አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ሹፌር እግሮች መሬት እንደነኩ ካልቨርት
የቀኝ እጁን አንስቶ አንገቱ ስር ቢለው ጫትና መጠጥ የሽረሽሩት ሹፌር
ወርዶ እግሩ ስር ተቆለለ፡፡

“ምን ማድረግህ ነው? አብደሃል እንዴ?” ናትናኤል ከተቀመጠበት ወንበር ጋር እንደተጣበቅ ሁሉ ካለበት ሳይንቀሳቐስ ጮኸ፡፡

ካልቨርት የናትናኤልን ጩኸት ችላ ብሎ በእርጋታ የሾፌሩን እጆች ወደኋላ አዙሮ ግጥም አድርጎ አስረና አፉን በጨርቅ ጎስጉሶ ሲጨርስ ብብትና ብብቱ ውስጥ ገብቶ እያንዘላዘለ ከጭነት መኪናው ጀርባ በዕቃዎች መሃል የተጠቀለለ ምንጣፍ ገልጦ ከውስጥ አጋደመው፡፡

“ውረድና ከፊት ግባ፡፡” አለ ካልቨርት ምንም እንዳልተፈጸመ ሁሉ ናትናኤልን እየተመለከተ፡፡ ወዲያው ፊቱን አዙሮ ሹፌር በር በኩል ገባና መሪውን ጨበጠ፡፡

ናትናኤል ሁኔታውን ሲያይ በፍጥነት ከመኪናው ጀርባ ዘሎ ወረደና ከጎን ያለውን የጋቢና በር ከፍቶ ከካልቨርት ጎን ጋቢናው ውስጥ ገባ፡፡አብሮት የሚሸሸው ሰው ባህርይ ቀስ በቀስ እየተገለፀለት ሲመጣ ናትናኤል ስጋት ገባው፡፡

“ምንድነው የሠራኽው? ምን አደረገህ ሰውየው?” አለ ናትናኤል ድንጋጤ ፊቱን አገርጥቶት፡፡

“ናትናኤል ለሁሉ ነገር ጊዜ ኣለው:: ለግብረገብም ጊዜ አለው፡፡ ገና
ለገና መሪውን ስለያዘ የፈለገበት ሲወስደን እንደሰንጋ በሬ ከጀርባው ተቆልዬ
የምሄድበት ምክንያት የለም:: መሄድ የምፈልገው ወደ አዲስ አበባ ነው፡፡
የአዲስ አበበ አቅጣጫ ደግሞ በዚህ አይደለም፡፡”

-ካልቨርት ያለ ጥድፊያ የጭነት መኪናዋን እሽክርክሮ ተገንጥለው ወደ መጡበት መንገድ ተመለሰና ከዋናው መንገድ ሲደርስ ወደ ቀኝ ታጥፎ የመኪናውን ኣፍንጫ ወደ አዲስ አበባ መለሰው፡፡ ከኪሱ ውስጥ ያችነ ትንሽ የመንገደኛ ካርታ አወጣና ከመሃላቸው ዘረጋት፡፡

“ስለሚቀጥለው ከተማ ንገረኝ፡፡ ርቀቱን፣ ፀባዩን የምታውቀውን ሁሉ:፡” አለ ካልቨርት ቁርጥ ባለ ድምፅ፡፡ ሰውየው ሰካራሙ ካልቨርት ድንገት ቆፍጣና ወታደር ሲሆንበት ናትናኤል ግራ ተጋባ፡፡

“እ...አፍደም ይላል. አላውቀውም፡፡” አላ
የሚናገረው ግራ ገብቶት::

“ስለእየሱስ ብለህ ርቀቱን ንገረኝ! የያዝከው'ኮ ካርታ ነው!” አለ
ካልቨርት በስጨት ብሎ፡፡

እ..አርባ አርባ አምስት ኪሎ ሜትር ይሆናል፡” አለ ናትናኤል ከበኩ መገንጠያ እስክ አፍደም ያለውን ርቀት ለመገመት እየሞከረ፡፡
“የሚቀጥለው ከተማ ከነርቀቱ?”
“ሚኤሶ፡፡ ርቀቱ... እጥፍ ይሆናል… ዘጠና
መቶ…”

ካልቨርት ስዓቱን ተመለክተ:: አስራ ኣንድ ከሃያ ይላል፡፡

የሚቀጥለውስ ከተማ?”
“እንጃ፡፡ እይነበብም:: አንድ ነገር አፍስሰህበታል፡፡”
“ተወው አረቄ ይሆናል የሚቀጥለውስ ከተማ ከነርቀቱ ?

“አዋሽ፡፡ ርቀቱ እንጃ:: ሩቅ ነው፡፡” አለ ናትናኤል መገሙቱ ቢያስቸግረው
ካርታ እንዴት መነበብ እንዳለበት የሚያውቀው ነገር የለም፡፡

“አምጣ፡፡” አለ ካልቨርት መኪናውን ጥግ አስደዞ:: ካርታውን ከናትናኤል እጅ ተቀብሎ ሲያጠናው ቆየና ቀና አለ

“ዛሬ ሌሊቱን አዋሽ ደርሰን እናድራለን፡፡ በጠዋት ተነስተን በሌላ ተሽከርካሪ እንቀጥላለን፡፡”
“ነዳጅስ ይበቃናል? ”
“እሱን የሚያውቅ እንድ ዲያብሎስ ብቻ ነው::”

ቀኑ እየሸሽ ምሽቱ እየደመቀ ሲመጣ ዝምታ ተጫናቸው:: የሚጓዙበት አሮጌ የሴት ዕቃ የጫነች አሮጌ መኪና ከምታሰማው ኳኳታ በስተቀር ጋቢናው ውስጥ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ ጨለማው ሊጋርዳቸው ሲዳዳው ካልቨርት
አንዱ ይህን አንዴ ያንን ሲጫን ከቆየ በኋላ የመኪናውን የፊት መብራት አበራው፡፡የበራው ግን የግራው ወገን አንድ መብራት ብቻ ነበር፡፡ ፍጥነታቸ
ውን ቀንስው ወደፊት ቀጠሉ::
በመንገዳቸው ላይ ትናንሽና ከፍ ከፍ ያሉ ጥቂት ከተሞት ቢያጋጥሟቸውም ጉዟቸውን ያለማቋረጥ ቀጠሉ፡፡ ምሽቱ ከገፋ በኋላ አንድ ከፍ ያለች ከተማ ኢጋጠመቻቸው፡፡

“መኢሶ የሚሏች መሆን አለባት ይሀች፡፡” እለ ናትናኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ፀጥታውን አደፍርሶ፡፡

ከተማዋን አልፈው ድጋሚ ጭልጥ ባለው በረሃ ውስጥ ሰመጡ፡፡ከከተማው ብዙም ሳይርቁ ከጀርባቸው ድምፅ ይሰማቸው ጀመር፡፡

“ምንድነው” አለ ናትናኤል ፊቱን ወደኋላ መልሶ፡፡

ካልርት በፍጥነት መኪናዎን ጥግ እስይዞ በሩን ከፍ ዘሎ ወረደና ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ተመልሶ መጣ፡፡
“ምንድነው?” አለ ናትናኤል
“ሰውየው ነው፡፡”
ነቅቶ ነው አለ ናትናኤል ካልቨርት ሹፌሩን ማለቱ እንደሆ ስለገባው
አዎ፡፡”
“ምን አደረከው?” አለ ናትናኤል ሃሳብ ገብቶት።

“አስተኝቼው መጣሁ”

ሌሊቱ ከተጋመሰ በኋላ ካሉበት መንገድ በስተቀኝ ተገንጥሉ የሚሄደውን የአሰብን መንገድ ሲያዩ ከፊታቸው የተንጣለለችው አነስተኛ ከተማ የአዋሽ ከተማ እንደሆነች ገምቱ።

ወደ ከተማዋ እየተጠጉ ሲመጡ በግራና በቀኝ ያለው በረሃ ድንገት በትናንሽ ቤቶች የተሞላ መሰለ፡፡ ወደ ከተማዋ ዘልቀው ከመግባታቸው በፊት ካልቨርት መኪናቸውን ጥግ አስያዝና በሮቻቸውን እየከፈቱ ወረዱ፡፡ጊዜው እጅግ በመግፋቱ ይሆናል በአካባቢው የሚዘዋወር ሰው አይታይም ከተማዋን መሃል ለመሃል ሰንጥቆ የሚያልፈውን መገድ ይዘው ወደ ትንሿ ከተማ እምብርት በእግራቸው ቀጠሉ፡፡

አልፎ አልፎ ከተዘጉ በሮችና መስኮቶች የሚያመልጥ የብርሃን ጭላንጭል ይታያል፡፡ ልብሳቸውን የሚያርገበግበው ደረቅ ቀዝቃቅ የሌሊት ንፋስ ፊት ፊታቸውን ሲላቸው አይኖቻቸው እምባ አቀረዘዙ።

“በዚህ ሰዓት ማደሪያ ማፈላለግ ኣትኩሮት መሳብ ይመስሉኛል፡፡” አለ ካልቨርት በትክሻው ያነገበውን ቦርሳ አወርዶ ደሪት ደረቱን የሚሰውን ንፋስ ይከላከልለት ይመስል ደረቱ ላይ ለጥፎ ይዞ፡፡
“አዎ…እነዛ የጭነት መኪናዎች ይታዩሃል?” አለ ናትናኤል አገጩን
ማዶ በጨለማው ውስጥ ጭነታቸውን ጋራ አሳክለው ሽራቸውን ተጀቡነው
ወደተደረደሩ ከባድ የጭነት መኪናዎች አሹሎ “…ከነሱ ውስጥ ጠዋት ወደ
አዲስ አበባ የሚነቃነቅ ኣይጠፋም፡፡ አንዳንዶቹን አነጋግረን ከተስማማን
አሁኑኑ እንሳፈርና በጠዋት ጉዞ መጀመር እንችላለን፡፡”

በፊት ወዳዩአቸው የጭነት መኪናዎች እንደቀረቡ ናትናኤል ወደ አንደኛው የጭነት መኪና ተጠግቶ በመወጣጫው ላይ ተንጠላጠለና ፊቱን በጎን መስተዋቱ ላይ ለጥፎ ወደ ጋቢናው ውስጥ ተመለከተ፡፡ አንድ ሰው ጋቢ ተጀቡኖ ከመሪው ጎን ባለው ወንበር ላይ ተኝቶኣል፡፡ መስኮቱን በዝግታ
አንኳኳ፡፡ ሰውየው ባንኖ ተነስቶ እያመነታ መስኮቱን ዝቅ አደረገና
“ምንድነው?” አለ በእንቅልፍ ልቡ ጋቢውን ከጭንቅላቱ ላይ እየገፈፈ፡፡

“ይቅርታ ረበሽኩህ፡፡ ባክህ መንገድ ላይ መኪና ተሰብሮብን ነው::ዛሬ ጠዋት ወደ አዲስ አበባ ለመነሳት ነበር ያሰብነው፡፡ ጠዋት ወደዛው ትነሱ እንደሆነ የምታደርስልኝ ፖስታ ነበር።” አለ ናትናኤል፡፡

“ወደ አዲስ አቦ እይደለም የምንሄደው፤ ሚሌ ነው፡፡” አለ ሰውየው ናትናኤል ከመናሩ ፊት መስኮቱን እየዘጋበት፡፡

ናትናኤል ታስፋ ሳይቆርጥ ከመኪና መኪና እየቀያየረ መጠየቁን ቀጠለ፡፡ አራተኛው መኪና ውስጥ ያገኘው አውታንቲ ወደ አዲስ አበባ የሚሄድ መሆኑን ሲነግረው መጣሁ ደብዳቤውን ይዤ ብሎት ወደ ካልቨርት
ተመለስ፡፡

ለአውታንቲው ሳይነግሩት ድምፅ ሳያሰሙ ወደ አዲስ አበባ ከሚሄደው የጭነት ጀርባ ላይ እየተንጠላጠሉ ወጥተው ከጭነቱ የፊት ጫፍ ሸራ ገልጠው ገብተው ተደበቁ፡፡ የለበሱት አቧራማ ሽራ ከጨካኙ ንፋስ ቢያተርፋቸውም ሰውነታቸው ተረጋግቶ ለማረፍና እንቅልፍ ለማሰብ አልቻሉም፡፡

ማለዳ ላይ የተደበቁበት የጭነት መኪና የአዋሽን ከተማ ለቆ እያጓራ እያገሳ አቧራውን እያቦነነ ወደ አዲስ አበባ ለመክነፍ የመጀመሪያ ባይሆንም
የኋላ ኋላ የቀደሙትን መኪናዎች ተከትሎ ረጅሙን በረሃማ መንገድ በጠዋቱ ተያያዘው፡፡

አልፎ አልፎ ብቻ
👍1
የተሸፋፈኑበትን ሸራ ገሰጥ እያደረጉ ከፊት ለፊታቸው እየተሽቀዳደመ ወደ መኪና ሆድ ስር የሚገባውን የአስፋልት መንገድ እያዩ ቆዩ፡፡ ሲረፋፍድ ፀሃይዋ እየጋለች እየጠነከረች ስትመጣ ከስራቸው ስር የሚፍለቀለቀው ሙቀት ሰውነታቸውን እሳት እንደገላመጠው ጎማ አልፈሰፈሰው፡፡ ከሽራው ውስጥ ለመውጣት ግን አልደፈሩም።

አልቻልኩም ሙቀቱን፡፡ አለ ናትናኤል ሽራውን ገለጥ አድርጎ ይዞ በተቻለ መጠን ከፊት የሚከንፈውን ንፋስ ወደ ሸራው ስር ለማስገባት እየሞከረ::

ለመተኛት ሞክር::

ወለጪቲን እንዳለፉ የተሳፈሩበት መኪና ድንገት ፍጥነቱን ቀንሶ ጥግ ሲይዝ ሁሉቱም በጥያቄ ተያዩ፡፡ ወዲያው የሌላ መኪና ድምፅ ተስማቸው:: የተሳፈሩት ከጭነቱ በላይ ስለሆነ እታች ክጭነት መኪናው ጎን ለጎን የሚሄደው መኪና አልታያቸውም። ወዲያው ያሉበት መኪና ጥግ ይዞ እንደቆመ አንድ ጥቁር ሬንጅር ሮቨር አለፍ ብሎ ከፊት ቆመ።

"እነሱ ናቸው"አለ ካልቨርት በጥድፊያ ሸራውን መልሶ በጭላንጭል ቁልቁል እየተመለከተ፡፡

ጥግ ይዛ የቆመችው ሬንጅሮቨር የፊትና የኋላ በሮች ተከፍተው አራት ሰዎች ወረዱ በእጃቸው አጫጭር አውቶማቲክ ጠመንጃዎች ይዘዋል የያዟቸውን መሳርያዎች ለመድበቅ ሙከራ ሳያደርጉ ወደፊት ደግነው ይዘው በፍጥነት ወደ ጭነት መኪናለሁ ተጠጉና በግማሽ ክብ ቅርፅ ፈንጠር ፈንጠር ብለው ቆሙ::

“እርግጠኛ ነህ? እነሱ ናቸው? አንሾካሾክ ናትናኤል ከሸራው ስር።

ዝም በል! አለ ካልቨርት ሸሪውን በግራ እጁ በስሱ ከፈት አድርጎ እንደያዘ ቀኝ እጁን በሽራው ስር ቁልቁል ሰድዶ ሽጉጡን ከኪሱ ውስጥ እያወጣ

ከሬንጅሮቨር ከወረዱት ሰዎች መሃል ሦስቱ ግራና ቀኝ በተን ብለው ሲቆሙ አራተኛው አውቶማቲክ ጠመንጃውን ወደፊት እንደደገነ ወደ ከባድ መኪናው ሹፌር ተጠግቶ እንዲወርድ ምልክት ሰጠው:: ሹፌሩና ረዳቱ ያለክርክር ከጭነት መኪናው ወረዱ፡፡

እንዳትነቃነቅ” ራቅ ብሎ የቆመው ሰው ሹፌሩ ላየ ጮኸበት::

ሹፌሩና ረዳቱ ከመኪናው ስር በመሆናቸው ከዓይን ቢከለሉም
ካልቨርት አራቱን አዲስ መጤዎች በጥንቃቄ ይከታተላቸው ጀመር።

የጫናችሁት ሰው አለ?” አለ አራተኛው ስው በቁጠ ድምፅ የያዘውን አውቶማቲክ መሣሪያ አፈሙዝ በከባድ መኪናው ሹፌር አቅጣጫ ደግኖ፡፡

“የለም፡፡ ሁለታችን ብቻ ነን፡፡” የሹፌሩ ድምፅ ከበስተግራ ተሰማ፡፡

“ጭነታችሁን ገልጠን አንድ በአንድ እንፈትሻለን፡፡ ሰው ብናገኝ ወየውላችሁ፡፡ የምንከታተለው ከፍተኛ ወንጀለኞችን ነው:: እውነቱን ንገረኝ::” አለ መሣሪያውን የያዘው ሰው አየተቁነጠነጠ፡፡ “ፖሊሶች ነን የምንከታተለው የመንግሥት ወንጀለኞችን ነው::"

“እንደፈለጋችሁ ፈትሹ፤ ሁለታችን ብቻ ነን፡፡” አለ ትርፍ ሰው እንዳልጫነ ለራሱ እርግጠኛ የሆነው ሹፌር በሚንቀጠቀጥ ድምፅ:: ......


