አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምንትዋብ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


“እምዬ ጐንደር እንግዳ ተቀባይ እኮ ናት።”

ጥላዬ፣ እምነቱንና ተስፋውን ጐንደር ላይ ጥሎ ሐሙስ ቀን እዚያች ብርቅየ ከተማ ገባ። ጨለማ የከተማዋን ሰማይ ለማልበስ በመጣደፍ ላይ
ነው። ጐንደሬዎች ቤታቸው ለመከተት ፈጠን ፈጠን እያሉ ሲራመዱ፣ጥላዬ፣ ብዛታቸው ብቻ ሳይሆን ዓይነታቸው አስደነቀው። እንደ ግሪኮች፣ አርመኖች፣ ህንዶችና አረቦች የመሳሰሉ የውጭ ሃገር ዜጎች ሕዝቡ መሃል ውር ውር ሲሉ፣ የቆዳቸው፣ የመልካቸውና የአለባበሳቸው
መለየት አስደመመው።

ጭቃ ምርጎቹን ባለሳር ክዳን ጎጆዎች ትክ ብሎ አያቸው። ባዘቶ
የለበሱ የሚመስሉ ዋንዛ ዛፎች ስር ችምችም ማለታቸውና እንደ ቋራ ተሰባጥረው አለመቀመጣቸው ገረመው። በየቦታው ጣል ጣል ያሉት
የድንጋይ ግንቦችና ነገሥታት ብቻ የታደሉባቸው የኖራ ቅብ ቤቶች
የከተማዋ ጌጥ መስለው ታዩት። ያየው ሁሉ ከቋራ የተለየ ሆነበት።
ጐንደር ልዩ ስፍራ ሆነችበት፤ አስገረመችው።

ዐዲስ ሕይወት ልትሰጠው ቃል ኪዳን ገባችለት። እየተዘዋወረ ከተማዋን ማየት ፈልጎ ጨለማው በፍጥነት ማደሪያ እንዲፈልግ አስገደደው። ቤተክርስቲያን ፍለጋ ዐይኑን ሲያዘዋውር፣ አንድ የቆሎ ተማሪ በፍጥነት ሲራመድ አየና ሮጦ ደረሰበት።

“ከርመህ ነው? ላገሩ እንግዳ፣ ለሰዉ ባዳ ነኝ። ማደሪያ ሚሆነኝ
ደጀሰላም ባገኝ ብየ” አለው።

“ኸደብረብርሃን ሥላሤ ማታድር? ምን የመሰለ ዛኒጋባ በቤተክሲያን
ዙሪያ እያለልህ። ወደዛው ነው ምኸድ፤ በል ና። አገርህ ወየት ነው?”

“እማር ብየ መጥቸ” አለ ጥላዬ፣ መናገር አልፈለገም።

“ጐንደር ደሞ ለትምርት። ኸየቦታው ሚመጡ ተማሮች፣ ሊቃውንት፣ ካህናትና መምህሮች ሁሉ ኸዝሁ ማዶል ያሉት?” ብሎ ነጫጭ ጥርሶቹን አሳየው፣ ተማሪው።

ገራ ገር ፈገግታው ጥላዬን ማረከው። ዕድሜ ልኩን የሚያውቀው መስሎ ተሰማው። ቀደም ብሎ ማደሪያውን ሲያስብ ባይተዋርነት የተሰማውን ያህል፣ ከትከሻው ሸክም እንደወረደ ሁሉ ቀለል አለው።

“ቅኔ ልትማር ነው የመጣህ?”

“ሥዕል ልማር ብየ ነው የመጣሁ።”

“ዛዲያ ጐንደር ምን ገዷት! እደብረብርሃን ሥላሤ መምህሮቹም ተማሮቹም አሉልህ፡፡”

ጥላዬ ተደሰተ። ተማሪው ገዱ ሆኖ ተሰማው። ልባዊ ፈገግታው ደግ
ሰው እጅ ላይ እንደወደቀ ጠቆመው። “ምን እየተማርህ ነው?” ሲል ጠየቀው።

“ቅኔ እየተማርሁ ነው። መወድስ እያኸድሁ ነው።”

“ደሕና አኸደሀል።”

“አንተስ ሞካክረኻል?”

“ሥላሤ ደርሻለሁ። ማድርበት ደጀሰላም የት አገኝ ይሆን እያልሁ?”

“ጐንደር መጥተህ ነው ስጋት ሚያድርብህ? አንተስ አለማወቅህ ...እምዬ ጐንደር እንግዳ ተቀባይ እኮ ናት። ሴቶች ወጥ ሲሰሩ ኸደረስህ
ይሽተዋል ብለው ሳትበላ ማትኸድባት አገር እኮ ናት። ጐንደር የሁሉ ናት፤ ማንም ኸየት መጣ ኸየት ቤቴ፣ የኔ ብሎ ሚኖርባት። አልሰማህም
እንዴ፣
ቤተስኪያን ስሞ ለመኖር፣
መልካም አገር ነው ጐንደር።
ሲባልላት?” እያለ ግጥሙን በዜማ አወረደለት።

ጥላዬ ሳቅ አለና፣ “ገና መድረሴ፣ ምኔ ሰምቸ? ጐንደሬ ሁሉ እንዳንተ
ጥሩ ነው?” ሲል ጠየቀው።

“እኔስ ኸተምብየን ነው የመጣሁ። ዐራት ዓመት አርጌያለሁ ኸዝኸ።”
ተማሪው ከላይ የደረበውን ለምድ፣ ትከሻው ላይ ያንጠለጠለውን
አኮፋዳና ለውሻ መከላከያ የያዛቸውን ሁለት በትሮች ጥላዬ ትክ ብሎ ተመለከተና ከልመና እንደመጣ ገባው። ወደ ቤተክርስቲያኑ ሲደርሱ
ደጀሰላሙን ተሳልመው ውስጥ ገቡ።

“እንዴት ያለ ቤተክሲያን ነው በል” አለው፣ ጥላዬ።

“አጤ አድያም ሰገድ ኢያሱ መዠመሪያ አሠሩትና ተቃጠለ። ኸዚያ በኋላ፣ ልዣቸው... ሦስተኛው ሚባሉት አጤ ዳዊት እንደገና አሠሩት።

እሳቸው ግና ባባታቸው ስም እንዲጠራ ስለፈለጉ እኔ አሰራዋለሁ ስሙ ግን ባባቴ ይሁን አሉ።”

ጥላዬ ፈዞ ቆሞ የቤተክርስቲያኑን አሰራር ሲያደንቅ ተማሪው፣ “እኛ
ስንገባ ስንወጣ ለምደነዋል። እንግዲህ አንዱን ጥግ ይዘህ ተኛ። ኸኛ ዘንድ ምኝታ የለም ሁኖ ነው” ብሎት ሄደ።

ጥላዬ ቤተክርስቲያኑን እንደገና ተሳልሞ ዙርያውን ሲመለከት፣
እየጨለመ በመምጣቱ በወንዶቹ መግቢያ በኩል ጭንቅላቱን ጉልበቶቹ መሃል ቀብሮ ተቀመጠ። ግቢው ጭር ብሏል። መንገድ ሲመሽበት፣
“ቤት ያብርሃሙ ሥላሤ ነው” እያሉ ቁርበት ጣል፣ ትኩስ ሽሮ እንጀራ
ላይ ፈሰስ አድርገውለት፣ አለበለዚያ ቆሎ እንዲቆረጥም ወይ ቂጣ እንዲያላምጥ ሰጥተውት ያሳደሩት ሁሉ ትዝ አሉት። ከነጋ እህል አፉ አላደረገም። ሆዱ ከረሀብ ብዛት ዋይ ዋይ አለበት፤ ያለማቋረጥ
አዛጋው።

በዕድሜ ከእሱ ትንሽ ከፍ ስለሚለው ተማሪ አሰበና ባይለየው መረጠ። ስሙን እንኳ ሳይጠይቀው በመሄዱ ተቆጨ። አንገቱን እንደደፋ ሲያሰላስል ድምፅ ሰማ። ቀና ሲል ተማሪዎች ወደ መማሪያ ቦታቸው ወደ ቤተክርስቲያኑ ጀርባ ይሄዳሉ። ተማሪው ከእነሱ ነጠል ብሎ ወደእሱ ሲመጣ አየው። ሁለመናው ተበራታ።

“ራት ቢጤ አመጣሁልህ። የውሃ ቅሌን ልተውልህና ገሠሣ ሲያበቃ
መጥቸ ወስደዋለሁ። ስትተኛ ኸዚሁ ተወው። አነሳዋለሁ” ብሎት
መንገድ ሲጀምር ጥላዬ ከተቀመጠበት ተነስቶ፣ “ሥላሤ ያክብሩልኝ።ስሜንም ሳልነግርህ... ጥላዬ እባላለሁ... ከቋራ ነው የዘለቅሁ” አለው::

ቀደም ብሎ አባቱ ፈልገው እንዳያገኙት ሲል ማንነቱን ደብቆ፣
አሁን የተማሪው ደግነት ምሥጢሩን አሟሸሸበት።

“በል ነገ ያገናኘን። አብርሃ ነው ስሜ። ገሠሣ እንዳያመልጠኝ
ብሎት ተማሪዎቹ ወደሄዱበት አቅጣጫ አመራ።

ጥላዬ፣ አብርሃ የሰጠውን ፍርፋሪ በልቶ፣ ውሃውን በላዩ ቸልሶና
አምላኩን አመስግኖ የመንገድ ድካም ስለተጫጫነው አንዱ ዛኒጋባ ጋ ተጠግቶ ጋደም እንዳለ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደው።

ጠዋት ድምፅ ሲሰማ ብንን አለ። የት እንዳለ ለማወቅ ጥቂት ጊዜ
ወሰደበት። የሌሊቱ ብርድ፣ ልብሱን ውሃ የነካው አስመስሉታል። አንድ ጋቢ መኝታም ከላይ የሚለበስም ሆኖ አገልግሎታል። ከተቀመጠበት
ተነስቶ የቤተክርስቲያኑን መግቢያ በር ተሳለመና ወንዶቹ መግቢያ
ትይዩ ያለ አንድ ዋንዛ ዛፍ ስር ሄዶ ዳዊቱን አውጥቶ መድገም ጀመረ።

“አድረህ ነው?” የሚል ድምፅ ሲሰማ ቀና አለ። አብርሃ ነው ።

“ደሕና... ደሕና ... ይመስገነው።”

“አንደዜ ጠሎት ላድርስና ኸየንታ ሔኖክ ዘንድ ወስድሀለሁ” ብሎት
ሄደ።

ጥላዬ፣ በእሽታ ራሱን ነቀነቀለትና ወደ ዳዊቱ ተመለሰ። የዕለቱን
አድርሶ ሲጨርስ ዳዊቱን ማኅደሩ ውስጥ ጨምሮ፣ ስንጥር አንስቶ
መሬት ላይ መሞነጫጨር ጀመረ። እንደለመደው የወለተጊዮርጊስን ምስል ሊሥል ፈልጎ እዚያ ያደረሰው ምን እንደሆነ ትዝ ሲለው
ስንጥሩን ወረወረው።

ከቤት የወጣበት ምክንያት በመንገድ ድካምና በረሐብ በአእምሮው ውስጥ እየደበዘዘ መጥቶ ነበርና አሁን ቁጭ ሲል ሁሉ ነገር ፊቱ ላይ ድቅን አለበት። ወለተጊዮርጊስ ጐንደር መግባት ከለመግባቷን የማወቅ ፍላጎቱ ጸና። እሷ ሐር ቀሚስ ለብሳ ከቤት እንደወጣችው ሳይሆን፣ እሱ
እሑድ ቤተክርስቲያን ስትሳለም እንደሚያያት የዐዘቦት ልብሷን ለብሳ፣ ነጠላ ተከናንባ በበቅሎ ስትሰግር በዓይነ ኅሊናው ታየው፤ ሆዱ ባባ።

ያርባ ቀን ዕድሌ ነው እንግዲህ ምን አረጋለሁ? አለ፣ ለራሱ።
እናቱንና አባቱን አስታወሰ። በእሱ መጥፋት እናቱ እንዴት ጨርቃቸውን እንደሚጥሉ አሰበና ሆድ ባሰው። አባቱም ቢሆኑ አመል ሆኖባቸው ይነዛነዙ እንጂ፣ የእሱ ነገር እንደማይሆንላቸው ያውቃልና ጉዳታቸው ተሰምቶት ለመጀመሪያ ጊዜ አዘነላቸው። ሳያስበው ፊቱ በእንባ ርሷል። በጋቢው ፊቱን ጠራርጎ ቀና ሲል አብርሃ ፊቱ ቆሟል።
👍152
“ታለቅሳለህ እንዴ ጎበዝ? በርታ እንጂ! ሁላችን ኸሞቀ ቤታችን
ወጥተን የቀረነው ትምርት ፍለጋ ማዶል እንዴ? አይዞህ ትለምዳለህ።ቋራ ደሞ ቅርብ ነው:: በል ተነስ አሁን አለቃ ሔኖክ ዘንድ እንኸድ።ብቻ አንድ ምነግርህ ነገር አለቃ ሔኖክ እያረዥሁ ነውና ማስተማር ይበቃኛል እያሉ ነው ሲሉ ሰምቻለሁ። ለማንኛውም ኸደን ሚሉትን እንስማ። እሳቸው የለም አልችልም ኻሉ ሌሎች ደሞ አሉ።”

ጥላዬ ከተቀመጠበት ተነሣ።

አለቃ ሔኖክ ቤት ሲደርሱ፣ አብርሃ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “አድራችሁ
ነው?” ሲል፣ ደንደን ያለችውና ሰላሳ መጨረሻዎቹን የምትጠጋው
ባለቤታቸው ብቅ ብላ ሰላምታ ሰጠቻቸው።

“አድረው ነው? አለቃ አሉ?” አላት፣ አብርሃ።

ዘመድ ሙቷቸው ወደ ጎርጎራ ኸደዋል። እሑድ ይመለሳሉ
አለችው።

“እንግዲያማ ወደ ጃን ተከል እንውረድ” አለው፣ ለጥላዬ ።
ባለቤትየዋን ተሰናብተው እየተጨዋወቱ ከግቢ ሲወጡ፣ “እኔ ምልህ አለቃ ሔኖክ የቤተክሲያን አስተዳዳሪ ነበሩ እንዴ?”

“ስለምን ጠየቀኸኝ?”

“አለቃ ስትላቸው ግዝየ።”

“እ... አለቃ የተባሉትማ አሁን በኛ በቅኔ ቤት መምሮቻችንን መሪጌታ እንል የለ? ልክ እንደዛ ነው። ሹመት ነው። ሥዕል ተምረውና
ረዥም ጊዜ ሰርተው ሲያበቁ ሊቀጠበብት ኸዛም አለቃ ይባላሉ። አለቃ ትልቁ ሹመት ነው።”

“እህ” አለ ጥላዬ፣ እንደገባው ለማሳወቅ።

ፋሲል ቤተመንግሥትጋ ሲቃረቡ፣ “እኼ አጤ ፋሲል የተባሉት
ንጉሥ ግቢ ነው። ነገሥታቱ ኸዝኸ ግንብ እየሠሩ ነው የኖሩት” አለው
አብርሃ፣ በጣቱ እየጠቆመው።
“ትናንት ሳልፍ አይቸው እኮ ምን እንደ ሆነ አላወቅሁም።”
ጃን ተከል እንደ ደረሱ ወሬ ፈላጊ ሁሉ ግማሹ በቡድን ሌላው
ተሰባጥሮ ዋርካው ሥር ቆሟል። ጃን ተከል ጐንደሬዎች የክተት፡
የነገሥታት ሞት፡ የምሕረት ሆነ ሌላ አዋጅ የሚሰሙበት፣ የትኛው
መኰንን እንዳመጸ፣ ግዛቱን እንደተነጠቀ፣ የትኛው እንደተሾመ፣ የትኛው እንደተሻረ፣ ማንኛው ሹመቱ አነሰኝ ብሎ እንዳኮረፈ፣
ስለቤተመንግሥት የሥልጣን ፍትጊያና የሚቀጥለው ግብር መቼ እንደሆነ የሚከታተሉበት ቦታ ነው። እናም ጐንደሬዎች ጃን ተከል አካባቢ ሲያንዣብቡ፣ ወሬ ሲቀባበሉ፣ ፍሬውን ከገለባው ሲለዩ፣ ሐሳብ ሲለዋወጡ፣ ሲተነብዩና ሲሟገቱ ይወላሉ።

ጥላዬና አብርሃ ዋርካው ሥር እንደቆሙ፣ አብርሃ የሚያውቀው ሰው አግኝቶ ከእሱ ጋር ሲያወራ ጥላዬ ከጎኑ የቆሙ ሰዎች ሲያወሩ ጆሮውን ጣለ።

“ዛሬ ትገባለች አሉ።”

"ዛሬ?”

