አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ወየውልሽ ሄዋን እንኳን በአንድ የከረከሰች ቶዮታ አውሮፕላን ብታቀርቢላት አስቻለው ሳይመጣ ክብረ መንግስት አትሄድም ገባሽ ካለ በኋላ በልሁ ቀጠል አድርጎም
«ይህ ለአንቺም ሆነ ላባለ ኪናው የመጨረሻ ማስጠንቀቅያ ነው።» በማለት እግረ መንገዱን በድሉንም ወረፍ አድሮጎት ነበር ለነገሩ በድሉ ምንም አልተናገረም እንጂ አንዲት ቃል ተንፍሶ ቢሆን ኖሮ በልሁ ከዚያው ሊደፍቀው ከጀል አድርጎት ነበር።
«እ..እሺ ነበር ያለችው ሸዋ'ዩ በድንጋጤ ድምጿ እየተቆራረጠ፡፡
በድሉ አሸናፊ ታዲያ ይህን ሁለ ውርደት ተሽክሞ ሲኖር ጠላቱ አደርጎ የሚያስባት ሔዋንን ነው፡፡ ዛሬ ያ ሁሉ መጥፎ ስሜት መጣበትና «ግን በአንቺ የተነሳም ሲደነፋብኝ የምኖር ይመስልሻል?» ሲል ክንዷን ጠበቅ አደረገ ጠየቃት።
«ምን አርጊ ነው የምትለኝ?» አለችው ሔዋን ጮክ ቆጣ ባለ አነጋገር፡፡»
«የምትሰሚ ከሆነ አንድ ነገር ልነግርሽ እፈልጋለሁ::!»
«..ሌላ ጊዜ ትነግረኛለህ፡፡»
«ሌላ ጊዜማ የምነግርሽ ነገር እውነት መሆኑን የምታረጋግጪበት ነው፡፡ ብሎ በድሉ ክንዷን ነቅነቅ እያረጋት ሞኝ አትሁኝ! ኤርትራ የሂደ ሰው
ይመለሳል ብለሽ ወርቃማ ጊዜሽን በከንቱ አታሳልፊ። አላት፡፡

ሔዋን ድንገት ዋ……ይ…..ብላ በረጅሙ ጮኸች፡፡ የመጮኋ ምክንያት ቀድሞ እንዳሰበችው በድሉ እንዲለቃት ብላ
አልነበረም' የአስቻለውን ከኤርትራ ያለ መመለስ ጉዳይ ከተላያዩ ነገሮች ጋር አያይዛው እውነትም ሊቀር እንደሚችል ድንገት ታይቷት ደንግጣና ተሳቃ ነው።
እስቻለሁ ከመዘግየቱ፡ በተጨማሪ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ስለ ሰው ሲያወሩ እገሌ ኤርትራ ዘምቶ ነበር ነገር ግን አለ አይባል ፡ ሞተ አይባል ይኸው ደብዛው ጠፋ
ሲባል ደጋግማ ሰምታለች፡፡ የበድሉ አስተያየት .ከዚህ የመነጨነና እውነትም
እስቻለው እዚያው የሚቀር መስሏት አንጀቷ ተቆርጧ ነው፡፡ በድሉም ጩህቷ አስደንግጦት ወዳያው ለቀቃትና ወደ መኪና በመሮጥ አስነስቶ ተፈተላከ::
ሔዋንም እያለቀሰች በትርፌ ድጋፍ ወደ ቤቷ አመራች፡፡
በልሁና መርዕድ የትርፌንና የሔዋንን የሙዚቃ ምሽት ቆይታ ሊጠይቁና በዚያውም ትንሽ ሊያጫውቷቸው በማሰብ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ሄደው ከቤት ሲገቡ የሔዋንን ስሜት ልውጥውጥ ብሎ አገኙት። ያለቀሰችበት ዐይኗ ሁሉ አባብጧል፡፡ እንዲት ወረቀት በእጇ ጭብጥ አድርጋ ይዛ ትክዝ ብላ ተቀምጣለች ።
«ምነው ሒዩ! ሙዚቃው አስለቃሽ ነበር እንዴ?» ሲል በልሁ ፊትለፊቷ
እንደቆመ ጠየቃት።
«አይ» አለችና ሔዋን እንባዋ በዓይኗ ላይ ግጥም ሲልባት ወደ መሬት አቀረቀረች።
«ምንድነው ችግሩ?» በማለት በልሁ የያዘቻችን ወረቀት ተጠራጠረና ከእጇ ላይ ንጥቅ አድርጎ ሲያያት ያው የአስቻለው የመጀመሪያም የመጨረሻም ደብዳቤ ሆና አገኛት።
«ዛሬም እዛው ነሽ» አላት ቆጣ ብሎ
መርዕድ ደግሞ ወደ ትርፌ ዞር አለና ምን ሆናለች? ሲል ጠይቋት
መልሷን ሲጠብቅ ሄዋን ድንገት ቀደመቻቸው።
«በልሁዬ አታለሉኝ ኤርትራ የሄደ ሰው አይመለስም። በቃ አስቹ
እንደሆን ቀርቷል።»አለችው ቀና ብላ ዓይን ዓይኑን እያያች።ዓይኖቿ በእንባ ተሞልተው ሰማይ መሰሉ።

«ምን።» አለ በልሁ ክው ብሎ በመደንገጥ፡፡
«በቃ አሁን ነገሩ ሁሉ ገብቶኛል። እስቻልው ከኤርትራ አይመጣም፡፡» ብላ ፊቷን በጉልበቷቾ ላይ እስደግፋ ስቅስቅ ብላ ታለቅስ ጀመር፡፡
በልሁ አንድ ነገር ፡ ወለል ብሎ ታየው! የአስቻለሁ ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለና ምናልባትም መመሰስ ባይችል በሔዋን አእምሮ ውስጥ ሊፈጠር የሚችለው አደጋ!!

💫ይቀጥላል💫
👍12
#መሰቀል_እና_መስቀል

“መሰቀል ምንድን ነው?
“መስቀልስ ምንድንነው?

በተሰቀልክ ቁጥር - ከፍ ከፍ ትላለህ
የሚሰቅልህን ሰው - ቁልቁል ታየዋለህ::
(ስትሰቅልም እንደዛው) -
'ስሙ' ድል ቢሆንም ፣ 'ወርቁ ግን ሽንፈት ነው
(የምትሰቅለውን ሰው) -
በሰቀልከው መጠን ፣ ከፍ እያረከው ነው::

🔘ሙሉቀን ሰለሞን🔘
6👍2
#ጣትና_ቅጣት

ብዕር ከወረቀት
ጣትም ከቀለበት
ተስማምተው እያረፉ
ምነው የሚስማሙ
ባለጣቶች ጠፋ

🔘ልዑል ሀይሌ🔘
👍64
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የታቦት አታስገቡም ፍጥጫው ቀጥሏል።
ታቦቷ ባለችበት እንድታድርም መወሰኑ ተነግሯል።

#SHARE_SHARE_SHARE ይደረግ።
አዲስ አበባ ጫፍ ቀራንዮ ወይብላ ማርያም #ኦሮሚያ ክልል
👍4
ጭራሽ...
ደሞ ልብ እንዳለው
ሴት ላፍቀር እላለሁ፤
ደሞ ነፍስ እንዳለው
ቅኖና ፣ንስሐ ፣ምናምን እላለሁ፤

ደሞ ሰማሻቸው?
ለመልኩ ፣ለዐይኑ
ግድ የለውሞ ሲሉ።
ጎኑ ላለ ተድላ፣
ጎኑ ላለ ለቅሶ፣
ጎኑ ላለ እድር፣
ጎኑ ላለ እቁብ፣
የለውም አንዳች ቁብ።
ሲሉ ሰማሻቸው?
ጺሙ በንዠረገግ ፣መሬት ቢዘረጋ፣
እሱ ግድ የለውሞ ፤ አፈር ቢኾን አልጋ።
ሲሉ ሰማሻቸው?
ዝም አትበያቸው፤
“በየትኛው ነፍሱ"
ይሄን ሁሉ ያስብ ፣ብለሽ ጠይቂያቸው።
በየትኛው ነፍሴ ፣ ከትናንቴ ልማር፤
አንቺን አገኝ ብዬ ፣ አስይዢዉ በቁማር።
(አስመልሽው ባክሽ)
ደሞ ልብ እንዳለው
ሴት ላፍቅር እላለሁ፤

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍152
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ምንትዋብ ማረፊያ ክፍሏ ቆይታ ማታ ላይ ራት ከበላች በኋላ፣ በሁለት ደንገጡሮች ታጅባ ወደ አፄ ፋሲል ቤተመንግሥት አቀናች። ደረጃውን ከወጡ በኋላ፣ ሁለት ያደገደጉ ደጅ አጋፋሪዎች መግቢያው በር ላይ ቆመው ለጥ ብለው እጅ ነሥተው መግቢያው ላይ ባለው በወንዶች የግብር አዳራሽ በኩል እንዲሄዱ መሯቸው።

ምንትዋብ ቆም አለች።

የግብር አዳራሹ ወለል ከፋርስ በመጣ ምንጣፍ አሸብርቋል። በክፍሉ ዙርያ ያሉት ባለመስተዋት መስኮቶች በሐር መጋረጃዎች ተሸፍነዋል ::በፋና ወጊዎች የተለኮሱት በየማዕዘኑ የተቀመጡት ትልልቅ ጧፎች
ክፍሉን አድምቀውታል።

ምንትዋብ ባየችው ሁሉ ተማረከች።

ሴቶቹ ግብር አዳራሽ ስትገባ ተመሳሳይ ድምቀት አይታ ሦስተኛ
ደርብ ላይ ወደሚገኘው የንጉሠ ነገሥቱ መኝታ ክፍል ለመግባት ደረጃ ስትወጣ፣ ደንገጡሮቹ እጅ ነሥተዋት ከኋላዋ ተመለሱ።

ደረጃውን ወጥታ ስትጨርስ፣ አፄ በካፋ ቀን አድርገውት የነበረውን
ዘውዳቸውንና ካባቸውን አውልቀው፣ ማምሻ ክፍል ውስጥ፣ ቀይ ከፋይ የለበሰ ሰፊ ወንበር ላይ ተቀምጠዋል። ከፊት ለፊታቸው ያለ ጠረጴዛ ላይ፣ ጠጅ በብርሌ ተቀምጧል። በክፍሉ ጥግ ጥግ የቆሙ፣ ረጃጅም
መቅረዞች ላይ የተቀመጡት ማሾዎች ለክፍሉ ልዩ ውበት ሰጥተውታል።

አፄ በካፋ፣ ምንትዋብ ስትገባ፣ በፈገግታ ተቀብለዋት፣ ከጎናቸው
ያለ ወንበር ላይ እንድትቀመጥ በእጃቸው አሳይዋት። ስትፈራ ስትቸር ተቀመጠች። ዐይናቸውን ማየት አቃታት።

እሳቸው ግን በእዚያ ምትሐታዊ ውበቷ ዳግም ተማርከው ዐይናቸውን ከእሷ ላይ ማንሳት ተስኗቸዋል። ወዲያው ግን መርበትበቷን አስተውለው፣
“አይዞሽ የኔ ዐይናማ፤ ምንም ሚያስፈራ ነገር የለም እኮ” አሏት፣ እጇን እጃቸው ውስጥ አድርገው።

አቀርቅራ ዝም አለች።

“ያረግሽልኝን ሁሉ መቸም አልረሳውም። ኸኪዳነ ምሕረት ጋር አስታመሽ አዳንሽኝ። የልዥ አዋቂ። ኪዳነ ምሕረት ታክብርሽ።
እንዳው ነገሩን ሁሉ ሳጤነው... እዝጊሃር እንድንገናኝ ፈልጎ ነው እንጂ ኸናንተ ቤት ታምሜ መምጣቴ ተጎድቸ ነበር፤ ኪዳነ ምሕረትና ሩፋኤል እንዳንቺ ባለች ዐይናማ ካሱኝ” አሉ፣ በሠርጋቸው ማግስት ስለሞተችው ሚስታቸው አስበው።

ምንትዋብ እጇን እያፍተለተለች ዝም ብላ አዳመጠቻቸው።
በተናገሩት ነገር ልቧ ተነካ። እኛ እንደዛ በወርቅና በዕንቁ ተንቆጥቁጠው፣ሩቅ ይመስሉ የነበሩት ንጉሠ ነገሥት እንደ እሷው ሰው መሰሏት።

“እስቲ ያነን ሚጥም ድምጥሽን አሰሚኝ፤ ተጫወቺ እስቲ። ኸናንተ
ቤት ሳለሁ ላነጋግርሽ እየፈለግሁ ማን መሆኔ እንዳይታወቅ ብየ ዝም አልሁ። ኸኛ ኸደግ አባትሽ ጋር ስንኳ ሳልጫወት ተመለስሁ” አሏት።

የምትለው ጠፋት። በመጨረሻ፣ ቁስቋም ታክብርልኝ። ለዝኽ
ላበቁኝ ለርሶም፤ እሷው ምላሹን ትስጥዎ” አለቻቸው።
“እኔ ምን ለዝኸ አበቃሻለሁ። ሁለተኛ እንዲ ስትይ እንዳልሰማ።
ሚገባሽ ቦታ ነው የመጣሽ። እኼ ደሞ ቤትሽ ነው፤ ቀስ እያልሽ ሁሉን ትማሪያለሽ። ሚቸግርሽ ነገር ሲኖር ሳትፈሪ ንገሪኝ። ደንገጡሮችሽም አሉ። ለኔም ኸንግዲህ ኻንቺ ሌላ ሚቀርበኝ የለም” አሉና ቀስ ብለው
ተነሥተው፣ ቀኝ እጇን ይዘው፣ መኝታ ክፍል ውስጥ ይዘዋት ሲገቡ፣ በአጎበር የተሸፈነውን ተደራራቢ የእንጨትና የጠፍር አልጋ ስታይ፣ ልቧ ተንተረከከ።

