አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ብላ አየችኝ። «የምን እደርሳለሁ ነው? እኔና ጋሻዩነህም እምብርት አለን። ነይ ቁጭ በይ!» ብዩ ከመናገሬ ተቀመጠች። ለሦስት ጠመድነው፡፡ ከቁርስ በኋላ
እናትና ልጅ ጥለውኝ ወጡ፡፡ ከዕለቱ ሥራ በገዛ ፈቃደ ቀረሁ። ዕቃ እንደ ጠፋበት ሰው በክፍሉ ውስጥ ስንቆራጠጥ ከሩብ ሰዓት በላይ አለፈ። አንጎሌ ውስጥ
ልዩ ልዩ ሐሳብ ተፍለቀለቀ። ሠልፍ እንደሚጎበኝ የጦር መኮንን ከወዲያ ወዲህ ተዘዋወርኩ። እግሮቼን እንደ ባላ እንጨት ገትሬ «ከእንግዲህ ወዲያ በሕይወቴ
ውስጥ ራሴ ለራሴ ውሳኔና ምርጫ ውሳኔ ሰጪ መሆን አለብኝ፡፡ ለብዙዎች
በሚስማማ ጎዳና ላይ እንጂ በግሌ ጎዳና ላይ አልጓዝም፡፡ የብዙሃኑ ጥንካሬና የሐሳብ አንድነት ለእኔ የትግል ፅናት መሠረቴ ነው። ይህ የእኔ ችግር በየቦታው አለ፡፡ መበታተን መሽነፍ ነው:: የራሴን ትክክለኛ እምነት ከሌላ ትክክለኛ አስተሳሰብ ጋር ማዋሐድ አለብኝ፡፡ አድራጎቴ ሁሉ ለግላዊ ነጻነቴ ከሆነ አሁንም
ዙሪያዩ በባርነት የተካበበ የተሸናፊነት መፈንጫ ይሆናል። ሐሳቤን ሁሉ እየቀረጣጠፈ የሚበላው ፍርሃት ነው:: በሕይወቴ ታላቁ ጠላቴ ፍርሃቴ ነው። ይህ ከሰንካላው አስተዳደጌ ያገኘት ሕሊና ሰባሪ ቀንበር ተሰባብሮ መውደቅ አለበት።
የወዲያነሽን ያጠቃትና ያስጠቃት የበታችነት ጨቋኝ ባህሪ በእኔም ውስጥ ተዘርቶ በቅሏል። ነጻ የሚወጡት የወዲያነሽና ጋሻዬነህ ብቻ አይደሉም፡፡ እኔ ራሴ ገና ነጻ አልወጣሁም፡፡ ራሱን ነፃ ያላወጣ ወይም ለማውጣት ያልተነሳ ዜጋና
ትውልድ ለሌሎች ነፃነት ሊቆም አይችልም፡፡ ስለዚህ ለእነርሱም ለራሴም እዋጋለሁ፡፡ ከእንግዲህ ያላግባብ የሚፃረሩኝን ሁሉ እቋቋማቸዋለሁ። እዋጋቸዋለሁ።
ከእንግዲህ ወዲህ ቀጥ ብዩ እራመዳለሁ። ይህም ለትምክህትና ለትዕቢት ሳይሆን
መኖሬን ለዘነጉት ሁሉ የትክክለኛ ማንነቴን ማሳወቂያ አርማ ነው:: ብቻዬን የማደርገው ማናቸውም ዐይነት ትግል ቅንጣት ፋይዳ አያመጣም ይሆናል። ሆኖም ሁላችንም ነጻ የምንወጣው በሁላችንም ትግልና ግብግብ ነው። ስለዚህም የነጻነት ቦይ ሲቆፈርና የነጻነት ሜዳ ሲደለደል እኔም ድርሻዩን ለማከናወን
በንቃት መሳተፍ አለብኝ፡፡

"አባቴ ቢሰማም ባይሰማም ግድ የለኝም። ቢደሰትም ቢከፋም ደንታ
የለኝም! በከንቱና ፍሬ ቢስ በሆነ ነቀፌታ አላምንም፡፡ በቂ ምክንያትና ሐቅን ይዞ
በእውነተኛነት ከመፋጠጥ የበለጠ አስደሳች ነገር የለም፡፡ ዓላማ የሰው ልጅ የኑሮ ለውጥ መሰላል ነው:: አባቴም ቢሆን ውሳኔዬን ማወቅና ጉዳዬን ማየት እንጂ
ከእንግዲህ ወዲህ ይኸ ወለገደ፣ ያኛው ቀና ብሎ በእርሱ ስንኩል እምነት ሊመራኝ አይገባም። አልመራለትምም:: ሕሊናዬ ለማናቸውም ዓይነት አምባገነንነት መንበርከክ የለባትም" ! በሐሰት አዳራሽ ውስጥ ከመኖር በደሳሳ የሐቅ ጐጆ ውስጥ መተሳሰብ ይበልጣል። የሐሰት ዕድሜዋ አጭር ነው:: እውነት ያለችው ከእኔና ከየወዲያዩ ጋር ነው:: በቃ! ማሳወቅ ብቻ! ማብሰር ሳይሆን
ማርዳት! ከእንግዲህ አባቴ የእኔንና የባለቤቴን ጋብቻ አጽዳቂም አፍራሽም ሊሆን
አይችልም በማለት በአንጎሌ ውስጥ ያውጠነጠንኩትን ሐሳብ ጮክ ብዬ ተናገርኩ «የሚሆነውን ነገር ራሱ መርጦ ራሱ ውሳኔ ለመስጠት የማይችል ሰው
ምነኛ የተበደለ ነው:: በቃ! ቅርንጫፍነት በቃኝ! እኔው ራሴ ሥር ሰድጄ መብቀልና ጠንካራ ግንድ መሆን አለብኝ! ከእኔ የሚገኙትንም ቅርንጫፎች
መሽከምና ነጻ ማውጣት ይገባኛል! » ካልኩ በኋላ የተዳቀቀውን አካላቴን ለማፍታታት ተንጠራራሁ፡፡ ያ ሁለ ሲያስጨንቀኝና ሲያስፈራራኝ የኖረ
ምስቅልቅል ሐሳብ አብሮ አደጌ በመሆኑ ከውስጤ እየፈለቀ የሚያሠቃየኝ ከንቱ ነገር እንጂ ሕሊናን የሚያለመልም ጸጋ አልነበረም፡፡ ሆኖም ለፍርሃቴና ለጭንቀቴ መነሾና ሰበብ የሆኑ ሁኔታዎች እንዳሉና ሕሊናዊ መብቴን የገፈፉኝ ጨቋኝ
ልማዶች አብረውኝ እንዳደጉ አወቅሁ፡፡ ኦና ቤት ውስጥ ቆሞ እንደሚለፈልፍ ወፈፌ እግሬን አንፈራጥጨ ቆምኩ፡፡ እስክስታ እንደሚወርድ ሰው ወገቤን በሁለት እጄ ያዝኩ፡፡ ጩኸት በራስ የመተማመን ወኔና ችሉታ ይሰጠኝ ይመስል የቤቱ ውስጥ ዕቃዎች ድምፄን እስኪያስተጋቡ ድረስ «እኔ የከዚህ ቀደሙ እኔ መሆን
የለብኝም! ሌላ አዲስ ከዚህ ቀደም ያልነበረ የሕይወት አመራር ጉዳናና እምነት የሚኖረኝ ሌላው የተሻሻለውና የተለወጠው ጌታነህ ነኝ! ከበላዬም ሆነው ከበታቼ
በደፈናው ከአካባቢዬ የሚመጡብኝን ጎታችና አውዳሚ ተግባሮች ሁሉ በሕዝባዊ
ስልት እና አሠራር ለራሴና ለሌሎች ነጻነት እዋጋለሁ፡፡ሕሊናዬን ተጭኖት አንደበቴንም አፍኖ እንዳልናገር ያገደኝን ማናቸውንም የባሕል ዐይነትና ልማድ ሁሉ እጋፈጠዋለሁ፡፡

በሚያስገኘው ውጤት ካልተስማማሁ ደግሜ ደጋግሜ እጥሰዋለሁ፣ እጥሰዋለሁ፡፡ ከእንግዲህ ብቻዬን አልቆምም! ትክክለኛ ያልሆነ መነጠል መበደል
ነው!» ብዬ ጓጎርኩ፡፡ ከራሱ በቀር ሌላ ሰሚ በሌለበት ቦታ መሰንቆ እንደሚመታ አዝማሪ የእኔንም ጩኸት በእኔው ብቻ ተሰምቶ ቀረ፡፡ ባለቤቴና ልጄ ኡኡታ
ሰምቶ ለርዳታ እንደሚሮጥ ሰው
በሩጫ ገቡ። ያሰማሁት ጩኸትና በፊቴ ላይ የሚታየው የቁጣ መልክ አስደነገጣት፡፡ ጋሻዬነህም እናቱ አጠገብ ቆሞ በፍርሃት
ይመለከተኝ ጀመር፡፡ ከበፊቱ በበለጠ ተንፈራጥጬ «አንቺ ከአሁኗ ሰዓትና ደቂቃ
ጀምሮ የነጻነት ትግል ትጀምሪያለሽ! ለአንተም ከዛሬ ጀምሮ ነጻ የምትሆንበትንና
ወደፊት መልካም ሕይወት የምታገኝበትን የኑሮና
የምትጎናፀፍበትን መንገድ ሁሉ በትግል እንቀይስልሃለን፡፡ ቅይሱን ከፍጻሜ የምታደርሱት አንተና መሰሎችህ ናችሁ! እኔንና ሌሎችን ካሠቃዩን የኑሮ አደጋዎች የምትድንበትን መንገድና ትክክለኛ ዘዴ እንድታገኝ እታገላለሁ!
እያንዳንዱ በየአካባቢው ባንድነት ከተነሣና ከተጠቃለለ፣ የማይስማማውንም ተገቢ
ያልሆነ ሕግና ልማድ ሁሉ ለመለወጥ በእንድነት ከታገለ፣ ሌላ አዲስና የተሻሻለ የሕይወት ጎዳና ያለው ትውልድ ሊኖረን ይችላል። መልካሙን ሁሉ መርጦ
የመቀበልና አስፈላጊ ያልሆኑትን ሁሉ መንግሉ የመጣል፣ በምትኩም ሌላ የመፍጠር እና የመገንባት አጠቃላይ ግዴታ አለብን፡፡ ሁላችንም ለየግላችን እና
በተናጠል መወጋት የለብንም፡፡ ሁላችንም ስለ ሁላችን የጋራ ነፃነትና ድል በአንድነት ታጥቀን መሰለፍ ይገባናል ያነዬ ድሉ የሁላችንም ይሆናል!» ብዩ
የማይገባቸውን ሁሉ ተናግሬ አደናርኳቸው:: በዚህ ዐይነት ደፋር አነጋገር ከራሴ ሐሳብ ጋር በግልፅ አምርሬ ስጋጭ የመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ እኔኑ መልሶ አስደነቀኝ።

ይኸው ድንገተኛ ሁኔታዬና ልፍለፋዬ ምን እንደሆነ ግራ የገባት የወዲያነሽ በፍርሃት ሳይሆን በርኅራኄና በአዘኔታ ተመለከተችኝ፡፡ አዎ የአንድ ጤነኛ ሰው የሕሊና ፈተና ነበር፡፡ በመካከላችን ረመጥ የፈሰሰ ወይም ጥልቅ ገደል የለየን ይመስል ካለችበት ሳትላወስ «ምን ሆነሃል ዛሬ? ምን ነካህ ጌታነህ?»
አለችና ፈገግታዋ እንደ ከዚያ ቀደሙ የሚያስደስተኝና ከመቅጽበት የሚለውጠኝ
መስሏት ፈገግ አለች፡፡ ሲያቀና ውሉ እንደ ከሠረ ቸርቻሪ ነጋዴ ከፋኝ እንጂ አልተደሰትኩም፡፡ ጥፋተኛ ልጁን ለመቅጣት ዘሎ እንደሚይዝ አባት እመር ብዬ
የወዲያነሽን ለቀም እደረግኋት። አያያዜ የብርቱ ንዴት ስለ መሰላት ደረቴ ላይ ተለጥፋ «አጥፍቼ ሆነ ንገረኝ? በድያህ ከሆነ ግለጽልኝ በሌላ ጉዳይ ተነክተህ ከሆነ በእኔ ይለፍልህ፡ በለኝ!» ብላ ጸጥ አለች፡፡ በአነጋገሯና በሁኔታችን
የደነገጠው ጋሻዬነህ የምደበድባት ስለመሰለው ዋይ!» ብሉ በቀጭኗ ጮኸና ተው ተው!” እያለ በእግሮቼ መኻል ፈልፍሉ ገብቶ በመካከላችን ቆመ። ፊቱን
ወደ እናቱ አዘሮ ተጠመጠመባት። «ሁለት የሥቃይ ፍሬዎች! » ብዩ
ገፈተርኳቸው፡፡ ሁለቱም እየተንገዳገዱ የኋሊት ሔዱ፡፡ አልሸሸችም፡፡
👍3
ጋሻዬነህ መለስ ብሎ ሲያየኝ ዐይኖቹ በእንባ ተዘፍቀዋል፡፡ «ና እስኪ ጋሻው » ብዬ ጠራሁት። የእናቱን ቀሚስ ጨመደደ እንጂ አልመጣም፡፡ እኳኋኔ የሚያስመጣ ስላልነበር አላዘንኩም፡፡ ወደፊት ራመድ ብዬ አጠገባቸው ቁጢጥ አልኩ፡፡ ና» አልኩት እንደገና፡፡ ከእናቱ ጀርባ ዞሮ ቀሚሷን ያዘ። ቀስ ብላ ወደ
ፊቷ ከሳበችው በኋላ ወደ እኔ ገፋ ስታደርገው አፈፍ አደረግሁት።
ከፊቴ ላይ አስፈሪ ነገር ያየ ይመስል ወለል ወለሉን እያየ አቀረቀረ። እንባው ቁልቁል በጉንጮቹ ላይ የሚንኳለልበት አግድመት በማጣቱ ነፋስ
ኣወዛወዛት የክረምት ዛፍ ላይ እንደሚረግፍ የዝናብ ውሃ ወለሉ ላይ ተንጠባጠበ። ሁላችንም ዝም አልን።

መንፈሴ መለስ ብሎ እንደተረጋጋ ንግግሬን አጢኜ ራሴን ታዘብኩት።
የተናገርኩት ሁሉ ከፅሑፍ ላይ ተጠንቶ የተነበነበ እንጂ ከተናደደ ሰው አንደበት የወጣ የወዲያው ንግግር አይመስልም ነበር፡፡ የጉልላት ቅጂ የሆንኩ መሰለኝ፡፡

«ምነው ጋሻዩ? ምን ሆነህ ነው የምታለቅሰው?» አልኩት። መልስ ነሣኝ፡፡ ዝምታም ተቃውሞ ነው። ሁላችንም ተቀመጥን። ጋሻዬነህ ከእኛ ፈንጠር ብሎ እንጨት ወንበር ላይ ተቀመጠ። መሬት ለመንካት ያልቻሉት እግሮቹ እንደ
አጭር ቆመጥ ተንጠለጠሉ። ያቃወስኩትን የየወዲያነሽን ስሜት ወዲያው ለማስተካከልና ልቧንም በፍጥነት ለማደስ እንደማልቸገር አውቃለሁ፡፡ የልቢ አካል ነችና።

ኣይዞሽ አትደንግጪ ምንም አልሆንኩ። ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ከራሴ ጋር ተፋልሚ ራሴን ፈትኛለሁ። ጥንካሬዬን ለክቼዋለሁ፡ፈሪውንና በርጋጊውን የቀድሞውን እኔን ጥዪ ቀጥ ብሎ መቆምና ጠላቴን መጋፈጥ የሚችለውን
አዲሱን እኔን ለመፍጠር እየታገልኩ ነው፡፡ በጠቅላላ ሲታይ እጅግ ብዙ ፈተናዎች አሉብኝ። እንደ ሰኞና እንደ ማክሰኛ በተከታታይ ይመጣሉ፡፡ ሁሉንም
ተራ በተራ እሸንፋቸዋለሁ። አሮጌው ሓሳብ ከእንግዲህ ወዲህ በሕሊናዬ ውስጥ
ቦታ የለውም፡፡ እየተገሸላለጠ ይወድቃል፡፡ ወደ አሁኑ ጉዳይ ልመለስና አባቴ ስለ አንቺ ኑሮ ምንም ስለማያውቅና አንዲትም ነገር ባለመስማቱ መስማትና ማወቅ አለበት፡፡ ግማሽ ፍቅርና ግማሽ ክብ ብሎ ነገር የለም፡፡ ምንም እንኳ ከሰማ በኋላ ምን እንደሚል ባላውቅም ከነባር ጠባዩና ከአስተሳሰቡ እየፈለቁ የሚወጡትን አንዳንድ ጥያቄዎች በልምድ አውቃቸዋለሁ። ቀደም ሲልም እንጎሌን በሁለት
የሐሳብ መድረክ ላይ ከፍዬ አባቴንና ራሴን ጠያቂና ተጠያቂ እድርጌ አቀረብኩ፡፡

በውስጤ የተፈጠረው የአባቴ የሐሳብ ወኪል ላቀረበልኝ ግትር ክርክርና ጥያቄ አስፈሳጊውን መልስ ሰጠሁ፡፡ የአባቴን የሐሳብ ወኪል ሳታዪና ባትሰሚውም በእኔ
በኩል ያለውን አካል ሲጮህና ሲያጓራ ሰምተሽዋል። ከእንግዲህ ወዲያ ግን ከዚያ ካፈሪና ከደንጋጭ ስውር አካሌ ለመላቀቅ ቆርጫለሁ። ከአባቴ ጋር ተከራክሬ
በማስረዳት ትክክለኛ ምርጫና እምነቴን እገልጽለታለሁ፡፡ አንጣጣምም ይሆናል፡፡ አዲሱ እምነቴ በአሮጌው እምነቱ ላይ በአዲስና ጽኑ መሠረት መገንባቱን
አሳየዋለሁ። ቢያይም አይታየውም፡፡ ተጨባጩን ጉልህ ነገር አሳየዋለሁ። ካላመነ
አስዳብሰዋለሁ፡፡ ለዘመናት አርጅቶ ትል የበላው የኑሮ እምነቱ ዐይኑ እያየ ይከዳዋል፡፡ እኔ ግን በማቀርቀርና ቀና ብሎ በማየት መካከል ያለውን ልዩነት ካአሁኑ ጩኸቴ ወዲህ ማየትና ማወቅ እፈልጋለሁ: ሥርም ግንድም መሆንን እንጂ ተራ ቅርንጫፍ ብቻ መሆንን አልቀበልም:: ህብረተሰቡ የኑሮው ሥርዓት ግንድ በመሆኑ የዚያ ግንድ አካል መሆን ግዴታዬ ነው::» ብዬ የደደረ ሐሳቤን
አሰማኋት፡፡ ሁለታችንም ፀጥ አልን፡፡ በዚያ አጭር ዝምታ ውስጥ ለአፍታ ያህል ሐሳቤን በረበርኩት። ያደረግሁት ንግግር ሁሉ ለሕዝብ መድረክ የተጠና መነባንብ
መሰለኝ፡፡ «የአንድ ጤነኛና ትክክለኛ እምነት ግንድ እንጂ የአንድ የበሰበሰ እምነት ሥር አዲስ ወይም ነባር ተቀጥላ መሆን አልሻም። ከዚህ ከተዳፈነ
ሕይወትሽና ከተርመጠመጠ ኑሮሽ ነጻ እንድትወጪና በእኩልነት ሽር እንድትይ እታገላለሁ፡፡ እንደ ዕብድ ያስጮኸኝም ይኸው የሕሊናዩ መዋለልና በውስጤ
የኖረው ውዥንብር ነው» አልኩና ደኅንነቴን ለማረጋገጥ ፈገግታ አሳየሁ።