“አዎ! ወደርም የላት አሉ።”

“ቋራ ድረስ ዘልቀው እንዴት አገኟት ጃል?”

“ለንጉሥ ምን ይሳነዋል? ንጉሥ ይተክላል፣ ንጉሥ ይነቅላል ሲሉም
አልሰማህ?”

ጥላዬ፣ ስለወለተጊዮርጊስ እንደሚያወሩ ገባው። ሐሞቱ ፈሰሰ፣ሰውነቱ ሽምቅቅ አለ። አደባባይ ላይ የብቸኝነት ስሜት ወረረው።ፈንጠር ብሎ ቆመ። አብርሃ ጨዋታውን ጨርሶ ወደእሱ ሲመጣ፣ ወደሌላ ቦታ እንዲሄዱ ጠየቀው።

“ሰውየው እኮ ንጉሡ ኸቋራ ምሽት አጭተዋልና ዛሬ ትገባለች ነው ሚለኝ። እንግዲህ ነገ ግብር ይገባል። ይዠህ መጣለሁ።”

“ግብር?”

“አዎ! ድኻ እኮ ገብቶ ይበላል። እነሱ በልተው ኸተነሡ ወዲያ ሌላው ይገባል። ለኛ ለተማሮችማ ደስታችን ነው። በልተን አኮፋዳችንንም ሞልተን እንመለሳለን። እንመጣለን ነገ።”

“እኔ ስንኳ ገና እንግዳ ነኝ፣ ምን ብየ ነው ኸንጉሥ ግብር ምኸድ?
እኔ አሁን ግብር ሳይሆን ብራና ነው ምፈልግ፡፡”

ለብራናውማ ትደርስበታለህ።”
እንዴት የቤተመንግሥት ግብር ሊፈልግ እንደማይችል ገረመው
አብርሃ። “በል ወደ ታች እንውረድ። አንድ ዘመድ አለኝ ኸወደ ደንጋይጌ... የክርስቲያኑ... የነጋዴው ሰፈር። በዛው ሞኝ መቆሚያ ኸደን ደሞ ወሬ እንሰማለን።”

ጥላዬ ፊቱ ጥላሸት ለብሷል።
አብርሃ፣ የጥላዬን ፊት መለዋወጥና ለምንም ነገር ፍላጎት ማጣት አስተዋለና ስሜቱ ከየት እንደመጣ ተመራመረ። ኸቤቱ የወጣ.. ናፍቆት ይሆናል አለ፤ ለራሱ።.....

ይቀጥላል
👍13
#የኔ_ምሥል

ጠንቅቆ እማያውቀኝ
“ጠንቅቄ አውቅሃለሁ!”
ሲል አስጠነቀቀኝ
አስጠንቃቂዬ ሆይ
“ባክህ አታስቀኝ
እንኳን አስጠንቃቂ
ጠንቃቂ'ኳ አያውቀኝ
ሞትም ስፈቅድ ነው
በገረሩ እጆቹ
አንገቴን የሚያንቀኝ

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍6
#እ_ን_ድ_ረ_ሳ_ሽ

አንቺን እንድረሳሽ
መንገድ ጥረጊልኝ
ይህቺን ብቻ አርጊልኝ

ስምሽን እያነሱ እንዳያስታውሱኝ
በሞተው ትዝታ እንዳይቀስቅሱኝ
ያንቺ አለመሆኔን ዛሬ እንዳሳያቸው
ጨረቃን ፀሐይን ምድር አውርጂያቸው
ውቅያኖስ ባህራን ሰማይ ስቀያቸው

#እ_ን_ድ_ረ_ሳ_ሽ

የረገጥነው አስፋልት የሄድንበት መንገድ
ያ ያለፈው ፍቅር ያ ያለፈው መውደድ
ፍፁም ውሽት ብዬ እንድሸመጥጠው
ተፈጥሮን አዛቢ መውደዴን እንድተው

#እ_ን_ድ_ረ_ሳ_ሽ

ገደሉን ሙዩና ተራራውን ናጂው
ደመናን አውርደሽ አፈሩን ውሰጂው
የረገጥሽው መሬት አምሮ እንዲታይበት
በአበባው ፋንታ ሳማ ትከይበት

#እ_ን_ድ_ረ_ሳ_ሽ

ያ ሁላ ቃል ኪዳን ተበትኖ እንዲቀር
አይጥ ሐይቅ ትዋኝ ዓሳ ሰማይ ይብረር
በህይወት ባሉት ምትክ ሙታኖች ይነሱ
ነገስታት ይውረዱ ባርያዎች ይንገሱ

ይሄን ካረግሺልኝ

መውደዴን ይቀርና መኖር አቆማለሁ
በመኖር ብረሳሽ
ባለመኖርም ውስጥ አስታውስሻለሁ።

🔘ልዑል ሀይሌ🔘
7👍3
#ምንትዋብ


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

...ጥላዬ ፊቱ ጥላሸት ለብሷል።
አብርሃ፣ የጥላዬን ፊት መለዋወጥና ለምንም ነገር ፍላጎት ማጣት አስተዋለና ስሜቱ ከየት እንደመጣ ተመራመረ። ኸቤቱ የወጣ..ናፍቆት ይሆናል አለ፤ ለራሱ።

በፋሲል ቤተመንግሥት በስተግራ በኩል ወደ ላይ ሲወጡ፣
ሰዎች ከላይ ወደእነሱ አቅጣጫ ሲመጡ፣ ወንዶች ቆባቸውን፣ ሴቶች ክንብንባቸውን እያወረዱ እጅ እየነሱ ሲያልፉ፣ ጥላዬ እርስ በርሳቸው ሰላምታ የሚሰጣጡ መስሎታል። ጥቂት እንደተራመዱ፣ አብርሃ የተማሪ
ቆቡን አውልቆ እጅ ሲነሳ አየው።
መንገዱ ላይ ካለሁለቱ በስተቀር
ማንም የለም።

ጥላዬ፣ “ማነን ነው እጅ ምትነሳ? ኸኔና ኻንተ በቀር ማነም የለ
በምንገዱ” ሲል ጠየቀው።
“ማነነም! ሰዎቹስ እጅ ሲነሱ አላየህም እንዴ? እኼን ምንገድ አየህ?”አለው፣ አገጩን ወደፊት ቀደም አድርጎ፣ ሰፊውን የእግር መንገድ እያሳየው። “የንጉሡ መኸጃ ነው። እሳቸው ሲወጡ ማንም በዝኽ አያልፍም። አየኸው ያን ደጋን የመሰለ የደንጊያ ግንብ መተላለፊያ?ንጉሡ ወደ ራስጌ
አጤ ፋሲል ያሠሩት የራሶቹ መኖሪያ ነው...ኸዝኸ ከፍ ብሎ ነው ያለ... ወይ ደሞ ወደ ሌላ ቦታ ሚሄዱበት ነው።እሳቸው ባይኖሩም ቆብ አውልቆ እጅ መንሳት ደንብ ነው። ቦታው
እስተስሙ ቆብ አስጥል ነው።”

“እንደቤተክሲያን ነው በለኛ!” አለ ጥላዬ፣ ፈገግ ብሎ።
“ንጉሥ እኮ ፊታቸው ተሸፍኖ ነው ሚሄዱ። አሁን ታቦት ትኩር
ብለህ ታያለህ? አታይም! እሳቸውንም ፊታቸውን ጨርሶ አታይም።
አብረዋቸው ሚኸዱት ስንኳ ኸጎናቸው ሲራመዱ መሬት መሬቱን
እያዩ ነው። ደሞም አለልህ ሊቀመኳሱ... ንጉሥ አሳሳች ሚባለው። ልክ
እንደሳቸው ሁኖ ይወጣል። ንጉሡ ኸቤት ተቀምጠው እሱ እሳቸውን
መስሎ ይወጣል። ያን ግዝየ ሰዉ ንጉሡ መጡ ብሎ ይሰግዳል።
እንዲህ ዋዛ መስሎሀል! ወሬ ስሰማ እቴጌዎቹ ደሞ ሲወጡ ምንግዝየም
በጃንደረሳ እየተጠበቁ ነው።”
“ጃንደረባ ደሞ ምንድርነው? ስለምንስ ይጠበቃሉ?”
“ጃንደረባማ ... እቴጌዋን ሚጠብቀው... ስልብ ነው። ሚጠብቀው
ያው እቴጌዋ ኸሌላ እንዳይኸዱ ነዋ!” አለ፣ ሳቅ ብሎ።
ጥላዬ ለራሱ፣ ወለቴ
ጉድ ፈላባታ አለና ለአብርሃ፣ “እኼ
ቤተመንግሥት ሚባል ነገር ብዙ ጣጣ አለው” አለው።
“ወጉ እንግዲህ እንደዝኸ ነው። እኼ ምታየው... ኸቤተመንግሥቱ
አጠገብ ያለው ሁሉ ደሞ የባለርስቶቹ ምንደር ነው።”
ጥላዬ ዞር ብሎም አልተመለከተ።
አብርሃ፣ ጥላዬ ለሚያየው ነገር ሁሉ እምብዛም ትኩረትና ፍላጎት
የሚያሳይ አልመስል አለው። ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ገባው።
“ትመለስ ይሆን?” አለው።
“እረገኝ ስለምን?”
“እንግዲያማ ተጫወት። እኔኮ ይህ የመጣሁት አገር ላላምድህ ብየ ነው። እኼ አሁን ምንኸድበት ዘመዴ መልካም ሰው ነው። አንዱም እሱን ብየ ነው እጐንደር የመጣሁት።”
አልፎ አልፎ እየተጫወቱ ቁልቁል ወርደው ረጅም መንገድ ተጓዙ።
ጥላዬ ከቦት የነበረው የመጫጫን ድባብ እየለቀቀው መጣ። ያየውን
ሁሉ እያደነቀና እየወደደ የሆዱን ባር ባር ማለት ረሳ።

“ኸዝኸ ወረድ ስትል የዕጨጌው ሰፈር አለ” አለው አብርሃ
ሊያጫውተው ፈልጎ። “ሸማኔውም ወዲያ ነው። ማዶ ደሞ የባለእጌዎች ምንደር አለ። ለብቻቸው ነው ሚኖሩ። መቸም ባለእጌዎቹ ግንበኞች
አናጢዎች፣ ሸማኔዎች፣ ቀጥቃጮችና ሸክላ ሠሪዎች ናቸው ቤተመንግሥትን ሚያስጌጡ እነሱ ማዶሉ? እስላምጌ ደሞ በዝያ ስትዘቀዘቅ አለልህ። የስላሞቹ የነጋዴዎቹ ሰፈር ነው። ብዙ ሰው ይኖራል ኸዛ። በቅሎና ፈረስ ገባያውም ኸዛው ነው።”

ድንጋይጌ ሲደርሱ፣ “እኼ ገባያው ነው። ቅዳሜ ነው ሚቆም። ዛሬ
ጭር ቢል እንዲህ እንዳይመስልህ። ነጋዴውም... ሁሉም ነው ሚወጣ። ነገ ማልደን እንመጣለን” አለው።

ጥላዬ መልስ አልሰጠውም። ወለተጊዮርጊስ ከንጉሥ ጋር ግብር
በምትቀመጥበት ቀን መውጣት አልፈለገም። ከቤተክርስቲያኑ ግቢ እንደማይወጣ ለራሱ አስገንዝቦ ዝም አለ።

አብርሃ ዘመድ ቤት ገብተው መልካም መስተንግዶ ተደረገላቸው።ጥላዬ አልፎ አልፎ የያዘውን ጠላ ፉት ከማለትና ከአብርሃ ዘመድ የሚቀርቡለትን አንዳንድ ጥያቄዎች ከመመለስ በስተቀር አብርሃና ዘመዱ በትግርኛ ስለሚያወሩ በዝምታ ተውጦ፣ ጠላውን እየተጎነጨ፣
አንዳንዴም እየሰለቸው ቆይቶ፣ ከሰዐት በኋላ፣ ተነሥተው ወጡ።
ደብረብርሃን ሥላሤ ሲደርሱ ተለያዩ። ጥላዬ ጠዋት ተቀምጦበት የነበረው ዋንዛ ዛፍ ሥር ተቀምጦ ያየውን ሁሉ አሰበ። ጐንደር ልዩ ቦታ፣ ከግምቱ በላይ ሆነችበት፤ ወደዳት። የገባ ዕለት ዐዲስ ሕይወት ልትሰጠው የገባችለትን ቃል ኪዳን አጸናችለት። ድንገት የፈሰሰ
ሐሞቱ ነፍስ ዘራ። የአለቃ ሔኖክ ምሽት እሑድ ይመለሳሉ ብለው
ነግረውናል። አብርሃ ደሞ ሰኞ ጠዋት እንኸዳለን ብሎኛል። ብቻ አንዴ እሳቸውን ላግኛቸው፣ ኸዝያ ወዲያ ማደርገውን እኔ አውቃለሁ አለ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ጐንደርና ቋራ ምንና ምን

ወለተጊዮርጊስ፣ አፄ ፋሲለደስ ቅጥር ግቢ ስትገባ፣ አያቷ
እርምጃቸውን ገታ አድርገው፣ “እኼ አጤ ፋሲለደስ ያስገነቡት አሁን ጃንሆይ ሚኖሩበት ነው። እንግዲህ አንቺም ኸዝኸ ነው ምትኖሪው”አሏት።

“ኸዝኸ?” ብላ ዐይኖቿ እስከመጨረሻው ተከፈቱ።

የባለሦስት ደርቡ ህንጻ ግዝፈት አስደነቃት። ሰማይ ጠቀስ
መሰላት። በግንቡ ማዕዘኖች የተሠሩትን የእንቁላል ቅርፅ ያላቸውን ግንቦች አይታ ተደነቀች። ሰገነቱ ላይ ያለው ሰቀሰቅ ለመተኮሻ ተብሎ እንደተሰራ መገመት አቃታት። በእንቁላል ግንቦቹ መሃል ወደ ሰገነቱ
የሚወስደውን የዕንጨት ደረጃ ተመልክታ ምን እንደሆነ አልገባ አላት።

ዮልያና ቀጠሉና፣ “ጃንሆይ ኸዚያ ኸሰገነቱ ቁመው ሁሉን ይቃኛሉ፤
አንዳንዴም ኸዚያው ላይ ሁነው አዋጅ ይነግራሉ። አንቺም እንግዲህ ኸዚያ ላይ ምትቆሚበት ቀን ሩቅ አዶለም” አሏት፣ ሳቅ ብለው።

ዝም አለች። ያን መሰል ነገር አይታ ባለማወቋ፣ ከመንገድ ድካም
ጋር ተደምሮ አእምሮዋ ያየችውን ሁሉ መመዝገብ አልሆንለት አለው።

የግንቡ ግዝፈት፣ የንጉሥ ሚስትነት ልኩ ምን ድረስ እንደሆነ
ገለፀላት። ስለዚህ ዓለም ያላትን ግንዛቤ ሁሉ ግልብጥብጡን አወጣባት።ስለራሷ የነበራትን ግምት አዛባባት። “ንግሥት እሌኒን አረግሻለሁ”እየተባለች፣ የአፄ ሚናስ ደም በደምስሯ እንደሚንቆረቆር እየተነገራትና
በእንክብካቤ ያደገችው ልጅ ለእዚያ ለምታየው ግርማ ሞገስ ሁሌ የማትመጥን መስሎ ተሰማት።

