#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...ይህ ትውውቅ በተከናወነ ከሁለት ወራት በኋላ የተፈጠረ አጋጣሚ ነው ለዛሬ የአስቻለው ጭንቀት መነሻ የሆነው። በዚያው በዋርካ ምግብ ቤት ቁጭ ብሎ ያንን ሁኔታ በዓይነ ህሊናው ይመለከተው ጀመር።
ትዝ ይለዋል፤ በነሐሴ ወር አጋማሽ በዕለተ እሁድ ነበር። አስቻለው ቤቱ ውስጥ አረፋፍዶ ወደ ምሳ ሲሄድ እግረ መንገዱን ከታፊሡ ቤት ጎራ ይላል።ከቤት ሲገባ ታፈሡና አንዲት እንግዳ ልጅ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለው ሲጨዋወቱ ያገኛቸዋል፡፡ እሱ ሲገባ ሁሉቱም ብድግ ብለው ተቀበሉት፡፡ ታፈሡ ወደ እንግዳዋ ልጅ እያመለከተች
“ተዋወቃት አስቹ የሽዋዬ እህት ናት» እለችው፡፡
«አስቻለው ካሰ - ሔዋን ተስፋዬ ተባብለው ስም በመለዋወጥ
ተጨባበጡ፡፡ አስቻለው ለአፍታ ቆይታ አብሮአቸው ሶፋ ላይ ተቀመጠ፡፡
"ሽዋዬን አውቅሃት አይደል?" አለችው ታፈሡ::
"ባለፈው ከአዋሳ አብረን የመጣነው መሰለችኝ"
"አዎ፣ የክረምቱን ዕረፍት ቤተሰቦቿ ጋር ክብረ መንግስት አሳልፋ ትናንት መጣች::
"የታለች ታዲያ?"
«እዚያ ስምንተኛ መንገድ ላይ ወይዘሮ ዘነቡ አስግድ ከሚባሉ ሴት ግቢ ውስጥ ሁለት ክፍሎች ያሉት ሰርቢስ ቤት እግኝቼላት ስለ ኪራይ ልትነጋገር ሄዳ ነው።
እንዴት ያሉ ፅድት ያሉ ክፍሎች መስሎህ፡ ስፋታቸውም በቂ ነው» አለችና ታፈሠ ወደ ሔዋን ዞር ብላ ፈገግ እያለች አይበቃችሁም የኔ ቆንጆ?» ስትል ጠየቀቻት።
"ኧረ ይበቃል።" አለች ሔዋንም ጎንበስ ብላ ፈገግ በማለት፡፡
"እህቷ ጋ ሆና ልትማር ነው የመጣችው፡፡ የአሥራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ናት" አለች ታፈሡ አሁንም።
"ጨርሳለቻ!" አለ አስቻለውም ሔዋንን በዓይኑ ቃኘት እያደረገ::
ሔዋን ዕድሜዋ ወደ አሥራ ዘጠኝ ዓመት ይጠጋል፡፡ መልኳ ድምቅ ያለ ቀይ ነው:: እንደ ጨረቃ ክብ በሆነ ፊቷ ላይ ዓይኖቿ እንደ ኮከብ ያበራሉ፡፡ የጥቁር ዟማ ፀጉሯን ለሁለት ከፍላ በመጎንጎን ያለ ጡት መያዣ ጉብ ጉብ ባሉ ጡቶቿ ላይ
ለቃቸዋለች። ደረቷ ሙልት ያለ፣ አፍንጫዋ ሰልከክ ብሎ የወረደና ቀዳዳዎቹ ሰፋ ሰፋ ያሉ ናቸው። ጥርስና ከንፈሮቿ የውብት ውድድር የያዙ ይመስል ዓይን በየትኛው ላይ ማረፍ እንደሚችል ያስቸግሪሉ ያምራሉ! ሁሉም ያሳሳሉ።በእለቱ ጥቁር ጉርድ ከፋይ ቀሚስና ነጣ ያለ ሰማያዊ ስስ ሸሚዝ ለብሳለች በመካከለኛ ቁመት ደልደል ያለ ሰውነቷ ዓይን እየጎተተ የግድ እዩኝ እዩኝ ይላል።
ስታምር!” አለ አስቻለው በሆዱ። ከፊቷ ቁጭ ብሎ በጨዋታ መሀል
ዓይኑን ጣል እያደረገ የሰለለው የሔዋን ውበት ለብዙ ቀናት ከልቡ አልጠፋ ብሎት ትዝ ባለችው ቁጥር ደግሞ ደጋግሞ እንዴት ቆንጆ ልጅ ናት በማለት ከራሱ ጋር
እየተነጋገረ በልቡም ሲያደንቃት ሰነበተ፡፡ ውሎ እያደረም ለፍቅር ይመኛትና ያስባት ጀመር፡፡
ሸዋዬ የተከራየችውን ቤት አፀዳድታ የገባችበት ዕለት ለማስመረቂያ በአዘጋጀቺው ምሳና ለአፈላችው ቡና አንዱ ተጋባዥ አስቻለው ነበር፡፡ ጥሪውን
አክብሮ ተገኝቷል። ግን ከበላው የጣፈጠ ወጥና ከጠጣው ወፍራም ቡና ይልቅ በጣም ያስደሰተው በዚያ ሰበብ የሸዋዬን ቤት ማየቱ ነው ፤ የሔዋንን አድራሻ ማወቁ በልቡ ለያዘው እቅድ መፈጸሚያ የመጀመሪያ ርምጃ ነውና። በእርግጥም ከዚያ በኋላ ያንን ቤት በሰበብ አስባቡ ይመላለስበት ጀመር፡፡ ሽዋዬም የቄስ እንግዳ እያደረገች
ሽር ጉድ ስትልለት እየሞቀውና እየተመቸው ሄደ። ከሔዋንም ጋር እየተቀራረቡ ሲሄዱ እሷም ከዓይን አፋርነት ወጣ በማለት እየተላመደችው ሄደች፡፡ አስቻለውም በቀረባት መጠን ከማራኪ አካላዊ ገጽታዋ ይበልጥ ውስጣዊ ውበቷም ስሜቱን
ይገዛው ጀመር::
አስቻለው ዛሬ በዋርካው ምግብ ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ ስለዚሁ ጉዳይ ሲያሰላስል በተለይ ሁለት አጋጣሚዎች ትዝ ብለውት ሳያውቀው ፈገግ አለ፡፡
ትዝ አለው፤ እለቱ ዓርብ ነበር፣ የጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት። በዕለቱ የከሰዓት ፈረቃ ስራ ነበር። በጠዋቱ ፈረቃ የመምህራን ጠቅላላ ስብሰባ
እንደነበርና ትምህርት እንደሌለ፣ በዚህም ምክንያት ሽዋዬ ስብሰባ ላይ እንደምትሆንና ሔዋን ደግሞ ቤቷ ውስጥ ብቻዋን እንደምትገኝ ቀደም ብሎ ያውቃል: ፍቅሩን ለሔዋን ሊገልጽበት የሚችል ጥሩ አጋጣሚ ሆኖ ታየው፡፡ በዚሁ
ጉዳይ ላይ ሌሊቱን ሙሉ ሲያስብና ሲያሰላስል አድሮ ልክ ከረፋዱ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ ሔዋን ለመሄድ ቆርጦ ተነሳ። ልቡ እየፈራ፣ ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ
ከንፈሩ በፍርሃት ሲደርቅበት በምላሱ እያራሰ፣ ጉሮሮውን እየሳለና ላብ ላብ እያለው
ከሽዋዩ ቤት ደረሰ። በዚያ ሰዓት ሔዋን መኝታዋም መቀመጫዋም የሆነች ከሸዋዬ ታጣፊ አልጋ ግርጌ በተነጠፈች ፍራሽ ላይ ቁጭ ብላ ስታጠና አገኛት፡፡
«እንዴት አደራችሁ?» አለ የሽዋዬን አለመኖር እንደማያቅ ሆኖ፡፡
«እንዴ እስቻለው ዛሬ እንዴት በዚህ ሰዓት? አለችው ሔዋን ብድግ ብላ
እየተቀበለችው፡፡ ለወትሮው የሚመጣው ማታ ማታ ስለነበር አመጣጡ ያልተለመደ ሆኖቧታል፡፡
"አንዳንዴ እንኳ በፀሐይ ልምጣ ብዪ» እያለ ዱካ ላይ ቁጭ አለ።
ሥራ እልነበረህም»
«የከሠዓት ፈረቃ ገቢ ስለሆንኩ ነው፡፡» ካለ በኋላ ሽዋዬስ?» ሲል ጠየቃት አሁንም እንደማያውቅ ሆኖ።
"ስብሰባ አላቸው።
"እስከ ስንት ሠዓት ይቆያሉ?"
«ምናልባት እስከ ስድስት ወይም እስከ ስባት፡፡አለችና ሔዋን
እንዲያውም እት አበባ ከታፈሡ ጋር እንመጣለን ቡና አፍልተሽ ጠብቂኝ ስላለች ልቆላ ስል ነው የመጣኸው::» አለችው።
"ሥራ ካለብሽማ ልመለስ"
"እየሰራሁ መጫወት አንችልም?»
አስቻለው ልቡ ፈርቷልና ሲቅበጠበጥ ሔዋን ታየዋለች:: አንዳንዴ ጣሪያ ጣሪያ፤ ሌላ ጊዜ ውጭ ውጭ ሲያይ ትመለከተዋለች። ከንፈሩንም ደጋግሞ በምላሱ ሲያርስ ይገርማታል። ያልተለመደ ስሜት ታነብበታለች::
«ምነው አስቻለው? ችግር አለ እንዴ?» አለችው፡፡
«ቢኖር ትፈቺያለሽ?»
«የምችለው ከሆነ!"
"ከማንም በላይ ላንቺ የሚቀል፡፡
«ምንድነው እሱ?»
አስቻለው ጉዳዩን በቃል ሊነግራት አልፈለገም፤ ከተቀመጠበት ብድግ በማለት ወደ ሔዋን ጠጋ አለና እስቲ አንዴ ቆም በይ!» ሲል ጠየቃት፡፡
ሔዋን የአስቻለው ሁኔታ አሁንም እየገረማት ብድግ አለች። በድንጋጤ አስተያየት ዓይን ዓይኑንም ስትመለከተው አስቻለው አሁንም የበለጠ ጠጋ በማለት
በሁለት እጆቹ ትከሻና ትከሻዋን ይዞ "ስሚ ሔዋን አላት።"
«አ..አቤት!» አለችው ሔዋን በድንጋጤ ድምጿ እየተቆራረጠ።
«እነሆ ከአየሁሽ ድፍን ሁለት ወር አለፈኝ:: አንቺን በማየት የገባሁትን ዕዳ ብቻዬን ልወጣው አልቻልኩም፡፡»
«የምን ዕዳ?» ሔዋን ዓይኖቿ በዓይኖቹ ላይ ስክት አሉ።
የፍቅር ዕዳ ፍቅርሽን ብቻዬን አልቻልኩትም::ክ
«ኣ ምነው አስቹ? አለችው ሔዋን የባሰ እየደነገጠች። ስለ ፈራች
ይተዋት ዘንድ አቆላመጠችው::
አስቻለው ግን አለቀቃትም አንገቷን እቅፍ እድርጎ ደረቱ ላይ ከለጠፋት በኋላ ! ሶ! እንግዲህ አንቺ አስቹ በይኝ እኔም ሔዩ ልበልሽ፡፡
ሔዋን ከመደንገጧ የተነሳ ምን እያላት እንደሆነ አልታወቃትም፡፡ በሁለት እጇቿ የአስቻለውን የቆዳ ጃኬት ጫፎች እንቅ አድርጋ በመያዝ

👍2❤1
"በእናትህ አስቻላው፣ ልቀቀኝ" እዠአለችው።
"አንድ ቃል ተንፍሽልኝና!!
"ምን. ምን ብዬ?"
"እወድሃለው በይኝ"
«እሺ እወድሃለው በል ልቀቀኝ" አለችው፡፡ በእሷ ሀሳብ እንዲለቃት
መለማመጧ ነው።
አስቻለው በቀኝ እጁ አንገቷን እቅፍ እንዳደረገ በግራ እጁ እገጯን ይዞ ቀና አደረጋትና ከንፈሮቿን ሶስት ጊዜ ሳም ሳም አድርጎ ለቀቃት።
ሔዋን ልክ አስቻለው እንደለቀቃት ፍራሿ ላይ ወጥታ ግድግዳ ተደግፋ በመቆም በድንጋጤ ጭብጥ ብላ በፍርሃት ዓይን ታየው ጀመር፡፡ ሰውነቷ በላብ
ተንክሮ መላ አካአላቷ ይንቀጠቀጣል፡፡
"አይዞሽ!» አላት እስቻለው በስስት ዓይን ፍዝዝ ብሎ እየተመለከታት፡፡
«እነ እት አበባ ሳይመጡ ቶሎ ሂድ!» እላችው የተሳሙ ክንፈሮቿን በምላሷ ላስ ላስ እያደረገች:: የአስቻለህ ከንፈሮች ከንፈሯ ላይ የቀሩ ይመስላታል፡፡
"ተመልሼ መቼ ልምጣ?» አላት እንደ ቀልድ ፈገግ ብሎ እያያት፡፡
«በእናትህ!! ሁለተኛ እንዳትመጣ!»
አስቻለው ዛሬ ከዋርካው ምግብ ቤት ቁጭ ብሎ ይህን ሁሉ ሲያስታውሰው ለራሱ ገርሞት ብቻውን ሳቀ። ራሱን ወዝወዝ አደረገና ማሰቡን ቀጠለ። እንዲያውም ሌላውና በተለይ ለዛሬው ጭንቀቱ ዋና ምክንያት የሆነው አጋጣሚ በሀሳብ ፊቱ ላይ
ድቅን አለበት፡፡ ፍቅሩን ለሔዋን ከገለጸ በኋላ ወደ ሸዋዬ ቤት የሚሄድበት ወቅትና ሰዓት ተቀይሮ እንደ ነበር አስታወሰ፡፡ ቀደም ሲል ወደዚያ ቤት የሚሄደው ለሳቅ
ለጨዋታ ስለሆነ የሽዋዬን ቤት ውስጥ መኖር ይፈልገው ነበር፡፡ በኋላ ግን የሰው ዓይን የሚፈራ የተለየ ጉዳይ አለውና በአብዛኛው ሔዋን በዚያ ቤት ውስጥ ብቻዋን
የምትገኝበትን ጊዜ ይወርጣል፡፡ ሸዋዬ በአለችበት የሚሄደው አልፎ አልፎ ለዚያውም ጥርጣሬ እንዳያስክትል ለማደናገር ብቻ ነበር።
ሔዋን ደግሞ ከዕለት ወደ ዕለት እየተመቸችው ሄዳለች:: ለሁለተኛው እና ለሶስተኛ ምናልባት እስከ አራተኛው ጊዚ ልክ እንደ መጀመሪያው ቀን እየተጨነቀች ታስቸግረው የነበረ ቢሆንም እያደር ግን መለወጥ ጀምራለች፡፡ ያዝ ሲያደርጋት ቁና
ቁና መተንፈሷን ትታ በስሜት መስለምለም፣ አንገቷን እቅፍ ሲያደርጋት በወገቡ ላይ ጥምጥም፧ ከንፈር ሲሰጣት የእሷን ማቀበል ተለማምዳለች። ከዚያም በላይ መናፈቅም ጀምራለች።
በዚያው ልክ የአስቻለውም ፍላጎት እያደገ ሄደ:: በሳማትና በተሻሻት ቁጥር እንደ ብረት እየጋለ የሚያቅበጠብጠውን ሰውነቱን እፎይ ሊያሰኘው ፈለገ። ለዚህ
የሚመች አጋጣሚና ሁኔታ ለመፍጠር እዕምሮውን ያዘጋጅ ጀመረ። ለዚህ ጉዳይ ደግሞ የራሱን ቤት መረጠ። ሔዋን ወደዚያ ቤት ብቅ ትልለት ዘንድ ሲያባብልም ሰነበተና አንድ ቀን ተሳካለት። ዕለቱ የህዳር ወር የመጨረሻው ማክሰኞ ነው፣....
