#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
.....ምነው ዶክተር? ሰላም አይደለህም እንዴ?» አለና ሰላም ብሎት ከአጠገቡ ቁጭ አለ፡፡ አስቻለው ነርስ ስለሆነ ጓደኞቹ ብዙ ጊዜ ዶክተር፡ አያሉ በመጥራት ያሾፉበታል፡፡
«ትንሽ ሳያመኝ አይቀርም» አለው የሚነበብበትን የጭንቀት ስሜት
ያስወገደ መስሎት የፊቱን ላብ በእጁ እየጠረገ፡፡
«ሀኪምም ያመዋል እንዴ?»
«ጠንቋይ ለራሱ አያውቅም ይባል የለ!»
ወዲያው ደግሞ መርዕድ ከውጭ ሲመጣ ሁለቱም አዩት፡፡ መርዕድ አጠር ያለ፣ መልኩ ደግሞ ጥቂር ነው:: ነጣ፣ ገጠጥ ያሉ ጥርሶቹ ከሩቅ ይታያሉ፡፡በተፈጥሮው ፈገግተኛ ቢሆንም ላኩርፍ፡ ቢል እንኳ ጥርሶቹ አይገጥሙለትም፡፡
አፍንጫው አጭርና ደፍጣጣ ናት፡፡ በጥቁር ፊቱ ላይ ቁልጭ ቁልጭ የሚሉት ዓይኖቹ እጥረቷን ይሸፍኑለታል፡፡ ሊቀላቀላቸው ሁለት ወይም ሶስት ርምጃዎች ሲቀሩት በልሁ እንደ ልማዱ በቀልድ ዓይነት፡-
«ስማ አንተ እስከ አሁን ቆይተህ ራት አልቋል ቢባል አንተኑ ነው
የምጎርስህ!» አለው።
አንተ እኮ የአቶ ተገኔ ልጅና የግብርና ስራተኛ ባትሆን ኖሮ ሰውጰአይተርፍህም ነበር!» በማለት መርዕድም የቀልድ ምላሽ እየሰጠ ተጠጋቸውና ሰላም
ብሏቸው ከአጠገባቸው ቁጭ አለ፡፡ በልሁና አስቻለው በመርዕድ መልስ ተገርመው እየተያዩ ሲሳሳቁ መርዕድ ቀጠለ፡፡
«ሀሰት ነው?» አለ በተለይ በልሁን ፈገግ ብሎ እያየ፡፡
"መቸም አንተ የምትለው አታጣ! አስተማሪ አይደለህ?» አለና በልሁ
በቀልድ ዓይነት ቡጢ ቃጣ አደረገበት።
የመርዕድ ቀልድ መሠረት አለው። በልሁ የባላባት የልጅ ልጅ ነው፡፡
አባቱ አቶ ተገኔ ክብረት ከደብረ ብርሃን በስተምዕራብ በኩል በግምት በሰላሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ገጠራማ ቀበሌ ይወለዳሉ:: ከአባታቸው የወረሱትን በርካታ ጋሻ መሬት ገና በንጉሡ ጊዜ ሽጠው ሽጠው በደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ
በርካታ የንግድ ድርጅቶችን አቋቁመዋል፡፡ ሆቴል የሸቀጣሸቀጥ መደብር፤ በርካታ
የእህል ወፍጮዎችን ከማደራጀታቸውም በላይ አንድ ከባድ የጭነት መኪናም
አላቸው። የእሳቸውን ያህል አይሁን እንጂ በዕድሜ ከብልሁ በላይ ያሉ አራት ልጆቻቸውንም በንግድ ሥራ አቋቁመዋቸዋል።
በልሁ ለአባትና ለእናቱ የመጨረሻ ልጅ ነው፡፡ በቤተሰቡ ውስጥ እንደ
ብርቅ ስለሚታይ በማር በወተት ያደገ ነው። በቤተሰቡ ውስጥ እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ የተማረው እሱ ብቻ ነው፡፡ ከዓለማያ እርሻ ኮሌጅ በድግሪ ተመርቆ በዲላ
ከተማ በአውራጃው ግብርና ጽህፈት ቤት ውስጥ በባለሙያነት ያገለግላል፡፡ በዘመኑ እስከ ዩኒቨቨርስቲ ደረጃ ተምሮ የመንግስት ስራ አለመያዝ የማይደገፍ በመሆኑ እንጂ
እንደ ቤተሰባዊ መሠረቱ ቢሆን ኖሮ ለሥራ ሲል ዲላ ድረስ መሄድ ባላስፈለገው ነበር፡፡ ያም ሆኖ በአስፈለገው ጊዜና መጠን ከቤተሰቡ ገንዘብ ይላክለታል። ደብረ ብርሃን ብቅ ካለም በገንዘብ ተንበሽብሾ ይመለሳል። በዚያ ላይ አዘውትሮ ለመስክ ስራ ስለሚወጣ አበል ሳያገኝ እንዲት ወር እንኳ አታልፍም፡፡
መርዕድ ግን በሐረርጌ ክፍለ ሀገር ከደሃ የገበሬ ቤተሰብ የተወለደ
ከመሆኑም በተጨማሪ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር በመሆኑ በአነስተኛ ገቢ የሚኖር ነው።ከደሞዙ ሌላ ምንም አያገኝም እናም በበልሁ ኑሮ ይጎመዣል::ደግነቱ በልሁ በተፈጥሮው ቸር ከመሆነም በላይ መርዕድን በጣም ስለሚወደው
በቸገረው ሁሉ ይረዳዋል።
የኑሮአቸውን ልዩነት ግን የዘወትር
መቀላለጂያና መለከፋያቸው አድርገውታል።
ሦስቱም ጓደኛሞች ራታቸውን አዝዘው አጥንት እየተሻሙ በልተው ከጨረሱ በኋላ አስቻለው ከቀልዳቸው ሠልሶ ከአንድ ቁም ነገር ውስጥ ከተታቸው።
«ዛሬ አንደ ልጅ ልልካችሁ ነው፡፡» አላቸው ዓይኑን በሁለቱም ላይ ዞር ዞር አድርጎ እያያቸው::
«የት?» ሲል ጠየቀው በልሁ።
«ከሸዋዩ ቤት»
«ለምን አለ መርእድ በተራው፡፡
«ለአንድ ብርቱ ጉዳይ:: አላቸው» አስቻለው ፈገግ ብሎ እያያቸው፡፡
በዚህ ጊዜ በልሁ ድንገት «ሃ-ሃ-ሃ-ሃ..." ብሎ ሳቀና «ብቻህን ሮጠህ ሮጠህ ሲሰለችህ ጊዜ ዛሬ ደግሞ ፖስተኛ አስፈለገህ እንዴ?» ሲል ቀለደበት። ሦስቱም
ተሳሳቁ:: አስቻለው ከሔዋን ጋር ከተዋወቀ ጊዜ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ለብቻው ወደ ሽዋዬ ቤት ስለሚሄድና ይለያቸው ስለነበረ ነው የአሁኑ ለበልሁ ቀልድ መሠረቱ፡፡
«አትቀልዱ ችግር ተፈጥሯል፡» አላቸው አስቻለው ኮስተር ብሎ፡፡
"እኮ" ምን?» ሲል በልሁ አሁንም እየሳቀ ጠየቀው::
አስቻለው ከታፈሡ ያገኘውን መረጃ ዘርዝሮ አስረዳቸው፡፡ ስለ ሔዋን ሁኔታ ያደረበትን ስጋት ገለፀላቸው፡፡ ቀጥሎም አስቻለው ጠፋብን፣ እዚህ መጥቶ ከሆነ ብለን ነው በሚል ሰበብ ሔዋን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች ሰልለው መረጃ ይዘውለት እንዲያወጡ ጠየቃቸው::
በልሁና መርዕድ የአስቻለውን ማሳሰቢያ በቀላሉ አላዩትም፡፡ ሔዋንን የእሱን ያህል ያውቋታል። በጣምም ይወዷታል። ባህሪዋንም! የነበረባትንም ስጋት
ሁሉ ያውቃሉ። የተፈጠረው ሁኔታ ከአስቻለው ባልተናነሰ መልኩ አሳሰባቸው፡፡ በዚህም ምክንያት እንደ ወትሮ ከእራት በኋሳ ሻይ ቡና ማለት አልፈለጉም በቀጥታ ወደ ሸዋዬ ቤት ሊሄዱ ተነሱ፡፡ በልሁ ቀልድ ይወዳልና
«ችግር ካለ ሔዩን ተሸክመንም ቢሆን ይዘንልህ እንምጣ እንዴ ዶክተር?»
ሲል አስቻለውን በፈገግታ እያየ ጠየቀው፡፡
«ያን ካደረገችሁማ ትሽለማላችሁ» አለው አስቻለውም እንደ ቀልድ።
“ትሰማለህ፣ መርዕድ!» አለ በልሁ ቀልዱን ለመቀጠል፡፡ «ሽልማት ካለው ችግር ኖረ አልኖረ ሐዩን ዝም ብለን አምጥተን እንጣልለትና እንዳረገ ያድርጋት።
እኛም ሽልማታችንን እንቀብል።»
«እኔ የለሁበትም» አለ መርዕድ ሳቅ እያለ።
በልሁና መርዕድ በደህና ቦታ ላይ ተቀላልደው ወደ ምሩ ቦታ ጉዞ ጀመሩ፡ ወደ ሸዋዬ ቤት።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሰው አይችለው የለ እንዲሉ ሸዋዬ በተለይ ከእንድ ቀን በፊት ጀምሮ
በአዕምሮዋ ውስጥ የሚተረማመስ የሃሳብ ብዛት ቢመዘን ክብደቱ፤ ቢለካ ርዝመቱ፣
በዓይን የሚታይ ቢሆን የብዛቱ ነገር የትየለሌ በሆነ ነበር፣ ያላሰበችው ዱብ ዕዳ ወርዶባት ምስቅልቅል ባለ ስሜት ውስጥ ገብታ ትቃትታለች::
የሃሳብና የጭንቀቷ ስር ያኔ ከአዋሳ ወደ ዲላ ከአስቻለው ጋር
እስከተጓዘችበት ቀን ድረስ የተዘረጋ ነው:: ትዝ ይላታል የጉዟቸው ሀኔታ፡፡ ትዝ ይላታል ከአስቻለው ጋር ያደረገት ጭውውት፡፡ ትዝ ይላታል አስቻለው ያደረገላት ዕርዳታ፡ ቆጠብ ያለ አነጋገሩ፣ እንዲሁም በጆሮዋ የተንቆረቆረው ማራኪ ድምጹ።
በተለይ ዲላ ደርሳ ከታፈሠ ጋር ተገናኝታ ለቀናት ያህል እዚያው በሰነበተችብት ወቅት ታፌ በጨዋታ መሀል እያነሳች አስቻለው የልጆቿ ክርስትና አባት
መሆኑን ከመግለጽ ጀምሮ ማንነቱን ባህሪውን ፣ ሙያውንና አኗኗሩን ሁሉ በሰፊው አስረድታት ነበር፡፡ የዚህ ሁሉ መድሃኒት የሽዋዬን ልብ በፍቅር ወደ እስቻለው ዘንበል እንዲል አድርጎት ደስ የሚል ወንድ እስከ ማለት ደርሳ ነበር፡፡
ክብረ መንግስት ሄዳ ለአንድ ወር ያህል ከወላጆቿ ጋር የዕረፍት ጊዜዋን ባሳለፈችበት ጊዜ ሁሉ አስቻለውን ለአንድም ቀን ረስታው አታውቅም:: ሁሉም ነገሮቹ በዓይነ ህሊናዋ ዉል ሲሏት ቆይተዋል። በደ ዲላ ስትመሰስ ምን ዓይነት

ዘዴ ፈጥራ ልትቀርበው እንደምትችል ታሰላስል ነበር፡፡ እሷ የታፈሡ ጓደኛ፣ እሱ ደግሞ ከጓደኝነትም በላይ የታፈሡ አበልጅ እንደ መሆኑ ሁሉንም ነገር በታፈሡ ጥላ ሥር ልትመክር እንደምትችል ይታያት ነበር፡፡ ከታፈሡ ቤት አይጠፋምና ነጋ
መሸ ልታየውና ልታገኘው እንደምትችል በማመን በፍቅር ቀርባ ልታቀርበው
የምትችልበትን መንገድ ስታሰላስል ከርማለች፡፡
በነሐሴ ወር አጋማሽ ላይ ዲላ መጥታ ቤት ተከራይታ የምርቃት ምሳ አዘጋጅታ አስቻለውን የጠራችው ለዚሁ ዓላማዋ አንድ ርምጃ መራመዷ ነበር፡፡ ጠርታው በመምጣቱ ደስ ብሏታል። ሽር ጉድ ብላም አስተናግዳዋለች፡፡ ከሁሉም በላይ በዚያ አጋጣሚ ቤቷን ማወቁ ለወደፊት ግንኙነታቸው መሠረት ሊጥል
እንደሚችልም ተስፋ አድርጋ ነበር፡፡
በእርግጥ አስቻለውም ወደ ቤቷ ብዙ ተመላልሷል፡፡ በተለይ ማታ ማታ ብቅ እያለ ሲያጫውታት ከርሟል፡፡ እንዳንዴም ወደ ከተማ ይዟት እየወጣ አዝናንቷታል። የሆቴል ምግብ አብረው በልተዋል፡፡ የመጠጥ ዓይነቶችንም ቀማምሰዋል፡፡ በርካታ ርዕሶችንም እያነሱ ተጨዋውተዋል፡፡ ነገር ግን እስቻለው ወደ ፍቅር ያዘነበለ ስሜት ሳታይበት ወራት አለፉ፡፡
አስቻለው የፍቅር ጥያቄ ሳያቀርብላት ሲቀር እየጨነቃት አንዳንድ ሰው ትሳለኝ በሃሳቧ የዕውን ሁለመና ሳያጠና ልቡን በፍቅር አይከፍትም፡፡ አንዴ
ከከፋተ ደሞ በቀላሉ አይዘጋም፡፡ ይህም ሰው ባህሪው እንደዚያ ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡” በማለት የራሷን ምክንያታዊ ግንዛቤ ትፈጥራለች፡፡
ቀን እየረዘመ ሲሄድ ደግሞ ሌላ ሃሳብ፡፡ (ይኸ ሰው ምናልባት ሰው
የማያውቃት ሌላ ሴት ትኖረው ይሆን እንዴ? ወይስ ንቆኝ? መቼም ቆንጆ ባልሆንም ገና አፍላ ነኝ፡፡ ሊያገባኝ ባይፈልግ እንኳ ለወዳጅነት ታንሳለች ብሎ አይገምተኝም።” ካለች በኋላ ግን እኮ! ዝምብሎ በእህትነት ሊያየኝ አስቦም ሊሆን ይችላል ወይ ደሞ" ይህን ያህል ጊዜ በእህታዊና ወንድማዊ ግንኙነት ስለቆየን እንደገና ሃሳቡን ለመቀየር ፈርቶ ሊሆን ይችላል በማለት ታስብ ጀመር፡፡
ይሄኛው ስጋት እያየለባት በመሄዱ ሰሞኑን አንድ መላ ፈጥራ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት ላይ ነበረች፡፡ ጠቀም ያለ ገንዘብ እጇ ላይ መያዝ አስቻለውን አስቻለውን
ራሷ ስትጋብዘው ልታመሽ ከአቅሙ በላይ እንዲጠጣ ልታደርገው ከተማ ውስጥ
ብዙ ልታስመሸው በኋላም በእሱ ቤት በኩል ወደ ቤታቸው ሊመለሱ ከእሱ ቤት አካባቢ ስትደርስ እልቻልኩም” ብላ ልትዝለፈለፍና ቤትህ አስገብተህ አሳርፈኝ
ልትለው ቅር እንደማይለው ታውቃለች፡ ገብታ በበልሁና በመርዕድ ጫት መቃሚያ ፍራሽ ላይ ልትተኛ ያኔ ስንፈተ ወሲብ ከሌለበት በቀር ነይ አልጋው
ላይ ተኚ ሊላት እንደሚችል በማሰብ ይህንኑ ልትፈጽም ወስና ቀን መምረጥ ብቻ ነበር የቀራት፡፡ ግን ደግሞ ሳታስበው ባልጠበቀችው ሁኔታ የስሚት እንቅፋት ተፈጥሮባት እነሆ ዛሬ ውልክፍክፍ ብላለች፡፡
ከታፈሡ በዕለተ ሰኞ ከመጣላቷ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በዕለተ እሁድ ከአንድ የሥራ ባልደረባዋ ጋር ስለ ፈተና ዝግጅት ልትነጋገር ከጠዋቱ ሁለት ሠዓት አካባቢ ከቤቷ ወጥታ ከረፈደች፡፡ ጉዳይዋን ጨርሳ ስትመለስ ቤቷ ተዘግቶ አገኘችው ፡፡ ትዝ ሲላት ሔዋን ወደ ገበያ ሄዳ የወጥ ቅመማ ቅመሞች እንድትገዛ
አዛታለች፡፡ ቤቱ የመዘጋቱ ምክንያት የእሷ ወደ ገበያ መሄድ መሆኑን ተገንዝባ ራሷ በያዘችው ቁልፍ፡ ከፍታ ለመግባት ወደ በሩ ስትራመድ ድንገት አንዲት ህጻን እት አበባ ስትል ጠራቻት፡፡ ሕጻኗ ለሽዋ ቤት የአከራዩዋት ወይዘሮ
ዘነቡ የሚያሳድጓት ዘመድ ልጅ ናት፡፡ ከአምስት እስከ ስድስት ዓመት ይሆናታል ከወይዘሮ ዘነቡ ቪላ ቤት በስተጓሮ በኩል ጥግ ይዛ ዕቃ ዕቃ ትጫወታለች:: ሔዋን
ሽዋዬን እት አበባ እያለች ስትጠራት እየሰጡ ያቺ ህጻንና ወይዘሮ ዘነቡ ሰራተኛ
ሸዋዬን በዚሁ ዕዠስም ነው የሚጠሯት።
«ውይ ሚሚዩ።!» በማለት ሸዋዬ ለሕጻኗ ጥሪ መልስ ሰጠችና በዚያው ቀጥላ «ቡናሽ ደርሷል?» ስትል በማየት ዓይነት ጠየቀቻት፡፡ ሕጻኗ ግን የሸዋዬን ጥያቄ ወደ ጎን ትታ የራሷን ቀጠለች፡፡
«የሔዋን አባት መጥቶ ቤቱ ሲዘጋበት ጊዜ ተመልሶ ሄደ፡፡» አለቻት።
«እ!» አለች ሽዋዬ ምንነቱን ያላወቀችው ስሜት መላ ሰውነቷን ነዘር እያደረጋት። ቤት መክፈቷን ትታ ወደ ህጻኗ ልጅ በማቆብቆብ ማነው የሔዋን አባት አንቺ» ስትልም ጠየቀቻት፡፡
«አስቻለው ነዋ! ህእ!» አለች ሕጻኗ አጎንብሳ ቆርኪዎቿን እየደረደረች፡፡
«እስቻለው?»
