#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
....ዲላ ሆስፒታል ውስጥ አንድ አነጋጋሪ የሆነ ክስተት ተፈጠረ፡፡ ሰበቡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከየጤና ተቋማቱ ነርሶች አወዳድሮ ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ በጤና መኮንንነት ለማሰልጠን ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ዲላ
ሆስፒታል የተመረጠውን ነርስ የማውቅ ውጤት ነው፡፡ የመወዳደሪያው ዋንኛ
መስፈርት የአገልግሎት ዘመን ሲሆን በማስታወቂያው ላይ የተጠየቀው አነስተኛ
የአገልግሎት ዘመን አምስት ዓመት ሆኖ ሳለ የተመረጠው ነርስ ግን ሦስት ዓመት እኳ ያልሞላው ሆኖ ተገኘ፡፡ ይህ ሁኔታ እንኳንስ መስፈርቱን የሚያሟሉ ነርሶችን
ውድድሩ የማይመለከታቸውንም የሆስፒታሉ ሠራተኞች ሁሉ ክፉኛ አስቆጫቸው።
ተመራጩ ነርስ የውድድሩን መስፈርት ካለማሟላቱም በላይ በሆስፒታሉ ውስጥ የሙያ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቀናት እንኳ እጅግ የተወሰኑ ነበሩ።
በአውራጃው የወጣቶች ማህበር ዕህፈት ቤት ውስጥ የአንድ ዘርፍ ሃላፊ በመሆኑ በመደበኛ ስራው ላይ አዘውትሮ አይገኝም። ከጤና ባለሙያነቱ ይልቅ ፖለቲከኛነቱ
ያመዝናል። ከዚሁ ማንነቱ የተነሳ በሠራተኞቹ ዘንድ አይወደድም፡፡ ጆሮ የሚል ቅጽል ስም ወጥቶለት ሰዎች ሁሉ ይሸሹታል። እሱ ባለበት ቦታ ወሬ አይሞከርም፡፡
እንዲያውም ወደ ሆስፒታሉ ብቅ ባይል የብዙ ሠራተኞች ፍላጎት ነው፡፡ ዛሬ ለከፍተኛ የሙያ ስልጠና የተመረጠበት ሁኔታ ቢያስቆጫቸውም በዚህ ሰበብ
ከመሀላቸው በመውጣቱ የተደሰቱም አይጠፉም።
ለአስቻለው ግን ይህ አይዋጥለትም፡፡ ጆሮ ለሁለትና ለሦስት ዓመታት ከአካባቢው ገለል ቢልም ኮርሱን ሲጨርስ ይበልጥ አብጦ እና ተኮፍሶ መመለሱ እንደማይቀር ይገነዘባል። የእሱ ጭንቀት ጆሮ በማይመለከተው ውድድር ውስጥ
ገብቶ ጭራሽ አሽናፊ የሆነበት ሁኔታ ነው፡፡ ፍላጎቱም የራሱን መብትና ጥቅም ለማስከበር መንቀሳቀስ ነው:: ይህን ጥረት ለብቻው ከማድረግ ይልቅ እንደ እሱ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ለማስተባበር ምክሮ ነበር፤ ነገር ግን አልተሳካለትም፡፡ሁሉም የሰጡት ምላሽ ማን ሊሰማኝ? ምን ለውጥ ሊመጣ? ምን ህግ አለና?...ወዘተ የሚሉ ተስፋ አስቆራጭ ቃላቶችን ነበር፡፡
ይህ ዓይነቱ የሰዎች አመለካከት የአስቻለው የዘወትር ራስ ምታቱ ነው። ገዢዎች በህዝብ ላይ ከሚፈጽሙት ግፍና በደል የበለጠ የዜጎች ልበ ሙትነት ያበሳጨዋል፡፡ መብትና ጥቅምን በፈቃደኝነት አሳልፎ የመስጠት ጅልነት
ያንገበግበዋል። አሁን ሲቆሏት ኋላ እንደሚቆረጥሟት እንደማታውቅ ጥሬ መብቱ ሲረገጥ፣ ጥቅሙ ሲጨፈለቅ ዝም ብሎ የሚመለከት ሰው አንጀቱን ያቆስለዋል።ሰው እንዴት ሰሚ በሌለበት፣ ህግ በማይከበርበት፣ ግፍና በደል በተንሰራፋበት፣
አድሎና ጭቆና በነገሰበት፥ አቤት ቢባል ፍትህ በማይጎኝበት ሥርዓት ውስጥ ለመኖር ፈቃደኛ ይሆናል? በዚህ ሁኔታ ውስጥ እየኖረስ እንዴት ስው ነኝ ብሎ
ያስባል? ይላል ዘውትር። ምንም እንኳ ሰውን ሁሉ ለዚህ ዓይነቱ የአመለካከትና የአስተሳሰብ ዝቅጠት ያበቃውን ታሪካዊ መነሻ የሚያውቀው ቢሆንም ግን እስከ
መቼ? ለሚል ጥያቄ መልስ እያጣ በእጅጉ ያዝናል፣ ይበሳጫል፡፡
ያም ሆኖ አስቻለው ወትሮም እንደሚያደርገው ሁሉ የበኩሉን ድርሻ ከመወጣት ወደ ኋላ አላለም። በዕለተ ሐሙስ ከጠዋቱ አንድ ሠዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሠዓት ባለው ፈረቃ ስራውን ሲያከናውን ውሎ ወዲያው ወደ ቤቱ መሄድ አልፈለገም፡፡ በቀጥታ ወደ ሆስፒታሉ የአስተዳደር አገልግሉት ሃላፊ ቢሮ አመራ፥ ወደ ባርናባስ። በሩን ከፈት አድርጎ ወደ ውስጥ አየት ሲያደርግ ባርናባስ
ወየሶ በጠረጴዛው ላይ አጎንብሶ ይጽፋል፡፡ አለባበሱ ያው የተለመደው ነው፡፡ በሩ ሲከፈት ሰምቶ ዞር ሲል አስቻለው የበሩን እጀታ እንደያዘ በር ላይ ቆሞ አየው፡፡
«አቤት!» አለው ዓይኑን በአስቻለው ላይ እንደተከለ፡፡
ላነጋግርህ ፈልጌ ነበር፡፡»
ባርናባስ ፈጥኖ መልስ አልሰጠውም። ለአፍታ ያህል መልከት ካለው በኋላ እጅግ በቀዘቀዘ ስሜት ትችላለህ» አለና በእጁ ወደ እንግዳ ወንበር አመለከተው፡፡አስቻለው ገባ። ከእንግዳ ወንበሮች መካከል አንዷን ሳብ አድርጎ ቁጭ አለና
ባርናባስን በጥርጣሬ ዓይን ያየው ጀመር።
«ምን ልርዳህ?» ሲል ጠየቀው ባርናባስ መነፅሩን አውልቆ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ እያደረጉ፡፡
«ለእጩ ጤና መኮንንነት ኮርስ ውድድር ተመዝግቤ ነበር።»
«እህ!» አለው ባርናባስ በሾፍ አነጋገር።
«በውጤቱ አልተደሰትኩም!»
«ምን ጠብቀህ ነበር?»
«እመረጣለሁ ብዬ ነበራ!»
«እህ! ዝም ብሎ መመረጥ አለ እንዴ?»
«ዝም ብዬማ አይደለም፡፡ በወጣው ማስታወቂያ መሠረት ከሆነ በአገልግሎት እኔ እበልጣለሁ፡፡ እንዲያውም ሁለት ዓመት ትርፍ አለኝ:: የተመረጠው ነርስ ግን ጭራሽ ከመስፈርቱ አነስተኛ መነሻ እንኳ ለመድረስ ሁለት ዓመት እንደሚቀረው አውቃለሁ፡፡ ታዲያ እንዴት ዝም ብለህ ትለኛለሀ?» ሲል ግንባሩን ቋጠር አድርጎ ጠየቀው::
ለመሆኑ በማስታወቂያው ላይ የተጠየቀው መስፈርት የአገልግሎት ዘመን ብቻ ነው እንዴ?
«ልጥፎችማ አሉ፤ ነገር ግን ዋናው መስፈርት የአገልግሎት ዘመን መሆኑን ማስታወቂያው በግልጽ አስቀምጧል።»
«ልጣፍ ስትል?» አለና ባርናባስ ዓይኑን ፈጠጥ አደረገ፡፡
«በቃ! ልጣፎች ማለቴ ነው፤ ለፍርደ ገምድልነት ምክንያት የሚሆኑ እንጂ ዋናውን መስፈርት የማያሽሩ!»
ቀይ ፊቱ የባሰ ደም መምሰል ጀመረ::
ባርናባስም ዓይኑ ፈጠጠ።
አፍንጫው ነፋ ሞሸሽ አለ። ወደ ጠረጴዛው መለስ ብሎ እጆቹን አቆላልፎ ተደገፈና
“ጉልህ እብዮታዊ ተሳትፎ ያደረገ የሚለውን መስፈርት ማለትህ ነው?» ሲል አስቻለውን ጠየቀው።
«ያ ይኼ አላልኩም፡፡ ግን ከሙያው ጋር የማይሄዱትን በሙሉ ማለቴ ነው::» አለው አስቻለው እሱም ጠረጴዛውን እየተደገፈ፡፡
ሁለቱም ተፋጠጡ:: ዓይን ማን ይስበር? ማን ይስበር? በሚል የሚጠባበቁ ይመስላሉ። ባርናባስ እንደገና ወደ ኋላ ወንበሩን ተደግፎ በረጅሙ ተነፈሰና
«ለማንኛውም አንተና የተመረጠው ጓድ በምንም መንገድ አንድ ልትሆነ አትችሉም።» አለው፡፡
«ምን አገናኝቶን?» አለ አስቻለው ፈርጠም ባለ አነጋገር፡፡ «የኔስ ችግር ይኸ አይደል?» አለና ባርናባስን አከታትሉ ይመለከተው ጀመር።
«ታዲያ ይኸን ካወቅህ ሌላ ምን ፈለክ?»
«እኔ እያለሁ እሱ እንዴት ተመረጠ ብዬ ነዋ!»
«ባላችሁ ልዩነት ምክንያት
ውድድሩ እኮ ለባለሙያነት እንጂ ለካድሬነት አይደለም አቶ ባርናባስ»
ባርናባስ ድንገት ቁጥት አለና «ጓድ በል! ደሞ የምን አቶ ነው?» በማለት በአስቻለው ላይ አፈጠጠ፡፡
አስቻለው ሳያስበው ፈገግ አለና ረጋ ለስለስ ባለ አነጋገርን “ ጓድ የሚለው ቃል እኮ በዓላማና
በተግባራቸው የሚመሳሰሉ
ግለሰቦች የሚጠራሩበትና
የሚሞካሹበት ቃል ነው:: ታዲያ እኔና አንተ…» ብሎ ሳይጨርስ ባርናባስ አቋረጠው፡፡
«የመጣህበትን ጨርሰሃል?»
«አልጨረስኩም!»
«ምን ቀረህ ደግሞ?»
«አመራረጡ ትክክል ስላልሆነ እንደገና ይታይ ነው የምለው! በዚህ ላይ ያለህን ኣስተያየት ስጠኝና እንጨርስ።» አላ አስቻለው ፊቱ በብስጭት ልውጥውጥ እያለ።
«በቃ! ጓዱ ባበረከተውና እያበረከተ ባለው አብዮታዊ አስተዋጽኦ ምክንያት

👍3❤1
ተመርጧል ነው የኔ መልስ፡» አለና በርናባስ እንደገና ወደ ኋላው ወንበሩን ተደገፈ፡
«በፖለቲካ?»
«አዎ!»
«ታዲያ ወደ ፖለቲካ ትምህርት ቤት ላኩታ! ወደዚያ ቢሄድ ነው እኮ ይበልጥ ጎልቶ ይበልጥ ሾላ የሚመለስላችሁ፡፡»
ባርናባስ በቁጣ ስሜቱ ተለዋወጠ፡፡ መናገር ሲያቅተው አስቻለው ራሱ ቀጠለ፡፡ «ሙያ ካስተማራችሁትማ አመለካከቱም ይቀየርና ምላሱንም ይሰበስባል፡፡
መዋሽት አይችልም፡፡ መቅጠፍ አይሆንለትም፡፡ ያ ከሆነ ደግሞ በእናንተ በኩል እንደ ደነዝ ስለሚታይ ለእናንተም አይጠቅማችሁ፡፡ ለራስም ነገሩ ሁሉ እየተምታታበት ግራ ይጋባና ይቸግራል፡፡» አለው አሁንም ፈገግ ባለ ኣስተያየት ባርናባስን
እየተመለከተ፡፡
«ኻኻኻኻ ...»ብሎ ባርናባስ ሳቀና «አሁንስ አሳከኝ!» ሲል በቃልም
ተናገረው።
የነገርኩህን በደንብ ተረድተኽኛል ማለት ነው::
«የኔ ወንድም! ያለ ስራህ የገባህ ይመስለኛል! ይልቅስ የሙያ ሥነ-
ምግባርህን አክብረህ መንቀሳቀስሱ ይበጅሃል። በማያገባህ ጉዳይ እየገባህ መዘባረቁ ግን…» ብሎ ሳይጨርስ አስቻለው አቋረጠው፡፡
«ትክክል! የሙያ ሥነ-ምግባርን ማክበር ማለት መርሁንም ከሚጥሱት ጋር መታገልን ያጠቃልላል፡፡» ሲለው የባርናባስ ስሜት ግን ድንገት ልውጥውጥ አለ፡፡
ባርናባስ አንድ ነገር ትዝ ብሉት በሀሳብ ጭልጥ ብሎ ሄደ፡፡
ባለፈው ዲላ ከተማ በማጅራት ገትር ወረርሽና በተናወጠበት ወቅት የሆስፒታሉ ሠራተኞች በአንድ ላይ ተሰብስበው በሽታውን የመከላከል ጥረታቸው በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ግምገማ ላይ ነበር። ያኔ በበርናባስ ወይስ በአስተዳደር አገልግሎት ሃላፊነቱና
በባርቲ መሠረታዊ ድርጅት አንደኛ ፀሃፊነቱ አስተያየቱን በሚሰጥበት
ግዜ ከሌሎች ሃሳቦች በተጨማሪ የተሰማውን ቅሬታ ሲገልጽ
በእንዲህ ዓይነት አደጋ ወቅት ከፍተኛ የሆነ ሀገራዊ አደራ ተሽክመው ደፋ ቀና ለሚሉ ጓዶች ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊና ተገቢ ቢሆንም አንዳንድ ለአብዮቱና ለአብዮቲ አራማጆች
ቀና አመለካከት የሌላቸው
ራስ ወዳዶች ግን የበላይ
አካል የሰጠውን አመራር ላለመቀበል ሲያንገራግሩ ተስተውለዋል በማለት በስብሰባው ላይ ተናግሮ ነበር፡፡
ይህ አሽሙር በቀጥታ እንደሚመለከተው የገባው አስቻለው ደግሞ
“በምንመራበት ፖሎቲካዊ ፍልስፍና መስረት ህዝባዊ አደራ መሸከም ማለት በቅድሚያ ስፊውን ህዝብ ማገልገል እንደሆነ ራሳቸው አራማጆቹ አስተምረውናል። በዚህም መሠረት ምናልባት የሚፈልጉትን አልፈጸምንላቸው እንደሆነ እንጂ
የሚነግሩንን ግን ሳናዛንፍ አከናውነናል፡፡ በዚህም በተጨማሪ ስልጣን በሙያ ስራ ላይ ሲገባ ሙያን ከማራከሱም ባሻገር በሂደት ራሱ ስልጣንም ዋጋ እያጣ
እንዳይሄድ ሰግተን ጥረት አድርገናል::"ካለ በኋላ ንግግሩን
ሲያጠቃልል «አንዳንድ ወገኖች ግን የስልጣን ወንበራቸው ከፍ ባለ ቁጥር እውቀታቸውም በዚያው መጠን ያደገ እየመሰላቸው የተለየ ክብርን ሲሹ
እንመለከታለን። በዚህ አጋጣሚ
ልናስገነዝባቸሁ የምንፈልገው ክብርና ሞገስ አእምሮአዊ ማንነት እንጂ ከሚቀመጥባት ወንበር ላይ እንደማይመነጭ እዲረዱልን ብቻ ነው::» በማለት ተናግር እንዳበቃ አዳራሹ በጭብጨባና በፉጨት
ተናውጦ ነበር፡፡ ያኔ የባርናባስ ከድንጋጤና በንዴት ፈቱ በቁጣ ከሰል መስሉ ነበር።
አስቻለው ዛሬም ያንኑ እየደገመ መሆኑ ተሰምቶት ባርናባስ ፊቱ በቁጣ ተለዋወጡ::
ስማ! አለ ባርናባስ ጣቱን ወደ አስቻለው እየቀስረ«ወሬና ተግባር
ለየቅል ናቸው። ያልተወለደ እየገደልክ በሃኪሞች ቋንቋ ማስወረድ መሆኑን ያውቃልና
የባርናባስ አነጋገር ከምን የተነሳ እንደሆነ ለማወቅ ፈለገ።
በደረስን ጥቆማ መሠረት መረጃዎችን አያሰባስብን ነው። ከዚያ በኋላ የምንነጋገርበት ይሆናል::"አለና ባርናባስ «አሁን ጨርሻለሁ። ከቢሮዩ እንድትወጣልኝ በትህትና እጠይቃለሁ:: ብሎት በረጅሙ ተነፈሰ፡፡
«አዲስ ነገር እየጀመርክ ምኑን ጨረስከው?» አለ አስቻለው አሁንም ዓይኑን በባርናባስ ላይ እንደተከለ፡፡
«ሌላ ጊዜ በአዲስ መልክ እንጀምረዋለን:: አሁን ከቢሮዬ ውጣልኝ፡፡»
አስቻለው በባርናባስ ጥያቄ ተቻኩሎ ከመቀመጫው ቶሎ አልተነሳም፡፡
እንዲያም ለአፍታ ያህል ትኩር ብሎ ከተመለከተው በኋላ «ያልተወለደ ገዳይ አልከኝ? በማለት "መልሶ አስታወሰውና በቃ! ገላግየዋለኋ ፣ ያንን ሳይወለድ ሟች አለው ባርናባስ የሚሰጠውን ምላሽ በመጠባበቅ ትኩር ብሎ እያየው፡፡
«በመግደል!!»
💫ይቀጥላል💫