💫ይቀጥላል💫
👍1
እስቲ እኛም እንጨክን፤
አስቲ አኛሞ እንጀግን፤
ይብቃን እንባባል፤
የምን ሚስት ፣የምን ባል፤
የተዘራው ቢያሽት፣ አርመን ሳንጨርስ
መዝፈን ያልታደልን ፣ #ክርፓ ሶሮሪንስ።
ብኩን...
አንቺን መደለሌን፣
ሠርክ መበደሌን ፣ የሞደጋግመው፣
በደል አስጨክኖሽ ፣ እንድትጠዪኝ ነው።
እስቲ አኛም እንጨክን፤
እስቲ እኛም እንጀግን፤
ይቅርብሽ ብዬ እንጂ ፣ የማልዘረዝረው፣
ላንቺ ስል እኮ ነው ፣ የማመነዝረው።
ስሕተት ስመ ብሩክ ፣ኹለት ግብር ያቅፋል፤
ተሳሳችን ጸጸት፣
ተበዳይን ምጸት ፣ወልዶ ያስታቅፋል።
ታቀፍኩት፤
ታዘልከት፤
ታመምኩት፤
መበደል ዕድሉ
ራስን በመጣል
እንኳን ትታኝ ሄደች ፣ ብሎ ማጃጃሉ፤
መጃጃል አይደል ፣ የመኖር ዐመሉ?

#ክርፖ_ሶሮሪ
በኮንሶ ባህል የለፉበትን የእርሻ ማሳቸውን ሲያርሙ ከድካሙ የሚበረቱበት ህብረ ዝማሬ ነው።

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
........መፅናኛ ለሰካራምች.......
ጌትነት እንየው


በቀን እንግድነት - ከአለም እልፍኝ ገብቶ
ባይተዋር ሲሆኑ የሚመስል ጠፍቶ
ህሊናን ሲሸብብ ፣ የሰው ተንኮል ደርቶ
መንፈስን ሲደፍቅ ፣ የሰው ግፉ ምልቶ
ንፁህ ልብ ሲያፍን ፣ ክፋቱ ከርፍቶ
ሚዛንን ሲስቱ ፣ በቀን ሰው ተገፍቶ
ይሄን ጊዜ ሰውን፦
ባይጠሉትም ፈርቶ
ባይፈሩትም ሰግቶ
ከምላሱ ሸሽቶ
ይህንን የቀን ሰው ፣ ከቀን ጋራ ትቶ
ምሽት ተከናንቦ ፣ መሸታ ቤት ገብቶ
ብርሌ አንደቅድቆ ፣ መለኪያ ለግቶ
ለግቶ ለግቶ
ጨልጦ ጠጥቶ
ቢሰደቡም ሰምቶ
ቢመቱም ተመቶ
ቢገደሉም ሞቶ
ብቻ እርሱ ፈጣሪ፦
"ይቅር" እንዲላቸው ፣ ለማርያም ልጅ ሰቶ
ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ ፣ ጨርቅ ሆኖ ቡትቶ
እንደ ህፃን ድሆ ፣ ተማደሪያ ገብቶ
ቢቻል በር ዘግቶ
ካልተቻለም ትቶ
ቀበቶ ሳይፈቱ፦
ጫማ ሳያወልቁ ፣ ታልጋ ተዘርግቶ
ከሞት ከፍ የሚል ፣ እንቅልፍ አንቀላፍቶ
ተ...ኝ...ቶ ተ....ኝ....ቶ
አሁንም ተኝቶ
ሌቱ አልቆ ቀን ሲሆን ፣ ማለዳ ነቅቶ
ማታ በጠጅ ጠርቶ
ማታ በጠጅ ነፅቶ
እራስን ካገኙት
ጠዋት እንደ ክፃን ሁሉንም እረስቶ
ንጡህ ወደኔ ይቅረቡ
ብሎ እንዳላላቸው ጌታ በመዝገቡ
የየዋህነት ገፅ የፍቅር ድርሳኑ
አርጎ እንደፃፋቸው ህፃናት ከሆኑ
ምናለ ቢጠጡ
ምናለ ቢሰክሩ
በቀን ያደፈትን በምሽት ካጠሩ
#ውርሰ-ውበት



ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...

በፈረሶች ፀጉር ለሚዋቡ ሴቶች
ውርስ ተይላቸው
አብሮሽ አይቀበር ውበት ይሁናቸው


ብዙ ኩል ቀላቅለው አሳር ለሚበሉ
ስራ አቅልይላቸው አይንሽን ይትከሉ


ለቁንጅና ድጋፍ አፍንጫ ጆሯቸው
ለጌጥ ለሚበሱ
ያንቺን አውርሻቸው ውብ ጌጥ ነው በራሱ


ሳቃቸው እንዲያምር
ተነቅሰው በመፋቅ አሳር ለሚበሉት
ጥርስሽን ስጫቸው ወስደው ያስተክሉት


ሁሉንም አካልሽን ከአፈር መበስበስ መቀበር አድኚ
ቆመሽ ብቻ አይደለም ሞተሽ ውበት ሁኚ


ፀባይሽ ግን ውዴ...

እኔ ያልቻልኩትን አፈሩ ከቻለው
አደራ አታውርሺ
ፀባይሽ ቢወረስ ትርፉ መቃጠል ነው


ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...

ውበትን ለሚሹ ሴቶች አውርሻቸው
እኔም ያንቺ አፍቃሪ....

እኔም ያንቺ አፍቃሪ
ውርስሽን ልካፈል እነሱን ላግባቸው
💔 ትዝታ እና ሻማ🔥

ከሰሙ ክምር ላይ አንድ ክር ይታያል
እሱን ባየው ቁጥር...
የክሩ አቀማመጥ ያንቺን ይመስለኛል


ብርሐንና ጥላ እሳትና ቅኔ
በጨለማ መሀል የምራመድ እኔ
ልፈታ እጥራለው
ላስር እጓጓለው
በትንሿ ቤቴ..
ከሻማችን በላይ መብራቱ ምንድነው?


በቤቴ ታሪክ ውስጥ በቤቴ ብራና በጉልህ የሰፈረ
``ሻማ ሂወቴ ነው`` የሚል ቃል ነበረ
ሻማ ሂወቴ ነው ክሩ ደግሞ አንቺ
በርግጥ ቅኔ አደለም ቢሆንም ግን በርቺ
ባንቺው ስለሚያምር አንቺው ቃሌን ፍቺ
ይላል ብራናዬ!
የቤቴ አንድ ገፅ አንዱ ምዕራፌ
ያኖርኩትኝ ለሷ በሻማዬ ፅፌ
(እንዴት ነው የፃፍኩት...)


ያው እንደምታውቂው
የዚ መብራት ነገር አይታመንም ብዬ ሻማ ገዝቻለው
ግን ከገዛው ወድያ ሻማ ነው ወዳጄ መብራቱን ትቻለው
ሁሌ ማታ ማታ እሱን እያበራው
ሳበራ ሳጠፋ ብዙ ሳምንት ቆየው
ከላታት ባንቺ ቀን ባንቺ ተከፍቼ
ቤቴ ተቀምጬ ሻማዬን አብርቼ
አንቺን እያሰብኩኝ ሻማውን እያየው
ቁጥሩን ባላውቀውም ብዙ ሰዐት ቆየው
ሻማዬ ሲበራ ሻማዬ ሲያልቅብኝ
ካይምሮዬ ሰፈር አንቺን ለኮሰብኝ
ፍቅርሽ ፍቅር ነበር ያውም ሰማያዊ
መዳፍሽ የመለአክ ሁሉን ቻይ ቤዛዊ
ትዝታሽ ግን ውዴ
ትዝታሽ ግን ውዴ እንደ ሻማዬ ክር
እያቀለጠኝ ነው ሰም አድርጎኝ ፍቅር
ሰም መሆን ክፋቱ
ወይ ሰው መሆን ከንቱ
ሲያቀልጠው ይኖራል የትዝታ እሳቱ


ካይምሮዬ ሰፈር የነደደው እሳት
ሰም ነበረች እና ልቤን አቀለጣት
ለነገሩ ትቅለጥ ድሮም የኔ አይደለች
ነዳ የምታነደኝ ክሬ ግን እሷ ነች
እኔ ምስኪን ሻማ ባልሞላ ኑሮዬ
እሳት ፍም ትዝታን ተሸክሜ ችዬ
አለው እኖራለው እድሜ ለሷ ብዬ
ትዝታና ሻማን በሳት አቃጥዬ!
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው


.....በመጨረሻም የሚፈልገውን ጥል እንዳሰበው አገኘው፡፡ ኬስሌ ጀምስ፡፡
ይህ ኬስሊ ጀምስ የተባለ ወጣት ዋት መንደር ውስጥ የተወለደ የወረደ
ህይወት ያለው ሴት አቃጣሪና በትርፍ ጊዜውም የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ
ሲሆን አውቆ የተሳሳተ መረጃ ሰጠውና የመጀመሪያውን ትልቁን የወንጀል
ምርመራ ጉዳዩን አሳጣው፡፡ ከፍርድ ቤት ከወጣ በኋላ ጄሪ በቀጥታ ጄምስን
ፍለጋ ጄምስ ወደሚገኝበት ቤት አመራ፡፡ ጄምስንም መኪናው ውስጥ አገኘው፡፡ ከመኪናው ጎትቶ አውርዶት ሰው ሁሉ እያየው እስኪበቃው ድረስ ቀጠቀጠው፡፡ ልጁ ለሶስት ሳምንት ያህል በፅኑ ህሙማን ክፍል ከቆየ በኋላ እንደምንም ብሎ ህይወቱ ተረፈ::፡ ነገር ግን ዕድሜውን በሙሉ በተሽከርካሪ
ወንበር ላይ እንደሚያሳልፍ እንዲሁም ደግሞ መሰረታዊ የሆኑ የተፈጥሮ
ግዴታዎቹን እንኳን ለመወጣት የግድ አጋዥ የሚያስፈልገው ሰው ሆነ::

ጄሪ በሰው መግደል የሙከራ ወንጀል ተከስሶ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ሁሉም
በፍርድ ቤቱ የሚገኙ ወንዶች ጄሪ በስራው ላይ እያለ ጄምስን ሊይዘው ሲል
ስለተቃወመውና እንደዚሁም ደግሞ መሳሪያ ሊመዝበት ስለነበረ ጄሪ ራሱን
ለመከላከል ሲል ያደረገው ነገር ነው ብለው መሰከሩለት፡፡ ነገር ግን የኬስሊ
ጄምስ እናት ፍርድ ቤት ቀርባ እየተንሰቀሰቀች እና እየጮኸች እህቶቹም ያኔ በፖሊስ እስኪሞት ድረስ የተደበደበው የመጨረሻ ዝቃጭ ወንድማቸውን
የወደፊቱን ብሩህ ህይወቱን እንደተነጠቀበት አድርገው አራገቡት፡፡

ሚክ ጆንስን የፍርድ ሂደቱን በየቀኑ ሲከታተል ነበር፡፡ ችሎቱን በማስኬድ ላይ የምትገኘውን ሊብራል (ነፃ አሳቢ፣ ለዘብተኛ) ጨጓራ የምትልጠው ሴት ዳኛ የጄምስ ቤተሰብ የሚናገረውን እያንዳንዱን ቃላት በውስጧ ስትይዝ እየታዘባት ነበር፡፡ በተለይ ደግሞ የጄምስ ቤተሰቦች ስለዚህ የማይረባ ልጃቸው የሌለውን የውሽት ነገሮች እያወሩ የጄሪን ጥሩ ሥም እንዲጨቀይ ስላደረጉ በንዴት ጨጓራው ይላጥ ነበር፡፡ ግን ምንም ማድረግ አይችልምና ዝም አለ፡፡ ጄሪ የግድ የዳኛውን ልብ የሚያሳዝን ታሪክ መፍጠር ያስፈልገዋል፡፡

የመጀመሪያው በሚስቱ ሞት የተነሳ ከፍተኛ ሀዘን ደርሶበት ስለነበር
የአዕምሮ አለመረጋጋት ስለደረሰበት ነው የሚል የመከላከያ ሀሳብን አቅርቦ
ጠበቃው ተከራከረለት፡፡ በመቀጠል ትንሿ ልጁን ጁሊን አቅርቦ ጁሊ እንዴት
አባቷን እንደምትወድ እና እናቷ ከሞተች ጀምሮ ቤተሰቡ በጣም እንደተጎዳ
ጭምር ተናገረች፡፡ የጄሪ የቀድሞ የትቤት እና የእግር ኳስ ክለቡ ጓደኞቹም
ለጄሪ መሰከሩለት፡፡ ምን ይሄ ብቻ የአካባቢው ፖስተርም ፍርድ ቤት ቀርቦ
ስለ ጄሪ መልካም ባህሪ እና ሃይማኖተኝነት ጭምር የምስክርነት ቃሉን
ሰጠ፡፡
ነገር ግን ይህቺ ሸርሙጣ ኒኪ ሮበርትስ የተባለችው ሴት የምስክርነት ሳጥን ውስጥ ገብታ የምስክርነት ቃሏን ስትሰጥ የጄሪ የመከራ ህይወት ተጀመረ፡፡ ዶክተር ሮበርትስ ከፍተኛ ሀዘን በሀዘንተኛው ላይ ስለሚያሳድረው የስነ ልቦና ችግር የባለሙያ ምስክር ሆና ነበር የቀረበችው፡፡ ከፍተኛ የሆነ ሀዘን ላይ ያለ ሰው ጄሪ ያደረገውን ነገር ያደርጋል? ከፍተኛ ሀዘን
ልንቆጣጠረው የማንችለውን የአመፃ ስሜትን በሰዎች ላይ ያሳድራል? ጄሪ
ከቫክ በጣም ከፍተኛ ሀዘን ውጥ ስለነበረ ሀዘኑም አዕምሮውን ኬስሊ ላይ
ጥቃት ሲሰራም በትክክለኛ አዕምሮው አልነበረም? የሚሉ የባለሙያ መልስ
የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች ለዶክተር ሮበርትስ ቀርቦላት ነበር፡፡ እሷ ግን
መልሶቹን ስትመልስ

“አያደርግም፡፡”

“አያሳድርም፡፡”

“እንደዚህ የሚባል ነገር የለም፡፡”