💫ይቀጥላል💫

👍3
#ሰው
ምን የአለት ግግር
የፀና ቢመስል
ምን የብረት ክምር
ጠንካራ ቢመስል
መሰረቱ ያው ነው
ስስ የህዋስ ንጥር፡፡
እሱም እንባ አለው
እንደ ጅረት ሚፈስ
እሱም ሀዘን አለው
እንደ ድንጋይ ሚከብድ
እሱም ስቃይ አለው
እንደ ምንጭ የሚፈልቅ
እንደ ዝናብ ሚወርድ፡፡
ያ ግዙፍ ማንነት
ከህይወት ራሷ ይገዝፍ የሚመስለው
እሱም እንባ አለው
እሱም ሀዘን አለው
ምን ኑሮ ባፀደይ
ምን ህይወት ቢሞላ
ለሀዘን የሚሆን ክፍተት እንዳይጠፋ፡፡
🔘መንግስቱ በስር🔘
ምን የአለት ግግር
የፀና ቢመስል
ምን የብረት ክምር
ጠንካራ ቢመስል
መሰረቱ ያው ነው
ስስ የህዋስ ንጥር፡፡
እሱም እንባ አለው
እንደ ጅረት ሚፈስ
እሱም ሀዘን አለው
እንደ ድንጋይ ሚከብድ
እሱም ስቃይ አለው
እንደ ምንጭ የሚፈልቅ
እንደ ዝናብ ሚወርድ፡፡
ያ ግዙፍ ማንነት
ከህይወት ራሷ ይገዝፍ የሚመስለው
እሱም እንባ አለው
እሱም ሀዘን አለው
ምን ኑሮ ባፀደይ
ምን ህይወት ቢሞላ
ለሀዘን የሚሆን ክፍተት እንዳይጠፋ፡፡
🔘መንግስቱ በስር🔘
👍4😱3❤1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
.....አምናን ካቻምናን ከዚያ በፊት የተቆጠሩ ዓመታትን ጨምሮ ለብዙ ጊዜ የደከሙበት ትምህርት የሚቋጨው ዘንድሮ ነው። ጌትነትና አማረች ከጓደኞቻቸው ጋር በቡድን በቡድን ሆነው እያሽመቁ ጥናታቸውን ሲለበልቡ የከረሙበት ላለፉት ረጅም አመታት ትምህርታቸውን በመከታተልና የሚሰጣቸውን አድካሚ የቤት ስራዎችን ከመደበኛ ሥራቸው ጋር አጣምረው በመስራት ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉበት የነዚያ ሁሉ አመታት ልፋት ድምር ውጤት የሚደመደምበትና የሚመረቁበት አመት ዘንድሮ ነው።
ሁለቱ ፍቅረኛሞች በአዋሳ ላንጋኖ ሃይቅ ውስጥ ተክለው ያለመለሙት ፍቅራቸው የሚያስቀና ሆኗል። ጌትነት የመልካሙ ተበጀ አዋሳ ላንጋኖ
ዘፈን አስቀድሞ የሚወደው ቢሆንም ለሱ የተዘፈነለት እስከሚመስለው ድረስ በይበልጥ የወደደውና አብሮ ማቀንቀን የጀመረው ከላንጋኖ ሽርሽር
በኋላ ነው።
አዋሳ ላንጋኖ ለሽርሽር ሄጄ ያየሁሽ፣
የሲዳሞ ቆንጆ እንዴት ነሽ?
ሽንጥና ተረከዝ ዳሌና ጡትሽ...
አዲስ አበባ ውስጥ ለሁለት አመታት ሲመኛት ቢኖርም በፍቅር ያወቃት በአዋሳ ላንጋኖ ሀይቅ ውስጥ ነበረና ያንን ዘፈን ሲሰማ የአዋሳ ላንጋኖው ሃይቅና ያ ውብና ምንጊዜም ከህሊና የማይጠፋ አስደሳች ዓለም ከነሙሉ
ጓዙ ተጠቅልሎ በሃሳቡ እየመጣበት ዘፈኑን ነፍሱ ምንጥቅ ብላ እስከምትወጣ ድረስ ወደደው። በዚህ የተነሳ የሲዳሞ ቆንጆ በሚለው ምትክ የአዲስ አበባ ቆንጆ እንዴት ነሽ በሚል ተክቶ ከዘፋኙ ጋራ አብሮ ሲያቀነቅን የሚሰማው ስሜት የተለዬ ነበር፡፡ አማረች ለሁለት አመታት ስትመኘው የነበረው ጉዳይ በመሳካቱ እጅግ ደስተኛ ከመሆኗ በላይ ከምትወደው ልጅ ጋር በትዳር ተሳስራ በመኖር የወላጆቿን ፍላጎት ለማሟላት
የሚያስችላት መልካም አጋጣሚ መፈጠሩ በአንድ ጠጠር ሁለት ወፍ ሆኖላታል። ወላጆቿ ልጃቸው ትዳር እንድትይዝላቸው ከፍተኛ ጉጉት አላቸው፡፡ “መቼ ይሆን የአያትነት ወግ ማእረግ የምታሳይኝ ልጄ? እንግዲህ ጀርባዬ ሳይጎብጥ ጉልበቴ ሳይዝል ጥሩ እስክስታ እንድመታልሽ ከፈለግሽ ይሄን ጊዜ ነው ጉልበቴን መሻማት” እያሉ የሚወተውቷት አባቷ
ይህንን ውሳኔዋን ሲሰሙ ደስታቸው ወደር እንደማይኖረው ጥርጥር አልነበራትም፡፡እናቷ አማረችን የሚያይዋት እንደ ልጃቸው ሳይሆን እንደ ታናሽ እህታቸው ነው። አማረችም እናቷን እንደ ታላቅ እህት እንጂ
እንደ እናት አይደለም የምታያቸው፡፡ ታሪኩን ያጫወተቻቸውም እሳቸው
በነገር ወጋ አድርገዋት ነው፡፡
“አማሩዬ? እኔ የምለው? እኛ የምናመጣልሽ ባል እንደማይኖር
በጠዋቱ አስጠነቀቅሽን
አንቺ የምታመጭውን ብንጠብቅ ደግሞ የማሚታይ ነገር ጠፋ።
ምን ይሻላል ልጄ? የሁልጊዜ ምክንያትሽ ትምህርቴን ልጨርስ ነው። ትዳር ተይዞ መማርን ምን ይከለክለዋል? አባትሽ ትዳር ትዳር እያልኩ ስጨቀጭቃት ሸክም ሆንሽብኝ ያልኳት እንዳይመስላት እንዳትሳቀቅብኝ እያለ እየፈራ እንጂ ከኔ የበለጠ የቸኮለ እሱ ነው፡፡ እንዲያው ለጤናው ያድርግለት ችኩል ብሏል”
የትዳሯ ነገር ያጓጓቸው፤ የሰርጉ ቀን የናፈቃቸው መሆኑን አጫወቷት።አማረች ቀኝ ክንዷን በቀኝ ጉልበቷ ላይ አገጯን በመዳፏ ደገፍ አድርጋ
በፍቅር ዐይን ዐይናቸውን እየተመለከተች ነበር የምታዳምጣቸው፡፡
ፊቷ ወይን ጠጅ መስሏል፡፡ ከረጅም ጊዜ ሚስጥር በኋላ እጮኛ ያላት መሆኑን ወላጆቿ ያላወቁት የትዳር ጥንስስ በልቧ ውስጥ ተጠንስሶ መቆየቱን ልትነግራቸው ፈለገች። ከዘንድሮ ምረቃ በኋላ ለትዳር የወጠነቸው
ጓደኛ ያላት መሆኑን ለእናቷ ለማብሰር ፈለገችና ጥርት ያለው ፊቷ በእፍረት ሲቀላባት የወይን ጠጅ መልክ እየያዘ ሄደ።
ከአማረች የመኝታ ክፍል ውስጥ ሆነው ነበር የሚጨዋወቱት፡፡ አማረች ስለፍቅረኛዋ ማስረዳቱን ቀጠለች፡፡ የዐይነ ህሊናዋ ካሜራ በጌትነት ላይ አነጣጥሮ ያሳለፉትን ጣፋጭ የፍቅር ጊዚያት አንድ በአንድ እንደ ፊልም
እየቀረፀና የአዋሳው ትዝታ ፊቷ ላይ ድቅን እያለ፡ “ትንሽ ነው የቀረኝ በጣም ትንሽ ጊዜ፡፡ በጣት የሚጠለቀውን ቀለበት አላጠለኩም እንጂ ታጭቻለሁ። ለረጅም ጊዜ የተዋወቅኩት የምወደው ፍቅረኛ አለኝ፡፡ እስከ አሁን በደንብ ተጠናንተናል። ተግባብተናል። ተዋደናል። ያንቺና የአባዬ ብቻ ሳይሆን በትዳር የመኖሩ ጉጉት በኔ ብሷል። ዩኒቨርስቲ አብሮኝ የሚማር
ልጅ ነው፡፡ ላንቺም ለአባዬም የማስተዋውቅበት ጊዜው ደርሷል። ሁላታችንም በዚህ ዓመት እንመረቃለን፡፡ እስከዛሬም የደበቅኩሽ ትምህርቴን
ከመጨረሴ በፊት ሠርጉ ይፋጠን የሚል ጥያቄ እንዳታቅርቡልኝ ነው።አሁንም ቢሆን ላንቺ ብቻ ነው የምነግረው፡፡ ለአባዬ ጊዜው ሲደርስ አንቺ ትነግሪዋለሽ” የአማረች እናት ልባቸው በደስታ ዘለለች። እንኳን የተማረ! እንኳን ያፈቀረችውን ይቅርና ሱሪ ይልበስ እንጂ እሷ ተመችቶኛል ትዳር
መያዝ እፈልጋለሁ ብላ ፈቃደኝነቷን ከገለፀች ከማንም ጋር ቢሆን ድል ባለ ሠርግ ሊድሯት ሁሌም የሚቃዡበት ምኞታቸው ነበረና፣ እንደ
ዕድሜ እኩዮቻቸው “ልጃችንን ዳርናት” እያሉ አፋቸውን ሞላ አድርገው ለመናገርና እርጅና ከመምጣቱ በፊት የአያትነት ወግ ማእረግ ሊያገኙ ነውና የሰሙት የምስራች እንደ ትንሽ ልጅ እያስቦረቃቸው የባለቤታቸውን ደስታ ጭምር አገላብጠው ሳሟት፡፡
“ለምን የፈለገው አይሆንም አማሩዬ? ይህችን አሁን ያሰማሽኝን የምስራች ይቺን እኔ የሰማኋትን ሚስጥር እሱም ቢሰማ ኖሮ በደስታ አስር
ዓመት ወደ ኋላ ያስቆጥር ነበር” በዜናው እጅግ ተደስተው ወደር የማይገኝለት የእናትነት ፍቅራቸውን እቅፍ አድርገው በመሳም ገለፁላት።አባቷ የሚወዷት የመጀመሪያ ልጃቸው ትምህርቷን ጨርሳ በዲግሪ ተመርቃ
የምትወደውን ፀባየ ሸጋና ጠንበለል ልጅ ይዛላቸው ከተፍ ስትልሳቸው ከደስታቸው የተነሳ ቦሌ አካባቢ ያሰሩትን አምስት ክፍል ቪላ ቤት ጀባ እንደሚሏቸው ጥርጥር የለውም፡፡ ይህንን ጠንቅቃ ስለምታውቅ ጌትነትና ስለመኖሪያ ቤት እያነሳ ሲጨናነቅ በልቧ ትስቅ ነበር። አማረች የምስራቹን ለእናቷ ባደረሰችበት በመመረቂያቸው ዓመት ላይ ጌትነትና እሷ የዓመት ዕረፍት ፈቃዳቸውን ወስደው ለመጨረሻው ፈተና እየተዘ
ጋጁ ነበር።
ትናንትና ለእናቷ የነገረቻቸውን ልትነግረው ፈለገች። አሁንም እንደ
አማረች በሆነ ባልሆነው “ጌትሽ ድረስ!” ሆኗል ዜማዋ፡፡ ዕቃ ሲሰበር አዲስ ፊቷ በእፍረት እየተለወጠ እየቀላ ሄደ፡፡ አሁን አሁን ደግሞ “ጌትዬ ድረስ!" ሆኗል ዜማዋ ምናምን ካስደነገጣት ጌትሽ” ብቻ ለሁሉም ነገር "ጌትሽ
ነጠላ ዜማ ሆኗል፡፡ ይሄ ነገር እናቷንም ግራ ሲያጋባቸው የኖረ ጉዳይ ነበር፡፡ በመጨረሻው ላይ እቅጩን ነገረቻቸው እንጂ ደጋግመው ስምተዋታል "ጌትዬ! ጌትዬ" ስትል፡፡
በዩኒቨርስቲው የመማሪያ ክፍል ውስጥ ከሁለቱ በስተቀር ማንም አልነበረም፡፡ባዶ ነው።ኃይለኛ ንፋስ መስኮቱን ጓ! አደረገና አላጋው። እንደልማዷ”ጌትሽ ድረስ!” በማለት ሄዳ ልጥፍ አለችበትና” ለማዘር ነገርኳት እኮ!"
አለችው እየተፍነከነከች።የመስኮቱ ጩኸት እፍረቷን አቡንኖታል።
“ምኑን?" ፈገግ እንዳለ ዘቅዝቆ እየተመለከታት፡፡
“በቃ ላስተዋውቅህ መሆኑን? እና እንትኔ መሆንህን፡ ባሌ መሆንህን!" አንገቱን እቅፍ አድርጋ ከንፈሩን ሳመችው። ቅብጥ ስትል ያለማጋነን ደስ ትላለች። የአንዳንዱ ቅብጠት ያስጠላል። አማረች ግን የቅብጠት ቅመሙን ጣል አድርጐባት ነው መሰል ቅብጥብጥ ስትል የበለጠ

👍3❤1
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
....ዕለቱ የህዳር ወር የመጨረሻው ማክሰኞ ነው የአስቻለው ከንፈሮች ከሔዋን ከንፈሮች ጋር ከተገናኘ ሃምሳ ሁለተኛ ቀን። ሔዋን ቀጠሮ አክብራ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ ከአስቻለው ቤት ደረሰች፡፡ አስቻለው ሔዋንን ከወስጥ አድርጎ ቤቱን ሲዘጋ ተሰምቶት የነበረ ደስታ አይረሳም።
በዚያ ዕለት ሔዋንን እንደ እንግዳ ወንበር ላይ ቁጭ በይ አላላትም፣
አንገቷን እቅፍ አድርጎ በቀጥታ ወደ አልጋ ወሰዳት፡፡ አልጋ ላይ ቁጭ ብለው ትንሽ ከተሟሟቁ በኋላ ስሜት በራሱ ሀይል ሲገፋቸው አንገት ለአንገት እንደተቃቀፋ፥ከንፈር ለከንፈር እንደተያያዙ ወደ ኋላ ከንብል አሉ፡፡ ጫማዎቻቸውን አወላልቀው
ወደ መሀል አልጋው ወጡና በሰፊው የፍቅር ሜዳ ላይ ሰፈሩ፡፡
ጉዞው ቀጠለ፡፡ ከንፈሮች በስራ ተጠመዱ፡፡ ዓይኖች ተስለመለሙ ትንፋሽ በረከተ፡፡ ገላጋይ የማያስፈልገው ትንቅንቅ ተጀመረ፣ የአስቻለው ቀኝ እጅ የሔዋንን
አንገት አቅፎ ግራው ደግሞ ሌላ ሥራ ያዘ። ከሔዋን ፀጉር ጀምሮ ማጅራቷን ይጎበኝና በወገቧ ላይ እየተስለክለክ ወደ ዳሌና ጭኖቿ ይወርዳል። ላይ ላዩን እንደ
ወረደ ሁሉ ወስጥ ውስጡን ለመመለስ በማሰብ ቀሚሷን ሰብሰብ እያደረገ ወደ
መሀል ጭኖቿ ጎራ ሊል ይቃጣዋል፡፡ ነገር ግን የሔዋን ጭኖች ወይ ፍንክች!!እንደገና ከላይ ይጀምራል፡፡ ይወርድ ይወርድና በአሰበው መንገድ ለመመሰስ ሲሞክር አሁንም ተቃውሞ ይገጥመዋል፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ ሞከረ:: የሔዋን ጭኖች ግን
አልበገር አሉ።
በአራተኛው ጊዜ ከንፈሮችም ድንገት ተላቀቁ:: ሔዋን ወደ ቀልቧ ተመልሳ ኖሮ ድንገት ፍንጥር ብላ በመነሳት አልጋው ላይ ቁጭ አለች። አስቻለውም አልዘገየም፣ ሔዋን በተነሳችበት ቅፅበት እሱም ፍንጥር ብሎ ጭራሽ ከአልጋው ላይ ወደ መሬት ወረደ:: ፊትለፊቷ ቆሞ በነጭ ካኒተራው ላይ ደረቱን እያሻሽ
"ስሜቱ አልገባሽም አይደል ሔዩ" አላት በስሜት ውስጥ ሆኖ
ቅልስልስ እያል፡፡
"ገብቶኛል"
"ታዲያ ለምን ታስጨንቂኛለሽ?"
"እኔም ስለጨነቀኝ፡፡
«እንዴት?"»
«የእናት እደራና የእህት ማስጠንቀቂያ ስላሉበኝ»
“አልገባኝም ሐዩ!
