አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
«ውይ እማማ ዘነቡ» አለችና ታፈሡ የቆረሰችውን እንጀራ ትሪው ላይ ትውት አድርጋ ተነስታ ተቀበለቻቸው:: ሔዋንም ብድግ አለች፡፡ ግን ሽዋዬ ተከትላቸው የምትገባ መስሏት ቀልቧ ግፍፍ አለ። ደነገጠች። ሦስቱም ተሳሳሙ:: ወይዘሮ ዘነቡ ከላይ እስከ ታች ጥቁር ለብሰው ስለነበር
«ምነው እማማ ዘነብ ጠቋቁሩ?» ስትል ታፈሡ ጠየቀቻቸው። ሔዋንም ትኩር ብላ ታያቸዋለች::
«የሰሞኑ መዓት ያልወረደበት ማን አለ ብለሽ ነው የኔ ልጅ!»
«ምነው? ዘመድ ሞተብዎት?»
«ከዘመድ የምትበልጥ ጓደኛዬን አሳጣኝ ልጄ! ያውም አብሮ አደጌን፡፡» ካሉ በኋላ «ምናልባት በስም ታውቅያት ተሆነ ወይዘሮ አቦነሽ ሀይሌ ትባል ነበር፣ እዚህ
ዜሮ ሰባት ቀበሌ ውስጥ የታወቀች ጠጅ ጣይ!» አሉና በለበሱት ጥቁር ነጠላ ዓይንና
አፍንጫቸውን ጠረግ አደረጉ።
««ውይ…ውይ…» አሉ ታፈሡና ሔዋን፡፡ የወይዘሮ ዘነቡ አለቃቀስ
አሳዘናቸው። ሟቿ ያኔ ከአስቻለው ግራ ጎን ቁጭ ብለው የነበሩ የሴት ጀግና መሆናቸውን ቢያቁማ ኖሮ ምን ያህል አንጀታቸው በተንሰፈሰፈ ነበር፡፡
ታፈሡ ወይዘሮ ዘነቡን ጋብዛ ሶፋ ላይ ከአስቀመጠቻቸው በኋላ
ፊቷን ወደ ጓዳ መለስ አድርጋ ለወይዘሮ ዘነቡ የእጅ ውብ ታመጣ ዘንድ ሠራተኛዋን አዘዘች፡፡
እሳቸው ግን ጠንከረው ተቃወመ፡፡
ጭውውቱ ብቻ ቀጠሉ፡፡
«የእኛንስ ጉድ ሰምተው ይሆን እማማ ዘነቡ ስትል ታፈሡ ጠየቀቻቸው፡፡»
«ምን ሆናችሁ?»
«ሸዋዬ አልነገረችዎትም?»
«ኧረ ድንግል ትመስክርብኝ ምንም አልነገረችኝ፡፡»
«ከአደጋው ወዲህ አልተገናኛችሁም»
««እንዴ! አብረን እየኖርን» አሉና «እሁንስ ቢሆን እዚህ አንቺ ደጃፍ
ያደረስችኝ እሷ አይደለች እንዴ?» አሉ እንደ መገረምም እያሉ።
ታፈሡ በመናደድ ዓይነት ራሷን እየወዘወዘች በጣም የምትገርም ሰው ናት፡፡ እጅግ በጣም፡፡» አለች።
«ግን እናንተ ማን ተጎዳባችሁ?» ሲሉ ጠየቁ ወይዘሮ ዘነቡ።
«እስቻለው ነዋ!»
«አ!» አሉ ወይዘሮ ዘነቡ ድንግጥ ብለው «አስቻለው የእናንተን» እንደገና፡፡
«ህይወቱ ለጥቂት ተረፈች እማማ ዘነብ፡፡»
«ውይ በሞትኩት! ውይ በሞትኩት ውይ በሞትኩትሄ አሉና ወይዘሮ ዘነቡ ደጋግመው ደረታቸውንም በቡጢ ደሰቅ ደሰቅ አድርገው
«አሁን ታዲያ እንዴት
ነው?» ሲሉ ጠየቋት፡፡
«ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገለት ነው፡፡»
«ውይ ልጄን! ውይ ልጀን! ውይ ልጄን እኔ መች ሰማሁ ልጄ፣ እኔ ምን ቁቤ!» አሉና «ለመሆኑ ሸዋዬም አልሰማች ይሆን እንዴ?» ሲሉ ጠየቋት።
«በደንብ ሰምታለች»
«ምን ነካት ልጄ? ታዲያ እንዴት እልነገረችኝም?» አሉና «እውነትም ሆዷ ክፉ ነው ልበል» እንደገና።
«ጥሩ ሰው ብትሆንማ ኖሮ እንኳንስ ለእርስዎ መንገር አዲስ አበባ ድረስ ሄዳም ልትጠይቀው በተገባት ነበር።»
አቤት አቤት አቤት!» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ «አሁንስ ታዘብኳት ልጄ
በጣምም አዘንኩባት፡፡ ይህን ሆዷን ባውቅ ኖሮ ወደዚህ የመጣሁብትን ጉዳይ እንኳ
እሺ ብዬ አልቀበላትም ነበር፡፡» በማለት ተፀፀቱ፡፡
«እሷ ናት እንዴ የላከችዎት?» ስትል ታፈሡ ጠየቀቻቸው።
ኋላስ ልጄ ይቺን ልጅ አምጥተሽ አስታርቂኝ ብላ» አሉና ሔዋንንም
አየት አደረጓት።
«እንኳን ለዚህ አበቃሽ ሔዩ፣ ልትሽመገይ ነው፡፡» አለችና ታፈሡ ሔዋንን እያየች ሳቅ አለች።
«የኔ ደማማ! አትሽመገይኝ ይሆን?» ሲሉ ወይዘሮ ዘነቡ ሔዋንን ጠየቋት።
ሔዋን ግን በሀፍረትም በድንጋጤም አቀርቅራ መሬት መሬት ታይ ጀመር፡፡
«ምን ቁርጥ አድርጓት!» አለች ታፈሡ ፈገግ ብላ ሔዋንን
እየተመለከተቻት፡፡ «አይደል የኔ ቆንጆ?» እንደገና።
«አዎ! የኔ ልጅ እምቢታ አይወጣትም፡፡» አሉ ወይዘሮ ዘነቡ ወደ ኋላቸው ሶፋውን ደገፍ እያሉ::
«ለመሆኑ ለምን አባረርኳት አለቸዎት እማማ ዘነብ?»
ፈገግ እያለች ጠየቀቻቸው።
«ልጄ! አሁን አሁን ሳያት ይቺ ሸማዬ የምትባል ሰው ቅጥ ያላት ሴት አትመስል አለችኝ፡፡ እንደው ምኗም ምኗም አላማረኝ አትታዘቡኝ እንጂ አትታዘቡኝ እንጂ» ብለው ዓይናቸውን በታፈሡና በሔዋን ላይ ጣል ነቀል አደረጉት::
«ግራ ገብቶናል እማማ፤ እባኮዎትን ምክሩልን» አለቻቸው ታፈሡ፡፡
«ኤዲያ!» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ እጃቸውን መንጨር አደረጉ፡፡ ተመክሮ ልብ አሉ! ሲመክሯትስ መች የምትሰማ ሆነች?» አሉና ታፈሡን አየት አደረጓት::
ለአፍታ ፀጥታ ሰፈነ።
"ታዲያ እንግዲህ አንዴ መጥቻለሁ፤ ይዤሽ ልሂድና ላስታርቃችሁ የኔ አበባ!» በማለት ወይዘሮ ዘነቡ ፀጥታውን ሰበሩት፡፡ እሳቸው ሔዋንን ፈገግ ብለው
ሲያዩዋት አሷ ግን መሬት መሬት ትመለከት ጀመር፡፡ ልቧም ፈራ፡፡
«ማስታረቁን ያስታርቋታል እማማ ዘነቡ፤ ነገር ግን የሚሆንልዎ ከሆነ
መጀመሪያ እኔና ሸዋዬን ያስታርቁን ከዚያ በፊት ሔዩ ከዚች ቤት ንቅንቅ አትልም» አለቻቸው ታፈሡ
ቀድማ፡፡ ቀጠል አድርጋም «በዚህ ጉዳይ ላይ ሰሞኑን ሔለንም ባለችበት ከበልሁ ጋር የተነጋገርነው ነገር አለ» ቸለችና በልሁን ያውቁት የለ» ስትል ጠየቀቻቸው።
የዚሁ ልጅ ጓደኛ መሆኑ ነው?»
አዎ፡፡ አሁንም ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ እያስታመመው ያለው እሱ ነው። የስሞኑን የሔለንን ሁኔታ ነግረነው እጅግ በጣም ተቆጭቶ እንደውም እሱ ሳይመጣ ሔዋን ከዚህ ቤት ወዴትም እንዳትሄድ አደራ ብሎኛል። ሆኖም አያያዙ ስላስፈራኝ እሱ ሳይመጣ ሔዋን ከእህቷ ጋር ብትታረቅ ደስ ይለኛል። ባይሆን እሱን
ይቅርታ እጠይቃለሁ::
ወይዘሮ ዘነቡ በታፈሡ ቅንነትና ግልፅነት ደስ እያላቸው ሀሳብሽ መልካም ነው የኔ ልጅ! ልብሽም እንደ መልክሽ የጠዳ! ድንግል ትባርክሽ፡፡» አሉና «መቼ
እናድርገው ታዲያ?» ሲሉ ጠየቋት፡፡
«መሸ እንጂ ዛሬም ይቻል ነበር። ነገ ከተመቸዎት እኔ ዝግጁ ነኝ::»
«ጥሩ የኔ ልጅ! ግን አደራ ወቀሳ እንዳይበዛ!» አሏት፡፡ የምን ወቀሳ እማማ ዘነብ! ኧረ ከቶ ትምጣልኝ እንጂ እግሯ ላይ ወድቄ ማሪኝ ነው የምላት! ያጠፋሁትን ግን እሷ ትወቀው። እጠፋሁ አላጠፋሁ እሷን ይቅርታ በመጠየቋ የትኛው ክብሬ ሊቀነስ?»
«ክብርና ሞገስማ ያንቺ ነው የኔ ልጅ! ሰው ለሰላም ሲል ባልሰራው ጥፋት ይቅርታ በመጠየቅ በላይ ምን ሊያስከብረው ይችላል? ይብላኝ ለልበ ክፉዎች እንጂ!» አሉና ድንግል ትባርክሽ ልጄ!» ብለው በረጅሙ ተነፈሱና እንደገና ወደ ሔዋን ዞር ብለው የአይዞሽ የኔ ልጅ፣ ማንም በልጅነቱ ሳያጠፋ ያለፈ የለም፡፡ ልብሽ አይፍራ፡፡ ጥፋተኛ ቢኖር አንቺን ለምን አጠፋሽ ብሎ ሰማይ ካልሰበርኩ የሚል ብቻ ነው:: አይዞሽ የኔ አበባ፡፡ ባይሆን ለነገ ተረጋግተሽ ጠበቂኝ::» አሏት። ወ/ሮ ዘነቡ ቡናቸውን ጠጥተው ወደ ቤታቸው ለመሄድ ሲዘጋጁ «ነገ ወደ
ማታ ላይ ብመጣ አይሻልም?» ሲሉ ስለ ነገው ቀጠሮ ጠየቋት።
«ልክ ዛሬ በመጡበት ስዓት!»....

💫ይቀጥላል💫
👍141
አይፈሪሞ የኖረ ፤ሕይወትን ተገርሞት፤
ና ግባ ፤ዘጠኝ ሞት።
የከረምኩት ኑረት ፣ከሞት ፊት አቁሞኝ
ዕድሜ ሕልሞ ሆነ ፤ እንቅልፍሽ አልሞኝ።
የእንቅልፍ ሰው ነኝ!
ኑሮዬ ሕልሞሽ ነው ምትመለከቺው፧
አንቺ ውስጥ የሚታይ ፤አንቺ ሞታስፈቺው።
ኑሮዬ በሕልሞሽ ፣ታይቶ እየተፈታ
ረዥም ዘመኔ ፣ተባለ እፍታ።
እፍታ አርጀና፤
እንደድሮ ዘፈን ፣ መልሼ ሰማሁሽ፤
እንደባሕር ቅርድድ ፣ ደግሜ ዐየሁሽ።
እፍታ እርጅና፤
ከመኖር መላወስ ፣ያዳንሽን ጸበሌ፤
ፍቅርሽ የሆንከስት
እገዛለት ጌታ ፣ እታዘዘው ሎሌ።
የከፋሽ እንደኾን ፣ ሞን ብኮን ጽናና፤
ብዬ እጀምሪለሁ ፣ ክሪር ወይ በገና፤
ምን በዓል ይደገሞ ፣ፋሲካ ወይ ኘና።
እፍታ እርጀና፤
ጥርስሽ እስኪነጥፍ ፣ሣቅሽ ይኹን መንታ ዘመኔን ልሸኘው
ይማርሽ እያልኩኝ ፣ ሲመጣሽ ትንታ።
አንድ አፍታ
አለሁኝ ለማለት
ላንቺ እየኳተንኩኝ ፣ ስኖር ለመጀገን
መጥፋትሽን ሳስብ ፣ አረጀሁ ተመስገን።


🔘ኤልያስ ሸታኹን🔘
👍1
#ምንትዋብ


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


እንደወትሮው ዓይነት ቀን መሆን ነበረበት።
ያን ቀን፣ ወለተጊዮርጊስ ወላጆቿ ቤት በራፍ ላይ ተቀምጣ፣ የእነዚያን አስታራቂ ሽማግሌዎች መምጣት ስትጠባበቅ፣ ሌሎች ሽማግሌዎች መጡ፡፡
ሰዎቹ እነማን እንደሆኑ ለማጣራት ከወዲያ ወዲህ ስትማትር፣ አጥር
ግቢው መግቢያ ላይ አንድ ሰው ጦሩን መሬት ላይ ሲተክል አየች።
ከተቀመጠችበት በፍጥነት ተነስታ፣ እረገኝ የምን ጦር ነው? ሰዎቹስ እነማን ናቸው? አለች በልቧ።
ሦስት ሰዎች ባለጦሩን አልፈው ወደፊት መጡ። እኒያ ሁለቱ
ባለፈው ኸኛ ዘንድ ከርመው የኸዱት ማዶሉ እንዴ? ምን መልሶ
አመጣቸው? እንግዲያማ ጦሩ ለደሕና ቢሆን ነው ብላ ዐይኗን ከሰዎቹ ላይ ሳታነሣ፣ “እንግዶቹ ተመልሰው መጥተዋል” አለች። የተናገረችው ለእናቷና ለአያቷ ነው።

“የትኞቹ እንግዶች?” አሉ፣ እናቷ ወይዘሮ እንኰዬ ። ቤት ውስጥ ሆነው እልፍኛቸው ሳይገቡ በተቀመጡበት ሸለብ ያደረጋቸውን ባለቤታቸውን ግራዝማች መንበርን እንዳይቀሰቅሱ ከእናታቸው ከወይዘሮ ዮልያና ጋር በሹክሹክታ ያወጋሉ።

“እንግዶቹ” አለች ወለተጊዮርጊስ፣ የትኞቹ እንግዶች እንደሆኑ ሳትናገር። ወደ ግቢ የሚገቡትን ሦስት ሰዎች ትመለከታለች።

“አንቺ ወለቴ ማትናገሪ? የትኞቹን እንግዶች ነው ምትዪ? ስንት
እንግዳ ይመጣል ኸዝኸ ቤት?” አሏት፣ አያቷ። ለእናቷ መልስ ሳትሰጥ በመቅረቷ ተገርመዋል ።

ሰዎቹ ግቢው ውስጥ መግባት ጀምረዋል።

“እኼው ነው ቤቱ። አልተሳሳትንም” አሉ፣ አንደኛው እንግዳ ።
“እኔ ያ ወዲያ ያለው መስሎኝ” አሉ ሌላው እንግዳ፣ በስተግራ በኩል
ያለውን የባላምባራስ ሁነኝን ቤት እያመለከቱ።
“ያችውና እኮ ልዥቱ” አሉ መጀመሪያ የተናገሩት እንግዳ፣ በር ላይ የቆመችውን ወለተጊዮርጊስን በአገጫቸው እያሳዩ።

የሁሉም ዐይን ወለተጊዮርጊስ ላይ ዐረፈ። ግቢውን እንደዛ ያስዋቡት
ዙርያውን ቦግ ብሎ የሚታየው አደይ አበባና የቋራ ቀትር ፀሐይ
ሳይሆኑ እሷ መሰለቻቸው።
አገልጋዮች እሷን ለማየት እየተገፋፉ እንግዶቹን ተከትለው፣
ፈረሶችና በቅሎዎች በየልጓማቸው ይዘው እየሳቡ ወደ ግቢው ዘለቁ።ጋማ ከብቶቹ ቀልባቸው ያረፈው ወለተጊዮርጊስ ላይ ሳይሆን፣ የክረምቱ ዝናብ ያለመለመው ሳር ላይ በመሆኑ አገልጋዮቹ ልጓሞቻቸውን
ፈቱላቸውና ወዲያው ግጦሹ ላይ ዘመቱበት።

ለወትሮው እረጭ የሚለው ቅጥር ግቢ ሞቅ ደመቅ አለ።
“አንቺ ወለቴ! መልስ ማትሰጪ? ምንን ሁነሽ ነው? የትኞቹን
እንግዶች ነው ምትዪ?” አሏት አያቷ፣ ቆጣ ብለው። ከተቀመጡበት ተነሥተው ነጠላቸውን አስተካከሉ።

“እመምተኛውን አጅበው መጥተው ኸነበሩት ሁለቱና አንድ ሌላ...ሴቶችም ... ወንዶችም አብረዋቸው አሉ" ነገራቸውን እንጃ ጦርም የያዙ አሉ አለች፣ ለብቻዋ እንደማልጐምጐም እያለች።
አሁንም ዐይኖቿ ከሰዎቹ ላይ አልነሣ ብለዋል። ከቆመችበት
ቦታ መንቀሳቀስ አቅቷት፣ አፏን በግራ እጇ ይዛ እኼ ሁሉ ዐጀብ
ስለምንድርነው? ትላለች።

“እንግዶቹ” ያለቻቸው ሰዎች ያለ ምክንያት ተመልሰው እንዳልመጡ
ገብቷታል ።

ትከሻዋ ላይ ጣል ያደረገችውን ባለቀይና ባለአረንጓዴ ጥልፍ ያንገት ልብሷን በፍጥነት አስተካከለች። ባለግማሽ ጥልፍ ቀሚሷን በተን በተን አድርጋ ያንን ትከሻዋ ላይ የወደቀውንና እንደ ሐር የለሰለሰውን ሹሩባዋንም ዘርዘር አደረገችው።

“ዛዲያ ግቡ አይባልም እንዴ?” አሏት እናቷ። እንዝርታቸውን
አስቀምጠው ከተቀመጡበት ተነሡ፤ ነጠላቸውንና ሻሻቸውንም
አስተካከሉ። "ነይና ጌቶችን ንገሪያቸው“ ብለዋት ከእናታቸው ጋር ወደ በሩ መጡ፡፡

ወለተጊዮርጊስ ወደ ውስጥ ስትገባ እሳቸው ከእናታቸው ጋር ሆነው ለእንግዶቹ የሞቀ ሰላምታ ሰጥተው እንዲገቡ ጋበዟቸው።
ወለተጊዮርጊስ፣ “አባባ ይነሡ፤ እንግዶቹ ተመልሰው መተዋል”
አለቻቸው አባቷን፣ ተጠግታ በጥድፊያ በእጇ እየነካካቻቸው። እንግዶቹ መግባት አለመግባታቸውን እየተገላመጠች ትመለከታለች።

“በስመአብ፣ እንደምን ያለ እንቅልፍ ጥሎኝ ኑሯል ባካችሁ?” አሉ፣ ግራዝማች መንበር ዐይናቸውን እያሻሹ። “የትኞቹን እንግዶች ነው ምትዪ?” ብለው ወደእሷ ሲዞሩና እንግዶቹ ሲገቡ አንድ ሆነ።

ወለተጊዮርጊስ፣ እንግዶቹን ለጥ ብላ እጅ ነሣቻቸው። አባቷ ጋደም
ብለውበት ከነበረው፣ ከሁሉም ከፍ ካለው መደብ አጠገብ ቆማለች። እንግዶቹም ዓጸፋውን መለሱ።
ግራዝማች መንበር ከመደቡ ላይ በፍጥነት ተነሥተው ፊታቸውን
እያባበሱ እንግዶቹን እጅ ነሡ። ጋቢያቸውን ትከሻቸው ላይ እያጣፉ፣ “ከርማችሁ ነው? እስቲ ዐረፍ በሉ” አሉና ቁርበት ጣል የተደረገበትን መደብ በእጃቸው አመለከቱ።

