አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
የሆዷን በሆዷ አድርጋ ግን ደግሞ ፈገግ እያለች፡፡
ሽዋ'ዩ በረጅሙ ተነፈሰችና ቀድሞ የተብላሽ ነገር ምን መላ አለው
ሳልጠነቀቅ ቀርቼ» ብላ ነገሯን ተወት ስታደርግ ታፈሡ ቀጠለች።
«ሁለተኛ ላትደግም ቃል ገብታለች፡፡» አለችና እኔና አንቺ ግን ስለ ወደፊቱ ትንሽ ብንነጋገርና ከተቻለም" ተማምነን ብንስማማ ደስ ይለኛል፡፡» አለቻት፡፡
ስለ እሷ ከሆነ የሚያነጋግረን ነገር የለም፡፡ አለች ሽዋዬ ኮስተር ብላ፡
«ብንነጋገር የሚከፋ እይመስለኝም ሽዋዬ፡፡ ሔዋን እኮ እህትሽ ናት፡፡ እኔን ያገኘችኝ በአንቺ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ለእሷ ማሰብ ያለብኝ ከኔ በላይ እንቺ ነሽ፡
“ይጠቅመኛል ያለችውንማ ይዛለች አለች ሸዋዬ አፏን ጠመም አድርጋ፡፡
«በኔና በአንቺ ዕድሜ እኮ ከሙያችንም አንፃር በሰል ያለ አመለካከት ይጠበቃል ሽዋዬ?» ስትል ታፈሡ አሁንም ረጋ ብላ አስታያየቷን ሰጠቻት፡፡
«ታዲያ ሽዋዬ ምን ጎደላት አሉሽ?»
«ቢንስ ቢያንስ በሔዋን ዙሪያ የያዝሽው አቋም ትክክል አይመስለኝም፡፡ነጋሪ ሳያስፈልገኝ ራሴ እያየሁት ነው::»
«እውነቴን እኮ ነው ሽዋዬ ለመሆኑ ሔዩን ለጥፋት ያነሳሳት ነገር ምን
እንደሆነ ታውቂያለሽ?» ስትል ጠየቀቻት፡፡
«አንቺ ነሽ በይኛ» አለች ሸዋዬ አሁንም ታፈሡን በመገላመጥ፡ ታፈሡ የሚጠይቅ ጉዳይ በልቧ አለና ስሜቷን ገታ አድርጋ ማንም ይሁን ማ ነገር ግን አስራ ስምንት ዓመት ባለፋት ልጃገረድ ላይ ዱላ ማንሳት አልነበረብሽም።» አለቻተት።

ሸዋዬ ወደ ወረሮ ዘነብ ፊቷን መለስ አድርጋ እማማ ዘነብ ለዚህ ነው እንዴ ያመጣኝ?» ስትል ዓይኗን ፈጠጥ አድርጋ ጠየቀቻቸው፡፡
እስቲ እኮ ቆይ አስጨርሻት!» አሉ ወ/ሮ ዘነቡ እረጋ ብለው፡፡
"ዝም ብለሽ ተመልከቻት እያለችኝ እኮ ነው»
"እኔ እኮ ቁም ነገር ነው የማወራው ሸዋዬ» ታፈሡ አሁንም፡፡
«ለአንቺ ይመስልሽ ይህናል፡፡»
በዚ ጊዜ ታፈሱ የበለጠ ተናድዳ ዳኝነት፡ የፈለገች ይመስል ወይዘሮ
ዘነቡን መልክት አለቻቸው፡፡ በእርግጥ እሳቸውም በመሀል ገቡ።
«ምነው ልጆቼ ረጋ ብላችሁ በትትና ብትነጋገሩ! አሉ በተለይ ሸዋዬን አየት እያደረጉ።
ሽዋዬ ፊቷን ወደ ወይዘሮ ዘነቡ "መለስ አድርጋ ቆጣ ባለ አነጋገር «እንዴት እንግባባለን?
እሷ ያደፈረሰችውንበኔ ላይ ለማጥለል ስትፈልግ እያዮአት»
አለችና …" እግረ መንገዷን ታፈሡን በዓይኗ ገርመም አድርጋት ውጭ ውጭ ታይ ጀመር፡፡
ታፈሡ ድንገት ኪ..ኪ ...ኪ ብላ ሳቀች::
«ተይ አይሆንም አንቺ ልጅ! ሰው
የሚልሽን ተቀበይ እንዲህ ያለው ሃገር ድንግልም አትወደው ኋላ አይሆንም»አሉና ወይዘሮ ዘነቡ ዓይናቸውን ወደ ቡና ሦነ ስርአቱ አዞሩ።
«የመጣንበት ጉዳይ ተረስቶ ሌላ መዘዝ ሲመዘዝ ምን ላድርግ?» አለች ሸዋዬ በተለይ ወይዘሮ ዘነቡን እያየች
«ምን አደረኩ ሽዋዩ? እኔ እኮ እንነጋገር ነው ያልኩት አለች ታፈሡ
«ያደረግሽውንማ፣ አድርገሻል»
“እስቲ ምን?»
«ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብኛላ!
ታፊሡ አሁንም «ኪ ኪ ኪ ብላ ሳቀችና፡ እስቲ አንድ ነገር
ልጠይቅሽ::» አለቻት ለየፈገግ ብላ፡፡ ሸዋዬ በዓይኗ ገርመም አድርጋት እንደጋና ፊቷን ወደ ውጭ ስታዞር ታፈሡ ቀጠለች።
«አንቺ በታላቅነትሽ እህትሽን ድረሽ ኩለሽ ለወግ ለማአረግ ማብቃትና አትችይም» «አይገባሽም?» ስትል ጠየቀቻት
«አስተምሪ እንጂ ዳራ ኳይ አልተባልኩም»
«የግድ መታዘዝ የለብሽም ሁኔታዎችን ቢያስገድዱሽስ ?»
«ማን አባቱ፣ ነው የሚያስገድደን?ታፈሡ የሸዋዩን ምላሽ ፍየል ወዲያ ቅዝምገም ወዲህ ብላ ከታዘበች በኋላ «አልገባሽም እንጂ ጉዳዩ እንደሆነ ዓይኑን አፍጥቶ መጥቶብሻል፡፡»
«ኣ!» አለች ሽዋዬ ድንገት በመጮህ። ታፈሡንም ፍጥጥ ብላ ትመለከታት ጀመረ።
«አንቺ የማይሆንልሽ ከሆነ እኔና በልሁ ልንፈፅመው ወስነናል፡፡»
«እንዴት አድርጋችሁ?››
«በጣም ቀላል ነው! ወደፊት ሐምልና ነሐሴ ትምህርት ቤት ሲዘጋ እኔና በልሁ ክብረ መንግስት እንሄድና የሒዩን አባትና እናት እናስፈቅዳለን:: ከዚያ በኋላ
የኔና ያቺን ድርሻ ድል ያለ ሰርግ ደግሰን አስቹና ኤዩን ማጋባት ነው በቃ!» ካለቻት በኋላ «ክብረ መንግስት ለመሄድም ያሰብነው
የሒዪን ችግር አይተን እንጃ ራሳቸው አስቼና ሒዩ ብቻ የሚፈፅሙት ጉዳይ ነበር፡፡» አለችና ታፈሡ እንደገና ጥብቅ ባለ
አነጋገር “ምን ቁርጥ ያረገው ሰው ይክለክላቸዋል!» አለች ፏ ብላ በፈገግታ በመሞላት እማማ ዘነቡ አለች ሸዋዬ የታፈሡን ሀሳብ ያስለውጣት የመስል።
«ወይ»
«እንዳመጡኝ በሰላም አይመልሱኝም» አለቻቸው ከንፈሯን በምላሷ እያራሰች።
«ከዚህ በላይምን ሰላም አለ የኔ ልጅ አንቺም ሀላፊነቱ እየወረደልሽ
ነው» አሉና እንደውም ወደ ክብረመንግስት የሚደረገውን ጉዞም እኔም ብቀላቀልበት ደስ ይለኛል» ከሏት ይውጣላት ብለው።

«ጎሽ እማማ ዘነብ» ብላ ታፈሡ
ኪ..ኪ..ኪ..ኪ ብላ ሳቀች
«ተማክራችሁበታላ» ሸዋዬ በንዴት
«ጣድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ» ሲባል አልሰማሽም በዚያውም ልብ ያለው ልብ ያርገው ማለቴ ነው» ካሉ በኋላ ወይዘሮ ዘነቡ«ይህን ቡና ቶሎ ቶሎ በዮው አንቺ ልጅ »አሉ ወደ ጀበናው እየተመለከቱ። በእርግጥ ቡናው ደርሶ ነበርና መቀዳት ጀመረ ።

«ሸዋዬ ቅር አይበልሽ!» አለቻት ታፈሡ አሁንም ፈገግ ብላ እያየቻት::

ሽዋዬ ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥሯ ውጭ እንደሆነ ተገነዘበች፡፡ በዚያችው ቅፅበት ባርናባስ ትዝ አላት፡፡
ሰሞነን ይነጋገሩበት የነበረ አንድ ጉዳይ አለና ሳንቀደም ቅደም በርሄ' አለች በሆዷ።
ቡናው ተጠጥቶ ሲያልቅ ለእለቱ ሔዋን ከእህቷ ጋር ወደ ቤቷ ተመለሰች።በተበጀላት ወጥመዶ ውስጥ ትግባ አትግባ ገና የሚታወቅ ነገር የለ። እሷ ግን መጠመዱን እንኳ አታቅም...

💫ይቀጥላል💫
👍8😱2
#የፀሎት_ለውጥ

ለፍተህ ጥረህ ብላ
የሚል ትዕዛዝህን ህግህ ተከትዬ
እጠባበቃለሁ
የማጥመጃ መረብ ከባሕረ ጥዩ
እንግዲያው ፈጣሪ...
የኔ አቅም ይህቺ ነች
ገመድ አጠላልፎ
ባሕር ሳይ ከመጣል በላይ ያልዘለለች

በል ፀሎቴን ስማ...
በጣልኩት መረብ ላይ የዓሳ ዘር ይሙላ
ወገኔ ይደሰት እስኪጠግብ ይብላ

ብዬህ ነበር...

አሁን ግን...
የጣልኩትን መረብ መልሼ ሰበሰብኩ
ጠግቤ ለማደር ሌላ መንገድ አሰብኩ
ምክንያቱም.....

እኔ መረብ ጥዬ
ዓሳ ስጠኝ እያልኩ እየተማፀንኩኝ
ከመረብ ጠብቀኝ
ብሎ የፀለየውን ዓሳውን አሰብኩኝ

የባሕሩ ዓሳ እንዲህ ሲለምንህ
እኔ እሱን ባጠምደው
ያንተን ጠባቂነት ነውና ማወርደው
ስለዚህ አምላኬ...
አዲሱን ልመና ፀሎቴን አድምጠኝ
የነፍሳትን ፀሎት
ማይጋፋ እንጀራ ምረጥና ስጠኝ

🔘ልዑል ሀይሌ🔘
👍8
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


... እሷ የሽማግሌዎቹ ቁርጥ ሳይታወቅ፣ ከጥላዬ ሌላ ለማንም እንድትሰጥ አትፈልግም። ብቻ አባባ ለዝኸ ትኩር ብሎ ሲያየኝ ለነበረው ሰውየ እንዳይሰጡኝ አለች፣ ኢሳያስን እያየች።
ተጨነቀች፤ ተጠበበች፣ ብረሪ ብረሪ አላት። ኸጥላዬ ጋር ተያይዘን እንጠፋለን እንጂ እሱን አላገባም አለች።

እሷ ይህንን ስታሰላስል አባቷ አላስችል ብሏቸው እንግዶቹ
ተመልሰው የመጡበትን ምክንያት በዘዴ ለማወቅ፣ “ኸጐንደር ነው
ኸሌላ የመጣችሁ?” ሲሉ ጠየቁ።
የወለተጊዮርጊስ ጀሮዎች ተነቃቁ።
“ኸጐንደር ነው የመጣን” አለ ኢሳያስ። ትንሽ ካመነታ በኋላ፣
“እንግዲህ እንንገርዎ እንጂ” አለና አብረውት የመጡትን ተመለከተ።
የተግባቡ መሰለው። ፊቱን ወደ ግራዝማች መልሶ ፈገግ አለ። ዐይን ዐይናቸውን እያየ፣ “ግራማች… የዛን ዕለቱ እመምተኛ እኮ ንጉሡ ራሳቸው... አጤ በካፋ ነበሩ” አላቸው።

ግራዝማች ከመደቡ ላይ ተወርውረው ተነሡና፣ “በወፍታው!” አሉ፤ ሰንበት የሚሳለሙትንና በየዓመቱ የሚዘክሩትን ደብራቸውን ወፍታ
ጊዮርጊስን ጠርተው።ራሳቸውን በሁለት እጆቻቸው ይዘው፣ “ጃንሆይ ራሳቸው? እኛ እንደ
ዋዛ ኸዝኸ ተኝተው የነበሩቱ?” አሉ፣ ተቀምጠውበት የነበረውን መደብ በሌባ ጣታቸው እያመለከቱ።

ግራዝማች በህመምና በሐዘን ምንክንያት የንጉሠ
ነገሥቱ የንግሥ ሥርዐት በተከበረበት ወቅትና በበዓል ጊዜ ንጉሠ ነገሥቱን በዐይን ለማየት ዕድል አግኝተው አያውቁም ነበርና ንጉሠ ነገሥቱን ባለማወቃቸው አዝነው ራሳቸውን ነቀነቁ።

“ምነዋ እንደዝኸ ጉድ ትሠሩኝ? እንዲያው እንዴት ያለ ፌዝ ነው
ምትነግሩኝ? እንዳው በወፍታው ምን ጉድ ነው ምትነገሩኝ?” እያሉ
ራሳቸውን በሁለት እጆቻቸው እንደያዙ ቆመው ቀሩ። ሰውነታቸው ብርክ እንደያዘው ተንቀጠቀጠ፤ ትከሻቸው ላይ ያጣፉት ጋቢ ወርዶ መሬት ነካ።

የተነገራቸው ቀልድ መሆኑን የሚያረጋግጥላቸው የፈለጉ
ይመስል ዐይኖቻቸውን ከአንዱ እንግዳ ወደ ሌላው አፈራረቁ።
እንግዶቹ በሁኔታቸው ተደናገጡ። እንኰዬ ባላቸውን እንባ ቀረሽ
ተመለከቱ፤ ተነሥተው ጋቢያቸውን ሊያስተካክሉላቸው ፈልገው
መነሣት አቃታቸው።

“በተክልየ ይቀመጡ ግራማች” አላቸው ኢሳያስ፣ ሁኔታቸው
አስደንግጦት።

ግራዝማች ራሳቸውን እየነቀነቁ ለመራመድ ዐቅም እንዳነሳቸው
ሁሉ ጋቢያቸውን ሰብሰብ አድርገው ቆም አሉና ጉልበታችው
የከዳቸው ይመስል፣ በሁለት እጃቸው ደግፈውት ተመልሰው መደቡ ላይ ተቀመጡ። የሚሉትን ቀርቶ የሚያስቡትን ማወቅ ተስኗቸው፣ ግንባራቸውን ኩምትር አድርገው፣ ዐይኖቻቸውን መሬት የተነጠፈው አጎዛ ላይ ተክለው ቀሩ።

ወይዘሮ እንኰዬና እናታቸው ትኩረታቸው ግራዝማች ላይ ነበርና
መቀመጣቸውን ተከትለው ዐዲስ እንደሰማ፣ “በቁስቋሟ!” አሉና
እርስበርስ ተያዩ። ወለተጊዮርጊስም በቁስቋሟ ብላ አማተበች። አያቷ ሆኑ ቅድመ
አያቶቿ የሚያከብሯትን፣ የሚማጸኗትን፣ የሚዘክሯትን፣ ባለውለታቸውን፣ በዕለተ ቀኗም ብዙ ድል የተቀዳጁባትንና እሷ ራሷም ብትሆን “ግጥሜ”
የምትላትን ቁስቋም ማርያምን ጠርታ። በግራ እጇ ኣፏን ይዛ፣ ንጉሡ ራሳቸው እኛ ኸዝኸ ኸመደብ ላይ ተኝተው የነበሩቱ? እኛ ፊታቸውን ሳጥብ፣ አጥሚት እየሠራሁ ሳጠጣ... እጃቸውን ሳስታጥባቸው የነበሩቱ
እንዴት ብለ? ንጉሡ ራሳቸው? ጉድ ጉድ! የዛሬውስ ቀን ምንያለውን ጉድ ይዞ መጣ እናንተዬ? አለች፣ መጋረጃውን ለቃ፣ ራሷን በሁለት እጆቿ ይዛ። ጥቂት ቆይታ መጋረጃውን እንደገና አጋጥማ ይዛ ወደ እንግዶቹ ተመለከተች፤ ያወጋሉ። የሚሉትን ለመስማት ሞከረች።
ሐሳቧ ግን አልሰበሰብ አለ።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሕመምተኛ የነበሩት፡ የአሁኑ ንጉስ። ፊቷ ላይ ድቅን እያሉ አስቸገሯት። መላ ቤተሰቡ ንጉሥ መሆናቸውን እንዴት ሳያውቅ፣ ሳይጠረጥር እንደቀረ ገረማት። ነገሩን በቅጡ ለመመርመር ሐሳቧ ወደ ኋላ ነጎደ።....

የመጡ ቀን፣ እንደ ልማዷ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ተቀምጣ የእነዚያን
የአስታራቂ ሽማግሌዎች መምጣት ትጠባበቃለች። ግቢው መግቢያ ላይ ሰዎች ስታይ ብድግ አለች። “እረ የታመመ ሰው ነው መሰል ይዘው የመጡ” አለች፣ ዛሬ ከመጡት እንግዶች ውስጥ ሁለቱና ሌሎች ሁለት ሰዎች አንድ ሰው ደግፈው ድንገት ግቢው ውስጥ ሲገቡ አይታ።

“እነማ?” እያሉ እናቷ፣ አባቷና አያቷ ከውስጥ በችኮላ ወጡ።
በርግጥም የታመመ ሰው እንደመጣ ሲያውቁ ደነገጡ፣ “ግቡ! ግቡ!” እያሉ መንገድ ለቀቁ። ነፍጥ የያዙ፣ ፈረስና በቅሎ ሳይቀር ያስከተሉ በርካታ ሰዎች እየተገፋፉ ገቡ። ሁሉም የመረበሽ መልክ ይታይባቸዋል።
እምብዛም ግርግር የማያውቀው ግቢ ትርምስምስ አለ። የተረጋጋው
የእነግራዝማች ቤት ለወከባና ለድንጋጤ ቦታ ለቀቀ።

አራቱ ሰዎች ወደ ቤቱ ውስጥ ገብተው፣ አቅፈው ደግፈው ያመጧቸውን ሕመምተኛ መደብ ላይ አሳረፏቸው። ወለተጊዮርጊስ፣ እኚህ መሣሪያ የያዘ ወጀብ የተከተላቸውና በጽኑ የታመሙ የሚመስሉት ሰው ማን መሆናቸውን ለማወቅ እጇን ደረቷ ላይ አድርጋ ተመለከተች፤ ግንባሯ
ኩምትር፣ አፏ ከፈት ብሏል። እናቷ፣ “ወለቴ እስቲ ውሃ” ሲሏት
በፍጥነት ወጥታ በቅምጫና አምጥታ አቀበለቻቸው።
ያን ሰዐት፣ ዙርያውን በቆሙት ሰዎች መሃል፣ ባለ ንቅሳት አንገቷን
ሰገግ አድርጋ ሕመምተኛውን አየች። በጽኑ እንደታመሙ አስተዋለች፤
ይቃዣሉ፤ ይቃትታሉ፤ ይወራጫሉ፤ ብርክ እንደያዘው ይንዘፈዘፋሉ።
ሮጥ ብላ ከመጋረጃው ጀርባ ቡሉኮ አምጥታ ደረበችላቸው።

ሰውየው የመጣላቸውን ውሃ መጠጣት ቀርቶ ዐይናቸውን መግለጥ ሆነ አፋቸውን መክፈት አልቻሉም። ግራዝማች መንበር ተደናግጠው፣
“ምንን ሁነው ነው? እመማቸው ምንድር ነው? እያሉ ከወተወቱ በኋላ፣ አንደኛው እንግዳ፣ “ንዳድ ሳትሆን አትቀርም። ቆላ ሲወርዱ ነድፋቸው ፊት ታመው ያቃሉ። ኸናንተ ዘንድ ይዘነ መጣነ” በማለት መልስ ሰጡ፣ ንጉሠ ነገሥቱን ይዘው ማንም ሰው ቤት ስለማይገቡ፣ ቋራ ውስጥ
የታወቁት ባላባት ቤት የትኛው እንደሆነ ጠይቀው የመጡት መሆኑን ሳይናገሩ።
ግራዝማችም፣ “ኧረ ደግ አረጋችሁ፤ ስንኳንም መጣችሁ። ቤት የአብርሃምም ማዶል?” ብለው አደግድጎ የቆመውን አሳላፊ፣ “እስቲ ኸድና ያነን በሪሁንን ተሎ ይዘህ ና” አሉት፡
መድኃኒተኛው በሪይሁን ከመቅጽበት መጥቶ አንድ እጁን
ሕመምተኛው ግንባር ላይ አስቀምጦ ራሱን ነቀነቀ። ጉንጫቸውን ዳበስ፣ እጆቻቸውን ጨበጥ፣ ጨበጥ አድርጎ መልሶ እጁን ግንባራቸው ላይ አሳረፈና፣ “ንዳድ ነች” አለ።

“ተሎ በልና መዳኒት አርግላቸዋ” አሉ፣ አንደኛው እንግዳ።

በሪሁን ለሰውየው መልስ ሳይሰጥ በቅዎጫና ተቀምጦ የነበረውን
ውሃ ደጅ ወጣ ብሎ ቀነሰለት። ይዞት ከመጣው ከረጢት ውስጥ
የደቀቀ ቅጠል መሳይ ነገር ቆንጠር አድርጎ በውሃው በጠበጠና በርከክ ብሎ የሕመምተኛውን ጭንቅላት በአንድ እጁ ቀና አድርጎ በመዳፉ
ጋታቸውና ቆሞ ተመለከታቸው።
ይህ ሁሉ ሲሆን ሰውየው ዐይናቸውን አልከፈቱም፤ አንገታቸው ወደ አንድ ወገን ዘንበል ብሎ ተኝተዋል። የሚሆነውን ሁሉ የሚያውቁ
አይመስሉም።
“በሪሁን ሁሉም አልገባም። ኸመዳኒቱ ትጨምርላቸው?” አሉ
ግራዝማች መንበር፣ ከሰውየው አፍ ቀስ እያለ የሚንጠባጠበውን ፈሳሽ እያዩ።

