#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...ሳትታሰብ የተገኘቶው ትርፌ በጋሻው ለብዙዎች ያልታሰበ ደስታ
እስግኝታለች፡፡ ከሁሉም በላይ አስቻለው ተመችቶታል፡፡ ቤቱ ተዘግቶ አይውልም አይዝረከረክም፣ ኦይመሰቃቀልም፤ ትርፌ ሽክፍ አደርጋ ይዛዋለች። የሆቴል ምግብ
ትቶ ቤቱ ውስጥ መመገብ ጀምሯል። እንጻራዊ የሆነ የመንፈስ መረጋጋትም አግኝቷል፡፡ በልሁና መርዕድ እንኳ እንደ ድሮው ፍራሽ በማንጠፍ ከሰል
በማያያዝና ሻይ ወይም ቡና በማፍላት ተራ መጨቃጨቃቸውን ትተዋል።ጫታቸውን ብቻ ገዝተው በተነጠፈና በተበጃጀ ፍራሽ ላይ እግራቸውን መዘርጋት ነው፡፡ ቀሪውን ስራ ትርፌ ታቀለጣጥፈው ይዛለች፡፡
የትርፈ በአስቻለው ቤት ተመልሳ መግባት ለሔዋንም የፀጋ ያህል ሆኗል።ሔዋን የአስራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰደች በኋላ በወቅቱ ግዳጅ በነበረው የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ ሥራ በመጀመሯ በከፊልም ቢሆን ከሸዋዬ ቁጥጥር ውጭ ሆናለች። አጋጣሚ ሆና የተመደበችው ደግሞ በዚያው በዲላ ከተማ
በዜሮ ስምንት ቀበሌ ውስጥ በመሆን ከቤት ወደ ስራ ከስራ ወደ ቤት የምትመላለሰው በአስቻለው ቤት በር ላይ ነው። እናም ስታልፍ ስታንድም ጎራ
ትልበታለች። ትርፌ ስላለች ዘወትር ክፍት ነውና አትቸገርም። ይህ ሁኔታ በእሷና በትርፌ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮት መነፋፈቅ ጀምረዋል።
አንድ ቀን ደግሞ ሁለቱን ለረጅም ሰዓት አብሮ የሚያቆይ አጋጣሚ
ተፈጠረ፡፡ የግንቦት ወር መጨረሻ አካባቢ ነው ሔዋን መሰረተ ትምህርት በምታስተምርበት ጣቢያ አካባቢ አንዲት ሴት ሞተው በለቅሶው ምክንያት በዕለቱ ማስተማር እንደማትችል ከጣቢያ ሃላፊው ይነገራታል፡፡ ከጠዋቱ ሦስት ሠዓት
አካባቢ ወደ ቤቷ ስትመለስ እግረ መንገዷን ወደ አስቻለው ቤት ጎራ ትላለች። ጊዜ ነበራትና ተረጋግታ ቁጭ በማለት ከትርፌ ጋራ ጭውውት ይጀምራሉ። ሔዋን
በአስቻለው አልጋ ላይ ትራስ ደገፍ ብላ ፣ ትርፌ ደግሞ በአልጋው ትይዩ በተነጠፈችው ፍራሽ ላይ ሆና ፊትለፊት እየተያዩ ይጫወታሉ።
«ትርፍዬ!» ስትል ጠራቻት ሔዋን፡
«ወይ እታለም፡፡»
«አገርሽ የት ነው?»
«ውይይ… እታለምዬ! በጣም ሩቅ ነው፣ ቢጠሩት እንኳ አይሰማም፡፡»
ትርፌ የገጠር ኑሮዋ ባያጎሳቁላት ኖሮ ቀይና ስልክክ ያለች፣ ዓይንና
ጥርሶቿ እዩኝ እዩኝ የሚሉ መልከ ቀና የነበረች ልጅ ትመስላለች፡፡ ያም ሆኖ አሁን ወደ አስቻለው ቤት ከተመለሰች ወዲህ ወዘናዋ እየተመለሰ መጥቷል።
«የት ቢሆን ነው ትርፍዬ?» ስትል ሔዋን ደግማ ጠየቀቻት የትርፌን
ሁለመና አየት ሰለል እያደረገች።
«ወሎዬ ነኝ፡፡»
«ውይይ... ከዚያ እዚህ ድረስ አንዴት መጣሽ?»
«ታሪኩ ብዙ ነው እታለም። ደግሞም ያሳዝናል።»
«እንዴት ትርፌ»
«በቃ ያሳዝናል፡፡»
«ከመማጣሽ ግን ምን ያህል ጊዜ ሆነሽ?»
«ወደ አስር ዓመት ሊሆነኝ ነው፡፡»
«ውይይ..» አለችና ሔዋን አሁንም ግን «ግን እንዴት መጣሽ?» ስትል
ጠየቀቻት
«ተጣጥዬ»
“ማለት?»
«የወሎ ድርቅ ሲባል ሰምተሽ ታውቂያለሽ?»
«አዎ»
«በድርቁ ዘመን እኔ ህጣን ልጅ ነብርኩ። የተወለድኩት ውጫሌ እሚባል ቦታ ነው።ያኔ በድርቁ ጊዜ በአገሩ ላይ የሚበላም የሚጠጣም ጠፋ። የአገሩ ሰው ሁሉ ተነቅሎ ተሰደደ።አባቴ በድርቁ ምክንያት ቀደም ብሎ ሞቶ ስለነበር እኔና እናቴም ሕዝቡ ሲሰደድ አብረን ተሰደድን
«ወደዚህ ወደ ሲዳሞ?»
«አይደለም ወደ ደሴ ወደሚባል ከተማ ነው።»
«ታዲያ እዚያ የሚበላና የሚጠጣ አገኛችሁ?»
«እየየ እታለም! ምን ይገኛል ብለሽ? ጣጣው ብዙ ነበር፡፡» አለችና ትርፌ አሁንም በትካዜ ባህር ውስጥ ገባች፡፡ ያን በልጅነት አዕምሮዋ የተቀረፀ የርሀብ
ሁኔታ የቻለችውን ያህል ለማስታወስ ትሞክር ጀመር፡፡ ትርፌ የዚያን ጊዜ ገና
የስድስት ወይም ሰባት ዓመት ህጻን ስለነበረች ሁሉን ነገር አታውቀውም እንጂ ሁኔታው እጅጉን አሳዛኝ ነበር፡፡
«አዎ፡ እንደ ሰው ጨክኗል! የወሎ ሰማያ፡፡ ከዝናብ ሰጪ ደመናዎች ጋር ላይታረቅ የተጣላ ይመስል ቁልጭ ጥርት እንዳላ ድፍን ሶስት ዓመታት አለፉ።ፀሐይና ጨረታ ለእንዴ እንኳ በደመና ውስጥ ብቅ ጥልቅ እያሉ የአየሁሽ ጨዋታ
ሳይጫወቱ በጠራው ሰማይ ላይ ተንቀለቀሉበት፡፡ በተለይ ፀሐይ በየቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት ሙሉ እየነደደች የወሎን ምድር ታነደውና ታቃጥለው ጀመር።ወንዞች ነጠፉ። ሳር ቅጠሉ ደረቀ። ዛፎች ወደ ጭራሮነት ተቀየሩ። ቢመጣ ንፋስ ቢነሳ አቧራ ብቻ ሆነ።
የወሎ ገበሬ የመጀመሪያውን የድርቅ ዓመት ቀድሞ የነበረውን ጥሪት ተጠቅሞ ሳይደናገጥ ተወጥቶት ነበር። የሁለተኛው ግን ወገቡን ሰበረው፡፡ ሶስተኛው ደግሞ ከሥሩ ነቀለው፡፡ እንኳን ለራሱ ለሰንጋ ፈረሱ የእህል ዓይነት ይመርጥ እንዳልነበረ ሁሉ እንኳን ያቀምሰው የሚቀምሰውም አጣ፡፡ በሰንጋ ፈረስ ይጋልብ የነበረ የወሎ መኳንንት፤ በሲናር በቅሎ ስትፈስ የነበረች የወሎ ወይዛዝርት ሁሉ እርካባቸው ወለቀ። ግላሳቸው ተጠቀለለ። በቅሎና ፈረሶቻቸው የአውሬና የአዕዋፍ
ሲሳይ ሆኑ። አጥንቶቻቸው ሜዳ ሙሉ ተረጩ። የረገመው ሳይታወቅ ወሎ ምዕዓት ወረደበት። የረሀብ እሳት ያቃጥለው ጀመር፡፡ በቸነፈር ተመታ።
በዚያን ጊዜ፣ በዚያን ዘመን፣ የወሎ ሕዝብ ምርጫው አንድ ብቻ ነበር፤ ስደት። አቅጣጫው ደግሞ ወደ ደሴ ከተማ፡፡ ይህም ምክንያት ነበረው፡፡ የወቅቱ
ንጉሥ ለጉብኝት ደሴ ከተማ እንደሚገቡ ተወርቶ ነበር፡፡ እሳቸው ደግሞ በሄዱበት ሁሉ ለልጆች ከረሜላ በመርጨታቸው ብቻ የቸርነት ዝናን ያተረፉ ነበሩና
የወሎ ርሃብተኛ ወደ «ቸሩ» ንጉስ በመሄድ የልመና እጁቹን ለመዘርጋት ዳር አስከዳር ተነጋግሮ ወደ ደሴ መጓዝ መትመም ጀመረ።
ከሰሜን አቅጣጫ የራያና የየጁ ሕዝብ በርሀብ የመነመነ ሰውነቱን
ብጥቅጣቂ ጨርቅ እየሸፈነ ሰንሰለት ሰርቶ ወደ ደሴ ሲግተለተል የአንባሰል ተራሮች ቁልቁል እየተመለከቱ ይታዘቡ ነበር፡፡ ከምዕራብና ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ የቦረና! የወረሂመኖ፣ የሳስታና የወገልጤና ሕዝብ ተነቅንቆ ወደ ደሴ ሲጓን በመሀል እየደከመው በገሪዶና በቦሩ ሜዳ ላይ ሲፈስ የጦሳ ተራራ መዓል ላይ ቆሞ ግራና ቀኝ እየተመለከተ ያለቅስ ነበር፡፡ ከምስራቅና ከደቡብ ምሥራቅ
ደግሞ የአውሳ የቃሎ፣ የእንቻሮና የከሚሴ ሕዝብ በበረሃ አለባበስ ዘይቤው ከወገብ በታች ሽርጥ መሳይ አገልድሞ ከወገቡ በላይ ሲያዩት ግጠው ግጠው የጣሉት
አጥንት መስሎ ወደ ደሴ ሲተምም የቦርከና ወንዝ «እናንተስ ወደ ንጉሳችሁ ሄዳችሁ፤ የእኔንስ ችግር ለአባይና ለተከዜ ማን ይንገርልኝ»
እያለ የሚያዝን ይመስል ነበር፡፡
በጋ ከክረምት የውሃ ፈረሰኛ ሲያጓራበት እንዳልነበረ ሁሉ ያኔ ግን ክው ብሎ ደርቋልና በውስጡ የነበሩ ቋጥኛች ጨው መስለው የፀሐይ ንዳድ እየፈነከታቸው ነበር፡፡
ያ ሁሉ የወሎ ርሀብተኛ በዚህ መልክ ተጉዞ ተጉዞ ደሴ ከተማ ሲደርስ ያሰበው አልሆነለትም። እንዲያውም ወደ መሀል ደሴ ከተማ መግባት እንኳ ሳይፈቀድለት ቀረ። የንጉሡ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶች በየመጣበት አቅጣጫ ተሰልፈው ጠበቁት። ከስሜን በኩል የመጣውን በሮቢት ገበያ ላይ፣ ከምዕራብ በኩል የመጣውን ከሰኞ ገበያ ላይ እንዲሁም ከምስራቅና ደቡብ ምስራቅ እቅጣጫ የመጣውን
ርሀብተኛ ሀረጎ አፋፍ ላይ በተሰራ የእንጨት አጥር ውስጥ እያስገቡ አጎሩት። በቀን አንዳንድ ዳቦ ለእያንዳንዱ ርሀብተኛ እንደ ውሻ ይጥሉለት ጀመር፡፡ እንዳይነቃነቅ ይጠብቁትም ጀመር።

👍9
ንጉሡ ደሴ ከተማ ገቡ። ከጦሳ ተራራ በስተ ደቡብ ምሥራቅ በኩል በምትገኝ ጎራ ላይ ተሰርቶ ፡ ከስፋቱና የገባ ቢገባበት በቃኝ የማይል ከመሆኑ የተነሳ
"አይጠየፍ" ተብሎ በሚታወቀው አዳራሽ ውስጥ በተመቻቸ መድረክ ላይ በተዘጋጀ
ዙፋናቸው ላይ ተሰየሙ። ቤተሰባቸውና የቅርብ ዘመዶቻቸው ግራና ቀኝ ከጎናቸውና ከኋላቸው ተኮለኮሉ፡፡ መሳፍንቶቻቸው ደግሞ እንደየማዕረጋቸው ቅደም ተከተል
ፊትለፊታቸው ተደረደሩ፡፡ የነቁ የበቁ አስተናጋጀች ነጠላቸውን አሸርጠው ያጋፍሩ ጀመር፡፡ እየተበላ እየተጠጣ ይሸለላል ይፎክር ጀመር፡ ምድር ቀውጢ ሆና የሚዘለልባትን ያህል እሷም ተንቀጠቀጠች፡፡
በዚህ ጊዜ ደሴ ከተማ ሁለት ተቃራኒ ትዕይንቶች በተመሳሳይ ሰዓት የሚከናወነባት አንድ መድረክ ሆነች። በአንድ በኩል አፍንጫ ከሚቆርጥ ቀይና አልጫ ወጥ በተጨማሪ ጮማ እየተቆረጠ ከጠጅ እስከ ውስኪ እየተጠጣና ሻምፓኝ እየተረጨ በፈንጠዚያ ጮቤ የሚረገጥባት ምድራዊ ገነት፡ በሌላ በኩል
ደግሞ የቀን ሀሩር እያቃጠለው የሌሊት ቁር እየጠበሰው እንደ ኩበት በበረት ውስጥ ታጎሮ በርሀብ አለንጋ በመገረፍ ላይ ካላ ሕዝብ የስቃይ ጩኸት የሚሰማባት ሲኦል!! ደሴ ከተማ አዘነች።ለሉሮ አመቺ ከመሆኗ የተነሳ እናት ከተማ ተብላ
ምትታወቀው ደሴ እወነትም በሕዝቧ የስቃይ ጩኸት የእናትነት ሆዷ ተምቦጫቦጨና እንደሰው አለቀሰች።
የአይጠፉ ትዕይንት አስተላለትም ሌላው የወቅቱ አስገራሚና እና አሳዛኝ ክስተት ነበር። ንጉሡ ባላምባራሱን ግራ አዝማች ግራዝማቹን ቀኝ አዝማች ቀኝ
አዝማቹን ፈታውራሪ ፊታውራሪውን ደጃዝማች ደጃዝማቹን ራስ ወዘተ እያሉ ከሾሙና ከሸለሙ በኋላ የሚያደርጉትን አጭር የመዝጊያ ንግግር መሀል የወሎን ረሃብ ጉዳይ አንስተው አንድ ነገር ሊሉ
