አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዝቅ_ያለ

ወዳጄ በማቀርቀሩ
አፍሮ ነው ብለው ተሳለቁ፣
በፍሬ የተሞላው ዛፍ
አንገት መድፋቱን ሳያውቁ፡፡
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....“እኔ ደግሞ ያለዚች ጠላ ደስ አይለኝም። እንዴት ይጣፍጣል መሰለህ?
ቆይ ላንተም ልጨምርልህ” ነጭ አረቄ ጨመረችበት። ጌትነት የሰማው ሻይ ኮረንቲ ሲባል ነበር፡፡ ጠላ ኮረንቲ ዛሬ ገና በዐይኑ ተመለከተ፡፡ ያንን ከውስጡ ጥርግርግ ብሎ ያልወጣለት ፍርሃቱን ጠራርጎ እንዲያስወጣለት የደረበችለት የፍርሃት ማስወገጃ ብርድ ልብስ መሆኑ ነው፡፡ ምንም እንኳ በሞቅታ ምክንያት የማመዛዘን ሃይሉ እየተዳከመ ቢመጣም ራሱን ሙሉ ለሙሉ አልሳተም ነበር፡፡ ሙሉ ለሙሉ በሷ ትዕዛዝና ቁጥጥር ስር ሊውል ትንሽ እንደቀረው ያወቀችው ሸዋዬ ተጨማሪ ነዳጅ ሰጠችው...

“ይሄንን ፈሪ ሰው ከዚህ በላይ ምን ላድርገው? ፍላጐቴን ከዚህ በላይ
በምን ልግለፅለት? እንግዲህ አንቄ አልይዘው?” በሀሳቧ ከራሷ ጋር ስትሟገት ከቆየች በኋላ የዚህን የፈሪ ሰው ዐይነ ጥላውን ለመግፈፍ ስሜቱን የበለጠ ለመቀስቀስ ጨዋታ ጀመረች፡፡

“መቼም የኛ የሴቶች ነገር ግርም! ይለኛል፡፡መጨረሻችን መውደቂያችን አይታወቅም፡፡ አሁን እኔ ስንቱ ወንድ እንደዚያ ሲንጋጋብኝ ስንቱ በገንዘብ ሲረባረብብኝ ስንቱ እርስ በርሱ ሲጣላ ሲጋደልብኝ አንድ ቀን እንኳ ወንድ መስሎ ታይቶኝ ከማያውቀው፣ ዐይኔ አርፎበት፣ ልቤ ደንግጦለት ከማያውቀው ከቶሎሳ እጅ ላይ ወስዶ ሲጥለኝ ለራሴ ድ.ን.ቅ
ይለኛል፡፡ እውነቴን ነው የምልህ ጌትነት! እንድ ቀን እንኳ ሰው መስሎ ታይቶኝ አያውቅም ነበር፡፡ ወንዶቹ ሁሉ እኔ ከሴቶቹ የተለየ ነገር ያለኝ ይመስል አንድ ጊዜ ከቀመሱኝ በኋላ ማበድ ነው! ካላገባንሽ ትንቅንቅ ነው! ቶሎሳም አንዴ ቀመሰኝና እብድ አለ!! ወቸ ጉድ! ታዲያ ያ ሁሉ ሰው ያ ሁሉ ሃብታም ያ ሁሉ መልከ መልካም ሲረባረብብኝ አሻፈረኝ ስል የኖርኩት ሴትዮ ምናምኑን አስነካኝ መሰለኝ ሌላው ወንድ ሁሉ አስጠልቶኝ ቶሎሳን! ደሃው ቶሎሳን! ወድጄ ቁጭ! ከዚያም በዐይኑ ያየኝን ትንሽ ያሳሳቀኝን ሁሉ ካልገደልኩ እያለ መተናነቅ ሲያበዛ በኔ ምክንያት ሰው ገድሎ አጉል እንዳይሆንና እኔንም አጉል እንዳያደርገኝ ፈራሁና ተጠቃልዬ ቁጭ! ግን ምን ዋጋ አለው? በጣም ቀናተኛ ነው። ያ ቅናቱ
ዛሬም ድረስ አልለቀቀውም” ያንን እሷ ከሴቶቹ ሁሉ ለየት ብላ የምትጣ
ፍጥበትን ሚስጥር ለማወቅና ለመቅመስ ጌትነት ጉጉት እንዲያድርበት
ተፈታተነችው፡፡

“እዚሁ ከቤቱ ተጠቃልዬ ቁጭ ባልኩበት እንኳን አያምነኝም፡፡ ስንት ጊዜ
መስለህ እንደዚህ የሚያደርገኝ? አሁን በቀደም እለት እንኳ ድሮ የማውቀውን ሰው መንገድ ላይ አግኝቼ ሰላም ብለው እብድ ሆኖ ያደረገኝን ባሳይህ ትስቃለህ”
“ምን...አደረገ...?” አላት በፈገግታ የተጥለቀለቀውን የሸዋዬን ገፅታ ፍዝዝ፣ ቡዝዝ ባሉት ዐይኖቹ እያየ። ስሜቱ በመጠኑ መለዋወጥ መረበሽ
ጀመረ። ያንን ወንዱ ሁሉ የሚያብድበትን ነገር ልታሳየው፣ ቶሎሳ ቅናቱ እንትኑ ጫፍ ላይ ሲደርስበት ሁል ጊዜ ምን እንደሚያደርጋት ልታሳየው፣ ያንን እንደ ህፃን ልጅ ገላ የተከፋፈለ ቅርጽ ያለውን እንደ መስታወት የሚያበራ ለስላሳ ጭኗን ልታሳየው ቀሚሷን ወደ ላይ ግልብ!..አደረገችው በዚህ ጊዜ የጌትነም ልብ አብሮ ተገለበ...የማመዛዘን ሃይሉ
ከቀሚሷ ጋር አብሮ ተገለበ...ያንን እንደተወለወለ መስታወት የሚያበራ
ጭኗን ድንገት ገልባ ስታሳየው በፍፁም ከዚያ በፊት አስቦትም አልሞትም የማያውቀው በጭኖቿ መካከል የመገኘት ፍላጎቱ ተቀሰቀሰና ወንድነቱ ዘራፍ!! እያለ ውስጥ ለውስጥ ይሯሯጥበት ጀመረ፡፡
“ይገርምሃል የኔ ሰውነት ደግሞ በጣም መጥፎ ነው። ትንሽ ነገር አይችልም፡፡ ጠቁሮ ቀረ! የውልህ!” ያንን የተቆነጠጠችበትን ቦታ በደንብ
አድርጋ ልታሳየው እንትኗ ሊታይ ትንሽ እስከሚቀረው ድረስ ቀሚሷን ከፍ አድርጋ ወደላይ ገለበችለት። ከዚያም የተቀመጠችበትን ኩርሲ ሞልተው ግራና ቀኝ የተከመሩ ጭኖቿን በመጠኑ ፈልቀቅ አደረገችና አሳየችው። እውነቱን ለመናገር ለጌትነት የታየው ምንም የጠቆረ ነገር
አልነበረም፡፡ እንኳንስ የሰከረው ልጅ ይቅርና ጠንቋይ ካልሆነ በስተቀር
ማንም ሰው ቢሆን ያንን የጠቆረ ቦታ ፈልጎ ለማግኘት አጉሊ መነፅር
የግድ ይለው ነበር፡፡ በዚያ ዘዴዋ ሽዋዬ ዓላማዋን አሳካች። የወንድነት
ስሜቱን በጭኖቿ መካከል አስገብታ ለመጭመቅ ቻለች። ያንን ውብ ሰውነቷን ሲመለከት እንደ እቶን የሚንቀለቀል የወሲብ እሳት አነደደው...ሸዋዬ ሁኔታውን በሚገባ እያጤነችው ነበር። እቅዷ ሊሳካ ጥቂት ብቻ እንደቀራት ተገነዘበች፡፡ ለሀጩ መንጠባጠብ ጀምሮ ነበር፡፡ ደስ አላት።

ሽዋዬ ማህፀኗ ዘር አላበቀለም፡፡ ቶሎሳ እሷ የምትሰጠው የፍቅር ሙቀት
የልጅ ፀጋ ታክሎበት ቢሆን ኖሮ ምንኛ ደስተኛ ይሆን እንደነበረ ዘወትር
ይወተውታል፡፡ከሸዋዬ ልጅ እንዲሰጠው ፈጣሪውን ይማፀናል። ሸዋዬ ግን ልጅ ባለመውለዷ አንድም ቀን ተቆጭታ አታውቅም፡፡ እንደ ጥሩ ሰንጋ ፈረስ ወገቧ ወደ ውስጥ ተለጥጦ መቀመጫና ዳሌዋ በህብረት እየደነሱ በኩራት እንዲያነጠንጡ ዕድል የፈጠረላት መሆኑን፣ያ ወንዱ ሁሉ አፉን ከፍቶ የሚቀርበትን ቅርፅ ይዛ ለመቆየት የቻለችው ልጅ ባለመውለዷ ምክንያት መሆኑን ስለምታምንበት ዳሌዋን በመዳፏ መታ መታ ሽንጧን ወዝወዝ.. ነቅነቅ.…እያደረገች “ልጅና ችግር ገደል ይግቡ! እነሱ ቢኖሩ ኖሮ ይሄንን የመሰለ ሀብት መቼ እናፈራ ነበር?” በማለት በሰውነቷ ቅርፅ ትኩራራለች።

ጌትነት እነዚያ የተጋጠሙ ወፍራም ጭኖችዋ ራቁታቸውን ሆነው ሲመለከታቸው የሚሆነውን አሳጣው! የሽዋዬ ጡቶች የበለጠ ትልቅ እየሆኑ
ሽንጧ የበለጠ እየቀጠነ ዳሌዋ የበለጠ እየሰፋ የሄደ መስሎ ታየው፡፡የስሜቱ መንጠራራት በእጆቹ መወራጨትን አስከተለ፡ ዐይኖቹ እንደፈዘዙ ናቸው።ወደ ሸዋዬ ጉያ ስር ውሽቅ አለና ከብርድ አስጥሉኝ የሚል ህፃን ልጅ መሰለ፡፡ እንደ ማግኔት እየሳበችው መሆኑን ያወቀችው ሸዋዬም እቅፍ አደረገችው። ከዚያም ያላዘዛቸው ጣቶቹ በራሳቸው ሥልጣን ሄዱና ከሸዋዬ ጭኖች መካከል አረፉ። ጭኖቿን ከፈት...አደረገችለት፡፡ሙቀቷ የሰራ አከላቱን አዳረሰው... ጊዜው እየመሽ በመሄድ ላይ ነው። ከምሽቱ አራት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ ሆኗል። ሽዋዬ ከእንግዲህ በኋላ ጊዜ ማጥፋት አስፈላጊ ሆኖ አልታያትም። ስሜቱን ገል
ፆላታል። ጣቶቹ በጭኖቿ መካከል አርፈው እየደባበሷት ናቸው። ወደ
አልጋ ልትወስደው ፈለገች።

የሁለት ወር ምኞቷን ለማሳካት ለሁለት ሙሉ ወራት የተዳፈነው እሳት እንዲነድ፣ እንዲንቦለቦል ፣እንዲንቦገቦግ በፍጥነት ማርገብገብ እንጂ ምን ጊዜ ማጥፋት ያስፈልጋታል?...
“ጌቱ ሰዓቱ መሽቷል። ተነስ! አልጋህ ላይ ጋደም ብለን እንጫወት” አንገቱን አቀፈችው፡፡ ጌትነት እሱ ሳይሆን እሷ የምታዝበት ገላውን ከወንበሩ ለማስነሳት ሞከረ። ኣልቻለም፡፡ እጁን ሳብ አደረገችና ወገቡን በግራ እጇ እቅፍ አድርጋ አስነሳችው። ለመቆም ሞከረ፡፡ አብዛኛው ሚዛኑ በሷ ላይ ወደቀ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ሽዋዬ አዘለችው እንጂ ደገፈችው ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነበር፡፡ በራቁት ክንዶቿ ወገቡን እቅፍ አድርጋ ካስነሳችው በኋላ ወስዳ አልጋው ላይ አንጋለለችው....ጌትነት በህልም ዓለም
ውስጥ ያለ መስለው፡፡ የማስታወስና የማመዛዘን ሃይሉን የታገለው ወንድነቱ በይሉኝታው ላይ አሽናፊነቱን አረጋግጦ እያቅራራ በአልጋው ላይ እንደተንጋለለ ሽዋዬን ሽቅብ ይመለከታት ጀመር፡፡

ሸዋዬ ደጋግማ በጠጣችው ጠላና በተለይ ደግሞ በጠላው ውስጥ በጨመረችው አረቄ ምክንያት ከበቂ በላይ ሙቀት አግኝታ ነበረና በተንጋለ
ለበት በፍቅር ትደባብለው፣ታሻሽው ጀመር፡፡ ቀስ በቀስ ጎንበስ አለች።
ጌትነት በፀጥታ ሆኖ ማንኛውንም
👍3
እንቅስቃሴዋን በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ
ሆኖ ጠበቃት። ወረድ አለች ወጥመድ የያዛት አይጥ መስሏል። ዐይኖቹ
ፈጠዋል፡፡ ነፍሱ በሰማይ ቤት ለፍርድ ቀርባ ከሲኦል ሊታደጋት ፈጣሪውን የሚማፀን መሰለው። ቀስ ብላ ወረደችና ጉንጬን ሳመችው። ጉንጩን ሰጣት። ከዚያም ወደ ከንፈሩ ተጠጋችና ደገመችው።አፉን በሰፊው ከፍቶ ከንፈሮቿን ጠቅልሎ መጉረሱ አልታወቀውም ነበር።

በዚያው ቅፅበት የሸዋዬ ጫማዎቿና የውስጥ ልብሷ ወልቀው ወደ መሬት ተሽቀነጠሩና በውስጥ ሱሪዋ ብቻ ቀረች። እሱም እንደ እባብ እጆቹን በወገቧ ዙሪያ ጠመጠማቸው። ከዚያም ቁና ቁና እየተነፈሱ ከን ፈሮቻቸው እስከሚያብጡ ድረስ ተሳሳሙ፡፡ ሸዋዬ አልቻለችም። እላይዋ ላይ የቀረውን ቀይ የውስጥ ሱሪዋን በፍጥነት አወለቀችና ወደ መሬት
ወረወረችው፡፡ጌትነት ራሱን መርዳት አልቻለም፡፡ ሱሪውን መፍታት አቃተው። ሸዋዬ ራቁቷን ሆና ሱሪውን ቶሎ ልታወልቅለት ከዚፑ ጋር ትግል ተያያዘች።
በከፍተኛ የወሲብ ስሜት እየነደደችና በሰውነቱ ላይ እየተንከባለለች ተወራጨች። በሷ ስሜት ልክ እንደ እሳት የነደደውን የጌትነት ገላ እያሸች የስሜቱን ምላጭ ቃታውን በመሳብ ልታፈነዳው ተጣደፈች።ከሁለት ወራት በላይ ስትመኝ፣ ስትጓጓለት፣ ስትቃዥበት የከረመ ገላውን በቁጥጥሯ ስር አድርጋ የልቧን ልታደርስ እንደ አውራ ዶሮ እላዩ ላይ ተከምራ ስታ
ረገርግ ዛር የፈለቀባት ትመስል ነበር።

ጌትነት ግን ወፍራም ሰውነቷ
ከብዶት አየር እያጠረው መሄድ ጀምሮ ነበር፡፡ በተቃራኒው ቀስ በቀስ ራሱን እያረጋጋ ሌላ ዓለም ውስጥ በመግባት ከተጋተው አልኮል በስተጀርባ ያለው እውነተኛ ማንነቱን ፍለጋ እየተጓዘ ነበር። እላዩ ላይ ተከምራ በስሜት እየነደደች ከምትወራጪው ሴት በስተጀርባ ያለውን ታሪክና እውነታ ማስላሰሉን ቀጠለ። በሁለመናዋ አቅፋ ከምትንከባለልበት ሴት ውስጥ የሆነ ብዥ ብዥ የሚል የደበዘዘ ስው ስዕል በርቀት ይታየው
ጀመር፡፡ ያ ስዕል እየጎላ እየጎላ.. እየቀረበ መጣና ሙሉ ለሙሉ የሰው ቅርፅ ያዘ፡፡

ልክ ነው! ቶሎሳ!! አጠገባቸው ቆሞ ታየው። ጣቶቹ እንደ አሞራ ጥፍር
ሾለው በጉሮሮው ላይ ሊቀረቀሩበት ያሰፈሰፉ መስለው። ቀስ በቀስ ያ
ፈሪነቱ ሲመጣ ቀስ በቀስ ያ ጀግንነትን ደፋርነትንና ወኔን ያላበሰው የጠላ ሃይል ከላዩ ላይ እየበነነ እየተነነ ሲሄድ ተሰማው። ሰውነቱ ቀስ በቀስ መንቀጥቀጥ፣ቀስ በቀስ መርበትበት ጀመረ። አሁን በመፈፀም ላይ ያለው ድርጊት ምን ያክል አፀያፊና አስነዋሪ እንደሆነ ይስማው ጀመር፡፡ ህሊናው ቀስ በቀስ እንደ መርፌ ጠቅ! ጠቅ! ሲያደርገው ታወቀው።ብርድ ብርድ፣ ፍርሃት..ፍርሃት አለው፡፡ ከዚያም ከዚያ ጭንቀት ለመገላገል ያንን የሸዋዬን ግዙፍ ሰውነት እንደ ኳስ ወደ ላይ አጉኖ ሲያነሳውና ሸዋዬ መሬት ላይ በጀርባዋ ተገልብጣ! ከአልጋው ስር ስትወተፍ
ከሚያስጨንቀው ጭንቀቱ ከባላንጣው ከአእምሮው ጋራ ውስጥ ለውስጥ
የከፈተው ጦርነት ገሃድ ወጣ ላሸዋዬ እጅግ አስደንጋጭና ስሜቷን በሚ
ያሸማቅቅ ሁኔታ አሽቀንጥሮ ጣላት።

ሽዋዬ ፍፁም ባልጠበቀችው ሁኔታ
ከአልጋ ላይ ወርውሮ ሊጥላት በላይዋ ላይ ተለኩሶ እየተንቦለቦላ ሲያንዳት የቆየው የወሲብ እሳት በድንገት ድርግም ብሎ ጠፋ፡፡ ጌትነት ባላጋራውን ጥሎ የሻምላውን ጫፍ አንገቱ ላይ የወደቀ ተፋላሚ መስሉ ቁልቁል አስተዋላት፡ ሸዋዬ የእፍረትና የውርደት ማቅ ተከናንባ ከበረዶ በቀዘቀዘ ስሜት ውስጥ ተዘፍቃ፣ ደም በጐረሱ ዐይኖቿ ትኩር ብላ ተመ
ለከተችው፡፡
“ባለጌ !”አላት በተኮላተፈ አማርኛ።
“ባለጌ ውሻስ አንተ! ብራሪ የድሃ ልጅ! ሱሪ ለብሰህ ስትታይ ወንድ የምትመስል የወንድ አልጫ! ሴት የሴት ልጅ! ልክህን ባላሳይህ እኔ ሸዋዬ አይደለሁም!!” ከአንገቷ ቀና ብላ ሀክታ የተቀላቀለበት ምራቋን ፊቱ ላይ ለጠፈችበትና እዚህም እዚያም የተጣሉ ልብሶቿን ለቃቅማ እየተመናቀረች ወደ መኝታ ክፍሏ ገባች፡፡

ጌትነት ፊቱ ላይ የተፋችበት መሆኑን
እንኳ አላስተዋለም፡፡ ደንዝዟል። በመካከላቸው ምን እንደተፈጠረ ሙሉ
ለሙሉ መገንዘብ ባይችልም ከሸዋዬ ጋር መጣላታቸው ትንሽ በትንሹ ተሰምቶታል። ልብሱን ሳያወልቅ በዚያው ተጋደመ::
ከእንቅልፉ ሳይነቃ ቶሎሳ በጠዋቱ መጥቶ በሩን አንኳኳ። ሽዋዬ መርዟን
ስትቀምም ሴራዋን ስትጠነስስ በንዴት ስትንጨረጨር ስትቃጠል ነበር
ያደረችው፡፡ እሷ እንደዚያ እንቅልፍ በዐይኗ ሳይዞር ፍጥጥ ብላ አነጋች።
ጌትነት ግን እስከ አሁን ድረስ እንቅልፉን ይለጥጣል። ቶሎሳ ገና የቤቱን
በር እንደከፈተችለት የጠበቀው ሁኔታ አእምሮውን የሚበጠብጥ ነበር፡፡

“ስማ የኛ አባ ወራ! ተጨማሪ ባል ነው እንዴ ያመጣህልኝ?!” አንባረቀችበት። አመዱ ቡን አለ፡፡ ግራ ተጋባ፡፡
“የምን ባል ነው የምትይኝ ሽዋዬ?! ደግሞስ የምን ጩኽት ነው? ቀስ
ብለሽ መናገር አትችይም እንዴ? የምን በጠዋቱ ሰውን በነገር መልከፍ
ነው?”
“አረ! ጭራሽ የምን ጩኽት?! ደባል ያመጣህልኝ አረቄውን እየከለበስ እን
ዲያስታውክብኝ ነዋ?! ያገባንሽ ለሁለት ነው የምትል ከሆነ ቁርጡን ብቻ
ንገረኝ! ይህን ብቻ ከአፍህ ልስማውና ቁርጡን ልወቀው!!...”