ይሁን እንጂ፣ ልጅነቷ ማክተሙን ብቻ ሳይሆን፣ የዚያን ዕለት
የጀመረችው ግንኙት ሕይወቷ የሚጓዝበትን መንገድ ዳግም እንደጠረገ አላስተዋለችም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

“ዕድል ኸሰማይ አይወድቅም።”

ሰኞ ጠዋት ጥላዬና አብርሃ አለቃ ሔኖክ ቤት ሲደርሱ ባለቤትየዋ
ወጥታ ተቀበለቻቸው። ውስጥ ሲገቡ ሰባዎቹ መጀመሪያ ያሉ፣
የግርማቸው፣ የብልኅነታቸውና የደግነታቸው ድባብ የሚያስተጋባ
አዛውንት መደብ ላይ ተቀምጠው ብራና ላይ የተጻፈ ጸሎት ያነባሉ።
የጥምጥማቸው ንጣት አካባቢውን ደመቅ አድርጎታል።

“የዠመሩትን እስቲጨርሱ ነው። ዐረፍ በሉ” አለቻቸው ባለቤቲቱ፣
ከአለቃ ሔኖክ ፊት ለፊት ያለ አጎዛ ጣል የተደረገበት መደብ በእጄ
እያሳየቻቸው።

ጥላዬ፣ አለቃ ሔኖክን በፈገግታ ከላይ እስከታች ተመለከታቸው።
ቀልቡ ወደዳቸው፣ ከእሳቸው ዘንድ ጉዳዩ እንደሚቃናለት አንዳች ነገር ነገረው። ከእሳቸው ሌላ ማንም ባያስተምረው ፈለገ። ቤቱን ሲቃኝ፣ ጥግ ላይ ካለው የጠፍር አልጋ በስተቀር እምብዛም ዕቃ አይታይበትም።ከአልጋው ግርጌ የቀለም ቀንዶች፣ የቀርከሀ ስንጥሮች፣ ብራናና በዕራፊ
ጨርቅ የተጠቀለሉ ዱቄት መሳይ ነገሮች ተቀምጠዋል። ይህንን
እየተመለከተ ሳለ አለቃ ሔኖክ፣ “አድራችሁ ነው ልጆት?” ሲሏቸው
ከአብርሃ እኩል ብድግ ብሎ ለሰላምታቸው የአክብሮት ዐጸፋ መለሰ።

“ምን ፈልጋችሁ ነው?” በሚል ዓይነት ሲያይዋቸው አብርሃ፣ “እሱ
ኸቋራ ነው የዘለቀ። ሥዕል መማር ፈልጋለሁ ቢለኝ ኸርሶ ዘንድ
ይዠው መጣሁ” አላቸው።

“መልካም... ሥዕል ለመሣል ቅኔ መማር አለብህ። ሞካክረኻል?”
“ወፍታ ጊዮርጊስ የንታ አምሳሉ ዘንድ ሥላሤ አድርሽ... ወዲህ
መጣሁ።”
“ሥዕል ሥለህ ታውቃለህ?” አሉት፣ ትክ ብለው እያዩት። ዞር አሉና፣ ምድጃ ላይ ድስት ጥዳ የነበረችውን ባለቤታቸውን፣ “ወርቄ እስቲ ሚቀመስ ታለ፤ ለዛሬ ዕንግዶቻችን ናቸው እኒኸ ተማሮች” አሏት።

ጥላዬ፣ ለጠየቁት ጥያቄ አዎም የለም አልሣልኩምም ማለት ፈለገና አመነታ። ዐይናቸው እሱ ላይ ተተክሎ ሲቀር፣ “ጥቂት ሞካክሬአለሁ፤ ግና ብራና ላይ ማይዶል” አላቸው።

“ዛዲያ ኸምን ላይ ሣልህ?”
ሊናገር ፈልጎ ዐፈረ። እሳቸው መልስ ፈልገው ተጠባበቁ። ያን
ችምችም ያለና ወተት የመሰለ ጥርሱን ብልጭ አደረገና፣ “ግድግዳ
ላይ” አላቸው።
“ግድግዳ ላይ? ግድግዳ ላይ እኮ ማነም ተነሥቶ አይሥልም።”
እንጀራ በድቁስና ጠላ ይዛ የመጣችው ወርቄ ከት ብላ ሳቀች። ያን ጊዜ ሁሉም፣ አለቃ ሔኖክ ጭምር ሳቁ። ጥላዬ፣ ወርቄ ጠላውን መጀመሪያ
ለአለቃ ሔኖክ ከዚያም ለእሱናኸ ለአብርሃ ቀድታ እስክታስቀምጥ
ጠበቀና፣ “ኸቤታችን ግድግዳ ላይ ነው። በእናቴ ወንፊት ዐመድ
እየነፋሁ፣ በውሃ ለቁጨ ሳበቃ ኸቤታችን ዠርባ ግድግዳ ላይ በእናቴጸ አክርማ እሥላለሁ። አባቴ ሲያዩት ይቆጣሉ። ግድግዳውን መልሰው
በጭቃ ያስመርጉታል” አለ።
ወርቄ እንደገና ከት ብላ ሳቀች፤ ሁሉም አብረዋት ሳቁ። ጥቂት
ቆይታ በድቁስ ከቀረበው እንጀራ ላይ ግማሹን ተቃምሰው መተዋቸውን ተመልክታ ለጠላው ማጣጫ በአነስተኛ ጮጮ ላይ ቆሎ ይዛ መጣች።

አለቃን አዘግናቸው እነጥላዬን፣ “እየቆረጠማችሁ” ብላ አስቀምጣላቸው ሄደችው ።
አለቃ ሔኖክ ከዘገኑት ቆሎ ላይ ቆንጠር አድርገው አፋቸው
አደረጉና፣ “ሥዕል መሣልህ ነው ወይስ ግድግዳ ላይ መሣልህ ኣባትህን ሚያስቆጣቸው?” ሲሉ ጠየቁት።

“ወታደር መሆን አለብህ እያሉኝ... ሥዕል እንድሥል አይፈልጉም።
በቅኔውም ቢሆን እንድገፋ አይፈልጉም። እሳቸው እስታሉ ድረስ አገሬ አልመለስም ብየ ጠፍቸ ወዲህ ዘለቅሁ።”

አለቃ ሔኖክ ራሳቸውን ነቀነቁ፣ መሆን የለበትም በሚል ዓይነት።
“ላባትህ መልክትም ቢሆን ላክባቸው። ያዝናሉ። እናትህም ቢሆኑ በልቅሶ ይሞታሉ። ብዙዎቻችን ለትምርት ብለን ጠፍተን ነው ኸቤት ምንወጣ ግና ኋላ እንመለሳለን። አባትህ ላንተ ሌላ ተመኙ፣ ከንተ ደሞ ሌላ ፈለግህ። ክፋት የለውም። ባባትህ ቂም እንዳትይዝ። ለማንኛውም
👍16
ሥዕል መሣል ፈልገህ እዝኸ ድረስ መምጣትህ ለሥዕል ያለህን ፍቅር
ያሳያል። እኔም እንዲህ ያለውን ተማሪ ነው ምወድ።”
“ባባቴስ ቂም አልይዝም። ለግዝየው ሥዕል አላሠራ ቢሉኝ
ተቀየምሁ እንጂ። የንታ ታዛዥዎ ነኝ። ሲያመቸኝ ኸጀ አያቸዋለሁ”
ኣለና ተነሥቶ እጅ ነሣ፡፡
“እንግዲህ ...” አሉት አለቃ ሔኖክ። “ሥዕል ስትሥል ኸየት ዠምረህ ወዴት እንደምትኸድ ማወቅ አለብህ። መዠመሪያ እጅህን ታፍታታለህ።
ኸዚያ በኋላ ዓለማውያንን... ቄሱን፣ መነኩሴውን... የመሳሰሉትን ትሥላለህ። ቀጥለህ ጻድቃንን፣ ኸዚያ ሰማዕታትን ትሥላለህ። እነዝኽ በግብራቸው ቢለያዩም ለባስያነ ሥጋ ወይንም ሰዎች ናቸው። እነዝኽን
ከሣልህ በኋላ መላዕክትን ትሥላለህ። ከዚያም የፍጡራን ሁሉ ፈጣሪ የሆነውንና ለዝች ዓለም ቤዛ ሆኖ የመጣውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ውልደት፣ ሥነ-ስቅለትና ጌታችንን የወለደችልንን ድንግል
ማርያምን ሥዕለ ማርያምን... ትሥላለህ። እመቤታችን ንፁህ ናት።

ለመላዕክት የቀረበች ናት። ከፍታዋም የጌታችን ማደሪያ... ማህደረ መለኮት መሆኗ ነው። ሌላውን ስትደርስበት ትማራለኸ አሁን እጅህን ለማፍታታት በጥቁር ቀለም እኩያኖቹን... እባብ፣ ቁራና ሳጥናኤል የመሳሰሉትን በመሣል ትዥምራለህ።”

“ሳጥናኤልን በጥቁር ቀለም?” አለ ጥላዬ፣ ከተቀመጠበት ተነስቶ፡
“አዎ! ምነው?” አሉት፣ ሊል የፈለገውን ጠርጥረው::
“ትናንት ኸደብረብርሃን ሥላሤ ግቢ ውስጥ ኻንድ መነኩሴ ጋር
ስንጨዋወት፣ ሥዕል መማር ፈልጌ ኸቋራ እንደመጣሁ ነግሬያቸው አሉኝ። አንደኛ ሳጥናኤልም ቢሆን መልዐክ ነበር። መላዕክት ደሞ .
በወሬ በወሬ ጥቁር ስለምን የሳጥናኤል መገለጫ እንደሚሆን አይገባኝም ፍጥረታቸው ኸብርሃንና ኸነፋስ ነው። ብርሃን ነጭ ነው። ነፋስ ደሞ ቀለም የለውም። እሱም ቢሆን ብርሃን ተሸካሚ ነበር። በዝኸ ላይ ደሞ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኸጥቁር ተወልጀ ኸጥቁር አስራ ሁለቱን
ሐዋርያት አመጣለሁ ብሏል እና ጥቁር ስለምን የከሀዲያን... የርኩሳን መገለጫ ይሆናል ሲሉ ነበር።”

አለቃ ሔኖክ ፈገግ አሉ። “እንደሱ ሚሉ አሉ። አየህ ኸጐንደር
ነገሥታት ዘመን ዠምሮ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል፤ ክርክሮችም ተደርገዋል። ከእነዝኸ መኻል አንዱ እኼ ነው። ለማንኛውም አሁን አንተ ሥዕል ልትማር ነው የመጣኸውና እኔ ደሞ ማስተምርህ የተማርሁትን ነው። ደሞስ ነፋስ ቀለም የለውም ያለ ማን ነው? 'እስመ ነፋስ ጸሊም በአርአያሁ' ይል የለምን? የነፋስ መልኩ ጥቁር ነው ማለትም አይደል?”
“ኧረ እኔ እሳቸው ሲሉ ብሰማ እንጂ ምኑን አውቄ!” አለና
ከተቀመጠበት ተነሥቶ፣ “ጥሩ ሠዓሊ ለመሆን ስንት ዓመት ይፈጃል?” ሲል ጠየቃቸው።
“የሰነፍ ተማሪ ጥያቄ ነው ይኸ። ለመጨረስ እሚቻኮል ተማሪ ጥበብ አይዝም። ጥበብ ትዕግስትን ትሻለች። በቀጠሮማ ከቶም አትገኝ።

ለማንኛውም ለዛሬ በእንግድነትህና ኸቋራ እዝኸ ድረስ በመዝለቅህ እነግርሃለሁ። የሥዕል ጥበብ እንደ ተማሪው ትጋት ነው እሚያዝ።
ይልቁንም ወደ ቅኔ ሳይቀርብ አይቀርም ምሳሌው። ቅኔ ማለቂያ
የለውም። እንዲያው መምህሩ ተማሪውን 'አሁንስ ይበቃዎታል፣ ኸኔ ያለውን ምሥጢር ወስደዋል፤ ይኸዱና ያስተምሩ' ብሎ መርቆ ይሰደዋል እንጂ። ተማሪው አልጠገብኩም ካለ ይቆያል፤ አለዚያም እሌላ መምር
ዘንድ ኸዶ ይገባል እንደገና። አስተምራለኹ ካለም ወንበሩን ዘርግቶ በያዘው ጥበብ ያነኑ እያስፋፋ ያስተምራል። ሥዕል ክፍልህ ተኾነና ተግተህም ኸያዝኸው ዋና ዋና ጥበቡን ተሎ ትይዛለህ።”

ትኩር ብለው አዩት። ወደ አብርሃም ዞር ብለው መልሰው ዐይናቸውን ጥላዬ ላይ አሳረፉ።
“አስቀድመህ” አሉት፣ “አስቀድመህ እጅህን እያፍታታህ ንድፍ ትማራለህ። ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብም ዋናው ትምህርትህ ነው። ቅኔ ብቻ ሳይሆን፣ ታሪክና አዕማደ ምሥጢር ማወቅ ይገባል።

የብሉይና የሐዲስ ታሪኮች እንደሐረግ የተሣሠሩ ናቸው፤ የብሉይ ነቢያት ለሐዲስ ሐዋርያት አርአያ ይኾናሉ። ስለዝኽ ነው መጽሐፍ ቅዱስን ሳያውቁ ሥዕል መሣል እማይቻለው።”

