#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሦስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ዛሬም በሱ የቡድን መሪነት ውስጥ በአባልነት በታቀፈው በሸጋው አንበሴ ቁመናና የዐይኖቹ ውበት ተማርካ በመልከ
መልካምነቱ ልቧ ተሸንፎ በፍቅሩ ነዳለት ጎንቻን ደብቃ ፍቅሯን እያስኮመኮመችው አለማቸውን እየቀጩ ነው።
ይሄንን ያላወቀው ጎንቻ ደግሞ ስሞኑን በብዙ አፈላላጊ ከተገናኘው ሰው ላይ ቀብድ ለመቀበል ተፈልጎ ሄዷል መቀስ ያንን ሹልክ እያለ እየመጣ
የሚቀምሰውን ፍቅር ለመቅመስ በዚያውም ተጨማሪ ገንዘብ ለመበደር ነበር የጎንቻን እግር ጠብቆ የገባው፡፡ እንደተገናኙ ተቃቀፉና አልጋው ላይ ወደቁ፡፡ ያንን የስርቆሽ ፍትወት ከፈፀሙ በኋላ በጀርባቸው ተንጋለሉ። ዓለሚቱ ልቧ ድው ድው ማለት ጀመረ።ስርቆሹን ትወደዋለች፡፡
ይጣፍጣታል።የሚያስከትለውን መዘዝ ስታሰላስለው ግን ትሰጋለች። ትርበተበታለች። በዚያ የስሜት እሳት ውስጥ ገብታ ፍሙን፣ ረመጡን እስከምታጣጥመው ድረስ ምንም አይነት የፍርሃት ስሜት አያድርባትም፡፡አደጋው አይታወሳትም፡፡ ሁሉ ነገር ጎልቶ የሚታያት ከዚያ በኋላ ነው፡፡ አሁንም የፍትወት ስሜቷን ካረካች በኋላ ስጋቷ በረታና መተንፈስ ግድ ሆነባት።
"አይታወቅም የሱ ነገር ወይ በመሀል ከተፍ ይላል። ቶሎ ቶሎ ተጨዋውተን በጊዜ ብትሄድ አይሻልም?" አለችው፡፡
"ልክ ነሽ፡፡ እውነትሽን ነው። እኔም ሳስበው ነበር። እሱ እኮ ስላቢ ነው፡፡ በድንገት ከች! ሊል ይችላል ፡ጉሮሮ ለጉሮሮ ሳንያያዝና በእጄ ሰበብ ሳይሆንብኝ ብሄድ ይሻላል” አለና ከአልጋው ላይ ተነስቶ ሱሪውን ማጥለቅ ጀመረ፡፡ እሷም ተነሳች፡፡ዓለምዬ ዛሬ ችስታ ወግሮኛል ሁለት መቶ ብር ትጨምሪልኛለሽ፡፡ አንድ
ላይ ወደ አንድ ሺህ መጠጋቱ ነው" አላት፡፡“ትቀልዳለህ እንዴ አንበሴ?! እንዲያውም ስሞኑን የሌለበትን የገንዘብ
መቆጣጠር ፀባይ እያሳየ ነው፡፡ አሁን በድንገት ውለጂ ቢለኝ ምን እመልስለታለሁ? ዛሬ ሁሉንም ይዘህ ትመጣለህ ብዬ ነበር የገመትኩት። አንተ ግን ጭራሽ በላይ በላዩ ልትጨምር ትፈልጋለህ፡ የበላችው ያስገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታልሆነ አሁንስ!" በስጨት ብላ ተናገረችው።
አንበሴ ያልጠበቀው ነበር፡፡ በሱ ቤት ተደብቆ እየመጣ የሚያቀምሳት ፍቅር ጣፍጧት ስለሚጠይቃት ገንዘብ ደንታ የሌላት መስሎት ነበር።
ተወድጃለሁ የፈለኩትን እንድታደርግልኝ ባዝዛት ትፈፅማለች ባይ ነበር፡፡
ለእንቢታው አንደበቷ የሚፈታ የተጠየቀችውን ገንዘብ ላጥ አድርጎ ለመስጠት እጅዋ የሚያጥር አልመሰለውም ነበር፡፡ በዓለሚቱና በገንዘብ መካከል ግን ቀልድ አልነበረም።
ሲቀር ፍቅሩ ተሽቀንጥሮ ይቀራል እንጂ ብሯን የምትበትን ሆና አልተገኘችም። እንደዚያም ሆኖ ግን ለሱ እጇ ብዙም አይጨክንም ነበር። ከዚያ በፊት ያለውን በደስታ ነው የሰጠችው
ዛሬ በዛባትና ፊት ነሳችው እንጂ፡፡ ባሏ ጎንቻ የቡድኑ ገንዘብ አዛዥ ሆኖ የበለጠውን ድርሻ መውሰዱ ውስጥ ውስጡን በቅናት ቢያቃጥለውም ቁልፉን በእጁ ይዟል። የገንዘቡን ካዝና የዓለሚቱን ልብ ተቆጣጥሯልና
በተዘዋዋሪ መንገድ እየተካስ ይፅናናል።ይሄ በመሆኑ እንጂ እንደ ጎንቻ አያያዝ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ድብልቅልቅ ብለው በተጣሉ ነበር፡፡ ዓለሚቱ ቀስ ትልና ብሩንም ፍቅሩንም እየሰረቀች ትሰጠዋለች። ይቀዘቅዛል፡፡
"ተይ እንጂ ዓለሚቱ! ምን ማለትሽ ነው? ገንዘቡን ለጥብቅ ጉዳይ ስለምፈልገው ነው እኮ!ደግሞ ብዙ ችግር እንደሌለብኝ ታውቂያለሽ፡፡ በሙሉ እምነት ነው ወዳንቺ የመጣሁት። ዓለሚቱ ካንቺ ሌላ ማንንም ብድር
መጠየቅ አልፈልግም!"
“አንበሴ ሙት አትቀልድ! ይልቁንስ የወሰድከውን ቶሎ መልስ እንዳን
ጣላ!"
ትቀልጃለሽ እንዴ ዓለሚቱ?"
አልቀለድኩም አንተ ነህ የምትቀልደው!"
“ኧረ በናትሽ ዓለሚቱ?!"
“አይገባህም እንዴ?!" ቁጣዋ ባሰ...የበለጠ ተደናገጠ፡፡ ፕሮግራሙ ሊከሽፍ ነው፡፡ የበርጫውና የጨብሲው... ከአዲሷ የሴት ጓደኛው ጋር የያዘው ቀጠሮ ዜሮ…ደግሞም ባለሥልጣን ነኝ ብሉ የዋሻት፣ ልቡ የወደዳት ቆንጆ ልጅ....
“በቃ እንጣላ?!"
«አንበሴ ሙት በዚህስ እንጣላ! በዚህስ የፈለከውን አምጣ እንጂ አላደርገውም! ትንሽ አታስብም እንዴ?! ያምነኛል እንጂ ገንዘቡን ያውቀዋል እኮ! ምን ልለው ነው በተለይ እንደዚህ መንገብገቡ ከሴት ጋር ቀጠሮ ቢኖረው ነው ብላ ስለገመተች ጨከነችበት።
“በዚህ ላይ አንተ ጋ ያለው ብቻ አይደለም፡፡ በአራጣ ያበደርኳቸው
ብዙዎቹ መክፈል እያቃታቸው አሮጌ ዕቃ እያግበሰበሱልኝ ነው። አሮጌ እቃ ለኔ ምን ያደርግልኛል? የረቡ ዕቃዎች ያየሃቸው ሀብሎችና ቀለበቶች ብቻ ናቸው። ሌላው ዝባዝንኬ ቅራቅንቦ ነው!”
"ገባኝ!... እኔን እኮ እንደሌላው አራጣ ተበዳሪ ማየት የለብሽም። ማወቅ ያለብሽ ነገር ገንዘቡን በጋራ የሰራነው መሆኑን ጭምር ነው! የንዴት ትኩሳት ማተኮስ ጀመረውና ሳያስበው ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ የወጣ
ንግግር ተናገራት፡፡
"ኧረ? በጋራ?! በል ተወው! የራስህን ድርሻማ እየላፍከው ሄደሃል። ከዚህ ውስጥ ሰባራ ሳንቲም የባለቤትነት መብት የለህም! በጠየከኝ ቁጥር እያ
ወጣሁ ያስታቀፍኩህ እኮ የተግባባን መስሎኝ ነበር! ለካስ የራስህ ገንዘብ አድርገህ ነዋ እስካሁን ያልመለስከው?! አንበሴ ሙት እንደዚህ አይነት የማይረባ አስተሳሰብ ያለህ ሰው አትመስለኝም ነበር፡፡ ወይ የሰው ነገር? ለካ ሰው እያደር ነው የሚታወቀው?! እና የወሰድከውን ለመመለስ ሀሳብ የለህም ማለት ነው?! እንዴት ያለኸው ቀላል ነህ ባክህ?! ይህንን ያዳፈረህ ጎንቻን ደብቄ ቀሚሴን ስለገለብኩልህ ይሆን እንዴ ? እሱ ይሆናል
እንጂ ያናናቀን! ለምነህ የወሰድከውን ከምስጋና ጋር መመለስ ሲገባህ ጭራሽ..." ፊቷ በንዴት ቀላ፡፡
“እና አሁን አትሰጭኝም?!"
“እስቲ ድብን ያደርግህ እንደሆነም ጉድ አያለሁ! ሰባራ ሳንቲም! " አንበሴ የዓለሚቱን ንዴት ሲመለከት አጉል እልህ ምንም ዋጋ እንደሌለው ተረዳ፡፡ ከብዙ ጉልበት ትንሽ ብልሃት የምትበልጥበትን ጊዜ አሰበ፡፡ በዘዴ አባብሎ ብዙ ነገር ማድረግ ሲችል ብጥብጥ ፈጥሮ ቢሄድ ራሱን ይጎዳል እንጂ እሷን አይጎዳትም ይሄን ማመዛዘን ጀመረ፡፡ ቀስ በቀስ ረገበና ልምምጡን ቀጠለ፡፡ ከውስጡ ንዴትና ብሽቀት ቢያቃጥሉትም ከውጭ ሌላ ሆነ፡፡ ፈገግ አለ፡፡
“እሺ ዓለምዬ እንዳልሽው ይሁን። ማወቅ ያለብሽ ግን እኔን ልቤን የነሳሽው ጣፋጭ ፍቅርሽ እንጂ ገንዘብሽ ያለመሆኑን ነው። ገንዘብ ገደል ይግባ! ፍላጎቴ ፍቅር ሳይሆን ገንዘብ ቢሆን ኖሮ በሴት ብር ብቻ ፎቅ ቤት መስራት እችል ነበር፡፡ ያንን ግን አልፈልገውም፡፡ እዚህ የባልሽን ኮቴ እየጠበኩ ስር ስርሽ የሚያስሮጠኝ ፍቅርሽ ብቻ ነው። አሁንም ቢሆን እኔ የምፈልገው ገንዘብሽን ሳይሆን ፍቅርሽን ነውና አለብህ የም
ትይኝን በሙሉ አምጥቼ እወረውርልሻለሁ። አንቺነትሽን እንደዚህ የለወጣው ገንዘብ ከሆነ ካንቺ የሚተርፍ ገንዘብ አስታቅፍሻለሁ። እውነቴን
ነው የምልሽ ሩቅ ቦታ ስላስቀመጥኩት እንጂ እንኳን ለራሴ ለሌላ የምትርፍ ስው ነኝ ጉራውን ቸረቸረላት።
ዓለሚቱ ልቧ ወከክ... አለ፡፡ እውነትም አንበሴ ገንዘብ በገንዘብ ሲያደርጋት ታያት። በአምስቱ ጣቶቹ ላይ የደረደራቸው የወርቅ ቀለበቶቹ በየቀኑ የሚቀያይራቸው ፋሽን ልብሶቹ ሁሉ ነገሩ የገንዘብ ችግር የሌለበት መሆኑን ይመሰክራሉ። ገንዘብ ስጠኝ ብላ ባለመጠየቋ እንጂ ብትጠይቀው ሊያንበሸብሻት እንደሚችል ተስፋ አደረገች፡፡ በአንድ ጊዜ' በደስታ

👍2😱1
ፈንድቃ ከንዴቷ ውስጥ ቦግ! ብሎ የወጣው የመቋመጥ ስሜት ለአንበሴ በጉልህ ታየው "የሴት ልጅ ልብ ሩብ ግራም ቅቤን ያክል ትመዝናለች እሷም በአግባቡ ከታሸችና ከሞቀች እንደ ሰም ቀልጣ እንደ ቅቤ መፍሰስ
ትጀምራለች” የሚለው አንበሴ በዓለሚቱ ላይ ተሳካለት፡፡ በሌለ ተስፋ ልቧን አቅልጦ በአንዴ አቀዘቀዛት እቅፍ አድርጎ ከንፈሯን እየሳመ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ገንዘቡን እንደሚያስታቅፋት ቃል ገባላት፡፡ ጉንጫን ቀና አድርጎ አይን አይኖቿን በፍቅር እያየ ግራ እጁን ትከሻዋ ላይ ሲያሳርፍ የዐይኖቿ ብሌኖች ሽቅብ ወጥተው ከአካባቢው ተሰወሩ ...
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የዲግሪ ተመራቂውና የረጅም ጊዜ ዕቅድ አላሚው፣ የአድማስ ባሻገር
ትዳር መስራቹ፣ የእናትና የእህቱ አለኝታና መከታ የሆነው ጌትነት
መኩሪያ ራሱን በእውቀት እያሳደገ መምጣቱ፣ ቀና ደፋ እያለ ለስራው
ሲታትር መገኘቱ ለአደጋ እያጋለጠው መሆኑን ለአንድ ቀን እንኳ አስቦት አያውቅም ነበር፡፡
የሱ ድካምና ጥረት በዚያ የብዙዎችን ትዳር ባፈረሰው፣ በዚያ የብዙ ንፁሀንን ህይወት በቀጠፈው፣በዚያ በንፁሀን ደም እጁን በታጠበው፣ በዚያ
በጭካኔው ወደር በማይገኝለት አደገኛ ሽፍታና ወንጀለኛ እጅ የሚጥለው መሆኑን እንኳንስ ጌትነት ማንም የጠረጠረ አልነበረም። ብሩህ ተስፋው
እንደ ጎህ እየቀደደ የጎመራውን ፍሬ አሻግሮ በሚያየው ቤተሰብ ላይም መዓተ ቁጣው ሊወርድ እየተቃረበ መምጣቱን ማንም የገመተ አልነበረም።
ጌትሽ በምረቃህ ላይ ባለመገኘቴ ይቅርታ አድርግልኝ”ብሎ አለቃው ልኡልስገድ ሲለምነው ከበስተጀርባው ተንኮል መኖሩን ለመገመት ጠንቋይ መሆንን የሚጠይቅ ነበር፡፡
“ጋሼ ልዑል ሰገድ ባይመችህ እንጂ የኔ ደስታ ያንተ ደስታ እንደሚሆን አልጠራጠርም፡፡ ምንም ቅሬታ አልተሰማኝም" በማለት ስሜቱን በቅንነት አረጋግጦለት ነበር፡፡
"ጌትሽ የደስታህ ተካፋይ ባለመሆኔ ቅር ያልተሰኘህ መሆኑን የማውቀው ዛሬ ካሳዬን ስትቀበለኝ ብቻ ነው፡፡ ቅሬታ አልተሰማኝም ብትለኝ አላምንም
አጥፍቻለሁና መንፈሴ ርካታ እንዲያገኝ የዛሬ ግብዣዬን ተቀበለኝ?" ሲል ተማፀነው።
ጋሽ ልዑል ሰገድ እባክህ
ይቅርታህን?”በማለት የመጠጥ ግብዣውን እንዲምረው ጌትነት ልመና አቀረበለት።
“ተው ጌትነት አታስቀይመኝ አንድ ብቻ ሌላ አላስገድድህም" በማለት የተማፅኖ ጥያቄውን ሲደግምለት አማረችን እንኳ እንቢ ያላትን ለማድረግ ተገደደ። መቼም መርዝ ማለት ነው፡፡ አለቃውን ላለማስቀየም፣ የተጨነቀለትን ሰው ለማስደሰት ከህይወቱ ላይ አንድ ነገር አጉድሎ ልመናውን
ሊቀበል ወሰነ።ጥያቄው “አንድ ጠብታ በሞቴ?” ብሎ የለመነውን ሰው ለማስደሰት መርዝ የመጠጣትን ያክል ከባድ ሆኖ ቢሰማውም የውስጥ
ስሜቱን ደብቆ አብሮት ከመጠጥ ቤት ገባ፡፡ ከዚያም አንድ ቀዝቃዛ
ቢራ አስከፈተለትና በፈጠራ የታገዘ የመስሪያ ቤቱን ታሪክ ይዘረግፍለት ጀመር፡፡ የጌትነትን የስራ ብቃት እያደነቀ በሌላ ጊዜ የማይደግመውን ተረት ይቀባጥርለት ጀመር፡፡ ጌትነት ምንም ሳይታወቀው ከምሽቱ
አራት ሰዓት ሆነ።
“ጋሽ ልዑል ሰገድ በጣም መሽ፡፡ መቼም ያንተ ነገር ሆኖብኝ እንጂ
እስከዛሬ ድረስ ሞክሬው አላውቅም። እህቴ ትንሽ ልጅ ናት ትሰጋላች እባክህ ልሂድ..." አለው፡፡ ልኡል ሰገድ እየቀበጣጠረ እንደምንም ብሎ እስከ አራት ሰዓት ተኩል አዘገየው፡፡ የመጨረሻዋ ሰዓት እየተቃረበች
መጣች። ይህን የሚያውቁት ጎንቻ ጓደኞቹና ልዑል ሰገድ ብቻ ነበሩ።
ምስኪኑ የዛሬው የአለቃው ግብዣ አስጨንቆት ውለታው እየከበደው
ሰዓቱ በመምሽቱ ሳይወድ በግዱ ቆየና ሊሰናበተው ተዘጋጀ።
“እኔ እንደሆንኩ እስከተፈቀደልኝ መንፈቀ ለሊት ድረስ ማምሽቴ የማይቀር ነው በል ጌትሽ መሽቶብሃል ሂድ ደህና እደር ሃ..ሃ! ሃ! ሃ!" አይ አንቺ ከርፋፋ ድግስሽን ያላወቅሽ መሆኑ ነው። በምፀት አስካካበት ጌትነት እውነተኛ ስንብት መስሎትና እንደ እንቆቆ መራራ የሆነው የልኡልስገድ ምፀታዊ የሳቅ ሚስጥር በውል ሳይገባው አብሮት ሳቀና ተሰናብቶት ሆቴሉን ለቀቀ... ልዑል ሰገድ ጠላቱን ሊበቀል ወደ አዲስ ህይወት...
ጌትነት ደግሞ ወደ ድቅድቅ ጨለማው ወደ ፅልመት አዘቅት...
✨ይቀጥላል✨

