#ሕልመኛ_ተጓዥ
( .. ተቀበል . . . )
በመንገድኽ ኹሉ ዕንቅፋት አትፍራ
ተማርበት እንጂ በእውቀት አትኩራ።
መውደቅኽ ምሳሌ ፣ ሸክፈው እንደ ጓዝ።
ድሎትን አትውደድ ፣ የንዋይን ጉዝጓዝ፡፡
ስሕተትኽን ግደፍ ፤ መርምር በረቂቁ
በመጠረቡ ነው ፤ አልማዝ ማብረቅረቁ፡፡
የጅራፍ ቁግ አጥብቅ ፤ ግመድ አታቅማማ
ካልገረፉት አይጮኽ ፣ ካልጮኸ አይሰማ።
ደዌን አትሽሸው ፣ መርምር በጽሞና
ከችግር አይደል ወይ? መፍትሔ ሚጠና።
አስተውል ፣ ተመልከት! መርምር በአርምሞ
ማንም ሰው አይድንም! ካልታመመ ቀድሞ።
(ደዌን አትሽሸው ፣ ይልቅስ መርምረው
ከመታመም ላይ ነው! መድኅን ሚገኘው።)
“የሕልሜ ሳቢሳ፤
ሾተልኽን አንሣ
ሊበላኝ ነበረ ፣ ቶሎ ባልነሣ።
የሕልሜ ነብር
ይብላኝ ነበረ ፣ ተኝቼ ብቀር።”
ይህ ነው ያ'ንተ ግጥም!
ይህ ነው ያ'ንተ ዜማ !
በነቂስ አትመን . . .!
ግምትም አትጣ . . .!
ልብኽንም ስማ።
ይህ ነው ያ'ንተ ዜማ !
ይህ ነው ያ'ንተ ግጥም !
ያለ መሰናክል፣
ያለ አንዳች ዕክል፣
ሕይወት ፍጹም አይጥም።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
( .. ተቀበል . . . )
በመንገድኽ ኹሉ ዕንቅፋት አትፍራ
ተማርበት እንጂ በእውቀት አትኩራ።
መውደቅኽ ምሳሌ ፣ ሸክፈው እንደ ጓዝ።
ድሎትን አትውደድ ፣ የንዋይን ጉዝጓዝ፡፡
ስሕተትኽን ግደፍ ፤ መርምር በረቂቁ
በመጠረቡ ነው ፤ አልማዝ ማብረቅረቁ፡፡
የጅራፍ ቁግ አጥብቅ ፤ ግመድ አታቅማማ
ካልገረፉት አይጮኽ ፣ ካልጮኸ አይሰማ።
ደዌን አትሽሸው ፣ መርምር በጽሞና
ከችግር አይደል ወይ? መፍትሔ ሚጠና።
አስተውል ፣ ተመልከት! መርምር በአርምሞ
ማንም ሰው አይድንም! ካልታመመ ቀድሞ።
(ደዌን አትሽሸው ፣ ይልቅስ መርምረው
ከመታመም ላይ ነው! መድኅን ሚገኘው።)
“የሕልሜ ሳቢሳ፤
ሾተልኽን አንሣ
ሊበላኝ ነበረ ፣ ቶሎ ባልነሣ።
የሕልሜ ነብር
ይብላኝ ነበረ ፣ ተኝቼ ብቀር።”
ይህ ነው ያ'ንተ ግጥም!
ይህ ነው ያ'ንተ ዜማ !
በነቂስ አትመን . . .!
ግምትም አትጣ . . .!
ልብኽንም ስማ።
ይህ ነው ያ'ንተ ዜማ !
ይህ ነው ያ'ንተ ግጥም !
ያለ መሰናክል፣
ያለ አንዳች ዕክል፣
ሕይወት ፍጹም አይጥም።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
👍2
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....“ትሬይን ያስገደልከው አንተ ነህ አይደል?”
ብላ ኒኪ መሳሪያውን በድጋሚ አንስቶ ሊተኩስባት በተዘጋጀው ሉዊስ
ላይ አፍጥጣ እየተመለከተች ጠየቀችው።
ስለ አኔ ካወራት በኋላ ቅናቱ በጣም ስለጨመረበት እና ስለተናደደ እሷን
ቶሎ ገድሎ ለመገላገል ፈልጓል። የኒኪ ብቸኛ ተስፋ ደግሞ እሱ ወሬውን
እንዳያቋርጥ በማድረግ ለትንሽ ደቂቃም ቢሆን በህይወት መቆየት እንድትችል ማድረግ ነው። መቆየት ደጉ ይባል አይደል?
መሳሪያውን ወደ ታች አውርዶ ሉዊስ አይኑን እያንከባለለ ከተመለከታት በኋላ
እሱ በጣም ደደብ ልጅ ነው። ቢፈልግ ኖሮ በህይወት መቆየት ይችል ነበር። እያንዳንዱን ዕድል ሰጥተነው ነበር፡፡”
“ምን ማለትህ ነው “እያንዳንዱን ዕድል ስትል? የምን እድል? ገንዘብ ተበድሮህ ነበር እንዴ?” አለችው የዴሪክ ዊሊያምስ ትሬይ ዌስትመንት ውስጥ በዕፅ አዘዋዋሪነት ይሰራ ነበር ያላትን ነገርን እና እንዲሁም ደግሞ የዊሊ ባደን አፍ ውስጥ የተጎስጎሱትን ገንዘቦች አስታውሳ
“ትንሽ ብር ነበረበት ግን ለዚያ ብዬ አልነበረም ያስወገድኩት” አላት፡፡
“እና ለምንድን ነው ታዲያ? አዲስ ህይወት በመጀመሩ ተናደህ ነው?
ከሱስ በመፅዳቱ እና ከወሮበላ ቡድኖች ጋር መሥራት ስላቆመ ነው?”
ሉዊስም ፈገግ ካለ በኋላ “ዶክተር ሮበርትስ እኔ ስለ ትሬይ ሬይሞንድ
ህይወት ያን ያህል የሚያገባኝ ከመሰለሽ ተሳስተሻል፡፡ እኔ የቢዝነስ ሰው ነኝ፡፡
ትሬይ ደግሞ የእኔ ድርጅት ቤተሰብ አይደለም፡፡ እሱ የዕፅ ተጠቃሚ ነው።
ማለቴ ገዢ ነው፡፡ ገዢ ሲሄድ ደግሞ ሌላ ገዢ ይመጣል።” ኒኪም ኮስተር
ብላ እያየችው “ትሬይ በጣም ተሰቃይቶ ነው እንዲሞት የተደረገው። ምን
ቢበድልህ ነው ይህንን ያስደረግከው?”
ሮድሪጌዝ በስልቹነት ስሜት ሲያዛጋ ስታየው ከውስጧ ሀይለኛ ንዴት
እና ጥላቻ እየተግተለተለ ሲወጣ ይሰማታል፡፡ በውስጧም አኔ እንዴት ነው
ይህንን አውሬ ሰው አፍቅራው ልታገባው የቻለችው?' ብላ አሰበች።
“ሬይ ሬይሞንድ ጋ እኔ የምፈልገው አንድ ነገር ነበር።” አላት እና ሉዊስ በመቀጠልም “ለዚያም ልዋጭ ጥሩ ዋጋን አቅርቤለት ነበር፡፡ እሱ ግን
እምቢ ብሎ ደረቀ፡፡ ይሄ ደግሞ ለሞት የሚያበቃው ስህተቱ ነው።”
“ሬይ ጋ ያለ አንተ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነበር?” ብላ ኒኪ ጠየቀችው በኋላ ወዲያውኑ አይኗ በእምባ ተሞላ። በጣም ብዙ አሰቃቂ ነገሮች በዙሪያዋ ተከስቶባት ስለነበር የትሬይን ሞት እና በእሱ ሞት ምክንያት የተሰማትን ግብር እና ሀዘን ከእሷ ገፍታ አስወግዳው ነበር። አሁን ግን ሞት ደጃፍ ላይ ስለቆመች ነው መሰል ሀዘኑ እና ሽብሩ ሁለመናዋን
ተቆጣጠሩት፡፡ “አንተ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አለህ፡፡ ትሬይ ግን
ምንም የለውም! በጣም ውድ የሚባለው ዕቃው እኮ ዶውግ የገዛለት የመንገድ ላይ መንሸራተቻው (ስኬት ቦርዱ) ብቻ ነበር” አለችው በምሬት፡፡
“መረጃ ነበረው:: ማለትም አንቺ በቢሮሽ ውስጥ ሚስቴን ቴራፒ ስታደርጊ እሷን አስመልክቶ የምትወስጂውን የማስታወሻ ፅሁፍ እንዲሰጠኝ በትህትና ጠይቄው ነበር፡፡ እምቢ አለ ገደልኩት” አላት፡፡
“ግን እኮ እሱ ምንም አያውቅም” ብላ አየር ሳበች እና
“የእኔ እና የእሷን ምልልስን አስመልክቶ እኮ ማስታወሻ አልይዝም ነበር”
አለችው።
“ውሸታም!” ብሎ ጮኸባት እና “አንቺ ማስታወሻ ትይዢ ነበር::
የማስታወሻዎችሽ ኮፒዎች ደግሞ ፖሊሶቹ ጋር እንዳሉ አውቃለሁ።” አላት::
“በእውነት ከእሷ ጋር የቴራፒ ህክምናዬን ሳደርግ ማስታወሻ አልይዝም
ነበር” ሉዊስም ግር ብሎት “ለምን?” አላት፡፡
“ምክንያቱም እሷ አትፈልግም ነበር፡፡ ግን መያዝ ነበረብኝ” አለችው እና ኒኪ ፀፀት ተሰማት፡፡ በመቀጠልም “ትሬይን እኮ ስትጠይቀው የነበረው እኮ ሊያገኘው የማይችለውን መረጃ ነበር፡፡ ማንም
ሰው ሊያገኘው አይችልምም፡፡ ምክንያቱም መረጃው እዚህ ውስጥ ነው የሚገኘው” ብላ በጣቷ ጭንቅላቷን እየተመተመች ነገረችው። ሉዊስ ለአፍታ ያህል ዝም ብሎ የሰማውን ነገር ሲያዳምጥ ከቆየና በጣም ከት ብሎ ከሳቀ በኋላ
“ይገርማል አስቂኞቹ የስህተት ሰማዕቶች እስከ አሁን ድረስ አላለቁም!” ብሎ በሳቁ ብዛት የፈሰሰውን እምባውን በአይኑ ላይ በአይበሉባው ከጠረገ በኋላ “ዶክተር ሮበርትስ ይህንን ነገር ስላሳወቅሽኝ በጣም ነው የማመሰግነው፡፡ የሚደነቅ ነገር ነው ባክሽ፡፡ ለማንኛውም የምትገደይበትን እውነተኛ ምክንያት አውቀሽ መሞትሽ መልካም ነው::” አላት እና ለሦስተኛ ጊዜ መሳሪያውን ፊቷ ላይ ሲደቅን ኒኪ ጊዜዋ እንዳበቃ ገባት፡፡
“እንግዲህ ሁሉም ቲያትሮች በመጨረሻ ላይ የሆነ ጥሩ መዝጊያዐይኖራቸዋል፡፡ ደህና ሁኚ ዶክተር ሮበርት”
“ነፍስህ በገሃነም ይቃጠል!” ብላ ጮኸችበት ኒኪ፡፡
ከዚያም አንድ ጆሮ የሚያደነቁር ፍንዳታ ተሰማ እና ሁሉም ነገር ጨለማ ሆነ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በመጀመሪያ ጭለማው ተቆጣጠራት፡፡
ከዚያም ሁሉ ነገር ፀጥ አለ፡፡
ምንም አይነት ትንፋሽ፤ ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም፡፡ በቃ ሁሉም
ነገር ፀጥ ብሏል፡፡
ሰላም ብቻ::
እና ሞት እንደዚህ ነው ማለት ነው?'
ጨለማው እንዳለ ቢሆንም የልብ ምቷ ለራሷ ይሰማታል፡፡ ልክ ከረዥም
እንቅልፍ እንደሚነቃ እንስሳ ሁሉ እየተንጠራራች ነቃች፡፡ ስትነቃ ግን
ህመሙ ተሰማት፤ ያውም በደንብ ስል እና በጣም እሳት ሆኖ።
እግሬን' ብላ እጇን ወደ ታች ስትሰድ ሙቁ የሚያጣብቅ ደሟ ተቀበላት። ስለሆነም ጨለማው ራሷን በመሳቷ ሳይሆን የአዳራሹ መብራት በመጥፋቱ ምክንያት የመጣ እንደሆነ ገባት፡፡ ምንም እንኳን ኒኪ በእግዚአብሔር ባታምንም የሆነ ተዓምር መብራቱን እንዳጠፋላትና ሉዊስም በዚህ ግራ ተጋብቶ ተሳስቶ እግሯን እንደመታት ግልፅ ሆነላት። ምን ያህል ደም እንደፈሰሳት እያሰበችም እጇን ወደ ቁስሉ ስትልክ አመማት እና ቀጭን
ነው ድምፅ አወጣች፡፡
ድምፅ ማውጣቷ ስህተት ነበር፡፡ ይሄኔም ሉዊስ ድምፁን ወደሰማበት አቅጣጫ የእውር ድንብሩን ሲንቀሳቀስ ሰማች፡፡ ወዲያውኑ ግን ወለሉ ላይ
ስለወደቀ በስፓኒሽ ሲራገም ሰማች። ተጎድቶ ይሆን? በፍፁም፡፡ ምክንያቱም
መናገር ሲጀምር ድምፁ ጥርት ያለ ነበር። ድምፁ ውስጥ ህመምም ሆነ
ንዴት አይሰማም፡፡
“አንቺ ሸርሙጣ! ሰምቼሻለሁ”
ዝም ብላ ቆየች፡፡ በጣም ቀርቧታል፡፡ ምናልባትም አጠገቧ ሊደርስ አንድ
እርምጃ ብቻ ይሆናል የሚቀረው፡፡
“እየመጣሁልሽ ነው!”
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የጨለመው በጥልቅ እና በፍጥነት ነበር፡፡
ምድር ቤት የሚገኘው ዋናውን ፊዩዝ ያጠፋው ሉዊስን እና ፎቁ ውስጥ
ሊገኙ የሚችሉ የሉዊስ ሰዎችን ለማደናበር አስቦ ነው:: ይህን በማድረጉም ትንሽ የመዘጋጂያ ጊዜ ይኖረዋል፡፡ ጨለማው ሲውጠው ግን ጉድማን መብራቱን በማጥፋቱ ተፀፀተ።
ምድር ቤት ውስጥ አንገቱን አቀርቅሮ በጉልበቱ ተንበርክኮ ነው፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ጭለማው እና የምድር ቤቱ እምክ እምክ መሽተት ልክ የሬሳ ሳጥን ውስጥ ያለ መሰለው፡፡ ምንም አይነት ብርሃን የለም፧ ስለዚህ ማምለጥ አይችልም፡፡ ልቡ በጣም መምታት ጀመረ። ስለዚህም ቶሎ ቶሎ አየር በማስወጣት እና በማስገባት ራሱን እንደምንም ብሎ ለማረጋጋት ቻለ::
“አሁን አስብ' ብሎ ለራሱ ተናገረ፡፡
የሱሪ ኪሱ ውስጥ ስልኩን መፈለግ ጀመረ ሁሉንም ኪሶች ሲፈትሻቸው ስልኩን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ቢሮ ትቶት እንደመጣ ገመተ በመቀጠልም የመኪናው ቁልፍ ላይ ማግላይት
እንዳለው አስታወሰ እና ከኪሱ አውጥቶ አበራው፡፡ ምድር ቤቱ ጣራ ላይ