በሪሁን፣ “ግድ የለም የገባው ይበቃል” ሲል ሰውየው አስመለሳቸው።
ወለተጊዮርጊስ ፈጠን ብላ ንፁህ ሀጨርቅና ውሃ አምጥታ የሰውየውን አፍ ጠራረገችላቸው፤ አካባቢውንም አጸዳች።

“መዳኒቱ ወጥቷል። እንደገና አርግላቸዋ” አሉ ግራዝማች፣ በሪሁንን።
“ትንሽ ይርጋላቸውና አረግላቸዋለሁ።”
መድኃኒቱን እንደገና ግቷቸው በርከክ ብሎ ተጠባበቀ፡፡ ሰውየው
አላስመለሳቸውም።
👍112
“ይረጋላቸዋል። እንቅልፍ ኻገኙ ምንም አይላቸው። ራስ ምታትም
ስለሚኖራቸው ራሳቸውን ደገፍ ማረግበት ጨርቅ ቢጤ ብትሰጡኝ” ብሎ እንኰየን ቀና ብሎ አያቸው።

ወለተጊዮርጊስ የአንገት ልብሷን ከትከሻዋ ላይ መንጭቃ፣ “እኼው...
አንተ አንገታቸውን ቀና አርግልኝ እኔ ራሳቸው ላይ ልሰርላቸው”
አለችው።
አንገታቸውን ቀና ሲያደርግላት፣ አንገት ልብሱን ጠበቅ አድርጋ
አሰረችላቸው። እንግዶቹ በቅልጥፍናዋ ተገርመው በአንድ ቃል፣
“ተባረኪ... ተባረኪ” አሏት።
በሪሁን፣ “ኸባሰባቸው ጥሩኝ። ኋላ ተመልሸ መጣለሁ” ብሎ፣ እጅ
ነስቶ ከግቢ ወጣ።

ሰውየው እንቅልፍ ሲጥላቸው እንግዶቹ ምግብ ቀረበላቸው። ከየት እንደመጡ ሳይናገሩ በልተው ጨረሱ።።
ወለተጊዮርጊስ ሰዎቹ ተራሰዎች እንዳልሆኑ አውቃለች። አነጋገራቸው የተመጠነ፣ ኮራ ያሉም ናቸው። ከእነሱም የበለጠ ሕመምተኛው የተለየ ላህይ አላቸው። ወጣት ቢሆኑም፣ ሰዎቹ የማያሳይዋቸው ክብር ተራ
ሰው እንዳልሆኑ ይናገራል። የጋሻ ጃግሬዎች፣ የሙስሊም ነፍጠኞችና ሠይፈ ጃግሬዎች ብዛት ብቻ ሳይሆን የያዙት ነፍጥ፣ ቀስትና ጦር ቁጥር ቀላል አልነበረም። ፈረሶቹና በቅሎዎቹም ያጌጡና ደሕና የተቀለቡ ናቸው። ሰዎቹ ይዘው የመጧቸው ድንኳኖች ተተክለው ማሩ፣ ቅቤው፣ አዋዜው፣ ጠጁና አረቄው ተራገፈ።ወለተጊዮርጊስ ይህንን ስታሰላስልና እኛ ሕመምተኛ እንግዳ አፄ በካፋ
በመሆናቸው ስትደነቅ፣ አንደኛው እንግዳ መናገር ስለጀመሩ ትኩረቷን ወደ እሳቸው አደረገች።

“ግራማች፤ “እንዴት ያለ ፌዝ ነው ምነግሩኝ ላሉት ፌዝ ስንኳ
ማዶል” ብለው አስተባበሉ። ቀጥለው፣ “ጃንሆይ አንዳንዴ ሰዋቸው እንዴት እንደሚኖር እየተዘዋወሩ ያያሉ። አደንም ይወዳሉ። የዛን ዕለትም እኮ ወደ ቆላ ወርደን ያልታሰበ ነገር... ያቺ ንዳድ ተነስታባቸው ኸርሶ ዘንድ አመጣችነ። አሁንም ተመለስነ። እንዳው ምክኛት ሆነች”
ካሉ በኋላ፣ ደንገጥ ብለው፣ ኢሳያስን የጎንዮሽ ተመለከቱት።
ኢሳያስም ለመናገር ጉሮሮውን ጠራርጎ፣ “የመጣነው” ሲል
ግራዝማች አቋረጡት።

“ኧረ ስንኳን መጣችሁ። ብቻ እንዳው እሳቸው መሆናቸውን
ሳናውቅ... ድንገት ሁኖብን እንደ ነገሩ ነበር... ለንጉሥ ሚገባ
አላረግንም” አሉ። ንጉሠ ነገሥቱ እሳቸው ቤት ለቀናት ተቀምጠው
መሄዳቸው በራሱ ትልቅ ክብር ቢመስላቸውም፣ ለንጉሥ የሚመጥን መስተንግዶ ማድረጋቸውን ተጠራጠሩ።

“ግራማች እጅጉን አስተናገዱን እንጂ። ኸያ በላይ ምን ያረጉ ኑሯል? ልዥዎትስ ብትሆን እንዳው እሳቸውን እንደዛ አርጋ ስታስታምም አይተን ተገርመንስ ማልነበር? እንዳው የልዥ አዋቂ” አሉ፣ አንደኛው እንግዳ ።

“ብቻ አውቀን ቢሆን ኑሮ ደግ ነበር። እንዳው መቸም...” አሉ፣
ግራዝማች መገረም፣ ድንጋጤ ሌላም ሌላም ስሜት በውስጣቸው ተራ እየወሰደ። አንተ የወፍታው እንዳው ያጎደልሁት ነገር ይኖር ይሆን አረ ለመሆኑ ያቺ ወለቴ በደንብ አስታማቸው ይሆን ልዤ ስንኳ ሚቀርባት የለም። ቤት አያያዝ እሷን ሚያህል አለ? የአያቷን ቤት ቀጥ አርጋ የያዘች እሷ ማዶለች እንዳው ማስታመሙን ለሷው ነበር
የተውነው ብየ ቢጨንቀኝ ነው እንጂ፤ ብለው ወደ መጋረጃው ሰረቅ አድርገው ተመለከቱ።
ኸያ በላይ እንዴት አርጌ ላስታምም ኑሯል? ደሞ እንደ ነገሩ ቢሆንም፣ መቸም ቤት ያፈራው አንድም አልቀረ። እንዴ ያነን ሁሉ ዐጀብ ለስንት ቀን ተቀበልኘ ኸያ ወዲያ ምን ልናረግ ኑሯል? አባባ እንዳው አለቅጥ ለሰው መጨነቅ ያበዛሉ አለች ወለተጊዮርጊስ፣ የሰማቻቸው ያህል። ትዕግስቷ አለቀ። እንግዶቹን አንድ በአንድ ተመለከተቻቸው።

ይልቅስ የመጣችሁበትን ጉዳይ ተናገሩ! አለች።.....

ይቀጥላል
👍10
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ... እሷ የሽማግሌዎቹ ቁርጥ ሳይታወቅ፣ ከጥላዬ ሌላ ለማንም እንድትሰጥ አትፈልግም። ብቻ አባባ ለዝኸ ትኩር ብሎ ሲያየኝ ለነበረው ሰውየ እንዳይሰጡኝ አለች፣ ኢሳያስን እያየች። ተጨነቀች፤ ተጠበበች፣ ብረሪ ብረሪ አላት። ኸጥላዬ ጋር ተያይዘን እንጠፋለን እንጂ እሱን አላገባም አለች። እሷ ይህንን ስታሰላስል አባቷ አላስችል ብሏቸው እንግዶቹ…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

..አንድ ወር ተኩል አላፈ፡፡ አስቻለው ከደረሰበት የመኪና አደጋ ጉዳት አገግሞ ዲላ ከተመለሰ አስር ቀን ሆኖታል።
የወዳጆቹን የእንኳን አተረፈህ
የመልካም ምኞቱ መግለጫ ተቀብሎ ጨርሷል፡፡ ዲላ በገባ ሶስተኛው ቀን ላይ ከሔዋን ጋር ተገናኝተው የሰቀቀን እንባቸውን አፍስሰዋል። የአስቻለው የአጥንት ስብራትና በቆዳው ላይ ተከስቶ የነበሩ ቁስለቶች ፈጥነው የሻሩ ቢሆንም በተለይ በቀኝ እግሩ ጣቶችና በግንባሩ እካበቢ የደረሰበት ጉዳት ጠባሳቸው ባለመጥፋቱ የሔዋንን አንጀት አላውሰውታል። በእጇ እየዳበሰቻቸው በመሳቀቀ ያወረደችው እንባ ከአስቻለው እዕምሮ ምንጊዜም አያጠፋም፡፡ እሱም ቢሆን ባለፈው ጊዜ ከእሱ ጋር በማደሯ ምክንያት ተፈጥሮባት የነበረውን ችግር ሰምቶ
አሳዝኖታል።

ዛሬም ሲገናኙ ቀጠሮ ነበራቸው፤ በሚያዚያ ወር ሁለተኛ ሳምንት ላይ በዕለተ ሰኞ፡ አስቻለው በሀኪም ዕረፍት ሳይ ስለሆነ ስራ አይገባም፡፡ ዕለቱ ደግሞ ለአስራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወሳጆች የፈተና አስራር ማብራሪያ
የሚሰጥበት በመሆኑ ሔዋን ከማብራሪያው በኋላ ወደ ቤቱ ብቅ ብላ ልታየው ቃል ገብታለት ነበር፡፡ ነገር ግን ትናንት ምሽት ላይ በልሁና መርዕድ በአስቻለው ቤት
ጫት እየቃሙ ሳሉ ታፈሡ ድንገት ብቅ ብላ «አስቹ» ብላው ነበር፡፡
«ወይ»
«ነገ ከሔዩ ጋር ልትገናኙ ቀጠሮ ነበራችሁ አይደል!? »
«አዎ»
ቅድም
ቅድም መንገድ ላይ አግኝቻት ስላልተመቸኝ አልመጣምና
እንዳትጠብቀኝ ብላሀለች» በማለት መልዕክት አድርሳለታለች በዚህ መሰረት አስቻለው ዛሬ ስለ ቀጠሮው ማሰብ ትቶ ማርፈጃውን ሁሉ አልጋው ላይ ጋለል እንዳለ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳብ ያውጠነጥን ጀመር፡፡ ከምንም ባላይ አልረሳ ብሎ ያስቸገረው የደረሰበት የመኪና አደጋ ነው። በአደጋው የተጎዳ ሰውነቱ
ቢያገግምም መንፈሱ ግን ክፉኛ ቆስሏል። ሀገርና ወገኑን በሙያው እያገለገለ በሰላም ሰርቶ በሰላም ውሎ ማደር ሲችል ነገር ግን በእሱ አመለካከት ለምንም ነገር
በማይበጁ፤ ለክፋትና ለተንኮል ብቻ በተፈጠሩ እብሪተኞች አስተዳደራዊ ተፅዕኖ
በመማረር አካባቢውን ለቆ ለመሄድ ለዝውውር ጥያቄ ሲጓዝ ያን የመሰለ አሰቃቂ አደጋ ደርሶበት ለጥቂት መትረፉ ትዝ ባለው ቁጥር ዝግንን ይለዋል። ሁል ጊዜ ይቆጨዋል። ዘወትር ያበሳጨዋል፡፡ ሞቼስ ቢሆን ኖሮ? እያለ ሲያስበው እልህና ንዴት እየተናነቀው መንፈሱ ውጥርጥር፣ ውስጡ እርር ድብን እያለ ከንፈሩን
እያስነከሰ ራሱን ያስወዘውዘዋል፡፡ የአስቻለው ችግር ይህ ብቻ አይደለም፤ ያለፈውን
እንዳለፈ ቆጥሮ መጽናናት እንዳይችል እንኳ ሌላም አደጋ ከፊቱ እንደተደቀነበት ያወቀው ገና ህክምናውን ጨርሶ ዲላ በገባ ማግስት ነበር።
በመሰረቱ የዶክተር ደጀኔ አሜሪካ መግባት እርግጥ ሆኗል። በእሱ እግር የተተካው የዲላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ደግሞ ከመልካቸው በስተቀር በአስተሳሰብ ከባርናባስ ወየሶ ጋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። እንዲያውም በመላ የሆስፒታሉ ሰራተኞች አፈራረጅ ከበርናባስ የባሰ አኘር አጥፊ
የተባለ ሰው ነው። ለአስቻለውማ ጭራሽ ሰው የሚበላ የስው አውሬ!
አዲሰ ሹመኛ በሙያው ዶክተር ቢሆንም በባህሪው ግን ወትሮም ካድራ ካድሪ የሚሸት ነበር። በሚናገርበት መድረክ ላይ ሁሉ የሚሰነዘረው ሃሳብና ሀሳቡን
የሚገልፅባቸው ቃላት ስልጣን
መለመኛ ይመስላሉ፡፡ አንዳንዴ ሊፈላሰፍም የሚቃጣው ነው
ነገር ግን ከባዶነቱ የተነሳ የጀመረውን ዐረፍተ ነገር እንኳ በግስ መዝጋት የማይችል
ግብዝና ዘባራቂ ዓይነት ሰው ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ ስልጣን
አግኝቷልዐተናግሮ ማሳመን ባይችል ተናጋሪዎችን ዝም ፀጥ የሚያሰኝ በትር" አዎ ስልጣን! በእብሪተኞች ጎራ በተስላፉ ደንቆሮዎች እጅ በገባ ቁጥር የሩቅ አሳቢ አሰተወዬችን የሚቀላ ሰይፍ

አስቻለው በዚህና በዚሁ ዙሪያ ሲያስብ ሲያሰላስል ቆይቶ የተሰማው ንዴትና ቁጭት አዕምሮው ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ሲሆንበት ትንሽ የሚቀለው
መሰለውና ከመኝታው ሊነሳ አንሶላና ብርድ ልብሱን ከላዩ ላይ አስቀጥሮ ጣለው፡፡ ሱሪና “
ጫማውን እንዲሁም ሽሚዙን ለበሰ፡፡ ጥርሶቹ ግን ከንፌሩን ንክስ እንዳደረጉ ናቸው፡፡ ጭንቅላቱን ደጋግሞ እየወዘወዘ ፊቱን ሊታጠብ ውሃ ይዞ ወደ በረንዳ ወጣ።

ስዓቱ ከሶስት አለፍ ብሏል። አስቻለው ታጥቦና አበጥሮ ከጨረሰም በኋላ ወደየትም መሄድ አልፈለገም። የቁርስ ሰዓት አልፏል። ቀዽሞ ነገር ሆዱም እህል አላስኘውም። ወንበር ይዞ ከቤት ወጣና ጀርባውን ለፀሐይ ሰጥቶ ግቢው ውስጥ ቁጭ አለ።

ፀጥ ረጭ ብሎ የዲላ ህይወቱን ሲያሰላስለው በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ምቾት እንደማይሰጠው ተሰማው። ቢሆንም ባይሆንም አንዲት ተስፋ ብቻ ታየችው። ዶክተር ደጀኔ በገባለት ቃል መሰረት የአዲስ አበባውን ባለስልጣን አነጋግሮለት ኖሯል፡፡ አስቻለው ከሆስፒታል እንደ ወጣ ወደ ፅህፈት ቤቱ በመሄድ ያን ባለስልጣን አግኝቶታል። እሱም ዶክተር ደጀኔ በገለፀለት መሰረት የአስቻለውን ችግር እንደተረዳለትና ሊያዛውረው እንደሚችል ቃል ገብቶለታል። ግን ደግሞ ይህን
ተስፋ የሚያጨልሙ ሁኔታዎች ከአስቻለው እዕምሮ ውስጥ ድቅን ይላሉ።
ከአሁን በፊት ስለ ዝውውር ጉዳይ ከዶክተር ደጀኔ ጋር ሲነጋገር ...የት
ቢኬድ ይሻላል? ባለው ጊዜ ዶክተር ደጀኔ ... መሄጃው ላይገድ ይችላል፤ ችግሩ የተሻለ ሁኔታ ከማግኘቱ ላይ እንደሆነ እንጂ ብሎት ነበር፡፡ እንዲህም ለዝውውር ጥያቄ ወደ አዲስ አበባ በሚሄድበት ጊዜ በመኪና ጉዞ ላይ ከሟቿ ከወይዘሮ አቦነሽ
ሀይሌ ጋር ሲነጋገር ወይዘሮ አቦነሽም ለመሆኑ እነሱ የሌሉበት አገር አለ እንዴ?? ብለውት እንደነበር አስታወሰ፡፡ በዚሁ አጋጣሚ የወይዘሮ አቦነሽ ሓይሌ እና የጠይሟ ልጃገረድ ሞት ትዝ አለውና አሟሟታቸው አሳዝኖት በሀዘን ስሜት ከንፈሩን መጥጦ ራሱን ወዘወዘና ወደ ንዴቱና ብስጭቱ ተመለሰ።
«ቆይ ግን!» አለ ድንገት ጮክ ባለ ድምፅና በእልህ አነጋገር። ምናልባት ፀሐዩም በዝቶበት ሊሆን ይችላል፤ ከተቀመጠበት ወንበርም ላይ ፍንጥር ብሎ፣
ተነሳ፡፡ አንገቱን ደፋ አድርጎ በዚያው በግቢው ውስጥ ጎርደድ እያለ «ሰው በገዛ ሀገሩ በሰላም ሰርቶ በሰላም መኖር ላይችል!? » አለና መልስ የሚጠብቅ ይመስል
ፀጥ ብሎ በመቆም አቀርቅሮ መሬት መሬት ያይ ጀመር፡፡ ብስጭቱ ጨመረና
«ቀድሞ ነገር ንዴትስ ለምን? ብስጭትስ ለምን? በምሪት የተነሳ የዝውውር ጥያቃ ለምን? ይህ ሁሉ ጣጣ የመጣው ሰዎች በሌላ ሰው ኑሮና ህይወት ላይ ይወስኑ
ዘንድ ገደብ የሌላው ስልጣን ስለ ተስጣቸው አይደል!» አለ በንዴት ስሜት እጆቹን ጥብቅ በመጨበጥ ሰውነቱንም በእልህ እያጠነከረ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያያዘና
ሰፊዋ ሀገር ኢትዮጵያ እንደ ኳስ ተድቦልበላ እዕምሮ ውስጥ ድንገት ዘው ብላ ገባች፡ በሀሳብ፡፡ እንደ እሱ በበደልና በእንግልት ቁም ስቅላቸውን አጥተው
የሚሰቃዩና የሚያለቅሱ ዜጎቿ አብረው ገቡበት፡፡ ነዢዎችና አጫፋሪዎቻቸውም አልቀሩ ከነድንፋታቸው፣ ከነጭካኔያቸውና እነቅጥፈታቸው እየገቡ ታጨቁበት።በሆድና በህሊና ጎራ ለሁለት የተከፈሉ የአንድ ሀገር ዜጎች በአዕምሮው ውስጥ ገብተው እየተን፡ እየተንጬጩ ተርመሰመሱበት፡፡ በዚህ እስጨናቂ ስሜት ውስጥ ሲገባ
👍7
ከመንፈሱም በላይ የአካል ድካም ተሰማው ወገቡ ተንቀጠቀጠ፡፡ መቆምም አቃተው። ያን ፀሐይ ላይ የነበረ ወንበር ወደ ጥላ ቦታ ወሰደና ቁጭ አለ፡፡ የሀሳብ ሸክሙን ያቀለለ መስሎት « ኡህህህ» ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ።
«አንቺ ኢትዮጵያ!» አለ ትንሽ ቆይቶ። ሀገሩን ሊወቅሳት ይሁን
ሊያለቅስላት ገና ሃሳቡን አላዘጋጀም፡፡ ብቻ ከንፈሩን ንክስ አድርጎ ራሱን ወዘወዘ፡፡
ከትንሽ ቆይታ በኃላ ግን ከራሱ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ የሚያዳምጠው
ቢኖር እስከ ውጭ ድረስ በሚሰማ ድምፅ «አንቺ አገር አንቺ ኢትዮጵያ፣ እስከ መቼ ይሆን ጥቂቶች ሲፈነጩብሽ፣ ብዙሃን ሲያለቅሰብሽ፣ እብሪት እንደነገሰብሽ፣ ፍትህ እንደጎደለብሽ የምትኖሪው? ከቶ መቼ ይሆን ደም ያልተቃቡ መንግስትና ሕዝብ የሚኖሩብሽ? እኮ እስከ መቼ!? » ካለ በኃላ አሁንም ትንሽ ተንፈስ ብሎ
«በእርግጥ እብሪት ለማስተዋል፣ ተንኮል ለግልጽነት! ውሸትና ቅጥፈት ለሀቅና ለእውነት ቦታቸውን ሰተው የሰላምና የነፃነት አየር የሚተነፍስብሽ ሀገር ለመሆን ያበቃሽ ይሆን? በእርግጥ የእናትነት እቅፍሽ ለሁሉም ዜጎችሽ እኩል የሚሞቅበት ጊዜና ዘመን ይመጣ ይሆን!? » አለና ላነሳቸው ጥያቄዎች ሁሉ መልስ የሚጠብቅ ይመስል ዝም ፀጥ፣ ፍዝዝ ትክክዝ እንዳለ ለደቂቃዎች ያህል ቆየ፡፡ በሀሳቡ ግን ሌላ
ነገር ያሰላስል ነበርና እንደገና መናገር ጀመረ። «ደግሞ እኮ አያፍሩም!» አለ በመሳቅ
ዓይነት በደረቁ ፈገግ እያለ፡፡ በዚህ ጊዜ ትዝ ያለው ገዢዎች ከመጋረጃ ጀርባ ያላቸውን ድብቅ አጀንዳ ይበልጥ ለመሸፈንና የአኮረፈ ሕዝብ ለመደለል ሲሉ
በቁጥጥራቸው ስር በአደረጉት ራዲዮና ቴሌቪዝን አዘውትረው የሚወሻክቱት ባዶ ተስፋ ነው፡፡ እናም ይህንኑ በራሱ ቃል ይናገረው ጀመር፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ አገራችን፣ የአሥራ ሦስት ወር ፀጋ! ይሏታል! ደሞ የመከራ ቀን ሲያራዝሙ! (አገራችን ኢትዮጵያ ፡ የሰው ዘር መገኛ ይሏታል! ነገር ግን ነሮውን አጐሳቅለው፣
አስተሳሰቡን አዛብተው፣ አመለካከቱን አላሽቀው በሁሉም ነገር ከዓለም ህዝብ ሁሉ
ወደ ኋላ የቀረ ሕዝብ የሚኖርባትን ሀገር ለምለሟ ኢትዮጵያ» ይሏታል፤ ድርቅና ረሀብ መለያዋ ሆኖ ዓለም በሚያውቀው መዝገብ ላይ በምሳሌነት ስሟ እንዲመዘገብ ያደረጓትን ያልታደለች ሀገር! የነፃነት ተምሳሌት ይሏታል፤ ነገር ግን ላይናገር የታፈነ፣ ላያይ ዓይኑ የተጋረደ፣ ሳይላወስ እግር ከወርች የታሰረ ሕዝብ የሚኖርባትን የሲኦል አምባ!» ላይኖሩብሽ የሚፈጠሩብሽ አገር!» አለና ለአፍታ ያህል ፀጥ ብሎ ሀሳቡን ሲያዳምጥ ቆየና ድንገት «ኤድያ»
በማለት እጁን አወናጭፎ ከወንበሩ ብድግ አለ፡፡ ሁለት
እጆቹን በሁለት የሱሪ ኪሶቹ ውስጥ ከትቶ በዚያው አካባቢ አጎንብሶ ጎርደድ እያለ
«ላይኖርብሽ የሚፈጠሩብሽ አገር» አለ አሁንም።