ወደ ባለቤታቸው ዞር ብለው፣ “ወርቄ ኸጠላው ቅጅላቸዋ” አሏት።ወርቄ ጠላውን እስክትቀዳ ጠብቀው ስትሄድ፣ “አየህ ልዣ” አሉት ጥላዬን ትኩር ብለው እየተመለከቱት። “ሥዕል መሣል ማለት የአንድን ሥዕል ንድፍ ማወቅና ብራና ላይ አሳምሮ መገልበጥ ብቻ አዶለም።
ብዙ ማወቅ ያለብህ ነገር አለ። ስለምትሥለው ነገር ምሥጢሩን
ማወቅ ያስፈልጋል። ከባዱ ነገርም እኼው ነው። የምትሥለውን ሥዕል
ታሪክ ማወቅም ብቻ ሳይሆን ሥዕሉ ቤተክሲያን ውስጥ የሚሣልበትን ቦታ…. በግራ ይሁን በቀኝ..እ... ሚሣልበትን ቀለም ሁሉ ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል። ምትለውን ሥዕል እንደ ተሣዩ ማንነትና ታሪክ ምትመርጠው ቀለም ይለያያል ማለቴ ነው። ጽፈትህ... አጣጣልህ
እንዴት ነው?”
“የንታ ኣምሳሉ መልካም ነው ይሉኝ ነበር።”
“ማለፊያ።”
አብርሃ፣ ከተቀመጠበት ተነስቶ።
“አለቃ ጥላዬ ማደሪያ የለውም።

ኸደጀሰላም ነው ሚያድር” አለ
“ጥሩ ግዝየ መጥተሃል” አሉት፣ ጥላዬን እያዩ። “ኸኛ ዘንድ ይኖር
የነበረ ተማሪ በቅርቡ ትምርቱን ኸኔ ዘንድ ጨርሶ ወደ ደብረ ወርቅ
ኸዷል። እኔም ባንዳንድ ነገር ሚረዳኝ ሰው ስለምፈልግ በጓሮ አንዲት የተማሪ ጎገር ምታህል ቤት አለችኝ። ኸዛ ትቀመጣለህ። የዕለት ጉርስህን አንነሳህም። ዛሬም ቢሆን ከኛ ዘንድ መጥተህ ማደር ትችላለህ።”

ጥላዬና ኣብርሃ፣ ሊሄዱ ሲነሱ ወርቄ፣ “ወጡ ደርሷል፣ ሳትበሉማ
አትኸዱም” አለቻቸው። ተመልሰው ተቀመጡና ምሳ በልተው፣ አለቃ ሔኖክን እጅ ነሥተው ወርቄን አመስግነው ወጡ።

ጥላዬ፣ ሥዕል የመማር ዕድል ማግኘት ብቻ ሳይሆን፣ ጎኑን ማሳረፊያ ቤት ማግኘቱ አስደሰተው። ዕድል ለመጀመሪያ ጊዜ በእሱ ጎን የቆመች መሰለው። ሕልሙንና ምኞቱን ሊያጨናግፉበት የሞከሩትን አባቱን ይቅር አላቸው። አባቴ እስታሉ አገሬ አልመለስም ያልሁትን ሁሉ እዝጊሃር ይቅር ይበለኝ። እናቴ፡ “ዕርቅ፣ ደም ያደርቅ” ትል የለ? አለቃ ሔኖክም ቢሆኑ ባባቴ ቂም እንዳልይዝ መክረውኛል። እኔም
ቃል እገባለሁ። አባቴ ባሉበት ደሕና ይሁኑ። እዝጊሃር ያለ ቀን ኸጀ አያቸዋለሁ አለ፣ ለራሱ።
የኔና የወለቴ ነገር ገና ሳንወለድ ተጥፎ የተቀመጠ ይመስለኝ ነበር።

የእዝጊሃር ነገር ይገርመኛል። ባንድ እጁ ሰጥቶ በሌላው ይነጥቃል።
ወለቴን ለሌላ ሰጥቶ ለኔ ሥዕል ሰጠኝ። ሁለቱንም ቢሰጠኝ ይከብደው ኑሯል? ወይስ ዕጣ ፈንታዬ ወለቴ ሳትሆን ሥዕል ብቻ ኑሯል?
ኸዝጊሃር አልጣላ መቸም። ለነገሩ ነው እንጂ እኔ እንደ ንጉሥ ላኖራት
አልችል። ለማንኛውም እሱ ባለቤቱ ያውቃል፤ ምስጋና ይግባው።

ጐንደርም ትባረክ! ዕድል ተርታየን አበጃጀችልኝ፡ እንደኔ ያሉት
መጥተው አይፈሩባት ሲል አሰላሰለ።

ከሐሳቡ ሲመለስ አብርሃ ከጎኑ ይራመዳል። “በደስታ አሳብ ይዞኝ
ጭልጥ አለ” አለው።

“አይቸህ እኮ ነው ዝም ያልሁት። ደካክሜአለሁ ይበቃኛል ሲሉ
የነበሩት የንታ አንተን ሳያቅማሙ ተቀበሉህ። ኣንዳች ያዩብህ ተስፋ
አለ። መምህራን እንዲህ በአንድ ቀን ትምህርቱንም ማደሪያውንም
ቀለቡንም እሰጥሃለሁ አይሉም፤ እንዲያው አንዳች ብርቱ ሆሳዕና
ይዘሃል መሰለኝ” ሲል ቀለደ።

“አየ! ትምህርቱን በውል ሳልይዘው መድኃኒቱንና አስማቱን በየት ደርሼበት ብለኽ? ሆሳዕና ለእንደኔ ላለው ማን ያሳያል ብለኽ ነው? ባይኾን ያንተ ሆሳዕና ሳይኾን ይቀራል እንዲኽ ግንባር የሰጠኝ?” ሲል ቀልዱን በቀልድና በምር አዋዝቶ መለሰ ጥላዬ።
👍7
“አረ ቆይ እስቲ፤ እንዲያው ቀልዱ ይቈየንና አለቃ ኻሉት ውስጥ
የገረመኝ እጅህን ምታፍታታው ክፉ ክፉውን በመሣል ነው ያሉት
ነው። ለመሆኑ ሳጥናኤልን እንዴት አርገህ ልትሥለው ነው? መክሥተ
ኣጋንንት ልትደግም?” አለ አብርሃ “መክሥተ አጋንንት ልትደግም”
የሚለው አባባሉ ራሱን ሳይቀር እያሳቀው።

“በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ! የምን መክሥተ አጋንንት
አመጣህብኝ ወንድሜ! እንዲያው ክፉ ሰው አስመስየ ቁጭ አላረገውም እንዴ! ዐይኑን ያጐረጠ፣ ገባሮውን እንደ ቀንድ ያሾለ፣ ጥርሱን እንደካራ የሳለ አድርጌ ብሥለው ማንነቱ ግልጥ ነው። እንግዲያማ እሱን በድግምት በዐይነ ሥጋ አይቼ ብሥለው ሚካኤልን በምን ላየው
ነው? ከቶስ ሥላሴን በምን አስማት ላያቸው እችላለሁ? ሥዕል ግብርን እንጂ መልክን ሚከተል አይመስለኝም። እደብረብርሃን ሥላሤ ውስጥ ያየኋቸው ድንቅ ሥዕሎች ቅዱሳኑንም ሆነ ርኩሳኑን በዐይነ ሥጋ በተመለከቱ ሠዓሊያን አይደለም የተሣሉ። ቅድም የንታ እንዳሉት ታሪካቸውን፣ ገድላቸውን፣ ተአምራታቸውን ወይም እኩይ ግብራቸውን ባነበቡ ሠዓሊያን እንጂ' ብሎ ያንን እየቆጠበ የሚሰጠውን ፈገግታውን
አሳየው።

አብርሃ ተፍለቀለቀ። “ድንቅ ብለኻል፤ መምሩ ዛዲያ ምን ሊነግሩህ ሰይጣንን ስትሥለው ቁመቱን ኣለቅጥ ረዥም አርገው። ሰይጣን ከሀዲ ነው በል ይኸን ኹሉ ኻወቅህ?” አለና ቀልዱን በመቀጠል፣ “ለማንኛውም
ነው፣ እባብ አሳሳች ነው... ቁራ ምንድር ነው?” ሲል ጠየቀው።
“ሚመስለኝ ያው ቁራ አይታመንም። ተልኮ ሳይመለስ የቀረ በዋል ፈሰስ ማዶል?”
“ውነትህን ነው። እስቲ ጃን ተከል ወረድ ብለን ጥቂት ወሬ
እንቀላውጥና እኔም ወደ ቅኔየ ልኸድ።”
ጥላዬ ግን መሄድ አልፈለገም። የሰሞኑ ወሬ የምንትዋብ መምጣት በመሆኑ ሰምቶ ልቡን እንደገና ማድማት አልታየውም። ግን ደግሞ ያን ሁሉ ውለታ የዋለለትን አብርሃን ማስቀየም አልፈለገም።.....

