አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
«ኣ!» አለ አስቻለው ድንገት ሳያስበው፡፡ ቀና ብሎ ሠርካዓለምን አየት ካደረጋት በኋላ ወደ ብዳቤው ተመለሰና ማንበብ ጀመረ፡ ሲጨርስ «ምን?» አለ
በድንጋጤና በቁጣ ስሜት ጮክ፡፡ ሕልም ሕልም መሰለውና እንደገና አነበበው፡፡
መልዕክቱ ግን አልተቀየረም፤ ያው መጀመሪያ እንዳነበበው ነው፡፡
«አልገባኝም ሠርኬ ይኼ ነገር!» አላት ወደ ሠርካዓለም ዞር ብሎ።
«ለማንኛውም ረጋ በል አስቻለው!» አለችው ሠርከዓለም በማረጋጋት አይነት አይነት እሷም
ቀለስለስ እያለች።
«በርናባስ አሁን ቢሮ ወስጥ አለ?»
«ይኖራሉ። ግን አሁን አትግባ! ባይሆን ነገ ተነገ ወዲያ ይሻላል።»
አስቻለው ለአፍታ ያህል ሠርክዓለምን መልከት ካለ በኋላ ከወንበሩ ላይ ብድግ ብሎ ከቢሮ ወጣ፡፡ ያን ደብዳቤ እንደ ያዘ በቀጥታ ወደ ባርናባስ ቢሮ አመራ። ሳያንኳኳ በሩን በርግዶት ገባ::
ባርናባስ በተለመደው አለባበሱ ሆኖ ጠረጴዛው ላይ አጎንብሶ ይፅፋል፡፡ ወደ በሩ ቀና ሲል አስቻለውን አየው፡፡ የአስቻለው ስሜት መለዋወጡን አይቶ
ለሰላም እንዳልመጣ በመገመት ልቡ ድንግጥ አለና «አቤት» አለው መነፅሩን ወለቅ እያደረገ።

ምንድነው ይኼ?» አለና አስቻለው ያን ደብዳቤ በባርናባስ ፊት ጠረጴዛው ላይ ውርውር አደረገው፡፡ ጋወኑን ወደ ኋላው ሰብሰብ በማድረግ ሽንጥና ሽንጡን ይዞ ቁና ቁና እየተነፈሰ በባርናባስ ፊት ቆመና ቁልቁል ይመለከተው ጀመር፡፡
በርናባስ ይህን የአስቻለውን ሁኔታ ቀድሞም አስቦት ነበር፡፡ ይሁንና አሁን በትክክል ሲከሰት ቀድሞ ከገመተው በላይ ፍርሀት አደረበት፡፡ በሙሉ ቀልቡ
የአስቻለውን እንቅስቃሌ እየተከታተለ ለይምሰል ያህል ወደ ደብዳቤው መልከት እያለ
«የበላይ አካል ውሳኔ እኮ ነው::»
ምን አይነት ውሳኔ? አለ አስቻለው ድንገት አፉ ላይ የመጣለትን አይኑ
ከመፍጠጡም በላይ ትንፋሹ በርክቶ ደረቱ ሞላ ሞሸሽ፤ ሞላ ሞሸሽ ይላል፡፡
በቃ! ወሳኔ ነዋ አለ ባርናባስ ከአሁን አሁን ዘሎ አነቀኝ በማለት
አስቻለውን እየፈራ።
በእርግጥ እናት ሀገሬ ናት የጠራችኝ ወይስ እናንተ ናችሁ ያዘዛችሁኝ ሲል ጠየቀው አስቻለው የፊቱን ላብ በእጁ እየጠረገ::
«ሁለቱም ተያያዥ ናቸው::»
«ግን ደግሞ ሁለታችሁ መለያየት አለባችሁ፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መለያየታችሁ አይቀርም፡፡ እኔም የሐገሬን ጥሪ በደስታ የምቀበለው ሁለታችሁን ለማለያየት የክተት ጥሪ ነጋሪት የተጎሰመ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ይኸኛውን ግን አልቀበለውም፡፡» አለ ዓይኑን በባርናባስ ላይ ፍጥጥ እንዳደረገ።.....

💫ይቀጥላል💫
👍6
#እከተልሻለሁ

ቤት ስትሔጂ ስመጣ
ስትመጪ ስመጣ
ስትጠጪ ስጠጣ
ስትሄጂ ስከተል
መች ይሰለቸኛል
ያንቺ ጥላ ሆኜ እርምጃሽን መቁጠር

እከተልሻለሁ መቼም ተስፋ አልቆርጥም
ባለንባት ዓለም
ጫማና ካልሲ እንጂ ተረከዝ አያለቅም

🔘ልዑል ሀይሌ🔘
8👍3
#ፍትሕ_ዘ_ሆድ

ኡሁ!...ኡሁ!...

ረሃብ የጠናበት አባባል መች ያውቃል
ይሉኝታውን ትቶ ሳል ይዞ ይሰርቃል


ኡሁ!...ኡሁ!

ማሳልም መብላትም
እኩል የታደለ የገጠመው ገላ
ነፍሱን ለማዳን ነው ከራሱ ሚጣላ

ኡሁ!!

ስለዚህ...

በረሃብተኛ ፊት ፍትሕ አትበሉ
በሆዱ አጋድሏል ህሊና ሚዛኑ

ኡሁ!!...ኡሁ!!..

🔘ልዑል ሀይሌ🔘
👍4🤩2
አንድ ነገር ሁሉ፣ብዙ ከመሰለኝ ፣
እርግጠኛ ሁኚ..
ወይን ጠጥቻለሁ ፤ ሰው እየደለለኝ፡፡
ብዙ ነገር ሁሉ...
አንድ ነው በሚል ቃል ፣ ከዘጋሁት በሬን፣
እርግጠኛ ሁኚ...
የሌለኝን ሁሉን ከፍዬ መስከሬን።
አንድሞ ነገር ሁሉ...
ሁሉም ነገር ሁሉ፣ካልኩሽ በእግዜር ነው፤
እርግጠኛ ሁኚ..
ከከተማ ቄስ ጋር ፣ዝክር ቀምቅሜ ነው።
ሕይወት ሁሉም ነገር ባንድ ነገር ሥር ነው፣
እያልኩኝ ከሰማሽ ካየሽው ማሞረሬን፣
እርግጠኛ ሁኚ...
በፊደራል ዱላ፣ ታጅቤ ማደሬን።
ሁሉም ነገር የለም!
አንድም ነገር የለም፤ የሚል ቃል ከወጣኝ፣
እርግጠኛ ሁኚ...
ጀማሪ ፈላስፋ ፣ አረቄ እንዳጠጣኝ።
ሁሉም አንድ ነገር ፤ሁሉም ነገር አለው፤
ብዬ ጸጥ ካልኩኝ ፣ ከበቃኝ ክርክር፣
እርግጠኛ ሁኚ..
እንዲህ የምሆነው፣ባንቺ ቃል ስሰክር።

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍84
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

...እንዲህ እንዳይመስሉሽ። ኸግር እስተራስሽ እያገላበጡ ነው ሚያዩሽ።ቄንጥ ሲያወጡ አይጣል ነው” ሲሉ መከሯት።

“እሚታዬ ልቤ ፈራ” አለቻቸው፣ እጆቿን እያፍተለተለች።

“ምን ሚያስፈራ ነገር አለ?” አሉ፣ ቆጣ ብለው። ለራሳቸው፣ እንደዛ
ቆፍጣና ምትመስለኝ ልዥ ምን ሆነች? ማታውቀው ቦታ ስለምትኸድ ነው? አሉና ለእሷ፣ “አብሬሽ ማዶል እንዴ ምመጣው? ንጉሥ የሆኑ እንደሁ ልዣችንን እንዳው ዝም ብለን ምንሰድ ይመስልሻል? ጐንደርንም ቢሆን አገላብጨ ነው ማውቃት። ጃንሆይ ሳይነግሡ በፊት... ነፍሳቸውን ይማርና ኸነእንኰዬ አባት ጋር ኑረናል። ጃንሆይ ኸነገሡ በኋላ አልኸድኹም እንጂ” አሏት።

“አብረሽኝ ምትመጪ ባትኾኚ ምን ይውጠኝ ኑሯል?” ብላ፣አንገታቸው ሥር ገብታ ሳይታሰብ ተንሰቀሰቀች። ውስጥ ውስጡን
ያስለቀሳት ግን ከጥላዬ መለያየቷ ነው።

“ደሞ ለክፉ ሆነ ለደግ ግዝየ ሚሆን ወልደልዑልን የመሰለ ወንድም አለሽ። ስንኳን ላንቺ ለእህቱ፣ አላየሽም እንዴ ላገር ሲተርፍ? አርከሌድስም አለ። ልዤ ነው ብዬ ማዶል ። አንቺም ብትሆኚ ታውቂያሽ እንዴት ብርቱና ታማኝ እንደሆነ። እንደ ኒቆላዎስስ ቢሆን... ጋሻና መከታ እንደሚሆንሽ አንቺም ታቂያለሽ” አሉ፡ ደረታቸውን መታ፣ አንገታቸውን ነቀነቅ አድርገው።

ምንጊዜም ቢሆን ስለሚወዱት ታናሽ ወንድማቸው ስለኒቆላዎስ
ሲያወሩ ደስ ይላቸዋል፤ ይኮሩበታል ። ቀጠለና፣ “አጎትሽ እሽቴም አለ። ደሞስ ያጎቶችሽ ልዦች ጌታ፣ አውሳቢዮስና፣ ነጮ አሉ ማዶል እንዴ? የወገን ጥላ አያሳጣኝ ማለት ነው” እያሉ እንባዋን በነጠላቸው ከፊቷ
ላይ ጠራረጉላት።

“ግና የቤተመንግሥት ወግ ኸየት አባቴ አውቄ?” አለች።

“አንቺ ደሞ ያልቸገረሽን። ወጉንስ እኼው እያስተማርሁ ማዶል
እንዴ? ሌላውን ደሞ ግዝየው ሲደርስ ትማሪያለሽ።”

“እሚታዬ፣ ቤተመንግሥት ልገባ?”

“ቤተመንግሥት ለመግባት ምን ያንስሻል? አጥንተ ጥሩ... ያውስ
የንጉሥ ዘር ማዶለሽ? አባትሽስ ቢሆኑ የደንብያው ባላባት የአቤቴ
ተክለሃይማኖት ልዥ ማዶለ? መልክስ ቢሆን ማን ደረሰብሽ? ቀይ ሰው መልክ አይፈጅም ይላሉ፤ አንቺ ፈጅተሻል። ቅላትሽ እኮ የኔና የናትሽ ነው። እንዳባትሽ ጠይም ብትሆኚ ኑሮኮ ምን የመሰለች ጠይም አሳ መሳይ ትሆኚ ነበር። ምግባርና ብሩህ አይምሮም አክሎልሻል።
ለዝህም እኮ ነው ጃንሆይ የመረጡሽ። እቴ ኸንግዲህ ማቄን ጨርቄን የለም፤ መኸድ ብቻ ነው።”

“ልጄ ዕድል ነው። ተሰጥቶሽ ነው። ደግ ሁኖልሻል፤ ሁሉን
አብዝቶልሻል” አሏት፣ እስከዛ ድረስ እናታቸው የሚሉትንና
የሚያደርጉትን በፀጥታ ሲታዘቡ የቆዩት እናቷ።

“የምን ዕድል ነው ምትይ? ዕድል ከሰማይ ይወድቃል? እንዲሁ
ነው እንዴ ንጉሡ ልዣችንን ሊያገቡ የፈለጉ? ልዣችን ሚገባትን ነው ያገኘችው። በደም ግባቷ፣ በብሩህ አይምሮዋ፣ በመልካም ምግባሯና
ጎንበስ ቀና ብላ ስላስታመመቻቸው ነው ንጉሡ ለንግሥትነት የመረጧት፣ ንግሥትነት እንደሚገባት አይተው መዝነው ነው እንጂ እንደ መደዴው ለውበቷ ወይም እንደገበሬ ለሙያዋ ብቻ ብለው
አይደለም።” ዮልያና ልጃቸውን ቆጣ አሉ።

“መቸም ደመ ግቡ ሁሉ... ያስታመመ ሁሉ ንጉሥ ባል አያገኝም። እንዳው የዕድል ነገር ይገርማል። እኼን ማን አሰበው?” አሉ፣ የእናታቸውን አፍ ብዙም የማይዳፈሩት ወይዘሮ እንኰዬ።

“የኔ ልዥ ገና ንግሥት እሌኒን አረግሻለሁ” አሉ፣ አያትየው።

“እሳቸውን መሆን እንዴት ይቻለኛል?”