ሀሳቡ ሁሉ ከዚሁ ጉዳይ ሳይርቅ አንዳንዴ መሬት መሬት ሌላ ጊዜ ሰማይ ሰማይ እያየ እንደገና ራመድ ጎርደድ ሲል ደቂቃዎችን
አሳለፈ፡፡ አልፎ አልፎም
በልቡ እያራ ከንፈሮቹ፣ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በዚህ ጊዚ ብሶቱን መግለጫ የሚሆኑ አንዳንድ ቃሎችና ሐረጎች ውስጥ ውስጡን ይንገዋለልበት ጀመር፡፡ በልቡ
አመላለሳቸው፡፡ እያደር ነፍስ እየዘሩ ይሄዱበት ጀመር። እሱም ስጋ ሊያለብሳቸው ድንገት ከሃሳቡ እንደመባነን እለና ፈጠን ቀልጠፍ ብሉ ወንበሩን ይዞ ወደ ቤት ገባ፡ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ አለና ብዕርና ወረቀት አዘጋጀ፡፡ መሞነጫጨር
ጀመረ፡፡

«ህሊና ታሰረ ከወይኒ ወረደ
አእምሮኖ ተክቶ ሆድ እየፈረደ።
ሲያለቅስ አገኘሁት ህግ ተንሰቅስቆ
መክሰስም መፍረድም ለአንድ ሰው ተለቆ፡፡
ጊዜ በቅሎህን ጫን ገስግስ በፈረስ፡፡
እውነት ዳኛ ትሁን ተራዋ ይድረስ፡፡
ይኽ ለሊት ይንጋ እንይ ያ ቀን መጥቶ፡-
ሁሉም እንደ ስራው እንዲበላ አንጉቶ፡፡
ዝምታ ወርቅ ነው ያለው ሰው ይሙት፡

አገር ይዞ ጠፍቷል ሁሉን ፀጥ አርጎት፡፡
እርጥብ ደረቅ በልተህ የጠገብክ መስሉሀል፡-
ወገኔ ልንገርህ እውነት ተርበሀል።
ምነዋ ሰው ሆዬ ሰው መሆነን ተውከው፡-
ቁንጫ ትኋኑ ሲበላህ ዝም አልከው።
መኖር ስቃይ ሲሆን መከራ ጎራ አክሎ፡
ሞትም ጀግንነት ነው እምቢ አልኖርም ብሎ፡፡»

አስቻለው የራሱ ስንኞች ለራሱ ደስ አሉት። እንዲያውም አንዳንዶቹ
ቃለችና ሀረጎች ልክ እንደ እሱ ሲያለቅሱ ተስሙት። ሌሎቹ ደግሞ ሲጣሩ!ለዚያውም ከፍ ባለ ድምፅ፡፡ ስንኞቹ የራሱ ናቸውና እሱን እሱን ሽተቱት።
«ለካ!» አለ አስቻለው አሁንም ለራሱ በመናገር፡ ሰው ብዕርና መወረቀት የሚያነሳው ወዶ አደለም የሀሳብ እጭቃ አእምሮውን ሲወጥረው ቀነስ አድርጎ ለመተንፈስ ነው አልያም ሀሳብ በገዛ ሀይሉ ሞልታ ሲፈስስበት በዚያ አጋጣሚ የደራሲ ሀይወት በትንሹም ቢሆን ገብቶት ሊሆን ይችላል የደራሲ
ሕክፍ! እርርም እድርጎ ለማስቀመጥ ሲፈልግ ነው፡፡» አለና ምናልባት በዘሁ አጋጣሚ
የደራሲ ሕይወት በቶኝሹም ቢሆንና ገብቶት ሊሆን ይችላል
«የደራሲ ኑሮ ሕይወት እንዴት ነው ሁል ጋዜ መጨነቅ? ሁልግዜ መጠበብ? ይገርማል እያለ ራሱን ደጋግሞ ወዘወዘ።

ሰዓቱ ወደ ስድስት ተጠጋ የአስቻለው አንጀት እህል እህል ማለት ጀመረ። ምሳ ትዝ አለው። እርግጥ መንፈሱንም ማሳረፍ ፈለገ፡፡ ያቺን ግጥም የፃፈበትን ወረቀት በስነ ስርአት አስቀመጠና
ከወንበር ላየሰ ብድግ ብሎ ጃኬቱን ደረበ ቤቱን ቆልፎ ቀጥታ ወደ ዋርካው ምግብ ቤት አመራ።
ወትሮም ቢሆን አስቻለውና ጓዴኞቹ ለምሳ አይጠባበቁም እንደያ ስራቸው ባህሪ ነስራ መግቢያና መውጫ ሰዓታቸው ስለሚለያይ ሁሉም በየደረሱበት ሰዓትና ደስ ባላቸው ምግብ ቤት ነው የሚበሉት፡፡ እስቻለውም ማንንም ሳይጠብቅ ቆርሱን
ምሳውን በአንዴ በላ፡፡ ቀዝቀዝ ያለ ውሃ ጠጥቶ ቡና ሲጨምርበት መንፈሱም ተረጋጋ።
በዚያው ምግብ ቤት ውስጥ ትንሽ
ለመቆየት ፈልጎ ነበር፤ ነገር ግን
በተለይ ዛሬ ማርፈጃውን እንደ ዱቄት ሲፈጨው ከነበረ ሀሳብ ጋር የማይጣጣሙ ሁኔታዎች ተከሰቱበት። በርካታ ሀሳብ የለሽ የሆኑ ወጣቶችና ጎልማሶች በሆነ
ባልሆነ ወሬ ሲያዋክቡት ለስሜቱ አልመች አለው፡፡ አንዳንዶቹ ያቧርቃሉ፡ በሳቅ ይንከተከታሉ፤ በቀን በጠራራ ከሴት ጋር ይገፋሉ፤ ይዳራሉ። በዚያ ላይ ንፋሱ ፡
አባራው ! የሻይ ማሽን ሿሿታ፤ የራዲዮ፣ የቴፕ'... ወዘተ ጫጫታ ብቻ ሁሉ ነገር የአዕምሮ እረፍት አሳጣው፡፡ እዚህ ሁሉ ግርግር የሚገላገለውን ቦታ መረጠ!
የገዛ ቤቱን፡፡ ብድግ አለና በቀጥታ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ የተለመደ የዲላ ቀትር ፀሐይ አናት አናቱን እያለው ደረሰና ቤቱን ከፍቶ ገባ፡፡ ከዚያም ወደ አልጋው:: የተንዘረፈፈ ከንሶላና ብርድ ልብሱን ሰብሰብ አድርጎ ጫማውን ብቻ አመለቀና
በጀርባው ጋለል አለ፡፡ ደካከመው፡፡ እንደ እንቅልፍም ይሞካክረው ጀመር፡፡.....

💫ይቀጥላል💫
👍17
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሦስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


...“ኸንጉሥ እጅ እንዴት እናመልጣለን?...”
ኢሳያስ፣ የሰማት ይመስል ወደ ጉዳዩ መግባት ፈለገ። አንዴ
ዮልያናንና እንኰዬን ሌላ ጊዜ ደግሞ ግራዝማችን ዐይኑን ተክሎ
ተመለከተ። ፊቱን ወደ ዮልያና አዞረና ፈገግታ ለገሣቸው።

ዮልያና የሆነ ነገር ሊነግረኝ ነው ብለው ጠረጠሩ፤ ለመስማት ጓጉ።

“እመቤቴ... ዋናው የመጣንበት ጉዳይ...” ብሎ እንደገና ሁሉንም
ተመለከተ። ቀጠለና፣ “እመቤቴ... ዋናው የመጣንበት ጉዳይ... ጃንሆይ...በተለይም እኔን ልከውኝ ነው። እርሶ እንዳሳደጓት ስላወቁ የልዥ ልዥዎን እጅ ስለፈለጉ እኼን ለማብሰር ነው የመጣን። ቅድም ግቢው መግቢያ ላይ ልዣችሁ መሬት ላይ ጦር ሲተከል አይታ፣ ደንግጣ ነው መሰል፣ ኸተቀመጠችበት ተነሣች። ለበጎ እንደመጣን ንጉሥ እጅ ሲጠይቅ እንደሱ መሆኑን ሳታውቅ ቀርታ” አለ።

ወለተጊዮርጊስ አመዷ ቡን አለ፤ ሰማይ ምድሩ ዞረባት። ንጉሡ?
እንዴ ንጉሡ የኔን እጅ ሊጠይቁ? እንዴት ሁኖ አለች። እንግዶቹ የሷን
እጅ ሊጠይቁ እንደመጡ ደመነፍሷ ቢነግራትም ለንጉሥ ሚስትነት መሆኑ ግን ከግምት በላይ ሆነባት፤ ተደናገጠች፤ ተርበተበተች፤ ፊቷ የበሰለ ቲማቲም መሰለ፤ ጉንጮቿ ተቃጠሉ። ዐይኖቿን ጨፍና ራሷን
ነቀነቀች፤ ሊሆን አይችልም በሚል መልክ። አንዴ በኔና በጥላዬ
ማይመጣ የለም ማለት ነው? እንባ እንባ አላት። የምታስበው ጠፋት፣ ጭንቅላቷ ባዶ ሆኖ ተሰማት። ጣሪያው ላይ አፈጠጠች- ለዚህ አስደናቂ
ለሆነባት ጉዳይ መልስ ይሰጣት ይመስል። አያቷም በሰሙት ነገር ቢደናገጡም ስሜታቸውን ሰብሰብ አድርገው፣
“እኔ ላሳድጋት እንጂ የወለዱ እኮ እነሱ ናቸው” አሉ፣ መብረቅ
የመታቸው ያህል ድርቅ ብለው የተቀመጡትን ልጃቸውንና ግራዝማችን በአገጫቸው እያመለከቱ። “እነሱ ናቸው መጠየቅ ያለባቸው” አሉ፣
ራሳቸውን እየነቀነቁ።

ኢሳያስ፣ “ርግጥ ነው። የጃንሆይም ፍላጎት ያ ነው። ኻለነሱማ እንዴት ይሆናል? ለመቤቴም ለግራማችም ነው ጥያቄው የቀረበ። እመቤቴ..
ግራማች... ዛዲያ ምን ታስባላችሁ?” አለ። ንጉሥ ልጃችሁን ስጡኝ ሲል ለማንም ቢሆን ብስራት ነው የሚል ቃና ድምጹ ላይ አክሎበት።እመቤት እንኰዬንና ግራዝማች መንበርን በተራ ተመለከተ። የዮልያናን
ቅሬታ ያዘለ አነጋገር ማርገብ ችሎም እንደሆን ፊቱን መለስ አድርጎ አያቸው።

ዮልያና ግን ሐሳባቸው ሌላጋ ከንፏል። ከዓመታት በፊት አንድ
ሌሊት አይተውት የነበረውና ምንጊዜም ቢሆን ሲያስደንቃቸውና ላገኙት ሁሉ ሲያወሩት የነበረው ሕልማቸው ትዝ ብሏቸዋል።

ያን ሌሊት፣ እንደወትሯቸው ጸሎት አድርሰው ከተኙ በኋላ፣ ፀሐይ
ቤታቸው ሰተት ብላ ገብታ ተጎናጽፈዋት ተኝተው አዩ። ከእንቅልፋቸው ብንን ብለው ነቅተው ተቀመጡ። ባዩት ሕልም ተደነቁ። ጠሐይ ቤቴ የገባችው አለነገር ማዶል። ጠሐይ መሪ ነው፤ ብርሃን ነው ይላሉ፡፡
አገር ብርሃን ትሆናለች ማለት ነው። ግና እንዴት? አሉ፤ ለራሳቸው።

የሕልማቸውን ትርጉም ለማወቅ ተመራመሩ። መቸም አለምኸኛት
እንዲህ ያለ እልም አላሳየኝም፡፡ አንድ ነገር ቢኖር ነው። እስቲ ነገ
ጠዋት እኛ መነኩሴ ዘንድ ኸጀ ሚሉትን ሰማለሁ። አይ የነእንኰዬ
አባት በኖሩ። እሳቸው እኮ ኸኔ የተሻለ እልም መፍታት ይችላሉ እያሉ ሲገላበጡ አደሩ። እንቅልፍ ባይጠግቡም፣ ማለዳ ከመኝታቸው ተነሡ።ውዳሴ ማርያማቸውንና ዳዊታቸውን ደግመው መነኩሴውጋ ለመሄድ
ሲዘገጃጁ የደስ ደስ ስሜት አቅበጠበጣቸው። ቁርስ ላድርግ ሳይሉ አሽከር አስከትለው ወጡ።
መነኩሴው ወፍታ ጊዮርጊስ ግቢ ውስጥ ጥድ ስር ተቀምጠው
መቁጠሪያ ይዘው ይጸልያሉ። ዮልያና ወደቤተክርስቲያኑ ሄደው
ከተሳለሙ በኋላ፣ መነኩሴው ጸሎታቸውን እስኪጨርሱ ድረስ ፈንጠር ብለው ድንጋይ ላይ ተቀመጡ። መነኩሴው ጸሎታቸውን ሲጨርሱ፣
ለዮልያና እጅ ነሡ። ዮልያና ተነሥተው እጅ ነሥተው ሲቆሙ
እንዲቀመጡ መነኩሴው በምልክት ነገሯቸው።

ዮልያና ድጋሚ እጅ ነሥተው ጠጋ ብለው ተቀመጡ። ስለጤንነታቸው
ከጠያየቁ በኋላ፣ “ያው መቸም ኸርሶ ዘንድ ምመጣው አንድ ነገር
ሲገጥመኝ ነው። ዛሬ ስንኳ አንድ ዘመዴ እልም አይታ ሚፈታልኝ
ብትለኝ ነው የመጣሁት። ድቅድቅ ያለ ጨለማ ይመስለኛል አለች...
ጠሐይ ኸተኛሁበት ድረስ ገብታ ቤቴንና መላ ሰውነቴን አበራችው።
ኸያ በኋላ ጠሐይቱን ተጎናጽፌያት የተኛሁ ይመስለኛል ብላ ነገረችኝ።”

መነኩሴው በጥሞና ካዳመጡ በኋላ፣ “ብርሃን ሥልጣን ነው። እኼን እልም ያየች ሴት ንጉሥ ትወልዳለች” አሏቸው።
ዮልያና ደነገጡ። “እልሙን ያየችው ሴት ኸንግዲህ መውለድ
አትችልም። ዕድሜዋ አልፏል፤ የወር አበባም የላት” አሉ።

“ኸዘር ይፈጠማል። ኸልዥ ልዥም ይሆናል።”

ዮልያና በሐሳብ ከሄዱበት ተመለሱና እልሜ ገሀድ መሆኑ ነው። ድንቅ! የእዝጊሃር ፈቃድ ይፈጠም ብለው ልጃቸውን የጎንዮሽ ተመለከቱ። ወይዘሮ እንኰዬ ግን የቅድስት ወለተጴጥሮስን ንግርት
አስታውሰው እናታቸው እያይዋቸው መሆኑን ልብ አላሉም።

በአፄ ስሱንዮስ ዘመን የቆራጣ ገዳም እመምኔት የነበረችው ቅድስት ወለተጴጥሮስ መንገድ መሽቶባት ለአንድ ምሽት አያቶቻቸው ቤት ዐርፋለች። የቤቱ እመቤት ሌሊት ላይ ድንገት ምጥ ጸንቶባት ወደ በረት ተወስዳ፣ ሴቶች መቀነቻቸውን ወንዶች መታጠቂያቸውን ፈተው ሲጸልዩ፣ ወለተጴጥሮስም መቀነቷን ፈትታ ፊቷን ወደ ምስራቅዐመልሳ አጥብቃ ጸለየች። ሴቲቱም ወንድ ልጅ በደሕና ተገላገለች።
ወለተጴጥሮስ በማግስቱ መንገድ ከመጀመሯ በፊት፣ “ኸዝኸ እጣን ዘር መልካም ዝናው ሚነሣ ንጉሥ ይወለዳል። ንግሥቲቱም በሥራዋ ስሟ ሲወሳ ይኖራል። ኸዳር እዳርም አገሯን ታስከብራለች” ብላ ቋራን፣ “ምን ግዝየም አብቅይ፣ መልካም ፍሬ ይብቀልብሽ” ብላ ተሰናብታ ወጣች።

እረገኝ ንግሥቲቱ ወለቴ መሆኗ ነው። ንጉሡ ደሞ ኸሷ ሚወለደው ነው አሉ እንኰዬ።

ኢሳያስ “ምን ታስባላችሁ?” ለሚለው ጥያቄው መልስ ባለማግኘቱ ልጠይቅ አልጠይቅ እያለ ከራሱ ጋር እየተሟገተ ቆይቶ፣ “ዛዲያ ምን አሰባችሁ ግራማች?” አላቸው።
ግራዝማች መልስ መስጠት ፈልገው ምላሳቸው ተቆለፈ። “እ... እረ.. እንዳው...መቸም...” ድምፃቸው ተቆራረጠ፤ የጀመሩትን ለመጨረስ ቃል አጠራቸው።

ኢሳያስ ካቆመበት ቀጥሎ፣ “መቸም...” ብሎ ግራዝማችን አያቸው።
“መቸም ለልዥዎ ለንጉሥ ሚስትነት ኸመታጨት የበለጠ ዕድል ኸየት ይመጣል? የጐንደር ወይዛዝርት ሆኑ የጦቢያ የነገሥታት ዘሮች ሁሉ ያላገኙትን ዕድል እኮ ነው ያገኘች” አላቸው።
ዕድል? እንዴት ሁኖ ነው ዕድል ሚሆን? አለች ወለተጊዮርጊስ፣
እያየችው። ዞር ብላ አባቷን ተመለከተቻቸው። እሳቸው የጭንቀት ስሜት አጥብቆ የተሰማቸው ይመስላሉ። ግንባራቸው ላይ ቸፍ ያለው
ላብ ቁልቁል ሊወርድ ይጋበዛል። ሆዷ ውስጥ አንዳች ነገር ተላወሰ።
ግንባሯን ያራሰውን ላብ በእጅጌዋ ጫፍ አባበሰች።

ከበድ ያለ ፀጥታ ሰፈነ።

“ግራማች ዛዲያ ምን ያስባሉ?” አሉ፣ ከሁሉም ተለቅ ያሉት እንግዳ።

እንዳው ለነገሩ ጠየቁ እንጂ ግራዝማች ምርጫ እንደሌላቸው ያውቃሉ።ግራዝማች ግን በልባቸው ወይ አንተ የወፍታው አያልቅብህ፡፡ ያ ሁሉ ባላባት ዐይናማ ልዥህን እያለ ለራሱ ሆነ ለልዡ አማላጅ ሲልክ ሁነኝ ጋር አንድ ቀን እንታረቃለን፣ ልጄን ለልዥህ ብየ ሳበቃ እንዴት
👍12
ለሌላ እሰጣለሁ እያልሁ የቆየሁት ለካስ ልዤ እጣ ፈንታዋ እኼ ሁኖ
ኑራል? አቤቱ እንዴት ድንቅ ነው ያንተ ሥራ? እያሉ ይደነቃሉ።
አየ ሁነኝ! የዘለፍኸኝን ሁሉ የወፍታው ይቅር ይበልህ... በተልካሻ ነገር ተቀይመህ እኼው አሁን ጉድ ሆንህ፡ ያነን የተባረከ... ገራም.. ልዥህን በደልህ፤ ይብላኝ ላንተ፤ የኔንስ የወፍታው ግዝየውን ጠብቆ ለዝኽ አብቅቶልኛል እያሉ ያስባሉ።

ልጃቸው ቤተመንግሥት ስትገባ፣ እሳቸው ስማቸው ሲገን፣ ሲሾሙ
ሲሸለሙ፣ ልጃቸው ወልደልዑል የቤተመንግሥት ባለሟል ሲሆን ወለል ብሎ ታያቸው። ኢሳያስን መልከት አደረጉና፣ እኼ ሰው ልዤን ከግር እስተ ራሷ ሲያይ የነበረው ለካስ እኼን ይዞ መጥቶ ኑሯል? ሲሉ ተገረሙ። እኒህስ ቢሆኑ እግራቸው ርጥብ በጎ ነገር ይዘው መጡ አሉ፣ ሌሎቹን እንግዶች እያዩ። ኸንግዲህ ዘመድ ወዳጅ ደስ ይበለው። ጠላት ሁሉ ይፈር። እኛን ለዝኸ ያበቃን የወፍታው ያውቃል። ልዤ
ዕድል ፈንታዋ ቀድሞውኑ ተመድቦላት ኑሯል...

