አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አንቺም ብትሆኚ ስትመጪ ለቅያሪ የሚሆኑሽን ልብሶች በትንሽ ሻንጣ
አዘጋጂ። ሁለታችንም አደጋ ላይ ነን፡፡ ስለዚህ ለጥቂት ጊዜ ያህል ነገሮች
እስኪረጋጉ ድረስ ተደብቅን መቆየት ይኖርብናል።”

ኒኪ ብዙ ጥያቄ ልትጠይቀው ስትል ስልኩ ተዘግቷል። ይህ አይነት
ፍርሃትን በእሱ ላይ አይታ ባታውቅም ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ስለ ጣውንቷ
ማወቅ እንደምትችል ስታስብ ደስ አላት፡፡

ስለ ጣውንቴ ካወቅኩኝ በኋላ ንዴቴን ሁሉ ትቼ ከራሴ ጋር እታረቃለሁ ብላ በማሰብ ላይ እያለች ስልኳ ጮኸ፡፡

ስልኩን ስለማታውቀው ምናልባት ዴሪክ በሌላ ሲም የደወለላት መስሏት
በቶሎ ስልኩን አነሳች እና “ዴሪክ” አለችው፡፡

ከዚያኛው የስልክ መስመር ግን የሚመጣው ድምፅ በጣም በሰቆቃ
የተሞላ እና ፍፁም የሚረብሽ ድምፅ ነበር። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን
የድምፁን ባለቤት ስታውቅ

“ይሄማ በፍፁም ሊሆን የማይችል ነገር ነው!”

“ዶክተር ሮበርትስ?” አላት ብራንዶን ግሮልሽ እና በማስከትልም “አንቺ
ነሽ?” ብሎ ጠየቃት፡፡

“አዎ ነኝ ብራንዶን” ብላው ልቧ በጣም እየደለቀባትም “የት ነው ያለኸው?”

“እርዳታሽ ያስፈልገኛል” ብሎ ሳግ አፈነው እና “ሊገድሉኝ ነው መሰለኝ
“አይዞህ እኔ አለሁልህ፡፡ ግን የት እንዳለህ ንገረኝ በመጀመሪያ

“እሺ” አለ እና በረዥሙ አየር ስቦ “እኔ... እኔ... ጥግ ላይ...”

ተናግሮ ሳይጨርስ የምት ድምፅ ተሰማት እና ስልኩ ተቋረጠ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኒኪ ኤስ ኤል ኤስ ሆቴል ቁጭ ብላ ዴሪክ ዊሊያምስን እየጠበቀች
ትገኛለች:: ዴሪክ ዊሊያምስ እንደነገራትም በትንሽ ሻንጣ ልብስ ይዛ መጥታለች፡፡ ይህንን ደግሞ ያደረገችው በተለይ ብራንዶንን ካዋራችው በኋላ ነው። በተለይ ደግሞ አሰቃቂው ድምፁ ትንሽ እንድትፈራ እና ዊሊያምስ አድርጊ ያላትን ነገር እንድታደርግ አስገድዷታል። ብዙ ልብስ ይዛ አልመጣችም፡፡ ሮድሪጌዝ ከቤቷ እንዲያስወጣት አትፈልግም።
ስለ ብራንዶን ስትነግረው ምን ሊል ይችላል ብላ አሰበች። እያወራት
እያለ ስለ ስማችው የምት ድምፅ ትነግረውና ሀሳቡን እንዲያካፍላት
ትጠይቀዋለች፡፡ ይህንን ነገር ለፖሊሶች እስከ አሁን አላሳወቀችም።በመጀመሪያ ይህንን የብራንዶንን ነገር ለዊሊያምስ ነው ልትነግረው የፈለገችው::
ኒኪ ፈዘዝ ያለ ጥቁር ሱሪ ከአረንጓዴ ቦዲ ጋር አድርጋለች። ቦዲዋ አንገቱ ክፍት ስለሆነ የጡቷ መካፈቻ ከጡት ማስያዢያዋ አፈትልኮ ይታያል። ይህንን አይነት ልብስ ለብሳ የመጣችው ዴሪክ ዊሊያምስን ለማማለል ሳይሆን ስለ ጣውንቷ ስትስማ ፅድት ብላ ለብሳ መሆን እንዳለበት ወስና ነው። ልክ ከዶውግ አጠገብ ሁለቱ ቆመው የሚወዳደሩ ይመስል ዝንጥ ብላ ነው የመጣችው።

ሌንካ የወደፊት ህይወቷን ብቻ ሳይሆን ያበላሸችባት ከዶውግ ጋር
አብረው ያሳለፉትን ጥሩ የፍቅር ጊዜዎችን እና ትዝታውን ጭምር
እንዳታስብ አድርጋ ነው የነጠቀቻት። ለጓደኛዋ ግሬቸን የነገረችውን የሌንካን
እርግዝና ለዴሪክ ዊሊያምስ ለምን እንደደበቀችው አሁን ግልፅ ሆኖላታል።
የዚህ ምክንያቷ ደግሞ እሷ ታግላ ያልተሳካላትን ነገር ሌንካ እንደቀልድ
ማድረግ መቻሏ ነው። እሱም ልጅ ማርገዝ ነው። ሌንካ ለዶውግ ልጅ
አርግዛላታለች፡፡ ኒኪ ግን ልታረግዝለት አልቻለችም፡፡ ይሄ ደግሞ በጣም
አሳፍሯታል።

ኒኪ ግድግዳው ላይ ያለውን ሰዓት ስትመለከት ከምሽቱ 1፡22 ይላል፡፡
ዊሊያምስ ከቀጠሮው 22 ደቂቃ አሳልፏል። ይህ ደግሞ የዴሪክ ፀባይ
እንዳልሆነ ታውቃለች። ለማንኛውም ዛሬ የጣውንቷን ሌንካን ማንነትና ለምን ባሏ ከሌንካ ጋር የፍቅር ግንኙነት የመሰረተበትን ዋነኛ ምክንያትን
ታውቃለች፡፡ እና ዊሊያምስ እስኪመጣ ታግሳ መቆየት አያቅታትም።

አሁን ከምሽቱ 1፡30 ይላል ኒኪ ትዕግስቷ አለቀና ስልኳን አውጥታ
“የት ነው ያለኸው? በሰላም ነው?” የሚል መልዕክት ላከችለት።
ዴሪክ ዊሊያምስ ጠረጴዛው ላይ ያስቀመጠውን የስልኩን የንዝረት ድምፅ
ሲሰማ ገና ከመታጠቢያ ክፍሉ ወጥቶ ልብሱን ሊለብስ ነበር። ስልኩን
ሲመለከት የኒኪን መልዕክት አየ።

“እየመጣሁ ነው፡፡ ይቅርታ ስለዘገየሁ” የሚል መልዕክትን ላከላት። ኒኪም መልዕክቱ ሲደርሳት ትንሽ ተረጋጋችና ብርጭቆዋን አንስታ መጠጡን
ተጎነጨች፡፡

ዴሪክ ዊሊያምስ ማስታወሻ ለመፃፍና በኢሜይል ለሚያምነው ሰው ለመላክ ብዙ ጊዜ ፈጅቶበታል። የከተማው ከንቲባ ፎንቴስ የቀድሞ ፀሐፊ ከነበረችው ቲና ድሬይ ያገኘችው መረጃ በጣም አደገኛ እና ሁለቱንም ሊያስገድል የሚችል ነገር ነው:: እርግጥ ነው መረጃ ሀይል ነው፤ በዚያው ልክም መረጃ ህይወትን ሊያሳጣ እንደሚችል ያውቃል። እንደምንም ፅፎ
የጨረሰውን መረጃ ለጓደኛው አላን በ ኢ ሜይል ከላከለት በኋላ ላፕቶፑን
ዘግቶ ቦርሳው ውስጥ ከተተው:: ጫማውን እያሰረ እያለም ደውል ተደወለ፡፡

“አሁን ሊመጡ አይችሉም መቼስ? ማን ሊሆን ይችላል? እነዚያ የሎሬን
ጠበቃዎች ፍርድ ቤቱ የወሰነብኝን ክፍያ እንድፈፅም ሊነዝንዙኝ ይሆናል ወደ እዚህ የመጡት ብሎ እያሰበ ትንሽዬ የጉዞ ሻንጣውን በጀርባው አንግቶ ወደ በሩ ሄደና በሩን ሲከፍት በሩ ላይ የሚያውቀን ሰው ስለተመለከት ተገረመ::

ሰውዬውንም “ይቅርታ አሁን ጥሩ ሰዓት ላይ አልመጣህም፡፡ እኔ አሁን
በጣም እቸኩላለሁ.…” ብሎ ተናግሮ ሳይጨርስ ስውዬው በመጀሪያው ጥይት
የዊሊያምስን አናት ነደለው፡፡ ቀጥሎም ሁለት ጥይቶችን በደረቱ ለቀቀበትና
የቤቱ ወለል ላይ ሲወድቅ ትቶት ወጣ።

ኒኪ ከዚህ በኋላ ዊሊያምስ የቀጠሮው ቦታ ላይ እንደማይመጣ አውቃለች። ስለዚህ ሦስት አማራጮች አሏት። የመጀመሪያው አማራጫ ዊሊያምስ እንደነገራት ከዚህ ከተማ ርቃ የሆነ ሆቴል ውስጥ ተደብቃ ዊሊያምስ እስኪደውልላት ድረስ መጠበቅ ነው፡፡

ሁለተኛው አማራጫ ደግሞ በቀጥታ ወደ ቤቷ መመለስ ነው።

ሦስተኛዋ አማራጭ ደግሞ ዝም ብሎ መጠጣት ነው፡፡

ኒኪ ስለ ሊዛ እና ትሬይ ግድያ፣ ስለ ሮድሪጌዝ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር
እናም ደግሞ ስለ ማዘጋጃ ቤት ባለስልጣኖች የሙስና ወንጀል ደንታ
የላትም፡፡ እሷ በጣም ጓጉታ የመጣችው ስለ ሌንካ ለመስማት እና እፎይ
ብላም ከንዴቷ መገላገል ነበር። ግን አልሆነም፡፡ የቋመጠችለትን የሌንካን
ነገር አሁን መስማት አልቻለችም፡፡ ምናልባትም ለወደፊቱ ጭምር አትሰማ
ይሆናል፡፡

ስለዚህ ሦስተኛ ምርጫዋን መረጠች እና መጠጣት ጀመረች።

ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ኒኪን ባር ማኑ ቀሰቀሳት እና “መኝታ ላስይዝልሽ፡፡ የእኔ እመቤት” ብሎ ጠየቃት፡፡
“ችግር የለውም እኔ አስይዛታለሁ።” ብሎ ከጎኗ ከሚገኘው ወንበር ወደ እሷ ጠረጴዛ ተሻገረ እና ለባር ማኑ ክሬዲት ካርዱን እየሰጠው “ደብል ስፔራሶ እና አንድ ብርጭቆ በረዶ የሌለው ውሃ አቅርብላት” አለው፡፡

“እሺ ጌታዬ” ብሎ ባርማኑ ከአጠገባቸው ሄደ እና ብቻቸውን ቀሩ፡፡

ኒኪም ከፊት ለፊቷ የተቀመጠው ሰው ፊት ሁለት እየሆነ ስላስቸገራት እና ጉድማንን እና ዴሪክን መለየት አቅቷት በጣቷ ደረቱን እየመታች አንተ ዴሪክ አይደለህም አይደል?” “አዎን አደለሁም” አላት፡፡

“ዴሪክ እኮ አልመጣም:: ቀጠሮ ይዘን ነበር። አንተ ለምን መጣህ?አሁንም ትከታተለኛለህ ማለት ነው?” ብላ በስካር አንደበት ተናገረችው::

ኒኪ ነቅተሽ አዳምጪኝ” አላት፡፡

ይሄኔም ያዘዘው ኤስፔሪሶ መጣለት።

ኒኪም ትኩሱን ኤስፔሪሶ አንስታ
ቶሎ ቶሎ ጠጥታ ጨረሰች:: እና በትንሹ ነቃች፡፡

ሚኪ ነቃ ብለሽ አዳምጪኝ፡፡ መጥፎ ዜና አለኝ፡፡ ዴሪክ ዊሊያምስ ሞቷል። “አላት፡፡

“ምን? ዛሬ ማታ እኮ ሜሴጅ ተላልከን ነበር፡፡”

“መቼ?”

“አሁን ምሽቱን” ብላ ኒኪ የሞባይል ሰዓቷን አይታም “ከሦስት ሰዓት
👍2
በፊት ነው።”

ጉድማን ስልኳን ተቀበላት እና የተላላኩትን ሜሴጅ አይቶ እየመለሰላት
“አዎን ላንቺ ሜሴጁን ከላከ በኋላ ነው አፓርታማው ውስጥ የተገደለው።
አንድ ጊዜ ግምባሩን፣ ሁለት ጊዜ ደግሞ ደረቱን በጥይት ተመትቶ ነው ህይወቱ ያለፈው:: ሽጉጡ ላይ ሳይለንሰር ተገጥሞለት ስለነበር የሽጉጡን
ድምፅ ጎረቤቶቹ አልሰሙም::” አላት።
ኒኪ ከዚያ በኋላ የጉድማን ከንፈር ሲንቀሳቀስ ታያለች እንጂ የሚያወራው ነገር አይሰማትም: “ምስኪን ዴሪክ በጣም ጥሩ ሰው ነበር እኮ፡፡ በቃ ለእኔ እውነትን ለማውጣት ብሎ ነው እኮ ህይወቱን ያጣው” እያለች ቡዝዝ ብላ ብርጭቆው ላይ የሚንሳፈፈውን ሎሚ መመልከቷን ቀጠለች::

ጉድማንም ትከሻዋን ይዞ እየነቀነቀ ሚክ እባክሽን ዴሪክ ምን ሊነግርሽ ነበር የቀጠረሽ?” አላት፡፡ ስለ ሌንካ ነበር ሊነግረኝ የነበረው::” አለችው፡፡

“ስለ ባልሽ ውሽማ? ስለ እርግዝናዋ ነበር ሊነግርሽ የነበረው?”

ኒኪም የግርምት ፊት እያሳየችው “ታውቅ ነበር ማለት ነው?”

“አዎን ጆንሰን ነው መረጃውን ያገኘው፡፡ ግን ለምን ደበቅሺን?”

“አልደበቅኳችሁም ግን በቃ መናገር አልፈለግኩም:: ደግሞም ሁሉ
ነገሬን ለእናንተ የግድ መናገር አለብኝ እንዴ?” አለችው ተኮሳትራ::

“እንደሱ ማለቴ አይደለም። ነገር ግን ምናልባት ግድያዎቹ ከእሱ አደጋ
ጋር ሊገናኙ ስለሚችሉ ነው::” አላት፡፡

ኒኪም ትከሻዋን ሰብቃ ዝም አለችው::

ጉድማን በጣም ትዕግስት ባጣ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እየተመለከታት
“ዴሪክም አንቺም የጉዞ ሻንጣ ይዛችኋል፡፡ ከተገናኛችሁ በኋላ ወዴች ልትሄዱ ነበር?” ብሎ ጠየቃት፡፡

“አንድ ላይ አይደለም የምንሄደው። ከተገናኘን እና ካወራን በኋላ ተለያይተን ለመሄድ ነበር ዕቅዳችን፡ ዴሪክ እኛ እዚህ ከቆየን ኣደን እንደሚገጥመን ጭምር ነው ያስጠነቀቀኝ እና ከዚህ መሸሽ እንደሚኖርብን ነበር ያስጠነቀቀኝ። ግን ምን ያደርጋል አሁን ዴሪክ የፈራው ደርሶበታል”

“ከማን ነበር የምትሸሹት? ሥም እፈልጋለሁ። ንገሪኝ” አላት እየጮኸባት፡፡

ኒኪ ግን መልስ ከመመለስ ይልቅ ዝም ስላለቺው ጉድማን ከንፈሯን
በሀይል ሳማት። እሷ ግን በድን ሆና ምንም የመሳም ምላሽ አልሰጠችውም።
የዴሪክ ዊሊያምስ ሞት ይህንን ስሜቷን አጥፍቶባታል። ከዚያ በኋላ ኒክ ስለ
ሮድሪጌዝ፣ ስለ ማዘጋጃ ቤት ሙሰኞች፣ ስለ ዊሊ ባደን እና ስለ የተለያዩ
ባንኮች የአደንዛዥ ዕፁን ገንዘብ የማስተላለፍ ሁኔታን ጭምር ልክ ዴሪክ
ዊሊያምስ ፅንስ ሀሳቡን በገለፀላት መልኩ ገለፀችለት።

ጉድማንም የተለያየ ጥያቄን ሲጠይቃት ቆይቶ በቂ ነው የሚለውን መልስ ካገኘ በኋላ ሻንጣዋን በእጁ ይዞ ተነሳ፡፡

“እኔ ነኝ ቤት የምወስድሽ፡፡” አላት፡፡
“ቤት መሄድ አልችልም አደጋ ሊኖረው ይችላል” አለችው፡፡
እሱም “ያንቺ ቤት ሳይሆን የእኔ ቤት ነው የምወስድሽ” አላት።
ኒኪም ከእሱ ጋር ህይወት መስርታ ብትኖር ምን አይነት ድንቅ ነገር
ሊሆንላት እንደሚችል በአዕምሮዋ ሳለች። ማለትም ሲንከባከባት እና ከማንም
ሰላይ መከታ ሲሆናት በውስጧ ስትስል ቆይታ ነገሩ ሊሆን እንደማይችል
ገባት::
ከተቀመጠችበት ተንስታም ከንፈሩን በስሜት ከሳመችው በኋላ “በጣም
ጣፋጭ ስው ነህ፡፡ ግን ከአንተ ጋር አብረን ልንሆን አንችልም::”

“ለምን?”

“ምክንያቱም ልቤን ለዶውግ ሙሉ በሙሉ ሰጥቼው ነበር፡፡ እሱ ግን
እንዳይመለስ አድርጎ ልቤን ሰብሮታል።” ብላው ሻንጣዋን ተቀብላው ከሆቴሉ
ወጣች::

ይቀጥላል
👍2
አትሮኖስ pinned «#የፍቅር_ሰመመን ፡ ፡ #ክፍል_አርባ_ስድስት ፡ ፡ #ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን ፡ ፡ #ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው ...ከኮሪያውያን የፍል ውሃ ቦታ ወጡ እና ወደ ሱሺ ባራቸው አመሩ፡፡ ሱሺ ባር ውስጥም ተቀምጠው እየበሉ እያሉ ግሬቸን “ይህንን ቀጠርኩት ያልሺውን የግል መርማሪሽን ከየት ነው ያገኘሽው?” ብላ ኒኪን ጠየቀቻት፡፡ ኒኪም “ከጎግል ላይ ነው:: ስለ እሱም በደንብ አድርጌ ካነበብኩኝ በኋላ ነው…»
#የወድያነሽ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


አንዳንድ ቀን አካባቢውን መልከትከት ብዩ ሰው ያለመኖሩን አረጋግጥና ሥጋዊ ስሜቷን ለመቀስቀስ የሚችለውን የአካላቷን ክፍል ከፍ ወይም ዝቅ ብዬ
መደባበስና መጎነታተል አዘወተርኩ፡፡ ከወደ ውስጥ እየጋፈረ የሚያጠልማት
የኃፍረቷ ጎርፍ አፏን አፍና የሣቋን ግፊት እንድታምቅ ያስገድዳታል። ፊቷን
ሽፍና መሽኮርመምና ሰብሰብ ብላ መቀመጥ የዘወትር ልማዷ ነበር፡፡ እንደ ዘበት ሽብ ያደረገችውን ሻሿን ድንገት ስቤ እይዝና ያንን ውብ ኑግ መሳይ ጸጉር
በታትኖ ማየት ወደ እርሷ ከሚስቡኝ ሁኔታዎች ሁሉ የበላይነትን ያዘ፡፡

እንድ ቀን እንደ ልማዴ የጊዜና የአካባቢውን ሁኔታ ተመልክቼ እጅዋን
እያልመዘሙዝኩ አፌን ለወሬ ሾል ሾል ሳደርግ “ዋ" እለችኝና ዐይኔን እያየች
እናትዎ ያዩዎትና አጉል ቅሊት ይቀልላሉ፡ የኔ እንደሁ ዕውቅ ነው፡ ያው ሂጂ
ውጪ ከቤቴ ብለው ማባረር ነው» ብላ የተሰደሩ ጥርሶቿን ፈልቅቃ አስጐበኘችኝ፡፡ ለወጉ ያህል ጥቂት ተላፋን፡፡ ልባችን ተቀራርቦ ስሜታችን ይበልጥ ተዋሐደ፡፡ በፍቅራዊ ስሜት ለሚከታተሏት ዐይኖቼ የምትሰጠው ምላሽ አርኪ በመሆኑ የፍቅራችን ጋቢ ዐርቡ እየሰፋ ሒደ፡፡

እሑድ ጠዋት ነበር። ወላጆቼ የውብነሽን አስከትለው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደዋል፡፡ እናቴ ስለ እኔ ወደ ቤተ ክርስቲያን ያለመሔድ ስትናገር
«የሱን ነገር ተዉኝ! የእናንተ ጸሎት ለሁላችንም ይበቃል” ይላል። አይጣል
እቴ! ይኸስ የጤናም አይደል» ትላለች፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የምታቀርበውን
ነቀፌታ ከጉዳይም አልቆጥረው:: ተኝቼ አረፈድኩ፡፡ ጋቢ ለብሼ የመኝታ ቤቴን
በር ስከፍት የወዲያነሽ አረንጓዴ የውስጥ ልብስ ብቻ ለብሳ እንግዳ መቀበያ
ክፍል ውስጥ መወልወያ ጨርቅ ይዛ ቆማለች፡፡ ጸጉሯ በተንተን ብሉ በአንገቷ
ዙሪያ ተሽመልምሉ ይዘናከታል፡፡

የአካላቷ ሙላት የመጨረሻውን ደረጃ ይዟል። ያ ከዓመት በፊት በርኅራኄና በአኗኗሯ በዐዘኔታ ላይ ተመሥርቶ የነበረው ስሜቴ ፍጹም ተለውጦ
አሁን ወደ ልዩ ሥጋዊ ውዴታ አጋድሏል፡፡ ዛሬ በተለይ በልቤ ውስጥ የጉርምስና
ደም ተንሽከሽከ፡፡

በትዕዛዛዊ አቀራረብ ሳይሆን ልዩ የመቀራረብን ስሜት ለማብሠር
በምታስችል ለስላሳ ድምፅ "ነይ እስኪ የወዲያነሽ?» ብዬ ጠራኋትና አልጋው
ጫፍ ላይ ተቀመጥኩ። የመስታወት መወልወያዋን እንደ ያዘች በአለባበሷ አፍራ መዝጊያው አጠገብ ቆመች። ስልክክ ባለው ጠይም ፊቷ ላይ ወርዶ ከጉንጫ ላይ ሲደርስ የሚርመሰመሰው የወጣትነት ሙሉ ደም ግባቷ የምሆነውን አሳጣኝ፡፡

«ግቢ እንጂ ምን ያስፈራሻል?» ብዩ ለማግባባት ሞከርኩ። ዐፈር ከድቷት እንደ ዘመመች የድሃ ጎጆ አንገቷን ወደ ግራ ጎን ሰበር አድርጋ ቆመች።