ከቋራ መጥታ ያን መሰል ኑሮ ውስጥ መግባት ምን ማለት እንደሆን ማወቅ ተሳናት። እኛ እናት አባቷ ቤት መደብ ላይ ተኝተው የነበሩት ሰው ንጉሥ ናቸው ሲባል ድንገት እንደ ጨረቃ የራቁባትን ያህል ዛሬ ደግሞ የሚኖሩበትን ቤት ስታይና ልትኖር እንደታጨችበት ጭምር
ስታስብ፣ የእሷም ሕይወት ምን መልክ ሊይዝ እንደሚችል ለመጀመሪያ ጊዜ ተገነዘበች።

ጐንደር ታላቅ የሕይወት ግብዣ እንዳቀረበችላት ታወቃት። ሁሉም ካሰበችው፣ ከገመተችውና ካለመችው በላይ ሆነባት::
ፍርሐት ፍርሐት አላት።አካባቢዋን እንደ ዋዛ ታልፍ የነበረችው ወለተጊዮርጊስ፣ ቋራ እንደዚያ ቆማ የምታደንቀው ሰው ሰራሽ ነገር ባለማየቷ ለመጀመሪያ
ጊዜ ያየችውን ውበት አደነቀች። ጐንደርና ቋራ ምንና ምን አለች።
ያየችው ሁሉ የሰው ልጅ የእጅ ጥበብ ውጤት መሆኑን ተጠራጠረች።ያንን የመሰለ ውበት የቀረጹትን ሰዎችና እጆች ማየት ተመኘች።
👍101
የጥበብ ፍቅር በልቧ ውስጥ ሲሰርጽ ታወቃት።ቀደም ብሎ ቅጥር ግቢው መግቢያ ላይ ትጥቃቸውን አሳምረውና
በተጠንቀቅ ቆመው የነበሩትን በርካታ የቤተመንግሥት ዘበኞች አይታ መደንገጧን ሁሉ ረሳችው። የዘበኞቹ ንቃትና ኮስታራነት አስፈርቷት እንደነበረም ዘነጋችው።

ወደ ግቢው ሲዘልቁ፣ የግቢውን ንጽህና አስጠባቂው የግቢ አዛዥ
ንጉሠ ነገሥቱን የሚጠብቁት የእልፍኝ ዘበኞቹ፤ የግቢው ኃላፊ ሊጋባው፣ ያልተፈቀደለት እንግዳ እንዳይገባ የሚያደርገው እልፍኝ አስከልካዩ፣ የንጉሠ ነገሥቱን መሣሪያ ተሸካሚ ጋሻ ጃግሬው፣ ጃንደረባው፣ የጋማ ከብት ተንካባካቢ ባልደራሱ፣ ነፍጠኛው፣ ባለሟሉ፣ አዛዥ፣ ፋና ወጊው
የውጭና የውስጥ አጋፋሪው ብዛት፣ ወደ ላይ፣ ወደታች፣ ወዲህ፣ ወዲያ ማለት፣ መጠራራት፣ ትዕዛዝ ማስተላለፍና መቀበል ግቢውን ሁካታ በሁካታ አድርጎታል። ያ ሲንጫጫና ሲተራመስ የነበረው ሰው ሁሉ
እነሱን ሲያይ ፀጥ እረጭ አለ።
እያንዳንዱ መንገድ ለመልቀቅ ጥግ ጥጉን ይዞ በተጠንቀቅ ሲቆም፣ ዐይኑን ወለተጊዮርጊስ ላይ ተከለ፤ በውበቷ ተደመመ።

ወለተጊዮርጊስና አያቷ ሰዉ ለጥ እያለ ሰላምታ እየሰጣቸው ወደ
ቤተመንግሥቱ መግቢያ ሲደርሱ፣ የዙፋን ቤት ሹሙም ሰላምታ
ሰጣቸው። እሱን ሲያልፉ፣ በንቃት ከቆሙት ወታደሮች ጀርባ
አደግድገው የቆሙ የውጭ አስተናጋጆችም ለጥ ብለው እጅ ነሷቸው።

አብረዋቸው የመጡት ወንዶች ወደኋላ ሲቀሩ፣ ከደንገጡሮቹ ጋር
የአፄ ፋሲልንና የአፄ አድያም ሰገድ ኢያሱን ቤተመንግሥታት አልፈው
ቋሪ አነስተኛ ወደ ሆነ ሕንጻ ሲወሰዱ ወታደሮች፣ አደግድገው የቆሙ የውጭ መሪ አስተናጋጆችና በር ላይ የቆሙ የእልፍኝ አስከልካዮች አክብረዋቸው ወደ ውስጥ ገቡ። አንደኛዋ ደንገጡር ለዮልያና ማረፊያ ክፍላቸውን ስታሳይ፣ ሌላኛዋ ወለተጊዮርጊስን ወደ ተዘጋጀላት ክፍል ወስዳ ዕቃዋን
አስቀምጣላት ትንሽ እረፍት እንድታደርግ ነግራት ወጣች።

ደንገጡሯ ስትወጣላት፣ ወለተጊዮርጊስ ክፍሉ መሃል ቆማ በየመን ምንጣፍ ያጌጠውን ሳንቃና አልጋ ልብስ የለበሰውን አልጋ ትኩር ብላ አየች። ወደ ግራዋ ስትዞር በእንጨት መዝጊያዎች የተዘጋው ረጅም
ባለመስተዋት መስኮት የሐር መጋረጃ ለብሷል ። አነስተኛ ጠረጴዛ ላይ የተለኮሱ ጧፎች ሸክላ ማስቀመጫ ውስጥ ተቀምጠው ክፍሉን
አድምቀውታል።

ክፍሉን አማተረች። አንድ ሰው አንድ መኝታ ክፍል ለብቻው
እንዴት ሊይዝ እንደሚችል ገርሟት ፈዛ ቆመች። ጫማዋን አውልቃ፣
አልጋው ላይ አረፍ ከማለቷ፣ አብረዋት ከመጡት ደንገጡሮች አንደኛዋ እንድትታጠብ ወደ መታጠቢያ ክፍል ይዛት ሄደች። እሷም አያቷም ታጥበው እንደተመለሱ፣ ራት በልተው በየክፍላቸው ገብተው ተኙ።...

ይቀጥላል
👍101
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ...ጥላዬ ፊቱ ጥላሸት ለብሷል። አብርሃ፣ የጥላዬን ፊት መለዋወጥና ለምንም ነገር ፍላጎት ማጣት አስተዋለና ስሜቱ ከየት እንደመጣ ተመራመረ። ኸቤቱ የወጣ..ናፍቆት ይሆናል አለ፤ ለራሱ። በፋሲል ቤተመንግሥት በስተግራ በኩል ወደ ላይ ሲወጡ፣ ሰዎች ከላይ ወደእነሱ አቅጣጫ ሲመጡ፣ ወንዶች ቆባቸውን፣ ሴቶች ክንብንባቸውን እያወረዱ እጅ እየነሱ…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...«አስቻለው!» አለችው ሔዋን፤ የዘመቻ ጥሪ ደብዳቤ በደረሰው አምስተኛ ቀን ላይ በዕለተ አርብ ከጠዋቱ ሦስት ሰአት አካባቢ ከቤቱ በመገኘት።

«ወይ!» አላት አስቻለው አልጋው ላይ ጋለል ብሎ ተኝቶ ከጎኑ ቁጭ
ያለችውን ሔዋንን ቀና ብሎ እየተመለከታት።
«ሰሞኑን የምሰማው ወሬ ምንድነው?» ስትል ዓይን ዓይኑን እያየች ጠየቀችው።
«ምን ሰማሽ?»
«ጥሩ ያልሆነ ወሬ::»
«ንገሪኛ!» አላት አስቻለው ፈገግ ብሎ እያያት፡፡
«ሳታውቀው ቀርተህ ነው?»
«ብዙ ይወራ የለ! የትኛውን ማለቴ ነው፡፡»
«በመሥሪያ ቤትህ በኩል ለስድስት ወር ያህል ዘመቻ ሂድ ተብለህ እምቢ ማለትህን ሰማሁ፡፡» አለችው በፍርሀት አስተያየት እያየችው።
«አዎ! አልሄድም ብያለሁ፡፡ አሁንም አልሄድም፡፡»
«ግን ለምን?»
«እንደማልሄድ የነገሩሽ ሰዎች
ምክንያቴንም ሳይነግሩሽ የቀሩ
አልመሰለኝም፡፡ አንቺም አትደብቂኝ፡፡» አላት የሔዋንን ግራ እጅ ይዞ እየደባበሳት፡፡
«ነግረውኛል። ግን ሆዴ በጣም ፈራ»
«ለምን ብለሽ?»
«ግዳጅ ላለመቀበልህ ምክንያቷ እኔ የምሆን ስለመሰለኝ፡» አለችና ሔዋን ዓይኖቿ ላይ ያቀረረ እንባዋን በለበሰችው ስከርፍ ጥርግ አደረገች።
«አይዞሽ ሔዩ፣ አትፍሪ! ምንም አይመጣም፡፡»
«ተው እስቹ ምንም አይመጣም አትበል። ኑሮህ ሁሎ ይበላሻል፡፡ ለአንተ ኑሮ መበላሽት እኔ ምክንያት መሆን የለብኝም፡፡ የአንተ ከተበላሸ የኔም ይበላሻል»
አለችና እንባዋን አሁንም በጉንጯ ላይ ታወርደው ጀመር።
“አታልቅሺ የኔ ፍቅር። የኔ ሕያወት የሚበላሸው አንቺን ከአጣው ብቻ
ነው:: ዘመቻ ከሄድኩ ደግሞ አንቺን ላጣሽ እችላለሁ። ስለዚህ አልሄድም»
«አንተ ዘመቻ ብትሄድ እኔ የት እሄድብሃለሁ?»
«እህትሽ እና ባርናባስ እየሰሩልሽ ያለውን መንገድ እጣሽውና ነው ወይስ አልገባሽ ይሆን?»
አውቃለሁ። ገብቶኛል::»
“ታዲያ የኔ ዘመቻ መሄድ እንዴት አንቺን አያሳጣኝም ብላሽ ትገምቻለሽ»
«ፈጽሞ አስቻለው ፈጽሞ አያለያየንም።
«እንዴት?»
«እኔም ላጣህ አልፈልግምና!»
«ወደሽ ሳይሆን ያስገድዱሻል»
«አንድ ነገር አትርሺ ሒዩ! ያለሽው በእህትሽ ቤት፤ የምትበይው
የምትጠጪው የእሷን፡ በዚያ ላይ ባርናባስን የሚያህል የፖለቲካ ስልጣን ያለው ወዳጅ አላት።
በዚሁ ላይ ያቀረቡልሽ ወዳጀ በከተማው ውስጥ አለ የተባለ ሀብታም 'በድሉ አሽናፊ' የባርናባስ ስልጣንና የበድሉ ገንዘብ ከተባበሩ እንዴት እኔና አንቺን
መለያየት ያቅታቸዋል?» አለ አስቻለው ከተንጋለለበት ቀና ብሎ ሔዋንን ፊትለፊት እያያት፡፡
«ይህን ሁሉ ግን የታመነ ልብ ያሸንፈዋል::» አለችው ሔዋን የአስቻለውን ደረት እየደባበሰች።
«ፈጽሞ፡ በበኩሌ ማመን ያስቸግረኛል።»
«ስማ አስቻለው!»
«ወይ የኔ ፍቅር»
«እኔንም አንተንም ለአደጋ የሚያጋልጥ አጋጣሚ የሚፈጠረው አንተ ዘመቻ አልሄድም ብለህ የቀረህ እንደሆነ ነው::»
«እንዴት?»
«ዘመቻ ካልሄድክ ከሥራ ያስወጡሃል! ወይም ያስሩሃል። ምናልባት ሊገድሉህ ወይም ሊያስገድሉህ ይችላሉ። አየህ አስቹ! ሥራ ከሌለህ ገንዘብ
አይኖርህም። ገንዘብ ከሌለህ ደግሞ ችግር ያበሳጭህና ለችግርህ ምክንያት በሆኑ
ሰዎች ላይ አደጋ አድርስህ በሌላ የከፋ ችግር ወስጥ ልትገባ ትችላለህ:: ያኔ ልብህ ለጭካኔ እንጂ ለፍቅር ቦታ አይኖረውም፡፡ ዞሮ ዞሮ ለኔ አልሆንከኝም። ታስረህ ማየቱም ለአዕምር'ዩ አይመቸውም፡፡ ብትሞትም ሀዘኔ መራርና የዕድሜ ልክ ነው፡፡
ግን ይህ ሁሉ ይወገድ ዘንድ ግዳጁን ተቀብለህ መሄድ ስትችል ለምን ሁለታችንም እንቸገራለን?» አለችው በትካዜ ውስጥ ሆና ዓይን ዓይኑን እያየች።
«ሔዩ የኔ ችግር አልገባሽም፡፡»
«ገብቶኛል። ግን እሱም ቢሆን መላ አለው::»
«ምን ታየሽ?»
«በቃ እኔ ከእት አበባ ቤት እወጣና አንተ በምትቆርጥልኝ ገንዘብ ከትርፍዬ ጋር በአንተ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፡፡ ግዳጅህን ፈጽመህ ስትመለስ እኔና አንተ ራሳችን በምንደግሰው ሰርግ ተጋብተን አብረን መኖር እንችላለን:: ለኔና
ለአንተ ፍቅር የሚበጀው ይሄ ብቻ ነው።
ከዚህ በኋላ ሁሉቱም ትካዜ ወስጥ ገቡ። ሁለቱም በየበኩላቸው ያስቡ ጀመር
በየልባቸው ያለውን ነገር በማስታወስ።

እሷ አላወቀችም እንጂ ዛሬ ሔዋን ያቀረበችው ሀሳብ አስቻለው ራሱ
በተካፈለበት ጉባዔ ላይ የተቀየስ አቅጣጫ ነበር፡፡ እርግጥ ነው የአስቻለው የዘመፍቻውን ግዳጅ ያለመቀበል ውሳኔው እጅግ ጠንካራ ነበር፡፡ ነገር ግን ታፈሡና
በልሁ መርእድን ጨምሮ ሀሳቡን እንዲቀይር ብዙ ታግለውታል የስድስት ወር ጊዜ አጭር
መሆኗን ዘመቻውን ባለ መቀበሉ
ከሥራ መባረር ምናልባት እስር፣ ከዚያም ያለፈ ክፉ ነገር ሊመጣ እንደሚችል እየጠቀሱ ሊያግባቡት ሞክረዋል በዚያው በራሱ ቤት መርዕድና በልሁ ጫት እየቃሙ ታፈሡ ራሷ እስከ ውድቀት ሌሊት ድረስ አብራቸው በመቆየት በዚሁ ጉዳይ ላይ ከአስቻለው ጋር የተፋጩት ገና ደብዳቤው በደረሰው ማግስት
በአስቻለው ግዳጅ የመቀበልና
ያላመቀበል ውይይት ወቅት ጉልህ ሥፍራ ተሰጥቶት የነበረው የአስቻ ለውና የሔዋን ፍቅር ጉዳይ ነበር።

