አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ጢስ ከክፍሉ አየር ጋር ተቀላቅሎ ከወዲያ ወዲህ ሲርመሰመስ ቤቱን ጭጋግ የለበስ ሜዳ አስመስሉታል፡፡

የውብነሽ መለስ ብላ ጥልፏን ቀጠለች፡፡ የእኔ ሐሳብ ግን ከሁለቱ መኻ ተነጥሎ በመሄድ ዐይኖቼ የሚመለከቱትና የሚከታተሉት አዲሷን ሠራተኛና
በአጠቃላይም አኳኋኗን ነበር። እናቴና እህቴ ስለምን ጉዳይ እንደሚያወሩና
እንደሚጫወቱ ለመከታተል አልቻልኩም፡፡ ዐይኔም ቀልቤም ከሠራተኛይቱ
አካባቢ ውልፍት ሳይል ቡናው ፈልቶ ወረደ።

«እስኪ ትንሽ ቁርስ አምጪ፡ ዕጣኑንም አጭሱልን» ብላ እናቴ ስትናገር
ከእንቅልፉ እንደ ባነነ ሰው ነቃሁ፡፡ ዕጣኑ ጨሶ ቡናው ሰከኖ ተቀዳ፡፡

እናቴ በትንሿ ሳህን ላይ የቀረበችውን የነጭ ጤፍ እንጀራ ጉልበቷ ላይ
አድርጋ ከቆራረሰቻት በኋላ በጥቃ ጎረሰች። እኔም ደረሰኝ፡፡ የውብነሽ ቡና ይዛ ወደ መኝታ ቤት በመግባቷ አባቴ እንደማይመጣ አረጋገጥኩ፡፡ እኅቴ ቡና
አደለችን፡፡ አዲስ ሠራተኛ በተቀጠረች ቁጥር ለአንድና ለሁለት ቀን መርዳትና
ሥራውን ሁሉ ቀላል ማስመሰል በቤታችን ውስጥ የተለመደ በመሆኑ የውብነሽ
ከሊጡ ወጡ ማለት አላስደነቀኝም፡፡ የአዲሲቷን ሠራተኛ የቡና አፈላል ችሎታ
ለማየት ስል አከተምኩ። የጠጣሁት ቡና ግን ከሌላው ጊዜ ልዩነት ወይም
የማይረሳ ጣዕም አልነበረውም። እንዲያ እንዲያ ስል ጊዜው ተዋገደና ከምሽቱ
ሦስት ሰዓት ሆነ።እህቴ የምትጠልፈውን ጨርቅ አስቀምጣ ጋቢ ለብሳ ጉብ
አለች። እናቴም ባዘቶውን አገልግሏ ውስጥ ለጉማ ወደ መኝታ ቤት ገባች፡፡

ረዘም ላለ ጊዜ በፀጥታና መላቅጡ ባልታወቀ ሃሳብ ተውጦ በመቀመጡ
መላ አካላቴ በድንገተኛ ትካዜ የተወረረ መሰለ። እናቴ ከወደ መኝታ ቤት
ብላ «እስኪ እነዚያን እነ አይገባሽን እነገልማጭ የለሽን ራት አቅርቡ በያቸው
ብላ ተመለለች፡፡ የውብነሽ ጋቢዋን ወንበር ላይ ጣል አድርጋ ከድሮዎቹ ሁለት
ሠራተኞች ጋር ራት ለማቅረብ መለስ ቀለስ አሉ፡፡ እንግዳይቱ ሠራተኛ ግን ወደ
ዕቃ ቤት በሚያስኬደው ጥግ አንገቷን ሰበር አድርጋ ቆመች፡፡ ያሰበችውን እንጃ!
እምብዛም ሳትቆይ ወደ ዕቃ ቤት ገባች፡፡

ከወላጆቻችን ራት በኋላ ሠራተኛቹ መዐዱን ወደ እንግዳ መቀበያ ክፍል
አምጥተው ትንሿ ክብ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጡት፡፡ መዐዱ ወደ ተቀመጠበት
ሄድኩ፡፡ ምን ጊዜም ቢሆን ራት የሚቀርብልን ከወላጆቻችን በኋላ ነበር፡፡
የውብነሽ ከጐኔ እንደ ተቀመጠች አንደኛዋ ሠራተኛ አስታጥባን ተመለሰች።
ወሬያችንን እያወራን መብላት ጀመርን። ከእኔና ከእኅቴ በስተቀር በክፍሉ ውስጥ
ሌላ ሰው አልነበረም፡፡ የሚበቃንን ያህል በልተን ለመጥገብ ብዙ ጊዜ አልፈጀብንም። ዝቅ ባለች ቀጭን ቀብራራ አጠራር «አንቺ አስካለ ! ነይ እንጂ
መዐዱን አንሺው» ብላ የውብነሽ ተጣራች፡፡ የማንኛቸው ስም እንደ ተጠራ
ያላወቁና ያላጣሩ ይመስል ሁለቱም ሠራተኞች ተግተልትለው መጡ፡፡ እንደገና
«ሌላ ዝርግ ሳህን ይዘሽ ነይ» በማለቷ እስካለ ቀልጠፍ ብላ ሔደች፡፡

ዝርግ ሳህኑን ይዛ እንደ ተመለሰች የውብነሽ ወጥ ከነካካው ትርፍራፊ
ላይ እንጀራ ቀንሳ በዝርጉ ሳህን ላይ በተን አደረገች። በሁለቱም ሳህኖች እንጀራ
ላይ ወጥ ከወጣ በኋላ አስካለ የተሰጣትን ገበታ ይዛ ወደ ዕቃ ቤት ስትገባ ያቺን እንግዳይቱን ልጅ ነይ ትባያለሽ በያት» ብላ አዘዘቻት፡፡ የታጠብንበትን ውሃ ከያዘችው ሠራተኛ ጋር ወደ ውስጥ ገቡ፡፡

የተጠራችው አዲስ ሠራተኛ አቀርቅራ መሬት መሬቱን እያየች ጥጉን ይዛ ቆመች፡፡ «ነይ እንቺ ራትሽን ወስደሽ ብዪ፡ ወጥ ያነሰሽ እንደሁ ያመጡልሻል፡ እንዲያውም እኔ አለሁ» ብላ በቀኝ እጅዋ የያዘችውን ሳህን ለማቀበል ስትዘረጋ ወዲያው ደርሳ ተቀበለቻትና ወደ መቀመጫዋ ተመለሰች።

ለመቀመጥ ጉልበቷን አጠፍ ስታደርገው ጉልበቶቿ ቀጫጭን ጭራሮዎች የተሰበሩ ያህል ቋቅጭ አሉ፡፡

አማከለች ከሔደች ጀምሮ የእኔንና የራሷን አልጋ የምታነጥፈው እኅቴ ስለነበረች አልጋዎቹን ለማንጠፍ ወደ መኝታ ቤት ገባች፡፡ ሠራተኛዋ እንጀራውን ከፊት ለፊቷ አስቀምጣ በረሃብ እንደ ተጉዳ ሰው ሳይሆን በጐረምሳ መኻል እንደምትመገብ ዐይነ አፋር ልጃገረድ በትንሿ እየቆረሰች መብላት ጀመረች።
እንጀራው ላይ አንዳች አስፈሪና ተናካሽ ነገር ያለ ይመስል ለጉርሻ የምትሆናትን
ቁራሽ ስታስተካክል እጅዋ ይንቀጠቀጥ ነበር። ጉልበቷ ወደ ኋላ ታጥፎ ስለ ነበር
ከወደ ወገቧ ወደ ፊት ጐብጥ ብላ ደረቷ ከጭንዋ ላይ ዐርፎአል። በጣም ቀስ ብላ
ስለምታላምጥ ከንፈሮቿ የሚላወሱት በጣም በዝግታ ነበር።

የአንድን ነገር የተፈጥሮ አቀማመጥና ቅርፅ፣ መልክ፣ ውስጣዊና ውጫዊ
እንቅስቃሴዎች እየመረመረ እንደሚያጠና ባለሙያ ሠዓሊ ሰውነቷንና አለባበሷን ስንዝር በስንዝር ዐይኔን እያንሸራተትሁ ተመለከትኳት።በክፍሉ ውስጥ የበራው ደማቅ ብርሃን የፈለግሁትን ነገር ሁሉ በበቂ ሁኔታ ለማሳየት በቂ ድምቀት ነበረው።

ዐልፎ ዐልፎ የአበባ ሥዕል ያለበትና እጅግ በጣም አዳፋው ቀሚሷ
ከጉልበቷ በታች ሆን ብለው ሁለት ሦስት ቦታ ላይ በስለት የተለተሉት ይመስላል። ያቀሚሷ ተራ ሽንሽን ተተርትሮ ቀሚሷ ከረጢት መስሏል። ትጥገብም እትገብም እንጃ መብላቷን ተወችው። በእጀ ጉርድ እጅጌዋ በኩል ብቅ ብሎ የሚታየው እጇ ጥላሸት የጠጣ ደረቅ ዕንጨት ይመስላል። ቀስ ብላ ከተነሣች በኋላ ሳህኑን ይዛ ወደ ዕቃ ቤት ገባች።

ጥቂት ቆየት ብላ እጅዋን በቀሚሷ ጠርዝ እየጠራረገች ተመለሰች፡፡ መጀመሪያ የነበረችበትን ሥፍራ ትታ ሌላ ቦታ ቆመች፡፡

ፊቷና መላ ሰውነቷ ወደ ምሥራቅ በመዞሩ ወደ ምዕራብ ለሚመለክቱት ዐይኖቼ እሷን ለማየትና ሁኔታዋን ሁሉ ለመገንዘብ መልካም አጋጣሚ ሆነላቸው።
ጣቶችዋ ለድመት ግልገል ተዘልዝሉ እንደ ሰነበተ ሳንባ በልዘው ጠቁረዋል፡፡
ክንዶችዋ ሥጋቸው ከውስጥ ተፈቅፍቆ ወጥቶ ቆዳ ብቻ የለበሱ ይመስላሉ።
የአጥንቶችዋ ቅርፅና ጠፍጣፋነት ከሩቅ ይለያል። ቀሚሷ ደረቷ ላይ በመቀደዱ
ጠቆር ባለው ገላዋ ላይ እንደ ጐባጣ ማገር የተጋደሙት አጥንቶቿ ፈጥጠዋል።
በቀጭኑ አንገቷ ላይ ቂጥጥ ያለችው ራሷ በቃጭን አገዳ ላይ የበቀለች ማሽላ
ትመስላለች። የቆዳዋ ወዝና ቅባት ደርቆ የነፈሰበት የዘንጋዳ እንጀራ መስሏል።
ሰውነቷን በጠቅላላ ሲመለከቱት ለብዙ ጊዜ አብሯት በከረመ እድፍ በመጥቆሩ
ከረግረግ የተመዘዘ የዕንጨት ጉማጅ መስሏል፡፡

ዐይኖችዋን በሰፊው ከፍታ ይህ ነው ወደማይባል አካባቢ ስትመለከት
እነዚያን የሐምሌ ልደታ ድፍርስ ውሃ የመሰሉ ዐይኖችዋን በደንብ ኣየኋቸው።
ከመኻል ኣፍንጫዋ ግራና ቀኝ ላይ እንደ ጉጥ የፈጠጠው የጉንጭዋ አጥንት
አዲስ በቀል የጥጃ ቀንድ መስሏል። ጉንጫ ወደ ውስጥ ተሠርጉዶ ከመንጋጋዋ ጋር የተጣበቀ ስለሚመስል የግንቦት ሐሩር ሲያንቃቃው የሰነበተ የቅል ቅጠል መስሏል፡፡ የሠለጠነ አናጢ ፈልፍሉ እንደ ጠረበው የጥድ ዕንጨት ስልክክ ብሎ የወረደው እፍንጫዋ ድንቅ አቀማመጥ አለው፡፡

ቢማ ቀለም የነበረው ሻሽዋ ዐፈር የላሰ ደባደቦ መስሏል። ከሻሽዋ ውስጥ
አፈትልኮ በግራ ቀኝ ጆሮዎችዋ በኩል የተንዛለለው ጸጉሯ ዞማ መሆኑ
ቢያስታውቅም በንጽሕና ባለመያዙ የእሳት ላንቃ የገረፈው “ጭራ ሲመስል፣
ከጉልበቷ በታች በጠቅላላ ቅልጥሟ በተደጋጋሚ በመፎከቱ ቆዳዋ ተሽነታትሯል። የጨቅላ ልጅ ቡጢ ያህል የፈጠጠው ቁርጭምጭሚቷ ተረከዝዋ በላይ የሚገኘው ወፍራም ወጣሪ ጅማቷ በኑሮ መጎዳትዋና መጎሳቆሏን በሚገባ ለማሳወቅ የቀረቡ አስረጂዎች ናቸው፡፡...


💫ይቀጥላል💫
👍1
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ_አራት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

....ኬቨን ቮስ በሴዳይ ሳናይ ሆስፒታል ውስጥ በሚገኘው የሆስፒታሉ ካፌ
ውስጥ ቁጭ ብሎ የፕላስቲክ ጠረጴዛውን በጣቱ እየቆረቆረ ነው::

የግል መርማሪው ደውሎ ቀጠሮ ያስያዘው ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ ነው::
አሁን 12:10 ይላል፡፡ 12:11 ሲል ደግሞ ኬቨን ቀጠሮው የውሸት መሰለው::
ምክንያቱም የሆነ ሰው ስለ ዶክተር ዶውግ ሮበርትስ እና ስለ ውሽማው
የምታውቀውን ነገር ከነገርከኝ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን እሰጥሃለሁ
ብሎት ነው እዚህ የቀጠረው። እርግጥ ነው ኬቨን ስለ እነርሱ ብዙ የሚናገረው ነገር የለም። አብዛኞቹ ነገሮች ወንድ እና ሴት ነርሶች ሲያወሯቸው የነበሩ የሐሜት ወሬዎች ናቸው። ኬቨን ቮስ ዕዳ ስላለበት
ክሬዲት ካርዱ እና ሌሎች ነገሮችም ሁሉ ባዶ ስለሆኑበትና የግድ ብሩ
ስለሚያስፈልገው ነበር ሰውዬውን ለማግኘት የተስማማው። በዚያ ላይ ደግሞ የወንድ ጓደኛው ኢንዞ በነርስነቱ ከሚከፈለው በላይ በጣም ብዙ ብሩን ግጦትባዶና ስላደረገው ነበር።

“ኤቨን?” አለው አንድ ወፍራም ሰው ወደ ካፍቴሪያው ተንደርድሮ እየገባ እና ኬቨን ወደ ተቀመጠበት ቦታ እየመጣ፡፡ አጠገቡ ደርሶም ላባማ እጆቹን ለሰላምታ እየዘረጋ ራሱን አስተዋወቀው:: ደግነቱ ቦታው ጭር ያለ ስለሆነ ኬቨን ደስ አለው::

ነርሱ ዙሪያውን ከቃኘ በኋላ እጁን ጨብጦ እንዲቀመጥ በአይኑ ጋበዘው።

“እዚህ ካፌ ምንድነው ጥሩ ምግባቸው?” ዊሊያም ከጠየቀ በኋላ “ማታ ቆይቼ ነበር እና ጥሩ ቁርስ እፈልጋለሁ::”
ኬቨን የዊሊያምስን ከብብቱ ሥር ያለውን ሸሚዝ ቅፍፍ እያለው አይን አይኑን እየተመለከተ “ብቻዬን ልታገኘኝ ነበር የፈለግከው።” አለው በሹክሹክታ፡፡

“አዎን ደግሞም እኮ እዚህ ማንም የለም::” ብሎ ዊሊያምስ ገለፈጠ እና
ሁለት የብሉ ቤሪ ዳቦ እና አንድ ትልቅ ላቴ አዝዞ ወደ ኬቨን በመመለስ
"እዚህ ስለ እኛ ደንታ ያለው ሰው የለም እመነኝ፡፡ ደግሞም እኮ እያወራን
ያለነው ስለ ድሮ ጓደኛዬ ስለሆነ ህገወጥ የሆነ ነገር አይደለም::”

እሺ” ብሎ ነርሱ የግዱን ፈገግ አለ እና ይሄ ዊሊያምስ የእውነት የዶ/ር
ሮበርትስ ጓደኛ ይሆን? ብሎ አሰበ።
ለማንኛውም ገንዘቡ የግድ ስለሚያስፈልገው የግድ ያወራዋል።

“ያን ያህል በጣም የቅርብ ጓደኛማቾች አይደለንም” ብሎ የመጣለትን ቁርስ አንድ ጊዜ አብዝቶ ጎርሶም የሆነ ጊዜ ላይ አብረን እንሰራ ነበር።እወደውም ነበር። ብዙ ሰዎች ይወዱታል” አለው፡፡

“እሺ ማን ነበር የማይወደው የነበረው?” ብሎ ዊሊያምስ ቡናውን በረዥሙ ድምፅ እያሰማ ፉት አለው።

“ምን ማለትህ ነው አልገባኝም?”
“ብዙ ሰዎች ይወዱት ነበር ብለኸኛል። ብዙ ማለት ደግሞ ሁሉም ማለት አይደለም። ስለዚህ እሱን የማይወድ ሰው ነበር?”

ኬቨን ፊቱን አጥቁሮ “በቃ ፀባዩ ተቀየረ ከሆነች ሴት ጋር ግንኙነትም ጀመረ። ሩሲያዊ ናት:: ከዚያ በኋላ ሁሉ ነገሩ ተቀየረ”

“ተቀየረ ስትል?” ብሎ ዊሊያምስ ጠየቀው ምግቡ ላይ አቀርቅሮ፡፡

የሩሲያኖች ሥም ነው ያላት። ሥሟ አሁን ተረሳኝ። ሞስኮ ነበር ትኖር የነበረው። ግን ሁሉ ነገሯ አሜሪካዊ ነበር ይመስል የነበረው:: ስታወራ ደግሞ እንግሊዝኛ ዘዬዋ የአሜሪካውያን ነበር፡፡ ብቻ ዶክተር ሮበርትስ በእሷ መተት የተሰራበት ይመስል ነበር። ደግሞ እኮ ያን ያህል
ቆንጆ አልነበረችም:: የሆነች የአለምን ሸክም የተሸከመች ነበር የምትመስለው።
እንዲያውም በወጣትነቷ የሚጠብሳት ወንድ ሁሉ ያለ አይመስለኝም፡፡ በጣም
ረዥም ናት” ብሎ በማስከተልም “ከዚያ በዘለለ ግን ከሚስቱ ጋር ስትነፃፀር
እዚህ ግቢ የሚባል የሴት ውበት ያላት አልነበረችም” አለው፡፡

ዊሊያምም በኬቨን ሀሳብ መስማማቱን ራሱን ነቀነቀ፤ በተለይ ደግሞ ደብዛዛ የሌንካ ጎርዴቪችን ፎቶዎች ሲመለከት ሌንካ ከኒኪ በዕድሜ ማነሷ
ብቻ ይበልጥ ወጣት እንድትመስል ያደርጋታል፡፡ ከዚያ በተረፈ
የፈለገቻቸውን ውድ ውድ ልብሶችን
ምንም እንኳን ብትለብስም
የማያምርባት ሴት እንደሆነች ለመረዳት ችሏል።

ዊሊያምስ ስለ እሷ የኋላ ህይወት ለማወቅ ያልቆፈረው ድንጋይ
ባይኖርም እንዳሰበው ስለ እሷ ማወቅ አልቻለም። ይሄው ከአከራይዋ ጀምሮ
እሷን አስመልክቶ ጥያቄን ቢጠይቅም ስለ ቤተሰቧ ስለ ስራዋ፣ ስለ ስራ
ቅጥሯ ወይንም ደግሞ ስለ ትምህርት ደረጃዋ አንድም አይነት መረጃና
ለማግኘት አልቻለም፡፡

ሀዶን ዶፎ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኝ የአደንዛዥ ዕፅ አስወጋጅ የግብረ
ሰናይ ድርጅት ውስጥ ነው የምትሰራው ቢለውም እዚያ ቦታ ላይ ይሰሩ
የነበሩ ሰዎችን ባወራቸው ጊዜ ስለ እሷ አንድም ነገር እንደማያውቁ
ነግረውት ነበር። ብቻ ሴትየዋ የሆነች መንፈስ ናት እንዴ? ብሎ እስከማሰብ
ደርሷል።

“አግኝተሃት ታውቅ ነበር?” “ለተወሰኑ ጊዜያት ያህል አዎ፡፡” ነርሱም ራሱን በአዎንታ ወዝውዞ “ብዙ ጊዜ ወደ ሆስፒታል ትመጣ ነበር፡፡ እዚህ
ካፌ ውስጥም ነበር ብዙውን ጊዜ ምሳቸውን ይበሉ የነበሩት። ይሄ ደግሞ
ያልተለመደ ነገር ነው:: ምክንያቱም የፍቅር ግንኙነታቸው በይፋ ነበር፡፡
ለሆስፒታሉ ሠራተኛ በሙሉ ነበር በግልፅ ያሳዩ የነበረው።” ይሄ ደግሞ
ብዙውን ጊዜ ዶክተር ዶፎ እና ዶክተር ሮበርትስ ያጣላቸው ነበር። “አዎን
በእሷ በሌንካ ምክንያት እንደሚጨቃጨቁ እርግጠኛ ነኝ። አሁን ሥሟ መጣልኝ ሌንካ ነው ሥሟ” አለው ኬቨን ስሟን በማግኘቱ ደስ እያለው፡፡

“ዶውግ ሮበርትስ እና ሌንካ እንዴት ነበር የተገናኙት?”

ኬቨን ለጥቂት ጊዜ ሲያስበው ቆየና “ኒውዮርክ ላይ ይመስለኛል። የሆነ
የበጎ አድራጎት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ። ዶክተር ሮበርትስ የሆነ
በነፃ አገልግሎት የሚስጥ ክሊኒክ...” ብሎ

“እሱን አውቃለሁ” አለው እና ካቋረጠው በኋላ “ስራዋ ምን እንደነበር
ታውቅ ነበር?”

“እሱን አላውቅም” ብሎ ኬቨን መቶዎቹ ዶላሮች በዚህ ምክንያት የሚያመልጠው ይመስል እየተጨነቀም “ግን እሷ በጣም ሀብታም ነበረች። ምናልባት ይሄ ይሆናል ያቀራረባቸው:: ግን አየህ ፕላቲንየም እና አልማዝ ያለባቸውን የእጅ ሰዓቶች ነበር የምታደርገው፡፡ አዎን ቶፓርድ!” አለው እና
በመቀጠልም “ማለቴ ሰዓቶቿ ቢያንስ ከአሥራ አምስት ሺ እስከ ሃያ ሺ
ዶላር የሚያወጡ ናቸው። ሁሌም ሄርሜስ ቦርሳዎችን ነው ይዛ የማያት።የሆነ ጊዜ ላይ ደግሞ እጅግ በጣም ውድ የሆነ ጃኬት አድርጋ መምጣቷን አስታውሳለሁ። ምክንያቱም ዶክተር ሮበርትስ ይህንን ለብሳ በመምጣቷ ተቆጥቷት ስለነበር ነው።”

“ምን ብሎ ነው የተቆጣት?”

“ማምለጥ ብትፈልጊም ሆነ ባትፈልጊ ይህንን ልብስ ለብሰሽ አትምጪ!”
ብሎ በጣም ተናድዶ ነበር የተናገራት::

እሺ እሷስ ምን መለሰችለት?” ብሎ ዊሊያምስ ጠየቀው፡፡ የተለየ ነገር
የሚገኝበት መስሎት እየጓጓ።

አለቀሰች” ብሎ ኬቨን ከመለሰለት በኋላም “ግን ያው እንደ ሁልጊዜውም
ወድያው ተረጋጋች”

“ከእሷ ሌላ ውሽማዎች ነበሩት?”

ኬቨን ራሱን በአሉታ ነቅንቆ “ከሌንካ ጋር ግንኙነት ከመጀመሩ በፊት
እንደምትፈልገው በጣም የምትፈልገው አይመስለኝም፡፡ ገባህ አይደል?”
ሁሌም ከሚስቱ ጋር ነበር፡፡ ግን አየህ ሚስቱም ዶክተር ስለሆነች ሩሲያዊቷ
ዊሊያምም እንደገባው ለማሳወቅ ራሱን በአዎንታ ወዘወዘለትና የማስታወሻ ደብተሩ ላይ ነገሮችን መፃፍ ጀመረ::

ከሆኑ አደገኛ ሰዎች ጋርም ግንኙነት እንዳላት ሰምቼ ነበር?” ብሎ ኬቨን ድምፁን ቀነሰና “ማለቴ በጣም ሀይለኛ ከሆኑ ሰዎች ጋር”

“ምን አይነት ሰዎች?” ብሎ ዊሊያምስ ጠየቀው፡፡

“አላውቅም” አለ እና ኬቨን በመቀጠልም “ዶውግ ሮበርትስ እነዚህን
👍3
ሰዎች ይወቃቸው፣ አይወቃቸው ግን የማውቀው ነገር የለም፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ላይ የሆነ የቀዶ ጥገና ዶክተር የከተማው ማዘጋጃ ቤት ለሚያሰራቸው የኮንትራት ሥራዎች እነዚህን ሰዎች እንደሚያውቃቸው
ሲያወራ ሰምቼ ነበር።”

ዊሊያምም ትንሽ አመነታ እና ተነስቶ የኪስ ቦርሳውን ካወጣ በኋላ
ሁለት መቶ ዶላር ጠረጴዛው ላይ ካስቀመጠለት በኋላ “ስለነበረን ጊዜ
አመስግናለሁ” እንዴ ሁለት መቶ ዶላር ብቻ?” ብሎ ነርሱ በንዴት እየተናገረ
ከጠረጴዛው ላይ ሁለት መቶ ዶላሩን አንስቶ ወደ ኪሱ ጨመረ፡፡

ዊሊያምስ ትከሻውን ከሰሰቀ በኋላ “ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን አልሰጠኸኝም።
ማለቴ እሷ ስለሚጠብቋት ሀይለኛ ሰዎች ሥም ውስጥ አንዱን አሊያም ደግሞ ስለ ማዘጋጃ ቤቱ የነገርከኝ ተጨባጭ ያልሆነ ሀሜትን ብቻ ነው!”