እንደሚችሉ ተጠብቀው ነበር፡፡ እሳቸው ዐግን ወይ ትንፍሽ" ይልቁንም ያኔ በማይጨው ጦርነት ጊዜ ተሸንፈው ወደ አዲስ
ወቅት የወሎ ሕዝብ እኛን ለጥቃት አገርህን ለጠላት ሰጥተህ ወዴት? በማለት መንገድ ዘግቶ አላሳልፍ ብሏቸው የነበረ ከመሆኑም በላይ ጥሰው
ለማለፍ፡ ሲሞክሩ ተዋግቷቸው እንደነበረ በማስታወስ ሳይሆን አይቀርም ወሎን በደጉም
በክፉም ቀን እናውቀዋለን በማለት ተሳልቀውበት ነበር በማግስቱ ወደ
ዙፋን መአከላቸው አዲስ አበባ የተመለሱት።
ወሎ ተከዳ፡፡ አዎ ወሎ ምርቱን በጉድጓድ፣ ዱቄቱን በጎተራ ይከት
የነበረ በሩሀሩህነቱና በቸርነቱ ይታወቅ የነበረ ወሎ እባ መስጠት ክፋትና ተንኮል! ሸርና ምቀኝነት የማያውቀው በገርነቱና በየዋህነቱ ታውቆ "ወሎ መጀን"
እየተባለ ሲመጀንበት የሚኖር አገር ወሎ እንኳን አዛውንቱ እረኛው ትንቢት ኢማሞች እንዲሁም የቃሉ አብረው የሚኖሩበት የፍቅርና የመቻቻል አገር፤ አብሮ የመኖር ተምሳሌት ወሎ! ሰውም አምላኩም በከንድነት ከዱት፡፡ በመከራው ጊዜ ደራሽ ከጥቶ የሰው ልጅ እንደ ቅጠል ረገፈ፣ በርሀብሄ
ትርፌ ግን ይህን ሁሉ ሁኔታ በዝርዝር አታወቀውም፡፡ ግን ደግሞ የችግሩ ወላፈን ጠብሷት ነበርና የምታውቀውንና የምታስታውሰውን ያህል ለሔዋን
ለማጫወት ከስባ ከትካዜዋ ብንን አለች።
«ምን መሰለሽ እታለምዬ!» ስትል ቀገለች። «እኔና እናቴ ከሕዝቡ ጋር
መጥተን ደሴ እንደ ደረስን ሮቢት በሚባል የገበያ ቦታ ላይ በእንጨት በታጠረ ግቢ
ውስጥ እንድንገባ ተደረግን፡፡ ከዚያም ትንንሽ ዳቦ በቀን አንዴ ይታደለን ጀመር።
እናቴ ግን ያንኑ የድርሻዋን ዳቦ ብዚ ጊዜ ለኔ ነበር የምትስጠኝ! ለኔ በግል የምትደርሰኝን አታጠግብሽም በማለት፡፡» አለችና ትርፌ እንባዋ በዓይኗ ላይ
አቀረረ። ንግግሯን ግን ቀጠለች።
ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ እናቴ ደከመችና መላወስም እያቃታት ሄደ። አንድ ቀን በጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ እሷ ተኝታ ቀረችብኝ፡፡ በመሀል ዳቦ
የሚያድሉት ስዎች መጡና ላእሷም ለኔም ትቀበልልኝ ዘንድ ልቀስቅሳት ብሞክር አልሰማ አለችኝ። ሰውነቷን ገፋ ገፋ ሳደርጋት መላ ሰውነቷ አብሮ ይነቃነቅ ጀመር። በጩኸት ስጠራት የሰማ አንድ ሰው ጠጋ ብሎ እናቴን ካያት በኋላ በቃ ተያት
እሷ፣ ተገላግላለች አለኝ፡፡ ለካስ እናቴ ሞታ ኖሯል፡፡» አለችና ትርፌ
ድንገት «እማይዬ...» ብላ ጮኸች፡፡
ሔዋን በእስከ አሁኑ የትርፌ አተራረክና በዓይኗ እንባ ማቅረር ምክንየመት አንጀቷ እየተላወሰና በ እሷንም እንባ እንባ ሲላት እንደነበረ ሁሉ እንደገና ስትጮህ
ድንግጥ ብላ ከአልጋው ላይ ተስንፈጥራ ታነሳችና ወደ ትርፌ እየተራመደች
«ተይ ትርፍዬ» አለቻት። ነገር ግን በልመናዋ አልገፋችበትም ሔዋን እራሷ ነገር ጥናዋ ነውና በትርፌ እናት ላይ የደረሰው ሁሉ ልክ በእሷም እናት ላይ የደረሰ ያህል ተሰምቷት የትርፌን አንገት እንቅ እድርጋ ይዛ አብረው ይላቀሱ ጀመር።
ትንሽ ቆይተው ተላቀቁ፡፡ ሔዋን ከትርፌ አጠገብ ቁጭ ብላ
ልታፅናናት ሞከረች። ትርፌ ግን አንባዋን እያፈሰሰች ትረካዋን ቀጠለች፡፡
ከዚያ በኋላ እታለምዩ ምን ሆነልሽ መሰለሽ፡ ረፋዱ ላይ አንድ መኪና
መጣ። የእናቴን አስከሬን ጭነው ወሰዱት። እኔም ያለ እናት ቀረሁ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ከዚያ ግቢ አውጥተው ወሰዱኝ፡፡ የሄድከብት ቦታ ብዙ ህፃናቶች ነበሩ። ከእነሱ ተቀላቀልኩና እንጀራ በወጥ መብላት ጀመርኩ፡» አለችና ዓይኗንም አፍንጫዋንም ትጠራርግ ጀመር፡፡
«እዚያው አሳደጉሽ?» ስትል ሔዋን ጠየቀቻት።
«አንዳንድ ሰዎች ወደ ህጣናቱ እየመጡ ደስ ያላቸውን እየመረጡ ይወስዱ ነበር፡፡ እኔም በዚያ ቦታ ላይ ጥቂት እንደ ቆየሁ አንድ ቀን አንዲት ሴትዮ መጣችና ከልጆቹ መሀል ስትዘዋወር ቆይታ ወደኔ ጋ ስትደርስ “ይቺን ልጅ ልውሰዳት
በማለት ህጣናት ጠባቂዎቹን ጠየቀቻቸው። ፈቀዱላትና ወደ ቤቷ ወሰደችኝ፡፡ እሷ ዘንድ ለአምስት ዓመታት ቆየሁ፡፡»
«ከዚያስ?» ስትል ሔዋን አሁንም ጠየቀቻት። የትርፌ ታሪክና አኳኋን
እያሳዘናት ከአንገቷ ገደድ ብላ በሀዘን ስሜት ትመለከታታለች።
«ከዚያ በኋላ ደግሞ ተማሪዎች በጠበጡ። እየተገደሉም በየመንገዱ ተዘርረው መዋል ጀመሩ፡፡» አለች ትርፌ የወቅቱን የተማሪዎች የተቃውሞ
ንቅናቄና የተፈፀመባቸውን የጭካኔ ግድያ በራሷ አመለካከትና ግንዛቤ መጠን
ስትገልፀው። «ከተማሪዎች ጋር አንዳንድ ሰው እየተጃለፈ ይገደል ስለነበር አንድ ቀን የዚያች ታሳድገኝ የነበረችው ሴትዮ ባለቤትም ሞቶ ተገኘ፡፡ የዚያች ሴትዮ እህት እዚህ ዲላ ውስጥ ትኖር ኖሯል! ለለቅሶ መጥታ ደሴ ሰነበተች። ከአሳዳጊዬ ጋር ተመካክረው ኖሮ ስትመለስ ተነሽ እንሂድ ብላ እዚህ ዲላ ይዛኝ መጣችና የቤት ሰራተኛዋ አደረገችኝ፡፡» አለች ትርፌ አሁንም እንባ እየተናነቃት፡፡
«አይዞሽ ትርፌ» አለቻት ሔዋን የትርፌ ሁኔታና ታሪክ እያሳዘናት።
ትርፌ ትረካዋን ቀጠለች፡፡ በዚህ ሁኔታ ጥቂት ዓመታት ከቆየሁ በኋላ እኔም አደግሁ መሰለኝ፤ የሴትዮዋ ባል ባለፍኩ ባገደምኩ ቁጥር ይጎነትለኝ ጀመር፡፡
አንድ ቀን ደግሞ ሲተናነቀኝ ባለቤቱ ደረሰችና አየችው። ከዚያም እኔን አስወጥታ
በአንድ ወቴል ቤት በእንጀራ ጋጋሪነት አስቀጠረችኝ። ከጋሽ አስቻለውም ጋር የተዋወኩት እዚያው ሆቴል ውስጥ ስሰራ ነው። ጠባዩ ጥሩ ስለሆነ እወደው ነበር።
እሱም እኔን እንደ ገረድ ሳይቆጥረኝ በትትና ነበር የሚያነጋግረኝ፡፡ በዚያ ቤት ትንሽ
እንደሰራሁ አሁንም ከአሰሪዬ ጋር ሳልስማማ ቀረሁና ወጣሁ። ጋሽ አስቻለውን ስራ እንዲያስገባኝ ጠየኩት። እሺ እፈልግልሻለሁ ብሎ ዋል አደር ካለ በኋላ እኔ ጋር ብትሆኒስ አለኝ ምን ገዶኝ!» አልኩት፡፡ በቃ በተነጋገርን ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ ታጋሽ አስቻለለው ጋር መኖር ጀመርኩ፡፡

👍7❤1
ሔዋን ከንፈሯን መጠጥ አድርጋ ዲላ ውስጥ ምንም ዘመድ የለሽማ ስትል ጠየቀቻት፡፡
«ምንም አታለምዬ የኔ ዜመድ ጋሽ እስቻለው ብቻ ነው። ምናልባት
ከእንግዲህ ወዲያ እንቺ ትጨመሪልኝ እንደሆነ እንጂ … አለቻት።
ሔዋን፣ ድንገት የትርፌን አንገት እንቅ አድርጋ በመያዝ ጉንጯ ላይ ሳም አደረገቻትና ምንም አትጠራጠሪ ትርፍዬ " እህት እሆንሻለሁ።» አለቻት
ትርፌ አሳዛኝ ታሪኳን ስትተርክ ሔዋንም በአንክሮ ስታዳምጥ
ሳያውቁት ሰአቱ ሄዶ ኖራል ልክ ከቀኑ ስድስት ሰአት ያ ሰአት ደግሞ እንደ ወትሮ ቢሆን ሔዋን ከቤቷ መድረሸዋ" ትርፌ ደግሞ ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት ከስራ
ወጥቶ ወደ ቤተ ለሚመጣው አስቻለው የምሳ ዝግጅት ማገባደጅዋ ነበር የሰአቱን
መድረስ ሁለቱም ሲያውቁ ድንገት ስሜታቸውን ቀየሩ። ሔዋን ወደ ቤቷ ለመሄድ ትርፌ የምሳ ዝግጅት ለመጀመር ከተቀመጡበት ብድግ ብድግ አሉ ሔዋን ትርፌን ተሰናብታ ከቤት ልትወጣ ስትል ትርፈ አናገረቻት፡፡
«ዛሬ የኔን ታሪክ ሰምተሻል እታለም። ሌላ ጊዜ ደግሞ አንቺና ጋሼ አስቻለው እንዴት እንደተገናኛችሁና እንደተዋወቃችሁ ተራሽን ታወሪልኛለሽ እሺ አለቻት ፈገግ ብላ በአይኗ እየተከተለቻት።
«እስከ አሁን እስቼ አልገረሽም» አለቻት ሔዋንም ዞር ብላ ትርፌን በፈገግታ እያየቻት
«ምንም እታላምዬ እኔ የማውቀው እያየሁት ያላውን ነገር ብቻ ነው፤
አለችና አንቺና ጋሼ አስቻለው መቼ ይሆን የምትጋቡትን» ስትልም እንደ ቀልድ ጠየቀቻት፡፡
በዚያች ቅፅበት አስቻለው በር ላይ ደርሶ ኖሯል፡፡ ትርፌ ለሔዋን
ያቀረበችላትም ጥያቄ ሰምቷል። ሔዋን ከመናገሯ በፊት ፈጠን ቀልጠፍ ብሎ በቅርቡ ትርፌ! በጣም በቅርቡ፡፡ ግፋ ቢል ከሁለት ወይም ከሶስት ወራት በኋላ እያለ ወደ ቤት ገባ። ትርፌና ሔዋን ፍጹም ያላሰቡት አጋጣሚ ስለነበር ሁለቱም ድንግጥ ድንግጥ አሉ።
ሔዋን ወዲያው «እንዴ አስቹ! በአሁኑ ሰዓት እንዴት መጣህ?» አለችው የአንቺን ቤቴ ወስጥ መኖር ቀልቤ ነግሮኝ አላት እየቀለደ፡፡ ጠጋ አለና
እንደ ቆመች እንገቷን እቅፍ አድርጎ ከንፈሮቿን ሳም አደረጋቸው፡፡ በእጁ ዳጎስ ያለ
የካኪ ፖስታ ይዟል።
ለአስቻለው በዚያ ሰዓት መምጣት ሰበቡ ሔዋንን ከመሰረተ ትምህርት ስራ ያቋረጠ ለቅሶ ነው። ሟቿ የስራ ባልደረባው እናት ኖረዋል። ለስድስት ሠዓት ቀብር
መጥቶ ነው። ከዚያ በኋላ ላላው አጭር የስራ ሠዓት ሲል ዲላ ሆስፒታል ድረስ ላለመሄድ ወስኖ
«ምነው ሔዩ በር ላይ ቆምሽ?» ሲል ጠየቃት፡፡......
💫ይቀጥላል💫

👍4
#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
....“ጉድ! ጉድ!” አለ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ ሳይቀደሙ ለመቅደም። ቆመው እጅና እግራቸውን በእርጥብ እጃቸው ያባብሳሉ።
ባላምባራስ ዝም አሉ።
ወይዘሮ ጌጤነሽ ባላቸው፣ “ምንድርነው?” ሳይሏቸው በመቅረታቸው ቅር ተሰኙ። ወሬውን ለማውራት የነበራቸውን ጉጉት ስለአመከኑባቸው
ወሽመጣቸው ተቆረጠ። የባላቸውን ዝምታ አሰቡና ነገሩ ከነከናቸው።.
“ምንድርነውም አይሉ?” አሏቸው፣ የጎሪጥ እያይዋቸው።
“የትም አምሽተሽ መተሽ ደሞ ጉድ ትያለሽ?” አሉ፣ ባላምባራስ።
“ነገረኛ፣ ታሞ አይተኛ አሉ” አሉ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ፣ ድምፃቸውን
ዝቅ አድርገው።
“ምን አልሽ?”