ለአስቻለው ለግዳጅ መመልመል የባርናባስ ሚና ወሳኝ ሊሆን እንደሚችል ሁሉም አምነውበታል እሱ ደግሞ ከራሱ ፍላጎት በተጨማሪ ሸዋዬ የምትጥልበትን
አደራ ለመወጣት ጭምር አስቦና ተገፋፍቶ የፈጸመው ስለመሆኑ አይጠራጠሩም።ሁለቱ ሰዎች የአስቻለውን አለመኖር ተጠቅመው ሊፈፅሙት ያቀዱት ነገር በሁሉም አእምሮ ውስጥ አለ። ሔዋንን ከበድሉ አሸናፊ ጋር ሊያላምዱ ነው። ይህ ደግሞ በአስቻለውና በሔዋን ፍቅር ላይ ጥላውን ሊያጠላ ነው።
ይህን አደጋ ለመከላከል ይቻል ዘንድ መላ መልምለዋል። በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ሔዋንን ከሸዋዬና ከባርናባስ መዳፍ ውስጥ ፈልቅቀው ማወጣት፣
ዋሽቶም ለምኖም ሔዋንን የችግሩ ፈቺ አንድ አካል ማድረግ፡፡ በዚህ ጉዳይ አስቻለውን ጨምሮ ሁሉም ተስማምተዋል። ሔዋንን የማሳመን ጉዳይ ለታፈሡ እንግዳሰው ተሰቷት እሷም የተጣለባትን ሃላፊነት ለመወጣት አልዘገየችም፡፡ለአስቻለው የዘመቻ ትእዛዝ በደረሰው አራተኛ ቀን ላይ ነበር ሔዋንን ከመሰረተ ትምህርት ሥራዋ ስትመለስ ወደ ቤቷ ጎራ እንድትል የጠየቀቻት፡፡ሔዋንም
ጥያቄውን ተቀብላ ከታፈሡ ቤት ተገኘች።
«ሔዩ ተቸግረናል» ነበር ያለቻት ታፈሡ ሔዋንን ሶፋ ላይ አስቀምጣ እሷም ከፊትለፊቷ በመቀመጥ፡፡
«ምን ሆናችሁ?»
«አስቻለው በመሥሪያ ቤቱ በኩል ዘመቻ ታዝዞ ነገር ግን አልሄድም
በማለቱ እኔም በልሁና መርዕድም ተጨንቀናል፡፡»
«ዘመቻ?»
«አዎ»ለስድስት ወር ብቻ ለሚቆይ የሙያ ዘመቻ ወደ ኤርትራ እንዲሄድ በደብዳቤ ታዟል።እሱ ግን ሔዋንን በሸዋዬ ቤት ውስጥ ትቼ አልሄድም እያለ አስቸግሮናል»
«ኤርትራ ማለት የጦርነቱ አገር አይደል?»
«አዎ፣ እሱ ግን የሚሄደው ሊዋጋ አይደለም በጦርነቱ ለሚጎዱ ቁስለኞች የህክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው።»
«ታዴያ አንዴት ይሻላል?»
«ችግሩ ያለ አንቺ አይፈታም»
«ምን አድርጌ እፈታዋለሁ?»
«አስቹ የሚለው ወደዚህ ዘመቻ እንድሄድ ያደረጉኝ ሸዋዬና በርናባስ ናቸው። ዓላማቸውም ሔዋንን ለበድሉ አሸናፊ ሊድሩ አስበው ነው።ስለዚህ ፍቅሬን ከማጣት እነሱ ላይ አደጋ አድርሼ እስር ቤት ብገባ ይሻለኛል እያለ ድርቅ አለብን»
👍12
«ያን ያህል ታጸሡዬ!»
«አዎ ሔዋን ፤ ስሜቱ ተለዋውጦብናል።»
«ምን አድርጊ ትይኛለሽ ታዲያ?»
«አንቺ ከሽዋዬ ቤት ውጭና በአስቻለው ደሞዝ ከትርፌ ጋር አስቻለው ቤት ኑሪ»
«አይከብድም ታፈሡዬ?»
ለፍቅር ሲባል ከዚህም በላይ መስዋዕትነት ይከፈላል። ይህን ካላደረግሽ የአስቻለው ህይወት መበላሽቱ ነው፡፡ አንቺም ታጭዋለሽ፡፡ እሱም ያጣሻል፡፡
ዘመቻ ካልሄደ ከስራ ያባርሩታል ያኔ ይቸግራል።ከተቸገረ ይበሳጫል ከተበሳጨ አደገኛ የሆነ የህይወት ርምጃ ይወስዳል። ኢላማዎቹ ደግሞ ሸዋዬና ባርናባስ ናቸው።
አስጨናቂው ነገር ይህ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአንቺ ቆራጥ ውሳኔ ሰላማዊ መፍትሄ ያገኛል።
«እኔ ቢሳካልኝ እሱ ግን ዘመቻውን እሺ ብሎ ይቀበላል?»
«አያወላውልም፡፡»

ይህ ነበር ከዛሬው የአስቻለውና የሔዋን ውይይት በስተጀርባ የነበረው ክንውን።
«አስጨነቅሽኝ ሔዋን!» አላት አስቻለው የሆዱን በሆዱ አድርጎ፡ ሔዋን ብታውቀው ኖሮ በዕለቱ አልጋ ላይ ተኝቶ ይጠባበቅ የነበረው እንኳ ይህንኑ ሀሳብ
ልታቀርብለት እንደምትመጣ ስለሚያውቅ ነበር፡፡
«ቢጨንቀኝ ነዋ አስቹ!»
«ግን ከልብሽ አምነሽበታል?»
«አሁን አሁን ሲገባኝ እንዲያውም የዘገየሁ እየመሰለኝ መጥቷል:: ራሴ እየተጨነኩ አንተንም ሳስጨንቅ መቆየት አልነበረብኝም። አንተ ጋር ሆኜ
የሚመጣውን ችግር ሁሉ በአንተ ከለላ ልከላከለው ወስኛለሁ::»
አስቻለው ከተንጋለለበት ብድግ ብሎ ሔዋን ሳማት እሷም ሳመችው። ግን ደግሞ ሁለቱም ሆዳቸው ባባና ተላቀሱ።

💫ይቀጥላል💫
👍9
#እቴጌና_እምዬ

ታሪክ ለመከወን ለዚች ላገሪቱ
ከፍ ብላ እንድትታይ ከልብ እየሻቱ
ካንድ ወንዝ ባንድ ቀን የተወለዱቱ
ልብ ላይ በፍቅር የተቀመጡቱ
እምዬ #ምኒልክ እቴጌ #ጣይቱ
ላድር ባዮች እንጂ
ለኛስ ሕያው ናቸው ዘላለም ሳይሞቱ!

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
11👍4🤩3
#እኔ_ላንቺ

"ምርኩዝና ባላ ምሶሶም አይሻ
ሁሉን ይሸከማል ያ'ፍቃሪ ትከሻ"

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍94
#የትዝታ_አልዛይመር

ረስቶኛል አትበይኝ ሞት ይርሳኝ ላልረሳሽ
በወዳጄ አልምልም ወዳጅሽን ይንሳሽ

ይኸው ለምሳሌ...
የህይወት ታሪክሽን
አብጠርጥሬ አውቃለሁ
ልደትሽን አልረሳም ጳጉሜ ሰላሳ ነው
በዛ በምርጡ ቀን
በናትሽ ምጥ ምክንያት ኩሽና ገብተሻል
በአውሮፓ አህጉር ኮንጎ ተወልደሻል

እናም ውዷለሜ...
ረስቶኛል አትበይኝ ሞት ይርሳኝ ሳልረሳሽ
በመዳጄ አልምልም ወዳጅሽን ይንሳሽ

ይኸው ለምሳሌ
ስሰ አቋምሽ ውበት ዛሬም አስባለሁ
ከጎኔ ብትርቂም በደንብ አውቀዋለሁ
ኪሎሽ ለምሳሌ ሜትር ካርባ ነበር
ቁመትሽ ርዝመቱ ሦስት ሰዓት ነበር
የቆዳ ቀለምሽ ትንሽ ወፈር ቢልም
የፀጉርሽ ርዝመቱ ዥንጉርጉር ቢሆንም
ቆንጆ ነበርሽ ያኔ...

እናም ውዷለሜ...
ረስቶኛል አትበይኝ ሞት ይርሳኝ ላልረሳሽ
በመዳጄ አልምልም ወዳጅሽን ይንሳሽ

ይኸው ለምሳሌ...
ያኔ በደስታችን
ሲኒማ ቤት ገብተን ሬዲዮውን አይተናል
ሶደሬም ተቃጥረን ሞተሩን ዋኝተናል
የፍቅር ቸኮሌት በፍቅር ዘፍነናል
ከዛም የሆነ ቀን
በሆነ አጋጣሚ የሩቅ ዘመድ ታሞ
ስጠፋብሽ ደሞ
ፖስታ ደዉለሻል
እንደ አቤ ቢቂላ ባዶ እጅሽ ሮጠሻል

አይ አንቺ...

የዋህኮ ነበርሽ..
የተቸገረውን እንጀራ አጠጥተሽ
የበረደውን ሰው ብርድ ልብስ አብልተሽ
ነበር የምትሸኚ
ትውስታዬ ይህ ነው እንዳትገረሚ
አዙሮ ከጣለሽ በፍጥነት ታከሚ
ቆይ ግን ስታስቢው
በክህደት ክፋትሽ ለቆሸሽ ፍቅር
ካይምሮዬ ጓዳ ምን ትዝታ ላስቀር?
እናም ስለዚህ ነው
በመርሳት በሽታ ራሴን ያሳመምኩት
በሚያየኝ ሰው ሁሉ ታሟል የተባልኩት

ትዝታሽን ብይዝ ላይገባኝ ላይረባኝ
'አልዛይመሩ' ቀርቶ
ደደብ ነህስ ብባል እኔ ምን አገባኝ?

🔘ልዑል ሀይሌ🔘
👍126
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ
በሰላም አደረሳችሁ!
👍8
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

...እሷም አያቷም ታጥበው እንደተመለሱ፣ ራት በልተው በየክፍላቸው ገብተው ተኙ።
ወለተጊዮርጊስ፣ ጠዋት ከእንቅልፏ ስትነቃ የት እንዳለች ግራ ገባት።ቀስ በቀስ ጐንደር ቤተመንግሥት፣ እንግዳ ማረፊያ ክፍል ውስጥ መሆኗ ተገለጠላት። በመስኮቱ ቀዳዳዎች የገባውን ብርሃን አይታ ፀሐይ መውጣቷን አወቀች። አርፍዳ እንደነቃች ገባት፡፡ ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ገብቷት እዛው አረፍ ብላ ቆየች። ሲሰለቻት ተነስታ ስትወጣ፣ በር ላይ ቆመው የእሷን መውጣት የሚጠባበቁ ሁለት
ደንገጡሮች አያቷ ወዳሉበት ክፍል ወሰዷት።

አያቷ መስኮቱን ከፍተው አልጋው ላይ ጋደም ብለው የጸሎት
መጽሐፍ ያነባሉ። ስትገባ መጽሐፉን አስቀምጠው፣ “አድረሽ ነው? ሲሏት ደሕና ማደሯን ለመግለጽ እግራቸው ላይ ተጠመጠመች።በይ ተነሽ አሏት፣ ስሜታቸው ተነክቶ። ትንሽ እንደቆዩ ደንገጡሮቹ መጡላቸው። መፀዳጃ ቤት ወስደዋቸው ሲመለሱ ቁርስ አደረጉ።
ዮልያና ያረፉበት ክፍል ተመልሰው ስለ ምሳው ተወያዩ።

“ዛሬ እንግዲህ ኸጃንሆይ ጋር ማድ ምቀርቢበት ቀን ነው። እናም የነገርሁሽን ሁሉ ልብ እንድትይ። እንደገባሽ ኸደሽ በቅጡ አጎንብሰሽ እጅ ትነሽና እግር ትስሚያለሽ። ተቀመጭ እስቲለሽ ትጠብቂና ያመላከቱሽ ቦታ ኸደሽ ትቀመጫለሽ...”

የጀመሩትን ሳይጨርሱ ሁለት ደንገጡሮች በር ላይ ሆነው ለጥ ብለው እጅ ከነሱ በኋላ፣ አንደኛዋ፣ “እመቤቶቼ እንፋሎት እጥበት
እንኸዳ” አለቻቸው።

ወለተጊዮርጊስና አያቷ በደንገጡሮቹ ተከታይነት የአፄ ፋሲልንና የታላቁ ኢያሱን ቤተመንግሥታት ከኋላቸው ትተው ወደ ታች ወረዱ። የጻድቁ ዮሐንስን ቤተመዛግብት በግራ በኩል፣ ቤተመንግሥታቸውን
ወለተጊዮርጊስ በወሬ እንጂ በአካል አይታቸው የማታውቃቸውንና በስተቀኝ አልፈው፣ አንበሶቹ ቤትጋ ሲደርሱ አያቷ፣ “አንበሶች” ሲሉ ጠዋት ላይ ሲያገሱ የሰማቻቸውን አንበሶች ለማየት ቆም አለች። በአድናቆት ካስተዋለቻቸው በኋላ፣ከአንበሶቹ ቤት ጀርባ ያለውን የሣልሳዊ ዳዊትን የሙዚቃ አዳራሽ አሁንም በቀኝ በኩል ትተው ወደ ፊት አመሩ። ወለተጊዮርጊስ በየቤተመንግሥታቱ መተላለፊያ ላይ የተሰደሩት ወታደሮችና በየበሩ ላይ የቆሙት እልፍኝ አስከልካዮች
ቁጥር አስገረማት፣ ከእነሱ ጋር የመፋጠጥ ያህል ተሰማት። በመጨረሻም ቁመቱ አጠር ያለ ነገር ግን ሰፋ ያለ ግንብ ውስጥ ገቡ።

“እመቤቶቼ እኼ ንጉሦቹና እቴጌዎቹ እንፋሎት ሚገቡበት ነው” አለቻቸው፣ ከደንገጡሮቹ አንዷ ። ቀጥላም፣ “አጤ ፋሲል ናቸው ያሠሩት። እኼኛው የእቴጌዎቹ ነው። የንጉሦቹ በያኛው በኩል ነው።ልብሳችሁን ታወልቁና እነዝኸ መንጠቆዎች ላይ ትሰቅላላችሁ።ጌጦቻችሁን ደሞ እነዝኸ ውስጥ ታኖራላችሁ” አለቻቸው፣ ትንንሾቹን የድንጋይ ፉካዎች በሌባ ጣቷ እያመለከተቻቸው።

“በዝኸ በር ግቡና ኸነዛ ዳርና ዳር ያሉ መቀመጫዎች ላይ ተቀመጡ። ያ ሚጨሰው አረግ እሬሳና ጦስኝ ነው። እኛ ከውጭ ሁነን እንጠብቃለን” ብላቸው ከሌላዋ ደንገጡር ጋር ተያይዘው ወጡ።

ወለተጊዮርጊስና ዮልያና ጌጦቻቸውን አስቀምጠው፣ ልብሳቸውን አውልቀው የተባለው ክፍል ውስጥ አጎንብሰው ገብተው ተቀመጡ።ክፍሉ መሃል ላይ የተደረደሩት ድንጋዮች ሲግሉ፣ “አየሽ ያነን ምታይውን ወናፍ በዚያች በምታያት ቀዳዳ አሳልፈው፣ ኸውጭ ሁነው
ደንጊያዎቹን ያግላሉ” አሏት።

ድንጋዮቹ ሲግሉ፣ ከውጭ በቀርከሀ ዋሽንት ውሃ ድንጋዮቹ ላይ ፈሰሰ። ላብ አጠመቃቸው። እንደመታፈን ሲሉ ከጣሪያው ላይ ያሉት ትንንሽ ቀዳዳዎች ከውጭ ተከፈቱላቸው።

“አየር እንዲገባ ቀዳዳዎቹን ከፈቱልን። አለያማ ታፍነን እንሞት
ነበር” አሏት።

ቀዳዳዎቹ ተመልሰው ተዘጉ።

“እንፋሎት ተመልሶ እንዲመጣልን መልሰው ዘጉት” አለች፣ ነገሩ
የገባት ወለተጊዮርጊስ።

“እንዲህ አይሁን እንጂ እኛም እኮ በእንፋሎት መታጠብ እናውቃለን
አሉ፣ ዮልያና።

እሷ ይህን ዓይነቱን ነገር ከእሳቸው ቀርቶ ከማንም ጋር አድርጋው
ባለማወቋ እፍረቱ አላስቀምጥ አላት። ሰውነቷ እየተሟሟቀ ሲመጣ ግን ዘና አለች። ከፊቷና ከራሷ ላይ የሚፈልቀውን ላብ አስር ጊዜ ስትጠራርግ አዩና፣ “አይዞሽ አሁን ያነን ሁሉ የምንገድ ድካም ድራሹን ነው ሚያጠፋልሽ” አሏት።

ሲጨርሱ ወደ ገላ መታጠቢያው ክፍል ሄደው ዙርያውን የተከበበ
ገንዳ ውስጥ መጀመሪያ እሳቸው፣ ቀጥሎ እሷ ታጥበው የክት ልብሳቸውን ለብሰው ሲወጡ፣ ወለተጊዮርጊስ ከመቼውም ጊዜ በላይ አለምልማለች።