“እዚያ የሚሰራ ሰው አለኝ፡፡ እሱ ብዙ ነገር ሊነግረኝ ይችላል”

ዊሊያምስም “ማን ነው?” ብሎ ዞሮ ጠየቀው፡፡ኬቨንም ተመልሶ ወንበሩ ላይ እየተቀመጠ “ለዚህ ሦስት መቶ ዶላር
ተጨማሪ እፈልጋለሁ” አለው:: ዊሊያምስ ጥሎት ሲራመድ

“ሁለት መቶ ዶላር?” አለው ኬቨን፡፡

“በእውነት ሚ/ር ዊልያምስ እሷ ልትረዳህ እንደምትችል እርግጠኛ ነኝ አለው፡፡

ዊሊያምስ ወደ ኬቨን ተመለሰና ሁለት መቶ ዶላር አውጥቶ ጠረጴዛው
ላይ አስቀመጠ። ኬቨንም እጁን ወደ ዶላሮቹ ሲሰድ ዊሊያምስ በእጁ
ሸፈነበት፡፡

“የዚህን ሰው ሥም አድራሻ እና የስልክ ቁጥር እፈልጋለሁ” አለው እና በእርጋታ “የምትሰጠኝ ነገር ግን ጠቃሚ መሆን ይኖርበታል” አለው።

ኬቨን የሰጠው መረጃ ያን ያህል ትክክል አልነበረም።

አድሬኔ ዋሽንግተን ከከተማው ማዘጋጃ ቤት ለቅቃ ወጥታ ነበር:: ከስድስት ወራት በፊት ከጁንየር የፀሀፊነት ስራዋ ተባርራ ነበር። እሷ የከንቲባው ቢሮ ውስጥ ነበር ስትሰራ የነበረው። አሁን ላይ ግን መሀል
ከተማ ውስጥ ለሚገኝ አንድ ኢንተርፕሩነር ረዳት ፀሐፊ በመሆን በትርፍ ሰዓት በመስራት ላይ ትገኛለች።

“ያንን ሥራ መልቀቄ ለበጎ ነው።” አለችው ዊሊያምስ አግኝቷት ምሳ እየበሉ እያሉ “በእውነት ሥራቸው የሚያሳፍር ነበር። ለማንኛውም የከንቲባውን ቢሮ ትቼ በመውጣቴ የተነሳ ሜካኤልን የመሰለ ምርጥ አለቃ ለማግኘት አስችሎኛል። በዚያ ላይ ደግሞ ደሞዙ እራሱ ማዘጋጃ ቤቱ ከሚከፍለኝ እጥፍ ነው::”

ዊሊያም አድሬኒን ሲያዳምጣት ሁለት ነገሮችን ለመታዘብ ችሏል። የመጀመሪያው ቁንጅናዋ ነው። ረዣዥም እግሮች፣ ቀጭን ወገብ እና ጥቅጥቅ ያለው ቀይ ፀጉሯ አንድን ወንድ በቀላሉ ማማለል መቻሉ ነው።ስለዚህ ከንቲባውም ሆነ የአሁኑ አለቃዋ ለደደብ አዕምሮዋ ብለው ሳይሆን የቀጠሯት ለአልጋ ላይ ጨዋታ እንደሆነ ግልፅ ነው:: ሁለተኛው ነገሯ ደግሞ ምንም ሚስጥር መቋጠር የማትችል በጥራቃ ሴት መሆኗ ነው።

“በመጀመሪያው ከንቲባው ፋውንቲስ እኔን ያባረረኝ ከእሱ ጋር አልተኛም ስላልኩኝ መስሎኝ ነበር፡፡” ብላ “አለ አይደል ሰውዬው ሁለመናዬን ይደባብሰኝ
ነበር። የምለው ገባህ አይደል? አለ አይደል እሱ እኮ ዕድሜው 50 ዓመት
ነው። በዚያ ላይ ባለትዳር ነው” አለችው፡፡

ሦስት ቃላቶቿ መሀል አለ አይደል የሚለው ቃሏን እየከተተች ስለምታወራ ዊሊያምስ ስልችት ብሎታል። እሱ አለቃዋ ቢሆን ኖሮ ለዚህ አለ አይደል በምትለው ነገር ብቻ ከሥራ ሁሉ ያባራት ነበር።

ነገር ግን በመጨረሻ ላይ እኔ ስለ እሱ ባወቅኩት ነገር የተነሳ እንደተባረርኩኝ ገባኝ::”

“ምን ነበር አንቺ የምታውቂው ነገር አድሬኔ?”

አለ አይደል ከንቲባው ከሩሲያኖች ገንዘብ ይወስድ ነበር” ልክ ስለ አየር ንብረት እንደምታወራ ሁሉ ቀለል አድርጋ ማውራቷን ቀጠለች እና “ጉቦ እና
የተለያዩ ውድ ውድ ስጦታዎችን እንደሚቀበል አለቃዬ ሚስተር ድሬይተን
ለሆነ የጋዜጣ ሪፖርተር በስልክ ስታወራ ሰምቼ ነበር”

“የኔ ቆንጆ አሁን በምትነግሪኝ ነገር እርግጠኛ ነሽ?” ብሎ ዊሊያምስ
በትህትና ጠየቃት እና “ይሄ እኮ ትልቅ ውንጀላ ነው። በዚያ ላይ ደግሞ
ከንቲባው በሙስና ጉዳይ ላይ ስሙን በአንድም ጋዜጣ ላይ አላነበብኩም”
“እንዴ እኔ ማንንም እየወነጀልኩ አይደለም!” ብላ እንደመገረም ነገር
አለች እና “እኔ የሰማሁትን ነገር ነው የነገርኩህ፡፡ አለ አይደል ለከንቲባ
ፋንቴስ የሰማሁትን ነገር እንደነገርኩት ማለት ነው። ከዚያ ወዲያውኑ
ከሥራ ተባረርኩኝ፡፡ ስለዚህም ነገሩ ከወሲብ ጋር እንዳልተያያዘ ለማወቅ
በቃሁ፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆን ሚስተር ዳሬንንም አባረራት። እንዲያውም እሷን
እንኳን ያባረራት አብሯት እንዲተኛ ስላልፈቀደችለት እንደሆነማ እርግጠኛ
ነኝ:: አሁን የእኔ አዲሱ አለቃዬን ስለ ጉዳዩ ስነግረው... አለ አይደል...”

ለሃያ ደቂቃዎች ያህል ከአድሬኔ ዋሽንግተን ያገኘው ነገር ቢኖር ስለ
እነዚህ ሩስያውያኖች እና ስለ ሌንካ ጎርዴቭስኪ ምንም ነገር እንደማታውቅ
ለአራት ሰዓታት ያህል ከፈለጋት እና ካስፈለጋት በኋላ ቲና ድሬይተን
የተባለችውን የአድሬኔን አለቃን አገኛት:: የተከራየችበትን ዕቃው የተሟላ አፓርትመንት በርን ስትከፍትለት በጣም ጠንካራ ሰንሰለት ከበሩ እና ከበሩ
ጎን ጋር ተጣብቆ ነበር፡፡ ስለሆነም በሩ በትንሹ ስለተከፈተ በተከፈተው በር
በኩል ያገኘው አንዲት በአርባዎቹ አጋማሽ ላይ የምትገኝ እና በፍርሃት
የተሞላ ፊት ያላትን ሴትዮ ነበር።

“ምን ነበር?” ብላ ጠየቀችው፡፡

“ዴሪክ ዊሊያምስ እባላለሁ ሚስ ዴሬይተን፡፡ እኔ የግል ወንጀል መርማሪ
ነኝ። መግባት እችላለሁ?” አላት፡፡ ቲናም ለትንሽ ጊዜ ስታመነታ ቆየች እና “ይቅርታ አሁን ጥሩ ጊዜ ላይ አይደለሁም” ብላ በሩን ልትዘጋበት ስትል ዊሊያምስ “ስላንቺ ያወቅኩት ከሥርሽ ሆና ትሰራ ከነበረችው አድሬኔ ዋሽንግተን ነው። ስለ አንቺ በጣም ነው የምትጨነቀው” አላት፡፡

“አድሬኔ?” ብላ አይኗን አፈጠጠች እና “ይህቺ ደደብ ልጅ መቼ ነው አፏን የምትዘጋው! እርግጥ እወዳታለሁ። ግን ብዙውን ጊዜ ስለምታወራቸው
ነገሮች ግማሹን እንኳን በቅጡ አታውቀውም፡፡ ሚ/ር ሥምህን?”
ማን አልከኝ

“ዊሊያምስ” ብሎ የቢዝነስ ካርዱን በትንሹ የበር ክፍተት በኩል አቀበላት
እና “ግን ዴሪክ ብለሽ ልትጠሪኝ ትችያለሽ፡፡ ጥርጣሬሽ ይገባኛል የኔ
እመቤት: ስለ አድሬኔ በተናገርሻቸው ነገሮችም እስማማለሁ። በሞኝነት
እራሷን ለአደጋ አጋልጣ የምትሰጥ ሴት ናት። እባክሽን ሚስተርስ ድሬይተን
ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል እንዳወራሽ ፍቀጂልኝ።” አላት።

“እሺ ጠብቀኝ” ብላ በሩን ከዘጋች በኋላ የበሩን ሰንሰለት ከውስጥ በኩል
ሙሉ በሙሉ አስለቅቃ በሩን ከፈተችለት፡፡

“ግባ እስቲ” ብላ በረዥሙ ከተነፈሰች በኋላም “ቲና በለኝ፡፡ ግን ብዙ
የማዋራህ ነገር ያለኝ አይመስለኝም። ዛሬ ከዚህ ቦታ መውጣት አለብኝ፡፡
ዴሪክ የግል ወንጀል መርማሪ ነኝ ብለኸኛል አይደል?”

“አዎን” ብሏት ወደ ውስጥ ገባ እና በላስቲክ የተጠቀለለ ወንበር ላይ
ቁጭ አለ፡፡ ክፍሉን ሲመለከት ግድግዳው ላይ አንድም ፎቶ ባለማየቱ
ሴትየዋ በየጊዜው አፓርታማ እንደምትቀያይር ገባው።
“ለማን እንደምትሰራ ማወቅ እችላለሁ?”
“ይቅርታ የደምበኞቼን ሥም ለማንም አልናገርም። ማለቴ ሚስጥር
መጠበቅ አንደኛው የሥራዬ ክፍል ነው:: ግን በጣም ጨዋ እና የሰዎችን
ሚስጥር ለምትጠብቅ ሴት ነው በመስራት ላይ ያለሁት:: አንቺን ከማዘጋጃ
ቤት እንድትባረሪ ያደረጉት ሰዎች ደምበኛዬ ላይ ጥቃት እያደረሱ ስለሆነ ስለ እነዚህ ሰዎች እሷ ማወቅ ትፈልጋለች” አላት፡፡

ቲናን አይኗን በፍርሃት ጎልጉላ እያየችው “ሚ/ር ዊሊያምስ እኔ ህይወቴን እፈልገዋለሁ። እንደ ድሮ ነፃ ሆኜ መኖር እፈልጋለሁ።” አለችው፡፡.....

ይቀጥላል
👍3
አትሮኖስ pinned «#የፍቅር_ሰመመን ፡ ፡ #ክፍል_አርባ_አራት ፡ ፡ #ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን ፡ ፡ #ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው ....ኬቨን ቮስ በሴዳይ ሳናይ ሆስፒታል ውስጥ በሚገኘው የሆስፒታሉ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብሎ የፕላስቲክ ጠረጴዛውን በጣቱ እየቆረቆረ ነው:: የግል መርማሪው ደውሎ ቀጠሮ ያስያዘው ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ ነው:: አሁን 12:10 ይላል፡፡ 12:11 ሲል ደግሞ ኬቨን ቀጠሮው የውሸት መሰለው:: ምክንያቱም…»
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሦስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

የጨቅላ ልጅ ቡጢ ያህል የፈጠጠው ቁርጭምጭሚቷ ተረከዝዋ በላይ የሚገኘው ወፍራም ወጣሪ ጅማቷ በኑሮ መጎዳትዋና መጎሳቆሏን በሚገባ ለማሳወቅ የቀረቡ አስረጂዎች ናቸው።
ከሳምንት በፊት እናቴና ወይዘሮ የውብዳር ሲነጋገሩ ካመጡልኝ አይቀር
ችግረኛዋንና ምንም ዘመድ የሌላትን የራባትንና እህል እህል ያሰኛትን ነው» ብላ
አደራ ያለቻቸው ትዝ አለኝና «ችግርንና እጦትን ረሃብንና እርዛትን ማስፈራርያ
እያደረገች ልትገዛት ፈልጋ ነው» በማለት መሪር ትዝብቴን ለራሴ አዋየሁት።
መላ ሰውነቴ በርኅራኄና በሃዘን ተነካ፡፡ ልቤ በትካዜ ሟሸሸች። በሥራ ብዛት
የተደቆስኩ ያህል ሕሊናዩ ዛለ፡፡

አዲሲቷ ሠራተኛ ያሳለፈችው ውራጅ ሕይወትና የዘቀጠ ኑሮ እስከ አጥንቷ ዘልቆ ታየኝ። ነገር ግን በእኔ ዕውቀትና በአጭር ጊዜ የምርምር ችሎታ
ገና በወጣትነቷ ለጨለመው ሕይወቷ አመርቂ ፍቺ አጣሁለት። ከዚያ ቀደም
ለማንም በዚያ ዐይነት አዘኔታና ልባዊ የስሜት ጭንቀት አንጎሌ ተብሰክስኮና
ተጠቦ አያውቅም፡፡

እናቴ የሠራተኛይቱን ሰውነትና ጠቅላላ ሁኔታ በመመልከት «ውይ! ምን በወጣኝ፡ ምን በደልኩዎት! ይቺማ በሽተኛ ናት፡. አልፈልግም» ሳትል በመቅረቷ በጣም ተገረምኩ፡፡

የውብነሽ አልጋዎቹን አንጥፋ ስትመለስ ልክ አራት ሰዓት ከሩብ ሆነ፡፡ እንግዳይቱ ሠራተኛ የየውብነሽን መምጣት ስታይ ጠንቀቅ ብላ በንቃት ቆመች።
ከእናቴ በታች አዛዥ መሆንዋን ማወቋ ነበር። የውብነሽ ያን አጠር ብሉ ከርደድ
ያለ ጸጉሯን በግራ እጅዋ ይዛ እያሻሽች ከተመለከተችኝ በኋላ «ተነጥፎልሃል
መተኛት ትችላለህ» አለችኝ፡፡ እጅዋን ወደ ኋላ መልሳ ከግድግዳው ጋር ተለጥቃ
ወደ ቆመችው ሠራተኛ ዘወር ብላ «አንቺም ዕቃ ቤት ውስጥ ከዚያ ከትልቁ
በርሜል አጠገብ አንጥፈሽ ተኚ» ብላ ለማሳየት ወደ ዕቃ ቤት ገባች።
ሠራተኛይቱ ተከትላ ስትገባ ንፋስ እንደሚያወዛውዛት መቃ ወገቧ ልምጥ ልምጥ ሲል ቀዳዳው ቀሚሷ ከወዲያ ወዲህ ተወናወነ፡፡

ቁጥጥር ለማድረግ የታዘዝኩ ይመስል ተከትያቸው ገባሁ፡፡ የውብነሽ
ግድግዳው ላይ ወደ ተንጠለጠለው አጎዛ እያመለከተች «ነገና ከነገ ወዲያ ሌላ
ምንጣፍ ፈልገን እስከምንሰጥሽ ድረስ ለዛሬው ያን አጐዛ እዚህ ወለሉ ላይ ጣል
አድርጊና ተኚ። አይዞሽ አትፍሪ፡ ትለምጃለሽ» አለቻት፡፡

ሠራተኛይቱ አጐዛውን ከተንጠለጠለበት ምስማር ላይ ተንጠራርታ አወረደችው:: አጐዛው መኻል ላይ ቁልቁል የተሸረከተ የሕፃን ጭንቅላት የሚያሾልክ ትልቅ ቀዳዳ አለ። ቀዳዳውን እንዳየሁ አንድ ነገር ትዝ አለኝ።
የቤታችን ዘበኛ የነበረው ዘለቀ በግ ሲገፍ ሳት ብሎት ቆዳውን በሹል ቢላዋ ስለ
ሽረከተው አባቴ በዚያች የተነሣ ከሥራ እንዳባረረው ታወሰኝ። ከውስጣዊ
ፍርሃትና ጭንቀት የተነሣ ያ ከሲታ ፊቷ ከመጠን በላይ ጠውልጐ ይብስኑ
ሕይወት አልባ መሰለ።

«እስኪ ትንሽ አራግፈው እለች የውብነሽ በፊቷ ላይ ጥርጣሬ እየታየ፡፡
ገና ሁለት ጊዜ መታ መታ እንዳደረገችው ያንጠለጠለችው እዛ እምልጧት
ወደቀ። አጐዛው ላይ የነበረው አቧራ በመጠኑ ቦነነ ።ደንግጥ እነሣችው::
የውብነሽ አቧራውን እየተጸየፈች እስኪ እንደገና ቀስ ብለሽ መታ መታ
አድርጊው» አለቻት፡፡ ሠራተኛይቱም ከእኛ ለመራቅ ያህል ወደ ኋላ ፈግፈግ ብላ
በወዙ በኩል ሦስት አራት ጊዜ መታታችው። ልሙ ኣቧራ ወርዶ እግሯን
አለበሰው፡፡ ዕቃ ቤቱ በአቧራ ቡናኝ ተሞላ እህቴ አፍና አፍንጫዋን በቀኝ እጇ
አፈነች። ሠራተኛይቱ የአቧራው መቡነን እኛን የሚያስቆጣን ስለ መሰላት ብናኙን
እፍ እያለችና በእጅዋ እያራገበች ለማራቅ ሞከረች። አጐዛውን ከትልቁ በርሜል
ሥር ጣል ካደረገችው በኋላ ዱር አማከለች የምታነጥፈውን አሮጌ ብርድ ልብስ አጣጥፋ አስተካከለችው፡፡ ጎንበስ ቀና ባለች ቁጥር ጉልበቷ ይንቋቋል። የውብነሽ ወደ እኔ ጠጋ ብላ ለምን ታሳፍራታለህ? ሂድ እንጂ እነጣጥፋ ትተኛበት አለችኝ፡፡ «አንድ ጊዜ እንዳይ ብዩ ነው እንጂ እሺ እሄዳለሁ» ብዬ ዐይኔን ወደ ወለሉ መለስኩት፡፡ በአሮጌ ቀሚስ የተጠቀለሉ ጨርቆች መኝታው መኻል ላይ ጣለች፡፡ ወዲያው ነጠልጠል ስታደርገው ቀደም ብዩ ካየኋቸው ይበልጥ በጣም የቆሸሹና የተቀዳደዱ ቀሚሶችና ጨርቆች ወጡ፡፡ ከሁሉም ጐላ ብሎ የሚታየው ግን እንድ ጠርዝ ጠርዙ የተሸነታተረ ዐመድማ ስስ ብርድ ልብስ ነበር፡፡

ተንበርክካ ቀሚሶችዋን ካጣጠፈች በኋላ ለትራስ እንዲሆኑ አንድ ላይ ሽበለለቻቸው፡፡ የእኔ ልብ በሥቃይ ታፍና በሃዘን ስትቀዘቅዝና ጅማቴ ሲኮማተር
ተሰማኝ፡፡ ጉንበስ ቀና ባለች ቀጥር በስተኋላዋ ያለው የቀሚሷ ትልትልና ቀዳዳ ያንን ሸካራ ገላዋን በከፊል ያሳያል። እኅቴ እነዚያን የተበታተኑ ልብሶች
እየተመለከተች «ለመሆኑ ይኸ ልብስሽ ተባይ የለበትም?» ብላ ጠየቀቻት።

በእንግድነት ኃፍረት የተሸበበው አፍዋ ዝምታን ማመቅ እንጂ ቃላት ማውጣት
ስላልሆነላት ዝም አለች፡፡ እንግዳይቱ ሠራተኛ ግን አሮጌውን ልብስ አንዴ
ወረቀት ከሽመለለችው በኋላ የእግርዋን ትቢያ ሳታራግፍ መኝታዋ ላይ
ተቀመጠች። የተጠቀለለውን ብርድ ልብስ ሳብ አድርጋ ጉልበቷን ሽፈነችው።
ተጣጥፈው በስተኋላዋ ለትራስነት የተጠቀለሉት ልብሶችዋ ማቃጠያ ውስጥ
ተከማችተው የተቃጠሉ ወረቀቶች ይመስላሉ። ግንጭሏ የታጠፈውን ጉልበቷን እስኪነካ ድረስ ካቀረቀረች በኋላ ቀሚሷን አወለቀች፡፡ ከላይኛው ቀሚሷ የባሰበትና በጣም ያረጀ የውስጥ ልብስ ብቅ አለ።

ትከሻዋ ላይ ያለው ማንገቻ ረዝሞ
በመቋጠሩ እብቱ የቄብ እንቁላል ያህላል። በእድፍ የተሰላው ልብሷ ምን ዐይነት ቀለም እንደ ነበረው አይለይም። ቀሚሷን ስታወልቅ ያንን ዐመድ መስሎ
የተጐሳቆለ ጸጉሯን ሸፍኖት የነበረው ሻሽ ከቀሚሷ ጋር ሾልኮ ዱብ አለ፡፡ አጉሯ
ወደ ፊትና ወደ ኋላ ተመነጫጨረ።አንዱ ዘለላ ጥምል ቀለም መሳይ አንገቷ
ላይ ተጥመልምሉ ወረደ። ጸጉሯ ላይ ነውር ነገር የታየበት ይመስል በጣም
ደነገጠች። ወዲያው እየተርበተበተች በዚያው በሻሽ ሸንከፍ አደረገችው። ብዙ
የኑሮ ጉስቁልና ስለ ደረሰባት የአፍላ ወጣትነቷ ጠይም ውበት ወደ ሸካራ
ጥቁረት ተለውጧል፡፡ እህቴ ያን የመሰለ ፀጉር በማየቷ በአድናቆት ተመስጣ
በውስጣዊ የቅናት ጸገግታ ተመለከተቻት:: እኔ ግን በጣም ስላሳዘነችኝ በትካዜ እንባ ባቀረሩ ዐይኖቼ ሁኔታዋን አጤንኩት። አሮጌውን የብርድ ልብስ ሳብ አድርጋ እስከ አጐጠጐጤዎቿ ካደረሰችው በኋላ ተኮራምታ ስትተኛ ጭብጥ አከለች።

የውብነሽ «ወንድም ጋሼ አንተ ብትፈልግ ቆመህ እደር፡ እኔ ምን በወጣኝ ነው» ብላ ጥላኝ ሄደች። እኔ ግን ያቺን ከፊት ለፊቴ ከበርሜል ሥር ከላይ አዳፋ ደርባ ከታች የቆሽሽ ልብስ አንጥፋ የተኛችውን ሴት ትክ ብዬ እያየሁ ሦስት ደቂቃ ያህል ቆምኩ፡፡ ለጊዜው አጥጋቢ ትርጉምና ምክንያት ያላገኘለት የሐሳብ ሞገድ አእምሮዬ ውስጥ ተነሣ፡፡ ልወጣ አቅራቢያ እንደ ራባት የውሻ ቡችላ በቀጭኗ ተንፍሳ ገልበጥ አለች። ከዚያም ምንም እንኳ የብርድ ልብሱን ዐልፌ ማየት ባልችልም እንቅስቃሴዋን ተከታተልኩ። እጅዋ ወደ ጀርባዋ ከዞረ በኋላ ከገላዋ ላይ የሚገለፈፍ ነገር ያለ ይመስል ጥፍሮቿ ያን ሲሰሙት ብቻ በድምፁ የሚያስታውቅ ሸካራ ጀርባዋን ማከክ ጀመሩ፡፡ ወዲያው ሥቃይና የስቅቅታ ፍርሃት የረመጠጣት ቀጭን ሳል ኃይሏን ወለሉ እየዋጠው ሁለት ጊዜ ተሰምታ እየሰለለች ወደመች፡፡ ከዚያ በኋላ ገመምተኛ ፀጥታ በመተካቱ መብራቱን አጥፍቼ ወጣሁ፡፡

አንጐሌ ውስጥ በቂ ኀዘናዊ ትርዒት አጭቄ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ፡፡
የመጀመሪያው ቀን በዚህ ሁኔታ ተፈጽሞ ዘልዓለም ወደማይመለስበት የትዝታ
ክልል ገባ፡፡
👍4
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በማግሥቱ ሰኞ ማለዳ በመስኮት በኩል ስመለከት ከዋናው ቤት በሰሜን ምዕራብ ሲል ባለው ገላጣ ሥፍራ ላይ አንድ አገር ልብስ ተቆልሏል፡፡ ውሃ በሁለት ትልልቅ ባሊ ተሞልቶ ተቀምጧል፡፡ አዲሲቱ ሠራተኛ በአንድ ሰፊ ብረት ምጣድ ላይ ልብስ ታጥባለች፡፡ የማለዳው ውሃ በጣም ቀዝቃዛ በመሆኑ ውርጩ ስለቆረጠማት እጅዋን ወደ እሷ አስጠግታ «እህህህህ» እያለች በትንፋሽዋ ታማሙቀዋለች፡፡ የቀረበላት የልብስ ብዛት በአንድ ቀን ውስጥ ታጥቦ የሚያልቅ አይመስልም፡፡ እንኳንስ ሊሠሩት በጣታቸው የማይነኩትን ሥራ ማሽከም የሚቀናቸውን ቤተሰቦቼን ታዝቤ ወጣሁ።