❤1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገ
...አፍንጫ ጎራዳነቷ ውበቷን አደመቀው እንጂ አላደበዘዘውም፡፡ ስላማዊት ብዙ ሰው ቢረባረብባትም ከሁሉ የበለጠ የምትቀርበውና ወዳጇ
መሆኑ በብዙዎቹ ዘንድ እየታወቀ የመጣው ታደሰ ነው። ታደሰ መልኩ ጥቁር ሆኖ ረዘም ያለ ጉብል ነው፡፡ እሱ ሲመጣ ሰላማዊት ማንንም አታነጋግርም፡፡ ሄዳ እሱ ላይ ጥብቅ ነው። ይሄ ሁኔታ በፅጌ አማካኝነት ለሰፈሩ ሴተኛ አዳሪዎች ሁሉ ስለተወራ ታደሰ ብቅ ማለቱን ሲያዩ ስሟን
እንደማስቲካ ሲያኝኩት ይውላሉ።
“አሳበዳት እንጂ! ነፍሷን አጠፋላት!ታደሰን አታውቂውም እንዴ? ደላላ ነው እኮ! ኸረ በሌላም የሚጠረጠር ሰው ነው አሉ። አንዱ ውሽማዬ ስለሱ ነግሮኛል።ነጭ ለባሽ ነው ተብሎ ይጠረጠራል ብሎ አጫውቶኛል”
“አረ እባክሽ?! ነጭ ለባሽ ?ምን አስነክቷት ይሆን እንደዚህ በፍቅር የከነፈችለት?”
“ትቀልጃለሽ እንዴ? ያቅማታላ! ብር እንደ አሸዋ ይበትንላታላ! እስቲ ይታይሽ? ደላላ ነው። በዚህ ላይ ደግሞ በነጭ ለባሽነቱ መንግሥት ይከፍለዋል! ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ ነው
“ምን እያቀመሰቻቸው ይሆን ወንዶቹ ሁሉ እንደዚህ በሷ ላይ የሚረባረቡት በናትሽ?”
“ወረት ነው እባክሽ! ወረት! አዲስ ጀማሪ አይደለችም? በወረት ነው እንደ ንብ የሚከቧት”
የታደሰ ደግሞ ባሰ፡፡ ፍቅር ድብን አድርጎ ገድሎታል እኮ፡፡ ምን ማለትሽ ነው? አሁን አሁንማ ግንባሯን ሳይሳለም አይውልምኮ! እኔም ሳላየው የዋልኩበት ቀን የለም”
“ምን ታደርጊዋለሽ አጅሬ የወረት ፍቅር ነዋ!” ተንሾካሾኩባት። እውነትም ከዚያ ሁሉ የወንድ መንጋ መካከል ለታደስ ልዩ ፍቅር ነበራት። ታደሰ ፍቅሩን በብዙ መልኩ የሚገለፅላትና የሚያስፈልጋትን ሁሉ የሚያሟላላት የስካር ሳይሆን እውነተኛ ጓደኛዋ ነበር።
ዛሬም እንደ ወትሮው ካፖርቱን ከላይ ጣል አድርጉ ባርኔጣውን ደፍቶ አንገቱ ላይ ሻርፕ ጠምጥሞ ተፍተፍ የሚለው ወደሷ ነበር፡፡ ከሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ቀኝ ተገንጥሎ ወደ እሪ በከንቱ የሚወስደውን ቀጭን የአስፋልት መንገድ ተከትሎ ወደ ፍቅረኛው ወደ ሰላማዊት ለመድረስ እየተጣደፈ ነበር፡፡
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሆኗል። በአላፊ አግዳሚ ላይ ዐይኖቻቸውን እያፈጠጡ የሚያስፈራሩ ሴተኛ አዳሪዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል። በዚህ
ሰዓት እብዱ ምንሽንሽ ከአካባቢው አይታጣም ነበር፡፡ አንዴ ወዲህ አንዴ ወዲያ እየዘለለ ድንጋይ እያነሳ ድንጋይ እየጣለ ይሯሯጥ ነበር፡፡ ሣንቲም
ይለምናል። ከሰጡት ይቀበላል፡፡ ዝም ካሉት ደንታም የለው። የሱ ቁም ነገር መዝለል፣ መዝለል፣ ድንጋይ መፈንቀል፣ ድንጋይ ማንሳት ድንጋይ መጣል ብቻ ነው፡፡ ዛሬ ግን በሱ ምትክ ሰካራሙ ታከለ ያንን የማያስከፍል ድራማውን እያሳየ ለሴተኛ አዳሪዎች መሳለቂያና መደበሪያ ሆኖላቸው ነበር፡፡ መጀመሪያ ቀይ አጣብቂኝ ሱሪ ለብሳ ፀጉሯን እንደ ገዳይ ጐፈሬ ወዳቆመችው ሴት ቤት ጥልቅ ብሎ ገባ..
ሰካራሙ ታከለ ትዳሩን በመጠጥ ምክንያት ካፈረሰ በኋላ መቅኖ አጥቶ በደሞዝ ሰሞን ሲጠጣ፣ያገኘውን ሲጋብዝ፣ ሲሸልም፣ ሲበትን ይከርምና
ባዶ ኪሱን ጨረቃ አስመስሎ መውጣት ልማዱ ነው። እንደምንሽንሽ ሲለይለት አንድ ሀሙስ ብቻ ነው የቀረው፡፡ ሴትዮዋ በሯን ዘጋችና...
“እሺ ሂሣብ በቅድሚያ!” አለችው።
“ም. ን. ድ. ነው... ቅርሚያ ቅርሚያ! የምትይው? እኔን አታ..
አታምኝ.. ኝ.. ኝምምም?” አላት ልፍድድ ባለ የስካር ንግግር።
“ኡፋ! ሰውዬ ወሬ አታብዛ ! የምትከፍል ከሆነ በቅድሚያ ክፈልና እሺ። አለበለዚያ ውጣልኝ!ገበያዬን አትዝጋ!” አለችና አንባረቀችበት። ታከለ በጠጅና በአረቄ ብዛት የደነበሹ ዐይኖቹን ብልጥጥ አድርጎ ሲመለከታት ተንኮል የቋጠረ አመፀኛ ዝንጀሮ እንጂ ለጉዳይ የገባ እንግዳ አይመስልም ነበር።
በል ተናገር?! ያለበለዚያ ውጣ!” የዘጋችውን በር መልሳ እየከፈተች ጭኽችበት።
“ቆይ .. እ- ሺ ቆይ! ቆይ!” አለና ወደ ኪሱ ገባ፡፡ ያገኘው ሰላሳ አምስት ሣንቲም ብቻ ነበር።
እሺ ያው..ልሽ!
አትፈልጊምምም.?” እየተንተባተበ፡፡ ብልጭ አለባት።
ከኋላው አሽቀንጥራ ስትወረውረው ከፊት ለፊቱ ካለው ቆሻሻ ውሃ ከሚ ወርድበት ቦይ ውስጥ ሂዶ ተወተፈ፡፡ ከዚያም እየተውተረተረ ተነሳና ሣንቲምቹን መለቃቀም ጀመረ፡፡ እንደምንም ብሎ ሃያ አምስት ሣንቲም አገኘ።
ትርዒቱን እያዩ ወደሚሳሳቁት ግራና ቀኙን ወደተኮለኮሉ ሴተኛ አዳሪዎች እየተመለከተ“ይህቺን... ፈላጊ!.. ይህቺን... ይህቺን.” እያለ ሳንቲ ሞቹን ሽክ... ሽክ... ሽክ ሲያደርጋቸው የበለጠ በሳቅ ፈነዱ።
“አንተ ጠንባራ ሰካራም ድራሽህ ይጥፋ! የቀረችህ እሷ ናት። ሂድና ለሚስትህ ቀሚስ ግዛበት ፉዞ!” የስድብ መአት አወረዱበት። እሱም እየተንገዳገደ ቁልቁል ወረደ። ታደሰ ይህ ትርዒት የሚካሄድበትን አካባቢ
አልፎ ወደ ሰላማዊት ዘንድ ሊደርስ ትንሽ ቀርቶታል። አስፋልቱን ከመሻገሩ በፊት ግን ቆም ብሎ ምን ይዞላት እንደሚሄድ አሰላሰለ። እንደ
ሴተኛ አዳሪነቷ ሳይሆን እንደ ሚስቱ ያስብላት ስለጀመረ ወደ መኖሪያ ቤቱ የሚሄድ አባወራ እንጂ ወደ መሸታ ቤት የሚሄድ ጠጪ አይመስልም ነበር፡፡ ሰላማዊትም ከልቧ ስለምትወደው እሱ ከመጣ ሌላው ጠጪ
ሰው መስሎ አይታያትም፡፡ እንደሚጨነቅላት ስለምታውቅ አፀፋውን ፍቅር እየሰጠችው ነው፡፡ ታደስ ከእማማ ወደሬ ቤት ከፍ ብሎ ወደሚገኘው ሉካንዳ ቤት ገባና ከሽንጥ ሥጋ ላይ ሁለት ኪሎ ግራም አስቆርጦ አስጠቅልሎ ሄደ። ወይዘሮ ወደሬ የታደሰ ውለታ እየከበዳቸው ስለመጣ በሱ ምክንያት ሰላማዊትን ማክበርና መፍራት ጀምረዋል። ታደሰ ወደ ቤት ሊገባ ካለ በኋላ ምናምን እንዳቋረጠው ሰው ወደ ኋላው ሰግጠጥ አለና ቆመ፡፡ቀስ ብሎ በጓሮ በኩል ዞረ። የጓሮውን በር ያለሱ የሚደፍረው የለም።
“ሰላምን ጥሪያት” አላት ላፅጌ። ሰላማዊት ፅጌ ስትነግራት ሮጣ መጣች።
“ውይ ታዴ!”እቅፍ አድርጋ ሳመችውና በእጁ የያዘውን ተቀበለችው።
በጓሮ በኩል ዞሮ የገባው የያዘውን ሊሰጣት መሰላት። ድርጊቱ የበለጠ ገረማት። ማንም እሱ የሚያደርገውን አያደርግላትም። የፈለገውን ያክል ገንዘብ አስታቅፈዋት ቢሄዱ ታደሰ የሚያስበውን ያክል አስበውላት አያውቁም፡፡ በበዓላት ቀን ሹልክ ብሎ ይመጣና ገንዘብ ይሰጣታል። እንዳይደብርሽ እያለ ትያትርና ሙዚቃ ቤት ወስዶ ያዝናናታል፡፡
“አይ ታደሰ?አሁንስ አበዛው ምነው እሱ እንዲህ ተጨነቀ? እኔ ውለታ
ሲበዛብኝ ደስ አይለኝም፡፡ ይከብደኛል። ከሌላው የተለየ ለሱ ምን የተደረገለት ነገር አለ?” ወይዘሮ ወደሬ ስለታደሰ ተጨነቁ፡፡
“ታድዬ እቤት ትገባለህ ወይስ እዚሁ ጠላ ይዤልህ ልምጣ?” ስትል ጠየቀችው።
“እቤት አልገባም እዚችው ጓሮ ቁጭ ብለን ትንሽ አጫውቺኝና ጠላ ጠጥቼ እሄዳለሁ” አሁን አሁን የገባው ጠጪ ሁሉ እንደፈለገው እየጎተተ ሲያሻሻት፣ ሲያቅፋት፣ ሲስማት፣ ሲደባብሳት ማየት እያስጠላው መጥቷል።
“እሺ የኔ ቆንጆ ይዤልህ ልምጣ” አለችና ተመልሳ ገባች።
“ታዴ ወደ ቤት አይገባም እንዴ ሰላም?” አሉ ወይዘሮ ወደሬ።
“ውጭ ይሻለኛል ብሉኝ እኮ ነው”

“አይበርደውም እንዴ?እዚህ ከሰው ጋር እየተጫወተ አይሻለውም?” አሉ የታደሰን ስሜት በሚገባ ያላጤኑትና ቅናት ትንሽ በትንሹ እየቆነጠጠው
የመጣ መሆኑ ያልገባቸው አሮጊት።ሰላማዊት ታደስን ያገኘችው በዚህ ሥራ ከተሰማራች ከአራት ዓመት በኋላ ነው። ባሳለፈችው የሴተኛ አዳሪነት ህይወት ውስጥ በፍቅር አበድንልሽ፣ ተቃጠልንልሽ የሚሏት ጥቂቶች አይደሉም፡፡ አንዳቸውም ቢሆኑ ግን እንደ ታደስ ሲያስቡላትና ሲጨነቁላት አልታዩም፡፡ ከታደሰ ጋር ከተዋወቁ ከስድስት ወር በላይ ሆኗቸዋል።
እየዋለ ሲያድር ታደሰን የሚሰማው ስሜት እየተለወጠ መጥቷል፡፡ ከሱ ሌላ ማንም ወንድ እንዳይነካትና ቀና ብሎ እንዳያያት ነው ፍላጐቱ፡፡
“ሥራ እንዴት ነው ታዴ?” አላችው እዚያው በጓሮ በኩል ከቤቷ ውሃ ልክ ላይ ተቃቅፈው እየተጨዋወቱ፡፡
“በጣም ጥሩ ነው በሁሉም ነገር እግዚአብሔር እየረዳኝ ነው። ገንዘብ አጥቼ አላውቅም፡፡ ፍቅር ከአንቺ አገኘሁ። የአእምሮ ሰላም የሚያሳጡኝን ነገሮች ቀስ በቀስ እያስወገድኳቸው ነው” ታደሰ ሽፍን ኮፍያ ከአናቱ፣ ፎጣ ከአንገቱ፣ ካፖርት ከትከሻው ላይ ተለይቶት አያውቅም፡፡ይህ አለባበሱ ደግሞ ራሱን ከብርድ ለመጠበቅ ሳይሆን ራሱን ላለማሳወቅ የሚያደርገው ጥረት ይመስል ነበር፡፡
“ታዴ ለፋሲካ እዚህ አድረህ አብረን ነው የምንፈስከው አይደል?”
“ስላምዬ እግዚአብሔር የልቤን ያሳካልኝ እንጂ ከፋሲካ ወዲህ ሳንጠቃለል እንቀራለን ብለሽ ነው? እስከዚያ ድረስማ አንቆይም” ሰላማዊት በታደስ
አነጋገር ውስጥ ውስጡን በደስታ ተፍነከነከች። አብራው እስከ መጨረሻው እንድትኖር ፍላጉቱን ሲገልፅላት አንቃ ልትስመው ከጀለች። ከዚህ እንደ ኮሶ ከመረራት ህይወት ተላቃ ከምታፈቅረው ሰው ጋር በትዳር
ተሳስራ የመኖሩ ጉጉት እንደ ህልም ሆኖ በሚታያት ሰዓት ይህንን የምስራች ሲያበስራት ብድግ ብላ እልልታዋን አታቃልጠው ነገር ውስጧ
በደስታ እየፈነደቀ አውቃ ልትሽኮረመም ፈለገች፡፡
ትቀልዳለህ እንዴ ታዴ? ዝም ብሎ ተያይዞ መሄድ አለ እንዴ? ይሄንን
ስታስብኮ በቅድሚያ ማጣራት ያለብህ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ መጀመሪያ የኔን ሀሣብ ከዚያ የእማማ ወደሬን ፈቃድ ከዚያ..በቃ ብዙ ነገሮች ...
“ዐይኖችዋን በፍቅር ስልምልም አድርጋ ከንፈሩን ሳመችው።
“ስላምዬ ያንቺን ሀሳብ አውቀዋለሁ እኔ እንደማስበው ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ፍቅር በመካከላችን እስካለ ድረስ ሃሳባችን የሚለያይ አይ መስለኝም፡፡ እትዬ ወደሬም ቢሆኑ እኔና አንቺ ከምናስበው ውጭ ያስባሉ ብዬ አልገምትም” እሱም ሳም አደረጋት። ቤት ተከራይቶ ጥቂት ከተደራጀ በኋላ በባልና ሚስትነት ተጠቃለው አብረው እንዲኖሩ እንጂ ከሚንጋጋው ጐረምሳ መንጋጋ የሚወዳትን ልጅ እንደ ቀበሮ እየተናጠቀ
መዝለቅን አልፈለገውም፡፡
“ኡ...ኡ! ያዘው! ...በለው! ሄደ! ኳኳ. ኳ ጓ ጋ.…......….በወይዘሮ ወደሬ ቤት ውስጥ ባሉት ጠጪዎች መካከል ፀብ ተፈጠረና ቤቷ በኳኳታ ተሞላች፡፡
“ወይኔ ታድዬ!” ሰላማዊት ደነገጠችና ታደሰ ጉያ ውስጥ ሽጉጥ አለችበት፡፡
“ደስ! ታደሰ! ምነው ዝም አልክ? ኸረ እባክህ እቃዬ አለቀ! ” ወይዘሮ ወደሬ ወደ ጓሮ ወደ ታደለ ሮጡ..ብርጭቆ፣መለኪያ፣ ጠርሙስ እንደ ድንጋይ ለመፈናከቻ አገልግሎት ዋሉ። የተሰረቀው ሰው ገዛኸኝን አንቆ
ይጮሃል “ገንዘቤን!.ገንዘቤ!..ብሬን!"
“አይዞዎት እማማ ረጋ ይበሉ ግድ የለም ይሄ የኔ ሥራ ነው።” አረጋጋቸውና ቆፍጠን ብሎ ወደ ውጭ ሮጠ፡፡ ከምንጊዜው ይዟቸው እንደመጣ
አይታወቅም። ሦስት የታጠቁ ፖሊሶች ደረሱ።
እጅ ወደ ላይ እንዳትንቀሳቀስ በታደስ ጥቆማ መሠረት ፖሊሶቹ በገዛኸኝ ግንባር ላይ ደገነበት።
እኔ አይደለሁም!እሱ ራሱ ነው! ወርውሮ የመታኝ!...እሱን ያዘው!”
ጮኸ፡፡ ታደሰ ገዛኸኝን በደንብ ያውቀዋል። ያሰለቸ ኪስ አውላቂ ነጣቂ ነው። ፀቡ ሊነሳ የቻለው እዚያ መጠጥ ቤት ውስጥ ከጉኑ ቁጭ ካለው ጠጪ ኪስ ሃምሣ ብር መንትፎ በአጋጣሚ ተነቅቶበት ነው። ሰውዬው
አንገቱን አንቆ ጮኸ፡፡
“ሌባ! ሌባ! ገንዘቤን! አምጣ! ገንዘቤን!” ተጠመጠመበት። በዚህ ጊዜ ከጉኑ የነበረው የሌባው ጓደኛ አየለ ገንዘቡ የተሰረቀበትን ሰውዬ በቦክስ አፍን
ጫው ላይ ሲያጐነው የመለኪያና የብርጭቆ ጦርነቱ ተነሣ። ታደሰም
ወደ ጓሮ የዞረው ለካስ ገዛኸኝን ስላየው ነበር፡፡ ይሄ ነገር እንደሚፈጠር አስቀድሞ ስለገመተ ከጓሮ ቁጭ ብሎ በንቃት እየተጠባበቀው ነበር::
በዚሁ መስረት ገዛኽኝ ኪሱ ሲፈተሽ አራት ባለ አስር ብር ኖቶችና አስር ባለ አንድ ብሮች ተዘረፍኩ የሚለው ግለስብ በሰጠው ቃል መሠረት ሳይጨምር ሳይቀንስ አንድ ላይ ጥቅልል ብለው ተገኙ፡፡ ገዛኸኝም ከኋላው በፖሊሶች እየተገፈተረ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰደ።...
✨ይቀጥላል✨