እንደገና ነይ እንጂ ግቢ የወዲያነሽ» ብዩ አባበልኳት። ውስጥ ውስጡን የበላይዋና አዛዥ መሆኔ ስለ ተሰማት በፍርሃት እየተናጠች ገባች፡፡ በሩን ዘጋሁት። ደነገጠች። የፈገግታዋ ንጋት ቀስ በቀስ ጠለሰ። እንደሚንበረከክ ተማሪ ጉልበቷን ሰበር አድርጋ ወለሉ ላይ ተቀመጠች፡፡ እኔም ስለ ወለሉ ላይ ትቢያ ምንም ሳልጨነቅ ከፊት ለፊቷ ቁጭ አልኩ፡፡ በስሜት ተቁነጠነጥኩ፡፡ ቤቱና በቤት ውስጥ ያለው ዕቃ ሁሉ «መጡብህ! ደረሱብህ! የሚሉኝ ስለ መሰለኝ ዐይኖቼ ቃበዙ፡፡ ድንገት ብድግ ብዬ «ተነሽ» አልኳት፡፡ አነጋገሬ ቁጣ ቅልቅል በመምሰሉ ወዲያው ተነሣች። ልፊያ ቢጤ ለመጀመር በማሰቤ ሽንጧ ላይ ነካኋት። ተሸማቀቀች። ታዲያ ምን ያደርጋል፡ ምን እንደምፈልግና እንደማደርግ መላ ቅጡ ጠፋኝ፡ መላ አካላቴ ብው ብሎ ጋለና ፍርሃቴን ገፈፈው፡፡ የለበስኩት ጋቢ ተንሸራትቶ እግሬ ሥር ወደቀና በእግራችን ረጋገጥነው። እጆቼን ባንገቷ ዙሪያ ጠምጥሜ በልዩ ደስታ እምነሽነሽ ስለ ነበር የወደቀውን ጋቢ ቁብም አላልኩት። ድንገት አፈትልካ ለመሄድ ሞከረች::
አልተሳካላትም፡፡ ፊቷን ወደ ተዘጋው በር አዙራ ተቀመጠች፡፡ ከበስተጀርባዋ ቆሜ
ጎንበስ አልኩና እጄን በትከሻዋ አኳያ ወደፊት ቁልቁል ሰደድኩት። እንደገና
ከፊት ለፊቷ ዞሬ ተንበረከከሁ፡፡

ሳትወድ በግድ በአገጯ ወደ ላይ ይዤ ፊቷን አየሁት። እንባዋ ይጎርፋል፡፡ በእጄ ስቢያት ተነሣሁ፡፡ «እኔ እኮ የቀልዴን ነው:: ደስ ይልሽ እንደሆን ብዩ ነው እንጂ ደስ የማይልሽ ከሆነማ ከዛሬ ጀምሮ ከደረስሽበትም አልደርስ እ! » ብዬ እጆቿን እንደ ያዝኩ ዝምታዬን ተጎናፀፍኩ። ለማስመሰል እንጂ ከልቤ አልነበረም፡፡ ተፋጠጥን፡፡ ዐይኖቼ ቦዙ። ዘንጉን በዳበሳ እንደሚፈልግ ዐይነ ሥውር እጆቿን ዘርግታ አንገቴ ላይ ተጠመጠመች፡፡ ደረቴ ላይ ተለጥፋ አገጬ ስር ከቀረቀረች፡፡ የፊቷ ትኩሳትና የደረቷ ሙቀት ሲገናኙ ኃይለኛ ነዛሪ
የርካታ ማዕበል አጥለቀለቀኝ፡፡ የተስተካከለ ንዝረት ግን አልነበረም፡፡ ደረቴ ላይ እንደ ተለከፈች በጉንጯ ላይ እያቋረጠ የሚወርደው እንባዋ ስሷን ልብሴን አረጠባት። አዲስ ሰመመናዊ ቆይታ ተጀመረ፡፡ ከከንዲት ሥር ላይ የበቀሉ መንታ መቃዎች መስልን። ፀጥ እና ቀጥ በማለታችን እካባቢውን ጸጥታ
ሰፈነበት።

ግድግዳው ላይ የተንጠለጠለው ገደ ቢስ ሰዓት ጥበባዊ ተግባሩን ለመፈጸም ደወለ፡፡ እኔና እርሷም በዚያቹ ቅፅበት ከሰመመናችን ባነንን፡፡ ከራሷ ቀና ብላ በእንባ የተከበቡ ዐይኖቿን እና ፊቷን አሳየችኝ::

የስሜቷ ዶፍ ተፍ እለ። በሰውነቴ ውስጥ ያለው ኃይል ተንጠፍጥፎ ያለቀ ይመስል እጆቼ ዛሉ፡፡ ቀስ በቀስ አየት ሳደርጋት ወለሉ ላይ የወደቀውን ጨርቅ ይዛ በዝግታ ወጥታ ሒደች:: ዐይኖቼ አብረዋት ተጓዙ፡፡ እኔም ወለሉ ላይ
ወድቆ ባቧራ የተልሞሰሞሰውን ጋቢ አራግፌ ወደ አልጋው ግርጌ ወረወርኩት።አልጋዩ ላይ ወጥቼ በጀርባዬ ተንጋለልኩ:: ተንጠራራሁ፡ አፋሸግሁ፥ እግሮቼን እያኮራመትኩ ዘረጋሁ። ጥልቅ ፍቅር በውስጤ ተፍለቀለቀች፡፡ የአልጋው ሽቦዎች እስኪያንሲያጢጡ ድረስ ተወራጨሁ፡፡ እንደገና ቀና ብዬ አልጋው መኻል ተቀመጥኩ፡፡በስተራስጌ በኩል በምስማር ላይ የተንጠለጠለውን ኮቴን ተንጠራርቼ አወረድኩና ከልብሲ ጋር የከረረ ጠብ ያለኝ ይመስል አሽቀንጥሪ ግድግዳው ላይ አላተምኩት፡፡ ከአልጋው ላይ እመር ብዩ ወርጄ የወዲያነሽ አጥባና ተኩሳ ያስቀመጠችልኝን ሱሪ ከሻንጣ አወጣሁ፡፡ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጬ እግሮቼን ባንድ ጊዜ ቁልቁል በሱሪው አቆልቋይ ሰደድኳቸውና ቀጥ ብዩ ቆምኩ፡፡ በዙሪያዩ ያለው ነገር ሁሉ አዲስና እንግዳ ነገር መስሎ ታየኝ፡፡ ሰማያዊ ሸሚዝ ለብሼና ግራጫ ኮት ደርቤ ጸጉሬን ሳላስጥርና ያደረ ፊቴን ውሃ ሳላስነካ መሰስ አልኩ፡፡ወዴት እንደምሒድ አልወሰንኩም፡፡

ደረጃውን ወርጀ ግቢው መኻል ደረስኩ፡፡ የወዲያነሽ የሚያምር ቢጫ ቀሚስ ለብሳና ዐመድማ ሻሽ አስራ ማድ ቤቱ በራፍ አጠገብ ቆማ አየኋት፡፡በግራ እጅዋ አንድ ንጹሕ ነጭ ጭልፋ ይዛ ነበር፡፡ በዚያ ሰምቼ በማልጠግበው ድምጿ «እጅዎን ላስታጥብዎት መምጣቴ ነበር፥ ቁርስ አዘጋጅቻለሁ ቆዩ አትሒዱ» አለችኝ፡፡ በአድራጐቴ ሁሉ እንዳልተቀየመችና ቅር እንዳላላት በማወቄ ልቤ በደስታ እንደ ፈረሰኛ ጎርፍ ሽቅብ ዘለለች። ላሳየችኝ ብሩህ ገጽ የተከማቸ ፈገግታ ላኩና «ተመልሼ እመጣለሁ አዘጋጅተሽ ጠብቂኝ» ብያት ወጣሁ። የትምዋልኩ እንጂ እንዳባባሌ አልተመለስኩም፡፡

ቤተሰቡ በሞላ ስለ ሁለታችን የስሜት ቁርኝት የሚያቀው አንዳችም ነገር
አልነበረም፡፡ የአባቴ የዕረፍት ሰዓታት ሃይማኖት ነክ መጻሕፍትን ለማንበብና
ያንኑ የሕግ መጽሐፉን በመነዝነዝ ላይ ስለተመደቡ ለሌላ ጉዳይ የሚውል ጊዜ
አልነበረውም፡፡ እናቴም የተማረ ሰው፣ ዐዋቂ ነው እያለች በጣም ስለምትመጣብኝዐበእርሷ እምነትና ልማድ ከ«ገረድ» ጋር ይህን መሰለን ግን
👍3
ኙነት ይፈጽማል ብላ አልጠረጠረችም፡፡ ከሁሉም በላይ የጠቀመኝና ከመሳቀቅም ያዳነኝ ግን፣
«በማንኛውም ጊዜ ቢሆን ቤተሰቦቼ ባሉበት አካባቢ ሁሉ እንኳንስ ፈገግ ማለትና ቀና ብለሽ እንዳታይኝ» ብዬ መክሬያት ስለ ነበር ቃሌን አክብራ በፈቃደኝነቷ መዝለቋ ነበር፡፡

ጊዜው እየጨመረ በሄደ ቁጥር የሁለታችን ፅኑ ፍቅራዊ ግንኙነት እየሰፋ
መጐልመሱን ቀጠለ፡፡ ሰው ከሌለና ቤተሰቦቼ ራቅ ወዳለ ሥፍራ መሄዳቸው
ከተረጋገጠ መኝታ ቤት ድረስ ቀጥ ብላ ትመጣና ያለ አንዳች ፍርሃት ተጫውታ
መሄድን ተላመደችው:: አበባና ንብ ሆንን። ተጣጣምን፡፡ በልቤ ውስጥ የፍቅር
እውነተኛ ቡቃያ በቀለ፡፡ የቡቃያውም የሕይወት መስኖ የሚፈልቀው ከየወዲያነሽ የፍቅር ምንጭ ሆነ፡፡

አንድ ነገር በማበላሸቷም ይሆን ወይም በመስበሯ እናቴ ስትቆጣትና ግልፍ ብሏት ስትገሥጻት በማይና በምሰንበት ጊዜ ሁሉ ግልጽ ባልሆነ የአነጋገር ዘዴ እየተጠቀምኩ የውክልና ያህል ጥብቅና እቆምላት ጀመር።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የዕለቷ ፀሐይ የምዕራቡን አድማስ ነክታለች፡፡ አካባቢያችን በጨለማ
መጋረጃ ሊጋረድ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ቀርተዋል፡፡ አትክልቱ ውስት በመዘዋወር ላይ እንዳለሁ ከመጠያየም ዐልፎ ለከይን ያዘ፡፡ ያው ምክንያት ሆኖ ወደ ቤት ገብቼ መስኮት አጠገብ እንደ ተቀመጥኩ የምሽቱ ከዋከብት ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። ከዋክብቱም፣ ትልቁ በትልቅነቱ ሲንቦለቦል፣ ትንሿም በዚያ በመጠኗ ትንተገተጋለች፡፡ ከወደ ሰሜን ፈጣንና ቀዝቃዛ ንፋስ እየተዥጎደጎደ ይነፍሳል። የተመሳሳዮቹ ዛፎች ቅርንጫፎች እርስ በእርሳቸው እየተሻሹ የትርምስ ልፊያ ይዘዋል። መታደል ነው። እነርሱ ዘንድ ፍርሃት ይሉኝታ የለ! ንፋሱ ለዘብ
ጠንከር እያለ ስለሚነፍስ ጸጥታና ውካታ ትንቅንቅ የገጠሙ መሰለ። ከሩቅ
ከቅርብ የሚታዩት ዛፎች በጨለማ ጥልቅ ውቅያኖስ ተወጠው እንደ ወራቢ
ይወዛወዛሉ።

በጨለማው ውስጥ የሚንዠቀዥቀው የከዋክብት ብርሃን በዕፅዋቱ መጠንና ቅርፅ ላይ ልዩ ኅብራዊ ትርኢት ሥሏል፡፡ ስሜቴ ስለ ተመሰቃቀለ ተንቆራጠጥኩ። ከመኝታ ቤት ወጥቼ እንግዳ መቀበያ ክፍል ገባሁ፡፡

የወዲያነሽና የውብነሽ ራት ለማቅረብ ተፍ ተፍ ይላሉ፡፡ የወዲያነሽ የእህቴን የአረማመድና አንዳንድ የሁኔታ ቄንጦች በመጠኑ አስተውላ በመቅሰሟ
ማራኪነቷ በጣም ጎላ፡፡ ከራት በኋላ እንደገና ተመልሼ መኝታ ቤት ገባሁ።
ከያዝኩት መጽሐፍ ላይ ገና አምስት ገጽ ያህል እንዳነበብኩ በሩ በዝግታ
ተከፈተ። የወዲያነሽ በእርጋታ ከገባች በኋላ ከትራስጌዬ አጠገብ ሁለት ነጫጭ
ጠርሙሶች ይዛ ወጣች፡፡ ደረጃዎቹን ወርዳ ስትጨርስ በመስኮቱ በኩል ብቅ ብዩ አየኋት። በሦስት ትልቅ ኮባዎች ከተከበበው ውሃ አጠገብ እንደ ደረሰች ጐንበስ ብላ አንዱን ጠርሙስ አስቀመጠችው::

የያዝኳትን 'የቀትር ጨለማ” እልባት አድርጌባት እንደ ዘበት ወጣሁ።
ከቤት ሲወጣ በመጀመሪያው ደረጃ ላይ ቆምኩ፡፡ ያሰብኩትን እንዳልፈጽምና
የፍላጐቴን ጥማት እንዳላረካ አንድ ነገር እክል ሆነብኝ፡፡

ማታ ማታ ደረጃ ስንወርድና ስንወጣ አልታየን አለ» ተብሎ ከሦስት ወር በፊት የተተከለው መብራት ግቢውን ወገግ ያለ ብርሃን ሰጥቶታል።

ደግነቱ የብርሃኑ ውጋገን ከሰሜን ምዕራብ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ብቻ ይዘልቅና ከዚያ ወዲያ ያለውን ቦታ ጨለማ ያሶመስምበታል፡፡ ዕንጨት ላይ
የተመታችውን ማብሪያ - ማጥፊያ ሦስት ጊዜ አንቀቅጬ አንተገተግኋት፡፡

የተንጠለጠለችው መብራት በዕረተ ሞገድ የተነካካች ይመስል እንደ
ውድቅት እሳት ራቅ ቦግ እልም፣ ቦግ እልም አለች። ተፈጥሮም ድጋፍ እንድትሰጥ የታደመች ይመስል ኃይለኛና ፈጣን ነፍስ ባናት ባናቱ ነፈሰ፡፡ ይህም መብራቲቱ ተቃጥላ ወደመች ለማለት ከእኔው ሽር ጋር የሚሰምር ምክንያት ሆነ።

ደረጃውን ገመሬ እንደ ለቀቀው ናዴ ተንደርድሬ ወረድኩት።የአወራረዱ ፍጥነት ስሕተት ነበር፡፡ ከዚያም በጣም ዝግ እያልኩና በጢሻ ውስጥ እያደባ እንደሚሽሎከሎክ አዳኝ እየተራመድኩ ከትልቁ ኮባ ጀርባ ቆምኩ።

ትንፋሼን ውጬ እያሰላሁ ከተጠጋሁ በኋላ ከበስተኋላዋ ዐይኖቿን
በጣቶቼ ሽፈንኳቸው። ባልተጠነቀቀው አካሏ ላይ ያረፉት ጣቶቼ ድንገተኛ
ድንጋጤ ፈጠሩባት፡፡

በቀጭን የድንጋጤ ድምዕ «ዋይ» ብላ ጮኸችና እኔ መሆኔን እንዳታውቅብኝ ድምፄን አጎርንኜ «ማን ነኝ? እስኪ ዕወቂኝ?» ብዬ ጠየቅኋት።

ምንም ቢሆን የውጪ ሰው አይሆንም በማለት ተረጋጋች፡፡ ሁለቱንም በውሃ የሞሉ ጠርሙሶች በአንድ እጅዋ ከሆድዋ ላይ ኣጣብቃ ከያዘች በኋላ የውሃ
ፍንጥቅጣቂ ባለባቸው የቀኝ እጅ ጣቶቿ የቀኝ ክንዴንና ጣቶቼን ዳበሰቻቸው።
የማወቂያ ምልክትና ዘዴ አጣች፡፡ እጅዋ ሌላውን እጄን ፍለጋ ሄደ። ግራ እጄን
ያዘችው:: ሰዓቴን አገኘቻት፡፡ በደስታ የተሽሞነሞነ ሣቅና ትንፋሽ አደባልቃ
ለቀቀች፡፡ «አሁንስ ዐውቄዎታለሁ፤ እርስዎ ነዎት» ብላ በረጅሙ ተነፈሰች።
ለቀቅኋት። ጠርሙሶቹን እግሯ ሥር ስታስቀምጥ እንደኛዋ ጠርሙስ ተከነበለች።

የወዲያነሽ በዚያች ሰዓት የሾመችው ጋን ቢተረተርም ግድ የላትም ነበር። ፊት ለፊቴ ቆመች፡፡ ውጋገን ያረፈበት የሚመስለው ጠይም ፊቷ የጨለማው ጥቁረት ይታገለዋል፡፡ የጨለማው ውስጥ ውበቷ እንጎሌ ውስጥ ተርከፈከፈ፡፡ የተጠሙት ዐይኖቼ በመመልከቻ ዋንጫቸው እየደነበቁ ጠጧት። ግን ቀመሱ እንጂ አልጠገቡምና ቦግ ብለው ተከፈቱ፡፡ በቀኝ እጅዋ እየሳብኩ ወደ ጓሮ ይዣት ዞርኩ፡፡ ማታ ማታ የትልቁ ቤት ጥላና የየዛፎቹ ውስብስብ ቅርንጫፎች የምድረ ግቢውን ደቡባዊ ክፍልና አካባቢውን ለየት ያለ ድፍርስ ጨለማው ይጥለብታል።

ተስካር ለመብላት እንደሚገሰግሱ ዲያቆናት ተመራርተን በስተደቡብ
በሚገኘው የግንብ አጥር ደረስን፡፡ በእኔና በእርሷ ሕሊና ውስጥ ሲፍለክለክ የቆየው
የፍቅር ስውር ኣካል ተጨባጭ ሕይወት ሆኖ ተከሠተ፡፡

እጆቼ አንገቷ ላይ ሲጠመጠሙ እጆቿ በወገቤ ዙሪያ እንደ ዝናር ዞሩ፡፡
" እንዲያ ሲሳብና ሲዥጎደጎድ የቆየው ነፋስ አቅጣጫውን ያስለወጡት ይመስል
ደብዛው ጠፋ፡፡ እንዲያውም አልአፍ የምትመጣ ደካማ ትንፋሽ መሰለ፡፡
በአቅራቢያችን ያለችው ኮካ ለጋ ቅርንጫፎች ደፋ ቀና እያሉ እርስ በእርሳቸው እየተሳሳሙ ይበተናሉ፡፡ ጉንጯ ላይ ሳም ሳደርጋት የፍቅር ደማቅ ችቦ ተለኮሰ አፌን ወደጎን አንሸራትቼ የከንፈሮቼን ነዲድ ከከንፎሮቿ አርኪ ገለት
በማጋጠም ምጣድና ክንባሉ ሆንን፡፡
በሕሊናችንም ውስጥ ያ የፍቅር ችቦ ፏ
ብሉ ሲቀጣጠል ታየኝ።

💫ይቀጥላል💫
👍4
#እንግዳ

በበጋ ወቅት ዝናብ በድንገት ቢመጣ፣
በሃምሌው ጉም መሃል ፀሃይዋ ብትወጣ
በቁርና በውርጭ ሃሩሩ ቢያስጨንቅ፣
በብርድ ቢጨበጡ በሃይለኛው ወበቅ፣
ድንገት ከተፍ ቢል ሁሉም ሳይጠበቅ፣
እንግዳ ይባላል ያለ ወቅቱ መጥቶ፣
አንድም ቀደም ብሎ አለያም ዘግይቶ፡፡
ታዲያ ዛሬ ዛሬ

ልብን ልብ ሲነሳ ቀልብ ሲያስት የኖረው፣
የህልም አለሙ እንጀራ የማይጠገበው፣
የአንጀት አንጀተኛ ስለት የማይለየው
በልብ ውስጥ ተቀብሮ በድብቁ ጓዳ፣
በድንገት ሲከሰት ልክ እንደ ዱብ ዕዳ፣
የተፈታ ህልም እንጂ ማን ሊለው እንግዳ፡፡


🔘ሻለቃ ወይን ሐረገ በቀለ🔘
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ_ሰባት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው


....አኔ ቤታማን እምባዋ እና የሚዘንበው ዝናብ መንገዱን እየጋረደባት መኪናዋን በደንብ እንዳታሽከረክር እያደረጋት ነው:: ግንቦት ላይ ሎስ አንጀለስ ውስጥ አይዘንብም ነበር፡፡ ግን የእሷን ስሜት ለማጀብ በሚመስል መልኩ ሰማዩም አብሯት እዬዬ እያለ ነው። አሁን እሷ ሰው ነው የሚያስፈልጋት። ውስጧ በጣም ሀዘን እና ተስፋ መቁረጥ እንደተሞላባት
ነው:: ስለዚህም ኒኪ ታስፈልጋታለች። ኒኪ የምትሰጣት አድናቆትን እና
ይቅርታን ለምዳዋለች። ልክ ሉዊስ ባሏ ያደርግላት የነበረውን ነገር ነው ኒኪ
የምታደርግላት እና ወደ ኒኪ መሄድ ይኖርባታል።

ዛሬ ማታ ነው እንግዲህ ለኒኪ ስትነግራት የነበረውን፣ ሉዊስ አይተወኝም የምትለው ነገር የተገላቢጦሽ መሆኑ የታወቃት። ባለፈው ማታ ሉዊስ ከፕሮግራሙ ላይ ሲቀር ነበር ከእሱ ጋር ያላት ግንኙነትን ማብቃት እንዳለበት ውሳኔ ላይ መድረስ የሚኖርባት።

አኔ የኒኪ ቤት ስትደርስ ዝናቡ ሀይሉን ቢቀንስም የመኪናው ጣራ ላይ
የሚያርፈው የዝናቡ ድምፅ ግን ይሰማታል። ከመኪናዋ ወርዳ የኒኪን ግቢ
ስትመለከት መኪናዋን ግቢ ውስጥ ስላገኘችው ኒኪ ቤት እንዳለች ለማወቅ
ቻለች:: ዝናቡ የእንጨት በሩን ስላረጠበው ነው መሰል በቀላሉ ቀጫጭን ጣቶቿን አሾልካ በሩን ከፈተችና ወደ ውስጥ ገባች፡፡

የኒኪ ቤት ሙሉ በሙሉ በጭለማ ተውጧል። ስለዚህም ኒኪ ተኝታ
ሊሆን ይችላል ብላ አስባ እንዳትረብሻት ብላ ልትመለስ ስትል ውስጧ እዚህ
ድረስ መጥተሻል እና ኒኪን ሳታገኚያት መመለስ የለብሽም አላት፡፡

በሩን ልታንኳኳ ስትል ግን ሀይለኛ የለቅሶ ድምፅ ሰማች፡፡ ድምፁ የሚመጣው ከጓሮ በኩል ስለሆነም አኔ እንዳትወድቅ ተጠንቅቃ በአጥሩ እና በቤቱ መሀል ባለው ክፍት ቦታ ወደ ጓሮ አመራች::

አየቻት፡፡ ወደ ኒኪ እየቀረበች ስትሄድም ኒኪ አይኗን ጨፍና እና ትንሽ
ጓሮው ጋር ስትደርስም ኒኪ ከአንድ ጃካራንዳ ዛፍ ሥር ተንበርክካ አየቻት። ወደ ኒኪ እየቀረበች ስትሄድም ኒኪ አይኗን ጨፍና እና ትንሽ ሽጉጥ ከጉሮሮዋ በኩል ወደ ላይ እንደ ደቀነች ተመለከተች እና በጣም ደነገጠች፡፡

ኒኪ እኔ ነኝ አኔ ነኝ!” ብላ ከዝናቡ ድምፅ በላይ በመጮህ ወደ ኒኪ እየሮጠች ሄደች፡፡ ኒኪም ድምፁን ሰምታ አይኗን ስትገልጥ አኔን በዝናቡ በስብሳ አጠገቧ ቆማ አየቻት፡፡

