የሀ'ምሳ አለቃ ጠየቀው፡፡
«አዎ፡ ቆየት አልኩ፡፡»
«በግዳጅ እንደ መጣህ! ሰማሁ፡፡ አልጨረስክም?»
«አሁንም በግዳጅ ላይ ነኝ፡፡»
«መቼ ነው የምትጨርስ?»
«ዕድሜ ልክ ሳይሆንብኝ አይቀርም»
የሀምሣ አለቃው በአስቻለው መልስ ተጠራጠረና እየቀለደ ስለመስለው ፈገግ እያለ «እንዴ..ት?» ሲል ጠየቀው፡ ወዲያው ደግሞ አንድ አስተናጋጅ ጠራና ቀድሞ ከነበረበት ጠረጴዛ ላይ የጀመረውን የቢራ ጠርሙስ እንዲያመጣለት አዘዘው::
«ምነው ጓደኛህን ትተህ?» አለው ከስቻለው ቀና ብሎ እያየው፡፡»
«ከሀገሬ ልጅ ጋር መጫወት ፈልኩ»:: አለና የሀምሳ አለቃ እስቲ ምናምኘሰ ውሰድ። ከነገ ወዲያ ወደ ሀገሬ ልመለስ ነውና የወጪ ልበልህ፡፡» ሲል ጋበዘው፡፡
«ይኸው ጠጣሁእኮ»! አለ አስቻለው ቀደም ሲል አጠገቡ የነበረ የለስላሳ ጠርሙስ እያሳየው፡፡
«ሌላ ነገር፡»
«ምንም እልጠጣም»
«ቢራ ጠጣ፡፡»
«አልኮል ጭራሽ አልጠጣም:: ሻይ ቡናም ቀደም ብዬ ጠጥቻለሁ አመሰግናለሁ::» አለ አስቻለው በማከታተል፡፡
የሀምሣ አለቃው ወደ ጨዋታው ተመለሰ። ወደ ሲዳሞ የመመለስ ዕቅድ የለህም?» ሲል ጠየቀው፡፡
«የለኝም»
«ለምን?»
«በቃ ስላልፈለኩ ብቻ ነው»
«እስከ መጨረሻው?»
በዚህ ጊዜ እስቻለው ፊቱን ወደ ጣሪያ መለስና ዓይኑን በኮርኒስ ላይ ሰካ ፍዝዝ ትክዝ አለ፡፡ ደስ የማይል ስሜት በፊቱ ላይ መነበብ ጀመረ፡፡ በዚያው ልክ የሃምሣ አለቃውም በአስቻለው ሆድ ውስጥ የተቀበረ አንድ ነገር እንዳለ ገባውና፡
«ችግር አለ እንዴ የኔ ወንድም?» ሲል ትኩር ብሎ እያየ ጠየቀው።
አስቻለው ድንገት ወደ ቀልቡ እንደመመለስ አለና «አይ አይ ችግር የለም። ወደ ሲዳሞ በስተርጅና ዕድሜዬ ብቅ ማለት አስባለሁ፡፡» ካለ በኋላ ወደ ሃምሳ አለቃው ቀና በማለት ፈገግ እያለ
«ግን ደግሞ ከሀገሬ በፊትእኔ ቀድሜ ካረጀሁ » አለው
«አልገባኝም::»
«የሀገር እርጅና፡፡»
አስቻለው ወደ መሬት አቀረቀረና ራሱን ወዘወዘ አውቆም ይሁን ሳያውቅ ከንፈሩን ነከሰ።....

💫ይቀጥላል💫
👍4😢1
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስድስት ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ....ምንትዋብ ከተንሴ ማሞ ጋር በተደረገው ውጊያ በእሱ ሆነ በእሷ በኩል ያለቀው ሰው ብዛት በአእምሮዋ እየተመላለሰ እያደር ሰላም ነሳት። ሰላም በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ይበልጥ እንድትገነዘብ አደረጋት። ሰላምን በሃገሯ ውስጥ ለማረጋገጥ የበለጠ ጠንክራ መስራትና የልጇን መንግሥት ማደላደል እንዳለባት…»
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


...የዛን ዕለት ጠዋት ኢያሱ ቤተመንግሥት እጅ ሊነሳ
ሲገባ ይኽ ሰው እንዲኽ መልከ መልካም ኑራል እንዴ? ያለችው ትዝ አላት።ምናልባትም እኮ እዝጊሃር ሊያመላክተኝ የፈለገው ነገር ይኖራል። ኸለዛ ኸሰው መኻል ስለምን እሱን በእልሜ ያመጣዋል? ነው አለወትሮየ
በእልሜ የመጣው? እያለች፣ አወጣች አወረደች። ተመልሳ ለመተኛት ሞከረች። እንቅልፍ አልወስድ ብሏት ስትገላበጥ ቆየች። ነገሩን የበለጠ
አሰበችበት፤ ከነከናት። እረ ስለምነው እንደዝኸ ለእልም መጨነቄ!ለዳግም ስለዝኸ ጉዳይ ማሰብ የለብኝም እያለች ስታሰላስል ነጋ።

ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢያሱን ከሐሳቧ ማውጣት አቃታት። ጭንቅላቷ
ከእሱ ሌላ ማሰብ ተሳነው። ይኸ ሰው እኮ የጃንሆይ እት ልዥ ነው።
እንዴት ሁኖ ነው ኸሱ ጋር ሰውስ ምን ይላል? ይቅርብኝ ይኸ ነገር፡
አግባብ ማዶል። የጃንሆይ አጥንት ይወቅሰኛል። ለስሜም ለልዥም
ክብር ተገቢ ማዶል። ልዝም ቢሆን ሲያድግ ያባቴ ክብር ተነካ
ብሎ መቀየሙ አይቀርም፡፡ አምላኬ ምነው እንደዝኸ ያለ መፈታተኛ ሰጠኸኝ? እያለች አምላኳን ሞገተች።

የራሷን ፍላጎትና የሰዉን አመለካከት ስታወዳድር፣ ስታመዛዝን፣ስትጨነቅ፣ ልቧ ሲማስን ወራት አለፉ። ኢያሱ፣ መጥቶ እንደወትሯቸው
እንዳይጫወቱ ምክንያት እየሰጠች ከቤተመንግሥት እንዲርቅ አደረገችው። ውስጧ ለሚንቀለቀለውም ስሜት ልጓም ልታበጅለት ፈለገች። ኅሊናዋ አንዴ ሲከሳት፣ ሌላ ጊዜ ሲፈርድባት፣ አንቺ የቁስቋሟ፡
ይኸን ነገር ኸልቤ አውጭልኝ እያለች ማርያምን ተማፀነች።

ልቧ ግን ወደ እሱ አዘነበለ። የፍቅርን ዕርከን እያዘገመ ወጣ። እንደ እምቡጥ ጽጌሬዳ ራሱ የፈነዳና የአበበ ንፁህ ፍቅር በውስጡ ሰረፀ። በሠራ አካላቷ ተበተነ፣ ዐዲስ ሕይወት በመላ ሰውነቷ ውስጥ አንሰራራ፣
የጎደለው ልቧ ሞላ።
ኢያሱም ቢሆን አጎቱ ከሞቱ በኋላ፣ ቤተመንግሥት አዘውትሮ
መምጣቱ አለነገሩ እንዳልሆነ ገባት። የእሱም ልብ መዋለሉን ተረዳች።ከሰው መሀል ዝምታው ሲያነጋግራት፣ ዐይኖቿ የፍቅር ግብር ሲልኩ፣ገፅታው ጥያቄዎቿን ሲመልስላት ልቧ ከልቡ እንደተጣመረ አወቀች።
ኅሊናዋ መሞገቱን ተወ። ጭራሽ ገፋፋት፤ አሻፈረኝ፣ ባህልና ሥርዐት አያግደኝ በይ አላት።

የወደደ የተሸሽገን አያጣውም እንዲሉ፣ ኢያሱን ለብቻው እልፍኟ
ማስጠራት ጀመረች። ሲመጣ፣ እንደ ማንኛውም ሰው ማውራትና
መጫወት ትፈልጋለች። ዘውዷን አውርዳ፣ ካባዋን ወርውራ፣ እቴጌ
ሳትሆን ሰው ሆና ትጠብቀዋለች።
መስተዋት ፊት ስትቆም፣ ዕድሜ አካሏ ላይ ያመጣውን ለውጥ
ለመፈተሽ ወደ መስተዋቱ ስትጠጋ፣ ያቺ ቋራን ስትለቅ ዐዲስ የፈነዳ አበባ የመሰለችው ወጣት ዛሬ ዕድሜ ሰውነቷን ሞልቶ፣ አካሏንና አእምሮዋን አዳብሮ በውበት ላይ ውበት አክሎላት ገና የደረሰ ፍሬ መምሰሏ አልታወቅ ይላታል። ግንባሯን ፈታ፣ ጨምደድ አድርጋ፣ ወደ መስተዋቱ ጠጋ፣ ራቅ ስትል ያሉትም የሌሉትም መስመሮች ይታይዋታል። እህል በልቶ የሚያውቅ የማይመስለውን ወገቧን ወደ ጎን፣ ወደ ፊትና ወደ ኋላ እያለች ትመለከትና ያች የቋራዋ ጉብል ኣልመስል ትላታለች፡፡

ያን ሰዐት ግዝየ ሌባ ነው ትላለች።

ኢያሱን ለብቻው ማግኘት ስትጀምር፣ ወሬው ከቤተመንግሥት ባለሟሎች ሹክሹክታ አልፎ መሣፍንቱ፣ መኳንንቱ፣ ካህናቱ፣ ሊቃውንቱና
ወይዛዝርቱ መሃል፣ ብሎም ሕዝቡጋ ደረሰ፤ “እቴጌ ኸባላቸው እት ልዥ ጋር ወዳጅነት ያዙ” እየተባለ ተናፈሰ።
ምንትዋብ ግን ወሬውን ከቁብም አልቆጠረችው።
ጭራሹን ከኢያሱ ጋር በድብቅ ተጋቡ። ጐንደሬዎች “ምልምል
የሚል ቅጽል ስም... የተመረጠው ለማለት... አወጡለት። ምንትዋብ
ምልምል እንዳይሉት ግራዝማች አለችው። ግራዝማች ኢያሱ የሰጣትን ዐዲስ የተገኘ ነፃነት ወደደችው። በልጅነቷ ቤተመንግሥት ገብታ ሕይወቷ በወግ ታጥሮ ቆይቶ አሁን እንደ ተራ ሰው መወደድ እናት መወደድ መቻሏ ለሕይወቷ ትልቅ ትርጉም ሰጠው።

አንድ ቀን ግን ይህንን ትርጉም የሚገዳደር፣ ነፃነቷን የሚያውክ ነገር ተፈጠረ። ጠዋት ላይ እልፍኟ ተቀምጣ በሐሳብ ዥው ብላለች፤ ከፊሉን ጊዜ ስለ ኢያሱ፣ ከፊሉን ጊዜ ደግሞ ስለ ግብር አዳራሽ ግንባታ ታስባለች።

ዋና የእልፍኝ አስከልካዩ አርከኤድስ ለጥ ብሎ እጅ ነሳና፣ “አንድ መነኩሴ ኸነማይ መልክት ይዤ መጥቻለሁ ብለው በር ላይ ናቸው።
የውጭ በር ላይ አላስገባ ብለዋቸው መመላለሳቸውን ብሰማ፣ ግቢ እንዲገቡ አርጌ አነጋገርኳቸው። 'ስመላለስ ከረምሁ፣ ብዙም ተጉላላሁ።
አገሬ መመለሻ ግዝየ በመጉላላት አለፈ። ለእቴጌ በእጅ ስጥ ተብየ
ይዤ የመጣሁትን መልክት እንዴት አድርጌ ይዤ መለሳለሁ እያልሁ
ኸዝሁ ከረምሁ እያሉ ቢጨነቁ ይጠብቁ ብያቸው መጣሁ” አላት።
“ኸነማይ?” አለች፣ ምንትዋብ ተገርማ። ከነማይ ማን መልዕክት
ሊልክላት እንዲሚችል መገመት አቅቷት።
“አዎ... ዘመድ ልኮኝ ነው አሉ። የተጠቀለለ ነገር ይዘዋል። “ለእቴጌ በጃቸው በቀር ለሌላ እንዳትሰጥ ብለው አስምለውኝ ነው ያመጣሁት ይላሉ።”
የማናቸው መነኩሴ? እያለች ትንሽ ካሰበች በኋላ፣ “ይግቡ!" አለችው።
አዛዥ አርከሌድስ እጅ ነስቶ ወጣ። ጥቂት ቆይቶ በእሱ መሪነት
ቆብ የደፉ፣ ረጅምና ሰፊ ቀሚስ ያጠለቁ፣ ሽማግሌ ሰው ገብተው
መሬት ሊስሙ ሲያጎነብሱ፣ “ግድ የለም አባቴ ይቀመጡ” አለቻቸው፣ ምንትዋብ።
ፈንጠር ብለው ወንበር ላይ ተቀመጡ።

“አባቴ ኸየት መጡ? ደሞስ ማን ልኮዎት ነው የመጡ?” አለቻቸው። መነኩሴው ከተቀመጡበት ተነሥተው ለጥ ብለው እጅ ነሱ። “እቴጌ ዝናዎን ስሰማ ቆይቸ ዛሬ እርሶን ለማየት ያበቃችኝ ኪዳነ ምረት
ምስጋና ይግባት። እቴጌ ኸነማይ ነው የመጣሁ። ደፈጫ ኪዳነ ምረት ስለት ነበረኝና እሱን ላደርስ መኸዴ ነው ብየ ስነሳ አንድ ኸኛ ዘንድ ሚመላለሱ ሰው፣ '
እኼን ለእቴጌ እንደምንም ብለው አድርሱልኝ። ዐደራ በእጅ ይስጡልኝ። ዘመድ ነኝ ቢሉኝ አመንኳቸው።”
“ሰውየው ማን ይባለሉ?”
“እቴጌ ዕቃውን ሲያዩ ማን እንደሆንሁ ያቃሉ ብለውኛል” ብለው ጥቅሉን አሳዩ።
ምንትዋብ፣ አርከሌድስን፣ “ተቀበልና ፍታው” አለችው።
“እቴጌ ኸርሶ በቀር ለሌላ አትስጥ ተብያለሁ” አሉ፣ መነኩሴው፣
ብድግ ብለው።
“ይቀመጡ... ይስጡትና እኔ ፈታዋለሁ።”
ጥቅሉን ለአርከሌድስ ሲሰጡት ተቀብላ ስትፈታው ዐራት ማዕዘን
እንጨት ላይ የተሣለ የራሷ ምስል ነው። ነጠላ ተከናንባ ወፍታ ጊዮርጊስ ደጀሰላም ላይ ነው። መብረቅ የመታት ያህል ክው ብላ ቀረች።
መነኩሴው የፊቷን መለዋወጥ አይተው ደነገጡ። ከተቀመጡበት
ተነሱ። “እቴጌ... ክፉ ነገር ኑሯል?” ሲሉ ጠየቋት።
የለ፣ ደግ ነው። ብቻ ያልጠበቅሁት ነገር ሁኖብኝ ነው። የላክሁ
ሰውየ ስማቸው ማነው ነበር ያሉኝ?”.
ስማቸውን ስንኳ አላወቅሁም። እኔ ብዙ ግዝየን ኸሰው ስለማልገናኝ
ስለሰዎች እምብዛም አላውቅም። 'እነማይ ለጉዳይ መጠቼ፣ ጐንደር“
ይኸዳሉ ሲሉ ብሰማ ተላኩኝ ብየ ነው። ለእቴጌም ዘመድ ነኝ። የእቴጌ አያቶች እኮ ትውልዳቸው ኸዝሁ ኸኛው ዘንድ ነው ቢሉኝ ምን ከፋኝ ብየ ይዤ መጣሁ።”

“ወደ እነማይ በቅርቡ ይመለሳሉ?”