“አንቺ ደሞ... እሌኒን ትሆኛለሽ ስልሽ እኮ ልክ እንደሳቸው ሁኚ
ማለቴም ማዶል። እንዴት እንደምኖሪ ማወቅ ያንቺ ፈንታ ነው። ሁሉ እየቅል ነው።”

ለጊዜው የአያቷ ምክር በመጠኑም ቢሆን አረጋጋት።

በነጋታው መንገደኛ ናትና ጥሩ እንቅልፍ እንድታገኝ እናትና አያት
ትኩስ ወተት በማር አጠጥተው አስተኟት። እሷ ግን እንደ ትናንቱ
ሁሉ ዛሬም እንቅልፍ በዐይኗ ሳያልፍ ፍርሐት፣ ጥላዬን ለመጨረሻ ጊዜ ሳታየው የመሄድ ጭንቀት፣ ብሎም ቀስ እያለ ውስጧ እየተጫረ የመጣው ቤተመንግሥት የመግባት ጉጉት መሳይ ነገር ሲፈራረቁባት
ሌሊቱ እንደመንጋት አለ።

ዶሮ ሲጮህ ቀሰቀሷትና ተጣጠበች። ቁርስ ብዪ ብለው ሲያቀርቡላት ግን ተናነቃት። እናቷ፣ “ትንሽ አፍሽ አርጊ፤ ምንገድ ባዶ አፍ አይከድም” እያሉ ሊያግባቧት ሞከሩ። እሷ ግን እንኳን እናቷን፣
አባቷን፣ ወንድሟን፣ ጥላዬንና የቤት አገልጋዮቹን ቋራን ራሱን ጥላ መሄዱ ዳገት ሆነባት።

ዐይኗ እንባ አቀረረ።

የእናቷን ፊት የተጫጫነውን ሐዘን ስታይ፣ ዐይኖቿ ጥግ ተጠልሎ
የነበረው እንባዋ ወደ ጉንጮቿ ኮለል አለ። እናቷ እስከዛ ሰዐት አምቀውት የነበረውን እንባ እንደ ድንገተኛ ዝናብ አወረዱት። ጉልበታቸው ላይ ተደፍታ፣ “እነየ መተሽ አታይኝም?” ስትላቸው፣ ትከሻዋ ላይ ተደፍተው
እዬዬ ሲሉ እሷም ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።

አያትየው ልጃቸውን፣ “እንደማበርታት ጭራሽ ታባቢያታለሽ?” ብለው ቆጣ አሉና፣ ወለተጊዮርጊስን ትከሻዋን ነካ አድርገው፣ “ተይ እኮ የኔ ልዥ፣ በቅጡ እንዳልተኛሽ ስንኳ ያስታውቃል። ምንገደኛ ነሽ። ገና
ምንገዱ ሚያጠወልግሽ ይበቃል። ፊትሽን አታበላሺ። የቀባሁሽንም
ኩል እንባሽ አጠበው። በቃ እንድች ብለሽ እንዳታለቅሺ። በይ ነይ” አሉና ፊቷን በእጃቸው አባብሰው፣ እንደገና ሥር ኩል ዐይኗ ላይ አደረጉላት።

እንግዶቹ እህል አፋቸው ካደረጉ በኋላ፣ ለመሄድ ወደ ውጭ ሲወጡ በአቅራቢያ ያለ ቤተዘመድ፣ የወለተጊዮርጊስን ጐንደር መሄድ የሰማ
ጎረቤትና ጓደኞቿ ተሰብስበዋል። ወለተጊዮርጊስ የአያቷን ረጅም የሐር ቀሚስ ለብሳ፣ ከቀሚሱ ሥር በሐር ክር ጫፉ የተጠለፈና ተረከዟን ጠበቅ አድርጎ የያዘ ሱሪ ታጥቃ፣ በአያቷ ወርቅ አሸግና ብቅ ስትል፣እንግዶቹ ትንግርት እንጂ እውን ሰው የሚያዩ አልመስል አላቸው።

ዘመድና ጎረቤት ግቢውን በዕልልታ ሲያደምቀው፣ የወለተጊዮርጊስ ጓደኞች ዐይናቸው እያየ በጓደኛቸው ሕይወት ውስጥ ያልገመቱት
ዓይነት ለውጥ መምጣቱ፣ ካጠገባቸው ተነስታ ለንግሥትነት መታጨቷ አስደነቃቸው። በዓመት መለወጫ ቀን አደይ አበባ እያስቀጠፈች፣ከቤት ቤት በድፍረት ይዛቸው እየዞረች፣ የምታስተባብራቸውና እንደ
መሪያቸው የሚቆጥሯት ጓደኛቸው ከመሃከላቸው በመለየቷ አዘኑ፤
በታላቁ ዕድሏ ቀኑ፣ ተደሰቱ። በዚኹም ድብልቅልቅ ስሜት መሃል ግን በመለያየታቸው አለቀሱ።

ግራዝማች የልጃቸውን ውበት ገና ያን ቀን ያዩ ይመስል ዐይናቸው
ውሃ አቆረ። እሷን ለመሰናበት ማልደው የመጡት ታላቅ ወንድሟ
ወልደልዑል፣ አጎቷ አርከሌድስ፣ የዮልያና ወንድም ኒቆላዎስ፣ አጎቷ
እሽቴና የአጎቷ ልጆች አውሳቢዮስ፣ ጌታና ነጮ በኩራት ተመለከቷት።
ንጉሥ ቤት ነውና የምትገባው በልባቸው ዙርያ የተስፋ ድር አደራችበት።

እናትና ልጅ በሠሩት ጥበብ ተደንቀው ዐይን ለዐይን ተያዩ።
አያትየዋ ያ ሁሉ እንባ ምልክት ስንኳ አልተወም፡፡ ድንቅ እኒያ
ደርሰው ትከሻ ሚሰጡ የጐንደር ወይዛዝርት እንግዲኽ ዐይናቸው
ይደፍርስ አሉ።

ለሱ አይቅርበት አሉ እናትየው፣ እንባቸውን በነጠላቸው እየጠራረጉ።

ጎረቤትና ቤተዘመድ ምርቃት ሲያዘንብላት፣ ዕልል ሲልላት፣ ጓደኞቿ የደስታ እንባ ሲራጩላት፣ ምቀኛው ግን፣ “ታመው የተኙ ግዝየ መዳኒት አርጋባቸው እንደሁ እንጂ ውነት አሁን ንጉሡ…” እያለ ወሻከተ።
👍111
ወለተጊዮርጊስ በቅሎ ላይ ተቀምጣ ቤተሰቧን፣ ጓደኞቿን፣
አገልጋዮቹን፣ ቤተዘመዱንና ጎረቤቱን እንባ ባዘለ ዐይን ተመለከተች።ከመሃከላቸው ጥላዬ ባለመኖሩ አዘነች። ተወልዳ ያደገችበትን ቋራን ጥሎ
መሄድ ብቻ ሳይሆን፣ የልጅነት ጊዜዋ እንዳከተመና ሕይወቷ ለአንዴ ለሁሌም እንደተቀየረ ገብቷት እንባዋ ጥንድ ጥንዱን ተዘረገፈ።

ከግቢ እንደወጡ፣ መንገዱ ላይ እንደ ንጋት ጮራ እያበራች፣ ከበስተኋላዋ የቀረው ቋራ ላይ ብርሃኗን ፈነጠቀች።

ለመጭው መንገድ ከፈተች።

ፀሐይ ስትገርር፣ እንግዶቹን ተከትለው ከመጡት ባለሟሎች መሃል አንደኛው ድባብ ይዞላት፣ ደስታ፣ ፍርሐትና ልታውቃቸው ያልቻለቻቸው ስሜቶች እየተፈራረቁባት፣ በሐሳብ ስትኳትን ትቆይና፣ አልፎ አልፎ
አያትየው ከሰዎቹ ነጠል ብለው ሲያጫውቷት ከሐሳቧ ትነቃለች።

እሳቸው ከመልዕክተኞቹ ጋር ወግ ሲይዙ ስለ ጥላዬ ታስባለች። ከእሱ መለየቱ ሞት መስሎ ይታያታል። ሕይወትና ምኞት እንደታሰበው እንደማይሄዱ ስታስብ ይደንቃታል ። ጊዜ ሁሉን ነገር ድንገት ሊቀይር እንደሚችል አስተውላ እንደ ሕመም ያለ ስሜት ይሰማታል። ሕልሟ ሁሉ ጥላዬን አግብታና ከእሱ ልጆች ወልዳ መኖር ስለነበር ከዚያ ሌላ
ሕይወት አስባም አልማም ባለማወቋ አሁን የተከፈተላት የሕይወት በር ይገርማታል።

ዘወትር እሑድ ዋርካ ስር ቆሞ የምታየው፣ ከቤተክርስቲያኑ
ውጭ ወጥታ እስከምታየው የነበራትን ጉጉት፣ እንደዛ ዓይነት ቅዱስ ቦታ ላይ ቆማ የተመኘችውን የማትነፈግ የሚመስላትንና የዛሬውን
ጉዞዋን ታወዳድርና ትገረማለች። እሱን የምታስብበትን፣ የአስታራቂ
ሽማግሌዎችን መምጣት የምትጠባበቅበትን የወላጆቿን ቤት ደጃፍ፣ያንን የተስፋዋንና የሕልሟን ቋት ታስብና ሆድ ይብሳታል።

ለመሆኑ ጥላዬ መኸዴን ሲሰማ ምን ብሎ ይሆን? ሳናስበው እንለያይ?ለመጨረሻ ግዝየ ስንኳ ሳላየው እያለች እንባዋ ቅርር ይላል። ስለእሱ
ስታስብ እናቱ ትዝ አሏት። እንዴ እንዴት ሊሰናበቱኝ አልመጡም?
አለች።

ሐሳቧ ከጥላዬ ወደ ልጅነቷ ሲሄድ ያሳለፈችው ሁሉ ፊቷ ድቅን
ይላል። ለዘመን መለወጫ ከጓደኞቿ ጋር ከደይ ኣበባ እየቀጠፉ ለጎረቤት የሰጡት፣ የዘፈኑትና የጨፈሩት ትውስ ይላትና እንደገና እንባዋ ይመጣል። ከትውስታዋ ስትመለስ ወዴት እየሄደች እንደሆነ
ትዝ ይላትና ደንገጥ ትላለች።

ደግሞ ፀሐይዋ ድንገት የመንገዷን ፋና ትወጋላታለች። ያን ሰዐት ከአድማሱ ባሻገር ብሩህ ዓለም ይታያታል። ንጉሠ ነገሥቱ እነሱ ቤት ተኝተው ልታስታምማቸው ጎንበስ ቀና ስትል ዐይናቸው ዳሌዋ ላይ
ተቆልፎ እንደነበረ ታስታውስና፣ “ላካንስ ወደውኝ ነበር” ብላ ታስብና ልቧ ይንቀሳቀሳል፤ አሁን አሁን ይላታል። ንጉሡም ቢሆኑ ልዥ እግር ናቸው፤ ዛዲያ እሳቸውን ባገባ ምን ከፋኝ ትልና ሐሳቧ ክንፍ አውጥቶ ያለ ከልካይ ዱሩን፣ ተራራውን፣ ወንዙንና ተረተሩን ተሻግሮ ጐንደር ይገባል።

ቤተመንግሥት ውስጥ በወሬ የምታውቀው ዙፋን ላይ ተቀምጣ፣
በወርቅና በሐር ተንቆጥቁጣ፣ ዝናቸውን የሰማቻቸውን የጐንደር
ወይዛዝርት ቁልቁል ታያቸዋለች። ወንድሟ ወልደልዑል ከጥቂት
ወራት በፊት ተራራ ላይ በወንበር ተቀምጣ ያለመውን ሕልም ደጋግማ እያስታወሰች ትገረማለች።