ጉዳዩ 'የሰው በልቶ…” ሆነና ቀን ለምሳ ወደ ቤት ስገባ ልብሶቹ ሁሉ ታጥበው በሁለት ረጃጂም መስቀያ ገመድ ላይ ተሰጥተዋል። ወደ ቤት ገባ ስል
አዲሲቱ ሠራተኛ ነጣ ያለች ትንሽ እራፊ ጨርቅ ይዛ የእንግዳ መቀበያ ክፍሉን
የዳርቻ መስኮት ስትወለውል ደረስኩ፡፡

ማን መሆነኔ ለማለየት የፈለገች ይመስል መለስ ብላ አየችኝና ወዲያው
አንገቷን ሰበር አድርጋ ሥራዋን ቀጠለች፡፡

ቀይ ጥለት ያለበት ቦርቃቃ ቀሚስ
ለብሳለች። የእናቴ ነበር፡፡

እናቴ በመጠኑ ደርጀት ብላ ሳይበዛ ወፍራም ስለሆነች ሠራተኛይቱን ዶሮ በጋን አስመስሏታል። በቀጭን ጨርቅ ሰቅስቃ ስለታጠቀችው ጉንፉ በሆዷ ላይና በስተጀርባዋ በኩል በንፋስ የተቀተተ ወናፍ መስሏል። ቀሚሱ ባለ ሙሉ እጅጌ ስለሆነ ያቺ ቀጭን እጅዋ በስልቻ ላይ ተሰክታ የታሠረች ማማሰያ መስላለች።
ሻል ያለ ድፍን አረንጓዴ ሻሽ ጥለውላታል። ገና ስገባ ስንዴ እየለቀመች ያየችኝ
አስካለ ምሳዬን አቀርባልኝ ተመለሰች፡፡ ያለ ልማዱ እንግዳ መቀበያ ክፍል ዳርቻ
ላይ ተቀምጦ ያንኑ የሕግ መጽሐፍ የሚያገላብጠው አባቴ መላ ሐሳቡ ከአካባቢው ሁኔታ ውጪ ሆኗል። በንባብ ላይ ሲሆን ዐመሉን ስለማውቅ ሰላምታ
አልሰጠሁትም። ደግነቱ ሁልጊዜ የሚያነብበው መኝታ ቤት ውስጥ በመሆኑ ዘወትር በዚያ አካባቢ ለምንቀመጠው ቤተሰቦች ችግር አልነበረብንም። እርሱ ባለበት አካባቢ እንደበታችን ይለጉማል። የሕግ ጉዳይና የፍርድ ቤት ንትርክ ፅሑፎችን ለማንበብም ሆነ ለመከታተል ስለማልፈልግ በዚሁ የተነሣ ከአባቴ ጋር
እጅግም አንቀራረብም።

«ትምህርት ይሉሃል ሕግ ነው፤ ሌላ ሌላው ሁሉ ቅጥያ ነው፡፡ እኔ እንኳ
ከብዙ ልፋትና ልምድ በኋላ ይኸው ዛሬ የማልቀመስ እሳት የላሰ ዳኛ ሆኛለሁ”
ሲለኝ አንዳንድ ቀን እሱና ጓደኞቹ ነግር ሲተበትቡ ስለምሰማ ውስጤ በንዴት
ይተናል፡፡ ተከራክሬ ሐሳቤን ለመግለጽና ለማብራራት ስለማይፈቅድልኝና «ከረ
ይኸ ዓይን አውጣ! ስድ አደግ!» ስለምባል ያሰብኩትን ሁሉ የፍርሃት ደሪባ
ደፍቼበት ዝም እላለሁ፡፡ ከሁሉም ከሁሉም የሚያበሳጨኝ ግን አባቴ በማይረባው ነገር ሁሉ እየተቆጣ በልጅነቴ ይገርፈኝ የነበረው ነው፡፡

ከየትም ከትም እየተሰባሰቡ ሠፈር ለሠፈር ከሚማግጡ ልቅምቃሚዎች
ጋር ሲያውደለድል ዋለ ተብሎ ለአባቴ የተነገረ ዕለት የሚጠብቀኝ የሚያርበደብድ የዓይን ግልምጫና ቅጣት አይጣል የሚያሰኝ ነበር።

«እኔ እኮ ምን ባደርግ ይሻለኛል? የሰው ልጅ ካንድም ሁለት ሦስት ጊዜ ይነገረዋል፡፡ ያንተ እኮ ሠርክ ሆነ፣ ከጨዋ መኻል ሰው መርጬ ከእነማን ጋር
መዋል እንዳለብህ ከመንገር አልፌ ምን ላድርግ? ከግራዝማች ሙሉጌታ፣
ከፊታውራሪ እሸቴ፣ ከቀኛዝማች ቃለአብ ልጆች ጋር ወስጄ አስተዋወቅሁህ!
ያንተ ከማንም ብራሪ ጋር መግጠም ምን ይባላል?» ብሎ ክፉኛ ገርፎ በእግር
ብረት ታስሬ የዋልኩበት ቀን ምን ጊዜም ትዝ ሲለኝ ይኖራል፡፡

እባቴ ያስተዋወቀኝ ሰዎች ልጆች ከየቤታቸው እንደ ልባቸው ወጥተው
ስለማይጫወቱ ጠላኋቸው:: የሠፈር ውስጥ ድብቅ ጓደኞቼ ግን እንደ ልብ
የሚጫወቱና የሚዛለሉ፣ ያንን መንገድ አለፋችሁ ቀበናን ተሻገራችሁ የማይባሉ
ስለ ነበሩ ከነእርሱ ጋር ለመዋል እና እንደነሱ ነፃ ለመሆን በጣሙን እጓጓ ነበር፡፡

እባቶቻቸው አናጢና ግንበኛ ከነበሩት ከአበራና ከረዳ ጋር በጣም እንቀራረብ ነበር፡፡ በተለይም አባቱ፡ የሐኪም ቤት ዘበኛ ከሆኑት ከአማረ የኋላሸት
ጋር በጣም እንፋቀር ነበር፡፡ ከእነርሱ መኖሪያ ቤት ይልቅ የእኛ ማድበት በጣም
የተሻለ ቢሆንም አማረ ኃፍረት አይሰማውም፡፡ «አቤት የናንተ ቤትና ግቢ ደስ ሲል! የኛ ቤት፣ የነአበሪ ቤት ሊፈርስ ነው አሉ፡ እሌላ ሠፈር ብንሔድ
ትመጣለህ? እኔ እመጣለሁ» እያለ ስለ መለያየት ነገር ሲያነሳብኝ ሆዱ ይባባ
ነበር አንዳንድ ቀን በሹልክታ ወደ ግቢያችን ይዤው እገባና ምድር ቤት ውስጥ ደብቄ የማቆይለትን ወጥ የነካካው ፍርፋሪ ቶሎ ቶሎ እንበላላና በመጨረሻም ከየጆንያው ላይ ከፈሰሰው ሽምብራና ባቄላ ኪሶቹን ሞልቼለት ተደብቀን እንወጣለን። እቤታችን ድግስ ተደግሶ የሠፈር ልጆች በትላልቅ ዝርግ ሳህን ፍርፋሪ ቀርቦላቸው እየተንጫጩና እየተሻሙ ሲበሉ አብሬ መብላት
ስለማይፈቀድልኝ አንጀቴ በንዴት እርር ይል ነበር፡፡ ዛሬ የእኔንና የእነዚያን
ልጆች አስተዳደግ ሳነጻጽረው ልዩነቱ የሰማይና የመሬት ያህል ይራራቃል። አንድ ጊዜ በክረምት ወራት እነ አማረ ቤት የምደብቃትን ጅራፈን ሳጮህ ሰንብቼ
የቡሄ ዕለት ማታ ከሆያ ሆዪ መልስ ገና ላይን ሳይዝ ከአማረ ጋር ሙልሙላችንን
እየገመጥን ወደ ቤት ሲሸኘኝ የቤታችን ዘበኛ ድንገት ደርሰው አፈፍ አደረጉኝ፡፡
ከዚያ በኋላ የሚጠብቀኝን ነገር ስለማውቀው ገና ከሩቁ ሽንቴ መጣ፡፡ እንባዬ ዱብ ዱብ አለ፡፡ እማረ ከኋላ ኋላችን እየተከተለ «አባባ አትናገሩበት! አባባ እዚሁ ነው ያገኘሁት በሉለት! ያሥሩታል እኮ! ይመቱታል እኮ» እያለ
ለመነልኝ:: ትልቁን የግቢ በር ከፍተን ስንገባ ግን እያለቀሰ ቆሞ ቀረ፡፡ የፈራሁት
አልቀረም፡፡ አባቴ እጅና እግሬን አስሮ የዋልክበትን እና ያደረግሁትን ሁሉ
አስወተወተኝ::

የማንም ጭቅትም ጭቅቅቱን ሲያንጨፈጭፍበትና የማንም እከካም
ሲንቦጫረቅበት ከዋለው ውሃ ውስጥ ማን አባክ ግባ አለሀ?! ደግሞ ከማንም
ውርጋጥ ጋር ሆያ ሆዬ ሲባልልኝ ተውሏል! ቆይ! አረ ገና ምን አይተህ!» ብሎ አይቀጡ ቅጣት ከቀጣኝ ወዲህ ያቺኑ አልፎ አልፎ ወጣ ወጣ የማለት ድብት ነጻነቴን ቀስ በቀስ አጣኋት፡፡....

💫ይቀጥላል💫
👍3👏1
#የወድያነሽ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


...ከማንም ውርጋጥ ጋር ሆያ ሆዬ ሲባልልኝ ተውሏል! ቆይ! አረ ገና ምን አይተህ!» ብሎ አይቀጡ ቅጣት ከቀጣኝ ወዲህ ያቺኑ አልፎ አልፎ ወጣ ወጣ የማለት ድብቅ ነጻነቴን ቀስ በቀስ አጣኋት፡፡

ከአባቴ ፊት ለፊት ቆሜም ሆነ ተቀምጨ የታየኝን መናገርና እንደ ልብ
መዝናናት እንደ ቅብጠትና ብልግና ስለሚቆጠር ፍርሃት ያልሞሰሞሰው ለጋ
መንፈሴ ሥቃይ ፈጥሮብኛል...

አባቴ ተነሥ ግባ የተባለ ይመስል ድንገት ተነሥቶ ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ። አባቴ በመሆኑ ባልጠላውም ተነሥቶ በመሔዱ ቀለለኝ፡፡

እንዲት አነስተኛ ጥፋት ባጠፋሁ ቁጥር በመመከርና በልዩ ዘዴ በመገሠጽ ፈንታ የምቆነጠጥና የምሠታ ስለሚመስለኝ ትንሽ የልጅነት ጥፋት ባጠፋሁ ቁጥር ፍርሃት ይንጠኝ ነበር፡፡

አንድን ነገር ለማሰብ ሳይሆን ያሰብኩትን ትክክለኛ ነገር ለመፈጸም ወኔ የሚከዳኝ በዚህ ስውር ጫና የተነሣ ነው::

መገረፍና መቆንጠጥ ከቀረልኝ ጥቂት ዓመታት ዐልፈዋል፡፡ ሆኖም ያ በልጅነቴ በፍርሃት የተበከለውና በቁጣ የበለዘው አንጎሌ ለብዙ ዓመታት ያህል ሊሽር አልቻለም፡፡

ምሳዩን በልቼ ስጨርስ ስምንት ሰዓት ከኻያ ደቂቃ ሆናል። እንግዴ መቀበያ ክፍል ውስጥ የሚገኘውን ትልቅ ራዲዮ ድምፁን ዝቅ አድርጌ ከፈትኩት። የአምባሰል ሙዚቃ ይዘፈን ነበር፡፡

አስካለ እንጀራውን ካነሣች በኋላ የእጅ ውሃ ይዛልኝ ተመለሰች።

«ውሃውን አስቀምጠሽ ሂጂ» ስላልኳት አስቀምጣ ሄደች። እጄን ሳልታጠብ ተነሳሁና የሙዚቃውን ሥልታዊ አነሳሥና አወዳደቅ እየተከተልኩ አንድ ቦታ ላይ ቆሜ ንፋስ እንደሚያወዛውዘው የመቃ ቀምበጥ ተወዛወዝኩ፡፡
የአዲሲቱ ሠራተኛ ከሲታና ጠውላጋ ፊት በጥቂቱ ፈገግ ሲል ታየኝ። እንደ
ኮቸሮ ደርቆ የተንቀፈረረው ከንፈሯ ላመል ታህል ተላቀቀ። አቀማመጣቸውና
ቅርፃቸው ቁመትና ስፋታቸው ከጠባቧ ፍንጭት ጋር ልብን የሚማርኩና ስሜትን
የሚያረኩ ጥርሶች ታዩ። በመጠኑ ወየብየብ ብለው ጐድፈዋል። ውበትን ጥቁር ደመና እንደ ጋረዳት ጨረቃ በፊት ለፊቴ አድፍጦ አየኋት፡፡ ደካማ ፈገግታዋ
ግን ወዲያው በንና ጠፋች።

የትዕዛዝ ሳይሆን የልመናን ሁኔታ በምትገልጽ ድምፅ «ለእጄ ውሃ
ብትስጪኝ?» ብዬ ጠየቅኋት። መወልወያውን መሬት ጣል አድርጋ መጣች፡፡
ማስታጠቢያውን አንስታ በቀጭኑ አንቆረቆረችልኝ:: ያን ከሩቅ ያየሁትን ጸጉሯን ከቅርበት እስተዋልኩት፡፡ አንዲት ነቀዝ መሳይ የራስ ቅማል በዞማው ጸጉሯ ላይ ስታዘግም ቆይታ፡ ወዲያው ፍልቅ መሸጐጫ አግኝታ ተሸጐጠች፡፡ ልቤ ግራር ፍም ላይ እንደ ወደቀች የጮማ ምታሪ በተመሰቃቀለ ስሜት ሟከከች፡፡ የአካላቷ ጠረን እጅግም ደስ ሳይለኝ አስታጥባኝ ሄደች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዋል እደር እንዳለች የተሰጣትን ሥራ ሁሉ በጥንቃቄ መሥራት በመቻ መላው ቤተሰብ ደስ ተሰኘ፡፡ ዋናው ምድብ ሥራዋ ግን የቤተሰቡን ልብሶች ማጠብና የምትችለውን መተኮስ ሲሆን አልጋ ማንጠፍና ቤት መወልወል ተጨማሪ ሥራዋ ነበር፡፡ ሰው ሁሉ ወደዳት። ትሕትናዋና ታዛዥነቷ ለተወዳጅነቷ
ዋና ምክንያት ነበሩ፡፡ ከመዋል ከማደር ከሲታው አካላቷ ሥጋ በመደረሱና
ደሟም መለስ በማለቱ በሦስት ወር ውስጥ መለል ብላ የምትታይና ማለፊያ
ፈገግታ ያላት አንገተ ሰባራ ወጣት ሆነች፡፡

ስለ ሠራተኛይቱ አሠራርና አስተያየት የነበረኝ ግምት ሁሉ ከቀን ወደ
ቀን ተለወጠ። ማንኛውንም ለእኔ የሚያስፈልገኝን ነገር ሁሉ እሷው እየሠራችና እያዘጋጀች እንድታቀርብልኝ ሙሉ ፍቃዴና ፍላጐቴ ሆነ፡፡ የልብሶቼን መቆሸሽና ያለመቆሸሽ እሷው ራሷ እየተመለከተች የተቻላትን ያህል ማጠብ አንዱ የሥራዋ ክፍል ለመሆን በቃ፡፡ ከዕለት ወደ ዕለት ትሁት አቀራረቧና ሥራዋ ሁሉ አስደሰተኝ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እህቴ ኖረችም እልኖረችም ራቴንም ሆነ ምሳየን የምታቀብርልኝ እሷው በመሆኗ ጠባይዋንና ሁኔታዋን በየጊዜው ለማወቅና ለመረዳት ቻልኩ፡፡

በአማከለች የእኩል ነኝ ባይነት» ንግግር አንጀቷ አርሮ የነበረው እናቴ እንደ ልብ ታዛዥና አቤት እመት የምትል ሠራተኛ በማግኘቷ ካሰችኝ እያለች ስትጠራት ጥቂት ልደታዎች አለፉ፡፡

ሰው ሁሉ ስሟን ጠይቆ ለማወቅ የፈራ ይመስል በማናውቀው በዋናው
ስሟ ሳትጠራ ከስድስት ወራት በላይ ዐለፉ፡፡ ትልቁም ትንሹም «አንቺ ልጅ
ወይም «አንቺ እንግዳይቱ» እያለ ስለሚጠራት የቀድሞ ስሟን የረሳች ወይም ስም የለሽ አስመሰላት፡፡

እሑድ አራት ሰዓት ገደማ ነበር፡፡ ቀላል የራስ ምታት ወረር ስላደረገችኝ
ከመኝታዩ ላይ ሳልነሣ አረፈድኩ፡፡ ተነሥቼ የወጣሁ ስለ መሰላት አልጋ ለማነጣጠፍና ክፍሉን ለመጠራረግ በቀስታ እያንጎራጎረች ዘው አለች። ቀጥ ብዬ በጀርባዬ ተንጋልዩ ስለ ነበር አልጋው ላይ ሰው ያለ አልመሰላትም፡፡በእንጉርጉሮ
የምታስኬዳትን ዜማዋን ሳታቋርጥ የብርድ ልብሱን መኻል በእጅዋ ነካችው።
ለአፍታ ያህል ጸጥ ብዬ ሳዳምጥ ከቆየሁበት ብርድ ልብስ ውስጥ ከመቅጽበት ራሴን ብቅ ሳደርግ በድንጋጤ ፈዝዛ ቆመች፡፡ አቀርቅራ ጥቂት ዝም ካለች በኋላ
“እኔ እኮ ወደ ውጪ የወጡ ስለመስለኝ ነው የገባሁት ብላ መሬት መሬቱን
ማየት ቀጠለች።ድንጋጤዋ እንዲለቃትና ፍርሃቷ እንዲወገድላት በማሰብ
ለጊዜው በዚያች ሰዓት የማያስፈልገኝን «እስኪ ሂጂና ለፊቴ ውሃ አምጭልኝ
ብዩ አዘዝኳት። እንዳቀረቀረች ወጣች። የውስጥ ቁምጣዬን እንዳጠለቅሁ እና ነጭ እጀ ጉርድ የውስጥ ጥብቆ እንደለበስኩ ብርድ ልብሱን ወደ ግርጌ ሽብልዩ ደረብኩና አልጋዬ ጫፍ ላይ ዐረፍ አልኩ፡፡ ለብ ያለ ውሃ በንጹሀ
ማንቆርቆሪያ ይዛ ተመለሰች።

በግራ እጅዋ የያዘችው ቀለሙ የተላላጠ እሮጌ ነጭ ሳሀን ዐልፎ ዐልፎ የተላከከና የማይለቅ እድፍ ነበረበት፡፡ ጋቢውን ከላዩ ላይ ገፍፌ አልጋው ላይ አኖርኩት፡፡ ማንቆርቆሪያውን እንዳንጠለጠለችና ሳሀኑን እንደ ዘረጋች ፊቷን ወደ ጎን አዙራ ቆመች። ራቁቴን የቆምኩ ስለ መሰላትና አለማፈሬም ስላስደነቃት የተገላቢጦሽ እሷ ማፈሯ ነበር፡፡ በቤታችን ውስጥ ሰው ባለመኖሩ በሩን ዘጋሁት።
አሁንም ፊቷ ወደ ተዘጋው በር እንደ ዞረ፡ ከመጠን በላይ አቀርቅራና በሙሉ
ዓይኗ ሳታየኝ አስታጠበችኝ፡፡ ያንቆረቆረችልኝ ውሃ አወራረድ እስከ መጨረሻ ሳይለወጥ ተንቀረቆረች።አፌን ለመጉመጥመጥ እንደ ፈለገ ሰው ጣቶቼን ቀልብሽ መዳፌን ውሃ ለማቆር እስኪችል አጐደጐድኩት። ውሃ እንድታንቆረቁርልኝ እጄን ዘረጋሁ። በዝግታ አንቆርቁራ ሞላችልኝ። አቀርቅራ ስታይ በሳህኑ ውስጥ የሚገኙትን የሳሙና አረፋዎች የምትቆጥር ትመስል ነበር፡፡ ጸጉሯ በሻሽ ባለመሸፈኑ በእጄ ላይ ያቆርኩትን ውሃ በዝግታ ጸጉሯ ላይ እንጠባጠብኩት፡፡ምንም እንኳ ውሃ እንዳፈሰስኩባት ወዲያውኑ ቢሰማትም ቀና ብላ አላየችኝም፡፡ቆየት ብላ ግን ራሷን እየነቀነቀች «እችክእችክ እችክ» ብላ ዝም አለች። ነገር ግን ባፍንጫዎ በኩል የተሰማችው ለዛማ ቀጭን የሣቅ ድምፅ መሣቋን አሳወቀችባት።
ውሃው በግንባሯ በኩል አኳልሞ ቁልቁል ወረደና ወለሉ ላይ ተንጠባጠበ፡፡
የፈገገውን ጠይም ፊቷን ለመመልከት በጣም ካጎነበስኩ በኋላ እንገቴን ወደ ጎን
ቆልምሜና ፊቴን ጋደል አድርጌ አሻቅቤ በማየት የፈገግታዋን መጠን ለካሁ፡፡
«ስምሽ ማን ነው? እስኪ ንገሪኝ?» ብዩ የአካላቴን አኳኋን ሳልለውጥ ጠየቅኋት።
አሽቆልቁለው ጉንጩን የሚመለከቱት ዐይኖቿ በሰፊው ከተከፈቱ በኋላ የማለዳ
ፍንድ አበባ የሚመስሉ ከንፈሮቿ ተላቀቁ፡፡ ቀጠን ብላ ቃናዋ እጅግ በሚማርክ
ድምፅ የወዲያነሽ» ብላ ከንፈሮቿን ወደ ውስጥ ቀልብሳ መጠጠቻቸው። ቀና
ብዩ በትክክል ቆምኩ፡፡ ልቤ ባንዳች የድንጋጤ ኃይል የተናወፀች ይምስል
👍91
ዷዷታና ንዝረቷ ተለወጠ፡፡

ስሟን በማወቄ ብቻ የመነሻው ምክንያት ያልተከሠተልኝ ሥውር ግን ብሩህ የሕሊና ደስታ ተሰማኝ፡፡ መላ ሰውነቴ ልገልፀው በማልችል ስሜት ተፍነከነከ፡፡

ማንቆርቆሪያውንና በጐድጓዳ ሳህን ውስጥ የነበረውን እጣቢ ይዛ ወጣች
ተልካ ስትመጣም ይሁን ወይም ባጋጣሚ ጉዳይ ጋሽ ጌታነህ ብላ በአንቱታ ስትጠራኝ በአክብሮቷ ሳይሆን ከድምጿ ለዛ ጋር አንቱ በማለቷ ብቻ
በእጅጉ ወደድኳት፡፡ስለ ቤት ሠራተኞች ሥራ ምንም የማያውቀውና ደንታ የሌለው አባቴ እንኳ ሲወራ በሰማው ትጉህ ሠራተኝነቷና ታዛዥነቷ ተደስቶ አንድ ሁለቴ ያህል አመስግኗል እናቴም በበኩሏ ከዚያ ቀደም ለማንኛዋም ሠራተኛ አሳይታ የማታውቀውን ደግነትና ቀረቤታ አሳይታለች። እናቴ ቀደም ሲል ያረጁ
ቀሚሶችዋንና ልብሶችዋን የምትሰጠው ላንዳንድ ድሃ ጐረቤቶቻችንና ለሌሎች
'የድሃ ዘመዶቼ ለምትላቸው ነበር፡፡

ዛሬ ግን በመጀመሪያ ተመርጦ የሚሰጠው ለየወዲያነሽ ሆነ፡፡ ከነባሮቹ
ሠራተኞች ጋር ባንዳንድ በጋርዮሽ በሚሠሩ ሥራዎች ካልተገናኙ በስተቀር
በማንኛውም ጊዜ እንዳትጠጋቸው ብዙ ጊዜ በጥብቅ ተነግሯታል፡፡ ምንም እንኳ
ረቂቅ የሆነ የበታችነት ስሜት ውስጥ ውስጡን ቢያነክታትም አብዛኛውን ጊዜ
የምታወራውና የምታቧልተው ከየውብነሽ ጋር ሆነ። ጠባይ ለጠባይ በደንብ እስከ
መተዋወቅና እስከ መግባባት ደረሱ፡፡ በእሷና በየወዲያነሽ መካከል ያለው
ግንኙነት ከዕለት ወደ ዕለት ደራ፡፡ መላ ቤተሰባችን እንደ ወደዳትና እናቴም
እሷን እኮ እንደ ልጄ ነው የማያት፡ ትሕትናዋ ብቻ ይበቃል» እንዳለች ዘጠኝ
ወሯ እንደ ዘጠኝ ቀን ዐለፈ።