“ለርሶ መልክቴን ካደረስሁ እንግዲህ ነገ እነሳለሁ።”

“እንግዲያማ ደሕና ግቡ። ለላኩዎም ሰው ባክዎን ወደ ጐንደር ብቅ ይበሉ። እንደርሶ ያለ ሠዓሊ ፈልጋለሁ ይበሉልኝ” አለቻቸው።
👍8
ወደ አርከሌድስ ዞራ ለመነኩሴውአስፈላጊው
እንዲደረግላቸው ነግራው አሰናበተቻቸው። እነሱ ከሄዱ በኋላ፣ ሥዕሉን ደግማ ደጋግማ አየችው። ሥዕሉን የላከላት ሰው ማን ሊሆን እንደሚችል
መገመት አቃታት። ለቀናት፣ ለሳምንታትና ለወራት በነገሩ ስትጨነቅ፣ ስታወጣና ስታወርድ ቆየች። መልስ ልታገኝለት ግን አልቻለችም።
ሆኖም እያደር ነገሩ ከነከናት። የመልዕክቱ ትርጉም አልገባ አላት። ሕይወቷ የተለየ መልክ ሲይዝ፣ ትርጉም እያገኘ ሲመጣ እንደዚህ ያለ ነገር መከሠቱ ገረማት፣ ተንኮል ይሆን ብላ አወጣች አወረደች። ግና
የምን ተንኮል? ስለምንስ? በኔና በኢያሱ መኻል የመጣ ነው? ግና
እንዴት ያለ ሠዓሊ ነው? እኼን ዓይነቱን ሠዓሊማ ፈልጌ አስፈልጌ
ነው ማስመጣት ያለብኝ፡፡ ቤተክሲያን ላሰራ ፈልግ የለ? ያን ግዝየ ይጠቅመኛል እያለች ለወራት አወጣች አወረደች።..

ይቀጥላል
👍4
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሰባት ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ...የዛን ዕለት ጠዋት ኢያሱ ቤተመንግሥት እጅ ሊነሳ ሲገባ ይኽ ሰው እንዲኽ መልከ መልካም ኑራል እንዴ? ያለችው ትዝ አላት።ምናልባትም እኮ እዝጊሃር ሊያመላክተኝ የፈለገው ነገር ይኖራል። ኸለዛ ኸሰው መኻል ስለምን እሱን በእልሜ ያመጣዋል? ነው አለወትሮየ በእልሜ የመጣው? እያለች፣ አወጣች አወረደች። ተመልሳ ለመተኛት ሞከረች።…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_ሦስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....ወደ ሲዳሞ በስተርጅና ዕድሜዬ ብቅ ማለት አስባለሁ፡፡» ካለ በኋላ ወደ ሃምሳ አለቃው ቀና በማለት ፈገግ እያለ
«ግን ደግሞ ከሀገሬ በፊትእኔ ቀድሜ ካረጀሁ » አለው
«አልገባኝም::»
«የሀገር እርጅና፡፡»
አስቻለው ወደ መሬት አቀረቀረና ራሱን ወዘወዘ አውቆም ይሁን ሳያውቅ ከንፈሩን ነከሰ፡፡ ስሮቹ በግንባሩ ላይ ተገተሩ። ፊቱ ተከፋ፡፡
«አስረዳኛ የኔ ወንድም አለው»
የሃምሳ አለቃ ክንዶቹን አቆላልፎ
ጠረጴዛውን በመደገፍ አስቻለውን እየተመለከተ።
«ሀገር በገዳዮቿ መዳፍ ወስጥ እስከ ገባኝ ድረስ ምናልባት እንደ ሰው አትቀበር እንደሆነ እንጂ ማርጀት ቀርቶ ልትሞትም ትችላለች» አለ አስቻለው ፊቱ ክፍት እያለውና ጣሪያ ጣሪያ እያየ፡፡
«ስትል?» ሲል ጠየቀው የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ፡ የአስቻለው አነጋገር ሚስጥሩ ለጊዜው ባይገባውም ግን ደግሞ በውስጡ ብዙ ነገር ስለመሆኑ ከወዲሁ ገምቷል።
«አየህ ሃምሳ አለቃ!» ሲል ቀጠለ እስቻለው፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥ ያሉ የህዝብና መንግስት ከተኮራረፈ ምድርና ሰማያዋም ይቀያየማሉ። ያኔ ከዜጎቿ ልብ
ውስጥ ተስፋ ይጠፋል፡፡ ተስፋ የሌለበው ሕዝብ ጭካኔ ይወልዳል።በተለይ ደሃ ከጨከነ
ጠላት የሚያደርገው የገዛ ሀገሩን ነው፡፡ አምባገነኖች የቱንም ያክል
ጡንቻቸው ቢፈረጥም ድሀን ማስተዳደርና መቆጣጠር አይችሉም፡፡ እንዲያውም
በቁጣው እነሱንም ያጠፋቸዋል፡፡ ያኔ ገዢና ተጎዢ አይኖርምና 'ጥፋት ይነግሳል::በዚህ ጊዜ ሀገር መታመም ትጀምራለች። ታዲያ ይህ ከሆነ ሀገር አልሞተችም፣?
የሃምሣ አለቃ ሲል ጠየቀው።
የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ ባላሰበውና አስቦትም በማያውቅ የተለየ እሳቤ ወስጥ ገባ፡፡ አንዳች አስፈሪ ስሜት ውስጥ ገባ። አንዳች አስፈሪ ስሜት መጣበት እስከዛሬም እንደ ሰው ስለመኖሩ ተጠራጠረ። ፍርሀትና ጭንቀትም አደረበት። በረጅሙ ተነፈሰና
«አስደነገጥከኝ አስቻለው» አለው፡፡
«ሊያስፈራም ሊያስደነግጥም ይችላል ሃምሣ አለቃ። በአሁኑ ሠዓት ሀገራችን ታማለች። ህመም ደግሞ በቶሉ ያስረጃል፡፡ ከሐገሬ በፊት እኔ ካረጀሁ ያልኩህም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ አለና አስቻለው የሃምሳ አለቃን ትኩር ብሎ
ተመለከተው።
«ይህ ገባኝ አስቻለው አለና የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ እንቆቅልሽ የሆነብኝ ግን ለምን ከዚያ ወዲህ ወደ ዲላ ላለመሄድ እንደነሰንክ ነው፡፡ ምናልባት
ይህም ምስጢር ይኖረው?» ሲል ፈራ ተባ እያለ ጠየቀው።
«ምስጢር የለውም፡፡ እኔ ግን መሄድ አልፈልግም::»
«አይመስለኝም አስቻለው፣ ይህ ውሳኔህ ምስጢር ሳይኖረው አይቀርም፡፡አይዞህ ምስጢር ቢኖረውም በበኩሌ እጠብቅልሃለሁና ንገረኝ፡፡» አለው።
«ወታደር አይደለህ! ለምስጢርማ ማን ብሎህ» አለና አስቻለው ፈገግ አለ፡፡
«ሙያዬ ስለሆነ ሳይሆን ባአንተ በመታመን።»
አስቻለው ጭንቅ አለው። የሃምሳ አለቃው ጥያቄ ከልቧ የመነጨ መሆኑ ይገባዋል ግን ደግሞ የሆዱን ምስጢር ለማንም ላለመናገር ወስኗል የሃምሳ አለቃው ልመና ግን መንፈሱን ወጥሮ ያዘው።ወደ ጣርያ ወደ መሬት ጎንበስ ቀና ካለ በኋላ
በቅድምያ በረጅሙ ተነፈሰ።
የሀምሳ አለቃውንም አየት ሲያደርገው በፊቱ ላይ የጭንቅ ስሜት አነበበበት። መጨነቁም ስለ እሱ መሆኑ ገባው። ከዚያ በኋላ ፍንጭ ሊሰጠው ፈለገ።
«አየህ ሃምሳ አለቃ! እኔ በአሁኑ ሰዓት ወደ ዲላ ብሄድ ያለ ጊዜዋ
የምትረግፍ አበባ አለች፡፡» አለና እንባው ከዓይኑ ላይ ዝርግፍ አለ፡፡
«እንዴት»
«አበባ የምልህ በእርግጥ ተክል አደለችም። ሔዋን ተስፋዬ የምትባል የሰው ልጅ ናት:: የምወዳት የምትወደኝ፣ የምሳሳላት የምትሳሳልኝን የመጀመርያ ፍቅረኛዩና እጮኛዬ ነበረች፡ ልንጋባ ሁለት ወር ሲቀረን ነበር እኔ ድንገት ወደዚህ ወደ አስመራ የመጣሁት።አሁን ግን ይህው እንደምታየኝ ግማሽ አካሌ ከጥቅም ውጭ ሆኗል ያለ ጊዜዋ ትረግፋለች የምልህም ያቺ አበባ እንዲህ ሁኜ ብታየኝ
የሚፈጠርባት፣ የስሜት ስቃይ ስለማውቅ ነው፡፡ እንደኔ እግሯ ባይቆረጥ እንኔ ፊቷ ባይጠበስ! እንደኔ ጆሮዋ ባይበላሽ፣ እንደኔ ዓይኗ ባይጠፋ እኔን በዚህ ሁኔታ
ካየች ግን በንዴት በቁጭት በብስጭትና በፀፀት የአእምሮ ህመምተኛ ትሆንብኛለች ብዬ እሰጋለሁ። ታዲያ ይህን እያወኩ ሄጄ የዚያችን አበባ ህይወት ላበላሸው ሃምሳ አለቃ?» አለውና በጉንጩ ላይ ይንቆረቆር የነበረ እንባውን በእጁ መዳፍ ሙሉ ሙዥቅ አድርጎ ጠረገው።
«አታልቅስ የኔ ወንድም!» አለው ሃምሣ አለቃ እሱም ዓይኑ በእንባ
እየሞላ።
«እኔማ ገና ብዙ ብዙ አለቅሳለሁ ሀምሳ አስቃ! እኔ ዕድለ ቢሱ ያቺን እድለ ቢስ አድርጊያት ቀርቻለሁ:: ስለ ሔዋን ተስፋዩ ገና ብዙ አለቅሳለሁ::በህይወት እስካለሁ ልረሳት አልችልምና ሳለቅስ እኖራለሁ፡፡» አለና አስቻለው
አሁንም እህህህህ …! በማለት መላ ሰውነቱ እስኪንቀጠቀጥ ድረስ በለቅሶ ሲቃ ተርገፈገፈ።
“ምናልባት ትጠየፈኛለች ብለህ ሰግተህ ይሆን የኔ ወንድም?» ሲል ሃምሣ አሐቃ የራሱንም አይን እየጠረገ ጠየቀው።
«ፍጹም ሀምሳ አለቃ! የኔዋ ሔዋን መልኳ አበባ እንደሚመስል ሁሉ
ትጠየፈኛለች ብዬ አይደለም፡፡ የኔዋ ሔዋን እንዲህ ያለ ተፈጥሮ የላትም። በራሴ በኩል ግን ከእንግዲህ እኔ ለእሷ አልገባም ብዬ ወስኛለሁ።» አለ እያለቀሰ።
“ታዲያ እሷ እየጠበቀችህ ቢሆንስ?»
«ተስፋ እንድትቆርጥ ብዩ የበኩሌን አንድ ርምጃ ወስጃለሁ። የምትኖረው በኔ ደመወዝ ስለነበር እንዲቋረጥባት ብዬ የመንግስት ስራ ለቅቄ በአንድ የፈረንጆች
ግብረ ሰናይ ድርጅት ክሊኒክ ውስጥ በአስተርጓሚነት ተቀጥሬአለሁ::»
«ምናልባት ርሀብ ላያሽንፋት ቢችልስ?»
«ይህ እኔንም ያሰጋኛል። ግን ልጅ ናትና ከመቆየት ሀሳቧን ብትቀይር
እያልኩ እጓጓለሁ:: በዚያ ላይ ደግሞ ገና እኔ እዚያው እያለሁ ሊድሯትና ሊያገቧትም እያሰቡ የሚያንዣብበ ሰዎች ነበሩና በእነሱ ጫና ተሸንፋ አዲስ
ህይወት ብትጀምር እያልኩም እፀልያለሁ::»
የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ የአስቻለውን ምኞትና ሃሳብ ሲሰማ ቆይቶ ወደ ዲላ ላለመሄድ የወሰኑበት ምክንያት ሲገባው በራሱ ውስጥ ያለው የመንፈስ ቁስል አመመውና ለአስቻለው ይገልፅለት ዘንድ ስሜቱ ገፋፋው።
«ስማ እስቻለው፡፡» አለው ፍዝዝ ትክዝ ብሎ እየተመለከተው እኔም እንዳተው ተገድጄ ወደዚህ ሀሄገር የመጣሁ ነኝ መጥቼ የፈፀምኩት ነገር ቢኖር ሰው መግደል ነው።እላዬ ላይ የምታየው የሃምሣ አለቅነት መአረግ የተሰጠኝም ሰው በመግደሌ ነው። የገደልኩት ደሞ የሀገሬን ልጆች ወንድሞቼን ነው ሶስት አራት ገድዬ ከሆነ በዛው መጠን በርካታ ዘመድ አዝማዶቻቸውን አስለቅሻለሁ አሳዝኛለሁ በዚህ ስራዬ ደግም ተሸልሜበታለሁ። ታድያ እኔ ይሄን ያህል የህሊና እዳ ተሸክሜ ወደ ሃገሬ ልገባ ስቸኩል አንተ ልታክም መተህ ራስክ ከቆሰልክ ልትረዳ
መጥተህ ራስህ በተጎዳህ ልትጠግን መጥተህ ራስክ ከተሰበርክ ምን የህሊና የፀፀት አለብህና ምን የሚያሳፍር ነገር ሰርተሃልና ከዚህ አይነት አሳዛኝ ውሳኔ ላይ ልትደርስ ቻልክ?» ሲል ጠየቀው።
«ሀሳብህን አደንቃለሁ ሃምሳ አለቃ!» ሲል ጀመረ አስቻለው «ልዩነቱ ግን አንተ የገደልካቸው ኢትዮጵያውያን ሞተው አርፈዋል። ቤተሰቦቻቸውም እርማቸውን አውተው ተገላግለዋል።ፀፀቴ ያለው በአንተ ልብ ብቻ ነው።
👍10
ምናልባት ራስህን ይፈጅህ እንደሆነ እንጂ የሞቱትና ያዘኑት ግን ሁሉንም ተወጥተውታል
የኔ መሄድ ግን ወዳጆቼን እንደ እሳት ያቃጥላቸዋል፡፡ ቅድም
እንዳልኩህ በተለይ የኔዋ አበባ ትረግፍብኛለች፡፡ የህይወትን ጣዕም ታጣብኛለች።
የልጅነት ህይወቷ የስቃይና የመከራ ይሆንብኛል። እሷ ከእንግዲህ እኔን አግብታ የዚያ የቆራጣው፣ የዛያ የእውሩ፣ የዛያ የደንቆሮ ሚስት እየተባለች
እንድትኖር አልፈልግም፡፡ ሞቷል ብላ እንድትረሳኝ ብቻ ነው የምፈልግ ይህን መስዋትነት ልከፍልላት ይገባል። እወዳታለሁ እና ስቃይዋን አልፈልግም
አፈቅራታለሁና የህይወቷን መበላሸት አልሻም።» አለና አስቻለው አሁንም እንባውን በጉንጩ ላይ አንቆረቆረ።
የሀ'ምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ያአስቻለውን አኳኋን እየተመለከተ የእሱም ዓይን ያነባ ጀመር። አንድ ነገር ትዝ አለውና አስቻለውን ደግሞ ጠየቀው።
«ለመሆኑ ከልጅቷ ሌላ ዲላ ውስጥ የሚኖር ዘመድ የለክም?»
«ከእህትም ወድምም የሚበልጡ ጓደኞች ነበሩኝ ናፍቆትና ትዝታቸው
እድሜ ልክ የማይረሳ። አዎ እነሱን ሳስባቸውና ሳስታውሳቸ እኖራለሁ»
«ታዲያ ከእነሱ ዕድሜ ልክ ተለያይተህ መኖሩ አይቆጭህም?»
«ይበልጥ የሚያንገበግበኝ ግን ቀድሞ ነገር ከእነሱም ከሔዋንም ተለይቼ ወደዚህ ቦታ መምጣቴ ነው፡፡ ወዲህ እንድመጣ የተደረኩት በተንኰልና በደባ ነው።
ተናንቄአቸው ቢሆን! ምነው አሻፈረኝ ብዬ ቃታ ስበውብኝ ምነው አስረው በገረፉኝ ወይ ከስራ ተባርሬ እንደ ሌላው ወገኔ በርሃብ ሞቼ ቢሆን እያልኩ ሳስብ
ነው የሚቆጨኝ፡፡ ላይቀርልኝ ነገር
ስሸሽ መሞቴ ነው የሚያቃጥለኝ የአሁኑ ውሳኔማ የራሴ ስለሆነ ለምን ይቆጨኛል?የሁሉንም ናፍቆት፤ የሁሉንም ትዝታ
እችለዋለሁ። ገፍቶ ቢመጣብኝ ሀዘንና ለቅሶ ነው። እያዘንኩና እያለቀስኩ እኖራለሁ።
እነሱን ግን መልካም እንዲገጥማቸው እመኛለሁ፡፡» አለና ዓይኑን በመዳፉ አበስ አደረገ