ስታድግ አያቷ፣ “ሲፈጥርሽ ነው የዋለ። ኻንቺ በላይ ደማም
ላሳር። ብሩህ አይምሮ እንደሁ አድሎሻል፤ ብርታትና አስተዋይነትም አክሎልሻል። ትልቅ ቦታ ትደርሻለሽ የኔ ልዥ ። የተራ ባላባት ልዥ ምሽትማ አትሆኚም” እያሉ ልቧን የሚያነሳሱት ትዝ ይላትና በውበቷና በሥራዋ ስትወደድ፣ ስትደነቅና ስትመሰገን ይታያትና ፊቷ ይበራል፣ልቧ እንደመሸፈት ይላል። ኸጥላዬ ኸተለየሁ አይቀር ስንኳንም ለንጉሥ ሆነ የተሰጠሁት ብላ በረጅሙ ትተነፍሳለች።

አያትየው በበኩላቸው ብዙም ዝምታ ያለመደው አፋቸው ሲያርፍ፣ የእሷን የቤተመንግሥት ኑሮ ይወጥናሉ፤ ምን እንደሚያስተምሩ ያስባሉ፣
ያወጣሉ፣ ያወርዳሉ፣ ይዝታሉ። መለስ ይሉና ያቺ በልጅነቷ ከእናቷ
ወስደው ያሳደጓት ትንሿ ወለቴ ዛሬ ለንጉሥ ሚስትነት በመብቃቷ
ይገረማሉ። የደስታ ሆድ ብሶትም ዐይናቸውን ያረጥባል።

ለአስተማሪ ቀለብ እየሰፈሩ እቤት ውስጥ እንድትማር ያደረጓትን፣
የቤተክህነት ወግና ሥርዐት ያስተማሯትን፣ በሃይማኖትና በመልካም ምግባር ታንጻ እንድትወጣ የደከሙባትን፣ ከፍ ስትል ስለ ነገሥታት ይበልጡንም ደግሞ የሴት ነገሥታትን - ታሪክ ያስተማሯትን፣ በቤት ባልትና ያሰለጠኗትን፣ ሰንበት ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ሥር ሥራቸው ኩስ ኩስ የምትለውንና ቤታቸውን ቀጥ አድርጋ የያዘችላቸውን ወለቴን
ያስቡና ሆድ ይብሳቸዋል። እንደዚህ አድጋ ለንጉሥ ሚስትነት
መብቃቷ ደስ ይላቸውና እንባቸው ይመጣል።

እንደዚህ እሳቸውም እሷም በሐሳብ እንደባዘኑ ቀትር ኾነ።

አገልጋዮች ቀድመው ማረፊያቸው ቦታ ደርሰው ድንኳን ተክለው
ጠብቀዋቸው ነበርና በወይዘሮ እንኰዬ የተሰናዳውን አገልግል
ደንገጡሮቹ አበሉ። ዮልያና እንደ ልጃቸው ሆነው “ብሉልኝ ጠጡልኝ” እያሉ ጋበዙ። ወለተጊዮርጊስ ግን የጎረሰችው እየተናነቃት መብላት
አቃታት።

ከሰዐት በኋላ፣ ጉዞ ቀጥለው እንደተለመደው አገልጋዮቹ ቀድመው ከማደርያው ቦታ ደርሰው ድንኳን ተክለው፣ ደንገጡሮች ከአቅራቢያ
ወንዝ ውሃ ቀድተው፣ ምግብ አብስለው ጠበቋቸው።

እንደዚህ እያሉ፣ አርብ አመሻሽ ገደማ ያቺ አገርን ያስደመመች
ጐንደር ግርጌ ሲደርሱ፣ ዮልያና ልዤ በዝኽ ምድር ላይ ገናና ትሆናለች።ብሩህ አይምሮ እንደ
ሆነ ኸማንም በላይ ተሰቷታል። ንግሥት እሌኒ አረጋታለሁ እያሉ ለልጅ ልጃቸው ያላቸውን የምኞት አጥናፍ ሲዘረጉ ወለተጊዮርጊስ የምትገባበትን የሕይወት ዕርገት ከፍታውን ያወቀችው ጐንደር ስትገባ ነው።....

ይቀጥላል
👍10
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_ሰባት ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ...እንዲህ እንዳይመስሉሽ። ኸግር እስተራስሽ እያገላበጡ ነው ሚያዩሽ።ቄንጥ ሲያወጡ አይጣል ነው” ሲሉ መከሯት። “እሚታዬ ልቤ ፈራ” አለቻቸው፣ እጆቿን እያፍተለተለች። “ምን ሚያስፈራ ነገር አለ?” አሉ፣ ቆጣ ብለው። ለራሳቸው፣ እንደዛ ቆፍጣና ምትመስለኝ ልዥ ምን ሆነች? ማታውቀው ቦታ ስለምትኸድ ነው? አሉና ለእሷ፣ “አብሬሽ ማዶል…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...እኔም የሀገሬን ጥሪ በደስታ የምቀበለው ሁለታችሁን ለመለያየት ሁለታችሁን ለመለያየት የክተት ጥሪ ነጋሪት የተጎሰመ እንደሆነ ብቻ ነው። ይኼኛውን ግን አልቀበለውም።» አለ ዓይኑን በባርናባስ ላይ ፍጥጥ እንዳደረገ
መቀበል ያለ መቀበሉ ጉዳይ የአንተ ነው፡፡ ነገር ግን ደብዳቤው በአድራሻህ የተጻፈና የመዝገብ ቁጥር የያዘ ስለሆነ አንተው ጋር ይቀመጥ፡፡» አለና በርናባስ
ደብዳቤውን መልሶ ወደ አስቻለው ዘረጋ፣
አስቻለው ደብዳቤውን የንጥቂያ ያህል ከባርናባስ እጅ ላይ ምንጭቅ እያረገ
«አምጣው! ለታሪክ ይቀመጣል፡፡» ብሎት ወደ ኋላው ተመልሶ ከቢሮው ወጣና በሩን ድርግም አድርጎ ዘግቶ እዚያው በኮሪደሩ ላይ በመቆም ያንኑ ደብዳቤ እንደገና ያነብበው ጀመር፡፡ ግን የደብዳቤው መልዕክት አሁንም ያው ነው፡፡ አስቻለው በንዴት
ስሜቱ ተለዋወጠና ለጊዜው ምን ማድረግ እንዳለበት ቅጡ ጠፋው:: ግን በስተቀኝ
አቅጣጫ በሚገኝው የኮሪደሩ መወጫ በኩል ጅው ብሎ ሄደና ከህንጻው ውስጥ ወጣ፡፡ በዚያው በመውጫው ዳር የግድግዳ ጥግ ተደግፍ እንደገና ያነብበው ጀመር::
በዚህ ጊዜ ግን «ኪኪኪኪ …. ብሎ ሳቀ፡፡ የንዴት ሳቅ አሁንም «ኪኪኪኪ በዚያችው ቅፅበት እዚያችው ቦታ ላይ እንደ ቆመ በሀሳብ ከብዙ ቦታ ረገጠ: ሔዋንን አስታወሳት ሸዋዬንም እንዲሁ፡፡ የሸዋዬንና የባርናባስን ግንኙነት
እንዲሁም ከሁለቱ ጋር ተለጥፎ ሒዋንን በማስቸገር ላይ ያለው በድሉ ኣሸናፊ ጭምር ታዩት: በእጁ የያዘው ደብዳቤ ይዘትም ከእነዚህ ሰዎች ግንኙነትና ፍላጎት
የመነጨ ስለመሆኑ ሳይጠራጠር አመነበት።

ወዲያው አንድ ነገር ብቻ ማድረግ ታየው፡፡ በዚያ ሆስፒታል ውስጥ
ያስቀመጠው ልብስም ሆን ማስታወሻ ምንም ሳይታሰበው ጋወን ስለ መልበሱ እንኳ ሳይታወቀው ከዚያ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ለመውጣት ወሰነ፡፡ በልቡ ውስጥ ያለው መድረሻ ደግሞ የአውራጃው ግብርና ፅህፈት ቤት።

ከዲላ ሆስፒታል አስከ ግብርና ጽህፈት ቤት በአማካይ ሠላሳ ደቂቃ የሚወስደው የእግር መንገድ ለአስቻለው ሃያ ደቂቃ እንኳ አልፈጀበትም፡፡ የቆፌን
ኮረኮንች መንገድ እየነጠረ ተረማምዶ፣ ዲላ ከተማን ለምስራቅና ለምዕራብ ለሁለት
በሚሰነጥቃት አስፋልት መንገድ ላይ ገስግሶ ወደ ዲላ ሰሜናዊ ጫፍ አቅራቢያ ሲደርስ ቀኙን በመያዝ ጥቂት ዳገታማ የሆነውን አባሯማ መንገድ ረምርሞ ከበልሁ
ቢሮ በር አጠገብ ደረሰ

«ኳ..ኳ..ኳ..ኳ....»

አንዴ ይጠብቁኝ አለ በልሁ ከውስጥ፡ በዚያ ሰዓት ከሁላት ባለ ጉዳዮች ጋር እየተነጋገረ ነበር፡ አስቻለው ዛሬስ አላስቻለውም። በሩን በርግዶት ገባና የበሩን እጀታ እንደያዘ በልሁን በተቀመጠበት አሻግሮ ተመለከተው።

በልሁ አስቻለው መሆኑን ሲያውቅና አጠቃላይ የፊቱን ገፅታ
ሲመለከት በድንጋጤ ፊቱ ኩምትርትር አለና «እንዴ» «ምነው አስቻለው?» አለው ፍጥጥ ብሎ እየተመለከተው። አስቻለው መልስ አልሰጠውም። ዝም ብሎ ወደውስጥ ገብቶ ሳይጋበዝ በእንግዳ ወንበር ላይ ቁጭ አለ።በረጅም ረጅም እየተነፈሰ ጣርያ ጣርያ ያይ ጀመር። በአስቻለው ሁኔታ የተገረመውና ምናልባትም ደንገጥ ያሉ የበልሁ እንግዶች በልሁን አየት አየት አደረጉት።

«እስቲ ወንድሞቼ! አንዴ ወጭ ሆናችሁ ጠብቁኝ»ሲል በትህትና
ጠየቃቸው። ሰዎቹ አላመነቱም ወዲያው ብድግ ብለው ተከታትለው ወጡ።
«አስቻለው!» ሲል ጠራው በልሁ በሁኔታው መለዋወጥ ሆዱ እያዘነ
«ወይ»አለው አስቻለው አሁንም አይኑን ከኮርኒሱ ላይ ሳይነቅል።
«ምነው? ምን ሆንክ?»
አስቻለው የሆነውን ነገር ከመናገር ይልቅ ያን የያዝውን ደብዳቤ ለበልሁ እየዘረጋ «እንካ አንብበው» አለና ሰጠው
በልሁና ልክ እንደ አስቻለው ቶሎ ወደ ሀሳቡ አልገባም፡፡ደብዳቤውን
ቅርጽ በቅድሚያ ቃኘው። ፕሮቶኮል የጨበጠ ደብዳቤ ነው፡፡ ፊሪሚው ባርናባስ ቲተሩም የሱ ነው ከዚያ በኋላ ወደ ዝርዝር ሁኔታ ገብቶ አንብቦ ከጨረሰ በኋላ
ድንግጥ ባለ አኳኋን «ከየት አመጣኸው?”» ሲል ጠየቀው።
ሰጡኝ እኔማ ከየት አመጣዋለሁ?» አለና አስቻለው ጉንጮቹን ነፋ አድርጎ «እሁሁ» ቡሎ በረጅሙ ተነፈሰና አንገቱን ወደ መሬት ደፋ።
በልሁ ለጊዜው ምንም ማለት አልቻለም፡፡ አስቻለውን ግን አከታትሎ ተመለከተው። የደብዳቤው ይዘትና መልዕክት በወስጡ ሊፈጥርበት የሚችለውን
ስሜት ያውቃልና እሱም ሆዱ እያዘነ «እስቲ ወጣ እንበልና ሻይ እየጠጣን እንነጋገር» አለ በልሁ የአስቼሐውን ምላሽ በአይኑም በጆሮውም እየጠበቀ። አስቻለው እሺ ወይም እምቢ ብሎ ቃል አልተናገረም ብቻ ዝም ብሎ ብድግ አለና ቸከታትለው ወጡ።

