#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
....ወደ ወላጆቼ ቤት በሔድኩ ቁጥር መኪናዬን የማቆማት ከአካባቢው
እርቄ ነበር። በሩን እንዳንኳኳሁ ወዲያው ተከፍቶልኝ ገባሁ። በአሁኑ ጊዜ እኔና
ያ ቤት ማንና ምን መሆናችንን ዘበኛው አሳምረው አውቀውታል። ምድረ ግቢው ውስጥ ያሉት የኮክ ዛፎች፣ ኮባዎችና ሌሉቹም አትክልቶች ሁሉ የቀድሞ
ውበታቸውን የተጎናጸፉ መስለው ታዩኝ። እንድ ጊዜ ቆም ብዩ ዙሪያውን ካየሁ
በኋላ በቀጥታ ወደ ቤት ገባሁ። መመላለሱንና ወጣ ገባ ማለቱን አዘውትሬው ስለነበር ፍርሃትም ሆነ ኃፍረት አልተጠጉኝም፡፡ እሑድ እሑድ ባለነገር እንግዳ ስለማይበዛ ከአባቴ እጅ ያንዱ መልአክ መልክአ እንቶኔ አይታጣም፡፡ ግባ ስል የአባቴ ነጭ ጋቢ ቤቱን ተጨማሪ ውበት ሰጥቶታል። እናቴ የለበሰቻት ወሃ ሰማያዊ ጥለት ያላት ቀሚስ ከሩቅ ሲመለከቷት ጭጋግ የጋረደው ሰማይ ትመስላለች።
የውብነሽ በጊዜው ስለ እኔ በምታወራው ወሬ የወላጆቼ ሸካራ ስሜት ለስልሶ ውጥረቱ በመላሳቱ መሠረታዊ አስተሳሰባቸው ሳይሆን ተራ ዕለታዊ
አስተያየታቸው በመጠኑ ተለውጧል፡፡ ሁለቱም በፈገግታ ተቀበሉኝ፡፡ በሕሊናዩ
ውስጥ የለውጥ ጮራ ጨረረ፡፡ በአቀባበላቸው የተዝናናው ሕሊናዩ እጅ አነሣሰንና ሰላምታ አሰጣጤን አሳመረው:: መምጣቴን በድምፄ ያወቀችው የውብነሽ የቤት ውስጥ ቀላል ልብስ ለብሳ ከጐኔ ተቀመጠች፡፡ በውስጤ የተጠነሰሰውን ዓላማና እምነት አባቴ ፊት በዐይነ ሐሳብ አቀረብኩት። የእኔ ለጋ እምነትና የአባቴ
ግብዝ ሐሳብ ተፋጠጡ፡፡ የእኔዋ ሐሳብ በዳመራ ነበልባል ውስጥ ዘሎ ለማለፍ
እንደሚፈልግ ሰው ስትዘጋጅና የአባቴ ግትርነት በፈሪዎች መካከል እየተጎማለለ
እንደሚያሳግድ ጀግና ተኮፍሶ ታየኝ፡፡ እናቴ ፈቷን ፈታ አድርጋ ለስስ ባለ
የእናትነት ድምዕ «አረ ዛሬስ አምሮብሃል እሰየው! አባትህ እንዳለው ልብ ልትገዛ
ነው መሰል? እየተመላለስክ መጠየቁንም ሥራዬ ብለህ ይዘኸዋል፡፡ ታዲያ እንዲህ
እንዳማረብህና ሙሽራ እንደ መሰልክ ወደ ቤትህ ናና እንደ ዱሯችን ተቻችለን
አብረን እንኑር፡፡ ዕድሜ ላባትህ እንጂ ምን ጠፍቶ! ለወግ ለማረጉ ነው እንጂ
አንተም ራስህን ችለሃል። ከእንግዲህ ልጅነት የለም። እኛም እኮ እያደር...»
አለችና ንግግሯን ሳትደመድም የተገረፈ ልጅ እንደምታባብል እናት አቆላመጠችኝ
እባቴ ወለድ ለመቀበል እንዳሰፈሰፈ አራጭ ዐይን ዐይኔን እያየ መልክአ
ጊዮርጊሱን ወደ ጋቢው ውስጥ ሸጎጠና «የውብነሽማ የእኅትነቷንም እንደሆነ
አላውቅም፡፡ ነጋ ጠባ "አገኘሁት” ነጋ ጠባ እንዴት ናችሁ ብሏል፥ እንዲህ
አድርጎ፤ እንዲህ ፈጥሮ እያለች ጥሩ ጥሩህን ታወራለች እኔስ ጉቦ ሰጥተሃታል
ልበል?» አለና ያቺን በሐሰት ተጀቡና በጉቦ የምትፌጸም ነገር ሳይታወቀው
ተናግሮ ሣቀ። በእናቴ መሪነት የሚረባ የማይረባውን ስናወራ ጥቂት ደቂቃዎች
ከቆየን በኋላ አባቴ ያቺው የወንጀለኛ መቅጫ መጽሐፉ ትዝ ስላለችው ወደ
መኝታ ቤት ገባ። ግልግል አልኩ በውስጤ። ያጠራቀምኩትን ድፍረት ቀስ በቀስ ልጠቀምበት በመፈለጌ ከናቴ ጎን ተቀመጥኩ፡፡ በእኔና በእናቴ መካከል ያለው የፍቅር ገመድ በየወዲያኒሽ የተነሣ ተገዝግዞ ላላ እንጂ ፈጽሞ ባለመበጠሱ
እንደገና ለማጥበቅ አያዳግትም፡፡ እስኪ ዛሬ እንኳ እንዲህ ጠጋ ብለህ
አጫውተኝ' የእናት ወጉ ይድረሰኝ ብላ ባሸበሸበው ፊቷ ላይ ፈገግታ
ረጨችበት። ፊቷ በመጠኑ ሽብሽብ ከማለቱ በስተቀር ወዝና ሙላቱ ባለመቀነሱ መልኳ እንደ ወጣት ሴት ባይማርክም አዲስ ርጥብ ሥጋ ትመስላለች፡፡ አንገቷን ወደ ጎን ዘንበል አድርጋ ዐይን ዐይኔን እያየች እስኪ አፈር ስበላልህ ንገረኝ፡፡ ወዲያ ወዲህ ቢሉት ምንም መላ የለው፡፡ ከእኔ ከእናትህ የምትበልጥብህና አይዞህ አይሀ የምትልህን አግኝተህ እንደሆነም አትደብቀኝ፡፡ ኧረ መቼ ነው ጓዝህን
ጠቅልለህ የምትመጣው?» አለችና ከመጀመሪያው በበለጠ ትኩር ብላ ተመለከተችኝ፡፡
ከዚያች ከምወዳትና እንደ ነፍሴ ከምሳሳላት ከየወዲያነሽ ጋር ትዳር
ይዤ ንብረት መሥርቻለሁ። ምን የመሰለ ታይቶ የማይጠገብ ወንድ ልጅ ወልደናል። እሷንም በቅርብ ጊዜ ይዣት እመጣለሁ። አስታርቃችኋለሁ” ብዬ ልንገራትና ለእኔ አንድ ግልግል፣ ለእርሷ ደግሞ ያልታሰበ መርዶ በማርዳት
'ጉዷን ልየው ይሆን?” በማለት ገና ያልበሰለና ከገለባ የቀለለ ሐሳብ አሰብኩ፡፡ ላቀረበችው ጥያቄ መልስ የምትጠባበቀዋ እናቴ በግራ እጅ ጣቶቿ አፏን እየተመተመች «በል እንጂ ንገረኝ? ምነው ሰምተህ ዝም አልክ?» ብላ ጥያቄዋን ደገመች። የጠየቀችኝን ትቼ ያሳለችኝን ጀመርኩ፡፡
«ለጠየቅሽኝ ጥያቄ መልስ ከመስጠቴ በፊት አንድ ነገር ብለምንሽ እሺ
ትይኛለሽ ወይ? አዎን ካልሽ እና ከማልሽልኝ እኔም ለጥያቄዎችሽ ሁሉ ደስ
በሚያሰኝ ሁኔታ እመልስልሻለሁ» ብዪ አዲስ ነገር ደቀንኩ፡፡
የእመ ብርሃን ያለህ! ደግሞ የምን ማይልኝ አመጣህ? እኔ እናትህ
ባልምልልህስ እንዴት ብዬ እንቢ እልሃለሁ፡፡ ካንተ ከልጂ የምሰስተው ምን ነገር አለና ነው?» ብላ የመሳቢያ ሐሳቧን አቀረበች፡፡ የአንደበቷ መላላት መንፈሴን
ሽምጥ ለማስጋለብ ረዳኝ፡፡ «ኧረ ለመሆኑ እኔ የምለምንሽንና የምጠይቅሽን ሁሉ
ዐይንሽን ሳታሺ ትፈጽሚልኛለሽ ወይ? ብዬ አዝማሚያዋን ለማወቅ በየዋህ መሰል አቀራረብ ስሜቷን ለመረዳት ጓጓሁ፡፡
«ልጄ ሙት አልልህም! የምትለኝን ሁሉ ባስፈለህ ጊዜ አደርግልሃለሁ፡፡ አንተ ልብ ግዛልኝ እንጂ፣ አንተን መንፈስ ቅዱስ ይጠጋህ እንጂ ለምን ባጉቼስ
አይሆንም» አለችና የልብ ልብ ሰጠችኝ፡፡ «ለመሆኑ» ብዬ ስጀምር ያን ምንም
ያልነበረበትን የቀሚሷን ጫፍ ልክ አቧራ እንደ ነካው እስመስዬ አራገፍኩና
ይህን አድርጌያለሁ፣ ይህን ፈጽሜያለሁ፣ ይህን አጥፍቻለሁ፣ የተጣሉ ወይም
የተኳረፉ ሰዎች አምጥቼ ታረቁልኝ እላለሁና፣ ታረቂልኝ ብዬ ብጠይቅሽ እሺ
ትይኛለሽ ወይ?» አልኩና ዙሪያ ጥምጥም ሄድኩ፡፡
እኔ ልሙትልህ! የምትጠይቀኝን ሁሉ እፈጽምልሃለሁ፡፡አንተ ደግሞ
በበኩልህ አባት እናቴ ቤት ብለህ ተመለስልኝ፡፡ በስተርጅና ወግ ማዕረግ አሳየኝ» ብላ ገና በመቀጠል ላይ እንዳለች ፋታ ሳልሰጥ «ምንጊዜም ብለምንሽና የፈለግሁትን ይዤ ብቀርብ ሳትቀያሚና ሳታሳፍሪ ትቀበይኛለሽ ወይ? ብዬ ውስጥ ውስጡን ለመጪው ጥቅሜ አደባሁ፡፡
የውብነሽ ጣልቃ ገብታ ወሬያችንን ባለማጨናገፏ ተደሰትኩ፡፡
«ታማኙን ወዳጄን አቡዩና!» ብላ በእምነት ፈረሷ ላይ አፈናጠጠችኝ::
«እኔ በበኩሌ ከጥቂት ቀናት በኋላ አንድ በጣም ድንቅ የሆነ ነገር ኣምጥቼ
አሳይሻለሁ» አልኩና ወደ የውብነሽ መለስ አልኩ፡፡ ልብ ለልብ በመተዋወቃችን በዐይናችን ተሣሣቅን፡፡ «እሰየው ተመስገን! አቡዩ ያውቃሉ! ምንጊዜም ረዳቴና ሰሚዩ ናቸው» ብላ እጄን ስባ ሳመችው:: ኃይለኛ ንፋስ በሌለበት ሰማይ ላይ እንደምትንሳፈፍ የማለዳ አሞራ አእምሮዬ በደስታ ተንሳፈፈች። አዝመራው ካማረልኝ የተግባር እርሻዪን ጀምሬያለሁ። የውብነሽ የወሬያችን ተካፋይ ለመሆን በመፈለጓ «አሁንስ እኔንም አስጎመዣችሁኝ የአሁኑ ፍቅራችሁስ ያጓጓል። ምነው እኔ አንድ ነገር ስለምንሽ ዓመት ሙሉ ታስደገድጊኛለሽ?» አለችና ለእኔ
የተሰጠኝን የተስፋ ቃል ሆን ብላ አጋነነችው፡፡
«አንቺ ምን ቸገረሽ ልጀ? እኔ ለስንቱ ታቦት እንደ ተሳልኩ የት አየሽና? ተማጥኜ ተማጥኜ ነው አሁንም ቢሆን ለዚህ የበቃልኝ፡፡ አንቺ ደግሞ በእኔና በልጄ መኻል ምን ጥልቅ ኣደረገሽ? የሚጠይቀኝን ሁሉ አደርግለታለሁ»
ካለች በኋላ ከደረቷ ውስጥ የምታምር አረንጓዴ መሓረብ ኣውጥታ ምንም
ጉድፍ ያልነበረባትን አፍንጫዋን ጠረገቻት፡፡
ነገር አቃኝልኝ ያልኳት ይመስል

👍3👏2
እኔው የመረጥኳትን ሴት እኔው ራሴ መርጨ አግብቻለሁ ወይም ላገባ ነውና መርቂልኝ ብሎ ቢመጣስ?» ብላ የአዲስ ነገር እሳት ለኮሰች፡፡ በድንጋጤ ደነዘዝኩ፡፡
«ኤጂ! ምነው ደኅና ወሬ አጣሽ እንዴ? ካባት ባሻ ያየህ ይራድን የመሰለ መኳንንት አባት፡ ከእናት እኔን የመሰለች ሴት ወይዘሮ እናት እያለው፣ ምነው ወግና ማረግ አለማየቱ በይ? አያደርገውም እንጂ ካደረገውም አጥንትና ደሟ የጠራ የጨዋ ልጅ፣ የደኅና ሰው ልጅ ከሆነች ምን ከፍቶኝ፡፡ መርጦ ማግባት በእርሱ አልተጀመረ? አያደርገውም እንጂ ከሆነ በኋላስ ምን ይባላል... አይጣል ነው፡፡
«እኔ የጠላሁበትና አገር ጉድ እንዳይል ብዬ ቆሽቴ የደበነው እሱም እስከ
ዛሬ ድረስ ጀርባውን የሰጠኝ ያቺን የምንተዋወቅባትን ካደረገ ወዲህ ነው» ብላ ያለፈው ነገር ሁሉ በጊዜ ደለል ተቀብሮ የተረሳ ለማስመሰል ዕድሜ በመጠኑ ያበለዛቸውን ጥርሶቿን ፈለቀቀች።
ከአሳላፊ ጋር ተመሳጥሮ አሁንም አሁንም ዋንጫው እንደምትሞላለት ዕድምተኛ ውስጤ በደስታ ሽቅብ ዘለለ። ደግ አደረግሽልኝ ይቺን ሙጢ አፉ
መዘዘኛ፡ የሰው መዘዘኛ ምን የምትለኝ መስሎሽ ነበር? እናቴ እንጂ ባላንጣ
መሰለችሽ እንዴ?» በማለት የውብነሽን በለሰለሰ አነጋገር አፏን አስያዝኳት።
«ያቺስ የዚያን ጊዜዋ ያቺ አንቺና እርሱ የምትተዋወቁባት ዘንካታዋ...»
ብላ የሐሳብ ጉማጅ ይዛ ስትቀርብ «አንቺ ደግሞ ነገር መጠንቆል ትወጃለሽ!
እኔስ ያንቺ ነገር ምን ይሻለኛል?» ብላ ነገሩ እንደ ገባት ገለጸች፡፡ ዝምታ ሰፈነ።
እንደገና «እሷም ስሟ ገረድ መሆኑ ነው እንጂ ማለፊያ ቆንጆ ነበረች። የባሻ ያየህ ይራድ ልጅ ከገረድ ተልከሰከሰ እንዳይባል ብዬ ነው እንጂ ምን እንከን ይወጣላታል? አሁን መቼም ጨዋታ ነው፣ በዚህ ላይ ያለፈ ነገር ነው። ሰው አክባሪ፣ ታዛዥ፣ በዚያ ላይ አንገተ ሰባራ ነበረች። እኔን የሚያንገበግበኝ ያንዩ አንዱ ጋ ኣስጠግቻት ከተገላገለች በኋላ ሰንበትበት ብዬ ልጁን መንጭቄ ያለማስቀረቴና እሷን ያለማባረሬ ነው:: እሷ እኮ የትልቅ ሰው ዘር ሳትሆን አትቀርም ነበር አቡየና! ታስታውቅ ነበር» አለችና በድንገተኛ ጸጸትና ትዝታ
ዝም አለች። በነገር ዙሪያ ሲያኮበኩብ የነበረው ምላስ ነገር ሳይዘነጥል በመቅረቱ በሥጋት የቋጠርኩትን እየር እንደ ልቤ ተነፈስኩ፡፡
«አያደርገውም እንጂ ቢያደርገውስ ከሆነ ወዲያ ምን ይባላል? ያለችውና «ገረድ መሆኗ ነው እንጂ የትልቅ ስው ዘር ሳትሆን አትቀርም ነበር» ያለችው አባባል ልቤን ገመሰው:: ከእሷ የሚወለደውን ልጅ ከፈቀደችና ከወደደችው እሷን የምትጠላበትና ዐይንሽ ላፈር የምትልበት ምክንያት ምንድነው? እያልኩ ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡ ስለ የወዲያነሽ በቀረበው ኣንዳንድ ትክክለኛ ምስክርነት ግን ከልብ ኩራት ተሰማኝ፡፡ ከወሬያችን ውስጥ ጠቃሚ ፍንጮችና አስተያየቶች በማግኘቴ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንዲፈጸም ላሰብኩት ጉዳይ ጥሩ መንገድ ከፈተልኝ:: የጉዳዬን የመጀመሪያ ደረጃ በማይረባ ጭቅጭቅና መካረር ሳይሆን በደኅና ደኅና ዘዴዎች ካስፈላጊው ፍጻሜ ላይ ላደርሰው እንደምችል አረጋገጥኩ፡፡ ምንም እንኳ የእናቴን አስተያየት በመጠኑ በመለወጥ
ጥቂት የድል ርምጃዎች እንደማደርግ ባውቅም፣ በአባቴ በኩል ግን ብዙ ውጣ
ውረድ፣ ዐይኑን ያፈጠጠ ኃይለኛ ግብ ግብ እንደሚጠብቀኝ ልቦናዩ በሚገባ
ያውቃል፡፡ ሆኖም ቀረም የመጣው ይምጣ እንጂ የየወዲያነሽ የሰው ልጅነት
ክብርና እኩልነት፣ እንዲሁም የሕሊና ነጻነት ከሁሉም ነገር በላይ ስለሆነ
ማናቸውንም አጥቂ እጋፈጠዋለሁ፡፡
ምሳ ቀርቦልን ከበላን በኋላ ወደ መኝታ ቤት ዘልቄ አባቴን ስሰናበት
«ይኸን ወራት ደኅና ሰው ሆነሃል፡፡ አባትና እናትን የሥጋ ዘመድን የሚያህል
የለም፡፡ ነገሩን ችላ ያልኩት አውቀህ እንደምትመለስ ኣውቄ ነውና አንተም
አስብበት። ሰሞኑን የማጫውትህ ነገር አለና እስኪ ብቅ ብቅ በል» ብሎ ወደ
ነጋሪት ጋዜጣው መለስ አለ፡፡ የውብነሽ ማእድ ከተነሣ ጀምራ ልብሷን
ስትቀያይርና በመጠኑም ስትዋዋብ ስለነበር ጥቂት ተቀምው እንደጠበቅኋት
ከተፍ አለች፡፡ መንገድ ገባን፡፡....
💫ይቀጥላል💫