ይቀጥላል
👍11
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሶስት ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ....ምንትዋብ ማረፊያ ክፍሏ ቆይታ ማታ ላይ ራት ከበላች በኋላ፣ በሁለት ደንገጡሮች ታጅባ ወደ አፄ ፋሲል ቤተመንግሥት አቀናች። ደረጃውን ከወጡ በኋላ፣ ሁለት ያደገደጉ ደጅ አጋፋሪዎች መግቢያው በር ላይ ቆመው ለጥ ብለው እጅ ነሥተው መግቢያው ላይ ባለው በወንዶች የግብር አዳራሽ በኩል እንዲሄዱ መሯቸው። ምንትዋብ ቆም አለች። …»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...የሰሜን ኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ድምፁ እየበረከት ሄደ። ተፋላሚ ወገኖች ዜናቸው ሁሉ የሞት ሆነ፡፡ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ገዢነት መወዳደሪያው በገደሉት ሰው ቁጥር እንዲሆን የተወሰነ ይመስል የአንዱ ወገን ራድዮ
"አንድ ሺ ገደልኩ"ካለ ሌላው ወገን ማታ ላይ "ሁለት ሺ ገደልኩ ይላል፡፡" በየቀኑ እንዲሁ ይቀጥላል፡፡ የሚገለፀው የሟች ቁጥሩ ከዕለት ወደ ዕለት እየበዛ ሄደ መንግስት በሁለት ግንባር ሰርጐ ገቦችን ደመሰስኩ» ሲል አማፂያን ደግሞ አራት
ቦታዎችን ከፋሽስት የጭቆና አገዛዝ ነፃ አወጣን ይላሉ። በየቀኑ ተመሳሳይ ወሬ ሀገሪቱ ምድሯ ብቻ ሳይሆን እየራም በደም ተለወሱ። በመግደል ውድድር
በመገዳደል ዜና! በመጨራረስ አባዜ።
የሀገራቸውን እውነተኛ ዜና መዋዕል በራሳቸው ሀገር የዜና አውታሮች ለመስማት ያልታደሉ ኢትዮጵያውያን ሁለቱንም ወገኖች አያምኑም፤ የውጭ ራዲዮዎችን መጐርጐር ግድ ብሏቸዋል። እነዚያም ቢሆኑ አንዳንዴ መንግስት እንዲህ ይላል፣አማፂያን ደግሞ እንዲያ… ነገር ግን በገለልተኛ ወገን አልተረጋገጠም
ይሉና የሕዝብ ልብ ያንጠለጥላሉ፡፡
አንድ ነገር ብቻ ግልጽ ነው፤ በሰሜናዊ የሐገሪቱ ክፍል በየቀኑ ጦርነት አለ። በየቀኑ መድፍና መትረየስ ይተኮሳል፡፡ በየቀኑ ሰው ይሞታል። በየቀኑ ሀገር
ትደማለች:: በየቀኑ ንብረት ይወድማል። ከቀን ወደ ቀን አንጡራ ሀብቷ ይቀንሳል። በየቀኑ የህዝብ ስቃይ አለ። በየቀኑ ዋይታና ጩኸት አለ፡፡
የአስቻለው ትዝታ ለዲላ የፍቅር ቤተሰቦቹ የሚደርስው በዚሁ የሰቆቃ ሽቴ እየተላወሰ መሆን ከጀመረ ሰነበተ ስጋትና ፍርሀት በሁሉም ልብ ማደር ጀመረ።
የጦርነት ወይም የሞት ዜና በተሰማሩበት ቁጥር አስቻለው በሁሉም አዕምሮ ውስጥ ብቅ
ድቅን ማለቱን ቀጠለ። ይፈሩ ጀመር:: ይጨነቁ ጀመር፡፡
ችግሩ በሔዋን ላይ ጠነከረ። ሳትወድ በግድ ራድዮ ጉርጓሪ ሆነች፡፡የምትሰማው ዜና ሁሉ ያስደነብራት ጀመር፡፡ በሆነ ቁጥር ሰው ሞተ ከተባለ ከንዱ አስቻለው እንደሆነ ታስብ ጀመር፡፡ ለእሷ አስቻለው ትናንት ሞቷል፡፡ ዛሬም
ይሞታል፡፡ ነገም እንዲሁ:: ልቧ በፍርሀትና በስጋት ቆሰለ። አንጀቷ በሀዘን ይታጠፍ ጀመር፡፡ ዓይኗ እንባ ከላቋርጥ አለ። በሀሳብ ብዛት የቀን ዕረፍትና የሌሊት
እንቅልፍ አጣች። ለራሷ ሰላም አጥታ ሌሎችንም ሰላም ነሳች፡፡ በሁሉም ዘንድ ወለሌ ሆነ፡፡
በእንቅርት ላይ እንዲሉ ልክ ሚያዚያ ወር መጨረሻ ላይ ከዲላ
ሆስፒታል አካባቢ አስደንጋጭ ወሬ ተሰማ:: የአስቻለው ደሞዝ ተቋረጠ፡፡ በልሁ በውክልናው መሰረት አስቻለው ኤርትራ ከሄደ ጀምሮ ሲቆጠር የአስረኛ ወር
ደመወዙን ሊቀበል ሲሄድ ገንዘብ በእጁ ሳይሆን ለጆሮው መጥፎ ዜና ሰጥተው መለሱት በተላለፈልን ስርኩላር መሰረት ደሞዙ እንዳይከፈል ተብሏል የሚል።
በልሁ ምክንያቱን ለማወቅ አጥብቆ ጠይቆ ነበር፣ ነገር ግን የተሰጠው ምላሽ የመጀመሪያው ደብዳቤ ከአስመራ ሊሆን እንደሚችልና ከዚያ ለዋናው መስሪያ ቤት፤ ቀጥሎ ለሲዳሞ ክፍለ ሀገር እንደገና ለአውራጃው ከዚያም ለዲላ ሆስፒታል ሲተላለፍ አንዱ ለሌላው ላይ ተመስርቶ ሲጽፍ ሲፃፃፍ የታገደበት ምክንያት አንዱ ጋር ተዘንግቶ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ከመግለፅ በቀር እቅጩን
አልነገሩትም፡፡ አንድ ነገር ብቻ በግልጽ ነገሩት፤ ከእንግዲህ በአስቻለው ስም ደመወዝ ወጪ ሊደረግ እንደማይችልህ! በልሁ መርዶውን ይዞ ተመለሰ:: ዜናው
ከታፈሡም ከመርዕድም ጆሮ ደረሰ፡፡ የአስቻለው ነገር ከዕለት ዕለት እየራቀ ሄደ።
ይህን ዜና ለሔዋን እንዴት አድርገው ይንገሯት? ዝም አይል ነገር የአስቻለው ደመወዝ የሕልውናዋ መስረት ነው። አይነግሯት ነገር ትሳቀቃለች ብለው ፈሩ።በእርግጥም'' እንደ ቁስል ፈሯት:: የዚያኑ ያህል ታሳዝናቸው ጀመር። ለቀናት ያህል
በሃሳብ ሲታመሱ ሰንብተው ሁሉም ለበጉ ነው የሚለውን ኢትዮጵያዊ ብሂል ለመጠቀም ወሰኑ። ደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ፡ የአስቻለው ደሞዝ ተቋረጠ። ይህ
የሚያመለክተው የአስቻለውን በሕይወት መኖር ነው፡፡ ነገር ግን የመንግስት ሥራ ለቋል ማለቴ ነው
በሕይወትህ ባይኖር ኖሮ ጡረታ ወይም ዳረጎት ውሰዱ እንባል ነበር። አስቻለው ዱሮም የከፋው ሰው ነበርና በአስብ ወይም በምጽዋ በኩል ደብዳቤውም በቅርቡ እንደሚደርስን እናምናለን፡፡ ማን ያውቃል? አንቺንም ሊወስድሸ ይችላል፡፡” እያሉ ሊያጽናኗት ተመካከሩ። ቀና ሲታጣ... እንዲሉ ምርጫቸው
ይኸው ብቻ ሆነ፡፡ ይህን ለመፈጸም በግንቦት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ ቅዳሜን
መረጡ፣ ሁለም ተሰብስበው በሔዋን ቤት ለመዋልና እየተረዳዱ
የሔዋንን ልብ ሊያደነቁሩ።
በዕለቱ ታፈሡ ከሁሉም ቀድማ ከሔዋን ቤት ስትደርስ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ተኩል አካባቢ ሆኗል፡፡ በትልቅ ሳህን ለሁሉም የሚበቃ ምግብ ይዛለች፡፡ ለራሷ
የነጭና የጥቁር ቡራቡሬ ድሪያዋን ለብሳ፣ እዝን አትለው አክፋይ ለሔዋን ደግሞ ለየት ያለች ስክርፍ ገዝታለች፤ ለስጦታ።
ቀጥሎ የደረሰው መርዕድ ነው አውሎ ላያስመሽ የሚችል ምርጥ የጫት ቅጠል ይዞ። የሐረሩ ልጅ መርዕድ የጫት ሥነ ስርዓቱን ያወቅበታልና ሁሉን ነገር
ወዲያው አመቻቸው:: በእሱ አመራር ሰጪነት ሰንደሉ ተሰኮሰ፡ እጣኑ ተጨሰ፡፡ቡናውም በብረት ምጣድ ላይ ይንቸሰቸስ ጀመር። የቤቱ መዓዛ ሙሉ በሙሉ
ተለወጠ። ሥነ ሥርዓቱን ለመጀመር የበልሁ መድረስ ብቻ ይጠብቅ ጀመር፡፡ የጫት
መቃም ልምድም ሆነ ሱስ የሌላት ታፈሡ ያለ ወትሮዋ በመሀል ፍራሽ ላይ ሙሽራ መስላ በመቀመጥ ቤቱን በቀልድና በጨዋታ
ሞልታ በሳቅ እያፍለቀለቀችው ሳለች ድንገት ከውጭ በኩል የሰው ድምጽ ተሰማ:: የሴት
ልጅ ጥሪ ይመስላል፡፡ ሔዋን ቡና እየቆላች ስለነበር ትርፌ ወደ ውጭ ወጣ አለች፡፡
የውጭው በር ላይ አንዲት የአሥራ ሁለት ወይም የአስራ ሶስት ዓመት ዕድሜ ያላት ልጅ ቆማ አየችና ወደ እሷ ተጠጋች፡፡
ከልጅቷ አጠገብ ደርሳ አንገቷን
ከውጭ በር ወጣ አድርጋ ስትመለከት ደግሞ ከልጅቷ ጋር አንዲት በዕድሜ ጠና ያሉ ሴት ቆመው አየች፡፡ ሴትዮዋ ጠይም ናቸው፡፡ የባላገር ሴት ይመስላሉ፡፡
የነጭና አረንጓዴ ቡራቡሬ ቀሚስ ቀነጭ ነጠላ ለብሰዋል። ሳሳ ያለች ሸራ ጫማ አድርገዋል፡፡ ፀጉራቸውን በነጭ ሻሽ ግጥም አድርገው አስረዋል፡፡ እጆቻቸውን
በነጠላቸው ውስጥ አድርገው ወገባቸው ላይ አጣምረው ቆመዋል፡፡
«ምነው?ማንን ፈለጋችሁ?» ስትል ትርፌ ልጅቷንም ሴትየዋንም ተራ
በተራ እያየች ጠየቀቻቸው፡፡
«ሔዋን የምትባል ልጅ እዚህ ቤት ውስጥ ናት?» ስትል ልጅቷ ትርፌን ጠየቀቻት።
«ግን ምነው?" አለች ትርፌ ደንገጥ እንደ ማለት እያለች።
«እስቲ ብቅ በይ በያት»
ትርፌ ግራ ገባ እያላትም ቢሆን ወደ ቤት ተመለሰችና እታለም! አንዲት ልጅና እንድ ተለቅ ያሉ ሴት ይፈልጉሻል፡፡» አለቻት፡፡ ሔዋን ደንገጥ ብላ ቀና በማለት ትርፌን በመመልከት ላይ ሳለች ታፈሡ ቀድማ«ምን አይነት ሴት እማማ ዘነብ ይሆኑ እንዴ?» ስትል ጠየቀች።
«እኔ እንጃ! ብላ ሔዋን ወደ ውጭ አመራቻ፡፡
ወዲያውኑ ልብ የሚሰነጥቅ ጩኸት ተሰማ:: የሔዋን ድምጽ ስለመሆኑ ሁሉም አልተጠራጠሩም። ታፈሡ መርድና ትርፌም በቅጽበት በመነሳት ወደ ውጭ ሮጡ፡፡ ሔዋን የሆነችውን ነገር ሳያውቁ ነገር ግን «ሔዋን አይዞሽ ሔዋን አይዞሽ! እያሉ በመጯጯሁ አጠገቧ ደረሱ
👍8🔥1
ከደረሱ በኋላ እኳ እየተከናወነ ያለውን ነገር በቶሎ ለመለየት ተሳናቸው። ሔዋን በሴትየዋ እግር ላይ ወድቃ እየተንፈራፈረች እማ…! እማዬ! እማይዩ-l በማለት
ትጮሀለች፡፡ ሴትዮዋም በሔዋን ጀርባ ላይ እንገታቸውን አንተርሰው ልጄ እሙ እመዪ!» ይላሉ። የእናትና ልጅ ናፍቆት የፈጠረው ድንገተኛ ትርምስ ኖሯል፡፡
ታፈሡ ፈጥና ወደ ትንቅንቁ በመግባት የእረ ምንድነው? ኧረ እባካችሁ እያለች የሔዋንን እናት ሔዋን ጀርባ ላይ ለማንሳት ስትታገል መርዕድ ደግሞ ሔዋንን
ከአናቷ እግር ላይ ለማንሳት ይፍጨረጨር ጀመር። ትርፌ ግራ ገብቷት ቆማ እናቷ ነኝ ልጆች! እስቲ እሷን እንሶልኝ! እረ እስቲ በርቱልኝ» አሉ ሴትዮዋ እንባቸውን እያዘሩ። ሔዋን እግራቸው ላይ ተጠምጥማ ስትጮህ
ታፈሡና መርዕድ ቀና ሊያደርጓት ሲሞክሩ በልሁ ድንገት ደረሰ፡፡
«ምንድነው ታፈሥ ምንድነው መርዕድ?» አላቸው ድንገጥ ብሎ ዓይኑን ወዲያ ወዲህ እያማተረ።
«ሔዋንን አንሳልን በልሁ። እናቷ ናቸው። ቶሎ በል!» አለችው ታፈሡ ሔዋንን ከእናቷ እግር ለማንሳት እየታገለች።
እጅሬ በልሁ ታፈሡንም መርዕድንም ገፈታትሮ ብቻውን ጐንበስ በማለት ሔዋንን ከእናቷ እግር ላይ ፈልቅቆ አነሳት፡፡ ሔዋን ግን ወዲያው ቀሚሳቸውን
ሙጥኝ አለች:: አሁንም «እማ! እማዬ እማይዬ! በማለት ማልቀሷን ቀጠለች እናቷም «አይዞሽ ልጄ! አይዞሽ እሙዬ!» እያለ እንደ ልጃቸው ያለቅሱ ጀመር።
ሔዋንና እናቷ እንደተነፋፈቁ እናትና ልጅ ሳይሆን በሙጫ እንደተጣበቁ ወረቀቶች ተያያዘው በበልሁና በታፈሡ ግፊት ወደ ቤት ገቡ፡፡ ፍራሽ ላይ ከተቀመጡም በኋላ አንገት ለአንገት ተያይዘው በለቅሶ ይንፈቀፈቁ ጀመር፡፡ ታፈሡ
በልሁና መርዕድ ክፊትለፊታቸው ቆመው ቢለምኗቸውም ቶሎ እሺ አላሉም፡፡በርካታ ደቂቃዎች አለፉ ልጅ እናቱን መውደድ፣ እናት ለልጅዋ መሳሳት እንኩዋንስ በሰው ልጅ በእንስሳትም ዘንድ የታወቀ ነው፤ የሔዋንና የእናቷ ሁኔታ ግን ከተለመደው መጠን በላይ ሆኖ ሲታይ እጀግ ያሳዝን ነበር፡፡ ታፈሡ ወድያው ወደ ፍራሹ ጎንበስ አለችና መርእድ በላስቲክ ጠቅልሎ ለቅሞሽ ያዘጋጀውን
ጫት አቅልሎ አድርጋ በማንሳት ወደ ጓዳ ይዛው ገባች፡፡ ጫቱን አስቀምጣ እንደገና ምልስ አለችና በልሁና መርዕድን በዓይኗ እየጠቀሰኝ ወደ ውጭ ወጣች፡፡ እነሱም ፈጥነው ተከተሏት።
«ምን እናድርግ?» ስትል ጠየቀቻቸው።
በልሁም መርዕድም “ምን ይሻላል? እንዴት እናድርግ የሚል ጥያቄ አከታተሉ። የመጨረሻ ውሳኔያቸው ለሔዋን እናት መስተንግዶ መጣደፍ ነበር፡፡
በዚሁ መሰረት በልሁና መርዕድ ሥጋ እና የመጠጥ ዓይነቶችን ሊገዛዙ ወደ ከተማ ሮጡ፡፡ ታፈሡ ወደ ቤት በመመለስ፡-
«ትርፌ» ስትል ጠራቻት።
«አቤት»
«በርካት አድርገሽ ቡና ቁይ አለቻትና ከሔዋን አጠገብ ፍራሿ ላይ ቁጭ አለች በዚያ ሰዓት ሔዋንና እናቷ ከለቁሷቸው ትንሽ በረድ እያሉ ናቸው፡፡እንባቸው ከዓይናቸው ላይ መፍሰሱን ባያቆምም ከመርገብገቡ ቀዝቀዝ እያሉ ሄዱ ታፈሡ በጨዋታ አሳብባ ስሜታቸውን ለመቀየር አስባ «እንደው ሳይታሰቡ ከየት ብቅ አሉ የእኔ እናት?» ስትል የሔዋንን እናትና ጠየቀቻቸው፡፡
«ምን ላድርግ ብለሽ ነው የእኔ ልጅ፣ ባዳምጥ ባዳምጥ የልጆቼ ድምጥ ጥፍትት አለብኝ፡፡ ባለፈው ክረምት ይመጣሉ ብዬ ስጠብቅ ቅርት እሉ፡፡ በጋውም ይኸው አለቀ፡፡ ሆዴ አልችል ቢለኝ መጣኋኮ አሏት በነጠላቸው ጫፍ ዓይንና አፍንጫቸውን አየጠረጉ።
«ሸዋዬ ደብዳቤ እትጽፍም ነበር?»
«ኧረ እሷ እቲ!»
«አንድ ጊዜ እንኳ?»
«በፍጡም!» አሉ የሔዋን እናት፡፡ በዚህ ጊዜ ሔዋን ባልጋለች በማለት ሸዋዬ የፃፈችው ደብዳቢ ትዝ ብሏቸው ሳይሆን አይቀርም ታፈሡና ሔዋን ተያዩ፡፡
«ለመሆኑ መቼ መጡ?» ስትል ታፈሡ እንደገና ጠየቀቻቸው።
«ትናንት ማታ» አሉና «አንድ አስተማሪ ነኝ ያለ የተባረከ ልጅ የሸዋዬን ቤት አሳይቶኝ እሷ ጋር አደርኩ፡፡»
«እዚህስ ማን አደረሰዎት?»
የሔዋን እናት እንዳጎነበሱ በረጅሙ ተነፈሱና «እንደ አደራረሴ ደረስኩ የኔ ልጅ፣ አይደረስ የለም፡፡» አሏት እዝን ትክዝ ባለ አነጋገር።
ታፈሡ አኳኋናቸውን ልብ ብላ ስታጤን ቆየችና የሔዋን እናት አንድ ደስ የማይል ስሜት በውስጣቸው እንዳለ ተረዳች። ከሔዋን ዙሪያ የማያልፍ መሆኑን
በመገንዘብ ቆረቆራት።ጠይቃ ለመረዳት ስትል “ሔለንን ከሸዋዬ ቤት ሲያጧት ምን ተሰማዎት እማማ?» ስትል ፈገግ ብላ እያየች ጠየቀቻቸው፡፡ በዚያው ሔዋንንም
ሰለል አደረገቻት፡፡ ሔዋን አሁንም በእናቷ ላይ ልጥፍ ብላ እንባዋን ታንቆረቁራለች፡፡
«የእሷንማ ነገር እዚያው አገሬ ሆኜ ሆዴ ነግሮኝ የለ ልጄ፣ ቀድሞም
ተረድቸዋለሁ::አሉና አገጫቸውን በመዳፋቸው ደግፈው ትክዝ አሉ፡፡ ትናንት ማታ ከሸዋዬ ቤት ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ ዛሬ ሔዋን ከአለችበት ቦታ እስከመቼ ደረሱበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሁኔታ በዓይነ ሕሊናቸው ይቃኙት ጀመር።

