አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የወድያነሽ


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


ፊት ለፊት የነበረውን ንጹሕ ግድግዳ በንዴት አፍጥጣ ተመለከተችው::
በዋለና ባደረ ብስጭት የደረቁ ከንፈሮችዋን በምላስዋ ጫፍ አወዛቻቸው:: ወደ ቀኝ መለስ አለችና «ወይኔ ልጂት! እኔን ያናደደኝ እኮ! » ብላ ዝም አለች፡፡ እኔና የውብነሽ ቀጥላ የምትናገረውን ለመስማት ጓጓን፡፡ እንደ ገና ደግሞ የግራ እጅ ጣቶችዋን ተራ በተራ ካንቋቋች በኋላ፣ ..ለምኔ ብዬ…. ሞልቷል ዕድሜ ለጉልበቴ እዚህ ቤት ብቻ ነው እንዴ ተሠርቶ የሚበላው! ማለቷና እኛን ማዋረዷ ነው» ብላ የታች ከንፈሯን የቀኝ ዳርቻ በላይና በታች ጥርሶችዋ
መካከል አስገብታ ነካከሰችው::

«አንችው በገዛ እጅሽ እኮ ነው ይህን ሁሉ ጣጣ የምታመጪው! » አለች የውብነሽ ያን በፍርሃት የሰለለ ድምዕዋን «እህህ» ብላ ለማስተካከል እየሞከረች፡፡

«እኩያዩ እኮ ብትሆን ኖሮ እንዲህ ባላንገበገበኝ! እንዴት አንድ ጥላ ብስ አውታታ ትዘንጥለኝ?» ብላ፣ ራሷ ላይ ሽብ ያደረገችውን ጥቅር ሻሽ አጠበቀችው፡፡ የሻሽ ጥብቅት ወደ ፊቷ የሚወርደውን ደም የገታው ይመስል የእናቴ ቀይዳማ ጉንጭ ጐርፍ የቦረቦረው መረሬ ዐፈር መሰለ፡፡

የውብነሽ ቀስ ብላ ከተነሣች በኋላ እናቴን ወደ ታች ያውጋር እያየች፣
«መቼም ቢሆን ሰውን ከዚያ በላይ መደብደብና ማንገላታት ደግ አይደለም፡
በምላሷ ልክ ገርፈሻታል፡፡ አሁን እንዲሀ ያስረቀረቀሽና ያስጨነቀሽ፡ ለምን
ተደፈርኩ ለምን መለሰችልኝ ብለሽ ነው” ብላ በፍርሃት የበረገገ ፊቷን በደረቅ
ፈገግታ አከሰመችው::

«ኧረ እንኳን የሄደችልኝ! ገላገለኝ፡፡ እንኳንም መኻል አናቷን ብዬ የሰው
ሰው ያልገደልኩ፡፡ ከቤቱ ነው ከምሰሶው! እኔ እንደሆነ ወይ ከዛሬ ወይ ከነገ
አንዷን ግልቱ አስመጣለሁ፡፡ እሷ ግን እግሯ እስኪነቃ ብትንከራተት፡ ሲሳዩ
የተትረፈረፈና እንደ ልብ ወጣ ገባ ተብሎ የሚጐረስበት፣ እንደ ባሻ ያየህ
ይራድና እንደ ተካበች ግፋ ወሰን ቤት ታገኛለች ማለት ዘበት ነው» ብላ
ከተካከዘች ሰኋላ ወደ መኝታ ቤት ገባች።

የውብነሽ፡ «ደበደበቻት፣ ደሟ እንደ ውሃ እስኪንቆረቆር ፈነከተቻት! እንግዲህ ከዚያ አልፋ ሥጋዋን ዘልዝላ አትሰቅለው» ብላ ራሷን በተራ ፀፀት እየነቀነቀች፣ ትልቁን የእንግዳ መቀበያ ክፍል በር ከፍታ ወጣች፡፡

ብቻዬን በመቅረቴ ንዴቱ ሁሉ የሚከመርብኝ ስለ መሰለኝ ተነሥቼ
ቆምኩ፡፡ «አልሠራም፣ አልታዘዝም ስትል ማሰናበት እንጂ ዱላን ምን አመጣው?
በማለት ቀደም ሲል በእናቴ ፊት ለመናገር የፈራሁትን ሐሳብ ለሪሴ ተነፈስኩና
ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ።

አባቴ አማካለችን ከተጉለት ሲያመጣት እኔ ገና የአራተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ፡፡ ስምንት ዓመት ሙሉ እምብዛም ጠባይዋ ሳይለወጥ፣ ትልቅ ትንሹን እየታዘዘች፣ የተሰጣትን ሁሉ ትሠራ እንደ ነበር ትዝ አለኝ፡፡

እሷም እንደ እኔዉ አባትና እናት እኔም እኮ ጊዜ ጥሎኝ ነው እንጂ ጨዋና የትልቅ ሰው ዘር ነኝ ግን ምን ይሆናል! የታባቷ ይቺ ዐመዳም ዕድል እያለች ታጉተመትም ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜማ ታግላ ከማትጥለው ሐሳብና ከማትፈጽመው ምኞት ጋር ትንቅንቅ ትጀምርና በተሸናፊነት ስትሰክን ከዐይኖቿ
የሚጉርፈው የእልህ እንባ እፎይታ ይሰባት ነበር፡፡ በውስጧ የተዳፈነው ከንቱ
ኩራት ብዙ ጊዜ አሠቃይቷታል፡፡ ያንቺ ነገር እኮ የበቃኝ” ብላታለች እናቴ፣
"አንድ ቀን ቅራሪ የመሰለ ቡና አፍልተሽ ካጠጣሽኝ በኋላ ቤተኛዉ ሁሉ
መተኛቱንና ቤቱ እረጭ ማለቱን አይተሽ ግን አባቱ ይናገረኛል ብለሽ ቤቱን
ከፍተሽ ደጅ ማደርሽን ከሰማሁ ወዲህ ነው” ብላ እስኪያንገሸግሻት ተቆጣቻት።

ከኻያ ሦስት ዓመት የማይበልጣትና የቤታችን ሠራተኛ የነበረችው አማከለች ከሄደች ጥቂት ቀናት ቢያልፍም የእናቴ ንዴት ግን አልበረደም ነበር፡፡ለመጣው ሰው ሁሉ የአማከለችን ክፋትና መጥፎነት አንድ ባንድ ዘርዝራ ትናገርና ወሬዋን ስትደመድም «የሌላ የሌላውስ ግድ የለም፡ ዕድሌ ነው እንጂ እኔ ከማን አንሳለሁ ትበለኝ?” » እያለች የራሷን ክብር ከፍ በማድረግ ከምኗም !እንደማትደርስ ለማስረዳት ራሷን እንደ ገበሎ ስትነቀንቅ ሰነበተች፡፡

በአማከለች እግር ከከተማም ሆነ ከገጠር ሌላ የቤት ሠራተኛ ሳትተካ ድፍን ወር ዐለፈ። ምንም እንኳ ሁለቱ ቀሪ ሠራተኞች ወፍ ሳይንጫጫ እየተነሡ እስካ ውድቅት ቢሠሩም የሚሠራውን ሁሉ ለማጠናቀቅና ፋታ ለማግኘት ሳይችሉ ቀሩ፡፡ በዋል አደርም እናቴ ቀስ በቀስ ንዴቷን ተወችና ረሳቻት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ችምችም ብለው በቅለው እንደ ደጋን በጎበጡት ቅንድቦቹ ራስጌ ባለው
ገላጣ ግንባሩ ላይ ሦስት ጨምደድ ያሉ መስመሮች ተጋድመዋል፡፡ ከቅንድቦቹ
መገናኛ ላይና ከዐይኖቹ፣ ጣብቂያ መኻል እንደ ፍልፍል እንጨት ተቀርፆ የወጣ
የሚመስለው አፍንጫው ቀጥ እንዳለ ይወርድና የተድበለበለች ጫፍ ያልቃል፡፡
የአፍንጫው ቀዳዶች ከገበታቸው የተነሳ የባቄላ ጥቁር ግራ ይመስላሉ። ጠየም
ያለው ጠባብ ሰልካካ ፊቱ ቀጠን ብሎ ወርዶ በቅርፀ እንቀላል አገጭ ይጨርሳል።ከዚያች ጫፍ ላይ ሲያወራና ነገር ሲያሰላስል ቁልቁል የሚልጋትና የ“ሚያሻሽት አጠር ያለች ጢም አለችው::
ዘለግ ያለው ቁመቱ ሳይወፍርና ሳይቀጥን በመካከለኛ ሁኔታ የተገነባው አካሉ ቀልጣፋ አረማመድና እንቅስቀሴ ሰጥቶታል። ቀጠን ብላ እንደ መረዋ
የምትሰማው ድምፁ በቤተሰብ አካባቢ ሲቆጣ ታስደነግጣለች፡፡ ሲጫወት ግን
በተለይም ሲስቅ ለጆሮ ደስ ትላለች።

አባቴ 10 ዓመት ያህል በወረዳ ፍርድ ቤት በዳኝነት ሠርቷል። የአውራጃው ፍርድ ቤት ዳኛ ከሆነ አሁን አራት ዓመቱ፡ ነው:: ከቀበና ወንዝና ከአካባቢው በሰውና በእንስሳ ጉልበት ተግዞ በመጣ ድንጋይ ካምስት ክንድ በላይ በሆነ ግንብ ዙሪያውን የታጠረው ግቢያችን፣ ከውጪ ይልቅ ወደ ውስጥ ሲዘልቁ የስፋቱ መጠን ጎልቶ ይታያል፡፡ አባቴ ባሰበብ ባስባቡ በአካባቢው ከተነቀለ ድሆች ላይ የተገኘውን መሬት ከብጤዎቹ ጋር ተካፍሎ በመያዙ የግቢያችን ስፋት
የሦስትና የአራት ሰው የቦታ ድርሻ መጠን መሆኑ በጭፍን ያስታውቃል፡፡

«ሰፊ ግቢ ገመና ከታች ነው:: ሠርግ ኣለ፡ መከራ አለ፡ ድግስ አለ፡ለሰማይ ቤትስ ካሁኑ መሠረት ካልተጣላ ለኔ ቢጤው በስመ እግዚአብሔር ስም ካላለበሱና ካላጎረሱ መንግሥተ ሰማያት በጥባ አትገኝም። እንደ እኔ ያለ ሰው
ድንኳን መትከያ እና ዳስ መጣያ ቦታ ልመና አይሔድም፡፡ አታዩትም እንዴ
የነግራዝማችንና የነ ቀኛዝማችን ግቢ. ብሎ ሰፋ ሰፋ ያለትን ግቢዎች እየጠቀሰ
የራሱን ለማሳነስ ይፈልጋል፡፡

«የመኳንንትና የጨዋ ልጅ ሠፈር ነው ማለት አይገቡ ገብቼ በዚያን
ጊዜው ዐቅሜ ይህን መሳይ ቤት የሠራሁት ሰው እንዳላንስ ብዬ ነው» ይላል ለማስመሰል::

አዲስ አበባ ከቀበና ወንዝ ማዶ ከኮከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት በስተቀኝ
በኩል ትንሽ ራቅ ብሎ የሚገኘው ባለ አንድ ፎቅ መኖሪያ ቤታችን ከተሠራ
ከኻያ ጊዜ በላይ ደመራ ተተኩሷል::
በየዓመቱ ሐምሌና ነሐሴ እየተናደ በሚካብ ጥቋቁር የወንዝ ሽሙልሙል
ድንጋይ እና በከፊል በሸክላ ግንብ የተከበበው አጥር ግቢ ከውጪ ይልቅ ገብተው ሲመለከቱትና ሲጐበኙት ስሜትን ያምነሸንሻል፡፡

የአበቦቹና የአትክልቱ ውበት፣ የግራዋውና
የብሳናው፣ የጉራውና የአጫጭሮቹ ጥዶች ልምላሜ የሣሩን ውበትና የልዩ ልዩ ዕፅዋት ቅጠሎችን ርጋፊ ሲያዩት ደስ ይላል፡፡ ያቆጠቆጡት የባሕር ዛፍ ለጋ ቅርንጫፎች፣ በውስጡ የሚርመሰመሱት አዕዋፍ፣ ከእነዚህ ሁሉ ተውጣጥቶ የሚገኘው ድንቅ የተፈጥሮ መዐዛ፣ በሰፊው ዐፀድ ውስጥ የሚነፍሰው ቀዝቃዛ የአየር ሽውታ መልካም
የመንፈስ ጸጋ ነው::

አታክልትና ንጽሕና ለጤንነት ጥሩ
👍6
ነው የሚለው አባቴ አትክልት ወዳድ በመሆኑ አንድ ወበኛ ባልባሌ ምክንያት ተባርሮ በምትኩ ሌላ ዘበኛ ሲቀጠር የሚነገረው ማስጠንቀቂያና አደራ፣ «ታያቸዋለህ እነዚህን አትክልቶች? እንደ ልጆቼ ነው የምወዳቸው አደራህን፡ በበዓልብበዓል ሳይሆን በሥራ ቀን ኮትኮት ኮትኮት እያደረግህ ውሃ ብታጠጣቸው ማለፊያ ነው:: አትክልት ሲሰባብርና ሲተናኮል የምታገኘውን ታዲያ ለእኔ ንገረኝ» የሚል ነበር፡፡

በየሳምንቱ እሑድ እሑድ ከቅዳሴ መልስ የነጭ ወፍ ላባ የመሰለ ጋቢውን ለብሶ እንደ ታቦት ሸኚ ቀስ ብሎ እየተራመደ ግቢውን መጎብኘት ልማዱ ነው፡፡

የአትክልቶቹን ጠቅላላ ሁኔታና አያያዝ ከተመለከተ በኋላ ለዘበኛው አንድ አደራ ወይም ምክር ሳይሰጥ ወደ ቤት አይገባም፡፡

እኔም ለአትክልቶቹ የነበረኝ ጥበቃና ፍቅር በጣም ከፍ ያለ ነበር፡፡

ከፎቁ ሥር የሚገኘው ሁለት ሠፋፊ ክፍል የእህል ቤትና የልዩ ልዩ ዕቃዎች ማከማቻ በመሆን ያገለግላል፡፡ ያገር ቤት ሰዎችና ጭሰኞች ለደጅ ጥናትና ለምልጃ ሲመጡ ያርፉበታል፡፡ ሆኖም ወደዚያ እየወረዱ የሚተኙት እንግዶች የኑሮ ደረጃና ዐይነት የተለየ ነው፡፡ ከዋናው ቤት ትንሽ ፈንጠር ብሎ በስተደቡብ ምሥራቅ ሲል የሚገኘው ትልቅ ማድ ቤት አርጅቶ ከዛገው ቆርቆሮ ጋር ሲታይ በሰደድ የጋየ የቆላ ውድማ ይመስላል። ከፎቁ ወስጥ አንድ ሠፊ የእንግዳ መቀበያ ክፍል አለ።
የወላጆቼ የየውብነሽና የእኔ መኝታ ክፍሎች ከእንግዳ መቀበያው ክፍል
በስተደቡብ በኩል መደዳውን ሲገኙ የወላጆቼ የመኝታ ክፍል በጣም ሰፊ በመሆኑ ራሱን የቻለ የእንግዳ ማስተናገጃ አለው:: ከእንግዳ መቀበያው ክፍል ፊቱን ወደ ደቡብ ምዕራብ አዙሮ የሚቀመጥ ሰው የእኔ መኝታ ቤት ስትከፈትና ስትዘጋ
በውስጧ የሚገኙትን ዕቃዎች ከሞላ ጎደል ሊያይ ይችላል።
የቤቱ ጠቅላላ አሠራርና አቀማመጥ በምህንድስና ጥበብ ሳይሆን በዘልማድ የአሠራር ዘዴ የተሠራ በመሆኑ የክፍሎቹ አቀማመጥ እስከዚህም ቅጥ
የለው:: ከእንግዳ መቀበያው ክፍል በስተሰሜን ሲል በየዕለቱ የሚፈለጉ ዕቃዎች የሚከማቹበት ክፍል አለ፡፡ የቤት ሠራተኞች ማደሪያ በዚሁ ክፍል በኩል በጣውላ ርብራብ መሰላል ወደ ምድር ቤት ከተወረደ በኋላ ይገኛል፡፡ ዕቃ ለማድረስም ይሁን ለማምጣት በሚመላለሰበት ጊዜ ሁሉ ስለሚረመረም የደረጃው እንጨቶች ይንሲያጠጣሉ፡፡ በቤት ውስጥ የሚገኙት ቁም ሳጥን፣ ራዲዮ፣ ትንቡኬ ወንበሮች እንዲሁም እያንዳንዱ የቤት ዕቃ የተገዛው ከ10 ዓመታት በፊት ነበር፡፡ ስለ ዕቃዎች ጥንካሬና ጥራት ወሬ በሚነሳበት ጊዜ አባቴ በጣም ብልህ ያለ ፈረንሣዊ ወዳጅ ነበረኝ፡ እሱ ታዲያ አንዲት ቀላል ክርክር ነበረችበት፡ ያቺን እንደ ምንም ብዬ ስላስፈጸምኩለት እንደትልቅ ውለታ መጥራት ሲኖር ወደ አገሩ ቪዛ በርካሽ ዋጋ ጥሉልኝ ሔደ» ይላል፡፡

አባቴ ለራሱ ጥቅም ከሆነና ደስ ያለው ዕለት እጁን የዘረጋ በጣም ለጋሥ
ነው:: በቤት ውስጥ ለሚዘጋጅ ማናቸውም ድግስና ግብዣ፣ ቤት ላፈራው ሲሳይ ሁሉ ሰው በልቶና ጠጥቶ የሚጠግብ አይመስለውም። አዲስ አበባ ውስጥ ከ15 ደጃፍ ቤቶች የማያንሱ የሚከራዩ ቤቶች አሠርቷል። ከየወለድ አገዱ ደግሞ ምን ጊዜም ቢሆን በርከት ያለ ጥቅም አያጣም፡፡ ከአዲስ አበባ መቶ ኪሎ ሜትር ያህል ርቆ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚገኙት ስድስት ጋሻ መሬቶች አፍ ሞልቶ ደረት ነፍቶ የሚያናግር ገቢ በያመቱ ያስገኛሉ፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ከሚገኘው ገቢ ሌላ ደግሞ በጥሩው የኑሮ ደረጃችን መጠን የሚወጣው ወጪና ለሌላው ጉዳይ ሁሉ እንደ ልብ ተቀናንሶለት በየወሩ የሚያስመካ ቀሪ ይገኛል፡፡

ሌላውን የገቢ ምንጭ ግን ቤተሰብ አያውቅውም። አንዳንድ ቀን የስሌት
ርዳታ እንዳደርግ ስታዘዝ ሁኔታውን በግምት አውቅ ነበር፡፡ እናቴ በገቢውም ሆነ በወጪው ላይ አረረ መረረ የማለት መብት የሌላት ከመሆኑም በላይ «በእንዲህ ያለው ጉዳይ ውስጥ ሴትና ልጅ እጃቸውን መስደድ የለባቸውም» ስለምትባል ለምና የመመጽወት ያህል እንጂ የመወሰን ድርሻ የላትም፡፡

የአባቴ ትልቁ በደልና ጭቆና ግን እንደ ልብ ተዝናንተንና በቂ የሐሳብ ነጻነት አግኝተን ሐሳባችንንም ሆነ ስሜታችንን እንደየዝንባሌያችን ማስረዳትና
መግለጽ እንዳንችል ማድረጉ ነበር፡፡ «ልጅ ከዐዋቂ ፊት እኩል መናገርና መዘባረቅ
የለበትም፡፡ የምን ቀደም ቀደም ነው! ማን ወልዶ ማን አሳደገው ሊባል ነው?»
ይላል። የመናገር ነጻነት ስለማይሰጠን ሁላችንም እንፈራዋለን። እኔ በበኩሌ ግልጽ ስሀተትም ቢሆን የአባቴን ትእዛዞችና ሐሳቦች ሁሉ እሺ ብዬ መቀበልና መፈጸም እንጂ ለመቃወምና የመቃወሚያዩንም ምክንያት ለማብራራት ሞክሬ አላውቅም።

ማንም ሰው ቢሆን የኑሮውና የዕውቀት ደረጃው ከእባቴ በታች ሆኖ ስለ ኣንድ
ጉዳይ ለማነጋገርና ለመጠየቅ ከመጣ ጎንበስ ቀና ብሉ በትሕትና እጅ ካልነሣና
ተገቢውን የአክብሮት ሰላምታ ካላቀረበ እንደ ጤነኛና እንደ ሙሉ ሰው
አይገመትም። ከአባቴ ዘንድ የወንጀለኛ መቅጫና የፍትሐ ብሔርን እንዲሁም
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት መጻሕፍትን ለማስረዳት የማይችል ሰው ተማርኩ ሊል አይችልም። «ገና በለግላጋነቴ ጸላዔ ሠናያት ተጠግቶኝና ጥጋብ አፍኖኝ ከደጀ ሰላሙ በረርኩ እንጂ ሁለት ዓመት ያህል ቀድሼአለሁ» ይላል በኩራት፡፡ ምን ጊዜም ቢሆን ጧት ድርሳነ ሚካኤልንና ውዳሴ ማርያምን ደግሞ አጁ ላይ እንትፍትፍ ብሎ ፊቱን ሳያባብስ ከቤት አይወጣም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዕለተ ሰኞ ነበር፡፡ ኣባቴ እንደ ልማዱ ወፍ ሲንጫጫ ተነሥቶ ድርሳኑን ሲደጋግም ከቆየ በኋላ ቡልኮውን ደርቦ መጽሐፉን እንደ ያዘ ትንቡኬው ላይ ተቀምጦ ቀሪ ጸሎቱን አድርሶ ቁርስ ይጠባበቃል። የማለዳዋ ፀሐይ ብርሃን በስተምሥራቅ በኩል ባለው መስኮት ገብቶ ቤቱን አድምቆታል። ሁለት ሰዓት ከሩብ ሆኗል። የግድግዳውን ሰዓት ሽቅብ ተመለከተና «የውብነሽ! ሰዎች! ዛሬ ምን ነካችሁ? መንጋቱንና መርፈዱን ረስታችሁታል መሰል» ብሉ የውጭ ጥሪ ያህል ጮክ ብሎ ተናገረ፡፡ የመኝታ ቤቴ በር ሳይበዛ ላቀቅ ብላ በመክፈቷ ወንበሬ ላይ እንደ ተቀመጥኩ የሚያደርገውን ሁለ ማየት እችል ነበር።

ከመኝታ ቤቴ ወደ እንግዳ መቀበያው ክፍል ስገባ እናቴ የውብነሽን አስከትላ በዕቃ ቤት በር በኩል ከተፍ አለች፡፡ የአባቴ የማለዳ ዐመል መጠነኛ ቁጣ በማስከትሏ «ምነው በይ? ነውርም አይደል እንዴ? ዛሬስ ደግሞ ብዬ ብዬ
ልጣራ!? ሌላውስ ይሁን በጄ እንዴት አንዲት ስኒ ቢና ልከልከል?» ብሎ እናቴን
ከእግር እስከ ራሷ በቁጣ ዐይን አያት።

እናቴም የአባቴ ድንገተኛ ቁጤ ምን እንደምታስከትል ስለምታውቅ
ንዴቱን ለማስታገስ ያህል ፈገግታዋን አሳየች፡፡ «አሁንስ መምጣቴ ነው፣
አድርሻለሁ» ብላ በዚያች ቀጠን ባለች ደርባባ ድምጿ መለሰች:: የገዛ ሐሳቡን
ለመመርመር ያህል አንድ አፍታ ዝም አለና ዛሬም አንቺው ነሽ እንዴ ቡና
የምታፈዪው? አንዷን ስጡኝ ብዬ ከአገር ቤት እስካስመጣ ድረስ ለጊዜው
አስፈልጊና ቅጠሪ ብዬ አልነገርኩሽም እንዴ ?» ብሎ የደረሰባትን ድካም
በማመዛዘን አዘኔታን በሚቸር ሁኔታ ተመለከታት፡፡ «እስከዚያውስ ቢሆን ይኸን
ቀላል ቀላሉን ማን ይሠራራልኝ ብለህ ነው? ገረዶቹ እንደሁ የልብ አያደርሱ፣
ለቤት ንብረቴም እኔ ነኝ ምሰሶዋ» ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ አንዷ ሠራተኛ
ባለጆሮ ስኒዎች እና በምታምር የባሕር ማዶ ነጭ የሸክላ ጀበና ቡና ይዛ ከቸች
አለች። እናቴ የሌሎቸን ድካም ለማምከን እንጂ የፈሰሰ እንደማታቀና ዐውቃለሁ። የመጣውን የቡና ዕቃ የውብነሽ ፈጠን ብላ ስለተቀበለቻት ወዲያው
ተመለሰች። የውብነሽ ቡናውን እስከምትቀጓ እናቴም በበኩሏ ቁርስ ይዛ ደረሰች። አባቴ ምን
👍3
ጊዜም ቢሆን ሠራተኞች ምንም ነገር እንዲያቀርቡለትና እንዲስጡት ስለማይፈልግ : «እነርሱን ካሩቅ ነው፣ እነ ውሃ እርሙ ጠረናቸው እኮ
አያስደርስም» እያለ በኩራት ይጠየፋቸዋል፡፡ ከቡናና ከቁርስ በኋሳ ወደ አውራጃ ፍርድ ቤት ለመሔድ ሲነሣ የቆዳ ኮሮጆውን ተሽከሞ የሚሸኘው ዘበኛ ተጠርቶ ገባ። በግራ እጁ ባርኔጣውን ይዞ ወደ በሩ ሲራመድ እንግዲህ በእኔ በኩል ገረድ አስፈልጌ ለማምጣነት አልችልም፡፡ አንቺው ራስሽ አፈላልገሽ ቅጠሪ፡፡ አለበለዚያ እንዲሀ ሆነሽ እትዘልቂውም» ብሎ ወጣ፡፡.....