👍3
በጣም ትልልቅ የአልሙኒየም ቱቦዎች በብሎን ከጣራው ጋር ታስረዋል፡፡ ከኋላው ወደ
ምድር ቤቱ የመጣበት እና ወደ ላይ ወደ ጠባቡ መንገድ የሚያወጣው ቱቦ
አለ። ከፊዩዝ ሳጥኑ ሃያ ጫማ ርቀት ላይ ደግሞ ከምድር ወደ ላይ የሚያወጣ የብረት ደረጃ (መሰላል) አለ፡፡
ጉድማን እየዳኸ ወደ መሰላሉ አመራ፡፡ ሁሉ ነገር ፀጥ ብሏል፡፡ መብራቱን ካጠፋ ከሰኮንዶች በኋላ የተኩስ ድምፅ ሰምቷል፤ ከዚያ በኋላ ግን ምንም ነገር ሊሰማ አልቻለም። ሉዊስ ሮድሪጌዝ ህንፃው ውስጥ ይሆን? ወይንስ ኒኪን ከገደላት በኋላ ህንፃውን ትቶ ወጥቶ ይሆን? “እንደዚያ ከሆነ ደግሞ ህንፃው ውስጥ ብቻዬን ነዋ የምገኘው?' ብሎ እያሰበ እያለ ከላይ ቀጭን የህመም ድምፅ ሰማ። “ኒኪ?” አለ እና ሽጉጡን ጨብጦ ወደ ላይ በመሰላሉ ላይ መውጣት ጀመረ፡፡
ሉዊስ ሮድሪጌዝ ልክ እንደ አዳኝ ተኩላ ፀጥ ብሎ ሲያዳምጥ ቆየ፡፡ አጠገቡ እንዳለች ይሰማዋል። ጥይቱ ስላቆሰላት ቶሎ ቶሎ ስትተነፍስ ይታወቀዋል፡፡
ሽጉጡን ጥብቅ አድርጎ እንደ ያዘ ድምፅ ወደሰማበት አቅጣጫ ተወረወረ፡፡ አንድ ጊዜ ካገኛት በኋላ አንገቷን አንቆ ጭንቅላቷን ወለሉ ላይ ይደፋዋል። ከዚያም ይሄንን የሚስቱን አኔን ልብ ሲመርዙበት የነበሩ ቃላትን ሲያወጣ የነበረ ጭንቅላቷን በጥይት ይበታትነዋል። በቃ ከዚያ በኋላ እሱ
እና አኔ በሰላም አብረው መኖር ይጀምራሉ።
“የት ነው ያለሺው?” ብሎም ወደ ፊት ተጠጋ። አሁን የትም ልታመልጠው አትችልም፡፡ ነገር ግን ወደ ፊት ሲጠጋ አየር እንጂ ምንም ነገር ሊያገኝ አልቻለም፡፡ 'የት አባቷ ነው የሄደችው?' አለ ለራሱ፡፡
ይሄኔም ሀይለኛ የሆነ ምት ከእግሮቼ መሀል ተሰማው፡፡ አዎን ድብን
ያለ ምት ቆለጡ ላይ ሲያርፍበት ህመሙ ከቁጥጥሩ በላይ ስለሆነበት ቆለጡን ታቅፎ ወደ ወለሉ ሸብረክ አለ። ከኋላውም ልክ አይጥ ወደ ጉድጓድ
ስትሮጥ የምታሰማው አይነት ድምፅ ተሰማው፡፡
'ወይኔ ይህቺ ሸርሙጣ በእግሬ ሥር ሾልካ አመለጠችኝ! አሁን በእርግጠኛነት ወደ ብረቶቹ ደረጃ ነው የምትሄደው! አለ ለራሱ፡፡
እንደምንም ብሎ ቀና አለና ጭለማው ውስጥ እየተኮሰ “እገድልሻለሁ!
እገድልሻለሁ!” እያለ ማጓራት ጀመረ፡፡
ተሳካልኝ! አመለጥኩኝ አለች ኒኪ ለራሷ፡፡
ኒኪ የተኩሶቹን ድምፅ የሰማቸው ለእሳት አደጋ መውጫ የተዘጋጀው ጫፍ ላይ ስትደርስ ነበር፡፡ ላይ ከደረሰች በኋላ በሩን ከፍታ በደረጃው ወደ ታች ወደ ምድር የሚያወርዳትን የብረት መሰላል ተመለከተች፡፡ ከታች ከውጪ በኩል የሚመጣ የምሽቱ ደብዘዝ ያለ ብርሃን ይታያታል። ታች ከወረደች በኋላ ቢያንስ የሆነ የሚረዳኝ ሰው አላጣም ብላ ኒኪ በተስፋ ተሞልታ መሰላሉን መውረድ ጀመረች፡፡ ከሁለት ደረጃዎች በኋላ ግን
በጥይት የተመታችው ቁስል ስቃይ ከመጠን በላይ ስለሆነባት የያዘችው
መስላል ከእጇ አምልጦ ወደ ታች ወረደ፡፡ “እግሬን” ብላ እየጮኸች ወደቀች፡፡
የመጀመሪያው ፎቅ ላይ ያለ ኮንክሪት ላይም አረፈች። ራሷን ለጥቂት
ሰኮንዶች ያህል ሳተችና ወደ ራሷ ተመለሰች። ወዲያውኑም ከኮንክሪቱ ጥግ ላይ ከሚገኝ አንድ ጓዳ መሰል ነገር ውስጥ እየተሳበች ገባች እና ጥቅልል
አለች።
ለአፍታ ያህል ከባድ ሀዘን ውስጧን ተሰማው፡፡ እምባዋም አይኗን ሞላው። አሁን ካለችበት ቦታ ሃያ ጫማ ያህል ወደ ታች የእሳት አደጋው መውጪያ በር ይታያታል፡፡ ለጥቂት ለማምለጥ ችላ ነበር፡፡ አሁን አንዱንም ጡንቻዋን ማንቀሳቀስ አትችልም፡፡ ስለዚህ ሮድሪጌዝ መጥቶ ይገድላታል። ከእንግዲህ ይህ ያለችበት የህይወቷ የመጨረሻ ክፍል ይሆናል ማለት ነው።
እዚያው ጥቅልል እንዳለች አይኗን ጨፈነች፡፡ ወዲያውኑም ያልጠበቀችው አይነት ሙቀት መላ ሰውነቷን ይሞቃት ጀመር፡፡ የሆነ ደስ የሚል ስሜትም ተሰማት። ውስጧ የነበረው ሀዘንም ፍርሃቷን እና የቁስሏን ህመም አስከትሎ ከውስጧ ተንኖ ሲወጣ ይታወቃታል። በምትኩም ወፍራም የድካም ብርድ ልብሱን ጫነባት፡፡
ተኚ ኒኪ፡፡ መተኛት አለብሽ አለች ለራሷ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጉድማን የመስላሉ ጫፍ ላይ ከደረሰ በኋላ ወደ ላይ ተስቦ ወለሉ ላይ ወጣ፡፡ ክፍሉ ውስጥ በሚገኙት ከሁለቱ የቆሽሹ መስኮቶች የሚገባው ብርሃን የምሽቱን ደብዛዛ ብርሃን ወደ ውስጥ ያስገባሉ፡፡ ምድር ቤቱ ከዚህ በጣም ጭለማ ስለነበረ ግን አይኑ ወዲያው ነበር የተላመደው:: እና ማግላይቱን አጠፋው። ክፍሉ ትልቅ እና ባዶ መሆኑን ሲመለከት በደንብ ተረጋጋ።
በመቀጠልም ወደ ላይኛው ፎቅ ወደሚያወጣ አሳንሰር እየተንቀሳቀሰ እያለ ከታች ከምድር ቤቱ የሚያውቀው ድምፅ ስሙን ሲጠራው ባለበት ቆመ::
“ጉድማን እዚህ ነው ያለኸው” የሚለው የሚክ ጆንሰን የቦስተን አይሪሽ ድምፅ በህንፃው ውስጥ አስተጋባ።
ይሄማ አይሆንም! እንዴት ይሄ ዘረጦ ድቡልቡል ሰው እዚህ ሊገኝ ቻለ? ብሎ ራሱን ጠየቀ፡፡
“ሉው የት ነው ያለኸው?”
ጉድማን ደሙ ቀዘቀዘበት። አሁን የሚፋለመው ከሁለት ሰዎች ጋር ነው
ማለት ነው፡፡ ከሮድሪጌዝ እና ከጆንሰን ጋር፡፡ ኒኪን ጆንሰን ከማግኘቱ በፊት
ማግኘት ይኖርበታል። አለበለዚያ ግን ሚክን መግደል ይኖርበታል፡፡ ያ ባይሆን ምርጫው ነው። አብረው በቆዩበት አንድ ዓመት ውስጥ ሚክ ጉድማንን እንደ አንድ ዘመዱ ነው የሚቆጥረው። አሁን ግን ነገሩ የሞት ሽረት ጉዳይ ነው፤ ለመጠራጠርም ሆነ ለሀዘኔታ ጊዜ የለውም፡፡
ወደ አሳንሰሩ መሮጥ ጀመረ፡፡
ምድር ውስጥ ተንበርክኮ እየዳኸ ያለው ሚክ ጆንሰን በእጁ ላይ ትንሽዬው የእጅ ባትሪው ሲወድቅ መራገም ጀመረ።
የተረገመ ጉድማን!”
ጆንስን የባልደረባውን መኪና ውጪ ላይ ካገኘ በኋላ ልክ እንደ ጉድማን የተከተለውን መንገድ ተከትሎ በቱቦው በኩል ነው ወደ ህንፃው ምድር ቤት
መድረስ የቻለው። ጉድማን እዚህ ድረስ መምጣት ችሏል። ይሄው የወለሉ
አቧራ ላይ የሚገኙት የእግሩ እና የእጁ ምልክቶች። ወለሉ ላይ “ጂ የሚል
ፊደል የተለጠፈበት የተሠራ መሀረብ ወድቆ አገኘ። መሀረቡ የጉድማን
መሆኑን ያወቀው ደግሞ የጉድማን ሥም የመጀመሪያው ፊደል ስለተፃፈበት
ነበር፡፡ አሁን በዚህ ዘመን ይሄ ሰው መሀረብ ይይዛል?” ብሎ ጆንስን
ተበሳጨበት፡፡ ሁሌም በጉድማን ነገሮች እንደተበሳጨ ነው። ለማንኛውም አሁን ጉድማን ከአበሳጭነት ወደ አደገኛነት ተሻግሯል። ስለዚህ ማንኛውንም አይነት መስዋዕትነት ከፍሎ ሊያስቆመው ይገባል።
ዶክተር ኒኪ ሮበርትስ እሱን በፍፁም ማመን አልነበረባትም። የጉድማን አለቃ ሉዊስ ሮድሪጌዝ ኒኪን ካልገደላት እና ይህቺን መልካም ዶክተር በህይወት ቢያገኛት ጆንስን ምን ማድረግ እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል።
የእጅ መብራቱን አንስቶ የምድር ቤቱን ሲቃኝ የፊዩዙን ሳጥን ተመለከተ፡፡ ወድያውኑም የፊዩዙን ዋና ማብሪያና ማጥፍያ ወደ ላይ ሊመልስው መብራቱ ክፍሉን አጥለቀለቀው እና አይኑንን አጭበረበረው። ከላይ በኩል የሆነ ሰው ሲሮጥ ይሰማዋል፡፡
“ሉዊስ!” ብሎ ጮክ ብሎ ተጣራ፤ ድምፁም በህንፃው ውስጥ እያስተጋባ፡፡
የብረቱን መሰላል ይዞ ወደ ላይ መውጣት ጀመረ፡፡......
✨ይቀጥላል✨

👍3👎1
#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል
...አንድ ሰዓት ገደማ ከፈጀው የኅብረተሰብ ኑሮ ክርክራችን በኋላ
ከየወዲያሽ ጋር በስውር ስለ ፈጸምነው ፍቅራዊ ግንኙነት ቦጨቅጨቅ አድርጌ
ገለጽኩለት። በአውራ ጣቱና በሌባ ጣቱ መካከል እያሽከረከረ ሲያፍተለትላት
የነበረችውን ወረቀት አሽቀንጥሮ ወረወራት። የሚናገረውን እጅግም ሳያሰላስል
“አንዳንድ ሰዎች መጥፎ ነገርን ለማቀድና ለመፈጸም ምንኛ ይቀናቸዋል?
ሕይወትን ከመገንባት ይልቅ መናድና መበታተን እንዴት ይከሠትላቸዋል? ሌሎችን እፍ ባለ ገደል ላይ መገፍተር ደስ ያሰኛቸዋል?» ብሎ ከፊት ለፊቱ ቆሞ የሚታይ ተናካሽ ሐሳብ የቆመ ይመስል አፈጠጠ፡፡ ቀላ ያለውን ዞማ ጸጉሩን በግራ እጁ ወደ ፊትና ወደ ኋላ ማሻሸት ጀመረ፡፡ ምን እንደሚያስብ ባላውቅም ተበሳጨ፡፡ ሐሳቤንም ሆነ መላ አስተያዬቴን ሳይቀበለኝ ቀረ። አድራጎቴ ሁሉ በተራ እንስሳዊ ባሕሪ የተፈጸመ ስሕተት ብቻ ሳይሆን ወንጀል መሆኑንም አስረዳኝ::
ጭንቀት አጥለቀለቀኝ። ተገናናንታ ለመናገርና ለመፀጫወት ተዝናንታ
የቆየችው ምላሴ እሳት ውስጥ እንደ ገባች ጅማት ተኮማተረች።
«ልጓም አልባ ሥጋዊ ፍላጎትህን ለማርካትና ቅንጣት የሕይወት ደስታ
ለመቅመስ ስትል የሌላዉን የሕይወት መስኖ መድፈንና ዙሪያው ገደል
እንዲሆንበት ማድረግ መጥፎ ጭካኔ ነው። ሆምጣጣ ኑሮ እንዲጠብቀውና
እንዲሠቃይ ማቀድም ሰዎች ከሚፈጽሟቸው ነውረኛ ድርጊቶች መካከል አንዱ ክፍል ነው::
ሌላዉን ወደ ምድረ ፋይድ አሽቀንጥረህ አንተ ሽቅብ መመንጠቅ እንደማይገባህ ማወቅ ነበረብህ፡፡ ለአንተ በቂና ትክክለኛ የመሰለህ ምክንያት ሁሉ ለሌላዉ ስሕተትና ከንቱ ነገር ሊሆን ይችላል። እንዴት ሕይወትን በአንዲት ጠባብ የሕሊና መስታወት ብቻ ትመለከታታለህ? የሕሊናህ መስታወት ሰፊና
ንጽሕ መሆን አለበት» ብሎ ግንባሩን ማሻሸት ጀመረ፡፡ ማባሪያው እንዳልደረሰ
ገባኝ…. እውነትም ቀጠለ፡፡ «ይህን በመፈፀምና በርኩሰት የተጠቀለለ ጥቅም በማነፍነፍሀ ወደእንተ የኑሮ ደረጃ ልታደርሳት አትችልም፡፡ በሌሎች ላይ
የተተበተብክና የተንጠለጠልክ ግንደቢስ ሐረግ እንጂ ጠንካራና ሥር ሰድዳ
የበቀለች ችፍርግ ታህል እንኳ አይደለህም፡፡ በአንድ የሕይወት ጀልባ ላይ ለመንሳፈፍ የጋራ ውሳኔ ቢኖራችሁ ኖሮ እኔም በሐሳብሀ በተስማማሁ ነበር። ነገር ግን አንተና ብጤዎችህ ሁሉ ከሥሯ መነጋግላችሁ ለማድረቅና አበስብሳችሁ
ለመጣል ያሰፈሰፋችሁ ስግብግቦች እንጂ ለሰብአዊ እኩልነት መሥዋዕት ለመሆን እጃችሁን የምታነሡ እንዳልሆናችሁ ዕውቅ ነው:: የዚህ ዐይነቱን የግድ የለሽነት ድርጊትማ አንድ ተራ ኣራዊትስ ይፈፅመው የለም እንዴ? ገና ለገና ትተናኮለኝ ይሆናል ወይም ለምግብነት ትጠቅመኝ ይሆናል በማለት ሌላዋን የዋህ እንስሳ የሚያበክት አራዊትስ መች ጠፋና? ... ብሎ ክፍሉ ውስጥ ከተንቆራጠጠ በኋላ ፈንጠር ብሎ ሌላ መቀመጫ ላይ ተቀመጠ። ቀኝ እግሩ ግራ እግሩ ላይ ተደርባ
ወደ ፊትና ወደ ኋላ ስትወዛወዝ የሱሪውም ጫፍ አብራ ትርገፈገፋለች። ነገር እየቆፈረ ነው፡፡ በመስኮት በኩል ገብቶ እንደ ውሃ አዙሪት እየተሽከረከረ
ከሚወጣው አየር በስተቀር ሌላውን ድምፅ ተፈጥሮ የገዘተችው ይመስል ቤቱ
ረጭ አለ።
የጉልላት ቁጣና የክፍሉ ውስጥ ደንዳና ጸጥታ ስሜቴን አደነዘዘው:: ዐይኖቹ ጨፈን ገለጥ ጨፈን ገለጥ እያሉ ይርገበገባሉ፡፡ የዐይኑ እንቅስቃሴ
ዝምታን ጥሶ አካባቢውን ተንቀሳቃሽ ድምፆ ሊነዛበት አይችልምና ክፍሉ አውሬ
የማይላወስበት ውድቀት መመስሉን ቀጠለ፡፡ ብስጭቱ እየባሰበት በመሄዱ
በውስጡ ሲፈራገጥ የቆየው ንዴት ከንፈሩን እንደ ገጠመ «ህ እ» አሠኝቶ ዝም አሠኘው። ዝም ብዬ ማዳመጥ ፀጥ ብዪ በሐሳብ በትር መደብደብ ስለ መሰለኝ በውስጤ ያለውን ምክንያትና ሐሳብ ሁሉ ዘክዝኬ ለማቅረብ ተነሣሁ:: «አይ እንግዲህስ ሳይበቃህ አልቀረም» ብዬ በመጀመር «ምስጢሬን ያንዶለዶልኩልህና ሐሳቤን ያካፈልኩህ እውነተኛ ጓደኝነት ጠንካራ የሕሊና ግንኙነት ድልድይ በመሆኑ ነው:: ብሳሳትም ባልሳሳትም ባጠፋም ባላጠፋም የአንተ ሐቀኛ አቋም
የእኔ የሕይወት ምስክር ነው:: ያሰብኩትንና የወጠንኩትን የቸገረኝንና
ያጋጠመኝን ሁሉ ካላወየሁህማ የጓደኝነታችን ጥልቅ ትርጉምና መሠረቱ ምንድን ነው ሳልንገዳገድና ፊት
ለፊቴ ሳይጨግግ ልራመድና ልመለከትበት የሚያስችለኝን የአስተያየት መላ በማቅረብ ወደ ተደላደለ አካባቢ አዝልቀኝ እንጂ፣ መሳሳቴንማ እኔም ራሴ ቀደም ብዬ ተረድቸዋለሁ! » በማለት ጨረስኩ።ትኩር ብሎ አይቶኝ አቀረቀረና፣
«ብሳሳትም ባልሳሳትም ማለት አትችልም። አዎ ጓደኝነት የሁለት
ሰዎች መገናኛ የሕሊና ጋብቻ ናት” ብሏል አንድ የፈረንሳይ ምሁር ብሉ ጀመረና፣ ሙሉ ልቦናህ ጭምር እንጂ ሥጋዊ አካልህ ብቻውን ዘላቂና ድርጁ
አያደርገውም፡፡
ያውም ይኸ የአንተ አድራጎት የሌሎችን ሕይወትና ኑሮ የማጥቆሪያና የማሰናከያ ግልጽ ዝሙት እንጂ የጋብቻን ጠርዝ እንኳ የሚነካ ኢምንት የታማኝነት ድርጊት አይደለም፡፡
«በአንተና በእኔ ዐይነት ኑሮ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ቁልቁል ወርዶ መኖር የሞት ያህል ያስፈራቸዋል። በሌሎች ትከሻ ላይ ቆመው ወደ ላይ መውጣት የሚጥማቸውን ያህል ወደ ታችኛው ኑሮና ዓለም መውረድ ግን እጅግ ስለሚመራቸው በኃይልና በግዴታ ካልተዘረጠጡ በቀር አይንበረከኩም፡፡
አይወርዱም፡፡»
“ምንም እንኳ የልብ ጓደኛዬ ብትሆን ለአካባቢህ ኅብረተሰብ መርዝ ሆነህ
የሌላውን ሕይወት ለማጨለም ስትጣጣር ላይም ሆነ ስሰማ ዝም አልልህም።አንድ ሰው 'ጓደኛዬ ነህ' ሲልህ ጠላቴ አይደለህም ማለቱ ነው:: ስለዚህም ከጠላት የሚለይበትን አብይ ቁም ነገር በሚገባ ማሳየት ይገባዋል» ብሎ ነገር ለማብላላት ተግ አለ፡፡ ውርጃብኙን ፈርቼ ዝም ኣልኩ። በቅሬታ ጉልበቱን መታ መታ አደረገና ያም ሆነ ይህ ጠላትህን ከማሞገስ ደካም ወዳጅህን ማሻሻልና ማረም ወደር የሌለው መልካም ተግባር ነው» ብሎ ከወንበሩ ላይ ተነሳ።
ቁጣውን በወንድማዊ ትህትናና ለዘብታ ለማቀዝቀዝና ለመግባባት በመፈለጌ ጥፋተኝነቴን በምታስረዳ ልም የጸጸት ፈገግታ ትክ ብዬ እያየሁ «መቼም በእኔ በኩል ያለው ነገር እንደ ከረመ እንቁላል በስብሷል። ከአንተ የምጠብቀው ደግሞ የቁጣ ቃላት ዶፍ ሳይሆን አራሚነት ያለው ተጨባጭ ድጋፍህን ነው» ብዬ ንግግሬን ሳልጨርስ ድጋፍ የምትጠይቀው አስነዋሪ ድርጊትህን የመደበቂያና ከማታመልጠው የሕሊና ፍርድ የማምለጫ ጥያቄ እንጂ እውነትን ለማፍረጥረጥ እና ለእርሷ እንደ ጸጉር የቀጠነችባትን የሕይወት ጐዳና
ለማስፋትና ለማደላደል አይደለም። እንደ ቀስተ ደመና አምረህ ለመጉበጥ እንጂ
መሰናክል እንዳላጋጠመው የብርሃን ጨረር ቀጥ ብለህ ለመጓዝ አይደለም» ብሎ ፊቱን አዙሮ ቆመ፡፡ «እኔ የምልህ እኮ፣ ዛሬ በምን ላይ ቆሜ ስለ ነገ በምን ሁኔታ መዘጋጀት እንደምችል ንገረኝ ነው:: በእኔ መዘዝ አስቸጋሪ ሕይውት
የሚያጋጥማትን ሰው በእጄ እየሳብኩ ወደ ትክክለኛ ዓለም የምትዘልቅበትን
መንገድና ዘዴ አሳየኝ ነው የምልህ» ብዬ በድፍረት መለስኩለት::
ድንገት ሳላስበው ፊቱን ወደ እኔ መለስ አደረገና የጊዜ ርዝመትም ሆነ እጥረት ያው ነው:: አንድን ተግባር ለማከናወን የሚፈጅብህን ጊዜ ማሳጠር ይቻላል፡፡ የአንዲት ደቂቃ የሕይወት ርዝማኔ ግን ምንጊዜም ቢሆን ያው ነው:: ትልቁ ግብግብ ያለው ካንተው ከራስህ ጋር ነው:: ሰው የለውጥ ምንጭ ነው፡ ነገ
ላይ ቆሜ፣ ዛሬ ላይ ተንበርክኬ ማለት የችግርህ ማቃለያ አይሆንም፡፡ ስንዘጋጅና
ዛሬ ነገ ስንል እፍኝ የማትሞላዋ ዕድሜያችን እንደ ማሰሻ ጨርቅ ነድዳ ነድዳ ታልቃለች ፡፡ የአንተ