#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...በዲላ ከተማ ዜሮ አምስት ቀበሌ ውስጥ ስምንተኛ መንገድ ላይ ፊቱን ለማታ ፀሃይ ሰጥቶ በተገነባው በወይዘሮ ዘነቡ አሰግድ ግቢ ውስጥ በስተጓሮ በኩል ያለው የሽዋዬና የሔዋን መኖሪያ ቤት ከጣሪያና ግድግዳው በስተቀር በውስጡ ይታይ የነበረ ትዕይንት ሁሉ ዛሬ መልኩን ቀይሯል፡፡ የሁለት የእትማማች
ጣውንቶች መኖሪያ ሆኖ ደስታ ርቆታል፡፡ በፍቅር ተስፋ ለምልመው የነበሩ ልቦች ዛሬ የሀዘን ድባብ ጥሎባቸዋል፡፡ በሳቅ ይፍለቀለቁ የነበሩ ጥርሶች ዛሬ ተከድነዋል።
ፏ ብለው ይታዩ የነበሩ ፊቶች ዛሬ ግን አኩርፈው እንደ ኩልኩልት
ተንጠልጥለዋል። የአስቻለው እግሮች ተሰብስበው ቤቱ እንግዳ ናፍቆታል።
ሽዋዬ ፣ ሔዋንና አስቻለው በየራሳቸው የሀሳብ ጎዳና ይነጉዳሉ፡፡ የሽዋዬ ግን
ከሁሉም በተለየ ሁኔታ እንቅፋት የበዛበት ሆኗል፡፡ የሚቆጫት አስቻለውን ማጣቷ ብቻ አይደለም፤ በእሷ እምነት አስቻለውን የነጠቀቻት እህቷ በመሆኗ ከዚሁ ጋር ተያይዘው ይመጣሉ ብላ የምታስባቸው ማህበራዊ ቀውሶች ከወዲሁ ያስጨንቋት ይዘዋል። አስቻለውን በማፍቀሯና ከግንኙነታቸው መጥበቅ የተነሳ የኔ ነው ብላ
ለሌላ ሰው ያወራችም ይመስላታል። ዛሬ በእህቷ ተነጠቀች የሚል አሉባልታ
የሚነሣ እየመስላት ትሳቀቃለች:: ምናልባት አስቻለውና ሔዋን ወደፊት ቢጋቡ
“ትልቋ እያለች ትንሿ፣ ሥራ ያላት እያለች ተማሪዋ አገባች የሚል የዘመድ አዝማድ ሹክሹክታም ሲነሳባት ይታያታል፡፡ ወደፊት በሚፈጠር ቤተስባዊ ግንኝነት ሁልጊዜ እያየችው በቅናት እየተቃጠለች ልትኖር ነው። ዛሬ የገጠማትን የስሜት ሰቀቀን ሁልጊዜ እያስታወስች እንዴት መኖር እንደምትችል ይቸግራታል።
አዕምሮ ደግሞ ትንሽ የሀሳብ ቀዳዳ ከከፈቱለት ያቺነ በማስፋት የጭንቅ ተባይ እየፈጠረ ያቅበጠብጣልና የሽዋዬ መንፈስ በስጋት ተወጠረ፡፡ ቀኑን ያለ ዕረፍት
ሌሊቱን ያለ እንቅልፍ ታቀያይረው ጀመር፡፡
ከዚህ ሁላ ጭንቅ የሚገላግላት ብቸኛ መንገድ አስቻለውና ሔዋንን
ማለያየት ብቻ መሆኑ ታያት፣ ጨለማ የሆነባት ግን ማለያያው ዘዴ፡፡ አንዳንዴ ሔዋንን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ መፍትሄ የሚሆን መስሎ ይታያታል፡፡ ነገር ግን አስቻለው ሔዋንን፣ ሔዋን ደግሞ አስቻለውን እስካሉ ድረስ ከዚያስ ሄዶ ቢያመጣት? ወይም አስቻለው ከቤቷ ድርሽ እንዳይል ማድረግ ብትሞክርስ? ያም
አያዋጣ፡፡ ሔዋን ራሷ ወደ እሱ ቤት ልትሄድ ትችላለች። እንደ በግ አትዘጋባት፣ እንደ ጥጃ አታስራት፡ ወይ ደግሞ ስራዋን ትታ እሷን ስትጠብቅ አትውል! ሁሉም
መንገድ የማይጨበጥ ህልም ሆኖባታል::
ከመዋል ከማደር አንድ የተስፋ ብልጭታ ብቻ ማየት ጀመረች፡ ለዚያውም ይህ ነው ብላ የምትጠብቀው ግልጽ ውጤት ሳይኖር፡፡ ያም ቢሆን ከራሱ ከአስቻለው ያገኘችው ፍንጭ ነው። ከጥቂት ወራት በፊት አንድ ቀን እሷና አስቻለው በአንድ
ቡና ቤት ውስጥ ይዝናናሉ፡፡ የተቀመጠበት ቦታ መስኮት አጠገብ ስለነበረ መንገዱ
ይታያቸዋል። አስቻለው ድንገት ባርናባስን መንገድ ላይ ያየውና ሽዋዬን ጎሽም አድርጎ «ያን ሰውዬ ተመልከች» ይላታል፡፡
«የቱን?»
«ደማቅ ስማያዊ ካኪ የለበሰውን፡፡
«እሺ አየሁት»
«ዲላ ሆስፒታል ውስጥ ድርብ ስልጣን ያለው ሰው ነው፡፡» ካለ በኋላ በእሱና በባርናባስ መሀከል ያለውን ያለመግባባት የመነሻ ጀምሮ አሁን እስካሉብት ጊዚ ድረስ ያለውን ሁኔታ እንደ ቀልድ ያጫውታታል። ይህ ነገር በሸዋዬ ልብ ውስጥ አለ።
ግን ደግሞ አስቻለው አላወቀም እንጂ ሸዋዬና ባርናባስ በደንብ
ይተዋዉቃሉ፤ ያውም ከስምንት ዓመታት በፊት ጀምር፡፡ ሰበቡ ሸዋዩ ትምህርቷን እንደ ጨረሰች መምህርነት ተመድባ ወደ ያቤሎ መሄዷና ባርናባስ ደግሞ በወቅቱ
የግሉ ጤና ጣብያ የአስተዳደር ክፍል ኃላፊ ሆኖ ይሰራ የነበረ መሆኑ ነው። ሸዋዬ ያቤሎ ደርሳ ከመኪና እንደ ወረደች ማረፊያ የት እንደምታገኝ ስትጠይቅ የመኪና
ተራ ልጆች ወደ አንድ የማረፊያ ቦታ ይወስዷታል፡፡ ቤቱ ሆቴል ቤት አልነበረም፤ ነገር ግን ግቢው መስክ በርካታ በአልቤርጎ ዓይነት የተስሩ ክፍሎች አሉት።
ድንገተኛ እንግዳም ያርፍባቸዋል። ለወር ኮንትራትም ይሰጣል፡፡ ባርናባስም ከእነዚያ ክፍሎች እንዷን በኮንትራት ይዞ" ብቻውን ይኖር ነበር::
ሸዋዬ ከእነዚያ ክፍሎች በአንዷ ውስጥ አድራ በማግስቱም እዚያው ትደግማለች። በሦስተኛ ቀንም እንዲሁ። በኋላም ከዚያ የተሻለ መኖሪያ እንደማታገኝ
ሲገባት ልክ እንደ ባርናባስ ክፍሏን በኮንትራት ይዛ ትቀመጣለች፡፡ ከመዋል ከማደር ከየባርናባስ ጋር ይተዋወቃሉ፡፡ ቀስ በቀስ ይተራረባሉ። ይግባቡና ይፋቀራሉ፡፡መጨረሻ ላይ ልክ እንደ ደባል ሆነው አብረው መኖር ይጀምራሉ፡፡ ባርናባስ
በዕድሜው ጠና ያለ ቢሆንም ለሽዋዬ ግን ይመቻታል። እሷም ላእሱ ትሞቀዋለች።ያ ሁሉ ሲሆን ባርናባስ ባለ ትዳርና የልጆች አባት መሆኑን እንዲሁም ቤተሰቦቹ ዲላ
ከተማ ወስጥ እንደሚኖሩ ሸዋዬ አታውቅም ነበር። በእርግጥ ወደ ዲላ አዘውትሮ እንደሚሄድ ታውቃለች፡፡ ነገር ግን ለስራ ጉዳይ እያለ ስለሚያታልላት እሷም
አትጠረጥር ነበር።
በዚሁ ሁኔታ ለአንድ ዓመት ያህል ከቆዩ በኋላ ድንገት የባርናባስ የሰባት ወር ህጻን ልጁ ይሞትና ከዲላ መልዕክት የተቀበሉ የመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች
ወርዶው እንዲደርሰው ያደርጋሉ። በወቅቱ ሸዋዬ ማመን ቢያቅታትም ነገር ግን
በማግስቱ ጀምሮ ከባርናባስ ቤት ወጥታ ትሄዳለች፡፡ በዚያው ትቀራለች::ፍቅራቸውም ይቋረጣል።
ባርናባስ ከልጁ መሞት በኋላ በያቤሎ ብዙ አልቆየም፡፡ እድገትና ዝውውር አግኝቶ ዲላ በመግባት ከቤተሰቡ ጋር ይቀላቀላል። ይሁንና የባርናባስና የሸዋዬ
መለያየት የከረረ ጠብ አላስከተለም፤ ቆይቶም ቢሆን የፍቅር ውጭ ያለ ግንኙነት
ማስቀጠል የሚችል እርቅ ፈጽመዋል። ሸዋዬ ዲላ ከመጣችም ወዲሀ ከአለፈ ገደም እየተገናኙ ሰላምታ ይለዋወጣሉ። አስቻለው ስለ ባርናባስ ያወራት በነበረ ጊዜ ሸዋዬ ይህን ሁሉ በሆዷ ይዛለች፡ እሷ ግን ስለ ባርናባስ ለአስቻለው ትንፍሽ አላለችም::
ምን ሊያደርግላት እንደሚችል በውል ባይታወቃትም ሸዋዬ ለዛሬው ጭንቋ መላ ስታፈላልግ ባርናባስ ትዝ ብሏታል፡፡ የአስቻለው አለቃ ነውና፣ በዚያ ላይ አይስማሙምና፣ ለችግሬ መፍትሄ የሚያመጣ መላ ያፈላልግልኝ ይሆን?› እያለች
ለአንድ ወይም በሌላ ጉዳይ በልቧ ታውጠነጥነው ጀመር።
ነጋሪ
የሸዋዬ ሀሳብ በዚህ መልኩ ሲነጉድ ሔዋን ግን ስለ ጭንቀቷ እንጂ ችግሯን ሰለምታቃልልበት መንገድ የሚታያት አንዳች ነገር የለም፡፡ ሆነም አልሆነ ነገሩ ይበርድላት ዘንድ መጓጓት ብቻ ነው። ከዚያ ባለፈ አስቻለው ወደዚያ ግድም ድርሽ እንዳይል የጠበቀ አደራ በታፈሡ በኩል ልካበታለች:: ነገር ግን አደራውን
ስለመቀበሉ እርግጠኛ አይደለችም ድንገት የመጣ እንደሆነ እያለች ከመሳሳቀቅ
አልዳነችም፡፡
እስቻለው ደግሞ ያኮረፈው ወይም የሚያኮርፈው ሰው ስለሌለ ቤቴ ሰላም ይሁን እንጂ እዕምሮው ግን እረፍት አጥቷል። ዓይኖቹም ተለያይተዋል። በአካል አልጋው ላይ ተኝቶ ሀሳቡ ያለው በሸዋዬ ቤት ወስጥ ነው፡፡
በልሁና መርዕድ የነገሩት የሽዋዬና የሔዋን የተበላሸ ግንኙነት የጭንቁ ሁሉ መነሻ ነው። በዚያ ላይ ወደዚያ ቤት ድርሽ እንዳይል ሔዋን በታፈሡ በኩል ልካበት

👍7
መልዕክቱ ደርሶታል። በሁለቱ እህትማማቾች መካከል ስላሰው ግንኙነት ለውጥ መኖሩን ወይም ያለመኖሩን ማወቅ እንዳይችል የመገናኛ መንገዶች ሁሉ
ተዘግተዋል። እሱም ቀረ ታፈሡም አትሄድ፡፡ የሔዋን ሁኔታ ጨለማ ሆኖበት በሀሳብና በጭንቀት ይሰቃያል፡፡ በዚህ ሁኔታ ለአንድ ሳምንት ያህል ቆይቶ ጭንቀቱ
መተንፈሻ ሲያሳጣው ድንገተኛ ስሜት ወደ ሽዋዬ ቤት ሂድ ሂድ አለው ሩጥ ሩጥ!
ዕለቱ እረቡ ነው! በዚያ ዕለት እሱ የዘጠኝ ሰዓት ሥራ ገቢ ነው፡፡ ሔዋን የጠዋት ተማሪ፣ ሸዋዬም የከሰዓት ፈረቃ ሥራ ገቢ መሆናቸውን ያውቃል። በዚህ
አጋጣሚ ለአፍታም ቢሆን ሔዋንን አየት አድርጓት በዚያው ወደ ሥራ ሊሄድ ወስኖ ከቀኑ ሰባት ሰዓት አካባቢ ሦስተኛ መንገድ ላይ ከሚገኘው ቤቱ ተነስቶ ወደ
ሸዋዬ ቤት አመራ፡ መንገዱ እስከ አሥር ደቂቃ ይወስድበት የነበረ ቢሆንም በዕለቱ ግን በአምስት ደቂቃ ውስጥ እረምርሞት ከወይዘሮ ዘነቡ ግቢ በር ላይ ደረስ፡ ገርበብ ብሎ በተከፈተው የውጭ በር በኩል አንገቱን ብቅ አድርጎ ወደ ውስጥ ሲመለከት ወይዘሮ ዘነቡ ቤታቸው በረንዳ ላይ ሆነው እፈር በተሞሉ ጣሳዎች ላይ የተከሏቸውን አበቦች ሲንከባክበ አያቸው። ወትሮም አይፈራቸውም ነበርና
ሲያያቸው አልደነገጠም:: ትህትና የተሞላበት ሠላምታ አቅርቦላቸው ወደ ጓሮ አለፈ፥ ወደ ሸዋዬ ቤት፡፡ ፊት ለፊት ሲያይ ቤቱ ክፍት ነው፡፡ እንደ ሌባ ግራ ቀኙን ሰላል እያደረገ በፍጥነት ተራምዶ በሩ ላይ ሲደርስ ሔዋን ፊትለፊት ባለችው ፍራሽ ላይ ቁጭ ብላ እንጀራ በሳህን አቅርባ ምሣ ስትበላ አያት፡፡ ፈገግ ብሎ ወደ ውስጥ ገባና ወደ እሷ ጠጋ ሊል ሲል ሔዋን በድንጋጤ ኩርምትምት ስትል አያት፡፡
«አይዞሽ ብሎ አቅፎ ደግፎ ሊያፅናናት አሁንም ወደ እሷ ጠጋ ሊል ሲል ድንገት «ኦ» የሚል ድዎምጽ ተሰማው:: ወደ ግራው ዞር ብሎ ሲያይ ሸዋዬም
ከጓዳዋ በር አጠገብ ቁጭ ብላ እንጀራ በሳህን ይዛ ትበላለች::
«እንዴ!» አለ እስቻለው ሳያውቀው ጮክ ባለ ድምጽ። በድንጋጤ ስሜት ወስጥ ሆኖ ሽዋዬን አከታትሎ ሲያያት ኣ!» ስትል ተከፍቶ በቀረው አፏ ውስጥ
የጎረሰችው እንጀራ ከነነፍሱ ታየው::
«ምነው?» አለ እስቻለው የሚለው ጠፍቶበት።
«ና ብላ» አለችው ሽዋዬም የመንተ ዕፍረቷን፡፡
እስቻለው ግብዣውንም አልተቀበለ፡፡ ለሠላምታም እጁን አልዘረጋ፡፡ ወደ ሔዋንም መጠጋት አልቃጣ። በድንጋጤ ታርገድግዶ የነበረውን ወገቡን ለማሳረፍ
ብቻ ዱካ ላይ ቁጭ አለና «ስላም ናችሁ?» አለ አጎንብሶ ግንባሩን እያሻሽ።
«ክብሩ ይስፋ!» አለችው ሸዋዩ ልቧ ድው ድው እያለና እጆ እንኳን
መቁረስ እቅቶት እየተንቀጠቀጠች
በመሀከላቸው ፀጥታ ሰፈነ።
በፀጥታው መሀል አንዳቸው ሌላኛቸውን በየቅንድባቸው ስር ይተያዬ ኖሯል። ሔዋን የሸዋዬን ሁኔታ ሰለል አድርጋ የማታያት መስሏት በእጅና በዓይን ምልክት አስቻለው ተመልሶ እንዲሄድ ስትጠቁመው ሸዋዬ ድንገት አየቻት።በዚያቺጡ ቅጽበት ሽዋዬ በእጇ ይዛው የነበረውን የእንጀራ ሳህን መሬት ላይ ልቅቅ አደረገችና፡-
እሱ ለምን ይሂድብሽ እረ እኔ እወጣልሻለሁ!» ብላት ከመቀመጫዋ ብድግ
በማለት ከቤት ምንጥቅ ብላ ወጣች፡፡ አስቻለውና ሔዋን በድንጋጤ ክው ብለው
ተፋጠጡ።
«በእናትህ አስቹ ሂድ! ተመለስ!እለችው ሔዋን እየተሽቆጠቆጠች፡፡
«አልሄድም» አላት እስቻለው በስጭት ባለ አነጋገር፡፡
«በእናትህ ለኔ ስትል» አለች ሔዋን እሁንም እጆቿን እያርገበገበች
«ምንድነው እህትሽን እንዲህ የሚያደርጋት?» ሲል ፊቱን ኮስተር አድርጎ በብስጭት አነጋገር ሔዋንን ጠየቃት፡፡
«እሷን ተዋት አስቹ እንተ ብቻ ለኔ ስትል ሂድ! በእናትህ! »
አስቻለው ለጊዜው የሚያደርገውን አጣና ግራ ግብትብት አለው፡፡ ውስጡ
ተጨንቆ ጎንበስ ብሎ ግንባሩን ሲያሻሽ ከቆየ በኋላ ድንገት ከተቀመጠበት ብድግ
አለና እስቲ ቆይ እሺ የምትል ከሆነ ልመልሳት፡፡” እያለ በፍጥነት ርምጃ ወደ ውጭ ገሰገሰ፡፡ ከግቢ ወጥቶ ግራና ቀኝ ሲመለከት ሸዋዬን በግራ በኩል በርቀት
አያት። ድምጹን ከፍ አድርጎ ሸዋዬ ሸዋዬ ሸዋዬ ሲል ተጣራ፡፡ ሸዋዬ ግን ዝም ብላው ርምጃዋን ቀጠለች፡፡ ልትሰማው እንደምትችል ይገምታል፣ ነገር ግን ዝም ስላለችው ተናደደና ወደ ሔዋን ተመለሰ።
«መኮብለሏ ነው? አለም ወደ ቤት እየገባ፡፡
«ሄደች» አለችው ሔዋንም ጭንቅ ጥብብ ባለ ሁኔታ አስቻለውን
እየተመለከተች፡፡ ዓይኖቿንም እንባ እንባ ያላቸው ጀመር፡፡
ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ እየጠራኋት ዝም ብላ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አቅጣጫ ሄድች:: አላት እዚያችው ዱካ ላይ ቁጭ ብሉ ግንባሩን እያሻሸ
«ግን ለምን መጣህ አስቹ? አለችው ሔዋን::
«ለመሆኑ ያከስዓት ፈረቃ ገቢ አልነበረችም እንዴ? በአሁነ ሠዓት ቤት ውስጥ አትኖርም ብዬ አንቺን ስለ አስነባበትሽ ጠይቄ ለመሄድ ነበር የመጣሁት!»
«የሁለቱም ፈረቃ ተማሪ ሥራ ዘመቻ ላይ ስላረፈደ ከሠዓት ትምህርት ስላልነበረ ነው፡፡ አሁንም ሂድ አስቹ! ደሞ ተመልሳ ከመጣች ጉድ ይፈላል።» ነ
«ሰሞኑን እንደት ነበራችሁ?»
«ሰላም ነበርን።»
አስቻለው በደረቁ ፈገግ ብሎ እያያት: «ስሳም እለመሆናችሁንማ ይኸው እያየሁት ነው:: ግን የተለየ ሁኔታ ገጥሞሽ ከሆነ ብዬ እንጂ!?»
«አንተ የምትረዳኝ ከሆነ ወደፊት የተሻለ ሰላም ላገኝ እችላለሁ::>>
«የምን ልርዳሽ?»
«ሰቃል አንተ ዳግመኛ መዲህ አትምጣ፡፡ እኔ አንዳንዴ ወደ አንተ ብመጣ ይሻላል፡፡»
«አይመስለኝም»
«እመነኝ አስቹ አልፍ አልፎም ቢሆን ሲመቸኝ እመጣለሁ፡፡ እኔ ወደ አንተ የምመጣው የእት አበባን ሁኔታ አጥንቼ ነው፡፡ አንተ ግን የለችም ብለህ ብትመጣ ልክ እንደ አሁኑ ልንጋለጥ እንችላለን፡፡ ስለዚህ አስቼ፤ እባካህ ዳግመኛ
ወደዚህ ላትመጣ ቃል ገብተህልኝ ሂድ፡፡
አስቻለው የሔዋን ዘዴና ዓላማዋ ገባው:: እሱም በቀላሉ ሊሸከመው የሚችለው አደራ ነው። በትካዜ አስተያየት ለአፍታ ያህል ሲመለከታት ቆየና
ከመቀመጫው ብድግ በማለት “ተቀብያለሁ ሔዩ:: አሁንም ልሂድልሽ፡፡ ግን ሸኚኝ»አላት።
የአስቻለው ሸኚኝ ቃል ለሔዋን ትርጉሙ እየገባት ሄዷል፡፡ እሷም
ከፍራሻ ላይ ብድግ ብላ ወደ አስቻለው ራመድ በማለት ከፍቶ በጠበቃት የእጆቹ እቅፍ ውስጥ ገብታ ደረቱ ላይ ልጥፍ አለች። በመሳሳም ናፍቆታቸውን ተወጡ፡፡
የፈለገው ችግር ይምጣ፤ ምንጊዜም ከአንቺ ጋር ነኝ፡፡» አላት አስቻለው አንገቷን እቅፍ አድርጎ ቁልቁል እያያት።
«እኔም እስቹ......
💫ይቀጥላል💫