👍4
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...«ሌላ ጊዜ በአዲስ መልክ እንጀምረዋለን:: አሁን ከቢሮዬ ውጣልኝ፡፡»
አስቻለው በባርናባስ ጥያቄ ተቻኩሎ ከመቀመጫው ቶሎ አልተነሳም፡፡
እንዲያም ለአፍታ ያህል ትኩር ብሎ ከተመለከተው በኋላ «ያልተወለደ ገዳይ አልከኝ? በማለት "መልሶ አስታወሰውና በቃ! ገላግየዋለኋ ፣ ያንን ሳይወለድ ሟች አለው ባርናባስ የሚሰጠውን ምላሽ በመጠባበቅ ትኩር ብሎ እያየው፡፡
«በመግደል!!»
«ቢወለድ ምን ያደርጋል? ያው አንተን ወይም እኔን ሆኖ መኖር ነው!»
«ስትል?»
«የአንተን ዕድሜ ቢያገኝ ሲበድል ይኖራል። የኔ ዕጣ ከደረሰው ደግሞ ሲበደል አየህ! በዚች አገር ሁለት ዓይነት አሰላለፎች አሉ በዳይና ተበዳይ።
የቁጥር ልዩነታቸው ግን የትየለሌ በዳዮች እፍኝ ተበዳዮች ግን እልፍ አዕላፍ፡ ታዲያ አዲስ መጪው ሰው ከእነዚህ የህዝብ ክፍሎች አንዱን ከመሆን የት ያመልጣል» ባርናባስ በቅድሚያ ስስ ከንፈሮቹን ወዲህ ወዲያ አሾራቸው፡፡
ቀጥሎም መነፅሩን ብድግ አድርጎ ወደ ዓይኑ እያስጠጋ ፍልስፍናውን ተወት አድርገህ ከቢሮዬ ብትወጣ የሚሻል መሰለኝ!» አለው፡፡
እስቻለው ለባርናባስ ማስጠንቀቂያ ብሎ ሳይሆን ጉዳዩንም ጨርሷልና ድንገት ብድግ እያለ አቶ ባርናባስ! ያልገባህን ሁሉ ከፍልስፍና የምትቆጥር ከሆነ ድንቁርናህን ያሳያል። እየገባህ ያልገባህ ለመምሰል የምትሞከርም ከሆነ የባሰ ትቀላለህ፡፡ ቅሌት ሲደጋገም መጨረሻው ሳይነሱ ሆኖ መውደቅን ያስከትላል፡፡» ካለ
በኋላ በዓይን የሚታይ በእጅ የሚዳሰስ ግልጽ ነገር ልትክድ ነው !?» ብሎት በሩን ከፍቶ ወጣና መልሶ ጓ አድርጎ ዘግቶት ሄደ፡፡
አስቻለጠ ከባርናባስ ክፍል እንደ ወጣ በንዴት ፈረስ ወደ አንድ አቅጣጫ እየተራመደ ነበር፡፡ ነገር ግን በዚያው በነበረበት ኮሪዶር ውስጥ ድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ። ያልተወለደ ገዳይነቱ ጉዳይ ስሜቱን ቆጠቆጠው፡፡ በዚህ ዙሪያ ለራሱ የሚያውቀው ነገር ባይኖርም ባርናባስ ግን ያለ አንድ ነገር እንዳላነሳው ገመተ፡፡ ብቻ
አንድ ነገር ታየው፡፡ ስለ ሁሉም ጉዳይ የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክተር ማነጋገር፡፡ በቀጥታ ወደ ዳይሬክተሩ ቢሮ እመራ፡፡
ዶክተር ደጀኔ አድማሱ ከሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተርነቱ በተጨማሪ የፖርቲ መሠረታዊ ድርጅት ሀለተኛ ፀሃፊ ነው ከባርናባስ ቀጥሎ ያለ የፖለቲካ
ባለ ስልጣን፡፡ ያም ህ'ኖ በሁሉም የሆስፒታሉ ሠራተኞች ዘንድ የሚወደድና የሚከበር ስው ነው። በሰከነ አመለካከቱና በረጋ አነጋገሩ የተመስገነ ነው፡፡
በዕድሜው ብዙ የገፋ ባይሆንም እንደ አባት የሚታይ ነው። እንደ አለቃ ሲያዝና ሲቆጣ አይታይም፡፡
ከዶክተር እስከ ዘበኛ ያሉትን የሆስፒታሉ ሠራተኞች በእኩል
ዓይን እያየ የማስተናገድ የተለየ ስጦታ ያለው ቅንና አስተዋይ ሰው ነው። በዚህ የተነሳ የሚያከብረው እንጂ የሚፈራው የለም::
ዶክተር ደጀኔ በተለይ ለአስቻለው ጥሩ አመለካከት አለው ሁለቱ በዲላ ሆስፒታል ውስጥ ከእራት ዓመት በላይ አብረው ሰርተዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ዶክተር ደጀኔ የእስቻለውን ማንነትና ምንነት እንዲሁም ሙያዊ ስነ-ምግባሩን
ከቅርብ ርቀት ተከታትሎታል። ስራውንና አሰራሩን ይወድለታል፡፡ የአቅሙን ያህል ሲፍጨረጨር ለብዙ ጊዜ አጢኖታል፡ በባህሪውም ትሁት መሆነን ታረድቶታል። ሙያዊ በሆኑና ባልሆነ ጉዳዮች ላይ ሃሳቦችን ሲያፈልቅና ደካማ መስለው በታዩት ላይ ሲከራከር በቅንነት መሆኑን ተገንዝቧል። ሀሳቡን ሲሰነዝር የማይፈራና
የማይጨነቅ ግልፅና ደፋር መሆኑን አጢኗል። ከሁሉም በላይ ሲዋሽና ሲያስመስል አይቶት ወይም ሰምቶት አያውቅም፡፡ ከዚህም አጠቃላይ ሁኔታ በመነሳት ለአስቻለው ጥሩ ስሜት አለው።
እስቻለው በር አንኳኩቶ ሲገባ ዶክተር ደጅኔ ብድግ ብሎ ተቀበለው፡፡
በእለቱ ቡላውን ካኪ ከውስጥ ለብሶ ከላይ ነጭ ጋዎን ደርቧል ፊቱ አነስ ያለችና ጠይም ነው። እንዲያውም አብዛኛው ፊቱ በረጅም ጥቁር ፂም የተሞላ በመሆኑ ያችው ትንሽና ጠይም ፊቱ ሁሌም ቦግ ብላ ትታያለች
ፀጉሩ ገባ በማለቱ ግንባሩ ሰፋ
ብሏል። ዓይኖቹ እነስ እነስ ያሉ ሆነው ነገር ግን ቁልጭ ያሉ ናቸው፡፡ አፍንጫው በፊቱ ልክ አጭር ናት። በጥቁር ፂም መሀል ብልጭ የሚሉት ጥርሶቹ ነጫጭ ናቸው ሁሉግዜ ፈገግታ አይለየውምና ደስተኛ ይመስላል
«ፈልጌህ ነበር ዶክተር» አለው አስቻለው ተጨባብጠው ከጨረሱ በኋላ፡ ይቻላል፡፡ ቁጭ በል!» ሲል ዶክተር ደጀኔ አስቻለው እንዲቀመጥ ጋበዘው፣ በግራ እጁ ፊትለፊት ግድግዳ ሥር የተቀመጠ ሶፋ እያሳየ።
እስስቻለው ሊቀመጥ ወደ ሶፋው ሲያመራ እንኳ ስሜቱ ጥሩ እንዳልሆነ አረማመዱ ያስታውቃል። ፈጠን ፈጠን ብሎ አተራመደ በኋላ ሶፋው ላይ ዘፍ
ብሎ በመቀመጥ የፊቱን ላብ በእጁ ይጠርግ ጀመር። ከንፈሩንም ደጋግሞ በምላሱ
ያርሳል። ዓይኖቹም ፍጥጥ ብለዋል። የአስቻለውን የውስጥ ስሜት የተረዳው
ዶክተር ደጀኔ ለእፍታ ያህል ትኩር ብሎ ከተመለከተው በኋላ፡-
«ምነው አስቻለው! ሰላም አይደለህም?» ሲል ረጋ ባለ አነጋገር ጠየቀው።
«ፍፁም ደህና እይደለሁም!» አለው እስቻለው ቁጭ ባለበት እየተቁነጠነጠ፡፡
«ምነው ምን ሆንክ?»
«በዚህ ሆስፒታል ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደሆን ሊገባኝ አልቻለም
ዶክተር። በጣም ግራ ተጋባሁ፡፡
«እንዴት?»
«በቃ! አልገባኝም!
ዶክተር ደጀኔ የአስቻለውን አኳኋን ሲመለከት ቆየና «ስማ አስቻለው!» ሲል ረጋ ባለ አነጋገር ጠራው።
«አቤት!»
«የዲላ ሆስፒታል ትልቅ ተቋም ነው። ከስልሳ በላይ ሠራተኞች አሉት። በርካታ ህመማን ይመላለሶበታል። አስታማሚዎችም እንዲሁ፡፡ አልፎ አልፎም የሥራ ሃላፊዎችና የፖለቲካ ባለ ስልጣኖችም ብቅ ብቅ ይሉበታል። በአጠቃላይ ብዙ
የሰው ዓይነት የሚመጣበትና የሚቀበል ትልቅ መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡ ታዲያ ዛሬ በእያንዳንዳችን የግል ህይወት ዙሪያ፣ በእያንዳንዳችን ቤትና ግቢ ውስጥ ምን እየተካሄደብን እንደሆነ እንኳ በውል የማናውቅበት ጊዜ ላይ ሆነን በዚህ ትልቅ ተቋም ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ነገር መረዳት ሲያቅተን ምን ያስገርማል!» ሲል
ጥያቄ አዘል በሆነ አስተያየት ስሜቱን ገልፀለት።
አስቻለው በዚህ የዶክተር ደጀኔ ንግግር ለአጠቃላይ ችግሩ አጠቃላይ መፍትሄ ያገኘ ያህል ደስ አለው:: እጅግ በጣም ረካ፡፡ በንዴትና በብስጭት ውጥርጥር ብሎ የነበረ ሰውነቱ ላላ ረጉብ ሲል ተሰማው፡፡ አተነፋፈስም ወደ
መደበኛ ፍጥነትና መጠን ተመለሰ። ዓይኖቹ ራሳቸው እንደገና ሲደላደለ ተሰማው::
አቀማመጡንም በአዲስ መልክ አስተካክሉ በረጅሙ ተነፈሰና
«ታዲያ ምን ብንሆን፣ ወዴትስ መሄድ ይሻለኛል?» ሲል ዶክተር ደጀኔን በትካዜ ዓይን እያየ ጠየቀው።
ምን መሆን እንዳለብን መናገር የምችል አይመስለኝም፡፡ መሄጃው ግን ላይገድ ይችላል፡፡ ችግሩ የተሻለ ቦታና ሁኔታ ማግኘቱ ላይ እንደሆነ እንጂ!» አለ ዶክተር ደጀኔ ሃሳብ ውስጥ የገባ እየመሰለ ጣሪያ ጣሪያ በማየት፡፡
አስቻለው ለችግሩ መፍትሄ ሊፈልግ የገባበት ቢሮ በሌላ ችግረኛ የተያዘ እስከሚመስለው ድረስ ዶክተር ደጀኔ እሳዘነው:: ከፊቱ ላይ የሚያነብበው ትካዜና

ከእነጋገሩ የሚረዳው የውስጥ ስሜት ራሱን መልሶ አስጨነቀው፡፡ በዚሁ ስሜት ውስጥ ሆኖ እያየው ሳለ ዶክተር ደጀኔ ፊቱን ወደ አስቻለው መለስ አደረገና፡፡
ግን የዛሬው የተለየ ችግርህ ምን ሆኖ ነው እኔን የፈለከኝ? ስሜትህም ጥሩ እንዳልሆነ ይሰማኛል::» ሲል ጠየቀው፡፡
የዚህ የጤና መኮንንነት ኮርስ ውድድር ውጤት አናደደኝ:: አንተ ደግሞ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ነህና ቢያንስ ቢያንስ ሙያ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ
እንዴት የመወሰን ስልጣን እንዳጣህ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ አመጣጤም ለኔ የማይገባኝ
የተለየ ችግር ካለብህ ብትገልፅልኝና ቁርጡን አውቄው ባርፍ ብዬ ነው፡፡ ምናልባት
ተገቢ ያልሆነ ጥያቄ አቅርቤልህ ከሆነ ይቅርታ!» አለው የይቅርታ ጥያቄው ከልብ የመነጨ መሆኑን በሚገልጽ አስተያየት እያየው፡፡
ዶክተር ደጀኔ የአስቻለው ጥያቄ ተገቢ መሆኑንና የዛሬም አመጣጡ ለዚሁ ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል ገና ሲገባ ጠርጥሮ ስሰነበር ሀሳቡ እንግዳ አልሆነበትም፡፡
ብዕሩን ከጠረጴዛው ላይ አንስቶ በጣቶቹ መሀል እያሽከረከረ በረጅሙ ተነፈሰና፡
«ከፋህ አይደል?» አለው አስቻለውን በይቅርታ ዓይን እያየ፡፡
«ተቃጠልኩ! እንዲያውም አመመኝ»
ዶክተር ደጀኔ አሁንም በረጅሙ ተነፈሰና «አይፈረድብህም አስቻለው!»
ብሎት በሁለት የእጅ መዳፎች ሙሉ ፊቱን ሸፍኖ ያስብ ጀመር፡፡
«ዶክተር!» ሲል እስቻለው ከሀሳቡ መለሰው፡፡ ዶክተር ደጀኔ አስቻለው
የሚለውን ለመስማት ትኩር ብሎ እያየው ሳለ አስቻለው ቀጠለ፡፡ «ይህን ውሳኔ እኮ
እንደማታምንበት ልቤ ይረዳል፡፡ እንደሚያስጨንቅህም እገነዘባለሁ፡፡ በዚህ ምክንያት
ልወቅስህም አልመጣሁም፡፡ የቆጨኝ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ሳነጋግረው ባርናባስ የሰጠኝ ምላሽ» ብሎ ሳይጨርስ ዶክተር ደጀኔ ድንገት አቋረጠው።
«አነጋገርከው?» ሲል ቀልጠፍ ብሎ ጠየቀው፡፡
«አዎ፡፡»
«ምን አለህ ታዲያ?»
«ጭራሽ ያልተወለደ ገዳይ ብሎኝ አረፈ፡፡»
ዶክተር ደጀኔ ቅስሙ ስብር ከለ፡፡ የውድድሩን አሸናፊ ለመምረጥና ቃለ ጉባዔ ለማፅደቅ በተገኘበት የኮሚቲ ስበሰባ ላይ በአንዳንድ ነርሶች የሥነ ምግባር ዙሪያ ውይይት ሲደረግ በእስቻለው ላይ እንዲህ ያለ አሉባልታ ሲነገር ሰምቷል።
በወቅቱም ሁኔታው እሳዝኖት ነበር። ለነገሩ በስብሰባም ላይ ጉዳዩ ሲነሳ በአሉባልታ ደረጃ የተጠቀሰ መሆንን ቢረዳም አስቻለው ይህን ነገር ቢስማው ምን ያህል ሊያሳዝነው እንደሚችል ተሰምቶት ሆዱ ፈርቶ ነበር፡፡ ለካ ባርናባስ አንስቶ
የአስቻለውን ስሜት ጎድቶታል፡፡
«ግን በዚህ ነገር የተነሳ ምንም እንዳይሰማህ እስቻለው፡፡» አለ ዶክተር ደጀኔ አስቻለውን በማፅናናት ዓይነት፡፡
«ያልተመረጥኩት በዚህ ምክንያት ይሆን?"....