“ምን እላለሁ ሳናግርዎ መልስ አይሰጡም ወይ ነው ያልሁት። ሌላ ምን እላለሁ?” አሉ፣ ራት ለመሥራት ምድጃ ላይ ድስት የጣደችውን የቤት አገልጋይ እያዩ።
“ሚሰማሽ ካገኘሽ ምላስሽ ረዥም ነው።”
“ኸርሶ አይበልጥ” አሉ፣ አሁንም ቀስ ብለው።
ባላምባራስ ቆጣ ብለው፣ “ምን አልሽ?” ካሉ በኋላ፣ ጉድ ከሰሙ
ስለ ሰነበቱ ጉዱን የመስማት ፍላጎት አደረባቸው። ቁጣቸውን ገታ አድርገው፣ “እና ምንድርነው ጉዱ?” አሉ፣ ለጠጥ ብለው እምብዛም ለወሬ የጓጉ እንዳይመስሉ።
ወይዘሮ ጌጤነሽ እንዳልሰማ ዝም አሉ፤ እንደ ማኩረፍ አድርጓቸዋል።
“ምንድርነው ጉዱ አልሁሽ እኮ” አሉ ባላምባራስ፣ ቆጣ ብለው።
ወይዘሮ ጌጤነሽ አሁንም ያልሰሙ መሰሉ።
“ሳናግርሽ መልስ 'ማሰጪ?” የባላምባራስ ቁጣ እየተጋጋለ ነው።
“ምን አሉኝ?” አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ። ፊታቸው ላይ ስስ ፈገግታ ይነበባል። ዛሬ አነስተኛ ቢሆንም ባላቸው ላይ ድል ተቀዳጅተዋል።
እነዚህን መሳይ ጥቃቅን ድሎች ናቸው አንዳንዴ ባላቸውን ያሸነፉ
እንዲመስላቸው የሚያደርጓቸው።
“ጉድ እያልሽ ገባሽ። ምንድርነው ብልሽ አለመጥሽ።” አሁንም
ድምፃቸው ገኗል፣ ባላምባራስ ሁነኝ።
“አልሰማሁ ሁኜ ነው” አሉ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ። የባላቸው ቁጣ
የሚገነፍልበትን አፍታ ስለሚያውቁ ያገኙትን ድል እያጣጣሙ፣
“የግራማች ልዥ ...” ሲሉ ጀመሩ።
“ግራማች?” ሲሉ አቋረጧቸው፣ ባላምባራስ። ወሬውን ለመስማት
ቸኩለዋል።
“ግራማች መንበር ናቸዋ።”
“ኸሷው ጋር ስታወሪ እንደቆየሽ አውቄያለሁ። ወልደልዑል ምንን
ሆነ?”
“ሴቷ ወለቴ።”
ጥላዬ፣ የሆነ ነገር እንዳለ ደመነፍሱ ነገረው። ነፍሱ ከዳችው። ጉዱን ለመስማት ቤት ውስጥ መግባት ፈልጎ፣ ወገቡ አልታዘዝ፣ ጉልበቱ አልንቀሳቀስ አለው። እንደምንም ብሎ ተነስቶ ውስጥ ገብቶ መደብ
ላይ ተቀመጠ።
ባላምባራስ በመገረም ተመለከቱት። እሳቸው ሳይተኙ ቤት ውስጥ ስለማይገባ፣ ዐይኑን ካዩት ከርመዋል። ሆዳቸው ተገላበጠ።
“እና ምንን ሆነች?” አሉ፣ መባባታቸው እንዳይታወቅባቸው
እየታገሉ።
ወይዘሮ ጌጤነሽ ከመናገር ተቆጠቡ። ጥላዬን ሰረቅ አድረገው አዩት።እሱ የሚሉትን ለመስማት ቢጓጓም ጎንበስ ብሎ መሬቱን በስንጥር መጫጫር ጀመረ።
“ዛሬ ምንን ነክቶሻል? ምንን ሆነች ስልሽ መልስ ማሰጪ?”
“በያ ሰሞን ንዳድ ይዟቸው ኸነሱ ዘንድ ተኝተው የነበሩት ለካስ
ንጉሡ ኑረዋል...”
“ንጉሠ?”
“አዎ።”
“አጤ በካፋ?”
“እሳቸው። ሌላ ንጉሥ አለ?”
“ምንድርነው ምታወሪው?” አሉ ባላምባራስ፣ የሚስታቸውን ትንኮሳ
ችላ ብለው።
መንን
“አጤ በካፋ ራሳቸው። ወለቴ አስታማቸው ስታበቃ ዛሬ ሰዎች
ኸጥሎሽ ጋር ሰደዱ።”
“ሊያገቧት?”
“ኋላ?”
ጥላዬ ዱብ ዕዳ ሆነበት፣ ድንጋጤ ሰውነቱን አብረከረከው። ተነስቶ
ሊወጣ ፈልጎ ወሬ ለመስማት ተቀመጠ።
“ሰው ለማንጓጠጥ ማን ብሎሽ። ወረኛ! ደሞ ማታመጪው የለ” አሉ
ባላምባራስ፣ ተደናግጠዋል፣ ንዴትም ተናንቋቸዋል።
“እንዴት በሉ? ምን ያልሆነ አምጥቸ አውቃለሁ? ኸመሽ አገር ሁሉ ሚያወራው እኼንኑ ማዶል? የጣ ፈንታ ነገር ይገርማል።”
“ውነት ነው፤ ዕጣ ፈንታ ነው” አለ ጥላዬ፣ የሞት ሞቱን። ሰውነቱ
እየራደ ነው። ለራሱ፣ እኔ ዕድል ፈንታየ ሁኖ ያልታደልሁ ሁኘ
የወፍታው እኼን አሰማኝ ብሎ በዐይኑ ውሃ ሞላ። እንባው እንዳይታይበት እደጅ ሲወጣ፣ አባቱ በዐይናቸው ተከተሉት።
“ያቺ አያትየው ኸደብተሮቹ ነው ውሎዋ። ኸተኙበት ቀባብታቸው
ይሆናል ይላል ድፍን ቋራ” አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ፣ አገልጋይዋ ራት
እንድታቀርብ በእጃቸው ምልክት እይሰጡ።
“ድፍን ቋራ ኸምኔው ሰምቶ ነው እኼን ሁሉ ሚለው? አንቺና
ጓደኞችሽ ጓሮ ሁናችሁ ያቦካችሁት ነው እንጂ። ለነገሩ ልዥቱ
ምንም አይወጣላት። ደማም... ቆፍጣና... ይገባታል፤ ይገባታል ::
ሚገባትን ነው ያገኘች። እኔ ለተክለሃይማኖት ተዋጋህ እየተባልሁ ስወቀስ የተክለሃይማኖትን ወንድም በካፋን አገባች?” አሉ ባላምባራስ፣
በመገረም ራሳቸውን እየነቀነቁ።
አገባች! እርምዎን ያውጡ እንግዲህ! በርሶው አጓጉል ጠባይ ነው እኼ ሁሉ የመጣው። እርስዎንስ ይበልዎ፣ ልጄን ጎዱብኝ እንጂ አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ፤ ለራሳቸው። ጮክ ብለው ሊናገሩ ፈለጉና በማታ ኸሳቸው ጋር ምን አጫጫኸኝ ብለው፣ “ኸቤታቸው ንግርት አለ ይባላል። ዘመዳቸው የሆነ ሰው ኸወለቴ ግንባር ጠሐይ ስትወጣ አይቷል” አሉ።
ባላምባራስ መልስ አልሰጧቸውም። ቁጭት ላይ ናቸው። ልዥህን ለልዤ ስባባል ቆይቶ፣ በትንሽ ነገር ኸጥብቅ ወዳጄ ተቀያይሜ፣ አሁን
እኼው ሌላ...ያውም ንጉሥ ወሰዳት። እንግዲህ ኸንጉሥ መንጋጋ አላስጥላት! ያቺ ቀን እንዴት ያለች የተረገመች ናት አሉ፣ ግራዝማች መንበርን የተቀየሙበትን ቀን አስታውሰው።
የጊዮርጊስ ማኅበር ነው። ግራዝማች መንበር ቤት ይበላል፤ ይጠጣል። ጨዋታው ደምቆ፣ እንደወትሮው ስለ ጦር ሜዳ ጀግንነት ይወሳል። ባላምባራስ ሁነኝ ራሳቸውን እንደ ጀግና ቢቆጥሩም፣ ስለ ጦር ሜዳ
ሲወራ አይወዱም።ከዚህ በፊት ሰድበውት የሚያውቁት ደብተራ ሞቅ ብሎታል። “አሁን በወፍታው ኸጦር ሜዳ ቋንጃውን የተመታ ዠግና ይባላል?” ብሎ በሳቅ
ተንተከተከ።
ማንም አልሳቀ። ሁሉም አንገቱን ደፋ። ሳቅና ቁም ነገር የሰፈነበት
ስብስብ ወደ መሸማቀቅ ተለወጠ።
ደብተራው የሳቀለት ሲጠፋ፣ “እኛ ባገራችን ምናቀው ሰው ቋንጃውን
ሚመታው ሲሸሽ ነው” አለ፣ የፌዝ ሳቅ እየሳቀ።
ባላምባራስ ከዓመታት በፊት ቋንጃቸውን ተመትተው ያነክሳሉና
እሳቸውን ሊነካ መሆኑን አውቀው ከተቀመጡበት ተነሥተው
ከዘራቸውን እየወዘወዙ፣ “አንት መተተኛ ደብተራ። እኔ ሁነኝ በንዳንተ ያለ ድግምተኛ አልሽረደድም። የት አባህ ጦር ሜዳ ውለህ ታውቃለህና
ስለ ጦር ሜዳ ታወራለህ? ጋን እያሸተትህ ኸድግስ ድግስ ዙር እንጂ።
ጥፋተኛው አንተ ሳትሆን አንተን ኸሰው መኻል የቀላቀለህ ነው” ብለው ከዘራቸውን ግራዝማች መንበር ላይ እየወዘወዙ፣ “መንበር አሰደብኸኝ ...
ያውም በዝህ በድውይ። ግድ የለም። እንዲህ ኻሰደብኸኝ ወዲያ እመቃብሬ እንዳትቆም... ኸዚህ ያላችሁ ሁሉ ቃሌን ቃል እንድትሉ”
ብለው እያነከሱ ወጡ።
ከዚያን ቀን ጀምሮ የግራዝማችና የባላምባራስ የረጅም ዘመን ጓደኝነት አከተመ፣ አብሮም የጥላዬና የወለተጊዮርጊስ ዕጮኛነት። ባላምባራስ፣
“በቤቱ አሰደበኝ” ብለው ቂም ያዙ። ግራዝማች፣ “ደብተራው ለሰደበው እኔ ምን አረግሁ?” ብለው ቅር ተሰኙ። አስታራቂ መሃከላቸው ቢገባ ባላምባራስ፣ “ሙቼ ነው ቁሜ ኸሱ ጋር ምታረቅ” አሉ። “ልዥህን
ለልጄ” የተባባሉት ጓደኛሞች ተቀያየሙ።
ግራዝማች መንበር፣ ሁነኝ ምንም ቢሆን የረጅም ጊዜ ወዳጄ ነውና
አንድ ቀን እንታረቅ ይሆናል እያሉ የወለተጊዮርጊስን እጅ ለጠየቀ ሁሉ አይሆንም እያሉ መለሱ።

👍15
ባላምባራስ ሁነኝ ወለተጊዮርጊስን ለልጃቸው
እየተመኙ ሳይጠይቁ ዓመታት አለፉ። ዛሬ ወለተጊዮርጊስ በንጉሥ መታጨቷን ሲሰሙ እንባ እንባ አላቸው። “ጥላዬን ልብ ታስገዛልኝ ነበር” ብለው በራሳቸው ግትርነት ተበሳጩ።
ጥላዬ፣ የወለተጊዮርጊስ ሶስት ዓመት ታላቅ ነው። ዐራት ዓመት
እንዳለፈው፣ ወፍታ ጊዮርጊስ ውስጥ መምሬ ጀምበሬ ዘንድ ቄስ
ትምህርት ቤት ገብቶ ዳዊት ደገመ። ብሎም ሌላ አስተማሪ ዘንድ ቅኔ እስከ ሥላሤ ተማረ።
ዕድሜው እየጨመረ ሲመጣ፣ አባቱና ግራዝማች መንበር “ልዥህን ለልዤ” መባባላቸውን ከሰፈር ልጆች ሰማ። ያንን ወሬ ከሰማበት ዕለት ጀምሮ ለወለተጊዮርጊስ በውል ያላወቀው ስሜት አደረበት። እያደገ
ሲመጣ፣ በእርግጥም በወለተጊዮርጊስ ፍቅር እንደተነደፈ ገባው።
ጠዋትና ማታ የሚያስበው ስለእሷ ሆነ። ጓደኞቹ ሌላ ቦታ ሄደው ቅኔ ሲማሩ፣ እሱ ከወለተጊዮርጊስ መራቅ ስላልፈለገ ወፍታ ጊዮርጊስ መጋቢ አምሳሉ ዘንድ መማር ጀመረ።
ሆኖም ልቡ ቅኔ ላይ ሳይሆን ሥዕል ላይ በመሆኑ ብዙውን ጊዜ
በስንጥር መሬት ላይ ወለተጊዮርጊስን አስመስሎ ይሥላል። አንድ ቀን
ታዲያ ኃይለኛ ንፋስ ነፍሶ፣ አሸዋውን አንስቶ ምስሉን ሸፈነበት፤ ደነገጠ። እንደ መጥፎ ገድ ምልክት አድርጎ ቆጠረው።
የእሱና የወለተጊዮርጊስ
ነገር እንደሳለው ምስል ተዳፍኖ የሚቀር ሆኖ ተሰማው።
ለቀናት ተጨነቀ። ከዚያን ቀን በኋላ፣ ምንም እንኳን የለመደበትን መሬት ላይ መሣል እርግፍ አድርጎ ባይተወውም፣ አብሮት ያደገውን ጥልቅ የሥዕል ፍቅር ለማርካት በቤታቸው የጓሮ ግድግዳ ላይ መሣል ጀመረ። ግድግዳውን
እበት ይቀባዋል፣ በእናቱ ወንፊት አመድ ይነፋና፣ በውሃ ለቁጦ
ያለብሰዋል። በማግስቱ፣ ሲደርቅለት፣ በእናቱ ቀይ ወይንም አርንጓዴ አክርማ እንስሳት፣ ተክሎች፣ ቤቶች ወይንም ሰዎች ይሥላል። አባቱ ያንን የሁለት ቀን ድካም ጭቃ ያስመርጉበትና እሱ ላይ የቁጣ ናዳ ያወርዳሉ። እሱ ግን ተስፋ አይቆርጥም፤ መልሶ መላልሶ ይቀባል፤ ይሥላል።
ከወለተጊዮርጊስ ፍቅር በተጨማሪ መላ አካላቱን ሰንጎ የያዘውን
የሥዕል ፍቅር ሲወጣ፣ መንፈሱ ይታደሳል። የአባቱን ቁጣ፣ የነገር
ጉንተላና የወለተጊዮርጊስን ፍቅር ረስቶ፣ የሠራ አካላቱ ሥዕሉ ላይ ብቻ ይሆናል፤ ሥዕል የሕይወቱ ምሰሶ የሆነ ይመስለዋል። ለሚቆይበትም አፍታ ዓለም የምትሽከረከረው እዛው ቦታ ላይ ብቻ ሆኖ ይሰማዋል።
የስሜቱ ግለት የእጁን ፍጥነት ይጨምርለታል። አክርማውን ከወዲያ ወዲህ፣ ከላይ ወደታች ሲያመላልሰው ይሰብረዋል። አጎንብሶ ከመሬት ላይ ሌላ ሲያነሳ፣ እጁ እንጂ ልቦናው ማስተዋል ያቅተዋል። ሥራውን
ራቅ ብሎ ይመለከተዋል፤ አልረካ ይላል። ያበጀዋል፤ ያበጃጀዋል፤
ያሽሞነሙነዋል። የመንደር ልጆች ታምር እንዳዩ ሁሉ የሚሠራውን
ፈዘው ሲመለከቱ፣ ልብ ማለት እንኳን ይሳነዋል።
ባላምባራስ ሁነኝ ግን ለአንድ ልጃቸው ሁለት ነገር እየተመኙ
አሳደጉት - ወለተጊዮርጊስን አግብቶ ዘር እንዲተውና ለአንዱ ባላባት አድሮ ተዋግቶ “ተደፈረ” የሚሉትን ክብራቸውን እንዲያስመልስ- እግረ
መንገዱንም ስለጦር ሜዳ ጀግንነት እየሰማ ያደገው ልጃቸው፣ የጀግንነት ድርጊት ፈጽሞ ጀግና ተብሎ እንዲጠራ።
ይህንን ምኞታቸውን ጥላዬ
ጭንቅላት ውስጥ ሊከቱ ደጋግመው ቢሞክሩ አልሆነላቸውም።
“ጥላዬ እንዳው ምናለ ላንዱ ታላቅ ባላባት ብታድር? ወታደርነት
ክቡር ነው። ደሞ ለአለቃህ ስትዋጋ ለአገርህ እንደተዋጋህ ቁጠረው” ይሉታል፣ አዘውትረው።
ጥላዬ መልስ አይሰጣቸውም። እሳቸውም ውትድርናውን
እንደማይፈልገው ያውቃሉ። “እና ምንን ሁነህ መኖር ነው ምትፈልግ?” ይሉታል።
አንድ ቀን፣ “እንዳው አንተ ጥላዬ እንዲሁ መልክህን አሳምረህ ዱላ
ይዘህ ስትንጎራደድ፣ ቤት ስትገባም ግድግዳ ስታበላሽ መኖር ነው ምትፈልገው?” ሲሉ ጠየቁት።
“አባባ ግድግዳ እንዳላበላሽ ብራና ላይ ልሣል ደብሬንም ላገልግልበት፣ ብልዎ ተቆጡ። እኔ ደሞ ያለሱ ሚታየኝ የለ። እሱን ማረግ ባልችል ስንኳ በቅኔው እገፋለሁ እንጂ ለማንም ባላባት አላድርም።”
“አንተ እንዲህ አድርጌ አሳድጌህ፣ ግዝየ ጥሎኝ የማንም መደዴ
ደብተራ ማላገጫ ስሆን፣ አንተ አባቴ ክብሩ ተነካ ብለህ እንኳ ዘራፍ ማትል? ስወድቅ ታነሳኛለህ፣ ያባትነት ክብሬን ታስጠብቀልኛለህ፣ ጥላ
ከለላ ትሆነኛለህ ብየ ያሳደግሁህ ዛዲያ ምን ታረግልኝ ኑሯል?