የሚሉ መልሶችን ሰጠች

ዶክተር ሮበርትስ በሰጠችው ሙያዊ ምስክርነት ውስጥ አንድም የጄሪን
ነገር ያካተተ ሚዛናዊ አስተያየት አላከለችም፡፡ በእሷ ሙያዊ አስተያየት
ደግሞ ጄሪ ምንም አይነት የአዕምሮ ችግር እንደሌለበት አስረዳች፡፡
ጥቃቱንም ሲፈፅም በድንገት ሳይሆን አቅዶበት ነው አለች፡፡ ምናልባትም ጄሪ
ባለው የዘረኝነት እና የራስ ወዳድነት ምክንያት ጥቃቱን ሲፈፅም ከሀዘን
ይልቅ የሀይለኝነት ስሜቱን ለማንፀባረቅ ስላሰበ ነው ብላ ሁሉ ነገሩን በጄሪ
ላይ ደፈደፈችበት፡፡ ሚክ ጆንሰን ይህቺ ቀጭን ዶክተር ተብዬ ባለሙያ ስለ
ጄሪም ሆነ በሥራ ላይ ስላሉ ፖሊሶች ምን ያህል አደጋን ከእንደነዚህ ኬስሊ
ጄምስን ከመሳሰሉ ሰዎች እንደሚቀበሉ አታውቅም እና እርር እያለ የእሷን
ምስክርነት ቁጭ ብሎ ሰማት፡፡

በመጨረሻም ጄሪ ኮቫክ ከፍተኛ ወንጀለኛ ሆኖ ተገኘና ይህቺ ለዘብተኛ
ዳኛ የሃያ አምስት ዓመት የእስር ፍርድን ፈረደችበት፡፡ ለሁለት ጊዜ ያህል
ይግባኝ ቢልም በእነዚህ ሁለቱ የይግባኝ ጊዜዎችም ይህቺ የተረገመች ኒኪ
ሮበርትስ የተባለች ሴት በፍቃደኝነት እየቀረበች ከጄሪ በተቃራኒ ሆና
ምስክርነቷን ሰጠች፡፡ በቃ እንዲሁ እንደቀልድ በኒኪ ሮበርትስ የተነሳ ሚክ
ጆንስን ጓደኛው ጄሪ ኮቫክ ቀሪ ዕድሜውን በእስር ቤት እንዲያሳልፍ
አስፈረደችበት፡፡
ወደ ድሮ ጓደኛው ዞሮ ፈገግ እያለም ለራሱ እንኳ የማይሰማውን በጎነትን ጓደኛው እንዳያጣ አስቦለት ሦስተኛውን ይግባኝ እንዳመለከተለት ነገረው፡፡

“ጥሩ ነገር የምናገኝ ይመስልሃል?” ብሎ ጄሪ ጠየቀው፡፡

“ይመስለኛል” ግን የአሁኑ ይግባኛችን ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡
ለሚቀጥሉት ስድስት ሳምንታትም ከፍርድ ቤት ምንም አይነት ምላሽ ላናገኝ እንችላለን” አለው ሚክ፡፡

“አታስብ እስር ቤት ውጥ ስትሆን እኮ የሚኖርህ ብቸኛ ነገር ጊዜ ብቻ
ነው። ይልቅ አንተ በመርማሪነት ስለያዝነው ጉዳይ ንገረኝ እስቲ? በጩቤ
ተወግተው ነው ሰዎቹ የተገደሉት ብለኸኝ ነበር አይደል?” ብሎ ጄሪ
ጠየቀው፡፡

“አዎን” ብሎ ጆንሰን ትንሽ ተንተባተበና “በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ይመስለኛል፡፡ ትንሽ መፍጠን ባንችልም ወደ መቋጫው እየቀረብን ሳይሆን አይቀርም”

ዶክተር ኒኪ ሮበርትስ ከዚህ የዞምቢ ግድያ ጋር ስላላት ግንኙነት ላጄሪ
ሊነግረው አልፈለገም ወይም ደግሞ ስለ ዝርዝር ነገሩ ሊያጫውተው ፈቃደኛ
አልሆነም፡፡ ሚክ ጆንሰን ኒኪ በባሏ የመኪና አደጋ ግድያ ላይ እጂ እንዳለበት
ሙሉ በሙሉ ያምናል፡፡ ያህንን ማረጋገጥ ግን ይጠበቅበታል፡፡ ከተሳካለት
በመረጃ አስደግፎ እሷን ፍርድ ቤት ያስቀርብና በጄሪ ላይ የሰጠችው
የምስክርነት ቃል ተቀባይነት እንዳያገኝ በማድረግ ጄሪን ያስለቅቀዋል፡፡
ወይም ደግሞ እሱ ላይ መስክራ ቀሪ ዕድሜውን በእስር ቤት እንዲያሳልፍ
ያስፈረደችበት ሴት፣ ልክ እንደ እሱ እስር ቤት ቀሪ እድሜዋን እንድታሳልፍ
ሲያደርግ ያሳውቀዋል፡፡ አሁን ግን ይህንን ሀሳቡን ላጄሪ ቢነግረው ያልሆነ
ተስፋ ያድርበትና ምናልባት ጉዳዩ እንዳስበው ባይሳካለት ይጎዳል ብሎ
በማስብ ሳይነግረው ቀረ፡፡

በቀረው የጥየቃ ሰዓታቸው ሁለቱ ሰዎች ብዙ ሳያወሩ ቁጭ ብለው ቆዩ፡፡ ሚክ በሚቀጥለው ወር መጥቶ እንደሚጠይቀው እና ጁሊ ልጁንም
አብራው እንድትሄድ እንደሚጠይቃት ቃል ገብቶለት ተሰናብቶት ወጣ፡፡ ሚክ
ጆንሰን ምንም እንኳን ልጅ ባይኖረውም የጓደኛው ብቸኛ ልጁ ጁሊ ኮቫክ
በአባቷ እንደዚህ መሆን ምንኛ እንደሚጎዳት ይገባዋል፡፡ በእርግጥም በድጋሜ ኒኪ ሮበርትስ ከጄሪ የነጠቀችው ሌላኛው ነገር ደግሞ ሴት ልጁን ነው፡፡።
ጁሊ አባቷ ጄሪ ኮቫክ ላይ የሃያ አምስት ዓመት የእስር ፍርድ ሲፈረድበት የ13 ዓመት ልጅ ነበረች፡፡ በዚህ ምክንያት በመካከላቸው ሊኖር የሚገባው የአባት እና የልጅ ግንኙነት ተበጠሰና ለመራራቅ በቁ፡፡

ያቺ ሸርሙጣ ዶክተር ጄሪ ኮቫክን ሁሉ ነገሩን ነው ያሳጣችው፡፡

ጆንሰን ወደ ሎስአንጀለስ እየተመለሰ እያለ መሀል ላይ
የመኪናው አየር ማቀዝቀዣ አልሰራም አለው፡፡ ሁሉንም የመኪናውን መስኮቶች ቢከፍትም
ሙቀቱ ልብሱን በላብ እንዳራሰው ነበር መኪናውን ሲያሽከረክር የነበረው፡፡
መሪ አጥብቆ እንዳይዝ እያስቸገረው በነበረበት ጊዜ ላይ ነው እንግዲህ አጋሩ
ጉድማን ወደ እሱ የደወለው፡፡ ስልኩን ሲያነሳም ልክ ፀሐይ እንዳቃጠለው
ውሻ እያለከለከ ነበር፡፡

“ምድነው?” ብሎ ጆንሰን በቁጣ ተሞልቶ ስልኩን አነሳ።

“የት ነው ያለኸው?” ብሎም ጉድማንም በቁጣ መለሰለት፡፡

“እየነዳሁ ነው”

“በኢየሱስ ምድነው ይሄ ሁሉ ማወጣጣት?” አለና ጆንሰን በመቀጠልም
“ማወቅ አለብኝ ካልክ ከቫሊ ስቴት እስር ቤት ወደ ሎስ አንጀለስ እየመጣሁ ነው።

“ጓደኛህ መርማሪ ፖሊስ ጄሪ ኮቫክን ጠይቀህ በመመለስ ላይ ነዋ
ያለኸው?” ብሎ ጉድማን ሸረደደውና በመቀጠልም “የሚገርም አጋጣሚ ነው
ባክህ የኮቫክን የችሎት ውሳኔ እና የምስክሮቹን ቃል እያነበብኩኝ ነበር።
ታዲያ በዚህ ሪፖርት ላይ የባለሙያ ምስክርነትን የሰጠችው ሰው ማን
እንደሆነች ገምት እስቲ?” አለው እና ጉድማን አሸናፊ በሆነ የኮራ ድምፅ
“ትላንትና ማታ ከኒኪ ሮበርትስ ጋር አብረን እራት በልተን ነበር” አለው፡፡

“እሱንማ አውቃለሁ” ብሎ ጆንሰን በምሬት በተሞላ ድምፅ መለሰለት።
“እናማ ማታ ላይ ስለ ፍርድ ቤት ተሞክሮዋ አንስታ አንዳንድ ነገር
አውርታኝ ነበር” ብሎ ጉድማን አውቆ ነገሩን ለማክረር በሚል ስሜት “ከእሷ
ከተለየሁ በኋላ በእሷ ዙሪያ ምርምራዎችን ሳደርግ ምን ባገኝ ጥሩ ነው? ሁለታችሁ ለካ የጋራ ታሪክ ነበራችሁ፡፡”

“እሺ እሺ አሁን ማሾመርህን ትተህ በቀጥታ ወደ ጉዳይህ ለምን
አትገባም?” አለው ጆንሰን፡፡

“ምንድነው ያልነገርከኝ?” ብሎ ጆንሰን ጠየቀ፡፡

“ምንም የሚነገር ነገር የለንም ነው ያልከኝ? ኧረ ባክህ? ለዚህ ነበር ለካ
የምትጠላት አይደል? ምክንያቱም የልብ ጓደኛህ ላይ የምስክርነት ቃሏን
ስለሰጠች ነው አይደል?”

“አይደለም” አለው እና ጆንሰን በዝግታ “እሷን የምጠላት ትፋታም ሸርሙጣ ስለሆነች ነው፡፡ እናም ደግሞ ሦስት ንፁሀን ሰዎችን ለመግደል ቅንብር የፈፀመች ሰው ነች ብዬ ስለማምን ነው” አለው፡፡

“ሚክ ከዚህ የምርምራ ጉዳይ ላይ ራስህን በፈቃደኝነት ልታነሳ ይገባሃል!” ጉድማን በንዴት ተሞልቶ ጮኸበት፡፡

“ለምን ብዬ?”

“ምክንያቱም አንተ ለእሷ ጥሩ አመለካከት የለህም”

“ኧረ ነው እንዴ? እሺ አንተስ ባክህ?” ብሎ ጆንሰን ራሱን ለመከላከል
እየሞከረም በመጀመሪያው ቀን ጀምሮ አንተ እሷን ወደ አልጋ ለመውሰድ
ስትቋምጥ ነበር፡፡ ትላንትና ማታ ከእሷ ጋር ራት በልትሃል እኮ በኢየሱስ
ስም! ታዲያ ይህ ነገርህ አንተንስ ለእሷ የተዛባ አመለካከት እንዲኖርህ
አያደርግህምን?”

“አያደርገኝም! ለማንኛውም ከእሷ ጋር ለመወሰብ ሳይሆን እንድትቀርበኝ
እና እንድታምነኝ ስል ነው እሺ” አለው ጉድማን፡፡

ጆንሰን ጉድማንን እያንቋሸሽ ቢስቅም ውስጡ ግን ተረብሾበታል።ጉድማን የኮቫክን፣ የእኔን እና የዶክተር ኒኪን ግንኙነት ይደርስበታል ብሎ አልገመተም ነበር፡፡ ስለዚህ ከአሁኑ በኋላ ስለ ኒኪ ሮበርትስ ሲያወራ በጣም መጠንቀቅ እንዳለበትም አሰበ፡፡

“ትላንትና ማታ በጣም እንድትቀርብህ አላደረግካትም፡፡ ብትቀርባት ኖሮ
ግን ስለ ግሮልሽ ጉዳይ የዋሸችውን ውሽት ታምንልህ ነበር አይደል?” ብሎ
ጆንስን ጉድማንን ጠየቀው፡፡ ምክንያቱም የጉድማን ደካማ ጎን ይህ እንደሆነ
እና በዶ/ር ሮበርትስ ላይም ያለውን እምነት የሚሸረሽርበት ጉዳይ እንደሆነ
ያውቃል፡፡

“እሱ ላይ በደንብ እየስራሁኝ ነው” ብሎ ጉድማን አመነለትና
“ለማንኛውም አሁን ለምነግርህ ነገር ተዘጋጅ፡፡ ኒኪ ሮበርትስ በአንተ ላይ
የአፀፋ ምላሿን ጀምራለች፡፡”

“የአፀፋ ምላሽ?” ብሎ ጆንሰን አሾፈበትና “እንደዚህ አይነት ያሉ ትላልቅ ቃላቶችን ሀርቫርድ እያላችሁ ያስተምሯችሁ ነበር እንዴ?”

“ሚክ እሷ የግል መርማሪ ዴሪክ ዊሊያምስን ቀጥራዋለች” ብሎ ጉድማን
ጉዳዩን አፈረጠለት፡፡

ይህን ሲሰማ ጆንሰን ከፊት ለፊቱ ይመጣ የነበረን መኪናን ከመግጨት የተረፈው ለጥቂት ነበር፡፡ እንደምንም ብሎ መሪውን ጠምዝዞ እና ፍሬን ይዞ መኪናውን አቆመ። ከዚያም ፀያፍ ስድቦችን ይሳደብ ጀመር፡፡

ጆንሰን ልክ በሀይለኛ ነፋስ ውስጥ እንደሚሄድ ሰው ሁሉ በሀይል
እየተነፈሰ “እያሾፍክብኝ ባልሆነ? የምርህን ነው ግን?”