መስተካከያና መታነጫ ዛሬ እንጂ ነገማ የፍጻሜህ ዕለት ሊሆን ይችላል፡፡ ራስህን ድል ሳታደርግ በሌላው ላይ አትዝመት፡ በእድፍ ቅመም የተሰራ ሳሙና ሊያቆሽሽ እንጂ ሊያጸዳ አይችልም» ብሎ ጥቂት ዝም ካለ በኋላ «ሐሳብና እምነታቸውን ታውቀዋለህ፡፡ የወላጆችህ አጥንት፣ ሥጋ፣ ደም ክብርና ከንቱ ዝና ሁሉ ባንድ ጊዜ ተረስቶና ስንኩል እምነታቸው በመንፈቅና በዓመት ውስጥ ተለውጦ እሷን የሚቀበሉልህ ይመስልሃል? እንጃ! ይህ በትላንትና እና በዛሬው ትውልድ መካከል የይለይለት ሰይፍ የሚመዘዝበት የአመለካከት ጦርነት ነው» ብሎ ገረመመኝ፡፡
«እኔ መኖርና መግኘት የምፈልገው እኔን በሚመስለኝና በሚስማማኝ የአኗኗርና የሐሳብ አካባቢ እንጂ በእነርሱ የእምነት እና የአመለካከት ክልል አይደለም» ብዬ ከተቀመጥኩበት እስከምነሣ ካፌ ላይ ቀልቦ «አይሆንላቸውም እንጂ ቄሶች ሲሰብኩ ገነት ይቺ ናት፣ ሲኦል ያቺ ናት እያሉ በማሳየት ቢያስተምሩ እንዴት ደስ ባላቸው! ያሻህን ያህል ዕወቅ፣ ያስፈለገህን ያህል ምጠቅ፣ አንተን በልዩ ልዩ ሁኔታዎች የሚዳኝህ አካባቢህ ነው:: ለብቻህ ተነጥለህ ልትንሳፈፍ አይቻልህም አንተ በምትፈልገው ዓለም ውስጥ መኖር የምትችልበት ጊዜና ትውልድ ገና አልደረሰም:: ሕይወት የምትስተካከልበት ጊዜ ገና ነው።በጣም በጣም ሩቅ ነው። ያም ቢሆን የራሱ ሕግና የኑሮ ሥርዓት ይኖረዋል፡፡
ቀልድና ምር የየራሳቸው ጊዜና ቦታ አላቸው የወንዝ ዓመቴ ከምትንሳፈፍበት
ወንዝ ላይ ተነሥታ እስከምትበርበት ጊዜ ድረስ መላ አካሏን የምታሳርፈው
በውሃው ላይ ነው። የሕዝቡን ሕይወት ለመለወጥ የምትችለው በሕዝቡ ሕይወት
ውስጥ እየኖርክ ነው” ይባላል፡፡ የአንተም አስተሳሰብና የአኗኗር አመራር የሚመራውና የሚታዘዘው በአካባቢህና በውስጡ በሚገኙት የአብዛኛዎቹ ሰዎች
ትክክለኛ አስተሳሰብ እንጂ በዘፈቀደ የሚመራ ልዩ የኑሮ ደሴት ልትመሠርት
አትችልም። አንዲት ጠብታ ወለላ በአንድ ጋን መርዝ ውስጥ ምን ያህል ለውጥ
ታመጣ ይመስልሃል? ካልተመጣጠንክ ትወድቃለህ፡፡» ብሎ መጀመሪያ ወደ
ተቀመጠበት ቦታ ተመለሰ።
«ያበላሽሁትንና ያሰናከልኩትን ለማስተካከልና ለማቃናት ከቻልኩ ሙሉ
ሰው መሆኔን ዐውቃለሁ፡፡ በግድ የለሽነትም ያደናቀፍኳት ሕይወት የጸጸት ረመጥ ሆና ስታቃጥለኝና ስታሠቃየኝ እንድትኖር አልሻም፡፡
«ባስገደደኝ ችኩል ስሜት ተመርቼ የፈጸምኩትን በደል ሁሉ ለመደምሰስና ከእርሷ ጋር እስከ ዳር ለመዝለቅ ቃል እገባለሁ» ብዬ ሌላው የማቀርበው ሐሳብ ስለ ጠፋብኝ ዝም አልኩ፡፡
“ይህን መሰሉን ማኅበራዊ ችግር ብቻዬን አቃልላለሁ ብለህ አትወጠር፡፡
ማኅበራዊ ችግር የሚፈታው በሕዝብ ማኅበራዊ ትግል ነው :: የውሽት ባሕር ጤዛ የምታህል እውነት ሊሆን አይችልም። የአንድ ነገር ምስጢርና ይዞታ እስኪገለጽና እስኪታወቅ ድረስ ተለዋዋጭነት ያለው አይመስልም ይሆናል፡፡ ሰዎች ስንባል ሐሳባችንን ቆልምመን ስሜታችንን ለመግታት ያለን ጥንካሬ የተለያየ ነው፡፡ እንዲያውም የሐሳባቸው እስረኞችና ተገዢዎችም አሉ» ብሎ አፉን አባበሰ፡፡
«አንዲት ውብ አበባ እስከምትጠወልግ ድረስ እንኳ ረጋ ብለን በትዕግሥት
እናያትም፡፡ የመጀመሪያ አፍላ ውበቷ እንጂ በድርቀቷ ውስጥ የሚገኘው መልኳ
አይታየንም፡፡ አንተም እንዲሁ የዛሬውን የለጋነት ውበቷን ከአካባቢህ ተኩላዎች
ጋር ከተሻማህ በኋላ የሕይወቷ ዓዕም ብቻ ሲቀር በጥላቻ ተፍተህ ከፍላጐትህ
ውጭ ታደርጋታለህ ! » ብሉ ከግንባሩ እስከ አገጩ ድረስ ፊቱን ጠረገ፡፡
«ይህን ዐይነቱን ስሕተት በመፈጸም እኮ የመጀመሪያው ሰው እኔ አይደለሁም» ብዩ ጀመር ሳደርግ የመጀመሪያዉም የመጨረሻዉም አለመሆንህንና እንደማትሆንም አሳምሬ ዐውቃለሁ፡፡ በመጀመሪያ የሚያጋጥምነገርና እጅግም ልብ ሳይባልና ሳይታረም ያልፍ ይሆናል። የእያንዳንዱ ሰው ባህሪም የየራሱ መታወቂያና መለያ መሆኑን በሚገባ ዐውቃለሁ» ብሎ አንደ ፌንጣ ዘሎ
ጥሉኝ ወጣ፡፡
ፊት ለፊቴ ግዙፍ የሐሳብ ተራራ ስለ ተደነቀረ ወደ ፊትም ወደ ኋላም
መሄድና መንቀሳቀስ አቃተኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ከራሴ ጋር የሐሳብ ትግልና ግብግብ ገጠምኩ።
ጌታነህ አልኩት ራሴን ከራሴ ጋር የማደርገውን ክርክርና ውጣ ውረድ
ስጀምር ቅንነቷንና ደጊቷን የወዲያነሽን እስከ መጨረሻዉ ለመሸከም አትችልም
ወይ? ጉልላት እንዳለው የሕይወቷን አፍላ ውበት በወረት ዐይን መግምገህ
ከልብህ ውስጥ ትተፋታለህ ወይ?” ብዬ ራሴን ጠየቅሁ፡፡ ሆኖም ጠቃሚ ነገር
እንደ ማሰብና እንደ መፈጸም አስቸጋሪ ነገር ስለሌለ ፈጣን ውሳኔ መስጠት
እያደር የሚንተገተግ እንጂ የሚጠፋ አለመሆኑን ስለማውቅ በልቤ ውስጥ
አቃተኝ፡፡ ራሴን የመፀየፍ ያህል ታዘብኩት። ከየወዲያነሽ ጋር ያለን ደማቅ ፍቅር የሚበራው ተስፋ ቀጠለ፡፡
ጉልላትም ቢሆን ይህን ጉዳይ እየዋለ እያደረ እንደሚረዳልኝ ጽኑነቴንም
ተመልክቶ እንደሚያበረታታኝ ዐውቅ ነበር፡፡ ጉልላት ፊቱን እንዳኮፋተረ ተመልሶ
ገባ።
ራሱን እየነቀነቀ ከተቀመጠ በኋላ «ተገዢነቷንና የበታችነቷን ምክንያት
በማድረግ የግዴታ ውዴታ ባስከተለው እሺታ ተጠቅመህ ለፈጸምከው በደል ምን ዓይነት ካሣ እንደምታቀርብ አላውቅም፡፡ እያንዳንዱ አእምሮ የየግሉ ዘዴ ይኖረዋል። እስከ መጨረሻው በእውነተኛ ቃልህ ተጠቅመህ ከጸናህም ሐቅን ለማግኘትና ውጤቷንም ለማየት እንደምትችል እርግጠኛ ነኝ፡፡ ግን የሕይወቷን ዳመራ ሳይሆን የሕይወቷን ዐመድ ለማየት የምትሻ ከሆንክ ሰው የመባያህ ቅመምና ትርጉም ሁሉ ከእለት ወደ እለት እየተፈቀፈቀ ይጠፋል። ነገም ከነገ ወዲያም የምታደርገውንና የምትፈጽመውን ሁሉ እየተከታተልኩ ሐሳቤንና ምክሬን አካፍልሃለሁ፡፡ ግን ወላዋይ መሆን የለብህም!» ብሎ ዝም አለ። ጉልላት ቀስ በቀስ ቀዘቀዘ፡፡ ሣቅና ጨዋታ ጀመርን፡፡ እንደተለመደው ቤቱን ፈገግታ አርከፈከፈበት። ከዚያ በኋላ ጠቅላላ ታሪኩን ከሥር መሠረቱ አንጠርጥሬ ነገርኩት።
ምንጊዜም ቢሆን በተለይ እሑድ እሑድ ከጉልላት ጋር ስለ ልዩ ልዩ ጉዳይ ቢያንስ ቢያንስ አንድ ሰዓት ያህል ክርክርና ውይይት ሳናደርጋ አንለያይም፡፡ ጉልላት ቁመቱ ዘለግ፣ ከወደ ትከሻው ሠፋ ብሎ ወደ ቅላቱ ወሰድሰድ ያደረገው ጸጉሩ ቀላ ያለ ዞማ ሲሆን ከወደ ግንባሩ ገለጥ ያለ ነው።ፊቱን ከግንባሩ የጀመሩ ወደ ታች ሲመለከቷት ሾጠጥ እያለች መጥበብ
የምታልቅ፡ የኻያ ስድስት ዓመት ወጣት ነው:: የንግድ ሥራ ኮሌጅ የሁለተኛ
ዓመት ተማሪ በነበረበት ጊዜ ትምህርቱን አቋርጦ ሥራ ጀመረ። ከአንድ ዓመት
ቆይታ በኋላ እንደገና የማታ ትምህርት ቀጠለ፡፡ «አብዛኛውን ጊዜ የሚመድቡኝ
ከሙያዩ ውጪ ነው:: የግብርና ሙያ የተማረውን የአናጢነት ሥራ ይሰጡታል።
ስለዚህ አመዳደባቸው ሁሉ ፍልስልሱ የወጣ ነው እያለ በመቃወም ከከራት
በማያንሱ የግል ሥራ ድርጅቶች ውስጥ እየተዘዋወረ ሠርቷል፡፡
አባቱ የሞቱት የ10 ዓመት ልጅ ሳለ ነበር። የነበራቸውን ሀብትና ንብረት ሁሉ ለእናቱ ለእርሱና ለእኅቱ በኑዛዜ አውርሰዋቸዋል። በከተማና በገጠር ያለው ንብረት ሁሉ መተዳደሪያቸው ነው፡፡ የሁለታችን ጓደኝነት ከልጅነታችን ጀምሮ የቆየና የደረጀ በመሆኑ እኔ ስለ እርሱ እርሱም ስለ እኔ ጠባይና ሁኔታ በሚገባ እናውቃለን፡፡ ምስጢረኞች ነን። የገንዘብም ይሁን የሌላ ጉዳይ ችግርና ሐሳብ ሲያጋጥመን በሙሉ ተስፋ ልቤን ሞልቼ የምሄደው ወደ ጉልላት ነው፡፡
አባቱ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ በሠሩት ቤት ውስጥ እርሱና አንድ ፈት የሆነችው እኅቱ ከእናታቸው ጋር ይኖራሉ። የሚናገረውን ሐሳብ በቆራጥ ልቦና
ሥራ ላይ ለማዋልና ለመፈጸም በሚያደርገው መልካም ጥረትና ትዕግሥት ወለድ አፈጻጸም ከራሱ ይልቅ ሌሎችን ይጠቅማል፡፡
ቆንጆ

ሴት ባየ ቁጥር ከዐይኑ እስክትሰወር ድረስ የግልብጥሽ እያየ ባይኑ ይከተላታል፡፡ ለምን በዐይኑ እንደሚሸኝና ትክ ብሎ እንደሚመለከት ሲጠየቅ «ቆንጆ ማየት ኃጢአት እይደለም» የምትል ከባሕር ማዶ የመጣች ፈሊጥ አለችው::
ከንግድ ሥራ ነክ መጻሕፍት ሌላ ስለ ማኅበራዊ ኑሮ የተደረሱ መጻሕፍት መከታተል እጅግ ሲያስደስተው የታላላቅ ሰዎችን ታሪክና የትግል ሕይወት አዘውትሮ ማንበብ ያረካዋል። ካለፍ ካለፍ የወደዳቸው ሴቶች ዐልፎ ዐልፎ በሚያሳየው ሐሳበ ግትርነት የተነሣ ስሜታቸው እንደ ማለዳ አመዳይ ረግፎ
ይለዩታል። እርሱም በበኩሉ እንደ አማጭ እያዘገመ መፈላለጉን አይተውም፡፡
በተገናኘን ቁጥር ስለ እኔና ስለ የወዲያነሽ ፍቅር ስለምተርክለት ሐሳብ ለሐሳብ ተግባባን።
መጋቢት አቦ ካለፉ አራት ወሮች ተቆጠሩ፡፡ የየወዲያነሽ ውበት እንደ
ክረምት ጅረት በተፈጥሮ አሳላፊነት መሙላቱን ቀጠለ።
💫ይቀጥላል💫

#ክፍል_ሃምሳ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
...የብረቱን መሰላል ይዞ ወደ ላይ መውጣት ጀመረ፡፡
ሉዊስ ሮድሪጌዝ የኮሪደሩ መብራቶች በሙሉ ሲበሩ አይኑን ሽጉጥ በያዘበት እጁ ከለለ፡፡ ከታች ስሙ ሲጠራ ሰምቷል። የእነርሱን ጉዳይ የኒኪን ጉዲይ ከጨረሰ በኋላ ያስኬደዋል። አሁን ግን ኒኪን መግደል አለበት፡፡ እሷን የመግደሉ ሀሳብ በጣም አስደስቶታል። ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆለጡ ላይ የሚሰማውን ህመም ችላ ብሎ ለእሳት አደጋ መውጫ ወደ ተሠራው የብረት ደረጃ አመራ።
እየመጣሁልሽ ነው አላት በዜማ ድምፅ እና ወደ ላይ ደረጃውን መውጣት ጀመረ። “የት ነው ያለሺው ነይ ወደ እዚህ!” እያለ ደረጃው ላይ የተንጠባጠበውን ጥቁር ደም እየተመለከተም ከደረጃው ጫፍ ላይ ከሚገኘው በር ላከ ደረሰ።
ሙሉ በሙሉ የበሩት የህንፃው መብራቶች ኒኪን ከእንቅልፏ አነቋት፡፡
ግን ተመልሳ ለዘላለም እንድታንቀላፋ ትደረጋለች፡፡ አዎን ልክ ዊሊ ባደንን
እንደገደለው እሷንም ያለችበት ቦታ ድረስ መጥቶ ሉዊስ ሮድሪጌዝ ይገድላታል። በቃ ከዚያ በኋላ ከባሏ ዶውግ ጋር ትገናኝ እና መልስ ላልተገኘላቸው ጥያቄዎቿ እራሱ መልስ ይሰጣታል። እውነታውንም
ታውቃለች ማለት ነው፡፡
“በጣም ነው የደከመኝ
ወደ ታች አይኗን ልካ በጥይት የተመታው እግሯን ተመለከተች፡፡ እንደ ቅድሙ ሀይለኛ ህመም አይሰማትም፡፡ ከዚያ ይልቅ ግን ቀዝቃዛ ውቅያኖስ
ውስጥ እንዳለች ሁሉ እግሯን በጣም ደንዝዟታል።
ከላይ በኩል ያለው የእሳት አደጋ መውጫ በር ተከፈተ እና የሮድሪጌዝን
ጭካኔ የተሞላበት የሹፈት ጥሪን ማዳመጥ ጀመረች።
“ዶክተርዬ የት ነሽ? እየመጣሁልሽ ነው እኮ” ይላታል፡፡
ፍርሃቷ ተመልሶ መጣባት፡፡ ከህመሟ የሚበልጠው ጥልቅ የመኖር ጉጉትም ውስጧን ተናነቃት፡፡ ስለሆነም ወደ ኋላ ወደ ጓዳው ግድግዳ እየተንፏቀቀች ተጠጋች እና ኮንክሪቱ ጋ ስትደርስ ተደግፋው ቁጭ አለች። ከተቀመጠችበት ቦታ ሆና በመጀመሪያ ጥቁሩን እና በደንብ ተደርጎ የተወለወለውን ጫማውን ተመለከተች፡፡ በመቀጠል ደግሞ እግሩን እና ሱሪውን፡ ከንፈሯም በፍርሃት የሆነ የልመና ድምፅ ሲያወጣ ይታወቃታል።
ይሄው አገኘሁሽ የኔ ውድ” አላት አጠገቧ እንደ ጅብራ ተገትሮ እንደቆመ፡፡ ሽጉጡን አዘቅዝቆ ይዞታል፡፡ ቀና ብለሽ ተመልከቺኝ” አላት፡፡ ኒኪም እንዳጎነበሰች ራሷን በአሉታ ነቀነቀች፡፡
ቀና ብለሽ እይኝ አንቺ ሸርሙጣ!” ብሎ ሲጮህባት ግን ኒኪ የግዷን ቀና
ብላ አየችው።
አቤት አይኖቹ! ውስጣቸው ያለው ጭካኔ ይታይባቸው ኖሮ እንዴት ያምሩ ነበር፡፡ ግን እነዚያ ቡናማ ውብ አይኖቹ ውስጥ የሚታዩት ጭካኔ ምህረት አልባነት እና ጥላቻ ስለሆነ ውበቱን አደብዝዞታል፡፡
ሽጉጡን ቀስ ብሎ ወደ እሷ ጭንቅላት አስጠግቶ በስስ ከንፈሮቹ ፈገግ
እያለ ተመለከታት።
“ሮድሪጌዝ መሳሪያህን ጣል ፖሊስ ነኝ
እንዳትተኩስባት!” የሚለው የጉድማን ድምፅ እንደ ህልም ሆኖ ይሰማት ጀመር፡፡
ሉዊስም ቢሆን ልክ እሷ የተሰማት አይነት ስሜት ነበር የተሰማው::
የሽጉጡን አፈሙዝ ግምባሯ ላይ ለጠፈው።
“ከኋላህ ነኝ ሉዊስ እንዳትተኩስባት” አለው፡፡
ኒኪም ጉድማን መሰላሉን ወርዶ ከሉዊስ ጀርባ ላይ ሽጉጡን እንዳነጣጠረ ተመለከተች፡፡ የደንብ ልብሱን ባይለብስም ሁሉ ነገሩ ግን በራስ
መተማመኑን እና ስልጣን ያለው መሆኑን ያሳያሉ። ግጥም ያለ መንጋጋው
እና ትዕዛዝ የሚሰጥበት ድምፁ ደግሞ ለዚያ ማሳያ ናቸው።
'የእኔ ህይወት ሊታደግልኝ ነው እዚህ ድረስ የመጣው! እና ጥልቅ የሆነ እፎይታ ሰውነቷን ወረራት።
ሮድሪጌዝም መሳሪያውን ወለሉ ላይ ጣላ እና ወደ ጉድማን ዞረ፡፡
ዘና ብሎ ጉድማንን ልክ በፊት እንደሚያውቀው ሰውም ያናግረው
ጀመር፡፡ “ፖሊስዬ አየህ አልገደልኳትም፡፡ ስለዚህ ለእሷ ያለህን ፍቅር ማሳየት ችለሃል” አለው እና ትንሽ ስቆ
“እሺ ከዚህ ቀጥሎስ ልታስረኝ ነው?” ብሎ ሁለቱን ክንዶቹን ወደ
ጉድማን ዘረጋ፡፡
ይሄ ሰውዬማ ዕብድ ነገር ነው፡፡ ብላ ኒኪ አሰበች። በቃ መጥፎ ብቻ ሳይሆን ዕብድ የአእዕምሮ ሆስፒታል ውስጥ ገብቶ ህክምና መከታተል የሚገባው ሰው ነው አለች በውስጧ፡፡
ጉድማንን ቀና ብላ እየተመለከተች በእስረኛው እጅ ላይ የእጅ ሰንሰለት
(ካቴና) ከማስገባቱ በፊት ለእስረኛው ስለመብቱ የሚናገረው ነገር ካለ ብላ
ጠበቀች፡፡ አዎን ሮድሪጌዝ ታስሮ ከአጠገቧ እስካልሄደ ድረስ ፍፁም ሰላም
አይሰማትም። መሳሪያ ባይዝ እንኳ በባዶ እጁ እንደሚጨርሳት..
ድው' የሚለው ብቸኛ የጥይት ድምፅ ተሰማት።
የሮድሪጌዝን ጭንቅላት አፈነዳው። የጭንቅላቱ የተበታተኑ አጥንቶች
እና አንጎሉም በብረት መሰላሉ ላይ፣ በኒኪ ልብስ ላይ፣ በኒኪ ፊት ላይ እና
እጆች ላይ ከደም ጋር ተቀላቅለው ተበታተኑ።
በዝግታ የጉድማንን ሬሳ ተሻግሮ ኒኪ ወደምትገኝበት ግድግዳ ተጠጋ እና
ለስላሳ እጁን ደም የነካውን ጉንጫ ላይ አሳረፈ።
“ልታስረው አልፈለግክም!”
“አዎን አልፈለግኩም!” ብሎ መለሰላት፡፡
ይሄኔም ኒኪ በሀይል መንቀጥቀጥ ጀመረች። በመቀጠልም በጣም
እየተንሰቀሰቀች አልቅሳ ተረጋጋች
“አመሰግናለሁ!” አለችው እና በሁለቱ እጆቿ አንገቱን አቅፋ ልጥፍ አለችበት።
ለጥቂት ጊዜ ያህል አቅፋው ከቆየች እና የደህንነት ስሜት ከተሰማት በኋላ ከእቅፉ ተላቅቃ ግድግዳውን ተደገፈች። እግሯ ሙሉ በሙሉ ደንዝዟል። ወደ ሆስፒታል በቶሎ መሄድ ይኖርባታል፡፡
“ህይወቴን ስላተረፍክልኝ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ።” አለች እና በአይኗ አይኑን ፈለገችው፡፡
እሱም አይኑን መልሶ አይኗን ሲያያት ግን ለሰከንዶች ያህል ኒኪ ግራ ተጋባች:: አይኑ ውስጥ ቅድም ሮድሪጌዝ ሊገድላት ሲል ያየችውን ነገር ተመለከተች። ሰይጣንን፡፡
“በጣም የምትገርሚ ደደብ ሴት ነሽ” አላት እና ሽጉጡን ጭንቅላቷ ላይ
ደገነባት፡፡
ከዚያም ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰማ እና ሁሉም ነገር ፀጥ አለ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ፊዮና ማክ ማን በጉድ ሰማርቲያን ሆስፒታል ውስጥ የምትሰራውን ስራ ትወደዋለች ፊዮና ነርስነትን እንደ ሥራ ሳይሆን እንደ የእጅ ሙያ ነው የምትቆጥረው፡፡ ማለትም ሌሎችን ለማገልገል በፈጣሪ ጥሪ እንደተደረገለት የቤተክርስቲያን አገልጋይ ነው የምታየው። “ጥሪያችንን ተከትለን በምንሥራው ሥራ አይደል እንዴ ገቢያችንን የምናገኘው?” እያለች እናቷ ጆኒ ትቀልድባታለች፡፡
እንደ ዕድል ሆኖ ደግሞ ሆስፒታሉ የሚከፍላት ክፍያ በጣም ጥሩ ነው።
በየቀኑ በጣም ጥሩ ሀኪሞች እና ነርሶች ጋር ነው የምትሰራው። በዚያ ላይ
ደግሞ የምታክማቸው ሰዎች የተለያዩ መሆናቸው ያዝናናታል። አንድ
አንዶቹ በጣም ህመም መቋቋም የሚችሉ ሰዎች ሲሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ
ደጎች እና ሰዎችን አክባሪ ናቸው። አለ አይደል ለተደረገላቸው አገልግሎት
ምስጋናን የሚያቀርቡ ናቸው፡፡ በእርግጥ ሌሎችም አይነት ሰዎች አሉ::
የሚያመናጭቁ ሱሰኞች፣ በሽታቸው በጣም የሚያስቃያቸው ሰዎች ወይንም
ደግሞ ቁስላቸው እና በሽታቸው ሊታከምላቸው የማይችሉ ሰዎችም
ይገጥሟታል፡፡
ፊዮና የክፍሉን መጋረጃ ገልጣ ፀሐይ እንዲገባ ካደረገች በኋላ ዞር ብላ
አልጋው ላይ የተኛችውን ታካሚ ተመለከተቻት፡፡ እግሯ ላይ በጥይት
ተመታ እና ብዙ ደም ከፈሰሳት በኋላ ነው ወደዚህ ሆስፒታል ሌሊቱን ይዘዋት የመጡት፡፡ በጥሩ ሁኔታ የቀዶ ጥገና ከተደረገላቸውም በኋላ ቢሆን
አንድ አንድ በሽተኞች በጣም ሊጎዱ ወይንም ደግሞ ልባቸው ላይ ጉዳት
ሊደርስባቸው ይችላል፡፡ ወይንም ደግሞ ለሰዓታት፣ ለቀናት ወይም ደግሞ
ሳምንታት ያህል በደረሰባቸው አደጋ ሊሰቃዩ አዕምሮአቸው ሊረበሽ ይችላል