ለበልሁ መሥሪያ ቤት ሠራተኞች የሻይ ፍላጎት እማራጩ ሁለት ነው፡፡በዚያው በመስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በምትገኝ የሻይ ክበብ በከሰል የተፈላ ሻይ ቡና መጠጣት አለበለዚያ ከግቢ ወቶ በአንደኛ መንገድ ላይ ከሚገኙ ሆቴሎች ድረስ በመሄድ
የማሽን ሻይ ቡና መጠቀም፡፡ በዚያን ዕለት ግን በልሁ ስለ አስቻለው ጉዳይ ጊዜ ወስዶ መነጋገር ስለ አሰበ በቀጥታ ወደ ከተማ ወረዱ፡፡ ወደ አንደኛ
መንገድ ከተዳረሰ በኋላ አስቻለው አንድ ሀሳብ አመጣ።
«ለምን ወደ ታፈሡ ጋ እንሄድም?» አለና በልሁን አየት እደረገው፡፡
በእርግጥ በልሁም ትዝ ስላላለው ነው እንጂ ያ ጉዳይ ወደ ታፈሡ ቤት የሚያሮጥ ነውና ሀሳቡን ተቀበለው።
ከበልሁ መስሪያ ቤት እስከ ታፈሡ ቤት ድረስ እስከ አሥራ አምስት ደቂቃ ሚወስደውን መንገድ በዝምታ ጨርሰው በሯ ላይ ሲደርሱ ታፈሡ የቤት ልብሷን
እንደለበሰች አገኟት፡፡
«አለሽ ታፈሥ?» አላት በልሁ ቀድሞ፡፡
እንዴ! ምን ዓይነት አመጣጥ ነው?» አለች ታፈሡ ድንግጥ ብላ፡፡ ከሰአቱ አጉልነት በተጨማሪ የአስቻለው ጋውን መልበስ ግራ አጋባት፡፡ አስቻለውና በልሁ
ፊታቸውን ክፍት እንዳላቸው ስላም እያሏት ወደ ሶፋ አለፍ እያሉ ተቀመጡ።
«እናንተ!» አለች ታፈሡ አሁንም ዓይኗን በሁለቱም ላይ እያንከራተቱተች።
«እስቲ ቁጭ በይ ታፈሥ» አላት በልሁ በተዳከመ ስሜት።
ታፈሡ ቁጭ አለችና ምን ሆናችኋል?» ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
በልሁ የያዛትን ወረቀት ከርቀት አቶከረችባት።
«አይዞሽ! ብዙም" አትደንግጭ!» አላት በልሁ::
«ትንሽም ቢሆን ንገሩኝ»
«መምህርት ሸዋዬ ገና ዛሬ ሳታሸንፈን አልቀረችም፡፡» አላት በልሁ በደፈረቁ ፈገግ ብሎ እያያት፡፡
«እንዴት አድርጋ?»
«ያን ባርናባስ የተባለ ሽማግሌዋን ተጠቅማ::»
«ማለት?»
«እንቺ ይኸን ወረቀት አንብቢው፡፡» አለና በልሁ ደብዳቤውን ለታፈሡ ዘረጋላት፡፡ ታፈሡ ያን ደብዳቤ ከበልሁ እጅ ላይ በችኮላ ተቀብላ ሁለመናውን አየችው።ቀንና ቁጥር የራስጌና የግርጌ መሀተም እንዲሁም የበርናባስ ፊርማና ቲተር ያለበት ደብዳቤ ነው፡፡ ማንበብ ጀመረች።

«ለጓድ አስቻለው ፍስሀ
ዲላ
ጉዳዩ ፡ የእናት ሀገር ጥሪን ይመለከታል፡

«እንደሚታወቀው ሁሉ በስሜኑ የሀገራችን ክፍል ጥቂት ተገንጣይ
ቡድኖችና ሌሎች ጎጠኞች በመተባበር የሀገራችንን ሉዓላዊነት በመፈታተን ላይ
ናቸው። የእነዚህኑ ተገንጣይ ቡድኖችና የውጭ ደጋፊዎቻቸውን ቅስም ለመስበር ጀግናው ሠራዊታችን ከውጭና ከውስጥ ጠላቶቻችን ጋር አንገት ለአንገት
👍9
በመተናነቅ ላይ ይገኛል። በመሆኑም አብዮታዊት እናት ሀገራችን በአሁኑ ሰዓት የቁርጥ ቀን ልጆቿን አብዮታዊ ተሳትፎ የምትሻበት ወቅት ነው።
«በዚሁ መሠረት እርስዎም በጦር ግንባር ተሰልፎ በመዋደቅ ላይ ለሚገኘው ጀግናው አብዮታዊ ሠራዊታችን በሙያዎ የህክምና አገልግሎት ይሰጡ ዘንድ
አብዮታዊ ጥሪዋን ያስተላለፈችልዎት በመሆኑ ወደ አስመራ በመሄድ ለስድስት
ወራት ያህል የሙያ አገልግሎት እንዲሰጡ ተመርጠዋል።
ስለሆነም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደ እርስዎ ወደ ተጠቀሰው አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ስላሉ ለትራንስፖርትና ለሌሎችም ዝግጅቶች ያመች ዘንድ ይህ
ደብዳቤ በደረሰዎት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባ በመድረስ ለጤና ጥበቃ
ሚኒስቴር ሪፖርት እንዲያደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

ባርናባስ ወየሶ

«ኣ!» አለች ታፈሡ ደብዳቤውን ጨርሳ ዓይኗን ወደ በልሁና ወደ
አስቻለው ቶሎ ቶሎ በመቀያየር እየተመለከተች።
“አየሽ አካሄዳቸውን ታፈሥ» አላት በልሁ አንገቱን ዘመም አድርጎ በትካዜ እያያት።
«አንተ አስቻለው»አለች ታፈሡ በዚያ ደብዳቤ ይዘት ምን ያህል መንፈሱ ሊጎዳ እንደሚችል አውቃ ስሜቱን ለመመርመር።
«እኔ ግን ፈጽሞ አልቀበላቸውም" በፍፁም አልሄድም» አለ አስቻለው
አሁንም አይኑን በኮርኒስ ላይ ሰክቶ።
ታፈሡና በልሁ እርስ በእርስ ተያዬ፡፡ እንደገና ሁለቱም ወደ አስቻለው ዞር ዞር በማለት ተመለከቱ። ዓይኑ ፍጥጥ ብሎ ከንፈሩን ነክሷል፡፡ በሀሳብም ጭልጥ ብሎ ሄዷል።
«ከውሳኔ በፊት ግን ምክክር ያስፈልገዋል፡፡» አለና በልሁ እንደገና ወደ ታፈሡ ዞር በማለት
«አይመስልሽም ታፈሥ?» ሲል ጠየ ቃት፡፡ታፈሡ ግን ዓይኖቿ በእንባ ሞልተው በሁለት እጆቿ ግንባሯን ደግፋ ወደ መሬት አቀረቀረች።....

💫ይቀጥላል💫
3👍2🔥1
#ልጠይቅሽ

ለትንታው ለቁርጠቱም
ለውጋቱም ለእንቅፋቱም
“እኔን!” እያልሽ እኔ እንድቆም
አንቺ ታመሽ እኔ ስድን
ብኩን ነፍሴን ሳደነድን
ልብ ያላልኩሽ ቀኔን ሳድን
እናታለም “እንዴት ነሽ ግን?”

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
3👍1
#ምንትዋብ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


“እምዬ ጐንደር እንግዳ ተቀባይ እኮ ናት።”

ጥላዬ፣ እምነቱንና ተስፋውን ጐንደር ላይ ጥሎ ሐሙስ ቀን እዚያች ብርቅየ ከተማ ገባ። ጨለማ የከተማዋን ሰማይ ለማልበስ በመጣደፍ ላይ
ነው። ጐንደሬዎች ቤታቸው ለመከተት ፈጠን ፈጠን እያሉ ሲራመዱ፣ጥላዬ፣ ብዛታቸው ብቻ ሳይሆን ዓይነታቸው አስደነቀው። እንደ ግሪኮች፣ አርመኖች፣ ህንዶችና አረቦች የመሳሰሉ የውጭ ሃገር ዜጎች ሕዝቡ መሃል ውር ውር ሲሉ፣ የቆዳቸው፣ የመልካቸውና የአለባበሳቸው
መለየት አስደመመው።

ጭቃ ምርጎቹን ባለሳር ክዳን ጎጆዎች ትክ ብሎ አያቸው። ባዘቶ
የለበሱ የሚመስሉ ዋንዛ ዛፎች ስር ችምችም ማለታቸውና እንደ ቋራ ተሰባጥረው አለመቀመጣቸው ገረመው። በየቦታው ጣል ጣል ያሉት
የድንጋይ ግንቦችና ነገሥታት ብቻ የታደሉባቸው የኖራ ቅብ ቤቶች
የከተማዋ ጌጥ መስለው ታዩት። ያየው ሁሉ ከቋራ የተለየ ሆነበት።
ጐንደር ልዩ ስፍራ ሆነችበት፤ አስገረመችው።

ዐዲስ ሕይወት ልትሰጠው ቃል ኪዳን ገባችለት። እየተዘዋወረ ከተማዋን ማየት ፈልጎ ጨለማው በፍጥነት ማደሪያ እንዲፈልግ አስገደደው። ቤተክርስቲያን ፍለጋ ዐይኑን ሲያዘዋውር፣ አንድ የቆሎ ተማሪ በፍጥነት ሲራመድ አየና ሮጦ ደረሰበት።

“ከርመህ ነው? ላገሩ እንግዳ፣ ለሰዉ ባዳ ነኝ። ማደሪያ ሚሆነኝ
ደጀሰላም ባገኝ ብየ” አለው።

“ኸደብረብርሃን ሥላሤ ማታድር? ምን የመሰለ ዛኒጋባ በቤተክሲያን
ዙሪያ እያለልህ። ወደዛው ነው ምኸድ፤ በል ና። አገርህ ወየት ነው?”

“እማር ብየ መጥቸ” አለ ጥላዬ፣ መናገር አልፈለገም።

“ጐንደር ደሞ ለትምርት። ኸየቦታው ሚመጡ ተማሮች፣ ሊቃውንት፣ ካህናትና መምህሮች ሁሉ ኸዝሁ ማዶል ያሉት?” ብሎ ነጫጭ ጥርሶቹን አሳየው፣ ተማሪው።

ገራ ገር ፈገግታው ጥላዬን ማረከው። ዕድሜ ልኩን የሚያውቀው መስሎ ተሰማው። ቀደም ብሎ ማደሪያውን ሲያስብ ባይተዋርነት የተሰማውን ያህል፣ ከትከሻው ሸክም እንደወረደ ሁሉ ቀለል አለው።

“ቅኔ ልትማር ነው የመጣህ?”

“ሥዕል ልማር ብየ ነው የመጣሁ።”

“ዛዲያ ጐንደር ምን ገዷት! እደብረብርሃን ሥላሤ መምህሮቹም ተማሮቹም አሉልህ፡፡”

ጥላዬ ተደሰተ። ተማሪው ገዱ ሆኖ ተሰማው። ልባዊ ፈገግታው ደግ
ሰው እጅ ላይ እንደወደቀ ጠቆመው። “ምን እየተማርህ ነው?” ሲል ጠየቀው።

“ቅኔ እየተማርሁ ነው። መወድስ እያኸድሁ ነው።”

“ደሕና አኸደሀል።”

“አንተስ ሞካክረኻል?”

“ሥላሤ ደርሻለሁ። ማድርበት ደጀሰላም የት አገኝ ይሆን እያልሁ?”