ልክ እንደ ሔዋን የእናቷ መምጣት
ለሸዋዬም ዱብ እዳ ነበር የሆነባት ስታያቸው ደንግጣ እቅፍ አድርጋ በመሳም በናፍቆት ነበር የተቀበለቻቸው በአክብሮት ጋብዛ ነበር ያስቀመጠቻቸው። ነገር መበላሸት የጀመረው ግን እናቷ ስለ ሔዋን መጠየቅ ሲጀምሩ ነው።
«እሙዬስ የሸዋ?» ሲሉ ነበር የጠየቋት ወድያውኑ እንደተቀመጡ «እሙዬ» የሔዋን የቤት ስሟ ነው «የሸዋ» ደግሞ የሸዋዬ የቁልምጫ መጠሪያ፡፡
«ትመጣለች::» አለቻቸው ሸዋዬ ነገሩን ቀለል አድርጋ፡
የሔዋን እናት ከሸዋዬ ቤት የደረሱት ከአመሻሹ አሥር ሰዓት አካባቢ ነው።ሔዋን ገና እየተማረች መስሏቸው የተማሪዎችን መውጫ ሰዓት ሲጠባበቁ ቆዩ፡፡ነገር ግን እየመሸ ሄደ፡፡ ሔዋን ደግሞ ብቅ አልል አለች። የሔዋን እናት አሁንም
«ይቺ ልጅ ምነው ቀረች የሸዋ?» ሲሉ ጠየቋት።
«ትመጣለች አልኩሽ እኮ» የሸዋዩ አነጋገር ግልምጫ ጭምር ነበር።
አሁንም በጣም መሽ፡፡ ለዓይን ያዘና መብራት በራ። ሸዋዬ ለእናቷ
እንግድነት ቶሎ ቶሎ የሰራችው ወጥ እንደ ደረስ ራት ልታቀርብ
ማስታጠቢያ ይዛ ወደ እናቷ ቀረበች፡፡
«እምዬ ሳትመጣ የሸዋ?»
«ያደረች እንደሆነ ጾምሽን ታድሪያለሽ?»
«እርቃ ነው እንዴ የሄደችው?
ማን ያውቃል? እሷ ራሷ እንደ ልቧ አዳሪ!»
የሔዋን እናት ግራ እየገባቸው ሄደ። እንጀራው ሬት ሬት እያላቸው
ራታቸውን በሉ:: ልባቸው ግን ለሔዋን ተሰቀለ። የሆነችውን ማወቅ አልቻለምና ናፍቆቱ ስጋቱ፣ ጭንቀቱ ሁሉ መንፈሳቸውን አመሰቃቀለው፡- ቆየት ብሎ መኝታ
ሲነጣጠፍላቸው አዩ። ቢያንስ ለዛሬ ሔዋንን ሊያዩዋት እንደማይችሉ አውቀው ።
ደግሞ እንደው ለምናልባቱ በማለት፡
«እሙዬ ማደሯ ነው የሸዋ» ሲሉ ሸዋዬን ጠየቋት፡
«ጠዋት እንፈልጋታለን፡፡»
የሔዋን እናት ሆዳቸው ቅይም አለ። ንዴትም ተሰማቸው፡፡ ግን መታገስ ነበረባቸውና የሆዳቸውን በሆዳቸው አድርገው ለስለስ ባለ አነጋገር፡፡
ምናለ የሸዋ፣ ልጄ የሆነችው ነገር ታለ ነግረሽኝ ቁርጤን ባውቀው
አሏት ዓይናቸውን በሽዋዬ ላይ እያንከራተቱ፡፡
ምን ትሆናለች ብለሽ ሰጋሽ አንቺ?»
«ለምን አልስጋ ልጄ፣ ኧረ ጭንቅ አለኝ የሸዋ!»
«ቁርጡን ልንገርሽ! እሷ እናት፣ እህት፣ ወንድም…. የሚባል ነገር ትታለች:: ሕይወቷን በአሻት መንገድ እየመራች ነው:: ነገ አለችበት ድረስ ትሄጃለሽ: እስከዚያ ድረስ እትጨቅጭቂኝ:: በቃ!» አለቻቸው ሸዋዬ ምንጭቅጭቅ እያለች። የሔዋን እናት አንጀታቸው የባሰውነ ቁርጥ አለ። ቢያንስ ቢያንስ ሁለቱ
👍121
ልጆቻቸው እንደተጣሉ ገባቸው፡፡ ልባቸው ተከፋ፡፡ በተዘጋጀላቸው መኝታ ላይ ልክ እንዳኮረፈ ሰው ኩርምት ብለው ተኙ:: የረባ እንቅልፍ ሳይወስዳቸው በየመሀሉ
እየባነኑ ያ ሌሊት አልቆ በቀን ተተካና ሰማይና ምድር ተላቀቁ፡፡ እየረፈደ ሄደ፡፡ቀኑም ተዳረስ፡፡ ስለ ሄዋን መጠየቃቸውን አቁመው የሽዋዩን እንቅስቃሴ ብቻ ሲጠባበቁ ቆዩ ።
ወደ ሰባት ሰዓት ተኩል አካባቢ ሸዋዪ ከቤት ወጣ ብላ ጥቂት ከቆየች በኋላ አንዲት ኮረዳ ቢጤ ይዛ ተመለሰች፡፡ ልጅቷን ይዛ ፊትለፊታቸው በመቆም «ከዚች
ልጅ ጋር ሂዱ! የልጀሸን ቤት ታሳይሻለች፡፡" አለቻቸው፡፡
የሔዋን እናት «ጎሽ ልጄ እሰይ!» በማለት ሽዋዬን እያመሰገኑ ብድግ አሉ።ሔዋንን እሰሰከዛ ሰአት ድረስ ማየት ባለመቻላቸው ግን አንጀታቸው አርሯል። ከዚያ በኋላ ልጅቷ እፊት እፊት እየመራች ወደ ሔዋን ቤት ወሰዳቸው ነው ልጅ
የልጃቸውን ያህል የሳቸውም ሆድ ባብቶ ያን ያህል ያነቡት።
ይህ ሁሉ ስሜት አሁንም በፊታቸው ላይ ይነበባልና ታፈሡ «ምነው እማዬ»ደስ ያለዎት አይመስሉኝም። የተቀየመብት ነገር ያለ ይመስላል?» ስትል ጠየቀቻቸው።
የሔዋን እናት አሁንም እጎንብሰው ግንባራቸውን እያሻሹ ቢከፋኝስየት
የት ልደርስ ብለሽ የኔ ልጅ! ብቻ እንኳን ልጄን አግኝቼ ዓይኗን ያየሁት» አሉና ወደ ሔዋን ዞር ብለው እያዩዋት እሙ! ደግሞ በአንቺ ሆድ ምን ይኖር ይሆን?» አሉና «አደራ የወላድ መካን እንዳታደርገኝ!» አሏትና ድንገት እንባቸው ድንቡቅ ብሎ ወረደ።
ሔዋንም በዚያው ሁኔታ ተከተለቻቸው፡፡ ታፈሡ በእናትና ልጅ ሁኔታ የእሷም ሆድ እየተንቦጫቦጨ ትንሽ ካለቀሰች በኋላ እንደገና ሁለቱን ማባበሏን ተያያዘችው። ከብዙ ልመና በኋላ ትንሽ በረድ ብለውላት በሀዘንና በትካዜ ዓይን አከታትላ ስታያቸው ሳለች በልሁና መርዕድ ድንገት ከተፍ አሉ፡፡ በሁለት ፊስታል
ዕቃ ይዘዋል። ታፈሡ ተቀበለቻቸውና ወደ ጓዳ ገባች:: ወዲያው የመመገቢያ ትሪና
ያን ከቤቷ ይዛ የመጣችውን ምግብ ይዛ በመመለስ ማቅረብ ጀመረች። በቀይ የሥጋ ወጥ የተፈተፈተ የነጭ ጤፍ እንጀራ ነው።ትሪው ላይ ዘርግፋ ሔዋንና እናቷን ተጨምሮበት ሁሉም ቀርበው እንዲበሉ አደረገች። በልሁና መርእድ ካመጡት ለስላሳ እየከፈተች ማደሏን ቀጠለች።
ታፈሡ በማስተናገድ ሽር-ጉድ ያንን ቤት ሞላችው።
ከምሳ ግብዣው መጠናቀቅ በኋላ ትርፌ ያፈላችው ቡና ተከተለ፡፡ ታፈሡ ፍራሽ ላይ ከሔዋን አጠገብ፣ በልሁና መርዕድ ደግሞ ከፊትለፊታቸው የግድግዳ
ጥግ ይዘው ወንበር ላይ ተኮለኮሉ፡፡ ቡናው ሊቀዳ ሲል ሔዋን እናቷ ከመጡ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ተናገረች።
«ጫቱን ተዋችሁት እንዴ በልሀዬ»
«እማማን ፈርተው ይሆናል፡፡» አለች ታፈሡ ፈገግ ብላ ሁሉንም እያየች፡፡
ውይ! ለምን ልጆቼ ሲዳሞ ውስጥ እየኖርኩ ጫት ትጠላለች ብላችሁ
ነው? የራሴ ልጆችስ ምድጃዬን ክብብ አድርገው አይደል ሲቀጨቅጩት የሚያመሹት! እኔንማ አትፍሩ። እንደውም ቤቱ ሲጫጫስ ደስ ይለኛል፡፡» አሉ፡፡
ይደብርዎት እንደሆን ብለን እኮ ነው:: አለ በልሁ ፈገግ ብሎ፡፡
«ኧረ በፍጡም ለምን ልጅ?»

«አምጡት እንግዲው!» አላች ታፈሡ በልሁና መርዕድን በፈገግታ አይን እያየቻቸው።......


💫ይቀጥላል💫
👍132
#ስም_ያለው_ሞኝ_ነው?

ስም ያለው በሙሉ ሞኝ ከተባለ
ሁሉም ባለስም ነው ብልጡ ወዴት አለ
ስም ያው ሞኝ ነው
ሃገሬ ስም አላት ሕዝቧ ስም አላቸው
ባለ ስም ሞኝ ነው ሁሉም ሞኞች ናቸው
ስለዚህም እኔ ሽሽት ጀምሪያለሁ
በሞኞች ሃገር ውስጥ
ብልጥ እንድሆን ብዬ ስሜን ትቼዋለሁ።

🔘ልዑል ሀይሌ🔘
9👍6
#የፍቅር_ግልባጭ

ያኔ ስንገናኝ መንገድ ላይ አስቁሜ
ሁሉም ሰው ስያየኝ ቁልቁል ተዘቅዝቄ
ይሉኝታውን ንቄ
አበባውን ይዤ በዕንባ ተሞልቼ
እየተርበተበትኩ ያልኩሽ አወድሻለሁ
እንዳትሽወጂ 'አፕሪል ዘ ፉል' ነው።

🔘ልዑል ሀይሌ🔘
👍7😱2
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

...ጃን ተከል ከወትሮው የበለጠ ሰው ተሰብስቦበታል። ወሬው ሁሉ ስለ ቅዳሜው ግብርና ስለ ምንትዋብ ውበት ነው። ቅዳሜ ዕለት ኣብርሃ ቤተመንግሥት በር ላይ የድኃ ተራ እስኪደርስ ጠብቆ ግብር ተካፍሎ ነበርና በአኮፋዳው
ከየዓይነቱ ምግብ ጠቅጥቆ መጥቶ ጥላዬን እንዲበላ
ሲጋብዘው አልበላም ብሎታል።
አብርሃ ምንትዋብን ባያያትም፣
ስለግብሩ ትልቅነት ሲያወራ አልበቃው በማለቱ ጥላዬ ደከመኝ ልተኛ ብሎት ተለያይተዋል።