👍4
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ሥራ ከጀመረ አንድ ዓመት ሞላው። ከእናትና ከእህቱ ተለይቶ በናፍቆታቸው እየተሰቃየ አንድ ድፍን ዓመት አስቆጠረ። በአማረችና በሱ መካከል የተጀመረው ጓደኝነትም ውስጥ ውስጡን የሚያብከነክን የሚያብስለስል ነገር ግን ገሀድ ያልወጣ ድብቅ ቢሆንባቸውም የሙቀት መጠኑንና የእድገት ደረጃውን ጠብቆ በመጓዝ የአንድ ዓመት ልደቱን አከበረ።
ለአዲሱ አለቃው ለልዑል ሰገድ አስጨናቂና ፈታኝ ሰው እየሆነበት
ከመጣ አንድ ዓመት ሞላው። በዩኒቨርስቲ የሚከታተለው ትምህርት አካውንቲንግ መሆኑ በፍጥነት ወደ ሂሳብ ክፍል ለመዛወር ያስቻለው ቢሆንም አዲሱ አለቃው ልኡልሰገድ በዝውውሩ ደስተኛ አልሆነም። ገናለገና በትምህርት ይበልጠኛል የወደፊት የዕድገት ተስፋዬን ያጨልምብኛል በሚል ፍርሃት ጥምድ አድርጎ ይዞታል። በአንፃሩ ደግሞ ከቀድሞው አለቃው ከሽመልስ ጋር የነበራቸው ግንኙነት ተጠናክሮ ላለፈው
አንድ ሙሉ አመት የሚያስቀኑ ጓደኛሞች በመሆን ዘልቀዋል፡፡ ሁለተኛው ዓመትስ በምን ይቀጥል ይሆን? በሱ በኩል ሁለተኛው ዓመት የእናቱንና የተወለደባት ቀዬውን ናፍቆት ለመወጣት የዓመት እረፍት ፈቃዱን ወስዶ ወደ ባሌ የሚሄድበት፣ ከአማረች ጋር ያለው ግንኙነት ይበልጥ የሚጠናከርበት፡ዘይኑን አምጥቶ አዲስ አበባ ትምህርት እንድትጀምር የሚያደርግበት ዓመት እንደሚሆን ዕቅድ ይዟል::
የጌትነት እናት ኑሮዋ እያማረ ደስታዋ እየጨመረ በመሄዱ “ ተመስገን
ፈጣሪዬ ላንተ ምን ይሳንሀል?"እያለች ፈጣሪዋን ማመስገን ከጀመረች አንድ ዓመት ሞላት። ዛሬ ዕድሜ ለጌትነት ችግር ተወግዷል። በየማሳው ላይ እየዋሉ በፀሃይ መጠበስ ቀርቷል። ደብዳቤው በየጊዜው ይጎርፋል አለሁልሽ የሚላት ልጅዋ ያለማቋረጥ ተቆራጭ አድርጎላታል።"ገበያ እንዳትወጪ አቅም የለሽም እኔ አለሁ አይዞሽ!” ነው የሚላት። ወደ ዓመቱ መጨረሻ ላይ የላከው ደብዳቤ ደግሞ በሚቀጥለው ዓመት ዘይኑን ወስዶ ለማስተማር ያለውን ሀሳብ የሚገልጽ ሆነ፡፡ ከእናቷ መለየቷን ባይወደውም በቅርበት አስፈላጊውን ክትትልና እገዛ እያደረገላት ጥሩ ደረጃ ላይ
እንድትደርስ ሌላ አማራጭ አልነበረውምና ይህንኑ ገልፆ ደብዳቤ ለእናቱ ጻፈላት፡፡
እናቱ አስካለ ደብዳቤው ሲደርሳት አላንገራገረችም፡፡ ሀሳቡን በደስታ ተቀበለችው። ዘይኑ ግን ሀሳብዋ ለሁለት ተከፈለ። የወንድሟን ናፍቆት ለመወጣት መሄዱን ስትፈልገው ከእናቷ መለየቱ ደግሞ ሆዷን አባባውና መንታ መንገድ ላይ ቆመች። ትንሿ ዘይኑ ለአንድና ብቸኛ ወንድሟም ሆነ ምትክ ለሌላት እናቷ ያላት ፍቅር እኩል ነው፡፡ እናት ደግሞ ዘይኑን ማጣቷ ትልቅ ጉዳት ነው። በተለይ "ማታ ማታ እቅፍ እያደረገቻት እስቲ ጀርባዬን እከኪልኝ ከፍ ዝቅ ጎሽ! አዎን እንደሱ!" የምትላት ደክሟት ስትገባ ቤቱን አሟሙቃ የምትጠብቃት ጉድ ጉድ የምትልላት
ሁሉ ሊቀር ነው። ዘይኑም ከዚያ ከምትወደው ከሚሞቃት የእናቷ ጉያ
ልትነጠል ነው፡፡ እንኮኮ እያለ ንፍጧን እየጠረገ ያሳደጋት ታላቅ ወንድሟ
ደግሞ የአባቷ ምትክ አባቷም ወንድሟም ነው። ወሬውን ከስማች በኋላ ልቧ ወደ ወንድሟ ሲጋልብ የእናቷ ፍቅር ደግሞ ሉጋም እየሆነባት በሀሳብ ስትባክን ከረመች፡ የስፈሯ ልጆች አዲስ አበባ ወንድም” አላት እያሉ ሲያደንቁላት ሲያጋንኑላት ትሰማለች፡፡ አዲስ አበባ የሚያምር የሚያጓጓ አገር መሆኑን ስለምትስማ የዘይኑ ትንሽ ልብ በመጨረሻ ላይ አዲስ አበባ በመሄድ ሃሳብ ተማረከች፡፡
"ለመሆኑ ልትልኪያት ወሰንሽ?" አሉ ወይዘሮ ዘለቃ የደብዳቤውን
መንፈስ ከተረዱ በኋላ፡፡
"ምን ይደረግ ታዲያ እትዬ ዘለቃ? ትምህርቷን መቀጠል አለባት። ያለበለዚያ ማቋረጧ ነውኮ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ብቸኝነት ነፍሱን ሊያወጣው ነው፡፡ ሄዳ ትማር ሌላ ምንም አማራጭ የለም" አለችና ዘይኑን ትኩር ብላ በጉጉትና በፍቅር አስተዋለቻት፡፡ በዘይኑ ውስጥ አልፋ ጌትነትን ቃኘች እንደ አህያ ጡት ያሏት ሁለት ልጆቿን አንዷን በእውን ሌላውን በምናቧ እያስተዋለች ሳትተነፍስ ለረጅም ጊዜ ፀጥ ብላ ቆየች። ዘይኑ ያንኑ መከረኛ ቡና እያፈላች ነበር፡፡
"አንቺ ዘይኑ አንቺስ ምን አሰብሽ?" ብለው ጠየቋት ወይዘሮ ዘለቃ።
"እኔ ምን አውቃለሁ ሂጂ ካለችኝ እሄዳለሁ ቅሪ ካለችኝ እቀራለሁ" አለች ዘይኑ።
"አየሽ ? አየሽ ?ይቺ መናጢ ልቧ ለመሄድ ከጅሏል ማለት ነው፡፡
እናትሽን ለማን ጥለሽ ነው የምትሄጂው አንቺ?! ትምህርት ቀስ ተብሎ ይደረሳል" አሏት፡፡ አሮጊቷ ልጇን መጨቅጨቃቸውን እናት አልወደደችውም፡፡ ሁለቱ ልጆቿ እርስ በርሳቸው እየተደጋገፉ "ወንድም
ጋሻዬ ዘይንዬ" እየተባባሉ እየተረዳዱ በፍቅር አብረው እንዲኖሩላት ነው
ፍላጎቷ። የራሷ ችግር ብቸኝነቷ አልታያትም፡፡ የነሱ ደስታ ነው ደስታዋ
ወንድሟ ትምጣልኝ ብሎ ከጠየቀ ምንም ማንገራገር አያስፈልግም፡፡ መነሳት ብቻ!
"ይተዋት ባክሁ አልሄድም ብትልስ መቼ እሺ እላታለሁ? ሄዳ ትማር፡፡ ዛሬ ከሁሉ የበለጠው ትምህርት ነው፡፡ ጌትዬም ሰው ሆኖ አለሁልሽ የሚለኝ ቢማር አይደል? ዋ! ልጄ በዚህ ላይ ደግሞ ማን አለው? ብቻውን በሰው ሀገር። ትሂድለትና ልቡ ትንሽ አረፍ ይበልንጂ...
የሱ ልብ ሳያርፍ እኔስ የምተኛው እንቅልፍ ምን እንቅልፍ ይሆነኛል? ትርፉ ቅዠት ነው" ዘይኑ በእናቷ አነጋገር ደስ አላት። በልቧ የአሮጊቷን ንግግር አልወደደችውም ነበር። ወደ ወንድም ጋሻዋ በሃሳቧ ተጓዘች።
አዲስ አበባ! ጓደኞቿ የሚያደንቁት ቆንጆ ከተማ! አዲስ አበባ ሄዳ ከወንድሟ ጋር የመኖሩ ነገር በጉጉት ታያት። ልቧ ወደ መሄዱ አደላ። አቤት የዘይኑ ነገር! ደስታ በደስታ ሆነች። ደግሞ ተደስታ ብዙ አልቆየችም፡፡
የእናቷ ነገር መጥቶ እንደገና ከፊቷ ድቅን አለባትና አለቀሰች። ማን እማምዬ እያለ ጀርባዋን ያሻሻታል? ማን ቡና ያፈላላታል? ማን ቤቱን ይጠራርግላታል? እናቷ በብዙ ነገር እንደምትጎዳባት ታያት። ኦና ቤት
ጣራና ግድግዳ ብቻ! አቤት ጣራና ግድግዳ ሰው ከሌለበት ሲያስጠላ?!
እንኳን ደሳሳ ጎጆ የተንጣለለ ቪላ ቤትም ቢሆን ያለሰው አያምርም። እሷ
እንደዚህ ትጨነቅ እንጂ እናቷ እንደሆነች ቆርጣለች። እህቴ ትምጣልኝ
ብሎ ከጠየቀ ጊዜ ሳታጠፋ ቶሎ ልትልክለት ወስናለች።
እናትነት ሰው በመሆን አስተዋይነት ውስጥ ብቻ ሳይሆን ሳይዘሩ ሳያርሙና ሳይኮተኩቱ በርረው በሚኖሩ አእዋፋት ላይ እንኳ ሚስጥሩ ረቂቅ ነው፡፡ ለልጇ ስትል ከድመትና ከጨለሌ ጋር ጦርነት ገጥማ በክንፏም በጥፍሯም ታግላ የምትከላከል ዶሮ፣ ግልገሏ ወደ ገደል ስትወረወር ረጅዋን ተከትላ ወደ ገደሉ የወረደችው አህያ እናት ለልጅዋ ያላትን
ልቅ ፍቅር የሚገልፅ ነው። ዘይኑም ይህንን በደንብ ታውቀዋለች። የሶስተኛ ክፍል ተማሪ ሆና ባነበበችው የተረት መፅሐፍ ውስጥ በጫካ የምትኖር ዋኔ ጫጩቶችዋን በጉያዋ እንዳቀፈች ከተነሳው የሰደድ እሳት ልታስጥላቸው የከፈለችውን የህይወት ዋጋ ታውቃለች። እሳቱን ፈርታ ሳትደነብር ሳትበረግግ ጫጩቶችዋን ለማዳን እንዳቀፈቻቸው በነበልባሉ ተጠብሳና ተቃጥላ ስትሞት በስሯ የተጠለሉት ጫጩቶች በሙሉ ሳይቃጠሉ መትረፋቸውን አንብባ የእናት ፍቅር ምን ያክል ከባድ እንደሆነ አስ
ደንቋታል። የዚያን ያክል ጥሩ እናቶች እንዳሉ ሁሉ ለልጆቻቸው ደንታ ቢስ የሆኑ ምንም አይነት የልጅ ፍቅር የሌላቸው የወለዱትን እያስራቡ ሆቴል ገብተው ጮማ የሚቆርጡ ወላጆች መኖራቸው የሚካድ ኣይደለም፡፡ አንዳንዴ የእናት አንጀት ከጨከነ ከደነደነ ቦታውን የሚረከበው ክፉ መንፈስ ይሆንና የወለዱትን ልጅ ጫካ ውስጥ እንደ ውሻ ወርውሮ እስከ መጥፋትና በምናምን ጠቅልሎ ሽንት ቤት ውስጥ እስከ መጨመር ያደርሳል

። የዘይኑ እናት ግን ለጫጩቶችዋ ስትል ራሷን ለእሳት አሳልፋ በሰጠችው የዱር ዋኔ የምትመስል ለልጆቿ የተለየ ፍቅር ያላት እውነ ተኛ እናት ናት።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የበሬሳ መንደር ተወልዶ አድጎባት ለቁም ነገር የበቃላት ታላቅ እንግዳዋን፣ ምሁር ልጇን ለማስተናገድ ሽብ እረብ በማለት ላይ ትገኛለች፡፡ ወዳጅ ጎረቤቱ ዘመድ አዝማዱ ተሰባስቧል። ጌትነት መኩሪያ ብርቅዬውን ልጅ እንኳን ደህና መጣህ!.. ለማለት፣ ልጃችን ወንድማችን ለማለት፣ እጅህ ከምን? ለማለት፡፡ ብዙዎቹ በዐይን እናውቅሀለን በማለት እጅ እጁን የሚመለከቱ ነበሩ። መቼም ሰው ብዙ ይመኛል።ከተማ ገንዘብ በአካፋ የሚዛቅበት ይመስለዋል። በዚህም የተነሳ የቅርቡም የሩቁም ሁሉም ሽልማት
ፈላጊ ነው፡፡ ጌትነት በጣም ቅርብ ለሆኑ ዘመዶቹና ለጎረቤቶቹ ያልቋጠረው ቅራቅንቦ አልነበረም፡፡ ጥብቆዎች፣ ቀሚስ፣ ቡና፣ ጨው፣ ስኳር... እንደ ቀረቤታቸው እያደለ እያከፋፈለ ሲመረቅ ሲመሰገን ከረመ። የሚቀጥለው ዓመት በአካውንቲንግ የዲግሪ ተመራቂው እናቱ ጎጆዋ መንደሪቱ ኩሌ በአጠቃላይ ጋራ ሸንተረሩ ሣር ቅጠሉ ጭምር ናፍቀውት በዐይኑ ላይ ሄደውበት የአባቱ የመቃብር ቦታ በትዝታ ጎድቶት ሁሉም በዐይኖቹ
ላይ እየተንከራተቱ ስላስቸገሩት ሊጎበኛቸውና የመንፈስ ረሃቡን ሊወጣ
ነው የመጣው፡፡ እናቱ አስካለ ዕድሜዋን ወደ ኋላ እያስቆጠረች በመሄድ
ላይ ያለች ትመስላለች፡፡
ልጅዋ ስራ ከያዘላት፣ ጭንቀትና ትካዜ ጥለዋት ከሸሹ ጊዜ ጀምሮ በየዓመቱ ከውስጧ ወጣትነት እየፈለቀ እንጂ እርጅና እየተጫጫናት አልሄደም፡ሰውነቷ ሞልቷል፡፡የአዲስ አበባን መንገድ የውሃ መንገድ አድርጋዋለች። ልጆቿ ትንሽ የናፈቋት እንደሆነ ሮጥ ብላ ደርሳ አይታቸው ትመለሳለች፡፡ ዛሬ ደግሞ ውድ ልጅዋ ከአዲስ አበባ ገስግሶ ከተፍ ብሉላታል። አቤት ሩጫ?! አቤት መስተንግዶ? ተፍተፍተፍ ከደስታዋ
ብዛት የተነሳ የሩጫ አትሌት መስላለች፡፡ ጎጆዋ ግጥም ብላ በሰዎች ተጨናንቃለች ጌትነት ከላይ ድብዳብ በተነጠፈለት መደብ ላይ ቁጭ ብሎ ዙሪያውን ከበው ዐይን ዐይኑን እያዩ በጥያቄ ለሚያዋክቡት የመንደሩ ነዋሪዎች መልስ ይሰጣል። አቶ አያልነህ ሞት ቀደማቸው እንጂ እንደ
መከሩት አዲስ አበባ ሂዶ ተሳክቶለት ስራ ይዞ እንደዚህ በብዙ ሁኔታ ተለውጦ አምሮበት ቢያዩት ደስታቸው ወደር አይኖረውም ነበር።
“ለመሆኑ ምን ያክል ደመወዝ ይከፍሉሃል?” አሮጊቷ ጉረቤት ናቸው
ጠያቂ፡፡ የወንድ ልጅ ደሞዝና የሴት ልጅ ዕድሜ አይጠየቅም እንደሚባለው ብዙ ሰው እንደዚህ አይነቱን ድፍረት የተሞላበት ጥያቄ አያቀርብም፡፡ ደፍሮ የሚጠይቅ ከተገኘ ደግሞ ሴት ልጅ ከሆነች በምትነግርዎ ዕድሜ ላይ አስር ዓመት ይጨምሩበት ወንድ ልጅ ከሚነግርዎ ደሞዝ ላይ ግማሹን ይቀንሱለት ይባላል። ለዚህ የቀልድ አባባል ቁብ የሌላቸው አሮጊት በየዋህነት ጥያቄውን ሲያቀርቡለት ጌትነት ሳቅ አለና የደመወዙን መጠን ገለፀላቸው።
“ለጊዜው ሶስት መቶ ብር ደርሻለሁ እማማ ወደ ፊት ትምህርቴን ስጨርስ
ደግሞ ደመወዜም ሳይሻሻል አይቀርም”
“ሶስት መቶ?! በወር ነው? በዓመት?”
“በወር ነው እማማኝ ሴትየዋ የገንዘቡ ብዛት አስደንቋቸው አፋቸውን ይዘው ቀሩ፡፡
(ሶስት መቶ ብር አፍ የሚያሲዝ ብር ነበር አይ ጊዜ ለማንኛውም ይሄ ከፁሁፉ ውጭ ነው😉)
የብዙዎቹ ዐይኖች የፈጠጡት የገንዘቡ ብዛት አስገርሟ ቸው ነበር፡፡ ከወዲያ ጥግ የተቀመጠው ዲሳሳ አጠገቡ ወዳለው ወደ ኢዶ ጆሮ ጠጋ አለና...“ይሄ በቡና ቁርስ ያደገ ህፃን ልጅ እኛ ዓመት ሙሉ
አፈር ጭረን የማናገኘውን እጆቹን አሽሞንሙኖ በየወሩ ይዛቀው?ወይ
መማር?!” አለና ቁጭቱን ገለፀ፡፡
ተው እንጂ ዲሳሳ! ጌትነት ነው በቡና ቁርስ ያደገው? ሙት ወቃሽ አትሁን! አባቱ ከሁላችን በላይ አንቀባሮ እንደ ድሃ ሳይሆን እንደ ሀብታም ልጅ ተንከባክቦ ነው ያሳደገው፡፡ ግፍ አትናገር፡፡ መኩሪያ እንኳንስ ለአንድ ልጁ ለሌላም የሚተርፍ ጎበዝ ገበሬ ነበር” በዲሳሳ ድምፅ መጠን ድምጹን ዝቅ አድርጎ ተቃወመው፡፡
ያም ሆነ ይህ በወር ሶስት መቶ ብር ሲበዛበት ነው” ቅንአት ቢጤ ቆነጠጠው
እሱ የኛ ጉዳይ አይደለም፡፡ መንግሥት የሚከፍለው ይገባዋል ብሎ አይደለም እንዴ?የመማርና ያለመማር ትርጉሙ ታዲያ ምኑ ላይ ነው? “በወር በወሩ ሶስት መቶ ብር?!” ነገሩ ያልገባው ሌላው ጎረቤት በድጋሚ ጠየቀ
“አዎን በየወሩ ነው በዓመት ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ብር መሆኑ ነው” አለና በደንብ እንዲገባቸው አድርጎ አስረዳቸው፡፡
“ሀብታም ነሀ! ሀብታም! ጎሽ! ጎሽ! እንዲያ ነው! ያድርግልህ! ልጅ ወልዶ ማስቀናት እንደ አስካላ ነው። የኛዎቹማ... ይቅር ብቻ..ወይ መማር? ወይ መኩሪያ? ከልቡ..” ስለ አባቱ ሊያወሩ የፈለጉት አሮጊት ሃሳባቸውን ሳይጨርሱ አንጠለጠሉት፡፡
“ለመሆኑ ያ ቶሎሳ እንዴት ነው?”
“እንዴ! ጋሽ ቶሎሳ በጣም ደህና ነው ...”
"አንድ ጊዜ የሆነ ወሬ ሰምቼ...እውነት ነው?” ጌትነት ደንገጥ አለ፡፡
“ትንሽ መቀያየማችሁን ሰምቼ ነበር ለመሆኑ አሁን እንዴት ናችሁ?”
“የለ... የለ...የሰው ወሬ ነው። የምቀኞች ወሬ ነው፡፡ የምን ቅያሜ?” ግራ
ቀኙን እያማተረ ፈገግ አለና ወሬ ለማጣራት አፉንና ጆሮዎቹን በጣምራ
ከፍቶ የሚጠባበቀውን ጠያቂ ችላ ብሎ ርእሱን በእንጭጩ ቀጨበትና
ወደ ሌላ ርዕስ ተሸጋገረ።
አስካለ ለመስተንግዶው ስትሯሯጥ ለመጣው እንግዳ ሁሉ ቡና ስትወቅጥ... ስትወቅጥ ...ስትወቅጥ ከርማ ጌትነት ሁሌም እንግዳ ሆኖ በስዎች እንደታጀበ ለአስራ አምስት ቀናት ያክል ቆየና የአባቱን መቃብር ከአንዴም ሁለት ጊዜ ከጎበኘ በኋላ የሁሉንም ናፍቆት በሚገባ ተወጥቶ
ወደ አዲስ አበባ ተመለስ።
✨ይሸጥላል✨