ከሁሉም ተለቅ ያሉት እንግዳ፣ “ግራማች…. ዛዲያ ምን አሰቡ?” ሲሉ ጥያቄያቸውን ደገሙ፤ መልስ ሳያገኙ በመቅረታቸው።
ግራዝማች ከእንቅልፋቸው እንደባነኑ ሁሉ ዐይናቸውን ጠራረጉ። ጥያቄው ትዝ አላቸው። ከግንባራቸው ወደ ጉንጫቸው ያሽቆለቆለውን ላብ በጋቢያቸው ጠርዝ ተም ተም እያደረጉ፣ “እንዴ ምን አስባለሁ፣ ጃንሆይ ሲያከብሩን። ንጉሥ ጠይቆ? ለኛስ ቢሆን ትልቅ ክብር ማዶል?”
ብለው በድንጋጤ የደረቀ አፋቸውን ለማላወስ ሞከሩ።

ወለተጊዮርጊስ አባቷ፣ “ንጉሥ ጠይቆ?” ያሉት ልቧን እንደ ጦር ወጋው። በርግጥም ንጉሥ ጠይቆ እንቢ ሊባል እንደማይቻል ታውቃለች አባባ እርሶና ባላምባራስ ሁነኝ ስትቀያየሙ እኔና ጥላዬን እንደጎዳችሁ አላወቃችሁም፡፡ እናንተ ባትቀያየሙ ኑሮኮ እስታሁን
ኸጥላዬ ጋር ተጋብተን እኼ ሁሉ አይመጣምም ነበር፡፡ የሰፈሩስ
ሽማግሎች ደግመው ደጋግመው እናስታርቅ ያላሉት ለምነው? እና
እስተዛሬ ሽማግሎቹ መጥተው ያስታርቃሉ እያልሁ በሩን በሩን ሳይ
ቆይቸ እኼው ዛሬ እጅ ጠያቂ ሽማግሎች መጡ። አይ አለመታደል!ዳሩ አባባ እርሶ ምን ያርጉ? ያመረሩት የጥላዬ አባት ናቸው። እርሶ ቂም አያቁም። ለመሆኑ ባላምባራስ ሁነኝ እኔና ጥላዬን እንደበደሉን፣ እንዳንጋባ እንዳረጉን አያቁም? ቤተሰቡንስ ቢሆን እንደዝኸ አለያይተው
መቀመጣቸው ትንሽም ስንኳ አይቆረቁራቸው በቁስቋሟ! ምን ያሉት ክፉ ምቀኛ ናቸው? አለች።

የሁለት ሰዎች የሕይወት አቅጣጫ በሌሎች መወሰኑ አብከነከናት።
እሷና ጥላዬ የባላምባራስ ሁነኝ እልህ እስረኛ መሆናቸው ደሟን
አፈላው።

አየ ጥላዬ... ጥላዬ የልዥነቴ... ሲሰማ ምን ይል ይሆን እስታሁን
ጠፍተን አንዱጋ ብንኸድ ኑሮ ምን ነበረበት? ኸንግዲህማ ጠፍተን
መኸድ አንችልም ሽንጉሥ እጅ እንዴት እናመልጣለን? ብላ እንባዋን ጠራረገች።

በዚያች ቅጽበት ሕይወቷ ሲቀየር፣ ዐዲስ መልክ ሲይዝ ታያት።
ጭንቀት ልቧን ተጫነው፤ መንፈሷ መላወሻ አጣ፤ እንባዋ ዐይኗን
ከለለው። ዐይኗን ለመጥረግ ስትሞክር መጋረጃውን ሳታስበው ለቀቀችው።
ያለችበት ቦታ ጠበባት፤ የበለጠ ጨለማ ሆነባት፤ የምትተነፍሰው
አየር ያጣች መሰላት፤ የተቀመጠችበት ዱካ ቆረቆራት። ጥያቄዎች በሐሳቧ እየተሸቀዳደሙ ተመላለሱ። መጋረጃውን መልሳ በአንድ እጇ
ይዛ መልስ ይሰጧት ይመስል ከእናቷ ወደ አያቷ፣ ከዛም ወደ አባቷ ዐይኖቿን አዘዋወረች። የአባቷ ሁኔታ አሳዘናት። እሚታዬ! አባባ እኮ ተጨንቀዋል፣ ተናገሪ እንጂ አለች፣ ወደ አያቷ እያየች።
አያቷ ጉሮሯቸውን ኮርኮር አደረጉ። ጀርባቸው ላይ የወደቀ ሹሩባቸው
ላይ ሸብ ያደረጉትን ከወተት የነጣ ሻሽ ነካኩና፣ “ልዣችንም እኮ ያጤ
ልብነድንግል ወገን ነች። ያጤ ልብነድንግልና የእቴጌ ሰብለወንጌል ልዥ፣ አቤቶ ፊቅጦር... ኸሳቸው ነነ። አጤ ሚናስና አጤ ገላውዲዎስ
የሳቸው ታናሽ ወንድሞች ማልነበሩ?” አሉ።

ወይዘሮ እንኰዬ የእናታቸውን ንግግር ሲሰሙ ከሐሳባቸው መለስ አሉና በኩራት የነጠላቸውን ባለ ደማቅ ጥልፍ ጥለት አስተካክለው፣
“ሰማህ?” በሚል ሁኔታ ኢሳያስን ተመለከቱት።.....


ይቀጥላል
👍6
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_ሦስት ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ...“ኸንጉሥ እጅ እንዴት እናመልጣለን?...” ኢሳያስ፣ የሰማት ይመስል ወደ ጉዳዩ መግባት ፈለገ። አንዴ ዮልያናንና እንኰዬን ሌላ ጊዜ ደግሞ ግራዝማችን ዐይኑን ተክሎ ተመለከተ። ፊቱን ወደ ዮልያና አዞረና ፈገግታ ለገሣቸው። ዮልያና የሆነ ነገር ሊነግረኝ ነው ብለው ጠረጠሩ፤ ለመስማት ጓጉ። “እመቤቴ... ዋናው የመጣንበት ጉዳይ...”…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...ባርናባስ የሔዋንን ሁለት እጆች ግጥም እድርጎ ይዟል። ሸዋዬ የአገኘችውን ነገር ሁሉ እያነሳች ትደበድባታለች። ሔዋን ኡኡ ድረሱልኝ እያለች ትጮሀለች።
እጆቿን ከባርናባስ ለማስለቀቅ ትታገላለች። እሱ ደግሞ እንዳታመልጠው ጥርሱን
ንክስ እያረገ ሀይሉን ያጠነክራል። ሸዋዬ አሁንም ትደበድባታለች፡፡ ሔዋንም ትጮሀለች፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን በርካታ ሰው ዙሪያውን ከብቦ ይመለከታል። ግን
“ማንም ሊገላግል አያስብም፡፡ አስቻለው ሊገላግል እየፈለግን ደግሞ መሮጥ ያቅተዋል። ይለፋል ግን አይችልም፡፡ ከያዘው ነገር ራሱን እንድምንም አላቅቆ ወደ
ድብድቡ ቦታ ሊሮጥ ሲል ድንገት ከእንቅልፉ ብንን አለ፡፡ «በስመ አብ ወወልድ መንፈስ ቅዱስ..." ብሎ ከተንጋለለበት ቀና በማለት ፊቱን በሁለት እጆቹ ሽፍን አድርጎ ወደ ፊት ወደ እግሮቹ ድፍት አለ ዝግንን አለው ደርጊቱን ያየው
በቅዠት እንዳልሆነ ሁሉ ሔዋን አሁንም በዚያው ሁኔታ ውስጥ
ሆና ትታየው ጀመር። አሳዘነችው። ከዚያ በኋላ መተኛት አልፈለገም
ከአልጋው ላይ ፈጠን ብሎ ወረደና ልብሱን ለባበሰ።

ምን ሊያግርን እንደሆነ ሳይታወቀው በቀጥታ ወደ ሸዋዬ ቤት መሄድ ፈለገ። ቤቱን ቆለፈና ከግቢ ወጥቶ ቁልቅል ወደሸዋዬ ቤት አቅጣጫ ወረደ ልክ በሸዋዬ ቤት አቅጣጫ ስምንተኛ መንገድ ላይ ሲደርስ መንገድ ላይ ቀጥ ብሎ ቆመና በቀኝ አቅጣጫ ያለውን የወይዘሮ ዘነቡን ግቢ በርቀት ይመለከተው ጀመር በሀሳቡ ሸዋዬ ቤት ገባ ሸዋዬንና በርናባስ ፍራሽ ላይ ቁጭ ብለው
ጫት ሲቅሙ ሔዋን ደሞ በከሰል
ላይ ጀበና ጥዳ የሁለቱ ብና አፋይ ሆና ሁሉም በአንድ ላይ እንደ ስዕል ታዩት።ልቡ ወደዚያው ቤት ሂድ ሂድ አለው። ነገር ግን ድንገት ዘው ቢል ሊፈጠር የሚችለው ሁኔታ ታየው፡፡ ከሁሉም በላይ ሔዋን ትሳቀቅበታለች !
በዚያ ምትክ ከንፈሩን ንክስ አድርጎ ራሱን በቁጭት ወዘወዘ።

በዚሁ ሁኔታ ጥቂት ቆየና ሳይወድ በግድ ሃሳቡን ለወጠ፡፡ በቃ ወደ ሸዋዩ ቤት መግባት አልፈለገም፡፡ ግን ደግሞ ወዴት እንደሚሄድ ጨነቀው ቤቱም ሰለቸው ወደ አንድ ቡና ቤት አይሄድ ነገር እዚያ ሄዶ የሚገጥመው ነገር ለመንፈሱ
አይመቸውም። ግራ ሲገባው ቁልቁል ወደ ከተማዋ ዳርቻ ይራመድ ጀመር ቁርጥ ያለ አድራሻ የለውም። ብቻ መሄድ ብቻ መራመድ፡፡ ብሎ ብሎ ከከተማው ወጣና ወደ እሮሬሳ ገበሬ ማህበር አዋሳኝ ላይ ደረሰ።እያደር ደግሞ
የገጠሩ ሽታ አማለለው፡፡ አሁንም ወደፊት ሊራመድ መሰነና ርምጃውን ቀጠለ። በዚያ መንገድ ላይ በርካታ የገጠር ነዋሪዎች ወደ ከተማ ያመራሉ።ከከተማ ወደ ገጠር ይሄዳሉ፡፡ አስቻለውም ርምጃውን ዝም ብሎ ወደ ፊት ቀጠለ፡፡በልቡ ግን አንድ ነገር ያስላስሳል ዐወደፊት ሐምሌ ላይ የሚጠብቀውን ዝውውርና
ከሔዋን ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት። 'ለመሆኑ' ይላል በሀሳቡ። ብዛወር የሐዩ ጉዳይ እንዴት ሊሆን ነው? ይዢያት ልሄድ ወይስ ትቻት? ይልና እንደገና
የታፈሡና የበልሁ ወደ ክብረ መንግስት የመሄድ ዕቅድ ይመጣበታል። ሄደውስ
ይሳካላቸው ይሆን? ወይስ የሔዩ እናትና አባት ሽዋዬ በፃፈችላቸው ደብዳቤ ምክንያት ሁኔታው አስግቷቸው ያንገራግሩ ይሆን እሺ ቢሉም ሰርግ ድግስ ምናምን ሊሉ ይችላሉ። ያ እስከሚሆን ጊዜ ይፈጃል፡፡ ዞሮ ዞሮ ላልተወሰነ ጊዜ
ከሒዩ ጋር መራራቀ አይቀርም፡፡» በማለት ራሱን እንደማረጋጋት አይነት እንግዲህ የሆነው ይሁን ብቻ ሰላምና ጤና ትሁንልኝ፡፡» እያለ አምላኩን ይማፀናል፡፡

ሳያውቀው ብዙ ተጉዟል በለየለት ገጠር ውስጥ ገብቶ ከዲላ ከተማ በግምት ሁለት ኪሎ ሜትር ያህል ርቋል። ከሀሳቡ ብንን በማለት ባለበት ቦታ ላይ ቆሞ ዓይኑን ወደ ቀኝ አቅጣጫ ጣል ሲያደርግ ዙሪያዋን በረጃጅም ዛፎች
የቸከበበችና፣ ሰፋ ያለች ደስ የምትል ገላጣ ሜዳ ታየችው፡፡ ከግጦሽ ከፍ ያለ የእድገት ደረጃ ላይ በደረሰ ለምለም ሳር ተሸፍናለች። በውስጧ አልፎ አልፎ
የደረቁ ጉቶዎች ጉብ ጉብ ብለው ይታያሉ፡ ወደዚያው ታጠፈና ሜዳዋ መሀል ገብቶ ከአንድ ጉቶ ላይ ቁጭ አለ፡፡ ዙሪያውን ሲመለከት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ነው፡፡ ዛፎች ደግሞ ረጃጅም፡ ወደ መሬት ሲያይ ያ ለምለም ሳር፡፡ በአፍንጫው የሚገባው አየር በራሱ የተለየ መዓዛ ያለው፡፡ መንፈስ የሚያድስ፡፡ እጆቹን በደረቱ ላይ አቆላልፎ ወደ ዛፎቹ ሲያይ ከአንዱ ወደ ሌላው እየተዘዋወሩ የሚንጫጬ ወፎች
ቀልቡን ሳቡት ከወፎቹ የጫጫታ ድግግሞሽ የተነሳ የወፍ ድምፅ ፂው ስትል ሲኮንድ አታልፍም:: የድምጻቸው ልዩነት ውበትና ህበሩ በጭንቅ በጥበብ ከተቀመረ
ዘመናዊ ሙዚቃ የበለጠ ስሜት ይማርካል፡፡

«እናንት ወፎች» አለ አስቻለው ሁኔታቸው ሁለ ግርም ብሎት፡፡ ዛፋ ሁሉ የሁላችሁ ለኔ ብቻ ባይ ስግብግብ በመሀላችሁ የለም
አዛዥ የላችሁ ገልማጭ ጠላት የላችሁ ምቀኛ ኑሮአችሁ በራሳችሁ፣ ውሸት አታውቁ ቅጥፈት ክፉ አቶለሙ ክፉ አትናገሩ አትቀየሙ አታስቀይሙ ጨኸታችሁ አይገደብ ጫጫታችሁ አይመዘገብ ቂም አታውቁ በቀል፤ በእናንተ ዘንድ ዛቻ የለ
ማስፈራራት፤ ፍርሀት የለ ጭንቀት፣ በዚች ምድር ሰላም ልትኖሩ የተፈጠራችሁ ሰላማዊ ፍጡሮች! በማለት ብቻውን ሲነጋገር ከቆየ በኋሳ ሀሳቡን ወደ ሰው ልጅ ባህሪና አኗኗር መለስ ሲያደርገው ጭራሽ አስጠላው።

«ያልታደለ ፍጡር»አለ በስጨት ባለ አነጋገር፡፡ ታየው የሰው ልጅ
ክፋቱና ተንኮሉ፣ ቂምና በቀሉ፣ ሸርና ምቀኝነቱ፤ ጠበና ጭቅጭቁ፣ ከሁሉም በላይ
እብሪቱና ጭካኔው፡ በቃሉም ይገልፀው ጀመር «የአሳር ሽክም የተጫነ መከረኛ ፍጡር፥ ሰው! የቱንም ያህል ቢማር ቢመራመር ከራሱ ጋር መታረቅ ያቃተው
ደካማ ፍጡር፡ ሰው ፈጣሪው ራሱ እሱን በመፍጠሩ የተፀፀተበት ብቸኛ እንስሳ ሰው!» ካለ በኋላ ራሱን ወዝወዝ አድርጎ ወደ መሬት ጎንበስ አለና ያን የለመለመ
ሳር ልብ ብሎ ይመለከተው ጀመር፡፡ ከሩቅ ሲያዩት ልምላሜ ያምራል:: ስሩ ሲታይ ግን ብዙ ጥቃንጥት አለበት፡፡ የደረቁ ቅጠሎችና ጭራሮዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ በርካታ ነገሮች ስር ስሩን ትብትብ እድርገው ይዘውታል። ይህ ሁኔታ ሔዋንን አስታወየው፡፡