“ከርመው ነው ጌቶች?” እንግዶቹም እየተቀባበሉ ለግራዝማች ሰላምታ አቀረቡ።
“ቸርነቱ አይለየኝ፤ ደግ ነኝ። እንዳው ጋደም ያልሁባት ሸለብ
አርጎኝ ኑሮ...” አሉ ግራዝማች መንበር፣ ይቅርታ ባዘለ አንደበት።
ሁለቱ እንግዶች ሰው ጨምረው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመልሰው
መምጣታቸው ቢገርማቸውም፣ በወቅቱ ተኝተው መገኘታቸው አግባብ አልመሰላቸውም። ፊታቸውን ደጋግመው አባበሱና ትከሻቸው ላይ እንደ ነገሩ የታጠፈውን ጋቢያቸውን አስተካከሉ። “ዐረፍ በሉ ስለእዝጊሃር” አሉ፣ ዘለግ ያለው ድምፃቸው እንግዳ ተቀባይነታቸውን እያበሰረ።

እንግዶቹ መደቡ ላይ ተቀምጠው በመንገድ የደከመ ወገባቸውን
አሳረፉ።

ከመሃላቸው ኢሳያስ የተባለው እንግዳ ወለተጊዮርጊስን በዐይኑ
ከእግር እስከ እራሷ አዳረሳት። እንዴት ያለች ዐይነ ግቡ ናት? አቤት እንዴት ያለ ሚያሳሳ ዐይን ነው? ለማንም አልሰጠ። ቁንዳላዋ ራሱ እስተ መቀመጫዋ ዘልቆ የለንዴ? ኸሰማሁትም በላይ ደመግቡ ናት አለ፣ በሐሳቡ።

ግራዝማች ትኩር ብለው አዩትና ምነው ልዤን እንደዝ ሚያይብኝ?
ነውር ማዶል እንዴ? አሉ፤ እሳቸውም ለራሳቸው።

እረገኝ፣ ሰውየው ዐይኑን ተከለብኝሳ? አለች፣ ወለተጊዮርጊስም።ቀደም ብላ፣ “አንድ ሌላ ሰው” ያለችው እሱን ነበር። እነዚያ ሁለቱ ደሞ አለነገር በይኸ ባጭር ግዝየ ተመልሰው አልመጡም ብላ፣ ቤቱን ከሁለት ወደ ከፈለው መጋረጃ ስታመራ እንግዶቹ በዐይኖቻቸው ሸኞት ።
ግራዝማች፣ “እስቲ ሚቀመስ” ሲሉ፣ ወይዘሮ እንኩዬ ለእንግዶቹና አብረዋቸው ለመጡት ምግብና መጠጥ እንዲቀርብ፣ ለፈረስና
ለበቅሎዎቻቸውም ጥሬና ውሃ እንዲሰጥ ትዕዛዝ እንድታስተላልፍ
ሊያዟት ወለተጊዮርጊስን በዐይናቸው ሲፈልጓት፣ ከጥጡ መጋረጃ ጀርባ ወጥታ፣ መልዕክቱን ማዕድ ቤት ለማድረስ ወደ ጓሮ ከነፈች። ወሬ
እንዳያመልጣት በፍጥነት ተመልሳ፣ ከመጋረጃው በስተጀርባ የእንጨት ዱካ ላይ ተቀመጠች። ከግርዶሹ ኋላ ጨለም ያለ በመሆኑ፣ በቀላሉ
እንደማትታይ ጠንቅቃ ታውቃለች።

“እሳቸው በረቱ ይሆን? ምንገድ ችለው ኽደው ይሆን እያልነ አሰብነ” ሲሉ ሰማቻቸው አባቷን።

እናቷና አያቷም የሁለቱ ሰዎች ተመልሶ መምጣት ቢገርማቸውም፣እነሱም ስለሰውየው ጤንነት አጥብቀው ጠየቁ፡፡
“ክብሩ ይስፋ ደሕና ናቸው። ዕድሜ ለናንተ በወግ አስታመማችዃቸው።
ተክልየ ምላሹን ይስጧችሁ... ወሮታችሁን ይክፈሏችሁ” አለ ኢሳያስ፣
“ምላሹን ይስጧችሁ” እና “ወሮታችሁን ይክፈሏችሁ” የሚሉትን ቃላት ጠበቅ አድርጎ፡፡
ወለተጊዮርጊስ ዛዲያ ሰውየው ማናቸው? ስምም የላቸው? ኸዝኸ ኸኛ ዘንድ ያን ያህል ግዝየ ተቀምጠው ማን መሆናቸውን ስንኳ ሳይናገሩ ማዶል እንዴ የኸዱ? እንዴ እስተመቸ ነው የሳቸው ማንነት ሚደበቅ?
ለም'ነው ሚሽሽጉ? ደሞስ እነዝኸ ኹለቱ ለምነው ሰዎች ጨምረው
የተመለሱ እያለች አውጠነጠነች።

ነገሩ ሁሉ እንቆቅልሽ ሆነባት።

ኢሳያስ ሲናገር፣ አንድ ዐይኗን በመጋረጃው መጋጠሚያ አጮልቃ ማየትና ማዳመጥ ቀጠለች።
👍22🤩31👎1
“እሳቸውም..” አለ ኢሳያስ፣ የሰውየውን ማንነት ሳይገልጽ። ወደ ግራዝማች እየተመለከተ፣ “እሳቸውም ኸርሶ ዘንድ መልክት እንድናደርስ ልከውናል” አለና በር ላይ አደግድጎ የቆመውን አሳላፊ፣ “ማሙየ በልና ያነን ዕቃ አምጣ በለው” አለው።

ወለተጊዮርጊስ ሚሰጥ ለማምጣት ነው እንዴ የመጡ? ብላ በመገረም ስትመለከት፣ ማሙዬ ገብቶ ግራዝማችን ለጥ ብሎ እጅ ነሳና የቆዳ ጥቅል እግራቸው ስር አኖረ።

ኢሳያስ ጥቅሉን እንዲፈታ ሲያዘው ቀልጠፍ ብሎ ፈታው። ግራዝማች ከዚህ ቀደም አይተውት የማያውቁት ዓይነት የሃገረ ህንድ
ስጋጃ እግራቸው ስር ተንከባለለ። ደንዳና ሰውነታቸው ሳያግዳቸው
ከተቀመጡበት ብድግ አሉ። እጆቻቸውን ዘርግተው፣ “እንዴ ምን
ስላረግሁ ነው እኼ ሁሉ? ስንኳንም እሳቸው ዳኑ እንጂ። እረ ተገቢም ማዶል። ቤት እኮ የአብርሃሙ ሥላሤ ነው” እያሉ ወተወቱ።

“ለእንግዳ ተቀባይነትዎ። ያነን ሁሉ ሰው እንደዚያ አርገው
ተቀብለው። ልዥዎም ብትሆን ሌት ተቀን እሳቸውን አስታማ” አሉ፣
አንደኛው እንግዳ።

ወለተጊዮርጊስ ዛዲያ ለኔስ ሚሰጥ መቶልኛል? ብላ ገጽታዋ ፈካ።

አባቷ ራሳቸውን እየነቀነቁ አዲሱን ስጋጃ አተኩረው ተመለከቱና፣
“ተገቢም ማዶል፣ ተገቢም ማዶል” ብለው ተመልሰው መደቡ ላይ ተቀመጡ።

ባለቤታቸው ወይዘሮ እንኰዬም፣ “ለምኑ ነው እኼ ሁሉ? ቁስቋም
ማርያም ታክብርልን” እያሉ ከተቀመጡበት ተነሥተው እጅ ነሱ።

ኢሳያስ፣ “ያነኛውን ደሞ አምጣ” አለው፣ ማሙዬን። ማሙዬ የቆዳ ጥቅል ይዞ ሲመጣ ኢሳያስ፣ “ኸሳቸው...” ብሎ በእጁ
ወደ ወይዘሮ ዮልያና ሲያመለክተው፣ ጥቅሉ ሲፈታ ተመሳሳይ ስጋጃ ከብለል አለ።

“ኧረ በቁስቋሟ! እኔ ደሞ ምን ስላረግሁ ነው? እረ አይገባም” ካሉ በኋላ ስጋጃውን ጥቂት በጥሞና አስተውለው፣ ቁስቋም ታክብርልኛ እንግዲህ” አሉና ተነሥተው እጅ ነሡ።

“ምን ስላረግሁ ነው አሉ? ያነን ሁሉ እንግዳ እንደዛ አስተናግደው?” አሉ አንደኛው እንግዳ፣ በእጃቸው የመስተንግዶውን ትልቅነት ለማሳየት እየሞከሩ። “ዝምድናም አተረፍን” አሉና ወይዘሮ እንኰዬን አየት አደረጉ።

ደርባባዋ እንኰዬ፣ “ዝምድናውማ የበለጠ ነው... ብቻ እንዳው እኼ
ሁሉ አይገባም ነበር እንጂ” አሉና እንግዶቹን ለማስተናገድ ወጥተው
ወደ ማዕድ ቤት ሄዱ።

እምብዛም ሳይቆይ አገልጋይ የእጅ ውሃ አምጥቶ የእንጨት
ማስታጠቢያ ሳህን ላይ እንግዶቹን አስታጠበ። በየዓይነቱ ምግብ በመሶብ ተሰየመ። እንግዶቹ መሶቡ ዙርያ ተቀምጠው አንዴ ግራዝማች፣ ሌላ ጊዜ እንኰዬ እንዲሁም ዮልያና እየደጋገሙ፣ “መቸም እንደነገሩ ነው፤
በሞቴ ብሉ እስቲ” ከማለት በስተቀር ሁሉም በዝምታ በልተው ጨረሱ።

ገበታ ከፍ ብሎ የእጅ ውሃ ቀረበ።
እንግዶቹ ግን የመጡበትን ጉዳይ ለመናገር ዝግጁ አልመሰሉም።
የእነግራዝማች ልብ ለምን እንደመጡ ለማወቅ መንጠልጠሉንም አላስተዋሉ።

ጠላው አናት በአናት እየተቀዳ፣ ጨዋታ ደርቶ፣ ከመንገድ
የገቡ ሳይሆን እዛው ሲጫወቱ የከረሙ መሰሉ። ጭራሽ ለጨዋታ
የመጡ እንጂ ጉዳይ የቀራቸው አልመስል አሉ። ወለተጊዮርጊስ ወሬ እንዳያመልጣት ምሳ ለመብላት እንኳን ፈቃደኛ
አልሆነችም። ከሰዎቹ ምንም ጭብጥ ያለው ንግግር ስላልሰማችና ወላጆቿና አያቷጋ የሷን እጅ ጠያቂዎች በየጊዜው በመጉረፋቸው፣ ሰዎቹ ለዚሁ ጉዳይ ነው የመጡት ብላ ገመተች። እጇን ጠያቂ ሽማግሌ በመጣ ቁጥር ነፍስና ሥጋዋ ይላቀቃል። ጊዜ አጓጉል ነገር ነው። አስራ ስድስት ዓመት ሆኗታል። አባቷ ተስፋቸው ሟምቶ ለሌላ ሊድሯት ይችላሉ። እሷ የሽማግሌዎቹ ቁርጥ ሳይታወቅ፣
ከጥላዬ ሌላ ለማንም እንድትሰጥ አትፈልግም።....

ይቀጥላል
👍61
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ እንደወትሮው ዓይነት ቀን መሆን ነበረበት። ያን ቀን፣ ወለተጊዮርጊስ ወላጆቿ ቤት በራፍ ላይ ተቀምጣ፣ የእነዚያን አስታራቂ ሽማግሌዎች መምጣት ስትጠባበቅ፣ ሌሎች ሽማግሌዎች መጡ፡፡ ሰዎቹ እነማን እንደሆኑ ለማጣራት ከወዲያ ወዲህ ስትማትር፣ አጥር ግቢው መግቢያ ላይ አንድ ሰው ጦሩን መሬት ላይ ሲተክል አየች። ከተቀመጠችበት በፍጥነት ተነስታ፣…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....የወይዘሮ ዘነቡና የታፈሡ ውይይት በዚህ መልኩ እየተከናወነ ባለበት ሰአት
ሸዋዬ አልጋዋ ላይ ቁጭ ብላ በሁለት እጇ ጆሮ ግንዶቿን ጠፍራ በመያዝና አተርትራ በማሰብ ላይ ናት። ታፈሡንና ወይዘሮ ዘነቡን እያሰበች ልክ በመሀላቸው ቁጭ ብላ እንደምታዳምጣቸው ዓይነት ስለ እሷ ሲያወራ በሀሳቧ "ቀንታ ነው እኮ ተቀጥላ ይስሟታል!
ሰው እንዴት በእህቱ ይቀናል! አረ የሷ የብቻው ነው ። አስቻለውን እንደሆነ አታገኘው ምን ያስለፋታል?» የሚሏት ይመስላታል። ወይዘሮ
ዘነቡ ታፈሡን ሲያሞካሹ!
ለአስቻለውና ለሄዋን ለሔዋን ፍቅር መልካም ሲመኙ እሷ በእሳቸው ፊት የምታሳየውን ድንጋጤና የብስጭት ስሜት ለታፈሡ ዝርዝር አድርገው ሲያወሩባት ሁሉ ይታያታል፡፡ በዚያ ልክ ቅጥል ንድድ ትችላለች፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ ግቢያቸው ውስጥ እንዴግቡ ወደ ቢታቸው ጎራ ሳይሉ
በቀጥታ ወደ ጓሮ ዞረው ወደ ሸዋዩ ቤት አመሩ። ሸዋዬ ድንገት የሰው ኮቴ ሰምታ ከአጎነሰችበት ቀና ስትል ወይዘሮ ዘነቡ ብቻቸውን ሲመጡ አየቻቻው። ወደ
ኋላቸው ዓይኗን ስታማትር ሔዋን የለችም። እንዴ አለችና እማማ ዘነብ! » ስትል ጠራቻቸው ገና ከሩቅ ሳሉ፡፡
«ወይ»
«አልተሳካሎትም?»
ወይዘሮ ዘነቡ ዝም ብለዋት ወደ ቤት ገቡና ዱካ ላይ ቁጭ ካሉ በኋላ ትሰሚያለሽ የኔ ልጅ!» አሏት ቀልብና ስሜቷን ሰብሰብ ለማድረግ፡፡
«እሺ» አለቻቸው በጉጉትና በፍርሀት ስሜት ተውጣ፡፡
ጓደኛሽም እህትሽሃም መልካም ሰዎች ናቸው። እህትሽ ጥፋቷን አምናለች፡፡ጓደኛሽም ተቆጥታለች። አንቺ የፈለግሽውን እርቅ እነሱ የበለጠ ፈልገውታል፡፡
እውነተኛ እርቅ ደግሞ አፍን ሳይሆን ልብን ከፍቶ ስለሆነ፣ ለዚህ ብርቱ ጉዳይ አንቺም ስትዘጋጂ እደሪና ነገ ሁለታችንም አብረን እንሂድና አንቺንም ከጓደኛሽ፣ እህትሽንም ከአንቺ በማስታረቅ ሁሉንም ነገር ፈጥሠን እንመጣለን። ከዚያ በኋላ እህትሽን ይዘናት እንመጣለን፡፡» ከማለት ውጭ ሌላ ምንም ሳይጨምሩ
ከተቀመጠበት ብድግ ብለው በይ ደህና እደሪl» ብለዋት ውልቅ አሉ፡፡
ሸዋዬ ድንግጥ አለች፡፡ እንዴ አለች በሆዷ፡፡ በዓይኗ ወይዘሮ ዘነቡን
እየተከተለች ይቺ አሮጊትና ያቺ ታፈሡ የምትባል መናጢ ምን ተማክረው ይሆን?' በማለት ብቻዋን ታወራ ጀመር። ሄደች በሀሳብ አሁንም ታፈሡ ከኔ ጋር
ታርቀ ሰላ እያለች ወደ ቤቴ በመምጣት የጀመረችውን ልትጨርስ!? እኔ ሳላውቅ
ከዚች አሮጊት ጋር ገጥማ ውስጥ ለውስጥ ሊያርዱኝ? በፍጹም ይህ የማይሆን ነው። ከታፈሡ ጋር እርቅ ብሎ ነገር የለም፡፡ ብቻ ያቺ ሰላቢ እህቴ እንደምንም ብላ
በእጄ ትግባልኝ፡፡ ይህ እንዲሆን የግድ ከታፈሡ ጋር ታረቂ ብባልም ለዚያች ቀን ብቻ በማግስቱ ግን አፈርሰዋለው በቃ።
ሸዋዬ ምሽቱን ሁሉ ስለዚሁ ስታስብ ቆይታ ሌሊቱንም ሳትረሳው መልሳ መላልሳ ስታመነዥገው አደረች። ፍላጎቷ አንድ! ሔዋንን በእጇ ማስገባት፤ ፉከራዋም እንድ፤ ከታፈሡ ጋር ፈጽሞ ከልብ ላለመታረቅ። ሀሳቧ ሁሉ ከዚሁ ሳይርቅ ሌቱ ነግቶ በጠዋቱ ፈረቃ ስራ ገባች፡፡
ከሰዓት በኋላ በታፈሡ ቤት የተያዘው የቀጠሮ ሠዓት ደረሰና ከወይዘሮ ዘነቡ ጋር ወደ ታፈሡ ቤት ጉዞ ጀመሩ።
«እማማ ዘነብ!» ስትል ጠራቻቸው ከጎናቸው ሆና እየተራመደች
«ወይ»
«ለመሆኑ ታፈሡ እኔን ምን አደረገችኝ እለችዎት?»
«እረ እሷ እቴ! ምንም ያለችው ነገር የለም::»
«ታዲያ ከእሷ ጋር መታረቁ ለምን አስፈለገ?»
«በአንቺ ሆድ ውስጥ ያለ ነገር ሊኖር ይችላል ብዬ ነዋ!»
«እሱማ ብዙ አለ። ግን ዝም ነው የምለው፡፡»
«ያማ ቂመኝነት ነው:: የነገር ብዛት ባይጠቅምም የቂም ቋጠሮ ካልተፈታ እርቅ አይኖርምና ቅር ያለሽን ነገር አጠር አርግሽ መግለጥ ይኖርብሻል፡፡»
«እኔና እሷን ያቀያየመን እኮ ይሄው የእህቴ ጉዳይ ነው::»
ወይዘሮ ዘነቡ ድንገት ቁጥት አሉ፡፡ «የእህትሽ ጉዳይ የአንቺና የእሷ ጉዳይ አይደለም የራሷ ብቻ ነው:: በእሷ አታሳቡ፤ ተዋት!! አሉ ጠበቅ ባለ አነጋገር፡፡
«እንዴት እማማ ዘነበ? እኔማ የእህቴ ጉዳይ ያገባኛል::»
«ስለምታበያትና ስለምታጠጫት ተሆነ ተሳስተሻል። ሆድ የትም ይሞላል፡፡
ጭንቅላት ግን ነጣነት የሚያገኝበትን መንገድ ይፈልጋል፡፡ አትሞኚ »
«መረን ልቀቂያት ነው የሚሉኝ!»
«ተይ አንቺ ልጅ! ኋላ እንዳልጠላሽ! እህትሽን እንኳን አንቺ እኔ አውቄአታለሁ፡፡ ሥነስራት ያላት ጨዋ ናት፡፡ የሆዷን አይታ ድንግል ያን የመሰለ ጨዋ ልጅ ሰጥታተለች:: እንደኔ ቢሆን በእነሱ መሀል ባትገቢ ጥሩ ይመስለኛል፡፡»
አሏት ፈርጠም ባለ አነጋገር፡፡
ሽዋዬ ወይዘሮ ዘነቡን ክፉኛ ጠላቻቸው፡፡ ዛሬ ሔዋንን በእጇ የማስገባት ዓላማ ባይኖርባት ኖሮ በዚያ ሠዓት ወደ ቤቷ ምልስ ብትል በወደደች ነበር፡፡ ከዚያ
በኋላ ፀጥ እንዳለች ከታፈሡ ቤት በር ላይ ደረሱ፡፡
የታፈሡ ቤት እንግዳ ለመቀበል ተዘጋጅቷል። ወለሉ ተወልውሎ- ፏ ብሏል::ከሰል ተያይዞ የቡና ዕቃዎች ቀርበዋል። ታፈሡም እምር ብላለች። ቀላ ያለ ጉርድ
ቀሚስ በነጭ ሽሚዝ ለብሳ ሀብሏ በደረቷ ላይ እንደ ፀሐይ ያበራል፡፡ ያን ረጅም የጥቁር ዞማ ፀጉሯን ጎንጉና በጀርባዋ ላይ ለቃዋለች፡፡ ወይዘሮ ዘነቡ ሸዋዬን አስከትለው ወደ ቤት ራመድ ሲሉ ፈልቀቅ ባለ ፈገግታ ተቀበለቻቸው፡፡ በዚያ
ሠዓት ሔዋን ድንግጥ ብላ ወደ ጓዳ ስትሮጥ ወይዘሮ ዘነቡ ተመልክተዋት ኖሯል።
«ዛሬ ፈርቶ መደበቅ፣ እኩርፎ መንጋደድ የለም፡፡» አሉና መሀል ወለል ላይ ቆመው «በሉ እናንተ ቀድማችሁ በይቅርባይነት ያለ ወቀሳ ተሳሳሙ፡፡» አሏቸው
ታፈሡና ሸዋዬን ግራና ቀኝ አየት አየት እያረጉ፡፡ ታፈሡ ሁለት እጆቿን ዘርግታ ወደ ሸዋዬ ጠጋ በማለት «ሸዋዬ!!
ከአጠፋሁ ይቅርታ!» ብላ እንገቷን እቅፍ አድርጋ በመሳም ጨመጨመቻት፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ አጠገባቸው ቆመው «እሰይ እሰይ እልልል…» አሉ፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ ታፈሡ በዚያ ዓይነት ፈገግታ እየሳመቻት ሳለች የሸዋዬ
ፊት ግን ፈታ አለማለቱ እያናደዳቸው ነገር ግን የጀመሩትን ለመጨረስ ሲሉ፡ «በይ ያቺንም አበባ ጥሪልኝ፡፡ በእህቷ እግር ላይ ትወደቅ» ብለው ሔዋን ወዳላችበት ጓዳ አይናቸውን ወረወሩ።
«አንቺ ሒዩ» ስትል ታፈሡ ተጣራችና ቀጥላም ነይ እማማ ዘነብ ይፈልጉሻል» ስትላት ሔዋን ሽቁጥቁጥ እያለች ከወደ ጓዳ ብቅ አሉች፡፡ ለአንዴም ቀና ሳትል አቀርቅራ በመራመድ ከመሀላቸው ደረሰችና ከሸዋዬ እግር ላይ ወደቀች፡፡ወይዘሮ ዘነቡና ታፈሡም እልልእልል» በማለት ዕርቁን አደመቁት ።
ወይዘሮ ዘነቡ አሁንም ሆዳቸው በገነ ሔዋን ያን ያህል በእግሯ ላይ
ስትደፋ ሸዋዬ ግን ለመግደርደር ስትል እንኳ ቀና እንድትል አልጋበዘቻትም።በሆዳቸው ምኗ ድንጋይ ናት በማሪያም አሉ፡፡
የእርቅ ስነ ሥርዓት በዚህ ሁኔታ ተጠናቆ ሔዋን ብቻ ወደ ጓዳ ፈጥና ስትመለስ ሶስቱም ሶፋ ላይ ቁጭ አሉ የታፈሡ ሠራተኛ ቡና መቁላት ጀምራለች
«ሰላም ነሽ ሸዋዬ!» አለቻት ታፈሡ ቀድማ ፈገግ ብላ እያየቻት»
«እግዜሔርን አይክፋው»
«ሰሞኑን እንደተበሳጨሽ ይገባኛል ሔዩ አጥፍታለች» አለቻት ታፈሡ
👍131
የሆዷን በሆዷ አድርጋ ግን ደግሞ ፈገግ እያለች፡፡
ሽዋ'ዩ በረጅሙ ተነፈሰችና ቀድሞ የተብላሽ ነገር ምን መላ አለው
ሳልጠነቀቅ ቀርቼ» ብላ ነገሯን ተወት ስታደርግ ታፈሡ ቀጠለች።
«ሁለተኛ ላትደግም ቃል ገብታለች፡፡» አለችና እኔና አንቺ ግን ስለ ወደፊቱ ትንሽ ብንነጋገርና ከተቻለም" ተማምነን ብንስማማ ደስ ይለኛል፡፡» አለቻት፡፡
ስለ እሷ ከሆነ የሚያነጋግረን ነገር የለም፡፡ አለች ሽዋዬ ኮስተር ብላ፡
«ብንነጋገር የሚከፋ እይመስለኝም ሽዋዬ፡፡ ሔዋን እኮ እህትሽ ናት፡፡ እኔን ያገኘችኝ በአንቺ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ለእሷ ማሰብ ያለብኝ ከኔ በላይ እንቺ ነሽ፡
“ይጠቅመኛል ያለችውንማ ይዛለች አለች ሸዋዬ አፏን ጠመም አድርጋ፡፡
«በኔና በአንቺ ዕድሜ እኮ ከሙያችንም አንፃር በሰል ያለ አመለካከት ይጠበቃል ሽዋዬ?» ስትል ታፈሡ አሁንም ረጋ ብላ አስታያየቷን ሰጠቻት፡፡
«ታዲያ ሽዋዬ ምን ጎደላት አሉሽ?»
«ቢንስ ቢያንስ በሔዋን ዙሪያ የያዝሽው አቋም ትክክል አይመስለኝም፡፡ነጋሪ ሳያስፈልገኝ ራሴ እያየሁት ነው::»
«እውነቴን እኮ ነው ሽዋዬ ለመሆኑ ሔዩን ለጥፋት ያነሳሳት ነገር ምን
እንደሆነ ታውቂያለሽ?» ስትል ጠየቀቻት፡፡
«አንቺ ነሽ በይኛ» አለች ሸዋዬ አሁንም ታፈሡን በመገላመጥ፡ ታፈሡ የሚጠይቅ ጉዳይ በልቧ አለና ስሜቷን ገታ አድርጋ ማንም ይሁን ማ ነገር ግን አስራ ስምንት ዓመት ባለፋት ልጃገረድ ላይ ዱላ ማንሳት አልነበረብሽም።» አለቻተት።