👍1
#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
...እናቴ ደረጃው ላይ ቆማ «አደራ በጊዜ እንድትመለሺ... ይኽ ወጣ ወጣ..» አለቻትና ተመልሳ ገባች። የቀኑ ሞቃት አየር እንደ ብረት ምጣድ ያሰማትን መኪና ከፍተን በቀጥታ ጉዞ ጀመርን፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከቤቴ አጥር በር አጠገብ ስንደርስ በደከሙ ዓይኖቹ ትናንሽ ፊደሉች እንደሚያነብ ዓይነ ደካማ ሽማግሌ፣ የውብነሽ በድንጋጤና በመገረም ዐይኗን ተክላ አየችኝ፡፡
«ያንተ ነገር እኮ አይታወቅም፡ ደረስን ልትለኝ እኮ ይሆናል» ብላ ወረቱ እንደ ረከሰበት ነጋደ ዐይኗ ቃበዘ፡፡ እጆቿ ተወራጩ፡፡ ቁልቁልም ሽቅብም
ወሰደቻቸው:: መጨረሻዋን ለማየት በጸጥታ ተቀመጥኩ፡፡ ቃላቷ በድንጋጤ
እየተቆራረጡ «እንዴት ብዩ ዐይኗን አየዋለሁ? ስንገናኝ ምን ምን ልበላት? በዚያ በሥቃይና መከራዋ ጊዜ ሳልጠይቃትና የት ገባች ሳልላት ኖሬ አሁን እንዲህ ብቅ ስል ምን ትለኛለች? ወይኔ ዛሬ 0ፈር በበላሁት!» አለችና ያንን ምድረ በዳ የሆነ ዐይኗን አቁለጨለጨችው::
«ይልቅ ነይ እንሒድ! እንዳንድ ጊዜ እዚህ ድረስ እየመጣች
ስለምትቀበለኝ አጉል ቦታ ላይ እንዳታገኝኽና ይብሱን እንዳትርበተበቺ ብዩ ከመናገሬ ጋሻዬነህ ከወደ ቤት «እባብዪ መጣ አባባ መጣ! » እያለ ሲጮህ ተሰማ፡፡ እናቱ ደግሞ በዚያች ቀጠን ብላ ቃናዋ በሚማርክ ድምጺ ና! ና
ተመለስ! ተው ትወድቃለህ! » እያለች ስትጣራና ስታስጠነቅቅ ሰማን። የውብነሽ
ማንቁርቱን እንቀው ዐይኑን እንዳስፈጠጡት ሰው አይኗ ፈጠጠ። የየወዲያነሽን ድምፅ ከሰማች ድፍን ስድስት ዓመት ኣልፏል። የውብነሽን ለማበረታታት ያህል
«አይዞሽ አትፍሪ! » ባለቤቴ እኮ ክፉ ሰው አይደለችም፡፡ ገና ገባ ስንል አንገቷ
ላይ ተጠምጥመሽ ሳሚያትና ኃፍረትሽን አስወግጂ፡፡ እንደገና ደግሞ ሳሚያት።
በእርሷ በኩል ሁሉንም ነገር በይቅርታ ትታዋለች፡፡ ከትናንት ጀምራ በጉጉት ነው
የምትጠባበቅሽ» አልኩና ከዚህም ከዚያም እምታትቼ እበረታታኋት፡፡ መለስ
ያለውን የአጥር በር ከፍተን ገባን።
ጋሻዬነህ ሰብሰቡ ሳይ ዝንጉርጉር ኳስ እያንከባለለ ይጫወት ነበር፡፡ ኳሱን
ጥሉ እየሮጠ መጥቶ አጠገቤ እንደደረሰ እጁን ዘረጋ፡፡ ቅብል ብዬ ታቀፍኩት፡፡
የየውብነሽ አእምሮ ያለ የሌለ ኃይሉን ፍርሃትን ለመቋቋሚያ አዋለው:: ዐይኖቿ
እንኳ በሚገባ ማየት የሚችሉ አይመስሉም ነበር፡፡ ቀይ ዳማ ፊቷ ከረመጥ የወጣ ካራ መስሎ ለሥቃይ መግለጫ ትሆን ዘንድ የተቀረፀች የመብ ሐውልት መሰለች፡፡ ወደ ቤት ገባ እንዳልን የወዲያነሽ ከወደ ጓዳ ወጣች፡፡ ባለ ወይን ጠጅ ጥለት ሽንሽን ቀሚስና ብሩህ እረንጓዴ እጀ ጉርድ ሹራብ ለብሳለች፡፡ ጸጉሯን በቀላሉ ጐንጉናና የቤት ውስጥ ቀላል ጫማ እድርጋ ወደ እኔ ስትመጣ
ከበስተጀርባዬ ያለችውን የውብነሽን ከወደ ጎኔ በኩል ኣየቻት። «እውይ የውብነሽ! አቤት የውቧ !» ብላ እጅዋን እስከ ትከሸዋ ከፍ ኣድርጋ ተንደርድራ
አንገቷ ላይ ተጠመጠመች። የየውብነሽ ኮሮጆ በድንጋጤም ይሁን ከደስታ ብዛት
አምልጧት ወደቀ፡፡ እንስቼ ወንበር ላይ አስቀመጥኩት። ተቃቅፈው ሲሳሳሙ
ልክየለሽ ደስታ አጥለቀለቀኝ፡፡ የምሆነው መላቅጡ ጠፋኝ፡፡ የየወዲያነሽ አለባበስ
እንደ ነገሩ ቢሆንም ደስ አለኝ እንጂ አልተከፋሁም። ጎን ለጎን ተቀምጠው
«ደኅና ነሽ ወይ?» እየተባባሉ በሣቅና በፈግታ ሲጠያየቁ ምንጊዜም በቃላት
እቀናብሬ ልገልጸው የማይቻለኝ ደስታ ተሰማኝ፡፡ ጋሻዬነህ ጭኔ ላይ አስቀምጬ
ፊት ለፊታቸው ጉብ አልኩ፡፡ ደቂቃዎች እየፈነጠዙ ተግተለተሉ፡፡ የየውብነሽ
ፍርሃትና ድንጋጤ ሙልጭ ብሎ ከላይዋ ላይ በመጥፋቱ ያለቻትን ፈገግታ ሁሉ
ሞጣጥጣ አወጣቻት። ጋሻዬነህ ከጭኔ ላይ ወርዶ ወደ እናቱ ሲሔድ የውብነሽ
አገላብጣ ሳመችው። ዐይን ዐይኑን እያየች «እንኳን ለዚህ አበቃችሁ እኔንም
እንኳን ይህን ለማየት አበቃኝ» ብላ ኣንስታ አቀፈችው::
የወዲያነሽን፡ ስለ የውብነሽ እንግድነት ይህን ይህን እንድታዘጋጂ ብዬ አልነገርኳትም። ደስ የሚያሰኘውንና መቅረብ የሚገባውን ነገር ሁሉ
ስለምታውቀው ይህን እንድትሠሪ ያንን እንዳትረሺ ማለት አላስፈለገኝም፡፡
የወዲያነሽ ንብ ነች! የውብነሽ አሁንም
አሁንም የማርያምን ጽዋ እያስቆሙ
እንደሚስሙ ሕፃናት የጋሻዬነህን ጉንጭ ደጋግማ ሳመች። ከሥቃይ በኋላ የሚገኝ
እውነተኛ ድል ከድሉች ሁሉ የበለጠ ድል ነው። የወዲያነሽ ግልጽና ቅን ከመሆኗ
የተነሣ ከየውብነሽ ጋር በምትነጋገርበት ጊዜ ሁሉ ካንጀቷ ስለምትሥቅና ፈገግ
ስለምትል አኳኋኗና አቀራረቧ ሁሉ የየውብነሽን ልብ ማረከው፡፡ ቀድሞም ቢሆን የውብነሽና የወዲያነሽ በጣም ይዋደዱ ስለነበር አሁን ከጥቂት ዓመታት በኋላ ሲገናኙ ፍቅራቸው ከትዝታቸው ሰታቴ ገንፍሎ ወጣ፡፡ የሁለቱ መግባባትና አዲስ ግንኙነት መጀመር ለእኔ አንድ ታላቅ የትግል ምርት ነበር። በእኅቴና በባለቤቴ መካከል ያለው ጋሻዬነህም በሁለት የሚያማምሩ አበቦች ዙሪያ እንደምትዞር የመስቀል ወፍ ይማርካል። የወዲያነሽ ከሁለታችን ተለይታ ወደ ጓዳ ገባች፡፡
በጋሻዬነህና በአክስቱ እንዲሁም በእኔ መካከል ውብ ትዝታው እስከ መቼም የማይረሳ ወሬ ቀጠለ፡፡ ጊዜ እንደ አበደ ውሻ ተክለፈለፈች። መሰለኝ እንጂ አትረዝም አታጥር! የወዲያነሽ ከሠራተኛይቱ ጋር በመረዳዳት ምግብና
መጠጥ አቀረቡ። ከግምቴ በላይ ሆኖ በማግኘቴ በአቀራረቧ ረክቼ ባይኔ ጠገብኩ፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ እኔ፤ ባለቤቴና እኅቴ በአንድ ማዕድ ዙሪያ ቀረብን፡፡ ድሉ ግን የእኔና የየወዲያዩ ነበር፡፡ ምንም እንኳ የውብነሽን ያ በአእምሮዋ ውስጥ
ተዳፍኖ በመጥፎ ትዝታ የሚጫረው ያንድ ቀን ስሕተቷ እያጸጸተ አንገቷን
እንድትደፋ ቢታገላትም እጅግም ስላላጠቃት ጨዋታው ደራ፡፡ የወዲያነሽ
በተደጋጋሚ ስታጎርሳት ቀጥ ያለ ዓቀበት ዘልቆ እፎይ እንዳለ መንገደኛ ተደሰትኩ፡፡ የውብነሽም በሌላ በኩል ብድር የምትመልስ ይመስል «ይቺን ብቻ
ጋሻው» እያለች ለጋሻዬነህ ታጎርሳለች፡፡
የማዕዱ ጣጣ ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ፡፡ እንደ ልብ
እንዲጠያየቁና እንዲጫወቱ ነጻነት መስጠቴ ነበር፡፡ ተቆርጦ እንደ ወደቀ የጥድ ዕንጨት ተዘረርኩ እንጂ እንቅልፍስ በዐይኔም አልተኳለ፡፡
የፈለግኸውን ነገር ብትጠይቀኝና አድርጊልኝ ብትለኝ እፈጽምልሃለሁ፡
የፈለግሁትን ሰው አምጥቼ ታረቁልኝ ብል እታረቅልሃለሁ ብለሽኛልና በይ
እንግዲህ እንደ መሐላሽና እንደ ቃልሽ ፈፅሚልኝ ብዬ እናቴን ሳስገድዳት እሺ
ብላ የወዲያነሽ ጋር ትታረቅልኛለች ወይ?» የሚለው ሓሳብ አንጎሌን በሥጋት
ሹል ወስፌ ዉቀዉቀው። ሌሎችም ተመሳሳይ ጥያቄዎች ደረደርኩ፡፡
እናቴ በአስገዳጅ ምክንያቶችና ሁኔታዎች ተገፋፍታ እሺ ብትለኝና ከባለቤቴ ጋር ብትታረቅልኝ የአባቴን ጉዳይ እንዴት ልወጣው እችላለሁ? የሚለው ሐሳብ ደግሞ የባሕር ላይ ኩበት አደረገኝ። ይህ ጉዳይ በእናቴ በኩል ቢደርሰው ይቀላል ወይስ በቀጥታ በእኔ አማካይነት? ይሁን ፈጽሞ ያላወቀውንና ይደርሳል ብሎ ያልጠረጠረውን ነገር ከሥር ከመሠረቱ አብራርቶ ለማስረዳት ቀላሉ ዘዴ ምንድነው? እያልኩ ራስን በራሲ በሐሳብ ቢላዋ ዘለከልኩት።
በቀላል ሐሳብም ሆነ በጊዜያዊ መግባባት ከአባቴ ይልቅ እናቴ ቅረብ
ስለምትለኝ በመጀመሪያ በእናቴ በኩል ያለውን ወደ ፍጻሚ ማድረስ አለብኝ
የሚለው ሐሳብ አመዘነ፡፡ በሐሳብ አዞሪት ውስጥ ተዘፍቄ ብቅ ጥልቅ በማለት ላይ
እንዳለው የውብነሽ ጋሻዬነህን
ስትገባ ከአሳቢ ተናጠብኩ፡፡
አልተንቀሳቀስኩም፡፡ ጎንበስ ብላ ጫማውን ካወለቀችለት በኋላ በላዩ ሳይ አሻግሬ አልጋው ላይ አስቀመችው::
ትንሽ ጎበጥ ብላ በሁለት እጅዋ አልጋውን በመመርኮዝ

👍3🥰1
ትመለሳለህ እያልኩ እኔ በር በሩን እያለሁ፡ ለካ አንተስ ተኝተሀ ዕንቅልፍሀን ልትነካው ኖሯል እንግዳ አስቀምጠህ ...» አለችና ተጨማሪ ሐሳብ እንዳላት ለማሳወቅ እንኳን ሆሄ
በጉሮሮዋ ውስጥ እየጎተተች «እ» ብላ ኣፏን በጠባቡ ካፈተች
«የምትነግሪኝ ነገር አለ እንዴ?» ብዬ ቀና አልኩ። «አዎ ግን እሺ የምትለኝና ፈቃድህ ከሆነ ነው» አለችና እንድ እንዲፈጸምላት የምትፈልገው ነገር
እንዳለ በእኳኋኗ ለማስረዳት ሞከረች
«በደንብ ነዋ! ለምን እሺ አልልሽም» ብዩ
የተንጠጠለውን ሐሳቧን ለመያዝ ቸኮልኩ «አንተንስ በእኅትነቴ ላስገድድሀ
እችላለሁ፡ የወጺያነሽን ግን...» ብላ አንገቷን በቅሬታ ወደ ጎን ሰበር አደረገች።
«ምን እንደ ፈለግሽ ንገሪኝ፥ በእኔና በእርሷ መካከል ልዩነት የለም፡፡ በቃ፡
ፈቃዷ ነው። ፈጽሚልኝ የምላትን ሁሉ ደስ እያላት ትፈጽምልኛለች» ብዬ በርግጠኛ
አንደበት መለስኩሳት፡፡ አጭር የዝምታ ጊዜ አለፈ።
«አንድ ትንሽ ስጦታ ላደርግላት አስቤአለሁ፡፡ አንተን ሳይሆን እርሷን
ፈራኋት። ከረዳኸኝ ግን...» ብላ ሐሳቧን በጥርጣሬና በሥጋት መኻል ጎተተችው።
ብትክክለኛ ሁኔታና በቅን ልቦና ተቀራረቡ እንጂ በስጦታ አትሽንግያት፡፡መግባባት በሚያዳብረው ፍቅር ተዋደዱ እንጂ በማስመሰያ ስጦታና በመዋዋል
እንድትታረቁ አልፈልግም» አልኩና ከጭቃ የከበዱ ቃላት ጭንቅላቷ ውስጥ
ዘፈዘፍኩ፡፡
የአንተንም ሆነ የእርሷን ሁኔታ ያቅሜን ያህል አውቃለሁ። ማናችሁንም በስጦታ
ለማታለል አስቤ ሳይሆን በስጦታዩ አማካይነት ውዴታዬን ለመግለጽ ስል ነው።
ከዚህ ቀደም ላጠፋሁት ጥፋት የመደለያ ካሣ ለማቅረብ ሳይሆን በዛሬዋ ዕለት
እንደገና ለምንጀምራት አዲስ ቤተሰባዊ ግንኙት መታሰቢያ እንድትሆን በማለት
ነው፡፡ ቅር የሚልህ ከሆነ…» ብላ ንግግሯን በዝምታ ዘጋች። ከተንጠለጠለ የሐምሌ ደመና ውስጥ ድንገት ብልጭ እንደሚል መብረቅ ከእኔም አንጎል አንድ ሐሳብ ተንተግትጎ ወጣ። የአሁኑ አነጋገሬና አመላለሴ ወደ ፊት ለማደርገው ዘዴያማ ግሥጋሴ እንቅፋት ይሆንብኝ ይሆን? በትሕትና ያቀረበችውን ጥያቄ ችላ ብዬ ባስቀረው እሷም የእኔን አስቸጋሪ ጉዳይ ችላ ትልብኝ ይሆን? በማለት
ተጠራጠርኩ፡፡
በነገርና በሙግት እንደ ተካነ ጠበቃ ቶሎ ብዪ ሐሳቤንና ሁኔታዬን ለወጥኩና ይህን ያህል ምን አሳሰበሽ? ለምን ቀደም ብለሽ አታማክሪኝም ነበር? ቅሬታን ለመፋቅ እና በመጨረሻም ለማስወገድ ብለሽ ያቀድሽው ፍቅራዊ ዘዴ ስለሆነ ሐሳብሽን እቀበለዋለሁ» ብዬ ተቃውሞዬን በመሠረዝ ሙሉ ፈቃደኛነቴን ገለጽኩላት። የወዲያነሽን በሚመለከት ጉዳይ ፈቃድና ውሳኔ ሰጪ በመሆኔ መብቷን የገፈፍኳት ያህል ቅር አለኝ። «እኔን ደስ እንዲለኝ ለማለት ያህል እንጂ ስጦታው እንኳ እስካዚህም የሚያናግር አይደለም» እለችና ቀይ ዳማ ፊቷን በፈገግታ አደሰችው::
አልጋው መኻል ላይ ስትቀመጥ በስተግርጌ ወርጀ ጫማዬን አጠለቅሁ፡፡
ጋሻዬነህ ጋደም ብሎ እንቅልፉን ይለጥጣል፡፡ «የወዲያነሽን ልጥራት» ብዩ
ወጣሁ። ማድ ቤት ውስጥ መሆኗን በተለምዶ ግምት ስላወቅሁ ከዋናው በር ላይ ቆሚ የወዲያ! የወዲያነሽ!» ብዩ ለዘግ ባለ ድምፅ ተጣራሁ፡፡ አልተሳሳትኩም፡፡ ከወደ ማድቤት «አቤት ! » አለችኝ። ወዲያው ከተፍ ብላ «ትንሽ ሥራ ብጤ ይዤ ነው:: አታውቅበትም፣ ታበላሽብኛለች ብዬ ነው» አለችና ከታከተ አካል የሚወጣ ረጂም ትንፋሽ አሰማች፡፡ «አሁንስ አበዛሽው የምን ድግስ አለብሽ?
ይልቅ አንድ የምነግርሽ ነገር አለ፡፡ አሁን ከእኔ ጋር ወደ መኝታ ቤት ስትገቢ
የውብነሽ አንድ ስጦታ ትሰጥሻለች፡፡ ስጦታው ምን እንደሆነ አላየሁትም፡
አልጠየቅኋትም፡፡ ኣንቺ ግን አሁን እኔ ምንም እንዳልነገርኩሽ ሆነሽ በደስታ
ቅረቢያት፡፡ እምቢ ማለት ወይም ምስጋና የማቅረቡ ጉዳይ ግን የግል ጉዳይሽ
ነው» አልኩና ሻጭና ገዢን ከዚህም ከዚያም እንደሚያስማማ ደላላ ከሁለቱም
ሁኔታዊ ጥቅም ለማግኘት በልቤ ኳተንኩ፡፡ ይህ ሁሉ ልፋቴ የዓላማዬን የመጨረሻ ፍጻሚ ለማሳመር ነበር። እኔና የወዲያነሽ ወደ መኝታ ቤት ስንገባ የውብነሽ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡
አንድ በጣም የሚያምር የወርቅ ሐብል ከነመስቀሉ በየወዲያነሽ አንገት
ላይ አጠለቀችላት፡፡ ለስጦታው ማድመቂያ ይሆን ዘንድ ዕቅፍ ኣድርጋ ሳመቻት እና አልጋው አጠገብ በነበሩት ወንበሮች ግራና ቀኝ ተቀመጡ፡፡ የወዲያነሽ ደረቷ ላይ የሚንተገተገውን አዲስ መስቀል እየተመለከተች ምነው ይህን ያህል የውቤ ለእኔ እኮ እኅትነትሽ ብቻ ይበቃኝ ነበር። ለዚህ ለአሁኑ ግንኙነት መብቃታችን
ለእኔ ሽልማቴ ነው! አሁንማ ምን እላለሁ! እግዚአብሔር ያክብርልኝ አይለምን
ብላ የምትናገረው ጠፍቷት ዝም አለች፡፡ «አረ አንደ ትልቅ ነገር ኣትቁጠረው
ይህም ስጦታ ሆነና! እኔን ደስ ይበለኝ ብዩ ነው» ብላ ምን ያህል ጊዜ እንደ
ቆየች ለማወቅ ሰዓቷን አየች፡፡ ከዚያ በኋላ ጨዋታና ሣቅ የሞላበት አንድ
አይጠገቤ የደስታ ሰዓት አሳለፍን፡፡ የዚያን ዕለት ጭውውታችን ከነለዛው አባራ።
ከእንቅልፉ የተነሣው ጋሻነህና የወዲያነሽ እስከ ትልቁ በር ሸኝተውን ተመለሱ።
እኔም እንደተለመደው ቀበና ድልድይ አደረስኳት.ባገኘሁት ውጤት ትንሽ
የሕሊና ዕረፍት አገኘሁ፡፡
የምሳ ሰዓት ነበር፡፡ ጋሻዩነህ የሚያምር አዲስ ልብስ ለብሶ በሳህን ሙሉ
የቀረበለትን ብርቱካንና ከረሜላ ሲያማርጥ የውብነሽ አጠገቡ ተቀምጣ በፈገግታ ትመለከተዋለች። «አባብዬ ! » ብሎ ተቀበለኝ፡፡ የውብነሽ ስትጨብጠኝ የወዲያነሽ ከወደ ጓዳ ወጣች። ቤታችን የቤትስብ ቤት ሆነች፡፡ ባለቤቴና እኅቴ ዕቃ ለመቀባበልም ሆነ ለመረዳዳት ከወዲያ ወዲህ ሲሉ ማየት ታላቅ ርካታ ይሰጥ ነበር ። ከምሳ በኋላ እንዲት የጎረቤት ሴት «አለሽ የወዲያ? ነይ ቡና ፈልቷል ብለው ጠርተዋት መጣሁኝ ብላን ወደ ተርቴቧ ስትሄድ፣ ጋሻዬነህም ኳሱን ይዞ ወጣ።
«አይ የወዲያነሽ! እንደት ደስ የሚል ልጅ ነው የወለደችው። ምኑም ምኑም ቁርጥ አባባን ነው። ዐይኑ ነሽ እፍንጫው፣ ልጅ ሆኖ ነው እንጂ በጣም ነው የገረመኝ። እንኳን ወዳጅ ጠላት ይለየዋል» ብላ የታያትን ተናገረች።
«አባቴንም መሰለ ቅድመ አያቴን ግድ የለም፡፡ ዋናው ቁም ነገር ይህ ልጅ የእኔና የየወዲያነሽ ልጅ ነው» አልኩና የነገሩን አዝማሚያ እኔ ወደምፈልገው አቅጣጫ ቀለበስኩት፡፡ የጉዳዩ ጦር እንደ እኔ ቀሥፎ ስላልወጋት አእምሮዋ ተዝናንቶ ይፈነጫል፡፡ እሷን ሳይሆን ውስጣዊ ተከራካሪዩን ማሸነፍ ስለ ተሳነኝ፣ እኔን የቸገረኝ የልጀ መልክ የማንን መልክ ይዞ እንደ መጣ ሳይሆን የአባቴ የአቀባበል ሁኔታ እንዴት ይሆን ይሆን ነው? ዘወትር የእቅድና የምኛት ሰው ሆኖ መኖር አስጠልቶኛል፣ ዐልፎ ተርፎም እንገሽግሾኛል፡፡ የሐሳብ ሰይፍ ስሉ ወደ አፎቱ መክተት ሳይሆን ቀንጥሶ የመጣል ትርዒት እምሮኛል።»
በማለት አዲስ ሐሳብ ለማጠረቃቀም ንግግሬን ገታሁ፡፡ ንግግሪ ሁሉ ተፅፎ
የሚነበብ ከመሰለ ቆይቷል። «ይኸ የሚያስፈራና የሚያሸሽ ነገር አይደለም።
ያለቀለት ነገር በመሆኑ አቅርቦ ማሳየትና ዘርዝሮ ማስረዳት ብቻ ነው ብላ የጉዳዩን አፈጻጸም የነፋስ ውልብልቢት እንደምታነሣት የሸንበቆ ቅጠል
አቀለለችው።
«አያስፈራም ካልሽ እስኪ በይ የማያስፈራበትን ንገሪና ልረዳ?» ብዬ
ልጃገረድ መኻል እንደ ለቀቁት ዐይን አፋር ወንድ አፌን ይዤ ዝም አልኩ።
በነገሩ አካሔድ ላይ ሙሉ እምነት ያላት መሆኗን ለማስረዳት ትከሻዋን ወደ ኋላ
ወጥራ ጠባብ ደረቷን እየለጠጠች ተንጠራራች። የከነገ ወዲያ ዓርብ ሳምንት
ከሰዓት በኋላ ኣባባ ርስቱን ለመጎብኘትና ቀድሰኞቹን ለመቆጣጠር ወደ ገጠር
ይሔዳል። ይኸን አበላሻችሁ፣ ያኛውን አጎደላችሁ፣ አንተን