«አንተ ለምለም ሳርና የኔዋ ሔዋን እንድ ናቸሁ፡ ከሩቅ ሲያዩአቸሁ ውብ ናችሁ:: ፍጹም የደላችሁ ትመስላላችሁ፡፡ ሥር ሥራችሁንና ውስጥ ውስጣችሁን ግን ብዙ ችግር አለባችሁ፡፡ ሳትጠሩት የመጣባችሁ፣ ሳትፈልጉት የተዳበላችሁ፡፡ አቁሳይ ጥገኛ አለባችሁ፡፡ አንተን የጭራሮና የቅጠል ርጋፊዎች ስርህን ተብትበው እንደ ያዘህ ሁሉ የኔዋ ሔዋንም የአፈቀረ ልቧን የሚወ,ጋ የስሜት እሾህ ኣለባት፡፡
ለመውደድና ለመወደድ የተፈጠረች ቆንጆ ነበረች:: ግን እሾሁ ጋሬጣው በዛባትና
መንፈሷ ቆሰለ፡፡ በአፈቀረች ተሰቃየች። ማልቀስና መተከዝ ዕጣ ፋንታዋ ሆነ።
እያለ ሲያስብ በዚያው ያ ቅዠት ውስጥ ያየው ሁኔታ ትዝ አለው፡፡ ድንግጥ ብሎ እንደ መደንበር አረገና በተቀመጠበት ጉቶ ላይ ብድግ አለ ሳያስበው በዚያ
በለመለመ ሳር ላያ ይዘዋወር ጀመር፡፡
እጆቹን በጀርባው ላይ አጣምሮ ጎንበስ በማለት በግምት ከአስር: እስከ አስራ አምስት ርምጃዎችን ከተራመደ በኋላ በግራ በኩል ወደ መንገዱ ዞር ብሎ ሲያይ አንድ ለየት ያለ ነገር አየ፡፡ በመንገዱ ላይ ሰዎች አሁንም ወደ ላይ ወደ ታችም አቅጣጫ ይሄዳሉ፡፡ ነገር ግን መንገደኛ፣ ለየት ባለ እኳኋን አንዲት በጀርባዋ ጓዝ የያዘች
👍101
ሴት ቆማ እሱን እሱን ስትመለከት አያት፡፡ ይኼኔ እብድ መስያት ይህናል ዝም ብሎ እርምጃውን ቀጠለ በምንጠን ቀጠለ፣ ደገሞ ስ.ያያት አሁንም ታየዋለች::ለራሱ
ገርሞት ቀና ጎንበስ እያለ ሲያያት ሴትዮዋ ንቅንቅ አትልም ድንገት ደግሞ ድምፅ ሰማ
« ጋሽ አስቻለው» የሚል የጥሪ ድምፅ።
«እንዴ» አለና አስቻለው እንደመገረም ብሎ ጆሮውን ጣል አድርጎ ሲያዳምጥ አሁንም “ጋሽ አስቻስው» ስትል ተጣራች ሴትየዋ «ምንድነው ነገሩ!» በማለት ከራሱ ጋር እየተነጋገረ ቆም ብሎ ወደ ሴትየዋ ሲመለከት አሁንም " አስቻለው አይደለህም እንዴ ስትለው ሰማ።
«በዚህ መንገድ የምታልፍ የገጠር ሴት እንዴት ልታውቀኝ ቻለች?»
በማለት እየተገረመ «አዎ ነኝ። እንቺ ግን ማነሽ?» ሲል ከርቀት ጠየቃት። ሴትዮዋ “እኔ እገሌ? ከማለት ይልቅ ጓዟን ከጀርባዋ ላይ አውርዳ ቁጭ አለች ከሩቅ ሲያያት የምታለቅስም መስለች:: አሁንም ግራ እየገባው «ማነሽ አንቺ?»
እያለ ተጠጋት፡፡ በትጠጋት ቁጥር እያለቀሰች መሆኗ በደንብ ታየው፡፡
አሉንም ተጨጋት። «ምን ሆነሽ ነው ሴትዮ?» ሲል ሽንጥና ሽንጡን ይዞ አጠገቧ በመቆም ጠየቃት
«አላወቅኸኝም?” አለችው ሴትዮዋ።
«ትርፌ በጋሻው ነኝ፡፡» አለችና እንባዋ በጉንጫ ላይ ድንቡቅ ብሎ ወረደ።
«ኣ?» አለ አስቻለው በድንጋጤ አፉን ከፍቶና ዓይኑን በሴትየዋ ላይ
አፍጥጦ የኔ ትርፌ በጋሻው?» እንደገና።
«አዎ»
ያቺ ለሦስት ዓመታት ያህል ቤቱን ቅልጥፍጥፍ አድርጋ በመያዝ ምቹ
የወንደ ላጤ ህይወት አስለምዳው ነገር ግን ድንገትና በማያውቀው ምክንያት ከአንድ ዓመት በፊት ጥላው የጠፋችው የቤት ሰራተኛው ናት፡፡
«እንዴት ሊሆን ይችላል?» አለም አስቻለው በሁለት እጆቹ ጉንጮቹን ይዞ፡፡ «ሆነ ጋሽ አስቻለሁ» አሁንም እያለቀሰች ለጊዜው ልክ ያን ቀደም ሲል ያየውን የቀን ቅዠት ዓይነት ስሜተ ተሰማውና ለሴኮንዶች ያህል ተጠራጠረ፡፡
ግን ደግሞ ወዲያው ወደ ትርፌ ጠጋ በማለት እቅፍ አድርጎ ሳማትና ከየት እየመጣሽ ነው?» ሲል ጠየቃት።
”ከባላገር?» አለች ትርፌ አጎንብሳ አሁንም እያሰቀሰች፡፡
«ለምን ሄድሽ?
«ቀን ጎሎብኝ»
ትርፊ ቀን የጎደለባት ስለመሆኗ ገጽታዋ ያስታውቃል፡፡ ቀይ የነበረው ፊቷ ማድያት አልብሶት ተዥጎርጉሯል። የለበሰቻቸው ቀሚስና ነጠላ ውሃ ነክቷቸው
የኮተ አይመስለም፡፡ ፀገሯ እብቅ የነስነስብት ይመስላል። ዓይኖቿም ጎድጉደዋል።የጉንጯ አጥንቶች በዓይኗ ሥር ሾለዋል። አንገቷ ላይ የሚታየው የሰውነት እድፍ
ጎደዳ ሰርቷል፡፡ በቃ የድሮዋ ትርፌ አይደለችም ተቀይራለች።አስቻለው
ይሄን ሁሉ ሁኔታዋን ዓይቶ ሆዱ እዘነና ከንፈሩን መጠጥ አድርጎ «አሁን ታዲያ አቅጣጨሽ ወዴት ነው እህትነሽ ወዴት ነው?» ሲል ጠየቃት::
«በቃ እግሬ እንዳደረስኝ::»
እስቻለው የባሰ አዘነ፡፡ በመጎሳቆሏ በተጨማሪ የተስፋ መቁረጥ ንግግሯ አንጀቴን በለው
ጓዟን አሳዘላትና እጇን ይዞ ወደ ከተማ መንገድ ጀመሩ። ብዙ ተጉዘው ወደ ከተማዋ ጫፍ
ሊደርሱ ሲሉ ትርፈ ከአስቻለው ግንባር ላይ ተፈጥሮ
የነበረውን ጠባሳ በዓይኗ ሰለል ስታደርግ ቆይታ ኖሯልና «ግንባርህን ምን በኖህ ነው
ጋሽ አስቻለው? ሰው መታህ?» ስትል ጠየቀችው::
የጉልበተኛ ዘመን አይደል ተደባዳቢ ምን ይጠፋል ብለሽ?» አለና እስቲ ቆይ ቤት ስንደርስ እናወራዋለን፡፡» ብሏት አሁንም ገሰገሰ ወደ ከተማ። አስቻለው
ትርፌን ይዞ ከቤቱ ሲገባ ከቀኑ አስራ አንድ ሠዓት ሆኗል::
ልክ እንደ ቀድሞው አቀማመጣቸው አስቻለው ጠረጴዛና ወንበር ላይ ትርፌ ደግሞ ከእሱ ፊትለፊት ጓዟን እንዳዘለች ዱካ ላይ ቁጭ አሉ፡፡ አስቻለው የትርፈን መልክ በሀዘን ዓይን ሲመለከት ትርፌ ደግሞ ድሮ ትጠቀምባቸው የነበሩ የአስቻለውን የቤት ቁሳቁሶች በዓይኗ ሰለል ታደርጋቸዋለች፡፡ አብዛኞቹ እሷ እንዳስቀመጠቻቸው ናቸው:: በአቧራ ቁሽሽ ብለዋል ሸረሪት ያደራባቸው ይመስላሉ እሷ እሄደች ወዲህ የተነኩ ወይም የተገላበጡ አይመስሉም። በልሁና መርዕድ ጫት ሲቅሙ የሚጠቀሙባቸው ብርጭቆዎች ብቻ ያብለጨልጫሉ::፥
«ሚስት አላገባህም ጋሽ አስቻለው?» ስትል ትርፌ ጠየቀችው፡፡
«ችግር መች ፈታችኝና ሚስት ልደርብባት ብለሽ ነው ትርፌ፡፡» ካለ በኋላ
«ለምን ጓዝሽን አታወርጃውም?» አላት
ጉንጨን ደገፍ አድርጎ እየተመለከታት፡
ትርፌ የነጠላዋን ቋጠሮ ፈትታ ጓዟን አወረደች፡፡ ከአጠገቧ ቁጭ አድርጋው መሬት መሬት ታይ ጀመር። ሀፍረትና መሳቀቅ የተሰማት ትመስላለች::
«ግን እንደው ትርፌ!» አላት እስቻለው ረጋ ባለ አነጋገር፡ «ምን
በደልኩሽና ድንገት እልም ብለሽ ጠፋሽ?» ሲል በትህትና ጠየቃት፡፡
«ምንም ጋሽ አስቻለው?»
«አንድ ነገርማ መኖር አለበት፡፡»
«ቢኖርም እኔ እንጂ ከአንተ አልነበረም::»
«እስቲ እሱንም ቢሆን ንገሪኝ፡፡»
«ተታለልኩ፡፡»
«ማነው ያታለለሽ?»
«ያኔ አንተም የምትመገብበት፣ እኔም እስራበት የነበረ ውቴል ውስጥ ከጎረቤት እየመጡ ከውቴሉ ባለቤት ጋር ቁጭ የሚሉ ወፍራም ሴት አልነበሩም?»
«አዎ»
«ገና እዚያው ውቴል ቤቱ ውስጥ እያለሁ እንደ ቀልድ እያረጉ ይቺን
ሰራትኛሽን ስጪኝና ለወንድሜ ልጅ ልዳራት እያሉ የውቴሉን ባለቤት ይጠይቋቸው ነበር፡፡
«እሺ!» አለና አስቻለው ፈገግ እያለ ያያት ጀመር፡፡ የትርፌ ወሬ ወዴት እንደሚያመራ ከወዲሁ ገባው::
«አንተ ጋ ከገባሁ በኋላም ባገኙኝ ቁጥር ይጨቀጭቁኝ ነበር»
«ምን እያሉ?»
«ወንድሜ አንድ ብቻ ወልዶ ሞቶብኛል። ልጁ የአባቱን ሀብት ብቻውን ወርሶ ሀብታም ሆኗል:: ሚስት የለውም:: እኔ የምፈልጋትን ሴት ሊያገባ ቃል ገብቶልኛል። እኔ ደሞ ለእሱ የምመኘው አንቺን ነው፡፡ አንቺም የሰው አገር ሰው
ስለሆንሽ ሁነኛ ሰው ያስፈልግሻል። ልጅ ወልደሽ ዓይንሽን በዓይንሽ ማየት
ይኖርብሻል፡፡ የሰው ቤት ኑሮስ እስከ መቼ ይዘለቃል?እያለ::»
«በቃ! እሺ አልሻቸው ማለት ነው?»
«መስሎኝ ተታለልኩ፡፡» አለችና ትርፌ አሁንም እንዳቀረቀረች ዓይንና አፍንጫዋን በለበሰቻት ቁሻሽ ያለች ነጠላ ትጠርግ ጀመር፡፡
«ከየት ወሰዱሽ ታዲያ?»
«ከገበያ ላይ፡፡»
አስቻለው በመገረም ዓይነት ራሱን እየወዘወዘ ለአፍታ ያህል ሲመለከታት ቆየና «ታዲያ ሀብታሙ ገበሬ እንዴት አድርጎ ቢይዝኸ ነው እንዲህ ያማረብሽ» ሲል በምፀት አነጋገር ጠየቃት::
«ምንም አልተጠቀምኩም ጋሽ አስቻለው»
«ሀብት የለውም?»
«ሙልጭ ያለ ድሀ ነው»
አስቻለው ድንገት ቂቂቂቂ» ብሎ ሳቀና እንዴት?» ስል ጠየቃት፡፡
«ቀድሞ ነገር የእሱ የሆነ ምንም ነገር አልነበረውም። ላሞች ቢኖሩም የእናቱ ናቸው፡፡ እሳቸው እነዚህን ላሞች በደንብ ተንከባከቢ አንዷ ስትወልድ ጥጃዋን ለአንቺና ለባልሽ እሰጣችኋለሁ ይሉኝ ጀመር ላም ወልዳ ጥጃው አድጎ
«ታዲያ ወዲያው ጥለሽው አትመልሽም ነበር?»
«ምስጢሩ እስከሚገባኝ ድረስ ለካ አርግዤ ኖሯል፡፡ መሄጃው ጨነቀኝ፡፡»
አስቻለው ድንግጥ አለና «በቃ ወልደሻላ?»
«ግን ገና በአንድ ወሩ ሞተብኝ።»
ብስመ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ!
«ሀዘንተኛ ነሽ?»
«እማዝነው ግን ለራሴ ነው፣ ልጀማ ተገላገለ፡፡»
«አይዞሽ!» አላት አስቻለው፡፡ ከመቀመጫው ብድግ አለና ወደ ትርፈ ጠጋ በማለት «ቢያንስ አይርብሽም፡፡ ፈቃደኛ ከሆንሽ ከኔው ጋር ትኖሪያለሽ፡፡» አላትና
እንደገናም «ቅር ይልሻል?» ሲል ጠየቃት።
ትርፌ ዓይኖቿን በእንባ ሰማይ አስመስላ ወደ አስቻለው ቀና በማለት
«አታምነኝማ ጋሽ አስቻለው?» አለችው ሽቁጥቁጥ እያለች::
«ዘርፈሽኝ አልሄድሽም እኮ! አይዞሽ አትፍሪ፡» አላትና ወደ መቀመጫው ተመልሶ ቁጭ አለ፡፡ ግንባሩን ወደ ጠረጴዛ ደፍቶ ያስብ ጀመር።
👍12
ሰዓቱ ወደ አስራ አንድ ተኩል ተጠጋ፡፡ አስቻለው የራት ነገር ትዝ ሲለው በቅድሚያ ለእሷ በሳህን ሊያመጣላት አሰበ፡፡ ከቤት ወጣ ሊል ሲል «እስቲ የሚበላ
ነገር ላምጣልሽ፣ እስከዚያው ገላሽን ተጣጥበሽ ጠብቂኝ አላት።
«ምግብ ይዣለሁ እኮ!» አለችው
«እስቲ ምን ይዘሻል?»
ትርፌ ቀና ብላ እያየችው፡፡
ትርፌ ጓዟን ፍትት አደረገችና በሌላ አሮጌ ጨርቅ የተቋጠረች ነገር
አወጣች፡፡ ያቺንም ፈታታችና ከውስጧ በቁጥር አምስት የሚሆኑ ድርቅ ያሉ ቂጣ
የሚመስሉ ነገሮች እያሳየችው «ይኸው!» አለችው::
አስቻለው አሁንም ሆዱ አዘነና «እሱን ነገ ትበይዋለሽ፣ ለዛሬ ግን መንገድ ላይ ውለሽ አንጀትሽ ስለ ታጠፈ ለስለስ ያለ ነገር ላምጣልሽ፡፡» ብሏት ወጣ፡፡
በግምት ከግማሽ ሰዓት በኋላ በዳንቴል የተሽፈነ ሳህን ይዞ ሲመለስ ትርፌ እነዚያን የቆሸሹ የአስቻለውን የቤት ዕቃዎች ሁሉ አውጥታ ግቢ ውስጥ ስታጣጥብ
አገኛት። ደንግጦም ገርሞትም ቀጥ ብሎ በመቆም «ምነው ትርፈ? ምን ነካሽ ነገ ከነገ ወዲያ አይደርስም እንዴ?» በማለት ቆጣ ባለ ንግግር ተናገራት፡፡
«ለምን ጋሽ አስቻለው? በጣም ነው እኮ የቆሽሽው፡፡ እኔ ጀግሞ አልደክመኝም::» አለችና ወደ እሱ ጠጋ በማለት በሹክሹክታ አነጋገር «ወዲያው አንተ እንደወጣህ አንዲት ልጅ መጥታ ቤት ውስጥ እየጠበቀች ነው፡፡» እለችው
«ምን ዓይነት ልጅ?» ሲል ጠየቃት ሆዱ እየጠረጠረ።
«ቆንጆ! በጣም የምታምር» አለችው ትርፌ ጥብቅ ባለ አነጋገር፡፡አስቻለው የልጅቷ ማንነት በትክክል ገባውና ትርፌን በፈገግታ አየት አድርጓት ወደ ቤት ሲገባ ሔዋንም በፈገግታ ተቀበለችው::
“ታዲያስ ሔዩ!» እያለ ሳህኑን ጠረጴዛ ላይ ከአስቀመጠ በኋላ «እዘናግተሽ መምጣት ጀመርሽ እያላት ሁለቱም በፈገግታ ተሞልተው ተሳሳሙ፡፡
ትርፌ!» ሲል እስቻለው ወደ ውጭ ተጣራ።
«አቤት»
«ነይ አንዴ።»
ትርፌ የእጇን ውሃ እያራገፈች ወደ ቤት ስትገባ አስቻለው የሔዋንን
አንገት አቅፎ፤ ሔዋን ደግሞ ወገቡን ያዝ አድርጋ ፎቶ እንደሚነሱ ሙሽሮች ፈገግ
ብለው ቆመው ጠበቋት። «ቅድም ስለሚስት ያነሳሽብኝ ነገር አልነበር ይቻት እጮኛዪ! ነይ ተዋወቁ::» አላት አስቻለው፡፡
ሔዋን - ትርፌ፡» ተባብለው ተጨባበጡ።
ያቺ የምወዳት የማምናት ሰራተኛዬ እያልኩ ስነግርሽ የነበረችው ትርፈ በጋሻው ማለት ይቺ ናት ሔዩ!» በማለት ለሔዋን ከገለፀላት በኋላ ትርፌን ደግሞ
ስም አውጭላታ!» አላት ፈገግ ብሎ እያያት፡፡
«እታለም ብያታለሁ::» አለች ትርፌ እንደ ማፈር እያለች፡፡
«አመሰግናለሁ::» አለች ሔዋንም ሳቅ እያለች፡፡
ሦስቱም ተሳሳቁ፡፡
ትርፌ ወደ ስራዋ ስትመለስ አስቻለውና ሔዋን ወንበር ላይ ቁጭ አሉና
«ቆየሽ እንዴ ከመጣሽ!» አላት አስቻለው፡፡
«አዎ! እንዲያውም ልመለስ ስል ነው የመጣኸው::»
«ጠዋት ግን ለምን ቀረሽ?»
«ስላልተመቸኝ:: ግን ይኼው አካካስኩ አይደል!»
«አመሰግናለሁ:: ከቸኮልሽ ሂጂ ልሽኚሽ፡፡» አለና አስቻለው ብድግ አለ፡፡
ሔዋንም ብድግ ስትል ከንፈሮቿን ሳም ሳም አደረጋቸው::
አስቻለውና ሔዋን ልክ ከግቢ እንደወጡ በቀኝ በኩል አየት ሲያደርጉ በልሁና መርዕድ ጫት ይዘው ሲመጠ አዩአቸው፡፡ ከእራት በፊት ጫታቸውን አስቀምጠው መቀመጫቸውን ሊያዘገጃጁ ነው፡፡
በልሁ ከርቀት ሔዋንን መናገር ጀመረ፡፡ «ትናንት አልመጣም ብለሽ ከላክሽ በኋላ አሁን የመጣሽበትን ምስጢር ሳታወጪ የሚለቅሽ የለም፡፡» እያለ ሔዋንን
ቀለደባት፡፡ በልሁና መርዕድ ከአስቻለውና ሔዋን ጋር ደረሱና ተሳስመው ሰላምታ ከተለዋወጠ በኋላ «ግን ትናንት ለምን አልመጣም ብለሽ ላክሽ? ምናልባት ያቺ እህትሽ የተለመደ መጥረጊያዋን አንስታብሽ ይሆን እንዴ?» ሲል ጠየቃት በልሁ
ኮስተር ብሎ፡፡
«ያ እንኳ አይደለም፡፡» አለች ሔዋን መሬት መሬት እያየች፡፡
«ሌላውስ?» አላት በልሁ በሔዋን ሁኔታ ተጠራጥሮ፡፡
«ብቻ ብላ እንደ ማቅማማት ስትል በልሁ አሁንም አጥብቆ ጠየቃት፡፡
ንገሪኝ! እኔና እሷ መቸም… ብሎ ሳይጨርስ ሔዋን ቸኮል ብላ
እቋረጠችው፡፡ ሸዋዩ በልሁን እንደምትፈራ በልሁም እንደማይወዳት ታውቃለችና
የሁለቱን የባሰ መራራቅ ለማስቀረት ስትል ወደ አላሰበችው ነገር አመራች።
«እንግዶች ይመጣሉና የትም እንዳትሄጂ ብላኝ ነው
«ከየት የሚመጡ? »አላት እስቻለው፡፡
የዚሁ ከተማ ናቸው፡፡ ባርናባስ የሚባሉት ሰውቁና የእሳቸው ጓደኛ ነው መስል አንድ በድሉ አሽናፊ የሚባል ነው፡፡» አለች በተለይ በልሁን እያየች፡፡
«በድሉ አሸናፊ?» ሲል ጠየቃት በልቡ ግንባሩን ቋጠር አድርጎ፡፡
መቸ ጀምሮ ነው እሱ ደግሞ ወደዚያ ቤት መምጣት የጀመረው?»
ከአሁን በፊት ሁለት ጊዜ መጥቶ ከባርናባስ ጋር ጫት ቅመዋል።
በድሉ አሸናፊን አስቻለው! በልሁና መርዕድም ያውቁታልና እርስ በርስ
ተያዩ፡፡ በከተማ ውስጥ አሉ የተባሉ የህዝብ ተሽከርካሪዎች ባለ ንብረት የሆኑ ሰው ልጅ ነው። ራሱም ባለ ሸራ ቶዬታ ይይዛል።
«ምን ብለው ከአንቺ ጋ አስተዋወቁሽ?» አላት አስቻለው ልቡ ተጠራጥሮ
«ሀብታም፣ የሀብታም ልጅ ምናምን አሉኝ፡፡»
«እሺ ከዚያስ»
«ዛሬ ደሞ ሁሉም ጫት ሲቅሙ ውለው የማታ ማታ ላይ ባርናባስና እት አበባ እኔና ሰውየውን ተጫወቱ ብለውን ወደ ከተማ ወጡ፡፡ ልክ እነሱ ሲወጡ
ጀምር ሰውየው ነይ አጠገቤ ቁጭ በይ እያለ ይጨቀጭቀኝ ጀመር። እምቢ ስለው እጄን ይዞ በመጎተት ፍራሽ ላይ ሊያስቀምጠኝ ሲሞክር አምልጪው ሮጬ እማማ ዘነብ ቤት ገባሁ።
«ከዚያስ?» አላት በልሁ ጥርሱን ነከስ እያረገ።
«እዚያው ስቆይበት የቤቱን በር መሰስ አድርጎት ወጣና ውጭ አቁሟት የነበረች መኪናውን አስነስቶ ሄደ፡፡ እኔም እት አበባና ባርናባስ አብረው ከወጡ እሷ
ቶሎ እንደማትመለስ ስለማውቅ በዚች ቀዳዳ ብቅ ብዬ ልመሰስ በማለት ወዲዚህ መጣሁ፡፡» አለች ሔዋን ዓይኗን በሁለም ላይ እያንከራተተች።
አስቻለው፣ በልሁና መርዕድ አሁንም እርስ በእርስ ተያዩ፡፡ በሽዋዩ ቤት ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ሳይነጋገሩ፤ ነገር ግን በደንብ ተግባቡ፡፡

💫ይቀጥላል💫
👍42🔥1🤩1
ካ.ካ.ካ.ካ.ካ.ካ

የሽኝትሽ ቀን ላይ፣
የስንብት ቀን ላይ፣
ለመቃብር ክተት፣፣
ተዘቅዝቆ ጥለት፤
የሚነበበው ፣ያንችን መሉ ታሪክ ፣ እንድጽፍ ታዝዤ፣
ታሪክሽን ተውኩት ፤በልቅሶሽ ፈዝዤ።
(ካ.ካ.ካ.ካ.ካ.ካ)
ሣቅ በሣቅ የሆነው
ለቅሶው ምን ሆኖ ነው?
የሚርመሰመሰው
ይክ ሁሉ እልፍ ሰው።
የወጣው የገባው ፣ በድሞጽ አልባ ዳና
ሞትሽን ሊያስረሳ ፣ዘርሽን ሊያጽናና።
መጽናናት ፣ማጽናናት ፣ በሚል ተረት ተረት፣
ሪሱን ያተርፋል ፤ከመታማት ክስረት።
(ካ.ካ.ካ.ካ.ካ.ካ)
በለቅሶ ቤትሽ ውስጥ
ሲሰማ ማሽካካት ፣ ይነጋል ይመሻል፤
የኔ ጥያቄ ግን
የዚኸን እሩቡን ፣ አንቺ መች ሥቀሻል?
የታሪክሽ ዘመን ፣ መዳፊ ሊጽፈው
መሃል መስመር ደርሶ ፣ ሞን አደናቀፈው?
(ዝም ብዬ ልጻፈው?)
በዐሥራ ዘጠኝ እንትን፣
የወታደር ትዕዛዝ ፣ ዐመፁን ሲበትን፣
ባርቾ ሲሰደድ ፣ በጎረምሶች ዘሪፍ፣
ዘረኛ ሲተካ ፣ በአራት ኪሎ በራፍ፣
(ተወለደች ልበል?)
ተወለደች ብቻ ፧ታሪክ ስላይደለ
የሆንሽውን ስጽፍ ፣ያልሆንሽው የታለ?
እያለ
የኑሮሽን ዘመን ፣መዳፌ ሊጽፈው
መሃል መስመር ደርሶ ፣ ሞን አደናቀፈው?
የዕድሜ ልክስ ደስታ ፣ ቢሰላ ቢቀመር
እንዴት ነው ማይሞላ ፣ ቢያንስ አንድ መስመር።
የሣቅሽበት
ቅጽበት
ከማነስም አንሶ ፣ የለም እስከሚባል
"ሣቅ አታውቅም” አለ ፤ የሙሾ አወሪጅስ ባል።
አንቺማ
ታዘበሽ አታወቂሞ ፧ ሕይወት ውሏን ስታ፤
ሐዘንሽን ሊደርስ
የመጣ በሙሉ ፣ሲበልጥሽ በደስታ።
ለቅሶኛስ
ሞትሽን አሳብቦ፣ ድምጹን ሲያንጠራራ፣
አንቺ ያልሣቅሽውን ፣ሢሥቅ እስከ ጣርያ፣
ርቃንሽን ቀበሮ ፣ ሁሉ ሲያሽቀረቅር፣
አረ ያንቺስ ይቅር፤
የመኖርን ሹፈት፣
የሕይወትን ሽፍደት፣
እመዝነው ሚዛን ፣ እለካበት ሜትር፣
የማዘኔን ባሕር ፣ እከፍልበት በትር፣
ፈልጌ አጥቼ
ጥያቄ ምስጥ ሆኖ ፣ ውስጥ ወስጤን ይበላል፤
እንዴት ከሰው ሕይወት
የሰው ልጅ ለቅሶ ቤት ፣ በሣቆች ይሞላል?
አረ ያንቺስ ይቅር!
ከሕይወት ፣ ከታሪክ ፣ከኑሮ ዘመንሽ፣
እንዴት ይበልጥሻል
ደጋግሞ በመሣቅ ፣ የገዛ ድንኳንሽ?
ካ.ካ.ካ.ካ.ካ.ካ

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
😢62👍2
#ምንትዋብ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ወይዘሮ እንኰዬ የእናታቸውን ንግግር ሲሰሙ ከሐሳባቸው መለስ አሉና በኩራት የነጠላቸውን ባለ ደማቅ ጥልፍ ጥለት አስተካክለው፣ “ሰማህ?” በሚል ሁኔታ ኢሳያስን ተመለከቱት።

ኢሳያስ ግን እጥር ምጥን ያሉትን ዮልያናን እያየ፣ “ጃንሆይም እኮ
ያጤ ሚናስ ነገድ መሆናችሁን አውቀዋል። ልዣችሁን የመረጡበት ዋናው ምክኛት ግን እሱ ማዶል። ባይናማነቷ፣ በጠባይዋና በብሩህ አይምሮዋ ደስ ተሰኝተው ነው” አላቸውና በራፍ ላይ የቆመውን አገልጋይ፣ “ያነን ማሙየን ሴቶቹ ዕቃውን ይዘው እንዲመጡ ንገራቸው
በለው” አለው።