“ማንን ነው የምትይኝ አንቺ ሴት?! ምንድነው የምትሂብኝ?! እባክሺን የምትናገሪውን አስበሽ ተናገሪ! ለራሴ እንቅልፍ አጥቼ ነው ያደርኩት። መናገር የምትፈልጊው ነገር ካለ ረጋ ብለሽ አስረጂኝ” ተወራጨ።

በጠዋቱ ሹልክ ብሎ የመጣው ትንሽ ለመተኛት ፈልጎ ነበር። ሽዋዬ እንደዚያ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ የጠበቀችው በጌትነት ላይ አፋጣኝ ርምጃ ለማስወሰድ ነበር፡፡ እሷ እንደዚያ ስታብድ ባሏ አብሯት ያለማበዱ አናደዳት። መረጋጋቱ አበሽቃት።

“አሀ! በል ተወው! ለቅሶ አለብኝ ብለህ ምክንያት ፈጥረህ ውጭ ያደርከው
ተራው ያንተ ነውና ስትጨፍርባት እደር ብለኽው ነዋ! ገባኝ.. ገባኝ!”
“ሴትዮ እባክሽ ጉረቤት እንዳይሰማ ጩኽትሽን ቀንሽው? እባክሽ ሰላም
ስጪኝ?” በሁኔታዋ መጨነቁን ወደ አልቃሽነት የሄደው ፊቱ እየመሰከረበት ለመናት፡ ሽዋዬ በንዴትና በቁጭት ያ ቀይ ፊቷ ጉበት እየመሰለ ሄደ።

“ኤዲያ! አትንተባተብብኝ ባክህ! ሄደህ ጉድህን ማየት ትችላለህ! እንቅልፌን አጥቼ እንደዚችው እንደፈጠረኝ ቁጭ ብዬ ነው ያደርኩት!” እጇን በጌትነት የመኝታ ክፍል ላይ ከቀሰረች በኋላ እንባዋን እንደ ጉድ እያፈሰስችና እየተመናቀረች ተመልሳ ወደ መኝታ ክፍሏ ገባች፡፡

ቶሎሳ ተደነባብሯል። በፍፁም ግራ ታጋብቷል። ፈራ ተባ እያለ ወደ ጌትነት የመኝታ ክፍል ገባ። ፊቱ በንዴትና በድንጋጤ ተለዋውጧል። በርግጥ ያልጠበቀው አዲስ ሁኔታ ተፈጥሯል። ጌትነት ልብሱን ሳያወ ልቅ አልጋ ላይ ተዘርሮ እንቅልፉን ይለጥጣል። ክፍሉ በመጠጥ ሽታ ታውዷል፡፡ ግራ ተጋባ፡፡ ወደ ሚስቱ ተመልሶ ሁኔታውን ለማጣራት
ፈልጉ አንድ ሁለት እርምጃ ተራመደና ቆመ:: ፈራት። ዘላ የምታንቀው መሰለው፡፡ ነገሮች ሁሉ ተምታቱበት። የሷ አነጋገር በፍፁም ከጌትነት ባህሪ ጋር የሚሄድ አልነበረም፡፡ አሁን ግን ጌትነት መጠጥ ጠጥቶ ልብሱን ሳያወልቅ አልጋው ላይ ተጋድሞ ሲመለከተው ተደናገጠ። ግራ
ተጋባ፡፡ በሌላ ነገር ባይሆንም ስክሮ አስቀይሟት ይሆናል ሲል ገመተ።
ፀባየ ሸጋ መሆኑ የተመሰከረለት ልጅ ሥራ ባለማግኘቱ ምክንያት ተበሳጭቶ መጠጥ ጠጥቶ በስካር መንፈስ ተናግሮ ያስቀየማት ስለመሰለው ከእንቅልፉ ቀስቅሶ ሊያስደነግጠው አልፈለገም፡፡ በሳሎኑ ውስጥ ወዲያና ወዲህ ሲንቆራጠጥ ከቆየ በኋላ እንደምንም ደፍሮ ወደ ሸዋዬ ሄደ።

የተቆጣ ነብር መስላ ሰውነቷ አብጦ ሊመለከታት ፈራት።
“ሽዉ ኮ! ማል ነጀላ ታቴ?” እንደ ሁል ጊዜው ሊለማመጣት “የኔ ሸዋዬ
ምን ሆንሽብኝ?” ሊል ጀመረ።
👍3
ከዚያም ጠጋ አላትና.“ግራ ገባኝ አኮ ሸዋዬ? እስቲ የተፈጠረውን ነገር በጥሞና አስረጅኝ?” እየተሽቆጠቆጠ ጠየቃት። ሸዋዬ ቱግ! ብላ ተነሳች።......

ይቀጥላል
አትሮኖስ pinned «#የተወጋ_ልብ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና ....“እኔ ደግሞ ያለዚች ጠላ ደስ አይለኝም። እንዴት ይጣፍጣል መሰለህ? ቆይ ላንተም ልጨምርልህ” ነጭ አረቄ ጨመረችበት። ጌትነት የሰማው ሻይ ኮረንቲ ሲባል ነበር፡፡ ጠላ ኮረንቲ ዛሬ ገና በዐይኑ ተመለከተ፡፡ ያንን ከውስጡ ጥርግርግ ብሎ ያልወጣለት ፍርሃቱን ጠራርጎ እንዲያስወጣለት የደረበችለት የፍርሃት ማስወገጃ ብርድ ልብስ መሆኑ…»
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


.....“ግራ ገባኝ አኮ ሸዋዬ? እስቲ የተፈጠረውን ነገር በጥሞና አስረጅኝ?” እየተሽቆጠቆጠ ጠየቃት። ሸዋዬ ቱግ! ብላ ተነሳች።

“ግራ ይግባህ!! የእናት የአባቴ አምላክ ግራ ያግባህ!! ድሮውንም ግራ
ነበርክ! አሁንም ግራ ነህ!” ብልጭ! አለበት፡፡ በቆመችበት በቃሪያ ጥፊ
ሲደረግምባት እንደ ብራቅ ጮኽችና አልጋዋ ላይ በጀርባዋ ፍንችር ብላ
ወደቀች። ከዚያም የመኝታ ክፍሉ በር እንደ ቦምብ ጮሆ የኮርኒሱን ቆሻሻ እስከሚያራግፈው ድረስ አላትሞ ዘጋባትና በቀጥታ ጌትነት ወደተኛበት ክፍል መጣ፡፡

“ኢልመ ሞክራ !” ጮኽበት፡፡ “የመኩሪያ ልጅ!!” በለበጣ አጠራር፡ ጌትነት
በስማው ጩኽት ተደናግጦ ብንን.. አለ፡፡ ጭንቅላቱ ላይ ከባድ ሸክም ያረፈበት መሰለው፡፡ የት እንዳለ የት እንደወደቀ የሚያውቀው ነገር አልነበረም።ጉርሽጥ የመሰሉ ዐይኖቹ እንደተቆጣ አንበሳ ቀልተው ካፈጠጡበት የቶሎሳ ዐይኖች ላይ ተተክለው ቀሩ።

“ቶሌ ኢቦ! ሌንጮ ኬኛ ሜ ዋን ተኤ ኦዴሲ?! ጂአ ለመ ኬሳ አመለኬ
ጶከቴ ባሉ ጀልቀብዴ? 'እሺ እባክህ የኛ አንበሳ? የተፈጠረውን ነገር አውራልን እስቲ! ገና በሁለት ወርህ ሽጋ አመልህን ታወጣው ጀመር?! የተደበቀ ቆንጆ አመልህን?” ባልገባው ቋንቋ አሽሟጠጠው፡፡ ጌትነት በድንጋጤ ተርበተበተ።

“እንዴ..ምን.አደርክ ጋሼ.ቶሎ ሳ?!ከተጋደመበት በፍጥነት ተነስቶ በአክብሮት ሊጨብጠው ተንደፋደፈ። አልቻለም፡፡ ያደረደበት ቶሎ እንዳይ
ነሳ ወደ ታች ጎትቶ ያዘው።
“ሲለኔ ሀዳር ማን ጠየቆ?! አሁን ሲለፈጠረው ታሪክ ቢቻ ቶሎ በሊና
ነጊር!” እየተንጎራደደ ትዕዛዝ ሰጠው፡፡ ጌትነት ስካሩ ሙሉ ለሙሉ አልለቀቀውም ነበር። የቶሎሳን ስሜት በሚገባ ማጤን አልቻለም። እንደዚያም ሆኖ ግን ሃይለ ቃሉ ያልተለመደ ሆነበት፡፡ ደነገጠ፡፡ መጠጥ ጠጥቶ ከነልብሱ ተኝቶ በመገኘቱ፣ ባሳየው አዲስ ያልተገባ ፀባይ ተናዶ የተቆጣው መስሎት በእፍረት ተሸማቀቀና ይቅርታ ሊጠይቀው ብድግ አለ፡፡ ሸዋዬ በቶሎሳ ጭንቅላት ውስጥ ያስቀመጠችው መርዝ መኖሩን የት አውቆት? ማታ ምን እንደሰራ ምን እንዳደረገ የሚያውቀው ነገር የለም።ጠዋት ውጤቱ በግልፅ የሚታየው ስካሩን እንጂ ከስካሩ ጋር ተያይዘው ከተፈ
ጠሩት አስደናቂ ትርኢቶች መካከል አንዷን እንኳ ማስታወስ አልቻለም፡፡
ሰክሮ መገኘቱ በራሱ ትልቅ ድፍረትና ሀጢአት ነውና ጋሼ ቶሎሳ ይቅር
እንዲለው ሊለምነው ፈልጎ እንደምንም ብሎ ከአልጋው ላይ ተነሳ።

“እባክህ ጋሼ ቶሎሳ አትቀየመኝ፡፡ የቤት ጠላ ነው ብዬ ነው ከአቅሜ በላይ
የጠጣሁት። ይቅርታ አድርግልኝ?” አንገቱን አቀረቀረ፡፡
“ኢሱ የራሱ ቺጊር ኖ! ሀቂሙን ገሚቶ ጠጣው የራሱ ጉዳይ ኖ! ቶሎሳ
ጉዳይ አዶለም! ሰካራም ! ቢራ አልጠጣውም ሀላልሺም?! አሁን ሚን
ገኘሺና ጠጣሺው?!” እነዚያ ትናንሽ ዐይኖቹን እንደ ነብር አጉረጠረጠበት። ጌትነት ትናንት እና ዛሬ ተቀላቅለውበት ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ሁሉ ትናንት አዲስ ክስተት አዲስ ትርዒት የተፈፀመበት ቀን እንዳልነበረ ሁሉ ተረጋግቶ ነበር የተኛው፡፡ ሆዱ የቀራጭ አቅማዳ እስከሚመስል ድረስ ጠላ ሲጋት ማምሸቱን እንጂ ስለሌላው ጣጣ አሁን ቶሎሳ ስለሚያወራው ታሪክ ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ራቱን ምን
እንደበላ እንኳ አያስታውስም፡፡ ቶሎሳ እንደዚያ ግስላ ሆኖ ሲያንባርቅ
ግራ ተጋባ፡፡ ተደነጋገረው።
“እባክህ ጋሼ ቶሎሳ ሁለተኛ አላደርገውም፡፡ አይለመደኝም። የዛሬን ብቻ ተለመነኝ፡፡ ቤቴ ነው ብዬ ተዝናንቼ ነው የጠጣሁት” በድጋሚ ተለማመነው። ቶሎሳ ብው አለ፡፡
“ኢሄ ሶዬ ጤና ኤለም ሂንዴ?!ሲለጠላ ወሬ አልፈሊጊም!! አይገባሂም
ሂንዴ?! ሲለሆነ ነገር ቢቻ ነጊር! ሲለፈጠረው ታሪክ ሀንዲም ሳታስቀሮ
ፊሪጥ ፊሪጥ አዲርጊና ነጊር!!”
ጌትነት ስለምን እንደሚያወራ ውሉን መጨበጥ ተሳነው።ድንብርብሩ
ወጣ! ዐይኖቹን ጭፍን ክድን... ጭፍን... ክድን... ጭፍን... ክድኝ...
አደረጋቸው። የቶሎሳን ያልተለመደ ቁጣና ጩኽት፣ በንዴት የተለዋወጠ ፊት ሲመለከት ክፉኛ ተደናገጠ፡፡ ዐይኖቹንም ጆሮዎቹንም ተጠራጠረ፡፡ ጆሮውን ኮረኮረ፡ እትዬ ሸዋዬ የቶሎሳን ጩኽት ስምታ ሮጣ
የምትመጣ መሰለው፡፡ እዚያ ደርሳ...“ምነው ቶሎሳ? ምን ሆናችሁ?
ምን ነካችሁ? ጉረቤት ሁሉ እስኲሚረበሽ ድረስ የምን ጩኽት ነው? ቢጠጣ ምን አለበት ታዲያ? የቤት ጠላ ነው የጠጣው። መሸታ ቤት ሄዶ
አልጠጣ? በል አሁን ይብቃህ!”ብላ ቶሎሳን ስትገስፀው በሀሳቡ ታየው።
እትዬ ሸዋዬ መጥታ እንድትገላግለው ተመኘ፡፡

“ምን እንደምትለኝ ማወቅ አልቻልኩም እኮ ጋሼ ቶሎሳ? እትዬ ሽዋዬ
ጩኽትህን ስትሰማ ትደነግጣለች። ሁለተኛ አይለመደኝም፡፡ እባክህ
የዛሬን ብቻ ይቅርታ አድርግልኝ?” እንዳይገረፍ የሚሽቆጠቆጥ ህፃን ልጅ
መሰለ፡፡ ቶሎሳ አውቆ ሊያታልለውና ሊቀልድበት የሚያደርገው የብልጣ
ብልጥነት ሙከራ መስሎት የበለጠ ተናደደ። ጨስ...“ሀቲቀባጢር!” አለና
ዘሎ አንገቱን አነቀው፡፡ መቼም የአደነጋገጡ ነገር አይነሳ። ከመውደቅ
ተረፈ እንጂ ሰማይ በላዩ ላይ የተደፋበት ነበር የመሰለው። ተርበደበደ::
“ምንድነው ነው የምትለኝ ጋሼ ቶሎሳ?!” እሱም ሰውነቱ በንዴት ማተኮስ ጀመረ። ቀስ አለና አንገቱን ጨምድዶ የያዘውን የቶሎሳን እጅ ከአንገቲ ላይ አላቀቀ። በጉልበት ቢያያዙ ቶሎሳን ጃርት የበላው ዱባ አስመስሎ እንደሚሄድ የታወቀ ነው። በፍፁም የሚመጣጠኑ አይደሉም፡፡ ጌትነት ጠፍሮ የያዘው የአክብሮትና የፍርሃት ልጓም ብቻ ነው። በሱ እምነት
ምንም የፈፀመው ወንጀል፣ ምንም የሰራው ሀጢአት የለም፡፡ የፈፀመው
ወንጀልና የስራው ሀጢአት ቢኖር ጠላ ጠጥቶ ሰክሮ መገኘቱ ነው::
ለዚህ ጥፋቱ ደግሞ እየተርበተበተ ቶሎሳን ይቅርታ እየጠየቀው ነው::
ነገሮች ቀስ በቀስ ግልፅ እየሆኑ የመጡት ቶሎሳ እንደታረደ በሬ በሚጓጉር ድምፅ ማጓራት ሲጀምር ነበር።
“ሸዋዬን ሚንዲኖ ያደረገች?!በሚን ሚኪናቲኖ ቀየመች?!ለሚንዲኖ ማቲናገሮ?!” ጮኽና በድጋሚ አንገቱን ሊያንቀው መጣበት፡፡ ጌትነት ክው አለ።
“ም..ምን….ምን?...” ከድንጋጤው የተነሳ በፍፁም የሱ የራሱ መሆኑን በሚያጠራጥር አንደበት ተንተባተበ፡፡

“ሚንዲኖ ደረካት?! ሚናባቲኖ ሆነች?!” በድጋሚ ጮኽበት።
“እ...እኔ....እኔን ...ነኝ...እኔን ምምንን ...አደረገኝ ..አለች ” አፉ
ተሳሰረ።
“አሃሃሃ!.…ሌባ ሀይና ደረቂ መሊሶ ሊብ ዲቂቂ ሀሉ! ኢንደ ታናሽ ሆንዲሙ መልኪቼው ኢንደ ታላቅ ሆንዲሙ አከቢራል መሲሎት ነበረው።አባቱ ሁለታ ከቢዶት ኢናቱና ኢቱን ኢንዲረዳው ፈለኩት።ተሪፎት አዳላም ከባሌ ጠራሁት። ካፊሎ ኢንዲበላው ሆንዲሙን አኪል ኢምነት ጣልኩት።አንታ አላ ቢሎ ሁጭ አደረው ሆንጀል ደረገና ሚስቱን
በሳጫት ሀደረው፡፡ ኢዝጋቤር ቢዲሩን ኪፈል! ስኪሮ ቲዳሩን ቢጥቢ ኡጡን ሲላወጣው መስጊናሎ!ሆ! ኢዝጋቤር!!” እሱ የሰማዩ ጌታ ብድሩን ብ
እንዲከፍለው ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ተመለከተ። ከዚያም ተስፋ በቆረጠ
ሁኔታ ጌትነትን ትክ ብሎ አየው፡፡ ያውም ቶሎሳ ጨርቅ ከመጋፈፍ ድንበር ወዲህ ባለ ምክንያት አስቀይሟት ይሆናል በሚል ግምት እንጂ ጉዳዩ ከዚያ የዘለለ አደገኛ ሙከራ እንደነበረ ቢያውቀው ኖሮ ትርዒቱ
ከዚህ የተለየ ገጽታ በኖረው ነበር፡፡ ቶሎሳ በጌትነት ላይ የተመሰረተበት ክስ ሌላ መሆኑን የተፈጠረው ተአምር ሊገምተው የማይችለው መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ ጉድ ይፈላ ነበር፡፡ ደግነቱ ጌትነትን እንደዚያ ሊያስጠረጥረው በሚያስችለው ሁኔታ ውስጥ አላገኘውም፡፡ ልብሱን እንኳ ሳያወልቅና ሰክሮ እንደተጋደመ ነው ያገኘው። ቶሎሳ በፍፁም
👍4
ሊገምተው የማይችለውንና አእምሮው ሊቀበለው የማይደፍረውን እሱና ሸዋዬ ብቻ የሚያውቁትን ያንን ትዕይንት ሙሉ
ለሙሉ የረሳው ቢሆንም እንደዚያ ተስፋ በቆረጠ አነጋገር ዐይን ዐይኑን ትክ ብሎ እያየ ልብ የሚያቆስል ወቀሳ ሲሰነዝርበት ገላው በድንጋጤ እየራደ... እየራደ ሄደና ትናንትናን በዛሬ ውስጥ፣ የትናንት ማታ ማንነቱን በዛሬው የቶሎሳ አእምሮን የሚፈልጡ ቃላት ውስጥ፣ ትናንትና
ነብዞና ደንዝዞ የነበረው ጭንቅላቱን ዛሬ ማስታወስና ማመዛዘን በጀመረው ህሊናው ውስጥ፣ የስካርን ጦስ ከቶሎሳ ውለታ ውስጥ፣ የቶሎሳን ወቀሳ ከተሸከመው ከባድ የቤተሰብ ሃላፊነትና ከአባቱ የአደራ ቃል ውስጥ በሃሳብ ይዳስስ ይለቅም ጀመር፡፡