የየወዲያነሽ አካላዊ ቅርፅና እቋም እየተስተካከለ አማረ፡፡ የተፈጥሮ ውበቷና ቁንጅናዋ ከያደፈጡበት ፉካ ቀስ በቀስ እያዘገሙ ወጡ፡፡ ጉንፎቿ ሞላ ብለው በትንቡክቡ የወጣትነት ደምና ሥጋ ጠረቁ። ምርጊቱ ተገሽልጦ እንደ
ወደቀ ግድግዳ ፈጥጦ የነበረው አጥንቷ በሥጋ ተሞልቶ በመጠርቃቱ ማለፊያ
ወጣት ሆነች፡፡ ድፍርስና ስርግ የነበሩት ዐይኖቿ ቅላታቸው ተገፍፎ በመጥራቱ፡
እንደ ውድቅት የጨለማ ውስጥ ጧፍ ቦግ ብለው ወጡ፡፡

ከሁሉም በላይ ደስ የሚያሰኘውና የሚማርከው ግን ፈገግ ብላ ስትሥቅ
ጠይሙ ጉንጫ ላይ ጉድጎድ ብለው የሚሰረሞጡት ድምብሉቿ የውበቷ ልዩ
ምንጮች ናቸው:: ያ ያረጀ ሞረድ ይመስል የነበረው ክንዷ እንደ መዳመጫ ድንጋይ ለስልሶ ውብ ገላ ሆነ። የውብነሽ ሁለትና ሦስት ገዜ ያሀል ከልብሶቿ መኻል የማይሆኗትንና ያረጁባትን መራርጣ ስለሰጠቻት የእናቴን ቦርቃቃ
ቀሚሶች አውልቃ ጣለች።

እኅቴና የወዲያነሽ በቁመትና በአካል መጠን አይተናነሱም፡፡ በዕድሜም
ቢሆን በጣም ተቀራራቢ ናቸው:: አብረው ሲቀመጡም ሆነ አጥር ግቢው ውስጥ
ከወዲያ ወዲህ ሲሉ በጣም ያምርባቸዋል። የወዲያነሽና እኅቴ ሲጠራሩ «አንቺ ስለሚባባሉ ጓደኝነታቸው እያደር ጠበቀ። የአንዳንድ ተራ ጉዳዮችም ምስጢረኛች የወዲያነሽ የተጣለላትን ልብስ ለብሳ ከየትኛውም አቅጣጫ ብቅኸ ስትል በውበቷና በደም ግባቷ ልቤ ክፉኛ መደንገጥ ጀመረ። አንዳንድ ቀን ያንን ጥቁር ዞማ ጸጉሯን ባራትና ባምስት ኣቅጣጫ በቀጭኑ ጐንጉና ትለቀዋለች።
የአጐናገኑን ዘዴ በመውደድ ዓይን መከታተል ልብ ያላልኩት ተግባሬ ሆነ፡፡

ደረጃ ስትወጣም ይሁን ስትወርድ የአካላቷ ንቅናቄና አካሒዷ ፀጉሯን ከወዲያ ወዲህ ሲያዘናፍለው የንፋስ ሽውሽውታ እንደሚያንቀሳቅሰው እንደ ለመለመ የወይን ሐረግ ቀንበጥ ደስ ይላል።

አልጋዬን ለማንጠፍ መኝታ ቤቴ በገባች ቁጥር የተዝረከረኩና የተበታኑ
መጻሕፍትና ወረቀቶች ሰብስባ ስለምታስቀምጥልኝ የግሌ ሠራተኛ ትመስል ነበር፡፡ወይዘሮ የውብዳር ወደ ቤት በመጡ ቁጥር ስለ እርሷ ጠባይና ሁኔታ እንዲሁም ታማኝነት ሳይጠይቁና
እ ..ሀ” ሳይሉ አይሔዱም፡፡

ከየወዲያነሽ ሳይሆን ከእናቴ ምስጋና ለማግኘት ሲሉ «ኪዳነምሕረትን፣ አቤት! ዛሬስ በጣም አምሮብሻል፡፡ እኔም እኮ ብየሻለሁ፡ እየሽው አይደል! ትልቅ
ሰው ቤት መግባት እንዲህ ያሳምራል፡፡ ወደፊትም ጠባይሽን አሳምረሽ በዚሁ
ዓይነት ዘለቅሽ እሜቴም ሆኑ ጌቶች ጥለው እይጥሉሽም» እያሉ ይሸነግሏታል።

እሑድ ዕለት ማታ ከራት በኋላ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ ተቀምጬ
መፅሐፍ ሳነብብ እናቴ ከወደ መኝታ ቤት መጥታ እንካ እስኪ ጌታነህ ዛሬ
ደግሞ ለዚች ለየወዲያነሽ የአራት ወር ደሞዜን ተቀብያለሁ አስብለህ አስፈርምና
ስጣት፡፡ ያለፈውን የአራት ወር ደሞዝዋን ግን እርስዎ ጋ ይሁንልኝ ብላ እኔውጋ
አስቀምጨላታለሁ» ብላ ኻያ ብር ሰጥታኝ ሔደች። ምንጊዜም ከኔ ዘንድ
የሚቀመጠውን የደረሰኙን ደብተር ለማምጣት ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ፡፡ ነገር ግን እንደገና መመለስ ስላልፈለግሁ እዚያው ተቀምጬ ቀረሁ፡፡ የድካሟን ዋጋ
ተጠራቅሞ በማግኘቷና እንደ ከዚያ ቀደሞቹ ሠራተኞች «ይህን ሰብረሻል ያን
አጥፍተሻል» ተብላ ደሞ ባለመቆረጡ በልቤ ዙሪያ ልዩ ደስታ ተግፈለፈሉ።
የውብነሽ ለነገ ተሠርቶ የሚቀርብ የሒሳብና የድርሰት ሥራ አለብኝ ብላ መኝታ ቤቷን ዘግታ ሥራ ከጀመረች ቆይታለች። ከአራት በማይበልጡ መስመሮች የአራት ወር ደሞዜ ደርሶኛል የሚል ሐተታ ከጻፍኩ በኋላ ከመኝታ ቤቴ በር ላይ ብቅ ብዩ በቀስታ "የወዲያነሽ" ብዬ ተጣራሁ፡፡ አረንጓዴ ሻሿን በአንገቷ ዙሪያ በልቡ ሸብ አድርጋና ጸጉሯን እንደ ለምድ ትልታይ በጆሮ ግንዷ አኳያ አንዠርጋ በመጠኑ ወደ ውስጥ ዘልቃ ቆመች፡፡ “ገባ በይ» ብዬ ስላዘዝኳት ሁለት አጫጭር ርምጃዎች ወደፊት ተጠጋች፡፡ «በይ እንግዲህ እዚች ላይ ፈርሚ» ብዩ የቀኝ እጅ ክንዷን ተንጠራርቼ ያዝኩ። የአካላቷ ትኩሳት በጣቶቼና በመዳፌ በኩል ተሻግሮ ወደ መላ ሰውነቴ በልዩ ስሜታዊ ፍጥነት ተሰራጨ።

ሰውነቴ ንዳዱ እንደ ተነሣበት ሰው ውስጥ ውስጡን ተንዘፈዘፈ። አውራ
ጣቷን ቀለም ቀብቼ ለማስፈረም ወደ እኔ ሳስጠጋት ሣቅ አመለጣትና ወደ ውጭ
እንዳይሰማ ኣፏን በግራ እጅዋ ኣፍና ተንከተከተች:: መነሸዋን ባላውቅም በመሳቋ ረካሁ እንጂ ቅር አላኝም። አስፈረምኳት፡፡ «መጻፍና ማንበብ ትችያለሽ እንዴ?”ብዬ ጠየቅኋት። ጠይም ፊቷ በፈገግታ ወገግ በማለቱ በመስከረም ወር ቡቃያ ላይ ብርሃኗን የፈነጠቀች የጧት ፀሐይ መሰለች።

ፈገግታዋ ሳይቀንስ ከንፈሯ ተከፈተ። የልቦናዋን እንጃ! አፏን ግን ዝምታ ገታው፡፡ ትንሽ ዘግየት ብላ ግን «ብቻ» ብላ ዝም አለች፡፡ ብቻ” በማለት
የገታችው ሐሳቧ ግን አንጎሌ ውስጥ አዲስ የሃሳብ ቦይ ቀደደ፡፡

ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ የወዲያነሽን አስተካክዬ ለማየት ምቹ ሥፍራና ጊዜ
በማግኘቴ በጣም ደስ አለኝ። ምንም እንኳ በዚያች ሰዓትና አካባቢ ሰው
አለመኖሩን አሳምሬ ባውቅም በፍርሃትና በጥርጣሬ ዙሪያውን ቃኘሁት። የውስጣዊ
ስሜቴ እሳተ ገሞራ ናጠኝ፡፡ አድፍጦ አይጥ ስትጠባበቅ እንደ ቆየች ድመት
ዘልዩ እንገቷ ላይ ተጠመጠምኩ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ግን ከእንቅልፉ እንደ ባነነ ሰው ወደ ትክክለኛው የውነት ዓለም ስመለስ አልጋዬ ላይ በግንባሬ ተደፍቼ ነበር። ማንም አጠገቤ ኣልነበረም። የወዲያነሽ እንዴት እንደ ሄደችና እንዴት እንደ ለቀቅኳት አልታወቀኝም። አልጋው ጫፍ ላይ የነበረው ደመወዟ ተበትኖ አገኘሁት፡፡

ገንዘቡን እንደገና ቆጥሬ ኮት ኪሴ ውስጥ ከተትኩ፡፡ ቀደም ሲል በፈጸምኩት ድርጊት ውስጣዊ ኃፍረት ተሰማኝ፡፡ መጠኑን የሳተ አካላዊ የስሜት ጥማት እንጂ አንዳችም እርካታ ሳላገኝ ቀረሁ፡፡ ልብሴን በማወላልቅበት ጊዜ
አቋቋሟና አነጋገሯ የዐይኖቿ ማራኪ ውበትና የአንገቷ አሰባበር በተለይም ከናፍሯ ከፊቴ መጥቶ ተደቀነ፡፡

በየዕለቱ ስለ እርሷ ማውጣትና ማውረድ መጨነቅና ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡
አዲስ የሕይወት መስታወት
👍5
ከፊት ለፈታ ታየኝ! ጋደም እንዳልኩ «እኔና እሷ እኮ እኩል ነን፡ የሰው ልጅነት ሚዛናዊ እኩልነታችንና የተፈጥሮ ክብራችን
አይሳሳቅም፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ እሷን እንደ በታቼና እንደ ተዋራጅ መቁጠር
የለብኝም» እያልኩ ልዩ ልዩ ምቶችንና በዐላማ ላይ የተመሠረቱ ተስፋዎችን
አንጎሌ ውስጥ ሸቅሽቄ ጥቂት ሰዓት አሳለፍኩ፡፡

በማግሥቱ ሰባት ሰዓት ተኩል ገደማ ላይ ለምሳ ወደ ቤት ስገባ ልብስ ስታጥብ ደረስኩ፡፡ መክረሚያዋን ቀና ብላ እንኳን አይታኝ አታውቅም ነበር፡፡እኔም እንደ ዘበት ነበር ኣልፌያት የምገባው:: በእጅዋ ላይ የነበረውን የሳሙና አረፋ እየፈነጠቀች ኃፍረት በሚያሳድዳት ፈገግታ አይታኝ ሥራዋን ቀጠለች፡፡
ምላሴ የተቋጠረች ወይም ከላንቃዬ ጋር የተሳከከች ይመስል «እንደምን ዋልሽ?»
ማለት እንኳ ተስኖኝ ዝም ብያት ገባሁ፡፡

አባቴና ሽምገልገል ያለ ሦስት አዛውንቶች ብዙ ወረቀቶች ዘርግተው ሲከራከሩና ሲጨቃጨቁ ደረስኩ፡፡ ጐንበስ ብዬ እጅ ነሣሁ፡፡ በትዕዛዝ የተነገሩ ይመስል ሁለም በአንድ ጊዜ ቀና ብለው አዩኝ፡፡ ከእንግዶች እንዱ ብቻ እንደምን ውለሃል» አሉኝ፡፡ ነገር እንደሚጎነጉኑና ጣለው ጠፍረው እንደሚሉ ስለ ገባኝ አንጎሌ እክ እንትፍ ብሏቸው በቀጥታ ወደ መኝታ ቤቴ ገብቼ በሩን ጎሰም አደረግሁት። የወዲያነሽ የእጅ ውሃ አምጥታ አስታጠበችኝ። ወጣ እንዳለች አካሌ
ልዩ ውስጣዊ እንቅስቃሴ ጀመረ። የልቤ እመታት ፍጥነት ተለወጠ።እያቁነጠነጠ
እንዳች የሚያንዘረዝር ነገር የተነሣብኝ ይመስል የሚያቅበጠብጥ ነገር ወረረኝ፡፡ ያመጣችልኝን እንጀራና ወጥ ባጠቧ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣልኝ ወጣች። ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ጸጉሯ አየኋት፡፡ ለምን ወጥ እንዳላመጣችልኝ ባላውቅም እኔው እያወጣሁ በላሁ። በጥቂት ወራት ውስጥ ሰውነቷ እንዲህ በመለወጡ በጣም ተደነቅሁ። ደለል እንደ ተኛበት ቦይ ጉሮሮዬ እህል አላወርድ አለ። ጎንበስ ብላ መዓዱን በምታነበት ጊዜ “የውበት ቡቃያ አልኳት፡፡ በለሆሳስ ነበር። እጄን አስታጥባኝ ከወጣች በኋላ ልብሴን ቀያይሬ አለባበሴን በመስተዋት ተመለከትኩ፡፡ መኝታ ቤቴ ውስጥ የተንጠለጠለችው መስተዋት ቁመቷ አንድ ክንድ ተኩል ወርዷ እንድ ክንድ ይሆናል፡፡

አሁንም ወረቀታቸውን ዘርግተው በሚወያዩት ሰዎች አጠገብ ዐልፌ ወደ
ውጭ ወጣሁ፡፡ ወዲያም ወዲህ ሳልል የወዲያነሽ ልብስ ወደምታጥብበት ቦታ
ሄድኩ፡፡ . ያ ከልጅነቴ ጀምሮ የቦረቅሁበት፣ ኩኩሉና ኳስ የተጫወትኩበት ግቢ በጣም አስደሰተኝ፡፡

የምታጥበውን ልብስ እያየሁ «እማማና የውብነሽ ወዴት ሄዱ?» ብዬ ጠየቅኋት። የእነርሱን መኖርና አለመኖር የሚያስጠይቅ ምንም ምክንያት
አልነበረኝም፡፡ የመጠየቂያዬን ምክንያት እንጠርጥሬ ባላውቅም ወደ የወዲያነሽ
እያዳፋ የወሰደኝ በውስጤ የተቀጣጠለው የወጣትነት ነዲድ መሆኑ ገና እሷን ማነጋገር ስጀምር ገባኝ፡፡ ምንም እንኳ ባለፉት ወራት በልዩ ልዩ ጊዜ ዘና ብላ ስታወራ ብሰማትም አሁን ግን ልዩ ደስታ የሚሰጥ መስሎ ታየኝ።

«'አንቺም በዚያው ወደ ትምህርትሽ ትሄጃለሽ፡ ነይ አብረን እንሒድ
ብለው አሁን አንቱ ልትመጡ አቅራቢያ ወጣ አሉ» ብላ በሚገመጥ ፈገግታና
ሕይወት በሚያረሰርስ ሁናቴ እጅዋ አረፋው ውስጥ እንደ ተነከረ መለሰችልኝ፡፡
ምላሴ ተሳስራ እምቢ ባትለኝ ኖሮ ባያሌው ለማውራት አስቤ ነበር፡፡ ሆኖም
በኃፍረት ከተለጐመ ኣንደበት ጋር የሚደረግ ጊዜያዊ ግብግብ ከባድ በመሆኑ ዝምታዩ አይሎ ሰጥ አሰኘኝ፡፡ ደመወዟ ከእኔ ጋር ውሉ በማደሩ ከኪሴ አውጥቼ “እንቺ» አልኳት። ትኩር ብላ አይታ ተቀበለችኝ። ስንት እንደ ሰጠኋት እንኳ ሳትቆጥር በደረቷ በኩል ወደ ቀሚሷ ጉንፍ ለቀቀችው:: ከዚያም ቀጥ ብላ ስትቆም በእጅዋ ላይ የነበሩት የሳሙና አረፋዎች በፀሐይዋ ብርሃን የቀስተ ደመና ቀለማት ኀብር እያሳዩ ተራ በተራ ፈነዱ። በአእምሮዬ ውስጥ ወዲያው እየተረገዙና በሐሳብ ምጥ እየተወለዱ የሚፈነዱትን የፍቅር አረፋዎችና የመውደድ ትርኢቶች ግን በገሃድ ማየት አልቻልኩም፡፡ አይቼ ሳልጠግባት ተለያቻት ሄድኩ።

በሳምንቱ የውብነሽ ጋር ወደ ገበያ ወጥታ አዲስ ልብስ አሠፍታና ሌሎች ነገሮችም ገዝታ መጣች። ያ ውብ ጸጉሯ በአዲስ ቡናማ ሻሽ ሸብ ተደር ዘንከት ዘንነከት ስትል እንደ ማለዳ የአበባ ላይ ጤዛ የወጣትነት ዐይኔን ማረከችው። በእንግድነትም ይሁን በሌላ ጉዳይ ሰዎች ወደ ቤት መጥተ በሚያወሩበትና በሚጫወቱበት ጊዜ አንድ ዕቃ ለማቀበልም ይሁን ወይም

ነገር ለማቅረብ ስትመላለስ ሰዎች ባይናቸው እንኳ ሲከታተሏት ካየሁ ውስጤ በቅናት በግኖ አንጀቴ ያርር ነበር፡፡ አይተው የሚጨርሷት እንጂ እንደ ውብ
ኮከብ ከሩቁ ተመልክተው የሚተዋት ስለማይመስለኝ በንዴት እተክናለሁ። በባዶ የቅናት ስሜት እርር ድብን እያልኩ ቅናቴን ለመሰወር ያለማቋረጥ ተሠቃየሁ፡፡ በጣም ልዩ የሆነብኝ ግን የገዛ አባቴ እንኳ እያሞጋገሰ ሲጠራትና እንደ ስንዴ ቡቃያ ደስ እያለችው በአረጋዊ ፈገግታ ሲመለከታት በምሰማና በማይበት ጊዜ የቅናቴ ጥርቅም ቆመጡን ይዞ አናት አናቴን ይተረትረኛል። ዐይን
እንዳይጥልባት እና ምናልባትም ሁኔታው ከዚያ እንዳያልፍ ለማድረግ የምችልበትን ዘዴ ሌት ተቀን ማውጠንጠን ጀመርኩ። ለጊዜውም ቢሆን የአባቴ ዐይኖች በፍትወት ተነድፈው በሥጋዊ አምሮት ሳይጠመዱ አልቀሩም፡፡ ሆኖም
በምንም ይሁን በምን ከአባቴ ጋር ተሽቀዳድሜ እና ተፎካክሬ ድል ማድረግ
እንዳለብኝ ወዲያው ገባኝ፡፡ ፍቅራዊ ፍላጐቴን ከግቡ ለማድረስ ውስጣዊ
ብርታትና ከተደቆሰው ወኔዬ ውስጥ የተወለደው አዲሱ እልሄ በልዩ ኃይል
ወደፊት ገፋፋኝ። ጥንካሬው ገና ወደፊት ሊለይለት ነው፡፡
አንድ ቀን ማታ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ እንደተሰበሰብን ቡና ተፈላ፡፡ የወዲያነሽ ቡና ለመስጠትና ስኒ ለመሰብሰብ ከወዲያ ወዲህ ትመላለስ
ነበር። የእኔና የአባቴ ዐይኖች የወዲያነሽ ዘንድ እየደረሱ ሲመለሱ ካንድም ሁለት
ሦስት ጊዜ ተጋጩ፡፡ በዚያች ሰዓት «ለምን ታያታለህ?» ብሎ ቢጠይቀኝ «አንተስ ለምን ታያታለህ?» ብዬ እመልስለታለሁ እያልኩ እኔዉ ከእኔው ጋር አተካራ ገጥሜ ተቀመጥኩ፡፡ በውስጤ ያልኩትን ሐሳብ ፊት ለፊት መናገር እንደማልችል ግን አሳምሬ ዐውቃለሁ፡፡

ቡናው ከተከተመ በኋላ ሒጂ እስኪ ከነ አስካለ ጋር ሆነሽ ያንን ጋን እጠኑት ብላ እናቴ ስላዘዘቻት የወዲያነሽ ወደ ምድር ቤት ወረደች።

የየወዲያሽን ከዚያ ግድም መሄድ ያወቀው አባቴ ታምቆ የከረመው
ስውር ፍላጐቱ ድንገት በመገንፈሉ ጉዳዩን አገላብጦ ሳያይ ውበቷን ገልጾ
ለመናገር ተገደደ።

ፊቱን በመጠነኛ ፈገግታ አፍክቶ ወደ እናቴ ዞር ካለ በኋላ «አንቺ ተካበች» አለ፡፡ እንደገና የምንትለኝ ይሆን የኃፍረት ገፅታ በፊቱ ላይ እየተነበበ።

«ይቺ ልጅ እንዴት አማረባት? ዘቢብ መሰለች አይደል እንዴ? እንዲህ ብስል ሎሚ የመሰለች ናትና!» ብሎ ንግግሩን ለመቀጠል አፉን እንደከፈተ፡ ያቺ ውስጥ ውስጡን በጥርጣሬ የተንሰዋለለችው እናቴን ቁጣዋን አዘጋጅታ የቆየች ይመስል“ያ በየሰው ቤት የምሰማውና ሆድ ሆዴን ሲበላኝ የኖረው ቅሌት ይባስ፧
ብሎ እዚሁ እቤቴ መጣ? 'አዛውንት ነኝ ልታፈር፡ ልከበር ማለት የለም፡፡ ቀሚስ ካጠለቀች፣ መቀነት ካዞረች አገባችበት መግባት ነው» ብላ ንዴት ስላዳፋት ዐይኖቿ ተጎለጎሉ፡፡ የሁለቱ ነገር እባብ ለእባብ ሆነብኝ፡፡ ቅፅበታዊ ቁጣዎ
እእምሮዋ ውስጥ ከተፀነሰ ነገር አፈትልኮ እንደወጣ ገባኝ። ለካስ ቀስ ብላ ትሰልል፣ ኖሯል አልኩ በውስጤ።....

💫ይቀጥላል💫
👍6
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ_አምስት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

....ቲናን አይኗን በፍርሃት ጎልጉላ እያየችው “ሚ/ር ዊሊያምስ እኔ ህይወቴን እፈልገዋለሁ። እንደ ድሮ ነፃ ሆኜ መኖር እፈልጋለሁ።” አለችው፡፡

አድሬኒ እንደነገረችው ከንቲባው ሴትየዋን በወሲብ የሚተነኩስበት አቋም የላትም። ባይሆን ቆንጆ እና ብልህ አዕምሮ እንዳላት ታስታውቃለች፡፡

“ብዙ ጊዜ ከቦታ ቦታ ቤት እየቀየርሽ ትዘዋወሪያለሽ?” ብሎ ጠየቃት፡፡
መልሷን ቢያውቀውም “አዎን። ምክንያቱም አንድ ቦታ ላይ ለብዙ ጊዜያት
መቆየት ለደህንነቴ ያሰጋኛል።” አለችው።

“ይሄ ደግሞ በጣም ወጪ ያበዛብሻል።” አላት እና በቀጥታ “ደንበኛዬ አንቺ ለምትሰጪኝ መረጃዎች በሙሉ ልትከፍልሽ ፈቃደኛ ናት” አላት፡፡

ቲና በእጇ ሀሳቡን አጣጣለችበት እና በመቀጠልም “አመሰግናለሁ ዴሪክ፡፡
ግን እውነቱን ስለተናገርኩ ብቻ ክፍያ መቀበሌ ምቾት አይሰጠኝም። አንተ
ጥሩ ሰው ትመስላለህ፡፡ ደምበኛህም ታማኝ ሳትሆን አትቀርም”
“ልክ ነሽ” አላት፡፡
“አንተ እንዳልከው እኛን አንድ አይነት ሰዎች የሚያስፈራሩን ከሆነ ከማን ጋር እየታገላችሁ እንደሆነ ጠንቅቃችሁ የምታውቁ አልመሰለኝም” አለችው፡፡

“ከሩሲያኖቹ ጋር ነው” አላት፡፡

ቲና ሥማቸውን እንኳን ገና ስትሰማ አይኗ በድንጋጤ ፈጠጠ፡፡

“አዎን” አላት በሹክሹክታ ድምፅ “ስለዚህ ደምበኛህን ከአካባቢው ዞር እንድትል ምከራት” ዊሊያም ስለ ኒኪ አሰበ እና ፈገግ ብሎ

“ይሄንን ያንቺን ምክር የምትቀበለው አይመስለኝም። እሷ በጣም ግትር
ሰው ናት” ብሎ መለሰላት፡፡

ይሄ እኮ ጨዋታ አይደለም” ብላ ቲና እየተቆጣች “ሰዎች እየሞቱ ነው፡፡
እኔ ያናገርኩት የኤልኤታይምስ ጋዜጣ ሪፖርተር እንኳን ሞቷል

”ዊሊያምስ ማስታወሻውን መውሰድ ጀመረ፡፡

“እነርሱ በልብ በሽታ ነው የሞተው ይላሉ:: ግን ገና የ33 ዓመት ወጣት
እና እንደ ፈረስ ጠንካራ ነበር።”

“ቲና አሁንም ሰዎች እየተገደሉ ነው” አላት እና ዊሊያምስ በመቀጠልም
“እኔም እዚህ የተገኘሁት በዚህ ምክንያት ነው” አላት፡፡

በመቀጠልም ስለ ሊዛ ፍላንገንን እና ትሬይ ሬይሞንድ ግድያ ሟቾቹ
ከኒኪ ሮበርትስ እና ከባሏ ዶውግ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ሮበርትስ ስላለው
ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር ስለሚገናኝ የበጎ አድራጎት ሥራዎቹ እና በሎስ አንጀለስ
ላይ የበላይነቱን ለመያዝ ሩስያኖቹ እና ሜክሲካኖቹ ስለሚያደርጉት ግብግብ
ጭምር ነገራት፡፡

“ዶውግ ሮበርትስ ባለፈው ዓመት ነው በአደጋ ህይወቱን ያጣው:: ከጎኑ
ደግሞ ለከንቲባ ፋንቴስን መኪና ከሚሰጡት ሩስያውያን ጋር ግንኙነት ያላት
ሴት ነበረች። እሷም በአደጋው ሞታለች” አላት፡፡

ቲናም እጇን አንስታ “ሙስና ነው ያልከው? አድሬኒ ናት ይህንን የነገረችህ? በእግዚአብሔር ሥም ይህቺ ልጅ በቅርቡ ትገደላለች እመነኝ:: ደግሞ የሚገርመው ነገር እኮ እሷ ስለጉዳዩ ምንም የምታውቀው ነገር ያለመኖሩ ነው::” አለችው፡፡

“ልክ ብለሻል እኔም እንደ አንቺ ነው የማስበው” አላት ዊሊያምስ፡፡

“በመጀመሪያ ደረጃ እኔ ፋንቴስ በግሉ ጉቦ ይቀበላል አይደለም ያልኩት።
ግን ማዘጋጃ ቤቱ ለእሱ ባወጣለት የባንክ አካውንት በኩል የተለያየ አይነት
ገንዘቦች ይገቡለታል ነው ያልኩት። የማወራህ ስለ ትልቅ ክፍያዎች ሲሆን
ክፍያውን ደግሞ የሚፈፅሙት ሩሲያዎኖቹ ናቸው”

ዊሊያምስም ማስታወሻ ደብተር ላይ እየፃፈ “ምን ያህል? እና ደግሞ
የትኞቹ ሩሲያኖች?”