ሰዉ ለአጤ ተክለሃይማኖት ስለተዋጋሁ፣ 'የአባቱን የአጤ አድያም ሰገድ ኢያሱን አልጋ ለመውረስ ብሎ ላስገደለ ለርጉም ተክለሃይማኖት አደረ' እያለ ሲያማኝ፣ ካህናቱም ቢሆኑ፣ ለዝኸ ለርጉም ንጉሥ አባቱን አስገዳይ የተገዛ ርጉም ይሁን' እያሉ ሲኮንኑ... ያ ጠውላጋ ደብተራ
እንኳ ባቅሙ ቀን ጥሎኝ አይቶ መዘባበቻ ሲያረገኝ እንዳው ትንሽም አይቆረቁርህ? ልዥነትህ ኸምኑ ላይ ነው? በል እስቲ ንገረኝ? አሁን ብራና ኸኔ ክብር በልጦብህ ነው ብራና ብራና ምትለው? መቃብሬ
ላይ ቁመህ ነው አንተ ብራና በጅህ ምትነካው” አሉት፣ ምርር ብለው።
ጥላዬ ደነገጠ። “አባባ የርሶን ክብር እንዳስመልስ ኑሯል እንዴ
ለታላቅ ባላባት እደር ሚሉኝ የነበረው? እኔኮ ለኔ አስበው መስሎኝ።
የወፍታው በሚያውቀው እኔ ኸብራና ሌላ አልፈልግም። ለማንም ባላባት ማደርም አልፈልግም። ብራናን ሚከለክለኝ እዝጊሃር እንጂ ሌላ ማንም አዶለም።”
“አንት ተላላ። አለማወቅህ ... ስምና ክብር ታተርፋለህ ብየ እንጂ። ደሞ ራስህን ስታስከብር... ዥግና ስትባል... የሱ አባት ተብዬ መጠራቴ ቀረ?” ብለው እንባ ተናነቃቸው። “አንድ ምወድህ ልጄ ... አየየ... እንዲህ ኻባትህ ቃል ወጥተህ... አፈንግጠህ ትዘልቀዋለህ? ደሞ ኸዛሬ
ወዲያ ግድግዳዬን ስታበላሽ እንዳላይህ።”
ምወድህ ልዤ ? አለ፣ ጥላዬ ለራሱ። እንዴት ነው ሚወዱኝ እኔ
ምወደውን እየነሱ አባባ እየወደዱ መከልከልማ የለም፡፡ ቢወዱኝ ኑሮ
ኸግራማች በታረቁና ወለቴን ባገባሁ። ያነን ደማም ፊቷን ሳያረዥ፡እንደርስዎ ፊት ሳይሸበሸብ በሣልሁ። ቢወዱኝ ኑሮ ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ ያየኋቸውን የመላዕክት ሥዕሎች በሣልሁ። የገዛ አባቴ ሁነው
ስለምን ተስፋቢስ ያረጉኛል? ልቤ እርሶ ኸተመኙልኝ ሌላ ስለፈለገ?
እርሶ እንዳሉኝማ አልሆንም። እኔ ለባላባት ስላደርሁ እርሶ ክብር
ሊያገኙ? የወለቴ ነገር አንዠቴን ሚበላው አንሶ፣ ሥዕል ከልክለው
ወታደር ሁን ይሉኛል? እርሶ ለኔ ብለው ሳይሆን ለራስዎ ክብር ሲሉ
ነው ለባላባት እደር ሚሉኝ እያለ አወጣ አወረደና ለሳቸው፣ “ቢወዱኝ ኑሮ ምፈልገውን አይከለክለኝም ነበር” አላቸው።
ባላምባራስ ስሜታቸው ተነካ። እንደገዛ ነፍሳቸው የሚወዱትን አንድ ልጃቸውን ተቀየሙት።
እሱ ጠላቸው። “አባቱን ላስገደለ ለርጉም ተክለሃይማኖት ያደረ
ርጉም ነው” እየተባሉ ሲታሙ ያዘነላቸውን ያህል፣ ያን ቀን አዘነባቸው፤ ዓመጸባቸው። የሚሉትን ሊፈጽም፣ ሊያነጋግራቸው ቀርቶ፣ በዐይኑ
ሊያያቸው ቸገረው።....
✨ይቀጥላል✨

👍10
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...«ምነው ሔዩ በር ላይ ቆምሽ?» ሲል ጠየቃት።
«ብዙ ስለቆየሁ ወደ ቤቴ ልሄድ ተነስቼ ነው፡፡ አለችው በእጆቿ ደረቱን እየደባበሰችና ቀና ብላ ዓይኖቹን በዓይኖቿ እየተመለከተች፡፡
«ለሔዩ ምን አደረግሽላት ትርፌ?» አለ እስቻለው ወደ ትርፌ ዞር ብሎ፡፡
«ምንም ጋሼ አስቻለው፤ ወሬ ብቻ»
«ምሳ በልተሽ ሂጂያ ሔዩ!!»
«በፍጹም አስቹ! እት አበባ ስራ መምጫዋ ስለሆነ ብሄድ ይሻላል»
«ስሞት»
«አይሆንም አስቹ በአጋጣሚ መገኛኘታችን በራሱ በቂ ነው፡፡»
አስቻለው አሁንም ከንፈሮቿን ሳም ካደረገ በኃላ «በይ እሺ ከቸኮልሽ»
ሂጂ አለና እስከ ውጭ በር ሸኝቶ ተሰናብቷት ወደ ቤቱ ተመልሶ ገባ፡፡
አልጋው ላይ ቁጭ አለና ያነ በእጁ ይዞት የነበረውን ካኪ ፖስታ በጥድፊያ ይከፍት ጀመር፡፡ ከአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ከዶክተር ደጀኔ አድማሱ የተላክለት ደብዳቤ ነው። አስቻለው ጫማውን አውልቆ አልጋው ላይ ወጣና ትራሶቹን አነባብሮ ከአንገቱ ቀና ብሎ በጀርባው ጋለል በማለት ደብዳቤውን ማንበብ ጀመረ።
«የምወድህና የማከብርህ እንዲሁም የምናፍቅህ ውድ ወንድሜ ነርስ አስቻለው ፍስሃ፥ ከቶ ለጤናህ እንደምን አለህ? ፈጣሪ አምላክ ይመስገን እኔ በጣም ደህና ነኝ።
«የምወድህ አስቻለው፡ የመኪና አደጋ ደርሶብህ እንደነበር አውቃለሁ፡፡ አደጋው ቀደረሰ
በሶስተኛ ቀን በተኛህበት ሆስፒታል ተገኝቼ ልጠይቅህም ሞክሪ ነበር። በወቅቱ ራስህን አታውቅም ነበርና፡ እኔ ደግሞ የበረራ ፕርግራሜ በማግስቱ
ስለነበር ሆዴ እያዘነ ትቼህ ሄጃለሁ። ይሁንና የኢትዮጵያ አየር ክልል ወጥቼ፣ በሱዳንና በግብጽ እንዲሁም በሜድትራኒያን ባህር፡ ከዚያም በአውሮጳ ሰማይ ላይ
ተንሳፍፌ በበረራ ላይ በነበርኩበት ጊዜ ሁሉ ስለ አንተ እያለቀስኩ ነበር፡፡ አሜሪካም ከገባሁ በኋላ የአንተ ነገር ከእዕምርዩ አልወጣ ብሎኝ ለቀናት ያህል ተሰቃይቻለሁ። የኋላ ኋላ ግን ከአደጋው ሙሉ በሙሉ አገግመህ ወደ ስራህ የመመለስህን ዜና
ስስማ አምላኬን ከልብ አመስግኛለሁ። ወደፊትም ፈጣሪህ ከሁሉም ነገር
እንዲጠብቅህ እፀልያለሁ።
«ውድ ወንድሜ አስቻለሁ። መቸም ደብዳቤዬ እንደ ደረሰህ መጀመሪያ የሚታሰብህ ምን ዓይነት ኑሮ እየኖርኩ ስለመሆኔ የምገልጽልህ ነገር ይመስለኛል።
መሰደዴ የመከፋት ውጤት ነውና አሜሪካ ውስጥ ምን ያሆሎ እንደደላኝ ወይም እንዳልደላኝ ለማውቅ ትጓጓ ይሆናል። በኔ በኩል 'ደላኝ' ወይም 'ከፋኝ'ብዬ
ልነግርህ አልፈልግም፡፡ አኗኗሬን ልግለጽልህና ምደባውን ራስህ ፈርጀው፡፡
«የአሜሪካ ውስጥ በእየዕለቱ ያገኘሁትን ሁሉ ስሰራ እውላለሁ። ስራዬን ሳጠናቅቅ ለስራው የተመደበው ገንዘብ በሙሉ ይከፈለኛል። ዛሬ አንዱ ጋር ስስራ
ውዩ ነገ ወደ ሌላው ብሄድ መልቂያ አልጠየቅም፡፡ በስራ ዘመቻ ሰበብ የጉልበቴን
ዋጋ ማንም አይነጥቀኝም፡፡ በስላም ስሰራ ውዬ የሰላም እንቅልፍ እተኛለሁ። «እገሌ
ስለኔ ምን ይላል? ነገ ምን ያደርገኝ ወይም ያስደርገኝ ይሆን? ብዬ አልጨነቅም፡፡
በሰራሁት መጠን ትክክለኛ ክፍያ ስለምቀበል የገንዘብ ችግር አይገባኝም። የልደታ ዕለት ደሞዝ ወስጄ እስከ ቀጣዩ ልደታ ቀቃኝ አልበቃኝ ብዬ ስጨነቅ አልሰነብትም፡፡
እለታዊ አዋዋሌና የሆዴ ነገር ይህን ይመስላል፡፡ የመንፈስህስ ነገር ካልከኝ ግን ጣጣው ብዙ ነው። በመሰረቱ ማንም ሰው በሀገሩ ውስጥ ተከፍቶ በተሰደደበት አገር ደስ ይለዋል ማለት ዘበት ነው ምናልባት 'ከመሞት መሰንበት' ለሚለው
የሃገራችን ብሂል ምላሽ ይሆን እንደሆን እንጂ። ስደት ደግሞ
የመንፈስ ርሃብ ውጤት ነው።
መንፈሱ የተራበ ሰው የቱንም ያህል የጣፈጠና የበዛ ምግበ ቢበላ ሁልጌዜም ውስጡ ባዶ ነው እኔም እንዲሁ ባዶዬን እኖራለሁ።
«አሜሪካ ደግሞ የጭፍን ፖለቲካል ሰለባ ሆነውለተሰደዱባት ሁሉ የባሰ የመንፈስ ረሃብ የምትለቅ ሃገር ነች፡፡ የዚች ደብዳቢየም ዋንኛ ይዘት በዚሁ ዙሪያ የሚያጠነጥን ነውና በፅሞና አንብብልኝ። በዚያው ውስጤንም ትረዳዋለህ።
«አየህ አስቻለው አሜሪካኖች ወደ ስልጣን ሲወጡ መንገዳቸው በህዝብ መሀል ነው። ለስልጣን የሚደረግ ትልቅ ጦርነት አለ። መሳሪያው ግን መድፍና
መትረየስ አይደለም የጠራና የነጠረ ሀሳብ' በሩቅ የሚታይ ራዕይ ከራእዕዩ ጫፍ
የሚደርስ የፖለቲካ አመለካከትና አሰራር ቅደም ተከተል ወይም ፕሮግራዎ" እንጂ።ባሩዳቸው የሰላ ምላስና ርቱዕ አንደበት ነው የጦርነቱ ቦታ ክብ ጠረጴዛ ነው።
የውጊያ ወረዳዎች እልፍ አእላፍን የሚይዙ ሰፋፊ አዳራሾች ናቸው
በዚህ የትግል ሜዳ አሸንፎ ስልጣን ላይ የወጣ ሁሉ ስራውን የሚያከናውነው በሕዝብ
ይሁንታ በፀደቀ ህገ መንግስት መሰረት ነው። ማንም የስልጣን ክልሉን አልፎ ሲገኝ ያለቀጠሮ በሕዝብ ጩህት ስልጣን ይለቃል
ስለሆነም አሜሪካ ባለስልጣን
ሕዝብን ፈርቶ የሚኖርባት እንጂ ሕዝብ ባለ ስልጣንን እየፈራ የሚኖርባት ሀገር አይደለችም።
እንዴት ደ.....ስ የምትል አገር መሰለችህ!!