የውሽቴን ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር፡፡” ብሎ ጉድማን ተነፈሰ እና “ትናንት ወደ እሱ ቢሮ ስትሄድ ተከትያት ነበር”

“ይሄ ድቡልቡል ዲቃላ...” ብሎ ጆንሰን ስድቡን ሲመርጥ ጉድማን በውስጡ ሁለታችሁም ያው አይደላችሁም እንዴ?” ብሎ ነገሩን በመቀጠል ሚኪ እንደነገረችኝ ከሆነ የቀጠረችው የሆኑ የምትፈልጋቸውን መልሶችን
ለማወቅ ስለፈለገች እና እኛ ደግሞ ምንም አይነት መልሶችን ልንሰጣት
ስላልቻልን፣ በተጨማሪም ደግሞ እንደ ተጠርጣሪ መታየቷም በጣም
ስላበሳጫት እንደሆነ ነው ያስረዳችኝ፡፡” አለው፡፡

“በጣም ብዙ መልሶችን እኮ ሰጥተናት ነበር ብሎ ጆንሰን አሰበ እና ንገር
ግን ሁሉም መልሶች ወደ እሷ ስለሚያመለክቱ አልወደደቻቸውም አእምሮው አሁን በሰማው አዲስ መረጃ እየታመሰ ራሱን እነዚህን ጥያቄዎችን ይጠይቅ ጀመር፡፡ “ዶክተር ሮበርትስ ለምንድነው ዴሪክ ዊሊያምስን የቀጠረችው?ጆንስን እውነቱን ከሆነ እና ኒኪ ደግሞ ከግድያዎቹ በስተጀርባ የምትገኝ ከሆነ የግል መርማሪን መቅጠር ምንም ፋይዳ የለውም፡፡ ማለትም እሱ በእኛ ላይ የማይረቡ ቆሻሻ ነገሮችን ቆፍሮ እንዲያወጣ ካደረገች በኋላ የእኛ የምርመራ ውጤት እንዲጣል፣ እሷም አንድያውን ከወንጀሏ ነፃ እንድትወጣ ያስችላታል” ብሎ ለራሱ ግምቱን አስቀመጠ፡፡

ይህንን ግምቱን ለጉድማን ሊያሳውቀው በግማሹ ቢፈልግም፣ አጋሩ ጉድማን እሱ በኒኪ ላይ የተዛባ አቋም ነው ብሎ እንደሚያምን ስለሚያውቅ ሊነግረው አይችልም፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ምንም የማይፈራውን ዊሊያምስን ተጠቅማ ምርመራቸውን ስታበላሽባቸው እጁን አጣምሮ ሊመለከታት አይችልም፡፡

“ልናስቆመው ይገባል” አለው ጆንስን፡፡

“በመጨረሻ የምንስማማበት አንድ ነገር አገኘን” አለና

“ግን እንዴት እናስቁመው ነው ጥያቄው”

ሁለቱም ለአፍታ ያህል ዝም ብለው ከቆዩ በኋላ ጆንስን “ከሁለት አንዳችን ልናገኘው ይገባል” አለው፡፡

“አንዳችን ብቻ አይሆንም” ብሎ ጉድማን በመቀጠልም “ሁለታችንም ነን
በጋራ ልናገኘው የሚገባን፡፡ እዚህ ከተመለስክ በኋላ እናወራበታለን አለ፡፡
ጉድማን ስልኩን ከዘጋ በኋላም የኮቫክን የችሎት ውሳኔ የያዘ ወረቀት ወደ ፋይሉ መለሰ፡፡

እንግዲህ በድጋሚ ጄንሰን ና እሱ አጋር ሊሆኑ ነው፡፡ ግን የማይተማመኑ አጋሮች ናቸው፡፡ በትክክለኛው መንገድ ለመሄድ ሊወስደው የሚገባው ጥቂቱ እርምጃውም ነው፡፡ የአባቱን ወዳጆችህን አቅርባቸው፣ ጠላቶችህን ደግሞ በጣም አቅርባቸው” የሚለውን ምክር አስታወሰ፡፡ ሎው ጉድማን ይህንን የአባቱን ምክር ሁሌም እየተገበረ ነበር ሲኖር የነበረው፡፡
እነዚህን መሰል ምክሮችን ለመተግበር በመቻሉም ነው እስካሁን ድረስ
በሕይወት መቆየት የቻለው፡፡

ይቀጥላል
👍21
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


....“ጥሩ እንዳትነቃነቅ::" አለ አራተኛው ሰው መሣሪያውን ደግኖ እንደያዘ ወደ ጭነት መኪናው እየተጠጋ፡፡ በእርጋታ ወደፊት እየተራመደ በዓይነ ጭነቱን ያዳብስ ጀመር፡

እራቅ ብለው ሁኔታውን በዝምታ ይከታተሉ የነበሩት ሦስት ሰዎች የመሃሉ ድንገት ተጣራና ጭንቅላቱን ወደኋላ መታ አደረገ፡፡ ወዲያው ወደ ጭነት መኪናው የተጠጋው አራተኛው ሰው ፊቱን መልሶ ወደ ጓደኞቹ ሮጥ ብሎ ተመለስና ሰብሰብ ብለው ይነጋገሩ ጀመር፡፡
“ጠዋት ምንያህል መኪናዎች ቀድመዋችሁ ወደ አዲስ አበባ
ተነስተዋል?” አለ አራተኛው ሰው ፊቱን ወደ ጭነት መኪናው ሹፌር
መልሶ ድምፁን ከፍ አድርጎ፡፡

“አንድ ሶስት አራት ይሆናሉ፡፡” አለ ከጭነት መኪናው ወርዶ የቆመው ሹፌር፡፡

ወዲያው አራቱ ሰዎች ሮጥ ሮጥ እያሉ ሬንጅሮቨራቸው ውስጥ ገቡና በአዲስ አበባ አቅጣጫ በረሩ፡፡
“ኡፍ .…ፍ!!” አለ ካልቨርት ጭንቅላቱን በተኛበት ጆንያ ላይ ጥሎ፡፡
“ሄዱ? ” አሉ ናትናኤል ሽራውን እንደተከናነበ በሹክሹክታ፡፡
“አዎ፡፡ ያለቀልን መስሎኝ ነበር::”

የጭነት መኪናው ሹፌር መኪናው ውስጥ ገብቶ ሲንቀሳቀሱ በተቻላቸው መጠን መንፈሳቸውን አረጋግተው መመካከር ያዙ፡፡

“ያላጥርጥር በየከተሞቹ ኬላዎች ላይ ይጠብቁናል፡፡ በተለይ ወደ አዲስ አበባ እየቀረብን ስንመጣ አስቸጋሪ ነው የሚሆንብን፡፡” እለ ናትናኤል፡፡
“አዎ፡፡ : ካአሁን ወዲያ ወደየትኛውም ከተማ መግባት የለብንም፡፡ ወደ ከተሞች ስንቀርብ እየወረድን ከጀርባ በግማሽ ክብ ቅርፅ በእግር ማለፍ ነው ያለን አማራጭ፡፡”

“ከናዝሬት ወዲያ ያለውን አካባቢ አውቀዋለሁ! መንገዱን በሩቅ
እይታ እስከተከተልን ድረስ ችግር አይገጥመንም::አለ ናትናኤል፡፡
ናዝሬት ከተማ ሲደርሱ እንድ አምስት ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው ከተደበቁበት ሸራ ውስጥ ብቅ ብቅ እያሉ ከኋላና ከፊት ሌላ ተሽከርካሪ አለመኖሩን ካረጋገጡ በኋላ በጭነት፡ ላይ እየዳሁ ወደ መኪናወ ኋላ ተጠጉ፡፡
ሸራው የተጠፈረባቸውን ወፋፍራሃም ገመዶች የሙጢኝ ጨምድደው ይዘው
ቁልቁል ተንጠለጠሉ፡፡

“ተጠንቀቅ፡፡ አስፋልቱ ላይ ኣንዳታርፍ፡፡ በሁለት እግሮችህ ለማረፍና ለመቆም አትሞክር፤ ከዘለልክ በኋላ ጭንቅላትህን ቀብረህ ተንከባለል፡፡ እኔ ስዘል ተመልከት፡፡” አለ ካልቨርት በወጣትነት ዘመኑ በአገሩ ውስጥ ያሳለፋቸውን የኮማንዶ ህይቱን እያስታወሰ፡፡ "

በሰላሳ ሜትር ርቀት ልዩነት ሁለቱም የተንጠላጠሉባቸውን ገመዶች እየለቀቁ ከጭነት መኪናው ላይ ተፈናጠሩ፡፡ ካልቨርት አልተጎዳም፤ ናትናኤል ግን ግራ ክንዱ ክፉኛ ተገሸለጠ፡፡

“አስፋልቱ ላይ አትረፍ፡ እያልኩህ እንዲያውም ተርፈሃል፡፡ወደጎን
ባትንከባለል ኖሮ ይሄ አስፋልት ጭንቅላትህን ነበር የሚፈረክስልሀ፡፡” አለ
ካልቨርት እየሮጠ መጥቶ ናትናኤልን ደግፎ እያነሳው፡፡

አውራ መንገዱን እየራቁ፤ እየሸሹ የናዝሬትን ከተማ በስተቀኝ
ጀርባዋ ዞሯት::

"መንገዱ ወደቀኝ የሚታጠፍ፡ ስለሆነ ከዚህ በኋላ በቀጥታ መስመር ብንሄድ ወይም በሃያ አምስት ኪሎ ሜትር ላይ በዱከምና በሞጆ መሃል መንገድ ላይ ብቅ እንላለን፡፡ አለ ካልቨርት ካርታውን አውጥተው ሲያጠኑት ከቆዩ በኋላ፡፡

እንዳለው ከሦስት ሰዓት ተኩል የእግር ጉዞ በኋላ በሞጆ ከተማ አልፈው ከአውራ ጎዳናው ጋር ተገናኙ:: ብዙም ሳይቆዩ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ የገጠር አውቶቡስ አስቁመው ተሳፈሩ፡፡

“አዲስ ፈለጥ!“ ይላሉ አውቶብሱ ውስጥ ከሹፌሩ ጀርባ የተቀመጡ አዛውንት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፡፡ “ከአውቶብሱ ገብቶ
መፈተሽ የአባት... “ቆብህን አውልቅ፤ ክንብንብህን አውርድ ብሎ ነገር
ምንድነው? ወቸጉድ!”

“የሚፈልጉት ሰው አለ መሰለኝ::” አለ ባሻገር የተቀመጠ ልጅ እግር፡፡

ታድያ ቢኖርስ ባለፍንበት ከተማ ሁሉ እየቆምን ቆብና ክንብንባችንን መገፈፍ የአባት ነው?ልማድ ነው? ወይ ፈጣሪ?” ሽማግሌው ተቆጠ፡፡

“ምንድነው?” አላቸው ናትናኤል ከጎኑ የተቀመጡትን ሴትዮ::

“እንጃ! ባለፍንበት ከተማ ሁሉ መሣሪያ ደግነው እንደ ሽፍታ ሲበረብሩን ቆዩ፡፡” አሉት ሴትየዋ መደነቃቸውን፣ መገረማቸውን ለማሳየት እጃቸውን አፋቸው ላይ ጣል አድርገው፡፡

“እነማን ናቸው?” ናትናኤል ግራ የተጋባ መስሎ ጠየቃቸው፡፡

“ምኑን አወቄው ብቻ ከወለንጭቲ የጀመሩ ሰባቴ እያስቆሙ ሁለት
ሁለት፥ሦስት ሦስት እየሆኑ እንዲህ እንዲህ እያደረጋቸው ሲበረብሩን ዋሉ፡፡
ሆ! እንደ አነሳሳችንኮ ገና ቅድም ታዲስ አበባ ደርስን ነበር ጊዮርጊስ ይይላቸው”

ናትናኤል ዞር ብሎ ካልቨርትን ሹክ አለው::

ደብረዞይት ሊደርሱ ትንሽ ሲቀራቸው ተጠቃቀሱና መጀመሪያ ካልቨርት እራቅ ብሎ ደግሞ ናትናኤል ተከታትላው ወረዱ፡፡

“ምንድነው?” አለ ካልቨርት አውቶቡሱ ውስጥ የተባለውን ሁሉ አጣርቶ ለመረዳት ጓጉቶ፡፡

ናትናኤል አውቶቡሱ ውስጥ የሰማውን ሁሉ ዘርዝሮ ነገረው፡፡

“ከአሁን ወዲያ መኪና ላይ መውጣት የለብንም::” አለ ካልቨርት፡፡
“ታዲያ እንዴት አናደርጋለን?”
“አሁን ሁለታችንም የተዳከምን ይመስለኛል፡፡ ለጊዜው ከመንገድ
ፈቀቅ ብለን እንረፍና ከጨለመ ወዲያ ሌሊቱን መንገዱን ተከትለን በእግራችን እንቀጥላለን፡፡ ከበረታንና ሰሰዓት አምስት ኪሎ ሜትር ብንጓዝ እንኳን ከምሽቱ አንድ እስከ ጠዋቱ አንድ ሰዓት ስልሳ ኪሎ ሜትር ሽፈንን ማለት ነው:: ፀሐይ ስለማይበረታብን የምንሸነፍ፡ አይመስለኝም፡፡”
ከመንገዱ በስተቀኝ እርቀው ገብተው
ለብቻዋ በቆመች የግራር ዛፍ ስር በደረታቸው ተደፍተው ለማረፍ
ሞከሩ::እየጠለቀች ያለችው ፀሐይ እንደጌጥ ብታብረቀርቅም ሙቀቷ እየከዳት መጣ፡፡ አውላላ ሜዳ ላይ ብቻውን እየተመላለሰ የሚጋልበው ቀዝቃዛ ነፋስ ሰውነታቸውን ጠዘጠዘው፤ ምግብ ሳያገኝ ሁለተኛ ቀኑን የያዘው
ሰውነታቸውም ከፊት የተደቀነውን መንገድ ቁጭ አድርጎ ተዳከመ፡፡ ቢሆንም ፀሐይ ልትሸሽግ ሲዳዳት ከተኙበት ተነስተው የመንገዱን ጥግ ይዘው በአዲስ አበባ አቅጣጫ ጉዞአቸውን በእግር ተያያዙት፡፡

“እርምጃህን አትቀያይር በአንድ ዓይነት ፍጥነት አንድ አይነት ስፋት ተራመድ አለበለዚያ ይደክምሃል፡፡” አለ ካልቨርት እጆቹን እያወናጨፈ፤ “ከጎን ከጎኑ የሚንቶሰቶሰውን ናትናኤልን ዞር ብሎ
ተመልክቶ፡፡

አልፎ አልፎ በሩቁ የመኪና መብራት ሲታያቸው ፈጠን ብለህ ከአውራ መንገዱ እራቅ እያሉ መሬቱ ላይ በደረታቸው አየተኙ እያሳለፉ መንገዳቸውን ያለንግግር ቀጠሉ፡፡ ሁለት ጊዜ ጅቦች ሲያጋጥሟቸውም ሁለቱንም ጌዜ የካልቨርት ሽጉጥ የጥይት ጩኹት አተረፋቸው፡፡

እንዳሰሱት እስከጠዋቱ አንድ ሰዓት ድረስ አልተጓዘም፡፡ ከጠዋቱ አስራ አንድ ሰዓት አካባቢ አቃቂ ከተማ እንደደረስ ያለዕረፍት መቀጠል እንደማይችሉ ስለተረዱ ከመንገዱ ወጥቶ እራቅ ካለ ጫካ ውስጥ ገብተው ካልቨርት እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡ናትናኤል እስካሁን ያሳለፋውን ሁኔታዎች አንድ በአንድ በህሊናው እየመላለሰ ይቃኝ ጀመር፡፡ ርብቃ…
አብርሃም… የቢሮ አለቃው.… ወታደራዊ አታሼዎቹ… ነጭዋ ሲትሮይን
የምሥራች ዘውዲቱ… አዲስ አበባ ድሬዳዋ…ካልቨርት ይህ ሁሉ ውጣ
ውረድ ከርብቃ ስቃይና ከእርግዝናዋ ጋር እየተሰባጠረ ይታየው ጀመር፡፡
ርብቃን ለማዳን ምን ማድረግ አለበት? አወሬዎቹን መጋፈጥ? ከአውሬዎቹ
ጋር መደራደር? ካልቨርት ምስጢሬን ይዤ ልሙት ባይ ነው፡፡ ካልቨርትን እንደገና ማግባባትና ማሳመን ይቻላል? ወይስ የሞተ ፡ ነገር ነው? ለማናቸውም ለካልቨርት ምንም ፍንጭ ማሳየት የለበትም… ማናቸውንም ጉዳይ ከካልቨርት መደበቅ ይኖርበታል፡፡

የተጫናቸው ድካም በዙሪያቸው ከነበረው የማለዳ ውርጭ የከበደ
👍1
ነበር፡፡ ሁለቱም ለበርካታ ሰዓታት ተኝተው አረፈዱ፡፡ በመጀመሪያ ከእንቅልፉ የነቃ ካልቨርት ነበር፡፡

“ረፍዷል... የምንበላው ምናምን ብናገኝ የቀረንን መንገድ ተጠናክረን እንቀጥል ነበር፡፡” አለ ካልቨርት፡፡
ከእንቅልፉ ነቅቶ ፡ እግሮቹን አንፈራጦ ከጀርባው ያለ የዛፍ ግንድ ተደጋግፎ የተቀመጠው ናትናኤል በመዳፉ ፊቱን ሲያሻሽ ቆየና ቀና አለ፡፡

“እስቲ አቃቂ ከተማ ቀስ ብዬ ገብቼ ምናምን እፈልጋለሁ፡፡”

ናትናኤል ከተደበቁበት ጫካ ወጥቶ ሰፊውን ሜዳ አቋርጦ በግራ ጎን በኩል ከተማዋን ለሁለት ከፍሉ ሲገባ የጠበቀውን ያህል ብዙ ችግር
አልገጠመውም::