«አዋ! ሀእ!»
ሽዋዩ የባሰ ደነገጠች፡፡ ዓይኗ እህጻኗ ላይ ሳይነቀል ፍጥጥ ብላ ታያት ጀመር፡፡ እሷም ሔዋንም በሌሉበት አስቻለው መጥቶ እንደተመለስ ገባት፡፡ የቸገራት
በዚያች ህጻን አንደበት አስቻለው የሔዋን አባት መባሉ ነው:: በዲላና አካባቢዋ ባለው ህብረተሰብ ውስጥ ባል አባት ተብሎ እንደሚገለጽ ታውቃለች:: እናማ አስቻለው የሔዋን ባል? በጣም ግራ የገባት ይኸ ብቻ ነው።
«እንዴ!አለችና ሽዋዬ አሁንም ህጻኗን ትኩር ብላ እየተመለከተች
«አስቻለው የሔዋን አባት መሆኑን ማን ነገረሽ አንቺ?» ስትል ጠየቀቻት፡፡......
💫ይቀጥላል💫

👍4
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አርባ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....እሱም ዓለሚቱም ለአገሩ እንግዶች በመሆናቸው ምክንያት ፍላጎቱን በአስቸኳይ ማሳካት አልቻለም፡፡ ይሁን እንጂ እየዋለ እያደረ እሱ የሚፈልጋት ወንጀል እሱ የተጠማት ደም ወዳጅዋን ፍለጋ ዳዴ እያለች እየመጣችለት ነበር።
እንደ ልማዱ የአንበሶቹን ግቢ አጥር አንቆ አንበሶቹን ይመለከታል።
“ሲያዩት ገና ከገጠር የመጣ ነው" አለ ከወዲያ ማዶ ሆኖ ሁኔታውን ሲከታተል የነበረው ጆብሬ፡፡በአዲስ ልብሱ በቦላሌ ሱሪው ውስጥ ደንበኛ ባላገርነቱን አነበበ፡፡ በሃሳቡ ከኮት ኪሱ ውስጥ ከብብቱ ስር ገብቶ ሲሞዠልቀው ታየው።
እጅሬ የእርሻ በሬዋን ወይንም የጎተራ ጥሬዋን ሸጣ በርካታ ብር ሳትይዝ አትቀርም"ብሎ ገመተና "ልዳብሳት!"ሲል ወሰነ፡፡ አስፋልቱን ተሻገረና ወደ አንበሶቹ ግቢ መጣ፡፡ ጠጋ አለ። ወደ ጎንቻ፡ ሽቦውን በሁለት እጆቹ ግጥም አድርጎ ይዞ "ፓ! ወይኔ! ኧረረረ!!…አፉን እንዴት ነው የሚከፍተው በእናታችሁ?!” የጎንቻን የባላገሯን ልብ ሰልቦ ትኩረቷን በአንበሳው
ላይ እንድትጥል ለማድረግና ከዚያም ያለ ሀሳብ ኪሷን ለመዳበስ ነበር።
በጆብሬ አመለካከት ጎንቻ አፏን ከፍታ የቀረችው አንበሳ አይታ ስለማታውቅ ነው፡፡ ያላወቁ አለቁ! አሉ?…ቀስ በቀስ ባላገሯን ተጠጋት። እባቡ ጎንቻ! እንኳንስ ስው ጥላውን የሚጠራጠረው ጎንቻ የጆብሬን እንቅስቃሴ ቀርቶ ሃሳቡን ከነቃበት ቆይቷል። የበግ ለምድ የለበስ የቀበሮ ባህታዊነቱን ያላወቀው ጆብሬ ሲፈርድበት እነዚያ በልምድ የዳበሩ ጣቶቹን
በመቀስ ፎርም ወደ ጎንቻ የኮት ኪስ ሰደዳቸው።
“ሌንጨ ቦሩ!!" አለና ፎከረ እንደ ልማዱ።
ሂድ!ጀጋ! ምን አባክ ሆነሃል?!! ገገማ!!. ጆብሬ ዐይኖቹ እንደፈጠጡ እንደማፈግፈግም እንደማስፈራራትም አደረገው፡፡ ጡንቻውንም እንደማሳየት ቃጣው። ዳሩ ምን ያደርጋል? ያ ባላገር ፤ላጆብሬም እንደ ህልም ሆኖ በሚታወሰው ኃይል ከብረት ምጣዱ ላይ ተሰቅስቆ እንደሚነሳ ቂጣ ሰቅስቆ ወደ ሰማይ አነሳና አስፋልቱ ላይ አነጠፈው። ሲሰርቀው ኪሱ ሊገባ የተመለከቱ ሰዎች ከበቡ። ጆብሬ ሌባ
መሆኑን ከሚመስክረው የተጫጫረ ፊቱ ሌላ የሚያውቁትም ነበሩ፡፡
“ጎሽ! ጎሽ! እሰይ! ወንድ!.. ይበለው! ይበለው ይንጫጩ ጀመር፡፡
“ባላገር መስላ አጅሬ ወንድ ናት!!" ጎንቻን አደነቁ፡፡ ጎንቻም አዲስ አበባ ከገባ ከአንድ ወር በኋላ ደም ካየ ደም ከተጠማ ከአንድ ወር በኋላ ምንም እንኳን ትርፍ የሌለውና ጥቅም የማያስገኝ ቢሆንም ደፍሮ ኪሱ የገባ
ጠላቱን ወደ መሬት ደፍቶ በአፍንጫና በአፉ ደም አስደፈቀው...ጎንቻ ደም አየ። ተደሰተ፡፡ በብዙ ሰው ኃይልና በበርካታ ክንዶች ወደ ላይ በግድ
ተጎትቶ ተነሳ። ቀልጣፋው ጆብሬ፣ አንበሳው ጆብሬ ጣቶቹ አነጣጥረው የማይስቱት ጆብሬ፣ ጉልበቱ የጅብ የነበረው ጆብሬ በጎንቻ ክንድ ውርደት ቀመሰ፡፡ ፍፁም ያልገመተው ነበርና ጎንቻን በአድናቆት ተመለከተው።
ጎንቻን ፈራው፡፡ በፍርሃትና በአድናቆቱ ውስጥም ወደደው። ደሙን ጠራረገና ሄደ። ራቅ ብሎ ከሄደ በኋላ እንደገና ዘወር ብሎ ጎንቻን በጥንቃቄ አስተዋለው፡፡ በአድናቆት ጭንቅላቱን እያከከ ተመልሶ መጣ፡፡
“ወንድ ነህ! ወንድ ጀግና!" እጁን በአድናቆት ዘረጋለት፡፡ ወንድነቱን አምኖ ተሸናፊነቱን ተቀብሎ እጁን የሰጠውን ምርኮኛ ሊያሳፍረው አልፈለገም::ያን ሲመኘው የነበረ፣ ያን ሲያቅበጠብጠው የከረመ ስራ የሚጀምርበትን ቀን ምክንያት አድርጎ ይሆን ጆብሬን የጣለለት? ማን ያውቃል?እጁን ሲዘረጋለት እሱም እየሳቀ ወዘወዘው፡፡ እንደገና ተቃቀፉ፡፡
"አንበሳ ነህ!" ሲል ጆብሬ በድጋሚ አደነቀው። ይሄ ሁሉ እርቀ ሰላም
የወረደው ፀቡ ከበረደና ለወሬ የተሰበሰበው ሰው ከተበተነ በኋላ ሆነ እንጂ ሁኔታቸውን ከመጀመሪያ ጀምሮ ለተከታተለ ሰው ጉድ የሚያሰኝ ነበር፡፡ እንደዚያ ተናንቀው ሲደባደቡ የነበሩት ሰዎች የደም ማግኔት አሳሳባቸውና አንደኛው አድናቂ ሌላው ተደናቂ ሆነው ጨዋታ ጀመሩ።
“ጆብሬ ጫን ያለው እባላለሁ!"
“ጎንቻ ሀጂ ቦሩ" እሰኛለሁ፡፡
"በጣም ወድጄሃለሁ ልጋብዝህ እፈልጋለሁ።"
“ዛሬ አልጋበዝልህም፡፡ ከፈለክ ለነገ እንቀጣጠር” አንድም ቶሎ ብሎ ተጋባዥ ላለመሆን ሁለተኛው ደግሞ የጆብሬን ቁም ነገረኛነት ለማወቅ
እንዲያስችለው በማግስቱ እዚያው አንበሶቹ ግቢ በራፉ ላይ ለመገናኘት ተቀጣጥረው ተለያዩ፡ ጆብሬ ሀቀኛ ስዓት አክባሪነቱንና ጎንቻን ለቁም ነገር የሚፈልገው መሆኑን አረጋገጠ፡፡ ከቀጠሮው ቀድሞ እየጠበቀው ነበር። ተቃቀፉ፡፡
“ቦታ ይዘን እንጫወት" አለውና ጆብሬ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ቁልቁል ይዞት ወረደ። ከዚያም አረቄ ቤት ይዞት ገባና አረቄ እየጠጡ ጨዋታው ደራ። ጆብሬ የህይወት ታሪኩን ይተርክለት ጀመር፡፡
"ወላጆች ነበሩኝ፡፡ መቼም ሰው ያለወላጅ አይፈጠርም! የኔ ወላጆች ግን በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ጥሩ ደመወዝ የሚከፈለው አንደኛው ራስ ወዳድ ሌላው ለኔ አሳቢ ሆኑና በሀሳብ ተለያዩ። አባቴ
ተቀጣሪ ነበር፡፡ እናቴ የቤት እመቤት ነበረች። ገና የሰባት ዓመት ልጅ ሆኜ በቤት ውስጥ ጭቅጭቅና ንትርክ በዛ። አባቴ መጠጥ ይወድ ነበር።
ወላ ሚስቴ የለ ወላ ልጄ የለ! ደመወዙን በአራጣ ለሚበደራቸውና በዱቤ
መጠጥ ለሚሸጡለት ሰዎች ከፋፍሎ ይጨርስና ዐይኑን አፍጥጦ በአል ኮል ነብዞ ይገባል። እናቴ ትንሽ ልትናገረው ከሞከረች አበቃላት። ዛሬን አያድርገው ዛሬን አትውደደኝና በጣም ትወደኝ፣ በጣም ታፈቅረኝ ነበር፡፡ለእኔ ስትል ታገሰችው፡፡ ሲደበድባት ተደብድባ ሲረግጣት መሬት ሆና ብዙ ቻለችው። እንደዚያ የሚያደርገው ቤቱን ጥላለት እንድትጠፋ ሆን
ብሎ ነበር። ጥላው እንዳትሄድ የኔ ነገር ጨነቃት። ከዚያ ቤት ውጭ
የማድግ አልመሰላትም። የአባት ፍቅር እጦት እንዳይጎዳኝ አሰበች፡፡ በመጨረሻ ላይ ግን ሁሉም ነገር ከአቅሟና ከትዕግስቷ በላይ ሆነባትና እኔን ይዛ ቤቱን ትታለት ጠፋች። ደስ አለው፡፡ ሊፈልጋት አልሞከረም፡፡ወዲያውኑ ሌላ ሚስት አገባ። እኔና እናቴ ከእህቷ ቤት ለኔ አክስት መሆኗ
ነው ከአክስቴ ቤት ገባን። አክስቴ ጠላና አረቄ ትሸጥ ነበር፡፡ እናቴ
እዚያው እሷን እየረዳች መኖር ጀመርን፡፡በዚሁ መሃል እናቴን አንዱ ካላገባሁሽ አላት። አገባችውና እኔን ይዛኝ ቤቱ ገባች፡፡ አዲሱ ባሏ እሷን ይወዳታል።እኔን ግን አይወደኝም፡፡ ዲቃላ! እያለ ይሰድበኝና ያሸማቅቀኝ ነበር።አባዬ ስለው አባት ይንሳህ የለማኝ ልጅ እያለ ያሳቅቀኝ ነበር።
ይሄን የሚያደርገው እናቴ ሳትሰማ ነው። እናቴ በጣም እንደምትወደኝ
ያውቃል። እሷ ፊት ይስመኛል። እሷ ዘወር ስትል ጭንቅላቴ እስከሚበሳ ድረስ በኩርኩም ያጋጨኝና ሳለቅስ እውላለሁ። የእንጀራ አባቴ ቀስ በቀስ ሰው ሳይሆን ጭራቅ እየመሰለኝ ሄደ። ሁል ጊዜ "ዲቃላ! ዲቃላ!
ዲቃላ!” እያለ እየሰደበ እየደበደበ ራሴንም እሱንም እንድጠላ አደረገኝ።
ይሄ ጥላቻዬ ደግሞ ለሱ ጥሩ እንዳልሆን መጥፎ ስራ እንድሰራ ይገፋፋኝ ጀመር፡፡ ቀስ በቀስ ገንዘብ ከኪሱ መስረቅ ጀመርኩ። የሱን ገንዘብ ሰርቄ ብስኩት ገዝቼ ስበላ ይጣፍጠኛል። የጠላት ገንዘብ ይጣፍጣል። እናቴ

❤1👍1
ተጨንቃ የምታዘጋጅልኝ ምግብ እንደዚያ አይጣፍጠኝም፡፡ ከሱ ሰርቄ ከሱ ነጥቄ የበላሁት እንደ ማር እየጣፈጠኝ ሱስ እየሆነብኝ ሄደ። እሱም ይበልጥ እየጠላኝ ሄደ:: "ሌባ! ሞሽላቃ" ሳንቲም ከኪሱ ባጣ ቁጥር ሌባ!