ሸዋዬ ወደ ወረሮ ዘነብ ፊቷን መለስ አድርጋ እማማ ዘነብ ለዚህ ነው እንዴ ያመጣኝ?» ስትል ዓይኗን ፈጠጥ አድርጋ ጠየቀቻቸው፡፡
እስቲ እኮ ቆይ አስጨርሻት!» አሉ ወ/ሮ ዘነቡ እረጋ ብለው፡፡
"ዝም ብለሽ ተመልከቻት እያለችኝ እኮ ነው»
"እኔ እኮ ቁም ነገር ነው የማወራው ሸዋዬ» ታፈሡ አሁንም፡፡
«ለአንቺ ይመስልሽ ይህናል፡፡»
በዚ ጊዜ ታፈሱ የበለጠ ተናድዳ ዳኝነት፡ የፈለገች ይመስል ወይዘሮ
ዘነቡን መልክት አለቻቸው፡፡ በእርግጥ እሳቸውም በመሀል ገቡ።
«ምነው ልጆቼ ረጋ ብላችሁ በትትና ብትነጋገሩ! አሉ በተለይ ሸዋዬን አየት እያደረጉ።
ሽዋዬ ፊቷን ወደ ወይዘሮ ዘነቡ "መለስ አድርጋ ቆጣ ባለ አነጋገር «እንዴት እንግባባለን?
እሷ ያደፈረሰችውንበኔ ላይ ለማጥለል ስትፈልግ እያዮአት»
አለችና …" እግረ መንገዷን ታፈሡን በዓይኗ ገርመም አድርጋት ውጭ ውጭ ታይ ጀመር፡፡
ታፈሡ ድንገት ኪ..ኪ ...ኪ ብላ ሳቀች::
«ተይ አይሆንም አንቺ ልጅ! ሰው
የሚልሽን ተቀበይ እንዲህ ያለው ሃገር ድንግልም አትወደው ኋላ አይሆንም»አሉና ወይዘሮ ዘነቡ ዓይናቸውን ወደ ቡና ሦነ ስርአቱ አዞሩ።
«የመጣንበት ጉዳይ ተረስቶ ሌላ መዘዝ ሲመዘዝ ምን ላድርግ?» አለች ሸዋዬ በተለይ ወይዘሮ ዘነቡን እያየች
«ምን አደረኩ ሽዋዩ? እኔ እኮ እንነጋገር ነው ያልኩት አለች ታፈሡ
«ያደረግሽውንማ፣ አድርገሻል»
“እስቲ ምን?»
«ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብኛላ!
ታፊሡ አሁንም «ኪ ኪ ኪ ብላ ሳቀችና፡ እስቲ አንድ ነገር
ልጠይቅሽ::» አለቻት ለየፈገግ ብላ፡፡ ሸዋዬ በዓይኗ ገርመም አድርጋት እንደጋና ፊቷን ወደ ውጭ ስታዞር ታፈሡ ቀጠለች።
«አንቺ በታላቅነትሽ እህትሽን ድረሽ ኩለሽ ለወግ ለማአረግ ማብቃትና አትችይም» «አይገባሽም?» ስትል ጠየቀቻት
«አስተምሪ እንጂ ዳራ ኳይ አልተባልኩም»
«የግድ መታዘዝ የለብሽም ሁኔታዎችን ቢያስገድዱሽስ ?»
«ማን አባቱ፣ ነው የሚያስገድደን?ታፈሡ የሸዋዩን ምላሽ ፍየል ወዲያ ቅዝምገም ወዲህ ብላ ከታዘበች በኋላ «አልገባሽም እንጂ ጉዳዩ እንደሆነ ዓይኑን አፍጥቶ መጥቶብሻል፡፡»
«ኣ!» አለች ሽዋዬ ድንገት በመጮህ። ታፈሡንም ፍጥጥ ብላ ትመለከታት ጀመረ።
«አንቺ የማይሆንልሽ ከሆነ እኔና በልሁ ልንፈፅመው ወስነናል፡፡»
«እንዴት አድርጋችሁ?››
«በጣም ቀላል ነው! ወደፊት ሐምልና ነሐሴ ትምህርት ቤት ሲዘጋ እኔና በልሁ ክብረ መንግስት እንሄድና የሒዩን አባትና እናት እናስፈቅዳለን:: ከዚያ በኋላ
የኔና ያቺን ድርሻ ድል ያለ ሰርግ ደግሰን አስቹና ኤዩን ማጋባት ነው በቃ!» ካለቻት በኋላ «ክብረ መንግስት ለመሄድም ያሰብነው
የሒዪን ችግር አይተን እንጃ ራሳቸው አስቼና ሒዩ ብቻ የሚፈፅሙት ጉዳይ ነበር፡፡» አለችና ታፈሡ እንደገና ጥብቅ ባለ
አነጋገር “ምን ቁርጥ ያረገው ሰው ይክለክላቸዋል!» አለች ፏ ብላ በፈገግታ በመሞላት እማማ ዘነቡ አለች ሸዋዬ የታፈሡን ሀሳብ ያስለውጣት የመስል።
«ወይ»
«እንዳመጡኝ በሰላም አይመልሱኝም» አለቻቸው ከንፈሯን በምላሷ እያራሰች።
«ከዚህ በላይምን ሰላም አለ የኔ ልጅ አንቺም ሀላፊነቱ እየወረደልሽ
ነው» አሉና እንደውም ወደ ክብረመንግስት የሚደረገውን ጉዞም እኔም ብቀላቀልበት ደስ ይለኛል» ከሏት ይውጣላት ብለው።

«ጎሽ እማማ ዘነብ» ብላ ታፈሡ
ኪ..ኪ..ኪ..ኪ ብላ ሳቀች
«ተማክራችሁበታላ» ሸዋዬ በንዴት
«ጣድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ» ሲባል አልሰማሽም በዚያውም ልብ ያለው ልብ ያርገው ማለቴ ነው» ካሉ በኋላ ወይዘሮ ዘነቡ«ይህን ቡና ቶሎ ቶሎ በዮው አንቺ ልጅ »አሉ ወደ ጀበናው እየተመለከቱ። በእርግጥ ቡናው ደርሶ ነበርና መቀዳት ጀመረ ።

«ሸዋዬ ቅር አይበልሽ!» አለቻት ታፈሡ አሁንም ፈገግ ብላ እያየቻት::

ሽዋዬ ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥሯ ውጭ እንደሆነ ተገነዘበች፡፡ በዚያችው ቅፅበት ባርናባስ ትዝ አላት፡፡
ሰሞነን ይነጋገሩበት የነበረ አንድ ጉዳይ አለና ሳንቀደም ቅደም በርሄ' አለች በሆዷ።
ቡናው ተጠጥቶ ሲያልቅ ለእለቱ ሔዋን ከእህቷ ጋር ወደ ቤቷ ተመለሰች።በተበጀላት ወጥመዶ ውስጥ ትግባ አትግባ ገና የሚታወቅ ነገር የለ። እሷ ግን መጠመዱን እንኳ አታቅም...

💫ይቀጥላል💫
👍8😱2
#የፀሎት_ለውጥ

ለፍተህ ጥረህ ብላ
የሚል ትዕዛዝህን ህግህ ተከትዬ
እጠባበቃለሁ
የማጥመጃ መረብ ከባሕረ ጥዩ
እንግዲያው ፈጣሪ...
የኔ አቅም ይህቺ ነች
ገመድ አጠላልፎ
ባሕር ሳይ ከመጣል በላይ ያልዘለለች

በል ፀሎቴን ስማ...
በጣልኩት መረብ ላይ የዓሳ ዘር ይሙላ
ወገኔ ይደሰት እስኪጠግብ ይብላ

ብዬህ ነበር...

አሁን ግን...
የጣልኩትን መረብ መልሼ ሰበሰብኩ
ጠግቤ ለማደር ሌላ መንገድ አሰብኩ
ምክንያቱም.....

እኔ መረብ ጥዬ
ዓሳ ስጠኝ እያልኩ እየተማፀንኩኝ
ከመረብ ጠብቀኝ
ብሎ የፀለየውን ዓሳውን አሰብኩኝ

የባሕሩ ዓሳ እንዲህ ሲለምንህ
እኔ እሱን ባጠምደው
ያንተን ጠባቂነት ነውና ማወርደው
ስለዚህ አምላኬ...
አዲሱን ልመና ፀሎቴን አድምጠኝ
የነፍሳትን ፀሎት
ማይጋፋ እንጀራ ምረጥና ስጠኝ

🔘ልዑል ሀይሌ🔘
👍8
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


... እሷ የሽማግሌዎቹ ቁርጥ ሳይታወቅ፣ ከጥላዬ ሌላ ለማንም እንድትሰጥ አትፈልግም። ብቻ አባባ ለዝኸ ትኩር ብሎ ሲያየኝ ለነበረው ሰውየ እንዳይሰጡኝ አለች፣ ኢሳያስን እያየች።
ተጨነቀች፤ ተጠበበች፣ ብረሪ ብረሪ አላት። ኸጥላዬ ጋር ተያይዘን እንጠፋለን እንጂ እሱን አላገባም አለች።

እሷ ይህንን ስታሰላስል አባቷ አላስችል ብሏቸው እንግዶቹ
ተመልሰው የመጡበትን ምክንያት በዘዴ ለማወቅ፣ “ኸጐንደር ነው
ኸሌላ የመጣችሁ?” ሲሉ ጠየቁ።
የወለተጊዮርጊስ ጀሮዎች ተነቃቁ።
“ኸጐንደር ነው የመጣን” አለ ኢሳያስ። ትንሽ ካመነታ በኋላ፣
“እንግዲህ እንንገርዎ እንጂ” አለና አብረውት የመጡትን ተመለከተ።
የተግባቡ መሰለው። ፊቱን ወደ ግራዝማች መልሶ ፈገግ አለ። ዐይን ዐይናቸውን እያየ፣ “ግራማች… የዛን ዕለቱ እመምተኛ እኮ ንጉሡ ራሳቸው... አጤ በካፋ ነበሩ” አላቸው።

ግራዝማች ከመደቡ ላይ ተወርውረው ተነሡና፣ “በወፍታው!” አሉ፤ ሰንበት የሚሳለሙትንና በየዓመቱ የሚዘክሩትን ደብራቸውን ወፍታ
ጊዮርጊስን ጠርተው።ራሳቸውን በሁለት እጆቻቸው ይዘው፣ “ጃንሆይ ራሳቸው? እኛ እንደ
ዋዛ ኸዝኸ ተኝተው የነበሩቱ?” አሉ፣ ተቀምጠውበት የነበረውን መደብ በሌባ ጣታቸው እያመለከቱ።

ግራዝማች በህመምና በሐዘን ምንክንያት የንጉሠ
ነገሥቱ የንግሥ ሥርዐት በተከበረበት ወቅትና በበዓል ጊዜ ንጉሠ ነገሥቱን በዐይን ለማየት ዕድል አግኝተው አያውቁም ነበርና ንጉሠ ነገሥቱን ባለማወቃቸው አዝነው ራሳቸውን ነቀነቁ።

“ምነዋ እንደዝኸ ጉድ ትሠሩኝ? እንዲያው እንዴት ያለ ፌዝ ነው
ምትነግሩኝ? እንዳው በወፍታው ምን ጉድ ነው ምትነገሩኝ?” እያሉ
ራሳቸውን በሁለት እጆቻቸው እንደያዙ ቆመው ቀሩ። ሰውነታቸው ብርክ እንደያዘው ተንቀጠቀጠ፤ ትከሻቸው ላይ ያጣፉት ጋቢ ወርዶ መሬት ነካ።

የተነገራቸው ቀልድ መሆኑን የሚያረጋግጥላቸው የፈለጉ
ይመስል ዐይኖቻቸውን ከአንዱ እንግዳ ወደ ሌላው አፈራረቁ።
እንግዶቹ በሁኔታቸው ተደናገጡ። እንኰዬ ባላቸውን እንባ ቀረሽ
ተመለከቱ፤ ተነሥተው ጋቢያቸውን ሊያስተካክሉላቸው ፈልገው
መነሣት አቃታቸው።

“በተክልየ ይቀመጡ ግራማች” አላቸው ኢሳያስ፣ ሁኔታቸው
አስደንግጦት።

ግራዝማች ራሳቸውን እየነቀነቁ ለመራመድ ዐቅም እንዳነሳቸው
ሁሉ ጋቢያቸውን ሰብሰብ አድርገው ቆም አሉና ጉልበታችው
የከዳቸው ይመስል፣ በሁለት እጃቸው ደግፈውት ተመልሰው መደቡ ላይ ተቀመጡ። የሚሉትን ቀርቶ የሚያስቡትን ማወቅ ተስኗቸው፣ ግንባራቸውን ኩምትር አድርገው፣ ዐይኖቻቸውን መሬት የተነጠፈው አጎዛ ላይ ተክለው ቀሩ።

ወይዘሮ እንኰዬና እናታቸው ትኩረታቸው ግራዝማች ላይ ነበርና
መቀመጣቸውን ተከትለው ዐዲስ እንደሰማ፣ “በቁስቋሟ!” አሉና
እርስበርስ ተያዩ። ወለተጊዮርጊስም በቁስቋሟ ብላ አማተበች። አያቷ ሆኑ ቅድመ
አያቶቿ የሚያከብሯትን፣ የሚማጸኗትን፣ የሚዘክሯትን፣ ባለውለታቸውን፣ በዕለተ ቀኗም ብዙ ድል የተቀዳጁባትንና እሷ ራሷም ብትሆን “ግጥሜ”
የምትላትን ቁስቋም ማርያምን ጠርታ። በግራ እጇ ኣፏን ይዛ፣ ንጉሡ ራሳቸው እኛ ኸዝኸ ኸመደብ ላይ ተኝተው የነበሩቱ? እኛ ፊታቸውን ሳጥብ፣ አጥሚት እየሠራሁ ሳጠጣ... እጃቸውን ሳስታጥባቸው የነበሩቱ
እንዴት ብለ? ንጉሡ ራሳቸው? ጉድ ጉድ! የዛሬውስ ቀን ምንያለውን ጉድ ይዞ መጣ እናንተዬ? አለች፣ መጋረጃውን ለቃ፣ ራሷን በሁለት እጆቿ ይዛ። ጥቂት ቆይታ መጋረጃውን እንደገና አጋጥማ ይዛ ወደ እንግዶቹ ተመለከተች፤ ያወጋሉ። የሚሉትን ለመስማት ሞከረች።
ሐሳቧ ግን አልሰበሰብ አለ።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሕመምተኛ የነበሩት፡ የአሁኑ ንጉስ። ፊቷ ላይ ድቅን እያሉ አስቸገሯት። መላ ቤተሰቡ ንጉሥ መሆናቸውን እንዴት ሳያውቅ፣ ሳይጠረጥር እንደቀረ ገረማት። ነገሩን በቅጡ ለመመርመር ሐሳቧ ወደ ኋላ ነጎደ።....