💫ይቀጥሌል💫
👍1
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ_ሶስት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

....“ልክ ነህ” ጉድማን ፈገግ ካለ በኋላ እኛ በሁለት የሰዎች ግድያዎች ላይ
ምርመራችንን የምናደርግ ፖሊሶች ስለሆንን አሁንም ስራችንን በመስራት
ላይ እንገኛለን፡፡ አንተ ልትሰራው ፈልገህ አለቆቻችን ሊቀጥሩህ ያልቻሉትን
የምትቋምጥለትን ስራ የምንሰራ... ስንት ጊዜ ነበር በፖሊስነት አመልክተህ
ያልተሳካልህ? አታስታውስ አንተ ደግሞ... ምን ነበር ቃሉ?” ብሎ ጉድ ማን ጣቶቹን እያጮኸ ቆየና አዎን ድንኳን ሰባሪ ነህ እርግጠኛ ነኝ የተጋበዝክበትን ደብዳቤ ወይም ካርድ ልታሳየኝ አትችልም” አለው፡፡

ዊልያምስ ከንፈሩን ነክሶ ቢችል በቦክስ ጥርሱን ቢያረግፈው እና የሚሞጣሞጥበትን አፉን ደም በደም ቢያደርገው ደስ ባለው፡፡ ዊልያምስም
“ውጪ እንውጣ እና የማሳይህ ነገር አለኝ ልጁ” አለው፡፡

ጉድማንም ቅንድቡን በግርምት እያነሳ “እየቀለድክ ባልሆነ?” አለው፡፡
ይመስልሃል?” ብሎ ዊልያምስ በብሽቀት ከመለሰላት በኋላ “ከኒኪ ጋር ያለህ
ነገር እንዴት እየሄደልህ ነው? እስከአሁን እንዳልተኛችህ ነው የነገረችኝ ይሄ
ደግሞ ያማል አይደል? ከፍለሃት ካልሆነ በስተቀር አንተ ለመጨረሻ ጊዜ
ከሴት ጋር የተኛኸው መቼ ነበር?” ጉድ ማን እያሾፈ “እኔ እንዳንተ አይደለሁም ስለዚህ በአእምሮዬ ነው የማስበው” አለው፡፡ ዊልያምስ “እኔ ከኒኪ ጋር ወሲብ አልፈልግም፡፡ እኔ እሷን ልረዳት እየሞከርኩ ነው፡፡ለዚያም መሰለኝ እኔን አምና ለአንተ እና ለዚያ አጋስስ አጋርህ በህልምዋም ቢሆን እንኳ ልታካፍላችሁ የማትፈልገውን ሚስጥሮቿን ለኔ የምትነግረኝ” አለው፡፡ በጆንሰን አቅጣጫ በአፍንጫው እየጠቆመው በነገር ሲወጋው የጉድ ማን ፊት በንዴት ሲቀላ ተመለከተና የደስታ ስሜት ተሰማው፡፡ ጉድ ማን በቁጣ እንዳበጠ ዊልያምስን “ሳልጠፈንግህ በፊት ከዚህ ጉዳይ ውጣ!” አለና አንባረቀበት፡፡

ዊልያምስም “ለምንድን ነው የምታስረኝ?” ብሎ ጠየቀውና ለወደፊቱ
ሌሎች ከጉድ ማን ጋር የሚጠብቁት ጸቦች እንዳሉ ሲገባው የአሁኑን ጸብ
መተው እንዳለበት ራሱን አሳምኖ “ሌላ ጊዜ አገኝሃለሁ” አለው፡፡

እኔ ነኝ ቀድሜ የማገኝህ” ብሎ ጉድማን መለሰለት፡፡ ዊልያምስ ኮቱን አንስቶ እየተንጀባረረ ከአዳራሹ ወጣ፡፡ ዊልያምስ ከአዳራሽ እንደወጣም የአኔ ቤታማን ቫዮሊን የመጀመሪያው ሶሎ ሙዚቃ መሰማት ጀመረ፡፡

ወንበሯ ላይ ደገፍ ብላ የነበረችው ኒኪም አኔ ቫዬሊኗን ለስለስ አድርጋ ቁጭ ብላ እና አይኗን ጨፍና ቫዬሊን መምቻዋን ወደ ኋላ እና ወደ ፊት መጫወት ስትጀምር አዳራሹ ጸጥ አለ፡፡ አኔ መድረኩ ላይ አንድ ወንበር ላይ እየሰበቀች መጫወቷን ቀጠለች፡፡ ሙዚቃው የታላቁ እንግሊዛዊ ሙዚቃ አዘጋጁ የቫውጋን ዊልያምስ ሲሆን ይህንን ሙዚቃ ደግሞ ባለቤትዋ ዶውግ በጣም የሚወደው ሙዚቃ ነበር፡፡ ይህንን ሙዚቃ ለቁጥር ለሚያታክት
ጊዜያት ያህል እሁድ እሁድ የቁርሳቸውን ፓን ኬክ እየሰሩ በመኪና ረጅም
ጉዞን ሲጓዙ እና የጫጉላ ጊዜያቸውን ከአልጋቸው ሳይወጡ ፍቅር እየሰሩ
በሚያሳልፉባቸው ጊዜያቶች ሁሉ አብረው ያዳምጡት ነበር፡፡

በድንገት የናፍቆት እና የሃዘን ስሜት የሞላው ሰውነቷን ወረራት::በሚያሳፍር ሁኔታም ድምጽ አውጥታ
እየተንቀሳቀሰችና እየተርገፈገፈች ጠረጴዛው ላይ ክንዷን ዘርግታ ጭንቅላቷን አንተራሰችበት::

“ሰላም አይደለሽም ውዴ?” ብሎ አጠገቧ የሚገኘው ኒሮሳይንቲስት
የሚንቀጠቀጠው እጁን ትከሻዋ ላይ አኑሮ “ ውጪ ወጥተሽ ትንሽ አየር
ትወስጂ?” አላት፡፡

ኒኪም ራሷን በአሉታ በመነቅነቅ ምንም እንደማትፈልግና ጉዳይዋ በእምባ የተሸፈነ እንደሆነ አሳወቀችው፡፡ በቅርብ ወራቶች ውስጥ በዙሪያዋ ባሉ ሰዎች ላይ በደረሱት አሰቃቂ ነገሮች የተነሳ የዶውግን ሃዘን ዘንግታው ነበር፡፡ አሁን ግን ዕድሜ ለአኔ ምርጥ የቫዩሊን ሙዚቃ! ውስጧ ታምቆ የነበረው የሃዘን ስሜት ቁልፍ ተከፈተ፡፡ አሁን ወደ ኋላ መመለስ የለም፡፡ እየተንዠቀዠቀ የሚፈስሰው እምባዋን ማቆም አትችልም፡፡ የሚርገፈገፍ ትከሻዋንና መላው ሰውነቷን በስልቱ እያስኬደች ለሁለት የሚሰነጥቃትን ሃዘን እና መከፋትን እንዲሁ እንደ ቀልድ ማቆም አትችልም፡፡

“ፕሮፌሰር ጀምሰን አትቸገር” የሚለው የሀዶን ዶፎ ጥልቀትና ስሜታዊ
ድምፅ በጆሮዋ ያንቃጭልባታል “እኔ እረጋጋለሁ” ሲል ይሰማታል፡፡

ኒኪ የሀዶንን እርዳታም ቢሆን አትፈልግም ነበር፤ ነገር ግን እምቢታዋን
እንደ ፕሮፌሰሩ ሳይቀበል ቀርቶ ክንዷን ይዞ አነሳትና እያለቀሰች ለእሳት
አደጋ መውጫ በተዘጋጀው በር በኩል ይዟት ከአዳራሹ ወጣ፡፡ ከአዳራሹ
ጀርባ በሚገኝ መናፈሻ ውስጥም ይዟት ገባ፡፡ እናም በትንሹ ከሚንፎለፎል
ፏፏቴ አጠገብ ከሚገኝ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብላ የአይኗ ሜክአፕ እስከሚበላሽ
ድረስ አምርራ ታለቅስ ጀመር፡፡ ሳጓ እና የትከሻዋ መርገፍገፍ እየቀነሰ መጣ
እና በመጨረሻ ላይ “እፎይ” ብላ ፀጥ አለች፡፡

“ምን ሆነሽ ነው?” ብሎ ሀዶን አጠገቧ እየተቀመጠ ጠየቃት። ፀጉሯን
ከፊቷ ላይ አንስቶ ከኪሱ የራሱን መሃረብ አውጥቶ አቀበላት፡፡
እኔ እንጃ ብላ ኒኪ መሃረቡን ተቀብላ ፊቷንና አፍንጫዋን ካፀዳች በኋላ
“ሙዚቃው መሰለኝ በቃ ስለ ዶውግ እንዳስብ አደረገኝ፡፡ በጣም ከፋኝ ሀዶን

ዶውግ እኮ ላይመለስ ነው የሄደው፡፡ ይህንን ደግሞ ልቋቋመው አልቻልኩም”
አለችው::

ሀዶንም በክንዱ እቅፍ አደረጋት እና ወደ ራሱ እያስጠጋት “ምስኪን የኔ ቆንጆ” አላት፡፡

በጣም የደከማት ኒኪም ደረቱ ላይ ልጥፍ አለች፡፡ ታላቅ ወንድም ባይኖራትም ሀዶንን የምታየው እንደዚያ ነው፡፡

ሀዶንም በጆሮዋ “አንቺ እኮ ለእሱ አትገቢውም ኒኪ፡፡ በእውነት እሱ
ላንቺ የሚገባ ሰው አልነበረም” ብሎ ማንሾካሾክ ጀመረ፡፡ ድምፁ ምቾት
የሚሰጥ ስለነበረ እና ጭንቅላቷም ይዞርባት ስለነበረ የተናገረውን ነገር
በደንብ አልተረዳችውም፡፡

ነገር ግን ቀሚሷን ወደ ላይ ሰብስቦ እጁን ከጭኖቿ መሀል ለመክተት በሚያቃጥሉት ስግብግብ ጣቶቹ ወደ ላይ መሰርሰር ሲጀምር ባነነች፡፡

“ሀዶን” ብላ ልትገፋው ብትሞክርም ጥብቅ አድርጎ ስለያዛት አልቻለችም፡፡ “ምን እያደረግክ ነው አንተ?” “ከአመታት በፊት ማድረግ የሚገባኝን ነገር ነዋ” ብሎ እያጉረመረመ በስሜት ባበደ ድምፅም እያቃተተ አትታገይኝ ኒኪ ይህን ነገር ትፈልጊዋለሽ፡፡ ሁለታችንም እንፈልገዋለን፡፡ከበፊት ጀምሮ በጣም ነበር የማፈቅርሽ...”

“ሀዶን አይሆንም ተው” ብላ በድንጋጤ በረዶ ሆነችበት። ሀዶንም ወደ ፊት ቀርቦ ከንፈሯን በከንፈሩ ግጥም አድርጎ እየተስገበገበ ይስማት ጀመር፡፡”
“አይሆንም” ብላ እየታገለችውም እንዳለ “እዚህ ችግር አለ!” የሚለው
የመርማሪ ፖሊስ ጉድማን ድምፅ ጨለማውን ሲስነጥቀው ሀዶን ዶፎ ዘልሎ ከላይዋ ላይ ተነሳ፡፡ ኒኪም ቀና ብላ ጉድማንን በእፎይታ ስሜት
ተመለከተችው:: ያኔ ከጥቁሩ ላንድክሩዘር መኪና ያዳናትን የቀዩ ስፖርት መኪና አሽክርካሪን ስታገኝ የተሰማት አይነት የእፎይታ ስሜት ነበር አሁንም
የተሰማት፡፡

“ሁሉም ነገር ሰላም ነው” ብላ ኒኪ ፀጉሯን እና ቀሚሷን እያስተካከለች
ተነሳች፡፡ በሀዶን ድንገተኛ ድርጊት ከተሰማት ድንጋጤ ውስጥ ሳትወጣም
ሀዶንን አየችው፡፡ እኔ እንደምፈልገው ያምናል ማለት ነው? እንደዚያ ነው
ኣይደል ያለኝ? ይህንን ነገር ትፈልጊዋለሽ ሁለታችንም እንፈልገዋለን ነው አይደል፡፡ እንዴ ሀሳቡ እራሱ ይዘገንናል እኮ! ሀዶን የዶውግ የልብ ጓደኛ የነበረ ሰው ነው እኮ ነው ኦ!' እያለች በውስጧ አሰበች፡፡
በሌላ መልኩ ደግሞ ሀዶን ኒኪን የእውነት ይወዳት ከነበረ በዶውግ የተካደ እና የተታለለ ስለ
👍4
ሚመስለው ከኒኪ በላይ ሊናደድበትም ይችላል፡፡

ግን ይወዳታል፡፡ በፍፁም አይሆንም ይሄ የዕለት ዕብደት ነው። እሷ ሳይኮሎጅስት
አይደለችም እንዴ?ስለዚህ ሀዶን ቢወዳት ኖሮ ብዙ የመውደድ ምልክቶችን ልታይበት ትችል አልነበር? አዎን ምንም አይነት መውደዱን የሚያሳይ ምልክቶችን እሱ ሲያሳያት አስተውላ አታውቅም::

ኒኪ እርግጠኛ ነሽ ሁሉም ነገር ሰላም ነው?” ብሎ ጉድማን ኒኪን
በድጋሜ ጠየቃት፡፡
ነገረችህ አይደል እንዴ!” ብሎ ሀዶን በቁጣ ድምፅ “በቃ ደህና ነኝ
አለችህ እኮ!” አለው፡፡

“ብዙ ጠጣሁ መሰለኝ ዞሮብኝ ነው ወደ ቤት መሔድ አለብኝ” ብላ ኒኪ
ለጉድማን መለሰችለት፡፡

“በመኪና ቤትሽ አደርስሻለሁ፡፡” አሏት ጉድማንና ሀዶን በአንድ ላይ፡፡

“አይይ ሁበር ጠርቼ እሄዳለሁ። ችግር የለውም” አለቻቸው፡፡

ኒኪ ከሆቴሉ ውጭ ከሚገኘው የሁበር ታክሲ መጠየቂያ ቦታ ላይ ስለቆመች የምሽቱ ብርድ ስካሯን በትንሹም ቢሆን አበረደላት፡፡ ሉዊስ ሮድሪጊዜን ለማየትና ለአኔ ያላትን ድጋፍ ልታሳያት ነበር እዚህ
የመጣችው፡፡ ነገር ግን በተገላቢጦሽ እገዛ የሚያስፈልጋት እሷ እንደሆነች
አስባ እየቆዘመች ሳለች

“የዶክተር ሮበርትስ መኪና” የሚለው ድምፅ ከሀሳቧ አባነናት እና ኒኪ
የሴዳን መኪናውን የኋላ በር ከፍታ ገባች፡፡ መኪናው የቆዳና ሹፌሩ የተቀባው ሎሚ ሎሚ የሚሽት አፍተር ሼቭ ድብልቅ ሽታ ይሸታል፡፡

ቀበቶዋን አደረገች ፤ የቤቷም አድራሻ ጠፋት።

“ምንድነው ዛሬ የሆንኩት?”

“ወደ ብሬንት ውድ ውሰደኝ፡፡ በታይገር ቴይል በኩል” አለችው ኒኪ ለሹፌሩ፡፡

ልክ ከሆቴሉ እንደወጡ ሹፌሩ ግጥም አድርጎ ፍሬን ሲይዝ የመኪናው
ቀበቶ ደረትዋን ስርስሮ እስኪገባ ድረስ ከመኪናው ወንበር ጋር ተለጠፈች።
አንድ በጣም የተሸበረ ሰው መንገዳቸው መሀል ላይ እያሽከረከረ ገብቶ
ወደ ሳንታ ሞኒካ መንገድ ሲሮጥ ተመለከተች።

በሀሳቤ ነው? ወይስ ካርተር በርክሌይን ነው ያየሁት?'

“ዕብድ ነህ እንዴ ደፍጥጬ ገድዬህ ነበር እኮ” ብሎ የሁበሩ ሹፌር አንገቱን በመኪናው መስኮት አውጥቶ የሚሮጠው ሰው ላይ ጮኸበት፡፡

በመቀጠልም ወደ ኒኪ ዞሮ ይቅርታ ጠየቃት፡፡

እርግጠኛ ነኝ ካርተር በርክሌይ ነው። ምንድነው እዚህ የሚሰራው?
ደግሞስ እንደዚህ ያስፈራው ነገርስ ምንድነው?

ከመኪናው የኋላ ወንበር ላይ ተቀምጣ በውስጧ የሚመላለሱትን ሀሳቦች
መስመር ለማስያዝ ብታስብም ምንም ሊሆንላት አልቻለም። ከዚያም ከት ብላ
መሳቅ ጀመረች።

ሁሉም የራሱ ጉዳይ ነው!

ካርተር በርክሌይ ከማን ይሽሽ አይሽሽ ምን ይመለከታታል? ሀዶን ዶፎ
ፍቅሩን ሲገልፅ ባይገልፅ ምን ከዕዳዋ? ሉዊስ ሮድሪጌዝ ቢመጣ ባይመጣ
ምን ይመለከታታል? አንድ ነገር ብቻ ነው እሷን የሚያገባት። አዎን ስለ ዶውግ ብቻ ነው የሚመለከታት።

የእሷ ዶውግ እኮ ላይመለስ ሄዷል!

ኒኪ እንደምንም ከስካሯ ጋር ታግላ ስልኳን አወጣች እና ለዊሊያምስ
“ስለ ሌንካ አዲስ ያገኘኸው ነገር አለ?” ብላ መልዕክት ላከችለት፡፡

ዊሊያምስም “የለም” የሚል መልስ ከላከላት በኋላ በድጋሚ እቤት
በሰላም መግባትሽን አሳውቂኝ” አላት፡፡
ኒኪ ቀጥራ በምታሰራው ሰው ቅንነት ልቧን ደስ አለው። ከሁሉም
ከምታውቃቸው ሰዎችም በላይ ያለምንም ተጨማሪ ምክንያት ለእሷ በማሰቡ
ብቻ ልቧ ተነካ።

“በእውነት እሱ መልካም ሰው ነው::”
አለች እና አይኗ እምባ አቀረረ።

ግን እኮ ዶውግም ወደ መጥፎነት ከመቀየሩ በፊት መልካም ሰው ነበር
አለች በውስጧ፡፡ ውስጧ ያለው ሀዘን በረታባት እና መኪናው ውስጥ ጥልቅ እንቅልፍ ወሰዳት። ደስ የሚል እረፍት፡፡ ምናለበት ከዚህ እረፍት ውስጥ ለዘላለም
ባትነቃ...

ይቀጥላል
👍2
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

ልዩ ልዩ ጠባይና ፍላጐት ያላቸው ወንድና ሴት እንግዶች በየጊዜው ወደ ቤታችን ይመጣሉ፡፡ ከእነሱም መኻከል ወይዘሮ የውብዳር ተፈራ የሟቹ የሻምበል ባሻ አማረ ባለቤት ከባለቤታቸው ሞት ወዲህ ለትንሹም ለትልቁም ነገር እከሌ አጠቃኝ እከሌ ዛተብኝ፣ እገሊት ባሽሙር ሰደበችኝ እያሉ ቢያንስ ቢያንስ በሳምንት ሁለት ጊዜ ያህል ይመጡ ነበር፡፡ ስላጋጠማቸው ጉዳይ ሁሉ ጨምረው ጨማምረው ቢያወሩም ከከንፈር መጠጣ በልፎ ሌላ ዕርዳታ የሚያደርግላቸው ግን አልነበረም፡፡ ሆኖም «እኔ እንኳ ባልኖር ትላለች እናቴ ከቅራሪው ከፍርፋሪው
አትከልክሏቸው፣ ማንን ብለው የመጡ ይመስላችኋል» እያለች ለሠራተኞች እደራ
ትነግር ነበር፡፡

ወይዘሮ የውብዳር ተቀምጠው እንኳን ረጂሙ ቁመታቸው የአጭር ሰው
ቁመት ሊያህል ምንም ያህል አይቀረውም፡፡ በቀዩ ፊታቸው ላይ የሚታየው ማዲያት አዲስ ሽማ ላይ የፈሰሰ የጥቀርሻ ንጣቢ ይመስላል። የውበታቸው ለዛ ከተገፈፈ ውሉ አድሯል፡፡ ቀጠን ቀጠን ብለው የረዘሙት የላይ ፊት ጥርሶቻቸው በጥቅምት ውርጭ የዛገ ካራ ይመስላሉ፡፡ መጠጥ በጣም ከመውደዳቸው የተነሣ የእኛ ቤት ሠራተኞች እንኳ «መጡ ደግሞ እኝህ የመጠንሰሻ እንስራ የሆኑ ሴትዮ፡ መጥኔ እቴ! ስንት አለ በየቤቱ» ይላሉ።

የአማከለችን መሔድ ከሰሙ ሰንብተዋል፡፡ «እንዴት ያለች ገረድ አመጣልዎታለሁ፡ ጥፍፍ ያለች፣ ሰው ቀና ብላ የማታይና ታማኝ፣ አቤት! ወዴት! ብላ የምታድር ችግረኛ፡ እኛ ሠፈር ከመጣች ገና ኣሁን አንድ ወሯ ዐለፈ። እስከ ዛሬም ያላመጣኋት ሁኔታዋን ሁሉ እስካጣራ ብዬ ነው» እያሉ ከሦስት አራት ጊዜ በላይ እየፎከሩ ሔደዋል፡፡

አንዳንድ ጊዜማ በንግግራቸው ውስጣዊ ርግጠኛነት ስለሚሰማቸው ድምፃቸውን ወፈር አድርገው በመናገር፣ መጠጥ ባበላሸው ፊታቸው ላይ የቆረፈደ
ቆዳ የመሰለ ፈገግታ ያሳያሉ፡፡

አማከለች ከሔደች ድፍን ወር ዐለፈ። ቀኑ እሑድ ከቀኑ አራት ሰዓት ተኩል ነበር፡፡ ኣባቴ ከቤታችን ጓሮ በስተደቡብ በኩል ባለው የአትክልት ሥፍራ ውስጥ
አንዲት ታጣፊ የሽራ ወንበር ላይ በሁለት የኮክ ዛፎች መኻል ተቀምጦ ለብ ያለውን የረፋድ አየር እየመገመገ መጽሐፍ ያነብባል። ከነጭ ቡሉኮው ጋር
ሲታይ ከዕብነበረድ የተሠራና በአትክልት ሥፍራ ውስጥ የተተከለ የአረጋዊ ሰው
ነጭ ሐውልት ይመስላል። የአባቴ ረዘም ላለ ጊዜ እዚያ መቀመጥ በቤት ውስጥ
ለነበርነው እንደ ልብ የማውራት ነፃነት ስለ ሰጠን የሚረባ እና የማይረባውንም
ስናወራና ስናወካ አረፈድን፡፡ በመኻሉ ፍሬቢሱ ወሬ ስለ ሰለቸኝ ወደ መኝታ
ክፍሌ ገባሁ። በመስኮቱ በኩል የአጥር ግቢውን ሰሜናዊ አካባቢና ትልቁን
የግቢያችንን የአጥር በር ማየት ይቻላል፡፡ መስኮቱን ወለል አድርጌ ከከፈትኩ
በኋላ ነጩን ስስ መጋረጃ ወደ ግራና ቀኝ ሰበሰብኩት፡፡ የእንጨት ወንበሬን
መስኮቱ አጠገብ አስጠግቼ ደጅ ደጁን እያየሁ ተቀመጥኩ፡፡ ቅርቡንም፣ ሩቁንም
አሽቆልቁዬና፣ አሻግሬ ተመለከትኩ።
የአጥር ግቢያችን አንደኛው ክፋይ መዝጊያ በዝግታ ተከፈተ፡፡ ወይዘሮ
የውብዳር ባዘቶ የመሰለ ነጭ ሻሽ አሥረው፣ ዘወትር ከእጃቸው የማይለይዋትን ቆሸሽ ያለች ቀይ መሐረብ በግራ እጃቸው ይዘው፣ ርዝማኔዋ ላመል ታህል ከቁርጭምጭሚታቸው በላይ ከፍ ያለችውን የጭቃ ጫማ አድርገው፣ ቢጫ ጥለት ያለው ቀሚስና ኩታ ለብሰው ገቡ፡፡

ከኋላቸው አንዲት አቀርቅራ የምትራመድ ከወደ ቁመቷ ዘለግ ያለች ቀጭን ከሲታ ልጅ እግር በአሮጌ አዳፋ ነጠላ የተጠቀለለ ጓዝ በምብርቢጣዋ ይዛ
ገባች። ያቺ ግድ የለም እሜትዬ! ሰው ቀና ብላ የማታይ ባለሙያ አመጣልዎታለሁ» እያሉ በስሟ ጠላ ሲጠጡና ወደ ቤታቸውም ሲሔዱ ምናምን ሲያስቋጥሩባት የነበረችው ሠራተኛ ይህች መሆኗ ወዲያው ገባኝ፡፡ ምንጊዜም ቢሆን ወይዘሮ የውብዳር ሲመጡ ደስ አይለኝም ነበር፡፡ ፀሐይ ሳትገር የመጡ ጀንበር የምዕራብን አድማስ ስትስምና እንዳንድ ቀንም ላይን ሲይዝ ዘንድሮ እንደሁ ያለው የሌለው አይሉም፡ ጨርቁ ነጣ ነጣ ካለ በል በለው ነው፣ ለጠላትና ለምቀኛ ደስ አይበለው» ብለው እስኪነሱ ድረስ አሰልቺ ሐሜታቸውና የማይረባ ወሬአቸው ማባሪያ የለውም፡፡ ወይዘሮ የውብዳር የትልቁን ቤት ደረጃ ትም ድም
እያደረጉት ወጥተው የእንግዳ መቀበያውን ክፍል በር ከፍተው ሲገቡ በሩ ተንሲያጠጠ። አብራ የመጣችው ሴት ግን ባዶ እግሯን ስለ ነበረች ኮቴ
አልተሰማም፡፡ እናቴ እንዲህ የአረማመዱ ድምፅ የማይሰማውን ሰው «ጥላ ቢስ
ከውካዋ» ትለዋለች፡፡ ከእናቴ ጋር ሰላምታ ሲለዋወጡ የወይዘሮ የውብዳር ድምፅ
ጎላ ብሉ ተሰማ። የመኝታ ክፍሉ በር በመዘጋቱ እየር ተሽክሞ የሚያመጣውን
ድምፃቸውን እንጂ የእነርሱን የአካል እንቅስቃሴ ማየት አልቻልኩም፡፡

«እንዴት ያለች ባለሙያ ጨዋ ልጅ መሰለቻችሁ» አሉ ወይዘሮ የውብዳር ውስጣዊ ፍላጎታቸውን ለማስረዳት ድምፃቸው በእያንዳንዱ ተለጣጣቂ
ቃል ሽቅብ እየናረ፡፡ «እንዳላችኋትና እንዳዘዛችኋት ሆና የምታድር ዘመድና ወገን የሌላት ናት» ብለው ዝም አሉ፡፡ እናቴ ቀጠን ባለች ድምፅ «ገና ዛሬ በነፍሴ ደረሱልኝ፡ እኔም እጇ ጥፍፍ ያለ ባለሙያ እወዳለሁ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ከጠይም ሰው ጋር ኮከብ ግብቡ ነው። ከሁሉም ከሁሉም የምጠላው የእጅ ዐመል ያለበትን ሰው ነው። ካለ ነገሬ ልክስክስ ሰው አልወድም ብላ ከዝምታቸው ተጋራች። ከወዲያም ከወዲህም ዝምታ ሆነ። ዐልፎ አልፎ ግን የመቀመጫው ሥር ሽቦ ዉሽጣ ጢሽ ሲል ይሰማ ነበር። የወይዘሮ የውብዳርን ወሬና ሐሜታ እየሰማሁ ከመበሳጨት ይልቅ ዞር ዞር ብዬ መመለስ የሚችል ስለ መሰለኝ ወደ እንግዳ መቀበያ ክፍል ዘለቅሁ፡፡ እናቴና ወይዘሮ የውብዳር ፊት ለፊት ተቀምጠው ነበር።
የውብነሽ በካባቢውም አልነበረች፡፡
እንደምትመስልና የት ቦታ እንደተቀመጠች ልብ ብዬ ሳላይ ውልቅ አልኩ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ተመልሼ ወደ ቤት ስገባ ዐሥራ አንድ ሰዓት ሆኖ ስለነበር ወይዘሮ የውብዳር ዛሬም እንደ ቀድሟቸው ያን ያህል ይቆያሉ ብዩ አልገመትኩም ነበር፡፡ ሆኖም እንደ ግምቴ አልሆነም፡፡ አንድ ጊዜ ሟቹ ባለቤታቸው በላያቸው ላይ ሌላ የጐረቤት ሴት የሚስት ያህል ወደው ስለነበር ወይዘሮ የውብዳር ጣውንታቸውን
እንዴት እንደ ደበደቧትና እንዳጠቋት በሞቀ ጉራና ዐልፎ ዐልፎ ሐሰት
ባድፌጠፈጠው ፈገግታ ወሬአቸውን ሲጠርቁ ደረስኩ። ደግነቱ መሔጃቸው
በመድረሱ በብርጭቆ ውስጥ የቀረቻቸውን ከግማሽ በላይ የምትሆን ጠላ ባንድ ትንፋሽ ሽመጠጡዋት፡፡