👍2
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ጭንቀት በጭንቀት ሆነች። ብቅ ጥልቅ ወጣ ገባ.አበዛች። ለመጀመሪያ ጊዜ ማምሸቱ ያሳሰባት ዘይኑ የምትሆነውን አጣች። ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ጀምሮ ነበር መጠባበቅ የጀመረችው። እንደበፊቱ ትምህርት ቤት እንዳትል ትምህርቱን ጨርሷል። ምን ነክቶት ይሆን? ተርበተበተች፡፡ ስዓቱ እየገፋ እየሄደ ነው። ስጋት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ጌትነት
አደጋ ላይ እስከወደቀበት እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ተኩል ድረስ...
ከዚያም ሙሉውን ለሊት ስታምጥ አነጋች፡፡ ወንድም ጋሻዋ..ድምጡ
ጠፋ፡፡ የውሃ ሽታ ሆነ፡፡ ለሊቱን ተቅማጥ ሲያጣድፋት አደረ። ጎረቤታቸው ወይዘሮ ጤናዳም ደግሞ ሲያፅናኗት አነጉ።
"ምንም አይደለም ወንድ ልጅ አንዳንድ ጊዜ አመሉ ነው። አይዞሽ ጠዋት ይመጣልሻል"እያሉ ሞራል ሲሰጧት አደሩ። መንጋት አይበለው እንደ ምንም ነጋላት። ወንድም ጋሻዋን የበላችባት ወፍ ግን ድምጿን አላሰማ አለች፡፡ እዬዬ... ኡኡታ... ዋይታ…ቁጭ ብድግ.. በዚያች እሷ በጭንቀት በምትሸበርባት ማለዳ አንድ ሰው ወደ ስራ በማምራት ላይ እያለ እሪ በከንቱ ዳገቱ ላይ ወደተፈጠረው ትርምስ ጎራ አለ።
ታደሰ ገብረማሪያም ይባላል። በአሰቃቂ ሁኔታ የተደበደበውን ወጣት ሲመለከት ዐይኖቹ በእንባ ተሞሉ፡፡ አደጋውን ለፖሊስ ቀድሞ ሪፖርት ያደረገው እሱ ነበር፡፡ ፖሊስ ከስፍራው ሲደርስ ነፍሱ አልወጣችም እንጂ ያ ወጣት የሞት ያክል ከባድ ጉዳት ደርሶበት ተገኘ፡፡ ወጣቱ በአንቡላንስ ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ታደስ ወደ መስሪያ
ቤቱ ቢያመራም የእለት ተግባሩን በአግባቡ መከወን ተስኖት ነበር። ገና በጠዋቱ ከቤቱ እንደወጣ ባየው አሰቃቂ አደጋ ቀኑን ሙሉ ሲረበሽ ውሎ ሲመሽ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡
ታደሰ የጨለማ ድባብ በዋጣት ጠባብ ክፍሉ ውስጥ ብረቱ የዛገ የሽቦ አልጋውን ተንተርሶ በሃሳቡ ጭልጥ ብሎ ሄደ። የዚያ በደም ተለውሶ የተንጋላለ ወጣት ሁኔታ ከፊቱ እየተመላለሰ ሰላም አየነሳው ነበር።
መንግሥትና ህግ ባሉበት አገር ውስጥ እዚያ ጥግ የደረሰ አስከፊ ወንጀል በአደባባይ መፈፀሙ እያስቀጨነቀው፣ የቀማኞችና የነፍሰ በላዎች መሸሽጊያ ዋሻ እሪ በከንቱ የሚፀዳበት ጊዜ እየናፈቀው እንቅልፍ የሚባል ነገር
በአይኑ ሳይዞር ሰማይና ምድር ተላቀቁ።
ታደሰ በጠዋቱ ተነሳና ወንበር ላይ አጣጥፎ ያስቀመጣቸው ልብሶቹን
ለባብሶ በየማዕዘኑ ሸረሪት ያደራባት ጎጆውን ከውጪ ቆለፈና እንደ ልማዱ ወደ መስሪያ ቤቱ የሚያደርሰውን ሰርቪስ ለመያዝ ወጣ፡፡ያ አሳዛኝ ወጣት ወድቆበት የነበረውን አካባቢ በጥላቻ ወደ ጎን እየተመለከተ ወደ ፊት በር አቀና፡፡
አንገቱን አቀርቅሮ እጆቹን እያወራጨ ሲራመድና ለራሱ ሲያወራ የተመለከተ ሰው ከአዕምሮው ጤነኛ አለመሆኑን ቢጠራጠር የሚፈረድበት
አይሆንም፡፡ ለሰው ልጅ ህይወት ደንታ ሳይኖራቸው እየነጠቁና ደም
እያፈሰሱ በእሪ በከንቱ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው የሚኖሩ ግፈኞች ጉዳይ በእጅጉ እያሳስበውና ነገ ከነገ ወዲያ የዚያ ወጣት እጣ ፈንታ በሱ ላይ
የማይደርስ ስለመሆኑ ዋስትና በማጣት ጭምር እየተጨነቀ ነው። ታደሰ ይሄ ጉዳይ ክፉኛ ስላሳሰበው አቅሙ በፈቀደ መጠን ወንጀልና ወንጀለኞችን ለመፋለም ለራሱ ቃል ገብቷል። "ምነው ታዴ እንደ እብድ ብቻሽን ታወሪ ጀመር እንዴ ?" አለው ጓደኛው አማኑኤል፡፡
"እብደት አልከኝ አማኑኤል? ልክ ነህ አእምሮ ጫና ሲበዛበትና ፊውዙ ሲቃጠል ተከታዩ እብደት ሊሆን ይችላል። የኔ አዕምሮ ፊውዝ ግን የነሱን ሳያቃጥል በቀላሉ አይቃጠልም!!" ፊቱን ቅጭም አደረገ፡፡ አማኑኤል በታደሰ አነጋገር ግራ ተጋባ፡፡
"እነማንን ነው የምትለው ታዴ?"
"እነዚያን የሰውን ልጅ ህይወት በጩቤ ጀልባ እየቀዘፉ በደም ውቅያኖስ ውስጥ የሚዋኙትን፣ እነዚያን የንፁሃንን ጉሮሮ ያለርህራሄ የሚበጥሱትን፣ እነዚያን ሳይሐፉ፣ሳይደክሙ በደም የተለወሰ እንጀራ የሚበሉትን!"
አማኑኤል ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ስራውን ከጀመረ ሁለት ዓመት እንኳን አልሞላውም ነበር፡፡ ከታደስ ጋር በዚህ መስሪያ ቤት ውስጥ ከተዋወቁበት ጊዜ ጀምሮ ተግባብተውና ተሳስቀው ስራቸውን በትጋት ከማከናወን
ባለፈ የዚህ ዓይነቱን የመረረ ሁኔታ አይቶበት አያውቅም ነበር ።
አስቃቂ ድርጊትም አከለለት።
“ባልና ሚስትን ደብድበው ንብረታቸውን ዘርፈው ተሰወሩ፣ እገሌን ማጅራቱን መቱት፣ የለበሰውን ልብስ ገፈው ቱቦ ውስጥ ጥለውት ሄዱ፤
እገሌን ሃንግ አደረጉ..." ሌላም ሌላም፡፡ በዚያ ወጣት ላይ ደርሶ ያየውን አሰቃቂ ድርጊት አከለለት
“ይሄ አረመኔነት የተጠናወተው ሰይጣናዊ ተግባር ነው። ይሄ እኩይ መቆሚያ ካልተበጀለት የእያንዳንዳችን ጉሮሮ ተራ በተራ መታነቁ የማይቀር ነው" አለ በብስጭት።
"አቦ ተወና ታዴ! ያልበላህን እያከክ ነው እንዴ?! እሱ የኛ ችግር አይደለም! ይሄ ለዚሁ ተግባር የተሰማሩ የፖሊሶች ስራ ነው፡፡ የሰው ስራ አትሻማ!” አለው።
“እንደሱ አይደለም አማኑኤል!.….በፍፁም አትሳሳት!…አንዱ ለሌላው ፖሊስ ሊሆን ይገባል፡፡ የኛ ድጋፍ፣ የኛ ትብብር በሌለበት ፖሊስ ብቻውን ተአምር ሊፈጥር አይችልም፡፡ የሌላው ቤት ሲፈተሽ፣ ሲበረበር፣ ሌላው አንገቱ ሲመታ፣ሲታነቅ እንደ ዶሮ ሲጠመዘዝ እያየን እንዳላየ ፊታችንን አዙረን የመሄዱን አስከፊ ልማድ እስካልቀየርነው ድረስ የደህንነት ዋስትናችን አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር ነው፡፡ የሰው ልጅ ጥሮ ግሮ ያፈራው አንጡራ ሀብቱን በገሃድ መነጠቁ አንሶ ህይወቱ መጥፋት የለበትም። በየሜዳውና በየድልድዩ ውስጥ መደፋት የለበትም፡፡ ወንጀለኞቹ
ገንዘብ ብቻ ዘርፈው አይሄዱም እኮ! እሱ ብቻውን አያረካቸውም፡፡የሚያረካቸው ደሙ ሲንዠቀዠቅ፣ እስትንፋሱ ስትቆም ማየት ነው"
እና መፍትሄው ምንድን ነው ታዴ ? ምንስ ማድረግ ትችላለህ?"
ከዚች ደቂቃና ሴኮንድ ጀምሮ ምሽጋቸውን ለመናድ ከተደራጀው ሰራዊት ጎን ቆሜ እኩይ ተግባራቸውን ለማስቆም የበኩሌን ጥረት አደርጋለሁ” አለው በፅናት፡፡
'ተው እንጂ ታደስ? ለምን በአንገትህ ላይ ሸምቀቆ ታስገባለህ? ለምን ራስህን ለአደጋ ተጋልጣለህ?ፖሊስ የሚፋለማቸውኮ በተገቢው ትጥቅ ተደራጅቶ ነው፡፡ አንተ ግን ባዶ እጅህን ነህ በባዶ እጅ ያዋጣል? እንኳን በባዶ እጅ በትጥቅም አልተቻሉም ወዳጄ!.."
ተራህ እስከሚደርስ ቁጭ ብለህ ጠብቃቸው እያልከኝ ነው?"
“ታዴ ብቻህን ተቆርቋሪ በመሆንህ ወይንም ራስህን ለጥቃት በማጋለጥህ ለችግሩ መፍትሄ ትሆናለህ ብዬ ስለማላምን ነው። ጨለምተኛ እንዳትለኝ እንጂ መፍትሄው ያለው በመንግሥት እጅ ብቻ ነው።ማጅራት መቺው፣ ቤት ሰርሳሪው፣ ኪስ አውላቂው ሁሉ የየራሳቸው የሆነ የተለያየ ታሪክ ያላቸውና በተለያዩ ጊዜያት ተይዘው እስር ቤት የገቡ፣ የተገረፉ፣ የተደበደቡ ጭምር ናቸው፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ የስራ መስክ አልተፈጠረልንም፣ ሰርተን የምንኖርበት ሁኔታ አልተመቻቸልንም የሚል ነው።
ዘላቂ መፍትሄ የሚገኘው እነሱን በማጥፋት ብቻ ሳይሆን እነሱን
የሚፈለፍለውን የኋላ ቀርነት ማሽን ከስር መሰረቱ በማጥፋት ነው።
ወንጀልና ወንጀለኛን መከላከል የሚቻለው ስራ አጥነትን፣ የትምህርት እድል እጦትን፣ ረሃብን ፣ በሽታን ፣ ድንቁርናን በአጠቃላይ በድህነት ሰፊ ማህፀን ውስጥ የሚፀነሱ ችግሮችን በመዋጋት ነው። ለዚህ ደግሞ በቂ የስራ እድል በመፍጠር፣ ህብረተሰቡ ለስራ ያለውን ዝቅተኛ አመለካከቱን እንዲለውጥ በማስተማር፣ መሃይምነትን በመታገል እና ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎችን በመስራት እንጂ ወንጀለኛን በማሳደድ ብቻ ማስቆም የሚቻል አይሆንም፡፡ ይሄ እጅግ ሰፊ አገራዊ ችግርና አጀንዳ ስለሆነ

👍1
በቀላሉ ከማትወጣው ባህር ውስጥ ገብተህ እንዳትዳክር እስጋለሁ። ከባለቤት ያወቀ ቡዳ ነው እንዳትለኝ እዚህ ላይ ባበቃና ምሳ ብጋብዝህ ምን ይመስልሃል?” ሰዓቱን ተመለከተ። እውነትም የምሳ ሰአት ደርሶ ነበረ።
ተያይዘው ወጡ።
አማኑኤል መኖሪያ ቤቱ ቅርብ ስለሆነ ምሳውን የሚበላው ቤቱ ሄዶ ነው። ታደስ ደግሞ በኮንትራት ወደሚመገብበት ሆቴል አመራ።
የሚቆርሰው እንጀራ ከፕላስቲክ እንደተሰራ ሁሉ አልቆረስልህ፣ እንደ ድንጋይ ደርቆ አልዋጥልህ እያለው ተቸገረና ላመል ያክል ከጎራረሰ በኋላ ምሳውን ከሚመገብበት ሆቴል አጠገብ ከሚገኘው "ቬኑስ" ሻይ ቤት ገብቶ
ሻይ አዘዘ።
ለምን እንደሆነ ባያውቀውም አእምሮው ያንን አሳዛኝ ወጣት ለደቂቃ እንኳ መዘንጋት ተስኖታል፡፡ እንዲሁ በሃሳብ ሲባክን ቆይቶ ያዘዘው ሻይ ቀዘቀዘበትና ሳይጠጣ ሂሳቡን ከፍሎ ወደ ቢሮው ተመለሰ ።
የአለቃው ፀሃፊ ትዕግስት ስራ ላይ ነበረች። ትዕግስት ያንን ለቄንጥ
ይሁን ወንዶችን ለማፍዘዝ ምክንያቱ በውል ያልለየለትን የዳሌ ማውረግረግ ልምዷን ለረጅም ጉዞ ብቻ ሳይሆን ከአንዱ ክፍል ወደ ሌላ ክፍል ስትገባ ጭምር ትጠቀምበታለች፡፡ ያንን ታማኝና ታዛዥ መቀመጫዋን
እያስደነሰች እንደ ጉድ ስታስጋልበው፣ አንዳንድ ጊዜም ያለቅጥ ስታስሬገርገው ያስተዋሉ ጓደኞቿ ይዞ ከመሬት እንዳይደባልቅሽ እያሉ ስጋታቸ
ውን ይገልፁላታል።
ትእግስት ለወንድ ልጅ ያላት መመዘኛ ከውሃ የቀጠነ ከመሆኑ የተነሳ በዚያ መስሪያ ቤት ውስጥ ይመጥነኛል ብላ የምትገምተው አንድ ሰው እንኳ አልነበረም፡፡ የሷን መመዘኛ ለማሟላት ምናልባት እንደ ፋብሪካ ዕቃ ተገጣጥሞ የጥራት ደረጃን ጠብቆ መገኘትን ሊጠይቅ ይችላል።መልካም ፀባይ ከዐይነግቡነት ጋር፣ የአነጋገር ለዛ፣ወንዳ ወንድነት ከማለፊያ ጥሪት ጋር አብረው ካልቀረቡ ማንም የሷን ፈተና ሊያልፍ አይችልም፡፡ ማለፍ ብቻም ሳይሆን ለውድድር አይቀርብም፡፡ በዚህ ሁሉ እንደ ውሃ በቀጠነ መመዘኛዋ ላይ ግን ሚዛን ይደፋም ለታደሰ የመንደርደሪያ ማርክ ስጥታዋለች። ከሌሎቹ ይሻላል ብላ ስለምታምን ለሱ የተለየ
አቀራረብ አላት። ቢሮውን ቀስ ብላ ከፈተች።
“ሃይ ታዴ! ስራስ?” ከወረቀት ማስቀመጫ ሳህን ላይ ያሉትን ደብዳቤዎች ማመሳቀል ጀመረች። ታደሰ መልስ አልሰጣትም፡፡ ዝም ብሎ ስራውን
ቀጠለ። ለወትሮው ፈገግ ብሎ ያናግራት ነበር። ገረማትና ቀስ ብላ ወደ ጎን ተመለከተቸው። አንገቱን እንዳቀረቀረ ነው፡፡ዝምታው ይበልጥ አናደዳትና የምትፈልገውን ወረቀት አንስታ በዚያ በሚያቅራራ ዳሌዋ ጎኑን
ጎሽማው እያስካካች ወጣች።
ታደሰ ከስራ እንደወጣ ወደዛች ወደ ወንደ ላጤ ቤቱ ወደ ኦናዋ ጎጆው አመራ። የሰሞኑ ሀሳብ ፣ የሰሞኑ ድካም ራሱን እንዲዘነጋ
አድርጎታል፡፡ የሸረሪት ድር መጥረግ አለመቻሉ፣ የቤቱ አቧራ መጠራቀሙ፣ ልብሶቹ መቆሽሻቸውን ሁሉ እስከሚረሳ ድረስ ስሜቱ ተጎድቷል፡፡ቤቷን
በስፊው ሊያድሳት ዕቅድ የያዘው ድሃ ቤተሰቦቹን እየረዳ በምትተርፈው መጠነኛ ገንዘብ ነው፡፡ እንደገባ ስውነቱን ላላ አደረገና ሽቦ አልጋው ላይ
በጀርባው ወደቀ፡፡ ከዚያም ያንን ተወልዶ ያደገበትን ገጠር ትቶ ወደዚህ ትርምስ ወደበዛበት ሰፊ ከተማ የመጣበትን ጊዜ እያሰላስለ በትዝታ ተዋጠ፡፡
እሱ ለከተማ የነበረው ግምት... አሁን ያጋጠመው ሁኔታ....
ከተማ! ከተማ! ልማት! ብልፅግና! ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰት! በዕድገት ገጠር ወደ ከተማነት ይለወጣል። በትምህርት፣ በጤና ተቋማት፣
በፋብሪካዎች ግንባታ፣ በአስተሳሰብ ልህቀት ከድንቁርና፣ ከበሽታና ከእርዛት መላቀቅ የሚቻልበት የመንደርደሪያ ተስፋ እንጂ የወሮበሎች፣ የሌቦች፣ የቀማኞችና የነፍስ ገዳዮች መሸሽጊያ ጫካ መሆኑ በእጅጉ
ኣሳዝኖታል።እሱ ለከተማ የነበረው አመለካከት እንደዚህ አልነበረም፡፡
ኣሁን ያየው እውነታ ግን ያንን የድሮ አመለካከቱን የሚሸረሽር ሆነበትና ያቺኑ የገጠር ህይወቱን ከሚመርጥበት ደረጃ ላይ ደረሰ። ታደሰ ያደገበት የገጠር ህይወት በመከባበር፣ በመተሳሰብ፣ በመረዳዳትና በመፈቃቀር እሴት ላይ የተመሰረት ነበር፡፡ እሱ ባደገበት የገጠር ህይወት ውስጥ
እንኳንስ የሰው ልጅ እንስሳትና አእዋፋት ክብር ነበራቸው። እሱም
የልጅነት ጊዜውን ያሳለፈው ያንን የገጠር ንፁህ አየር እየሳበ
በየገደላ ገደሉ በለምለም ሳር ላይ የሚቦርቁ የቤት እንስሳትና አራዊቶችን፣ አረንጓዴ
ቡቃያዎችን፣አበቦችን ለመቅስም የሚርመሰመሱ ንቦችን... እያየ እየተደስተ ነበር፡፡ በተጋደመበት ሆኖ ያንን የሚወደድ የገጠር ህይወቱን በሃሳብ እየቃኘ የአበቦችን መዓዛ በስሜት አጣጣመ። የከብቶቹን፣ የጥጆቹን፣ የበጎችና የፍየሎቹን መንጋ... አስታወስ፡ የአእዋፋትን ጣፋጭ ዝማሬ... ስለአዳመጠ፡፡ ድካሙ ቀለል አለውና እጅግ አስደሳች የሆነ ስሜት ተሰማው፡፡ ሳያውቀው በዚያው ጭልጥ ብሎ ሄደ፡፡ የሰመመን እንቅል
ፍም አሸለበው፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በጎንቻ ቤት ውስጥ አንበሴ፣ጆብሬና አበራ ተሰባስበዋል።
“ብዙም የሚያስቸግር ስራ አይደለም፡፡ ልዑል ሰገድ ለግብዣ አሳቦ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ተኩል ድረስ እንዲያቆየው ተነጋግረናል። ከአሁን በኋላ ሁለት ስዓት ስላለችን ትንሽ ዘና እንበል!” አላ ጎንቻ፡፡
“በጊዜ ሄዶ ስለማንነቱ በቂ መረጃ ማግኘት አያስፈልግም?” አንበሴ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት የሰጠው በሚመስል አነጋገር ጥያቄ አቀረበ።
“ያስፈልጋል እንጂ! አራት ሰዓት ሲሆን እኔ ቀድሜ እሄድና ማንነቱን
አረጋግጬ እወጣለሁ በዚህ ሁኔታ ለመፈፀም ከልዑል ስገድ ጋር ተነጋግረናል።
እሱ እንደሽኘልኝ ተከትዬው እወጣና ምልክት እሰጣችኋለሁ። ከዚያም ቀድመን ቦታ እንይዝና እንደ ዶሮ ሲጥ! ነዋ! አ..ሃ..ሃ..ሃ.. ለጊዜው የተሰጠን ቀብድ ግን ሦስት መቶ ብር ብቻ ነው። በውላችን መሰረት አቀላጥፈን እንደጨረስንላት ቀሪውን አራት መቶ ብር እቀበለዋለሁ" ሶስት
መቶ ብሩን አውጥቶ ካሳያቸው በኋላ የሚጠጣ ነገር ይፈልጉ እንደሆነ ጠየቃቸው።
“እሺ! እሺ!” አሉ ሁሉም በደስታ።
“ዓለሜ አንድ ጠርሙስ ጂን ይዘሽልን ነይ” አንድ ባለ መቶ ብር ኖት አቀበላት፡፡ ጂኑ ተገዝቶ መጣ፡፡ እየጠጡ መጫወት፣ መደሰት፣ መዝናናት ሆነ። ለገና በዓል እንደሚታረድ ከብት ከጠላቱ ጋር ቁጭ ብሎ ሞቱን የሚጠባበቀውን የጌትነት መኩሪያን ደም ለማፍሰስ በተቀበሉት ቀብድ አልኮል ገዙና ጠጡ፡፡ ሰከሩ፡፡ በአልኮሉ ውስጥ የሚስኪኑን ደም እንደ ውሃ ጨለጡት።ዓለሚቱ አብራቸው ፅዋዋን አነሳች። በተለይ አንበሴ
ባለፈው ጊዜ ካስቀየማት በኋላ የስርቆሽ ጨዋታ አልተጨዋወቱም ነበር አሳፍስሻለሁ ያላትንም ገንዘብ ብትጠብቅ ብትጠብቅ ሳያመጣ ቀረ። አላስችል አላትና ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ በሹክሹክታ ጠየቀችው፡፡ ገንዘብ አልጠግብ ባይ ሆና እንጂ ሁለመናዋ ወርቅ በወርቅ ሆኗል። ጎንቻ ንጉስ እሷ
ንግስት መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ለዚህ ደግሞ አበራና ጆብሬ ፍፁም ተገዢዎች ሆነውላቸዋል። ትንሽ ትዕቢት ልቡ ላይ ያለችበት አንበሴ ብቻ ነው
የጎንቻ ሚስት የኔም ሚስት እስከሆነች ድረስ፣ ጡንቻዬ
ጡንቻውን እስካከለ ድረስ እሱን አዛዥና ገዢ ማን አደረገው? ባይ ነው አንበሴ። ዛሬ ጎንቻ ጌትነትን ሊያቀላጥፈው እቅዱን በሚያወጣበት ሰዓት
ላይ እሱም በልቡ ሌላ ዕቅድ እያወጣ፣ ሌላ እቅድ እየቀየሰ ነበር፡፡ ሰውነታቸው በበቂ ሁኔታ ተጋጋለ። ማንኛውንም ተልዕኮ ለመፈፀም ዝግጁ ...ሆኑ!