ለማንኛውም አሁን አልጋ ላይ የምትገኘው በሽተኛ ፊት ገፅታ ጥሩ
ይመስላል። ደሟ ውስጥ ያለው የኦክሲጅን ደረጃም መልካም ይመስላል።
መስኮቱ ደፍ ላይ የሚገኙ አበቦችን እያስተካከለች ወደ ታች ስትመለከት
ከሆስፒታሉ ህንፃ መግቢያ በር ላይ ሪፖርተሮች፣ የቴሌቪዥን ጋዜጠኞችና
ቪዲዮ ቀራጮች እጅብ ብለው በመቀመጥ የበሽተኛዋን መንቃት በትጋት
እየጠበቁ ይገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ፖሊሶች ኮሪደሩ ላይ ተቀምጠው
የበሽተኛዋን መንቃት ይጠብቃሉ፡፡ በሽተኛዋ ላይ አደጋ ከደረሰ 48 ሰዓት
ያለፉ ቢሆንም አሁንም ቢሆን የዜና ማሰራጫዎች ሁሉ የሚዘግቡት እዚህ
ክፍል ስለተኛችው ታካሚ ነው::
“ሄሎ”
የሚል ድምፅ ከበሽተኛዋ አልጋ አካባቢ የሰማችው ፊዮናም “ኦ በእግዚአብሔር ነቃሽ እንዴ! ቆይ ዶክተር ራይሌን ልጥራው::” አለቻትና ወደ በሩ
ስታመራ የበሽተኛዋ በጭንቀት የተሞላው ድምፅ ክፍሉ ውስጥ እንድትቆይ
አደረጋት፡፡
እዚህ መገኘት አይገባኝም ነበር፡፡ ለምንድነው እዚህ የተገኘሁት?” ብላ
ጠየቀቻት፡፡
“አይዞሽ ተረጋጊ። አንቺ የምትገኘው በጉድ ሰማርተያን ሆስፒታል ውስጥ ነው። እዚህ የመጣሺውም ከ” ብላ ፊዮና ተናግራ ሳትጨርስ “አይሆንም!” ብላ ኒኪ ጮኸችና “እኔ ሞቻለሁ!” ብላ ራሷን ትራሱ ላይ ወረወረችና ራሷን ሳተች። ወዲያውም የተገጠመላት ማሽን ድምፅ ያሰማ ጀመር። የልብ ምቷን የሚያሳየውን ማሽን ስክሪን ላይ የሚታየው ቁጥር
ወደ ታች መውረድ ጀመረ::
ይህንን ያየችው ፊዮናም በጣም ደንግጣ የክፍሉን በር ከፈተች፡፡ ኮሪደሩ
ላይ ሆና “ዶክተር ራይሌ እዚህ ክፍል በአስቸኳይ ይፈለጋል።” ብላ
ተጣራች፡፡
ዶክተር ሳም ራይሌ እየሮጠ የክፍሉን በር በርግዶ ገባ። ሳም ራይሌ በጉድ ሰማርተያን ሆስፒታል ውስጥ ምርጥ የቀዶ ጥገና ሀኪም ነው።
ይህችን ታካሚውን ደግሞ በደንብ አድርጎ ነው ቀዶ ጥገናውን የሰራላት። እናም የግድ በህይወት መቆየት አለባት።
“ምን አድርገሻት ነው?” ብሎም ፊዮናን እየወነጀለ ጥያቄውን ካቀረበላት
በኋላ የኒኪን የተከደኑ አይኖች በእጁ እየከፈተ ሲመለከታት ቆየ። አሁን
ማሽኑ የሚያሰማውን ድምፅ አቁሟል። የልቧ ምት ተስተካክሏል። ያም ሆኖ
ግን እነዚህ ድንገተኛ ራስን መሳቶች ጥሩ ምልክቶች አይደሉም።
“ኧረ እኔ ምንም አላደረግኳትም” አለች እና ፊዮና “የመስኮቱን መጋረጃ
ከከፈትኩኝ በኋላ እሷ አይኗን ከፈተች እና “ሄሎ” አለች በእርጋታ፤ ከዚያም ወዲያው ተለወጠች:: ከዚያም እኔ ሞቻለሁ፡፡ እዚህ መገኘት አይገባኝም እያለች ጮኸች እና ራሷን ሳተች፡፡” አለችው፡፡
ዶክተር ሳም ራይሌ የዶክተር ናኪ ሮበትስን ፊት በጥሞና ሲመለከት
ቆየ፡፡ ሳም ዶክተር ሮበርትስን በቴሌቪዥን ለብዙ ጊዜ አይቷታል።ምክንያቱም በዚህ “የዞምቢ ግድያ” የሚል ስያሜ በተሰጠው ርዕስ ላይ ዋነኛ የዜና ርዕስ ሆኖ ለሳምንታት ቆይታ ነበር፡፡ ምናልባትም ቆንጆ ስለ ሆነች ሊሆን ይችላል ብዙ ጊዜ የቴሌቪዥን ዜናዎች ስለ እሷ ሲዘግቡ የነበሩት።
ዶክተር ሳም ራይሌ ለዘጠኝ ሰዓታት ያህል በጥይት የተመታውን የእግሯን ሥጋ እና ጅማቶች ቀዶ ጥገና ሰርቷታል፡፡ ያም ሆኖ ግን ኢንፌክሽን ወይንም ደግሞ ከቀዶ ጥገናው በኋላ የልብ ምት ችግር
ሊያጋጥማት ይችላል።
“ሞርፊኑን ንቀይላት!” ብሎ ነርስ ማክ ማኑስን አዘዛት።
“የሞርፊኑን መጠን ቀንሺላት ማለትህ ነው?” ብላ ፊዮና በየዋህነት
ጠየቀችው፡፡
ሳምም አፍጥጦ እያያት “እኔ እንደዚያ ብዬሻለሁ?” ብሎ ሲቆጣት
“ኧረ አይደለም፡፡” ብላ ፊዮና ተደናበረች። ዶክተር ራይሌ እንደዚህ ቁጡ አልነበረም፡፡ ነገር ግን የዜና አውታሮች አትኩሮት ሁሉ እዚህ ክፍል የተኛችው ታካሚ ላይ ስለሆነ ጉዳዩ ጫና አሳድሮባቸዋል፡፡ “ግን እኮ ዶክተር
ራይሌ ሞርፊኑን ካቋረጥኩባት የቁስሉ ህመም በጣም ከፍተኛ ይሆንባታል::”
“መንቃት ይኖርባታል።” አላት እና የኒኪ ክንድ ደም ስሯ ላይ የተሰካውን ሞርፊን ነቅሎ ሳሊኑን ተከለላት “በዚያ ላይ ደግሞ” ብሎ የኒኪን የተቦጫጨረ ፊት ቁልቁል እያየ “ይህቺ ሴት አካላዊ ስቃይን በደንብ መቋቋም የምትችል ሴት ናት።” አላት፡፡
ዶክተር ራይሌ በእርግጥም ልክ ነበር፡፡ ኒኪ ከአንድ ሰዓት በኋላ ስትነቃ
የቀኝ እግሯ ላይ የሆነ ስው አሲድ እየጨመረባት እስኪመስላት ድረስ ነበር
በጣም ያቃጥላት የነበረው። ለነርሷም ይህንን ከፍተኛ ስቃይን
የሚያስወግድላትን ነገር እንድትሰጣት ለመነቻት፡፡
“ሀይለኛ የሞርፊን ኪኒንን ከኮዳይን ጋር ቀላቅዬ እሰጥሻለሁ።” አለቻት እና ፊዮና ይቅርታ በሚጠይቅ ድምፀትም “ዶክተር ራይሌ ሞርፊን አትስጪያት ብሎ ስላዘዘኝ ነው። ይቅርታ” አለቻት።
ኒኪም ፊቷን መልሳ ለነርሷ ጀርባዋን ሰጠቻት እና ዝም አለቻት፡፡ የቁስሉ ከፍተኛ ህመም በድጋሚ በህይወት እንደምትገኝ በደንብ አሳወቃት።
ይሄ ግን እንዴት ሊሆን እንደቻለ ግልፅ አልሆነላትም። እዚያ የመጋዘን ህንፃ
ውስጥ የሆነውን ነገር ስታስታውስ ጓደኛዋ እና የእሷን ህይወት ሊታደግ
መጋዘኑ ድረስ የመጣው ጉድማን የሽጉጡን አፈሙዝ ግንበሯ ላይ ደቅኖ
ሊተኩስባት ሲል ነበር፡፡
“በእውነት አንቺ አስገራሚ ደደብ ሴት ነሽ ብሏት አይደል? ደግሞም ልክ ነበር። ምክንያቱም ሉው ጉድማን ለምን ብሎ ነው የእሷን ሞት የሚፈልገው? እንደዚያ ከሆነ ታዲያ ለምንድን ነው ሊዊስ ሮድሪጌዝን የገደለው? ስለዚህ እሱ በዚያ ሰዓት እዚያ ቦታ ላይ የተገኘው ሊገድላት
አልነበረም ማለት ነው። ከዚያ በኋላ ህንፃው ውስጥ ስለተከሰቱት ነገሮች
ምንም አታስታውስም::
የህመሙ ማስታገሻ ኪኒኒዎችን ነርሷ ከፈረካከሰችላት በኋላ በምትወስደው የግሉኮስ ከረጢት ላይ ወጋቻት። ኒኪም የሚያቅለሸልሽ ስሜቷን ካባረረች በኋላ ነርሷን የተለያዩ ጥያቄዎችን ትጠይቃት ጀመር፡፡ነርሷ የመጋዘን ህንፃ ውስጥ ምን እንደተከሰተ እና እንዴትስ የኒኪ ህይወት
ሊተርፍ እንደቻለ ምንም የምታውቀው ነገር እንደሌለ አወቀች::
“አንቺ እግርሽን በጥይት ስለተመታሽ ነው በአምቡላንስ ተጭነሽ ወደ ዚህ የመጣሺው” የሚለውን መልስ ብቻ ነበር የመለሰችላት፡፡ ኒኪ ሆስፒታል
እንደደረሰች በቀጥታ ወደ ቀዶ ጥገና ተወስዳ በዶክተር ራይሌ ዘጠኝ ሰዓት
የፈጀ ቀዶ ጥገና ተደረገላት። ቀዶ ጥገናው በደንብ እንደተካሄደ እና ዶክተር
ራይሌም “ተስፋ ያለው ቀዶ ጥገና ነው” ብሎ እንደነገራት፣ በዚህም የእግሯ
ቁስል በቶሎ ሊድንላት እንደሚችል መረዳቷን ጭምር ገለጠችላት፡፡
“ለማንኛውም እሱ ራሱ ሲመጣ ይህንን ነገር ይነግርሻል፡፡” አለቻት እና
ፊዮና ፈገግ ካለች በኋላም “ አንቺ እንደነቃሽ ደውዬ አሳውቄዋለሁ፡፡ ሌላኛው
ያንቺን ደህንነት አጥብቆ የሚጠይቀው ሰው ደግሞ ውጪ ኮሪደሩ ላይ
እየጠበቀሽ ነው፡፡ የቀዶ ጥገና ክፍሉ ውስጥ ከገባሽበት ጊዜ ጀምሮ እስከ
አሁን ድረስ ከሆስፒታሉ አልተንቀሳቀሰም። በእውነት የተባረከ ሰው ነው” አለቻትና ፈገግ አለች፡፡ ኒኪም ቆንጅዬዋን ባለ ቀይ ፀጉሯን ነርስ
እየተመለከተች
“ማነው የእኔን መንቃት ኮሪደሩ ላይ ሆኖ እየጠበቀኝ ያለው?” ብላ ጠየቀቻት፡፡
“ፖሊሱ ነዋ!” ብላ ነርሷ ከመለሰች በኋላ “ወደዚህ እንድትመጪ ያደረገው ፖሊስ ነው፡፡ በአምቡላንስ ካንቺ ጋር አብሮ ነው የመጣው። ምስኪን ሰው ነው:: በጣም ስላንቺ እንደተጨነቀ ያስታውቃል፡፡” አለቻት።
ኒኪ የተለያዩ ነገሮችን ማሰብ ጀመረች፡፡ ጉድማን ነው ማለት ነው እዚህ
ይዞኝ የመጣው? ግን እሱ ሊገድላት አልነበር እንዴ? ወይስ ሽጉጡን
ጭንቅላቷ ላይ የደቀነባት ነገር ብዙ ደም ስለፈሰሳት ያየችው ቅዥት ነው?
ወይስ ነገሩ ሌላ ነው?
“ፖሊሱን አሁን ላገኘው እችላለሁ?”
“እንዴታ ትችያለሽ እንጂ!” ብላ ነርሷ ፈገግ

👍2❤1
አለች እና “አንቺ የጤንነት ስሜት እስከተሰማሽ ድረስ ለእሱ ልታገኚው እንደፈለግሽ እነግረዋለሁ፡፡”
“ግን አብረሺው ትመጫለሽ አይደል?” ብላ ኒኪ ፊቷ ላይ ፍርሃት እየተነበበባት” ጠየቀቻት፡፡ “ምናልባት የሆነ ነገር ብፈልግ እንድታመጪልኝ ብዬ ነው” አለቻት
ፊዮናም ኒኪን እያሳየቻት ምናልባት ይህ የፍርሃት ስሜቷ የመጣባት ከዚህ በፊት በደረሰባት ስቃዮች የተነሳ ሊሆን ይችላል' ብላ አሰበች እና “ችግር የለውም አብሬሽ እሆናለሁ። ደግሞም ሰውዬው ካደከመሽ
እና ምቾትም ከነሳሽ ከዚህ ክፍል አስወጣልሻለሁ” አለቻትና ፖሊሱን
ልትጠራላት ወጣች።
ኒኪም አልጋዋ ላይ ተጋድማ ለዘላለም የጠበቀችው አይነት ስሜት
ተሰማት፡፡
“ጉድማንን ምን ብዬ ነው ልጠይቀው የምችለው?” ምናልባትም ሽጉጡን
ጭንቅላቷ ላይ ደቅኖ በመጨረሻ ላይ ስለተናገራት ነገር እንዲያብራራላት
ትጠይቀው ይሆናል። ለማንኛውም ለሁለተኛ ጊዜ ህይወቷን አትርፎላታል።
ነፍሷን ለማዳንም እዚህ ድረስ በአምቡላንስ አብሯት መጥቷል። መዳፏን
በፍርሃት እና በሚሰማት ከፍተኛ የስቃይ ስሜት ምክንያት እያላባት ነው::
እራሷን ለማረጋጋትም ክንዷን በጥፍሯ ወጋችው። ኮሪደሩ ላይ የነርሷ ድምፅ ይሰማታል። “ይሄው እዚህ ክፍል ውስጥ ነው የምትገኘው።” ብላው በሩን ከፍታ ገባች።
ነርሷን ተከትሎ ክፍሉ ውስጥ የገባው መርማሪ ፖሊስ ሚክ ጆንሰን ፊቱን በፈገግታ አብርቶ “ዶክተር ሮበርትስ እንኳን ከሞት ዓለም ወደ ሞት
ዓለም በሰላም መጣሽ!” አላት።.....