አፋቸውን በግራ እጅ መዳፋቸው ጠርገው በዚያች በቆሻሻ መሐረባቸው ደገሟት። ከዚያም እናቴን ትክ ብለው እያዩ «እሜትዩ እንግዲህስ ልሒድ ደኅና
እደሩ፡ እኔም ብቅ እያልኩ እጠይቃችኋለሁ። ፊት የሚሉ ነገር እንዳታሳዩዋት፡፡ ለገረድ ፊት ማሳየት መሣቅ ደግ አይደለም፡፡ ነባር ገረድ ደግሞ አጋላጭ ነው፡፡ከእነዚያ ከሾካኮችና መናጢዎች ጋር እየዋለች እንዳትማግጥና ቂጥ እንዳይገጥሙ ይቆጧት» አሉ፡፡ የሴትዮዋ እስከዚያ ጊዜ ድረስ መቆየት በጣም አናድዶኝ ስለ ነበር እነሱ ወዳሉበት ስገባ ማንንም ሰላም አላልኩም፡፡ ወይዘሮ የውብዳር
ያሻሻቸውን ሁኔታ በጃቸው ደባብሰው ካረጋገጡ በኋላ ትንሽ ራቅ ብላ መጽሐፍ
የምታገላብጠውን የውብነሽን አሻግረው እየተመለከቱ «አንቺ የኔ ልጅ! እስኪ
ሮጥ በይና ያቺን የዛሬይቱን ገረድ ጥሪልኝ» በማለት በትንሽ የመጠጥ ኃይል
በተገፋ ስሜት ጮክ ብለው ተናገሩ።

የውብነሽ መጽሐፏን እንደ ያዘች በዕቃ ቤት በኩል ወደ ማድ ቤት በሚያስኬደው መንገድ አዲሲቱን ሠራተኛ ለመጥራት ሄደች። የሴትዮዋ ቆመው ወሬ መቀጠል እናቴን
👍4
ቅር ስላሰኛት እሷም ተነሥታ ቆመች። ሌላው ቀርቶ የሴትዮዋን ፊት ማየት እንኳ ስላስጠላኝ አንድ ኪሲ ውስጥ የሰነበተ ደብዳቤ አውጥቼ ማንበብ ጀመርኩ።

የውብነሽና ሠራተኛይቱ ተከታትለው ገቡ። እህቴ በወይዘሮ የውብዳር ላይ የነበራትን ጥላቻ በሚገልጽ ቀጭን ሰላላ ድምፅ ይቺው መጣች፡ ቅድም ነግረዋት የለም እንዴ? አሁን ደግሞ ምን ቀረ?» ብላ ወደ መቀመጫዋ ተመለሰች። አልመለሱላትም፡፡ የማስጠንቀቅ ሁኔታን በሚገልፅ አነጋገር መጀመሪያውኑም ቢሆን ገና እዚህ ሳንመጣ ነግሬሻለሁ፡ ቤቱ የትልቅ ሰው ቤት ነው። የደጋጎች የለጋሦች ቤት ነው፡፡ ሲሳዩ እንደሁ እንደምታዪው ሞልቶ ተርፏል። ሪቁ የሻገተበት ቤት ነው የሚሉሽን ሁሉ እየሠራሽና እየታዘዝሽ መኖር ነው፡፡ እዚህ ቤት ካሉት ገረዶች ጋር እንዳትገጥሚ፡ አንቺ ማየትና መስማት ያለብሽ እሜትዬንና ጌቶችን ብቻ ነው:: ልጆቻቸው እንደሁ ይኸው እንደምታያቸው ትላልቆች ናቸው። በይ! እንግዲህ ነቃ ነቃ በይ!" ብለው ያስፈራሩዋትና ያሽቆጠቆጡዋት መሆናቸውን ለመግለጽ ፊታቸውን ከሰከሱ።
እናቴ ግን ርኅራኄ ባለበው ድምፅ “እስኪ ምን አለበት ልብስሽን እጠቢው ብለው እንኳ የሳሙና ሙርሟሪ ጣል ቢያደርጉላት አለች የሰራተኛይቱን
መቆሸሽ በተፀየፈ ዐይን እያየች። ወይዘሮ የውብዳርም «ከእንግዲህማ ዕድሜ ለእኔ ትበል፥ ቀን ሊወጣላት ነው:: እናንተ እንደሁ እንኳን ለራሳችሁ ቤት ሰውና ላላፊ አግዳሚው ትተርፋላችሁ::»

«ዋናው ቁም ነገር ዐመል ነው:: ዐመል ያላት አገልጋይ ከመቤቷ እኩል ትቀባለች” ይሉ ነበር ወይዘሮ ሸዋረገድ ሞገሴ» ብለው የድግስ ጠላና ፍርፋሪ በጉጉት እንደሚጠብቅ ለማኝ ዐይኖቻቸው በባዶው ብርጭቆዋቸው ዙሪያ
ተንቀዋለሉ፡፡ የውብነሽ በእናቴ የዐይን ጥቅሻ ትእዛዝ ሞላችላቸውኛ እንደገና
አቀማመጣቸውን አመቻቹ፡፡ አሁንም እንግዳዪቱን ሠራተኛ በሚገባ ትኩር ብዬ
ሳላያት ትመልሳ ወደ ማድቤት ወረደች።

ሰዎች እናቴን ሲያሞጋግሷትና ባለ ሙያ ሴት ወይዘሮ ናቸው” ሲሏት ደስ እንደሚላት የሚያውቁት ወይዘሮ የውብዳር ተጨማሪ መጠጥ ለማስቀዳት
ወይም ከየጥራጥሬው ለማስቋጠር ሲፈልጉ የተለመደ ሙገሳና ውዳሴያቸውን
ይጀምራሉ።

ከልጅነቴ ጀምሮ የማያውቁኝ ይመስል እኔንም እናቴንም ባንድ ጊዜ ለማስደሰት «እንዲያው እኮ የዚሀ የጌታነህ መልክ እየዋለ እያደረ ይወጣ ጀምር»
በማለት ጀመሩ፡፡

«ያፍንጫው ስልክክ እያለ መምጣት፣ የጸጉሩ መቸምቸምና የግንባሩ መግጠም ባካል ጌቶችን ሆነ፡፡ የርስዎን የመየቴን ጸጉርማ ቢይዝ ኖሮ… አረ ተውኝ! ከምኑም ከምኑም ደስ የሚሉኝ ደግሞ ክርክም ያሉት ነጫጭ ጥርሶቹ
ናቸው። ለዛ ነሽ፣ አሣሣቅ ነሽ ትልቁን ልጅሁን እኮ ነው የመሰለው» እሱና ስለ
እኔ የመልክ ሁኔታ የሰጡት አስተያየት ተቀባይነት እንዲያገኝላቸው ራሳቸውን
ለመርዳት ረጃጅም ብልዝ ጥርሶቻቸውን ውሃ በበላት ነጠላቸው ሸፍነው ከት
ብለው ሣቁ፡፡ እንደሳቸው አገላለጽ አንድ ቀን አባቴን፣ ሌላ ቀን ወንድሜን
እንደምመስል ስለሚነገር፣ እኔ ከአባቴና ከወንድሜ የተውጣጣ የመልክ ቅርስ
እንዳለኝ ሆኖ ይሰማኛል።

«ትልቁ ልጄ ግርማዬነህ የወጣው በኔ በናቱ ነው:: ጸጉር ብትሉ፣ ደም ግባት ብትሉ፣ የዚህኛው የግንባሩ ጠበብ ማለትና የቁመናው ነገር እንዳጎትየው
ነው፡፡ ይኸ እንዲያው የደስ ደስ ስላላው ያየው ሁሉ ይወደዋል እንጂ..» ብላ
ንግግሯን ሳትዉርስ ወይዘሮ የውብዳር ካፏ ቅልብ አድርገው

«ለወንድ ልጅ ከዚህ ወዲያ ምን ሊሆነው? የዋ ልጅ በጥላው ይለያል»
ብለው የናቴን አስተያየት ቀምተው ደመደሙ፡፡
እኔ ታዲያ ከእናቴ ቀይ ዳማ ፊት ደበብ ያለውን ፊቴን ቀይ፣ መካከኛ ቁመቴን መለሎ ስሱን ከንፈሬን ሞንዳላ እያሉ እየጨማመሩ ሲያሰማምሩኝ ኅፍረት ይሰማኝ ነበር። እነእመይቴ ቤት የሚሽተት ነገር አይጠፋም ብዬ ነው የመጣሁት» ብለው በሚመጡበት ቀን ወይ ከጉሹ ወይ ከቁራሽ አያጡም።በአባቴ ፊት ወሬአቸው ሁሉ ባጭሩ ስለሚቀጭ «ከጌቶች ጋር ጨዋታ አፍን ክርክም አድርጎ ነው» ይላሉ፡፡ ያንን ከእናቴ ጋር ተወርቶ፣ ተወርቶ የቆረፈደ ወሬአቸውን አባቴ ፊት ሲቀጥሉ እንዳጋጣሚ እኔ ወይም የውብነሽ በፊታቸው ካለፍን፣ በድንጋጤ ክው ይሉና ነፋስ እንዳዋከባት ጧፍ ልትጠፋ የተቃረበች ወሬአቸው ነፍስ እንድትዘራ እንደገና ስለ እኔ መልክ ወሬ ይቋጥራሉ። አባቴ ግን እሳቸው ባሉት በተቃራኒ ከትከሻው ሰፋ ብሎ፣ ካፍንጫው ቀጥ ማለቱና ወረሩ
ሟቹን ወንድሜን ይመስላል። ሟቹ ታዲያ ዐይኑ ጎላ ጎላ ያለ ነበር፡፡ ይኸ የቅንድብ ነዶ ብቻ ነው፥ ቁመቱ ግን ያም ልከኛ ነበር፡፡ ወንድነትና ሱሪ ታዲያ የትም የትም አልነበረችም! ይኸ እና ያ ምንና ምን! ምን አገናኝቷቸው» ብሎ ስለ እኔ መልክ የሰጡትን አስተያየት ባጭሩ ሲቀጨው ውሽቱ እንደተጋለጠበት ቀጣፊ ኩም ይላሉ፡፡

እናቴ ዘወትር እስከ አጥሩ በር ስለምትሸኛቸው አብራ ወጣች፡፡አንድ
እጅግ የምፈራው ነገር ከሕሊናዬ ውስጥ ተፍቆ የተወገደልኝ ያህል ደስ አለኝ።

እናቴ ለምን እንደምትወዳቸው ስትናገር የቆጡን የባጡን ሲቀበጣጥሩ
ደስ ይሉኛል። ሥራ የሌለ ቀን፣ ቀን ያማሻሉ፡፡ ታዲያ ያሉትን ቢሉ አላምናቸውም» ትላለች፡፡ አባቴ መኝታ ቤት ውስጥ ሆኖ ሲያነብ የቃላቱ ፍሬ
ነገር ሳይሆን ድምፁ ብቻ ይሰማል፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የእናቴ ድምፅ
ከወደ ዕቃ ቤት በመሰማቱ የውብነሽ ተነሥታ ሄደች። እኔም ሄጀ ጋደም አልኩ፡፡
አንድ እመም ያህል ደኅና እንቅልፍ ከወሰደኝ በኋላ ስነሳ ከምሽቱ አንድ ሰዓት
ዐለፍ ብሏል። ዐይኔን እያሻሸሁ ወደ እንግዳ መቀበያው ክፍል ስገባ የከፍሉ አየር ለብ ብሏል፡፡ እናቴ አንድ አገልግል ሙሉ ጥጥ አቅርባ ትፈለቅቃለች፡፡ ዐልፎ
ዐልፎ ወለሉ ላይ ጥፍጥሬ ይታያል። የውብነሽ ከጐኗ ተቀመጣ ሰማያዊ ጨርቅ ስትዘመዝም ድሪቶ የሚጥፍ ድኻ ትመስላለች።

ከቤቱ መኻል ትንሽ ራቅ ብሎ ዕቃ ቤቱ በር አጠገብ በትልቅ የብረት ምድጃ ላይ አንድ ቀበሌ የከሰል ፍም ተንተርኳል። ከእናቴ ጐን ሔጂ እንደተቀመጥኩ ጀምረውት የነበረውን ወሬ እንደ ገና ቀጠሉ፡፡

«አደራሽን ልጄ» አለች እናቴ በዐይኖቿ ከወደ ዕቃ ቤት በኩል የሚመጣ
ሰው እየተጠባበቀች። «ከእነዚህ ከሰላቢ ገረዶቻችን ጋር እንዳትገናኝና ክፉ ክፉውን እየነገሩ እንዳያበላሹብኝ ምከሪያት፡ ያቺም እንዲያ ራሴ ላይ የወጣችው
እንክንክ ስላልናት ነው» ብላ ከመጨረሷ አዲሲቱ ሠራተኛ አነስ ያለች የቡና
ብረት ምጣድና ጀበና ከነማቶቱ ይዛ መጣች:: ዕቃውን አስቀምጣ እንደ ገና
ተመልሳ ሄደች።
ማታ ማታ እጅግም እንግዳ በማይኖርበት ጊዜ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ ቡና ማፍላት የተለመደ ነው፡፡ እንደ ገና ደግሞ ስኒ በረከቦትና በትልቅ ነጭ ማንቆርቆሪያ ውሃ ይዛ መጣች። እጆቿን የኋሊት ወስዳ ከመዝጊያው ላይ ለጠፍ ብላ ቆመች። የቆመችበትን ምክንያት ያወቀችው እናቴ «የውብነሽ እስኪ ሂጂ ከዚያ ካሮጌው አገልግል በና ስጫት» ብላ አዘዘች። ትንሿን የአረቄ መርፌ ከጥልፉ ጨርቅ ላይ ሰክታ አስቀመጠችና ወደ ዕቃ ቤት ገባች፡፡

የቀኝ እግሬን ከግራ እግሬ ላይ ደርቤው ስለ ነበር የተንጠለጠለውን እግሬን ወደ ፊትና ወደ ኋላ እያወዛወዝኩ እመለከተዋለሁ።

የውብነሽ ቡናውን ይዛ ከተመለሰች በኋላ ሌሎቹ ሴቶች ከወዲያ ወዲህ ይንጐዳጐዳሉ። ሠራተኛይቱ ቡናውን በውሃ እየፈተገች ታጥብና እጣቢውን
አረንጓዴው ጐድጓዳ ሳህን ውስጥ ትደፋዋለች። ብረት ምጣዱን ጥዳ መቁላት ጀመረች። ቡናውን ከወዲያ ወዲህ ስታምስ የመቁላዪቱና የብረት ምጣዱ ግጭት በክፍሉ ውስጥ መጠነኛ ጉላት ያለው ድምፅ አሰማ፡፡ ሠራተኛይቱ አጭሩ ዱካ ላይ ተቀምጣ ፊቷን ወደ ምሥራቅ አዙራለች ከሚቆላው ቡና ላይ የሚወጣው ምኡዝ
👍4
ጢስ ከክፍሉ አየር ጋር ተቀላቅሎ ከወዲያ ወዲህ ሲርመሰመስ ቤቱን ጭጋግ የለበስ ሜዳ አስመስሉታል፡፡

የውብነሽ መለስ ብላ ጥልፏን ቀጠለች፡፡ የእኔ ሐሳብ ግን ከሁለቱ መኻ ተነጥሎ በመሄድ ዐይኖቼ የሚመለከቱትና የሚከታተሉት አዲሷን ሠራተኛና
በአጠቃላይም አኳኋኗን ነበር። እናቴና እህቴ ስለምን ጉዳይ እንደሚያወሩና
እንደሚጫወቱ ለመከታተል አልቻልኩም፡፡ ዐይኔም ቀልቤም ከሠራተኛይቱ
አካባቢ ውልፍት ሳይል ቡናው ፈልቶ ወረደ።

«እስኪ ትንሽ ቁርስ አምጪ፡ ዕጣኑንም አጭሱልን» ብላ እናቴ ስትናገር
ከእንቅልፉ እንደ ባነነ ሰው ነቃሁ፡፡ ዕጣኑ ጨሶ ቡናው ሰከኖ ተቀዳ፡፡

እናቴ በትንሿ ሳህን ላይ የቀረበችውን የነጭ ጤፍ እንጀራ ጉልበቷ ላይ
አድርጋ ከቆራረሰቻት በኋላ በጥቃ ጎረሰች። እኔም ደረሰኝ፡፡ የውብነሽ ቡና ይዛ ወደ መኝታ ቤት በመግባቷ አባቴ እንደማይመጣ አረጋገጥኩ፡፡ እኅቴ ቡና
አደለችን፡፡ አዲስ ሠራተኛ በተቀጠረች ቁጥር ለአንድና ለሁለት ቀን መርዳትና
ሥራውን ሁሉ ቀላል ማስመሰል በቤታችን ውስጥ የተለመደ በመሆኑ የውብነሽ
ከሊጡ ወጡ ማለት አላስደነቀኝም፡፡ የአዲሲቷን ሠራተኛ የቡና አፈላል ችሎታ
ለማየት ስል አከተምኩ። የጠጣሁት ቡና ግን ከሌላው ጊዜ ልዩነት ወይም
የማይረሳ ጣዕም አልነበረውም። እንዲያ እንዲያ ስል ጊዜው ተዋገደና ከምሽቱ
ሦስት ሰዓት ሆነ።እህቴ የምትጠልፈውን ጨርቅ አስቀምጣ ጋቢ ለብሳ ጉብ
አለች። እናቴም ባዘቶውን አገልግሏ ውስጥ ለጉማ ወደ መኝታ ቤት ገባች፡፡

ረዘም ላለ ጊዜ በፀጥታና መላቅጡ ባልታወቀ ሃሳብ ተውጦ በመቀመጡ
መላ አካላቴ በድንገተኛ ትካዜ የተወረረ መሰለ። እናቴ ከወደ መኝታ ቤት
ብላ «እስኪ እነዚያን እነ አይገባሽን እነገልማጭ የለሽን ራት አቅርቡ በያቸው
ብላ ተመለለች፡፡ የውብነሽ ጋቢዋን ወንበር ላይ ጣል አድርጋ ከድሮዎቹ ሁለት
ሠራተኞች ጋር ራት ለማቅረብ መለስ ቀለስ አሉ፡፡ እንግዳይቱ ሠራተኛ ግን ወደ
ዕቃ ቤት በሚያስኬደው ጥግ አንገቷን ሰበር አድርጋ ቆመች፡፡ ያሰበችውን እንጃ!
እምብዛም ሳትቆይ ወደ ዕቃ ቤት ገባች፡፡

ከወላጆቻችን ራት በኋላ ሠራተኛቹ መዐዱን ወደ እንግዳ መቀበያ ክፍል
አምጥተው ትንሿ ክብ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጡት፡፡ መዐዱ ወደ ተቀመጠበት
ሄድኩ፡፡ ምን ጊዜም ቢሆን ራት የሚቀርብልን ከወላጆቻችን በኋላ ነበር፡፡
የውብነሽ ከጐኔ እንደ ተቀመጠች አንደኛዋ ሠራተኛ አስታጥባን ተመለሰች።
ወሬያችንን እያወራን መብላት ጀመርን። ከእኔና ከእኅቴ በስተቀር በክፍሉ ውስጥ
ሌላ ሰው አልነበረም፡፡ የሚበቃንን ያህል በልተን ለመጥገብ ብዙ ጊዜ አልፈጀብንም። ዝቅ ባለች ቀጭን ቀብራራ አጠራር «አንቺ አስካለ ! ነይ እንጂ
መዐዱን አንሺው» ብላ የውብነሽ ተጣራች፡፡ የማንኛቸው ስም እንደ ተጠራ
ያላወቁና ያላጣሩ ይመስል ሁለቱም ሠራተኞች ተግተልትለው መጡ፡፡ እንደገና
«ሌላ ዝርግ ሳህን ይዘሽ ነይ» በማለቷ እስካለ ቀልጠፍ ብላ ሔደች፡፡

ዝርግ ሳህኑን ይዛ እንደ ተመለሰች የውብነሽ ወጥ ከነካካው ትርፍራፊ
ላይ እንጀራ ቀንሳ በዝርጉ ሳህን ላይ በተን አደረገች። በሁለቱም ሳህኖች እንጀራ
ላይ ወጥ ከወጣ በኋላ አስካለ የተሰጣትን ገበታ ይዛ ወደ ዕቃ ቤት ስትገባ ያቺን እንግዳይቱን ልጅ ነይ ትባያለሽ በያት» ብላ አዘዘቻት፡፡ የታጠብንበትን ውሃ ከያዘችው ሠራተኛ ጋር ወደ ውስጥ ገቡ፡፡

የተጠራችው አዲስ ሠራተኛ አቀርቅራ መሬት መሬቱን እያየች ጥጉን ይዛ ቆመች፡፡ «ነይ እንቺ ራትሽን ወስደሽ ብዪ፡ ወጥ ያነሰሽ እንደሁ ያመጡልሻል፡ እንዲያውም እኔ አለሁ» ብላ በቀኝ እጅዋ የያዘችውን ሳህን ለማቀበል ስትዘረጋ ወዲያው ደርሳ ተቀበለቻትና ወደ መቀመጫዋ ተመለሰች።

ለመቀመጥ ጉልበቷን አጠፍ ስታደርገው ጉልበቶቿ ቀጫጭን ጭራሮዎች የተሰበሩ ያህል ቋቅጭ አሉ፡፡

አማከለች ከሔደች ጀምሮ የእኔንና የራሷን አልጋ የምታነጥፈው እኅቴ ስለነበረች አልጋዎቹን ለማንጠፍ ወደ መኝታ ቤት ገባች፡፡ ሠራተኛዋ እንጀራውን ከፊት ለፊቷ አስቀምጣ በረሃብ እንደ ተጉዳ ሰው ሳይሆን በጐረምሳ መኻል እንደምትመገብ ዐይነ አፋር ልጃገረድ በትንሿ እየቆረሰች መብላት ጀመረች።
እንጀራው ላይ አንዳች አስፈሪና ተናካሽ ነገር ያለ ይመስል ለጉርሻ የምትሆናትን
ቁራሽ ስታስተካክል እጅዋ ይንቀጠቀጥ ነበር። ጉልበቷ ወደ ኋላ ታጥፎ ስለ ነበር
ከወደ ወገቧ ወደ ፊት ጐብጥ ብላ ደረቷ ከጭንዋ ላይ ዐርፎአል። በጣም ቀስ ብላ
ስለምታላምጥ ከንፈሮቿ የሚላወሱት በጣም በዝግታ ነበር።

የአንድን ነገር የተፈጥሮ አቀማመጥና ቅርፅ፣ መልክ፣ ውስጣዊና ውጫዊ
እንቅስቃሴዎች እየመረመረ እንደሚያጠና ባለሙያ ሠዓሊ ሰውነቷንና አለባበሷን ስንዝር በስንዝር ዐይኔን እያንሸራተትሁ ተመለከትኳት።በክፍሉ ውስጥ የበራው ደማቅ ብርሃን የፈለግሁትን ነገር ሁሉ በበቂ ሁኔታ ለማሳየት በቂ ድምቀት ነበረው።

ዐልፎ ዐልፎ የአበባ ሥዕል ያለበትና እጅግ በጣም አዳፋው ቀሚሷ
ከጉልበቷ በታች ሆን ብለው ሁለት ሦስት ቦታ ላይ በስለት የተለተሉት ይመስላል። ያቀሚሷ ተራ ሽንሽን ተተርትሮ ቀሚሷ ከረጢት መስሏል። ትጥገብም እትገብም እንጃ መብላቷን ተወችው። በእጀ ጉርድ እጅጌዋ በኩል ብቅ ብሎ የሚታየው እጇ ጥላሸት የጠጣ ደረቅ ዕንጨት ይመስላል። ቀስ ብላ ከተነሣች በኋላ ሳህኑን ይዛ ወደ ዕቃ ቤት ገባች።

ጥቂት ቆየት ብላ እጅዋን በቀሚሷ ጠርዝ እየጠራረገች ተመለሰች፡፡ መጀመሪያ የነበረችበትን ሥፍራ ትታ ሌላ ቦታ ቆመች፡፡

ፊቷና መላ ሰውነቷ ወደ ምሥራቅ በመዞሩ ወደ ምዕራብ ለሚመለክቱት ዐይኖቼ እሷን ለማየትና ሁኔታዋን ሁሉ ለመገንዘብ መልካም አጋጣሚ ሆነላቸው።
ጣቶችዋ ለድመት ግልገል ተዘልዝሉ እንደ ሰነበተ ሳንባ በልዘው ጠቁረዋል፡፡
ክንዶችዋ ሥጋቸው ከውስጥ ተፈቅፍቆ ወጥቶ ቆዳ ብቻ የለበሱ ይመስላሉ።
የአጥንቶችዋ ቅርፅና ጠፍጣፋነት ከሩቅ ይለያል። ቀሚሷ ደረቷ ላይ በመቀደዱ
ጠቆር ባለው ገላዋ ላይ እንደ ጐባጣ ማገር የተጋደሙት አጥንቶቿ ፈጥጠዋል።
በቀጭኑ አንገቷ ላይ ቂጥጥ ያለችው ራሷ በቃጭን አገዳ ላይ የበቀለች ማሽላ
ትመስላለች። የቆዳዋ ወዝና ቅባት ደርቆ የነፈሰበት የዘንጋዳ እንጀራ መስሏል።
ሰውነቷን በጠቅላላ ሲመለከቱት ለብዙ ጊዜ አብሯት በከረመ እድፍ በመጥቆሩ
ከረግረግ የተመዘዘ የዕንጨት ጉማጅ መስሏል፡፡

ዐይኖችዋን በሰፊው ከፍታ ይህ ነው ወደማይባል አካባቢ ስትመለከት
እነዚያን የሐምሌ ልደታ ድፍርስ ውሃ የመሰሉ ዐይኖችዋን በደንብ ኣየኋቸው።
ከመኻል ኣፍንጫዋ ግራና ቀኝ ላይ እንደ ጉጥ የፈጠጠው የጉንጭዋ አጥንት
አዲስ በቀል የጥጃ ቀንድ መስሏል። ጉንጫ ወደ ውስጥ ተሠርጉዶ ከመንጋጋዋ ጋር የተጣበቀ ስለሚመስል የግንቦት ሐሩር ሲያንቃቃው የሰነበተ የቅል ቅጠል መስሏል፡፡ የሠለጠነ አናጢ ፈልፍሉ እንደ ጠረበው የጥድ ዕንጨት ስልክክ ብሎ የወረደው እፍንጫዋ ድንቅ አቀማመጥ አለው፡፡

ቢማ ቀለም የነበረው ሻሽዋ ዐፈር የላሰ ደባደቦ መስሏል። ከሻሽዋ ውስጥ
አፈትልኮ በግራ ቀኝ ጆሮዎችዋ በኩል የተንዛለለው ጸጉሯ ዞማ መሆኑ
ቢያስታውቅም በንጽሕና ባለመያዙ የእሳት ላንቃ የገረፈው “ጭራ ሲመስል፣
ከጉልበቷ በታች በጠቅላላ ቅልጥሟ በተደጋጋሚ በመፎከቱ ቆዳዋ ተሽነታትሯል። የጨቅላ ልጅ ቡጢ ያህል የፈጠጠው ቁርጭምጭሚቷ ተረከዝዋ በላይ የሚገኘው ወፍራም ወጣሪ ጅማቷ በኑሮ መጎዳትዋና መጎሳቆሏን በሚገባ ለማሳወቅ የቀረቡ አስረጂዎች ናቸው፡፡...