ከአንድ አነስተኛ ኪዎስክ በሞላላ ላስቲክ ውሃ ይዞ ወደሌላ ሱቅ ተሻገረ፡፡ ከሱቁ ሁለት የላስቲክ ከረጢቶች ገዛና ዳቦ፣ የላስቲክ ወተትና ፍራፍሬዎች አጭቆባቸው በመጣበት መንገድ ከትንሿ ከተማ ሹልክ ብሎ ወጣ፡፡

“ውሃውን ስጠኝ፡፡” እል ካልቨርቱ ናትናኤል ሁለቱን የላስቲክ ከረጢቶች አስቀምጦ ያመጣውን ዕቃ እያወጣ ሲደረድር፡፡

“ብዙ ኣትጠጣ… ቁርጠት እዚሁ እንዳያውለን፡፡”

የውሃውን ላስቲክ ለካልቨርት እያቀበለው::
ዳቦውንና ፍራፍሬውን ተመግበው ወተቱን ጠጥተው ሲያበቁ ውሃውን ይዘው ጉዞአቸውን ቀጠሉ፡፡ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ አዲስ አበባ በሩቁ ታየቻቸው፡፡

• “ከእንግዲህ ነፃ ነን፡፡” አለ ካልቨርት፡፡
“ምን ማለትህ ነው?”
“ከጥቂት ቀናት በኋላ አፍሪካ አንድ ትሆናለች::» አለ ካልቨርት
ፊቱን ወደ አዲስ አበባ አቅጣጫ እንዳቀና ፈገግ እለና:: «ነፃ እንደመሆን
የሚጣፍጥ ምን ነገር አለ።”

“ምንም” አለ ናትናኤል ካልቨርት ሽጉጥ የከተተባትን ሻንጣውን እየተመለከተ፡፡

💫ይቀጥላል💫
#ቅኔ... 💚 💛 ❤️

ከቀስተ ደመና ቀለም ጠቅሶ
አምላክ ወደ ሃበሻ ምድር የላካት፣
ስንቶች ለክብሯ ዘብ ቆመው
ስለ ፍቅሯ የሞቱላት፣
የሺህ ዘመናት ታሪክ
በስፋትና ጥልቀቷ ልክ
ላይፋቅ የደመቀባት፣
የሁላችን የጋራ ክብር
ሰንደቅ አላማ ቅኔ ናት።


💚 💛

🔘ሻለቃ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሃምሳ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


...“አሁን ገና ሰው መሰልክ?” አለ ካልቨርት ፊቱ ፈገግታ ለብሶ፡፡
“አይዞህ አንተም ውሃ ሲገላምጥህ ሰው ትመስላለህ::” ናትናኤል ፀጉሩን በፎጣ እያደራረቅ ወደተከራዩት የሆቴል ክፍል ገብቶ ከኋላው በሩን ዘጋው፡፡
“ህ! ! ህ ለሁሉም ጊዜ አለው::”አለ ካልቨርት ከተቀመጠበት ተነስቶ የሚቀይረውን አዲስ ልብስ ተሸክሞ ወደ መታጠቢያ ቤት እየሄደ፡፡

ካልቨርት ከክፍሉ ወጣ እንዳለ ናትናኤል ፈጠን ብሎ ካልቨርት ከጥግ ያስቀመጠውን ቦርሳ ይፈትሽ ጀመር፡፡ እንደተመኘውና እንዳሰበው፣
እንዳቀደው የካልቨርትን ሽጉጥ ቦርሳው ውስጥ አገኘሁ፡፡ ሽጉጡን ቶሎ ብሎ
ከቦርሳው ውስጥ አወጣና ካርታን አውጥቶ ጥይቱን ቆጠረ፡፡ ሰባት ጥይት
በቂ ነው፡፡ ካርታውን በቦታው መለሰና ሽጉጠን አቀባብሎ መጠበቂያውን
ለቆ በሩን እያየ ካልቨርትን ይጠባበቅ ጀመር፡፡ ምርጫ የለውም... ሌላ
ምንም ምርጫ የለውም!

ባያስማማስ ጭራሽ ባይስማማስ ፍንክች አልል ቢልስ? የራሱ ጉዳደ:: እዚሁ ይጨርሰዋል፡፡ አለዛም ትቶት ይሄዳል፤ ብቻውን ይጋፈጣቸዋል:: የሚላቸውን ካልሰሙትም ጉዳቸውን ያዝረክርክዋል፡፡ ጊዜ የለውም:: ነገ ሳይመሽ ርብቃን እጁ ማድረግ አለበት አለበለዚያ የሚመጣው አይታወቅም...
ናትናኤል ከአልጋው ግርጌ እንደቆመ የርብቃን መጨረሻ ሲያስብ ሊደርስባት የሚችለውን አደጋ ሲያሰላስል ትንፋሽ አጠረው፡፡

የነገዋ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ርብቃን እጁ ማግባት አለበት፡፡አለበለዚያ በግርግርታ አንድ ነገር ሲያደርጓት…. - በማታወቀው ምስጢር የመስዋዕት በግ ቢያደርጓት...እርሱ ነፍሰን ስለወደደ የገዛ ደህንነቱን ስለፈለገ ብቻ ቢያጠፏት ከዚያ ወዲያ ምን ሊሆን ህይወቱ?' ናትናኤል ሽጉጡን ጨምድዶ እንደያዘ በተከራዩት ክፍል ውስጥ ካሉት አልጋዎች በአንደኛው ጫፍ ላይ ቁጭ አለና ካልቨርትን ይጠባበቅ : ጀመር፡፡ የራሱ ጉዳይ! ካልተስማማ ትቶት ይሄዳል፡፡ ሊቃወመው ወይ ሊያቆመው ከሞከረ ግን…. የራሱ ጉዳይ! ሞት ነው የሚጠብቀው፡፡ . ናትናኤል የጨመደደውን ሽጉጥ ወደግራ እጁ አዙሮ በላብ የተጠመቀውን የቀኝ እጁን ሱሪው ላይ ሞዥቀና ሽጉጡን ጨሰጠ፡፡

ብዙም ሳይቆይ ካልቨርት ፎጣውን ትከሻው ላይ ጥሎ መንገድ ላይ
ለብሶት የቆየውን በአቧራና በላብ የተበከለ ሽርጥና ሸሚዝ በጥያፌ በሁለት
ጣቶቹ አንጠልጥሎ የተከራዩትን ክፍል በር ከፍቶ ሲገባ የገጠመውን ትርዒት ማመን አቃተው፡፡

“ካልቨርት ምርጫ የለኝም...
የማይሆን ነገር እንዳደርግ
አታስገድደኝ::'' አለ ናትናኤል ከተቀመጠበት¨ ሳይንቀሳቀስ የያዘውን ሽጉጥ ቀና እያደረገ፡፡

“ምንድነው የምትሰራው? ምን ልትሆን ነው?” አለ ካልቨርት የተሸከመውን ቆሻሻ ልብስ ወለሉ ላይ እየዘረገፈ፡፡

“ከአንተ ምንም እርዳታ አልፈልግም፡፡ ርብቃ ያለችበትን ሁኔታ እያወቅሁ በዝምታ መጠበቅ ግን አልችልም:: አዝናለሁ ካልቨርት… ሽጉጥሀን ስለሰረቅሁ፡፡ ግን ምርጫ ያለኝም:: ይሀንን ካላደረግሁ እስረኛሀ እንደምታደርገኝ ግልጽ ነው፡፡”

“ስማ!” አለ ካልቨርት በንዴት መንፈስ ወደፊት አንድ እርምጃ እየተራመደ።

“አ! አ" ናትናኤል የሽጉጠን አፈሙዝ ካልቨርት ላይ ደግኖ ተነስቶ ቆመ፡፡ “እንዳትጠጋኝ፡፡ ሞኝ ነገር አትፈጽም:: ክፉ ነገር መፈጸም አልፈልግም፡፡ ግን ምርጫ የለኝም... ካስገደድከኝ ደፍቼህ ነው የምወጣው፡፡”

ካልቨርት ተስፋ በመቁረጥ አልጋው ላይ ቁጭ አለና ፊቱን ሁለት መዳፎቹ ውስጥ ቀበረ፡፡

ናትናኤል የምትሰራው ጥፋት ነው... ከአሁን ወዲያ ምንም ልትረዳት አትችልም፡፡ እጃቸው ውስጥ ነች፡፡”

“አስፈራራቸዋለሁ! አንተ የምስራችን እንዳይነኩ እንዳስፈራራሃቸው
አስፈራራቸዋለሁ፡፡”

“እናስ ከዛስ?”
“ይለቋታላ! ”
“ሞኝ አትሁን፡፡ እርግጥ ይለቋት ይሆናል… ግን ከለቀቋት ወዲያ እንደ ወጥመድ ነው የሚጠቀሙባት ምክንያቱም ወይ ሰስልክ ወይ በአካል ልትገናኛት መሞከርህ አይቀርም፡፡ እትጠራጠር ይይዙሃል።”

“ከያዙኝ ይያዙኝ ዝም ብዬ ግን አልቀመጥም”
“ባይስማሙስ? ባይለቋትስ?”
“አወጣዋለሁ ምሥጢራቸውን፡፡”

ካልቨርት ቀና ብሎ በቁጣ ፊት ናትናኤልን ገላመጠው፡፡

“እታደርገውም… የምትጎዳው እነሱን አይደለም አፍሪካን ነው፡፡ ነገሮችን አስፍቶ የሚያይ ጭንቅላት ካለህ የምልህ ይገባሃል፡፡ የዚህን ዓይነት ጥፋት ስታጠፋ ደግሞ በዝምታ አልመለከትህም፡፡”

“ሽጉጡ ያለው በእኔ እጅ ነው፡፡”

“ተኩስ! ፈሪ!” ካልቨርት ከተቀመጠበት ተፈናጥሮ ተነሳ፡፡

“ተጠንቀቅ ካልቨርት ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይመለሳል ብለህ አታስብ እንደዛፍ ነው በቁምህ የምጥልህ፡፡” ናትናኤል ጥርሱን ነክሶ አፈጠጠ፡፡

የናትናኤልን አዝማሚያ ሲመለከት ካልቨርት ራሱን ነቀነቀና ተመልሶ አልጋው ላይ ተቀመጠ፡፡

“እና አሁን ምን ልታደርግ አሰብክ?” አለ ካልቨርት፡፡
“ጠዋት ስልክ ደውዬ እነግራቸዋለሁ፤ አስጠነቅቃቸዋለሁ፡፡ ከዚያ
ወዲያ የራሳቸው ምርጫ ነው፡፡”
“ናትናኤል እስቲ አስበው በቀላሉ ድምፃችንን ብናጠፋ ሁሉ ነገር
ጊዜውን ጠብቆ መድኃኒት ያገኛል እመነኝ ይለቋታል፡፡”

“ባይሳካስ ዕቅዱ ቢከሽፍስ? ጉዳቸውን ልመሰክር ለመደበቅ እንደሚገድሏት አታውቅም። ካልቨርት መፍጠን አለብኝ! አንድ ነገር ብትሆን ለራሴ ይቅርታ አላደርግለትም::"

“ናትናኤል ስሜትህ ያገባኛል… ምናልባት እኔም በአንተ ቦታ ብሆን ተመሳሳይ ስህተት ለመፈጸም እገፋፋ ይሆናል፡፡ ለምን እንዲህ አናደርግም..ጥፋት ማጥፋታችን ካልቀረ አንስተኛ ጥፋት ይሻላል፡፡” ካልቨርት ያሰበውን እቅድ ለናትናኤል በእርጋታ ተነተነለት፡፡

“አይሆንም! ይይዙናል፡፡”

“ይገባናል ሊይዙን ይችላሉ
እንዳልከው በስልክ ልታስፈራራቸው ብትሞክርም መያዝሀ አይቀርም፡፡ የእኔ መንገድ ይሻላል፡፡ሁልጊዜ የተሻለው አስተማማኙ መንገድ ይበልጥ አደገኛና ይበልጥ አስፈሪ! ይበልጥ አስደንጋጭ የሆነው ጤነኛ ሰው በጤነኛ አእምሮ
የማይመርጠው መንገድ ነው አትጠራጠር፡፡”

“ግን ቢይዙንስ?”
“አለቀልና! ምነው ፈራህ እንዴ?” ካልቨርት ፈገግ አለ፡፡ ««ቢያዙኝም ይያዙኝ አላልክም ዋናው ነገር ፍቅረኛህን ከመዳፋቸው ማውጣታችን የእነሱንም ዕቅድ እለማደናቅፋችን ነው... ለዚህ ደግሞ የተሻለው መንገድ የእኔ ነው:: ትስማማለህ?

ናትናኤል በዝምታ ማውጣትና ማውረድ ያዘ፡፡

“እትፍራ፡፡” አለ ካልቨርት ፈገግ ብሎ፡፡
“አልፈራሁም!” በስጨት አለ ናትናኤል፡፡
“እንግዲያው እንስማማ…” ካልቨርት ቀኝ እጁን ዘረጋለት
“እንተማመን ናትናኤል ደግሞ እሱን ሽጉጥ ዞር አድርገው:: ቢባርቅ
ሆዴን ነው የምትዘረግፈው::”
“ካልቨርት ልታታልለኝ ብትሞክር…” አለ ናትናኤል በጥርጣሬ ፊት ካልቨርት የዘረጋለትን እጁን እየተመለከተ፡፡ “ከአሁን በኋላ ሁለቴ ለማሰብ ጊዜ የለኝም:: አንዲት አጉል እንቅስቃሴ ካደረክ አጓጉል ነው የምትሆነው፡፡”

“ቃል እገባልሃለሁ፡፡”አለ ካልቨርት እጁን ወደፊት እንደዘረጋ፡፡

ናትናኤል ሽጉጡን ወደግራው አሻግሮ የተዘረጋውን የካልቨርትን እጅ በቀኙ ጨበጠው፡፡

“ጥሩ አሁን እቅዳችንን አንድ በአንድ ተንትነን እንነጋገርበት ካጠፋን አይቀር፡፡” አለ ካልቨርት ሁለት ወንበሮች አምጥቶ አንዱን ለናትናኤል አቀብሎት በሁለተኛው ላይ እየተፈናጠጠ፡፡

ፊት ለፊት ቁጭ ብለው በማግስቱ ስለሚፈፅሙት ተግባር አንድ በአንድ ተነጋገሩ ተመካከሩ ፤ ተከራከሩ፤ ተስማሙ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሰማዩ ጥርት ብሏል፡፡ ለጋዋ ፀሐይ ከእንቅልፏ እንደነቃች ሁሉ ከረጅሙ የክረምት ጨለማ በኋላ በሰማዩ ላይ ብቻዋን ትምነሸነሽበታለች:: አለፍ አለፍ እያሉ እንደ
👍1
አረፋ የተኩረፈረፉት ነጫጭ ደመናዎች ዝናብ ያዘሉ ሳይሆን ለጌጥ የተንጠለጠሉ የጥጥ ንድፎች ይመስሳሱ፡፡ ንፋሱ ጠንክሯል፡፡ በየአውራጎዳናዎ ግና ጥግ የተሰቀሉት የአፍሪካ አገሮች ባንዲራዎች ያረግዳሉ፣ ያሽበሽባሉ፤ ይጨፍራሉ፤ ያጨበጭባሉ.. እርስ በእርስ እየተጎናተሉ ያውካሉ፤ ሊመጣ ያለውን የገመቱ የጠረጠሩ ይመስል…. ያንሾካሹካሉ፡፡

የአፍሪካን ታላላቅ መሪዎች ተቀብላ ለማስተናገድ ትንፋሽ አጥታ እላይ እታች ስትል የሰነበተችው አዲስ አበባ ቀኑ ሲደርስ ስዓቱ ሲቃረብ ለአንድ አፍታ ቆም ረጋ ብላ የገዛ የመስተንግዶ ዝግጅቷን እየጎበኘች እንደምታደንቅ ሴት ወይዘሮ አደብ ገዝታለች:: ከወትሮው በርከት ብለው የሚታዩት ፀጥታ አስከባሪ የፖሊስ አባላት የመገናኛ ሬድዮኖቻቸውን
በየጆሮዎቻቸው ላይ እንደለጠፉ በየኩርባው ባቆሟቸው ተሽከርካሪዎቻቸው ውስጥ ተቀምጠው በዙሪያቸን ይቃኛሉ፡፡

መሪዎች ወደ ከተማዋ መግባት ጀምረዋል፡፡ ከአውሮኘላን ማረፊያው ሜዳ ወደ ከተማዋ የሚወስደውን አንድ አውራ መንገድ ይዘው እየተከ ታተሉ በጥቂት ደቂቃዎች ልዩነት ውስጥ ፒም! ፖም!.…. ቲም! ፖም! እያሉ በተራ ወደ ከተማዋ እምብርት ይጎርፋሉ፡፡ ለፋሲካ እንደተገዙ
ዶሮዎች እያስካኩ አጀብ አጀብ ብለው ይተማሉ... ወደ አዲስ አበባ፡፡

“ማነው ይህኛው?” ይላል አንዱ መንገደኛ ለአንድ አፍታ ቆም ብሎ
አንደኛውን የአፍሪካ መሪ የያዘችው መኪና ከነአጃቢዎቿ ወደ መሃል ከተማ
ስትጣደፍ፡፡ “የዚህ አገር መሪ እገሌ ነው፡፡” ይላል ከመኪናዋ እፍንጫ ላይ የሚውለበለበውን ባንዲራ ተመልክቶ የመሪውን ማንነት የለየ ወይ የገመተ ሌላ መንገደኛ:: መኪናዎቹ ተከታትለው ሲነጉዱ… ለዓይን ሲርቁ መንገደኛው ሁሉ ፊቱን ወደየአቅጣጫው ይመልሳል። ፒም! ፖም!…. ፒም! ፖም! “ይሄ ደግሞ ማነው?” ፒም! ፖም! ፒም! ፖም!' “ይሄኛውስ ደግሞ?”