“መጠኖቹ በየጊዜው ይለያያሉ።” አለች እና ቲና በመቀጠልም

“አምስት መቶ ሺ ዶላር መቶ አምሳ ሺ ዶላር እና አንድ ጊዜ ደግሞ አንድ ሚሊዩን ዶላር፡፡ ብቻ በየአራት እና በየስድስት ሳምንቱ የተለያዩ ቼኮች
ይመጣሉ፡፡ ለማንኛውም ባጠቃላይ ወደ ሦስት ሚሊዩን ዶላር ይሆናል።”

“እሺ ክፍያውን የሚፈፅሙትን የሩሲያኖችን ሥም ታውቂዋለሽ?”
አላት፡፡

“አላውቅም” ብላ ወደ ወለሉ
ተመለከተች:: ዊሊያምስ ቲና በጣም
እንደፈራች ተመልክቶም

“እነርሱን የምትገልጪበት አካላዊ ሁኔታቸው? በአካልስ አግኝተሻቸው
ታውቂያለሽ?” ብሎ ጠየቃት። ቲናም ራሷን በአሉታ በሀይል ካወዛወዘች
በኋላ ከንፈሯን ነክሳ “ይቅርታ ይህንን ልነግርህ አልችልም” አለችው፡፡
የስልክ ጥሪዎችን ቢያንስ ተቀብለሽ ታውቂያለሽ? ወንዶች ናቸው ሴቶች?
ሁለት ናቸው ወይንስ ሃያ?”

“አይገባህም እኮ...”

ሌንካ ጎርደቪስኪ የምትባል ሴት ታውቂያለሽ?” ብሎ አይፎን ስልኩን
አወጣና የጎርዴቪስኪን ፎቶ አሳያት። የቲና አይን ላይ ሌንካን እንዳስታወሰች
የሚያሳብቅ ዕይታን ዊሊያምስ ተመለከተ።

“ዴ.ሪክ ስለዚህ ነገር መናገር አልችልም። እስከ አሁንም በጣም ብዙ ነገር
ነው የተናገርኩት”

“ቢያንስ የአንድ ካምፓኒ ሥምን ንገሪኝ፤ ያላወቅኩትን እንቆቅልሽ የምፈታበትን አንድ ነገርን እንኳን ንገሪኝ” ሲላት ጊዜ አናቷን በሀይል ወዝውዛ ይገድሉኛል!” አለችው፡፡

ዊሊያምም ለጥቂት ጊዜ ያህል አፍጥጦ ሲያያት ቆየና በቀስታ “ምናልባት ይገድሉሽ ይሆናል። ምናልባት ሁለታችንንም ይገድሉን ይሆናል፤ ግን አንቺ የያዝሺው ሚስጥር እንደወጣ በማሰብ ሌሎች ሰዎች እየተገደሉ ቢሆንስ? ይህንን ግድያቸውን የሚያስቆመው ደግሞ አንቺ
የያዝሺውን ሚስጥር ይፋ በማውጣት ነው። ይህንን ነገር አምነሽ አይደል
እንዴ ለሮቢን ሳንፎርድ ስልክ የደወልሺው?”

“አዎን” አለች እና ቲና ታፋዋ ላይ ያስቀመጠችው እጇ ይንቀጠቀጥባት
ጀመር፡፡ “በጣም እንደፈራሽ አውቃለሁ። እኔም እኮ በጣም ፈርቻለሁ፤ ቲና
ግን ይሄንን እኛ ካልተናገርን ማን ይናገራል እሺ?”

ዴሪክ ዊሊያምስ ከጎኑ በተቀመጠችው ሴትዮ ውስጥ የሚካሄደውን የሀሳቦች ፍልሚያን አሰበ። ቲና ድሬይተን በጣም ደፋር ሴት ነች። ይህንን ደግሞ አንድ ጊዜ ለማረጋገጥ ችሏል። ግን ሁሉም ሰው የድፍረት ገደብ አለው።
“እሺ” አለች እና በመጨረሻም “እነግርሃለሁ። ግን ከዚህ በኋላ እኔን ዳግመኛ በፍፁም ለማግኘት እንዳትሞክር፡፡ በፍፁም! ለማንኛውም ምክንያት ቢሆን።

ዊሊያምም ወንበሩ ላይ ተመልሶ ቁጭ አለ እና


“ይሄው ቃሌን እሰጥሻለሁ” ብሏት እስክሪብቶውን አወጣ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኒኪ እና ግሬቸን ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እያሉ ይሄዱበት ወደ
ነበረው የኮሪያውያን ፍልውሃ ውስጥ ራቁታቸውን ሆነው ሰውነታቸውን
እያደሱ ነው። ግሬቸን የወረዱ ጡቶቿን ከኒኪ ብርትኳን ከሚያካክሉ ጡቶች
ጋር፣ ሽንትርትር ያለውንና ዘልዘል ያለ ሆዷን ደግሞ ልጥፍ ካለው የኒኪ
ጡቶች ጋር አነፃፀረች፡፡ ጡቶቿ ሦስት ልጆችን ያጠባ እና ሆዷም ሦስት
ልጆችን የተሸከመ በመሆኑ የተነሳ እንደዚህ እንደሆነ አሰበች እና ተፅናናች::

ኒኪ ውሃው ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሰምጣ ከወጣች በኋላ የሴት ወሬያቸውን ጀመረች “ባለፈው የነበረው የእራት ግብዣ ላይ ሀዶን አስገድዶ ሳመኝ፤ ከበፊት ጀምሮም እወድሻለሁ አለኝ” አለች ኒኪ ላግሬቸን፡፡

ግሬቸንም “እኮ የኛ ሀዶን ነው?” ብላ ተገርማ ጠየቀቻት፡፡

“አዎን፣ ግን ጥሩ ስሜት አልተሰማኝም። ምክንያቱም እሱ እኮ ለዶውግ
ልክ እንደ ወንድሙ ነበር፡፡

“አአ ልክ እንደ ኦሪት ዘመን ነዋ? ማለትም አንዲት ሴት ቧሏ ከሞተ ወንድምዬው እንደሚጠቀልላት አይነት ነገር መሆኑ ነዋ” ብላ ግሬቸን አሾፈችባት፡፡

ኒኪም በግሬቸን ሹፈት ትንሽ ተከፍታ ዝም አለች። ግሬቸን ይሄ የኒኪ ጥቁር ደመና እስኪያልፍ ድረስ ዝም ብላት ውሃው ውስጥ ብቅ ጥልቅ ስትል ቆየች፡፡

ከጥቂት ጊዜ በኋላም ኒኪ “ይሄውልሽ ግሬች እኔ ችግር ሳይኖርብኝ
አይቀርም፡፡ ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት እንኳን የለኝም”
👍4
አለቻት፡፡

“የኔ ቆንጆ ይሄ እኮ ችግር አይደለም፤ ሀዘን ላይ ስለሆንሽ ነው”

“እንዴ ዓመት አለፈኝ እኮ” ብላ ኒኪ መለሰችላት፡፡

“በዙሪያሽ የተከሰቱት ግድያዎቹስ ቀልድ ናቸው እንዴ? እንዲያውም አንቺ ሆነሽ ነው ሌላ ሰው ቢሆን ያብድ ነበር።”

“ይልቅ የሆነ ስውን እያሰብኩኝ ነው” ብላ ኒኪ ፊቷ በእፍረት እየቀላ ለግሬቸን ነገረቻት፡፡
ግሬቸንም ወሬውን ለመስማት ጓግታ “ደግሞ ማነው?”

“ኧረ ያን ያህል እኮ አይደለም” አለቻት ኒኪ፡፡

“ማን ነው እኮ ነው ያልኩሽ?” ብላ ግሬቸን ሳቀችባት፡፡

ኒኪም ፍልቅልቅ እያለች “ሉው ጉድማን ይባላል፡፡ ከመርማሪዎቹ ውስጥ
እንዴ እኔን በግድያው ወንጀል ይጠረጥረኛል ያልሺው ሰው ነው?”
“አይደለም እሱማ ባልደረባው ነው። ጉድማን መልከ መልካም እና ለእኔ
አሳቢ ነገር ነው። በዚያ ላይ ደግሞ ጨዋ እና ቀና ሰው ይመስላል፡፡

እየተባባሉ ትንሽ ሲያወሩ ቆዩ፡፡ ኒኪ ይበልጥ እያፈረች እና ጓደኛዋ
አይሆንም እንድትላት እየፈለገች “ይልቅ ለአንዲት ታካሚዬ የተለየ ስሜት
ሳይስማኝ አይቀርም። ባለፈው የቀጠርኩት የግል መርማሪዬ እንደነገረኝ
ከሆነ ይህቺ ሴትዮ አንድ የአደንዛዥ ዕፅ አምራች ከበርቴ ሚስት ናት።ወጣት ናት፡፡ ባሏን ትታ ነው እዚህ ሎስ አንጀለስ ውስጥ የምትኖረው::”

“ከዚህ በፊት ከሴት ጋር አድርገሽ ታውቂያለሽ እንዴ?”

“በጭራሽ” አለች ኒኪ፡፡

“ኮሌጅም እያለሽ?”

“ሂጂ አብረን አልነበርን እንዴ? ባደርግማ ታውቂ ነበር” ብላ ስትመልስላት ግሬቸንም “እውነትሽን ነው ቢኖርማ ኖሮ አውቅ ነበር” አለቻት፡፡

“ይመስለኛል የመካከለኛ ዕድሜ ውዝግብ ውስጥ ሳልሆን አልቀርም...”
አለች እና ኒኪ ወደ ሀዘን ደመናዋ ውስጥ ተደበቀች፡፡ ይህ ስሜቷ ባሏ ከሞተ በኋላ ለተደጋጋሚ ጊዜ የሚሰማት መሆኑን የምታውቀው ግሬቸንም እንደ ሁልጊዜውም ሁሉ ኒኪ ከዚህ ስሜቷ እስክትወጣ ድረስ ዝም ብላ ጠበቀቻት።

ኒኪ ወደ ጥሩ ስሜቷ ስትመለስም ግሬቸን ስለ ልጆቿ የተለያዩወሬዎችን እያወራችላት ውሃው ውስጥ ቆይተው ሲበቃቸው ወደ መታሻው ክፍል ገቡ። መታሻው ክፍል ውስጥም ሰውነታቸው ፍም እስኪመስል ድረስ
በደንብ ከታሹ እና ሰውነታቸው ከተፍታታ በኋላም ልብሳቸውን ለብሰው ከኮሪያውያን የፍል ውሃ ቦታ ወጡ እና ወደ ሱሺ ባራቸው አመሩ፡፡....

ይቀጥላል
👍3
#የወድያነሽ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


....የአባቴ ተራ ድንጋጤና የእናቴ ያልታሰበ ተራ ድንፋታ ልቤን በደስታ አክናፍ አበረራት፡፡ የአባቴ ድብቅ ፍላጎት ሳያስበው በመጋለጡ የሁለቱ ፋይዳ ቢስ ጠብና ስሜት ለስሜት መሳለል በጣም ቢያስደስተኝ ምናልባት እናቴ በዚሁ በሰማችው ብቻ ቅናቷ እያደር ይጎለምስና የወዲያነሽን ታባርራት ይሆን? በማለት መጪውን ጊዜ በሥጋት ዐይን ተመለከትኩት የጨዋነቱ ክብር» የተገፈፈበት የመሰለው አባቴ ያ አይበገሬ መሳይ ወኔው ላመል ታህል በርግጎ ከቆየ በኋላ ለመከላከል ያህል «አማረባት አልኩ እንጂ ምን ሳደርግ አየሽኝ? እኔ ያየህ ይራድ ከማንም ብራሪና ውዳቂ ጋር የምልከሰከስ ነኝ እንዴ? ከጠረጠርሽኝ፣ ዛሬውኑ! አሁኑኑ መንጥቂያት!» ብሎ በንዴት ወደ መኝታ ቤት ገባ፡፡

የእናቴ ፊት በቁጣ ተከስክሶ ዐይኖቿ በሽሙጥ ሸኙት። ነገሩ ተባብሶና
እንደገና ሌላ ነገር ጭሮ ውጤቱ መጥፎ አይሁን እንጂ እሳትና ጭድ ያድርጋችሁ
ማለቴ አልቀረም፡፡

ከአባቴ ይበልጥ ያናደደኝና ውስጥ ውስጡን ያበሳጨኝ ግን የቤታችን
ዘበኛ ነበር። በእርሱ የተነሣ ልቤ በቅናት እሳት ተለብልባ ተሠቃይታለች።

በመልኩ፣ በሰውነት አገነባብና ለግላጋነት ከምኑም አልደርስ። ፈገግታውና የባቄላ አበባ የመሳሰሉ ጥርሶቹ ይማርካሉ። በሥራ ምክንያት በምድረ ግቢው ውስጥ ከወዲያ ወዲህ ሲል ከየወዲያነሽ ጋር የተገናኙ እንደሆነ ተሣሥቀውና ተጠቃቅሰው ይተላለፋሉ፡፡ ከነዚያ ልበሳቸው ብዬ ከሰጠሁት ሸሚዞችና ሱሪዎች መካከል የለበሰ ለትማ ማለፊያ ሙሽራ ስለሚመስል ለባብሶ ባጠገቧ ሲያልፍ ዐይኖቼ በቅናት ደም ይለብሳሉ። አውልቅ ብዩ የምነጥቅበትና ሰበቡ የማይደረስበት ስውር ደባ በማጣቴ ሐሳቤ እንደ ጨው ሟምቶ ቀረ።

ለሥራው ደፋ ቀና ሲል ሰርቄ ሽንት ቤት ውስጥ ለመክተት ያሰብኩበት ጊዜም ነበር፡፡ አንድ ቀን ማታ እርሱና የወዲያነሽ ተከታትለው ወደ ማድቤት
ሲገቡ በማየቴ ጨለማ ለብሼ ከአንድ ትይዩ ቦታ ላይ ከሩቅ አደፈጥኩ፡፡ ከአንድ
ጐድጓዳ ሳህን ውስጥ ፍትፍት ቢጤ ሳይሆን አይቀርም ቶሉ ቶሉ እያወጡ ግራና ቀኝ ቆመው መብላት ጀመሩ። አንድ ሁለት ጊዜ ያህል ለራሷ ትጎርስና ለእርሱም ያንኑ ያህል ታጐርሰዋለች። የአፉን ውስጥ አላምጦ ሳይውጥ ሌላውን ከከንፈሩ ጫፍ ትደቅንለታለች፡፡ ፍትፍት መሆኑ በግምት የሚያስታውቀው ከጉርሻዋ በኋላ ጣቶቿን በማራገፏ ነበር። ከቅናትና ከጥላቻ ብዛት የተነሣ ቁርጠት የቀሠፈኝ ይመስል ሰውነቴ ብው ብሉ- አንጀቴ በንዴት ተቋጨ።

«ና ውጣ ብዬ እርሱን ከእርሷ ነጥዩ የማስወጣበት ምክንያት እንደ ሰማይ
ኮከብ ራቀኝ፡፡ ነገር ግን ወዲያው አንድ ቀላል ነገር ትዝ አለኝ። ቀስ ብዬ
እያሰላሁ እንድ አራት ያህል ደህና ደህና ድንጋይ ከለቀምኩ በኋላ ትልቁን
የአጥር በር በድንጋይ ጠመድኩት።

አራት ጊዜ ያህል እንደ መታሁ ጅብ እንዳየች ቡችላ ሳህኑን ለቆላት ተፈተለከ፡፡ እሷ የበሩን መቃን ተደግፋ ቆመች፡፡ የወዲያነሽንም በመጠኑ ለማስደንገጥ ያህል አንዲት ትንሽ ድንጋይ ወደ ማድ ቤቱ በር እነጣጥሬ ወረወርኩ፡፡ በቀጭን የድንጋጤ ድምፅ «ውይ» ብላ ወደ ውስጥ ሮጠች። የሁለቱም ትኩስ ድንጋጤ ሳይበርድ ልክ ከቤት እንደ ወጣ ሰው ተመስዩ ከተደበቅሁበት ቦታ መሰስ አልኩና «ማን ነው? የማን ነው ባለጌ በጨለማ በር የሚደበድብ?» ብዬ ጮህኩ፡፡ ማንም አልመለሰልኝም፡፡

ዘበኛው የወረወረውን ሰው ለማወቅ በሩን ከፍቶ ወጣ፡፡ ባልተረጋገጠ የቅናት መነሾ የፈጸምኩት የተንኮል ድርጊት ራሴን እያሳፈረኝ እፈን አፍኜ ሣቅሁ፡፡ ነገር ግን ወደ ውጪ በመሄድ ፈንታ ወደ ቤት ገባሁ፡፡ ሆኖም መቀመጥም መቆምም የሚነሳ አንዳች ውስጣዊ ግፊት መላ አካላቴን ናጠው፡፡ አልቻልኩትም::

ሩብ ሰዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የወዲያነሽ ዕቃ ቤት ውስጥ
ስትንጐዳጉድ እገኘኋት። ጣቴን በቁጣ እየነቀነቅሁ «ከዚያ ከመድረሻ ቢስ ሴት
አውል ዘበኛ ጋር ያደረግሽውንና የምትሠሪውን ያላወቅሁ እንዳይመስልሽ!
የመጣው ይምጣ እንጂ የማደርገውን ዐውቃለሁ፡፡ እኔ ጌታነህ ትርክርክሽን ነው
የማወጣው» ብዬ አፍጥጨባት ተመለስኩ፡፡ ክፉኛ ክው ብላ ነበር።
በስውርና በግልጽ መቆጣጠሬን ቀጠልኩ፡፡ የወዲያነሽ ከእኔ ጋር ምንም
ዐይነት ፍቅራዊ ስሜትና ዝንባሌ እልነበራትም፡፡ ስለሆነም ስለ ግንኙነታችን
የምታደርገው አንዳችም ጥረት አልነበረም፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው «ሊያታልለኝና የምመልስለትን ለማወቅ ፈልጎ ነው» ብላ እንደሆነ እያደር ተገለጸልኝ፡፡

«ከዘበኛው ጋር ስትዳሪና ስትላፊ አይቼሻለሁ» ብዩ ከገሠጽኳትና
ከተንደራራሁባት ወዲህ ግን ወይ በፍርሃት አለበለዚያም በውስጧ ተሰዉሮ በነበረ ለጋ ውዴታ ምክንያት እርሱን ችላ ብላ ወደ እኔ መለስ አለች፡፡ ሆኖም
በቀድሞው አንገተ ሰባራነቷ ላይ በፍርሃትና በበታችነት ስሜት በመጠመዷ
የዝቅተኝነት ጭንቀት አጠቃት።

አንድ ቀን ማታ ከእኔና ከእርሷ በስተቀር መላው ቤተስብ ከላይ እታች በተኛበት ወቅት ኮቴዬን ሳላሰማ ከመኝታ ቤቴ አስልቼ ወጣሁ፡፡

ዕቃ ቤት ውስጥ ወዳለው ወደ የወዲያነሽ መኝታ ክፍል ለመሄድ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ ስደርስ ከበሩ አጠገብ ቆማ አየኋት። የተከፈተውን የዕቃ ቤት መዝጊያ ተደግፋ ቆማለች። አንዲት አራት ማዕዘን መስተዋት በግራ እጅ ይዛ በመስታወቱ ውስጥ ከምታየው ከሌላዋ ነፍስ አልባ «እርሷ» ጋር ፈገግ እያለች ትሥቃለች። ቀና ብላ በድንጋጤ ካየችኝ በኋላ በምን ይለኝ ኀፍረት በእጅዋ የያዘቻትን መስታወት ከቀኝ እጅ ብብቷ ውስጥ አጣብቃ ይዛ አቀርቅራ ቆመች። እግሬ ላይ መጫሚያ ባለመኖሩ በለስላሳው እግሬ ያደረግሁት እርምጃ በሥጋጃ ላይ የምትራመድ የድመት አካሔድ ሆኖ ነበር፡፡

እጠገቧ ደርሼ ቆም ስል ወደ ጎን ሽርተት አለች። ገፋፍቶ ያስወጣኝ ድፍረት እንደ ቅቤ ቀለጠ። ሰውነቴ በኃፍረት ተተብትቦ ግድግዳውን ተደግፌ ቆምኩ፡፡ አወጣጡ ግን ግድግዳ ተደግፌ ለመቀም አልነበረም፡፡

ትሰድበኝና አጉል ታዋርደኝ ይሆን» እያልኩ በፍራቻ ስሜት ውስጥ
ከቆየሁ በኋላ «እስካሁን ምን ታደርጊያለሽ የወዲያነሽ?» ብዬ ለማሽኮርመም ያህል ባቀጠንኳት ድምፅ ጠየቅኋት። እንዳቀረቀረች አሻግራ ወለል ወለሉን እየተመለከተች «ማድ ቤት ወርጀ ገላዩን ስታጠብ ቆየሁና ይኸ ጸጉሬ
እንዳያስጠላ ከመተኛቴ በፊት ልጎንጉነው ብዩ ነው» ብላ ዝምታዋን ተያያዘችው፡፡

ምናልባት ያ መዘዘኛ ዘበኛ ገብቶ አጫውቷት ይሆን? በማለት መላ
ሰውነቴ በቅናት ግው ብሉ ጋየ፡፡ «መታጠቡንስ ጥሩ አደረግሽ፡ ለመሆኑ ግን እያሸሽ ታጠብሽ?» ብዬ ጠየቅኋት።
“አስካለ፣ እስካለ ናት ፍትግ አድርጋ ያጠበችኝ» ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ በቅናት የተሥረቀረቀ ልቤን ለማፅናናት «እኔስ ያ ዘበኛ ነው ብዬ አልኳት፡፡ ፊቷ ጠወለገ፡፡ ከወደ ውስጥ የሚወጣውን ትካዜዋን ይገልፅ ይመስል የቀኝ እግሯን ሰበር አድርጋ «ውይ! ምነው ምን አልኩዎት፡ ከዚያች እርስዎ ከተቆጡኝ ቀን ወዲህ ቀና ብዬም አይቼው አላውቅ:: እኔስ ይቺው የድሃ እንጀራዬ ትበልጥብኛለች» ብላ ከፊቴ ላይ ሁኔታዬን ለመረዳት ሰረቅ አድርጋ አየችኝ። ነገሩን ለማቃለልና የእርሷም ያልተዘጋጀ እእምሮ ምን መልስ እንደሚሰጥ ለማወቅ ስል የቀኝ እጅ ጣቶቿን ያዝ አደረግሁና እረ ለመሆኑ እኔ እንደምወድሽ ታውቂያለሽ ወይ?» ብዩ በሙሉ ድፍረት ጠየቅኋት። ሆኖም ዝምታዋን ጥሶ የሚወጣ የመልስ ቃል ሳላገኝ ቀረሁ። አገጯን ይዤ ወደ ላይ
ቀና አደረግኋት። ያቺን ለስላሳ የምታምር ድቡልቡል እገጯን ስነካ ሰውነቴ
ውስጥ ተናዳፊ ንዝረት ለቀቀብኝ። እንደ ዱር ሀረግ አንገቷ ላይ ተጠምጥሜ
ብስማት እፎይታ እንደማገኝ ታወቀኝ፡
👍5
፡ ሆኖም ያንኑ ያሀል ኃፍረትና ወኔ ቢስነት
በላዩ ላይ ስለ ተቸለስ ሟሽሼ ቀረሁ፡፡