👍2
ነቅየሃለሁ፣ እርሱን ተተክየዋለሁ፣ ምን ተዘራ? መቼ ታጨደ? እያለ አገር እስኪያካልል ድረስ ከሳምንት በላይ ይቆያል። በዚህ መካከል ሐሳባችንን ለማቀነባበርና ወይም
የምናደርገውን በቅድሚያ ለማወቅ ከሚቀጥሉት ቀናት የተሻለ ጥሩ አጋጣሚ ጊዜ የለም፡፡ በእነዚህ ቀኖች ውስጥ እንደምንም ብለን እናታችንን ለመጨበጥና ድል ለማድረግ ከቻልን ከዚያ በኋላ አባታችንንም የምንማርክበትን ጊዜና ብልሃት
ማግኘት ይቻላል» ብላ ገና ሐሳቧን ውል ሳታሲዝ የወዲያነሽ ከቸች እለች።
ነገር ግን ግላዊ ምስጢር የያዝን ስለ መሰላት እንደማፈር እየቃጣት
«ብዕር ይዘሃል ጌታነህ? የተሰጠኝን የቤት ሥራ እልጨረስኩም፡ ያውም ዝብዝባም
ታሪክ» ብላ ጠየቀችኝ፡፡ ለአዲሱ ሐሳብ አፍላ ጉጉት በማሳደራ ዐይኔ ከየውብነሽ
ላይ ሳይነቀል በዳበሳ አውጥቼ ሰጠኋትና ተቀብላ ተመለሰች፡፡ የአባታችን ወደ
ገጠር መሔድና የእናታችንም ብቻዋን መግኘት እንድ ጥቅም እንደሚያስገኝልኝ
ዐውቃለሁ፡፡ ግንዱን በቀላሉ ለመጣል ቅርንጫፉን መገነጣጠል ያስፈልጋል።
«እናቴንስ በእንዴት ያለ አቀራረብና የአነጋገር ዘዴ ልንማርካትና እንድትደሰት
ማድረግ እንችላለን?» ብዬ ጥያቄ ደቀንኩ፡፡
«አየህ ከዚህ ቀደም ብዬ እንደነገርኩህ ይብዛም ይነስ በአባታችን ያለመኖር እንደ ልብ ልንሆን እንችላለን ማለት ነው:: በተጨማሪ ደግሞ የዚህ ልጅ መልክና የአባታችን መልክ መመሳሰል ከሁሉም በላይ የሚያደፋፍር ተጨማሪ ዕድል ነው፡፡ እንዲያውም ካለን ዕድል ሁሉ ታላቁ ነው ለማለት እችላለሁ» ብላ ንግግሯን ከመደምደሟ በፊት በጭንቀት ከሚታመሰው ኣእምሮዬ
“እንዴት?” የሚል ጥያቄ አቀረብኩላትና ግጥም እንደ ተቀበለ አዝማሪ ወዲያው
ንግግሯን'ቀጠለች፡፡
«እንዴት ማለት ጥሩ ነው:: የእናታችንን አስተያየት ሰምተኸዋል፡፡ የሰው ልጅ እያለች አሥር ጊዜ ስለምትወተውተው ነገር ከእኔ ይበልጥ አንተ ታውቃለህ፡፡ ይህን ኣባባሏን ለመደምሰስ የሚቻልበት ዘዴ እስከዚሀም አዳጋች አይሆንም፡፡ መገፋፋትና ማዋከብ ነው:: ይህንን አበባ የመሰለ ልጅ ይዞ መቅረብ
ያኮራል እንጂ አያሳፍርም። ስለ የወዲያነሽ ስትናገር የሰማኸው በቂ ምስክር ነው»
“እንዴት? የዚያን ዕለት የወዲያነሽንም ይዘናት እንሄዳለን እንዴ?» ብዬ
እየፈራሁ አየኋት።
«ቅዳሜ ከስምንት ሰዓት ተኩል በኋላ እኔና አንተ ጋሻዬነህን ይዘን እንሄዳለን፡፡ በዚህ መሃማሩ ላይ አለባበሱ አበባ መምሰል አለበት። የዚያን ዕለት
የወዲያነሽን ይዘን የምንሔድ በሆነ ጉዳያችን ብልሽትሽቱ ይወጣል፡፡ ስለዚህ
አንወስዳትም:: የእናቴን ጠባይ በደንብ አውቀዋለሁ።ቁጣዋን በቀላሉ ለማብረድ
ልቧን በለስላሳ ቃላት መጥለፍ ይቻላል፡፡ አንተ ከነልጅህ ከአጥር ውጪ
ስትጠብቀኝ እኔ ወደ ቤት ገባ ብዬ እንግዳ መኖርና ያለመኖሩን አረጋግጣለሁ፡፡ምናልባት ትልቁ ክፍል ውስጥ ካገኘኋት የምነግርሽ ነገር አለና መኝታ ቤት ውስጥ ጠብቂኝ ብያት ወደ አንተ እመለሳለሁ፡፡ ከዚያም ሦስታንችም ባንድ ላይ ወደ ቤት ከገባን በኋላ ልጁን ወደ መኝታ ቤት የሚያስገባውን መንገድ አሳይቶኝ ከኋላ ኋላው አንከተላለን፡፡ ፊት ለፊት ተቀምጣ የምናገኛት እናቴ ይህን የስንዴ እሸት የመሰለ ልጅ ስታይና የአባታችንንም መልክ በጋሻዬነህ ላይ ስትመለከት የምትለውና የምትሆነው ገና ከአሁኑ ታይቶኛል፡፡ ከዚያ በኋላ የመጀመሪያ ዕድልህ ነውና በንግግራችን ጣልቃ ለምታቀርብልህ ጥያቄ ሁሉ በሙሉ ልብ መልስሳት። ብዙ እንደማትከራከርህ ርግጠኛ ነኝ። ”እንዲያ ከሆነም ሙት ብለሽኛል፣ ቃል ገብተሽልኛል፣ የፈለግኸውን ጠይቀኝ ብለሽ ምለሽልኛል ብለህ ምንችክ ነው::” ቢሆንም በጣም አትዳፈር» ብላ ስታወጣና ስታወርድ የቆየችውን
ሐሳብና መላ ሁሉ ዘረገፈችልኝ፡፡
ምንም እንኳ ያቀረበችው ዘዴ እንጎሌ ውስጥ ገብቶ ቢጋዴምም የሚጎረብጠኝ ትልቁ ሐሳብ ግን ገና አልተነካም። ወላጆቼ ልጁን ደስ ብሏቸው
ከተቀበሉ በኋላ እናቲቱን ዐይንሽን ላፈር ቢሉብኝሳ? ፍሬውን ወዶ ዛፉን መጥላት
አይሆንም? እያልኩ በማሰላሰል በሐሳብ ጅራፍ ተገረፍኩ። ሆኖም ከማናቸውም
ውጊያና ፍልሚያ በፊት ቀደም ብሎ መሰናዶ ማድረግና የራስን ውስጣዊ ኃይል በሚገባ ዐውቆ ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ ጉዳዩን ማብላላት እንደሚገባኝ ግልጽ ሆነልኝ፡፡ ለየወዲያነሽ የተቃና ሕይወት ስል እሳት ራት መሆን እንደሚገባኝ ዳግመኛ ተገነዘብኩ። ይኸውም ሞታ የምትቀር የእሳት ራት ሳይሆን የጥላቻንና የመረገጥን ጨለማ አጥፍታ እንደገና ነፍስ የምትዘራ የእሳት ራት! ይህ ከየውብነሽ ጋር የሚደረግ አዲስ እቅድ ገና መብላላት እንዳለበት ተስማምተን ተነሳን። የገዛ ራስዋ ጥላ ወረቀቱ ላይ አጥልቶበት የምትጽፈውን የወዲያነሽን ተሰናብተናት ወጣን፡፡
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ነበር፡፡ ከያዝኩት መጽሐፍ ላይ አንዲትም ፍሬ ነገር
ሳልይዝ አንድ ሙሉ ምዕራፍ አንብቤ ጨረስኩ። የወዲያነሽ ከራት በኋላ መጽሐፍ ወይም መፅሔት ማነባበብና የመሰንቆ ዘፈን መስማት ስለምትወድ ሙዚቃውን ከፍታ አጠገቤ ተቀመጠች። አድብቼ ስጠባበቃት በመቆየቴ ጊዜ ሳላባክን «እኔና የውብነሽ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ጋሻዬነህን ይዘን ወደ ወላጆቼ ቤት ብንሒድ ምን ይመስልሻል?» ብዬ በጥያቄ ጨመደድኳት፡፡ መጽሔቱን አጠፍ አድርጋው ወደ እኔ ዘወር በማለት "እና?” ብላ በጥያቄ ማቅረቢያ ድምፅ ተናግራ ዝም አለች።
የምን እና ብሉ ዝም ነው? ለእናቴ ካሳየኋት በኋላ ይዤው እመለሳለሁ፡፡ እስከ መቼ ድረስ ተሸሽጌ እዘልቀዋለሁ፡፡ አቀርቅሮ መሔድ ይበቃኛል። ቁርጥ
ያጠግባል” ሲሉ አልሰማሽም፡፡ እስኪ አስቢው! የዚህ የኑሮአችን ጨለማ መንጋት አለበት። ለመከራችን ፍጻሜ ያሻዋል፡፡ አንድን መጥፎ ነገር
ከልተማገድንበት ውጦን ይቀራል፡፡» በዝምታችን መኻል ደቂቃዎች ሰገሩ።
አቀረቀረች፡፡ ልቅሶዋ የትካዜዋ ልዩ ምልክት በመሆኑ ገንፍሎ ከመፍሰሱ በፊት መከላከል እንደሚገባኝ አወቅሁ:: “ይህ ነገር ደስ የማይልሽና እሺ የማትይኝ ከሆነ እኔ የብስጭት ብዛት ራሴን ኣዘሮ ዕብድ ሳያደርገኝ አገር ጥዬ እጠፋለሁ፡፡ በጣም ቅር የሚለኝ ግን ከአንቺ በምለይበት ጊዜ እንጂ ከወላጆቼ ከተለየሁማ ቆይቻለሁ»
አልኩና ጥርሱን የነቀለ ውሸት ዋሸሁ፡፡ ሐሰቴ ከብልጠቷ በላይ በመንጠራራቱ
የተናገርኩት ሁሉ እውነት መሰላትና «ለምን?» ብላ ድንጋጤ ባቀጠናት የርኅራኄ ድምፅ ጠየቀችኝ፡፡ አልመለስኩላትም፡፡ ወዲያው ቀጠል አድርጋ «ደግነቱ እንኳን አንቺም አብረሽ መሔድ አለብሽ ያላልከኝ! ልጅህንስ እንዳሻህ አድርገው! ካንተ ወዲያ ማን አለው? የትም ብታደርሰው እኔ ምን ቸገረኝ:: ብትፈልግ ወስደህ
ስጣቸው:: ስለ እኔ እንደሆነ ብዙ አትጨነቅ:: እኔ እንደሆነ እንተ እስካለህልኝ ድረስ ክፉ አይነካኝም፡፡ ወላጅ ኤህ ሲልብህና ሲረግምህ ደግ አይደለም» በማለት ትእዛዜን ለማክበርና እኔን ለማስደሰት በልቧ ውስጥ የሚወራጨውን የንዴት ዘንዶ በትግዕሥቷ ሠይፍ ዘነጣጠለችው:: ቀና ብላ የእርሷ ያልሆነ ፈገግታ ካሳየች በኋላ
«ለሁሉም አንተ ታውቃለህ! መቼ አጣኸውና፣ አሁን ግን እንተኛ» ብላ ካጠገቤ ተነሣች፡፡ «ያም ሆነ ይህ እንመካከርበታለን እንጃ ጉዳዩማ መፈጸም አለበት» ብዬ እንደጨረስኩ ወደ መኝታ ቤት ገባች።
ጉዳዩን በእርሷ ዐይን ሲመለከቱትና ሕሊናዋን በመወከል ሲያመዛዝኑት
በጣም ያስፈራል፡፡ እኔ ግን በማያቋርጥ ፍርሃት ውስጥ ከመኖር ይልቅ በቁርጠኛ
ውሳኔ ሞትንም ቢሆን መጋፈጥ ይሻላል ብዬ በማመኔ የአባቴን ወደ ገጠር መሔድ በጓጓ ስሜት ጠበቅሁት:: ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከየወዲያናሽ ጎን ጋደም ብዪ ጥቂት የሐሳብ እግሮች እንደ ዘረጠጥኩ በእንቅልፍ ክንዶች ተማረኩ፡፡.....

#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....ቱሉ ሀጤ የተከናነበችውን የጨለማ ካባ አውልቃ ወደዚያ ለመጣል
በመሽኮርመም ላይ ትገኛለች። ጨለማው ብርታቱን ለማሳየት በሚያቅራራበት፣ ንጋትም ብርሃንን ካልፈነጠቅሁ እያለ በሚንጠራራበት በዚያ ውድቅት ለሊት እንቅልፍ በአይኑ አልዞርልህ ያለው ሰው አንዴ በቀኝ ጎኑ አንዴ ደግሞ በግራ ጎኑ እየተገላበጠ ምሽትና ንጋት የበላይነታት
ውን ለማረጋገጥ በገጠሙት የጦርነት አውድማ ላይ ትጥቅ ይዞ ሳይዋጋ
ጉዳት የደረስበት ቁስለኛ ሆኖ ያለዕረፍት ያቃስታል። ድቅድቁ ጨለማ ከዋጣት መንደር የበለጠ የጨለመበት ሙሉ ዳፍንት ሌሊት ሆኖበት ያደረውና ከሚስቱ ፀባይ መለዋወጥ ጋር ሰሞኑን ከህሊናው ጋር ጦርነት ገጥሞ የሰነበተው ገበየው ቱሉ ሃጤ ለበለችውጨለማ በከፋ ሁኔታ
ጨልሞበት ዙሪያው ገደል ሆኖበት በሃሳብና በጭንቀት መወራጨቱን ቀጥሏል...
ባክዎ እማማ ዓለም ፀባይዋን ለምን እንደለወጠችብኝ ይጠይቁልኝ፡፡ ሳላውቀው አስቀይሜአት ከሆነ ይቅርታ ታድርግልኝ፡፡ በድያት ከሆነ እክሳለሁ እንጂ የድሮዋ ዓለሚቱ አልሆነችልኝም” ብሎ ለአማቹ ስሞታ ነግሮ ነበር።
የዓለሚቱ እናት ልጃቸውን በጣም ስለሚወዷትና ስለሚፈሯትም ጭምር
ጣጣውን በልባቸው እያወቁት “እስቲ ቀስ ብለን እንጠይቃታለን ካጠፋች
እናስመክራታለን ጥፋቱ ያንተ ከሆነ ደግሞ ጥፋትህን እንድታርም ሽማግሌ
ፊት እናወቃቅሳችኋለን እስከዚያው ድረስ ታገሳት” ሲሉ ተስፋ ስጥተውት ነበረ፡፡ እሱም ያንን የተስፋ ቃል ስንቆ ሽማግሌ ተሰብስቦ አንተ አጥፍተሀል አንቺ አጥፍተሻል እየተባባሉ የሚወቃቀሱበትን ቀን በናፍቆት እየተጠባበቀ ነው። ዓለሚቱ ግን እየባሰባት እንጂ እየበረደች ልትሄድ
አልቻለችም፡፡ በተለይ የዛሬው ሁኔታዋ ከወትሮው በተለዬ ሁኔታ እጅግ
አስፈሪ ሆነበት።ያ የሚለሰልሰው ገላዋ እንደ አባጨጓሬ ኮሰኮሰው። ጀርባዋን አዞረችበት። ሊዳብሳት ሲፈልጋት ሽሽችው። እጁን ሲዘረጋ አመናጨቀችው። ኤጭ!.. በልቡ ብዙ ነገር ተመኘ፡፡ “ምን አባቱ ለየትኛው ኑሮ ነው? ብርር ብዬ ብጠፋስ? ዐይኔን ማየት ካስጠላት እስከ መጨረሻው ከዐይኗ ብርቅላትስ?” ዝም ብሎ ወደማያውቀው አገር ቢሄድ ዓለሚቱን ሸሽቶ ከአድማስ እስከ አድማስ ቢጓዝ ከዚያም ናፍቆቱ አንገብግቧት
ጥፋተኛነቷ ተሰምቷት እንደ ድሮው “ገበየሁዬ” እያለች እሱን ለማግኘት
እግሯ እስከሚነቃ ድረስ ፍለጋ ብትጓዝ ተመኘ፡፡ አገሩን ጥሉ መንኖ ገዳም ቢገባ፣ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ባህታዊ ሆኖ ጢሙን አሳድጎ ስለ ነፍሱ እንጂ ስለ ስጋው የማይጨነቅ መነኩሴ ሆኖ መኖርን ተመኘ፡፡
በዚች በማትጠገብና ነገር ግን በማትጣፍጥ ዓለም ውስጥ ምሬቷን እየተጎነጨ ከመኖር ይልቅ ምናኔን መረጠ፡፡ ግማሽ አካሉ፣ የመኖሩ አለኝታ
ጣፋጫ ዓለሚቱ ጀርባዋን ከሰጠችው ገሀዷ ዓለምም አልፈለገችውምና
ገሀዷ አለም ጠላት፡፡ በእርሻ ሲተዳደር ድካሙ ልፋቱ ሁሉ በዓለሚቱ
ፍቅር ይካካስለት ነበር፡፡ አሁን ግን እሷም ይኸውና ጀርባዋን ሰጥታዋለች፡፡ ለወትሮው ዓለምዬ እባክሽ ትንሽ ይንጋ አትነሺ ትንሽ እንቆይ?"እያላ ከእቅፉ ውስጥ እንዳትወጣ ጭምቅ አድርጎ ሲይዛት እሷም ከጉያው ውስጥ ላለመውጣት በልቧ እየተመኘች የውሽቷን ስትታገለው ለሊቱ ይነጋና ምቀኛው ዶሮ ኩኩሉ!” ኸረ እባካችሁ ነግቷል!” ሲል ያሳብቃል። ከዚያም እሷ ቀድማ ትነሳና ቤቱን ታጫጭስበታለች። ከብቶቹን ለግጦሽ ከማሰማራቱ በፊት ሻይ ታፈላለትና “እስኪ ሞቅ ያድርግህ ገበየሁዬ?” ትለዋለች። ይቺ ለሱ ማር የነበረች ዓለሚቱ፣የሱ አሳቢ ተንከባካቢ የነበረች ዓለሚቱ ፊቷ እንደ ሀምሌ ክረምት መክበድ፣ ሙቅ ሰውነቷ
እንደ በረዶ መቀዝቀዘ ከጀመረና ንግግሯ እንደ ሬት እየመረረ መምጣት ከጀመረ ውሎ አደረ። ሁሉንም መታገሴ ጥፋተኛነቴን ያመንኩ ያስመስልብኛል በማለት ትንሽ ለመቆጣት የሞከረ ቀን ፀቡ ይበልጥ እየተካረረ ይሄዳል። ከዚያም ይደነግጥና ተመልሶ ልምምጡን ይቀጥላል። አንዳንድ ጊዜ ንዴቱ ከኣቅሙ በላይ ይሆንበትና ብድግ ብሎ ቤቱን ጥሎላት ሊጠፋ ይከጅለዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ እነኝያ በግራና በቀኝ ከበውት ለሀጫቸውን የሚያዝረከርኩበት፣እነኝያ ልቡ ሊጋልብ ሲነሳ ልጓም የሚሆኑበት፣ እነኝያ ልቡ ሲቃጠል ውሃ የሚያፈሱበት ህፃናት ልጆቹ ትውስ ይሉትና ጥሏቸው ለመጥፋት በማሰቡ ራሱን ይወቅሳል።
የዛሬን አያድርገውና ያኔ እንደዚህ እንደ አሁኑ ከሁለትነት ወደ አራትነት ከመሸጋገራቸው በፊት“ዓለምዬ ፍቅራችን እጥፍ ድርብ የሚሆንበት ጊዜ መቼ
ነው?” ብሎ ሲጠይቃት ከፍተኛ የልጅ ጉጉትና ምኞት እንዳለው የምታውቀው ዓለሚቱ በስርጉድ ጉንጮቿ ሳቅ ትልለትና ያበጠ ሆዷን በጣቷ እየጠቆመችው “የማሙሽዬ ወይንም የማሚቱ እናት ስሆን።አንተም የአባትነት ወግ ማዕረግ ሲደርስህ አይደል ገበየሁ?” ትልና ጉንጩን ከንፈሩን ሳም ስታደርገው ደስታ ልቡን ይሞላውና ደግሞ እንደገና አንጠጋ
ገብ ብለው ተቃቅፈው ሲተሻሹ ሲላላሱ በልቧ ማህደር ውስጥ የተደበቀውን የፍቅር ሚስጢር ከዐይኖቿ ውስጥ እንደሚያነብባት ሁሉ ዐይን ዐይኖቿን በፍቅር ትኩር ብሎ ሲመለከታት እንደማፈር ትልና አንገቱ ስር ሽጉጥ ስትልበት ከዚያም ስሜታቸው በእጥፍ ይንርና እንደ ስስት እንጀራ እርስ በርስ መሻማት ሲጀምሩ ይሄ ሁሉ በወረት እንደ ባህር ዛፍ ቅጠል ቦግ ብሎ ወዲያውኑ ድርግም ብሎ የጠፋ ሳይሆን ሰባት ዓመት ሙሉ አብሮአቸው የዘለቀ ነበር፡፡ አሁን ግን ይሄ ሁሉ እንዳልነበረ ሆኖ ከጥቂት ወራት ወዲህ የዓለሚቱ ሙሉ ለሙሉ መለወጥ አእምሮውን ሲበጠብጠው ከረመ፡፡ አለሚቱ ግን ይሄ ሁሉ ገበየሁ የሚታወሰው ትዝታ አንድ
እንኳ ለምልክት ሳይተርፍ ከአእምሮዋ ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ የሠራ አካላቷን እንደ ሻማ ለሚያቀልጣት፣ በፍቅር ለተረታችለት፣ ቁመናው ቀጥ ያለ ሽመል ለሚመስለውና በአለንጋ መሳይ ጣቶቹ ሁለመናዋን እያሻሽ ነፍሷን ለሚያስደስትላት ለጎንቻ ፍቅር ስትል የገበየሁ ህይወት ኢምንት ሆኖ ታያት። በተለይ ደግሞ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አጠገቧ የተኛው ሰው ቀዝቃዛ በድን እንደሚሆን እየታወቃት እየፈራችው ሰውነቷን ሲነካት እየተሸማቀቀች ከምንጊዜውም በከፋ ሁኔታ ተጠየፈችው። ሸሸችው።ገበየሁ የሆዱን በሆዱ ችሎ የለሊት አዳሩ እየደነቀው ጋቢውን ከላይ ደረበና ቀስ ብሎ ተነሳ፡፡ ዓለሚቱን የያዛት እንቅልፍ የውሽት መሆኑን ሳያውቅ እንዳይቀሰቅሳት ተጠንቅቆ ከአልጋው ላይ ወረደና እንደወትሮው ከብቶቹ ከመታለባቸው በፊት ትንሽ ሳር እንዲግጡ በለሊቱ በረቱን ከፍቶ ይዟቸው ወጣ....
ሰው ከእናቱ ማህፀን ሲወለድ ተረግዞ፣
በሞት ጎዳና ላይ ይጀምራል ጉዞ፡፡
ፊት ለፊት እያየው ትልቁን አደጋ፣
ልቡ ሲያፈገፍግ ዕድሜው ግን ሲጠጋ፣
ሲያውቀው በመሞቱ በጣም ይጨነቃል፣
መሸሻ በማጣት ቆሞ ይጠብቃል፣
የእግዚአብሔርን ፀጋ!
በዕድሜ ባለፀጋነት በማይቀረው የሞት ጎዳና ላይ መጓዝ የተፈጥሮ ህግ ነው። ነገር ግን ወደ ህይወት ጎዳና ለመጓዝ የህይወትን ውጣ ውረድ ፈተና ለማለፍ በሚደረግ ትንቅንቅ ውስጥ ባልተጠበቀ ጊዜ በተለይም እንደ ገበየሁ ላለ ልጆቹን ስሞ ላልጠገበ ሰው ሞት እጅግ አስደንጋጭ ነው። ገበየሁ ከዛሬ ነገ የሚስቱ ፀባይ ተሻሽሉ የሻከረው ልቧ ለስልሶ እርቀ ሰላም በመካከላቸው ወርዶ ትዳሩ ሰምሮ ልጆቻቸውን በፍቅር
የሚያሳድጉበትን ቀን ሲናፍቅ በዚያኛው ወገን ደግሞ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይቺን ዓለም እንዲስናበታት የማድረግ እቅድ ወጥቶ ዝግጅቱ ተጠናቆ ወደተግባር የሚሽጋገርበት የሞት ድግስ ተደግሶለታል። እሱ በተበደለ እሱ ከነልጆቹ በተሰቃየ እሱ ፍቅሩን በተነጠቀ ጎንቻና አለሚቱ የሞት ፍርድ ከፈረዱበት ስንብተዋል። በዚሁ መሰረት ጎንቻ ሲዘጋጅ
ሾተሉን ሲሞርድ

ጦሩን ሲስብቅ የአገዳደል ስልቱን ሲያጠናና ሲያቀናብር ከረመ:: መቃብሩን ሲቆፍርለት ጉድጓዱን ሲምስለት ቆይቷልና በድግሱ መሰረት ዛሬ ገበየሁን የሚድርበት የመጨረሻው ቀን ነበር ከብቶቹን ከበረት አስወጥቶ ትንሽ ጨሌ ወደሚገኝበት ሥፍራ ወደ ጋራው
ራቅ አድርጎ ሲነዳቸው በስውር ይከታተለው ነበር። ሚዳቋ ለመያዝ እንደሚያደባ ነብር እያደፈጠ እየተሹለከለከ በደረቱ እንደ እባብ እየተሳበ ተጠጋው።ሚስኪኑ የትዳሩና የልጆቹ ነገር እያብከነከነው በብዙ ድካም ያፈራቸው ከብቶቹ ጠግበው እንዲበሉለት የግጦሽ ቦታ ለማማረጥ አንዴ ወዲህ አንዴ ወዲያ ሲል ቆም ብሎ በትካዜ ፍዝዝ ብሎ በሀሳብ ሲዋኝ...
“ስንቻ ኢልመ ቦሩ! ጎንቻ የቦሩ ልጅ! የሚል የሚያቅራራ ድምፅ ሰምቶ ከድንጋጤው ሳይመለስ አንድ ከባድ ነገርን የግራ ጎኑን በጥሶ በቀኝ ጎኑ ሊወጣ ለቅፅበት ተሰማው፡፡ “ህ.......ወይኔ...
ገበየሁ!”ብልጭ፣ድርግም፣ብልጭልጭ፣ድርግምግም፣ ጭ...ው...ው.
ጢ.ዝ.ዝ... ሽክርክርክር... ጓጓጓጓ!! የሁለት ዓመት ሴት ልጁ የአልኮ
ድምፅ። የአራት ዓመት ወንድ ልጁ የምትኬ ድምፅ፡፡ ስዕላቸው ሁሉ
ከፊቱ ላይ እንደ ገና መብራት ብልጭ ድርግም፣ ብልጭ ድርግም አለበት። ጣፋጭ ድምፃቸው እንደ ገደል ማሚቶ በጆሮው ውስጥ ሲስተጋባ ተሰማው፡፡ በወደቀበት ደም እንደ ጎርፍ ፈሰሰው... ከአንገቱ ቀና የሚያደርገው ሰው ቢደርስለት ኖሮ ምናልባት የመዳን ተስፋ በኖረው የልጆቹን ስም ነበር ዓ.ሊሜ! ደህና ሁኝልኝ፡፡ የልጆቼን ነገር አደራ!"
ነበር። ለመጨረሻ ጊዜ ከህይወቱ ስርቅታ በፊት የተጣራው የሚስቱንና እንደ ታረደ በሬ የሚፈሰውን ደሙን ሲያይ ጎንቻ ደም አሰከረው::
የበለጠ አረመኔነት ተሰማው፡፡ እኒያ ቀያይ ዐይኖቹ የበለጠ ደም ጎረሱ::
ከዚያም አረፋ እስከሚደፍቅ ድረስ እየፎከረ ጦሩን ከላዩ ላይ ነቀለና ከብ
ቶቹን ከፊት ለፊቱ እያሯሯጠ ቁልቁል ወረደ...የገበየሁ ደም የአውሬነት ስሜት ፈጠረበት። ሌላ ደም ተጠማ፡፡ ትንሽ ወንጀል የትልቅ ወንጀል ማህፀን ናት። ትንሽ በትልቅ ውስጥ ተፀንሶና ተረግዞ ይወለዳል። ወንጀል ግን ትንሽዋ ትልቁን ፀንሳና አርግዛ ትወልደዋለች። በሌብነት የጀመረው ወንጀል ወደ ሰው ህይወት ማጥፋት ተሸጋገረ። በቶላ ሊጀምር ያቀደውን ግድያ በገበየሁ ጀመረ። አ.ን...ድ!...
✨ይቀጥላል✨