አሳላፊው ቀልጠፍ ብሎ ወጥቶ ሲመለስ አብረውት ሁለት ደንገጡሮች የቀርከሀ ሰንዱቆች ይዘው ገቡ። ኢሳያስ ሰንዱቆቹን እንዲከፍቱና ዕቃዎቹን እንዲያሳዩ በእጁ ምልክት ሰጣቸው። ለጥሎሽ የመጡትን
የሐር ቀሚሶች፣ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ካባ፣ ቆዳ ጫማ፣ ከወርቅ የተሰሩ ያንገትና የጆሮ ጌጦች፣ እንዲሁም አምባሮች በእቅፋቸው አድርገው
ለተሰበሰበው ሰው አሳዩ።

እነግራዝማች ትንፋሻቸውን ውጠው ተመለከቱ። ተነሥተውም
በአክብሮት እጅ ነሡ፤ የምርቃት መዓት አዥጎደጎዱ።

ወለተጊዮርጊስ ጥሎሹን ለማየት ዐይኗን ከወዲያ ወዲህ አዘዋወረች።እንደልብ ማየት አቃታት። ቤተሰቦቿ ፊት ላይ ከሚንፀባረቀው የኩራትና የደስታ ስሜትና ከአዘነቡት የምስጋና ቃላት ግን የመጣላት ጥሎሽ ቀላል እንዳልሆነ ተገነዘበች።
እንዳው ሰውየው... አረ ንጉሥ ነው ሚባሉ... ንጉሡ ኸኛ ጋር ምን
አገጣጠማቸው? ንዳድ እንዲህ ጉድ ታምጣብን እያለች ስትገረም
ቆየችና ንጉሠ ነገሥቱ እነሱጋ፣ በነበሩ ጊዜ እሷን ለማግባት ማሰባቸውን የሚጠቁም ነገር እንዳው ፍንጭ አኸገኝ እንደሆን ብላ፣ ሐሳቧ ወደ ኋላ ሽምጥ ጋለበ።

ጨታመው በመጡ ማግስት እናቷ አዘዋት ፊታቸውን በጨርቅ ስታብስ ንጉሠ ነገሥቱ ዐይናቸውን ገለጥ አደረጉ፤ እንደደነገጡ አስተዋለች። ለምን እንደሆነ አልገባትም። እሳቸው ዐይናቸውን ከድነው በስመአብ አሉ። ዐይናቸውን ድጋሚ ሲከፍቱ፣ እነዚያው ይዘዋቸው የመጡት
ሰዎችና እነግራዝማች ናቸው የከበቧቸው። ቅዠት ኑሯል? ትኩሳቱ ነው ሴት ልዥ ያየሁ ያስመሰለኝ ብለው ዐይናቸውን መልሰው ከደኑት።

ወለተጊዮርጊስ አጥሚት ይዛ ተመልሳ መጥታ፣ በለሰለሰ አንደበት፣ “እስቲ ትንሽ ይቅመሱ” ስትላቸው በድንገት ከእንቅልፋቸው እንደባነኑ
የደከመ ዐይናቸውን ከፈት ሲያደርጉ፣ የተኙበት መደብ አጠገብ ሴት ልጅ ሸብረክ ብላለች። ቀደም ብለው ያይዋት ወጣት እንደሆነች ሲገነዘቡ፣ ዐይኖቿ እንደ ኮከብ እሚያበሩ፣ ቆዳዋ የማር ወለላ የመሰለ፣ እንዴት ያለች ዐይናማ ናት በሩፋኤል? አሉ፣ አንድም ቀን
ስለታቸውንና ጥያቄያቸውን አስተጓጉሎባቸው የማያውቀውንና እሳቸው ጐንደር ውስጥ የተከሉትን ሩፋኤልን ጠርተው።

ወለተጊዮርጊስ ፈገግታ ለገሠቻቸው። ዐይኗ ላይ ያዩት ርህራሄ መጽናናትን ሰጣቸው። ልባቸው በደስታና በአድናቆት ከቦታው ተነቃነቀ። አጥሚት የያዘውን የሸክላ ጽዋ ወደ አፋቸው ስታቀርብላቸው፣ ወይዘሮ እንኰዬ፣ “እስቲ ይቅመሱ፣ እሷው ናት የሠራችልዎ” አሏቸው። የምግብ ፍላጎት ባይኖራቸውም፣ እንደ ኩበት የደረቀ አፋቸውን ታግለው ከፈቱላት። አንገታቸውን በአንድ እጇ አቅንታ ከአጥሚቱ
አስጎነጨቻቸው። ከበዋቸው የተቀመጡት፣ “ተመስገን፣ ለሱ ምን ይሳነዋል?” ብለው ወደ ላይ አንጋጠጡ።
በሚቀጥሉት ቀናት ከበሪሁን መድኃኒት በተጨማሪ ወለተጊዮርጊስ ከምትኖርበት ከአያቷ ቤት ማልዳ እየመጣች ምግብ እየሠራች፣ እያጎረሰች፣ አጥሚት እያጠጣችና እየተንከባከበቻቸው ራሳቸውን
ሲችሉም፣ እጅ እያስታጠበችና ምግብ እያቀረበች፣ ደከመኝ ሳትል
አስታመመቻቸው። እሳቸውም በሩፋኤል እንዴት ያለች ዐለላ...ሰንደቅ የመሰለች ናት ትትናዋስ? እያሉ ተስተናገዱ።

በተኙበትም ሰው ውልብ ባለ ቁጥር እሷ እየመሰለቻቸው ዐይናቸው ሲባክን፣ ሲያይዋት ልባቸው ከአፎቱ ተመንጥቆ የወጣ ሲመስላቸው፣ፊታቸውን በውሃ ስታብስ የእጇ ልስላሴ ሊያስተኛቸው ሲቃጣው፣
ትንፋሿ በሽታቸውን ከላያቸው ሲገፍላቸው፣ ሕዝኸ ወድያ ጥድቅ
ኸየት ይገኛል? አቤት አቤት እንዴት ያለች መልከ መልካም ናት?
ደም ግባቷ የተደራጀ፣ ጠጉሯ እንደ ሜላት የተፈተለ፣ ወገቧ እንደ ንብ
ንግሥት የቀጠነ፣ እንደ እርጎ የረጋች በምግባር የታነጠች እያሰኘ አከረማቸው።

እንኳንስ አይተዋት፣ ሳያይዋት ስለእሷ ማሰቡ ብቻ በወባ የዛለ
አካላቸውን ዘና ሲያደርግላቸው፣ ከዐይናቸው ስትርቅ ምግብ፣ ውሃ
ወይንም አጥሚት ይዛ የምትመጣበትን ሰዐት ሲናፍቁ፣ ጀንበር መጥለቂያዋ ላይ ወደ አያቷ ቤት ስትመለስ ሆድ ሲብሳቸው፣ ጠዋት ስትመጣ ከእናቷና ከአያቷ የወረሰችውን እንደ ውሃ የጠሩ ዐይኖቿን
ከብለል እያደረገች የወደዱትን እየመረጠች የሠራችውን፣ “እስቲ ትንሽ ይቅመሱ፣ እኼኛው ይሻልዎ ይሆን?” ስትላቸው፣ ጆሯቸው የተዋበ ዜማ የሰማ ያህል ወደ እሷ ዘመም ሲል፣ ልባቸው ለማራኪ ዐይኖቿ ሲገዛ ቀናት አለፉ።

ሌሎች ውበቷን አይተው እጇን ሲጠይቁ እሳቸው ከመልኳ ባሻገር
ለጋሥ መንፈሷን፣ አስተዋይነቷን፣ ሠናይ ምግባሯንና ትሕትናዋን
አስተውለው ወደዷት። በአኳኋኗና በልባዊ መስተንግዶዋ ልባቸው
ተነካ። ተወዳጅ ገፅታዋ፣ አነጋገሯ፣ ርጋታዋ፣ ወደ ሙሉ ሴትነት
በመሻገር ላይ ያለው ዳሌዋና ለግላጋነቷ በወባ የተንገላታችው ልባቸው ላይ ነፍስ ዘሩበት።
ድኘ እጐንደር ስገባ ይችን ልዥ አገባለሁ እያሉ ደጋግመው ዛቱ።

እሳቸው እንደዚህ እያሉ ይዛቱ እንጂ፣ ወለተጊዮርጊስ ወደዋት
እንደነበር የሚያሳይ አንዳችም ፍንጭ አላገኘችም። እሳቸውም በግልጽ ያሳይዋት ነገር አልነበረም።

የሚሄዱ ቀን፣ ግራዝማችንና ቤተሰባቸውን ከታላቅ ምስጋና ጋር
ተሰናብተው፣ ውድ ንብረት ወደ ኋላ የተዉ ያኸል እየተገላመጡ፣ ያችን “የአጥቢያ ኮከብ የመሰለች” ሲሏት የከረሙትን የአስራ ስድስት ዓመት ጉብል በዐይናቸው ፈልገው አመሰገኑ። ወለተጊዮርጊስ በተለይ ለእሷ ለቀረበው ምስጋና እጅ ነሥታ ቀና ስትል ዐይኖቿ ከሰውየው ዐይኖች ጋር ተጋጩ።

ከእሳቸው ዐይነ ብሌን ባሻገር ግን ከቋራ እስከ ጐንደር የሚወስደው
መንገድ እንደተቃና አላስተዋለችም።
ከሐሳቧ ስትመለስ ጨዋታው ቀዝቀዝ ብሏል። እንግዶቹም የተዳከሙ መስለዋል። ቤቱም ጨለምለም ብሏል። ሥራ ቤት በየበኩሉ ማሾ ሊያበራ ሽር ብትን ይላል።

ኢሳያስ፣ “እንግዲህ ልዥቱን ይዘን ነገ ጐንደር እንዝለቃ” አለ፣
ግራዝማችን፣ እንኰዬንና ዮልያናን በየተራ እየተመለከተ።

ነገ አለች፣ ወለተጊዮርጊስ። በረጅሙ ተነፈሰች፣ ወላጆቿና አያቷ የሚሉትን ለመስማት ጆሮዋን አቀናች።

“ባይኾን ኸነገ ወዲያ ይሁን፣ ጥቂትም ቢኾን ልዣችንን እንድናዘጋጅ” አሉ፣ አያቷ።

“እንዳላችሁ ይሁን” አለ፣ ኢሳያስ።
ጐንደር መሄዷ ነው! ተጨነቀች። ተርበተበተች። ኸጐንደር ልኸድ? አለች። ንጉሥ ላገባ ጥላዬስ?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ወለቴን ንጉሥ ኸወሰዳት እኔ የሥዕል ንጉሥ ማልሆን”

ጥላዬ፣ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ተቀምጦ ስለራሱና ስለወለተጊዮርጊስ ዕጣ
ፈንታ ያስባል። እናቱ ወይዘሮ ጌጤነሽ የምሽቱን ግብር ውሃ ወጥተው ሲመለሱ አየት አደረጉት። “አምሽተህ ነው?” አሉትና ለራሳቸው ሰምቶ
ይሆን? አሉ። ዛሬ ከልባቸው አዝነውለታል። ወደ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት፣ “በምሽት እንኳ ዕረፍት አይኖርህ ልጄ?” አሉት፣ መሬት ላይ የሚጭረውን አይተው።
👍14
“እነዬ...” አለና ዝም አለ፣ በስጨት ብሏል። ሌት ተቀን እንደዚህ
ሲሉት መስማት አይፈልግም። ለእናቱ ታላቅ ፍቅርና አክብሮት
ስላለው እንደዚህ ባሉት ቁጥር ዝም ይላል፤ በመልሱ ሊያስቀይማቸው አይፈልግም። እንዲያውም እሳቸው ቤት ሲኖሩ ደስ ይለዋል።

ተጫዋችነታቸው የቁመታቸውን ያህል ትልቅ በመሆኑ፣ አባቱ ሲኖሩ
ቤት የሚያስጠላውን ያህል ከእናቱ ጋር እየተጫወተ ውሎ ቢያድር
አይሰለቸውም።

ወይዘሮ ጌጤነሽ ግን ደጅ ወጣ ብለው ሲመለሱ ቤታቸው
ያስጠላቸዋል። የባላቸውን የባላምባራስ ሁነኝን ንትርክ መስማት እጅ እጅ ይላቸዋል። የባላቸው ግትርነት፣ ቁጣና ንዝንዝ መድረሻ ያሳጣቸዋል። በወፍታው አሁን ምን ጎሏቸው ነው ዞትር 'ሚነዛነዙ? ተመስገን ስንኳ ማይለ? እኔስ ዘመድ እንደሌለው ኸኝህ ኸነዝናዛ ጋር ተቆራምጄ መኖሬ፣ ለአንድ ልጄ ስል ማዶል? የወፍታው ልጄን አንድ
ቦታ ቢያደርስልኝ አንድም ቀን አላድር እያሉ እያጉተመተሙ ቤት
ይገባሉ።

ዛሬ ዐዲስ ነገር ሰምተው ልባቸው ለልጃቸው ቢያዝንም፤ ባላቸው
ዜናውን ሲሰሙ የበለጠ እንደሚያዝኑና እንደሚቆጩ ስላወቁ፣ ለዘወትሩ ቤት ሊገቡ ሲሉ የሚሰማቸውን ቅሬታ ወደ ጎን ትተው ወሬውን እያዳነቁ
መግባት መረጡ።

ቤቱ ጨለምለም ብሏል።
ባላምባራስ ሁነኝ ድንክ አልጋቸው ላይ ጋደም ብለው፣ ሚስታቸውን
እንደ ተርብ ለመናደፍ አቆብቁበዋል። ትንሽ ሲያማቸው እንደ ሕፃን ልጅ ያደርጋቸዋል፤ ያነጫንጫቸዋል፣ ያቅበጠብጣቸዋል። ያን ጊዜ
ሚስታቸው ከቤት ባይወጡና አስር ጊዜ ይህን አምጪልኝ፣ ያን
አቅርቢልኝ ሲሏቸው ቢውሉ ደስ ይላቸዋል።

ወይዘሮ ጌጤነሽ ከወጡ፣ “የት ቆይተሽ ነው?”፣ “እስታሁን ምን
ስትሠሪ ቆይተሽ ነው? ወሬ ስታናፍሺ ነው እንጂ አሁን ማ ይሙት ደጅ መውጣት እኼን ያህል ያቆያል? እንደዝኸ ታምሜ መለስ ብለሽ እንኳ ምን ላርግለት 'ማትይ?” እያሉ በነገር ሲያዋክቧቸው ይቆያሉ።

ዛሬም እንደሁልጊዜው የነገር ግብዣ ደግሰውላቸዋል። ይበልጡንም ደግሞ ሚስታቸው ከወይዘሮ እንኰዬ ጋር ጥቂትም ቢሆን አውርተው መግባታቸው ስለሚያናድዳቸው አመሻሽ መተናኮያ ሰዐታቸው ከሆነ
ዓመታት አልፈዋል።

“ጉድ! ጉድ!” አለ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ ሳይቀደሙ ለመቅደም። ቆመው እጅና እግራቸውን በእርጥብ እጃቸው ያባብሳሉ።

ባላምባራስ ዝም አሉ።
ወይዘሮ ጌጤነሽ ባላቸው፣ “ምንድርነው?” ሳይሏቸው በመቅረታቸው ቅር ተሰኙ። ወሬውን ለማውራት የነበራቸውን ጉጉት ስለአመከኑባቸው
ወሽመጣቸው ተቆረጠ። የባላቸውን ዝምታ አሰቡና ነገሩ ከነከናቸው።.....

ይቀጥላል
👍8
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...ሳትታሰብ የተገኘቶው ትርፌ በጋሻው ለብዙዎች ያልታሰበ ደስታ
እስግኝታለች፡፡ ከሁሉም በላይ አስቻለው ተመችቶታል፡፡ ቤቱ ተዘግቶ አይውልም አይዝረከረክም፣ ኦይመሰቃቀልም፤ ትርፌ ሽክፍ አደርጋ ይዛዋለች። የሆቴል ምግብ
ትቶ ቤቱ ውስጥ መመገብ ጀምሯል። እንጻራዊ የሆነ የመንፈስ መረጋጋትም አግኝቷል፡፡ በልሁና መርዕድ እንኳ እንደ ድሮው ፍራሽ በማንጠፍ ከሰል
በማያያዝና ሻይ ወይም ቡና በማፍላት ተራ መጨቃጨቃቸውን ትተዋል።ጫታቸውን ብቻ ገዝተው በተነጠፈና በተበጃጀ ፍራሽ ላይ እግራቸውን መዘርጋት ነው፡፡ ቀሪውን ስራ ትርፌ ታቀለጣጥፈው ይዛለች፡፡

የትርፈ በአስቻለው ቤት ተመልሳ መግባት ለሔዋንም የፀጋ ያህል ሆኗል።ሔዋን የአስራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰደች በኋላ በወቅቱ ግዳጅ በነበረው የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ ሥራ በመጀመሯ በከፊልም ቢሆን ከሸዋዬ ቁጥጥር ውጭ ሆናለች። አጋጣሚ ሆና የተመደበችው ደግሞ በዚያው በዲላ ከተማ
በዜሮ ስምንት ቀበሌ ውስጥ በመሆን ከቤት ወደ ስራ ከስራ ወደ ቤት የምትመላለሰው በአስቻለው ቤት በር ላይ ነው። እናም ስታልፍ ስታንድም ጎራ
ትልበታለች። ትርፌ ስላለች ዘወትር ክፍት ነውና አትቸገርም። ይህ ሁኔታ በእሷና በትርፌ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮት መነፋፈቅ ጀምረዋል።
አንድ ቀን ደግሞ ሁለቱን ለረጅም ሰዓት አብሮ የሚያቆይ አጋጣሚ
ተፈጠረ፡፡ የግንቦት ወር መጨረሻ አካባቢ ነው ሔዋን መሰረተ ትምህርት በምታስተምርበት ጣቢያ አካባቢ አንዲት ሴት ሞተው በለቅሶው ምክንያት በዕለቱ ማስተማር እንደማትችል ከጣቢያ ሃላፊው ይነገራታል፡፡ ከጠዋቱ ሦስት ሠዓት
አካባቢ ወደ ቤቷ ስትመለስ እግረ መንገዷን ወደ አስቻለው ቤት ጎራ ትላለች። ጊዜ ነበራትና ተረጋግታ ቁጭ በማለት ከትርፌ ጋራ ጭውውት ይጀምራሉ። ሔዋን
በአስቻለው አልጋ ላይ ትራስ ደገፍ ብላ ፣ ትርፌ ደግሞ በአልጋው ትይዩ በተነጠፈችው ፍራሽ ላይ ሆና ፊትለፊት እየተያዩ ይጫወታሉ።

«ትርፍዬ!» ስትል ጠራቻት ሔዋን፡
«ወይ እታለም፡፡»
«አገርሽ የት ነው?»
«ውይይ… እታለምዬ! በጣም ሩቅ ነው፣ ቢጠሩት እንኳ አይሰማም፡፡»
ትርፌ የገጠር ኑሮዋ ባያጎሳቁላት ኖሮ ቀይና ስልክክ ያለች፣ ዓይንና
ጥርሶቿ እዩኝ እዩኝ የሚሉ መልከ ቀና የነበረች ልጅ ትመስላለች፡፡ ያም ሆኖ አሁን ወደ አስቻለው ቤት ከተመለሰች ወዲህ ወዘናዋ እየተመለሰ መጥቷል።
«የት ቢሆን ነው ትርፍዬ?» ስትል ሔዋን ደግማ ጠየቀቻት የትርፌን
ሁለመና አየት ሰለል እያደረገች።
«ወሎዬ ነኝ፡፡»
«ውይይ... ከዚያ እዚህ ድረስ አንዴት መጣሽ?»
«ታሪኩ ብዙ ነው እታለም። ደግሞም ያሳዝናል።»
«እንዴት ትርፌ»
«በቃ ያሳዝናል፡፡»
«ከመማጣሽ ግን ምን ያህል ጊዜ ሆነሽ?»
«ወደ አስር ዓመት ሊሆነኝ ነው፡፡»
«ውይይ..» አለችና ሔዋን አሁንም ግን «ግን እንዴት መጣሽ?» ስትል
ጠየቀቻት
«ተጣጥዬ»
“ማለት?»
«የወሎ ድርቅ ሲባል ሰምተሽ ታውቂያለሽ?»
«አዎ»
«በድርቁ ዘመን እኔ ህጣን ልጅ ነብርኩ። የተወለድኩት ውጫሌ እሚባል ቦታ ነው።ያኔ በድርቁ ጊዜ በአገሩ ላይ የሚበላም የሚጠጣም ጠፋ። የአገሩ ሰው ሁሉ ተነቅሎ ተሰደደ።አባቴ በድርቁ ምክንያት ቀደም ብሎ ሞቶ ስለነበር እኔና እናቴም ሕዝቡ ሲሰደድ አብረን ተሰደድን
«ወደዚህ ወደ ሲዳሞ?»
«አይደለም ወደ ደሴ ወደሚባል ከተማ ነው።»
«ታዲያ እዚያ የሚበላና የሚጠጣ አገኛችሁ?»
«እየየ እታለም! ምን ይገኛል ብለሽ? ጣጣው ብዙ ነበር፡፡» አለችና ትርፌ አሁንም በትካዜ ባህር ውስጥ ገባች፡፡ ያን በልጅነት አዕምሮዋ የተቀረፀ የርሀብ
ሁኔታ የቻለችውን ያህል ለማስታወስ ትሞክር ጀመር፡፡ ትርፌ የዚያን ጊዜ ገና
የስድስት ወይም ሰባት ዓመት ህጻን ስለነበረች ሁሉን ነገር አታውቀውም እንጂ ሁኔታው እጅጉን አሳዛኝ ነበር፡፡
«አዎ፡ እንደ ሰው ጨክኗል! የወሎ ሰማያ፡፡ ከዝናብ ሰጪ ደመናዎች ጋር ላይታረቅ የተጣላ ይመስል ቁልጭ ጥርት እንዳላ ድፍን ሶስት ዓመታት አለፉ።ፀሐይና ጨረታ ለእንዴ እንኳ በደመና ውስጥ ብቅ ጥልቅ እያሉ የአየሁሽ ጨዋታ
ሳይጫወቱ በጠራው ሰማይ ላይ ተንቀለቀሉበት፡፡ በተለይ ፀሐይ በየቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት ሙሉ እየነደደች የወሎን ምድር ታነደውና ታቃጥለው ጀመር።ወንዞች ነጠፉ። ሳር ቅጠሉ ደረቀ። ዛፎች ወደ ጭራሮነት ተቀየሩ። ቢመጣ ንፋስ ቢነሳ አቧራ ብቻ ሆነ።
የወሎ ገበሬ የመጀመሪያውን የድርቅ ዓመት ቀድሞ የነበረውን ጥሪት ተጠቅሞ ሳይደናገጥ ተወጥቶት ነበር። የሁለተኛው ግን ወገቡን ሰበረው፡፡ ሶስተኛው ደግሞ ከሥሩ ነቀለው፡፡ እንኳን ለራሱ ለሰንጋ ፈረሱ የእህል ዓይነት ይመርጥ እንዳልነበረ ሁሉ እንኳን ያቀምሰው የሚቀምሰውም አጣ፡፡ በሰንጋ ፈረስ ይጋልብ የነበረ የወሎ መኳንንት፤ በሲናር በቅሎ ስትፈስ የነበረች የወሎ ወይዛዝርት ሁሉ እርካባቸው ወለቀ። ግላሳቸው ተጠቀለለ። በቅሎና ፈረሶቻቸው የአውሬና የአዕዋፍ
ሲሳይ ሆኑ። አጥንቶቻቸው ሜዳ ሙሉ ተረጩ። የረገመው ሳይታወቅ ወሎ ምዕዓት ወረደበት። የረሀብ እሳት ያቃጥለው ጀመር፡፡ በቸነፈር ተመታ።
በዚያን ጊዜ፣ በዚያን ዘመን፣ የወሎ ሕዝብ ምርጫው አንድ ብቻ ነበር፤ ስደት። አቅጣጫው ደግሞ ወደ ደሴ ከተማ፡፡ ይህም ምክንያት ነበረው፡፡ የወቅቱ
ንጉሥ ለጉብኝት ደሴ ከተማ እንደሚገቡ ተወርቶ ነበር፡፡ እሳቸው ደግሞ በሄዱበት ሁሉ ለልጆች ከረሜላ በመርጨታቸው ብቻ የቸርነት ዝናን ያተረፉ ነበሩና
የወሎ ርሃብተኛ ወደ «ቸሩ» ንጉስ በመሄድ የልመና እጁቹን ለመዘርጋት ዳር አስከዳር ተነጋግሮ ወደ ደሴ መጓዝ መትመም ጀመረ።
ከሰሜን አቅጣጫ የራያና የየጁ ሕዝብ በርሀብ የመነመነ ሰውነቱን
ብጥቅጣቂ ጨርቅ እየሸፈነ ሰንሰለት ሰርቶ ወደ ደሴ ሲግተለተል የአንባሰል ተራሮች ቁልቁል እየተመለከቱ ይታዘቡ ነበር፡፡ ከምዕራብና ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ የቦረና! የወረሂመኖ፣ የሳስታና የወገልጤና ሕዝብ ተነቅንቆ ወደ ደሴ ሲጓን በመሀል እየደከመው በገሪዶና በቦሩ ሜዳ ላይ ሲፈስ የጦሳ ተራራ መዓል ላይ ቆሞ ግራና ቀኝ እየተመለከተ ያለቅስ ነበር፡፡ ከምስራቅና ከደቡብ ምሥራቅ
ደግሞ የአውሳ የቃሎ፣ የእንቻሮና የከሚሴ ሕዝብ በበረሃ አለባበስ ዘይቤው ከወገብ በታች ሽርጥ መሳይ አገልድሞ ከወገቡ በላይ ሲያዩት ግጠው ግጠው የጣሉት
አጥንት መስሎ ወደ ደሴ ሲተምም የቦርከና ወንዝ «እናንተስ ወደ ንጉሳችሁ ሄዳችሁ፤ የእኔንስ ችግር ለአባይና ለተከዜ ማን ይንገርልኝ»
እያለ የሚያዝን ይመስል ነበር፡፡
በጋ ከክረምት የውሃ ፈረሰኛ ሲያጓራበት እንዳልነበረ ሁሉ ያኔ ግን ክው ብሎ ደርቋልና በውስጡ የነበሩ ቋጥኛች ጨው መስለው የፀሐይ ንዳድ እየፈነከታቸው ነበር፡፡