«በእርጅና ዘመንህስ ጊዜ ለመሄድ ለምን አሰብክ?»
«ምናልባት ለኔዋ ሔዋን የማስበውና የምመኘው ሁሉ ተሳክቶላት ማየት የቻልኩ እንደሆነ ብዬ፡፡ በእርግጥም እኩያዋን አግብታ! ልጃች ወልዳ ለወግ ማእረግ አድርሳ ባገኛት የእሷን ከንፈር እንደሳምኩት ሁሉ የልጆቿን ጉንጮች ስሜአቸው ብሞት አጥንቴ በሰላም ሚተኛ አፋሩም የሚቀለኝ ይመስለኛል።»
የሀምሳ አስቀ መኮንን ዳርጌ የአስቻለው የፍቅር ፅናት! መልካም ምኞትና አርቆ አስተዋይነቱ እጅጉን ገርሞት ትክ ብሎ ሲመለከተው ድንገት ከቡና ቤቱ አንድ ሙዚቃ ተለቀቀ፡፡

ጊዜው ይርዘም እንጂ ማየት አይሻለሁ!
ጊዜው ይርዘም እንጂ ማየት አይሻለሁ፣
ሞት ካለየኝ በቀር በህይወት እያለሁ!
ሞት ካለየኝ በቀር በህይወት እያለሁ፡፡
አስቻለውና የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ እርስ በእርስ ተያዩ። ነገሩ አጋጣሚ እንደሆነ ሁለቱም ገብቷቸዋል፡፡ ግን ደገሞ ረዘም ላለ ጊዜ እንባ እንዲራጩ አደረጋቸው።
የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ዛሬ በዲላ ፖሊስ ጣቢያ ወስጥ ሔዋንን ከፊቱ አስቀምጦ በሀሳብ ወደ አስመራ በመኮብለል ይዞ የተመለሰው የትዝታ ጓዝ ይህን
ነበር፡፡ ደግነቱ ትዝታ የእውናዊ ክንውን ያህል ጊዜ አይወስድምና በትንሽ ደቂቃዎች ውስጥ ይሄን ሁሉ ቆይቶ ያነቃወም የራሱ ለቅሶ ነው፡፡ ድንገት «ህእ»የሚሰኝ የለቅሶ ትንታ ተናነቀው፡፡ እንባውም በጉንጮቹቿ ዧ ብሎ ወረዴ። ስሜቱን ከሔዋን ለመደበቅ አሰበና ወድያው ቀልጠፍ ብሎ።
«ምን እንዳስለቀስኝ ታውያለሽ?» አላት።
«ኧረ አላወኩም፡፡» አላችው ሔዋን እንባ ባቀረሩ ዓይኖቿ እየችው
«ልክ እንደ አንቺ ከፍቅረኛዬ ተለይቼ ስለምኖር እሷ ትዝ ብላኝ ነው፡፡» አላት እንባውን በመሀረብ እየጠራረገ፡፡ ሔዋን ለምን እትሄድላትም ልትለው ነበር፡፡
ግን ፈራችና ወደ መሬት አቀርቅራ እሷም ኣስቻለውን አስታወሳ ታለቅስ ጀመር።
«ለመሆን አሁን እንደት እየኖርሽ ነው?›› ሲል ጠየቃት ሀምሳ አለቃ።የዓለሙንና የመበራቱን ነገር እርግፍ አድርጎ ተወና ከአስቻለው ምኞትና ተስፋ አኳያ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች ለማወቅ ጓጓ፡፡
«ቀድሞ የአስቻለሁ ሰራተኛ፣ ዛሬ ደግሞ ለኔ ጓደኛ ከሆነች ትርፈ በጋሻው እምትባል ልጅ ጋር ቤት ተከራይተን አብረን እየኖርን ነው፡፡»
የሃምሳ አለቃ ያኔ አስቻለው ሞቷል ብላ ተስፋ እንድትቆርጥና ደሞዝ
ስታጣ ሌላ አማራጭ እንድትፈልግ ብዬ የመንግስት ስራ ለቅቄያለሁ ያለውን አስታውሶ «በምን ትተዳደራላችሁ?» ሲል ጠየቃት።
«በልሁ ተገኔ የሚባል የአስቻለው ጓደኛ እኔን በአውራጃው ግብርና ጽህፈት ቤት ውስጥ በተላላኪነት አስቀጥሮኛል፡፡ ለትርፌ ደግሞ መንቀሳቀሻ ወረት ሰጥቷት
ሻይና ዳቦ እየሸጠች እየተረዳዳን አብረን እንኖራለን፡፡»
«በዚህ ሁኔታ ለምን ያህል ጊዜ ቆያችሁ?»
«ሁለት ወር ይሆነናል፡፡ ትርፌ እሰው ቤት ተቀጥራ ትሰራ ነበር። እኔ ደግሞ ከእህቴ ጋር እኖር ነበር። ግን አህቴ ጋር ሳንስማማ ቀረን በልሁ ትርፌን ከሰው አውጥቶ አብረን እንድንኖር አደረገን።
«ባል ለማግባት አልሞከርሽም?»
«አስቻለውን ትቼ?» አለችው ዓይኖቿን በአይኖቹ ላይ ስክት አድርጋ።
«ምናልባት ባይመጣስ»
«ባይመጣም አላገባም'፡፡»
«ጭራሽ»
«ዕድሜ ልኬን፡፡»
ሀምሳ አለቃ አሁንም እንባው በዓይኑ ሞላ፡፡ የአሰሰቻለው ተስፋና ምኞት የመረብን ወንዝ አልተሻገረም በኤርትራ ሰማይ ላይ ተንሳፎ ቀርቷል። ሃምሳ አለቃ
እንባውን ጠርጎ ምራቄን ዋጥ አደረገና «ለመሆኑ በልሁ የሚባል የአስቻለው ጓደኛ እዚ ከታሰርሽ ወዲህ ጠይቆሻል?»ሲል ጠየቃት።
«አልሰማም መሰል እስካሁን አልመጣም»
ሃምሳ አለቃ መኮንን ከዚህ በኋላ ጊዜ ማጥፋት አልፈለገም ረዳቱን በደውል ጠራና ሔዋንን ወደ እስር ቤት አስወሰደ ረዴቱን እንደገና ጠራና ቀጭን ትዕዛዝ ሰጠው፡፡ «ይቺን ልጅ ሊጠይት በልሁ ተገኔ የሚባል ሰው ሲመጣ ከልጅቱ
ጋር ከመገናኘቱ በፊት ወደኔ አምጣልኝ፡፡" አለው፡፡...