💫ይቀጥላል💫
👍1
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ_አራት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

....ኬቨን ቮስ በሴዳይ ሳናይ ሆስፒታል ውስጥ በሚገኘው የሆስፒታሉ ካፌ
ውስጥ ቁጭ ብሎ የፕላስቲክ ጠረጴዛውን በጣቱ እየቆረቆረ ነው::

የግል መርማሪው ደውሎ ቀጠሮ ያስያዘው ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ ነው::
አሁን 12:10 ይላል፡፡ 12:11 ሲል ደግሞ ኬቨን ቀጠሮው የውሸት መሰለው::
ምክንያቱም የሆነ ሰው ስለ ዶክተር ዶውግ ሮበርትስ እና ስለ ውሽማው
የምታውቀውን ነገር ከነገርከኝ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን እሰጥሃለሁ
ብሎት ነው እዚህ የቀጠረው። እርግጥ ነው ኬቨን ስለ እነርሱ ብዙ የሚናገረው ነገር የለም። አብዛኞቹ ነገሮች ወንድ እና ሴት ነርሶች ሲያወሯቸው የነበሩ የሐሜት ወሬዎች ናቸው። ኬቨን ቮስ ዕዳ ስላለበት
ክሬዲት ካርዱ እና ሌሎች ነገሮችም ሁሉ ባዶ ስለሆኑበትና የግድ ብሩ
ስለሚያስፈልገው ነበር ሰውዬውን ለማግኘት የተስማማው። በዚያ ላይ ደግሞ የወንድ ጓደኛው ኢንዞ በነርስነቱ ከሚከፈለው በላይ በጣም ብዙ ብሩን ግጦትባዶና ስላደረገው ነበር።

“ኤቨን?” አለው አንድ ወፍራም ሰው ወደ ካፍቴሪያው ተንደርድሮ እየገባ እና ኬቨን ወደ ተቀመጠበት ቦታ እየመጣ፡፡ አጠገቡ ደርሶም ላባማ እጆቹን ለሰላምታ እየዘረጋ ራሱን አስተዋወቀው:: ደግነቱ ቦታው ጭር ያለ ስለሆነ ኬቨን ደስ አለው::

ነርሱ ዙሪያውን ከቃኘ በኋላ እጁን ጨብጦ እንዲቀመጥ በአይኑ ጋበዘው።

“እዚህ ካፌ ምንድነው ጥሩ ምግባቸው?” ዊሊያም ከጠየቀ በኋላ “ማታ ቆይቼ ነበር እና ጥሩ ቁርስ እፈልጋለሁ::”
ኬቨን የዊሊያምስን ከብብቱ ሥር ያለውን ሸሚዝ ቅፍፍ እያለው አይን አይኑን እየተመለከተ “ብቻዬን ልታገኘኝ ነበር የፈለግከው።” አለው በሹክሹክታ፡፡

“አዎን ደግሞም እኮ እዚህ ማንም የለም::” ብሎ ዊሊያምስ ገለፈጠ እና
ሁለት የብሉ ቤሪ ዳቦ እና አንድ ትልቅ ላቴ አዝዞ ወደ ኬቨን በመመለስ
"እዚህ ስለ እኛ ደንታ ያለው ሰው የለም እመነኝ፡፡ ደግሞም እኮ እያወራን
ያለነው ስለ ድሮ ጓደኛዬ ስለሆነ ህገወጥ የሆነ ነገር አይደለም::”

እሺ” ብሎ ነርሱ የግዱን ፈገግ አለ እና ይሄ ዊሊያምስ የእውነት የዶ/ር
ሮበርትስ ጓደኛ ይሆን? ብሎ አሰበ።
ለማንኛውም ገንዘቡ የግድ ስለሚያስፈልገው የግድ ያወራዋል።

“ያን ያህል በጣም የቅርብ ጓደኛማቾች አይደለንም” ብሎ የመጣለትን ቁርስ አንድ ጊዜ አብዝቶ ጎርሶም የሆነ ጊዜ ላይ አብረን እንሰራ ነበር።እወደውም ነበር። ብዙ ሰዎች ይወዱታል” አለው፡፡

“እሺ ማን ነበር የማይወደው የነበረው?” ብሎ ዊሊያምስ ቡናውን በረዥሙ ድምፅ እያሰማ ፉት አለው።

“ምን ማለትህ ነው አልገባኝም?”
“ብዙ ሰዎች ይወዱት ነበር ብለኸኛል። ብዙ ማለት ደግሞ ሁሉም ማለት አይደለም። ስለዚህ እሱን የማይወድ ሰው ነበር?”

ኬቨን ፊቱን አጥቁሮ “በቃ ፀባዩ ተቀየረ ከሆነች ሴት ጋር ግንኙነትም ጀመረ። ሩሲያዊ ናት:: ከዚያ በኋላ ሁሉ ነገሩ ተቀየረ”

“ተቀየረ ስትል?” ብሎ ዊሊያምስ ጠየቀው ምግቡ ላይ አቀርቅሮ፡፡

የሩሲያኖች ሥም ነው ያላት። ሥሟ አሁን ተረሳኝ። ሞስኮ ነበር ትኖር የነበረው። ግን ሁሉ ነገሯ አሜሪካዊ ነበር ይመስል የነበረው:: ስታወራ ደግሞ እንግሊዝኛ ዘዬዋ የአሜሪካውያን ነበር፡፡ ብቻ ዶክተር ሮበርትስ በእሷ መተት የተሰራበት ይመስል ነበር። ደግሞ እኮ ያን ያህል
ቆንጆ አልነበረችም:: የሆነች የአለምን ሸክም የተሸከመች ነበር የምትመስለው።
እንዲያውም በወጣትነቷ የሚጠብሳት ወንድ ሁሉ ያለ አይመስለኝም፡፡ በጣም
ረዥም ናት” ብሎ በማስከተልም “ከዚያ በዘለለ ግን ከሚስቱ ጋር ስትነፃፀር
እዚህ ግቢ የሚባል የሴት ውበት ያላት አልነበረችም” አለው፡፡

ዊሊያምም በኬቨን ሀሳብ መስማማቱን ራሱን ነቀነቀ፤ በተለይ ደግሞ ደብዛዛ የሌንካ ጎርዴቪችን ፎቶዎች ሲመለከት ሌንካ ከኒኪ በዕድሜ ማነሷ
ብቻ ይበልጥ ወጣት እንድትመስል ያደርጋታል፡፡ ከዚያ በተረፈ
የፈለገቻቸውን ውድ ውድ ልብሶችን
ምንም እንኳን ብትለብስም
የማያምርባት ሴት እንደሆነች ለመረዳት ችሏል።

ዊሊያምስ ስለ እሷ የኋላ ህይወት ለማወቅ ያልቆፈረው ድንጋይ
ባይኖርም እንዳሰበው ስለ እሷ ማወቅ አልቻለም። ይሄው ከአከራይዋ ጀምሮ
እሷን አስመልክቶ ጥያቄን ቢጠይቅም ስለ ቤተሰቧ ስለ ስራዋ፣ ስለ ስራ
ቅጥሯ ወይንም ደግሞ ስለ ትምህርት ደረጃዋ አንድም አይነት መረጃና
ለማግኘት አልቻለም፡፡

ሀዶን ዶፎ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኝ የአደንዛዥ ዕፅ አስወጋጅ የግብረ
ሰናይ ድርጅት ውስጥ ነው የምትሰራው ቢለውም እዚያ ቦታ ላይ ይሰሩ
የነበሩ ሰዎችን ባወራቸው ጊዜ ስለ እሷ አንድም ነገር እንደማያውቁ
ነግረውት ነበር። ብቻ ሴትየዋ የሆነች መንፈስ ናት እንዴ? ብሎ እስከማሰብ
ደርሷል።

“አግኝተሃት ታውቅ ነበር?” “ለተወሰኑ ጊዜያት ያህል አዎ፡፡” ነርሱም ራሱን በአዎንታ ወዝውዞ “ብዙ ጊዜ ወደ ሆስፒታል ትመጣ ነበር፡፡ እዚህ
ካፌ ውስጥም ነበር ብዙውን ጊዜ ምሳቸውን ይበሉ የነበሩት። ይሄ ደግሞ
ያልተለመደ ነገር ነው:: ምክንያቱም የፍቅር ግንኙነታቸው በይፋ ነበር፡፡
ለሆስፒታሉ ሠራተኛ በሙሉ ነበር በግልፅ ያሳዩ የነበረው።” ይሄ ደግሞ
ብዙውን ጊዜ ዶክተር ዶፎ እና ዶክተር ሮበርትስ ያጣላቸው ነበር። “አዎን
በእሷ በሌንካ ምክንያት እንደሚጨቃጨቁ እርግጠኛ ነኝ። አሁን ሥሟ መጣልኝ ሌንካ ነው ሥሟ” አለው ኬቨን ስሟን በማግኘቱ ደስ እያለው፡፡

“ዶውግ ሮበርትስ እና ሌንካ እንዴት ነበር የተገናኙት?”

ኬቨን ለጥቂት ጊዜ ሲያስበው ቆየና “ኒውዮርክ ላይ ይመስለኛል። የሆነ
የበጎ አድራጎት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ። ዶክተር ሮበርትስ የሆነ
በነፃ አገልግሎት የሚስጥ ክሊኒክ...” ብሎ

“እሱን አውቃለሁ” አለው እና ካቋረጠው በኋላ “ስራዋ ምን እንደነበር
ታውቅ ነበር?”

“እሱን አላውቅም” ብሎ ኬቨን መቶዎቹ ዶላሮች በዚህ ምክንያት የሚያመልጠው ይመስል እየተጨነቀም “ግን እሷ በጣም ሀብታም ነበረች። ምናልባት ይሄ ይሆናል ያቀራረባቸው:: ግን አየህ ፕላቲንየም እና አልማዝ ያለባቸውን የእጅ ሰዓቶች ነበር የምታደርገው፡፡ አዎን ቶፓርድ!” አለው እና
በመቀጠልም “ማለቴ ሰዓቶቿ ቢያንስ ከአሥራ አምስት ሺ እስከ ሃያ ሺ
ዶላር የሚያወጡ ናቸው። ሁሌም ሄርሜስ ቦርሳዎችን ነው ይዛ የማያት።የሆነ ጊዜ ላይ ደግሞ እጅግ በጣም ውድ የሆነ ጃኬት አድርጋ መምጣቷን አስታውሳለሁ። ምክንያቱም ዶክተር ሮበርትስ ይህንን ለብሳ በመምጣቷ ተቆጥቷት ስለነበር ነው።”

“ምን ብሎ ነው የተቆጣት?”

“ማምለጥ ብትፈልጊም ሆነ ባትፈልጊ ይህንን ልብስ ለብሰሽ አትምጪ!”
ብሎ በጣም ተናድዶ ነበር የተናገራት::

እሺ እሷስ ምን መለሰችለት?” ብሎ ዊሊያምስ ጠየቀው፡፡ የተለየ ነገር
የሚገኝበት መስሎት እየጓጓ።

አለቀሰች” ብሎ ኬቨን ከመለሰለት በኋላም “ግን ያው እንደ ሁልጊዜውም
ወድያው ተረጋጋች”

“ከእሷ ሌላ ውሽማዎች ነበሩት?”

ኬቨን ራሱን በአሉታ ነቅንቆ “ከሌንካ ጋር ግንኙነት ከመጀመሩ በፊት
እንደምትፈልገው በጣም የምትፈልገው አይመስለኝም፡፡ ገባህ አይደል?”
ሁሌም ከሚስቱ ጋር ነበር፡፡ ግን አየህ ሚስቱም ዶክተር ስለሆነች ሩሲያዊቷ
ዊሊያምም እንደገባው ለማሳወቅ ራሱን በአዎንታ ወዘወዘለትና የማስታወሻ ደብተሩ ላይ ነገሮችን መፃፍ ጀመረ::

ከሆኑ አደገኛ ሰዎች ጋርም ግንኙነት እንዳላት ሰምቼ ነበር?” ብሎ ኬቨን ድምፁን ቀነሰና “ማለቴ በጣም ሀይለኛ ከሆኑ ሰዎች ጋር”

“ምን አይነት ሰዎች?” ብሎ ዊሊያምስ ጠየቀው፡፡

“አላውቅም” አለ እና ኬቨን በመቀጠልም “ዶውግ ሮበርትስ እነዚህን
👍3
ሰዎች ይወቃቸው፣ አይወቃቸው ግን የማውቀው ነገር የለም፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ላይ የሆነ የቀዶ ጥገና ዶክተር የከተማው ማዘጋጃ ቤት ለሚያሰራቸው የኮንትራት ሥራዎች እነዚህን ሰዎች እንደሚያውቃቸው
ሲያወራ ሰምቼ ነበር።”

ዊሊያምም ትንሽ አመነታ እና ተነስቶ የኪስ ቦርሳውን ካወጣ በኋላ
ሁለት መቶ ዶላር ጠረጴዛው ላይ ካስቀመጠለት በኋላ “ስለነበረን ጊዜ
አመስግናለሁ” እንዴ ሁለት መቶ ዶላር ብቻ?” ብሎ ነርሱ በንዴት እየተናገረ
ከጠረጴዛው ላይ ሁለት መቶ ዶላሩን አንስቶ ወደ ኪሱ ጨመረ፡፡

ዊሊያምስ ትከሻውን ከሰሰቀ በኋላ “ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን አልሰጠኸኝም።
ማለቴ እሷ ስለሚጠብቋት ሀይለኛ ሰዎች ሥም ውስጥ አንዱን አሊያም ደግሞ ስለ ማዘጋጃ ቤቱ የነገርከኝ ተጨባጭ ያልሆነ ሀሜትን ብቻ ነው!”

“እዚያ የሚሰራ ሰው አለኝ፡፡ እሱ ብዙ ነገር ሊነግረኝ ይችላል”

ዊሊያምስም “ማን ነው?” ብሎ ዞሮ ጠየቀው፡፡ኬቨንም ተመልሶ ወንበሩ ላይ እየተቀመጠ “ለዚህ ሦስት መቶ ዶላር
ተጨማሪ እፈልጋለሁ” አለው:: ዊሊያምስ ጥሎት ሲራመድ

“ሁለት መቶ ዶላር?” አለው ኬቨን፡፡

“በእውነት ሚ/ር ዊልያምስ እሷ ልትረዳህ እንደምትችል እርግጠኛ ነኝ አለው፡፡

ዊሊያምስ ወደ ኬቨን ተመለሰና ሁለት መቶ ዶላር አውጥቶ ጠረጴዛው
ላይ አስቀመጠ። ኬቨንም እጁን ወደ ዶላሮቹ ሲሰድ ዊሊያምስ በእጁ
ሸፈነበት፡፡

“የዚህን ሰው ሥም አድራሻ እና የስልክ ቁጥር እፈልጋለሁ” አለው እና በእርጋታ “የምትሰጠኝ ነገር ግን ጠቃሚ መሆን ይኖርበታል” አለው።

ኬቨን የሰጠው መረጃ ያን ያህል ትክክል አልነበረም።

አድሬኔ ዋሽንግተን ከከተማው ማዘጋጃ ቤት ለቅቃ ወጥታ ነበር:: ከስድስት ወራት በፊት ከጁንየር የፀሀፊነት ስራዋ ተባርራ ነበር። እሷ የከንቲባው ቢሮ ውስጥ ነበር ስትሰራ የነበረው። አሁን ላይ ግን መሀል
ከተማ ውስጥ ለሚገኝ አንድ ኢንተርፕሩነር ረዳት ፀሐፊ በመሆን በትርፍ ሰዓት በመስራት ላይ ትገኛለች።

“ያንን ሥራ መልቀቄ ለበጎ ነው።” አለችው ዊሊያምስ አግኝቷት ምሳ እየበሉ እያሉ “በእውነት ሥራቸው የሚያሳፍር ነበር። ለማንኛውም የከንቲባውን ቢሮ ትቼ በመውጣቴ የተነሳ ሜካኤልን የመሰለ ምርጥ አለቃ ለማግኘት አስችሎኛል። በዚያ ላይ ደግሞ ደሞዙ እራሱ ማዘጋጃ ቤቱ ከሚከፍለኝ እጥፍ ነው::”

ዊሊያም አድሬኒን ሲያዳምጣት ሁለት ነገሮችን ለመታዘብ ችሏል። የመጀመሪያው ቁንጅናዋ ነው። ረዣዥም እግሮች፣ ቀጭን ወገብ እና ጥቅጥቅ ያለው ቀይ ፀጉሯ አንድን ወንድ በቀላሉ ማማለል መቻሉ ነው።ስለዚህ ከንቲባውም ሆነ የአሁኑ አለቃዋ ለደደብ አዕምሮዋ ብለው ሳይሆን የቀጠሯት ለአልጋ ላይ ጨዋታ እንደሆነ ግልፅ ነው:: ሁለተኛው ነገሯ ደግሞ ምንም ሚስጥር መቋጠር የማትችል በጥራቃ ሴት መሆኗ ነው።

“በመጀመሪያው ከንቲባው ፋውንቲስ እኔን ያባረረኝ ከእሱ ጋር አልተኛም ስላልኩኝ መስሎኝ ነበር፡፡” ብላ “አለ አይደል ሰውዬው ሁለመናዬን ይደባብሰኝ
ነበር። የምለው ገባህ አይደል? አለ አይደል እሱ እኮ ዕድሜው 50 ዓመት
ነው። በዚያ ላይ ባለትዳር ነው” አለችው፡፡

ሦስት ቃላቶቿ መሀል አለ አይደል የሚለው ቃሏን እየከተተች ስለምታወራ ዊሊያምስ ስልችት ብሎታል። እሱ አለቃዋ ቢሆን ኖሮ ለዚህ አለ አይደል በምትለው ነገር ብቻ ከሥራ ሁሉ ያባራት ነበር።

ነገር ግን በመጨረሻ ላይ እኔ ስለ እሱ ባወቅኩት ነገር የተነሳ እንደተባረርኩኝ ገባኝ::”

“ምን ነበር አንቺ የምታውቂው ነገር አድሬኔ?”

አለ አይደል ከንቲባው ከሩሲያኖች ገንዘብ ይወስድ ነበር” ልክ ስለ አየር ንብረት እንደምታወራ ሁሉ ቀለል አድርጋ ማውራቷን ቀጠለች እና “ጉቦ እና
የተለያዩ ውድ ውድ ስጦታዎችን እንደሚቀበል አለቃዬ ሚስተር ድሬይተን
ለሆነ የጋዜጣ ሪፖርተር በስልክ ስታወራ ሰምቼ ነበር”

“የኔ ቆንጆ አሁን በምትነግሪኝ ነገር እርግጠኛ ነሽ?” ብሎ ዊሊያምስ
በትህትና ጠየቃት እና “ይሄ እኮ ትልቅ ውንጀላ ነው። በዚያ ላይ ደግሞ
ከንቲባው በሙስና ጉዳይ ላይ ስሙን በአንድም ጋዜጣ ላይ አላነበብኩም”
“እንዴ እኔ ማንንም እየወነጀልኩ አይደለም!” ብላ እንደመገረም ነገር
አለች እና “እኔ የሰማሁትን ነገር ነው የነገርኩህ፡፡ አለ አይደል ለከንቲባ
ፋንቴስ የሰማሁትን ነገር እንደነገርኩት ማለት ነው። ከዚያ ወዲያውኑ
ከሥራ ተባረርኩኝ፡፡ ስለዚህም ነገሩ ከወሲብ ጋር እንዳልተያያዘ ለማወቅ
በቃሁ፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆን ሚስተር ዳሬንንም አባረራት። እንዲያውም እሷን
እንኳን ያባረራት አብሯት እንዲተኛ ስላልፈቀደችለት እንደሆነማ እርግጠኛ
ነኝ:: አሁን የእኔ አዲሱ አለቃዬን ስለ ጉዳዩ ስነግረው... አለ አይደል...”

ለሃያ ደቂቃዎች ያህል ከአድሬኔ ዋሽንግተን ያገኘው ነገር ቢኖር ስለ
እነዚህ ሩስያውያኖች እና ስለ ሌንካ ጎርዴቭስኪ ምንም ነገር እንደማታውቅ
ለአራት ሰዓታት ያህል ከፈለጋት እና ካስፈለጋት በኋላ ቲና ድሬይተን
የተባለችውን የአድሬኔን አለቃን አገኛት:: የተከራየችበትን ዕቃው የተሟላ አፓርትመንት በርን ስትከፍትለት በጣም ጠንካራ ሰንሰለት ከበሩ እና ከበሩ
ጎን ጋር ተጣብቆ ነበር፡፡ ስለሆነም በሩ በትንሹ ስለተከፈተ በተከፈተው በር
በኩል ያገኘው አንዲት በአርባዎቹ አጋማሽ ላይ የምትገኝ እና በፍርሃት
የተሞላ ፊት ያላትን ሴትዮ ነበር።

“ምን ነበር?” ብላ ጠየቀችው፡፡

“ዴሪክ ዊሊያምስ እባላለሁ ሚስ ዴሬይተን፡፡ እኔ የግል ወንጀል መርማሪ
ነኝ። መግባት እችላለሁ?” አላት፡፡ ቲናም ለትንሽ ጊዜ ስታመነታ ቆየች እና “ይቅርታ አሁን ጥሩ ጊዜ ላይ አይደለሁም” ብላ በሩን ልትዘጋበት ስትል ዊሊያምስ “ስላንቺ ያወቅኩት ከሥርሽ ሆና ትሰራ ከነበረችው አድሬኔ ዋሽንግተን ነው። ስለ አንቺ በጣም ነው የምትጨነቀው” አላት፡፡

“አድሬኔ?” ብላ አይኗን አፈጠጠች እና “ይህቺ ደደብ ልጅ መቼ ነው አፏን የምትዘጋው! እርግጥ እወዳታለሁ። ግን ብዙውን ጊዜ ስለምታወራቸው
ነገሮች ግማሹን እንኳን በቅጡ አታውቀውም፡፡ ሚ/ር ሥምህን?”
ማን አልከኝ

“ዊሊያምስ” ብሎ የቢዝነስ ካርዱን በትንሹ የበር ክፍተት በኩል አቀበላት
እና “ግን ዴሪክ ብለሽ ልትጠሪኝ ትችያለሽ፡፡ ጥርጣሬሽ ይገባኛል የኔ
እመቤት: ስለ አድሬኔ በተናገርሻቸው ነገሮችም እስማማለሁ። በሞኝነት
እራሷን ለአደጋ አጋልጣ የምትሰጥ ሴት ናት። እባክሽን ሚስተርስ ድሬይተን
ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል እንዳወራሽ ፍቀጂልኝ።” አላት።

“እሺ ጠብቀኝ” ብላ በሩን ከዘጋች በኋላ የበሩን ሰንሰለት ከውስጥ በኩል
ሙሉ በሙሉ አስለቅቃ በሩን ከፈተችለት፡፡

“ግባ እስቲ” ብላ በረዥሙ ከተነፈሰች በኋላም “ቲና በለኝ፡፡ ግን ብዙ
የማዋራህ ነገር ያለኝ አይመስለኝም። ዛሬ ከዚህ ቦታ መውጣት አለብኝ፡፡
ዴሪክ የግል ወንጀል መርማሪ ነኝ ብለኸኛል አይደል?”

“አዎን” ብሏት ወደ ውስጥ ገባ እና በላስቲክ የተጠቀለለ ወንበር ላይ
ቁጭ አለ፡፡ ክፍሉን ሲመለከት ግድግዳው ላይ አንድም ፎቶ ባለማየቱ
ሴትየዋ በየጊዜው አፓርታማ እንደምትቀያይር ገባው።
“ለማን እንደምትሰራ ማወቅ እችላለሁ?”
“ይቅርታ የደምበኞቼን ሥም ለማንም አልናገርም። ማለቴ ሚስጥር
መጠበቅ አንደኛው የሥራዬ ክፍል ነው:: ግን በጣም ጨዋ እና የሰዎችን
ሚስጥር ለምትጠብቅ ሴት ነው በመስራት ላይ ያለሁት:: አንቺን ከማዘጋጃ
ቤት እንድትባረሪ ያደረጉት ሰዎች ደምበኛዬ ላይ ጥቃት እያደረሱ ስለሆነ ስለ እነዚህ ሰዎች እሷ ማወቅ ትፈልጋለች” አላት፡፡

ቲናን አይኗን በፍርሃት ጎልጉላ እያየችው “ሚ/ር ዊሊያምስ እኔ ህይወቴን እፈልገዋለሁ። እንደ ድሮ ነፃ ሆኜ መኖር እፈልጋለሁ።” አለችው፡፡.....