«ና ቁጭ በል ልንገርህ»
አስቻለው ፈጥኖ ከአጠገቧ ቁጭ አለ። በመሀል ሔዋን በሀሳብ ጭልጥ ብሳ ሄደች:: ያኔ በነሐሴ ወር አጋማሽ ላይ ከሸዋዬ ጋር ጠዋት ከክብረ መንግሥት ወደ
ዲላ ሊመጡ ሲሉ ማታ በዝግጅት ላይ በነበሩበት ወቅት ሽዋዩ ሔዋንን እፊቷ ቁጭ አድርጋ ከእናቷ ጋር የተነጋገሩት ነገር።
ስሚ እማዬ » ብላ ነበር ሽዋዬ ወሬ የጀመረችው። «ይቺን ሔዋንን
ከአሁኑ ምክሪልኝ:: ዲላ የቡና አገር ነው ሀብታም ሁሉ ሰው በገንዘብ መግዛት ይፈልጋል:: እሷ ደሞ ቆንጆ ስለሆነች በገንዘብ እያታለሉ ትምህርቷን አስትተው ብልግና ሊያስተምሯት ይችላሉ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ህይወቷ ሊበላሽ ይችላል። እኔም ብሆን እንኳን ብልግና ፈጽማ ፡ የወንድ እጅ ጨበጠች ያሉኝ ዕለት ባለጌሽን አምጥቼ አስረክብሻለሁ።» ብላቸው ነበር፡፡ እናቷ ከተል እንዲህ ዓይነት ብልግና ትፈጥማለች ብዬ አልገምትም::
ያን ያህል ለፍቼ አሳድጌታለሁና
ክብሯን ጠብቃ ወግ ማረግ ታሳየኛለች ብዬ እጠብቃለሁ፡፡ ያ
ሳይሆን ቀርቶ ብልግና ፈጥማ አንቺ ወደኔ ብታመጫት እኔም የዚያኑ ዕለት ገደል ገደል ገብቼ እሞትና ቀብረሽኝ ትመለሻለሽ በማለት ተናግረው ነበር። ሔዋን ይህን የናቷን አደራና የእህቷን የማስጠንቀቂያ ቃል በሀሳቧ እያዳመጠች በነበረችበት ወቅት
«እስቲ ያስጨነቀሽን ነገር ንገሪኝ ሲል አስቻለሁ ከሀሳቧ ቀሰቀሳት፡፡
«ለመኑ ገርል መሆኔን ታውቃለህ?» አለችው ድንግል
መሆኗን ስትገልፅለት፡፡
«ኦ!» አለ አስቻለው ያላሰበው ነገር ሆኖበት።
«አትጠራጠር»። አለችውና ሔዋን እናቷ የጣለችባትን አደራና እህቷ ሸዋዬ የሰጠቻትን ማስጠንቀቂያ በዝርዝር አስረዳችው፡፡
ያ እንደ ብረት ግለ" የነበረ የአስቻለው ሰውነት ድንገት ቅዝትዝ ብርድ! ስንፍናና አለ።
«አደራ የምልህ አስቹ!» ስትል ቀጠለች ሔዋን። «ይህን የፍቅር ጉዳያችንን አንድ ቀን እታ አበባ የሰማች እንደሆነ መግቢያ ቀዳዳ የለኝም፡፡ ስለዚህ ሚስጥራችንን ከታፈሱና ጓደኞችህ" በቀር ሌላ ማንም ስለማያውቅ ሁሉም
በሚስጥር እንዲይዙልን አደራ እንድትላቸው ነው። እለችው::
አስቻለው በሁኔታው ተገርሞ ግንባሩን ይዞ መሬት መሬት ሲያይ ቆየና ድንገት ብድግ ብሎ ሔዋን ፊት በመቆም «እስቲ ወደኔ ነይ ሒዩ!» አላት፡፡
ሔዋንም ቡድግ ብላ በመቆም የአስቻለውን ዓይኖች ማየት ጀመረች፡፡
አስቻለው በሁለት እጆቹ የሔዋን ትክሻና ትክሻ ያዝ አድርጎ ቁልቁል
እየተመለከታት፡ ቃል ልገባ ነው ሐዩ፡»
«ምን ብለህ?»
የበሕይወት እስካለሁ ድረስ ፍጹም አልለይሽም። ከሠርጋችንም በፊት
ምንም አላደርግሽም» አላት፡፡
«እሺ» አለችው ሔዋን፡፡
አንገት ለአንገት ተቃተፉ። ምናልባት በሁለተኛው የህይወት ምዕራፍ ውስጥ እንደ ገቡ ታውቋቸው ሳይሆን አይቀርም ሆዳቸው ባብቶ ሁለቱም ተላቀሱ።
ይህ ዓይነቱ የፍቅር ከመሰራረት ሂደትና በውስጡ ያለው የሔዋን አደራ ነው ዛሬ አስቻለውን የከበደውና መንፈሱን ወጥሮ ነፍሱን ያስጨነቃት። አዎ
ተጨነቀ። ሔዋን በተፈጥሮ ፈሪና ሽቁጥቁጥ መሆኗን ያውቃል፡፡ ዛሬ በሸዋዬ ፊት እንደ ጭብጦ ጭርምትምት ብላ ታየችው:: ችግሩን በምን መላ ሊፈታው
እንደሚችል ግራ ገብቶት ፍዝዝ ትክዝ እንዳለ በዋርካው ምግብ ቤት ለብዙ ጊዜ የእራት ሠዓት ደርሶ ኖሯል። ድንገት ጓደኛው በልሁ በበር በኩል ወደ እሱ ሲያመራ አየወ፡፡ በልሁ ቁመቱ፡፡ ዘለግ ሰውነቱም ፈርጠምጠም ያለ ነው፡፡ ሰፋ ባለ የቀይ ዳማ ፊቱ ላይ በትር ወስሉ የተገተረው አፍንጫው ግርማ ሞገስ
አላብሶታል:: ዓይኑ ጎላ ጎላ ያለና ፈገግ ሲል ጥርሱ የሚያምር ነው:: ከውጭ ሲመጣ አስቻለው ትክዝ ብሉ በርቀት ዓይቶት ኖሮ ቀረብ ብሎ ሲያጤነውም ስሜቱ
መመሳቀሉን በመገንዘብ፡ ምነው ይክተር? ሰላም አይደለህም እንዴ?» አለና ሰላም ብሎት ከአጠገቡ ቁጭ አለ፡፡ አስቻለው ነርስ ስለሆነ ጓደኞቹ ብዙ ጊዜ ይክተር አያሉ በመጥራት ያሾፉበታል፡፡......

👍4
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ፀጉሩን ተላጨና ቁምጣ ሱሪውን አወለቀ! በምትኩ ቀጭን ቦላሌውን ለበሰ፡፡ ከላይ ሸሚዝና ኮቱን ደርቦ ሽክ.. ኳ! ብሎ ሲታይ ያ ጎንቻ! ያ አስፈሪው ጎንቻ! ያ ባለጎፈሬው ሽፍታ! መሆኑን እንኳንስ የማያውቀው የሚ
ያውቀውም ቢሆን ለማመን ይቸገር ነበር፡፡ውስጣዊ እሱነቱ ሳይሆን ውጫዊ ማንነቱ ተቀይሯል። የከተማው ሰው
የሚለብሰውን ልብስ ለብሶ ሰው መሰል አውሬነቱን የሚያሳስት አይነት ሆኗል።
በዚያች ምሽት በጠፍ ጨረቃ ከዓለሚቱ ጋር ተያይዘው ጠፉ... ከኢተያ ከተማ እስከ ዴራ ከተማ በእግራቸው ተጓዙ በሌሊት መኪና ተሳፈሩና ናዝሬት ገቡ፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ወደዚያ የከተማ ጫካ፣ ወደዚያ የከተማ ዋሻ ገብተው ሊደባለቁ በአዲስ አበባ መኪና ላይ ተሳፈሩ። ከእንግዲህ በኋላ ጎንቻን ፈልጎ ማግኘት ከእንግዲህ በኋላ ዓላሚቱን ፈልጎ
ማግኘት ቁና አሸዋ ውስጥ የወደቀች ጤፍ ለማግኘት እንደመሞከር ነው፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ዓለሚቱ ባሏን ያስገደለች እየተባለች ከምትጠበስበት የሀሜት ምላስ ልትድን እፎይ ልትል ነው፡፡ እነኝያ የገደ ቢስ
ልጆች ጨርሰው ከዐይኖቿ ሊርቁላትና ሰላማዊ ሰዎች መስለው ከአዲስ አበባ ህዝብ ጋር ሊቀላቀሉ የቀራቸው በሰዓታት የሚቆጠር ጊዜ ብቻ
ነው፡፡
ከእንግዲህ ወዲያ የጎንቻን ፍቅር ሙቀቱ እስከሚያቃጥላት ድረስ እንደ ልቧ ልትሟሟቀው ሁኔታው ተመቻችቶላታል። ከእንግዲህ በኋላ የልታጌጥ፣ እንደፈለገችው ልትዘል፣ ልትቦርቅ ልጓሙ ተፈቶላታል።
ጎንቻም አንጎሉን ሲያዞረው በኖረው በዓለሚቱ ፍቅር ወፈፍ በሚያደርገው በዓለሚቱ ናፍቆት ክፉኛ ተጎድቶ ነበር። አብዛኛውን ጊዜ በጫካ ውስጥ ትዝታዋን ብቻ እያቀፈ በማደር ሲሰቃይ ኖሯልና ናፍቆቷ ነፍሱን መንጥቆ ሳያወጣው በፊት ጥሩ ዘዴ ፈጥራ ይዛው በመኮብለሏ አልተከፋም፡፡ያንን ቢያሽተው ቢምገው የማይጠግበው መዓዛዋን በየቀኑ በየደቂቃው ሊያጣጥመው ነውና ኩብለላው ብዙም አላስጨነቀውም ነበር። የተሳፈሩበት ሎንቺና ወስዶ ለገሃር ጣላቸው፡፡
ጎንቻ ከጫካ ያመለጠ አውሬነቱ የታወቀው ገና ከመኪና ላይ እንደወረደ ነበር፡፡ ተይዛ ያመለጠች ሚዳቋ መሰለ፡፡ ሽው!...ሽው!... ውር!... ውር
በሚሉት መኪኖች መሀል ሲገባ ሮጦ ሊያመልጥ ሞከረ። እንጣጥ!
እንጣጥ! እያለ የአንዱ መኪና ራት ሊሆን ትንሽ ቀረው። መንገዱ መሀል ሲደርስ ሰግጠጥ.. ሰግጠጥ እያደረገው አንዴ ወደ ፊት አንዴ ደግሞ ወደ ኋላ ለማምለጥ ዓለሚቱን ክፉኛ ታገላት።እሷም መደናበሯ አልቀረም ቆይ ጎንቻዬ እኔን ተከተለኝ፡፡ ቀስ በል። እኔ ወደምሄድበት ረጋ ብለህ ተራመድ። መኪኖቹን አትመልከት። ያዞርሃል ... ቀስ ...አዎ እንደሱ ጎሽ
..እጆቹን ግጥም አድርጋ ያዘችው እንደምንም ብለው እየተጓተቱ አስፋልቱን ተሻገሩ።
“እሺ ...አዞረኝ እኮ…ቆይ ቁጭ ልበል" አላት፡፡ ደገፈችውና ወደ አንድ ህንፃ አጥር ጥግ ሄዱ፡፡ ተረከዙ ላይ እንደ ዝንጀሮ ቁጢጥ አለ፡፡ ጭውው..አለበት። ጭንቅላቱን በሁለት እጆቹ ያዘው። ዐይኖቹ ጭፍን ክድን ጭፍን
ክድን አሉ፡፡ መኪና ላይ ያልተሰማው የማጥወልወል ስሜት ተሰማው፡፡
"ርቦህ ይሆናል ጌታዬ ርቦህ ነው። ቆይ እዚህ ጋር የማየው ሆቴል ቤት ነው መሰለኝ" ባሻገር ከሚታየው ቤት ላይ ጣቷን ቀስራ አሳየችው።ቆዳቸው የተገፈፈ በጎች ሳይበለቱ ተሰቅለዋል። የሰንጋ ብልቶች በአይነት በአይነታቸው በስርአት ተዘጋጅተው በወረንጦ ላይ ተንጠልጥለዋል፡፡
ልክ ነው ምግብ ቤት ነው" አለችውና ከተቀመጠበት አስነስታው ተያይዘው
ትደጋግፈው ወደ ስጋ ቤቱ አመሩ....
የሚበላ ነገር አለ?" ብላ ጠየቀች፡፡
“አዎን!” አለ ሻጩ፡፡
“ምን አለ?"
“ሁሉም ነገር አለ፡፡ የፈለጋችሁትን..." ወደ ውስጥ እንደመዝለቅ አለችና የሻጩን ዐይን ዐይን በልምምጥ ተመለከተችው።
“በል እስቲ ቀይ ወጥ በእንጀራ..“ፈራ ተባ እያለች ጠየቀቸው። ዓለሚቱ ከልጁ ጋር ስትነጋገር ጎንቻን እንደ ህፃን ልጅ ግራ እጁን ግጥም አድርጋ
ይዛው ነበር፡፡ ጎንቻ...ያ ወንዱ..ጎንቻ... ያ አስፈሪው ጎንቻ አስፈሪነቱ ጀግንነቱ ከሹሩባው ጋር አብሮ እንደተላጨ ሁሉ ወኔው በኛሮ ጫካ ውስጥ ተጥሎ እንደቀረ ሁሉ ዐይኖቹ ፈጠው ርቦት ሲቁለጨለጭ ቀበሮ
የፈሳባት ጦጣ መስሎ ሲታይ እሱነቱን የማይክድ አልነበረም።
“በሉ ጥፉ ከዚህ! ፋራዎች! ገገማዎች! ይሄ የሥጋ መሸጫ ሉካንዳ እንጂ የእንጀራ መሽጫ ጉሊት መስለሽ?! አይተሽ አትጠይቂም?!” ጮኸባት።
ሽምቅቅ አሉ፡፡ አቤት አደነጋገጥ ወጥቶ ፀብ እንዳይፈጥር ጎንቻም በንዴት እልህ ውስጥ እንዳይገባና ገና አንዱንም ሳይይዙት መዘዝ ውስጥ እንዳይገባ ፈራች ፀብ ከተፈጠረ ፖሊስ ይዞ እንዳያንገላታቸው ስጋት አደረባትና
ዐይኖቹ መቅላት ልቡ የንዴት ደም መርጨት ሰውነቱ መቆጣት
የጀመረው ጎንቻን ሙጭጭ አድርጋ ይዛ የስድብ መዓት ከሚያወርድባቸው ጎረምሳ ሽሹ...ጎንቻ አንድ ቂም በልቡ ቋጠረ፡፡ ርቦት ሆዱ የእህል
ያለህ! በሚልበት ሰዓት ወስፋት የሚቆልፍና ወሽመጥ የሚበጥስ የስድብ መርዝ ቀመሰ። እንደምንም ብለው እየተጓተቱ ሄዱና እንጀራ የሚሽጥበት ምግብ ቤት በጠቋሚ አገኙ። በሉ፣ጠጡ፣ ጠገቡ። ጊዜው እየመሸ
ሲመጣ አሁንም በጥቆማ አልቤርጎ ተከራዩ። ምን ችግር አለ? ብር እንደሆነ ዕድሜ ለጎንቻ! በሽበሽ ነው፡፡ ከሰባት ሺህ ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ይዘዋል። ጎንቻን ትንሽ ያስቸገረው መብራቱ ነበር፡፡ ብርሃን በጣም በዛበት። ዐይኑ በአንድ ጊዜ የአምፖሉን ብርሃን መቋቋም አልቻለም፡፡
ሊተኙ አካባቢ አምፖሉን ቀድሞ ለማጥፋት የሞከረው እሱ ነበር፡፡ “ኡፍ ኡፍፍ. ኡፍፍፍ..!" እንደ ኩራዙ ሞከረ። በኋላ ግን ዓለሚቱ በድርጊቱ እየሳቀች ማጥፊያውን ቀጭ... ቋ! አድርጋ አጠፋችውና በችሎታዋ እየተኩራራችበት ተቃቅፈው ተኙ፡፡
ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት አካባቢ ጎንቻ ሽንቱ ወጠረውና የመኝታ ቤቱን በር ቷ! አድርጎ ከፍቶ ወጣ፡፡ የተከፈተውን ድምፅ የሰማው ሽማግሌ ዘበኛ
“ማነው?” አለ በተጎተተ ድምፅ፡፡
"እኔ ነኝ!" አለ ጎንቻ።
"ወዴት ነው?"
ለውሃ ሽንት!"
“የውሃ ሽንት ተሆነ ቦቦው አለልህ አይደለም?! የት ልትሸና ነው? አሁን የሽንት ቤቱ በር ቁልፍ ነው" አለና ዘበኛው ቁጣ ቀረሽ መልስ ሰጠው፡፡
"የምን ቦቦ ነው የምትለኝ ጃል?! ሽንቴ መጥቷል እኮ ነው የምልህ!... "
በዘበኛው ኃይለ ቃል ልክ መለሰለት።
“ጤናም የለው እንዴ ሰውየው?" ዘበኛው ካፖርቱን እላዩ ላይ ጣል
አድርጎ አጭር ዱላውን ይዞ ወጣ፡፡
ሂድ ግባ! ቦቦው የተዘጋጀው ላንተ እኮ ነው!" አለና ጮኹ፡፡
“የት ነው የምሄድልህ?!"