💫ይቀጥላል💫
👍12
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_አራት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...እንደ ሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ከትዝታ ጋር የተቀላቀለ አይሁን እንጂ መርዕድ እሽቴም በደረቅ ጭንቀት ተወጥሮ ነው ያረፈደው የጀመረው ደግሞ ጠዋት ሁለት ሰዓት በፊት፡፡ መኖሪያው በዜሮ ሁለት ቀበሌ የታችኛው ጥግ ሲሆን የሚያስተምረው ደግሞ የዲላ ከተማ የላይኛው ጫፍ
በሆነ ቀበሌውስጥ በማገኘው
የአፄ ዳዊት ትምህርት ቤት ውስጥ ነው። ሔዋንና ትርፊ የተከራዬት መንገዱ ላይ በመሆኑ ሲወጣም ሲወርድም ጎራ እያለ ይጠይቃቸው ነበር፡፡ ዛሬ ጠዋት ግን ወደ ሥራው ሲሄድ ያ ቤት በጠዋት ከውጭ ተዘግቶ አየው ወዴት እንደሄዱ የጎረቤት ስዎችን ሲጠይቅ ማታ ሲሆንና ሲባል ያመሸው ሁሉ ሁሉ የዝርዝር ተነገረው።
በሰማው ወሬ የተሰማው ድንጋጤ ጭራሽ ራስ ምታት ለቀቀበት። ዛሬ
ቢቸግረው ወደ በልሁ ቢሮ ሮጠ፡፡ ነገር ግን ዘንግቶ ነበር እንጂ በልሁ
ለመስክ ስራ ወጥቷል መስሪያ ቤት ደርሶ ይኸው ሲነግረው ያለ ውጤት ተመለሰ።
እንደገና ወደ ታፈሠ ቤት ላሮጥ አሰበ፡፡ ግን ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ክፍለ ጊዜ አስተምሮ ሌሎቹን ክፍለ ጊዜያት ነፃ እንደሆነ አስታወሰና በአንድ ፊት ስራውን
አጠናቆ ለመሄድ ወስኖ እየተጨነቀም ቢሆን ወደ ትምህርት ቤት አመራ፡
ልክ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ሥራውን ጨርሶ ወደ ታፈሡ ቤት
በመገስገስ ላይ ሳለ አስፋልቱን አቋርጦ ሊያልፍ ሲል ከይርጋ ጨፌ አቅጣጫ ትመጣ የነበረች ቶዮታ መኪና ደጋግማ ክላክስ ስታደርግ ሰማ። ዞር ብሎ ሲመለከት የበልሁ የመስክ መኪና ናት:: በክላክስ ያስጠራውም ራሱ በልሁ ኖሯል፡፡ በአለበት ላይ ቆሞ መኪናዋን ጠበቀ።
«ዛሬ ስራ የለም እንዴ?» ሲል ጠየቀው በልሁ አጠገቡ ሲደርስ አንገቱን በመስኮት አውጥቶ መርዕድን እየተመለከተ፡፡
«እስቲ ና ውረድ!» አለ መርዕድ ፊቱ በድንጋጤ ጭምትርትር እንዳለ።በልሁም የመርዕድ ሁኔታ ገና ሲያየው እስደንግጦታል። «ምነው? ምን ሆነካል?
«ችግር አለ፡፡»
በልሁ ከመኪናዋ ላይ ዱብ ብሎ ወደ መርዕድ በመጠጋት ምንድን ነው ችግሩ? ሲል ጠየቀው።
«ሔዋን ታስራለች!»
«ምን አድርጋ?»
መርዕድ ከሰው የሰማውን በሙሉ ነገረው::
«ያምሀል እንዴ አንተ ሰው?»
«የነገሩኝን ነው እኔ የምነግርህ?»
“ከታሰረች ጠይቀሃታል?»
« አሁን ወዚያው እየሄድኩ ነበር፡፡»
ለነበሩበት ቦታ ፖሊስ ጣቢያው ቅርብ ነው፡፡ በልሁ ሾፈሩን ወደ ቤቱ እንዲሄድ አሰናበተውና ከመርዕድ ጋር ወደ ፖሊስ ጣቢያው ገሰገሱ፡፡ እርምጃቸው
ፈጣን ስለነበር ከአምስት ደቂቃ በላይ አልወሰደባቸውም።
ትርፌ ገና በጠዋት ለሔዋን ቁርስ ይዛ እንደሄደች አልተመለሰችም ኖሯል፡እንዲያውም በእስረኞች ግቢ እንድትገባ ተፈቅዶላት ኖሮ ፊት ለፊት ሔዋን ጋር አብረው ተቀምጠው በልሁና መርዕድን ከሩቅ ሲያዩአቸው ተንጫጬ «በልሁ! መርዕድ! በልሁ! መርዕድ!» በማለት።
በልሁና መርዕድ ጣቢያው በር ላይ እንደ ደረሱ አንድ ፖሊስ ጠጋ
አላቸውና ««ከእናንተ ወስጥ በልሁ ተገኒ የሚባል ማነው?» ሲል ጠየቃቸው፡፡
«እኔ!» አለው በልሁ በሌባ ጣቱ ወደ ራሱ እያመለከተ፡፡
«ሃምሳ አለቃ ይፈልጉሃል።»
«በሰላም?»
«አላወቅሁም አለና ፖሊስ ወደ እነ ሔዋን ዞር ብሎ አየት አደረገና ፊቱን ወደ በልሁ በመመለስ ከልጅቷ ጋር ሳይገናኝ ወደኔ አምጡት ነው ያሉት» አለው።
«ቢሮው የት ነው?» አለ በልሁ ቁና ቁና እየተነፈሰ፡፡
«ተከተለኝ! አለና ፖሊስ በልሁን ከፊት ከፊት እየመራ ወስዶ ካሃምሳ አለቃው ቢሮ አስገባው፡፡
የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ጆሮግንዶቹን በእጆቹ ይዞ
ጠረጴዛው ላይ በማቀርተር ሀሳብ ውስጥ ገብቶ ሳለ ፖሊስ በልሁን ይዞ በመድረስ «አቶ በልሁ
እኒህ ናቸው አለው፡፡ ሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ለካ በልሁን ከተማ ውስጥ በዓይን ያወቀው ኖሯል:: እንዲያውም በአለባበስ፣ በተክለ ሰውነቱና አጠቃላይ አቋሙ
ያደንቀው የነበረ ሰው ሆኖ ሲያገኘው ‹‹በልሁ ተገኒ ማለት አንተ ኖረሀል እንዴ?
እያለ ብድግ ብሎ ጨበጠው::
«አዎ ነኝ» አለ በልሁ ቁና ቁና እየተነፈሰ፡፡
«ቁጭ በል እስቲ! ሁለቱም ፊት ለፊት ተቀመጡና ተፋጠጡ፡፡
«የተበሳጨህ ትመስላለህ!» አለው የሃምሣ አለቃ፡፡
«አዎ እጅግ በጣም ተናድጃለሁ፡፡
«ምነው?»
«የማትታሰር ሰው አስራችኋላ» አለው በልሁ ቁጭ እንዳለ በቀኝ
ሽንጡን በመያዝ ሃምሳ አለቃውን እየተመለከተ።
«ወንጀል ፈጽማ እንሆነስ» አለ ሃምሳ አለቃው ፈገግ እያለ።
«የተባለው ከሆነ አላምንም።» አለና በልሁ የሃምሳ አለቃውን ጠረጴዛ መታ መታ እያደረገ «ቀድሞ ነገር የተሰራ ሁሉ ወንጀለኛ የአሰረ ሁሉ ዳኛ ነው ብዬ ማመን ከተውኩ ቆይቼአለሁ።» አለው።
«አይፈረድብህም»
«አሁን ለምን ፈለከኝ።» ሲል በልሁ ዓይኑን ፈጠጥ አድርጎ ጠየቀው።
«ለብርቱ ጉዳይ !» አለና ሃምሳ አለቃ በረጅሙ ተንፍሶ "ግን አቶ በልሁ አሁን የምነግርህ ጉዳይ ሔዋን ለምትባል ልጅ ፈፅሞ መነገር የለበትም ባይሆን
ለአንተና ለቅርብ ጓደኞችህ ከነገርኳችሁ በኋላ አስባችሁበት የሚሆን ነገር ነው።"
«ምንድነው እሱ?»
«አስቻለው ፍስሀ የሚባል ጓደኛ እንደነበረህ ሰማው።»
«አሁንም አለኝ::»
«አብራችሁ ያላችሁ አይመስለኝም።»
«ከልቤ አይወጣምና ምንጊዜም አብረን የምንኖር ይመስለኛል»
«በአካል ማለቴ ነው፡፡»
«ክፉዎች አለያይተውናል፡፡ አሁን የትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ
አላውቅም።» ካለ በኋላ በልሁ «ለአንተ ማን ነገረህ? ሲል ጠየቀን
«በህይወት አለ ብልህ ታምናለህ?
«የት አገር?»
«እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ፡፡»
«ኦ?» አፉ ተከፍቶ ቀረ ዓይኖቹ በሃምሳ አለቃው ላይ ተተከሉ
«እስቲ ከሚቀርበህ ሰዎች ጋር በመሆን ተሰባሰቡልኝና ስለ እሱ ሁኔታ በጋራ ላናጋገራችሁ፡፡ እኔ የማውቀው ነገር አለኝ፡፡
«ዛሬ ማታ ቢሆንስ?»
«ይቻላል»
«ቦታና ሰአት ወስነው ተለያዩ፡፡»
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ፖሊስ ሆኖ ከተቀጠረ ጀምሮ አሁን
ያጋጠመውን ዓይነት አስደሳች ሥራ እግኝቶ አያውቅም። የሔዋንና በእሷ ምክንያት ተጣላን ያሉ ሰዎችን ጉዳይ እንደ የመንግስት ተቀጣሪነቱ ሳይሆን ልክ እንደ ራሱ
ገዳይ በተለየ ስሜትና ትኩረት ሊከታተለው ወሰነ።
የስራው የመጀመሪያ ዕቅድ የሔዋንን ድንግልና በሐኪም ማረጋገጥ ነበር።በእርግጥም ፈፀመው ሔዋን ያልተሟሸ ገላ ባለቤት ሆና አገኛት። የምስክር
ወረቀቱንም በእጁ ያዘ፡፡ ለምርመራው የሚያወመቹ በርካታ ፍንጮችን ከእነበልሁ አግኝቷል፡፡ የምርመራው ሂደት በዚያው አቅጣጫ እንዲጓዝ አድርጎ እቅድና
ስልቱንም ቀይሶታል፡፡ ስለ አስቻለው ሁኔታ ታፈሡን በልዑንና መርዕድን ሲያነጋግር ባመሽበት ሶስተኛ ቀን ላይ ዓለሙ መርጋንና መብራቴ ባዩን ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ከቢሮው አስቀረባቸውና «ልብ ብላችሁ አድምጡኝ» ሲል ሀምሳ አለቃ አስጠነቀቃቸው፥ ዓለሙና መብራቴ ከፊቱ ተቀምጠው የሚሆኑት ሁኔታ በራሱ ውስጣቸውን ያስነብበዋል።
«ሔዋን ተስፋዬ የምትባል ሴት ወዳጃችሁ እንደሆነች ቃል በሰጣችሁበት ወረቀት ላይ ፊርማችሁን አኑራችኋል ነው ወይስ እይደለም?» ሲል ጠየቃቸው።
👍12🔥1
«ነው! ነው!» አሉ በፍርሀት ስሜት ይቁነጠነጡ ጀመር።
ሃምሳ አለቃ አንዲት ወረቀት ከጠረጴዛው ላይ ብድግ አድርጎ እያሳያቸው ይቺ ወረቀት ግን ቅጥፈታችሁን አረጋግጣባችኋለች
ሔዋን ድንግል ስለመሆኗ
የምታረጋግጥ የሐኪም ወረቀት ናት፡፡» ብሎ ወረቀቱን ጠረጴዛ ላይ በክብር ከአስቀመጠ በኋላ እንደገና አየት እያደረጋቸው
«ዋሽታችኋል ወይስ እልዋሻችሁም» ሲል ጠየቃቸው፡፡ ዓለሙና መብራቴ እርስ በእርስ ተያዩ፡፡ ከንፈራቸውን በምላሳቸው
እያራሱ ይቅበጠበጡ ጀመር።
«ተናገሯ!»
ዓለሙ መርጋ ድንገት ብድግ አለና «እውነቱን አወጣለሁ ጌታዬ » አለ እጆቹን ወደ ኋላ አቆላልፎ እጅ እየነሳ።
«እንተስ?» አለና ሀምሳ አለቃ በመብራቴ ላይ አፈጠጠ፡፡ መብራቲም ልክ እንደ ዓለሙ ብድግ ብሎ ግልጥ አድርጌ አወጣለሁ ጌታዬ!» አለና እጅ ነሳ፡፡
ሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ከመቀመጫው ብድግ አለ፡፡ ከጠረጴዛው ላይ ሁለት ንፁህ ወረቀቶችን እያነሳ። ወደ ሀለቱም ጠጋ በማለት አንዳንድ እያደላቸው
ምን ዓይነት ውለታ ሊከፈላችሁ ቃል እንደተገባላችሁ፣ እንዲሁም በዚህ ጉዳይ ላይ የት፣ መቼና ከማን ጋር እንደተነጋገራችሁ በራሳችሁ እጅ ጽፋችሁ ታመጣላችሁ፡»ካለ በኋላ በማስጠንቀቂያ ዓይነት ሌባ ጣቱን ቀስሮ «ልብ በሉ በሁለታችሁ ጽሁፍ ላይ እንዲት ልዩነት ብትገኝ ሁለታችሁም ዕዳ ትገባላችሁ፡፡» አለና ወደ በሩ ራመድ እያለ «ኑ ተከተሉኝ:: አላቸው:: ይዟቸወ ወጣ፡፡ በፖሊስ ጣቢያው ግቢ ውስጥዐበሚገኙ ሁለት የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ለየብቻ አስገብቶ ቆለፈባቸው፡ በግምት አንድ ሰዓት በኋላ የተከፈተላቸው ዓለሙና መብራቴ ያቀረቡለት ፅሁፍ ለሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ
ለከሰዓት በኋላ ስራው ምቹ ሁኔታ ፈጠረለት። በዚያው መሰረት ሸዋዬንና በድሉን ከእያሉበት እየለቀመ ለዚያውም አንዱ ስለሌሳ በማያውቁበት ሁኔታ ለየብቻ እስር ቤት ከቷቸው አደረ፡፡ በነጋታው ጠዋት በቅድሚያ ዓለሙንና መብራቴን ወደ ቢሮ አስጠራና ጎን ለጎን አስቀምጦ
«ስሙ! አላቸው ተራ በተራ እየተመለከተ።
«አቤት! አቤት አሉ በየተራ፡፡»
«ከጻፋችሁት ወረቀት ለይ እንደተረዳሁት፣ ዓለሙ የመኪና ሾፌር፡ መብራቴ ደግሞ ረዳትና ገንዘብ ያዥ ሆናችሁ ልትቀጠሩ በበድሉ አሸናፊ በተገባላችሁ ቃል መሰረት በንጹህ ሰው ላይ አሳፋሪ የስም ማጥፋት ወንጀል
ፈጽማችኋል። ከእንግዲህ እናንተን ነጻ ሊያደርጋችሁ የሚችለው በዋና ጠንሳሾች ላይ ቋሚ ምስክር ሆናችሁ ስትገኙ ብቻ ነው:» አለና «አሁን ዋናዎቹን ወንጀለኞች እዚሁ አላችሁበት ላቀርባቸው ነው፡፡ እናንተም ከፊታቸው ቆማችሁ ወንጀሉን
ትፈጽሙ ዘንድ በእነሱ የተነገራችሁን ሁሉ በዝርዝር ስለመናገራቸው ቀድማችሁ
ልትገልጹላቸው ይገባል፡፡ አለና «ታደርጋላችሁ ወይስ አታደርጉትም» ሲል ቆጣ ብሎ ጠየቃቸው።
«እናደርጋለን::» አሉ ሁለቱም በአንድ ላይ
ሃምሳ እለቃው ሽዋዬና በድሉን ወዲያው አስቀረባቸው። እነሱን በአንድ በኩል አለሙና መብራቱን ደግሞ በሌላ በኩል አስቁሞ ፊት ለፊት አፋጠጣቸው ትናት በዓለሙና በመብራቴ ተጽፈው የቀረበትን ወረቀቶች በእጁ ጠልጠል አድርጎ ያዘና «አለሙና መብራቴ» ሲል ጠራችው።
«አቤት! አቤት!» አሉ በተከታታይ።
«እነዚህ ወረቀቶች እናኖተ በሔዋን ተስፋዬ ለይ እንድትፈጽሙ በበዶሉና ሸዋዬ የታቀደውን ሁሉ የዘረዘራችሁበት ናቸው።» አለና
ረዓዕተኛ ምብራቱ» ሲል«ዋሸሁ?» ሲል ጠየቃቸው።
«እውነት ነው ትክክል ነው። አሉ ዓለመዳ መብራቱ»
ሃምሳ አለቃው ወደ ሸዋዬና በድሉ ዞር ብሎ «ላታመልጡ መያዛችሁን አወቃችሁ?» ሲል ጠየቃቸው።
«ሁለቱም አንገታቸውን ደፉ፡፡»
ሃምሳ አለቃው የጠረጴዛ ደውል አቃጨለና ረዳቱ ፖሊስ ሲመጣለት ሸዋዬን ዓለሙን እና መብርሃቴን ወደ እስር ቤት አስወሰዳቸው በድሉ አሸናፊ
ብቻውን ተገኘ።
«አቶ በድሉ» ሲል ጠራው የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ፡፡
«አቤተ!»
«ሔዋን ተስፋዬ ምን ዓይነት በደል ብትፈጽምብህ ነው የወሮ መንጋ
ያዘምትክባት?» ሲል ረጋ ብሎ ጠየቀው፡፡
«እስደብድባኛለች»
«በማን?»
«በልሁ ተገኔ በሚባል ጥጋበኛ»
«ሥነ ሥርዓት» ሲል ጮኸበት ሀምሳ አለቃ ዓይኑን አፍጥጦ እያየው ጣቱን ቀስሮ፡፡ከበልሁ ተገኔ ቡጢ ያተረፈህን አምላክ ማመስገን ትተህ ደግሞ
በህግ ቦታ ላይ ተቀምጠህ ልትዘልፈው ትሞክራለህ?» አለው እልህ እየተናነቀውና በንዴት ፊቱ ልውጥውጥ እያለ።
በድሉ ከመደንገጡ የተነሳ በዓይኑ መግቢያ ቀዳዳ የሚፈልግ ይመስል ወደ ላይ ወደ ታች፣ ወደ ቀኝ ወደ ግራ ዓይኑን እያማተረ ይቁነጥነጥ ጀመር።
«በምን ተገናኝታችሁ ነው ያስደበደበችህ?
«እወዳታለሁ!»
«ለምን ወደድከኝ ብላ አስደበደበችህ?»
«መሰለኝ::»
«ስለዚህ ልትበቀላት ፈለክ?»
«የራሷ እህት ናት የገፋፋችኝና መላውን የፈጠረችልኝ::»
«ስሟን ጥራታ!»
«ሸዋዬ::» አለና በድሉ እነዚያን ገጣጣ ጥርሶቹን የባስ ግጥጥ አደረጋቸው፡፡
ላብ ላብ ብሎት ጭንቀቱ ይታወቅበታል።.....

💫ይቀጥላል💫
10👍7
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

“መንግሥታችሁን ታጥናላችሁ፤ አልጋችሁን ትጠብቅላችሁ” እያሉ
መረቋቸው።

ሕዝቡ ከሚፈልጋቸው ነገሮች አንዱ አብያተ ክርስቲያናት
እንዲሠሩለት በመሆኑ ምንትዋብ ስለጉዳዩ ከልጇ ከብርሃን ሰገድ
ኢያሱ ጋር መከረች። ኢያሱ አስራ አንድ ዓመት አልፎታል። ንጉሠ
ነገሥቱ እሱ በመሆኑ፣ሳታማክረው የምታደርገው ነገር የለም።

አንድ ከሰዐት በኋላ፣ ቤተመንግሥት እንግዳ መቀበያው ክፍል ተቀምጠዋል። ሁለቱም ያንን መጠነኛ ስፋት ያለውን ክፍል ይወዱታል።ቅልብጭ ያለ በመሆኑ፣ የልባቸውን ለመጫወትና ስለመንግሥት ሆነ
ስለራሳቸው ጉዳይ ለማውራት ይመቻቸዋል።

ቀይ ከፋይ ጨርቅ የለበሱ ወንበሮች ዙርያውን ተደርድረዋል።
ምንትዋብ ከመግቢያው በስተቀኝ በኩል ከቀንድ የተሠራው የካባና
የባርኔጣ ማሳረፊያ ላይ ጎን ለጎን የተሰቀሉትን የእሷንና የእሱን ካባዎች ትመለከታለች። የቀረበላትን ጠጅ ቀመሰችና ቀና ብላ አየችው።

ኢያሱ ደረስህልኝ። እንዲህ አድገህ በማየቴ ታላቅ ደስታ
ይሰማኛል። ደጅ ኻልወጣሁ እያልክ ምታስቸግርበት ግዝየ ስንኳ ሩቅ አልነበረም። ያነዜ ዛዲያ አንዱ ይገድልብኛል እያልሁ እጨነቅ ነበር።አሁን እያደግህ ስትመጣ ሁሉ ነገር እየገባህ መጣ። እዝጊሃር ይመስገን” አለችው።

“አንቺ እኮ ለኔ በጣም ስለምትጨነቂ ነው እንጂ ምወጣውና ምገባው ኸሰው ጋር ነው። ምኑ ነው ሲጨንቅሽ የነበረው?”