#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል
...ሌላ የሕይወት ምዕራፍ ተከፈተ። የየወዲያነሽ የፈገግታ አበባ ቀስ በቀስ
ጠወለገ፡፡ አልደረቀም።
ድንገት በመኻሉ የየወዲያነሽ ቀንጣ ቀንጣ ማለት ሰካነ፡፡ እንቅስቃሴዋ ዝግ በዝግ ቀዘቀዘ፡፡ ዐቅም እያነሳት እንደ ጠራራ ቅጠል መጠወላለግ ጀመረች፡፡
ድምጿ ደቆ አካላቷ ዝሉ አረማመዷ ዳ አለ፡፡ ፊቷ ድምቡጭ ብላ ከመወፈሯም በላይ ግንባሯ አካባቢ ላመል ታህል ላብ አይታጣም። ፈገግታዋን ፍዘት ቢይዛትም የጠይምነቷ ውበት ተንደረበበ፡፡ ከወደ ዳሌዋ ኮራ አለች፡፡ ገላዋ ዳበረ ዐይኖቿ ንጸሕ የጠራራ ምንጭ ውሃ መስለው ጎደሉ፡፡ በአቋቋሟም ሆነ በአለባበሷ ግድ የለሽ ሆነች። እንዲህም ሆና ውበቷ ታይቶ አይጠገብም፡አብሶ ለእኔ፡፡
«ምን ነካት?» በማለት ውስጥ ውስጡን በሐሳብ ተብሰለሰልኩ። አንድ ቀን ወደ ሥራ ለመሔድ የሰበሰቡን ደረጃ መውረድ እንደ ጀመርኩ ከወደ ኋላዩ ከች አለችብኝ።
አንገቷን ሰበር አድርጋ ቁልቁል ደረጃ ደረጃውን እያየች ጊትዬ ብርቱካንና ሙዝ ገዝተህልኝ ለመምጣት ትችላለህ?» ብላ ጠየቀችኝ::
«አማረሽ እንዴ? ማታ ይዤልሽ እገባለሁ፡፡ በምሳ ሰዓት ግን አምጥቶ መስጠት ያስቸግራል» ብያት እሷ ወደ ቤት ስትመለስ እኔ ደረጃውን ወርጄ
ሂድኩ።
ማታ በወረቀት ከረጢት ጠቅልዬ ይዤላት ገባሁ፡፡ ከዚያች ቀን ጀምራ ልዩ ልዩ ነገሮች 'አማረኝ ግዛልኝ' አምጣልኝ ማለት ጀመረች። ባለርስቱ ሳያየው እሽት ሰርቆ እንደሚገባ ጭሰኛ እንደ ምንም ደብቄና አመሻሽቼ ይዤላት እገባለሁ፡፡ ከየውብነሽ ጋር የምታደርገው ወሬና አንዳንድ ተራ ድብቅ ልፊያም በጣም ቀነሰ። ተቀምጣም ሆነ ቆማ ብቻዋን ትተክዛለች። አንጎሏ ከባድ ሐሳብ
የተጠመደ መሰለ።
አንድ ቀን ማታ ከራት በኋላ ከመኝታ ቤቴ ወጥቼ እንግዳ መቀበያ ክፍል ስገባ ወደ መኝታ ክፍሏ በሚያስገባው በር አቅራቢያ እንጨት ወንበር ላይ ተቀምጣ አገኘኋት። አቀማመጧ ስሜቴን ነካው:: ኣጠገቧ ሄጄ ቆምኩ። እንባዋ በጉንጫ ላይ እንደ ካፊያ ጠፈጠፍ ይወርዳል፡፡ በተንተን : ያለው ጸጉሯ ባለመጎንጎኑ የተፈጥሮ ኅብሩ ሳይሆን ተጨማሪ ውበቱ ቀንሷል፡፡ ስታለቅስ በማየቴ እኔንም ተናነቀኝ፡፡ ትካዜዋ ልቤን ቦረቦረው:: ተነስታ ወደ ክፍሏ ስትገባ እኔም የክፍለሉን መብራት አጥፍቼ ተከትያት ገባሁ፡፡
ልብሶቿ ሁሉ ንጹሕ በመሆናቸው ደስ ይላሉ፡፡ እሷ አልጋዋ ጫፍ ላይ
ስትቀመጥ ፊት ለፊት ቆሜ እጅዋን ያዝኩና የወዲያ ምን ሆነሻል? ምን ነካሽ?
ደኅና አይደለሽም እንዴ?» አልኳት።
«ምንም አልሆንኩ» ብላ ባጭሩ
መለሰችልኝ።
“ታዲያ ለምን ታለቅሻለሽ?» ብዬ ጥያቄዬን ስደግም «እንዲያው በዕድሌ
ነው የማለቅሰው» ብላ የሚተናነቃትን እንባና የትካዜ ቁራሽ ለመዋጥ ሞከረች።
«ዕድልሽ ምን ሆነ? ምን መጥፎ ነገር ኢጋጠመሽ?» ብዪ አይኖቿን
ጠረግሁላት፡፡
«አይ ጌታነህ! ምን ብዬ ልንገርህ? አንተ ወንድ ነህ፡ ምን ቢሉህ ምን ታውቃለህ? እኔስ እንደዬ ከርታታ ነኝ፡፡ እንተ ደግሞ..» ብላ ሐሳቧን ሳትጨርስ ድምጿ በእንባና በልቅሶ ኃያል ተሸነፈ፡፡ መሪር ኀዘን ተሰማኝ፡፡ ብድግ ብላ አንገቴ ላይ ተጠመጠመች፡፡ እያንዳንዱ ስሜት የየራሱ ጊዜ አለው፡፡ ባየሁት ነገር ስሜቴ
በጨነቀ የከዚያ ቀደሙ የወንድነት ሥጋዊ ፍላጐቴ ሟሽሽ፡፡
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አስተኝቻት ወጣሁ። ምን እንደ ሆነችና ምን እንደ ነካት ለማወቅ ባለመቻሌ አእምሮዬ ምክንያት ፍለጋ ኳተነ። በማግሥቱ
ጧት ፊቴን ስታስታጥበኝ ትንሽ ፈገግታ አየሁባት፡፡ ፊቴን በፎጣ እየጠራረግሁ
አጠገቧ ቆም እንዳልኩ የትእዛዝ ሳይሆን የልመናን ሥልት በያዘች ዜማ «ጌታነህ፡
አትመረረኝና አሁንስ አበዛሽው አትበልና፣ ዛሬ የትም የትም አይቡ ገብተህ ዓሣ
ይዘህልኝ ና» አለችና ቀስ ብላ ከአጠገቤ ዘወር አለች።
ከአንድ ከታወቀ የሀገር ባሕል ምግብ ቤት በእንጀራ አስጠቅልዩ በንጹሕ ወፍራም ወረቀት ሸፍኜ በድብቅ ይዤላት ገባሁ፡፡ የዕቃ ቤቱን በር ዘግታ ዐፈር
አስጋጠችው፡፡
ከሁለት ሳምንት በኋላ አንድ ቀን ማታ ትልቁ ክፍል ውስጥ እንደ ተቀመጥኩ የወዲያነሽ ሰው የለም ብላ በመገመት የክፍሉን መብራት ለማጥፋት በውስጥ ልብሷ ብቻ መጣች፡፡ ያልታሰበ አጋጣሚ ነበር! የእናቱን ሞት እንዳረዱት ሰው ክው ብላ ደነገጠች። አይደበቄው ስውር ሸክሟ ተጋለጠ፡፡የደበቀችውን ችግርና የልቅሶዋን መነሾ በገሃድ አየሁት፣ ለየሁት። የወዲያነሽ አርግዛለች!!
በዚያች ደቂቃ ውስጥ የሥቃይዋ መነሾ ዋናዉ ጦስ እኔ እንደሆንኩ ስለ ታወቀኝ ራሴን በጸያፍ ወራዳ ደረጃ አየኋት፡፡ ሕይወቴንም እንደ ልክስክስና መርዘኛ አውሬ ቆጠርኳት። የጉልላት ቁጣና ተግሣጽ እንዲሁም አስተያየቶች ሁሉ
መንጋጋና ጥርስ አውጥተው ነቸፉኝ፡፡ ሕሊናዬ የማረፊያ ቦታ አጥታ በስቃይ
ገመድ ተንጠለጠለች። ስለ ችግሯ የማውጠነጥነው ሐሳብ ሁሉ እንደ ጥላ ነፍስ የለሽና የማይጨበጥ ሆነ፡፡ ማርገዝዋን ካወቅሁ አንድ ወር እንደ አንድ ሳምንት ዐለፈች።
የየወዲያነሽ ማሕፀን ተንቀሳቃሽ ሕይወት ሲያረግዝ የእኔ የአንጎል ማሕፀን ደግሞ ረቂቅ የጭንቀት ሐሳብ ፀነሰ። ያም ሆነ ይህ አንድ ቀን ቢስቱ ዓመት ይጸጸቱ” በመሆኑ የወዲያነሽ ይህን መሰሉን የተፈጥሮ ጉዳይ “ማታለልና መሸሽግ ስለማትችል እርግዝናዋን እናቴና እኅቴ በየተራ አወቁ፡፡ ከዚያም በኋላ
የእኔና የወዲያነሽ ነገር ከሆድ ያኖሩት ያድናል የተናገሩት ያስገድላል ሆነና
አባቴ እንዳይሰማና መሬት ቃጤ እንዳትሆን ተፈርቶ እርሱ ፊት እንዳትቀርብና ጉዳዩ እንዳይጋለጥ በእናቴና በእኅቴ በኩል ምስጤር ሆኖ ቆየ። የእናቴ የጥርጣሬ ዓይን በእኔ ላይ ተተከለ። ምን ይኸ ብቻ
«እኔ ልጂት እንኳንስ ይቺን ቀላሏን ሌላም ነገር ዐውቃለሁ፡፡ ከዘር ነው ካጥንት» ብላ ባሽሙር ነካካችኝ። ፊቴን ማየት አስጠላት። የነገሩን አዝማሚያ
ለመከታተልና ድንገት የሚሆነውን ለማወቅ ወፍራም ትዕግሥት ተከናነብኩ። ያም ሆነ ይህ በሕይወቴ ውስጥ የመጀመሪያዋ አስፈሪና አሳዛኝ ቀን መድረሷ አልቀረም፡፡
አንድ ቀን ማታ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ ላይ የወዲያነሽ እንዳመጣላት የጠየቀችኝን እሽግ አሣ ይዤ ገባሁ፡፡ ለወትሮው ወደ ቤት ስገባ ማድ ቤት አካባቢ አለዚያም ትልቁ ክፍል ውስጥ አገኛት ወይም ኣሻግሬ አያት ነበር፡፡ ያን ዕለት ማታ ግን እንኳንስ አካሏ ድምጻም ጠፋ፡፡ መኝታ ቤት ውስጥ ከገባሁ በኋላ ካሁን አሁን ብቅ ትል ይሆናል በማለት ብዙ ጠበቅሁ፡፡ ምናልባት መግባቴን አላወቀች ይሆን በማለት በመስኮት በኩል ብቅ ብዬ በቀጭኗ አፏጨሁ፡፡ ፉጨቴን የአካባቢው አየር ከርስ ዋጣት፡፡ እንደገና ደግሞ ዘፈን መስል ፉጨት ሞከርኩ፡፡ እንደ ቀዳሚዋ ወደመች፡፡ ሰሚ በሌለበት አካባቢ ምንም መልስ አይኖርምና ሙከራይ ከንቱ ሆነ፡፡
ከወዴ ወላጆቼ መኝታ ክፍል ውስጥ ተራ እየጠበቀ የሚነሣ ሣቅ ይሰማል። ምናልባት እዚያ ትኖር ይሆን? እናቴ ሥራ አስይዛት ይሆን? የሚል ጥርጣሬ ገባኝ፡፡ የምሰማው ሣቅ ልቅሶ መስሎ ተሰማኝ። ቤቱ የኀዘን አዳራሽ መሰለኝ፡፡ መርዶ መጣብህ! ያውም አሳዛኝ መርዶ” እያሉ የሚነግሩኝም መሰለኝ፡፡
የማየውና ከፊት ለፊቴ የነበረው ነገር ሁሉ አስፈራኝ:: ሽሽ፣ አምልጥ? የሚል ቃል በሐሳቤ እየተመላለሰ አስጨነቀኝ፡፡ የተንጠለጠለው መብራት የብርሃን
ሳይሆን የሥቃይ ማሠራጫ መሳለኝ፡፡ የመጣው ይምጣ ብዬ መኝታ ክፍሏ ውስጥ ዘው ኣልኩ፡፡ የዕቃ ቤቱ ዕቃ ቤትነት አልተለወጠም፡፡ የየወዲያነሽ አልጋ መለመላውን ተዘርግቷል።
ልብሷና ሌላዉ ኮተቷ የለም፡፡ በቁሜ በደንኩ! ወደ ፊት ራመድ ብዬ ሽቅብም ቁልቁልም ተመለከትኩ። ቤቱ ኦና ሆነብኝ።
ግድግዳው ላይ