የወዲያነሽ የጥልቅ እምነትኛ የሙሉ ተስፋ ገፅታ ሳይሆን አንድ ተራ ፈገግታ አሳየች። ለአንድ በድንገት ለተሠቃየ እእምሮ ፈዋሽ ማብራሪያ አቅርቦ ወዲያውኑ ማሳመን በመጠኑ አዳጋች በመሆኑ እዚያው በዚያው እንድታምን አላስገደድኳትም፡፡ ከጥቂት የዝምታ ደቂቃዎች በኋላ ካጠገቤ ተነሥታ ሄደች።ጋሻዬነህ እናቱን ተከትሉ ወጣ፡፡ የሚቀጥሉትን ሰዓታት በንባብ ለማሳለፍ የጀመርኩትን መጽሐፍ አነሣሁት። አሥራ ሦስተኛው ምዕራፍ አጋማሽ ላይ
«መገዛት መጨቆንና መገፋት አንገሸገሸኝ! ነጻነት ጠማኝ! ነጻነት ራበኝ የአካልና የሕሊና ባርነት መረረኝ! ሕይወቴና ጉልበቴ በገዢዎች ተመዘመዘ፡፡
ወገኖቼን የተጫናቸው የሥቃይ ቀንበር ክብደት ተሰማኝ፡፡

እኔን በማሰር የማይሞተውን ትክክለኛና ሕያው ዓላማዬን አይገድሉትም። ለሕዝቦች ነፃነት በሚደረገው ትግል ውስጥ የእኔ ድርሻና መሥዋዕትነት ተሰናክሉና ታስሮ መቅረት የለበትም፡፡ በሰፊው የሕዝቦች እስር ቤት ውስጥ
ታስረው የሚረገጡትን ሁሉ ነፃ ለማውጣት በሚደረገው ሐቀኛ ውጊያ ላይ ለመካፈልና የመሥዋዕትነት ድርሻዬን ለመወጣት ከዚህ ጠባብ እስር ቤት መውጣት አለብኝ» ብሎ አሥር ቀን ሙሉ ሲዘጋጅና ሲያደባ ቆየ። ማንንም ስላላመነ ምስጢሩን አላካፈለም ማንምም ሳያይና ሳይሰማ ቦላሌውን አይጥ እንደ በላው የቋንጣ ማስቀመጫ ከረጢት ቀረጣጥፎ ቁምጣ ሱሪ አደረጋት፡፡ አንድ ጊዜ ቆርጦ በመነሣቱ ሐሳቡን ለመፈጸም ተወጋጀ። እስረኞቹ ሁሉ እንደ ተመነጠረ ቁጥቋጦ ተለሽልሸዋል። አልፎ አልፎ በእንቅልፍ ልቡ ከሚያከውና በቅዠት ልቡ ከሚገላበጠ በስተቀር በጨለማው ክፍል ውስጥ እንደ እስረኞቹ የታሰረ ዝምታ ተጋድሟል፡፡ ከእስረኞቹ መኻል ኮሽ ሳይል ቀስ ብሎ ከተነሣ በኋላ በሩን በዝግታ
ከፍቶ ወጣ፡፡ ወዲያው በደረቱ መሬቱ ላይ ተዘርሮ ለጥ አለ፡፡ በሰበሰቡ ጥላ ውስጥ በደረቱ እየተሳበ አያሌ ርምጃዎች ያህል ሄደ። ከቤቱ ጥግ የስቀለችውን ዛፍ
ለመያዝ ትንሽ እንደ ቀረው ትንፋሽ አጠረው:: የመጣው ይምጣ ብሎ ተነሳና ግንቡ ላይ ተለጥፎ እየታከከ ከተጓዘ በኋላ ተንጠራርቶ ግንዷ ላይ ተጠመጠመ፡፡
በማምለጥ ፍላጎትና በእያዝ ይሆን ስሜት መካከል አካላዊ ሽብር ስለ ተነሣበት ተንዘፈዘፈ፡፡ ሽቅብ ዘለለ። እጁ ከፍ ሲል ሁለት እግሩ ከጉልበቱ ላይ አጠፍ ብሎ
ግንዱን ረገጠ፡፡ ሳብ! መዘዝ ከፍ! ጎተት! እያለ አንዱን ቅርንጫፍ በቀኝ እጁ ጨበጠ፡፡ ሞትና ሽረት ነው ሌላ የመላቀቂያ ምርጫ የለም! ሽቅብ ተስቦ ባላ ረገጠ። ከፍ አለ፣ ወጣ፣ ከፍ አለ፡፡ አንዲት ለጋ ቅርንጫፍ እቀጭ ብላ
ተቀለጠመች፡፡ ነፍሱሥጋው ተለያየች:: ወዲያው ከቤቱ አናት ላይ ፊጥ አለ። ከወዲያም ከወዲህም ተንጓጓ፡፡ ጣሪያው ቁልቁል የሚካዳው መሰለው። እንደገና በደረቱ ተኝቶ ቢቆርቆሮው ላይ እንደ እባብ ተሳበ። ከሕፃን ዐይን ውስጥ ጉድፍ እንደሚያወጣ ሰው ተጠነቀቀ።

የውጥኑ ከፊል ተጠናቀቀ!
ከጠባቧ እሰር ቤት ወጥቶ ወደ ሰፊው እስር ቤት ግቢ ዳርቻ ላይ ዘሎ ወረደ! ቆርቆሮው በትልቅ ድንጋይ የተመታ ያህል የጥይት ድምፅ ተሰማ! ከተያዘ ከፍተኛ ስቃይና መከራ እንደሚደርስበት
የሚያውቀው አምላጭ ከጥይት ፍጥነት ጋር መሽቀዳደም ይችል ይመስል በ ን ፊደል ቅርዕ ዓይነት እየተቅመደመደ ሩጫውን ተያያዘው። ትኩሱ ተደጋገመ፡፡
👍2
ከተተኮሱት ጥይቶች መካካል እንጂ የግራ እጁን መታችውና ደንግጦ ተዘረረ» የሚለው የድርጊት ገላጭ ሐተታ ላይ እንደደረስኩ ሁኔታው በእኔ ላይ
የደረሰ ስለ መስለኝ ተሰቅተጩ ዐይኔን ጨፈነኩ። ፋጻሜውን ለማወቅ ንብበን ቀጠልኩ፡፡ «እንደገና ተፍጨርጭሮ ተነሣና እየተፍገመገመ ሩጫውን ቀጠለ፡፡
አልተያዘም፡፡ አገሩንም ነፃ ለማውጣት ወደ በረሃ ገባ» ሲል ከጭንቀት ምጥ ተገላገለኩ፡፡

እርሱስ ወደሚገባበት ገባ፤ እኔና የእኔ ትግል ግን ፊት ለፊት
እንደተፋጠጥን ከወዲያ ወዲህ ስትመላለስ መጽሐፍ መያዜን
የተመለከተችው የወዲያነሽ ከመነኩሴ አጠገብ የዳቦ ፍራፋሪዎች ለመለቃቀም
እንደምትጠጋ ለማዳ የደብር ርግብ ቀስ ብሳ ከተጠጋች በኋላ «እፎይ እኔስ ምን ነካህ ብዬ ተጨንቄ ነበር። እውነትም ደህና ነህ፡፡ ረጋ ደርበብ ብለህ ስትቀመጥ ደስ ማለትህ» አለችኝ፡፡

«ምነው ነግሬሽ የወዲያነሽ፣ ደኅና ነኝ እኮ ብየሻለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኮ መናደድ መድኃኒትነት አለው ይባላል» ብዬ መለስኩላትና ወደ ንባቤ ዞርኩ፡፡

ማታ ከትምህርት ቤት መልስ ከየወዲያነሽ ጋር በቀጥታ ወደ ወላጆቼ ቤት ሄድን፡፡

እናቴ እኔን ሳይሆን ከጎኔ ያለችውን የወዲያነሽን በአስደሳች ፈገግታ
ትቀበለቻት፡፡ እኔ ከእኅቴ፤ እናቴ ከባለቤቴ ጋር ተቀመጥን፡፡ በየበኩላችን ወሬ ጀመርን ፡፡ እኛን ሲጠባበቅ የነበረው ቡና ዕጣን ጨሶ ተቀዳ፡፡ የየበኩላችንም ወሬ
ደራ።

የውብነሽ ከጥቂት ገለጻ በኋላ ተማሪዎቹን እንደሚጠይቅ መምህር ጧት የነገርኩህን ሁሉ ታስታውስ የለ? ያልኩህስ ሁሉ ገብቶህ የለ?» ብላ መልሴን
ለመስማት በተዘጋጀ ስሜታዊ ንቃት አየችኝ። ምንም እንኳ አብሮ አደግ ልማዱንና ጠባዬን በጥቂት ቀናት ውስጥ መለወጥ የማልችል መሆኔን ባውቅም!
አንድ አዲስና የማይሻር ውሳኔ መወሰኔ ግን ታወሰኝ። «አዎ ገብቶኛል፣አስታውሳለሁ፡ ግን እኮ ታዲያ...” ብዩ ሙሉ ሐሳቤን ሳልገልጽላት ዝም አልኩ።
የዝምታዬ መነሾና ጥጥር ምክንያት ግን አዲሱ እኔ በመሆኑ እሷ ልታውቀው አትችልም፡፡....


💫ይቀጥላል💫
1
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


....“አንተን ለማግኘት ስል ያልገባሁበት ዋሻ፣ያልፈነቀልኩት ድንጋይ አልነበረም፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል?እንደ ሌሎቹ በቀላሉ የምትገኝ ሰው አልሆንክም፡፡ የተፈፀመብኝ ጥቃት ከባድና ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ ልቤ እያወቀው፣ ልቤ እየጠረጠረ ከማይረቡ ምናምንቴዎች ጋር ውለታ ውስጥ ገባሁ። እንዳንተ ስማቸው ያልገነነ፣ ቱስ ቱስ ማለት የጀመሩ ሾላኮች በመሆናቸው ብዙ ገንዘብ ካስወጡኝ በኋላ አንዳች ቁም ነገር ሳይፈፅሙ ሸሽተውኛል ተደብቀውኛል። በዚህ ምክንያት ተበሳጭቼ ቀን ከለሊት አፈላልጌ መልዕክተኛ ልኬብህ በብዙ ድካም ሳገኝህ የተሰማኝ ደስታ
ወደር አልነበረውም፡፡ እንደዚህ በግንባር ልታነጋግረኝ መወሰንህን ስሰማ ደግሞ ደስታዬ እጅግ ከፍተኛ ሆኖ ነበር፡፡ጎንቻ የልቤን የሚፈፅምልኝ ካንተ ወዲያ ሊኖር እንደማይችል ቀድሞውኑ የታወቀ ነው” በማለት አንጀቱን ከበላው በኋላ ዝርዝሩን ይተርክለት ጀመር፡፡

“የሹመት ጓደኛዬ ነው። ባላባት ጃኖ ይባላል። በባህላችን በወልገራ የጋብቻ ደንብ እህቴን ስድርለት እሱ ደግሞ በለውጡ እህቱን ድሮልኝ ነበር፡፡ እኔ የሱን እህት በወግ በማዕረግ አክብሬ ነበር የያዝኳት። እሱ ግን እህቴን
እንደ ባሪያ እየረገጠ በደል ሲያበዛባት፣ ሲያሰቃያት ተማረረች። በመጨረሻም የሱ ሚስት የኔ እህት በደሉ አንገሽገሻትና በድንገት ጥላው ጠፋች። ከዚያ በኋላ ሰላም ይነሳኝ፣ ይበጠብጠኝ ጀመር፡፡ እኔ ጥለሽው ጥፊ፣ እኔ ትዳርሽን አፍርሺ ብዬ እንደመከርኳት ሁሉ ሚስቴን መልስልኝ ያለበለዚያ ዝምድናችን ይበላሻል እያለ ያስፈራራኝ ጀመር።መልዕክተኛ በተደጋጋሚ ላከብኝ፡፡ በግንባር ተገናኝተን ተነጋገርን፡፡ ጭቅጭቁ ሲብስብኝ መቆሚያ መቀመጫ ሲያሳጣኝ እህቴን ካለችበት ቦታ አስጠርቼ ላግባባት ሞከርኩ፡፡ ወደ ትዳሯ እንድትመለስ እግሯ ላይ ወድቄ ለመንኳት ወደዚያ የስቃይ ኑሮ ተመለሺ የምትለኝ ከሆነ ህይወቴን አጠፋለሁ ካንተ
ምንም የምፈልገው ነገር የለም በነፃነቴ ውስጥ ግን አትግባ ብላ እያለቀሰች በምሬት መለሰችልኝ፡፡ በጣም አስፈራራችኝ፡፡ ከፍላጎቷ ውጭ እንድትመለስ ባስገድዳት ህይወቷን ታጠፋለች የሚል ፍርሃት አደረብኝ፡፡ያደረኩትን ጥረትና የሰጠችኝን መልስ በዝርዝር አጫወትኩት፡፡ በወዳጅነታችን ውስጥ በፍፁም ቅያሜ እንዳይኖር ለመንኩት። እህቴ ብትሆንም በሱ ሚስት ህይወት ላይ ማዘዝ እንደማልችል አስረዳሁት፡፡ ምን ዋጋ አለው? ድንጋይ ራስ ነው! በፍፁም ማመዛዘን የማይችል ድንጋይ ራስ!! ችግሬን ሊረዳ አልቻለም፡፡ ያንን ሁሉ ልፋቴንና ጥረቴን ዋጋ አሳጥቶት ቂም ቋጠረብኝ፡፡ የኔን ትዳር ለመበጥበጥ፣የኔን ትዳር ለማፍረስ እንቅልፍ አጣ። ለእህቱ በተደጋጋሚ መልዕክተኛ ላከባት፡፡ የሱ እህት ብቸኛ አድርጋኝ ጥላኝ ስትጠፋ፣ ትዳሬን አፍርሳ ስትሄድ አንቺ ግን የሱን ጎጆ ታሞቂያለሽ፡፡ የወንድምሽ በደል የማይሰማሽ ለወንድምሽ የማትቆረቆሪ አህያ
ነሽ።እህቱ ጥላኝ እንደጠፋች ጥለሽው ካልጠፋሽ ዳግመኛ እህት አለችኝ ብዬ አላወራም እያለ ነዘነዛትና ፍቅራችን እንዲደፈርስ ትዳራችን እንዲ ፈራርስ አደረገ፡፡ ከዚያም የምወዳት ሚስቴ ሳልበድላት ምንም ሳላስቀይማት በድንገት.. በድንገት ጥላኝ ጠፋች”

የስድስት ሚስቶች ባል የሆነው ባላባት ቱሬ የሚያወራው ተረት አፉን እንኳን ወለም አላደረገውም ነበር፡፡ የደረሰበት በደል ከፍተኛ መሆኑን ጎንቻ እንዲረዳለትና ቁጭት እንዲያድርበት ለማድረግ ሰሞኑን ሲያጠና የከረመውን ልብ ወለድ እንደ እውነተኛ ታሪክ ሲያወራለት እዚያ የነበሩት በሙሉ አፋቸውን ከፍተው እንደ አዲስ ያዳምጡት ነበር፡፡ በተገላቢጦሽ በጃኖ ላይ የደረሰውን በደል በራሱ ላይ እንደደረስ አድርጎ ጃኖን በዳይ ራሱን ተበዳይ አድርጎ ፊቱን በእንባ ቀረሽ ንዴት ቁጥር ፈታ እያ
ደረገ ማስረዳቱን ቀጠለ።

“ስው ቢበድለኝም ጓደኛዬ ቢከዳኝም እግዚአብሔር አልከዳኝምና በደሌን አይቶ ካለኝ፡፡ ሀዘኔን አይቶ ፈጣሪ አስደሰተኝ፡ እምባዬን አበሰልኝ፡፡ አለላ የመሰለች ልጁን በቦሩ ጃዊ ባላባትነት ውስጥ ጭቃሹም የሆነው አቶ ገመቹ ዳረልኝ፡፡ በዚህ ጊዜ የበለጠ ቅናት አቃጠለው:: እህቱ ጥላኝ እንድትጠፋ፣ ረግጣኝ እንድትሄድ ካደረገ በኋላ ለእህቱ ተቆርቋሪ መስሎ እህቴ የደከመችበትን ንብረት፣ እህቴ ጎንበስ ቀና ብላ ያቆመችውን ጎጆ
ማንም መንገደኛ ገብቶ አይንደላቀቅበትም ሲል ዛተብኝ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ የሱ እህት ይዛልኝ የመጣችው ሰባራ ሳንቲም አልነበረም፡፡ በሞላ በተትረፈረፈ ቤት ገብታ መሞላቀቁ አጥግቧት ጠፋች እንጂ እሷ ያመጣችው አንድም ነገር አልነበረም፡፡ ከኔ ምን ጎድሎ? ምን ጠፍቶ? እሱ ግን ለእህቱ የተቆረቆረ በማስመሰል ለካንስ ሊያጠቃኝ አስቦ ኖሯል፡፡ የሱ እህት ለዚችኛዋ ሚስቴ ገረዷ የእግሯ እጣቢ እንኳ አትሆንም ነበር፡፡ ያጠቃኛል የዚያን አይነት አስከፊ በደል ያደርስብኛል ብዬ በፍፁም ባልጠበኩት ሰዓት ባላባት ጃኖ አጠቃኝ፡፡ ተዘጋጅቶ ዘመድ አዝማዱን አሰባስቦ
ጦሩን ጭኖ በሌሊት ከበበኝ፡ ሚስቴን…. ሚስቴን... በሃይል... ሳልዘጋጅበት.ሳላስበው ...ነጥቆኝ ሄደ” እንባ እየተናነቀው አስረዳ፡፡