“አየ ኢያሱ የእናት ሆድ ምን ያለ እንደሆነ አለማወቅህ ነው
እንዲህ ሚያስብልህ። አሁን እንደምታየው አገራችን ሰላም ሁኗል እኔም እንግዲህ ፊት አንስቸልህ እንደነበረው ልቤ ያለው ቤተክሲያን ማሠራት ላይ ነው። ድኻው ቤተክሲያን እንድናሠራለት ይፈልጋል ። እኔም ብሆን ነፍስ ካወቅሁ ዠምሮ ክፍሌ ለሆነችው ለቁስቋም ማርያም ቤተክሲያን ማሳነጽ ፈልጋለሁ። ጃንሆይም እኮ በነገሡ ባመታቸው ነው
ኸዝኸ ኸጐንደር ቅዱስ ሩፋኤልን የተከሉት። ደፈጫ ኪዳነ ምረትንም
እሳቸው ናቸው የደበሩ። አያትህ ታላቁ ኢያሱም ቢሆኑ ደብረብርሃን
ሥላሴንና አደባባይ ተክለሃይማኖትን የመሳሰሉ ቤተክሲያኖች ተክለዋል። ታቦት ተሸክመው እደብረብርሃን ሥላሤ ከመንበሩ ሲያገቡ ማዶል እንዴ፡-

ወዴት ሂዶ ኑራል ሰሞነኛ ቄሱ፣
ታቦት ተሸከመ ዘውዱን ትቶ ኢያሱ።
የተሸሽገውን ያባቱን ቅስና፤
ገለጠው ኢያሱ ታቦት አነሳና።
አየነው ኢያሱ ደብረብርሃን ቁሞ፣
ሰውነቱን ትቶ መላክ ሆነ ደሞ።
ሥላሴን ቢሸከም ኢያሱ ገነነ፤
ላራቱ ኪሩቤል አምስተኛ ሆነ።
ተብሎ የተገጠመላቸው?” አለችው።

ፈገግ አለ።

ጐንደር የገባች ቀን ያየቻቸውን፣ ከዚያ በኋላ የተሳለመቻቸውን፣
የደጎመቻቸውንና ሳትሰስት ጉልት እና መሬት የሰጠቻቸውን አብያት
ክርስቲያናት ሁሉ ባየችና ባሰበች ቁጥር፣ ጐንደር የቤተክርስቲያን
ባለፀጋ እንደሆነች ብታውቅም፣ የኔ የምትላትን እንደምታሠራ ስትዝት ቆየታ ጊዜው አሁን ነው pብላለች። ከባሏ ሞት በኋላ፣ “ሁሉን በግዝየው ማረግ” የሚለው ሐሳብ አእምሮዋን በመግዛቱ ጊዜ ሳታባክን ማድረግ
ያለባትን ማድረግ እንዳለባት ራሷን ስታስታውስ ቆይታለች።

እናም እንዳልሁህ ለቁስቋም ቤተክሲያን ላቆምላት ተነስቻለሁ።"

“አንቺ እናቴ እንዳልሽው ይሁን” አላት።

“ያባቶችህ በረከት አይለይህ። እኔ መቸም አሳቤ ብዙ ነው።
ቤተክሲያን ብቻ ሳይሆን ለኔም ቤተመንግሥትና ሌላም ሌላም ማሠራት ፈልጋለሁ። አንተም የራስህ መኖሪያ ያስፈልግሀል። ይኸ ላንተ ሊሆንህ ይችላል” አለችው።

አሁን የሚኖሩበት አፄ ፋሲለደስ ቅጥር ግቢ ውስጥ ስላሠራችው
ቤተመንግሥት እያወራች። ቀጥላም፣ “ሙያ ያላቸው ጠርአና ሶሪያዎቹ ኸኛ ሰዎች ጋር ሁነው ቢሠሩ ብዬ አስቤያለሁ። እንዳው እንደ ገብረሥላሤ ያለ ግንበኛ ባገኝማ! እንዳው እንዴት ያለ ግንበኛ ነበር ይላሉ። በአያትህ ግዝየ ዠምሮ ነበረ። ኸኛ ሰዎችም አላፊ ሁነው ሚሠሩም መድባለሁ።”
ባለችው ተስማማ።

ሳይውል ሳያድር ግንበኞችና ባለሙያዎች ተቀጥረው ከፋሲለደስ ቤተመንግሥት እምብዛም ሳይርቅ፣ ጉብታ ላይ የደብረ ፀሐይ ቁስቋም ግንባታ ተጀመረ። ባጭር ጊዜ መቃረቢያው ተሠርቶ አልቆ ቅዳሜ
ቀን ታቦተ ሕጉ ከአቡነ ክርስቶዶሉ ቤት ተነስቶ ወደ ቁስቋም ሲወሰድ፣የፊት ዐጀብ ከፊት እየመራ፣ የጎንና የኋላ ዐጀብ ተከትሎ፣ አስቴር ብላ የሰየመቻትን ሕፃን ከግራዝማች ኢያሱ በቅርቡ የወለደችው አራሷ ምንትዋብ በበቅሎ፣ ዳግማዊ ኢያሱ በፈረስ ሆነው፣ የወርቅ በትረ መንግሥታቸውን ጨብጠውና ግርማ ሞገስ ተጎናጽፈው፣ ለሽኝት
ወጡ።
ዐቃቤ ሰዐቱና ዕጨጌው እነሱን ሲከተሉ፣ ካህናቱ ቀይና አረንጓዴ
ለብሰው ሰንደቅ እያውለበለቡ፣ የወርቅና የብር መስቀልና የወርቅ
ፀናፅል ይዘው፣ እየዘመሩና እያሸበሸቡ፣ ነጋሪት እየተጎሰመ፣ መኳንንቱ፣ሊቃውንቱ፣ ወይዛዝርቱና ባለሟሉ ደግሞ እንደየደረጃቸው ተሰልፈው
ተከተሉ።

ሕዝቡ መንገድ ዳር ቆሞ መሬት እየሳመ በዕልልታና በሆታ
ተቀበላቸው። ታቦተ ሕጉ በአቡኑ ተባርኮ ቤተመቅደስ ገባ።

ምንትዋብም ዋናውን የቁስቋም ማርያም ሆነ የሌሎች ግንባታዎችን እንዲከታተሉ አዛዥ ተክለሃይማኖትን፣ አዛዥ ሕርያቆስን፣ አዛዥ ናቡቴን፣ አዛዥ ማሞንና በጅሮንድ ኢሳያስን የበላይ ተቆጣጣሪ አድርጋ
ሾመች። ግሪክና ሶርያውያን ሕንጻ ሥራ አዋቂዎችም ተፈልገው
መጥተው ከሃገሬው ሰው ጋር ሆነው እንዲሠሩ ተደረገ።

ምንትዋብና ኢያሱ ከሥራው አልተለዩም። ምንትዋብ ዘወትር
ጠዋት የቤተመንግሥት ጉዳይ ከፈጸመችና ካስፈጸመች በኋላ፣ እሷ በቅሎ ላይ፣ ኢያሱ ፈረስ ላይ ሆነው በባልደራስ በር ወጥተው ቁስቋም ግንባታ ስፍራ ይሄዳሉ።

ኢያሱ ከቀቢዎች ጎን ሆኖ እየቀባ፣ እሷ እየተቸች፣ ያልወደደችውን
እያስፈረሰች፣ ራሷ በምትፈልገው መሠረት እያሰራች፣ ዕንጨት
ከአርማጨሆና ከወልቃይት እያስመጣች፣ በድንጋይ ባለ ሰባት በሯ ቁስቋም ማርያም ተሠራች። ውስጥ መግቢያ ደረጃዎቿ ከሕንድ በመጣ ሸክላ ተሰሩላት። ግቢዋ ዝግባ፣ ጥድና ወይራ ተተከለበት፣ አፈር ደብረ
ቍስቋም ከምትገኝበት ሃገር ከግብፅ መጥቶ ተበተነበት። ቁስቋም ከውስጥና ከውጭ በወርቅ አሸበረቀች።

ምንትዋብ በሥዕል ልታስጌጣት ብላ ያንን የልጅነት ምስሏን የላከውን ሠዓሊ ማስመጣት ፈለገች። ትዝ ሲላት የሰውየውን ሆነ የመነኩሴውን ስም አታውቅም። መነኩሴውን ራሳቸውን ማን ብላ እንምታስፈልጋቸው ግራ ገባት፤ ተበሳጨች።
በመጨረሻም ቁስቋም ጐንደር ባሉ ሠዓሊዎች ሥራዎች አጌጠች።ምንትዋብ ከውስጥ የማርያምን ሥዕል አሥላ፣ ከፋይ ካባዋን በትንንሹ አስቀድዳ ዙርያውን አስለጠፈችበት::

ግንባታ መጠናቀቂያው ላይ ማስጌጫ ገንዘብ ሲያጥር፣ ሥራው እንዳይቋረጥ ምንትዋብ ከራሷ ወርቅ፣ ቀለበቷ ሳይቀር፣ ሰጠች።አንድ ሰሞን ጐንደር “ጉድ” አለ፤ “እቴጌ የጣታቸው ቀለበት ሳይቀር ለቤተክሲያን ማሠሪያ ሰጡ” እያለ አደነቀ።

የቁስቋም ማርያም ግንባታ በሦስት ዓመት ውስጥ ተጠናቀቀ።

ታቦቷ በታላቅ በዓል ቋሚ ማደሪያዋ ስትገባ ሕዝቡ፣ “እሰይ! እሰይ!” አለ፣ አመሰገነ። ካህናቱ ምንትዋብንና ኢያሱን፣ “
ለማርያም ቁስቋምን
እንዳቆማችሁላት፣ ቤተመቅደሷንም ዐይናችሁ እንቅልፍ ሳያይ ደፋ ቀና
ብላችሁ እንደሠራችሁላት፣ ለናንተም ትቁምላችሁ። መንግሥታችሁን ታጥናላችሁ፤ አልጋችሁን ትጠብቅላችሁ” እያሉ መረቋቸው።

ምንትዋብ ከልጇ ጋር ቁስቋም ማርያምን ማደራጀት ላይ አተኮረች። አንድ ቀን፣ የየደብሩን ካህናትና ሊቃውንት ወርቅ ሰቀላ ሰበሰበቻቸው።

“እቴጌ ምን ሊሉን ነው?” እያሉ እርስ በእርስ ተጠያየቁ።
👍10
“ዛሬ የፈለግኋችሁ...” አለቻቸው፣ “ዛሬ የፈለግኋችሁ ለደብረ ጠሐይ
ቁስቋም አስተዳዳሪ ሚሆን ብልህና አስተዋይ የሆነ፣ ባህላችንንና ወጋችንን ሚያቅ፣ አገርንና ወገንን ሚያኮራ፣ ቤተክሲያንን በወጉ ሚመራ፣ የተማረና የተመራመረ፣ ዐራቱን ጉባኤ ያጠናቀቀ ሰው
እንድትመርጡልኝ ነው።”
ካህናቱና ሊቃውንቱ እርስ በእርስ ተነጋገሩ። እሷ ከመሃላቸው ማንን
እንደሚመርጡ ለመስማት ተጠባበቀች።

“እቴጌ ለዝኸ ማዕረግ ኸሮብዓም ወዲያ ማን ሊመጣ?” ሲሉ
ተንጫጩ።

ሮብዓም ማነው?”

“ሮብዓምማ የመርጡ ለማርያም ተወላጅ የሆነው ሊቅ ነው” አሏት,
መምህር አእምሮ የተባሉት የቅኔ ሊቅ፣ ከመቀመጫቸው ተነሥተው:
“ኸዝሁ ኸጐንደር ሐዲሳትን መምህር ኤስድሮስ ዘንድ ነው የተማረ፣ብሉያትንም ኸዝሁ ያጠና። መቸም በካህናት ሆነ በሊቃውንት ዘንድ እሱን ሚያህል ዝና ማንስ አተረፈ? እቴጌ ሮብዓም ታላቅ ሊቅ ነው፣ኸሱ ወዲያ ማን ሊመጣ?”

የተሰበሰበው ካህንና ሊቅ፣ “ይበጅ! ይበጅ! ኸሱ ወዲያ ማን ሊመጣ?” አለ።

“አሁን የት ነው ያለ?” ሲል ጠየቀ፣ ኢያሱ።
“እዛው እመርጡለማርያም ነው ያለ” አሉ፣ መምህር አእምሮ።
“እንግዲያስ ባስቸኳይ ይምጣ” አለች፣ ምንትዋብ።
ስብሰባው ሲበተን ሮብዓምን ይዞ የሚመጣ ሰው ወደ መርጡለማርያም
ተላከ።በዚያው ሰሞን
ካህናቱንና ሊቃውንቱን ድጋሚ ሰበሰበች ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚውሉ መጻሕፍት ዝርዝር እንዲሰጧት።በዝርዝሩ መሠረት በመቶዎች የሚቆጠሩ መጻሕፍት እንዲሰበሰቡ
ተደርጎ ዕቃ ቤት ተሠርቶላቸው መጻሕፍቱ እዚያ ተቀመጡ።

በቁመናቸው ማማርና በዕውቀታቸው ጥልቀት አወዳድራ “ድምጠ መረዋ” የሆኑ መቶ ኃምሳ ካህናት፣ መቶ አስራ ሰባት የብራና ሊቃውንትና ኃምሳ ዘበኞች አስመደበች። ለቁስቋም ማርያም አገልግሎት የሚውል
ዕጨጌው፣ ዐቃቤ ሰዐቱ፣ ሊቃውንቱና ካህናቱ ባሉበት ተመዝግቦ ምንትዋብና ኢያሱ ቁጥሩ በርካታ የሆነ የቤተክርስቲያን መገልገየና
ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚውል መሬት ለአገልጋዮችም ጭምር ሰጡ።

ሳምንታት አልፈዋል። ሮብዓም ጐንደር ደርሶ ምንትዋብ ፊት ቀረበ።ስታየው የተባለው ሰው ዓይነት መሆኑ ገባት። ገጽታው ላይ ሊቅነቱን አየች። ዐይኖቹ የዕውቀት ብርሃን ሲረጩ፣ መላ ሰውነቱ ታማኝነቱን ለቁስቋም አስተዳዳሪነት የሰጠቻቸውን
መመዘኛዎች በሙሉ ማሟላቱን ፊቱ ላይ አነበበች። ካህናቱና
ሊቃውንቱ፣ “ከሮብዓም ወዲያ ማን ሊመጣ” ያሉት እውነት መሆኑን ሲመሰክር አስተዋለች።
አረጋገጠች።

ስታነጋግረው ከተባለውም በላይ ሆኖ አገኘችው። ቁስቋም ያለጥርጥር አስተዳዳሪ እንዳገኘች አውቃ ልቧ ተደላደለ። መልአከ ፀሐይ ብላ የደብረ ፀሐይ ቁስቋም አለቃ አድርጋ ሾመችው። የራስ ወርቅ ታሠረለት። ለክብሩም የወርቅ መስቀል፣ የወርቅ ጫማና በወርቅ ያጌጠ ካባ ተሸለመ። ለደብረ ፀሐይ ቁስቋም ለተደረገው መደራጀት ሁሉ
በካህናቱ፣ በሊቃውንቱና በሕዝቡ ዘንድ ታላቅ ደስታና ፈንጠዝያ ሆነ።
ፈንጠዝያው በደንብ ሳያልቅ ደፈረሰ። ጐንደርና ዙርያዋ ፈንጣጣ ገብቶ አስራ አምስት ዓመት እየተጠጋው ያለው ኢያሱ በበሽታው ተጠቃ፤ በጠና ታመመ። ሁለተኛ ልጇን እርጉዝ የነበረችው ምንትዋብ ይሞትብኛል ብላ ሰጋች። መሠሪ ወስዳ ከእናቷ ጋር መኝታውን የሙጥኝ ብላ አስታመመች። የማርያምን ምስል ራስጌው አስቀምጣ ጠዋት ማታ ጤንነቱ እንዲመለስለት ጸለየች።
ጐንደሬዎች ወሬውን ሲሰሙ ጭንቅ ያዛቸው።

ከጐንደር ውጭ ሳይቀር መኳንንት ሊጠይቁ መጡ። ቀስ በቀስ
ላጋው ንጉሠ ነገሥት ከተኛበት ቀና አለ። ምንትዋብና እናቷ
በእፎይታ ተነፈሱ። ቤተመንግሥት ውስጥ ታላቅ ደስታ ሆነ።
መኳንንቱ አሸርጠው እስክስታ ወረዱ። ካህናት ፈጣሪን አመሰገኑ፤ ወረቡ፤ ዘመሩ። ሊቃውንት ቅኔ ተቀኙ።

ጐንደሬዎች መንገድ ላይ ፈሰው ደስታቸውን በዘፈን፣ በዕልልታና
በጭፈራ ገለጹ።....

ይቀጥላል
👍17
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስምንት ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ “መንግሥታችሁን ታጥናላችሁ፤ አልጋችሁን ትጠብቅላችሁ” እያሉ መረቋቸው። ሕዝቡ ከሚፈልጋቸው ነገሮች አንዱ አብያተ ክርስቲያናት እንዲሠሩለት በመሆኑ ምንትዋብ ስለጉዳዩ ከልጇ ከብርሃን ሰገድ ኢያሱ ጋር መከረች። ኢያሱ አስራ አንድ ዓመት አልፎታል። ንጉሠ ነገሥቱ እሱ በመሆኑ፣ሳታማክረው የምታደርገው ነገር የለም። አንድ ከሰዐት በኋላ፣…»
#ቅፅበትና_ቅፅፈት

“ጠብ” ይላል ዝናቡ
“ጧ” ይላል መሬቱ
“ድም” ይላል ነጋሪት
“ግው” ይላል ብረቱ
“ቋ” ይላል መዘውር
“ቲክ” ይላል ሰዓቱ
እቱ እቱ እቱ
ያንቺ ፍቅር ነበር
እንደ አዲስ ሚወልደኝ
ዋዛ አያውቅም ጊዜ
“መሽቶብሃል” ብሎ
ጠምዝዞ አጎበጠኝ!