ጥላዬ፣ ዋርካው ጠርዝ ላይ ቆሞ፣ “ምንትዋብ ብለው ስም አወጡላት እያሉ ወሬውን ሲቀባበሉ ሰማ። አብርሃን ሲያየው ካንዱ ወደ ሌላው እየሄደ ወሬ ይጨልፋል። ምነው እንደሱ የማላውቃት ባረገኝ። ወደ
ቅጥር ውጭ እኔ ዛፉ ስር ቁሜ አንቺ ነጠላ ተከናንበሽ ገና ኸደጀሰላሙ የልቤን ሳላወጋሽ። የቅርብ ሩቅ ሁኜ ስላንቺ ሰማለሁ። ኸዛ ኸበተክሲያን ወለቴ ምንትዋብ አሉሽ ለኔ ሁሌም ወለቴ ነሽ፡፡ አንድ ቀን ስንኳ ብቅ ስትይ ልቤ ሚተረከከውን ምን ግዝየም አልረሳው። አንድ ቀን ያነን ድንቅ ፊትሽን እሥል ይሆናል። እስተዛው የወፍታው ኻንቺ ጋር ይሁን ብሎ የፍቅራቸውን ምዕራፍ መዝጋት እንዳለበት ለልቡ አስገነዘበ።

አብርሃ የቃረመውን ወሬ ሊነግረው ሲመጣ፣ ጥላዬ መስማት አልፈለገም። “ኸዛው እንኸድና ለሥላሤ ምስጋናዬን ላቅርብ” አለው፣ ወሬውን ሳይጀምር።

“ምናለ፣ እንኸዳ” አለው፣ ግራ የተጋባው አብርሃ።አብርሃ ወደቤቱ ሲሄድ ጥላዬ ቤተክርስቲያኑ ደጅ ላይ ተደፍቶ ምስጋናውን አቀረበ። የተሰበረ ልቡን ሥላሤ እንዲጠግኑለትም ጸሎት
አድርጎ ከዐይኑ ያመለጠውን እንባ ሰው ሳያየው በጋቢው ጠራርጎ ተነሣ።ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ሲቀመጥበት የነበረው ዋንዛ ዛፍ ሥር ተቀምጦአካባቢውን ሲቃኝ፣ የቆሎ ተማሪው ግማሹ የለቀመውን ዕንጨት በእቅፉ
ይዞ ወደቤቱ ይሄዳል፣ ሌላው ውሃ ቀድቶ መመለሱ ነው። በየአጥሩ ጥግ መነኮሳትና አረጋውያን ተቀምጠው ዳዊት ይደግማሉ፣ የቁም ጸሐፊው ብራና ላይ ይጽፋል፣ አንዱ ብራና ሲደጉስ ሌላው ቅዱሳት መጻሕፍትን
ያስጌጣል።

ጥላዬ፣ ለሥራቸው በሚሰጡት ትኩረት ተገረመ። እሱም እንደነሱ
ተቀምጦ ሥራውን የሚሠራበትን ቀን ናፈቀ። አለቃ ሔኖክ ትምህርት
እስኪያስጀምሩት ቸኮለ። እዚያው ግቢውን ሲቃኝ ቆይቶ፣ ከሰዐት
በኋላ፣ ወደ እሳቸው ቤት አመራ።
እሳቸው ስላልነበሩ ደጅ ተቀመጠ። ወርቄ በር ላይ ቆማ የሆነ
ያልሆነውን ስትጠይቀውና ሲመልስ ቆይተው፣ ወደ ውስጥ እንደገባች አለቃ ሔኖክ ቅጥር ግቢው ገቡ።

“አምሽተህ ነው?” ብለውት ወደ ውስጥ ገቡ።ቆየት ብለው ወጥተው ወደ ጓሮ እንዲመጣ በእጃቸው አመለከቱት ኩታውን እያስተካከለ ተከተላቸው። ጎጆውጋ ሲደርሱ፣ “ይህቻት
እንግዲህ ማደሪያህ” አሉት።
"እመቤቴ ትስጥልኝ” አላቸው፣ ለጥ ብሎ እጅ ነሥቶ።

አንገቱን ወደ ውስጥ መዘዝ አድርጎ ተመለከተ። ከአንድ አነስተኛ ቁርበት በስተቀር ጎጆዋ ውስጥ ሌላ ምንም ነገር የለም። የአቧራዋ ሽታ ይሰነፍጣል ።

“እዝች ሁነህ ሥራህን ትሠራለህ። የትምርት ግዝየ ሲደርስ እኔ አለሁ።ምግብ ወርቄ ትሰጥኻለች። አንተ ዛዲያ እንጨት ትለቅምላታለህ፣ ውሃ
ትቀዳላታለህ፣ ልብስም ታጥባለህ” አሉት።

“እረ ምን ገዶኝ!”

አለቃ ወደ ቤት ሲመለሱ፣ ቁርበቱ ላይ ጋደም እንዳለ መላ አካላቱ
በሐሳብ ደክሞ ነበርና እንቅልፍ ወሰደው። ምሽት ላይ፣ ወርቄ እራቱን ይዛለት መጣች። ራቱን በልቶ ተኛ።በነጋታው አለቃ ሔኖክ በወርቄ አስጠርተውት ሲገባ እሳቸው መደብ ላይ ተቀምጠዋል። ሰላምታ ሰጥቷቸው በእሳቸው ትይዩ ተቀመጠ።
ወርቄ ቁርስ አቅርባላቸው ከበሉ በኋላ፣ አለቃ ሔኖክ፣ አነስተኛ ብራናና የቀለም ቀንድ ይዘው አብሯቸው ደጅ እንዲወጣ ነገሩት።

“ብራናና ቀለም እኔ ሰጥኻለሁ። ወደፊት ብራና ሆነ ቀለም ራስህ
ታዘጋጃለህ። ቀለም አቀማመም አሳይሀለሁ። ንድፍም አሳይህና በዚያ መሠረት ኸርኩሳኑ መኻል ምትፈልገውን ሠርተህ ታመጣልኛለኸ አሉት።

እጅ ነሥቶ ትኩረቱን እጃቸው ላይ ያለው ብራና ላይ አደረገ።
ቀስ ብለው ንድፍ እንዴት እንደሚሠራና ቀለም እንዴት እንደሚቀባ አሳዩት።
“ለነገሩ ንድፍ አይቸግርህም። በአክርማ ስትሠራ ቆይተህ የለ?”
አሉት፣ እየሳቁ።
ዐይኑን ከብራናውና ንድፉን ከሚሠሩበት የቀርከሀ ስንጥር ላይ
ሳያነሳ በአዎንታ ራሱን ነቀነቀ።

ትምህርቱን ጨርሰው እሳቸው ወደ ውስጥ ሲገቡ፣ እሱ ወደ ቤቱ
ሄደ። ጋቢውን ቁርበቱ ላይ ወርውሮ ደጅ ድንጋይ ላይ ተቀምጦ፣ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመኝ የኖረው ብራና እጁ በመግባቱ ሊስመው ቃጣው።

ሕይወቱ ዐዲስ ምዕራፍ የያዘ መሰለው።ሥዕሉን በምን እንደሚጀምር አወጣ አወረደ... እባብ? ሳጥናኤል? ቁራ? በመጨረሻም ስለምን ሳጥናኤኔልን አልሰራም አለ፣ ለራሱ።አለቃ ሔኖክ ባሳዩት መሠረት ንድፍ ሞከረ፤ ተንጋደደበት። ብራናውን
ያበላሽ ስለመሰለው ደነገጠ። ሆኖም መሣሉን ቀጠለ። አለቅጥ ረጀም፣ግራና ቀኝ አስፈሪ ቀንዶች ያለው፣ ጆሮዎቹ በጣም ትልልቅና ጭራ ያለው ፍጡር ሣለ። ቤቱ ደጃፍ ላይ ተቀምጦ፣ ብራናውን ደጋግሞ እየተመለከተ ስቆ እንደማያውቀው ሳቀ። በነጋታው ፈራ ተባ እያለ አለቃ ሔኖክጋ ሲሄድ ወርቄ፣ “ኣፍህን እንድትሽር ልጠራህ ስል መጣህ” አለችው።

“ለመብልማ እስትትጠራ አትጠብቅ። ቤትህ እኮ ነው” አሉት፣ አለቃ ሔኖክ።

ቁርስ አድርገው ከጨረሱ በኋላ፣ “እስቲ ምን ሠራህ?” አሉት።

ብራናውን ብድግ ብሎ ሲያቀብላቸው፣ ቀረብ፣ ራቅ አድርገው ተመለከቱትና ሳቁ። “ሳጥናኤል... ማለፊያ ነው። ንድፉም መልካም ነው። ተሰጥኦ እንዳለህ ያስታውቃል” አሉት።

“ንድፉ ተንጋደደብኝ እንጂ።”

ርኩሳንን ከሀዲያንን፣ አጋንንትንና ክፉዎችን ስትሥል ንድፉ ቢንጋደድ ምንም አዶለም። ባሕሪያቸው ነው፤ መንጋደድ ይስማማቸዋል። ላንተ ግን ዋናው እጅ ማፍታታትህ ነው። ወደፊት ቅዱሳንን፣ መላዕክትንና ሌሎችን ስትሥል ግን ንድፍ ማንሻሽፍ
አይፈቀድም። በል በርታ” ብለው ብራናውን መልሰው ሰጡት።

እጅ ነሥቶ ወጣ።

በሚቀጥሉት ቀናት፣ እሳቸው በነገሩት መሠረት ጥቁር ቀለም ከተለያዩ ዕጽዋት ቀምሞ ሥዕል መሣሉን ተያያዘው። እንደሱ ቢሆን፣ ርኩሳንን ብቻ ሳይሆን የፈለገውን ቢሰራ በመረጠ። ብዙውን ጊዜ የምንትዋብ
መልክ ፊቱ ላይ ድቅን ይላል። እንደበፊቱ እንስሳውን ቤቶቹን ሁሉ
መሣል ይፈልጋል። አንዳንዴ የፈለገውን የሚሥልበት የቤታቸው ጓሮ ይናፍቀዋል።

ሥዕል በማይሥልበት፣ ለወርቄ ውሃ በማይቀዳበት፣ ዕንጨት
በማይለቅምበትና የአለቃ ሔኖክን ልብስ በማያጥብበት ጊዜ፣ ከአብርሃ ጋር ጃን ተከል እየሄደ ወሬ ይሰማል። ጃን ተከል ብቅ ማለት እሱስ ሆኖበታል። ቤተመንግሥት ግብር ሲጣል፣ አብርሃ ምግብ ብቻ ሳይሆን
ስለ ምንትዋብ ወሬ ይዞለት ይመጣል ።

በትምህርቱ እየጎበዘ ሲመጣ፣ አለቃ ሔኖክ በሥራው ቢደሰቱም፣
“መልካም ነው፣ በርታ” ከማለት በስተቀር ብዙ ስለማያብራሩ ጥቂት ቅር ይሰኛል፣ ቢያሞጋግሱት ይመርጣል። የሠራውን ሲመለከቱ፣ ፊታቸው
ላይ የሚንፀባረቀውን አድናቆት ለምን በቃላት እንደማይገልጹለት
ይገርመዋል።

አንድ ቀን አስደሰቱት። ግቢው ውስጥ ተቀምጠዋል። እንዴትና
የት እንደዋለ ከጠየቁት በኋላ፣ “ጥላዬ፣ ሥዕል ኸዠመርህ ወራት
አልፈውሀል። እጅህም ጥሩ ተፍታቷል። እንደነገርሁህ ጥቂት ቆይተህ ቄሶችን፣ መሪጌታዎችን፣ ሊቀጠበብቶችን ቤተክስቲያን አካባቢ ያሉ ሰዎችን መሣል ትዝምራለህ” አሉት።

ደስ ተሰኘ።
👍15😱1
“በርታ እንግዲህ። እስታሁን ጥሩ እየሠራህ ነው። ወደፊት ደሞ
የበለጠ እየተፈተንህ ትኸዳለህ።”
ማንን እንደሚሥል ሲያስብ ከረመ።.....
፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡
በእነዚያ ወራት፣ “እቴጌ አርግዘዋል መሰል ጠዋት ጠዋት ወደላይ
ይላቸዋል” የሚል ወሬ ቤተመንግሥቱን አልፎ ጃን ተከል ሲመጣ እሱምጋ ደረሰ። የምንትዋብ እርግዝና የሁሉ ጉዳይ በመሆኑ ተገረመ።

አንድ ቀን፣ ጃን ተከል ከምንጊዜውም የበለጠ ተጣቧል። እሱና አብርሃ ገና መድረሳቸው ነው። ሰዉ በቡድን በቡድን ሆኖ ይወያያል፣ ይከራከራል፣ ይሟገታል። ጥላዬ አንዱጋ ተጠግቶ ሲያዳምጥ ወሬው ዛሬም ስለምንትዋብ እርግዝና ነው፡፡

“እቴጌይቱ ወንድ ኻልወለዱ ንጉሡ እንዴት አርገው ነው አልጋ
ወራሽ ሚያገኙ?”
ፊት የወለዷትም ሴት ናት አለ።”

“እቴጌም ሴት ኸወለዱ ጉድ ነው በለኛ!”

“ኸጉድም ጉድ ነው እንጂ።”

ጥላዬ አላስቻለውም። ጣልቃ ገባና፣ “ኸምኑ ላይ ነው ጉዱ?” አለ።
“ኧረገኝ ምን ያለ ዥል ነው በሉ? የተዣዣለ። ሴት መንገሥ
እንደማትችል አያውቅም ሁኖ ነው? አይበለውና እቴጌ ሴት ቢወልዱ እንዴት ሁኖ ነው ንጉሡ አልጋ ወራሽ ሚኖራቸው? በል እስቲ ንገረኝ?”
ጥላዬ፣ ሊቀጥለው የማይችልበት ሙግት ሆነበትና ዝም አለ።
አብርሃን በዐይኑ ፈልጎ ሲያገኘው አብርሃ የአንገቱ ስሮች እስኪገታተሩ ድረስ ከሁለት ሰዎች ጋር ይከራከራል። ጥቂት ጠብቆት ወደቤቱ ሄደ።

ቤት ሲደርስ፣ አለቃ ሔኖክ ከሰዐት በኋላ እንደሚያደርጉት ጥላ ስር
ተቀምጠው ቀለም ይቀምማሉ። አጠገባቸው ሄዶ ተቀመጠ።

“የት ቆይተህ ነው?” አሉት
“ከአብርሃ ጋር ጃን ተከል ወርደን የሰዉ ክርክር ለብቻው
አላቸው።

“ስለምን ነው ሚከራከሩ?”