ዲቃላ! እያለ የጥላቻ ክሱን አበዛ፡፡ ይሄን ጨምላቃ ሌባ ልጅሽን...” እያለ ዘወትር ለእናቴ ስሞታ ማቅረቡን ተያያዘው። ሌብነት እንድጀምር የገፋፋኝ የአባትነት ፍቅሩን ነፍጎ ያገለልኝ እሱ መሆኑን ዘንግቶ ዲቃላ! ዲቃላ! ሌባ! ሌባ!...እያለ የልጅነት አእምሮዬን አቆሰለው፡፡ እኔም ቤቱ እያስጠላኝ ሄደ። ከሰፈር ልጆች ጋር ወደ ገበያ እየሄድኩ ዕንቁላልና ዶሮ
ሌላም ያገኘሁትን ነገር መስረቅ ጀመርኩ። ስርቆሽ ሱስ እየሆነብኝ ሄደ።
በነገራችን ላይ እናቴ ለእንጀራ አባቴ ለዚያ ለሚጠላኝ አውሬ ወንድ ልጅ የወለደችለት ቢሆንም ለኔ የነበራት ፍቅሯን ግን ለአንድ ቀን እንኳ አጉድላብኝ አታውቅም ነበር፡፡ እኔም ፍቅሬን አልቀነስኩባትም ነበር።የጠላቴ ልጅ ወንድሜ ከተወለደ በኋላ የእንጀራ አባቴ በኔ ላይ ጥላቻው
በእጥፍ እየጨመረ መጣ፡፡ የሱ ልጅ ጥሩ እንዲበላ ጥሩ እንዲለብስ እኔ የሱን ትራፊ እንድበላ የሱን ውራጅ እንድለብስ አደረገ።"ዲቃላ! የምናምንቴ ልጅ! ከልጄ እኩል መሆን ትፈልጋለህ?" እያለ በከፋ ሁኔታ ያሳቅቀኝ ጀመር፡፡ ለልጁ ልብስ ሲገዛ ለኔ አይገዛልኝም፡፡እሱን ትምህርት ቤት
ሲያስገባ እኔን ከቤት አስቀረኝ። ወንድሜን እንደ አባቱ አየሁት። እየጠላሁት ሄድኩ፡፡ የትም ውዬ ባድር ብታመም ብሞት እንጀራ አባቴ ለኔ ደንታ አልነበረውም፡፡ እንዲያውም ሞቴን ለማየትና ለመገላገል ይፈልግ ነበር፡፡ እኔም በጥላቻዬ ገፋሁበት። እናቴን ከማንም በላይ እወዳት ነበር።
በዓለም ላይ የቀረችኝ እሷ ብቻ ነበረች፡፡ ምን ያደርጋል ገና የአስራ ሁለት ዓመት ልጅ እንዳለሁ የምወዳት እናቴ በበሞት ተለየችኝ ዕንባው በዐይኖቹ ግጥም አለ፡፡
"የኔም ተስፋ የኔም ፍቅር ከእናቴ ጋር አብሯት ሞተ፡፡ለሰው ከነበረኝ ፍቅር ውስጥ የቀረኝ የናቴ ፍቅር ብቻ ነበረ። እሷ ስትቀበር ለሰው ያለኝ ፍቅር አብሯት ተቀበረ፡፡ በትምህርቴ እንዳልመካ የእንጀራ አባቴ አላስተማረኝም፡፡ መኖር እፈልጋለሁ፡፡ እናቴ ከሞተች በኋላ
የእንጀራ አባቴ አንተ ገፊ ዲቃላ እዚህ ቤት አይንህን እንዳላየው ብሎ አባረረኝና የምለብሳትን ቡቱቶ አውጥቶ ደጅ ጣላት። ውጭ በጎዳና ላይ ማደር ጀመርኩ። ከዚያም ሙሉ ለሙሉ ቤቱን ለቀኩለትና ጠፋሁ። የደረሰብኝ ችግር የእንጀራ አባቴ የሰጠኝ ትምህርት ለራስ ብቻ የመኖርን ትምህርት ሆነ፡፡ ለኔ የምኖረው እኔ ብቻ ነኝ፡፡ ስለ ራሴ የማስበው እኔ ራሴ ነኝ፡፡ ለራሴ ብቻ የማስብ ሰው ሆንኩ፡ስለ ሌላው ደንታ የለኝም።
እየነጠኩ እየሰረቅሁ ተይዤ ስደበደብ ዱላውን እየቻልኩ እኖራለሁ።
አንተን ባየሁ ጊዜ አንበሳ አይተህ የማታውቅ ባላገርነትህን እንጂ በባላገር ቆዳ ውስጥ የተደበቅክ አንበሳ መሆንህን በፍፁም አልገመትኩም ነበር፡፡
የዚያን እለት ተመልሼ ይቅርታ የጠየኩህ ንቃትና ጉልበትህ ስላስደነቀኝ ነው። ተመልከት ይሄ ሁሉ ስሰርቅ እየተያዝኩ በደረሰብኝ ዱላ ምክንያት ያረፈብኝ አሻራ ነው" ከፊቱ ላይ በግልፅ ከሚታየው ጠባሳ ሌላ በሆዱና
በጀርባው አካባቢ ያለውን ጭምር ያሳየው ጀመር፡፡ ፊቱ፣ ክንዱ፣ ሆዱ
ሁለመናው ተጠባብሷል። ጩቤ የፈተፈተው ሞት የጠላው መሆኑን ከሰውነቱ ላይ ባረፉት በርካታ ጠባሳዎች ውስጥ በጉልህ አስነበበው። ጆብሬ በጎንቻ ላይ በፈፀመው የስርቆሽ ሙከራ ያደረበትን ፀፀት ጭምር እየተ
ናዘዘ ቢሆንም ጎንቻ ግን በተቃራኒው ጆብሬን የመሰለ ሰው በማግኘቱ ውስጥ ውስጡን ልቡ በደስታ እየሞቀች ነበር። ቀስ በቀስ ያንን ሲያቁነጠንጠው የሰነበተውን ጥሙን ሊቆርጥ እየተቃረበ መምጣቱ ታወቀው።
የዛሬዋ ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ብሩህ ተስፋ ያየባት ልዩ ቀን ሆና ታየችው፡፡ ጨዋታው እየጣመው ቢመጣም ከመኖሪያ ቤቱ ርቆ ነበረና መውጣት ፈለገ።
“ቦታ ቀይረን እንጫወት?" ሲል ለጆብሬ ጥያቄ አቀረበለት። ጆብሬም በደስታ ፈንድቆ አካባቢ አስመረጠው።
'ለማንኛውም ወደ ላይ እንሂድ" አለ ጎንቻ፡፡ መቼም ቶሎ ብሎ ሰው አያምንም። ተጠራጣሪ ነው። ዓለሚቱ ሰውን ቶሎ እንዳያምን አስጠንቅቃዋለች።ቢከፋም ቢለማም ብሎ ወደ ራሱ ሰፈር ይዞት ሄደና የዘወትር ደንበኛው ከሆኑት ከወይዘሮ መደምደሚያሽ አረቄ ቤት ገቡ፡፡
እንደምን ዋሉ እትዬ መደምደሚያሽ?” አለ ጎንቻ፡፡
ደህና ዋልክ? ልጅ ጎንቻ! ምነው ዛሬ ዓለምዬን ጥለሃት መጣህ?
አዲስ ጓደኛ አገኘህ መሰለኝ?" ጆብሬን ከላይ ታች እያዩት።
“አዎን እስቲ ዛሬ እንኳ እንደ ሴቶቹ እቤት ትዋል ብዬ ነው” እየሳቀ
መለስላቸውና ተያይዘው ወደ ውስጥ ዘለቁ። በወይዘሮ መደምደሚያሽ ቤት ጠጪ ባለመኖሩ ጆብሬ ጎንቻ የልባቸውን ለመጨዋወት ቻሉ፡፡
ይሄንን አረቄ በላይ በላዩ እየከለበሱ መጋል ሲጀምሩ ጆብሬ ያጋጠመውን ታሪክ የፈፀማቸውን አኩሪ የሌብነት ታሪኮች በኩራት ይዘረዝርለት ጀመር፡፡ ጎንቻ ደም ሳያይ በጭንቀት ያሳለፈው ጊዜ ረጅም ሆኖ ታየው።
የሰው ቢጠፋ የአውሬ ደም ሳያይ አይውልም ነበር፡፡ ይሄንን ችግሩን አይቶለት ይሆን ጆብሬን ጀባ ያለለት? የሰፈረበት?…
“የኔን ታሪክ ደግሞ በሌላ ጊዜ አጫውትሃለሁ በሌላ ጊዜ እንገናኛ!” አለው፡፡
“መቼ እንገናኝ ታዲያ?” በጉጉት ጠየቀ ጆብሬ፡፡ ጎንቻ ሆን ብሎ ቆዳውን ለማዋደድ እንጂ ጆብሬን ሊለየው አልፈለገም ነበር፡፡
“መቼ ይሻላል?” ማሰፍሰፉን ሲያይ ጀነን አለ፡፡
ነገ አንገናኝም?" ጀብሬ በልምምጥ ዐይን ዐይኑን አየው።
እንገናኝ ብለህ ነው?ይሁን እሺ ግን በስንት ሰዓት?” የሚገናኙበትን ቦታና ሰዓት ተቀጣጥረው ተለያዩ፡በጣም ስለመሽ አለሚቱ ትሰጋለች
ብሎ ፈርቶ ነበር፡፡ ቤቱን ጆብሬ እንዳያይበት አርቆ ቁልቁል ከሸኘው በኋላ አድብቶ ተመለሰ፡፡
ምነው ጎንቻዬ አመሸህ?” አለሚቱ የወጡን ድስት እያማለለች ጠየቀ
ችው፡፡ ቀደም ሲል ከስው ጋር መጣላቱን አልነገራትም ነበር። ከመስሎቹ ጋር በአስቸኳይ ተቀላቅሎ ስራውን በፍጥነት እንዲጀምር እንጂ ረብ የለሽ ፀብ ፈጥሮ ተይዞ ታስሮ የሱ ምግብ አመላላሽ ሆና መቅረት አይደለም ፍላጎቷ፡፡ ይሄን ፍላጎቷን ደጋግማ ስለገለፀችለት ከጆብሬ ጋር መጣላቱን ደብቋት ነበር።
"እባክሽ ከሆነ ሰው ጋር ተዋውቄ ስንጨዋወት ሳላውቀው መሽ” አላት።
"ጎሽ! ሰው መተዋወቅ ጀመርክ ማለት ነው? ጎበዝ! ግን ጠንቀቅ በል።ሰውን ቶሎ አትመን እሺ? የምትተዋወቀውን ሰው ፀባይ አጥና። ሰላይ ሊሆን ስለሚችል እጅህን እንዳያስይዝህ"
"ግድ የለሽም ለኔ በጣም ጠቃሚ የሆነ ሰው ነው ያገኘሁት። እትዬ መደምደሚያሽ ቤት ስንጨዋወት ነው ያመሽነው፡፡ስለራሱ የህይወት ታሪክ አጠናሁ እንጂ ስለራሴ ምንም ያወራሁለት ነገር የለም፡፡ ይሄን ያክል በግ አደረግሽኝ እንዴ? እኔ ባልሽ ጠንቃቃ ነኝ እኮ” ሳቅ አለ፡፡ አሁን አሁን እኔ ባልሽ ነው የሚላት።ሙሉ የባልነት መብቱን አረጋግጧል፡፡ ጆብሬም
ጥሩ ጓደኛ ከተባለ ማለፊያ ትውውቅ ነው።
ዓለሚቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባን ተዘዋውራ በርካታ ቦታዎችን ማወቅ ችላለች። ዕቃ ለመግዛት ወደ መርካቶና ፒያሳ መውጣት አዘውትራለች፡፡ ዓለሚቱን ይዛት የምትወጣው የወይዘሮ መደምደሚያሽ

👍1
ሴት ልጃቸው ነበረች። ከዚያ መልስ ግን በጎንቻ ላይ ጉራዋ አይጣል ነው። የልዩ ልዩ ሰፈሮችን ስም እየጠራች የሄደችበትንም በወሬ የሰማችውንም ጨማምራ ሲኒማ ቤቶችን ትያትር ቤቶችን ስም እየቆጠረች መርካቶን፣ ፒያሳን፣ ጉለሌን፣ ኮልፌን፣ ተክለሀይማኖትን..." እያለች
ጉራዋን ትቸረችርበታለች፡፡
"አንቺ ሴትዮ ስትዞሪ ነው እንዴ የምትውይው?" ይላታል ላይ ላዩን እየሳቀና ውስጥ ውስጡን የቅናት ስሜት እየለበለበው፡፡
"አገሩን የማስሰው ጉድጓዱን የምምሰው ለወደፊት ኑሯችን ብዬ ነውኮ፡፡
አንተም ስራህን ቶሎ እንድትጀምር እኔም ቤት ውስጥ ከመቀመጥ አንዳንድ ነገሮችን እየሰራሁ መንቀሳቀስ እንድችል አካባቢውን አገሩን በደንብ ማጥናት አለብን አይመስልህም ጎንቻዬ?" በዚህ ንግግሯ ይስማማል።
የከተማ ዋሻ፣ የከተማ ዱር፣ የከተማ ጢሻዎችን ለመምረጥ ለንጥቂያ የሚመቸውን ሰፈር ለማጥናት፣ እሱን መሳዮች ለመተዋወቅና ስራውን
ብአፋጣኝ ለመጀመር አዲስ አበባን በደንብ ሊያውቋት ይገባል። ስለዚህ? ዓለሚቱ ሙሉ ቀን ከተማውን ስታስስ፣ ስትሯሯጥ ብትውል እግሯ እስከሚቀጥን ድረስ አዲስ አበባን ብትሽከረከር ለጋራ ጥቅም ነውና ሊከፋው
አይገባም፡፡
ጆብሬ መጀመሪያ ከተዋወቁበት ቦታ ከቀጠሮው ቀድሞ በመገኘት ምስጉን ሰዓት አክባሪነቱን በድጋሚ አስመሰከረ፡፡ ጎንቻን ለጥብቅ ጉዳይ እንደሚፈልገው የማረጋገጫ ምልክቶቹን ደጋግሞ አሳየ፡፡ እንደመጣ እቅፍ አድርጎ
ሳመው፡፡
ጎንቻ በባላገር ቆዳው ውስጥ የተደበቀ አስገራሚ ስብዕና ያለው ሰው መሆኑን ተገንዝቧል። ደፋርነቱ፣ ንቁነቱ፣ ጉልበታምነቱ ሁሉ ከበስተጀርባው ያለውን ሚስጥር እንደ መስታወት ወለል አድርጎ አሳይቶታል። በተለይ የህይወት ታሪኩን ሊነግረው ይጀምርና እንደ ስስፔንስ ፊልም እያንጠለጠለ በመሃሉ እያቋረጠበት ስለሚለያዩ የጎንቻን
ማንነት ለማወቅ አሰፍስፏል። በዐይኖቹ ቅላት በአነጋገሩ፣ በእንቅስቃሴው፣ በቀዥቃዣነቱ፣ የሱ ቢጤ ቀማኛ መሆኑን ስለገመተ ይበልጥ ስለጎንቻ ለማወቅ ልቡ ተሰቅላለች።
"ዛሬ እኔ ይሆናል ወደምለው ቦታ ወስጄ እንድጋብዝህ ምርጫውን ለኔ ብትተውልኝስ?" አለው ጆብሬ፡፡
"መልካም! ደስ ይለኛል የፈለከው ቦታ መሄድ እንችላለንአለ ጎንቻ
ከፊል እምነት ከፊል ጥርጣሬ ባደረበት አንደበቱ ።
ጆብሬ ጎንቻን ይዞት የሄደው ወደዚያ አንዱን ብርሌ ሲቀምሱለት እንደ ኤሌክትሪክ የሚያነዝር፣ ወደዚያ ቁልቁል ሲውጡት ጉሮሮ እያቃጠለ ኃይሉ እንደ ሚሳኤል ሽቅብ አናት ላይ ወደሚምዘገዘገው አራት ኪሎ
ከሚገኘው ትርንጎ ጠጅ ቤት ነበር፡፡ ጠጃቸውን ያለገደብ እየኮመኮሙ ቀስ በቀስ እየተፍታቱ እየተዝናኑ እየተጋጋሉ ሄዱ። ከዚያም መተቃቀፍ ጀመሩና የልባቸውን ተጨዋወቱ።ተማመኑ። ተማማሉ። ጎንቻ ከህይወት ታሪኩ ውስጥ ጥቂቱን አቀመሰው። የጆብሬ ዐይኖች በድንጋ
ጤና በአድናቆት እንደተበለጠጡ... አፉንም ጆሮዎቹንም በሰፊው ከፍቶ
ጎንቻ ከፈፀማቸው አሰቃቂ ተራጄዲ ትዕይንቶቹ መካከል ጥቂት ክፍሉችን ማዳመጥ ቻለ፡፡
ጆብሬ በተደጋጋሚ ተገናኝተን ተጨዋውተናል። የሰው ልጅ ቁም ነገረኛነቱ የሚለካው አብሮ በሚቆይበት ጊዜ ርዝመት አይደለም። ሙሉ ዕድሜ አብሮ መኖር ብቻውን ዋጋ የለውም፡፡ ቁም ነገሩ በአጭር ጊዜ
ትውውቅ ጠቃሚ ነገር ሰርቶ መገኘት ነው።በዚች አጭር ጊዜ ውስጥ እኔና አንተ ብዙ ቁም ነገሮችን ተጨዋውተናል። ሂድ ሂድ ይለኛል፣
ጥፋ ጥፋ ይለኛል። እልም ብዬ እንዳልጠፋ ደግሞ ፍቅር አለብኝ።ፍቅሬ ከሌለች መኖር አልችልምና እሷ ፍቅሬ ዓለሚቱን ጥዬ እንዳልጠፋ ተቸገርኩ። ልቤ ጫካ ውስጥ ዋሻ ውስጥ ነው ያለው። እኔ ደግሞ ያለሁት
እዚህ ነው።እኔና ልቤ እንዴት መገናኘት እንደምንችል መላ የሚፈልግልኝ አጣሁ። ምን አድርግ ትለኛለህ?" ዋሻው፣ ዱሩ፣ ጫካው የናፈቀው መሆኑን፣ደም የተጠማ አነር መሆኑን፣ የዘረፋው ትርኢት በዐይኑ ላይ የሄደበት የግድያ መድረክ የጠበበው ተዋናይ መሆኑን ከሞቅታ ጋር በስሜት ተውጦ በጋለ መንፈስ ገለፀለት። ጆብሬም የጎንቻ ፍላጎት ገባው።
"አይዞህ! የምትፈልገው የምትመኘው ሁሉ እዚሁ የተሟላ ነው። እንዲያውም ስላልለመድከው እንጂ ይሄኛው የበለጠ ያረካሃል። ፍቅርህን ጓደኛህን ትተህ የትም አትሄድም፡፡ እሷ እያለች እሷን ሳትርቅ ሁሉንም ከእኔ ጋር ሆነን እንወጣዋለን፡፡ዋሻውም ጫካውም እዚሁ አለልህ፡፡ አዲስ አበባ የስራ ቦታ ነች፡፡ ተረጋጋ" አንገቱን አቅፎ አይዞህ አብረን ነን በማለት .