ከትናንትናው የቅብጠት ግርዶሽ በስተጀርባ የሆነ ነገር ቀስ በቀስ ደብዝዞ
ይታየው ጀመር፡፡ በፈጠጡ ገሀዳዊ ዐይኖቹ ውስጥ የተሸሽጉ የትዝብት
ዐይኖቹ የትናንትና ማታ እሱነቱን አቀጭጨውና አሳንሰው ያሳዩት
ጀመር፡፡ ብዥ ብዥ....ብዥዥ... ብዥዥዥዥ.. አለበት። ማሰብ፣ ማስታወስ፣ ማመዛዘን የጀመረው አእምሮው የወለዳቸው ጥቃቅን ጥርሶች ቀርጨጭቀርጨጭቀርጨጨጭ...እያደረጉ ሲቆረጣጥሙት ይሰማው ጀመር....
“ልክ ነው...አዎን! አዎን! ወይኔ ልክ ነው...እንዴ!...”አለ። የዶሮ ወጥ
ሲበላ እንደነበረ ትዝ አለው። በደንብ እንጂ! ያውም ሸዋዬ እያጉረስችው
ነበር የበላው። ከዚያስ? ሸዋዬ እየተላፋችው ነበር። ወገቡን እቅፍ አድ
ርጋው ነበር...አልጋው ላይ ወስዳ ያንጋለለችው... ልክ ነው!!….ከንፈር
ለከንፈር ተዋስበዋል..ጣቶቹን በጭኖቿ መካከል አመላልሷቸው ነበር!..
ራቁቷን እላዩ ላይ ተኝታ እየተንከባለለች ትስመው ነበር!...አዎን! አዎን! እንዴ?!..ልክ ነው! ልክ ነው! አሁን ገና የቶሎሳ ንግግር የቶሎሳ ብስጭት ከምን ጋር እንደተያያዘ ገባው። እነኝያ ዘና ብለው የቶሎሳን እጅ ከአንገቱ ላይ ፈልቅቀው ያላቀቁት ጣቶቹ መንቀጥቀጥ ጀመሩ።
ሸዋዬ በደረቱ ላይ እየተንከባለለች ስትስመው ከቆየች በኋላ ፊቱ ላይ
ተፍታበት መሄዷ ታወሰው፡፡ወባ እንደተነሳበት ሰው የሰራ አከላቱ መንቀጥቀጥ፣ መንዘፍዘፍ ጀመረ፡፡ ሸዋዬን ከላዩ ላይ አሽቀንጥሮ ሲወረውራ
ትና ቁልቁል ሲመለከታት በሃሳቡ ታየው ። ዐይኖቹ ቀስ በቀስ የቶሎሳን ዐይኖች መሸሽ ጀመሩ፡፡ ጠንካራና ደንዳና የነበረው ልቡ ቀስ በቀስ እንደ ቅቤ መቅለጥ፣መፍሰስ ጀመረች፡፡ ከፍርሃቱ የተነሳ እግሮቹ መቆም ሲሳናቸው ታወቀው።ቶሎሳ ያንን የጌትነትን አኳኋን በትዝብት ቆሞ ሲመለከት ቆየና ወደ ኋላው ሄዶ ወንበር ላይ ዘጭ አለ። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የነበረው ጌትነት ነው ብሎ ለመናገር ይከብድ ነበር፡፡ ቅድም ይታይበት የነበረው በራስ የመተማመን ስሜት እንደ ጉም በኖ ጠፍቷል።እሱ መሆኑን እስከሚያጠራጥር ድረስ ተቀይሮ ውሃ ውስጥ የገባች አይጥ
መስሏል። ሸዋዬ ያለምክንያት እንዳልተበሳጨች፣ ፊቷ ሳምባ እስከሚመ
ስል ድረስ ቀልቶ በንዴት እየተንጨረጨረች በሃይለ ቃል የተናገረችው ያለምክንያት እንዳልሆነ ለቶሎሳ አሁን ግልፅ ሆነለት፡፡ ለዚህ ደግሞ ጌትነት ጉልህ ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፡፡ የሚንጣጣው አንደበቱ ታነቀ።
ፊቱ ተለዋወጠ። ፀሀይ እንደመታው ቡቃያ አንገቱን ጣለ፡፡ እነዚህ ሁሉ ለሸዋዬ ተበዳይነት ተጨማሪ ማስረጃ የማያስፈልጋቸው ጉልህ ማረጋገጫዎች ናቸውና ለዚህ ለማይረባ ሰው ብሎ የሚወዳት ሚስቱን በጥፊ አላግቶ መምጣቱ ቆጨው። አንገበገበው፡፡ ከዚያም ብድግ ብሎ መጣና
“ሽዋዬን ጠባይ ሀቅሎ፣ ሞክራን ሀቃሉ፣ ኢናቱን ሀቃሎ፣ በሬሳን ሀቃሉ፣
አንቴን ጊን ሀላቂም! ሞክራ ሊጅ አዶለም አንቴ !ቲዳሩን ኪፍቱን ቲቼው
ከረምኩት ደደብ ነበርኩት፡፡ አንዲ ቀን ሁጪ አደረ ቢሉት ቲዳሩን ቢጥ ቢጡን አወጣው ሶዬ ሀጋጣሚ አገኘ ጊዜ ሚስቱን ሂቀማል፡፡ ሌላ ጣጣ
ሁስጥ ሳይገባ ቤቴን ለቂቂና ሁጣ! ሲራውን ሙያውን ለኢናቱ ነጊራሉ!”
ሹልክ ብሎ እንዲወጣ ቀጭን ትዕዛዝ ከሰጠው በኋላ የቤቱን በር በጣቱ
ጠቆመውና ከወንበሩ ተነሳ።

ዋ! ጌትነትን ያየ ? የአሳዛኞች አሳዛኝ፣ የድንጉጦች ድንጉጥ የተስፋ ቢሶች ቁንጮ! ሆኗል። በቶሎሳ ንግግር አእምሮው እየተወጋ፣ልቡ እሳት
ላይ እንደወደቀ ስጋ እየተጠበሰች ቶሎሳ ንግግሩን እስከሚጨርስ ድረስ
ጠበቀው። በመጠጡ ብዛት ደንብሾ ካደረው ፊቱ ጋር ድንጋጤው ተጨምሮበት አመድ ከመልበሱ የተነሳ ያላለቀ የሰነፍ ተማሪ ስዕል መስሎ
ነበር፡፡ በልቡ ሸዋዬን አብጠለጠላት። ረገማት፡፡ እግዚአብሄር ይይልሽ
አላት፡፡ ሸዋዬ ወስውሳ፣ ወስውሳ በወጥመዷ ውስጥ ካስገባቸውና ለወሲብ ካነሳሳችው በኋላ ያሰበችው አልሳካ ሲላት ራሷን ከደሙ ንፁህ አድርጋ
የሀጢአቱን ተራራ ለብቻው እንዳሸከመችው አወቀ፡፡ ጅራፍ ራሱ ገርፎ
ራሱ ይጮሀል እንዲሉ እስራልሃለሁ! ብላ እንደፎከረችው ማድረጓን፣ ሌሊቱን በሙሉ የተንኮል ቅመሟን ስትቀምም አድራ ቶሎሳን ለጦርነት እንዳዘመተችበት ሲገባው አእምሮው በሃሳብና በጭንቀት ተወጠረ።
በርግጥ ከሸዋዬ ጋር ክርና መርፌ ሆኖ ወሲብ አልፈፀመም። ወሲብ ባለ
መፈፀሙ እጅግ ደስተኛ ቢሆንም ከወሲብ በመለስ ያለውን ግን ሙሉ
በሙሉ ፈፅሟል፡፡ ግን እሱንስ ቢሆን እንዴት ሊፈፅም ቻለ? ጣቶቹ
እንዴት ብለው የሽዋዬን ጭኖች ለመዳበስ ደፈሩ? ከንፈሮቹስ እንዴት
አድርገው በከንፈሮቿ ላይ ለማረፍ ወኔ አገኙ? ድፍረቱ ጥጋቡ ከየት መጣ? የጠላን ጦስ የአረቄን መዘዝ የመጠጥን አስቀያሚ ውጤት ሊያስበው መጠጥን እስከ ወዲያኛው ጠላው፡፡ ተጠየፈው። የበለጠ በእፍረት ተሸማቀቀ፡፡ ስካሩ ሲለቀውና አእምሮውን መግዛት ሲጀምር ትናንትና ምሽትን በጥላቻና በፀፀት ያወግዝ ጀመር፡፡ ያንን እንዲያደርግ የገፋፋችው ሸዋዬን በልቡ ኮነናት። እሱ እንደሆነ ሁለመናውን ትምህርቱ ሰጥቶ
የኖረና ወንድነቱን ለውሃ ሽንት ከመጠቀም ባለፈ አንድም ቀን ፈትሾ
የማያውቅ ድንግል ነበር፡፡ በሸዋዬ ግን ከሞላ ጎደል ተሳሳተ።

ዋ! በአዲስ አበባ ውስጥ የተጠራቀሙ ሽዋዬዎች!አሳሳቾች ! አዲስ አበባን
ጠላት። እንደ ሸዋዬ ባሉ አሳሳቾች የተሞላች የተንኮለኞች መጠራቀሚያ
አድርጎ ቆጠራት፡፡ያንን የትናንትናውን ትርዒት አስታውሶ መፈጠሩን
በጠላበት ቅፅበት ቶሎሳ በስተመጨረሻ ላይ የተናገረውን ሲሰማ ደግሞ ልቡ ትንሽ ተረጋጋች፡፡ ያንን እሱና ሸዋዬ ብቻ የሚያውቁትን ብልግና ቶሎሳ በትክክል ያለማወቁን ሲገነዘብ ትንፋሹ መለስ አለች። ከዚህ በኋላ ትዳሬን ከመመኘት ወደ ኋላ እንደማትል አረጋግጫለሁ ነበር ያለው፡፡ ከሸዋዬ ጋር የፈፀሙት ድርጊት ከመመኘት የዘለለ ነው። ቶሎሳ ይሄንን
አውቆ ቢሆን ኖሮ ወደፊት ትዳሬን ትመኛለህ የሚል ጨቅላ ፍራቻ
ሊያሳድር አይችልም፡፡ ሸዋዬ እንደዚህ አድርጎኛል ብላ ያደረጋትን ሁሉ
አፍረጥርጣ እንዳልነገረችው ገመተ። በሱ ምክንያት በፍቅር የኖሩ ባለትዳሮች እንዳይጣሉ፣ ትዳራቸው እንዳይፈርስ ሃጢአቱን ለብቻው ተሸክሞ
የቶሎሳን ትዳር ሊታደግ ወሰነና ጋሼ ቶሉ. ሳ.ሳ” አለ እንባ ከሚተናነቀው ጉሮሮው ውስጥ እየተፈናጠሩ በሚወጡ ቃላት።

“በድዬሃለሁ... አጥፍቻለሁ ለበደሌም ሆነ ለፈፀምኩት አስነዋሪ ድርጊት
ካንተ የበለጠ አእምሮዬ ቀጥቶኛል። አንተ. እኔ.እኔ አንተ ያንተ ታላቅ
ወንድሜ እናቴ ያልወለደችልኝን..የታላቅ.…ወንድምነት ፍቅርን...የአይዞህ ባይ አለኝታነት ኩራት የሰጠኽኝ... ወን…. ወንድሜ ነህ... እት... እትዬ... ሸዋዬም....ወንድሜ... ባለቤት.. እህ..እህቴ.ነች..ግን.ሰክሬ..ሰው.....ነኝና...እንደማንኛውም...ደካማ ሰው...አስ....አስቀይሜያታለሁና በሁለታችሁም..ስም…ይቅርታ.. አድርግልኝ?” ተንበረከከና ጉልበቱ
ስር ወድቆ ለመነው። እያለቀስ ከልቡ ይቅር እንዲለው ብቻ ተለማመ
👍51
ጠው። ቶሎሳ በጌትነት አነጋገርና በሁኔታው ግራ ተጋብቶ ፈዟል።

“ጋሼ ቶሎሳ የምለምንህ አንድ ነገር ቢኖር ከእትዬ ሸዋዬ ጋር በኔ ምክንያት እንዳትጣሉ ብቻ ነው፡፡ የሞቀው ፍቅራችሁ በኔ ምክንያት እንዳይቀዘቅዝ በፈጣሪ ስም እማፀንሃለሁ። እኔ ከዛሬ ጀምሮ ወደምሄድበት እሄዳለሁ፡፡ውለታህን ምንጊዜም የምረሳው አይሆንም፡፡ በድዬህ ሄድኩ እንጂ በድለህ አላባረርከኝምና ቅር እንዳይልህ” በማለት ልመናውን አቅርቦ ቶሎሳ ባሳየው በር በኩል ሹልክ ብሎ ለመውጣት ያቺኑ መከረኛ ሻንጣውን ሊያንጠለጥል አጎነበሰ፡፡ ቶሎሳ ሁሉም ነገር ተምታታበት። ለሁለት ነው እንዴ ያገባችሁኝ?! ተራው ያንተ ነው ስትጨፍርባት እደር ብለኽዋል እንዴ?!… ያንን የፈፀምኩት በስካር መንፈስ ነው!..በድያታለሁ !ለፈፀምኩት አስነዋሪ ድርጊት አእምሮዬ ቀጥቶኛል!” ምን ማለታ
ቸው ይሆን? በመካከላቸው የተፈጠረው ምንድነው?” ድንብርብሩ ወጣ፡፡
ያንን አእምሮው እንዲጠረጥር የማይፈልገውን ድርጊት ፈፅመው ቢሆን
ኖሮ ሰምና ወርቅ ሆነው ውስልትናቸውን በድብቅ ያጧጡፉት እንደሆነ
እንጂ እንደዚህ እሳትና ጭድ ሆነው አይጠብቁትም ነበር። በሌላ በኩል
ደግሞ ሽዋዬ ከፍላጐቷ ውጭ የተፈፀመባት በደል ሳይኖር እንደዚያ በሰ
ውነቷ ላይ እሳት እየነደደ ስሞታ ልታቀርብለት አትችልም፡፡ሚስጥሩ
ምን ይሆን? ጌትነት ዛሬም እንደሁልጊዜው እህቴን እትዬ ሸዋዬን በድያታለሁ” እያለ ስሟን በአክብሮት እየጠራ እያለቀስ ነው፡፡ በዚህ ላይ እስከዛሬ ድረስ አድርጐት የማያውቀውን መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ልብሱን
እንኳን ማውለቅ ተስኖት አልጋው ላይ እንደወደቀ ነው ያገኘው። ወቸ ጉድ! ለቶሎሳ ኣእምሮን የሚፈትን ጣጣ!....

“ኢሺ በሚንዲኖ ጣላቹ ታዳ? ሰኪሬኖ፣ ሰኪሬኖ ኢላል ሰኪሮ ሚን ደረገ? በዲያታሎ ኢላል በደለው ነገር ሚንዲኖ? ለሚን ጊልጥ ሀታደርጊም?” ሻንጣውን ከማንሳቱ በፊት ትከሻውን ያዝ አድርጉ ረጋ ብሎ ጠየቀው። ጌትነት ምን ብሎ ይንገረው? እንደምን ብሎ የሚወዳት የሚያከብራት የታላቅ ወንድሙ ሚስት በመጠጥ ሃይል ገፋፍታኝ አሳስታኝ..
ምን አደረኳት ብሎ ይንገረው? ከትናንትናው ምሽት በፊት ሁሉ እሱ
መኝታ ክፍል ራቁቷን እየገባች ጡቷን፣ ባቷን፣ ላቷን እያስጎበኘች ዕቃ
የምታነሳ እየመሰለች አጭር ቀሚስ እየለበሰች ፊት ለፊቱ ሄዳ እያጐነበሰች ስትፈታተነው መክረሟን እንዴት ብሎ ይንገረው? እንኳን ከአንደበቱ ሊያወጣው ሲያስበው ይጨንቀዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ቶሎሳ ከሞቀ ትዳሩ ከሚወዳት ሚስቱ ለምን ይቀያየማል? ለምን ይጣላሉ? ጥፋተኛነቱን ሙሉ ለሙሉ አምኖ ተቀብሎ ያንን ለዚህ ያበቃውን ጠላ እየረገመ
የሆዱን በሆዱ ቀብሮ ሹልክ ብሎ መሄድን መረጠ። “ምንም የተፈጠረ አዲስ ነገር የለም ጋሼ ቶሎሳ። ብቻ እትዬ ሸዋዬ አስቀይሞኛል ብላ የነገረችህ በሙሉ የኔ ጥፋት ነው። ላጠፋሁት ጥፋት ይቅርታ የምጠይቀው ደግሞ አንተንም እሷንም ነው” አለው ትክዝ ብሎ።

“ሆድ ባባን ሲቂል ሆጣል ኢያላ ኖ?” ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል መሆኑ ነው።

“በፍፁም ጋሼ ቶሎሳ እንደሱ አታስብ፡ችግሬን አይታችሁ ልትረዱኝ ከማስጠጋትና አይዞህ በርታ እያላችሁ ሞራል ከመስጠት ሌላ ምን አደረጋ
ችሁኝና በእናንተ ላይ የምቋጥረው ቂምና በስካር መንፈስ የማወጣው የሆድ ብሶት ይኖራል ?”

“ታዳ ሚን ሊበለው? አሲር ጊዜ ሰኪሬ ሰኪሬ ቲላለሽ” ትከሻውን ወደ ላይ ገፋ አደረገ፡፡ አሁን የጌትነትን የፈሰሰ እንባ ሲመለከት፣ የውለታውን ነገር አክብዶ ሲገልፅለት፣ ታላቅ ወንድሜ ነህ ይቅርታ አድርግልኝ እያለ እግሩ ላይ ወድቆ ሲለማመጠው የሆነ የሃዘኔታ ስሜት ተሰማው። በብስጭት ከቤት እንዲወጣ የሰጠው አስቸኳይ ትእዛዝ ሁሉ ትዕግስት የጉደለው ግብታዊ ውሳኔ መሆኑ ታወቀው። አዲስ አበባ ውስጥ አንድም
ዘመድ እንደሌለው እያወቀ ከቤት ማባረሩ በህይወቱ ላይ መፍረድ እንደ ሆነ ገባውና ውሳኔውን ሊያሻሽልለት ፈለገ። በመካከላቸው የተፈጠረው
መጠነኛ ግጭት ሊሆን እንደሚችል ገመተና “በል ሻንጣውን ቀሚጥ!
ኢሷ አሁን ሀራስ ነቢር ሆናለች። ቲኒሽ በርዲላት ጊዜ ቀስ ቢዬ ነጋጊራሉ፡፡ ሄዳሎ ሚናሚን ቶው! ጮህኩቢሽ በሷ ናዲጄ ኖ” ሲል ተለሳለሰ።

የሽዋዬን ትርጉሙ ያልታወቀ ጩኽት፣ የጌትነትን ምክንያቱ በውል ያልታወቀ በደለኛ ነኝ ባይነት ሶስቱ በጋራ በሚያደርጉት ውይይት ግልጥ ልጥ ብሎ እንዲወጣ ፈለገና ሻንጣውን ተቀብሎት ከነበረበት መልሶ አስ ቀመጠው፡፡

“ሂዲና ፊቱን አጢብ! ፀጉሩን በጢር! ሊብሱን ቀዪር! ኢሷም ኢስከዛ
ዲረስ በርዲላታል፡፡ አሁን ሆጣ ቢሎ ቁርሱን ኢኒብላው” ልብሱን እንዲቀይርና ፊቱን እንዲታጠብ አድርጐ ቁርስ ሊጋብዘው ይዞት ወጣ።መብላት አይበለው ሬትሬት እያለው ቁርስ ተጋበዘና ማታ አስራ ሁለት ሰዓት ሲሆን ከቤት ለመገናኘት ተቀጣጥረው ተሰነባብተው ቶሎሳ ወደ ስራ ሲሄድ እሱ ደግሞ ቀስ ብሎ ወደ ቤት ተመለስ፡፡ከቤት ሲደርስ ሽዋዬ መኝታ ክፍሏ ውስጥ መስታወት እያየች በጥፊው ምክንያት ያበጠ ፊቷን
እየደባበሰችና በብሽቀት እየተከነች ከአልጋዋ ላይ ጋደም ብላ ነበር። በት
ናንትናው ሁኔታ እጢዋ ዱብ...ብሏል፡፡ የውርደት ስሜቱ እስከአሁን ድረስ አልለቀቃትም፡፡ ሰውነቷ አልጨስም እንጂ ተቃጥላለች። ጌትነት ሹልክ ብሎ ገባና ያለችውን አንድ የቅያሬ ሱሪና ሁለት የደካከሙ ሽሚዞቹን በአሮጌ ሻንጣው ቆጣጥሮ ድምፅ ሳያሰማ ውለቅ አለ፡፡ ያቺን ቤት ዳግም ላይመለስባት ተሰናብቷት ወጣ...


ይቀጥላል
👍31
አትሮኖስ pinned «#የተወጋ_ልብ ፡ ፡ #ክፍል_ስድስት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና .....“ግራ ገባኝ አኮ ሸዋዬ? እስቲ የተፈጠረውን ነገር በጥሞና አስረጅኝ?” እየተሽቆጠቆጠ ጠየቃት። ሸዋዬ ቱግ! ብላ ተነሳች። “ግራ ይግባህ!! የእናት የአባቴ አምላክ ግራ ያግባህ!! ድሮውንም ግራ ነበርክ! አሁንም ግራ ነህ!” ብልጭ! አለበት፡፡ በቆመችበት በቃሪያ ጥፊ ሲደረግምባት እንደ ብራቅ ጮኽችና አልጋዋ ላይ በጀርባዋ ፍንችር…»
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


...በጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ ከሁለት ወራት በላይ በፍቅርና መተሳሰብ
ያሳለፉባትን የቶሎሳን ጎጆ ስሞና ተሳልሞ ከውስጥ ስሜቱ ባዶነት ጋር ብቻውን እንደ እብድ እያወራ ከፊት ለፊቱ ከአድማስ ባሻገር ይታየው የነበረውን የተስፋ ጭላንጭል ድቅድቁ ተስፋ ማጣት ተረክቦት፣ ወዴት እንደሚሄድ እንኳ ሳያውቀው ወደ ጐዳናው...ወደ ሰፊው የመኪና አስፋ ልት መንገድ ላይ ወጣ....


አዲስ አበባ የደመና ቡልኮዋን ተከናንባለች። የጠዋቱ ቁር አይነሳ! በጣም ይበርዳል። ጌትነት መኩሪያ በህይወት ገጠመኝ ጠርዝ ላይ እየተንጠራወዘ ለሁለት ወር ከሃያ አንድ ቀናት በላይ በአዲስ አበባ ውስጥ ቆይቷል።ጌትነት አዲስ አበባን እየለመዳት ነው። መልመድ ያልቻለው የእናትና
የእህቱን ናፍቆት ብቻ ነው።ሁልጊዜም ናፍቆታቸው ለሱ አዲስ ነው። ትንሽ የሚያስከፋው ነገር ካጋጠመው ናፍቆታቸው ይብስበታል። ልቡ
ይሽበራል። ሆዱ ይባባል። የበሬሳ ልምላሜ.. የህዝቡ ፍቅር... የእንስሳት
ትዝታ የኩሌ ትንፋሽ፣ ጠረኗ የበረቷ መአዛ የጫካው ውበት...የአእዋፋቱ ዝማሬ..የዱር አራዊቱ ቡረቃና ዝላይ... በሃሳብ ዐይኑ ይታዩታል በሃሳብ እፍንጫው በመአዛቸው ያውዱታል...