ዕረፍት እንዲያደርጉ ማረፊያ ክፍሎቻቸው ተወሰዱ።

ብዙም ሳይቆዩ ደንገጡሮቹ ለወለተጊዮርጊስ በእቅፋቸው ነጭ ረጅም የሐር ቀሚስ፣ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች ያጌጠ ጥቁር ካባ፣ የቆዳ ጫማ፣ ነጭ የሐር ሻሽና ከወርቅ የተሠሩ የአንገትና የጆሮ ጌጦች ይዘው መጡ። አንደኛዋ ታጥቦ የነበረውን ፀጉሯን ሾርባላት ሄዱ።ወለተጊዮርጊስ የመጣላትን ልብስ፣ ካባ፣ ሻሽ፣ ጫማና ጌጦች ግልጽ በሆነ አድናቆት አገላብጣ ስታይ፣ ጋደም ብለው የነበሩት አያቷ አይዋት።
በለጋ ዕድሜዋ እዚህ ደረጃ በመድረሷ ተደስተው እንባቸው ቀረር አለ። እንባቸው እንዳታይባቸው በነጠላቸው ተሸፍነው ፊታቸውን ወደ
ግድግዳው አዞሩ። ራሳቸውን አረጋግተው ነጠላቸውን ከፊታቸው ላይ ገለጥ አደረጉና ወደ እሷ ዞሩ። አሁንም የመጣላትን ዕቃ ታገላብጣለች።

“ጥሎሽ የመጣልሽም ኸዝኸ ይበልጥ እንጂ አይተናነስም። እሱን ልበሺ ስልሽ ለመንገድ አይሆንም ብለሽ የኔን ለበሽ። ለማንኛውም ጥሎሽ ይለቅ። አሁን እሱን አስቀምጭና ወደ ጃንሆይ ስትኸጂ እንዴት እንደሆነ አንዴ ተወጪልኝ” አሏት።
ልብሶቹን አልጋው ላይ በጥንቃቄ አኑራ፣ ክብ ዐይኖቿን ሰበር አድርጋ
በተመጠነ፣ ንግሥታዊ በሚመስል እርምጃ ወደ እሳቸው ስትጠጋ፣ “እኼ ነው የኔ ልዥ ። ያሳየሁሽን ሁሉ አረሳሽም። እንዲያውም አክለሽበታል” አሉና ጠጋ እንድትላቸው በእጃቸው ጠቆሟት። ተጠግታቸው
ስታጎነብስ፣ “እንዲህ ያለች ምሽት ኸየትም አያገኙ” ብለው ጉንጫን
መታ አደረጓት።

ቀና አለችና የእፍረት ሳቅ ሳቀች። “ስንት መልከ መልካም ወይዛዝርት
አለ በሚባልበት... ስንት የንጉሥ ዘር ባለበት አገር?” አለቻቸው።

በስጨት እንደማለት ብለው፣ “አንቺ ደሞ እንግዲህ ሰው ሚልሽን ስሚ አሉና ከተጋደሙበት ተነሥተው ተቀመጡ። ወገባቸውን በሁለት እጃቸው ይዘው፣ “የንጉሥ ዘር የሆነ ሁሉ መልክ አለው መሰለሽ? አንቺ ሁሉን አሟልቶ ሰቶሻል። ደሞ ጃንሆይ የንጉሥ ዘር ቢፈልጉ አጥተው? አንቺስ ብትሆኚ የንጉሥ ዘር ማዶለሽ? አንድ መኰንን አልገዛም ብሎ
ሲያውክ በጋብቻ ለማሰር፣ ጥቅም ለማስጠበቅ አሊያም ደሞ አመጥ
ለማብረድ ሲሉ መሰለሽ አንቺን ማግባት የፈለጉ? ወደውሽ ነው።
ትምርትም ቢሆን ዳዊት ደግመሻል። ጥፈትም ቢሆን ሚደርስብሽ የለ። የጐንደር ወይዛዝርት እኩሌታዎቹ ስንኳ ዳዊት አልደገሙም...
ይቅር ኻንቺ ሊተካከሉ... ኧረ እንዲያው ምንሽም አይደርሱ።”

“አየ እሚታዬ ልዥሽ ስለ ሆንኩ ነው እንደሱ ምትይው። ግና ኣንድ
ጥያቄ ልጠይቅሽ... ጃንሆይ ኸዝኸ በፊት አላገቡም ነበር እንዴ?”

“አግብተው ነበር እንጂ።”

“እህስ?”

“በእንዴት ያለ ወግ ተጋብተው እሷ የሠርጉ ምሽት እንደ ወጉ ግብር
አብልታ፣ እህል ውሃ ስንኳ ሳትቀምስ በጥኑ ታማ በበነጋው ሞተች።እደብረብርሃን ሥላሤ ነው የተቀበረች፤ ኸዛው እናታቸው ኻሉበት። መርዝ ነው ይላሉ። እንዴት ያለች አለላና ብርቱ ሴት ነበረች አሉ። ደማምና ብርቱ ይሆናቸዋል።”

“እንዴ?” አለች ወለተጊዮርጊስ፣ ሰውነቷን ያልታወቀ ነገር ወረር
አድርጓት። ተነስታ ቆመች። “እኔስ ፈራሁ። እኔንስ በመርዝ ቢገሉኝ?"
👍171🔥1
“አንቺ ደሞ ማይሆን ነገር አታውሪ። ይልቅስ ተቀመጭ። መርዝ አሉ እንጂ ማን አወቀ? ያልታወቀላት እመም ኖሯት ቢሆንስ? ያንቺና የሷ እየብቻ ዕድል ነው። መኳንንቱና ወይዛዝርቱ ባንቺ ቢያጉረመርሙ ኸቋራ የመጣች በሚል ነው።”

“ኸቋራ ብመጣ ምን ሞገድ አለው?” በነገሩ ተገረመች። ተቀመጠችና እንደ ሁልጊዜዋ ቀሚሳቸውን ከፍ አድርጋ እግራቸውን ማሻሸት
ጀመረች።

“ጎሽ የኔ ልዥ። የቅድሙ ሙቀት እኮ አድክሞኛል። አየ አንቺ ደሞ
ንቀታቸው... ወደ ፊት ታቂዋለሽ ሁሉንም። አሁን አንቺ እኼን እኼን
ማሰብ የለብሽም” አሉ፣ መንገራቸው ቆጭቷቸው።

ዝም ብላ ቆየችና፣ “ጃንሆይ መቸ ነው የነገሡት?”

“ዓመት አለፋቸው። በልዥነታቸው ነበር እኮ እወህኒ አምባ የወጡ።
ኻንዴም ሁለቴ ነግሣለሁ ብለው አምልጠው፣ ኋላ ተይዘው ታሠሩ።
በንጉሥ ዮስጦስ ግዝየ ነው እኼ ሁሉ የሆነው።”

“ወህኒ አምባ የት ነው? እሳቸውስ ለምነው የኸዱ?” አለች፣ አገጫን
በቀኝ እጇ ይዛ።

“አየ የልዥ ነገር... መች እሳቸው ኸዱ። ንጉሡ ሰደዋቸው እንጂ።
ወጉ እግዲህ ነገሥታቱ እስቲሞቱ ድረስ ሌሎች መሣፍንትን ሆነ የገዛ
ልዥቻቸውን እወህኒ አምባ አስሮ ማቆየት የተለመደ ነው።”

“ለምነው ሚያስሯቸው?” ግንባሯ ኩምትር አለ። ነገሩ ሁሉ ግራ
አጋባት።

“እንንገሥ ብለው ጦር እንዳያነሱባቸው... ባላልጋ ነን ብለው አልጋ እንዳይነቀንቁ።”

“አልጋ?”
“አልጋማ ዙፋኑ ነው። ነገሥታቱ የራሳቸውን ልዥች በልዥነታቸው
እወህኒ አይሰዱም። ጠላት እንዳይገድልባቸው ማንነታቸው ሳይታወቅ ኸሚኖሩበት ራቅ ያለ ቦታ ኸዘመድ ወይ ኸወዳጅ ዘንድ ይሰዱና ትምርት ጥፈት፣ ንባብ፣ ዳዊት መድገም፣ ፈረስ ግልቢያ፣ ዋና፣ ቀስት ውርወራና አደን እንዲማሩ ያረጋሉ። ልዥቹ ዕድሜያቸው ከፍ ሲል ይመለሱና ደሞ የቤተመንግሥት ወግ ይማራሉ። ነገሥታቱ በሕይወት
እያሉ እንደዝኸ ነው አልጋ ወራሾቻቸውን ሚያዘጋጁ። የሞቱ ነገሥታት ዝርያዎች ግን እወህኒ ይላኩና ብዙዎቹ እዛው እስር ላይ እንዳሉ፣ ሌላ ነገር ሳያዩ አርዥተው ይሞታሉ።”

መስማት ከፈለገች ብለው፣ “ነገሩ እንዴት መሰለሽ?” ሲሉ ቀጠሉ፣
“ኸንጉሥ የተወለደ ሁሉ አልጋውን መውረስ ይችላል። ዛዲያ ለዛች
ላልጋ ሲሉ ስለምንም አይጨነቁ። ግና እነሱ ጦር ባነሱ ቁጥር ድኻውን ያስፈጃሉ። እነሱን ሚደግፉ መኳንንት ወታደሮቻቸውን ያሰማራሉ።
የአንድ መኰንን ገባር እኮ ሲያስፈልግ ወታደር እየሆነም ያገለግላል።ዛዲያ እነዝኸ ንግሥ ይገባናል ሚሉት ጦር ያነሱ ግዝየ፣ እንዲያው እልሻለሁ አገር ያምሳሉ። በተለይማ ጐንደር ሁሌም እንደታወከችና
እንደተዘረፈች ናት. ሕዝቡ ዘላለም ስጋት ላይ እንደወደቀ። ወግ
ነበር እኮ ዛዲያ፤ ብቻ ሚያከብረው ጥቂቱ ነና ነው እንጂ። ፍታ
ነገሥቱ ሚለውማ ንጉሡ ሲሞት ኸልገቦቹ መኻል ትልቁ ወንድ ልዥ፣ ወይም ንጉሡ ራሱ የመረጠውና መኳንንቱ፣ የጦር አላፊዎቹና ካህናቱ የመረጡት ነው ሚነግሥ። አልጋውን ለመጠበቅ፣ አንዱ ባሻው ግዝየ
ተነስቶ ልንገሥ እንዳይል... አገር እንዳይታወክ ሲባል ደሞ ሌሎቹ
የነገሥታት ዘሮች እንደነገርሁሽ እወህኒ አምባ ይላካሉ። ቅጡ እንዲያ ነው እንግዲህ።”

“እኼማ መሆን የለበትም” አለች።

“ምኑ?”

“እወህኒ አምባ አስሮ ማቆየቱ።”

“ቤተመንግሥት ገብተሻል አሁን ዐዲስ ወግ አምጫ እንግዲህ
አሏት፣ ምጸት በተቀላቀለው አነጋገር። ቀጠሉና፣ “አንቺ ብትሆኚ ኑሮ ምን ታረጊ ኑሯል? እስቲ በይ ንገሪኝ” አሏት።....

ይቀጥላል
👍101
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_አስር ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ...እሷም አያቷም ታጥበው እንደተመለሱ፣ ራት በልተው በየክፍላቸው ገብተው ተኙ። ወለተጊዮርጊስ፣ ጠዋት ከእንቅልፏ ስትነቃ የት እንዳለች ግራ ገባት።ቀስ በቀስ ጐንደር ቤተመንግሥት፣ እንግዳ ማረፊያ ክፍል ውስጥ መሆኗ ተገለጠላት። በመስኮቱ ቀዳዳዎች የገባውን ብርሃን አይታ ፀሐይ መውጣቷን አወቀች። አርፍዳ እንደነቃች ገባት፡፡ ምን ማድረግ…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...አስቻለው ከተንጋለለበት ብድግ ብሎ ሔዋን ሳማት እሷም ሳመችው። ግን ደግሞ ሁለቱም ሆዳቸው ባባና ተላቀሱ።
ቀጣዬቹ ቀናት የአስቻለው የጉዞ ዝግጅት ጊዜ ሆኑ። ከሁለቱ በፊት የደምወዙን ውክልና ለበልሁ ሰጠ። ቀጥሎም ሔዋንና ትርፌን አስቀምጦበት የሚሄደው ቤት ከግለሰብ የተከራየው በመሆኑ እሱ በሌለበት ችግር እንዴይፈጠርባየው ከባለቤቱ ጋር የቃልም ሆነ የፅሁፍ ውል ማሰር ነበረበትና ጥረቱን ጀመረ።
የቤቱ ባለቤት አቶ ከድር አህመድ በቀበሌ ዜሮ ሰባት ውስጥ የኖራሉ።የሚኖሩበት ቤት ከመጥበቧ የተነሳ ከአንድ ፍራሽ የተረፈችው የሳሎን ቦታ ሌላ
ፍራሽ አታዘረጋም ከጫት መቃምያ ፍራሻቸው ፊት ለፊት ሁለት ወይም ሶስት የዱካ መቀመጫዎች ብቻ ተደርድረዋል። አስቻለውና ሔዋን በተወያዩ በሁለተኛው ቀን ከምሽቱ አስራ አንድ ሰአት አካባቢ አስቻለውና በልሁ አብረው ሄዱ ከአቶ ከድር ቤት ሲገቡ ከባለቤታቸው ጋር ፍራሽ ላይ ጎን ለጎን ቁጭ ብለው ጫት ሲቅሙ አገኛቸው።
«ምን እግር ጣላችሁ ዛሬ ልጆች?» ሲሉ አቶ ከድር አስቻለውና በልሁን ጠየቋቸው።አቶ ከድር በጣም ጥቀር ከመሆናቸው የተነሳ ነጭ ጥርሳቸውን ገለጥ ሲያደርጉት
የሰው ዝጉርጉር መስለው ይታያሉ፡፡ በዚያ ላይ ሰፌድ የሚያህል የእይታ መነጽራቸው ግማሽ ፊታቸውን ሸፍኖት ሲታዩ ሁኔታቸው ያስፈራራል። እድሜአቸው ወደ ሰባ ዓመት የሚጠጋ ሲሆን ሰውነታቸውም መጨማደድ ጀምሯል።