የመጡ ቀን፣ እንደ ልማዷ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ተቀምጣ የእነዚያን
የአስታራቂ ሽማግሌዎች መምጣት ትጠባበቃለች። ግቢው መግቢያ ላይ ሰዎች ስታይ ብድግ አለች። “እረ የታመመ ሰው ነው መሰል ይዘው የመጡ” አለች፣ ዛሬ ከመጡት እንግዶች ውስጥ ሁለቱና ሌሎች ሁለት ሰዎች አንድ ሰው ደግፈው ድንገት ግቢው ውስጥ ሲገቡ አይታ።

“እነማ?” እያሉ እናቷ፣ አባቷና አያቷ ከውስጥ በችኮላ ወጡ።
በርግጥም የታመመ ሰው እንደመጣ ሲያውቁ ደነገጡ፣ “ግቡ! ግቡ!” እያሉ መንገድ ለቀቁ። ነፍጥ የያዙ፣ ፈረስና በቅሎ ሳይቀር ያስከተሉ በርካታ ሰዎች እየተገፋፉ ገቡ። ሁሉም የመረበሽ መልክ ይታይባቸዋል።
እምብዛም ግርግር የማያውቀው ግቢ ትርምስምስ አለ። የተረጋጋው
የእነግራዝማች ቤት ለወከባና ለድንጋጤ ቦታ ለቀቀ።

አራቱ ሰዎች ወደ ቤቱ ውስጥ ገብተው፣ አቅፈው ደግፈው ያመጧቸውን ሕመምተኛ መደብ ላይ አሳረፏቸው። ወለተጊዮርጊስ፣ እኚህ መሣሪያ የያዘ ወጀብ የተከተላቸውና በጽኑ የታመሙ የሚመስሉት ሰው ማን መሆናቸውን ለማወቅ እጇን ደረቷ ላይ አድርጋ ተመለከተች፤ ግንባሯ
ኩምትር፣ አፏ ከፈት ብሏል። እናቷ፣ “ወለቴ እስቲ ውሃ” ሲሏት
በፍጥነት ወጥታ በቅምጫና አምጥታ አቀበለቻቸው።
ያን ሰዐት፣ ዙርያውን በቆሙት ሰዎች መሃል፣ ባለ ንቅሳት አንገቷን
ሰገግ አድርጋ ሕመምተኛውን አየች። በጽኑ እንደታመሙ አስተዋለች፤
ይቃዣሉ፤ ይቃትታሉ፤ ይወራጫሉ፤ ብርክ እንደያዘው ይንዘፈዘፋሉ።
ሮጥ ብላ ከመጋረጃው ጀርባ ቡሉኮ አምጥታ ደረበችላቸው።

ሰውየው የመጣላቸውን ውሃ መጠጣት ቀርቶ ዐይናቸውን መግለጥ ሆነ አፋቸውን መክፈት አልቻሉም። ግራዝማች መንበር ተደናግጠው፣
“ምንን ሁነው ነው? እመማቸው ምንድር ነው? እያሉ ከወተወቱ በኋላ፣ አንደኛው እንግዳ፣ “ንዳድ ሳትሆን አትቀርም። ቆላ ሲወርዱ ነድፋቸው ፊት ታመው ያቃሉ። ኸናንተ ዘንድ ይዘነ መጣነ” በማለት መልስ ሰጡ፣ ንጉሠ ነገሥቱን ይዘው ማንም ሰው ቤት ስለማይገቡ፣ ቋራ ውስጥ
የታወቁት ባላባት ቤት የትኛው እንደሆነ ጠይቀው የመጡት መሆኑን ሳይናገሩ።
ግራዝማችም፣ “ኧረ ደግ አረጋችሁ፤ ስንኳንም መጣችሁ። ቤት የአብርሃምም ማዶል?” ብለው አደግድጎ የቆመውን አሳላፊ፣ “እስቲ ኸድና ያነን በሪሁንን ተሎ ይዘህ ና” አሉት፡
መድኃኒተኛው በሪይሁን ከመቅጽበት መጥቶ አንድ እጁን
ሕመምተኛው ግንባር ላይ አስቀምጦ ራሱን ነቀነቀ። ጉንጫቸውን ዳበስ፣ እጆቻቸውን ጨበጥ፣ ጨበጥ አድርጎ መልሶ እጁን ግንባራቸው ላይ አሳረፈና፣ “ንዳድ ነች” አለ።

“ተሎ በልና መዳኒት አርግላቸዋ” አሉ፣ አንደኛው እንግዳ።

በሪሁን ለሰውየው መልስ ሳይሰጥ በቅዎጫና ተቀምጦ የነበረውን
ውሃ ደጅ ወጣ ብሎ ቀነሰለት። ይዞት ከመጣው ከረጢት ውስጥ
የደቀቀ ቅጠል መሳይ ነገር ቆንጠር አድርጎ በውሃው በጠበጠና በርከክ ብሎ የሕመምተኛውን ጭንቅላት በአንድ እጁ ቀና አድርጎ በመዳፉ
ጋታቸውና ቆሞ ተመለከታቸው።
ይህ ሁሉ ሲሆን ሰውየው ዐይናቸውን አልከፈቱም፤ አንገታቸው ወደ አንድ ወገን ዘንበል ብሎ ተኝተዋል። የሚሆነውን ሁሉ የሚያውቁ
አይመስሉም።
“በሪሁን ሁሉም አልገባም። ኸመዳኒቱ ትጨምርላቸው?” አሉ
ግራዝማች መንበር፣ ከሰውየው አፍ ቀስ እያለ የሚንጠባጠበውን ፈሳሽ እያዩ።

በሪሁን፣ “ግድ የለም የገባው ይበቃል” ሲል ሰውየው አስመለሳቸው።
ወለተጊዮርጊስ ፈጠን ብላ ንፁህ ሀጨርቅና ውሃ አምጥታ የሰውየውን አፍ ጠራረገችላቸው፤ አካባቢውንም አጸዳች።

“መዳኒቱ ወጥቷል። እንደገና አርግላቸዋ” አሉ ግራዝማች፣ በሪሁንን።
“ትንሽ ይርጋላቸውና አረግላቸዋለሁ።”
መድኃኒቱን እንደገና ግቷቸው በርከክ ብሎ ተጠባበቀ፡፡ ሰውየው
አላስመለሳቸውም።
👍112
“ይረጋላቸዋል። እንቅልፍ ኻገኙ ምንም አይላቸው። ራስ ምታትም
ስለሚኖራቸው ራሳቸውን ደገፍ ማረግበት ጨርቅ ቢጤ ብትሰጡኝ” ብሎ እንኰየን ቀና ብሎ አያቸው።

ወለተጊዮርጊስ የአንገት ልብሷን ከትከሻዋ ላይ መንጭቃ፣ “እኼው...
አንተ አንገታቸውን ቀና አርግልኝ እኔ ራሳቸው ላይ ልሰርላቸው”
አለችው።
አንገታቸውን ቀና ሲያደርግላት፣ አንገት ልብሱን ጠበቅ አድርጋ
አሰረችላቸው። እንግዶቹ በቅልጥፍናዋ ተገርመው በአንድ ቃል፣
“ተባረኪ... ተባረኪ” አሏት።
በሪሁን፣ “ኸባሰባቸው ጥሩኝ። ኋላ ተመልሸ መጣለሁ” ብሎ፣ እጅ
ነስቶ ከግቢ ወጣ።

ሰውየው እንቅልፍ ሲጥላቸው እንግዶቹ ምግብ ቀረበላቸው። ከየት እንደመጡ ሳይናገሩ በልተው ጨረሱ።።
ወለተጊዮርጊስ ሰዎቹ ተራሰዎች እንዳልሆኑ አውቃለች። አነጋገራቸው የተመጠነ፣ ኮራ ያሉም ናቸው። ከእነሱም የበለጠ ሕመምተኛው የተለየ ላህይ አላቸው። ወጣት ቢሆኑም፣ ሰዎቹ የማያሳይዋቸው ክብር ተራ
ሰው እንዳልሆኑ ይናገራል። የጋሻ ጃግሬዎች፣ የሙስሊም ነፍጠኞችና ሠይፈ ጃግሬዎች ብዛት ብቻ ሳይሆን የያዙት ነፍጥ፣ ቀስትና ጦር ቁጥር ቀላል አልነበረም። ፈረሶቹና በቅሎዎቹም ያጌጡና ደሕና የተቀለቡ ናቸው። ሰዎቹ ይዘው የመጧቸው ድንኳኖች ተተክለው ማሩ፣ ቅቤው፣ አዋዜው፣ ጠጁና አረቄው ተራገፈ።ወለተጊዮርጊስ ይህንን ስታሰላስልና እኛ ሕመምተኛ እንግዳ አፄ በካፋ
በመሆናቸው ስትደነቅ፣ አንደኛው እንግዳ መናገር ስለጀመሩ ትኩረቷን ወደ እሳቸው አደረገች።

“ግራማች፤ “እንዴት ያለ ፌዝ ነው ምነግሩኝ ላሉት ፌዝ ስንኳ
ማዶል” ብለው አስተባበሉ። ቀጥለው፣ “ጃንሆይ አንዳንዴ ሰዋቸው እንዴት እንደሚኖር እየተዘዋወሩ ያያሉ። አደንም ይወዳሉ። የዛን ዕለትም እኮ ወደ ቆላ ወርደን ያልታሰበ ነገር... ያቺ ንዳድ ተነስታባቸው ኸርሶ ዘንድ አመጣችነ። አሁንም ተመለስነ። እንዳው ምክኛት ሆነች”
ካሉ በኋላ፣ ደንገጥ ብለው፣ ኢሳያስን የጎንዮሽ ተመለከቱት።
ኢሳያስም ለመናገር ጉሮሮውን ጠራርጎ፣ “የመጣነው” ሲል
ግራዝማች አቋረጡት።

“ኧረ ስንኳን መጣችሁ። ብቻ እንዳው እሳቸው መሆናቸውን
ሳናውቅ... ድንገት ሁኖብን እንደ ነገሩ ነበር... ለንጉሥ ሚገባ
አላረግንም” አሉ። ንጉሠ ነገሥቱ እሳቸው ቤት ለቀናት ተቀምጠው
መሄዳቸው በራሱ ትልቅ ክብር ቢመስላቸውም፣ ለንጉሥ የሚመጥን መስተንግዶ ማድረጋቸውን ተጠራጠሩ።

“ግራማች እጅጉን አስተናገዱን እንጂ። ኸያ በላይ ምን ያረጉ ኑሯል? ልዥዎትስ ብትሆን እንዳው እሳቸውን እንደዛ አርጋ ስታስታምም አይተን ተገርመንስ ማልነበር? እንዳው የልዥ አዋቂ” አሉ፣ አንደኛው እንግዳ ።

“ብቻ አውቀን ቢሆን ኑሮ ደግ ነበር። እንዳው መቸም...” አሉ፣
ግራዝማች መገረም፣ ድንጋጤ ሌላም ሌላም ስሜት በውስጣቸው ተራ እየወሰደ። አንተ የወፍታው እንዳው ያጎደልሁት ነገር ይኖር ይሆን አረ ለመሆኑ ያቺ ወለቴ በደንብ አስታማቸው ይሆን ልዤ ስንኳ ሚቀርባት የለም። ቤት አያያዝ እሷን ሚያህል አለ? የአያቷን ቤት ቀጥ አርጋ የያዘች እሷ ማዶለች እንዳው ማስታመሙን ለሷው ነበር
የተውነው ብየ ቢጨንቀኝ ነው እንጂ፤ ብለው ወደ መጋረጃው ሰረቅ አድርገው ተመለከቱ።
ኸያ በላይ እንዴት አርጌ ላስታምም ኑሯል? ደሞ እንደ ነገሩ ቢሆንም፣ መቸም ቤት ያፈራው አንድም አልቀረ። እንዴ ያነን ሁሉ ዐጀብ ለስንት ቀን ተቀበልኘ ኸያ ወዲያ ምን ልናረግ ኑሯል? አባባ እንዳው አለቅጥ ለሰው መጨነቅ ያበዛሉ አለች ወለተጊዮርጊስ፣ የሰማቻቸው ያህል። ትዕግስቷ አለቀ። እንግዶቹን አንድ በአንድ ተመለከተቻቸው።

ይልቅስ የመጣችሁበትን ጉዳይ ተናገሩ! አለች።.....

ይቀጥላል
👍10
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ... እሷ የሽማግሌዎቹ ቁርጥ ሳይታወቅ፣ ከጥላዬ ሌላ ለማንም እንድትሰጥ አትፈልግም። ብቻ አባባ ለዝኸ ትኩር ብሎ ሲያየኝ ለነበረው ሰውየ እንዳይሰጡኝ አለች፣ ኢሳያስን እያየች። ተጨነቀች፤ ተጠበበች፣ ብረሪ ብረሪ አላት። ኸጥላዬ ጋር ተያይዘን እንጠፋለን እንጂ እሱን አላገባም አለች። እሷ ይህንን ስታሰላስል አባቷ አላስችል ብሏቸው እንግዶቹ…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

..አንድ ወር ተኩል አላፈ፡፡ አስቻለው ከደረሰበት የመኪና አደጋ ጉዳት አገግሞ ዲላ ከተመለሰ አስር ቀን ሆኖታል።
የወዳጆቹን የእንኳን አተረፈህ
የመልካም ምኞቱ መግለጫ ተቀብሎ ጨርሷል፡፡ ዲላ በገባ ሶስተኛው ቀን ላይ ከሔዋን ጋር ተገናኝተው የሰቀቀን እንባቸውን አፍስሰዋል። የአስቻለው የአጥንት ስብራትና በቆዳው ላይ ተከስቶ የነበሩ ቁስለቶች ፈጥነው የሻሩ ቢሆንም በተለይ በቀኝ እግሩ ጣቶችና በግንባሩ እካበቢ የደረሰበት ጉዳት ጠባሳቸው ባለመጥፋቱ የሔዋንን አንጀት አላውሰውታል። በእጇ እየዳበሰቻቸው በመሳቀቀ ያወረደችው እንባ ከአስቻለው እዕምሮ ምንጊዜም አያጠፋም፡፡ እሱም ቢሆን ባለፈው ጊዜ ከእሱ ጋር በማደሯ ምክንያት ተፈጥሮባት የነበረውን ችግር ሰምቶ
አሳዝኖታል።

ዛሬም ሲገናኙ ቀጠሮ ነበራቸው፤ በሚያዚያ ወር ሁለተኛ ሳምንት ላይ በዕለተ ሰኞ፡ አስቻለው በሀኪም ዕረፍት ሳይ ስለሆነ ስራ አይገባም፡፡ ዕለቱ ደግሞ ለአስራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወሳጆች የፈተና አስራር ማብራሪያ
የሚሰጥበት በመሆኑ ሔዋን ከማብራሪያው በኋላ ወደ ቤቱ ብቅ ብላ ልታየው ቃል ገብታለት ነበር፡፡ ነገር ግን ትናንት ምሽት ላይ በልሁና መርዕድ በአስቻለው ቤት
ጫት እየቃሙ ሳሉ ታፈሡ ድንገት ብቅ ብላ «አስቹ» ብላው ነበር፡፡
«ወይ»
«ነገ ከሔዩ ጋር ልትገናኙ ቀጠሮ ነበራችሁ አይደል!? »
«አዎ»
ቅድም
ቅድም መንገድ ላይ አግኝቻት ስላልተመቸኝ አልመጣምና
እንዳትጠብቀኝ ብላሀለች» በማለት መልዕክት አድርሳለታለች በዚህ መሰረት አስቻለው ዛሬ ስለ ቀጠሮው ማሰብ ትቶ ማርፈጃውን ሁሉ አልጋው ላይ ጋለል እንዳለ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳብ ያውጠነጥን ጀመር፡፡ ከምንም ባላይ አልረሳ ብሎ ያስቸገረው የደረሰበት የመኪና አደጋ ነው። በአደጋው የተጎዳ ሰውነቱ
ቢያገግምም መንፈሱ ግን ክፉኛ ቆስሏል። ሀገርና ወገኑን በሙያው እያገለገለ በሰላም ሰርቶ በሰላም ውሎ ማደር ሲችል ነገር ግን በእሱ አመለካከት ለምንም ነገር
በማይበጁ፤ ለክፋትና ለተንኮል ብቻ በተፈጠሩ እብሪተኞች አስተዳደራዊ ተፅዕኖ
በመማረር አካባቢውን ለቆ ለመሄድ ለዝውውር ጥያቄ ሲጓዝ ያን የመሰለ አሰቃቂ አደጋ ደርሶበት ለጥቂት መትረፉ ትዝ ባለው ቁጥር ዝግንን ይለዋል። ሁል ጊዜ ይቆጨዋል። ዘወትር ያበሳጨዋል፡፡ ሞቼስ ቢሆን ኖሮ? እያለ ሲያስበው እልህና ንዴት እየተናነቀው መንፈሱ ውጥርጥር፣ ውስጡ እርር ድብን እያለ ከንፈሩን
እያስነከሰ ራሱን ያስወዘውዘዋል፡፡ የአስቻለው ችግር ይህ ብቻ አይደለም፤ ያለፈውን
እንዳለፈ ቆጥሮ መጽናናት እንዳይችል እንኳ ሌላም አደጋ ከፊቱ እንደተደቀነበት ያወቀው ገና ህክምናውን ጨርሶ ዲላ በገባ ማግስት ነበር።
በመሰረቱ የዶክተር ደጀኔ አሜሪካ መግባት እርግጥ ሆኗል። በእሱ እግር የተተካው የዲላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ደግሞ ከመልካቸው በስተቀር በአስተሳሰብ ከባርናባስ ወየሶ ጋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። እንዲያውም በመላ የሆስፒታሉ ሰራተኞች አፈራረጅ ከበርናባስ የባሰ አኘር አጥፊ
የተባለ ሰው ነው። ለአስቻለውማ ጭራሽ ሰው የሚበላ የስው አውሬ!
አዲሰ ሹመኛ በሙያው ዶክተር ቢሆንም በባህሪው ግን ወትሮም ካድራ ካድሪ የሚሸት ነበር። በሚናገርበት መድረክ ላይ ሁሉ የሚሰነዘረው ሃሳብና ሀሳቡን
የሚገልፅባቸው ቃላት ስልጣን
መለመኛ ይመስላሉ፡፡ አንዳንዴ ሊፈላሰፍም የሚቃጣው ነው
ነገር ግን ከባዶነቱ የተነሳ የጀመረውን ዐረፍተ ነገር እንኳ በግስ መዝጋት የማይችል
ግብዝና ዘባራቂ ዓይነት ሰው ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ ስልጣን
አግኝቷልዐተናግሮ ማሳመን ባይችል ተናጋሪዎችን ዝም ፀጥ የሚያሰኝ በትር" አዎ ስልጣን! በእብሪተኞች ጎራ በተስላፉ ደንቆሮዎች እጅ በገባ ቁጥር የሩቅ አሳቢ አሰተወዬችን የሚቀላ ሰይፍ

አስቻለው በዚህና በዚሁ ዙሪያ ሲያስብ ሲያሰላስል ቆይቶ የተሰማው ንዴትና ቁጭት አዕምሮው ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ሲሆንበት ትንሽ የሚቀለው
መሰለውና ከመኝታው ሊነሳ አንሶላና ብርድ ልብሱን ከላዩ ላይ አስቀጥሮ ጣለው፡፡ ሱሪና “
ጫማውን እንዲሁም ሽሚዙን ለበሰ፡፡ ጥርሶቹ ግን ከንፌሩን ንክስ እንዳደረጉ ናቸው፡፡ ጭንቅላቱን ደጋግሞ እየወዘወዘ ፊቱን ሊታጠብ ውሃ ይዞ ወደ በረንዳ ወጣ።

ስዓቱ ከሶስት አለፍ ብሏል። አስቻለው ታጥቦና አበጥሮ ከጨረሰም በኋላ ወደየትም መሄድ አልፈለገም። የቁርስ ሰዓት አልፏል። ቀዽሞ ነገር ሆዱም እህል አላስኘውም። ወንበር ይዞ ከቤት ወጣና ጀርባውን ለፀሐይ ሰጥቶ ግቢው ውስጥ ቁጭ አለ።