ለጥቂት ሰከንዶች ያህል ሁለቱ ዝም ብለው ሲተያዩ ከቆዩ በኋላም ኒኪ
ነይ ወደ ውስጥ ግቢ እና በዝናብ የበሰበሰውን ልብስሽን ቀይሪ” ብላት ይዛት ወደ ቤቱ ውስጥ ገባች፡፡

ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ ኒኪ ብርድ ልብስ ለብሳ ሶፋ ላይ እንደ ህፃን ለጥ ብላለች፡፡ ዶውግ እና እሷ ልጅ ነበር ይፈልጉ የነበሩት። በመሆኑም ለመውለድ ያስችላት የነበረው ህክምና ሳይሳካለት ሲቀር ያለመውለድን እንደ ትልቅ ሀዘን ነበር የቆጠረችው፡፡ ግን በተደጋጋሚ ከደረሱባት ሀዘኖች በኋላ ትልቅ ሀዘን ምን ማለት እንደሆነ ገባት።

ምናልባት አኔ ባትመጣ ኖሮ ቃታውን ስቤ ራሴን አጠፋ ነበር? ብላ ራሷን ጠየቀች፡፡ ምናልባትም አኔ በእግዚአብሔር የተላከች መልአኳ ሆና ህይወቷን ታድጋዋለች፡፡

“ምናልባት አኔን የላከልኝ ከሞት ባሻገር የሚገኘው ዶውግ ባሌ ይሆን?'
የሚለው ሀሳብ ደግሞ ጥሩ ስሜትን ስለሰጣት ደስ አላት::

ዛሬ መሞት አትፈልግም። በፍፁም! ከዚህ በኋላ ብዙ የምታከናውናቸው ነገሮች ስላሏት ቢያንስ እነዚህን ነገሮች ካከናወነች በኋላ ምናልባት ሞቷን
ትፈልግ ይሆናል፡፡ አሁን ግን ቢያንስ ዴሪክ ያገኘውን እውነት እስክታውቅ ድረስ በህይወት መቆየት አለባት፡፡

ከኒኪ ቤት በትንሽ ርቀት ላይ ከቆመው መኪና ውስጥ የሚገኝ አንድ ሰው በጎግል መነጽሩ ወደ ኒኪ መኖሪያ ቤት ሲመለከት ቆየና መነፅሩን አውርዶ የመኪናው ዳሽ ቦርድ ላይ አስቀመጠው።

“በቅርቡ ሁሉ ነገር ይስተካከላል” ብሎም ለራሱ አጉረመረመ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጉድማን ከዳየርስ ሆቴል የጎጆ ቤት ማረፊያ ቁጭ ብሎ እያሰበ ይገኛል።
ወደዚህ የመጡት በዴሪክ ዊሊያምስ ሞት ግድያ ላይ የፎሬንሲክ ምርመራ
የሚያደርጉ ባለሙያዎችን ውጤት ለማወቅ ነው:: ባልደረባው ጉድማን ከሃያ
ደቂቃ በፊት የጠጣው ቡና ስላልተስማማው ለሦስተኛ ጊዜ ሽንት ቤት ገብቶ እያማጠ ነው:: ሌሊት 11 ሰዓት ላይ ኒኪ የላከችለትን ኢ ሜይል ስልኩን ከፍቶ በድጋሚ ማንበብ ጀመረ::

“ሌሊቱን በሙሉ ሳስብበት ነው ያደርኩት። አሁን ዴሪክ ዊሊያምስ በህይወት የለም። ይህንን ነገር ላንተ መንገር ሳይኖርብኝ አይቀርም፡፡ብራንዶን ግሮልሽ ትላንትና ማታ በጣም በከፍተኛ ፍርሃት እና ጭንቀት ውስጥ ሆኖ ደውሎልኝ ነበር። ስለ ግሮልሽ ዋሽቻለሁ፡፡ አዎን ብራንዶን
ግሮልሽን ከዚህ በፊት አውቀው ነበር፡፡ እሱ ከዚህ ግድያ ጋር ይያዝ አይያዝ
የማውቀው ነገር የለም” የሚል መልዕክቷ ይቀጥልና

“ምናልባት ዊሊያምስ ትክክል ከሆነና እሱ በሚገልፀው የአደንዛዥ ዕፅ
ቀለበት ውስጥ ፖሊሶች የሚገኙበት ከሆነ ጆንሰን እዚህ ነገር ውስጥ
እንደሚገኝበት አልጠራጠርም። ለምን ብትለኝ፣ እሱ የቀድሞ የፀረ አደንዛዥ
ዕፅ የፖሊስ ቡድን አባል ነበር፡፡ በዚያ ላይ ሲነየር ነው። ይህ የግድያ ወንጀል ምርመራ እንዲሰጠውም የጠየቀው እራሱ ነው:: የወንጀል ምርመራውንም ሆን ብሎ እያበላሽ እና ውንጀላውንም ወደ እኔ እያቀረበ ምርመራውን እርባና ቢስ እያደረገው ነው።”

እያለ ይቀጥላል። እርግጥ ነው በተለይ ከዊሊያምስ ሞት በኋላ የኒኪ የጭፍን ፍራቻ እና ግምት ቢጨምር አይፈረድባትም:: ስለ ጆንሰን ጉድማን
ምንም ሊያደርግ አይችልም፡፡ ምክንያቱም አብሮት የሚሰራ ባልደረባው ነው።

“ሎው ከጆንሰን ጋር እየሰራህ እስከሆነ ድረስ አደጋ ውስጥ ነህ፤ እና ራስህን ጠብቅ:: እንድትጎዳ አልፈልግም። እኔም ብሆን አደጋ ውስጥ ስላለሁ ላልተወሰነ ጊዜ ከማንኛውም የግንኙነት መስመር ውጪ ነኝ።

ኒኪ ሮበርትስ”

ይላል የላከችለት ኢ ሜይል፡፡

ለምን ያህል ጊዜ ከግንኙነት መስመር ውጪ እንደምትሆን ያለማወቁ
ጉድማንን አሳስቦታል፡፡ ኢ ሜይሏ ከደረሰው እና ካነበበው በኋላ ሁለት ጊዜ
ደውሎላታል፡፡ ኢ ሜይልም ልኮላታል ግን ስልኳ ዝግ ነበር፡፡ ጆንሰን ከመፀዳጃ ቤት ተመልሶ ቦርጫም ሆዱን እያሻሸ “ቡናው ውስጥ ምንድነው የጨመሩበት? መፀዳጃ ቤት ውስጥ እኮ ተቀምጬ ልክ በምጥ ልጅ እየወለድኩኝ ያህል ነበር የተሰማኝ” አለ፡፡
ጉድማንም አፍንጫውን እያራገበ “ምነው በጣም አብራራኸውሳ? አሁን ወደ ፎሬንሲክ መርማሪዎቹ አንሄድም?” አለው፡፡

“አንተ ዝግጁ ከሆንክ ምን ገዶኝ፡፡ መቼስ ፎሬንሲኮቹ አንድ ነገር ሳያገኙ አይቀሩም፡፡ ምክንያቱም ዊሊያምስ ቢያንስ ግማሽ የሎስ አንጀለስ ህዝብ
ጠላቱ ነው። እኔም ልገድለው ትንሽ ነበር የቀረኝ።” አለውና ተነስቶ ሲወጣ
ጉድማንም ተከተለው።

ከሎስ አንጀለስ ሃምሳ ማይል ርቀት ላይ በርሃው ውስጥ የሚገኘው የሲኞራ ማርቼስ የገጠር ሆቴል ቀለል ተደርጎ ነው የተሰራው፡፡ ምንም እንኳን ሆቴሉ በርሃ ላይ ቢሰራም የየክፍሎቹ ኮርኒስ ላይ ካለው ፋን በስተቀር ሌላ ኤየር ኮንዲሽነር አልተገጠመለትም፡፡ ያም ሆኖ የሆቴሉ ነጭ ግድግዳ እና በዙሪያው የተተከሉት የዘንባባ ዛፎች ሁሉንም የእንግዳ ማረፊያ
ክፍሎች ቀዘቅዝ ያደርጓቸዋል።

ኒኪ ወደዚህ የእንግዳ ማረፊያ የመጣችው ዊሊያምስ ከሎስ አንጀለስ ርቃ የማትታወቅበት ቦታ እንድትደበቅ ስለነገራት እና ለማረፍም ጭምር ነው::
የእንግዳ ማረፊያውን ያሳያት ዶውግ ነው። የተጋቡበትን አንደኛ ዓመት
ሲያከብሩ ነው እዚህ ይዟት የመጣው ትዝ ይላታል ቦታው
👍4
ላይ ስላመጣት በኩራት ተሞልቶ እና ወገቧን አቅፏት አይኗን በፍቅር እያየ “ስለዚህ ቦታ
ከሀብታም ጓደኛቹ ስምቶ የነገረኝ ሀዶን ነው። ቦታውን ወደሽዋል አይደል?”

“እጅግ በጣም” ብላው ነጠላ ጫማዋን ክፍሉ ውስጥ ወርውራ እንደ ህፃን
እየቦረቀች ወደ መታጠቢያ ቤት የገባችበትን ሁኔታ አስታወሰችና አሁን ምን ያህል ከዚያን ጊዜዋ ኒኪ እንደተለየች አሰበች። እዚህ ቦታ ለመጨረሻ ጊዜ የመጣችው የዛሬ አምስት ዓመት ከዶውግ ጋር ቢሆንም እሷ ግን በጣም የቆየች ነው የመሰላት።

ትላንትና ማታ ይዛው የነበረውን ሻንጣ ነው ያመጣችው። ሻንጣውን አልጋው ጎን አስቀምጣ አልጋው ላይ አረፍ ካለች በኋላ ስልኳን ስትከፍት የመልዕክት መዓት በሰልፍ ይገባላት ጀመር፡፡ ጉድማን፣ ጉድማን፣ ጉድማን፣ ግሬቸን፣
ግሬቸን... ስልኳን መልሳ አጠፋችው::
ማንንም ማናገር አትፈልግም። የእንግዳ ቤቱ ባለቤት እና አስተዳዳሪ የሆኑት ሲኞራ ማርቼስ በሩን በዝግታ አንኳክተው ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ “ዶክተር ሮበርትስ ለምን ያህል ጊዜ ነው ለመቆየት የፈለግሽው? ያው በፊትም እንደምታውቂው ይህ ክፍል እስከ ሰኔ
ድረስ ክፍት ነው::” አሏት፡፡
ኒኪም እስቲ ዝም ብለው ለጥቂት ቀናት ብለው ይያዙልኝ፡፡ ሀሳቤን ከቀየርኩኝ ደግሞ አሳውቅዎታለሁ።” አለቻቻው እና ተሰናብተዋት ወጡ።

ኒኪ ሲኞራ ማርቼስን ስታናግር ፊቷን የግድ ፈገግ አድርጋ ነበር። ልክ ክፍሉን ለቀው እንደወጡ ግን ወደ ድብርቷ ተመለሰች። ለጥቂት ሰከንዶች
እንኳን ደስተኛ መምሰሏ ህመም ነው የሆነባት። ልቧ በነበረበት ቦታ ላይ
የሆነ በእሳተ ጎመራ ፍም የሆነ፣ ሲነኩት እጅግ የሚያቃጥል እና በንዴት
የሚንቀለቀል የአለት ቅርፊት ያለ ነው የሚመስላት።

ደውግ ሆይ ደስተኛ ለነበርንባቸው ትዝታዎቻችን ሁሉ የተረገምክ ሁን
ዶውግ ሆይ ስለ ውሽትህ፣ በእኔ ላይ ሴት ስለመደረብህም የተረገምክ ሁን! ከዚያች ሩሲያዊት እና ካልተወለደው ልጃችሁ ጋር ለዘላለም በገሃነምእሳትም ተቃጠሉ!

ሊነጋጋ ሲል ኒኪ ለአኔ ቴራፒስቷ ሆና እንደማትቀጠል ነገረቻት “አኔ ሌላ ሰው ጋር የቴራፒ ህክምናውን መውሰድ ይኖርብሻል። አኔ አሁን በጥሩ
ሁኔታ ውስጥ ስላልሆንኩኝ ልረዳሽ አልችልም።” ስትላት አኔ ቅር እያላትም
ቢሆን ተቀብላዋለች፡፡

ማታ ላይ በኒኪ እጅ ላይ ስላየችው ሽጉጥ አኔ ምንም ነገር አልጠየቀቻትም። አዎን ኒኪ ከዚህ በኋላ አኔን እንደ ብረት ልታያት አትችልም:: ኒኪ ውስጥ ያለው ትልቅ የንዴት ሰይጣን እስካልሞተ ድረስም ኒኪ የማንም ረዳት ለመሆን እንደማትችል ገብቷታል። ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ተሰነባብተው ሲለያዩ ሁለቱም ዳግመኛ እንደማይገናኙ እያሰቡ ነበር።

አኔን ከሸኘቻት በኋላ ኒኪ አራት ኢ ሜይሎችን ፃፈች። የመጀመሪያው
ለጉድማን የፃፈችው ደብዳቤ ነው፡፡ ሁለተኛው እና ሦስተኛው ኢ ሜይል
ደግሞ ለካርተር በርክሌይ እና ለላና ግሬይ ሲሆን የቴራፒስት አገልግሎቷን
ማቋረጧን እና ሌላ ቴራፒስት እንዲፈልጉ የሚያሳስብ ደብዳቤ ነው።
አራተኛው ኢ ሜይል ደግሞ ለዕደለ ቢሷ ረዳት ሰራተኛዋ ኪም ቾይ ከስራዋ
እንደተሰናበተች እና የሦስት ወር ደሞዟንም በአካውንቷ እንደላከችላት
የሚገልፅ ደብዳቤ ነበር፡፡

ለልብ ጓደኛዋ ግሬቸን ኢ ሜይሏን ስትፅፍ ግን ልቧን በጣም ከብዷት ነበር። ደብዳቤው የስንብት እንዳይሆንም ፈርታለች:: ትላንትና ሲያወሩ ኒውዮርክ ሄዳ አዲስ ኑሮ እንድትጀምር የመከረቻትን ነገር አስታውሳ ቢሆንልኝ ብላ ተመኘች። ከዚያማ ግሬቸን እና ቤተሰቧ እሷ ጋር መጥተው የምስጋና ቀን እራትን አብረው ይበላሉ፡፡ ኒውዮርክ የሚገኙ ገበያዎችን
አውደ ርዕዮችን እያዩም እንዲዝናኑ ጭምር እየተመኘች ነበር ደብዳቤውን የፃፈችው።

ኢ ሜይሎቿን ከላከች በኋላ ቁርሷን በላች እና የሎስ አንጀለስ መንገዶች
በትራፊክ ከመጨናነቃቸው በፊት ወደ በርሃው ላይ ወደምትገኘው ሀይኬንዳ
መንደር መኪናዋን ማሽከርከር ጀመረች:: በፊት ላይ ወደ በርሃው ስትጓዝ ከፊት ለፊቷ የተዘረጋውን፣ የማያልቀውን ድንጋያማ እና አሸዋማ በርሃን
እያየች መንዳቱ እራሱ ነፃነትን ነበር ይሰጣት የነበረው። አሁን ግን የዚያን
አይነት ስሜት አልሰጣትም፡፡

ጋቢናው ውስጥ ከጎኗ ከሚገኘው ወንበር ላይ ያጠፋችው ስልኳ እና ትላንትና ኪም ቾይ ከቢሮ የኒኪ ቤት ድረስ ይዛላት የመጣችው ዴሪክ ዊሊያምስ የላከላት ደብዳቤ ተቀምጠዋል። ደብዳቤው ወደ ኒኪ ቢሮ የደረሰው ዊሊያምስ ከመሞቱ ከአራት ሰዓት በፊት ነበር፡፡ ኪም ቾይ ፖሊሶች እንደተለመደው መጥተው ብርበራ ከማካሄዳቸው በፊት አስቀድማ ወደ ኒኪ ቤት በመሄድ ነበር የፓስታ ሳጥን ውስጥ ያስቀመጠችላት። ኒኪም ጠዋት
ላይ ሳጥኑን ስትፈትሽ ነበር ደብዳቤውን አግኝታው ይዛው የመጣችው::
ውስጡ ምን እንደተፃፈ እያሰበች መኪናውን ማሽከርከሩ እራሱ ጣር ነው
የሆነባት፡፡

ራሷን አደፋፍራ ደብዳቤውን ለማንበብ ስትዘጋጅ ነበር እንግዲህ ሲኞራ
ማርቼስ ያቋረጠቻት። በድጋሚ ድፍረት ለማግኘት ስላልቻለች ደብዳቤውን
አስቀመጠች:: ፒኪኒ እና የጡት ማስያዢያዋን አድርጋ እና ቀዝቃዛ መጠጥ ከፍሪጅ ውስጥ አውጥታ ስልኳንም ከፍታ እና ይዛው የእንግዳ ማረፊያው ግቢ ውስጥ ወደሚገኘው የዋና ቦታ አመራች። ዋናው አጠገብ ከሚገኘው የማረፊያ አልጋ ላይ ጋደም አለች። የበርሃው ሙቅ ነፋስ ሰውነቷን
እየዳስሰው ሲያልፍ ቀዝቃዛውን መጠጥ ጨለጠችው።

ከምኔው እንደተኛች አልታወቃትም:: ብቻ ፀሀዩ መላ ሰውነቷን አንድዷታል፡፡ አፏም ክው ብሎ ደርቋል፡፡ ቀና ስትል አንዲት ሰፊ የፀሐይ ባርኔጣ ያደረግች ሴት ቁልቁል እያየቻት “ምን ሆነሽ ነው? ለምንድነው
ስልኩን የማታነሺው? እዚህ እኮ ልናርፍ ነው የመጣነው:: ያለበዚያ ደግሞ
ስልኩን ማጥፋት ነው::” ስትላት የሚንጫረረው ስልኳ ተሰማት።

“ሄሎ” አለች ኒኪ፡፡

“ሆ እግዚአብሔር ይመስገን... ብደወል ብደውል እኮ አታነሺም” አለቻት
አኔ፡፡ እና በመቀጠልም “ኒኪ የማወራሽ ነገር አለ በቶሎ መገናኘት አለብን”
“ጠዋት ላይ አውርተን ተለያይተን አይደል እንዴ ይቅርታ አኔ ልረዳሽ አልችልም፡፡” አለቻት ኒኪ፡፡

አኔም እያለቀሰች “የግድ መገናኘት አለብን ስለ ሉዊስ ያወቅኩት አዲስ
ነገር አለ፤ ነገሩ አንቺንም የሚመለከት አደገኛ ነገር ነው::” ስትላት ኒኪ
ምናልባት ዊሊያምስ የነገራት ነገርን አኔ ያወቀች መሰላት።

“ታዲያ ለምንድነው ወደ ፖሊስ የማትሄጂው?” ብላ ኒኪ ጠየቀቻት፡፡

“በፍፁም አይሆንም ፖሊስ ጋ መሄድ የለብኝም:: እባክሽን አንዴ ብቻ
ላግኝሽ፤ ከዚያ በኋላ ሁለተኛ አላስቸግርሽም” ብላ አኔ እያለቀሰች ለመነቻት።

ኒኪም ትላንትና ማታ አኔ የእሷን ህይወት እንዳተረፈችላት ከግምት ውስጥ አስገብታ ልታገኛት ወሰነች::

“እሺ ነገ ማታ 12 ሰዓት ላይ ቢሮዬ ላግኝሽ”
“ቢሮሽ አይሆንም። ሉዊስ በአንቺ ቢሮ፣ በእኔ ቤት፣በ አንቺ ቤት እና
ትራ በኦርኬስትራ ቦታ ጭምር ሰዎች አሉት። ባይሆን የልብስ ማምረቻው ሰፈር
ውስጥ አንድ ባዶ የመጋዘን ህንፃ አለ፤ እዚያ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ እንገናኝ::” ብላ አኔ መጋዘኑ የሚገኝበትን ትክክለኛ ቦታ እና የህንፃውን ቁጥር ከእነ በሩ ኮድ ነግራት ስልኩን ዘጋች:: ኒኪም አኔ በዚህ ሁኔታ እጅግ በጣም ተረብሻ አይታት ስለማታውቅ በቀጠሮው ላይ ለመገኘት ወሰነች።......

ይቀጥላል
👍1
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

...ኒኪ ጠዋት ላይ ከእንቅልፏ ስትነቃ ሙሉ በሙሉ የእረፍት ስሜት ነው የተሰማት:: ምናልባትም ከብዙ ቀናት በኋላ ያልተቋረጠ እንቅልፍ ስለተኛች
ሊሆን ይችላል እንደዚህ አይነት ስሜት ሊሰማት የቻለው። ትላንትና የተሰማት ሀዘን እና ንዴትም በእንቅልፍ ወጥቶላታል፡፡ ትላንትና ማታ ሰውነቷን ያስመታችው ፀሐይ አፍንጫዋን እና ትከሻዋን በደንብ አድርጎ ስለጠበሰው ቀይ ሆኗል፡፡ ስለዚህም የሎዕ ጄል ተቀብታ ለጥቂት ጊዜ ያህል ቆየች እና ገላዋን ታጠበች ቁርሷንም እንቁላል ፍርፍር ከተጠበሰ ፍራፍሬ ጋር በልታ በላዩ ላይ ሁለት ኩባያ ጠንካራውን የኢጣሊያን ቡና ጠጣችበት።

ዛሬ ማታ አኔን ማግኘት አትፈራም፡፡ አኔን ካገኘቻት እና ስለ ሉዊስ አገኘሁት ያለችውን መረጃንም ከአኔ ከተቀበለች በኋላ አኔን በደንብ መክራት እንድትረጋጋ ካደረገቻት በኋላ መረጃውን ለሉው አሳልፋ ትሰጣለች፡፡ ከዚያም ነገሮች እስኪረጋጉ ድረስ ወደ ፓልም ስፕሪንግ፣ ወደ አሪዞና ወይንም ደግሞ ወደ ሆታሆ አምርታ ተደብቃ መቆየት ትችላለች፡፡
ወደ እንግዳ መቀበያው አምርታ “ሲኞራ ማርቼስ አሁን ወጥቼ በጣም አምሽቼ ነው የምመለሰው እና ምናልባት የግቢው በር ቁልፍ ያስፈልግ። ይሆን?”

“አያስፈልግሽም ዶክተር በክፍልሽ ቊልፍ የግቢውን በር መክፈት ትቺያለሽ፡፡ ይልቅ እራት ፍሪጅ ውስጥ ላስቀምጥልሽ?”