ይቀጥላል
👍3
አትሮኖስ pinned «#የፍቅር_ሰመመን ፡ ፡ #ክፍል_አርባ_አራት ፡ ፡ #ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን ፡ ፡ #ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው ....ኬቨን ቮስ በሴዳይ ሳናይ ሆስፒታል ውስጥ በሚገኘው የሆስፒታሉ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብሎ የፕላስቲክ ጠረጴዛውን በጣቱ እየቆረቆረ ነው:: የግል መርማሪው ደውሎ ቀጠሮ ያስያዘው ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ ነው:: አሁን 12:10 ይላል፡፡ 12:11 ሲል ደግሞ ኬቨን ቀጠሮው የውሸት መሰለው:: ምክንያቱም…»
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሦስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

የጨቅላ ልጅ ቡጢ ያህል የፈጠጠው ቁርጭምጭሚቷ ተረከዝዋ በላይ የሚገኘው ወፍራም ወጣሪ ጅማቷ በኑሮ መጎዳትዋና መጎሳቆሏን በሚገባ ለማሳወቅ የቀረቡ አስረጂዎች ናቸው።
ከሳምንት በፊት እናቴና ወይዘሮ የውብዳር ሲነጋገሩ ካመጡልኝ አይቀር
ችግረኛዋንና ምንም ዘመድ የሌላትን የራባትንና እህል እህል ያሰኛትን ነው» ብላ
አደራ ያለቻቸው ትዝ አለኝና «ችግርንና እጦትን ረሃብንና እርዛትን ማስፈራርያ
እያደረገች ልትገዛት ፈልጋ ነው» በማለት መሪር ትዝብቴን ለራሴ አዋየሁት።
መላ ሰውነቴ በርኅራኄና በሃዘን ተነካ፡፡ ልቤ በትካዜ ሟሸሸች። በሥራ ብዛት
የተደቆስኩ ያህል ሕሊናዩ ዛለ፡፡

አዲሲቷ ሠራተኛ ያሳለፈችው ውራጅ ሕይወትና የዘቀጠ ኑሮ እስከ አጥንቷ ዘልቆ ታየኝ። ነገር ግን በእኔ ዕውቀትና በአጭር ጊዜ የምርምር ችሎታ
ገና በወጣትነቷ ለጨለመው ሕይወቷ አመርቂ ፍቺ አጣሁለት። ከዚያ ቀደም
ለማንም በዚያ ዐይነት አዘኔታና ልባዊ የስሜት ጭንቀት አንጎሌ ተብሰክስኮና
ተጠቦ አያውቅም፡፡

እናቴ የሠራተኛይቱን ሰውነትና ጠቅላላ ሁኔታ በመመልከት «ውይ! ምን በወጣኝ፡ ምን በደልኩዎት! ይቺማ በሽተኛ ናት፡. አልፈልግም» ሳትል በመቅረቷ በጣም ተገረምኩ፡፡

የውብነሽ አልጋዎቹን አንጥፋ ስትመለስ ልክ አራት ሰዓት ከሩብ ሆነ፡፡ እንግዳይቱ ሠራተኛ የየውብነሽን መምጣት ስታይ ጠንቀቅ ብላ በንቃት ቆመች።
ከእናቴ በታች አዛዥ መሆንዋን ማወቋ ነበር። የውብነሽ ያን አጠር ብሉ ከርደድ
ያለ ጸጉሯን በግራ እጅዋ ይዛ እያሻሽች ከተመለከተችኝ በኋላ «ተነጥፎልሃል
መተኛት ትችላለህ» አለችኝ፡፡ እጅዋን ወደ ኋላ መልሳ ከግድግዳው ጋር ተለጥቃ
ወደ ቆመችው ሠራተኛ ዘወር ብላ «አንቺም ዕቃ ቤት ውስጥ ከዚያ ከትልቁ
በርሜል አጠገብ አንጥፈሽ ተኚ» ብላ ለማሳየት ወደ ዕቃ ቤት ገባች።
ሠራተኛይቱ ተከትላ ስትገባ ንፋስ እንደሚያወዛውዛት መቃ ወገቧ ልምጥ ልምጥ ሲል ቀዳዳው ቀሚሷ ከወዲያ ወዲህ ተወናወነ፡፡

ቁጥጥር ለማድረግ የታዘዝኩ ይመስል ተከትያቸው ገባሁ፡፡ የውብነሽ
ግድግዳው ላይ ወደ ተንጠለጠለው አጎዛ እያመለከተች «ነገና ከነገ ወዲያ ሌላ
ምንጣፍ ፈልገን እስከምንሰጥሽ ድረስ ለዛሬው ያን አጐዛ እዚህ ወለሉ ላይ ጣል
አድርጊና ተኚ። አይዞሽ አትፍሪ፡ ትለምጃለሽ» አለቻት፡፡

ሠራተኛይቱ አጐዛውን ከተንጠለጠለበት ምስማር ላይ ተንጠራርታ አወረደችው:: አጐዛው መኻል ላይ ቁልቁል የተሸረከተ የሕፃን ጭንቅላት የሚያሾልክ ትልቅ ቀዳዳ አለ። ቀዳዳውን እንዳየሁ አንድ ነገር ትዝ አለኝ።
የቤታችን ዘበኛ የነበረው ዘለቀ በግ ሲገፍ ሳት ብሎት ቆዳውን በሹል ቢላዋ ስለ
ሽረከተው አባቴ በዚያች የተነሣ ከሥራ እንዳባረረው ታወሰኝ። ከውስጣዊ
ፍርሃትና ጭንቀት የተነሣ ያ ከሲታ ፊቷ ከመጠን በላይ ጠውልጐ ይብስኑ
ሕይወት አልባ መሰለ።

«እስኪ ትንሽ አራግፈው እለች የውብነሽ በፊቷ ላይ ጥርጣሬ እየታየ፡፡
ገና ሁለት ጊዜ መታ መታ እንዳደረገችው ያንጠለጠለችው እዛ እምልጧት
ወደቀ። አጐዛው ላይ የነበረው አቧራ በመጠኑ ቦነነ ።ደንግጥ እነሣችው::
የውብነሽ አቧራውን እየተጸየፈች እስኪ እንደገና ቀስ ብለሽ መታ መታ
አድርጊው» አለቻት፡፡ ሠራተኛይቱም ከእኛ ለመራቅ ያህል ወደ ኋላ ፈግፈግ ብላ
በወዙ በኩል ሦስት አራት ጊዜ መታታችው። ልሙ ኣቧራ ወርዶ እግሯን
አለበሰው፡፡ ዕቃ ቤቱ በአቧራ ቡናኝ ተሞላ እህቴ አፍና አፍንጫዋን በቀኝ እጇ
አፈነች። ሠራተኛይቱ የአቧራው መቡነን እኛን የሚያስቆጣን ስለ መሰላት ብናኙን
እፍ እያለችና በእጅዋ እያራገበች ለማራቅ ሞከረች። አጐዛውን ከትልቁ በርሜል
ሥር ጣል ካደረገችው በኋላ ዱር አማከለች የምታነጥፈውን አሮጌ ብርድ ልብስ አጣጥፋ አስተካከለችው፡፡ ጎንበስ ቀና ባለች ቁጥር ጉልበቷ ይንቋቋል። የውብነሽ ወደ እኔ ጠጋ ብላ ለምን ታሳፍራታለህ? ሂድ እንጂ እነጣጥፋ ትተኛበት አለችኝ፡፡ «አንድ ጊዜ እንዳይ ብዩ ነው እንጂ እሺ እሄዳለሁ» ብዬ ዐይኔን ወደ ወለሉ መለስኩት፡፡ በአሮጌ ቀሚስ የተጠቀለሉ ጨርቆች መኝታው መኻል ላይ ጣለች፡፡ ወዲያው ነጠልጠል ስታደርገው ቀደም ብዩ ካየኋቸው ይበልጥ በጣም የቆሸሹና የተቀዳደዱ ቀሚሶችና ጨርቆች ወጡ፡፡ ከሁሉም ጐላ ብሎ የሚታየው ግን እንድ ጠርዝ ጠርዙ የተሸነታተረ ዐመድማ ስስ ብርድ ልብስ ነበር፡፡

ተንበርክካ ቀሚሶችዋን ካጣጠፈች በኋላ ለትራስ እንዲሆኑ አንድ ላይ ሽበለለቻቸው፡፡ የእኔ ልብ በሥቃይ ታፍና በሃዘን ስትቀዘቅዝና ጅማቴ ሲኮማተር
ተሰማኝ፡፡ ጉንበስ ቀና ባለች ቀጥር በስተኋላዋ ያለው የቀሚሷ ትልትልና ቀዳዳ ያንን ሸካራ ገላዋን በከፊል ያሳያል። እኅቴ እነዚያን የተበታተኑ ልብሶች
እየተመለከተች «ለመሆኑ ይኸ ልብስሽ ተባይ የለበትም?» ብላ ጠየቀቻት።

በእንግድነት ኃፍረት የተሸበበው አፍዋ ዝምታን ማመቅ እንጂ ቃላት ማውጣት
ስላልሆነላት ዝም አለች፡፡ እንግዳይቱ ሠራተኛ ግን አሮጌውን ልብስ አንዴ
ወረቀት ከሽመለለችው በኋላ የእግርዋን ትቢያ ሳታራግፍ መኝታዋ ላይ
ተቀመጠች። የተጠቀለለውን ብርድ ልብስ ሳብ አድርጋ ጉልበቷን ሽፈነችው።
ተጣጥፈው በስተኋላዋ ለትራስነት የተጠቀለሉት ልብሶችዋ ማቃጠያ ውስጥ
ተከማችተው የተቃጠሉ ወረቀቶች ይመስላሉ። ግንጭሏ የታጠፈውን ጉልበቷን እስኪነካ ድረስ ካቀረቀረች በኋላ ቀሚሷን አወለቀች፡፡ ከላይኛው ቀሚሷ የባሰበትና በጣም ያረጀ የውስጥ ልብስ ብቅ አለ።

ትከሻዋ ላይ ያለው ማንገቻ ረዝሞ
በመቋጠሩ እብቱ የቄብ እንቁላል ያህላል። በእድፍ የተሰላው ልብሷ ምን ዐይነት ቀለም እንደ ነበረው አይለይም። ቀሚሷን ስታወልቅ ያንን ዐመድ መስሎ
የተጐሳቆለ ጸጉሯን ሸፍኖት የነበረው ሻሽ ከቀሚሷ ጋር ሾልኮ ዱብ አለ፡፡ አጉሯ
ወደ ፊትና ወደ ኋላ ተመነጫጨረ።አንዱ ዘለላ ጥምል ቀለም መሳይ አንገቷ
ላይ ተጥመልምሉ ወረደ። ጸጉሯ ላይ ነውር ነገር የታየበት ይመስል በጣም
ደነገጠች። ወዲያው እየተርበተበተች በዚያው በሻሽ ሸንከፍ አደረገችው። ብዙ
የኑሮ ጉስቁልና ስለ ደረሰባት የአፍላ ወጣትነቷ ጠይም ውበት ወደ ሸካራ
ጥቁረት ተለውጧል፡፡ እህቴ ያን የመሰለ ፀጉር በማየቷ በአድናቆት ተመስጣ
በውስጣዊ የቅናት ጸገግታ ተመለከተቻት:: እኔ ግን በጣም ስላሳዘነችኝ በትካዜ እንባ ባቀረሩ ዐይኖቼ ሁኔታዋን አጤንኩት። አሮጌውን የብርድ ልብስ ሳብ አድርጋ እስከ አጐጠጐጤዎቿ ካደረሰችው በኋላ ተኮራምታ ስትተኛ ጭብጥ አከለች።

የውብነሽ «ወንድም ጋሼ አንተ ብትፈልግ ቆመህ እደር፡ እኔ ምን በወጣኝ ነው» ብላ ጥላኝ ሄደች። እኔ ግን ያቺን ከፊት ለፊቴ ከበርሜል ሥር ከላይ አዳፋ ደርባ ከታች የቆሽሽ ልብስ አንጥፋ የተኛችውን ሴት ትክ ብዬ እያየሁ ሦስት ደቂቃ ያህል ቆምኩ፡፡ ለጊዜው አጥጋቢ ትርጉምና ምክንያት ያላገኘለት የሐሳብ ሞገድ አእምሮዬ ውስጥ ተነሣ፡፡ ልወጣ አቅራቢያ እንደ ራባት የውሻ ቡችላ በቀጭኗ ተንፍሳ ገልበጥ አለች። ከዚያም ምንም እንኳ የብርድ ልብሱን ዐልፌ ማየት ባልችልም እንቅስቃሴዋን ተከታተልኩ። እጅዋ ወደ ጀርባዋ ከዞረ በኋላ ከገላዋ ላይ የሚገለፈፍ ነገር ያለ ይመስል ጥፍሮቿ ያን ሲሰሙት ብቻ በድምፁ የሚያስታውቅ ሸካራ ጀርባዋን ማከክ ጀመሩ፡፡ ወዲያው ሥቃይና የስቅቅታ ፍርሃት የረመጠጣት ቀጭን ሳል ኃይሏን ወለሉ እየዋጠው ሁለት ጊዜ ተሰምታ እየሰለለች ወደመች፡፡ ከዚያ በኋላ ገመምተኛ ፀጥታ በመተካቱ መብራቱን አጥፍቼ ወጣሁ፡፡

አንጐሌ ውስጥ በቂ ኀዘናዊ ትርዒት አጭቄ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ፡፡
የመጀመሪያው ቀን በዚህ ሁኔታ ተፈጽሞ ዘልዓለም ወደማይመለስበት የትዝታ
ክልል ገባ፡፡
👍4
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በማግሥቱ ሰኞ ማለዳ በመስኮት በኩል ስመለከት ከዋናው ቤት በሰሜን ምዕራብ ሲል ባለው ገላጣ ሥፍራ ላይ አንድ አገር ልብስ ተቆልሏል፡፡ ውሃ በሁለት ትልልቅ ባሊ ተሞልቶ ተቀምጧል፡፡ አዲሲቱ ሠራተኛ በአንድ ሰፊ ብረት ምጣድ ላይ ልብስ ታጥባለች፡፡ የማለዳው ውሃ በጣም ቀዝቃዛ በመሆኑ ውርጩ ስለቆረጠማት እጅዋን ወደ እሷ አስጠግታ «እህህህህ» እያለች በትንፋሽዋ ታማሙቀዋለች፡፡ የቀረበላት የልብስ ብዛት በአንድ ቀን ውስጥ ታጥቦ የሚያልቅ አይመስልም፡፡ እንኳንስ ሊሠሩት በጣታቸው የማይነኩትን ሥራ ማሽከም የሚቀናቸውን ቤተሰቦቼን ታዝቤ ወጣሁ።

ጉዳዩ 'የሰው በልቶ…” ሆነና ቀን ለምሳ ወደ ቤት ስገባ ልብሶቹ ሁሉ ታጥበው በሁለት ረጃጂም መስቀያ ገመድ ላይ ተሰጥተዋል። ወደ ቤት ገባ ስል
አዲሲቱ ሠራተኛ ነጣ ያለች ትንሽ እራፊ ጨርቅ ይዛ የእንግዳ መቀበያ ክፍሉን
የዳርቻ መስኮት ስትወለውል ደረስኩ፡፡

ማን መሆነኔ ለማለየት የፈለገች ይመስል መለስ ብላ አየችኝና ወዲያው
አንገቷን ሰበር አድርጋ ሥራዋን ቀጠለች፡፡

ቀይ ጥለት ያለበት ቦርቃቃ ቀሚስ
ለብሳለች። የእናቴ ነበር፡፡

እናቴ በመጠኑ ደርጀት ብላ ሳይበዛ ወፍራም ስለሆነች ሠራተኛይቱን ዶሮ በጋን አስመስሏታል። በቀጭን ጨርቅ ሰቅስቃ ስለታጠቀችው ጉንፉ በሆዷ ላይና በስተጀርባዋ በኩል በንፋስ የተቀተተ ወናፍ መስሏል። ቀሚሱ ባለ ሙሉ እጅጌ ስለሆነ ያቺ ቀጭን እጅዋ በስልቻ ላይ ተሰክታ የታሠረች ማማሰያ መስላለች።
ሻል ያለ ድፍን አረንጓዴ ሻሽ ጥለውላታል። ገና ስገባ ስንዴ እየለቀመች ያየችኝ
አስካለ ምሳዬን አቀርባልኝ ተመለሰች፡፡ ያለ ልማዱ እንግዳ መቀበያ ክፍል ዳርቻ
ላይ ተቀምጦ ያንኑ የሕግ መጽሐፍ የሚያገላብጠው አባቴ መላ ሐሳቡ ከአካባቢው ሁኔታ ውጪ ሆኗል። በንባብ ላይ ሲሆን ዐመሉን ስለማውቅ ሰላምታ
አልሰጠሁትም። ደግነቱ ሁልጊዜ የሚያነብበው መኝታ ቤት ውስጥ በመሆኑ ዘወትር በዚያ አካባቢ ለምንቀመጠው ቤተሰቦች ችግር አልነበረብንም። እርሱ ባለበት አካባቢ እንደበታችን ይለጉማል። የሕግ ጉዳይና የፍርድ ቤት ንትርክ ፅሑፎችን ለማንበብም ሆነ ለመከታተል ስለማልፈልግ በዚሁ የተነሣ ከአባቴ ጋር
እጅግም አንቀራረብም።

«ትምህርት ይሉሃል ሕግ ነው፤ ሌላ ሌላው ሁሉ ቅጥያ ነው፡፡ እኔ እንኳ
ከብዙ ልፋትና ልምድ በኋላ ይኸው ዛሬ የማልቀመስ እሳት የላሰ ዳኛ ሆኛለሁ”
ሲለኝ አንዳንድ ቀን እሱና ጓደኞቹ ነግር ሲተበትቡ ስለምሰማ ውስጤ በንዴት
ይተናል፡፡ ተከራክሬ ሐሳቤን ለመግለጽና ለማብራራት ስለማይፈቅድልኝና «ከረ
ይኸ ዓይን አውጣ! ስድ አደግ!» ስለምባል ያሰብኩትን ሁሉ የፍርሃት ደሪባ
ደፍቼበት ዝም እላለሁ፡፡ ከሁሉም ከሁሉም የሚያበሳጨኝ ግን አባቴ በማይረባው ነገር ሁሉ እየተቆጣ በልጅነቴ ይገርፈኝ የነበረው ነው፡፡

ከየትም ከትም እየተሰባሰቡ ሠፈር ለሠፈር ከሚማግጡ ልቅምቃሚዎች
ጋር ሲያውደለድል ዋለ ተብሎ ለአባቴ የተነገረ ዕለት የሚጠብቀኝ የሚያርበደብድ የዓይን ግልምጫና ቅጣት አይጣል የሚያሰኝ ነበር።

«እኔ እኮ ምን ባደርግ ይሻለኛል? የሰው ልጅ ካንድም ሁለት ሦስት ጊዜ ይነገረዋል፡፡ ያንተ እኮ ሠርክ ሆነ፣ ከጨዋ መኻል ሰው መርጬ ከእነማን ጋር
መዋል እንዳለብህ ከመንገር አልፌ ምን ላድርግ? ከግራዝማች ሙሉጌታ፣
ከፊታውራሪ እሸቴ፣ ከቀኛዝማች ቃለአብ ልጆች ጋር ወስጄ አስተዋወቅሁህ!
ያንተ ከማንም ብራሪ ጋር መግጠም ምን ይባላል?» ብሎ ክፉኛ ገርፎ በእግር
ብረት ታስሬ የዋልኩበት ቀን ምን ጊዜም ትዝ ሲለኝ ይኖራል፡፡

እባቴ ያስተዋወቀኝ ሰዎች ልጆች ከየቤታቸው እንደ ልባቸው ወጥተው
ስለማይጫወቱ ጠላኋቸው:: የሠፈር ውስጥ ድብቅ ጓደኞቼ ግን እንደ ልብ
የሚጫወቱና የሚዛለሉ፣ ያንን መንገድ አለፋችሁ ቀበናን ተሻገራችሁ የማይባሉ
ስለ ነበሩ ከነእርሱ ጋር ለመዋል እና እንደነሱ ነፃ ለመሆን በጣሙን እጓጓ ነበር፡፡

እባቶቻቸው አናጢና ግንበኛ ከነበሩት ከአበራና ከረዳ ጋር በጣም እንቀራረብ ነበር፡፡ በተለይም አባቱ፡ የሐኪም ቤት ዘበኛ ከሆኑት ከአማረ የኋላሸት
ጋር በጣም እንፋቀር ነበር፡፡ ከእነርሱ መኖሪያ ቤት ይልቅ የእኛ ማድበት በጣም
የተሻለ ቢሆንም አማረ ኃፍረት አይሰማውም፡፡ «አቤት የናንተ ቤትና ግቢ ደስ ሲል! የኛ ቤት፣ የነአበሪ ቤት ሊፈርስ ነው አሉ፡ እሌላ ሠፈር ብንሔድ
ትመጣለህ? እኔ እመጣለሁ» እያለ ስለ መለያየት ነገር ሲያነሳብኝ ሆዱ ይባባ
ነበር አንዳንድ ቀን በሹልክታ ወደ ግቢያችን ይዤው እገባና ምድር ቤት ውስጥ ደብቄ የማቆይለትን ወጥ የነካካው ፍርፋሪ ቶሎ ቶሎ እንበላላና በመጨረሻም ከየጆንያው ላይ ከፈሰሰው ሽምብራና ባቄላ ኪሶቹን ሞልቼለት ተደብቀን እንወጣለን። እቤታችን ድግስ ተደግሶ የሠፈር ልጆች በትላልቅ ዝርግ ሳህን ፍርፋሪ ቀርቦላቸው እየተንጫጩና እየተሻሙ ሲበሉ አብሬ መብላት
ስለማይፈቀድልኝ አንጀቴ በንዴት እርር ይል ነበር፡፡ ዛሬ የእኔንና የእነዚያን
ልጆች አስተዳደግ ሳነጻጽረው ልዩነቱ የሰማይና የመሬት ያህል ይራራቃል። አንድ ጊዜ በክረምት ወራት እነ አማረ ቤት የምደብቃትን ጅራፈን ሳጮህ ሰንብቼ
የቡሄ ዕለት ማታ ከሆያ ሆዪ መልስ ገና ላይን ሳይዝ ከአማረ ጋር ሙልሙላችንን
እየገመጥን ወደ ቤት ሲሸኘኝ የቤታችን ዘበኛ ድንገት ደርሰው አፈፍ አደረጉኝ፡፡
ከዚያ በኋላ የሚጠብቀኝን ነገር ስለማውቀው ገና ከሩቁ ሽንቴ መጣ፡፡ እንባዬ ዱብ ዱብ አለ፡፡ እማረ ከኋላ ኋላችን እየተከተለ «አባባ አትናገሩበት! አባባ እዚሁ ነው ያገኘሁት በሉለት! ያሥሩታል እኮ! ይመቱታል እኮ» እያለ
ለመነልኝ:: ትልቁን የግቢ በር ከፍተን ስንገባ ግን እያለቀሰ ቆሞ ቀረ፡፡ የፈራሁት
አልቀረም፡፡ አባቴ እጅና እግሬን አስሮ የዋልክበትን እና ያደረግሁትን ሁሉ
አስወተወተኝ::

የማንም ጭቅትም ጭቅቅቱን ሲያንጨፈጭፍበትና የማንም እከካም
ሲንቦጫረቅበት ከዋለው ውሃ ውስጥ ማን አባክ ግባ አለሀ?! ደግሞ ከማንም
ውርጋጥ ጋር ሆያ ሆዬ ሲባልልኝ ተውሏል! ቆይ! አረ ገና ምን አይተህ!» ብሎ አይቀጡ ቅጣት ከቀጣኝ ወዲህ ያቺኑ አልፎ አልፎ ወጣ ወጣ የማለት ድብት ነጻነቴን ቀስ በቀስ አጣኋት፡፡....

💫ይቀጥላል💫
👍3👏1
#የወድያነሽ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


...ከማንም ውርጋጥ ጋር ሆያ ሆዬ ሲባልልኝ ተውሏል! ቆይ! አረ ገና ምን አይተህ!» ብሎ አይቀጡ ቅጣት ከቀጣኝ ወዲህ ያቺኑ አልፎ አልፎ ወጣ ወጣ የማለት ድብቅ ነጻነቴን ቀስ በቀስ አጣኋት፡፡

ከአባቴ ፊት ለፊት ቆሜም ሆነ ተቀምጨ የታየኝን መናገርና እንደ ልብ
መዝናናት እንደ ቅብጠትና ብልግና ስለሚቆጠር ፍርሃት ያልሞሰሞሰው ለጋ
መንፈሴ ሥቃይ ፈጥሮብኛል...

አባቴ ተነሥ ግባ የተባለ ይመስል ድንገት ተነሥቶ ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ። አባቴ በመሆኑ ባልጠላውም ተነሥቶ በመሔዱ ቀለለኝ፡፡

እንዲት አነስተኛ ጥፋት ባጠፋሁ ቁጥር በመመከርና በልዩ ዘዴ በመገሠጽ ፈንታ የምቆነጠጥና የምሠታ ስለሚመስለኝ ትንሽ የልጅነት ጥፋት ባጠፋሁ ቁጥር ፍርሃት ይንጠኝ ነበር፡፡

አንድን ነገር ለማሰብ ሳይሆን ያሰብኩትን ትክክለኛ ነገር ለመፈጸም ወኔ የሚከዳኝ በዚህ ስውር ጫና የተነሣ ነው::

መገረፍና መቆንጠጥ ከቀረልኝ ጥቂት ዓመታት ዐልፈዋል፡፡ ሆኖም ያ በልጅነቴ በፍርሃት የተበከለውና በቁጣ የበለዘው አንጎሌ ለብዙ ዓመታት ያህል ሊሽር አልቻለም፡፡

ምሳዩን በልቼ ስጨርስ ስምንት ሰዓት ከኻያ ደቂቃ ሆናል። እንግዴ መቀበያ ክፍል ውስጥ የሚገኘውን ትልቅ ራዲዮ ድምፁን ዝቅ አድርጌ ከፈትኩት። የአምባሰል ሙዚቃ ይዘፈን ነበር፡፡

አስካለ እንጀራውን ካነሣች በኋላ የእጅ ውሃ ይዛልኝ ተመለሰች።

«ውሃውን አስቀምጠሽ ሂጂ» ስላልኳት አስቀምጣ ሄደች። እጄን ሳልታጠብ ተነሳሁና የሙዚቃውን ሥልታዊ አነሳሥና አወዳደቅ እየተከተልኩ አንድ ቦታ ላይ ቆሜ ንፋስ እንደሚያወዛውዘው የመቃ ቀምበጥ ተወዛወዝኩ፡፡
የአዲሲቱ ሠራተኛ ከሲታና ጠውላጋ ፊት በጥቂቱ ፈገግ ሲል ታየኝ። እንደ
ኮቸሮ ደርቆ የተንቀፈረረው ከንፈሯ ላመል ታህል ተላቀቀ። አቀማመጣቸውና
ቅርፃቸው ቁመትና ስፋታቸው ከጠባቧ ፍንጭት ጋር ልብን የሚማርኩና ስሜትን
የሚያረኩ ጥርሶች ታዩ። በመጠኑ ወየብየብ ብለው ጐድፈዋል። ውበትን ጥቁር ደመና እንደ ጋረዳት ጨረቃ በፊት ለፊቴ አድፍጦ አየኋት፡፡ ደካማ ፈገግታዋ
ግን ወዲያው በንና ጠፋች።

የትዕዛዝ ሳይሆን የልመናን ሁኔታ በምትገልጽ ድምፅ «ለእጄ ውሃ
ብትስጪኝ?» ብዬ ጠየቅኋት። መወልወያውን መሬት ጣል አድርጋ መጣች፡፡
ማስታጠቢያውን አንስታ በቀጭኑ አንቆረቆረችልኝ:: ያን ከሩቅ ያየሁትን ጸጉሯን ከቅርበት እስተዋልኩት፡፡ አንዲት ነቀዝ መሳይ የራስ ቅማል በዞማው ጸጉሯ ላይ ስታዘግም ቆይታ፡ ወዲያው ፍልቅ መሸጐጫ አግኝታ ተሸጐጠች፡፡ ልቤ ግራር ፍም ላይ እንደ ወደቀች የጮማ ምታሪ በተመሰቃቀለ ስሜት ሟከከች፡፡ የአካላቷ ጠረን እጅግም ደስ ሳይለኝ አስታጥባኝ ሄደች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዋል እደር እንዳለች የተሰጣትን ሥራ ሁሉ በጥንቃቄ መሥራት በመቻ መላው ቤተሰብ ደስ ተሰኘ፡፡ ዋናው ምድብ ሥራዋ ግን የቤተሰቡን ልብሶች ማጠብና የምትችለውን መተኮስ ሲሆን አልጋ ማንጠፍና ቤት መወልወል ተጨማሪ ሥራዋ ነበር፡፡ ሰው ሁሉ ወደዳት። ትሕትናዋና ታዛዥነቷ ለተወዳጅነቷ
ዋና ምክንያት ነበሩ፡፡ ከመዋል ከማደር ከሲታው አካላቷ ሥጋ በመደረሱና
ደሟም መለስ በማለቱ በሦስት ወር ውስጥ መለል ብላ የምትታይና ማለፊያ
ፈገግታ ያላት አንገተ ሰባራ ወጣት ሆነች፡፡