በዛፍ ጫካ የተሞላች ባትሆንም በህዝብ ጫካ የተሞላች አስተማማኝ እውነተኛ ጓደኛነቱን ለመግለፅ ቃላት አጠሩት። ጎንቻ በእውነትም ከዓለሚቱ ጋር ለአንድ ቀን እንኳ ከተለየ የሚሞት እየመሰለው መሄድ ጀምሯል። አንዳንዱ ፍቅር እያደር ይቀዘቅዛል ይሰክናል፡፡ የጎንቻ ፍቅር ግን እየተባዛ.እየተደመረ እንጂ እየተቀነሰና እየተካፈለ የሚሄድ የፍቅር ሂሳብ ስሌት ሊሆን አልቻለም። በዚህም የተነሳ ከዓለሚቱ ሳይለይ ያንንፍላጎቱን ማሳካት እንዲችል አይዞህ እያለ ሞራል የሚሰጠውን ሰው
የበለጠ ወደደው። አመነው።
የቀማኞች ጓደኝነት የሚመሰረተው በዘረፋ የጋራ አጀንዳቸው ውስጥ
ነውና እንደዚያ ህይወት ንጥቂያ ቀረሽ ዱላ ተደባድበው በጎንቻ ጉልበተኛነት በጆብሬ የፈሰሰ ደም ውስጥ የፍቅራቸው አበባ ተተክላ ላፍሬ ልትበቃ እየለመለመች መሄድ ጀምራለች፡፡....
✨ይቀጥላል✨

#ፍርሀት_ወለድ_ድፍረት
ቃጭል እንዳንጠለጠለች ፍየል
የቱን ፀበል ብትጠመቅ መደንበሩ እንዳይለቃት
አዳኝ እንዳየች ሚዳቋ
የቱን ምስል ብትሳለም ድንጋጤው እንዳይተዋት
ጠላቷን እንዳየች ሸለምጥማጥ
የእድሜዋን ሁሉ ሩጫ እንድትሮጥ በዚያች ሠዓት
ፍርሀት የወለዳት ድፍረት፡-
የትኛው ልጓም ሊገራት!
የቱ ክትር ሊያስቆማት!
🔘መንግስቱ በስር🔘
ቃጭል እንዳንጠለጠለች ፍየል
የቱን ፀበል ብትጠመቅ መደንበሩ እንዳይለቃት
አዳኝ እንዳየች ሚዳቋ
የቱን ምስል ብትሳለም ድንጋጤው እንዳይተዋት
ጠላቷን እንዳየች ሸለምጥማጥ
የእድሜዋን ሁሉ ሩጫ እንድትሮጥ በዚያች ሠዓት
ፍርሀት የወለዳት ድፍረት፡-
የትኛው ልጓም ሊገራት!
የቱ ክትር ሊያስቆማት!
🔘መንግስቱ በስር🔘
#የበቀል_ጎርፍ
ምን ያውቃሉ ህፃናቱ
ስለ ሸፍጥ ፖለቲካ-ጭፍን ጥላቻ-ሞኛሞኝ ብቀላ
ደግሞስ ምን ሊያቁ
እነሱ
ከአባሮሽ በቀር ካኩኩሉ
ከአይጤን አያችሁ አላያችሁ
ካልነጋም ወይ ኩኩሉ
ግና ምን ያደርጋል
ጥላቻ ህግ የለው ፤ ህሊና አይገድበው
በቀልም እውር ነው ፤ እውርም አይን የለው
እሾህን ካበባ ለይቶ ላይፈጀው
ግን ለምን ጥላቻ
ግን ለምን ብቀላ
አውሬነቱስ ለምን
መሰይጠኑስ ለምን
ለምን!
በቀል በቀልን ያረግዝ እንጂ አይገድል
ጥላቻ ጥላቻን እንጂ ፍቅርን አያበቅል፡፡
እኮ ለምን ?!
ለነገሩ ያዳም ልጅ አይደለን
እንዳልተገባ እያወቅን ያልተገባን የምንከውን
እሺ. . ይሁን
እንጠላላ ... እንገዳደል
አንጠላለፍ. . .እንበቃቀል
ግን ለምን ህፃናት
አንዳች ፋይዳ ላያመጣ
ሚጡን ማረድ፣ ቢጠን መቅላት
ምን ይሉት እርኩሰት. . .ምን ይሉት ጥንውት?
ደርሶ ሄሮድስነት ...እየሱስ ከሌለበት
ደርሶ ቦቅቧቃነት ተቀናቃኝ ካልዋለበት::
ግን ለምን ጥላቻ
ግን ለምን ብቀላ
አውሬነቱስ ለምን
መሰይጠኑስ ለምን
ለምን?
🔘መንግስቱ በስር🔘
መታሰቢያነቱ፡-
የጦርነት ሰስባ ለሆኑ ህጻናት
ምን ያውቃሉ ህፃናቱ
ስለ ሸፍጥ ፖለቲካ-ጭፍን ጥላቻ-ሞኛሞኝ ብቀላ
ደግሞስ ምን ሊያቁ
እነሱ
ከአባሮሽ በቀር ካኩኩሉ
ከአይጤን አያችሁ አላያችሁ
ካልነጋም ወይ ኩኩሉ
ግና ምን ያደርጋል
ጥላቻ ህግ የለው ፤ ህሊና አይገድበው
በቀልም እውር ነው ፤ እውርም አይን የለው
እሾህን ካበባ ለይቶ ላይፈጀው
ግን ለምን ጥላቻ
ግን ለምን ብቀላ
አውሬነቱስ ለምን
መሰይጠኑስ ለምን
ለምን!
በቀል በቀልን ያረግዝ እንጂ አይገድል
ጥላቻ ጥላቻን እንጂ ፍቅርን አያበቅል፡፡
እኮ ለምን ?!
ለነገሩ ያዳም ልጅ አይደለን
እንዳልተገባ እያወቅን ያልተገባን የምንከውን
እሺ. . ይሁን
እንጠላላ ... እንገዳደል
አንጠላለፍ. . .እንበቃቀል
ግን ለምን ህፃናት
አንዳች ፋይዳ ላያመጣ
ሚጡን ማረድ፣ ቢጠን መቅላት
ምን ይሉት እርኩሰት. . .ምን ይሉት ጥንውት?
ደርሶ ሄሮድስነት ...እየሱስ ከሌለበት
ደርሶ ቦቅቧቃነት ተቀናቃኝ ካልዋለበት::
ግን ለምን ጥላቻ
ግን ለምን ብቀላ
አውሬነቱስ ለምን
መሰይጠኑስ ለምን
ለምን?
🔘መንግስቱ በስር🔘
መታሰቢያነቱ፡-
የጦርነት ሰስባ ለሆኑ ህጻናት
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....አሜሪካን ግቢ፣ጌሾ ተራ፣ ዶሮ ማነቂያ፣ ሠራተኛ ሰፈር፣ እሪ በከንቱ በጎንቻ ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ የጆብሬና የጎንቻ ጓደኝነት ከሁለትነት ወደ አራትነት ተሸጋገረ። ጎንቻ ጀግንነቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመሰከረው
በፈጣን የአንገት ጥምዘዛ ነበር፡
አንድ ምሽት በሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ ለወሊድ የደረሰች ሚስቱን በሌሊት ሆስፒታል አድርሶ የመመለሻ መኪና አጥቶ ወደ ቤቱ ኩስ ኩስ የሚል ምስኪን አንገት እንደ ዶሮ ጠምዝዞ በመጣል ማንነቱን አሳየው።
ጆብሬ ፍጥነቱንና ቅልጥፍናውን የበለጠ አደነቀው።ከዚያን ግዜ ጀምሮ የበለጠ እያከበረውና እየፈራው መጣ፡፡ገንዘብ በሽበሽ ሆነ፡፡ ጆብሬ ኪስ ይዳብሳል።ጎንቻ ማጅራት ይመታል። ክርክር ከበዛ አንገት እንደ ፎጣ ጠምዝዞ ይጨምቅና ይበረብራል"ለካስ በከንቱ ኖሯል ኛሮ ኛሮ ያሰኘኝ?”