«ንገሪኝ እንጂ ለምን ዝም ትያለሽ? ሰው ሁሉ እስኪተኛ ድረስ ጠብቄ የመጣሁት እኮ እንድትነግሪኝና ቁርጤን እንዳውቅ ብዬ ነው» አልኩና የያዝኩትን እጅዋን ትከሻዬ ላይ ሰቀልኩት። ብብቷ ሥር የነበረችው መስተዋት ወደቀች፡፡
አልተሰበረችም፡፡ እጇን ትከሻዬ ላይ የሰቀልኩት በእሺታና በፍቃዷ ባለመሆኑ
የጓያ ፍንካች የምታህል ደስታ አልተሰማኝም፡፡ አሁንም ቢሆን ከዝምታዋ ጥልቀት ውስጥ መልስ ማግኘት ባለመቻሌ ልቤ በንዴት ተጥመለመለች። ሳልወድ በግድ ለቅቄያት ወደ መኝታ ቤቴ ተመለስኩ፡፡ ሥጋዊ አካሌ ዟ ብሉ ሲንጋለል አእምሮዬ ግን በሐሳብ ዋዠቀ፡፡ ከራሴ ጋር ክርክር ገጠምኩ፡፡

ሐሳቧንና አስተያየቷን ሳላጠናና ሳላውቅ «ወደድኩሽ ብዩ ለምን ዘላበድኩ? «ምናልባት ይህን ነገር እንደ ክብር ቆጥራ ያላልኳትንና ያልጠየቅኋትን ሁሉ ጨምራ ጨማምራ ታወራ ይሆን?» በማለት ከአንድ ሰዓት በላይ እየተሠቃየሁ ተገላበጥኩ። ተጸጸትኩ። ጸጸቴ ግን እንደ አለብላቢት ቅጠል አእምሮዬን ለበለበው እንጂ ሌላ ፍቺ አልሰጠኝም፡፡ ሐሳቤን አንድ ፈር ሳላሲዝ አንቀላፋሁ። ጊዜው ጐረፈ።

ዘወትር እሑድ እሑድ ከቤተ ክርስቲያን መልስ ረፋዱ ላይ የሚፈላው ቡና የተለየ ክብርና የአከታተም ዝግታ አለው፡፡ በአጋጣሚ እሑድ ላይ ተደርቦ የሚውል ዕውቅ ተራዳዒ ቅዱስ መልኣክ ወይም ባለገድል ሰማዕት ከዋለ እሑድ
ተጣማሪ የክት ስም ይሰጠዋል፡፡

ዕለተ ሰንበትና ሥላሴዎች ናቸው:: ዕለተ ሰንበትና ሊቀ መላኩ ነው፣ ዕለተ ሰንበትና እመ ብርሃን ወላዲተ አምላክ ናት ይባልና ሦስት አራት እነባበሮ በቅቤ ጫፍ እስኪል ርሶ ይቆረሳል ጾም ካልሆነ። ውለታ የዋለና ስለት ያደረሰ ታቦት ለሆነማ አንድ ሁለት ጋን ጠላና ሾላ የመሰለ ድፎ ዳቦ አያጣም፡፡ ምን ጠፍቶ

ያንድ ቀን ለታው እሑድ ባለ አጋጣሚ ተረኛ መድኃኔዓለም ስለ ነበር እናትና አባቴ ስደተኛው መድኃኔ ዓለም አስቀድሰው እንደተመለሱ እንግዳ
መቀበያ ክፍል ውስጥ ቡና ተፈልቶና አነባበሮ ተቆርሶ የቤተሰብ ወሬ ደራ፡፡ ስለ
አገር ቤትና ስለ ከተማ፣ ስለ ዘመድና ባዳ ሙገሳና ወቀሳ አንዱ ካንዱ እየተቀበለ
አወራ።

እናቴ በግልጽ ስለምታውቃትና ስለ ተካሠችባት የአባቴ የቀድሞ ወጻጅ
ስለተጠረጠረባቸው ሴቶች እንኳ ሳይቀር እንደ ቀልድ እየተነሣ ተሣቀ፡፡
የወዲያነሽ ድንገት ብድግ ብላንደ ዕቃ ቤት ሄደች። ያረጀ ያፈጀ ወሬ ስለነበር
አልታፈረበትም በመኻሉ በእናቴ አእምሮ ውስጥ የየወዲያነሽ ሐሳብ ድንገት
ድንቅር ብሎ ኖሮ እናቴ ተዘብንና ሳቀችና ያንተ ነገር ደግሞ ምን ማለቂያ
አለው? መቼም ልብ እይሞት! ውሽትና ስንቅ እያደር ይቀላል ከሚሉ ወንድና
ስንቅ እያደር ይቀላል ቢሉ ኖሮ ጥሩ ነበር፡፡» አለችው ሕሊና በማይጎዳ ሽሙጥ
«አፍ ተጅ ባይሆንብህ ኖሮ እንዳንተ አስተያየትማ የትናየት በተዳረስን ነበር፡፡
ብላ ስለማን መናገር ላይ እንደፈለገች እንዲያውቅ ላፍታ ያህል ትኩር ብላ
አየችውና “ደግነቱ የሷ ቀና ተብላ
ሰው ያለ ማየት በጀ እንጂ ብላ በወሬ መኻል የቀዘቀዘች ቡናዋን ጨልጣ ንግግሯን እንደ መቀጠል ስትል
«አንቺም እኮ እንደዚያ ዕለቱ አድርገሽ አዋርደሽኝ አታውቂ! በሌላ ነገር
ቢሆን እንዴት ደስ ባለኝ፡ ሚስት ገመና ከታች ናት ይባል ነበር፡፡ እኔ ላይ
በስተርጅና ታዘብኩሽ! አንዲት ቃል ሳት ብላኝ ብታመልጠኝ እንዴት ከገረድ
ጋር ታውይኝ?» አለና አባቴ ያለፈውን ንዴትና ቂሙን ከወቀሳ ጋር አደባልቆ
ተናገረና መጽሐፉን ለመመልከት አቀረቀረ።

«ያልጠረጠረ ተመነጠረ» አለች እናቴ በአነጋገሯ ኩራትና ግድየለሽነቷን
እያሳወቀች፡፡ «ታዲያ የማንም ብራሪና መድረሻ ቢስ በስተርጅና ትዳሬን
ትበትነው ብለህ ነው?» ብላ ወደ እኔና ወደ የውብነሽ ተመለከተች። በእንግዳ
መቀበያው ክፍል ውስጥ ከአራታችን በቀር ሌላ ሰው ባለመኖሩ አባቴ በጉዳዩ ላይ ተዝናንቶ ለመናገርና ንጽሕናውን ለመናዘዝ ይሉኝታ እልተጫነውም፡፡

ከሚያነበው መጽሐፍ ላይ ቀና ብሎ ከሠላሳ ስድስት ዓመት በኋላማ
ኸገረድ ተገናኘ፣ ተጠረጠረ ብባል የሞት ሞት እይደለም ወይ? እንዴት ብዬ
አደባባይ ልወጣ? በመጠርጠሬ እንኳ ቆሽቴ ተልጧል። ትልልቆቹስ ሥፍራ
ሥፍራቸውን ይዘዋል፡ እነኚህ ምን ይሉን?» ብሉ» ራሱን ነቀነቀና እንደገና ወደ መጽሐፉ መለስ አለ።

«እስኪ እንዲያው ተካበች ሙች፣ ፍቅራችንን በለኝ፡ ልቦናህም አልከጀላት?» ብላ ጠየቀችው:: የዝቋላው ና» ብሎ በመሐላ ነገሩን ከሥር ከመሠረቱ መንግሎ በመጣል ከጥርጣሬ ቅጥር ውጪ አሽቀነጠረው፡፡

የወዲያነሽ ስለ እርሷ ምን እንደተባለና እንደተወራ ባለማወቋ ሥራዋና ሁኔታዋ ሁሉ አልተለወጠም። ይልቁንም ለእናቴ ያላት አክብሮትና ታዛዥነት እያደር በመጨመሩ ሁሉንም ነገር የቸልታ ጉሮሮ ዋጠው:: የእናቴም ጥርጣሬ
በአባቴ መሐላ እንደ ጢስ በንኖ ጠፋ፡፡ አባቴም ከዚያ ወዲህ ስለ የወዲያነሽ
አኳኋንና አሠራር ትንፍሽም አሌለ።

እኔና የወዲያነሽ ከቀድሞው በበለጠ ሁኔታ ጠባይ ለጠባይ በመተዋወቃችንና በመግባባታችን ምን ጊዜም አንድ እፍኝ ሙሉ ፈገግታ ፈገግ ባልኩላት ቁጥር አጸፋውን በእንቅብ መቀበል ቋሚ ልማዳ ሆነ፡፡ የወዳያነሽ አእምሮ ውስጥ ብዙ አስጨናቂ የሐሳብ ውጣ ውረድ እንደሚተራመስ የሚታወቀው ከእያንዳንዱ ፈገግታ በኋላ ፊቷ ስለሚጠወልግ ነበር።

💫ይቀጥላል💫
👍5
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

...ከኮሪያውያን የፍል ውሃ ቦታ ወጡ እና ወደ ሱሺ ባራቸው አመሩ፡፡
ሱሺ ባር ውስጥም ተቀምጠው እየበሉ እያሉ ግሬቸን “ይህንን ቀጠርኩት
ያልሺውን የግል መርማሪሽን ከየት ነው ያገኘሽው?” ብላ ኒኪን ጠየቀቻት፡፡

ኒኪም “ከጎግል ላይ ነው:: ስለ እሱም በደንብ አድርጌ ካነበብኩኝ በኋላ
ነው የቀጠርኩት፡፡ ይልቅ ከ 10 ዓመት በፊት ለማን ተቀጥሮ ይሰራ እንደነበር እስቲ ገምቺ?”

ግሬቸንም በኒኪ ጥያቄ ከት ብላ ከሳቀች በኋላ “እኔ ይሄንን እንዴት ላውቅ እችላለሁ፡፡ በይ ንገሪኝ እስቲ”
“ለክላንሲ ቤተሰቦች ነበር። ባለፈው ምሳ ስንበላ እንዲያውም አንቺ ነሽ የነገርሺኝ፡፡ ሜክሲኮ ውስጥ ጠፋች ምናምን ብለሽ፡፡ ትዝ አለሽ?”

“አዎ ቻርሎቴ ክላንሲ። አባቷ የእሳት አደጋ ሠራተኛ ነው::”

“ልክ ነሽ ተከር ክላንሲ ይባላል፡፡ ባይገርምሽ እሷ የእኔ ታካሚ ከሆነች
አንዲት ሴት ባል ጓደኛ ጋር ግንኙነት ነበራት። የክላንሲ ወዳጅ ባንከር ሲሆን
የሚሰራው ደግሞ ሮድሪጌዝ ከሚባል የአደንዛዥ ዕፅ አምራች ባለቤት ጋር
ነው:: የአደንዛዥ ዕፁንም እዚህ ሎስ አንጀለስ ውስጥ እየሸጠ ነው ብሎ ነው
ዴሪክ ዊሊያምስ የሚባለው መርማሪዬ የነገረኝ” አለቻት ኒኪ፡፡

ግሬቸንም ጓደኛዋ በዚህ መልኩ ነግሮችን እያገናኘች ማሰቧን እና መርማሪዋ የነገራትን ሁሉ አምና በመቀበሏ እየተገረመች እያየቻት

“እሺ ከዚያስ የክላንሲን ቤተሰብ ጉዳይ ይዞ የነበረው መርማሪሽ በመጨረሻ ላይ ምን ሆነ?” ብላ ኒኪን ጠየቀቻት፡፡

“አባረሩት”
“ለምን?”
“ምክንያቱም ቻርሎቴ ከባለትዳር ጋር ግንኙነት ነበራት ብሎ ስለነገራቸው ነው፡፡ በነገራችን ላይ ቻርሎቴ ጨዋ አልነበረችም። እሷ ሜክሲኮ ላይ የሰው ትዳር ለማፍረስ ስትንቀዥቀዥ የነበረች ሴት በመሆኗ የእጇን ነው ያገኘችው። ስለዚህ አላዝንላትም” አለች ኒኪ ትንሽ ምሬት ባዘለ ድምፅ፡፡

ግሬችንም ቀና ብላ በቅሬታ እያየቻት ኒኪ ከመቼ ጀምሮ ነው ደግሞ በሰዎች ሞት ደስተኛ መሆን የጀመርሺው? መቼስ አንዲት ሴት ከባለትዳር ጋር የፍቅር ግንኙነት ስላደረገች ትሙት ብለሽ አትፈርጂም?” ብላ ጠየቀቻት፡፡
“ለምን ብዬ ነው የማልፈርደው?” ብላ በቁጣ በሚንቀለቀል አይኗ አየቻት
እንደቀልድ ስታይ አዳም ሲያቀብጣት የነበረች አንዲት ሸርሙጣ ሴት እና” የሆነ ማታ ላይ የአዳምን አይ ፓድ ስትከፍቺ እና ፎቶዎችን የራቁት ፎቶን ብታይስ ምን ይሰማሻል?”

“በእርግጥ ነገሩ ያሳቅቃል፡፡ ግንንንን...”
እሺ ልጅቷ እርጉዝ ብትሆንስ?” ብላ ኒኪ ልክ ሰይጣን እንደያዘው ሰው
ጮክ ብላ መለፍለፍ ስትጀምር ቤቱ ውስጥ ያሉ ሰዎች ዞር ዞር እያሉ ወደ
እነርሱ መመልከት ጀመሩ። “እሺ አንቺ ለባለፉት አምስት ዓመታት ያህል
ውጤት አልባ እና በጣም የሚያሳምም መውለድ የሚያስችልሽን ህክምና
እያደረግሽ እያለ ባልሽ ከጀርባሽ ሌላ ሴትን እያወጣ ቢያስርግዛትስ?” ብላ ኒኪ
አይኗ በእምባ ተሞላ፡፡ “የሆነ ማታ ላይ የባልሽ አይፖድ ላይ እርጉዝ ሆዷን
የሚያሳይ የራቁት ፎቶን በኢ ሜይል ብትልክልሽስ? በቃ ህይወትሽ በሰከንድ
ውስጥ ግልብጥብጡ ቢወጣስ!?” አለቻት።

ግሬቸን በሰማችው ነገር በጣም ደንግጣ እና ሆዷ ታውኮ ሀሞቷ ሊወጣ እየታገላት ፍጥጥ ብላ ኒኪን አየቻት እና

“ሌንካ እርጉዝ ነበረች?”
ኒኪም መልስ ሳትመልስላት ዝም ብላ አይኗን አፍጥጣ ግሬቸንን ተመለከተች፡፡

ግሬቸንም “ግን እኮ ለሁላችንም የነገርሺን ከአደጋው በፊት ስለ እሷ ስምተሽ እንደማታውቂ ነበር።”

ኒኪ ራሷን ነቅንቃ ከድንዛዜዋ ወጣች እና ዝምታዋን ቀጠለች፡፡

“በኢየሱስ ሥም! ግን አንቺ ፎቶዎችን አይተሽ ነበር ስለ እሷም ታውቂ
ነበር ኒኪ?” ብላ ግሬቸን በፍርሃት ተንቀጠቀጠች፡፡

ምናልባት በአደጋው ውስጥ ኒኪ እጇ ይኖርበት ይሆን እንዴ? ብላ
ግሬቸን አሰበች፡፡

ተነስታ ለመሄድም እያመነታች እጇን ቦርሳዋ ላይ አስቀመጠች፡፡ ይህንን
ግሬቸንን ሁኔታ ያየችው ኒኪም ዶውግን አፈቅረዋለሁ። እሱ ላይ አንዳችም ክፋ ነገር አላደርግም:: እሱ ግን በጣም ነው ልቤን የሰበረው” ብላ አዘነች፡፡

“ግን ታውቂ ነበር?”

ኒኪ ራሷን በአወንታ ነቀነቀች፡፡

“ፎቶዎችንም አይተሻል? ሌንካ እርጉዝ ነበረች?”
“አዎ” አለቻት እና “
ከመሞቱ ከወር በፊት ነው ፎቶዎቹን ያየሁት::”ካለቻት በኋላ ማልቀስ ጀመረች፡፡

ግሬቸንም ወንበሯን አስጠግታ አቀፈቻትና “ለምን አልነገርሺኝም ያን ጊዜ የኔ ቆንጆ?”
“እንዴ ይሄ እኮ የሚያሳፍር ነገር ነው እንዴት ይነገራል?”
“እና ዶውግን ዝም አልሺው?”

“አውቃለሁ ዶውግን ከቤቴ ላባርረው እችል ነበር፡፡ ግን በቃ ትዳሩን ብሎ
ይመለሳል ብዬ ዝም አልኩኝ። ምንም ነገር እንዳላየሁ ሆኜ አሳለፍኩኝ::
ታውቂ አይደል ግሬች ዶውግ እኮ ዓለሜ ነው።”

“እንዴ የተረገዘው ልጅስ?”
“አላውቅም! ነገሩ እኮ ለእኔ አዲስ ነገር ነበር። ሁሉ ነገር እኮ በጣም ነበር ግራ ያጋባኝ የነበረው። እናም በመጨረሻ ምንም ሳላወራው ሞተብኝ።
በጣም ዘግይቼ ነበር።” ብላ ኒኪ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።

ኒኪ አልቅሳ ከወጣላት በኋላ ለአንድ ሰዓት ያህል ሲያወሩ ቆዩ።
ግሬቸንም ለኒኪ ለምን ወደ ኒውዮርክ ሄደሽ አዲስ ህይወት አትጀምሪም?
ብላ ሀሳብ አቀረበችላት፣ እና ኒኪም እንደምታስብበት ነግራት ተለያዩ።

ኒኪ ለዓመት ያህል ውስጧን ሲያኝከው የነበረውን የሌንካን የእርግዝና
ጉዳይ ለግሬቸን ስላወራች ትንሽ ቀለል ብሏታል። መኪናዋን እያሽከረከረች
ወደ ቤቷ እየሄደች እያለችም ዴሪክ ዊሊያምስ ደወለላት።

መኪናዋን መንገድ ዳር ከሚገኝ የጃካራንዳ ዛፍ ስር አቆመች እና ስልኩን
ስፒከር ላይ አድርጋ ማውራት ጀመረች::
“ሄሎ ዴሪክ ባለፈው ለእኔ አስበህ መልዕክት ስለላክልኝ አመሰግናለሁ።
እቤት ከገባሁ በኋላ እንዳልደውልልህ...”

ኒኪ የግድ በቶሎ ዛሬ ማታ መገናኘት ይኖርብናል” አላት። ለመጀመሪያ
ጊዜ ድምፁ ውስጥ ፍርሃት እና አለመረጋጋትን ያስተዋለችው ኒኪም ምን
ሆኖ ነው እንደዚህ የፈራው? ለእኔ ነው ወይስ ለራሱ ነው የፈራው?' ብላ

“ምነው ችግር አለ እንዴ?” ብላ ጠየቀችው።

በሩሲያውያን እና በሮድሪጌዝ መካከል የሚደረገው የአደንዛዥ ዕፅ ጦርነት ቀላል አይደለም። ነገሩ እስከ ከተማው ማዘጋጃ ቤት ድረስ ይዘልቃል። መሉው የሎስ አንጀለስ ከተማ በዚህ የአደንዛዥ ዕፅ ቀለበት ውሰጥ ነው የሚገኘው።” አላት እና ስሜቱ የተረበሽ እና የፈራ መሆኑ
እየታወቀበትም ባንኮችና እና የበጎ አድራጊ ተቋማት ሁሉ የዚህን አደንዛዥ ዕፅ ገንዘብ በህግ ወጥ መንገድ ስለሚያዘዋውሩ ሁሉም የድርሻቸውን ያገኛሉ። አላት።

ኒኪም የዊሊያምስ አለመረጋጋት እና መፍራት ትንሽ አሳስቧት “እሺ ተረጋጋ። ከግድያው ጋር የሚገናኝ ነገር አግኝተሃል? ማለትም ግድያው ከእኔ ጋር ይገናኛል ?

“ምናልባት አዎን” ብሎ ሲመልስላት ኒኪ እርግጠኛ ለመሆን ብላ

“ስማቸውን ልትነግረኝ ትችላለህ?”

“አሁን በስልክ ልነግርሽ አልችልም።” ብሎ ዊሊያምስ በመቀጠልም “የሆነ ስወር ያለ ቦታ ከተገናኘን በኋላ ነው የምነግርሽ” አላት እና የሚገናኙበትን ሆቴል ተስማሙ::

“ስለ ሌንካስ ያገኘኸው ነገር አለ?” ብላ ኒኪ ጠየቀችው።

“አዎ አለ፤ የእሷም ነገር ከዚህ ጉዳይ ጋር ይያያዛል፡፡ እሱንም ስንገናኝ አወራሻለሁ።”

“በስልክ ልትነግረኝ አትችልም?” ብላ ኒኪ ተለማመጠችው፡፡ ስለ ጣውንቷ ለማወቅ ዓመት ፈጅቶባታል፤ እና ከዚህ በኋላ ለደቂቃ እንኳን መጠበቅ ስቃይ ነው የሚሆንባት

“አልችልም፡፡ አሁን ቤት ሄጄ ልብሶቼን በሻንጣ ማዘጋጀት አለብኝ
👍3😁1🤩1
አንቺም ብትሆኚ ስትመጪ ለቅያሪ የሚሆኑሽን ልብሶች በትንሽ ሻንጣ
አዘጋጂ። ሁለታችንም አደጋ ላይ ነን፡፡ ስለዚህ ለጥቂት ጊዜ ያህል ነገሮች
እስኪረጋጉ ድረስ ተደብቅን መቆየት ይኖርብናል።”

ኒኪ ብዙ ጥያቄ ልትጠይቀው ስትል ስልኩ ተዘግቷል። ይህ አይነት
ፍርሃትን በእሱ ላይ አይታ ባታውቅም ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ስለ ጣውንቷ
ማወቅ እንደምትችል ስታስብ ደስ አላት፡፡

ስለ ጣውንቴ ካወቅኩኝ በኋላ ንዴቴን ሁሉ ትቼ ከራሴ ጋር እታረቃለሁ ብላ በማሰብ ላይ እያለች ስልኳ ጮኸ፡፡

ስልኩን ስለማታውቀው ምናልባት ዴሪክ በሌላ ሲም የደወለላት መስሏት
በቶሎ ስልኩን አነሳች እና “ዴሪክ” አለችው፡፡

ከዚያኛው የስልክ መስመር ግን የሚመጣው ድምፅ በጣም በሰቆቃ
የተሞላ እና ፍፁም የሚረብሽ ድምፅ ነበር። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን
የድምፁን ባለቤት ስታውቅ

“ይሄማ በፍፁም ሊሆን የማይችል ነገር ነው!”

“ዶክተር ሮበርትስ?” አላት ብራንዶን ግሮልሽ እና በማስከትልም “አንቺ
ነሽ?” ብሎ ጠየቃት፡፡

“አዎ ነኝ ብራንዶን” ብላው ልቧ በጣም እየደለቀባትም “የት ነው ያለኸው?”

“እርዳታሽ ያስፈልገኛል” ብሎ ሳግ አፈነው እና “ሊገድሉኝ ነው መሰለኝ
“አይዞህ እኔ አለሁልህ፡፡ ግን የት እንዳለህ ንገረኝ በመጀመሪያ

“እሺ” አለ እና በረዥሙ አየር ስቦ “እኔ... እኔ... ጥግ ላይ...”