👍4
“ጎበዝ እንግዲህ ሰዓቱ እየደረሰ ነው እንውጣ!” ሀሳብ አቅርቦ ጎንቻ ብድግ አሉ። ሁሉም ተከትለውት ተነሱና ተያይዘው ቁልቁል በእሪ በከንቱ ድልድይ ወደታች ወረዱ፡፡
"እዚሁ ጠብቁኝ " አለና ቀደመ::
በዚያች ስም በሌላት ጠባብ ቡና ቤት ውስጥ ጠጪው እየተጋፋ
ይጠጣል፡፡ ይጫጫሃሉ። ልዑልሰገድም ይቀባጥራል። ልክ አራት ሰዓት ላይ ዐይኖቹ በወጪና በገቢው ላይ መቀላወጥ አበዙ። አንዷ ደቂቃ በጣም ብዙ መሰለችው።ጎንቻ ውሉን ያፈረሰ መሰለው። ሶስት መቶ ብሩ የቀለጠ መስሉት ሳምባ እንዳየች ድመት ተቁለጨለጨ። ተጨነቀ።ልቡ ድው ድው አለች፡፡ አስር ጊዜ ሰዓቱን ይመለከት ገባ።ሰዓቱ መሽብህ ያለው
መስለውና ጌትነት ስለመምሸቱ ያስብ ጀመር። በዚያ በጭንቀቱ መሀል ግን ልዑል ሰገድ ትንፋሹ መልስ... ፊቱ ፈገግ አለ፡፡ ጎንቻ !! ነጭ መለዮ ደፍቶ ሰማያዊ ጂንስ ሱሪ ለብሶ እጁን ኪሱ ውስጥ ከትቶ ደረቱን ነፍቶ ሲገባ አየው፡፡ የጎንቻ ዐይኖች በቀጥታ ከልዑል ሰገድ ዐይኖች ጋር ተጋጩ። ጥቅሻ!!
“ሰዓቱ ደርሷል ሸኝልኝ መሆኑ ነው፡፡ ጌትነት የአለቃው ውለታ ከብዶት ይሄን ያክል ስለሱ መጨነቁ ገርሞት ተደነቀ፡፡ ለሱ ዕድገት መድከሙን የሱን ታታሪ ሰራተኛነት ለበላዮቹ ለማሳወቅ ያደረገውን ጥረት በሰፊው
ሲተረትርለት እውነት መስሎት በልቡ ሲያመሰግነው አመሸ፡፡ ይህንን የመሰለ መልካም አለቃውን ጥሩ እንደማይመኝለት አድርገው ያወሩ አንዳንድ ወሬኞችን ታዘባቸው፡፡ ሰውን እንደዚህ ቀርበው ሳያዩት የልቡን
ሳይረዱ ጥሩ ነው መጥፎ ነው ብሎ መወሰን ስህተት መሆኑን ተገነዘበ፡፡ ልዑል ሰገድ እሱን አክብሮ ለመካስና ለማስደስት ብሎ ልዩ ቀጠሮ
ይዞለት ይህን የመሰለ ግብዣ ስላደረገለት ከልቡ ወደደው። አከበረው። በመጨረሻም ጥልቅ የሆነ ምስጋናውን አቀረበለትና በአራት ሰዓት ተኩል ላይ በሁለት እጆቹ ጨብጦት ተሰናብቶት ለመሄድ ተነሳ፡፡
“በል እንግዲህ ጌትሽ ሰዓት ደርሶብሃል የበለጠውን ደግሞ ወደፊት ሰፊ ጊዜ ይዘን በሰፊው እንጨዋወታለን፡፡ አይዞህ! ከጎንህ ነኝ! ቻዎ... ቻዎ!እስከወዲያኛው!." በጨለማው ውስጥ ያደፈጡት ጎንቻ ብዙም ሳይቆይ የእርድ በሬአቸውን ከፊት ከፊት እየነዳ ብቅ... ሲል ተመለከቱ...
“እኔ በዚያኛው በኩል ልጠባበቀው እናንተ ደግሞ በዚህኛው በኩል ጠብቁት” አለና አንበሴ መለስ ብሎ ወደ ጨለማው ገባና ከዐይናቸው
ተሰወረ። እነሱ ደግሞ በወዲህኛው በኩል ከጨለማው ውስጥ ገብተው ተሸሸጉ..የእህቱ ጭንቀት እየታየው ቶሎ ሊደርስላት በሩጫ ቀረሽ ርምጃ
መንገዱን ተያይዞታል። ጎንቻ ደግሞ ከመንገዱ ፈንጠር ብሎ ወጣና በጨለማ ውስጥ ተሸሽጎ ከፊት ከፊቱ እየሮጠ ቀደመውና አደፈጠ።
ሌሎቹ ሁኔታውን በንቃት ይከታተላሉ፡፡ ንቃት የሌለው ዙሪያውን አደጋ ያንዣበበት መሆኑን ያላወቀው ጌትነት ተፍ ተፍ ይላል። ድልድዩን ተሻግሮ ወደ ቀኝ እጥፍ ብሎ ሲያቀና ነበር የዚያ የጎንቻ ፈጣን እርምጃ
ተግባራዊ የሆነው። የእርዳታ ድምፅ እንዳያሰማ አድርገው ተረባርበው አፍነው ሁሉንም ነገር በውለታቸው መሰረት ፈፀሙ። በድርጊቱ ላይ ግን አንድ ሰው አልተገኘም ነበረና ግራ ተጋቡ።
"አንበሴስ?!" ጎንቻ ደም ያበላሸው እጁን በመሀረቡ እየጠራረገ ጠየቃቸው።
አበራና ጆብሬ እርስ በርሳቸው ተያዩ።
“ምን ነካው?" በዚያኛው በኩል አደፍጣለሁ ነበር ያለው እኔ እንጃ!” "ተወው የራሱ ጉዳይ! አምስት ሳንቲም አይቀምሳትም!! አሁንስ አበዛው! ወንድ አይደለሁም! ሰባራ ሳንቲም ቢደርሰው! በሉ እኛ እንሂድ እንጠጣ!..ጎንቻ ደም ያበላሸውን መሃረብ በንዴት ወረወረው... ከዚያም ተያይዘው ከሴተኛ አዳሪዎች ቤት ጥልቅ! ብለው ገቡ።ትልቅ ጀብዱ ፈፅመው
የሀገር ጠላት መክተው በሳይንስ ምርምር ተራቀው ውጤት ያስመዘገቡት ሳይንቲስቶች በፈፀሙት ድርጊት እየተደሰቱ በሰፊው.. ሊበሉ…ሊጠጡ... ሊጨፍሩ... ገቡ ጎንቻ እስከ ምሽቱ ስድስት ሰዓት ተኩል ድረስ አብሯቸው ሲጠጣ ከቆየ በኋላ “በሉ ጎበዝ እኔ ልሂድ! ዓለም ይሄኔ ተጨንቃለች ከሷ ጋር ቢሆን
ኖሮ ሙሉውን ለሊት አብረን ስንጨፍር እናድር ነበር። ስለምትጠብቀኝ እኔ ልሂድ እናንተ ተዝናኑ" አለና አንድ መቶ ብር ሰጣቸው።
አበራና ጆብሬ ያለገደብ እየጠጡ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር መዳራታቸውን ሊቀጥሉ ጎንቻ ደግሞ ከነሱ ተለይቶ ፍቅረኛው ዘንድ ለመድረስ እየተጣደፈ ሄደ። ከቤት ሲደርስ በሩ አልተቆለፈም ነበር፡፡ ዓለሚቱ በዚያን ሰዓት
በሯን ክፍት አድርጋ አትተኛም፡፡ ያልተለመደ ነገር ሆነበት። አምሽቶ
ሲመጣ ተነስታ ትከፍትለታለች እንጂ በር ሳትዘጋ ተኝታ አታውቅም።
ተጠራጠረ፡፡ ቀስ ብሎ በሩን ገፋ አደረገና አንገቱን ወደ ውስጥ አስገባ፡፡ጎንቻ ባየው ነገር እጅግ ከመደንገጡ የተነሳ የሆነ ከባድ ነገር መሀል አናቱን ሰንጥቆት ሲያልፍ ተሰማው፡፡ ደሙ በውስጡ ቀዘቀዘ፡፡ትንፋሹ ቆመ፡፡ በእብደትና በቅዠት መካከል ተዘፍቆ ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ወደ ውስጥ ዘለቀ። በፍፁም ሊታመን የማይችል ነገር ነው፡፡ ከህይወቱ አስበልጦ የሚወዳት፣ የሚንሰፈሰፍሳት፣ ከምንም ከማንም በላይ የሚያፈቅራት ዓለሚቱ አይሆኑ ሁናለች። እንደዚህ በድንገት ትከዳኛለች ብሎ ለአንድ ቀን እንኳ ጠርጥሯት አያውቅም ነበር። የልቡ ትኩሳት ዓለሚቱ፣ የፍቅሩ ዋልታና ካዝማ ዓለሚቱ፣ ለደቂቃ ከአይኑ እንዳትለየው የሚሳሳ
የምታፈቅራትና የምትወዳትን ዓለም እስከ ወዲያኛው ተሰናብታ በምትላት ጣፋጫ ዓለሚቱ
እጅግ በሚሰቀጥጥ ሁኔታ ይቺን ከልጆቿ አስበልጣ የምታፈቅራትን የምትወዳትን ዓለም እስከ ወድያኛው ተሰናብታ በምትወደውና በምታፈቅረው በጎንቻ ላይ እንኳ ጨክና ጥላው ኮብልላለች።
በውስጡ በቅሎ ቀንድ ባወጣ ጭካኔው ልክ ፍቅሩና ርህራሄው ለአንድ ቀን ያልጎደለባት ዓለሚቱ፣ እሷን ብሎ የሚያፈቅረው ኛሮን ትቶ የመጣላት ዓለሚቱ፣ ህይወቱን አሳልፎ የሚሰጥላት ዓለሚቱ፣ የመጀመሪያ ትኩስ ፍቅሩን ሰጥቷት የማይጠገብ ፍቅሯን እንደ ንብ ስታስቀስመው
የኖረችው ከረሜላ ከድታው ሄዳለች። በአሰቃቂ ሁኔታ ከመኖር ወደ አለመኖር ተሸጋግራለች። አንገቷ በስለት ተወግቶ አፏ ተከፍቶ ዐይኖቿ ተገልብጠው በደም ተጨማልቃ ጭንቅላቷ በበሩ መግቢያ በኩል ተዘቅዝቆ
ፀጥ እረጭ ብላለች፡፡ ጎንቻ! ለህይወት ቁብ የሌለው ጐንቻ! በጨካኝነቱ ወደር ያልነበረው ጎንቻ! የስንቱን ህይወት እንደጎመን ሲቀነጥስ የኖረው ጎንቻ! ስንቱን ደም ሲያስለቅስ የስንቱን ደም ሲያፈስ የኖረው ጎንቻ! የሚወዳት የሚሞትላት የፍቅረኛው የዓለሚቱ ደም እንደ ውሃ እየተንዠቀዠቀ ሲወርድ ቆሞ የማየት ወኔና ብርታቱን ሙሉ በሙሉ በአንዳች ሀይል ተነጠቀ፡፡
ጎንቻ ዛሬ ገና ሞትን ፈራው፡፡ የፍቅር እጦት የሚያስከትለውን ሰቀቀን፣ጭካኔ የሚያስከትለውን የልብ ስብራት፣ ያውም እንደሱና እንደ ዓለሚቱ ያለውን የፍቅር እሳት የሚያጠፋው ጨካኙ ሞት መሆኑን ያወቀው ገና ዛሬ በሱ ላይ ሲደርስበት ነው፡፡ ቢጮህ ጐረቤት ተሰብስቦ የሚይዘው መሰለው። እንዴትስ ዝም ይበል? በቆንጅዬዋ፣ በጣፋጯ ዓለሚቱ ላይ ያለውን ከፍተኛ ጭካኔ የተሞላበት ክንዱን ሊያነሳበት የሚችል ሰው በአለም ላይ ይኖራል ብሎ ለደቂቃ እንኳ ተጠራጥሮ አያውቅም ነበር፡፡ ነገሩ ሁሉ እንቆቅልሽ ሆኖበት ግራ ግብት ብሎት ድምፁን ውጦ

በዓለሚቱ ሬሳ ላይ እየተንከባለለ አነባ..ምን ያድርገው? ለመጨረሻ ጊዜ የሚሸኛት ግማሽ አካሉ ወደ አፈር ልትገባ ነውና ውስጥ አንጀቱ እየተርገፈገፈ ድምፁን ዋጥ አድርጎ የልቡን ያዋያት ጀመር።
ዓለምዬ!...ዓለሜ ...የኔ ፍቅር..የኔ እመቤት...ጨከንሽ ዓለም? ምን አደረኩሽ የኔ እናት? ለማን ትተሽኝ የኔ አበባ? አልከዳህም ብለሽኝ? አንቺን እንጂ ማንን ተከትዬ መጣሁና ዓለም? አገሬን ትቼ የወጣሁት ላንቺ አይደለም እንዴ? ይሄ ሁሉ ጭካኔ ባንቺ ላይ?! ማነው እንደዚህ ጉድ ያደረገኝ እስቲ ንገሪኝ የኔ ቆንጆ? አንጀቱ እየተንሰፈሰፈ የእንባ ከረጢቱ ጦሽ
ብሎ ፈንድቶ እስከሚንጠፈጠፍ ድረስ ሙሉውን ለሊት ትንፋሹን ውጦ ለሚጠይቃት ጥያቄ ምላሽ እንደሚጠብቅ ሰው የፍቅሩን ፅናት እያነበነበላት በደም የተጨማለቀ አስከሬኗን ታቅፎ ሲያነባ፣ ሲንገበገብ አደረ።
ጉንቻ !! አንገት አንገታቸውን እንደ ጎመን ሲቀነጥስና ...ሲሰጥሳቸው
የኖሩ ሚስኪኖች በዓይነት በዓይነታቸው ተደርድረው እንደ ሥጋ ትል እየተርመሰመሱ ጭንቅላቱ እስከሚቃጠል ድረስ ተላወሱበት... ተንጫ ጩበት፡፡
ልጅን ከእናቱ ፍቅረኛን ከፍቅረኛ ወንድምን ከወንድሙ መነጠል... የሚያስከትሉት የስቃይ ስሜት. ግድያ... ዘረፋ...ድብደባ. የህይወት ተቃራኒዎች ህይወት ጣፋጭነቷ ሲታወስ ሞት ደግሞ ከሬት የበለጠ መራራ መሆኑን አሁን ገና አወቀው፡፡ ጎንቻ ሞትን በደንብ አድርጎ ፈራው፡፡
ዛሬ ገና ጉንቻ ፈሪ ሆነ፡፡ ጣፋጫን የሚወዳት፣ የሚሞትላት ዓለሚቱን ሳይቀብራት፣ እዬዬ ብሎ አልቅሶ አፈር ሳያለብሳት ብቻዋን ጥሏት
ሊጠፋ ነው። ከሞት ሁሉ ሞት የሚወዱትን የሚያፈቅሩትን አልቅሶ መቅበር አለመቻል ነው፡፡ ሙሉውን ለሊት አእምሮውን ስቶ ሲንሰቀሰቅ ሲያነባ አደረና ከመንጋቱ በፊት ድንገት እንዳስደነገጡት አውሬ ብርግግ
ብሎ ተነሳ፡፡ ከዚያም እንደ ደም ቀልተው በደፈረሱት ዐይኖቹ አስከሬኑን ለመጨረሻ ጊዜ ትኩር ብሎ ቁልቁል ተመለከተው። ከድንጋጤው ብዛት የትነሳ እንደ ጥርብ ድንጋይ ህይወት አልባ የሆነውን ደረቅ ፊቱን በሁለቱም እጆቹ በሃይል እየሞዥቀ በቤቱ ውስጥ ወዲያና ወዲህ ሲንጎራደድ ከቆየ በኋላ በሩን በሃይል አላትሞ በመዝጋት አስከሬኑን ባለበት ቦታ ላይ
ጥሎ እየተገላመጠና እየጮኽ ወደ ፊት አፈተለከ...
አንበሴ ከጓደኞቹ ተነጥሎ ሹልክ ብሎ ሲመጣ የተለመደ የስርቆሽ ፍቅሩን የሚያካፍላት እዳውን የሚከፍላትና ያንን አስታቅፍሻለሁ
ያላትን ገንዘብም የሚያስታቅፋት መስሏት ነበር አንገቱ ላይ የተጠመጠመችበት። እሱ ግን ደጋግሞ ወሲብ ፈፅሞ ከረካባትና አንገቷን እንደ ዶሮ ጠምዝዞ
ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ከገደላት በኋላ ያላትን ንብረት አንድም ሳያስቀር ዘረፈ። አንበሴ ወርቁንና ገንዘቡን የት እንደምታስቀምጥ ጠንቅቆ የሚያውቅ ውስጥ አዋቂ በመሆኑ ሬሳዋን አጋድሞ ብዙም ሳይረበሽ እንደ ሰላማዊ ሰው እየተዝናና ሳጥኗን ሰብሮ እየበረበረ፣ ቦርሳዋን ገልብጦ ቤቱን እያራገፈ አንድ በአንድ ሲፈትሽ ከቆየ በኋላ ሰባራ ሳንቲም እንኳ ያላስቀረ መሆኑን በሚገባ አረጋግጦ ነው የወጣው። የግፉ ግፍ ያጌጠችበትን የጆሮ ጉትቻና የአንገት ሀብሏን እንኳ ከሬሳዋ ላይ ሳይቀር በጥሶ ቤቷን ኦና አድርጐት ነበር የተሰወረው።...