ያ ሁሉ የወሎ ርሀብተኛ በዚህ መልክ ተጉዞ ተጉዞ ደሴ ከተማ ሲደርስ ያሰበው አልሆነለትም። እንዲያውም ወደ መሀል ደሴ ከተማ መግባት እንኳ ሳይፈቀድለት ቀረ። የንጉሡ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶች በየመጣበት አቅጣጫ ተሰልፈው ጠበቁት። ከስሜን በኩል የመጣውን በሮቢት ገበያ ላይ፣ ከምዕራብ በኩል የመጣውን ከሰኞ ገበያ ላይ እንዲሁም ከምስራቅና ደቡብ ምስራቅ እቅጣጫ የመጣውን
ርሀብተኛ ሀረጎ አፋፍ ላይ በተሰራ የእንጨት አጥር ውስጥ እያስገቡ አጎሩት። በቀን አንዳንድ ዳቦ ለእያንዳንዱ ርሀብተኛ እንደ ውሻ ይጥሉለት ጀመር፡፡ እንዳይነቃነቅ ይጠብቁትም ጀመር።
👍9
ንጉሡ ደሴ ከተማ ገቡ። ከጦሳ ተራራ በስተ ደቡብ ምሥራቅ በኩል በምትገኝ ጎራ ላይ ተሰርቶ ፡ ከስፋቱና የገባ ቢገባበት በቃኝ የማይል ከመሆኑ የተነሳ
"አይጠየፍ" ተብሎ በሚታወቀው አዳራሽ ውስጥ በተመቻቸ መድረክ ላይ በተዘጋጀ
ዙፋናቸው ላይ ተሰየሙ። ቤተሰባቸውና የቅርብ ዘመዶቻቸው ግራና ቀኝ ከጎናቸውና ከኋላቸው ተኮለኮሉ፡፡ መሳፍንቶቻቸው ደግሞ እንደየማዕረጋቸው ቅደም ተከተል
ፊትለፊታቸው ተደረደሩ፡፡ የነቁ የበቁ አስተናጋጀች ነጠላቸውን አሸርጠው ያጋፍሩ ጀመር፡፡ እየተበላ እየተጠጣ ይሸለላል ይፎክር ጀመር፡ ምድር ቀውጢ ሆና የሚዘለልባትን ያህል እሷም ተንቀጠቀጠች፡፡

በዚህ ጊዜ ደሴ ከተማ ሁለት ተቃራኒ ትዕይንቶች በተመሳሳይ ሰዓት የሚከናወነባት አንድ መድረክ ሆነች። በአንድ በኩል አፍንጫ ከሚቆርጥ ቀይና አልጫ ወጥ በተጨማሪ ጮማ እየተቆረጠ ከጠጅ እስከ ውስኪ እየተጠጣና ሻምፓኝ እየተረጨ በፈንጠዚያ ጮቤ የሚረገጥባት ምድራዊ ገነት፡ በሌላ በኩል
ደግሞ የቀን ሀሩር እያቃጠለው የሌሊት ቁር እየጠበሰው እንደ ኩበት በበረት ውስጥ ታጎሮ በርሀብ አለንጋ በመገረፍ ላይ ካላ ሕዝብ የስቃይ ጩኸት የሚሰማባት ሲኦል!! ደሴ ከተማ አዘነች።ለሉሮ አመቺ ከመሆኗ የተነሳ እናት ከተማ ተብላ
ምትታወቀው ደሴ እወነትም በሕዝቧ የስቃይ ጩኸት የእናትነት ሆዷ ተምቦጫቦጨና እንደሰው አለቀሰች።
የአይጠፉ ትዕይንት አስተላለትም ሌላው የወቅቱ አስገራሚና እና አሳዛኝ ክስተት ነበር። ንጉሡ ባላምባራሱን ግራ አዝማች ግራዝማቹን ቀኝ አዝማች ቀኝ
አዝማቹን ፈታውራሪ ፊታውራሪውን ደጃዝማች ደጃዝማቹን ራስ ወዘተ እያሉ ከሾሙና ከሸለሙ በኋላ የሚያደርጉትን አጭር የመዝጊያ ንግግር መሀል የወሎን ረሃብ ጉዳይ አንስተው አንድ ነገር ሊሉ
እንደሚችሉ ተጠብቀው ነበር፡፡ እሳቸው ዐግን ወይ ትንፍሽ" ይልቁንም ያኔ በማይጨው ጦርነት ጊዜ ተሸንፈው ወደ አዲስ
ወቅት የወሎ ሕዝብ እኛን ለጥቃት አገርህን ለጠላት ሰጥተህ ወዴት? በማለት መንገድ ዘግቶ አላሳልፍ ብሏቸው የነበረ ከመሆኑም በላይ ጥሰው
ለማለፍ፡ ሲሞክሩ ተዋግቷቸው እንደነበረ በማስታወስ ሳይሆን አይቀርም ወሎን በደጉም
በክፉም ቀን እናውቀዋለን በማለት ተሳልቀውበት ነበር በማግስቱ ወደ
ዙፋን መአከላቸው አዲስ አበባ የተመለሱት።

ወሎ ተከዳ፡፡ አዎ ወሎ ምርቱን በጉድጓድ፣ ዱቄቱን በጎተራ ይከት
የነበረ በሩሀሩህነቱና በቸርነቱ ይታወቅ የነበረ ወሎ እባ መስጠት ክፋትና ተንኮል! ሸርና ምቀኝነት የማያውቀው በገርነቱና በየዋህነቱ ታውቆ "ወሎ መጀን"
እየተባለ ሲመጀንበት የሚኖር አገር ወሎ እንኳን አዛውንቱ እረኛው ትንቢት ኢማሞች እንዲሁም የቃሉ አብረው የሚኖሩበት የፍቅርና የመቻቻል አገር፤ አብሮ የመኖር ተምሳሌት ወሎ! ሰውም አምላኩም በከንድነት ከዱት፡፡ በመከራው ጊዜ ደራሽ ከጥቶ የሰው ልጅ እንደ ቅጠል ረገፈ፣ በርሀብሄ
ትርፌ ግን ይህን ሁሉ ሁኔታ በዝርዝር አታወቀውም፡፡ ግን ደግሞ የችግሩ ወላፈን ጠብሷት ነበርና የምታውቀውንና የምታስታውሰውን ያህል ለሔዋን
ለማጫወት ከስባ ከትካዜዋ ብንን አለች።
«ምን መሰለሽ እታለምዬ!» ስትል ቀገለች። «እኔና እናቴ ከሕዝቡ ጋር
መጥተን ደሴ እንደ ደረስን ሮቢት በሚባል የገበያ ቦታ ላይ በእንጨት በታጠረ ግቢ
ውስጥ እንድንገባ ተደረግን፡፡ ከዚያም ትንንሽ ዳቦ በቀን አንዴ ይታደለን ጀመር።
እናቴ ግን ያንኑ የድርሻዋን ዳቦ ብዚ ጊዜ ለኔ ነበር የምትስጠኝ! ለኔ በግል የምትደርሰኝን አታጠግብሽም በማለት፡፡» አለችና ትርፌ እንባዋ በዓይኗ ላይ
አቀረረ። ንግግሯን ግን ቀጠለች።
ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ እናቴ ደከመችና መላወስም እያቃታት ሄደ። አንድ ቀን በጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ እሷ ተኝታ ቀረችብኝ፡፡ በመሀል ዳቦ
የሚያድሉት ስዎች መጡና ላእሷም ለኔም ትቀበልልኝ ዘንድ ልቀስቅሳት ብሞክር አልሰማ አለችኝ። ሰውነቷን ገፋ ገፋ ሳደርጋት መላ ሰውነቷ አብሮ ይነቃነቅ ጀመር። በጩኸት ስጠራት የሰማ አንድ ሰው ጠጋ ብሎ እናቴን ካያት በኋላ በቃ ተያት
እሷ፣ ተገላግላለች አለኝ፡፡ ለካስ እናቴ ሞታ ኖሯል፡፡» አለችና ትርፌ
ድንገት «እማይዬ...» ብላ ጮኸች፡፡
ሔዋን በእስከ አሁኑ የትርፌ አተራረክና በዓይኗ እንባ ማቅረር ምክንየመት አንጀቷ እየተላወሰና በ እሷንም እንባ እንባ ሲላት እንደነበረ ሁሉ እንደገና ስትጮህ
ድንግጥ ብላ ከአልጋው ላይ ተስንፈጥራ ታነሳችና ወደ ትርፌ እየተራመደች
«ተይ ትርፍዬ» አለቻት። ነገር ግን በልመናዋ አልገፋችበትም ሔዋን እራሷ ነገር ጥናዋ ነውና በትርፌ እናት ላይ የደረሰው ሁሉ ልክ በእሷም እናት ላይ የደረሰ ያህል ተሰምቷት የትርፌን አንገት እንቅ እድርጋ ይዛ አብረው ይላቀሱ ጀመር።
ትንሽ ቆይተው ተላቀቁ፡፡ ሔዋን ከትርፌ አጠገብ ቁጭ ብላ
ልታፅናናት ሞከረች። ትርፌ ግን አንባዋን እያፈሰሰች ትረካዋን ቀጠለች፡፡
ከዚያ በኋላ እታለምዩ ምን ሆነልሽ መሰለሽ፡ ረፋዱ ላይ አንድ መኪና
መጣ። የእናቴን አስከሬን ጭነው ወሰዱት። እኔም ያለ እናት ቀረሁ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ከዚያ ግቢ አውጥተው ወሰዱኝ፡፡ የሄድከብት ቦታ ብዙ ህፃናቶች ነበሩ። ከእነሱ ተቀላቀልኩና እንጀራ በወጥ መብላት ጀመርኩ፡» አለችና ዓይኗንም አፍንጫዋንም ትጠራርግ ጀመር፡፡

«እዚያው አሳደጉሽ?» ስትል ሔዋን ጠየቀቻት።
«አንዳንድ ሰዎች ወደ ህጣናቱ እየመጡ ደስ ያላቸውን እየመረጡ ይወስዱ ነበር፡፡ እኔም በዚያ ቦታ ላይ ጥቂት እንደ ቆየሁ አንድ ቀን አንዲት ሴትዮ መጣችና ከልጆቹ መሀል ስትዘዋወር ቆይታ ወደኔ ጋ ስትደርስ “ይቺን ልጅ ልውሰዳት
በማለት ህጣናት ጠባቂዎቹን ጠየቀቻቸው። ፈቀዱላትና ወደ ቤቷ ወሰደችኝ፡፡ እሷ ዘንድ ለአምስት ዓመታት ቆየሁ፡፡»
«ከዚያስ?» ስትል ሔዋን አሁንም ጠየቀቻት። የትርፌ ታሪክና አኳኋን
እያሳዘናት ከአንገቷ ገደድ ብላ በሀዘን ስሜት ትመለከታታለች።
«ከዚያ በኋላ ደግሞ ተማሪዎች በጠበጡ። እየተገደሉም በየመንገዱ ተዘርረው መዋል ጀመሩ፡፡» አለች ትርፌ የወቅቱን የተማሪዎች የተቃውሞ
ንቅናቄና የተፈፀመባቸውን የጭካኔ ግድያ በራሷ አመለካከትና ግንዛቤ መጠን
ስትገልፀው። «ከተማሪዎች ጋር አንዳንድ ሰው እየተጃለፈ ይገደል ስለነበር አንድ ቀን የዚያች ታሳድገኝ የነበረችው ሴትዮ ባለቤትም ሞቶ ተገኘ፡፡ የዚያች ሴትዮ እህት እዚህ ዲላ ውስጥ ትኖር ኖሯል! ለለቅሶ መጥታ ደሴ ሰነበተች። ከአሳዳጊዬ ጋር ተመካክረው ኖሮ ስትመለስ ተነሽ እንሂድ ብላ እዚህ ዲላ ይዛኝ መጣችና የቤት ሰራተኛዋ አደረገችኝ፡፡» አለች ትርፌ አሁንም እንባ እየተናነቃት፡፡
«አይዞሽ ትርፌ» አለቻት ሔዋን የትርፌ ሁኔታና ታሪክ እያሳዘናት።
ትርፌ ትረካዋን ቀጠለች፡፡ በዚህ ሁኔታ ጥቂት ዓመታት ከቆየሁ በኋላ እኔም አደግሁ መሰለኝ፤ የሴትዮዋ ባል ባለፍኩ ባገደምኩ ቁጥር ይጎነትለኝ ጀመር፡፡
አንድ ቀን ደግሞ ሲተናነቀኝ ባለቤቱ ደረሰችና አየችው። ከዚያም እኔን አስወጥታ
በአንድ ወቴል ቤት በእንጀራ ጋጋሪነት አስቀጠረችኝ። ከጋሽ አስቻለውም ጋር የተዋወኩት እዚያው ሆቴል ውስጥ ስሰራ ነው። ጠባዩ ጥሩ ስለሆነ እወደው ነበር።
እሱም እኔን እንደ ገረድ ሳይቆጥረኝ በትትና ነበር የሚያነጋግረኝ፡፡ በዚያ ቤት ትንሽ
እንደሰራሁ አሁንም ከአሰሪዬ ጋር ሳልስማማ ቀረሁና ወጣሁ። ጋሽ አስቻለውን ስራ እንዲያስገባኝ ጠየኩት። እሺ እፈልግልሻለሁ ብሎ ዋል አደር ካለ በኋላ እኔ ጋር ብትሆኒስ አለኝ ምን ገዶኝ!» አልኩት፡፡ በቃ በተነጋገርን ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ ታጋሽ አስቻለለው ጋር መኖር ጀመርኩ፡፡
👍71
ሔዋን ከንፈሯን መጠጥ አድርጋ ዲላ ውስጥ ምንም ዘመድ የለሽማ ስትል ጠየቀቻት፡፡
«ምንም አታለምዬ የኔ ዜመድ ጋሽ እስቻለው ብቻ ነው። ምናልባት
ከእንግዲህ ወዲያ እንቺ ትጨመሪልኝ እንደሆነ እንጂ … አለቻት።
ሔዋን፣ ድንገት የትርፌን አንገት እንቅ አድርጋ በመያዝ ጉንጯ ላይ ሳም አደረገቻትና ምንም አትጠራጠሪ ትርፍዬ " እህት እሆንሻለሁ።» አለቻት
ትርፌ አሳዛኝ ታሪኳን ስትተርክ ሔዋንም በአንክሮ ስታዳምጥ
ሳያውቁት ሰአቱ ሄዶ ኖራል ልክ ከቀኑ ስድስት ሰአት ያ ሰአት ደግሞ እንደ ወትሮ ቢሆን ሔዋን ከቤቷ መድረሸዋ" ትርፌ ደግሞ ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት ከስራ
ወጥቶ ወደ ቤተ ለሚመጣው አስቻለው የምሳ ዝግጅት ማገባደጅዋ ነበር የሰአቱን
መድረስ ሁለቱም ሲያውቁ ድንገት ስሜታቸውን ቀየሩ። ሔዋን ወደ ቤቷ ለመሄድ ትርፌ የምሳ ዝግጅት ለመጀመር ከተቀመጡበት ብድግ ብድግ አሉ ሔዋን ትርፌን ተሰናብታ ከቤት ልትወጣ ስትል ትርፈ አናገረቻት፡፡
«ዛሬ የኔን ታሪክ ሰምተሻል እታለም። ሌላ ጊዜ ደግሞ አንቺና ጋሼ አስቻለው እንዴት እንደተገናኛችሁና እንደተዋወቃችሁ ተራሽን ታወሪልኛለሽ እሺ አለቻት ፈገግ ብላ በአይኗ እየተከተለቻት።
«እስከ አሁን እስቼ አልገረሽም» አለቻት ሔዋንም ዞር ብላ ትርፌን በፈገግታ እያየቻት
«ምንም እታላምዬ እኔ የማውቀው እያየሁት ያላውን ነገር ብቻ ነው፤
አለችና አንቺና ጋሼ አስቻለው መቼ ይሆን የምትጋቡትን» ስትልም እንደ ቀልድ ጠየቀቻት፡፡
በዚያች ቅፅበት አስቻለው በር ላይ ደርሶ ኖሯል፡፡ ትርፌ ለሔዋን
ያቀረበችላትም ጥያቄ ሰምቷል። ሔዋን ከመናገሯ በፊት ፈጠን ቀልጠፍ ብሎ በቅርቡ ትርፌ! በጣም በቅርቡ፡፡ ግፋ ቢል ከሁለት ወይም ከሶስት ወራት በኋላ እያለ ወደ ቤት ገባ። ትርፌና ሔዋን ፍጹም ያላሰቡት አጋጣሚ ስለነበር ሁለቱም ድንግጥ ድንግጥ አሉ።
ሔዋን ወዲያው «እንዴ አስቹ! በአሁኑ ሰዓት እንዴት መጣህ?» አለችው የአንቺን ቤቴ ወስጥ መኖር ቀልቤ ነግሮኝ አላት እየቀለደ፡፡ ጠጋ አለና
እንደ ቆመች እንገቷን እቅፍ አድርጎ ከንፈሮቿን ሳም አደረጋቸው፡፡ በእጁ ዳጎስ ያለ
የካኪ ፖስታ ይዟል።
ለአስቻለው በዚያ ሰዓት መምጣት ሰበቡ ሔዋንን ከመሰረተ ትምህርት ስራ ያቋረጠ ለቅሶ ነው። ሟቿ የስራ ባልደረባው እናት ኖረዋል። ለስድስት ሠዓት ቀብር
መጥቶ ነው። ከዚያ በኋላ ላላው አጭር የስራ ሠዓት ሲል ዲላ ሆስፒታል ድረስ ላለመሄድ ወስኖ

«ምነው ሔዩ በር ላይ ቆምሽ?» ሲል ጠየቃት፡፡......

💫ይቀጥላል💫
👍4
#ምንትዋብ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


....“ጉድ! ጉድ!” አለ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ ሳይቀደሙ ለመቅደም። ቆመው እጅና እግራቸውን በእርጥብ እጃቸው ያባብሳሉ።

ባላምባራስ ዝም አሉ።
ወይዘሮ ጌጤነሽ ባላቸው፣ “ምንድርነው?” ሳይሏቸው በመቅረታቸው ቅር ተሰኙ። ወሬውን ለማውራት የነበራቸውን ጉጉት ስለአመከኑባቸው
ወሽመጣቸው ተቆረጠ። የባላቸውን ዝምታ አሰቡና ነገሩ ከነከናቸው።.

“ምንድርነውም አይሉ?” አሏቸው፣ የጎሪጥ እያይዋቸው።
“የትም አምሽተሽ መተሽ ደሞ ጉድ ትያለሽ?” አሉ፣ ባላምባራስ።

“ነገረኛ፣ ታሞ አይተኛ አሉ” አሉ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ፣ ድምፃቸውን
ዝቅ አድርገው።

“ምን አልሽ?”