“ፍራፍሬ ብቻ ይቀመጥልኝ” ብላቸው ወደ መኪና ማቆሚያው ሥፍራ አመራች። መኪናዋንም አስነስታ ከግቢው መውጣቷን የተመለከቱት ሲኞራ
ማርቼስ የስልኩን እጀታ አንስተው የሆነ ቁጥር ላይ ደወሉና “አሁን ከዚህ
ተነስታለች” ብለው ስልኩን ዘጉ።

ኒኪ መኪናዋን እያሽከረከረች ፓልም ስፕሪንግ ደረሰች እና የክፍያ መንገዱ ውስጥ ከመግባቷ በፊት ነዳጅ ለመቅዳት ነዳጅ ማደያ ቆመች:: ወደ ቦርሳዋም እጇን ሰድዳ የገንዝብ ዋሌቷን ልታወጣ ስትል እጇ የዊሊያምስን ኤንቨሎፕ ነካ። ኤንቨሎፕን ቀደደችውና ውስጡ ያለውን ወረቀት አንድ በአንድ አወጣች።

መሪዋ ላዩ ተደፍታ ሰውነቷ የሚርገፈግፈውን ሴት ያየው የነዳጅ
ማደያው አስተናጋጅ ወደ እሷ ቀረበ እና “ችግር አለ የኔ እመቤት?” ብሎ
ጠየቃት፡፡ ኒኪም ቀና ብላ ስታየው በአንድ ጊዜ እያለቀሰች እና እየሳቀች መሆኗን
አየና ትንሽ ቀለል አለው:: በእጇ ላይ የያዘቸውንም ወረቀት እያሳየችው
“ደረሰኝ (ቢል) እኮ ነው አይገርምም?” ብላ ከት ብላ ሳቀች እና “አይገርምም
እሱ ከሞት መንደር የላከልኝ የመጨረሻው መልዕክት የሚያዚያ እና
የግንቦት ወር ክፍያ መጠየቂያ ቢሉን ነው” ብላ ከት ብላ መሳቋን ቀጠለች።

የነዳጅ ማደያው ሰራተኛ ሴትዮዋ ቢሉን እያሳየችው እንደ ዕብድ የሳቀችበት ምክንያት አልገባውም፡፡ እዚህ ፓልም ስፕሪንግ ውስጥ እንደ እሷ ያሉ ዕብዶችን እያስተናገደ በሚያገኘው ዶላር ዕዳውን የሚከፍለው በሚመጡለት ቢሎች ነውና ቢል ይሄንን ያህል ሊያስቅ አይችልም ብሎ በኒኪ ተበሳጨባት፡፡

ጉድማን ቢሮው ቁጭ ብሎ በዴሪክ ዊሊያምስ ላይ የቀረበውን የፎሬንሲክ
ሪፖርት ደግሞ እያነበበ ነው:: ሪፖርቱ እንደሚገልፀው ከሆነ በሟቹ ላይ
ምንም አይነት አሻራም ሆነ የገዳይ ዲ.ኤን.ኤ ሊገኝ አልቻለም:: የተመታበት
ጥይትም ቢሆን አብዛኛው የሎስ አንጀለስ ህብረተሰብ በሚይዘው የሽጉጥ ጥይት ነው:: ነገር ግን ሽጉጡ ላይ የተገጠመው ሳይለንሰር በጣም ልዩ እና በፍፁም ድምፅ እንዳያሰማ የሚጠቅም በመሆኑ፣ እንዲሁም ደግሞ እነዚህን ልዩ ሳይለንሰር የሚሸጡት የጦር መሳሪያ መደብሮች የሚሽጡለትን ሰው አድራሻ እና ማንነት መዝግበው ስለሚሸጡ፣ ይህንን ሊያጣራ ጆንሰን በከተማው ውስጥ የሚገኙ መደብሮች ውስጥ እየዞረ ይገኛል፡፡

ጉድማን የዴሪክን ገዳይ እንደዚህ በቀላሉ እንደማያገኙት እርግጠኛ ነው።
አሁን እያሳሰበው ያለው ነገር የኒኪ ሮበርትስ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም እሷ
የገባችበትን አደጋ አታውቅም። የእሷ ከተማውን ለቆ መውጣትን ለጆንሰን
አላሳወቀውም። ይሄ ደግሞ ሌላ ችግር ነው የሚፈጥርበት። ምንም እንኳን እሷ በዊሊያምስ ግድያ ውስጥ ባትሳተፍም የግል መርማሪዋ በተገደለ ማግስት ሎስ አንጀለስን ለቅቃ መጥፋቷ ጥሩ ነገር እንዳልሆነ በደንብ ይገባዋል።

በዚህ ሀሳብ ውስጥ እያለም ላቲሻ ሀል የምትባለው የጣቢያው መልዕክት
አቀባይ አንድ የተከፈተ ኤንቨሎፕ አምጥታ ሰጠችው::ጉድማንም የኢንቬሎፑን መከፈት ተመልክቶ “ኢንቨሎፕን አንቺ ነሽ
እንዴ የከፈትሺው!?” ብሎ በቁጣ ጠየቃት፡፡

“ኧረ በፍፁም” ብላ እሷም ኮስተር ብላ መለሰችለት፡፡

“እና ቅድም ከሁለት ሰዓት በፊት ፖስታ በሚከፋፈልበት ጊዜ ለምን
አልሰጠሺኝም?”

“ምክንያቱም መፀዳጃ ቤት በነበርኩበት ጊዜ ነው የሆነ ሰው መጥቶ ዴስኩ ላይ ያስቀመጠው:: ኤንቨሎፕ ላይም ለሎው ጉድማን የሚል ፅሁፍ ስለተፃፈበትም ነው ላንተ ይዤልህ የመጣሁት” አለችው፡፡
ጉድማን ከኤንቬሎፑ ውስጥ ያለውን ወረቀት ሲያወጣው ዴሪክ ዊሊያምስ ለኒኪ የላከው የሚያዚያ/ግንቦት ወር የክፍያ መጠየቂያ ደረሰኝ እና
ከደረሰኙ ላይ የተቀደደ እና ኒኪ የፃፈችበት ወረቀትን አገኘ። ከደረሰኙ ጀርባ ላይ 777 የሚል ፅሁፍ ተፅፎበታል፡፡ ከደረሰኙ በተቆረጠው ወረቀት ላይ ደግሞ “ይሄን መልዕክት እንደምታገኝው ተስፋ አለኝ፡፡ ነገሩ ከእኔ ይልቅ ለአንተ አስፈላጊ ነው። ሉው
ሁሌም ራስህን ጠብቅ፡ እኔን በፍፁም
እንዳትከተለኝ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ጆንሰን እዚህ ነገር ውስጥ እስከ አፍንጫው
ነው የተዘፈቀበት ኒሮ

የሚለውን መልዕክት እንዳነበበወደ መስኮቱ በፍጥነት አመራና ወደታች ወደ ታች ወደ መኪና ማቆሚያው ተመለከተ፡፡
መንገዱ ግራና ቀኝ ላይ።
ከሚራመዱት ሰዎች ውስጥ ኒኪን በአይኑ ቢፈልጋት ሊያገኛት አልቻለም።
ኒኪ ለጥቂት ከእጁ ስላመለጠችውም በጣም ተናደደ፡፡

ወዳ ላቲሻ ዞሮም “ጆንሰን ጋ ደውይለት:”
“ደውዬ ምን ልበለው?” አለችው ላቲሻ ግራ ተጋብታ፡፡

“በአስቸኳይ ወደ ቢሮ እንዲመጣ ንገሪው።” አላት፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኒኪ ለአኔ የሰጠቻት አድራሻ በሳን ጁሊያን መንገድ ላይ የሚገኝ የድሮ መጋዘን የነበረ ህንፃ ነው። ህንፃው በአንድ ማተሚያ ቤት እና በአንድ የሴቶች ልብስ ስፌት ፋብሪካ መሀከል የሚገኝ ድብቅ ህንፃ ነው::

በእነዚህ ምንም በሌለባቸው ህንፃዎች ውስጥ በፊት ላይ ቤት አልባ
ሰዎች ይኖሩባቸው ነበር፡፡ አሁን ላይ ግን የከተማው ከንቲባ ለቤት አልባ ሰዎች ማደሪያ ስላዘጋጁላቸው አብዛኛዎቹ እዚህ አካባቢ የሚገኙ ህንፃዎች ባዷቸውን ነው የሚያድሩት።

ኒኪ መኪናዋን በቅርብ ርቀት ከሚገኙት ብሎኮች አጠገብ አቁማ ወደ ቀጠረቻት ህንፃ ስታመራ ለአኔ ይበልጥ መጨነቅ ጀመረች። ኒኪ ጭር ባለ ቦታ አኔ ላግኝሽ እና ላውራሽ ማለቷ በተለይ ደግሞ ይሄንን ቦታ መምረጧ ልታካፍላት ያሰበችው ሚስጥር ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ አብረውም እንዳይታዩ በመፈለጓ የተነሳ ነው ብላ አሰበች፡፡ “ይሄ የመገናኛ ቦታ ሳይሆን የመደበቂያ ቦታ ነው። ግን ከማን ነው የምትደበቀው?”

የመጀመሪያ ግምቷ ሉዊስ ነው ሊጎዳት ያስበው የሚል ነበር። ግን ከዚህ
ሁሉ ጊዜ በኋላ ለምንድነው ሉዊስ አኔ ላይ ጉዳት የሚያደርሰው? ምናልባት
ሉዊስ ቀናተኛ እና ሁሉንም ነገሮቿን መቆጣጠር የሚወድ ሰው ስለሆነ
ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ሊያስፈራራት እና ተመልሳ ወደ ቤቷ እንድትሄድ
ማድረግ ነው የሚችለው እንጂ አንድም ቀን እጁን አንስቶባት አያውቅም።
ምክንያቱም በጣም ነው የሚወዳት

ትናንት አኔን በስልክ ስታወራት ከድምጿ ውስጥ ከፍተኛ ፍራቻ እና ተስፋ መቁረጥን
👍1
ለመስማት ችላለች፡፡ ስለዚህም አኔን ለአንዴ እና ለመጨረሻ
ጊዜ ከረዳቻት በኋላ ወደ መደበቂያዋ ለመመለስ ወስና ነበር ወደ እዚህ ቦታ
የመጣችው::
የተቃጠሩበት ህንፃ በር ላይ እንደ ደረሰች የእጅ ሰዓቷን ስትመለከት ከቀኑ 11:15 ነበር።አኔ የሰጠቻትን ባለ አምስት ዲጂት ቁጥርን ከግድግዳው ላይ ከሚገኘው ማሽን ላይ ስትጫንም በሩ መከፈት ጀመረ። በሩ ሙሉ በሙሉ እንደተከፈተም ከፊት ለፊቷ ወደ ፎቁ የሚያስወጣ ደረጃን
ተመለከተች። የሚንሸራተተው በር
ነው የተከፈተው፡፡ አኔ እንዳለቻትም “ወደ ውስጥ ከገባሽ በኋላ እኔ እንኳን ብዘገይ ውስጥ ሆነሽ እንደምትጠብቂኝ ቃል ግቢልኝ” ብላት ነበር።

ወደ ውስጥ ከገባች በኋላ ኒኪ የለበሰችውን ልብስ ወደ ራሷ አጥብቃ
በእጁ ያዘችው። ህንፃው ከመቀዝቀዙም በላይ ምንም አይነት መብራት አይታያትም፡፡ ከግድግዳው ላይ በሚገኙት ሁለቱ ቆሻሻ መስኮቶች በኩል
በሚገባው ደብዛዛ ብርሃን ግራጫ የአዳራሹን ወለል በየቦታው የተቀመጡ
የፕላስቲክ ወንበር እና ጠረጴዛዎች እና ወለሉ ላይ ተበታትነው የተቀመጡ
ውዳቂ ቁርጥራጭ ጨርቆች ይታይዋታል። ከጥግ ግድግዳው ላይ ሁለት ትላልቅ በር ያለው አሳንሰር ቆሟል። አሳንሰሩ ትልቅ ነው፡፡ ከአሳንሰሩ ግራ
እና ቀኝ በኩልም ለእሳት አደጋ ጊዜ መውጫ የሚያገለግሉ ሁለት የብረት
ደረጃዎች ወደ ላይ ወደ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ፎቅ የሚያስወጡ ናቸው::

“እኔ” ብላ ኒኪ ስትጠራ አዳራሹ ውስጥ ድምጿ አስተጋባ፡፡ ምንም አይነት መልስ አላገኘችም::

ወደ የእሳት አደጋ መውጫው ደረጃ አመራች። ወደ ላይ መድረክ
የሚመስለው ቦታ ላይ ወጣች። ወደሚቀጥለው ህንፃም በደረጃውም ላይ ወጣች። እዚህኛው ህንፃ ላይ ስትደርስ ደግሞ ረዥም ኮሪደር አጋጠማት። በኮሪደሩ ዳር እና ዳር የተከፋፈሉ ክፍሎች ይገኛሉ። ይህ ህንፃ ከታችኛው ህንፃ ይበልጥ ይጨልማል፡፡ ኮሪደሩ በጣም መጥፎ ሽታ አለው። ሽታው የሰው ሰገራ እንደሆነ ማሽተት ችላለች። ኒኪ ግድግዳው ላይ የሚገኘውን ማብሪያ ማጥፊያ ተጫነችው፡፡ የፍሎረሰንቱ መብራትም መስኮት አልባ በሆነው ክፍል ውስጥ በራ።

እንደ ክርስቶስ ጣውላ ላይ በምስማር ተመትቶ ራቁቱን የተሰቀለ ሬሳ ኒኪ በግማሽ ጉሮሮዋ ተከፍቶ በጣም ደንግጣ ጮኸች። ከፊት ለፊቷ ልክ
ይታያታል። ሬሳው በጣም ከመደብደቡ እና በስለት ከመተልተሉ የተነሳ
የሰውዬው ፊት አይለይም:: ግን ኒኪ በጣም ትኩር ብላ ስትመለከተው
ማንነቱን ለማወቅ ቻለች፡፡ ዊሊ ባደን!

የሆነ ሰው ብዙ ዶላሮችን አፉ ውስጥ ጠቅጥቆበታል። ይሄ ደግሞ በጣም
አሰቃቂ ግድያ እንደተፈፀመበት ያሳያል። ኤክስፐርት ባትሆንም ከሬሳው ላይ
ደም ስለሚንጠባጠብ ዊሊ በቅርቡ እንደሞተ ገመተች።

ኒኪ! እዚህ አለሽ?!” ብላ አኔ ድምጿን አቅጥና ተጣራች::

“አኔ!” ብላ ከባደን ሬሳ ወደ ኋላ ፊቷን ስታዞር አይኗ ላይ ሀይለኛ ብርሃን አረፈበት “የት ነው ያለሺው? ላይሽ አልቻልኩም”

ይሄኔም አንድ ትልቅ ሳጥን ከሚመስለው ቢሮ ውስጥ ወጣች እና በረዥሙ ኮሪደር ላይ ወደ ኒኪ መራመድ ጀመረች፡ የተሰቀለውን ሬሳ በጨረፍታ ካየች በኋላም እየተንገዳገደች ወደ ኒኪ መምጣት ጀመረች። አኔ ኒኪ አጠገብ ስትደርስ ኒኪ በአኔ ፊት ላይ ቧጨሮዎችን ተመለከተች::አይኗ፣ የቀኝ ጉንጫ እና አንገቷ ሰማያዊ ግራጫማ ከመሆናቸውም በላይ አባብጠዋል።

ኒኪም ወደ አኔ ተንደርድራ እየሄደች “መታሽ እንዴ?!”
አኔም በጣም አፍራ የታችኛውን ከንፈሯን ነከሰች።

“ዊሊ ባደንን የገደለው እሱ ነው?” ብላ ኒኪ አኔን አቀፈቻት እና ወደ
ተሰቀለው ሬሳ እንዳታይ እየተከታተለቻት “ሲገድለው እዚህ ነበርሽ? በጣም
አሰቃይቶ እኮ ነው የገደለው”
“ይቅርታ” አለቻት አኔ በጣም እየተንተባተበች። እስከ አሁን ድረስ እጅግ
በጣም ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ነው የምትገኘው።

“ለምንድነው ይቅርታ የምትይኝ?” ብላ ኒኪ በመቀጠልም “ይሄ እኮ ያንቺ
ችግር አይደለም። እዚህ የተደረገው ነገር ሁሉ እኮ አንቺ አይደለሽም ያደረግሽው።”

“ተሳስተሻል” አለች አኔ ሳግ እያነቃት፡፡

“ይሄውልሽ ከዚህ በቶሎ መውጣት አለብን” ብላት ኒኪ በመቀጠል
“እዚህ መቼም ደህንነታችን የሚጠበቅበት ቦታ አይደለም…”

“ጥፋቱ የእኔ ነው” ብላ አኔ አቋረጠቻት እና “በእውነት እኔ ይህንን ባላደርግ... ነገሮች ከዚህ የተለዩ ሊሆኑ ይችሉ ነበር:: ግን እሱ ግድያውን ሲያደርግ እኔ በግድ እንዳየው ነው ያደረገኝ።” አለች እና የባደንን ሬሳ እየተመለከተችም “በቪዲዮ እንድቀርፀው አስገደደኝ ብላ ስልኳን
በሚንቀጠቀጥ እጇ ካሳየቻት በኋላ “አንቺንም ወደ እዚህ እንድጠራሽ
አደረገኝ። በጣም ይቅርታ እሱ ሊያወራሽ ይፈልጋል” አለቻት፡፡

ይሄኔም ከሌላኛው ክፍል ሁለት ግዙፍ ሰዎች ሙሉ ጥቁር ልብሳቸውን
እንደለበሱ ወደ እነርሱ መጡ። እና አጠገባቸው ከደረሱ በኋላም “በዚህ በኩል እንሂድ ሚስዝ ሮድሪጌዝ” ብሎ በትህትና ሲጠይቃት ሌላኛው ወንድ ደግሞ ክንዷን ያዛት። ኒኪም የአኔን ክንድ የያዘው ሰው እጅ ላይ የደረቀ ደም
እየች ሆዷ ተገላበጠባት። ደሙ የሚስኪኑ ዊሊ ባደን እንደሆነ ስላወቀችም
ባደን እዚህ ውስጥ ምን ያደርጋል?” ብላ ራሷን ጠየቀች::

አኔ በሳግ ታፍና እያለቀሰች በሁለቱ ግዙፍ ሰዎች መሀል እየተጎተተች ወደ አሳንስሩ ውስጥ ሲገቡ እያየች ምንም ማድረግ አልቻለችም፡፡

“አንዴ ቆዩኝ!” ብላ ኒኪ እየጠራቻቸው

“እባካችሁ እንዳትጎዷት! እንዳትነኳት!” ብላ ብትናገርም የአሳንሰሩ በር
ተዘጋ።

ኒኪ ሀሳቧን ሰብስባ ለመረጋጋት ሞከረች። ሁለቱን ወንዶች በማየቷ አኔ
ስትበሳጭ እንጂ ስትገረም እንዳላየቻት አሰበች፡፡ ስለዚህም መጥተው
እንደሚወስዷት ታውቅ ነበር ማለት ነው። ምን ነበር ያለቻት “አንቺን እንድጠራሽ አስገድዶኛል ሊያገኝሽ ይፈልጋል ነው አይደል ያለቻት?

ኒኪ ከዚህ ቶሎ መውጣት አለባት። አኔን እንኳን ማትረፍ ባትችል ራሷን ማዳን ይኖርባታል። ወደ ኋላ ተመልሳም በመጣችበት መንገድ ስትመለስ በህይወት እያለ የሊዛ ፍላንገን አፍቃሪ የሆነውን ሰው ሬሳ ትታ በኮሪደሩ ላይ መሮጥ ጀመረች:: ጥቂት ያርድ ያህል ከሄደች በኋላም አንድ ረዥም እና የምታውቀው ሰው ሙሉ ጥቁር ልብሱን እንዳደረገ መንገዱን ዘጋባት::

በጣም ዘና ብሎ ፈገግ ብሎ ቆሞ ሲመለከታት ፎቶውን ዴሪክ ዊሊያምስ
ከጎግል ፎቶ ላይ እንዳሳያት ትዝ አላት፡፡

“ሚስተር ሮድሪጌዝ አለችው፡፡

ሉዊስም ፈገግ ብሎ በቡናማ አይኖቹ እየተመለከታት “ዶክተር ሮበርትስ
በመጨረሻ ላይ በአካል ለመገናኘት በቃን አይደል? ስለመጣሽ ደስ ብሎኛል” አላት

ከኮቱ ውስጥም ሽጉጥ መዝዞ በአይኗ መሀል ላይ ደቀነባት፡፡....

ይቀጥላል
👍2
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

...በአቅራቢያችን ያለችው ኮክ ለጋ ቅርንጫፎች ደፋ ቀና እያሉ እርስ በእርሳቸው እየተሳሳሙ ይበተናሉ፡፡ ጉንጯ ላይ ሳም ሳደርጋት የፍቅር ደማቅ ችቦ ተሀኮሰ አፌን ወደጎን አንሸራትቼ የከንፈሮቼን ነዲድ ከከንፎሮቿ አርኪ ገለት ጋር በማጋጠም ምጣድና አክንባሉ ሆንን፡፡ በሕሊናችንም ውስጥ ያ የፍቅር ችቦ ፏ ብሎ ሲቀጣጠል ታየኝ።

የወጣትነት ጣዕም፣ የፍቅር ማራኪ ለዛ፣ አንድ የመሆን ፍላጎት በዝግታ ወደ ውስጣችን ሠረፀ፡፡ ሰማይ እንደ አክንባሎ በላያችን ላይ ተደፍታ ቁልቁል ታስተውለናለች። ምን ግዳችን! የሚንቦገቦጉት ክዋክብት በጨለማው ከርስ ውስጥ የሚገኘውን ነገር ሁሉ ብርሃናዊ ውበት ሊዘሩበት ይታገላሉ። እንደ ገና ለስለስ ብሎ ከሚነፍሰው ነፋስ በተገኘው የቅጠላ ቅጠሎች ውዝዋዜ ላይ የከዋክብት ኅብራዊ ቀዝቃዛ ብርሃን ሲያርፍበት በወርቃማ ቀለም የተለበጠ ዕፅኖታዊ ሥዕል ታየ

እኔ በእርሷ የሕይወት ሰበካ፣ እሷም በእኔ የሕይወት መስክ እየተኩነሰነስን ወደማይታይና ወደማይዳስስ የሰመመን ዓለም ተጓዝን። ጥቂት ደቂቃዎች ዕለፉ፡፡

«እኔ የምልሽ» ብዩ ጀመርኩና «እስኪ ይኸው አሁን ብቻችንን ነን እውነቱን ንገሪኝ ታፈቅሪኛለሽ?» ብዬ ጠየቅኋት። የምትመልስልኝን ለመስማት ጆሮዩን ቀሰርኩ፡፡ አንደበቷን ከባድ ኃፍረት እየተጫነው «የትልቅ ሰው ዘር
ናቸው:: ዞር ብለውም አያዩኝ፣ እኔም የሰው አገር ሰው ነኝ እያልኩ ነው እንጂ
ማፍቀሩንማ መጀመሪያውኑ...» ብላ በዚያ ስስ ጨለማ ውስጥ የፊቴን ሁኔታ
ማየት ትችል ይመስል ትኩር ብላ አየችኝ።

«እንዲሀ አድርገናል፣ እንዲህ ሠርተናል ብለሽ አትናገሪም? ከዚህ ቀደም
በተናገርኩሽና በተቆጣሁሽ ምክንያት አልተቀየምሽም?» ብዬ ሁለቱንም ትከሻዋን ያዝኩ፡፡

«የምን መቀየም? ኸረ እኔ ከየቴ! እንዲያውም ደስ ደስ ነበር የሚለኝ።
እኔ ምክንያታቸውን እንጃ፡ አንድ ሰሞን እናትዎ ፊት ሲነሡኝ ነገሩሩን ሁሉ
ውጩ ዝም ያልኩት እርስዎን በማየት ነበር» ብላ በትኩስ ደም ጢም ያሉ
ጣቶቿን ባንገቴ ዙሪያ ዘረጋቻቸው:: ደቂቃዎቹ ጭልፊት እንዳየች ጫጩት
በነበር ጢሻ ውስጥ ለመሰግሰግ ሸመጠጡ፡፡

«እሜቴና ጌቶች ከተኙ ቆይተዋል» ብሎ በሹሉክታ ገብቶ ምድር ቤት ውስጥ የተኛው ዘበኛ እንዳይሰማን ኮሽታ ሳናሰማ ወደ ውሃው ቧንቧ ተመለስንና ተላያየን፡፡
የውጪውን ደረጃ በቀስታ ከዘለቅሁ በኋላ መብራቱን አብርቼ ወደ ክፍሌ ገባሁ። ወዲያው ልብሴን አወላልቄ አልጋዬ ላይ ተሸመለልኩ፡፡ አምስት ደቂቃ
በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመኝታ ቤቴ በር በዝግታ ተከፈተ፡፡ እሷው መሆኗን
በአረማመዷ ለይቻት ነበር፡፡ ያመጣችውን ውሃ አልጋዩ ሥር ከትራስጌ በኩል
ስታስቀምጥ «ገጭ» የሚል አጭር ወፍራም ድምፅ ሁለት ጊዜ ሰማሁ። በውሃ የረጠቡ እጆቿን በቀሚሷ እያደራረቀች በሩን ቀስ ብላ ከወደ ውስጥ ዘጋችው፡፡ብርድ ልብሱን ከወደ ትከሻዩ በኩል ገልጣ እጅዋን ወደ ውስጥ አሾለከች።ደረቴን አንገቴን ግንባሬንና ጉንጩን ደባበሰችኝ፡፡ እጅዋ ከግንባሬ ላይ እንደተለጠፈ ከተዘጋው የመኝታ ቤቴ መዝጊያ ውጪ ትንሽ ራቅ ብሎ የሚከፈት
በር ሲንሲያጠጥ በመስማቴ ሰውነቴ በጥርጣሬ ተንዘፈዘፈ፡፡ ልቤ በድንጋጤ
የተሰነጣጠቀች መሰለኝ፡፡

የሰው ኮቴ ተሰማ፡፡ ቁልቁል ወደ አልጋው ሥር ለመስረግ ፈለግሁ። የማይሆን አይሆንምና አልቻልኩም፡፡ የኮቴው ድምፅ እየቀረበና እየጎላ መጣ ቀረበ መጣ ቀረበ በሁኔታው ቁጥጥር ሥር በመዋሌ ፈጣን ውሳኔ ለመስጠት አዳገተኝ፡፡ የወዲያነሽ እጅዋን በፍጥነት ከግንባሬ ላይ አነሳችው::ፊቴን ገለጥ አድርጌ ሳይ ከመዝጊያው በስተጀርባ ተለጥፋለች፡፡

በሩ ከወደ ውጪ ተንኳኩቶ መጨበጫው ተነቃነቀ እና ወደ ውስጥ ተገፋ። የወዲያነሽ ከበሩ ላይ ተለጥፋ አብራ እየተገፋች የኋሊት ሄደች፡፡
ረዢም የውስጥ ልብስና ወፍራም ጋቢ ደርባ ራሷን ከፈት ባለው መዝጊያ
በኩል ወደ ውስጥ በማስገባት «ተኝተሃል እንዴ? ምነው ድምዕህ ጠፋ? ደኅና
አይደለህም እንዴ?» ያለችኝ እናቴ ነበረች። ጉድ ፈላብኝ!!