ቀትር ላይ የኢትዮጵያ ዜና ኣገልግሎት ወደ ከተማዋ የገቡትን መሪዎች ዝርዝር ጠቅሶ የተቀሩትም ከሰዓት በኋላ ወደ ከተማዋ ገብተው እንደሚጠቃለሉ ስብሰባወም ምሽት ላይ በወቅቱ ሊቀመንበር የመክፈቻ ንግግር እንደሚከፈት በአድናቆት አወሳ፡፡

ባንዲራዎች ተርገበገቡ… አጨበጨቡ አወኩ... አንሾካሾኩ... እንደተጠበቀው ከሰዓት በኋላም የመላው አፍሪካ መሪዎች ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን ቀጠሉ፡፡

መሃል ፒያሳ ውስጥ ሁለት የቴሌኮሙኒኬሽን ሠራተኞች መንገድ
ጥግ የቆመ የስልክ መስመር ማከፋፈያ የብረት ሳጥን ከፍተው ብልሽት ይጠግናሉ። ከመንገድ ባሻገር ሠራተኞቹን ይዛ የመጣችው
የቴሌኮሙኒኬሽን አነስተኛ የጭነት መኪና ከጀርባ የብረት መሰላሏን እንደጫነች ጥግ ይዛ ቆማለች:: ስራ የፈታው ሹፌር የስራ ባልደረቦቹ ብልሽቱን ጠግነው እስኪጨርሱ ድረስ እዚያው ባለበት መኪናው ውስጥ እንደተቀመጠ ጋዜጣ ያነባል፡፡

አንድ ካኪ የለበሰ ቀጠን ረዘም ያለ ሰው መንገዷን ተሻግሮ ወደ ቴሌኮሙኒኬሽኗ መኪና ተጠጋ፡፡ ከጀርባዋ ከዞራት በኋላ ቀልጠፍ ብሎ ከሹፌሩ ባሻገር ያለን በር ከፍቶ ጥልቅ አለ፡፡

ሹፌሩ ጋዜጣውን መደጎን ብሎ መኪናው ወስጥ የገባን እንግዳ ሰው በጥያቄና ግራ በመጋባት ይመለከተው ጀመር፡፡
“ምን ትፈልጋለህ?” አለ ግራ የተጋባው ሹፌር የመኪናዋን በር በርግዶ የገባውን ሰው እብድ እንደሆነ ሁሉ አፍጦ እየተመለከተው፡፡ ወደ መኪናዋ የገባው ሰው እጁን ከኪሱ ውስጥ አውጥቶ የጨበጠውን ሽጉጥ ሹፌሩ ላይ ደገነበት፡፡

“ለጭቅጭቅና ለማስፈራራት ጊዜ የለኝም የምልህን ብቻ ትፈጽማለህ፡፡”አለ ሽጉጡን የያዘው ሰው ድንገት በፍርሃት በገረጣው ሹፌር ላይ አፍጥጦ። “መኪናውን አስነስተህ ወዴፊት ቀጥል፡፡ ማንም ቢጠራህ ወይም ሊያስቆምህ ቢሞክር እንዳታቆም:: ቀጥል፡፡”

ኣንድ ጌዜ ሽጉጡን አንድ ጊዜ ከጎኑ የተቀመጠኑን እብድ በፍርሃት
ሲመለከት የነበረው ሹፌር የማይሰማ ፀሉት እያነበነበ መኪናዋን አስነስቶ
ከመንገድ ገባ፡፡

“ፍጥነት ጨምር…አዎ… አየተገላመጥክ እኔን ማየትህን ተውና ዝም ብለህ ንዳ! አቁም::” አለ ሽጉጥ የያዘው ሰው ብዙም ርቀው ሳያሄዱ፡፡

አለቅጥ የተሸበረው ሹፌር የመኪናዋን ፍጥነት ቀንሶ ጥግ ያዘ፡፡ከመንገድ ጥግ ለጠፍ ብሎ ቆሞ የነበረ አነስተኛ የሸራ ቦርሳ ያነገበና ካኪ ቱታ ያጠለቀ አጠር ብሎ ከትከሻው ሰፋ ያለ ሰው ራመድ ራመድ ብሎ መኪናዋን ከፊት በኩል ዞረና በሹፌሩ በኩል ያለውን በር ከፈተው፡፡

“ጠጋ በልለት ወዲህ፡፡” አለ ሽጉጡን የያዘው የመጀመሪያው ሰው የመሣሪያውን አፈሙዝ ሹፌሩ ብብት ውስጥ ደግሞ፡፡

ሹፌሩ በሁለቱ ካኪ ቱታ በለበሱ ሰዎች መሃል ተቀምጦ ሽጉጡን በብብቱ ታቅፎ የሚያደርጉትን በፍርሃት ይክታተል ጀመር።

“የተከተለኝ ሰው አለ?” አሳ ሽጉጥ የያlው ሰው እዲስ መጡን በእንግሊዝኛ ቋንቋ፡፡
“ማንም እልተካተለህም፡፡” አለ አዲስ መጤው ጥቁር ሰው የመኪናዋን ሞተር አስነስቶ ወደ መንገድ እየገባ፡፡

የቴሌኮሙኒኬሽኗ መኪና ከጀርባ የብረት መስላሏን እንደጫነች ከፒያሳ ግርግርታ መሃል ወጥታ ቁልቁል በቸርችል ጎዳና ወርዳ በለገሃር አድርጋ ፊቷን ወደ አስመራ መንገድ መለሰች::

መሃል ኣስመራ መንገድ ላይ መኪናዋ : ወደ ቀኝ ታጥፋ ከአንድ የሆቴል አጥር ግቢ ገባች፡፡ በግቢው ውስጥ ጥቂት መኪናዎች ፈንጠር ፈንጠር ብለው ቆመዋል፡፡ ጥቂቶቹ ተጋባዥች ከየመኪናዎቻቸው ወርደው ሲገቡ የተቀሩት እዛው በየመኪናዎቻቸው ውስጥ : የሚፈልጉትን አስመጥተው ተቀምጠዋል፡፡ የቴሌኮሙኒኬሽኗ መኪና አንድ ጥግ ይዛ ቆመች::

“ለመጮኸ ወይ ለመሮጥ ወይ ሌላ ጅላጅል ሁኔታ ለመፍጠር ብትሞtር እከርካሪህን ነው የምመነግልልህ፡፡” አለ ሽጉጥ የያዘው ሰው በጓደኛውና በራሱ መሃል ወደተቀመጠው የቴሌኮሙኒኬሽን ሹፌር ፊቱን መልሶ፡፡ ልሳኑ የከዳው ሹፌር በመስማማት ራሱን ነቀነቀ፡፡

ሽጉጡን የያዘው ሰውና ጓደኛው ከተጠቃቀሱ በኋላ በሮቻቸውን
እየከፈቱ፡ ወረዱ፡፡

“ውረድ፡፡” አለ ሽጉጠን የጨበጠው ሰው መሣሪያውን ከካኪ ቱታው ኪስ ውስጥ ወሽቆ::

ሾፌሩ እንደታዘዘው ወረደ፡፡ ግራና ቀኝ አጅበውት በሆቴሉ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ወደተከራዩት ክፍል ይዘወት ሄዱ፡፡ ከክፍሉ
እንደደረሱ ባለሽጉጦ ከኪሱ ቁልፍ አውጥቶ በሩን ከፈተና የሹፌሩን ክንድ
በግራው አፈፍ አድርጎ ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ከኋላቸው ጓደኝየው ከተል አለና
በሩን ከውስጥ ቀረቀረው፡፡

ጊዜ ኣልወሰደባቸውም፡፡ የቴሌኮሙኒኬሽኑን ሹፌር ከአንድ ወንበር
ላይ አስቀምጠው እግሮቹን ከወንበሩ እግሮች ጋር እጆቹን ደግሞ ከድጋፍ፡
ቋሚዎች ጋር የኋሊት ግጥም አድርገው ካሰሩት ሰኋላ አፉን በጨርቅ ጠቅጥቀው ለጎሙት:: ስራቸውን እንደጨረሱ ከሆቴሉ ክፍል ወጥተው ወደ አነስተኛዋ የጭነት መኪና ተጣደፉ፡፡.....

💫ይቀጥላል💫
👍3
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው


...ዴሪክ ዊሊያምስ የዚህ ሳምንቱን አንጆሊኖ መፅሄት እያገላበጠ ከሆደን
ደፎ የቤቬርሊ ሂልስ የግል ክሊኒኩ እንግዳ መቀበያ ቢሮ ውስጥ ቁጭ
ብሏል፡፡ ቀና እያለም ግርግዳው ላይ ያለውን ሰዓት ይመለከታል። የእንግዳ
መቀበያው ዶክተር ሆደን ዶፎ ታካሚዎችን በጣም እንደሚያስከፍላቸው
ዊሊያምስ ግምቱን አስቀመጠ፡፡

ስለ ዶፎ ያደገረው ምርምር እንደሚያሳየው ከሆነ ሀዶን ዶፎ ብዙውን
ጊዜውን የሚያሳልፈው ድሃ እና ሱሰኛ የሆኑ ሰዎችን በማከም እንደሆነ
ነው፡፡ እርግጥ ነው የቤቨርሊ ሂልስ ቢሮው እና ፓልሳይድ ሪቬራ ውስጥ
የሚገኘው የተንደላቀቀ ቪላው እንዲሁም ደግሞ የድምፅ አልባ የፊልም
ስብስቦቹ ቢሮው ውስጥ የተለቀቀውን የክላሲካል ሙዚቃ የሚያሰማው
የስቴት ኦፍ አርት ስፒከሮቹ በሙሉ የዶክተሩን ሀብት ያሳብቃሉ፡፡

“ሚ/ር ዊሊያምስ” ብላ ጠራችው ጠይም ቆንጆ የዶፎን ፀሐፊ ወደ ቢሮው እየገባችና እጇን ዘርግታም “አሁን
ዶክተር ዶፎን ልታገኘው ትችላለህ” አለችው፡፡

ዊሊያምስ ከተቀመጠበት የጣሊያን ሌዘር ወንበር ላይ ወንበሩን እያንጫጫ ተነስቶ የዶፎን ቢሮ ከፍቶ ገባ፡፡
“ሚ/ር ዊሊያምስ ሀሎ! ምን ልርዳህ?” አለው ዶፎ ሞቅ ባለ ድምፅ፡፡
ሸሚዙን ጠቅልሎ ከተቀመጠበት ዴስክ በመነሳትም እጁን ለሰላምታ ዘረጋለት
እና ከተጨባበጡ በኋላ ቁጭ አሉ፡፡

ወዲያውኑም “ስለዶውግ ሮበርትስ ልታወራኝ ነው የፈለግከው አይደል?”

“አዎን ልክ ነህ፡፡” አለው እና ዊሊያምስ በመቀጠልም ባለቤቱ ደስ የማይል ማስፈራሪያ ስለደረሰባት ነው እኔን እንደግል መርማሪዋ የቀጠረችኝ፡፡ ምናልባት ይኼንን ማስፈራሪያ የላከላት ሰው ከሞተው ባሏ ጋር ግንኙነት ይኖረው ይሆን ብዬ ስላሰብኩኝ ነው ወደ አንተ የመጣሁት፡፡”

ኒኪን የሆነ ስው አስፈራርቷታል ነው የምትለኝ?” ብሎ ዶፎን ፊቱን አጠቆረ እና በመቀጠልም “ይህንን ነገር አልነገረችኝም፡፡ ግን ላንተ ልትነግርህ
ይገባ ነበር እንዴ? ማለቴ ያን ያህል ትቀራረባላችሁ ማለቴ እኔ " ብሎ
ሀዶን ራሱን ገደበ እና በመቀጠልም “ለፖሊሶች ጉዳዩን አሳውቃለች?” ብሎ
ጠየቀ።

ዊሊያምም እያንጓጠጠ ሳቀ እና “ፖሊሶች አውቀውታል ግን የዶ/ር
ሮበርትስ ደህንነት ለእነርሱ ቅድሚያ የሚሰጡት ነገራቸው አይደለም፡፡
ለዚያም ነው እሷ እኔን የቀጠረችኝ” አለው እና ካርዱን አውጥቶ ለሀዶን
ሰጠው እና “ለዚያና ለሌሎችም ጉዳዮች” አለው፡፡

ሀዶንም የዊሊያምስን ካርድ እያየ ቆየና “ሌላኛውስ ምክንያቶቿ?” ብሎ
ጠየቀው።

ዊሊያምስ ጉሮሮውን አጥርቶ “ዶውግ ሮበርትስ ሲሞት መኪናው ውስጥ
ከጎኑ ውሽማው ነበረች?” ብሎ ጠየቀው፡፡

“ኦ! እና” ሀዶን ኮስተር አለ፡፡

“እና ነገሩ እውነት ነው ማለት ነው?”

“አዎን እውነት ነው፡፡ እና እሱን ጉዳይ እንድትመረምርላት ነው አንተን
የቀጠረችህ?”

እሱ አንደኛው ነው፡፡ እሷ እንደነገረችኝ ከሆነ ስለ ዶውግ ውሽማ ያወቀችው የአደጋው ዕለት እንደሆነ ነው፡፡ ይህ ያስገርምሃል?”

ሀዶንም አጉረምርሞ አገጩን ከዳበሰ በኋላ “አያስገርመኝም”

“ግን አንተ ስለውሽማዋ ታውቅ ነበር?” ብሎ ዊሊያምስ ኮስተር አለ፡፡
“እና ማለቴ አንተና እሱ ጓደኛሞች እና አብራችሁ ስለምትሠሩ ስለጉዳዩ
አስቀድመህ ታውቃለህ?” አለው፡፡

“አዎን የቅርብ ጓደኛማቾች ነበርን” አለው እና የቅድሙ ሞቅ ያለው ሰላምታው ውስጥ ያለውን የመተባበር ስሜት አውጥቶ እየተናደደም “ኒኪ
ይህንን ጉዳይ ለራሷ ብላ ብትተወው ደስ ይለኝ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር
ዶውግም ሌንካም ሞተዋል አይደል?”