#ክፍል_ሃምሳ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ከቀኑ አስራ አንድ ሰዓት ሆኗል። እማማ ወደሬ የፀበል ፃዲቅ ተጋባዦቻቸውን ለማስተናገድ ጉድ ጉድ እያሉ ናቸው። ወዳጃቸው ታደሰንም ፀበል ቅመስልኝ ብለው ስለጠሩት በጊዜ ተገኝቷል። ሌሉች ፀበል ፃዲቅ እንዲቀምሱ የተጠሩ እንግዶችም የእማማ ወደሬን ቤት አጨናንቀዋታል።ከፊሉቹ ደጅ አግዳሚ ወንበር ላይ ተኰልኩለው ጠበል ጠዲቁን እየቀማመሱ ይጨዋወታሉ።
ጥሪ ሳይደረግለት ፀበል ፃዲቅ ለመቅመስ በራሱ ፍላጐት የመጣ እንግዳም አለ፡፡ እብዱ ምንሽንሽ፡፡ ከአጥሩ ውጭ ድንጋይ ላይ ተቀምጧል።የሰፈሩ ስዎች ለምደውታል፡፡ እሱም ለማዳ እንስሳ እንጂ እንደ እብደቱና እንደ አስፈሪነቱ ተናካሽ አውሬ አልነበረም፡፡ የአንዳንዱ እብድ ጥሩ ፀባዩ ስው ያለመንካቱ ጉዳት ያላማድረሱ ሲሆን አንዳንዱ እብድ ደግሞ ስው አያሳየኝ በሚል ልክፍት የተለከፈ ይመስል ድንጋይ ተሸክሞ መንገደኛውን ሁሉ ሲያስበረግግ የሚውል ነው። ምንሽንሽ በፍፁም ሰው አይነካም፡፡ ዛሬም እንደ ወትሮው ሰውነቱ በምናምን ተድበስብሶ አመድ ላይ የተንከባለለች እንትን መስሏል፡፡ ወይዘሮ ወደሬ ወደ ደጅ ወጣ ሲሉ ምንሽንሽን አዩት።
“ምንሽንሽ እንደምን ዋልክ?! እንካ!” አሉና ኩባያ አቀበሉት። ምንሽንሽ አንገቱን በአክብሮት አቀርቅሮ ኩባያውን ተቀበለ። የሚያውቁት ምንም ።መስሎ አይታያቸውም። የማያውቁት ግን ድንገት ሲያዩት ይደነግጣሉ።
ምንሽንሽ ዛሬም የለበሳት ያቺኑ ቀንም ሆነ ማታ ከላዩ የማትወልቀውን፣ ጭቅቅት የበላትና የተበጫጨቀች ሱሪውን ነው፡፡ ፀሀይ አያቃጥለው፣
ብርድ አይበርደው፣ ቅማል አያሳክከው ለሁሉ ነገር ደንታ ቢስ ነው።ከላይኛው ከንፈሩ ላይ የበቀለው ጢሙ አድጎ የተዘቀዘቀ የፍየል ቀንድ መስሏል። ፊቱም ደም የማይዘዋወርበት ያልታሸ ቁርበት መስሏል።
በስመአብ ወልድ አለች ከዚህ ቀደሞ ምንሽንሽን አይታ የማታውቅ አንድ ልጅ እግር የጠበል ጠዲቅ ተጋባዥ በግርምት አፏን በእጅዋ እየሽፈነች
አይዞሽ ምነው?አታውቂውም እንዴ ምንሽንሽን?” አጠገቧ የነበሩት አሮጊት በድንጋጤ የተሸማቀቀችውን ልጅ አተኩረው እያዩ።
“አሁን ተነስቶ በድንጋይ ቢጨርስንስ?!” አለች በፍርሀት ተውጣ፡፡
“አይዞሽ የኔ ልጅ አትፍሪ ምንሽንሽ ድንጋይ ይዘሽ ብታሯሩጪው እንኳ
የሚሸሽ እንጂ የሚተናኮል አይደለም፡፡ አህያ ነው” በማለት ሊያረጋጓት ሞከሩ፡፡የአሮጊቷ አነጋገር ልጅቷን ሊያረጋጋት አልቻለም፡፡ እሷ እንደዚያ
ተጨነቀች እንጂ ምንሽንሽ እንደሆነ ዳቦ እየገመጠ በጠላ ከማወራራድ ውጪ የሚያስበው ሌላ ጉዳይ፥ አልነበረውም። ሀሣቡ በሙሉ በጠላውና በዳቦው ላይ ተጠምዷል። ሌሎቹም እንደ ዝንጀሮ ቁጢጥ ብሉ ዳቦውን
ስለሚገምጠው እብድ እያወሩ ነበር።
“ፍቅር ነው ያሳበደው ይባላል!” አለ አንዱ።
“ፍቅር ደግሞ ያሳብዳል እንዴ?” ሌላው።
“እሱን የደረሰበት ነው የሚያውቀው። ምን ማለትህ ነው? እንኳን ማሳበድ ህይወት ያስጠፋ የለም እንዴ? ሮሚዎና ጁልዬትን አላነበብክም መሰለኝ፡፡ኦቴሎ ዴዝዴሞናን የገደላትና በኋላ የሞተላት በፍቅር ምክንያት አይደለም እንዴ? ፍቅር ይዞህ አያውቅ እንደሆነ እንጂ!”
“ምንሽንሽን በጤነኛነቱ ጊዜ እናውቀዋለን የሚሉ ሰዎች ሲናገሩ የሰማሁት አንተ ከምትለው የተለየ ነው ! ብዙ ሰው የገደለ አረመኔ ነበር አሉ፡ የሟቾቹ ዘመዶች ተከታትለው ሊያገኙት ባለመቻላቸው በሴት ካጠመዱት በኋላ መድኃኒት አጠጥተው ጨርቁን ጥሎ እንዲሄድ አደረጉት
ሲባል ነው የሰማሁት”
“አቤት! አቤት! የሰው ወሬ” አለ ከወዲያ ማዶ የተቀመጠው፡፡ እሱ
ስለምንሽንሽ የስማው ሌላ ነበረ። ሰው እየፈጠረ የሚያወራው ወሬ አስደንቆት “በእናታችሁ ስው ዝም ብሎ ሲያወራ አይገርምም? እኔ የሰማሁት እናንተ ከምታወሩት ፍፁም የተለየ ነው። ሰውዬው በጣም የተማረና ፈረንጅ አገር ብዙ ዓመት የኖረ ነው አሉ፡፡ ያበደው ደግሞ በትምህርት ብዛት አንጐሉ ተቃጥሎ ነው አሉ” ሌሎቹ የተናገሩት ሀሰት፣
ሌሎቹ የሰሙት የፈጠራ ወሬ እሱ የሰማው ወሬ ግን እንከን የሌለበት
እውነተኛ ታሪክ መሆኑን ለማስረዳት ቀበጣጠረ፡ታደስ ስለ እብዱ ምንሽንሽ የተለያዩ ወሬዎችን ሰምቷል፡፡ እሱ የሰማውንም ያልሰማውንም እየ
ጨማመሩ ሲያወሩ እያዳመጠና እሱ የሚያውቀውን እውነታ በልቡ እያብሰለስለ አይ መቀስ?አይ አንበሴ? መጨረሻህ እንደዚህ ይሆን? ሲል በልቡ አወራ፡፡ የእብደቱ መንስኤ በትምርት ብዛት አለመሆኑን በሚገባ ያውቃል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን እንደሚባለው ወይ በፍቅር፣ ወይ በጭካኔ፣ወይ በመድኃኒት ወይንም ደግሞ በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች በእብደት ላይ ሌላ እብደት እየጨመረ፣ የእብደትን ሪኮርድ የሰበረ አዲስ ፍጡር ስለመሆኑ ግን እርግጠኛ መሆን አልቻለም፡፡ ምናልባት በፍቅር ማበድ
ከዚያም መዳን፡፡ቀጥሎ በመድኃኒት ማበድ ከዚያ መዳን፡፡ ከጭካኔ ብዛት ለእብደት ተዳርጎ ጨርቅ መጣል...ማን ያውቃል ሌላውም እንደዚሁ ስለ ምንሽንሽ ቢጠየቅ ሌላ የእብደት ምክንያት ሊጨምርለት ይችላል።
“ስላምዬ አንቺስ ስለምንሽንሽ እብደት የሰማሽው የለም?” እየሳቀ
ጠየቃት፡፡
ገለል ብለው ሁለቱ ከቤቷ ጥግ ላይ ተቀምጠው ነበር፡፡ ሰላማዊትም እየሳቀች “አይ ታዴ? እንኳንስ ስለምንሽንሽ እብደት ላጠና ይቅርና ስለ ራሴ
ህይወት ስለ ራሴ እብደት የማሰላስልበት ጊዜ የለኝም”
“አንቺ ደግሞ ታሳብጃለሽ እንጂ ታብጃልሽ እንዴ ሰላም?”
“ማንን ነው ደግሞ የማሳብደው?” ጨዋታውን ወዳዋለች። የታደሰን
የፍቅር ጽናት ከአንደበቱ እንደ አዲስ መስማት ያስደስታታል።
“ፍቅር እንደሚያሳብድ እየሰማሽው መሰለኝ?”
“እና?”
“ያው ነዋ! ፍቅርሽ እኔንም እንዳያሳብደኝ ማሰብ አለብሽ”
“ያንተን ፍራልኝ እንጂ የኔ እንደማይነካህ እርግጠኛ ነኝ ታዴ። ስውን የሚያሳብድ ፍቅር የፍቅር ወንጀለኛ ነው፡፡የኔ ፍቅር ወንጀለኛ ሳይሆን ጤናማ ፍቅር ነውና አይዞህ አትፍራ” እብዱ ምንሽንሽን በሃዘኔታ እያስተዋለች ሳም አደረገችው።
ልክ ነሽ ስላም ጤናማ ፍቅር አፍቃሪና ተፈቃሪን የሚያስጨንቅ የሚያሳብድ መሆን የለበትም፡፡ጤናማ ፍቅር መተሳሰብን ኣንቺ ትብሽ አንተ ትብስን የሚፈጥር በጋብቻ አጣምሮ ቤተሰብን ለማፍራት የሚያስችል የህይወት ቅመም ነው”
“በትክክል”
“እና?”
“እናማ ያው እንዳልከው ነዋ ታዴ!”
“ያንቺ ሃሳብ ምንድነው ሰላም? የኔን ዳር ዳር እያልኩ ስገልፅልሽ ኖሬአለሁ። የኔ ብቻውን ደግሞ ውጤት ሊኖረው ስለማይችል በአንድ እጅ ማጨብጨብ እንዳይሆን እሰጋለሁ”
“ታዴ ዛሬ እኮ ፀበል እንድትቀምስ እንጂ ሚስት እንድትለምን አልተጠራህም” የተለመደውን የከንፈር ካሳ ልትሰጠው አንገቷን ቀና ካደረገች በኋላ መቅበጥ መሰላትና እያማራት ተወችው፡፡ ይህንን የሚጨዋወቱት
ሰው እንዳይሰማቸው አፍ ለአፍ ገጥመው ነበር፡፡
“የምጠጣው ጠላ አስካሪ ፈሳሽ ሳይሆን ፈዋሽ ፀበል እንዲሆንልኝ በዛሬዋ ዕለት ሃሳቤን ልትደግፊ ምኞቴ ምኞትሽ ሊሆን በእትዬ ወደሬ የማርያም ፀበል ፍቅራችን እንድትለመልምና አንድ ሆነን እንድንጠመቅ ፍላጐትህ
ፍላጐቴ ነው በይና ቃል ግቢልኝ...”
“ተነስ ወደ ጓዳ እንግባ!” እጁን ሳብ አድርጋ አስነሳችው፡፡ አነጋገሩ ልቧንነካው። የሆነ ስሜት ተሰማት፡፡እንዲህ እንደዋዛ እሱ ደጋግሞ እየጠየቃት እሷ እየሳቀች ስታሳልፈው እውነቱ ሁሉ ቀልድ ይሆንና እምቢ ካለችኝ ሁለተኛ አልጠይቃትም ይልና በእማማ ወደሬ የማርያም ፀበል ስትይ የልብሽን ግለጭልኝ እያለ ሲማጠናት አይሆንም ብትለው በዚያው አኩርፎ እስከ መጨረሻው የሚሄድ መሰላትና ሃሳቧን ልትገልፅለት ምኞቷን ልታስረዳው ማንም ሰው ወደሌለበት ወደ ጓዳዋ ውስጥ ይዛው ገባች።ቀና ብላ

👍5
ልብ በሚሰርቁ ዐይኖቿ በልምምጥ አስተያየት ተመለከተችው።
“ታድዬ እውነቱን ንገሪኝ ነው ያልከኝ?”
“አዎን የኔ ቆንጆ እስቲ ዛሬ ደስ ይበለኝ” ትክ ብሎ ተመለከታት። ከዐይኖቿ ውስጥ ፍቅሯን፣ ከዐይኖቿ ውስጥ ፍላጐቷን፣ ከዐይኖቿ ውስጥ ስሜቷን አጠናው፡፡ሀሳቡን እንደተቀበለችው ፍላጐቱ ፍላጐቷ እንደ ሆነ ልትገልጽለት ቀና ስትል ዐይኖቿ እንባ ቋጠሩባት። የፍቅር እንባ፣
የደስታ እንባ፣ የሀሴት እንባ... አጋር መከታ የሚሆን፣ የሚወድ፣የሚያፈቅር ባል በባልነቱ ብቻ ሳይሆን በብዙ ነገር አለኝታ ነው፡፡ እንደ አባት እንደ ወንድም የሚያኮራ የሚያፅናና እንደ እናት የሚያስብ እውነተኛ ባል መመኪያ ነው።
ሰላማዊት መድረሻ አጥታ የኑሮ ዝቃጭ የሆነው የሴተኛ አዳሪነት ኑሮ አስጠልቷት አንገሽግሿት መውጫ ማምለጫ ስትፈልግ ታደሰን የመሰለ እውነተኛ ፍቅርን እየለገስ ከዚህ አስከፊ ኑሮ ምንጥቅ አድርጎ አውጥቶ
ለትዳር የሚያጫት አፍቃሪ ሲጥልላት እንዴት እምቢ ትበል? ጭካኔውን ከየት ታምጣው?
ከደስታዋ ብዛት የተነሳ እምባዋ በዐይኖቿ ግጥም ብሎ ሞላ፡፡
“ሀሳብህ ሀሳቤ ምኞትህ ምኞቴ ነው ታድዬ” ከንፈሩን ስትስመው በዐይኖቿ ላይ ያጤዙት የእንባ እንክብሎች ክብልል...ክብልል. እያሉ ወረዱ.....
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
መርካቶ እንደ ልማዷ በመተራመስ ላይ ትገኛለች። የእህል በረንዳ
በጆንያ ተጣቧል፡፡ ከየጠቅላይ ግዛቱ በመጡ የጭነት መኪኖች ተሞልቶ መረማመጃ የለም፡፡ የእህል ነጋዴዎች ለስንዴው ለገብሱ ለጤፉ ለማሽላው ለአተር ለባቄላው... በአጠቃላይ ለእህል ዘር ባወጡት ተመን መሠረት ጆንያው ከሚዛኑ ላይ በግዙፍ ተሸካሚዎች እየወደቀ ሲነሳ
መቶ ኪሎ ግራም የሚመዝን መሆኑ አጠራጣሪ ነው፡፡ በእህል በረንዳ አካባቢ በድለላ ሥራው ወደር የማይገኝለት ቀልጣፋው ታደሰም በነጋዴዎችና በሻጮች መካከል እየተራወጠ የድለላ ሥራውን ያቀላጥፈዋል።
ሻጮቹም ሆኑ ነጋዴዎቹ ለሁሉም ነገር አድራጊ ፈጣሪ አድርገው እስከ ሚያምኑበት ድረስ በድለላ ሥራው የረቀቀ ሰው ነው፡፡ መቼም አንዳንዱ በተሰማራበት ሙያ ይቀናዋል። ታደሰ በተለይ ዛሬ ሁለመናው በደስታ ስቆ ስራውን እያቀላጠፈው ነው። ፋሲካ ሊፈሰክ ሁለት ሳምንት ብቻ
ቀርቶታል፡፡ ሰላማዊት የሱ የግሉ ብቻ የምትሆንበት ያላተሻሚ ፍቅሩን በግሉ የሚያጣጥምበት ቀን ደርሶለታል። በዚህ ላይ ደግሞ ጥሩ ቤት አግኝቷል፡፡ ጉለሌ አካባቢ የተከራያት ክፍል ከአንድ ትልቅ ግቢ ውስጥ የምትገኝ ስትሆን አከራዮቹ ዋናውን ቤት በመኖሪያነት ሲጠቀሙበት ይቺኛዋን ደግሞ ሲያከራዩዋት ኖረዋል። ታደሰ ቤቷን በደንብ አፀድቶ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ቁሳቁሶች አሟልቷል።
አልጋ፣ ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ መደርደሪያ፣ ሳህኖች፣ ድስቶች፣ ብርጭቆዎች አዲስ የትዳር ህይወት ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን እያፋጠነው
ነው፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ቀንደኛ ቀንደኛ የሆኑትን ወንጀለኞች እያስለቀመ ነው፡፡ ትዳር በቀኝ በኩል ወደ እሱ ስትመጣ በግራ በኩል ደግሞ አጥፊዎችን እያስቀጣ ውጤት እያገኘ የሄደበት ወቅት ስለነበረ ከምንጊዜውም
የበለጠ ደስተኛ ሆኗል፡፡ ዛሬም በመደበኛ ሥራው ላይ እንዳለ አንዲት ልጅ ልትፈልገው መጣች፡፡ “እባክህ ያንን ሰው ጥራልኝ?” አለችው በጣቷ ወደ ታደስን እየጠቆመችው፡፡
“የቱን?” አለ ጩሎው።
“ያንን... ረጅሙን ጃኬት የለበሰውን ታዴን” መለያውን ነገረችው።
ስሙን ልጁ እንደሚያውቀው ሁሉ ታዴን አለችው፡፡ ታደሰ ምን ጊዜም
ቀን ቀን የሚለብሰው ሹራብ ወይንም ጃኬት ነው፡፡ እንደዚያ የሚያደርገው ራሱን ላለማሳወቅ ነው። ጠዋት በዚህ ሁኔታ የተመለከተው ሰው አመሻሽ ላይ ሽፍን ባርኔጣ አድርጐ ሻርፕ በአንገቱ ላይ ጠምጥሞ ካፖርቱን ደርቦ ሽማግሌ መስሎ ሲታይ እሱ ነው ማለትን አይደፍርም፡፡
በጣም ይለዋወጣል። ልጁ እንደተላከው እየሮጠ ሄደ።
“ጋሼ ያቺ ልጅ ትጠራዎታለች”ወደ ልጅቷ በጣቱ ጠቆመው፡፡ ታደሰ
ሰላማዊትን ሲያያት ደነገጠ፡፡ እሷ በመሆኗ ደስ ቢለውም ሥራ ቦታው ድረስ የመጣችበት ምክንያት ደግሞ አስደነገጠው፡ እየበረረ መጣና እቅፍ አድርጎ ሳማት።
“ምነው ስላም? ደህናም አይደለሽ እንዴ?” ተጨንቆ ጠየቃት፡፡
“ቶሎ በል እባክህ እማማን በጣም አሟቸዋል!”
“ይሄን ያክል ባሰባቸው?”
“ታዴ ሙት በጣም ባስባቸው። የሚሞቱ እየመሰላቸው ታዴ! ታዴ!
እያሉ ወተወቱን፡፡ የሚሞቱ ከሆነ ዐይንህን ሳያዩ ቢሞቱ ፀፀት ይሆንብናል ብዬ ነው ስሮጥ የመጣሁት” ወይዘሮ ወደሬ ስሞኑን ጤናቸው ትንሽ ተጓድሎ ነበር፡፡ የታደሰ ውለታ እጅግ ሲከብዳቸው ሰንብቷል፡፡ እንደምኞ
ታቸው በአንድ ነገር እንኳ ሳይክሱት በበሽታ በመውደቃቸው የሱ ነገር ጨንቋቸው ነው የከረሙት፡፡
“ታዲያስ እማማ? ዛሬ እንዴት ነዎት? ተሻለዎት?” ከግርጌአቸው ቁጭ ይልና ጀርባቸውን አሽት አሽት እያደረገ ሲያቃስቱ አብሮ እያቃሰተ ያስታምማቸዋል። ወደ ቤት ሲገባ ባዶ እጁን ገብቶ አያውቅም።ምናምን
ጥቅልል እያደረገ ነው።ሥጋውን፣ ብርቱካኑን፣ ሙዙን፣ ለስላሳውን...
በዚህ ሁኔታ ከአስር ቀን በላይ ታመሙ:: ዛሬ ግን ባሰባቸው። ለዚህ ነው ሰላማዊት ወደ ታደሰ የሮጠችው። ታደሰ ሳያቅማማመጣሁ ጠብቂኝ”
አለና ምክንያቱን ለባለጉዳዮች አስረድቶ ከሰላማዊት ጋር ተያይዘው ታክሲ ውስጥ ገቡ። ከቤት ሲደርሱ ግን ወይዘሮ ወደሬ እነሱ እንደገመቱት ብሶባቸው ሳይሆን መለስ ብሎላቸው ነፍሳቸውን አውቀው አገኟቸው።
“ታዴ ሙት! ገዳም ነህ ወዳንተ ለመምጣት ስነሳኮ አበቃቅተው ነበር፡፡
እኔ እንዲያውም እስከምንመለስ ድረስ ልቤ ፈርቶ ነበር” አለች ሰላማዊት ታደሰ ላይ ጥምጥም እያለች።
“ታዴ! ታድዬ..” አሉ አሮጊቷ ታደሰን በልጅ ዐይን እያስተዋሉ።
ስሞት ተረፍኩ፡፡ ነፍሴ ትንሽ መለስ አለች። አቤት... እህ... አቤት
ኣቤት ለመሆኑ ከምኔው መጣህ ልጄ?”ፍጥነቱ ገርሟቸው እንደሮጠ ሰው ቁና ቁና እየተነፈሱ ጠየቁት።
ኣሁን እንዴት ነዎት እማማ? ትንሽ ለቀቅ አደረገዎት” ትኩሳታቸውን
ላመለካት ግንባራቸውን እየዳበለ ጠየቃቸው። እንደ እሳት ይፋጁ ነበር፡፡ “ታድዬ እውነትም ታድዬ፡፡ አይ እናት ስም ማውጣት ታውቃላች።ሳልሞት ነፍሴ ሳትወጣ በመምጣትህ ዕድለኛ ነኝ፡፡ ያንተ ነገር አንጀት አንጀቴን እንደበላው ብሞት ኖሮ ለኔ ሁለተኛ ሞት ነበር። እህ... እህ...
ታዴ! ና እስቲ ወደዚህ፡፡ ሰላም! ነይ የኔ ልጅ እጅሽን ስጭኝ ታደሰንና
ሰላማዊትን እጅ ለእጅ አያያዟቸው፡፡
“እንዳትለያዩ፣ እንዳትራራቁ፡፡ ማርያም ረድታኝ የሁለታችሁን ውጤት ለማየት ብችል ደስታዬ ነበር፡፡ በዚሁ ይብቃሽ ካለችኝና ምናልባት ከሞትኩ ግን ፈቃዴን ገልላችሁ እንድሞት ነው ምኞቴ፡፡ ሠርጋችሁን ባልደግስም ልቤ ደግሷል፡፡ ከእንግዲህ በኋላ ሰላም የታዴ ታዴም የሰላም ልትሆኑ ቃል ግቡልኝ'በሽታ የደቆሰው ገላቸው እየተንዘፈዘፈ ሁለቱን እጅ ለጅ አያይዘው ከአንገታቸው ቀና አሉ። ሰላማዊትና እሱ ቢፈቃቀዱም
የአሮጊቷ የእማማ ወደሬን ፈቃድ መጠየቅ አለብህ ብላው ነበር፡፡ እማማ ወደሬ ደግሞ ይኽውና ዛሬ ክፉኛ በበሽታ በሚደቆሱበት ሰዓት እንኳ የሱ ነገር አሳስቧቸው ምኞታቸውን እየገለፁለት ነው። ደስታውን ኣልቼለውም፡፡ እማማ ወደሬም ደስ እንዲላቸው ምኞታቸው ምኞቱ መሆኑን
ሊገልፅላቸው እግረ መንገዱን የሚወደውን የፍቅረኛውን ከንፈር ሊሳለመው ፈለገና ሰላማዊትን በፊታቸው እቅፍ አድርጎ ከንፈሯን ሳማት፡፡
ሁለቱም በደስታ ተቃቅፈው የሰጧቸውን የአደራ ቃል ቀለበት አድርግው ባልና ሚስት ሆነው መተጫጨታቸውን ደጋግመው በመሳሳም በከንፈሮቻቸው ማህተም አረጋገጡላቸው፡፡