ፀጥ ረጭ ብሎ የዲላ ህይወቱን ሲያሰላስለው በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ምቾት እንደማይሰጠው ተሰማው። ቢሆንም ባይሆንም አንዲት ተስፋ ብቻ ታየችው። ዶክተር ደጀኔ በገባለት ቃል መሰረት የአዲስ አበባውን ባለስልጣን አነጋግሮለት ኖሯል፡፡ አስቻለው ከሆስፒታል እንደ ወጣ ወደ ፅህፈት ቤቱ በመሄድ ያን ባለስልጣን አግኝቶታል። እሱም ዶክተር ደጀኔ በገለፀለት መሰረት የአስቻለውን ችግር እንደተረዳለትና ሊያዛውረው እንደሚችል ቃል ገብቶለታል። ግን ደግሞ ይህን
ተስፋ የሚያጨልሙ ሁኔታዎች ከአስቻለው እዕምሮ ውስጥ ድቅን ይላሉ።
ከአሁን በፊት ስለ ዝውውር ጉዳይ ከዶክተር ደጀኔ ጋር ሲነጋገር ...የት
ቢኬድ ይሻላል? ባለው ጊዜ ዶክተር ደጀኔ ... መሄጃው ላይገድ ይችላል፤ ችግሩ የተሻለ ሁኔታ ከማግኘቱ ላይ እንደሆነ እንጂ ብሎት ነበር፡፡ እንዲህም ለዝውውር ጥያቄ ወደ አዲስ አበባ በሚሄድበት ጊዜ በመኪና ጉዞ ላይ ከሟቿ ከወይዘሮ አቦነሽ
ሀይሌ ጋር ሲነጋገር ወይዘሮ አቦነሽም ለመሆኑ እነሱ የሌሉበት አገር አለ እንዴ?? ብለውት እንደነበር አስታወሰ፡፡ በዚሁ አጋጣሚ የወይዘሮ አቦነሽ ሓይሌ እና የጠይሟ ልጃገረድ ሞት ትዝ አለውና አሟሟታቸው አሳዝኖት በሀዘን ስሜት ከንፈሩን መጥጦ ራሱን ወዘወዘና ወደ ንዴቱና ብስጭቱ ተመለሰ።
«ቆይ ግን!» አለ ድንገት ጮክ ባለ ድምፅና በእልህ አነጋገር። ምናልባት ፀሐዩም በዝቶበት ሊሆን ይችላል፤ ከተቀመጠበት ወንበርም ላይ ፍንጥር ብሎ፣
ተነሳ፡፡ አንገቱን ደፋ አድርጎ በዚያው በግቢው ውስጥ ጎርደድ እያለ «ሰው በገዛ ሀገሩ በሰላም ሰርቶ በሰላም መኖር ላይችል!? » አለና መልስ የሚጠብቅ ይመስል
ፀጥ ብሎ በመቆም አቀርቅሮ መሬት መሬት ያይ ጀመር፡፡ ብስጭቱ ጨመረና
«ቀድሞ ነገር ንዴትስ ለምን? ብስጭትስ ለምን? በምሪት የተነሳ የዝውውር ጥያቃ ለምን? ይህ ሁሉ ጣጣ የመጣው ሰዎች በሌላ ሰው ኑሮና ህይወት ላይ ይወስኑ
ዘንድ ገደብ የሌላው ስልጣን ስለ ተስጣቸው አይደል!» አለ በንዴት ስሜት እጆቹን ጥብቅ በመጨበጥ ሰውነቱንም በእልህ እያጠነከረ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያያዘና
ሰፊዋ ሀገር ኢትዮጵያ እንደ ኳስ ተድቦልበላ እዕምሮ ውስጥ ድንገት ዘው ብላ ገባች፡ በሀሳብ፡፡ እንደ እሱ በበደልና በእንግልት ቁም ስቅላቸውን አጥተው
የሚሰቃዩና የሚያለቅሱ ዜጎቿ አብረው ገቡበት፡፡ ነዢዎችና አጫፋሪዎቻቸውም አልቀሩ ከነድንፋታቸው፣ ከነጭካኔያቸውና እነቅጥፈታቸው እየገቡ ታጨቁበት።በሆድና በህሊና ጎራ ለሁለት የተከፈሉ የአንድ ሀገር ዜጎች በአዕምሮው ውስጥ ገብተው እየተን፡ እየተንጬጩ ተርመሰመሱበት፡፡ በዚህ እስጨናቂ ስሜት ውስጥ ሲገባ
👍7
ከመንፈሱም በላይ የአካል ድካም ተሰማው ወገቡ ተንቀጠቀጠ፡፡ መቆምም አቃተው። ያን ፀሐይ ላይ የነበረ ወንበር ወደ ጥላ ቦታ ወሰደና ቁጭ አለ፡፡ የሀሳብ ሸክሙን ያቀለለ መስሎት « ኡህህህ» ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ።
«አንቺ ኢትዮጵያ!» አለ ትንሽ ቆይቶ። ሀገሩን ሊወቅሳት ይሁን
ሊያለቅስላት ገና ሃሳቡን አላዘጋጀም፡፡ ብቻ ከንፈሩን ንክስ አድርጎ ራሱን ወዘወዘ፡፡
ከትንሽ ቆይታ በኃላ ግን ከራሱ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ የሚያዳምጠው
ቢኖር እስከ ውጭ ድረስ በሚሰማ ድምፅ «አንቺ አገር አንቺ ኢትዮጵያ፣ እስከ መቼ ይሆን ጥቂቶች ሲፈነጩብሽ፣ ብዙሃን ሲያለቅሰብሽ፣ እብሪት እንደነገሰብሽ፣ ፍትህ እንደጎደለብሽ የምትኖሪው? ከቶ መቼ ይሆን ደም ያልተቃቡ መንግስትና ሕዝብ የሚኖሩብሽ? እኮ እስከ መቼ!? » ካለ በኃላ አሁንም ትንሽ ተንፈስ ብሎ
«በእርግጥ እብሪት ለማስተዋል፣ ተንኮል ለግልጽነት! ውሸትና ቅጥፈት ለሀቅና ለእውነት ቦታቸውን ሰተው የሰላምና የነፃነት አየር የሚተነፍስብሽ ሀገር ለመሆን ያበቃሽ ይሆን? በእርግጥ የእናትነት እቅፍሽ ለሁሉም ዜጎችሽ እኩል የሚሞቅበት ጊዜና ዘመን ይመጣ ይሆን!? » አለና ላነሳቸው ጥያቄዎች ሁሉ መልስ የሚጠብቅ ይመስል ዝም ፀጥ፣ ፍዝዝ ትክክዝ እንዳለ ለደቂቃዎች ያህል ቆየ፡፡ በሀሳቡ ግን ሌላ
ነገር ያሰላስል ነበርና እንደገና መናገር ጀመረ። «ደግሞ እኮ አያፍሩም!» አለ በመሳቅ
ዓይነት በደረቁ ፈገግ እያለ፡፡ በዚህ ጊዜ ትዝ ያለው ገዢዎች ከመጋረጃ ጀርባ ያላቸውን ድብቅ አጀንዳ ይበልጥ ለመሸፈንና የአኮረፈ ሕዝብ ለመደለል ሲሉ
በቁጥጥራቸው ስር በአደረጉት ራዲዮና ቴሌቪዝን አዘውትረው የሚወሻክቱት ባዶ ተስፋ ነው፡፡ እናም ይህንኑ በራሱ ቃል ይናገረው ጀመር፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ አገራችን፣ የአሥራ ሦስት ወር ፀጋ! ይሏታል! ደሞ የመከራ ቀን ሲያራዝሙ! (አገራችን ኢትዮጵያ ፡ የሰው ዘር መገኛ ይሏታል! ነገር ግን ነሮውን አጐሳቅለው፣
አስተሳሰቡን አዛብተው፣ አመለካከቱን አላሽቀው በሁሉም ነገር ከዓለም ህዝብ ሁሉ
ወደ ኋላ የቀረ ሕዝብ የሚኖርባትን ሀገር ለምለሟ ኢትዮጵያ» ይሏታል፤ ድርቅና ረሀብ መለያዋ ሆኖ ዓለም በሚያውቀው መዝገብ ላይ በምሳሌነት ስሟ እንዲመዘገብ ያደረጓትን ያልታደለች ሀገር! የነፃነት ተምሳሌት ይሏታል፤ ነገር ግን ላይናገር የታፈነ፣ ላያይ ዓይኑ የተጋረደ፣ ሳይላወስ እግር ከወርች የታሰረ ሕዝብ የሚኖርባትን የሲኦል አምባ!» ላይኖሩብሽ የሚፈጠሩብሽ አገር!» አለና ለአፍታ ያህል ፀጥ ብሎ ሀሳቡን ሲያዳምጥ ቆየና ድንገት «ኤድያ»
በማለት እጁን አወናጭፎ ከወንበሩ ብድግ አለ፡፡ ሁለት
እጆቹን በሁለት የሱሪ ኪሶቹ ውስጥ ከትቶ በዚያው አካባቢ አጎንብሶ ጎርደድ እያለ
«ላይኖርብሽ የሚፈጠሩብሽ አገር» አለ አሁንም።

ሀሳቡ ሁሉ ከዚሁ ጉዳይ ሳይርቅ አንዳንዴ መሬት መሬት ሌላ ጊዜ ሰማይ ሰማይ እያየ እንደገና ራመድ ጎርደድ ሲል ደቂቃዎችን
አሳለፈ፡፡ አልፎ አልፎም
በልቡ እያራ ከንፈሮቹ፣ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በዚህ ጊዚ ብሶቱን መግለጫ የሚሆኑ አንዳንድ ቃሎችና ሐረጎች ውስጥ ውስጡን ይንገዋለልበት ጀመር፡፡ በልቡ
አመላለሳቸው፡፡ እያደር ነፍስ እየዘሩ ይሄዱበት ጀመር። እሱም ስጋ ሊያለብሳቸው ድንገት ከሃሳቡ እንደመባነን እለና ፈጠን ቀልጠፍ ብሉ ወንበሩን ይዞ ወደ ቤት ገባ፡ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ አለና ብዕርና ወረቀት አዘጋጀ፡፡ መሞነጫጨር
ጀመረ፡፡

«ህሊና ታሰረ ከወይኒ ወረደ
አእምሮኖ ተክቶ ሆድ እየፈረደ።
ሲያለቅስ አገኘሁት ህግ ተንሰቅስቆ
መክሰስም መፍረድም ለአንድ ሰው ተለቆ፡፡
ጊዜ በቅሎህን ጫን ገስግስ በፈረስ፡፡
እውነት ዳኛ ትሁን ተራዋ ይድረስ፡፡
ይኽ ለሊት ይንጋ እንይ ያ ቀን መጥቶ፡-
ሁሉም እንደ ስራው እንዲበላ አንጉቶ፡፡
ዝምታ ወርቅ ነው ያለው ሰው ይሙት፡

አገር ይዞ ጠፍቷል ሁሉን ፀጥ አርጎት፡፡
እርጥብ ደረቅ በልተህ የጠገብክ መስሉሀል፡-
ወገኔ ልንገርህ እውነት ተርበሀል።
ምነዋ ሰው ሆዬ ሰው መሆነን ተውከው፡-
ቁንጫ ትኋኑ ሲበላህ ዝም አልከው።
መኖር ስቃይ ሲሆን መከራ ጎራ አክሎ፡
ሞትም ጀግንነት ነው እምቢ አልኖርም ብሎ፡፡»

አስቻለው የራሱ ስንኞች ለራሱ ደስ አሉት። እንዲያውም አንዳንዶቹ
ቃለችና ሀረጎች ልክ እንደ እሱ ሲያለቅሱ ተስሙት። ሌሎቹ ደግሞ ሲጣሩ!ለዚያውም ከፍ ባለ ድምፅ፡፡ ስንኞቹ የራሱ ናቸውና እሱን እሱን ሽተቱት።
«ለካ!» አለ አስቻለው አሁንም ለራሱ በመናገር፡ ሰው ብዕርና መወረቀት የሚያነሳው ወዶ አደለም የሀሳብ እጭቃ አእምሮውን ሲወጥረው ቀነስ አድርጎ ለመተንፈስ ነው አልያም ሀሳብ በገዛ ሀይሉ ሞልታ ሲፈስስበት በዚያ አጋጣሚ የደራሲ ሀይወት በትንሹም ቢሆን ገብቶት ሊሆን ይችላል የደራሲ
ሕክፍ! እርርም እድርጎ ለማስቀመጥ ሲፈልግ ነው፡፡» አለና ምናልባት በዘሁ አጋጣሚ
የደራሲ ሕይወት በቶኝሹም ቢሆንና ገብቶት ሊሆን ይችላል
«የደራሲ ኑሮ ሕይወት እንዴት ነው ሁል ጋዜ መጨነቅ? ሁልግዜ መጠበብ? ይገርማል እያለ ራሱን ደጋግሞ ወዘወዘ።

ሰዓቱ ወደ ስድስት ተጠጋ የአስቻለው አንጀት እህል እህል ማለት ጀመረ። ምሳ ትዝ አለው። እርግጥ መንፈሱንም ማሳረፍ ፈለገ፡፡ ያቺን ግጥም የፃፈበትን ወረቀት በስነ ስርአት አስቀመጠና
ከወንበር ላየሰ ብድግ ብሎ ጃኬቱን ደረበ ቤቱን ቆልፎ ቀጥታ ወደ ዋርካው ምግብ ቤት አመራ።
ወትሮም ቢሆን አስቻለውና ጓዴኞቹ ለምሳ አይጠባበቁም እንደያ ስራቸው ባህሪ ነስራ መግቢያና መውጫ ሰዓታቸው ስለሚለያይ ሁሉም በየደረሱበት ሰዓትና ደስ ባላቸው ምግብ ቤት ነው የሚበሉት፡፡ እስቻለውም ማንንም ሳይጠብቅ ቆርሱን
ምሳውን በአንዴ በላ፡፡ ቀዝቀዝ ያለ ውሃ ጠጥቶ ቡና ሲጨምርበት መንፈሱም ተረጋጋ።
በዚያው ምግብ ቤት ውስጥ ትንሽ
ለመቆየት ፈልጎ ነበር፤ ነገር ግን
በተለይ ዛሬ ማርፈጃውን እንደ ዱቄት ሲፈጨው ከነበረ ሀሳብ ጋር የማይጣጣሙ ሁኔታዎች ተከሰቱበት። በርካታ ሀሳብ የለሽ የሆኑ ወጣቶችና ጎልማሶች በሆነ
ባልሆነ ወሬ ሲያዋክቡት ለስሜቱ አልመች አለው፡፡ አንዳንዶቹ ያቧርቃሉ፡ በሳቅ ይንከተከታሉ፤ በቀን በጠራራ ከሴት ጋር ይገፋሉ፤ ይዳራሉ። በዚያ ላይ ንፋሱ ፡
አባራው ! የሻይ ማሽን ሿሿታ፤ የራዲዮ፣ የቴፕ'... ወዘተ ጫጫታ ብቻ ሁሉ ነገር የአዕምሮ እረፍት አሳጣው፡፡ እዚህ ሁሉ ግርግር የሚገላገለውን ቦታ መረጠ!
የገዛ ቤቱን፡፡ ብድግ አለና በቀጥታ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ የተለመደ የዲላ ቀትር ፀሐይ አናት አናቱን እያለው ደረሰና ቤቱን ከፍቶ ገባ፡፡ ከዚያም ወደ አልጋው:: የተንዘረፈፈ ከንሶላና ብርድ ልብሱን ሰብሰብ አድርጎ ጫማውን ብቻ አመለቀና
በጀርባው ጋለል አለ፡፡ ደካከመው፡፡ እንደ እንቅልፍም ይሞካክረው ጀመር፡፡.....

💫ይቀጥላል💫
👍17
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሦስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


...“ኸንጉሥ እጅ እንዴት እናመልጣለን?...”
ኢሳያስ፣ የሰማት ይመስል ወደ ጉዳዩ መግባት ፈለገ። አንዴ
ዮልያናንና እንኰዬን ሌላ ጊዜ ደግሞ ግራዝማችን ዐይኑን ተክሎ
ተመለከተ። ፊቱን ወደ ዮልያና አዞረና ፈገግታ ለገሣቸው።

ዮልያና የሆነ ነገር ሊነግረኝ ነው ብለው ጠረጠሩ፤ ለመስማት ጓጉ።

“እመቤቴ... ዋናው የመጣንበት ጉዳይ...” ብሎ እንደገና ሁሉንም
ተመለከተ። ቀጠለና፣ “እመቤቴ... ዋናው የመጣንበት ጉዳይ... ጃንሆይ...በተለይም እኔን ልከውኝ ነው። እርሶ እንዳሳደጓት ስላወቁ የልዥ ልዥዎን እጅ ስለፈለጉ እኼን ለማብሰር ነው የመጣን። ቅድም ግቢው መግቢያ ላይ ልዣችሁ መሬት ላይ ጦር ሲተከል አይታ፣ ደንግጣ ነው መሰል፣ ኸተቀመጠችበት ተነሣች። ለበጎ እንደመጣን ንጉሥ እጅ ሲጠይቅ እንደሱ መሆኑን ሳታውቅ ቀርታ” አለ።

ወለተጊዮርጊስ አመዷ ቡን አለ፤ ሰማይ ምድሩ ዞረባት። ንጉሡ?
እንዴ ንጉሡ የኔን እጅ ሊጠይቁ? እንዴት ሁኖ አለች። እንግዶቹ የሷን
እጅ ሊጠይቁ እንደመጡ ደመነፍሷ ቢነግራትም ለንጉሥ ሚስትነት መሆኑ ግን ከግምት በላይ ሆነባት፤ ተደናገጠች፤ ተርበተበተች፤ ፊቷ የበሰለ ቲማቲም መሰለ፤ ጉንጮቿ ተቃጠሉ። ዐይኖቿን ጨፍና ራሷን
ነቀነቀች፤ ሊሆን አይችልም በሚል መልክ። አንዴ በኔና በጥላዬ
ማይመጣ የለም ማለት ነው? እንባ እንባ አላት። የምታስበው ጠፋት፣ ጭንቅላቷ ባዶ ሆኖ ተሰማት። ጣሪያው ላይ አፈጠጠች- ለዚህ አስደናቂ
ለሆነባት ጉዳይ መልስ ይሰጣት ይመስል። አያቷም በሰሙት ነገር ቢደናገጡም ስሜታቸውን ሰብሰብ አድርገው፣
“እኔ ላሳድጋት እንጂ የወለዱ እኮ እነሱ ናቸው” አሉ፣ መብረቅ
የመታቸው ያህል ድርቅ ብለው የተቀመጡትን ልጃቸውንና ግራዝማችን በአገጫቸው እያመለከቱ። “እነሱ ናቸው መጠየቅ ያለባቸው” አሉ፣
ራሳቸውን እየነቀነቁ።

ኢሳያስ፣ “ርግጥ ነው። የጃንሆይም ፍላጎት ያ ነው። ኻለነሱማ እንዴት ይሆናል? ለመቤቴም ለግራማችም ነው ጥያቄው የቀረበ። እመቤቴ..
ግራማች... ዛዲያ ምን ታስባላችሁ?” አለ። ንጉሥ ልጃችሁን ስጡኝ ሲል ለማንም ቢሆን ብስራት ነው የሚል ቃና ድምጹ ላይ አክሎበት።እመቤት እንኰዬንና ግራዝማች መንበርን በተራ ተመለከተ። የዮልያናን
ቅሬታ ያዘለ አነጋገር ማርገብ ችሎም እንደሆን ፊቱን መለስ አድርጎ አያቸው።

ዮልያና ግን ሐሳባቸው ሌላጋ ከንፏል። ከዓመታት በፊት አንድ
ሌሊት አይተውት የነበረውና ምንጊዜም ቢሆን ሲያስደንቃቸውና ላገኙት ሁሉ ሲያወሩት የነበረው ሕልማቸው ትዝ ብሏቸዋል።

ያን ሌሊት፣ እንደወትሯቸው ጸሎት አድርሰው ከተኙ በኋላ፣ ፀሐይ
ቤታቸው ሰተት ብላ ገብታ ተጎናጽፈዋት ተኝተው አዩ። ከእንቅልፋቸው ብንን ብለው ነቅተው ተቀመጡ። ባዩት ሕልም ተደነቁ። ጠሐይ ቤቴ የገባችው አለነገር ማዶል። ጠሐይ መሪ ነው፤ ብርሃን ነው ይላሉ፡፡
አገር ብርሃን ትሆናለች ማለት ነው። ግና እንዴት? አሉ፤ ለራሳቸው።

የሕልማቸውን ትርጉም ለማወቅ ተመራመሩ። መቸም አለምኸኛት
እንዲህ ያለ እልም አላሳየኝም፡፡ አንድ ነገር ቢኖር ነው። እስቲ ነገ
ጠዋት እኛ መነኩሴ ዘንድ ኸጀ ሚሉትን ሰማለሁ። አይ የነእንኰዬ
አባት በኖሩ። እሳቸው እኮ ኸኔ የተሻለ እልም መፍታት ይችላሉ እያሉ ሲገላበጡ አደሩ። እንቅልፍ ባይጠግቡም፣ ማለዳ ከመኝታቸው ተነሡ።ውዳሴ ማርያማቸውንና ዳዊታቸውን ደግመው መነኩሴውጋ ለመሄድ
ሲዘገጃጁ የደስ ደስ ስሜት አቅበጠበጣቸው። ቁርስ ላድርግ ሳይሉ አሽከር አስከትለው ወጡ።
መነኩሴው ወፍታ ጊዮርጊስ ግቢ ውስጥ ጥድ ስር ተቀምጠው
መቁጠሪያ ይዘው ይጸልያሉ። ዮልያና ወደቤተክርስቲያኑ ሄደው
ከተሳለሙ በኋላ፣ መነኩሴው ጸሎታቸውን እስኪጨርሱ ድረስ ፈንጠር ብለው ድንጋይ ላይ ተቀመጡ። መነኩሴው ጸሎታቸውን ሲጨርሱ፣
ለዮልያና እጅ ነሡ። ዮልያና ተነሥተው እጅ ነሥተው ሲቆሙ
እንዲቀመጡ መነኩሴው በምልክት ነገሯቸው።

ዮልያና ድጋሚ እጅ ነሥተው ጠጋ ብለው ተቀመጡ። ስለጤንነታቸው
ከጠያየቁ በኋላ፣ “ያው መቸም ኸርሶ ዘንድ ምመጣው አንድ ነገር
ሲገጥመኝ ነው። ዛሬ ስንኳ አንድ ዘመዴ እልም አይታ ሚፈታልኝ
ብትለኝ ነው የመጣሁት። ድቅድቅ ያለ ጨለማ ይመስለኛል አለች...
ጠሐይ ኸተኛሁበት ድረስ ገብታ ቤቴንና መላ ሰውነቴን አበራችው።
ኸያ በኋላ ጠሐይቱን ተጎናጽፌያት የተኛሁ ይመስለኛል ብላ ነገረችኝ።”

መነኩሴው በጥሞና ካዳመጡ በኋላ፣ “ብርሃን ሥልጣን ነው። እኼን እልም ያየች ሴት ንጉሥ ትወልዳለች” አሏቸው።
ዮልያና ደነገጡ። “እልሙን ያየችው ሴት ኸንግዲህ መውለድ
አትችልም። ዕድሜዋ አልፏል፤ የወር አበባም የላት” አሉ።