"አልጋው ስር አለልህ እኮ ነው የምልህ!"
“አልጋ ስር ሽና ነው የምትለኝ?!"
እዚህ ደጅ ግን መሽኛ ቦታ የለም! ያንተ ቢጤ ሰካራሞች ናቸው እዚህ እንኳን አልጋ ስር አልጋህም ላይ ሽናው! እሱ የኔ ችግር አይደለም!
ሽንታቸውን እየሸኑ የጉንፋን መጫወቻ ያደረጉኝ!” በንዴት ጮኸ፡ በዚህ በሁለቱ ጭቅጭቅ መሃል ዓለሚቱ ልቧ በፍርሃት ተውጦ እያዳመጠች ና። የውሽማዋን አመል ስለምታውቅ ሽማግሌውን ሲጥ!

👍4❤2
እንዳያደርጋቸው ፈራችና ልብሷን መለባበስ ጀመረች፡፡
"እኔ ወንዱ ነኝ አልጋ ላይ የምሸናው?!” ሰውነቱ እንደ አራስ ነበር እየተቆጣ መጣ፡፡
“ሂድ ግባ!…ወሬኛ!" ሽማግሌው በንቀት ወደዚያ ገፈተረውና በያዛት
አጭር ዱላ ከወደ መቀመጫው አካባቢ ዦበድ አደረገው ወይ አለማወቅ አይ ፍርጃ "ሌንጨ ቦሩ!! 'የቦሩ አንበሳ!! አለና ዘሎ ጉብ! አለበት። አይ የሽማግሌው
ዘበኛ ነገር? ሱሪው ሳይበላሽ ቀረ እንጂ መትረፍ አይበለው። ድመት
የያዛት አይጥ ሆነ፡፡ ፍፁም ያልገመተውና ያልጠበቀው ጣጣ ውስጥ ገባ፡፡ ሰውዬው ሲያዩት ባላገር ቢጤ ነው አስፈራርቼ እመልሰዋለሁ ነበር ግምቱ፡፡ አልሆነም፡፡ እጁ ከጉሮሮው ላይ እንዳረፈ አለሚቱ ደርሳ
እጆቹን ግጥም አድርጋ ከኋላ በኩል ባትይዘው ኖሮ ውጤቱ አሳዛኝ በሆነ ነበር፡፡ የአፈጣጠኗ ነገር፣ ከምኔው ሮጣ እንደደረሰች ጎንቻን ገርሞታል።ሽማግሌው እንደ በረዶ ቀዘቀዘና ነፍሱን ለማዳን አንገቱን ደፍቶ ሹልክ
ብሎ ወደ ዘበኛ ቤቱ አመራ። ጭራውን እንደተመታ ውሻ ኩምሽሽ ብሎ ገብቶ በብርድ ልብሱ ተጠቀለለ፡፡
“ምን ሰይጣን የለከፈው ሰው ነው እባካችሁ? ምነው ምላሴን በቆረጠው ኖሮ? የፈለገው ቦታ ቢሽና ምን አገባኝ? እንኳን እኔ ባለቤቶቹ ተቆጣጥረው ያልቻሉትን ጣጣ ከየሰካራሙ ጋር መተናነቅ?!”እያልጎመጎመ ወደ
እንቅልፉ ተመለሰ፡፡ ጎንቻ እንደ ፍላጎቱ ወደ አጥሩ ጥግ ተጠግቶ ሽና፡፡ እሱ እንደፈለገው አድርጎ በመመለሱ የሽንፈትና የውርደት ሽማ ያለመልበሱ አስደስቶት የሰላም ዕንቅልፍ ወስዶት አደረ።
በደንብ ሳይነጋ በሌሊቱ ተነሱና ተያይዘው ከአልቤርጎው ወጡ... ጎንቻ ሁለመናውን ከብዶታል። እንደተደነባበረ ነው። ከየሰዉ ጋር መተናነቅ፣ መያያዝ ይፈልጋል። ጥቅም የሌለበት ትንቅንቅ ቢፈጥርና ደም ቢያፈስ ደግሞ ትርጉም የሌለው ትርምስ መፍጠር ነው የሚሆነው። ገና በአንድ ቀኑ ደበረው፡፡ ከየስጋ ሻጩ ከየዘበኛው ጋር መለካከፍ ኤዲያ..
የአዲስ አበባ ግርግር የአዲስ አበባ ጫጫታ ከመጧጧፉ በፊት ቀድመው የተነሱት አካባቢውን ለማጥናት ነበር። እየተዘዋወሩ ከተማዋን በምልክት ሲያስሱ አረፈዱ። ከጠዋቱ አራት ሰዓት አካባቢ ሲሆን" እስቲ እህል እንቅመስ” አለች ዓለሚቱ። ጎንቻ ማታ ብዙ ጠጥቶ ስላደረ የምግብ ፍላጎቱ እምብዛም ነበር፡፡
"ያውና ያ ሆቴል ቤት ይመስለኛል። እስቲ ሄደን እንጠይቅ?" አላት
በጣቱ እያሳያት። ትልቅ ሻይ ቤት ነበር። ሁለት ክፍሎች አሉት።
ሙዚቃው ይጮኻል።ከወዲህኛው ክፍል ገብተው ተቀመጡ፡፡
"ምን ልታዘዝ?" ባሻሪው እየሮጠ መጥቶ፡፡
እስቲ እንጀራ በወጥ አምጣልን” ትእዛዙን የሰጠችው አለሚቱ ነበረች።
እንጀራ በወጥ እንኳን የለንም፡፡ ያለው ፉል፣ ፈታ፣ ዕንቁላል ስልስ፣
ዕንቁላል ፍርፍር፣ ፓስታ" እርስ በርሳቸው ተያዩ፡፡ "የቱ ይምጣልን?" ሌላ ጣጣ ውስጥ ከሠግባታቸው በፊት የሚያውቁትን ዕንቁላል ፍርፍር አዘዙና ተሰርቶ እስኪመጣላቸው ድረስ ጨዋታ ጀመሩ።
"ይሄ ሰፈር አላስደሰተኝም ዓለሜ ወደ ሌላ ደስ ወደሚል ሠፈር ብንሄድ ይሻላል" አላት የሰንጋ ተራ ትርምስ አስጠልቶት።
"ይቺን ሃይልህን ብቻ አደራህን ትንሽ ቀንሳት፡፡ ታገስ። ሁሉ ቦታ
እልኸኛ መሆን አያስፈልግም፡፡ ኃይልም ከትዕግስትና ከዘዴ ጋር ነው። ይሄ አዲስ አበባ እንጂ ኛሮ አይደለም፡፡ ችግር ውስጥ እንዳንገባ እሺ ጎንቻዬ?" ዐይን ዐይኑን በልምምጥ እያየችው።
“ኢልመ ቦሩ!!!…"አለና ፎከረ።ኳ!.ኳ! ኳ!....!ጋ! ወንበር ከወንበር አጋጭቶ ወደ ኋላው ሲያፈገፍግ ዓለሚቱ በድንጋጤ አመዷ ቡን አለ። እሷም ቱር ብላ ቆመችና ያስደነገጠውን ነገር ለማየት ዞር አለች። ዐይኖቹ
ከወዲያኛው ክፍል ውስጥ በሚመገበው ተመጋቢ ላይ ፈጠዋል። እሱ የሚያውቀውን መስለው፡፡ ዐይኖቹ ይበልጥ ተበለጠጡ። ተመጋቢው ግን
እሱ የመሰለውን ሳይሆን ከዱቄት የተሰራውን ፓስታ ነበር የሚበላው። ጉድ አየሽልኝ? በጣቱ ሲጠቁማት ዓለሚቱ በሳቅ ፍርስ አለች።“… ካ. ካ... ካ… ኪ. ኪ. ኪ. ምን ዓይነቱ ነህ? እንዴት አስደነገ
ጥከኝ?" ተመጋቢውም አስተናጋጁም ፀብ ሳይፈጥሩባቸው አፏን በእጇ
ሸፍና እየሳቀች እጁን ይዛ ቶሎ ብላ ወደ ወንበሩ መለሰችው።
“ "የሞትክ እኔን አትጠይቀኝም ነበር? ይሄኮ ልጁ ቅድም ባስታ ያለን ነው። ባስታኮ እህል ነው። አፈር ብላ! አሁን አንተስ ያንን ማሰብህ?" ተረጋጋችና ቁርሱን ትጠባበቅ ጀመር፡፡ ጎንቻ ግን መረጋጋት አልቻለም፡፡
"በቃኝ አልበላም፡፡ እዚህ ቤት ምንም ነገር አልቀምስም" አለ። ቀድሞውኑ የተዘጋው የምግብ ፍላጎቱ ድራሹ ጠፋ። ዓለሚቱ ግን የቀረበላትን ዕንቁላል ፍርፍር ግጥም አድርጋ በላችና ስትጨርስ ተያይዘው ወጡ።
ጎንቻ የሚናፍቀውን የለመደውን የተራበውን የኛሮን ትዝታ የኛሮን
ፀጥታ እያሰበ የመኪናው ኳኳታና ግርግር አስጠልቶት ብረር.ብረር...
አለው።
"ዓለምዬ" አላት።
"አቤት ጎንቻዬ?"
"ከዚህ ቦታ ቶሎ እንሂድ! ከዚህ ቦታ ቶሎ እንጥፋ! ወደዚያ ወደዚያ! ወደዚያ!" ዞር ብላ ተመለከተችው። ዐይኖቹ ወደ እንጦጦ ተራራ ወደ ጫካው ተወርውረው ፈጠዋል። ጭንቀቱ፣ ጥበቱ ዛፍ ያጣ ጉሬዛ አስመስሎታል።ጊዜም አላጠፉም፡፡ ደላላ አፈላልገው ወደ እንጦጦ ገሠገሡ።
ወደ ጫካው አካባቢ የኪራይ ቤት አፈላለጉና አንዲት ትንሽ ክፍል ቤት
አገኙ። ጎንቻ ልቡ ትንሽ መለስ አለች። በመጠኑም ቢሆን ተረጋጋ።
ቀን ቀን ጫካ ጫካውን ይዞ እየተዘዋወረ ሲናፈስ ይውልና ሲመሽ ሹልክ ብሎ የማትሰለቸው ዓለሚቱን እንደ ሎሚ እየመጠጠ ለአንድ ወር ያክል ወደ ከተማው ብቅ ሳይል ጊዜውን አሳለፈ፡፡ በቂ ገንዘብ ይኑራቸው እንጂ ከስር ከስሩ ካልተተካበት እያለቀ መሄዱ የማይቀር ነው። ጎንቻ ደም ካየ ብዙ ጊዜ ሆኖታል። ፈዛዛ ሊሆን ነው። ንቃት የሚያገኘው ደስ ደስ
የሚለው ደም ሲያይ ነበር፡፡ ጎሮሮ ማነቅ፣ መንጠቅ ይፈልጋል። ግን
እንዴት አድርጎ?ይህን ፍላጎቱን ለማሳካት አካባቢውን ቶሎ ለማወቅ ፈለገ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ወደ ስድስት ኪሎ እየሄደ የአንበሶቹን ግቢ ሽቦ አንቆ ሲያያቸው ይውላል። አንበሶቹ አፋቸውን ሲከፍቱ ጎፈሬአቸውን
ሲበትኑ ሲያራግፉት ሥጋ ሲነጩ እያየ ትንሽ ትንሽ እፎይ ይላል።
የአንበሶቹን ህይወት ከራሱ ህይወት ጋር እያዛመደ የአንበሶቹን ግቢ የበለጠ ወደደው፡፡ እሱ ጎፈሬውን ተላጭቷል፡፡ አንበሳው ግን ጎፈሬውን አልተላጨም፡፡ እሱ እንደ ልቡ ይዘዋወራል ወደፈለገው ይሄዳል አንበሳው ግን ወደፈለገው መሄድ አይችልም፡፡ በሽቦ ውስጥ ታፍኖ አንዱ ወዲህ አንዴ ወዲያ ይንጎራደዳል። የጫካ ንጉስ ሆኖ የፈለገውን ደቁሶ ደም አፍስሶ ትኩስ ስጋ መንጨት አልቻለም፡፡ የተሰጠውን ደም የሌለበት
የቀዘቀዘ ስጋ ይነጫል፡፡ እሱ ደግሞ እንደፈለገው በሰፊው ከተማ ውስጥ እየተንጎራደደ ጉሮሮ አንቆ ደም አፍስሶ መንጠቅ እየፈለገ ያንን ማድረግ አልቻለም፡፡ ይሄን የራሱን ህይወት በአንበሶቹ በተለይ ደግሞ በዚያ በትልቁ በጎፈሪያሙ አንበሳ ህይወት ውስጥ እየተመለከተ ያንን አካባቢ
አዘወተረ። ዘሎ ሰው ቢያንቅ ጣጣው አጉል ነው፡፡ ዋሻውን ገደላ ገደሉን መደበቂያ መሽሽጊያውን በሚገባ ማጤን ዘዴውን ማጥናት አለበት።
ለዚህ ስራው ተባባሪዎች ማግኘት አለበት፡፡ አዲስ አበባ እንደ ኛሮ ዋሻ እንድትሆንለት በአዲስ አበባ ውስጥ ኛሮን ለመፍጠር ከከተማ ሽፍቶች ከከተማ ወንበዴዎች ጋር በአስቸኳይ በመቀላቀል ስራውን መጀመር አለበት። እሱም ዓለሚቱም ለአገሩ እንግዶች በመሆናቸው ምክንያት ፍላጎቱን በአስቸኳይ ማሳካት አልቻለም፡፡....
✨ይቀጥላል✨

#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
.....ምነው ዶክተር? ሰላም አይደለህም እንዴ?» አለና ሰላም ብሎት ከአጠገቡ ቁጭ አለ፡፡ አስቻለው ነርስ ስለሆነ ጓደኞቹ ብዙ ጊዜ ዶክተር፡ አያሉ በመጥራት ያሾፉበታል፡፡
«ትንሽ ሳያመኝ አይቀርም» አለው የሚነበብበትን የጭንቀት ስሜት
ያስወገደ መስሎት የፊቱን ላብ በእጁ እየጠረገ፡፡
«ሀኪምም ያመዋል እንዴ?»
«ጠንቋይ ለራሱ አያውቅም ይባል የለ!»