«የምወድህ አስቻለው፡- እዚህ አሜሪካ ውስጥ ባገኘሁት ብርሃን የሀገሪን ጨለማ አሻግሬ ሳየው አቤት ማስፈራራቱ! አቤት ማስጠላቱ! አቤት ማስጨነቁ!
የመንፈስ ርሀብ የሚለቅብኝም ይህ ሁኔታ ነው። በእውነት ያንቀጠቅጣል! በእውነት ይዘገንናል! በእውነት ያንገፈግፋል! የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት እንቅልፍ እያሳጣ እኔንም ሁል ጊዜ ያስለቅሰኛል።
የሀገራችን አምባገነኖች ከየትም ይነሱ፤ በየትም ይምጡ፣ መቸም
ይድረሱ፥ ነገር ግን አንድ የጋራ መለያ ባህሪ አላቸው፤ ይህም በፊትለፊት በህዝባቸው ስም እየማሉ በስውር ግን የገዛ ሕዝባቸውን በጠላትነት የመፈረጅ
መስሪነታቸው ነው። መሠረታዊ ምክንያቱ ደግሞ ስልጣን ላይ የሚወጡት በሀይል እንጂ የህዝብ ይሁንታ አግኝተው ስላልሆነ ነው፡፡ ግን ደግሞ ስልጣኑን ይፈልጉታል። በድሀ ሀገር ስልጣን የሀብት ምንጭ ነውና ከያዙትም በኋላ ሙጭኝ ይሉበታል። ይቆዩበት ዘንድ ጠላታችን የሚሉትን ሕዝብ ያተረማምሱታል።ቢያንስ በሁለት እንዳንዴም ከዚያ በላይ በሆነ አመዳደብ ይከፋፍሉታል። አንዱን
ወገን ወዳጅ አድርገው ሌላውን በጠላትነት ይፈርጁታል። የጠሉትን ወገን የተለያየ
ስም እየለጠፉ ይበልጥ እንዲጠላ አውርተው ያስወሩበታል። በዚህም የጠላታቸውን እርስ በእርስ ጠላትነት ይፈጥራሉ፡፡ ሕዝብና ሕገብ የጎሪጥ እንዲተያይ ያደርጉና
ጥላቻና ጥርጣሬን ያነግሱበታል። በዚህ ጊዜ የራሳቸውን የስልጣን ኮርቻ ያደላድላሉ፣ የችሎታ ሳይሆን የብልጠት አካሄድ
በመነዘረቱ የግጭቶች ሁሉ! የጦርነቶች ሁሉ፣የቅራኔዎች ሁሉ
መሠረታዊ ምክንያት ኢኮኖሚ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ጥቅም!! ፖለቲካ የሚባላው ነገር የዚሁ ፍላጎት ልጣጭ ነው። በተላይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ድሀ አገሮች አምባገነኖች ከስልጣን ላይ የሚወጡት ይህንኑ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለመቆጣጠር ነው።ሁሉን ነገር በመዳፋቸው ውስጥ ማስገባት የአምባገነኖች ልዩ ባህሪ ነውና፡፡
በዚህ አያበቁም፡ የስልጣን ጊዜያቸው እስከ መቼ ድረስ መሆኑን በውል ስለማያቁት 'ክፉ ቀን' ቢመጣ እያሉ በተለያየ መንገድ መዘጋጀት ይጀምራሉ

ልጆቻቸውን ያበሏቸውን ብርቱካን እያስመሰሉ ካሳደጉ በኋላ ወደ ምዕራባውያን ሀገሮች እየላኩ ምርጥና ድንቅ በሆኑ የትምህርት ተቋማት በማስተማር በሙያ ክህሎት ያስታጥቃሉ። የሃገር አንጡራ ሃብት እየሟጠጡ በመዝረፍ በራሳቸውና በልጆቻቸው ስም በውጭ ባንኮች ያስቀምጣሉ።
«የምወድህ እስቻለው፡ እውነት እልሀለሁ! በዚህ ዙሪያ በአሰብኩና
በሰላሰልኩ ቁጥር በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ተጉዞ ተጉዞ የሚመጣ ታላቅ አገራዊ አደጋ ወለል ብሎ ይታየኛል። በሀገር ሀብትና ንብረት የተለያየ ሙያ
በመካን ላይ ያሉት የጥቂት የገዥ መደብና የቅርብ ወገናቻቸው ልጆች የተካኑትን ሙያና በውጭ ባንኮች የተቀመጠላቸውን ገንዘብ በዚያው ይዘውት ቢቀሩ ሀገራዊ
ኪሳራው የትየለሌ። ምናልባት ይዘውኑት ወደ ሀገር ቢመለሱም አደጋው ከዚያ የሚያንስና እንዲያውም የከፋ የሚሆንበት ሁኔታም ሊኖር እንደሚችል እንዳንዴ በአእምሮዬ ወስጥ ድቅን እያለ ያሳስበኛል።
መቸም አባቱ ለበደለ ልጁ ይቀጣ የሚል የህግ አንቃጽ የለም። እነዚህ ዕድለኛ ልጆች በአባቶቻቸው ተዘርፎ የተሰጣቸውን ሀብትና የተካኑትን ሙያ ይዘው በአንድ ወቅት ወደ አገር ቤት ቢመለሱ ውጤቱ ምን ይሆናል ከተባለ ነገሩ ከግምት ያለፈ ግሀድ ነው። እነዚህ ወገኖች ታላላቅ ኢንዱስትሪዎችን ያቋቋሙና በየከተማ ምርጥ ቦታዎች ላይ ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን ይገነቡና፣ ግዙፍ
የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን በየቦታው ይከፍቱና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸው አይቀርም፡፡ ይህ ከሆነ ትርፍ የሚያስገኙ የኢኮኖሚ
ተቋማት በሙሉ በጥቂቶች እጅ ጥቅልል ብሎ ገባ ማለት ነው፡፡ የዚህ ውጤት በአንድ ሀገር ውስጥ ሁለት የተራራቁ መደቦችን መፍጠሩ አይቀርም፡፡ በአንድ
በኩል ሁሉን ነገር በእጃቸው ካስገቡ ወገኖች የሚመሰረት ፖለቲካ ፈጠር፡ የከበርቴ መደብ፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉን ነገር ተነጥቆ ያጣ የነጣ እልፍ አዕላፍ
የሚመስረት የድሀ መደብ፡
የምፈራው አደጋ ከዚህ ይመነጫል። ከጥቂት ወገኖች የተውጣጣ ፖለቲካ ፈጠር የከበርቴ መደብና ዓይኑ እያየ፣ ጆርው እየሰማ ደሙን የተመጠጠ፣
ስጋውን የተጋጠ ድሀ ሕዝብ አብረው ከሚኖሩበት አገር ይልቅ አይጥና ድመት በአንድ ላይ በሚያድሩበት ጎታ ውስጥ የተሻለ ስላም አለ። ኋለኞቹ አንዱ በሌላው ተበልቶ በይው ወገን ተጠቃሚ ይሆናል። የፊተኞቹ ዕጣ ፈንታ ግን ከዚህ በእጅጉ ይለያል። ከበርቴዎቹም በእጃቸው ያስገቡትን ገንዘብ ከየት እንዳመጡት ልባቸው
ያውቃልና፤ ድሀውም መዘረፉንና መነጠቁን ፍፁም አይረሳምና በስላም ጊዜ እንኳ ቢሆን በእነዚህ ሁለት ወገኖች መካከል እውነተኛ ሰላም ሊኖር አይችልም፡፡ ሁልጊዜ
ተዳፍጦ ኑሮ ነው ደሃ ጊዜ በመጠበቅ ሀብታም በመሸማቀቅ! ምናልባት ከአንድ
ወቅት ተፈጥሮም ይከዳና የሚላስ የሚቀመስ ጠፍቶ ደሀ ጦሙን ያደረ ዕለት ሊፈጠር የሚችለውን
አደጋ ማን ይመልሰው ይሆን እኔ እንደሚታየኝ ያ አደጋ የተከሰተ እንደሆነ የሚጠፋ ነገር ሁሉ ሳያልቅ የሚያጠፉ እጆች ያቆሙ
አይመስለኝም፡ በእርግጥም" ይህ ዓይነቱ አደጋ ከተፈጠረ ሀገራችን ኢትዮጵያ እጅግ ቢያንስ አንድ የጨለማ ዘመን ታሪክ አስመዝግባ ማለፍ ግድ የሚላት መስሎ እየታየኝ በእውነት ስቅስቅ ብዬ አለቅሳለሁ።ለነገሩማ እንድ ሀገር ለተራዘመ ጊዜ በአምባገነኖች የጭቆና ቀንበር ሥር ወድቃ
ከቆየች መጨረሻዋ ጥፋትና ውድቀት ሊሆን እንደሚችል ከማን ሊሰወር።
በእርግጥ ይህን መሰሉ አደጋ በሀገሩ ላይ ይደርስ ዘንድ ምናልባት 'እኔ ከሞትኩ ሰርዶ ኢይብቀል' እንዳለችው እንስሳ ማስተዋል የጎደላቸው እምባገነኖች ይጠብቅ እንደሆን እንጂ “ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ኢትዮጵያዊ የሚፈልገው
አይደለም። ዳሩ ግን ቁምነገሩ ያለመፈለጉ ብቻ ከልነበረም፤ ችግሩ እንዳይፈጠር ቁርጠኛ አቋም መውሰድን ይጠይቃል እንጂ። መፍትሔው ደግሞ የችግሩን ምንጭ ጠንቅቆ ከማወቅ ይጀምራል ችግሮቻችን አምባገነኖች ናቸው። መፍትሄውም አምባገኖችን ከህዝብ ትክሻ ላይ አሽቀንጥሮ መጣል ነው። መሳሪያው ደግሞ
የተቀናጀ ህዝባዊ አመፅ ብቻ።
«ውድ ወንድሜ አስቻለው 'አመፅ' ሲባል ለብዙዎቻችን የሚገባን
ጠመንጃ አንስቶ ጫካ መግባት ብቻ ነው ለኔ ግን የአመፅ ትርጉም ይህ ብቻ አደለም በአሁኑ ሰአት በአገራችን ዳርና ዳር የሚጎሰሙ የጦርነት ነጋሪቶችም ሀገራችንንና ሕዝባችንን ነጻ አውጥተው የሰላም ድባብ ይሰጣሉ ብዬ ተስፋ
አላደርግም። ቀድሞ ነገር ከጠመንጃ አፈ ሙዝ የተገኘ ነጻነት ያለ ሳሙና የታጠበ ጨርቅ ነው፥ ለጊዜው ጠረኑ ይቀየር እንደሆነ እንጂ እድፉ ግን የማይለቅ፣ ውሎ
አድሮ የሚሸት ሲሰነብት የሚከረፋ።
የጠመንጃ ነጻነት ሌላም ችግር አለው። በመሠረቱ ድሉ የሀይል እንጂ የሀሳብና የአመለካከት
ብልጫ አይደለም፡፡ የድሉ ባለቤቶች ጦረኞች እንጂ ሕዝቡ
አይደለም፡፡ ጦረኞች በጫካ ውስጥ ቆይታቸው የሚማሩት የውጊያ ስልት እንጂ የአሠራር ጥበብ አይደለም፡፡ ሲያሽንፉ እንኳ ስልጣን ሲይዙ ግራ መጋባታቸው
አይቀረም። በዚህ ውጤት ፍትህ ይጓደላል። ሕዝብም ይማረራል።
ለውጥ በሚፈለግ ስሜት ሕዝቡ ድንገት ነቅነቅ ያላ እንደሆነ የድሉ ባለቤቶች ያኔ ጫካ ውስጥ ሳሉ "ተነስ ለነጻነትህ!" እንዳላሉት ሁሉ በኋላ ግን እረፍ ለሕይወትህ! ቢሉትስ? ይሄም ሌላ ብልሽት።
ጦረኞች ከጫካ እስከ ቤተመንግስት እስኪደርሱ ድረስ እያንዳንዱ ርምጃቸው በደም የጨቀየ ነው። እየሞቱ ቢሆንም ይበልጥ እየገደሉ ነው የሚመጡት። በዚህ ምክንያት በቀልን ይፈራሉና ስልጣን ከያዙም በኋላ ጠመንጃቸውን አይጥሉም።
ጠመንጃ ተሸክመው በሰነበቱ ቁጥር በዚያው ልክ ልባቸውም ይደነቁራል። ደንቆሮ ደግሞ የራሱን እንጂ የሰው አይሰማም፡፡ ሀይለኛ የህዝብ ጩኸት ቢያውካቸው እንኳ ፀጥ ማሰኛቸው ያው ጠመንጃ ነው፣ ከምንም በላይ እሱን የመጠቀም ልምድ አካብተዋልና፡
«ሌላም አይቀሬ ችግር አለ፡፡ ጦረኞች ከጫካ ውስጥ ከጠመንጃ በቀር ሌላ
ምንም ነገር ይዘው አይመጡም። ስልጣን ከያዙ በኋላ ግን መክበራቸውም አይቀርም።
ፖሎቲከኛ ከበረ ከተባለ ነግዶ አተረፈ፡ ወይም አርሶ አመረተ ሊባል አይቻልም። የሀብት ምንጫቸው ያው የሀገርና ሕዝብ ሀብትና ንብረት ነው፡፡ ታድያ
ሀገርና ሕዝብ ከጠመንጃ ነፃነት ምን ያተርፋሉ? ወደ እውነተኛ ፍትህና ነጻነት የሚያመራው መንገድ ግን ወዲህ ነው የተቀናጀና የተባበረ ህዝባዊ አመፅ በእያንዳንዱ የነፃነት ቀናዒ
ስሜት ውስጥ የሚፈጠር የልብ አመጽ!