ተናግሮ ሳይጨርስ የምት ድምፅ ተሰማት እና ስልኩ ተቋረጠ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኒኪ ኤስ ኤል ኤስ ሆቴል ቁጭ ብላ ዴሪክ ዊሊያምስን እየጠበቀች
ትገኛለች:: ዴሪክ ዊሊያምስ እንደነገራትም በትንሽ ሻንጣ ልብስ ይዛ መጥታለች፡፡ ይህንን ደግሞ ያደረገችው በተለይ ብራንዶንን ካዋራችው በኋላ ነው። በተለይ ደግሞ አሰቃቂው ድምፁ ትንሽ እንድትፈራ እና ዊሊያምስ አድርጊ ያላትን ነገር እንድታደርግ አስገድዷታል። ብዙ ልብስ ይዛ አልመጣችም፡፡ ሮድሪጌዝ ከቤቷ እንዲያስወጣት አትፈልግም።
ስለ ብራንዶን ስትነግረው ምን ሊል ይችላል ብላ አሰበች። እያወራት
እያለ ስለ ስማችው የምት ድምፅ ትነግረውና ሀሳቡን እንዲያካፍላት
ትጠይቀዋለች፡፡ ይህንን ነገር ለፖሊሶች እስከ አሁን አላሳወቀችም።በመጀመሪያ ይህንን የብራንዶንን ነገር ለዊሊያምስ ነው ልትነግረው የፈለገችው::
ኒኪ ፈዘዝ ያለ ጥቁር ሱሪ ከአረንጓዴ ቦዲ ጋር አድርጋለች። ቦዲዋ አንገቱ ክፍት ስለሆነ የጡቷ መካፈቻ ከጡት ማስያዢያዋ አፈትልኮ ይታያል። ይህንን አይነት ልብስ ለብሳ የመጣችው ዴሪክ ዊሊያምስን ለማማለል ሳይሆን ስለ ጣውንቷ ስትስማ ፅድት ብላ ለብሳ መሆን እንዳለበት ወስና ነው። ልክ ከዶውግ አጠገብ ሁለቱ ቆመው የሚወዳደሩ ይመስል ዝንጥ ብላ ነው የመጣችው።

ሌንካ የወደፊት ህይወቷን ብቻ ሳይሆን ያበላሸችባት ከዶውግ ጋር
አብረው ያሳለፉትን ጥሩ የፍቅር ጊዜዎችን እና ትዝታውን ጭምር
እንዳታስብ አድርጋ ነው የነጠቀቻት። ለጓደኛዋ ግሬቸን የነገረችውን የሌንካን
እርግዝና ለዴሪክ ዊሊያምስ ለምን እንደደበቀችው አሁን ግልፅ ሆኖላታል።
የዚህ ምክንያቷ ደግሞ እሷ ታግላ ያልተሳካላትን ነገር ሌንካ እንደቀልድ
ማድረግ መቻሏ ነው። እሱም ልጅ ማርገዝ ነው። ሌንካ ለዶውግ ልጅ
አርግዛላታለች፡፡ ኒኪ ግን ልታረግዝለት አልቻለችም፡፡ ይሄ ደግሞ በጣም
አሳፍሯታል።

ኒኪ ግድግዳው ላይ ያለውን ሰዓት ስትመለከት ከምሽቱ 1፡22 ይላል፡፡
ዊሊያምስ ከቀጠሮው 22 ደቂቃ አሳልፏል። ይህ ደግሞ የዴሪክ ፀባይ
እንዳልሆነ ታውቃለች። ለማንኛውም ዛሬ የጣውንቷን ሌንካን ማንነትና ለምን ባሏ ከሌንካ ጋር የፍቅር ግንኙነት የመሰረተበትን ዋነኛ ምክንያትን
ታውቃለች፡፡ እና ዊሊያምስ እስኪመጣ ታግሳ መቆየት አያቅታትም።

አሁን ከምሽቱ 1፡30 ይላል ኒኪ ትዕግስቷ አለቀና ስልኳን አውጥታ
“የት ነው ያለኸው? በሰላም ነው?” የሚል መልዕክት ላከችለት።
ዴሪክ ዊሊያምስ ጠረጴዛው ላይ ያስቀመጠውን የስልኩን የንዝረት ድምፅ
ሲሰማ ገና ከመታጠቢያ ክፍሉ ወጥቶ ልብሱን ሊለብስ ነበር። ስልኩን
ሲመለከት የኒኪን መልዕክት አየ።

“እየመጣሁ ነው፡፡ ይቅርታ ስለዘገየሁ” የሚል መልዕክትን ላከላት። ኒኪም መልዕክቱ ሲደርሳት ትንሽ ተረጋጋችና ብርጭቆዋን አንስታ መጠጡን
ተጎነጨች፡፡

ዴሪክ ዊሊያምስ ማስታወሻ ለመፃፍና በኢሜይል ለሚያምነው ሰው ለመላክ ብዙ ጊዜ ፈጅቶበታል። የከተማው ከንቲባ ፎንቴስ የቀድሞ ፀሐፊ ከነበረችው ቲና ድሬይ ያገኘችው መረጃ በጣም አደገኛ እና ሁለቱንም ሊያስገድል የሚችል ነገር ነው:: እርግጥ ነው መረጃ ሀይል ነው፤ በዚያው ልክም መረጃ ህይወትን ሊያሳጣ እንደሚችል ያውቃል። እንደምንም ፅፎ
የጨረሰውን መረጃ ለጓደኛው አላን በ ኢ ሜይል ከላከለት በኋላ ላፕቶፑን
ዘግቶ ቦርሳው ውስጥ ከተተው:: ጫማውን እያሰረ እያለም ደውል ተደወለ፡፡

“አሁን ሊመጡ አይችሉም መቼስ? ማን ሊሆን ይችላል? እነዚያ የሎሬን
ጠበቃዎች ፍርድ ቤቱ የወሰነብኝን ክፍያ እንድፈፅም ሊነዝንዙኝ ይሆናል ወደ እዚህ የመጡት ብሎ እያሰበ ትንሽዬ የጉዞ ሻንጣውን በጀርባው አንግቶ ወደ በሩ ሄደና በሩን ሲከፍት በሩ ላይ የሚያውቀን ሰው ስለተመለከት ተገረመ::

ሰውዬውንም “ይቅርታ አሁን ጥሩ ሰዓት ላይ አልመጣህም፡፡ እኔ አሁን
በጣም እቸኩላለሁ.…” ብሎ ተናግሮ ሳይጨርስ ስውዬው በመጀሪያው ጥይት
የዊሊያምስን አናት ነደለው፡፡ ቀጥሎም ሁለት ጥይቶችን በደረቱ ለቀቀበትና
የቤቱ ወለል ላይ ሲወድቅ ትቶት ወጣ።

ኒኪ ከዚህ በኋላ ዊሊያምስ የቀጠሮው ቦታ ላይ እንደማይመጣ አውቃለች። ስለዚህ ሦስት አማራጮች አሏት። የመጀመሪያው አማራጫ ዊሊያምስ እንደነገራት ከዚህ ከተማ ርቃ የሆነ ሆቴል ውስጥ ተደብቃ ዊሊያምስ እስኪደውልላት ድረስ መጠበቅ ነው፡፡

ሁለተኛው አማራጫ ደግሞ በቀጥታ ወደ ቤቷ መመለስ ነው።

ሦስተኛዋ አማራጭ ደግሞ ዝም ብሎ መጠጣት ነው፡፡

ኒኪ ስለ ሊዛ እና ትሬይ ግድያ፣ ስለ ሮድሪጌዝ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር
እናም ደግሞ ስለ ማዘጋጃ ቤት ባለስልጣኖች የሙስና ወንጀል ደንታ
የላትም፡፡ እሷ በጣም ጓጉታ የመጣችው ስለ ሌንካ ለመስማት እና እፎይ
ብላም ከንዴቷ መገላገል ነበር። ግን አልሆነም፡፡ የቋመጠችለትን የሌንካን
ነገር አሁን መስማት አልቻለችም፡፡ ምናልባትም ለወደፊቱ ጭምር አትሰማ
ይሆናል፡፡

ስለዚህ ሦስተኛ ምርጫዋን መረጠች እና መጠጣት ጀመረች።

ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ኒኪን ባር ማኑ ቀሰቀሳት እና “መኝታ ላስይዝልሽ፡፡ የእኔ እመቤት” ብሎ ጠየቃት፡፡
“ችግር የለውም እኔ አስይዛታለሁ።” ብሎ ከጎኗ ከሚገኘው ወንበር ወደ እሷ ጠረጴዛ ተሻገረ እና ለባር ማኑ ክሬዲት ካርዱን እየሰጠው “ደብል ስፔራሶ እና አንድ ብርጭቆ በረዶ የሌለው ውሃ አቅርብላት” አለው፡፡

“እሺ ጌታዬ” ብሎ ባርማኑ ከአጠገባቸው ሄደ እና ብቻቸውን ቀሩ፡፡

ኒኪም ከፊት ለፊቷ የተቀመጠው ሰው ፊት ሁለት እየሆነ ስላስቸገራት እና ጉድማንን እና ዴሪክን መለየት አቅቷት በጣቷ ደረቱን እየመታች አንተ ዴሪክ አይደለህም አይደል?” “አዎን አደለሁም” አላት፡፡

“ዴሪክ እኮ አልመጣም:: ቀጠሮ ይዘን ነበር። አንተ ለምን መጣህ?አሁንም ትከታተለኛለህ ማለት ነው?” ብላ በስካር አንደበት ተናገረችው::

ኒኪ ነቅተሽ አዳምጪኝ” አላት፡፡

ይሄኔም ያዘዘው ኤስፔሪሶ መጣለት።

ኒኪም ትኩሱን ኤስፔሪሶ አንስታ
ቶሎ ቶሎ ጠጥታ ጨረሰች:: እና በትንሹ ነቃች፡፡

ሚኪ ነቃ ብለሽ አዳምጪኝ፡፡ መጥፎ ዜና አለኝ፡፡ ዴሪክ ዊሊያምስ ሞቷል። “አላት፡፡

“ምን? ዛሬ ማታ እኮ ሜሴጅ ተላልከን ነበር፡፡”

“መቼ?”

“አሁን ምሽቱን” ብላ ኒኪ የሞባይል ሰዓቷን አይታም “ከሦስት ሰዓት
👍2
በፊት ነው።”

ጉድማን ስልኳን ተቀበላት እና የተላላኩትን ሜሴጅ አይቶ እየመለሰላት
“አዎን ላንቺ ሜሴጁን ከላከ በኋላ ነው አፓርታማው ውስጥ የተገደለው።
አንድ ጊዜ ግምባሩን፣ ሁለት ጊዜ ደግሞ ደረቱን በጥይት ተመትቶ ነው ህይወቱ ያለፈው:: ሽጉጡ ላይ ሳይለንሰር ተገጥሞለት ስለነበር የሽጉጡን
ድምፅ ጎረቤቶቹ አልሰሙም::” አላት።
ኒኪ ከዚያ በኋላ የጉድማን ከንፈር ሲንቀሳቀስ ታያለች እንጂ የሚያወራው ነገር አይሰማትም: “ምስኪን ዴሪክ በጣም ጥሩ ሰው ነበር እኮ፡፡ በቃ ለእኔ እውነትን ለማውጣት ብሎ ነው እኮ ህይወቱን ያጣው” እያለች ቡዝዝ ብላ ብርጭቆው ላይ የሚንሳፈፈውን ሎሚ መመልከቷን ቀጠለች::

ጉድማንም ትከሻዋን ይዞ እየነቀነቀ ሚክ እባክሽን ዴሪክ ምን ሊነግርሽ ነበር የቀጠረሽ?” አላት፡፡ ስለ ሌንካ ነበር ሊነግረኝ የነበረው::” አለችው፡፡

“ስለ ባልሽ ውሽማ? ስለ እርግዝናዋ ነበር ሊነግርሽ የነበረው?”

ኒኪም የግርምት ፊት እያሳየችው “ታውቅ ነበር ማለት ነው?”

“አዎን ጆንሰን ነው መረጃውን ያገኘው፡፡ ግን ለምን ደበቅሺን?”

“አልደበቅኳችሁም ግን በቃ መናገር አልፈለግኩም:: ደግሞም ሁሉ
ነገሬን ለእናንተ የግድ መናገር አለብኝ እንዴ?” አለችው ተኮሳትራ::

“እንደሱ ማለቴ አይደለም። ነገር ግን ምናልባት ግድያዎቹ ከእሱ አደጋ
ጋር ሊገናኙ ስለሚችሉ ነው::” አላት፡፡

ኒኪም ትከሻዋን ሰብቃ ዝም አለችው::

ጉድማን በጣም ትዕግስት ባጣ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እየተመለከታት
“ዴሪክም አንቺም የጉዞ ሻንጣ ይዛችኋል፡፡ ከተገናኛችሁ በኋላ ወዴች ልትሄዱ ነበር?” ብሎ ጠየቃት፡፡

“አንድ ላይ አይደለም የምንሄደው። ከተገናኘን እና ካወራን በኋላ ተለያይተን ለመሄድ ነበር ዕቅዳችን፡ ዴሪክ እኛ እዚህ ከቆየን ኣደን እንደሚገጥመን ጭምር ነው ያስጠነቀቀኝ እና ከዚህ መሸሽ እንደሚኖርብን ነበር ያስጠነቀቀኝ። ግን ምን ያደርጋል አሁን ዴሪክ የፈራው ደርሶበታል”

“ከማን ነበር የምትሸሹት? ሥም እፈልጋለሁ። ንገሪኝ” አላት እየጮኸባት፡፡

ኒኪ ግን መልስ ከመመለስ ይልቅ ዝም ስላለቺው ጉድማን ከንፈሯን
በሀይል ሳማት። እሷ ግን በድን ሆና ምንም የመሳም ምላሽ አልሰጠችውም።
የዴሪክ ዊሊያምስ ሞት ይህንን ስሜቷን አጥፍቶባታል። ከዚያ በኋላ ኒክ ስለ
ሮድሪጌዝ፣ ስለ ማዘጋጃ ቤት ሙሰኞች፣ ስለ ዊሊ ባደን እና ስለ የተለያዩ
ባንኮች የአደንዛዥ ዕፁን ገንዘብ የማስተላለፍ ሁኔታን ጭምር ልክ ዴሪክ
ዊሊያምስ ፅንስ ሀሳቡን በገለፀላት መልኩ ገለፀችለት።

ጉድማንም የተለያየ ጥያቄን ሲጠይቃት ቆይቶ በቂ ነው የሚለውን መልስ ካገኘ በኋላ ሻንጣዋን በእጁ ይዞ ተነሳ፡፡

“እኔ ነኝ ቤት የምወስድሽ፡፡” አላት፡፡
“ቤት መሄድ አልችልም አደጋ ሊኖረው ይችላል” አለችው፡፡
እሱም “ያንቺ ቤት ሳይሆን የእኔ ቤት ነው የምወስድሽ” አላት።
ኒኪም ከእሱ ጋር ህይወት መስርታ ብትኖር ምን አይነት ድንቅ ነገር
ሊሆንላት እንደሚችል በአዕምሮዋ ሳለች። ማለትም ሲንከባከባት እና ከማንም
ሰላይ መከታ ሲሆናት በውስጧ ስትስል ቆይታ ነገሩ ሊሆን እንደማይችል
ገባት::
ከተቀመጠችበት ተንስታም ከንፈሩን በስሜት ከሳመችው በኋላ “በጣም
ጣፋጭ ስው ነህ፡፡ ግን ከአንተ ጋር አብረን ልንሆን አንችልም::”

“ለምን?”

“ምክንያቱም ልቤን ለዶውግ ሙሉ በሙሉ ሰጥቼው ነበር፡፡ እሱ ግን
እንዳይመለስ አድርጎ ልቤን ሰብሮታል።” ብላው ሻንጣዋን ተቀብላው ከሆቴሉ
ወጣች::

ይቀጥላል
👍2
አትሮኖስ pinned «#የፍቅር_ሰመመን ፡ ፡ #ክፍል_አርባ_ስድስት ፡ ፡ #ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን ፡ ፡ #ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው ...ከኮሪያውያን የፍል ውሃ ቦታ ወጡ እና ወደ ሱሺ ባራቸው አመሩ፡፡ ሱሺ ባር ውስጥም ተቀምጠው እየበሉ እያሉ ግሬቸን “ይህንን ቀጠርኩት ያልሺውን የግል መርማሪሽን ከየት ነው ያገኘሽው?” ብላ ኒኪን ጠየቀቻት፡፡ ኒኪም “ከጎግል ላይ ነው:: ስለ እሱም በደንብ አድርጌ ካነበብኩኝ በኋላ ነው…»
#የወድያነሽ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


አንዳንድ ቀን አካባቢውን መልከትከት ብዩ ሰው ያለመኖሩን አረጋግጥና ሥጋዊ ስሜቷን ለመቀስቀስ የሚችለውን የአካላቷን ክፍል ከፍ ወይም ዝቅ ብዬ
መደባበስና መጎነታተል አዘወተርኩ፡፡ ከወደ ውስጥ እየጋፈረ የሚያጠልማት
የኃፍረቷ ጎርፍ አፏን አፍና የሣቋን ግፊት እንድታምቅ ያስገድዳታል። ፊቷን
ሽፍና መሽኮርመምና ሰብሰብ ብላ መቀመጥ የዘወትር ልማዷ ነበር፡፡ እንደ ዘበት ሽብ ያደረገችውን ሻሿን ድንገት ስቤ እይዝና ያንን ውብ ኑግ መሳይ ጸጉር
በታትኖ ማየት ወደ እርሷ ከሚስቡኝ ሁኔታዎች ሁሉ የበላይነትን ያዘ፡፡

እንድ ቀን እንደ ልማዴ የጊዜና የአካባቢውን ሁኔታ ተመልክቼ እጅዋን
እያልመዘሙዝኩ አፌን ለወሬ ሾል ሾል ሳደርግ “ዋ" እለችኝና ዐይኔን እያየች
እናትዎ ያዩዎትና አጉል ቅሊት ይቀልላሉ፡ የኔ እንደሁ ዕውቅ ነው፡ ያው ሂጂ
ውጪ ከቤቴ ብለው ማባረር ነው» ብላ የተሰደሩ ጥርሶቿን ፈልቅቃ አስጐበኘችኝ፡፡ ለወጉ ያህል ጥቂት ተላፋን፡፡ ልባችን ተቀራርቦ ስሜታችን ይበልጥ ተዋሐደ፡፡ በፍቅራዊ ስሜት ለሚከታተሏት ዐይኖቼ የምትሰጠው ምላሽ አርኪ በመሆኑ የፍቅራችን ጋቢ ዐርቡ እየሰፋ ሒደ፡፡

እሑድ ጠዋት ነበር። ወላጆቼ የውብነሽን አስከትለው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደዋል፡፡ እናቴ ስለ እኔ ወደ ቤተ ክርስቲያን ያለመሔድ ስትናገር
«የሱን ነገር ተዉኝ! የእናንተ ጸሎት ለሁላችንም ይበቃል” ይላል። አይጣል
እቴ! ይኸስ የጤናም አይደል» ትላለች፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የምታቀርበውን
ነቀፌታ ከጉዳይም አልቆጥረው:: ተኝቼ አረፈድኩ፡፡ ጋቢ ለብሼ የመኝታ ቤቴን
በር ስከፍት የወዲያነሽ አረንጓዴ የውስጥ ልብስ ብቻ ለብሳ እንግዳ መቀበያ
ክፍል ውስጥ መወልወያ ጨርቅ ይዛ ቆማለች፡፡ ጸጉሯ በተንተን ብሉ በአንገቷ
ዙሪያ ተሽመልምሉ ይዘናከታል፡፡

የአካላቷ ሙላት የመጨረሻውን ደረጃ ይዟል። ያ ከዓመት በፊት በርኅራኄና በአኗኗሯ በዐዘኔታ ላይ ተመሥርቶ የነበረው ስሜቴ ፍጹም ተለውጦ
አሁን ወደ ልዩ ሥጋዊ ውዴታ አጋድሏል፡፡ ዛሬ በተለይ በልቤ ውስጥ የጉርምስና
ደም ተንሽከሽከ፡፡

በትዕዛዛዊ አቀራረብ ሳይሆን ልዩ የመቀራረብን ስሜት ለማብሠር
በምታስችል ለስላሳ ድምፅ "ነይ እስኪ የወዲያነሽ?» ብዬ ጠራኋትና አልጋው
ጫፍ ላይ ተቀመጥኩ። የመስታወት መወልወያዋን እንደ ያዘች በአለባበሷ አፍራ መዝጊያው አጠገብ ቆመች። ስልክክ ባለው ጠይም ፊቷ ላይ ወርዶ ከጉንጫ ላይ ሲደርስ የሚርመሰመሰው የወጣትነት ሙሉ ደም ግባቷ የምሆነውን አሳጣኝ፡፡

«ግቢ እንጂ ምን ያስፈራሻል?» ብዩ ለማግባባት ሞከርኩ። ዐፈር ከድቷት እንደ ዘመመች የድሃ ጎጆ አንገቷን ወደ ግራ ጎን ሰበር አድርጋ ቆመች።

እንደገና ነይ እንጂ ግቢ የወዲያነሽ» ብዩ አባበልኳት። ውስጥ ውስጡን የበላይዋና አዛዥ መሆኔ ስለ ተሰማት በፍርሃት እየተናጠች ገባች፡፡ በሩን ዘጋሁት። ደነገጠች። የፈገግታዋ ንጋት ቀስ በቀስ ጠለሰ። እንደሚንበረከክ ተማሪ ጉልበቷን ሰበር አድርጋ ወለሉ ላይ ተቀመጠች፡፡ እኔም ስለ ወለሉ ላይ ትቢያ ምንም ሳልጨነቅ ከፊት ለፊቷ ቁጭ አልኩ፡፡ በስሜት ተቁነጠነጥኩ፡፡ ቤቱና በቤት ውስጥ ያለው ዕቃ ሁሉ «መጡብህ! ደረሱብህ! የሚሉኝ ስለ መሰለኝ ዐይኖቼ ቃበዙ፡፡ ድንገት ብድግ ብዬ «ተነሽ» አልኳት፡፡ አነጋገሬ ቁጣ ቅልቅል በመምሰሉ ወዲያው ተነሣች። ልፊያ ቢጤ ለመጀመር በማሰቤ ሽንጧ ላይ ነካኋት። ተሸማቀቀች። ታዲያ ምን ያደርጋል፡ ምን እንደምፈልግና እንደማደርግ መላ ቅጡ ጠፋኝ፡ መላ አካላቴ ብው ብሎ ጋለና ፍርሃቴን ገፈፈው፡፡ የለበስኩት ጋቢ ተንሸራትቶ እግሬ ሥር ወደቀና በእግራችን ረጋገጥነው። እጆቼን ባንገቷ ዙሪያ ጠምጥሜ በልዩ ደስታ እምነሽነሽ ስለ ነበር የወደቀውን ጋቢ ቁብም አላልኩት። ድንገት አፈትልካ ለመሄድ ሞከረች::
አልተሳካላትም፡፡ ፊቷን ወደ ተዘጋው በር አዙራ ተቀመጠች፡፡ ከበስተጀርባዋ ቆሜ
ጎንበስ አልኩና እጄን በትከሻዋ አኳያ ወደፊት ቁልቁል ሰደድኩት። እንደገና
ከፊት ለፊቷ ዞሬ ተንበረከከሁ፡፡

ሳትወድ በግድ በአገጯ ወደ ላይ ይዤ ፊቷን አየሁት። እንባዋ ይጎርፋል፡፡ በእጄ ስቢያት ተነሣሁ፡፡ «እኔ እኮ የቀልዴን ነው:: ደስ ይልሽ እንደሆን ብዩ ነው እንጂ ደስ የማይልሽ ከሆነማ ከዛሬ ጀምሮ ከደረስሽበትም አልደርስ እ! » ብዬ እጆቿን እንደ ያዝኩ ዝምታዬን ተጎናፀፍኩ። ለማስመሰል እንጂ ከልቤ አልነበረም፡፡ ተፋጠጥን፡፡ ዐይኖቼ ቦዙ። ዘንጉን በዳበሳ እንደሚፈልግ ዐይነ ሥውር እጆቿን ዘርግታ አንገቴ ላይ ተጠመጠመች፡፡ ደረቴ ላይ ተለጥፋ አገጬ ስር ከቀረቀረች፡፡ የፊቷ ትኩሳትና የደረቷ ሙቀት ሲገናኙ ኃይለኛ ነዛሪ
የርካታ ማዕበል አጥለቀለቀኝ፡፡ የተስተካከለ ንዝረት ግን አልነበረም፡፡ ደረቴ ላይ እንደ ተለከፈች በጉንጯ ላይ እያቋረጠ የሚወርደው እንባዋ ስሷን ልብሴን አረጠባት። አዲስ ሰመመናዊ ቆይታ ተጀመረ፡፡ ከከንዲት ሥር ላይ የበቀሉ መንታ መቃዎች መስልን። ፀጥ እና ቀጥ በማለታችን እካባቢውን ጸጥታ
ሰፈነበት።

ግድግዳው ላይ የተንጠለጠለው ገደ ቢስ ሰዓት ጥበባዊ ተግባሩን ለመፈጸም ደወለ፡፡ እኔና እርሷም በዚያቹ ቅፅበት ከሰመመናችን ባነንን፡፡ ከራሷ ቀና ብላ በእንባ የተከበቡ ዐይኖቿን እና ፊቷን አሳየችኝ::

የስሜቷ ዶፍ ተፍ እለ። በሰውነቴ ውስጥ ያለው ኃይል ተንጠፍጥፎ ያለቀ ይመስል እጆቼ ዛሉ፡፡ ቀስ በቀስ አየት ሳደርጋት ወለሉ ላይ የወደቀውን ጨርቅ ይዛ በዝግታ ወጥታ ሒደች:: ዐይኖቼ አብረዋት ተጓዙ፡፡ እኔም ወለሉ ላይ
ወድቆ ባቧራ የተልሞሰሞሰውን ጋቢ አራግፌ ወደ አልጋው ግርጌ ወረወርኩት።አልጋዩ ላይ ወጥቼ በጀርባዬ ተንጋለልኩ:: ተንጠራራሁ፡ አፋሸግሁ፥ እግሮቼን እያኮራመትኩ ዘረጋሁ። ጥልቅ ፍቅር በውስጤ ተፍለቀለቀች፡፡ የአልጋው ሽቦዎች እስኪያንሲያጢጡ ድረስ ተወራጨሁ፡፡ እንደገና ቀና ብዬ አልጋው መኻል ተቀመጥኩ፡፡በስተራስጌ በኩል በምስማር ላይ የተንጠለጠለውን ኮቴን ተንጠራርቼ አወረድኩና ከልብሲ ጋር የከረረ ጠብ ያለኝ ይመስል አሽቀንጥሪ ግድግዳው ላይ አላተምኩት፡፡ ከአልጋው ላይ እመር ብዩ ወርጄ የወዲያነሽ አጥባና ተኩሳ ያስቀመጠችልኝን ሱሪ ከሻንጣ አወጣሁ፡፡ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጬ እግሮቼን ባንድ ጊዜ ቁልቁል በሱሪው አቆልቋይ ሰደድኳቸውና ቀጥ ብዩ ቆምኩ፡፡ በዙሪያዩ ያለው ነገር ሁሉ አዲስና እንግዳ ነገር መስሎ ታየኝ፡፡ ሰማያዊ ሸሚዝ ለብሼና ግራጫ ኮት ደርቤ ጸጉሬን ሳላስጥርና ያደረ ፊቴን ውሃ ሳላስነካ መሰስ አልኩ፡፡ወዴት እንደምሒድ አልወሰንኩም፡፡

ደረጃውን ወርጀ ግቢው መኻል ደረስኩ፡፡ የወዲያነሽ የሚያምር ቢጫ ቀሚስ ለብሳና ዐመድማ ሻሽ አስራ ማድ ቤቱ በራፍ አጠገብ ቆማ አየኋት፡፡በግራ እጅዋ አንድ ንጹሕ ነጭ ጭልፋ ይዛ ነበር፡፡ በዚያ ሰምቼ በማልጠግበው ድምጿ «እጅዎን ላስታጥብዎት መምጣቴ ነበር፥ ቁርስ አዘጋጅቻለሁ ቆዩ አትሒዱ» አለችኝ፡፡ በአድራጐቴ ሁሉ እንዳልተቀየመችና ቅር እንዳላላት በማወቄ ልቤ በደስታ እንደ ፈረሰኛ ጎርፍ ሽቅብ ዘለለች። ላሳየችኝ ብሩህ ገጽ የተከማቸ ፈገግታ ላኩና «ተመልሼ እመጣለሁ አዘጋጅተሽ ጠብቂኝ» ብያት ወጣሁ። የትምዋልኩ እንጂ እንዳባባሌ አልተመለስኩም፡፡