“ጐንደር መጥተህ ነው ስጋት ሚያድርብህ? አንተስ አለማወቅህ ...እምዬ ጐንደር እንግዳ ተቀባይ እኮ ናት። ሴቶች ወጥ ሲሰሩ ኸደረስህ
ይሽተዋል ብለው ሳትበላ ማትኸድባት አገር እኮ ናት። ጐንደር የሁሉ ናት፤ ማንም ኸየት መጣ ኸየት ቤቴ፣ የኔ ብሎ ሚኖርባት። አልሰማህም
እንዴ፣
ቤተስኪያን ስሞ ለመኖር፣
መልካም አገር ነው ጐንደር።
ሲባልላት?” እያለ ግጥሙን በዜማ አወረደለት።

ጥላዬ ሳቅ አለና፣ “ገና መድረሴ፣ ምኔ ሰምቸ? ጐንደሬ ሁሉ እንዳንተ
ጥሩ ነው?” ሲል ጠየቀው።

“እኔስ ኸተምብየን ነው የመጣሁ። ዐራት ዓመት አርጌያለሁ ኸዝኸ።”
ተማሪው ከላይ የደረበውን ለምድ፣ ትከሻው ላይ ያንጠለጠለውን
አኮፋዳና ለውሻ መከላከያ የያዛቸውን ሁለት በትሮች ጥላዬ ትክ ብሎ ተመለከተና ከልመና እንደመጣ ገባው። ወደ ቤተክርስቲያኑ ሲደርሱ
ደጀሰላሙን ተሳልመው ውስጥ ገቡ።

“እንዴት ያለ ቤተክሲያን ነው በል” አለው፣ ጥላዬ።

“አጤ አድያም ሰገድ ኢያሱ መዠመሪያ አሠሩትና ተቃጠለ። ኸዚያ በኋላ፣ ልዣቸው... ሦስተኛው ሚባሉት አጤ ዳዊት እንደገና አሠሩት።

እሳቸው ግና ባባታቸው ስም እንዲጠራ ስለፈለጉ እኔ አሰራዋለሁ ስሙ ግን ባባቴ ይሁን አሉ።”

ጥላዬ ፈዞ ቆሞ የቤተክርስቲያኑን አሰራር ሲያደንቅ ተማሪው፣ “እኛ
ስንገባ ስንወጣ ለምደነዋል። እንግዲህ አንዱን ጥግ ይዘህ ተኛ። ኸኛ ዘንድ ምኝታ የለም ሁኖ ነው” ብሎት ሄደ።

ጥላዬ ቤተክርስቲያኑን እንደገና ተሳልሞ ዙርያውን ሲመለከት፣
እየጨለመ በመምጣቱ በወንዶቹ መግቢያ በኩል ጭንቅላቱን ጉልበቶቹ መሃል ቀብሮ ተቀመጠ። ግቢው ጭር ብሏል። መንገድ ሲመሽበት፣
“ቤት ያብርሃሙ ሥላሤ ነው” እያሉ ቁርበት ጣል፣ ትኩስ ሽሮ እንጀራ
ላይ ፈሰስ አድርገውለት፣ አለበለዚያ ቆሎ እንዲቆረጥም ወይ ቂጣ እንዲያላምጥ ሰጥተውት ያሳደሩት ሁሉ ትዝ አሉት። ከነጋ እህል አፉ አላደረገም። ሆዱ ከረሀብ ብዛት ዋይ ዋይ አለበት፤ ያለማቋረጥ
አዛጋው።

በዕድሜ ከእሱ ትንሽ ከፍ ስለሚለው ተማሪ አሰበና ባይለየው መረጠ። ስሙን እንኳ ሳይጠይቀው በመሄዱ ተቆጨ። አንገቱን እንደደፋ ሲያሰላስል ድምፅ ሰማ። ቀና ሲል ተማሪዎች ወደ መማሪያ ቦታቸው ወደ ቤተክርስቲያኑ ጀርባ ይሄዳሉ። ተማሪው ከእነሱ ነጠል ብሎ ወደእሱ ሲመጣ አየው። ሁለመናው ተበራታ።

“ራት ቢጤ አመጣሁልህ። የውሃ ቅሌን ልተውልህና ገሠሣ ሲያበቃ
መጥቸ ወስደዋለሁ። ስትተኛ ኸዚሁ ተወው። አነሳዋለሁ” ብሎት
መንገድ ሲጀምር ጥላዬ ከተቀመጠበት ተነስቶ፣ “ሥላሤ ያክብሩልኝ።ስሜንም ሳልነግርህ... ጥላዬ እባላለሁ... ከቋራ ነው የዘለቅሁ” አለው::

ቀደም ብሎ አባቱ ፈልገው እንዳያገኙት ሲል ማንነቱን ደብቆ፣
አሁን የተማሪው ደግነት ምሥጢሩን አሟሸሸበት።

“በል ነገ ያገናኘን። አብርሃ ነው ስሜ። ገሠሣ እንዳያመልጠኝ
ብሎት ተማሪዎቹ ወደሄዱበት አቅጣጫ አመራ።

ጥላዬ፣ አብርሃ የሰጠውን ፍርፋሪ በልቶ፣ ውሃውን በላዩ ቸልሶና
አምላኩን አመስግኖ የመንገድ ድካም ስለተጫጫነው አንዱ ዛኒጋባ ጋ ተጠግቶ ጋደም እንዳለ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደው።

ጠዋት ድምፅ ሲሰማ ብንን አለ። የት እንዳለ ለማወቅ ጥቂት ጊዜ
ወሰደበት። የሌሊቱ ብርድ፣ ልብሱን ውሃ የነካው አስመስሉታል። አንድ ጋቢ መኝታም ከላይ የሚለበስም ሆኖ አገልግሎታል። ከተቀመጠበት
ተነስቶ የቤተክርስቲያኑን መግቢያ በር ተሳለመና ወንዶቹ መግቢያ
ትይዩ ያለ አንድ ዋንዛ ዛፍ ስር ሄዶ ዳዊቱን አውጥቶ መድገም ጀመረ።

“አድረህ ነው?” የሚል ድምፅ ሲሰማ ቀና አለ። አብርሃ ነው ።

“ደሕና... ደሕና ... ይመስገነው።”

“አንደዜ ጠሎት ላድርስና ኸየንታ ሔኖክ ዘንድ ወስድሀለሁ” ብሎት
ሄደ።

ጥላዬ፣ በእሽታ ራሱን ነቀነቀለትና ወደ ዳዊቱ ተመለሰ። የዕለቱን
አድርሶ ሲጨርስ ዳዊቱን ማኅደሩ ውስጥ ጨምሮ፣ ስንጥር አንስቶ
መሬት ላይ መሞነጫጨር ጀመረ። እንደለመደው የወለተጊዮርጊስን ምስል ሊሥል ፈልጎ እዚያ ያደረሰው ምን እንደሆነ ትዝ ሲለው
ስንጥሩን ወረወረው።

ከቤት የወጣበት ምክንያት በመንገድ ድካምና በረሐብ በአእምሮው ውስጥ እየደበዘዘ መጥቶ ነበርና አሁን ቁጭ ሲል ሁሉ ነገር ፊቱ ላይ ድቅን አለበት። ወለተጊዮርጊስ ጐንደር መግባት ከለመግባቷን የማወቅ ፍላጎቱ ጸና። እሷ ሐር ቀሚስ ለብሳ ከቤት እንደወጣችው ሳይሆን፣ እሱ
እሑድ ቤተክርስቲያን ስትሳለም እንደሚያያት የዐዘቦት ልብሷን ለብሳ፣ ነጠላ ተከናንባ በበቅሎ ስትሰግር በዓይነ ኅሊናው ታየው፤ ሆዱ ባባ።

ያርባ ቀን ዕድሌ ነው እንግዲህ ምን አረጋለሁ? አለ፣ ለራሱ።
እናቱንና አባቱን አስታወሰ። በእሱ መጥፋት እናቱ እንዴት ጨርቃቸውን እንደሚጥሉ አሰበና ሆድ ባሰው። አባቱም ቢሆኑ አመል ሆኖባቸው ይነዛነዙ እንጂ፣ የእሱ ነገር እንደማይሆንላቸው ያውቃልና ጉዳታቸው ተሰምቶት ለመጀመሪያ ጊዜ አዘነላቸው። ሳያስበው ፊቱ በእንባ ርሷል። በጋቢው ፊቱን ጠራርጎ ቀና ሲል አብርሃ ፊቱ ቆሟል።
👍152
“ታለቅሳለህ እንዴ ጎበዝ? በርታ እንጂ! ሁላችን ኸሞቀ ቤታችን
ወጥተን የቀረነው ትምርት ፍለጋ ማዶል እንዴ? አይዞህ ትለምዳለህ።ቋራ ደሞ ቅርብ ነው:: በል ተነስ አሁን አለቃ ሔኖክ ዘንድ እንኸድ።ብቻ አንድ ምነግርህ ነገር አለቃ ሔኖክ እያረዥሁ ነውና ማስተማር ይበቃኛል እያሉ ነው ሲሉ ሰምቻለሁ። ለማንኛውም ኸደን ሚሉትን እንስማ። እሳቸው የለም አልችልም ኻሉ ሌሎች ደሞ አሉ።”

ጥላዬ ከተቀመጠበት ተነሣ።

አለቃ ሔኖክ ቤት ሲደርሱ፣ አብርሃ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “አድራችሁ
ነው?” ሲል፣ ደንደን ያለችውና ሰላሳ መጨረሻዎቹን የምትጠጋው
ባለቤታቸው ብቅ ብላ ሰላምታ ሰጠቻቸው።

“አድረው ነው? አለቃ አሉ?” አላት፣ አብርሃ።

ዘመድ ሙቷቸው ወደ ጎርጎራ ኸደዋል። እሑድ ይመለሳሉ
አለችው።

“እንግዲያማ ወደ ጃን ተከል እንውረድ” አለው፣ ለጥላዬ ።
ባለቤትየዋን ተሰናብተው እየተጨዋወቱ ከግቢ ሲወጡ፣ “እኔ ምልህ አለቃ ሔኖክ የቤተክሲያን አስተዳዳሪ ነበሩ እንዴ?”

“ስለምን ጠየቀኸኝ?”

“አለቃ ስትላቸው ግዝየ።”

“እ... አለቃ የተባሉትማ አሁን በኛ በቅኔ ቤት መምሮቻችንን መሪጌታ እንል የለ? ልክ እንደዛ ነው። ሹመት ነው። ሥዕል ተምረውና
ረዥም ጊዜ ሰርተው ሲያበቁ ሊቀጠበብት ኸዛም አለቃ ይባላሉ። አለቃ ትልቁ ሹመት ነው።”

“እህ” አለ ጥላዬ፣ እንደገባው ለማሳወቅ።

ፋሲል ቤተመንግሥትጋ ሲቃረቡ፣ “እኼ አጤ ፋሲል የተባሉት
ንጉሥ ግቢ ነው። ነገሥታቱ ኸዝኸ ግንብ እየሠሩ ነው የኖሩት” አለው
አብርሃ፣ በጣቱ እየጠቆመው።
“ትናንት ሳልፍ አይቸው እኮ ምን እንደ ሆነ አላወቅሁም።”
ጃን ተከል እንደ ደረሱ ወሬ ፈላጊ ሁሉ ግማሹ በቡድን ሌላው
ተሰባጥሮ ዋርካው ሥር ቆሟል። ጃን ተከል ጐንደሬዎች የክተት፡
የነገሥታት ሞት፡ የምሕረት ሆነ ሌላ አዋጅ የሚሰሙበት፣ የትኛው
መኰንን እንዳመጸ፣ ግዛቱን እንደተነጠቀ፣ የትኛው እንደተሾመ፣ የትኛው እንደተሻረ፣ ማንኛው ሹመቱ አነሰኝ ብሎ እንዳኮረፈ፣
ስለቤተመንግሥት የሥልጣን ፍትጊያና የሚቀጥለው ግብር መቼ እንደሆነ የሚከታተሉበት ቦታ ነው። እናም ጐንደሬዎች ጃን ተከል አካባቢ ሲያንዣብቡ፣ ወሬ ሲቀባበሉ፣ ፍሬውን ከገለባው ሲለዩ፣ ሐሳብ ሲለዋወጡ፣ ሲተነብዩና ሲሟገቱ ይወላሉ።

ጥላዬና አብርሃ ዋርካው ሥር እንደቆሙ፣ አብርሃ የሚያውቀው ሰው አግኝቶ ከእሱ ጋር ሲያወራ ጥላዬ ከጎኑ የቆሙ ሰዎች ሲያወሩ ጆሮውን ጣለ።

“ዛሬ ትገባለች አሉ።”

"ዛሬ?”

“አዎ! ወደርም የላት አሉ።”

“ቋራ ድረስ ዘልቀው እንዴት አገኟት ጃል?”

“ለንጉሥ ምን ይሳነዋል? ንጉሥ ይተክላል፣ ንጉሥ ይነቅላል ሲሉም
አልሰማህ?”