እማማ ወደሬ በደስታ ፈነደቁ።
በሽታው የበለጠ ቀለለ አለላቸው፡፡ ብርታትም አገኙ።
“እማማ እኔና ሰላም ተፈቃቅደን በባልና ሚስትነት አብረን ለመኖር ተስማምተን የርስዎን ምርቃት በመጠባበቅ ላይ ነበርን፡፡ አሁን ያንን ፈቃድዎን በማግኘታችንና የልባችን በመሳካቱ ደስታችን ወደር የለውም፡፡
ከዚህ የበለጠ ደግሞ ፍቅራችን ፍቅር ደስታችንም የበለጠ ደስታ የሚሆ ነው ከበሽታዎ ድነው በሳቅ በፈገግታ እያጨበጨቡ ሙሽሪት ልመጂ...ሙሽሪት ልመጂ...
እያሉ ሰላምን ቢሰጡኝ ነው። ያንን ዕድል ካገኘሁ ለፈጣሪዬ ምስጋናዬ ትልቅ ይሆናል” በማለት ልባቸውን ይበልጥ በደስታ አሞቀላቸው፡፡
“ታዴ? እኔ ከንግዲህ በኋላ ምን ጊዜም ወደማይቀርልኝ የሞት ቀጠሮ ተጓዥ ነኝ፡፡ እህ...እህ...ይህን የዛሬውን ሁኔታ ለማየት ሁሌም ልቤ ይጓጓ ይመኘው ነበር። ያንተን ሀሳብ የሰላምን ውሳኔ ሳላውቅ እኔ ብቻ
ብመኘው ዋጋ አልነበረውም፡፡ እህ...እህ... ይሄንን ፈርቼ እስከዛሬ አልገለጥኩትም እንጂ ሁሌም ሀሳቤ ይኸው ነበር፡፡ ዛሬ ያስጠራሁህ ሞት ሳይቀድመኝ ይሄንን ምኞቴን ገልጩ የእናንተንም ሃሳብ አውቄ እሺ
ካላችሁኝ ደስ ብሎኝ ደስ እያለኝ መንፈሴ ታድሶ እህ... እህ...እንድሞት ነበር። በእውነቱ እመቤቴ ማሪያም ረድታኛለች፡፡ የምኞቴ ተሳክቷል። ደስ አሰኝታችሁኛል ጥርሴ ባይስቅ እጄ ባያጨበጭብ ጉሮሮዬ ባይዘፍን ልቤ አምሯል ሽገይ ብሎ ዘፍኗል፡፡ ይሁን ብለናል ይሁን ብሎ አጨቦጭቧል ከእንግዲህ ዛሬ ነገ ሳትሉ ጎጄችሁን አሙቁ። ሁሉ ነገር በልጅነት ያምራል።ሰላምም እስቲ ይብቃት ከእንግዲህ ያንተው ሀብት ስላሆነች እንደ ሀብትነቷ ጠበቅ አድርገህ ያዛት፡፡
እህ... እህ...” ሰላማዊት የእማማ ወደሬ ንግግር ከአንጀቷ ጠብ ብሏል። ተደስታለች። የምትወደው ታዴን ለማግባትና ከዚያ አስቀያሚ ኑሮ ለመላቀቅ የአሮጊቷን ምርቃት ትፈልገው ነበር፡፡ ዘወትር ስለ ታደስ ቁምነገ ረኛነት ስለ ታደሰ አዋቂነት ሲያወድሱ እየሰማች ልቧ የበለጠ እየወደዳቸው ሄዶ ነበር። ሰው መቼም የወደደውን ነገር ሲወዱለት እሰይ እሰይ
ብለው ሲያደንቁለት ደስ ይለዋል፡፡ እማማ ወደሬም ታደሰን የሚያመሰግኑበት ቃላት እያጠራቸው ሲክቡት ልቧ በደስታ ይጠግብ ነበር፡፡
“ሆስፒታል ይዤዎት ሊሂዳ እማማ?” ሲል ከአንገታቸው ቀና እያደረገ ጠየቃቸው፡፡
“ቆይ እስቲ ታዴ እትዬ ስመኝ የሚያመጡልኝ የአበሻ መድኃኒት አለች መጀመሪያ እሷን ልሞክርና ካልተሻለኝ ትወስደኛለህ አሁን እኮ ቀላል እያለኝ ነው”
“ታዴ ይሄ የአበሻ መድኃኒት እኔ አላምንበትም ምን ያክል ያስተማምናል? ሆስፒታል ይዘናቸው ብንሄድ አይሻልም?” አለች ሰላማዊት።
“እንደሱ እንኳን አትበይ ሰላም አንዳንድ ጊዜ ቁና ሙሉ ኪኒን ብትቅሚ፣ አንድ ሺህ መርፌ ብትጠቀጠቂ የማይድነውን በሽታ ከስሩ ነቅሉ የሚጥለው የአበሻ መድሃኒት አይደለም እንዴ?”
“ይሄን ያክል?!”
“ምን ማለትሽ ነው ሰላም? የአበሻ መድኃኒትኮ መጠኑን ካለማወቅ እንጂ ፍቱንነቱን ራሳቸው ሀኪሞቹ የሚክዱት አይደለም”
የሚነቀል..ሥር... የሚበጠስ... ቅጠል... የሚዋጥ፣ የሚታኘክ፣
የሚጠጣ...” አንገሽገሻትና ትከሻዋን ስበቀች፡፡
ዕድሜ ልካችንን የኖርነው በአበሻ መድኃኒት ነው። ለትንሹም ለትልቁም ወደ ሀኪም ቤት መሮጥ አሁን አሁን የመጣ ፈሊጥ እህ...እህ..ነው” አሉና ወይዘሮ ወደሬ የታደስን ሀሳብ ደገፉት።
ለመሆኑ ምን ዓይነት መድኃኒት ነው ወይዘሮ ስመኝ የሚያመጡት
እማማ?” ሰላማዊት ተናግራ ሳትጨርስ...
እንደምን ዋላችሁ? ቤቶች!” አሉና ወይዘሮ ስመኝ ወደ ቤት ዘለቁ፡፡
“እግዚአብሔር ይመስገን እትዬ ስመኝ በጉ ሆኛለሁ ዐይኔም ትንሽ ገላጥ ብሏል። ደስ ደስም ብሎኛል” አሉ ወይዘሮ ወደሬ፡፡
“ድነሽ የለም እንዴ? ቅድም ጽጌ ስትጠራኝ እኮ አበቃቅታ ነበር፡፡ ሆች ጉድ!ስመጣ አላየሁሽም የት ሄደሽ ነበር ሰላማዊት?” አንዴ የማያውቁትን አዲሱን እንግዳ አንዴ ደግሞ ሰላማዊትን ተራ በተራ እየተመለከቱ
ወደ ወይዘሮ ወደሬ አመሩ።
“በጣም ሲብስባቸው ጊዜ ሆስፒታል እንዲወስዳቸው እሱን ለመጥራት ሄጄ ነው”ወደ ታደሰ ለማመልከት አንገቷን ወደሱ እየሰበረች።
“ኤድያ! ሆስፒታል! ሆስፒታል! ለሁሉ ነገር ሆስፒታል መሮጥ ምን ያስፈልጋል?! ትንሽ የምች መድኃኒት አምጥቼላታለሁ አሁን ነው ቀጥ የሚያደርግላት፡፡ እንደዚህ እስከሚብስባት ድረስ ሳትነግሩኝ በመቅረታችሁ
እንጂ ገና ድሮ ነበር ቀጥ የማደርግላት። ምን አለበት ይሄንን ያክል ቤቴ ሩቅ አይደል? እንኳን ለሷ አዳሜ በኔው አይደለም እንዴ ቆሞ የሚሄደው?” በስጨት ብለው ተናገሩና ያመጡትን ቅጠል በውሃ እሽት እሽት አድርገው በብርጭቆ ውስጥ ከጨመቁት በኋላ አረንጓዴ እየሆነ የወጣ
ውን ፈሳሽ ነቅነቅ አድርገው ወደ በሽተኛዋ አፍ አስጠጉላቸው...
“በይ ሳታጣጥሚ ጅው አድርጊው!”
የምሬቱ ነገር አይነሳ፡፡ ቢያድናቸውም ቢገድላቸውም ዐይናቸውን ጨፍነው ጅው...አድርገው ጨለጡት። ሠላማዊት ፊቷን አዞረች።
“እንዲያ ነው! ጉሽ! ኸረ ጉበዝ ነሽ አንቺ በዚህ አይነት ቶሎ ነው ድነሽ
የምትነሺው” አሉ ወይዘሮ ስመኝ፡፡
“እስቲ እምዬ ማሪያም እጅዎን መድኃኒት ታድርግልኝ እትዬ ስመኝ” አሉ በሽተኛዋ ተመልሰው ጋደም እያሉ፡ ወይዘሮ ስመኝም ቡና ተፈልቶላቸው እየተጨዋወቱ ቆዩና ተሰናብተው ሄዱ...

#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
«በፍፁም» አለ ዶክተር ደጀኔ እርግጠኛ ስለመሆኑ ለመግለፅ ጭንቅላቱንም እየወዘወዘ"ቀድሞ ነገር ውድድር አልተካሄደም ነገሩ ከላይ ተወስኖ ነው የመጣው አለው»
«ከላይ ማለት?» ሲል ጠየቀ አስቻለው በእርግጥ የቃሉ ትርጉም ጠፍቶአልና አልነበረም።
ነገር ግን ከዚያው ከአውራጃው ወይስ ከክፍለ ሀገር አለያም ከማዕከል ለማለት ፈልጎ እንጂ።
«ብቻ ከላይ ሌላው ምን ያደርጋል።»ካለ በኋላ ዶክተር ደጀኔ ድንገት ወደ ሌላ ሐሳብ ውስጥ ገባና መሬት መሬት እያየ
ይተክዝ ጀመር አስቻለው በበኩሉ በንዴት አንጀቱ ተቃጥሎ በእግሩ መሬቱን መታ መታ ያደርግ ጀምር።
«ግን አስቻለው» ሲል ዶክተር ደጀኔ ለራሱ አለና አስቻለውንም አነቃው።
«አቤት ዶክተር»
«ለመሆኑ እዚህ ሆስፒታል ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ ሰራህ ?»
«ሰባት አመት አለፈኝ!»
«ዝውውር ሞክረክ አታውቅም?»
«አልሞከርኩም»
«አሁንስ ለመሞከር አታስብም?»
«ይሳካል ብለህ ነው ዶክተር?»
«እርግጠኛ ነኝ በዚህ ከተማ ውስጥ የምትጦራቸው አሮጊትና ሽማግሌ የለህም።»
«ምንም » አለ አስቻለው፡፡ ግን ደግሞ ወድያው ሔዋንን ጨምሮ ታፈሡ በልሁና መርዕድ ትዝ አሉት፡፡ ከእናትና አባቱ ባልተናነሰ ሊለያቸው የማይፈልጋቸው የፍቅር ቤተሰቦች ናቸውና።
እንደኔ እንደኔ ከዚህ ሆስፒታል ወደሌላ ብትዛወር የተሻለ ርምጃ መስሎ ይታየኛል፡፡ ለምን መስለህ አስቻለው!»
«እሺ ዶክተር »
አስቻለው በጽሞና እያዳመጠው "መሆኑን የተረዳሁ ዶክተር ደጀኔ ሀሳቡን ቀየር አደረገና በቅድሚያ አንድ ነገር ልጠይቅህና አንተም ትክክለኛውን ንገረኝ::ሲል ፈገግ እያለ በማየት አሳሰበው::
«ምንም አልደብቅም ዶክተር፣»
«ለመሆን እዚህ ከተማ ውስጥ 'የሴት ጓደኛ አለች» ሲል አሁንም ፈገግ ብሎ እያተ ጠየቀ። አስቻለው ድንግጥ ብሎ ድንገት ስሜቱ ሲለዋወጥ አይቶ
ዶክተር ደጀኔ አሁንም ፈገግ እያለ “ምነው ደነገጥክ?» ሲል ደግሞ ጠየቀው፡፡
አስቻለው የምንተነፍረቱን «አይ …ማለት» አለና እንደ መርበትበት
ከአደረገው በኋላ «መኖር አለችኝ ግን ምነው?» ሲል ዶክተር ደጀኔን መልሶ ጠየቀው።
«እስከገባኝ ድረስ አልጅቷ ጋር አብራችሁ አይደላችሁም፡፡ ልጅቷ
ምትኖረው ከእህቷ ጋር ነው። ልክ ነኝ?»
«እንዴት ልታውቅ ቻልክ ዶክተር»
ዶክተር ደጀኔ በያዘው እስርቢቶ ጠረጴዛጠን መታ መታ አደረገና እንደገና ወደ አስቻለው ቀና በማለት «ቅድም በቤታችንና በግቢያችን ወስጥ የሚከናወነውን እንኳ አናውቅም ብዬህ ተማምነንስ እልነበረም!» እለው፡፡
«ልጅቷ ገና በልቤ ወስጥ ነው ያለችው»
ዶክተር ደጀኔ ድንገት ሃ..ሃ..ሃ...ሃ ብሎ ሳቀና አየህ! ግማሽ አካሏ ከውጭ ቀርቶ ኗሯል አለና አሁንም ሃ ሃ ሃ ሃሃ
«የ'ሷን ነገር ለምን አነሳኸው አለው አስቻለው ዶክተሩ ሳቁን ሲጨርስ፡፡
«ግን እንደው አርግዛብህ ታዉቃለችን።?»
«በፍጹም ዶክተር እንዲያውም አታምነኝ እንደሆነ እንጂ ልጅቷ ገና ድንግል ናት።»
ዶክተር ደጀኔ እንደ መደነቅ ብሎ «ድንግል! ድንግል!»
«ከልቤ ነው የምነግርህ ዶክተር»
ዶክተር ደጀኔ በመገረም ዓይነት ፍዝዝ ብሎ አስቻለውን ሲመለከት ቆየና ራሱንም ወዘወዘ «ገና ብር አምባር ሰበረልዎ እንላለና»
«እዚያ ካደረሰን! አለና አስቻለው ግን የእሷን ነገር ለምን እንዳነሳህ
አለገባኝም ዶክተር አለ አሁንም ዓይኑን በዶክተር ደጀኔ ላይ እያንከራተተ፡፡
«ምክንያት አለኝ!»
«ምን?»
«ያልተወለደ ገዳይ የሆንከው ከእሷ ጋር በተገናኘ ሁኔታ ነው፡፡
እኔ ግን ነገሩ አሉባልታ ስለመሆኑ በትክክል ገብቶኛል፡፡» አለው፡፡
«ምኑ ከምን ጋር ተገናኝቶ?»
አሁን አሁን እየተበሳሽ ነው::
«ምኑም ከምንም!» አለና ዶክተር ደጀኔ በአጭር ቃል መለሰለትና ራሱ ቀጠለ፡፡ «እንደሚመስለኝ የአንተና የልጅቷ እህት ግንኙነታችሁ ጥሩ አይደለም፡፡
የልጅቷ እህትና ባርናባስ እንደሚግባቡስ ታውቃለህን?»
«ሰሞኑን ሲደንቀኝ የሰነበተው ይህ ነው ብትነግረኝ ይከብድህ ይሆን?"
«ብዙ የማውቀው ነገር የለም፡፡ አንድ ቀን ግን እኔና ባርናባስ ከተማ ውስጥ አብረን ስንዘዋወር መንገድ ላይ ከአንዲት ሴት ጋር ተነጋግሮ ወደኔ እንደመጣ
«ህቺ ሴት መምህርት ናት፡ ያቤሎ በነበርኩበት ወቅት እሷም እዚያ ስለነበረች እንተዋወቃለን፡፡ ብቻ ነው ያለኝ አለው ዶክተር ደጀኔ፡፡ አስቻለው የሁለቱን የትውውቅ መሠረት በማውቁ ሳይሆን አይቀርም አንገቱን ደጋግሞ ነቀነቀና «አሁን ብዙ ነገር ገባኝ ዶክተር፡፡» አለው::
«አዎ እስቻለው! የጓደኛህ እህትና ባርናባስ ከፈጠሩት ግንኙነት በመነጨ ነው ያልወሊደ ገዳይነትህ የተወራብህ፡፡ ይህን ደግሞ የነገረኝ ራሱ ባርናባስ ነው!
መምህርቷ ነገረችኝ ብሎ። ግን ደግሞ ይህን ሁሉ የምነግርህ ብዙ ጊዜ አካሄድ ፊትለፊት ስለሆነ ድንገት ሳታውቀው እንዳትጠለፍ ለጥንቃቄ ይረዳሃል ብዬ ነውና
አስብበትት፡፡ የዝውውሩንም ጉዳይ ችላ ባትለው መልካም
ይመስለኛል።» አለው፡፡
እስቻለው በረጅሙ ተንፍሶ ጥቂት ካሰላሰለ በኋላ
«የሰሞኑ እንቆቅልሽ ገና ዛሬውኑ ተፈታልኝ ዶክተር» ብሎ ከንፈሩን ነክሶ ጣሪያ ጣሪያ እያየ በሀሳብ ጭልጥ ብሎ ሄደ፡፡ የዶክተር ደጀኔን የዝውውር ሃሳብ በቀላሉ አልተመለከተውም፤ እንዲያውም በርካታ ነገሮች በተዘዋዋሪ መንገድ ይህንኑ ጉዳይ ሲያሳስቡት ሰንብተዋል። በልሁና መርዕድ ታፈሡና ሽዋዬን ለማስታረቅ ከሞከሩ በኋላ
ተመልሰው የገለፁለት ነገር ሔዋን በሃሳብ ምን ጊዜም ከአንተ ጋር ናት። ሸዋዩ ባለችበት አካባቢ ግን እንጃ….” የሚል ፍሬ ሃሳብ የነበረው ነው። ከዚያም በላይ
የእርቅ ሙከራ በተደረገ ሶስተኛ ቀን ረፋዱ ላይ ሔዋን ሳያስባት ለዚያውም ፊቷ በእንባ ረስርሶ ወደ ቤቱ መጥታ ነበር።
«ምነው ሔዩ» ነበር የአስቻለው ጥያቄ።
«እንካ ይኸን ወረቀት አንብብ ብላ አንዲት ወረቀት ሰጠችው።
አስቻለው ወረቀቷን ገለጥ አድርጎ ሲያነብ የሚከተለውን መልዕክት
አገኘባት።
«ለተከበራችሁ አባትና እናቴ ለአቶ ተስፋዩ ይርጋ እና ለወይዘር ስንዱ በላቸው፣ለጤናችሁ እንደምን አላችሁ። እኔ ግን በጣም ተቸግሬያለሁ። እናንተንም እሷንም
ለመርዳት ስል ሔዋን የተባለች ልጃችሁን ወደ ዲላ ይዣት መጥቼ ነበር። እሷ ግን ትምህርቷን እርግፍ አድርጋ ትታ ሥራዋ ወንድ ማባረር ብቻ ሆኗል። እንዲያውም
መዘዟ ለኔ ተርፎ ችግር ላይ ወድቄአለሁ።ከመቸገሬ የተነሳ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከቤቴ ላባርራት ነው ።ምናልባት ልጃችን ባክና መቅረት የለባትም የምትሉ ከሆነ ከሁለት አንዳቹ መጥታችሁ ውሰዷት። መጥተን እንወስድም ካላችሁ ውርድ ከራሴ።
ልጃችሁ ሽዋዬ ተስፋዬ
አስቻለው ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ በኋላ በንዴት እሳት ለብሶ እሳት ጉርሶ ፈጠን ባለ አነጋገር ሴትዮዋ ምን እያለች ነው?» ሲል ሔዋንን ጠየቃት፡፡
«እኔ እንጃ አስቹ፣ ግራ ገባኝ» ሔዋን እያለቀሰች፡፡
«የት አገኘሽው?»
«ዛሬ ጠዋት ሥራ ስትሄድ ረስታው መሰለኝ አልጋዋ ላይ ተቀምጦ አገኘሁት።»
«ቀዳድጄ ልጣለው?»
«ተው አስቹ፣ ነገር ይባባስብኛል። ግን አንድ ነገር ላማክርህ?