እውነተኛው ታሪክ ግን ባላባት ቱሬ እንደሚያወራው ሳይሆን የምስኪኑ
ገበሬ የጃኖን እዚህ ቀረሽ የማትባል እጮኛውን ባላባት ቱሬ በሀብትና በሥልጣኑ ተመክቶ፣ ወላጆቿን በከብትና በገንዘብ ገበራ ዐይናቸውን አሳውሮ የአሥራ ስምንት ዓመቷን ልጃገረድ ሌቱናን ጠልፎ ከወሰዳት በኋላ በባላባትነት ግዛቱ ውስጥ ድል ባለ ሠርግ ያገባት መሆኑ ነው ሀቁ። ገንዘብና ሀብት ባይኖረውም ዛሬ በቱሬ አንደበት የባላባትነት ማዕረግ የተሰጠው ጃኖ የጉልበትና የወኔ ደሃ አልነበረም። እንደ ነፍሱ የሚወዳት እጮኛውን ጉብሏን ሌቱናን ቱሬ በገንዘብ ኃይል አፍኗት ሲሄድ፣ የድንግልነት ክብሯን ሲወስድ እየታየው ገላው እስከሚቃጠል ድረስ በንዴት
ቢጋይም፣ እልህ ቢተናነቀውም አንድ ቀን የሱ አንጡራ ሀብት መሆኗን እንደሚያረጋግጥና እጮኛውን በነጠቅው በቱሬ ላይ አደጋ ጥሎ እንደሚወስዳት ጥርጥር አልነበረውም፡፡ ቱሬ የጓጓው ያንን የቀዘቀዘ ገላውን የም
ታሞቅለትን፣ ብዙ ንብረት ያወጣባትን ቆንጆዋን ሌቱናን ጎንቻ እንዲያስመልስለት ነው። ጎንቻ ተራ ውንብድና አይፈፅምም የሚለውን ዜና በመስማቱ የሌላ ታሪክ እየፈጠረ ገበሬውን ባላባት አድርጎ በመሾም ለመተረክ የተገደደውም ከዚህ እውነታ በመነሳት ነው፡፡

በእርግጥም ጎንቻ ትንሽ ስራ፣ ትልቅ ስራ በሚል የወንጀል አይነትን የሚያማርጥ ቢሆንም ጥሩ ገንዘብ እስካስታቀፉት ድረስ የህፃን ጉሮሮ ከመቀንጠስ ወደ ኋላ የማይል ጨካኝ መሆኑን ቢያውቀው ኖሮ ይሄንን ያክል
መጨነቅ ባላስፈለገው ነበር፡፡

“የፈለከውን ያክል ብር ብትስጠኝ አንድ ተራ ገበሬ ለመግደል አገር
አቋርጬ አልሄድም” ይለኛል ብሎ ስለፈራ እንባውን እየጠራረገ እጅግ ከፍተኛ የሆነ በደል የተፈፀመበት ሰው መስሎ እየተንቀጠቀጠ ኑዛዜውን ቀጠለ፡፡

“ምንም እንኳ እድሜዬ ቢገፋ፣ አቅሜ ቢዳከም አባቴ የወለደኝ ወንድ ጀግና ነበርኩ፡፡ ጃኖ ግን ወንድነቴን ጀግንነቴን ሰልቦታል። ልቤን በሀዘን አኮስምኖታል። ዝናዬን አጉድፎታል። ተኝቶ ሚስቱን ያስነጠቀ ባላባት አሰኝቶ በባላባትነት ግዛቴ ውስጥ አዋርዶኛል። ህዝቡ እንዲንቀኝ፣ እንዳይታዘዘኝ አድርጓል፡፡ ጉልበት በነበረኝ ጊዜ አባርሬ ይዣለሁ። ገድዬ ፎክሬአለሁ።ጃኖ ግን አቅሜ ቢደክም፣ዕድሜ ቢጫጫነኝ ንቆኝ የለበስኩትን ሱሪ አስወልቆ ቀሚስ አልብሶኛል። ጉልበት የእግዚአብሔር መሆኑን
2🥰1
ዘንግቶ ጉልበት አለኝ ብሎ ሚስቴን ነጥቆኝ ሄዷልና፣ ወንድነቴን አኮላሽቶታልና ወንድነቱን ንጠቅልኝ፡፡ በጉልበቱ ተመክቶ ዐይኔ እያየ የምወዳት ሚስቴን እጇን አንጠልጥሉ እንደሄደ ሁሉ ዐይኗ እያየ ሴት አድርገኸው ቁጭቴን ተወጣልኝና እንደ ዶሮ ዘቅዝቀህ እጂን አንጠልጥለህ አምጣልኝ፡፡ ይህንን የምታደርግልኝ ከሆነ የምትጠይቀኝን ሁሉ ለመፈፀም
ዝግጁ ነኝ” ሲል ተማፀነው፡፡

ባላባቱ ይህንን ንግግር በሚናገርበት ጊዜ ግራና ቀኙ የቆሙት ጭቃ ሹሞቹ ንግግሩ ትክክለኛ መሆኑን፣ የደረሰበት በደል የተፈፀመበት ግፍ በማንም ላይ ደርሶ የማያውቅ መሆኑን ለመመስከር እንዴ ወደ ጎንቻ
አንዴ ደግሞ ወደ ባላባቱ መለስ ቀለስ እያሉ በንዴት ከንፈራቸውን እየነከሱ የጎንቻን የበቀል ስሜት ይኮረኩሩት ነበር። ባላባቱ የሚፈልገው ጎንቻ የሰለቸውን ተራ ግድያ ሳይሆን በአይነቱ አዲስ
የሆነ የጥቃት ስልት ተጠቅሞ ብቀላ እንዲፈፅም መሆኑን ሲሰማ የደስታ ስሜት በሰራ አካላቱ ውስጥ ተራወጠ። ፊቱ ፈገገ፡፡ ከዚህ በፊት ሞክሮት የማያውቀውን አዲስ አይነት የቅጣት በትር እንዲሰነዝር፣ ለየት ያለ የበቀል ዱላውን እንዲያነሳና አዲስ የብቀላ ሪከርድ እንዲያስመዘግብ የቀረበለት የድርድር ሃሳብ ከገንዘቡ የበለጠ አስፈነደቀው።
እሱ የሚያውቀው በልጅነቱ አባቱ ወጠጤውን ፍየል ሙክት ለማድረግ ሲያኮላሹ የፍየሉን ሚ.. !አ/አ! አ! አ!”የሚል ጆሮ የሚሰነጥቅ ጩኸት ነበር። እሱ የሚያውቀው ኮርማውን በሬ ለማድረግ በመጫኛ ተጭሎ
የዘር ማመንጫ ፍሬዎቹ ሲወረወሩ ደምስሮቹ ሲበጠሱ፣ ሊዘነጠሉ
ከበሬው ውስጥ የሚወጣውን የጓጎረ የጣእር ድምፅ ነበር፡፡ አሁን ግን የሰውን ልጅ እንደ ወጠጤ ፍየል፣ እንደ ኮርማ ሲቀጠቅጠው፣ ደምስሩን ሲበጥሰው፣ የዘር ማመንጫ ፍሬዎቹን ሲያሻቸው ከውስጡ የሚወጣውን የስቃይ ድምጽ፣ የሰቆቃ ጩኸት አይነቱን ለማወቅ ጓጓና በደስታ
ቃል ገባለት::

ሃሳብህ በሙሉ ፍላጎትህ አንድም ሳይጓደል ይፈፀምልሀል! ከዚህ በፊት በነፃ የተወስደብህን ያክል ትከፍላለህ”ሲል በኩራት ገለፀለት፡፡ ባላባቱ መስማማቱን በደስታ ገልፆ ወዲያውኑ ለቀብድ አምስት መቶ ብር ካስጨበጠው በኋላ የገባውን ቃል ፈፅሞ ሲመጣ የሚሰጠውን ቀሪውን ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር እፊቱ ቆጠረለት፡፡
በዚሁ በውለታቸው መስረት የባላባት ጃኖን ቤት የሚያሳይ ጠቋሚና ሚስቱ ሌቱና የምትጫንበት ሠንጋ ፈረስ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡
የጉዞው ቀን ተቆርጦ ጠቋሚዎቹ በሌሊት ፈረሶቹን ይዘው የሚቀርቡበት ቦታና ሰዓት ተወስኖ በፍቅር ተሰነባበቱ፡፡ ጎንቻ የተቀበለውን ገንዘብ ወደ
ኪሱ ከተተ ። በቀጠሮው ቀን ሲገሠግሥ አድሮ ቀን ቀን በየጫካው እየተደበቀ ሌሊት ሌሊት ተጉዞ የባላባቱን ባላንጣ ሊያስጮህ፣ ሊያስለቅስ፣ አዲስ አይነት የጭንቀትና የጣእር ድምፅ ሊሰማ ያደረበትን ጉጉት በሚገልፅ ግጥም እየፎከረ ባላባቱን አስደሰተውና ተሰናብቶት ወጣ.....

ይቀጥላል
👍3
አትሮኖስ pinned «#የተወጋ_ልብ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስምንት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና ....“አንተን ለማግኘት ስል ያልገባሁበት ዋሻ፣ያልፈነቀልኩት ድንጋይ አልነበረም፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል?እንደ ሌሎቹ በቀላሉ የምትገኝ ሰው አልሆንክም፡፡ የተፈፀመብኝ ጥቃት ከባድና ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ ልቤ እያወቀው፣ ልቤ እየጠረጠረ ከማይረቡ ምናምንቴዎች ጋር ውለታ ውስጥ ገባሁ። እንዳንተ ስማቸው ያልገነነ፣ ቱስ ቱስ ማለት የጀመሩ…»
#የወዲያነሽ


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...አስታውሳለሁ ግን እኮ ታዲያ...” ብዩ ሙሉ ሐሳቤን ሳልገልጽላት ዝም አልኩ።የዝምታዬ መነሾና ጥጥር ምክንያት ግን አዲሱ እኔ በመሆኑ እሷ ልታውቀው
አትችልም፡፡

«ና በል እንሒድ ቶሉ እንመለሳለን» አለችና ተነሣች። የእኔ ጉዳይ
በእርሷና በእናቴ መካከል ተመክሮበት ያለቀ በመሆኑ እንግዲህ አደራሽን እንደዚያቹ እንደ ምክራችን አድርገሽ ንገሪው፡፡ እኔና አንቺ እንደ ተባባልነው
ቢሆን ይሻላል፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ እኔ ደኅና አድርጌ እነግረዋለሁ፤ አደራሽን አደራችሁን» ብላ እናቴ በዐይኗ ሸኘችኝ፡፡ «ሂዱ» የምትለን ወደ እኔ ቤት መሆኑን አወቅሁ፡፡ የወዲያነሽን ለመጠበቅ ቆምኩ። «ሂዱ እንጂ ምን ቀረህ?
እናቷ እኮ ነኝ! ሌላ እናት ያላት መሰለህ? አይዞህ! ለሌላ ሰው አልሰጥብህም፣ እሷም በጀ አትልም» ብላ ስቃ አሣቀችኝ፡፡ የወዲያነሽ እናቴን በዐይኗ እየጠበቀች 'የሂዱ' ምልክት በጣቷ አሳየችኝ። ምርቱን እንደከተተ ሰው ተደስቼ ወጣሁ፡፡ወደ እኔ ቤት የመሄዱን ነገር ሰርዘን መኪና ውስጥ ተቀመጥን።

«አባቴ ስለ አንተና ስለ የወዲያነሽ ምንም ነገር ፈጽሞ እንዳልሰማና እስከ ዛሬም እንዳላወቀ ታውቃለህ:: ምስጢሩን የቀበርነው ሁላችንም ስለ ፈራነው ነው»
በማለት ንግግሯን ጀመረች፡፡ ጠንቃቃነቴንና ለጉዳዩ ያለኝን ከፍተኛ ግምት በግልጽ ለማስረዳት «አንቺና እማማስ ብትሆኑ ካባረራችኋት በኋላ ስለ እርሷ ምን የምታውቁት ነገር ነበር? ምስጢሩ ያልተነዛው ከእርሷ ጋር በመባረሩና እስር ቤት
በመውረዱ ነበር» ብዩ ተራ ለቀቅሁ፡፡

«ነገሩን በብልሃትና በዘዴ ካላስኬድነው በስተቀር ከአባታችን ጋር ብዙ ንትርክና ጭቅጭቅ እንደሚነሳ የታወቀ ነው፡፡ እኛ ግን ስለ ነገሩ ፍንጭ አግኝቶ
እንዲጠራጠር በማድረግ ጉዳዩን ለመጀመር አስበናል፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ አንተም እኛም ጥሩ ጥሩ ሽማግሌዎች መርጠን...» ብላ ሳትጨርስ «የብልሃቴ አቀነባባሪ እኔ ነኝ፡፡ የአዲሱ ሕይወቴ ጎዳና ቀያሽና ደልዳይ ራሴ ነኝ።
እያስፈልግም፡ በቃኝ! አባቴንም እንደ እናቴ በማስማልና በፍርሃት
እየተርበደበድኩ በመጠጋት የሚለኝንና የሚወስንብኝን ሁሉ አቀርቅሬ በመስማት ዕድል ለሚሏት አጋጣሚ ነገር አልንበረከክም! መጠራጠር ማለት ስለ አንድ ነገር ቢያንስ በጥቂቱ ማወቅ ወይም መገመት ማለት ነው። የትላንቱን ስሕተቴን ዛሬና
ነገ መድገም የለብኝም፡፡ አታስቡ! እኔ ለአባቴ የራሴ ዝግጅት አለኝ፡፡ በቀጥታ ቀርቤ ፊት ለፊት አስረዳዋለሁ፡፡ ለጥያቄዎቹም መልስ እሰጣለሁ» በማለት ጣልቃ
ገብቼ ተናገርኩ። ድንገት ደሟ ፈላና «ከንትርክና ብዙ ጣጣን ከሚያስከትል ጭቅጭቅ ይልቅ መግባባት ይበልጣል። በንትርክና በአሻፈረኝ ባይነት የምታገኘው
ድል አድራጊነት ሁሉ እስከ መጨረሻው አያረካህም፡፡ አባቴ በመጀመሪያ ጋሻዬነን አይቶ ከተደሰተና የሐሳቡ አቅጣጫ ካማረ ሁሉም ነገር ይሳካልናል።
የወዲያነሽንና የአንተን ግንኙነት፣ የደረሰባትን መከራና ሥቃይ ሁሉ ቀስ በቀስ እተርክለታለሁ፡፡ ልቡ ካዘነና መንፈሱ በርህራሄ ከተነካ፡ በሉ ሂዱና አምጧት ይላል” ብላ ነገሯን ልታራዝም ስትል «አይቻልም! ማን አስተርጓሚ አደረገሽና!
መሸሸግም ሆነ መደበቅ የለበትም፡፡ አልለማመጥም:: እጅግ አርኪው ድል አድራጊነትም ከትግልና ከሥቃይ በኋላ የሚገኝ ድል አድራጊነት ነው፡፡ እኔና
የወዲያነሽ ጋሻዬነህን አስከትለን ባንድ ላይ እንቀርባለን፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት “እንቺም ሆንሽ እናቴ አንዲት ቃል መናገርም ሆነ ማሰማት የለባችሁም፡፡ በምንቀርብበት ቀን እንግዶች ቢኖሩም ባይኖሩም ግድ የለኝም። እንዲያውም ወሬው እንዲስፋፋና እንዲዛመት ብዙ ሰዎች ቢኖሩ በጣም ጥሩ ነው:: በዚህ ብትስማሙ ተስማሙ፡ አለበለዚያ ግን የማደርገውንና የማላደርገውን እኔ ራሴ አውቃለሁ፡፡ እኔ የምፈልገው እንዲያውቅ ብቻ እንጂ እንዲስማማ ወይም መርቆ
እንዲቀበለን አይደለም፡፡ ከባለቤቴ ጋር ባለን ግንኙነት ውስጥ ጣልቃ ገብቶ አስተያየትም ሆነ ሌላ ሐሳብ እንዲያቀርብ አይደለም» በማለት ቀጥ እንዳለ አቀበት ስትፈራው የቆየችውን ጉዳይ አውላላ ሜዳ አደረግሁላት፡፡ በእኔ ላይ የነበራት ግምትና አስተሳሰብ ሁሉ ነፋስ እንደ መታው ልም ዱቄት ተበተነ፡፡በሁለታችን መካከል በጣም ግዙፍ የሆነ የሐሳብ ልዩነት ተፈጠረ፡፡ በእኔ ላይ የሐሳብ በላይነት ለማግኘት ባለመቻሏ ተከዘች። ምክራቸውንና መላቸውን ሁሉ ባለምቀበሌ ንዴቷ ናረ። የመዥገር ሞት ያህል አላሳዘነችኝም፡፡ ቁርጡን ለማወቅ
የጓጓው አእምሮዋ ራሱ የዘጋውን የዝምታ በር ከፈተው፡፡ «እኔ እና የግሌን የአቀራረብ መንገድና ሐሳብ አዘጋጃለሁ እንጂ የእናንተን አልቀበልም ማለትህ ነው?» ብላ ሁኔታዬንም አብራ ለመረዳት ፊቷን ወደ እኔ አዞረች፡፡

ባጭሩና በቀላሉ ”አዎ” አልኩና ተጨማሪ ምክንያትና ማብራሪያ
ለማቅረብ ስዘጋጅ «በቃኝ አያስፈልገኝም! አልሰማም ቀኙን ሲያሳዩህ ግራ ግራውን ትመርጣለህ፡፡ እኔን ያናደደኝ ያንተ እምቢታና የመጣው ይምጣ ባይነት ሳይሆን በዚሀ ይሻላል በዚያ፡ ይኸ ያዋጣል ያኛው ይበልጣል እያልኩ ከእናቴ ጋር
ስነታረክና ስከራከር መሰንበቴ ነው» ብላ ፊቷን አዞረች።

አልደነገጥኩም፡፡ «የአንቺም ይሁን የእናቴ ርዳታ እያስፈልገኝም፡፡ ጥገና እና ድረታ አልፈልግም፡ ጥገና አይዋጥልኝም! ጥገና ማለት ውስጠ ሰባራ ማለት ነው፡፡
ከሆነላችሁ እናንተም ተደርባችሁ በጥያቄና መልስ አዋከቡኝ! ዝግጁ ነኝ። ነገር ግን እኔ በማልገኝበት ወቅት አባቴን እንድትለምኑልኝና እኔን፣ ባለቤቴንና ልጄን ዝቅ አድርጋችሁ እንድትለማመጡልኝ አልፈልግም፡፡ እኔ ራሴ ባለጉዳዩ ፍላጎቴንና ውሳኔዩን ለማስረዳት በሚገባ ዝግጁ ሆኛለሁ» ብዬ ፋታ ሰጠሁ፡፡

«አያዋጣም እንጂ ቢያዋጣማ ጥሩ ነው:: ለፍተህ ለፍተህ እዚህ ከደረስክ በኋላ እንዴት እንዲህ በቀላሉ ትገነፍላለህ?» ብላ ራሷን ነቀነቀች።

«በቃኝ ነው የምልሽ! በሐሳቤና በእምነቴ እንድትስማሚ አላስገድድሽም። የገዛ መብቴን አልመፀወትም:: የሕሊናዬን ቁስል የማድንበትን መድኃኒት ቀስ በቀስ እያወቅሁ ነው:: ከአባቴ መሠረተቢስ እምነት ጋር እንድጋጭና እንድታተር
እንጂ እንደ ከዚህ ቀደሙ አንገቴን ሰብሬ የሚኖረው የሚያቀርበውን
ዝባዝንኪ ሐሳብ ሁሉ ያለ አንዳች ክርክር እንድቀበል አልፈልግም! ጨቋኝ ግዴታውን አልቀበልም:: ሐሳባችሁንም ሰርዙ። ከዚህ አሁን ከነገርኩሽ አፈጻጻም ውጪ አንዳችም የምቀበለውና የምስማማበት ሐሳብ ስለ ሌለ ነገር ሳናንዛዛ ወደ ቤት እንግባ» አልኩና ለጠላቱ የመጭረሻ ማስጠንቀቂያ እንደሚሰጥ
ሰው የማያወላዳውን ነገርኳት። ለወለላ ገሥግላ ፊት ዛቀች!