«በእውነት እልሀለሁ አስቻለው፡- የእያንዳንዱ ሰው ነጻነት በራሱ ልብ ውስጥ በሚፈጠር የአመጽ ስሜት ወስጥ ትጸነሳለች። ጥይትን ጫካ ውስጥ የመሸገ ማንም ፈሪ ሊተኩሳት ይችላል። ነገር ግን ክብርና ነጻነቱን ለሚሻ እውነተኛ ጀግና ሁሉ ያለ ምንም ወጪ ደጋግሞ የሚተኩሳት ግፈኞችን መርዝ ሆና የምታቃጥል አንድ ጥይት በገዛ አንደበቱ ውስጥ አለች እምቢ አሻፈረኝ! የምትሰኝ የአመጽ ቃል።
የሀገራችን ህዝብ መሠረታዊ ችግር የሚያስፈራ ነገር በሌለበት መፍራት ነው። እንዲሁም አድር ባይነትና በሌላው ተከሻ ላይ ነጻነትን የማግኘት እጓጉል
ምኞት ነው። ይህ ሁሉ እንዳልጠቀመ ከእኛ ከኢትዮጵያውያን የተሻለ ምስክር የለም የሰው ልጅ የወደፊት ችግሩ

👍3❤1🥰1
ዛሬ ላይሆኖ በማያስበው በሚፈፅመው ተግባር ውስጥ ይፈጠራል። የዛሬው ዝምታችን የወደፊት ዋይታችንን ከማስከተሉ
በፊት ሁላችንም በየፊናችን መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል። ራሳችን ያመጣነውን የፍርሀት የአድርባይነትና ነጻነትን ከሌሎች
የመጠበቅ በሽታ ራሳችን ፈውሰን፥ በአምባገነኖችና አቀንቃኞቻቸው ላይ ፈጥነን ልናምጽ ይገባል። አዎ ፍጥነት
ፍጥነት! ፍጥነት! ቀድሞስ ቢሆን እየተከፋ የማያምጽ ልብ ምንድነው? እያረረ እየተነነ የማይቆርጥ እንጀት ምንድነው? እያወቀስ የማይወስን አእምሮ ምንድነው? አንዲት ሀገር ታላቅ ለመሆን ታላቅ ሕዝብ ሊኖራት ይገባል። ታላላቅ መሪዎች
ታላቅ ሕዝብ መሀል ይወጣሉ እንጂ በራሳቸው ታላቅ ሕዝበ መፍጠር ከቶ አይቻላቸውም። የሕዝብ ታላቅነት መለኪያ ደግሞ ለራሱ ክብርና ነፃነት እንዲሁም
ሀገሩ የምትጠይቀውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል ያለው ዝግጁነት ነው።
መስዋዕትነትን ሲሽሽ የሚጓዙበት መንገድ ሁሉ የሚያደርስው ከውርደት ጫፍ ነው። በሁሉ ነገር እጅ ስጥቶ አንገቱን ከደፋ ህዝብ መሀል የሚወጡ መሪዎችም
ከራሱ ከሕዝብ የባሱ ናቸው፣ ቢያስቡ ለሆዳቸው ፣ ቢጨነቁ ለስልጣናቸው፡፡ ያኔ ሕዝብም ሀገርም ወደ ታች! ጅውዉ ጭል.ጥ.. ወደ ገደል! ወደ አረንቋ!
«ሀገራችን ታላቅ ነበረች። ታላቅ ሕዝብና ታላላቅ መሪዎች ነበራት።
ዝናዎ በዓለም ዙሪያ ሲሰማ ኖራል። ዛሬስ? ዛሬማ... ዛሬማ... መልሱ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ይገኛል። ስጋት! ፍርሃት ጭንቀት!! የታላቅነት ዝናና
ታሪክ ያለው ሕዝብ ወደ ታላቅነቱ ለመመለስ አቋራጩ መንገድ! እያንዳንዱ ዜጋ የየራሱን ልብ እየመረመረ ወደ ሀሊናው መመለስና ከዕምሮውን ከፍቶ፣ ዓይኑን ገልጦ ማየት መቻል ነው። ምንም ሳይቆይ የውርደቱን መንስዔዎች ያገኛቸዋል፣
አምባገነኖች ይበልጥ በእነሱ ዙሪያ ተሰልፈው የሚያጨበጭቡ ሆድ አደር ሹማምቶችና ፋርፋሪ ናፋቂ ጆሮ አደሮች ናቸው። የእነዚህ ዓይነቶቹ ሰዎች በየትኛውም ጊዜና ሀገር ውስጥ አይጠፉም። በሀገራችንማ እንደ አሸን ፈልተዋል እንዴውም አምባገነኖች በሕዝብ ጫንቃ ላይ እንዲፈናጠጡ መውጣጫ እርካብ የሆኖቸው እነሱ ናቸው። ስብዕናቸው በጥቂት ሀረጎች ይገለፃል ራሳቸውን የከዱ ህሊና ቢሶች፡ የሚበለትን እንጂ የሚሰሩትን የማያውቁ አሳማዎች
እኳን ለሰው ሊስረዱ ለራሳቸውም ባልገባቸው የአምባገነኖች ፍልስፍና ህዝብን ለማደንቆር የሚጮሁ ጡሩምባዎች ናቸው! ሕዝባዊ የልብ አመፅም በዚህ ጊዜና በእነዚህ ሰዎች ላይ ሊጀምር ይገባል።
በአምባገነኖች ዘመን ህግ አለ ብለህ ህጋዊ የመብት ክርክር አታንሳ።ህጉን የሚያወጡት እራሳቸው ለራሳቸው ብቻ ስለሆነ
ያልጠቀማቸው እለት በማግስቱ ይሽሩታል እንዲያውም ዛሬ የተከራክርክበት የህግ አንቀጽ ነገ
በወንጀል ሊያስጠይቅህ ይችላል። ዕድለኛ ከሆንክ ወህኒ ትወርዳለህ ነገሩ ከጠና ማን ያውቃል፤ እነ አጀሮች የልባቸውን ስርተው ተሰውሯል ቢሉህስ? ዘርፈ ብዙ
በሆኑ ችግሮች በተተበተበች አገር ውስጥ ሲኖሩ ህልውናን ለማቆየት ጥበብ ያስፈልጋልና ወንድሜ ጥበቀኛ ብትሆን!! ጊዜያዊ እፎይታን እንኳ ማግኘት ትችል
ዘንድ ከዲላ ወደ ሌላ አገር ብትዛወር ብዬ ወንድማዊ ምክሬን አስከትላለሁ፡፡
« በተረፈ ፈጣሪ አምላክ እኔንም ወደ ሀገራ እንዲመልሰኝ፤ ለሀገሬ ሕዝብም ልቦና ሰጥቶት ከእንቅልፉ ይነቃ ዘንድ እንዲሁም ሀገሬ ኢትዮጵያን ከጥፋት
ይጠብቃት ዘንድ ዘወትር በፀሎት እተጋለሁ።
ያንተው ደጀኔ አድማሱ(ዶ/ር)
እስቻለው ይህን ደብዳቤ ሲያነበ ፀጥ ረጭ ብሎ፣ ትንፋሹን ዋጥ አድርጎና በስሜትና በተመስጥኦ ነበር፡፡ አንብቦ እንደ ጨረሰ ግን እንዳች ስሜት መላ ሰውነቱን ወረረው፡፡ ተሸበረ። ጭንቅ ጭንቅ አለው፡፡ እራሱን እንደ ማዞር! ልቡንም እንደ ማጥወልወል አለውና ከዚህ ስሜት ያመለጠ መስሎት ያን ደብዳቢ ከአጠገቡ
ራቅ አድርጎ አልጋው ላይ በማስቀመጥ ሁለት ዓይኖቹን ጨምሮ ሙሉ ፊቱን
በሁለት እጆቹ ሽፍን አደረገና አልጋው ላይ ተደፋ። በዚሁ ሁኔታ ለረጅም ጊዜ ቆየ፡፡ ትርፌ ምሳውን አድርሳ ኖሮ ልታስታጥበው ውሃና ማስታጠቢያ ይዛ ወደ አልጋው ቀረብ በማለት፡
«ጋሼ አስቻለው!» ስትል ጠራችው። አስቻለው ግን ስምቶ እንዳልሰማ ዝም አላት።
እንቅልፍ ወሰደህ እንዴ?» እንደገና። አስቻለው ፈጠን ብሎ ብድግ በማለት ዓይኖቹን ጭፍን እንዳደረገ «አየ ትርፌ! የእንቅልፍን ነገር ተይው ከእንግዲህ እንኳን ለቀነ ለሌሊቱም ሰጋሁ፡፡» እያለ ሊታጠብ አንድ እጁን ዘረጋ።...

👍3🤩1
#የፈላስፎች_ንግግር ።
ሀብታም ፡ ይደኸያል ፡ ሐኪምዎ፡ ይሞታል
ጐበዝ ፡ ይሸነፋል ፡ ብልኅ ፡ ይሳሳታል
የበራውም ፡ ጠፍቶ ፡ የሠሩት ፡ ይፈርሳል !
የቆመው ፡ ወድቆ ፡ የሣቀ ፡ ያለቅሳል
ጌጥም ፡ ሆነ ፡ ጥበብ ፡ ውበት ፡ሆነ ክብርም
ያማረበት፡ነገር ፡ ማስቀየሙ ፡ አይቀርም
🔘ከበደ ሚካኤል🔘
ሀብታም ፡ ይደኸያል ፡ ሐኪምዎ፡ ይሞታል
ጐበዝ ፡ ይሸነፋል ፡ ብልኅ ፡ ይሳሳታል
የበራውም ፡ ጠፍቶ ፡ የሠሩት ፡ ይፈርሳል !
የቆመው ፡ ወድቆ ፡ የሣቀ ፡ ያለቅሳል
ጌጥም ፡ ሆነ ፡ ጥበብ ፡ ውበት ፡ሆነ ክብርም
ያማረበት፡ነገር ፡ ማስቀየሙ ፡ አይቀርም
🔘ከበደ ሚካኤል🔘
👍6❤2
#ፊኛ_እና_ቦርጭ
በሰው ልጅ ተፈጥሮ - በሰው እጅ ተሰርቶ
ትንሽ የነበረው-ድንገት አይን ውስጥ ገብቶ፣
ከቦታው ተነስቶ
አየር አስገብቶ፣
ሆዱን ቢያሳብጥም - የሰው ትንፋሽ በልቶ
በሰው አፍ ተነፍቶ
ተነፍቶ
ተነፍቶ. . .
መበታተኑ አይቀር - ጧ ብሎ ፈንድቶ!!!
✍ ?
በሰው ልጅ ተፈጥሮ - በሰው እጅ ተሰርቶ
ትንሽ የነበረው-ድንገት አይን ውስጥ ገብቶ፣
ከቦታው ተነስቶ
አየር አስገብቶ፣
ሆዱን ቢያሳብጥም - የሰው ትንፋሽ በልቶ
በሰው አፍ ተነፍቶ
ተነፍቶ
ተነፍቶ. . .
መበታተኑ አይቀር - ጧ ብሎ ፈንድቶ!!!
✍ ?
👍9
#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
....“አባቱን ላስገደለ ለርጉም ተክለሃይማኖት ያደረ ርጉም ነው” እየተባሉ ሲታሙ ያዘነላቸውን ያህል፣ ያን ቀን አዘነባቸው፤
ዓመጸባቸው።የሚሉትን ሊፈጽም፣ ሊያነጋግራቸው ቀርቶ፣ በዐይኑ
ሊያያቸው ቸገረው።
ጉልምስና ዕድሜ ላይ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ነገር ተመኝቶ
አደገ - ወለተጊዮርጊስን አግብቶ ሥዕል እየሣለ መኖር፡፡
ወለተጊዮርጊስን ብዙ ጊዜ የሚያያት እሑድ ቤተክርስቲያን ከቅዳሴ በኋላ ሲሆን፣ ከቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውጭ ያለው ዋርካ ስር
ጥምጥሙን አድርጎ፣ ዱላውን መሬት ላይ፣ ዐይኑን ደጀሰላሙ ላይ ተክሎ የሷን ከግቢ መውጣት ይጠባበቃል። በመልኩ ማማርና በቁመቱ ርዝመት የተማረኩ ኮረዶች እሱን እያዩ ሲሽኮረመሙ፣ እሱ ዐይኑ ደጀሰላሙ ላይ ልቡ ወለተጊዮርጊስ ጋ ነው። ነጠላ ተከናንባ ብቅ ስትል ልቡ ይደልቃል። ዐይኖቹ የሚያርፉበት ይጠፋቸዋል ። ከአያቷና
ከእናቷ ኋላ እየተራመደች ዐይኖቻቸው ሲጋጩ ፈገግታ ይመጋገባሉ። ሰላምታ ይለዋወጣሉ።
ይህ ለሳምንት ስንቅ ይሆነዋል።
በዚህ የተነሳ ዋርካውን ይወደዋል ፤ ለእሱ ብቻ የተተከለለት
ይመስለዋል። ዋርካው ሥር ቆሞ የወለተጊዮርጊስን መውጣት
ሲጠባበቅ፣ ብቅ ስትል ልቡ ሲመታ፣ ዐይኑ ማረፊያ ሲያጣ፣ ፍቅሩ ሲግል፣ ምኞቱ ሲበረታ፣ ጊዮርጊስ ዝም ብሎ አይመለከተኝም፣ ያባቴን
ልብ ያራራልኛል እያለ ዐዲስ ተስፋ ውስጡ ሲጫር ይሰማዋል።
ሌሎች ጎረምሶች አጠገቡ ሲቆሙ፣ አቅሉን ያጣል። ወለተጊዮርጊስ ከቤተስኪያኑ ከመውጣቷ በፊት ቢሄዱ ደስ ይለዋል። “እስቲ ዞር በሉ”
ለማለት ይቃጣዋል።
ወለተጊዮርጊስና እሱ ቁጭ ብለው የልባቸውን ተነጋግረው ባያውቁም፣ አባቶቻቸው ቢቀያየሙም፣ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አብሮ መኖር ዕጣ ተርታቸው እንደሆነ ሁለቱም በልባቸው አምነዋል፤ ሳይነጋገሩ ቃል
ተገባብተዋል። አንዱ ለአንዱ ልቡንና ሕይወቱን ሰጥቷል። ምንም እንኳን እሱ ያ ንፋስ አሸዋውን አንስቶ የተሸፈነበት የእሷ ምስል ልቡ ውስጥ ተቀርጾ አልፎ አልፎ ፍርሐት ቢያሳድርበትም፣ አላገኛት ይሆን?