«ስለ ቤት ጉዳይ ላነጋግርዎት ነበር፡፡» አላቸው አስቻለው ከፊት ለፊታቸው ባለች ዱካ ላይ ከበልሁ ጎን ተቀምጦ፡፡
«ልትለቅ ነው?»
“አይ! አይደለም፡፡»
«እንግድያማ ኪራይ ልትጨምር ማሰብህን ልትነግረኝ ነው የመጣኸው ሲሉ አቶ ከድር ቀለዱ፡፡ ጎንበስ ብለው ፈገግ በማለት ጫት ይቀነጣጥባሎ፡፡
«ቢሆንስ ምን ችግር አለው?» አለ አስቻለው በፈገግታ እየተመለከታቸወ፡፡
«ጎሽ የኔ ምሁር አፍክን በዳቦ»
በዚህ ጊዜ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሰሚራ አሊ ጭምር በቢቱ ውስጥ ያሉት በሙሉ ሳቁ፡፡
«ለአንድ ስድስት ወር ያህል ወደ ሌላ አገር በጊዜያዊነት ልሄድ ስለሆነ ቤቴ ውስጥ አስቀምጫቸው ስለምሄደው ሰዎች ጉዳይ እንድንጋገር ብዬ ነው የመጣሁት አላቸው አስቻለው ወደ ቁም ነገሩ በመመለስ፡፡
የት ልትሄድ ነው!»
ወደ ኤርትራ ነው ፤ ዘመቻ!»
«አኪምነቱን ትተህ ወታደር ሆንክ እንዴ?» እሉ አቶ ከድር በዚያ
መነፅራቸው ውስጥ ቀና ብለው እያዩት። አስቻለው የአስተሳሰባቸው ከቅጣጫ እንደ
መገረም ብሎት በልሁን እያየ ፈገግ ካለ በኋላ፡-
«አይ ለሌላ ሥራ ነው::» አላቸው፡፡
«ወደዚያ የሚኬደው ለጦርነት ስለሆነ ብዬ ነዋ» ካሎት በኋላ «ታዲያ ማንን ልታስቀምጥበት ፈለግህ?» ሲሉ ጠየቁት፡፡
«ሰራተኛዬንና እጮኛዬን!»
«ሁለቱም ሴቶች ?»
«አዎ» አለና አስቻለው ወደበልሁ እያመለከተ «ይሄ ወንድሜ የቤት ኪራዩን እቤቶ ድረስ እያመጣ ይከፍሎታል።»
«አዬ..» አሉና እንደማቅማማት አሉ። ወደ ባለቤታቸው ዞር በማለት «ይኸን ነገር እንዴት ታይዋለሽ ሰሚራን» ሲሉ ጠየቋቸው፡፡ እርጅና ወደቅ ያለባቸው ቀይ ፋታቸው ጨምደድ ማለት የጀመረው ወይዘሮ ሰሚራ ሙሉ ሰውነታቸውን በሰፊና ረጅም ቀሚሳቸው ሸፍነው በቀይና ነጭ ቡራቡሬ ጉፍታ አንገትና ጭቅላታቸውን ተከናንበው በመቀመጥ ጫት ይቅማሉ። ጀበናና የሲና ረከቦት ከፊታቸው ደርድረዋል።
«እኔ ደሞ ምን አውቄ!» አሏቸው አቶ ከድርን ማየት ከፊታቸው
ያለውን ከሰል እሳት ቆሰቆስ እረጉት፡፡
«ችግር እኮ የለውም አባ አድር!» አላቸው አስቻለው የባልና ሚስቱ
ምልልስ ትንሽም ቢሆን ወደ ስጋት ስሜት ወሰድ አደረገውና ለማስተማመን::
«ስማ የኔ ልጅ!» አሉ አቶ ከድር አጎንብሰው “ጫታቸውን እየቀነጣጠቡ።
«አቤት»
«የሴት ነገር ያው የሴት ነው፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ አንተ የምትሄደው ወደ ጦር ሜዳ ነው።
ድንገት መጃለፍም ሊኖር ይችላል። በመሀል ታድያ ችግር የተፈጠረ እንደሆነ ሰዶ ማሳደድ አይሆንም ብለህ ነው?» ሲሉ ጥያቄ አዘል አስተያየት ሰጡና ቀና ብለው ተመለከቱት፡፡
በዚህ ጊዜ በልሁ ንድድ ብሎት በሆዱ ምን ዓይነት ፈልፈላ ሽማግሌ ነው አለና « የሆነው ቢሆን በእርስዎ ቤት ላይ ምን ይመጣል ብለው ፈሩ፣» ሲል ኮስቴር ብሎ ጠየቃቸው፡፡
«አይደለም! አይደለም! መፍራት ጥሩ ነው። ባይሆን ሰሞኑን ከሰሚራ ጋር ተነጋግረን የደረሰበትን ሁኔታ እንገልጥላችሁ
እንዲሆን እንጂ…» ብለው ነገራቸውን ጎተት ሲያደርጉት በልሁ ድንገት ከተቀመጠበት ብድግ አለና፡
«ቢቃ ጌታዬ! ምንም አያስፈልግም፣ ነገ መጥተው ቤትዎን ይረከቡ፡፡» አለና
ወደ እስቻለው ዞር ብሎ «ተነስ እንሂድ!» ብሎት ቀድሞ ከቤት ወጣ::
አስቻለው በአቶ ከድር ሁኔታ ሆዱ እየበሽቀ ነገር ግን በልሁ ምን አስቦ እንደሆነ ግራ እየገባው ብድግ ብሎ ተከተለው፡፡ ከደረሰበትም በኋላ ምንም የተለየ
አማራጭ አልነገረውም። ብቻ «ና ወደ ታፈሡ ጋ ሄደን በጋራ እንነጋገርበታለን::»
ብሎት ሁለቱም ዝም ብለው ወደ ታፈሡ ቤት አመሩ፡፡ በልሁ ገና ሔዋን ከሸዋዬ ቤት መውጣት እንዳለባት ሀሳብ ከቀረበ ጀምሮ
ምናልባት እሺ ብላ ከወጣች በማለት ስለምትኖርበት ቤት አንድ ነገር ሲያሰላስል ቆይቷል። በእሱ እምነት የሸዋዬና የአስቻለው ቤት ተቀራራቢ በመሆኑ ሽዋዬ ነጋ
መሽ እየተመላለሰች ሰላም ልትነሳት ትችላለች። የእሱ ቤት ደግሞ በዜሮ ሁለት ቀበሌ ውስጥ ለዚያውም ዙሪያው በግንብ የታጠረና የተከበረ የትልቅ ሰው ግቢ ነው:: ለርቀቱም ለፀጥታውም ምቹ ስለሆነ ሔዋንን ከትርፌ ጋር እዚያ አስገብቶ
እሱ በአስቻለው ቤት ውስጥ የመኖር ሀሳብ ነበረው። አቶ ከድር ግን እቅዱን አበላሹበት።
በልሁ ይሄንኑ እያሰበ ከአስቻለው ጋ ተጉዞ ከታፈሡ ቤት ደረሱ ሁለቱም ገብተው ከታፈሡ ጋር ቁጭ ሲሉ በልሁ አንድ ነገርም ብቻ ለሁለቱም ነገራቸው።
«ስለ ቤት ጉዳይ ምንም አታስቡ፡፡ ቢቻል ነገ ካልሆነ ግን ከነገ ወዲያ
ሔዋን ጓዟን ጠቅልላ ከሸዋዬ ቤት የምትወጣበትን ሁኔታ ብቻ አስቡ፡፡ ሌላውን ነገር ለኔ ተውት አላቸው።

የሆነውም ይኸው ነበር፡፡ በልሁ ያንዕትን ልብሶችና የመጽሐፍ መደርደሪያ ይዞ ከአንድ ሆቴል ውስጥ ኮንትራት አልጋ ይዞ ገባ፡፡ ሔዋንም እንኳንስ ጫማ እና ልብሶቿ!! የአለቀ የእስክሪብቶ ቀፎ እንኳ ሳይቀራት ጓዟን ጠቅልላ በሚቀጥለው ቀን ወደ ታፈሡ ቤት መጣች፡፡ ያ ቀን ማግስት ምሽት ላይ ደግሞ ከትርፌ ጋር በበልሁ ቤት ውስጥ 'ቤት ለንሞባሳ ብለው ገቡ።
የዚያኑ ዕለት ለአስቻለው አጠር ያለ ሽኝት ተዘጋጀ። አዎ! ለነገሩ ጥሩ ምግብ ተበላ መጠጦች በያይነቱ ተጠጡ።። ነገር ግን መስፈሪያ ኖሮት የሚለካ ቢሆን ኖሮ በሽኝቱ እለት ሲወርድ ያመሸው እንባ ምን ያህል ከመያዣው ተርፎ በፈሰሰ ነበር፡፡ ሔዋን በሰቀቀን "እየዮ” ስትል አስቻለው በቁጭት "እህህ" ሲል
አፆናኝና ጋባዦቹ ታፈሡ በልዑና መርዕድም ከእጃቸው ላይ መሀረብ ሳይለይ ሌሊቱ ወለል ብሎ ነጋ።
አስቻለው በጠዋት በማለዳ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ዋለና በሶስተኛው ቀን ቀትር ላይ ደግሞ በአይሮፕላን ወደ አስመራ።
👍11
በተሳፈረበት አይሮኘላን ውስጥ አየር ላይ ተንሳፎ ሳለ ሁለት ሀሳቦች ተፈራረቁበት። በአንድ በኩል የሽኝቱ ዕለት ማታ ሔዋን ስትሆን ያመሸችው እና
ጠዋት ከዲላ አውቶቡስ መናኸሪያ ወደ አዲስ አበባ ስትሸኘው መላ ሰውነቷ በለቅሶ
እየተንሰቀሰቀ፣ ሙሉ ፊቷ በእንባ እንደ ረሰረሰ ባልተለመደ ሁኔታ ማንቁርቱ ላይ ተጣብቃ "ክፉ አይንካህ አስቹ! ያለችው ትዝ ብሎት ሆዱ ባባና ከፉኛ አለቀሰ፡፡
በሌላ በኩል ግፈኞች ለራሳቸው ህልውና ሲሉ በቀስቀሱትና እሱ በማያምንበት ጦርነት በተፅዕኖ ተሳታፊ እንዲሆን የመደረጉ ቁጭት አንገበገበው። ከንፈሩን
እየነከሰ ራሱን እንደ ወዘወዝ ! አይሮኘላን ውስጥ ስለመሆኑ አንዴም ሳይታወቀው! በሀሳብ እንደዋለለ ከአንድ ሰዓት ተኩል በረራ በኋላ ልክ ዘጠኝ ሰዓት
ላይ አስመራ ከተማ ደረሰ ኤርትራ!!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
«ሄሎ ! ሄሎ!አስደሳች ዜና ለዲላና አካባቢዋ ነዋሪዎች በሙሉ ታዋቂውና ዝነኛው የፖሊስ ኦርኬስትራ የሙዚቃ ቡድን የተለያዩ አዝናኝና አስደሳች ጣእመ ዜማዎችን ይዞ እንሆ በመካከላችሁ ተገኝቷል!! ቦታ በዲላ የህዝብ መሰብሰብያ
አዳራሽ ሰዓት ከምሽቱ አስራ ሁለት ጀምሮ! የመግቢያ ዋጋ አሥር ብር ብቻ ይላል አንድ የሙዚቃ ቡድን አስተዋዋቂ በፖሊስ መርሴዲስ መኪና ከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ላይ እየተዘዋወረ፡፡ አስተዋዋቂው ተናግሮ ሲያበቃ ጆሮ የሚበጥስ
ሙዚቃ በድምጽ ማጉያ ይለቀቃል።

የከተማዋ ነዋሪ ለማስታወቂያው የተለያየ ምላሽ ይሰጣል፡፡ አንዳንዱ በዓመት ከአንድ ወይም ሁለት ላልበለጠ ጊዜ የማይገኝ ዕድል በመሆኑ እንደ መልካም አጋጣሚ እየቆጠረው ኦ! ብራቮ ይላል። ሌላው ደግሞ የመግቢያ ዋጋው ለእሱ አቅም የማይቀመስ እየሆነበት እምበላው ባገኘሁ እንኳን ለአንተ አስር ላወጣ!» ሲል የአብዮት ዘፈን በሬዲዮም ሰልችቶኛል የሚልም ነበር፡፡
ዕለቱ የሥራ ቀን ነበርና የመንግስት ሰራተኞች ማስታወቂያውን የሰሙት
ከሥራ ሲወጡ ነው፡፡ በልሁ ከአንድ የሥራ ባልደረባው ጋር ወደ ዋናው የከተማዋ መንገድ ሲያመራ መኪናው የመንገድ ዳር ይዞ በመቆም ቲኬት ሲሸጥ አዩት
«ለእንዳህ አይነት ነገር ባለቤቴ በጣም ትጓጓለች እንደምንም ብዬ ይዣት መግባት አለብኝ፡፡» አለ የበልሁ የሥራ ባልደረባ፡፡
«እኔስ ማንን ይዤ ልግባ?» አለ በልሁ ፈገግ ብሎ የሥራ ባልደረባውን እየተመለከተ፡፡
«እንደ ፈረደብህ ብቻህን ተጎለታ!» አለው ሰውዬው ሳቅ እያለ፡፡
ግን ሁለቱም ቲኬት ወደሚሸጥበት ቦታና መኪና አመሩ፡፡ የበልሁ የሥራ ባልደረባ ሃያ ብር አውጥቶ ሁለት ቲክት ሲገዛ በልሁም «ለኔም ሁለት» ሲል የሰማው የሥራ ባልደረባው በልሁን ሳቅ ብሎ አየት እያደረገው፡-
«ማምሻህን ልትገባ!» ሲል በነገር ወረፍ አደረገው፡፡
«ማን ያውቃል! ትንታና ፍቅር ድንገት አይደል፡ ምናልባት አንዷን
ቢያጋጥመኝስ!» አለ በልሁም ፈገግ እያለ፡፡
በልሁ እንዲህና እንዲያ እያለ ከሰውየው ጋር ይቀልድ እንጂ በሆዱ ግን ሔዋንና ትርፌን የዕለቱ የሙዚቃ ታዳሚዎች አድርጎ ሊያዝናናቸው እያሰበ ነበር፡፡
ሔዋንና ትርፌን በሙዚቃ የማዝናናት ሀሳብ ለእነሱ ካለው ፍቅርና ከቸርነቱ ብቻ የፈለቀ አልነበረም። በሆዱ ሌላም ብዙ ብዙ የሀሳብ ጓዝ አለ።
እነሆ ልጓም አልባው ጊዜ የራሱን ኡደት ተከትሎ ሄዷል ተምዘግዝጓል፡፡ አስቻለው ወደ አስመራ ከሄደበት ካለፈው ሰኔ ወር ቀጥሉ የነበሩት ሐምሌና ነሐሴ ሽው እልም ብለዋል። ቀጣዩቹ መስከረምና ጥቅምትም በፍጥነት ጥቅልል ብለዋል።
ህዳርና ታህሳስም እንዲሁ ሳይመለሱ ተሸኝተው ወርሃ ጥር ከች ብሎ ራሱም ተጋምሷል። የፖሊስ ኦርኬስትራ የሙዚቃ ቡድን ወደ ዲላ ብቅ ያለው በዚሁ ወር ሶስተኛ ሳምንት ላይ ነው፡፡
ይህ ሁሉ ጊዜ ሲያልፍ አስቻለውን የበላ ጅብ ለአንዴም ጮሆ አያውቅም ቢደመጥ ቢደመጥ ቢጠመቅ ቢጠበቅ ትንፍሽ አልል ብሎ ድራሹን አጥፍቷል።
ስድስት ወር ተብሎ የሄደው አስቻለው እንኳን መመለስ ድምፁ እንኳ ሳይሰማ ድፍን ሰባቶ ወረሰ አልፈዋል። ይህ ሁኔታ በዲላ የፍቅር ቤተሰቦቹ ላይ ስጋትና
ጭንቀት ፈጥሮ ያተረማምሳቸው ይዟል ከሁሉም በላይ ደግሞ ሔዋንን።......

💫ይቀጥላል💫
5👍4
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

...“ቤተመንግሥት ገብተሻል አሁን ዐዲስ ወግ አምጫ እንግዲህ
አሏት፣ ምጸት በተቀላቀለው አነጋገር። ቀጠሉና፣ “አንቺ ብትሆኚ ኑሮ ምን ታረጊ ኑሯል? እስቲ በይ ንገሪኝ” አሏት።

“እኔማ እዚያ ማን አድርሶኝ ... ብቻ መላ ፈልግ ነበር።”

“መላ? ለነገሩ አንቺ መለኛ ነሽ።”

ፈገግ ብላ ዝም አለች።

“ምን አይተሽ የኔ እህት” ሲሉ ቀጠሉ። “አንዳንዶቹ ሲነግሡ
ሲሻቸው የገዛ ወንድሞቻቸውን እጅና እግር እየቆረጡ ነው እወህኒ
ሚሰዱ... እንዳይነግሡ” አሉና አፄ በካፋ ወንድማቸውን አቤቶ ዮሐንስን አንድ እጃቸውን ማስቆረጣቸውን ሊነግሯት ፈለጉና ለራሳቸው ወደ ፊት ትደርስበት የለ? ብለው ለእሷ፣ “ኣካሉ የጎደለ ደሞ መንገሥ አይችል” አሏት።

“ስለምን? አካሉ ቢጎልስ?”

“አካሉ ኸጎደለ እንዴት ብሎ ጦር ይመራል? እስቲ ንገሪኝ በይ?
ብቻ አሁን እሱን ተይውና ስንት የሞቱ ነገሥታት ዝርያዎች አሉ
መሰለሽ ኸተራራው... እወህኒ አምባ። ወህኒ አምባ ማለት ለጐንደር ቅርብ ናት... ኸማክሰኚት ብዙም አትርቅ። ብቻዋን የቆመች ተራራ ናት። አንድ በር ብቻ ነው ያላት። አናቷ ሜዳ፣ መውጫም መውረጃም የላት። ኸዛው ኻምባው ላይ የደንጊያ ቤቶችም አሉ።”

ወለተጊዮርጊስ የሰማችው ሁሉ እንግዳ ነገር ሆነባት። “ዛዲያ እንዴት ነው ሰዎቹ ከተራራው ሚወጡ ሚወርዱ?”