ጥላዬ፣ ስለወለተጊዮርጊስ እንደሚያወሩ ገባው። ሐሞቱ ፈሰሰ፣ሰውነቱ ሽምቅቅ አለ። አደባባይ ላይ የብቸኝነት ስሜት ወረረው።ፈንጠር ብሎ ቆመ። አብርሃ ጨዋታውን ጨርሶ ወደእሱ ሲመጣ፣ ወደሌላ ቦታ እንዲሄዱ ጠየቀው።

“ሰውየው እኮ ንጉሡ ኸቋራ ምሽት አጭተዋልና ዛሬ ትገባለች ነው ሚለኝ። እንግዲህ ነገ ግብር ይገባል። ይዠህ መጣለሁ።”

“ግብር?”

“አዎ! ድኻ እኮ ገብቶ ይበላል። እነሱ በልተው ኸተነሡ ወዲያ ሌላው ይገባል። ለኛ ለተማሮችማ ደስታችን ነው። በልተን አኮፋዳችንንም ሞልተን እንመለሳለን። እንመጣለን ነገ።”

“እኔ ስንኳ ገና እንግዳ ነኝ፣ ምን ብየ ነው ኸንጉሥ ግብር ምኸድ?
እኔ አሁን ግብር ሳይሆን ብራና ነው ምፈልግ፡፡”

ለብራናውማ ትደርስበታለህ።”
እንዴት የቤተመንግሥት ግብር ሊፈልግ እንደማይችል ገረመው
አብርሃ። “በል ወደ ታች እንውረድ። አንድ ዘመድ አለኝ ኸወደ ደንጋይጌ... የክርስቲያኑ... የነጋዴው ሰፈር። በዛው ሞኝ መቆሚያ ኸደን ደሞ ወሬ እንሰማለን።”

ጥላዬ ፊቱ ጥላሸት ለብሷል።
አብርሃ፣ የጥላዬን ፊት መለዋወጥና ለምንም ነገር ፍላጎት ማጣት አስተዋለና ስሜቱ ከየት እንደመጣ ተመራመረ። ኸቤቱ የወጣ.. ናፍቆት ይሆናል አለ፤ ለራሱ።.....

ይቀጥላል
👍13
#የኔ_ምሥል

ጠንቅቆ እማያውቀኝ
“ጠንቅቄ አውቅሃለሁ!”
ሲል አስጠነቀቀኝ
አስጠንቃቂዬ ሆይ
“ባክህ አታስቀኝ
እንኳን አስጠንቃቂ
ጠንቃቂ'ኳ አያውቀኝ
ሞትም ስፈቅድ ነው
በገረሩ እጆቹ
አንገቴን የሚያንቀኝ

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍6
#እ_ን_ድ_ረ_ሳ_ሽ

አንቺን እንድረሳሽ
መንገድ ጥረጊልኝ
ይህቺን ብቻ አርጊልኝ

ስምሽን እያነሱ እንዳያስታውሱኝ
በሞተው ትዝታ እንዳይቀስቅሱኝ
ያንቺ አለመሆኔን ዛሬ እንዳሳያቸው
ጨረቃን ፀሐይን ምድር አውርጂያቸው
ውቅያኖስ ባህራን ሰማይ ስቀያቸው

#እ_ን_ድ_ረ_ሳ_ሽ

የረገጥነው አስፋልት የሄድንበት መንገድ
ያ ያለፈው ፍቅር ያ ያለፈው መውደድ
ፍፁም ውሽት ብዬ እንድሸመጥጠው
ተፈጥሮን አዛቢ መውደዴን እንድተው

#እ_ን_ድ_ረ_ሳ_ሽ

ገደሉን ሙዩና ተራራውን ናጂው
ደመናን አውርደሽ አፈሩን ውሰጂው
የረገጥሽው መሬት አምሮ እንዲታይበት
በአበባው ፋንታ ሳማ ትከይበት

#እ_ን_ድ_ረ_ሳ_ሽ

ያ ሁላ ቃል ኪዳን ተበትኖ እንዲቀር
አይጥ ሐይቅ ትዋኝ ዓሳ ሰማይ ይብረር
በህይወት ባሉት ምትክ ሙታኖች ይነሱ
ነገስታት ይውረዱ ባርያዎች ይንገሱ

ይሄን ካረግሺልኝ

መውደዴን ይቀርና መኖር አቆማለሁ
በመኖር ብረሳሽ
ባለመኖርም ውስጥ አስታውስሻለሁ።

🔘ልዑል ሀይሌ🔘
7👍3
#ምንትዋብ


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

...ጥላዬ ፊቱ ጥላሸት ለብሷል።
አብርሃ፣ የጥላዬን ፊት መለዋወጥና ለምንም ነገር ፍላጎት ማጣት አስተዋለና ስሜቱ ከየት እንደመጣ ተመራመረ። ኸቤቱ የወጣ..ናፍቆት ይሆናል አለ፤ ለራሱ።

በፋሲል ቤተመንግሥት በስተግራ በኩል ወደ ላይ ሲወጡ፣
ሰዎች ከላይ ወደእነሱ አቅጣጫ ሲመጡ፣ ወንዶች ቆባቸውን፣ ሴቶች ክንብንባቸውን እያወረዱ እጅ እየነሱ ሲያልፉ፣ ጥላዬ እርስ በርሳቸው ሰላምታ የሚሰጣጡ መስሎታል። ጥቂት እንደተራመዱ፣ አብርሃ የተማሪ
ቆቡን አውልቆ እጅ ሲነሳ አየው።
መንገዱ ላይ ካለሁለቱ በስተቀር
ማንም የለም።

ጥላዬ፣ “ማነን ነው እጅ ምትነሳ? ኸኔና ኻንተ በቀር ማነም የለ
በምንገዱ” ሲል ጠየቀው።
“ማነነም! ሰዎቹስ እጅ ሲነሱ አላየህም እንዴ? እኼን ምንገድ አየህ?”አለው፣ አገጩን ወደፊት ቀደም አድርጎ፣ ሰፊውን የእግር መንገድ እያሳየው። “የንጉሡ መኸጃ ነው። እሳቸው ሲወጡ ማንም በዝኽ አያልፍም። አየኸው ያን ደጋን የመሰለ የደንጊያ ግንብ መተላለፊያ?ንጉሡ ወደ ራስጌ
አጤ ፋሲል ያሠሩት የራሶቹ መኖሪያ ነው...ኸዝኸ ከፍ ብሎ ነው ያለ... ወይ ደሞ ወደ ሌላ ቦታ ሚሄዱበት ነው።እሳቸው ባይኖሩም ቆብ አውልቆ እጅ መንሳት ደንብ ነው። ቦታው
እስተስሙ ቆብ አስጥል ነው።”

“እንደቤተክሲያን ነው በለኛ!” አለ ጥላዬ፣ ፈገግ ብሎ።
“ንጉሥ እኮ ፊታቸው ተሸፍኖ ነው ሚሄዱ። አሁን ታቦት ትኩር
ብለህ ታያለህ? አታይም! እሳቸውንም ፊታቸውን ጨርሶ አታይም።
አብረዋቸው ሚኸዱት ስንኳ ኸጎናቸው ሲራመዱ መሬት መሬቱን
እያዩ ነው። ደሞም አለልህ ሊቀመኳሱ... ንጉሥ አሳሳች ሚባለው። ልክ
እንደሳቸው ሁኖ ይወጣል። ንጉሡ ኸቤት ተቀምጠው እሱ እሳቸውን
መስሎ ይወጣል። ያን ግዝየ ሰዉ ንጉሡ መጡ ብሎ ይሰግዳል።
እንዲህ ዋዛ መስሎሀል! ወሬ ስሰማ እቴጌዎቹ ደሞ ሲወጡ ምንግዝየም
በጃንደረሳ እየተጠበቁ ነው።”
“ጃንደረባ ደሞ ምንድርነው? ስለምንስ ይጠበቃሉ?”
“ጃንደረባማ ... እቴጌዋን ሚጠብቀው... ስልብ ነው። ሚጠብቀው
ያው እቴጌዋ ኸሌላ እንዳይኸዱ ነዋ!” አለ፣ ሳቅ ብሎ።
ጥላዬ ለራሱ፣ ወለቴ
ጉድ ፈላባታ አለና ለአብርሃ፣ “እኼ
ቤተመንግሥት ሚባል ነገር ብዙ ጣጣ አለው” አለው።
“ወጉ እንግዲህ እንደዝኸ ነው። እኼ ምታየው... ኸቤተመንግሥቱ
አጠገብ ያለው ሁሉ ደሞ የባለርስቶቹ ምንደር ነው።”
ጥላዬ ዞር ብሎም አልተመለከተ።
አብርሃ፣ ጥላዬ ለሚያየው ነገር ሁሉ እምብዛም ትኩረትና ፍላጎት
የሚያሳይ አልመስል አለው። ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ገባው።
“ትመለስ ይሆን?” አለው።
“እረገኝ ስለምን?”
“እንግዲያማ ተጫወት። እኔኮ ይህ የመጣሁት አገር ላላምድህ ብየ ነው። እኼ አሁን ምንኸድበት ዘመዴ መልካም ሰው ነው። አንዱም እሱን ብየ ነው እጐንደር የመጣሁት።”
አልፎ አልፎ እየተጫወቱ ቁልቁል ወርደው ረጅም መንገድ ተጓዙ።
ጥላዬ ከቦት የነበረው የመጫጫን ድባብ እየለቀቀው መጣ። ያየውን
ሁሉ እያደነቀና እየወደደ የሆዱን ባር ባር ማለት ረሳ።

“ኸዝኸ ወረድ ስትል የዕጨጌው ሰፈር አለ” አለው አብርሃ
ሊያጫውተው ፈልጎ። “ሸማኔውም ወዲያ ነው። ማዶ ደሞ የባለእጌዎች ምንደር አለ። ለብቻቸው ነው ሚኖሩ። መቸም ባለእጌዎቹ ግንበኞች
አናጢዎች፣ ሸማኔዎች፣ ቀጥቃጮችና ሸክላ ሠሪዎች ናቸው ቤተመንግሥትን ሚያስጌጡ እነሱ ማዶሉ? እስላምጌ ደሞ በዝያ ስትዘቀዘቅ አለልህ። የስላሞቹ የነጋዴዎቹ ሰፈር ነው። ብዙ ሰው ይኖራል ኸዛ። በቅሎና ፈረስ ገባያውም ኸዛው ነው።”

ድንጋይጌ ሲደርሱ፣ “እኼ ገባያው ነው። ቅዳሜ ነው ሚቆም። ዛሬ
ጭር ቢል እንዲህ እንዳይመስልህ። ነጋዴውም... ሁሉም ነው ሚወጣ። ነገ ማልደን እንመጣለን” አለው።

ጥላዬ መልስ አልሰጠውም። ወለተጊዮርጊስ ከንጉሥ ጋር ግብር
በምትቀመጥበት ቀን መውጣት አልፈለገም። ከቤተክርስቲያኑ ግቢ እንደማይወጣ ለራሱ አስገንዝቦ ዝም አለ።

አብርሃ ዘመድ ቤት ገብተው መልካም መስተንግዶ ተደረገላቸው።ጥላዬ አልፎ አልፎ የያዘውን ጠላ ፉት ከማለትና ከአብርሃ ዘመድ የሚቀርቡለትን አንዳንድ ጥያቄዎች ከመመለስ በስተቀር አብርሃና ዘመዱ በትግርኛ ስለሚያወሩ በዝምታ ተውጦ፣ ጠላውን እየተጎነጨ፣
አንዳንዴም እየሰለቸው ቆይቶ፣ ከሰዐት በኋላ፣ ተነሥተው ወጡ።
ደብረብርሃን ሥላሤ ሲደርሱ ተለያዩ። ጥላዬ ጠዋት ተቀምጦበት የነበረው ዋንዛ ዛፍ ሥር ተቀምጦ ያየውን ሁሉ አሰበ። ጐንደር ልዩ ቦታ፣ ከግምቱ በላይ ሆነችበት፤ ወደዳት። የገባ ዕለት ዐዲስ ሕይወት ልትሰጠው የገባችለትን ቃል ኪዳን አጸናችለት። ድንገት የፈሰሰ
ሐሞቱ ነፍስ ዘራ። የአለቃ ሔኖክ ምሽት እሑድ ይመለሳሉ ብለው
ነግረውናል። አብርሃ ደሞ ሰኞ ጠዋት እንኸዳለን ብሎኛል። ብቻ አንዴ እሳቸውን ላግኛቸው፣ ኸዝያ ወዲያ ማደርገውን እኔ አውቃለሁ አለ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ጐንደርና ቋራ ምንና ምን