“ኸዘር ይፈጠማል። ኸልዥ ልዥም ይሆናል።”

ዮልያና በሐሳብ ከሄዱበት ተመለሱና እልሜ ገሀድ መሆኑ ነው። ድንቅ! የእዝጊሃር ፈቃድ ይፈጠም ብለው ልጃቸውን የጎንዮሽ ተመለከቱ። ወይዘሮ እንኰዬ ግን የቅድስት ወለተጴጥሮስን ንግርት
አስታውሰው እናታቸው እያይዋቸው መሆኑን ልብ አላሉም።

በአፄ ስሱንዮስ ዘመን የቆራጣ ገዳም እመምኔት የነበረችው ቅድስት ወለተጴጥሮስ መንገድ መሽቶባት ለአንድ ምሽት አያቶቻቸው ቤት ዐርፋለች። የቤቱ እመቤት ሌሊት ላይ ድንገት ምጥ ጸንቶባት ወደ በረት ተወስዳ፣ ሴቶች መቀነቻቸውን ወንዶች መታጠቂያቸውን ፈተው ሲጸልዩ፣ ወለተጴጥሮስም መቀነቷን ፈትታ ፊቷን ወደ ምስራቅዐመልሳ አጥብቃ ጸለየች። ሴቲቱም ወንድ ልጅ በደሕና ተገላገለች።
ወለተጴጥሮስ በማግስቱ መንገድ ከመጀመሯ በፊት፣ “ኸዝኸ እጣን ዘር መልካም ዝናው ሚነሣ ንጉሥ ይወለዳል። ንግሥቲቱም በሥራዋ ስሟ ሲወሳ ይኖራል። ኸዳር እዳርም አገሯን ታስከብራለች” ብላ ቋራን፣ “ምን ግዝየም አብቅይ፣ መልካም ፍሬ ይብቀልብሽ” ብላ ተሰናብታ ወጣች።

እረገኝ ንግሥቲቱ ወለቴ መሆኗ ነው። ንጉሡ ደሞ ኸሷ ሚወለደው ነው አሉ እንኰዬ።

ኢሳያስ “ምን ታስባላችሁ?” ለሚለው ጥያቄው መልስ ባለማግኘቱ ልጠይቅ አልጠይቅ እያለ ከራሱ ጋር እየተሟገተ ቆይቶ፣ “ዛዲያ ምን አሰባችሁ ግራማች?” አላቸው።
ግራዝማች መልስ መስጠት ፈልገው ምላሳቸው ተቆለፈ። “እ... እረ.. እንዳው...መቸም...” ድምፃቸው ተቆራረጠ፤ የጀመሩትን ለመጨረስ ቃል አጠራቸው።

ኢሳያስ ካቆመበት ቀጥሎ፣ “መቸም...” ብሎ ግራዝማችን አያቸው።
“መቸም ለልዥዎ ለንጉሥ ሚስትነት ኸመታጨት የበለጠ ዕድል ኸየት ይመጣል? የጐንደር ወይዛዝርት ሆኑ የጦቢያ የነገሥታት ዘሮች ሁሉ ያላገኙትን ዕድል እኮ ነው ያገኘች” አላቸው።
ዕድል? እንዴት ሁኖ ነው ዕድል ሚሆን? አለች ወለተጊዮርጊስ፣
እያየችው። ዞር ብላ አባቷን ተመለከተቻቸው። እሳቸው የጭንቀት ስሜት አጥብቆ የተሰማቸው ይመስላሉ። ግንባራቸው ላይ ቸፍ ያለው
ላብ ቁልቁል ሊወርድ ይጋበዛል። ሆዷ ውስጥ አንዳች ነገር ተላወሰ።
ግንባሯን ያራሰውን ላብ በእጅጌዋ ጫፍ አባበሰች።

ከበድ ያለ ፀጥታ ሰፈነ።

“ግራማች ዛዲያ ምን ያስባሉ?” አሉ፣ ከሁሉም ተለቅ ያሉት እንግዳ።

እንዳው ለነገሩ ጠየቁ እንጂ ግራዝማች ምርጫ እንደሌላቸው ያውቃሉ።ግራዝማች ግን በልባቸው ወይ አንተ የወፍታው አያልቅብህ፡፡ ያ ሁሉ ባላባት ዐይናማ ልዥህን እያለ ለራሱ ሆነ ለልዡ አማላጅ ሲልክ ሁነኝ ጋር አንድ ቀን እንታረቃለን፣ ልጄን ለልዥህ ብየ ሳበቃ እንዴት
👍12
ለሌላ እሰጣለሁ እያልሁ የቆየሁት ለካስ ልዤ እጣ ፈንታዋ እኼ ሁኖ
ኑራል? አቤቱ እንዴት ድንቅ ነው ያንተ ሥራ? እያሉ ይደነቃሉ።
አየ ሁነኝ! የዘለፍኸኝን ሁሉ የወፍታው ይቅር ይበልህ... በተልካሻ ነገር ተቀይመህ እኼው አሁን ጉድ ሆንህ፡ ያነን የተባረከ... ገራም.. ልዥህን በደልህ፤ ይብላኝ ላንተ፤ የኔንስ የወፍታው ግዝየውን ጠብቆ ለዝኽ አብቅቶልኛል እያሉ ያስባሉ።

ልጃቸው ቤተመንግሥት ስትገባ፣ እሳቸው ስማቸው ሲገን፣ ሲሾሙ
ሲሸለሙ፣ ልጃቸው ወልደልዑል የቤተመንግሥት ባለሟል ሲሆን ወለል ብሎ ታያቸው። ኢሳያስን መልከት አደረጉና፣ እኼ ሰው ልዤን ከግር እስተ ራሷ ሲያይ የነበረው ለካስ እኼን ይዞ መጥቶ ኑሯል? ሲሉ ተገረሙ። እኒህስ ቢሆኑ እግራቸው ርጥብ በጎ ነገር ይዘው መጡ አሉ፣ ሌሎቹን እንግዶች እያዩ። ኸንግዲህ ዘመድ ወዳጅ ደስ ይበለው። ጠላት ሁሉ ይፈር። እኛን ለዝኸ ያበቃን የወፍታው ያውቃል። ልዤ
ዕድል ፈንታዋ ቀድሞውኑ ተመድቦላት ኑሯል...

ከሁሉም ተለቅ ያሉት እንግዳ፣ “ግራማች…. ዛዲያ ምን አሰቡ?” ሲሉ ጥያቄያቸውን ደገሙ፤ መልስ ሳያገኙ በመቅረታቸው።
ግራዝማች ከእንቅልፋቸው እንደባነኑ ሁሉ ዐይናቸውን ጠራረጉ። ጥያቄው ትዝ አላቸው። ከግንባራቸው ወደ ጉንጫቸው ያሽቆለቆለውን ላብ በጋቢያቸው ጠርዝ ተም ተም እያደረጉ፣ “እንዴ ምን አስባለሁ፣ ጃንሆይ ሲያከብሩን። ንጉሥ ጠይቆ? ለኛስ ቢሆን ትልቅ ክብር ማዶል?”
ብለው በድንጋጤ የደረቀ አፋቸውን ለማላወስ ሞከሩ።

ወለተጊዮርጊስ አባቷ፣ “ንጉሥ ጠይቆ?” ያሉት ልቧን እንደ ጦር ወጋው። በርግጥም ንጉሥ ጠይቆ እንቢ ሊባል እንደማይቻል ታውቃለች አባባ እርሶና ባላምባራስ ሁነኝ ስትቀያየሙ እኔና ጥላዬን እንደጎዳችሁ አላወቃችሁም፡፡ እናንተ ባትቀያየሙ ኑሮኮ እስታሁን
ኸጥላዬ ጋር ተጋብተን እኼ ሁሉ አይመጣምም ነበር፡፡ የሰፈሩስ
ሽማግሎች ደግመው ደጋግመው እናስታርቅ ያላሉት ለምነው? እና
እስተዛሬ ሽማግሎቹ መጥተው ያስታርቃሉ እያልሁ በሩን በሩን ሳይ
ቆይቸ እኼው ዛሬ እጅ ጠያቂ ሽማግሎች መጡ። አይ አለመታደል!ዳሩ አባባ እርሶ ምን ያርጉ? ያመረሩት የጥላዬ አባት ናቸው። እርሶ ቂም አያቁም። ለመሆኑ ባላምባራስ ሁነኝ እኔና ጥላዬን እንደበደሉን፣ እንዳንጋባ እንዳረጉን አያቁም? ቤተሰቡንስ ቢሆን እንደዝኸ አለያይተው
መቀመጣቸው ትንሽም ስንኳ አይቆረቁራቸው በቁስቋሟ! ምን ያሉት ክፉ ምቀኛ ናቸው? አለች።

የሁለት ሰዎች የሕይወት አቅጣጫ በሌሎች መወሰኑ አብከነከናት።
እሷና ጥላዬ የባላምባራስ ሁነኝ እልህ እስረኛ መሆናቸው ደሟን
አፈላው።

አየ ጥላዬ... ጥላዬ የልዥነቴ... ሲሰማ ምን ይል ይሆን እስታሁን
ጠፍተን አንዱጋ ብንኸድ ኑሮ ምን ነበረበት? ኸንግዲህማ ጠፍተን
መኸድ አንችልም ሽንጉሥ እጅ እንዴት እናመልጣለን? ብላ እንባዋን ጠራረገች።

በዚያች ቅጽበት ሕይወቷ ሲቀየር፣ ዐዲስ መልክ ሲይዝ ታያት።
ጭንቀት ልቧን ተጫነው፤ መንፈሷ መላወሻ አጣ፤ እንባዋ ዐይኗን
ከለለው። ዐይኗን ለመጥረግ ስትሞክር መጋረጃውን ሳታስበው ለቀቀችው።
ያለችበት ቦታ ጠበባት፤ የበለጠ ጨለማ ሆነባት፤ የምትተነፍሰው
አየር ያጣች መሰላት፤ የተቀመጠችበት ዱካ ቆረቆራት። ጥያቄዎች በሐሳቧ እየተሸቀዳደሙ ተመላለሱ። መጋረጃውን መልሳ በአንድ እጇ
ይዛ መልስ ይሰጧት ይመስል ከእናቷ ወደ አያቷ፣ ከዛም ወደ አባቷ ዐይኖቿን አዘዋወረች። የአባቷ ሁኔታ አሳዘናት። እሚታዬ! አባባ እኮ ተጨንቀዋል፣ ተናገሪ እንጂ አለች፣ ወደ አያቷ እያየች።
አያቷ ጉሮሯቸውን ኮርኮር አደረጉ። ጀርባቸው ላይ የወደቀ ሹሩባቸው
ላይ ሸብ ያደረጉትን ከወተት የነጣ ሻሽ ነካኩና፣ “ልዣችንም እኮ ያጤ
ልብነድንግል ወገን ነች። ያጤ ልብነድንግልና የእቴጌ ሰብለወንጌል ልዥ፣ አቤቶ ፊቅጦር... ኸሳቸው ነነ። አጤ ሚናስና አጤ ገላውዲዎስ
የሳቸው ታናሽ ወንድሞች ማልነበሩ?” አሉ።

ወይዘሮ እንኰዬ የእናታቸውን ንግግር ሲሰሙ ከሐሳባቸው መለስ አሉና በኩራት የነጠላቸውን ባለ ደማቅ ጥልፍ ጥለት አስተካክለው፣
“ሰማህ?” በሚል ሁኔታ ኢሳያስን ተመለከቱት።.....


ይቀጥላል
👍6
አትሮኖስ pinned «#ምንትዋብ ፡ ፡ #ክፍል_ሦስት ፡ ፡ #ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ ...“ኸንጉሥ እጅ እንዴት እናመልጣለን?...” ኢሳያስ፣ የሰማት ይመስል ወደ ጉዳዩ መግባት ፈለገ። አንዴ ዮልያናንና እንኰዬን ሌላ ጊዜ ደግሞ ግራዝማችን ዐይኑን ተክሎ ተመለከተ። ፊቱን ወደ ዮልያና አዞረና ፈገግታ ለገሣቸው። ዮልያና የሆነ ነገር ሊነግረኝ ነው ብለው ጠረጠሩ፤ ለመስማት ጓጉ። “እመቤቴ... ዋናው የመጣንበት ጉዳይ...”…»
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...ባርናባስ የሔዋንን ሁለት እጆች ግጥም እድርጎ ይዟል። ሸዋዬ የአገኘችውን ነገር ሁሉ እያነሳች ትደበድባታለች። ሔዋን ኡኡ ድረሱልኝ እያለች ትጮሀለች።
እጆቿን ከባርናባስ ለማስለቀቅ ትታገላለች። እሱ ደግሞ እንዳታመልጠው ጥርሱን
ንክስ እያረገ ሀይሉን ያጠነክራል። ሸዋዬ አሁንም ትደበድባታለች፡፡ ሔዋንም ትጮሀለች፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን በርካታ ሰው ዙሪያውን ከብቦ ይመለከታል። ግን
“ማንም ሊገላግል አያስብም፡፡ አስቻለው ሊገላግል እየፈለግን ደግሞ መሮጥ ያቅተዋል። ይለፋል ግን አይችልም፡፡ ከያዘው ነገር ራሱን እንድምንም አላቅቆ ወደ
ድብድቡ ቦታ ሊሮጥ ሲል ድንገት ከእንቅልፉ ብንን አለ፡፡ «በስመ አብ ወወልድ መንፈስ ቅዱስ..." ብሎ ከተንጋለለበት ቀና በማለት ፊቱን በሁለት እጆቹ ሽፍን አድርጎ ወደ ፊት ወደ እግሮቹ ድፍት አለ ዝግንን አለው ደርጊቱን ያየው
በቅዠት እንዳልሆነ ሁሉ ሔዋን አሁንም በዚያው ሁኔታ ውስጥ
ሆና ትታየው ጀመር። አሳዘነችው። ከዚያ በኋላ መተኛት አልፈለገም
ከአልጋው ላይ ፈጠን ብሎ ወረደና ልብሱን ለባበሰ።

ምን ሊያግርን እንደሆነ ሳይታወቀው በቀጥታ ወደ ሸዋዬ ቤት መሄድ ፈለገ። ቤቱን ቆለፈና ከግቢ ወጥቶ ቁልቅል ወደሸዋዬ ቤት አቅጣጫ ወረደ ልክ በሸዋዬ ቤት አቅጣጫ ስምንተኛ መንገድ ላይ ሲደርስ መንገድ ላይ ቀጥ ብሎ ቆመና በቀኝ አቅጣጫ ያለውን የወይዘሮ ዘነቡን ግቢ በርቀት ይመለከተው ጀመር በሀሳቡ ሸዋዬ ቤት ገባ ሸዋዬንና በርናባስ ፍራሽ ላይ ቁጭ ብለው
ጫት ሲቅሙ ሔዋን ደሞ በከሰል
ላይ ጀበና ጥዳ የሁለቱ ብና አፋይ ሆና ሁሉም በአንድ ላይ እንደ ስዕል ታዩት።ልቡ ወደዚያው ቤት ሂድ ሂድ አለው። ነገር ግን ድንገት ዘው ቢል ሊፈጠር የሚችለው ሁኔታ ታየው፡፡ ከሁሉም በላይ ሔዋን ትሳቀቅበታለች !
በዚያ ምትክ ከንፈሩን ንክስ አድርጎ ራሱን በቁጭት ወዘወዘ።

በዚሁ ሁኔታ ጥቂት ቆየና ሳይወድ በግድ ሃሳቡን ለወጠ፡፡ በቃ ወደ ሸዋዩ ቤት መግባት አልፈለገም፡፡ ግን ደግሞ ወዴት እንደሚሄድ ጨነቀው ቤቱም ሰለቸው ወደ አንድ ቡና ቤት አይሄድ ነገር እዚያ ሄዶ የሚገጥመው ነገር ለመንፈሱ
አይመቸውም። ግራ ሲገባው ቁልቁል ወደ ከተማዋ ዳርቻ ይራመድ ጀመር ቁርጥ ያለ አድራሻ የለውም። ብቻ መሄድ ብቻ መራመድ፡፡ ብሎ ብሎ ከከተማው ወጣና ወደ እሮሬሳ ገበሬ ማህበር አዋሳኝ ላይ ደረሰ።እያደር ደግሞ
የገጠሩ ሽታ አማለለው፡፡ አሁንም ወደፊት ሊራመድ መሰነና ርምጃውን ቀጠለ። በዚያ መንገድ ላይ በርካታ የገጠር ነዋሪዎች ወደ ከተማ ያመራሉ።ከከተማ ወደ ገጠር ይሄዳሉ፡፡ አስቻለውም ርምጃውን ዝም ብሎ ወደ ፊት ቀጠለ፡፡በልቡ ግን አንድ ነገር ያስላስሳል ዐወደፊት ሐምሌ ላይ የሚጠብቀውን ዝውውርና
ከሔዋን ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት። 'ለመሆኑ' ይላል በሀሳቡ። ብዛወር የሐዩ ጉዳይ እንዴት ሊሆን ነው? ይዢያት ልሄድ ወይስ ትቻት? ይልና እንደገና
የታፈሡና የበልሁ ወደ ክብረ መንግስት የመሄድ ዕቅድ ይመጣበታል። ሄደውስ
ይሳካላቸው ይሆን? ወይስ የሔዩ እናትና አባት ሽዋዬ በፃፈችላቸው ደብዳቤ ምክንያት ሁኔታው አስግቷቸው ያንገራግሩ ይሆን እሺ ቢሉም ሰርግ ድግስ ምናምን ሊሉ ይችላሉ። ያ እስከሚሆን ጊዜ ይፈጃል፡፡ ዞሮ ዞሮ ላልተወሰነ ጊዜ
ከሒዩ ጋር መራራቀ አይቀርም፡፡» በማለት ራሱን እንደማረጋጋት አይነት እንግዲህ የሆነው ይሁን ብቻ ሰላምና ጤና ትሁንልኝ፡፡» እያለ አምላኩን ይማፀናል፡፡

ሳያውቀው ብዙ ተጉዟል በለየለት ገጠር ውስጥ ገብቶ ከዲላ ከተማ በግምት ሁለት ኪሎ ሜትር ያህል ርቋል። ከሀሳቡ ብንን በማለት ባለበት ቦታ ላይ ቆሞ ዓይኑን ወደ ቀኝ አቅጣጫ ጣል ሲያደርግ ዙሪያዋን በረጃጅም ዛፎች
የቸከበበችና፣ ሰፋ ያለች ደስ የምትል ገላጣ ሜዳ ታየችው፡፡ ከግጦሽ ከፍ ያለ የእድገት ደረጃ ላይ በደረሰ ለምለም ሳር ተሸፍናለች። በውስጧ አልፎ አልፎ
የደረቁ ጉቶዎች ጉብ ጉብ ብለው ይታያሉ፡ ወደዚያው ታጠፈና ሜዳዋ መሀል ገብቶ ከአንድ ጉቶ ላይ ቁጭ አለ፡፡ ዙሪያውን ሲመለከት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ነው፡፡ ዛፎች ደግሞ ረጃጅም፡ ወደ መሬት ሲያይ ያ ለምለም ሳር፡፡ በአፍንጫው የሚገባው አየር በራሱ የተለየ መዓዛ ያለው፡፡ መንፈስ የሚያድስ፡፡ እጆቹን በደረቱ ላይ አቆላልፎ ወደ ዛፎቹ ሲያይ ከአንዱ ወደ ሌላው እየተዘዋወሩ የሚንጫጬ ወፎች
ቀልቡን ሳቡት ከወፎቹ የጫጫታ ድግግሞሽ የተነሳ የወፍ ድምፅ ፂው ስትል ሲኮንድ አታልፍም:: የድምጻቸው ልዩነት ውበትና ህበሩ በጭንቅ በጥበብ ከተቀመረ
ዘመናዊ ሙዚቃ የበለጠ ስሜት ይማርካል፡፡

«እናንት ወፎች» አለ አስቻለው ሁኔታቸው ሁለ ግርም ብሎት፡፡ ዛፋ ሁሉ የሁላችሁ ለኔ ብቻ ባይ ስግብግብ በመሀላችሁ የለም
አዛዥ የላችሁ ገልማጭ ጠላት የላችሁ ምቀኛ ኑሮአችሁ በራሳችሁ፣ ውሸት አታውቁ ቅጥፈት ክፉ አቶለሙ ክፉ አትናገሩ አትቀየሙ አታስቀይሙ ጨኸታችሁ አይገደብ ጫጫታችሁ አይመዘገብ ቂም አታውቁ በቀል፤ በእናንተ ዘንድ ዛቻ የለ
ማስፈራራት፤ ፍርሀት የለ ጭንቀት፣ በዚች ምድር ሰላም ልትኖሩ የተፈጠራችሁ ሰላማዊ ፍጡሮች! በማለት ብቻውን ሲነጋገር ከቆየ በኋሳ ሀሳቡን ወደ ሰው ልጅ ባህሪና አኗኗር መለስ ሲያደርገው ጭራሽ አስጠላው።