የሚል ጥርጣሬ ውስጥ ቢከተውም፣ ሁለቱም በአባቶቻቸው መሃል ዕርቅ
ወርዶ የሚጋቡበትን ቀን በተስፋ ተጠባብቀዋል።
ጥላዬ፣ አባቶቻቸው የገቡትን ቃል አጥፈው፣ ለዓመታት እንደ
ጠላት ለመተያየታቸው ብቻ ሳይሆን፣ ወለተጊዮርጊስን ሳያገባ
ለመቅረቱ ምክንያቱ የእሱው አባት በመሆናቸውና ሥዕል የመሣል
ፍላጎቱን ሊያመክኑበት የሚታገሉትም እኝሁ አባቱ በመሆናቸው ቁርሾ ይዞባቸዋል።
ዐይናቸውን ላለማየት፣ እናቱን በሆነ ባልሆነው ሲጨቀጭቁና ቀን ያገኙትን ሁሉ ማታ ሲራገሙ ላለመስማት፣ ማታ ዳዊታቸውን ደግመው እስኪተኙ ውጭ ጨለማ ውስጥ ተቀምጦ ራቱን በልቶ መግባትና መተኛት፣ ጠዋት ውዳሴ ማርያማቸውንና ዳዊታቸውን ሲይዙ እናቱ
የሚያስጨብጡትን ቂጣ ቋጥሮ መውጣት የዘወትር ተግባሩ ሆነ።
ለእናቱ ቢያዝንም፣ ምኞቱና ፍላጎቱ ሁሉ ከዚያ የቁጭትና የበቀል ስሜት ከተጠናወተውና “የግዞት” ቦታ መሄድ ብቻ ከሆነ ሰንብቷል።የት እንደሚሄድ ያሰላና የወለተጊዮርጊስን ቁርጥ ሳያውቅ ቋራን ጥሎ ለመሄድ አንጀቱ አልችል ይለዋል።
ዛሬ ግን ወለተጊዮርጊስ ለንጉሥ መታጨቷን ሲሰማ ማመን አቃተው፤ ለዘላለም እንዳጣትም አወቀ። ከጥቂት ዓመታት በፊት ምስሏ በአሸዋ ሲዳፈን የተመለከተው ትዝ አለውና በእርግጥም ያ ንፋስ ንግርት
እንደነበረው ተረዳ ። ሕይወቱ በዐይኑ ሥር ስታልፍ፣ ስታመልጠው ተሰማው። ምንጊዜም ቢሆን የሚፈራውና ባሰበው ቁጥር የሚባንንበት፣
አካሉ ቦታ የማይበቃው የሚመስለው ነገር ዛሬ በመድረሱ አባቱን ወነጀለ።
ወለቴን ንጉሡ አልወሰዱብኝም፡ አባቴ አሳልፈው ሰጡብኝ እንጂ
አለ። እንባውን በኩታው እየጠራረገ፣ ለመሆኑ ወለተጊዮርጊስ ለንጉሡ
መታጨቷን ስትሰማ ምን ብላ ይሆን? መቸም ልብ ለልብ ተገናኝተናልና ምንስ ቢሆን እኔን ሳታስብ ትቀራለች? አለ፣ ሲተያዩ ፊታቸው ላይ የሚዋልለውን ደስታ እያሰበ። ስለምን እስታሁን ተያይዘን አልጠፋንም ነበር? ብንጠፋ ንሮ እኼ ሁሉ አይመጣም ነበር፡፡ ነገሩን እያሰበው ሲመጣ ድንጋጤውና ቁጭቱ ወደ ንዴት ተለወጡበት። ድንገት ንዴቱ እንደ ቋያ እሳት በሠራ አከላቱ ተሰራጨ።
እጆቹ ተንቀጠቀጡ፣ ጉሮሮው ደረቀበት፤ ቁና ቁና ተነፈሰ።
እናቱ ራቱን አመጡለት። መብላት እንደማይፈልግ ነገራቸው። ቤት
ውስጥ ተመልሰው ገብተው ቆሎ በአነስተኛ ቁና፣ ውሃ ደግሞ በቅምጫና ይዘው መጥተው፣ ቅምጫናውን መሬት ላይ አስቀምጠው ቁናውንም
በእጁ እንዲቀበላቸው ጥቂት አባብለው አስይዘውት አጠገቡ ተቀመጡ።
“አይዞህ የኔ ልዥ ። ዕድሜ ኻላነሰው፣ ጊዜ አለው ሰው ይላል ያገሬ ሰው። አንድ ቀን ሰው ትሆናለህ” ብለውት ለመውረድ ያቆበቆበውን እንባቸውን በእጅጌያቸው ጠራረጉ።
“እነየ አትጨነቂ።”
“ያባትህ ነገር መላ የለው ሁኖ አንተም ተቸገርህ። እኔስ እንዳሻው::ኸዝኸ ወዲያ ምን አረጋለሁ። የሳቸው ነገር ያስቸጋሪ በሬ ነገር ሆነ እኮ።”
“ያስቸጋሪ በሬ?”
“የሴቲቱ ባል ማልዶ ተነስቶ ወደርሻ ሲኸድ በሬው ገደል ይገባበታል።ዛዲያ ዳገት ላይ ቁሞ፣ 'ኧረ እርዱኝ በሬየ ገደል ገባ! ብሎ ይጮሀል። ያን ግዝየ ምሽቱ ኸቤት ትወጣና ኸየት ያመጣኸው በሬ ነው? በራሴ
በሬ' ብላው ትገባለች..” ሲሉ ጥላዬ ከት ብሎ ሲስቅ ትን አለው።
“ውሃ ፉት በልበት” አሉና ቅምጫናውን አቀበሉት። ውሃውን ጨልጦ ሲጨርስ ጠብቀው፣ “እናልህ እንደዛ ብላው ቤት ስትገባ ባልየው፣ ኧረ በሬያችን ገደል ገባ እርዱኝ አለ። ሴትየይቱ እንደገና ወጥታ፣ ኸየት
ያመጣኸው በሬ ነውና ነው በሬያችን ምትለው? የድሮ ባሌ የሰጠኝን ብላው ቤት ገባች። በመጨረሻ ሰውየው ሚለው ቢያጣ፣ እረ ያስቸጋሪ በሬ ገደል ገባ እርዱኝ አለ ይባላል አለ” አሉት።
ጥላዬ እንደገና ከት ብሎ ሳቀ። እናቱ ለሁሉ ነገር ምሳሌ የሚሆን
ተረትና ጨዋታ አላቸው። “አይ እነየ” ብሎ መልሶ ሳቀ። “የግዞት”
ቦታ የሚለውን ቤታቸውን እናቱ በተጫዋችነታቸው፣ ነገሮችን ቀለል አድርገው በማየታቸው፣ በተረቶቻቸውና በቀልዶቻቸው ነፍስ ባይዘሩበት ኖሮ፣ ኑሮ ከባላምባራስ ሁነኝ ጋር ምን ያህል አስቸጋሪ ሊሆን ይችል
እንደነበረና እናቱ የቻሉትን፣ የታገሱትን፣ ስቀውና ቀልደው ያሳለፉትን አሰበና፣ “እነየ ስንኳንም አንቺን ሰጠኝ” አላቸው።
ወይዘሮ ጌጤነሽ ሳቅ ብለው፣ “አየ ያንተ ነገር... እንኳንም አንተን
ሰጠኝ እንጂ አለበለዚያማ...” አሉት። ትንሽም ቢሆን ሊያስቁት
በመቻላቸው ደስ ብሏቸው፣ “አሁንስ ራት አትበላም?”
ራሱን በአሉታ ነቀነቀ።
ቅር እያላቸው ወደቤት ሲገቡ እሱ ስለ ሕይወቱ ማሰላሰል ጀመረ።
አንተ የወፍታው ምነው ዝም አልኸኝ? አለ ኹለት ነገር ጠይቄህ
ስንኳ አላውቅ። እኔ ልቤ ውስጥ እሳት አለ - ወለቴና ሥዕል፡ ወለቴን
ኸነጠቅኸኝ፣ ሥዕል መስጠት አቃተህ እኔ ጠበቅሁ፤
ጠበቅሁ፤ ሰው እስተመቸ ይጠብቃል? ለመጠበቅ ብቻ መፈጠርማ የለብኝም፡፡
ኸንግዲህ ምጠብቀው ነገር ስለሌለ ቋራ ሚያስቀምጠኝ ነገር የለም። እሳቸውን ችየ የኖርሁት ወለቴን አገባለሁ ብየ እንጂ፣ እሷ ለንጉሥ ኸተዳረችማ መኸድ በቀር ሌላ ምን አለኝ? ወለቴን ንጉሥ ኸወሰዳት እኔ የሥዕል ንጉሥ ማልሆን? አለ፣ ለራሱ።
ወለተጊዮርጊስን ማጣቱና እናቱን ለአባቱ ትቶ መሄድ ማሰቡ
ቢያሳዝነውም በወጣትነት ዕድሜው ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሱ መወሰን መቻሉ ዐቅም ሆነው፤ አደፋፈረው፣ የነፃነት መንፈስ አለበሰው። አባቱ ከፊቱ የደነቀሩበትን ጋሬጣ፣ ዙርያውን የተበተቡበትን ገመድ
በጣጥሶ የወጣ መሰለው።

👍12🔥1
ሰማዩን ሳያይ ቤት የማይገባው ጥላዬ ወደላይ ቀና አለ።
እንደሁልጊዜው በከዋክብቱ ተመሰጠ፤ ምድራዊ ፍላጎቱንና እጦቱን ረሳ። ዛሬም ጨረቃዋ ከከዋክብት ጋር ተባብራ ለሰማዩም ለምድሩም
ድምቀት ሰጥታዋለች። የሆነ የተስፋ ስሜት ጫረችበት፤ አደፋፈረችው፤ የሕይወትን ጫፍ ያስያዘችው መሰለው። ጠፍቶ ለመሄድ በማሰቡ፣ ስለ
ወለተጊዮጊስ የሰማው አስደንጋጭና አሳዛኝ ዜና ለእሱ የዕድል በር የከፈተለት ሆኖ ተሰማው። አሁንስ በቃኝ፤ ሥዕል ምማርበት ኸዳለሁ አለና ኣባቱ ስለተኙለት ወደ ቤት ገባ።
ሌሊቱን ወለተጊዮርጊስንና እናቱን እያሰበ ሲገላበጥ አደረ። ሰኞ
ንጋት ላይ ቁምጣውን ታጥቆ፣ እጀጠባቡን ለብሶ፣ ኩታውን ደርቦ፣
በዳዊት ማኅደሩ ላይ መቀየሪያ ጥብቆውን ይዞ፣ ዱላውን ትከሻው
ላይ፣ የውሃ ቅሉን ዱላው ላይ አንጠልጥለ፣ አባቱ እስካሉ ድረስ ቋራ ላይመለስ ምሎ ከቤት ወጣ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ዕድል ከሰማይ ይወድቃል?”
በማግስቱ ወለተጊዮርጊስ ወላጆቿ ቤት ስትደርስ፣ የእናቷ ነፍስ
አባት መጥተው ዕድሏ እንዲቀና፣ ሕይወቷ እንዲሳካ ጸለዩላት፤
ባረኳት። እናቷም የአንገት መስቀሏን በዐዲስና ወፈር ባለ የሐር ፈትል አሠሩላት።
ቄሱ እንደሄዱ፣ ቅቤ የተቀባውን ፀጉሯን ከዚያም ገላዋን ታጥባ
በዕጣንና በብርጉድ ታጠነች። ከእንግዶቹ ጋር ከጐንደር ከመጡት አንደኛዋ ደንገጡር ፀጉሯንም በጐንደሬ ዓይነት ሾረበቻት። እናቷና አያቷ ብቻ ባሉበት ለደንገጡሮቹ እንግዶች ወደተዘጋጀው ድንኳን
ተወስዳ አያቷ፣ “አሁን እንግዲህ አረማመድ፣ አነጋገር፣ ኣሳሳቅ፣ አበላል፣ አስተያየት የመሳሰሉትን መማር አለብሽ” ብለው ጐንደር በነበሩ ጊዜ የሰሙትን የቤተመንግሥት ሥርዐት ሲያስተምሯት ዋሉ።
“እስቲ እጅ ንሽ።”
“ፈገግታሽ እንደ ሥራ ቤት እንዳይኾን አፍሽን በሙሉ አትክፈቺ።”
“አ...ዎ እንደሱ።”
“ዐይንሽን ደሞ ሰበር አርጊ።”
“እስቲ ወዲያ ኸድ በይና ተመለሽ።”
“እኼ ነው የኔ ልዥ” ሲሏት ቆዩና፣ “ደሞ እዛ እነሱን እያየሽና
እየሰማሽ እንደነሱ ታረጊያለሽ፣ ትናገሪያለሽ። የጐንደር ወይዛዝርት
እንዲህ እንዳይመስሉሽ። ኸግር እስተራስሽ እያገላበጡ ነው ሚያዩሽ።ቄንጥ ሲያወጡ አይጣል ነው” ሲሉ መከሯት።...

👍7
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...የሰኔ ወር ገብቶ እንዲያውም ተጋመሰ። እዲስ የበጀት ዓመት መቃረቡን ተከትሎ የመንግስት ሠራተኞች የዝውውር ጥያቄ መልስ መስጫው ጊዜም ተዳረሰ፡፡
ከዝውውር ጠያቂዎች አንዱ የሆነው አስቻለው ያን ወቅት በጉጉት ሲጠብቀው ቆይቷልና ከጊዜው መቃረብ የተነሳ ሀሳቡ ሁሉ ስለ ዝውወርና ከዚያ ጋር ተያያዥ ስለሆኑ ነገሮች ብቻ ሆኖ ሰንብቷል። ብዙ ነገሮች ያሳስቡታል። ከዲላ መዛወር
የፈለገው ወዶ አይደለም! ተችግሮ ነው፡፡ ግን በሚዛወርበት ቦታ ዲላ የገጠሙት ችግሮች ከይኖሩ ይሆን? ዲላ የተፈጠሩበት ችግሮች መነሻቸው የግልፅነቱና የተናጋሪነቱ ውጤቶች ናቸው፡፡ ወደ አዲሱ ቦታ ሄዶ ዝም ይል ይሆን? ተናጋሪነቱ የተፈጥሮ ባህሪው ነው፡፡ የሰው ልጅ ደግሞ የተለያዩ አመሎችን መተው ይሻል
እንደሆነ እንጂ የተፈጥሮ ባህሪውን ግን እንዴት?
ዲላ ከተማ ለአስቻለው በሥራ ሕይወት የኖረባት የመጀመሪያዋ ከተማ ናት፡ ጣፋጭ ማሀበራዊ ሕይወት የጀመረው በዚያችው ከተማ ነው፡፡ ዕድሉ ሆኖ ጥሩና ዕድሜ ልኩን የማይረሳቸው የባዕድ ወገኖች አግኝቶባታል፣ ታፈሡን በልሁና መርዕድን ከእነሱ ተለይቶ መሄዱ ያስጨንቀዋል፡፡ ዝውውር የጠየቀው ወደ ሽዋ
ክፍለ ሀገር ቢሆንም የሚመደብበትን የጤና ተቋም ግን አያውቅም፡፡ ከነታፈሡ በልሁና መርዕድ ጋር በቀላሉ መገናኘት በሚያስቸግር ቦታ ቢሄድስ? ልቡ ይፈራል። ድንገት ትዝ ሲለው ሆዱን ባር ባር ይለዋል።
የሔዋን ጉዳይስ? በወላጆቿ ፈቃድና እውቅና ለፍቅራቸው እልባት ለማግኘት የሚሞክረው ገና ወደፊት ባሉት ወራት ነው! ሐምሌ ወይም ነሐሴ። በእርግጥ
በጉዳዩ ላይ ታፈሡና በልሁ አስበውበታል ምናልባት
ወይዘሮ ዘነቡም ይጨመራሉ፡፡ ግን ይሳካ ይሆን? ወደሚዛወርበት ቦታ ሔዋንን ይዞ መሄድ ይችል
ይሆን?ይህ ጉዳይ ዛሬ ሌሊትም እንቅልፍ ነስቶት አድሯል፤ እሁድ ለሰኞ አጥቢያ። ሊነጋጋ ሲል ግን ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዶት ኖሯል፡፡ ተኝቶ አረፈደ፡፡
አስቻለው የጠዋት ፈረቃ ሥራ ገቢ መሆኑን የምታውቀው ትርፌ
በሁኔታው ግራ ተጋባች፡፡ ለወትሮው ወደ ሥራ ለመሄድ ቀስቃሽ አያስፈልገውም ነበር። ዛሬ ግን ሁኔታው ተለየባት፡፡ ልትቀሰቅሰው እያሰበች ፈራ ተባ ስትል ቆየችና መጨረሻ ላየሰ ግን ልታነቃው ወሰነች።
«.ጋሽ እስቻለው!» አለችው ወደ አልጋው ቀረብ ብላ፡፡ እስቻለው ግን በአንዴ አልሰማትም «ጋሽ አስቻለው!» አሁንም ደግማ፡
አስቻለው ብንን አለ፡፡ ፊቱን ኩብርድ ልብስና አንሶላ ሽፋን ገለጥ አድርጎ ከአንገቱም ቀና በማለት «ወይ» አላት።
«ዛሬ ሥራ የለህም እንዴ?»