“ጌትነት እስቲ ወጣ ብለን ምናምን ገዝተን እንምጣ” ባለ ሱቁ አብዱላሂ ነበር፡፡ጌትነት ፈጠን ብሎ ጃኬቱን እላዩ ላይ ጣል አደረገና ወደ አብዱላሂ
ሮጠ... ተያይዘው ጉዞ ጀመሩ።
አብዱላሂ ባሌ ተወልዶ ባሌ ያደገ ሰው ነው። አዲስ አበባ ሲገባ በቀጥታ
የተሰማራው በጥቃቅን የንግድ ስራዎች ላይ ሲሆን በአሁኑ ሰአት የአንድ
ሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ባለቤት ለመሆን የቻለ የቶሎሳ ጓደኛ ነው። ጌትነትን ከአብዱላሂ ጋር ያስተዋወቀውም ቶሎሳ ነው፡፡ ከቶሎሳ ጋር ከመለያየታቸው በፊት እንደዋዛ ያስተዋወቀው ሰው ለጊዜውም ቢሆን መሽሽጊያ ሆኖት ለሶስት ሳምንታት ያክል አብሮት ሊቆይ ችሏል። የቶሎሳን ቤት ለቆ ወዴት እንደሚራመድ ግራ ተጋብቶ ሲንጠራወዝ ወዴት አባቴ ነው የምሄደው? ለጊዜውስ ቢሆን ማን ያስጠጋኛል? ወደ ቶሎሳ ልመለስ ወይስ ወደ ባሌ ልገስግስ? ምን አማራጭ አለኝ? እያለ በጭንቀት ተወጥሮ ራሱን በሚጠይቅበት በዚያ አስጨናቂ ሰዓት አብዱላሂ በሀሳቡ መጥቶ ድቅን አለበት፡፡

“ምን ብዬ? ለምንስ ከቤት ወጣሁ ብዬ? ከቶሎሳ ጋር በምን ተጣላን ብዬ ነው ለአብዱላሂ የምነግረው?” እያለ አንዴ ለመቅረት አንዴ ደግሞ ጨክኖ ለመሄድ ሲያመነታ፣ ይሉኝታና ፍራቻ ወደ ኋላ ሲጉትቱት፣ እግሩና ችግሩ ደግሞ ወደ ፊት እያሽቀነጠሩ ሲወረውሩት ሳያስበው ከአ
ብዱላሂ ሱቅ ላይ በድንገት ገጭ አለ፡፡

“አሰላም አሌይኩም ጌትነት! ዛሬ ከወዴት ተገኘህ?” አብዱላሂ በሞቀ ፈገግታ ተቀበለው። ጌትነትም ሞቅ አድርጎ አፀፋውን መለሰ፡፡

“ግባ ጌትነት!ወደ ውስጥ ዝለቅ!” ወደ ሱቁ ውስጥ ካስገባው በኋላ ከምን
ጣፉ ላይ እንዲቀመጥ ጋበዘውና ጨዋታ ጀመሩ። ጌትነት ለበአል የተጠመቀ ጠላ ጠጥቶ በመስከሩ ምክንያት ከቶሎሳ ጋር መቀያየማቸውን ለአብዱላሂ አጫውተው።

“ወላሂ! ቶሎሳ ልክ ነው! ይሄ መጠጥ እሱንም ሱስ ሆኖበት እንደተቸገረ
ነግሮኛል። ከባለቤቱ ጋርም አልፎ አልፎ የሚጋጩት በመጠጥ ጉዳይ እንደሆነ አጫውቶኛል ታዲያ አንተን የመሰለ ጨዋ ልጅ ሰክረህ ሲያገኝህ ቢቀየም ይፈረድበታል? የምን መጠጥ ነው ጌትነት? አንተስ ብትሆን የሌለብህን አዲስ አመል ምን አጋጥሞህ አደረግከው? መጠጥ እኮ ከይር አያ
ሳይህም፡፡ ወላሂ!! መጠጥ በጣም መጥፎ ነገር ነው ነጂስ!! እኔም የወደድ
ኩልህ መጠጥና ሲጃራ መጥላትህን ነበር! ታዲያ ቢሆንስ ከሰው ስህተት
ከብረት ዝገት አይጠፋም ይባላል በአንድ ቀን ስህተት አመረረብህ?”

“አዎን ጋሽ አብዱላሂ፡፡ ንዴቱ እስከሚበርድለትና ጥፋቴን እስከሚረሳልኝ ድረስ ለአንድ ሳምንት ያክል አንተ ዘንድ ለመቆየት ነው የመጣሁት።ከሱ ቀጥሉ አዲስ አበባ ውስጥ አለኝ የምለው ዘመድ አንተ ብቻ ነህ” ንግግሩን ሳይጨርስ አብዱላሂ ከአፉ ነጠቀው
“በደስታ!...ወላሂ! .አንተኮ ወንድማችን ነህ ጌትነት! የባሌ ልጅ! እንኳን
አንተን ማንንም እናስተናግዳለን። ብቻ ቶሎሳ እንዳይጨነቅ ስልክ ደውለን
ብንነግረውስ?”
“የለም!..ለም!..ፍፁም አይጨነቅም! ስወጣ ነግሬዋለሁ! ለትንሽ ጊዜ
ቆይቼ እንደምመለስ ያውቃል። ስትመለስ የጀመርከውን አዲስ ፀባይ እዚያው አስቀምጠህ ና ነው ያለኝ፡፡ መደወል አያስፈልግም!”
“ምንም አያስብም ነው የምትለኝ?” .
“አዎን ጋሽ አብዱላሂ! የማያውቀው ነገር ቢኖር አንተ ዘንድ የምቆይ መሆኑን ብቻ ነው!” አጥብቆ ተከራከረውና ስልክ መደወል እንደማያስፈልግ አሳመነው። ጌትነት ለአጭር ጊዜም ቢሆን ማረፊያ በማግኘቱ ከመደስቱ በተጨማሪ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ ሳይዘናጋ ስራ ፍለጋውን በማጧጧፍ ራሱን ለመቻል አቅዷል፡፡በዚሁ መሰረት ሱቅ እየዋለ አብዱላሂን በስራ ይረዳው ነበር፡፡ አብዱላሂ የእለት ሽያጭ ገቢውን ከመቆጣጠር በተጨማሪ ሆን ብሉ የዘነጋ እያስመስለ ገንዘቡን በየስፍራው እየጣለ ጌትነትን እየፈተነው ነበር፡፡ ጌትነት በአብዱላሂ የተዘጋጁለትን ተደጋጋሚ
የመሰናክል ፈተናዎች ማለፉን ሳያውቅ ሳምንታት ተቆጠሩ። አብዱላሂ
የጌትነትን መልካም ባህሪና ታማኝነት ካረጋገጠ በኋላ አብሮት እንዲቆይና ቶሎሳ መጥቶ እንዳይወስድበት መጨነቅ ሲጀምር ጌትነት ደግሞ የአብዱላሂ ሸክም ሆኖ መቆየት እየከበደው ሄዶ ነበር

ዛሬ የሙስሊሞች በአል የሚከበርበት እለት በመሆኑ አብዱላሂ ፊቱ በደስታ አብርቷል። አብዱላሂ ለበአሉ ማድመቂያ የሚሆን የፍየል ሙክት ለማረድ ስለፈለገ ጌትነትን ይዞ ወደ ገበያ አመራ። በአጋጣሚ ዕለቱ ለአብዱላሂ ሃይማኖታዊ ለጌትነት ደግሞ የተስፋ ጭላንጭል የታየበት የደስታ ቀን ሆኖ ዋለ፡፡ መርካቶ ሄደው የሚያስፈልጋቸውን ሸቀጣ ሸቀጥ ከሽመቱና ወደ ቄራ ወርደው ጥሩ የፍየል ሙክት መርጠው ከጫኑ በኋላ አብዱላሂ ሙክቱን ይዞ በኮንትራት ታክሲ ወደ ቤቱ ሲመለስ ጌትነት ደግሞ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ ሊመለከት ወደ ህዝባዊ ኑሮ ዕድገት ጽህፈት ቤት አመራ..

ጌትነት አዲስ አበባን ቀስ በቀስ እየተላመዳት ቢመጣም በዚያው ልክ
ደግሞ እየሰለቸችው ሄዳለች፡፡ ሴት የሚባል በአይኑ ማየት አስፈርቶታል፡፡የተንኮል መረባቸው፣ ክፋታቸው እንጂ ጥሩ ስራቸው አልታይህ ብሎታል።ሁሉም የአዲስ አበባ ሴቶች እንደ ሸዋዬ ተናዳፊዎች መስለው እየታዩት ዳግመኛ በመርዛቸው እንዳይነደፍ መጠንቀቅ አብዝቷል። በዚህ የተነሳ ሴት ልጅና ኤሌክትሪክን በሩቁ! ኮሚል ውሳኔ ላይ ደርሷል።በተለይ መልኳ ቀላ ሰውነቷ ሞላ ያለች ሴት ካጋጠመችው ሽዋዬን ስለምትመስለው ሰውነቱ እንደ አራስ ነብር ይቆጣል። ከዚህ ስሜቱ የተነሳ
የአብዱላሂን ልጅ እግር ሚስት ፋጡማን በእጅጉ ይሸሻት ነበር።ከሄዋን ሙሉ በሙሉ ራሱን እንዳያርቅ ደግሞ የሚያፈቅራቸው እናቱና እህቱ አሉ። ለሶስት ሳምንታት በአብዱላሂ ቤት ሲቀመጥ የሶስት ዓመት ዕድሜ
ያክል ያስቆጠረ ነው የመሰለው፡፡
አብዱላሂ ወንደላጤ ቢሆን ኖሮ ያን
ያክል ባልተጨነቀ ነበር

በፖስታ ቤት በኩል ሰሞኑን የደረሰው የአደራ ደብዳቤ የአስራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ውጤቱን ይዞላት ከተፍ ብሏል፡፡ውጤቱን አይቶ እስከሚያረጋግጥ ድረስ ቸኩሎ ልቡ ተንጠልጥላ ነበር እጆቹ እየተንቀጠቀጡ ከፍቶ ሲመለከተው ግን እንደጠበቀው ሆኖ አገኘው።ከወሰዳቸው ሰባት የትምህርት አይነቶች ውስጥ በአራቱ የትምህርት አይነቶች 'ኤ' በሁለት የትምህርት አይነቶች 'ቢ ሲያመጣ በአማርኛ ትምህርት ደግሞ “ሲ ማግኘቱን አወቀ፡፡ይህ ውጤት በከፍተኛ ማእረግ ያለፈ መሆኑን ስላረጋገጠለት
👍7
ደስተኛ ቢሆንም የአብዱላሂ ሸክም ሆኖ መቆየቱ
ደስታውን ሙሉ ሊያደርግለት አልቻለም፡፡
“የሰው ሸክም ሆኖ በድሎት ከመኖር ጥሬ እየቆረጠሙ በነፃነት መኖር ይሻላል” የሚል እምነት ነው ያለው። አንዳንድ ጊዜ ገለብ ሲያደርገው ተነስተህ ወደ ባሌ ብረር ብረር ያሰኘዋል። ሲያሰላስል፣ ሲያመነታ ሲታገስ.. ነገ አንድ ተጨማሪ የተስፋ ቀን ነው ሲል፣ሲጠባበቅ ሶስት ሳምንታትን በአብዱላሂ ቤት ካገባደደ በኋላ በዛሬው በሙስሊሞች የበአል ቀን
የሚከተለውን ክፍት የስራ ማስታወቂያ ተመለከተ።
የትምህርት ደረጃ አስራ ሁለተኛ ክፍል ያጠናቀቀ
ፆታ
አይለይም
የስራ ልምድ
አይጠይቅም
በአስራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ጥሩ ውጤት ያለው በቋንቋው ጥሩ የመናገርና የመፃፍ ችሉታ ያለው ይላል። ለወትሮው የስራ ልምድ ወይንም የኮሌጅ ዲፕሎማ የሚጠየቅበት የሥራ ማስታወቂያ እያነበበ ተስፋ እየቆረጠ ሲመላለስ ነበር የከረመው፡፡ ዛሬ ግን እሱን የሚመጥን ማስታወቂያ በማየቱ ደስታ ልቡን
ወከክ አደረገው። ለሶስት ወራት እግሩ እስከሚቀጥን ድረስ የተመላለስባቸው መስሪያ ቤቶች ብዛት በሃሳቡ ታዩት። አንዳንዶቹ “ክፍት የስራ ቦታ
የለንም!” የሚል አስደንጋጭና ተስፋ አስቆራጭ ማስታወቂያ ለጥፈው
ሲጠብቁት ገና ብቅ ሲል በርቀት ማስታወቂያውን አይቶ ሽምቅቅ ሲል
ተስፋ ቆርጦ ሲመለስ ደግሞ ሌላ ቦታ በጥቆማ ሲሄድ እዚያም ምንም
ክፍት የስራ ቦታ የለንም እያሉ ተስፋ እያስቆረጡ ሲመልሱት ህዝባዊ
ኑሮ እድገት መስሪያ ቤት እግሩ እሰከሚቀጥን ድረስ በቀን ሶስቴና
አራቴ ሲመላለስ የከረመበት ጊዜ እያበቃ መሆኑ ታወቀው። ማስታወቂያው በስሙ ተፅፎ የወጣ ለሱ የተጋገረ እንጀራ መሆኑን በሙሉ ልቡ ተማመነ፡፡
እናቱና ዘይኑ እየሳቁ እየተፍነከነኩ... በሀሳቡ ታዩት።ሥራ ይዞ አለኝታነቱን ሲገልጽ፣ የልጅነት ግዴታውን ሲወጣ፣የአባቱን የአደራ ቃል ሲያከብር ታየው...“አንተ ታውቃለህ” አለና ወደ ሰማይ አንጋጠጠ። ከደስታው
ብዛት የተነሳ በእግሩ የሚረግጠውን እንኳ አይመርጥም ነበር። የእውር ድንብሩን እየተራመደ ሁለመናው ጥርስ በጥርስ እንደሆነ ከሱቅ ደረሰና የገጠመውን ተስፋ ለአብዱላሂ አበሰረው፡፡
አብዱላሂ ጌትነት ስራ ከያዘ ጥሎት እንደሚሄድ ያውቃል። ዜናውን
ሲሰማ ሃዘን ቢሰማውም በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ተስፋ ያለው የተማረ
ወጣት ሞራሉ ተነክቶ የሱ ሱቅ አሻሻጭ ሆኖ እንዲቀር አልፈለገም፡፡ቤተ ሰቦቹን ለመርዳት ያለው ከፍተኛ ጉጉት እንዲሳካለት ፈጣሪን ሊለምንለትና ሊመርቀው አሰበ።

“ወላሂ! በጣም ደስ የሚል ዜና ነው የነገርከኝ ጌትነት! ዛሬ ጫታችንን እየቃምን ዱአ እናደርጋለን፡፡ አላህ ይረዳሃል! አይዞህ!…” አለና ተስፋ በተስፋ
አደረገው። አብዱላሂ ከአላህ ጋር ተነጋግሮ ይሄ ዕድል ከሱ እንዳያልፍ የሚያስፈቅድለት ነቢይ ሆኖ ታየው፡፡ ራት ተበልቶና ሾርባ በሚገባ ተጠጥቶ በፕሮግራሙ መሰረት የጫቱ ሥነ ሥርአት ቀጠለ... ስጋጃው ተነጥፏል፡፡ በላዩ ላይ የጥጥ ፍራሽ ተደርጓል። ፍራሹ ደግሞ በደማቅ ባለ ቀይ አበባ ምንጣፍ ተሽቆጥቁጧል፡፡ ጌትነትና አብዱላሂ ዱአ ለማድረግ ቦታ ቦታቸውን ያዙ፡፡ ሰንደሉ ጣፋጭ መዓዛውን በተነ...የከሰሉ ሙቀት
ክፍሏን አሟሟቃት። ሼክ አብዱላሂ ጥምጥሙን እንደጠመጠመ ነው።
መልኩ የቀይ ዳማ ሆኖ ከቁመቱ አጠር ያለውና ፊቱ በፂም የተወረ ረው አብዱላሂ ጫቱ የተጠቀለለበትን የእንሰት ቅጠል ፈታና ዘርዘር... ዘርዘር ካደረገው በኋላ መልሶ ፍራሹ ላይ አስቀመጠው። ከዚያም ዐይኖቹን ጫቱ ላይ በትኩረት አሳረፋቸው።ጌትነት በፀጥታ ተውጦ እጆቹንም እግሮቹንም ልክ እንደ ሼክ አብዱላሂ አጣምሮ አይን አይኑን ያስተ
ውለዋል። አብዱላሂ በላቦራቶሪው ውስጥ ምርምር የሚያካሂድ ሳይንቲስት ሲመስል ጌትነት ደግሞ ዕድሉን በሼክ አብዱላሂ ላቦራቶሪ ውስጥ አስመርምሮ የይለፍ ካርድ ውጤቱን የሚጠባበቅ ተስፈኛ መስሏል።በደስታና በጭንቀት መካከል ተውጧል። ጭንቀቱ ምናልባት ዕድሉን ካላገኘሁ ከሚል ስጋት የመነጨ ሲሆን ደስታው ደግሞ ሲመኘው የቆየው
የስራ ጉጉቱ የሚሳካበት ጊዜ እየተቃረበ ከመምጣቱ የተነሳ ነው፡፡ደስታው
እውን ደስታ ካልሆነ የሚደርስበት የሞራል ውድቀት ከወዲሁ ሲታስበው ደግሞ ጭንቅ ይለውና ስሜቱ ለሁለት ይከፈላል። ይሄንን ጭንቀቱን በማስወገድ በደስታና በተስፋ ስሜት እስከ መጨረሻው ለመዝለቅ ሼክ አብዱላሂን እንደ ጥሩ አማላጅ ቆጥሮት የሱን ፀሎት የሱን ምርቃት ለመስማት በጉጉት እየተጠባበቀ ነው።አብዱላሂ ጫቱን በትኩረት እየተመለከተ በውስጡ ሲያነበንብ ከቆየ በኋላ “እህህ...!” አለና ጉሮሮውን ላለ፡፡ በዚህ ጊዜ ጌትነት ከመቀመጫው ነቅነቅ አለ፡፡ ከዚያም ሼክ አብዱላሂ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በአድናቆትና በጉጉት ተውጦ ይመለከት
ጀመር፡፡ ፈገግ...አለ ሼክ አብዱላሂ። ጌትነትም የሱን ተከትሎ ጥርሶቹን
ብልጭ... አደረገ፡፡
“ሀጃህ የሞላ ነው! ወላሂ ቢላሂ! ገድህ ቀና ሆኗል!
ጌነት አላህ ምኞትህን አሳክቶታል! ይሄ ተስፋ ያለምክንያት አልመጣም፡፡ አላህ የልብህን መሻትና የቤተሰብህን ችግር አይቶ የፈቀደው ስለሆነ ካንተ የሚያልፍ
አይደለም!አብሽር!” ተስፋ በተስፋ አደረገውና ለስለስ ለስለስ ያለውን ጫት
መርጦ ካወጣ በኋላ በቀኝ እጁ ይዞ ከግራ መዳፉ ላይ ቸብ..ቸብ..በማድረግ እጁን ዘረጋለት። ጌትነትም ሰዎች ሲያደርጉ ያየውን አደረገ፡፡ ጫቱን
የያዙትን የአብዱላሂ እጆች በአክብሮትና በፍቅር ከጫቱ ጋር አንድ ላይ
ጭብጥ አድርጎ ስሞና ተሳልሞ ጫቱን ተቀበለ።
ከአብዱላሂ የተሰጠው ጫት በልቡ ውስጥ የሚጉላላውን ምኞቱን ለማሳካ
ትና ጭንቀቱን ለማስወገድ የተቀመመ የፈውስ መድሃኒት እንደሆነ ሁሉ ያንን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አፉ የሚያስጠጋውን ጫት በልዩ ስሜት
ተውጦ ቀንበጥ ቀንበጡን እየቀነጠስ በደስታ ሲያላምጠው ያየ ሰው
ጀማሪ ጫት ቃሚነቱን ሳይሆን ረሃቡን ለማስታገስ ጥሬ ጎመን የሚያኝክ
ረሃብተኛነቱን በፍጥነት ሊመሰክር ይችላል።