ድንጋጤ ባፈናት ደቃቃ ድምፅ ምላሴ አፌ ውስጥ እየተርበተበተች
«ደኅህ ነኝ፡ ምንም አልሆንኩም። ገና በጊዜ እኮ ነው የተኛሁት። ሂጂ ግቢ ብርድ አይምታሽ» አልኳት የሞት ሞቴን።
የወዲያነሽን ካጋጠማት የጉድ ፍላት ሥቃይና የድንጋጤ ረግረግ ውስጥ
ባስቸኳይ ለማውጣት ስል እናቴ እዚያው እንደቆመች ተሸፋፈንኩ፡፡ ሰውነቴ
ተንቀጠቀጠ። እናቴ ፊት እንደነሡት ቀላዋጭ በሩን ዘግታው ተመለሰች።

የወዲያነሽ በድንጋጤ ድርቅ ብላ ብቻዋን እንደ ቀረች ያጥር ዕንጨት ቆማለች። እጆቿ ደረቷ ላይ ተለጥፈዋል፡፡ እናቴ የመኝታ ክፍሏን በር ስትዘጋና
ትልቅ እፎይታና ግልግል! የወዲያነሽ ከወጥመድ እንዳመለጠች እይጥ በሩን ከፍታ እግሬ አውጭኝ አለች። በላዩ ላይ የወረደው የድንጋጤ ዶፍና ውርጃብኝ ወዲያው ጎደለ። በምትኩም ትዝታ እና ሰመመን እንደገና ደግሞ ትኩስ የፍቅር ሐሳብ አእምሮዬ ውስጥ “ዳንኪራና ሆታ ጀመረ::የወዲያነሽ ፈገግታ ለዛና ግልፅነት ሲነካካኝ ታወቀኝ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
...አባቴ የታላቅ ወንድሙን ጭምትነትና ልበኛነት እያስታወሰ በሚያወራበት ጊዜ ሁሉ ትዝታው በሐሳብ ፈረስ አፈናጣው ወደ አለፉት ዓመታት የኋሊት ትሰግርና ትካዜ መቀመቅ ውስጥ አገርግራ ትጥለዋለች:: መጋቢት አቦን በያመቱ እንደሚዘከርና በታላቅ መንፈሳዊ እምነት
እንደሚያምናቸው ሲያብራራ ፊቱ በኅዘን ተኮፋትሮ ዐይኖቹ በቁጣ ይጎለጎላሉ።

«ወንድሜን የገደለው የገዛ አራሹ ነው። ያውም የዋንጫውን ልቅላቂ ጠጥቶ የገበታውን ፍርፋሪ በልቶ ያደገ፡፡ የወንድሜን ገዳይ ለማስያዝና ከሕግ ፊት
አቅርቤ ለማስቀጣት በተጉላላሁ ጊዜ የደረሰብኝን ከባድ ስቃይ እስከ ዕለተ
ሞቴም አልረሳው:: ታዲያ ስፈልግና ሳስፈልግ ኖሬ ወሎ ውስጥ ከደሴ የትናየት ተንታ ከምትባል ትንሽ ከተማ ውስጥ መኖሩ በጭምጭምታ ታወቀ። ስገሠግሥ ሄድኩ፡፡ እዚያች ከተማ የገባሁት መጋቢት አራት ነበር። በማግሥቱ አሮጌ ሽማዩን ተከናንቤ ስፈልግና ሳስፈልግ ዋልኩ፡፡ መሸታ ቤቶቹ በቁጥር ናቸው።የሰው ደም አይለቅ አይደል! አንዷ ኮማሪት ቤት ተወዝፎ አምቡላውን ሲግፍ አገኘሁት፡፡ ወዲያው በነጭ ለባሽ አስያዝኩና እያካለብኩ ደሴ አስመጣሁት፡፡ገድሎ ዱር መግባቱ ቀድሞውኑ ተመስክሮና ተረጋግጦ አልቆ ስለ ነበር የኋላ ኋላ በስቅላት ተቀጣ፡፡

ልክ ባመቱ ደግሞ የአቦ ዕለት የአጥቢያ ዳኛ ሆኜ ተሾምኩ፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ ልክ የአቦ ዕለት ተካበች፣ ሙሉነህን ተገላገለች። ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ እንደ ተራዱኝ ነው:: ከዚያ ወዲህ እንደ አቅሜ ጠበል ጠዲቃቸውን አስታጉዬ አላውቅም። አሁንም ቢሆን ሁልጊዜ ከጐኔ እንደ ቆሙ ናቸው፡፡ በጠበላቸውና በቃል ኪዳናቸው ነው ነፍሴ ቆማ የምትሔደው፡፡ እንደ
ሐኪሞቹ በሩን መቀባጠርማ ይኸነዬ እጓሯቸው ነበርኩ፡፡ አሁንም በሆነ
ባልሆነውና በትልቅ በትንሹ በተበሳጨሁ ቁጥር የደም ብዛቴን የሚያስታግሣልኝ
እሳቸው ናቸው። በሳቸው ጠበል ተነክሬ ከእምነታቸው ስቀምስ ዐይኔ ሁሉ
ያበራል» በማለት ያስረዳል።

በያመቱ መጋቢት አምስት ቀን በቤታችን ውስጥ ቅልጥ ያለ ድግስ ይደገሳል፡፡ የሚጠመቀው ጠላ የሚጣለው ጠጅ የሚሠራው ወጥና የሚጋገረው
እንጀራ መጠንና ብዛቱ ምን ያህል እንደሆነ የሚያውቁት እናቴና በየዓመቱ
ለዚሁ ጉዳይ የሚመጡት ሠራተኛ ሴቶች ብቻ ናቸው።

በግቢው ውስጥ ባለው ሰፊ ገላጣ ቦታ ላይ ባንድ ጊዜ ከሁለት መቶ ሰዎች በላይ ለመያዝ የሚችል ድንኳን ይጣላል፡፡ አባቴን ፍርድ ቤቱ የሚያውቀውና ዝናውን የሰማ ዘመድ
👍3
ይሁን እየተግተለተለ ይመጣል፡፡

ከአገር ቤት ካመጡት ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ ሦስትና አራት ቀን
አድሪውና ሰንበትበት ብለው አተላ አፋሰው ይሔዳሉ:: ከዋዜማው ጀምሮ
ከደኅነኛው ይልቅ ሰካራሙ ስለሚበዛ ምድረ ግቢው ድብልቅልቁ ይወጣል ፡ የዕለቱ ዕለት ማታ የከተማው ሰው ጥርግ ብሎ ሲሔድ የገጠሮቹ ምድር ቤትና ድንኳን ውስጥ ሲያድሩ ቀሪዎቹ ደግሞ በያታክልቱ ስር ይለሽልሻሉ ጠምብዞ የትም የሚወድቀው ደግሞ ብዙ ነው።

የዓመቱ አቦ አሁንም ጊዜውን ቆጥሮ ደረሰ። ማንኛውም ነገር በቀድሞው
ሁኔታ ተዘጋጀ፡፡ ዕድምተኛውና ቤተኛ ነኝ ባዩ ሁሉ ከያለበት ተሰበሰበ፡፡

የወዲያነሽ በልኳ ያሰፋቸውን የሚያምር ቀሚስ ለብሳና እኅቴ ላንድ ቀን
ያዋስቻትን ሹራብ ደርባ እርጀት ያለ ውራጅ ጫማ አድርጋ በተጋባዦች መኻል
መለስ ቀሰስ ስትል ያዩዋት ሁሉ አይናቸውን ጣሉባት፡፡ ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ተጋባዡና ጠባል ቀማሹ እየቀለለ በመሔዱ ቀሪዎቹና ቤተኛው ሁሉ በድንኳኑ ውስጥ በተንተን ብሎ እርስ በእርሱ መገባበዝ ቀጠለ:: ቀስ በቀስ
አብዛኛዎቸ ሞቅ እላቸው::

እባቴ በበኩላ የፍርድ ቤቶችና በየሙግቱ ምክንያት የሚያውቃቸውን ብዙ ሰዎች ጠርቶ ስለ ነበር ብሉልኝ ጠጡልኝ እያለ ሲጋብዝና ሲሯሯጥ በመዋሉ፣

እናቴም በፊናዋ የግል እንግዶችዋንና እንዲሁም ሌላዉን ሁሉ ወዲያ ወዲህ ስትባዝን በመዋሏ የማታ ማታ ሁለቱን በድካም ዝለው ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ተኙ፡፡ የውብነሽም ከግማሽ ሰዓት በኋላ
ተከተለች::

ቀደም ሲል ከሶስት ወራት በፊት እናቴ ለወጂያነሽ ታዛዥነትና መልካም ጠባይ ተደስታ ለበዙ ጊዜ ምድር ቤት ውስጥ ተገትሮ የኖረ አንድ አሮጌ የብረት አልጋ ሰጥታት ነበር። እኔም ይህንን ስጦታ አስታክኬ አሮጌ ፍራሼን ጨመርኩላት፡፡

የአቦ ዕለት ማታ ግን ከገጠር የመጡ ጭሰኛ ሽማግሌ በየወዲያነሽ አልጋ
ላይ እንዲተኙ ተደረገ፡፡ አባቴ ስለ እርሳቸው ሲናገር «ታማኝ ሰው ናቸው፡
ምርት ሲሠፍሩ እፍኝ የሰው ገንዘብ አይፈልጉም፡፡ ቀኝ እጅ ናቸው» ይላል፡፡

የወዲያነሽ በድካም የዛለ ሰውነቷን የምታሳርፍበት ምቹ ጥግ አጣች።
የእኔን ልዩ እርዳታ ለማግኘት ዐይኖቿ በዐይኔ ዙሪያ ተንከራተቱ። አፍ አውጥታ
ለመናገር ኃፍረት ስለ ተጫናት ግድግዳውን ተደግፋ መቆም አበዛች።

በእንግዳ መቀበያው ክፍልና በአካባቢው ሰው አለመኖሩ እንደአረጋገጥኩ በቅድሚያ የመኝታ ቤቴን መብራት አጠፋሁ እና ዕቃ ቤቱ በር አጠገብ አንገቷን ሰበር አድርጋ የቆመችውን የወዲያነሽ ነይ አሁን ለጊዜው እዚያ ተኚ» ብዬ በክንዷ ስቢያት ገባሁ፡፡ በሩን በሚገባ ከዘጋሁት በኋላ መብራቱን አበራሁት።

«አይዞሽ አትፍሪ! እዚህ እኔ አልጋ ላይ ወጥተሽ ተኚ፡ ስንገባ ማንም አላየ» ብዬ እየተርበተበትኩ በሩን ዘግቼባት ውልቅ አልኩ፡፡

💫ይቀጥላል💫
👍1
#ፖለቲካ

ምን አስጨነቀህ ----ባታነብ
ባትመራመር -----ባትበቃ፣
ምን ችግር አለው----- ባትበስል
ባትሰለጥን ባትነቃ፡፡
አዳማጭ ባይኖር---- ምንተዳህ
መሰሎችህን አትጣ፣
አጥብቆ ጠያቂ እንዳይገጥምህ
ዙሪያህን እጠር በጋሬጣ፡፡
ክፉ ክፉውን ተናገር
በጎ በጎውን አትንካ፣
ያንተን ጭንቅላት የሚመጥን
ቀላል ስራ ነው ፖለቲካ፡፡

🔘ሻለቃ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
👍1
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

....ከኮቱ ውስጥም ሽጉጥ መዝዞ በአይኗ መሀል ላይ ደቀነባት።

...ሚክ ጆንሰን ፖሊሷ ላቲሻ ሆልን ልክ እንደ ቆሻሻ እየተመለከታት

“ጉድማን በቶሎ ይፈልግሃል ብለሺኝ ነበር የመጣሁት” አላት፡፡

“አዎን መርማሪ ፖሊስ ጉድማን እንደዚያ ብለሽ ነው ደውይለት ያለኝ ጌታዬ” ብላ መለሰችለት።

ላቲሻ ከጉድማን ይልቅ ጆንሰን በጣም ንዴተኛ እንደሆነ ስለምታውቅ በጣም
ተጠንቅቃ በትህትና ነበር መልስ የምትሰጠው።ሁሉምዐየዲፓርትመንቱ ሰራተኞች ከሚክ ጆንሰን ጋር ፊት ለፊት መጋፈጥ እንደሚያዋርድ ያውቃሉ። በተለይ ደግሞ የሚጋፈጠው ሰው አይሪሽ ካቶሊክ ነጭ እና ወንድ ከሆነ ጉዱ ነው የሚፈላው፡፡

“እና የታለ እሱ?” ብሎ ጆንሰን ጥርሱን ነክሶ ጠየቃት፡፡

“አላውቅም ጌታዬ!”

“አታውቂም?!” ብሎ ጆንሰን በሹፈት መልክ ድምፁን ቀንሶ ጠየቃት::ክፍሉ ውስጥ ከሚገኘው ሶፋ ወንበር ላይም ሰምጦ ከተቀመጠ በኋላ አይኑን
በመጨፈን ንዴቱን ተቆጣጠረ። ለእሷ አስቦ ሳይሆን ሀይሉን መቆጠብ
ስላለበት ነው ንዴቱን ያላሳያት። አሁን ነገሮች በጣም አደገኛ ሆነዋል።
ስለዚህ አሁን ማወቅ ያለበት ጉድማን የት እንደሚገኝ ብቻ ነው።

ሁለቱ መርማሪ ፖሊሶች እየተወሻሹ እስከ አሁን ድረስ ዘልቀዋል። ዛሬ ላይ ደግሞ ጆንሰን የሽጉጥ ድምፅ አፋኝ የሚሸጡ ሰዎችን ሲያፈላልግ እንዳልዋለ ሁሉ ጉድማንም የመተግበሪያ አፕሊኬሽን ፈቃዱ የማን እንደሆነ ሲመረምር እንደዋለ ያውቃል። ጆንሰን የካርተር በርክሌን ባንክ ወደ ሆነው በርክሌይ ሀሞንድ ሩድ ባንክ ሄዶ ለምርመራ የሚፈልገውን ፋይል ኮፒ ሲያስደርግ በነበረበት ጊዜ ነበር በአስቸኳይ እንደሚፈለግ ይህቺ ደነዝ ሴት
ደውላ የነገረችው፡፡

ዛሬ በርክሌይ ቢሮ ውስጥ ሆኖ ነበር ጉድማን እየዋሸው ሁለቱንም ባሳወራቸው የማይገባው ዓለም ውስጥ አብሮት እንደሚሰራ የገባው። እርግጥ
ነው ገና ይሄንን ጉዳይ አብረው ምርመራ ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ
ደመ ነፍሱ ጉድማንን እንደማያምነው ሲነግረው ነበር።

“መርማሪ ፖሊስ ጉድማን እዚህ አንተን እየጠበቀ ባለበት ጊዜ ላይ ነበር
ስልክ የተደወለለት::” አለች እና ላቲሻ በመቀጠልም “የደወለለትን ሰው ማንነት ባላውቅም ስልኩን ካወራ በኋላ ልክ ከሲኦል ተመንጥቆ እንደወጣ የሌሊት ወፍ በፍጥነት ነበር ከዚህ ቢሮ የወጣው። ፊቱ ላይ የሚታየው ነገርን ሳልጨምር ማለት ነው”

የጆንስን አዕምሮ የተለያዩ ነገሮችን እያሰበ ሆዱን ፍርሃት ፍርሀት አለው።

ላቲሻን ከእሱ እና ጉድማን የጋራ ቢሮ አስወጣት እና በሩን ዘግቶ የጉድማን ወንበር ላይ ቁጭ አለ።

አሁን ነገሩ እየከረረ ነው ፤ ነገር ግን ተስፋ መቁረጥ አይኖርበትም፡፡

አስብ!”

የጉድማን ዴስክ ሁሌም ጥርት ያለ እና የተደራጀ ነው። የዶክተር ሮበርትስ አድራሻ ከጀርባው የተፃፈበት ኤንቨሎፕ እና የጉድማን ስልክ ዴስኩ ላይ ይገኛሉ። ይሄ ደግሞ ጉድማን በጣም በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ በመሆኑ የተነሳ ነው እንጂ ጉድማን ስልኩን ረስቶ መቼም እንደማይሄድ ያውቀዋል። ጆንሰን ኤንቨሎፕን አንስቶ የዊሊያምስን ደረሰኝ እና ከጀርባው የተፃፈውን የኒኪን እጅ ፅሁፍ ማስታወሻውን በጥንቃቄ ሲመለከት ቆየ።
በተለይ ደግሞ የእሱን ስም ከኤንቨሎፕ ላይ ሲያነብ ልቡን አፈነው። ጆንሰን
እዚህ ነገር ውስጥ እስከ አንገቱ ነው ያለበት! የማትረባ ሴት! አንገት ድረስ
መጥለቅ ምን ማለት እንደሆነ ሊያሳያት ነበር።

ኤንቨሎፕን ኪሱ ውስጥ ከተተ እና የጉድማንን ስልክ አንስቶ ከበፊት
ጀምሮ ሸምድዶ የያዘውን የስልኩን ኮድ ቁጥር ፃፈ እና ከፈተው።የመልዕክት ሳጥኑን እና የደወላቸውን ቁጥሮች በጣቱ ወደ ታች ሲያደርግ ቆይቶ በመጨረሻ ላይ የሚፈልገውን ነገር አገኘ።

ወደ ራሱ ስልክም ከጉድማን ስልክ ላይ ያለውን መረጃ አዘዋወረ እና የተላከ መልዕክት የሚለው ቦታ ላይ ገብቶም መረጃውን አጠፋ:: ሰዓቱን ሲመለከትም ልቡ በፍርሃት መደለቅ ጀመረች፡፡ 12:20 ይላል! ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ? ምናልባት ዘግይቶ ቢሆንስ?

ሽጉጡን እና ተጨማሪ የሽጉጡ ካርታዎች ቀልሃቸው ሙሉ መሆኑን አረጋግጦም በሩን ከፍቶ እየሮጠ ወጣ፡፡

አሁን ይህንን የተረገመ ምርመራ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መጨረስ ይኖርበታል።

ኒኪ አይኗን ጨፍና ህይወቷን የሚያሳጣትን ጥይት ድምፅ እየጠበቀች
ነው። የዊሊን ሬሳ ስታይ የተሰማት ከፍተኛ ፍርሃት በንኖ ጠፋ እና በተስፋ መቁረጥ ተተካ፡፡ በተለይ ደግሞ ለማወቅ የምትፈልጋቸውን ነገሮች ሳታውቅ
መሞቷን ስታስብ ድንዛዜ ተቆጣጠራት፡፡

የምትጠብቀው የጥይት ድምፅን መስማት አልቻለችም። አይኗን
ስትገልፅም የሮድሪጌዝ አይኖች ላይ ጭካኔን እና መገረምን ተመለከተች፡፡

“ምን ያስቸኩልሻል ዶክተር ሮበርትስ፡፡ ወደ ፈጣሪሽ ከመሄድሽ በፊት ማውራት አትፈልጊም እንዴ?” አላት፡፡

“ዊሊ ባደንን አንተ ነህ የገደልከው?” ብላ በእርጋታ ጠየቀችው። እርግጥ ነው ሊገድላት ነው። ግን ከመሞቷ በፊት መልሶችን መስማት ትፈልጋላች፡፡

“ታዲያስ?” ብሎ ምስጋና የሚሰጣት ይመስል አጎነበሰ፡፡

“ለምን?

“ለምን አልገድለውም?” ብሎ ሳቀባት እና “እንዴ ያደረግኩትን ሥራ እንዳልወደድሽው እያየሁ እንዳይሆን ብቻ! የሆነ አጭበርባሪ አሳማ ነገር እኮ
ነው።”

“ለምን?”

“ተስገበገበአ!” አላት እና በመቀጠልም “አብረን በምንሰራው ቢዝነስ ውስጥ
ሜክሲኮ ውስጥ ከተስማማነው ውጪ ብዙ ገንዘብ ከእኔ ላይ መውሰድ
ጀመረ። ሜክሲኮ እያለን ጠንቃቃ ነበር፡፡ እዚህ ሎስ አንጀለስ ከመጣ በኋላ
ግን ራሱን አይነኬ አድርጎ መቁጠር ጀመረ፡፡” አላት እና ወደ ዊሊ ሬሳ ዞሮ
“ይህ ሀሳቡ ደግሞ የማይረባ እና ስህተት እንደሆነ ላሳየው ፈለግኩኝ። ማንም ሰው ከእኔ ጋር ጠላትነት ውስጥ ከገባ የትም ቢገባ ፈልጌ አገኘዋለሁ::” ካላት በኋላ በጣም በሚያስፈራ ሁኔታ አፍጥጦ ሲያያት ኒኪ ወዲያውኑ ተኩሶ የሚገድላት መስላት:: “እሺ ሌላ ጥያቄ አለሽ?” አላት፡፡

“እኔን ምንድነው ያደረግካት?”