ወዲያው ደግሞ መርዕድ ከውጭ ሲመጣ ሁለቱም አዩት፡፡ መርዕድ አጠር ያለ፣ መልኩ ደግሞ ጥቂር ነው:: ነጣ፣ ገጠጥ ያሉ ጥርሶቹ ከሩቅ ይታያሉ፡፡በተፈጥሮው ፈገግተኛ ቢሆንም ላኩርፍ፡ ቢል እንኳ ጥርሶቹ አይገጥሙለትም፡፡
አፍንጫው አጭርና ደፍጣጣ ናት፡፡ በጥቁር ፊቱ ላይ ቁልጭ ቁልጭ የሚሉት ዓይኖቹ እጥረቷን ይሸፍኑለታል፡፡ ሊቀላቀላቸው ሁለት ወይም ሶስት ርምጃዎች ሲቀሩት በልሁ እንደ ልማዱ በቀልድ ዓይነት፡-
«ስማ አንተ እስከ አሁን ቆይተህ ራት አልቋል ቢባል አንተኑ ነው
የምጎርስህ!» አለው።
አንተ እኮ የአቶ ተገኔ ልጅና የግብርና ስራተኛ ባትሆን ኖሮ ሰውጰአይተርፍህም ነበር!» በማለት መርዕድም የቀልድ ምላሽ እየሰጠ ተጠጋቸውና ሰላም
ብሏቸው ከአጠገባቸው ቁጭ አለ፡፡ በልሁና አስቻለው በመርዕድ መልስ ተገርመው እየተያዩ ሲሳሳቁ መርዕድ ቀጠለ፡፡
«ሀሰት ነው?» አለ በተለይ በልሁን ፈገግ ብሎ እያየ፡፡
"መቸም አንተ የምትለው አታጣ! አስተማሪ አይደለህ?» አለና በልሁ
በቀልድ ዓይነት ቡጢ ቃጣ አደረገበት።
የመርዕድ ቀልድ መሠረት አለው። በልሁ የባላባት የልጅ ልጅ ነው፡፡
አባቱ አቶ ተገኔ ክብረት ከደብረ ብርሃን በስተምዕራብ በኩል በግምት በሰላሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ገጠራማ ቀበሌ ይወለዳሉ:: ከአባታቸው የወረሱትን በርካታ ጋሻ መሬት ገና በንጉሡ ጊዜ ሽጠው ሽጠው በደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ
በርካታ የንግድ ድርጅቶችን አቋቁመዋል፡፡ ሆቴል የሸቀጣሸቀጥ መደብር፤ በርካታ
የእህል ወፍጮዎችን ከማደራጀታቸውም በላይ አንድ ከባድ የጭነት መኪናም
አላቸው። የእሳቸውን ያህል አይሁን እንጂ በዕድሜ ከብልሁ በላይ ያሉ አራት ልጆቻቸውንም በንግድ ሥራ አቋቁመዋቸዋል።
በልሁ ለአባትና ለእናቱ የመጨረሻ ልጅ ነው፡፡ በቤተሰቡ ውስጥ እንደ
ብርቅ ስለሚታይ በማር በወተት ያደገ ነው። በቤተሰቡ ውስጥ እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ የተማረው እሱ ብቻ ነው፡፡ ከዓለማያ እርሻ ኮሌጅ በድግሪ ተመርቆ በዲላ
ከተማ በአውራጃው ግብርና ጽህፈት ቤት ውስጥ በባለሙያነት ያገለግላል፡፡ በዘመኑ እስከ ዩኒቨቨርስቲ ደረጃ ተምሮ የመንግስት ስራ አለመያዝ የማይደገፍ በመሆኑ እንጂ
እንደ ቤተሰባዊ መሠረቱ ቢሆን ኖሮ ለሥራ ሲል ዲላ ድረስ መሄድ ባላስፈለገው ነበር፡፡ ያም ሆኖ በአስፈለገው ጊዜና መጠን ከቤተሰቡ ገንዘብ ይላክለታል። ደብረ ብርሃን ብቅ ካለም በገንዘብ ተንበሽብሾ ይመለሳል። በዚያ ላይ አዘውትሮ ለመስክ ስራ ስለሚወጣ አበል ሳያገኝ እንዲት ወር እንኳ አታልፍም፡፡
መርዕድ ግን በሐረርጌ ክፍለ ሀገር ከደሃ የገበሬ ቤተሰብ የተወለደ
ከመሆኑም በተጨማሪ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር በመሆኑ በአነስተኛ ገቢ የሚኖር ነው።ከደሞዙ ሌላ ምንም አያገኝም እናም በበልሁ ኑሮ ይጎመዣል::ደግነቱ በልሁ በተፈጥሮው ቸር ከመሆነም በላይ መርዕድን በጣም ስለሚወደው
በቸገረው ሁሉ ይረዳዋል።
የኑሮአቸውን ልዩነት ግን የዘወትር
መቀላለጂያና መለከፋያቸው አድርገውታል።
ሦስቱም ጓደኛሞች ራታቸውን አዝዘው አጥንት እየተሻሙ በልተው ከጨረሱ በኋላ አስቻለው ከቀልዳቸው ሠልሶ ከአንድ ቁም ነገር ውስጥ ከተታቸው።
«ዛሬ አንደ ልጅ ልልካችሁ ነው፡፡» አላቸው ዓይኑን በሁለቱም ላይ ዞር ዞር አድርጎ እያያቸው::
«የት?» ሲል ጠየቀው በልሁ።
«ከሸዋዩ ቤት»
«ለምን አለ መርእድ በተራው፡፡
«ለአንድ ብርቱ ጉዳይ:: አላቸው» አስቻለው ፈገግ ብሎ እያያቸው፡፡
በዚህ ጊዜ በልሁ ድንገት «ሃ-ሃ-ሃ-ሃ..." ብሎ ሳቀና «ብቻህን ሮጠህ ሮጠህ ሲሰለችህ ጊዜ ዛሬ ደግሞ ፖስተኛ አስፈለገህ እንዴ?» ሲል ቀለደበት። ሦስቱም
ተሳሳቁ:: አስቻለው ከሔዋን ጋር ከተዋወቀ ጊዜ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ለብቻው ወደ ሽዋዬ ቤት ስለሚሄድና ይለያቸው ስለነበረ ነው የአሁኑ ለበልሁ ቀልድ መሠረቱ፡፡
«አትቀልዱ ችግር ተፈጥሯል፡» አላቸው አስቻለው ኮስተር ብሎ፡፡
"እኮ" ምን?» ሲል በልሁ አሁንም እየሳቀ ጠየቀው::
አስቻለው ከታፈሡ ያገኘውን መረጃ ዘርዝሮ አስረዳቸው፡፡ ስለ ሔዋን ሁኔታ ያደረበትን ስጋት ገለፀላቸው፡፡ ቀጥሎም አስቻለው ጠፋብን፣ እዚህ መጥቶ ከሆነ ብለን ነው በሚል ሰበብ ሔዋን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች ሰልለው መረጃ ይዘውለት እንዲያወጡ ጠየቃቸው::
በልሁና መርዕድ የአስቻለውን ማሳሰቢያ በቀላሉ አላዩትም፡፡ ሔዋንን የእሱን ያህል ያውቋታል። በጣምም ይወዷታል። ባህሪዋንም! የነበረባትንም ስጋት
ሁሉ ያውቃሉ። የተፈጠረው ሁኔታ ከአስቻለው ባልተናነሰ መልኩ አሳሰባቸው፡፡ በዚህም ምክንያት እንደ ወትሮ ከእራት በኋሳ ሻይ ቡና ማለት አልፈለጉም በቀጥታ ወደ ሸዋዬ ቤት ሊሄዱ ተነሱ፡፡ በልሁ ቀልድ ይወዳልና
«ችግር ካለ ሔዩን ተሸክመንም ቢሆን ይዘንልህ እንምጣ እንዴ ዶክተር?»
ሲል አስቻለውን በፈገግታ እያየ ጠየቀው፡፡
«ያን ካደረገችሁማ ትሽለማላችሁ» አለው አስቻለውም እንደ ቀልድ።
“ትሰማለህ፣ መርዕድ!» አለ በልሁ ቀልዱን ለመቀጠል፡፡ «ሽልማት ካለው ችግር ኖረ አልኖረ ሐዩን ዝም ብለን አምጥተን እንጣልለትና እንዳረገ ያድርጋት።
እኛም ሽልማታችንን እንቀብል።»
«እኔ የለሁበትም» አለ መርዕድ ሳቅ እያለ።
በልሁና መርዕድ በደህና ቦታ ላይ ተቀላልደው ወደ ምሩ ቦታ ጉዞ ጀመሩ፡ ወደ ሸዋዬ ቤት።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሰው አይችለው የለ እንዲሉ ሸዋዬ በተለይ ከእንድ ቀን በፊት ጀምሮ
በአዕምሮዋ ውስጥ የሚተረማመስ የሃሳብ ብዛት ቢመዘን ክብደቱ፤ ቢለካ ርዝመቱ፣
በዓይን የሚታይ ቢሆን የብዛቱ ነገር የትየለሌ በሆነ ነበር፣ ያላሰበችው ዱብ ዕዳ ወርዶባት ምስቅልቅል ባለ ስሜት ውስጥ ገብታ ትቃትታለች::
የሃሳብና የጭንቀቷ ስር ያኔ ከአዋሳ ወደ ዲላ ከአስቻለው ጋር
እስከተጓዘችበት ቀን ድረስ የተዘረጋ ነው:: ትዝ ይላታል የጉዟቸው ሀኔታ፡፡ ትዝ ይላታል ከአስቻለው ጋር ያደረገት ጭውውት፡፡ ትዝ ይላታል አስቻለው ያደረገላት ዕርዳታ፡ ቆጠብ ያለ አነጋገሩ፣ እንዲሁም በጆሮዋ የተንቆረቆረው ማራኪ ድምጹ።
በተለይ ዲላ ደርሳ ከታፈሠ ጋር ተገናኝታ ለቀናት ያህል እዚያው በሰነበተችብት ወቅት ታፌ በጨዋታ መሀል እያነሳች አስቻለው የልጆቿ ክርስትና አባት
መሆኑን ከመግለጽ ጀምሮ ማንነቱን ባህሪውን ፣ ሙያውንና አኗኗሩን ሁሉ በሰፊው አስረድታት ነበር፡፡ የዚህ ሁሉ መድሃኒት የሽዋዬን ልብ በፍቅር ወደ እስቻለው ዘንበል እንዲል አድርጎት ደስ የሚል ወንድ እስከ ማለት ደርሳ ነበር፡፡
ክብረ መንግስት ሄዳ ለአንድ ወር ያህል ከወላጆቿ ጋር የዕረፍት ጊዜዋን ባሳለፈችበት ጊዜ ሁሉ አስቻለውን ለአንድም ቀን ረስታው አታውቅም:: ሁሉም ነገሮቹ በዓይነ ህሊናዋ ዉል ሲሏት ቆይተዋል። በደ ዲላ ስትመሰስ ምን ዓይነት

ዘዴ ፈጥራ ልትቀርበው እንደምትችል ታሰላስል ነበር፡፡ እሷ የታፈሡ ጓደኛ፣ እሱ ደግሞ ከጓደኝነትም በላይ የታፈሡ አበልጅ እንደ መሆኑ ሁሉንም ነገር በታፈሡ ጥላ ሥር ልትመክር እንደምትችል ይታያት ነበር፡፡ ከታፈሡ ቤት አይጠፋምና ነጋ
መሸ ልታየውና ልታገኘው እንደምትችል በማመን በፍቅር ቀርባ ልታቀርበው
የምትችልበትን መንገድ ስታሰላስል ከርማለች፡፡
በነሐሴ ወር አጋማሽ ላይ ዲላ መጥታ ቤት ተከራይታ የምርቃት ምሳ አዘጋጅታ አስቻለውን የጠራችው ለዚሁ ዓላማዋ አንድ ርምጃ መራመዷ ነበር፡፡ ጠርታው በመምጣቱ ደስ ብሏታል። ሽር ጉድ ብላም አስተናግዳዋለች፡፡ ከሁሉም በላይ በዚያ አጋጣሚ ቤቷን ማወቁ ለወደፊት ግንኙነታቸው መሠረት ሊጥል
እንደሚችልም ተስፋ አድርጋ ነበር፡፡
በእርግጥ አስቻለውም ወደ ቤቷ ብዙ ተመላልሷል፡፡ በተለይ ማታ ማታ ብቅ እያለ ሲያጫውታት ከርሟል፡፡ እንዳንዴም ወደ ከተማ ይዟት እየወጣ አዝናንቷታል። የሆቴል ምግብ አብረው በልተዋል፡፡ የመጠጥ ዓይነቶችንም ቀማምሰዋል፡፡ በርካታ ርዕሶችንም እያነሱ ተጨዋውተዋል፡፡ ነገር ግን እስቻለው ወደ ፍቅር ያዘነበለ ስሜት ሳታይበት ወራት አለፉ፡፡
አስቻለው የፍቅር ጥያቄ ሳያቀርብላት ሲቀር እየጨነቃት አንዳንድ ሰው ትሳለኝ በሃሳቧ የዕውን ሁለመና ሳያጠና ልቡን በፍቅር አይከፍትም፡፡ አንዴ
ከከፋተ ደሞ በቀላሉ አይዘጋም፡፡ ይህም ሰው ባህሪው እንደዚያ ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡” በማለት የራሷን ምክንያታዊ ግንዛቤ ትፈጥራለች፡፡
ቀን እየረዘመ ሲሄድ ደግሞ ሌላ ሃሳብ፡፡ (ይኸ ሰው ምናልባት ሰው
የማያውቃት ሌላ ሴት ትኖረው ይሆን እንዴ? ወይስ ንቆኝ? መቼም ቆንጆ ባልሆንም ገና አፍላ ነኝ፡፡ ሊያገባኝ ባይፈልግ እንኳ ለወዳጅነት ታንሳለች ብሎ አይገምተኝም።” ካለች በኋላ ግን እኮ! ዝምብሎ በእህትነት ሊያየኝ አስቦም ሊሆን ይችላል ወይ ደሞ" ይህን ያህል ጊዜ በእህታዊና ወንድማዊ ግንኙነት ስለቆየን እንደገና ሃሳቡን ለመቀየር ፈርቶ ሊሆን ይችላል በማለት ታስብ ጀመር፡፡
ይሄኛው ስጋት እያየለባት በመሄዱ ሰሞኑን አንድ መላ ፈጥራ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት ላይ ነበረች፡፡ ጠቀም ያለ ገንዘብ እጇ ላይ መያዝ አስቻለውን አስቻለውን
ራሷ ስትጋብዘው ልታመሽ ከአቅሙ በላይ እንዲጠጣ ልታደርገው ከተማ ውስጥ
ብዙ ልታስመሸው በኋላም በእሱ ቤት በኩል ወደ ቤታቸው ሊመለሱ ከእሱ ቤት አካባቢ ስትደርስ እልቻልኩም” ብላ ልትዝለፈለፍና ቤትህ አስገብተህ አሳርፈኝ
ልትለው ቅር እንደማይለው ታውቃለች፡ ገብታ በበልሁና በመርዕድ ጫት መቃሚያ ፍራሽ ላይ ልትተኛ ያኔ ስንፈተ ወሲብ ከሌለበት በቀር ነይ አልጋው
ላይ ተኚ ሊላት እንደሚችል በማሰብ ይህንኑ ልትፈጽም ወስና ቀን መምረጥ ብቻ ነበር የቀራት፡፡ ግን ደግሞ ሳታስበው ባልጠበቀችው ሁኔታ የስሚት እንቅፋት ተፈጥሮባት እነሆ ዛሬ ውልክፍክፍ ብላለች፡፡
ከታፈሡ በዕለተ ሰኞ ከመጣላቷ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በዕለተ እሁድ ከአንድ የሥራ ባልደረባዋ ጋር ስለ ፈተና ዝግጅት ልትነጋገር ከጠዋቱ ሁለት ሠዓት አካባቢ ከቤቷ ወጥታ ከረፈደች፡፡ ጉዳይዋን ጨርሳ ስትመለስ ቤቷ ተዘግቶ አገኘችው ፡፡ ትዝ ሲላት ሔዋን ወደ ገበያ ሄዳ የወጥ ቅመማ ቅመሞች እንድትገዛ
አዛታለች፡፡ ቤቱ የመዘጋቱ ምክንያት የእሷ ወደ ገበያ መሄድ መሆኑን ተገንዝባ ራሷ በያዘችው ቁልፍ፡ ከፍታ ለመግባት ወደ በሩ ስትራመድ ድንገት አንዲት ህጻን እት አበባ ስትል ጠራቻት፡፡ ሕጻኗ ለሽዋ ቤት የአከራዩዋት ወይዘሮ
ዘነቡ የሚያሳድጓት ዘመድ ልጅ ናት፡፡ ከአምስት እስከ ስድስት ዓመት ይሆናታል ከወይዘሮ ዘነቡ ቪላ ቤት በስተጓሮ በኩል ጥግ ይዛ ዕቃ ዕቃ ትጫወታለች:: ሔዋን
ሽዋዬን እት አበባ እያለች ስትጠራት እየሰጡ ያቺ ህጻንና ወይዘሮ ዘነቡ ሰራተኛ
ሸዋዬን በዚሁ ዕዠስም ነው የሚጠሯት።
«ውይ ሚሚዩ።!» በማለት ሸዋዬ ለሕጻኗ ጥሪ መልስ ሰጠችና በዚያው ቀጥላ «ቡናሽ ደርሷል?» ስትል በማየት ዓይነት ጠየቀቻት፡፡ ሕጻኗ ግን የሸዋዬን ጥያቄ ወደ ጎን ትታ የራሷን ቀጠለች፡፡
«የሔዋን አባት መጥቶ ቤቱ ሲዘጋበት ጊዜ ተመልሶ ሄደ፡፡» አለቻት።
«እ!» አለች ሽዋዬ ምንነቱን ያላወቀችው ስሜት መላ ሰውነቷን ነዘር እያደረጋት። ቤት መክፈቷን ትታ ወደ ህጻኗ ልጅ በማቆብቆብ ማነው የሔዋን አባት አንቺ» ስትልም ጠየቀቻት፡፡
«አስቻለው ነዋ! ህእ!» አለች ሕጻኗ አጎንብሳ ቆርኪዎቿን እየደረደረች፡፡
«እስቻለው?»
«አዋ! ሀእ!»
ሽዋዩ የባሰ ደነገጠች፡፡ ዓይኗ እህጻኗ ላይ ሳይነቀል ፍጥጥ ብላ ታያት ጀመር፡፡ እሷም ሔዋንም በሌሉበት አስቻለው መጥቶ እንደተመለስ ገባት፡፡ የቸገራት
በዚያች ህጻን አንደበት አስቻለው የሔዋን አባት መባሉ ነው:: በዲላና አካባቢዋ ባለው ህብረተሰብ ውስጥ ባል አባት ተብሎ እንደሚገለጽ ታውቃለች:: እናማ አስቻለው የሔዋን ባል? በጣም ግራ የገባት ይኸ ብቻ ነው።
«እንዴ!አለችና ሽዋዬ አሁንም ህጻኗን ትኩር ብላ እየተመለከተች
«አስቻለው የሔዋን አባት መሆኑን ማን ነገረሽ አንቺ?» ስትል ጠየቀቻት፡፡......