“ለኒኪ ሌንካን አግኝተሃት እንደማታውቅ ነው የነገርካት አይደል?” ብሎ ዊሊያምስ እንደቀልድ ጥያቄውን አቀረበ፡፡

“አዎን ልክ ነው አግኝቻት አላውቅም” ብሎ ሀዶን መለሰ፡፡

ዊሊያምስ “ህምም ይህ ደግሞ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው” ብሎ ትንሽ ካሰበ በኋላም ስልኩን አወጣና ለዶፎ አሳልፎ እየሰጠው “ምክንያቱም ይኼ
ፎቶ የሦስታችሁ ነው፡፡ የተነሳችሁትም የዛሬ ሁለት ዓመት በሱስ ለተጎዱ
ሰዎች ማከሚያ ክሊኒክ በተጠራው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ነው።
ይመስለኛል ያንን ምሽት አታስታውሰውም” ብሎ ጠየቀው፡፡

ሀዶንም በዝምታ ቆይቶ ስልኩን ለዊሊያምስ ከመመለሱ በፊት ዶውግ
አቅፎ የያዛትን ረዥም ሴት ሲመለከት ቆየ፡፡

“አልረሳሁትም፡፡ እኔ ብዙ ፈንድ ሬይዚንጎችን አውቃለሁ፡፡ እሷ ቢጫ
ፀጉር ያላት ሴት ናት አይደለም?” ብሎ ሀዶን ጠየቀ፡፡

“አዎን ልክ ነህ፡፡ ሌላ አንድ ነገር ላስታውስህ መሰለኝ፡፡ አንተው ራስህ
ነህ እዚህ ፕሮግራም ላይ የጋበዝካት፤ የዚያን ዕለትም መሰለኝ ከእሱ ጋር
ያስተዋወቅካት” አለው፡፡

ሀዶንም ፈገግ አለ እና “ዋው የቤት ሥራህን በደንብ ነው የሠራኸው
ሚ/ር ዊሊያምስ፡፡ ኒኪ ትክክለኛ ሰው ነው ለጉዳይዋ የመረጠችው።”

ዊሊያምስ መንጋጋው አካባቢ ጡንቻው እየተወጣጠረበት የሚገኘው ሀዶን ዶፎን እያየ በውስጡ ይኼ ቀለል ያለ ሰው ይመስላል

“ግን ጓደኞቿን እና ባሏን በትክክል አስባበት የመረጠች አይመስለኝም”
አለ ዊሊያምስ የአጸፋ ፈገግታን እየሰጠው፡፡

“እንደዚያ እንኳን አይመስለኝም፡፡ ዶውግ እና ኒኪ ምርጥ የትዳር ሕይወት ነበራቸው፡፡ እኔ ደግሞ የዶውግ የቅርብ ጓደኛ ነኝ እና የእሱን ምስጢር መጠበቅ አለብኝ፡፡ በተለይ ደግሞ አሁን ላይ ሞቶ እያለ ምስጢሩን ማውጣቴ ጥሩ አይመስለኝም፡፡ በሕይወታችን
ሁላችንም ስህተቶችን እንሠራለን፡፡ ሚ/ር ዊሊያምስ ዶውግ በሚስቱ ላይ በሠራው ሥራ ምናልባት ተገቢውን ቅጣት አግኝቷል እና ለምን አትተወውም?”

“እሺ እሱስ የሥራውን አግኝቷል። አንተስ ሚ/ር ዶፎ?” ብሎ ዊልያምስ
ጠየቀው፡፡

ሀዶንም ዓይኑን አጥብቦ እያየው “ምን ለማለት ፈልገህ ነው?”
ዊልያም ወንበሩ ላይ ተለጥጦ “እኔ እንደዚህ አስባለሁ፡፡ አንተ በዶውግ
ሮበርትስ ጓደኛዬ ነው በምትለው ሰው በጣም ትቀናለህ፡፡ እሱ በሁሉም
ነገሮች ሲያሸንፍህና ሲበልጥህ ነበር፡፡ በሕክምና ፈተናዎች ከፍተኛ ውጤት
ሲያመጣ ነበር፡፡ ጥሩና የተከበረ የህክምና ኢንስቲትዩት ውስጥ ነው
ኢንተርንሺፕ ሆኖ ሲሠራ የነበረው፡፡ አሁን አንተ የምትሠራበትን የበጎ አድራጎት ክሊኒክን የጀመረው እሱ ነው፡፡ አንተ ሁሌም ከእሱ ተከታይ ነህ፡፡
አብራችሁ በነበራችሁበት ጊዜ ላይ ሁሌም እሱ በእያንዳንዱ ነገር እየቀደመህ
ነበር።” አለው፡፡

ሀዶንም በሰማው ነገር በጣም ከሳቀ በኋላ “አታስቀኝ ወንድሜ! እንዴ
ይኼ እኮ የበጎ አድራጎት ጉዳይ ነው እንጂ ውድድር አልነበረም

“በጣም ቆንጆ ሴት አገባ፡፡ አንተ ደግሞ ይህቺን ሴት ሁሌም ስትፈልጋት
የነበረች ሴት ናት፡፡ ቅድም እንዳልከኝም ትዳራቸው ጥሩ እና ለረዥም
ዓመት የቆየ ነበር፡፡ ያንተ ትዳር ግን የፈረሰው በዓመት ውስጥ ነው፡፡
አይደል?” ብሎ ዊሊያምስ ጠየቀው፡፡

“በአስራ ስምንት ወራት ውስጥ ነው” ብሎ ሀዶን ጥርሱን ነክሶም እና
የፈታት ሚስቱ ክሪስቲ” ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ላይ እንዴት አዋርዳው
እንደማትፈልገው የነገረችውን ነገር አስታወሰ።

“ዶውግ ግን በጣም የጠላኸው ደግሞ በሴዳርስ የአደንዛዥ እፅ ማገገሚያ
ክሊኒክ ውስጥ ከፍተኛውን እና አንተ የምትፈልገውን ቦታ ስለያዘብህ ነበር።
ሁለታችሁም ለቦታው አመልክታችሁ ነበር፡፡ ሥራው ለአንተ እንደሚገባ
እርግጠኛ ነበርክ አይደል? ነገር ግን ይህ ያንተው ምርጥ እና በሰዎች ፊት
ሞገስ ያለው ጓደኛህ ሥራውን ከአንተ ነጠቀህ..”

“ሚ/ር ዊሊያምስ ቀጥል ባክህ፡፡ እኔ የልቦለድ ታሪኮችን እወዳለሁ።
እናም ይህ የከመርከው ትረካ እንዴት እንደሚያልቅ ለማወቅ
ጓጉቻለሁ” አለው፡፡

“የሚያልቀውማ አንተ ዶውግን ሌንካ ጎርዴቭስኪ ከምትባል ሴት ጋር
አስተዋውቀህ ትዳሩን በማፍረስህ ይሆናል”

ሀዶንም ራሱን በሀዘኔታ ነቅንቆ “አንዳንዶቹ ከላይ የተናገርካቸው ነገሮች
ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ እሺ ምናልባት እኔ በዶውግ ልቀና እችላለሁ፡፡

ደግሞስ በዶውግ ያልተቀና በማን ሊቀና ነው? እሱ እኮ ከስንት አንዴ የሚገኝ አስገራሚ ሰው ነበር፡፡ ነገር ግን ጓደኛውም ነበርኩኝ፡፡ ከእሷ ጋርም
አስተዋውቄዋለሁ፡፡ እውነት ነው ኒኪ ይህን አታውቅም፡፡ እኔም እሷ
እንድታውቀው አልፈልግም”

“እሱማ ልክ ነህ እንዴት እሷ እንድታውቅ ትፈልጋለህ” ብሎ ዊሊያምስ
ሲናገር ሀዶን አቋረጠው እና
“አንተ እንዳሰብከው ግን አልነበረም፡፡ የሆነ የበጎ አድጎራት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ኒው ዮርክ ውስጥ ነው ያገኘኋት። በጣም ሀብታም ናት። እኔና ዶውንግ ልንሰራው ስላሰብነው ነገር ልትረዳን እንደምትችል ስላሳወቀችኝ ነበር ያስተዋወቅኳቸው፡፡ ከእሷ ጋር የፍቅር
ግንኙነት ይመሰርታል ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡ ደግሞስ ለምን እንደዚያ አስባለሁ?

ዴሪክ ለአፍታ ያህል በውስጡ ሲያመነታ ቆየ፡፡ ሀዶን ዶፎ እንደዋሸው ውስጡ እየነገረው ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን መጨረሻ ላይ የተናገረው ትንሽ የሚያሳምን ነገር አለው

“ስለ ሌንካ የኋላ ታሪክ ምን ያህል ታውቃለህ? ማለቴ ሩሲያ ውስጥ
ስትኖረው የነበረውን ህይወቷን?” ብሎ ዊሊያምስ ሀዶንን ጠየቀው::

“ምንም አላውቅም፡፡ ያው እንደነገርኩህ በአጋጣሚ ነው ያወቅኳት”

ዊሊያምስም ራሱን በአሉታ ወዝውዞ “ይህንን እንኳን አላምንህም፡፡ ያን
ሳምንት በሚ/ር ጎርዴቭስኪ ላይ ምርመራውን ሳካሂድ ነበር፡፡ የሚገርመው
ነገር ግን ስለ እሷ ምንም ዓይነት መረጃ ሊገኝ አልቻለም፡፡

“አልገባኝም” ብሉ ሀዶን ጠየቀ፡፡

“እኔም አልገባኝም” አለ እና ዊሊያምስ ይኼ ደግሞ የሚገርም ነገር ነው፡፡ መቼ ሩሲያን እንደለቀቀች ወይንም ደግሞ አሜሪካን እንደገባች የሚናገር የተመዘገበ ነገር የለም፡፡ ሎስ አንጀለስ ከመምጣቷ በፊትም የት ትኖር እንደነበር የሚያሳይ አድራሻ የላትም፡፡ በስሟ ክሬዲት ካርድ የላትም፡፡አንተ ብዙ ገንዘብ አላት ብትለኝም የትኛውም ባንክ ውስጥ አካውንት የላትም፡፡ እዚህ ሎስ አንጀለስ ውስጥ ቤት ያከራያት ሰው ሲነግረኝ ደግሞ ሁሌም በጥሬ ገንዘብ ነው ክፍያዎችን የምትፈጽመው ብሎኛል፡፡ አለ አይደል ልክ እንደ ሰላይ ነገር ትመስለኛለች” አለና ዊሊያምስ ሳቅ አለና “ወይም ደግሞ እሷ እዚህ የምትኖረው በመንግሥት ስር በሚገኘው በሰው ምስክር ከለላ ውስጥ ይሆን እንዴ?”

ነገርኩህ እኮ ስለ እሷ ብዙም አላውቅም ብዬሃለሁ“

ለአንድ ዓመት ሙሉ የልብ ጓደኛህ፣ ፍቅረኛህ ነበረች እኮ ለብዙ ጊዜያትም አብራችሁ ሳትገናኙ አትቀሩም፡፡ ነገር ግን ስለ እሷ ስትጠይቅህ አንተ ኒክን ዋሽተሃታል፡፡ አሁን ደግሞ እኔንም እየዋሸኸኝ ነው፡፡ ማን ናት እሷ ዶክተር ዶፎ?”

“አላውቅም!” ብሎ ሀዶን ጮሆ መለስለት እና “በእግዚአብሔር ስም ምንድነው ችግርህ?አዎን ኒክን ዋሽቻታለሁ፡፡ ግን አንተስ በእኔ ቦታ ብትሆን ምን ነበር ልትመልስላት የምትችለው? ዶውግ እኮ ኒኪን ይወዳት ነበር። እንደ ሰው ደግሞ ተሳስቷል፤ ከስህተቱ ይመለሳል ብዬ ነበር ግን መጨረሻው ሳይሆን ቀረ::”

“መጨረሻውማ የእነርሱ ከመኪናው ጋር አብሮ መቃጠል ሆነ፡፡ አንተም ሆስፒታል ውስጥም የእሱን ቦታ ተክተህ ለመስራት ማመልከቻህን አስገባህ አይደል ዶክተር ዶፍ።

ይህንን ከዊሊያምስ ሲሰማ ከቁጣ ይልቅ ገላመጠውና “እንዴ የእሱን ቦታ
ተክቶ ለመስራት ማመልከቴ እኮ ቦታው ላይ ለመስራት የሚያስችለኝ ብቃት ስላለኝ ነው ዶውግ ደግሞ እንደዚህ አይነት ነገሮችን እንዳደርግ ሲያበረታታኝ ነበር። ይልቅ ያልገባኝ ነገር ቢኖር ቢሮዬ ድረስ መጥተህ እየወነጀልከኝ መሆኑ ነው፡፡”

እየወነጀልኩህ አይደለም እኔ ሥራዬን እየሰራሁ መሆኔን ብቻ ነው
የማውቀው።”

እየወነጀልከኝማ ነው።” ብሎ ሀዶን በሀይለ ቃል መናገሩን ቀጠለ እና
እንዴ እኔን እኮ የዶውግን ሞት ክፉኛ ፈላጊ አድርገህ ነው ያሰብከኝ፡፡
ባይገርምህ ዶውግ በጣም የምወደው ጓደኛዬ ነው። ይሄንንስ በጥናትህ ላይ
አላገኘኸውም!? ይሄ ግን እውነታ ነው፤ አንተ ብታምንበትም ባታምንበት
የእኔ ሀቅ ይሄው ነው እሺ?” ብሎ ዶን ተናገረው፡፡

ዊሊያምስም ለመናገር አፉን ሊከፍት ሲል ሀዶን አቋረጠው እና “በል ከዚህ በላይ ምንም ልታገስህ አልችልም ከቢሮዬ ውጣልኝ!” ብሎ ጮኸበት፡፡

ዴሪክ ዊሊያምስ ከሀዶን ቢሮ ወጥቶ የእግረኛ መንገዱ ላይ ወደ ላይ እና
ወደ ታች እየተመላለሰ በሀዶን ቢሮ ውስጥ ስላሳለፈው ነገር ያስባል።

ምናልባት ሀዶን ስለ ዛሬ ውሏችን ለኒኪ ደውሎ ይነግራት ይሆን? ግን
አያደርገውም፡፡ ምክንያቱም እሱ ስለ ሌንካ ስለዋሻት ይሄንን ሊያደርግ
አይችልም:: ምናልባት ሀዶንን ይበልጥ ተጭኜው ይሆን እንዴ? ይህንን
ደግሞ ማድረግ ነበረብኝ:: ብሎ ሲያስብ ቆይቶ መኪናውን አስነሳ እና ወደ
ቢሮው አመራ፡፡

ሀዶን በቢሮው መስኮት ወደ ውጭ ሲመለከት የኒኪ የግል መርማሪ
ከመንገዱ ዳር በሃሳብ ቆዝሞ እንደቆመ ተመለከተ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላም
ዴሬክ ዊሊያምስ መኪናውን አስነስቶ ሲንቀሳቀስ ተመለከተ፡፡

የሀዶን ፊት ላይ ምንም ዓይነት ስሜት አይነበብበትም። ግን ውስጡ
ጨጓራው ሲቋጠር ይታወቀዋል፡፡
የቢሮውን ስልክ አነሳ እና ወደ ግል አገልግሎት የጥሪ ማዕከል ደወለ፡፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ስልኩ እንደማይጠለፍ እርግጠኛ ከሆነ በኋላም ማውራት ጀመረ።

“የግል ወንጀል መርማሪው እዚህ መጥቶ ነበር፡፡” አለ እና ሀዶንበመቀጠልም ሚኪ የቀጠረችው፣ ዊሊያምስ” አለ፡፡

“እና?” ጠየቀ ሌላኛው መስመር ላይ የሚገኘው ሰው፡፡ “ ችግር የሚፈጥርብን ይመስለኛል፡፡ የሆነ ነገር ሊደረግ ይገባል” ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡.....