👍3
«ምን?»
«በቃ አንተም ወደዚያ ቤት አትምጣ፡፡ እኔም ከዚህ ቤት ልቅር?»
«እስከ መቼ?»
«ጊዜና ቦታ እስኪገጥመን ድረስ?» ብላው ነበር፡፡
አስቻለው ይህን ሁሉ በሃሳቡ ከቃኘ በኋላ «ለመሆኑ ዝውውሩስ በቀላል ይሳካል ብለህ ነው ዶክተር?» በማለት ዶክተር ደጀኔን ጠየቀው፡፡
«መሞከር ጥሩ ነው፡፡ አሁን ደግሞ የካቲት እየገባ ነውና የዝውውር ፎርም መሙያው ጊዜ ስለሆነ አታሳልፈው::"
«አንተ ልትረዳኝ የምትችለው ነገር ሊኖር ይችል ይሆን?»
ዶክተር ደጀኔ ለአስቻለው መልስ ከመስጠቱ በፊት ትክዝ ብሎ ያስብ ጀመር፡፡ እስኪርቢቶውን በጣቶቹ ውስጥ ይዞ እያሽከረከረ በታችኛው ጥርሱ የላይኛውን ከፈሩን ነክሶ ወደ ጠረጴዛው ያይ ጀመር፡፡
«ይህን ያህልም አትጨነቅ ዶክተር፡፡ ምናልባት ዝውውር ብጠይቅ እንኳን በዚሁ ባርናባስ በሚባል ሰው ተንኮል ሊጨናገፍ የሚችል ነገር ቢኖር ልትከላከልልኝ
የምትችልበት መንገድ ካለ ብዬ እንጂ የተለየ…» ብሎ አስቻለው ሳይጨርስ ዶክተር ደጀኔ አቋረጠው።
«አንድ ነገር ማድረግ እችል ይመስለኛል።»
«ምን ይሆን ዶክተር?»
«የዋናው መሥሪያ ቤት አስተዳደር አገልግሎት ኃላፊ በቅርብ የማውቀው ሰው ነው:: ዝውውሩ ደግሞ በማዕከል ስለሚፈፀም የገጠመህን ማኀበራዊ ችግር
ሁሉ ብነግረውና ሥራውን እስካላበላሸበት ድረስ ሊረዳህ ቢሞክር ደስ ይለኛል። ግን
ደግሞ ፈጠን ያልክ እንደሆነ ነው፡፡» አለው፡፡
«ፈጠን ማለት?» ሲል ጠየቀ አስቻለው።
«ማለቴ…» አለና ዶክተር ደጀኔ እንደገና አመነታ፡፡ ፊቱንም ክፍት እያለው ሲሄድ ውስጥ ውስጡን የሚያስጨንቀው ነገር ያለ ይመስላል። እንደ ምንም ራሱን
አረጋግቶ «በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ የምትሄድ ከሆነ ማስታወሻ ልጻፍልህና ሰውየውን አግኘው፡፡ ምናልባት በሚሰጥህ ምላሽ መሠረት ሌላም አማራጭ እንፈልግ ይሆናል። ፍጠን ያልኩህ ግን ያለ ምክንያት አይደለም በሆዴ አንድ ምስጢር ስላለ ነው፡፡ አምንሀለሁና ብነግርህ ቅር አይለኝም፡፡» አለው በደረቁ ፈገግ
እያለ።
«ምን ይሆን ዶክተር?»
«እኔም በበኩሌ እየፈጠንኩ ነወ፡፡»
«ማለት?» አለ አስቻለው ለሚሰማው ነገር እየጓጓ።
«አንተን ከዚህ አገር ተዛውረህ ሂድ ስልህ የኔም ልብ ቀድሞ መሽፈቱን
ልነግርህ ወደድኩ፡፡»
«ወዴት?» አለ አስቻለው ግራ ገባ እያለው።
«ራቅ ወዳለ ቦታ፡፡» አለና ዶክተር ደጀኔ ድንገት ዓይኑ በእንባ ሞላ፡፡
«ከሀገር ውጪ?»
«አዎ! ስደት ከህሊና ቅኝ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት!»....

👍2
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ከምሽቱ አምስት ሰዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ከአስፋልቱ መንገድ ፈንጠር ብሎ
ከአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ወደ መርካቶ በሚወስደው መንገድ ላይ በስተቀኝ በኩል እርስ በርሳቸው ተደጋግፈው
ከቆሙት የጭቃ ቤቶች መካከል በአንደኛዋ ዳንኪራው ጦፏል፡፡
ቀን ቀን ቡና ቤት ውስጥ በገንዘብ ተቀባይነት በምትሰራውና ማታ ማታ ደግሞ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ የአልኮል መጠጦች እየሸጠች እንግዶቿን
በምታስተናግደው በማህሌት ቤት እየተደነከረ፣ እየተጨፈረ ነው።
ማህሌት በዚያ አጭር ቁመቷ ላይ የለበሰችው ጮማ ተከምሮ በድንገት ስትታይ የምትገላበጥ እንጂ የምትራመድ መሆኗ የሚያጠራጥር ቀይ አፍንጫ ጎራዳ ሴት ናት። ማህሌት ወደዚያ ስትሄድ ወደዚህ የመጣች እየመሰላቸው ቁጭ ብለው የጠበቋት ጓደኞቿን ብዙ ቀን ጉድ
ያደረገች ጉደኛ ሰው ነች።በዚች ጠባብ ቤቷ ውስጥ የመሽኛ ግብዣ የተደረገላቸው ሰዎች ተሸኝተዋል። በመሥሪያ ቤት እድገት ያገኙ ሠራተኞች ማህሌት ቤት እያሉ እየተቀጣጠሩ ፅዋቸውን አንስተዋል፡፡ ለእንኳን
ደህና መጣችሁ እንግዶች ተጋብዘዋል፡፡ የተለያዩ የግብዣ ሥነ ሥርዓቶች በተለያዩ ጊዜያትና አጋጣሚዎች ተካሂደዋል፡፡ ማለፊያ ገንዘብ እስከተከፈላት ድረስ ማህሌት የሚያምሩ ጥርሶቿን ፍልቅቅ፣ ትሙክ፣
ትሙክ የሚሉ ጉንጮቿን ስርጉድ እያደረገች በጥሩ አስተናጋጅነት እንግዶቿን አስደስታ ሽኝታበታለች። ዛሬ በታደሰ አስተባባሪነት የመሸኛ ይሁን የመዝናኛ ውሉ ያልታወቀ ግብዣ እንድታዘጋጅ ተነግሯት አልኮል በያይነቱ ቀርቦ ጮማ እየተቆረጠ ሊጠጣ... ሊዘለል... ሊጨፈር... የጠየቀችው ሞቅ ያለ ክፍያ ተከፍሏታል። በዚህ የግብዣ ሥነ ሥርዓት ላይ የሚገኙት አምስት ወንዶች ናቸው።
ሙዚቃው ጦፏል!ተጋባዦቹ ከሙቀቱና ከሙዚቃው ጋር እንደ ውሃ የሚጨልጡት አልኮል ተጨምሮበት መስከር ብቻ ሳይሆን እብደት ቀረሽ ዝላይ እየዘለሉ ናቸው። በስካር ላይ ስካር የሚጨምረው የሚያብረከርከው ሙዚቃ ደግሞ በረጅሙ ተለቋል...
አንቺ ከቶ ግድ የለሽም፣
ስለፍቅር አልገባሽም፣
ሁሉን ነገር እረስተሽው፣
ችላ ብለሽ ስለተውሽው፣
ቻልኩት ፍቅርን... ለብቻዬ፣
ስለዚህ ትቼሻለሁ ይቅር፣
ስላልገባሽ የፍቅር ሚስጥር፣
ትቼሻለሁ አትምጪ ይቅር፣
እችክ፣ እችክ፣ እችክ፣ እችክ፣እችክ.....
ወገብ ብጥስ ቅንጥስ ይላል፡፡ አንዳንዱ ደናሽ ሳይሆን ዳንግላሳ የሚመታ ፈረስ ይመስላል፡፡ ማህሌት የወንዶቹ ጭፈራና ዝላይ ፈንቅሏት እዚያ እመሀላቸው ገብታ እንደ ግንድ እየተገላበጠች ነው።መቼም ከጭንቅላት ቀጥሎ ያለው የሰው ልጅ አካል በማህሌት ዘንድ አለ ለማለት የሚያስደፍር አልነበረም፡፡ ያቺኑ አንገት ተብዬ እየወዘወዘች ከትከሻዋ እየ
ተርገፈገፈች እያሳበደቻቸው ነው። በአምስት ወንዶች መካከል የተገኘች ብርቅዬ... ሞናሊዛ ሆናላቸው ደብለል. ደብለል.. ዞር ዞር...ደግሞ ከትከሻዋ መታ መታ ወረድ... ቀና... እያለች ልባቸውን እያጠፋችላቸው ነው፡፡
ከታደሰ በስተቀር ሌሎቹ በደስታ ብዛት የሚሆኑትን አሳጥቷቸዋል።
አራቱም በየልባቸው ማህሌትን ተመኝተዋታል፡፡ ምን ችግር አለ? የራሳቸውን ስሜት የሚያረኩበት ብቻ ሳይሆን የሌላ ሰው ስሜት ጭምር የሚማርኩበት ረብጣ ገንዘብ ተይዟል። በዚሁ መካከል ግን ሰዓቱ እየበረረ ነበር። ማህሌት ወደ ታደሰ ጆሮ ጠጋ አለችና.....
“ታደስ እስከ ስድስት ሰዓት ብቻ አልነበረም እንዴ የተነጋገርነው? ሩብ ጉዳይ ሆነ እኮ! ሁኔታችሁን ስመለከተው ሙሉ ሌሊት የሚበቃችሁ አልመስለኝም” አለችው።ታደሰ እጇን ሳብ አደረገና
ወደ ጓዳዋ ውስጥ ይዟት ገባ።
“ማህሌት ከስድስት ሰዓት አንድ ደቂቃ ቢያልፍ የተነጋገርንበትን ዋጋበእጥፍ እከፍልሻለሁ፡፡ በዚህ በኩል በፍፁም ሃሳብ አይግባሽ፡፡ በኔ ተይው። ሰዓት አልፏል ብለሽ ጨዋታሽን እንዳትቀንሺባቸው ፊት እንዳትነሻቸው፡፡ እንደ ልባቸው ይጨፍሩ ይዝለሉ። ዛሬ የመዝለያ የመጨፈሪያ ቀናቸው ስለሆነ ሌላ ንግግር ተናግረሽ እንዳታስቀይሚያቸው”
ለስለስ ደግሞም ኮስተር ባለ አነጋገር አስጠነቃቃት። ልቧ ተረጋጋና ተያይዘው ወደ ጭፈራው መሃል ገቡ... አንዱ በአንዱ ላይ እየወጣ እየቦረቀ ለጤናችን እያለ መለኪያ ለመለኪያ እያጋጨ ተዝናና። ለሁሉም ነገር
ድፍረትና ወኔ የሚስጠውን አልኮል በብዛት ወስዶ ሰውነቱን በሚገባ
ወደ ሁለተኛዋ ክፍል አሟሟቀ፡፡ ታደሰ ወጣ ገባ እያለ አካባቢውን ያጠናል።
“የሙዚቃ ድምፅ ይቀነስ... ጩኸት ቀንሱ” እያለ የአካባቢው ነዋሪ እንዳይረበሽ ማስጠንቀቂያ እየስጠ ብቅ ጥልቅ ይላል።በዚያ ሀድራው በሚጨስበት፣ሙቀቱ ጨፋሪዎቹን በትኩስ ላብ በሚዘፍቅበት፣ ሙዚቃው
ልብ እየነጠቀ እንደ ጋላቢ ውሃ ሽቅብ በሚያዘልልበት፣ አልኮል እንደ ፏፏቴ በሚፈስበት፣ የሚገኘው የወደፊት ብሩህ ተስፋ የሚቆጠረው የገንዘብ ብዛት በሚያጓጓበት አስደሳች ዓለም ውስጥ እያሉ ልክ ስድስት
ሰዓት አናቱ ላይ ሲሆን “እጅ ወደ ላይ!” የሚል ድምፅ ሲሰማና በሩ ሲበረገድ አንድ ሆነ፡፡
ማህሌት ከድንጋጤዋ የተነሳ ያ ዝሆን የሚያክለው ግዙፍ ሰውነቷ እንደ ባሉን ቀላላትና እንደ ህፃን ልጅ ሮጣ አልጋዋ ስር ገብታ ተደበቀች።ከሁሉ ቀድሞ እጁን ያነሳው ታደሰ ነበር።
አለቃቸው እጅ መስጠቱን ሲያስተውሉ ሁሉም ተስፋ ቆረጡና እጆቻቸውን ወደ ሰማይ ሰቀሉ።በየኪሳቸውና በጉያቸው የደበቋቸውን ሰንጢዎች፣ ስንስለቶች፣ መሰርሰሪያ ለመሽሽግ ወይንም ለመወርወር ፋታ ኣላገኙም ነበር፡፡ ፖሊሶቹ እጅግ ቅልጥፍና በተሞላበት መንገድ ኪሶቻቸውን ፈተሹና መሳሪያዎቹን በቁጥጥር ስር አዋሉ፡፡ ብዛት ያለው ገንዘብና
ከታደሰ ኪስ የተገኘው አንድ ሽጉጥም በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደረገ፡፡በዚህ ሁሉ ትርምስ ውስጥ ግን ያ ሽለምጥማጥ አበራ በጓዳ በር በኩል ተሽሎክሉኮ በር በርግዶ አጥር ጥሶ አጥር ዘሎ ሲያመልጥ ከታደስ ጋር አራቱ ተያዙ።
ፖሊሶቹ ወሮበሎቹን በቁጥጥር ሥር በማዋላቸው ምክንያት ዛሬ በሌሊት ቤቱን ሰብረው በመግባት ህይወቱን ለማጥፋት ቀብድ የተቀበሉበት የቡና ነጋዴው የአደም ሁሴን ህይወት ተረፈች። አስር ሺህ ብር ከአደም ላይ
የተበደረው ኡስማን አብደላ የተበደረውን ገንዘብ ለመመለስ ፈቃደኛ ሆኖ አልተገኘም። ጫማው ላይ ወድቆ ምሎ ተገዘቶ የተበደረውን ገንዘብ ከለከለው።
"ኡስማን ገንዘቡን ስትቀበለኝ የነበረህን ሁኔታ ታስታውሳለህ አይደለም?
ዘመድ አዝማድ ልከህ ደጅ ጠንተህ ከነወለዱ ለመክፈል ተስማምተህ ነበር። የኔ ፍላጎት ወለዱ ቀርቶ ዋናውን ብቻ እንድትመልስልኝ ነው፡፡
ከገባኸው ውለታ ውጪ አራት ወር ከአስራ አምስት ቀን ጠብቄሃለሁ።
እምቢ የምትለኝ ከሆነ ግን በህግ ልጠይቅህ እገደዳለሁ” ሲል አስጠንቅ ቆት ነበር።
ኡስማን የአደምን ማስጠንቀቂያ ከሰማ በኋላ አደም ገንዘቡን ስታበድረኝ የጽሁፍም ሆነ የሰው ማስረጃ እንዳለህ አውቃለሁ። እኔም ገንዘብህን ላለ
መስጠት ሳይሆን ሀጃዬ ስላልሞላልኝ ነው። እባክህ ትንሽ ጊዜ ስጠኝ?"በማለት ዋሽቶት ነበር። ጊዜ ስጠኝ ያለው ዕዳውን ለመክፈል ሳይሆን ነፍሰ ገዳዮችን በሁለት ሺህ ብር ገዝቶ አደምን ለማስገደልና ስምንት ሺህ
ብር ለማትረፍ ነበር፡፡ በዚሁ መሰረት እነኝህ ኡስማን የገዛቸው የወሮበላ ቡድን አባላት ለወንጀል መፈፀሚያ ከያዟቸው መሳሪያዎች በተጨማሪ ወንጀሉን ለመፈፀም የተቀበሉት ቀብድ ታደስ በሰጠው መረጃ መሠረት በቡድኑ አባል በጥጋቡ ኪስ ተገኘ፡፡ ታደስም ከወሮበሎቹ ጋር አብሮ እየተነዳ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደ፡፡

ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ነው። የፖሊስ ጣቢያው አዛዥ ከፊት ለፊታቸው ባለው መዝገብ ላይ አንገታቸውን ደፍተው ስነዶችን ይመረምራሉ፡፡ቁመታቸው አጠር ያለና ፀጉራቸው ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት ከእድሜአቸው ገፋ ሲሉም በእንቅስቃሴአቸው ቆፍጠን ያሉት የፖሊስ አዛዥ በሩን
ቆርቁሮ በደስታ እየፈነደቀ ወደሳቸው የሚመጣውን ሰው ሲያዩ ፋይሉን መልሰው ዘጉና አፀፋውን በደስታ እየሳቁ እጆቻቸውን ግራና ቀኝ ዘርግ
ተው በእቅፋቸው ተቀበሉት።
“ይህ ነው የንፁህ ዜጋ መለያው! ይህ ነው የራስን ክብረ ህሊና ከወቀሳ የሚያድን አኩሪ ተግባር! በረቀቀ ዘዴ ወንጀለኞችን የማጥመጃ መረብ...
በሰጠኸው ትክክለኛ መረጃ መሠረት ሁሉም ተደጋጋሚ የወንጀል ሪኮርድ ያለባቸው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ እያስመዘገብክ ያለው ተግባር ሠራዊታችን እንዲኮራብህ የሚያደርግ ነው፡፡ በርታ!" ጥልቅ ምሥጋናና የሞራል
ድጋፍ ሰጡት፡፡
ታደስ ለተሰጠው የሞራል ድጋፍ እጅ ከነሳ በኃላ ስለወደፊቱ ከአዛዥ ጋር ሲወያይ አረፈደ። ታደሰ በስራው መልካም ስራ አደም ከሞት ተረፈ። በኡስማን አማካኝነት የተገዙ ወሮበሎች ሊሰነዝሩበት የነበረው የሞት ሰይፍም ወደ ሰገባው ተከተተ። ዕድሜ ለታደሰ። በአንጻሩ ደግሞ ኡስማን በአደም ህይወት ነግዶ ለማትረፍ አቅዶ በፈፀመው የወንጀል ድርጊት ምክንያት ተጠያቂ ከመሆኑ በተጨማሪ ከአስር ሺህ ብር ዕዳ ለመዳን የቀየሰው ዘዴ ከሽፎና ለነፍስ ገዳዮች ከከፈለው ተጨማሪ
ሁለት ሺህ ብር ጋር ተደምሮ ከአስራ ሁለት ሺህ ብር ባለዕዳነቱ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጠ፡፡
ታደሰ ይህንን ሁኔታ በቀጥታ ለአደም ሪፖርት አደረገለት። ኡስማን በነገሩ ክፉኛ ደነገጠ። አደም ወሮበሎችን በገንዘብ ገዝቶ ደግሶለት ስለነበረው የግድያ እቅድ ሀቁን በዝርዝር አጣርቶ አረጋገጠ፡፡ በመጨረሻም
ህይወቱ እንድትተርፍ ለተባበረው ለታደስ ጥልቅ ምስጋናውን አቅረበና ከጠላቱ ሊሰነዝርበት የሚችለውን ማንኛውንም አደጋ ለመከላከል አስፈላጊውን ጥንቃቄ መውስድ ጀመረ፡፡....
✨ይቀጦላል✨

#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
"አላሁ አክበር....አላሁ አክበር“አለ ኢማሙ የዕለተለን የማለዳ እስላማዊ ፀሎት ሊያደርስ
አስቻለው ዛሬ መንገደኛ ስለሆነ ከእንቅልፉ ያነቃው ዘንድ ሲጠብቀው የነበረ ድምፅ ነው
ልክ እንደነቃ ከአንገቱ ቀና ብሎ ነቅነቅ ሲል አልቀለለውም ከሰውነቱ ልጥፍ ብላ የተኛች ደሴት አለች ሔዋን ተስፋዬ።
በወርሃ የካቲት ሁልታኛ ሳምንት ላይ ሽዋዬ ዲላ ውስጥ አልነበረችም፡፡ለአንድ ሳምንት የሚቆይ አጭር የስራ ላይ ስልጠና ልትካፈል ወደ አዲስ አበባን ሄዳለች። በዚያው ሳምንት በዕለተ ሐሙስ አስቻለው ወደ አዲስ አበበ ሊሄድ ተነስቷል ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዋና መስርያ ቤት የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርብ።
በአስገዳጅ ሁኔታ ግንኙነታቸውን ለጊዜው ለማቋረጥ ወስነው የነበሩት አስቻለውና ሔዋን ለዚያች እለት የጋራ ቃላቸውን በጋራ አፍርሰዋል የሸዋዬን አለመኖር አጋጣሚ ተጠቅመው አብረው ለማደር።በዚሁ መሰረት ትላንት ምሽት ላይ አስቻለውና በልሁ ከቤቷ አምጥተዋት ሔዋን በአስቻለው ቤት አስቻለው
አልጋ ላይ ከአስቻለው ገር አድራለች::
አስቻለው መብራት አብርቶ የሔዋንን አስተኛኘት አየት ሲያደርገው አሳዘነችው:: አንድ እግሯን ከጭኖቹ መሀል አስገብታ፤ በግራ እጇ አንገቱን አቅፋ በቀኝ
እጇ ደግሞ ወገቡ ላይ ጥምጥም ብላ ተኝታለች፡፡ ከአንገቱ፡ ቀና ብሎ ለአፍታ ያህል ቁልቁል ሲያያት ቆየና ግንባሯ ላይ ሳም አደረጋት
ምናልባት በእንቅልፍ ሰመመን ውስጥ ሆና የእስቻለው እንቅስቃሴ ተሰምቷት ሳይሆን አይቀርም ሔዋን አይኗን ገለጥ ስታደረግ ሁለቱም ተያዩ
«ነጋ እንዴ አስቹ?» ስትል ጠየከቸው
«እረፍዶ!!»
ሔዋን ከአንገቷ ቀና ብላ ወደ መስኮት አየት ስታደርግ የውጭ ብርሃን የለም:: ዋሽህ' ብላ ተመልሳ ተኛች::
«ለኔ ማለቴ እኮ ነው መንገደኛ አይደለሁ!»
«ህልም እያ'የሁ ነበር አስቹ፣»
«ጥሩ ወይስ መጥፎ?»
«የት እንዳለሁ አይታወቀኝም፣ ግን እናትህ ይመስሉኛል። እፊቴ ቆመው ልጄን ከምታመጭበተ አምጪ! የት ነው የደበቅሽው? ኋላ አንድ ነገር ቢሆን ነገ ከአንቺ ራስ ላይ አልወርድም" ይሉኛል::
«ምን አልሻት ታዲያ? አላት አስቻለው እንደ መሳቅ እያለ፡፡»
ምንም! ዝም ብዬ ሳያቸው ከእንቅልፌ ነቃሁ::
«አትዋሺ! አለና አስቻለው አሁንም በቀልድ ዓይነት «ይኼኔ ልጄን
አምጪ ስትልሽ አልሰጥም የት ነው የደበቅሽው ስትልሽ ልቤ ውስጥ ኋላ ልጁ አንድ ነገር ቢሆን» ስትልሽ ደግሞ የግድ የለዎትም እኔ ጋር የተቀመጠ ነገር
አይበላሽም ብለሻት ይሆናል::» አለና ለራሱ እየሳቀ ሔዋንንም አሳቃት፡፡
አስቻለው ሳቁን ከጨረሰ በኋላ ወደ ቁም ነገር በመመለስ ይኼኔ እናቴ በህይወት ብትኖርልኝማ ኖሮ ብዙ ችግርቼ በቀላሉ ይፈቱ ነበር፡፡ በተለይ አንቺን የመሰለች ምራት በማግኘቷ እየተደሰተች አንቺን በማለቴ ስለተፈጠረብኝ ችግርም
መላ ትፈልግልኝ ነበር፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው፤ እኔም እሷም ሳንታደል ቀረንና በልጇ ሀዘን ተቃጥላ ሞተች፡፡» አላት እውነትም በመጥፎ ትዝታ ፊቱን እየከፋው።
«ልጅ ሞቶባቸው ነበር፡፡»
«ያውም የኔ ታላቅ ! እሷንም እኔንም በገንዘብ ይረዳ የነበረ እውሮች ለምን አየህ?» ብለው ገደሉት፡፡ አላት፡፡
«እውሮች!» አለች ሔዋን አባባሉ ግራ ገባ ብሏት።
«ዓይን ቢኖራቸውም "ማስተዋል የጎደላቸው ህሊና ቢሶች፡፡ እስና ያን አሰቃቂ የቀይ ሽብር ዘመን በዓይነ ህሊናወኑ ለአፍታ ያህል ዳሰስ አደረገው::
«እየነጋ ነው ሔዩ፡» አላት ከሃሳቡ መለስ ሲል፡፡
«ትሄድ አስቹ?»
«በቅድሚያ ግን የወጭ በይኝ፡፡» ብሎ ዓይኖቹን ፈዘዝ አድርጎ ሲመለከታት ምላሹን ሰጠች። አንገቱን እቅፍ አድርጋ ከንፈሮቿን በነከንፈሩ ላይ ጣል አደረገቻቸው፡፡ ወሰዳት፡፡ ወስደችው:: ዓይኖቻቸው ተስለመለሙ፡፡ ሰውነታቸው ሞቀ፡፡ ገላቸው ተጣበቀ። ትንፋሻቸው በረከተ። በስሜት ባህር ወስጥ ሰጠሙ፡፡
ምድር ላይ ሆነው ገነትን ለአንድ አፍታ ተመላለሱባት፡፡ ከስሜት ገዞ መልስ እስቻለው ከእልጋ ላይ ወረደ:: ታጠበ፡፡ አበጠረ፡፡
ለባብሶ የመንገድ ሻንጣውን ትከሻው ላይ አነገተና አልጋው ስር ቆሞ ሔዋንን ቁልቁል እየተመለከተ ከአዲስ አበባ ምን ገዝቼልሽ ልምጣ ሔዩ?» ሲል ጠየቃት፡፡
«ምንም አስቹ!››
«ለምን? ጫማ ልብስ' ወይም ሌላ ነገር ብገዛልሽስ»
«ማን ገዛልኝ ብዬ ልለብሰው አስቹ?» አለችው አልጋው ላይ በክንዷ ደገፍ ብላ ከእንገቷ ቀና በማለት እየተመለከታችው፡፡ አስቻለው የዘነጋው ነገር ነበር፡፡ እንደ አዲስ ትዝ ብሎት ድንገት ቅስሙ ስብር ከለና ለአፍታ ያህል በሀዘን አይን ተመለነታት፡፡
«እንተ ብቻ በሰላም ተመለስ፡፡» አለችው ሔዋን ዓይን ዓይነን እያየች።
«አሜን የኔ ፍቅር» ብሏት ሳም አድርጎ ተሰናበታት፡፡
ሰአቱ ገና ማለዳ ስለነበር ሔዋን ወዲያው አልተነሳችም፡፡ አልጋው ላይ ጋለል ብላ ጣሪያ ጣሪያ እያየች አስተዳደሯን በትዝታ ታየው ጀመር፡፡ ደስ የሚል ሌሊት ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ አስቻለው ቃሉን ማክበሩ አስደስታት:: ለግማሽ ሌሊት ያህል ከንፈሮቻቸው ሳይላቀቁ፤ በመተሻሸት ብዛት በስሜት ሲፈራገጠ ያላደሩትን
ያህል አስቻለህ ለአንዴ እንኳ ወደ ጭኖቿ መሃል ሳያመራ በማደሩ ከልቧ አደነቀችው:: ከመቸውም ጊዜ በላይ በእሱ ላይ ያላት እምነት የፀና ሆነ፡፡ ያ ሌሊት
ሔዋን ሴት እንደመሆኗ ወንድ እንደሚያስፈልጋት በውል የተረዳችበትም ነበር!
ከሆንም አስቻለው ፍስሀ ብቻ!
ሔዋን መልካም የፍቅር ተስፋ የምታይበት አዕምሮዋን ስጋትም ጠቅ ያረገው ነበር፤ ከሁሉም በላይ እህቷ ሸዋዬ በሁለቱ ፍቅር ላይ ያላት መጥፎ አመለካከት፡፡ ከዚያ ቀጥሎ ለቤተሰቦቿ የጻፈችባት ደብዳቤ፡፡ ሁለቱም እንደ ትልቅ የፍቅር እንቅፋት ያሰጓታል፡፡ ያስጨንቋታል። ለመሆኑ አስቻለው የዝውውሩ ጉዳይ ቢቀናውስ! ወደ ሄዴበት ቦታ አብራው ትሄድ ይሆን! በምን ሁኔታ ጠፍታ ወይም በቤተሰቦቿ ፈቃድ የሚታወቅ ነገር የለም። ይህም እንዱ የሀሳቧ ዘርፍ ነበር፡፡
በዚህና በመሳሰሉት የፍቅር ጉዳዮች ዙሪያ ስታወጣ ስታወርድ ሳታውቀው እረፍዶ ኖሯል፥ በግምት ወደ አንድ ሠዓት ተኩል አካባቢ ተጠግቷል። የጠዋት
ፈረቃ ተማሪ ናትና ፈጥና ተነሳች፡፡ የአስቻለውን አልጋ ስምር አድርጋ
አነጣጠፈች፡፡ ታጥባ ፀጉሯን ጎነጎነች በኮመዲኖው ላይ የተቀመጠ የአስቻለውን
ፎቶ ግራፍ ሳም ሳም አድርጋ ቤቱን ቆላልፋ ወጣች፡፡ ከዛም ወደ ቤቷ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አስቻለው ከሾፌሩ ኋላ ሦስት ሰዎችን በሚያስቀምጠው የመጀመሪያ ወንበር ላይ በሁለት ሰዎች መካከል ተቀምጦ ወደ አዲስ አበባ ይጓዛል በጎራ በኩል የመስኮት ጥግ ይዘው ዕድሜያቸው ወደ ሀምሳዎቹ የገባ የሚመስል፤ ነገር ግን በምቾት ኑሮ ፊታቸው ደንቡሽቡሽ ያለ ቀይ መልከ መልካም ሴት ተቀምጠዋል፡፡ የጥቁርና ነጭ
ቡራቡሬ ቀሚስና ባለ ጥለት ነጭ ነጠላ ለብሰዋል። እራሳቸውን
በጥቁር ሻሽ ሽክፍ አድርገው አስረዋል። ከቀኙ በኩል ደግሞ አንዲት ዕድሜዋ ከአስራ ሰባት ዓመት የማይበልጣት ጠይም ልጃገራድ ተቀምጣለች፡፡ ነጣ ያለ ጉርድ ቀሚስ በቀይ ሹራብ ለብሳለች። ስልክክ ያለች የጠይም ቆንጆ ናት። ሦስቱም እየተጨዋወቱ ይጓዛሉ።

👍1
ከዲላ እስከ አዲስ አበባ ድረስ ያለውን የሦስት መቶ ስልሳ አምስት ኪሎ ሜትር መንገድ በዘመናዊ አውቶቡሶች ከአራት እስከ አምስት ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ
ተጉዞ በተጨረ ነበር፡፡ ነገር ግን በዚያ መስመር ላይ ከዘጠኝ ያላነሱ የፍተሻ ኬላዎች ትልቅ እንቅፋቶች ስለነበሩ ከአመሻሹ አስራ አንድ ሠዓት በፊቱ አዲስ አበባ መድረስ አይታሰብም፡፡መዘዙ ደግሞ ቡና፣ እህል ሆኖ ላይበላ፣ ውሃ ሆኖ ላይጠጣ፣ እንደው ባህላዊ ልማድ በመሆኑ ብቻ፡፡ ህዝብ ደግሞ ቋጠር አድርጎት መጓዝ ያወዳል:: መንግስት ደግሞ በጥብቅ ይከለክላል። ከዚህ የተነሳ በኬላው በፍተሻ የሚባክነው ጊዜ ያን መንገድ ረጅምና አሰልቺ ያደርገዋል።
ከጊዜው መባከንና መውጣት መውረድ የሚደርስ እንግልት ይልቅ መንገደኞችን ክፉኛ የሚያማርራቸው የፈታሾቹ እብሪት ነው፡፡ መኪና ልክ ኬላው
ላይ እንደ ደረሰ ውረድ! የሚል ጩኸታቸው፤ ፈትሸው ሲያስገቡ ተሰለፍ!” የሚል ግልምጫቸው፤ ሻንጣ ሲፈትሽ በውስጡ ያለውን ዕቃ ሃላፊነት በጎድለው ሁኔታ
ሲመነቃቅሩት፤ አንድም ትሁን ሁሉት ኢሎ የምትሆን የቡና ቋጠሮ ካገኙም በባለ ቋጠሮው ተጓዥ ላይ የሚያደርሱት እንግልት፤ በቃ ሁለ ነገራቸው ያስመርራል።ያበሳጫል።
አስቻለው የተሳፈረበት አንደኛ በራሪ አውቶብስ ከዲላ መውጫ ኬላ ጀምሮ በጩኮ፤ በአፖስቶ በአቢላ እና በአዋሳ ጥቁር ውሃ ፍተሻ ጣቢያዎች ላይ ፍዳውን
ጨርሶ ከሻሽመኔው ኬላ ላይ ከእረፋዱ አራት ሠዓት አካባቢ ደረሰ። የማይቀረው ዕዳ ሊከፈል ተጓዥ ሁሉ ከመኪና ላይ ወረደ:: ከአስቻለሁ አጠገብ በስተግራ በኩል የመስኮት ጥግ ይዘው ተቀምጠው የነበሩት ወይዘሮ ግን አልወረዱም፡፡......