የበርጫው ስነ ስርአት ቀጠለ። የጌትነት ልብ ድቤውን እየደለቀ ከትልቁ ቴፕ ቀስ ብሎ ከሚንቆረቆረው የመንዙማ ድቤ ድምጽ ጋር ተቀናጅቶ ዝየራው ጦፈ። የኣብዱላሂን የዝየራ ስልት እየተከተለ ኣብዱላሂ ግራና ቀኝ ሲናጥ እሱም አብሮ ግራና ቀኝ እየተናጠ ለፈጣሪያቸው አቀነቀኑ።
በስሜት ከነፉ..በጫት መረቀኑ ጌትነት በደስታ ሰከረ። ተስፋው ተስፋን
ወልዶ በሀሳብ በረረ...አብዱላሂ ሲመረቅን ላብ ይበዛበታል።በተለይ ዛሬ የባለጉዳዩን የጌትነትን ችግር ላአላህ አስረድቶ መፍትሄ የሚያስገኝበት እለት በመሆኑ ስራ በዝቶበት ምርቃናው ከበድ ያለ ነበር፡፡ከመንዙማው ጋር ድምፁን ከፍ!አድርጉ “ያ ነቢ! ያ ረሱላ ነቢ! ሆይ !ሆይ!ሆይ!” እያለ በየመሀሉ ይጮህ
ነበር፡፡ ጌትነት በዚያች የዕድሉ በር መክፈቻ እንደሆነች ሙሉ እምነት
በጣለባት ማስታወቂያ ላይ ቀልቡን ጥሏል። አብዱላሂም ዱአ አድርጉለት ዕድሉን የሚነጥቀው ማንም እንደሌለ አረጋግጦለታል። ከዚህ በኋላ
መጠነኛ ደመወዝ እያገኘ ቀን ቀን ሥራውን እየሰራ ማታ ማታ ደግሞ
ዩኒቨርሲቲ ገብቶ እየተማረ ራሱን በእውቀትም ሆነ በኑሮ ሲያሻሽል
እነኝያ ከሱ ሌላ መመኪያ የሌላቸው በየእርሻው ላይ እየወደቁና እየተነሱ
አፈር መስለው አፈር ለብሰው ኑሮን የሚታገሉ እናትና እህቱን ሊታደጋቸው በሃሳቡ እየታየው በውኑ መቃዠት፣ የህልም እንጀራ መብላት ጀምሯል። ከቀረቡት ተወዳዳሪዎች መካከል ለፅሁፍ ፈተና የተጠሩት ስድስት ብቻ ሲሆኑ ጌትነት ሲጨነቅበት የከረመው የፅሁፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀኑ ደረሰና ወደመፈተኛ ክፍል ገቡ። ሁለት ሰዓት የፈጀውን ፈተና ጨርሰው ከወጡ በኋላ ውጤት የሚገለፅበት ቀን ይነገራችኋል
👍2
ጠብቁ ተባሉና ሁሉም በጉጉት መጠባበቅ ጀመሩ።

“በጣም ቀላል ፈተና ነው! እኔ በበኩሌ እንደዚህ ያለ ኤለመንተሪ ፈተና
ይመጣል ብዬ አልገመትኩም ነበር”

መልኳ እንደ ኮከብ የሚያበራው
ፀሀይ ነበረች፡፡

“ቻሌንጅ የሚያደርግ ጥያቄ ነው ምኑ ነው ኤለመንተሪ?” ከጌትነት አጠገብ የነበረው ስይፉ ተቃወማት።

“ምኑ ነው ቻሌንጅ የሚያደርገው በናትህ? ስንቱን ፈተና ባየንበት! አሁን ይሄ ፈተና ከባድ የሚባል ነው? እኔ በበኩሌ በጣም ቀላል ሆኖ ነው ያገኘሁት” የጎድን ተመለከተችው፡፡

“ስንትና ስንት ፈተና መውሰዱ አይደለም እኮ ቁም ነገሩ እትዬ ፀሀይ!
ቁም ነገሩ ተፈትኖ ማለፉ ላይ ነው!” እሱም ወደ ጐን አያትና አሽሟጠጣት፡፡ ከፀሃይ አጠገብ የነበረችው ሌላዋ ተፈታኝ መስከረም አስተያየት ከመስጠት ተቆጠበች። የጌትነት አቋም ከመስከረም ጋር ተመሳሳይነት ነበረው። ሳምሶን ግን በፀሃይ ኣነጋገር በሽቆ ነበረና ከት ብሎ በመሳቅ ለሰይፉ ድጋፉን ገለፀለት፡፡

“አቦ ተዉና! ቀለለም ከበደም፣አረረም መረረም የሚያልፈው አንድ ሰው
ብቻ ነው! የዘመድ ስራ እስካልተጨመረበት ድረስ ጥሩ የስራ ማለፉ ላይቀር ምን ያነታርከናል?!” ሌላው ተፈታኝ ዳንኤል አትጨቅጭቁን አስ
ተያየቱን ስንዝሮ ፈንጠር አለ፡፡ በዚሁ መሃል ሳምሶን የፀሃይ በራስ የመተማመን ስሜት ከምን እንደመነጨ ለማወቅ ፈለገና የማትሪክ ውጤቱን አውጥቶ አሳያት። በሶስት የትምህርት አይነቶች 'ሲ እና በሁለት የትምህርት አይነቶች ደግሞ 'ዲ' አለው፡፡
ፀሃይ ያንን ውጤት ስታይ አላባት። እየተፈታተናት መሆኑ ገባት። እሷ
በአምስቱም የትምህርት አይነቶች 'ዲ'ነበር ያገኘችው።ውጤቷ በሙሉ
'ዲ' መሆኑን ባየችበት እለት ወይ ለዲግሪ ወይንም ደግሞ ለዲፕሎማ አልፈሻል የተባለች መስሏት የምትገባበትን ኮሌጅ ማማረጥ ጀምራ ነበር። ያገኘችው ውጤት ግን በአጥሩ ላይ ዘላ ካልሆነ በስተቀር በኮሌጁ በር ሊያስገባት የማይችል ዝቅተኛ ውጤት መሆኑን ጓደኞቿ አረጋግተው ሲያስረዷት አርፋ ተቀመጠች። ፀሀይ ማትሪክን ሶስት ጊዜ የወሰደች ቢሆንም ውጤቷ ለውጥ ሊያሳይ አልቻለም፡፡ በዚህ የተነሳ ውጤቷን ለማንም አሳይታ አታውቅም ነበር፡፡ ሳምሶን የፈለገው በእልህ ውጤቷን እንድታሳየው ቢሆንም ሳታደርገው ቀረች፡፡ ጭራሽ ማብሽቋን ቀጠለች።

“ወደ ፈተና አታግባን ከክፉ አድነን ነው እንጂ አንዴ ወደ ፈተና ከገባን ደግሞላችሁ እንኳንስ ስው ያዘጋጀውን የእግዜር ፈተናም ቢሆን ይታለፋል ስትል አከለች። እነሱ ሲነታረኩ ጌትነት አንዳቸውንም ከሙሉ ልቡ እያዳመጣቸው አልነበረም፡፡ ከገባበት ሰመመን በድንገት ነቃና “ውጤቱ መቼይሆን የሚገለፀው?” ሲል ጠየቀ፡፡ውጤቱ የሚገለፅበት ቀን ይነገርሀል ተብሎ እየጠበቀ መልሶ ከተፈታኞቹ አንደበት ሊሰማ እንደ አዲስ ጥያቄ ሲያቀርብላቸው ፀሃይቱ አላሳፈረችውም፡፡ መልስ ሰጠችው።
“አሁን ያወጡታል! ግፋ ቢል ሁለትና ሶስት ቀን ቢያቆዩት ነው!” ሁኔታዋን ያየ የፈታኝ ኮሚቴው አባል እንጂ ተፈታኝ ነች ብሎ ለማመን ይቸገር ነበር፡፡ በዚያው ቀጠለች “ከሁሉ የበለጠ ያስደስተኝ ስራው ቢዝነስ
መሆኑና የኔ ኢንትረስት ደግሞ ቢዝነስ መሆኑ ነው! በዚህ ላይ ደግሞ
መስሪያ ቤቱ ለሰፈሬ በጣም ቅርብ ነው:: ቀንቶኝ ካለፍኩ መቼም ለኔ
ድርብ ድል ነው”
“ዋ! እቴ!...”አለ ጌትነት በልቡ። ፀህይስ ዝንባሌዋ ቢዝነስ በመሆኑና መስሪያ ቤቱ ለሰፈሯ ቅርብ ስለሆነ ነው፡፡ ምናልባትም ይህንን ስራ ለማግኘት በታክሲ ሁለት ቀበሌ አቋርጣ ሊሆን ይችላል። እሱ ግን ከባሌ ድረስአገርም አቋርጦ ነው የመጣው፡፡ በዚህ ላይ ለሱ ያ የስራ ዕድል የህልውና ጉዳይ ነው። የመኖር ወይንም ያለመኖር ጉዳይ። ካልተሳካለት ትዕግስቱ
ተሟጦ ወደ ባሌ ተመልሶ ሲገሰግስ በሀሳቡ ታየው፡ተፈታኞቹ በተረብ
ሲጠዛጠዙ አረፈዱና ውጤቱ የሚገለፅበት ቀን ከተነገራቸው በኋላ የመ
ስሪያ ቤቱን ግቢ ለቀው ወጡ፡፡ ሌሎቹ ትራንስፖርት ለመያዝ ወደ ኋላ
ሲቀሩ ጌትነት እንደተለመደው በእግሩ ያስነካው ጀመር፡፡ የፅሁፍ ፈተናውን በወሰዱ በሶስተኛ ቀኑ ፀሃይ እንዳለችው ውጤቱ በማስታወቂያ
ሰሌዳ ላይ ተለጠፈ፡፡

ጌትነት መኩሪያ.
90%
ፀሀይ አስፋው
80%
ሰይፉ አበራ
65%
“ከላይ የስም ዝርዝራችሁ የተጠቀሰው ተወዳዳሪዎች ለፅሁፍ ፈተና ቀር
ባችሁ በስማችሁ አንፃር የተገለፀውን ውጤት ያገኛችሁ ስለሆነ ለቃለ
መጠይቅ ፈተና ረቡዕ ከጧቱ ሶስት ሰዓት ተኩል አስተዳደር ክፍል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናስታውቃለን' ይላል። ጌትነት ባላሰበው
መንገድ በተፈጠረ ችግር ቶሎሳ እንደተቀየመው ሁሉ ከአብዱላሂ ጋርም
ሳይቀያየሙ ቀንቶት በፍቅር የሚለያዩበት ቀን ናፍቆታል። የማትሪክ ውጤቱ ከፍተኛ ደስታን አጐናፅፎት ያለፈ ቢሆንም ደስታው ዘላቂና ሙሉ የሚሆነው የሰው እጅ ከመጠበቅ ተገላግሎ በራሱ ላብ በራሱ ወዝ ሰርቶ ለመኖር የስራ ዕድል በሯን ስትከፍትለት ብቻ ነው። በዚሁ
መሰረት ያንን የመጨረሻውን ውጤት ሊመለከት በጠዋቱ ተነስቶ ካዛንቺስ አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ቀጣሪው መስሪያ ቤት ሄደ።
ከመቸኮሉ የተነሳ ሠራተኞች ሳይገቡ ነበር የደረሰው። እዚያ መስሪያ ቤቱ
አካባቢ ወዲያና ወዲህ ሲንከላወስ ከቆየ በኋላ ውጤቱን ሊመለከት ወደ
መስሪያ ቤቱ መጣ፡፡ ተፈትሾ የግቢውን በር እንደዘለቀ አቅርቦ የሚያሳይ
መነጽር ያደረገ ይመስል ዐይኖቹ በርቀት ከሚታየው የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ አነጣጠሩ...ወደ ሰሌዳው እየተቃረበ ሲመጣ ደግሞ ፈራ። ከሰሌዳው
ላይ ተናዳፊ እባብ ያለበት ይመስል ልቡ ድው! ድው!.. አለበት።
እንደምንም ብሉ ተጠጋ፡፡ ዐይኖቹን ማመን አቃተው። ደጋግሞ አስተዋ
ለው፡፡ በትክክል የሱ ስም ነው። ተጠራጠረ። ዐይኖቹን አሻሸ፡፡ ልክ ነው!
አልተሳሳተም ውጤቱን ተመለከተው። የፅሁፉ ቀለም እስከሚለቅ ድረስ
ደጋግሞ አነበበው።
“እፎይ ተመስገን ፈጣሪዩ” በረጅሙ ተነፈስ፡፡ 'ለመጨረሻው ድል ግማሹ መንገድ ተጠናቀቅ እለ በልቡ። “
አዎን እግዚአብሄር ያውቃል!
የቃለ መጠይቁን ፈተናም እንደዚሁ ከቀናኝ ሃሳቤ ተሳካ ማለት ነው፡፡ በዚሁ በቃህ ሊለኝ ነው መሰለኝ? አቤት አምላኬ! የዚያች የሚስኪን እናቴ አምላክ አንተ እርዳኝ” በልቡ ትንሽ ፀሎት ቢጤ አደረሰ፡፡.....


ይቀጥላል
👍1👏1
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል



...የካቲት ነበር፣ የመጀመሪያዉ እሑድ። ከዚያ ቀደም እንደማደርገው ልዩ ልዩ ነገሮች ይዤላት ወህኒ ቤት ሄድኩ። የወዲያነሽን ለማስጠራት ዐይኔ
እየዋተተ ጠሪ ስፈልግ ከስድስት ዓመታት በፊት በነበራት የፈገግታ ዐይነት ፊቷ
ፈክቶ ሣቅ ሣቅ እያለች «አንተ ጌታነህ! » ብላ ጠራችኝ፡፡ የአሁኑ ፈገግታዋ
ከቀድሞው የሚለየው ፊቷ ከሲታ ሆኖ በመገርጣቱ ብቻ ነው፡፡ ለምን ከአንጀቷ
ፈገግ እንዳለች የምከንያቱ መነሾ ጠፋኝ፡፡ ለወትሮው የወዲያነሽን የማገኛት
እያስጠራሁ ነበር፡፡ የዚያን ዕለት ግን ቀደም ብላ መጥታ ስትጠብቀኝ በመድረሴ ለውጡ ግራ ገባኝ፡፡

ምንም እንኳን ፈገግታዋና ሣቋ ደስ ቢያሰኘኝም ለጊዜው ደስታዬን አምቄ «ደኅና ነሽ ወይ? ደኅና ሰነበትሽ ወይ?» አልኳት። የደስታ ሲቃ እየተናነቃት አይታ የማትጠግበኝ ይመስል ዓይኖቿ ቃበዙ፡፡ አጥሩን ዘላ የምትወጣ መሰለች፡፡

አጥሩ ግን የሥቃይ ሕግ ግድግዳ እንጂ ተራ እንጨት አልነበረም፡፡አፏን ሁለትና ሦስት ጊዜ ከፍታ መልሳ ገጠመችው:: የወሰድኩላትን ጥቂት ዕቃና ምግብ በወታደሯ አማካይነት እንዲደርሳት አደረግሁ፡፡ በማስቀመጥ ፈንታ
ዐቅፋው ቆመች፡፡ የደነገጥን ይመስል
ዝም ተባባልን፡፡ የታቀፈችው ዕቃ
አምልጧት እግሯ ሥር ዱብ አለ፡፡ ተሰባሪ ነገር ስላልነበረበት አልደነገጥኩም፡፡
እዚያው እንዳለ ጎንበስ ብላ እግሮቿ መኻል አስገብታ እጣብቃ ይዛው ቆመች።
ባላት አካላዊ ሁኔታ ላይ ፈገግታዋ የመጨረሻውን ደረጃ ያዘ፡፡

«ጌታነህ» ብላ በዚያች ውብ የሴታ ሴት ድምጺ ከጠራችኝ በኋላ «ነገ ሮብ እኮ» ብላ ዝም እለች፡፡ ከበፊቱ በበለጠ ጥንቃቄ አቆብቁቤና አፍጥጬ
ተመለከትኳት። ዝግ ብላ ምራቋን ዋጠችና «ሮብ እኮሮብ እኮ ትለቀቂያለሽ'
ትፈቺያለሽ ተባልኩ» ብላ በዐይኖቿ ዙሪያ እንባ ከተረ፡፡ የሰማሁት ነገር እውነት
ስላልመሰለኝ ድንገተኛ የደስታ እና የድንጋጤ ሲቃ ያዘኝ፡፡ «ምን?! ምን
አልሽ?!» አልኩና ነፋስ እንዳስጎነበሳት ለጋ ቅርንጫፍ አንገቴን ወደፊት
አሰገግሁ።

«ሮብ ትለቀቂያለሽ ብለውኛል ነው የምልህ» ብላ ጥርሶቿን እንደ ፈለቀቀች ከነፈገግታዋ ዝም አለች፡፡ ዘልዬ በአንገቷ ዙሪያ እንዳልጠመጠምባትና ጮቤ እየዘለልሁ ደስታዬን እንዳልገልጽ በመካከላችን የተጋረጠው ዐፅሙ የገጠጠ አጥር የመከራ ገረገራ ሆኖ አገደኝ፡፡ የምይዝ የምጨብጠው ጠፋኝ። የደስታ ዕብደት አበድኩ፡፡ አዲስ የሕይወት ብርሃን ፏ አለ፡፡ የሰማይን ሰማያዊ ውብ ጣራ አንጋጥጬ ተመለከትኩ፡፡ በውብ የመስክ አበቦች መካከል እየተዘዋወረች ያሻትን አበባ እንደምትቀስም ንብ ሕሊናዬ ባስፈለጋት የደስታ ዐይነት መካከል
እያማረጠች ቦረቀች።

አምስቱ የሥቃይ ዓመታት እንደ አንድ ረዘም ያለ አስፈሪና አስደንጋጭ ሕልም አለፉ። የደስታ ዘለላዎች እየተሸመጠጡ የሚታደለ ተጨባጭ ነገሮች ቢሆኑ ኖሮ በዚያች ሰዓት ውስጥ ለአያሌ ሰዎች እተርፍ ነበር። በደስታ የሚንከባለሉትንና ብዙ ነገር ለማየት የጓጉትን ዐይኖቿን እየተመለከትኩ በይ እንግዲህ መሔዴ ነው፣ ለጉልላትም ልንገረው:: ሮብ ጧት ከሁለት ሰዓት ጀምሮ ካጥር ውጪ እጠብቅሻለሁ» አልኳት፡፡

«ሮብ ዕለት መጥተህ ወዴት ትወስደኛለህ? ከእንግዲህ ወዲያ ደግሞ
አንተን ላስቸግር ነው?» ብላ ተከዘች፡፡
የማያወላውል ዓላማና ግቤን ስለማውቅ በጊዜያዊ ትካዜዋ አልተበሳጨሁም፡፡
ለ ሮብ ዕለተ ጉዳይ የማውቅው እኔ ነኝ፡፡ ጉዳዩን ሁሉ ለእኔ ተይው:: አሁን ግን
ደኅና ዋይ! እንደ ልቤ ልፈንድቅበት!» ብያት ለመጀመሪያ ጊዜ በርግጠኛ ተስፋ
ተሰናብቻት መንገድ ገባሁ፡፡

ከዕለቱ የደስታ ማሕበል የተወለዱ አስደሳች ትርዒቶች በአንጎሌ ውስጥ
እያሸበሸቡ በመደዳ ከነፉ::

ወዲያ ወዲህ ሳልል በቀጥታ ወደ ጉልላት ቤት አመራሁ። የተሣፈርኩባት መኪና በጣም ያዘገመች ስለ መሰለኝ «ቶሎ ቶሎ በል ጃል» እያልኩ በተደጋጋሚ ወተወትኩ፡፡

ጉልላት «መቼ አነሱኝና · ይበቁኛል፣ ከብዙ ደረቅ ጥቂት ርጥብ ይበልጣል» የሚላቸውን የግቢውን አባቦችና አትክልቶች ዐልፌ ወደ ቤት ገባሁ።

እንግዳ መቀበያ ክፍላቸው ውስጥ ጉልላትና እናቱ ወይዘሮ አማከለች ጐን
ለጐን ተቀምጠው ሲያወሩ ደረስኩ፡፡ እንዴት ሰላምታ ሰጥቻቸው እንደ
ተቀመጥኩ አላስታውስም፡፡ ከእናትዬው ጋር ያደረግሁት «የእንደምን ሰነበቱ?
ሰላምታ በምን አኳኋን እንደ ተፈጸመች ሃች አምና የታየ ሕልምን ያህል እንኳ
አትታወሰኝም፡፡

«ጌታነህ» አሉ ከተቀመጡበት እየተነሡ «እስኪ አሁን ደግሞ ያንተ ተራ ይሁን ተጫወቱ » ብለው ወደ ውጪ ወጡ። እንዴት ብዬ እንደምጀምር ስለጰ ጠፋኝ ሁለት ጊዜ ሀይኔን ጨፈንኩ፡፡ አልከሠትልህ ስላለኝ ድንገት ተነሣሁ።

ጸጉሬን ካወዲያ ወዲህ አሽቼ መነጨርኩት፡፡ የፍርሃቴ ሸክም ከጭንቅላቴ ላይ ዘጭ ብሎ የወደቀልኝ ይመስል የምሥራች ጉልላት!» አልኩት።

አንጋጦ ዐይን ዐይኔን እያዬ «ምሥር ብላ! ምን አገኘህ?» ብሎ ለመስማት ተጣደፈ። በሕይወቴ ውስጥ ትልቁ ደስታ ሊጀመር፣ ነባሩ የትግላችን ምዕራፍ የፊታችን ሮብ ሲዘጋ ሌላው ደግሞ ወዲያው ይከፈታል!» ብዬ እንደገና አዲስ ብርታት በመጨመር የፊታችን ሮብ የወዲያነሽ ትፈታለች!» አልኩት ጮክ ብዩ።

«እስኪ ሙት በለኝ!» ብሎ አንገቴ ላይ ተጠመጠመ። ለብዙ ዓመታት
እንደ ተለያዩ ጓደኛሞች ተሳሳምን፡፡ ጉልላት በደስታ ባሕር ውስጥ ተዘፍቆ
ውስጣዊ ስሜቱን በይፋ ገለጠ፡፡ ትከሻዩን ያዝ እንዳደረገ ግራና ቀኝ ተቀመጥን።
ፈገግታ በፊቱ ላይ እስክስ አለች። «አየህ እኔና አንተ ባለፈው ቅዳሜ የተሳሳትነው አንድ ነገር ነበር። እጅዋ ከተያዘበት ዕለት ጀምሮ የሚለውን የፍርድ ውሳኔ ዘንግተነዋል። የሰባት ወር ጊዜ ሲጠቃለል ሙሉ አምስት ዓመት
ይሆናል ማለት ነው» ካልኩ በኋላ ጣራ ግድግዳውን በጠቅላላ የቤቱን ዙሪያ
ተመለከትኩት፡፡ «እንግዲህ እኔ እንኳን ደስ ያለህ ነው ወይስ እንኳን ደስ ያለሽ
የምለው?» አለና በደስታ የፈዘዘ አእምሮዬን ለማንቃት ትከሻዬን ይዞ ነቀነቀኝ፡፡