#ክፍል_ሰላሳ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
...«አባባ ትላንት ከሰዓት በኋላ ሔደ፡፡ ከሳምንት በላይ ይቆያል፡፡ሲያተራምስ ነው የሚሰነብተው:: ያሰብነው ጉዳይ እንደፈለግነው ሊፈጸም ይችላል ማለት ነው» አለች የውብነሽ ቅዳሜ ማለዳ በቁርስ ሰዓት የምሥራች ነው
የምትለውን ወሬ እያወራች፡፡
ለግብግቤ አንድ ተጨማሪ ርምጃ እንደሚሆን በማመኔ ደስ አለኝ።
ጠረጴዛውን ተደግፋ ወደ ቆመችው ባለቤቴ ዞር አልኩና ዛሬ ጋሻዬነህ አብሮኝ
ለቁርቁስ የሚሔድበት ቀን በመሆኑ አደይ አበባ እስመስለሽው ቆይኝ፣ የሚያምርበትን ልብስ አንቺ ታውቂዋለሽ፡፡ ወዴት እንደሚሄድና ጉዳዩ ምን እንደሆነ ነግሬሻለሁ» ብዬ ወደ ውስጥ ገባሁ፡፡ ልክ እንደ እዲስ ወፈፌ ያቅበዝብዝ
ያዘኝ፡፡ “ጭንቅላት በደስታ ሲሰክር! ለብሼ ስመለስ እኅቴና ባለቤቴ ወሬያቸውን
ተያይዘውታል፡፡ አልተጋራኋቸውም፡፡ መኪናይቱን እስከማሟሙቅ ድረስ ደረሱብኝ፡፡መንገድ ስንጀምር የወዲያነሽ ተመለሰች። «የውብነሽ፣ ሰባት ሰዓት ሲሆን እዚሁ ጠብቂኝ» ብያት ከመሥሪያ ቤቷ በር ላይ ተመለስኩ፡፡ የሥራ መግቢያ ሰዓት ሞልቶ ስለ ነበር ሠራተኛው በሙሉ ነጠላና ጥንድ ሆኖ እያውካካ ወደ ክፍሉ ገባ፡፡ ገና ቁጭ ከማለቴ ቅናት እንደሚያንዘፈዝፈው ሰው መላ አካላቴ እየተንቀጠቀጠ አወከኝ፡፡ በአካባቢዬ ያለው ዕቃ ሁለ ጥያቄ የሚያቀርብልኝ እየመሰለኝ ”እስቲ አባክ! አንድ ቃል ይውጣህ! እንደሚል ሰው እጉርጩ አየሁት።
በጦርነት ዋዜማ እንደምትሸበር የፈሪ ልብ የልቤ ትርታ ከገደቡ በላይ ናረ፡፡ ለቆላ ቁስል የሆድ ቁርጠት መድኃነት መዋጥ ሆነብኝ፡፡ ብናኝ የምታህል የመንፈስ ጸጥታ ሳላገኝ ቀረሁ። የሰዓቴን ጠቋሚ ዘንግ ወደፊት በማስኬድ የጊዜን
ሥርዓታዊ ጉዞ ለመለወጥ ያስችለኝ ይመስል ሦስት ከኻያ የነበረውን አራት ከኻያ አደረግሁት፡፡ራሴን በማጭበርበሬና ሕሊናዬን በታለሌ ረቂቅ ኃፍረት ተሰማኝና
መልሼ አስተካከልኳት። እርሳሱ፣ ወረቀቱ፣ ብዕሩ፣ ወንበርና ጠረጴዛዉ ደመኛዩ
መሰሉኝ፡፡ ሒድ ሒድ ውጣ ውጣ የሚል ነገር ያዘኝ። በቀጥታ አለቃዬ ቢሮ ገባሁ፡፡
አእምሮው ተቃውሶ ሁኔታዎችን እንደ ዘነጋ ሰው ከፊታቸው ተገተርኩ፡፡ ቀና
ብለው ሲያዩኝ «ዛሬ በጣም አሞኛል ምናልባት ቢሻለኝ ብዬ ነበር የመጣሁት።
እያመመኝ ከመቀመጥ ብሄድ ይሻላል» አልኩና በዙሪያዬ የውሸት ገረገራ አጠርኩ።አለቃዩ ዘለው ለመግባት አልቻሉም። ካመመሕማ ሂድ፣ በጎ ካልሆንክ ደግሞ ሰኞ ሰው ላክ» አለና ያስደስተዋል ብለው ያሰቡትን በሞኝ ሰው ፊት ላይ የሚታይ የፈገግታ ዐይነት አቀረቡልኝ፡፡ ልቤ በደስታ ከመነረቱ የተነሣ ሣቄ ፈንድቶ አጉል እንዳያደርገኝ ነገር ሳላበዛ አመስግኜ ሹልክ አልኩ፡፡
ጭንቀትና ሥጋት ተንጠርዞ እንደ ከበደኝ በመኪናዩ ገሠገሥኩ። በራሴ
ለመተማመን ያልቻልኩበትን ምክንያት ፈልፍዬ ማውጣት ባለመቻሌ በውስጡ
ትልቅ ችግር ተፈጠረ። ከመኪናዬ ወርጄ ወደ ቤት ስራመድ ምንና የት
እንደምረግጥ የማውቅ አልመስልም። ማንም ሳያየኝ ሰተት ብዬ እንግዳ መቀበያ
ክፍላችንም ገባሁ፡፡ በቀስታ ሄጄ ከመስተዋቱ ፊት ለፊት ቆምኩ። አኳኋኔ
ስላላስደሰተኝ ምናልባት በፈገግታ ቢለወጥልኝ ብዬ ፈገግ አልኩ። ከውስጥ
ያልመነው ፈገግታ በመሆኑ ወዲያው ከሰመ፡፡ እንዲያውም ስካሩ ያልበረደለት
ሰው መሰልኩ እንጂ ጤነኛውን ጌታነህን ለመሆን አልቻልኩም፡፡ ከወደ መኝታ
ቤት እየኮረኮሩ የሚያሥት የልጅ ሣቅ አሁንም አሁንም ይሰማል። ወዲያው
ከሚከታተሉትና ሊይዙት ከተዘረጉት እጆች ለማምለጥ ግማሽ ኃይሉን ለሣቅ ያዋለ
ልጅ ከወደጓዳ እየሮጠ መጣ። ከእኔ ራቅ ብሉ ድካም የዋጣት ሣቅ እየሣቀ ቆመ፡፡
አላየኝም። የወዲያነሽ ጥቂት ዘግየት ብላ ጫጩቷን ተከትላ እንደምትሄድ ዶሮ
እሱን ለመያዝ እየሮጠች መጣች።
በልፊያ የተበታተነው ጸጉሯ እንደ ጋሽበ አዝመራ የራሱን ግላዊ ውበት ፈጥሯል። በዚያች ሰዓት ወደ ቤት ይመለሳል ብለው ስለማይጠረጥሩ እናትና ልጅ አላዩኝም፡፡ ፊቷ እንደ በጋ ወራት ሙሉ ጨረቃ ደምቆ «መጣሁብህ! ያዝኩህ!» ብላ ወደ እርሱ ተራመደች፡፡
በመሮጥ ፈንታ ሆዱን ወደ ውስጥ እጥፍ ሣቁን ለቀቀው። አፈፍ አደረገችው:: ከቡችላዋ ጋር እንደምትላፋ እናቲት ወሻ ጎበስ ብላ ወገቡን ያዘችውና ትግል ገጠሙ:: ከወዲያ ወዲህ አባተለችው፡፡ የጋሻዬነህ ሣቅ ገነነች፡፡ ትርዒቱ እንዲቀጥል እንጂ እንዲቋረጥ ባለመፈለጌ እንደ ምሰሶ ጸጥ ብዩ
ተገተርኩ፡፡ ወደ ላይ እንሥታ አንጋጣ ስትመለከተው ውብ ጥርሶቿ ተፈለቀቁ፡፡
ስለ ከበዳት አወረደችው:: ወለሉ ላይ ስታቆመው ጸጉሯን በጣቶቹ በተነባት፡፡
ሲናከሱና ሲናጩ ውለው እንደ ደከሙ አውራ ዶሮዎች እናትና ልጅ ፊት ለፊት
ቆመው ተያዩ። ጋሻዬነህ በአጋጣሚ እኔ ወዳለሁበት ዐይኑን መለስ ሲያደርግ
ድንገት አየኝና «አባብዬ! » ብሉ በሩጫ መጥቶ እግሬ ላይ ተጠመጠመ፡፡
አንሥቼ ታቀፍኩት፡፡ የወጂያነሽ ባደረገችው ልፊያ ፍቅራዊ ኃፍረት ስለ ተሰማት ከበስተጀርባዬ ቆማ አንገቴ ላይ ተጠመጠመች፡፡ በአፍንጫዋ በኩል የሚወጣው ትንፋሽ እየተናጠች እንደምትስቅ ያስታውቃል። ወደ መስታወቱ ላይ የፊተኛው ጨምዳዳ ገጽታዩ ጠፍቶ በአዲስ ፈገግታ ተተክቷል። ከግራናከቀኝ አማከለውኝ ተቀመጡ፡፡ ያ ሲያዋክበኝ የነበረው ጭንቀት ለጊዜው ገለል ስላለልኝ ጥቂት ተዝናናሁ፡፡ . የጋሻዩነህ ወለላ አንደበትና የየወዲያነሽ ለዛሚ ቃላት አያረኩኝ አምስት ተኩል ሆነ። ከዚያ በኋላ ግን እሷ ወደ ማድ ቤት፣ ልጃችን ከቤት ውጪ ወጣ፡፡ ወጣ ከማለታቸው ሥጋትና ጭንቀት ተቃረጡኝ:: እንቅልፍ የሥጋትን
እድፍ አጥቦ ይወስድልኝ ይመስል ገብቼ ጋደም አልኩ፡፡ ዳሩ ግን አስጨናቂ
ሐሳብ ከጣራው ላይ የተንጠባጠበ ያህል ልዩ ልዩ ሐሳብ እንደ ጉንዳን ወረረኝ።
ታገልኩት፡፡ በመጨረሻ ግን «ዛሬ ድል ማድረግ አለብኝ የሕሊናዩ ትክክለኛ ወኔ
መገንፈል አለበት። ምንም እንኳ ከንትርክ ይልቅ መግባባት ለመቀራረቢያ የተሻለ
ቢሆንም ዛሬ ደግሞ አንድ ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ ሰፊ የኑሮ ምዕራፍ
የምደመድምበት ቀን ነው» አልኩ፡፡ አእምሮዬ ጥቂት ሰከን በማለቱ ለዐርባ
ደቂቃ ያህል ደህና እንቅልፍ ወሰደኝ። ከሩቅ የሚሰማው የኤሌትሪክ እምቢልታ
በወፍራሙ ጀምሮ በቀጭኑ በመዉረስ ሰባት ሰዓት መሙላቱን አሰማ፡፡ የጋለ ሽቦ
እንዳ ነካው ሰው ደንግጬ ተነሳሁ። እመር ብዬ ወርጄ ጫማዬን አደረግሁና ወደ እንግዳ መቀበያ ክፍል ገባሁ፡፡ ለካስ የውብነሽ ቀደም ብላ ገብታ ኖሮ የውጪ
አገር መጽሔት እያገላበጠች ተዝናንታ ትጠብቀኛለች፡፡ አንዳችም ሐሳብና ሥጋት
ያለባት አትመስልም፡፡
ከምሳ በኋላ የአለባበስ ችሎታዬን ሁሉ አጠቃልዩ በዕለቱ አለባበሴ ላይ
አዋልኩት፡፡ ሙሽራ ሆኜ ባላውቅም ሙሽራ መሰልኩ። አንጎሌ የኑሮ ፈተናውን
ውጤት ለማየት አሰፈሰፈ። የወዲያነሽ የመሄጃችን ጊዜ መዳረሱን በማወቋ
ጋሻዬነህን ይዛ ወደ መኝታ ቤት ገባች፡፡ አሥር ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ
አጥቢያ ኮከብ አስመስላው መጣች። በእኔና በየውብነሽ ዝምታ ጭር ብሎ
የነበረው ክፍል በጋሻነህ የልብስ ውበት እንደገና ነፍስ ዘራ፡፡
«በሉ እንግዲህ በርቱ ይኸውላችሁ! ይቅናችሁ! አድባር ትቀበላችሁ ነው
የሚባለው» ብላ አስረከበችን፡፡ «ጨክነሽ?» አልኳት የምትለውን ለመስማት። ከዚህ አልፈ ምን ለማለት እችላለሁ በሚል አስተያየት አየችኝ። የውብነሽ ጋሻዩነህን ይዛ ፊት ለፊቴ ቆመች፡፡ ልማደኛው ሐሳቤ ተመሳቀለ፡፡ እኔንና ልጄን ወደ ሰው አለባ ምድረበዳ የምትገፈትረን መሰለኝ፡፡
«ተነሥ እንጂ ምን ትጠብቃለህ» ተባልኩ፡፡ በድካም እንደ ተጠቃ ሰው
በዝግታ ተነሣሁ።
የመጨረሻው ግብ ግብ የመጀመሪያው ምዕራፍ ተከፈተ፡፡

👍5
የጉዳዩንና የሕይወቴን የጀርባ አጥንት ትቻት መንገድ ገባን የወዲያነሽ ከወደ ኋላችን ከተል ብላ ደረሰችብን ቀድማን ከፊት ለፊታችን ቆመችና ጎንበስ ብላ ልጅዋን ሳመችው
ርህሩኅ የእናትነት ባሕሪ ስላስጨነቃት ሆዷ ሳሳ፡፡ ፊቷ ጠወለገ። ተከዘች።
እንባዋ በዕየኖቿ ዙሪያ ከተረ። ከጨቀጨቅ እንደ ታጨደ ቄጠማ በጉንጫ ላይ ገሠገሠ:: የሥጋት ዋዜማ ነበር፡፡
”የማይቀር ጉዳይ ነው፣ ተነጋግረንበትና ተስማምተንበት ወስነነዋል አልኩና ወደፊት ተራመድን። እጆቿን ወደ ራሷ ወስዳ ሰማያዊ መስመሮች የተጋደመበትን ነጭ ሻሽን ከራሷ ላይ ሳበችው:: ያ ለመንሽራተት ሰበብ
የሚጠብቀው የጸጉሯ ነዶ ተበተነ፡፡
ወደ ማታምንበት ዘመቻ የሚሔድ ልጅዋን ተስፋ በቆረጠ ዐይን እንደምትሸኝ እናት ዐይኖቿን አቡዛ እያየችው ቆመች። የግቢውን በር ከፍተን ስንወጣ «ጋሻዬነህ! ጋሻሙ! ብላ ተጣራች፡፡ የማይጠገበው የእናት ድምፅ በመሆኑ መለስ ብሎ አያት፡፡ የውብነሽ «ተዋት እባክህ አላስችል ብሏት ነው !» ብላ
ጉዞአችንን እንድንቀጥል አደረገች፡፡
ያልተነካ ግልግል ያውቃል፡ ቢሆንም የውብነሽን አልተቃወምኳትም።
ለዘልዓለም የምንለያትና የማንገናኝ መስሎ ቢታያትም በሩን መለስ አድርገነው
ካይኗ ተሰወርን፡፡ መኪናዩን ለማንቀሳቀስ ጊዜ ባይፈጅብኝም የአነዳዴ ፍጥነት ግን
እግርቿ እንደ ተቀየሩ በቅሉ ተጎተተ። መድረስ አይቀርምና ደረስን።
ለመጀመሪያ ጊዜ ያለአንዳች ፍርሃት መኪናዩን ከወላጆቼ ቤት የአጥር
በር አጠገብ አቆምኳት፡፡ እንደ ምክራችን የውብነሽ በሩጫ ወደ ቤት ገሠገሠች። ንዳድ እንዳንቀጠቀጠው ሰው
እካላቴ ተንዘፈዘፈ። ጋሻዩነህ
የመኪናይቱን ዕቃዎች እየነካካ እንደ ልቡ ይጫወት ነበር፡፡ ሁኔታው የበግ
ግልገልና የተኩላ ጨዋታ፣ የአጥፊና ጠፊ ሽኩቻ መሰለ። ሦስትና አራት ደቂቃዎች ዕድሜያቸው እያለቀ ዕለፉ፡፡ ሥጋት እያካለበው በከፍተኛ ፍጥነት
የሚሽከረከረው ደሜ ከትንቅንቅ መኻል የወጣ ሰው አስመስሉኛል፡፡ ከንፈሩን
ላቀቅ እንዳደረገ ሰው በመጠኑ ገርበብ ያለው ትልቁ የአጥር በር እንደገና
ተከፈተ፡፡
የውብነሽ በፈገግታ ብቅ አለች፡፡ ለጊዜው እንደሠመረላትና መልካም አቅጣጫ እንደ ያዘላት ከአረማመዷ ገባኝ፡፡ ዳሩ ግን ሥቃይን ለማክበድና ሥጋትን ለመጨመር ያህል የተከናወነ እንጂ ወደ ድል አደባባይ የሚያዘልቅ የነገር ውጥን አልመስል አለኝ፡፡
በመኪናይቱ መስኮት በኩል ብቅ ብላ «ከእሷ በስተቀር ማንም የለም፣
ሊሳካልን ነው። ዋናው ነገር ፍርሃትና ኃፍረትን በድፍረት ተክቶ ነገሩን ከፍጻሜ
ለማድረስ መበርታት ነው:: ለምታቀርብልህ ጥያቄ ሁሉ ሳትርበተበት
መልስላት፡፡ የምናገኛት መኝታ ቤት ውስጥ በመሆኑ በሩን ዘግተን ነገሩን ማፈን እንችላለን» ብላ መልሴን ለመስማት ሻቀለች። እንደ ሐቀኛ የሕዝብ መብት ከየትም እስከ የትም እንዲነዛ የምፈልገውን ጉዳይ ይታፈን ማለቷ ራሴን ክፉኛ ጎጠጎጠኝ። «በል ተነሥ! ከእንግዲህ የሚያስፈራን ፍርሃት መሽነፈያችንና መውደቂያችን ይሆናል» ብላ የመኪናይቱን በር ከፈተችልኝ፡፡ እኔ ግን ፍርሃቴ አልለቀቀኝም፡፡ የማይቀር ውጥን በመሆኑ መንገድ ጀመርን፡፡ ድንገት የየዋህነት ሞኝነት ተጠናወተኝና ጋሻዬነህን ቁልቁል እየሁት። እስኪ ያንተ የልበ ንጹሑ ዕድል ይርዳን። የዚያች የቅንና የደጓ እናትህ እንባዎች የእናቴን ልብ ወደ ርኅራኄ ይመልሱት» ብዬ የግቢውን በር ከፍተን ገባን፡፡ ከወላጆቼ ቤት ብቻዬን የወጣሁት ጌታነህ ሁለት ሆኜ ተመለስኩ። ሆኖም ለድል አድራጊነት ሳይሆን ለምርኮኝነት የምንገሠግስ መሰለኝ፡፡ ደረጃውን መውጣት ስንጀምር ከወደ ቤት ቀጠን ያለች የሴት አሳሳል ሰማሁ፡፡ ደረጃው ላይ መቀመጥ ፈለግሁ፡፡ የማይሆን ሆነና ቀጠልኩ። እንግዳ መቀበያ ክፍል ደረስን። ጋሻዬነህ ወደ ሌላ ሰው ቤት ሄዶ ስለማያውቅ ባጋጠመው አዲስ አካባቢ የተፈጥሮ ፈገግታው በእንግድነት ገጽታ ተተካ። ሕይወት ትግል ነው! መኝታ ቤት ለመግባት አምስት ርምጃዎች
የማትሞላ ርቀት ብቻ ቀረችን፡፡ ድንጋጤና እርብትባቴ ልቤን ናጧት።
አቅጣጫው አንድ ነው። ወደ ነፃነት አደባባይ በሚያስኬደው በዚህ ጉዞ ላይ
ሌላ የትግል ጉዞ ሌላ የመለዋለያ አማራጭ መንገድ የለም። የውብነሽ
የመኝታ ቤቱን በር ከፈተችው:: ተንደርድሮ ወጥቶ ሰው የሚውጥ አውሬ ዘሉ
የሚይዘኝ ይመስል ቀጥ አልኩ። «እኔ ነኝ የትላንቱ ትውልድ የመከራ ውርስና
የነገው ትውልድ መሠረት!» ብዪ ፊት ለፊቴን አየሁት፡፡ ያረጀ ጥቁር
የሕይወት ማቅ ታየኝ። በዕብደት ራስን መሳት ከዚህ የተለየ ስሜትና ሁኔታ
አይኖረውም፡፡ ይኖረው ይሆን? የውብነሽ በድል አድራጊነት እንደተመለሰ ጀግና
ጋሻዬነህን ይዛ ሰተት ብላ ገባች። ከበሩ ገለል አልኩ፡፡ ወደ ፊትም ወደ ኋላ
መንቀሳቀስ አቃተኝ፡፡ የየውብነሽ ተግባር ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም
በመሆኑ የተተበተብኩበትን የመጥፎ ልማድ ሰንሰለት መበጣጠስ ያለብኝ እኔው ራሴ ብቻ ነኝ። የእናቴ ድምፅ ከወደ ውስጥ «የማንን ሞንዳላ ታሞናድያለሽ በይ የማን ነው ደንቧሻ ? እስኪ ና ወዲህ! ከየት አመጣሽው ልጄ? የመዝሪያ ስንዱ
የመሰለ ልጅ! የማን ነህ ጉንጫም? ና እስኪ ወዲህ ሳመኝ ስትል ሰማሁ::
አእምሮዬ ውስጥ አንድ ነገር ዱሽ ብሎ የፈነዳ መሰለኝ፡፡ ዙሪያዬን በአዲስ
የተስፋ ዐይን እየሁት፡፡ ከፊት ለፊቴ ያለው ነገር ሁሉ ደምቆና ፈክቶ ታየኝ::
አንጎሌ የሁኔታዎች መፈራረቂያ በመሆኑ ውስጣዊ እንቅስቃሴዬ ሁሉ በየቅጽበቱ
ይለዋወጣል፡፡ በአዲስ ዓመት መግቢያ ዋዜማ ማታ «ዓመት ዓመት ድገመኝ
እያለ የችቦ እሳት እንደሚሻገር ሰው አንድ ርምጃ ወደ ፊት አንድ ርምጃ ወደ
ኋላ በመሄድና በመመለስ እንደገና ቀጥ አልኩ፡፡
«ንገሪኝ እንጂ የማን ነው ልጅ? ጉንጩ የሚቆነጠር ልጅ ማን ሰጠሽ?»
ብላ ጠየቀቻት። «ይህን የመሰለ ልጅ ስሞ ዝም አይባልም፡፡ እስኪ ትክ ብለሽ
እዪው፡፡ የማን ልጅ ይመስላል? ማንን ይመስላል?» ብላ መልስ ሳይሆን ጥያቄ
አቀረበች፡፡
የማይታየኝ አካባቢ ጸጥ ብሎ ከቆየ በኋላ እንደገና የውብነሽ አባባን
አይመስልም እንዴ? አንቺም እንደ እኔ ይገርምሽ እንደሆነ ብዬ ነው ያመጣሁት
ብላ ጥያቄና አስተያየት አከታተለች።
«አንቺው እያየሽው ምኑን ትጠይቂኛለሽ? እኔስ የገረመኝ ምኑ ሆነና?
እኔ የማን ነው እልሻለሁ አንቺ ደግሞ ሌላ ሌላውንም ታትቺያለሽ» አለችና ድምፅ
ጠፋ፡፡ የተስፋዩ አድማስ ሰፋ! «እንግዲያውስ የምሥራች! ደስ ይበልሽ!
እያገላበጥሽ ሳሚው። ያንቺው የራስሽ አጥንትና ሥጋሽ በመሆኑ በእልልታና
በደስታ ተቀበይው» ካለች በኋላ ድምጺን አጉልታ «ይኸ ልጅ የልጅሽ ልጅ ነው። እረ እስከ መቼ ድረስ ፈርተንና ተጨንቀን ልንኖር ነው?» አለችና ያን አንጎሌ ውስጥ እንደ አጥንት ልጅ ተረግዞ የኖረውን ቋጥኝ የሚያህል ሐሳብና ጭንቀት በቀላል ቃላት አፈንድታ ገላገለችኝ፡፡
የእናቴ አንደበት በጥርጣሬ የተሸበበ መሰለኝ፡፡ የየትኛው? የማንኛው
ልጄ? ምን ግራ ታጋቢኛለሽ!! እኔማ ምን ቸገረኝ! የነጋሲ ዲቃላ የመሰለ ልጅ
አምጥተሽ ስትሰጪኝ እልል ብዬ መቀበል ይጠፋኝ መሰለሽ? እመብርሃን
ትስጥሽ። የልጄም ልጅ ከሆነ በጣም ደስ ይለኛል ምን ከፍቶኝ። ይልቅስ ቀልድ
ከቀልዱ አያልፍም አለችና አንዳች ነገር ያፈናት ይመስል ዝም እለች። አንድ
ደቂቃ ምንም ሳይፈጸምባት ሞተች፡፡
ቀልዳ ቀልዱን ተይውና የማን ነው ልጅ?» ብላ አምርራ ጠየቀች፡፡ አሁንስ እውነትሽን ነው:: እኔም ልንገርሽና ልገላገል፡፡ እንኳንስ ይህን የሱፍ አበባ የመሰለ ልጅ የምሥራች ይዞ መቅረብና ሰው የእናት ሞት ያረደ የለ! ከነገርኩሽ በኋላ ግን የደስደሱን የመረጥኩትን ነገር ትሽልሚኛለሽ ብላ ሳትጨርስ ወየ ጉድ!