«እረፈደ?» በማለት የእጁን ሠዓት አየት ሲያደርግ ከጠዋቱ ሁለት ሠዓት ከአምስት ደቂቃ ሆኗል። «እንዴ!» ብሉ በድንጋጤ ዓይን ትርፌን ፍጥጥ ብሎ ተመለከታት።
እኔ እኮ ሥራ የማትገባ መሰለኝ!» አለችው ትርፌ ሳትቀስቅለው
መትረቷ ቅር ያለው መስሏት አፈር እያለች::
«ምን ነካኝ እባካችሁ?» አለና አንሶላና ብርድ ልብሱን ጣል አድርጎ ከአልጋው ላይ እየተነሳ «ውሃ ውሃ» አላት በችኮላ አነጋገር፡፡
«በረንዳ ላይ አውጥቼልሀለሁ፡፡»
አስቻለሁ በጥድፊያ ልብሱን ለባበሰና ሊታጠብ ወደ በረንዱ ወጣ፡ ቶሎ ቶሎ ታጥቦ አበጣጠረና ወንበር ላይ የሰቀላትን የቆዳ ጃኬት ብድግ አደረገ፡፡
«ቁርስ ሳትበላ አለች ትርፌ እንቅስቃሴውን እየተከታተለች፡፡
«ረፍዷል ትርፌ፤ ቻው » ብሏት በፍጥነት ርምጃ ከቤት ወጥቶ ሄደ።
መንገድ ላይ ሳለ በልቡ እንድ ነገር ያሰላስላል። ካአሁን በፊት ለብዙ ጊዜ እንደተከታተለው የሠራተኞች የሠዓት መቆጣጠሪያ መፈረሚያ ጠዋትም ይሁን ከሰዓት ከቦታው የሚነሳበት ወቅት ከእሱ መፈረም ወይም ያለ መፈረም ጋር ሲያያዝ አይቷል፡፡ እሱ በጠዋት ወይም በጊዜ ገብቶ ከፈረመ ያ የሠዓት
መቆጣጠሪያ መፊረሚያ ለሩብ ሠዓት ያህል በአለበት ቦታ ሊቆይ ይችላል፡፡ እሱ ለደቂቃዎች ያህል
ከዘገየ ግን ለአፍታ እንኳ ሳይቆይ ወደ ቢሮው ይገባል። ዓላማው
እሱ በአርፋጅነት የሚመዘገብበትን ቀናት ለማበርከት እንደሆን ይጠረጥራል.ስለዚህም በጣም ይጠነቀቅ ነበር፡፡ ለዛሬው ግን አልተሳካለትም።ብዙ
ባያስጨንቀውም ነገር ግን ባርናባስ ወይሶነ በመጥፎ ስሜት እያስታወሰ በፍጥነት ርምጃ ግስጋሴውን ቀጠለ::
ከሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ሲደርስ ሁለት ሠዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ያ ሰዓት ደግሞ የፈረቀው ገቢ የሆኑ የህክምና ባለሙያዎች ከሥራ በፊት የተለመደ ከጭር
ስብሰባ ሊያጠናቅቁ የሚደርሱበት ጊዜ ነው፡፡ ባለቀ ሠዓት ወደ ስብሰባው መግባት አልፈለገም። ዝምብሎ ወደ መልበሻ ክፍል አመራና ጋወኑን ለበሰ፡፡ ቀጥሎም
የሠዓት መፈረሚያው ወደ ሚገኝበት የባርናባስ ወይሶ ፀሃፊ ቢሮ ሄዶ አንኳክቶ ገባ፡፡
“ዛሬ እንኳ አረፈድኩ ከይባልም! ውያለሁ እንጂ!» አለ አስቻለው ፈገግ ብሎ የባርናባስ ወየሶ ፀሃፊ የሆነችውን ሠርካለምን እየተመለከተ፡፡
የአንድ ቀን ደሞዝ ቀለጠች፡፡» አለችው ሠርካዓለም እሷም እንደ አስቻለው ፈገግ ብላ እየቀለደች ሠርካለም የሚያምር ፈገግታ ያላትና ቀጠን ያለች ቀይ ዳማ
ቢጤ ናት። በዕለቱ ጥቁር ኮትና ጉርድ ቀሚስ ለብሳለች። ዕድሜዋ እስከ ሰላሳ ሊደርስ የሚችል ይመስላል።
«ግድየለም፤ ሌላ ጊዜ ከአልደገምኩ ለዚህ ወር የሃያ ዘጠኙ ቀን ደሞዜ ይበቃኛል::" አለና አስቻለው በቀይ እስክርብቶ የጥያቄ ምልክት ከተደረገበት ጎን
ፊርማውን አስቀመጠ፡፡
ዛሬ ግን ያለ ወትሮህ ከርፍደሃል! በሰላም ነው?» አለችው ሠርክዓለም አንድ በውስጧ የምታውቀውና የአስጨነቃት ጉዳይ ያለ ስለመሆኑ በሚያጠራጥር ስሜት አስቻለውን እያየችው::
«የሆነ ሀሳብ ገብቶኝ ያለ እንቅልፍ አደርኩና ከነጋ በኋላ ድብን አድርጎ
ወሰደኝ:: ሌላ እንኳ ችግር እልነበረበኝም፡፡»
«ምነው? ምን አሳሰበህ?»
«ሀሳብ ይጠፋል ብለሽ ነው» አለና አስቻለው ወደ ውጭ ሊራመድ ሲል ሠርከዓለም ንግግሯን ቀጠለች::
«ፈልጌህ ነበር እስቻለው::»
«በደህና!»
«እስቲ ቁጭ በል፡፡»
አስቻለው የሠርካዓለም ስሜት ጥሩ እንዳልሆነ ገመተ። ይበልጥ ሊያነበው እየተፍጨረጨሪ ዓይኖቹን በዓይኖቿ ላይ ሰክቶ ከሰርካዓለም ጠረጴዛ አጠገብ
በምትገኝ የእንግዳ ወንበር ላይ አረፍ አለና “ስላም ከይደለሽም" ሲል ጠየቃት፡
«እኔ እንኳ ደህና ነኝ»
«ታዲያ ሌላው ምን ሆነ?»
«ዓርብ ዕለት ከሰዓት በኋላ ለአንተ አንድ ደብዳቤ ስጪ ብለውኝ ቅዳሜና እሁድን በጭንቀት ነው ያሳለፍኩት። ከዛሬ ስለማያልፍ ልስጥህ ብዬ ነው፡፡» አለችው ሠርካለም መንፈሷ ጭንቅ ጥብብ እያለ፡፡
«የምን ደብዳቤ! ዝውወር» አላት አስቻለው በድንጋጤ ዓይኖቹ ጉልንል ብለው በሰርካዓለም'' ላይ በማፍጠጥ፡፡ ትንፋሹም በርከትከት! ፈጠን ፈጠን አለ፡፡
«አይደለም ነገሩ ብዝም ችግር ያለው ሆኖ አይደለም! ምናልባት
ግን አንተ የማትቀበለው ከሆነ በመሀል ችግር እንዳይፈጥርብህ እስቤ ነው።»
«ማን የጻፈው ደብዳቤ ነው?»
ሠርካለም የጻፈው ሰው እገሌ ብላ መግለጽ አልፈለገችም፡፡ ደብዳቤውን ከመሳብያ ውስጥ አውጥታ ሰጠችው።
አስቻለው ደብዳቤውን ተቀብሎ ገጹን በሙሉ ቃኘት ሲያደርገው ሙሉ ፕሮቶኮል የጨበጠ ነው፡፡ የፈረመበት ባርናባስ ወየሶ ነው፡፡ የደብዳቤውን አድራሻ ሲመለከት ለጓድ አስቻለው ፍሰሃ» ይላል፡፡

👍3❤1
«ኣ!» አለ አስቻለው ድንገት ሳያስበው፡፡ ቀና ብሎ ሠርካዓለምን አየት ካደረጋት በኋላ ወደ ብዳቤው ተመለሰና ማንበብ ጀመረ፡ ሲጨርስ «ምን?» አለ
በድንጋጤና በቁጣ ስሜት ጮክ፡፡ ሕልም ሕልም መሰለውና እንደገና አነበበው፡፡
መልዕክቱ ግን አልተቀየረም፤ ያው መጀመሪያ እንዳነበበው ነው፡፡
«አልገባኝም ሠርኬ ይኼ ነገር!» አላት ወደ ሠርካዓለም ዞር ብሎ።
«ለማንኛውም ረጋ በል አስቻለው!» አለችው ሠርከዓለም በማረጋጋት አይነት አይነት እሷም
ቀለስለስ እያለች።
«በርናባስ አሁን ቢሮ ወስጥ አለ?»
«ይኖራሉ። ግን አሁን አትግባ! ባይሆን ነገ ተነገ ወዲያ ይሻላል።»
አስቻለው ለአፍታ ያህል ሠርክዓለምን መልከት ካለ በኋላ ከወንበሩ ላይ ብድግ ብሎ ከቢሮ ወጣ፡፡ ያን ደብዳቤ እንደ ያዘ በቀጥታ ወደ ባርናባስ ቢሮ አመራ። ሳያንኳኳ በሩን በርግዶት ገባ::
ባርናባስ በተለመደው አለባበሱ ሆኖ ጠረጴዛው ላይ አጎንብሶ ይፅፋል፡፡ ወደ በሩ ቀና ሲል አስቻለውን አየው፡፡ የአስቻለው ስሜት መለዋወጡን አይቶ
ለሰላም እንዳልመጣ በመገመት ልቡ ድንግጥ አለና «አቤት» አለው መነፅሩን ወለቅ እያደረገ።
ምንድነው ይኼ?» አለና አስቻለው ያን ደብዳቤ በባርናባስ ፊት ጠረጴዛው ላይ ውርውር አደረገው፡፡ ጋወኑን ወደ ኋላው ሰብሰብ በማድረግ ሽንጥና ሽንጡን ይዞ ቁና ቁና እየተነፈሰ በባርናባስ ፊት ቆመና ቁልቁል ይመለከተው ጀመር፡፡
በርናባስ ይህን የአስቻለውን ሁኔታ ቀድሞም አስቦት ነበር፡፡ ይሁንና አሁን በትክክል ሲከሰት ቀድሞ ከገመተው በላይ ፍርሀት አደረበት፡፡ በሙሉ ቀልቡ
የአስቻለውን እንቅስቃሌ እየተከታተለ ለይምሰል ያህል ወደ ደብዳቤው መልከት እያለ
«የበላይ አካል ውሳኔ እኮ ነው::»
ምን አይነት ውሳኔ? አለ አስቻለው ድንገት አፉ ላይ የመጣለትን አይኑ
ከመፍጠጡም በላይ ትንፋሹ በርክቶ ደረቱ ሞላ ሞሸሽ፤ ሞላ ሞሸሽ ይላል፡፡
በቃ! ወሳኔ ነዋ አለ ባርናባስ ከአሁን አሁን ዘሎ አነቀኝ በማለት
አስቻለውን እየፈራ።
በእርግጥ እናት ሀገሬ ናት የጠራችኝ ወይስ እናንተ ናችሁ ያዘዛችሁኝ ሲል ጠየቀው አስቻለው የፊቱን ላብ በእጁ እየጠረገ::
«ሁለቱም ተያያዥ ናቸው::»
«ግን ደግሞ ሁለታችሁ መለያየት አለባችሁ፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መለያየታችሁ አይቀርም፡፡ እኔም የሐገሬን ጥሪ በደስታ የምቀበለው ሁለታችሁን ለማለያየት የክተት ጥሪ ነጋሪት የተጎሰመ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ይኸኛውን ግን አልቀበለውም፡፡» አለ ዓይኑን በባርናባስ ላይ ፍጥጥ እንዳደረገ።.....

👍6
አንድ ነገር ሁሉ፣ብዙ ከመሰለኝ ፣
እርግጠኛ ሁኚ..
ወይን ጠጥቻለሁ ፤ ሰው እየደለለኝ፡፡
ብዙ ነገር ሁሉ...
አንድ ነው በሚል ቃል ፣ ከዘጋሁት በሬን፣
እርግጠኛ ሁኚ...
የሌለኝን ሁሉን ከፍዬ መስከሬን።
አንድሞ ነገር ሁሉ...
ሁሉም ነገር ሁሉ፣ካልኩሽ በእግዜር ነው፤
እርግጠኛ ሁኚ..
ከከተማ ቄስ ጋር ፣ዝክር ቀምቅሜ ነው።
ሕይወት ሁሉም ነገር ባንድ ነገር ሥር ነው፣
እያልኩኝ ከሰማሽ ካየሽው ማሞረሬን፣
እርግጠኛ ሁኚ...
በፊደራል ዱላ፣ ታጅቤ ማደሬን።
ሁሉም ነገር የለም!
አንድም ነገር የለም፤ የሚል ቃል ከወጣኝ፣
እርግጠኛ ሁኚ...
ጀማሪ ፈላስፋ ፣ አረቄ እንዳጠጣኝ።
ሁሉም አንድ ነገር ፤ሁሉም ነገር አለው፤
ብዬ ጸጥ ካልኩኝ ፣ ከበቃኝ ክርክር፣
እርግጠኛ ሁኚ..
እንዲህ የምሆነው፣ባንቺ ቃል ስሰክር።
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
እርግጠኛ ሁኚ..
ወይን ጠጥቻለሁ ፤ ሰው እየደለለኝ፡፡
ብዙ ነገር ሁሉ...
አንድ ነው በሚል ቃል ፣ ከዘጋሁት በሬን፣
እርግጠኛ ሁኚ...
የሌለኝን ሁሉን ከፍዬ መስከሬን።
አንድሞ ነገር ሁሉ...
ሁሉም ነገር ሁሉ፣ካልኩሽ በእግዜር ነው፤
እርግጠኛ ሁኚ..
ከከተማ ቄስ ጋር ፣ዝክር ቀምቅሜ ነው።
ሕይወት ሁሉም ነገር ባንድ ነገር ሥር ነው፣
እያልኩኝ ከሰማሽ ካየሽው ማሞረሬን፣
እርግጠኛ ሁኚ...
በፊደራል ዱላ፣ ታጅቤ ማደሬን።
ሁሉም ነገር የለም!
አንድም ነገር የለም፤ የሚል ቃል ከወጣኝ፣
እርግጠኛ ሁኚ...
ጀማሪ ፈላስፋ ፣ አረቄ እንዳጠጣኝ።
ሁሉም አንድ ነገር ፤ሁሉም ነገር አለው፤
ብዬ ጸጥ ካልኩኝ ፣ ከበቃኝ ክርክር፣
እርግጠኛ ሁኚ..
እንዲህ የምሆነው፣ባንቺ ቃል ስሰክር።
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍8❤4