#ክፍል_አርባ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....እሱም ዓለሚቱም ለአገሩ እንግዶች በመሆናቸው ምክንያት ፍላጎቱን በአስቸኳይ ማሳካት አልቻለም፡፡ ይሁን እንጂ እየዋለ እያደረ እሱ የሚፈልጋት ወንጀል እሱ የተጠማት ደም ወዳጅዋን ፍለጋ ዳዴ እያለች እየመጣችለት ነበር።
እንደ ልማዱ የአንበሶቹን ግቢ አጥር አንቆ አንበሶቹን ይመለከታል።
“ሲያዩት ገና ከገጠር የመጣ ነው" አለ ከወዲያ ማዶ ሆኖ ሁኔታውን ሲከታተል የነበረው ጆብሬ፡፡በአዲስ ልብሱ በቦላሌ ሱሪው ውስጥ ደንበኛ ባላገርነቱን አነበበ፡፡ በሃሳቡ ከኮት ኪሱ ውስጥ ከብብቱ ስር ገብቶ ሲሞዠልቀው ታየው።
እጅሬ የእርሻ በሬዋን ወይንም የጎተራ ጥሬዋን ሸጣ በርካታ ብር ሳትይዝ አትቀርም"ብሎ ገመተና "ልዳብሳት!"ሲል ወሰነ፡፡ አስፋልቱን ተሻገረና ወደ አንበሶቹ ግቢ መጣ፡፡ ጠጋ አለ። ወደ ጎንቻ፡ ሽቦውን በሁለት እጆቹ ግጥም አድርጎ ይዞ "ፓ! ወይኔ! ኧረረረ!!…አፉን እንዴት ነው የሚከፍተው በእናታችሁ?!” የጎንቻን የባላገሯን ልብ ሰልቦ ትኩረቷን በአንበሳው
ላይ እንድትጥል ለማድረግና ከዚያም ያለ ሀሳብ ኪሷን ለመዳበስ ነበር።
በጆብሬ አመለካከት ጎንቻ አፏን ከፍታ የቀረችው አንበሳ አይታ ስለማታውቅ ነው፡፡ ያላወቁ አለቁ! አሉ?…ቀስ በቀስ ባላገሯን ተጠጋት። እባቡ ጎንቻ! እንኳንስ ስው ጥላውን የሚጠራጠረው ጎንቻ የጆብሬን እንቅስቃሴ ቀርቶ ሃሳቡን ከነቃበት ቆይቷል። የበግ ለምድ የለበስ የቀበሮ ባህታዊነቱን ያላወቀው ጆብሬ ሲፈርድበት እነዚያ በልምድ የዳበሩ ጣቶቹን
በመቀስ ፎርም ወደ ጎንቻ የኮት ኪስ ሰደዳቸው።
“ሌንጨ ቦሩ!!" አለና ፎከረ እንደ ልማዱ።
ሂድ!ጀጋ! ምን አባክ ሆነሃል?!! ገገማ!!. ጆብሬ ዐይኖቹ እንደፈጠጡ እንደማፈግፈግም እንደማስፈራራትም አደረገው፡፡ ጡንቻውንም እንደማሳየት ቃጣው። ዳሩ ምን ያደርጋል? ያ ባላገር ፤ላጆብሬም እንደ ህልም ሆኖ በሚታወሰው ኃይል ከብረት ምጣዱ ላይ ተሰቅስቆ እንደሚነሳ ቂጣ ሰቅስቆ ወደ ሰማይ አነሳና አስፋልቱ ላይ አነጠፈው። ሲሰርቀው ኪሱ ሊገባ የተመለከቱ ሰዎች ከበቡ። ጆብሬ ሌባ
መሆኑን ከሚመስክረው የተጫጫረ ፊቱ ሌላ የሚያውቁትም ነበሩ፡፡
“ጎሽ! ጎሽ! እሰይ! ወንድ!.. ይበለው! ይበለው ይንጫጩ ጀመር፡፡
“ባላገር መስላ አጅሬ ወንድ ናት!!" ጎንቻን አደነቁ፡፡ ጎንቻም አዲስ አበባ ከገባ ከአንድ ወር በኋላ ደም ካየ ደም ከተጠማ ከአንድ ወር በኋላ ምንም እንኳን ትርፍ የሌለውና ጥቅም የማያስገኝ ቢሆንም ደፍሮ ኪሱ የገባ
ጠላቱን ወደ መሬት ደፍቶ በአፍንጫና በአፉ ደም አስደፈቀው...ጎንቻ ደም አየ። ተደሰተ፡፡ በብዙ ሰው ኃይልና በበርካታ ክንዶች ወደ ላይ በግድ
ተጎትቶ ተነሳ። ቀልጣፋው ጆብሬ፣ አንበሳው ጆብሬ ጣቶቹ አነጣጥረው የማይስቱት ጆብሬ፣ ጉልበቱ የጅብ የነበረው ጆብሬ በጎንቻ ክንድ ውርደት ቀመሰ፡፡ ፍፁም ያልገመተው ነበርና ጎንቻን በአድናቆት ተመለከተው።
ጎንቻን ፈራው፡፡ በፍርሃትና በአድናቆቱ ውስጥም ወደደው። ደሙን ጠራረገና ሄደ። ራቅ ብሎ ከሄደ በኋላ እንደገና ዘወር ብሎ ጎንቻን በጥንቃቄ አስተዋለው፡፡ በአድናቆት ጭንቅላቱን እያከከ ተመልሶ መጣ፡፡
“ወንድ ነህ! ወንድ ጀግና!" እጁን በአድናቆት ዘረጋለት፡፡ ወንድነቱን አምኖ ተሸናፊነቱን ተቀብሎ እጁን የሰጠውን ምርኮኛ ሊያሳፍረው አልፈለገም::ያን ሲመኘው የነበረ፣ ያን ሲያቅበጠብጠው የከረመ ስራ የሚጀምርበትን ቀን ምክንያት አድርጎ ይሆን ጆብሬን የጣለለት? ማን ያውቃል?እጁን ሲዘረጋለት እሱም እየሳቀ ወዘወዘው፡፡ እንደገና ተቃቀፉ፡፡
"አንበሳ ነህ!" ሲል ጆብሬ በድጋሚ አደነቀው። ይሄ ሁሉ እርቀ ሰላም
የወረደው ፀቡ ከበረደና ለወሬ የተሰበሰበው ሰው ከተበተነ በኋላ ሆነ እንጂ ሁኔታቸውን ከመጀመሪያ ጀምሮ ለተከታተለ ሰው ጉድ የሚያሰኝ ነበር፡፡ እንደዚያ ተናንቀው ሲደባደቡ የነበሩት ሰዎች የደም ማግኔት አሳሳባቸውና አንደኛው አድናቂ ሌላው ተደናቂ ሆነው ጨዋታ ጀመሩ።
“ጆብሬ ጫን ያለው እባላለሁ!"
“ጎንቻ ሀጂ ቦሩ" እሰኛለሁ፡፡
"በጣም ወድጄሃለሁ ልጋብዝህ እፈልጋለሁ።"
“ዛሬ አልጋበዝልህም፡፡ ከፈለክ ለነገ እንቀጣጠር” አንድም ቶሎ ብሎ ተጋባዥ ላለመሆን ሁለተኛው ደግሞ የጆብሬን ቁም ነገረኛነት ለማወቅ
እንዲያስችለው በማግስቱ እዚያው አንበሶቹ ግቢ በራፉ ላይ ለመገናኘት ተቀጣጥረው ተለያዩ፡ ጆብሬ ሀቀኛ ስዓት አክባሪነቱንና ጎንቻን ለቁም ነገር የሚፈልገው መሆኑን አረጋገጠ፡፡ ከቀጠሮው ቀድሞ እየጠበቀው ነበር። ተቃቀፉ፡፡
“ቦታ ይዘን እንጫወት" አለውና ጆብሬ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ቁልቁል ይዞት ወረደ። ከዚያም አረቄ ቤት ይዞት ገባና አረቄ እየጠጡ ጨዋታው ደራ። ጆብሬ የህይወት ታሪኩን ይተርክለት ጀመር፡፡
"ወላጆች ነበሩኝ፡፡ መቼም ሰው ያለወላጅ አይፈጠርም! የኔ ወላጆች ግን በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ጥሩ ደመወዝ የሚከፈለው አንደኛው ራስ ወዳድ ሌላው ለኔ አሳቢ ሆኑና በሀሳብ ተለያዩ። አባቴ
ተቀጣሪ ነበር፡፡ እናቴ የቤት እመቤት ነበረች። ገና የሰባት ዓመት ልጅ ሆኜ በቤት ውስጥ ጭቅጭቅና ንትርክ በዛ። አባቴ መጠጥ ይወድ ነበር።
ወላ ሚስቴ የለ ወላ ልጄ የለ! ደመወዙን በአራጣ ለሚበደራቸውና በዱቤ
መጠጥ ለሚሸጡለት ሰዎች ከፋፍሎ ይጨርስና ዐይኑን አፍጥጦ በአል ኮል ነብዞ ይገባል። እናቴ ትንሽ ልትናገረው ከሞከረች አበቃላት። ዛሬን አያድርገው ዛሬን አትውደደኝና በጣም ትወደኝ፣ በጣም ታፈቅረኝ ነበር፡፡ለእኔ ስትል ታገሰችው፡፡ ሲደበድባት ተደብድባ ሲረግጣት መሬት ሆና ብዙ ቻለችው። እንደዚያ የሚያደርገው ቤቱን ጥላለት እንድትጠፋ ሆን
ብሎ ነበር። ጥላው እንዳትሄድ የኔ ነገር ጨነቃት። ከዚያ ቤት ውጭ
የማድግ አልመሰላትም። የአባት ፍቅር እጦት እንዳይጎዳኝ አሰበች፡፡ በመጨረሻ ላይ ግን ሁሉም ነገር ከአቅሟና ከትዕግስቷ በላይ ሆነባትና እኔን ይዛ ቤቱን ትታለት ጠፋች። ደስ አለው፡፡ ሊፈልጋት አልሞከረም፡፡ወዲያውኑ ሌላ ሚስት አገባ። እኔና እናቴ ከእህቷ ቤት ለኔ አክስት መሆኗ
ነው ከአክስቴ ቤት ገባን። አክስቴ ጠላና አረቄ ትሸጥ ነበር፡፡ እናቴ
እዚያው እሷን እየረዳች መኖር ጀመርን፡፡በዚሁ መሃል እናቴን አንዱ ካላገባሁሽ አላት። አገባችውና እኔን ይዛኝ ቤቱ ገባች፡፡ አዲሱ ባሏ እሷን ይወዳታል።እኔን ግን አይወደኝም፡፡ ዲቃላ! እያለ ይሰድበኝና ያሸማቅቀኝ ነበር።አባዬ ስለው አባት ይንሳህ የለማኝ ልጅ እያለ ያሳቅቀኝ ነበር።
ይሄን የሚያደርገው እናቴ ሳትሰማ ነው። እናቴ በጣም እንደምትወደኝ
ያውቃል። እሷ ፊት ይስመኛል። እሷ ዘወር ስትል ጭንቅላቴ እስከሚበሳ ድረስ በኩርኩም ያጋጨኝና ሳለቅስ እውላለሁ። የእንጀራ አባቴ ቀስ በቀስ ሰው ሳይሆን ጭራቅ እየመሰለኝ ሄደ። ሁል ጊዜ "ዲቃላ! ዲቃላ!
ዲቃላ!” እያለ እየሰደበ እየደበደበ ራሴንም እሱንም እንድጠላ አደረገኝ።
ይሄ ጥላቻዬ ደግሞ ለሱ ጥሩ እንዳልሆን መጥፎ ስራ እንድሰራ ይገፋፋኝ ጀመር፡፡ ቀስ በቀስ ገንዘብ ከኪሱ መስረቅ ጀመርኩ። የሱን ገንዘብ ሰርቄ ብስኩት ገዝቼ ስበላ ይጣፍጠኛል። የጠላት ገንዘብ ይጣፍጣል። እናቴ

❤1👍1
ተጨንቃ የምታዘጋጅልኝ ምግብ እንደዚያ አይጣፍጠኝም፡፡ ከሱ ሰርቄ ከሱ ነጥቄ የበላሁት እንደ ማር እየጣፈጠኝ ሱስ እየሆነብኝ ሄደ። እሱም ይበልጥ እየጠላኝ ሄደ:: "ሌባ! ሞሽላቃ" ሳንቲም ከኪሱ ባጣ ቁጥር ሌባ!
ዲቃላ! እያለ የጥላቻ ክሱን አበዛ፡፡ ይሄን ጨምላቃ ሌባ ልጅሽን...” እያለ ዘወትር ለእናቴ ስሞታ ማቅረቡን ተያያዘው። ሌብነት እንድጀምር የገፋፋኝ የአባትነት ፍቅሩን ነፍጎ ያገለልኝ እሱ መሆኑን ዘንግቶ ዲቃላ! ዲቃላ! ሌባ! ሌባ!...እያለ የልጅነት አእምሮዬን አቆሰለው፡፡ እኔም ቤቱ እያስጠላኝ ሄደ። ከሰፈር ልጆች ጋር ወደ ገበያ እየሄድኩ ዕንቁላልና ዶሮ
ሌላም ያገኘሁትን ነገር መስረቅ ጀመርኩ። ስርቆሽ ሱስ እየሆነብኝ ሄደ።
በነገራችን ላይ እናቴ ለእንጀራ አባቴ ለዚያ ለሚጠላኝ አውሬ ወንድ ልጅ የወለደችለት ቢሆንም ለኔ የነበራት ፍቅሯን ግን ለአንድ ቀን እንኳ አጉድላብኝ አታውቅም ነበር፡፡ እኔም ፍቅሬን አልቀነስኩባትም ነበር።የጠላቴ ልጅ ወንድሜ ከተወለደ በኋላ የእንጀራ አባቴ በኔ ላይ ጥላቻው
በእጥፍ እየጨመረ መጣ፡፡ የሱ ልጅ ጥሩ እንዲበላ ጥሩ እንዲለብስ እኔ የሱን ትራፊ እንድበላ የሱን ውራጅ እንድለብስ አደረገ።"ዲቃላ! የምናምንቴ ልጅ! ከልጄ እኩል መሆን ትፈልጋለህ?" እያለ በከፋ ሁኔታ ያሳቅቀኝ ጀመር፡፡ ለልጁ ልብስ ሲገዛ ለኔ አይገዛልኝም፡፡እሱን ትምህርት ቤት
ሲያስገባ እኔን ከቤት አስቀረኝ። ወንድሜን እንደ አባቱ አየሁት። እየጠላሁት ሄድኩ፡፡ የትም ውዬ ባድር ብታመም ብሞት እንጀራ አባቴ ለኔ ደንታ አልነበረውም፡፡ እንዲያውም ሞቴን ለማየትና ለመገላገል ይፈልግ ነበር፡፡ እኔም በጥላቻዬ ገፋሁበት። እናቴን ከማንም በላይ እወዳት ነበር።
በዓለም ላይ የቀረችኝ እሷ ብቻ ነበረች፡፡ ምን ያደርጋል ገና የአስራ ሁለት ዓመት ልጅ እንዳለሁ የምወዳት እናቴ በበሞት ተለየችኝ ዕንባው በዐይኖቹ ግጥም አለ፡፡
"የኔም ተስፋ የኔም ፍቅር ከእናቴ ጋር አብሯት ሞተ፡፡ለሰው ከነበረኝ ፍቅር ውስጥ የቀረኝ የናቴ ፍቅር ብቻ ነበረ። እሷ ስትቀበር ለሰው ያለኝ ፍቅር አብሯት ተቀበረ፡፡ በትምህርቴ እንዳልመካ የእንጀራ አባቴ አላስተማረኝም፡፡ መኖር እፈልጋለሁ፡፡ እናቴ ከሞተች በኋላ
የእንጀራ አባቴ አንተ ገፊ ዲቃላ እዚህ ቤት አይንህን እንዳላየው ብሎ አባረረኝና የምለብሳትን ቡቱቶ አውጥቶ ደጅ ጣላት። ውጭ በጎዳና ላይ ማደር ጀመርኩ። ከዚያም ሙሉ ለሙሉ ቤቱን ለቀኩለትና ጠፋሁ። የደረሰብኝ ችግር የእንጀራ አባቴ የሰጠኝ ትምህርት ለራስ ብቻ የመኖርን ትምህርት ሆነ፡፡ ለኔ የምኖረው እኔ ብቻ ነኝ፡፡ ስለ ራሴ የማስበው እኔ ራሴ ነኝ፡፡ ለራሴ ብቻ የማስብ ሰው ሆንኩ፡ስለ ሌላው ደንታ የለኝም።
እየነጠኩ እየሰረቅሁ ተይዤ ስደበደብ ዱላውን እየቻልኩ እኖራለሁ።
አንተን ባየሁ ጊዜ አንበሳ አይተህ የማታውቅ ባላገርነትህን እንጂ በባላገር ቆዳ ውስጥ የተደበቅክ አንበሳ መሆንህን በፍፁም አልገመትኩም ነበር፡፡
የዚያን እለት ተመልሼ ይቅርታ የጠየኩህ ንቃትና ጉልበትህ ስላስደነቀኝ ነው። ተመልከት ይሄ ሁሉ ስሰርቅ እየተያዝኩ በደረሰብኝ ዱላ ምክንያት ያረፈብኝ አሻራ ነው" ከፊቱ ላይ በግልፅ ከሚታየው ጠባሳ ሌላ በሆዱና
በጀርባው አካባቢ ያለውን ጭምር ያሳየው ጀመር፡፡ ፊቱ፣ ክንዱ፣ ሆዱ
ሁለመናው ተጠባብሷል። ጩቤ የፈተፈተው ሞት የጠላው መሆኑን ከሰውነቱ ላይ ባረፉት በርካታ ጠባሳዎች ውስጥ በጉልህ አስነበበው። ጆብሬ በጎንቻ ላይ በፈፀመው የስርቆሽ ሙከራ ያደረበትን ፀፀት ጭምር እየተ
ናዘዘ ቢሆንም ጎንቻ ግን በተቃራኒው ጆብሬን የመሰለ ሰው በማግኘቱ ውስጥ ውስጡን ልቡ በደስታ እየሞቀች ነበር። ቀስ በቀስ ያንን ሲያቁነጠንጠው የሰነበተውን ጥሙን ሊቆርጥ እየተቃረበ መምጣቱ ታወቀው።
የዛሬዋ ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ብሩህ ተስፋ ያየባት ልዩ ቀን ሆና ታየችው፡፡ ጨዋታው እየጣመው ቢመጣም ከመኖሪያ ቤቱ ርቆ ነበረና መውጣት ፈለገ።
“ቦታ ቀይረን እንጫወት?" ሲል ለጆብሬ ጥያቄ አቀረበለት። ጆብሬም በደስታ ፈንድቆ አካባቢ አስመረጠው።
'ለማንኛውም ወደ ላይ እንሂድ" አለ ጎንቻ፡፡ መቼም ቶሎ ብሎ ሰው አያምንም። ተጠራጣሪ ነው። ዓለሚቱ ሰውን ቶሎ እንዳያምን አስጠንቅቃዋለች።ቢከፋም ቢለማም ብሎ ወደ ራሱ ሰፈር ይዞት ሄደና የዘወትር ደንበኛው ከሆኑት ከወይዘሮ መደምደሚያሽ አረቄ ቤት ገቡ፡፡
እንደምን ዋሉ እትዬ መደምደሚያሽ?” አለ ጎንቻ፡፡
ደህና ዋልክ? ልጅ ጎንቻ! ምነው ዛሬ ዓለምዬን ጥለሃት መጣህ?