አለ፡፡ ኛሮን በአሜሪካ ግቢ ውስጥ፣ ኛሮን በጌሾ ተራ ውስጥ፣ ኛሮን በዶሮ ማነቂያ ውስጥ፣ ኛሮን በሠራተኛ ሰፈር ውስጥ፣ ኛሮን በእሪ በከንቱ ውስጥ አገኘው
ከኛሮ የቀረ የቀረበት ነገር ቢኖር
ዋሻውና የአውሬ ስጋው ብቻ ነበር፡፡በአዲስ አበባ ውስጥ የወላጆቹን ሃይማኖት ቀይሮ የዓለሚቱ ሃይማኖት ተከታይ ሆኖ አብረው ጮማ ይቆርጣሉ፡፡
አልኮል ይጨልጣሉ። ከዓለሚቱ ጋር በአረግራጊ ሽቦ አልጋ ላይ ያረገርጋሉ። ከዓላሚቱ ጋር እንደዚህ ዓለምን እየቀጩ በአዲስ አበባ ውስጥ መኖርን ቀስ በቀስ እየለመደው፣ እየወደደው መጣ፡፡ አዲስ አበባ ጣመችው፡፡ ጆብሬም
እውነተኛ ታማኝ ጓደኛነቱን አስመሰከረ ጎንቻን ጋሻ መከታው አደረገ፡፡ፀብ ከተነሳ ጎንቻ ገላጋይ መስሎ ተበዳይ ላይ ጉብ ነው፡፡ ጆብሬ የደነዘዘ ሰውነት ካገኘ ሞሽልቆ ያመልጣል። ከተነቃበትም ጎንቻ አለኝታው
ነው። ትርዒቱ ቀጠለ፡፡ አንደኛው የአደጋ ጣይ ቡድን ከሌላው ጋር
ተዋወቀ። በጎንቻ የበላይነት በዓለሚቱ ንብረት ተቀባይነትና አስቀማጭነት ወዳጅነቱ ተጧጧፈ።ሌሎቹ የቡድኑ አባላትም ዓለሚቱን በጥሩ አስተናጋጅነቷ ወደዷት። ፍቅር በፍቅር ሆኑ። መኖሪያ ቤታቸውንም ከእንጦጦ ወደ ዋናው መስሪያ ቤታቸው ወደ እሪ በከንቱ አዛወሩና አንድ ሰፊ ክፍል ቤት ተከራዩ።
በገንዘብ ላይ ገንዘብ ተጨመረ፡፡ እያለቀ፣ እየመነመነ የመጣው ገንዘብ ሲያሳስባት የቆየችው ዓለሚቱ ለመቁጠር እስከሚታክታት ድረስ ተንበሽበሸች፡፡ አራጣ በማበደር ሌላ የገቢ ምንጭ ከፈተች፡፡ በውበቷ ላይ ውበት፣
በጌጣጌጦቿ ላይ ጌጣጌጥ፣ በብር ላይ ብር አከማቸች።
ዛሬም በዓለሚቱ ካዳሚነት ጫት እየተቃመ የተዘረፈው ንብረት የሚቆጠርበት፣ ክፍፍል የሚደረግበት፣ እየተመረቀነ፣ እየተፈረሽ ውይይት የሚካ
ሄድበት፣ ተጨማሪ ዕቅድ የሚወጣበት፣ ስትራቴጂ የሚቀየስበትና ስልት
የሚነደፍበት ዕለት ነው፡፡ በቤቱ ውስጥ ያሉት ከዓለሚቱ ጋር አምስት ሲሆኑ ከጆብሬ ሌላ በቅፅል ስሙ “መቀስ" እየተባለ የሚጠራው አንበሴና
በጫት ምርቃና ላይ የሚንተፋተፈው አበራም ይገኙበታል። ጫት ከመጀመሩ በፊት ዓለሚቱ ሳር ጎዝጉዛ ፍራሽ አንጥፋ፣ ከሰል አያይዛ ሁሉን
ነገር አዘገጃጅታለች፡፡
የሜቱ ሥነ ሥርዓት የሚጠይቀው የቄጤማው ጉዝጓዝ ሰንደሉ ዕጣኑ
ሁሉ የተሟላ ነው፡፡ እውነተኛ ካዳሚነቷን አረጋግጣለች ማለት ይቻላል። የሰላም አምባሳደሮች፣ የሳይንስና ምርምር ፕሮፌሰሮች፣ የዕድገት መሀንዲሶች፣ ጥበበኞች እና ምሁራኖችን የምታስተናግድ ካዳሚ..እግሮቻቸውን አጣጥፈው ቦታ ቦታቸውን እንደያዙ ጎንቻ ግድግዳው ላይ ወዳን
ጠለጠለው ኮት ኪሱ ውስጥ ገባና በርካታ ነገሮችን ማውጣት ጀመረ።
በደም የተለወስ የአንገት ሀብል... ትላልቅ የጆሮ ጉትቻዎች… ከወርቅ
የተሰሩ የሴት የእጅ አምባሮች የተለያዩ የብር ኖቶች ያሉበት ትንሽ
ቦርሳ ያ ሁሉ ንብረት ከጥቂት ሰዓታት በፊት አንቆ የዘረፋት ሴት
ሀብት ነበር፡፡ ጆብሬ ዛሬ የሰራውን ሁለት መቶ ብር ከደረት ኪሱ ላጥ
አድርጎ አወጣና አስቀመጠ፡፡ አበራ አልቀናውም፡፡ አንበሴ ዛሬ እንደ አንበሳነቱ ሳይሆን ውርደት ቀምሶ ቡጢ ልሶ ነው የመጣው። ሁለቱ የሰሩትን ሲያወጡ ሁለቱ አፈጠጡ። ወላ ሀባ ጭቅጭቅ ንትርክ የለም። አንዱ ከቀናው ላልቀናው ያካፍላል ዛሬ ባይቀናው ነገ እንደሚክስ የታወቀ ነው፡፡
ይሁን እንጂ መቀስ በጣም አብዝቶታል። ያንን መልካም ቁመናውን ብቻ ዋቤ አድርጎ ዕይኖቹን ያስለመልምና ድርሻውን ላፍ አድርጎ መሰስ ይላል። የቀናው ዕለት እንኳ የረባ ነገር አበርክቶ አያውቅም። እፍኝ ቆሎ ይዞ ከአሻሮ መጠጋት አብዝቷል፡፡ በማንኪያ ሰጥቶ በአካፋ መዛቁን እየደጋገመ መጥቷል።
የተማመነው በማን ይሆን? ጎንቻ ጆብሬ ያስቀመጠውን አየና ወደ ሁለቱ ፊቱን አዙሮ በምልክት
እጃችሁ ከምን? ሲል በእንቅስቃሴ ጠየቃቸው፡፡ ያገኘው መልስ ግን የፈጠጡ አራት ዐይኖች ሲንከባሉና ሲቁለጨለጩ ከማየት ሊዘል አልቻለም።
“ስማ መቀስ ብዙ ብልጥ መሆን አያስፈልግም! የምታገኘውን ላፍ አድርገህ ትሄዳለህ፡፡ ይዘህ የምትመጣው የሰራኸውን ሳይሆን በብልጠት እየቀነጨብክለት መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን። በመካከላችን ዋናው ቁም ነገር መተማመን ነው! አንተ ግን ሁኔታህን ደጋግሜ ስመለከ
ተው እምነት የጎደለህ ትመስላለህ፡፡ ሁል ጊዜ የሌላውን ድካም ጠባቂ መሆን ብልጥነት ብቻ ሳይሆን ዐይን አውጣነት ነው!” ተቆጣ፡፡ 'የአበራ ጉዳይ እንኳ ምንም አይደለም የታወቀ ነው። ቶሉ ቶሎ ባይቀናውም
አንዴ ከቀናው በሽ በሽ ስለሆነ ግድ የለም። አንተ ግን አበዛኸው። ከዚህ ውስጥ ምንም የሚደርስህ ነገር እንደማይኖር አረጋግጥልሀለሁ! በርጫህን ቅመህ ለጨብሲ የምትሆን አስር ብር በቂህ ስለሆነ ሌላውን እን
ዳትጠብቅ!" ቁርጡን ነገረው፡፡ ከጎንቻ ያላነሰ የአረመኔነት ባህሪ የነበረው መቀስ ለግላጋ ቁመቱና ወንዳወንድነቱ ከውጭ ለሚያየው ሰው የሚስብ ነው። መቀስ በጎንቻ አነጋገር ወሽመጡ ብጥስ አለ። በጉምዥት አፉን የሞላው ምራቅ በድንገት ደረቀ፡፡ ጎንቻ የበላይነቱን በመያዙ እኔስ ከማን አንሼ? በማለት ሊቀናቀነው የሚሞክር ሰው ነው። የቡድኑን የመሪነት ሥልጣን ለመውሰድ ከመመኘት ባለፈ በጎንቻ ላይ ንቀት ነበረው። ይህንን ንቀቱን በተግባር ለማሳየት ደግሞ ዓለሚቱን አጥምዷታል። ጎንቻ ያን የመሰለ አንጀት
የሚበጥስ ንግግር ሲናገረው ቀስ ብሎ ዓለሚቱን በቆረጣ ተመለከታት፡፡ እሷም የጎንቻን ዐይኖችና የሌሎቹንም
እንቅስቃሴ ጠብቃ ማንም ሳያያት ተደብቃ "ጥቅስ" አደረገችው። ፀብ አትፍጠር ማለቷ ነው፡፡ ምን አሳስበህ? ማለቷ ነው። ተረጋጋ....
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከሶስት ዓመታት የላምበረት ኑሮ በኋላ ዘይኑን ዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት አስገባት። ከላምበረት ዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት ከምትመላለስ በአቅራቢያው ቤት መከራየት ፈለገና እሪ በከንቱ አካባቢ ሰራተኛ
ስፈር ሁለት ክፍል ያላት ቤት አግኝቶ ተከራየ፡፡ ዘይኑ ለትምህርት ቤቷ ቅርብ የሆነ ቤት አገኘች። ትንሽ ደስ ያላላት ላምበረት የትውልድ መንደሯን ዓይነት ፀጥታ የሰፈነበት ሲሆን እሪ በከንቱ ግን የተጨናነቀና ሁካታ የበዛበት መሆኑ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ረጅም መንገድ ከመመላለስ ታድጓታልና ጉዳቱን በጥቅሙ አካክሳ ተቀብላዋለች፡፡ ጌትነት እህቱን በቅርበት እየተከታተለ ለጥሩ ውጤት እንድትበቃ ማድረጉ፣ በትምህርት ቤት ተጀምሮ ለሁለት አመታት የዘለቀውና ውስጥ ውስጡን ሲያሰቃየው የኖረው ፍቅር መቋጫው አምሮ ከሚወዳት ከአማረች ጋር አስደሳች

የፍቅር ህይወት መምራት መጀመሩ፣ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ ሰፊ የእድገት እድል ወዳለበትና ከትምህርቱ ጋር ተዛማጅነት ወዳለው ወደ ሂሳብ ክፍል ዝውውር አግኝቶ ልምዱን እያዳበረ መምጣቱ ፣ በዩኒቨርሲቲ የሚ
ከታተለው ትምህርትና ያገኘው አመርቂ ውጤት ስኬታማነቱን እያረጋገጡለት በመሆኑ እጅግ ደስተኛ ሆኗል፡፡ አለቃው ልኡልሰገድ ግን ደስተኛ
አልነበረም፡፡ ዲግሪውን ካገኘ ሲቋምጥለት የኖረውን የሃላፊነት ቦታ እንደ ሚረከበው ስለሚያውቅ በቅንዓት ተንገብግቧል። በዚህም የተነሳ ሌላ የተንኮል መረቡን ዘርግቶ በሰፊው መንቀሳቀስ ጀምሯል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምድረ ግቢ በሰንደቅ ዓላማና በጌጣጌጥ አሸብርቋል፡፡ የህዝቡ ብዛት ለጉድ ነው። ይተራመሳል፡፡ ለምረቃው የተጠሩ ወላጆች.. ዘመድ አዝማዱ ሁሉ እቅፍ አበባ እየያዙ ተመራቂዎችን "እንኳን ደስ አላችሁ" ለማለት ወደ ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመጉረፍ ላይ ናቸው፡፡
ዝግጅቱ "ልደት የስብሰባ አዳራሽ" እየተባለ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ ነበር፡፡ በዲግሪና በዲፕሎማ የሚመረቁ ተመራቂዎች ጋውናቸውን ለብሰው
ጥቁር ቆባቸውን ደፍተው በተለያየ ቀለም ሪቫን አምረውና ደምቀው ለበርካታ ዓመታት የደከሙበትን ውጤታቸውን በደስታ ሊቀበሉ ሽር ጉድ እያሉ ናቸው። እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ! የሚለው የዩኒቨርሲቲው ታዋቂ መዝሙር በድምቀት ይሰማል። ሁካታው፣ ጫጫታው፤ደስታው ልዩ ነበር የመድረኩ መሪ ሁሉም ተመራቂዎች ከመቀመጫቸው ብድግ እንዲሉና የቆባቸውን ገመድ ወደ ግራ እንደዚሁም ወደ ቀኝ እንዲያዞሩ ጠየቁ፡፡
“የዲግሪና የዲፕሎማ ተመራቂዎች የሆናችሁ በዛሬው ዕለት በዚህ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተገኛችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!” በማለት ስነስርአቱን ከከፈቱና ልባዊ የደስታ መግለጫ ንግግር ካደረጉ በኋላ የምረቃ
ሥነ ሥርዐቱ በይፋ መጀመሩን አበሰሩ። ተመራቂዎችም በከፍተኛ ጭብጨባና ጩኽት አዳራሹን አናወጡት። በመቀጠል በየትምህርት መስኩ ስም እየተጠራ በውጤታቸው ብልጫ ላገኙ ተመራቂዎች የተዘጋጀው
ልዩ ሽልማት በእለቱ የክብር እንግዳ አማካኝነት መስጠት ጀመረ፡፡ከነዚህ መካከል ጌትነት መኩሪያ አንዱ ነበር። የተመረቀው በከፍተኛ ማዕረግ ነው። ያገኘው ውጤት ተገልፆ የወርቅ ሰዓት በእጁ ላይ ሲታሰርስትና እን
ደዚያ አዳራሹ በጭብጨባና በፉጨት ሲናወጥ እናቱ አስካለ የተሰማትን ስሜት እንዲህ ነበር ብሎ መግለፅ ይከብዳል። ከደስታ ብዛት የምትሆነውን አጣች። ብድግ አለችና እልልታዋን አቀለጠችው፡፡ በስስትና በጉጉት
ወልዳ ያሳደገችው ልጅዋን ዓለምና ደስታ ከማየት የበለጠ ምን የሚያስደስት ነገር ይኖራል? በዚያ በጥቁር ቆብና ገዋን አምሮ በዩኒቨርስቲው ውስጥ ልዩ አድናቆት አግኝቶ ሲሽለምና የማያቋርጥ ጭብጨባ ሲስተጋባለት ከማየት በላይ ምን ልብን የሚነካ ነገር ሊኖር ይችላል? መመረቅ የትዳርን ያክል ያስደስታልና ልጂ የተዳረላትን ያክል በደስታ ሰከረች።
እንዲያውም መመረቅ ከትዳር በላይ አስደሳች የሚሆነው ተፈጥሮአዊ የፆታ ብቃትን ብቻ ሳይሆን የረጅም አመት ድካምና መስዋዕትነትን የሚጠይቅ በመሆኑ ነው፡፡
የጌትነት እናት ልጇ ለብዙ አመታት ደክሞ ተምሮ በከፍተኛ ማእረግ
ሲመረቅላት የተሰማት ደስታ ከዚህ አኳያ ሲመዘን ተገቢና የሚመጥን
ነው የሚያሰኝ ነበር፡፡ የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ እንዳበቃ የማስታወሻ ፎቶ
ግራፍ ለመነሳት ተመራቂዎች በዩኒቨርስቲው ምድረ ግቢ ላይ ፈሰሱ።
ከውጭ ሆና ትጠባበቅ የነበረችው ዘይኑ ወደግቢው የመግባት እድሉን አግኝታ እቅፍ አበባዋን ይዛ በደስታ እየተፍነከነከች ወንድሟ ላይ ተጠመጠመችበት፡፡ሽመልስ የሙሽራው ሚዜነቱን በለበሰው ሱፍና ባንጠለጠለው ክራቫት አረጋግጧል። ለምረቃው እንዲገኝ ያደረገለትን ጥሪ ሳይቀበል የቀረው ልኡልስገድ ብቻ ነበር። እሱን ምን የሚያስደስተው ነገር
አለና ይመጣል? ምቀኝነትና ቅንዓት አቃጥሎት የቋመጠለትን የዕድገት ቦታ ይሻማኛል በሚል ስጋት ተወጥሮ ዕንቅልፉን አጥቶ ተንኮል ሲያውጠነጥን ነበር የከረመው። ልዑል ሰገድ ሰውነቱ ግዙፍ ነው። ጢሙን ማሳደግ ያዘወትራል። ከውጭ ሲመለከቱት ትሁትና አዛኝ የሚመስል ሀሳዊ መሲህ ነው። የሰውን ችግር አዳምጦ መፍትሄ የሚሰጥ ተቆርቋሪ መሳይ መስሪ! ከአጠገቡ ዘወር ካሉለት ደግሞ የሰው መቃብር ሲምስ የሚገኝ እባብ ይህንን ፀባዩን ብዙዎቹ ሰራተኞች እያወቁበት መጥተዋል። የስንተኛ ክፍል ተማሪ መሆኑን ለሚያውቁት ጭምር ዕይኑን በጨው ታጥቦ" ይሄ አመዳም ትናትንና መጥቶ ሊበልጠኝ ነው እኮ እያለ ሲያወራ እፍረት የሚባል ነገር አልፈጠረበትም፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ አቶ አባይነህ ስራቸው ተጋልጦ ከሥልጣናቸው ዝቅ እንዲሉ ምክንያት በመሆኑ እያቶኮቶኩ ነገር ያቀጣጥላሉ።....