#ክፍል_አርባ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ሰሞኑን ያየችው ህልም ክፉኛ ያስደነገጣት እናት አመዱን ይነሰንስባት ጀምሯል። የወትሮ ህልሟ ተስፋን የሚያበስር መሆኑን ስለምታውቅ ፊቷ እንደ ፀሀይ እያበራ በደስታ መንፈስ ለቡና ማህበረተኞቿ ታወራላቸው ነበር፡፡ ከማህበርተኞቿ ውስጥ ደግሞ በህልም ፈቺነታቸው ወይዘሮ
ተዋበችን የሚደርስባቸው የለም፡፡ ህልም ሲፈቱ እንከን አይወጣላቸውም ተብሎ በአብዛኛው ነዋሪ ስለሚታመንባቸው ህልም ለመፍታት ኩራታቸው አይጣል ነው። ትንሽ ካላስለመኑ ህልም አይፈቱም፡፡ ከልመና በኋላ ግን መተንተን ይጀምራሉ፡፡
ሲሳይ ነው! ዓለም ነው!አቤት ደስታ! ልጅ ልትወልጂ ነው...ስለትሽ ሊደርስ ነው፣ በዚህ ሊገባ በዚህ ሊወጣ ነው፡፡ የተጣላው ሊታረቅ፣ የደለው ሊሞላ.. ብቻ ጥሩ ጥሩውን ሁሉ ልታገኙ ነው እያሉ አላሚውን
ተስፋ በተስፋ ያደርጉታል፡፡ ከሁሉ የበለጠ የህልም ደንበኛቸው ግን
አስካለ ነበረች። ያየችውን ህልም ስትነግራቸው ሁሌም የሚያያይዙት ከልጆቿ ጋር ነው፡፡
አቤት! አቤት! በውነት ህልም አይደለም ያየሽለት ራዕይ ነው፡፡ ጉድ! ደሞዙ ከፍ ሥልጣኑም ከፍ ሊል ነው፡፡ ጥሩ ደረጃ ላይ ሊደርስልሽ ነው! ትንሿም ደስ ብሏታል ያንቺ ናፍቆት አለባት መሰለኝ እዚህ ጋ ትንሽ ቅር
እንዳላት አያለሁ፡፡ ይሁን ግድ የለም ትምህርት ቤት ሲዘጋ ትመጣለች።
ጥሩ ህልም ነው ይሏታል የቡናው አሻራ ያረፈበትን ባዶ ስኒ ዘቅዝቀው እየተመለከቱ፡፡ ከዚያም አስካለ በደስታ መፈንደቅ ነው። በዚህ ሁሉ ቆንጆ ቆንጆ ህልሞቿ ጣልቃ ስሞኑን ያየችው መጥፎ ህልም ግን ክፉኛ አስደንግጧታል
ለማንም ሳትናገር ፍርሃትና ሃሣብ ውስጥ ውስጡን ሲያካት ቆይቶ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ወዛም ነበረ ፊቷ ላይ አመዱን ይነዛበት ገባ።
"ተነሳብሽ ደግሞ አንቺ ሴት! ለመሆኑ ሄደሽ ከመጣሽ ሁለት ወር እንኳ ይሞላዋል እንዴ? ናፈቁኝ ነው ወይስ ምን አዲስ ነገር ተገኘና ነው እንዴዚህ ነጭ እስከምትሆኚ ድረስ ራስሽን መጣል ያመጣሽው?” ለመሽፋፈን ጥረት ብታደርግም ሃሳብ እየወዘወዛት መሆኑ የገባቸው ወይዘሮ ተዋቡ ተቆጡ።አስካለ የመጀመሪያ መጥፎ ህልሟን አይታ መረበሽ ከጀመረች
በኋላ ጭንቀቱ ነው መሰል በላይ በላዩ የሚያስፈራራ ህልም እየደጋገመ አስቸገራት። የአሁኑ ደግሞ ፍፁም የተለየ ሆነባት።
ጌትነት ይመስላታል፡፡ እንደ ልጅነቱ አብሯት እንጨት ለቀማ ይሄዳሉ።
ከአንዱ ዛፍ ወደ ሌላው ዛፍ እየዘለለ ጥሩ ጥሩውን እንጨት እየሰበረ ኢያቀበላት የቆመበት ቅርንጫፍ ተገንጥሎ መሬት ላይ ይወድቃል። ከዚያም
ይንከባለላል. በዚያው እንደ ሙቀጫ ጅው ብሎ ተንከባሎ ቁልቁል ይወርዳል። ለካስ ከስሩ ገደል ነበር፡፡ ከታች ገደል መኖሩን፣ ልጅዋ አደጋ ላይ መውደቁን ያየች እናት ኡኡ! ልጄን! ልጄን!.. ልጄን! እየጮኸች አብራው ልትገባ ወደ እሱ ትሮጣለች። ጌትነት ገደሉ ውስጥ ተወርውሮ ከመግባት ለትንሽ የተረፈው የሆነ ቁጥቋጦ ነገር እጁ ውስጥ ስለገባ ነበር፡፡
ከዚያም እናቱ ጉዳት ላይ እንዳትወድቅበት ውትወታውን ይቀጥላል።
“እማዬ! እማዬ!ደህና ነኝ! ምንም አልሆንኩም! እዚያው ቁሚ! መጣሁ! መጣሁ! መጣሁ!" ወደሱ ስትሮጥ ወድቃ እንዳትሰበር ፈርቶ ይጮሀል። እሷ ደግሞ አሻፈረኝ ብላ ወደ ገደሉ እየሮጠች ትመጣና ገደሉ ጫፍ ላይ
ሆና “ጌትዬ! ተረፍክ የኔ ጌታ?!” ቁልቁል እያየችው ትጠይቀዋለች::
"ተርፌአለሁ! ተርፌአለሁ!አይዞሽ! ምንም አልሆንኩም በቃ እዚያው ጋ ሁኚ!" ይላትና በአንድ ትልቅ ቋጥኝ ላይ ተጋድሞ በተንጠለጠለ ወፍራም
ሀረግ አማካኝነት እየተሳበ ሽቅብ መውጣት ጀመረ። ወጣ ወጣ...
ወጣና አጠገቧ ሊደርስ ትንሽ ቀረው። ደክሞታል። አልቦታል። ..
“አይዞህ ጌትዬ በርታ የኔ ልጅ... ቆይ እጅህን ልያዝልህ" ጐንበስ
ትላለች።
“ተይ !ተይ! እማዬ ተይ! እንዳያንሸራትትሽ !እኔ ቀስ እያልኩ እወጣ ለሁ ተይ!!"
“ግዴለህም ይልቁንስ እጅህን አቀብለኝ" ትለውና ሄዳ ከገደሉ ጫፍ ላይ ተንጠልጥላ የቀኝ እጇን ትልክለታለች። አልደርስብሽ ይላታል። እንደገና ብሃይል ወደሱ ተንጠራርታ እጇን ልትስጠው ጐንበስ ትላለች። በግራ እጅዋ አንድ ትልቅ ጉቶ ይዛ ነበር፡፡ አሁንም አልደርስብሽ ይላታል።
ጭንቅቱ አስጨንቋት ቶሎ ልታወጣው ቸኩላለች። እሱም አወጣዋለሁ ብላ ስትፍጨረጨር ጉዳት ላይ እንዳትወድቅ ፈርቶ እጅዋን ቶሎ ለመያዝ ይንደፋደፋል። ተቃረበ ። ሊይዛት ትንሽ ብቻ ቀረው። በጣም
ተንጠራራ። እጇን ልታስይዘው አብዛኛው ሚዛኗን በገደሉ አፋፍ ላይ ወጥራ በሃይል ተንጠራራች። ጣቶቻቸው ሊነካኩ የስንዝር ያክል ልዩነት ብቻ ነበር የቀራቸው። በዚሁ መሀል ግን ከየት መጣ ሳይባል አንድ ትልቅ ጭልፊት አሞራ ይመጣና ፊቷን በጥፊ ይላታል። ደንግጣ አሞራውን ለማየት ቀና ስትል ጌትነት የተንጠለጠለበት ሀረግ ቷ!! ብሎ ከመስረቱ ተነቀለና ቁልቁል እየተምዘገዘገ ይዞት ሲወርድ አየች።
ገደሉ ርቀት ነበረው። ጌትነት ጥረቱ ሳይሳካለት ቀረና ሄዶ በአናቱ ተደፋ። ጭንቅላቱ ያረፈው አለት ድንጋይ ላይ ነበር፡፡ በጀርባው እንደተዘረረ ደሙ እንደ ምንጭ ውሃ ቡልቅ! ሲል እናቱ ተመለከተች፡፡
“ወይኔ..ልጄን!እኔ ልደፋ!” ባለ በሌለ ሀይሏ ወደ ገደሉ ራሷን ወረወረች... ከእንቅልፏ እየተወራጨች የባነነችው በዚህ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ እያለች ነበር፡፡ በዚህ እጅግ አሰቃቂ በሆነ ህልሟ ምክንያት ሰውነቷ ይንዘፈዘፍ፣ ወባ እንደተነሳበት ስው ይንቀጠቀጥ ጀመር፡፡
እውን... እውን መሰላት። ከአልጋዋ ላይ ተነሳችና መንታ መንታውን
አወረደችው። ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡ ማልቀስ ካቆመች ረጅም ጊዜ ሆኗት ነበር፡፡ የተጠራቀመ እምባዋን እንደ ጐርፍ ለቀቀችው
"ወይኔ ጉዴ?! ወይኔ ልጆቼ?! ምን ዓይነት ህልም ነው? የኔ ደም
ክንብል ይበል። ዛሬ ፈጣሪዬ ምኑን አሳየኽኝ? ደግሞ የምን ጭልፊት
ነው? ዐይኔን ሊያጠፋው ነበረኮ! እስቲ አንተ ታውቃለህ? " ከዚህ አሰቃቂ ህልሟ በኋላ መንፈሷ በፍፁም አልረጋጋ አላት። ጭንቀቱ እረፍት ነሳትና ዳቦ ቆሎ መቁረጥ ጀመረች። በሌላ ጊዜ ደግሞ ትልቅ እባብ ሲያባርረው አየች። ይሄንን ግን ለወይዘሮ ተዋበች አልደበቀቻቸውም፡፡
“ምቀኛ ነው! ምቀኛ! ለመሆኑ ነደፈው?" ብለው ጠየቋት።
የለም! የለም! አልነደፈውም ብቻ ሲያባርረው ሮጦ አመለጠው'
ባለመነደፉ ነው ህልሟን የተናገረችው እንጂ ነድፎት ቢሆን ኖሮ አትነግራቸውም ነበር፡፡
“ጐሽ!...ጎሽ! እባብ ምቀኛ ነው። ምቀኞቹን ሁሉ ድል አድርጓል ማለት ነው፡፡ ቢነድፈው ኖሮ ጥሩ አልነበረም፡፡ ካመለጠው እንኳ ከጠላት፣ ከምቀኛ ተንኮል አምልጧል ማለት ነው፡፡ ማለፊያ ህልም ነው ያየሽለት!”
ሲሉ አጽናኗት። የወላድ አንጀት፣ የልብ ፍቅር እውነትም አንዳንድ ጊዜ ሹክ የሚለው መንፈስ አለ፡፡ ጌትነት የዚያን አይነት አሳዛኝ አደጋ ሊደርስበት ሳምንት ሲቀረው ጀምሮ በሃሣብና በጭንቀት ተወጥራ እየተብሰለሰላች በሆነ ባልሆነው ልቧ ድንግጥ ድንግጥ እያለባት እንቅልፍ እንቢ እያላት
እያቃዣት ሰውነቷ መጨማደድ ጀመረና በጥቂት ቀናት ውስጥ
ተለወጠች፡፡ ለተመልካች ግራ እስከሚገባው ድረስ በአንድ ጊዜ ቆረቆዘች።ጉዷን ያላወቀች እናት። በሷ ቤት የሳምንት ተጓዥ መንገደኛ ናት።የስንቅ ጣጣዋን ጨርሳ ወደ ልጅዋ ለመሄድ ዝግጅቷን በማጠናቀቅ ላይ

የምትገኝ እናት....
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጌትነት በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ሪከቨሪ ክፍል እንዲገባ ተደረገ፡፡ብዙ ደም ስለፈሰሰው በአስቸኳይ ደም ተሰጥቶት በአፍንጫው ላይ ኦክስጂን በክንዱ ላይ ደግሞ ግሉኮስ ተሰካለት። ዕድሜ ልኩን ሲንከራተት የኖረው ልጅ ስራ ይዞ ትምህርቱን አጠናቆ የትዳር ውጥን ወጥኖ እናትና እህቱን የመርዳት ህልሙን ማሳካት ሲጀምር በዚያ የብዙ ሰው ህይወት ማቅ እያለበሰ፣ ደም እያስለቀሰ፣ ከኛሮ ጫካ እስከ አዲስ አበባ ዋሻዎች ድረስ የጥፋት አዝመራውን ሲዘራ በኖረው ክፉ ሽፍታ እጅ ላይ ወደቀ።
ጎንቻ ገንዘብ እስከተከፈለው ድረስ ለማንም አይመለስም፡፡ ለሱ ገንዘቡ እንጂ ጥቃት የሚሰነዝርባቸው ሰዎች ማንነት ምኑም አይደለም፡፡ እንደ
ጌትነት ተስፋ የነበራቸው ብዙዎችን ጉድ አድርጓል። ደም እንባ አስነብቷል። ጎጇቸውን አፍርሷል።
ጌትነት በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ ምክንያት ነፍሱ በሞትና በህይወት
ቀጭን ክር ላይ ተንጠልጥላ እየተወናወነች ናት። ሃኪሞች ያቺን በሞት ጠርዝ ላይ ተንጠልጥላ የምትንጠራወዝ ነፍስ ለማትረፍና የሙያ ግዴታቸውን ለመወጣት በመረባረብ ላይ ናቸው።ማንነቱን የሚገልፀው የመስሪያ ቤት መታወቂያው በኪሱ ውስጥ በመገኘቱ ሁኔታው በፖሊስ አማ
ካኝነት ለድርጅቱ እንዲገለፅ ተደርጓል፡፡
በጌትነት ላይ የደረሰውን አሰቃቂ አደጋ ሲስማ ክፉኛ የደነገጠው ሽመልስ ነበር፡፡ ሽመልስ ከሁሉም በፊት ፈጥኖ ሆስፒታል በመገኘት በጌትነት ላይ የደረስው ጉዳት ከባድ መሆኑን ካየ በኋላ አይተርፍም በሚል ግምት
ልቡ ወደ ውስጥ አለቀሰች።
ሽመልስ በብእሩ አንጥሮ በወረቀት ላይ ባያሰፍረውም የጌትነትን ታሪክ በልቡ ሲደርስ የኖረ ሰው ነው፡፡ የዚያ ወጣት ህይወት ጉዞ ለሱ ልዩ ትርጉም ነበረው፡፡ያ ወጣት በስራው ላይ የነበረው ትጋትና ችሎታ፣ ትምህርቱን በከፍተኛ ማእረግ በማጠናቀቀ ራሱን ለትዳርና ለከፍተኛ ሃላፊነት ያዘጋጀ ድሃ ቤተሰቦቹን በመርዳት ላይ የሚገኝና በብዙ ውጣ ውረድ
የህይወት ፈተናን የተፈተነ በስነ ምግባር የታነፀ ጠንካራ የገበሬ ልጅ በመሆኑ ይወደውና ያከብረው ነበር። ሽመልስ እነዚህን ሁሉ የህይወት ገጠመኞቹን በልቡ እየደረሰለት የሚገኝ የጌትነት ህይወት ታሪክ ደራሲ ነበረና ባልተጠበቀ ሁኔታ በድንገት በሞት የሚነጠቅ ከሆነ ለሱ የጌትነት
እሟሟት ከደራሲ ሞት ተለይቶ የሚታይ አልሆነም፡፡ ጌትነት የዋናው ገፀ ባህሪ ተዋናይ ነው። ዋናው ገፀ ባህሪ ከሞተ ድርሰቱ አብሮ መሞቱ ነውና የዋናው ገፀ ባህሪ ሞት ከራሱ ከደራሲው ሞት የማይተናነስ ሆኖ ነው የተሰማው።
ደራሲው ታሪክ ፈጥሮ፣ ታሪክ ቀምሮ፣ ገፀ ባህሪያት ስሎና አስተሳስሮ ልብ እያንጠለጠለ ከአንዱ ምእራፍ ወደ ሌላው ምእራፍ በምናብ እያሽጋገረ ታሪኩን ተርኮ ሳይጨርስ በድንገት በሞት ቢለይ ምን ሊፈጠር
ይችላል? በዚያው ልክ ደግሞ ደራሲው የፈጠረው ዋና ገፀ
ባህሪ በድንገት በሞት የሚነጠቅ ከሆነ ሊፈጠር የሚችለው ሁኔታ ከደራሲው ሞት ያልተናነስ ይሆናል።
ታሪኩ እያጓጓ ልብ እያንጠለጠለ ባልተጠበቀ ጊዜና ቦታ ዋናው ገፀ ባህሪ ላይመለስ ከሄደ ታሪኩ ቀጥ ዐይን ፍጥጥ ማለቱ አይቀርምና ዋናው ገፀ ባህሪ እንዳይሞትበትና ድርሰቱ አሰቃቂ ትራጄዲ እንዳይሆንበት ፈጣሪውን ተማፀነ።
ሽመልስ ጭንቅላቱን በሁለት እጆቹ ይዞ ምን ማድረግ እንዳለበት በጭንቀት ሲያሰላስል በምረቃው እለት ያስተዋወቀው ጓደኛው ባልቻ ትዝ አለው፡፡ ከዚያም ለባልቻ ስልክ ደወለለትና በአስቸኳይ ዳግማዊ ሚኒሊክ
ሆስፒታል እንዲመጣ ነግሮት ስልኩን ዘጋ።ባልቻ ሚኒሊክ ሆስፒታል እንደደረሰ ከሽመልስ ጋር ተገናኙና አስደንጋጩን ዜና ሰማ፡፡ከዚያም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከሽመልስ ጋር ተመካከሩ፡፡
በቅድሚያ ለእህቱ ቀጥሎ ደግሞ ለአማረች ሁኔታውን ለማሳወቅ ተስ
ማሙና ተያይዘው ወደ ሰራተኛ ሰፈር፣ በምረቃ ስነስርአቱ ላይ ተገኝተው ደስታን ወዳሳለፉባት ጎጆ አሳዛኙን ዜና ይዘው መሄድ ግድ ሆነባቸው። እዚያ ሲደርሱ ዘይኑ በድንጋጤ ማቅ ለብሳ ስታለቅስ አገኙዋት።
አደጋውን በዚያ ሁኔታ ለዘይኑ ለመግለፅ ጭካኔን የሚጠይቅ ቢሆንም“ አማራጭ አልነበራቸውምና ሊያደርጉት ተገደዱ። ለጋ አእምሮዋ ሊሽከመው የማይችለውን አስደንጋጭና እጅግ አሳዛኝ ዜና እንድታውቀው አደረጉ።አስቀድማ ወንድም ጋሻዋ የውሃ ሽታ ሆኖ ያደረበትን ምክንያት ተጠራጥራ ሙሉ ለሊት ስታለቅስ ተቅማጥ ሲያጣድፋት ያደረችው ልጅ
የስራ አካሏ በድን ሆኖ ሃቁን አዳመጠች።
ታናሽ እህቱ ያንን አስደንጋጭ ዜና ስትሰማ በድን ሆና መቅረቷን ያስተዋለ ሰው ያቺ እናቱ ደግሞ ይህንን መርዶ ስትሰማ የምትሆነውን፣ የሚደርስባት ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል አለማሰቡን ይመርጣል።
እጮኛው አማረችስ ምን ይሰማት ይሆን? የሚወዱት ጓደኞቹ ምን ይሉ ይሆን? ሽመልስና ባልቻ ያንን ሃላፊነት ሙሉ በሙሉ ወስደው አማረችንም ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ አደጋውን እንድታውቅ አደረጉና ሁለቱንም በኮንትራት ታክሲ ይዘዋቸው ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል በረሩ...
አማረችና ዘይኑ እዬዬአቸውን እያሰሙ ከሆስፒታሉ ሪከቨሪ ሲደርሱ መግባት ክልክል ነው ተባሉ፡፡ከብዙ ልመና በኋላ በርቀት እንዲያዩት ተፈቀደላቸው። ጌትነት በጀርባው ተንጋሏል። በአፍና በአፍንጫው ላይ የተሰካለት ግሉኮሱ ጠብ ጠብ...እያለ ይወርዳል። ፊቱ በፋሻ ተጠቅልሏል፡፡ እስትንፋስ ያለው አይመስልም፡፡ እህቱና ፍቅረኛው እንደዚያ ሆኖ ሲያዩት እግራቸው ተብረክርኮ መቆም ተሳናቸው። ከዚያም ወደ መሬት በርከክ ብለው እዬዬ እያሉ አለቀሱ፡፡ ጌትነት ተጨማሪ ደም አስፈልጎት
ነበረና ሁለቱም የደም ግፊታቸውንና ክብደታቸውን ከተለኩ በኋላ ደም እንዲሰጡ ተደረገ፡፡
አማረችና ዘይኑ ከክንዶቻቸው የተቀዳው ደም ሲቆም ከዐይኖቻቸው የሚቀዳው የእምባ ጅረት ግን በቶሉ ሊቆም አልቻለም፡፡ የጌትነትን ሁኔታ
እያዩ እምባቸው እንደ ደራሽ ውሃ ክምብል እያለ ፊታቸውን አጠበው፡፡ለመሆኑ ማን ነው በጌትነት ላይ እንደዚህ የሚጨክን ልብ ያለው? እስቲ ማን ነው አንድ ቀን እንኳ ሰውን በክፉ ዐይኖቹ አይቶ በማያውቅ ትሁት ልጅ ላይ ያንን የመሰለ ዘግናኝ ድርጊት ለመፈፀም የደፈረው? የማን
ልብ ነው እንደዚያ ጨክኖ ለሞት በሚያበቃ አሰቃቂ ሁኔታ ደሙን ያፈሰሰው? ለሁለቱም ይህ ጥያቄአቸው መልስ ያላገኙለት እንቆቅልሽ ሆኖ ባቸው ነበር።...