(ይሄ ሁሉ ሆኖ
ከምፅኣት በፊት ከቦታው ስትደርሺ
እኔ ያንቺ ድኩም
ጎብጨ አልቀረሁም ሬሳዬን አንሺ)

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍7
#ሳገኝሽ_የሚሆነው

ትናንት...
እንደ ከሰረ ሰው
ወዘናዬ ጠፍቶ ጭው ብዬ ነጣሁ
በደበኞች ደባ
አንገቴን ደፍቼ ግፍ እንደ ውሃ ጠጣሁ
ዝም ብዬ ተቀጣሁ..
ጮክ ብዬ ተቆጣሁ...
ልክ አንቺን ሳገኝሽ
ከሲኦል ሆድ ወጣሁ
ዛሬ...
የዛሬውን ትርጉም የዛሬውን ፍቺ
እንዲህ ነሽ ይልሻል ተቀበይው እንቺ
ውስብስብ ቋጠሮን ስቀሽ የምትፈቺ
ቀና እምታደርጊ ቀና ሰው ነሽ አንቺ

ምንም እንዳይገርምሽ!!!

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
6👍5😁1
#አንድ_ሌላ_መንገድ

ገደል ዋሻ ጥቁር እሳት
ተንኮል ክፋት ምቀኝነት
ሸር ደባ ሀጣ ብኩን
በግራ ጎን በቀኝ ጎን
ሕልም ራዕይ አዲስ ሕይወት
ትግል ስኬት ጣፋጭ ስሜት
ረዥም መንገድ ከፊት ለፊት

ትእዛዝ ቁጣ መርገምት ሥራይ

ያ'ዳም ቅርሻት ክፉ ክፋይ
ከላይ
እሾህ ጉድፍ አሜኬላ
ከኋላ
የድካም ድግ ጎታችና ተጎታች
ከታች
.
.
.
አንድ ተአምር ተፈጥሮ
ሕይወት መጋረጃ ቢኖራት
የሚጋረደውን ጋርጄ
ፊት ለፊት ነበረ የማያት።

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
8👍4
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


....ምንትዋብ አልጣሽ የተባለችውን ሁለተኛ ልጇን ወልዳ ከአራስ ቤት እንደወጣች እንደገና በግዛት ዘመኗ ልትፈጽማቸው ያሰበቻቸው ነገሮች ላይ ትኩረት አደረገች።

ትምህርት ቁስቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ ለማስጀመር ከብርሃን ሰገድ ኢያሱ ጋር መከረች። ብዙ ጊዜ እንደሚያደርጉት አንድ ቀን እንግዳ መቀበያው ክፍል ተቀምጠዋል።

ትክ ብላ አየችው። ፈንጣጣ ፊቱ ላይ ምንም ምልክት ሳይተው
ማለፉ ገረማት። በቁስቋም ረድኤት መዳኒቱ ሠርቷል። ይኸን የመሰለ መልኩን ሊያበላሽብኝ እሷ የቁስቋሟ ማረችልኝ፡፡ አሁን ኢያሱን የመሰለ ልዥ አለ? የተባረኩ እያለች በሐሳብ ጭልጥ ብላ ሄደች።

ኢያሱ በሐሳብ እንደነጎደች ኣውቆ ከሄደችበት እስክትመለስ ዐይን
ዐይኗን እያየ ጠበቃት።

“አያትህ ታላቁ ኢያሱ ለትምርት ብዙ ዋጋ ሚሰጡ ሰው ነበሩ…
አለችው፣ ከሄደችበት ስትመለስ።

“አውቃለሁ። አንቺም ነገርሽ ሁላ እንደሳቸው ነው። ደሞስ የሳቸው
ስም መቸ ኻፍሽ ጠፍቶ ያውቃል?”

ከት ብላ ስትስቅ እሱም ሳቀ።

“ስለ ትምርት ላወራህ ፈልጌ ነው የሳቸውን ስም ያነሳሁ” አለችው፣
ፈገግ ብላ። “በሳቸው ዘመን የተማሮች ቁጥር ኸዝኸ ኸደብረሥላሤ ስንኳ ብዙ ነበር ይላሉ። ስንክሳርም በብዛት የተጣፈው በሳቸው ግዝየ
ነው። እንደ ክፍለ ዮሐንስ የመሰሉ ሊቃውንትም ኸጎዣም ያመጡ
እሳቸው ናቸው። ሊቁ አዛዥ ከናፍሮም ቢሆኑ በሳቸው ግዝየ ነው የነበሩ። ዛዲያ ልነግርህ የፈለግሁት ቁስቋም ውስጥ ትምርት ቤት ማቆም ብቻ ሳይሆን፣ ለተማሮቹና ላስተማሮቹ ድጋፍ ማረግ አለብን
ሚለውን ነው።”
“እኔም ስለሱ ነግርሻለሁ እያልሁ ነበር። ሌላ ደሞ ባለፈው መጻሕፍት ኻረብኛና ኸዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ እንዲመለሱ ፈልጋለሁ ስትይ
ማልነበር?”

"ትርጉም.... አዎ ስል ነበር። ሁሉ ባግባቡ ነው። ባለፈው መላከ
ጠሐይ ሮብዓምን ትርጉም ላይ ቢበረታ ብያቸው ኻረብኛና ኸዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ ሚመልሱ ሰዎች አምጥተው ሥራ እንዲዠምሩ ተደርጓል።
ለእነመላከ ጠሐይ ሃይማኖትን ሚያስተምረውንና ላገር ሚጠቅመውን ሁሉ እንዲያስተረጉሙ ነግሬያቸው እነሱ ተመካክረው ወስነዋል።”

"የትርጉም ሥራ ለገዳማቱ ቢሰጥ ጥሩ ነው ሲሉ ሰምቸ።”

“ዛዲያ ምን አለ... ይሰጣል ። በጎ አሳብ ነው። ትዛዝ ሰጣለሁ። እኔ
መቸም ቢሞላልኝ አገር ሁሉ መጻፍ በመጻፍ እንዲሆንና ትምርት
እንዲስፋፋ ነው ምፈልግ። እኔ ራሴም ብሆን አንድ ቀን ስለ እመቤታችን ማርያም ታምር አስጥፋለሁ ብየ አስባለሁ። ደሞ እሑድ እሑድ ለሊቃውንቱና ለካህናቱ ግብር እናግባላቸው። አንተም ለነሱ ትልቅ ክብር አለህ። ቅኔም ተምረሀል። ቅኔ እውቀቴ እንዳንተ ባይሆንም፣ሊቃውንቱ ቅኔ ሲቀኙ ስሰማ መንፈሴ ሁሉ ይታደሳል። በተለይማ
የአክስትህን ልዥ እመት ወለተብርሃንን ስሰማ እንዳው እንደሳቸው ቅኔ በቻልሁ እላለሁ፡፡ አንተማ ኸኔም የበለጠ ትወዳቸዋለህ።”

የአክስቱ ልጅ ነገር ሲነሳ ፈገግ አለ። “ውነትሽ ነው እመት ወለተብርሃን ታላቅ የቅኔ ሊቅ ናቸው። እሑድ እሑድ ግብር ለሊቃውንቱና ለካህናቱ ማግባት ያልሽው ተገቢ ነው። በተነጋገርነው መሠረትም በአካባቢው ወይን እንዲተከል ቦታ ብታስጠኚ። ቃሮዳ አየሩ ለወይን ተስማሚ ነው ሲሉ ሰምቻለሁ። ቅርብም ነው።”

“ውነትህ ነው። ዛሬውኑ ሰው ይላካል።”

ሁለቱም ዝም አሉ።

“ግና ካህናቱና ሊቃውንቱ... ምናለ ልብሳቸውን ቢያጠዱ?” አላት።

ያልጠበቀችው በመሆኑ ከት ብላ ሳቀች። “ልብሳቸውን እንዲያጥቡ
ማረግ ይቻላል ። በጐንደር ዙርያና በየገዳማቱ እንዶድ ኣስተክለን
ልብሳቸውን እንዲያጥቡ እናረጋለና” አለችው፣ አሁንም እየሳቀች።

“ዋናዎቹ ካህናት ደሞ የወርቅ ጫማ እንዲያረጉ ፈልጋለሁ።”

“ወርቅ አሳብ ነው። ይታዘዝላቸዋል። የአክብሮትህ ምልክት ነው።

እንደገና ዝም ብለው ተቀመጡ። ኢያሱ ሐሳብ የገባው ይመስላል።
እሷም ዝም ብላ ታየዋለች።

ዐይን ዐይኗን እያየ፣ “አደን ብኸድ ትፈቅጅልኛለሽ?” እናቱን ፈሪና
አክባሪ ነው።

ዕጢዋ ዱብ አለ። አፏ ተያዘ። ሊመጣበት የሚችለው አደጋ
አሳሰባት። ጥያቄው ግን አንድ ቀን እንደሚመጣ ታውቃለች።

“ኣባትህ ስንኳ በኸዱ ቁጥር እጨነቅ ነበር። ኢያሱ እንድትኸድ
አልፈልግም፤ ጭንቀቱን አልችለውም።”

“ምን ችግር አለው?”

“ባትኸድ መርጣለሁ። ኢያሱ አልጋውን እኮ ባየነቁራኛ ሚጠባበቅአለ!”

“ሁሉስ እያደኑ ማዶል እንዴ የኖሩት?”

“ገና ልዥ እኮ ነህ ኢያሱ።”
ድምጽዋ ተርበተበተ።

“አትጨነቂ። ምንም ሚመጣ ነገር የለም። ሰዎች ይዠ ነው ምኸደው
በዝኸ ላይ ደሞ አልቆይም።”

“ኻንተ መለየት አልፈቅድም ኢያሱ ... መቸ ትነሳለህ?”
ነገ።”
“ነገ?”
“አዎ! ነገ።”
“ታሰብህበት ቆይተሀል ማለት ነዋ! መቸስ ምን ኣረጋለሁ። ቁስቋም
ደሕና ትመልስህ። በጠሎቴ አልለይህም።”

አይዞሽ አትጨነቂ። በጠዋት ስለምኸድ ካሁኑ ልሰናበትሽ” አላት፣ጠዋት መጥቶ ቢሰናበታት እንባዋን ማየት ስለማይችል። ተነስታ ወደ እልፍኟ ስትሄድ በጭንቀት ተመለከታት።

በማግስቱ ጠዋት ከእናቷ ጋር በመስኮት ቆመው የአደን ዕቃው
በቅሎ ላይ ሲጫን አይተው ሆዳቸው ባባ። ኢያሱ ፈረሱ ቀርቦለት፡ በሹሩባው ዙርያ ነጭ ሻሽ አስሮ፣ ካባውን ደርቦ ከዐጀቡ ጋር ብቅ ሲል፣ የቤተመንግሥት ባለሟሉ፣ ወታደሩ፣ ጋሻ ጃግሬውና ሌላው ሰገደ።ምንትዋብና እናቷ ግን ሲቃ ያዛቸው።
ከቤተመንግሥት ግቢ ሲወጣ፣
ምንትዋብ ጩሂ ጩሂ አላት። እንኰዬ ትከሻዋን መታ መታ አደረጓት።እሳቸውም እንባ እንባ ብሏቸዋል፤ ግን እሷን ማረጋጋት መረጡ።

ሁለቱም በየክፍላቸው ገብተው ወገባቸውን በገመድ አስረው ሱባዔ ገቡ። መሬት ላይ ተኙ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ጸሎታቸው ሠምሮ ኢያሱ በሰላም ተመለሰ። እናትና ልጅ ገመድ ትጥቃቸውን ፈቱ።የነበሩበትን ጭንቀት ሳይናገሩ በደስታ ተቀበሉት።

እያደር የአደን ፍቅር በረታበት፤ መዝናኛው አደረገው። በሄደ ቁጥር
እናቱና አያቱ ወገባቸውን በገመድ ጠፍረው መሬት መተኛትና ሱባዔ
መግባት፣ ሲመጣ ደግሞ ገመዳቸውን ፈትተው መጣል፣ ጸማቸውን መፍታት ልማድ አደረጉት። እንደዚህ እያለም ኢያሱ የከፋ ነገር ሳይገጥመው ቀለል ያለ አደን ማካሄዱን ቀጠለ።

ከእናቱ ጋር በተስማሙት መሠረት ከንባብ ቤት እስከ ትርጓሜ ቤት
ደብረ ፀሐይ ቁስቋም ማርያምን በትምህርት ለማደራጀት ወጡ ወረዱ።ሁለት መቶ የሚጠጉ ምርጥ ሊቃውንት ከጐንደር ገዳማትና ከሌላ የሃገሪቱ ክፍሎች እየመጡ ወንበር ዘረጉ
የተማሪ ጎጆዎች ተቀለሱ። ትምህርት ከቁስቋም ሌላ በየገዳማቱና በየደብሮቹ ተስፋፋ። ወሬውን የሰማ ተማሪ ከየቦታው ፈልሶ ጐንደር ገባ፡፡ ጐንደር ከመቼውም ጊዜ የበለጠ የሊቃውንት ማፍሪያና
መሰብሰቢያ ሆነች። ከጐንደር ውጭም ትምህርት ቤቶች ተስፋፉ።

የዜማ ሊቃውንት ድርጎ በማግኘታቸው ሙያቸውን አበለፀጉ ቤተክርስቲያንን አገለገሉ፤ ቤተመንግሥትንም አዝናኑ።

የሥዕል ሥራ በአያሌው አደገ። ቀለም አጠቃቀም ጥንት ከነበረው
ለውጥ አመጣ፣ የአቀራረብና የይዘት ለውጦች መጡ። ሠዓሊዎች ድጎማ እየተደረገላቸው አብያተ ክርስቲያናትን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አስጌጡ።
👍9
ቁስቋምም ተደራጀች። ወደ ከፍተኛ የትምህርት ማመንጫነት፣
የታወቁ ሊቃውንትና ካህናት መሰብሰቢያነት፣ የዕውቀትና መንፈሳዊ ማዕከልነት ገሰገሰች።
በየገዳማቱና ጐንደር ዙርያ እንዶድ ተተከለ። ካህናቱና ሊቃውንቱ
ልብሳቸውን በእንዶድ እያጠቡ አምረው ወጡ። ለካህንና ለሊቅ የቆሸሽ ልብስ መልበስ ነውር ሆነ። አንድ ሰሞን፣ “ዕድሜ ለጃንሆይና ለእቴጌ ካንና ሊቅ ልብሱን በእንዶድ አጠበ። አዳፋ ልብስ መልበስ ነውር ሆነ እያለ ጐንደሬ ወሬውን ከጥግ ጥግ አዳረሰ።

ሌላው ሕዝብም ቆሻሻ
ልብስ መልበስ አስነዋሪ ሆነበት።
ምንትዋብና ኢያሱ ምኞታቸው ሁሉ ሠመረላቸው። ያመጡትም
ለውጥ፣ “የቋረኞች የተድላ፣ የአዱኛና የደስታ ዘመን” የሚል ስያሜ አተረፈላቸው።....