👍6
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...«አስቻለው የሔዋን አባት መሆኑን ማን ነገረሽ አንቺ?» ስትል ጠየቀቻት።
«ነዋ! እንዴ ሆእ!» አለች ሕጻኗ አሁንም፡፡
ሸዋዬ የበለጠ ግራ ገባት፡፡ ህጻኗ ያለ አንድ መነሻ ያን ንግግር
እንዳልተናገረች ገመተች፡፡ ወይዘሮ ዘነቡንና ሰራተኛ'ቸውን አስበቻቸው፡፡ ለጊዜው
ግን «እንዴ! እንዴ.! እንዴ.! እያለች ቤቷን ከፍታ ገባች። አልጋዋ ላይ ቁጭ አለችና
«እንዴት ነው ይኸ ነገር? በማለት ቁና ቁና እየተነፈሰች ለረጂም ጊዜ ቆየች።
ሔዋን የገዛቻቸውን የወጥ ቅመማ ቅመሞች በዘንቢል ይዛ ወደ ቤት ስትገባ የሽዋዬ ዓይን ፈጥጦ አገኘችው፡፡ ሁኔታዋ አላማራትም'ና
«እት አበባ አለቻት ዘንቢሏን እንደያዘች ከፊቷ በመቆም። ሸዋዬ ግን ገልመጥጥ ከማድረግ በቀር ምላሽ ሳትሰጣት ቀረች::
«ምነው?» አለቻት ሔዋን አሁንም፡፡
«አትተይኝም? አለቻት ሽዋዬ ቁጣ በተቀላቀለበት አነጋገር፡፡ ወዲያው ወደ አልጋዋ በመውጣት አንሶላና ብርድ ልብስ ውስጥ ገብታ ሽፍንፍን ብላ ተኛች።
ሔዋን የእህቷ ሀኔታ ግራ አጋባት፡፡ በዚያው ልክ ፈራች፡፡ ድንጋጤም
ተሰማት፡፡ ወደ ጓዳ ገብታ ዘንቢሏን ከአስቀመጠች በኃላ ጓዳው በር በኩል አንገቷን ብቅ እያረገች የሸዋዬን ሁኒታ ትከታተል ጀመር፡፡ አይታ አይታ ምንም ለውጥ
ልታገኝ ባለመቻሏ የምሣሤ ወጥ ስራዋን ጀመረች፡፡
ሽዋዬ ከተኛች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀስቀስ ያለችው የወይዘሮ ዘነቡ የቀትር ቡና ሲወቀጥ ነው፡፡
ወትሮም ቢሆን በተለይ ቅዳሜና እሁድ ከምሳ በኋላ ለሚጠጣው ቡና ሽዋዬ ወደ ወይዘሮ ዘነቡ ቤት ትጠራ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ገና ሳትጠራ ለመሄድ ብድግ አለች፡፡ ያቺ ህጻን በዚያ ቤት ውስጥ ሲወራ ያልሰማችውን ነገር
ከየትም ከምጥታ ልትነግራት እንዳልቻለች ገምታ የወሬዉን ምንጭ ከስሩ ለመጎርጎር ወስነኝ፡፡ ፒጃማ ዓይነት ጀወለል ቢጤ የቤት ልብስ እንደለበሰች ነጠላ
ጫማ አድርጋ ወደዚያው አመራች በጓሮ በኩል ወደ ሳሎን በሚያስገባው የወይዘሮ
ዘነቡ ቤት በር በኩል እየገባች፡-
ደህና ዋላችሁ» አላቻቸው፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ ነጭ በነጭ የሆነ የሐገር ልብሳቸውን ለብሰው ሶፋ ላይ ጉብ ተብለዋል ፡፡ ቀይ ናቸው:: የአንገታቸው ንቅሳት ከቅላታቸው ጋር አለላ መስሎ ይታያል። የአገጭ ስር ጅማቶቻቸው ገተር ገተር ማለት የዕድሜያቸውን መግፋት ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ጥቁር መነፅራቸው ከቀይ ፊታቸው ጋር ደምቆ ሲታይ ዕድሜያቸውን ወደ ኋላ ለመመለስ የሚታገል ይመስላል፡፡ ኑሮአቸውን የቤታቸው
ሁኔታ ያመለክታል፡፡ በዘመናዊ ዕቃ የተሞላ ነው። የሳሎኑ ስፋት ፈረስ ያስጋልባል የሚባል ዓይነት ነው፡፡ በቡና ንግድ የናጠጡ ሀብታም የነበሩት ሟቹ ባለቤታቸው
ያደራጁላቸው ንብረት ነው።
‹ደህና ዋልሽ የኔ ልጅ!» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ «ይኸውልሽ፣ የጎረቤት ደንቡ ይኸ ነው፡፡ ጥሪ የሚፈልግ ከሆነ ግን ንፉግነቱን ያመለክታል፡፡» እሷት ሸዋዬ
ሳትጠራ በመምጣቷ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽ::
«አንዳንዴም ቀላዋጭ ያሰኛል!»
«እሱም የስስታም ሰው አባባል ነው፡፡ በእኛ ቤት ደሞ እንደዚያ ብሎ ነገር የለም፡፡ ለወደፊቱም ይልመድብሽ፡፡» ብለው ፊታቸውን ከሶፋው አጠገብ በነጭ ረኮበት ላይ ወደ ተደረደረው ሲኒ መለስ አደረጉ ሰራተኛቸው ፋንትዩ ቡናውን ጀበና ውስጥ እየጨመረት ናት፡፡
ጉዳይ ስላለኝም ነው ቀድም ብዬ የመጣሁት፡፡» አለች ሽዋዩ በወይዘሮ ዘነቡ ፊትለፊት ሶፋ ላይ ተቀምጣ ዓይን ዓይናቸውን እያየች፡፡
"ምነው" ድህና አሏት ወይዘሮ ዘነቡ ፊታቸውን ወደ ሽዋዩ መለስ
አድርገው
«ተቀይሜብዎታለሁ::»
«ውይ ነኔ ልጅ!ድንግል ትባርክሽ ቅያሜሽን ፊት ለፊት ተነገርሽኝማ
ድንግልም ትወድሻለች፡፡» አሉና «ግን ሳላውቅ ምን እጥፍቼ ይሆን ሲሉ አንገታቸውን ዘመም አድርገው እያዩ ጠየቋት።
«አንድ ነገር እያወቁ ደብቀውኛል።»
«ምን ይሆን የኔ ልጅ»
«በኔ ሰበብ ግቢዎት ሲደፈር እያዩ ዝም ማለትዎ!»
«ምን ያገባው ሰው ነው ግቢዩን የሚደፍረው?»
ብልግና ከተፈጸመበት ያው ተደፈረ ማለት አይደል?»
«የምን ብልግና?»
«አይዋሹኝ እማማ ዘነቡ!»
«ድንግል ትመስክር ምንም የምዋሽው ነገር የለም፡፡ ከንቺ ግን ምን ሰምተሸ ነው?» ሲሉ መነፅራቸውን ወለቅ አድርገው እያዩ ጠየቋት::
«ይቺ የኔ እህት ከዚያ አስቻለው ከሚባል ልጅ ጋር እየባለገች መሆኑን ሳያውቁ ቀርተው ነው?» ስትል ጠየቀቻቸው አንገቷን ጠመም አድርጋ በጎ አስተያየት እየተመለከተቻቸው::
«ውይ! ይኼ ነው እንዴ ነገሩ?» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ ቀለል አድርገው
«ለመሆኑ አንቺ እስተ ዛሬ ምንም የምታውቂው ነገር አልነበረም?» ሲሉ ጠየቋት፡፡
«ምኑን?» አለች ሸዋዬ እንደ አዲስ፡፡ ነገሩ እርግጥ መሆኑ ሲገባት በድንጋጤ ሰውነቷ ሁሉ ክፍልፍል ያለ መሰላት።
«ስለ ሁለቱ ልጆች ፍቅር ነዋ!»
ምናልባት እኩያሞች ስለሆኑ ነው መሰል የእነሱን ፍቅር ልቤ
ይወደዋል፡፡»
«እማማ ዘነቡ!» ስትል ጮኸች ሸዋዬ ድንገት። ዓይኗ በወይዘሮ ዘነቡ ላይ ፍጥጥ አለና መላ ሰውነቷንም ያንቀጠቀጣት ጀመር።
«ወይ የኔ ልጅ!»
«ምን እያወሩ እንደሆነ ያውቃሉ?»
«ዘባርቄ ይሆን እንዴ ልጄን» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ እውነትም ድንግጥ
ብለው ሽዋዬን ትኩር ብለው ያዩዋት ጀመር።
«ቀላል!»
«ምን አልኩኝ?»
«ሊያጋቧቸው እስበዋል እንዴ?»
«ኧረ ምን ቁርጥ አድርጎኝ ልጄ! ቢሆን አይከፋም ማለቴ ነው
እንጂ!»
ሸዋዬ ውስጧ ተቃጠለ፡፡ አረረች። በወይዘሮ ዘነቡ ሀሳብ ከመበሳጨቷ የተነሳ ያን ከሰል ላይ የተጣደ ጀበና ብድግ አድርጋ በመሀል እናታቸው ላይ
ብትከስክሰው እየተመኘች «የሚሉት ነገር ሁሉ ሊገባኝ አልቻለም!» አለቻቸው
ዓይኗን ፍጥጥ፣ ጥርሷን ግጥጥ አድርጋ እያየቻቸው፡፡
ግልጥልጥ አድርጌ እየነገርኩሽ! እንዴት እይገባሽም?» አሏት የሸዋዬ የወስጥ ስሜት ያልገባቸው ወይዘሮ ዘነቡ፡፡
«ቆይ ግን አለችና ሸዋዪ ንዴት ያወላከፈውን ጉሮሮዋን «እህህ» ብላ ሞረደችና የሁለቱን መፋቀር እንዴት አወቁ?» ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
«ድንግል ምስክሬ ናት፤ በበኩሌ ክርና መርፌ ሆንሁ በዓይኔ አላየሁም፡፡ ግን መቸም ትንሽ ሳይያዝ ብዙ አይወራም ብዬ ነው፡፡» ብለው ፊታቸውን ወደ
ረከቦቱ መለስ አደረጉ፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ አንድ ነገር በሆዳቸው አለ። አንድ ቀን አስቻለውና ሔዋን ተዘናግተው ሳይሆን አይቀርም በሩን መለስ እንኳ ሳያደርጉት ቆመው ሲሳሳሙ
ሰራተኛቸው ፋንዩ በበር በኩል አለፍ ስትል አይታቸው ኖሯል። ወይዘሮ ዘነቡ በአቅራቢያዋ ስለነበሩ ወደ ጆሮትእው ጠጋ ብላ በሽንሹክታ ዓይነት እማማ ሂዱ
ወደ እታ አበባ በር አጠገብ፤ የሚያዩት ነገር አለ ብላቸው ነበር፡፡ እሳቸውም ሌላ ነገር መስሏቸው ቤቱን ሰለል እያረጉ በበሩ አጠገብ አለፍ ሲሉ ፋንትዩ ያየችውን
ያያሉ፡፡ በእርግጥ በወቅቱ በፋንትዪ ድርጊት ተቆጥተው ነበር፡፡ ግን ደግሞ ያዩትን
ማመን ችለዋል፡፡
«ለመሆኑ ይህን ወሬ የሚያወራው ማነው?» ስትል ሽዋዬ ጠየቀቻቸው፡፡
ሠፈር ሙሉ ነዋ! እኔ እንደውም የስማሁት በወይዘሮ እልፍነሽ ቤት
ውስጥ ሲወራ ነው፡፡» አሏት።

👍3
«እሳቸውም ያውቃሉ?»
«እንዴ! ቤቷ ወስጥ እየተወራ!?»
ሸዋዬ አንዳች ነገር ሰቅስቆ ያስነሳት ይመስል ከሶፋው ላይ ድንገት ብድግ አለችና በጓሮ በር በኩል ወጥታ ወደ ወይዘሮ እልፍነሽ ቤት አመራች፡፡
ውይ! እንዲህ ያለች ስው ኖራለች እንዴ ልጄ!?» በማለት ወይዘሮ ዘነቡ በመገረም ሠራተኛቸውን ፋንትዬን መልከት አሏት፡፡
«ኧረ እኔ እንጃ እማማ!» አለቻቸው ዕድሜዋ ወደ ሃያ የሚጠጋት የጥቁር ደማም የሆነችው ፋንትዬ፡፡
ቤቱ ቅርብ በመሆኑ ሸዋዬ ከወይዘሮ እልፍነሽ ግቢ የውጭ በር ደርሳ በር ስታንኳኳ ጊዜ አልፈጀባትም። ጀላላ የቤት ውስጥ ቀሚሷን በቀኝ እጇ ወደ ጉያዋ ሰብስብ እንዳረገች ለአንኳኳችው በር ምላሽ ትጠበቅ ጀመር።
«ማነው?» አሏት ወይዘሮ እልፍነሽ እቤታቸው በረንዳ ላይ ቆመው።
«እንግዳ!»
ወይዘሮ እልፍነሽ ወደ ውጭ በር መጥተው በሩን ከፍተው ሸዋዬን
ሲያዩዋት ድንግጥ እንደማለት ብለው «ውይ! የኔው ነሽ
እንዴ? ምነው በዚህ በጠሐይ?» አሏት ፍንጭታቸው ከመስፋቱ የተነሳ ከመሀሉ አንድ ጥርስ የወለቀለት የሚመስል ጥርሳቸውን ብልጭ እያረጉ::
«ኑ ወደ ቤት እንግባ! ጉዳይ አለኝ፡፡» አለቻቸው በችኮላ አነጋገር። በቀጥታ ወደ ቤት እያመራች ወይዘሮ እልፍነሽን በገዛ ቤታቸው ጋበዘቻቸው፡፡ ወይዘሮ
እልፍነሽ እጆቻቸውን በወገባቸው ላይ አጣምረው ከኋላ ከኋላ ተከተሏት።.....