“ስለ እቴጌ...” ምንትዋብ ይበላት ወለቴ ቸገረው። ገና ምንትዋብ
የሚለውን ስም አልተለማመደውም። “እቴጌዋ አርግዘዋልና ወንድ በሆነ
እያለ ሰዉ ይነታረካል።”

“መቸም ውነት ነው። ለእቴጌም ሆነ ለንጉሡ ወንድ መሆኑ ይጠቅማል።በዝኸ ግዝየ እቴጌስ ቢሆኑ ተኝተው ያድሩ መሰለህ? ቤተመንግሥት ውስጥ ያለ ወሬ ስንኳ አያስተኛቸውም። ወንድ ቢሆንላቸው ንጉሡን የሳቸው ደጋፊ የሆኑትን መኳንንት ጭምር ያስደስታሉ። እሳቸውም
ልባቸው ያርፋል።”

“ፈርዶባቸዋላ!”

“እዝጊሃር ይርዳቸው። በዝኸ ላይ ኸቋራ ናቸው።”

“ኸቋራ ቢሆኑ ምን ሞገድ አለው?”

“አየ ጥላዬ! አለው እንጂ። በአንድ በኩል መኳንንቱ የቋራ ደም
ያለው አልጋው ላይ እንዲወጣ አይፈልጉም። ቋራ እንደ ጐንደር
ማዶል። ባላገር ነው ብለው ያስባሉ። በሌላ በኩል ደሞ እወህኒ አምባ ስንቱ የነጋሢ ዘር መሰለህ አሰፍስፎ ሚወለደው ወንድ ይሁን ሴት ሚጠባበቀው። ወንድ ኸተወለደ የመንገሥ ዕድላችን ይዘገይብናል
አለያም ያመልጠናል ብለው ይሰጋሉ። ሴት የሆነች እንደሁ እነሱም ይደሰታሉ፣ ከንጉሡ ጋር ጠብ ያላቸው መኳንንትም የልባቸው ይደርሳል። ንጉሡም ቢሆኑ ዳግም ሴት ኸተወለደችላቸው ያዝናሉ።
አየህ ነገሥታቱ አልጋቸውን አሳልፈው መስጠት ስለማይፈልጉ ወንድ ልዥ ለማግኘት ሲሉ ዕቁባት ይይዛሉ። አሁን አጤ ቴዎፍሎስ...
የታላቁ ኢያሱ ወንድም፣ የጃንሆይ አጎት መሆናቸው ነው... ከሕግ
ባለቤታቸው ኸእቴጌ ወለተጽዮን ጠንተው ሲኖሩ እቴጌዋ መካን ነበሩና አልጋ ሚወርስ ልዥ አልነበራቸውም። ስለዝኸ የነጋሲ ዘር የሌላቸው የአጤ ቴዎፍሎስ እንደራሴ የነበሩት ዮስጦስ ነገሡ። አሁንም ጃንሆይ ቢሞቱ ስንኳ አልጋቸውን ሚወርስ ልዥ የለም። ለዝኸ ነው ያ ሁሉ ክርክር።”

“እቴጌ ሴት ኸወለዱ ጉድ ነው ቢሉ ጉዱ ምኑ ላይ ነው ብል አንዱ ዥል የተዣዣለ ብሎ ሰደበኝ” አላቸው፣ እየሳቀ።

አለቃ ሔኖክ እንባቸው ጠብ እስኪል ሳቁና፣ “እንግዲህ ለእቴጌ
እንጸልይላቸዋለን” አሉት።
ኧረ አጥብቄ ጸልይላታለሁ አለ፣ ለራሱ።......

ይቀጥላል
👍15
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አራት ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ...ጃን ተከል ከወትሮው የበለጠ ሰው ተሰብስቦበታል። ወሬው ሁሉ ስለ ቅዳሜው ግብርና ስለ ምንትዋብ ውበት ነው። ቅዳሜ ዕለት ኣብርሃ ቤተመንግሥት በር ላይ የድኃ ተራ እስኪደርስ ጠብቆ ግብር ተካፍሎ ነበርና በአኮፋዳው ከየዓይነቱ ምግብ ጠቅጥቆ መጥቶ ጥላዬን እንዲበላ ሲጋብዘው አልበላም ብሎታል። አብርሃ ምንትዋብን ባያያትም፣ ስለግብሩ…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...«አምጡት እንግዲው!» አላች ታፈሡ በልሁና መርዕድን በፈገግታ አይን እያየቻቸው።.

መርዕድ አልዘገየም፤ የመቃሚያውን ቦታ በአዲስ መልክ አበጃጀው ጫቱን ከጋዳ ውስጥ አወጣ። ያ ቤት እንደገና ነፍስ ዘራ። የጫቱ መጀመር በተለይ በታፈሡና በሔዋን እናት መካከል ተጨማሪ ውይይት እንዲፈጠር ምክንያት ሆነ።
«በልሁ» ስትል ታፈሡ መጀመሪያ ጠራችው፡፡
«አቤት»
«የሒዩ እናት ትናንት ሸዌዬ ቤት እንዳደሩ ነገሩኝ፡፡ ነገር ግን ደስ ያላቸው አልመስለኝም፡፡» አለች በተለይ የሔዋንን እናት አየት እያደረገች::

«ከፋዎት እንዴ እማማ?» ሲል ጠየቃቸው በልሁ፡፡ቢከፋኝስ የት እደርሳለሁ ብለህ የኔ ልጅ አሉ የሔዋን እናት ጉንበሰ ብለው መሬት መሬት እያዩ።
ቀድሞ ነገር በልጅዎ ቤት ለምን ይከፋዎታል? አለ በልሁ አሁንም፡፡
«ምኑን አወቅት ብለህ የኔ ልጅ! እንግዲህ እያደር ሳውቀው ይገባኝ እንደሆነ እንጂ እስታሁንስ ነገሩ ሁሉ ግራ ግብት ነው ያለኝ» አሉ የሔዋን እናት::
ታፈሡ ወደ ሔዋን አየት እያረገች ሔዩ! ለእማማ ሁሉንም ነገር
ልነግራቸው ነው ከፋሽስት አልከፋሽ የራስሽ ጉዳይ» አለቻት በመቀለድ ዓይነት
ሔዋን አንገቷን ወደ መሬት ቀበረች፡፡ እናቷ ሳይቀሩ በልሁ፣ መርዕድና ታፈሡም ያዩዋት ጀምር። በዚህ ግዜ እናቷ፣
ነውር የሆነ ነገር ሰራሽ እንዴ እመ'ዩ?» ሲሉ ጠየቋት፡፡
የእርስዎ ልጄ ነወር ልትሰራ አልተፈጠረችም::» አለች ታፈሡ እንደገና ወደ በልሁና መርዕድ ዞር ብላ «ያ ሲያስጨንቀን የነበረ ሸዋዬ ስለ ሔዋን ለወላጆቿ
የፃፈችው ደብዳቤ እኮ አልተላከልንም» አሉ አለቻቸው ሁለቱንም አየት አየት
እያረገቻቸው
«ሙት በይኝ» አለ በልሁ።
አያችሁ! ሔዩም ስትጨነቅ፣ አስቻለውም እኛም ስንታመስ የኖርነው እንዲሁ በከንቱ ኖሯል» አለችና የተፃፈው ደብዳቤ ይዘት ምን እንደነበረ ዘርዘር አድርጋ ለሔዋን እናት አሰረዳቻቸው፡፡ ሸዋዬ ያን ደብዳቤ ሔዋንን ለማስፈራራትና ለማስደንገጥ እንጂ ልትልከው እስባ እንዳልነበር እንደ አዲስ ታሰባቸው፡፡
የሔዋን እናት የደብዳቤውን ይዘት ከታፈሡ ገለፃ ከተረዱ በኋላ “ይህን ነገር እሙዬ ፈፅማው ነው ወይስ ...» ብለው ታፈሡም ሔዋንንም ሲመለከቱ ታፈሡ ራሷ ቀጠለች::
«አዩ እማማ! መቸም ሔዩም ሽዋዬም ልጆችዎ ናቸው። በእርስዎ ፊት አንዷን ወግነን ሌላዋን ብናማ ትዝብት እንደሆነ እንጂ ሌላ እንደማናተርፍ
እናውቃለን፡፡ ግን ደግሞ እውነቱን ግልጥልጥ አድርገን ልንነግርዎት እንፈልጋለን።አለቻቸው አንድ የጫት እግር ይዛ ወዝወዝ ወዝወዝ እያደረገች፡፡
«በጄ» አሏት የሔዋን እናት ለነገሩ እየጓጉ።
«ሔዩና ሽዋዬ በሚያጣላ ነገር ተጣልተው ለማስታረቅ ብዙ ጥረን ነገር ግን በሸዋዬ እምቢተኝነት ሳይሳካልን ቀረ፡፡
«ምን አጣላቸው የኔ ልጅ?»
ታፈሡ ነገሩን ከሥሩ ጀመረችላቸው በቅድሚያ እሷና ሸዋዪ የትና እንዴት እንደሚተዋወቁ ሸዋዬ ከያቤሎ
ወደ ዲላ ስትመጣ ያደረገችላትን
አቀባበለ፤ ቀጥላም የእስቻለውን ምንነትና ማንነት፤ ከእሷ ጋር የነበረውን ግንኝነትም እንዲሁ ገለፀችላቸው፡፡ በመጨረሻም የአስቻለውንና የሔዋንን ጉዳዩ
ከአጀማመሩ እስከ የወደፋት አላማቸው ድረስ አስረዳቻቸው
ለዚህ ነገር የሸዋዬ አቋም ምን ይመስል እንደነበር ችግሩን ለመፍታት የተደረገውንና ሊደርግ
የነበረውን ጥረት ሁሉ ዘረዘረቾላቸው።
የሔዋን እናት በነገሩ መመሰጣቸው የተነሳ በወሬው መሀል ቢጠሯቸው
እንኳ "ወያ" የሚሉ አይመስሉም፡። እንዲያውም እንባቸው እየመጣ በለበሱት ነጠላ ዓይናቸውን ጨመቅ ያደርጋሉ፡፡ ሔዋንንም ዞር እያሉ ስሜቷን ሲሰልሉ እንባዋ
በጉንጯ ላይ ሲፈስ ያያሉ በዚያው ልክ ሆዳቸው ይንቦጫቦጫል የእሳቸው ሁኔታ የሁሉንም ቀልብ ስቦ ሁሉም በትካዜ አስተያየት ያዩአቸዋል፡፡
ታፈሡ አሁንም የሔዋንና የሸዋዬን ለየብቻ የመኖር ምክንያት ልትጠቁማቸው ፈልጋ ሸዋዬ ሔዋንና አስቻለውን ለመለያየት ያደረገችውን ጥረትና ሔዋንም በማትፈልገው ሰው ልታስደፍራት መሞከሯን ጭምር ነገረቻቸው።
የሔዋን እናት ነገሩ ሁሉ ግርም አላቸውና «እንዴት ነው ይኸ ነገር
እሙዬ» ሲሉ በተላይ ሔዋንን እያዩ ጠየቋት፡፡ ምናልባት እሷም በሆዷ ውስጥ ያለ ነገር ካለ ብለው ብትነግራቸው ፈለጉ።
«ሔዋን ፤ ኢይዞሽ ንገሪያቸው!» አለች ታፈሡ በልጃቸው አንደበት ቢሰሙ የበለጠ ላያምኑ እንደሚችሉ በመገመት።
ሔዋን ግን አልቻለችም። ለቅሶ ቀደማትና በእናቷ “ጭን ላይ ድፍት በማለት ትንሰቀሰቅ ጀመር፡፡ እናቷም ታፈሡም ቢያባብሏት ዝም ልትል አልቻለችም በመሀል በልሁ ተቆጣት።
“እንቺ ሔዋን» አለና ከመቀመጫው ብድግ አለ፡፡ «ቀና ብለሽ ቁጭ በይ።ለምን የእናትሽን ሆድ ታባቢያለሽ?» አለና አንገቷን ደገፍ አድርጐ ቀና አደረጋት፡፡
«እናትሽ የጠየቁሽን መልሽላቸው።» አላት እንደገና።