“በመጫኛ። ተራራይቱን ኻየሻት ዝንዥሮ ወይ ጦጣ መሆን ኣለብሽ
እዛ ላይ ለመውጣትም ሆነ ለመውረድ። ዙርያዋ ጥድ ነው። ምሽግም አላት አሉ። ብቻ እንዳው ንጉሥ ሞተ ኸተባለ ወይ ደሞ አንዱን እናንግሥ ያሉ እንደሁ፣ በቃ እግር ብረቱን ፈታተው ያኮበልሉታል።”

“ጠባቂም የለባቸው?”
“አሉዋቸው እንጂ! ያውም ንጉሡ ራሳቸው የመረጧቸው ወታደሮች
ናቸዋ ሚጠብቁ! ወታደሮቹ ዘብ ሚቆሙበት ቦታ ሁሉ አለ እኮ።

ወታደሮቹ ኸቀደሙ ነገሥታት ልገባች እንዳይመሳጠሩ፣ ለንጉሡ
መሐላ ገብተው ነው ሚጠብቁ። ኸዛ ቦታ ያለ ንጉሡ ፈቃድ ማንም
ሊገባ ወይም ሊወጣ አይችልም። ግና ለዘበኞቹ ጉርሻ ይሰጧቸዋል።
ለጉርሻ ማይተኛ ስንት አለ? የሰው ልዥ እኮ ተላላ ነው፣ በቀላሉ
ይደለላል። ዛዲያ ለእንዲህ ያለው ክደት ቅጣቱ ሞት ነው። እንንገሥ
ባዮቹም አንዴ ኸተራራይቱ ኸወረዱ፣ ጭፍራ አስከትለው ጫካ ይገባሉ፣ ኸዚያ ነፍጥ ይዘው ገስግሰው ይመጣሉ። እልቂት ነው አልሁሽ ኸዝያ ወዲያ። አንዴ ያችን አልጋ ኸመዳፋቸው ኻረጉ ወዲያ ደሞ ሹም ሽር ያረጋሉ። ኸባላገሩ ርስት እህላሙን መሬት እየመረጡ ለሚፈልጉት በጉልት ይሰጣሉ፣ ሲፈልጉ ርስት ይተክላሉ፣ ገባርም ይሰጣሉ፣ ከብትም እንዲወስዱ ያረጋሉ። የጃንሆይ አባት አጤ አድያም ሰገድ ኢያሱ ሰላም አምጥተው እሳቸው ከሞቱ በኋላ፣ ረብሻ፣ ጦር ሰበቃ ሆነ።
የጭንቅ ዘመን ነበር።”

ዮልያና፣ ስመ መንግሥታቸው አድያም ሰገድ የሆነው ቀዳማዊ ኢያሱ ከሞቱ በኋላ፣ የነገሡ ነገሥታት ተክለሃይማኖት፣ ቴዎፍሎስ፣ ዮስጦስና ሣልሳዊ ዳዊት፣ እያንዳንዳቸው ለአጭር ጊዜ እየገዙ ሃገሪቱ ሰላም
አጥታ ስትታመስ፣ በሃይማኖት ክርክርና ንትርክ ስትብረከረክ ብሎም በእልቂት ስትንጠራወዝ እንደነበረች በዝርዝር ሊነግሯት ፈልገው፣ ፊቷ ላይ በግልፅ የሚታየውን የመሸበር ስሜት አስተውለው ዝም አሉ።

ወለተጊዮርጊስ የሰማችው ነገር ሁሉ ከበዳት። ቤተመንግሥት
መግባት አስፈሪ ነገር ሆነባት። ፋሲል ቤተመንግሥት ቅጥር ግቢ
ስትገባ ያየችው ግርማ ሞገስ ሁሉ በውስጡ የማይመጥኑት አናሣ
ነገሮች ያቀፈ መሰላት።

“ማትቀመጪ? ቁመሽ ትዘልቂዋለሽ?” አሏት።

“እሚታዬ ለመሆኑ ሰዎቹ ምን እየበሉ ይኖራሉ፣ኸተራራ
ተቀምጠው?”

“ንጉሡ እኮ ቀለብ ይሰጣል። ውሃም ቢሆን ኸታች ምንጭ አለ::
እነሱም ኸዛው ይዋለዳሉ። ትምርት ይማራሉ፤ ቤተክሲያንም..
ጊዮርጊስና ማርያምም እኮ አሉ ኸዛው።”

“ሚገርም ነው። ስለዝኸ ስታወሪ ሰምቸሽም አላውቅ።”

ትናንት ፋሲለደስ ቤተመንግሥት ግቢ ስትገባ የነበራት የመደነቅ
ስሜት ኹሉ ጠፍቶባት ጭንቀት ያዛት። ለራሷ እኼ ቤተመንግሥት
ሚባል ነገር አስፈሪ ነው አለችና ወደ አልጋው ጫፍ አመራች።

ልብሶቹን በጥንቃቄ ወደ ኋላ ገፋ አድርጋ ተቀመጠች።

“ጌጦቹን አልጋው ላይ አኑሪያቸው” ብለው በቀኝ እጃቸው ኣልጋውን መታ አደረጉት።

“ልብሶቹን ደሞ እመንጠቆዎቹ ላይ ስቀያቸው” አሏት፣ ግድግዳ ላይ የተተከሉትን ከቀንድ የተሰሩ የልብስ መስቀያዎች
በእጃቸው እየጠቆሟት።
ጌጦቹን አልጋው ላይ ትታ ሄዳ ልብሶቹን አንድ በአንድ
ሰቀለቻቸውና ጫማዎቹን መሬት ላይ አስቀምጣ ተመልሳ አልጋው
ጫፍ ላይ ተቀመጠች።

“ምን እያልሽኝ ነበር? አዎ 'ስለዝህ ስታወሪ ሰምቸሽም አላውቅ
ነው ያልሽኝ” አለና፣ “ፊት ብታቂ ኑሮ ምን ይጠቅምሽ ኑሯል?
የዠመርሁትን ልጨርስልሽ እንጂ። ጃንሆይ እንዳልሁሽ በንጉሥ
ዮስጦስ ግዝየ ኸወህኒ አምባ ሲያመልጡ እኝሁ ዮስጦስ መልሰው አሰሯቸው። ያለቤታቸው ገብተው።”

“ያለቤታቸው ገብተው?”

“ዮስጦስ ማለት ልደታ ማርያምን እዝሁ እጐንደር የተከሉት
ያጤ ቴዎፍሎስ እንደራሴ ነበሩ እንጂ የነጋሢ ዘር የላቸውም። ኋላ
ጃንሆይ ደሞ ሲነግሡ ወህኒ አምባ ያሉ የነጋሢ ዝርያዎች ሁሉ የገዛ ወንድሞቻቸው ሳይቀሩ ተንጫጩ።”
“ምን ይሁን ብለው?”
“ሚነግሠውን እኛ እንመርጣለን፤ በካፋ ኃይለኛና ጨካኝ ነው
ብለው። ያው አልቀረም መሲሕ ሰገድ ተብለው ነገሡ። ይነግሣሉ ሚል ንግርትም ነበር። ጃንሆይ ወህኒ ሳሉ በሳቸው ልክ ጧሚና ጠሎተኛ አልነበረም ነው ሚሉ።

ምጥዋትም መስደድ ያዘወትሩ፣ መጻሕፍቱንም ያገላብጡ ነበር። ቅኔ አዋቂም ናቸው። ኸዛው እናታቸው አገር... ዲማ ነው ቅኔውን የተማሩ። ደሞ ምን የመሰለ ታንኳም አሠርተዋል እኮ።
ግብጦች ናቸው አሉ የሠሩላቸው። ኸጣና ነው ያለ...”

ድንገት ደንገጡሮቹ ሲገቡ ዝም አሉ። ሴቶቹ ወለተጊዮርጊስን
አልብሰው፣ አስጊጠውና እላይዋ ላይ ሽቱ አርከፍክፈው ግብር መታደሚያ ሰዐት ሲደርስ እንደሚመለሱና ግብር እንደ ንጉሠ ነገሥቱ ፍላጎትና
እንደ ሁኔታው የተለያየ አዳራሽ ውስጥ እንደሚደረግና ለዛሬ ግን ባለ ሁለት ደርቡ ወርቅ ሰቀላ ምድር ቤት አዳራሽ ውስጥ እንደሚሆን ነግረዋቸው ወጡ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

“ምንትዋብ ብያታለሁ።”

ወርቅ ሰቀላ ጥቁር እንግዳ ለመቀበል ዝግጁ ሆኗል። የእልፍኝ
አስከልካዩ በሥሩ ያሉትን እንደየደረጃቸው ነጠላ ያደገደጉትን፣ ወይም ካባ የደረቡትን ዐራቱን ጭፍሮቹን አሰማርቷል። ጠርዙ ባለወርቅ ቅብ
የሆነው የንጉሠ ነገሥቱ መንበረ መንግሥት የለበሰው የፋርስ ባለቀይ፣ባለሰማያዊና ባለነጭ ምንጣፍ በትክክል መነጠፉን፣ ከጎኑ ያለው ጠርዙ የወርቅ ቅብ የሆነው ድንክ አልጋ ዝግጁ መሆኑንና ከአልጋዎቹ ሥር
የተነጠፈው ቀይ የፋርስ ስጋጃ ላይ የሐር ምንጣፍ በትክክል መነጠፉን አረጋግጧል።

ከንጉሡ መንበር በስተጀርባ ያለውን ግድግዳ በቀይና በልዩ ልዩ
ቀለማት ያጌጠ ከቱርክ የመጣ ምንጣፍ ሸፍኖታል። ድንክ አልጋዎቹ የተቀመጡበትን አካባቢ ከሐር የተሠራ ነጭ አጎበር ከላይ ከልሎታል።አናቱ ላይ የዘውድ ቅርጽ ያለው ጉልላት ተቀምጦለታል። ንጉሠ
ነገሥቱ ሆኑ አብረዋቸው የሚቀመጡት እንግዶች እስኪገቡ አጎበሩ በግራና በቀኝ ያሉ እንጨቶች ላይ በቀጭን ሐር ሻሽ ታስሯል።ሲያስፈልግ የሚጋርዱትና የሚገልጡት ሁለት የቤተመንግሥት ባለሟሎች አደግድገው ግራና ቀኙን ቆመዋል። በአዳራሹ ግራና ቀኝ
ያሉ መስኮቶች የሐር መጋረጃ ተጋርደውባቸዋል።
👍181
ከንጉሠ ነገሥቱ በስተግራ መጋረጃ ውስጥ የሚመገቡት መሣፍንቱ፣ራሶቹና የቤተመንግሥቱን መማክርት የሚይዙት፡ የቤተመንግሥቱ
ዋነኛ አባላት የሆኑት ዐቃቤ ሰዐቱ፣ ጸሐፌ ትዕዛዙ፣ አፈ ንጉሡ፣ አዞዦች (ሕግ አዋቂዎቹና ፈራጅ ሊቃውንቱ)፣ የቤተክህነት አባላቱ፡ ከቡኑ ዕጨጌው፣ ሊቀ ካህናቱ እንዲሁም የየግዛቶቹ አስተዳዳሪ መኳንንት የጦር አበጋዞቹና ሊጋባው እንደ ቅደም ተከተላቸው ተርታውን መቀመጫዎች ተዘጋጅተውላቸው ግቡ እስኪባሉ ድረስ ሌላ ክፍል ውስጥ መከዳ ላይ ተቀምጠው ሲጠብቁ ቆይተው ገብተው ተቀምጠዋል።
እግራቸው ሥር እንደየማዕረጋቸው ብርሌዎችና ዋንጫዎች ተደርድረውላቸዋል ።

ከንጉሠ ነገሥቱ በስተቀኝ የሚቀመጡት ቢትወደዱ፣ ብላቴን ጌታው ፊታውራሪዎቹ፣ ከንቲባው፣ ካባ መልበስ የተፈቀደላቸው መኳንንት
በፈርጥና በልዩ ልዩ ጌጦች የተዋበውን ካባቸውን ደርበው፣ ወገባቸው
ላይ ከሐር የተሸመነ መቀነት ታጥቀው፣ ቆዳ ጫማ ተጫምተው
ጎምለል፣ ከብለል፣ ጀነን፣ ቀብረር፤ ድክ ድክ እያሉ፣ ወይዛዝርት ቁንን፣
ኮራ እያሉና አረማመዳቸውን እየመጠኑ መደዳውን እንደየማዕረጋቸው
በተሰናዱት መናብርት ላይ ገብተው ተሰትረዋል።
እግራቸው ሥር እንደየክብራቸው ለአረቄ ዋንጫ፣ ለጠጅ ብርሌ
ተቀምጦላቸዋል።

ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስና ባሻ ያሉት በማዕረግ ዝቅ ያሉት ደግሞ እንደየደረጃቸው የተዘጋጀላቸው መቀመጫ ላይ ቦታቸውን ከያዙ በኋላ፣ ሊቃውንትና ካህናት ገብተው እንደየክብራቸው ተሰይመዋል።

በመጨረሻም የውጭ አጋፋሪው አዳራሹ መሃል ቆሞ ከበር ላይ
የላካቸው እንግዶች እንደየክብራቸውና ማዕረጋቸው መቀመጣቸውንና መግባት የሌለበት እንግዳ አለመግባቱን ለማረጋገጥ ዐይኑን ከወዲያ
ወዲህ አዘዋወረ። ሁሉ ትክክል ሲመስለው የመኳንንቱ መጠጫ
ዋንጫዎች እንደዚሁ እንደየማዕረጋቸው መቅረባቸውንና ስሕተት አለመኖሩን ዞር ዞር ብሎ ተመለከተ።

ሁሉ በአግባቡ ነው።

ለማዕረጉ የማይመጥነው ቦታ ላይ በስሕተት እንዲቀመጥ የተደረገ፣
ወይንም ለማዕረጉ የሚገባ ዋንጫ ያልቀረበለት መኰንን ማኩረፍ ብቻ ሳይሆን ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ሊጋጭ የሚችልበት ጉዳይ በመሆኑ የእልፍኝ አስከልካዩ ልዩ ጥንቃቄ ያደርጋል።

ዝቅተኛ ማዕረግ-በማዕረግ ያለው መኰንን ለክብሩ የማይገባ ገበታ
ላይ በስሕተት ከፍ ብሎ እንዲቀመጥ ከተደረገ ማዕረግ-
በማዕረግ የሚበልጡት መኳንንት “ክብሬ ተነካ” ብለው ኣካኪ ዘራፍ በማለታቸው፣ እልፍኝ አስከልካዩ ሁሉም በደንቡ መሠረት መደረጉን ማረጋገጥ አለበት።

ማንኛውም ዓይነት ግድፈት ሆነ ተብሎ የተደረገ ሊመስል ስለሚችል መኳንንቱን ቂም ማስያዝና ማስኮረፍ ብቻ ሳይሆን፣ የፖለቲካ አሰላለፍንና
የኃይል ሚዛንን የሚያዛባ፣ ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር የሚያጋጭና እሳቸውንም ቢሆን የሚያስቆጣ በመሆኑ በቀላሉ የሚወሰድ ጉዳይ አይሆንም። ከዛም
አልፎ እልፍኝ አስከልካዩ እሱንም ሆነ ጭፍሮቹን የሚያስቀጣ ብሎም ከሥራ የሚያስባርር ጉዳይ ስለሚሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ ወስዷል።