👍2
#ገና_ለገና
ገና ለገና
በቅዱሱ ቀን በልደቱ
ከመጣሽ ብዬ በጠዋቱ፤
ቤቴን ጠርጌ አሳምሬ
እቃዎቼን በወግ ደርድሬ፣
ፈጣሪዬን ተለማምኜ
ዙሪያየን በሺቶ አጥኜ፣
ወደ ደጅ አማትራለሁ
መምጣትሽን እናፍቃለሁ፡፡
ገና ለገና
ትመጫለሽ ብዬ የ'ገና፧
ክራሬን እየደረደርኩ
ጉሮሮዬን እየሞራረድኩ፤
ስትመጪ ወዳለሁበት
ደስ ቢልሽ ብየ ድንገት፤
ስንኞችን እያዋቀርኩ
በዜማ እያንጎራጎርኩ፤
በር በሩን አያለሁ
መምጣትሽን እናፍቃለሁ፡፡
እስካሁን እኮ የኔ ቆንጆ
በልቤ ግዛት ነግሰሽበት - ፍቅርሽ ቀልሶ ጎጆ
አንቺን በጉጉት ስጠብቅ
አይንሽን ማየት ስናፍቅ፣
እድሜየ 'አንድ' ብሎ ብዙ ቢልም
አኗኗርኩ እንጅ ኖርኩ አልልም፡፡
ከመጣሽ ግን
ከቅዱሱ ልደት ጋራ- የኔም ልደት ይሆናል
መኖር እጀምራለሁ- እድሜየ ያኔ አንድ ይላል፡፡
🔘ሙሉቀን ሰለሞን🔘
ገና ለገና
በቅዱሱ ቀን በልደቱ
ከመጣሽ ብዬ በጠዋቱ፤
ቤቴን ጠርጌ አሳምሬ
እቃዎቼን በወግ ደርድሬ፣
ፈጣሪዬን ተለማምኜ
ዙሪያየን በሺቶ አጥኜ፣
ወደ ደጅ አማትራለሁ
መምጣትሽን እናፍቃለሁ፡፡
ገና ለገና
ትመጫለሽ ብዬ የ'ገና፧
ክራሬን እየደረደርኩ
ጉሮሮዬን እየሞራረድኩ፤
ስትመጪ ወዳለሁበት
ደስ ቢልሽ ብየ ድንገት፤
ስንኞችን እያዋቀርኩ
በዜማ እያንጎራጎርኩ፤
በር በሩን አያለሁ
መምጣትሽን እናፍቃለሁ፡፡
እስካሁን እኮ የኔ ቆንጆ
በልቤ ግዛት ነግሰሽበት - ፍቅርሽ ቀልሶ ጎጆ
አንቺን በጉጉት ስጠብቅ
አይንሽን ማየት ስናፍቅ፣
እድሜየ 'አንድ' ብሎ ብዙ ቢልም
አኗኗርኩ እንጅ ኖርኩ አልልም፡፡
ከመጣሽ ግን
ከቅዱሱ ልደት ጋራ- የኔም ልደት ይሆናል
መኖር እጀምራለሁ- እድሜየ ያኔ አንድ ይላል፡፡
🔘ሙሉቀን ሰለሞን🔘
👍2❤1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....በዚህ ላይ ደግሞ አቶ አባይነህ ስራቸው ተጋልጦ ከሥልጣናቸው ዝቅ እንዲሉ ምክንያት በመሆኑ እያቶኮቶኩ ነገር ያቀጣጥላሉ።
እውነትህን ነው ይሄ ጦሰኛ ጦሳችንን ይዞ ካልሄደ በስተቀር ምን ሰላም እናገኛለን?!” በማለት ብሶቱን ያባብሳሉ፡፡ በዚህ ምክንያት የምረቃ በአሉ ለጌትነት ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ ልዩ የደስታ ቀን ሆኖ ሲውል
ለልኡልሰገድ ግን መርዶ ነው የሆነበት። ይህንን መጥፎ ስሜቱን ለማብረድ ደግሞ ሰሞኑን ሲሯሯጥ ሰንብቷል። ትጉህ ሰራተኛነቱ እንኳንስ አብረውት በሚሰሩ የስራ ባልደረቦቹ ቀርቶ በሚጠሉት ሰራተኞች ጭምር
የታወቀ ነው፡፡ ዲግሪውን ይዞ ሲመጣ ያንን እንደቀላዋጭ ውሻ ከንፈሩን እየላሰ ሲጎመዥለት የኖረውን የሂሳብ ዋና ክፍል ሃላፊ ቦታ እንደ ሚወስደው የታወቀ ነው፡፡ በሱ እምነት ያንን እድገት ለማግኘት ጌትነት ከዚያ አካባቢ ገለል ማለት አለበት።እሱ ገለል እስካላለ ድረስ ሊረጋጋ አይችልም፡፡ አንዳንዱ ሰው እድገት ለማግኘት ሲል ከፊት ለፊቱ የቆመው ሰው በሆነ ምክንያት ገለል እንዲልለት ይመኛል። ፀሎት ያደርሳል፡በዚህ የተነሳ ከፊት ለፊቱ በሚታየው የተስፋ ጭላንጭል ላይ የተንጠለጠለ የምኞት እስረኛ ሆኖ ይቀራል።ከጭላንጭሉ በስተጀርባ ዕድል ደማቅ የብርሃን ውጋጋኗን አብርታ እየጠበቀችው መሆኑን በፍጹም አያስብም፡፡ በፈጠራት ጠባብ ዓለም ውስጥ ራሱን ወስኖ በማስቀረት ለትንሹ
ነገር ሲጓጓ የሱ የነበረው ትልቁና መልካሙ ነገር በድቅድቁ ጨለማ
ውስጥ ተውጦ ይቀራል። ልኡልሰገድም ተምሮ ራሱን በመለወጥ ከዚያ የተሻለ ወፍራም እንጀራ መብላት ሲችል የተመኛትን ትንሽ ሹመት እንዳይቀማው በመስጋት የጌትነትን ሞት ተመኘ፡፡ በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይም ሳይገኝ ቀረ። ጌትነት አለቃው በጥሪው ቦታ ሳይገኝ በመቅረቱ ቅር ቢለውም ጥሪውን አክብረው የመጡ ጓደኞቹ እቅፍ አበባ እያበረከቱ ሲስሙት ተፅናና፡፡ እናቱን እቅፍ እያደረገ ከአማረች እና ከቤተሰቦቿ ጋር እንደዚሁም ከትምህርት ቤት ጓደኞቹና ከሽመልስ ጋር በርከት ያሉ ፎቶ
ግራፎችን ተነሱ፡፡ እናቱ እጮኛነቷን ባታውቅም የልጇ ፍቅረኛ መሆን
ዋን ገምታ ከአማረች ጋር በፍቅር እየተቃቀፈች በርከት ያሉ የማስታወሻፎቶግራፎችን ስትነሳ ዋለች::
የፎቶ ግራፍ ስነ ስርአቱ እንዳበቃ ጥሪውን አክብረው በመጡ ጓደኞቹ ታጅቦ ከእናትና ከእህቱ ጋርም ተያይዘው ወደ መኖሪያ ቤቱ ሄዱ። ጌትነት እምብዛም በማይወደው ሰፈር ውስጥ የተከራያት ጎጆውን የወደዳት ገና ዛሬ ነው፡፡ ዛሬ ከጓደኞቹና ከሚወዳቸው ቤተሰቦቹ ጋር ደማቅ የደስታ ጊዜ እያሳለፈባት ነውና ሰፈሩን ዘንግቶ ጎጆውን ቢወድ የሚደንቅ አይሆንም ጌትነት የተከራያት ቤት መሀሏ በመጋረጃ ተከፍሎ ከመጋረጃው ውስጥ
አንድ ሰፊ የሞዝቮልድ አልጋና ዘይኑ የምትተኛበት አንድ ታጣፊ
አልጋ አለ፡፡ የወዲህኛው ክፍል በሳሎንነት የሚጠቀሙበት ሲሆን አንድ ትልቅ ጠረጴዛና አራት የእንጨት ወንበሮች መሀል ላይ ጉብ ብለዋል።
ከጥግ ላይ አንድ አግዳሚ ወንበር አለ፡፡ ቤቱ ከውጭ እንደሚታየው
አይደለም፡፡ በዘይኑ ከፍተኛ ጥንቃቄና ጥረት ፅዳቱ ተጠብቆ ያምራል።
ዘይኑና እናቷ ላባቸውን ጠብ አድርገው የጠመቁት ጠላ ከውስኪ ያስንቃል።
"በሉ አረፍ በሉ!" አለች የጌትነት እናት ለመስተንግዶው ተፍ ተፍ
እያለች። ጌትነት ግን ልቡ ወደ አማረች በሯል። የሱን ደሳሳ ጎጆ የምታያት ዛሬ ነበር፡፡ከወዳጅ ዘመዱ ጋር በይፋ የሚያስተዋውቃትና በቅርቡ
የሚያገባት እጮኛው መሆንኗ የሚያበስርበት ቆንጆ አጋጣሚ ዛሬ በደስታው ቀን ነበር፡፡ ግን ምን ያደርጋል? እሷም ተመራቂ ነችና በወላጆቿ ቤት ከሠርግ መልስ ግብዣ ተደርጎ ዓለም እየታየ በመሆኑ አልተቻለም፡፡
“ሰውዬው በል እንጂ ምሳችንን ቶሎ አስቀርብልን፡፡ አንተ ልብህ ወዴት እንደኮበለለ አውቄዋለሁ"ባልቻ እየሳቀ በነገር ወጋ አደረገው፡፡
"አንተ ቡዳ! ምንድነው የምታውቀው ደግሞ?" እሱም ሳቀና ጎሽመው ባልቻ የአማረችና የጌትነትን ፍቅርን ጠንቅቆ የሚያውቅ የትምህርት ቤት
ጓደኛው ነው።እሱም የሚቀጥለው ዓመት ተመራቂ ነው፡፡
“ዘይንዬ! እባክሽ ገላግይኝ ሰዎቹ ጠላው አናታቸው ላይ እየወጣ ነው መስለኝ ምሳ! ምሳ!! ቶሎ በይ!” አለና ዘይኑን ተጣራ። ዘይኑ ከእናቷ ጋር ተጋግዛ በፍጥነት ምሳ አቀረበችና መመገብ ጀመሩ።
"እንግዲህ እርስዎም እዚሁ ከልጆችዎ ጋር መጠቃለል አለብዎት እማማ በመመላለስ ይጎዳሉ..." አለ ዘበነ፡፡
“አይ የኔ ልጅ እዚህ ከልጆቼ ጋር መቀመጡን ጠልቼው መሰለህ ? ደስታውን አልችለውም ነበር፡፡ እነሱን ተለይቼ የምኖረው ኑሮ አይደለም፡፡
በሬሳ ውስጥ አስሮ ያስቀመጠኝ የሟች አባታቸው ቃል ነው "
“እንዴ?! ለምን?” ባልቻና ዘበነ በአንድ ላይ ጠየቁ፡፡
“መኩሪያ አሁን ያለሁበትን ቤት ተአባቱ የወረሰው ነው። የአባቱ አስክሬን ከወጣበት ቤት ነው የሱም የወጣው፡፡ ታዲያ ሊሞት ሲያጣጥር ከዚች ቀዬ ንቅንቅ እንዳትይ መታመሚያሽ፣ መሞቻሽ መቀበሪያሽ እዚች ጎጆ እዚች መንድር ውስጥ ይሁን አደራ! ብሎ አስሮኝ ነው ያረፈው"
በሬሳን መልቀቅ የማትችልበትን ምክንያት አጫወተቻቸው። ለነገሩ በመኩሪያ ቃል አሳበበች እንጂ ያቺን ጎጆ መልቀቅ የማትፈልግበት እንዲህ ነው ብላ ልትገልፀው የማትችለው የራሷ ምክንያት ነበራት፡፡ጌትነት ሽመልስን ለእናቱ ሲያስተዋውቃት "እማዬ ሽመልስ ማለት እሱ ነው በህይወቴም ሆነ በህይወታችን ውስጥ ታላቅ ለውጥን ያስገኘልን ወንድሜ ነው፡፡
ስለ እውነት ሲል የተሟገተ፡፡ የገባውን ቃል ያከበረ.." ቃላት አጥረውት ስለ ሽመልስ ማንነት ገለፀላት፡፡
“እሰይ! እስይ! እግዚአብሔር የሱንም ኑሮ እንደዚሁ ያሳምርለት። ለሰው ደግ መስራት ከምድር ባይገኝ እሱ ፈጣሪ ውለታውን በሰማይ ይከፍለዋል" ሽመልስን አመሰገነችለት፡፡ በዚህ ሁኔታ በተሰባስቡ ወዳጅ ዘመዶቹና ጎረቤቶቹ የጌትነት ቤት ተጣባ ደስታውን ተደስተው ፅዋቸውን
እያነሱ ሲያጋጩ ሲጫወቱ ሲጨፍሩ ዋሉ.....
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የወይዘሮ ባንቺደሩ ጎጆ የሞት ጥላ እያንዣበበባት ነው። ጨካኙ
ሞት ህፃን፣ አዋቂ፣ ሴት፣ ወንድ አይመርጥም፡፡ እንደ ቋያ እሳት ያገ
ኘውን በእጁ የወደቀለትን ሁሉ እየበላ እያኘከ መሄድ ነው። ምህረት የለም፡፡ አሮጊቷ ወይዘሮ ባንቺደሩ በአንድ በኩል የዕድሜ ጫና በሌላ በኩል ደግሞ የሙት ልጆችና እናታቸው ጥላቸው የኮበለለች ሁለት ህፃናትን ለማሳደግ መከራቸውን እያዩ ናቸው፡፡ የአያትነት ግዴታ በላያቸው ወድቆ በስተርጅና የልጃቸውን ልጆች በህይወት ለማቆየት ብዙ ደከሙ፡፡ በበሽታ ክፉኛ የተደቆሰው ምትኬ እናቱንና አባቱን ክፉኛ እየናፈቀ አባቱን በአካል ሲያጣው እየተሳቀቀ እናቱ እንደ ድሮው እንድትሆንለት እየተመኘ እናቱ ስትጨክንበት፣ ሀሳብ አደቀቀውና፣ ተሳቀቀና ለጋ
የህፃንነት አዕምሮው በሀዘን ቆስለ። ቀስ በቀስ እየመነመነ በሽተኛ እየሆነ ሄደ፡፡ አሮጊቷ በአብዛኛው የሚሰጡት ርዳታ እንባቸውን ማፍሰስ ብቻ
ነበር። "አብዬ የኔ ጌታ አይዞህ!...እኔ ልጨነቅ. እኔ ልጠበብ እህ!...”ምትኬ ግን በሳቸው እንባ ሊጠነክርና ሊለመልም አልቻለም፡፡

እህ! እህ!.. እህ!... እማማ... እማዬ...አትመታም?እማዬ ናፈከችኝ? በሽታው እየበረታበት ሲሄድ የእናቱ ስም በጭራሽ ከአፉ አልለይ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ አሮጊቷ አንጀታቸው እየተገላበጠ ሆድ ይብሳቸውና ዐይናቸው እስከሚጠፋ ድረስ ያለቅሳሉ፡ ማልቀስ ማልቀስ ማልቀስ
በዚህ ሁኔታ ሶስት ሣምንታት አለፉ። ምትኬ እየባሰበት ሄደ። ታናሽእህቱም አብሯት የሚጫወተው ጓደኛዋ ቢደላቸውም ቢከፋቸውም የሚ
ያሳስቃት ታላቅ ወንድሟ በበሽታ ተለክፎ የአልጋ ቁራኛ ከሆነ ወዲህ
ሀዘኗ ከብዷል። ብቸኝነት ጎድቷታል። አያት ቢቸግራቸው ጠንቋይ ቤት ይዘውት ሄዱ፡፡ ጠንቋዩ የተቀቀለ ጫት አውዛ ፊቱ ላይ እየተፋ በወጠጤ ፍየል ድምጥ “አብሽር! አብሽር! ተፈውሷል! ድኗል ልጅሽ.... ጥቁር
ዶሮ ሰላዩ ላይ አዙረሽ እረጂና ደሙን እየፈነጠቅሽ ፊቱን እጠቢው ስቡን አቅልጠሽ አውጪው! ይሄን በአንገቱ ላይ እሰሪለት!" የተባሉትን ሁሉ አደረጉ፡፡ ምትኬ ግን ሊሻለው አልቻለም፡፡ በመጨረሻ ላይ ተስፋ
ቆረጡ፡፡ የቀራቸው ዘመናዊ ህክምና ብቻ ነበር፡፡ ለመጨረሻ ሙከራ ወደ ሀኪም ቤት ይዘውት ሄዱ፡፡ በወቅቱ የህክምና ርዳታ ተደርጎለት ቢሆን ኖሮ ምናልባት የመዳን ተስፋ ሊኖረው በቻለ ነበር። ወቅታዊ የሆነ የህክምና ርዳታ ባለማግኘቱ ተዳክሟል፡፡ በጊዜው ያልተሰጠ ህክምና ተስፋ
የሌለው ህክምና ሆነ፡፡ የሀኪም መድሃኒት ከህይወት ወደ ሞት የሚደረገውን ጉዞ ይከላከላል እንደሁ እንጂ ከሞት ውስጥ ህይወትን አያስገኝም፡፡
መታመሙን መሰቃየቱን እንጂ ከህመሙ በኋላ ወዴት እንደሚሄድ የማያውቀውን ህፃን ስለሞት ለደቂቃ እንኳ አስቦ የማያውቀውን ጨቅላ
አስፈሪው ሞት ሊበላው ተዘጋጅቷል። የሚወዳት ታናሽ እህቱን ጥሎ..የሚወዱት አያቱን ከድቶ እናቱ ሳታየው ወደ አባቱ ዘንድ ሊኮበልል. እንደ ጋለ ካውያ አተኮስ፡፡ ተፋጀ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ እንደበረዶ
ቀዘቀዘ፡፡ አባቱ ምትኬ ብሎ ስም ያወጣለት የሚተካኝ ልጅ አገኘሁ ብሎ ነበር፡፡ ምትኬ ግን አባቱን ተክቶ በዚች ምድር ላይ አስር ዓመት እንኳ ለመኖር ሳይታደል እንደተሳቀቀ እንደተሰቃየ በአጭሩ ተቀጨና አባቱ የለበሰውን አፈር ለበሰ፡፡ እናቴነሽ ያለወንድም ቀረች።አሁን ገናሞት ምን
እንደሆነ አወቀች፡፡ ወንድሟ እንደማይመለስ ተረዳች። አባቷን የበላው አውሬ ምትኬን የምታፈቅረው ወንድሟን መብላቱን አባቷ ወጥቶ እን
ደቀረ ሁሉ ምትኬም ዳግም ላይመለስ መሄዱ በደመ ነፍስ ታወቃትና ትንሿ ልጅ በሀዘን ሙሽሽ አለች። ወይዘሮ ባንቺደሩ እርጅና ባዳከመው አቅማቸው የልጃቸውን ልጅ ቀበሩ። እናታቸው ሳትሰማ ሳታውቅ ልጅዋ
በመሞቱ ለልጃቸው አዘኑላት። አለቀሱላት፡፡ ነዋሪውም ዘንግቶት የነበረውን የዓለሚቱን ነገር እንደ አዲስ የመወያያ ርዕስ አደረገው።
"ሽፍታ ወዳ ባሏን አስገድላ ልጆቿን ሜዳ ላይ በትና ኮበለለች.. አቤት!