«አ- አንቺ ን- ንገሪያት ታፈሡዪ!» አለች ሔዋን ድምጿ እየተቆራረጠ፡፡ታፈሡ ቀጠለች:: በመሀል ደሞ አንድ ችግር ተፈጠረብን እማማ። ይህ
እስቻለው ያልከዎት ወንድማችን ሳያሰበው በዘመቻ ስም በግዳጅ ወደ ኤርትራ መሄድ ግድ ሆነበት።
ይህም አጋጣሚ የተፈጠረው በሸዋዬ አማካኝነት ልጁንና
ሔዋንን ለመነጣጠል የተዶለተ ሴራ መስሉ ታየንና ሔዋን ያለ ፍላጎቷ ከመደፈሯ በፊት ማሸሽ ፈለግን። ልጁም ደሞዙን ለእሷ መተዳደርያ እንዲሆን አድርጎ ስለነበረ ከሽዋዬ ቤት ወጥታ እዚህ ቤት እንድትኖር አደረግን፡፡ በቃ ሔዋን ከሸዋዬ ቤት የወጣችብት ምስጢሩ ይህ ነው የኔ እናት» አለቻቸውና ምላሻቸውን በመጠበቅ ዓይኗን በዓይኖቻቸው ላይ ስክት አደረገቻቸው።
ለልጁ መዝመት መዘዘኛዋ ያቸው የእኔ ልጅ ናት በይኛ» አሉና የሔዋን እናት ታፈሡን ያዩዋት ጀመር።
«እውነተኛውን ነገር እግዜር ይወቅ እማማ በኛ በኩል ግን እንደዚያ
ገመትን፡፡» አለችና ታፈሡ እጆቿን ጨብጣ አገጯን በማስደገፍ የሔዋንን እናት እየተመለከተች «አስቻለው ከመስሪያ ቤት አለቃው ጋር አይስማማም ነበር። ሽዋዬ
ደግሞ ከዚያ ሰው ጥብቅ የሆነ ግንኙነት ፈጠረች፡፡ እኛም በዚህ ጉዳይ የተነጋገሩበትና በጋራ የፈጠሩት መላ ሊሆን እንደሚችል ጠረጠር።አለቻቸው
የሔዋን እናት ያላሰቡት ስሜት ተፈጠረባቸው፡፡ በግራ እጅ መዳፋቸው ጉንጫቸውን ደገፍ አድርገው «እየየ እኔ! እየየ እኔ! ..» በማለት የተሰማቸውን ሃዘን ሲገልፁ እንባቸውም ከአይናቸው ላይ ድንቡቅ ብሎ ወረደ በዚህ ጊዜ በልሁ ብድግ ብሎ ወደ ጓዳ ገባና ቀድሞ የአስቻለው አሁን ደግሞ የሔዋን ከሆነው አልጋ የራስጌ ኮመዲኖ ላይ ሁለት ትላልቅ ፎቶግራፎች ይዞ ተመለሰ አንዱ አስቻለው ለብቻው የተነሳው ሌላው ደግሞ ወደ ኤርትራ ከመሄዱ አንድ ቀን በፊት ከሔዋን ጋር በመሆን በቁም የተነሱት ነበር። ሁለቱንም ፎቶግራፎች ለሔዋን እናት እየሰጠ እዩት እማማ! «ልጁም ይህ ነበር» አላቸው።
የሔዋን እናት ፎቶግራፎቹን በጭናቸው ላይ አስቀምጠው ልክ እንደ ፊት መስታወት እያዩ በቀኝ እጃቸው ቡጢ ደረታቸውን ደስቅ ደሰቅ እያደረጉ እ - እ እ ካሉ በኋላ ዓይኔ ይፍለስ! ዓይኔ ይፍስስ! ዓይኔ ይፍሰስ» አሉና «ምነው ይኽን ጉድ ሳነልሰማ ሞቼ አርፊው ቢሆን!» በማለት ከሁንም ዓይንና አፍንጫቸውን በነጠላቸው ይጠራቸው ጀመር።
👍91
«አይቀየሙኝኛ» አለ በልሁ ሔዋንና ሽዋዬ ከአንድ እናት ማህፀን የወጡ
አይመስለኝም እማማ ቅር ይልዎት ይሆን?» ሲል ጠየቃቸው፡፡
«የእናት ሆድ ዥንጉርጉር የተባለው ስለዚህ አይደል የኔ ልጅ! አንተም
በኔም ሆድ ብዙ አለ፡፡» አሉና ድንገት በሀሳብና በትካዜ ውስጥ ጭልጥ ብለው ገቡ።
የሸዋዬን የልጅነት አስተዳደግ እያስታወሱ ነው፡፡ ሽዋዬ በህፃንነቷ ገና በእቅፋቸው ውስጥ ሆና ጡታቸውን ጠብታ ጠብታ ስትጠግብ እንዴት አድርጋ ትነክሳቸው እንደነበር ትዝ አላቸው፡፡ ጠንክር ብላ ወደ ውጭ
መውጣት ስትጀምር ደግሞ
ከጎረቤት ልጆች ጋር ባለመስማማት ወይ አልቅሳ አለያም አስለቅሳ በመመለስ
የምታመጣባቸውን ስሞታ ሁሉ አስታወሱ። በቤት ውስጥ ደግሞ አጥፊ አውዳሚ፣ ምንም ነገር፣ የትም ቦታ ቢደበቅ የማያመልጣት ሰርሳሪ በዚያ ላይ ደግሞ ሰባቂ፣ የእናቷን ሚስጢር ለአባቷ፣ የአባቷን ደግሞ ለእናቷ እየነገረች
የምታሳጣቸው ሰላም እንኳ እልቀራቸውም፡፡ “ይቺ መሄጃዋ የማይታወቅ መዘዘኛ እያሉ ገና በልጅነቷ ይማረሩባት የነበረው ሁሉ ትዝ አላቸው።
ለአፍታ ያህል ፀጥታ ሰፈነና ከቆይታ በኋላ ግን የፀጥታውን ድባብ ራሳቸው' የሔዋን እናት ቀድመው ሰበሩት፡፡ ለመሆኑ ልጁ መቼ ይሆን የሚመለሰው?» ሲሉ ጠየቋቸው።
ታፈሡና በልሁ ድንገት ድንግጥ ድንግጥ አሉና እርስ በርስ ተያዩ።
መርዕድ ግን ከእነሱ በባሰ ሁኔታ ደንግጦ ውጭ ውጭ ያይ ጀመር፡፡
«ግራ ገብቶናል እማማ::» አለች ታፈሡ እሷም ብትሆን ቀጥላ የምትለው ነገር አስፈርቷት መሬት መሬት እያየች፡፡

«እንዴት የኔ ልጅ?»
የሄደው ለስድስት ወር ተብሎ ነበር፤ አሁን ግን ይኸው ዓመት ሊሞላው ነው። ግን እልም ብሎ ጠፍቶብን በሀሳብ ላይ ነው ያለነው::» አለችና ወደ በልሁ
ዞር ብላ ምናልባት ግን ሰሞኑን አንድ ነገር ስምተናልና የተስፋ ጭላንጭል ነው ብለን ገምተናል ብላ በልሁን 'ተናገር' በሚል ስሜት
በዓይኗ ጠቀስ አደረገቻቸው ተግባብተዋልና በልሁ ቀጠለ።
«ይህን ነገር ለሔዋንም ልንነግራት ነበር ዛሬ የተሰበሰብነው ሲል ጀመረ። «ደሞዙን ከመስሪያ ቤቱ እያመጣሁ ለሔዋን የምሰጣት እኔ ነበርኩ። ከጥቂት ቀናት በፊት ሄጄ ስጠይቅ ግን ደሞዝ ተቋርጧል የሚል ወሬ ሰማሁ፡፡» አለና ቀና ብሎ ሔዋንና እናቷን እየተመለከተ
ያን ቀደም ሲል ከእነታፈሡ ጋር ሆነው የፈጠሩትን ሔዋንን የማረጋጊያ ዘዴ መተረክ ጀመረ። አስቻለው በምጽዋ በኩል ወደ ውጭ ሄዶ ሊሆን እንደሚችል፤ ጀርመን ወይም ጣሊያን ሀገር ገብቶ ሊሆን እንደሚችል
ደብዳቢው በቅርቡ ሊመጣ እንደሚችል …ወዘተ። በልሁ በዚህ ዙሪያ ብዙ ብዙ ተናገረ።
በዚህ ትረካ ምናልባት የሔዋን እናት ተታልለው ሊሆን ይችላል፣ ሔዋን ግን የአስቻለውን ደሞዝ መቋረጥ ስትሰማ አይኗቿ ወደ ዳር ወተው ተጎለጎሉ ትን ትንፋሿም በርከት በርከት ፈጠን ፈጠን ማለት ጀመረ:: ታፈሱና በልሁ ስሜቷ ገብቷቸው በፍርሃት አስተያየት ሲመለከቷት ሔዋን ድንገት ተናገረች.
«ምን እያልክ ነወ በልሁ?» ስትል ጠየቀችው፡፡
«አትጠራጠሪ ሔዋን፣ ይሄ ነገር ለበጉ ነው፡» አላት ምላሽ የምትሰጥ ከሆነ ብሎ አይን አይኗን እያየ።
የሔዋን ሁኔታ የበለጠ እያስፈራራ ሄደ። ዓይኖቿ እንደፈጠጡ ቀሩ፡፡
በታፈሡና በበልሁ እንዲሁም በመርዕድ ላይ አከታትላ ታንከራትታቸው ጀመር።ወዲያው ደግሞ በረጅሙ ተነፈሰችና ወደ መሬት አጎነበሰች 'ኤርትራ የሄደ ይመለሳል ብለሽ.." የሚለው የበድሉ አነጋገርም ድንገት ፊቷ ላይ ድቅን አለባት፡፡
የሔዋን እናት ልጃቸውና ጎደኞቿ የተግባቡት ነገር እንዳለ ገባቸው
«ለመሆኑ እናቱ በሕይወት አሉ?» ሲሉ ጠየቁ፡፡
«እናትም አባትም የለውም፣ ሁለቱም ሞተውበታል፡፡» አለች ታፈሡ፡፡
የሔዋን እናት ከንፈራቸውን መጥጠው ዝም አሉ፡፡ አገጫቸውን በመደገፍ ወደ መሬት አጎነበሱ፡፡ ለአፍታ ያህል እሁንም ፀጥታ ሰፈነ። በመሀል ታፈሡ አንድ ነገር ትዝ አላት፡፡ ወዲያውም ማደናገሪያ ይሆናል ብላ በማሰብ ሳይሆን አይቅርም በልሁና መርዕድ የገዙትን ሥጋ ከጓዳ ወደ ሳሎን አመጣችና የእራት ወጥ
ለመስራት መከታተፍ ጀመረች። ፀጥታው ግን አሁንም ቀጠለ፡፡
«ተጫወቱ እማማት» አለ በልሁ ከብዙ ቆይታ በኋላ፡፡
«ልጆቼ» ሲሉ የሔዋን እናት ሁሉንም በአንዴ ጠሯቸው::
«አቤት እማማ?» አለች ታፈሡ ቀድማ፡፡ ግን ሁሉም ቀና ቀና ብለው ያይዋቸው ጀመር
«ታዲያ የእሙዬን ነገር እንዴት ባደርግ ይሻላል?» ሲሉ ጠየቁ፡፡
«እንዴት?” እላቸው በልሁ።
«የልጁ መምጫ ቀን አልታወቀም አላችሁ፡፡ በያ ላይ ደሞዙ ተቋረጠ ነው የምትሉኝ:፡ ታዲያ ወይ ይዣት ልሂድ?» ሲሉ ፈራ ተባ እያሉ ጠየቁ፡፡
ሁሉም ደነገጡና ዝም ዝም አሉ፡፡ ግን ደግሞ እርስ በእርስ ተያዩ።
«አይሻልም ብላችሁ ነው ልጆቼ? ወይስ ቅር ይላችሁ ይሆን?»
ሔዋን ስትል ታፈሠ ጠራቻት። ከመደንገጧ የተነሳ እንጂ ወይ ብትላት ቀጥላ የምትናግሪውን ነገር ታፈሡ አላዘጋጀችም።
«እሄዳለሁ» አለች ሔዋን ድንገት ሳትታስብ፡፡
«እ» አለ በልሁም ድንገጥ ብሎ።
«አዎ ከእማዬ ጋር ወደ ሃገሬን እሄዳለሁ።»አለች ሔዋን አሁንም ድርቅ ባለ ስሜትና ማጠንከር ባለ አነጋገር።አይኖቿ ግን አሁንም እንደተጎለጎሉ ናቸው። አንዳች ከብር ውስጧን ያናወጠባት ትመስላለች በዚህ ጊዜ ያልታሰበ ድምጽ፤ ባልታሰበ አኳኋን ካልታሰበ ሰው ተሰማ
ትርፌ እኔስ እታለምዬ ብላ ልክ እንደ ልጅነቷ ግንባሯን በክንዷ ሸፍና እይይይ…" ብላ አለቀሰች፡፡
ተይ እንጂ! ምን ነካሽ? እኛ እያለን! እኛ እያለን!» በማለት ታፈሡም በልሁም መርእድም አከታትለው ተንጫጩባት
እሷ ግን ዝም አላለችም፡፡ እንዲያውም በለቅሶዋ መሀል ልክ ቤት ውስጥ እንደምትጠሪው አይነት “ጋሽ አስቻለው…!» ስትል በርቀትና በጩኸት ድምጽ ተጣራች። አስቻለው ወደ አስመራ፣ ሔዋን ወደ ክብረ መንግስት
ተነጣጥለው ሲሄዱ እሷ ጭር ባለ በረሃ ውስጥ ብቻዋን የቀረች መሰላት። ሆዷም ባባና ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።
«ታፈሡዬ አለች ሔዋን በመሀል
በዚያው ድርቅ ባለ ስሜት ውስጥ ሆና።
«ወይ የኔ ቆንጆ»
ሔዋን ግን ጥሪዋን ቀጠለች፡፡ «በልሀዬ! መርዕድ!» አለች በማከታተል።
«ወይ! አቤት» አሏት ሁለቱም፡፡
ለእስቹ ፀልዩለት። ትርፍዬን ደግሞ አደራ!!» አለቻቸው።......

💫ይቀጥላል💫
👍121
#ሞገሰኛ_ኑሮ

ተስፋ ያልቆረጠ
ወድቆ የተነሳ
በሕይወት መዝገብ ላይ
ታሪኩ ይፃፋል
ባለ ድል ነውና
የሄደበት ሁሉ
አሻራው ይሰፋል
እንኳንስ በገሃድ
በጥላው ይገዝፋል!!!

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍94
#የተልባ_ስፍር

ሕልምና ምኞትሽን
ሃፍረት ሳይለጉምሽ አስበሽ ነገርሽው
“አንጉደል እንሙላ
እሺ በለኝና ያንተ ልሁን” አልሽው
ላንች ግልግል ነው
ሃቁን ተናግረሻል ለ'ሱ እንጂ ሰቀቀን
ቃል ያጠፈ ዝናብ
ሞልቶ ያፈሰሰው በርሚል ሳይደቀን
ሂያጇም ብላው ነበር
እሺታውን ሳትገድል ከዕለታት ባንዱ ቀን!

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
12👍5