ንጉሠ ነገሥቱ ማዕድ እንደቀረበ ተነግሯቸዋል። እንግዶቹ
ከተቀመጡበት ተነሥተው በንቃት ይጠባበቃሉ።

አፄ በካፋ በወርቅና የተለያየ ቀለም ባሏቸው ልዩ ልዩ የከበሩ
ድንጋዮች ያጌጠውን ዘውዳቸውን በሐር ሻሽ የተሸፈነ ሹሩባቸው ላይ
ጭነው፣ ፊታቸው ከዐይናቸው በስተቀር በሐር ጨርቅ ተሸፍኖ፣ ከወርቅ የተሠራ በትረ መንግሥታቸውን በቀኝ እጃቸው ጨብጠው፣ ጠርዙ በሐር ክር የተጠለፈ ነጭ ተነፋነፍ ሱሪያቸው ላይ ነጠላ አጣፍተው፣
በነጠላው ላይ በወርቅና በልዩ ልዩ ጌጦች ያሸበረቀውን ካባቸውን
ደርበው፣ አንገታቸው ላይ ወፍራም የወርቅ ሀብል ከትልቅ የወርቅ
መስቀል ጋር አድርገው፣ ከቆዳ የተሠራ ጫማ ተጫምተውና ንጉሣዊ ግርማ ተጎናፅፈውና ታጅበው ሲገቡ እንግዶቹ ለጥ ብለው እጅ ነሷቸው።

በተመጠነ እርምጃ እየተራመዱ መንበረ መንግሥታቸው ላይ
ሲቀመጡ መሣፍንቱና ራስ አጃቢዎቻቸው ቦታቸውን ያዙ ::
እሳቸው ግን ትንፋሻቸውን ውጠው ዐይናቸውን የአዳራሹ
ላይ ተክለው የሚጠባበቁት የወለተጊዮርጊስን መምጣት ነው። የመምጣቷ ዜና በመላ ጐንደር አስተጋብቶ ኖሮ እንግዶቹም ዐይናቸውን አዴራሹ መግቢያ ላይ ሰክተው ሲጠባበቁ ወለተጊዮርጊስ ብቅ ስትል፣ የአፄ ባካፊ ዐይን ሲርገበገብ፣ አዳራሹ በሁካታ ተናወጠ።

“ኸቋራ ነው አሉ የመጣች።”
“በተክልየ ኸቋራ? ስንት አጥንተ ጥሩ የጐንደር ወይዛዝርት እያለን
“ያጤ ሚናስ ነገድ ናት አሉ።”
“ደመ ግቡ ናት!”
“አብረዋት ያሉት እሚታዋ ወይዘሮ ዮልያና ናቸው።”
ጫጫታው ጋብ አልል በማለቱ፣ እልፍኝ አስከልካዩ አዳራሽ ውስጥ
ፀጥታ የማስከበር ኃላፊነት አለበትና ዐይኑን ከወዲያ ወዲህ ሲያማትር አዳራሹ ባንድ ጊዜ እረጭ አለ።

ወለተጊዮርጊስ ያንን ያህል ሕዝብ አንድ ቦታ ተሰብስቦ አይታ
ባለማወቋ ተደናገጠች። ልቧ ድቅ ድቅ ሲልባት፣ እጆቿ ላብ ሲያርሳቸው ጉንጮቿ በጥፊ እንደተመቱ ሲግሉ፣ እግሮቿ ተሳሰሩ። እንደምንም አንገቷን ሰበር ደረቷን ቀና አድርጋ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ አመራች።

እንግዶቹ ትንግርት ያዩ ያህል ቀልባቸው እሷ ላይ ሲያድር፣ አያቷ
እንዳሉት ወይዛዝርቱ ዐይናቸው ደፈረሰ። እሷ ይህን ሁሉ ማስተዋያ ልብም፣ ጊዜም የላት። ማድረግ ያለባት ሰዐቱና ሁኔታው የሚጠይቀውን ብቻ በመሆኑ፣ ቀጥ ብላ ሄዳ ወገቧ የሚሰበር እስኪመስል አጎንብሳ፣
ንጉሠ ነገሥቱን እጅ ነሳች። እግራቸውን ልትስም ስታጎነብስ አገጫን በእጃቸው ቀና አደረጉት።

በአድናቆትና በደስታ ብዛት እጃቸው ተንቀጠቀጠ። እንደምንም ብለው፣ “እንከንም የለሽ” አሏት። መቀጠል ፈልገው ግን ቃል አጠራቸው።

ብርታታቸውን አከማቹና፣ “ምንተ ምንውህብ?” አለ፣ በግዕዝ። ምን
እንስጥ? - መልከ መልካም ቆንጆ ናት እንደማለት። በመጨረሻም፣
ምንትዋብ ብያታለሁ” ብለው በቀኛቸው ያለው ድንክ አልጋ ላይ
እንድትቀመጥ አደረጓት። እሷን ተከትለው የገቡት አያቷ፣ በካፋን
ለጥ ብለው እጅ ነስተው በእልፍኝ አስከልካዩ መሪነት ከንጉሣውያን
ቤተሰቦች ጋር የተዘጋጀላቸው ቦታ ሄደው ተቀመጡ።.....

ይቀጥላል
👍11
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....ስድስት ወር ተብሎ የሄደው አስቻለው እንኳን መመለስ ድምፁ እንኳ ሳይሰማ ድፍን ሰባቶ ወረሰ አልፈዋል። ይህ ሁኔታ በዲላ የፍቅር ቤተሰቦቹ ላይ ስጋትና
ጭንቀት ፈጥሮ ያተረማምሳቸው ይዟል ከሁሉም በላይ ደግሞ ሔዋንን።
አስቻለው ወደ አስመራ ሲሄድ ለዲላ የፍቅር ቤተሰቦቹ የገባው ቃል ነበር ቶሎ ቶሎ ደብዳቤ ሊፅፍ ሁኔታዎች በፈቀዱለት መጠን ስልክም ሊደውል ለነገሩ አንዲት ደብዳቤ ፅፏል።ያቺም ብትሆን ገና አስመራ በገባ ሦስተኛ ቀን ላይ ድንገት ወደ አዲስ አበባ የሚመለስ ሰው አግኝቶ ኖሮ ደህና መድረሱን የገለፀበት እንጂ
ዝርዝር የናፍቆት ሀሳብና የተሟላ አድራሻውን የያዘች አልነበረችም። በዚያች ደብዳቤ ላይ የጠለፀው ነገር ቢኖር ወደፊት ቋሚ አድራሻውን ሲያውቅ ሌላ ደብዳቤ እንደሚፅፍና ምናልባት ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ በአውሮፕላን ላይ በነበረበት ወቅት ከሔዋን በመለየቱ ምክንያት ሆዱ ባብቶ በናፍቆት ስሜት ውስጥ ሆኖ የቋጠራቸው እንደሆኑ የሚገመቱ ጥቂት የግጥም ስንኞችን ብቻ ነበር።ያቺ ደብዳቤ ዲላ የደረሰችውም ስትጣጣል ሰንብታ ከተጻፈች ከአንድ ወር በኋላ ነበር፡፡
በቃ ሌላ የለም።
ሔዋን በልቧ ከአንድ ድምዳሜ ላይ ደርሳለች፤ እስቻለው ደህና ባይሆን ነው። ከሚል። የአስቻለውን ደህና አለመሆን ባሰበች ቁጥር ሁለት ነገሮች በሁለት ቦይ እየፈሰሱ በሀሳብ ይወስዷታል። በአንድ በኩል የአስቻለው ደህና አለመሆን
ፍቅሯን ሊያሳጣት ነው የዕድሜ ልክ የመንፈስ ስብራት፡፡ በሌላ በኩል ስለ እሷ "ብልግና" ሸዋዬ ለቤተሰቦቿ የጻፈችባትን ደብዳቤ ታስታውሳለች። ያ ደግሞ የቤተሰቦቿን በተለይም የእናቷን ሆድ እንዳሻከረባት ትገምታለች፡፡ ይህን ሁኔታ ማስቀየር ያስችላል ብላ የምትገምተው የአስቻለውን መልካም ሰውነት ነበር፡፡
እናትና አባቷ አንድ ቀን አስቻለውን ሲያውቁትና መልካም ሰውነቱን ሲረዱት ምርጫዋ ትክክል እንደሆነ በመረዳት የሻከረ ሆዳቸው ይሽርልኛል ብላ ትጓጓ ነበር፡፡አስቻለው ደህና ካልሆነና ምናልባትም ያልተመለሰ እንደሆነ ግን ከሁለት ዛፍ የወደቀች ልትሆን ነው። ጭንቅና ፍርሀቷም ከዚሁ ስጋት ይመነጫል።
ታፈሡ፣ በልሁና መርዕድ የሔዋንን ጭንቀት በብዙ መንገድ ይጋሩታል።
የአስቻለው ደብዳቤ አለመጻፍ፣ ስልክ አለመደወልና የመምጫው ጊዜም በአንድ ወር የዘመኑን እውነታዎች በራሳቸው መንገድ እየተረጎሙ ራሳቸውንም ሆነ ሔዋንን ማፅናናት አልቦዘኑም፡፡ ወትሮም እንደሚያደርጉት ሁሉ ጫት በመቃም ሰበብ ቀደም ሲል በልሁ፤ አሁን ደግሞ ሔዋንና ትርፌ በሚኖሩበት ቤት እየተሰበሰቡ መዋልና ማምሸታቸውን ቀጥለዋል፡፡ በዚያው ሂደት በበርካታ ጉዳዮች ላይ ደጋግመው ይነጋገራሉ፡፡ የአስቻለውን ደብዳቤ አለመጻፍ ጉዳይ ያነሱና ከወቅቱ ሁኔታ ጋር ለማገናዘብ ይሞክራሉ። በዚያን ወቅት መንግስት በፖስታ ቅብብሎሽ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ያደርግ ነበር። ተቃዋሚዎች ከደጋፊዎቻቸው ጋር ምስጢር
ይለዋወጣሉ በሚል ስጋት በተለይ የተጠርጣሪ ሰዎችን ፖስታ እየቀደዱ መንገድ ላይ ያስቀሩ እንደነበር በሰፊው ይታወቃል። በተለይ ከኤርትራ ወደ ሌሎች
የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚላኩ ደብዳቤዎች ለተላከሳቸው ሰዎች የመድረሳቸው ዕድል
አስተማማኝ አልነበረም፡፡ ምናልባት አስቻለውም የሚጽፈው ደብዳቤ መንገድ ላይ ተቀዶ እየቀረ ይሆናል። እሱ ደግሞ የተከፋ ብሶተኛ ነውና ይህንኑ ስሜት በደብዳቤው ላይ አስፍሮ ከተገኘ የባሰ ይጠረጠርና ሁለተኛውም ሦስተኛም ደብዳቤዎቹ የዚሁ ሰለባ እየሆኑ ቀርተው ሊሆን ይችላል በማለት
ግምትና ጥርጣሪዎቹን ይገልፃሉ። ስልክ ያለመደወሉንም ጉዳይ ከዚሁ ከወቅቱ እውነታ ለይተው
አያዩትም።በወቅቱ ከአዲስ አበባም ሆነ ከሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች አስመራን በሽቦ የሚያገናኝ ስልክ አልነበረም፣ በዓመታት ጦርነት ተበጣጥሰው
አልቀዋልና። አማራጭ የመገናኛ መንገዶች ራዲዮና ቴሌ ግራም አሊያም ገመድ አልባ ማይክሮ ዌቭ ስልክ ናቸው። ራዲዮና ቴሌ ግራም ደግሞ ለአብዛኛው ሰው እንደ ልብ አይገኙም፡፡ የማይክሮ ዌብ ስልክም ገና በጅምር የቴክኖሎጂ ደረጃ ላይ ነው
ከሚሰራበት ጊዜ የማይሰራበት ጊዜ ይበልጣል። በሚሰራበትም ወቅት ወረፋው አስልቺ ነው፡፡ የእነታፈሡ ግምት ታዲያ አስቻለው በዚህም ቢል በዚያ አልሆንለት እያለ ተቸግሮ ነው›› በሚል ሀሳብ ይደመድማል። የአስቻለው የመመለሻ ጊዜ ማለፉንም ካነሱ ምናልባት የአይሮፕላን ጉዞ ወረፋ አልደርስ ብሎት ይሆናል ከሚል ግምት አያልፍም፡፡
ይህ ሁሉ ምክንያታዊ ትንተና ግን ለሔዋን አይገባትም ትሰማቸዋለች እንጂ አታዳምጣቸውም፡፡ ለእሷ አንድ ነገር ብቻ ግልፅ ነው፤ በቃ አስቻለው አልመጣም ድምፁም አልተሰማም ምክንያቱ ደግሞ ደህና አለመሆኑ ነው። የሚያስጨንቃት የእሱ ደህና አለመሆንና ምናልባትም ያልመጣ እንደሆነ የሚፈጠርባት የመንፈስ ቁስል ነው። የዚህ ሁሉ አጠቃላይ ውጤት ታዲያ ራሷ ተጨንቃ እነታፈሡንም ማስጨነቋ ነው።
ሁኔታዋ ሁሉ ያሳዝናቸው ይዟል።
በልሁ ታዲያ ይህንን ችግር አንድ ቀንም ቢሆን የቀረፈ መስሎት ነው በሙዚቃ ዘና ትልለት ዘንድ የመግቢያ ትኬት መግዛቱ።
በልሁ ትኬቶቹን ይዞ በቀጥታ ያመራው ቀድሞ የእሱ፣ ዛሬ ደግሞ የሔዋንና የትርፌ መኖሪያ ወደ ሆነው ቤት አቅጣጫ ነበር። ነገር ግን ከአንደኛ መንገድ ብዙም ሳይርቅ መርዕድ ከታች በኩል አስፋልቱን ይዞ ወደ ላይ ለመጣው አገኘውና «ትኬት ገዝተሃል?» ሲል በቅድሚያ ጠየቀው፡፡ የምን ትኬት?» አለ መርዕድ በርገግ ብሎ።
«ዛሬ እኮ የፖሊስ ኦርኬስትራ መጥቷል»
ባክህ ተው ለአንድ ቀን ምሽት እሥር ብር ከማወጣ በቋሚነት የምስማው አንድ ካሴት ብገዛ አይሻልም?» አለው።
«እስቲ በልጅ እግርህ ወደነ ሔዋን ልላክህ!»
«ለምን?»
በልሁ ቲኬቶቹን ከኪሱ አውጥቶ እያሳየው «ሔዋንና ትርፌ ዛሬ እንኳ ይዝናኑ ብዬ ትኬት ገዝቼላቸዋለሁ:: ስጣቸውና ስዓቱ ሲደርስ አዳራሹ ድረስ
እንዲመጡ ንገራቸው:: እነሱን አስገብተን እኛ ወደየጉዳያችን እንሄዳለን» አለው።መርዕድ አላቅማማም፣ ቲኬቶቹን ተቀበለውና ሲመለስ የት እንደሚገናኙ ቀጠሮ ይዘው ወደ ሔዋንና ትርፌ ቤት ገሰገሰ፡፡
የሙዚቃ ድግሱ ማስታወቂያ በድምጽ ማጉያ ይነገር በነበረበት ወቅት ብዙዎች ያለ መታደም
አዝማሚያ የሚያመለክት አስተያየት ይሰጡ የነበረ ቢሆንም
በወቅቱ እስከ ሰላሳ ሺህ ህዝብ የሚኖርባት ዲላ ከተማ ውስጥ ከእንድ ሺ በላይ የማይዘውን የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚሞላ የሙዚቃ አፍቃሪ አልጠፋም፡፡ሰዓቱ ደርሶ ሔዋንን እና ትርፌን በቀጠሩበት ቦታ አግኝተዋቸው ወደ አዳራሹ ይዘዋቸው በመግባት ቦታ ሊያሲዟቸው ቢሞክሩም እነሱ
ቲኬት ስላልያዙ ወደ አዳራሹ ለመግባት ተከለከሉ።በዚያ ምትክ ትዕይንቱ፡ እንዳይርቃቸው ወደፊት ሄደው መቀመጥ እንዳለባቸው
መከሯቸውና እነሱ ወደ ውጭ ተመለሱ።
ሔዋን እና ትርፌ ግን አገባቡ ጭንቅ አላቸው፡፡ በዚህ ዓይነት ዝግጅትና አዳራሽ ውስጥ ታዳሚ ሁነው አያውቁም፡፡ የዝግጅቱ ተካፋይ ለመሆን የጓጉ ቢሆንም
ሌላ ሰው እንደሚያደርገው ቦታ መርጠው ለመቀመጥ ድፍረቱን አጡ። እንዲያውም
👍10