ይቀጥላል
👍14😁2
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_አምስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....በድሉ ከመደንገጡ የተነሳ በዓይኑ መግቢያ ቀዳዳ የሚፈልግ ይመስል ወደ ላይ ወደ ታች፣ ወደ ቀኝ ወደ ግራ ዓይኑን እያማተረ ይቁነጥነጥ ጀመር።
«በምን ተገናኝታችሁ ነው ያስደበደበችህ?
«እወዳታለሁ!»
«ለምን ወደድከኝ ብላ አስደበደበችህ?»
«መሰለኝ::»
«ስለዚህ ልትበቀላት ፈለክ?»
«የራሷ እህት ናት የገፋፋችኝና መላውን የፈጠረችልኝ::»
«ስሟን ጥራታ!»
«ሸዋዬ::» አለና በድሉ እነዚያን ገጣጣ ጥርሶቹን የባስ ግጥጥ አደረጋቸው፡፡
ላብ ላብ ብሎት ጭንቀቱ ይታወቅበታል።.
“ 'ተደበደበ ሰው ቢደበድብ ወይም ቢያስደበድብ ድርጊቱ ወንጀል ቢሆንም ነገር ግን ስም አለው:: «ግን ወንድ አደባደበች» ብሎ ማስወራቱ ምንድንነው
ዓላማው? ሲል ጠየቀው፡፡
«ስሟን ለማጥፋት::»
«ማለት?»
«ልጅቷ አስመራ ሄዶ የቀረ እጮኛ' አላት፡፡»
«እሺ»
«እዚህ ያሉት ጓደኞቿ ግን ከማንም ጋር እንዳትገናኝ ይጠብቋታል፡፡
እሷም ትፈራቸዋለች። ወንድ አደባደበች ተብሎ ከተወራባት ግን እነሱ ያርቋታል፡፡እሷም ተስፋ ትቆርጥና የኔን ጥያቄ ትቀበላለች ብዬ በማሰብ ነው፡፡» አለና በድሉ
በተቀመጠበት ላይ ተቁነጠነጠ፡፡
«ስማ » አለው የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ቁጣ በተቀላቀለበት አነጋገር።
«አቤት»
«እዚሁ እንዳለህ የሴራ መሀንዲስህን አስጠራታለሁ፡፡ እጥር ምጥን ባለ ቃል
ሁሉን ነገር እንደተናገርንክ ትነግራታለህ። ነገር አደፋፍናለሁ ካልክ ጠብክ ከመንግስት ጋር ብቻ ሳይሆን ከእኔም ጋር በግል እንደሚሆን እወቅ!!»
«ኧረ እነግራታለሁ!»።
ሃምሳ አለቃ ረዳቱን በደውል ጠራና እንደቀረበለት ሽዋዬን እንዲያመጣ አዘዘው። ረዳቱ ሸዋዬን ወዲያው አቀረባት። በበድሉ ፊትለፊት
እንድትቀመጥ ታዝዛ አለፍ ብላ ተቀመጠች፡፡ ከመርማሪው ፖሊስ ይልቅ በድሉን በፍርሀት ዓይን ታየው ጀመር።
«ቀጥላ!» አለ ሃምሣ አለቃው በድሉ ላይ በማፍጠጥ::
በድሉ ከተቀመጠበት ብድግ አለና ወደ ሽዋዬ ጣቱን ቀስሮ «የቀይ ሽብሩን ጉዳይ ሙልጭ አድርጌ ተናግሬያለሁ፡፡ ብትዋሽ ውርድ ከራሴ!» አላትና ተመልሶ ቁጭ አለ። የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ቀይ ሽብር የሚለውን ቃል ሲሰማ መላ ሰውነቱን አንቀጠቀጠው፡፡ አጠገቡ ያሉት ሰዎች ነፍሰ ገዳዮች መስለው ታዩት። ልክ በቀይ ሽብር ጊዜ እንደተፈጸመው ሁሉ እሱም እነዚህን ሰዎች ዘቅዝቆ ቢለበልባቸው ደስ ባለው ነበር። ግን ደሞ ጨካኞች የፈፀሙትን የጭካኔ ተግባር መድገም የባስ አረመኔነት መሆኑን ይገነዘባልና በቁጭት ራሱን ወዝውዞ ተወው።
ወድያው ረዳቱን በደውል ጠራ። በድሉን ወደ እስር ቤት አስወሰደና ሸዋዬን ብቻዋን አገኛት።
ሽዋዬ በዕለቱ አጠር ያለ ሰማያዊ ጉርድ ቀሚስና ቡናማ ሹራብ ለብሳለች፡፡
ቀላ ያለች ስካርፍ አንገቷ ላይ ጣል አድርጋለች:: ሳታስበው ታስራ በማደሯ ፀጉሯ አላበጠረቾም፣ አልተቀባባችም:: አመዷ ወጥቷል፡፡ ማንደፍሮ ሜዳ ላይ የደፈጠጠው ፊቷ ጠባሳው አልጠፋም፡፡ ተዥጎርጉራለች። ያ አጭር ፀጉሯ ተንጨፍሯል፡፡
ቀጫጭን እግርቿን ስታክካቸው አድራ መስመር ሰርተዋል። በድንጋጤ ዓይኗ ፍጥጥ ብሎ የሴትነት ጥላዋ ተገፏል። ታስጠላለች::
«መምሀርት ሸዋዬ!» ሲል ጠራት የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ሁለት እጆቹ ላይ አገጩን አስደግፎ ዘንበል ብሎ እየተመለከታት፡፡
«አቤት!»
«ሙያሽን ምን ያህል ትወጅዋለሽ?»
«በጣም እወደዋለሁ፣ አከብረዋለሁ፣ ተማሪዎቼም በጣም ይወዱኛል::»
«ምን እያስተማርሻቸው እንደሆነ ስለሚገባቸው ይሆናላ!» አላት በምፀት።
«ትንትን ብትንትን አድርጌ ነው የማስተምራቸው»
የሃምሳ አለቃው በረጅሙ ተነፈሰና ወደ ጠረጴዛው ጎንበስ አለ።
ራሱን ወዝወዝ አድርጎ ብዕርና ወረቀቱን ከአመቻቸ በኋላ «እስቲ እኔም እንደተማሪዎችሽ እንድወድሽ ስለ ቀይ ሽብሩ ጉዳይ ትንትን ብትንትን አድርጎአል ንገሪኝ፡፡» አላት።
ሽዋዬ የደረቀ ከንፈሯን በምላሷ እያራሰች ወደ ላይ ወደ ታች በማየት ከተቅበጠበጠች በኋላ «ቀይ ሽብሩኮ» ብላ ልትጀምር ስትል እንደገና ወደ ሃምሳ አለቃው
ዞር ብላ «በድሉ ነግሮህ የለ?»
አለችው።
ሀምሳ አለቃው በሸዋዩ አስተሳሰብ እንደ መገረም ብሎ ድንገት ፈገግ እንደ ማለት አለና እሱ ብቻ ሳይሆን ዓለሙም መብራቴም በሰፊው ዘርዝረውታል ግን መጀመርያ ሀሳቡን ያፈለቅሽው አንቺ ስለሆንሽ ከባለቤቷ መስማት ፈልጌ ነው::
እግረ መንገዴን ምን ያህል እውነተኛ እንደሆነሽ ለማወቅ ፈልጌ ነው፡፡» ብሎ አየት ሲያደርጋት ሸዋዬ ቀጠለች።
«እኔ እኮ ውሽት አላቅም!» አለችው ቀበጥበጥ እያለች
«እኔስ መች ወጣኝ? በይ እውነቱን ንገሪኝ።»
«ቀይ ሽብር ማለት ያው ቀይ ሽብር ማለት ነው አለችው አይኖቿን በዓይኖቹ ላይ እያንከባለለች።
«ነገርኩሽ አንቺ ሴትዮ አላት ተናዶ፡፡ ምኗ ደነዝ ናት በሆዱ።
«ምን ልበል ታዲያ?» ሽዋዬ ድንግጥ አለች። ተጨነቀችም።
«ዝርዝር ሂደቱን ንገሪኝ ነው ያልኩሽ አለና «ቀይ ሽብርስ ምን አስፈለ»
«ሔዋን አስቸገረችኝ::»
«ምን አድርጊኝ ብላ?
«በቃ! እሷ እያለች ባልም ትዳርም ሌኖረኝ አልቻሉም፡፡»
«ነጠቀችሽ ወይስ አፋታችሽ?»
«ሁለቱንም።»
«እንዴት እያረገች?»
«መጀመሪያ በልቤ የወደድኩትን ሰው ውስጥ ለውስጥ ሄዳ በጎን
ጠለፈችብኝ፡፡» እንደገና ብላ ልትቀጥል ስትል ሃምሣ አለቃ ቀደማት።
«የነጠቀችሽ ሰው ማን ይባላል?»
«አስቻለው ፍሰህ ይባል ነበር፡፡»
«እንዴ!» አለ ሃምሣ አለቃ በመገረምም በመደነቅም ዓይነት ትኩር ብሎ ሸዋዬን ሲመለከታት ከቆየ በኋሳ አስቻለውን ትወጂው ነበር?» ሲል ጠየቃት፡፡
«ነፍሴ እስክትወጣ!»
ሃምሣ አለቃ ግራ ገባው፡፡ ልክ ሔዋንን ያነጋገረ ዕለት እንደሆነው ሁሉ እስኪርብቶውን ወረቀት ላይ ጣል አደረገና ጉንጮቹን ደግፎ ወደ ጠረጴዛው አቀረቀረ፡፡ በዚያው ሀሳብ ውስጥ እንዳለ ሸዋዬ በልቤ የወደድኩትን… ያለችውን አስታወሰና ቅናት ከአጎመነበሰበ ቀና በማለት
«እሺ፣ ደግሞ ከማን አፋታችሽ?» ሲል ጠየቃት።
««ያን እንኳ ባናወራው ይሻላል::»
«ለምን?»
«ደስ አይልማ!»
«ሀምሣ አለቃ የሸዋዬ ባዶነት አስገረመውና አሁንም ጎንበስ ብሎ እንደ መሳቅ አለና። እንደገና ቀና ብሎ “ታዲያ ለኔ የሚያስደስተኝ ደስ የማይለውን ነገር ማወቅ መሆኑን አጣሽው? ወይስ ፖለስ ጣቢያ ውስጥ መሆንሽን ረሳሽው አለና ወረቀቶች ብድግ አድርጎ «ታሪክሽ ሁሉ እኮ እዚህ ላይ ተዘርዝሯል መደበቁ ያዋጣሽ መሰለሽ?» አላት። በእርግጥ ስለ ፍቺ ነገር የተጠቀሰ ነገር አልነበረም፡፡ ነገር ግን ሸዋዬን ለማስፈራራትና ለማስወትወት ተጠቀመበት፡፡
«ሰዎቹ ያንንም አውታዋል? »አለች ሽዋዬ ደንግጣ ብላ፡፡
«በእነሱ ላይ ጨምሮ ቀድሉ አጋልጦሻል::»
«ቅሌታም ነው።»
የሀሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ ድንገት ቂቂቂቂቂ...» ብሎ ሳቀ፡፡ ሸዋዬ ፊደል ከመቁጠሯ በቀር
ምንም እንዳልተማረች ታስበው፡፡፦ እውቀት" ሥርዓትም አጣባት።
በዚያ ምትክ የክፋትና የተንኮል ሰው መሆኗን በውል ተገነዘበና
«ጊዜዬን እትግደያ መምህርት ሸዋዬ!» ሲል ቆጣ ብሎ ተናገራት፡፡ በዚያኑ ልክ
👍15🥰1😁1
ሸዋዬም በድንጋጤ ሽምቅቅ አለች::
«የነገሩህ ሁሉ ልክ ነው::» አለችው በአቋራጭ የተገላገለች መስሏት፡፡
«ዝርዝሩን ከአንቺም እፈልጋለሁ። ቀጥያ!»
ሸዋዬ እንደማይቀርላት ተረዳች:: በሔዋን ላይ ልትፈጽም የነበረውን
የማስደፈርና የማስረገዝ ዕቅድ ሳይቀራት ቤቷ ወስጥ ባርናባስና ማንደፍሮ የተዳረጉትንና ማንደፍሮ ጋር ተለያይታ መቅረቷን በዝርዝር ተናገረች፡፡
የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ ፀጥ ብሎ ሲያዳምጣት ከቆየ በኋላ በረጅሙ ተነፈስና ሁኔታው ገርሞት ራሱን ወዘወዘ፡፡ በተለያ ባርናባስና ማንደፍሮ ከመዝጊያ
ጋር ያደረጉትን ትንቅንቅ የመጨረሻውንም ሁኔታ በነገረችው ጊዜ ሁናታው ሁሉ በእዝነ ልቦናው ታየውና ድንገት
‹‹ቂቂቂቂቂ...»ብሎ ሳቀና ለመሆኑ በርናባስ የተባለው ሰውዬ እዚሁ ደሐላ ውስጥ አለ?» ሲል ጠየቃት።
«የታለና ስራው አሳፍሮት ካገር
እልም ብሎ ጠፍቶ» አለችው፡፡
እናም ይህን ሁሉ ወርደት ለማካካስና ሔዋንን ለመበቀል ተነሳሽና የቀይ ሽብር ዕቅድ አወጣሽ?»
«ስታናድደኝ ታዲያ ምን ላርጋት?»
ሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ሁሉም ነገር በትክክል ገባው፡፡ ዋናውን
የምርመራ ሥራ ስለማጠናቀቁ፡ እርግጠኛ ሆነ፡፡

💫ይቀጥላል💫
👍9
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


“አንተ የሥዕል ንጉሥ ነህ።”

ጥላዬ፣ የአለቃ ሔኖክን አርባ አውጥቶ፣ የምንትዋብን ንግሥ በዐይኑ በብረቱ አይቶ ደብረ ወርቅ ከተመለሰ በኋላ፣ ከዐዲሱ መምህሩ ከአለቃ ግዕዛን ጋር ትምህሩቱን ቀጠለ።

ብራና እያስጌጠ የሚያገኘውን እህል ወይም አሞሌ ጨው ምግብ ለምታቀርብለት ኮማሪት.. እንጎች.. እየሰጠ፣ የዓመት ልብሱን እየለበሰ ትምህርቱን ተያያዘው። ሥነ-ስቅለትን ከሠራ በኋላ በሙያው ትልቅ ዕመርታ አሳየ። ስሙ በደብረ ወርቅ ብቻ ሳይሆን ዲማና ሌሎችም ቦታዎች ድረስ ተዛመተ።

ለምንትዋብ የላከላት ሥዕል ምን ዓይነት ስሜት እንዳሳደረባት
ለማወቅ እየሞከረ መልስ ስለማያገኝለት ነገሩን ይተወዋል። እነማይ መነኩሴው ዘንድ ሄዶ ሊጠይቃቸው ያስብና ስሙ በአካባቢው እየታወቀ
በመምጣቱ ከመሄድ ይቆጠባል ።

በትምህርቱ ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለበት ወስኖ ወደሚቀጥለውና
የመመረቂያ ሥራው ወደሆነው ትኩረቱን አደረገ።

“እንግዲህ እስታሁን የሣልኻቸው በሙሉ ፍጡራን ናቸው። አሁን
አንድ ቀን፣ አለቃ ግዕዛን ቤት ተቀምጠው ሲጫወቱ፣ አለቃ ግዕዛን፣የፍጡራን ሁሉ ፈጣሪ የሆነውን አምላካችንን... አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሤን - የኃያላኑ መቀመጫ የሆነውን - መንበረ ፀባኦትን መሣያ ግዝየህ ነው” አሉና፣ ባለቤታቸው ባፈና እንዲሰሙት ያልፈለጉትን ነገር
ለመናገር እጁን ይዘው ወደ ውጭ ወጡ።

ወደ ጥላዬ ዞረው፣ “የሥላሤ ምሥጢር ሴትና ምሥጢሩን ማወቅ የሌለበት ሰው ፊት አይወራም። ሥላሤ ምሥጢራቸው ጥልቅ፣ ሐሳቡ
ረቂቅ ስለሆነ ነው። ይኸ አሁን ምትሥለውና የመጨረሻ የሆነው፣
ከሁሉም ሚከብደውና ለመሣልም ጥንቃቄ ሚጠይቀው ሥራ ነው.
ምሥጢሩም ጥልቅ፣ ሐሳቡም ረቂቅ ነውና” አሉት።

“ሦስት አካል በአንድ አምሳል፣ ያለ ምንም ልዩነት መሣሉ ነው?
ሲል ጠየቀ፣ ከተቀመጠበት ተነሥቶ።

“ኣየ... እሱማ ተስተውሎ ይሠራል።”

“ዛዲያ ምኑ ነው ሚከብድ?”