የለችም! የለችም!” የሚል ጽሑፍ የሚነበብበት መሰለኝ፡፡ ከአልጋዋ ፊት ለፊት ግድግዳውን ተደግፈ ቆምኩ። የየወዲያነሽ መልክና ፈገግታ ውበትና ለዛ ሁሉ እንደ ደንከል ግመል እየተጓተተ በሕሊናዬ ውስጥ በሰልፍ አለፈ። በመጨረሻም ድንገት ከባሕር ውስጥ ብቅ እንደሚል ዓሳ በሕልም መስል ትርዒት በአንጎሌ መድረክ ላይ ብቅ ብላ "ጌትዬ የእኔ ጌታ!
ምን ላድርግ ትለኛለህ? ያ የፈራሁት ሁሉ ደረሰ፡፡ ዐይንህን እንኳ ባያትና ችግሬን
ብገልጽልህ ደስታዬ ነበር፡፡ ግን ደኅና ሁን ሳልልሀና ሳልሰናበትህ፣ አንተንም
ጭንቅና ጣጣ ውስጥ ነክሬህ ለመንከራተትና ለመሠቃየት ወጣሁ!" እያለች የምትነግረኝ መሰለኝ። ዐይኔን በሰፊው ከፈት ሳደርገው ትርዒቱ እንደ እንኩቶ ጢስ በንኖ ጠፋ።
“ኡ! ኡ!” ብዪ ቤቱን በጩኸት ለማናጋት ሁለት ሦስት ጊዜ አፌን ከፈትኩት፡፡ የማላውቀው ኃይል ጉሮሮዩን አፍኖ ኸለከለኝ፡፡ ክፍሉ የሙታን አዳራሽ ስለ መሰለኝ ወደ መኝታ ክፍሌ ተመለስኩ፡፡ ውሻ እንዳየች የድመት ግልገል በፍጥነት ተመልሼ ወጣሁ፡፡
ያን እሽግ ዓሣ ይዤ ወደ ዘበኛው ዘንድ ሄድኩ፡፡ አሮጌ ብርድ ልብስ ለብሶ በበትሩ መሬቱን እየደቀደቀ ካአንዲት ለጊዜው ማን መሆኗን ካልለየኋት ሴት ጋር ሲያወራ ደረስኩ፡፡ እዚያ ታች ያለችው ሕይወትም የምትጎሽመው የፍቅር ነጋሪት ያው ኖሯል! ሴቲቱ በድንጋጤ ብር ብላ ወደ ማድ ቤት ገባች።
አዲሱ ዘበኛ ከተቀጠረ አራት ወር በልፎታል። ጠጋ ብዩ «ያች እዚህ
እኛ ቤት የምትሠራው ጠይም ልጅ ወዴት ገባች? ብዬ ጠየቅሁት፡፡ ክንብንቡን
ወረድ ካደረገ በኋላ “ዐሥር ሰዓት ገደማ ነው መሰል ከእሜትዬ ጋር ምን
እንዳገናኛቸው እንጃ አላወቅሁም፣ ደማቸው ፈልቶ በከዘራ ከደበደቧት በኋላ ጓዟን አስይዘው ”ዳግመኛ እዚች ቀዬና አካባቢ ዐይንሽን እንዳላያት ወየውልሽ!' '
ብለው አባረዋታል» ብሎ አረዳኝ፡፡ ሕሊናዬን እንደ ጦር የሚወጋ ጭንቀት
ወረራት! እሽጉን ዓሣ ካጥር ውጪ እሽቀንጥሬዉ ገባሁ፡፡
መስኮቱን ደገፍ ብዬ ጥቅጥቅ ያለውን ጨለማ በተዳከሙ ዐይኖቼ ስመለከትና ከትካዜ ጋር የትካዜ ቅልልቦሽ ስቀባበል የመኝታ ቤቴ በር በኃይል ተበርግዶ ተከፈተ።
“እንዲሁ ቆመህ በቀረኸው! " አለኝ አንድ ቀጠን ያለ ቁጡ ድምፅ፡፡ መለስ አልኩ፡፡ «ልክስክስ ውሽ! ዘር አሰዳቢ! አጥንት አርካሽ! ወይኔ ልጂት! ወይኔ ተካበች! » ብላ በንዴት እየተንዘፈዘፈች ቆመች፡፡ በሩን ከፍታ የገባችው እናቴ ነበረች፡፡
«አንት ምናምንቴ! ያ ከሩቅ ስጠላውና ስፈራው የነበረው ጉድ በእኔ ላይ
ይድረስ? ብለህ ብለህ ደግሞ ከማንም ብራሪ ገረድ ጋር እንዲህ ያለ ነገር ትሠራ?
አንት ቅሌታም ቀላል! በቁማችን ትቀብረን? እስኪ ምን ትሆነው ይሆን? መጫኛ ትሰቅልም እንደሁ እናያለን! ቅልጥሜ ቀልጥሜ! እንክቼ! አንክቼ አባረርኳት! ፣ምነው ቀደም ብዪ ዐውቄ ቢሆን ኖሮ! » ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ «አይ እንግዲህ ! » ብዬ ተቃውሞዬን ለመግለጽ ጀመር ሳደርግ ቁጣዋ ይበልጥ በመገንፈሉ ያላትን ጠቅላላ ኃይል አሟጣ ተንደርድራ ገፈተረችኝ፡፡ ካንድ ርምጃ በላይ አልተነቃነቅሁም፡፡ አንድ ጊዜ በጥፊ ኣላሰችኝ፡፡ «ምን ይሆናል! » አለችና ከንፈሯን ነከሰች።
“አባትህ ይሰማና ጉዳችን አደባባይ ይወጣል ብዬ ነው እንጂ አንተንስ
እንዲህ አልነበረም፡፡ ወይ ነዶ! ». ብላ ወጣች።
እኔን ግን ከዚያ ይበልጥ የመረረና የከፋ ዮኀዘን ጉም ሽፍኖኝ ስለማያውቅ
አፌን ደም ደም እያለኝ ኩርምት ጭብጥ ብዬ ወንበር ላይ ተቀመጥኩ። የዐይኖቼ
የእንባ ምንጭች ትኩስ እንባ አንፎለፎሉ፡፡ የየወዲያነሽ ሕይወት እንደ ለት ፀሐይ ስትጠልቅ ታየኝ። ትክን አልኩ፡፡
የምትገባበት አጥታና የምትሄድበት ግራ ገብቷት ከመንገድ ዳር ቆማ እያለቀሰች ስትንሰቀሰቅ በዐይኔ ዙሪያ በሚንቀዋለለው እንባ ውስጥ ታየችኝ:
አሁንም እንደ ገና በሩ ተከፈተ። ቀና ብዬ አየሁ። የውብነሽ ፈገግ ብላ እልጋው
ጫፍ ላይ ቁጭ አለች፡፡ ቀና ብዬ ሳያት ዓይኗ እንደ ጦር ይዋጋል፡፡ ከቁም ነገር
እልቆጠርኳትም። ለነገር ይሁን ለመናገር አልገባኝም፣ «እህህህ» ብላ ዝም አለች፡፡
ድንገት ደሜ ፈልቶ ብልጭ ስላለብኝ ከወንበሬ ላይ ቱግ ብዬ ተነስቼ ውጪ
ውጪልኝ! አያያዥ!» ብዩ ጮህኩባት፡፡
ክው ብላና ጥላዋ ተገፎ አንዳችም ሳትመልስ ፈጥና ወጣች። ኣባቴ ራት
በልቶ ጋደም ካለ ቆይቷል፡ ብዙ ደግም ክፉም ልዩ ልዩ ነገሮች አሰብኩ፡፡ አሰብኩ
እንጂ አልፈጸምኩም፡፡
ያጋጠመኝ ምስቅልቅል ችግር በቀላሉና ባጭሩ ሊቃለል የማይችል በመሆኑ ብዙ የሥቃይ ጉዞ ከፊት ለፊቴ ጥቁር መጋረጃውን ጋርዶ ታየኝ።ወገቡን እንደ ተመታ እባብ መንቀሳቀስ አቃተኝ፡፡
ልብሴን ሳላወልቅና መብራቱን
ሳላጠፋው ተኛሁ:: በኀዘን ማዕበል የተናወጠው አእምሮዬ የሚያዝ የሚጨበጥ ሐሳብ በማጣቱ የምወጥነው ነገር ሁሉ ካፊያ ቆጠራ ሆነ።
የወዲያነሽ ቀጠን ባለ ድምዕ ብዬህ ነበር፣ የእኔ መጨረሻ እንዲህ ሆነ!
ለእኔስ አዲስ ነገር አይደለም' እያላች የምታነጋግረኝ ስለ መሰለኝ ከሦስት ጊዜ
በላይ ባነንኩ፡፡ ሊነጋጋ ሲል መብራቱን አጥፍቼ መስኮቱን ከፈትኩት በመዝጊያው
ሥርና በደፉ መካከል ባለው ጣብቂያ የፀሐይ ብርሃን በስሱ ጠፍጠፍ ብላ ገብታ ላመል ታህል ወለሉን አወገገችው:: ከወለሉ ላይ የተንፀባረቀው ብርሃን ክፍሊቱን አፈንጋት።
የወዲያነሽ ከሦስት ቀናት በፊት በጠርሙስ ሞልታ ባስቀመጠችው ውሃ አንገቴን በመስኮት ብቅ አድርጌ ፊቴን ታጠብኩ፡፡ በፊቴ ላይ የሚታየውን ኀዘን ግን አጥቤ ማስወገድ አልቻልኩም፡፡ ጸጉሬን አበጥሬ እህል ውሃ ሳልቀምስ ወጥቼ ሄደኩ።የሕይወቴ ብርሃን የጠፋችና የዓላማዩ ምሰሶ የተገረሰሰች መሰለኝ፡፡ በውስጤ የነበረው ምኞቴና ውጥኔ ሁሉ እንደ ቆላ ኩሬ ቀስ በቀስ ሲደርቅ ተሰማኝ፡፡
ያን ዕለት ጽሕፈት ቤቴ ውስጥ ተቀምጬ የሠራሁት ሥራ ሁሉ የተስተካከለና የታረመ አሠራር አልነበረም፡፡ አንዳችም ርባና ያለው ሥራ ሳልሠራ የምሳ ሰዓት ደረሰ፡፡
የወረቀትና የጽሕፈት መኪናዎች ሻሽታና ኳኳታ ጸጥ አለ፡፡ ሁሉም ወደ ምሳው ለመሔድ ከዚህም ከዚያም ሲነሳ ጫጫታ፣ ቀልድና ሳቅ አስተጋባ፡፡
የወዲያነሽ ሁኔታ ከፊት ለፊቴ ስለተደቀነ እኔም ፈጥኜ ወጣሁ። እሀል ውሃ የሚሉ ነገር ሳልቀምስ መንገድ ለመንገድ ስንቀዋለል ከቆየሁ በኋላ ልክ እንደ
ወትሮዬ በሰዓቱ ተመልሼ ገባሁ::
ብስጭቴ ግን ናላዬን አዙሮ ራሴን እንድጠላ አደረገኝ እንጂ የሰጠኝ
አንዳችም የማረሳሻ መፍትሔ አልነበረም፡፡ ያልተለመደው ኩርፊያ መሰል ዝምታዬ የሥራ ባልደረቦቼን ሁሉ ግራ አጋባ፡፡ ደፍሮ የጠየቀኝና ምክንያቴን ፈልፍሎ ለመረዳት የሞከረ ግን አልነበረም፡፡
የመሬት ሥርዓተ ዑደት ዐሥራ
ሁለት ሰዓትን አደረሰውና ወጣሁ፡፡
በስተጓሮ በኩል ማድቤት ጥግ አስደግፈው ያቆሙትን ያን የወዲያነሽ
ስትተኛበት የነበረውን አልጋ ባየሁ ቁጥር ሰው የመግደል ኃይል ያለውና የመጥፎ
ተግባር ምልኪ መስሎ ስለታየኝ በዚያ በኩል ወደ ሽንት ቤት መሄድን ተውኩ።
ያ ማንም ሳያይና ሳይሰማ ቆመንም ይሁን ተቀምጠን ስንጫወትበት የነበረው የአትክልት ሥፍራ ሕዝብ የተረፈረፈበትና በሰው ደም ርሶ የጨቀየ የጦር ሜዳ መሰለኝ፡፡ የአትክልቶቹ ቅርንጫፎች የፃዕረ ሞት መጥሪያ መለከት፣አበቦቹ እና ዕፅዋቱ ከኀዘን ማሕፀን ተወልደው ለመከራና ለሥቃይ ትርዒት የተዘሩ አሜኬላዎች እንጂ በተፈጥሮ ውብ ኅብረ ቀለም እንኳ ያሸበረቁ አካባቢያዊ
ፀጋ አልመስል አሉኝ፡፡
በእኔና በእናቴ መካከል የነበረው የእናትና የልጅነት ለከት፣ ጨዋታ፣እንዲሁም ፍቅራዊ ውይይት ሁሉ ቀስ በቀስ የተሠበረ ቅርንጫፍ ሆነ፡፡ እኅቴ ግን
በሁኔታዬ ሁለ በመሥጋቷና በመጠኑም በመጨነቋ

👍4
የጀመርኩትን የብቸኝነት
ሕይወት ባጭሩ ለመቅጣት በተደጋጋሚ ሞከረች፡፡ እኔ ግን ሙከራዋን ሁሉ
ለደንቆሮ የቀረበ የሙዚቃ ቅኝት አደረግሁት። እባቴ ስለ ጉጻዩ ምንም
ባለመስማቱና ባለማወቁ ከነገሩ ሁሉ ገለልተኛ ነበር፡፡ ጊዜው ነጎደ። የወድያነሽን የቤታችን ሰዎች ሁሉ እንደተመለሰ የተውሶ ዕቃ ረሷት። የእኔ ፍቅርና ትዝታ ግን እያደር ወደ አጥንቴ መስረፁን ቀጠለ። የማትረሳዋን የወዲያነሽን መርሳት” አንድ ራሱን የቻለ መሪር ፈተና ነው::
ቅዳሜ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላና እሑድ እንዲሁም በልዩ ልዩ አጋጣሚዎች
ሁሉ ከሠፈር ወደ ሠፈር እየተዘዋወርኩ የወዲያነሽን ለማግኘት ብዙ ጊዜ ባከንኩ::ድካሜ ሁለ ንፋስ ማሳደድ ሆነ፡፡ ምንም እንኳ ከተማውን አስሼ ለማዳረስ በፍጹም ከዐቅሜ በላይና የማይሞከር ቢሆንብኝም የጠረጠርኩ የጠረጠርኩትን ቦታ ሁሉ በዘዴ እያጠያየቅሁ ከሰስኩ። ምናልባት አንዱ ጋ ተቀጥራ ይሆን በሚል ጥርጣሬ የተቻለኝን ያህል በየጠላና በየጠጅ ቤቱ ሁሉ ሞከርኩ፡፡ ያም ሆነ ይህ ልፋቴ ሁሉ እንደ ጨው ሟሙቶ የትዝታዋ አካል ብቻ በልቤ ውስጥ ተገንብቶ ቀረ፡፡
ነጋም መሽም ከጥቁር ትዝታዬ ውስጥ የተንሰዋለለ ደስታ እንኳ ለማግኘት ሳልችል ቀረሁ፡፡ በባዶ የተስፋ ማሳ ላይ የበቀለው ምኞቴም በየዕለቱ
እየቀነጨረ መቆርቆዝ እንጂ መፋፋትን ሳያሳይ ቀን በቀን ላይ ተደራረበ.....

❤1👍1
#ፍቅር_ይዞኝ_እንጂ
መች አስቤው እንደ ሥራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
ጭው ባለው በረሃ ውስጥ
መንከራተቴ ያለ እፎይታ
ቀጥ ባለው ተራራ ላይ
ላቤን ማፍሰሴ ጠዋት ማታ
መች አስቤው እንደ ስራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
የልጆቼ ዓይን በዓይኔ ላይ
ያለ እረፍት ሲመላለስ
ልቻለው ከሃገሬ አይበልጡም
እያልኩኝ የምንከላወስ
ዘመን በዘመን ሲቀየር
በዓል አውድ ዓመት ሲመጣ
ለእንጀራዬ ብዬ ነው እንዴ
ከበረሃ የማልወጣ?
ከዘመድ አዝማድ የማልበላ
ከአብሮ አደጎቼ የማልጠጣ
የያዘ ይዞኝ እንጂ
የሀገር ፍቅር----- የሚሉት ልክፍት
እኔ ሁለት ሆድ የለኝ
እስክሞት የሚንከራትት
መች አስቤው እንደ ሥራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
ላቤ በጀርባዬ ላይ
የጨው አምድ መስሎ እስኪታይ
ከእረፍት ከእንቅልፍ ተፋትቼ
የማጣው የቅጽበት ፋታ
ቀናትን በእግሬ የምኳትን
ጫማዬን ከእግሬ ሳልፈታ
ለእንጀራዬ ብዬ ነው እንዴ
ቀዝቃዛ ውሃ እየናፈቀኝ
ትኩስ መመገብ እያማረኝ
ጨዋማ ውሃ እየጠጣሁ
በድካም ጨው የሚያልበኝ
ለእጀራዬ ብዬ አይደለም
ርቄ ከመሃል ማዶ
በቀበሮ ጉድጓድ ሆኜ
ምሰማው የናቴን መርዶ
ለእንጀራዬ ብዬ አይደለም
በእህቴ ሰርግ የማልገኝ
በወንድሜ ህመም የማልመጣ
ከሃገሬ አስተሳስሮኝ እንጂ
ወታደር የመሆኔ እጣ
ለእንጀራዬ ብዬ አይደለም
የምቃጠል በበረሃ
የሚያነደኝ ቦምብ ፈንጂ
ቃልኪዳኔ ከሆነችው
ከሀገሬ ፍቅር ይዞኝ እንጂ
🔘ሻለቃ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
መች አስቤው እንደ ሥራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
ጭው ባለው በረሃ ውስጥ
መንከራተቴ ያለ እፎይታ
ቀጥ ባለው ተራራ ላይ
ላቤን ማፍሰሴ ጠዋት ማታ
መች አስቤው እንደ ስራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
የልጆቼ ዓይን በዓይኔ ላይ
ያለ እረፍት ሲመላለስ
ልቻለው ከሃገሬ አይበልጡም
እያልኩኝ የምንከላወስ
ዘመን በዘመን ሲቀየር
በዓል አውድ ዓመት ሲመጣ
ለእንጀራዬ ብዬ ነው እንዴ
ከበረሃ የማልወጣ?
ከዘመድ አዝማድ የማልበላ
ከአብሮ አደጎቼ የማልጠጣ
የያዘ ይዞኝ እንጂ
የሀገር ፍቅር----- የሚሉት ልክፍት
እኔ ሁለት ሆድ የለኝ
እስክሞት የሚንከራትት
መች አስቤው እንደ ሥራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
ላቤ በጀርባዬ ላይ
የጨው አምድ መስሎ እስኪታይ
ከእረፍት ከእንቅልፍ ተፋትቼ
የማጣው የቅጽበት ፋታ
ቀናትን በእግሬ የምኳትን
ጫማዬን ከእግሬ ሳልፈታ
ለእንጀራዬ ብዬ ነው እንዴ
ቀዝቃዛ ውሃ እየናፈቀኝ
ትኩስ መመገብ እያማረኝ
ጨዋማ ውሃ እየጠጣሁ
በድካም ጨው የሚያልበኝ
ለእጀራዬ ብዬ አይደለም
ርቄ ከመሃል ማዶ
በቀበሮ ጉድጓድ ሆኜ
ምሰማው የናቴን መርዶ
ለእንጀራዬ ብዬ አይደለም
በእህቴ ሰርግ የማልገኝ
በወንድሜ ህመም የማልመጣ
ከሃገሬ አስተሳስሮኝ እንጂ
ወታደር የመሆኔ እጣ
ለእንጀራዬ ብዬ አይደለም
የምቃጠል በበረሃ
የሚያነደኝ ቦምብ ፈንጂ
ቃልኪዳኔ ከሆነችው
ከሀገሬ ፍቅር ይዞኝ እንጂ
🔘ሻለቃ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....“አንተ?...” አለች፡፡
ኒኪ አይኗን አጥብባ የምትጠላውን መርማሪ ፖሊስ ፊትን መመልከት
ጀመረች፡፡ ይህ መርማሪ ፖሊስ ያለፉት ጥቂት ሳምንታት ህይወቷን የማይቻል እና አስቸጋሪ አድርጎባታል። “እዚህ ደግሞ ምን ትሰራለህ?” ብላ ጠየቀችው፡፡
“አንቺ እስክትነቂ ድረስ እየጠበቅኩሽ ነበር” አላት እና አሁንም ፊቱ በደስታg እንዳበራ አፍጥጣ በቁጣ የምታየውን ነገሩን ችላ ብሎ “እግርሽ በቅርቡ ሰላም እንደሚሆን ሰማሁ:: በእውነት ደስ የሚል ነገር ነው ዶክ፡፡ ደግሞም ሁሌም የሚያምሩ እግሮችሽን ይዘሽ ትቆያለሽ” አላት፡፡
ኒኪም በቁጣ አይን እያየችው “ይሄ ሰው ከዘረኝነቱ እና ከተሳዳቢነቱ በተጨማሪ ለሴት የሚባሉና የማይባሉ ነገሮችን ያውቃል ብላ አሰበች።
“አንቺ ሁሌም ደስ የምትይ ቆንጆ ሴት ነሽ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ አንድ አንዴ እንኳን ትንሽ ፈገግ በይበት እስቲ” አላት እና ጆንሰን በመቀጠልም “ማለቴ ድሌን በደንብ እንዳጣጥመው ብታደርጊኝ ደስ ይለኛል፡፡ መቼስ ህይወትሽን ያተረፍኩልሽ እኔ አይደለሁ?”
“ምን ማለትህ ነው ባክህ?” ብላ ኒኪ ከተኛችበት ቀና ብላ በጀርባዋ ትራሷን ተደገፈች። ስለተንቀሳቀሰችም ነው መሰል
የእግሯ ህመም ስለተሰማት ፊቷን ጭፍግግ አድርጋ እያየችው ቆየች፡፡ ደመነፍሷ እሱን ከክፍሏ ውስጥ ምን እንደተከሰተ እንድትጠይቅ አደረጋት፡፡
“አንተ እንዴት ነው የተከሰተው?” ብላ ጠየቀችው፡፡
ጆንሰንም ልክ እንደ እሷ ቀና ብሎ አያት እና “እውነትሽን ነው ምንም ነገር አታስታውሺም?” ብሎ መለሰላት፡፡
ኒኪም “በእርግጥ አንዳንድ ነገሮችን አስታውሳለሁ” ብላ ግራ እየተጋባች
ኮስተር አለች እና “እዚያ ቦታ የሄድኩት አኔ በርሃው ላይ እያለሁ ደውላ በጣም እንደተጨነቀች እና ልታገኘኝ እንደምትፈልግ ከነገረችኝ በኋላ ነው።
ቦታው ላይ ስደርስም ዊሊ ባደን ልክ እንደ ቄራ ሥጋ ተሰቅሎ ነው ያገኘሁት።” ብላ ሁኔታውን ስላስታወሰች ፊቷ ኩምትር አለባት።
“እሺ ሌላስ?” ብሎ ጆንሰን ጠየቃት፡፡
“ሁለት ሰዎች መጡና አኔን ወሰዷት። ባሏ ሉዊስ ሮድሪጌዝ እዚያው ነበር። ደብድቧት በግድ ለእኔ እንድትደውልልኝ ያስደረገውም እሱ ነው።”
“አንቺን ብሆን ለእሷ አንድም እምባ አላባክንም ነበር፡፡” አላት እና ጆንሰን
“ብትመታም ባትመታም አንቺ እዛ ስትመጪ ባሏ ምን ሊያደርግሽ
እንደሚችል ታውቅ ነበር እና ልትደውልልሽ ባልተገባ ነበር።”
“ሉዊስ ሁለት ጊዜ በጥይት ሊገድለኝ ነበር” ብላ ኒኪ በስጨት አለች እና
ከዚህም በተጨማሪ ሁሉንም ያደረጋቸውን እና ያስደረጋቸውን ነገሮች
ካርተር በርክሌይን ነገረኝ፡፡ ማለትም ቻርሎቴ እንዲመለከት እንዳደረገ፡፡ ዊሊ ባደን ስላጭበረበረው እንደገደለው እና አኔም እሱን ሲገድል ቪዲዩ እንድትቀርፅ ማድረጉን፣ ብራንዶንን ቅጥር ነፍሰ ገዳይ
አድርጎ ሊያስገድለኝ እንደነበረ እና በስህተት ሊዛ ፍላንገንን እንደገደላት፣
ትሬይ ስለ እኔ መረጃ አልሰጥም ያለ መስሉት እንደገደለው ከነገረኝ በኋላ
ሊገድለኝ ሲል የመጋዘኑ መብራት ጠፋ፡፡ ለዚያም መሰለኝ እግሬን በጥይት የመታኝ። ጭለማው ውስጥ በነበርንበት ጊዜ ቆለጡን መትቼው እንዳመለጥኩኝ ጭምር አስታውሳለሁ።”
ጆንሰን ራሱን በአዎንታ እየነቀነቀ ትክክል መሆኗን ገለፀላት፡፡ ይሄኔም ፊዮና በመሀል ገብታ “ዶክተር ሮበርትስ ራስሽን ለማረጋጋት ሞክሪ ሰውነትሽ ብዙ ደም ስለፈሰሰው እና በተደረገልሽ ቀዶ ጥገና ሁሉ ስላደከመሽ ብዙ...” ብላ ሳትጨርሰው
ኒኪ በእጇ ደህና ነኝ የሚል ምልክት አሳየቻት እና ለጆንሰን ማውራቷን
ቀጠለች።
“እናም መብራቱ በድጋሚ ሲበራ... የእሳት አደጋ መውጫ ደረጃ ላይ
ነበርኩኝ” ብላ ጆንሰንን ስታየው
“ልክ ነሽ” ብሎ አረጋገጠላት።
“ሮድሪጌዝ ሊጨርስኝ ሲል ነው ጉድማን የተከሰተው:: እሱ ነው ህይወቴን ያዳነው” ብላ ጆንሰንን ተመለከተችው እና “ሮድሪጌዝን በጥይት አናቱን አፈንድቶ ገደለው” ብላ ነገረችው፡፡
ጆንስንም “መልካም ከዚያ በኋላስ?” ብሎ ጠየቃት፡፡ ኒኪም ፊቷ ገረጣና መንቀጥቀጥ ጀመረች። አዎን የጉድማን ፊት እሷ ላይ የማላገጡን ሁኔታ
እና አረመኔ አይኑን አስታወሰችና “ከዚያ በኋላ.. ምንም ነገር አላስታውስም።” አለችው፡፡ “እኔ ግን የምታስታውሺ ይመስለኛል።” ብሎ ጆንሰን በመቀጠልም
“ጉድማን ሊገድልሽ ነበር” አላት፡፡
“አልነበረም” አለች ኒኪ ጭንቅላቷን ግራ እና ቀኝ እየወዘወዘች፡፡ “እንደርሱ ሊያደርግ አልነበረም፡፡ ደግሞም አያደርግም፤ እንዴ እኔ እና እሱ
እኮ ጓደኛሞች ነበርን።”
“ማለት ልክ ከብራንዶን ግሮልሽ ጋር ጓደኛ እንደሆናችሁ ሁሉ ማለትሽ ነው?” ብሎ የንዴት ሳቅ ሳቀባትና “ሉው ጉድማን ውሸታም እና አጭበርባሪ ነበር። እኔ በመሀል ገብቼ ባልገላግለው ኖሮ ጭንቅላትሽን ልክ እንደ ሮድሪጌዝ ጭንቅላት ይበትንልሽ ነበር።”
“በፍፁም!” ብላ ተወራጨችና “ይሄ በፍፁም እውነት ሊሆን አይችልም!”
አለችው::
“እውነት ነው እንጂ” አላት እና ጆንሰን ብስጭት ብሎ
“ጉድማን ሮድሪጌዝ እየከፈለው ለሁለት ዓመታት ያህል ወይንም ከዚያ በላይ ተቀጥሮ ሲሰራለት ነበር። ደሀ ሆኖ እንዳደገ ነግሮሻል አይደል? ሁሉን
ነገር ማጣት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያወቀው ገና በልጅነቱ ነበር። በቃ
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የህይወቴ ዋስትና ሊሆን የሚገባው ነገር ቢኖር ገንዘብነው ብሎ ማስብ ጀመረ፡፡ ሮድሪጌዝ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥቂት ሚሊዮን ዶላሮችን ሲሰጠውም በሁለቱ ስግብግብ እጆቹ ተቀበለው፡፡
በዚህም ዴሪክ ዊሊያምስን እና አንቺን ጭምር እስከመግደል ደረጃ ደረሰ”
“እየዋሸሽኝ ነው!” አለችው ኒኪ፡፡
ይሄኔም ነርሷ ማክማኑስ ጣልቃ ገብታ “እባክህን ውጣልን!” ብላ መርማሪ ፖሊስ ጆንሰን ላይ እያፈጠጠችበት፡፡ “እዚህ ክፍል ከመግባትህ በፊት ተነጋግረን ነበር አይደል? ሰውነቷ ስለተጎዳ ማረፍ አለባት። እሷን እንደዚህ እንደምታበሳጫት አስቀድሜ ባውቅ ኖሮ እንድታገኝህ አላደርግም ነበር።” አለችው፡፡
ጆንሰንም በጣም ተናድዶ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ፍንጥር ብሎ ከተነሳ በኋላ “እኔ ደግሞ እሷ ሁሉን ነገር ካወቀች በኋላ እንኳን እንደዚህ የማታምን ደረቅ መሆኗን ባውቅ ኖሮ የሥራ ባልደረባዬ እና አጋሬ ጉድማን እንዲገድላት ብተወው ጥሩ ነበር!” አላት፡፡
ነርሷ ልታወራ ስትል ጆንሰን በንዴት አቋረጣት እና
“ለማንኛውም የነገርኩሽን ነገሮች የማታምኚኝ ከሆነ ቴሌቪዥኑን ከፍተሽ
ዜናዎችን ማየት ትችያለሽ፡፡ መልካም ዕድል ዶክተር ሮበርትስ” ብሏት በንዴት እየተመናጨቀ ኒኪ ከተኛችበት ክፍል ወጣ፡፡
“በጣም ይቅርታ” እያለች ፊዮና በጣም ተጨንቃ ዶክተር ሮበርትስን ይቅርታ ጠየቀቻት:: ምክንያቱም ዶክተር ራይሌ እሷ ፈቅዳ ፖሊሱ ወደ እዚህ ክፍል ገብቶ ኒኪን ማበሳጨቱን ቢያውቅ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ትገምታለች፡፡ “ ውጪ እኮ ሳወራው በጣም ትሁት ሰው ነበር፡፡ በእውነት እንደዚህ የሚያበሳጭሽ ሰው መሆኑን ባውቅ ኖሮ አላስገባውም ነበር”
አለቻት፡፡
ኒኪም “ምንም አይደል” አለቻት እና ጆንስን የነገራትን እያንዳንዱን ነገር
በአዕምሮዋ ማብሰልሰል ጀመረች፡፡ በእርግጥም ደግሞ ጉድማን ሊገድላት
እንደነበር ታስታውሳለች፡፡ የሆነ ሰው ምናልባትም ጆንሰን ነው ህይወቷን
ሊያድንላት የሚችለው፡፡ አሁን ሉዊስ ሮድሪጌዝም ሆነ ጉድማን በህይወት
የሉም። ስለሆነም ሌሎች የምታውቃቸው ሁለት ሰዎች በተጨማሪ ህይወታቸውን ሊያጡ ችለዋል ማለት ነው፡፡ ከዶውግ ሌንካ ሊዛ ትሬይ እና ዊሊያምስ ላይ ሁለቱ ሰዎች ጉድማን እና ሮድሪጌዝ