አዲስ ጓደኛ አገኘህ መሰለኝ?" ጆብሬን ከላይ ታች እያዩት።
“አዎን እስቲ ዛሬ እንኳ እንደ ሴቶቹ እቤት ትዋል ብዬ ነው” እየሳቀ
መለስላቸውና ተያይዘው ወደ ውስጥ ዘለቁ። በወይዘሮ መደምደሚያሽ ቤት ጠጪ ባለመኖሩ ጆብሬ ጎንቻ የልባቸውን ለመጨዋወት ቻሉ፡፡
ይሄንን አረቄ በላይ በላዩ እየከለበሱ መጋል ሲጀምሩ ጆብሬ ያጋጠመውን ታሪክ የፈፀማቸውን አኩሪ የሌብነት ታሪኮች በኩራት ይዘረዝርለት ጀመር፡፡ ጎንቻ ደም ሳያይ በጭንቀት ያሳለፈው ጊዜ ረጅም ሆኖ ታየው።
የሰው ቢጠፋ የአውሬ ደም ሳያይ አይውልም ነበር፡፡ ይሄንን ችግሩን አይቶለት ይሆን ጆብሬን ጀባ ያለለት? የሰፈረበት?…
“የኔን ታሪክ ደግሞ በሌላ ጊዜ አጫውትሃለሁ በሌላ ጊዜ እንገናኛ!” አለው፡፡
“መቼ እንገናኝ ታዲያ?” በጉጉት ጠየቀ ጆብሬ፡፡ ጎንቻ ሆን ብሎ ቆዳውን ለማዋደድ እንጂ ጆብሬን ሊለየው አልፈለገም ነበር፡፡
“መቼ ይሻላል?” ማሰፍሰፉን ሲያይ ጀነን አለ፡፡
ነገ አንገናኝም?" ጀብሬ በልምምጥ ዐይን ዐይኑን አየው።
እንገናኝ ብለህ ነው?ይሁን እሺ ግን በስንት ሰዓት?” የሚገናኙበትን ቦታና ሰዓት ተቀጣጥረው ተለያዩ፡በጣም ስለመሽ አለሚቱ ትሰጋለች
ብሎ ፈርቶ ነበር፡፡ ቤቱን ጆብሬ እንዳያይበት አርቆ ቁልቁል ከሸኘው በኋላ አድብቶ ተመለሰ፡፡
ምነው ጎንቻዬ አመሸህ?” አለሚቱ የወጡን ድስት እያማለለች ጠየቀ
ችው፡፡ ቀደም ሲል ከስው ጋር መጣላቱን አልነገራትም ነበር። ከመስሎቹ ጋር በአስቸኳይ ተቀላቅሎ ስራውን በፍጥነት እንዲጀምር እንጂ ረብ የለሽ ፀብ ፈጥሮ ተይዞ ታስሮ የሱ ምግብ አመላላሽ ሆና መቅረት አይደለም ፍላጎቷ፡፡ ይሄን ፍላጎቷን ደጋግማ ስለገለፀችለት ከጆብሬ ጋር መጣላቱን ደብቋት ነበር።
"እባክሽ ከሆነ ሰው ጋር ተዋውቄ ስንጨዋወት ሳላውቀው መሽ” አላት።
"ጎሽ! ሰው መተዋወቅ ጀመርክ ማለት ነው? ጎበዝ! ግን ጠንቀቅ በል።ሰውን ቶሎ አትመን እሺ? የምትተዋወቀውን ሰው ፀባይ አጥና። ሰላይ ሊሆን ስለሚችል እጅህን እንዳያስይዝህ"
"ግድ የለሽም ለኔ በጣም ጠቃሚ የሆነ ሰው ነው ያገኘሁት። እትዬ መደምደሚያሽ ቤት ስንጨዋወት ነው ያመሽነው፡፡ስለራሱ የህይወት ታሪክ አጠናሁ እንጂ ስለራሴ ምንም ያወራሁለት ነገር የለም፡፡ ይሄን ያክል በግ አደረግሽኝ እንዴ? እኔ ባልሽ ጠንቃቃ ነኝ እኮ” ሳቅ አለ፡፡ አሁን አሁን እኔ ባልሽ ነው የሚላት።ሙሉ የባልነት መብቱን አረጋግጧል፡፡ ጆብሬም
ጥሩ ጓደኛ ከተባለ ማለፊያ ትውውቅ ነው።
ዓለሚቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባን ተዘዋውራ በርካታ ቦታዎችን ማወቅ ችላለች። ዕቃ ለመግዛት ወደ መርካቶና ፒያሳ መውጣት አዘውትራለች፡፡ ዓለሚቱን ይዛት የምትወጣው የወይዘሮ መደምደሚያሽ

👍1
ሴት ልጃቸው ነበረች። ከዚያ መልስ ግን በጎንቻ ላይ ጉራዋ አይጣል ነው። የልዩ ልዩ ሰፈሮችን ስም እየጠራች የሄደችበትንም በወሬ የሰማችውንም ጨማምራ ሲኒማ ቤቶችን ትያትር ቤቶችን ስም እየቆጠረች መርካቶን፣ ፒያሳን፣ ጉለሌን፣ ኮልፌን፣ ተክለሀይማኖትን..." እያለች
ጉራዋን ትቸረችርበታለች፡፡
"አንቺ ሴትዮ ስትዞሪ ነው እንዴ የምትውይው?" ይላታል ላይ ላዩን እየሳቀና ውስጥ ውስጡን የቅናት ስሜት እየለበለበው፡፡
"አገሩን የማስሰው ጉድጓዱን የምምሰው ለወደፊት ኑሯችን ብዬ ነውኮ፡፡
አንተም ስራህን ቶሎ እንድትጀምር እኔም ቤት ውስጥ ከመቀመጥ አንዳንድ ነገሮችን እየሰራሁ መንቀሳቀስ እንድችል አካባቢውን አገሩን በደንብ ማጥናት አለብን አይመስልህም ጎንቻዬ?" በዚህ ንግግሯ ይስማማል።
የከተማ ዋሻ፣ የከተማ ዱር፣ የከተማ ጢሻዎችን ለመምረጥ ለንጥቂያ የሚመቸውን ሰፈር ለማጥናት፣ እሱን መሳዮች ለመተዋወቅና ስራውን
ብአፋጣኝ ለመጀመር አዲስ አበባን በደንብ ሊያውቋት ይገባል። ስለዚህ? ዓለሚቱ ሙሉ ቀን ከተማውን ስታስስ፣ ስትሯሯጥ ብትውል እግሯ እስከሚቀጥን ድረስ አዲስ አበባን ብትሽከረከር ለጋራ ጥቅም ነውና ሊከፋው
አይገባም፡፡
ጆብሬ መጀመሪያ ከተዋወቁበት ቦታ ከቀጠሮው ቀድሞ በመገኘት ምስጉን ሰዓት አክባሪነቱን በድጋሚ አስመሰከረ፡፡ ጎንቻን ለጥብቅ ጉዳይ እንደሚፈልገው የማረጋገጫ ምልክቶቹን ደጋግሞ አሳየ፡፡ እንደመጣ እቅፍ አድርጎ
ሳመው፡፡
ጎንቻ በባላገር ቆዳው ውስጥ የተደበቀ አስገራሚ ስብዕና ያለው ሰው መሆኑን ተገንዝቧል። ደፋርነቱ፣ ንቁነቱ፣ ጉልበታምነቱ ሁሉ ከበስተጀርባው ያለውን ሚስጥር እንደ መስታወት ወለል አድርጎ አሳይቶታል። በተለይ የህይወት ታሪኩን ሊነግረው ይጀምርና እንደ ስስፔንስ ፊልም እያንጠለጠለ በመሃሉ እያቋረጠበት ስለሚለያዩ የጎንቻን
ማንነት ለማወቅ አሰፍስፏል። በዐይኖቹ ቅላት በአነጋገሩ፣ በእንቅስቃሴው፣ በቀዥቃዣነቱ፣ የሱ ቢጤ ቀማኛ መሆኑን ስለገመተ ይበልጥ ስለጎንቻ ለማወቅ ልቡ ተሰቅላለች።
"ዛሬ እኔ ይሆናል ወደምለው ቦታ ወስጄ እንድጋብዝህ ምርጫውን ለኔ ብትተውልኝስ?" አለው ጆብሬ፡፡
"መልካም! ደስ ይለኛል የፈለከው ቦታ መሄድ እንችላለንአለ ጎንቻ
ከፊል እምነት ከፊል ጥርጣሬ ባደረበት አንደበቱ ።
ጆብሬ ጎንቻን ይዞት የሄደው ወደዚያ አንዱን ብርሌ ሲቀምሱለት እንደ ኤሌክትሪክ የሚያነዝር፣ ወደዚያ ቁልቁል ሲውጡት ጉሮሮ እያቃጠለ ኃይሉ እንደ ሚሳኤል ሽቅብ አናት ላይ ወደሚምዘገዘገው አራት ኪሎ
ከሚገኘው ትርንጎ ጠጅ ቤት ነበር፡፡ ጠጃቸውን ያለገደብ እየኮመኮሙ ቀስ በቀስ እየተፍታቱ እየተዝናኑ እየተጋጋሉ ሄዱ። ከዚያም መተቃቀፍ ጀመሩና የልባቸውን ተጨዋወቱ።ተማመኑ። ተማማሉ። ጎንቻ ከህይወት ታሪኩ ውስጥ ጥቂቱን አቀመሰው። የጆብሬ ዐይኖች በድንጋ
ጤና በአድናቆት እንደተበለጠጡ... አፉንም ጆሮዎቹንም በሰፊው ከፍቶ
ጎንቻ ከፈፀማቸው አሰቃቂ ተራጄዲ ትዕይንቶቹ መካከል ጥቂት ክፍሉችን ማዳመጥ ቻለ፡፡
ጆብሬ በተደጋጋሚ ተገናኝተን ተጨዋውተናል። የሰው ልጅ ቁም ነገረኛነቱ የሚለካው አብሮ በሚቆይበት ጊዜ ርዝመት አይደለም። ሙሉ ዕድሜ አብሮ መኖር ብቻውን ዋጋ የለውም፡፡ ቁም ነገሩ በአጭር ጊዜ
ትውውቅ ጠቃሚ ነገር ሰርቶ መገኘት ነው።በዚች አጭር ጊዜ ውስጥ እኔና አንተ ብዙ ቁም ነገሮችን ተጨዋውተናል። ሂድ ሂድ ይለኛል፣
ጥፋ ጥፋ ይለኛል። እልም ብዬ እንዳልጠፋ ደግሞ ፍቅር አለብኝ።ፍቅሬ ከሌለች መኖር አልችልምና እሷ ፍቅሬ ዓለሚቱን ጥዬ እንዳልጠፋ ተቸገርኩ። ልቤ ጫካ ውስጥ ዋሻ ውስጥ ነው ያለው። እኔ ደግሞ ያለሁት
እዚህ ነው።እኔና ልቤ እንዴት መገናኘት እንደምንችል መላ የሚፈልግልኝ አጣሁ። ምን አድርግ ትለኛለህ?" ዋሻው፣ ዱሩ፣ ጫካው የናፈቀው መሆኑን፣ደም የተጠማ አነር መሆኑን፣ የዘረፋው ትርኢት በዐይኑ ላይ የሄደበት የግድያ መድረክ የጠበበው ተዋናይ መሆኑን ከሞቅታ ጋር በስሜት ተውጦ በጋለ መንፈስ ገለፀለት። ጆብሬም የጎንቻ ፍላጎት ገባው።
"አይዞህ! የምትፈልገው የምትመኘው ሁሉ እዚሁ የተሟላ ነው። እንዲያውም ስላልለመድከው እንጂ ይሄኛው የበለጠ ያረካሃል። ፍቅርህን ጓደኛህን ትተህ የትም አትሄድም፡፡ እሷ እያለች እሷን ሳትርቅ ሁሉንም ከእኔ ጋር ሆነን እንወጣዋለን፡፡ዋሻውም ጫካውም እዚሁ አለልህ፡፡ አዲስ አበባ የስራ ቦታ ነች፡፡ ተረጋጋ" አንገቱን አቅፎ አይዞህ አብረን ነን በማለት .
በዛፍ ጫካ የተሞላች ባትሆንም በህዝብ ጫካ የተሞላች አስተማማኝ እውነተኛ ጓደኛነቱን ለመግለፅ ቃላት አጠሩት። ጎንቻ በእውነትም ከዓለሚቱ ጋር ለአንድ ቀን እንኳ ከተለየ የሚሞት እየመሰለው መሄድ ጀምሯል። አንዳንዱ ፍቅር እያደር ይቀዘቅዛል ይሰክናል፡፡ የጎንቻ ፍቅር ግን እየተባዛ.እየተደመረ እንጂ እየተቀነሰና እየተካፈለ የሚሄድ የፍቅር ሂሳብ ስሌት ሊሆን አልቻለም። በዚህም የተነሳ ከዓለሚቱ ሳይለይ ያንንፍላጎቱን ማሳካት እንዲችል አይዞህ እያለ ሞራል የሚሰጠውን ሰው
የበለጠ ወደደው። አመነው።
የቀማኞች ጓደኝነት የሚመሰረተው በዘረፋ የጋራ አጀንዳቸው ውስጥ
ነውና እንደዚያ ህይወት ንጥቂያ ቀረሽ ዱላ ተደባድበው በጎንቻ ጉልበተኛነት በጆብሬ የፈሰሰ ደም ውስጥ የፍቅራቸው አበባ ተተክላ ላፍሬ ልትበቃ እየለመለመች መሄድ ጀምራለች፡፡....

#ፍርሀት_ወለድ_ድፍረት
ቃጭል እንዳንጠለጠለች ፍየል
የቱን ፀበል ብትጠመቅ መደንበሩ እንዳይለቃት
አዳኝ እንዳየች ሚዳቋ
የቱን ምስል ብትሳለም ድንጋጤው እንዳይተዋት
ጠላቷን እንዳየች ሸለምጥማጥ
የእድሜዋን ሁሉ ሩጫ እንድትሮጥ በዚያች ሠዓት
ፍርሀት የወለዳት ድፍረት፡-
የትኛው ልጓም ሊገራት!