“ምን እላለሁ ሳናግርዎ መልስ አይሰጡም ወይ ነው ያልሁት። ሌላ ምን እላለሁ?” አሉ፣ ራት ለመሥራት ምድጃ ላይ ድስት የጣደችውን የቤት አገልጋይ እያዩ።

“ሚሰማሽ ካገኘሽ ምላስሽ ረዥም ነው።”

“ኸርሶ አይበልጥ” አሉ፣ አሁንም ቀስ ብለው።

ባላምባራስ ቆጣ ብለው፣ “ምን አልሽ?” ካሉ በኋላ፣ ጉድ ከሰሙ
ስለ ሰነበቱ ጉዱን የመስማት ፍላጎት አደረባቸው። ቁጣቸውን ገታ አድርገው፣ “እና ምንድርነው ጉዱ?” አሉ፣ ለጠጥ ብለው እምብዛም ለወሬ የጓጉ እንዳይመስሉ።

ወይዘሮ ጌጤነሽ እንዳልሰማ ዝም አሉ፤ እንደ ማኩረፍ አድርጓቸዋል።

“ምንድርነው ጉዱ አልሁሽ እኮ” አሉ ባላምባራስ፣ ቆጣ ብለው።

ወይዘሮ ጌጤነሽ አሁንም ያልሰሙ መሰሉ።

“ሳናግርሽ መልስ 'ማሰጪ?” የባላምባራስ ቁጣ እየተጋጋለ ነው።

“ምን አሉኝ?” አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ። ፊታቸው ላይ ስስ ፈገግታ ይነበባል። ዛሬ አነስተኛ ቢሆንም ባላቸው ላይ ድል ተቀዳጅተዋል።

እነዚህን መሳይ ጥቃቅን ድሎች ናቸው አንዳንዴ ባላቸውን ያሸነፉ
እንዲመስላቸው የሚያደርጓቸው።

“ጉድ እያልሽ ገባሽ። ምንድርነው ብልሽ አለመጥሽ።” አሁንም
ድምፃቸው ገኗል፣ ባላምባራስ ሁነኝ።

“አልሰማሁ ሁኜ ነው” አሉ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ። የባላቸው ቁጣ
የሚገነፍልበትን አፍታ ስለሚያውቁ ያገኙትን ድል እያጣጣሙ፣
“የግራማች ልዥ ...” ሲሉ ጀመሩ።

“ግራማች?” ሲሉ አቋረጧቸው፣ ባላምባራስ። ወሬውን ለመስማት
ቸኩለዋል።

“ግራማች መንበር ናቸዋ።”

“ኸሷው ጋር ስታወሪ እንደቆየሽ አውቄያለሁ። ወልደልዑል ምንን
ሆነ?”

“ሴቷ ወለቴ።”

ጥላዬ፣ የሆነ ነገር እንዳለ ደመነፍሱ ነገረው። ነፍሱ ከዳችው። ጉዱን ለመስማት ቤት ውስጥ መግባት ፈልጎ፣ ወገቡ አልታዘዝ፣ ጉልበቱ አልንቀሳቀስ አለው። እንደምንም ብሎ ተነስቶ ውስጥ ገብቶ መደብ
ላይ ተቀመጠ።

ባላምባራስ በመገረም ተመለከቱት። እሳቸው ሳይተኙ ቤት ውስጥ ስለማይገባ፣ ዐይኑን ካዩት ከርመዋል። ሆዳቸው ተገላበጠ።

“እና ምንን ሆነች?” አሉ፣ መባባታቸው እንዳይታወቅባቸው
እየታገሉ።

ወይዘሮ ጌጤነሽ ከመናገር ተቆጠቡ። ጥላዬን ሰረቅ አድረገው አዩት።እሱ የሚሉትን ለመስማት ቢጓጓም ጎንበስ ብሎ መሬቱን በስንጥር መጫጫር ጀመረ።

“ዛሬ ምንን ነክቶሻል? ምንን ሆነች ስልሽ መልስ ማሰጪ?”

“በያ ሰሞን ንዳድ ይዟቸው ኸነሱ ዘንድ ተኝተው የነበሩት ለካስ
ንጉሡ ኑረዋል...”
“ንጉሠ?”
“አዎ።”
“አጤ በካፋ?”
“እሳቸው። ሌላ ንጉሥ አለ?”
“ምንድርነው ምታወሪው?” አሉ ባላምባራስ፣ የሚስታቸውን ትንኮሳ
ችላ ብለው።
መንን
“አጤ በካፋ ራሳቸው። ወለቴ አስታማቸው ስታበቃ ዛሬ ሰዎች
ኸጥሎሽ ጋር ሰደዱ።”
“ሊያገቧት?”
“ኋላ?”
ጥላዬ ዱብ ዕዳ ሆነበት፣ ድንጋጤ ሰውነቱን አብረከረከው። ተነስቶ
ሊወጣ ፈልጎ ወሬ ለመስማት ተቀመጠ።

“ሰው ለማንጓጠጥ ማን ብሎሽ። ወረኛ! ደሞ ማታመጪው የለ” አሉ
ባላምባራስ፣ ተደናግጠዋል፣ ንዴትም ተናንቋቸዋል።
“እንዴት በሉ? ምን ያልሆነ አምጥቸ አውቃለሁ? ኸመሽ አገር ሁሉ ሚያወራው እኼንኑ ማዶል? የጣ ፈንታ ነገር ይገርማል።”

“ውነት ነው፤ ዕጣ ፈንታ ነው” አለ ጥላዬ፣ የሞት ሞቱን። ሰውነቱ
እየራደ ነው። ለራሱ፣ እኔ ዕድል ፈንታየ ሁኖ ያልታደልሁ ሁኘ
የወፍታው እኼን አሰማኝ ብሎ በዐይኑ ውሃ ሞላ። እንባው እንዳይታይበት እደጅ ሲወጣ፣ አባቱ በዐይናቸው ተከተሉት።

“ያቺ አያትየው ኸደብተሮቹ ነው ውሎዋ። ኸተኙበት ቀባብታቸው
ይሆናል ይላል ድፍን ቋራ” አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ፣ አገልጋይዋ ራት
እንድታቀርብ በእጃቸው ምልክት እይሰጡ።

“ድፍን ቋራ ኸምኔው ሰምቶ ነው እኼን ሁሉ ሚለው? አንቺና
ጓደኞችሽ ጓሮ ሁናችሁ ያቦካችሁት ነው እንጂ። ለነገሩ ልዥቱ
ምንም አይወጣላት። ደማም... ቆፍጣና... ይገባታል፤ ይገባታል ::
ሚገባትን ነው ያገኘች። እኔ ለተክለሃይማኖት ተዋጋህ እየተባልሁ ስወቀስ የተክለሃይማኖትን ወንድም በካፋን አገባች?” አሉ ባላምባራስ፣
በመገረም ራሳቸውን እየነቀነቁ።

አገባች! እርምዎን ያውጡ እንግዲህ! በርሶው አጓጉል ጠባይ ነው እኼ ሁሉ የመጣው። እርስዎንስ ይበልዎ፣ ልጄን ጎዱብኝ እንጂ አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ፤ ለራሳቸው። ጮክ ብለው ሊናገሩ ፈለጉና በማታ ኸሳቸው ጋር ምን አጫጫኸኝ ብለው፣ “ኸቤታቸው ንግርት አለ ይባላል። ዘመዳቸው የሆነ ሰው ኸወለቴ ግንባር ጠሐይ ስትወጣ አይቷል” አሉ።
ባላምባራስ መልስ አልሰጧቸውም። ቁጭት ላይ ናቸው። ልዥህን ለልዤ ስባባል ቆይቶ፣ በትንሽ ነገር ኸጥብቅ ወዳጄ ተቀያይሜ፣ አሁን
እኼው ሌላ...ያውም ንጉሥ ወሰዳት። እንግዲህ ኸንጉሥ መንጋጋ አላስጥላት! ያቺ ቀን እንዴት ያለች የተረገመች ናት አሉ፣ ግራዝማች መንበርን የተቀየሙበትን ቀን አስታውሰው።

የጊዮርጊስ ማኅበር ነው። ግራዝማች መንበር ቤት ይበላል፤ ይጠጣል። ጨዋታው ደምቆ፣ እንደወትሮው ስለ ጦር ሜዳ ጀግንነት ይወሳል። ባላምባራስ ሁነኝ ራሳቸውን እንደ ጀግና ቢቆጥሩም፣ ስለ ጦር ሜዳ
ሲወራ አይወዱም።ከዚህ በፊት ሰድበውት የሚያውቁት ደብተራ ሞቅ ብሎታል። “አሁን በወፍታው ኸጦር ሜዳ ቋንጃውን የተመታ ዠግና ይባላል?” ብሎ በሳቅ
ተንተከተከ።

ማንም አልሳቀ። ሁሉም አንገቱን ደፋ። ሳቅና ቁም ነገር የሰፈነበት
ስብስብ ወደ መሸማቀቅ ተለወጠ።

ደብተራው የሳቀለት ሲጠፋ፣ “እኛ ባገራችን ምናቀው ሰው ቋንጃውን
ሚመታው ሲሸሽ ነው” አለ፣ የፌዝ ሳቅ እየሳቀ።
ባላምባራስ ከዓመታት በፊት ቋንጃቸውን ተመትተው ያነክሳሉና
እሳቸውን ሊነካ መሆኑን አውቀው ከተቀመጡበት ተነሥተው
ከዘራቸውን እየወዘወዙ፣ “አንት መተተኛ ደብተራ። እኔ ሁነኝ በንዳንተ ያለ ድግምተኛ አልሽረደድም። የት አባህ ጦር ሜዳ ውለህ ታውቃለህና
ስለ ጦር ሜዳ ታወራለህ? ጋን እያሸተትህ ኸድግስ ድግስ ዙር እንጂ።

ጥፋተኛው አንተ ሳትሆን አንተን ኸሰው መኻል የቀላቀለህ ነው” ብለው ከዘራቸውን ግራዝማች መንበር ላይ እየወዘወዙ፣ “መንበር አሰደብኸኝ ...
ያውም በዝህ በድውይ። ግድ የለም። እንዲህ ኻሰደብኸኝ ወዲያ እመቃብሬ እንዳትቆም... ኸዚህ ያላችሁ ሁሉ ቃሌን ቃል እንድትሉ”
ብለው እያነከሱ ወጡ።
ከዚያን ቀን ጀምሮ የግራዝማችና የባላምባራስ የረጅም ዘመን ጓደኝነት አከተመ፣ አብሮም የጥላዬና የወለተጊዮርጊስ ዕጮኛነት። ባላምባራስ፣
“በቤቱ አሰደበኝ” ብለው ቂም ያዙ። ግራዝማች፣ “ደብተራው ለሰደበው እኔ ምን አረግሁ?” ብለው ቅር ተሰኙ። አስታራቂ መሃከላቸው ቢገባ ባላምባራስ፣ “ሙቼ ነው ቁሜ ኸሱ ጋር ምታረቅ” አሉ። “ልዥህን
ለልጄ” የተባባሉት ጓደኛሞች ተቀያየሙ።

ግራዝማች መንበር፣ ሁነኝ ምንም ቢሆን የረጅም ጊዜ ወዳጄ ነውና
አንድ ቀን እንታረቅ ይሆናል እያሉ የወለተጊዮርጊስን እጅ ለጠየቀ ሁሉ አይሆንም እያሉ መለሱ።
👍15
ባላምባራስ ሁነኝ ወለተጊዮርጊስን ለልጃቸው
እየተመኙ ሳይጠይቁ ዓመታት አለፉ። ዛሬ ወለተጊዮርጊስ በንጉሥ መታጨቷን ሲሰሙ እንባ እንባ አላቸው። “ጥላዬን ልብ ታስገዛልኝ ነበር” ብለው በራሳቸው ግትርነት ተበሳጩ።

ጥላዬ፣ የወለተጊዮርጊስ ሶስት ዓመት ታላቅ ነው። ዐራት ዓመት
እንዳለፈው፣ ወፍታ ጊዮርጊስ ውስጥ መምሬ ጀምበሬ ዘንድ ቄስ
ትምህርት ቤት ገብቶ ዳዊት ደገመ። ብሎም ሌላ አስተማሪ ዘንድ ቅኔ እስከ ሥላሤ ተማረ።
ዕድሜው እየጨመረ ሲመጣ፣ አባቱና ግራዝማች መንበር “ልዥህን ለልዤ” መባባላቸውን ከሰፈር ልጆች ሰማ። ያንን ወሬ ከሰማበት ዕለት ጀምሮ ለወለተጊዮርጊስ በውል ያላወቀው ስሜት አደረበት። እያደገ
ሲመጣ፣ በእርግጥም በወለተጊዮርጊስ ፍቅር እንደተነደፈ ገባው።
ጠዋትና ማታ የሚያስበው ስለእሷ ሆነ። ጓደኞቹ ሌላ ቦታ ሄደው ቅኔ ሲማሩ፣ እሱ ከወለተጊዮርጊስ መራቅ ስላልፈለገ ወፍታ ጊዮርጊስ መጋቢ አምሳሉ ዘንድ መማር ጀመረ።

ሆኖም ልቡ ቅኔ ላይ ሳይሆን ሥዕል ላይ በመሆኑ ብዙውን ጊዜ
በስንጥር መሬት ላይ ወለተጊዮርጊስን አስመስሎ ይሥላል። አንድ ቀን
ታዲያ ኃይለኛ ንፋስ ነፍሶ፣ አሸዋውን አንስቶ ምስሉን ሸፈነበት፤ ደነገጠ። እንደ መጥፎ ገድ ምልክት አድርጎ ቆጠረው።

የእሱና የወለተጊዮርጊስ
ነገር እንደሳለው ምስል ተዳፍኖ የሚቀር ሆኖ ተሰማው።
ለቀናት ተጨነቀ። ከዚያን ቀን በኋላ፣ ምንም እንኳን የለመደበትን መሬት ላይ መሣል እርግፍ አድርጎ ባይተወውም፣ አብሮት ያደገውን ጥልቅ የሥዕል ፍቅር ለማርካት በቤታቸው የጓሮ ግድግዳ ላይ መሣል ጀመረ። ግድግዳውን
እበት ይቀባዋል፣ በእናቱ ወንፊት አመድ ይነፋና፣ በውሃ ለቁጦ
ያለብሰዋል። በማግስቱ፣ ሲደርቅለት፣ በእናቱ ቀይ ወይንም አርንጓዴ አክርማ እንስሳት፣ ተክሎች፣ ቤቶች ወይንም ሰዎች ይሥላል። አባቱ ያንን የሁለት ቀን ድካም ጭቃ ያስመርጉበትና እሱ ላይ የቁጣ ናዳ ያወርዳሉ። እሱ ግን ተስፋ አይቆርጥም፤ መልሶ መላልሶ ይቀባል፤ ይሥላል።
ከወለተጊዮርጊስ ፍቅር በተጨማሪ መላ አካላቱን ሰንጎ የያዘውን
የሥዕል ፍቅር ሲወጣ፣ መንፈሱ ይታደሳል። የአባቱን ቁጣ፣ የነገር
ጉንተላና የወለተጊዮርጊስን ፍቅር ረስቶ፣ የሠራ አካላቱ ሥዕሉ ላይ ብቻ ይሆናል፤ ሥዕል የሕይወቱ ምሰሶ የሆነ ይመስለዋል። ለሚቆይበትም አፍታ ዓለም የምትሽከረከረው እዛው ቦታ ላይ ብቻ ሆኖ ይሰማዋል።

የስሜቱ ግለት የእጁን ፍጥነት ይጨምርለታል። አክርማውን ከወዲያ ወዲህ፣ ከላይ ወደታች ሲያመላልሰው ይሰብረዋል። አጎንብሶ ከመሬት ላይ ሌላ ሲያነሳ፣ እጁ እንጂ ልቦናው ማስተዋል ያቅተዋል። ሥራውን
ራቅ ብሎ ይመለከተዋል፤ አልረካ ይላል። ያበጀዋል፤ ያበጃጀዋል፤
ያሽሞነሙነዋል። የመንደር ልጆች ታምር እንዳዩ ሁሉ የሚሠራውን
ፈዘው ሲመለከቱ፣ ልብ ማለት እንኳን ይሳነዋል።

ባላምባራስ ሁነኝ ግን ለአንድ ልጃቸው ሁለት ነገር እየተመኙ
አሳደጉት - ወለተጊዮርጊስን አግብቶ ዘር እንዲተውና ለአንዱ ባላባት አድሮ ተዋግቶ “ተደፈረ” የሚሉትን ክብራቸውን እንዲያስመልስ- እግረ
መንገዱንም ስለጦር ሜዳ ጀግንነት እየሰማ ያደገው ልጃቸው፣ የጀግንነት ድርጊት ፈጽሞ ጀግና ተብሎ እንዲጠራ።

ይህንን ምኞታቸውን ጥላዬ
ጭንቅላት ውስጥ ሊከቱ ደጋግመው ቢሞክሩ አልሆነላቸውም።
“ጥላዬ እንዳው ምናለ ላንዱ ታላቅ ባላባት ብታድር? ወታደርነት
ክቡር ነው። ደሞ ለአለቃህ ስትዋጋ ለአገርህ እንደተዋጋህ ቁጠረው” ይሉታል፣ አዘውትረው።
ጥላዬ መልስ አይሰጣቸውም። እሳቸውም ውትድርናውን
እንደማይፈልገው ያውቃሉ። “እና ምንን ሁነህ መኖር ነው ምትፈልግ?” ይሉታል።
አንድ ቀን፣ “እንዳው አንተ ጥላዬ እንዲሁ መልክህን አሳምረህ ዱላ
ይዘህ ስትንጎራደድ፣ ቤት ስትገባም ግድግዳ ስታበላሽ መኖር ነው ምትፈልገው?” ሲሉ ጠየቁት።

“አባባ ግድግዳ እንዳላበላሽ ብራና ላይ ልሣል ደብሬንም ላገልግልበት፣ ብልዎ ተቆጡ። እኔ ደሞ ያለሱ ሚታየኝ የለ። እሱን ማረግ ባልችል ስንኳ በቅኔው እገፋለሁ እንጂ ለማንም ባላባት አላድርም።”
“አንተ እንዲህ አድርጌ አሳድጌህ፣ ግዝየ ጥሎኝ የማንም መደዴ
ደብተራ ማላገጫ ስሆን፣ አንተ አባቴ ክብሩ ተነካ ብለህ እንኳ ዘራፍ ማትል? ስወድቅ ታነሳኛለህ፣ ያባትነት ክብሬን ታስጠብቀልኛለህ፣ ጥላ
ከለላ ትሆነኛለህ ብየ ያሳደግሁህ ዛዲያ ምን ታረግልኝ ኑሯል?
ሰዉ ለአጤ ተክለሃይማኖት ስለተዋጋሁ፣ 'የአባቱን የአጤ አድያም ሰገድ ኢያሱን አልጋ ለመውረስ ብሎ ላስገደለ ለርጉም ተክለሃይማኖት አደረ' እያለ ሲያማኝ፣ ካህናቱም ቢሆኑ፣ ለዝኸ ለርጉም ንጉሥ አባቱን አስገዳይ የተገዛ ርጉም ይሁን' እያሉ ሲኮንኑ... ያ ጠውላጋ ደብተራ
እንኳ ባቅሙ ቀን ጥሎኝ አይቶ መዘባበቻ ሲያረገኝ እንዳው ትንሽም አይቆረቁርህ? ልዥነትህ ኸምኑ ላይ ነው? በል እስቲ ንገረኝ? አሁን ብራና ኸኔ ክብር በልጦብህ ነው ብራና ብራና ምትለው? መቃብሬ
ላይ ቁመህ ነው አንተ ብራና በጅህ ምትነካው” አሉት፣ ምርር ብለው።

ጥላዬ ደነገጠ። “አባባ የርሶን ክብር እንዳስመልስ ኑሯል እንዴ
ለታላቅ ባላባት እደር ሚሉኝ የነበረው? እኔኮ ለኔ አስበው መስሎኝ።

የወፍታው በሚያውቀው እኔ ኸብራና ሌላ አልፈልግም። ለማንም ባላባት ማደርም አልፈልግም። ብራናን ሚከለክለኝ እዝጊሃር እንጂ ሌላ ማንም አዶለም።”
“አንት ተላላ። አለማወቅህ ... ስምና ክብር ታተርፋለህ ብየ እንጂ። ደሞ ራስህን ስታስከብር... ዥግና ስትባል... የሱ አባት ተብዬ መጠራቴ ቀረ?” ብለው እንባ ተናነቃቸው። “አንድ ምወድህ ልጄ ... አየየ... እንዲህ ኻባትህ ቃል ወጥተህ... አፈንግጠህ ትዘልቀዋለህ? ደሞ ኸዛሬ
ወዲያ ግድግዳዬን ስታበላሽ እንዳላይህ።”

ምወድህ ልዤ ? አለ፣ ጥላዬ ለራሱ። እንዴት ነው ሚወዱኝ እኔ
ምወደውን እየነሱ አባባ እየወደዱ መከልከልማ የለም፡፡ ቢወዱኝ ኑሮ
ኸግራማች በታረቁና ወለቴን ባገባሁ። ያነን ደማም ፊቷን ሳያረዥ፡እንደርስዎ ፊት ሳይሸበሸብ በሣልሁ። ቢወዱኝ ኑሮ ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ ያየኋቸውን የመላዕክት ሥዕሎች በሣልሁ። የገዛ አባቴ ሁነው
ስለምን ተስፋቢስ ያረጉኛል? ልቤ እርሶ ኸተመኙልኝ ሌላ ስለፈለገ?
እርሶ እንዳሉኝማ አልሆንም። እኔ ለባላባት ስላደርሁ እርሶ ክብር
ሊያገኙ? የወለቴ ነገር አንዠቴን ሚበላው አንሶ፣ ሥዕል ከልክለው
ወታደር ሁን ይሉኛል? እርሶ ለኔ ብለው ሳይሆን ለራስዎ ክብር ሲሉ
ነው ለባላባት እደር ሚሉኝ እያለ አወጣ አወረደና ለሳቸው፣ “ቢወዱኝ ኑሮ ምፈልገውን አይከለክለኝም ነበር” አላቸው።

ባላምባራስ ስሜታቸው ተነካ። እንደገዛ ነፍሳቸው የሚወዱትን አንድ ልጃቸውን ተቀየሙት።
እሱ ጠላቸው። “አባቱን ላስገደለ ለርጉም ተክለሃይማኖት ያደረ
ርጉም ነው” እየተባሉ ሲታሙ ያዘነላቸውን ያህል፣ ያን ቀን አዘነባቸው፤ ዓመጸባቸው። የሚሉትን ሊፈጽም፣ ሊያነጋግራቸው ቀርቶ፣ በዐይኑ
ሊያያቸው ቸገረው።....

ይቀጥላል
👍10