#ክፍል_ሀያ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
...ከወደ ጋራው አካባቢ እሪታና ዋይታ ተሰማ፡፡ “ኡ! ኡ!.ኡ.!! የሀገር ያለህ! የመንግሥት ያለህ! የወገን ያለህ! ኡ.ኡ.ኡ. እሪ!” የሚሉ ሰዎች ቁጥራቸው እየተበራከተ ሄደና የህብረት ጩኸታቸውን ያቀልጡት ጀመር፡፡
የመንደሪቱ ነዋሪዎች ዱላ የያዘ ዱላውን ጠመንጃ ያለው ጠመንጃውን እያነሳ የተጣደፈው ባዶ እጁን ለእርዳታ ወደ ዋይታና እሪታው ቦታ ገስገስ በተፈጠረው ድርጊት በመደናገጥ የበለጠ የሰው ሀይል ለማስባሰብ ተኩስ ተተኮስ፡፡
“ቷ! ቷ! . ዷ! ዷ! ህፃናትና ሴቶች ሲቀሩ ሌላው ግልብጥ ብሎ ወጥቶ አካባቢውን አጣበበው። ድርጊቱ እጅግ የሚያስደነግጥ ፍፁም ዐይን ሊያምነው የማይችል ጆሮ ቢሰማው የሚሰቀጥጥ ሆነ፡፡ የዚህ አይነቱ ወንጀል ለብዙ ሰዎች አዲስ ከመሆኑም ሌላ ወንጀሉ የተፈፀመበት ሰው ገበየሁ መሆኑ ደግሞ ህዝቡን እርስ በርሱ አባለው። አንጫጫው። ቀድሞ እዚያ የደረስው ጭንቅላቱን ይዞ “
እግዚኦ! እግዚኦ! ያንተ ያለህ!” እያለ አንዱ
በሌላው ላይ እየዘለለ ያየው ነገር አስደንግጦት ድርጊቱ አስበርግጎት
ቁጣው ከስማይ እንደወረደ ሁሉ ወደ ስማይ ያንጋጥጣል፡፡ መልካም ባህሪ የነበረው ትህትናው ለአንድ ቀን እንኳን ተጓድሎ የማያውቀው ስሙ በክፉ ተነስቶ የማያውቀው ገበየሁ፣ ለትዳሩ ቀና ደፋ የሚለው ገበየሁ፣ ትዳሩ ለሌሎች ምሳሌነት የሚበቃው ገበየሁ የዚህ አይነቱ አስቃቂ ዕጣ ፈንታ ደርሶበት በጫካ ውስጥ ተደፍቶ ይቀራል ብሎ ማመን እጅግ አስቸጋሪ ሆነባቸው፡፡ መሞቱን የሚጠራጠሩ በፍፁም እሱ ሊሆን አይችልም በማለት የሚከራከሩም አልጠፉም ነበር፡፡ ወዲያና ወዲህ ተሯሩጠው ከብቶቹ መዘረፋቸውን ሲያረጋግጡ ግን ከብቶቹን ለመዝረፍ
በመጣ ወንበዴ እጅ የተገደለ እሱ ራሱ ገበየሁ መሆኑን ሳይወዱ በግድ
እያመኑ መጡ፡፡
“እባካችሁ ጎበዝ! እባካችሁ እስቲ ቶሎ ቶሎ ብላችሁ ቅደሙ! ትኩስ ደም ላይ ከደረሰች ልክፍት ነው የሚገድላት! ድንጋጤው ሰው አያደርጋትም!
እባካችሁ ወደ ቤት እሩጡ! ጉዷን ያላወቀች ወደዚሁ እየመጣች ይሆናል
ዋ! እቴን! እሪታው የቤቷ ጉድ መሆኑን ሳታውቅ ድንገት ደሙ ላይ እንዳትቆምና እንዳትጎዳ ፍጠኑ!” አለ አንዱ የቅርብ ጎረቤት ዓላሚቱ እሪታውን ሰምታ እንዳትመጣ እየሰጋ፡፡
“ጎበዝ! ምናልባት ተጠራጥራ ካስቸገረቻችሁ በጉልበትም ቢሆን ይዛችሁ አቆዩአት። ከሞት ታድነው ደሙ ላይ ደርሳ እንዳትለከፍ! አጉል ራሷን
አደጋ ላይ እንዳትጥል ተጠንቀቁ!” ሲሉ ሌላው ጎረቤት አክለው አሳሰቡ፡፡
በዚሁ መሰረት ደህና ደህና ጡንቻ ያላቸው ስድስት ጎረምሶች ወደ ገበየሁ መኖሪያ ቤት ሮጡ፡፡ ዓለሚቱ ምን እንደተፈጠረ ምን በመፈጠር ላይ እንዳለ ቀድማ አውቃዋለች።ባሏ ከብቶቹን ለግጦሽ ካሰማራበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ሁኔታ ጠንቅቃ ታውቃለች። ጎንቻ እንደፎከረ ያደረገው መሆኑን የተረዳችው ገበየሁ ከብቶቹ እንዲታለቡ ወደ ቤት ይዟቸው
የሚመለስበት ሰዓት ሲያልፍ ነበር፡፡
የተፈፀመውን ድርጊት ፍፁም እንዳላወቀች ሆና ተጨንቃ ሰው ካላስጨነቀች በስተቀር ሀሜትና አሉባልታው እንደማያስቀምጣት ስለምታውቅ ተዘጋጀች።
ተከታትለው የደረሱትን ወንዶች በጭንቀት መልክ እያስተዋለች... እንዴ! ምነው?! ምንድነው? እንዴ! ምን ተፈጠረ?! ገበየሁ ደህና አይደለም እንዴ!? ወየው ጉዴ! ኸረ ባካችሁ ንገሩኝ?! ምንድነው ግርግሩ?!
ጨኸት…የምን ጩኸት ነው? ወየው! ኸረ ዘንድሮ! እኔ እኮ ሲዘገይብኝ ነው ልቤ የነገረኝ ኸረ! ኡኡ ኡ በዚህ ጊዜ ወንዶቹ የምታብድና ራሷን የምትገድል ስለመሰላቸው ደንግጠው ከግራና ቀኝ ሁለቱንም እጆችዋን አፈፍ ፣አፈፍ አድርገው ያዟት። በዚህ ጊዜ ለየላት። እንባዋ ግድቡን እንደ ጣሰ ጎርፍ መንታ መንታ ሆኖ እየተንዶለዶላ በጥፍሯም በንክሻም የተሰበሰበውን ሰው ሁሉ ትፈጀው ጀመር። ጠቅላላ ቤቱን ቀበሮ የገባበት የበግ መንጋ አስመሰለችው። አተራመሰችው። በዚህ ቅፅበት ወዳጅ ጎረቤቱ መጀመሪያ ቤቷን ከዚያም ቀስ በቀስ ደጁን እየሞላው መጣ፡፡
የቅርብ ዘመድ የሆነው ኡኡታውን እዬዬና ዋይታውን ከርቀት እያስማ መጉረፍ ጀመረ። “ዓለሚቱ ጉድ ሆን! ዓላምዬ እጃችን ተቆረጠ! ዓለምዬ ጉድ ፈላ! ውሽታሙ ገበየሁ! አታላዩ ገበየሁ! ልጆችህን ሳትሰናበት ገበየሁ! እሪ” እያለ ከአንጀቱ አለቀሰ፡፡ ዓለሚቱም ለያዥ ለገናዥ እስከምታስቸግር ድረስ እየጮኽች ደረቷን ደለቀች፡፡ያንን አስደናቂ የማስመሰል ችሎታዋን የታዘበ ሰው የዓለሚቱን እንከን የለሽ መሪ የፊልም ተዋናይነት ያለ አንዳች ጥርጥር ይመሰክርላታል፡፡ ያንን የተዋጣለት ድራማ ሰርታ ካጠናቀቀችና የሚስኪኑ ገበየሁ አሟሟት ለፖሊስ ሪፖርት ተደርጎ አስከሬኑ አሰላ ከተማ ሆስፒታል ተወስዶ ከተመረመረ በኋላ በተወለደ በሰላሳ
ሶስተኛ ዓመት ዕድሜው ወደ ዘለዓለማዊ ቤቱ ወደ መቃብር ወረደ።
“ቤቴን ትዳሬን ልጆቼን ሚስቴን” እንዳለ ሳያስበው እንደወጣ ቀረ። መሪር ሀዘንና የማይጠፋ ፀፀትን በወላጆቹና በወዳጅ ዘመዶቹ ልብ ውስጥ ጥሎ አለፈ... ዓለሚቱ ሀዘኑ ያደከማት፣ የደቆሳት መሰለች።
“ከእንግዲህ ጠንከር በይ እንጂ ዓለሚቱ? ከዚህ በላይ ራስሽን መጉዳት የለብሽም፡፡ ራስሽን ከዚህ በላይ ጎድተሽ እነዚህ ልጆች ሜዳ ላይ እንዳይቀሩ አስቢ! እሱ እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥሽ እንጂ ምን ይደረጋል?! አይ መከራ ሁለት ጨቅላ ልጆቹን አስታቅፏት ጉድ አደርጓት ሄደ
እኮ!...” የሰው ወሬ... ገዳይ ማን እንደሆነ የታወቀው ገበየሁ በሞተ ዕለት ነበር፡፡ ከብቶቹን ፊት ከፊት እያሯሯጠ ሲገሰግስ ሰዎች ተመልክተውት ነበር፡፡ሚስጢሩ
አልተከሰተላቸውም እንጂ፣ ገበየሁን ገድሎ ከብቶቹን ዘርፎ መሄዱን አላወቁም እንጂ አይተውታል።
· “አታውቁትም እንዴ? ጎንቻ የሚባለው ነው እኮ! ኽረ በደንብ እናውቀዋላን! ጥቁር ረዥም? አዎን! ከኢተያ ከተማ አንድም ቀን ጠፍቶ የማያውቅ? ኸረ ሌባ ነው እየተባለ ሲታማ ሰምቻለሁ! ጎንቻ ሌባው ነው እንዴ?! አዎን ጥቁሩ አውቀዋለሁ! ምነው ከወይዘሮ ባንቺይደሩ ቤት የማይጠፋው የሃጂ ቦሩ ልጅ አይደለም እንዴ?! ኸረ ከባለቤቱም ጋር ይታማል ጉድ ነው! ጉድ! አቤት! አቤት!” ውስጥ ውስጡን ሰው ያወራ ጀመር፡፡ ቀስ
በቀስ ደግሞ ጎንቻ ዓለሚቱን የወሸማት መሆኑ ሹክሹክታው ማምለጥ
ጀመረ።
ስልስቱም አርባውም እንደ ቀልድ አለፈ፡፡ ከዓለሚቱ ጭንቅላት ውስጥ የገበየሁ ምስልና ትዝታ ሙሉ ለሙሉ ጠፋ። ትዝታውና ስሙ ያልጠፊው አባባ የታለ? እያሉ ዘወትር ከሚጠይቁት ከእነኝያ በአእምሮም ሆነ በአካል ካልበሰሉ ጨቅላ ህፃናት ጣፋጭ አንደበት ብቻ ነበር።በለቅሶው ዕለት አባታቸው ለዘለዓለም በተለያቸው በዚያን ቀን የነበረው ትርምስና ግርግር ለነሱ ሰርግና ምላሽ ነበር፡፡ ምናልባት የእናታቸው ለቅሶ ቢያስደነግጣቸው እንጂ ከዚያ በኋላ ያለአባት የሚቀሩ የሙት ልጅነታቸው
አልታወቃቸውም ነበር፡፡ ለዚያውም ወንዱ ምትኬ ይሻላል። እሱ ትንሽ ትንሽ በደመነፍሱ ሳይታወቀው አልቀረም፡፡ “እማምዬ አባዬ የታለ አይመታም?”ብሎ ሳይጠይቅ የዋለና ያደረበት ቀን አልነበረም፡፡ ከሁሉ የበለጠ
የምታሳዝነው ደግሞ ትንሿ ሴት ልጁ ነበረች። የዛሬን አይጥራትና በስሟ
ሳይሆን “እናቴ፣ እናቴነሽ” እያለ እያቆላመጠ ነበር የሚጠራት። እሷም
እንደ ወንድሟ አባቷ እየናፈቃት ስለመጣ ታላቅ ወንድሟ የአባቱን ስም እያነሳ ሲጠይቅ የሷም ጥያቄ በመሆኑ ዐይኖቿን በእናቷ ዐይኖች ላይ ታቁለጨልጭ ነበር።
ሁለቱ ህፃናት አባታቸውን ከእናታቸው ዐይኖች ውስጥ እንደሚያገኙት
ሁሉ ዘወትር ዐይን ዐይኖቿን በልምምጥ እያስተዋሉ መወትወታቸውን አላቋረጡም ነበር። የምትመልሳቸው

መልስ ጥፍት ሲልባት “ቆይ ይመጣል። ሩቅ አገር ሄዶ ነው አሁን ይመለሳል ትላቸዋለች።ልጅ የዋህ ነው፡፡ ያውም ማመዛዘን የማይችሉ ህፃናትን ስትዋሻቸው የአባታቸው
ናፍቆት እንደሚበረታባቸው ከአሁን አሁን ይመጣል ብለው በየዋህነት
እንደሚጠብቁት አጥታው አልነበረም፡፡ ነገር ግን በሟቹ ባሏ ላይ ያደረባት ደንታ ቢስነት፣ ለባሏ የነበራት ፍቅር ከባሏ ጋር አብሮ በመሞቱ የባሏን ልጆች ጭምር አስጠላትና በህፃናት ልጆቿ በኒያ በሞትና በህይወት መካከል ያለውን ልዩነት በማያውቁ ምስኪኖች ላይ እንኳ ጨከነችባቸው፡፡ ከዛሬ ነገ ይመጣል እያለች በናፍቆት አለንጋ ቀጣቻቸው። በዚህላይ ደግሞ ጎንቻ ወሽሚት እንደነበረ ለገበየሁ ሞት የሷ እጅ እንዳለበት ከስሞኑ ሀሜትና ሹክሹክታ ወሬው ሲናፈስ ከርሞ ከጆሮዋ ደረሰና
ልጆቹን የበለጠ ጠላቻቸው። የመዘበኛ ልጆች" ስትል በልቧ ረገመቻቸው።.....