«እኔን አይደለም እርሷን መሆን አለበት፡፡ የእኔማ ጉዳይ ገና ምኑ ተነካና! ገና ብዙ ፈተናና ተከታታይ ችግር ይጠብቀኛል። እሷንና ቤተሰቦቼን ለማገናኘት ወይም ዘላቂ መብትና የእኩልነት ሕልውናዋን ለማረጋገጥ ከመጪው ሮብ ጀምሮ አንድ ትልቅ ተጋድሎና ጦርነት እጀምራለሁ፡፡ የወዲያነሽ ሙሉ የሕሊና ነጻነት እስከምትጎናጸፍ ድረስ እታገላለሁ፡፡ በተመሳሳይ የሕሊና ባርነት ውስጥ የሚገኙ እልፍ አዕላፍ ሰዎች ስላሉ ብቻችንን አይደለንም፡፡ ያም ሆነ ይህ
ከወላጆቼ ጋር ያለኝ ግንኙነት ግን ከሮብ ጀምሮ ከዋናው ግንድ ላይ ተሰብራ
በልጧ ብቻ የተንጠለጠለች ቅርንጫፍ እምሳያ መሆኑ ነው» ብዬ መለስኩለት፡፡
በንግግሬ ውስጥ ያለውን የሐሳብ ይዘት እያሰላሰለ ጥቂት ዝም ስላለ «ብዙ ጊዜ
ቢፈጅም አንድ ቀን ድል እንደማደርግ አውቃለሁ፡፡ ይህን አስፈሪ መሳይ ያረጀ
አፍራሽ የልማድ ድልድይ እንዴት ኣድርጌ እንደማልፈውና እንደምሻገረው ካሁኑ
ጭንቅ ጥብብ ብሎኛል። የምፈራውና የሚያርበተብተኝ ምን እንደሆነ አሣምረህ
ታውቀዋለህ፡፡ ፍርሃቴ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ ግን የወዲያነሽን ለመከራ አሳልፈ መስጠቴ ነው» ብዪ እንደ ጨረስኩ ወደ ጉዳዩ ዝርዝር ክርክርና ፍሬ ነገር ገባን።

ያን ዕለት ከሰዓት በኋላ ወደ ዕጓለ ማውታ ሳልሄድ ቀረሁ። ከቤቱ ውስጥ ወበቅ ደጁ ይሻል ይሆናል በማለት ከቤት ከወጣን በኋላ ግራና ቀኝ ቆም እንዳልን
«እንግዲህ የወዲያነሽ ነገ ሮብ መፈታቷ ነው:: ከወህኒ ቤት እንደ ወጣች ከእኔ
ሌላ ምንም መግቢያና መጠጊያ የላትም፡፡ ስለዚህ ነገም ይሁን ከነገ ወዲያ ባፋጣኝ
👍2
ቤት ተከራይቼና ዕቃ ገዛዝቼ እቀበላታለሁ» ብዬ ሐሳቤ አልቋጠርና አልያያዝ ስላለኝ ያለ ውድ በግድ ዝም አልኩ

«ቤት መከራየትም ሆነ ዕቃ መግዛት ቀላል ነገር ነው:: ከባዱ ነገርስ ከዚያ በኋላ ከማን ጋር ታስቀምጣታለህ? ብቻዋን መቼም እንጃ?» ብሉ ድምፁን
ለጥያቄ አቀጠነ።

«ለጊዜው የምትገባበትና የምታርፍበት ካገኘችልኝ ሕይወቴ ከሕይወቷ
ተለይታ መኖር እንደማትችል አውቃለሁና የሚመጣውን ነገር ሁሉ እንዳመጣጡ
እየተቋቋምኩ ቀስ በቀስ ከወላጆቼ እለያያለሁ። ለእሷ የሚስማሙ ሁኔታዎችን እያመቻቸሁ ሰብአዊ ክብሯን በማይፃረርና በማይነካ ደረጃ ቀስ በቀስ ከቤተሰቦቼ እንድትቀላቀል በተገቢ ትሕትና ጥረት አደርጋለሁ፡፡ እነርሱ ግን
በአክብሮትና በፈቃደኝነት ካልተቀበሉኝ ከዚያ በኋላ የጠላቶቼ ያህል ናቸው::
አሁን ግን ጠግቦኛ ባልጎ ወጣ ነው ሌላ ምን ይለኝ መሰለህ? አንድ ቀን ከቤት
ውጪ፣ ሁለት ቀን ቤት ውስጥ፣ ሦስት ቀን መደዳውን ውጪ፣ እንደገና ደግሞ
አንድ ቀን ቤት ውስጥ ማደርና መቅረት ሁኔታውን ዝግ በዝግ ይለውጠዋል።
በማለት በሐሳቤ ርግጠኛ ሆኜ ተናገርኩ፡፡

ለጊዜው ይህን አስቸጋሪ የሆነ ጉዳይ፣ ይህ ቢሆን ማለፊያ ነው፣ እንዲያ
ከሆነ ደግሞ አያዛልቅም ለማለት በጣም አስቸጋሪ ስለነበር ከፊት ለፊቱ ያለውን
ደረቅ የበጋ ዐፈር እየተመለከተ ዝም ብሎ ቆመ፡፡ ጉልላት ለወትሮው ረዘም ላለ
ጊዜ ዝም ብሎ ከቆየ አንድ ቁም ነገር ያለበት ብልሃትና መወጣጫ ማቅረብ
እንደሚችል ስለማውቅ ከሐሳቡ ጋር በሚያደርገው ውይይት መኻል እጄን
መስደድ አልሞከርኩም፡፡

«ከሁሉ አስቀድሞ» አለ ጉልላት ዐይኑን ከዐፈሩ ላይ ነቅሉ ወደ እኔ መለስ ካደረገ በኋላ፣ የምንከራየው ቤት ከወላጆችህ ቤት በጣም ሩቅና ደባቃ፣ የማይታወቅ ቦታ መሆን ይኖርበታል፡፡ እሷን ለመቀበል የምናደርገው ማናቸውም ዝግጅት ነገና ከነገ ወዲያ ይጠቃለላል። አሁን በአንድ ነገር ደስ ተሠኝቻለሁ፡፡ ጊዜው መልካም አጋጣሚ ነው:: ላጎቴ ወኪል ሆኜ የማከራየው ቤት እንዳለ ታውቃለህ፣ ታውቅ የለ?» ብሎ መልሱን ለመስማት አየኝ::

«አዎን» አልኩት ባጭሩ፡፡ «በነጻ እንድትቀመጥ ልፈቅድልህ አልችልም»
አለና አባባሉ እንደ ገባኝ ለማሳወቅ ፈገግ ብሎ ሣቀ፡፡ የቤቱን ኪራይ በየወሩ
እየተቀበልኩ ባንክ ስለማስቀምጥ የጓደኝነት ርዳታዬ በሌላ በኩል ይቀርብልሃል።ባለ ሦስት ክፍል የሆነው ኣንደኛው ቤት ሳይከራይ ከሁለት ወር በላይ ሆኖታል፡፡ለአንተና ለየወዲያነሽ በቂ ነው:: ቤቱ የሚገኝበትን ሥፍራ ከዚህ ቀደም አይተኸዋል፡፡ ከእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ጀርባ ወደ መንገዱ ዳርቻ ጠጋ ያለ ነው። ቤቱ ተስማሚ የሚሆንበት አንድ ትልቅ ምክንያት አለ። ወላጆችህም ሆኑ እኅትህ ወደዚያ ሥፍራ በፍጹም ዝር አይሉም። ተስማሚ ርቀትም አለው» ብሎ
ትከሻዩን በግራ እጁ ያዝ አደረገና ካጥር ግቢው ወጥተን ሄድን።

ከሩብ ሰዓት በኋላ በእግርም በታክሲም ተጉዘን እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ጀርባ ከሚገኘው ቤት ደረስን፡፡ ቤቱንና ዙሪያውን የኑዛዜ ዕቃ ተረካቢ ይመስል እየተዘዋወርን ጎበኘነው:: የቦታው ደባቃነትም ተስማሚ እንደሚሆን
ተማመንኩ፡፡

በማግሥቱ ሰኞ ጠዋት ጉልላት ሠራተኛ ልኮ ቤቱን አስጠረገው። ከሰአት በኋላ ከሥራ ቀርተን ለጊዜው ዋጋቸው ረከስከስ ያለ ጠረጴዛና ወንበሮች፣
እንዲሁም አንዳንድ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ገዛንና በኪራይ መኪና ወስደን
አስገባነው፡፡

ማታውኑ ላይን ያዝ እንዳደረገ ጠፈፉ ላይ ቆመን ስናወራ ፊቴን ወደ ቤቴ” መለስ አደረግሁና በአንክሮ ተመለከትኩ፡፡ ልቢ እንደ በረዶ ቀዘቀዘች፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ቤቴ ብዬ የምጠራው ቤት በእንደዚያ ዐይነትና ሁናቴ
በመወጠኑና በመመሥረቱ አንጎሌ በጥቁር የሥቃይ ጉም ትሸፈነ። ከጓደኞቼ ጋር ስለ ትዳርና ስለ ጋብቻ እንመኝ በነበረበት ጊዜ የተመኘሁትና ይሆናል ብዩ
ያሰብኩት ሁሉ ዐመድ ላይ እንደ ተዘራ እህል ቢል ብል ብሉ በምኞት ማሳዩ ላይ
መድረቁ ታየኝ፡፡ የውድቀትና የብቸኝነት ክብደት ደቆሰኝ፡፡ የሕይወት ጠል ሳይሆን ረጂም የኑሮ ቦና ተዘርግቶ ታየኝ። ሆኖም የሰው ትልቁ ትግል ሕይወት
ያመጣችውን መቀበል ብቻ ሳይሆን መጥፎውን እየደመሰሱ ማስተካከልና ማሳደግ ነው” የሚለው ሐሳብም የትግል ተስፋ ሰጠኝ፡፡ 'ምኞት ተጨባጭ ፍሬ የሚሆነው በሥራ ነው” የሚለው ሌላ ሐሳብ ደግሞ ተደራቢ ሆኖ ቀረበ፡፡ ሕሊናዩ ዋዠቀ፡፡
"ጌታነህ” አልኩት ራሴን። 'ዛሬና ነገ እኮ በሕይወትህ የወንደላጤነትህ ቀናት
ናቸው:: ከነገ ወዲያ ግን ባለትዳር ነህ!” ብዪ እኔው ለእኔው ነገርኩት። አስፈሪና
እስደንጋጭ የኑሮ ወላፈን ከፊት ለፊቴ ሲተም ታየኝ፡፡ የተገዛው ዕቃ ሁሉ
መከራን ለመቀበልና ሥቃይን ለማስተናገድ የተዘጋጀ ትርኪ ምርኪ መሰለኝ፡፡

መለስ ብዩ ባሻገር የሚታዩን ባሕር ዛፎች እየተመለከትኩ "ምኞትና ተስፋ፣ ከፍና ዝቅ ምንድን ነው?” ብዬ ራሴን ጠየቅሁ፡፡ ልቦናዬ እንደ ኅዳር ጢ በመበታተኑ ለራሴ ጥያቄ መልስ አላገኘለትም፡፡ እኛ እዚያው እንደ ቆምን አንዲት አጠር ያሉ ወፍራም ሴት እሳት በገል ይዘው መጡ፡፡ መለስ ቀለስ እያሉ ጀበና፣ ስኒ፣ ማቶት፣ ረከቦትና ሌላም የቡና ዕቃ ይዘው ገቡ፡፡ ቆየት ብሎ ከቤት ውስጥ ቀጭን ስስ ጢስ በመስኮትም በበርም ወጣ፡፡

'የእኔ ቤት' እያልኩ በማስብበት ጊዜ ሁሉ መነሻውን ባልደረስኩበት ሁናቴ ልቤ ክፍል ማለት አበዛች፡፡ የሚያስጨንቀኝም ፍርሃት 'ቤቴ' በምልበት ደቂቃ ሁሉ ደነደነ። «ቡናው ተፈልቶ እስከሚወርድ ድረስ እመለሳለሁ፣ አሁን መጣሁ» ብሎ ጉልላት ጥሎኝ ሔደ፡፡ እኔም ወደ ቤት ገባሁ፡፡

ከሴትዮዋ ጋር ምንና ስለምን እንደማወራ ግራ ስለ ገባኝ አዲሱ ወንበር ላይ ተቀምጩ በዚያው በጀመርኩት ሐሳብ መመላለስ ቀጠልኩ፡፡ የቤቱ ውስጥ
አየር ከተቆላው በና በተገኘው ሽታና ከከሰሉ በወጣው ሙቀት አዲስ መዓዛ
አዘለ። ሲኒውን ካጣጠቡ በኋላ ወጣ ብለው ጊርጊራና ሳሀን ይዘው ተመለሱ።
እሳቸው በሥራ፣ እኔ በሐሳብ ስንንጎዳጎድ ጥቂት ደቂቃዎች ያለፉ። እንዴት
እንዳፈጠነው አላውቅም ጉልላት አንድ ትልቅ የነፋስ ሬዲዮ ይዞ መጣ። ቁጭ
ከማለቱ ዕጣኑን አጪሰው ቡና ቀዱ፡፡ ሚጥሚጣ በተን አድርገው ያመጧትን
የቡና ቁርስ ከፊታችን አስቀመጧት፡፡ ጉልላት ከቆራረሳት በኋላ እንደ ነገሩ
ተቃመስናት። ዐልፎ ዐልፎ ወሬ ተወራ፡፡ ቤቱን እንደተርበኞች ባናደምቀውም
ቡናው ተከተመ። ቤቱ የሥቃይ አዳራሽ መሰለኝ፡፡ ከጣራው ላይ ረመጥ የሚፈስ
ይመስል አካላቴ ብው ብሎ ጋለ፡፡ የገሃነምን የሞከርኩት ይመስል የገሃነም ኣካል እያልኩ ውስጥ ውስጡን ተነጫነጭኩ፡፡ ሴትዮዋ ያመጡትን የቡና ዕቃ ሁሉ ወደ ዕቃ ቤት ከወሰዱ በኋላ «ደኅና እደሩ» ብለው ሔዱ።

ራቅ ወዳለ ስፍራ ሄደን ራት በላን። ያሉትን ይበሉ ብዬ በዛ ስልጣኔ ከወላጆቼ ቤት ወጥቼ ሳድር የመጀመሪያ ጊዜዪ ነበር። «እናትህ የት ጠፋ ብለው እንዳይጨነቀ ብትሔድ ይሻላል፡፡» አልኩት ጉልላትን፡፡ «ራዲዮ ይዤ ስመጣ እንደማልመለስ ነግሬያታለሁ፡፡ እኔ እኮ እንዳንተ አይደለሁም፣ አስለምጃለሁ»
ብሎ እየሣቀ መለሰልኝ፡

አዲሱ አልጋ ላይ ባንድ ላይ አደርን፡፡ አሠቃቂ ትንቢት የተነገረኝ ይመስል ነገንና ከነገወዲያን በጠቅላላው መጪውን ጊዜ ፈራሁት በትላንትና መሠረትነት ዛሬ ላይ ቆሜ የነገን ዘላቂ ዕቅድ የምገነባ በመሆኔ ወደ ፊት ወይስ ወደ ኋላ ወዴት ማየት እንደሚገባኝ ዛሬ ላይ ቆሜ ተቸገርኩ፡፡ ሌላው ቀርቶ የአንዲት ቅፅበት ሙሉ ሰው እንኳ መሆን አቃተኝ ሕይወት ማለት በኑሮ እየቃተቱ መኖር ይሆን? ባላሰብኩት ቀንና ሰዓት በድንገተኛ ዝግጅትና ጥድፊያ ከቤተሰቦቼ ተለይቼ ለማደርና ለመኖር በመውጣቴ ወደ ወላጆቼ ቤት በትዝታ
👍3
ተመለስኩ፡፡ ሁኔታዎችን ቀስ በቀስ መቆጣጠርና መለማመድ የሰው የመኖር ግዴታ ሆነና ከየአቅጣጫው የፈለቀውን አስፈሪ የሐሳብ ድርጊት ተቋቋምኩት።

ማክሰኞ ዕለት ማታ ከሥራ መልስ ከበድበድ እንዳለ ወደ አዲሱ ቤት
ገብቼ መብራት እበራሁ፡፡ በኦና ቤት ውስጥ ብቻውን እንደሚንቆራጠጥ ዕብድ
ትንሽ ከተንቆራጠጥኩ በኋላ ለማታ ትምህርት ቸኩዬ ስለ ነበር ሰበብ ሆኖኝ
ወጣሁ፡፡ ማታ ወደ ቤት ስመለስ የመንገዱና የመንደሩ ጨለማ ጥቂት ኣወካኝ፡፡ብቸኝነት ተሰማኝ። ከፊት ለፊቴ በሥውር ተጋርጦ የሚተናኮለኝን የሥጋት ኣካል ለማውደም የምችልበት ወኔና ድፍረት በየደቂቃው ቸገረኝ፡፡

ሕይወት ማለት የሥቃይና የፈተና አውድማ ማለት ናትን?» እያልኩ
ናጅ የሆነውን ገጽታ ማየት አበዛሁ፡፡ በዚህ ፀጥ ባለ ቤት ውስጥ የዝምታ ባሕር
ብቻ በመንጣለሉ ከፀጥታው ውስጥ የሚነሣው የብቸኝነት ማዕበል አንገላታኝ፡፡
ጠረጴዛው ልብስ ላይ ያሉት የአበባ ሥዕሎች የማቀቀች ውበት እንኳ
ሊያቀርቡልኝ አልቻሉም፡፡ ቀስ በቀስ ሐሳቤ ሦስት ላይ ተከፈለ። አንዱ ወደ ዕጓለ ማውታ ሲጓዝ፣ ሌላው ወደ ወህኒ ቤት ወረደ። ሦስተኛው የእኔው ልዩ መሪር
ድርሻ በውስጤ አደፈጠ። አንድ አንገቱን የደፋ ሕሊና በሚገባ ቀና ብሉ የኑሮን
ትክክለኛ ትግል እንዲቋቋም የበሰለ ጠንካራ ወኔ ያስፈልጋል፡፡

ኮት ኪሴ ውስጥ የዋለች አንዲት «ታዳጊ ፍልስፍና የምትል መጽሐፍ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ሁለት አጫጭር ምዕራፎች እንዳነበብኩ በሦስተኛው ምዕራፍ
መግቢያ ላይ ማናቸውም ደስታ የተመሠረተው ለራስ ከሚገኝ ይልቅ ለሌላ ሊደረግ ወይም ሊበረከት የሚችል ጉዳይ ነው ብሎ በትእምርተ ጥቅስ
በመጀመር ሰፊ ሐተታ በመቀጠሉ ከጥቅሱ ላይ ባገኘሁት ሐሳብ ረክቼ ከቤት ወጣሁ፡፡ በጠራው የምሽት ሰማይ ላይ ከዋክብት እየተንተገተጉ ውበታማ ብርሃን ያንዥቀዥቃሉ፡፡ ድምቀት፣ ፍዘት፣ ቅርበት ርቀት፣ ሁኔታዎችን ለያይቷቸዋል::
አንጸባራቂና ኅብራዊ ውበታቸው ግን አለት ላይ እንዳረፈች አለሎ ተንከባልሉ
ወጣ እንጃ በሶ ላይ እንዳረፈ ቅቤ ወደ ውስጤ አልሠረፀም፡፡

ባሻገር ያሉት የባሕር ዛፎች በጨለማ ግርማ ተውጠው በለዘበች የበጋ ነፋስ እየተወዛወዙ ያንጎላጃሉ፡፡ ሁኔታው ከአባቴ ጭሰኞች አንዱ ስለ ኑሮና
ሕይወት ያለውን አስታወሰኝ፡፡ «ጌቶች! የእኛ ኑሮ እኮ ጨለማ ነው ኑሮዋችን
ኑሮ አይምሰልዎት» ብሎ በመናገሩ ብቻ በከዘራ ተደብድቦ የተነቀለው ጭሰኛ
ትዝ አለኝ።

ፊቴን መለስ ኣድርጌ በተከፈተው በር በኩል ባዶውን ቤት ለደቂቃ ያህል አየሁት፡፡ ወንበሮቹ ለሙታን የተደረደሩ ስለመሰለኝ ቶሉ ዞርኩ። አባቴ
«ወኔው የተገፈፈ ትውልድ» የሚለው እንዲህ ዓይነቱን የመንፈስ ረብሻ ውጤት
ይሆን? መነሻ ሓሳብና እምነቱ ይህ ከሆነ ይህን ትውልድ የፈጠረው ትውልድስ
ምን ሊባልለት ነው? አእምሮዬ ውስጥ ከሚተራመሱት አያሌ ቃላት መኻል
ሁለቱ ብቻ አፈተለኩ። «የሕይወት ጥቀርሻ» ብዬ ዝም አልኩ። ለምን እንደሆነ በግልጽ ባላውቅም ባፈተለኩት ቃላት ተደሰትኩ፡፡ ጥቂት ቆየት ብሎ ግን
ያፈተለኩት ቃላት ነፋስ እንዳውለበለባት የጧፍ ብርሃን ተዋከቡ። «አንድ ቀን
ከእውነት ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተን የምንተያይበትና ትክክለኛ ፍርዷን
የምቀበልበት ጊዜ የግድ መምጣት አለበት» ብዬ ለሐሳቤ ብርታትና ድጋፍ
ለመስጠት ወደፊት ተራመድኩ፡፡

በሕይወቴ ከዚያች ምሽት በፊት እንደዚያ ያለ የአእምሮ ነውፅ አጋጥሞኝ
ስለማያውቅ ራሴን የምከላከልበት የምክንያት ምሽግ አጣሁ፡፡ በሐሳቤ ቤተሰቦቼ ጋር ክርክርና ንትርክ ይዤ ሽብ ረብ ስል ጉልላት እጠቤ ደርሶ ቆመ። «ኦ!
የሕይወት ጥቀርሻ! » ብዬ ባነንኩ። በቀኝ እጁ ዕቃ ይዞ ስለ ነበር ከእፍ ሰላምታ
በስተቀር አልተጨባበጥንም፡፡ አእምሮዬ ውስጥ የተንጎዳጎደ ይመስል፤ ሁኔታዩን
አውቆታል፡፡

«የጉልበት ማባከኛ በሆነ ሐሳብና ጭንቀት ራስን ከማደንዘዝ ይልቅ ትንሽ ጠቃሚ ተጨባጭ ነገር መሥራት ይበልጣል፡፡ ይልቅስ ግባ!» ብሎኝ ወደ
ቤት ገባ፡፡

የጉልላት ምክሩ እንደሚያስደስተኝ ሁሉ ተግሣጹም ፈውሴ በመሆኑ ቃሉን አክብሬ ተከተልኩት፡፡ ሞቅ ያለ ለዛማ ክርክርና ጨዋታ የነበረበት የደስታ ሌሊት አሳለፍን፡፡


💫ይቀጥላል💫
👍3
#እንዲኽ_ቀላል_ኖሯል ?!