👍2❤1
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...ሽዋዬ ከቤቷ ስትወጣ የት መሄድ እንደነበረባት አቅዳ አልነበረም። ሰሞኑን ነገሮች ሁሉ ረገብ ብለው ስታይ ትንሽም ቢሆን ቀዝቀዝ ብላ የነበረ ቢሆንም የዛሬው አስቻለው ቤቷ ድረስ መምጣት ግን እሳት ለኩሰባት ንዴቷን ቀስትሶባታል፡፡
ከወጣችም በኋሳ ጅው ብላ መሄዷ አስቻለውና ሔዋን ብስጭቷን አይተው ለወደፊቱም እንዲፈሩ ማድረግ ነበር፡፡ ያ ሁሉ ሆኖ አሁንም ጉዞዋን ወደፊት
ቀጠለች። የዲላ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱን ወደ ቀኝ በመተው ሂዳ ሂዳ ወደ ኳስ ሜዳው ደረሰች። በሜዳው እሻግራ ፊት ለፊት ስትመለከት የዲላ ሆስፒታል ለጥ ባለ ሜዳ ላይ ተንጣሎ ታያት፡፡ ያኔ ባርናባስ ወየሶ ትዝ አላት፡፡
««አሃ» አለኝ ቀጥ ብላ በመቆም ብቻዋን እየተነጋገረች፡፡ አሁንም ለራሷ
«ለምን ባርኒ ጋ አልሄድም?» አለች። ባርናባስን ስታቆላምጠው ባርኔ እያለች ነው፡፡
ለኳስ ሜዳ ተብሎ የተናደውን ገደል ተንደርድራ ወረደችው፡ ሜዳዋንም አቋርጣት አለፈች። እዚያም አልፋ ከዲላ ወደ ሞያሌ የሚወስደውን የአስፋልት
መንገድ ተሻገረች:: ብላ ብላ የቆፌን የኮረንኮች መንገድ ትውረገረገበት ጀመር፡፡
ደግነቱ ከቤቷ የወጣችው ትምህርት ቤት ስትሄድ የለበሰችውን ልብስ እንደለበስች
ስለሆነ አለባበሷ ወዴትም ብትሄድ አያሳፍራትም፡፡ ከቦርሳ በስተቀር የሚቀራት ነገር የለምና :: አንገቷ ላይ ቀላ ያለ ቡኒ ቀለም ያላት ስካርፍ አጣፍታለች፡፡
ለሆስፒታሉ እንግዳ ናት:: ታማ ልትታከም ወይም ታማሚ ልትጠይቅ እንኳ ገብታበት አታውቅም፡፡ ይሁን እንጂ ሆስፒታሉ አደናጋሪ ሁኔታ የለውም፡፡
ህንፃዎቹ በአንድ አካባቢ ችምችም ብለው የተሰሩ ናቸው። ቀሪው ደግሞ ወለል ያለ
ሜዳ፡፡ ቀጥታ ወደ ህንጻዎቹ ስትጠጋ የተጓዘችበት መንገድ ከድንገተኛ መቀበያ ክፍሎች አካባቢ አደረሳት።
ሰዓቱ ወደ ስምንት ተኩል ገደማ ይሆናል። በርካታ ህመምተኞት በአግዳሚ ወንበሮቻ ላይ ተቀምጠው ወረፋቸውን ይጠባበቃሉ፡፡ የህመምተኞቹ ጀርባ ቆም ብላ ወደ ቀኝ አቅጣጫ ስትመለከት ረጅም የመተላለፊያ ኮሪደር ታያት፡፡ ጎርደድ ልትልበት አስባ ጥቂት ከተራመደች በኋላ አሁን ወደ አስተዳደር አገልግሎት ሃላፊ» የሚል የቢሮ መለያ አነበበች፡፡
«አሃ! የባርኔ ቢሮ ይኸ መሆን አለበት» አለችና ቆም ብላ ወደ በሩ ስትመለከት ከኋላ በል የሰው እጅ ትክሻዋ ላይ ቸብ አደረጋት፤ ባርናባስ ወየሶ፣
ሽዋ'ዩ ድንግጥ አለች ። «እንዴ! አለህ እንዴ?» ስትል ጠየቀችው ምን እያለች እንደሆነ ለሷም ሳይገባት።
«የሸዋ ዛሬ ከየት ተገኘሽን»አለና ባርናባስ እጇን ጨብጦ እንደገና ደረት ልደረት ተሳሳመ።: ባርናባስ ሸዋዬን ሲያቆላምጥ የሸዋ እያለ ነው፡፡
«ጉብኝት መጥቼ::» አለችው ሸዋዬ ሳቅ እያለች።
ጥሩ ነዋ! የሚጎበኝም ሞልቷል የሚያስጎበኝም አለ።» አላት ባርናባስ እጁን ትክሻዋ ላይ ጣል አድርጎ በረጅም ቁመቱ ቁልቁል እየተመለከታት፡፡
«አለፈልኛ! ኪኪኪኪ ……!
እኔ ጋ ነው የመጣሽው?» ሲል ጠየቃት እሷንም ቢሮውንም ተራ በተራ እየተመለከተ፡
«አይ!» ሽዋዬ ተሽኮረመመች።
«ቢሮዬ አጠገብ ቆመሽ ሳገኝሽ ጊዜ እኮ ነወ፡፡ ጎራ በያ፣ ሻይ በና ልበልሽ»
«በዚህ ሙቀት ሻይ ቡና?»
«ለስላሳም ይኖራል»::አለና ባርናባስ እጇን ይዟት ወደ ቢሮው አመራ::
በሽዋዬ ዓይን የባርናባስ ቢሮ ልዩ ነው፡፡ ስፋቱ፣ ጽዳቱ፣ የመስኮቶቹ
መጋረጃዎችና የወለለ ምንጣፍ ዓይን ይማርካሉ፡፡ የመጋረጃው ቀለም ነጣ ያለ ብርቱካናማ ነው ለቢሮው ልዩ ብርሃን ሰጥቶታል፡፡ እንግዳ መቀበያው ጠረጴዛ
ስፋትና የወንበሮቹ ብዛት አስደነቃት፡፡ በቢሮው የግድግዳ ጥግ ዙሪያ ተጨማሪ ወንበሮችም አሉ፡፡ ያቤሎ ጤና ጣቢያ ውስጥ በነበረበት ጊዜ በአንድ ጠበብ ባለች ክፍል ውስጥ ከአንድ ሜትር የማትበልጥ ጠረጴዛውንና የሚቀመጥባትን ደረቅ
ወንበር አስታውሳ ስታወዳድር አሁን ግን ገነት ወስጥ እንደገባ ቆጠረችው::
«አንተ! ቢሮህ ግን እንዴት ያምራል!?» አለችው የቢሮውን ዙሪያ በዓይኗ እየቃኘች፡፡
ከዚህ የበለጠ ስንት ዓይነት ቢሮ አለ እባክሽ! ደሞ ይኸ ቢሮ ሆኖ?» አለና ወንበር ሳብ አድርጎ እንድትቀመጥ ጋበዛት።
«ጡር አትናገር»
ባርናባስ በእንግዳ መቀበያው ጠረጴዛ ላይ ከሸዋዬ ፊትለፊት ቁጭ አለና በደወል ተላላኪ ጠርቶ ለእሱ ቡና ስሸዋዬ ለስላሳ አዘዘ
«ይኸ ሁሉ ወንበር ምን ያረጋል?» ስትል ጠየቀችው፡፡
ህእ! የባለ ስልጣን ቢሮ እኮ ነው፣ ስንት ዓይነት ስብሰባ የሚካሄድበትና ውሳኔ የሚሰጥበት። አለና ባርናባስ በተቀመጠበት ላይ ፈነስነስ አለ።
በምን በምን ጉዳይ ላይ ትወስናለህ?»
«በፖለቲካ በትይ፥ በአስተዳደር ጉዳይ ብትይ፣ በደረጃ ዕድገት፣
በዲስፕሊን.…ወዘተ!» አለና ሽዋዬን ፈገግ ብሎ እያየ በቀልድ ዓይነት አነጋገር፣
«በፍቅር ላይ ብቻ ነው መወሰን ያቃተኝ!» አለና ሃሃሃሃ…» ብሎ ለራሱ ስቆ ሸዋዬንም አሳቃት፡፡
«ስትልን» አለች ሽዋዪ በቅንድቧ ስር እያየችው፡፡
«የምወዳት ሴት እንዳትጠላኝ አድርጌ መወሰን! ሃሃሃሃ….
«ውይ አልቀረብህም»
"ያን ማድረግ ብችል ኖሮ አንቺ መች ታመልጪኝ ነበር» አለና እንደ ቁም ነገር አድርጎ ግን የሸዋ፡ ይህን ያህል ወራት ዲላ ውስጥ ስትኖሪ እንዴት ወደ ቢሮው ሄጄ ልጠይቀው አላልሽም?» ሲል ጠየቃት፡፡
«ሆሆይ! ደሞ የሰው ባል ለአለፈውም ይቅር ይበለኝ፡፡ ያም ቢሆን ሳላውቅ ያደረኩት ስለሆነ ኩነኔው የአንተ ነው፡፡» አለችና የቀረበላትን ሚሪንዳ ጎንጨት
አለች፡፡
ባርናባስ በስጨት እንዳለ ዓይነት እጁን ወንጨፍ እያረገ የሸዋ ደሞ ዝም ብለሽ ነው፣ ይኸን ሚስት፣ ድስት፣ ትዳር ምናምን የምትይውን ነገር ለምን አትተይም? ፍቅር በትዳርና በስማኒያ ይገለጽ መስለሽ እንዴ?” አላት ቡናውን
እያማሰለ፡፡
«ብታርፍ ይሻልሃል» .
«በተለይ በአንቺ ነገር መቼም ቢሆን የምቆርጥ አይመስለኝም።
ግን ባለቤትህ ደህና ናት?»
«ለራሷ ትኖራለች።
«እዚህ ገባህ፣ ከዚያ ወጣህ አትለኝም!»
«መረን ለቃሃለቻ!»
«ኧረ ዛሬ ከየት ተገኘሽ የሽዋ? እስቲ ስለ አንቺ እንጨዋወት?» ብሎ ቡናውን ፉት አለ፡፡
«አንተን ልጠይቅ ኪኪኪኪ...»
«ጎሽ የኔ ወለላ! አንቺ እኮ ዱሮም ቁም ነገርኛ ነሽ ሰውየው እኔ ሆኜ እንጂ» ብሉ ነገሩን ተወት ሲያደርገው ሽዋዬ ቀጠላች።
«ባትሆንስ?»
«ልብ ቢኖረኝ ኖሮ እግርሽ ላይ ወድቄ ይቅርታ መጠየቅ ነበረብኝ። ግን ዛሬነገ ስል» አለና ንግግሩን ቆረጥ አድርጎ አሁንም ቡናውን ፉት አለ፡፡
«ደሞ እንደገና?»
«የቆየ ነገር እኮ ሲታደስ ከበፊቱ ይበልጣል። ሃሃሃሃ…»
«ይልቅስ ስለ መጣሁበት ጉዳይ ልጠይቅህ!»
«ምን ልርዳሽ?»
«አንድ ሴት፣ በተለይ ልጃገረድ ማስወረድ አስማስወረዷን በሀኪም ምርመራ ማወቅ ይቻላል?» ስትል ጠየቀችው፡፡
«ሀኪሞችን አነጋግሮ መረዳት ይቻላል። ግን በዚህ ዙሪያ ምን ችግር ገጠመሽ?» ሲል ጠየቃት።
«በእናትህ ባርኔ ዶክተሮችን ጠይቅና ንገረኝ!»
«ማነጋገር እችላለሁ!»
«ይገርምሃል! በአንዲት እህቴ ገዳይ ተቸግሬአለሁ፡፡»
«አስወርዳ?»
«መሰለኝ፡፡»
«በአገር ባህል ወይስ በሀኪም?»
«አረ የእናንተ ሰራተኛ በሆነ ሰው!»
ደሞ የምን ባህል አመጣህ ያን ቤሆን ራሴ ተከታትዩ ለሕግ አቀርበው አልነበር? ያስቸገረኝ ብላ ሸዋዬ የተበሳጨች ለመምሰል ራሷን ወዘወዘች።

"ማነው የኛ ሰው?" ሲል ጠየቃት ባርናባስ ግንባሩን ቋጠር አድርጎ፡፡
"ሆሆይ! ደሞ ያለ በቂ ማስረጃ የሰው ስም ጠርቼ ዕዳ ልግባ።" አለችና ዓይኖቿን ወደ ጣሪያ ሰካች
«እንዴ! የምታወሪው እኮ ለኔ ነወ፡፡ «ፖሊስ ጣቢያ ወይ ለፍርድ ቤት የምታወሪ መሰለሽ እንዴ?»
«አንተስ ብትሆን የፖርቲ አባል አይደለህ?"
«ታዲያ እኮ የኛ ዋንኛ መለያ ምስጢር መጠበቅ ነው::"
«ለማንም አታወራ?»
«እንዴ...ያንችን ሚስጥር!»
ሽዋዬ እንደ ማቅማማት ብላ የላይኛውን ከንፈሯን በጥርሷ ነከስ አድርጋ ወደ ላይ እንጋጣ እያየች ታስብ ጀመር፡፡ ወይዘሮ እልፍነሽም ትዝ አሏት።ከእሳቸው የሰማችው ወሬ ነውና እውነትነቱንም ተጠራጥራ ፍርሀት ተሰማት።
«አትፍሪ የሸዋ! እንደውም እንዲህ ያለ ነገር በራሳችን ባለመያዎች ተሰርቶ ካገኘን ርምጃችን የከፋ ነው።» አላት ተመልሶ ወደ ጠረጴዛው ደገፍ እያለ::
«እኔ እኮ የጨነቀኝ የማስረጃው ጉዳይ ነው፡፡››
«ለዚያ ምን አስጨነቀሽ? ፍንጭ ካገኘን እኛው ራሳችን እየሰረሰርን
እንገባበት የለ ዋናው ጥቆማሁ ነው::"
«አስቻለው የሚባለውን ነርስ በደንብ ታውቀዋለህ?
ባርናባስ አንገቱን መዘዝ፣ ዓይኑን ፈጠጥ አድርጎ እንደውም ሾከክ ባል አነጋገር «እሱ ነው እንዴ?» ሲል ጠየቃት፡፡
ሽዋዬ ከንፈሮቿን አጣብቃ እንገቷን በአዎንታ በመነቅነቅ አረጋገጠችለት።
በዚህ ጊዜ ባርናባስ ፈጠን ብሎ በመነሳት ወደ ወንበሩ አለፈ። ወረቀትና እስኪርብቶ አዘጋጀ:: የአስቻለውን ስም ጻፈና፡
«ድርጊቱን የፈጸመበትን ወቅት ታውቂዋለሽ?» ሲል ጠየቃት::
«በትክክል አላውቅም፡፡»
«እንደው በግምት?»
«ምናልባት ሁለት ወይም ሦስት ወራት!»
«እንዴ! ይኸማ ትናንትና ነው በይኛ!» በማለት አዳነቀና የእህትሽ ስም ማን ይባላል?» ሲል ጠየቃት።
«ሔዋን ተስፋዩ::»
«በእሷ በኩል ፍንጭ ማግኘት ይቻል ይሆን?»
«''ሆሆይ!» አለች ሸዋዬ ጮክ ብላ። «እሷ ብትጠየቅ አስቻለው የሚባል ሰው አላውቅም ነው የምትለው:: በዚያ በኩል አትልፋ::»
«ቆንጠጥ ብናደርጋትስ?»
“ብትፈነክታትም! እንዲያውም አንዳች ነገር ሳያስነካት የቀረ አይመስለኝም፤ የእሱ ነገር ሲነሳባት አትወድም::» አለችው በመስኮት በኩል ወደ ውጭ እያየች፡፡
“በቃ ተይው ይህን ያህል ፍንጭ ከተገኘ የትም አያመልጥም። ቀስ ተብሎ ይመረመራል፡፡" አለና ደስታ ይሁን ንዴት ብቻ የያዘውን ብዕር የምት ያህል ወርውሮ ወረቀቱ ላይ ጣል አደረገው፣
“ውጤቱን እንዴት ልንከታተል?» አለችው ሽዋዬ የባርናባስ ስሜት ጋል ብሎ ስታይ ጓጓ ብላ፡፡
“የት ልትተጣጣ?» አለና ቤትሽን ባውቀው እኮ እኔው ራሴ እየመጣሁ የደረስኩበትን እገልጽልሽ ነበር» አላት አንገቱን ጠመም አድርጎ በፈገግታ እያያት።
«ደሞ አንዴ ካወከው በኋላ ነጋ ጠባ እየተመላለስክ ..." ብላ ሽዋዬ ነገሯን ተወት ስታደርግ ባርናባስ ራሱ ቀጠለ።
«ያልተመቸሁሽ ዕለት በቃኝ ትይኝ የለም፡፡» ብሎ “ወይ ስልክ ቁጥር
ስጪኝ፡፡» አላት የአንተን ሰልክ ስጠኝ፣ ቁምነገር ከሰራህ ልጠራህም እችላለሁ፡፡
“ይኸማ ጥሩ» አለና የስልክ ቁጥሩን ወረቀት ላይ ጽፎ ሰጣት፡፡
ሸዋዬ ሠዓት አየት ስታደርግ ወደ አሥር ተጠግቷል፡፡ «በቃ ልሂድ!» ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡
ግብዣው እንደማይዘገይ እተማመናለሁ:: ከላት ባርናባስ ፈገግ እያለና ትከሻዋን ቸብ እያረገ፡፡
«ገና ጠላው ተሰምቆ ነዋ ኪ. ኪ ኪ ኪ...
«ጥሩ አርግሽ ጥመቂው እንጂ ይደርሳል፡፡»
ሸዋዬ ለጊዜውም ቢሆን የንዴትና የብስጭት ሽክሟን በጨዋታ ሰበብ ቀለል አድርጋ ፈገግ እያለች ከቀርናባስ ቢሮ ልትወጣ በሩን ከፈት ስታደርግ ጋውን ለብሶ
በኮሪደሩ ላይ በአንድ አቅጣጫ ወደ ሌላ በመሄድ ላይ ከነበረው አስቻለውኑ ፍስህ ጋር ድንገት ዓይን ለዓይን ግጥምጥም አሉ፡፡ እሷም ፍጥጥ! እሱም ፍጥጥ!...