«ያልታደለ ፍጡር»አለ በስጨት ባለ አነጋገር፡፡ ታየው የሰው ልጅ
ክፋቱና ተንኮሉ፣ ቂምና በቀሉ፣ ሸርና ምቀኝነቱ፤ ጠበና ጭቅጭቁ፣ ከሁሉም በላይ
እብሪቱና ጭካኔው፡ በቃሉም ይገልፀው ጀመር «የአሳር ሽክም የተጫነ መከረኛ ፍጡር፥ ሰው! የቱንም ያህል ቢማር ቢመራመር ከራሱ ጋር መታረቅ ያቃተው
ደካማ ፍጡር፡ ሰው ፈጣሪው ራሱ እሱን በመፍጠሩ የተፀፀተበት ብቸኛ እንስሳ ሰው!» ካለ በኋላ ራሱን ወዝወዝ አድርጎ ወደ መሬት ጎንበስ አለና ያን የለመለመ
ሳር ልብ ብሎ ይመለከተው ጀመር፡፡ ከሩቅ ሲያዩት ልምላሜ ያምራል:: ስሩ ሲታይ ግን ብዙ ጥቃንጥት አለበት፡፡ የደረቁ ቅጠሎችና ጭራሮዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ በርካታ ነገሮች ስር ስሩን ትብትብ እድርገው ይዘውታል። ይህ ሁኔታ ሔዋንን አስታወየው፡፡

«አንተ ለምለም ሳርና የኔዋ ሔዋን እንድ ናቸሁ፡ ከሩቅ ሲያዩአቸሁ ውብ ናችሁ:: ፍጹም የደላችሁ ትመስላላችሁ፡፡ ሥር ሥራችሁንና ውስጥ ውስጣችሁን ግን ብዙ ችግር አለባችሁ፡፡ ሳትጠሩት የመጣባችሁ፣ ሳትፈልጉት የተዳበላችሁ፡፡ አቁሳይ ጥገኛ አለባችሁ፡፡ አንተን የጭራሮና የቅጠል ርጋፊዎች ስርህን ተብትበው እንደ ያዘህ ሁሉ የኔዋ ሔዋንም የአፈቀረ ልቧን የሚወ,ጋ የስሜት እሾህ ኣለባት፡፡
ለመውደድና ለመወደድ የተፈጠረች ቆንጆ ነበረች:: ግን እሾሁ ጋሬጣው በዛባትና
መንፈሷ ቆሰለ፡፡ በአፈቀረች ተሰቃየች። ማልቀስና መተከዝ ዕጣ ፋንታዋ ሆነ።
እያለ ሲያስብ በዚያው ያ ቅዠት ውስጥ ያየው ሁኔታ ትዝ አለው፡፡ ድንግጥ ብሎ እንደ መደንበር አረገና በተቀመጠበት ጉቶ ላይ ብድግ አለ ሳያስበው በዚያ
በለመለመ ሳር ላያ ይዘዋወር ጀመር፡፡
እጆቹን በጀርባው ላይ አጣምሮ ጎንበስ በማለት በግምት ከአስር: እስከ አስራ አምስት ርምጃዎችን ከተራመደ በኋላ በግራ በኩል ወደ መንገዱ ዞር ብሎ ሲያይ አንድ ለየት ያለ ነገር አየ፡፡ በመንገዱ ላይ ሰዎች አሁንም ወደ ላይ ወደ ታችም አቅጣጫ ይሄዳሉ፡፡ ነገር ግን መንገደኛ፣ ለየት ባለ እኳኋን አንዲት በጀርባዋ ጓዝ የያዘች
👍101
ሴት ቆማ እሱን እሱን ስትመለከት አያት፡፡ ይኼኔ እብድ መስያት ይህናል ዝም ብሎ እርምጃውን ቀጠለ በምንጠን ቀጠለ፣ ደገሞ ስ.ያያት አሁንም ታየዋለች::ለራሱ
ገርሞት ቀና ጎንበስ እያለ ሲያያት ሴትዮዋ ንቅንቅ አትልም ድንገት ደግሞ ድምፅ ሰማ
« ጋሽ አስቻለው» የሚል የጥሪ ድምፅ።
«እንዴ» አለና አስቻለው እንደመገረም ብሎ ጆሮውን ጣል አድርጎ ሲያዳምጥ አሁንም “ጋሽ አስቻስው» ስትል ተጣራች ሴትየዋ «ምንድነው ነገሩ!» በማለት ከራሱ ጋር እየተነጋገረ ቆም ብሎ ወደ ሴትየዋ ሲመለከት አሁንም " አስቻለው አይደለህም እንዴ ስትለው ሰማ።
«በዚህ መንገድ የምታልፍ የገጠር ሴት እንዴት ልታውቀኝ ቻለች?»
በማለት እየተገረመ «አዎ ነኝ። እንቺ ግን ማነሽ?» ሲል ከርቀት ጠየቃት። ሴትዮዋ “እኔ እገሌ? ከማለት ይልቅ ጓዟን ከጀርባዋ ላይ አውርዳ ቁጭ አለች ከሩቅ ሲያያት የምታለቅስም መስለች:: አሁንም ግራ እየገባው «ማነሽ አንቺ?»
እያለ ተጠጋት፡፡ በትጠጋት ቁጥር እያለቀሰች መሆኗ በደንብ ታየው፡፡
አሉንም ተጨጋት። «ምን ሆነሽ ነው ሴትዮ?» ሲል ሽንጥና ሽንጡን ይዞ አጠገቧ በመቆም ጠየቃት
«አላወቅኸኝም?” አለችው ሴትዮዋ።
«ትርፌ በጋሻው ነኝ፡፡» አለችና እንባዋ በጉንጫ ላይ ድንቡቅ ብሎ ወረደ።
«ኣ?» አለ አስቻለው በድንጋጤ አፉን ከፍቶና ዓይኑን በሴትየዋ ላይ
አፍጥጦ የኔ ትርፌ በጋሻው?» እንደገና።
«አዎ»
ያቺ ለሦስት ዓመታት ያህል ቤቱን ቅልጥፍጥፍ አድርጋ በመያዝ ምቹ
የወንደ ላጤ ህይወት አስለምዳው ነገር ግን ድንገትና በማያውቀው ምክንያት ከአንድ ዓመት በፊት ጥላው የጠፋችው የቤት ሰራተኛው ናት፡፡
«እንዴት ሊሆን ይችላል?» አለም አስቻለው በሁለት እጆቹ ጉንጮቹን ይዞ፡፡ «ሆነ ጋሽ አስቻለሁ» አሁንም እያለቀሰች ለጊዜው ልክ ያን ቀደም ሲል ያየውን የቀን ቅዠት ዓይነት ስሜተ ተሰማውና ለሴኮንዶች ያህል ተጠራጠረ፡፡
ግን ደግሞ ወዲያው ወደ ትርፌ ጠጋ በማለት እቅፍ አድርጎ ሳማትና ከየት እየመጣሽ ነው?» ሲል ጠየቃት።
”ከባላገር?» አለች ትርፌ አጎንብሳ አሁንም እያሰቀሰች፡፡
«ለምን ሄድሽ?
«ቀን ጎሎብኝ»
ትርፊ ቀን የጎደለባት ስለመሆኗ ገጽታዋ ያስታውቃል፡፡ ቀይ የነበረው ፊቷ ማድያት አልብሶት ተዥጎርጉሯል። የለበሰቻቸው ቀሚስና ነጠላ ውሃ ነክቷቸው
የኮተ አይመስለም፡፡ ፀገሯ እብቅ የነስነስብት ይመስላል። ዓይኖቿም ጎድጉደዋል።የጉንጯ አጥንቶች በዓይኗ ሥር ሾለዋል። አንገቷ ላይ የሚታየው የሰውነት እድፍ
ጎደዳ ሰርቷል፡፡ በቃ የድሮዋ ትርፌ አይደለችም ተቀይራለች።አስቻለው
ይሄን ሁሉ ሁኔታዋን ዓይቶ ሆዱ እዘነና ከንፈሩን መጠጥ አድርጎ «አሁን ታዲያ አቅጣጨሽ ወዴት ነው እህትነሽ ወዴት ነው?» ሲል ጠየቃት::
«በቃ እግሬ እንዳደረስኝ::»
እስቻለው የባሰ አዘነ፡፡ በመጎሳቆሏ በተጨማሪ የተስፋ መቁረጥ ንግግሯ አንጀቴን በለው
ጓዟን አሳዘላትና እጇን ይዞ ወደ ከተማ መንገድ ጀመሩ። ብዙ ተጉዘው ወደ ከተማዋ ጫፍ
ሊደርሱ ሲሉ ትርፈ ከአስቻለው ግንባር ላይ ተፈጥሮ
የነበረውን ጠባሳ በዓይኗ ሰለል ስታደርግ ቆይታ ኖሯልና «ግንባርህን ምን በኖህ ነው
ጋሽ አስቻለው? ሰው መታህ?» ስትል ጠየቀችው::
የጉልበተኛ ዘመን አይደል ተደባዳቢ ምን ይጠፋል ብለሽ?» አለና እስቲ ቆይ ቤት ስንደርስ እናወራዋለን፡፡» ብሏት አሁንም ገሰገሰ ወደ ከተማ። አስቻለው
ትርፌን ይዞ ከቤቱ ሲገባ ከቀኑ አስራ አንድ ሠዓት ሆኗል::
ልክ እንደ ቀድሞው አቀማመጣቸው አስቻለው ጠረጴዛና ወንበር ላይ ትርፌ ደግሞ ከእሱ ፊትለፊት ጓዟን እንዳዘለች ዱካ ላይ ቁጭ አሉ፡፡ አስቻለው የትርፈን መልክ በሀዘን ዓይን ሲመለከት ትርፌ ደግሞ ድሮ ትጠቀምባቸው የነበሩ የአስቻለውን የቤት ቁሳቁሶች በዓይኗ ሰለል ታደርጋቸዋለች፡፡ አብዛኞቹ እሷ እንዳስቀመጠቻቸው ናቸው:: በአቧራ ቁሽሽ ብለዋል ሸረሪት ያደራባቸው ይመስላሉ እሷ እሄደች ወዲህ የተነኩ ወይም የተገላበጡ አይመስሉም። በልሁና መርዕድ ጫት ሲቅሙ የሚጠቀሙባቸው ብርጭቆዎች ብቻ ያብለጨልጫሉ::፥
«ሚስት አላገባህም ጋሽ አስቻለው?» ስትል ትርፌ ጠየቀችው፡፡
«ችግር መች ፈታችኝና ሚስት ልደርብባት ብለሽ ነው ትርፌ፡፡» ካለ በኋላ
«ለምን ጓዝሽን አታወርጃውም?» አላት
ጉንጨን ደገፍ አድርጎ እየተመለከታት፡
ትርፌ የነጠላዋን ቋጠሮ ፈትታ ጓዟን አወረደች፡፡ ከአጠገቧ ቁጭ አድርጋው መሬት መሬት ታይ ጀመር። ሀፍረትና መሳቀቅ የተሰማት ትመስላለች::
«ግን እንደው ትርፌ!» አላት እስቻለው ረጋ ባለ አነጋገር፡ «ምን
በደልኩሽና ድንገት እልም ብለሽ ጠፋሽ?» ሲል በትህትና ጠየቃት፡፡
«ምንም ጋሽ አስቻለው?»
«አንድ ነገርማ መኖር አለበት፡፡»
«ቢኖርም እኔ እንጂ ከአንተ አልነበረም::»
«እስቲ እሱንም ቢሆን ንገሪኝ፡፡»
«ተታለልኩ፡፡»
«ማነው ያታለለሽ?»
«ያኔ አንተም የምትመገብበት፣ እኔም እስራበት የነበረ ውቴል ውስጥ ከጎረቤት እየመጡ ከውቴሉ ባለቤት ጋር ቁጭ የሚሉ ወፍራም ሴት አልነበሩም?»
«አዎ»
«ገና እዚያው ውቴል ቤቱ ውስጥ እያለሁ እንደ ቀልድ እያረጉ ይቺን
ሰራትኛሽን ስጪኝና ለወንድሜ ልጅ ልዳራት እያሉ የውቴሉን ባለቤት ይጠይቋቸው ነበር፡፡
«እሺ!» አለና አስቻለው ፈገግ እያለ ያያት ጀመር፡፡ የትርፌ ወሬ ወዴት እንደሚያመራ ከወዲሁ ገባው::
«አንተ ጋ ከገባሁ በኋላም ባገኙኝ ቁጥር ይጨቀጭቁኝ ነበር»
«ምን እያሉ?»
«ወንድሜ አንድ ብቻ ወልዶ ሞቶብኛል። ልጁ የአባቱን ሀብት ብቻውን ወርሶ ሀብታም ሆኗል:: ሚስት የለውም:: እኔ የምፈልጋትን ሴት ሊያገባ ቃል ገብቶልኛል። እኔ ደሞ ለእሱ የምመኘው አንቺን ነው፡፡ አንቺም የሰው አገር ሰው
ስለሆንሽ ሁነኛ ሰው ያስፈልግሻል። ልጅ ወልደሽ ዓይንሽን በዓይንሽ ማየት
ይኖርብሻል፡፡ የሰው ቤት ኑሮስ እስከ መቼ ይዘለቃል?እያለ::»
«በቃ! እሺ አልሻቸው ማለት ነው?»
«መስሎኝ ተታለልኩ፡፡» አለችና ትርፌ አሁንም እንዳቀረቀረች ዓይንና አፍንጫዋን በለበሰቻት ቁሻሽ ያለች ነጠላ ትጠርግ ጀመር፡፡
«ከየት ወሰዱሽ ታዲያ?»
«ከገበያ ላይ፡፡»
አስቻለው በመገረም ዓይነት ራሱን እየወዘወዘ ለአፍታ ያህል ሲመለከታት ቆየና «ታዲያ ሀብታሙ ገበሬ እንዴት አድርጎ ቢይዝኸ ነው እንዲህ ያማረብሽ» ሲል በምፀት አነጋገር ጠየቃት::
«ምንም አልተጠቀምኩም ጋሽ አስቻለው»
«ሀብት የለውም?»
«ሙልጭ ያለ ድሀ ነው»
አስቻለው ድንገት ቂቂቂቂ» ብሎ ሳቀና እንዴት?» ስል ጠየቃት፡፡
«ቀድሞ ነገር የእሱ የሆነ ምንም ነገር አልነበረውም። ላሞች ቢኖሩም የእናቱ ናቸው፡፡ እሳቸው እነዚህን ላሞች በደንብ ተንከባከቢ አንዷ ስትወልድ ጥጃዋን ለአንቺና ለባልሽ እሰጣችኋለሁ ይሉኝ ጀመር ላም ወልዳ ጥጃው አድጎ
«ታዲያ ወዲያው ጥለሽው አትመልሽም ነበር?»
«ምስጢሩ እስከሚገባኝ ድረስ ለካ አርግዤ ኖሯል፡፡ መሄጃው ጨነቀኝ፡፡»
አስቻለው ድንግጥ አለና «በቃ ወልደሻላ?»
«ግን ገና በአንድ ወሩ ሞተብኝ።»
ብስመ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ!
«ሀዘንተኛ ነሽ?»
«እማዝነው ግን ለራሴ ነው፣ ልጀማ ተገላገለ፡፡»
«አይዞሽ!» አላት አስቻለው፡፡ ከመቀመጫው ብድግ አለና ወደ ትርፈ ጠጋ በማለት «ቢያንስ አይርብሽም፡፡ ፈቃደኛ ከሆንሽ ከኔው ጋር ትኖሪያለሽ፡፡» አላትና
እንደገናም «ቅር ይልሻል?» ሲል ጠየቃት።
ትርፌ ዓይኖቿን በእንባ ሰማይ አስመስላ ወደ አስቻለው ቀና በማለት
«አታምነኝማ ጋሽ አስቻለው?» አለችው ሽቁጥቁጥ እያለች::
«ዘርፈሽኝ አልሄድሽም እኮ! አይዞሽ አትፍሪ፡» አላትና ወደ መቀመጫው ተመልሶ ቁጭ አለ፡፡ ግንባሩን ወደ ጠረጴዛ ደፍቶ ያስብ ጀመር።
👍12
ሰዓቱ ወደ አስራ አንድ ተኩል ተጠጋ፡፡ አስቻለው የራት ነገር ትዝ ሲለው በቅድሚያ ለእሷ በሳህን ሊያመጣላት አሰበ፡፡ ከቤት ወጣ ሊል ሲል «እስቲ የሚበላ
ነገር ላምጣልሽ፣ እስከዚያው ገላሽን ተጣጥበሽ ጠብቂኝ አላት።
«ምግብ ይዣለሁ እኮ!» አለችው
«እስቲ ምን ይዘሻል?»
ትርፌ ቀና ብላ እያየችው፡፡
ትርፌ ጓዟን ፍትት አደረገችና በሌላ አሮጌ ጨርቅ የተቋጠረች ነገር
አወጣች፡፡ ያቺንም ፈታታችና ከውስጧ በቁጥር አምስት የሚሆኑ ድርቅ ያሉ ቂጣ
የሚመስሉ ነገሮች እያሳየችው «ይኸው!» አለችው::
አስቻለው አሁንም ሆዱ አዘነና «እሱን ነገ ትበይዋለሽ፣ ለዛሬ ግን መንገድ ላይ ውለሽ አንጀትሽ ስለ ታጠፈ ለስለስ ያለ ነገር ላምጣልሽ፡፡» ብሏት ወጣ፡፡
በግምት ከግማሽ ሰዓት በኋላ በዳንቴል የተሽፈነ ሳህን ይዞ ሲመለስ ትርፌ እነዚያን የቆሸሹ የአስቻለውን የቤት ዕቃዎች ሁሉ አውጥታ ግቢ ውስጥ ስታጣጥብ
አገኛት። ደንግጦም ገርሞትም ቀጥ ብሎ በመቆም «ምነው ትርፈ? ምን ነካሽ ነገ ከነገ ወዲያ አይደርስም እንዴ?» በማለት ቆጣ ባለ ንግግር ተናገራት፡፡
«ለምን ጋሽ አስቻለው? በጣም ነው እኮ የቆሽሽው፡፡ እኔ ጀግሞ አልደክመኝም::» አለችና ወደ እሱ ጠጋ በማለት በሹክሹክታ አነጋገር «ወዲያው አንተ እንደወጣህ አንዲት ልጅ መጥታ ቤት ውስጥ እየጠበቀች ነው፡፡» እለችው
«ምን ዓይነት ልጅ?» ሲል ጠየቃት ሆዱ እየጠረጠረ።
«ቆንጆ! በጣም የምታምር» አለችው ትርፌ ጥብቅ ባለ አነጋገር፡፡አስቻለው የልጅቷ ማንነት በትክክል ገባውና ትርፌን በፈገግታ አየት አድርጓት ወደ ቤት ሲገባ ሔዋንም በፈገግታ ተቀበለችው::
“ታዲያስ ሔዩ!» እያለ ሳህኑን ጠረጴዛ ላይ ከአስቀመጠ በኋላ «እዘናግተሽ መምጣት ጀመርሽ እያላት ሁለቱም በፈገግታ ተሞልተው ተሳሳሙ፡፡
ትርፌ!» ሲል እስቻለው ወደ ውጭ ተጣራ።
«አቤት»
«ነይ አንዴ።»
ትርፌ የእጇን ውሃ እያራገፈች ወደ ቤት ስትገባ አስቻለው የሔዋንን
አንገት አቅፎ፤ ሔዋን ደግሞ ወገቡን ያዝ አድርጋ ፎቶ እንደሚነሱ ሙሽሮች ፈገግ
ብለው ቆመው ጠበቋት። «ቅድም ስለሚስት ያነሳሽብኝ ነገር አልነበር ይቻት እጮኛዪ! ነይ ተዋወቁ::» አላት አስቻለው፡፡
ሔዋን - ትርፌ፡» ተባብለው ተጨባበጡ።
ያቺ የምወዳት የማምናት ሰራተኛዬ እያልኩ ስነግርሽ የነበረችው ትርፈ በጋሻው ማለት ይቺ ናት ሔዩ!» በማለት ለሔዋን ከገለፀላት በኋላ ትርፌን ደግሞ
ስም አውጭላታ!» አላት ፈገግ ብሎ እያያት፡፡
«እታለም ብያታለሁ::» አለች ትርፌ እንደ ማፈር እያለች፡፡
«አመሰግናለሁ::» አለች ሔዋንም ሳቅ እያለች፡፡
ሦስቱም ተሳሳቁ፡፡
ትርፌ ወደ ስራዋ ስትመለስ አስቻለውና ሔዋን ወንበር ላይ ቁጭ አሉና
«ቆየሽ እንዴ ከመጣሽ!» አላት አስቻለው፡፡
«አዎ! እንዲያውም ልመለስ ስል ነው የመጣኸው::»
«ጠዋት ግን ለምን ቀረሽ?»
«ስላልተመቸኝ:: ግን ይኼው አካካስኩ አይደል!»
«አመሰግናለሁ:: ከቸኮልሽ ሂጂ ልሽኚሽ፡፡» አለና አስቻለው ብድግ አለ፡፡
ሔዋንም ብድግ ስትል ከንፈሮቿን ሳም ሳም አደረጋቸው::
አስቻለውና ሔዋን ልክ ከግቢ እንደወጡ በቀኝ በኩል አየት ሲያደርጉ በልሁና መርዕድ ጫት ይዘው ሲመጠ አዩአቸው፡፡ ከእራት በፊት ጫታቸውን አስቀምጠው መቀመጫቸውን ሊያዘገጃጁ ነው፡፡
በልሁ ከርቀት ሔዋንን መናገር ጀመረ፡፡ «ትናንት አልመጣም ብለሽ ከላክሽ በኋላ አሁን የመጣሽበትን ምስጢር ሳታወጪ የሚለቅሽ የለም፡፡» እያለ ሔዋንን
ቀለደባት፡፡ በልሁና መርዕድ ከአስቻለውና ሔዋን ጋር ደረሱና ተሳስመው ሰላምታ ከተለዋወጠ በኋላ «ግን ትናንት ለምን አልመጣም ብለሽ ላክሽ? ምናልባት ያቺ እህትሽ የተለመደ መጥረጊያዋን አንስታብሽ ይሆን እንዴ?» ሲል ጠየቃት በልሁ
ኮስተር ብሎ፡፡
«ያ እንኳ አይደለም፡፡» አለች ሔዋን መሬት መሬት እያየች፡፡
«ሌላውስ?» አላት በልሁ በሔዋን ሁኔታ ተጠራጥሮ፡፡
«ብቻ ብላ እንደ ማቅማማት ስትል በልሁ አሁንም አጥብቆ ጠየቃት፡፡
ንገሪኝ! እኔና እሷ መቸም… ብሎ ሳይጨርስ ሔዋን ቸኮል ብላ
እቋረጠችው፡፡ ሸዋዩ በልሁን እንደምትፈራ በልሁም እንደማይወዳት ታውቃለችና
የሁለቱን የባሰ መራራቅ ለማስቀረት ስትል ወደ አላሰበችው ነገር አመራች።
«እንግዶች ይመጣሉና የትም እንዳትሄጂ ብላኝ ነው
«ከየት የሚመጡ? »አላት እስቻለው፡፡
የዚሁ ከተማ ናቸው፡፡ ባርናባስ የሚባሉት ሰውቁና የእሳቸው ጓደኛ ነው መስል አንድ በድሉ አሽናፊ የሚባል ነው፡፡» አለች በተለይ በልሁን እያየች፡፡
«በድሉ አሸናፊ?» ሲል ጠየቃት በልቡ ግንባሩን ቋጠር አድርጎ፡፡
መቸ ጀምሮ ነው እሱ ደግሞ ወደዚያ ቤት መምጣት የጀመረው?»
ከአሁን በፊት ሁለት ጊዜ መጥቶ ከባርናባስ ጋር ጫት ቅመዋል።
በድሉ አሸናፊን አስቻለው! በልሁና መርዕድም ያውቁታልና እርስ በርስ
ተያዩ፡፡ በከተማ ውስጥ አሉ የተባሉ የህዝብ ተሽከርካሪዎች ባለ ንብረት የሆኑ ሰው ልጅ ነው። ራሱም ባለ ሸራ ቶዬታ ይይዛል።
«ምን ብለው ከአንቺ ጋ አስተዋወቁሽ?» አላት አስቻለው ልቡ ተጠራጥሮ
«ሀብታም፣ የሀብታም ልጅ ምናምን አሉኝ፡፡»
«እሺ ከዚያስ»
«ዛሬ ደሞ ሁሉም ጫት ሲቅሙ ውለው የማታ ማታ ላይ ባርናባስና እት አበባ እኔና ሰውየውን ተጫወቱ ብለውን ወደ ከተማ ወጡ፡፡ ልክ እነሱ ሲወጡ
ጀምር ሰውየው ነይ አጠገቤ ቁጭ በይ እያለ ይጨቀጭቀኝ ጀመር። እምቢ ስለው እጄን ይዞ በመጎተት ፍራሽ ላይ ሊያስቀምጠኝ ሲሞክር አምልጪው ሮጬ እማማ ዘነብ ቤት ገባሁ።
«ከዚያስ?» አላት በልሁ ጥርሱን ነከስ እያረገ።
«እዚያው ስቆይበት የቤቱን በር መሰስ አድርጎት ወጣና ውጭ አቁሟት የነበረች መኪናውን አስነስቶ ሄደ፡፡ እኔም እት አበባና ባርናባስ አብረው ከወጡ እሷ
ቶሎ እንደማትመለስ ስለማውቅ በዚች ቀዳዳ ብቅ ብዬ ልመሰስ በማለት ወዲዚህ መጣሁ፡፡» አለች ሔዋን ዓይኗን በሁለም ላይ እያንከራተተች።
አስቻለው፣ በልሁና መርዕድ አሁንም እርስ በእርስ ተያዩ፡፡ በሽዋዩ ቤት ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ሳይነጋገሩ፤ ነገር ግን በደንብ ተግባቡ፡፡