የቱ ክትር ሊያስቆማት!
🔘መንግስቱ በስር🔘
ቃጭል እንዳንጠለጠለች ፍየል
የቱን ፀበል ብትጠመቅ መደንበሩ እንዳይለቃት
አዳኝ እንዳየች ሚዳቋ
የቱን ምስል ብትሳለም ድንጋጤው እንዳይተዋት
ጠላቷን እንዳየች ሸለምጥማጥ
የእድሜዋን ሁሉ ሩጫ እንድትሮጥ በዚያች ሠዓት
ፍርሀት የወለዳት ድፍረት፡-
የትኛው ልጓም ሊገራት!
የቱ ክትር ሊያስቆማት!
🔘መንግስቱ በስር🔘
#የበቀል_ጎርፍ
ምን ያውቃሉ ህፃናቱ
ስለ ሸፍጥ ፖለቲካ-ጭፍን ጥላቻ-ሞኛሞኝ ብቀላ
ደግሞስ ምን ሊያቁ
እነሱ
ከአባሮሽ በቀር ካኩኩሉ
ከአይጤን አያችሁ አላያችሁ
ካልነጋም ወይ ኩኩሉ
ግና ምን ያደርጋል
ጥላቻ ህግ የለው ፤ ህሊና አይገድበው
በቀልም እውር ነው ፤ እውርም አይን የለው
እሾህን ካበባ ለይቶ ላይፈጀው
ግን ለምን ጥላቻ
ግን ለምን ብቀላ
አውሬነቱስ ለምን
መሰይጠኑስ ለምን
ለምን!
በቀል በቀልን ያረግዝ እንጂ አይገድል
ጥላቻ ጥላቻን እንጂ ፍቅርን አያበቅል፡፡
እኮ ለምን ?!
ለነገሩ ያዳም ልጅ አይደለን
እንዳልተገባ እያወቅን ያልተገባን የምንከውን
እሺ. . ይሁን
እንጠላላ ... እንገዳደል
አንጠላለፍ. . .እንበቃቀል
ግን ለምን ህፃናት
አንዳች ፋይዳ ላያመጣ
ሚጡን ማረድ፣ ቢጠን መቅላት
ምን ይሉት እርኩሰት. . .ምን ይሉት ጥንውት?
ደርሶ ሄሮድስነት ...እየሱስ ከሌለበት
ደርሶ ቦቅቧቃነት ተቀናቃኝ ካልዋለበት::
ግን ለምን ጥላቻ
ግን ለምን ብቀላ
አውሬነቱስ ለምን
መሰይጠኑስ ለምን
ለምን?
🔘መንግስቱ በስር🔘
መታሰቢያነቱ፡-
የጦርነት ሰስባ ለሆኑ ህጻናት
ምን ያውቃሉ ህፃናቱ
ስለ ሸፍጥ ፖለቲካ-ጭፍን ጥላቻ-ሞኛሞኝ ብቀላ
ደግሞስ ምን ሊያቁ
እነሱ
ከአባሮሽ በቀር ካኩኩሉ
ከአይጤን አያችሁ አላያችሁ
ካልነጋም ወይ ኩኩሉ
ግና ምን ያደርጋል
ጥላቻ ህግ የለው ፤ ህሊና አይገድበው
በቀልም እውር ነው ፤ እውርም አይን የለው
እሾህን ካበባ ለይቶ ላይፈጀው
ግን ለምን ጥላቻ
ግን ለምን ብቀላ
አውሬነቱስ ለምን
መሰይጠኑስ ለምን
ለምን!
በቀል በቀልን ያረግዝ እንጂ አይገድል
ጥላቻ ጥላቻን እንጂ ፍቅርን አያበቅል፡፡
እኮ ለምን ?!
ለነገሩ ያዳም ልጅ አይደለን
እንዳልተገባ እያወቅን ያልተገባን የምንከውን
እሺ. . ይሁን
እንጠላላ ... እንገዳደል
አንጠላለፍ. . .እንበቃቀል
ግን ለምን ህፃናት
አንዳች ፋይዳ ላያመጣ
ሚጡን ማረድ፣ ቢጠን መቅላት
ምን ይሉት እርኩሰት. . .ምን ይሉት ጥንውት?
ደርሶ ሄሮድስነት ...እየሱስ ከሌለበት
ደርሶ ቦቅቧቃነት ተቀናቃኝ ካልዋለበት::
ግን ለምን ጥላቻ
ግን ለምን ብቀላ
አውሬነቱስ ለምን
መሰይጠኑስ ለምን
ለምን?
🔘መንግስቱ በስር🔘
መታሰቢያነቱ፡-
የጦርነት ሰስባ ለሆኑ ህጻናት
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....አሜሪካን ግቢ፣ጌሾ ተራ፣ ዶሮ ማነቂያ፣ ሠራተኛ ሰፈር፣ እሪ በከንቱ በጎንቻ ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ የጆብሬና የጎንቻ ጓደኝነት ከሁለትነት ወደ አራትነት ተሸጋገረ። ጎንቻ ጀግንነቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመሰከረው
በፈጣን የአንገት ጥምዘዛ ነበር፡
አንድ ምሽት በሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ ለወሊድ የደረሰች ሚስቱን በሌሊት ሆስፒታል አድርሶ የመመለሻ መኪና አጥቶ ወደ ቤቱ ኩስ ኩስ የሚል ምስኪን አንገት እንደ ዶሮ ጠምዝዞ በመጣል ማንነቱን አሳየው።
ጆብሬ ፍጥነቱንና ቅልጥፍናውን የበለጠ አደነቀው።ከዚያን ግዜ ጀምሮ የበለጠ እያከበረውና እየፈራው መጣ፡፡ገንዘብ በሽበሽ ሆነ፡፡ ጆብሬ ኪስ ይዳብሳል።ጎንቻ ማጅራት ይመታል። ክርክር ከበዛ አንገት እንደ ፎጣ ጠምዝዞ ይጨምቅና ይበረብራል"ለካስ በከንቱ ኖሯል ኛሮ ኛሮ ያሰኘኝ?”
አለ፡፡ ኛሮን በአሜሪካ ግቢ ውስጥ፣ ኛሮን በጌሾ ተራ ውስጥ፣ ኛሮን በዶሮ ማነቂያ ውስጥ፣ ኛሮን በሠራተኛ ሰፈር ውስጥ፣ ኛሮን በእሪ በከንቱ ውስጥ አገኘው
ከኛሮ የቀረ የቀረበት ነገር ቢኖር
ዋሻውና የአውሬ ስጋው ብቻ ነበር፡፡በአዲስ አበባ ውስጥ የወላጆቹን ሃይማኖት ቀይሮ የዓለሚቱ ሃይማኖት ተከታይ ሆኖ አብረው ጮማ ይቆርጣሉ፡፡
አልኮል ይጨልጣሉ። ከዓለሚቱ ጋር በአረግራጊ ሽቦ አልጋ ላይ ያረገርጋሉ። ከዓላሚቱ ጋር እንደዚህ ዓለምን እየቀጩ በአዲስ አበባ ውስጥ መኖርን ቀስ በቀስ እየለመደው፣ እየወደደው መጣ፡፡ አዲስ አበባ ጣመችው፡፡ ጆብሬም
እውነተኛ ታማኝ ጓደኛነቱን አስመሰከረ ጎንቻን ጋሻ መከታው አደረገ፡፡ፀብ ከተነሳ ጎንቻ ገላጋይ መስሎ ተበዳይ ላይ ጉብ ነው፡፡ ጆብሬ የደነዘዘ ሰውነት ካገኘ ሞሽልቆ ያመልጣል። ከተነቃበትም ጎንቻ አለኝታው
ነው። ትርዒቱ ቀጠለ፡፡ አንደኛው የአደጋ ጣይ ቡድን ከሌላው ጋር
ተዋወቀ። በጎንቻ የበላይነት በዓለሚቱ ንብረት ተቀባይነትና አስቀማጭነት ወዳጅነቱ ተጧጧፈ።ሌሎቹ የቡድኑ አባላትም ዓለሚቱን በጥሩ አስተናጋጅነቷ ወደዷት። ፍቅር በፍቅር ሆኑ። መኖሪያ ቤታቸውንም ከእንጦጦ ወደ ዋናው መስሪያ ቤታቸው ወደ እሪ በከንቱ አዛወሩና አንድ ሰፊ ክፍል ቤት ተከራዩ።
በገንዘብ ላይ ገንዘብ ተጨመረ፡፡ እያለቀ፣ እየመነመነ የመጣው ገንዘብ ሲያሳስባት የቆየችው ዓለሚቱ ለመቁጠር እስከሚታክታት ድረስ ተንበሽበሸች፡፡ አራጣ በማበደር ሌላ የገቢ ምንጭ ከፈተች፡፡ በውበቷ ላይ ውበት፣
በጌጣጌጦቿ ላይ ጌጣጌጥ፣ በብር ላይ ብር አከማቸች።
ዛሬም በዓለሚቱ ካዳሚነት ጫት እየተቃመ የተዘረፈው ንብረት የሚቆጠርበት፣ ክፍፍል የሚደረግበት፣ እየተመረቀነ፣ እየተፈረሽ ውይይት የሚካ
ሄድበት፣ ተጨማሪ ዕቅድ የሚወጣበት፣ ስትራቴጂ የሚቀየስበትና ስልት
የሚነደፍበት ዕለት ነው፡፡ በቤቱ ውስጥ ያሉት ከዓለሚቱ ጋር አምስት ሲሆኑ ከጆብሬ ሌላ በቅፅል ስሙ “መቀስ" እየተባለ የሚጠራው አንበሴና
በጫት ምርቃና ላይ የሚንተፋተፈው አበራም ይገኙበታል። ጫት ከመጀመሩ በፊት ዓለሚቱ ሳር ጎዝጉዛ ፍራሽ አንጥፋ፣ ከሰል አያይዛ ሁሉን
ነገር አዘገጃጅታለች፡፡
የሜቱ ሥነ ሥርዓት የሚጠይቀው የቄጤማው ጉዝጓዝ ሰንደሉ ዕጣኑ
ሁሉ የተሟላ ነው፡፡ እውነተኛ ካዳሚነቷን አረጋግጣለች ማለት ይቻላል። የሰላም አምባሳደሮች፣ የሳይንስና ምርምር ፕሮፌሰሮች፣ የዕድገት መሀንዲሶች፣ ጥበበኞች እና ምሁራኖችን የምታስተናግድ ካዳሚ..እግሮቻቸውን አጣጥፈው ቦታ ቦታቸውን እንደያዙ ጎንቻ ግድግዳው ላይ ወዳን
ጠለጠለው ኮት ኪሱ ውስጥ ገባና በርካታ ነገሮችን ማውጣት ጀመረ።
በደም የተለወስ የአንገት ሀብል... ትላልቅ የጆሮ ጉትቻዎች… ከወርቅ
የተሰሩ የሴት የእጅ አምባሮች የተለያዩ የብር ኖቶች ያሉበት ትንሽ
ቦርሳ ያ ሁሉ ንብረት ከጥቂት ሰዓታት በፊት አንቆ የዘረፋት ሴት
ሀብት ነበር፡፡ ጆብሬ ዛሬ የሰራውን ሁለት መቶ ብር ከደረት ኪሱ ላጥ
አድርጎ አወጣና አስቀመጠ፡፡ አበራ አልቀናውም፡፡ አንበሴ ዛሬ እንደ አንበሳነቱ ሳይሆን ውርደት ቀምሶ ቡጢ ልሶ ነው የመጣው። ሁለቱ የሰሩትን ሲያወጡ ሁለቱ አፈጠጡ። ወላ ሀባ ጭቅጭቅ ንትርክ የለም። አንዱ ከቀናው ላልቀናው ያካፍላል ዛሬ ባይቀናው ነገ እንደሚክስ የታወቀ ነው፡፡
ይሁን እንጂ መቀስ በጣም አብዝቶታል። ያንን መልካም ቁመናውን ብቻ ዋቤ አድርጎ ዕይኖቹን ያስለመልምና ድርሻውን ላፍ አድርጎ መሰስ ይላል። የቀናው ዕለት እንኳ የረባ ነገር አበርክቶ አያውቅም። እፍኝ ቆሎ ይዞ ከአሻሮ መጠጋት አብዝቷል፡፡ በማንኪያ ሰጥቶ በአካፋ መዛቁን እየደጋገመ መጥቷል።
የተማመነው በማን ይሆን? ጎንቻ ጆብሬ ያስቀመጠውን አየና ወደ ሁለቱ ፊቱን አዙሮ በምልክት
እጃችሁ ከምን? ሲል በእንቅስቃሴ ጠየቃቸው፡፡ ያገኘው መልስ ግን የፈጠጡ አራት ዐይኖች ሲንከባሉና ሲቁለጨለጩ ከማየት ሊዘል አልቻለም።
“ስማ መቀስ ብዙ ብልጥ መሆን አያስፈልግም! የምታገኘውን ላፍ አድርገህ ትሄዳለህ፡፡ ይዘህ የምትመጣው የሰራኸውን ሳይሆን በብልጠት እየቀነጨብክለት መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን። በመካከላችን ዋናው ቁም ነገር መተማመን ነው! አንተ ግን ሁኔታህን ደጋግሜ ስመለከ
ተው እምነት የጎደለህ ትመስላለህ፡፡ ሁል ጊዜ የሌላውን ድካም ጠባቂ መሆን ብልጥነት ብቻ ሳይሆን ዐይን አውጣነት ነው!” ተቆጣ፡፡ 'የአበራ ጉዳይ እንኳ ምንም አይደለም የታወቀ ነው። ቶሉ ቶሎ ባይቀናውም
አንዴ ከቀናው በሽ በሽ ስለሆነ ግድ የለም። አንተ ግን አበዛኸው። ከዚህ ውስጥ ምንም የሚደርስህ ነገር እንደማይኖር አረጋግጥልሀለሁ! በርጫህን ቅመህ ለጨብሲ የምትሆን አስር ብር በቂህ ስለሆነ ሌላውን እን
ዳትጠብቅ!" ቁርጡን ነገረው፡፡ ከጎንቻ ያላነሰ የአረመኔነት ባህሪ የነበረው መቀስ ለግላጋ ቁመቱና ወንዳወንድነቱ ከውጭ ለሚያየው ሰው የሚስብ ነው። መቀስ በጎንቻ አነጋገር ወሽመጡ ብጥስ አለ። በጉምዥት አፉን የሞላው ምራቅ በድንገት ደረቀ፡፡ ጎንቻ የበላይነቱን በመያዙ እኔስ ከማን አንሼ? በማለት ሊቀናቀነው የሚሞክር ሰው ነው። የቡድኑን የመሪነት ሥልጣን ለመውሰድ ከመመኘት ባለፈ በጎንቻ ላይ ንቀት ነበረው። ይህንን ንቀቱን በተግባር ለማሳየት ደግሞ ዓለሚቱን አጥምዷታል። ጎንቻ ያን የመሰለ አንጀት
የሚበጥስ ንግግር ሲናገረው ቀስ ብሎ ዓለሚቱን በቆረጣ ተመለከታት፡፡ እሷም የጎንቻን ዐይኖችና የሌሎቹንም
እንቅስቃሴ ጠብቃ ማንም ሳያያት ተደብቃ "ጥቅስ" አደረገችው። ፀብ አትፍጠር ማለቷ ነው፡፡ ምን አሳስበህ? ማለቷ ነው። ተረጋጋ....
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከሶስት ዓመታት የላምበረት ኑሮ በኋላ ዘይኑን ዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት አስገባት። ከላምበረት ዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት ከምትመላለስ በአቅራቢያው ቤት መከራየት ፈለገና እሪ በከንቱ አካባቢ ሰራተኛ
ስፈር ሁለት ክፍል ያላት ቤት አግኝቶ ተከራየ፡፡ ዘይኑ ለትምህርት ቤቷ ቅርብ የሆነ ቤት አገኘች። ትንሽ ደስ ያላላት ላምበረት የትውልድ መንደሯን ዓይነት ፀጥታ የሰፈነበት ሲሆን እሪ በከንቱ ግን የተጨናነቀና ሁካታ የበዛበት መሆኑ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ረጅም መንገድ ከመመላለስ ታድጓታልና ጉዳቱን በጥቅሙ አካክሳ ተቀብላዋለች፡፡ ጌትነት እህቱን በቅርበት እየተከታተለ ለጥሩ ውጤት እንድትበቃ ማድረጉ፣ በትምህርት ቤት ተጀምሮ ለሁለት አመታት የዘለቀውና ውስጥ ውስጡን ሲያሰቃየው የኖረው ፍቅር መቋጫው አምሮ ከሚወዳት ከአማረች ጋር አስደሳች