#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ጉለሌ አካባቢ ታደሰ የተከራያት ሁለት ክፍል ቤት ለብዙ ጊዜ ተዘግታ የከረመች ሸረሪት ያደራባትና ግድግዳዋ የተላላጠ ነበር፡፡ አሁን ግን ቀለም ተቀብታ ሲረግጡት ቡን... ይል የነበረ ጣውላዋ በሰም ታሽቶ አብረቅርቃለች፡፡ ጠረጴዛና ወንበሮች ተኮልኩለዋል፡፡ ጠጅና ጠላ በጠርሙስ ተሞልቶ ከላይ በነጭ ወረቀት በቄንጥ ተሸፍኖ በየጠረጴዛው ላይ ተደርድራል። ሸክላ ሳህኖች በየጠርሙሶቹ መሀል መደዳውን ተቀምጠዋል፡፡
የሸረሪቶችና የአይጦች መፈንጫ ሆና የከረመችው ጎጆ ሰርገኞች የሚታደሙባት፣ ዋንጫዎቻቸውን እያጋጩ የሚጨፍሩባት፣ ሙሽሮች ደግሞ የፍቅር አክርማቸውን የሚቀጩባት ጫጉላ ቤት ለመሆን ቅድመ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡ ልዩ ሆና ደምቃለች፡፡ አዎን ታደሰ ሰላማዊትን የሚያገባበት ቀን፡፡ ዕለተ እሁድ.…የዛሬዎቹ ሙሽሮች በማዘጋጃ ቤት በሽማግሌ
ዎች ፊት በወረቀት ፊርማ ሳይሆን ተፈቃቅደውና ተማምነው ሊቆራኙ
የተዘጋጁበት ቀን ነው፡፡
ዛሬ ሰላማዊት ከእሥር ቤት ወጥታ ወደ ነፃ ህይወት ለመቀላቀል ከዚያ ስቃይ ከበዛበት የሴተኛ አዳሪነት ህይወት ተላቃ ከምትወደው ሰው ጋር አብራ ለመኖር እምነትን ብቻ ውል አድርጋ ፍቅርን ብቻ ሰማንያ አድርጋ አዲስ ህይወት ለመጀመር የተዘጋጀችበት ቀን ነው።
እማማ ወደሬ ዕድለኛ ሆኑ። የወይዘሮ ስመኝን እጅ መድኃኒት አድርጎላቸው ከሞት ተረፉና በልባቸው ስቀው፣ አጨብጭበው መርቀው ያስተሳሰሯቸው ልጆቻቸውን ለመዳር በቁ፡፡ እንደተመኙት በጥርሶቻቸው
እየሳቁ በእጆቻቸው እያጨበጨቡና ልባቸው በደስታ እየጨፈረች በአዲስ ነጭ የአገር ባህል ልብስ አጊጠው በእናትነት ወግ ሙሽሪትን ለሙሽራው ለማስረከብ ጉድ ጉድ ለማለት ታደሉ፡፡ ሰላማዊት አምራለች። ተውባለች፡፡ የውቦች ውብ! የቆንጆዎች ቆንጆ! ሆናለች። ባማረ አለባበስ አጊጣ ፀጉሯን በወጉ ተሰርታ ዐይኖቿ ኩል ተኩለው እንደ ጽጌረዳ አበባ ፈክታላች። ሸርሙጣ ከሚል ወራዳ ስም ተላቃ ሙሽሪት የመባል ወግ ማዕግረ ደርሷታል፡፡ የተለያዩ ወንዶችን በወሲብ እያስተናገደች መኖር ከጀመረች ወዲህ ወደር የሌለው ደስታ ያገኘችበትና እንደ አዲስ የተወለደችበት ቀን
ሆኖ የተሰማት ገና ዛሬ ነው። ከዛሬዋ ዕለት ጀምሮ ከምትወደው ሰው ጋር እስከመጨረሻው በፍቅርና በደስታ ልትኖር የእገሌ ሚስት ባለ ትዳር ተብላ ልትጠራ ነው፡፡
"ሰላም እንግዲህ ጣጣችሁን ቶሎ ቶሎ በሉና ጨርሱ። የመምጫ ሰዓታቸው እየደረሰ ነው” አሉ ወይዘሮ ወደሬ ተፍ ተፍ እያሉና የምትኳኳላውን ልጅ በፍቅር እየተመለከቱ።
ዛሬ ሰላማዊትን በማስዋብና አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረግ በኩል ሙሉ ሃላፊነቱን የወሰደችው ጽጌ ነች።ያቺ
ገበያዋን የዘጋችባት ልጅ
ያቺ ለሰፈሩ ሴተኛ አዳሪዎች ምላስ አሳልፋ የሰጠቻት ልጅ ሰፈሩን እስከመጨረሻው ጥላላት ልትሄድላት ነውና ከዚያ በፊት የነበረውን ቂም ከዚያ በፊት የነበረውን የጥላቻ ስሜት ፍፁም እርግፍ አድርጋ ረስታ እንደ ታላቅ እህት እየተንከባከበች የውበቷን እንከን እየነቀሰች አሳምራ
እያዘጋጀቻት ነው።
“እሺ እማማ ጨርሰናል እኮ!" አለች ጽጌ እየተጣደፈች፡፡ ወይዘሮ ወደሬ የዛሬ ሁኔታቸው መቼም ለጉድ ነው። ወልደው አሳድገው ለትዳር እንዳበቋት ልጃገረድ ሰላማዊትን አሥር ጊዜ እየተመለከቱ ውበቷን እያደነቁ
ሁለመናቸው በደስታ ስቋል። የፊታቸው ፈገግታ ከእርጅናቸው ውስጥ ደብዝዞ ብቅ ባለው የልጅነት ውበታቸው ምክንያት ለወትሮው መወላገዱ ከሩቁ ይታይ የነበረው ጥርሳቸውን ሁሉ አሳምሮታል። ሰላማዊት
ጣጣዋን ጨራረሰች።ዝግጁ ሙሽሪት! ሽቅርቅር፣ ዝንጥ አለች። የዛሬው የሰላማዊት ሙሽርነት በሚስጥር ቢያዝም አልፎ አልፎ ማፈትለኩ አልቀረም ነበር፡፡ ጽጌ ለጓደኞቿ ሹክ... ብላቸው ውስጥ ውስጡን ወሬው ተዳርሶ ለአንዳንዶቹ የቡና ማጣጫ ሆኖላቸዋል።
በሰላማዊት ጉዳይ የተነጋገሩባት ሴተኛ አዳሪዎቹ ብቻ አልነበሩም፡፡
ከእማማ ወደሬ መሸታ ቤት ፊት ለፊት ባለው ትልቅ የመኖሪያ ግቢ
ውስጥ የሚኖሩት የነጋዴው የአቶ ዘላለም ልጅ ተማሪዋ ምንተስኖትም የዚሁ የሃሜት ሱሰኞች በሽታ ለክፏት የውጪውን በር ከፍታ ጓደኛዋ ሊባኖን ስታስገባት ሰላማዊትን እያማችላት ነበር፡፡
“ኡ. ኡ. ቴ! የሸርሙጣ ሙሽራ አይተንም ሰምተንም አናውቅ!” ከንፈሯን ወደ ጎን እየሽረመመች፡፡
“በቀደም የነገርሽኝን ነው አይደል? እውነት ልታገባ ነው እንዴ?” አለች
ሊባኖስ ወደ ግቢው እየዘለቀች።
"ከየት የመጣ ፋራ ነው በናትሽ ? የጠላ ቤት ሸርሙጣ ሚስቱ ለማድረግ አበሳውን የሚያይ አይገርምም? አ.ሃ..ሃ..ሃ.ሃ." እንጥሏ እስከሚታይ ድረስ አፏን ከፍታ ሳቀች።
"ፍቅር ከያዘው ምን ታደርጊዋለሽ? እንኳን ሴተኛ አዳሪ ሰው ከወደደ
ቆማጣና እውር ማግባቱ ይቀራል ?” አለች ሊባኖስ፡
“ከሽርሙጣ ቆማጣ ይሻላል።ለጊዜው መደበሪያ ልታደርገው ካልሆነ በስተቀር አብራው ትኖራለች የሚል እምነትም የለኝም" “እንደሱ ብለሽ ባትደምድሚ ይሻላል። አብዛኛዎቹ ሴተኛ አዳሪዎች የችግር ማእበል ገፍትሮ ዳር ላይ ሲጥላቸውና ዙሪያው ገደል ሲሆንባቸው እንጂ ፈልገው የገቡበት አይደለም፡፡
አጋጣሚውን ካገኙ ቤተሰብ
መስርተው በታማኝነት ለመኖር ምንም የሚያግዳቸው ነገር ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ ቅድስት እንደነገረችኝ ከሆነ ደግሞ ሰላማዊት በጣም የምታሳዝን ልጅ ናት። ወላጆቿ የሞቱባት፣ምን የመሰለ ወንድሟን ማጅራት
መቺዎች ደብድበው ያለረዳት ያስቀሯትና ትምህርቷን አቋርጣ በዚህ ህይወት ውስጥ ለመግባት የተገደደች አሳዛኝ ልጅ መሆኗን አጫውታኛለች። እንደኔ እሷን ያገኘ ባል የታደለ ነው" ስትል ሊባኖስ ምንተስኖትን ተቃወመቻት።
"ምነው ጠበቃ ሆንሽላት በናትሽ ? እኔ በበኩሌ በየቀኑ አዳዲስ ባሎችን እያገባችና ገላዋን እየቸረቸረች የኖረች ሴት ስፊ ልማዷን እርግፍ አድርጋ
በጠባብ ጐጆ ውስጥ ዲቃላዋን እያጫወተች መኖርን በቀላሉ ትለምደዋ ለች ብዬ አላስብም”
“ምን እያልሽ ነው ምንተስኖት? በአልኮል የተሟሽ የሰካራም አፍ ጠረን እንደ ሰንደል እየታጠኑ የአባለዘር በሽታን በጅምላና በችርቻሮ ከሚያከፋፍሉ ዝሙተኞች ጋር ለግብረ ሥጋ መውደቅና መነሳት ኑሮ መሆኑ
ነው እንዴ? ሰፊ ልማድ የምትይውስ ከፍላጐት ውጪ ስሜት አልባ ገላን እየቸረቸሩ ሳንቲም በመለቃቀም የሚገኝ ነው እንዴ? በየቀኑ መኳኳሉና
አዳዲስ ልብስ መቀያየሩ ትርጉም ያለው መሰለሽ? ውጫዊ መብለጭለጭ እኮ ውስጣዊ መብለጭለጭን አያመጣም፡፡ ቢከፍቱት ተልባ ነው፡፡ የምትወጂውና የሚወድሽ የትዳር ጓደኛ ስታገኚ፣ተስመው የማይጠገቡ ህፃናት እናት ሆነሽ መኖር ስትጀምሪ ብቻ ነው ኑሮ ኑሮ የሚሆነው። ትዳሬን ሚስቴን ልጆቼን የሚል አሳቢ ባል ካገኘሽ ደግሞ ከዚያ በላይ ደስታ ከዚያ
በላይ እርካታ ይኖራል ብዬ አላስብም”
“አንቺ እንደምትይው አይነት ባል እንደዚህ በቀላሉ የሚገኝ ቢሆን እሰየው ነበር፡፡ ትዳሬን፣ ልጆቼን የሚልና ከራሱ በፊት ለትዳሩና ለልጆቹ የሚያስብ ወንድ ደግሞ ሚስት ለማግባት የጠላ ቤት ሽርሙጣን የመጀመሪያ
ምርጫው ያደርጋል የሚል እምነት የለኝም” አለች ምንተስኖት ባለመሸነፍ ስሜት ።

👍2❤1
“መገናኛ ቦታቸው ጠላ ቤትም ሆነ መናፈሻ ውስጥ ዋናው ቁም ነገሩ
መግባባቱና ልብ ለልብ መተዋወቁ ነው፡፡ የባሏን ቀላዋጭ ዐይኖች እንደ ጋሪ ፈረስ የመከለል አቅም ያላትና ከትዳሩ ውጭ እንዳያይ የማድረግ ችሎታ ያላት ሚስት ከሆነች የተገናኙበት ቦታ የተለየ ትርጉም ይኖረዋል
ብዬ አላስብም፡፡ መገናኛ ቦታ በትዳር አብሮ ለመዝለቅ ልዩ መመዘኛ አይሆንም፡፡ ባሏ ፍቅርን ሲፈልግ ኤጭ! የምትለው ከሆነና የራሷን ስሜት ብቻ የምታዳምጥ ከሆነ ግን መገናኛ ቦታቸው ቤተ መንግስት ውስጥ ቢሆን እንኳ አብረው ሊዘልቁ አይችሉም፡፡ የትም ተገናኙ የት እውነተኛ ፍቅርን ከሚስቱ የሚያገኝ ባል ፍቅሩን ወደ ጎን ትቶ ስለተገናኙበት ቦታ በመጨነቅ ትዳሩን ያፈርሳል ብዬ አላስብም። ዋናው ቁም ነገር ልብ
ለልብ መፈቃቀዱ ነው፡፡ ከመሸታ ቤት ሚስት የማትገኝ መስሎሽ ከሆነ ግን በተጋቡ ማግስት በየፍርድ ቤቱ ለፍቺ የሚጓተቱ በሙሉ ከመሽታ ቤት የተገኙ ሚስቶች ያለመሆናቸውን ጠይቀሽ እውነቱን ስትረጂ ያን ጊዜ የበለጠ ይገባሻል። እንደኔ እንደኔ ከመሸታ ቤት የሚገኙ ሚስቶች ችግሩን በሚገባ ቀምሰው የተቀጡ በመሆናቸው ትዳራቸውን ጠበቅ አድርገው ለመያዝ የሚሻሉ ይመስለኛል”
“ስለ ሰላማዊት መሰለኝ የምናወራው ቀስ በቀስ ወደ ሌላ ፍልስፍና ውስጥ እየገባን ስለሆነ እዚሁ ላይ አቁመን ወደ ዋናው ጉዳያችን ብናመራ አይሻልም? ” አለች ምንተስኖት።
“አንቺ ስላመጣሽው ነው እኮ ምንቲ! ደግሞም ርእሳችንን ብዙም የለቀቅን አልመስለኝም፡፡አንቺም እኔም በፆታችን ሴቶች በመሆናችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይመለከተናል።
ለዛሬው ግን እንዳልሽው በዚሁ እናብቃና ወደ ጥናታችን እንግባ” አለች ሊባኖስ።
ምንተስኖትና ሊባኖስ ብቻ ሳይሆኑ የሰላማዊትን ጋብቻ አስመልክቶ ሹክሹክታውን የስሙ ሴተኛ አዳሪዎች በሙሉ ሲንሾካሾኩና ስሟን እንደ ማስቲካ ሊያኝኩት ነበር የከረሙት።ግማሹ እሰይ ሊል ግማሹ በቅናት እንደ ሽንኩርት ሲልጣት ነው የሰነበተው። በአካባቢዋ ያሉት ብዙዎቹ ሴተኛ አዳሪዎች ሲቀኑባትም በአንድ በኩል ደግሞ እፎይ ብለዋል።
ወንዱን ሁሉ ያንጋጋች፣ እርስ በርሱ ያተራመሰች፣ ገበያቸውን ያቀዘቀዘች ናትና ከዚያ አካባቢ ስትነቀልላቸው ገበያቸው ተመልሶ እንደሚደራ ተስፋ ሰንቀዋል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ታደሰ ሙሉ ጥቁር ኮትና ሱሪ ከነጭ ሸሚዝና ከቀይ ክራቫት ጋር
ለብሶ ሽክ ብሎ አምሮበታል። ሠርገኞችም ሚዜዎችም ታዛቢዎችም ሆነው በሱ በኩል የተገኙት ሦስት አጃቢዎች ናቸው። በዚህ ሁኔታ ታዴ ሠርገኞቹን ይዞ ወደ ወይዘሮ ወደሬ ቤት በታክሲ በረሩ.... ከቤት ሲደርሱ
ሳሙትና ሦስቱን ጓደኞቹን ተራ በተራ እጅ እየነሱ አስገቧቸው፡፡ እንደዚያ ተውቦ ልዩ ግርማ ሞገስ ተጎናፅፎ በአዲስ ልብስ አሸብርቆና ደምቆ ፊቱ በደስታ እንደበራ ወደ ውስጥ ሲዘልቅ ሰላማዊት ደስታዋ እጥፍ
ድርብ ሆነ።
ከሦስቱ የታደሰ ጓደኞቹ መካከል የአስር አለቃ ንጉሤ መብራቱ ለታደሰ ልዩ ፍቅርና አክብሮት ያለው ጓደኛው ነው፡፡ እንደ አቅሚቲ ሠርግ ከተባለ አንደኛ ሚዜ ያደረገውስ ለዚሁ አይደል? የክብር እንግዶቹ የተዘጋጀላቸውን ስፍራ ያዙ። ሙሽራና ሙሽሪት መሆናቸው ነው።በጥቁርና
ነጭ ዊስኪ ጠርሙስ ላይ እንደሚታዩት ድመቶች ጥቁርና ነጭ ሆነው ግራና ቀኝ ጉብ ብለው አምረውና ተውበው ሲታዩ ያስቀናሉ። ሁለቱም ከደስታ ብዛት ሁለመናቸው ስቋል፡፡ ምሳው ቀርቦ መብላት መጠጣት ተጀመረ፡፡ እማማ ወደሬ ኃይሉንና ጉልበቱን ከየት እንዳመጡት አይታ
ወቅም፡፡ ለዛሬዋ እለት ብለው በቁጠባ ያጠራቀሙት ጉልበት ነው የሚመስለው፡፡ መስተንግዶው ቀጠለ..በዚህ ሁኔታ ብዙ ቆዩ።ሁሉም እስከ
ሚጠግብ ድረስ በላ... ጠጣ፡፡ ጠጅ፣ ጠላ፣ አረቄ... እንደ ልብ ተወሰደ።
አስር አለቃ ንጉሤ ገበታው ከተነሳ በኋላ በልቡ ውስጥ ሲብላላ የቆየው ስሜቱን ለመግለጽ ተስተካከለ፡፡ አስር አለቃ ከታደሰ ጋር የዕድሜ አቻነት ይታይበታል፡፡ መልኩ ቀይ ሆኖ ቁመቱ አጠር ያለ አፍንጫው ቀጥ ብሎ የወረደና ዐይኖቹ ጐላ ጐላ ያሉ ናቸው። እነ ታደሰን ለመቀበል የተገኙት ሦስት በዕድሜ ገፋ ያሉ ወንዶችና አምስት ሴቶች ሲሆኑ ሁሉም
ወይዘሮ ወደሬ በጉርብትናና በዝምድና የጠሯቸው እንግዶች ነበሩ። በሰላማዊት በኩል የተገኙት ሠርገኞች ቁጥር ከጽጌና ከወይዘሮ ወደሬ ጋር በድምሩ አስራ አንድ ሰዎች መሆናቸው ነው። አሥር አለቃ ንጉሤ ብድግ
አለ፡፡ በቤቱ ውስጥ ያሉቱ በሙሉ ዐይኖቻቸውን ተከሉበት።
“እህህ..እህ... እናቶቼ ወንድሞቼና እህቶቼ..” ጉሮሮውን አፀዳና ቀጠለ....