ስለ ሠራተኛይቱ አሠራርና አስተያየት የነበረኝ ግምት ሁሉ ከቀን ወደ
ቀን ተለወጠ። ማንኛውንም ለእኔ የሚያስፈልገኝን ነገር ሁሉ እሷው እየሠራችና እያዘጋጀች እንድታቀርብልኝ ሙሉ ፍቃዴና ፍላጐቴ ሆነ፡፡ የልብሶቼን መቆሸሽና ያለመቆሸሽ እሷው ራሷ እየተመለከተች የተቻላትን ያህል ማጠብ አንዱ የሥራዋ ክፍል ለመሆን በቃ፡፡ ከዕለት ወደ ዕለት ትሁት አቀራረቧና ሥራዋ ሁሉ አስደሰተኝ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እህቴ ኖረችም እልኖረችም ራቴንም ሆነ ምሳየን የምታቀብርልኝ እሷው በመሆኗ ጠባይዋንና ሁኔታዋን በየጊዜው ለማወቅና ለመረዳት ቻልኩ፡፡

በአማከለች የእኩል ነኝ ባይነት» ንግግር አንጀቷ አርሮ የነበረው እናቴ እንደ ልብ ታዛዥና አቤት እመት የምትል ሠራተኛ በማግኘቷ ካሰችኝ እያለች ስትጠራት ጥቂት ልደታዎች አለፉ፡፡

ሰው ሁሉ ስሟን ጠይቆ ለማወቅ የፈራ ይመስል በማናውቀው በዋናው
ስሟ ሳትጠራ ከስድስት ወራት በላይ ዐለፉ፡፡ ትልቁም ትንሹም «አንቺ ልጅ
ወይም «አንቺ እንግዳይቱ» እያለ ስለሚጠራት የቀድሞ ስሟን የረሳች ወይም ስም የለሽ አስመሰላት፡፡

እሑድ አራት ሰዓት ገደማ ነበር፡፡ ቀላል የራስ ምታት ወረር ስላደረገችኝ
ከመኝታዩ ላይ ሳልነሣ አረፈድኩ፡፡ ተነሥቼ የወጣሁ ስለ መሰላት አልጋ ለማነጣጠፍና ክፍሉን ለመጠራረግ በቀስታ እያንጎራጎረች ዘው አለች። ቀጥ ብዬ በጀርባዬ ተንጋልዩ ስለ ነበር አልጋው ላይ ሰው ያለ አልመሰላትም፡፡በእንጉርጉሮ
የምታስኬዳትን ዜማዋን ሳታቋርጥ የብርድ ልብሱን መኻል በእጅዋ ነካችው።
ለአፍታ ያህል ጸጥ ብዬ ሳዳምጥ ከቆየሁበት ብርድ ልብስ ውስጥ ከመቅጽበት ራሴን ብቅ ሳደርግ በድንጋጤ ፈዝዛ ቆመች፡፡ አቀርቅራ ጥቂት ዝም ካለች በኋላ
“እኔ እኮ ወደ ውጪ የወጡ ስለመስለኝ ነው የገባሁት ብላ መሬት መሬቱን
ማየት ቀጠለች።ድንጋጤዋ እንዲለቃትና ፍርሃቷ እንዲወገድላት በማሰብ
ለጊዜው በዚያች ሰዓት የማያስፈልገኝን «እስኪ ሂጂና ለፊቴ ውሃ አምጭልኝ
ብዩ አዘዝኳት። እንዳቀረቀረች ወጣች። የውስጥ ቁምጣዬን እንዳጠለቅሁ እና ነጭ እጀ ጉርድ የውስጥ ጥብቆ እንደለበስኩ ብርድ ልብሱን ወደ ግርጌ ሽብልዩ ደረብኩና አልጋዬ ጫፍ ላይ ዐረፍ አልኩ፡፡ ለብ ያለ ውሃ በንጹሀ
ማንቆርቆሪያ ይዛ ተመለሰች።

በግራ እጅዋ የያዘችው ቀለሙ የተላላጠ እሮጌ ነጭ ሳሀን ዐልፎ ዐልፎ የተላከከና የማይለቅ እድፍ ነበረበት፡፡ ጋቢውን ከላዩ ላይ ገፍፌ አልጋው ላይ አኖርኩት፡፡ ማንቆርቆሪያውን እንዳንጠለጠለችና ሳሀኑን እንደ ዘረጋች ፊቷን ወደ ጎን አዙራ ቆመች። ራቁቴን የቆምኩ ስለ መሰላትና አለማፈሬም ስላስደነቃት የተገላቢጦሽ እሷ ማፈሯ ነበር፡፡ በቤታችን ውስጥ ሰው ባለመኖሩ በሩን ዘጋሁት።
አሁንም ፊቷ ወደ ተዘጋው በር እንደ ዞረ፡ ከመጠን በላይ አቀርቅራና በሙሉ
ዓይኗ ሳታየኝ አስታጠበችኝ፡፡ ያንቆረቆረችልኝ ውሃ አወራረድ እስከ መጨረሻ ሳይለወጥ ተንቀረቆረች።አፌን ለመጉመጥመጥ እንደ ፈለገ ሰው ጣቶቼን ቀልብሽ መዳፌን ውሃ ለማቆር እስኪችል አጐደጐድኩት። ውሃ እንድታንቆረቁርልኝ እጄን ዘረጋሁ። በዝግታ አንቆርቁራ ሞላችልኝ። አቀርቅራ ስታይ በሳህኑ ውስጥ የሚገኙትን የሳሙና አረፋዎች የምትቆጥር ትመስል ነበር፡፡ ጸጉሯ በሻሽ ባለመሸፈኑ በእጄ ላይ ያቆርኩትን ውሃ በዝግታ ጸጉሯ ላይ እንጠባጠብኩት፡፡ምንም እንኳ ውሃ እንዳፈሰስኩባት ወዲያውኑ ቢሰማትም ቀና ብላ አላየችኝም፡፡ቆየት ብላ ግን ራሷን እየነቀነቀች «እችክእችክ እችክ» ብላ ዝም አለች። ነገር ግን ባፍንጫዎ በኩል የተሰማችው ለዛማ ቀጭን የሣቅ ድምፅ መሣቋን አሳወቀችባት።
ውሃው በግንባሯ በኩል አኳልሞ ቁልቁል ወረደና ወለሉ ላይ ተንጠባጠበ፡፡
የፈገገውን ጠይም ፊቷን ለመመልከት በጣም ካጎነበስኩ በኋላ እንገቴን ወደ ጎን
ቆልምሜና ፊቴን ጋደል አድርጌ አሻቅቤ በማየት የፈገግታዋን መጠን ለካሁ፡፡
«ስምሽ ማን ነው? እስኪ ንገሪኝ?» ብዩ የአካላቴን አኳኋን ሳልለውጥ ጠየቅኋት።
አሽቆልቁለው ጉንጩን የሚመለከቱት ዐይኖቿ በሰፊው ከተከፈቱ በኋላ የማለዳ
ፍንድ አበባ የሚመስሉ ከንፈሮቿ ተላቀቁ፡፡ ቀጠን ብላ ቃናዋ እጅግ በሚማርክ
ድምፅ የወዲያነሽ» ብላ ከንፈሮቿን ወደ ውስጥ ቀልብሳ መጠጠቻቸው። ቀና
ብዩ በትክክል ቆምኩ፡፡ ልቤ ባንዳች የድንጋጤ ኃይል የተናወፀች ይምስል
👍91
ዷዷታና ንዝረቷ ተለወጠ፡፡

ስሟን በማወቄ ብቻ የመነሻው ምክንያት ያልተከሠተልኝ ሥውር ግን ብሩህ የሕሊና ደስታ ተሰማኝ፡፡ መላ ሰውነቴ ልገልፀው በማልችል ስሜት ተፍነከነከ፡፡

ማንቆርቆሪያውንና በጐድጓዳ ሳህን ውስጥ የነበረውን እጣቢ ይዛ ወጣች
ተልካ ስትመጣም ይሁን ወይም ባጋጣሚ ጉዳይ ጋሽ ጌታነህ ብላ በአንቱታ ስትጠራኝ በአክብሮቷ ሳይሆን ከድምጿ ለዛ ጋር አንቱ በማለቷ ብቻ
በእጅጉ ወደድኳት፡፡ስለ ቤት ሠራተኞች ሥራ ምንም የማያውቀውና ደንታ የሌለው አባቴ እንኳ ሲወራ በሰማው ትጉህ ሠራተኝነቷና ታዛዥነቷ ተደስቶ አንድ ሁለቴ ያህል አመስግኗል እናቴም በበኩሏ ከዚያ ቀደም ለማንኛዋም ሠራተኛ አሳይታ የማታውቀውን ደግነትና ቀረቤታ አሳይታለች። እናቴ ቀደም ሲል ያረጁ
ቀሚሶችዋንና ልብሶችዋን የምትሰጠው ላንዳንድ ድሃ ጐረቤቶቻችንና ለሌሎች
'የድሃ ዘመዶቼ ለምትላቸው ነበር፡፡

ዛሬ ግን በመጀመሪያ ተመርጦ የሚሰጠው ለየወዲያነሽ ሆነ፡፡ ከነባሮቹ
ሠራተኞች ጋር ባንዳንድ በጋርዮሽ በሚሠሩ ሥራዎች ካልተገናኙ በስተቀር
በማንኛውም ጊዜ እንዳትጠጋቸው ብዙ ጊዜ በጥብቅ ተነግሯታል፡፡ ምንም እንኳ
ረቂቅ የሆነ የበታችነት ስሜት ውስጥ ውስጡን ቢያነክታትም አብዛኛውን ጊዜ
የምታወራውና የምታቧልተው ከየውብነሽ ጋር ሆነ። ጠባይ ለጠባይ በደንብ እስከ
መተዋወቅና እስከ መግባባት ደረሱ፡፡ በእሷና በየወዲያነሽ መካከል ያለው
ግንኙነት ከዕለት ወደ ዕለት ደራ፡፡ መላ ቤተሰባችን እንደ ወደዳትና እናቴም
እሷን እኮ እንደ ልጄ ነው የማያት፡ ትሕትናዋ ብቻ ይበቃል» እንዳለች ዘጠኝ
ወሯ እንደ ዘጠኝ ቀን ዐለፈ።

የየወዲያነሽ አካላዊ ቅርፅና እቋም እየተስተካከለ አማረ፡፡ የተፈጥሮ ውበቷና ቁንጅናዋ ከያደፈጡበት ፉካ ቀስ በቀስ እያዘገሙ ወጡ፡፡ ጉንፎቿ ሞላ ብለው በትንቡክቡ የወጣትነት ደምና ሥጋ ጠረቁ። ምርጊቱ ተገሽልጦ እንደ
ወደቀ ግድግዳ ፈጥጦ የነበረው አጥንቷ በሥጋ ተሞልቶ በመጠርቃቱ ማለፊያ
ወጣት ሆነች፡፡ ድፍርስና ስርግ የነበሩት ዐይኖቿ ቅላታቸው ተገፍፎ በመጥራቱ፡
እንደ ውድቅት የጨለማ ውስጥ ጧፍ ቦግ ብለው ወጡ፡፡

ከሁሉም በላይ ደስ የሚያሰኘውና የሚማርከው ግን ፈገግ ብላ ስትሥቅ
ጠይሙ ጉንጫ ላይ ጉድጎድ ብለው የሚሰረሞጡት ድምብሉቿ የውበቷ ልዩ
ምንጮች ናቸው:: ያ ያረጀ ሞረድ ይመስል የነበረው ክንዷ እንደ መዳመጫ ድንጋይ ለስልሶ ውብ ገላ ሆነ። የውብነሽ ሁለትና ሦስት ገዜ ያሀል ከልብሶቿ መኻል የማይሆኗትንና ያረጁባትን መራርጣ ስለሰጠቻት የእናቴን ቦርቃቃ
ቀሚሶች አውልቃ ጣለች።

እኅቴና የወዲያነሽ በቁመትና በአካል መጠን አይተናነሱም፡፡ በዕድሜም
ቢሆን በጣም ተቀራራቢ ናቸው:: አብረው ሲቀመጡም ሆነ አጥር ግቢው ውስጥ
ከወዲያ ወዲህ ሲሉ በጣም ያምርባቸዋል። የወዲያነሽና እኅቴ ሲጠራሩ «አንቺ ስለሚባባሉ ጓደኝነታቸው እያደር ጠበቀ። የአንዳንድ ተራ ጉዳዮችም ምስጢረኛች የወዲያነሽ የተጣለላትን ልብስ ለብሳ ከየትኛውም አቅጣጫ ብቅኸ ስትል በውበቷና በደም ግባቷ ልቤ ክፉኛ መደንገጥ ጀመረ። አንዳንድ ቀን ያንን ጥቁር ዞማ ጸጉሯን ባራትና ባምስት ኣቅጣጫ በቀጭኑ ጐንጉና ትለቀዋለች።
የአጐናገኑን ዘዴ በመውደድ ዓይን መከታተል ልብ ያላልኩት ተግባሬ ሆነ፡፡

ደረጃ ስትወጣም ይሁን ስትወርድ የአካላቷ ንቅናቄና አካሒዷ ፀጉሯን ከወዲያ ወዲህ ሲያዘናፍለው የንፋስ ሽውሽውታ እንደሚያንቀሳቅሰው እንደ ለመለመ የወይን ሐረግ ቀንበጥ ደስ ይላል።

አልጋዬን ለማንጠፍ መኝታ ቤቴ በገባች ቁጥር የተዝረከረኩና የተበታኑ
መጻሕፍትና ወረቀቶች ሰብስባ ስለምታስቀምጥልኝ የግሌ ሠራተኛ ትመስል ነበር፡፡ወይዘሮ የውብዳር ወደ ቤት በመጡ ቁጥር ስለ እርሷ ጠባይና ሁኔታ እንዲሁም ታማኝነት ሳይጠይቁና
እ ..ሀ” ሳይሉ አይሔዱም፡፡

ከየወዲያነሽ ሳይሆን ከእናቴ ምስጋና ለማግኘት ሲሉ «ኪዳነምሕረትን፣ አቤት! ዛሬስ በጣም አምሮብሻል፡፡ እኔም እኮ ብየሻለሁ፡ እየሽው አይደል! ትልቅ
ሰው ቤት መግባት እንዲህ ያሳምራል፡፡ ወደፊትም ጠባይሽን አሳምረሽ በዚሁ
ዓይነት ዘለቅሽ እሜቴም ሆኑ ጌቶች ጥለው እይጥሉሽም» እያሉ ይሸነግሏታል።

እሑድ ዕለት ማታ ከራት በኋላ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ ተቀምጬ
መፅሐፍ ሳነብብ እናቴ ከወደ መኝታ ቤት መጥታ እንካ እስኪ ጌታነህ ዛሬ
ደግሞ ለዚች ለየወዲያነሽ የአራት ወር ደሞዜን ተቀብያለሁ አስብለህ አስፈርምና
ስጣት፡፡ ያለፈውን የአራት ወር ደሞዝዋን ግን እርስዎ ጋ ይሁንልኝ ብላ እኔውጋ
አስቀምጨላታለሁ» ብላ ኻያ ብር ሰጥታኝ ሔደች። ምንጊዜም ከኔ ዘንድ
የሚቀመጠውን የደረሰኙን ደብተር ለማምጣት ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ፡፡ ነገር ግን እንደገና መመለስ ስላልፈለግሁ እዚያው ተቀምጬ ቀረሁ፡፡ የድካሟን ዋጋ
ተጠራቅሞ በማግኘቷና እንደ ከዚያ ቀደሞቹ ሠራተኞች «ይህን ሰብረሻል ያን
አጥፍተሻል» ተብላ ደሞ ባለመቆረጡ በልቤ ዙሪያ ልዩ ደስታ ተግፈለፈሉ።
የውብነሽ ለነገ ተሠርቶ የሚቀርብ የሒሳብና የድርሰት ሥራ አለብኝ ብላ መኝታ ቤቷን ዘግታ ሥራ ከጀመረች ቆይታለች። ከአራት በማይበልጡ መስመሮች የአራት ወር ደሞዜ ደርሶኛል የሚል ሐተታ ከጻፍኩ በኋላ ከመኝታ ቤቴ በር ላይ ብቅ ብዩ በቀስታ "የወዲያነሽ" ብዬ ተጣራሁ፡፡ አረንጓዴ ሻሿን በአንገቷ ዙሪያ በልቡ ሸብ አድርጋና ጸጉሯን እንደ ለምድ ትልታይ በጆሮ ግንዷ አኳያ አንዠርጋ በመጠኑ ወደ ውስጥ ዘልቃ ቆመች፡፡ “ገባ በይ» ብዬ ስላዘዝኳት ሁለት አጫጭር ርምጃዎች ወደፊት ተጠጋች፡፡ «በይ እንግዲህ እዚች ላይ ፈርሚ» ብዩ የቀኝ እጅ ክንዷን ተንጠራርቼ ያዝኩ። የአካላቷ ትኩሳት በጣቶቼና በመዳፌ በኩል ተሻግሮ ወደ መላ ሰውነቴ በልዩ ስሜታዊ ፍጥነት ተሰራጨ።

ሰውነቴ ንዳዱ እንደ ተነሣበት ሰው ውስጥ ውስጡን ተንዘፈዘፈ። አውራ
ጣቷን ቀለም ቀብቼ ለማስፈረም ወደ እኔ ሳስጠጋት ሣቅ አመለጣትና ወደ ውጭ
እንዳይሰማ ኣፏን በግራ እጅዋ ኣፍና ተንከተከተች:: መነሸዋን ባላውቅም በመሳቋ ረካሁ እንጂ ቅር አላኝም። አስፈረምኳት፡፡ «መጻፍና ማንበብ ትችያለሽ እንዴ?”ብዬ ጠየቅኋት። ጠይም ፊቷ በፈገግታ ወገግ በማለቱ በመስከረም ወር ቡቃያ ላይ ብርሃኗን የፈነጠቀች የጧት ፀሐይ መሰለች።

ፈገግታዋ ሳይቀንስ ከንፈሯ ተከፈተ። የልቦናዋን እንጃ! አፏን ግን ዝምታ ገታው፡፡ ትንሽ ዘግየት ብላ ግን «ብቻ» ብላ ዝም አለች፡፡ ብቻ” በማለት
የገታችው ሐሳቧ ግን አንጎሌ ውስጥ አዲስ የሃሳብ ቦይ ቀደደ፡፡

ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ የወዲያነሽን አስተካክዬ ለማየት ምቹ ሥፍራና ጊዜ
በማግኘቴ በጣም ደስ አለኝ። ምንም እንኳ በዚያች ሰዓትና አካባቢ ሰው
አለመኖሩን አሳምሬ ባውቅም በፍርሃትና በጥርጣሬ ዙሪያውን ቃኘሁት። የውስጣዊ
ስሜቴ እሳተ ገሞራ ናጠኝ፡፡ አድፍጦ አይጥ ስትጠባበቅ እንደ ቆየች ድመት
ዘልዩ እንገቷ ላይ ተጠመጠምኩ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ግን ከእንቅልፉ እንደ ባነነ ሰው ወደ ትክክለኛው የውነት ዓለም ስመለስ አልጋዬ ላይ በግንባሬ ተደፍቼ ነበር። ማንም አጠገቤ ኣልነበረም። የወዲያነሽ እንዴት እንደ ሄደችና እንዴት እንደ ለቀቅኳት አልታወቀኝም። አልጋው ጫፍ ላይ የነበረው ደመወዟ ተበትኖ አገኘሁት፡፡

ገንዘቡን እንደገና ቆጥሬ ኮት ኪሴ ውስጥ ከተትኩ፡፡ ቀደም ሲል በፈጸምኩት ድርጊት ውስጣዊ ኃፍረት ተሰማኝ፡፡ መጠኑን የሳተ አካላዊ የስሜት ጥማት እንጂ አንዳችም እርካታ ሳላገኝ ቀረሁ፡፡ ልብሴን በማወላልቅበት ጊዜ
አቋቋሟና አነጋገሯ የዐይኖቿ ማራኪ ውበትና የአንገቷ አሰባበር በተለይም ከናፍሯ ከፊቴ መጥቶ ተደቀነ፡፡

በየዕለቱ ስለ እርሷ ማውጣትና ማውረድ መጨነቅና ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡
አዲስ የሕይወት መስታወት
👍5
ከፊት ለፈታ ታየኝ! ጋደም እንዳልኩ «እኔና እሷ እኮ እኩል ነን፡ የሰው ልጅነት ሚዛናዊ እኩልነታችንና የተፈጥሮ ክብራችን
አይሳሳቅም፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ እሷን እንደ በታቼና እንደ ተዋራጅ መቁጠር
የለብኝም» እያልኩ ልዩ ልዩ ምቶችንና በዐላማ ላይ የተመሠረቱ ተስፋዎችን
አንጎሌ ውስጥ ሸቅሽቄ ጥቂት ሰዓት አሳለፍኩ፡፡

በማግሥቱ ሰባት ሰዓት ተኩል ገደማ ላይ ለምሳ ወደ ቤት ስገባ ልብስ ስታጥብ ደረስኩ፡፡ መክረሚያዋን ቀና ብላ እንኳን አይታኝ አታውቅም ነበር፡፡እኔም እንደ ዘበት ነበር ኣልፌያት የምገባው:: በእጅዋ ላይ የነበረውን የሳሙና አረፋ እየፈነጠቀች ኃፍረት በሚያሳድዳት ፈገግታ አይታኝ ሥራዋን ቀጠለች፡፡
ምላሴ የተቋጠረች ወይም ከላንቃዬ ጋር የተሳከከች ይመስል «እንደምን ዋልሽ?»
ማለት እንኳ ተስኖኝ ዝም ብያት ገባሁ፡፡

አባቴና ሽምገልገል ያለ ሦስት አዛውንቶች ብዙ ወረቀቶች ዘርግተው ሲከራከሩና ሲጨቃጨቁ ደረስኩ፡፡ ጐንበስ ብዬ እጅ ነሣሁ፡፡ በትዕዛዝ የተነገሩ ይመስል ሁለም በአንድ ጊዜ ቀና ብለው አዩኝ፡፡ ከእንግዶች እንዱ ብቻ እንደምን ውለሃል» አሉኝ፡፡ ነገር እንደሚጎነጉኑና ጣለው ጠፍረው እንደሚሉ ስለ ገባኝ አንጎሌ እክ እንትፍ ብሏቸው በቀጥታ ወደ መኝታ ቤቴ ገብቼ በሩን ጎሰም አደረግሁት። የወዲያነሽ የእጅ ውሃ አምጥታ አስታጠበችኝ። ወጣ እንዳለች አካሌ
ልዩ ውስጣዊ እንቅስቃሴ ጀመረ። የልቤ እመታት ፍጥነት ተለወጠ።እያቁነጠነጠ
እንዳች የሚያንዘረዝር ነገር የተነሣብኝ ይመስል የሚያቅበጠብጥ ነገር ወረረኝ፡፡ ያመጣችልኝን እንጀራና ወጥ ባጠቧ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣልኝ ወጣች። ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ጸጉሯ አየኋት፡፡ ለምን ወጥ እንዳላመጣችልኝ ባላውቅም እኔው እያወጣሁ በላሁ። በጥቂት ወራት ውስጥ ሰውነቷ እንዲህ በመለወጡ በጣም ተደነቅሁ። ደለል እንደ ተኛበት ቦይ ጉሮሮዬ እህል አላወርድ አለ። ጎንበስ ብላ መዓዱን በምታነበት ጊዜ “የውበት ቡቃያ አልኳት፡፡ በለሆሳስ ነበር። እጄን አስታጥባኝ ከወጣች በኋላ ልብሴን ቀያይሬ አለባበሴን በመስተዋት ተመለከትኩ፡፡ መኝታ ቤቴ ውስጥ የተንጠለጠለችው መስተዋት ቁመቷ አንድ ክንድ ተኩል ወርዷ እንድ ክንድ ይሆናል፡፡

አሁንም ወረቀታቸውን ዘርግተው በሚወያዩት ሰዎች አጠገብ ዐልፌ ወደ
ውጭ ወጣሁ፡፡ ወዲያም ወዲህ ሳልል የወዲያነሽ ልብስ ወደምታጥብበት ቦታ
ሄድኩ፡፡ . ያ ከልጅነቴ ጀምሮ የቦረቅሁበት፣ ኩኩሉና ኳስ የተጫወትኩበት ግቢ በጣም አስደሰተኝ፡፡

የምታጥበውን ልብስ እያየሁ «እማማና የውብነሽ ወዴት ሄዱ?» ብዬ ጠየቅኋት። የእነርሱን መኖርና አለመኖር የሚያስጠይቅ ምንም ምክንያት
አልነበረኝም፡፡ የመጠየቂያዬን ምክንያት እንጠርጥሬ ባላውቅም ወደ የወዲያነሽ
እያዳፋ የወሰደኝ በውስጤ የተቀጣጠለው የወጣትነት ነዲድ መሆኑ ገና እሷን ማነጋገር ስጀምር ገባኝ፡፡ ምንም እንኳ ባለፉት ወራት በልዩ ልዩ ጊዜ ዘና ብላ ስታወራ ብሰማትም አሁን ግን ልዩ ደስታ የሚሰጥ መስሎ ታየኝ።

«'አንቺም በዚያው ወደ ትምህርትሽ ትሄጃለሽ፡ ነይ አብረን እንሒድ
ብለው አሁን አንቱ ልትመጡ አቅራቢያ ወጣ አሉ» ብላ በሚገመጥ ፈገግታና
ሕይወት በሚያረሰርስ ሁናቴ እጅዋ አረፋው ውስጥ እንደ ተነከረ መለሰችልኝ፡፡
ምላሴ ተሳስራ እምቢ ባትለኝ ኖሮ ባያሌው ለማውራት አስቤ ነበር፡፡ ሆኖም
በኃፍረት ከተለጐመ ኣንደበት ጋር የሚደረግ ጊዜያዊ ግብግብ ከባድ በመሆኑ ዝምታዩ አይሎ ሰጥ አሰኘኝ፡፡ ደመወዟ ከእኔ ጋር ውሉ በማደሩ ከኪሴ አውጥቼ “እንቺ» አልኳት። ትኩር ብላ አይታ ተቀበለችኝ። ስንት እንደ ሰጠኋት እንኳ ሳትቆጥር በደረቷ በኩል ወደ ቀሚሷ ጉንፍ ለቀቀችው:: ከዚያም ቀጥ ብላ ስትቆም በእጅዋ ላይ የነበሩት የሳሙና አረፋዎች በፀሐይዋ ብርሃን የቀስተ ደመና ቀለማት ኀብር እያሳዩ ተራ በተራ ፈነዱ። በአእምሮዬ ውስጥ ወዲያው እየተረገዙና በሐሳብ ምጥ እየተወለዱ የሚፈነዱትን የፍቅር አረፋዎችና የመውደድ ትርኢቶች ግን በገሃድ ማየት አልቻልኩም፡፡ አይቼ ሳልጠግባት ተለያቻት ሄድኩ።

በሳምንቱ የውብነሽ ጋር ወደ ገበያ ወጥታ አዲስ ልብስ አሠፍታና ሌሎች ነገሮችም ገዝታ መጣች። ያ ውብ ጸጉሯ በአዲስ ቡናማ ሻሽ ሸብ ተደር ዘንከት ዘንነከት ስትል እንደ ማለዳ የአበባ ላይ ጤዛ የወጣትነት ዐይኔን ማረከችው። በእንግድነትም ይሁን በሌላ ጉዳይ ሰዎች ወደ ቤት መጥተ በሚያወሩበትና በሚጫወቱበት ጊዜ አንድ ዕቃ ለማቀበልም ይሁን ወይም