ቤተሰቡ በሞላ ስለ ሁለታችን የስሜት ቁርኝት የሚያቀው አንዳችም ነገር
አልነበረም፡፡ የአባቴ የዕረፍት ሰዓታት ሃይማኖት ነክ መጻሕፍትን ለማንበብና
ያንኑ የሕግ መጽሐፉን በመነዝነዝ ላይ ስለተመደቡ ለሌላ ጉዳይ የሚውል ጊዜ
አልነበረውም፡፡ እናቴም የተማረ ሰው፣ ዐዋቂ ነው እያለች በጣም ስለምትመጣብኝዐበእርሷ እምነትና ልማድ ከ«ገረድ» ጋር ይህን መሰለን ግን
👍3
ኙነት ይፈጽማል ብላ አልጠረጠረችም፡፡ ከሁሉም በላይ የጠቀመኝና ከመሳቀቅም ያዳነኝ ግን፣
«በማንኛውም ጊዜ ቢሆን ቤተሰቦቼ ባሉበት አካባቢ ሁሉ እንኳንስ ፈገግ ማለትና ቀና ብለሽ እንዳታይኝ» ብዬ መክሬያት ስለ ነበር ቃሌን አክብራ በፈቃደኝነቷ መዝለቋ ነበር፡፡

ጊዜው እየጨመረ በሄደ ቁጥር የሁለታችን ፅኑ ፍቅራዊ ግንኙነት እየሰፋ
መጐልመሱን ቀጠለ፡፡ ሰው ከሌለና ቤተሰቦቼ ራቅ ወዳለ ሥፍራ መሄዳቸው
ከተረጋገጠ መኝታ ቤት ድረስ ቀጥ ብላ ትመጣና ያለ አንዳች ፍርሃት ተጫውታ
መሄድን ተላመደችው:: አበባና ንብ ሆንን። ተጣጣምን፡፡ በልቤ ውስጥ የፍቅር
እውነተኛ ቡቃያ በቀለ፡፡ የቡቃያውም የሕይወት መስኖ የሚፈልቀው ከየወዲያነሽ የፍቅር ምንጭ ሆነ፡፡

አንድ ነገር በማበላሸቷም ይሆን ወይም በመስበሯ እናቴ ስትቆጣትና ግልፍ ብሏት ስትገሥጻት በማይና በምሰንበት ጊዜ ሁሉ ግልጽ ባልሆነ የአነጋገር ዘዴ እየተጠቀምኩ የውክልና ያህል ጥብቅና እቆምላት ጀመር።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የዕለቷ ፀሐይ የምዕራቡን አድማስ ነክታለች፡፡ አካባቢያችን በጨለማ
መጋረጃ ሊጋረድ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ቀርተዋል፡፡ አትክልቱ ውስት በመዘዋወር ላይ እንዳለሁ ከመጠያየም ዐልፎ ለከይን ያዘ፡፡ ያው ምክንያት ሆኖ ወደ ቤት ገብቼ መስኮት አጠገብ እንደ ተቀመጥኩ የምሽቱ ከዋከብት ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። ከዋክብቱም፣ ትልቁ በትልቅነቱ ሲንቦለቦል፣ ትንሿም በዚያ በመጠኗ ትንተገተጋለች፡፡ ከወደ ሰሜን ፈጣንና ቀዝቃዛ ንፋስ እየተዥጎደጎደ ይነፍሳል። የተመሳሳዮቹ ዛፎች ቅርንጫፎች እርስ በእርሳቸው እየተሻሹ የትርምስ ልፊያ ይዘዋል። መታደል ነው። እነርሱ ዘንድ ፍርሃት ይሉኝታ የለ! ንፋሱ ለዘብ
ጠንከር እያለ ስለሚነፍስ ጸጥታና ውካታ ትንቅንቅ የገጠሙ መሰለ። ከሩቅ
ከቅርብ የሚታዩት ዛፎች በጨለማ ጥልቅ ውቅያኖስ ተወጠው እንደ ወራቢ
ይወዛወዛሉ።

በጨለማው ውስጥ የሚንዠቀዥቀው የከዋክብት ብርሃን በዕፅዋቱ መጠንና ቅርፅ ላይ ልዩ ኅብራዊ ትርኢት ሥሏል፡፡ ስሜቴ ስለ ተመሰቃቀለ ተንቆራጠጥኩ። ከመኝታ ቤት ወጥቼ እንግዳ መቀበያ ክፍል ገባሁ፡፡

የወዲያነሽና የውብነሽ ራት ለማቅረብ ተፍ ተፍ ይላሉ፡፡ የወዲያነሽ የእህቴን የአረማመድና አንዳንድ የሁኔታ ቄንጦች በመጠኑ አስተውላ በመቅሰሟ
ማራኪነቷ በጣም ጎላ፡፡ ከራት በኋላ እንደገና ተመልሼ መኝታ ቤት ገባሁ።
ከያዝኩት መጽሐፍ ላይ ገና አምስት ገጽ ያህል እንዳነበብኩ በሩ በዝግታ
ተከፈተ። የወዲያነሽ በእርጋታ ከገባች በኋላ ከትራስጌዬ አጠገብ ሁለት ነጫጭ
ጠርሙሶች ይዛ ወጣች፡፡ ደረጃዎቹን ወርዳ ስትጨርስ በመስኮቱ በኩል ብቅ ብዩ አየኋት። በሦስት ትልቅ ኮባዎች ከተከበበው ውሃ አጠገብ እንደ ደረሰች ጐንበስ ብላ አንዱን ጠርሙስ አስቀመጠችው::

የያዝኳትን 'የቀትር ጨለማ” እልባት አድርጌባት እንደ ዘበት ወጣሁ።
ከቤት ሲወጣ በመጀመሪያው ደረጃ ላይ ቆምኩ፡፡ ያሰብኩትን እንዳልፈጽምና
የፍላጐቴን ጥማት እንዳላረካ አንድ ነገር እክል ሆነብኝ፡፡

ማታ ማታ ደረጃ ስንወርድና ስንወጣ አልታየን አለ» ተብሎ ከሦስት ወር በፊት የተተከለው መብራት ግቢውን ወገግ ያለ ብርሃን ሰጥቶታል።

ደግነቱ የብርሃኑ ውጋገን ከሰሜን ምዕራብ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ብቻ ይዘልቅና ከዚያ ወዲያ ያለውን ቦታ ጨለማ ያሶመስምበታል፡፡ ዕንጨት ላይ
የተመታችውን ማብሪያ - ማጥፊያ ሦስት ጊዜ አንቀቅጬ አንተገተግኋት፡፡

የተንጠለጠለችው መብራት በዕረተ ሞገድ የተነካካች ይመስል እንደ
ውድቅት እሳት ራቅ ቦግ እልም፣ ቦግ እልም አለች። ተፈጥሮም ድጋፍ እንድትሰጥ የታደመች ይመስል ኃይለኛና ፈጣን ነፍስ ባናት ባናቱ ነፈሰ፡፡ ይህም መብራቲቱ ተቃጥላ ወደመች ለማለት ከእኔው ሽር ጋር የሚሰምር ምክንያት ሆነ።

ደረጃውን ገመሬ እንደ ለቀቀው ናዴ ተንደርድሬ ወረድኩት።የአወራረዱ ፍጥነት ስሕተት ነበር፡፡ ከዚያም በጣም ዝግ እያልኩና በጢሻ ውስጥ እያደባ እንደሚሽሎከሎክ አዳኝ እየተራመድኩ ከትልቁ ኮባ ጀርባ ቆምኩ።

ትንፋሼን ውጬ እያሰላሁ ከተጠጋሁ በኋላ ከበስተኋላዋ ዐይኖቿን
በጣቶቼ ሽፈንኳቸው። ባልተጠነቀቀው አካሏ ላይ ያረፉት ጣቶቼ ድንገተኛ
ድንጋጤ ፈጠሩባት፡፡

በቀጭን የድንጋጤ ድምዕ «ዋይ» ብላ ጮኸችና እኔ መሆኔን እንዳታውቅብኝ ድምፄን አጎርንኜ «ማን ነኝ? እስኪ ዕወቂኝ?» ብዬ ጠየቅኋት።

ምንም ቢሆን የውጪ ሰው አይሆንም በማለት ተረጋጋች፡፡ ሁለቱንም በውሃ የሞሉ ጠርሙሶች በአንድ እጅዋ ከሆድዋ ላይ ኣጣብቃ ከያዘች በኋላ የውሃ
ፍንጥቅጣቂ ባለባቸው የቀኝ እጅ ጣቶቿ የቀኝ ክንዴንና ጣቶቼን ዳበሰቻቸው።
የማወቂያ ምልክትና ዘዴ አጣች፡፡ እጅዋ ሌላውን እጄን ፍለጋ ሄደ። ግራ እጄን
ያዘችው:: ሰዓቴን አገኘቻት፡፡ በደስታ የተሽሞነሞነ ሣቅና ትንፋሽ አደባልቃ
ለቀቀች፡፡ «አሁንስ ዐውቄዎታለሁ፤ እርስዎ ነዎት» ብላ በረጅሙ ተነፈሰች።
ለቀቅኋት። ጠርሙሶቹን እግሯ ሥር ስታስቀምጥ እንደኛዋ ጠርሙስ ተከነበለች።

የወዲያነሽ በዚያች ሰዓት የሾመችው ጋን ቢተረተርም ግድ የላትም ነበር። ፊት ለፊቴ ቆመች፡፡ ውጋገን ያረፈበት የሚመስለው ጠይም ፊቷ የጨለማው ጥቁረት ይታገለዋል፡፡ የጨለማው ውስጥ ውበቷ እንጎሌ ውስጥ ተርከፈከፈ፡፡ የተጠሙት ዐይኖቼ በመመልከቻ ዋንጫቸው እየደነበቁ ጠጧት። ግን ቀመሱ እንጂ አልጠገቡምና ቦግ ብለው ተከፈቱ፡፡ በቀኝ እጅዋ እየሳብኩ ወደ ጓሮ ይዣት ዞርኩ፡፡ ማታ ማታ የትልቁ ቤት ጥላና የየዛፎቹ ውስብስብ ቅርንጫፎች የምድረ ግቢውን ደቡባዊ ክፍልና አካባቢውን ለየት ያለ ድፍርስ ጨለማው ይጥለብታል።

ተስካር ለመብላት እንደሚገሰግሱ ዲያቆናት ተመራርተን በስተደቡብ
በሚገኘው የግንብ አጥር ደረስን፡፡ በእኔና በእርሷ ሕሊና ውስጥ ሲፍለክለክ የቆየው
የፍቅር ስውር ኣካል ተጨባጭ ሕይወት ሆኖ ተከሠተ፡፡

እጆቼ አንገቷ ላይ ሲጠመጠሙ እጆቿ በወገቤ ዙሪያ እንደ ዝናር ዞሩ፡፡
" እንዲያ ሲሳብና ሲዥጎደጎድ የቆየው ነፋስ አቅጣጫውን ያስለወጡት ይመስል
ደብዛው ጠፋ፡፡ እንዲያውም አልአፍ የምትመጣ ደካማ ትንፋሽ መሰለ፡፡
በአቅራቢያችን ያለችው ኮካ ለጋ ቅርንጫፎች ደፋ ቀና እያሉ እርስ በእርሳቸው እየተሳሳሙ ይበተናሉ፡፡ ጉንጯ ላይ ሳም ሳደርጋት የፍቅር ደማቅ ችቦ ተለኮሰ አፌን ወደጎን አንሸራትቼ የከንፈሮቼን ነዲድ ከከንፎሮቿ አርኪ ገለት
በማጋጠም ምጣድና ክንባሉ ሆንን፡፡
በሕሊናችንም ውስጥ ያ የፍቅር ችቦ ፏ
ብሉ ሲቀጣጠል ታየኝ።

💫ይቀጥላል💫
👍4
#እንግዳ

በበጋ ወቅት ዝናብ በድንገት ቢመጣ፣
በሃምሌው ጉም መሃል ፀሃይዋ ብትወጣ
በቁርና በውርጭ ሃሩሩ ቢያስጨንቅ፣
በብርድ ቢጨበጡ በሃይለኛው ወበቅ፣
ድንገት ከተፍ ቢል ሁሉም ሳይጠበቅ፣
እንግዳ ይባላል ያለ ወቅቱ መጥቶ፣
አንድም ቀደም ብሎ አለያም ዘግይቶ፡፡
ታዲያ ዛሬ ዛሬ

ልብን ልብ ሲነሳ ቀልብ ሲያስት የኖረው፣
የህልም አለሙ እንጀራ የማይጠገበው፣
የአንጀት አንጀተኛ ስለት የማይለየው
በልብ ውስጥ ተቀብሮ በድብቁ ጓዳ፣
በድንገት ሲከሰት ልክ እንደ ዱብ ዕዳ፣
የተፈታ ህልም እንጂ ማን ሊለው እንግዳ፡፡


🔘ሻለቃ ወይን ሐረገ በቀለ🔘
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ_ሰባት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው


....አኔ ቤታማን እምባዋ እና የሚዘንበው ዝናብ መንገዱን እየጋረደባት መኪናዋን በደንብ እንዳታሽከረክር እያደረጋት ነው:: ግንቦት ላይ ሎስ አንጀለስ ውስጥ አይዘንብም ነበር፡፡ ግን የእሷን ስሜት ለማጀብ በሚመስል መልኩ ሰማዩም አብሯት እዬዬ እያለ ነው። አሁን እሷ ሰው ነው የሚያስፈልጋት። ውስጧ በጣም ሀዘን እና ተስፋ መቁረጥ እንደተሞላባት
ነው:: ስለዚህም ኒኪ ታስፈልጋታለች። ኒኪ የምትሰጣት አድናቆትን እና
ይቅርታን ለምዳዋለች። ልክ ሉዊስ ባሏ ያደርግላት የነበረውን ነገር ነው ኒኪ
የምታደርግላት እና ወደ ኒኪ መሄድ ይኖርባታል።

ዛሬ ማታ ነው እንግዲህ ለኒኪ ስትነግራት የነበረውን፣ ሉዊስ አይተወኝም የምትለው ነገር የተገላቢጦሽ መሆኑ የታወቃት። ባለፈው ማታ ሉዊስ ከፕሮግራሙ ላይ ሲቀር ነበር ከእሱ ጋር ያላት ግንኙነትን ማብቃት እንዳለበት ውሳኔ ላይ መድረስ የሚኖርባት።

አኔ የኒኪ ቤት ስትደርስ ዝናቡ ሀይሉን ቢቀንስም የመኪናው ጣራ ላይ
የሚያርፈው የዝናቡ ድምፅ ግን ይሰማታል። ከመኪናዋ ወርዳ የኒኪን ግቢ
ስትመለከት መኪናዋን ግቢ ውስጥ ስላገኘችው ኒኪ ቤት እንዳለች ለማወቅ
ቻለች:: ዝናቡ የእንጨት በሩን ስላረጠበው ነው መሰል በቀላሉ ቀጫጭን ጣቶቿን አሾልካ በሩን ከፈተችና ወደ ውስጥ ገባች፡፡

የኒኪ ቤት ሙሉ በሙሉ በጭለማ ተውጧል። ስለዚህም ኒኪ ተኝታ
ሊሆን ይችላል ብላ አስባ እንዳትረብሻት ብላ ልትመለስ ስትል ውስጧ እዚህ
ድረስ መጥተሻል እና ኒኪን ሳታገኚያት መመለስ የለብሽም አላት፡፡

በሩን ልታንኳኳ ስትል ግን ሀይለኛ የለቅሶ ድምፅ ሰማች፡፡ ድምፁ የሚመጣው ከጓሮ በኩል ስለሆነም አኔ እንዳትወድቅ ተጠንቅቃ በአጥሩ እና በቤቱ መሀል ባለው ክፍት ቦታ ወደ ጓሮ አመራች::

አየቻት፡፡ ወደ ኒኪ እየቀረበች ስትሄድም ኒኪ አይኗን ጨፍና እና ትንሽ
ጓሮው ጋር ስትደርስም ኒኪ ከአንድ ጃካራንዳ ዛፍ ሥር ተንበርክካ አየቻት። ወደ ኒኪ እየቀረበች ስትሄድም ኒኪ አይኗን ጨፍና እና ትንሽ ሽጉጥ ከጉሮሮዋ በኩል ወደ ላይ እንደ ደቀነች ተመለከተች እና በጣም ደነገጠች፡፡

ኒኪ እኔ ነኝ አኔ ነኝ!” ብላ ከዝናቡ ድምፅ በላይ በመጮህ ወደ ኒኪ እየሮጠች ሄደች፡፡ ኒኪም ድምፁን ሰምታ አይኗን ስትገልጥ አኔን በዝናቡ በስብሳ አጠገቧ ቆማ አየቻት፡፡

ለጥቂት ሰከንዶች ያህል ሁለቱ ዝም ብለው ሲተያዩ ከቆዩ በኋላም ኒኪ
ነይ ወደ ውስጥ ግቢ እና በዝናብ የበሰበሰውን ልብስሽን ቀይሪ” ብላት ይዛት ወደ ቤቱ ውስጥ ገባች፡፡

ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ ኒኪ ብርድ ልብስ ለብሳ ሶፋ ላይ እንደ ህፃን ለጥ ብላለች፡፡ ዶውግ እና እሷ ልጅ ነበር ይፈልጉ የነበሩት። በመሆኑም ለመውለድ ያስችላት የነበረው ህክምና ሳይሳካለት ሲቀር ያለመውለድን እንደ ትልቅ ሀዘን ነበር የቆጠረችው፡፡ ግን በተደጋጋሚ ከደረሱባት ሀዘኖች በኋላ ትልቅ ሀዘን ምን ማለት እንደሆነ ገባት።

ምናልባት አኔ ባትመጣ ኖሮ ቃታውን ስቤ ራሴን አጠፋ ነበር? ብላ ራሷን ጠየቀች፡፡ ምናልባትም አኔ በእግዚአብሔር የተላከች መልአኳ ሆና ህይወቷን ታድጋዋለች፡፡

“ምናልባት አኔን የላከልኝ ከሞት ባሻገር የሚገኘው ዶውግ ባሌ ይሆን?'
የሚለው ሀሳብ ደግሞ ጥሩ ስሜትን ስለሰጣት ደስ አላት::

ዛሬ መሞት አትፈልግም። በፍፁም! ከዚህ በኋላ ብዙ የምታከናውናቸው ነገሮች ስላሏት ቢያንስ እነዚህን ነገሮች ካከናወነች በኋላ ምናልባት ሞቷን
ትፈልግ ይሆናል፡፡ አሁን ግን ቢያንስ ዴሪክ ያገኘውን እውነት እስክታውቅ ድረስ በህይወት መቆየት አለባት፡፡

ከኒኪ ቤት በትንሽ ርቀት ላይ ከቆመው መኪና ውስጥ የሚገኝ አንድ ሰው በጎግል መነጽሩ ወደ ኒኪ መኖሪያ ቤት ሲመለከት ቆየና መነፅሩን አውርዶ የመኪናው ዳሽ ቦርድ ላይ አስቀመጠው።

“በቅርቡ ሁሉ ነገር ይስተካከላል” ብሎም ለራሱ አጉረመረመ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጉድማን ከዳየርስ ሆቴል የጎጆ ቤት ማረፊያ ቁጭ ብሎ እያሰበ ይገኛል።
ወደዚህ የመጡት በዴሪክ ዊሊያምስ ሞት ግድያ ላይ የፎሬንሲክ ምርመራ
የሚያደርጉ ባለሙያዎችን ውጤት ለማወቅ ነው:: ባልደረባው ጉድማን ከሃያ
ደቂቃ በፊት የጠጣው ቡና ስላልተስማማው ለሦስተኛ ጊዜ ሽንት ቤት ገብቶ እያማጠ ነው:: ሌሊት 11 ሰዓት ላይ ኒኪ የላከችለትን ኢ ሜይል ስልኩን ከፍቶ በድጋሚ ማንበብ ጀመረ::

“ሌሊቱን በሙሉ ሳስብበት ነው ያደርኩት። አሁን ዴሪክ ዊሊያምስ በህይወት የለም። ይህንን ነገር ላንተ መንገር ሳይኖርብኝ አይቀርም፡፡ብራንዶን ግሮልሽ ትላንትና ማታ በጣም በከፍተኛ ፍርሃት እና ጭንቀት ውስጥ ሆኖ ደውሎልኝ ነበር። ስለ ግሮልሽ ዋሽቻለሁ፡፡ አዎን ብራንዶን
ግሮልሽን ከዚህ በፊት አውቀው ነበር፡፡ እሱ ከዚህ ግድያ ጋር ይያዝ አይያዝ
የማውቀው ነገር የለም” የሚል መልዕክቷ ይቀጥልና

“ምናልባት ዊሊያምስ ትክክል ከሆነና እሱ በሚገልፀው የአደንዛዥ ዕፅ
ቀለበት ውስጥ ፖሊሶች የሚገኙበት ከሆነ ጆንሰን እዚህ ነገር ውስጥ
እንደሚገኝበት አልጠራጠርም። ለምን ብትለኝ፣ እሱ የቀድሞ የፀረ አደንዛዥ
ዕፅ የፖሊስ ቡድን አባል ነበር፡፡ በዚያ ላይ ሲነየር ነው። ይህ የግድያ ወንጀል ምርመራ እንዲሰጠውም የጠየቀው እራሱ ነው:: የወንጀል ምርመራውንም ሆን ብሎ እያበላሽ እና ውንጀላውንም ወደ እኔ እያቀረበ ምርመራውን እርባና ቢስ እያደረገው ነው።”

እያለ ይቀጥላል። እርግጥ ነው በተለይ ከዊሊያምስ ሞት በኋላ የኒኪ የጭፍን ፍራቻ እና ግምት ቢጨምር አይፈረድባትም:: ስለ ጆንሰን ጉድማን
ምንም ሊያደርግ አይችልም፡፡ ምክንያቱም አብሮት የሚሰራ ባልደረባው ነው።

“ሎው ከጆንሰን ጋር እየሰራህ እስከሆነ ድረስ አደጋ ውስጥ ነህ፤ እና ራስህን ጠብቅ:: እንድትጎዳ አልፈልግም። እኔም ብሆን አደጋ ውስጥ ስላለሁ ላልተወሰነ ጊዜ ከማንኛውም የግንኙነት መስመር ውጪ ነኝ።

ኒኪ ሮበርትስ”

ይላል የላከችለት ኢ ሜይል፡፡

ለምን ያህል ጊዜ ከግንኙነት መስመር ውጪ እንደምትሆን ያለማወቁ
ጉድማንን አሳስቦታል፡፡ ኢ ሜይሏ ከደረሰው እና ካነበበው በኋላ ሁለት ጊዜ
ደውሎላታል፡፡ ኢ ሜይልም ልኮላታል ግን ስልኳ ዝግ ነበር፡፡ ጆንሰን ከመፀዳጃ ቤት ተመልሶ ቦርጫም ሆዱን እያሻሸ “ቡናው ውስጥ ምንድነው የጨመሩበት? መፀዳጃ ቤት ውስጥ እኮ ተቀምጬ ልክ በምጥ ልጅ እየወለድኩኝ ያህል ነበር የተሰማኝ” አለ፡፡
ጉድማንም አፍንጫውን እያራገበ “ምነው በጣም አብራራኸውሳ? አሁን ወደ ፎሬንሲክ መርማሪዎቹ አንሄድም?” አለው፡፡

“አንተ ዝግጁ ከሆንክ ምን ገዶኝ፡፡ መቼስ ፎሬንሲኮቹ አንድ ነገር ሳያገኙ አይቀሩም፡፡ ምክንያቱም ዊሊያምስ ቢያንስ ግማሽ የሎስ አንጀለስ ህዝብ
ጠላቱ ነው። እኔም ልገድለው ትንሽ ነበር የቀረኝ።” አለውና ተነስቶ ሲወጣ
ጉድማንም ተከተለው።

ከሎስ አንጀለስ ሃምሳ ማይል ርቀት ላይ በርሃው ውስጥ የሚገኘው የሲኞራ ማርቼስ የገጠር ሆቴል ቀለል ተደርጎ ነው የተሰራው፡፡ ምንም እንኳን ሆቴሉ በርሃ ላይ ቢሰራም የየክፍሎቹ ኮርኒስ ላይ ካለው ፋን በስተቀር ሌላ ኤየር ኮንዲሽነር አልተገጠመለትም፡፡ ያም ሆኖ የሆቴሉ ነጭ ግድግዳ እና በዙሪያው የተተከሉት የዘንባባ ዛፎች ሁሉንም የእንግዳ ማረፊያ
ክፍሎች ቀዘቅዝ ያደርጓቸዋል።

ኒኪ ወደዚህ የእንግዳ ማረፊያ የመጣችው ዊሊያምስ ከሎስ አንጀለስ ርቃ የማትታወቅበት ቦታ እንድትደበቅ ስለነገራት እና ለማረፍም ጭምር ነው::
የእንግዳ ማረፊያውን ያሳያት ዶውግ ነው። የተጋቡበትን አንደኛ ዓመት
ሲያከብሩ ነው እዚህ ይዟት የመጣው ትዝ ይላታል ቦታው
👍4