💫ይቀጥላል💫
👍42🔥1🤩1
ካ.ካ.ካ.ካ.ካ.ካ

የሽኝትሽ ቀን ላይ፣
የስንብት ቀን ላይ፣
ለመቃብር ክተት፣፣
ተዘቅዝቆ ጥለት፤
የሚነበበው ፣ያንችን መሉ ታሪክ ፣ እንድጽፍ ታዝዤ፣
ታሪክሽን ተውኩት ፤በልቅሶሽ ፈዝዤ።
(ካ.ካ.ካ.ካ.ካ.ካ)
ሣቅ በሣቅ የሆነው
ለቅሶው ምን ሆኖ ነው?
የሚርመሰመሰው
ይክ ሁሉ እልፍ ሰው።
የወጣው የገባው ፣ በድሞጽ አልባ ዳና
ሞትሽን ሊያስረሳ ፣ዘርሽን ሊያጽናና።
መጽናናት ፣ማጽናናት ፣ በሚል ተረት ተረት፣
ሪሱን ያተርፋል ፤ከመታማት ክስረት።
(ካ.ካ.ካ.ካ.ካ.ካ)
በለቅሶ ቤትሽ ውስጥ
ሲሰማ ማሽካካት ፣ ይነጋል ይመሻል፤
የኔ ጥያቄ ግን
የዚኸን እሩቡን ፣ አንቺ መች ሥቀሻል?
የታሪክሽ ዘመን ፣ መዳፊ ሊጽፈው
መሃል መስመር ደርሶ ፣ ሞን አደናቀፈው?
(ዝም ብዬ ልጻፈው?)
በዐሥራ ዘጠኝ እንትን፣
የወታደር ትዕዛዝ ፣ ዐመፁን ሲበትን፣
ባርቾ ሲሰደድ ፣ በጎረምሶች ዘሪፍ፣
ዘረኛ ሲተካ ፣ በአራት ኪሎ በራፍ፣
(ተወለደች ልበል?)
ተወለደች ብቻ ፧ታሪክ ስላይደለ
የሆንሽውን ስጽፍ ፣ያልሆንሽው የታለ?
እያለ
የኑሮሽን ዘመን ፣መዳፌ ሊጽፈው
መሃል መስመር ደርሶ ፣ ሞን አደናቀፈው?
የዕድሜ ልክስ ደስታ ፣ ቢሰላ ቢቀመር
እንዴት ነው ማይሞላ ፣ ቢያንስ አንድ መስመር።
የሣቅሽበት
ቅጽበት
ከማነስም አንሶ ፣ የለም እስከሚባል
"ሣቅ አታውቅም” አለ ፤ የሙሾ አወሪጅስ ባል።
አንቺማ
ታዘበሽ አታወቂሞ ፧ ሕይወት ውሏን ስታ፤
ሐዘንሽን ሊደርስ
የመጣ በሙሉ ፣ሲበልጥሽ በደስታ።
ለቅሶኛስ
ሞትሽን አሳብቦ፣ ድምጹን ሲያንጠራራ፣
አንቺ ያልሣቅሽውን ፣ሢሥቅ እስከ ጣርያ፣
ርቃንሽን ቀበሮ ፣ ሁሉ ሲያሽቀረቅር፣
አረ ያንቺስ ይቅር፤
የመኖርን ሹፈት፣
የሕይወትን ሽፍደት፣
እመዝነው ሚዛን ፣ እለካበት ሜትር፣
የማዘኔን ባሕር ፣ እከፍልበት በትር፣
ፈልጌ አጥቼ
ጥያቄ ምስጥ ሆኖ ፣ ውስጥ ወስጤን ይበላል፤
እንዴት ከሰው ሕይወት
የሰው ልጅ ለቅሶ ቤት ፣ በሣቆች ይሞላል?
አረ ያንቺስ ይቅር!
ከሕይወት ፣ ከታሪክ ፣ከኑሮ ዘመንሽ፣
እንዴት ይበልጥሻል
ደጋግሞ በመሣቅ ፣ የገዛ ድንኳንሽ?
ካ.ካ.ካ.ካ.ካ.ካ

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
😢62👍2
#ምንትዋብ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ወይዘሮ እንኰዬ የእናታቸውን ንግግር ሲሰሙ ከሐሳባቸው መለስ አሉና በኩራት የነጠላቸውን ባለ ደማቅ ጥልፍ ጥለት አስተካክለው፣ “ሰማህ?” በሚል ሁኔታ ኢሳያስን ተመለከቱት።

ኢሳያስ ግን እጥር ምጥን ያሉትን ዮልያናን እያየ፣ “ጃንሆይም እኮ
ያጤ ሚናስ ነገድ መሆናችሁን አውቀዋል። ልዣችሁን የመረጡበት ዋናው ምክኛት ግን እሱ ማዶል። ባይናማነቷ፣ በጠባይዋና በብሩህ አይምሮዋ ደስ ተሰኝተው ነው” አላቸውና በራፍ ላይ የቆመውን አገልጋይ፣ “ያነን ማሙየን ሴቶቹ ዕቃውን ይዘው እንዲመጡ ንገራቸው
በለው” አለው።

አሳላፊው ቀልጠፍ ብሎ ወጥቶ ሲመለስ አብረውት ሁለት ደንገጡሮች የቀርከሀ ሰንዱቆች ይዘው ገቡ። ኢሳያስ ሰንዱቆቹን እንዲከፍቱና ዕቃዎቹን እንዲያሳዩ በእጁ ምልክት ሰጣቸው። ለጥሎሽ የመጡትን
የሐር ቀሚሶች፣ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ካባ፣ ቆዳ ጫማ፣ ከወርቅ የተሰሩ ያንገትና የጆሮ ጌጦች፣ እንዲሁም አምባሮች በእቅፋቸው አድርገው
ለተሰበሰበው ሰው አሳዩ።

እነግራዝማች ትንፋሻቸውን ውጠው ተመለከቱ። ተነሥተውም
በአክብሮት እጅ ነሡ፤ የምርቃት መዓት አዥጎደጎዱ።

ወለተጊዮርጊስ ጥሎሹን ለማየት ዐይኗን ከወዲያ ወዲህ አዘዋወረች።እንደልብ ማየት አቃታት። ቤተሰቦቿ ፊት ላይ ከሚንፀባረቀው የኩራትና የደስታ ስሜትና ከአዘነቡት የምስጋና ቃላት ግን የመጣላት ጥሎሽ ቀላል እንዳልሆነ ተገነዘበች።
እንዳው ሰውየው... አረ ንጉሥ ነው ሚባሉ... ንጉሡ ኸኛ ጋር ምን
አገጣጠማቸው? ንዳድ እንዲህ ጉድ ታምጣብን እያለች ስትገረም
ቆየችና ንጉሠ ነገሥቱ እነሱጋ፣ በነበሩ ጊዜ እሷን ለማግባት ማሰባቸውን የሚጠቁም ነገር እንዳው ፍንጭ አኸገኝ እንደሆን ብላ፣ ሐሳቧ ወደ ኋላ ሽምጥ ጋለበ።

ጨታመው በመጡ ማግስት እናቷ አዘዋት ፊታቸውን በጨርቅ ስታብስ ንጉሠ ነገሥቱ ዐይናቸውን ገለጥ አደረጉ፤ እንደደነገጡ አስተዋለች። ለምን እንደሆነ አልገባትም። እሳቸው ዐይናቸውን ከድነው በስመአብ አሉ። ዐይናቸውን ድጋሚ ሲከፍቱ፣ እነዚያው ይዘዋቸው የመጡት
ሰዎችና እነግራዝማች ናቸው የከበቧቸው። ቅዠት ኑሯል? ትኩሳቱ ነው ሴት ልዥ ያየሁ ያስመሰለኝ ብለው ዐይናቸውን መልሰው ከደኑት።

ወለተጊዮርጊስ አጥሚት ይዛ ተመልሳ መጥታ፣ በለሰለሰ አንደበት፣ “እስቲ ትንሽ ይቅመሱ” ስትላቸው በድንገት ከእንቅልፋቸው እንደባነኑ
የደከመ ዐይናቸውን ከፈት ሲያደርጉ፣ የተኙበት መደብ አጠገብ ሴት ልጅ ሸብረክ ብላለች። ቀደም ብለው ያይዋት ወጣት እንደሆነች ሲገነዘቡ፣ ዐይኖቿ እንደ ኮከብ እሚያበሩ፣ ቆዳዋ የማር ወለላ የመሰለ፣ እንዴት ያለች ዐይናማ ናት በሩፋኤል? አሉ፣ አንድም ቀን
ስለታቸውንና ጥያቄያቸውን አስተጓጉሎባቸው የማያውቀውንና እሳቸው ጐንደር ውስጥ የተከሉትን ሩፋኤልን ጠርተው።

ወለተጊዮርጊስ ፈገግታ ለገሠቻቸው። ዐይኗ ላይ ያዩት ርህራሄ መጽናናትን ሰጣቸው። ልባቸው በደስታና በአድናቆት ከቦታው ተነቃነቀ። አጥሚት የያዘውን የሸክላ ጽዋ ወደ አፋቸው ስታቀርብላቸው፣ ወይዘሮ እንኰዬ፣ “እስቲ ይቅመሱ፣ እሷው ናት የሠራችልዎ” አሏቸው። የምግብ ፍላጎት ባይኖራቸውም፣ እንደ ኩበት የደረቀ አፋቸውን ታግለው ከፈቱላት። አንገታቸውን በአንድ እጇ አቅንታ ከአጥሚቱ
አስጎነጨቻቸው። ከበዋቸው የተቀመጡት፣ “ተመስገን፣ ለሱ ምን ይሳነዋል?” ብለው ወደ ላይ አንጋጠጡ።
በሚቀጥሉት ቀናት ከበሪሁን መድኃኒት በተጨማሪ ወለተጊዮርጊስ ከምትኖርበት ከአያቷ ቤት ማልዳ እየመጣች ምግብ እየሠራች፣ እያጎረሰች፣ አጥሚት እያጠጣችና እየተንከባከበቻቸው ራሳቸውን
ሲችሉም፣ እጅ እያስታጠበችና ምግብ እያቀረበች፣ ደከመኝ ሳትል
አስታመመቻቸው። እሳቸውም በሩፋኤል እንዴት ያለች ዐለላ...ሰንደቅ የመሰለች ናት ትትናዋስ? እያሉ ተስተናገዱ።

በተኙበትም ሰው ውልብ ባለ ቁጥር እሷ እየመሰለቻቸው ዐይናቸው ሲባክን፣ ሲያይዋት ልባቸው ከአፎቱ ተመንጥቆ የወጣ ሲመስላቸው፣ፊታቸውን በውሃ ስታብስ የእጇ ልስላሴ ሊያስተኛቸው ሲቃጣው፣
ትንፋሿ በሽታቸውን ከላያቸው ሲገፍላቸው፣ ሕዝኸ ወድያ ጥድቅ
ኸየት ይገኛል? አቤት አቤት እንዴት ያለች መልከ መልካም ናት?
ደም ግባቷ የተደራጀ፣ ጠጉሯ እንደ ሜላት የተፈተለ፣ ወገቧ እንደ ንብ
ንግሥት የቀጠነ፣ እንደ እርጎ የረጋች በምግባር የታነጠች እያሰኘ አከረማቸው።

እንኳንስ አይተዋት፣ ሳያይዋት ስለእሷ ማሰቡ ብቻ በወባ የዛለ
አካላቸውን ዘና ሲያደርግላቸው፣ ከዐይናቸው ስትርቅ ምግብ፣ ውሃ
ወይንም አጥሚት ይዛ የምትመጣበትን ሰዐት ሲናፍቁ፣ ጀንበር መጥለቂያዋ ላይ ወደ አያቷ ቤት ስትመለስ ሆድ ሲብሳቸው፣ ጠዋት ስትመጣ ከእናቷና ከአያቷ የወረሰችውን እንደ ውሃ የጠሩ ዐይኖቿን
ከብለል እያደረገች የወደዱትን እየመረጠች የሠራችውን፣ “እስቲ ትንሽ ይቅመሱ፣ እኼኛው ይሻልዎ ይሆን?” ስትላቸው፣ ጆሯቸው የተዋበ ዜማ የሰማ ያህል ወደ እሷ ዘመም ሲል፣ ልባቸው ለማራኪ ዐይኖቿ ሲገዛ ቀናት አለፉ።

ሌሎች ውበቷን አይተው እጇን ሲጠይቁ እሳቸው ከመልኳ ባሻገር
ለጋሥ መንፈሷን፣ አስተዋይነቷን፣ ሠናይ ምግባሯንና ትሕትናዋን
አስተውለው ወደዷት። በአኳኋኗና በልባዊ መስተንግዶዋ ልባቸው
ተነካ። ተወዳጅ ገፅታዋ፣ አነጋገሯ፣ ርጋታዋ፣ ወደ ሙሉ ሴትነት
በመሻገር ላይ ያለው ዳሌዋና ለግላጋነቷ በወባ የተንገላታችው ልባቸው ላይ ነፍስ ዘሩበት።
ድኘ እጐንደር ስገባ ይችን ልዥ አገባለሁ እያሉ ደጋግመው ዛቱ።

እሳቸው እንደዚህ እያሉ ይዛቱ እንጂ፣ ወለተጊዮርጊስ ወደዋት
እንደነበር የሚያሳይ አንዳችም ፍንጭ አላገኘችም። እሳቸውም በግልጽ ያሳይዋት ነገር አልነበረም።

የሚሄዱ ቀን፣ ግራዝማችንና ቤተሰባቸውን ከታላቅ ምስጋና ጋር
ተሰናብተው፣ ውድ ንብረት ወደ ኋላ የተዉ ያኸል እየተገላመጡ፣ ያችን “የአጥቢያ ኮከብ የመሰለች” ሲሏት የከረሙትን የአስራ ስድስት ዓመት ጉብል በዐይናቸው ፈልገው አመሰገኑ። ወለተጊዮርጊስ በተለይ ለእሷ ለቀረበው ምስጋና እጅ ነሥታ ቀና ስትል ዐይኖቿ ከሰውየው ዐይኖች ጋር ተጋጩ።

ከእሳቸው ዐይነ ብሌን ባሻገር ግን ከቋራ እስከ ጐንደር የሚወስደው
መንገድ እንደተቃና አላስተዋለችም።
ከሐሳቧ ስትመለስ ጨዋታው ቀዝቀዝ ብሏል። እንግዶቹም የተዳከሙ መስለዋል። ቤቱም ጨለምለም ብሏል። ሥራ ቤት በየበኩሉ ማሾ ሊያበራ ሽር ብትን ይላል።

ኢሳያስ፣ “እንግዲህ ልዥቱን ይዘን ነገ ጐንደር እንዝለቃ” አለ፣
ግራዝማችን፣ እንኰዬንና ዮልያናን በየተራ እየተመለከተ።

ነገ አለች፣ ወለተጊዮርጊስ። በረጅሙ ተነፈሰች፣ ወላጆቿና አያቷ የሚሉትን ለመስማት ጆሮዋን አቀናች።

“ባይኾን ኸነገ ወዲያ ይሁን፣ ጥቂትም ቢኾን ልዣችንን እንድናዘጋጅ” አሉ፣ አያቷ።

“እንዳላችሁ ይሁን” አለ፣ ኢሳያስ።
ጐንደር መሄዷ ነው! ተጨነቀች። ተርበተበተች። ኸጐንደር ልኸድ? አለች። ንጉሥ ላገባ ጥላዬስ?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ወለቴን ንጉሥ ኸወሰዳት እኔ የሥዕል ንጉሥ ማልሆን”

ጥላዬ፣ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ተቀምጦ ስለራሱና ስለወለተጊዮርጊስ ዕጣ
ፈንታ ያስባል። እናቱ ወይዘሮ ጌጤነሽ የምሽቱን ግብር ውሃ ወጥተው ሲመለሱ አየት አደረጉት። “አምሽተህ ነው?” አሉትና ለራሳቸው ሰምቶ
ይሆን? አሉ። ዛሬ ከልባቸው አዝነውለታል። ወደ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት፣ “በምሽት እንኳ ዕረፍት አይኖርህ ልጄ?” አሉት፣ መሬት ላይ የሚጭረውን አይተው።
👍14