አፈኛ ማንነት ፣ ቋትን እየሞላ
ደም ያፋስሰናል ፤
ከላይና ከታች ፣ ባልሰላ ቢላዋ
ጥርስ ያሳብረናል ፤
መደብ ዐበጅቶ ፣ ባደለበው ሰንጋ
በካራ ይገፋል ፤
ከየዐይነቱ ሥጋ ፣ ብልት ለመጣጣል
ስያሜ ይጽፋል።

ቅርጫ ተቃራጩ . .
ቅርጫት ልኬት ኾኖት ፣ በፍሬ አልባ ቅርጫ
መግቢያው ሲነገረው ፣ መች ዐሰበ መውጫ ?!

መገን እናንተዬ
አገባብን አይቶ መውጫ እንደመመኘት
አመጣጥን አይቶ መኼጂያ እንደማግኘት
በአፍ የቃል ስፍር ፣ ማወቅ የሰው እውነት።

እንዲኽ ቀላል ኖሯል !? . . .

ባራት የቆመውን ባ'ቅጣጫ ጠቋሚ
አጋድመው ጣሉና ፣ ሰጡት ለሰያሚ፣
በዱልዱም ካራቸው ተሻምተው በለቱት ፤
አራቱንም እግር . . .
ባ'ራት ዐይነት ቦታ ፣ ለያይተው ሸለቱት።

ከሥጋ ተሻምቶ ለፈራሽ ክርፋቱ
ዐጥንት ለይቶ ለደዌ ቅርሻቱ ፣

ከመገጣጠሚያው ፣ ውሉ ተራርቆ
ቅንጥብጣቢ ኾነ ! ክብሩ ኹሉ ወድቆ!
ከኹሉ ተካፍለው ከጮማ ፣ ከጥሬ
ምላስ አፋፋቸው መገን እነ አጅሬ።

መገን እናንተዬ . . .
ምላስ ሕይወት ብለው ፣ ባ'ፍ የተማመኑ
ጭንቅላቱን ጥለው የቀንዱን ታመኑ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
👍1
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


...የቃለ መጠይቅ ፈተና ሊፈተኑ ሶስቱ ተወዳዳሪዎች በተጠቀሰው ሰዓት
በአስተዳዳሪው ቢሮ ተገኝተዋል፡፡ ሆዳቸው መለስተኛ እንስራ የሚያክለውና ከወደመቀመጫቸው አካባቢ እንደ ጥሩ ሴት ወይዘሮ ሰፋ ያሉት የአስተዳደር ክፍል ሀላፊ አቶ ዐባይነህ ዋጋዬ ትልቅ የሳይት መነፅራቸውን እንደገደገዱ ደብለል ደብለል እያሉ እየተገላበጡ መጡ።
“የኮሚቴ አባላት እስከሚሰባስሱልኝ ድረስ ትንሽ ጠብቁኝ” አሉና እነዚያ
ጥቃቅን ጥርሶቻቸውን ብልጭ አደረጉላቸው፡፡ ሶስቱም በአክብሮት ተነስተው ቆመው ነበር፡፡ አቶ አባይነህ እየተገላበጡ ወደ ቢሮአቸው ሲመለሱ
ተፈታኞች ከቢሮው ፊት ለፊት ካለው የእንግዶች መቀመጫ ወንበር ላይ
አረፍ አሉ።
“እኔ የቃለ መጠይቅ ፈተና እንደሚያስፈራኝ ምንም ነገር አያስፈራኝም፡፡
አባቴ ይሙት! እዚያ ከበው ዐይናቸውን ሲያፈጡብኝ የሚበሉኝ ነው
የሚመስለኝ። በብዛት የሚያቀርቡት ጥያቄ ደግሞ ከስራው ጋር ምንም
አይነት ግንኙነት የሌለው ነው። ትልቅ ነጥብ የሚሰጡት ደግሞ ለፐር ሰናሊት ነው” የፀሃይን ንግግር ሲሰማ ጌትነት ከጀርባው አካባሲ ርጥበት
ተሰማው። ነጭ ላብ ወርዶት ነበር፡፡ ጠርዟ በመተሻሸት ብዛት ብን...
ያለች ሸሚዙን ሰረቅ አድርጐ ተመለከታት። ከላይ ጣል ያደረጋት ጃኬት ውሃ ይዞት ሊሄድ አንድ ሀሙስ ብቻ ነው የቀራት። እሷም እንደ ሸሚዙ ሳስታ ነበር። ጫማውም ቢሆን እድሜ ለቀለም እንጂ በቦታው አልነበረም። አብረውት ለቃለ መጠይቅ የቀረቡትን ኣሁን ገና ትኩረት ሰጥቶ ተመለከታቸው። ሽቅርቅር፣ ዝንጥ ብለዋል። “የጉድ ነው!” አለ በልቡ፡፡
ይሄም አለ ለካ? እሱ እንደሆነ ስለፐርሰናሊቲ አንድም ቀን ትዝ ብሎት
አያውቅም ነበር። ልብሱ ንፁህ መሆኑን ብቻ ነበር ያየው፡፡ አይ ፀሀይ
እግዜር ይይላት የዚህ ችግር ሰለባ እሱ ብቻ መሆኑን እያወቀች ጭንቀት
ለቀቀችበት፡፡ በውጤቱ ስለፈራችው አስቀድማ የስነ ልቦና ጦርነት እየ
ከፈተችበት ነበር።
ጌትነት ለጊዜው ክው ብሎ ቢደነግጥም ቀስ በቀስ ራሱን አረጋጋ፡፡ ከውስጥ
የድህነት ስሜቱ ጋር በስውር ሲሟገት ቆየና“ልብሱ ሳይሆን ስራውን
የሚሰራው ጭንቅላት ነው!” ሲል ለራሱ ሞራል ሰጠ። ተወዳዳሪዎቹ በችሎታና በዕውቀታቸው እስካልበለጡት ድረስ በልብስ ብልጫ ሊመረጡ እንደማይችሉ፣ ፈታኞቹ የውበት ውድድር ሳይሆን የብቃት ውድድር እንደሚያካሂዱ ተማምኖ ተፅናና፡፡ ፀሀይ ግን ዛሬም ቢሆን የፅሁፍ ፈተናውን በተፈተኑበት ዕለት ከነበራት በራስ የመተማመን ሁኔታ ለውጥ አለ
ማሳየቷ ሁለቱንም አስገርሟቸዋል። እንደ ልማዷ ትቀበጣጥራለች። ቃለ
መጠይቁን ያለጥርጥር እንደምታልፍ በማውራት ላይ ነች፡፡
“ፈታኞቹ የፈለጉትን ያክል ቢበዙ አልፈራቸውም እማዬ ትሙት! ጉዳዬ
አይደለም፡፡ የሚያቀርቡልኝን ጥያቄ ያለምንም ፍርሃት ነው የምመልስላቸው፡፡ ይቺን ታክል አልፈራቸውም!!” የጣቷን ጥፍር እያሳየቻቸው።
“አቦ ለምን ፈርተሽ ታስፈራሪናለሽ ታዲያ? እሱን በኋላ ብናየው አይሻልም? የፅሁፍ ፈተና ሌላ! ቃለ መጠይቅ ሌላ!” በፅሁፍ ፈተና ስለበለጠችው ቁጭት የተስማው ሰይፉ የእልህ መልስ ሰጣት። በዚሁ መሀል ሁለት ሰዎች አጀንዳዎቻቸውን ይዘው ወደ አቶ አባይነህ ቢሮ አመሩ።
የፈታኝ ኮሚቴ አባላት መሆናቸውን ለተወዳዳሪዎቹ ለማሳወቅ ደረታች
ውን ነፋ! አድርገው ጀነን ብለው አለፉ፡፡
የመጀመሪያው ተፈታኝ ሰይፉ ነበር፡፡ ገለብ ገለብ አድርገው አስወጡት::
ቀጥሎ የተጠራው ጌትነት መኩሪያ ነበር፡፡ ራሱን እንዲያስተዋውቅ ከተደረገ በኋላ ስለ ህይወት ታሪኩ በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲያስረዳ ተጠየቀ::
ዘና ብሎ ተረጋግቶ ከትውልድ ዘመኑ ጀምሮ ያለው የህይወት ታሪኩን ገለፀ፡፡ ስለ ዕቃ ግዥ አፈፃፀም ሥርዐት መፅሀፍ በማንበብና አብዱላሂ ካስተዋወቀው ከአብነት ስፊ መረጃ በመሰብሰብ ለፈተናው በሚገባ ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ አብነት በትራንስፖርት ድርጅት ውስጥ በግዢ ሰራተኛነት ተቀጥሮ የሚያገለግል የአብዱላሂ ደንበኛ ሲሆን ሰፊ ጊዜ ወስዶ ስለግዢ ስርአት አስረድቶት ነበር፡፡ እንደገመቱት አልቀረም ቀለል ባለ መልኩ ስለ ግዢ አፈፃፀም ሂደትና የግዢ አይነቶችን እንዲገልፅ ጥያቄ አቀረቡለት።
በልቡ አብነትን እያመሰገነ የውጭ አገር ዕቃ ግዥንና የአገር ውስጥ ዕቃ
ግርን ለሁለት ከፍሉ ይተነትንላቸው ጀመር፡፡ በሁለቱ የግዢ ሂደቶች
መካከል ያለውን አንድነትና ልዩነትም በአግባቡ ገለፀ። ከጥያቄአቸው
እልፍ ብሎም ከግዢ እስከ ክምችት ድረስ በመዝለቅ ያለውን አሰራር፣ ግዥ ለመፈፀም የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ከግዢ ጥያቄ እስከ ርክክብ ድረስ ያለውን ሂደት ከዚያም አልፎ በግዢ ወቅት የባንክና የኢንሹራንስን ሚና ሲያብራራላቸው ፈታኞቹ አፋቸውን ከፍተው ቀሩ።በልባቸው ትንሽ ንዴት ቢጤ የተስማቸው አስተዳዳሪ በደፈረሱ ዐይኖቻቸው ትኩር ብለው
አዩትና “ የኔ ወንድም!የሽያጭ ስራ ልምድህን ደብቀህ ነው እንዴ የተወ
ዳደርከው?!” ሲሉ አፈጠጡ፡፡ በተለይ የሽመልስን ልብ እያሽነፈ መምጣቱ
ስጋት ላይ ጥሏቸው ነበር፡፡ አቶ አባይነህ ይህን ጥያቄ ያቀረቡለት ከመመዘኛው በላይ (ኦቨር ኳሊፊኬሽን) በሚል ሰበብ ሊያሰናብቱት ቢሆንም በሌላ ጎኑ የጌትነትን ብቃት እያደነቁ መሆኑን አልተገነዘቡትም፡፡ በፍጥነት የተገላገሉት ሰይፉ በደስታ እንዳላስፈነደቃቸው ሁሉ ይሄኛው ባልጠበቁት ሁኔታ አበሳቸውን እያሳየ የፈታኞቹን ልብ ለመስረቅ የሚታገል የጐን ውጋት ሆነባቸው።

“የለም አልሰራሁም የትም መስሪያ ቤት ተቀጥሬ ሰርቼ አላውቅም”
“ታዲያ እንዴት ነው እያንዳንዷን ነጥብ ልቅም አድርገህ ለማወቅ የቻልከው?” በአቋም ከአቶ አባይነህ ጐን የተሰለፈው አቶ ማን አየህ ነበር ይህንን ጥያቄ ያቀረበለት፡፡

“አንድን ነገር ለማወቅ በቦታው ላይ መገኘት ግዴታ ላይሆን ይችላል።
ስለ አስራሩ መጠነኛ እወቀት ያገኘሁት በሙያው ላይ ልምድ ያላቸውን
ሰዎች በመጠየቅና በማንበብ ነው። የስራ ልምዱ ሲኖረኝ ደግሞ ከዚህ በተሻለ ሁኔታ መግለፅ እችል ነበር” ሲል ምላሽ ሰጠ። አቶ ሽመልስ በፀጥታ ተውጦ ጌትነትን ሲያዳምጠው ቆየና የተወዳዳሪዎቹ ማስረጃ የተቀመጠበትን ፋይል ከአቶ አባይነህ እጅ ተቀብሎ የሁሉንም ውጤት እንደ አዲስ መመርመር ጀመረ። የጌትነት የብሔራዊ ፈተና ውጤት በፍፁም ያልጠበቀው ነበር፡፡ ለምን ዪኒቨርሲቲ ገብቶ መማር እንዳልፈለገ ግራ ቢገባውም ለቀረቡለት ጥያቄዎች የሰጣቸው ምላሾች ከጠበቀው በላይ አስደስቶታል።አቶ አባይነህና አቶ ማንአየህ እየተጋገዙ ሊያደናብሩት ቢሞክሩም እሱ ግን ከፊቱ ገፅታም ሆነ ከአንደበቱ ፈታ ብሎ አድናቆቱን ሳይቆጥብ እየገለፀለት ለአንድ ሰዓት ያክል ካቆዩት በኋላ ጨርሰሃል ብለው አሰናበቱት።

“ምነው ቀዶ ጥገና ነበር እንዴ ?” ሰይፉ ነበር።

“ቀላል ቀዶ ጥገና?!” ፀሃይ በሰይፉ ላይ ተጨማሪ አድርጋ በጣም መቆየቱን አጋነነች። የሷ እንኳ የቅናት ነበር፡፡ ያንን ያክል ያቆዩት ቢፈልጉት እንጂ ባይፈልጉት ኖሮ እንደ ሰይፉ ቶሎ ብለው ያሰናብቱት ነበርስትል አሰበች፡፡ አሁን ገና በልቧ ትንሽ ስጋት ቢጤ አሳደረች፡፡ያ በራስ
የመተማመን ስሜቷ በመጠኑም ቢሆን ተሸረሽረ።ጥርጣሬ ገባት። ከቅላቷና ከዐይኖቿ ትላልቅነት ጋር ተዳምሮ ትልቅ የፈረንጅ አሻንጉሊት የምትመስለው ፀሀይ ከውስጥ አንጀቷ ቢቃጠልም ላይ ላዩን እየሳቀች የቆየበትን ምክንያት ጠየቀችው፡፡ የቀረቡለት ጥያቄዎች በርካታ እንደነበሩ አስረዳት።

“ምነው ታዲያ እኔን ተስተካክዬ ቁጭ ሳልል አካልበው ሸኙኝ በናትህ?”
አለና ሰይፉ ሳቁን ለቀቀው፡፡ለምን አጣድፈው እንዳባረሩት በሆዱ አወ
ቆታል። ለቀረቡለት ጥያቄዎች በሙሉ ለአንዳቸውም ቢሆን ቀጥተኛ
👍4
መልስ መስጠት አልቻለም ነበር፡፡ መልሶቹ በሙሉ አባትሽ ማነው ብው
ቢጠይቋት ፈረስ አጐቴ ነው ብላ መልስ የሰጠችውን እንስሳ አይነት ነበሩ።

“የፈተናው ባለድል አንተ መሆንህን አውቀው ይሆናላ! ብዙ የሚያውቅ
እኮ ብዙ አይፈተንም፡፡ ከአንደበቱ የምትወጣ ምን ቃል ሙሉ ቀን ከመ
ለፍለፍ የበለጠ ዋጋ አላት!” ስይፉን በጠረባ ስታነሳው ጌትነትን ደግሞ
በጦር ምላሷ ወጋችው። መቼም ስትናገር ሰው ይቀየመኛልን አልፈጠረባትም፡፡
“ይሄ አጉል ፉገራ ነው እትዬ ፀሃይ!ሰይፉ ቀልዷ አልጣመውም። ጌትነት
ሁለቱ ሲያወሩ እየሰማ እንጂ እያዳመጣቸው አልነበረም፡፡ ዐይኖቹም
እነሱ ላይ ተተከሉ እንጂ እያስተዋሏቸው አልነበሩም። ዐይነ ህሊናው ወደ ፈተና ክፍሉ ውስጥ ገብቶ የእያንዳንዳቸውን የፈታኞቹን ሁኔታ እየፈተሸ ነበር፡፡የቀረቡለት ጥያቄዎች በአጋጣሚ ሙሉ ለሙሉ የተዘጋጀባቸው ሆነው መገኘታቸው አስገርሞታል። እውነትም አብዱላሂ እንዳለው ይሄ እንጀራ ለሱ የተጋገረ መሆኑን፣ የስራ ዕድል ወደ ቤቱ ልትገባ በሩ ላይ ቆማ እያንኳኳች መሆኑን አመነ፡፡ ውጤቱን ለማወቅ ቸኩሎ አንዷ
ደቂቃ የዓመት ያክል ረዘመችበት፡፡ በሃሳቡ በላዩ ላይ እያለቀች የመጣችው ሸሚዝ መቀየሪያ ልታገኝ አዲስ ሱሪ፣ አዲስ ጫማ፣ አዲስ ካልሲ፣አዲስ እንትን...ገዝቶ ሰው መስሎ አምሮበት ሊታይ ተቀጣሪ የወር ደመወዝተኛ ሆኖ የግዢ ስራውን ሊያቀላጥፍ ዘይኑን ከአገር ቤት አስመ
ጥቶ ሊያስተምራት ለእናቱ በየወሩ ተቆራጭ ሊያደርግላት... እነዚህ
ሁሉ ሲመኛቸው የነበሩ ምኞቶቹ ሊሳኩ በመቃረባቸው ልቡ በደስታ
ዘለለች። በየጊዜው ለእናቱ ደብዳቤ እየጻፈላት “አይዞሽ እማምዬ አለሁ
ልሽ!” የሚላት እየታየው ቁጭ ባለበት በሃሳብ ፈረሱ ላይ ወጣና ወደ ባሌ
ጋለበ... የቅጥር ኮሚቴው በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ሳይግባባ ቀርቶ ሲወዛገብ ከቆየ በኋላ ተረኛዋ ፀሃይ አስፋው ተጠራች።

ፀሀይ አስፋው ወደ ክፍሉ ስትገባ የአስተዳደር ሃላፊው ፊታቸውን ፈካ
ጥርሶቻቸውን ብልጭ አደረጉላት። በጭቅጭቁ ምክንያት የሁሉም ፊት
ተለዋውጦ ጉም መስሎ ነበር። በተለይ ደግሞ የአቶ ሽመልስ ፊት ሊዘንብ የተቃረበ ጭጋግ በመምስሉ እንዳትደነግጥና የመጨነቅ ስሜት
እንዳይሰማት በማስብ ቆመው ከማስተናገድ ባልተናነሰ ትህትና ጠብ
እርግፍ ብለው እንድትቀመጥ ጋበዟት።
እውነትም የሳቸውን ሁኔታ ስትመለከት ፀሃይ ፈገግታዋ ልዩ ሆነ፡፡ ተዝናናች። የእንግሊዝኛ ነገር እንደማይሆንላት አስቀድሞ የታወቀ ነበረና በቀጥታ በአማርኛ ቋንቋ ወደ ዋናው ጥያቄ ይዘዋት ገቡ።

“እሺ ወይዘሪት ፀሃይ የፅሁፍ ፈተናውን በጥሩ ሁኔታ በመስራትሽ በሁለተኛ ደረጃ አልፈሽ ለቃለ መጠይቅ ቀርበሻል። እስቲ ስለ ዕቃ ግዢ የምታውቂውን ብታስረጂን?”እሷ የምታውቀው የሽንኩርትና የቃሪያ ግዢ መሰላት።