#ክፍል_ሰላሳ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
...ጋሻዬነህ ጌታነህ ይባላል» ብላ ጸጥ አለች። ከወዲህም ከወዲያም ከጣራውም ከወለሉም ላይ ድምፅ ስደት ገባ።
ከማን የተወለደ? የመቼው? የት የነበረ? ብላ የተሰደደውን ድምፅ መለሰችው:: ነገሩ በመፋፋሙና ጥያቄው በመድራቱ የመጣው ይምጣ ብዩ ዐይኔን ጨፍኜ ገባሁ፡፡
ምንም ሳልናር ተቀመጥኩ፡፡ ጋሻይነህ እናቴ እግሮች መካከል ቆሟል።
የውብነሽ ከእናቴ ፊት ለፊት ቆማ የአቤቱታ መልስ የሚጠባበቅ ድኃ መስላለች።እናቴ ዘወር ብላ ካየችኝ በኋላ ለዛ ባጣ ፈገግታ ገረመመችኝ፡፡ «የጌታነህማ ልጅ ከሆነ እሱው ራሱ ይናገር፣ ይኸው መጣ! አንቺ ምን ታጎበጉቢያለሽ» አለችና ዐይኖቿን ወደ ጋሻዬነህ መለሰቻቸው:: አቀረቀርኩ፡፡ ከንፈሮቼ ተጣበቁ፡፡
ያመጣኸውን ብታመጣ በደስታ እቀበልልሃለሁ፣ እፈጽምልሃለሁ ብለሽ
የአቦን ስም ጠርተሽ ምለሻል:: አሁን ወዲያ ወዲህ እንዳትይ! በዚህ ወጥቶ በዚያ ወርዶ ብሎ ነገር የለም፡፡ ታሪኩንና ሁኔታን ሁሉ ቀስ በቀስ ነገና ከነገ ወዲያ
እንዘረዝርልሻለን፡፡ አሁን ግን ምንም ምንም ሳትይ ይህን የአተር ክክ የመሰለ ልጅ ደስ ብሎሽ ተቀበይን፡፡ የሚያኮራና የሚያስደስት ነው:: ከዛሬ ስድስት ዓመት
በፊት የተወለደ የጌታነህ ልጅ ነው» ብላ በሙሉ ልብ ተዝናንታ ተቀመጠች፡፡
ከተሽከምኩት የሐሳብ ቀንበር ላይ ትንሽ ተጎርዶ ወደቀ፡፡ ደቂቃዎች ተውዘገዘጉ፡፡
እናቴ በሐሳብ ላይ እንዳለች ጋሻዬነህ ከእግሮቿ መኻል ሹልክ ብሎ ወጣና ትከሻዬን ይዞ ከጐኔ ቆመ:: ጉልህ መልስና ድንቅ ምስክርነት ነበር፡፡
እናቴ ወደ ጎን ዘወር ብላ ስታይ ሰርቀው ከሚመለከቷት ዐይኖቼ ጋር ተጋጨች፡፡ የእኔዎቹ ተሰበሩ፡፡ ፍርሃት ሳይሆን ትሕትና ሰበራቸው።
«ይሁና! አበጀህ! ደግ አረክ! ታዲያ ምን ኣለበት እንኳን ወንድ ልጅና፣ሴትም ልጅ ወልዳ ትመጣለች ! ቀና በል! የምን ማቀርቀር ነው:: ያንበሳ ግልገል
የመሰለ ልጅ ነው ያመጣኸው! እኔ እናትህ ባልምል ባልገዘትስ አንተን ልጄን
አሳፍርሃለሁ እንዴ? ደስ የሚል እንጂ የሚያሳፍር አይደለም፡፡ ያኔዬስ ቢሆን
መላውን አጥቼውና የሴት ነገር ሆኖ ተበሳጭቼ ነው እንጂ የኋላ ኋላ ሳልጠጣትና ሳያንገበግበኝ ቀርቶ መሰለህ: ሽንፍላችን ስስ ነው:: አንችልም! አንኳን አንድ ሁለትና ሦስት ቢሆንሳ? እስከ ዛሬ ድረስ ደብቀሽኝ በመኖርሀ ግን ቀስ ብለን እንወቃቀስበታለን» ብላ ጋሻዬነህን ወስዳ አገላብጣ ሳመችው። የደስታና የርኅራኄ እንባ ዐይኖቿ ላይ ተንቀዋለለ።
ጨምደድ ባለው ፊቷ ላይ የኃፍረትና የጸጸት ስስ ፈገግታ ታየ። አምጣ አምጣ እንደ ተገላገለች ነፍሰ ጡር እኔም የሐሳቤን እትብት አስቆርጡ አፎይ
አልኩ፡፡
«አቤት እኔ! ይኸስ እውነትም እልል በይ የሚያሰኝ ነው፡፡ በል አንተ ትልቁ ልጅ
ደግሞ ሳመኝ፡፡ ምንስ ቢሆን ከጥጃይቱ በፊት እናቲቱ” ይሉ የለ፡፡ ከዚህ የበለጠ
ዓለም የት ይገኛል» ብላ ከመናገሯ እመር ብዬ ሄጀ ተሳሳምን፡፡ የውብነሽ በደስታ
ተፍነከነከች፡፡ ደሜ የፈንጠዚያ ግልቢያ ጋለበ። ዐይኖቼ በእናቴ በኩል የሚደረገውን የተስፋና የጉጉት ውጤት አፍጥጠው ተመለከቱ። በእናቴ የፍቅር
ሚዛን ላይ የዱሮው ጌታነህ ለመሆን ተቃረብኩ፡፡ ወንዙን ላደነቀ ምንጩን
ማሳየት አስፈላጊ በመሆኑ የጋሻዬነህን ምንጭ ማሳየት አስፈላጊ ነው፡፡
ተመስገን! ተመስገን! ክብርህ ይስፋ! እንኳን ለዚህ ያበቃኸኝ! ኖረህ ኖረህ ይህን የመሰለ ልጅ ይዘህልኝ ስትመጣ ምን ከፍቶኝ! አቦዬም ስለታቸውን አገኙ፡፡ ትንሽም ቅር የሚለኝ እንደ ወንድሞችህና እኅቶችህ ወግ ማረግ...አረ ምን አባቱ! ይሁን! ዞሮ ዞሮ ለዚሁ አይደል?» አለችና ከሕሊናዋ ጋር ለመግባባት አስተያየቷን መለወጥ ሞከረች፡፡ እንደ ወንድሞቼና እህቶቼ እንድሆንላት ስትመኝ የነበረው ምኞቷና ፍላጎቷ ሁሉ በዚህ ባልጠበቀችው ሁኔታና ኢጋጣሚ ከሰመ፡፡
«ደስ አለሽ? እኛማ በጣም ፈርተንና ተጨንቀን ነበር፡፡ እንዲህ በቀላሉ
ይቀናናል፣ እንዲህ ባለ ሁኔታ ይሳካልናል ብለን በፍፁም አላሰብንም ነበር?» ብላ
የእናቴን ኃይለኛነትና ትፈሪነት ለማስገንዘብ ሞከረች፡፡ እግረ መንገዷንም የእናቴ ስሜት ወደ እኛ እንዲያዘነብል ማጎሳመሷ ነበር፡፡
«እስኪ ተይኝ ልጀ! የዛሬዋን ደስታዩን ዝግ ብለን ልባችንን አስፍተን እንጫወታለን፡፡ ጌታነህ እንበሳ ከነነፍሱ ይዞልኝ መጥቷል» ካለች በኋላ ጋሻዬነህን
ለየውብነሽ ሰጥታ ወደ እንግዳ መቀበያ ክፍል ሄደች። እኔና የውብነሽ በደስታ
ተቃቅፈን ተሳሳምን። ጋሻዬነህንም ለሁለት ኣንሥተን «አንተ ዕድለኛ» ብለን
በየአቅጣጫችን ያለውን ጉንጩን ስመን ወደየነበርንበት ቦታ ተመልሰን
ተቀመጥን። ሰው በደስታ ይፈነዳ ሲሆን ያለጥርጥር እፈነዳ ነበር። አንዲት
ሠራተኛ የእጅ ውሃ አምጥታ እንዳስታጠበችን እናታችን ገባች። ይኽነዩ ነበር የቀድሞው የየወዲያነሽ ሕይወት ትዝ ያለኝና መንፈሴ ስለ ባለቤቴ
የተሠቃየው:: በሌሎች ሁለት ሠራተኞች ደግሞ ምግብና መጠጥ በየተራ ቀረበ።
«የቤታችንን የሲሳይ ርጥበት አሳምሬ ስለማውቀው በቀረበው መስተንግዶ
አልተደነቅሁም፡፡
እህል ብቻ ሳይሆን የደስታ እንክብክብ ጎረስኩ፡፡ ባልገመትኩት አኳኋን ወኔና ብርታት አካበትኩ፡፡ አዲስ የኑሮ ተስፋ ከፊት ለፊቴ ተዘረጋ፡፡ አጋጣሚና
ድል የሚባለው ይኸ ይሆን? እስከ ማለት ደረስኩ፡፡ እናቴ ወደ እፏ ከላከችው
ይልቅ ለእኔና ለጋሻዬነህ ያጎረሰችን ይበልጣል። የጣቶቿ ጫፎች ከንፈሮቼን
እየነኩ ሲመለሱ የእናትነቷን ውድ ፍቅር እያቀበሉኝ ተመለሱ።
ጋሻዬነህ አካባቢውን ስለተለማመደው ያ በግርታ መጦ የነበረው ፊቱ እጥፍ ፈገግታ አንዠረገገ። ገበታው ከፍ ኣለ። የአዲሱ ግንኙነት ማዕድ ግን በሰፊው ቀጠለ። እናቴ ብርጭቆዋ ውስጥ የነበረችውን ጠላዋን ተጎንጭታ
ጉሮሮዋን ካራሰች በኋላ እናንተ ግን ምስጥ ናችሁ፣ ልባችሁ አይገኝም፡፡
የገረመኝ ደግሞ ሆን ብላችሁ አባታችሁ በሌለበት ቀን መምጣታችሁ ነው::
የናንተን ብልጠት ማን ያገኘዋል» አለችና ተንኮል የሌለበት ሣቅ ሣቀች፡፡
«ከአባታችን ይልቅ አንቺን በመጀመሪያ ብንጠይቅና ብናሸንፍ፣ አንቺ
ካየሽው በኋላ የምትይንን ለማወቅ ብለን ነው:: በተለይ የዛሬዋን ቀን ጠብቀን
የመጣነው» ብላ የውብነሽ በጠላዋ ውስጥ የምትታየውን የገዛ ፊቷን ምስል
ለማየት አንገቷን ወደ ብርጭቆው አሰገገችው።
«ኧረ ለመሆኑ አንቺ ይኸ ልጅ መወለዱን የሰማሽውና ያወቅሽው መቼ ነው?» ብላ መገረሟን በሚገልጽ ስሜት ጠየቀቻት። የውብነሽ ካቀረቀረችበት ቀና ብላ «አጅሬ መች እንዲህ የዋዛ ሰው ነውና! እኔም ያየሁት አሁን በቅርቡ ነው:: ያም ሆነ ይህ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ የቀረውን ተይኝ» በማለት ወቀሳ የቦረቦረው ድጋፍ አደረገችልኝ። የጋሻዬነህ እናት ማንነት እና ስሟ ተጠቅሶ ባለመነገሩ በውስጤ የሚፈራገጠውን ጭንቀቴን አጠቃልዬ አልገደልኩም፡፡
«ኧረ ለመሆኑ እናቱ ማን ትባላለች? የማን ልጅ ትሆን? አልነገራችሁኝም እኮ?» ብላ ሁለታችንንም. በየተራ አየችን፡፡ እኔና የውብነሽ ተፋጠጥን! ይህን ለጊዜው በምሥራችነት የማይነገር ታላቅ ጉዳይ ማን ያርዳ?
የውብነሽ መልስ ለመስጠት አልዘገየችም፡፡ «የእናቱ ጉዳይ ግልጽም
??ስውርም ነው:: ከዚህ ቤት ይጀምርና ወደ ሌላ ሰፊ ሥፍራ ይጓዛል። ዳቦውን
ገምጦ ምጣዱን መጥላት አይገባም፡፡ የዚህ ልጅ እናት አንቺ እንደምትመኘው
የማንም ትልቅ ሰው ልጅ አይደለችም፡፡ በደፈናው የሰው ልጅ ነች፡፡ እስከ አሁን
ድረስ ፈርተናል ፣ተጨንቀናል፣ ከእንግዲህ ግን በቃ! የዚህ ልጅ እናት የመከራ
እሳት የለበለባት፡ የሥቃይ ቀንበር የተጫናት፣ የሰው ፊት እንደ እሳት ነበልባል

👍3❤1👏1
የገረፍት፡ አንቺና እኔም አንድ ቀን ያሠቃየናት የወዲያነሽ ነች፡፡» ብላ
በድፍረት እንደ ጀመረች በድፍረት ጨረሰች፡፡
“ጉዱ ገና ነው ! » ብላ በሁለት እጆቿ ራሷን ያዘች። እንኳን አንድ ጊዜ ለርሷ መርዶ ለእኔ ግን የምሥራች የሆነውን ጉዳይ አረዳናት እንጂ ኡኡ ብትል ግድ አልነበረኝም:: እጅዋን ከራሷ ላይ ካወረደች በኋላ ትካዜዋን ተከናነበች። እኔና የውብነሽ አፋችንን አፍነን ድምፅ የሌለው ሣቅ እየሣቅን ተያየን፡፡ ጋሻዬነህ ወዲያ ወዲህ በመመላለስ አዲስ መስሎ የታየውን ሁሉ ይመለከታል፡፡ ዐይኖቼ እግሮቹን ይከተላሉ። እናቴ የጀመረችው ዝምታ ጎለመሰ የእኔ እፎይታ ግን ከመዳህ ዐልፎ በእግሩ ቆመ፡፡ ጋሻዬነህ አጠገቤ መጥቶ ለጠቅ ሲል ወደ እናቴ አስተላለፍኩት። ነገሩ ሁሉ ላም እሳት ወለደች….ሆነባት: ከሐዘኗ ይልቅ የደስታዋ መጠን በመብዛቱ ትካዜዋ ተፈነቸረ። «የእኔስ ግድ የለም ይኸው ዕዳው ገብስ ነው፣ አንድ ጊዜ መጫወቻችሁ ሆኛለሁ፡፡ እንዲያው
ያ አባታችሁ የሚነገረው እንዴት ተደርጎና ተብሎ ነው?» ብላ ንግግሯን
ሳታከትም የውብነሽ ሌላ ንዑስ መርዶ አዘጋጅታ ኖሮ እኔ እንደሆነ ይቅርታ
አድርጋልኝ በሚገባ ታርቀናል» ብላ ባቋራጭ ጠለፈቻት፡፡
መልቲ! የሰው መልቲ! ምነው አዋከብሽኝ ዛሬ? የት እባሽ አግኝተሻት ነው ይቅርታ ያደረገችልሽ?» ብላ ፈዝ ቅልቅል ተቆጣች።
«እሷን ካላገኘናትማ ልጅዋን ከየት አመጣነው?» ብላ የእናቴን ቁጣ
በትሕትና ቀነጠሰችው፡፡ እናታችን እንደማትመታት ብታውቅም የውብነሽ
ከመምህሩ አለንጋ እንደሚሽሽ ተማሪ ተነሥታ አቆበቆበች፡፡
«እቅጩን ልንገርሽ! የዚህ ልጅ እናት ያቺ በቀደም ያሞጋገስሻትና ያመሰጋገንሻት የወዲያነሽ የልጅሽ የጌታነህ ሚስት ሆናለች፡፡ እንድ ላይ በአንድ ቤት ውስጥ አብረው እየኖሩ ነው፡፡ ዛሬ ይዘናት ያልመጣነው አንቺን በመፍራታችን ነው» ብላ ከነሙሉ ንቃቷ ቆመች። የእናቴ ድንጋጤ ከበደ።ጋሻዬነህ ሽርተት ብሎ ከላይዋ ላይ ወረደ፡፡ ብስጭትን በሚገልፅ ሁኔታ ሦስት ጊዜ አጨበጪበች፡፡ “ለካ እንዲህ ኖሯልና ነገሩ! እንዲሁ በከንቱ ኖሯልና ስወተውት የኖርኩት? ተጋብተዋል ማለት ነዋ! ኧረ ለመሆኑ የት አግኝቷት ነው ይህን ያህል ዓመት ተሸሽገው የኖሩት፡፡ እኛ እዚህ እከሊት ትሻላለች፣ እከሊት አንገተ ሰባራ ነች እያልን አራባና ቆቦ እንዘሳለን፣ ለካ እሱስ በጎን ደበቅ ብሎ የልቡን እድርሷል! » ብላ በነጭና ጥቁር ዳውጃ ያማረውን ወለል ማየት ጀመረች። አነጋገሯና ሁኔታዋ እንደገና አስደነገጠኝ፡፡
ነገሬ የተበላሸና እንዳይሆን የሆነ ስለ መሰለኝ ተንደርቦ ከነበረው የተስፋዬ ሥፍር ላይ ሳያሌው ቀነስኩ። «የእኔና የልጅ ሕይወት በእናቴ በኩል አምሮ ከሠመረ በኋላ የየወዲያነሽ ሕይወት ይበላሽና ይናድብኝ ይሆን?» ብዬ
ራሴን ጠየቅሁ።
ከወደ ሕሊናዩ የተገኘው መልስ ግን ስለ የወዲያነሽ መሥዋዕት ሁን! ተስፋዋና አለኝታዋ አንተ ነህና ስለ እርሷ በርታ» የሚል ነበር፡፡
«ወይኔ ልጂት!» አለች እናቴ እንደ ልማዷ ራሷን እየነቀነቀች።
«ወይነዶ! ደኅናው ስማችን ይጠፋል፣ የሰማ ሰውስ ምን ይለናል? ብዬ
ደኅናይቱን ልጅ በከዘራ አንክቼ አንክቼ ያባረርኳት እኮ ላንተው ብዬ ነበር፡፡
እኔንማ ካክብሮት ሌላ እማማ ምን ልታዘዝ ምን ላድርግ ከማለት ሌላ ምን
በደለችኝ? ከልክ በላይ ትወደኝ ነበር፡፡ የማታ ማታ እንዲህ እንደሚሆን በየት አቤቴ አስቤው ብላ በመጨረሻ ምን እንደምትል ለማሰላሰል አፏን በእጇ ከደነችው :: ጋሻዬነህ ፈንጠር ብሎ ወንበር ላይ ተቀምጧል።
የሆነስ ሆነና ልጅዋን መንጭቃችሁ ስታመጡ እናትየዋን ለምን ተዋችኋት? ይዂማ ደግ ሥራ አይደለም። እናንተ ከተስማማችሁና ከተፋቀራችሁ፣ እኛ ምን ቸገረን፡፡ አንደዬ እንዳይሆን ሆኗል፡ ክብሩ፡ ወጉና ማረጉ የቀረብህ አንተ። እኛማ ከዚህ ቀደም አሳምረን ድረናል ኩለናል፡፡ ባገር በዘመድ ፊት ተንቀባረናል መሸኘቱንም መቀበሉንም አይተነዋል። ያንተ ግን እርግማን ያለብህ ይመስል ተግማምቶ ቀረ፡፡ አሁንማ ምን የሚባልና የሚነገር ነገር አለና? አለቀ በቃ! ! ዱሮውንስ ቢሆን እኔን ምን የበደለችኝ መሰለህ? ላንተው ብዬ ነበር ሰው አይሠራው ሥራ የሠራኋት፡፡ እኔማ ጥንቱንም ቢሆን ውቃቢ አምላኬ ይወዳታል፡፡ አሁን አሥሩን ቢያወሩ ቢቀባጥሩት ምን ያረባል እንጂ ኮከባችንም ግጥም ነበር፡፡ መልኳ እንደሆነ ታጥቦ የሠራት ነች! ቀለም
የመሰለች ዘንካታ! ምንም የሚነቀስ ጉድፍ የሌለባት! ደርባባ! ዘንካታ ልጅ
ነች» ብላ ያን ቀደም ሲል በቁጣ ግሎ የቀላውን ፊቷን በመጨረሻዎቹ
የአድናቆት ቃላት ወደ ቀዘቀዘ ደግነት እና ርህራሄ አንሽራተተችው፡፡ የውብነሽ
ቁርጡን ለማወቅ «ነገ ከሰዓት በኋላ ይዘናት ብንመጣ ደስ ብሎሽ ትቀበይልናለሽ ማለት ነዋ?» ብላ እየተፍነከነከች ተቀመጠችና እንደገና
«እሺ ብለሽ በደስታ የምትታረቂልን ከሆነ ዛሬም ቢሆን ይዘናት እንመጣለን» አለችና የጠለለችውን ጠላዋን ጠጣች፡፡
«ምነው በይ! ምነው ሥራ ፈታሽብኝ! የምን ዕርቅ አመጣሽ? ይህን መሳይ
ሞንዳላ ልጅ ልካልኝ! የምን ዕርቅ ነው እሱ? ምን ባጠፋች? ምን በበደለች? ያየህ ይራድን ዳግመኛ ፍጥር ባደረገች? እስኪ ተዪኝ ልጄ! እስኪ ተዪኝ! በገራገርነቴ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ የማውቀው እኔ ነኝ፡፡ እግሯ ላይ ወድቄ ማሪኝ ማለት ያለብኝማ እኔ ነኝ። እሷ በምን አበሳዋ? ፈንካቺቱ እያለሁ ተፈንካችዋ? ምን በወጣት!? ይህን ያቡን መስቀል የመሰለ ልጅ ከሸለመችኝ በኋላ ነገር ባወላግድኛ ባጣምም እግዜሩም አይወደው፡፡ ሰውም ቢሆን ላመሉ ያህል
መክረሚያውን አወራርቶ ይረሳዋል፡፡ እንዲህ እንደናንተ እዚሁ ተወልዳና አድጋ
ትምህርት ብትማር ኖሮ ስንት ሽማግሌ እየተላከ፡ ስንቱ ባደገደገ ነበር፡፡ ምን
አዲስ ነገር አለ? አምጡልኝ! ይኸነዩ እሷም የልጅዋ ነገር አላስችል ብሏታል፡፡
ነገር ኣናበዛ፣ ነገውኑ ይዛችኋት ኑ፡፡ በደልኳት እንጂ አልበደለችኝም፡፡ ከእንግዲህ ምን ያህል ሊቀረኝ፣ ስለ ሌላው ቀስ ብለን እንመክርበታለን» ብላ የልቧን ዘከዘካችው፡፡
እኔም «እረ ምን ሲደረግ ብለው ያባርሩኛል አያስገቡኝም፣አያስጠጉኝም ብላ ማታ ነው እንጂ እዚህ ድረስ መጥታ ይቅርታ ልትጠይቅሽ ፈልጋለች። ጉዳዩ ሁሉ በሚገባ ገብቷታል» ብዩ ባልተያያዘና ቅደም ተከተሉን ባልጠበቀ አኳኋን ተናገርኩ፡፡
እናቴ አዘኔታ በሚታየበት ፊት ወደ እኔ መለስ አለችና “ሞኝነትህ፣ ሞኝነትህ ነው ልጄ! አይዞሽ ግድ የለሽም' ብለህ ይዘሃት ና፡፡ እኔ እናህ አሳምሬ እቀበልልሃለሁ። አትፍሪ! አትፍሪ' ነዪና እንታረቅ፣ ከእንግዲህ ወዲያ እኔና አንቺ እናትና ልጅ ነን፣ ልጄ ልጄ ብላሻለች ብለህ አሳምረህ ንገርልኝ በማለት ያን በውስጤ ሲገላበጥ የዋለ ሥጋትና የመንፈስ ሽብር ገደለችልኝ።....