ነገር ለማቅረብ ስትመላለስ ሰዎች ባይናቸው እንኳ ሲከታተሏት ካየሁ ውስጤ በቅናት በግኖ አንጀቴ ያርር ነበር፡፡ አይተው የሚጨርሷት እንጂ እንደ ውብ
ኮከብ ከሩቁ ተመልክተው የሚተዋት ስለማይመስለኝ በንዴት እተክናለሁ። በባዶ የቅናት ስሜት እርር ድብን እያልኩ ቅናቴን ለመሰወር ያለማቋረጥ ተሠቃየሁ፡፡ በጣም ልዩ የሆነብኝ ግን የገዛ አባቴ እንኳ እያሞጋገሰ ሲጠራትና እንደ ስንዴ ቡቃያ ደስ እያለችው በአረጋዊ ፈገግታ ሲመለከታት በምሰማና በማይበት ጊዜ የቅናቴ ጥርቅም ቆመጡን ይዞ አናት አናቴን ይተረትረኛል። ዐይን
እንዳይጥልባት እና ምናልባትም ሁኔታው ከዚያ እንዳያልፍ ለማድረግ የምችልበትን ዘዴ ሌት ተቀን ማውጠንጠን ጀመርኩ። ለጊዜውም ቢሆን የአባቴ ዐይኖች በፍትወት ተነድፈው በሥጋዊ አምሮት ሳይጠመዱ አልቀሩም፡፡ ሆኖም
በምንም ይሁን በምን ከአባቴ ጋር ተሽቀዳድሜ እና ተፎካክሬ ድል ማድረግ
እንዳለብኝ ወዲያው ገባኝ፡፡ ፍቅራዊ ፍላጐቴን ከግቡ ለማድረስ ውስጣዊ
ብርታትና ከተደቆሰው ወኔዬ ውስጥ የተወለደው አዲሱ እልሄ በልዩ ኃይል
ወደፊት ገፋፋኝ። ጥንካሬው ገና ወደፊት ሊለይለት ነው፡፡
አንድ ቀን ማታ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ እንደተሰበሰብን ቡና ተፈላ፡፡ የወዲያነሽ ቡና ለመስጠትና ስኒ ለመሰብሰብ ከወዲያ ወዲህ ትመላለስ
ነበር። የእኔና የአባቴ ዐይኖች የወዲያነሽ ዘንድ እየደረሱ ሲመለሱ ካንድም ሁለት
ሦስት ጊዜ ተጋጩ፡፡ በዚያች ሰዓት «ለምን ታያታለህ?» ብሎ ቢጠይቀኝ «አንተስ ለምን ታያታለህ?» ብዬ እመልስለታለሁ እያልኩ እኔዉ ከእኔው ጋር አተካራ ገጥሜ ተቀመጥኩ፡፡ በውስጤ ያልኩትን ሐሳብ ፊት ለፊት መናገር እንደማልችል ግን አሳምሬ ዐውቃለሁ፡፡

ቡናው ከተከተመ በኋላ ሒጂ እስኪ ከነ አስካለ ጋር ሆነሽ ያንን ጋን እጠኑት ብላ እናቴ ስላዘዘቻት የወዲያነሽ ወደ ምድር ቤት ወረደች።

የየወዲያሽን ከዚያ ግድም መሄድ ያወቀው አባቴ ታምቆ የከረመው
ስውር ፍላጐቱ ድንገት በመገንፈሉ ጉዳዩን አገላብጦ ሳያይ ውበቷን ገልጾ
ለመናገር ተገደደ።

ፊቱን በመጠነኛ ፈገግታ አፍክቶ ወደ እናቴ ዞር ካለ በኋላ «አንቺ ተካበች» አለ፡፡ እንደገና የምንትለኝ ይሆን የኃፍረት ገፅታ በፊቱ ላይ እየተነበበ።

«ይቺ ልጅ እንዴት አማረባት? ዘቢብ መሰለች አይደል እንዴ? እንዲህ ብስል ሎሚ የመሰለች ናትና!» ብሎ ንግግሩን ለመቀጠል አፉን እንደከፈተ፡ ያቺ ውስጥ ውስጡን በጥርጣሬ የተንሰዋለለችው እናቴን ቁጣዋን አዘጋጅታ የቆየች ይመስል“ያ በየሰው ቤት የምሰማውና ሆድ ሆዴን ሲበላኝ የኖረው ቅሌት ይባስ፧
ብሎ እዚሁ እቤቴ መጣ? 'አዛውንት ነኝ ልታፈር፡ ልከበር ማለት የለም፡፡ ቀሚስ ካጠለቀች፣ መቀነት ካዞረች አገባችበት መግባት ነው» ብላ ንዴት ስላዳፋት ዐይኖቿ ተጎለጎሉ፡፡ የሁለቱ ነገር እባብ ለእባብ ሆነብኝ፡፡ ቅፅበታዊ ቁጣዎ
እእምሮዋ ውስጥ ከተፀነሰ ነገር አፈትልኮ እንደወጣ ገባኝ። ለካስ ቀስ ብላ ትሰልል፣ ኖሯል አልኩ በውስጤ።....

💫ይቀጥላል💫
👍6
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ_አምስት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

....ቲናን አይኗን በፍርሃት ጎልጉላ እያየችው “ሚ/ር ዊሊያምስ እኔ ህይወቴን እፈልገዋለሁ። እንደ ድሮ ነፃ ሆኜ መኖር እፈልጋለሁ።” አለችው፡፡

አድሬኒ እንደነገረችው ከንቲባው ሴትየዋን በወሲብ የሚተነኩስበት አቋም የላትም። ባይሆን ቆንጆ እና ብልህ አዕምሮ እንዳላት ታስታውቃለች፡፡

“ብዙ ጊዜ ከቦታ ቦታ ቤት እየቀየርሽ ትዘዋወሪያለሽ?” ብሎ ጠየቃት፡፡
መልሷን ቢያውቀውም “አዎን። ምክንያቱም አንድ ቦታ ላይ ለብዙ ጊዜያት
መቆየት ለደህንነቴ ያሰጋኛል።” አለችው።

“ይሄ ደግሞ በጣም ወጪ ያበዛብሻል።” አላት እና በቀጥታ “ደንበኛዬ አንቺ ለምትሰጪኝ መረጃዎች በሙሉ ልትከፍልሽ ፈቃደኛ ናት” አላት፡፡

ቲና በእጇ ሀሳቡን አጣጣለችበት እና በመቀጠልም “አመሰግናለሁ ዴሪክ፡፡
ግን እውነቱን ስለተናገርኩ ብቻ ክፍያ መቀበሌ ምቾት አይሰጠኝም። አንተ
ጥሩ ሰው ትመስላለህ፡፡ ደምበኛህም ታማኝ ሳትሆን አትቀርም”
“ልክ ነሽ” አላት፡፡
“አንተ እንዳልከው እኛን አንድ አይነት ሰዎች የሚያስፈራሩን ከሆነ ከማን ጋር እየታገላችሁ እንደሆነ ጠንቅቃችሁ የምታውቁ አልመሰለኝም” አለችው፡፡

“ከሩሲያኖቹ ጋር ነው” አላት፡፡

ቲና ሥማቸውን እንኳን ገና ስትሰማ አይኗ በድንጋጤ ፈጠጠ፡፡

“አዎን” አላት በሹክሹክታ ድምፅ “ስለዚህ ደምበኛህን ከአካባቢው ዞር እንድትል ምከራት” ዊሊያም ስለ ኒኪ አሰበ እና ፈገግ ብሎ

“ይሄንን ያንቺን ምክር የምትቀበለው አይመስለኝም። እሷ በጣም ግትር
ሰው ናት” ብሎ መለሰላት፡፡

ይሄ እኮ ጨዋታ አይደለም” ብላ ቲና እየተቆጣች “ሰዎች እየሞቱ ነው፡፡
እኔ ያናገርኩት የኤልኤታይምስ ጋዜጣ ሪፖርተር እንኳን ሞቷል

”ዊሊያምስ ማስታወሻውን መውሰድ ጀመረ፡፡

“እነርሱ በልብ በሽታ ነው የሞተው ይላሉ:: ግን ገና የ33 ዓመት ወጣት
እና እንደ ፈረስ ጠንካራ ነበር።”

“ቲና አሁንም ሰዎች እየተገደሉ ነው” አላት እና ዊሊያምስ በመቀጠልም
“እኔም እዚህ የተገኘሁት በዚህ ምክንያት ነው” አላት፡፡

በመቀጠልም ስለ ሊዛ ፍላንገንን እና ትሬይ ሬይሞንድ ግድያ ሟቾቹ
ከኒኪ ሮበርትስ እና ከባሏ ዶውግ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ሮበርትስ ስላለው
ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር ስለሚገናኝ የበጎ አድራጎት ሥራዎቹ እና በሎስ አንጀለስ
ላይ የበላይነቱን ለመያዝ ሩስያኖቹ እና ሜክሲካኖቹ ስለሚያደርጉት ግብግብ
ጭምር ነገራት፡፡

“ዶውግ ሮበርትስ ባለፈው ዓመት ነው በአደጋ ህይወቱን ያጣው:: ከጎኑ
ደግሞ ለከንቲባ ፋንቴስን መኪና ከሚሰጡት ሩስያውያን ጋር ግንኙነት ያላት
ሴት ነበረች። እሷም በአደጋው ሞታለች” አላት፡፡

ቲናም እጇን አንስታ “ሙስና ነው ያልከው? አድሬኒ ናት ይህንን የነገረችህ? በእግዚአብሔር ሥም ይህቺ ልጅ በቅርቡ ትገደላለች እመነኝ:: ደግሞ የሚገርመው ነገር እኮ እሷ ስለጉዳዩ ምንም የምታውቀው ነገር ያለመኖሩ ነው::” አለችው፡፡

“ልክ ብለሻል እኔም እንደ አንቺ ነው የማስበው” አላት ዊሊያምስ፡፡

“በመጀመሪያ ደረጃ እኔ ፋንቴስ በግሉ ጉቦ ይቀበላል አይደለም ያልኩት።
ግን ማዘጋጃ ቤቱ ለእሱ ባወጣለት የባንክ አካውንት በኩል የተለያየ አይነት
ገንዘቦች ይገቡለታል ነው ያልኩት። የማወራህ ስለ ትልቅ ክፍያዎች ሲሆን
ክፍያውን ደግሞ የሚፈፅሙት ሩሲያዎኖቹ ናቸው”

ዊሊያምስም ማስታወሻ ደብተር ላይ እየፃፈ “ምን ያህል? እና ደግሞ
የትኞቹ ሩሲያኖች?”

“መጠኖቹ በየጊዜው ይለያያሉ።” አለች እና ቲና በመቀጠልም

“አምስት መቶ ሺ ዶላር መቶ አምሳ ሺ ዶላር እና አንድ ጊዜ ደግሞ አንድ ሚሊዩን ዶላር፡፡ ብቻ በየአራት እና በየስድስት ሳምንቱ የተለያዩ ቼኮች
ይመጣሉ፡፡ ለማንኛውም ባጠቃላይ ወደ ሦስት ሚሊዩን ዶላር ይሆናል።”

“እሺ ክፍያውን የሚፈፅሙትን የሩሲያኖችን ሥም ታውቂዋለሽ?”
አላት፡፡

“አላውቅም” ብላ ወደ ወለሉ
ተመለከተች:: ዊሊያምስ ቲና በጣም
እንደፈራች ተመልክቶም

“እነርሱን የምትገልጪበት አካላዊ ሁኔታቸው? በአካልስ አግኝተሻቸው
ታውቂያለሽ?” ብሎ ጠየቃት። ቲናም ራሷን በአሉታ በሀይል ካወዛወዘች
በኋላ ከንፈሯን ነክሳ “ይቅርታ ይህንን ልነግርህ አልችልም” አለችው፡፡
የስልክ ጥሪዎችን ቢያንስ ተቀብለሽ ታውቂያለሽ? ወንዶች ናቸው ሴቶች?
ሁለት ናቸው ወይንስ ሃያ?”

“አይገባህም እኮ...”

ሌንካ ጎርደቪስኪ የምትባል ሴት ታውቂያለሽ?” ብሎ አይፎን ስልኩን
አወጣና የጎርዴቪስኪን ፎቶ አሳያት። የቲና አይን ላይ ሌንካን እንዳስታወሰች
የሚያሳብቅ ዕይታን ዊሊያምስ ተመለከተ።

“ዴ.ሪክ ስለዚህ ነገር መናገር አልችልም። እስከ አሁንም በጣም ብዙ ነገር
ነው የተናገርኩት”

“ቢያንስ የአንድ ካምፓኒ ሥምን ንገሪኝ፤ ያላወቅኩትን እንቆቅልሽ የምፈታበትን አንድ ነገርን እንኳን ንገሪኝ” ሲላት ጊዜ አናቷን በሀይል ወዝውዛ ይገድሉኛል!” አለችው፡፡

ዊሊያምም ለጥቂት ጊዜ ያህል አፍጥጦ ሲያያት ቆየና በቀስታ “ምናልባት ይገድሉሽ ይሆናል። ምናልባት ሁለታችንንም ይገድሉን ይሆናል፤ ግን አንቺ የያዝሺው ሚስጥር እንደወጣ በማሰብ ሌሎች ሰዎች እየተገደሉ ቢሆንስ? ይህንን ግድያቸውን የሚያስቆመው ደግሞ አንቺ
የያዝሺውን ሚስጥር ይፋ በማውጣት ነው። ይህንን ነገር አምነሽ አይደል
እንዴ ለሮቢን ሳንፎርድ ስልክ የደወልሺው?”

“አዎን” አለች እና ቲና ታፋዋ ላይ ያስቀመጠችው እጇ ይንቀጠቀጥባት
ጀመር፡፡ “በጣም እንደፈራሽ አውቃለሁ። እኔም እኮ በጣም ፈርቻለሁ፤ ቲና
ግን ይሄንን እኛ ካልተናገርን ማን ይናገራል እሺ?”

ዴሪክ ዊሊያምስ ከጎኑ በተቀመጠችው ሴትዮ ውስጥ የሚካሄደውን የሀሳቦች ፍልሚያን አሰበ። ቲና ድሬይተን በጣም ደፋር ሴት ነች። ይህንን ደግሞ አንድ ጊዜ ለማረጋገጥ ችሏል። ግን ሁሉም ሰው የድፍረት ገደብ አለው።
“እሺ” አለች እና በመጨረሻም “እነግርሃለሁ። ግን ከዚህ በኋላ እኔን ዳግመኛ በፍፁም ለማግኘት እንዳትሞክር፡፡ በፍፁም! ለማንኛውም ምክንያት ቢሆን።

ዊሊያምም ወንበሩ ላይ ተመልሶ ቁጭ አለ እና


“ይሄው ቃሌን እሰጥሻለሁ” ብሏት እስክሪብቶውን አወጣ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኒኪ እና ግሬቸን ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እያሉ ይሄዱበት ወደ
ነበረው የኮሪያውያን ፍልውሃ ውስጥ ራቁታቸውን ሆነው ሰውነታቸውን
እያደሱ ነው። ግሬቸን የወረዱ ጡቶቿን ከኒኪ ብርትኳን ከሚያካክሉ ጡቶች
ጋር፣ ሽንትርትር ያለውንና ዘልዘል ያለ ሆዷን ደግሞ ልጥፍ ካለው የኒኪ
ጡቶች ጋር አነፃፀረች፡፡ ጡቶቿ ሦስት ልጆችን ያጠባ እና ሆዷም ሦስት
ልጆችን የተሸከመ በመሆኑ የተነሳ እንደዚህ እንደሆነ አሰበች እና ተፅናናች::

ኒኪ ውሃው ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሰምጣ ከወጣች በኋላ የሴት ወሬያቸውን ጀመረች “ባለፈው የነበረው የእራት ግብዣ ላይ ሀዶን አስገድዶ ሳመኝ፤ ከበፊት ጀምሮም እወድሻለሁ አለኝ” አለች ኒኪ ላግሬቸን፡፡

ግሬቸንም “እኮ የኛ ሀዶን ነው?” ብላ ተገርማ ጠየቀቻት፡፡

“አዎን፣ ግን ጥሩ ስሜት አልተሰማኝም። ምክንያቱም እሱ እኮ ለዶውግ
ልክ እንደ ወንድሙ ነበር፡፡

“አአ ልክ እንደ ኦሪት ዘመን ነዋ? ማለትም አንዲት ሴት ቧሏ ከሞተ ወንድምዬው እንደሚጠቀልላት አይነት ነገር መሆኑ ነዋ” ብላ ግሬቸን አሾፈችባት፡፡

ኒኪም በግሬቸን ሹፈት ትንሽ ተከፍታ ዝም አለች። ግሬቸን ይሄ የኒኪ ጥቁር ደመና እስኪያልፍ ድረስ ዝም ብላት ውሃው ውስጥ ብቅ ጥልቅ ስትል ቆየች፡፡

ከጥቂት ጊዜ በኋላም ኒኪ “ይሄውልሽ ግሬች እኔ ችግር ሳይኖርብኝ
አይቀርም፡፡ ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት እንኳን የለኝም”
👍4
አለቻት፡፡

“የኔ ቆንጆ ይሄ እኮ ችግር አይደለም፤ ሀዘን ላይ ስለሆንሽ ነው”

“እንዴ ዓመት አለፈኝ እኮ” ብላ ኒኪ መለሰችላት፡፡

“በዙሪያሽ የተከሰቱት ግድያዎቹስ ቀልድ ናቸው እንዴ? እንዲያውም አንቺ ሆነሽ ነው ሌላ ሰው ቢሆን ያብድ ነበር።”

“ይልቅ የሆነ ስውን እያሰብኩኝ ነው” ብላ ኒኪ ፊቷ በእፍረት እየቀላ ለግሬቸን ነገረቻት፡፡
ግሬቸንም ወሬውን ለመስማት ጓግታ “ደግሞ ማነው?”

“ኧረ ያን ያህል እኮ አይደለም” አለቻት ኒኪ፡፡

“ማን ነው እኮ ነው ያልኩሽ?” ብላ ግሬቸን ሳቀችባት፡፡

ኒኪም ፍልቅልቅ እያለች “ሉው ጉድማን ይባላል፡፡ ከመርማሪዎቹ ውስጥ
እንዴ እኔን በግድያው ወንጀል ይጠረጥረኛል ያልሺው ሰው ነው?”
“አይደለም እሱማ ባልደረባው ነው። ጉድማን መልከ መልካም እና ለእኔ
አሳቢ ነገር ነው። በዚያ ላይ ደግሞ ጨዋ እና ቀና ሰው ይመስላል፡፡

እየተባባሉ ትንሽ ሲያወሩ ቆዩ፡፡ ኒኪ ይበልጥ እያፈረች እና ጓደኛዋ
አይሆንም እንድትላት እየፈለገች “ይልቅ ለአንዲት ታካሚዬ የተለየ ስሜት
ሳይስማኝ አይቀርም። ባለፈው የቀጠርኩት የግል መርማሪዬ እንደነገረኝ
ከሆነ ይህቺ ሴትዮ አንድ የአደንዛዥ ዕፅ አምራች ከበርቴ ሚስት ናት።ወጣት ናት፡፡ ባሏን ትታ ነው እዚህ ሎስ አንጀለስ ውስጥ የምትኖረው::”

“ከዚህ በፊት ከሴት ጋር አድርገሽ ታውቂያለሽ እንዴ?”

“በጭራሽ” አለች ኒኪ፡፡

“ኮሌጅም እያለሽ?”

“ሂጂ አብረን አልነበርን እንዴ? ባደርግማ ታውቂ ነበር” ብላ ስትመልስላት ግሬቸንም “እውነትሽን ነው ቢኖርማ ኖሮ አውቅ ነበር” አለቻት፡፡

“ይመስለኛል የመካከለኛ ዕድሜ ውዝግብ ውስጥ ሳልሆን አልቀርም...”
አለች እና ኒኪ ወደ ሀዘን ደመናዋ ውስጥ ተደበቀች፡፡ ይህ ስሜቷ ባሏ ከሞተ በኋላ ለተደጋጋሚ ጊዜ የሚሰማት መሆኑን የምታውቀው ግሬቸንም እንደ ሁልጊዜውም ሁሉ ኒኪ ከዚህ ስሜቷ እስክትወጣ ድረስ ዝም ብላ ጠበቀቻት።

ኒኪ ወደ ጥሩ ስሜቷ ስትመለስም ግሬቸን ስለ ልጆቿ የተለያዩወሬዎችን እያወራችላት ውሃው ውስጥ ቆይተው ሲበቃቸው ወደ መታሻው ክፍል ገቡ። መታሻው ክፍል ውስጥም ሰውነታቸው ፍም እስኪመስል ድረስ
በደንብ ከታሹ እና ሰውነታቸው ከተፍታታ በኋላም ልብሳቸውን ለብሰው ከኮሪያውያን የፍል ውሃ ቦታ ወጡ እና ወደ ሱሺ ባራቸው አመሩ፡፡....

ይቀጥላል
👍3
#የወድያነሽ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


....የአባቴ ተራ ድንጋጤና የእናቴ ያልታሰበ ተራ ድንፋታ ልቤን በደስታ አክናፍ አበረራት፡፡ የአባቴ ድብቅ ፍላጎት ሳያስበው በመጋለጡ የሁለቱ ፋይዳ ቢስ ጠብና ስሜት ለስሜት መሳለል በጣም ቢያስደስተኝ ምናልባት እናቴ በዚሁ በሰማችው ብቻ ቅናቷ እያደር ይጎለምስና የወዲያነሽን ታባርራት ይሆን? በማለት መጪውን ጊዜ በሥጋት ዐይን ተመለከትኩት የጨዋነቱ ክብር» የተገፈፈበት የመሰለው አባቴ ያ አይበገሬ መሳይ ወኔው ላመል ታህል በርግጎ ከቆየ በኋላ ለመከላከል ያህል «አማረባት አልኩ እንጂ ምን ሳደርግ አየሽኝ? እኔ ያየህ ይራድ ከማንም ብራሪና ውዳቂ ጋር የምልከሰከስ ነኝ እንዴ? ከጠረጠርሽኝ፣ ዛሬውኑ! አሁኑኑ መንጥቂያት!» ብሎ በንዴት ወደ መኝታ ቤት ገባ፡፡

የእናቴ ፊት በቁጣ ተከስክሶ ዐይኖቿ በሽሙጥ ሸኙት። ነገሩ ተባብሶና
እንደገና ሌላ ነገር ጭሮ ውጤቱ መጥፎ አይሁን እንጂ እሳትና ጭድ ያድርጋችሁ
ማለቴ አልቀረም፡፡

ከአባቴ ይበልጥ ያናደደኝና ውስጥ ውስጡን ያበሳጨኝ ግን የቤታችን
ዘበኛ ነበር። በእርሱ የተነሣ ልቤ በቅናት እሳት ተለብልባ ተሠቃይታለች።

በመልኩ፣ በሰውነት አገነባብና ለግላጋነት ከምኑም አልደርስ። ፈገግታውና የባቄላ አበባ የመሳሰሉ ጥርሶቹ ይማርካሉ። በሥራ ምክንያት በምድረ ግቢው ውስጥ ከወዲያ ወዲህ ሲል ከየወዲያነሽ ጋር የተገናኙ እንደሆነ ተሣሥቀውና ተጠቃቅሰው ይተላለፋሉ፡፡ ከነዚያ ልበሳቸው ብዬ ከሰጠሁት ሸሚዞችና ሱሪዎች መካከል የለበሰ ለትማ ማለፊያ ሙሽራ ስለሚመስል ለባብሶ ባጠገቧ ሲያልፍ ዐይኖቼ በቅናት ደም ይለብሳሉ። አውልቅ ብዩ የምነጥቅበትና ሰበቡ የማይደረስበት ስውር ደባ በማጣቴ ሐሳቤ እንደ ጨው ሟምቶ ቀረ።

ለሥራው ደፋ ቀና ሲል ሰርቄ ሽንት ቤት ውስጥ ለመክተት ያሰብኩበት ጊዜም ነበር፡፡ አንድ ቀን ማታ እርሱና የወዲያነሽ ተከታትለው ወደ ማድቤት
ሲገቡ በማየቴ ጨለማ ለብሼ ከአንድ ትይዩ ቦታ ላይ ከሩቅ አደፈጥኩ፡፡ ከአንድ
ጐድጓዳ ሳህን ውስጥ ፍትፍት ቢጤ ሳይሆን አይቀርም ቶሉ ቶሉ እያወጡ ግራና ቀኝ ቆመው መብላት ጀመሩ። አንድ ሁለት ጊዜ ያህል ለራሷ ትጎርስና ለእርሱም ያንኑ ያህል ታጐርሰዋለች። የአፉን ውስጥ አላምጦ ሳይውጥ ሌላውን ከከንፈሩ ጫፍ ትደቅንለታለች፡፡ ፍትፍት መሆኑ በግምት የሚያስታውቀው ከጉርሻዋ በኋላ ጣቶቿን በማራገፏ ነበር። ከቅናትና ከጥላቻ ብዛት የተነሣ ቁርጠት የቀሠፈኝ ይመስል ሰውነቴ ብው ብሉ- አንጀቴ በንዴት ተቋጨ።

«ና ውጣ ብዬ እርሱን ከእርሷ ነጥዩ የማስወጣበት ምክንያት እንደ ሰማይ
ኮከብ ራቀኝ፡፡ ነገር ግን ወዲያው አንድ ቀላል ነገር ትዝ አለኝ። ቀስ ብዬ
እያሰላሁ እንድ አራት ያህል ደህና ደህና ድንጋይ ከለቀምኩ በኋላ ትልቁን
የአጥር በር በድንጋይ ጠመድኩት።

አራት ጊዜ ያህል እንደ መታሁ ጅብ እንዳየች ቡችላ ሳህኑን ለቆላት ተፈተለከ፡፡ እሷ የበሩን መቃን ተደግፋ ቆመች፡፡ የወዲያነሽንም በመጠኑ ለማስደንገጥ ያህል አንዲት ትንሽ ድንጋይ ወደ ማድ ቤቱ በር እነጣጥሬ ወረወርኩ፡፡ በቀጭን የድንጋጤ ድምፅ «ውይ» ብላ ወደ ውስጥ ሮጠች። የሁለቱም ትኩስ ድንጋጤ ሳይበርድ ልክ ከቤት እንደ ወጣ ሰው ተመስዩ ከተደበቅሁበት ቦታ መሰስ አልኩና «ማን ነው? የማን ነው ባለጌ በጨለማ በር የሚደበድብ?» ብዬ ጮህኩ፡፡ ማንም አልመለሰልኝም፡፡

ዘበኛው የወረወረውን ሰው ለማወቅ በሩን ከፍቶ ወጣ፡፡ ባልተረጋገጠ የቅናት መነሾ የፈጸምኩት የተንኮል ድርጊት ራሴን እያሳፈረኝ እፈን አፍኜ ሣቅሁ፡፡ ነገር ግን ወደ ውጪ በመሄድ ፈንታ ወደ ቤት ገባሁ፡፡ ሆኖም መቀመጥም መቆምም የሚነሳ አንዳች ውስጣዊ ግፊት መላ አካላቴን ናጠው፡፡ አልቻልኩትም::