ሮድሪጌዝም በጥያቄዋ ተገርሞ አያት እና
“እኔን እሷ እንዲደረግባት ከምትፈልጋቸው ነገሮች ውጪ ምንም ነገር አላደረኳትም” አለ እና ፈገግ ብሎም
“ሚስቴ ሰዎች እንዲጫኗት ትፈልጋለች። ዶክተር ሮበርትስ አንቺ ይሄ የሚስቴ ነገር ለምን እንዳልገባሽ አላውቅም። አሁንም ቢሆን ይሄ ነገር አይገባሽም። ምክንያቱም አኔን ከእኔ በላይ አታውቂያትም።”

“በጣም እንደምትፈራህ አውቃለሁ” አለችው እና ኒኪ በመቀጠልም
አንተ ሸሽታ ወደ እዚህ የመጣችው አንተ አስረሃት የምትኖረው ኑሮ ከአቅሟ በላይ ስለሆነባት ነው” ስትለው ፈገግታው ጨለመ::

አንቺ ስለ እሷ ስትከራከሪላት ሳይ በጣም ይገርመኛል፡፡ እንዴ! ወደዚህ
ልታስገድልሽ እንደሆነ እያወቅሽ መሆኑ ደግሞ የባሰ አስደምሞኛል።” አላት፡፡

“ምክንያቱም ስላስገደድካት ነው! የዊሊ ባድንን ግድያ አስገድደህ እንድታየው እንዳደረካት ሁሉ ማለት ነው።” አለችው፡፡
ሊዊስም ራሱን በአሉታ ነቅንቆ “ዶክተር ሮበርትስ ነገሩ እስካሁን አልገባሽም ማለት ነው? እሷ ይህንን ነገር የምታደርግልኝ እኮ በጣም
ስለምትወደኝ ነው። ላንቺ ምንም አይነት ስሜት ቢኖራትም በመጨረሻ ላይ
አኔ እኔን ለመከላከል ስትል ማንኛውንም ነገር ታደርግልኛለች። ምንም እንኳን በመካከላችን ያለውን ፍቅር ልታጠፊ ያላደረግሽው ነገር ባይኖርም
አኔ ልቧ አሁንም ከእኔ ጋር ነው።”

“ውሸት!” ብላ ኒኪ ከመለሰችለት በኋላ ግን ደውላ ወደዚህ እንዳስመጣቻትና እንዲሁም ደግሞ በዊሊ ባደን ግድያ ላይ ስለነበራት ድርሻ ምን ይሆን? ብላ
1👍1
ራሷን ስትጠይቅ ስሜቷን አረጋጋች፡፡

“ከብዙ ጊዜ በፊት ነበር አንቺን ማስወገድ የነበረብኝ” ብሎ ሉዊስ ማውራቱን ቀጠለ “ባይገርምሽ ገና ከሚስቴ ጋር ከመገናኘታችሁ በፊት ነበር
ላስወግድሽ የነበረው:: አየሽ ገና በርክሌ ወደ አንቺ ቢሮ ለቴራፒ ህክምና
ሲመጣ እና ዕብደቱ ሲጀምረው ነበር ላጠፋሽ የነበረው።”

“ካርተርን ነው የምትለኝ?” አለችው ኒኪ በግርምት ተሞልታ። ካርተር
በርክሌይ ከዚህ ጋር ምን የሚያገናኘው ነገር አለው::”

ሉዊስም ፈገግ ብሎ “የእውነት አታውቂም አይደል?”

“አላውቅም” ብላ መለሰችለት፡፡

መልካም ዶክተር ሮበርትስ እንደርሱ ከሆነማ አጭር ተረት ልንገርሻ?
ነገሮችን አገጣጥመሽ እንድትደርሺባቸው እና ዘና እንድትይ አስቤ ነው
ታዲያ ይህንን ተረት የምተርክልሽ፡፡ በድሮ ጊዜ አንድ ሰውዬ ነበር። ይሄ ሰው ግን ወጣት ሳይሆን ከወጣትነት ዕድሜው በትንሹ ያለፈ ሰው ነበር::

ብሎ ሉዊስ የተዋናይ ድምፅ በሆነ መልኩ ትረካውን ቀጠለ፡፡ ድምፁ
የሆነ ደስ የሚል እና ድንዘዝ የሚያደርግ ነገር አለው። ስለዚህም ኒኪ እሱ
እንዴት አድርጎ ወጣቷን አኔን በዚህ መልኩ እንደሚጫወትባት እያሰበች
ትረካውን ማዳመጥ ቀጠለች።

“ሰውዬውን ከሜክሲኮ ሲቲ ከተማ በጥቂት ማይል ርቀት ላይ ከሚገኝ
ጫካ ውስጥ እንደሚገኝ አስቢው፡፡ ቦታው ሞቃት ነው፤ ጨለማ ጊዜ ላይ::
ጨረቃዋ ሙሉ ናት፡፡ ለወራቶች ያህል በጣም የሚያስደስተውን ለስላሳ
የወጣት ገላውን እንደዚያን ቀን አስደስቶት አያውቅም። ያን ዕለት ማታ ሰውዬውን በጣም የተለየ ምርጥ ምሽትን እንዲያሳልፍ ታደርገዋለች::”

ኒኪ ውስጧን ብርድ ብርድ
ሲላት ይታወቃታል። ሰውነቷም
መንቀጥቀጥ ጀመረ። ይህንን ሲያይ ደግሞ የሮድሪጌዝ ፊት በደስታ በራ::
ባለፈው ካርተር በርክሌይን ስታክመው የነገራትን ነገር እያስታወሰች በቀድሞ
ትውስታዋ ውስጥ ተመስጣ ትስመው ጀመር “ቦታው የተመነጠረ ነው::
ምሽት ነበር፡፡ ጭለማ ቢሆንም የጨረቃ ብርሃን ግን ነበር። በጣም ይሞቃል”
የሚለው የካርተር በርክሌይ ድምፅ ጆሮዋ ላይ ደወለባት።

“ስትመጣ አያት” ሮድሪጌዝ ትረካውን ቀጠለ “ሜዳውን እየተደናቀፈች
አቋርጣ ስልኳ ላይ ያለውን የካርታ አድራሻንም ተመለከተች፡፡ ቀይ ፀጉሯ
እሷ ስትራመድ በግራ እና በቀኝ ይወዛወዛል። ረዥም ናት። በጣም ረዥም
ቀጭን ሸንቀጥ ያለች። በእግሮቿ የተሰባበሩትን የዛፍ ቅርንጫፎችን
እየረገጠች ስትመጣ የአዳኝ አይን ውስጥ የገባች ሚዳቆ ትመስል ነበር። ምርጥ ነገር! በጣም ቆንጆ ናት። በዚያ ላይ ደግሞ ገና ለጋ ወጣት? ከእኔ
ጋር ነሽ ዶክተር ሮበርትስ?”

ኒኪ ራሷን በአዎንታ ነቀነቀችለት፡፡ አሁን ሁሉ ነገር ግልፅ ሆነላት። ነገሮቹን ገጣጥማ የሆነ ነገር ላይ ደርሳለች፡፡

“ቻርሎቴ ክላንስ! የምታወራው ስለ ቻርሎቴ ክላንሲ ነው አይደል?”

“በጣም ጎበዝ ነሽ” ብሎ ሮድሪጌዝ ገለፈጠና “ ከሁሉም ነገሯ ሰውዬው
ወደ እሷ እንዲሳብ ያደረገው የዋህነቷ ነበር:: የሆነ እሱ ጋር የሌለው ነገር
ስለነበር ይህንን ነገሯን በጣም ይወድላታል፡፡ ከረዥም ጊዜያት በፊት እሱም ወጣት ነበር፡፡ ግን እንደ እሷ አልነበረም። ሁለቱም የተለያዩ ዓለም ሰዎች ናቸው። ኮከባቸው ሊገጥም የማይገባ ነበር ግን እንዲሁ በድንገት የገጠመ ሆነ። ይሄው ወደ እሱ እየሮጠች ስትመጣ ያያታል።”

“ከዚያስ ምን ተከሰተ?” ብላ ኒኪ ጠየቀችው:: ስትጠይቀው ልክ
ታካሚዎቿን ውስጣቸው ያለውን ነገር እንዲያወጡ በምትጠይቅበት መልኩ
“ከዚያማ ሰውዬው ከመኪናው ውስጥ ወጣ እና ቀስ እያለ ለመቶ ጫማ
ያህል ወደተመነጠረው ቦታ ሄደ። እዚያ ስትደርስ ሰላም ብሎ ሊቀበላት አስቦ
ነው እንግዲህ።” አላት እና ሮድሪጌዝ
የወሲብ ስሜት ተቀስቅሶበታል። ደስ ብሎታል፡፡ ይህንን ነገር ደግሞ
በጣም ይፈልገዋል እና እዚያው ጭለማው ውስጥ እንዳለም

“ቻራ!” ብሎ ጠራት፡፡

“እዚህ ነኝ ፍቅሬ!” አላት ልክ የቻርሎቴን ድምፅ አስመስሎ፡፡ “ከዚያም የተመነጠረው ቦታ ላይ ደረሰች፡፡ ከእሱ 10 ጫማ ርቀት ላይ እያፈረች ቆመች። ወደ እሱ ልትመጣ ስትንቀሳቀስ ግን በእጁ እዚያው እንድትቆም ነገራት፡፡ እዚህ ቦታ ላይ እንደዚህ ቆማ ለዘላለም ሊያስባት እንደሚፈልግም ነገራት።

ይታይሻል አይደል?” አላት ሉዊስ ኒኪን፡፡
“አዎን ትታየኛለች” አለችው እና በመቀጠልም “ግን እኮ ገና 18 ዓመት
የሆናት ልጅ ናት፡፡ ሉዊስ ምንድነው ያደረግካት?” ብላ ጠየቀችው፡፡

እሱም በትንሹ ጎንበስ ብሎ አመስግኖ አሾፈባት እና ትንሽ ስቆም “ልክ ነሽ በድጋሚ ዶክተር ሮበርትስ። ወጣቷ ልጅ ቻርሎቴ ስትሆን ሰውዬው ደግሞ እኔ ነበርኩኝ፡፡ ደርሰሽበታል በእውነት ጎበዝ ነሽ፡፡ ያኔ ከሁለተኛዋ ሚስቴ ጋር ተጋብቼ እኖር ነበር፡፡ ይሄ የሆነው አኔን ከማግኘቴ ከጥቂት ዓመታት በፊት ነበር፡፡ የሚገርም የበጋ ወራት ከቻርሎቴ ጋር በፍቅር
አሳልፌ ነበር፡፡ ግን እንደ አለመታደል ሆኖ ቻርሎቴ መሄድ የማይገባትን
መንገድ ሄዳ ድንበሬን አለፈች፡፡
የጀመርኩትን ነገሮች ከመጨረስ በስተቀር ምንም አይነት ምርጫ አልተወችልኝም ነበር።”

ምን አደረግኳት? አዎን ቀሚሷን እንድታወልቀው ነገርኳት። ልክ እንደ
አኔ ሁሉ እሷም እኔ ጫና እንዳሳድርባት ትፈልጋለች: ትዕዛዞቼን ለመፈፀም
ሁሌም ዝግጁ እና ጉጉም ነበረች” አላት እና ሁኔታውን አስታውሶ ምራቁን
ከዋጠ በኋላ አቤት እጇን ወደ ላይ ከፍ አድርጋ ከጥጥ የተሰራው ልብሷን
ስታወልቅ አሁን ድረስ አይኔ ላይ አለ።
ፖም የሚያካክሉ የሚጣፍጡ መካከለኛ ጡቶች አላት። ልሙጥ ያለው ሆዷም ከፖንቷ በላይ ይታየኛል፡፡ ዋው! ምንኛ ተአምር ነበር መሰለሽ ዶክተር ሮበርት። ከዚያም ደንሺልኝ አልኳት። እሷ ግን በጣም ከማፈሯ የተነሳ ልትደንስልኝ አልቻለችም። ስለዚህ እንድትደንስልኝ ትንሽ እገዛ አደረኩላት፡፡ ከዚህ በፊት የሰው ልጅ በአውቶማቲክ ጠመንጃ በተከታታይ ሲመታ አይተሽ ታውቂያለሽ?” አላት እና አስፈሪ ሳቁን ስቆ “አይተሽ
የምታውቂ አይመስለኝም፤ መሬት ላይ ከመውደቃቸው በፊት ህይወታችው
ወጥቷል፡፡ ግን መሬት ላይ ከመውደቃቸው በፊት አየር ላይ የሚያደርጉት መንቀጥቀጥ፣ መዝለል፣ መንዘፍዘፍ እና እግራቸውን በተለያዩ አቅጣጫዎች በማይታመን ሁኔታ የሚያወናጭፋቸው ነገር እንዴት ደስ ይላል መሰለሽ:: ምን ያደርጋል ታዲያ መጨረሻ ላይ መሬት ሲወድቁ ይሄ ሁሉ አስደናቂ ዳንሳቸው ያበቃል።” ቀጠለናም

ካርተር በርክሌይ የእኔ ባንከር ነበር፡፡ ደስ ይለኝ ነበር። ግን በቃ በጣም ሁሉ ነገሩ የተቋጠረ ሰው ነበር። ለማንኛውም ቻርሎቴ በምታሳየው ትርዒት ትንሽ ይዝናና ብዬ ስላሰብኩኝ ነበር ያን ቀን ይሄው ወደ ቦታው ያመራሁት፡፡ እሱ ስለሆነ ያስተዋወቀን ቢያንስ ትንሽዬ
ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህም እሱን የሚያስደስት ነገር እንዳዘጋጀሁለት ነግሬው ነበር በእኔ መኪና ይዤው የወጣሁት፡፡ ግን ምን ያደርጋል ባየው ነገር መኪና ውስጥ ተቀምጦ በፍርሃት እና በድንጋጤ ይንቀጠቀጥ ጀመር።
ይመስለኛል ቻርሎቴ እንደዋዛ የምፈቅድለት መስሎት ነበር እዚህ
የመጣው።” አላት እና ከት ብሎ ሳቁን ለቀቀው፡፡

“ደግሞስ ለምንድነው በቻርሎቴ እንዲዝናና የምፈቅድለት? ምክንያቱም
የእኔ የሆነ ነገር ሁሉ የእኔ ብቻ ነው”
ኒኪም የነገራትን ነገር ለሰኮንዶች ያህል እያሰበች ዊሊያምስ ከመሞቱ
በፊት የነገራትን ነገር አስታውሳም
“ስለዚህ ካርተር አሜሪካዊ ባንከር እና ባለ አረንጓዴ ጃጉዋር መኪና ባለቤት ብቻ ነበር ማለት ነው:: ስለዚህ እሱ ሳይሆን አንተ ነበርክ ፍቅረኛዋ?”

“እኔ እንጃ ፍቅረኛ እባላለሁ ብለሽ ነው?” አላት

ካርተር እስከ አሁን ላንተ እየሰራ ነው?”
ሉዊስም ፊቱን አጥቁሮ “የእኔ ድርጅት
👍4
እኮ እንደ ባንክ ያለ ድርጅት አይደለም፡፡ ሰዎች በፈለጋቸው ጊዜ ተቀጥረው የሚሰሩበት ባልፈለጉ ጊዜ ደግሞ ለቅቀው የሚወጡበት ድርጅት አይደለም፡፡ አንዴ የእኔን ድርጅት ከተቀላቀልሽ የእኔ ቤተሰብ ሆንሽ ማለት ነው። መውጣት አይቻልም” አላት በጣም ምርር ባለ ድምፅ፡፡...
እንዳለመታደል ሆኖ ከዓመታት በኋላ ካርተር በርክሌይ ሥራውን በአግባቡ የማይሰራ የድርጅታችን አባል ሆኖ አረፈው። በተለይ ደግሞ አንቺ ጋ
መታከም ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ”

“ድርጅት ስትል የአደንዛዥ ዕፅ አምራቹን ድርጅትህን ማለትህ ነው?” ብላ ኒኪ ጠየቀችው፡፡

እንደዚያ እንኳን አይደለም ናርኮቲክስ እና የሪል ስቴት ቢዝነሳችን ቅርንጫፎች ናቸው፡፡

አበት!” አለችው ኒኪ ጠንከር አድርጋ። መሞት ካለባት እሱ በሚፈልገው መንገድ መሆን የለበትም፡፡

“ያንተ ሪል ስቴት ቢዝነስ እኮ ከአደንዛዥ ዕፅ ያገኘኸውን ከፍተኛ ትርፍ የምታዘዋውርበት ቢዝነስህ ነው፡፡ ለጋሽነትህም ቢሆን ያው ነው። አንተ
ክሮክ በመሸጥ ነው ህይወትህን የምትኖረው። ስለዚህ አንተ ተራ ኑሮ
በመኖር ላይ ያለህ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ ነህ።” አለችው።

ሉዊስም ራሱን ግራ እና ቀኝ ወዘወዘ፡፡ ምንም የንዴት ፊት አላሳያትም።
ምናልባት ሰዎች ሲገዳደሩ ደስ የሚለው አይነት ሰው ነው።

“ዶክተር ሮበርትስ በመጀመሪያ ደረጃ እኔ ክሮክዲል አይደለም ዋነኛ ንግዴ፡፡ እኔ የማቀርበው ኮኬይን ነው። ምክንያቱም ይህንን ምርት ሰዎች ይፈልጉታል። ኮኬይንን የፈጠርኩት እኔ አይደለሁም። በቃ መንገድ ላይ ነው የተገናኘው::” አላት፡፡

ኒኪ አይኗን አጥብባ በጥላቻ አይን እያየችው “ይሄ ዕፅ ሰዎችን ምን
እንደሚያደርጋቸው መቼስ አይጠፋህም?”

“አውቃለሁ። እኔ ብቻ ሳልሆን ተጠቃሚዎቹም ጭምር ያውቁታል፡፡ እኔ
በደንበኞቼ ምርጫ ተጠያቂ ልሆን አልችልም” አላት እና ያለ ምንም እፍረት
ከመለሰላት በኋላም በርክሌይም በዚህ ጉዳይ ላይ ሊጠየቅ አይችልም፡፡
በምዕራቡ የሀገሪቱ ዳርቻ ላይ ምርጥ የሂሳብ ሠራተኛዬ በመሆን ለብዙ ጊዜ
ቆይቷል፡፡ በቃ ፍራቻው ሳይጀምረው በፊት ምርጥ ሠራተኛዬ በመሆን ለብዙ
ጊዜ ቆይቷል። ከጊዜ በኋላ የሆነ ነገርን መልሶ ማሰብ ተገቢ አይደለም”
“ለማንኛውም በድንገት በርክሌይ ለእነዚህ ደሀ እና የማይረቡ የአደንዛዥ
ዕፅ ተጠቃሚዎች ከልቡ ማዘን ጀመረ።” አለ እና ሮድሪጌዝ በመቀጠልም
“ደግሞ ባይገርምሽ የድርሻውን ሂሳብ ከተቆረጠለት በኋላ መሆኑ ያስቀኛል::
የተሰማውን ሀዘን ለቴራፒስት መዘርገፉን አይጠላውም። ነገር ግን ከእኔ ቢዝነስ የወሰደችውን ሚሊዮን ዶላሮችን መመለስ አይፈልግም። አየሽ በጣም
ስግብግብ እና ደካማ ሆነ። ልክ እዚህ ተሰቅሎ እንዳየሽው ሚ/ር ባደን ነው
ሥራው የሆነብኝ፡፡”

ኒኪም በሀሳቧ ካርተርም የዚህ ቀለበት አካል ነበር ማለት ነው። ለዚህ
ነው ሲያስጠነቅቀኝ የነበረው አለች፡፡ “ባደን እዚህ ውስጥ እንዳለበት ይሄው
ራሱ ነግሮኛል። ደግሞ ሌሎቹ ፓለቲከኞች ወይም ደግሞ ከንቲባው ራሱ እዚህ ውስጥ ይገኛል ብሎ ነበር ዊሊያምስ የነገረኝ? ፖሊሶች እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በሙሉ ከሮድሪጌዝ የክሮክዲል ትርፍ ተቋዳሽ ናቸው ማለት ነው:: ብላ እያሰበች እያለች

“ዶክተር ሮበርትስ ሎስ አንጀለስ ውስጥ ብዙ ስህተቶችን ስሠራ ነበር፡፡” አላት እና ሮድሪጌዝ ሽጉጡን ተመልክቶም “የመጀመሪያው ስህተቴ በርክሌይን ማመኔ ነው:: ካርተር ብልህ ሰው ቢሆንም ቦጅቧጃ ነገር ነው::ደፋር ሰዎች ደግሞ ለዚህ ቢዝነስ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ሁለተኛው ስህተቴ ደግሞ ቫለንቲና ባደን ከባሏ ዊሊ ጋር ሥራን እንድሠራ ስትጠይቀኝ እሺ
ማለቴ ነው፡፡ በዚህም ደግሞ ሌላኛውን ትልቁን ስህተት ሰራሁኝ ማለትም
አንድ ሽባ ግሮልሽ የተባለ ልጅን አንቺን እንዲገድልልኝ መቅጠሬ ነበር።
በዚህም በጣም የሚያስጠላ ስህተትን ሊፈፅም በቃ::”

ይህንን የሰማችው ኒኪም ሽምቅቅ አለች፡፡ ምክንያቱም ብራንዶን እንኳን ሰው ዝምብ ሁሉ የሚገድልበት ጨካኝ ልብ አለው ብላ ልታምን አልቻለችም፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ከማንም በላይ የረዳችውን ወይንም ደግሞ ልትረዳው የሞከረችውን ሴት ሊገድል መስማማቱ ምን ያህል የሮድሪጌዝ አደንዛዥ ዕፅ እሱ ላይ እንደተጫወተበት ነው ያሳያት።

“ልጁ በጣም ሱስ ውስጥ ጠልቆ እንደገባ እና እንደዚህ አይነት ሥራ
ሊሰራ እንደማይችል ማወቅ ነበረብኝ፡፡ ግን ቫለንቲና እሱ ጉዳዩን እንደፈጸመው ክፉኛ አምናበት ነበር። ሱሱ ሰውነቱን በጣም ሳይጎዳው በፊት እሱ እና እሷ ፍቅረኛሞች ነበሩ።” አላት፡፡

“ይህ በፍፁም የማይሆን ነገር ነው። ቫለንቲና እኮ በዕድሜ አያቱ ልትሆን የምትችል ሴት ናት” አለችው ኒኪ፡፡
ሮድሪጌዝም ትከሻውን ሰብቆ “ሱስ እና ፍቅር ውስጥ ምንም አይነት የዕድሜ ገደብ የለም ዶክተር ሮበርትስ። ሟቹ ባልሽ ይሄ ይገባው ነበር፡፡አንቺ ግን አሁንም እርጥብ ነሽ፡፡ ለማንኛውም ይህቺ ሸርሙጣ አሮጊት የእሷ
የሆነ ፍቅረኛ ለእሷ ብሎ ሰው የሚገድልላት ሀሳብ በራሱ መስጧት ነበር
ብራንዶን ዶክተር ሮበርትስን ያውቃታል፤ የእሷ ችግር የለውም ዕድሉን ስጠው ብላ ነበር በጉዳዩ ላይ ያሳመነችኝ፡፡ እኔም በወቅቱ ገና ከጓደኞቼ ጋር ሥራ የጀመርኩበት ጊዜ ስለነበር እነርሱን ለማስደሰት ብዬ የእሷን ሀሳብ
ተቀበልኩኝ፡፡ ይሄ ግን ድድብና ነበር” ብሎ ሉዊስ ጭንቅላቱን በምሬት ወዘወዘ፡ እና “በጣም አሰቃቂ ነገር እኮ ነው። በቃ ግሮልሽ ማድረግ የነበረበት ነገር ሲኖር አንቺን ከቢሮሽ እስክትወጪ ድረስ ጠብቆ ልብሽ ላይ ጩቤ መሰካት ብቻ ነበር። ማለቴ ይሄን ማድረግ እንዴት ነው የሚከብደው? እናም የዚያን ምሽት ሊዛ ፍላንገን ያንቺን የዝናብ ኮት ደርባ ካንቺ ቢሮ ስትወጣ ተመልክቶ ተከተላት እና ገደላት፡፡ ወይም ደግሞ ልክ እንደ ጨርቅ
ቆራረጣት። ምን አይነት ስህተት እንደሆነ ይገባሻል?