አቤት! ምን አይነቱን አንጀት ነው ለሷስ የሰጣት?! ሞታቸውን በሚጠባበቁ አሮጊት እናቷ ላይ ወርውራቸው የሄደች ዕለት ነው የሞቱት። አፈር አልተጫነባቸውም እንጂ የቁም ሞት ከሞቱ ቆይተዋል፡፡ አንደኛውን ተገላገለው፡፡ ሴቷም ልጅ ዕድሏ ይሄው ነው" ለቀብር የወጣው ሁሉ ተነጋገረባት። ለቀረችው ህፃን ከንፈራቸውን መጠጡላት። በትዳር መካከል በተፈጠረው ውስልትና ጠንቅ ምክንያት በመጀመሪያ አባት ቀጥሎ ደግሞ ልጅ ሰለባዎች ሆኑ። ጎንቻ የብዙ ሰው ቤት አፍርሷል። ህይወትን ለመኖር ደፋ ቀና እያሉ ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት የሚባዝኑትን በአሰቃቂ ሁኔታ
እየዘረፈ በርካታ ቤተሰቦችን ያለ ረዳት አስቀርቷል፡፡ የህብረተሰቡ ሸክም እንዲሆኑና ህይወታቸው እንዲጠፋ አድርጓል፡፡
ጎንቻ !! የክፉ ስራ መሀንዲስ፣ የሰላማዊ ህይወት በጥባጭ... በፈፀማቸው በርካታ ወንጀሎች የብዙዎች ቤት ፈርሷል። ትናንትና በአባቱ ላይ በሰነዘረው የሞት በትር ምክንያት ጨቅላውን ህፃን ያለ አባት፣ ያለ ተንከባካቢ አስቀርቶ፣ እናቱን አስኮብልሎ ለጨካኙ ሞት አሳልፎ እንደሰጠው ሁሉ ዛሬ ደግሞ የሌላ ሰው ህይወት ሊቀጥፍ የሌላ ሰው ተስፋ ሊያጨ ልም ተዘጋጅቷል፡፡
ለሰው ልጆች መልም አሳቢ፣ በስነምግባር ተኮትኩቶ ያደገ፣ ከሱ ሌላ መመኪያና ረዳት የሌላቸውንና እሱ ከሌላ የእነሱም ህይወት ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚወድቀውን የድሃ ቤተሰብ ምሰሶ ገርስሶ ለመጣል አሰፍስ
ፏል ...
ዓለሚቱ ወረተኛዋ ዓለሚቱ… የፍቅር ሌባዋ ዓለሚቱ የገበየሁን ፍቅር ሰርቃ ለጎንቻ ያስኮመኮመችው ዓለሚቱ... ሌብነቷ መከራ፣ አመንዝራነቷ ረቂቅ ነው፡፡ ከጎንቻ እየሰረቀች ፍቅሯን ለብዙ ሰው በሚስጥር አቅ
ምሳለች፡፡ ኢተያ ውስጥ አደባድባለች። አፈናክታለች። ጎንቻ ግን ይሄንን ሁሉ አያውቅም ነበር፡፡ እሱ ገበየሁን እንደሰረቀ ሁሉ ሌሎች እሱን እየሰረቁት መሆኑን በፍፁም አያውቅም ነበር። አለሚቱን ማን ያውቅባታል?
በጣፋጭነቷ የሰው ልብ እየሰወረች በዐይኖቿ እየገለደች…ከአፏ እንደ ማር በሚንጠባጠቡ ቃላቶቿ እያደነዘዘች የመርዝ ብልቃጥ መሆኗን ማን ያውቅባታል?" ካንተ ሌላ ወንድ... ከገበየሁ እስር ነፃ ካወጣኸኝ ከጀ
ግናው ጎንቻ ሌላ ጭኔን ማንም አይዳብሰውም" ብላዋለች። ሱሪ መሳይ ቀሚስ የለበሰ ሁሉ! እያለች ሌላውን ወንድ እያናናቀች ከሱ ሌላ ጀግና፣ከሱ ሌላ አንበሳ አለመኖሩን መስክራለታለች መሸፈቱ የጀግና ልጅ ስራ መሆኑን በኩራት ገልፃለታለች፡ ውስጥ ውስጡን የልቧን እያደረሰች
ከሱ ሌላ ማንንም እንደማትመኝ አሳምና ጥርጣሬ እንዳያድርበት ደህና አድርጋ አፍዝዛዋለች፡፡ ዛሬም በሱ የቡድን መሪነት ውስጥ በአባልነት በታቀፈው በሸጋው አንበሴ ቁመናና የዐይኖቹ ውበት ተማርካ በመልከ መልካምነቱ ልቧ ተሸንፎ በፍቅሩ ነዳለት ጎንቻን ደብቃ ፍቅሯን እያስኮመኮመችው አለማቸውን እየቀጩ ነው።....

#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...ወይዘሮ እልፍነሽ አጭር ወፍራም ናቸው፣ ከወገባቸው ጎንበስ ያሉ ፀጉራቸወም በአጭርና ሸበቶ፤ በባህሪያቸው ወራኛ የሚባሉ ናቸው፤ አንዷን ከአስር
በላይ የሚያባዙ፤ ለውሸት ልክ የሌላቸው:: ከዚሁ ባህሪያቸው በመነጨ የጎረቤት ሰው ሁሉ እልፍነሽ ወሬ እፈሽ ይላቸዋል፡፡
ሽዋዬ ቤት ወስጥ ገብታ ራሷ ወንበር ሳብ አድርጋ ስትቀመጥ ወይዘሮ እልፍነሽ እጆቻቸውን በወገባቸው ላይ አጣምረው ከፊቷ ቆሙ፡፡ ለወሬው በጣም
የቸኮሉ ይመስላለ::
«እንደው ምን አግኝቶሽ ይሆን ልጄ?» ሲሉ ጠየቋት::
«ቁጭ በሏ!» አለቻቸው ሸዋዬ ከንፈሯን በምላሷ እያራስች፡፡ የእጆቿን መዳፎች አጋጥማ በጉልበቶቿ መሀል አጥብቃ ይዛቸዋለች፡፡
ወይዘሮ እልፍነሽ ለወሬው ሰፍ ብለዋል። ጠበብ ካለች አፋቸው ውስጥ ከአራት በላይ የማይታዩ ጥርሶቻቸውን ገለጥ አድርገው ፈገግ እያሉ ተቀመጡና፡-
«እስቲ ንገሪኝ ልጄ!» አሏት፡፡
«ጉድ የምትሰሩኝ እኮ እናንተ ጎረቤቶቼ ናችሁ!» አለቻቸው ሽዋዬ ምላሷን በከንፈሮቿ ዳር እና ዳር ግራና ቀኝ ወጣ ገባ እያረገች ወይዘሮ እልፍነሽ ደረታቸውን በእጃቸው ደሰቅ አረጉና «ውይ በሞትኩት! ምነው? ምን አደረግን?»
«የእህቴ ህይወት ሲበላሽ እያያችሁ ዝም ትሉኛላችሁ?»
«ምነው? ምን አገኛት?»
«አርግዛ ትምህርቷን ብታቋርጥስ?»
«እንዴ!» አሉ ወይዘሮ አልፍነሽ ነገሩን እንደማቃለል ዓይነት በሚያስመስል አነጋገር፡፡ «እጮኛዋ ባለሙያ አይደል እንዴ! ችግር ቢፈጥር ኣሽቀንጥሮ ይጥልላት የለ!» ካሉ በኋላ አፋቸውን የበለጠ ወደ ሸዋዬ ጠጋ በማድረግ «አአሁን ቀደምስ
ችግሩ ተፈጥሮ ገላገላት ተብሎ ብለው ሳይጨርሰ ሽዋዬ ቀደመቻቸው::
«ምን አሉ?» አለች ዓይኗን ፍጥጥ አድርጋ እያየቻቸው። እጮኛዋ ያሏት ነገር ከተቀመጠችበት አንጥሮ ሊያነሳት ሲል ደሞ የወርጃ ነገር ጨመሩባትና
በአለችበት ኩርምትምት አለች።
«ኧረ ተይኝ እቴ!» ብለው ወይዘሮ እልፍነሽ እንደ መግደርደር ዓይነት ወደ ውጭጉዳይ አየት ካደረጉ በኋላ እንደገና ወደ ሽዋዬ መለስ በማለት «በአንቺ እህት ስንት
ልጃገረዶች እየቀኑባት ደሞ እንዲህ ያለ ሥጋት ይደረብሽ እንዴ? ሆሆይ...»
ሸዋዬ በባሰ ድንጋጤ ሰውነቷ ሽምቅቅ ብሎ መንፈሷ ድክም፣ ልቧም ስንፍ አለና በተራዘመ የቃል አወጣጥ «አ ሶ ር ዳ ለ ች ነው የሚሉኝ ስትል ጠየቀቻቸው::
«ገላግሏት!»
ሸዋዬ አሁንም ድክም ባለ መንፈስ «አ መ ስ ግ ና ለ ሀ:!» አለቻቸውና
ከተቀመጠችበት በቀስታ ብድግ አለች። ወይዘሮ እልፍነሽ እወነትም አፍሰው አቃሟት፡፡
«ጠሐይ ይብረድልሽ እንጂ!» አሏት ወይዘሮ እልፍነሽ እኚያኑ
ጥርሶቻቸውን ገለጥ እያደረጉ፡፡
«ቤቴ ሄጄ ማረፍ እፈልጋለሁ። ደህና ዋሉ!» ብላቸው ወጣች፡፡
ወይዘሮ እልፍነሽ አሁንም እጃቸውን በወገባቸው ላይ አጣምረው እስር እስሯ እየሄዱ በሹክሹክታ ዓይነት «እይው ልጄ፧ እኔ እኮ ቀድሜ ጠርጥሪያለሁ፣
ብታይ አንቺ እግርሽ ወጣ ያለ ጊዜ እሱ ዘሎ ጥልቅ! ትናት ዘሎ ጥልቅ! ዛሬም ዘሎ ጥልቅ ሲል እያየሁ ሆዴ በጣም ይፈራ ነበር፡፡» አሏት፡፡
ከቤት ይዟት ወጥቶ ያውቃል?»
«ኧረ በገዛ ቤትሽ ውስጥ እቴ! ደሞ የምን ወደ ውጪ ሆይ…?» አሉና
«ማናት ይቺ እቴ ስሟን አምጪልኝ፡ ይቺ የወይዘሮ ዘነቡ ሠራተኛ?»
«ፋንታዬ?»
“እ! እሷ ቲራቲር ስታይ አይደል እንዴ የምትውለው፤ እሷን ብትጠይቂያት እኮ ጉድ ትነግርሻለች፡፡»
ሽዋዬ ነገሩ ሁሉ ገባት። ወሬው ሁሉ ከፋንትዬ እንደሚመነጭ ተረዳች፡፡
ይሁንና ብትጠይቃት ደፍራ እውነቱን ላትነግራት እንደምትችል ገመተች። ለነገሩ ወሬ በቅቷታል፡፡ ከእንግዲህ ታፈሡ ብቻ ቀረቻት፣ በእሷ ግምት አስቻለውና
ሔዋንን የምታገናኝ ታፈሡ እንደምትሆን በማመን፡፡
ሸዋዬ በዕለቱ እህል ውሃ አላሰኛትም ሔዋን ምሳ አዘጋጅታ እየጠበቀቻት ቢሆንም ቤቷ እንደ ደረሰች የሔዋንን ዓይኖች ቀና ብላ እንኳ ሳታይ በቀጥታ አልጋዋ ላይ ወጥታ ጥቅልል ብላ ተኛች፡፡ በዚያው መሽ፡፡ ቀኑም በለሊት ተተካ፡፡ ያ ሁሉ ሆና ሽዋዬ በዓይኗ ላይ እንቅልፍ አልዞረም፡፡ ይልቁንም እንኳን ራሷ ለአልጋዋም አልመቻት ብላ በየደቂቃው በመገላበጥ ስታንቋቋት አደረች፡፡
በማግስቱ ጠዋት ሔዋን ወደ ትምህርት ቤት ስትሄድ ልክ እግሯ ከቤት እንደ ወጣ ሸዋዬ ልታደርግ ስታስብ ከአደረችው እቅድ ውስጥ የመጀመሪያውን መፈፀም ጀመረች:: ሔዋንና አስቻለው የተፃፃፉት የፍቅር ደብዳቤ ካለ ብላ ደብተሮቿን መፈተሽ ያዘች ፤ ገፅ በገፅ እያገላበጠች፣ የደብተሮቹን መሸፈኛ እየገለጠችና ዘቅዝቃ እያራገፈች በረበረቻቸው። የሔዋን ቅያሪ ልብሶች
አልቀሯትም፡፡ ኪሶቿን ሁሉ ዳበሰቻቸው፡፡ ግን ምንም ነገር ሳታገኝ ቀረች፡፡
ሲደክማት አልጋዋ ላይ ቁጭ አለች:: ግን ደግሞ አንድ ነገር ትዝ አላት። የድካሟ ምክንያት ርሀብ ጭምር ነው:: ከትናንት ምሣ ጀምሮ እስከ ዛሬ ቁርስ ሰዓት ድረስ ምንም አልቀመሰችምና ወደ ምግብ አዘነበለች፡፡ በእርግጥም ከነውዝፉ አጠቃለለችው:: በንዴት ውስጥ ስለነበረች አጎራረሷ እንኳ ጤናማ አልነበረም ቶሎ
ቶሎ ጎሰጎሰችው።
ከታፈሡ ጋር የምትገናኝበት ስዓት በመከራ ደረሰ። ጠዋት ወደ ታፈሡ ቤት መሄድ አልቃጣችም፤ በአንድ በኩል ለጠብ ነው የምትፈልጋት! በሌላ በኩል ደግሞ አስቻለውም ቢሆን ከታፈሡ ቤት አይጠፋምና፡፡ በሁለተኛው ፈረቃ
የዕረፍት ሰዓት ነው ከታፈሡ ጋር የተገናኘችው፡፡ በዲላ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ መሀል ላይ በምትገኘው ባንዲራ ሥር ሆና
ጠራቻትና አብረው እንደተቀመጡ ሸዋዬ ዓይኗን እፍጣ፣ ጥርሷን አግጣ፡-
«ስሚ አንቺ!» አለቻት፡፡
«ወይ» ታፈሡ ድንግጥ በማለት፡፡
«እህቴን ከአበ-ልጅሽ ጋር አቃጥረሽ አበላሽሻት አይደል?? »
«ኦ» ታፈሡ ሁለመናዋን ነዘር እያደረጋት።
« አላደረኩም በያ?»
«ጓደኛዬ ምን እያልሽ ነው?»
«ኧረ ጓደኛሽን ወዲያ ፈልጊ!»
«ከአንቺ የበለጠ ምን ጓደኛ እለኝ?» አለቻት ታፈሡ ነገሩ እየገባት ሂዶ ፈገግ እያለች።
«ጥሩ አቃጣሪ ኖረሻል፤ ጉድሽ ሁሉ ወጣ?»
«አቀዛሽው ሽዋዬ»
« አቃጣሪ ማለቱ? እንዲያውም ሲያንስሽ ነው»
«ጨምሪልኛ ኪም ኪም ኪም ኪም!
« አሁን ሳቂ! የምታለቅሽበት ጊዜ ይመጣል::»
«እጠብቃለኋ ኪም ኪም ኪም ኪም» ታፈው እሁንም፡፡
«እንዲህ ስትንከተከች ትንሽም አታፍሪ?» ሽዋዬ ውስጧ ብግን እያለ፡፡
«ምንም አላፍር ሽዋዬ! ምንም በማላውቀው ነገር ይህን ያህል ካልሽኝ ምናልባት ሁለቱ ተዋድደው ከአገኘኋቸው እንዲያውም እንዲያውም አጋባቸዋለሁ::»
«ኣ» ሸዋዬ ቆሽቷ እያረረ፡፡
«በእርግጥ ሁለቱ ተዋደው ከሆነ ወደ ኋላ አልልም! ታይኝ የለ!» ብላት ታፈሡ ከሸዋዬ ፊት ዘወር አለች።
ሸዋዬ ግራ ግብት እንዳላት ነበር ከዚያ በኋላ ያለውን ጊዜ ያሳለፈችው፡፡
የታፈሠ ሁኔታ ስለ ሔዋንና አስቻለው ፍቅር ብዙም ፍንጭ አልሰጣትም።
በእርግጥ ስለዚሁ ጉዳይ ባለፈው ለሊት በምታስላስልበት ጊዜ በተለይ ከወይዘሮ እልፍነሽ የሰማችው ወሬ ለጊዘው ቢያናድዳትም በእውነትነቱ ግን ተጠራጥረዋለች፡፡