ወለተጊዮርጊስ፣ አፄ ፋሲለደስ ቅጥር ግቢ ስትገባ፣ አያቷ
እርምጃቸውን ገታ አድርገው፣ “እኼ አጤ ፋሲለደስ ያስገነቡት አሁን ጃንሆይ ሚኖሩበት ነው። እንግዲህ አንቺም ኸዝኸ ነው ምትኖሪው”አሏት።

“ኸዝኸ?” ብላ ዐይኖቿ እስከመጨረሻው ተከፈቱ።

የባለሦስት ደርቡ ህንጻ ግዝፈት አስደነቃት። ሰማይ ጠቀስ
መሰላት። በግንቡ ማዕዘኖች የተሠሩትን የእንቁላል ቅርፅ ያላቸውን ግንቦች አይታ ተደነቀች። ሰገነቱ ላይ ያለው ሰቀሰቅ ለመተኮሻ ተብሎ እንደተሰራ መገመት አቃታት። በእንቁላል ግንቦቹ መሃል ወደ ሰገነቱ
የሚወስደውን የዕንጨት ደረጃ ተመልክታ ምን እንደሆነ አልገባ አላት።

ዮልያና ቀጠሉና፣ “ጃንሆይ ኸዚያ ኸሰገነቱ ቁመው ሁሉን ይቃኛሉ፤
አንዳንዴም ኸዚያው ላይ ሁነው አዋጅ ይነግራሉ። አንቺም እንግዲህ ኸዚያ ላይ ምትቆሚበት ቀን ሩቅ አዶለም” አሏት፣ ሳቅ ብለው።

ዝም አለች። ያን መሰል ነገር አይታ ባለማወቋ፣ ከመንገድ ድካም
ጋር ተደምሮ አእምሮዋ ያየችውን ሁሉ መመዝገብ አልሆንለት አለው።

የግንቡ ግዝፈት፣ የንጉሥ ሚስትነት ልኩ ምን ድረስ እንደሆነ
ገለፀላት። ስለዚህ ዓለም ያላትን ግንዛቤ ሁሉ ግልብጥብጡን አወጣባት።ስለራሷ የነበራትን ግምት አዛባባት። “ንግሥት እሌኒን አረግሻለሁ”እየተባለች፣ የአፄ ሚናስ ደም በደምስሯ እንደሚንቆረቆር እየተነገራትና
በእንክብካቤ ያደገችው ልጅ ለእዚያ ለምታየው ግርማ ሞገስ ሁሌ የማትመጥን መስሎ ተሰማት።

ከቋራ መጥታ ያን መሰል ኑሮ ውስጥ መግባት ምን ማለት እንደሆን ማወቅ ተሳናት። እኛ እናት አባቷ ቤት መደብ ላይ ተኝተው የነበሩት ሰው ንጉሥ ናቸው ሲባል ድንገት እንደ ጨረቃ የራቁባትን ያህል ዛሬ ደግሞ የሚኖሩበትን ቤት ስታይና ልትኖር እንደታጨችበት ጭምር
ስታስብ፣ የእሷም ሕይወት ምን መልክ ሊይዝ እንደሚችል ለመጀመሪያ ጊዜ ተገነዘበች።

ጐንደር ታላቅ የሕይወት ግብዣ እንዳቀረበችላት ታወቃት። ሁሉም ካሰበችው፣ ከገመተችውና ካለመችው በላይ ሆነባት::
ፍርሐት ፍርሐት አላት።አካባቢዋን እንደ ዋዛ ታልፍ የነበረችው ወለተጊዮርጊስ፣ ቋራ እንደዚያ ቆማ የምታደንቀው ሰው ሰራሽ ነገር ባለማየቷ ለመጀመሪያ
ጊዜ ያየችውን ውበት አደነቀች። ጐንደርና ቋራ ምንና ምን አለች።
ያየችው ሁሉ የሰው ልጅ የእጅ ጥበብ ውጤት መሆኑን ተጠራጠረች።ያንን የመሰለ ውበት የቀረጹትን ሰዎችና እጆች ማየት ተመኘች።
👍101
የጥበብ ፍቅር በልቧ ውስጥ ሲሰርጽ ታወቃት።ቀደም ብሎ ቅጥር ግቢው መግቢያ ላይ ትጥቃቸውን አሳምረውና
በተጠንቀቅ ቆመው የነበሩትን በርካታ የቤተመንግሥት ዘበኞች አይታ መደንገጧን ሁሉ ረሳችው። የዘበኞቹ ንቃትና ኮስታራነት አስፈርቷት እንደነበረም ዘነጋችው።

ወደ ግቢው ሲዘልቁ፣ የግቢውን ንጽህና አስጠባቂው የግቢ አዛዥ
ንጉሠ ነገሥቱን የሚጠብቁት የእልፍኝ ዘበኞቹ፤ የግቢው ኃላፊ ሊጋባው፣ ያልተፈቀደለት እንግዳ እንዳይገባ የሚያደርገው እልፍኝ አስከልካዩ፣ የንጉሠ ነገሥቱን መሣሪያ ተሸካሚ ጋሻ ጃግሬው፣ ጃንደረባው፣ የጋማ ከብት ተንካባካቢ ባልደራሱ፣ ነፍጠኛው፣ ባለሟሉ፣ አዛዥ፣ ፋና ወጊው
የውጭና የውስጥ አጋፋሪው ብዛት፣ ወደ ላይ፣ ወደታች፣ ወዲህ፣ ወዲያ ማለት፣ መጠራራት፣ ትዕዛዝ ማስተላለፍና መቀበል ግቢውን ሁካታ በሁካታ አድርጎታል። ያ ሲንጫጫና ሲተራመስ የነበረው ሰው ሁሉ
እነሱን ሲያይ ፀጥ እረጭ አለ።
እያንዳንዱ መንገድ ለመልቀቅ ጥግ ጥጉን ይዞ በተጠንቀቅ ሲቆም፣ ዐይኑን ወለተጊዮርጊስ ላይ ተከለ፤ በውበቷ ተደመመ።

ወለተጊዮርጊስና አያቷ ሰዉ ለጥ እያለ ሰላምታ እየሰጣቸው ወደ
ቤተመንግሥቱ መግቢያ ሲደርሱ፣ የዙፋን ቤት ሹሙም ሰላምታ
ሰጣቸው። እሱን ሲያልፉ፣ በንቃት ከቆሙት ወታደሮች ጀርባ
አደግድገው የቆሙ የውጭ አስተናጋጆችም ለጥ ብለው እጅ ነሷቸው።

አብረዋቸው የመጡት ወንዶች ወደኋላ ሲቀሩ፣ ከደንገጡሮቹ ጋር
የአፄ ፋሲልንና የአፄ አድያም ሰገድ ኢያሱን ቤተመንግሥታት አልፈው
ቋሪ አነስተኛ ወደ ሆነ ሕንጻ ሲወሰዱ ወታደሮች፣ አደግድገው የቆሙ የውጭ መሪ አስተናጋጆችና በር ላይ የቆሙ የእልፍኝ አስከልካዮች አክብረዋቸው ወደ ውስጥ ገቡ። አንደኛዋ ደንገጡር ለዮልያና ማረፊያ ክፍላቸውን ስታሳይ፣ ሌላኛዋ ወለተጊዮርጊስን ወደ ተዘጋጀላት ክፍል ወስዳ ዕቃዋን
አስቀምጣላት ትንሽ እረፍት እንድታደርግ ነግራት ወጣች።

ደንገጡሯ ስትወጣላት፣ ወለተጊዮርጊስ ክፍሉ መሃል ቆማ በየመን ምንጣፍ ያጌጠውን ሳንቃና አልጋ ልብስ የለበሰውን አልጋ ትኩር ብላ አየች። ወደ ግራዋ ስትዞር በእንጨት መዝጊያዎች የተዘጋው ረጅም
ባለመስተዋት መስኮት የሐር መጋረጃ ለብሷል ። አነስተኛ ጠረጴዛ ላይ የተለኮሱ ጧፎች ሸክላ ማስቀመጫ ውስጥ ተቀምጠው ክፍሉን
አድምቀውታል።

ክፍሉን አማተረች። አንድ ሰው አንድ መኝታ ክፍል ለብቻው
እንዴት ሊይዝ እንደሚችል ገርሟት ፈዛ ቆመች። ጫማዋን አውልቃ፣
አልጋው ላይ አረፍ ከማለቷ፣ አብረዋት ከመጡት ደንገጡሮች አንደኛዋ እንድትታጠብ ወደ መታጠቢያ ክፍል ይዛት ሄደች። እሷም አያቷም ታጥበው እንደተመለሱ፣ ራት በልተው በየክፍላቸው ገብተው ተኙ።...

ይቀጥላል
👍101
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ...ጥላዬ ፊቱ ጥላሸት ለብሷል። አብርሃ፣ የጥላዬን ፊት መለዋወጥና ለምንም ነገር ፍላጎት ማጣት አስተዋለና ስሜቱ ከየት እንደመጣ ተመራመረ። ኸቤቱ የወጣ..ናፍቆት ይሆናል አለ፤ ለራሱ። በፋሲል ቤተመንግሥት በስተግራ በኩል ወደ ላይ ሲወጡ፣ ሰዎች ከላይ ወደእነሱ አቅጣጫ ሲመጡ፣ ወንዶች ቆባቸውን፣ ሴቶች ክንብንባቸውን እያወረዱ እጅ እየነሱ…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...«አስቻለው!» አለችው ሔዋን፤ የዘመቻ ጥሪ ደብዳቤ በደረሰው አምስተኛ ቀን ላይ በዕለተ አርብ ከጠዋቱ ሦስት ሰአት አካባቢ ከቤቱ በመገኘት።