ያለውን ይበል ብላ እንዴት አታስብም? እንዴት አይገባህም? ነገሩን ረጋ ብለህ ተመልከተው፡ ራስህን ብቻ አትውደድ፡ ይኸማ ይበጣበጡ' ይጣሉ፡ ይጋደሉ ማለትህ እኮ ነው? ስንትና ስንት ዓመት ሙሉ ምስጢሩን ደብቀህ
ከኖርክ በኋላ አሁን በመጨረሻ ጣጣን አመጣህ። ለካስ በጄም በግሬም ገብተህ የተለማመጥከኝ እንዲህ ለመሆን ኖሯል? አሁን አንተ በምትለው ሁኔታ ከሆነ
አገር ምድሩን እንደሚበጠብጥ አውቃለሁ፡፡ እናቴ ግን ያን ሁሉ አድራጎት ያደረገችው ላንተው ስትል እንደነበር ታውቃለህ» ብላ ፊት ለፊት ወደ ጨለማው
👍3
አፈጠጠች። ቀለል ያለች የማናናቂያ ሣቅ ከሣቅሁ በኋላ «ለካ በደንብ አውቀሽልኛል! አሁን ገና ተገናኘን። እኔም የምፈልገው ይኸንኑ ነበር፡፡ አንቺ በፈራሽው አኳኋን ከጠየቀኝማ... እሰየው! ደስታውንም አልችለው! ፈቅ ነቅ
በማይለው በአባቴ እምነት ታስሬ ለመኖር አልሻም፡፡ መሠረቱን ማፈራረስና ሰንሰለቱን መበጣጠስ አለብን። ከአያት ከቅድመ አያት የወረሰውን መጥፎ ልምድ
ጥለን መቅበር ይገባናል።
«የእኔና የየወዲያነሽ ጉዳይ ምስጢር ሆኖ የተጠበቀው ከጨለማ የጠቆሩ ምክንያቶች ስለ ነበሩት ነው። ለሚያቀርብልኝ ጥያቄ ሁሉ የምሰጠው አጥጋቢ
መልስ አፍንጫዬ ሥር ተንጠልጥሏል፡፡ አትታደስ፣ አትለወጥ ነው የምትሉኝ?
ሕይወት ያለማቋረጥ የምትታደስና የምትለወጥበት የራሷ የሆነ ባህሪ አላት።

የወዲያነሽንና የመሰሉቿን ሕይወት አስተካክዬ ለመገንባት የእናንተን ከንቱ እምነትና ኑሮ መናድና ማፈራረስ አለብኝ» ብዬ የንዴቷን ቃጠሎ እንደገና
ቆሰቆስኩት፡፡ ምክንያትም ካስፈለገ ነፍስ ያለው ምክንያት» እንዳልኩ፡

«ምክንያት! ድንቄም ምክንያት እቴ! ይህን ቆሽት የሚያሳርረውንና
አንጀት የሚጎምደውን ነው ምክንያት የምትለው? ለረብሻና ለብጥብጥ የሚቀርበውን ምክንያት ሁሉ ምክንያት አልለውም፡፡ እንደ ርግብ ገብቶ እንደ እባብ መናደፍ የሰው ልጅ ሥራ አይደለም» ብላ ከነንዴቷ ጸጥ አለች። በጥፊ ልጋጋት ፈለግሁ፡፡ ትልቅ ጦርነት ባንዲት ጥይት ጩኸት ይጀምራል ቢባልም
ታገሥኩ፡፡

«ሁልጊዜ ርግብነት አያስፈልግም፡፡ ቀስ ብሎ አድፍጦ እና ሠርጎ ገብቶ ጠላት የጠላትን አጨብጫቢ አፋሽ አከንፋሽ ሁሉ እየነደፉ መፍጀት ያስፈልጋል፡፡

እንዲሁ እንደ ግመል ብቅ ማለትማ ሞኝነት ነው፡፡ መጀመሪያ
አዲሱ ሐሳቤ እንደማይለወጥ ዐወቂ፡ አሳውቂ፡ ዓላማዬ ደረጃ በደረጃ ማደጉን ለፍሬ መቃረቡን አትዘንጊ፡፡ ምኑ ተይዞና ያድጋል ይፋፋል። ከእንግዲህ”
የመከራ ጊዜ ካለፈ በኋላ ለመገናኘት የቻልነው ምስጢር መሆን የሌለበትን ጉዳይ
ወዲህ እኔ የማውቀውንና በትክክል ያቀድኩትን ሁሉ እፈጽማለሁ። ያ ሁሉ የመከራ ጊዜ ካለፈ በኋላ ለመገናኘት የቻልነው ሚስጥር መሆን የሌለበት ጉዳይ
አምቄ የሁለቱን ሥቃይ በትዕግሥት ለመቋጠር በመቻሌ ነው፡፡ ዛሬ ግን በቃኝ በቃኝ አንገፈገፈኝ!” ብዬ ጃግመኛ ላለመናገር ዝምታዬን ታከናነብኩ፡፡ ዝምታ የንግግሬ ማክተሚያ መሆኑን የተረዳችው የውብነሽ “የእኛ ነገር ሞተ” ማለት
ነው? እዚህ ተወዝፌ የምጫጫሁበት ምንም ምክንያት የለም! ብላ ከመጨረሷ ዕቅጩን ለማሰማት ያህል «አዎ እዚህ ላይ አብቅቷል፡ ሌላ ወሬ ካስፈለገው ግን ዶሮ እስኪደጋግም ማውራት እችላለሁ” ብዪ የምንተያይባትን የሐሳብ መስኮት ሽጎርኳት። ሲያስጨንቃትና ሲያሠቃያት የቆየው ንዴቷ ድንገት በቡጢ መትተው እንዳፈነዷት ፊኛ በመፈንዳቷ “አንተም ያሰብከውን ፈጽም፡ እኛም ባንተ የተነሣ
ከቤት እንባረር፡ ይኽ ሁሉ የምንቸገረኝ ሥራ ነው እንጂ የችግሩ ከባድነት ጠፍቶህ አይደለም፡፡ ካባረርናት በኋላ የት እንደ ገባችና የት እንደ ደረሰች
አናውቅም፣ አልሰማንም ማለት አይጠፋንም» ብላ ትንፋሿን ለመዋጥ ንግግሯን ስታቋርጥ፡

«እከድዬ.» አለች የወዲያነሽ፡፡ እኔስ ሌላ ምን ፍጠሩልኝ ምን
እድርጉልኝ አልኩና? ከዚያ ወዲያ ስላለውን ነገር እኔ ነኝ ባለመብቱ፥ አብራሪው እኔ ነኝ! እናንተማ ካባረራችኋት በኋላ ትሙት ትኑር ምን ታውቃላችሁ? ትልቁ ችግራችሁና አፋችሁንስ ያፈነው ምኑ ሆነና? ስንተዋወቅ.. መግቢያና መጠጊያ በማጣት ሰማይ መሬቱ የሚደፋባት እንደ እኔዋ የወዲያነሽ ያለችው እንጂ
የእናንተ ብጤዋማ ይልቅ አይምሽብን ብዪ የማያዳግመውን አረዳኋት፡፡

«ስመጣም እየከበደኝ ነበር የመጣሁት፡ አሁን እንዲህ የምትሆነው ራሴንችያለሁ ብለህ እኮ ነው! ለእኛም እግዚአብሔር ያውቅልናል፡፡ ራሲንና እናቴን
ማስተዳደር አያቅተኝም፡፡ ይቺ ከነማን ጋር እንደ ተመከረች አውቃለሁ» አለችና የመኪናይቱን በር በርግዳው ወጣች፡፡ ተከተልኳት። እኔ ስንት ዓመት ሙሉ
በመከራና በንዴት ምድጃ ላይ ተገላብጬ ውስጥ ውስጡን እንደ ነፈርኩ መቼ አየሽና?» ብዬ ለሁለታችን ብቻ በሚሰማ ድምፅ ተናገርኩ፡፡ ፈጠን ብዩ ልደርስባት ሞከርኩ፡፡ ደረጃውን ጨርሳ የሰበሰቡን ወለል ስትጀምር እኔ አጋማሹ ላይ ደረስኩ፡፡ ንዴቷን በትዕግሥት ለማሸነፍ ባለመቻሏ ወደ መኝታ ቤት ገባች።
እናቴና የወዲያነሽ እየተሣሣቁ ያወሩ ስለ ነበር በአቸኳኮሏ ሳይገረሙ አልቀሩም፡፡

«ምነው ምን ነካት? ተጣላችሁ እንዴ? የእናንተ ነገር እኮ..» ብላ ዕድሜ የተጫናት ደካማ ሣቅ ሣቀች፡፡ ከፊት ለፊቷ ዘርፈጥ ካልኩ በኋላ አሁን እዚህ ቤት አጠገብ እንደ ደረስን እንዴት ያለ ባል አግኝቼልሻለሁና እሺ ትያለሽ
ወይ?» ብዩ እንደ ቀልድ ጠየቅኋት «አንተ ነህ ወይ የምትመርጥልኝ? ምን አገባህ?» ብላ አፍንጫዋን ነፍታብኝ ሮጠች፡፡ የማታደርገው ትመስላለች» ብዬ ዓይን ያወጣ ውሽት ዋሽሁ። እናቴም «ምን የሷ ነገር ይኸው አይደለች» ብላ
ነገሩን ችላ አለችው:: ወደ ቁምነገር መለስ ብላ ነገረችህ አይደል ሁሉንም? ቀስ ብለን ብናሰማውና ብንፈጥመው ይሻላል ብዬ ነው:: አለበለዚያማ የአባትህን ጠባይ ታውቀዋለህ፣ ቀስ ብለን አስልተን ብንይዘው ይሻላል» በማለት ከሣቅ ገለል ያለ
መልክ አሳየች፡፡

«አዎ ተስማምተናል፡ ጥሬና ጠጠር ሆነናል የቀረውን ደግሞ ነገ ጧት እንጨርሰዋለን፡ ገና እኮ ሳምንት አለ» ብያት እኔና ባለቤቴ ወደ ቤታችን ተመለስን.….

«መርፈድስ አልረፈደም፡ የሚያስቸኩል ጉዳይ ስላለብኝ ነው አልኳት ያለወትሮዬ በማለዳ ተነስቼ ለመሔድ መዘጋጀቴ አዲስ ነገር ለሆነባት ባለቤቴ::
ከነሙሉ የጧት ንቃቷ ቆም እንዳለች «በይ ደኀና ዋይ! ምናልባት በምሳ ሰዓት ከጉልላት ጋር ሳንመጣ አንቀርም» ብያት መንገድ ገባሁ፡፡ሩጫ በተደባለቀበት አረማመድ ከተል ብላ «ትላንትና ማታ ከነእማማ ጋር ምን ነበር የተባባላችሁት?
ረሳኸው እንዴ? ብቻዬን ነው እንዴ የምሔደው?» አለችኝ፡፡ ማን አለሽና? ማን አዘዘሽና ነው የምትሄጂው? አርፈሽ ተቀመጪ። የምናደርገው ነገር ሁሉ በአንቺና
በእኔ የጋራ ውሳኔ ብቻ መፈጸም አለበት፡፡ ሐሳቤን ሁሉ ለውጫለሁ፡፡ መብትሽን ከቀሙሽ ሰዎች እጅ መብትሽን መንጠቅ እንጂ መለመን የለብሽም፡ ብያት
ወጣሁ፡፡ ወዲያ ወዲህ ሳልል ወደ ወላጆቼ ቤት ሄድኩ።

ትልቁ የአጥር በር ተከፍቶ ስለ ቆየኝ ዘው አልኩ፡፡ ዘበኛው በረጂም ዕንጨት ላይ የጥድ ቅርንጫፍ አስሮ ግቢውን ይጠርጋል። እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ እንደ ደረስኩ የውብነሽ ጋቢ ለብሳ እንደ ቆመች አገኘኋት፡፡ ፊቷ ተነቅሎ የተጣለ የአረም ቅጠል መስሏል፡፡ ንዴቷ አልበረደም፡፡ የአዲሱን ሐሳቤንና የእኔን ግንኙነት ስለማውቅ ትቻት ወደ ውስጥ ገባሁ፡፡ ከየውብነሽ ጋር ከመታገል ከእናቴ ጋር መነታረክን መረጥኩ፡፡ አውቆ ካጎበደደ ሳያውቅ መሬት የላሰ ይሻላል። እናቴ ከፊቷ ለቆመችው ሠራተኛ ስለ ማድ ቤት ጣጣ የሥራ ትእዛዝ ትሰጥ ነበር። ገባ
ብዬ ቆም ከማለቴ «ቆየት ብዩ እጠራሻለሁ ሂጂ» ብላ አስወጣቻት፡፡ እንዴት አደርሽ» ብዬ ተቀመጥኩ፡፡ ከእግር እስከ ራሴ ቁጣ ባነደደው ዐይን አየችኝ፡፡
መልኳ ተለዋወጠ። እኔ ግን ወይ ፍንክች! በፈገግታ ላይ ፈገግታ ደረብኩ፡፡ እንደ ከዚያ ቀደሙ መሽበሬ ቀርቶ ብርታትና ድፍረት ተሰማኝ። ቆርጦ የተነሣ
ለነፍሱም እይሳሳ» ነው፡፡
👍4
የውብነሽ እምቢታዬንና ዕቅዴን ሁሉ ተከራካሪ እና ሀይ ባይ በሌለበት እንዳስፈለጋት እየተነተነች እንደ ነገረቻትና እናቴም በዚሁ የተነሣ መናደዷ
ገባኝ፡፡ እኔ ግን እንኳንስ አንዲት የውብነሽ አእላፋት መሰሎቿ እንኳ ተሰብስበው የሆነ ያልሆነውን ሲወሻክቱ ቢያድሩ. ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ አልኩና ዝምታን
ቀጠልኩ፡፡ ወለሉንና የጫማዬን አካባቢ በግልዕ ቅሬታ አፈጠጠችበት።

«ምነው ልጄ? እንዲያ ሳምንህና ስወድህ ሰው ሆንክልኝ ብዬ ስደሰት እንዲህ ታደርግ? ይኸስ የጤናም አይደለም፡፡ ይግደላት ይዘልዝላት ብለህ ነው? ያዳፍንባት ብለህ ነው? ያባትህን ጠባይ ታውቀዋለህ፡ ቀስ ብለን በዘዴና በምክር ከዚያም በሽማግሌ ነው እንጂ አለበለዚያማ ይፈጀናል። መስሎህ ነው እንጂ አንተም አይቀርልህ፡ ምን አደረግሁህ? ምን በደልኩ? ልጄ ተው? የእኔ የእናትህ ምክር ነው የሚበጅህ?» አለች። ዐይኖቿ ፈዘዙ፡፡ የውብነሽ በዝግታ ገብታ ቆመች። በጭራሽ አላደርገውም፡፡ እኔ የማደርገውን እኔ አውቃለሁ፡፡ በማይረባ ዘዴና በሽማግሌ አማካይነት መብቴን መለመን አልፈልግም፡፡ በእኔ በኩል አልቋል፤ ተጠናቋል። በእኔ ዕቅድና ሐሳብ መሠረት መከናወን አለበት፡፡ የአባቴን ቁጣና ግትርነት በመፍራት በጭንቀትና በሥቃይ እግረሙቅ ታስሬ መኖርና መቆየት የለብኝም» ብዬ ንግግሬን ልቀጥል ስል «አንተስ ማምለጫህንና
መውጫህን ሁሉ ይዘህ የመጣው ይምጣ አልክ፡ እኛስ ምን ይዋጠን? እለቁ ማለትህ ነው? 'ከዚህ ቤት ስታባርሪያት እርጉዝ መሆኗን ካወቅሽ ለምን ያን ጊዜ
አላማከርሽኝም? አልነገርሽኝም?” ብሎ ነው ጉሮሮዬን ይዞ ሲል የሚያደርገኝ፡፡ኧረ ተው በጡቴ ይሁንብህ?» ብላ ልቅሶ ቃጣት።

«አባቴ ከዚህ ቀደም ለምን እንዳልሰማኛ ምስጢሩም እንዴት ሊደበቅ እንደቻለ አፍረጥርጬ የማስረዳው እኔ እንጂ እናንተ አይደላችሁም። መልሶቼን
በሚገባ ስላዘጋጀሁ እናንተን በፍፁም የሚያስነካና የሚያስወቅስ ነገር የለም ብዬ
የየውብነሽን ሁኔታ ለመረዳት መለስ ብዬ አየኋት።

«እንዳጋጣሚ ሆኖ የአንተ ዝግጅት አንተን ብቻ ጠቅሞ እኛን የሚጎዳና የሚያጉላላ ከሆነ ምን ጥቅም አለው? መጀመሪያ የተለማመጥከንና ቀስ በቀስ
የተጠጋኸን ለዚህ ኖሯል እንዴ?» ብላ በንቀት ዐይን አየችኝ፡፡ መናናቅ ከሕሊና መሻከር የሚመነጭ ጥላቻ መሆኑን ስለማውቅ ለጊዜው ንቀቷን በንቀት አልደቃሁትም፡፡

«አዎ ልክ ነሽ፡ አጋጣሚ ግን ሙሉ መተማመኛ አይደለም፡፡ እኔ ስለ
ራሴ ብቻ የማስብበትና የምጨነቅበት ጊዜ እየበቃ ነው:: 'የየራስህን ማሳ ብቻ እረስ” ማለት ጠባብ ከራስ በላይ ንፋስ ፍልስፍና ነው፡፡ ለሌሎች መልካም እና ጠቃሚ ውጤት ለማስገኘት ስል እናንተንም ቢሆን አጋልጣለሁ፡፡ የሌሉች የቆሰለና የተሠቃየ ጀርባ ለእናንተ የድሎት ሜዳ መሆን የለበትም፡፡ አትጨነቁ ! በማቀርበው አስተያየትና የመከራከሪያ ሐሳብ ሁሉ አትደንግጡ፡፡የሚያወጣችሁ ተግባራችሁ እንጂ ፋይዳ ቢሱ ፍርሃታችሁ አይደለም። ሰው
እውነትን መፍራት የለበትም፡፡ እኔ ግን አባቴ የሚሽሻትንና የሚጠላትን እውነት እሻታለሁ፡፡ እውነት የብዙዎች መብት በመሆኗ በኃይለኛች መዳፍ ውስጥ
ላዝንታለም አትኖርም፡፡ እውነት የራሷ ትንሣኤ አላት። የተበደሉ ሁሉ በመራራ ትግል ያገኟታል። ከተበደሉት መኻል አንዷ የወዲያነሽ ናት። እውነት ስትናገር
የሚፈራና ተናጋሪውንም የሚያፍን የእውነትና የሕዝብ ጠላት ብቻ ነው።

«ከእንግዲህ ወዲያ የወዲያነሽ አግባብነት ለሌለው የይቅርታ ጥያቄ ጫማ አትልስም፡፡ ከእንግዲህ ለተገዢነት አታጎበድድም፡፡ ክብረ ሕሊናዋን
በማይነካና እኩልነቷን በማይፃረር አቀራረብ ብቻ እጅ ትነሣ ወይም ትታረቅ ይሆናልም ፡፡ይህ የማይሻር እምነቴ ነው ብዬ ለእናቴ የሚገባትንና የማይገባትን
ሐሳብ ተናገርኩ። የተናገርኩት ሁሉ ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ሆነ፡፡ በትካዜ ያመቀችውን አየር ወደ ውጪ ከለቀቀች በኋላ «አይሄሄ! ይኸማ ምን መላ
አለው! ምንም መላ የለው! ልጅህን ካየና ከሰማ በኋላ ያንን ሁሉ ታሪክ ሊሰማ ደግሞ ሌላ ማንንም አይደለም፣ እኔኑ ነው አናቴን የሚገምሰኝ፡፡ ይህን የመሰለ ልጅ በከንቱ አሳጥተሽኝ ነበር፡ እረ እንዲያውም የገደልሽኝ ያህል ነው ብሎ ነው እንደ ነብር ዘሎ የሚከመርብኝ፡፡ በቀላሉም አንገላገል» ብላ ውስጥ ውስጡን
እድራጎቴንና ሐሳቤን ለመራገም ወደ ሰማይ አንጋጣ እየች፡፡ አቡዩ አንተ ታውቁልኛለሁ፡ አንቱዉ እርዱኝ ኧረ እንዲያውም እፈራርዱኝ' ማለቷ ነበር።
ባቀረብኩት ሐሳብ ሳንጣጣጣምና ሳንግባባ ቀረን፡፡ እናቴ ለዚያች ለጭንቅ አማላጅዋ
አቤት እንደምትልብኝ አውቃለሁ። እሷ ግን ለእናቴም ሆነ ለባለቤቴ ኣታዳላም፡፡ የውብነሽ ግን "ልዝብ እባብ ማለቷ የማይቀር ነው፡፡ «ደኅና ዋሉ» ብያቸው ስወጣ መልስ አልመለሱልኝም፡፡..

💫ይቀጥላል💫
👍4
#አይብቀልብሽ

የተንቤን እቅፍ የናፈቀው
የወሎ ሸህ የመረቀው
እንደጴጥሮስ ግፍና ሞት የሰቀቀው
እንደሉላ ዳር ድንበሩ ያስጨነቀው
እምቢ ባይ ነው ዓለም ሲያውቀው::
ያደፈረሱት እንዲጠራ በዕንባ ፀሎተኞች
በደመም ወንዝም ጅረት የምንጠራ አንደኞች
ከመንገድ የተሰነካከልን
በስልጣኔ ሰማይ ያከልን
ወጥተው ቀሩ መባላችን
ግድ ያልሰጠን ሞት ምናችን
ሰው ምናችን?
ደም ምናችን?
አሜን በይ አንቺዬ ደግሞም እንዳይሰጥሽ
እንዲህ አይነቱ እሾህ አይብቀል በቅጥርሽ፡፡
አሜን በይ አንቺዬ ይበቃሽ የቃል ቁማር
በፊደል ነው እንጂ በበደል ከመማር
ሀ ሲባል ቆጥረናል የሞት አቦጊዳ
ጦርነት ለመደሽ መስሎልሽ እንግዳ
አይብቀል
በሰሜን
የሚያርሳኝ ስሜን፡፡
አይብቀል
በደቡብ
ይጥፋ የዘር ህሙም፡፡
አይብቀል
በምዕራብ
ችግርና መራብ፡፡
አይብቀል
በምስራቅ
ጭንቅሽ በዛው ይራቅ፡፡
የተንቤን እቅፍ የናፈቀው
የወሎ ሸህ የመረቀው
እንደጴጥሮስ ግፍና ሞት የሰቀቀው
እንደሉላ ዳር ድንበሩ ያስጨነቀው
እምቢ ባይ ነው ዓለም ሲያውቀው፡፡

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍2
ይቸም እድሜ ሆና፣
'ያላየሁት የለም' ስትይ ነበር አሉ?
ይችም ዘመን ሆና፣
አንቺም እንደሌሎች
'አቤት ወንዶች' ብለሽ አማረሻል አሉ።

አይገርምም?
ልብ 'ለጋ' የለውም!

ያው የመኖር ቀመር...
በዚህ ክፉ ዘመን አንዳች ደፍሮ ማፍቀር፣
ልብን አሰብሮ ሰባራውን መቁጠር።

አይ ወንዶች አትበይ ወይ ሴቶች አልልም፣
ከዘመን ተቃርኖ ያሸነፈ የለም።

ይልቅ ነይ ግቢ፣
ለጋ ልብ ይዘሽ ማጣት ካዘለው ደሳሳ ቤቴ፣
አካልሽን ልልበስ ሁኝ አካላቴ፡፡
ነይ እንፋቀር፣
ነይ ልብ እንስበር!

?
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በትክክል_ገና


በሌቱና ወላጆች ቤት ላይ የሥጋት አሞራ ረጃጅም ክንፎቹን ዘርግቶ
በቅርብ ርቀት በማንዣበብ ላይ ይገኛል፡፡ መጀመሪያ ጃኖ ከዛሬ ነገ ምን ያመጣብን ይሆን? ምን ያደርገን ይሆን? በሚል ጭንቀት ተውጠው ከከረሙ በኋላ በተፈጠረው ትንቅንቅ ጉዳት የደረሰበት ባላባት ቱሬ ደግሞ ምን ፍጠሩ? ምን ውለዱ ይለን ይሆን? ምንስ ያስደርገን ይሆን? በሚል ተጨማሪ ጭንቀት ተውጠው እንቅልፍ አጥተው ከርመዋል።

ሴት ልጅ ስትወልድ ወላጆች በደስታ ይፈነድቃሉ። ሴት ልጅ ብር ነች።ሴት ልጅ ንብረት ነች፡፡ ለአቅመ ሄዋን ደርሳ በባህሉ መሰረት ለጋብቻ ስትጠየቅ በገበራ ቤተሰቦቿን ትክሳለች፡፡ በተለይ መልኳ ቀንቶ ዕድሏ ተሳክቶ ባለንብረት ለትዳር የሚጠይቃት ከሆነ ደስታው እጥፍ ድርብ
ነው፡፡ የቁም ከብቶች ከበግና ከፍየል ጀምሮ ሰንጋ ፈረስ ወይንም ምርጥ ሰጋር በቅሎ ለወላጆቿ በገበራ መልክ ታመጣለች ታሸልማለች። የሌቱና
ወላጆች ምኞታቸውና ተስፋቸው ይሄው ነበር፡፡ ሌቱና ተድራ የምታንጋጋው የገበራ ንብረት እየታያቸው በደስታ ነበር የኖሩት፡፡ ሴት ልጅ ለትዳር ምርጫ ዕድል አይሰጣትም፡፡ የወደደችውን ያፈቀረችውን ማግባት አትችልም፡፡ ቢጥማትም ባይጥማትም ወደደችም ጠላችም ፊቷ በነጠላ
ተሸፍኖ ወላጆቿ ከተስማሙበት ጋር ተቆራኝታ መነዳት ግዴታዋ ነው።የሷ ትዳር ጣዕም የሚቀመሰው በወላጆቿ ምላስ ጫፍ ነው። በራሷ ስሜት አጣጥማ የጣፈጣትን የመብላት ያልጣፈጣትን የመተው መብት
ማን ፈቅዶላት? እነሱ ቀምሰው ካጣጣሙላት መቼ አነሳትና?!

ሴቱና ግን ምኞቷና ፍላጎቷ ይሄ እንዲሆን አልነበረም፡፡ ዕድለኛ ሆና
አብሯት ባደገ ወጣት ፍቅር ላይ ከወደቀች ወዲህ ሁል ጊዜም የምትመኘውና የምታልመው እሱን አግብታ ልጅ ወልዳ መሳምን ዘር ዘርቶ መቃምን ነበር፡፡ አዎን ጃኖን! ከጭቃ ማቡካት ጀምሮ አብሯት ያደገው ጃኖን! ለአካለ መጠን ደርሰው መተፋፈር የጀመሩት ጃኖን! የልጅነት ትንሿ ልቧ የደነገጠችለት ጃኖን ብቻ ነው ቀን ከለሊት የምታሰላስለው።
ጃኖም ሌቱናን አግብቶ ልጅ ወልዶ የሚስምበትን በፍቅር ተደስተው የሚኖሩበትን አዲስ ህይወት በዐይነ ህሊናው አሻግሮ እየተመለከተ በተስፋ ሲጠባበቅ ቆየ፡፡ ይሁን እንጂ እሱ እንደሚያስበው ሁሉ እሱ እንደሚመኘው ሁሉ ሌቱናን ታስብ ይሆን? ሌቱናስ ትመኝ ይሆን? ለዚህ ጥያቄው ምላሽ የሚያገኝበትና ቁርጡን የሚያውቅበት ቀን እጅግ ራቀበት። “ጃኖ! አንተ እኮ አብሮ አደግ ወንድሜ ነህ እንዴት እንደዚህ ያለውን ከንቱ ሀሳብ ታስባለህ?” ብላ ቅስሙን የምትሰብረው ወይንም ደግሞ ፍላጎትህ
ፍላጎቴ ምኞትህ ምኞቴ ነው ብላ በደስታ ፈንድቃ እሱንም የምታስፈ
ነድቀውና የምታስቦርቀው ከነኝህ ከሁለቱ አማራጮች አንዱን መርጣ
ቁርጡን የምታሳውቀው ቀን እስከሚደርስለት ድረስ ውስጥ ውስጡን በፍቅር ሲሰቃይ ለብዙ ጊዜ ቆየ፡፡ ጊዜው ይቆይ እንጂ ትዕግስቱ መራራ ሬት ሳይሆን ጣፋጭ የወይን ፍሬ በማፍራት ላይ ነበረች፡፡ ቀስ በቀስ ያቺ ጣፋጭ የፍቅር ወይን በስላ ለመበላት መድረሷን የሚያውቅበት አስገገራሚ ዕለት እየደረሰችለት ነበር፡፡ ምንግዜም ከዐይነ ህሊናው የማትጠፋው ያቺ ውብ ቀን የብሩህ ተስፋ እቅፍ አበባዋን ለጃኖ ይዛ ከተፍ
አለች፡፡

አዝመራው ተንዠርጎ ምርቱን አግቶ ማስጎምጀት በጀመረበት በክረምቱ ወቅት በግብርና ሙያው የሚደነቀው ጃኖ ሹሩባ ማውጣት በመጀመረው የበቆሎ ማሳው ውስጥ ደፋ ቀና እያለ አረሙን በማጭድ በመመንጠር ላይ ነበር፡፡ ዝናቡ ያካፋል፡፡ እሱ ደግሞ እንጉርጉሮውን በዚያ ማለፊያ ድምፁ እያዥጎደጎደ አረሙን ያቀላጥፈዋል።“ጠቀሲስስ መዕስ
ስስስ ..ቋ!...ቋ!” እያደረገ የበቆሎ አገዳውን ግራና ቀኝ እየገፋ ወደሱ የሚመጣ ኮቴ ተሰማው። ጆሮውን አቀና፡፡ፊቱን ድምፅ ወደስማበት አቅጣጫ አዞረ። ማጭዱን አስተካከለና እንደ ማድባት አለ፡፡ ያንን ያማረ ቡቃያውን ሊያጠፋ ጮርቃውን በቆሎ እየገሽለጠ ሊቦጠቡጥ የመጣ ከርከሮ ወይንም ጃርት ይሆናል ብሎ ገመተ።በዚያ በማጭድ አንገቱን ሊቆርጠው አደፈጠ። የሆነ ነገር ውልብ አለበት። ዐይኑ ያየውን ነገር ተጠራጠረ፡፡ ጨፈነውና ገለጠው፡፡ እንደገና እንደገና.. እንደገና የማይታመን ነው። አይኖቹን ተጠራጠረ፡፡ ግን ልክ
ነው። ራሷ ሌቱና ነበረች። ፍልቅ... ፍልቅልቅ.. እያለች ተጠጋችው፡፡
“የትአባቱ! እስከመቼ ድረስ ጫካ ይመስል ሚስጥሬን ደብቄ እኖራለሁ?እስከመቼ ድረስ ውስጥ ውስጡን በፍቅር እነዳለሁ!” ብላ ቁርጡን ተናግራ ቁርጡን ከጃኖ አንደበት ለመስማት ስሜቷ ሂጂ! ሂጂ! ብሉ ገፋፍቷት ደመ ነፍሷ እየነዳ ወሰዳትና ከበቆሎው ማሳ ከአረንጓዴው ሰፊ ሳሎን ከጃኖ የበቆሎ እርሻ ውስጥ አምጥቶ ጣላት። “እኔ እኮ አብሮ አደግ ወንድምሽ ነኝ እንዴት እንደዚህ ታስቢያለሽ? ብሎ የሚያሳፍራት ከሆነም ጉዷን ለማወቅ ቆርጣ ነበር የመጣችው። ካፊያው አበስብሷታል። ጤዛው አርሷታል፡፡ጨጎጊት ቀሚሷ ላይ ተጣብቋል። እሷ ግን አንዱም ስሜት አልሰጣትም፡፡ አልተሰማትም ነበር። ከጃኖ ጋር ያላት ግንኙነት ቁርጡ የሚለይበት የመጨረሻው ቀን ነበርና እንዴት እንደመጣች ዝናቡ እንዴት አድርጎ እንደደበደባት ምንም የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ሰው እንደዚያ አድርጎ ይደሰታል ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅም። ወደ ሰማይ እንጣጥ! ብሎ የደስታ ጮቤ ሊረግጥ ከጀለው። ማጭዱን ዳግም እንደማ ይፈልገው ሁሉ አሽቀንጥሮ ጣለው ..ከርከሮ ወይንም ጃርት መስሉት የተሰበቀው ለካስ በለይቱና ላይ ነበር? “የትአባቱ!” ብሎ ለለይቱና መዘጋጀቱ አናዶት ወደዚያ ወረወረው፡፡

በአካባቢው ያለነሱ በስተቀር ወፍ እንኳን ለምስክርነት በሌለበት በዚያ በካፊያ ውስጥ ሹልክ ብላ ከቤቷ ተደብቃ ወጥታ ገስግሳ የመጣችለትን የፍቅር ልዕልት ፍፁም በሆነ የደስታ ስሜት ተውጦ ወደ ውስጡ ጠቅልሎ ሊያስገባት እጆቹን እንደ አሞራ ክንፍ ግራና ቀኝ ዘረጋላትና
“ቱ!” ብሎ ጮኽ፡፡ ሌቱናም ግራና ቀኝ በተዘረጉት እጆቹ መካከል ሄዳ
ልክክ አለች፡፡ ከሚያካፋው ካፊያ ከቅዝቃዜው እንዲያድናት ጭምር ከተገላጠው ደረቱ ላይ ጥብቅ አለችበት፡፡ ጃኖ በህልሙ እንጂ በውኑ አልመስለውም፡፡ የሱ ሌቱና የሱ ፍቅር የዛሬ አመጣጧ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሳ ቁርጧን ለማወቅ አስባበት መሆኑን አወቀ። እሱ እንደሚያፈቅራት ሁሉ እሷም የምታፈቅረው መሆኑን ተገነዘበ፡፡ እንዳቀፋት ሰውነቱ ሙቀት የሚያመነጭ ጀነሬተር ሆነ። ትኩሳቱ አሻቀበ፡፡ ለዘመናት ውስጥ ውስጡን ሲንተከተክ የኖረ ፍቅር ያመነጨው ትኩሳት! ሌቱናም በትኩሳቱ ውስጥ አተኮሰች፡፡ በሙቅ ሰውነቱ ውስጥ በስሜት ፈሰሰች፡፡ ከዚያም
በእፍረት ስሜት በተዋጡት ዐይኖቿ ዐይን ዐይኖቹን ሽቅብ እያየች “ጃኖ! ጃኖ! ትወደኛለህ? ታፈቅረኛለህ? ቁርጡን ብቻ። የመጨረሻውን ንገረኝና
ቁርጤን ልወቀው። አንድ ቃል በቃ... አንድ..ቃል” ዐይኖቿ በእንባ ተሞሉባት። ፀጥ አለች።

ለምን እስከዛሬ ድረስ ቁርጡን አልነገርከኝም፣ ለምን ያንቺው ነኝ አላልክኝም መሆኑ ነው፡፡ እንባና ሳግ ተናነቋትና ልሳኗ ተዘጋ፡፡ ጃኖም ቁልቁል ተመለከታት። በደስታ እንደሰከረ ፍዝዝ ባሉት ዐይኖቹ በስስት አስተዋላት፡ የፍቅሩን ጥልቀት ለመግለፅ ቃላት አጠሩት፡፡ ውስጥ ውስጡን
👍3
ሲንገበገብ መቆየቱን፣ ያንተው ነኝ የሚለው ቃሏን ከአንደበቷ ለመስማት በጭንቀት ተወጥሮ በጉጉት ሲጠባበቀው የኖረ መሆኑን የሚገልፅበት አንደበት አጣ፡፡ እንደዚያ ሲያያት ልቡ ፍስስ የሚለው፣ የሚሽኮረመመው፣ የሚያልበው፣ የሚርበተበተው፣ ዐይኖቿን በሙሉ ዐይኖቹ
ለማየት ድፍረት የሚያጣው በሌላ ምክንያት ሳይሆን በፍቅሯ ምክንያት መሆኑን፣ እወድሻለሁ የሚለውን ቃል ለመተንፈስ ወኔ እያጣ እንጂ እንደነፍሱ የሚወዳት መሆኑን የሚገልፅበት ቃላት አጠሩትና ዐይኖቹ ፈጠው ቀሩ።የሱም ዐይኖች የሷን ተከትለው እንባ አቋቱ...

የሾሉ ጡቶቿ በደረቱ ላይ ልክክ እንዳሉ ሁለት ፍቅርን የተራቡ ነፍሶች የናፍቆት ረሀባቸውን ለመወጣት እርስ በርስ ተፈላለጉና ከንፈሮቹ ከንፈሮቿን፣ ከንፈሮቿ ደግሞ የሱን ከንፈሮች ጎርሰው እንደ አፍለኛ እንጀራ እየተሻሙ እጅግ አስደሳች ወደሆነ ልዩ ዓለም ውስጥ ገቡ። ከዚያም ከገቡበት ዓለም ቶሎ ብለው መውጣት ተሳናቸውና እንደተቃቀፉ በስሜት
ተንሳፈው ከደመናው በላይ በህዋው ላይ ናኙ... ካፊያውን ተክትሎ በድንገት የመጣው ሃይለኛ ዝናብም እንደ ጥምቀት ፀበል ጠመቃቸው። ይሁን
ብለናል ይሁን ብሎ እያረበረበ ደስታውን ገለፀላቸው፡፡ አእዋፋት በጣፉጭ ዝማሬአቸው እየተንጫጩ አጀቧቸው፡፡ የበቆሎ ማሳውን እሽቱን ለአብነት ቆጥረው የፍቅራቸውን ውል ቋጠሩ፡፡
የቤተሰብን ፍቃድ ሳይጠይቁ
እሱ የሷ እሷም የሱ ሆነው ተፈቃቅዱ።የፍቅርን ግርዶሽ በጣጥሰውና ቀደው ጥለው በራሳቸው ስልጣን ለትዳር ተጫጩ።

በዚያች ቅፅበት ጃኖ በወጣትነት ስሜት ግሎ ሴትነቷን ፍለጋ ጣቶቹን አሰማራ። ሌቱና ግን ጣቶቹን ከድንበር አካባቢ እንዲርቁ አደረገቻቸው።
ጃኖ እሱ ያላዘዛቸው ጣቶቹ በራሳቸው ፈቃድ ሄደው በፈፀሙት
ድርጊት ተሸማቀቀና እጁን ሰበሰበ፡፡ የሱ ለሆነው ምንግዜም ለማያጣው ነገር መቸኮል እንደሌለበት በከንፈር ማህተም አረጋገጠችለትና በዚሁ ተለያዩ። ሁለቱም ልብ ለልብ ከተዋወቁ በኋላ የሚቀራቸው ወላጆቻቸውን ማስጠየቅ ነበር፡፡ ጃኖ በአገሩ ባህል መሰረት ሽማግሌዎች ላከ፡፡
ኒካ” ወይንም ሰማንያ ከመታሰሩ በፊት ግን ጃኖ ለገበራ (ለጥሎሽ) ያዘጋጀው ከብትና የገንዘብ መጠን መታወቅ አለበት ተባለ፡፡ ደህና አድርጎ ካልገበረ፣ ሙክት እየሳበ ካላስገባ፣ ምርጥ ቡልኮ እያለበስ አኩሪ አማችነቱን ካላስመሰከረ፣ የሚያስይዘው በቂ ገንዘብና በቂ ንብረት መኖሩን በተግባር ካላረጋገጠ ደረቅ ፍቅር በማስያዝ ብቻ ሌቱናን ሊያገኛት እንደማይችል ተነገረ። ጃኖ ጎበዝ ገበሬ ነው። አምስት በሬዎች፣ ሁለት ላሞች፣ አንድ ጊደር፣አንድ ጥጃ፣ አስር ፍየሎች፣ሁለት በጎች አሉት።ጥሩ አድርጎ ስለሚቀልባቸው ለዐይን የሚያስደስቱ ገላቸው የሚያብለጨልጭ ቅልቦች ነበሩ።
ሌቱና ለጋብቻ መለመኗ አልተገለፀላትም፡፡ የመስማት መብትም የላትም፡፡ መብቱ የአባትና የእናት ብቻ ነው። በተለይ ደግሞ የአባት። ሌቱና ግን መለመኗን በስውር ታውቀዋለች። ጃኖ ሌቱናን ማግኘት ከፈለገ በባህሉ መሰረት ደህና አድርጎ ለወላጆቿ መገበር እንዳለበት
የታወቀ ነውና ጥሩ ገባሪ አገኘን ብለው አሳልፈው እንዳይሰጧት ያደረባትን ፍርሃት ሳትደብቅ ገለፀችለት፡፡
“ “ጃኖ የወላጆቼን ነገር የምታውቀው ነው፡፡ ስለኔና ስላንተ ፍቅር ሲሉ ጥቅማቸውን አሳልፈው የሚሰጡ አይደሉም፡፡ የተሻለ ካገኙ ለሌላ እንደ ሚሸጡኝ አትጠራጠር፡፡ ይህን እንዳያስቡ በተቻለህ መጠን አስደስታቸው
”ስትል መከረችው፡፡ ጃኖም ጥርሶቹን ንክስ አድርጎ ሁለቱን በሬዎቹን፣ አንዲት ጊደሩንና አምስት ፍየሎቹን በገበራ መልክ ሊያቀርብ አንደኛውን በሬውን ደግሞ ሽጠና ለእናትና ለአባቷ ዑልኮ ገዝቶ በማልበስ ጥሩ አማ
ችነቱን አረጋገጠ፡፡ በሱ ቤት ጣጣውን ሁሉ ጨረሰ፡፡ የልጅቷ ወላጆች ግን እጀማመሩን አደነቁለት፡፡ በጃኖ ቤት ግማሽ ንብረቱን ያጣው የመጀመሪያና የመጨረሻ የሆነውን ገበራውን ለማጠናቀቅ ነበር፡፡ ያውም የሌይቱና ነገር የሌይቱና ፍቅር ሆኖበት እንጂ ከእጁ የሚወጡ ከብቶች አልነበሩም፡፡ አንጀት አንጀቱን እየበሉት አሳልፎ ሰጣቸው፡፡

የሌቱና አባት አቶ ገመቹ ጉቶሌ ከጃኖ ገበራውን ሲቀበል ፈገግ፣ ፈገግ ደስ፣ ደስ እያለው ነበር፡፡ጃኖ ግን እንደጠበቀው ሳያንበሸብሸው ቀረ።ይባስ ብሎ በገበራው መሰረት ኒካ ይታሰርልኝ የሰርጉ ቀን ይቆረጥልኝ ሚስቴ መሆኗ ይረጋገጥልኝ እያለ ሌይቱና ከእጮኛነት ወደሚስትነት እን
ድትሸጋገርለት ደጅ ጥናቱንና ውትወታውን አጥብቆ ተያያዘው፡፡ በዚሁ መካከል ለአቶ ገመቹ አዲስ መልዕክት ደረሰው፡፡ ያልታሰበ ሲሳይ።
ተዝቆ የማያልቅ የሀብት ምንጭ የሆነው ባላባት ቱሬ ልጁን ለጋብቻ የፈለጋት መሆኑን የሚገልጽ መልዕክተኛ ላከበት። የአቶ ገመቹ ልብ በደስታ ሳቀች። መልዕክተኛው ይታዘበኛል ብሎ እንጂ እንደ ህፃን ልጅ ሊቦርቅ
ከጅሎት ነበር፡፡ የገንዘቡ ነገር አጓጓው፡፡ በዐይን ህሊናው የተከመረ ብር በብዛት ቆጠረ…የቁም ከብቶች በብዛትና በዓይነት ተደርድረው በፊቱ ላይ ተሯሯጡበት ያውም ለባላባት፣ ያውም ለታወቀ ባላባት ቱሬ አማችነት መታጨቱ እጅግ አስደሰተው፡፡ አኮራው፡፡ ደስታው ልቡን ቢያጠፋውም
የንብረቱ ብዛት ቢያስገበግበውም ሰው ነውና ትንሽ ማሰቡ፣ ትንሽ ግራ መጋባቱ አልቀረም፡፡

ገበራ የተበላባት ልጅ ናት፡፡ ጃኖ በግብርና ሞያውና በመልካም ስነ
ምግባሩ ዝናው የተሰማ ተወዳጅ ወጣት ነው፡፡ ይሄ ነገር በህዝቡ ዘንድ ቢሰማ ምን ያመጣ ይሆን? ጃኖ ምን ይለኝ ይሆን? ገበራውን ተቀብዬ ፈቃደኛነቴን ከገለፅኩለት በኋላ የተሻለ ገንዘብ በመፈለግ “የለም ላንተ አልድርልህም” ብዬ ስክደው ችግር መፍጠሩ ይቀራል? ሲል አሰበ። ልቡ
ፈራ። በመጨረሻ ሀሳቡ ላይ ግን ልቡ ደነደነ፡፡

“ልጅቷ ታጭታለች፡፡ ያጫት ደሃ ገበሬ በመሆኑ በሠርጉ ቀን ችግር እንዳይፈጠር እንጂ በእኛ በኩል አማችነቱን በደስታ ተቀብለነዋል፡፡ ወደነዋል” በማለት ስምምነቱን ከገለፀ በኋላ ችግሩን ለማቃለል ደግሞ ጠለፋን በመፍትሄነት አስቀምጦ ለባላባቱ መልዕክት ላከበት። “ለጃኖ የወረወረልንን ሙትቻ በሬዎችና ብጫቂ ብልኮ መልስን ፊቱ ላይ መወርወር ነው።
ምን ያመጣል?ቢፈልግ እጥፍ ድርብ አድርገን እንመልስለታለን፡፡ ንብረቱን መልሶ ካገኘ ምን አባቱ ይፈልጋል? በእጥፍ ከተከፈለው ሊደስት እንጂ ሊከፋው አይችልም! ስለዚህ?” የጃኖን ነገር ችላ አለው።
“አይ ሴት ልጅ መውለድ? አሁንስ ልቤ ፈራ። የሚመጣውን መዘዝ ማስተዋል ተስኖን ገንዘብ ብቻ ስናሳድድ ጉድ እንዳንሆን ገመቹ!፡፡ በበኩሌ አንተ እንደምትለው ገንዘቡ ከተመለሰለት አሜን ብሎ በደስታ ይቀበላል ለማለት አልደፍርም፡፡ ይሄ ነገር ሄዶ ሄዶ ወይ በልጃችን ላይ ወይ በራሳችን ህይወት ላይ አደጋ እንደሚያስከትል አትጠራጠር!” አሉ የሌይቱና እናት ወይዘሮ ሀዊ፡፡

“ምን አባቱ እንዳይሆን?! የገበራውን ነገር በደንብ አድርጎ እንዲያስብበት ለላካቸው ሽማግሌዎች አጥብቄ አስረድቻለሁ! አቅሙ የማይፈቅድ
ከሆነ እንዳይሞክረው በጠዋቱ ነው ያስጠነቀቅኩት። ሁለት የሞቱ በሬወችና አንዲት ቁራጭ ቡልኮ ወርውሮ ሚስት ሊገኝ?ወይ ጥጋብ?! በይ ይሄን ጉዳይ ለኔ ተይው!! ይሄ አንቺ የምትይውን ሁሉ አስቀድሜ ያሰብኩበት ነው፡፡ ማንኛውንም ነገር እንደአመጣጡ እኔ ራሴ እጋፈጠዋለሁ!!
የሰጠው ገንዘብ በእጥፍ ድርብ ይመለስለታል እንጂ ከብርድ የማታስጥል ጋቢ ቡልኮ ተብላ፣ ሞፈር የማይጎትቱ ጥጆች በሬ ተብለው በገበራ ስም ሊጠሩ አይችሉም!! ወቸ ጉድ!! ገበራ ተሰጥቶ ተሙቷልና ዐይኔ
እያየ ይሄ ሁሉ የባላባት ቱሬ ሃብትና አማችነት ሊያመልጠኝ አይገባም!!በፍፁም ሊሆን አይችልም !!” ከንፈሩን በንዴት ነከሰ፡፡
👍1
ልጃቸው ከጃኖ ጋር ውስጥ ውስጡን እንደምትገናኝ ያወቁ እናት ሥጋታቸውን ለባላቸው ቢገልፁም ባላባት ቱሬ የሚሰጠው የገበራ ንብረት በሀሳባቸው እየተመላለሰ ማቃዠት ጀማምራቸው ነበር፡፡ በጥባጭ ካለ ንፁህ ውሃ አይጠጣም ሆነና ጃኖ ያንን የመሰለ የማታ ሲሳይ እንዳይቋደሱት በመሀል ገብቶ ስለበጠበጣቸው“ አይ ሴት ልጅ መውለድ”ብለው ተማረሩ።
የጎመዥለትን ነገር ለማግኘት እየተመኙ እንዳያገኙት ደግሞ መዘዙን እያሰቡ በቁጭት ተንገበገቡ።

የሌቱና አባት ለባላባት ቱሬ ልጁን ለመዳር ባደረገው ስምምነት መሰረት የገበራው ዝርዝር መጠኑና ዓይነቱ ተገልፆ እንዲላክለት መልዕክተኛ
በድጋሚ ላከ፡፡

መልዕክተኛው መልሱን ይዞ የመጣ እለት ሌቱና ለአንድ ደሃ ገበሬ በመታጨቷ ምክንያት አቶ ገመቹ ያደረባቸው ፍርሃት ያሳዘነው መሆኑን፣ እንኳንስ ለአንድ ምናምንቴ ድሃ ገበሬ ይቅርና እኔ ነኝ ላለ ለታወቀ ሀብታም ታጭታ ቢሆን እንኳ ሙሉ ኃላፊነት የሚወስድ መሆኑን በኩራት ገልፆ አቶ ገመቹን ላለማስቀየም ግን ጠለፋው በለሊት እንዲከናወን በቀረበው
ሀሳብ መስማማቱን ጭምር መልዕክተኛው አስረዳ፡፡ መልዕክተኛው የባላባት ቱሬን ሀሳብና የገበራውን ዝርዝር ይዞ ነበር የመጣው። የንብረቱን
ዝርዝር ሲያይ አቶ ገመቹ በደስታ ሰክሮ የሚሆነውን አሳጣው። አንዳንዱን መጠጥ ያሰክረዋል አንዳንዱን ደግሞ የሀብት ፍቅር ያሰክረዋል።
አቶ ገመቹ ሳያስበው የወረደለት የሀብት መና ገና በእጁ ሳይገባ አረቄ እንደጠጣ ሰው አናቱ ላይ ወጣበትና አሰከረው። የቀረበለት ገፀ በረከት ፍፁም ከገመተውና ከጠበቀው በላይ ሆነበት፡፡ ባላባት ቱሬ ያንን ያደረገው ሆን ብሎ በገበራ ብዛት የገመቹን ልብ ለመስረቅ አስቦ ነበር፡፡ የልጅቷን ውበትና ለግላጋነት ስላወቀ እንዳታመልጠውና አባቷ የተሻለ ገበራካገኘ አሳልፎ እንዳይስጥበት ስለፈራ ነው ሞቅ ያለ ገበራ ለመስጠት የተስማማው። ስልሳ የቀንድ ከብቶች፣ ሁለት ሰንጋ ፈረሶች፣ አንድ ሰጋር በቅሎ፣ ሃያ አምስት በጎችና ፍየሎች፣ በጥሬ ገንዘብ አምስት ሺህ ብር...
እግዚኦ! አቶ ገመቹ ዐይኑን አላምን አለ፡፡ ጆሮውን ተጠራጠረው:

የጃኖና የባላባትቱሬ የገበራ ልዩነት?! በዚሁ መሰረት ንብረቱን
ቶሎ በእጁ ማድረግ ፈለገ፡፡ የሠርጉ ቀን እንዲቃረብ እንዲፋጠን ተጣደፈ።ማን ያውቃል? በዚህ አጋጣሚ ብትኮበልልስ? ጃኖ ይህንን ሚስጥር ደርሶበትይዟት ቢጠፋስ? አንዳንድ ጊዜ ስለህይወቷም ይጠራጠርና ሞቷ እንኳ እዚያ ባላባቱ ዘንድ ከደረሰች ንብረቱን በእጁ ካስገባ በኋላ እንዲሆን እስከመመኘት ደረሰ፡፡ ባስቸኳይ የዚያ ሁሉ ንብረት ጌታ ለመሆን ቋመጠና ጉዳዩ በከፍተኛ ሚስጢር እንዲያዝ አደረገ፡፡ ጃኖም ሆነ ዘመዶቹ ምንም
አይነት ፍንጭ እንዳያገኙና ሌቱና በፍፁም እንዳታውቅ ሚስጥሩ በከፍተኛ ደረጃ እንዲጠበቅ ካደረገ በኋላ በተለመነች አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ጋብቻው እንዲፈፀም አደረገ፡፡

መቼም ሌቱና በሌሊት ታፍና ስትወሰድ የነበረባትን የሰቆቃ ስሜት፣ የተሰማትን ድንጋጤና ብርክ በቃላት እንዲህ ነበር ብሎ መግለፅ ያስቸግራል። የሰራ አካላቷ በድን እስከሚሆን ድረስ በጭንቀትና በፍርሃት ተዋጠች፡፡

የደረሰባት መዓት በፍፁም ልትቋቋመው የምትችለው አልነበረም፡፡ እንደ ፈራቸውና ጓደኞቿ ሲጠለፉ እንደሰማችው ወላጆቿ ውስጥ ለውስጥ ተነጋግረው አንድም ቀን ስሙን ሰምታና ዐይኑን አይታ ለማታውቀው ሰው አሳልፈው እንደሰጧት፣ በገንዘብ እንደሽጧት ተገነዘበች።
ጃኖ…ጃኖ…ጃኖ የልጅነት ጓደኛዋ ጃኖ የወጣትነት አፍላ የፍቅር
ሙቀት ያሞቃት ጃኖ...ሚስኪኑ ጃኖ ይህን ጉድ ሲሰማ የሚሆነው
ታያት፡፡ በዚያች በበቆሎ ማሳ ውስጥ ያሳለፉት ሁኔታ መጣባት። ለሷ ሲል ያፈራው ንብረቱን ሙልጭ አድርጎ መሸጡ “ሌቱ!” እያለ በፍቅር የሚያቆላምጣት የምትወደው ጃኖ ሜዳ ላይ መቅረቱ አንገበገባት። ከራሷ
መከራና ጭንቀት የበለጠ የሱ ጭንቀት የሱ ስቃይ ተሰማት። ወዴት እንደምትወሰድ ለማታውቀው ለራሷ ሳይሆን፣ማንን እንደምታገባ ላላ
ወቀችው ለራሷ ሳይሆን፣ ፀባዩን፣ መልኩን፣ ዕድሜውን ወደማታው
ቀው ሰው እንደ ከብት እየተነዳች ለምትሄደው ለራሷ ሳይሆን ስለ
ምስኪኑ ጃኖ እያስላሰለች ልቧ በሀዘን ቆስለ፡፡ ይህንን ጉድ ሲስማ የሚሆነው ሁኔታ የሚደርስበት ጭንቀትና ስቃይ ታያት የዚያን እለት በበቆሎ ማሳ ውስጥ ትኩስ ስሜቱን ሊገልፅላት በሞከረበት፣ አብሯት ባደገው የልጅነት ፍቅሩ ውስጥ ሴትነቷን ፍለጋ በተጓዘበት ቅፅበት እጁን ወደታች ውርውር አድርጋ የተቆጣችው ታወሳት፡፡ ምን አጣደፈህ?! ብላ የገለፀችው ሁሉ በምሬት ፊቷ ላይ ድቅን አለባት፡፡ አሁን ግን ያንን ጃኖ
እንዳይቸኩል እንዳይጣደፍ የተከለከለውን ምንጊዜም የሱ መሆኑ የተረጋገጠለትን የሴትነት ክብሯን፣ የጨዋነት ምልክቷን ስሙን ሰምታ መልኩን አይታ ለማታውቀው ሰው ልታስረክበው መሆኑ አበሳጫት፡፡ አቃጠላት፡፡ አንገበገባት።....

ይቀጥላል
🥰1
#የወዲያነሽ


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...ሰኞና ማክሰኛ ተከታታዮቹም ቀናት በየተራ አልፈው ቅዳሜ ደረሰ፡፡ሁላችንም በሐሳባችን እንደ ጸናን ሰነበትን

ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ዘጠኝ ተኩል ገደማ ላይ ደርሶ ብርድ ብርድ ስላለኝ ፀሐይ ለመሞቅ ምድረ ግቢው መኻል ተቀመጥኩ በየወዲያነሽ አእምሮ ውስጥ
ያለው ጥያቄ ሳይመለስ በመሰንበቱ ሥጋቷ አልተወገደም፡፡ በአንዲት ትንሽ ነጭ ፎጣ ብርጭቆ እየወለወለች ዝግ ብላ መጣችና “አሁን ነው እንዴ የምንሄደው? እ...!» ብላ ንግግሯን በጥያቄ አንጠለጠለችው::

«አንቺና ጋሻዬነህ የምትሄዱት ሌላ ጊዜ ነው:: ቀኑን እኔና አንቺ
እንወስነዋለን፡፡ ዛሬም ሆነ ነገ የምሄደው እኔ ነኝ። ከነዚያ ከተከለከሉ መጻሕፍት አንብባ የነገረችሽን የእስረኛዋን ጓደኛሽን የምክር ቃላት አትርሺ፡ መብት
የሚገኘው በትግል ነው፡፡ ጨቋኞች በሰላምና በውዴታ መብት እይሰጡም ብላ
ነግራኛለች አላልሽም? እኔና አንቺም» ብዬ ዝም አልኳት። ከጀመርኩት አርእስት ውጪ «አዎ እውነትህን ነው: ከመንገድ ሲገቡ ያላሰቡትን ያልሰሙትን ነገር ተናግሮ ክፉም ደግም መስማትና መናገር ለእርሳቸውም ሆነ
ለእኛ ነገር ማበላሸት ነው» ብላ የብርጭቆይቱን ጥራት ለማረጋገጥ ትክ ብላ ተመለከተቻት ንግግሯን ሰምቼ ዝም ስላልኩ ወደ ቤት ገባች፡፡

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አባቴን እንኳን ደኅና” መጣህ ለማለት ወደ ወላጆቼ ቤት ገሠገሥኩ፡፡

ባለፈው ጊዜ ወላጆቼን ለመጠየቅ ስሔድ ይጨመድደኝ የነበረው
ሥጋትና ፍርሃት እንዲሁም የሕሊና ረብሻ እጅግ በጣም ተቀነሰ። እረጋገጤ ደልዳላ ከመሆኑም በላይ ቀና ብዬ ተራመድኩ፡፡ ዱሮ ደረጃውን የምወጣው አንድ
በአንድ ሲሆን ዛሬ ግን ሁለትና ሦስቱን በአንድ ጊዜ አጠቃለልኩት። ደረጃውን
ጨርሼ ፊቴን ወደ በሩ መለስ ሳደርግ የብዙ ሰዎች ድምፅ ሰማሁ፡፡ ወደ ውስጥ ለመዝለቅ የነበረኝ ድፍረት ከፍ አለ። እቤቱ ውስጥ ለነበሩት ሁሉ ጎንበስ ብዬ
እጅ ነሣሁ፡፡ ከዚያም በቀጥታ ወደ አባቴ ሄድኩና እጅ ነሥቼ ጨበጥኩት።
«እንኳን ደኅና ገባህ! የሄድክበት ሁሉ ቀናህ! » አልኩና አንገቴን በትሕትና ሰበር አድርጌ ከፊቱ ገለል ብዬ ቆምኩ፡፡
እንኳን ደኅና ቆያችሁኝ አዎ ደኅና ደርሼ መጣ። ሁሉም ደህና
ቆየኝ። ክብሩ ይስፋ!ና! እዚች አጠገቤ ና አጠገቡ የነበረውን ወንበር በጣቱ አሳየኝ። እንኳን በደህና ገቡ ለማለት ያመጡትንና ሌሎችንም እንግዶች አንድ
በአንድ አየኋቸው፡፡ በሰዎች ላይ የሚታየው ፈገግታና የአቀማመጣቸው ሁናቴ
የተለያየ በመሆኑ አባቴን በተለያየ የአስተሳሰብ ደረጃ እንደሚመለከቱት ያስታውቃል። አንዳንዱ ውስጣዊ ጭንቀት አስገድዶት በግድ ፈገግ ብሏል።
ለማስደሰትና በግድ ለመደሰት ብሉ በደረቅ ፈገግታ ፊቱን ያጨማደደም አለ።የአንዳንዶቹን ፊት ደግሞ የበታችነት ስሜት ስለተጫነው ፊታቸው ከልቅሶ በኋላ የሚታይ ፊት እንጂ ለደስታ የቀረበ ገጽታ አይመስልም፡፡

ሁለትና ሦስቱን እንደ አባቴ የቅርብ ጓደኞች ስለምመለከታቸው በእነርሱ ላይ የነበረኝን ጥላቻ ለመርሳትም ሆነ ለማሻሻል ያለኝ አቅም በጣም አነስተኛ ነበር። ሕሊናዬ ዘወትር ይበቀላቸዋል፡፡ ወረቀት እያገላበጡ የሚዶልቱት ሁሉ ትውስ ሲለኝ፡ የሰውን ሕልውና አርደውና አወራርደው የሚገድሉ ይመስሉኛል።
ክርክርና ወሬ ሲጀምሩ ማንም በአጠገባቸው እንዲያልፍ ስለማይፈልጉ ዓለምን
የተንኮል ገበያ እንጂ የመልካም ምግባር አደባባይ እንድትሆን የሚያስቡ አይመስሉም፡፡ እናቴ እንኳን ደበቅ እያለች «መጡ ደግሞ እነ ጋጠው ገሽልጠው»
ትላቸው ነበር፡፡

ለእኔም እንደ እንግዶቹ ጠላ ደረሰኝ፡፡ ከዚህም ከዚያም የሚመጣውን ወሬ እየሰማሁ ጠላዬን ሁለት፣ ሦስት ጊዜ አስሞላሁ፡፡ እንግዶቹ አንድና ሁለት እየሆኑ ተራ በተራ እጅ እያነሡ ሄዱ።

እናቴና የውብነሽ ከአሁን አሁን ተናግሮ ጉድ ይፈላ ይሆን በማለት
በአስጨናቂ ሐሳብ እንደሚሠቃዩ ስጋታቸው በየፊታቸው ላይ ይታወቃል፡፡ ከእኔ ጋር ማዶ ለማዶ መፋጠጡን ስለ ጠሉት ሁለቱም ወደ ማድ ቤት ወረዱ፡፡

እኔና አባቴ በጣም በመጠነኛ መግባባት ስለ ጭሰኛ' ስለ ግብር' ስለ ሲሶና እርቦ ስለ ገሚስና ከአሥር አንድ፣ እንዲሁም ስለ ሕግና ስለ እኔ የልጅነት ዓመታት እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት እንደነገሩ አወራን። ከዚያ በኋላ
ግን፡ እነዚያ ለሁለት ሳምንት የተለዩት የወንጀለኛ መቅጫና የፍትሐ ብሔር ሕግ መጻሕፍት ትዝ ስላሉት «ትንሽ ሥራ አለብኝ፡ ከእናትህና ከአጎትህ ጋር ተጫወት» ብሎኝ ወደ መኝታ ቤት ገባ።

ከአባቴ ጋር ተዝናንቼ ሳወራና ስጫወት በመልሶቼም እየተማመንኩ ስመልስ የመጀመሪያ ጊዜ ነበር፡፡ አባቴ ገባ ከማለቱ እኅቴና እናቴ ተካ አሉ።
የፌሩት ጉዳይ ባለመነገሩ የሁለቱም ፊት ፈገግታ አጋተ። ሩብ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አባቴ እንደገና ተመልሶ መጣ። ኖር ብለን ተቀበልነው። እምብዛም
ሳይጠጋ ቆም አለና እነዚያን በዕድሜና በክርክር ጽሑፍ ንባብ የተዳከሙ ዐይኖቹን በግራ እጅ ጣቶች እያሻሸ ሳልነግርህ እንዳትሄድ ብዬ ነው የተመለስኩት ዘንድሮስ በጣም ጎብዘሃል አሉ፡፡ መቼ እንደሆነ አላውቅም፡ አንድ ወዳጂ ሰዉ ጋር መንገድ ላይ አየሁት ብሉ ነገረኝ። አዎ ምንም ይሁን ምን እያደር ልብ
ሲገዙ ነው የሚታወቀው» አለና የቤቱን ግድግዳ ባይኑ ዞረው፡፡ የእናቴን የየውብነሽ ልብ በፍርሃት ተበዝብዞ ፊታቸው ድንጋጢ በሚያሯሩጠው ደም ጢም
ኣለ።

ከተቀመጥኩበት ተነሥቼ «ምን ነገሩሁ? ምን አሉህ?» አልኩና የሰማውን ለመስማት ጓጓሁ። «እሱስ ይሁን፡ እንዲያው እስከ ዛሬ ለምን ደብቀሽኝ ብዬ ነው:: ነገ እነግርሃለሁ፡፡ አበጀህ! ጠላትም ወዳጅም ደስ አይበለው ብሎ ለመመለስ ሲጀምር «አሁኑኑ ብትነግረኝስ?» አልኩት፡፡

«ነገም እኮ ሩቅ አይደለም። ነገ ይሻላል» ብሎ ሊገባ ሲል «እኔም ብዙ ነገር እነግርሃለሁ» አልኩና እኔም ነገሩን ችላ አልኩት፡፡ እናቴ በፍርሃትና በጥርጣሬ እየዋለለች «ምን ሰምቶ ይሆን? ምን ነግረውት ይሆን ጌታዬ?» አለች
ከንፈሯ ሥር በሚንደፋደፉ ቃላት።

«ነገ በአንድ ላይ እንሰማዋለን» ብዬ ሊንቀሳቀስ የነበረውን ነገር እንዳጠፋ ልጅ ኮረኮምኩት፡፡ ነገሩ ሁለት ቤት ያለው ሆነና ራቴን በልቼ ወደ ቤቴ ተመለስኩ።

የዕለቱን ወሬ ለመስማት በከፍተኛ ጉጉት የምትጠባበቀዋ የወዲያነሽ፣ ከልጅዋ ጋር ስታወራ ደረስኩ እና ከጎኗ ተቀመጥኩ፡፡ ከእኛ ራቅ ብሎ በብረት
ምድጃ ውስጥ የተንተረከከው የከሰል ፍም የቢቱን አየር አሙቆታል። በወላጆቼ ቤት ስላጋጠመኝ ነገር አንድ በአንድ ጠየቀችኝ፡፡ የየወዲያነሽ ነገር ስለሆነብኝ ደከመኝና ታከተኝ ሳልል መለስኩላት፡፡ «እኛንስ መቼ ነው የምትወስደንና እጅ
ነሥተን፤ ጫማ ስመን፤ የሚሉንን የሚሉን?» አለችና የመንፈስ ጭንቀት ስለ ተሰማት አቀረቀረች። «በክብርና በይፋ ነው ይዤሽ የምቀርበው! ይህቺ የማከብራትና የምወዳት ባለቤቴ ናት ብዬ የምናገረውና የማስረዳው እኔ ነኝ፡፡በመለማመጥና በማጎብደድ ሳይሆን አባቴ በመሆኑና ለወላጅነቱ ክብር ብቻ ብዩ ያውም ክብረ ሕሊናሽን በማይነካ ሁኔታ እጅ ትነሺ ይሆናል» ብዬ አገጫን ይዤ አበረታታኋት።

«አንተ እንዳልከ! እኔ እንዲሁ ነው የምቀባጥረው» ብላ፤ ረጋ ባለ
እረማመድ ወደ ጓዳ ገባች፡፡ በውስጧ ፍርሃት እንደልቡ ይጨፍራል፡፡ከሠራተኛይቱ ጋር ራት አቀረቡ፡፡ መብላቴን ሳልናገር ደስ ይላት ዘንድ ዝግ ብዬ በላሁ። ጋሻዬነህ እንኳ ወግ ደርሶት «በእማምዬ ሞት፡ በእኔ ሞት» እያለ ደጋግሞ አጎረሰኝ፡፡ ዕለታዊ ድርጊት የአካባቢ ቅጂ ነው፡፡
👍3
በማግሥቱ እሑድ ከእንቅልፌ ስነቃ ረፍዶ ነበር፡፡ በዕድሜዩ ላይ
እየተደመሩ የሚከንፉትን ደቂቃዎች አልጋዬ ላይ ተክልዩ አሳለፍኳቸው። ለቁርስ አይሉት ለምሳ ተቀመጥኩ። የወዲያነሽ ይኸን ሰሞን ድካም ድካም
ይለኛል” ካለች ጥቂት ሳምንታት አልፈዋል። ከቀሚሶቿ መኻል አንዳንዶቹ ከወደፊቷ ሰቀል ማለት ይዘዋል። እጄን ታጥቤ ቆም እንዳልኩ አጠገብ ያለውን
መንበር ደገፍ ብላ ቆመች። «ምነው ደካክመሽ? ይቺ ከረጢትሽ ከበደችሽ
መሰለኝ?» ብዬ ከግንባሯ ላይ እንደ አልቦ ከባ ወደ ላይ የተሽጎጠችውን የጸጉሯን
ዘለላ በግራ እጄ መዘዝኳት። በጣቶቼ አሽቼ ስለቃት እንደለጋ ሐረግ ጫፍ ተጠምላ ተንጠለጠለች።

«አዎ ድካም ድካም ይለኛል። አላስታወቀም እንዴ ብላ አፈር አለች። «ልብ ብሎ ላየሽ በቀላሉ ያስታውቃል» ብዬ እርግዝናዋ በሌሉችም ሊታወቅ እንደሚችል አረጋገጥኩላት። አሁን ግን እንደ ዱሮዋ፡ ይኸ ያምረኛል፡ ይኸ
ያስፈልገኛል ብላ አትጠይቀኝም፡፡ «ምን ይመስልሻል? ማሚቱ ናት ማሞን» ብዬ ሆዷን ትኩር ብዬ አየሁት፡፡ «የዕለቱ ዕለት እናየዋለን፡ ለእኔ ግን ሚቱዩ ትሁንልኝ» ብላ እየሳቀች የተንጠለጠለችውን ጸጉሯን ወደ ዋናው ነዶ መለለቻት።

ልክ ዘጠኝ ሰዓት ወደ ወላጆቼ ቤት ሄድኩ። እኔ አሰፍስፈ የምጠባበቀው በእኔና በየወዲያነሽ የጋራ ውሳኔ በአንድ ላይ ወደ ወላጆቼ ቤት የምሄድበትን
እሑድ እንጂ የአሁኗን እሑድ ባለመሆኑ፡ ውስጣዊ እንቅስቃሴዩ ሁሉ የበጋ ወንዝ ሆኗል፡፡ ደረጃዎቹን አልፌ ወደ ቤት ስገባ አባቴ፡ እናቴና እኅቴ ስለምን
እንደሚያወሩ ባላውቅም ሁሉም ፈገግ ብለው ነበር።

ሰላምታ አቅርቤ እንደተቀመጥኩ የወሬአቸው ተካፋይ ለመሆን
እስከምችል ድረስ ዝም አልኩ፡፡ ግን ጨዋታቸው ወዲያው ቀዘቀዘ፡፡

አባቴ፡ «እስከ አሁን የት ዋልክ፡ እንዲህ ስትጠፋ ያልሞላለት ባለትዳር ትመስላለህ» አለና ትክ ብሎ እየኝ።

«አሁን ይሻላል ብዬ ነው! ባሁኑ ሰዓት የመጣሁት» ከማለቴ «ጨዋታና ወሬ ቀረብሀ እንጂ፡ ለእኔማ ምን ስታደርግልኝ ነው፡፡ ይቺን ወራት ደግሞ አምሮብሃል፡፡ እየፈተፈተች የምታጎርስ አገኘ መሰል» አለና የንቀት ዓይነት ፈዝ
ሣቀ፡፡

«አምሮብኛል እንዴ? ብዙ ሰዎች አምሮብሃል ሲሉኝ እሰማለሁ፡፡ ኻያ ስምንተኛ ዓመቴን ጀምሬያለሁ፡፡ ጠጋ ጠጋ ካሉ የምትፈተፍትና በሞቴ እያለች የምታጎርስ
መች ትጠፋለች» ብዬ ቀልዱን በቀልድ መለስኩ፡፡

«ደርሶ ወንድ መምሰል! የት ታውቅበትና? አሁን እንዳንተ ያለው ነው አጥር ዘሎ እና ጨለማ ጥሶ ከሴት እጅ ጎርሶ የሚመለሰው? ሰነፍ!» ብሎ እንደ ቀልድ ወረፈኝ።

“አረ ቆይ ዋል አደር ብለህ ትሰማለህ! የእኔ ጀግንነት ካንተ ጀግንነት ይበልጣል። እንዲህ በቀላሉ፤ በሽሮ እና በዶሮ አልመለስም! እኔ የዘለልኩት
አጥርና እኔ የጣስኩት የመከራ ዉለማ አንተ ከምታውቀው ሁሉ ይብሳል። አረ የምን አጥር መዝለል አጥር የምታዘልልና ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ ውስጥ
የምታስሮጥ ዘንካታ አለችኝ አልኩና እናቴና የውብነሽን አየኋቸው። ክፉኛ ደንግጠዋል።

💫ይቀጥላል💫
አትሮኖስ pinned «#የተወጋ_ልብ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና በሌቱና ወላጆች ቤት ላይ የሥጋት አሞራ ረጃጅም ክንፎቹን ዘርግቶ በቅርብ ርቀት በማንዣበብ ላይ ይገኛል፡፡ መጀመሪያ ጃኖ ከዛሬ ነገ ምን ያመጣብን ይሆን? ምን ያደርገን ይሆን? በሚል ጭንቀት ተውጠው ከከረሙ በኋላ በተፈጠረው ትንቅንቅ ጉዳት የደረሰበት ባላባት ቱሬ ደግሞ ምን ፍጠሩ? ምን ውለዱ ይለን ይሆን? ምንስ ያስደርገን ይሆን?…»
ብርቅርቅርታ ከሚለው የልብወለድ መፅሐፍ የተወሰደ
ደራሲ-ዳኔል ስቲል

#ሕይወት!!
ስልምልመታ...ዝርፍልፍታ...ጭልምልምታ
ፍልቅልቅታ...ውልብልብልታ...ብርቅርቅታ

እውነትም ሕይወት...
እንደማለዳ ፀሀይ...ብርሃን ስትፈነጥቅ
እንደ ባህር አልማዝ...ስትፍለቀለቅ
እንደ እሳት ላንቃ...አብረቅርቃ
ከቀትር ፀሀይ...በርታ ደምቃ
ስትጀምር ማለት...ድንግዝግዝ
መባባት አይቀር...መተከዝ

#ሕይወት...
ፀፀት ትዝታን...ደርድራ
ምኞትን ከህልም...አዋቅራ
በብቸኝነት...ስታማቅቅ
ቀን ከሌት አትልም...ስታሰጨንቅ

ግን ሕይወት...
ብርቅርቅታ ናትና ታበራለች ቀን ጠብቃ
እንደጨለመች አትቀርም እንዳኮረፈች ተደብቃ
ውሎ ቢያድርም ታበራለች በሕብረ ቀለም አሸብርቃ ።
👍2
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሰላሳ


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....መልኩን አይታ ለማታውቀው ሰው ልታስረክበው መሆኑ አበሳጫት፡፡አቃጠላት፡፡ አንገበገባት።

“ምን ነበረበት ያን ጊዜ ባልተቆጣሁት ኖሮ? ብላ በፀፀት ተከነች፡፡ ይሄንን እያብሰለሰለች በንዴት ብትንጨረጨርና በእንባ ብትታጠብም ወላጆቿ በዕድሜ አቻዋ ከሚሆን ግፋ ቢል ደግሞ አባቷ ሊሆን ከሚችል ሰው
ጋር እንጂ አያቷን እንድታገባ የፈረዱባት መሆኑን በፍፁም አልገመተችም ነበር።

ከጭንቀት በላይ ጭንቀት ከሀዘን በላይ ሀዘን የተሰማትና ልቧ ደም
እንባ ያለቀሰው ግን ለመጨረሻ ጊዜ ሙሽራ ተብዬው ነጭ የሀገር ባህል ልብሱን ለብሶ ቅቤ በአናቱ ላይ ተመርጎበት በለምድና በዝናር በተለበጠ ሠንጋ ፈረስ ላይ ጉብ ተደርጎ ከፈረስ ላይ ወድቆ እንዳይሰበር ደግሞ በሰው ተደግፎ ይዟት ሊሄድ የመጣው የሰባ አምስት አመቱን አዛውንት ባላባት ቱሬን ስታየው ነው። በዚህ ግዜ ነው ከሙቀት አውጥተው
ወደ በረዶ ውስጥ የጣሏትን የለግላጋነት ዕድሜ ፀጋዋን ሳትጎነጭ የህይወትን ትርጉም ያውም የወጣትነትን ትኩስ ስሜትና ጣፋጭ ጣዕም
ሳታጣጥም እንድትኖር የፈረዱባት ወላጆቿን በምሬት የጠላቻቸው። ከእንግዲህ በኋላ በሰሳ አምስት ዓመት ዕድሜ ውስጥ የምትኖር አሮጊት እንጂ በአሥራ ስምንት ዓመት ለጋ የወጣትነት ዕድሜ ውስጥ መኖር የምትችል ኮረዳ አይደለችም፡፡ በአስተሳሰብም፣ በአነጋገርም፣ በፍቅርም እሷን ከማይመስል ሰው ጋር ነው የምትኖረው። ስለዚህ የባሏ ዕቃ የባሏ ስሜት ጠባቂ ባል ከተባለ የአዛውንት ቱሬ የጎበጠ ወገብ ማሞቂያ ምድጃ እንጂ ተፈጥሮ ያደለቻት የወጣትነት ዘመን ትኩስ ስሜቷን ማጣጣም የማትችል ፍላጎቷን የሚረዳላት አቻ የሌላት የተጣለች ፍጡር መሆኗ
በመሪር ሀዘን ተሰማት፡፡ ጃኖ... ጃኖ... የሚለው ፍቅረኛዋ ስሙ በሀሳቧ እንደ ገደል ማሚቱ ሲያስተጋባ ቢውል ምን ዋጋ አለው? ልቧ ወደሱ
ሲገሰግስ ቢከርም፣ አካሏ አካሉን ተለይቶ ርቆ መሄዱ የማይቀር ቁርጥ ነው፡፡ “እንቢ እሪ” ብትልስ ማን ሊለቃት?! ለዚሁ የተዘጋጁ ወጠምሾች ደቁሰው ያፍኗታል። እሷም ይሄንን በሆዷ ስለምታውቅ እሪታውን አልሞከረችውም::ጃኖ ይህንን በሰማ ጊዜ ህይወቱ ትጠፋለች እንጂ ከዚህ ከገባችበት አዘቅት፣ ከዚህ ከገባችበት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ መንጥቆ እንደሚያወጣት ግን ጥርጥር አልነበራትም፡፡

አቶ ገመቹ ልጁን ሸጠና በውላቸው መስረት የገበራ ንብረቱን በሙሉ
ተረከበ፡፡ የለሊት የገበያ ልውውጡን አጠናቀቀ፡፡ ባላባት ቱሬም ከቁብ ዶሮ በሚወጣ ድምፅ ዓይነት “ኢኪኪኪኪ...” እያለ በደስታ ሳቀ::ይቺን ወይን ልጦ ለመብላት፣ ይቺን የልጁ ልጅ የምትሆነውን እንቡጥ ለማፍረጥ ጎመጀ፡፡ ቤቱ እስከሚደርስ ድረስ ተቁነጠነጠ፡፡ በጠላፊዎቹ
አጀብ በበቅሎዎችና በፈረሶች እያካለቡ የገዛትን ልጅ ይዞ ወደ ቤቱ ጋለበ፡፡ ሚስኪኑ ጃኖ መርዶውን የሰማው ከዚህ ሁሉ ትርዒት በኋላ ነበር፡፡ “ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” ጠብ እርግፍ ቢል ቢወድቅ ቢነሳ ዋጋ አልነበረውም፡፡ ሌቱና እንደሆነች ወደሩቅ አገር ነጉዳለች። የሰጠኸው የገበራ
ገንዘብ ተብሎ አፍንጫው ላይ የተወረወረለት ለሱ ምንም ደንታ የሚሰጠው አልሆነም፡፡ ሺህ ጊዜ በእጥፍ ቢከፈለው ሊያረካው አይችልም፡፡
ሌቱና! ሌቱና! ሌቱና ቆንጅዬዋ! አቻው ሌቱናተጠልፋ መወሰዷን
በእዬዬ ውስጥ ጉዱን ሰማ፡፡ ዐይኑም ልቡም ደም እያለቀሰ ጆሮው ታሪክማ። ያልተጠበቀ ያልታሰበውን ዱብ ዕዳ... ሰማ፡፡ ጃኖ እስከዛሬ ድረስ በግብርና ሙያው ባለው ጀግንነት እንጂ የእርሻ መሳሪያዎቹን በመሳል
በመሞረድ እንጂ ለበቀል ሰው ለማጥቃት ልቡ ጭካኔን ሞርዶ አያውቅም ነበር፡፡ አሁን ግን በህይወቱ በኑሮው መጥተውበታል ልቡ የቁጭት ሞረዱን ሞረደ፡፡ ጉበቱ የቂም ሀሞት ረጨ...ለዚህ ሁሉ በደል የመጀመሪያው ተጠያቂ የሆነው የሌቱናን አባት ለመግደል ከዚያም ባላባት ቱሬን ገድሎ የሚወዳት የሚያፈቅራት እጮኛው ሌቱናን ከታሰረችበት የእስር ሰንስለት በማላቀቅ ይዟት ለመጥፋት ወሰነ። አቶ ገመቹ ግን ብልጥ
ሆነ፡፡ የሚከተለውን መዘዝ ስላወቀ ብልሀት ሲፈጥር ሰነበተ። ጃኖ ህይወቱን ከማጥፋት እንደማይመለስ ገምቶ ፈርቶ ነበረና በወላጅ በወዳጆቹ በኩል አማላጅ እየላከ ተማፀነው። ተለማመጠው፡፡ ባላባቱ ሥልጣኑን መከታ በማድረግ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ሌቱናን ነጥቆት የሄደ
መሆኑን ልጅቷ የታጨች መሆኑን እየተነገረው በለሊት ጠልፏት ከሄደ
በኋላ ለእርቅ ብሎ የሰጣቸው የገበራ ንብረቶች እንጂ በሱ ስምምነት የትፈፀመ ጋብቻ ያለመሆኑን አስረዳ፡፡ ለገበራ የተሰጠውም ንብረት ባላባቱ
ለራሱ ክብር ለራሉ ዝና ሲል ያደረገው እንጂ በሱ ፍላጎት ያለመሆኑን ወተወተ፡ ባላባትን የሚያክል ክብር ያለው ሰው ጠልፎ አይጠፋም፡፡ ከጠለፈም በከፍተኛ ገበራ ይክሳል፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ እገሌ ለገበራ የሰጠው
ከብት ብዛት እየተባለ ይነገርለታል በይበልጥ የሚሞገሰው ብዙ ገበራ የተቀበለው ሳይሆን ብዙ ገበራ መስጠት የቻለው ነው፡፡ ስለዚህ ባላባቱ ስሙን ለማስጠበቅ እንጂ እሱ ፈልጎ ያመጣው ሃብት አለመሆኑን እየተንቀጠቀጠ በሽማግሌዎች ፊት ተናዘዘ፡፡

አቶ ገመቹ ሌቱናን ለጃኖ መርቆ የሰጠው መሆኑንና በመሀሉ ይሄ
ድርጊት የተፈፀመው ከአቅሙ በላይ በሆነ አስገዳጅ ጠለፋ ምክንያት እንደሆነ አስተባብሎ አሳመነና ህይወቱን በዘዴ አተረፋት፡፡ ጃኖም በተደጋጋሚ ሽማግሌ እየላከ ሲማፀነው የሰጠውን የገበራ ገንዘብ በእጥፍ ድርብ ለመመለስ እያለቀስ ሲያስረዳው ልቡ ተለሳለሰ፡፡ አቅጣጫውን ወደ አንድ ወገን ብቻ አዞረ። ሾተሉን ወደ ቱሬ ብቻ ቀሰረ፡፡ ጊዜ ሲጠብቅ ሁኔታዎችን ሲያጠና ከከረመ በኋላ እጮኛው ታፍና ወደተወሰደችበት አገር
ገሠገሠ...
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ባላባት ቱሬ ዕድለኛ ሆነና በዚያን ዕለት ያደረው ለሱ ስድስተኛ ሚስቱ ከሆነችው ከሌቱና ጋር ሳይሆን ከባለተራዋ ከአማኔ ጋር ነበር፡፡ ባለተራዋ ሞቅ ያደረገችው እንደሆነ ሆዱን በጥንቃቄ የሞላች እንደሆነ እንክብካቤዋ ከፍተኛ ሆኖ ለሱ ከታየው የባለተራነት ኮታዋ ከፍ ይላል።ይሄንን ሁኔታ ሚስቶችም ስለሚያውቁ በመካከላቸው እኔ እበልጥ፣እኔ እበልጥ ፉክክር ይደረጋል፡፡
ይሄን ያደረገች ሚስት ዛሬ እጎበኛለሁ ብላ የምትጠባበቀውን ባለተራ ጉልበቷን አሳቅፋ ታሳድራታለች። ቱሬን ትደግመዋለች መድገም ብቻም ሳይሆን ልታስልሰውም ትችላለች። ዛሬ ግን ቱሬ ህይወቱን ለማትረፍ ዕድለኛ ሆነና ያደረው ብዙ ጊዜ የወረት ፍቅሩን አብሯት ከሚያሳልፈው
ከሌቱና ጋር ሳይሆን ከአቻ ሚስቱ ከአማኔ ጋር ነበር፡፡ ጃኖ አድብቶ
ምንሽር ታጥቆ ቱሬ ያንን ቀዝቃዛ ክንዱን አንተርሷት ያገኘውና በተኛ
በት እሱን ድብን አድርጎ የሚያፈቅራት እጮኛውን ይዞ ለማምለጥ እስከ ውድቅት ለሊት ድረስ ተጉዞ እኩለ ለሊት ላይ ከባላባቱ ቤት ደረሰ፡፡ በከፍተኛ ጥንቃቄና በዘዴ የባላባቱን ቤት አጥር ዘሎ ሌቱና የምትገኝበትን
ቤት በር በርግዶ ሲገባ ምስኪኗ ብቻዋን እንደ በረዶ በቀዘቀዘ ቁርበት ላይ ተጋድማ በሀዘን በትካዜና በናፍቆት ከስታና ጠቁራ አገኛት። ሌቱና ጃኖን ስታየው ማመን አልቻለችም፡፡ ደስታዋ ያመነጨው ይህ ነው የማይባል
👍31🔥1
የድንጋጤ ስሜት ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ጠጉሯ ድረስ ወረራት።
ነፍሷን ከሲኦል ሊያወጣት ከስማይ የወረደ መልአክ መሰላት። ዘላ ተጠመጠመችበት፡፡ እሱም ተጠመጠመባት፡፡ የስማ ሰው አልነበረም፡፡ ያንን ደስታ የፈነቀለው ልቧን ተረጋግታ ለማዳመጥና ግድቡን እንደጣስ ጎርፍ
ሊያጥለቀልቃት የመጣ እንባዋን ለመርጨት ፋታ አላገኘችም። እምባዋን ዋጥ አድርጋ እየተጣደፈች ተነሳችና ልብሷን ለባብሳ ጨረሰች::
( ጃኖ አሁን አመጣጡን አስተካክሏል፡፡ መጀመሪያ ቱሬን የሚያገኘው መስሎት ሊፋለመው ተዘጋጅቶ ነበር። አሁን ግን ቱሬ የለም። የሚፈልገው የቱሬን ነፍስ አይደለም፡፡ ሊገድለው ያሰበው አብረው ከሌቱና ጋር ሆነው ካገኛቸው ሚስቴ ነች አልሰጥም ብሎ ግብግብ የሚገጥመው
ከሆነና አደጋ ሊጥልበት የሚያንገራግር ከሆነ እንጂ እንደዚህ በሰላም እጮኛውን ብቻዋን አስቀምጦ ከጠበቀው ይዞ መሰስ ከማለት በስተቀር
ሌላው በጃኖ ዘንድ ቦታ አልነበረውም፡፡ የቱሬን ልትወጣ ጊዜዋ የተቃረበ ነፍስ የማጥፋት፣ ልጡ የተራሰ ጉድጓዱ የተማስ አዛውንት ነፍስ አጥፍቶ በስማይ ቤት ተጠያቂ የመሆን ፍላጎት አልነበረውምና በፍጥነት
ይዟት ጠፋ። በጠፍ ጨረቃ ሲገስግሱ አድረው ሲገሰግሱ ውለው በሁለተኛው ቀን አመሻሽ ላይ ቤቱ ይዟት ገባ፡፡

ሌቱና ክብሯን ጃኖ ባለመውሰዱ በፀፀት ብትብሰለሰልም የዚያን ዕለት እያለች ቢከነክናትም ጃኖ የሚፈልገው እሷነቷን ብቻ ነበረና የሚወዳት ፍቅረኛውን መልሶ ከእጁ በማስገባቱ በደስታ ሰከረ። የሚያፈቅራት የሚንስፈስፍላት የሱ ሌቱ! አምልጣው ባለመቅረቷ
እንደ እምቦሳ ጥጃ ቦረቀ፡፡ ፈነደቀ፡፡

ባላባት ቱሬ ሚስቱ የጠፋችበትን ምክንያት ያወቀው ከሳምንት በኋላ
ነበር፡፡ መጀመሪያ ያጫት ያ እሱ ድሃ ገበሬ ብሎ የናቀው ወጣት እልፍኙን ጥሶ አጥሩን ዘሎ ቤቱን ከደፈረ በኋላ በገበራ የገዛትን ልጅ ይዞ መኮብለሉን ሲያውቅ በንዴት ተቃጠለ፡፡ በዚሁ መሰረት ስለጃኖ ከፍተኛ ጥናት አካሄደና የሚበቀልበትን ዘዴ ሲያሰላስል ከረመ፡፡በመጨረሻ ጃኖን
የጋየው ጭንቅላቱ የሚረካበትን የበቀል ቅጣት ጭምር ሲያውጠነጥን በሽፍታ ለማስጠቃትና ሚስቱን ለማስመለስ በገንዘቡ ተማመነ። በንዴት ከረመና ከሽፍቶቹ ጋር ግንኙነት ፈጠረ። ሽፍቶቹ ግን የሚስጣቸውን ገንዘብ እየተቀበሉ አንሷል ጨምር እያሉ አሁንም ሲሰጥ ያንንም እየወሰዱ
አያዋጣም ሲሉት መጀመሪያ የሰጠው ገንዘብ እንዳይቀልጥ በላዩ ላይ ሲጨምር በመጨረሻ መረረውና የልቡን ሊያደርሱለት ያለመቻላቸውን ተረዳና ውሉን ከሌላ ሽፍታ ጋር ለመዋዋል አቅጣጫውን ቀየረ።በባላባት ጉደታ ግዛት ውስጥ የታወቀና ዝናው ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ
የተነገረ ሽፍታ መኖሩን ካረጋገጠ በኋላ በብዙ ውጣ ውረድና በብዙ ድካም ከጎንቻ ጋር ተገናኘ ። ቱሬ አላሰበበትም አንጂ ለባላባት ጉደታ አስቀድሞ ነግሮት ቢሆን ኖሮ ብዙ ባልደከመና የዚያን ያክል ረጅም ጊዜ ባልወሰደበት ነበር፡፡ ባላባት ቱሬ ጃኖን በሽፍታ በማስጠቃት ብቀላ ሊፈፅም የወሰነው በብዙ አቅጣጫዎች መዝኖት የተሻለ አማራጭ ሆኖ ስላገኘው ነው።
አንዱ ምክንያቱ የታጨችና ገበራ የተበላባት መሆኗ የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ ሳለ ንጥቂያ ቀረሽ ጋብቻ ፈፅሞ ለአንድ ድሀ ገበሬ የታጨች ልጅ ይዞ መጥፋቱ በእኩዮቹና በሚያስተዳድረው ህዝብ ዘንድ የሚያስገምትና
ክብሩንም የሚያስነካው መሆኑን ስላወቀ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ጃኖ በግዛቱ ስፋት ብቻ ሳይሆን በሀብትና በጀግንነቱ ዝናው የተሰማው የባላባት ጃዊሣ ወገን የሄጦሳ ጎሣ አባል በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ጦር
ይዞ ጦር ጭኖ ጃኖን ሊበቀል ቢሄድ ነገሩ ወደ ጎሣ ጦርነት እንዳይራመድ ፈራና ጃኖን ለመቅጣት ምንም አማራጭ የሌለው መድሃኒቱ በታወቀ
ሽፍታ መበቀል ብቻ ነው ሲል ወሰነ። ለዚሁም ጎንቻ !!...

ይቀጥላል
👍1
አትሮኖስ pinned «#የተወጋ_ልብ ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና ....መልኩን አይታ ለማታውቀው ሰው ልታስረክበው መሆኑ አበሳጫት፡፡አቃጠላት፡፡ አንገበገባት። “ምን ነበረበት ያን ጊዜ ባልተቆጣሁት ኖሮ? ብላ በፀፀት ተከነች፡፡ ይሄንን እያብሰለሰለች በንዴት ብትንጨረጨርና በእንባ ብትታጠብም ወላጆቿ በዕድሜ አቻዋ ከሚሆን ግፋ ቢል ደግሞ አባቷ ሊሆን ከሚችል ሰው ጋር እንጂ አያቷን እንድታገባ የፈረዱባት…»