#ክፍል_አርባ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
#አዲስ_ዓለም
..የመንገዱ መብራቶች ተበላሽተው ብርሃን አይሰጡም። አካባቢው ፀጥ እረጭ ብሏል። ትናንትና ማታ እስከ ስድስት ሰዓት የነበረው ጩኸት፣ ሁካታ የሰካራሞች ልፍለፋ፣ የሴተኛ አዳሪዎች ስድብ፣ በየቀይ መብራቱ ውስጥ የነበዙ ጠጪዎች ዳንኪራና ጭፈራ ትርምሱ ሁሉ እዚህ ቦታ
የነበረ መሆኑ የሚያጠራጥር ነው፡፡ የሥጋ ቤቶቹ ብርሃን ድምቀት፣ከቡና ቤት ቡና ቤት የሚያማርጠው ጠጪ ብዛት፣ የሙዚቃው ጩኽትና የመኪናው ኳኳታ ጆሮ ሲያደነቁር እንዳላመሽ ሁሉ እንደዚህ እንደ አሁኑ እረጭ ብሎ ሲታይ በግርግርና በፀጥታ መካከል ያለውን ልዩነት
ለማሳየት ደፈጣ የያዘ ይመስል ነበር፡፡
የወዳደቀ አጥንት ለመለቃቀም የሚያነፈንፉ ውሾች ውር ውር
ይላሉ፡፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ ግን ያን ሰው የማይታይበትን አካባቢ ፀጥታ በማደፍረስ የጠዋት ገበያዋን ለመላፍ የተጣደፈች ታክሲ ከእሪ በከንቱ ወደ አራት ኪሎ አቅጣጫ በረረች፡፡ በዚያው ቅጽበት ደግሞ
ቁልቁል ከፒያሳ ወደ እሪ በከንቱ እየዘለለ የሚወርድ ሰው ታዬ። መላ ሰውነቱን ሬንጅና ጥላሸት የተቀባ ፀጉሩ እዚህም እዚያም ተገምዶ እንደ ጭራሮ የቆመ፣ ጎድኖቹ ሥጋ ባልለበሰ አጥንት የገጠጡት እብዱ ምን ሽንሽ! ብቻውን በመንገዱ ግራና ቀኝ ቱር ቱር እያለ እየተሯሯጠ ሽቅብ
ይወጣል ቁልቁል ይወርዳል። ዐይኖቹ እንደ በርበሬ ቀልተው ለተመልካች ያስፈራራሉ። ከወገቡ በታች እዚህም እዚያም የተቦጫጨቀ ሱሪ መልበስ
ከተባለ ለብሷል። ቆም ይልና ድንጋይ ይፈነቅላል ያነሳውን መልሶ ይወረውረዋል። ደግሞ ወደታች ይወርዳል። ከዚያም ጉንበስ ይልና የሲጋራ ቁራጭ ለመልቀም ያነፈንፋል።እንደገና ወደ ላይ ይወጣል። የዚያ አስፈሪ
የጨለማ ንጉሥ ሁሉም በየቤቱ በተከተተበት ሰዓት እሱ እየዘለለና እየቦረቀ ብቻውን በየመንገዱ ላይ ሲሯሯጥ ምሽቱን ለብርሃን ለማስረከብ የተዘጋጀ ባለሥልጣን ይመስል ነበር።
ከለሊቱ አሥራ አንድ ሰዓት ሆኗል። ወደየጠቅላይ ግዛቱ የሚጓዙ መንገደኞች አውቶቡስ ተራ ለመድረስ በዋናው አስፋልት መንገድ ላይ ብቅ ብቅ ብለዋል። በዚያ ሰዓት በእግር የሚጓዝ መንገደኛ አንድም በራሱ የተማመነ አሊያም ከወሮበላና ከማጅራት መቺው ሰይፍ እግዚአብሔር እንዲጠብቀው በልቡ ፀሎት እያደረስ በፍርሃት የሚራመድበት እንጂ ልቡ
በድፍረት ተሞልቶ የሚንቀሳቀስበት ሰዓት አልነበረም፡፡ ለሁሉ ነገር ግድ
የለሌው ለማጅራት መቺው ለብርዱ ለፀሀዩ ለሞትም ለህይወትም ደንታ የሌለው እብዱ ምንሽንሽ ብቻ ነበር። የእሪ በከንቱን ድልድይ ተሻግሮ
ወደ አራት ኪሎ ሲያቀና አንድ ዕድሜው ከሰላሳ ስምንት እስከ አርባ አመት የሚገመት ወደ ወሎ ጠቅላይ ግዛት ለመሄድ የሚገስግስ ሰው ብቅ! አለ። ሰውዬው ምንሽንሽን ሲያየው “በስመአብ ወልድ ጌታዬ” አለና
አማተበ፡ የሰይጣን ቤት አጋፋሪ የመሰለውን እብድ ሲመለከት ከመንገዱ ፈንጠር አለና ወደ ዳር ወጣ፡፡ ካደረበት ከዘውዲቱ ሆቴል ቁልቁል ወደ እሪ በከንቱ የሚወስደውን መንገድ ሲጀምረው ዳፍንቱ በብርሃን ባለመተካቱ ልቡ ፈራ ተባ እያለ ጉዞውን ቀጠለ፡፡
የአራት ልጆች አባት የሆነው ጓንጉል ቢሆነኝ አዲስ አበባ የመጣው ያደለባቸውን ሁለት ሠንጋዎች ወልዲያ ገበያ ሸጦ ባገኘው ገንዘብ ለሚስቱና ለልጆቹ ልብስና ጫማ ለራሱ ደግሞ የፋሲካን በዓል መዋያ ልብስ
አማርጦ በርካሽ ዋጋ ገዝቶ ቀሪውን ገንዘብ ለልዩ ልዩ ችግሮች ማቃለያ ሊያደርግና በኮተቤ መምህራን ማሰልጠኛ የመጀመሪያ አመት ተማሪ የሆነችው የታናሽ እህቱን ልጅ ሊጠይቅ በዚያውም የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የሆነችው አዲስ አበባን ሊጎበኛት ነው።
በዚሁ መሠረት ጣጣውን ጨርሶ ለአራቱ ልጆቹ ልብስ ሲያማርጥ ቆይቶ ሻንጣ ገዝቶ ከቆጣጠረና አዳሩን ዘውዲቱ ሆቴል ካደረገ በኋላ ወደ ቤተሰቦቹ ለመገስገስ ከዚያም ቤት ደርሶ ልጆቹና ሚስቱ ከበውት ሲንጫጩ የኔ ያምራል የኔ ይበልጣል እያሉ ህፃናቱ እርስ በርሳቸው ሲሟገቱ፣ሚስቱ ደግሞ የገዛላትን ቀሚስ እየላካች ረዝሞ ከሆነ ሰነፍ ልኬን እንኳን
የማታውቅ? ስትለው፣ ልኳ ከሆነ ደግሞ እሰይ የኔ አንበሳ” ብላ ስታደንቀው፣ ጉንጬን ሳም ስታደርገው በሀሳቡ እየታየው ቶሎ ሊደርስላቸው ነበር ለሊቱ አልነጋልህ ብሎት ዐይኑ ፈጥጦ ያደረውና ከለሊቱ ለአሥራ
አንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ ያውም የረፈደበት መስሎት ልብሱን በፍጥነት ለባብሶ የወጣው...
ጓንጉል ምንሽንሽን ሲያየው በድንገጤ እግሩ ተሽመደመደበት እንደዚህ አይነት አጋንንት መሳይ ሰው ሚልኪው ጥሩ አይደለም አለ በልቡ። የሰው ዘር ሳያይ ዐይኑ ያረፈው በእብዱ ላይ ነበር። እብዱ ምንሽንሽ ወደሱ እንደመጠጋት ብሎ ፊት ለፊት ሲመጣበት በድንጋጤ ወደ ግራ
በኩል እሸሻለሁ ሲል አደናቀፈው።
“ወንዱ!” አለና ፎክሮ ተንገዳገደ። እብዱ ጠጋ አለውና እጁን ዘረጋለት።
ፍራንክ እንደሚጠይቀው አወቀ። ወይ ይቺ ፍራንክ? አለ በልቡ።እብዱም፣ጤነኛውም፣አዋቂውም፣ ህፃኑም ሁሉም ይወዷታል ሲል ተገረመ::
የመጨረሻዋ የስድስት ወር ህፃን ልጁ እንኳን ወሪቀት በግራ እጁ ብር በቀኝ እጁ ይዞ ሲያስጠጋላት እጅዋ ወደ ቀኝ እጁ ነበር የሄደው። ይሄን አስታወሰና ትንሽ እንደ መሳቅ ብሎ እጁን ወደ ኪሱ ከተተና ያገኘውን ድፍን ሃያ አምስት ሣንቲም ኣውጥቶ ወረወረለት። ምንሽንሽ ሳንቲሟን
ለማንሳት ጐንበስ ሲል እሱ ደግሞ አውቶቡሱ እንዳያመልጠው በሩጫ ዳገቱን ተያያዘው፡፡
የሆነ ነገር ውልብ አለበት፡፡ የሰው ቁመና መስለው። ከግራ ወደ ቀኝ
የሮጠ ነገር ነበር፡፡
“ጅብ ነው! ጅብ መሆን አለበት። ከወዲህኛው ገደል ዘሎ ወደዚያኛው መግባቱ ነው! ልክ ነው አውሬ መሆን አለበት! አቋረጠኝ እኮ ልክ ነው ደግሞ ጠቆር ያለ ነገር ነው! ወይኔ ዛሬ እግዚአብሔር ከዚህ ጉድ ያውጣኝ እንጂ ያጋጠመኝን ሁሉ ቤት ገብቼ ለሚስቴ ነው የማጫውታት፡፡ ገና በጠዋቱ ቀንዳም ጋኔን የመሰለ እብድ ለከፈኝ እሱን ሳልፍ ደግሞ ይኸውና ጥቁር ጅብ አቋረጠኝ። እግዚአብሔር ያውቃል” እያለ በልቡ እያወራ ወደ ድልድዩ ተጠጋ፡፡ ሰግጠጥ እንደማለት
አደረገው። ድልድዩ ላይ ሲደርስ ከበደው፡፡ ገልመጥ፣ ገልመጥ አለ። ሰላም ይመስላል። ፀጥ ረጭ ብሏል። ብቅ ብቅ ብለው መታየት የጀመ ሩት ሰዎች በተለያየ አቅጣጫ ሄደዋል። በዚያ መንገድ ላይ ተፍ ተፍ የሚለው እሱ ብቻ ነበር፡፡
“ስው ሊሆን አይችልም፡፡ በዚህ ሰዓት ሰው እዚህ ድንጋይ ውስጥ እገደል ስር ምን ይሰራል? ሰው አይደለም አውሬ መሆን አለበት...” ፈራ ተባ እያለ ወደ ድልድዩ ገባ፡፡ እንደፈራው አይደለም፡፡ ምንም ነገር የለም።
ወደ ኋላው ገልመጥ ብሎ አየ፡፡ እብዱ በተሰጠው ሳንቲም ተደስቶ እየዘለለ ወደ አራት ኪሎ ሲያቀና ተመለከተው፡፡ አካባቢው ጭር.እረጭ...ያሉ የሞት ጥላ የሚያንዣብብበት መሰለ፡፡ ሁለቱን ሠንጋዎቹን ሸጦ ሸቀጣ ሸቀጥ ከሽመተበት ሌላ በኪሱ ውስጥ ሁለት መቶ አርባ ብር ቀርታዋለች፡፡
እሷንም ጥሩ ቦታ አስቀምጧታል፡፡ መጀመሪያ ከሱሪው ኪስ ከተታት፡፡ ደስ አላለውም፡፡ ወደ ኮቱ የውስጥ ኪስ ወሰዳት። አላመናትም፡፡ የአንድ ዓመት ሙሉ የልፋቱ ውጤት እነዚያ ቤት ቤት የሚያካክሉ ሠንጋዎቹ የተለወጡባት ትንሽ ነገር ብትጠፋ ሁለት ሠንጋዎች ቀለጡ ማለት ነው። በየኪሱ ሁሉ አዟዟራት። በመጨረሻ ላይ ጥሩ የማስቀመጫ ቦታ አገኘላት። በጥንቃቄ የሚደብቀበት አስተማማኝ ቦታ! ወደ ጫማው ወረደ። እንደገና እጁን መለሰው። አሁንም አሰላስለ። ፊቱ ፈካ አለ፡፡የመጨረሻውን አስተማማኝ ቦታ አገኘላት። በመታጠቂያው ዘልቆ በውስጥ ሱሪው መካከል በደንብ አድርጐ አጣጥፎ ቀረቀራት። የአሁኑ ከፍተኛ ሥጋቱ ይቺኑ እንቅልፍ ያጣባትን