👍3🤔1
#ይድረስ_ላንተ
ጀግናዬ የቤትህ ድባብ
ቢናፍቅህ አውዳመቱ፣
ምንም ባይንህ ላይ ሽው ቢል
የዘመድ አዝማድ ጨዋታ
የቤተሰብ ናፍቆቱ፣
የኩበቱ ጭስ ሽታ
የዶሮ ወጥ አምሮቱ፣
የእህት የወንድም ትዝታ፣
ያባት ጠረን የናት ሽታ
የአደይ አበባው ውበት በለው
የገበያው ድምቀቱ፣
ከአብሮ አደጎች ጋር መቃለድ
አብሮ መብላት መጠጣቱ፣
እርግጥ ነው ይናፍቅሃል
አድባር ቀዬው አውዳመቱ፡
መቻል አንተ ልማድህ ነው
ናፍቆት ችለህ መክፈል ዋጋ፣
ማንም ይወቀው ልክህን
በዋዛ አይደለም ጀግናዬ
ሞተህልኝ ነው የምታነጋ፡፡
ቤተሰብ በማእድ ዙሪያ
ስለ አውደ አመት ሲስባስብ፣
አንተ ዛሬም በድንበር ላይ
ስለ ሰላም ነው የምታስብ፡፡
ልጆች ከአባቶቻቸው . . . የገና ስጦታን ሲቀበሉ፣
ጀግናዬ ያንተ ምስኪኖች . . . አይንህን ይናፍቃሉ፣
የሃገር የቁርጥ ቀን ልጅ
አንተ ወገን አፍቃሪ፣
አንተ ስለ ሰላም ሟች
አንተ ቃልህን አክባሪ፣
አንተ የሃገር ማገሯ
አንተ ስለ ህዝቧ ኗሪ፣
ከምትክ የለሽ ህይወት ላይ
እሷኑ ለድንበር ገባሪ፣
ደስ እያለህ ያበረከትክ
ነብስን የሚያህል ስጦታ፣
ጀግናዬ የሰውነት ልክ
ወታደር የፍቅር ጌታ፣
አውደ ዓመት ሲከበር በፌሽታ፣
በድንበርህ ላይ ዘብ ቆመህ
የሚያረካህ የወገንህ ደስታ።
በማን ሆነና መንጋቱ፣
የአዲስ ዘመን ጀንበር መታየቱ፣
ዘመን እንዲብትልን
ቀናችን መሽቶ እንዲነጋ፣
አንተ ነህ ከአምላክ ቀጥሎ
የከፈልክልን ውድ ዋጋ፡፡
በለሰለሰ መኝታ ጣፋጩን እንቅልፍ የጠገብነው፣
አሸዋ ልብሱ ወጥቶ አደር
እንቅልፍህን ጾመህልን ነው፣
ቀዝቃዛ ውሃ ጠጥተን
ስለ እርካታችን ስንናገር፣
የምትጎነጨውን ውሃ ግለት
የምታውቅ ኮዳህ ትመስክር፡፡
አዎ አዲስ ዘመን ባተ
እውነት ነው መስከረም መጣ፣
ክረምቱ አልፎ ተሻገርን
አየናት ምድር አጊጣ፣
ልዩ ነው ነብስ ያስደስታል
መስጠት መቀበል ስጦታ፣
የማይደበዝዝ ሃቅ ግን
ወታደር ያንተ ውለታ፡፡
እውነት ነው ወታደርነት
ስለ ሃገር ክብር መክፈል ህይወት፣
ስለ ህዝብ ፍቅር ኖሮ መሞት፡፡
ከተጋፈጥከው ተራራ
ካቋረጥከው ቆንጥር ጀርባ፣
አዲስ ፀሃይ እኛ አይተናልተ
በመስዋእትነትህ ታጅባ፡፡
በአንተ ነው አንተ ያገሬ ልጅ
ባንተ ነው ጨለማው የነጋ፣
ሃገርና ህዝብን አስቀድመህ
በከፈልክልን ውድ ዋጋ፡፡
ሃገር እስከ ጥግ ተጠራርቶ
አንዱ ለሌላው መልካም ሲመኝ፣
ስለ ሃገሩ ወጥቶ አዳሪው
አንተን ቢረሱህ አመመኝ፡፡
አድምጠኝ ጀግናዬ ጓዴ....
አንተ ባለህበት በረሃ
ባይኖርም እርጥብ ቄጠማ፣
ክትፎውን ከቁርጥ ባታማርጥ
ቀዝቃዛ ውሃን ብትጠማ፣
ወታደር ባንተ ልፋት ነው
መድመቁ በአል አውደ አመት፣
ለጥቁር አፈርህ ክብር
አፈር መስለህ የደከምክበት፡፡
እየሞትክ የምታቆማት ሃገር
ዛሬ ዘመኗን ስትቀይር፣
እንኳን አደረሰህ ልልህ ወደድኩ
ክብር ምስጋና ላንተ ይሁን
ለራስህ ያልኖርከው ወታደር፡፡
🔘ሻለቃ ወይንሐረግ በቀለ🔘
ጀግናዬ የቤትህ ድባብ
ቢናፍቅህ አውዳመቱ፣
ምንም ባይንህ ላይ ሽው ቢል
የዘመድ አዝማድ ጨዋታ
የቤተሰብ ናፍቆቱ፣
የኩበቱ ጭስ ሽታ
የዶሮ ወጥ አምሮቱ፣
የእህት የወንድም ትዝታ፣
ያባት ጠረን የናት ሽታ
የአደይ አበባው ውበት በለው
የገበያው ድምቀቱ፣
ከአብሮ አደጎች ጋር መቃለድ
አብሮ መብላት መጠጣቱ፣
እርግጥ ነው ይናፍቅሃል
አድባር ቀዬው አውዳመቱ፡
መቻል አንተ ልማድህ ነው
ናፍቆት ችለህ መክፈል ዋጋ፣
ማንም ይወቀው ልክህን
በዋዛ አይደለም ጀግናዬ
ሞተህልኝ ነው የምታነጋ፡፡
ቤተሰብ በማእድ ዙሪያ
ስለ አውደ አመት ሲስባስብ፣
አንተ ዛሬም በድንበር ላይ
ስለ ሰላም ነው የምታስብ፡፡
ልጆች ከአባቶቻቸው . . . የገና ስጦታን ሲቀበሉ፣
ጀግናዬ ያንተ ምስኪኖች . . . አይንህን ይናፍቃሉ፣
የሃገር የቁርጥ ቀን ልጅ
አንተ ወገን አፍቃሪ፣
አንተ ስለ ሰላም ሟች
አንተ ቃልህን አክባሪ፣
አንተ የሃገር ማገሯ
አንተ ስለ ህዝቧ ኗሪ፣
ከምትክ የለሽ ህይወት ላይ
እሷኑ ለድንበር ገባሪ፣
ደስ እያለህ ያበረከትክ
ነብስን የሚያህል ስጦታ፣
ጀግናዬ የሰውነት ልክ
ወታደር የፍቅር ጌታ፣
አውደ ዓመት ሲከበር በፌሽታ፣
በድንበርህ ላይ ዘብ ቆመህ
የሚያረካህ የወገንህ ደስታ።
በማን ሆነና መንጋቱ፣
የአዲስ ዘመን ጀንበር መታየቱ፣
ዘመን እንዲብትልን
ቀናችን መሽቶ እንዲነጋ፣
አንተ ነህ ከአምላክ ቀጥሎ
የከፈልክልን ውድ ዋጋ፡፡
በለሰለሰ መኝታ ጣፋጩን እንቅልፍ የጠገብነው፣
አሸዋ ልብሱ ወጥቶ አደር
እንቅልፍህን ጾመህልን ነው፣
ቀዝቃዛ ውሃ ጠጥተን
ስለ እርካታችን ስንናገር፣
የምትጎነጨውን ውሃ ግለት
የምታውቅ ኮዳህ ትመስክር፡፡
አዎ አዲስ ዘመን ባተ
እውነት ነው መስከረም መጣ፣
ክረምቱ አልፎ ተሻገርን
አየናት ምድር አጊጣ፣
ልዩ ነው ነብስ ያስደስታል
መስጠት መቀበል ስጦታ፣
የማይደበዝዝ ሃቅ ግን
ወታደር ያንተ ውለታ፡፡
እውነት ነው ወታደርነት
ስለ ሃገር ክብር መክፈል ህይወት፣
ስለ ህዝብ ፍቅር ኖሮ መሞት፡፡
ከተጋፈጥከው ተራራ
ካቋረጥከው ቆንጥር ጀርባ፣
አዲስ ፀሃይ እኛ አይተናልተ
በመስዋእትነትህ ታጅባ፡፡
በአንተ ነው አንተ ያገሬ ልጅ
ባንተ ነው ጨለማው የነጋ፣
ሃገርና ህዝብን አስቀድመህ
በከፈልክልን ውድ ዋጋ፡፡
ሃገር እስከ ጥግ ተጠራርቶ
አንዱ ለሌላው መልካም ሲመኝ፣
ስለ ሃገሩ ወጥቶ አዳሪው
አንተን ቢረሱህ አመመኝ፡፡
አድምጠኝ ጀግናዬ ጓዴ....
አንተ ባለህበት በረሃ
ባይኖርም እርጥብ ቄጠማ፣
ክትፎውን ከቁርጥ ባታማርጥ
ቀዝቃዛ ውሃን ብትጠማ፣
ወታደር ባንተ ልፋት ነው
መድመቁ በአል አውደ አመት፣
ለጥቁር አፈርህ ክብር
አፈር መስለህ የደከምክበት፡፡
እየሞትክ የምታቆማት ሃገር
ዛሬ ዘመኗን ስትቀይር፣
እንኳን አደረሰህ ልልህ ወደድኩ
ክብር ምስጋና ላንተ ይሁን
ለራስህ ያልኖርከው ወታደር፡፡
🔘ሻለቃ ወይንሐረግ በቀለ🔘
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....ጎንቻ ቦሩ የዘረፋቸውን ከብቶች በርካሽ ዋጋ ከቸበቸባቸው በኋላ ጫካ ገባ፡፡ የሟቹ ወንድሞች ከየአገሩ ተሰባስበው መምጣታቸውንና ገዳዩን ገድለው ለመበቀል ከፍተኛ እልህና ቁጭት ሲተናነቃቸው መክረሙን የሚገልፅ መልዕክትም ደረሰው፡፡ መልዕክቱን የላከችለት ዓለሚቱ ነበረች።
ልቡ በየቀኑ ወደ ዓለሚቱ ይበርራል። ይከንፋል። ጠረኗ፣ሰውነቷ ሁለመናዋ በዐይኑ ላይ ይንከራተትበታል፡፡ ዐይኖቹን ጨፍኖ ጨክኖ ሄዶ እንዳይጎበኛት ደግሞ አደጋ ውስጥ እወድቃለሁ ብሎ ይፈራል። ጎንቻ ላውንብድና ስራው የሚያገለግለው አንድ አጭር ምንሽር ከገዛ በኋላ በጫካ
ውስጥ እንደ አውሬ እየኖረ ለሊት ለሊት ብቻ ሊጎበኛት ወስኗል።
ጎንቻ የጫካውን ኑሮ እየተለማመደው፣ አውሬነት እየተዋሀደው ሄደና ከተራ ሌብነት ወደ ሽፍታነት አመራ። ፀጉሩን ገመደና ሹሩባ አሰራው።ሁለት ጀሌዎችንም ማስከተል ቻለ። በሱ አዛዥነት የሚመራ የወንበዴ ቡድን አቋቁሞ ዘረፋውን በሰፊው ተያያዘው።
ጎንቻና ዓለሚቱ ከተገናኙ በጣም ረጅም ጊዜ ቢሆናቸውም ለአንድም ቀን ከሀሳቡ ወጥታ አታውቅም ነበር ናፍቆቷ ዐይኑን ሊያወጣው ደርሷል። በልቡ አንድ ቀን በለሊት ሂዶ ይዟት ጫካ እንደሚገባ ጥርጣሬ አልነበረውም፡፡ ዓለሚቱን ይዞ የሚጠፋው ግን ያንን ለብዙ ጊዜ የበቀል
ካራ ሲስልለት የሰነበተውን የቶላን ጉዳይ አንድ መላ ካበጀለት በኋላ እንጂ ከዚያ በፊት እንደማይሆን ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ በሱ ዘንድ ቶላ ፍፁም ምህረት ሊደረግለት የማይገባው ጥፋተኛ ሆኖ ነው የተገኘው። ልቡ ቂም አርግዟል፡፡ ጭንቅላቱ በቁጭትና በቂም ተበክሏል፡፡ ገበየሁን ከገደለ በኋላ ወንበዴነቱ ለይቶለት ልበ ደንዳና ሆኗልና በል በል ! ሂድ ግፋበት እያለው ነው፡ርህራሄ የሚባል ነገር ከውስጡ እየሟሽሽ ሄዶ የሌላ ሰው
ደም ለማፍሰስ እያቅበጠበጠው ነው፡፡ የመጀመሪያውን ፅዋ ገበየሁ ጨለጠበት እንጂ እሱ ያዘጋጀው ለቶላ ነበር። ሁልጊዜም በሀሳቡ በዚያ በገበያው መሀል በህዝብ ፊት እየወደቀ እየተነሳ የሮጠው አሯሯጥ፣ የቶላን ጩኸት ሲስማ የደነገጠው ድንጋጤ፣ እነኝያ የጎመጀባቸውን ከብቶች ሳይቸበችባቸው መቅረቱ የፈጠረበት ቁጭት ይሄ ሁሉ አሳፋሪ ትዝታ ፊቱ ላይም ድቅን እያለበት በአስቸኳይ ቶላን ተበቅሎ ያንን ውርደቱን ለማካካስ ስሜቱ ሂድ! ሂድ! እያለ ይገፋፋው ነበር፡፡ በዚሁ ዕቅዱ መሰረት ጀሌዎቹ ጊርቦ ዋዶን እና ቱሲ ቤንኪን አስከትሎ ለመሄድ ተዘጋጀ።
“ጎበዝ! ዛሬ የምንጎበኘው ሰው ደመኛ ጠላቴ ነው! ማንኛውንም ነገር
በአጭር ጊዜ ውስጥ አቀላጥፈን በቶሎ መመለስ ይኖርብናል! ጥንቃቄ
እንዳይጎድላችሁ!” ቆፍጠን ያለ ትዕዛዝ ሰጣቸው፡፡ ጀሌዎቹ በተጠንቀቅ ቆሙና በአለቃቸው ጠላት ላይ ጥቃት ሰንዝረው ንብረቱን ለመዝረፍ በመታደላቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገለፁለት፡፡ ትእዛዙን በሙሉ ልባቸው ተቀብለው ለመፈፀም ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋገጡለት፡፡ በዕቅዳቸው መሰረት ሲዘጋጁ አደሩና በለሊት ጉዞ ጀመሩ፡፡ ጫካ ለጫካ እየተሹለከለኩ፣ የገደሉትን አውሬ ስጋ እየበሉ ወደ ትውልድ መንደሩ ወደ ወላጆቹ ጎረቤት ወደ ቶላ ሠፈር መገስገሳቸውን ቀጠሉ...
በድቅድቅ ጨለማ እየወደቁና እየተነሱ ሲሮጡ ለተመለከተታቸው ወገንን
ከጥፋት ለመታደግ እንጂ የአንድ ሰላማዊ ገበሬን ህይወትን ለመቅጠፍ
ያስፈሰፉ ወንጀለኞች አይመስሉም ነበር፡፡ እርኩስ ዓላማቸውን ለማሳካት እንቅልፋቸውን አጥተው በጨለማ ሲጓዙ ካደሩ በኋላ ወደ መንደሪቱ ተጠጉ፡፡ ቶላና ቤተሰቦቹ ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዷቸዋል። ጀሌዎቹ አለቃቸው የሚሰጣቸውን የቃልና የምልክት ትዕዛዝ ተግባራዊ ለማድረግ በተጠንቀቅ ቆሙ:: ውሾቹ ትንሽ “ዋይ! ዋይ” በማለት ሊያስቸግሩ ሞከሩ፡፡ ጎንቻ ቀደም ብሎ የተዘጋጀበት ጉዳይ ነበረና በኪሱ ውስጥ ይዞት የነበረውን ትኩስ የአውሬ ሥጋ አውጥቶ ወረወረላቸው፡፡ በዚህ ላይ የጀሌዎቹን እንጂ አንዳንዶቹ ውሾች ጠረኑን ስለሚያውቁት በጥቂት ጊዜ
ውስጥ ሰላም ሰፈነ። ቀሪው ተግባር የጎንቻን ፈጣን ርምጃ የሚጠብቅ
ነበር።
ቶላ ከባለቤቱና ከአንዲት ሴት ልጁ ጋር በሞቀች የሳር ጎጆው ውስጥ
አገር ሰላም ነው ብለው ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዷቸዋል። ሀሳባቸውን ጣል አድርገው ስፊውን የእንቅልፍ ዓለም በሚጎበኙበት ምሽት፣ በጣፋጭ እንቅልፍ ውስጥ ሆነው በስራ የደከመ ጎናቸውን ባሳረፉበት በዚያ ውድቅት ለሊት ይህ ነው በማይባል ኃይል የተበረገደችው የእንጨት በር ተስፈንጥራ ከመሀል ምሰሶው ጋር ተላጋች፡፡ በዚያው ቅፅበት
ጎንቻ እንደ ፀሀይ የሚያበራ ጩቤውን በቶላ አንገት ላይ ደቀነበት፡፡ ከእንቅልፉ እንደዚያ በድንገት ለባነነ ሰው የጎንቻ ሁኔታ እጅግ የሚያስፈራ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበር፡፡ የተጎነጎነ ጎፈሬውን ቁልቁል አንዠርጎ፣ ምንሽሩን በትከሻው ላይ አጋድሞ፣ በወገቡ ዙሪያ ዝናር ታጥቆ ሰይፍ የሚያክል ረዥም ጩቤውን አገልድሞ ሲታይ“እባክህ አምላኬ በኪነ ጥበብህ ህይወቴን እንዲጠብቅ የተላከ መልአክ አድርግልኝ” የሚያሰኝ ነበር፡፡
ጎንቻ ግን በመልአከ ሚካኤል ተመስሎ የቶላን ህይወት ከክፉ ሊታደጋት የመጣ የነፍሱ ጠባቂ ሳይሆን ጉሮሮውን ለመበጠስ የመጣ አረመኔ ነበር፡፡እናትና ልጅ አፋቸው ታፍኖ ከአልጋው እግር ጋር እንዲታሰሩ ትዕዛዝ ሰጠ። ትእዛዙን ሲፈፅሙ ተናግሮ አልጨረሰም ነበር፡፡ እጅግ ፈጣኖች ናቸው። እሱ ደግሞ ቶላን ርቃነ ሥጋውን አስነስቶ ከጎጆዋ መሃል ከቆመው ምሰሶ ጋር በመጫኛ ተበተበውና በአፉ ውስጥ ጨርቅ
ጎስጎሰበት። ቤቱ በሶስት ወሮበሎች እየተበረበረ ምስቅልቅሉ ይወጣ
- ጀመር፡፡ በፍተሻው መሰረት አንድ መለስተኛ ገንቦ ቅቤ፣ በጮጮ የተሞላ
ነጭ ወለላ ማር ተገኘ፡፡ ከዚህ ሁሉ የበለጠ ቶላን ያስደስተው ሳጥኑ
ነበር፡፡ በሣጥኑ ውስጥ የተገኘው ጥሬ ብር ሲቆጥረው አራት መቶ ሃያ
ሆነ፡ ልዩ ልዩ ከመዳብ የተሰሩ ጌጣጌጦች በዚህ ላይ ደግሞ አንድ አሮጊ ፊሊፕስ ሬዲዮም ተገኘ፡፡ ከቶላ ይህንን ሁሉ ቁምነገር ያልጠበቀው ጎንቻ
በጣም ተደሰተ፡በአጠቃላይ በቤቱ ውስጥ በጥሪትነት የተገኘው ነገር ሁሉ
ተበዘበዘና አንዱ ተሸካሚ ሌላው አሸካሚ ሆኑ። ምንም ነገር ያልተረፈ መሆኑን ሲያረጋግጡ ጎንቻ ከቤት ውስጥ እንዳለ ጊርቦ አካባቢውን ለመሰለል ወጣ ገባ አለ፡፡ ፀጥ እረጭ... ያለ ነበር። ጊርቦ መለስ ብሎ ወደ ጎንቻ ጆሮ ተጠጋና “እንሂዳ ጌታዬ ከእንግዲህ ምን እንጠብቃለን? የምታደርገውን አድርግና ፈጠን ብለን እንውጣ፡፡ እንዳይነጋብን” አለው፡፡
ጎንቻ ከቶላ የዘረፈው ንብረት ያልጠበቀው በመሆኑ ደስተኛ ቢሆንም በእልህና በቁጭት ትኩር ብሎ ተመለከተውና ፊቱ ላይ ተፋበት፡፡
ቶላ እንዳይጮህ፣ እንዳይናገር፣ እንዳይሳደብና በአጠቃላይ ምሬቱን
ተንፍሶ እንዳይወጣለት አፉ ተወትፏል። በሚያየው ድርጊት አእምሮውን
እስከሚስት ድረስ ውስጡ በግኖና ፊቱ ጥላሸት መስሎ ዐይኖቹ እንደፈጠጡ ቁና ቁና ይተነፍሳል። በደፈረሱት ዐይኖቹ ጎንቻን በጥልቀት አስተዋለው፡፡ ያሳደገው ውርጋጥ በሱና በቤተሰቡ ላይ ስብዕናቸውን የሚያዋርድ አፀያፊ ተግባር ፈፅሞባቸው ሲሄድ ከማየት ይልቅ ሞቱን መረጠ፡፡በቤቱ ውስጥ ያንን የመሰለ ወራዳ ድርጊት ከፈፀመ በኋላ ደግሞ እነዚያን ባለፈው ጊዜ አተረፍኳቸው ብሎ በደስታ የሰከረባቸው ከብቶቹን ነድቶ
መሄዱ የማይቀር ነው። ተቃጠለ። ጢስ የማይወጣው እሳት በላዩ ላይ ነደደበት፡፡ ነፍስ አንድ ጊዜ ብትወጣ ምን ነበረበት? ግልግል ነበር። ጎንቻ ግን በሚያደርጋቸው ድርጊቶች ሁሉ ቶላን ቀስ በቀስ እየገደለው ነበር።ከሞት ሁሉ ሞት በባለቤቱ እና በትንሽ ልጁ ፊት ራቁቱን ከምሰሶ ጋር አስሮ ምራቁን ሲተፋበት፣

👍3
ሲሰድበው፣ ንብረቱ ሲታመስ፣ ሲሰበር፣ ሊቦረበር፣ ባለፈው ጊዜ አተረፍኳቸው ብሎ ያለቀሰላቸው እንደ ልጆቹ የሚሳሳላቸው ከብቶቹ በተለይ እያጎረሰ ያሳደጋቸው በሬዎቹ ተነድተው
ሲታረዱ፣ የቤተሰቡ ጉሮሮ ሲዘጋ፣ ባዶ እጁን ሲቀር ይሄ ሁሉ እየታየው አረረ።
ጎንቻ የመጀመሪያ ፍላጎቱ መግደል ነበር፡፡ አሁን ግን ከቶላ ያልተጠበቀና እዚህ ቀረሽ የማይባል ገንዘብ አፈሰ፡፡ ብሩን በሳጥን ውስጥ አዘጋጅቶ ጠበቀው፡፡ ያገኘው ገንዘብ በደስታ አቁነጠነጠው፡፡ ከዚያ በላይ ቶላ ሊክደው አይችልም፡፡ ነፍሱን ሊምርለት ፈለገ፡፡ “የሱ ነፍስ ምን ያመጣ
ልኛል?” የሚል ስሜት ተሰማው። ሁለቱ ጀሌዎቹ ወጥተዋል።ቱሲ የተዘረፈውን ዕቃ ተሸክሟል።ጊርቦ ፈጠን አለና የከብቶቹን በረት ከፈተ።
ወዲያውኑ ወደ ጎንቻ መለስ ብሎ መጣና ከብቶቹን ከበረት ማስወጣታቸውንና በፍጥነት አካባቢውን ለቀው መሄድ እንዳለባቸው አሳስበው።
ጎንቻ ያንን የህፃን ልጅ ጭንቅላት የሚያክል የእጅ ባትሪ በቶላ ፊት ላይ
ቦግ! አደረገበትና በድጋሚ ትክ ብሎ ተመለከተው።“ግደል! አትግደል!”
የሚል ስሜት ተሟገተው። ዳሩ ጎንቻ ለዚህ ደረሰና ወንድ ተባለና ቤቱን
ሊሰረስር ሊያዋርደው መጣ እንጂ እሱም ቢሆን ጎንቻን በልጅነቱ እንደ አባት ያፈቅረው፣ ይወደው ነበር። በተለይ ወንድ ልጅ ስለሌለው ጎንቻን እንደ ልጁ ነበር የሚያየው። ቶላ የአባቱ የሐጂ ቦሩ የቅርብ ጓደኛቸው ነው። ከቶላ ቤት ገብቶ ወተት ሳይቀምስ፣ ማር ሳይልስ ሄዶ አያውቅም ነበር፡፡ ጎንቻ ግን የበላበትን እጅ ነካሽ ሆነና ያንን ሁሉ ውለታውን በመ
ርሳት በሌሊት መጥቶ እንደዚህ ያለውን አፀያፊ ውንብድና ፈፀመበት።
ቶላ አፉ ተለጉሞ አንጀቱ ተቃጥሎ እየተሰቃየ መናገር እየፈለገ ታፍኖ
በእልህ እየጋየ በንዴት ደም ከጎረሱት ዐይኖቹ ውስጥ እሳት ወጥቶ
ጎንቻን ቢያቃጥለውና ዐይኖቹ ለዘለዓለም ቢጠፉ ምንኛ በረካ? ያልተያዙት ያልታሰሩት ዐይኖቹ ብቻ ነበሩ፡፡ ጎንቻ ያንን የእጅ ባትሪውን ቦግ!ድርግም፣ ቦግ! ድርምግ አደረገው፡፡ ጣራ ግድግዳውን በባትሪ ተመለከተው።ፈተሽው፡፡ ምንም የቀረው ነገር የለም፡፡ ጀሌዎቹ ቀደም ብለው መሄዳቸውን ነግረውታል፡፡ ጣጣውን ሁሉ ስለጨረሰ ለመውጣት ተዘጋጀ።
“እወቅ! ወንዱ ጎንቻ መሆኔን፣ ጥቃት ደርሶብኝ በሽንፈት እጄን የማልሰጥና አርፌ የማልተኛ መሆኔን ለማያውቀው አሳውቅ! እንትፍ!” አለበትና ለመውጣት ወደ በሩ አመራ፡፡ ነገር ግን ቶላ አንድ ምልክት እየስጠው መሆኑን አወቀ፡፡ መለስ አለና አየው። እየጠራው ነበር። ገረመውና ቀስ ብሎ ተጠጋው። ጨርቁን ከአፉ ውስጥ እንዲያወጣለት ምልክት
ሰጠው።
አንድ የሚናገረው ቁም ነገር ሊኖር እንደሚችል ገመትና አደርገዋለሁ ብሎ ተማመነና የሚናገረውን ለመስማት ብቻ ቀስ ብሎ መስማት ፈለገ፡፡ ደግሞ ይጮኸል ብሎ ፈራ። ለመጮህ ቢሞክር ሲጥ አደርገዋለሁ ብሎ ተማመነና የሚናገረውን ለመስማት ጨርቁን ከአፉ ውስጥ አወጣለት።በእልህ የተቃጠለው ቶላ አፉ ሲፈታለት ሰውነቱ በንዴት ይንቀጠቀጥ፣ ይንዘፈዘፍ ጀመር። እናትና ልጅ እንዲያዝንለት ዐይኖቻቸውን በጎንቻ ላይ አቁለጨለጨ።
“ጎንቻ! ቂጥህን ጠርጌ አሳድጌህ አንተም ሰው ሆንክና ለዚህ አበቃኸኝ?!” አለው በሚርበተበት ድምፅ፡፡ ጎንቻ ብልጭ! አለበት። “አንተም ሰው ሆንክና?” የሚለው የንቀት አነጋገር የንዴት ክብሪቱን በላዩ ላይ ጫረበት። መታገስ አቃተው፡፡ ከመቅፅበት እጁ በወገቡ ላይ ከዚያም
ከቶላ አንገት ጋር ተዋህዶ ጭንቅላቱ እያሽካካ ከበሩ ላይ ሲወድቅ የነበ
ረው ፍጥነት እግዚኦ! የሚያሰኝ ነበር፡፡ ይህንን ትዕይንት ለሚያዩ እናትና ልጅ ጥናቱን ይስጣቸው እንጂ ጎንቻ ዶሮ ያረደ እንኳ አልመሰለውም፡፡
አወራረደውና እንጣጥ እንጣጥ….እያለ የወደቀውን አንገት ተራምዶት
ሄደ .......