ህይወታቸውን በህይወት ሊያጡ ችለዋል።
“እኔ ግን እዚህ በህይወት እገኛለሁ፡፡ ስለዚህስ ደረቁን ጆንሰን ህይወቴን
ስላዳነልኝ ላመሰግነው ይገባል? ዜና ከፍተሽ ተመልከቺ ማለቱ ምንድነው
ብላ ኒኪ ፊዮናን ጠየቀቻት፡፡
“ምንም ማለቱ አይደለም፡፡ መጋዘኑ ውስጥ በነበሩት ግድያዎች ላይ
ዜናዎች እየታዩ ስለሆነ እሱን ማለቱ ሊሆን ይችላል። አሁን ግን አንቺ ዕረፍት መውሰድ አለብሽ፤ እኔ ዶክተር ራይሌን ይዤው እመለሳለሁ::”ብላት ክፍሉን ለቅቃ ወጣች፡፡
ኒኪም ከአልጋዋ ጋር በሽቦ ታስሮ የተንጠለጠለውን የቴሌቭዢኑን ሪሞት
አንስታ ቲቪውን ከፈተችው። ቻናሉንም A B C ላይ ስታደርገው ባሏ ዶውግ
ከመሞቱ በፊት የተነሳችውን ፎቶ የቴሌቭዥኑ ስክሪን ሞልቶት አየች፡፡
ፎቶው ያኔ በጣም ነፃ እና ደስተኛ በነበረችበት ጊዜ ላይ የተነሳ በመሆኑ
ከታች ሥሟ ባይፃፍ ኖሮ የእሷ መሆኑን ሁሉ ላታውቅ ትችል ነበር።
ቴሌቭዥኑ በመጋዘኑ ውስጥ ስለተካሄዱት ግድያዎች በደንብ እያብራራ
ያሳያት ጀመር። ጉዳዩ በአደንዛዥ ዕፅ ንግድ ቀለበት ውስጥ ያሉ ሰዎችን
የሚያካትት መሆኑን ከገለፀ በኋላ ከዚህ ጋር በተያያዘም አኔ ቤታማን፣
ካርተር በርክሌይ፣ ዶክተር ሀዶን ዶፎ እና የማዘጋጃ ቤቱ ከፍተኛ ባለስልጣን
የሆነው ፍራንኪ ጄይ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ሲዘግብ አይታ
ቴሌቭዥኑን አጠፋችው።
ዊሊያምስ ሲነግራት የነበረው ነገር ሁሉ እውነት ነበር ብላ ነገር መጎንጎኗን ቀጠለች፡፡ ጉድማን፣ሀዶን፣ ካርተር እና ባደን በጉዳዩ ውስጥ ነበሩበት ማለት ነው፡፡ በሚገርም ሁኔታ ደግሞ እሷ ትጠላው የነበረው ግትር እና ሙሰኛ ነው ብላ ታስበው የነበረው፣ ውሸታም ነው ብላ የምታምነው ጆንሰን ግን በተቃራኒው መልካም፣ ሀቀኛ እና እውነተኛ ሆኖ አገኘችው።
እሱ ህይወቴን አትርፎልኛል ብላ በሀሳብ ተመስጣ ኮርኒሱን እያየች እያለ ጥገና ያደረገላት ዶክተር ወደ ክፍሏ ገባ፡፡
“እንዴት ነሽ አሁን?” አላት በጉንጫ ላይ የሚወርደውን እምባ ከቁስሉ ህመም የመጣ እንደሆነ አስቦ፡፡ “አውቃለሁ በጣም ነው የሚያመው ይቅርታ፡፡ ሞርፊኑን ልሰጥሽ ግን አልችልም:: አሁን ላይ የህመም ስሜቱ
ሊሰማሽ ግድ ነው። ለማንኛውም ስቃዩ ከባድ ቢሆንም እውነቱን ይዘሽ ጨክነሽ መቆየቱ ግድ ነው።” አላት።
"ገባኝ” አለች፡፡ እምባዋን በሁለቱም ጉንጮቿ ላይ እያፈሰሰች፡፡
በእርግጥ ደግሞ ከብዙ ወራቶች በኋላም ቢሆን ነገሮች በደንብ ነው የገቧት:....

#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል
...«አዎ ይኸው ነው! ጨርሻለሁ! አንዲት ሕይወት አንጋድጃለሁ! ቅንና ገር ሕይወት ቀርድጄ ጥያለሁ» ብዪ አጠገቤ ያለውን ጠረጴዛ በቡጢ መታሁት፡፡
ጉልላትም «እኔም እኮ መጀመሪያውኑ ያውም ገና ከቡቃያነቱ ከፍ ሳይል
ነግሬህ ነበር» ብሎ ሲያነብ የቆየውን መፍሐፍ በሌባ ጣቱ አለበና «እንደ ጨው
ካሟሟሃት በኋላ ወደየትም ቦታ ትረጫታለህ፡ ወይም እንደ እንኮይ ከበላሃትና እንደ አጥንት ከጋጥሃት በኋላ እንትፍ ብለህ ትጥላታለህ ብዬህ ነበር፡፡ ክልልህና ክልሏ አንድ ካለመሆኑ የተነሣ እንዴ አጋጣሚ እንኳን ሆኖ ብትንጠለጠልባት እንደ ተልባ ሥፍር ትንሽራተታለህ፥ በአንተና በእርሷ መካከል: የኮርማና የአምቦሳ ያህል ልዩነት አለ» ብሎ ቁልቁል ወለል ወለሉን አየ። በየወጂያነሽ ላይ የደረሰውን ማንኛውንም ነገርና ሁኔታ ሁሉ ተርኬ ጨርሼለት ስለ ነበር አሁን ከእርሱ የምጠብቀው ምክሩን እንጂ በሰነበተው ሐሳቡ ውስጥ የነበረውን አፍራሽ ነቀፌታ አልነበረም፡፡
«ስማ» አለኝ የመጽሐፉን ገጾች እየገለባበጠና ዐይኑን በሐሳብ እያቦዘ፣
«ከእንግዲህ ምስጢርህ ሁሉ ያንተ እስረኛና ምርኮኛ መሆን አለበት፡፡ ከበተንከውና ከረጨኸው ግን አንተው የምስጢርህ ምርኮኛና ግዳይ ትሆናለህ፡፡ ምስጢርህን በውስጥህ ለማዳፈን የምትችል ከሆንክና እሷንም እንደማትከዳት ከራስህ ጋር
እውነተኛ ቃል ኪዳን ከገባ ዓላማህን ለመፈጸምና የትግልህን ምርት ለማፈስ
ነገሩ የካባድ ቀላል ይሆናል፡፡ አሁንም እንደገና ልንገርህ፤ ያለ ጥርጥር ድል
ማድረግ ትችላለህ !» ብሎ አንገቱን ወደ ኋላ ቀልሶ ጣራ ጣራውን ማየት ጀመረ።
ሳይታወቀው እግሩን ዘረጋ።
«ያጠፋሁትን የሕይወቷን ቀንዲል እንደገና ለመለኮስና በተደላደለ የኑሮ
መሠረት ላይ እንድትገኝ ለማድረግ ታጥቄ ተነሥቻለሁ! ዛሬ ባላገኛት ነገ፣ ነገ
ባይሳካልኝ ከነገ ወዲያ ከዚያም ከዚያም በኋላ ቢሆን አገኛት ይሆናል። ሆነም
ቀረም ያስጨበጥኳትን መራራ የኑሮ ጽዋ ከንብዬ ሌላ ጣፋጭ የሕይወት ጽዋ
እስጨብጣታላሁ! ሕይወቴም እፎይታና ልባዊ እርካታ ማግኘት የምትችለው
የተጉደፈደፈችበትን የጸጸት ዕድፍ አጥባ ስታጠራ ብቻ ነውና እስከ ዘለቄታው
እታገላለሁ:: ከጥንትን፣ ሥጋንና ደምን፣ ክብርንና ርካሽ አዋራጅ ቃላትንም
በቆራጥነት እቋቋማቸዋለሁ» ብዩ ተራ ለቀቅሁ።
ጣራ ጣራውን ሲመለከተ የቆዩትን ዐይኖቹን ወደ እኔ መለስ አደረገና
አንገቱን አስተካከሎ
«ሌላ ነገር ባደርግልሀና ብመክርህ ይሻለኛል፡፡ እኔም የሐሳብ እንጂ ሙሉ
የተግባር ሰው አይደለሁም፡፡ የወላጆችህን እምነትና አስተሳሰብ በቀላሉ መለወጥ እችላለሁ ብዬ አልናገርም፡፡ አስተሳሰብን መለወጥ እንደሚቻል ባውቅም አፈፃፀሙ ግን ብዙ ውጣ ወረድ አለበት፡፡ ለዘመናት የኖረን የሕዝብን እምነት መለወጥ ቀላል ጉዳይ አይደለም፡፡ አንተም ውስጥ እኮ ያ እምነት አለ፡፡ እኔም ዘንድ አለ:: ኋላ ቀር አመለካከትን ከሕሊና ላይ አጥቦ ለማፅዳት አያሌ ዓመታት ይፈጃል። በዚያ ላይ ርዝራዥ እስኪወገድ ብዙ ፈተና አለ። ይህ ጉዳይ ከተራው ዜጋ እስከ ከፍተኛው ባለሥልጣን ድረስ ይዘልቃል፡፡ ያም ሆነ ይህ አንተ ግን ከዛሬ ጀምረህ በዓለም ላይ ያለውን አንድ ተራ አድካሚ ሥራ ለማከናወን ሞክር፡፡«በመጠኑ እንኳ ከተሳካልህ ጥሩ ታጋይ ነህ ማለት ነው። አዎ ሌላ አይደለም፡ እስኪ በመጀመሪያ ራስህን ለማወቅና ለማሽነፍ ሞክር፡፡ ብልህ መሆን ማለት ስለ አንድ ስለ አጣኸው ወይም ስለማታገኘው ነገር ተጎልተህ መተከዝ አይደለም፡፡ ይልቅስ እሷ በአካልና በሕሊና የምትካስበትንና መልሰህም ማግኘት የምትችልበትን መንገድ መፈለግ ነው» ብሎ ጸጉሩን ማሻሸት ጀመረ።
ምንም እንኳ ሐሳቡ ረቅቆ የሚያመራምር ባይሆንም ለጊዜው ብቻዬን ሆኜ በአእምሮዬ ሰለቅሁት። በየበኩላችን ሐሳብ በማንሣትና በመጣል ላይ እንዳለን
እኅቱ ሻይ ይዛልን ከተፍ አለች፡፡
«ግን» አለ ያንን ሁለትና ሦስት ጊዜ ያህል እ-ፍ-እ-ፍ ብሎ ፉት ያለውን ሻይ ኣፉ ውስጥ አቀዝቅዞ ከዋጠው በኋላ፡፡
«ይኸው ለእኔ እንኳ ከምስጢርህ ውስጥ ጥቂቱን ነግረኸኛል፤ ቀሪውን ቀብረህ ለመጠበቅ የሚኖርህ ኃይል ግን አነስተኛ መሆን የለበትም። አደራህን! አንተ ልታምቀው ያልተቻለህን የገዛ ራስህን ምስጢር ሌላ ሰው ሊጠብቅልህ
አይችልምና ማንም የማይከፍተው የልብ ሳጥን ይኑርህ! ዓላማህን ለመፈጸምና
ከግብህ ለመድረስ ለራስህ ከራስህ የሚቀርብህና በፍጹም ተግባራዊ መሰልህ ሌላ ማንም እንደማይገኝ አትዘንጋ» ብሎ ወደ ሻዩ ዞረ።
ጓደኝነቱን በቃል ሳይሆን በተግባር ያከናወነልኝ ስለመሰለኝ ጉልላትን
ከቀድሞው በበለጠ ከራሴ ጋር አዋሐድኩት፡፡
ሐሳቡን ለአንድ አፍታ ቆም አድርጎ ደረጃ በደረጃ ፈገግ ካለ በኋላ ለዛ የሌለው ሣቅ ሣቀ። «ለመሆኑ አሁን ብታገኛት ምን ትላታልሀ? ” ምንስ ታደርግላታለህ?» ብሎ ደረቅ ፈገግታውን አሳየኝ፡፡
ድንገተኛ ጥያቄው ድንገተኛ መልስ እንድሰጥ ያስገደደኝ ይመስል
የንግግሬን አካሔድ ሳልመለከት የመጣው ይምጣ እንጂ ቤት ተከራይቼ
አብሬያት እኖራለሁ፡፡ ከዚያ ወዲያ ማንም ያሻውን ቢልና በእኔና በእርሷ የተነሣ
ቤተሰቦቼ እንኳ ብትንትናቸው ቢወጣ ግድ የለኝም» ብዬ መለስኩለት፡፡ አሁንም
ሐሳብ ሊሽከሽክ ሰምቶ ዝም አለ፡፡
ጉልላትን ከማደንቅበት አንደኛዉ ዋና ምክንያት የግል ሐሳቡን ስፋት ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ሰዎች ያገኘውን ዕውቀትና አነጋገር ሳይረሳ ለሌላ
የማስተላፍ ችሎታዉን ነው::
«መቼም በራስ መተማመንና ሕሊናን መግዛት የጀግንነት ምሰሶ ነው ብሏል አንድ ሊቅ» ብሎ ንግግሩን በመጀመር «የሚያዋጣትን ትክክለኛ መንገድ
ለማግኘት ስትል የምትፈራና የምትጨነቅ አእምሮ ፍጻሜዋ ያማረና የሠመረ
ይሆናል” ብሏል አንዱ ሌላ ሊቅ ደግሞ» በማለት የማዳምጥ መሆኔን ለመገንዘብ
ትኩር ብሎ አየኝ::
«እኔም ለፅኑ ጓደኝነታችንና ለፍቅራችን ዘላቂ ሕይወት ስል የችግሮችህ
ሁሉ ሙሉ ተካፋይ እሆናለሁ፡፡ በምታደርገው የውጣ ውረድ ትግልም ይሁን በሌላ ማናቸውም ነገር እኔ አንዱ ግማሽህ ነኝ፡፡ የብርሃናዊም ይሁን የጽልመታዊ ፍጻሜህ ማኅበርተኛ እሆናለሁ» ብሎ የማያወላውል ልበዊ ጓደኝነቱን አረጋገጠልኝ፡፡ የዕለቱ ምከራችንና ሐሳባችን ሰምና ወርቅ ሆኖ አለቀ።
የወዲያነሽ አድራሻና መገኛ ትላንትም ከትላንት ወዲያም እንደሆነው
ሁሉ፣ ወደፊት ግን የሕልም ሩጫ ሆኖ እንደማይቀር ሙሉ ተስፋ ነበረኝ።
የወዲያነሽን ፍለጋ ጉልላትም አብሮኝ ባዘነ፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል! የሁለታችንም
ልፋት የማይገኝ የቅዠት ወርቅ ሆኖ ቀረ።
እናቴን በጥላቻ ጥቁር ዐይኖች ተመለከትኳት። በቤተሰቤ መኻል እያለሁ
የከለልኩት የብቸኝነት ክልል ግን እኔኑ እንጂ ማንንም አልጎዳ፡፡ እኔ የእኔዉ
ረመጥ ነኝና የሕሊናዬ ረመጥ እኔኑ መልሶ ፈጀኝ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጥቅምት ኸያ አራት ቀን አንድ ያልተጠበቀና ያልታሰበ ምንም ዝግጅት
ያልተደረገለት ትልቅ የደስታ ቀን ሆኖ ዋለ፡ ቤታችን በእንግዶች እና በልዩ ልዩ
ስዎች ተጣበበ፡፡ ላለው ምን ይሳነው፡ ሆንና ለተገኘው ደስታ የተፋጠነ ድግስና
መጠነኛ ግብዣ ተደረገ፡፡ አባቴ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ እንዲሆን ተሾመ ትልቁ ክፍል ውስጥ መላወሻ ጠፍቶ ዋለ። አንዳንዶቹ ያልፈጸመውን እየጨመሩና እያሞጋገሱ የሆነና ያልሆነውን ዝና እየሰጡ አወሩ።
አንዳንዶቹ ደግሞ ግራ ቀኛቸውን መልከትከት ብለው ቤተኛ ሰው ያለመኖሩን ካረጋገጡ በኋላ ከሐሜታው
ወርወር አደጉ። አባቴ የመጣውን ሰው ሁሉ በደስታና በፈገግታ እየተቀበለ ሸኘ።
ሹመት ያዳብር ጌታዩ” እያለ የሚመላለሰውና እጅ የሚነሳው