ሩብ ሰዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የወዲያነሽ ዕቃ ቤት ውስጥ
ስትንጐዳጉድ እገኘኋት። ጣቴን በቁጣ እየነቀነቅሁ «ከዚያ ከመድረሻ ቢስ ሴት
አውል ዘበኛ ጋር ያደረግሽውንና የምትሠሪውን ያላወቅሁ እንዳይመስልሽ!
የመጣው ይምጣ እንጂ የማደርገውን ዐውቃለሁ፡፡ እኔ ጌታነህ ትርክርክሽን ነው
የማወጣው» ብዬ አፍጥጨባት ተመለስኩ፡፡ ክፉኛ ክው ብላ ነበር።
በስውርና በግልጽ መቆጣጠሬን ቀጠልኩ፡፡ የወዲያነሽ ከእኔ ጋር ምንም
ዐይነት ፍቅራዊ ስሜትና ዝንባሌ እልነበራትም፡፡ ስለሆነም ስለ ግንኙነታችን
የምታደርገው አንዳችም ጥረት አልነበረም፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው «ሊያታልለኝና የምመልስለትን ለማወቅ ፈልጎ ነው» ብላ እንደሆነ እያደር ተገለጸልኝ፡፡

«ከዘበኛው ጋር ስትዳሪና ስትላፊ አይቼሻለሁ» ብዩ ከገሠጽኳትና
ከተንደራራሁባት ወዲህ ግን ወይ በፍርሃት አለበለዚያም በውስጧ ተሰዉሮ በነበረ ለጋ ውዴታ ምክንያት እርሱን ችላ ብላ ወደ እኔ መለስ አለች፡፡ ሆኖም
በቀድሞው አንገተ ሰባራነቷ ላይ በፍርሃትና በበታችነት ስሜት በመጠመዷ
የዝቅተኝነት ጭንቀት አጠቃት።

አንድ ቀን ማታ ከእኔና ከእርሷ በስተቀር መላው ቤተስብ ከላይ እታች በተኛበት ወቅት ኮቴዬን ሳላሰማ ከመኝታ ቤቴ አስልቼ ወጣሁ፡፡

ዕቃ ቤት ውስጥ ወዳለው ወደ የወዲያነሽ መኝታ ክፍል ለመሄድ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ ስደርስ ከበሩ አጠገብ ቆማ አየኋት። የተከፈተውን የዕቃ ቤት መዝጊያ ተደግፋ ቆማለች። አንዲት አራት ማዕዘን መስተዋት በግራ እጅ ይዛ በመስታወቱ ውስጥ ከምታየው ከሌላዋ ነፍስ አልባ «እርሷ» ጋር ፈገግ እያለች ትሥቃለች። ቀና ብላ በድንጋጤ ካየችኝ በኋላ በምን ይለኝ ኀፍረት በእጅዋ የያዘቻትን መስታወት ከቀኝ እጅ ብብቷ ውስጥ አጣብቃ ይዛ አቀርቅራ ቆመች። እግሬ ላይ መጫሚያ ባለመኖሩ በለስላሳው እግሬ ያደረግሁት እርምጃ በሥጋጃ ላይ የምትራመድ የድመት አካሔድ ሆኖ ነበር፡፡

እጠገቧ ደርሼ ቆም ስል ወደ ጎን ሽርተት አለች። ገፋፍቶ ያስወጣኝ ድፍረት እንደ ቅቤ ቀለጠ። ሰውነቴ በኃፍረት ተተብትቦ ግድግዳውን ተደግፌ ቆምኩ፡፡ አወጣጡ ግን ግድግዳ ተደግፌ ለመቀም አልነበረም፡፡

ትሰድበኝና አጉል ታዋርደኝ ይሆን» እያልኩ በፍራቻ ስሜት ውስጥ
ከቆየሁ በኋላ «እስካሁን ምን ታደርጊያለሽ የወዲያነሽ?» ብዬ ለማሽኮርመም ያህል ባቀጠንኳት ድምፅ ጠየቅኋት። እንዳቀረቀረች አሻግራ ወለል ወለሉን እየተመለከተች «ማድ ቤት ወርጀ ገላዩን ስታጠብ ቆየሁና ይኸ ጸጉሬ
እንዳያስጠላ ከመተኛቴ በፊት ልጎንጉነው ብዩ ነው» ብላ ዝምታዋን ተያያዘችው፡፡

ምናልባት ያ መዘዘኛ ዘበኛ ገብቶ አጫውቷት ይሆን? በማለት መላ
ሰውነቴ በቅናት ግው ብሉ ጋየ፡፡ «መታጠቡንስ ጥሩ አደረግሽ፡ ለመሆኑ ግን እያሸሽ ታጠብሽ?» ብዬ ጠየቅኋት።
“አስካለ፣ እስካለ ናት ፍትግ አድርጋ ያጠበችኝ» ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ በቅናት የተሥረቀረቀ ልቤን ለማፅናናት «እኔስ ያ ዘበኛ ነው ብዬ አልኳት፡፡ ፊቷ ጠወለገ፡፡ ከወደ ውስጥ የሚወጣውን ትካዜዋን ይገልፅ ይመስል የቀኝ እግሯን ሰበር አድርጋ «ውይ! ምነው ምን አልኩዎት፡ ከዚያች እርስዎ ከተቆጡኝ ቀን ወዲህ ቀና ብዬም አይቼው አላውቅ:: እኔስ ይቺው የድሃ እንጀራዬ ትበልጥብኛለች» ብላ ከፊቴ ላይ ሁኔታዬን ለመረዳት ሰረቅ አድርጋ አየችኝ። ነገሩን ለማቃለልና የእርሷም ያልተዘጋጀ እእምሮ ምን መልስ እንደሚሰጥ ለማወቅ ስል የቀኝ እጅ ጣቶቿን ያዝ አደረግሁና እረ ለመሆኑ እኔ እንደምወድሽ ታውቂያለሽ ወይ?» ብዩ በሙሉ ድፍረት ጠየቅኋት። ሆኖም ዝምታዋን ጥሶ የሚወጣ የመልስ ቃል ሳላገኝ ቀረሁ። አገጯን ይዤ ወደ ላይ
ቀና አደረግኋት። ያቺን ለስላሳ የምታምር ድቡልቡል እገጯን ስነካ ሰውነቴ
ውስጥ ተናዳፊ ንዝረት ለቀቀብኝ። እንደ ዱር ሀረግ አንገቷ ላይ ተጠምጥሜ
ብስማት እፎይታ እንደማገኝ ታወቀኝ፡
👍5
፡ ሆኖም ያንኑ ያሀል ኃፍረትና ወኔ ቢስነት
በላዩ ላይ ስለ ተቸለስ ሟሽሼ ቀረሁ፡፡

«ንገሪኝ እንጂ ለምን ዝም ትያለሽ? ሰው ሁሉ እስኪተኛ ድረስ ጠብቄ የመጣሁት እኮ እንድትነግሪኝና ቁርጤን እንዳውቅ ብዬ ነው» አልኩና የያዝኩትን እጅዋን ትከሻዬ ላይ ሰቀልኩት። ብብቷ ሥር የነበረችው መስተዋት ወደቀች፡፡
አልተሰበረችም፡፡ እጇን ትከሻዬ ላይ የሰቀልኩት በእሺታና በፍቃዷ ባለመሆኑ
የጓያ ፍንካች የምታህል ደስታ አልተሰማኝም፡፡ አሁንም ቢሆን ከዝምታዋ ጥልቀት ውስጥ መልስ ማግኘት ባለመቻሌ ልቤ በንዴት ተጥመለመለች። ሳልወድ በግድ ለቅቄያት ወደ መኝታ ቤቴ ተመለስኩ፡፡ ሥጋዊ አካሌ ዟ ብሉ ሲንጋለል አእምሮዬ ግን በሐሳብ ዋዠቀ፡፡ ከራሴ ጋር ክርክር ገጠምኩ፡፡

ሐሳቧንና አስተያየቷን ሳላጠናና ሳላውቅ «ወደድኩሽ ብዩ ለምን ዘላበድኩ? «ምናልባት ይህን ነገር እንደ ክብር ቆጥራ ያላልኳትንና ያልጠየቅኋትን ሁሉ ጨምራ ጨማምራ ታወራ ይሆን?» በማለት ከአንድ ሰዓት በላይ እየተሠቃየሁ ተገላበጥኩ። ተጸጸትኩ። ጸጸቴ ግን እንደ አለብላቢት ቅጠል አእምሮዬን ለበለበው እንጂ ሌላ ፍቺ አልሰጠኝም፡፡ ሐሳቤን አንድ ፈር ሳላሲዝ አንቀላፋሁ። ጊዜው ጐረፈ።

ዘወትር እሑድ እሑድ ከቤተ ክርስቲያን መልስ ረፋዱ ላይ የሚፈላው ቡና የተለየ ክብርና የአከታተም ዝግታ አለው፡፡ በአጋጣሚ እሑድ ላይ ተደርቦ የሚውል ዕውቅ ተራዳዒ ቅዱስ መልኣክ ወይም ባለገድል ሰማዕት ከዋለ እሑድ
ተጣማሪ የክት ስም ይሰጠዋል፡፡

ዕለተ ሰንበትና ሥላሴዎች ናቸው:: ዕለተ ሰንበትና ሊቀ መላኩ ነው፣ ዕለተ ሰንበትና እመ ብርሃን ወላዲተ አምላክ ናት ይባልና ሦስት አራት እነባበሮ በቅቤ ጫፍ እስኪል ርሶ ይቆረሳል ጾም ካልሆነ። ውለታ የዋለና ስለት ያደረሰ ታቦት ለሆነማ አንድ ሁለት ጋን ጠላና ሾላ የመሰለ ድፎ ዳቦ አያጣም፡፡ ምን ጠፍቶ

ያንድ ቀን ለታው እሑድ ባለ አጋጣሚ ተረኛ መድኃኔዓለም ስለ ነበር እናትና አባቴ ስደተኛው መድኃኔ ዓለም አስቀድሰው እንደተመለሱ እንግዳ
መቀበያ ክፍል ውስጥ ቡና ተፈልቶና አነባበሮ ተቆርሶ የቤተሰብ ወሬ ደራ፡፡ ስለ
አገር ቤትና ስለ ከተማ፣ ስለ ዘመድና ባዳ ሙገሳና ወቀሳ አንዱ ካንዱ እየተቀበለ
አወራ።

እናቴ በግልጽ ስለምታውቃትና ስለ ተካሠችባት የአባቴ የቀድሞ ወጻጅ
ስለተጠረጠረባቸው ሴቶች እንኳ ሳይቀር እንደ ቀልድ እየተነሣ ተሣቀ፡፡
የወዲያነሽ ድንገት ብድግ ብላንደ ዕቃ ቤት ሄደች። ያረጀ ያፈጀ ወሬ ስለነበር
አልታፈረበትም በመኻሉ በእናቴ አእምሮ ውስጥ የየወዲያነሽ ሐሳብ ድንገት
ድንቅር ብሎ ኖሮ እናቴ ተዘብንና ሳቀችና ያንተ ነገር ደግሞ ምን ማለቂያ
አለው? መቼም ልብ እይሞት! ውሽትና ስንቅ እያደር ይቀላል ከሚሉ ወንድና
ስንቅ እያደር ይቀላል ቢሉ ኖሮ ጥሩ ነበር፡፡» አለችው ሕሊና በማይጎዳ ሽሙጥ
«አፍ ተጅ ባይሆንብህ ኖሮ እንዳንተ አስተያየትማ የትናየት በተዳረስን ነበር፡፡
ብላ ስለማን መናገር ላይ እንደፈለገች እንዲያውቅ ላፍታ ያህል ትኩር ብላ
አየችውና “ደግነቱ የሷ ቀና ተብላ
ሰው ያለ ማየት በጀ እንጂ ብላ በወሬ መኻል የቀዘቀዘች ቡናዋን ጨልጣ ንግግሯን እንደ መቀጠል ስትል
«አንቺም እኮ እንደዚያ ዕለቱ አድርገሽ አዋርደሽኝ አታውቂ! በሌላ ነገር
ቢሆን እንዴት ደስ ባለኝ፡ ሚስት ገመና ከታች ናት ይባል ነበር፡፡ እኔ ላይ
በስተርጅና ታዘብኩሽ! አንዲት ቃል ሳት ብላኝ ብታመልጠኝ እንዴት ከገረድ
ጋር ታውይኝ?» አለና አባቴ ያለፈውን ንዴትና ቂሙን ከወቀሳ ጋር አደባልቆ
ተናገረና መጽሐፉን ለመመልከት አቀረቀረ።

«ያልጠረጠረ ተመነጠረ» አለች እናቴ በአነጋገሯ ኩራትና ግድየለሽነቷን
እያሳወቀች፡፡ «ታዲያ የማንም ብራሪና መድረሻ ቢስ በስተርጅና ትዳሬን
ትበትነው ብለህ ነው?» ብላ ወደ እኔና ወደ የውብነሽ ተመለከተች። በእንግዳ
መቀበያው ክፍል ውስጥ ከአራታችን በቀር ሌላ ሰው ባለመኖሩ አባቴ በጉዳዩ ላይ ተዝናንቶ ለመናገርና ንጽሕናውን ለመናዘዝ ይሉኝታ እልተጫነውም፡፡

ከሚያነበው መጽሐፍ ላይ ቀና ብሎ ከሠላሳ ስድስት ዓመት በኋላማ
ኸገረድ ተገናኘ፣ ተጠረጠረ ብባል የሞት ሞት እይደለም ወይ? እንዴት ብዬ
አደባባይ ልወጣ? በመጠርጠሬ እንኳ ቆሽቴ ተልጧል። ትልልቆቹስ ሥፍራ
ሥፍራቸውን ይዘዋል፡ እነኚህ ምን ይሉን?» ብሉ» ራሱን ነቀነቀና እንደገና ወደ መጽሐፉ መለስ አለ።

«እስኪ እንዲያው ተካበች ሙች፣ ፍቅራችንን በለኝ፡ ልቦናህም አልከጀላት?» ብላ ጠየቀችው:: የዝቋላው ና» ብሎ በመሐላ ነገሩን ከሥር ከመሠረቱ መንግሎ በመጣል ከጥርጣሬ ቅጥር ውጪ አሽቀነጠረው፡፡

የወዲያነሽ ስለ እርሷ ምን እንደተባለና እንደተወራ ባለማወቋ ሥራዋና ሁኔታዋ ሁሉ አልተለወጠም። ይልቁንም ለእናቴ ያላት አክብሮትና ታዛዥነት እያደር በመጨመሩ ሁሉንም ነገር የቸልታ ጉሮሮ ዋጠው:: የእናቴም ጥርጣሬ
በአባቴ መሐላ እንደ ጢስ በንኖ ጠፋ፡፡ አባቴም ከዚያ ወዲህ ስለ የወዲያነሽ
አኳኋንና አሠራር ትንፍሽም አሌለ።

እኔና የወዲያነሽ ከቀድሞው በበለጠ ሁኔታ ጠባይ ለጠባይ በመተዋወቃችንና በመግባባታችን ምን ጊዜም አንድ እፍኝ ሙሉ ፈገግታ ፈገግ ባልኩላት ቁጥር አጸፋውን በእንቅብ መቀበል ቋሚ ልማዳ ሆነ፡፡ የወዳያነሽ አእምሮ ውስጥ ብዙ አስጨናቂ የሐሳብ ውጣ ውረድ እንደሚተራመስ የሚታወቀው ከእያንዳንዱ ፈገግታ በኋላ ፊቷ ስለሚጠወልግ ነበር።

💫ይቀጥላል💫
👍5
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

...ከኮሪያውያን የፍል ውሃ ቦታ ወጡ እና ወደ ሱሺ ባራቸው አመሩ፡፡
ሱሺ ባር ውስጥም ተቀምጠው እየበሉ እያሉ ግሬቸን “ይህንን ቀጠርኩት
ያልሺውን የግል መርማሪሽን ከየት ነው ያገኘሽው?” ብላ ኒኪን ጠየቀቻት፡፡

ኒኪም “ከጎግል ላይ ነው:: ስለ እሱም በደንብ አድርጌ ካነበብኩኝ በኋላ
ነው የቀጠርኩት፡፡ ይልቅ ከ 10 ዓመት በፊት ለማን ተቀጥሮ ይሰራ እንደነበር እስቲ ገምቺ?”

ግሬቸንም በኒኪ ጥያቄ ከት ብላ ከሳቀች በኋላ “እኔ ይሄንን እንዴት ላውቅ እችላለሁ፡፡ በይ ንገሪኝ እስቲ”
“ለክላንሲ ቤተሰቦች ነበር። ባለፈው ምሳ ስንበላ እንዲያውም አንቺ ነሽ የነገርሺኝ፡፡ ሜክሲኮ ውስጥ ጠፋች ምናምን ብለሽ፡፡ ትዝ አለሽ?”

“አዎ ቻርሎቴ ክላንሲ። አባቷ የእሳት አደጋ ሠራተኛ ነው::”

“ልክ ነሽ ተከር ክላንሲ ይባላል፡፡ ባይገርምሽ እሷ የእኔ ታካሚ ከሆነች
አንዲት ሴት ባል ጓደኛ ጋር ግንኙነት ነበራት። የክላንሲ ወዳጅ ባንከር ሲሆን
የሚሰራው ደግሞ ሮድሪጌዝ ከሚባል የአደንዛዥ ዕፅ አምራች ባለቤት ጋር
ነው:: የአደንዛዥ ዕፁንም እዚህ ሎስ አንጀለስ ውስጥ እየሸጠ ነው ብሎ ነው
ዴሪክ ዊሊያምስ የሚባለው መርማሪዬ የነገረኝ” አለቻት ኒኪ፡፡

ግሬቸንም ጓደኛዋ በዚህ መልኩ ነግሮችን እያገናኘች ማሰቧን እና መርማሪዋ የነገራትን ሁሉ አምና በመቀበሏ እየተገረመች እያየቻት

“እሺ ከዚያስ የክላንሲን ቤተሰብ ጉዳይ ይዞ የነበረው መርማሪሽ በመጨረሻ ላይ ምን ሆነ?” ብላ ኒኪን ጠየቀቻት፡፡

“አባረሩት”
“ለምን?”
“ምክንያቱም ቻርሎቴ ከባለትዳር ጋር ግንኙነት ነበራት ብሎ ስለነገራቸው ነው፡፡ በነገራችን ላይ ቻርሎቴ ጨዋ አልነበረችም። እሷ ሜክሲኮ ላይ የሰው ትዳር ለማፍረስ ስትንቀዥቀዥ የነበረች ሴት በመሆኗ የእጇን ነው ያገኘችው። ስለዚህ አላዝንላትም” አለች ኒኪ ትንሽ ምሬት ባዘለ ድምፅ፡፡

ግሬችንም ቀና ብላ በቅሬታ እያየቻት ኒኪ ከመቼ ጀምሮ ነው ደግሞ በሰዎች ሞት ደስተኛ መሆን የጀመርሺው? መቼስ አንዲት ሴት ከባለትዳር ጋር የፍቅር ግንኙነት ስላደረገች ትሙት ብለሽ አትፈርጂም?” ብላ ጠየቀቻት፡፡
“ለምን ብዬ ነው የማልፈርደው?” ብላ በቁጣ በሚንቀለቀል አይኗ አየቻት
እንደቀልድ ስታይ አዳም ሲያቀብጣት የነበረች አንዲት ሸርሙጣ ሴት እና” የሆነ ማታ ላይ የአዳምን አይ ፓድ ስትከፍቺ እና ፎቶዎችን የራቁት ፎቶን ብታይስ ምን ይሰማሻል?”

“በእርግጥ ነገሩ ያሳቅቃል፡፡ ግንንንን...”
እሺ ልጅቷ እርጉዝ ብትሆንስ?” ብላ ኒኪ ልክ ሰይጣን እንደያዘው ሰው
ጮክ ብላ መለፍለፍ ስትጀምር ቤቱ ውስጥ ያሉ ሰዎች ዞር ዞር እያሉ ወደ
እነርሱ መመልከት ጀመሩ። “እሺ አንቺ ለባለፉት አምስት ዓመታት ያህል
ውጤት አልባ እና በጣም የሚያሳምም መውለድ የሚያስችልሽን ህክምና
እያደረግሽ እያለ ባልሽ ከጀርባሽ ሌላ ሴትን እያወጣ ቢያስርግዛትስ?” ብላ ኒኪ
አይኗ በእምባ ተሞላ፡፡ “የሆነ ማታ ላይ የባልሽ አይፖድ ላይ እርጉዝ ሆዷን
የሚያሳይ የራቁት ፎቶን በኢ ሜይል ብትልክልሽስ? በቃ ህይወትሽ በሰከንድ
ውስጥ ግልብጥብጡ ቢወጣስ!?” አለቻት።

ግሬቸን በሰማችው ነገር በጣም ደንግጣ እና ሆዷ ታውኮ ሀሞቷ ሊወጣ እየታገላት ፍጥጥ ብላ ኒኪን አየቻት እና

“ሌንካ እርጉዝ ነበረች?”
ኒኪም መልስ ሳትመልስላት ዝም ብላ አይኗን አፍጥጣ ግሬቸንን ተመለከተች፡፡

ግሬቸንም “ግን እኮ ለሁላችንም የነገርሺን ከአደጋው በፊት ስለ እሷ ስምተሽ እንደማታውቂ ነበር።”

ኒኪ ራሷን ነቅንቃ ከድንዛዜዋ ወጣች እና ዝምታዋን ቀጠለች፡፡

“በኢየሱስ ሥም! ግን አንቺ ፎቶዎችን አይተሽ ነበር ስለ እሷም ታውቂ
ነበር ኒኪ?” ብላ ግሬቸን በፍርሃት ተንቀጠቀጠች፡፡

ምናልባት በአደጋው ውስጥ ኒኪ እጇ ይኖርበት ይሆን እንዴ? ብላ
ግሬቸን አሰበች፡፡

ተነስታ ለመሄድም እያመነታች እጇን ቦርሳዋ ላይ አስቀመጠች፡፡ ይህንን
ግሬቸንን ሁኔታ ያየችው ኒኪም ዶውግን አፈቅረዋለሁ። እሱ ላይ አንዳችም ክፋ ነገር አላደርግም:: እሱ ግን በጣም ነው ልቤን የሰበረው” ብላ አዘነች፡፡

“ግን ታውቂ ነበር?”

ኒኪ ራሷን በአወንታ ነቀነቀች፡፡

“ፎቶዎችንም አይተሻል? ሌንካ እርጉዝ ነበረች?”
“አዎ” አለቻት እና “
ከመሞቱ ከወር በፊት ነው ፎቶዎቹን ያየሁት::”ካለቻት በኋላ ማልቀስ ጀመረች፡፡

ግሬቸንም ወንበሯን አስጠግታ አቀፈቻትና “ለምን አልነገርሺኝም ያን ጊዜ የኔ ቆንጆ?”
“እንዴ ይሄ እኮ የሚያሳፍር ነገር ነው እንዴት ይነገራል?”
“እና ዶውግን ዝም አልሺው?”

“አውቃለሁ ዶውግን ከቤቴ ላባርረው እችል ነበር፡፡ ግን በቃ ትዳሩን ብሎ
ይመለሳል ብዬ ዝም አልኩኝ። ምንም ነገር እንዳላየሁ ሆኜ አሳለፍኩኝ::
ታውቂ አይደል ግሬች ዶውግ እኮ ዓለሜ ነው።”

“እንዴ የተረገዘው ልጅስ?”
“አላውቅም! ነገሩ እኮ ለእኔ አዲስ ነገር ነበር። ሁሉ ነገር እኮ በጣም ነበር ግራ ያጋባኝ የነበረው። እናም በመጨረሻ ምንም ሳላወራው ሞተብኝ።
በጣም ዘግይቼ ነበር።” ብላ ኒኪ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።

ኒኪ አልቅሳ ከወጣላት በኋላ ለአንድ ሰዓት ያህል ሲያወሩ ቆዩ።
ግሬቸንም ለኒኪ ለምን ወደ ኒውዮርክ ሄደሽ አዲስ ህይወት አትጀምሪም?
ብላ ሀሳብ አቀረበችላት፣ እና ኒኪም እንደምታስብበት ነግራት ተለያዩ።

ኒኪ ለዓመት ያህል ውስጧን ሲያኝከው የነበረውን የሌንካን የእርግዝና
ጉዳይ ለግሬቸን ስላወራች ትንሽ ቀለል ብሏታል። መኪናዋን እያሽከረከረች
ወደ ቤቷ እየሄደች እያለችም ዴሪክ ዊሊያምስ ደወለላት።

መኪናዋን መንገድ ዳር ከሚገኝ የጃካራንዳ ዛፍ ስር አቆመች እና ስልኩን
ስፒከር ላይ አድርጋ ማውራት ጀመረች::
“ሄሎ ዴሪክ ባለፈው ለእኔ አስበህ መልዕክት ስለላክልኝ አመሰግናለሁ።
እቤት ከገባሁ በኋላ እንዳልደውልልህ...”

ኒኪ የግድ በቶሎ ዛሬ ማታ መገናኘት ይኖርብናል” አላት። ለመጀመሪያ
ጊዜ ድምፁ ውስጥ ፍርሃት እና አለመረጋጋትን ያስተዋለችው ኒኪም ምን
ሆኖ ነው እንደዚህ የፈራው? ለእኔ ነው ወይስ ለራሱ ነው የፈራው?' ብላ

“ምነው ችግር አለ እንዴ?” ብላ ጠየቀችው።

በሩሲያውያን እና በሮድሪጌዝ መካከል የሚደረገው የአደንዛዥ ዕፅ ጦርነት ቀላል አይደለም። ነገሩ እስከ ከተማው ማዘጋጃ ቤት ድረስ ይዘልቃል። መሉው የሎስ አንጀለስ ከተማ በዚህ የአደንዛዥ ዕፅ ቀለበት ውሰጥ ነው የሚገኘው።” አላት እና ስሜቱ የተረበሽ እና የፈራ መሆኑ
እየታወቀበትም ባንኮችና እና የበጎ አድራጊ ተቋማት ሁሉ የዚህን አደንዛዥ ዕፅ ገንዘብ በህግ ወጥ መንገድ ስለሚያዘዋውሩ ሁሉም የድርሻቸውን ያገኛሉ። አላት።

ኒኪም የዊሊያምስ አለመረጋጋት እና መፍራት ትንሽ አሳስቧት “እሺ ተረጋጋ። ከግድያው ጋር የሚገናኝ ነገር አግኝተሃል? ማለትም ግድያው ከእኔ ጋር ይገናኛል ?

“ምናልባት አዎን” ብሎ ሲመልስላት ኒኪ እርግጠኛ ለመሆን ብላ

“ስማቸውን ልትነግረኝ ትችላለህ?”

“አሁን በስልክ ልነግርሽ አልችልም።” ብሎ ዊሊያምስ በመቀጠልም “የሆነ ስወር ያለ ቦታ ከተገናኘን በኋላ ነው የምነግርሽ” አላት እና የሚገናኙበትን ሆቴል ተስማሙ::

“ስለ ሌንካስ ያገኘኸው ነገር አለ?” ብላ ኒኪ ጠየቀችው።

“አዎ አለ፤ የእሷም ነገር ከዚህ ጉዳይ ጋር ይያያዛል፡፡ እሱንም ስንገናኝ አወራሻለሁ።”

“በስልክ ልትነግረኝ አትችልም?” ብላ ኒኪ ተለማመጠችው፡፡ ስለ ጣውንቷ ለማወቅ ዓመት ፈጅቶባታል፤ እና ከዚህ በኋላ ለደቂቃ እንኳን መጠበቅ ስቃይ ነው የሚሆንባት

“አልችልም፡፡ አሁን ቤት ሄጄ ልብሶቼን በሻንጣ ማዘጋጀት አለብኝ
👍3😁1🤩1