“ብራንዶን ልጅቷን ከገደላት በኋላ የእኔ ሰዎች ሬሳዋን የማፅዳት ሥራቸውን ሲሠሩም ስህተት ተፈጠረ። በችኮላ ሥራቸውን ስለሰሩም ጥፍሯ
ውስጥ የዚያን በክሮክ ሱስ የነተበውን እና የበሰበሰውን የቆዳ ህዋስ ሳያፀዱ
ቀሩ። ፖሊሶችም የህዋሱን ባለቤት በዲ.ኤን.ኤው ሊለዩት ቻሉ፡፡ ስለሆነም
የግድያ ምርመራ እና ሚዲያዎች ዜናውን በማራገብ ቡድኖች እና ብራንዶንን
ተስፋ እንዲቆርጡ አደረጓቸው:: በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ ግን አንቺ በህይወት
መኖር ቀጠልሽ፤ በተለይ ደግሞ የኔን አኔን እያገኘሽ”

ብሎ የሚስቱን ሥም ከጠራ በኋላ ሙሉ ፊቱ ተቀያየረ፡፡ በድንገትም ዘና ብሎ የሚያወራ ድምፁ ተቀየረ እና ጥላቻውን በደንብ በሚገልፅ መልኩ
እያፈጠጠባትም ሎስ አንጀለስ ውስጥ ከሚገኙ ከ1000 በላይ ቴራፒስቶች ውስጥ ሚስቴ አንቺ ጋ መጥታ ህክምና መጀመሯ ይገርመኛል፡፡ አይገርምም? ባንከሬ የሆዱን ክፋት ለማውራት የመረጣት ሴትን እሷም መምረጧ ግን
አይደንቅሽም?”

ላይገርም ይችላል ምናልባት ካርተር እኔ ጋ መጥቶ ህክምናውን እንደሚከታተል የሚያውቅ ሰው ይበልጥ አደጋ ውስጥ ለመክተት አስቦ ወደ እኔ ጠቁሟት ሊሆን ይችላል ስትል አሰበች ኒኪ፡፡

በተጨማሪ ብራንዶን ግሮልሽ እሷን ለመግደል ገንዘብ መቀበሉን እና
በስህተት ምስኪኗ ሊዛን መግደሉ ምን አይነት አጋጣሚ ሊሆን ይችላል?
እንድትረዳው እና ይቅርታ እንድታደርግለት ጭምር ለምኗት አልነበር?ድንቄም ይቅርታ! እያለች በውስጧ ተብሰለሰለች፡፡ አእምሮዋን ያነበበ ይመስል

“አትሳሳች” አላት እና ሉዊስ ከሀሳቧ አናጠባት፡፡ “ገና ካርተር ወደ አንቺ
ቢሮ መጥቶ ህክምናውን መውሰድ የጀመረ ቀን ላይ ነበር ያንቺ የሞት ወረቀት የተፈረመው ግን አየሽ ያኔ ጉዳዩ በግል የሚመለከተኝ አልነበረም።ነገር ግን አኔን ማግኘት ስትጀምሪ
👍2
ነገሮች ሙሉ በሙሉ ተለወጡ።” አላት አይኖቹን አጥብቦ እየተመለከታት ቀጠለናም “ዶክተር ሮበርትስ በጣም ነው የጠላሁሽ” አላትና ሮድሪጌዝ ስለ አኔ ማውራቱን ቀጠለ። እንዴት በመኪናዋ እና በኪስ ማስታወሻዋ ላይ የመቅጂያ መሳሪያ ገጥሞ ሲሰልላት እንደቆየ ነገራት። በዚህም የእሱን አኔን ለመቀማት ብላ እንዴት አድርጋ አዕምሮዋን ስትመርዛት እንደነበር በማወቁ የተነሳ እጅግ እንደጠላት ጭምር ነገራት::

ሉዊስ ስለ አኔ እያወራት እያለም ኒኪ ልታመልጥበት የምትችልበት መንገድ እንዳለ ማሰብ ጀመረች። ሉዊስ ሮድሪጌዝ ትንሽ አዕምሮው የተወሳሰበበት ሰው እንደሆነ ለማየት በቅታለች። ይህንን ደግሞ ልትጠቀምበት ትችላለች። ያለበለዚያማ ምኑን ሳይኮሎጂስት ሆነችው ታዲያ? ማውራቱን እንዲቀጥል እና ለራሱ የሚሰጠው ከፍተኛ ግምትም
ጊዜን እንደሚሰጣት ጭምር አሰበች። በህይወት ለመቆየት እስከፈለገች ድረስ
ደግሞ አዘናግታው ሽጉጡን ከእጁ ላይ ማስጣል ይኖርባታል።

ከዚያስ? መሮጥ ይኖርባታል። ወዴት? ምናልባት ሁለቱ ሰዎች አኔን ይዘው በወረዱበት አሳንሰር ወደ ታች መውረድ ትችል ይሆናል። ግን ደግሞ
ሽጉጡን አስጥላው እሷ እጅ ውስጥ ማስገባት ከቻለች ያኔ አሽናፊ ትሆናለች፡፡ ያም ሆኖ ግን ኮሪደሩ ላይም ሆነ በኮሪደሩ ግራ ቀኝ ከሚገኙት
ቢሮዎች ውስጥ የእሱን ሽጉጥ ለማስጣል የሚረዷት ነገሮች የሉም።
ቦርሳዋን እንኳን አልያዘችም፡፡ እጇ ላይ የሚገኘውም የመኪናዋ ቁልፍ ብቻ
ነው፡፡

በይበልጥ በትክክለኛዋ አዕምሮዋ ስለማምለጥ ባሰበች ቁጥር ውስጧ
የነበረው መረጋጋት እየጠፋ እና ፍርሃቷም እየተቆጣጠራት መጣ፡፡ አሁን ለመሞት ዝግጁ አይደለችም፡፡ በተለይ ደግሞ ዛሬ ማታ ያውም በአንድ በሰው ስቃይ በሚደሰት ሰው እጅ:: ስለዚህ ከዚህ ሞት የምታመልጥበት መንገድ የግድ ሊኖር ይገባል።

ጉድማን ወደ ሳን ጁሊያን መንገድ ሲታጠፍ ሸሚዙ በላብ ከመበስበሱም
በላይ የእጁ ላብም የመኪናውን መሪ እንዲያሟልጭበት አድርጎታል፡፡
ፍርሃት ሆዱን አሞታል፡፡ ፊቱንም አገርጥቶታል፡፡ አፉ ክው ብሎ
ከመድረቁም በላይ የልቡ ምት በጣም ስለፈጠነበት መተንፈስ አቅቶታል፡፡

በውስጡ ያለው አድሬናሊን ግን ፍርሃቱን አሸንፎ እርምጃ እንዲወስድ አስገድዶታል። መኪናውን አቆመና ከመኪናው ወርዶ ሽጉጡን በማውጣት
እየሮጠ ወደ ህንፃው መጠጋት ጀመረ። በውስጡ የሚገኘው በህይወት
የመቆየት ደመነፍሱ አሸናፊ እንደሚሆን ነግሮታል፡፡ ይህም ፍርሃቱን በግድም ቢሆን እንዲውጠው አድርጎታል።

ይሄ ነው ጉዳዩ። አድርግ ወይንም ሙት!

ህይወት ወይንም ሞት!

መንገዱ ጭር ብሏል። አንዳንድ ከሴቶች ልብስ ማምረቻ የሚወጡ አርፋጅ ሰራተኞች ስምንተኛው ጎዳና ላይ ወደሚገኘው ባቡር ጣቢያ እያመሩ
ይገኛሉ። ማንም ሰው ጉድማን መኪናውን አቁሞ ወደ መጋዘኑ ህንፃ ሲያመራ ጉዳዬ አላለውም፡፡ ከህንፃው ሰላሳ ያርድ ሲቀረው ግን ሁለቱ ጥቁር በ ሙሉ ልብስ የለበሱ ሰዎች አንዲት ሴትን መሀል አድርገው ሲመጡ ተመለከታቸው እና ተደበቀ፡፡ ከተደበቀበት ቦታ ሆኖ ሲመለከት ሴቷ አኔ ቤታማን መሆኗን አወቀ፡፡ ሰዎቹ አኔን አንድ መኪና ውስጥ አስገቧት እና ከመኪናው ሹፌር ጋር ጥቂት አውርተው እንዳበቁም መኪናው ወደ ሌላኛው የሳን ጁሊያን መንገድ ጫፍ በፍጥነት መንቀሳቀስ ጀመረ። ሁለቱ ሰዎችም መኪናው ከተንቀሳቀስ በኋላ ሽጉጣቸውን አወጡ። በህንፃው በተለያየ
አቅጣጫም ተንቀሳቀሱ፡፡ ከሁለቱ ውስጥ አንደኛው ሰው ከህንፃው ፊት ለፊት ቁጢጥ ብሎ አካባቢውን መቃኘት ጀመረ፡፡

ጉድማን ከሁለቱ አንደኛው ሰው እጅ ላይ ያየው ደም የማን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ጀመረ:: ገና ፖሊስ ጣቢያ ሆኖ የገመተው ነገር ትክክል እንደሆነ እርግጠኛ ሆኗል፡፡ አዎን ሉዊስ ሮድሪጌዝ እዚህ ህንፃ ውስጥ ይገኛል፡፡ ሉዊስ ደግሞ ዶክተር ሮበርትስን በፍፁም እንደማይምራት ያውቃል።

ሽጉጡን በእጁ ጨብጦ ምን ማድረግ እንደሚገባው ማውጣት እና ማወረዱን ቀጠለ። እሱ ብቻውን ነው ሮድሪጌዝ ደግሞ ቢያንስ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ሰዎች አሉት፡፡ ተጨማሪ ሀይል እንዲመጣለት ማድረግም ይችላል፡፡ ትክክለኛው አሰራሩም እንደዚያ ነው፡፡ ሁለቱን የሮድሪጌዝን ሰዎች አሸንፎ ወደ ውስጥ መግባትን ማሰብ ደግሞ እጅግ አደገኛ ቁማር ነው::

ምናልባት ህንፃው ውስጥ ብዙ የሮድሪጌዝ ሰዎችን ሊያገኝ ይችላል። ይሄ
ደግሞ ሞትን መሻት ነው የሚሆነው።

ዙሪያውን ሲቃኝ በቀኝ በኩል ቀጭን መተላለፊያ እንዳለ ለማየት ቻለ። ስፋቱ ሞተር ሳይክል ብቻ ነው ሊያሳልፍ የሚችለው፡፡ ምናልባትም ህንፃውን
ለመጠገን ሲባል የተተው ቦታ ሊሆን ይችላል። እንደምንም ተደብቆ ከጠባቡ
ቆጣሪዎችን ተመለከተ። ወለሉ ላይም የትቦ መድፈኛ የሆነ ፍርግርግ ብረትን
መተላለፊያ ውስጥ ገባ፡፡ ግድግዳው ላይም ሁለት የተቆለፈባቸው የመብራት
ቆጣሪዎች ተመለከተ።ወለሉ ላይም የትቦ መድፈኛ የሆነ ፍርግርግ ብረትን
ተመለከተ፡፡ ብረቱን በሀይል ወደ ላይ ሲስበውም ወደ ህንፃው የምድር ክፍል
የሚያስገባው ጠባብ ዋሻ መሰል ቱቦን ለማየት ቻለ፡፡

ወጥመድ ውስጥ የገባ አይጥ አይነት ስሜት እንዲሰማው ስለሚያደርጉት
ጉድማን እንደዚህ ያሉ ጠባብ ቦታዎችን
አይወድም ለማንኛውም ብረቱን
በሀይል ወደ ላይ ሲስበውም ወደ ህንፃው የምድር ክፍል የሚያስገባ ጠባብ
ዋሻ መሰል ቱቦን ለማየት ቻለ።
ለማንኛውም ብረቱን ሲስብ ድምፁ ስለተሰ ውጪ ካሉት ሁለት ሰዎች አንዱ ወደ እዚህ ቦታ መምጣቱ አይቀርም::
ሲመጣ እና ጉድማንን ሲያገኘው ደግሞ ምንምንኩዋ ሳይጠይቀው እንደሚተኩስበት እርግጠኛ ነው፡፡ ይሄ በራሱ ደግሞ ሌላ ችግርን መፍጠር ስለሆነ ብረቱን እንደያዘ ወደ ውስጥ ገባ እና በላዩ ላይ ብረቱን ዘጋ፡፡

በጠባቡ ዋሻ መሰል ቱቦ ወደ ታች እየወረደም በውስጡ በኒኪ ሮበርትስ
መናደድ ጀመረ፡፡

ደደብ አመፀኛ ሴት! ለምንድነው እዚህ ድረስ ብቻዋን የመጣችው? የአኔ
ቤታማንን ትዕዛዝ ሰምታ እና እንደ በግ ለመታረድ እንዴት እዚህ ነገር ውስጥ ዘልላ ትገባለች? የዴሪክ ዊሊያምስ ሞት በራሱ እንዴት ማስጠንቀቂያ
ሊሆናት አልቻለም እያለ በውስጡ ይቃጠል ጀመር፡፡

ኒኪ ቆንጆ እና ብልህ ሴት ልትሆን ትችል ይሆናል፤ ነገር ግን ራሷን ልትወጣበት ከማትችለው ጥልቅ ውሃ ውስጥ ነው የተከተተችው፡፡ የውሃውን ጥልቀት ደግሞ በደንብ የሚያውቀው ጉድማን ነው::....

ይቀጥላል
👍1
#የወድያነሽ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


...«አይዞሽ አትፍሪ! እዚህ እኔ አልጋ ላይ ወጥተሽ ተኚ፡ ስንገባ ማንም አላየ» ብዬ እየተርበተበትኩ በሩን ዘግቼባት ውልቅ አልኩ፡፡

በድንኳኑና በምድረ ግቢው ውስጥ ግማሽ ሰዓት ያህል ከተዘዋወርኩ በኋላ
አንዳች አካላዊ ኃይል እየገፈትረና እያፍነከነከ ወደ መኝታ ቤቴ ወሰደኝ፡፡ ሰውነቷ በሥራ ድካም በመቀጥቀጡ አንቀላፍታ ስለ ነበር ከደረቷ በላይ ገልጬ አየኋት:: ዘና ብላ በጀርባዋ በመተኛቷ እንቅስቃሴው የሰከነ ውበት ረቦባታል።

የአካላቴን ኃይለኛ ሰደድ ለመቀነስ የተከደኑ ዐይኖችዋን እና የተገጠሙ
ከንፈሮቿን ዳበስኳቸው:: በወዲያነሽ ልብ ውስጥ ልዩ የሆነ የመኖሪያ ዓለም
አሰስኩ።

አንድ ራሴን ለመቆጣጠርና ለመግታት ያልቻልኩበት የነዳድና የአካላዊ
ውጥረት ቅፅበት ደረሰ፡፡ በስተራስጌ በኩል አልጋው ጫፍ ላይ ዐረፍ ስል ነቃች።

ዐይኖቿ በፍቅር ቦግታ ልባዊ መስተንግዶ አደረጉልኝ፡፡ ወዲያው ፊቷን አዙሪ ሆድና ጉልበቷን አጣብቃ በፍርሃት እየተንቀረቀበች ተኛች፡፡ ከጎኗ ጋደም
አልኩ፡፡

ከገላዋ ላይ በወጣው ሙቀት ለብ ያለው የብርድ ልብስ ውስጥ ኣየር የሚያፍነከንክ ደስታ ሰጠኝ፡፡ ልብሷን በሙሉ አወላልቃ በመተኛቷ ገራገርነቷ ከፍላጎቴ ኃይል ጋር ትንቅንቅ ገጠመ፡፡

አንድ ኃይለኛ የሥጋዊ ፍላጎት ግፊት ናጠኝ። ራስን በመግታት ለፍላጐት በመንበርከክ መካከል የቀበጠ ፍልሚያ ተፈጠረ፡፡ የየወዲያነሽ ሕይወት
በእኔ ግድየለሽነት የሚሰናከል መሰለኝ፡፡

«ፍላጐቴን ፈጽሜ ስሜቴን ካረካሁ በኋላ የወዲ ያነሽን እስከ ዘለቄታው
ለመርዳትና በፍቅር ፀንቼ አብሬያት ለመኖር ያለኝ ቆራጥነትና የሕሊና ጥንካሬ
እስከ ምን ድረስ ነው?» እያልኩ በማውጣትና በማውረድ ከራሴ ጋር ትግል ጀምርኩ፡፡ ከራሴ ጋር የማደርገውን ክርክር ሳልደመድምና ኃላፊነቱን ለመሸከም ሳልወስን፡ የየወዲያነሽንም የሕይወትና የኑሮ ሁኔታ አንድ አቅጣጫ እስይዤ ሳልወስን ዕቅፌ አባበልኳት፡፡

ተመሳሳይ ፍላጎቶች ይዋሐዳሉ ሆነና ሰምና ወርቅ ሆንን፡ የልቧ ምት አየለ። የአተነፋፈሷ ፍጥነት በውስጧ ከፍተኛ የስሜት ሲቃ እንዳለ እወጣጡ
ይገልጻል። ለአጭር ጊዜ ትንፋሿን ዋጠች፡፡ ድንገት በመኻሉ የልቅሶ ድምፅ
ሰማሁ፡፡

«ወይኔ እናቴ! ምነው ያንቺን ቀን በሰጠኝ፡፡ ወይኔ ዕድሌ ወይ አለመታደሌ” ብላ ያመቀችውን ትኩስ አየር ለቀቀችው:: እንባዋ እንደ ጎርፍ ይወርድ ጀመር፡፡ በረጂሙ ከተነፈሰች በኋላ ወይኔ ዛሬ ፡ አዬ መከራዪ አዬዬ አበሳዬ!» ብላ በግንባሯ ተደፋች፡፡ ቀጣዮቹ ደቂቃዎች ምን ሊገጥማት እንደሚችል ወለል ብሎ ታይቷታል፡፡ ምንም እንኳ ለቅሶዋና የሚንስፈሰፈው ሰውነቷ ርኅራኄ ቢያሳድሩብኝም አካላዊ ፍላጎቴን ጎትተው የሕሊና ገደብ ሊገድቡብኝ አልቻሉም፡፡ የስሜቴ ልጓም ተበጠሰ፡፡ የልመናዋን መንደርደሪያ ቃላት ከመጤፍ አልቆጠርኳቸውም፡፡

“ይህ ሁሉ ልቅሶና ልመና ይከዳኛል ብለሽ ይሆን? ቃል እገባልሻለሁ አልከዳሽም፡፡ ምንም ቢባል ምንም ቢመጣ እስከመቼም ቢሆን አልከዳሽም፡ ይህ
ፍቅራችን ምስክሬ ነው » ብዬ ደንበኛ የልብ ማጥመጃ ቃል ገባሁ፡፡

ከዚያ በኋላ ቦርቧራ ልቧንና ንጹሕ ልቦናን በአንደበቴ ተጫንኳቸው:: ከግማሽ ሰዓት በኋላ የድንግልናዋን ኪላ ጣስኩት፡፡ እዩዩዋ አንጎሌ ውስጥ ሠረፀ።በመኻሉ የወዲያነሽ እኔ በምሰማው ሁኔታ ብቻ ኡኡ ልትል ስትል አፏን በአፌ ከደንኩት፡፡ ሕሊናዋን ስታ ዧ ብላ ተዘረረች፡፡ ተዝለፈለፈች፡፡ ልቤ በርህራሄና በሀዘኔታ ተንፈራፈረች፡፡

ከአልጋው ላይ ዘልዬ ወረድኩና የተቻለኝን ያህል ረዳኋት፡፡ የሌሊቱን ቀዝቃዛ አየር አርገበገብኩላት፡፡ ድካሟን አቃልዩ ብርታት ልሰጣት ባለመቻሌ በንዴት ተከንኩ። ያም ሆነ ይህ አንዴ ለተፈጸመ ነገር ሌላ አዲስ ፈጻሚ የለውምና እንደገና መብራቱን አጥፍቼ ከጐኗ ጋደም አልኩ። በደረቷ ተደፍታ ለጥ አለች፡፡

ከእንቅልፌ ስነቃ ከሌለቱ ዐሥር ሰዓት ነበር፡፡ በደማቁ የመብራት ብርሃን
በጥቃት የፈዘዘ ውበቷን አየሁት። መኝታችን ተበክሏል። የየወዲያሽ ማራኪ
ዐይኖች ትንገርበዋል፡፡ መብራቱን አጥፍቼ እንደገና ጋደም አልኩ፡፡ ሕልም መሰል
ቅዠቶች እየረከረኩኝ አለፉ፡፡ ዳግመኛ ስነቃ ዐሥራ አንድ ሰዓት ከሃያ ነበር፡፡
የጭንቀትና የፍርሃት ናዳዎች አንጎሌ ውስጥ እየጓኑና እየተውዘገዘጉ ሰላም
አሳጡኝ፡፡ ልብሴን ለበስኩ፡፡ የመኝታ ክፍሌን መስኮት ከፍቼ አሻግሬ ማየት
ጀመርኩ፡፡

የማለዳዋ ፀሐይ ልትወጣ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ቀርተዋል፡፡ ከሩቅ
የሚታየው ምሥጢራዊ አድማስ ያልያዘ ግሽርጥ መስሏA። ጎህ ቀደደ። ሰማዩ
በብርሃን አውታሮች ተሽነሸነ፡፡ ጋቢዬን ደርቤና የመስኮቱን ደፍ ተደግፋ የምድረ
ግቢውን የጨለማና የንጋት ውጋት የመጨረሻ ግፊትና የተተከለውን ድንኳን
በዐይነ ችላ አየሁት። ወገገ፡፡ የማለዳው ቀዝቃዛ አየር አካባቢውን በዝግታ ሲያስስ
የእኔም አንጐል በልዩ ልዩ ሐሳብ ተፈተሽ፡፡

የድግሱ አሳላፊዎችና አስተናባሪዎች እንዲሁም እንግዶች ከመነሣታቸው
በፊት የወዲያነሽ መውጣት ስላለባት አልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጥኩ፡፡

ግራ እጄን አሾልኬ ርኅራኄ ባጀበው ሁኔታ አንገትና ደረቷን ዳበስኩ:: እውነትም ጥሩ መላ ኖሮ ሳትደነግጥ ነቃች፡፡ ገለጥ ስትል ዐይን ለዐይን በመጋጨታችን ዐይኖቿ በኃፍረት ተሰበሩና ተሸፋፈነች፡፡

የተፈጸመው ሁሉ መታየትም ሆነ መሰማት ስለሌለበት በስጋት ተቅበጠበጥኩ፡፡ ከወላጆቼ በኩል እጅግ ከፍ ያለ የውርደትና የቅሌት ዶፍ
ቃላት እንደሚደርስብኝ ዐውቃለሁ፡፡ እሷም ባልታሰበ የመከራ ውርጂብኝ
እንዳትጐዳ በማሰብ «እስኪ እንደ ምንም ብለሽ ቀና በዪና ተነሽ» ብዩ ትሕትና
ባልተለየው አኳኋት ጠየቅኋት።

ፈገግ ብላ ቀና ስትል ልቤ በደስታ ተለጠጠች፡፡ የደቂቃዎቹ መደራረብና
መተካካት ሙሉ ንጋትን አስከተለ። የአፍንጫዋን ጫፍ በጣቴ እያነቃነቅሁ ከእኔ ጋር ተኝተሽ ማደርሽ እንዳይታወቅና እንዳይሰማ ሰው ሁሉ አንዳንድ እያለ
ከመነሣቱ በፊት ሹልክ ብለሽ ሒጂ» ብዩ ግዴታ የተቀላቀለበትን ንግግሬን
አሰማኋት። ምንም እንኳ ተኝታ ለማርፈድ እንደማትችል ብታውቅም ለጊዜው
ፊቷ በኃዘን ቅጭም አለ። ዐይኖቿ ቀዘዙ፡፡ የሐሳብ ጋሬጣ ጠቀጠቃት፡፡ ልብሷን
ለባብሳና ጸጉሯን እንደ ነገሩ ጎንጉና ከፊት ለፊቴ ቆመች፡፡ ሥቃይዋ አንጀቴን
አላወሰው:: እንደ ሰረቀ ሰው ተሸሽጋ እና ሹክክ ብላ ማንም ሳያይና ሳይሰማ
ወጥታ ሔደች፡፡ ያደረግሁት ድርጊት አስጸያፊና የግድ የለሽነት አሠቃቂ
ተግባር እንደሆነ ገባኝ፡፡ በፍቅር ስም የተፈፀመ ወንጀል፡፡ የእኔ ነገር ግመል ሠርቆ አጎንብሶ ሆነ፡፡ ሆኖም ግብ የለሽ ጸጸት ከተቃወሰ ሕሊና የሚፈልቅ የልቦና እድፍ በመሆኑ በብስጭት ታጥቦ አይጠራምና ድርጊቴ ክፉ አፉን እንደ ከፈተ ቀረ።