“እቃማ ያው እንደሚታወቀው በኪሎ ግራም ወይም በሊትር ወይንም
ደግሞ በሜትር ተለክቶ ይገዛላ!” ሶስቱም በሳቅ ፈነዱ።
“እንዴ ምነው ልክ አይደለም እንዴ?!ጨውና ስኳር በኪሎ፣ ዘይትና ጋዝ
በሊትር፣ጨርቅ ምናምኑ ደግሞ በሜትር ተለክቶ ይገዛል። ይሽጣል፡፡
ልክ አይደለም እንዴ?!” ዐይኖቿን ፈጠጥ አደረገቻቸው። አስተዳዳሪው ብቻ ድንገተኛ ሳቃቸውን ቶሎ ሲያቋርጡ ሁለቱ እንባቸው እስከሚፈስ ድረስ ሳቃቸውን ቀጠሉ።

“በሉ ወደ ቁም ነገሩ እንመለስ”አሉ ፈታኞቹ ሳቃቸውን እንዲያቆሙ በመ
ጠየቅ፡፡ በተለይ አቶ ማን አየህ የዚያን ያክል በሳቅ መፈንዳቱ ትንሽ አበ
ሳጭቷቸዋል።
“ወይዘሪት ፀሃይ ምናልባት ከኛ አጠያየቅ ስህተት ሊሆን ይችላል። የጠየቅንሽ ጥያቄ የሸቀጣ ሸቀጥ ግዢን የሚመለከት አይደለም። እንደምታውቂው ይሄ ድርጅታችን የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ከውጭ አገር እያ
ስመጣ የሚሽጥ ድርጅት ነው። የዕቃ ግዢ ብለን የጠየቅንሽም ከዚሁ
መስሪያ ቤታችን ከሚያከናውነው ተግባር ጋር የተያያዘውን በሚመለከት
ስለሆነ የምታውቂውን ብትገልጭልን?”
“ታዲያ እንደሱ ብላችሁ አትጠይቁኝም ነበር?” ወላጆቿ የተቆጧት ትንሽ
ልጅ መሰለች፡፡ ከንፈሯን ጣል ዐይኖቿን ከብልል፣ ክብልል አደረገችና
ገለፃዋን ቀጠለች።
“እሱማ በርካሽ ከሚገኝበት ቦታ አፈላልጐ በመግዛት መጋዘን ውስጥ ማስ
ቀመጥና በጥሩ ትርፍ መሽጥ ነዋ! ገዢ ሲመጣ ከመደርደሪያ ላይ እያወረዱ የሚፈልገውን በማስመረጥ ዋጋውን ተቀብሎ በካዝና ውስጥ ቆልፎ
መያዝ ነዋ!”
አስተዳዳሪው “የአንተ ያለህ!!” አሉ በልባቸው። በተለይ የሽመልስን
ዐይኖች ማየት አፈሩ፡፡ የጽሁፍ ፈተናውን አስቀድሞ በተሰጣት መረጃ
መስረት እንድታልፍ ቢደረግም በዚህ አያያዟ ሰማንያ ከመቶ የማግኝ
ቷን ተአምር እንዴት አድርገው ለሽመልስ ማስረዳት እንደሚችሉ ሲያስቡት ጨነቃቸው።
“ስለጨውና ስኳር ሽያጭ አይደለም የምናወራው ወይዘሪት ፀሀይ!! የዕቃ
ግዢ በሁለት ይከፈላል! የአገር ውስጥና የውጭ አገር ግዢ ይባላል። የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች የሚመጡት ከውጭ አገር በመሆኑ የምናካሂደው ግዢ የውጭ አገር ግዢ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እና እንዴት ነው? ማለቴ...ግዥ ለመፈፀም ምን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው?
ለምሳሌ የዕቃው የክምችት ደረጃ ሪኦርደር ሌቨል' ላይ ስለመድረሱ፣
የግዢ መጠየቂያ ከጠያቂው ክፍል ተሞልቶ ስልመቅረቡ፣ በአጠቃላይ
ግዢን ለመፈፀም አስፈላጊ ፎርማሊቲዎች መሟላታቸው ...”ስስጨት አሉና ፍንጭ የመስጠት ሙከራቸውን አጠናቀው ከወደ መቀመጫቸው ተቁነጠነጡ። ከዚያም በእፍረትና በፍርሀት ስሜት ውስጥ ሆነው ሽመልስን ገልመጥ አደረጉት፡፡
ሽመልስ ፊቱ በንዴት ተለዋውጧል።አቶ አባይነህ ፀሃይን ለመርዳት
በሚያደርጉት ዐይኑን ያፈጠጠ ወገንተኝነት ተበሳጭቷል።በዚህ ሁኔታዋ
እንዴት አድርጋ ሰማንያ ከመቶ በማግኘት ለቃለ መጠይቅ ፈተና ልትቀርብ እንደቻለች በእጅጉ ተገርሞ በትዝብት እያስተዋላት ነበር።

የፅሁፍ ፈተናው አስቀድሞ እንዲደርሳት መደረጉን መጠርጠሩና የቃለ መጠይቅ ጥያቄዎቹን ራሱ በጥንቃቄ በማዘጋጀት በሚስጥር እንዲያዙ ማድረጉ ምን ያክል ትክክለኛ እርምጃ እንደሆነ በይበልጥ ያረጋገጠው የአ ሁኑን የፀሃይን ሁኔታና የአቶ አባይነህን አካሄድ ከተመለከተ በኋላ ነው፡፡
“ቆይ እንጂ አቶ አባይነህ! አንድ ጊዜ እንደማመጥ!መልሱ በጥያቄው
ውስጥ እየተነገረ የሚደረግ ቃለ መጠይቅ ታይቶም ተሰምቶም አይታወ
ቅም! እንደዚህ ያለውን አካሄድ ቢያስተካክሉ ይሻላል!ይህ አካሄድ በቀጣይ አሰራራችን ላይ ችግር የሚፈጥር ነው። ካልሆነ ደግሞ ጥያቄውን እኛ ብቻ እንድናቀርብ ዕድሉን ይስጡን!!” ተፈታኝዋ እስከምትወጣ ድረስ እንኳ መታገስ አቅቶት እዚያው በፀሀይ ፊት ተቃውሞውን ገለፀላቸው።
ሁለተኛው ፈታኝ አቶ ማን አየህ በአቶ አባይነህ በኩል'አደራ!” የተባለ ሰው
ነው። አቶ ዐባይነህ ሰሞኑን አንድ ዘመዱን ስለቀጠሩለት ምንም አይነት
ተቃውሞ ከማሰማት ተቆጥቧል፡፡ አቶ ሽመልስ ብቻውን እንደሆነ አላወ
ቀም ነበር፡፡ ድካሙ ሁሉ በአንድ እጅ ብቻ ማጨብጨብ መሆኑን በውል ሳይገነዘብ ሙግቱን ከአቶ አባይነህ ጋር ቀጠለ። አቶ አባይነህ በከንቱ ደከሙ እንጂ ፀህይቱ የሚነግሯትን ሪኦርደር' ምናምን ይቅርና የዕቃ መጋዘኑን ከነነፍሱ አምጥተው ቢያስታቅፏት እንኳ አንድም የምታው
ቀው ነገር አልነበረም፡፡ እሷ አንድ የህይወት መመሪያ ብቻ ነው ያላት።
“ስራ የሚለመደው እየተሰራ ነው። ማንም ከእናቱ ማህፀን ተምሮ አልተወለደም፡፡ዋናው ነገር ስራን መቆናጠጥ ነው”የሚል!ለዚህ ደግሞ ምንም
ጥርጥር አልነበራትም፡፡ የጭኖቿን ሙቀት ያቋደሰችው ወፍራሙ ዘመዷ“አይዞሽ አለሁልሽ! ”ብሏታል።አንዴ ወዲህ አንዴ ወዲያ ስትል ስትቀለማምድ ቆይታ ጨርሰሻል ተባለችና ተሸኘች። በመጨረሻም ተወዳዳሪ
ዎች ተጠርተው ውጤቱ ከሶስት ቀን
👍4
በኋላ በማስታወቂያ እንደሚገለፅ
ተነገራቸውና አድራሻቸውን እንዲያስመዘግቡ ተደርጐ ተሰናበቱ።...

ይቀጥላል
አትሮኖስ pinned «#የተወጋ_ልብ ፡ ፡ #ክፍል_ስምንት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና ...የቃለ መጠይቅ ፈተና ሊፈተኑ ሶስቱ ተወዳዳሪዎች በተጠቀሰው ሰዓት በአስተዳዳሪው ቢሮ ተገኝተዋል፡፡ ሆዳቸው መለስተኛ እንስራ የሚያክለውና ከወደመቀመጫቸው አካባቢ እንደ ጥሩ ሴት ወይዘሮ ሰፋ ያሉት የአስተዳደር ክፍል ሀላፊ አቶ ዐባይነህ ዋጋዬ ትልቅ የሳይት መነፅራቸውን እንደገደገዱ ደብለል ደብለል እያሉ እየተገላበጡ መጡ። “የኮሚቴ…»
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል



...ጉልላት ከመንቃቱ በፊት ለዐሥራ ሁለት ሰዓት ኻያ አምስት ጉዳይ እንደሆነ ልብሴን ለባበስኩ፡፡ የማክሰኛ ውሱን ዕድሜ ከማለቋ በፊት ወደ ውጪ
ወጣሁ፡፡ ምሥራቃዊው አድማስ ቀይ ሽንብራ መስሏል፡፡ ቆሜ አካባቢዩን
ስመለከት ንጣትና ቅላት ተጋጩ፡፡ የአዲሱ ዛሬና የአሮጌው ትላንትና የመጨረሻ
ግብ ግብ ነበር! አሽናፊውን በመለየት ላይ ሳለሁ አዲሷ ሮብ ተማጠች። ዐሥራ
ሁለት ሰዓት ማለቂያ ላይ እንደ ተወለደች አዕዋፍ የዕለቱን የመጨረሻ የእልልታ
ድምፅ አሰሙ፡፡ ምንጊዜም ለዘላለም የማትመለሰዋን ሮብ በፍርሃትና በጉጉት
ተቀበልኳት፡፡ ፊቴን ታጥቤና ጸጉሬን አበጥሬ እንደ ጨረስኩ ጉልላት ነቃ፡፡
ልብሱን ለባብሶና ተጣጥቦ ሲጨርስ ልክ ሁለት ሰዓት ደፈነ። እያንዳንዷ የሰውነቴ
ጡንቻ፣ ተባርኮ ሕይወቱ በማለፍ ላይ እንዳለ ወጠጤ ተፈራገጠች፡፡ የተዘጋጀ
ወይም ሊዘጋጅ የሚችል ቁርስ ስላልነበረን በባዶ አፋችን ከቤት ወጣን፡፡

የሰዓቴ የደቂቃ ዘንግ ኻያ ደቂቃ ጨመረ። ጉልላት ጠንቀቅ ባለ ስሜት
«እኔ አሁን አደርስህና ሠራተኛ ለማምጣት እመለሳለሁ። የቤት ሠራተኛ ያስፈልጋል። ሥራ ቦታ አሁኑኑ ስለምመለስ የቤቱን ቁልፍ ስጠኝ ብሎ ወሰደ።የሕሊና ምጥ ያዘኝ፡፡ የግልግሌ ደቂቃ እየተቃረበች ብትመጣም ሙሉ እፎይታ ለማግኘት ገና የትናየት ይቀረኛል፡፡ ልክ ለሦስት ሰዓት ኻያ ጉዳይ ሲሆን በጉልላት ቮልስዋገን ወህኒ ቤት ደረስን። «እኔ አሁኑኑ ከሥራ እመለሳለሁ! ሁሉንም ነገር አሰናድቼ እጠብቅሃለሁ:: አይዞህ በርታ! አእምሮዋ በድንጋጤና በጥርጣሬ እንዳይታመስ ከአሁኑ ደቂቃ ጀምረህ ሙሉ ረዳቷና አለኝታዋ መሆንህን በተግባር ግለጽላት፡፡ በል እንግዲህ አብሬህ ከምቆይ ይልቅ ሄጄ የማከናውነው ይበልጣልና ልሒድ!» ብሎ መኪናውን ሲያስነሣ በሩን ከፍቼ
ወጣሁ፡፡

ከውጪ በመስኮቱ በኩል «እምብዛም አትጨነቅ የወዲያነሽን ባለኝ ነገር
ብቻ ተሰናድቼ እንድቀበላት እንጂ በጭንቀት ተከብቤ እንዳስተናግዳት አልሻም፡፡ያም ሆነ ይህ ሁሉንም ታውቀዋለህና ሂድ» አልኩት፡፡ መኪናውን ጠምዝዞ ሔደ።ከወህኒ ቤቱ ትልቅ የብረት በር አጠገብ ያለውን ግንብ ተደግፌ የጊዜን ፍጥነት እታዘብ ጀመር፡፡ እያንዳንዷ ደቂቃ የአንድ ሰዓት ያህል የርዝማኔ ቆይታ በማድረግ ላይ ያለች መሰለኝ። እጄ ላይ ያሰርኳት ሰዓት የጊዜን የፍሰሰት ሕግ መለወጥ ትችል ይመስል ደጋግሜ ኣየኋት።

አይቻልም እንጂ የሚቻለኝ ቢሆን ኖሮ ተሽከርካሪዋን ዓለም በቡጢ ነርቼ
ካላት ፍጥነት በላይ እንድትሾር የማድረግ ከንቱ ፍላጎት ነበረኝ፡፡ የጊዜና የስሜት
ቁርኝት ገረመኝ፡፡ ጊዜ በአእምሯችን የስሜት ፍላጎት መጠን ሲያጥርና ሲረዝም ተሰማኝ፡፡ ሆኖም ስለ ሕልም ማለም ምን ይጠቅማል? በዚያች ቀን አንድ ሰዓት ስድሳ ካልኢቶች ብቻ መሆኗ አጠራጠረኝ፡፡ የቢሮ ውስጥ ጣጣ እስኪፈጸምና የሕይወቴ ክፋይ በሩን አልፋ እንደ ንጋት ጮራ ብቅ እስከምትል' ከአንድ ሰዓት በላይ መጠባበቅ ነበረብኝ፡፡
የናፍቆት የትዝታ፣ የደስታና የአዲስ ሕይወት ስሜት አቅበጠበጠኝ። ድንጋዩ ጠጠሩ' ሣር ቅጠሉ' ግንቡ' ከሩቅ የሚታዩት ዛፎች፣ አላፈ እግዳሚው ሁሉ ደስታ ፈጣሪ ትርዒቶች ሆኑ፡፡ አንጎሌ በደስታ እና በኃዘን በሽብር እና በተስፋ ጥንስስ ተዥጎረጎረ። በአንድ በማላውቀው አስደሳችና ሸንተራራማ ለምላሚ ውስጥ ያለሁ መሰለኝ። በቅኔው ሲኦል ወርዶ በደስታና በኃዘን እንደባዘነው ባለቅኔ እኔም ወህኒ ቤት በር ላይ ተቀምጩ የወዲያነሽን በመጠባበቅ ደስታና ኃዘንን እያፈራረቅሁ ገመጥኩ። ከጊዜ ጋር ተፋጠጥን። የእኔ ልብ በጉጉትና በጥድፊያ ተጠምዳ ድው…ድው እንደምትል ሁሉ፣ የወዲያነሽም
ካጥሩ ወዲያ ባለው ምድራዊ ሲኦል ውስጥ እንደ እኔው እንደምትሆን ታወቀኝ፡፡ የጊዜ ሕግ ሆነና ግማሽ ሰዓት ዐለፈ፡፡

በሕይወቴ ውስጥ ትልቁ የኑሮ ፍሥሓ መረዋ ተደወለ። ግዙፉ የብረት በር ገርገጭ አለ፡፡ የሰውነቴ ውስጣዊ እንቅስቃሴ አብሮ ተንገራገጨ። የት
እንዳለሁና ምን እንደማደርግ ማወቅ ተሳነኝ፡፡ በሩ እንደገና ሲጢጢጢጢጢ
የሚል ቀጭን የብረት ፍጭት ድምፅ አሰማ፡፡ እንደ አይጥ መንጋ የጮኸው በር
ተርገፈገፈ የተጠበቀ የትግል ምዕራፍ! በሩ ወለል ብሎ ተከፈተ! ሁለት ወንዶችና ኣዲት ቀጠን ብላ ቁመቷ ዘለግ፣ መልኳ ጠቆር ያለ ሴት በሩን ዐልፈው ወጡ፡፡ አዎ ውዲቱ የሕይወቴ ግርማ ሞገስ የወህኒ ቤቱን በር ዐልፋ ወጣች! ሕይወት ውብ ዝማሬ ዘመረች አዝማቿን ተቀበልኩ፡፡

«የወዲያነሽ! የወዲያ! እዚህ ነኝ! መጥቻለሁ!» ብዬ ጠራኋት፡፡ እኔ ወደሷ፣ እሷ ወደ እኔ ገሠገሥን፡፡ እጆቿን ዘርግታ ስትጠመጠምብኝ የፍቅራችን
ዳግማዊ ትንሣኤ ሆነ!! የሰውነቷ ጠረን ውሃ ያርከፈከፉበት ዐፈር ዐፈር ይላል። በእጅዎ የያዘቻት ቁራጭ ወረቀት ጫማዩን መታ አድርጋ ከእግሬ ሥር ወደቀች።አብረዋት የተለቀቁት ሁለት ወንዶች መለስ ብለው እንኳ ሳያዩን ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ በደስታ የተዝለፈለፈው አካላቴ አልንቀሳቀስ አለኝ፡፡ ዐሥር የማይሞሉ እርምጃዎች እንደ ተራመድን ከመንገድ ዳር ለምለም ሣር ላይ ተቀመጥን።
እይቼ አልጠግባት አልኩ፡፡ የወዲያነሽ እይታ ስላልጠገበችኝና የናፍቆቷም ከርስ
ስላልሞላች እንደገና ተሳሳምን፡፡ ዐይኖቿን አሻሽቻቸው:: እጆቿ ሲነሡ እንባዋ
ተዘረገፈ፡፡ ወደ ወህኒ ቤት ከወሰድኩላት ልብሶች መካከል አንድም ይዛ አልወጣችም። ቀኝ እጄን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጌ በትዝታ ተመለከትኳት።
የአንገቷና የደረቷ አካባቢ ቀሚሷም ጭምር በጭቅቅት ተበልቷል፡፡ ፊቷ ጠቆር ብሎ ከመክሳቱ በስተቀር ልዩ ለውጥ አይታይበትም፡፡ ዐይኖቿ ፈዘዝ ብለው ቀልተዋል፡፡ ቆዳ ጫማዋ በቀለም እጦት ተላልጧል። አንጀቴ እርር በማለቱ
ከንፈሬን በንዴት ነከስኩት፡፡ ትንሽ አዘገምን፡፡ ዳሩ ግን የየወዲያነሽ እግር
በመቀያየዱ በታክሲ ተሳፈርን፡፡

ከእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ትንሽ እልፍ ብለን ድልድዩ ጋ ሳይደርስ ወረድን፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የምታሻቅበውን አጭር አቀበት እጅ ለእጅ ተያይዘን ወጣናት፡፡ የወዲያነሽ እጅዋን ከእጄ ኣላቅቃ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር በር ሄደች። ተከተልኳት። በብረቱ በር ላይ ያለውን የብረት መስቀል በግንባሯ እየገጨች «አንተ ታውቅልኛለህ ጌታዬ! ለዚህ ያበቃኸኝ ጌታ ተመስገን! አንተው ሁነኝ» ብላ በሻከረ ድምፅ ተናገረች፡፡ ወዴት እንደምወስዳት ስለማታውቅ ዝም ብላ ተከተለችኝ፡፡ የአዲሱ ቤታችን በር ወለል ብሎ ተከፍቷል፡፡ ከማድ ቤት
የሚወጣው ጢስ በመስኮትና በመዝጊያው በኩል እንደ ሐምሌ ጉም ዝግ እያለ ይትጎለጎላል።

በኑሮ ተጐሳቁላ በእስራት የማቀቀችውን የወዲያነሽን ባለፉት ሁለት ቀናት የእኔ ባልኩትና ዛሬ ደግሞ በሁለታችን ውሕደት የእኛ ወደምለው ቤት ይዣት ስገባ በረጂሙ ትግሌ ውስጥ አነስተኛ ድል አድራጊነት ተሰማኝ፡፡

እንዲት ቀጠን ረዘም ያሉ ቀይ ሴትዮ ቀሚሳቸውን በቀኝ እጃቸው ከፍ
ሰብሰብ እያደረጉና የአዘኔታ ገጽታ እያሳዩ መጣችሁ? እሰየው እሰይ! በሉ ግቡ!
ግቡ!» ብለው እኛን እኛን እያዩ ቆሙ። «ኧረ በእግዚአብሔር ምነው ምነው?
በሉ ተቀመጡ! » ብዬ እንዲቀመጡ አደረግሁ፡፡ የወዲያነሽም ባቀረብኩላት
ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡ ሴትዮዋ ትንሽ ከእኛ ፈንጠር ብለው ስኒ በረከቦትና
የሚሰክን ጀበና አጠገባቸው አለ፡፡
ቀበርቾ፣ ዕጣን፣ ደረቅ የሎሚ ልጣጭ፣
መዝጊያው ሥር ጊርጊራ ላይ ይጨሳሉ፡፡ ሽታው አብሮ አደጌ ሽታ በመሆኑ ደስ
አለኝ፡፡

«እሱም እዚሁ ከቤት ውስጥ ነው ሲሠራና ዕቃውን ሲያስተካክል የዋለው: እሁን እመጣለሁ ብሎ ነው ወጣ ያለው፣ እንዲህ ቶሎ የምትመጣም አልመሰለው» አሉና ጀበናይቱን አነሱ