«ወይ!» አላት አስቻለው አልጋው ላይ ጋለል ብሎ ተኝቶ ከጎኑ ቁጭ
ያለችውን ሔዋንን ቀና ብሎ እየተመለከታት።
«ሰሞኑን የምሰማው ወሬ ምንድነው?» ስትል ዓይን ዓይኑን እያየች ጠየቀችው።
«ምን ሰማሽ?»
«ጥሩ ያልሆነ ወሬ::»
«ንገሪኛ!» አላት አስቻለው ፈገግ ብሎ እያያት፡፡
«ሳታውቀው ቀርተህ ነው?»
«ብዙ ይወራ የለ! የትኛውን ማለቴ ነው፡፡»
«በመሥሪያ ቤትህ በኩል ለስድስት ወር ያህል ዘመቻ ሂድ ተብለህ እምቢ ማለትህን ሰማሁ፡፡» አለችው በፍርሀት አስተያየት እያየችው።
«አዎ! አልሄድም ብያለሁ፡፡ አሁንም አልሄድም፡፡»
«ግን ለምን?»
«እንደማልሄድ የነገሩሽ ሰዎች
ምክንያቴንም ሳይነግሩሽ የቀሩ
አልመሰለኝም፡፡ አንቺም አትደብቂኝ፡፡» አላት የሔዋንን ግራ እጅ ይዞ እየደባበሳት፡፡
«ነግረውኛል። ግን ሆዴ በጣም ፈራ»
«ለምን ብለሽ?»
«ግዳጅ ላለመቀበልህ ምክንያቷ እኔ የምሆን ስለመሰለኝ፡» አለችና ሔዋን ዓይኖቿ ላይ ያቀረረ እንባዋን በለበሰችው ስከርፍ ጥርግ አደረገች።
«አይዞሽ ሔዩ፣ አትፍሪ! ምንም አይመጣም፡፡»
«ተው እስቹ ምንም አይመጣም አትበል። ኑሮህ ሁሎ ይበላሻል፡፡ ለአንተ ኑሮ መበላሽት እኔ ምክንያት መሆን የለብኝም፡፡ የአንተ ከተበላሸ የኔም ይበላሻል»
አለችና እንባዋን አሁንም በጉንጯ ላይ ታወርደው ጀመር።
“አታልቅሺ የኔ ፍቅር። የኔ ሕያወት የሚበላሸው አንቺን ከአጣው ብቻ
ነው:: ዘመቻ ከሄድኩ ደግሞ አንቺን ላጣሽ እችላለሁ። ስለዚህ አልሄድም»
«አንተ ዘመቻ ብትሄድ እኔ የት እሄድብሃለሁ?»
«እህትሽ እና ባርናባስ እየሰሩልሽ ያለውን መንገድ እጣሽውና ነው ወይስ አልገባሽ ይሆን?»
አውቃለሁ። ገብቶኛል::»
“ታዲያ የኔ ዘመቻ መሄድ እንዴት አንቺን አያሳጣኝም ብላሽ ትገምቻለሽ»
«ፈጽሞ አስቻለው ፈጽሞ አያለያየንም።
«እንዴት?»
«እኔም ላጣህ አልፈልግምና!»
«ወደሽ ሳይሆን ያስገድዱሻል»
«አንድ ነገር አትርሺ ሒዩ! ያለሽው በእህትሽ ቤት፤ የምትበይው
የምትጠጪው የእሷን፡ በዚያ ላይ ባርናባስን የሚያህል የፖለቲካ ስልጣን ያለው ወዳጅ አላት።
በዚሁ ላይ ያቀረቡልሽ ወዳጀ በከተማው ውስጥ አለ የተባለ ሀብታም 'በድሉ አሽናፊ' የባርናባስ ስልጣንና የበድሉ ገንዘብ ከተባበሩ እንዴት እኔና አንቺን
መለያየት ያቅታቸዋል?» አለ አስቻለው ከተንጋለለበት ቀና ብሎ ሔዋንን ፊትለፊት እያያት፡፡
«ይህን ሁሉ ግን የታመነ ልብ ያሸንፈዋል::» አለችው ሔዋን የአስቻለውን ደረት እየደባበሰች።
«ፈጽሞ፡ በበኩሌ ማመን ያስቸግረኛል።»
«ስማ አስቻለው!»
«ወይ የኔ ፍቅር»
«እኔንም አንተንም ለአደጋ የሚያጋልጥ አጋጣሚ የሚፈጠረው አንተ ዘመቻ አልሄድም ብለህ የቀረህ እንደሆነ ነው::»
«እንዴት?»
«ዘመቻ ካልሄድክ ከሥራ ያስወጡሃል! ወይም ያስሩሃል። ምናልባት ሊገድሉህ ወይም ሊያስገድሉህ ይችላሉ። አየህ አስቹ! ሥራ ከሌለህ ገንዘብ
አይኖርህም። ገንዘብ ከሌለህ ደግሞ ችግር ያበሳጭህና ለችግርህ ምክንያት በሆኑ
ሰዎች ላይ አደጋ አድርስህ በሌላ የከፋ ችግር ወስጥ ልትገባ ትችላለህ:: ያኔ ልብህ ለጭካኔ እንጂ ለፍቅር ቦታ አይኖረውም፡፡ ዞሮ ዞሮ ለኔ አልሆንከኝም። ታስረህ ማየቱም ለአዕምር'ዩ አይመቸውም፡፡ ብትሞትም ሀዘኔ መራርና የዕድሜ ልክ ነው፡፡
ግን ይህ ሁሉ ይወገድ ዘንድ ግዳጁን ተቀብለህ መሄድ ስትችል ለምን ሁለታችንም እንቸገራለን?» አለችው በትካዜ ውስጥ ሆና ዓይን ዓይኑን እያየች።
«ሔዩ የኔ ችግር አልገባሽም፡፡»
«ገብቶኛል። ግን እሱም ቢሆን መላ አለው::»
«ምን ታየሽ?»
«በቃ እኔ ከእት አበባ ቤት እወጣና አንተ በምትቆርጥልኝ ገንዘብ ከትርፍዬ ጋር በአንተ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፡፡ ግዳጅህን ፈጽመህ ስትመለስ እኔና አንተ ራሳችን በምንደግሰው ሰርግ ተጋብተን አብረን መኖር እንችላለን:: ለኔና
ለአንተ ፍቅር የሚበጀው ይሄ ብቻ ነው።
ከዚህ በኋላ ሁሉቱም ትካዜ ወስጥ ገቡ። ሁለቱም በየበኩላቸው ያስቡ ጀመር
በየልባቸው ያለውን ነገር በማስታወስ።

እሷ አላወቀችም እንጂ ዛሬ ሔዋን ያቀረበችው ሀሳብ አስቻለው ራሱ
በተካፈለበት ጉባዔ ላይ የተቀየስ አቅጣጫ ነበር፡፡ እርግጥ ነው የአስቻለው የዘመፍቻውን ግዳጅ ያለመቀበል ውሳኔው እጅግ ጠንካራ ነበር፡፡ ነገር ግን ታፈሡና
በልሁ መርእድን ጨምሮ ሀሳቡን እንዲቀይር ብዙ ታግለውታል የስድስት ወር ጊዜ አጭር
መሆኗን ዘመቻውን ባለ መቀበሉ
ከሥራ መባረር ምናልባት እስር፣ ከዚያም ያለፈ ክፉ ነገር ሊመጣ እንደሚችል እየጠቀሱ ሊያግባቡት ሞክረዋል በዚያው በራሱ ቤት መርዕድና በልሁ ጫት እየቃሙ ታፈሡ ራሷ እስከ ውድቀት ሌሊት ድረስ አብራቸው በመቆየት በዚሁ ጉዳይ ላይ ከአስቻለው ጋር የተፋጩት ገና ደብዳቤው በደረሰው ማግስት
በአስቻለው ግዳጅ የመቀበልና
ያላመቀበል ውይይት ወቅት ጉልህ ሥፍራ ተሰጥቶት የነበረው የአስቻ ለውና የሔዋን ፍቅር ጉዳይ ነበር።

ለአስቻለው ለግዳጅ መመልመል የባርናባስ ሚና ወሳኝ ሊሆን እንደሚችል ሁሉም አምነውበታል እሱ ደግሞ ከራሱ ፍላጎት በተጨማሪ ሸዋዬ የምትጥልበትን
አደራ ለመወጣት ጭምር አስቦና ተገፋፍቶ የፈጸመው ስለመሆኑ አይጠራጠሩም።ሁለቱ ሰዎች የአስቻለውን አለመኖር ተጠቅመው ሊፈፅሙት ያቀዱት ነገር በሁሉም አእምሮ ውስጥ አለ። ሔዋንን ከበድሉ አሸናፊ ጋር ሊያላምዱ ነው። ይህ ደግሞ በአስቻለውና በሔዋን ፍቅር ላይ ጥላውን ሊያጠላ ነው።
ይህን አደጋ ለመከላከል ይቻል ዘንድ መላ መልምለዋል። በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ሔዋንን ከሸዋዬና ከባርናባስ መዳፍ ውስጥ ፈልቅቀው ማወጣት፣
ዋሽቶም ለምኖም ሔዋንን የችግሩ ፈቺ አንድ አካል ማድረግ፡፡ በዚህ ጉዳይ አስቻለውን ጨምሮ ሁሉም ተስማምተዋል። ሔዋንን የማሳመን ጉዳይ ለታፈሡ እንግዳሰው ተሰቷት እሷም የተጣለባትን ሃላፊነት ለመወጣት አልዘገየችም፡፡ለአስቻለው የዘመቻ ትእዛዝ በደረሰው አራተኛ ቀን ላይ ነበር ሔዋንን ከመሰረተ ትምህርት ሥራዋ ስትመለስ ወደ ቤቷ ጎራ እንድትል የጠየቀቻት፡፡ሔዋንም
ጥያቄውን ተቀብላ ከታፈሡ ቤት ተገኘች።
«ሔዩ ተቸግረናል» ነበር ያለቻት ታፈሡ ሔዋንን ሶፋ ላይ አስቀምጣ እሷም ከፊትለፊቷ በመቀመጥ፡፡
«ምን ሆናችሁ?»
«አስቻለው በመሥሪያ ቤቱ በኩል ዘመቻ ታዝዞ ነገር ግን አልሄድም
በማለቱ እኔም በልሁና መርዕድም ተጨንቀናል፡፡»
«ዘመቻ?»
«አዎ»ለስድስት ወር ብቻ ለሚቆይ የሙያ ዘመቻ ወደ ኤርትራ እንዲሄድ በደብዳቤ ታዟል።እሱ ግን ሔዋንን በሸዋዬ ቤት ውስጥ ትቼ አልሄድም እያለ አስቸግሮናል»
«ኤርትራ ማለት የጦርነቱ አገር አይደል?»
«አዎ፣ እሱ ግን የሚሄደው ሊዋጋ አይደለም በጦርነቱ ለሚጎዱ ቁስለኞች የህክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው።»
«ታዴያ አንዴት ይሻላል?»
«ችግሩ ያለ አንቺ አይፈታም»
«ምን አድርጌ እፈታዋለሁ?»
«አስቹ የሚለው ወደዚህ ዘመቻ እንድሄድ ያደረጉኝ ሸዋዬና በርናባስ ናቸው። ዓላማቸውም ሔዋንን ለበድሉ አሸናፊ ሊድሩ አስበው ነው።ስለዚህ ፍቅሬን ከማጣት እነሱ ላይ አደጋ አድርሼ እስር ቤት ብገባ ይሻለኛል እያለ ድርቅ አለብን»
👍12
«ያን ያህል ታጸሡዬ!»
«አዎ ሔዋን ፤ ስሜቱ ተለዋውጦብናል።»
«ምን አድርጊ ትይኛለሽ ታዲያ?»
«አንቺ ከሽዋዬ ቤት ውጭና በአስቻለው ደሞዝ ከትርፌ ጋር አስቻለው ቤት ኑሪ»
«አይከብድም ታፈሡዬ?»
ለፍቅር ሲባል ከዚህም በላይ መስዋዕትነት ይከፈላል። ይህን ካላደረግሽ የአስቻለው ህይወት መበላሽቱ ነው፡፡ አንቺም ታጭዋለሽ፡፡ እሱም ያጣሻል፡፡
ዘመቻ ካልሄደ ከስራ ያባርሩታል ያኔ ይቸግራል።ከተቸገረ ይበሳጫል ከተበሳጨ አደገኛ የሆነ የህይወት ርምጃ ይወስዳል። ኢላማዎቹ ደግሞ ሸዋዬና ባርናባስ ናቸው።
አስጨናቂው ነገር ይህ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአንቺ ቆራጥ ውሳኔ ሰላማዊ መፍትሄ ያገኛል።
«እኔ ቢሳካልኝ እሱ ግን ዘመቻውን እሺ ብሎ ይቀበላል?»
«አያወላውልም፡፡»

ይህ ነበር ከዛሬው የአስቻለውና የሔዋን ውይይት በስተጀርባ የነበረው ክንውን።
«አስጨነቅሽኝ ሔዋን!» አላት አስቻለው የሆዱን በሆዱ አድርጎ፡ ሔዋን ብታውቀው ኖሮ በዕለቱ አልጋ ላይ ተኝቶ ይጠባበቅ የነበረው እንኳ ይህንኑ ሀሳብ
ልታቀርብለት እንደምትመጣ ስለሚያውቅ ነበር፡፡
«ቢጨንቀኝ ነዋ አስቹ!»
«ግን ከልብሽ አምነሽበታል?»
«አሁን አሁን ሲገባኝ እንዲያውም የዘገየሁ እየመሰለኝ መጥቷል:: ራሴ እየተጨነኩ አንተንም ሳስጨንቅ መቆየት አልነበረብኝም። አንተ ጋር ሆኜ
የሚመጣውን ችግር ሁሉ በአንተ ከለላ ልከላከለው ወስኛለሁ::»
አስቻለው ከተንጋለለበት ብድግ ብሎ ሔዋን ሳማት እሷም ሳመችው። ግን ደግሞ ሁለቱም ሆዳቸው ባባና ተላቀሱ።

💫ይቀጥላል💫
👍9
#እቴጌና_እምዬ

ታሪክ ለመከወን ለዚች ላገሪቱ
ከፍ ብላ እንድትታይ ከልብ እየሻቱ
ካንድ ወንዝ ባንድ ቀን የተወለዱቱ
ልብ ላይ በፍቅር የተቀመጡቱ
እምዬ #ምኒልክ እቴጌ #ጣይቱ
ላድር ባዮች እንጂ
ለኛስ ሕያው ናቸው ዘላለም ሳይሞቱ!

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
11👍4🤩3
#እኔ_ላንቺ

"ምርኩዝና ባላ ምሶሶም አይሻ
ሁሉን ይሸከማል ያ'ፍቃሪ ትከሻ"

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍94