#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
ለተከታታይ ቀናት ድርሰቶቹን ባለመልቀቄ
ይቅርታ እጠይቃለው የ Telegram app Update መደረግ እንዳለበት text ይመጣልኝ ነበር ባለማድረጌ አንድ ሁለት ቀን እስከሚስተካከል አስቸግሮኝ ነበር አሁን ግን የተስተካከለ ይመስለኛል እንቀጥላለን መልካም ንባብ።👇
.....“ጎንቻ! ቂጥህን ጠርጌ አሳድጌህ አንተም ሰው ሆንክና ለዚህ አበቃኸኝ?!” አለው በሚርበተበት ድምፅ፡፡ ጎንቻ ብልጭ! አለበት። “አንተም ሰው ሆንክና?” የሚለው የንቀት አነጋገር የንዴት ክብሪቱን በላዩ ላይ ጫረበት። መታገስ አቃተው፡፡ ከመቅፅበት እጁ በወገቡ ላይ ከዚያም
ከቶላ አንገት ጋር ተዋህዶ ጭንቅላቱ እያሽካካ ከበሩ ላይ ሲወድቅ የነበረው ፍጥነት እግዚኦ! የሚያሰኝ ነበር፡፡ ይህንን ትዕይንት ለሚያዩ እናትና ልጅ ጥናቱን ይስጣቸው እንጂ ጎንቻ ዶሮ ያረደ እንኳ አልመሰለውም፡፡
አወራረደውና እንጣጥ እንጣጥ….እያለ የወደቀውን አንገት ተራምዶት ሄደ ...
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከማህፀኗ በወጣው ጉድ እንደ እሳት እየተለበለበች ነጋ ጠባ እንደተሸበረች የከረመችው ወልአርጊ ለጥቂት ጊዜ ሰላም ሰፍኖባት ነበር። ዛሬ ግን የተፈጠረው ትርዒት ከወትሮው ለየት ያለ በመሆኑ መከራዋና ሀዘኗ ሁሉ መሪር ሆኗል፡፡ እናትና ልጅ ከአልጋ ጋር ተጠፍረው ታስረው አኖቻቸው እየተቁለጨለጩ የቶላ አንገት ሲቀላ ተመለከቱ..ጩኸቱ ከአንደኛው ጎጆ ወደ ሌላው ከዚህኛው መንደር ወደዚያኛው መንደር አስተጋባ።ብራቅ...ከወልአርጊ ዘወትር ፊቷ ወደማይፈታው በጭጋግ ወደ
ተሸፈነችው ወደ ሞዬ መንደር ደረሰ፡፡ ከዚያም ወደ አኖሌ...ከዚያም ወደ ዩያ...መቼም በዘረፋው በኩል በትንሹ ፍየል ያልተሰረቀበት ጥቂቱ በመሆኑ ሁሉም ንብረቱን በዐይነ ቁራኛ በመጠባበቅ ብርቱ ጥንቃቄ በማድረግ ላይ ነው፡፡ ዛሬ የተከሰተው በአይነቱ ለየት ያለ ከተራ ሌብነት የዘለለና ለመንደሪቱ ነዋሪዎች እጅግ አስደንጋጭ የሆነ ግድያ የታከለበት የከብቶች ዝርፊያ ወንጀል ነበር። ወልአርጊ አሰቃቂውን መርዶ ለማርዳት እኩለሌሊት ለሊቱን ስታምጥ አንግታ ከጠዋቱ አሥራ ሁለት ሰዓት አካባቢ ጭንቀቷን በእሪታ ተነፈሰችው...ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ዘላለም ሲያለቅስ ይኖራል ሆነና የሐጂ ቦሩ ጎረቤት ቶላና ቤተሰቦቹ በጎንቻ ምክንያት በተደጋጋሚ ከማንባት ባለፈ የቶላን የህይወት ዋጋ እስከማስከፈል
የደረስ ጥቃት ሰለባዎች ሆኑ፡፡ በቶላ ቤተሰቦች ጩኽት ምክንያት የተቀሰቀሰው ህዝብ ለመስቀል በዓል እንደሚጎርፍ ምእመን ተመመና የቶላን ግቢ አጨናነቃት። የጎንቻ ወላጆች ምጥ በምጥ ሆኑ፡፡ እህ! እህ! ጭንቀት
በጭንቀት። ቀስ በቀስ ቤታቸውን አራቁቶ ከብቶቹን ሸጦ ከጨረሰ በኋላ
በአብዛኛው የሚተዳደሩት በትላልቅ ልጆቻቸው ድጎማ ነበር፡፡ ሽብር የተቀላቀለበት ዘረፋ መፈፀም የጀመረው ልጃቸው እያጎረሰ፣ ጭንቅላቱን እየደባበስ፣ ንፍጡን እየጠራረገ እንደ ወላጅ ያሳደገው ቶላን በአሰቃቂ ሁኔታ
አንገቱን እንደ ጎመን ቀንጥሶት ሄደ መቼም የእናቱ የወይዘሮ ዋሪቴ ሁኔታ አይነሳ፡፡እግራቸው መሬቱን ቆንጥጦ መያዝ አቃተውና ተብረከረኩ፡፡ የህዝቡ ዋይታና ለቅሶ በነሱ ላይ መዓቱን ያውርድባችሁ በሚል የእርግማን ጩኸት የተሞላ ነበር፡፡
“ጎንቻ! ጎንቻ! በላን! ፈጀን!የአውሬ የጅብ እናት! የአውሬ አባት! እግዚአብሔር ይይላችሁ! አይዞህ እያላችሁ በሌብነት አሳድጋችሁ አስፈጃችሁን! የዚህ ሁሉ ቁጣ የዚህ ሁሉ ግፍ ተጠያቂዎች እናንተ ናችሁ! ጥፉ ያጥፋችሁ!” የማይል የአልቃሽ አንደበት አልነበረም።
ሐጂ ቦሩ በባለቤታቸው ምክር መስረት ዘመድ አዝማዱን እየተማፀኑ
ወደ ቤቱ እንዲመለስ ሽማግሌ ልከው የሚያስለምኑበትን ቀን በተስፋ
ሲጠባበቁ፣ ገበየሁን ገድሎ መሸፈቱ ተሰማ፡፡ በዚህም ምክንያት ተስፋ
ቆርጠው ዕለተ ሞቱ እንዲቃረብ፣ የጅብ ራት ሆኖ እንዲቀርና በመቃብሩ ላይ አልቃሽ እንዳይቆምለት ፈጣሪያቸውን ሲለምኑ እሱ ግን በአቋራጭ መጣና ልክ እንደ ትንሽ ወንድማቸው የሚወዱት የክፉ ቀን ወዳጃቸው ቶላን እንደ በግ አርዶ ሄደ፡፡ ማን ያውቃል? ነገ ተነገወዲያ ደግሞ ተራው የእናትና የአባቱ ሳይሆን ይቀራል? “ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይቀርም”
ነውና ጎንቻ በውስጡ ያበቀለው ቀንዳም ጋኔን ቀጥሎ የሚጠማው የዘመዶቹን ደም አለመሆኑን ማን በእርግጠኝነት መናገር ይችላል? የሰው ልጅ የማስተዋልና የማመዛዘን ችሎታው ሲዛባ፣ ከስነ ምግባር ማንነቱ ሲወጣ፣ በክፉና በመልካም ድርጊት መካከል ያለውን ልዩነት ከሚገነዘብበት የአእምሮ ብቃት ሊሸሽ፣ ራሱን ከመጠን በላይ በመውደድ መስገብገብ ሲጀምር ወደ አውሬነት መለወጡ የማይቀር ነውና ጎንቻ ከሰውነት ባህሪው ወጥቶ የክፉ ስግብግብ አውሬ ባህሪን ተላበሰ፡፡ በዚህ አካሄዱ ለሳቸውም ቢሆን እንደማይመለስላቸው የጠረጠሩት ሐጂ ቦሩ የጎንቻ ጩቤ በአንገታቸው ላይ እስከሚስካ፣ የተስበቀ ጦሩ በደረታቸው ላይ እስከሚቀረቀር ድረስ ለመጠበቅ ትዕግስት አጡ፡፡ የህዝቡን እርግማንና ጥላቻ በመቋቋም የከፈሉት ዋጋ ሳያንሳቸው የክፉም ሆነ የበጎ ጊዜ ወዳጃቸው የሚስጥረኛቸው የቶላ አሰቃቂ ግድያ በልጃቸው በጎንቻ እጅ ተፈፅሞ ማየት ግን ፍፁም ሊቋቋሙት የማይችሉት ጥቃት ሆነባቸውና በራሳቸው
እርምጃ ለመውሰድ ቆረጡ። አሮጊቷ እናትም ማህፀናቸው ጭራቕ በማፍራቱ መፈጠራቸውን ጠሉት፡፡ እግዚአብሔርን ወቀሱት። በስተመጨረሻ የተገኘው ጉድ ሰይጣን ጎብኝቷቸው እንደሆነ እንጂ እውነትም ከሐጂቦሩ የተገኘ ፍሬ መሆኑን ተጠራጠሩ፡፡ ለሁሉም ነገር አቅም አጡ፡፡ ለዋይታና ለእሪታው ልሳናቸው ተዘጋ፡፡ እምባቸው ደረቀ።
“እህህ..ጎንቻ ፈጣሪ የስራህን ይስጥህ!ከልጆቼ ሁሉ አስበልጬ አቀማጥዬ አሳድጌህ እንደሆነ ውለታውን ከሱ አትጣው! በስተርጅና በመውደቂያ ዘመኔ እናቴ ምን ልርዳሽ? ብለህ ጎኔን ልትደግፍ ተስፋ ልትሆነኝ በሚገባህ ሰዓት ከሰው እንዳልቀርብ የአውሬ እናት እየተባልኩ
ሰው እንዲሽሽኝ በመቃብሬ ላይ አልቃሽ እንዳይቆም ላደረግህልኝ ውለታ
ሼህ ሀና ሁሴን ብድሩን ይክፈሉህ! የእጅህን አትጣው።ወንድ ነኝ ብለህ
እንደፎከርክ ወንድ ይዘዝብህ...!” ብለው አለቀሱ። ከወዳጅ ዘመዶቻቸው አቆራርጦ ስማቸውን የቡና መጠጫ ባደረገው ልጃቸው የተሰማቸውን ምሬት ለፈጣሪያቸው በእምባ ገለፁ።እህቶቹና ወንድሞቹ የሚኖሩት ሩቅ ቦታ ቢሆንም ጎንቻ በየጊዜው ስለሚፈፅመው አሰቃቂ የውንብድና ተግባር እየሰሙ ተበጥብጠዋል።እነሱ ብቻ ሳይሆኑ የአካባቢው ባለስልጣን ባላባት ጉደታም ውንብድናው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና የጥቃት አድማሱን እያሰፋ በመጣው በጎንቻ አስከፊ ወንጀል ምክንያት ከህዝቡ በሚቀርብለት እሮሮ አእምሮው እረፍት እስከሚያጣ ድረስ ተበጥብጧል። ባልታሰበ ጊዜ ከተፍ ይልና ያምሳል፣ ያስለቅሳል፣ ያንጫጫል። አንዴ ከተሰወረ ደግሞ መኖሩ እስከሚያጠራጥር ድረስ ደብዛውን ያጠፋል። ደግሞ ሳይታሰብ ከተፍ ይልና የተለመደውን ጫጫታና ዋይታ ያስቀጥላል፡፡
የቶላ የቀብር ሥነ ሥርዓት በተካሄደ ዕለት ባላባት ጉደታ ህዝቡን በአንድ ትልቅ ዋርካ ጥላ ስር ስብስቦ የሚከተለውን ንግግር አሰማ፡፡

👍4
“በበጎችና በፍየሎች ሌብነት የሚታወቀው የመንደራችሁ ውርጋጥ ቀስ በቀስ ወደ ሽፍታነት ተሽጋግሮ በአሁኑ ሰአት
በቃላት ሊገለፁ የማይችሉ አሰቃቂ የግድያና የዘረፋ ወንጀሎችን በመፈፀም ላይ ይገኛል፡፡ ከዚች ጠባብ መንደር ውስጥ እንኳ ሶስት ሰዎችን ገድሉብን ሶስት ጊዜ በህብረት አልቅሰን በህብረት ቀብረናቸዋል። በጎንቻ ምክንያት ህይወት ጠፍቷል፣ንብረት ወድሟል፣ ትዳር ፈርሷል፣ ህፃናት ያለአሳዳጊ ሜዳ ላይ
ተበትነዋል። በዚህ አካሄዱ እያንዳንዳችሁን ተራ በተራ ለቅሞ ከመጨረስ ወደ ኋላ እንደማይል የታወቀ ነውና ሳይቀድማችሁ ልትቀድሙት ይገባል። በባላባትነት ግዛቴ ውስጥ የምትገኙ ነዋሪዎች ተባብራችሁ
ይሄን ወሮበላ በቁጥጥር ስር በማዋል ለፍርድ እንድታቀርቡትና በቁጥጥር ስር ልታውሉት የማትችሉ ከሆነ ደግሞ ገድላችሁትም ቢሆን ራስችሁን ከጥቃት መከላከል እንድትችሉ ከፍተኛ ጥረት ሳደርግ ቆይቻ ከብዙ ውጣ ውረድና ከብዙ ድካም በኋላ ጥረቴ ተሳክቶ ከዚህ
አደገኛ ሽፍታ ራሳችሁን መጠበቅ የምትችሉበትን የበላይ አካል ፍቃድ
አግኝቻለሁ። ከዛሬ ጀምሮ ምንም አይነት ፍርሃትና ጥርጣሬ ሳያድርባችሁ ጎንቻን በአፋጣኝ በቁጥጥር ስር አውላችሁ ወይንም ደግሞ ገድላችሁ ነፃ መውጣት በህግ የተፈቀደ መብታችሁ መሆኑን አረጋግጥላችኋለሁ!!” በማለት ንግግሩን አጠቃለላ፡፡
“መንግሥት ካልተባበረን በስተቀር ማነው ጎንቻን የሚቋቋመው? እንደዚህ ከሜዳ ላይ እጁ የሚያዝ ተራ ሰው ሆነ እንዴ? እንደ እባብ በደረቱ ይሳባል፣ እንደ ሽኮኮ ድንጋይ ለድንጋይ ይሹለከለካል፣ እንደ እስስት መልኩን ይለዋውጣል ሰላቢ! ቀድሞ በዐይንስ መቼ ይታያል? ፊት ለፊት
ቢመጣስ ማን ነው ደፍሮ እጁን የሚይዘው? ህይወቱን የጠላ ማን አለ?
ኸረ ግድ የለም! እሱም የለበሰው አንድ ሱሪ ነው! አንገቱን አንቀን ነው ለፍርድ የምናቀርበው! እጁን መያዝ ቢያቅተን ተኩሰን መጣል አያቅተንም!...” ግማሹ የፍርሀቱን ግማሹ የቁጭቱን ሁሉም የመሰለውን በየግሉ አወራ አወካ፣ ተንጫጫ... ባላባት ጉደታ በጎንቻ ላይ እርምጃ እንዲወስድበት መመሪያ ሰጥቶ የሟች ቤተሰቦችን “ያጥናችሁ” ብሎ ተሰናበተ።
ጎንቻ ግን እንደ ባላባቱ አነጋገር በቀላሉ የሚገኝ ሰው አልሆነም፡፡ በጣም
አስቸጋሪና በወንጀል ላይ ወንጀል እየደጋገመ ዱካው የማይገኝ የእኩለ
ለሊት መቅስፍት እየሆነ ሄደ፡፡ ይሄ ሁኔታ ደግሞ እንኳንስ ተራውን ነዋሪ ቀርቶ ራሱ ባላባት ጉደታን ጭምር እያስጋው መጣ፡፡ እንደ ዶሮ ዘቅዝቃችሁ እጁን አንጠልጥላችሁ አምጡልኝ እንዳለው ሳይሆን ቀረ።ባላባት ጉደታ በአደባባይ የወሰነበትን የሞት ውሳኔ የሰማው ጎንቻ ሳይውል ሳያድር በራሱ በባላባቱ ላይ አደጋ ጥሎ ሊያስደነግጠው ወሰነ፡፡
“ግዴለም! በሰላም መኖር ካልፈለገ እሱንም እበጠብጠዋለሁ! እኔ ጎንቻ
እኔ ወንዱ ለማንም የማልመለስ ሞት አይፈሬ መሆኔን አሳየዋለሁ!” ሲል በጀሌዎቹ ፊት በእልህ ተናገረ። በዚሁ መሰረት ቀን ሲጠብቅለት ሲያደባ ቆየና ጨለማን ምሽጉ አድርጎ ወደ ባላባቱ መኖሪያ ቤት በለሊቱ እንዳለውም የባላባቱን አጥር ጥሶ በመግባት ሁለት ቅልብ ውሾቹን ገደለና ሬሳቸውን በመውጫና በመግቢያ በራፉ ላይ ከዘረጋ በኋላ አራት የሰቡ ሙክት ፍየሎቹን ዘርፎ ተሰወረ። በዚያ ሌሊት የባላባቱን
ቤት ዘበኛ አፍኖ “ወንዱ ጎንቻ! ጀግናው ጎንቻ! እንኳንስ ሞት ለተመኘለት ቀርቶ ለእናት ለአባቱ ደንታ የሌለው ጎንቻ! ይሄንን ፈፅሞ ሄዷል ብለህ እንድታስረዳ፡፡ ህይወትህን አላጠፋትም፡፡ ይሄንን ቃል ብትቀንስ ወይንም ብትጨምር ባገኝህ ግን ወዮልህ!” ብሎ አስጠንቅቆት ሄደ።
የባላባቱ ቤት ጠባቂ በብርክና በድንጋጤ ተውጦ ጎንቻን እየተማጠነ ቃሉን
ሳይጨምር ሳይቀንስ ለባላባቱ ሊያስረዳ ቃል ገባና ህይወቱን አተረፈ::
ጠዋት በማለዳ ባላባቱ የተፈጠረውን አስደንጋጭ ሁኔታ በዐይኖቹ ካየና
በጆሮዎቹ ከሰማ በኋላ የሚይዝ የሚጨብጠው ጠፋው፡፡ ሰውነቱ በእልህና በንዴት ግሎ ተንቆራጠጠ...
“ወይኔ ጉደታ የማንም ጨምላቃ እረኛ መቀለጃ ልሁን?! በዚህ አይነትማ እረኛ ሁሉ እየተነሳ እየፎከረ ጫካ ሊገባ ነው ማለት ነው?! ሲሶ አናርስም ግብር አንገብርም ሊል ነው ማለት ነው?! የድሃ የገበሬ ልጅ ሁሉ ሊያምፅ ነው ማለት ነው?! እበቀለዋለሁ!! እጁን ይዤ በህዝብ ፊት አርባ ጅራፍ እቀጣዋለሁ፡፡ ማረኝ አሰኘዋለሁ!” በጣም ፎከረ። ቀስ በቀስ
ግን ዘመድ ኣዝማዱ መከረና ከሽፍታው ጋር እልህ መጋባቱ በሌሎች የቅርብ ዘመዶቹም ሆነ በራሱ ላይ አደጋ መጋበዝ መሆኑን በጥሞና አስረዱት፡፡ ጎንቻን የሚያጠፋው ቢሆን እንኳ በቀላሉ ሊያጠፋው እንደ ማይችል ከሚጠፋበት ደረጃ ላይ የሚያደርሰው ከሆነም ብዙ አደጋ ጥሎ አጥፍቶ የሚጠፋ መሆኑን ገለፁለት።
ባላባቱም ንዴቱን ተቆጣጥሮ የሚከተለውን መዘዝ ማሰላሰል ጀመረና ከሽፍታው ጋር እርቀ ሰላም ማውረድ ፈልጎ አማላጅ ላከበት። ጎንቻ ለእርቅ ሰላሙ ፈቃደኛነቱን በገለፀበት ምሽት ሙክት ታረደለት፡፡ በዚያን እለት
ጎንቻ ለባላባቱ ቅን ታዛዥ እንዲሆን፣ የባላባቱን ጥቅም ለሚፃረሩ ሁሉ
የቅጣት በትር እንዲሆን፣ እናምፅብሀለን ብለው ቀና ቀና የሚሉ ቢገኙ
የሚኮረኩምለት ጋሻ ጃግሬ እንዲሆነው ባላባቱም ጎንቻን አሳልፎ ለበላይ
እንዳይስጠው፣ የሚፈፅመውን ዝርፊያና የግድያ ወንጀል እንዳያጋልጥና
አቤት ባዮችን አፍኖ እንዲይዝለት ከጋራ ስምምነት ላይ ደረሱ። ነገሩ
እከክልኝ ልከክልህ ሆነና ጎንቻ የበለጠ ደረቱን አሳበጠ፡፡ ወንጀሉም እንደ
ህጋዊ ድርጊት ተቆጠረለት፡፡.....
✨ይቀጥላል✨

👍2
#የወዲያነሽ
፡
፡
#ክፍል__ሰላሳ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በሐይለመለኮት_መዋል
....እናቴ አዘኔታ በሚታየበት ፊት ወደ እኔ መለስ አለችና ሞኝነትህ፣ ሞኝነትህ ነው ልጄ! 'አይዞሽ ግድ የለሽም' ብለህ ይዘሃት ና፡፡ እኔ እናትህ አሳምሬ እቀበልልሃለሁ። አትፍሪ! አትፍሪ ነዪና እንታረቅ፣ ከእንግዲህ ወዲያ እኔና አንቺ እናትና ልጅ ነን፣ ልጄ ልጄ ብላሻለች” ብለህ አሳምረህ ንገርልኝ በማለት ያን በውስጤ ሲገላበጥ የዋለ ሥጋትና የመንፈስ ሽብር ገደለችልኝ
እናቴ ጋሻዬነህን ፍለጋ መልከት መልከት ስትል እንቅልፉ ሊጥለው ሲያንጎላጅ
አየችውና «አፈር በበላሁት! ልጄን! ልጄን! ያቺ እናትህ እንኳን አላየች!» ብላ
ካነሣችው በኋላ እግሩን እያንዘላዘለች ወደ የውብነሽ መኝታ ቤት ይዛው ገባች::
የእናቴ እግር ወጣ እንዳለ የውብነሽ ድንገት ብድግ ብላ አለቀ! ጨብጠኝ
ወዳ አይምሰልህ የግዷን ነው» ብላ ደስታዋን ገለጸችልኝ።
«አዎ ከእንግዲህ ደግሞ አንድ አስቸጋሪና የለየለት ግብግብ ብቻ ይቀረኛል» ብዬ መለስኩላት
የወዲያነሽ ምነው ቆየህ? ና እንጂ ጌታነህ! ቁርጤን ልወቅ? የምትል
መሰለኝ፡፡ ሰዓቴን ብመለከት ዐሥራ ሁለት ሰዓት አልፏል። እናቴ ከተቀመጠች
በኋላ ጥያቄና መልስ ቀጠለ። ከመጠን በላይ ተዝናናሁ፡፡ መላ አካላቴ
ተንፈላሰሰ፡፡ የወዲያነሽን ሥቃይና መከራ ባጭር ባጭሩ አንዲትም ሳላስቀርና
ሳልዘነጋ እንደ ተረት ነጋሪ አሳምሬ ወጣሁላት። የእኔንም ልፋትና ውጣውረድ
ሁሉ ገለጽኩላት፡፡ ንግግሬን እንደ ጀመርኩ ፊቷ ትንሽ በትንሽ ጠወለገ፡፡ እንባዋ
እየተሽቀዳደመ ሲወርድ ማዘንና መፀፀቷ ገባኝ። የእናቴ ርኅራኄና ገራገርነት እንደ ኮረብታ ጎልቶ ታየኝ፡፡ በኀዘን ጠውልጎ በእንባ የራሰውን ጉንጯን በማየቴ
በጣም ረካሁ፡፡ በሕዝብ ኃይል ሥልጣን እንደ ያዘ መንግሥት ደስ አለኝ።
የወዲያነሽም ድል ስታደርግ ወለል ብሎ ታየኝ፡፡
«አሠቃይቻታለሁ በቁሟ ቀብሪያታለሁ» አለችና ልቅሶዋን ቀጠለች።
«ያለፈው አልፏል ከነገ ጀምሮ ታርቃችሁ ተፋቀሩ እንጂ እሷ በበኩሏ ሁለንም
ነገር ይቅር ብላ ትታዋለች በጣም እኮ ነው የምትወድሽ» ብዬ ትካዜዋን ለማቅለል ሞከርኩ፡፡ ሙሉ ፈገግታዋ ሳይመለስ ለመሄድ ተነሣሁ፡፡ «ጋሻዬን አምጪልኝ የውብነሽ!» አልኳት፡፡
«አንት ጨምላቃ ጨመለቅ! እኔ እጅ ገብቶ ነው የምትወስደው?ባይሆን እንኳ ዋንየዋ ከመጣች በኋላ የሆነው ይሆናል!» ብላ ቱግ አለች። ልቤ ጮቤ ረገጠች፡፡ ተደሰትኩ እንጂ አልከፋኝም፡፡ የወሬ ሠንጋ ጥለን ስናወራርድ ሁለት ሰዓት ተኩል አለፈ። የውብነሽን ለብቻዋ ጠርቼ «ነገ አራት ሰዓት እንድትመጪ» አልኳትና «ደኅና እደሩ» ብዩ ወጣሁ፡፡
የቤቴን አጥር ግቢ ከፍቼ ስገባ የወዲያነሽ ጋቢዋን ለብሳና የሰበሰቡን አግዳሚ ተደግፋ ስትጠብቀኝ ደረስኩ እንደ ወትሮዋ ነቃ መብላት ስላልተቀበለችኝ
አእምሮዋ በሐሳብ ጉልበቷ በመቆም እንደ ተዳከሙ ገባኝ። እጅዋን ያዝ አድርጌ ዐይን ዐይኗን እያየሁ አመሸው እንዴ የወዲያ ደስ ይበልሽ! ደስ ብሎኛል
የሄድኩበት ጉዳይ ተሳክቷል» አልኩና በምሽቱ አየር የቀዘቀዙ ጉንጮቿን ሳምኳቸው፡፡
«እንኳን ደኅና መጣህ? እንኳን ደስ ያለህ? ጋሻዬስ? ከእጅህ ላይ ሳጣው ጊዜ አፌ ተሳሰረ» አለችና በልከኛው የመብራት ውጋጋን ውስጥ ትክ ብላ ተመለከተችኝ፡፡ ተያይዘን ከገባን በኋላ እንዴት ብዬ ልግለጽልሽ? እናቴ በጣም ተደሰተች። ምነው የዛሬዋ ዕለት የሁለትና የሦስት ቀን ያህል በረዘመች ! ስለ አንቺና እኔም አንዳችም ሳላስቀርና ሳልደብቅ ነገርኳት። በጸጸት ተቃጥላ እንባ በእንባ ሆነች። ርኅራኄዋንና የእናትነት ልባዊ ፍቅሯን ለማግኘት ችያለሁ፡፡በመጨረሻ ግን ጋሻነህን ልውሰድ ብዬ ብጠይቅ አፈን አስያዘችኝ፡፡ «እሷን እዚህ ይዘህ መጥተህ ይቅርታ አድርጊልኝ ብዬ ሳንታረቅና እንደ እናትና ልጅ ሳንሳሳም፣ ልጅ የሚሉ ነገር አልሰጥም ብላ ማለች» ብዪ ጋሻዬነህ የቀረበትን ምክንያት አብራራሁላት፡፡
የወዲያነሽ እውነት ስላልመሰላት «መቼ ሥራ አጡና! እንኳን ጥራትና አምጣት ሊሉህ ይቅርና ይህንኑ ዐይኗን እንዳታሳየኝ ብለውህ ይሆናል፡፡ ያንተን ሥራ መች አጣኋትና! ታዝናለች፣ ይከፋታል ብለህ ነው:: አትጨነቅ ቢከፋኝስ ምን እንዳላመጣ ነው? አጀብ እቴ ! ያም ሆነ ይህ እንኳን ደስ ያለህ» ብላ አሻግራ ስትመለከት «አምጪ እጅሽን፣ የወዲያነሽ ሙች! » ብዩ ለእውነተኛነቴ ማረጋገጫ እንዲሆን እጅዋን ስቢ ጠፋሁት፡፡
ከጥቂት ቆይታ በኋላ ራት አቀረበች። ሆዴ በቀኑ ምግብ ደስታና ፈንጠዝያ በመጎሰሩ ምንም አላሰኘኝም፡፡ የወዲያነሽ «በቃኝ! በቃኝ!» እስከምትል ማጉረስ በመቻሌ እንደገና ደግሞ አጋጣሚው አስደሰተኝ። ከራት በኋላ ከቀኑ ወሬ ውስጥ ቀነጫጭቤ አወራሁላት። በጥርጣሬና በሥጋት ታፍኖ የነበረው አእምሮዋ ገለጥለጥ ስሳለላት ጥርጣሬዋ ከላይዋ ላይ በንኖ ጠፋ፡፡
«እኔ በበኩሌ ቂም የሚሉ ነገር አልያዝኩም፡፡ ላንተ ስል ሁሉንም ነገር ትቼዋለሁ፡፡ የፈራሁትና የሠጋሁት አሻፈረኝ ይላሉ ብዬ ነው እንጂ፣ እሺ ካሉንማ ምን ቆርጦኝ። ጫማቸው ላይ ወድቄ ይቅርታ አድርጉለኝ ብላቸው ምን ነውር አለበትና ነው?» በማለት እቅጩን ነግራኝ ወደ መኝታ ቤት ገባች። መላ ሰውነቴ ጥርስ አውጥቶ ሣቀ፡፡ ተከትያት ገባሁ። ምንጊዜም ከዚያ ቀደም ወስዶኝ በማያውቅ ሁኔታ እንቅልፌን ስለጥጥ አደርኩ፡፡ እውነተኛ ፍቅርና የሕሊና ጸጥታ ምንኛ ሰላም ይሰጣሉ!
የወዲያነሽ ቀኝ እጅዋን በብርድ ልብስ ውስጥ አሾልካ ግንባሬን
እየዳበሰች «እንዴ? የዛሬውስ እንቅልፍ ለብቻው ነው፣ ለጤና ያድርግልህ» ብላ በማያስደነግጥ ሁኔታ ባትቀሰቅሰኝ ኖሮ ተኝቼ አረፍድ ነበር። ከአንገቴ ቀና
ብዬ «ረፍዷል እንዴ? ስንት ሰዓት ሆነ?» አልኳት፡፡ ሰዓቷን አየት አድርጋ «ሦስት ሰዓት ከሐያ አምስት» ብላኝ ሄደች።
በመስኮቱ በኩል የገባው የረፋዷ ፀሐይ ጮራ ክፍሉን አወግጎታል።
ተጣጥቤና ለባብሼ ለመቀመጥ ቸኮልኩ፡ ሠራተኛይቱ ያመጣችልኝ ሽግ ያል ውሃ ደህና አዝናናኝ፡፡ ጊዜው በመገሥገሡ ተደሰትኩ በእናቴ ፊት «የሚያስከብረኝን» ልብስ ለብሼ ስጨርስ አራት ሰዓት ተኩል አለፈ፡፡
የወዲያነሽ ከፊት ለፊቴ ቆም አለችና ምን ዓይነት ልብስ ልልበስ? እስኪ ንገረኝ?» ብላ ዐይኖቼን በዐይኖቿ አቆላመጠቻቸው ደረቷ ላይ ዠቅ
ያለውን ሐብልና መስቀል እየተመለከትኩ «መጨነቅና መጠበብ አያስፈልግም የአንቺ መጎናፀፊያና ግርማ ሞገስሽ የሰው ልጅነትሽ ብቻ ነው። የሐር ድርብና የወርቅ ቁርጥራጭ አይደለም፡፡ ይህን የአጣና ያአገኘ የመለያ ምልክት በግብግብ
እናስወግደዋለን። ደስ ያለሽን ልበሽ?» አልኳት። ባለ ወይን ጠጅ ጥለት ኩታና ቀሚስ ለብሳ፣ ተረከዘ
አጭር ጫማ ተጫምታ ጸጉሯን በቀላሉ ጎነጎነችው፡፡
ምንም እንኳ ቀደም ሲል በሕወይቷ ላይ በደረሰው ተደጋጋሚ ችግርና የሕሊና
ሥቃይ የተነሣ አካላቷ ሲፈካና ሲጠወልግ፣ ሲከሳና ሲኮስስ ቢኖርም፣ የወዲያነሽ በአሁኑ ጊዜ በምቹ ቦታ ላይ በቅላ በማለፊያ ዳስ ላይ እንደ ተንሰራፋች የወይን
ተክል ሐረግ ቀስ በቀስ አምሮባታል።
የችግርና የሠቀቀን ኑሮ ያሟሰሰው ለዛና ዛላዋ፣ ውበትና ደም ግባትዋ
እንደገና እንደ ሐምሌ ጎርፍ እየሞላ፣ እንደ መስከረም ወንዝ እየጠራ፣ እንደ ጥቅምት አዝመራ አሺቷል። ከአገርና ከሕዝብ መኻል በተለይ ተመርጣ የምትጠቀስ ልዩ ቆንጆ ባትሆንም የወዲያነሽ የምትኮክብ የውበት ጉልላት
ሆነች። ጠበብ ካለው ግንባሯ ግርጌ ከቅንድቦቿ ድባብ ሥር ያሉት ተንተግታጊ ውብ ዐይኖቿ ከሥጋ ቅምር ሳይሆን ከሚጨበጥ ንጥረ ብርሃን የተሠሩ መሰሉ፡፡

👍5❤1
እንኳንና እንዲህ ዛሬ ሕሊናዋ በተስፋ ተሞለቶና አካላቷ እፎይታ
አግኝቶ ይቅርና፣ ከጥቂት ዓመታት በፊትም ቢሆን «ይቺ ልጅ እኮ ፈገግ ብላ ስትሥቅ ካፏ ማር ጠብ ይላል፣ ጥንቅሽ የመሰለች ልጅ ነች» በማለት በዕድሜ ጎዳና ላይ ለአያሌ ዓመታት የተጓዘችው እናቴ እንኳ የወዲያነሽን ከልብ
አድንቃለች፡፡
የጠጠር ላይ ውሃ መሳዩ ጠይም ተርፋላ ጉንጫን ያማከለው አወራረድ ሸጋ አፍንጫዋ ከሞንዳላ ከናፍሯ ጋር ሲታይ የውበቷን ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።
መለሎው ቁመናዋ ተንኮልና ክፋት አልባ የሆነው ሕሊናዋ ባንድነት ከሕያው ፍቅሯ ጋር ዳግመኛ አቆራኙኝ።
«እስኪ እየኝ አምራለሁ? ባለምርም ያንተ በመሆኔ ብቻ ታምሪያለሽ ማለትህ አይቀርም» ብላ ፊት ለፊቴ ቆመች፡፡ ብእንስላል መኻል የበቀለች
የባቄላ አበባ መስለሻል» ብዬ አላባበሷን አደነቅሁ፡፡ አባባሉ የእኔ ሳይሆን ከሌሎች የሰማሁት ነበር፡፡ «አቤት አንተ! እኔስ ከዩት ይመጣለሃል? አሳምረህ
መናገሩን ታውቅበታለህ» ብላ ወደ ጓዳ ስትገባ የውብነሽ ከውጪ ከቸት አለች።
እንዴት አደርክ ከሰላምታ በኋላ ከጎኔ አረፍ አለች፡፡ ረብ የለሽ ወሬ
አወራራንና «አንተስ ታስታውቃለህ ተዘጋጅተሃል። ለየወዲያነሽስ ሁሉንም ነገር ነገርካት? አለችኝ። የበጋ ሌሊት ጨረቃ መስላልሻለች» በማለት ተጨማሪ
ውበት የሰጠኋት ይመስል ጉራ ነዛሁ::
«እኔ ቀድሞም ቢሆን የሠጋሁትና እንደ ጦር የፈራሁት በእናንተ በኩል ያለውን ነው እንጂ በየወዲያነሽ በኩል ያለውንማ ያለ አንዳች ችግር ልፈጽመው
እንደምችል አሳምሬ ዐውቃለሁ» አልኩና የነገሩን ማለቅ እስረዳኋት። «አንተ ወጣ እንዳልክ) የጀመረች እስከ ውድቅት በልቅሶ አላስተኛ ብላኝ አደረች። ዛሬ ደግሞ በጣም ከመቸኮሏ የተነሣ ሂጂ ቶሎ ብላችሁ ይዛችሁልኝ ኑ» ብላ አላስቆም አላስቀምጥ ብላኝ አረፈደች፡፡ ከሁሉም በላይ ያስደሰታት ደግሞ ጋሻዬነህ ነው።
አባዩ የለ እማዬ! ዝም ብሎ ለጥ አይልልህም» ብላ ተጨማሪውን የምሥራች ነግራኝ ወደ ቁም ሣጥኑ መስታወት ሄደች። የወዲያነሽ ከተመልካች ዐይን
የጋረዳትን ተራራ አልፋ ብቅ እንደምትል የምሽት ጨረቃ ከወደ ጓዳ ከተፍ አለች። ተሳሳሙ፡፡
ማለፊያ ቁርስ ቀርቦ ሦስታችንም እንደበላን የውብነሽ ወደ ውጪ
ወጣች። ለመፈታተን ሳይሆን መልሷን ለመስማት ያህል የመሄጃችን ጊዜ እንደ ተዳረሰ «አሁን ሄደን ገባ ስንል ድንገት ሳታስቢውና ሳትጠነቀቁ እናቴ እግርሽ ላይ ወድቃ ማሪኝ ልጄ! አጥፍቻለሁ! ያለችሽ እንደሆነ ፈጠን ብለሽ እንድታነሺያት» ብዬ ሐሳቤን ሳላጠናቅቅ፣
«ምነው አንተ? ምንስ ቢሆንና ምንስ ቢያደርጉ እናትህ እኮ ናቸው:: የጋሻዬነህ እናት ማለት ናቸው! ቀድሞውንስ ለምን ቀድመውኝ? ጫማቸው ላይ
ወድቄ ይቅርታ የምጠይቅ እኔ እንጂ እሳቸው አይደሉም። እኛ ባገራችን ዱሮውንም ቢሆን ትልቁ ቢበድልና ቢያጠፋ ለክብሩ ሲባል ትንሽየው ነው እግር ስሞ፣ ድንጋይ ተሸክሞ፣ ከታላቁ ጋር የሚታረቅ» አለችና በማያዳግም ሁኔታ
ሓሳቧንና አስተያየቷን ሰጠች፡፡ የትሕትናው አፈፃፀምና መከባበሩ ደስ ቢለኝም ዋናው ሐሳብ ትክክል ስላልነበር አእምሮዬ ወደ ውጪ ተፋው:: አላስችል ስላለኝ ወደ ጆሮዋ ላግ ብዬ «ይህን ያረጀና የበሰበሰ ልማድ ወዲያ ጣይው። የእስር ቤቷን ጓደኛሽን ትምህርት ረሳሽው እንዴ? እኔ የጠየቅሁሽ የምትይውን ለመስማት ያህል ነው:: ስለዚህ አንቺ እንደምትይው መደረግ የለበትም አልኳት፡፡
«ኧረ ዝም በል! እንኳን እንዲህ ጤና ሆኜ ልቤን እንኳ ቢነሳኝ፡
እማማ ጎንበስ እንዲሉ አላደርግም! ምነው በል! ምን ቢሉ፣ ምንም ቢያደርጉ እኮ እናታችን ናቸው:: ያክስቴ ባል ንጉሥ ለታቦት ይሰግዳል ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡እኔ እኮ እማማ እንዴት ይወዱኝ እንደነበር አይረሳኝም» ብላ አለባበሷን ለማየት ወደ መስተዋቱ ሄደች፡፡
መንገድ ስንጀምር አምስት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡ አቋራጩን ለማወቅም
ሆነ በደንብ ለማሽከርከር እንደዚያ ቀን ተሳክቶልኝ አያውቅም፡፡ ከወላጆቼ ቤት አጠገብ ደርሰን መኪናይቱን እንዳቆምኩ የወዲየነሽ ፊት በፍርሃት ተለዋወጠ::አእምሮዋ በሽብርና በሥጋት ተናወጠ፡፡ ከመኪናይቱ ወጥተን ባንድ ላይ ቆም እንዳልን የወዲያነሽ ቀኝ እጄን ያዝ እያደረገችና «ጌታነህ እኔ አልሆነልኝም ፍርሃት ፍርሃት አለኝ፣ አንቀጠቀጠኝ ምን ይሻለኛል?» ብላ በሥጋት ዐይን አየችኝ፡፡ ሲበረግግ ከኖረ አእምሮ ውስጥ የሚፈልቅ ምክንያታዊ ችግር በመሆኑ ፍርሃትና ድንጋጤዋ እንደሚያገረሽ የታወቀ ነበር፡፡
«ምነው ተነጋግረንበት። አነጣጥሮ ሽሽት የለም፡፡ ምንም የሚያስፈራ
ነገር የለምና አትሥጊ። የምን መርበትበት ነው? የቀረው ይቀራል አንጂ.. ብዬ በፍቅራዊ ቃላት ፍቅራዊ ግሣጼና ማበረታቻ ሰጠሁ፡፡ የውብነሽ ቀደም ብላ
የግቢውን በር እንኳኳች። ዘበኛው በተጠንቀቅ ቆሞ የቆየ ይመስል ወዲያው ከፈተ፡፡ የየወዲያነሽ ፊት በፍርሃት መለዋወጡን ቀጠለ። የትግል ስንቄን ሰንቄ ዘመቻ ጀምሬያለሁና ፊቴን አላዞርም፡፡ ብትንቀጠቀጥም ብትናጥም የማይቀር ነውና በሩን አልፈን አጥር ግቢው መኻል ደረስን። ዱሮ ልብስ ታጥብበት የነበረውን ቦታ አስታወስኳት፡፡ በእትክልቶቹ ውስጥ እየተሸሽግን የፈጸምናቸው
የፍቅር ኩኩሉዎች ሁሉ ተራ በተራ ትዝ አሉኝ፡፡ በከፊል ነጻ የሆነችው
የወዲያነሽ በከፈል ይፋ ሆና ተመለሰች፡፡
የወዲያነሽ እጀን ጫን ብላ ይዛ «አንተ እያለህልኝ ምን ያስፈራኛል
ሞኝነቴ ነው እኮ፡፡ ምን እንዳልሆን ነው?» ብላ ከሚተናነቃት የጥርጣሬ ፍርሃት ውስጥ ደማቅ ፈገግታ አሳየች፡፡ ደረጃውን ወጥተን እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ ደረስን፡፡ የውብነሽ ቀደም ብላ ወደ መኝታ ቤት ገባች፡፡ የወዲያነሽን ይዤ ክፍሉ መኻል ላይ ቆምኩ፡፡ አይጣል እኮ ነው! ለእኔ ሳይሆን ስለእርሷ ፈራሁ፡፡
እሷም ዘወር መለስ እያለች ስትመለከት ያቺን የዱሮ መኝታ ቤቷን እይታ ዐይኖቿ በዚያው ቦዘዙ፡፡ እጅዋን ስቤ ገላገልኳት፡፡
እናቴ ግራጫ ሹራብ ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጋ ባለ አረንጓዴ ጥለት
ቀሚስ ለብሳ ጸጉሯን በጥቁር ሻሽ አስራ ጋሻዬነህን እንደ ያዘች ከተፍ አለች።
በዚያች ቅፅበታዊ ጊዜ ውስጥ በእናቴ ፊት ላይ ያየሁትን የፈገግታ ፀዳል፡ ነፍስ ካወቅሁበት ጊዜ ጀምሮ አይቼው አላውቅም፡፡ ያልተጠበቀ ደስታ እንዳገኘ ሰው
የማየው ነገር ጠፋኝ፡፡ የወዲያነሽ አንገቷን ሰበር አድርጋ ወደፊት
ተንደረደረችና እጆችዋን በደስታ ከፍ አድርጋ ዘርግታ ወደምትጠብቃት እናቴ በመሄድ ጎንበስ ብላ ጉልበቷ ላይ ልትወድቅ ስትል፡ እናቴ ባልገመትኩት ፍጥነት ለቀም አድርጋ አነሳቻት፡፡ የማየውን ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ
እገላብጣ ሳመቻት፡፡ የየወዲያነሽም እፀፋ ከዚያ የባሰ ነበር፡፡ ነፍሲ ተንፈስ ብትልም ያ ሁሉ በደልና ሥቃይ የደረሰባት፣ የተንገላታችና የተንከራተተችው
የወዲያነሽ፣ በዚህ አኳኋን ከተባባልነው እና ሕሊናዬ ከሚያምንበት ውጪ አጎንብሳ ይቅርታ ጠያቂ በመሆኗ ነፍሴ ምርር ብላ አነባች፡፡ ወዲያ ማዶ
ለመዝለል ከወዲህ ማዶ መንደርደር ግድ ሆነብኝና ነፍሴን በትእግስት አፍኜ ዝም አሰኘኋት፡፡ ቢመረኝም ዋጥኩት፡፡ የእናቴ ዐይኖች የእንባ መዘውራቸውን
ከፈቱ። የጉንጪ ላይ ሽብሽብ የቆዳ ተረትር የእንባ መስኖ ሆነ። የወዲያነሽ ቀና ብላ እንዳታይ የተከለከለች ይመስል በፍርሃት አቀረቀረች። ጋሻዬነህ ጠጋ

👍10❤1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....በአርሲ ጠቅላይ ግዛት በጭላሎ አውራጃ በሄጦሳ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው ኛሮ እንኳን ለአንድ ሽፍታ ይቅርና ለእልፍ አእላፍ ሽፍቶች መሽሽጊያ ሊሆን የሚችል ሰፊ ባህር ነው፡፡ ከትንንሽ ቁጥቋጦ ጀምሮ ሶስት ሰው እጅ ለእጅ ተያይዞ ቢያቅፋቸው የማይሞሉ ከመቶ አመታት በላይ እድሜን ያስቆጠሩ ግዙፍ አገር በቀል ዛፎች የተጠቀጠቁበት ዱር ከመሆኑም በላይ በውስጡ ያሉት እጅግ በርካታ የዱር አራዊቶች ላኛሮ አስተማማኝ የሽፍታ መኖሪያነት በቂ ምስክር ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ዘላይ አራዊት፣
በደረት የሚሳቡ፣ በጉድጓድ የሚኖሩ፣ በየድንጋዩ ውስጥ የሚሹሎከሎኩ
በብዛት ይገኙበታል።አጋዘን፣ ድኩላ፣ የሜዳ ፍየል፣ ሚዳቋ፣ ነብር፣
ከርከሮ፣ ሰስ፣ ቀበሮ፣ ጅብ፣ እባብ፣ ዘንዶ... የሚርመሰመሱበት የቀለጠ
ዱር ...
የሳለን ተራራ እንደሰንሰለት ተያይዞ ሽቅብ ሲታይ ሰማዩን አቅፎና ደግፎ ያቆመው ሲመስል ኛሮ ደግሞ የታችኛው የቆላው አገረ ገዥነቱን ያለተቀናቃኝ ይዞ ተንሰራፍቷል። የተማመነበትን ሙጥኝ ያለበትን ሽሽቶ የተደበቀበትን አሳልፎ እንደማይሰጥ በኩራት ደረቱን ነፍቶ የሚመሰክር ዱር..
ኛሮ ዳገቱ ላይ ቡልቅ እያለ ከመሬት ውስጥ የሚወጣው የእሳተ ገሞራው
ሲስ በአካባቢው አጠራር “አርቱ” ይባላል። መሬቱ ማስ፣ ማስ ይደረግና ጉድጓድ ከተበጀ በኋላ የጉድጓዱ አፍ በጋቢ ወይንም በቁርበት ይሽፈናል። ከዚያ ምን ያስፈልጋል? ከውስጡ ቁጭ ማለት ነው።በዚያ ትኩስ እሳተ ገሞራ ጢስ እየተቀቀሉ እንደ ቅቤ ሲቀልጡ እንደ ዥረት የሚንቆረቆረው ላብ ቆሻሻውን ሙልጭ አድርጎ ይዞት ይወጣል። በዘመናዊ አጠራር “ሳውና ባዝ እንደሚባለው መሆኑ ነው። ኛሮ ለቤተሰብ አባሎቹ ለተለያዩ የዱር አራዊቶች ገነት ነው፡፡ እንደ ፍላጎታቸው ሁሉንም ችሎ
አቻችሎ ይዟቸዋል፡፡ የሚጋጥ ሳር ለሚጠይቀው ከጨሌው ጀምሮ የሰው
አንገት እስከሚውጠው ሰንበሌጥ ድረስ አብቅሎለታል። ሥጋ ለሚፈልገው በውስጡ ያቀፋቸው ሳር በል አራዊቶች በሽበሽ ስለሆኑ አድፍጦ ጉብ ማለት ብቻ ነው የሚያስፈልገው እንጂ በኛሮ በኩል የተጓደለ ነገር የለም፡፡ ኛሮ የገባን ፈልጎ ማግኘት ቀይ ባህር ውስጥ የወደቀ ቀለበት ለማግኘት እንደመፈለግ ሆኖ ዋሻነቱ ይጋነንለታል፡፡
ፀሀይዋ ደማቅ ጨረሯን በመለገሷ ሙቀቷን ለመቋደስ የሚፈልጉ አራዊ
ቶች ከየዋሻው፣ ከየጢሻውና ከየድንጋዩ ውስጥ እየወጡ ብቅ ብቅ ማለት
ጀምረዋል። ከእነዚህ መካከል ኛሮ በአይነቱም ሆነ በአፈጣጠሩ ለየት
ያለውን በሁለት እግሩ ቆሞ የሚራመደውን አውሬ ከነጀሌዎቹ በቤተሰብ አባልነት ከመዘገባቸው ውሎ አድሯል። ጎንቻ ዘረፋውን በስውር በሌሊት ያከናውንና ወደ ሐሮ ጫካ ተመልሶ ይሰምጣል። ከተራ ሌብነት በደረጃ ዕድገት ሽፍታ ተብሏል፡፡
“ጎንቻ! ጎንቻ ጎንቻ” በበርካታ ሰዎች
አንደበት በፍርሃት የሚጠራ ገናና ስም ሆኗል። በድንገት እየተከስተ መአተ ቁጣውን ካወረደው በኋላ በፍጥነት ስለሚሰወር ስሙ ሲጠራ በፍርሃት የሚርበደበዱና ብርክ የሚይዛቸው ሰዎች ቁጥር እየበራከተ ሄዷል። የጎንቻ ስም ሲጠራ ወንዱ ሱሪው ሊከዳው ይዳዳዋል፡፡ ሴቱ ደግሞ “የጎንቻ አምላክ” ብሎ በፍርሀት ያመልክበት ጀምሯል፡፡ በዚህ ሁኔታ የጎንቻ ዝና ከዳር እስከ ዳር አስተጋባ፡፡ ያንን አስከፊ ወንጀል እያፋፋመው ሲሄድ በቸልታ የተመለከተው ሁሉ ቀስ በቀስ በመቅሰፍት ጅራፉ
እየተሸነቆጠ ነው፡፡ የሌላው ህመም ያልተሰማው “እኔ እስካልተነካሁ ድረስ ምን አገባኝ?” በሚል መንፈስ ተሸብቦ የኖረው ሁሉ ከባድ ችግር ውስጥ እየወደቀ መጥቷል። ገና በእንጭጩ በቁጥጥር ስር ማዋል ሲቻል ጎንቻን የቂም መበቀያ ለማድረግ የሁለት፣የሶስት፣ የአስርና የሃያ ዓመት ቂም እየፈለጉ “እገሌ በሙግት ከመሬቴ ከእርስቴ ነቅሎኛልና ንቀልልኝ ቢቻል በራሱ ላይ ባይቻል በንብረቱ፣ በልጆቹ፣ ወይንም ደግሞ በሚስቱ ላይ አደጋ ጣልልኝ፣ እገሌ በህዝብ ፊት ሰድቦ አዋርዶኛልና አዋርድልኝ።
ይህን ያክል ዋጋ እከፍልሃለሁ” የሚሉ አማላጅ የሚልኩ ስዎች እየበዙ
መጡና በትዕቢት ልቡን አሳበጡት። ጎንቻም በድርድር ገንዘብ እየተቀበለ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ባደረገው ጥረት የብዙዎችን አንጀት አራሰ፡፡
አሁን ጎንቻ የዋሻውን ኑሮ እጅግ እየተላመደው መጥቷል። ከሰው ይልቅ
የአራዊት ጠረን ተዋህዶታል፡፡ ከሞቀ ቤት፣ ከሞቀ አልጋ ይልቅ አስፈሪውን ጨለማ፣ዋሻና ጢሻውን የሚመርጥ ሆኗል። ለሰው ልጅ ህይወት ያለው ግምት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ሄዶ የወፍ ያክል እንኳ ዋጋ ሊሰጠው አልቻለም፡፡ ምንም ቢሆን ግን ከአውሬነት ባህሪው ውስጥ ሰው የመሆን ፍጥረቱ ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም ነበረና ዘወትር ዓለሚቱን ያስ
ታውሳታል፡፡ ዘወትር ዓለሚቱን ይራባል፡፡ ይናፍቃታል፡፡ ኛሮ ዋሻ ከገባ በኋላ አንድ ሁለት ጊዜ ጨለማን ተገን አድርጎና ራሱን ለውጦ ጎብኝቷታል፡፡ ይሄ ግን ለሱ በቂ አልነበረም፡፡ ምኞቱና ፍላጎቱ ምንግዜም ከአጠገቡ እንዳትለየው አብራው ጫካ እንድትኖር ነው። እሱ የጫካው ንጉሥ
እሷ ደግሞ ንግስት ሆና ያለ አዛዥ ያለተቆጣጣሪ እያዘዙ እየተቆጣጠሩ
እየነጠቀ እየቀማ በድሎት አብሯት መኖር ይፈልጋል። እንደፈለገው እየበላ እየጠጣ ጥጋብ ሲያንጠራራው፣ እንደ ተዋጊ ኮርማ እያነጠነጠ የወሲብ ፍላጎቱ ሲቀሰቀስ የዓለሚቱ ገላ አእምሮውን እስከሚስት ድረስ በዐይኑ ላይ ይሄድበታል...
በኛሮ ጫካ ውስጥ በጎኑ ጋደም ብሎ፣ ጎፈሬውን ወደ ፊትና ወደ ኋላ
አመሳቅሎ፣ ጠመንጃውን እንደሚሰስቱለት ህፃን ልጅ በደረቱ ሸጉጦ የጠዋቷን ፀሀይ ሙቀት በመጋራት ስለሚያከናውናቸው ተግባራት እቅድ
ያወጣል፣ ያወርዳል። የመልኩ ጥቁረት አይነሳ! ከጥቁር አዝሙድ ጋር ይቀራረባል፡፡ ቁመቱ ረዥም ነው፡፡ ጎንቻ! ጎንቻ!! ጎንቻ! የፍርሀት ጌታ!!... የሰቀቀን አምላክ! በበርካታ ህዝብ አንደበት የሚነገረው ዝናው ሰው መሆኑን እንዲጠራጠር አድርጎታል። “ቀላል እና ከባድ ዘረፋን በመለየት ቀላሉን የዘረፋ ትርዒት የሚንቅ ከባዱን የሚወድ፣ ፈታኝ በሆነ ዘረፋና ግድያ የሚረካ በጥቃቅን
ዘረፋና ሌብነት ላይ እጁን የማያስገባ ዝናው የተፈራ ሽፍታ ሆኖ ለመኖር
ራሱን አሳምኗል፡፡ ከኛሮ አልፎ ግዛቱን ወደ ሌላ አስፋፍቶ፣ ጀሌዎቹን
በእጥፍ ድርብ አበራክቶ ዘረፋውን በማጧጧፍ ሀብታም መሆንን እየተመኘ ነው።
ይሄ ምኞቱ እንደሚሳካ ደግሞ ጥርጥር አልነበረውም፡፡ በተለይ ሰሞኑን
መልእክት የላከበት ባላባት ምን ያክል ለቁም ነገር ተፈላጊ ሰው እየሆነ
መምጣቱን አረጋግጦለታል። ወላጅ አባቱ በቶላ ሞት ምክንያት ተበሳጭተው ራሳቸውን በራሳቸው ያጠፉ መሆናቸውን ከጀሌዎቹ አንደበት በሰማበት ዕለት የቀለደው ቀልድ ጀሌዎቹን ጭምር ያስደነገጠ ነበር። ተበድሮ
ያልመለሰለትን ገንዘብ ሊቀበለው ነው አብሮት የሄደው ከተቀበለው በኋላ
ተመልሶ ይመጣልና አታስቡ በማለት ሊያረጋጋቸው መሞከሩ አለቃቸው
ምን ያክል ጨካኝ ሰው እንደሆነ አረጋግጦላቸዋል። ጎንቻ በደም ስሩ
ውስጥ የሚዘዋወረው የወንጀል ዕፅ የመረዘው መራራ ደም ነበረና የባላባቱን ነገር ሲያብሰለስል ከቆየ በኋላ በአፋጣኝ ሄዶ ማንነቱን ሊያስመስ ክር ፈለገ፡፡ ከዚያም ወደ ጀሌዎቹ ዘወር አለና በደፈረሱት ዐይኖቹ አካባቢውን በመቃኘት ጊርቦን አናገረው፡፡
“ስማ ጊርቦ! የሽማግሌው ጉዳይ?!” አለው፡፡ ጊርቦ አለቃው ጎንቻን በጣም የሚያከብር የሚፈራም ሰው ነው፡፡ በተዘረፈ ንብረት ተሸካሚነትና በወንጀል ተባባሪነት ብቻ ሳይሆን ጠቃሚ መረጃዎችን በመስብስብ በኩል ለጎንቻ ቀኝ እጁ ነው፡፡

👍3
ጉዳዩ ያንተን ፈቃድ ብቻ የሚጠብቅ ነው እኮ ጌታዬ? ቦታው አርባ ጉጉ አውራጃ ውስጥ ነው።ባላባቱ ሚስትህን እናስመልሳለን በሚሉ አጭበር
ባሪዎች ከሶስት ሺህ ብር በላይ ተበልቷል።ሚስቱን መልሰህ በእጁ የምታስገባለት ከሆነ የምትጠይቀውን ገንዘብ ወዲያውኑ ለመክፈል ዝግጁ
ሆኖ እየጠበቀህ መሆኑን ለአቤቱታ የላካቸው ሰዎች አረጋግጠውልኛል'
ከአቋቋሙ ቆፍጠን ብሎ አስረዳ፡፡
ሶስት ሺህ ብር የሚለውን ቃል ሲሰማ ምራቁን ዋጠ። “የተከበረ ባላበት
ነው።ሚስትህን እናስመልሳለን ያሉ አጭበርባሪዎች ገንዘቡን በልተው
ጠፍተዋል።ሚስቱን የምትመልስለት ከሆነ…ይህ አነጋገር ጎንቻ ቃሉን
የማያጥፍ፣ ከፎከረ የማይመለስ፣ ምንም የሚሳነው ነገር እንደሌለ የሚያሳይ ከመሆኑ በተጨማሪ እንደ ቱሬ ባሉ ባላባቶች ዘንድ ጭምር ክብር እያገኘ መምጣቱን የሚጠቁም ነውና ልቡ በኩራት ተሞላች፡፡ አላመነታም፡፡ ሌሎች መፈፀም ያቃታቸውን ጀብዱ ፈፅሞ ሽማግሌውን ባላባት ለመካስና ማንነቱን አስመስክሮ ጥሩ ክፍያ ለመቀበል ተቁነጠነጠ፡፡
“የምጠይቀውን የሚከፍለኝ ከሆነ በጉዳዩ መስማማቴንና በሶስት ቀን ውስጥ ፈቃዱን ፈፅሜ ውጤቱን የማሳየው መሆኑን ለላካቸው ሰዎች አስረዱና በኔ ስም ቃል ይገባለት!” አንዴ ወደ ቱሲ አንዴ ወደ ጊርቦ መለስ ቀለስ አለና ደረቱን ነፋ አደረገ፡፡ ወዲያውኑ ግን አንድ ሀሳብ መጥቶ ድቅን አለበት። ባላባት ቱሬና ባላባት ጉደታ የማይዋደዱ ቢሆንስ? ከባላባት ጉደታ ጋር መቀያየሙ ነው፡፡ “ቆይ! ቆይ! መጀመሪያ ባላባት
ጉደታ ተቃውሞ ያለው መሆን አለመሆኑን ላረጋግጥ።እሱን ካረጋገጥኩ በኋላ በመልዕክተኛ ሳይሆን እኔ ራሴ ሄጄ በግንባር ባነጋግረው ይሻላል”
በማለት ሃሳቡን ቀየረ፡፡
“መልካም ሀሳብ ነው ጌታዬ እኔም ትንሽ ቅር ያለኝ እሱ ነበር። ምናልባት ባላባት ጉደታ በጉዳዩ የማይስማማ ከሆነ ከመቀያየማችሁ በፊት መወያየቱ መልካም ነው” ቱሲ የከነከነውን ጉዳይ አስረዳና የአለቃውን ሀሳብ ደገፈ፡፡
“ልክ ነህ! ባላባት ጉደታ የሚስማማ ከሆነ በስማበለው ሳይሆን እኔ ራሴ
አርባጉጉ ሄጄ ሽማግሌውን አነጋግረዋለሁ። ፍላጎቱን በሚገባ ለማወቅና የሚከፍለኝን ክፍያ ለመወስን ሽማግሌውን በግንባር ቀርቦ ማነጋገሩ ይመረጣል” አለና ውለታ ውስጥ ከመግባቱ በፊት የባላባት ጉደታን ይሁንታ
ለመጠየቅ በሌሊቱ ጉዞ ጀመረ፡፡ አገር አቋርጦ ሄዶ ስለሚፈፅመው ጉዳይ
አስረድቶ ባላባቱ “ሂድ ግፋበት ይቅናህ” ብሎ የሚመርቀው ከሆነ ሊሄድ
“አይሆንም ለባላባት ቱሬ ምንም አይነት የበቀል ቅጣት እንድትፈፅምለት
አልፈቅድም” የሚለው ከሆነ ደግሞ ውለታ ውስጥ ላለመግባት ቃሉን
ሊሰማ ሄደ፡፡ ባላባት ጉደታ ግን የባላባት ቱሬን ደመኛ ጠላት እንደ ራሱ ጠላት የሚቆጥረው መሆኑን፣ባላባቱ የቅርብ ወዳጁ እንደሆነና በሚፈልግው የብቀላ አይነት ጠላቱን ቢቀጣለት ደስተኛ መሆኑን አረጋገጠለት፡፡
የጎንቻ መቅስፍት በጠራራ ፀሃይ እንደሚወርድ መብረቅ የሚቆጠር
መሆኑን በተደጋጋሚ አስደንጋጭ ወንጀሎች እያስመሰከረ ሲመጣና
የጎንቻ አምላክ” ተብሎ ሊመለክበት ሲቃጣው ባላባት ጉደታ ከፍርሃቱ
ጋር ተዳምሮ ከጎንቻ ጋር የጀመረውን ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ አሽጋግሮት ነበር፡፡ ጎንቻም ከባላባቱ ጋር ወዳጅነቱን የበለጠ ቢያጠናክር ለውንብድና ስራው እጅግ አስተማማኝ መከታ እንደሚሆነው በማመኑ ተገዥነቱን በመሀላና በተግባር ከማረጋገጥ ባሻገር ለሚፈጽመው ወንጀል በቅድሚያ የባላባቱን ፍቃድ እስከመጠየቅ በሚደርስ ውለታ ትስስር ፈጥሮ ነበር።በዚሁ መሰረት በለሊቱ ገስግሶ ባላባት ጉደታ ዘንድ ቀረበና “እንዲህ አይነቱን ድርጊት ልፈፅም ነውና ፍቃድህን? አሊያም ደግሞ ተቃውሞ
ህን” ሲል ጥያቄ አቀረበለት፡፡ ባላባቱ ምንም ሳያወላውል፡
"ሂድ! ግፋበት!ይቅናህ!" ሲል የይለፍ ካርድ ሰጠው፡፡ጎንቻ ረጅሙን የጫካ ኑሮ ለማደራጀት ያቀደው በባላባቱ ሙሉ እምነት ስላደረበት ጭምር ነው። ባለፉት ከፈፀማቸው ከባድ ከባድ ወንጀሎች
ውስጥ ግማሾቹ በራሱ በባላባት ጉደታ ትዕዛዝ የተፈፀሙ ነበሩ። ጎንቻ በወር በሁለት ወር ውስጥ ጨለማን ለብሶና ጨለማን ተንተርሶ ከባላባት ጉደታ ጋር በስውር እየተገናኘ ይመለሳል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ራሱ ባላባት ጉደታ እስከ ዋሻው ድረስ እንደ ቅቤ የቀለው ሙክቶችን ይልክለታል።
ግብር አንገብርም ሲሶ አናርስም የሚሉ አመፀኞች በጎንቻ ድንገተኛ ቡጢ
እንዲመቱ በሱ ግዛት ውስጥ ጣልቃ ለመግባት የሚሞክሩ ተቀናቃኞች
ሲገኙ በጎንቻ ክርን እንዲደቆሱ ባላባቱ ጎንቻን አለኝታና መከታ ስላደረገው ጎንቻ በሽፍታነቱ እንዲገፋበትና የልብ ልብ እንዲስማው አድርጎታል፡፡ በዚሁ መሰረት አርባ ጉጉ አውራጃ ውስጥ የሚኖረው ባላባት ቱሬ ጠላቱ ጃኖን እንዲበቀልለት ለጎንቻ ጥያቄ ሲያቀርብለት የእሺታ መልሱን ከመስጠቱ በፊት ባላባት ጉደታን አማክሮ ሂድ ይቅናህ የሚል ቡራኬውን
ስላገኘ ራሱን ለበቀል ማዘጋጀት ጀመረ፡፡
ከተቀመጠበት አለታማው ድንጋይ ላይ በድንገት ቱር.! ብሎ ተነሳ። አንገቱን ቀና ደፋ! ቀና ደፋ! አደረገና ጎፈሬውን እንደሚያራግፍ አንበሳ ሹሩባውን አርገፈገፈው፡፡ አነሳሱ የጤነኛ ሰው አይመስልም፡፡ እንደ ጉሽ ጠላ
የደፈረሱ ትላልቅ ዐይኖቹ ደም ለብሰው ደም ጎርሰዋል፡፡ ድርጊቱ ሰው የመሆን ባህሪውን የተነጠቀ አዲስ የጫካ ፍጡር አስመስሎታል፡፡ የቀወሰ ይመስላል። ጊርቦና ቱሊ ተስፈንጥሮ ከአጠገባቸው ሲነሳና ረጅም ሹሩባውን ሲያርገፈግፈው ደነገጡ። ያንን ከውስጡ አምጣ አምጣ እያለ እንደ ቡና ሱስ የሚያዛጋ፣ የሚያንጠራራ ስሜቱን ለማስታገስ በእነዚያ ተቅለብላቢ ጣቶቹ ምንሽሩን አቀባበለና ጢሻ ለጢሻ እየተሹለከለከ ተሰወረ ከዐይናቸው ብዙም አልቆየም፡፡ ወዲያውኑ የተኩስ ድምፅ ተስማ። “ኢልመ ቦሩ "አለና ፎከረ። ዒላማው ለጉድ ነው፡፡ ክር ይበጥሳል። ጤዛው ያልረገፈ
ጨሌ እየቀነጣጠበች የነበረችውን ሚዳቋ መሀል ግንባሯን ሲበጠርቃት ሚዳቋ ወደ ሰማይ ወጥታ ተፈጠፈጠች፡፡ ከመቅፅበት ደርሶ በግራ ጎኑ ላይ አጋድሞት የነበረውን ካራውን መዘዘና ጉሮሮዋን በጠሰው። ከዚያም አፉን በጉሮሮዋ ላይ ለጉሞ ትኩስ ደሟን ምጥጥ አድርጎ ጠጥቶ አጠነፈፈና ወደዚያ ወረወራት፡ የአሁኑ ድርጊቱ ደግሞ የሰውነት ባህሪውን ክዶ ወደ ነብርነት የተለወጠ አስመስሎት ነበር፡፡
በዛሬው ዕለት ብዙ ብር የሚያስገኝለት የባላባት ቱሬን ባላንጣ ደም በሚዳቋዋ ደም ውስጥ እንደጠጣ ሁሉ የበቀል ጥሙን ቆረጠለት። በተላከበት
ሁኔታ ደርሶ የቱሬን ባላንጣ አንገቱን ጠምዝዞ ጉሮሮውን ለመበጠስ፣
ደሙን እንደ ውሃ ለማፍሰስ ተጣደፈ፡፡
“ባላባት ጉደታ ድርጊቱን አፅድቆለታልና ባላባት ቱሬን በግንባር ለማነጋገር
እንደተለመደው የሌሊት ጉዞውን ጀመረ ጀሌዎቹን እንዳስከተለ ነው፡፡ አሁን አሁንማ ዐይኖቹ በጨለማ ውስጥ የማየት ችሎታቸው እያደገ መጥቶ በዚህ ፀባዩ ደግሞ የጅብ ዝርያ ያለበት ሊያስመስለው ተቃርቧል፡፡
ብቻ ጎንቻ ከዚህም ከዚያም የተጠረቃቀሙ የልዩ ልዩ አራዊቶች ባህሪ
የተጠናወተው አዲስ ፍጡር ሆኗል።
ጎንቻ በዛሬው ዕለት ሊያነጋግረው የሚመጣ መሆኑን አውቆ እንዲዘጋጅ
ለባላባት ቱሬ መልዕክተኛ ተልኮበታል። ባላባት ቱሬ መልእክቱ እንደደረሰው ያንን ዝናው ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ያስተጋባ ሽፍታ ለማነጋገር ሽር ጉድ ሲል አመሽ፡፡ ጎንቻ በውድቅት ለሊት ከባላባቱ እልፍኝ ሲደርስ እንቅልፍ አጥተው የሚጠብቁት ባለጉዳዮች በከፍተኛ አክብሮትና በአጀብ

❤1👍1
አቀባበል አደረጉላት። ባላባት ቱሬ ቁጭ ብድግ አለበት። ሰገደለት። ጎንቻ ዘወትር ጠንቃቃነትና ተጠራጣሪነት የማይለየው ሰው ነው። ቀምንም ዓይነት አይዘናጋም። ሲቀመጥ እንኳ ግድግዳ ተደግፎ ፊት ለፊቱን በሚገባ እየተቆጣጠረ ነው። ምንሽሩን እንዳቀባበላት ነች። ጣቶቹ እንደ
ወትሮው ከቃታው አካባቢ አልራቁም፡፡ እንኳንስ ሌሎቹን የራሱን ጀሌዎችም ስለሚጠራጠራቸው አይዝናናም፡፡
ወዲያውኑ ለክብሩ ሲባል ተዘጋጅቶ የነበረው በሬ የሚያክል ነጭ ቅጥቅጥ
የፍየል ሙክት ተባረከና ግብዣው ተጧጧፈ፡፡ ሽብ ረብ ሆነለት። የሁሉም
ሆድ የቀራጭ አቅማዳ እስከሚመስል ድረስ ጠገቡ፡፡ ተንቀረበቡ። የሚጠጣው ቢለዋ የማይቆርጠው እርጎ ነበር። ጎንቻ በአናቱ ላይ ቅቤ ተመረገበት፡ ቅቤው ጥምጥም የጠመጠመ ቄስ እስከሚያስመስለው፣ ለሸክም እስከሚከብደው ድረስ በጎፈሬው ላይ ተቆለለበት፡፡ የጥፋት መልዕክቱን
ፈፅሞ በድል እንዲመለስ የመልካም ምኞት መግለጫ መሆኑ ነው። ይሄ
ሁሉ ሥነ ሥርዓት ተከናውኖ እንዳበቃ “እሺ ወደ ዋናው ቁም ነገራችን
እንመለስ!” አለ ጎንቻ፡፡
ባላባት ቱሬም በገበታው ላይ ከነበሩት መካከል የቅርብ አማካሪዎቹ ብቻ
እንዲቀሩና ሌሎቹ ከክፍሉ እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዋናውን ጉዳይ በቤቱ ውስጥ የነበሩት በሙሉ በልባቸው የሚያውቁት ቢሆንም እንደ አዲስ ዐይኖቻቸውን አፈጠጡ። በተለይ ባላባት ቱሬና አማካሪዎቹ ከዚያ ዕይኑ ከሚያስፈራ፣ ስራው ከሚያስደነግጥ ሽፍታ አንደበት የሚወጣውን ቃል፣ የሚወጣውን አስፈሪ ንግግር ለመስማት ከፊል ፍርሃት ከፊል አድ ናቆት በተቀላቀለበት ስሜት አሰፈስፉ።....

😁1
#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
....ጋሻዬነህ ከእናቴ ጋር ውሉ አደረ፡፡ የየወዲያነሽ የእናትነት አንጀት በናፍቆት ተላወሰ፡፡ ሮብ ጧት ለቁርስ እንደ ተቀመጥን «ምነው ዝም አልክ ጌታነህ? ረሳኸው እንዴ? ከጋሼ ጉልላት ጋር ምን ምን ነበር የተባባላችሁት?
ሂድና አምጣው እንጂ» አለችኝ፡፡
“ምናልባት ዛሬ የውብነሽ ታመጣው ይሆናል» አልኩና እንደገና ደግሞ
«ምናለባት ጋሻዬነህን ለእነርሱ ብንሰጣቸውና እኔና አንቺ ደግሞ….ሌላ» ብዬ ንግግሬን ሳልጨርስ ደረቷን ሁለት ጊዜ በጥፊ ደቃችና «ህ! እንዴት ያለህው ዓለመኛ ነህ! ምነው ምን በወጣኝ! ዕድሜ ላንተ እያልኩ ዐይን ዐይኑን እንዳላይ ነው!» ብላ ከነጥርጣሬዋ ዝም አለች።
ሐሳብን ማሻሻልና ፈጽሞም መለወጥ አንድ ዐይነት ዕድገት በሆኑ የሐሳቧ መለወጥና ተቃውሞዋ ደስ አለኝ፡፡ ለጥያቄዋ መልስ ሳልሰጥ ወደ ሥራ ሄድኩ፡፡
የውብነሽ ቀንም ሆነ ማታ ብቅ ሳትል ቀረች፡፡ የሮብ ጀንበር ጠልቃ የሐሙሷ ተወለደች፡፡ አዲሱ የፍርሃት ሸክም ከየወዲያነሽ ይልቅ እኔን ከበደኝ፡፡ ከማታ
ትምህርት መልስ ሻይ እየጠጣን ስናወራ አንዱን ተረስቶ የቀረ የጋሻዬነህን የሒሳብ ደብተር እያገላበጠች «እሷ መች ሥራ አጣችና ነው ይዛው ትመጣለች
የምትለው? እኔ እኮ ነገሩ የገባኝ የመማሪያ ደብተሩን ይዛ ስትሒድ ነው» ብላ ወደ ራሷ ደብተሮች መለስ አለች፡፡
«እኔን ያሠጋኝ ሌላው አይደለም.....አባባ ይመለሳል ከተባለበት ቀን ቀደም ብሎ ቢመለስና ይኸ ልጅ የማን ነው ልጅ? ብሎ ቢጠየቅ ምን ይላሉ?
እናቴ ገና እንማከራለን ነው ያለችኝ እንጂ ሌላ የተነጋገርነው ነገር የለም ከማለቴ፣ የማን ልጅ እንዲባልልህ ትፈልጋለህ? የጌታነህ ልጅ ነው ብለው
ይነግሩልሃላ» ብላ ኩታ አጣፍቶ የመልበስ ያህል ጉዳዩን አቃልላ መለሰችልኝ።
«እንዴት አንቺ? እኔ እኮ ገና ብዙ ግብግብና ትግል ይጠብቀኛል።
የሙሉ ድሌ ቀኔ ገና ነው:: ምኑ ተያዘና!ምኑ ተነካና! እንዴት አድርጌ እንደምገጥመውና ድል እንደማደርገው ዕቅድና ብልሃቴ አልተጠናቀቀም፡፡ወደፊት የሚቀረኝ የትግል ጉራንጉር ያለፉትን የመከራና የትግል ገድሎች ሁሉ ሊያጠቃልል ይችላል፡፡ ቀሪው ትግል በዕድልና በአጋጣሚ የማምንበት ነገር
የለም፡፡ የሚጠብቀኝ ውጣ ውረድ ሁሉ በበቂ ምክንያትና በተግባር የሚመራ ነው። «የዘልማድ ዝላይና ባወጣ ያውጣኝ በቃው! በቂ ምክንያት ጥሩ የተግባር
ዋስትና» ብዬ በመጀመር ለወደፊት ከሚያጋጠሙኝ አንደንድ ችግሮች መኻል አንዳንዶቹን በከፊል አዋየኋት፡፡
ዓርብ ከጧቱ ሁለት ሰዓት ላይ የውብነሽ ጋሻዬነህን ይዛ መጣች።
የሚያምር አዲስ ልብስ ለብሶ
ከፈገግታው ጋር ሲታይ የመስከረም ዝናብ ያጠባት
የለጋ ዘንባባ ተክል መስሏል። የወዲያነሽ ግልገሏን አስከትላ ጢሻ ውስጥ እንደምትገባ ሰስ ልጅዋን አስከትላ ወደ ጓዳ ገባች። እኔና የውብነሽ ወጣ ብለን ሰበሰቡ ላይ እንደቆምን «አባባ የነገ ሳምንት ከሰዓት በኋላ ይገባል፡፡ ባለቢትህን እንዴት አድርገን እሱ ፊት እንደምናቀርባት፡ አንተም ምንና ምን እያልክ መናገርና ማስረዳት እንዳለብህ አንድ ባንድ አውጥተን አውርደን ጨርሰናል» ብላ ስለ እኛ ሕይወት እኔና ባለቤቴ ያልተካፈልንበትን የአፈጻጸም ዕቅድ አረዳችኝ፡፡
የችግሬን ዐይነትና ዓላማዬን የማውቀው እኔ ሆኜ ሳለሁ መወከልና ማስፈጸም
የማይገባቸው እኅቴና እናቴ አፈ ቀላጤ ሆነን እንገኝ ሲሉ በመስማቴ ተናደድኩ፡፡
አልተዋጠልኝም፡፡
የአባቴ ግብዝነትና ቁጣዉ፣ ግትርነቱንና የመጣ ይምጣ ባይነቱ፣ እንደ ጨካኝ አገረ ገዢ ፊት ለፊት ቆሞ እንደ እሳት ፈጀኝ፡፡ «ማታ ከትምህርት ቤት
መልስ ከየወዲያነሽ ጋር እንድትመጡ፣ ነገሩን አብራራልሃለሁ። አሁን ግን
ቸኩያለሁ ደኀና ዋል» ብላኝ ቶሉ ብለህ ና እንደ ተባለ መልእክተኛ ጥላኝ ሄደች። አእምሮዬ በሐሳብ ተወቃ፡፡ ሁለመናዬ ብው ብሎ ጋመ፡፡ አዳዲስ ጭንቀቶች በውስጤ ተራወጡ፡፡ የሐሳቤ አድማስ ለመጥበብም ሆነ ለመስፋት ባለመቻሉ መረጋጊያ አጣሁ፡፡
ጎርፍ እንደ ገረሰሰው ዛፍ ግድግዳውን ተደግፌ ቆምኩ፡፡ የወዲያነሽ ከወደ ውስጥ መጥታ «ከምን ጊዜው ሄደች? ያንተ ነገር እኮ...አናደድካት እንዴ?» ብላ
በሥጋት አዘል ሁኔታ ጠየቀችኝ፡፡ «ቸኩላ ነበር፡ ታናድደኛለች እንጂ ምን አናድዳታለሁ፡፡ የማይጠቅሙሽ እጠቅምሻለሁ፣ የሚያጠፉሽ አለማሻለሁ፣
የሚገድሉሽ አድንሻለሁ ሲሉሽ አትናደጂም? አሁን የነገረችኝን ማታ ስትነግረኝ ትሰሚያታለሽ፡፡ አሁን ወደ ሥራሽ ሂጂ» ብያት ዝም አልኩ፡፡ የእርሷ ከአጠገቤ
ገለል ማለት የሚረዳኝ ስለ መሰላት ተመልሳ ገባች፡፡ በአካባቢዬ የሚገኙት ነገሮች
ሁሉ ለችግሮች ማቃለያ የሚሆን ብልሃት ያቀርቡልኝ ይመስል ትክ ብዬ አየኋቸው:: ሆኖም ከበድን መልስ የለምና አፍጥጨ ቀረሁ። ሳላስበው ከቤት ወጣ ብዬ ቆምኩ፡፡ የማለዳዋ ፀሐይ ደጋናማ ጉዞዋን ጀምራለች፡፡ ደመና የማይታይበትን ሰማይ ትኩር ብሎ ላየው ኣስፈሪነቱ አይጣል! ዘልዓለም የሚሉት ይህን ርቀትና
ጥልቀት ይሆን? አንጋጥጬ ስመለከት ሐሳብ አሽቆልቁሎ አየኝ፡፡ አካባቢዬን ፈራሁት፡፡ ጥቂት ርምጃ ተራምጄ ግቢው መኻል ተገተርኩ፡፡ ከመሬት ውስጥ
መልስ ይፈልቅልኝ ይመስል ደቃቁን አፈርና ኮረት ባይኔ ሰለልኩት። ቀዝቃዛና ለስላሳ ትንሽ እጅ የቀኝ እጄን ከበስተኋላዬ ስትነካው ከፍዘቴ ነቃሁ። ጋሻዬነህን እጁን ስቤ ወደፊት አዞርኩት፡፡ ከፍ ብለው የሚበርሩ አዕዋፋትን እንደሚከታተል
ወፍ ጠባቂ ዐይኖቼን አሻቅቦ ከፈለገ በኋላ ና ቶሎ! አሁኑኑ ና ቶሎ ብላሃለች እማማዬ» ብሎ መልሴን ለመስማት ኣፉን እንደ ከፈተ ዝም አለ፡፡ ከቁመቱ ጋር ለማስተካከል ጉልበቴን አጥፈ ቁጢጥ አልኩና፣ እኔን ነው እማማዬህን ነው የምትወደው ጋሻዬነህ?» አልኩት።ፊቱ በፈገግታ ፈክቶ የደብር ጉልላት የሚመስሉት ዐይኖቹ በሰፊው ተከፈቱ። «አንተንም እማማዬንም እወዳችኋለሁ...ያንን ቀይ ሽጉጥ እገዛልሃለሁ አላልከኝም ነበር፡ መቼ ትገዛልኛለህ?» ብሎ ዐይን ዐይኔን ሲያይ ዐይኖቹ በዐይኖቼ ውስጥ ሠረጉ፡፡ ትልቋ እማማስ እዚያ ትልቁ ቤት ውስጥ ያየሃቸው
የእኔ እናት አያትህ ጥሩ ናቸው? በል እስኪ ንገረኝ፡ ያንን ሽጉጥ እንድገዛልህ?»አልኩት። ከንፈሩን ትንሽ ሾል ካደረገ በኋላ «እሳቸው ደግሞ በጣም ደስ ሊሉኝ፡
ጥሩ ናቸው፡፡ ያንተ እማማ ናቸው እንዴ? እወዳቸዋለሁ» ካለ በኋላ ትልቅ በመሆኔ ከእናት ያልተወለድኩ ይመስል አወጣጧ የምታምር ሞንሟና ሣቅ ሣቀ።
«እስኪ ትወደኝ እንደሆነ ሳመኝ?» አልኩት፡፡ ጉንጩን ተራ በተራ ሳመ። «ኧረ እባካችሁ ኑ ግቡ! እባትና ልጅ ምን ትማከራላችሁ? እኔ እንዳልሰማችሁ ነው?» የሚል ድምፅ ከወደ ቤት ተሰማ፡፡ የወዲያነሽ ፍቅራዊ ትእዛዝ ስለሆነብኝ ጋሻዬነህን ይዤ ገባሁ፡፡ ቁርስ ይዛ ከተፍ አለች፡፡ የጀመረችውን ሥራ ለመዉረስ
መለስ ስትል «በይ አንሺና ይዘሽው ሂጂ!» ብዩ የካንገት በላይ ቁጣን በሚገልጽ
ስሜት ተናገርኩ፡፡ ደንገጥ ብላ ተመለሰችና «ምነው? ምን አጠፋሁ? የት ልሄድ
ነው? እደርሳለሁ ብዬ ነው ! » በማለት በፍርሃት ሳይሆን በፍቅራዊ ስሜት ትኩር

👍6
ብላ አየችኝ። «የምን እደርሳለሁ ነው? እኔና ጋሻዩነህም እምብርት አለን። ነይ ቁጭ በይ!» ብዩ ከመናገሬ ተቀመጠች። ለሦስት ጠመድነው፡፡ ከቁርስ በኋላ
እናትና ልጅ ጥለውኝ ወጡ፡፡ ከዕለቱ ሥራ በገዛ ፈቃደ ቀረሁ። ዕቃ እንደ ጠፋበት ሰው በክፍሉ ውስጥ ስንቆራጠጥ ከሩብ ሰዓት በላይ አለፈ። አንጎሌ ውስጥ
ልዩ ልዩ ሐሳብ ተፍለቀለቀ። ሠልፍ እንደሚጎበኝ የጦር መኮንን ከወዲያ ወዲህ ተዘዋወርኩ። እግሮቼን እንደ ባላ እንጨት ገትሬ «ከእንግዲህ ወዲያ በሕይወቴ
ውስጥ ራሴ ለራሴ ውሳኔና ምርጫ ውሳኔ ሰጪ መሆን አለብኝ፡፡ ለብዙዎች
በሚስማማ ጎዳና ላይ እንጂ በግሌ ጎዳና ላይ አልጓዝም፡፡ የብዙሃኑ ጥንካሬና የሐሳብ አንድነት ለእኔ የትግል ፅናት መሠረቴ ነው። ይህ የእኔ ችግር በየቦታው አለ፡፡ መበታተን መሽነፍ ነው:: የራሴን ትክክለኛ እምነት ከሌላ ትክክለኛ አስተሳሰብ ጋር ማዋሐድ አለብኝ፡፡ አድራጎቴ ሁሉ ለግላዊ ነጻነቴ ከሆነ አሁንም
ዙሪያዩ በባርነት የተካበበ የተሸናፊነት መፈንጫ ይሆናል። ሐሳቤን ሁሉ እየቀረጣጠፈ የሚበላው ፍርሃት ነው:: በሕይወቴ ታላቁ ጠላቴ ፍርሃቴ ነው። ይህ ከሰንካላው አስተዳደጌ ያገኘት ሕሊና ሰባሪ ቀንበር ተሰባብሮ መውደቅ አለበት።
የወዲያነሽን ያጠቃትና ያስጠቃት የበታችነት ጨቋኝ ባህሪ በእኔም ውስጥ ተዘርቶ በቅሏል። ነጻ የሚወጡት የወዲያነሽና ጋሻዬነህ ብቻ አይደሉም፡፡ እኔ ራሴ ገና ነጻ አልወጣሁም፡፡ ራሱን ነፃ ያላወጣ ወይም ለማውጣት ያልተነሳ ዜጋና
ትውልድ ለሌሎች ነፃነት ሊቆም አይችልም፡፡ ስለዚህ ለእነርሱም ለራሴም እዋጋለሁ፡፡ ከእንግዲህ ያላግባብ የሚፃረሩኝን ሁሉ እቋቋማቸዋለሁ። እዋጋቸዋለሁ።
ከእንግዲህ ወዲህ ቀጥ ብዩ እራመዳለሁ። ይህም ለትምክህትና ለትዕቢት ሳይሆን
መኖሬን ለዘነጉት ሁሉ የትክክለኛ ማንነቴን ማሳወቂያ አርማ ነው:: ብቻዬን የማደርገው ማናቸውም ዐይነት ትግል ቅንጣት ፋይዳ አያመጣም ይሆናል። ሆኖም ሁላችንም ነጻ የምንወጣው በሁላችንም ትግልና ግብግብ ነው። ስለዚህም የነጻነት ቦይ ሲቆፈርና የነጻነት ሜዳ ሲደለደል እኔም ድርሻዩን ለማከናወን
በንቃት መሳተፍ አለብኝ፡፡
"አባቴ ቢሰማም ባይሰማም ግድ የለኝም። ቢደሰትም ቢከፋም ደንታ
የለኝም! በከንቱና ፍሬ ቢስ በሆነ ነቀፌታ አላምንም፡፡ በቂ ምክንያትና ሐቅን ይዞ
በእውነተኛነት ከመፋጠጥ የበለጠ አስደሳች ነገር የለም፡፡ ዓላማ የሰው ልጅ የኑሮ ለውጥ መሰላል ነው:: አባቴም ቢሆን ውሳኔዬን ማወቅና ጉዳዬን ማየት እንጂ
ከእንግዲህ ወዲህ ይኸ ወለገደ፣ ያኛው ቀና ብሎ በእርሱ ስንኩል እምነት ሊመራኝ አይገባም። አልመራለትምም:: ሕሊናዬ ለማናቸውም ዓይነት አምባገነንነት መንበርከክ የለባትም" ! በሐሰት አዳራሽ ውስጥ ከመኖር በደሳሳ የሐቅ ጐጆ ውስጥ መተሳሰብ ይበልጣል። የሐሰት ዕድሜዋ አጭር ነው:: እውነት ያለችው ከእኔና ከየወዲያዩ ጋር ነው:: በቃ! ማሳወቅ ብቻ! ማብሰር ሳይሆን
ማርዳት! ከእንግዲህ አባቴ የእኔንና የባለቤቴን ጋብቻ አጽዳቂም አፍራሽም ሊሆን
አይችልም በማለት በአንጎሌ ውስጥ ያውጠነጠንኩትን ሐሳብ ጮክ ብዬ ተናገርኩ «የሚሆነውን ነገር ራሱ መርጦ ራሱ ውሳኔ ለመስጠት የማይችል ሰው
ምነኛ የተበደለ ነው:: በቃ! ቅርንጫፍነት በቃኝ! እኔው ራሴ ሥር ሰድጄ መብቀልና ጠንካራ ግንድ መሆን አለብኝ! ከእኔ የሚገኙትንም ቅርንጫፎች
መሽከምና ነጻ ማውጣት ይገባኛል! » ካልኩ በኋላ የተዳቀቀውን አካላቴን ለማፍታታት ተንጠራራሁ፡፡ ያ ሁለ ሲያስጨንቀኝና ሲያስፈራራኝ የኖረ
ምስቅልቅል ሐሳብ አብሮ አደጌ በመሆኑ ከውስጤ እየፈለቀ የሚያሠቃየኝ ከንቱ ነገር እንጂ ሕሊናን የሚያለመልም ጸጋ አልነበረም፡፡ ሆኖም ለፍርሃቴና ለጭንቀቴ መነሾና ሰበብ የሆኑ ሁኔታዎች እንዳሉና ሕሊናዊ መብቴን የገፈፉኝ ጨቋኝ
ልማዶች አብረውኝ እንዳደጉ አወቅሁ፡፡ ኦና ቤት ውስጥ ቆሞ እንደሚለፈልፍ ወፈፌ እግሬን አንፈራጥጨ ቆምኩ፡፡ እስክስታ እንደሚወርድ ሰው ወገቤን በሁለት እጄ ያዝኩ፡፡ ጩኸት በራስ የመተማመን ወኔና ችሉታ ይሰጠኝ ይመስል የቤቱ ውስጥ ዕቃዎች ድምፄን እስኪያስተጋቡ ድረስ «እኔ የከዚህ ቀደሙ እኔ መሆን
የለብኝም! ሌላ አዲስ ከዚህ ቀደም ያልነበረ የሕይወት አመራር ጉዳናና እምነት የሚኖረኝ ሌላው የተሻሻለውና የተለወጠው ጌታነህ ነኝ! ከበላዬም ሆነው ከበታቼ
በደፈናው ከአካባቢዬ የሚመጡብኝን ጎታችና አውዳሚ ተግባሮች ሁሉ በሕዝባዊ
ስልት እና አሠራር ለራሴና ለሌሎች ነጻነት እዋጋለሁ፡፡ሕሊናዬን ተጭኖት አንደበቴንም አፍኖ እንዳልናገር ያገደኝን ማናቸውንም የባሕል ዐይነትና ልማድ ሁሉ እጋፈጠዋለሁ፡፡
በሚያስገኘው ውጤት ካልተስማማሁ ደግሜ ደጋግሜ እጥሰዋለሁ፣ እጥሰዋለሁ፡፡ ከእንግዲህ ብቻዬን አልቆምም! ትክክለኛ ያልሆነ መነጠል መበደል
ነው!» ብዬ ጓጎርኩ፡፡ ከራሱ በቀር ሌላ ሰሚ በሌለበት ቦታ መሰንቆ እንደሚመታ አዝማሪ የእኔንም ጩኸት በእኔው ብቻ ተሰምቶ ቀረ፡፡ ባለቤቴና ልጄ ኡኡታ
ሰምቶ ለርዳታ እንደሚሮጥ ሰው
በሩጫ ገቡ። ያሰማሁት ጩኸትና በፊቴ ላይ የሚታየው የቁጣ መልክ አስደነገጣት፡፡ ጋሻዬነህም እናቱ አጠገብ ቆሞ በፍርሃት
ይመለከተኝ ጀመር፡፡ ከበፊቱ በበለጠ ተንፈራጥጬ «አንቺ ከአሁኗ ሰዓትና ደቂቃ
ጀምሮ የነጻነት ትግል ትጀምሪያለሽ! ለአንተም ከዛሬ ጀምሮ ነጻ የምትሆንበትንና
ወደፊት መልካም ሕይወት የምታገኝበትን የኑሮና
የምትጎናፀፍበትን መንገድ ሁሉ በትግል እንቀይስልሃለን፡፡ ቅይሱን ከፍጻሜ የምታደርሱት አንተና መሰሎችህ ናችሁ! እኔንና ሌሎችን ካሠቃዩን የኑሮ አደጋዎች የምትድንበትን መንገድና ትክክለኛ ዘዴ እንድታገኝ እታገላለሁ!
እያንዳንዱ በየአካባቢው ባንድነት ከተነሣና ከተጠቃለለ፣ የማይስማማውንም ተገቢ
ያልሆነ ሕግና ልማድ ሁሉ ለመለወጥ በእንድነት ከታገለ፣ ሌላ አዲስና የተሻሻለ የሕይወት ጎዳና ያለው ትውልድ ሊኖረን ይችላል። መልካሙን ሁሉ መርጦ
የመቀበልና አስፈላጊ ያልሆኑትን ሁሉ መንግሉ የመጣል፣ በምትኩም ሌላ የመፍጠር እና የመገንባት አጠቃላይ ግዴታ አለብን፡፡ ሁላችንም ለየግላችን እና
በተናጠል መወጋት የለብንም፡፡ ሁላችንም ስለ ሁላችን የጋራ ነፃነትና ድል በአንድነት ታጥቀን መሰለፍ ይገባናል ያነዬ ድሉ የሁላችንም ይሆናል!» ብዩ
የማይገባቸውን ሁሉ ተናግሬ አደናርኳቸው:: በዚህ ዐይነት ደፋር አነጋገር ከራሴ ሐሳብ ጋር በግልፅ አምርሬ ስጋጭ የመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ እኔኑ መልሶ አስደነቀኝ።
ይኸው ድንገተኛ ሁኔታዬና ልፍለፋዬ ምን እንደሆነ ግራ የገባት የወዲያነሽ በፍርሃት ሳይሆን በርኅራኄና በአዘኔታ ተመለከተችኝ፡፡ አዎ የአንድ ጤነኛ ሰው የሕሊና ፈተና ነበር፡፡ በመካከላችን ረመጥ የፈሰሰ ወይም ጥልቅ ገደል የለየን ይመስል ካለችበት ሳትላወስ «ምን ሆነሃል ዛሬ? ምን ነካህ ጌታነህ?»
አለችና ፈገግታዋ እንደ ከዚያ ቀደሙ የሚያስደስተኝና ከመቅጽበት የሚለውጠኝ
መስሏት ፈገግ አለች፡፡ ሲያቀና ውሉ እንደ ከሠረ ቸርቻሪ ነጋዴ ከፋኝ እንጂ አልተደሰትኩም፡፡ ጥፋተኛ ልጁን ለመቅጣት ዘሎ እንደሚይዝ አባት እመር ብዬ
የወዲያነሽን ለቀም እደረግኋት። አያያዜ የብርቱ ንዴት ስለ መሰላት ደረቴ ላይ ተለጥፋ «አጥፍቼ ሆነ ንገረኝ? በድያህ ከሆነ ግለጽልኝ በሌላ ጉዳይ ተነክተህ ከሆነ በእኔ ይለፍልህ፡ በለኝ!» ብላ ጸጥ አለች፡፡ በአነጋገሯና በሁኔታችን
የደነገጠው ጋሻዬነህ የምደበድባት ስለመሰለው ዋይ!» ብሉ በቀጭኗ ጮኸና ተው ተው!” እያለ በእግሮቼ መኻል ፈልፍሉ ገብቶ በመካከላችን ቆመ። ፊቱን
ወደ እናቱ አዘሮ ተጠመጠመባት። «ሁለት የሥቃይ ፍሬዎች! » ብዩ
ገፈተርኳቸው፡፡ ሁለቱም እየተንገዳገዱ የኋሊት ሔዱ፡፡ አልሸሸችም፡፡

ጋሻዬነህ መለስ ብሎ ሲያየኝ ዐይኖቹ በእንባ ተዘፍቀዋል፡፡ «ና እስኪ ጋሻው » ብዬ ጠራሁት። የእናቱን ቀሚስ ጨመደደ እንጂ አልመጣም፡፡ እኳኋኔ የሚያስመጣ ስላልነበር አላዘንኩም፡፡ ወደፊት ራመድ ብዬ አጠገባቸው ቁጢጥ አልኩ፡፡ ና» አልኩት እንደገና፡፡ ከእናቱ ጀርባ ዞሮ ቀሚሷን ያዘ። ቀስ ብላ ወደ
ፊቷ ከሳበችው በኋላ ወደ እኔ ገፋ ስታደርገው አፈፍ አደረግሁት።
ከፊቴ ላይ አስፈሪ ነገር ያየ ይመስል ወለል ወለሉን እያየ አቀረቀረ። እንባው ቁልቁል በጉንጮቹ ላይ የሚንኳለልበት አግድመት በማጣቱ ነፋስ
ኣወዛወዛት የክረምት ዛፍ ላይ እንደሚረግፍ የዝናብ ውሃ ወለሉ ላይ ተንጠባጠበ። ሁላችንም ዝም አልን።
መንፈሴ መለስ ብሎ እንደተረጋጋ ንግግሬን አጢኜ ራሴን ታዘብኩት።
የተናገርኩት ሁሉ ከፅሑፍ ላይ ተጠንቶ የተነበነበ እንጂ ከተናደደ ሰው አንደበት የወጣ የወዲያው ንግግር አይመስልም ነበር፡፡ የጉልላት ቅጂ የሆንኩ መሰለኝ፡፡
«ምነው ጋሻዩ? ምን ሆነህ ነው የምታለቅሰው?» አልኩት። መልስ ነሣኝ፡፡ ዝምታም ተቃውሞ ነው። ሁላችንም ተቀመጥን። ጋሻዬነህ ከእኛ ፈንጠር ብሎ እንጨት ወንበር ላይ ተቀመጠ። መሬት ለመንካት ያልቻሉት እግሮቹ እንደ
አጭር ቆመጥ ተንጠለጠሉ። ያቃወስኩትን የየወዲያነሽን ስሜት ወዲያው ለማስተካከልና ልቧንም በፍጥነት ለማደስ እንደማልቸገር አውቃለሁ፡፡ የልቢ አካል ነችና።
ኣይዞሽ አትደንግጪ ምንም አልሆንኩ። ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ከራሴ ጋር ተፋልሚ ራሴን ፈትኛለሁ። ጥንካሬዬን ለክቼዋለሁ፡ፈሪውንና በርጋጊውን የቀድሞውን እኔን ጥዪ ቀጥ ብሎ መቆምና ጠላቴን መጋፈጥ የሚችለውን
አዲሱን እኔን ለመፍጠር እየታገልኩ ነው፡፡ በጠቅላላ ሲታይ እጅግ ብዙ ፈተናዎች አሉብኝ። እንደ ሰኞና እንደ ማክሰኛ በተከታታይ ይመጣሉ፡፡ ሁሉንም
ተራ በተራ እሸንፋቸዋለሁ። አሮጌው ሓሳብ ከእንግዲህ ወዲህ በሕሊናዬ ውስጥ
ቦታ የለውም፡፡ እየተገሸላለጠ ይወድቃል፡፡ ወደ አሁኑ ጉዳይ ልመለስና አባቴ ስለ አንቺ ኑሮ ምንም ስለማያውቅና አንዲትም ነገር ባለመስማቱ መስማትና ማወቅ አለበት፡፡ ግማሽ ፍቅርና ግማሽ ክብ ብሎ ነገር የለም፡፡ ምንም እንኳ ከሰማ በኋላ ምን እንደሚል ባላውቅም ከነባር ጠባዩና ከአስተሳሰቡ እየፈለቁ የሚወጡትን አንዳንድ ጥያቄዎች በልምድ አውቃቸዋለሁ። ቀደም ሲልም እንጎሌን በሁለት
የሐሳብ መድረክ ላይ ከፍዬ አባቴንና ራሴን ጠያቂና ተጠያቂ እድርጌ አቀረብኩ፡፡
በውስጤ የተፈጠረው የአባቴ የሐሳብ ወኪል ላቀረበልኝ ግትር ክርክርና ጥያቄ አስፈሳጊውን መልስ ሰጠሁ፡፡ የአባቴን የሐሳብ ወኪል ሳታዪና ባትሰሚውም በእኔ
በኩል ያለውን አካል ሲጮህና ሲያጓራ ሰምተሽዋል። ከእንግዲህ ወዲያ ግን ከዚያ ካፈሪና ከደንጋጭ ስውር አካሌ ለመላቀቅ ቆርጫለሁ። ከአባቴ ጋር ተከራክሬ
በማስረዳት ትክክለኛ ምርጫና እምነቴን እገልጽለታለሁ፡፡ አንጣጣምም ይሆናል፡፡ አዲሱ እምነቴ በአሮጌው እምነቱ ላይ በአዲስና ጽኑ መሠረት መገንባቱን
አሳየዋለሁ። ቢያይም አይታየውም፡፡ ተጨባጩን ጉልህ ነገር አሳየዋለሁ። ካላመነ
አስዳብሰዋለሁ፡፡ ለዘመናት አርጅቶ ትል የበላው የኑሮ እምነቱ ዐይኑ እያየ ይከዳዋል፡፡ እኔ ግን በማቀርቀርና ቀና ብሎ በማየት መካከል ያለውን ልዩነት ካአሁኑ ጩኸቴ ወዲህ ማየትና ማወቅ እፈልጋለሁ: ሥርም ግንድም መሆንን እንጂ ተራ ቅርንጫፍ ብቻ መሆንን አልቀበልም:: ህብረተሰቡ የኑሮው ሥርዓት ግንድ በመሆኑ የዚያ ግንድ አካል መሆን ግዴታዬ ነው::» ብዬ የደደረ ሐሳቤን
አሰማኋት፡፡ ሁለታችንም ፀጥ አልን፡፡ በዚያ አጭር ዝምታ ውስጥ ለአፍታ ያህል ሐሳቤን በረበርኩት። ያደረግሁት ንግግር ሁሉ ለሕዝብ መድረክ የተጠና መነባንብ
መሰለኝ፡፡ «የአንድ ጤነኛና ትክክለኛ እምነት ግንድ እንጂ የአንድ የበሰበሰ እምነት ሥር አዲስ ወይም ነባር ተቀጥላ መሆን አልሻም። ከዚህ ከተዳፈነ
ሕይወትሽና ከተርመጠመጠ ኑሮሽ ነጻ እንድትወጪና በእኩልነት ሽር እንድትይ እታገላለሁ፡፡ እንደ ዕብድ ያስጮኸኝም ይኸው የሕሊናዩ መዋለልና በውስጤ
የኖረው ውዥንብር ነው» አልኩና ደኅንነቴን ለማረጋገጥ ፈገግታ አሳየሁ።
የወዲያነሽ የጥልቅ እምነትኛ የሙሉ ተስፋ ገፅታ ሳይሆን አንድ ተራ ፈገግታ አሳየች። ለአንድ በድንገት ለተሠቃየ እእምሮ ፈዋሽ ማብራሪያ አቅርቦ ወዲያውኑ ማሳመን በመጠኑ አዳጋች በመሆኑ እዚያው በዚያው እንድታምን አላስገደድኳትም፡፡ ከጥቂት የዝምታ ደቂቃዎች በኋላ ካጠገቤ ተነሥታ ሄደች።ጋሻዬነህ እናቱን ተከትሉ ወጣ፡፡ የሚቀጥሉትን ሰዓታት በንባብ ለማሳለፍ የጀመርኩትን መጽሐፍ አነሣሁት። አሥራ ሦስተኛው ምዕራፍ አጋማሽ ላይ
«መገዛት መጨቆንና መገፋት አንገሸገሸኝ! ነጻነት ጠማኝ! ነጻነት ራበኝ የአካልና የሕሊና ባርነት መረረኝ! ሕይወቴና ጉልበቴ በገዢዎች ተመዘመዘ፡፡
ወገኖቼን የተጫናቸው የሥቃይ ቀንበር ክብደት ተሰማኝ፡፡
እኔን በማሰር የማይሞተውን ትክክለኛና ሕያው ዓላማዬን አይገድሉትም። ለሕዝቦች ነፃነት በሚደረገው ትግል ውስጥ የእኔ ድርሻና መሥዋዕትነት ተሰናክሉና ታስሮ መቅረት የለበትም፡፡ በሰፊው የሕዝቦች እስር ቤት ውስጥ
ታስረው የሚረገጡትን ሁሉ ነፃ ለማውጣት በሚደረገው ሐቀኛ ውጊያ ላይ ለመካፈልና የመሥዋዕትነት ድርሻዬን ለመወጣት ከዚህ ጠባብ እስር ቤት መውጣት አለብኝ» ብሎ አሥር ቀን ሙሉ ሲዘጋጅና ሲያደባ ቆየ። ማንንም ስላላመነ ምስጢሩን አላካፈለም ማንምም ሳያይና ሳይሰማ ቦላሌውን አይጥ እንደ በላው የቋንጣ ማስቀመጫ ከረጢት ቀረጣጥፎ ቁምጣ ሱሪ አደረጋት፡፡ አንድ ጊዜ ቆርጦ በመነሣቱ ሐሳቡን ለመፈጸም ተወጋጀ። እስረኞቹ ሁሉ እንደ ተመነጠረ ቁጥቋጦ ተለሽልሸዋል። አልፎ አልፎ በእንቅልፍ ልቡ ከሚያከውና በቅዠት ልቡ ከሚገላበጠ በስተቀር በጨለማው ክፍል ውስጥ እንደ እስረኞቹ የታሰረ ዝምታ ተጋድሟል፡፡ ከእስረኞቹ መኻል ኮሽ ሳይል ቀስ ብሎ ከተነሣ በኋላ በሩን በዝግታ
ከፍቶ ወጣ፡፡ ወዲያው በደረቱ መሬቱ ላይ ተዘርሮ ለጥ አለ፡፡ በሰበሰቡ ጥላ ውስጥ በደረቱ እየተሳበ አያሌ ርምጃዎች ያህል ሄደ። ከቤቱ ጥግ የስቀለችውን ዛፍ
ለመያዝ ትንሽ እንደ ቀረው ትንፋሽ አጠረው:: የመጣው ይምጣ ብሎ ተነሳና ግንቡ ላይ ተለጥፎ እየታከከ ከተጓዘ በኋላ ተንጠራርቶ ግንዷ ላይ ተጠመጠመ፡፡
በማምለጥ ፍላጎትና በእያዝ ይሆን ስሜት መካከል አካላዊ ሽብር ስለ ተነሣበት ተንዘፈዘፈ፡፡ ሽቅብ ዘለለ። እጁ ከፍ ሲል ሁለት እግሩ ከጉልበቱ ላይ አጠፍ ብሎ
ግንዱን ረገጠ፡፡ ሳብ! መዘዝ ከፍ! ጎተት! እያለ አንዱን ቅርንጫፍ በቀኝ እጁ ጨበጠ፡፡ ሞትና ሽረት ነው ሌላ የመላቀቂያ ምርጫ የለም! ሽቅብ ተስቦ ባላ ረገጠ። ከፍ አለ፣ ወጣ፣ ከፍ አለ፡፡ አንዲት ለጋ ቅርንጫፍ እቀጭ ብላ
ተቀለጠመች፡፡ ነፍሱሥጋው ተለያየች:: ወዲያው ከቤቱ አናት ላይ ፊጥ አለ። ከወዲያም ከወዲህም ተንጓጓ፡፡ ጣሪያው ቁልቁል የሚካዳው መሰለው። እንደገና በደረቱ ተኝቶ ቢቆርቆሮው ላይ እንደ እባብ ተሳበ። ከሕፃን ዐይን ውስጥ ጉድፍ እንደሚያወጣ ሰው ተጠነቀቀ።
የውጥኑ ከፊል ተጠናቀቀ!
ከጠባቧ እሰር ቤት ወጥቶ ወደ ሰፊው እስር ቤት ግቢ ዳርቻ ላይ ዘሎ ወረደ! ቆርቆሮው በትልቅ ድንጋይ የተመታ ያህል የጥይት ድምፅ ተሰማ! ከተያዘ ከፍተኛ ስቃይና መከራ እንደሚደርስበት
የሚያውቀው አምላጭ ከጥይት ፍጥነት ጋር መሽቀዳደም ይችል ይመስል በ ን ፊደል ቅርዕ ዓይነት እየተቅመደመደ ሩጫውን ተያያዘው። ትኩሱ ተደጋገመ፡፡

ከተተኮሱት ጥይቶች መካካል እንጂ የግራ እጁን መታችውና ደንግጦ ተዘረረ» የሚለው የድርጊት ገላጭ ሐተታ ላይ እንደደረስኩ ሁኔታው በእኔ ላይ
የደረሰ ስለ መስለኝ ተሰቅተጩ ዐይኔን ጨፈነኩ። ፋጻሜውን ለማወቅ ንብበን ቀጠልኩ፡፡ «እንደገና ተፍጨርጭሮ ተነሣና እየተፍገመገመ ሩጫውን ቀጠለ፡፡
አልተያዘም፡፡ አገሩንም ነፃ ለማውጣት ወደ በረሃ ገባ» ሲል ከጭንቀት ምጥ ተገላገለኩ፡፡
እርሱስ ወደሚገባበት ገባ፤ እኔና የእኔ ትግል ግን ፊት ለፊት
እንደተፋጠጥን ከወዲያ ወዲህ ስትመላለስ መጽሐፍ መያዜን
የተመለከተችው የወዲያነሽ ከመነኩሴ አጠገብ የዳቦ ፍራፋሪዎች ለመለቃቀም
እንደምትጠጋ ለማዳ የደብር ርግብ ቀስ ብሳ ከተጠጋች በኋላ «እፎይ እኔስ ምን ነካህ ብዬ ተጨንቄ ነበር። እውነትም ደህና ነህ፡፡ ረጋ ደርበብ ብለህ ስትቀመጥ ደስ ማለትህ» አለችኝ፡፡
«ምነው ነግሬሽ የወዲያነሽ፣ ደኅና ነኝ እኮ ብየሻለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኮ መናደድ መድኃኒትነት አለው ይባላል» ብዬ መለስኩላትና ወደ ንባቤ ዞርኩ፡፡
ማታ ከትምህርት ቤት መልስ ከየወዲያነሽ ጋር በቀጥታ ወደ ወላጆቼ ቤት ሄድን፡፡
እናቴ እኔን ሳይሆን ከጎኔ ያለችውን የወዲያነሽን በአስደሳች ፈገግታ
ትቀበለቻት፡፡ እኔ ከእኅቴ፤ እናቴ ከባለቤቴ ጋር ተቀመጥን፡፡ በየበኩላችን ወሬ ጀመርን ፡፡ እኛን ሲጠባበቅ የነበረው ቡና ዕጣን ጨሶ ተቀዳ፡፡ የየበኩላችንም ወሬ
ደራ።
የውብነሽ ከጥቂት ገለጻ በኋላ ተማሪዎቹን እንደሚጠይቅ መምህር ጧት የነገርኩህን ሁሉ ታስታውስ የለ? ያልኩህስ ሁሉ ገብቶህ የለ?» ብላ መልሴን
ለመስማት በተዘጋጀ ስሜታዊ ንቃት አየችኝ። ምንም እንኳ አብሮ አደግ ልማዱንና ጠባዬን በጥቂት ቀናት ውስጥ መለወጥ የማልችል መሆኔን ባውቅም!
አንድ አዲስና የማይሻር ውሳኔ መወሰኔ ግን ታወሰኝ። «አዎ ገብቶኛል፣አስታውሳለሁ፡ ግን እኮ ታዲያ...” ብዩ ሙሉ ሐሳቤን ሳልገልጽላት ዝም አልኩ።
የዝምታዬ መነሾና ጥጥር ምክንያት ግን አዲሱ እኔ በመሆኑ እሷ ልታውቀው አትችልም፡፡....
💫ይቀጥላል💫

❤1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....“አንተን ለማግኘት ስል ያልገባሁበት ዋሻ፣ያልፈነቀልኩት ድንጋይ አልነበረም፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል?እንደ ሌሎቹ በቀላሉ የምትገኝ ሰው አልሆንክም፡፡ የተፈፀመብኝ ጥቃት ከባድና ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ ልቤ እያወቀው፣ ልቤ እየጠረጠረ ከማይረቡ ምናምንቴዎች ጋር ውለታ ውስጥ ገባሁ። እንዳንተ ስማቸው ያልገነነ፣ ቱስ ቱስ ማለት የጀመሩ ሾላኮች በመሆናቸው ብዙ ገንዘብ ካስወጡኝ በኋላ አንዳች ቁም ነገር ሳይፈፅሙ ሸሽተውኛል ተደብቀውኛል። በዚህ ምክንያት ተበሳጭቼ ቀን ከለሊት አፈላልጌ መልዕክተኛ ልኬብህ በብዙ ድካም ሳገኝህ የተሰማኝ ደስታ
ወደር አልነበረውም፡፡ እንደዚህ በግንባር ልታነጋግረኝ መወሰንህን ስሰማ ደግሞ ደስታዬ እጅግ ከፍተኛ ሆኖ ነበር፡፡ጎንቻ የልቤን የሚፈፅምልኝ ካንተ ወዲያ ሊኖር እንደማይችል ቀድሞውኑ የታወቀ ነው” በማለት አንጀቱን ከበላው በኋላ ዝርዝሩን ይተርክለት ጀመር፡፡
“የሹመት ጓደኛዬ ነው። ባላባት ጃኖ ይባላል። በባህላችን በወልገራ የጋብቻ ደንብ እህቴን ስድርለት እሱ ደግሞ በለውጡ እህቱን ድሮልኝ ነበር፡፡ እኔ የሱን እህት በወግ በማዕረግ አክብሬ ነበር የያዝኳት። እሱ ግን እህቴን
እንደ ባሪያ እየረገጠ በደል ሲያበዛባት፣ ሲያሰቃያት ተማረረች። በመጨረሻም የሱ ሚስት የኔ እህት በደሉ አንገሽገሻትና በድንገት ጥላው ጠፋች። ከዚያ በኋላ ሰላም ይነሳኝ፣ ይበጠብጠኝ ጀመር፡፡ እኔ ጥለሽው ጥፊ፣ እኔ ትዳርሽን አፍርሺ ብዬ እንደመከርኳት ሁሉ ሚስቴን መልስልኝ ያለበለዚያ ዝምድናችን ይበላሻል እያለ ያስፈራራኝ ጀመር።መልዕክተኛ በተደጋጋሚ ላከብኝ፡፡ በግንባር ተገናኝተን ተነጋገርን፡፡ ጭቅጭቁ ሲብስብኝ መቆሚያ መቀመጫ ሲያሳጣኝ እህቴን ካለችበት ቦታ አስጠርቼ ላግባባት ሞከርኩ፡፡ ወደ ትዳሯ እንድትመለስ እግሯ ላይ ወድቄ ለመንኳት ወደዚያ የስቃይ ኑሮ ተመለሺ የምትለኝ ከሆነ ህይወቴን አጠፋለሁ ካንተ
ምንም የምፈልገው ነገር የለም በነፃነቴ ውስጥ ግን አትግባ ብላ እያለቀሰች በምሬት መለሰችልኝ፡፡ በጣም አስፈራራችኝ፡፡ ከፍላጎቷ ውጭ እንድትመለስ ባስገድዳት ህይወቷን ታጠፋለች የሚል ፍርሃት አደረብኝ፡፡ያደረኩትን ጥረትና የሰጠችኝን መልስ በዝርዝር አጫወትኩት፡፡ በወዳጅነታችን ውስጥ በፍፁም ቅያሜ እንዳይኖር ለመንኩት። እህቴ ብትሆንም በሱ ሚስት ህይወት ላይ ማዘዝ እንደማልችል አስረዳሁት፡፡ ምን ዋጋ አለው? ድንጋይ ራስ ነው! በፍፁም ማመዛዘን የማይችል ድንጋይ ራስ!! ችግሬን ሊረዳ አልቻለም፡፡ ያንን ሁሉ ልፋቴንና ጥረቴን ዋጋ አሳጥቶት ቂም ቋጠረብኝ፡፡ የኔን ትዳር ለመበጥበጥ፣የኔን ትዳር ለማፍረስ እንቅልፍ አጣ። ለእህቱ በተደጋጋሚ መልዕክተኛ ላከባት፡፡ የሱ እህት ብቸኛ አድርጋኝ ጥላኝ ስትጠፋ፣ ትዳሬን አፍርሳ ስትሄድ አንቺ ግን የሱን ጎጆ ታሞቂያለሽ፡፡ የወንድምሽ በደል የማይሰማሽ ለወንድምሽ የማትቆረቆሪ አህያ
ነሽ።እህቱ ጥላኝ እንደጠፋች ጥለሽው ካልጠፋሽ ዳግመኛ እህት አለችኝ ብዬ አላወራም እያለ ነዘነዛትና ፍቅራችን እንዲደፈርስ ትዳራችን እንዲ ፈራርስ አደረገ፡፡ ከዚያም የምወዳት ሚስቴ ሳልበድላት ምንም ሳላስቀይማት በድንገት.. በድንገት ጥላኝ ጠፋች”
የስድስት ሚስቶች ባል የሆነው ባላባት ቱሬ የሚያወራው ተረት አፉን እንኳን ወለም አላደረገውም ነበር፡፡ የደረሰበት በደል ከፍተኛ መሆኑን ጎንቻ እንዲረዳለትና ቁጭት እንዲያድርበት ለማድረግ ሰሞኑን ሲያጠና የከረመውን ልብ ወለድ እንደ እውነተኛ ታሪክ ሲያወራለት እዚያ የነበሩት በሙሉ አፋቸውን ከፍተው እንደ አዲስ ያዳምጡት ነበር፡፡ በተገላቢጦሽ በጃኖ ላይ የደረሰውን በደል በራሱ ላይ እንደደረስ አድርጎ ጃኖን በዳይ ራሱን ተበዳይ አድርጎ ፊቱን በእንባ ቀረሽ ንዴት ቁጥር ፈታ እያ
ደረገ ማስረዳቱን ቀጠለ።
“ስው ቢበድለኝም ጓደኛዬ ቢከዳኝም እግዚአብሔር አልከዳኝምና በደሌን አይቶ ካለኝ፡፡ ሀዘኔን አይቶ ፈጣሪ አስደሰተኝ፡ እምባዬን አበሰልኝ፡፡ አለላ የመሰለች ልጁን በቦሩ ጃዊ ባላባትነት ውስጥ ጭቃሹም የሆነው አቶ ገመቹ ዳረልኝ፡፡ በዚህ ጊዜ የበለጠ ቅናት አቃጠለው:: እህቱ ጥላኝ እንድትጠፋ፣ ረግጣኝ እንድትሄድ ካደረገ በኋላ ለእህቱ ተቆርቋሪ መስሎ እህቴ የደከመችበትን ንብረት፣ እህቴ ጎንበስ ቀና ብላ ያቆመችውን ጎጆ
ማንም መንገደኛ ገብቶ አይንደላቀቅበትም ሲል ዛተብኝ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ የሱ እህት ይዛልኝ የመጣችው ሰባራ ሳንቲም አልነበረም፡፡ በሞላ በተትረፈረፈ ቤት ገብታ መሞላቀቁ አጥግቧት ጠፋች እንጂ እሷ ያመጣችው አንድም ነገር አልነበረም፡፡ ከኔ ምን ጎድሎ? ምን ጠፍቶ? እሱ ግን ለእህቱ የተቆረቆረ በማስመሰል ለካንስ ሊያጠቃኝ አስቦ ኖሯል፡፡ የሱ እህት ለዚችኛዋ ሚስቴ ገረዷ የእግሯ እጣቢ እንኳ አትሆንም ነበር፡፡ ያጠቃኛል የዚያን አይነት አስከፊ በደል ያደርስብኛል ብዬ በፍፁም ባልጠበኩት ሰዓት ባላባት ጃኖ አጠቃኝ፡፡ ተዘጋጅቶ ዘመድ አዝማዱን አሰባስቦ
ጦሩን ጭኖ በሌሊት ከበበኝ፡ ሚስቴን…. ሚስቴን... በሃይል... ሳልዘጋጅበት.ሳላስበው ...ነጥቆኝ ሄደ” እንባ እየተናነቀው አስረዳ፡፡
እውነተኛው ታሪክ ግን ባላባት ቱሬ እንደሚያወራው ሳይሆን የምስኪኑ
ገበሬ የጃኖን እዚህ ቀረሽ የማትባል እጮኛውን ባላባት ቱሬ በሀብትና በሥልጣኑ ተመክቶ፣ ወላጆቿን በከብትና በገንዘብ ገበራ ዐይናቸውን አሳውሮ የአሥራ ስምንት ዓመቷን ልጃገረድ ሌቱናን ጠልፎ ከወሰዳት በኋላ በባላባትነት ግዛቱ ውስጥ ድል ባለ ሠርግ ያገባት መሆኑ ነው ሀቁ። ገንዘብና ሀብት ባይኖረውም ዛሬ በቱሬ አንደበት የባላባትነት ማዕረግ የተሰጠው ጃኖ የጉልበትና የወኔ ደሃ አልነበረም። እንደ ነፍሱ የሚወዳት እጮኛውን ጉብሏን ሌቱናን ቱሬ በገንዘብ ኃይል አፍኗት ሲሄድ፣ የድንግልነት ክብሯን ሲወስድ እየታየው ገላው እስከሚቃጠል ድረስ በንዴት
ቢጋይም፣ እልህ ቢተናነቀውም አንድ ቀን የሱ አንጡራ ሀብት መሆኗን እንደሚያረጋግጥና እጮኛውን በነጠቅው በቱሬ ላይ አደጋ ጥሎ እንደሚወስዳት ጥርጥር አልነበረውም፡፡ ቱሬ የጓጓው ያንን የቀዘቀዘ ገላውን የም
ታሞቅለትን፣ ብዙ ንብረት ያወጣባትን ቆንጆዋን ሌቱናን ጎንቻ እንዲያስመልስለት ነው። ጎንቻ ተራ ውንብድና አይፈፅምም የሚለውን ዜና በመስማቱ የሌላ ታሪክ እየፈጠረ ገበሬውን ባላባት አድርጎ በመሾም ለመተረክ የተገደደውም ከዚህ እውነታ በመነሳት ነው፡፡
በእርግጥም ጎንቻ ትንሽ ስራ፣ ትልቅ ስራ በሚል የወንጀል አይነትን የሚያማርጥ ቢሆንም ጥሩ ገንዘብ እስካስታቀፉት ድረስ የህፃን ጉሮሮ ከመቀንጠስ ወደ ኋላ የማይል ጨካኝ መሆኑን ቢያውቀው ኖሮ ይሄንን ያክል
መጨነቅ ባላስፈለገው ነበር፡፡
“የፈለከውን ያክል ብር ብትስጠኝ አንድ ተራ ገበሬ ለመግደል አገር
አቋርጬ አልሄድም” ይለኛል ብሎ ስለፈራ እንባውን እየጠራረገ እጅግ ከፍተኛ የሆነ በደል የተፈፀመበት ሰው መስሎ እየተንቀጠቀጠ ኑዛዜውን ቀጠለ፡፡
“ምንም እንኳ እድሜዬ ቢገፋ፣ አቅሜ ቢዳከም አባቴ የወለደኝ ወንድ ጀግና ነበርኩ፡፡ ጃኖ ግን ወንድነቴን ጀግንነቴን ሰልቦታል። ልቤን በሀዘን አኮስምኖታል። ዝናዬን አጉድፎታል። ተኝቶ ሚስቱን ያስነጠቀ ባላባት አሰኝቶ በባላባትነት ግዛቴ ውስጥ አዋርዶኛል። ህዝቡ እንዲንቀኝ፣ እንዳይታዘዘኝ አድርጓል፡፡ ጉልበት በነበረኝ ጊዜ አባርሬ ይዣለሁ። ገድዬ ፎክሬአለሁ።ጃኖ ግን አቅሜ ቢደክም፣ዕድሜ ቢጫጫነኝ ንቆኝ የለበስኩትን ሱሪ አስወልቆ ቀሚስ አልብሶኛል። ጉልበት የእግዚአብሔር መሆኑን

❤2🥰1
ዘንግቶ ጉልበት አለኝ ብሎ ሚስቴን ነጥቆኝ ሄዷልና፣ ወንድነቴን አኮላሽቶታልና ወንድነቱን ንጠቅልኝ፡፡ በጉልበቱ ተመክቶ ዐይኔ እያየ የምወዳት ሚስቴን እጇን አንጠልጥሉ እንደሄደ ሁሉ ዐይኗ እያየ ሴት አድርገኸው ቁጭቴን ተወጣልኝና እንደ ዶሮ ዘቅዝቀህ እጂን አንጠልጥለህ አምጣልኝ፡፡ ይህንን የምታደርግልኝ ከሆነ የምትጠይቀኝን ሁሉ ለመፈፀም
ዝግጁ ነኝ” ሲል ተማፀነው፡፡
ባላባቱ ይህንን ንግግር በሚናገርበት ጊዜ ግራና ቀኙ የቆሙት ጭቃ ሹሞቹ ንግግሩ ትክክለኛ መሆኑን፣ የደረሰበት በደል የተፈፀመበት ግፍ በማንም ላይ ደርሶ የማያውቅ መሆኑን ለመመስከር እንዴ ወደ ጎንቻ
አንዴ ደግሞ ወደ ባላባቱ መለስ ቀለስ እያሉ በንዴት ከንፈራቸውን እየነከሱ የጎንቻን የበቀል ስሜት ይኮረኩሩት ነበር። ባላባቱ የሚፈልገው ጎንቻ የሰለቸውን ተራ ግድያ ሳይሆን በአይነቱ አዲስ
የሆነ የጥቃት ስልት ተጠቅሞ ብቀላ እንዲፈፅም መሆኑን ሲሰማ የደስታ ስሜት በሰራ አካላቱ ውስጥ ተራወጠ። ፊቱ ፈገገ፡፡ ከዚህ በፊት ሞክሮት የማያውቀውን አዲስ አይነት የቅጣት በትር እንዲሰነዝር፣ ለየት ያለ የበቀል ዱላውን እንዲያነሳና አዲስ የብቀላ ሪከርድ እንዲያስመዘግብ የቀረበለት የድርድር ሃሳብ ከገንዘቡ የበለጠ አስፈነደቀው።
እሱ የሚያውቀው በልጅነቱ አባቱ ወጠጤውን ፍየል ሙክት ለማድረግ ሲያኮላሹ የፍየሉን ሚ.. !አ/አ! አ! አ!”የሚል ጆሮ የሚሰነጥቅ ጩኸት ነበር። እሱ የሚያውቀው ኮርማውን በሬ ለማድረግ በመጫኛ ተጭሎ
የዘር ማመንጫ ፍሬዎቹ ሲወረወሩ ደምስሮቹ ሲበጠሱ፣ ሊዘነጠሉ
ከበሬው ውስጥ የሚወጣውን የጓጎረ የጣእር ድምፅ ነበር፡፡ አሁን ግን የሰውን ልጅ እንደ ወጠጤ ፍየል፣ እንደ ኮርማ ሲቀጠቅጠው፣ ደምስሩን ሲበጥሰው፣ የዘር ማመንጫ ፍሬዎቹን ሲያሻቸው ከውስጡ የሚወጣውን የስቃይ ድምጽ፣ የሰቆቃ ጩኸት አይነቱን ለማወቅ ጓጓና በደስታ
ቃል ገባለት::
ሃሳብህ በሙሉ ፍላጎትህ አንድም ሳይጓደል ይፈፀምልሀል! ከዚህ በፊት በነፃ የተወስደብህን ያክል ትከፍላለህ”ሲል በኩራት ገለፀለት፡፡ ባላባቱ መስማማቱን በደስታ ገልፆ ወዲያውኑ ለቀብድ አምስት መቶ ብር ካስጨበጠው በኋላ የገባውን ቃል ፈፅሞ ሲመጣ የሚሰጠውን ቀሪውን ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር እፊቱ ቆጠረለት፡፡
በዚሁ በውለታቸው መስረት የባላባት ጃኖን ቤት የሚያሳይ ጠቋሚና ሚስቱ ሌቱና የምትጫንበት ሠንጋ ፈረስ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡
የጉዞው ቀን ተቆርጦ ጠቋሚዎቹ በሌሊት ፈረሶቹን ይዘው የሚቀርቡበት ቦታና ሰዓት ተወስኖ በፍቅር ተሰነባበቱ፡፡ ጎንቻ የተቀበለውን ገንዘብ ወደ
ኪሱ ከተተ ። በቀጠሮው ቀን ሲገሠግሥ አድሮ ቀን ቀን በየጫካው እየተደበቀ ሌሊት ሌሊት ተጉዞ የባላባቱን ባላንጣ ሊያስጮህ፣ ሊያስለቅስ፣ አዲስ አይነት የጭንቀትና የጣእር ድምፅ ሊሰማ ያደረበትን ጉጉት በሚገልፅ ግጥም እየፎከረ ባላባቱን አስደሰተውና ተሰናብቶት ወጣ.....

#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
...አስታውሳለሁ ግን እኮ ታዲያ...” ብዩ ሙሉ ሐሳቤን ሳልገልጽላት ዝም አልኩ።የዝምታዬ መነሾና ጥጥር ምክንያት ግን አዲሱ እኔ በመሆኑ እሷ ልታውቀው
አትችልም፡፡
«ና በል እንሒድ ቶሉ እንመለሳለን» አለችና ተነሣች። የእኔ ጉዳይ
በእርሷና በእናቴ መካከል ተመክሮበት ያለቀ በመሆኑ እንግዲህ አደራሽን እንደዚያቹ እንደ ምክራችን አድርገሽ ንገሪው፡፡ እኔና አንቺ እንደ ተባባልነው
ቢሆን ይሻላል፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ እኔ ደኅና አድርጌ እነግረዋለሁ፤ አደራሽን አደራችሁን» ብላ እናቴ በዐይኗ ሸኘችኝ፡፡ «ሂዱ» የምትለን ወደ እኔ ቤት መሆኑን አወቅሁ፡፡ የወዲያነሽን ለመጠበቅ ቆምኩ። «ሂዱ እንጂ ምን ቀረህ?
እናቷ እኮ ነኝ! ሌላ እናት ያላት መሰለህ? አይዞህ! ለሌላ ሰው አልሰጥብህም፣ እሷም በጀ አትልም» ብላ ስቃ አሣቀችኝ፡፡ የወዲያነሽ እናቴን በዐይኗ እየጠበቀች 'የሂዱ' ምልክት በጣቷ አሳየችኝ። ምርቱን እንደከተተ ሰው ተደስቼ ወጣሁ፡፡ወደ እኔ ቤት የመሄዱን ነገር ሰርዘን መኪና ውስጥ ተቀመጥን።
«አባቴ ስለ አንተና ስለ የወዲያነሽ ምንም ነገር ፈጽሞ እንዳልሰማና እስከ ዛሬም እንዳላወቀ ታውቃለህ:: ምስጢሩን የቀበርነው ሁላችንም ስለ ፈራነው ነው»
በማለት ንግግሯን ጀመረች፡፡ ጠንቃቃነቴንና ለጉዳዩ ያለኝን ከፍተኛ ግምት በግልጽ ለማስረዳት «አንቺና እማማስ ብትሆኑ ካባረራችኋት በኋላ ስለ እርሷ ምን የምታውቁት ነገር ነበር? ምስጢሩ ያልተነዛው ከእርሷ ጋር በመባረሩና እስር ቤት
በመውረዱ ነበር» ብዩ ተራ ለቀቅሁ፡፡
«ነገሩን በብልሃትና በዘዴ ካላስኬድነው በስተቀር ከአባታችን ጋር ብዙ ንትርክና ጭቅጭቅ እንደሚነሳ የታወቀ ነው፡፡ እኛ ግን ስለ ነገሩ ፍንጭ አግኝቶ
እንዲጠራጠር በማድረግ ጉዳዩን ለመጀመር አስበናል፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ አንተም እኛም ጥሩ ጥሩ ሽማግሌዎች መርጠን...» ብላ ሳትጨርስ «የብልሃቴ አቀነባባሪ እኔ ነኝ፡፡ የአዲሱ ሕይወቴ ጎዳና ቀያሽና ደልዳይ ራሴ ነኝ።
እያስፈልግም፡ በቃኝ! አባቴንም እንደ እናቴ በማስማልና በፍርሃት
እየተርበደበድኩ በመጠጋት የሚለኝንና የሚወስንብኝን ሁሉ አቀርቅሬ በመስማት ዕድል ለሚሏት አጋጣሚ ነገር አልንበረከክም! መጠራጠር ማለት ስለ አንድ ነገር ቢያንስ በጥቂቱ ማወቅ ወይም መገመት ማለት ነው። የትላንቱን ስሕተቴን ዛሬና
ነገ መድገም የለብኝም፡፡ አታስቡ! እኔ ለአባቴ የራሴ ዝግጅት አለኝ፡፡ በቀጥታ ቀርቤ ፊት ለፊት አስረዳዋለሁ፡፡ ለጥያቄዎቹም መልስ እሰጣለሁ» በማለት ጣልቃ
ገብቼ ተናገርኩ። ድንገት ደሟ ፈላና «ከንትርክና ብዙ ጣጣን ከሚያስከትል ጭቅጭቅ ይልቅ መግባባት ይበልጣል። በንትርክና በአሻፈረኝ ባይነት የምታገኘው
ድል አድራጊነት ሁሉ እስከ መጨረሻው አያረካህም፡፡ አባቴ በመጀመሪያ ጋሻዬነን አይቶ ከተደሰተና የሐሳቡ አቅጣጫ ካማረ ሁሉም ነገር ይሳካልናል።
የወዲያነሽንና የአንተን ግንኙነት፣ የደረሰባትን መከራና ሥቃይ ሁሉ ቀስ በቀስ እተርክለታለሁ፡፡ ልቡ ካዘነና መንፈሱ በርህራሄ ከተነካ፡ በሉ ሂዱና አምጧት ይላል” ብላ ነገሯን ልታራዝም ስትል «አይቻልም! ማን አስተርጓሚ አደረገሽና!
መሸሸግም ሆነ መደበቅ የለበትም፡፡ አልለማመጥም:: እጅግ አርኪው ድል አድራጊነትም ከትግልና ከሥቃይ በኋላ የሚገኝ ድል አድራጊነት ነው፡፡ እኔና
የወዲያነሽ ጋሻዬነህን አስከትለን ባንድ ላይ እንቀርባለን፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት “እንቺም ሆንሽ እናቴ አንዲት ቃል መናገርም ሆነ ማሰማት የለባችሁም፡፡ በምንቀርብበት ቀን እንግዶች ቢኖሩም ባይኖሩም ግድ የለኝም። እንዲያውም ወሬው እንዲስፋፋና እንዲዛመት ብዙ ሰዎች ቢኖሩ በጣም ጥሩ ነው:: በዚህ ብትስማሙ ተስማሙ፡ አለበለዚያ ግን የማደርገውንና የማላደርገውን እኔ ራሴ አውቃለሁ፡፡ እኔ የምፈልገው እንዲያውቅ ብቻ እንጂ እንዲስማማ ወይም መርቆ
እንዲቀበለን አይደለም፡፡ ከባለቤቴ ጋር ባለን ግንኙነት ውስጥ ጣልቃ ገብቶ አስተያየትም ሆነ ሌላ ሐሳብ እንዲያቀርብ አይደለም» በማለት ቀጥ እንዳለ አቀበት ስትፈራው የቆየችውን ጉዳይ አውላላ ሜዳ አደረግሁላት፡፡ በእኔ ላይ የነበራት ግምትና አስተሳሰብ ሁሉ ነፋስ እንደ መታው ልም ዱቄት ተበተነ፡፡በሁለታችን መካከል በጣም ግዙፍ የሆነ የሐሳብ ልዩነት ተፈጠረ፡፡ በእኔ ላይ የሐሳብ በላይነት ለማግኘት ባለመቻሏ ተከዘች። ምክራቸውንና መላቸውን ሁሉ ባለምቀበሌ ንዴቷ ናረ። የመዥገር ሞት ያህል አላሳዘነችኝም፡፡ ቁርጡን ለማወቅ
የጓጓው አእምሮዋ ራሱ የዘጋውን የዝምታ በር ከፈተው፡፡ «እኔ እና የግሌን የአቀራረብ መንገድና ሐሳብ አዘጋጃለሁ እንጂ የእናንተን አልቀበልም ማለትህ ነው?» ብላ ሁኔታዬንም አብራ ለመረዳት ፊቷን ወደ እኔ አዞረች፡፡
ባጭሩና በቀላሉ ”አዎ” አልኩና ተጨማሪ ምክንያትና ማብራሪያ
ለማቅረብ ስዘጋጅ «በቃኝ አያስፈልገኝም! አልሰማም ቀኙን ሲያሳዩህ ግራ ግራውን ትመርጣለህ፡፡ እኔን ያናደደኝ ያንተ እምቢታና የመጣው ይምጣ ባይነት ሳይሆን በዚሀ ይሻላል በዚያ፡ ይኸ ያዋጣል ያኛው ይበልጣል እያልኩ ከእናቴ ጋር
ስነታረክና ስከራከር መሰንበቴ ነው» ብላ ፊቷን አዞረች።
አልደነገጥኩም፡፡ «የአንቺም ይሁን የእናቴ ርዳታ እያስፈልገኝም፡፡ ጥገና እና ድረታ አልፈልግም፡ ጥገና አይዋጥልኝም! ጥገና ማለት ውስጠ ሰባራ ማለት ነው፡፡
ከሆነላችሁ እናንተም ተደርባችሁ በጥያቄና መልስ አዋከቡኝ! ዝግጁ ነኝ። ነገር ግን እኔ በማልገኝበት ወቅት አባቴን እንድትለምኑልኝና እኔን፣ ባለቤቴንና ልጄን ዝቅ አድርጋችሁ እንድትለማመጡልኝ አልፈልግም፡፡ እኔ ራሴ ባለጉዳዩ ፍላጎቴንና ውሳኔዩን ለማስረዳት በሚገባ ዝግጁ ሆኛለሁ» ብዬ ፋታ ሰጠሁ፡፡
«አያዋጣም እንጂ ቢያዋጣማ ጥሩ ነው:: ለፍተህ ለፍተህ እዚህ ከደረስክ በኋላ እንዴት እንዲህ በቀላሉ ትገነፍላለህ?» ብላ ራሷን ነቀነቀች።
«በቃኝ ነው የምልሽ! በሐሳቤና በእምነቴ እንድትስማሚ አላስገድድሽም። የገዛ መብቴን አልመፀወትም:: የሕሊናዬን ቁስል የማድንበትን መድኃኒት ቀስ በቀስ እያወቅሁ ነው:: ከአባቴ መሠረተቢስ እምነት ጋር እንድጋጭና እንድታተር
እንጂ እንደ ከዚህ ቀደሙ አንገቴን ሰብሬ የሚኖረው የሚያቀርበውን
ዝባዝንኪ ሐሳብ ሁሉ ያለ አንዳች ክርክር እንድቀበል አልፈልግም! ጨቋኝ ግዴታውን አልቀበልም:: ሐሳባችሁንም ሰርዙ። ከዚህ አሁን ከነገርኩሽ አፈጻጻም ውጪ አንዳችም የምቀበለውና የምስማማበት ሐሳብ ስለ ሌለ ነገር ሳናንዛዛ ወደ ቤት እንግባ» አልኩና ለጠላቱ የመጭረሻ ማስጠንቀቂያ እንደሚሰጥ
ሰው የማያወላዳውን ነገርኳት። ለወለላ ገሥግላ ፊት ዛቀች!
ያለውን ይበል ብላ እንዴት አታስብም? እንዴት አይገባህም? ነገሩን ረጋ ብለህ ተመልከተው፡ ራስህን ብቻ አትውደድ፡ ይኸማ ይበጣበጡ' ይጣሉ፡ ይጋደሉ ማለትህ እኮ ነው? ስንትና ስንት ዓመት ሙሉ ምስጢሩን ደብቀህ
ከኖርክ በኋላ አሁን በመጨረሻ ጣጣን አመጣህ። ለካስ በጄም በግሬም ገብተህ የተለማመጥከኝ እንዲህ ለመሆን ኖሯል? አሁን አንተ በምትለው ሁኔታ ከሆነ
አገር ምድሩን እንደሚበጠብጥ አውቃለሁ፡፡ እናቴ ግን ያን ሁሉ አድራጎት ያደረገችው ላንተው ስትል እንደነበር ታውቃለህ» ብላ ፊት ለፊት ወደ ጨለማው

አፈጠጠች። ቀለል ያለች የማናናቂያ ሣቅ ከሣቅሁ በኋላ «ለካ በደንብ አውቀሽልኛል! አሁን ገና ተገናኘን። እኔም የምፈልገው ይኸንኑ ነበር፡፡ አንቺ በፈራሽው አኳኋን ከጠየቀኝማ... እሰየው! ደስታውንም አልችለው! ፈቅ ነቅ
በማይለው በአባቴ እምነት ታስሬ ለመኖር አልሻም፡፡ መሠረቱን ማፈራረስና ሰንሰለቱን መበጣጠስ አለብን። ከአያት ከቅድመ አያት የወረሰውን መጥፎ ልምድ
ጥለን መቅበር ይገባናል።
«የእኔና የየወዲያነሽ ጉዳይ ምስጢር ሆኖ የተጠበቀው ከጨለማ የጠቆሩ ምክንያቶች ስለ ነበሩት ነው። ለሚያቀርብልኝ ጥያቄ ሁሉ የምሰጠው አጥጋቢ
መልስ አፍንጫዬ ሥር ተንጠልጥሏል፡፡ አትታደስ፣ አትለወጥ ነው የምትሉኝ?
ሕይወት ያለማቋረጥ የምትታደስና የምትለወጥበት የራሷ የሆነ ባህሪ አላት።
የወዲያነሽንና የመሰሉቿን ሕይወት አስተካክዬ ለመገንባት የእናንተን ከንቱ እምነትና ኑሮ መናድና ማፈራረስ አለብኝ» ብዬ የንዴቷን ቃጠሎ እንደገና
ቆሰቆስኩት፡፡ ምክንያትም ካስፈለገ ነፍስ ያለው ምክንያት» እንዳልኩ፡
«ምክንያት! ድንቄም ምክንያት እቴ! ይህን ቆሽት የሚያሳርረውንና
አንጀት የሚጎምደውን ነው ምክንያት የምትለው? ለረብሻና ለብጥብጥ የሚቀርበውን ምክንያት ሁሉ ምክንያት አልለውም፡፡ እንደ ርግብ ገብቶ እንደ እባብ መናደፍ የሰው ልጅ ሥራ አይደለም» ብላ ከነንዴቷ ጸጥ አለች። በጥፊ ልጋጋት ፈለግሁ፡፡ ትልቅ ጦርነት ባንዲት ጥይት ጩኸት ይጀምራል ቢባልም
ታገሥኩ፡፡
«ሁልጊዜ ርግብነት አያስፈልግም፡፡ ቀስ ብሎ አድፍጦ እና ሠርጎ ገብቶ ጠላት የጠላትን አጨብጫቢ አፋሽ አከንፋሽ ሁሉ እየነደፉ መፍጀት ያስፈልጋል፡፡
እንዲሁ እንደ ግመል ብቅ ማለትማ ሞኝነት ነው፡፡ መጀመሪያ
አዲሱ ሐሳቤ እንደማይለወጥ ዐወቂ፡ አሳውቂ፡ ዓላማዬ ደረጃ በደረጃ ማደጉን ለፍሬ መቃረቡን አትዘንጊ፡፡ ምኑ ተይዞና ያድጋል ይፋፋል። ከእንግዲህ”
የመከራ ጊዜ ካለፈ በኋላ ለመገናኘት የቻልነው ምስጢር መሆን የሌለበትን ጉዳይ
ወዲህ እኔ የማውቀውንና በትክክል ያቀድኩትን ሁሉ እፈጽማለሁ። ያ ሁሉ የመከራ ጊዜ ካለፈ በኋላ ለመገናኘት የቻልነው ሚስጥር መሆን የሌለበት ጉዳይ
አምቄ የሁለቱን ሥቃይ በትዕግሥት ለመቋጠር በመቻሌ ነው፡፡ ዛሬ ግን በቃኝ በቃኝ አንገፈገፈኝ!” ብዬ ጃግመኛ ላለመናገር ዝምታዬን ታከናነብኩ፡፡ ዝምታ የንግግሬ ማክተሚያ መሆኑን የተረዳችው የውብነሽ “የእኛ ነገር ሞተ” ማለት
ነው? እዚህ ተወዝፌ የምጫጫሁበት ምንም ምክንያት የለም! ብላ ከመጨረሷ ዕቅጩን ለማሰማት ያህል «አዎ እዚህ ላይ አብቅቷል፡ ሌላ ወሬ ካስፈለገው ግን ዶሮ እስኪደጋግም ማውራት እችላለሁ” ብዪ የምንተያይባትን የሐሳብ መስኮት ሽጎርኳት። ሲያስጨንቃትና ሲያሠቃያት የቆየው ንዴቷ ድንገት በቡጢ መትተው እንዳፈነዷት ፊኛ በመፈንዳቷ “አንተም ያሰብከውን ፈጽም፡ እኛም ባንተ የተነሣ
ከቤት እንባረር፡ ይኽ ሁሉ የምንቸገረኝ ሥራ ነው እንጂ የችግሩ ከባድነት ጠፍቶህ አይደለም፡፡ ካባረርናት በኋላ የት እንደ ገባችና የት እንደ ደረሰች
አናውቅም፣ አልሰማንም ማለት አይጠፋንም» ብላ ትንፋሿን ለመዋጥ ንግግሯን ስታቋርጥ፡
«እከድዬ.» አለች የወዲያነሽ፡፡ እኔስ ሌላ ምን ፍጠሩልኝ ምን
እድርጉልኝ አልኩና? ከዚያ ወዲያ ስላለውን ነገር እኔ ነኝ ባለመብቱ፥ አብራሪው እኔ ነኝ! እናንተማ ካባረራችኋት በኋላ ትሙት ትኑር ምን ታውቃላችሁ? ትልቁ ችግራችሁና አፋችሁንስ ያፈነው ምኑ ሆነና? ስንተዋወቅ.. መግቢያና መጠጊያ በማጣት ሰማይ መሬቱ የሚደፋባት እንደ እኔዋ የወዲያነሽ ያለችው እንጂ
የእናንተ ብጤዋማ ይልቅ አይምሽብን ብዪ የማያዳግመውን አረዳኋት፡፡
«ስመጣም እየከበደኝ ነበር የመጣሁት፡ አሁን እንዲህ የምትሆነው ራሴንችያለሁ ብለህ እኮ ነው! ለእኛም እግዚአብሔር ያውቅልናል፡፡ ራሲንና እናቴን
ማስተዳደር አያቅተኝም፡፡ ይቺ ከነማን ጋር እንደ ተመከረች አውቃለሁ» አለችና የመኪናይቱን በር በርግዳው ወጣች፡፡ ተከተልኳት። እኔ ስንት ዓመት ሙሉ
በመከራና በንዴት ምድጃ ላይ ተገላብጬ ውስጥ ውስጡን እንደ ነፈርኩ መቼ አየሽና?» ብዬ ለሁለታችን ብቻ በሚሰማ ድምፅ ተናገርኩ፡፡ ፈጠን ብዩ ልደርስባት ሞከርኩ፡፡ ደረጃውን ጨርሳ የሰበሰቡን ወለል ስትጀምር እኔ አጋማሹ ላይ ደረስኩ፡፡ ንዴቷን በትዕግሥት ለማሸነፍ ባለመቻሏ ወደ መኝታ ቤት ገባች።
እናቴና የወዲያነሽ እየተሣሣቁ ያወሩ ስለ ነበር በአቸኳኮሏ ሳይገረሙ አልቀሩም፡፡
«ምነው ምን ነካት? ተጣላችሁ እንዴ? የእናንተ ነገር እኮ..» ብላ ዕድሜ የተጫናት ደካማ ሣቅ ሣቀች፡፡ ከፊት ለፊቷ ዘርፈጥ ካልኩ በኋላ አሁን እዚህ ቤት አጠገብ እንደ ደረስን እንዴት ያለ ባል አግኝቼልሻለሁና እሺ ትያለሽ
ወይ?» ብዩ እንደ ቀልድ ጠየቅኋት «አንተ ነህ ወይ የምትመርጥልኝ? ምን አገባህ?» ብላ አፍንጫዋን ነፍታብኝ ሮጠች፡፡ የማታደርገው ትመስላለች» ብዬ ዓይን ያወጣ ውሽት ዋሽሁ። እናቴም «ምን የሷ ነገር ይኸው አይደለች» ብላ
ነገሩን ችላ አለችው:: ወደ ቁምነገር መለስ ብላ ነገረችህ አይደል ሁሉንም? ቀስ ብለን ብናሰማውና ብንፈጥመው ይሻላል ብዬ ነው:: አለበለዚያማ የአባትህን ጠባይ ታውቀዋለህ፣ ቀስ ብለን አስልተን ብንይዘው ይሻላል» በማለት ከሣቅ ገለል ያለ
መልክ አሳየች፡፡
«አዎ ተስማምተናል፡ ጥሬና ጠጠር ሆነናል የቀረውን ደግሞ ነገ ጧት እንጨርሰዋለን፡ ገና እኮ ሳምንት አለ» ብያት እኔና ባለቤቴ ወደ ቤታችን ተመለስን.….
«መርፈድስ አልረፈደም፡ የሚያስቸኩል ጉዳይ ስላለብኝ ነው አልኳት ያለወትሮዬ በማለዳ ተነስቼ ለመሔድ መዘጋጀቴ አዲስ ነገር ለሆነባት ባለቤቴ::
ከነሙሉ የጧት ንቃቷ ቆም እንዳለች «በይ ደኀና ዋይ! ምናልባት በምሳ ሰዓት ከጉልላት ጋር ሳንመጣ አንቀርም» ብያት መንገድ ገባሁ፡፡ሩጫ በተደባለቀበት አረማመድ ከተል ብላ «ትላንትና ማታ ከነእማማ ጋር ምን ነበር የተባባላችሁት?
ረሳኸው እንዴ? ብቻዬን ነው እንዴ የምሔደው?» አለችኝ፡፡ ማን አለሽና? ማን አዘዘሽና ነው የምትሄጂው? አርፈሽ ተቀመጪ። የምናደርገው ነገር ሁሉ በአንቺና
በእኔ የጋራ ውሳኔ ብቻ መፈጸም አለበት፡፡ ሐሳቤን ሁሉ ለውጫለሁ፡፡ መብትሽን ከቀሙሽ ሰዎች እጅ መብትሽን መንጠቅ እንጂ መለመን የለብሽም፡ ብያት
ወጣሁ፡፡ ወዲያ ወዲህ ሳልል ወደ ወላጆቼ ቤት ሄድኩ።
ትልቁ የአጥር በር ተከፍቶ ስለ ቆየኝ ዘው አልኩ፡፡ ዘበኛው በረጂም ዕንጨት ላይ የጥድ ቅርንጫፍ አስሮ ግቢውን ይጠርጋል። እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ እንደ ደረስኩ የውብነሽ ጋቢ ለብሳ እንደ ቆመች አገኘኋት፡፡ ፊቷ ተነቅሎ የተጣለ የአረም ቅጠል መስሏል፡፡ ንዴቷ አልበረደም፡፡ የአዲሱን ሐሳቤንና የእኔን ግንኙነት ስለማውቅ ትቻት ወደ ውስጥ ገባሁ፡፡ ከየውብነሽ ጋር ከመታገል ከእናቴ ጋር መነታረክን መረጥኩ፡፡ አውቆ ካጎበደደ ሳያውቅ መሬት የላሰ ይሻላል። እናቴ ከፊቷ ለቆመችው ሠራተኛ ስለ ማድ ቤት ጣጣ የሥራ ትእዛዝ ትሰጥ ነበር። ገባ
ብዬ ቆም ከማለቴ «ቆየት ብዩ እጠራሻለሁ ሂጂ» ብላ አስወጣቻት፡፡ እንዴት አደርሽ» ብዬ ተቀመጥኩ፡፡ ከእግር እስከ ራሴ ቁጣ ባነደደው ዐይን አየችኝ፡፡
መልኳ ተለዋወጠ። እኔ ግን ወይ ፍንክች! በፈገግታ ላይ ፈገግታ ደረብኩ፡፡ እንደ ከዚያ ቀደሙ መሽበሬ ቀርቶ ብርታትና ድፍረት ተሰማኝ። ቆርጦ የተነሣ
ለነፍሱም እይሳሳ» ነው፡፡

የውብነሽ እምቢታዬንና ዕቅዴን ሁሉ ተከራካሪ እና ሀይ ባይ በሌለበት እንዳስፈለጋት እየተነተነች እንደ ነገረቻትና እናቴም በዚሁ የተነሣ መናደዷ
ገባኝ፡፡ እኔ ግን እንኳንስ አንዲት የውብነሽ አእላፋት መሰሎቿ እንኳ ተሰብስበው የሆነ ያልሆነውን ሲወሻክቱ ቢያድሩ. ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ አልኩና ዝምታን
ቀጠልኩ፡፡ ወለሉንና የጫማዬን አካባቢ በግልዕ ቅሬታ አፈጠጠችበት።
«ምነው ልጄ? እንዲያ ሳምንህና ስወድህ ሰው ሆንክልኝ ብዬ ስደሰት እንዲህ ታደርግ? ይኸስ የጤናም አይደለም፡፡ ይግደላት ይዘልዝላት ብለህ ነው? ያዳፍንባት ብለህ ነው? ያባትህን ጠባይ ታውቀዋለህ፡ ቀስ ብለን በዘዴና በምክር ከዚያም በሽማግሌ ነው እንጂ አለበለዚያማ ይፈጀናል። መስሎህ ነው እንጂ አንተም አይቀርልህ፡ ምን አደረግሁህ? ምን በደልኩ? ልጄ ተው? የእኔ የእናትህ ምክር ነው የሚበጅህ?» አለች። ዐይኖቿ ፈዘዙ፡፡ የውብነሽ በዝግታ ገብታ ቆመች። በጭራሽ አላደርገውም፡፡ እኔ የማደርገውን እኔ አውቃለሁ፡፡ በማይረባ ዘዴና በሽማግሌ አማካይነት መብቴን መለመን አልፈልግም፡፡ በእኔ በኩል አልቋል፤ ተጠናቋል። በእኔ ዕቅድና ሐሳብ መሠረት መከናወን አለበት፡፡ የአባቴን ቁጣና ግትርነት በመፍራት በጭንቀትና በሥቃይ እግረሙቅ ታስሬ መኖርና መቆየት የለብኝም» ብዬ ንግግሬን ልቀጥል ስል «አንተስ ማምለጫህንና
መውጫህን ሁሉ ይዘህ የመጣው ይምጣ አልክ፡ እኛስ ምን ይዋጠን? እለቁ ማለትህ ነው? 'ከዚህ ቤት ስታባርሪያት እርጉዝ መሆኗን ካወቅሽ ለምን ያን ጊዜ
አላማከርሽኝም? አልነገርሽኝም?” ብሎ ነው ጉሮሮዬን ይዞ ሲል የሚያደርገኝ፡፡ኧረ ተው በጡቴ ይሁንብህ?» ብላ ልቅሶ ቃጣት።
«አባቴ ከዚህ ቀደም ለምን እንዳልሰማኛ ምስጢሩም እንዴት ሊደበቅ እንደቻለ አፍረጥርጬ የማስረዳው እኔ እንጂ እናንተ አይደላችሁም። መልሶቼን
በሚገባ ስላዘጋጀሁ እናንተን በፍፁም የሚያስነካና የሚያስወቅስ ነገር የለም ብዬ
የየውብነሽን ሁኔታ ለመረዳት መለስ ብዬ አየኋት።
«እንዳጋጣሚ ሆኖ የአንተ ዝግጅት አንተን ብቻ ጠቅሞ እኛን የሚጎዳና የሚያጉላላ ከሆነ ምን ጥቅም አለው? መጀመሪያ የተለማመጥከንና ቀስ በቀስ
የተጠጋኸን ለዚህ ኖሯል እንዴ?» ብላ በንቀት ዐይን አየችኝ፡፡ መናናቅ ከሕሊና መሻከር የሚመነጭ ጥላቻ መሆኑን ስለማውቅ ለጊዜው ንቀቷን በንቀት አልደቃሁትም፡፡
«አዎ ልክ ነሽ፡ አጋጣሚ ግን ሙሉ መተማመኛ አይደለም፡፡ እኔ ስለ
ራሴ ብቻ የማስብበትና የምጨነቅበት ጊዜ እየበቃ ነው:: 'የየራስህን ማሳ ብቻ እረስ” ማለት ጠባብ ከራስ በላይ ንፋስ ፍልስፍና ነው፡፡ ለሌሎች መልካም እና ጠቃሚ ውጤት ለማስገኘት ስል እናንተንም ቢሆን አጋልጣለሁ፡፡ የሌሉች የቆሰለና የተሠቃየ ጀርባ ለእናንተ የድሎት ሜዳ መሆን የለበትም፡፡ አትጨነቁ ! በማቀርበው አስተያየትና የመከራከሪያ ሐሳብ ሁሉ አትደንግጡ፡፡የሚያወጣችሁ ተግባራችሁ እንጂ ፋይዳ ቢሱ ፍርሃታችሁ አይደለም። ሰው
እውነትን መፍራት የለበትም፡፡ እኔ ግን አባቴ የሚሽሻትንና የሚጠላትን እውነት እሻታለሁ፡፡ እውነት የብዙዎች መብት በመሆኗ በኃይለኛች መዳፍ ውስጥ
ላዝንታለም አትኖርም፡፡ እውነት የራሷ ትንሣኤ አላት። የተበደሉ ሁሉ በመራራ ትግል ያገኟታል። ከተበደሉት መኻል አንዷ የወዲያነሽ ናት። እውነት ስትናገር
የሚፈራና ተናጋሪውንም የሚያፍን የእውነትና የሕዝብ ጠላት ብቻ ነው።
«ከእንግዲህ ወዲያ የወዲያነሽ አግባብነት ለሌለው የይቅርታ ጥያቄ ጫማ አትልስም፡፡ ከእንግዲህ ለተገዢነት አታጎበድድም፡፡ ክብረ ሕሊናዋን
በማይነካና እኩልነቷን በማይፃረር አቀራረብ ብቻ እጅ ትነሣ ወይም ትታረቅ ይሆናልም ፡፡ይህ የማይሻር እምነቴ ነው ብዬ ለእናቴ የሚገባትንና የማይገባትን
ሐሳብ ተናገርኩ። የተናገርኩት ሁሉ ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ሆነ፡፡ በትካዜ ያመቀችውን አየር ወደ ውጪ ከለቀቀች በኋላ «አይሄሄ! ይኸማ ምን መላ
አለው! ምንም መላ የለው! ልጅህን ካየና ከሰማ በኋላ ያንን ሁሉ ታሪክ ሊሰማ ደግሞ ሌላ ማንንም አይደለም፣ እኔኑ ነው አናቴን የሚገምሰኝ፡፡ ይህን የመሰለ ልጅ በከንቱ አሳጥተሽኝ ነበር፡ እረ እንዲያውም የገደልሽኝ ያህል ነው ብሎ ነው እንደ ነብር ዘሎ የሚከመርብኝ፡፡ በቀላሉም አንገላገል» ብላ ውስጥ ውስጡን
እድራጎቴንና ሐሳቤን ለመራገም ወደ ሰማይ አንጋጣ እየች፡፡ አቡዩ አንተ ታውቁልኛለሁ፡ አንቱዉ እርዱኝ ኧረ እንዲያውም እፈራርዱኝ' ማለቷ ነበር።
ባቀረብኩት ሐሳብ ሳንጣጣጣምና ሳንግባባ ቀረን፡፡ እናቴ ለዚያች ለጭንቅ አማላጅዋ
አቤት እንደምትልብኝ አውቃለሁ። እሷ ግን ለእናቴም ሆነ ለባለቤቴ ኣታዳላም፡፡ የውብነሽ ግን "ልዝብ እባብ ማለቷ የማይቀር ነው፡፡ «ደኅና ዋሉ» ብያቸው ስወጣ መልስ አልመለሱልኝም፡፡..

#አይብቀልብሽ
የተንቤን እቅፍ የናፈቀው
የወሎ ሸህ የመረቀው
እንደጴጥሮስ ግፍና ሞት የሰቀቀው
እንደሉላ ዳር ድንበሩ ያስጨነቀው
እምቢ ባይ ነው ዓለም ሲያውቀው::
ያደፈረሱት እንዲጠራ በዕንባ ፀሎተኞች
በደመም ወንዝም ጅረት የምንጠራ አንደኞች
ከመንገድ የተሰነካከልን
በስልጣኔ ሰማይ ያከልን
ወጥተው ቀሩ መባላችን
ግድ ያልሰጠን ሞት ምናችን
ሰው ምናችን?
ደም ምናችን?
አሜን በይ አንቺዬ ደግሞም እንዳይሰጥሽ
እንዲህ አይነቱ እሾህ አይብቀል በቅጥርሽ፡፡
አሜን በይ አንቺዬ ይበቃሽ የቃል ቁማር
በፊደል ነው እንጂ በበደል ከመማር
ሀ ሲባል ቆጥረናል የሞት አቦጊዳ
ጦርነት ለመደሽ መስሎልሽ እንግዳ
አይብቀል
በሰሜን
የሚያርሳኝ ስሜን፡፡
አይብቀል
በደቡብ
ይጥፋ የዘር ህሙም፡፡
አይብቀል
በምዕራብ
ችግርና መራብ፡፡
አይብቀል
በምስራቅ
ጭንቅሽ በዛው ይራቅ፡፡
የተንቤን እቅፍ የናፈቀው
የወሎ ሸህ የመረቀው
እንደጴጥሮስ ግፍና ሞት የሰቀቀው
እንደሉላ ዳር ድንበሩ ያስጨነቀው
እምቢ ባይ ነው ዓለም ሲያውቀው፡፡
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
የተንቤን እቅፍ የናፈቀው
የወሎ ሸህ የመረቀው
እንደጴጥሮስ ግፍና ሞት የሰቀቀው
እንደሉላ ዳር ድንበሩ ያስጨነቀው
እምቢ ባይ ነው ዓለም ሲያውቀው::
ያደፈረሱት እንዲጠራ በዕንባ ፀሎተኞች
በደመም ወንዝም ጅረት የምንጠራ አንደኞች
ከመንገድ የተሰነካከልን
በስልጣኔ ሰማይ ያከልን
ወጥተው ቀሩ መባላችን
ግድ ያልሰጠን ሞት ምናችን
ሰው ምናችን?
ደም ምናችን?
አሜን በይ አንቺዬ ደግሞም እንዳይሰጥሽ
እንዲህ አይነቱ እሾህ አይብቀል በቅጥርሽ፡፡
አሜን በይ አንቺዬ ይበቃሽ የቃል ቁማር
በፊደል ነው እንጂ በበደል ከመማር
ሀ ሲባል ቆጥረናል የሞት አቦጊዳ
ጦርነት ለመደሽ መስሎልሽ እንግዳ
አይብቀል
በሰሜን
የሚያርሳኝ ስሜን፡፡
አይብቀል
በደቡብ
ይጥፋ የዘር ህሙም፡፡
አይብቀል
በምዕራብ
ችግርና መራብ፡፡
አይብቀል
በምስራቅ
ጭንቅሽ በዛው ይራቅ፡፡
የተንቤን እቅፍ የናፈቀው
የወሎ ሸህ የመረቀው
እንደጴጥሮስ ግፍና ሞት የሰቀቀው
እንደሉላ ዳር ድንበሩ ያስጨነቀው
እምቢ ባይ ነው ዓለም ሲያውቀው፡፡
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍2
ይቸም እድሜ ሆና፣
'ያላየሁት የለም' ስትይ ነበር አሉ?
ይችም ዘመን ሆና፣
አንቺም እንደሌሎች
'አቤት ወንዶች' ብለሽ አማረሻል አሉ።
አይገርምም?
ልብ 'ለጋ' የለውም!
ያው የመኖር ቀመር...
በዚህ ክፉ ዘመን አንዳች ደፍሮ ማፍቀር፣
ልብን አሰብሮ ሰባራውን መቁጠር።
አይ ወንዶች አትበይ ወይ ሴቶች አልልም፣
ከዘመን ተቃርኖ ያሸነፈ የለም።
ይልቅ ነይ ግቢ፣
ለጋ ልብ ይዘሽ ማጣት ካዘለው ደሳሳ ቤቴ፣
አካልሽን ልልበስ ሁኝ አካላቴ፡፡
ነይ እንፋቀር፣
ነይ ልብ እንስበር!
✍ ?
'ያላየሁት የለም' ስትይ ነበር አሉ?
ይችም ዘመን ሆና፣
አንቺም እንደሌሎች
'አቤት ወንዶች' ብለሽ አማረሻል አሉ።
አይገርምም?
ልብ 'ለጋ' የለውም!
ያው የመኖር ቀመር...
በዚህ ክፉ ዘመን አንዳች ደፍሮ ማፍቀር፣
ልብን አሰብሮ ሰባራውን መቁጠር።
አይ ወንዶች አትበይ ወይ ሴቶች አልልም፣
ከዘመን ተቃርኖ ያሸነፈ የለም።
ይልቅ ነይ ግቢ፣
ለጋ ልብ ይዘሽ ማጣት ካዘለው ደሳሳ ቤቴ፣
አካልሽን ልልበስ ሁኝ አካላቴ፡፡
ነይ እንፋቀር፣
ነይ ልብ እንስበር!
✍ ?