👍3
የድካሙን ለህፃናት ልጆቹ የገዛቸው ጥብቆዎች ለራሱና ለሚስቱ አማርጦ የገዛቸው ልብሶች የሚወስዱበት መስሎት ነበር፡፡ እንደፍርሀቱ አልሆነም፡፡ ድልድዩን የሚሻገር መስሎ አልታየውም ነበር፡፡
ድልድዩን ተሻገረ። ሰውነቱን የከበደው ነገር ቀለል አለለት። ልቡ በትክክል መምታት ሲጀምር ያንን ጭንቀቱን ለማስወገድ ትንፋሹን ዋጠና...
እፎፎፎ...” “ይ” ን ሳይጠራ እንደ መብረቅ ጆሮ የሚወጋ እንደ ጅራፍ
የሚጋረፍ አስደንጋጭና አስፈሪ ድምጽ ቁ ም!” ሲል አንባረቀበት፡፡
ጓንጉል ብርክ ብርክ አለው፡፡ የያዛትን ሻንጣ አንዴ ወደ ቀኝ አንዴ ወደ ግራ እያዟዟረ የተሰጠው ትዕዛዝ ከፈጣሪው ይሁን ከሰው ለማረጋገጥ ዙሪያ ገባውን ተመለከተ። ድምፁን አስከትሎ ከፊት ለፊቱ ብቅ ባለው
ስው ላይ ዐይኖቹ ተተክለው በቀሩበት ቅፅበት ከማጅራቱ ላይ ሰላሣ ሁለት ጥርሶቹን ያንገጫገጨ ከባድ ነገር አረፈበት። ጓንጉል ሰማይ
ምድሩ ተደበላለቀበትና በቆመበት ቦታ ላይ በጀርባው ተዘረረ። ወዲያውኑ ሦስት ወጠምሾች ከየት መጡ ሳይባል በፍጥነት ደረሱና እንደ ቅርጫ ሥጋ ይቀራመቱት ጀመር። እጅግ አስደናቂ ነው! ዘራፊዎቹ ገንዘቡን የደበቀበትን ቦታ በጠረን እንደሚለዩት ሁሉ ጣቶቻቸው ብር እንደሚያሸቱ ሁሉ ስድስት እጆች በቅድሚያ የተረባረቡት በውስጥ ሱሪው ላይ ነበር፡፡
ጓንጉል ነፍሱን ስቶ ከላይ ከላይ
ትንፍስ፣ ትንፍስ ይላል። ሻንጣው
በአንድ በኩል እሱ ደግሞ በሌላ በኩል አውላላ ሜዳ ላይ እንደ ብቅል ተሰጥተዋል። ሲስቅ ወደ ፈረስ ድምጽ የሚወስደው መልኩ ጥቁርና ፊቱ ላይ ብዙ ጠባሳዎች የሚታዩበት ወጠምሻ በትንባሆ የበለዙ ጥርሶቹን ለማሳየት ቀይ ድዱን በለጠጠ... ያለማጋነን በአፍንጫው ቀዳዳ እንጥሉ ይታያል፡፡
“ኢሂሂሂሂ... ታያታለህ አጅሬን?
ቢሳካላት ጥሩ ቀርቃሪ ነበረች።
ከፖንቷ ጋር ጥሩ አድርጋ ሰፍታዋለች” አለና ያንን የተጠቀለለ ብር ይፈታ ጀመር፡፡ ስድስት ዐይኖች በተጠቀለለው ብር ላይ አጉረጡ።
ቆጠረው፡፡ሁለት መቶ አርባ ብር ነው፡፡ ብዙ ባይደሰቱም የድካማችን ዋጋ በከንቱ አልቀረም በሚል ፊታቸው መለስ ፈካ አለ። በደንብ አገላበጥካት?” አለ ሌላው።
“ምናምኗም አልቀረኝ!ኢሂሂሂ...እሱን ብቻ ነው የቀረቀረችው ማለት ነው”
አለና የተዘረረው ጓንጉልን እንደ ገብስ ነዶ እያገላበጠ በእግሩ ከመሬቱ ጋር ኣሸው::
“ተዋት ይበቃታል. ከአስራ አምስት ደቂቃ በኋላ ነፍሷን ትዘራለች። አቤት ሩጫ?! መቼም ስትነቃ እንደ ጄት ነው የምትሮጠው፡፡ አባቴ ይሙት አሯሯጧን ቁጭ ብሎ መመልከት ነበር! አሃሃሃ...” እየተሳሳቁ ሻንጣውን ተሸክመው ከአካባቢው ተሰወሩ።
ምስኪኑ ጓንጉል የገዛ ንብረቱ ጠላት ሆኖበት፣ገንዘቡ ዘራፊ ጠርቶበት ማጅራቱ እስከሚሰበር ድረስ ባረፈበት ከፍተኛ ምት ነፍሱን ሳያውቅ ከሃያ ደቂቃ ላላነሰ ጊዜ በወደቀበት ቦታ ላይ ተደፍቶ ቆየ። ከሃያ ደቂቃ በኋላ ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ሰው ብንን አለ የሰመመን እንቅልፍ ያሽለበው መሰለው፡፡ በመኖሪያ ቤቱ ከጠፍር አልጋው ላይ ያለ መስለው::
አጠገቡ ሚስቱ የለችም፡፡ ጠዋት ቁርስ ለማዘጋጀት የተነሳች መሰለው::
የልጆቹን ጫጫታና ጨዋታ የሚያዳምጥ መሰለው፡፡የአይጦች ኮሽታ፣ የውሾች ጩኸት፣ የጅብ ሣቅ፣ የጥጆች ድምፅ በዚያች በመኖሪያ ጉጆው ውስጥ ጠዋት ሊነጋጋ ሲል የሚሰማቸውን ድምፆች በሙሉ የሚሰማ
መሰለው። ዐይኖቹን ገለጥ አድርጉ የሚመለከተው ጥቁር ሰማይ በጭስ የጠቆረች የቆርቆሮ ቤቱ ጣሪያ መስላ ታየችው። ጊዜው ረፍዷል። ከብቶች
አላስወጣም።“ከብቶች ከበረት የማስወጫው ሰዓት ደረሰ መሰለኝ?” አለ በሀሣቡ፡፡ ቶሎ ለመነሳት ሞከረ፡፡ የተኛው ግን በዚያች በመኖሪያ ቤቱ
ውስጥ በጠፍር አልጋው ላይ ሳይሆን በጥቁር አስፋልት ላይ ነበር።አንገቱ ላይ ትልቅ ሸክም ተሰማው። የህመም ስሜት ነው። አዎን! አሁን ገና ህመሙ ይቆጠቁጠው ጀመር። በደረቱ እንደተኛ እንደምንም ብሎ ከአንገቱ ቀና አለና አካባቢውን ቁልቁል ተመለከተው። የእሪ
በከንቱ አስፋልት ጭው...ብሎ ታየው። ከሩቅ የታክሲ ኳኳታና የክላክስ ድምፅ ተሰማው፡፡ አሁን ገና የት እንዳለ አወቀ፡፡ አሁን ገና ምን እንደ ሆነ ተረዳ፡፡
ኡ! ኡ! ኡ!.ለማለት ነበር፡፡ የአገር ያለህ! የወገን ያለህ! ብሎ እርዳታ
ለመጠየቅ ነበር፡፡ አፉ ተከፈተ እንጂ ድምፅ አልነበረውም። ድምፅ አልባ ጩኸት ጮኸ፡፡ እንባ የሌለው ደረቅ እንባ አነባ፡፡ የደረስለት ሰው አልነበረም። ስሪያ የያዙ ውሾች በላዩ ላይ እየዘለሉ አለፉት። ለልጆቹና ለሚስቱ
የገዛቸው ልብሶች ከነሻንጣው የመዘረፋቸውን መርዶ ተመሰቃቅለው ወደ ውጭ የተገለበጡት ኪሶቹ አፋቸውን ከፍተው አረዱት። ገንዘቡን አርቆ
ሲያስቀምጠውም ሊድንለት አለመቻሉን ተገነዘበ፡፡ የለበሰው አሮጌ እዚህ ግባ የማይባል ጨርቅ በመሆኑ እንጂ አዲስ ቢሆን ኖሮ እርቃነ ገመናውን አስጥተውት ይሄዱ እንደነበር ገመተ።
ቁም!!ቁም!!” የሚል ድምፅ አሁን ገና በጆሮው ውስጥ እንደ ገደል ማሚቶ አስተጋባበት ። ከኋላ ከማጅራቱ ላይ ያረፈበት ዱላ ትውስ አለው። ወሮበሎች!! አዎን ልክ ነው! በወሮበሎች በማጅራት መቺዎች ተዘርፌ ነው! ወይኔ ጓንጉል! ሁለት ዓመት ሙሉ ደክሜ አሞሌ አልሼ ገብስ ቀልቤ ያደለብኳቸው ከብቶቼን ዋጋ ሜዳ ላይ ቀረ። እጄ ተቆረጠ፡፡ ኸረ
የወገን ያለህ?! ኸረ የረዳት ያለህ?!” ከሱ ከራሱ አልፎ ለሌላ ሰው በማይስማ ድምጽ ጮኸ፡፡ ጋት ታክል የጨመረው ነገር አልነበረም፡፡ ለልጆቹ የገዛቸው ልብሶች ዓይነት በአይነት ፊቱ ላይ ድቅን አሉበት፡፡ በተለይ ትንሽዋ ድክ ድክ የምትለው እላዩ ላይ ቁጭ ብላ ፊቱን በጥፍሯም በን
ክሻም የምትለው ልጁ ሁሉንም ልብስ ስብስብ አድርጋ ሁሉም የኔ
ነው እያለች ስታለቅስ ስብስብ አድርጋ እላዩ ላይ ስትተኛበት በሃሳብ እየታ የው ገስግሶ ደርሶ ሊያስደስታቸው በለሊት በርሮ ወጥቶ የማጅራት መቺ ሲሳይ መሆኑ፣ ብዙ ዕቅድ የያዘበት የከብቶቹ ዋጋ ውሃ በልቶት መቅረቱ ውስጥ አንጀቱን አንሰፈሰፈው። አንገበገበው።
“አሁን እንዴት አድርጌ ነው አገሬ የምገባው? የመሳፈሪያ ገንዘብ እንኳን ምን ነበረበት ትንሽ ትተውልኝ ቢሆን ኖሮ?" አሁን ገና ትኩስ እንባ ጉንጩን እያራሰው ወረደ። እንደምንም ብሎ እጆቹን ስአስፋልቱ ላይ ግራና ቀኝ ወጠረና ወደ ላይ እየተንገዳገደ ተነስቶ ቆመ። ድልድዩን
ተደግፎ ያንን ዙሪያውን የጨለመበትን ከተወሰኑ ደቂቃዎች በፊት ጊዜያዊ ሞት የሞተበትን አስፈሪ ቦታ በፍርሀት እየተንቀጠቀጠ ተመለከተው፡፡
ሊነጋ ሰማዩ እያዛጋ ነው፡፡ ሴተኛ አዳሪዎች ጎጇቸውን መክፈት ጀምረዋል፡ ውሃ በጣሳ እየያዙ የሚወጡ ልቅላቂ የሚደፉ ሴቶች አልፎ አልፎ ይታያሉ፡፡ የት እንዳደረ እንዳይታወቅበት ሹልክ እያለ ፀጉሩን ሳያበጥር የሚወጣ ወንድ ከኋላው እንዳባረሩት ሁሉ ገልመጥ ገልመጥ እያለ ሲያ
ፈተልክ ይታያል።
አልኮሉን ሲጋት አድሮ በየሴተኛ አዳሪው ቤርሙዳ ሰምጦ የቀረው
ሁሉ የሚበሳጨውና መፈጠሩን የሚጠላው ሊነጋጋ ሲል ነው።
ነፍሱን ሲያውቅ፣ የት እንዳደረ ማገናዘብ ሲጀምር ይበሳጫል። ከዚያም በለሊት ተነስቶ እየተመናጨቀ፣ እየተቆናጠረ ያመልጣል፡፡ ጓንጉል እዚያው ድልድዩን ተደግፎ ጨሌ ያጣች ሚዳቋ መስሎ ሲታይ አሳዛኝነቱ አንጀት ይበላ ነበር፡፡ በርቀት ሲመለከት እብዱ ምንሽንሽ ብቻውን አንዴ ወደ ላይ አንዴ ወደ ታች እየዘለለ ድንጋይ እያነሳ ድንጋይ እየጣለ ሲቦርቅ ተመለከተው። ከጥቂት ጊዜ በፊት የወረወረለትን ሣንቲም አስተወሰ። “አዎን እብድ መሆን ጥሩ ነው። እብዱ እንኳ ያቺን የወረወርኩለትን ሣንቲም ሲያይ እየተደሰተ እየጨፈረ ነው የሄደው። እነኝህ አረመኔዎች ግን የእብዱን ያክል የማመዛዘን ችሎታ የላቸውም፡፡

በሰው ልጅ ጭንቀት በሰው
ልጅ ስቃይ አይሸበሩም፡፡በቀላሉ የሚጠግቡ አይደሉም፡፡ሆዳም አውሬዎች ናቸው። ሣንቲም ለማግኘት ስው ቢገድሉ ደንታ ቢሶች ናቸው። ዘነጣጥለው በልተው የመጨረሻውን ጠብታ ልሰው ካላጣጣሙ መቼ ይጠግባሉ? ጅቦች!” በምሬት ብሶቱን ለራሱ ተነፈሰ፡ለእብዱ የወረወረለትን ሃያ አምስት ሣንቲም ቢመልስለት ተመኘ፡፡ ከሆቴሉ የወጣው ባዶ አፉን
ነበር፡፡
“ያቺን ሃያ አምስት ሣንቲም እብዱ ቢመልስልኝ ኖሮ አንድ ዳቦ በሻሂ
እበላበት ነበር...” ሲል ምኞቱን ለራሱ አወራ።....

#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...ታፈሡ እንግዳሰው በሽዋዬ ሆድ ውስጥ እየነደደ ስላለው የቅናት እሳት ምንም አታውቅም፡፡ በአስቻለውና በሔዋን መካከል ከተፈጠረ የፍቅር ግንኙነት ጋር
በተያያዘ የሸዋዬን ንዴትና ብስጭት ማንኛዋም ታላቅ እህት ታናሽ እህቷ በፍቅር ተዘናግታ ከትምህርቷ እንዳትስተጓጉል ለመቆጣጠር ከምታደርገዉ ጥረት ለይታ አልተመለከተችውም፡፡ "አቃጣሪ" ብላ የሰደበቻትንም ቢሆን ከቁብ አልቆጠረችውም።
የታፈሡና የአስቻለው ግንኙነት የጠበቀ እንደመሆኑ ለሁለቱ የፍቅር ግንኙነት በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ድጋፍና ርዳታ ያደረገች መስሎ ቢታያት አያስገርምም በማለት የሽዋዬን ግልምጫና ስድብ በቀላሉ አልፋዋለች፡፡ ይህ ሁሉ ችግር በእርቅና በመግባባት ሊፈታ እንደሚችል በፅኑ ታምናለች። ሰሞኑን ስታወጣ ስታወርድ
የቆየችውም እርቁና መግባባቱ በእንዴት ያለ ሁኔታና አኳኋን መከናወን እንዳለበት ዘዴና ብልሀት ስታፈላልግ ነው፡፡
በእሷ በኩል የታያትን ለዋናው ባለ ጉዳይ ለአስቻለው ፍሰሀና ምናልባት በልሁና መርዕድም ከተገኙ በጋራ ተነጋግረው ከአንድ ውሳኔ ላይ ለመድረስ በማሰብ
ታፈሡ በዕለተ ቅዳሜ ከሠዓት በኋላ ላይ ወደ አስቻለው ቤት ስትሄድ የአስቻለው ቤት በጠበቀው ሁኔታ አገኘችው፡፡ እስቻለውን ጨምሮ በልሁና መርዕድ ቤት ውስጥ አሉ። በልሁና መርዕድ እንደ ልማዳቸው ጫት ይዘው ፍራሽ ላይ
ተቀምጠዋል። አስቻለው ደግሞ አልጋው ላይ ጋደም ብሎ እነበልሁን ፊትለፊት እየተመለከተ ይጫወታሉ። ቤቱ በሰንደል ጭስና በመፈላት ላይ ነበረ የሻይ ሽታ
ደስ በሚል መዓዛ ታውዷል።
«እነ አጅሮች! ከአሁኑ ፈርሻችኋል?» አለች ታፈሠ ፏ ባለ
ፈገግታ እያየቻቸው ወደ ውስጥ በመግባት።
«እናትሽ ታፈሡ እስቲ ዛሬ እንኳ ተቀላቀይን፡፡» አላት በልሁ።
«ከኔ ይልቅ አስቹ አይቀርባችሁም እሱን እልጋ ላይ አስተኝታችሁ እኔን
ከሩቅ የምመጣውን ትጋብዛላችሁ፡፡» እያለች ታፈሡ ሁሉም ወዳሉበት እየተጠጋች ሰላም አለቻቸው፡፡
«ባክሽ ዶክተር ነገር በሆዱ ገብቶ እየተብሰለሰለ ነው። ምናለ ከሴት
ብልሀት አይጠፋምና አንድ ዘዴ ፈጥረሽ ከበሽታው ብትፈውሽው!» አለ በልሁ ፈገግ ብሎ አስቻለውንም ታፈሡንም እየተመለከተ፡፡
«እኔ እህቱ ሁሉንም ነገር እስተካክልለታለሁ፡፡» አለች ታፈሡ ፍራሿ ላይ ከበልሁ አጠገብ ቁጭ እያለች።
«በእናትሽ ታፈሡ ፍጠኝ አሁን ደግሞ አንድ አዲስ ነገር ተፈጥሮ በዚሁ ጉዳይ ላይ ስንነጋገር ነው የመጣሽው፡፡» አላት በልሁ አሁንም፡፡
«ደሞ ምን ተፈጠረ?» አለች ታፈሡ ፈገግታዋን ቀነስ በማድረግ በቁም ነገር በልሁንም አስቻለውንም አየት አየት እያረገች።
«ሁለቱ ወዳጆቹ ማህበር እየፈጠሩ ስለመሆኑ ተሰማ፡፡»
«ማለት?»
«ሸዋዬን በባርናባስ ቢሮ ውስጥ አየኋት ይለናል፡፡»
«የት ይተዋወቃሉና?»
«የሰው መሄጃው ይታወቃል ብለሽ ነው?»
«አስቻለው!» ስትል ታፈሡ ጠራችውና በተለይ ወደ አስቻለው ዓይኖቿን ተከለች። እውነት ነው እንዴ የምሰማው ነገር?»
«ምን እንዳሰቡ አላውቅም፤ ሸዋዬን ግን በእርግጥም በባርናባስ ቢሮ አይቻታለሁ፡፡»
«መቼ?» አለች ታፈሡ እንደ መገረም እያለች።
«ሳምንት ሊሆን ነው ነው።»
«እንዴ! እንዴት ነው ይኸ ነገር?» አለችና ታፈሠ ሁሉንም በዓይኗ
ትቃኛቸው ጀመር፡፡
«ለነገሩ እነሱ የሚያመጡት ነገር የለም። አሁን አሳሳቢ የሆነብን ግን ፣ የሔዋን ጉዳይ ነው። የእህትማማቾቹ ግንኙነት መልካም እንዳልሆነ ነው
የሚሰማው በዚህ መሀል የምትሰቃየው ሔዩ ናት፡፡ ታዲያ ምን ቢደረግ ይሻላል ትያለሽ ታፈሥ?» ሲል በልሁ ጠየቃት።
«የእኔም እኮ አመጣጥ ለዚሁ ጉዳይ ነበር፡፡» አለች ታፈሡ በተለይ በልሁን እየተመለከተች፡፡
«ምን አሰብሽ ታፈሥ»
«ሔዩን ከሸዋዬ እንዲሁም አስቻለውኑንም ከእሷው ጋር አስታርቀን ሰላም የምንፈጥር ከሆነ ብዩ! »
«ሸዋዬ እሺ ትለን ይሆን ታፈሥ» በልሁ አሁንም፡፡
«ምን ትሆናለች? ቁጣዋ እያደር ይበርዳል። የአስቹና የሔዩን ጉዳይ
ቁርጡን እያወቀችው ስትሄድ የግዷን ትቀበላለች፡፡ ለዚህ ደግሞ እኔ ማግባባቱን እቀጥላለሁ፡፡»
«ይኸ ጥሩ ነገር ነው ታፈሥ!» አለ በልሁ በእጁ ጫቱን እየቀነጠበና
በዓይኑ ግን ታፈሡን እየተመለከተ።
«አስቹ እንዴት ትላለህ?» አለች ታፈሡ ወደ አስቻለው እየተመለከተች፡፡
«ይቻላል ብለሽ ነው ታፈሥ»
«ይቺ ሽዋዬ የምትባል ሰው ግን እሺ የምትል እይመስለኝም፡፡ የሆነች» ብሎ መርዕድ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲናገር በልሁ በመሀል አቋረጠው።
«አንተ ደሞ አታሟርት!»
ሁሉም ተሳሳቁ፡፡
«ማሟረት ሳይሆን እንደው ሁኔታዋ ሁሉ ቅፍፍ እያለኝ ነው፡፡»
«ግድየላሁችም፤ ብቻ እናንተም ተባበሩኝ እንጂ ዋናውን ነገር እኔ
እፈጽማለሁ፡፡ አለች ታፈሡ አሁንም፡፡
«መቼ እናድርገው ታዲያ?» አለ በልሁ ታፈሡን በቁም ነገር
እየተመለከተ፡፡
«እኔ ምን ጊዜም ይመቸኛል። ሳስብበትም ሰንብቻለሁ። እናንተ ብቻ ተዘጋጅታችሁ ንገሩኝ፡፡
«በኔ እምነት ባይውል ባያድር ደስ ይለኛል፡፡» አለ በልሁ ታፈሡንም
አስቻለውንም እየተመለከተ።
«ዛሬ እናድርገው?» ስትል ጠየቀች ታፈሡ።
«ምን ችግር አለ? ቄስ መነከሴ እንጠራ! ሽዋዬ እሺ ካለች ጥሩ፤ ካላስችም ሌላ ዘዴ ይቀየሳል፡፡» አለ በልሁ።
ለአፍታ ያህል በመሀላቸው ፀጥታ ሰፍኖ ቆየና ታፈሡ ከተቀመጠችበት ድንገት ብድግ እያለች እንዲያውም ጥሩ ሀሳብ ነው። ልብሴን ቀይሬ ልምጣ፡፡
እናንተም ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ» ብላቸው ከአስቻለው ቤት ወጥታ በፍጥነት ርምጃ ወደ ቤቷ ገሰገሰች።
ታፈሡ ወደ ቤቷ በምትገስግስበት ሰዓት በሀሳቧ አንድ ነገር ይመላለሳል፡፡ በሁለት ዓመት የኮሌጅ ቆይታቸው የሽዋዬን ልዩ ባህሪ ጠንቅቃ አውቃዋለች።
ሸዋዬ ከምንም በላይ ራስ ወዳድ መሆኗን፣ እርምጃዋ ሁሉ የጭካኔ፣ ጥላቻዋ ጭፍን፣ ቀናተኛ፣ ነገረኛ፣ አስመሳይና ግብዝ መሆኗን ታውቃለች፡፡ የሔዋንና የአስቻለው የፍቅር ግንኙነት ከልብ ያናደዳትና ያስቆጫት ከሆነም በሁለቱ ተዋዳጆች ላይ የምትሸርበው ተንኮል አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ትገምታላች። በተለይ አስቻለውና ባርናባስ የጎሪጥ የሚተያዩ አለቃና ምንዝር እንደ መሆናቸው ሸዋዬ፡
አስቻለውን ጠልታ ከባርናባስ ጋር እስከ ገጠመች ድረስ ብዙ ነገር ልታበላሽ እንደምትችልም ይታያታል።
ቤቷ ሄዳ ብዙ አልቆየችም ወትሮም በሰንበት ቀናት ከቤቷ ወጣ ስትል እንደምታደርገው ሁሉ ነጫጭ የሀገር ልብሶቿን ለብሳ ነጭ ጫማ አድርጋ አነስ ያለች ነጭ የእጅ ቦርሳዋን በመያዝ የሀገር ልብስ አላባሽ ነጭ የአንገት ልብሷን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጋ እፍንጫ የሚሰነፍጥ የፈረንሳይ ሽቶዋን በልብሷ ላይ
እርክፍክፍ አድርጋ በቀጥታ ወደ አስቻለው ቤት የመልስ ጉዞ ጀመረች ።
በልሁና መርዕድም ተዘጋጅተው
ጠብቀዋታል። አፋቸውን
ተጉመጥምጠው፥ የጫት መቃሚያ ሽርጦቻቸውን አውልቀውና ልብሶቻቸውን ሰብስበው አገኘቻቸው።
ታፈሡ ከቤት እንደ ደረሰች መቀመጥ አልፈለገችም፤ ወዲያው ጉዞው ወደ ሸዋዬ ቤት እንዲጀመር የእነበልሁን ፈቃድ ጠየቀች። ሁሉም ተስማሙ፡፡ አንድ
ስምምነትም አደረጉ። በእርቁ ጥረት ሂደት ሽዋዬ በንዴት ወይም በብስጭት ምንም ብትል ምን ማንም ላይቀየም፤ ማንም ሳይናደድና የቁጣ ቃል ሳይናገር ተስማምተው ወደ ሸዋዬ ቤት ልክ ከቀኑ ዘጠኝ ዓት ተኩል ላይ ጉዞ ተጀመረ። በልሁና መርዕድ ግራና ቀኝ፣ ታፈሡ ደግሞ እመሀል ሆነው ሲራመዱ ልዩ ቀጠሮ