ራሴን ከሐሳብ ወጥመድ ነፃ ሳላወጣ፣ ከግራም ከቀኝም ከደጅም ከቤትም
የሰው ድምፅ ተስማ። አንድ ሰዓት ተኩል ላይ ከሰው ጋር ተደባለቅሁ፡፡ ወዲያ
ወዲህ አላልኩም፡፡ ከመኝታ ቤቴ ፊት ለፊት እንግዳ መቀበያው ክፍል ውስጥ
ጉብ አልኩ፡፡

በየወዲያነሽ ልብ ውስጥ አንጸባራቂ እምነት በማስቀመጤ ትነግርብኝ ይሆን? ጉዴን ፀሐይ ታሞቀው ይሆን? በማለት እምብዛም አልሠጋሁ። የውብነሽ
ያደረ ፊቷን ውሃ እንኳ ሳታስነካ ተፍተፍ ስትል መጥታ ያንን የእኔን እረንጓዴ
ፎጣ አንተ መኝታ ቤት ውስጥ አይቼው ነበር» ብላ ብሩን ከፍታ ዘው አለች።
ሰውነቴ የጥቅምት ውርጭ እንዳደረበት ብረት በድንጋጤ ቀዘቀዘ፡፡ ተነሥቼ ለመሸሽ ትንሽ ነበር የቀረኝ ዐይኔ በድንጋጤ ፈጥጦ አፌ ከመቅፅበት ኩበት ሆነ።ድንገት ከጭንቀቴ ምጥ ተገላገልኩ ፎጣውን አንጠልጥላ ተመለሰች፡፡ ልክ እንደ ሰከረ
👍3
ሰው እየተፍገመገምኩ መኝታ ቤቴ ውስጥ ገባሁ፡፡የእኔና የወድያነሽን ድብቅ ድርጋት ግን ያ በሚገባ ያልተነጠፈውና በዘፈቀደ
የተዘረጋው የብርድ ልብስና የአልጋ ልብስ ሽፍነው ሰወሩት።

መጀመሪያውኑ ያለመጠንቀቄና ልብሶቼን ገለል ያለማድረጌ የፈጠረው ስሕተት እንደ ትልቅ ጋራ ተገትሮ ታየኝ። ሁኔታው ባለመጋለጡ የልቤ ምት ቀነሰ፡ ረቂቅ ውስጣዊ እፎይታ አገኘሁ።

እናቴ የቤቱንና የእንግዶቹን ሁኔታ ለመመልከት ከላይ ታች ስትል
እኔም ለወሬ ቃሪማ ተከትያት ምድር ቤት ወረድኩ።

የወዲያነሽ ከአንድ ትልቅ የብረት በርሜል አጠገብ ለደረቆት ማስጫና ለኮቸሮ ማድረቂያ ተብሎ በተገዛ አዲስ ሰሌን ላይ ተኮራምታ ተኝታ አገኘናት። ከሰሌኑ ላይ ቀሚሷን ጣል አድርጋ ነጠላ ብጤ ለብሳለች።

ከአባቴ ጋር አንዳችም ግንኙነት እንደሌላት በመረጋገጡ የእናቴ ጥርጣሬ
ተወግዷል። የወዲያነሽን በጣም ስለ ወደደቻትና በሥራዋም አንጀቷ በራሱ
ወዲያው እንዳየቻት «ውይ! ዐፈር በበላሁት! ይቺን ልጅ ምን ነካብኝ?» ብላ
አጎነበሰች፡፡ «እቴ እመመሽ እንዴ?» ብላ ርኅራኄዋን በሚያስረዳ ለዛማ ድምፅ
ጠየቀቻት። እናቴ «እቴ» ብሎ የመጥራት ልማድ አለባት። የወዲያነሽ ቀና ብላ
ከተቀመጠች በኋላ «ይኸ ራሴ እንደ ድንጋይ ነው የከበደኝ፡ መነሣት አቅቶኝ ነው “ዝም ብዩ የተኛሁት» ብላ ጉልበቷ ላይ በግንባሯ ደፋ ኣለች።

እናቴ እንደገና ከመናገሯ በፊት «ታዲያ ምንስ ቢያምንና መነሣትስ ቢያቅትሽ ከዚህ ከመንገዱ ላይና ከሰው ፊት ዘወር ማለት አቃተሽ እንዴ? ምን ነውር የማትፈራ ናት እባካችሁ?» በማለት አደናጋሪ የውሸት ቁጣ ተቆጣሁ፡፡

እናቴ ወደ እኔ መለስ ብላ «አንተ ምን ችግር አለብህ ልጄ! የሞላለት
ድመት ሳምባ ያማርጣል” ይላሉ መምሬ መታፈሪያ፡፡ «ታዲያ ለጊዜውስ ቢሆን
የት ትተኛ ብለህ ነው? አልጋዋን እንደሆነ ለእንግዳ ሰጠንባት፡፡ እሳቸውም
የትላንቱ ስካር ተጭኗቸው ይኸው እስካሁን ንቅንቅ አላሉም፡፡ ኧረ ምን በወጣት ድሃዋ ! ለእኔስ አይመምብኝ፡፡ እሷው ናት ያለችኝ፡ ግን ከወዲያ ወዲህ ብሎ ሊሠራልኝ?» ብላ ዐይኖቿን ወደ የወዲያነሽ መለሰቻቸው፡፡

እሱስ እውነትሽን ነው» እልኳት ሐሳቧን ከሐሳቤ ጋር ለማገናኘት ያህል። «ግን እንደ አህያ ሬሳ እዚህ ሜዳ ላይ ተፈንችራ ብትታይ ምን ጥቅም አለው?» ብዬ ልቀጥል ስል እናቴ በፀያፉ ንግግሬ ተቆጥታ ክፉኛ ገላመጠችኝ፡፡
እኔም ውስጤ እንደቀለለ ተሰማኝ፡፡ “ማለቴ» ብዬ ነገሬን ለማረቅ ተነሳሁ «ሌላ
ቦታ ሔዳ አንጥፋ ትተኛ ወይም ለጊዜው እኔ መኝታ ቤት ወለሉን ጠርጋ ጋዳም ትበል። ባይሆነ ማታ በደንብ አድረጋ ትወለውለዋለች» ብዬ ስውር ጥቅም
ያንዠረገገ ሐሳብ አቀረብኩ፡፡ እናቴ በሐሳቡ በመስማማቷ፡ የወዲያነሽ ሌላ ንጹሕ ሥጋጃ አንጥፋ እኔ መኝታ ክፍል ውስጥ ተኛች፡፡ በእኔ ስውር ምክንያትና በእናቴ የዋህነት መካካል አንዳች የሚሐል የሐሳብ ልዩነት ነበር ከጥቂት
ደቂቃዎች በኋላ ነገሩን በማረሳሳት ቀስ ብዬ ገብቼ ያን አልፎ አልፎ ጃኖ የመሰለ
አንሶላ ሽምልዩ ሳጥን ውስጥ ቆለፍኩበት፡፡ በምትኩም ሌላ ልብስ እነጣጥፈ ወጣሁ፡፡

ሰው ሁሉ ያደረ ሆዱን ለመሙላት በየመዐዱ ዙሪያ ተኮልኩሎ ስለ ነበር
እኔም «ለእኔ ነው» ብዬ ለየወዲያነሽ ጥሩ ቁርስ ይዤላት ገባሁ።ሽብረክ ብዬ ፊቷን ካየሁ በኋላ «በይ ተነሺና አልጋው ላይ ወጥተሽ ተኚ፡ ማንም ገብቶ እንዳያይሽ በሩን ቆልፌብሽ እሔዳለሁ፡፡ ቅድም በእናቴ ፊት የተቆጣሁሽና የጮሁኩብሽ ዐውቄ ነው:: እንዲያ ባልቆጣና ይህን ብልሃት ባልጣበብ ኖሮ አንቺን እዚህ ማስገባት አልችልም ነበር፡፡ ማታ ተመልሼ ስመጣና ይህን በር ስከፍት ኣልጋው ላይ መተኛትሽን ሌላ ሰው እንዳያይ ድምፄን ከሩቅ ስትሰሚ ቶሎ ወርደሽ ወለሉ ላይ ተኚ» ብያት ስነሣ ቀና ብላ ተቀመጠች፡፡ ድንገት ሳላስበው ጫማዩ ላይ ዘፍ አለች፡ እድራጎቷ ከመጠን በላይ ዘገነነኝ። ሆኖም ሆነ ! ቀስ ብዪ አልጋው ላይ ካስተኛኋት በኋላ በሩን ከውጭ ቆልፈባት ሔድኩ፡፡
ሊደረግላት የሚገባው ክብካቤ ይህ ባይሆንም በአካሏ ላይ ለደረሰው ጉዳት
ጸጥታማ ዕረፍት እንኳ ታገኝ ዘንድ ሆን ብዬ ወደ ቤት ሳለመለስ ዋልኩ።

ከዐስራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤት ገባሁ፡፡ ብቻዋን ተዳፍኖባት በመዋሏ
ልባዊ ቅሬታ እንከረደደኝ፡፡ ምንም እንኳ ከአልጋ ወርዳ መሬት ላይ መተኛቷን
ደስ ባልሰኝበትም ጊዜውና ሁኔታው በማስገደዱ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ እንደ ደረስኩ ከእናቴና ከየውብነሽ ጋር ጎላ ባለ ድምዕ ሰላምታ ተለዋወጥኩ። የድምፂ ጉላት የሚጠቅመው ግን እኔን በመጠባበቅ ላይ ለነበረችው ለየወዲያነሽ ነበር፡፡ በሩን ከፍቼ ስገባ እንደተባባልነው ተኝታ አገኘኋት። በየወዲያነሽ አልጋ ላይ ያደሩት ሽማግሌ ሌላ አሮጌ አልጋ ስለ ተሰጣቸው የወዲያነሽ እልጋዋ ላይ ተኛች።

ቀን በቀን ላይ ተደራረበ፡፡ አድራጎታችን ሁሉ ሳይሰማ አያሌ ሳምንታት ዐለፉ፡፡ እያደር ግንኙነታችን እየለማ የፍቅራችን አዝመራ አበበ። የልቦቻችን ብርሃናዊ የፍቅር ገመድ እየጠበቀ ደመቀ፡፡ ከዚያም ምን ጊዜም ቢሆን በሌሎች ሰዎችና በቤተሰቦቼ ፊት አንቱ» ለብቻችን ስንሆን ግን «አንተ» ወይም «ጌታነሀ» ብላ እንድትጠራኝ ተስማማን፡፡ ለተዋሃዱ ተማማኝ ልቦች አዳጋች ነገር የለምና ወዲያው ለመደችው:: ምንኛ ደስ ይላል፡፡

ጊዜው ገሠገሠ፡፡ አንድ ዓመት ከመንፈቋ እንደዘበት ነበር ሆነ። የውብነሽ
እዳዲስ ልብሶች ባስቀደደች ቁጥር አርጀትጀት ያለባትንና ወረቱ ያለቀበትን
ትሰጣት ነበር፡፡ ይህም የሁለቱ መግባባትና መፋቀር በእናቴና በየወዲያነሽ መካከል የነበረውን ተራ ግንኙነት ኮላው።
የየወዲያነሽ ሕይወትና ኑሮ ሌላው የሕይወቴ ገጽታ በመሆኑ ዕለታዊ
ብስጭቷና የኑሮዋ ሽክረት ይቆረቁረኛል። ከትምህርት ቤትና ከዚያም ውጭ
ጥቂት ሴቶች ዐውቅ ነበር፡፡ ዐልፎ ዐልፎም አንድና ሁለቱን የወደድኩበት ጊዜ ነበር።

የወዲያነሽን ካፈቀርኩ በኋላ ግን አኳኋኔ ሁሉ ከቀድሞው የተለየ ሆነ፡፡ ስለ ቀድሞዎቹ የነበረኝ ስሜት ሁሉ ተራ ትዝታ ሆነ፡፡ ያጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ ያጋጠሙኝ ሴቶች ወረተኞች ስለ ነበሩ ግንኙነታችን ሁሉ ውሎ ሲያድር የተቀጠፈ አበባ ውበት ሆኖ ቀረ። ይህም በመሆኑ ስሜቴ ተገማሽሮ የፍቅርን ልዩ ለዛ ያሞገስኩበት ቀን አይታወሰኝም፡፡

ከየወዲያነሽ ጋር ያለኝ ምዑዝ ፍቅር ግን ልዩና ጠንካራ በመሆኑ ሌሎቹን ሁሉ ደመሰሳቸው:: የእርሷም በቤታችን ውስጥ ሠራተኛ መሆን ቅንጣት ታህል ቅር አላሠኘኝም፡፡

አንዳንድ ጊዜ ያቺ በውስጤ የምትፍለከለከዋ ጤዛ የምታህል ወኔዬ
ድንገት በምትገነፍልበት ጊዜ «ከዛሬ ጀምሮ ከትክክለኛ አመለካከት ውጭ
የሆነውን አስተሳሰብ ለመቋቋምና ለመበረቃቀስ ቆራጩ እነሣለሁ፡፡ በወዲያነሽ የተነሣ ምንም ዐይነት መጥፎ ሁኔታና አደጋ ቢደርስብኝ ግንባሬን አላጥፍም፡፡

«ከእንግዲህ ወዲያ የትልቅ ሰው ልጅ አጥንተ ጥሩ እና ደመ ንጹሕ
በሚለው ከንቱ አሮጌ እምነት በጭራሽ አላምንም፡፡ በእኔና በእርሷ መካከል የኑሮ
ደረጃ፣ ሀብታምና ድሃ ሆኖ የመወለድ ልዩነት እንጂ በተፈጥሮ ሰዉነት መበላለጥ ስለ ሌለ እስከ ዘለቄታው ከእርሷ ጋር መኖር እችላለሁ፡፡

«የአስተሳሰባችን ያለ መቀራረብ የሚያስከትለውም ችግር እንዲወገድ
የጋራ ጥረት ማድረግ ይቻላል፡፡ እኔና እርሷ በሰውነታችን ፍፁም እኩል መሆናችንን እኔዉ ለእኔ ማረጋገጥና ማሳወቅ ይኖርብኛል» እያልኩ በሐሳብ ሽቅብ
እመጥቅና እንደገና ደግሞ ቁልቁል ወርጄ ዘጭ እላለሁ፡፡ በሐሳብ ሠረገላ ላይ
ተቀምጩ የሐሳብ ልጓም ስስብና ስለቅ አያሌ ቀናት ዐለፉ፡፡

እናቴ ከራት በኋላ የተፈላውን ቡና እንዳከተመች ከተቀመጠችበት
ትንቡኬ ወንበር ላይ በዝግታ ተነሥታ ከደረቷ
👍5
ውስጥ የተቋጠረ መሐረብ
አወጣች፡፡ ቁም ነገረኛነትን ለመግለጽ በሚውተረተሩ ቃላት ለመናገር ፊቷን
ፈገግታ እየነሣች የድሃ ጉልበት ጥሩ አይደለም ልጄ! የድሃ እንባም ለልጅና
ለልጅ ልጅ ይቆያል፡፡ ትውሰድና ያፈቀዳትን ታድርገው፡ ይኸውልህ የአራት ወር
ደሞዟ» ብላ በመሐረብ የተቋጠረ ገንዘብ ጥላልኝ ወደ መኝታ ቤት ገባች። ከራት
በኋላ የውብነሽ ወደ መኝታ ቤቷ ስትገባ እኔም ወደ ክፍሏ ሄድኩ፡፡ የደሞዝ
መፈረሚያውን መዝገብ አውጥቼ አጭሯን የደመወዜን ተቀብያለሁ ሐተታ
ከጻፍኩ በኋላ የወዲያነሽን እንደ ተለመደው ጠራኋት፡፡

በጻፍኩት ውስጥ ተጨማሪው አዲስ ነገር፡ ላለፉት አራት ወሮች ጉልበቷ
ለእያንዳንዱ ወር የአንድ ብር ጭማሪ ማግኘቷ ብቻ ነበር፡፡

እንደ ቀድሞው ሳይሆን በጣም ተጠግታ አጠገቤ ቆመች፡፡ ደሞዟ ከፌት ለፊቷ ተቀምጦ ነበር፡፡ የቀኝ እጅ አውራ ጣቷን ነጥዩ ይዤ ቀለም ልለቀልቃት እጄን ሾል ሾል ሳደርግ አውራ ጣቷን ከእጄ ውስጥ እሾለከቻት፡፡ ጣቷን ወደ ውስጥ ዐጥፋ ባራቱ ጣቶቿ ሥር ቆለፈቻት፡፡ በአካባቢው ሰው ያለመኖሩን ቀደም ብላ በማረጋገጧ በሩን ዘጋችው:: ከዚያም ጎንበስ ብላ የተጻፈውን ጽሑፍ አንጠርጥራ አነበበችው:: የያዝኩትን ብዕር ወስዳ ከጽሑፉ በስተቀኝ ግርጌ
«የወዲያነሽ አሽናፊ» ብላ እሳምራ ጻፈች፡፡ ብዕሩን ጣል አድርጋ ትከሻዬን ተመርኩዛ ቆመች፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ደነገጥኩ። ያየሁትን ማመን አቃተኝ፡፡ ለመቀመጥም ለመነሣትም ዐቅም አጣሁ፡፡ መንፈሴን አንዳች አስደሳች
ነገር ከወዲያ ወዲህ ናጣት፡፡ ቀና አልኩና ትኩር ብዬ ተመለከትኳት፡፡ በፊቷ ላይ
የተለመደው እንጂ ልዩና አዲስ ፈገግታ አልታየባትም።

እኔ ግን ስለ አዲሷ «እሷ» ሳስብና በማላውቀው የሕይወቷ ምስጢር
ውስጥ ስጠልምና ስወጣ ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ፡፡ ማንበብና መጻፍ የምትችል በመሆኗ ወሰን የለሽ ደስታና ተስፋ አጥለቀለቀኝ። ወዲያው 'ለምን? ብባል ወዲያው መልስ መስጠት አልችልም።

የአቀማመጤን አቅጣጫ ቀይሬ የወዲያነሽ ከፊት ለፊቴ እንድትቆም
አደረግሁ፡፡ ከዚያም ሁለቱንም እጆቿን ይዤ አንጋጥጬ እያየሁ «የወዲያነሽ የት
ተማርሽ? ማን አስተማረሽ?» ብዬ ባጭሩ ጠየቅኋት፡፡ ፈገግታዋ ውስጥ ውስጡን
ለሚንፈቀፈቀው የደስታ ስሜት እጁን ሰጠ፡፡ ውብ ማራኪ ድምጿም ሰለለ።

«ወይኔ ተላሊት! አንተን ያስደሰትኩ መስሎኝ ተሳሳትኩ» ብላ ከንፈሯን
መጠጠች። ከጥቂት ዝምታ በኋላ «ከተውኩት ይኸው እንግዲህ ከሁለት ዓመት በላይ ሊሆን ነው» ብላ አሁንም እንደገና ትንፋሿን አንዳች ዝም አርጌ ነገር ወደ ውስጥ የመጠጠው ይመስል በዚያው ጸጥ አለች።

«እናሳ?» ብዩ ከያዛት የዝምታ ወጥመድ ባላላቅቃት ኖሮ ዝምታዋ በዚያው ማርኮ ሊያስቀራት ነበር፡፡ «ምኑን እናሳ' አልከኝ፡ አሁን እንዲህ ውሃ በልቶት ሊቀር ለወጉ ያህል እስከ ሰባተኛ ክፍል ተምሬ ነበር» ብላ ትጨርስ እንባ ካረገዙት ዐይኖቿ ላይ የእንባ እንክብሎች እየተሽቀዳደሙ ወረዱ፡፡
ኀዘኗና እንባዋ የልቤን ጣራና ወጋግራ አነቃነቀው:: አንጀቴ ተላወሰ፡ ነፍሴ ሰተት ብላ ትካዜ ረግረግ ውስጥ ተዘፈቀች፡፡

ገንዘቡን አንስታ ከቆጠረች በኋላ ኀዘን ባደቅቃት ድምዕ “እንካ አንተው ጋ
አስቀምጥልኝ» ብላ ኮቴ ኪሴ ውስጥ ወሽቃው ጥላኝ ወጣች።

አንዳንድ ቀን ማንም ሳይሰማና ሳያውቅ ወደ መኝታ ቤት እየገባች ከእኔ ጋር ማደሯ በታላቅ ጥንቃቄ ቀጠለ። ሆኖም ሁል ጊዜ በሕሊና ዐይኖቼ ፊት ፈታኝ የሆነ የውድቀት ፈተና እንጂ የተስፋ ውጋገን አልታየኝ አለ፡፡

የፈጸምኩትንና ያጋጠመኝን ነገር ሁሉ ብቻዬን ስለተሸከምኩት የሐሳብ ጭነት ከበደኝ፡፡ ምስጢሬን አፍኜ እስከወዲያኛው ለመዝለቅ ያለኝ ቆራጥነትና ብርታት እንደ ትቢያ በነነ፡፡ አካላቴ በሥጋት ተመነጠረ፡፡

አስፈላጊውን ምክርና ብልሃት ወይም ሌላ ርዳታ ሊያገኝልኝና ሊያደርግልኝ፡ የወዲያነሽንም ከመከራ ለማዳን የሚቻልበትን ቀና ሐሳብ ሊያካፍለኝ የሚችለው ልብ ሰፊዉ የልብ ጓደኛዬ ጉልላት ብቻ እንደሆነ ተገነዘብኩ፡፡....

💫ይቀጥላል💫


ግን እንዴት ነው ድርሰቱ እየተመቻቹ ነው? ዝም አላችሁ እኮ እስኪ አብሮነታችሁን Like 👍 በማድረግ አሳውቁኝ።
👍6
#ሕልመኛ_ተጓዥ

( .. ተቀበል . . . )

በመንገድኽ ኹሉ ዕንቅፋት አትፍራ
ተማርበት እንጂ በእውቀት አትኩራ።

መውደቅኽ ምሳሌ ፣ ሸክፈው እንደ ጓዝ።
ድሎትን አትውደድ ፣ የንዋይን ጉዝጓዝ፡፡

ስሕተትኽን ግደፍ ፤ መርምር በረቂቁ
በመጠረቡ ነው ፤ አልማዝ ማብረቅረቁ፡፡

የጅራፍ ቁግ አጥብቅ ፤ ግመድ አታቅማማ
ካልገረፉት አይጮኽ ፣ ካልጮኸ አይሰማ።

ደዌን አትሽሸው ፣ መርምር በጽሞና
ከችግር አይደል ወይ? መፍትሔ ሚጠና።
አስተውል ፣ ተመልከት! መርምር በአርምሞ
ማንም ሰው አይድንም! ካልታመመ ቀድሞ።
(ደዌን አትሽሸው ፣ ይልቅስ መርምረው
ከመታመም ላይ ነው! መድኅን ሚገኘው።)

“የሕልሜ ሳቢሳ፤
ሾተልኽን አንሣ
ሊበላኝ ነበረ ፣ ቶሎ ባልነሣ።
የሕልሜ ነብር
ይብላኝ ነበረ ፣ ተኝቼ ብቀር።”
ይህ ነው ያ'ንተ ግጥም!
ይህ ነው ያ'ንተ ዜማ !
በነቂስ አትመን . . .!
ግምትም አትጣ . . .!
ልብኽንም ስማ።
ይህ ነው ያ'ንተ ዜማ !
ይህ ነው ያ'ንተ ግጥም !
ያለ መሰናክል፣
ያለ አንዳች ዕክል፣
ሕይወት ፍጹም አይጥም።


🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
👍2