👍4❤1
ሳያቋርጥ ላይን ያዘ፡፡ አንዳንዶቹ ሁለትና ሦስት
ሆነው ደረጃውን ሲወርዱ ይገባቸዋል፡ ዐዋቂ ሰው እኮ ናቸው፥ ያውም የመኳንንት ዘር” ይባባላሉ፡፡ ከቤት ውስጥ በመጨረሻ የወጡት እንግዳ የተጣሉ
የሠፈር ሰዎች በማስታረቅ የታወቁት አለቃ ዘሪሁን ሞገሴ መለኪያቸው ውስጥ
የቀረችውን ዐረቄ ጨልጠው ለመሔድ ሲነሡ በረጂሙ ከመረቀ በኋላ
«ለመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ለኃጢኣት መደምሰሻ ያድርግልሀ» ብለው ወጡ።
አባቴ በጥሩ ስምና ዝና የሚያምን እስፈላጊም ከሆነ ከብር እና ጥቅም
ያስገኛል ብሎ ለሚያምንበት ነገር ሁለ መሥዋዕት እስከመሆን የማይመለስ ነው። የማታ ማታ 'ዘመድ ነኝ፣ የቅርብ ወዳጅ ነኝ ባዩ ሁሉ ሙልጭ ብሎ ሔደ፡፡ የደስታ ቀን ስለ ነበር ያን ዕለት ማታ ሁላችንም ተሰብስስን በመዓድ
ዙሪያ ከበን ራት በላን፡፡ የሆዴን በሆዴ አድርጌ እንደ እኅቴና እንደ እናቴ
የተደሰትኩ በመምሰል ሣቅ ሣቅ ስል አመሸሁ፡፡ ከራት በኋላ ለቤተሰብ ተብሎ
ከተከፈተው ኮኛክ ላይ በረጅም መለኪያ ተቀዳልኝና በወጉ ተቀመጥኩ። ለቡና
ማፍሊያ ተብሎ ትልቁ ክፍል ወስጥ የተያያዘው እንግልጥ ፍም ቤቱን
ስላሚሚቀው ከውጪ እየሾለከ የሚገባው የጥቅምት ብርድ እምብዛም አጥቂነት አላገኘም::
አባቴ የመጠጥ ዐመል ባይኖርበትም የዕለቱን ሁኔታንና ደስታ ስለ ገፋፋው
ሦስትና አራት መለኪያ ወሪውሯል፡፡ የሁሉም ስሜት የተገናኘ መሰለ። የእኔን
ሕሊና ግን የወዲያነሽ ትዝታ ያዟት ፈረጠጠ። ልቤ አመታቷን ለወጠች።
የወዲያነሽ ' 'ጌታነህ ጌትዩ ” የምትለኝ መስለኝ፡፡ የተሟሟቀዉ ሰውነቴ
የማስታወስ ችሎታ የደረበልኝ ይመስል የወዲያነሽ' ዘፈንና ዜማ በጆሮዬ ውስጥ
ተርመሰመሰ።
«ምድርና ሰማዩን አንድ አርገህ ስትሠራ
ማኖር ቸገረህ ወይ እሱን ከኔ ጋራ»
የምትለው ዘፈኗ ትውስ አለችኝ። የዘፈኗ ይዘት ትርጉም ወለል ብሎ ታየኝ፡፡ ምንም እንኳ የሚያወሩትንና የሚጫወቱትን ሁሉ የማዳምጥ ተመስዬ በመካከላቸው ብቀመጥም የሰማሁትና ሥራዪ ብዪ የተከታተልኩት ነገር አልነበረም፡፡
የወዲያነሽ ርቧት፡ በርዷት፤ ከስታና ገርጥታ፣ ዙሪያው ገደል ሆኖባት
ጉልበቷን ኣቅፋ ስታለቅስ አካላዊ ምስሏ በሕሊናዬ ውስጥ እየተንጎዳጎደ
አስጨነቀኝ::
ቀስ በቀስ ከአካሌ ተነጥሎ ሄዶ የነበረው መንፈስ መለስ በማለት ጤነኛ
ሕይወት ዘራሁ። በመኻሉ ሰው ትዕግሥተኛና ሠራተኛ ከሆነ ምን ጊዜም ቢሆን ይዋል ይደር እንጂ ከአምላክና ከንጉሡ የድካሙን ዋጋ አያጣም» እያለ አባቴ ሲናገር ሰማሁ፡፡ ምንም እንኳ ወሬው ቀደም ብሎ ቢጀምርም ተሳታፊ ንቁ ስሜት ስላልነበረኝ ያዳመጥኩት ነገር አልነበረም፡፡ የቀመስኳት ሁለት መለኪያ ሰውነቴን ስላሟሟቀችልኝ ለጊዜው ነባሩ ፍርሃቴ ከላዪ ላይ ጠፋ፡፡ ከነበረኝ ልማድ በላይ ከአባቴ ጋር ለመከራከርና ለማውራት ድንገተኛ ውስጣዊ ፍላጉትና ድፍረት ገፋፋኝ፡፡
እኔና አባቴ ፊት ለፊት ተቀምጠን በመካከላችን አጠር ያለች ክብ
ጠረጴዛ ነበረች፡፡ መለኪያዬን ወደ ጠረጴዛው መኻል ገፋሁና እግሬን ሰብስቤ ተቀመጥኩ። «አባባብዬ ንግግሬን ስጀምር ትክ ብሎ ተመለከተኝ፡፡
«ሰው በሕይወቱ ዘመን ምንና ምን ይፈልግ ይመስልሃል?» በሚል ጥያቄ
ጀመርኩ፡፡ በግራ እጁ የጨበጣትን መለኪያ ወደ ላይ ከፍ አድርጎ ከተመለከታት በኋላ ሐሳብ ለማሰላሰል ላፍታ ያሀል ዝም አለና «ሰው ሁሉ የተለያየ ነገር ይፈልጋል፣ የሰው ፍላጐት እንደ ባሕር ውሃ ወይም ከዚያ በላይ የሚገመት ነው። ባጭሩ ወሰን የለውም፡፡ ሆኖም ሰው ሲባል ሁለት ነገሮች ይፈልጋል። በመጀመሪያ
የሚፈልገውን ነገር ያላንዳች ተቀናቃኝ ማግኘት፣ ካገኘም በኋላ እንዲጠቀምበትና እንዲደሰትበት ነው። ባገኘውና ባጋጠመው ነገር በደንብ የሚጠቀምና የሚረካ ግን
ብልህ ብቻ ነው» ብሎ መለሰልኝ፡፡ ያልጠበቅሁትን የመልስ ዐይነት በማግኘቴ ሌላ ጥያቄ ለማቅረብ ፍላጎቴ አሞጠሞጠ።
«እስከ ዛሬ ካጋጠሙህ ከባድ ነገሮች አንዱ ምንድነው?» ብዬ ሣቅ ሣቅ
በሚል ፊት አየሁት፡፡ ያን በአጭሩ የተስተካከለውን ገብስማ ጸጉሩን በቀኝ እጁ ካሻሽ በኋላ ጉልበቱን በቡጢ መታ መታ አደረገ።
«ለመታመን እና ለመታወቅ ያደረግሁት ከባድ ጥረትና ልፋት ከእኩዮቼ በላይ ለመዋል የለፋሁት ልፋት፣ ምቀኞቼን ለመጣል የጣርኩት ጥረትና ያሳለፍኩት ውጣ ውረድ፣ እረ ስንቱ? በቀላሉ ልንገርህ! ለኑሮ መታገልን የመሰለ ምንም ከባድ ነገር የለም፡፡ ኑሮን መንካት ወይም መታከክ እንጂ ሙሉ በሙሉ መጨበጥ የለም» አለኝ፡፡
ከአባቴ ጋር እምብዛም የመጫወትና
ቀርቦ የመወያየት ልማድ ስላልነበረኝ፡ ምናልባት ተዳፈርክ ይለኝ ይሆን?” በማለት ውስጥ ውስጡን በስጋት
ነፈርኩ፡፡
አባቴ ምን ጊዜም ከሰው ጋር ሲያወራም ይሁን ሲከራከር የነብዩ ሰሎሞንን
ምሳሌዎች መጠቃቀስ ስለሚያዘወትር ከአሁን አሁን አንዷን ይጠቅስብኝ ይሆን?
እያልኩ ተጠባበቅሁ። እንዳጋጣሚ ሳይጠቅስ ቀረ፡፡
የሥራውን ጠባይና አካባቢ የሚያነብባቸውን ልዩ ልዩ ሥጋዊና መንፈሳዊ መጻሕፍት መሠረት በማድረግ በሰጠኝ አስተያየትና ሐሳብ አልትደነቅሁም፡፡ «ለመሆኑ አንድን ሰው ደስ የሚያሰኘው ምንድን ነው?» አልኩት፡፡
«ሰው ምድርና ሰማይንስ አጣምሮ ቢገዛ መች በቃኝ ይላል? ከዚያ ወዲያ ከዚያ በላይ መጓዝና ማግኘት ይፈልጋል። ሰውን ማጥናትና ስለ ሰው የፍላጎት መጠን መመራመር የሰማይን ርቀት እንደ መለካት ነው:: ግን እንዲያው ባጭሩ !በቀላሉ ላስረዳህ፣ ተሟግቶ ሲረታ፣ ወዶና ተዋዶ ሲያገባ፣ ከድካሙ በኋላ ጥሩ ፍሬ ሲያገኝ፣ የተናገረው ሲደመጥለት፣ ከሚያሸንፋቸውና ከበታቾቹ ጋር ሲኖር፣
የአያት ቅድመ አያቱን ክብርና ዝና፣ አጥንትና ደም፣ ርስትና ጉልት ሲያስከብር
...አያልቅም እኮ ብየሃለሁ፡፡ እነዚህ በመጠኑም ቢሆን ያስደስቱታል» በማለት
አሁንም ያልጠበቅሁትን ያህል መልስ ሰጠኝ፡፡ ማዳመጥ እንጂ እንዴት? ለምን?
ብሎ መከራከር ቁጣን ያስከትላል በሚል ነባር ፍርሃት ላጭር አፍታ ያህል ዝም
አልኩ፡፡ ሆኖም የሕሊናዬ ግፊት ስላስጨነቀኝ «በዚህ ዐይነትማ ምንጊዜም ቢሆን የሰው አእምሮ ሊጠግብና በቃኝ ሊል አይችልም ማለትህ ነው?» ብዬ ተነፈስኩ።
«አጀብ አንተ! ከዚህ ቀደምም ሲሆን በቃኝ ብሎ አያውቅም። በቃኝ
እማ ካለ ኣይችልም እንጂ ነገሩ ሁሉ አከተመ:: ግን በቃኝ አይልም፡፡ ዘወትር
ሽቅብ እንደተንጠራራና እንዳሰበ ነው ሰው ሁሉ በየተራ የሚያልፈው። ሁሉም
በያቅሙና በየችሎታው ያውም አንዳንድየስ ከዚህ ውጪ እንደየተፈጥሮው ብዙ ነው ሐሳቡ፡፡ ኑሮ ግን ከአንድ የፍላጐት ትግል ፍጻሜ ወደ ሌላ አዲስ ፍላጎት መሸጋገር እንጂ ከደስታ ወደ ደስታ መተላለፊያ ብቻ አይደለም፡፡ ሁሉም ነገር የሚገኘው አፈር መሬት እየጋጡ ነው፡፡ እንዲህ ዋዛ! » ብሎ ወደ ዐረቄው መለስ አለ።
«እኔ የምለው ግን» አልኩት የያዛትን መለከያ ሲያስቀምጥ ካየሁ በኋላ
የሰው ልጅ ሁሉ በተፈጥሮ እኩል ነው ብዬ ነው የማምነው» በማለት ፍርሃት
ባደቀቃት ድምፅ አዲስ ሐሳብ ደቀንኩ። ትንሽ ለብ ካለኝ በኋላ እንኳ ለምን
እንደ ፈራሁ አላውቅም።
«እግዚኣብሔርማ ሲፈጥረው እርግጥ ነው ሁሉም ሰው እኩል ነው:: ሁላችንም በአርእያ እግዚኣብሔር ነው የተፈጠርነው ቢሆንም እኮ ታዲያ ጎበዞችና ሰነፎች፣ ጨዋና ባለጌ፣ እስተዋይና ሞኝ፣ ጀግናና ፈሪ ኧረ ስንቱ! አለ፡፡ ድኀነትና ሀብት ግን በሥራ ነው:: ሰው ሁሉ በርትቶ ከሠራ ጦሙን አያድርም፡፡ ከአያት ከቅድመ አያትም የሚወረስ አለ፡፡ እነርሱም ቢሆኑ በዘመናቸው ታጥቀው ሠርተው ያቆዩን ነው:: የድሀ ልጅ ድኃ የሚሆነው አባቱ ሰነፍና እዛባ ስለ ነበረ ብቻ ነው፡፡ ይኸ ሁሉ ድኃ፣ ድኃ የሆነው ባለመሥራቱ ነው:: ሰው ሲዳርና ሲያገባ ደግሞ ከየዘር ሐረጉና

የደረጃው ሲሆን ያምራል፡ ይሠምራል፡፡ አጥንቱ፣ ደሙ እና ሥጋው መከበር አለበት፡፡ የትም የሚወድቅ ባለጌ ብቻ ነው:: የምናምኑና ከእላፊ አግዳሚው ጋር መደባለቅ ራስን ማዋረድና ያለማወቅ ጭምር ነው፡፡
የጨዋ ልጅ ደግሞ ጠንቃቃና ብልህ በዚያ ላይ ደግሞ ታጋሽና አንደበተ ሰፊ መሆን አለበት፡፡ ለዚህ ብዬ ነው ከፈኛና ባለጌ እንዳትሆን ዘወትር የምገሥጽህና የምቆጣህ፡፡ እንደ አንዳንዶቹ አግድም አደጎች የትም እየተልከሰከሱ አጥንትን ማራከስ ትልቅ ውርደት ነው:: እኔ አባትህ እያለሁልህ ከአሁኑ በርታ፡ ብዙ ብዙ ከፍ ያለ ነገር ኣስቤልሃለሁ፡፡ ደኅና ሰው ቤት ልገባልህ እያማረጥኩ ነው በማለት በሞቅታ እየተገፉ የሚወጡ ቃላቱን ጨረሰ። እኔም የጠጣሁት መጠጥ ስለ ተጫጫነኝ ነገር ሳላበሳሽ ሹልክ ብዬ ወጥቼ ተኛሁ። ወደ ኋላ የማይመለሰው ጊዜ ከነፈ፡፡
እኔና የወዲያነሽ ከተለያየን ከአራት ወር በላይ ሆነ፡፡ አእምሮዬ ውስጥ የሚከማቹት የትካዜ ነጥቦች ግን እያደር ጨመሩ እንጂ አልተነሱም፡፡ ቢመር
ቢጎመዝዘኝም ካቤተሰቦቼ ጋር መጫወትንና ማውራትን ሕልም ሕልም በሚል ሁኔታ ቀጠልኩ፡፡ ዘወትር ማታ ማታ ከመተኛቴ በፊት መስኮቴን ከፈት አደርግና ጥቁሩን ጨለማ በጥቁር የትዝታ ዐይን እመለከተዋለሁ። ምንም ወደማይታይበት ጨለማ አፈጥና የማይጋገር ሐሳብ አቦካለሁ፡፡ ታዲያ፡ ድሪቶ ለብሳ ወንድ ወይም ሴት ልጅ አቅፋ ረሃብ፣ ብሮድና አቀራምዷት ስትሠቃይ ዐይኖቿ ጎመን መስለው ጸጉሯ ተበጤጥሶ አንዱ መንገድ ዳር ቁምጣ ስለ ማርያም የራበኝ የሰው አገር እመጫት፡ የማርያም አራስ እያለች ስትለምን የማያትና የምሰማት
ይመስለኝ ነበር፡፡ ጨለማ ውጦ የማያስቀረው ሐሳቤ ከዐይኔ ችሉታ ወዲያ ወዲያ ማዶ እስከ ሥፍር የለሽ ርቀት ይጓዛል።
እየፎካካተች ስታለቅስ አይተው «ታጸድቀናለች፡ ካምላክ ታስታርቀናለች፡
የሰማይ በር ታስከፍትልናለች» ብለው ያስጠጓት ሰዎች ራት አቅርበው ሲበሉ፣
የእመጫትነቷን ጠረን እየጠሉና ሰውነቷን እየተጸየፉ፣ ካንገት በላይ «ነይ እስኪ
አንቺ እመጫት፣ ነይ ራት እንብላ?» ሲሏት ልቧ እየፈለገና ዐይኗ እየጓጓ «አይ
ብሉ! በልቻለሁ... ይበቃኛል» እያለች ስትግደረደር ታየኝ፡፡
ወደ ሩቅ አድማስ የለሽ ርቀት የተጓዘው የሕሊናዩ ሥርጭት እየተንሰላጀጀ ይመለሳል። አይጠቅመኝም፡፡ ሐሳቤ እንደ ተቆረጠ የእንሽላሊት ጅራት አንጎሌ ውስጥ የሚንደፋደፍ ይመስለኛል፡፡ ጸጥታና ሰብአዊ ደስታ ራቀኝ፡፡
በራሴ የሐሳብና የብስጭት ወጥመድ ውስጥ ታሠርኩ፡፡ ድንገት ሐሳብና
ኑሮ ይሰበጣጠርብኝና «የወዲያነሽ መቼም ቢሆን የእኔ መሆን አለባት!
እንዲያውም የእኔ ናት! አንድ ቀን ተገናኝተን እስከ ዕለተ ሞታችን አብረን
እንኖራለን» እላለሁ፡፡ሕይወት እንደ ሸረሪት ድር ቀጠነችብኝ፡፡.....

🔥1