“የሥላሴን ሥዕል ኣይተኻል?”

“ኣብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሉ?”

“አድምጠኝና ልንገርህ። ሥላሤ ሚሣሉበት ሠሌዳ ዐራት ማዕዘን
ይሆንና በዐራቱም የማዕዘኖች መገናኛ ላይ ሌሎች ዐራት እኩል
ማዕዘኖች ይሠመራሉ። ስምንት አልሆኑም?”

ጥላዬ በአዎንታ ራሱን ነቀነቀ።

“የሥላሤ በስምንት ማዕዘን መሣል ሚያመለክትህ፣ አንደኛ የስምንቱ
የሰማይ መስኮቶች ምሳሌ መሆናቸው፣ ሁለተኛ የዓለም ቅርፅ ይዘው በክብ እኩል ማዕዘን ውስጥ መቀመጣቸው ሲሆን ሦስተኛ በተመሳሳይ መልክ መሣላቸው ነው። በስምንቱ መስመሮቹ ውስጥ፣ የሰው፣ የአንበሳ፡ የላምና የንስር ምስሎች ይሣላሉ። አየህ ያልተመራመረ ተመልካች እነዝኸን በየማዕዘኑ የተሣሉ ዐራት ፍጡራን ምንነት ብትጠይቀው ዐራቱ ወንጌላውያን ናቸው ብሎ ይመልስልህና ያልፋል።”

“ዛዲያ የምንድር ናቸው?”

“አትቸኩል ላስረዳህ ነው። አየህ የነሱን ምንነት ለመገንዘብ
በመዠመሪያ በእኩል ነጥብ መኻል ላይ ከሚይዙት ክብ ነገር መዠመር አለብህ። ከክቡ ተነስተህ ደሞ ወደ ስምንቱም አቅጣጫ ብታሰምር፣ ሚከተለውን ክብ ንድፍ ታገኛለህ” ኣሉት፣ መሬት ላይ በስንጥር ክብ
ቅርፅ ሰርተውና በክቡ ቅርፅ ውስጥ ስምንት መስመሮች አስምረው።

ጥላዬ፣ ራሱን እየነቀነቀ የሚሥሉትን ይመለከታል።

“እንግዲህ የክቡ ትርጓሜ ዓለም በመዳፋቸው ላይ መሆኗ ነው።
ክብ የዓለማችን ቅርጥ መሆኑንና የዓለማችን ፈጣሪም መዠመሪያውም ፍጻሜውም የማይታወቀው የኅያው እዝጊሃር ምሥጢር ነው። አሁን
ዐውደ ዓመት በዐራቱ ወንጌላውያን ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ እየተመሰለ በየዐራት ዓመቱ ይመላለሳል አዶለም? በነገራችን ላይ
ማቴዎስ በሰው፣ ማርቆስ በአንበሳ፣ ሉቃስ በላም ሲመሰሉ ዮሐንስ ደሞ በንስር ይመሰላል። ይኸም ምሳሌ በዘፈቀደ የተሰጠ እንዳይመስልኸ።
የየወንጌላቸው አካኼድ ተጠንቶ ነው ይኸ ምሳሌ መሰጠቱ። እንዲያው ለአብነት ብናይ ማቴዎስ በሰው መመሰሉ 'አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፣
ይስሐቅ ያዕቆብን እያለ የክርስቶስን ሰዋዊ የዘር ሐረግ በመዘርዘር ስለሚጀምር ነው። ዮሐንስም ንሥር መባሉ 'ዘልዑለ ይሠርር' ይለዋል ከፍ ብሎ የሚበር በመኾኑ።
ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ በመጀመሪያ
ቃል ነበረ ብሎ የመጠቀ አሳብ በማምጣቱ ነው። ማርቆስና ሉቃስም የየራሳቸው ትርጓሜ አላቸው፤ መጣፉን ተመልከተው። እና ዐውድ ማለት ክብ ማለት ነው። የክቡ መኻል የብርሃን መገኛ ምንጭ ነው ጠሐይ ማለት ነው። ጠሐይ ሙቀት አላት ማዶል? ሙቀቱ እንግዲህ
አብ ነው። አካሉ ደሞ ወልድ ነው... ጠሐይ አካል ማዶለች? ብርሃኑ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ጠሐይ ብርሃን እንዳላት ሁሉ። እና እኼን ሁሉ አውቀህና ተረድተህ ነው ሥላሤን መሣል ምትችለው። ደሞም በሥላሤ ራስ ላይ እግረ ፀሐይ ትሥላለኸ፤ የብርሃን ክበብ ነው። ዛዲያ ሥላሤ ብቻ ሳይኾኑ ቅዱሳን ኹሉ እግረ ፀሐይ በአናታቸው ዙሪያ ሳይደረግ
አይሣሉም። ለምን ቢሉ የሥላሤ ብርሃን ያረፈባቸው፤ መንፈስ ቅዱስ የዋጃቸው መኾኑን ማሳያችን፣ ኸጥንት የነበረ ትውፊታችን ነው።”

“ይኸ ራሱ ነገሩን ያከብደዋል።”

“ሥላሤ አንድም ሦስትም ስለሆኑ በተመሳሳይ ምንገድ ይሣላሉ።
በተመሳሳይ ምንገድ መሣላቸው ደሞ ቅድም እንዳልሁህ የፍጹም
አንድነታቸው ማሳያ ነው። ስለዝኸ የተለያዩ ገጥታዎችን አንድ ገጥታ
ሰጥተህ ነው ምትሥላቸው።”

“ተረድቻለሁ።”

“መልካም... ሥላሤን ስትሥል ግራም ቀኝም፣ ኸላይም ኸታችም
እኩል ማረግ አለብህ። ምትሥልበትን ቦታ ጭምር አመጣጥነህ ነው ምትሥል። እነሱ ጉድለት የለባቸውምና ምንም ዓይነት እንከን ሳይኖርባቸው... ምንም ዓይነት ጉድለት ሳታሳይ... ሳታዛንፍ ነው መሣል ያለብህ። አንዱን ከፍ ሌላውን ዝቅ ማረግ አይቻልም። ፊታቸው ላይ
ሚታየውንም ገጥታ አንድ ማረግ ያስፈልጋል። ይኸን ሁሉ ስታውቅ፡
ችሎታህ ሲዳብር ነው፣ ቤተክሲያን ውስጥ መሣል ሚፈቀድልህ።፥

“እህ...”

“አዎ እንደሱ ነው ደንቡ።"

ከዚያ በኋላ፣ ጥላዬ ንባብ ላይ ተጠመደ፡፡ አለቃ ግዕዛን በአስተማሩት ላይ ተጨማሪ ንባብ አደረገ፤ ብራናዎችን አገላበጠ፤ ከሊቃውንት ጋር ተቀምጦ ተወያየ።

አለቃ ግዕዛን ሥላሤን ለመሣል በቂ እውቀት አከማችቷል ብለው
ሲያስቡ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቶ እንዲስል ፈቀዱለት።

የመጨሻዎቹ ቀናት ቤቱ ውስጥ በር ዘግቶ ጾምና ጸሎት ያዘ። ተንበርክኮ፣ “አምላኬ ሆይ፣ ማደርያህ የሆነችው ቤተክርስቲያንህ ውስጥ ገብቸ መዐዛቸው ዕጣን ሳይሆን ወንጌል የሆነውን ሥላሤን መሣያ ግዝዬ ስለደረሰ ጥበብን ስጠኝ። መልካቸውን ግለጥልኝ። አንተ አበርታኝ”ሲል አምላኩን ተማጸነ። በረከት ይሆነው ዘንድ የቅዱሳንን ገድል እንዲሁም ወንጌልን እየደጋገመ አነበበ።

ከሦስት ተከታታይ ሱባኤያት በኋላ፣ እሑድ ቀን ሥጋ ወደሙን
ተቀበለ። ሰኞ ጠዋት፣ ከእንቅልፉ ሲነቃ የፀሐይ ጨረር በበሩ ቀዳዳ
ገብታለች። የረፈደበት መስሎት ሥላሤ ፊት መቅረቢያ ሰዐቱ ስለደረሰ ተጣጠበ። የክት ልብሱን ለብሶ፣ ራሱ ላይ እንደወተት የነጣ ጥምጥም አድርጎ፣ በባዶ ሆዱ፣ ደጅ ሲወጣ ፀሐይቱ ሞቅ ብላለች። ብርሃኗ ዐይን
ያጥበረብራል። ሰማዩ ጥርት ብሏል።

ደስ ደስ አለው። የሰማዩ ጥራት ማረከው። ፀሐይቱና ሰማዩ የዛሬ
ውሎው የተቃና እንደሚሆንለት ቃል ኪዳን የገቡለት መሰለው።
መንፈሱን አበረቱት። በዚያች ቀን በሕይወት መኖሩም አስደሰተው።
አቤቱ አምላኬ! ይችን ቀን ስላሳየኸኝ ከልቤ አመሰግንሀለሁ። የዛሬ
ሥራየንም እንደዝች ጠሐይ የበራ እንደዝኸ ሰማይ የጠራ አድርግልኝ
ኣለ።
👍134
ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲገባ፣ መሬት ላይ ተደፍቶ፣ “አምላኬ
እኔን ኃጢያተኛውን እዝኸ ደረጃ አድርሰህ ሥላሤን እሥል ዘንድ
ስለፈቀድህልኝ ምስጋና ይግባህ” ሲል እየዘመረ ምስጋናውን አቀረበ።

የመመረቂያ ሥራው ብቻ ሳይሆን፣ ሥላሤን ለዘላለም ግርግዳ ላይ
ቀርፆ የሚያስቀምጥበት ሰዐት በመድረሱ ከባድ የሆነ የኃላፊነት ሸክም ተሰማው። የተመደበለት ግርግዳጋ ሲጠጋ እጁ ተንቀጠቀጠ። መንፈሱ
ታወከ። የተረበሸው መንፈሱ እንዲረጋጋለት ተንበርክኮ ድጋሚ ጸሎት አደረገ። ይዞት የመጣው ዕጣን ማጨሻ ላይ የነበረው ፍም ላይ ዕጣን በተን በተን አደረገበት። ጭሱ ሲንቦለቦል መንፈሱም ተንቦለቦለ።ቅጽበቷን በእጁ ለማድረግ በፍጥነት የሥዕል መሣሪያዎቹንና ቀለሞቹን
ከከረጢት ውስጥ አወጣ።
አለቃ ግዕዛን፣ “ሥላሤ ሲሣሉ ቁመታቸው አጠር፣ ዐይኖቻቸው
ጎላ ማለት አለበት። ዐይኖቻቸው ጎላ ሚሉት ለተመልካች የማየትንና
የማስተዋልን ችሎታ እንዲሰጡ ነው። ዐይናቸውም ውስጡ ነጭ
መሆን አለበት። የኃጢያን ዐይኖች ብቻ ናቸው ሚደፈርሱት” ያሉትን
አስታወሰ።

ቀርከሀ አንስቶ ንድፉን ሠራ። እንደጨረሰ፣ ቀርከሀውን ቀለም
ውስጥ ነክሮ ንድፉን ማቅለም ጀመረ። ሙሉ ቀን ውሎ ሲጨርስ፣
የት እንደነበረ እንኳን አያውቅም። ሰመመን ውስጥ ገብቷል። ራሱን
አዙሮታል። ከምጥቀት ወደ ምድር የተመለሰ መሆኑን ለማረጋገጥ
ይመስል መሬት ላይ ተቀመጠ። ፊቱን በእጆቹ ሸፍኖ የሆነውን ሁሉ
ለማወቅ ሞከረ። ቀስ በቀስ ወደ እራሱ ሲመለስ፣ በርግጥም ሌላውን ዓለም ጎብኝቶ የመጣ መሰለው።

ግንባሩን ኩምትር አድርጎ ሥዕሉን ተመለከተ። የዓይናቸው
መጉላት አንገቱን በፍርሐትና በአክብሮት አስደፋው። የፀጉራቸው ንጣት፣ በየሰውነት ከፍላቸው ላይ የተቀቡት ደማቅ ብጫ፣ ቀይና ሰማያዊ ቀለማት ልዩ ስሜት አሳደሩበት። አናታቸው ዙርያ የከበባቸው ወርቃማው የብርሃን አክሊል መስሎ አፍዝ አደንግዝ ሆነበት።

የስቅለትን ሥዕል ሲሠራ ያደረበትን ከባድ ሐዘን፣ ጥልቅ አክብሮት፣ በእዚያ ግዙፍ ተምሳሌት ፊት የተሰማውን የመኮሰስ ስሜት፣ የሰው
ልጅ ሊደርስበት የሚችለውን የመጨረሻውን የጭካኔ ልክ፣ ስለሰዎች ሲል የተሰማውን ሐፍረት፣ የራሱን የእምነት ዕመርታና ሥዕል የሰውን ልጅ ቀልብ ለመሳብና ከቀን ተቀን ሕይወት ውስጥ አውጥቶ ሌላ ዓለም ወስዶ የመመለስ ችሎታውን ያስተዋለውን አስታወሰ።

ዛሬ ከሥላሤ ጋር የመንፈስ አንድነት የፈጠረ፣ እነሱ ያሉበት ረቂቅ ዓለም ውስጥ ተሳታፊ የሆነና፣ ምሥጢራቸውን ሁሉ ያካፈሉትና የተረዳ ብሎም ዘላለማዊ ሕይወት ያገኘ መሰለው።
ተንበርክኮ የምስጋና ጸሎት ኣድርሶ ቀና ሲል ፊቱ በእንባ ርሷል።
ቀርበብ እያለ ወደ ውጭ ሲወጣ፣ እግሩ መሬት አልረግጥለት አለው።አየር ላይ የተንሳፈፈ መሰለው። ደጁ፣ ሰዉ፣ ዛፉና ቅጠሉ ተለወጡበት።
እንደምንም ብሎ ወይራ ዛፍ ሥር ተቀምጦ ዳግም ራሱን ለማረጋጋት
ሞከረ። ምን ያህል እንደቆየ ሳያውቅ ለዓይን ያዝ ሲያደርግ ተነስቶ ቤቱ ሄደ።

እንደገባ፣ ነጠላውን ወርውሮ መደብ ላይ ሲጋደም፣ ድካሙ ያን ጊዜ ታወቀው። ቀኑን ሙሉ ቆሞ ሲሠራ መቆየቱ፣ የነበረበት ተመስጦና የሰሞኑ ጾም ተደማምረው ጉልበቱን ሸርሽረውታል።

እንጎች በሩን ከፍታ ራት ይዛለት ገባች። “ደሕናም አላመሸህ?”
ስትለው፣ ዝም አለ። “ሚበላ ይዠልህ መጥቸ” ስትለው ቀና ብሎ አላያትም፣ ብትሄድለት መረጠ። ደግማ “ራት፣ ይዠልህ መጥቸ” አለችው። አልፈልግም እንደማለት እጁን አራገበላት። ታጥባና ታጥና የመጣችው ኮማሪት ተሸማቀቀች። ሰሞኑን ለምን ሲሸሻት እንደነበረ
ስላላወቀች ግራ ገባት። ዝም ብላ ቆመች።

መቆሟ አበሳጨው። በዐይኑ ስላያት ብቻ ንፅህናው የሚጎድፍ፣ ንፁህ መንፈሱና ሥጋው የሚረክሱ መስሎ ታየው። እንድትወጣለት እጁን
ኣራገበላት።

በኩርፊያ በሩን ዘግታ ወጣች።

መውጣቷን ሲያረጋግጥ እፎይ አለ። ቀለሞቹ ሲደርቁለት ሥዕሉን
እንዴት እንደሚሞሽረው ለማሰብ ሞከረና አልሆንልህ አለው። ጭንቅላቱ ባዶ ሆኖ ተሰማው። እምብዛም ሳይቆይ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደው።.....

ይቀጥላል
👍14🔥3