ይቀጥላል
👍2
አትሮኖስ pinned «#የፍቅር_ሰመመን ፡ ፡ #ክፍል_አርባ ፡ ፡ #ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን ፡ ፡ #ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው ...ዴሪክ ዊሊያምስ የዚህ ሳምንቱን አንጆሊኖ መፅሄት እያገላበጠ ከሆደን ደፎ የቤቬርሊ ሂልስ የግል ክሊኒኩ እንግዳ መቀበያ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብሏል፡፡ ቀና እያለም ግርግዳው ላይ ያለውን ሰዓት ይመለከታል። የእንግዳ መቀበያው ዶክተር ሆደን ዶፎ ታካሚዎችን በጣም እንደሚያስከፍላቸው ዊሊያምስ ግምቱን አስቀመጠ፡፡…»
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሃምሳ_አንድ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


....ከዋናው መንገድ ብዙም ሳይርቁ የመኖሪያ ቤቶች ከተደረደሩበት
የሠፈር ውስጥ መንገድ ዳር አንድ ጥግ ላይ መኪናቸውን አቆሙ፡፡

መኪናዋ ጥግ ይዛ እንደቆመች ፡ ናትናኤል የመኪናዋን ሬድዮ ከፈተው፡፡ ጎርናና የጋዜጠኛ ድምፅ መኪናዋ ውስጥ አስተጋባ፡፡

እንዲሁም የአንጎላና የሞሮኮ የሴኔጋልና የቡሩንዲ መሪዎች ከሰዓት በኋላ አቀባበል ሲደረግላቸው እስካሁን ወደ አፍሪካዋ ያልገቡት ሦስት የአፍሪካ መሪዎች ማለትም የሴራሊዮን የጋቦንና
የቡርኪናፋሶ መሪዎች ምሽቱን ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በወጣው ኘሮግራም መሠረት ዛሬ ሰኞ መስከረም አራት ምሽት በሁለት ሰዓት ተኩል ያልገቡት ሦስት የአፍሪካ መሪዎች ማለትም የሴራሊዮን የጋቦንና የቡርኪናፋሶ መሪዎች ምሽቱን ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በወጣው
ፕሮግራም መሠረት ዛሬ ሰኞ መስከረም አራት ምሽት በሁለት ሰዓት ተኩል
ላይ ጠቅላላ ፡ የአፍሪካ መሪዎች የሚገኙበት ስብሰባ ሲከፈት ይቅርታ
አድማጮቻችን አሁን ዘግይቶ የደረሰን ዜና አለ የሴራሊዮኑን መሪ
የያዘችው አውሮኘላን አዲስ አበባ ኢንተርናሽናል አውሮኘላን ማረፊያ
አርፋለች ኘሬዚዳንቱ፡ የክብር ሰላምታ ላቀረበላቸው.. አፀፋውን..…”

ናትናኤል ሬዲዮኑን ዘጋው፡፡
“ሁለት ቀሩ::” አለ ናትናኤል አይኖቹን አቦዝዞ ለራሱ እንደሚናገር ሁል፡፡

ጊዜው እየሄደ . ሰዓቱ እየቀረበ ሲመጣ ተራርቀው የዋሉት ደመናዎች እየተጠራሩ እጅ ለእጅ መያያዝ ጀመሩ:: ቀኑን ሙሉ ማን አለብኝ ብላ ያለርህራሄ ምድሪቷን ስትወቃት የዋለችው ፀሃይ የተባበሩትን
ደመናዎች ማለፍ ሲያቅታት ዙሪያው ቀዝቅዝ ተንፈስ አለ፡፡ ንፋሱ ብቻ
እንደ ወሬ ነጋሪ ከወዲያ ወዲህ ይመላለስ ጀመር፡፡

ሁለት ሰዎች የጫነች የቴሌኮሙኒኬሽን የጥገና መኪና ከአስመራ መንገድ ተነስታ በላይኛው ቤተመንግስት አድርጋ ፒያሳን ለሁላት ከፍላ ሲኒማ ኢትዮጵያ አጠገብ ስትደርስ ሊመሻሽ ተቃርቦ ነበር፡፡ መኪናዋ
አደባባዩን ዞረችና ቁልቁል ወረደች፡፡ ብዙም ሳትርቅ ከአንድ አፓርትመንት
ህንፃ የአጥር በር ፊት ለፊት ቆመች፡፡

“አቤት::” አለ አፈርማ ካፖርት የደረቡ የአፖርትመንቱ የማታ ዘበኛ የብረቱን በር ከፈት አድርገው ብቅ አሉና፡፡

“አንዴ ይክፈቱልን እባክዎት፡፡” አለ ከሾፌሩ ጎን የተቀመጠው ሰው ጭንቅላቱን በመስኮት ብቅ አድርጎ። “ስልከኞች ነን.… የተበላሸ ስልክ
ለመጠገን ነው፡፡”

ሽማግሌው እያቅማሙ የብረቱን በር ወለል አድርገው ከፈቱት፡፡
የቴሌኮሙኒኬሽኗ መኪና ወደ አፖርታማው ግቢ ገብታ ጥግ ይዛ ቆመች፡፡ወዲያው ካኪ ቱታ የለበሱ ሠራተኞች ፈጠን ብለው ከመኪናዋ ወርደው የጥገና መሣሪያዎቻቸውን የያዙባቸውን ቦርሳዎቻቸውንና ሌሎችንም
ዕቃዎቻቸውን አንግበው ወደ አፖርትመንቱ በር ተጣደፉ፡፡

ከመጀመሪያው ደርብ እንደደረሱ ወደግራ ብለው በጠባቡ መተላለፊያ ፊትና ኋላ ራመድ ራመድ እያሉ ቀጠሉ፡፡ 21 የተላጠፈበት በር አጠገብ እንደደረሱ ተያዩ:: ወዲያው በሩን አልፈው 22 የሚል ቁጥር የተለጠፈበትን የሚቀጥለውን በር አንኳኩ፡፡
“አቤት"አለች በሩን የከፈተችው ልጅ እግር ሴት ህፃን ልጅ እንደታቀፈች፡፡

“ከቴሌኮሙኒኬሽን ነው፡፡ በአካባቢው የተበሳሹ ስልኮች አሉ፡፡ የናንተንም ለማየት ነበር፡፡አላት ቀጠን ቀላ ያለው፡፡

“ደህና ነው የኔ ስልክ፡፡” አለች ሴትየዋ በተራ እያየቻቸው፡፡
“ገብተን እንየው?” አላት የመጀመሪያው ሰው፡፡
“ግቡ ግቡ፡፡“ አለች ሴትያዊ የታቀፈቻትን ህፃን ከመሬት አውርዳ በሩን በሰፊው እየከፈታችላቸው::

ካኪ ቱታ የለበሱት ሁለት ሰዎች ተከታትለው ገቡ፡፡
“ቅድም ስንደውል ያነጋገሩን እርሶ ኖት?” አላት ቀጠን ያለው፡፡
“አይ እዚህ አልደወላችሁም::”
“ምናልባት ሌላ ሰው አንስቶት እንዳይሆን…”
“እኔ ብቻ ነኝ ያለሁት በቤቱ፤ ከሷ በስተቀር፡፡” አለች ሴትየዋ ፈገግ
ብሳ የህፃን ልጇን ጭንቅላት እየደባበሰች፡፡ “እዚህ አልደወላችሁም፡፡”
ሰውየው የፈለገውን ያገኘ ይመስል ጊዜ ሳይወስድ ከቱታው ከስ ውስጥ ሽጉጥ አውጥቶ ሴትየዋ ላይ ደገነባት፡፡ ከጎኑ ቆሞ የነበረው ጥቁር ስው ያንጠለጠለውን የሸራ ቦርሳ ወደጎን ጥሎ በሚያስደንቅ ፍጥነት አፏን አፍኖ ወንበር ላይ አስቀመጣት፡፡ ሽጉጥ የያዘው ሰው ማልቀስ የዳዳትን ህፃን ልጅ ከመሬት አንስቶ ታቀፋት።

“ኣይዞሽ አንቺንም ሆነ ልጅሽን የመጉዳት ሃሳብ የለንም:: ነገር ግን ለመጮህ ወይ ለመሮጥ ብትሞክሪ ጥሩ አይሆንም ውጤቱ፡፡” አለ መሣሪያ የያዘው ሰው የሽጉጡን አፈሙዝ ህፃኗ ለስላሳ አንገት ውስጥ እያፍተለተለ፡፡

ሽጉጡን የያዘው ሰው ምልክት ሲሰጠው ኣፍዋን አፍኖ የያዛት ሰው ለቀቃት::

“ምንድነው የምትፈልጉት? የምትፈልጉትን ያዙና ውጡልኝ፡፡” አለች ልጇ አንጎት ስር የተሸጎጠውን ሽጉጥ የተመለከተችው እናት እየተርበተበተች::

“ሌቦችና ቀማኞች እይደለንም፡፡ ጉዳት ልናደርስብሽም አይደለም የመጣነው፡፡ እርዳታሽን ብቻ ነው የምንፈልገው፡፡” አላት ቀጠን ያለው ሰው ህፃኗን እንደታቀፈ ከተቀመጠችበት ወንበር አጠገብ በርከክ ብሎ፡፡
ምንድነው የምትፈልጉት?” አለች ሴትየዋ ኣይኖቿን በሁለቱ አፋኞች ላይ ተራ እያንከራተተች፡፡

እዚህ ጎረቤትሽ 21 ቁጥር ውስጥ ያለችውን ሴት ታውቂያታለሽ?"
አለ ልጇን የታቀፈው ሰውዬ ማልቀስ የጀመረችውን ህፃን በማባበል እየጣረ

“አዎ… ርብቃ ትባላለች… ልጄን ልቀቅልኝ፡፡”

ሀዋኗን የታቀፈው ሰው እየተቁነጠነጠች ያስቸገረችውን ህፃን ለእናቷ ካቅበለ በኋላ ወንበር ስቦ አጠገቧ ተቀመጠ፡፡

“ይህን ሰሞን አይተሻታል?” “ አለ የያዘውን መሣሪያ ከቱታው ኪስ
ውስጥ እየጨመረ::

“ኣሳየኋትም፡፡ ረጅም ጊዜ ነው ካየኋት.. ግን ሌሎች ሰዎች ወደ ክፍሏ ሲገቡና ሲወጠ አይቻለሁ፡፡ ምንድነው የምትፈልጉት ከኔ?” ሴትየዋ ልጇን እቅፍ አድርጋ ይዛ እየደባበሰች አፈጠሰችበት፡፡
“ምን ያህል ይሆናሉ ሰዎቹ?" ጠየቃት፡፡
“የቶቹ ሰዎች?” መልሳ ጠየቀችኑ፡፡
“ክፍሏ ውስጥ ያሉት ሰዎች፡፡"
“እኔ እንጁ ሲገቡና ሲወጡ ነው ያየኋቸው.. ውስጥ ይኑሩ አይኖሩ አላውቅም።

ቀጠን ያለው ሰው በርከክ ካለበት ተነስቶ በፀጥታ ከቆመው ጓደኛው ጋር በእንግሊዝኛ ቋንቋ በሹክሸከታ ያወራ ጀመር፡፡ ወዲያው ፊቱን ወደ
ሴትየዋ መለሰ፡፡

“እንዳልኩሽ እርዳታሽን እንፈልጋለን፡፡ ጉዳት ላይ እንድትወድቂ አንፈልግም። የምልሽን ያለማወላወል መፈጸም አለብሽ፡፡ አለበለዚያ ግን ያልጠበቅነው አደጋ ሊደርስ ይችላል፡፡”

“ምንድነው የምትፈልጉት?” አለች ሴትየዋ ግራ ተጋብታ፡፡ ተራ ሌቦችና ቀማኞች አለመሆናቸውን ስታረጋግጥ ድፍረቷ ተሰባስበላት፡፡ ኮስተር ብላ ተመለከተችው።

“አብረሽን ወደሚቀጥለው ክፍል ትሄጅና በሩን ታንኳኪያለሽ፡፡”
“እኔ የማላውቀው ሰው ቤት ሄጄ ኣላንኳኳም::” አለች ነገሩ ያልጣማት ሴትዮ የልጇን ጭንቅላት ጡቶቿ መሃል ቀብራ፡፡
“ምርጫ የለም፡፡ እምቢ ካልሽን እኛም የማንወደውን እንድንፈጽም እንገደዳለን፡፡” አለ ሽጉጡን የያዘው ሰው ጎንበስ ብሉ የህፃን ልጇን ጭንቅላት እየደባበሰ፡፡ “ተነሽ የፍርሃት መልክ አታሳዬ፡ በሯን
ካንኳኳሽ በኋላ ትጠባበቂያለሽ፡፡ በሩ ሲከፈት…” ማድረግ የሚገባትን ሁሉ
አንድ በአንድ እያስረዳ ክንዷን ይዞ ከተቀመጠችበት አስነሳት፡፡

ሴትየዋ ህፃን ልጇን እንደታቀፈች ከሁለቱ አፋኞቿ ጋር ክክፍሏ ወጥታ ጭር ባለው መተላለፊያ ወደሚቀጥለው ክፍል አመራች፡፡ ከጎረቤቷ ክፍል መዝጊያ እንደደረሱ ሁለቱ ሰዎች በበሩ ግራና ቀኝ ጀርባቸውን ለጥፈው ቆሙ:: ቀጠን ያለው ሰው ሽጉጡን አውጥቶ ደረቱ ላይ ለጥፎ
ያዘው በስተግራዋ ያለው ሰው ደግሞ ከሽራ
👍2
ሶርሳው ውስጥ አውጥቶ
የያዘውን ወፍራም የብረት ቱቦ ጫፍና ጫፍ በሁለት እጆቹ ጨብጦ
የተጠመጠመ የኤሌክትሪክ ሽቦ በትከሻው ላይ እንዳነገበ ጀርባውን ግድግዳው ላይ ለጠፈው፡፡

ለአንድ አፍታ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ ህፃን ልጅ ይዛ በሩ ፊት የቆመችው ሴት በጭንቀትና በፍርሃት በተራ ትመለከተቻቸው፡፡

“አንኳኪ፡፡” አላት በጆሮዋ ቀጠን ያለው ሰው በሽጉጡ ወደ በሩ እያመለከታት::

ሴትየዋ በግራ እጇ ህፃን ልጇን እንቅ አድርጋ እንዱቀፈች ወደ በሩ ጠጋ አለችና በቀስታ በሩን አንኳኳች። መልስ የለም:: በቀኟ የቆመው ሰው ጭንቅላቱን መታ አድርጎ ድጋሚ እንድታንኳኳ ምልክት ሰጣት፡፡ - በግንባሩ ላይ ሽፍ ያለው ላብና ነክሶ የያዘው የታች ከንፈሩ ስሜቱን ያሳጣሉ፡፡

ሴትየዋ ድጋሚ በሩን አንኳኳች:: ከውስጥ የእግር ኮቴ ተሰማ:: የበር ቁልፍ ሲከፈት የሚያሰማው ድምዕ ለሦስቱም ተሰማቸው::

ናትናኤል የሌባ ጣቱን ሽጉጡ ቃታ ላያ ላለማሳረፍ፡ ከራሱ ጋር ታገለ፡፡ ጥይት መተኮስ የለበትም፡፡ ሁሉንም በፀጥታ መፈጸም አለባቸው::በተስማሙት መሠረት ቀድሞ መግባት ያለበት ጉልበቱና ልምዱ ያለው ካልቨርት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ነው እሱ ሽጉጡን ደግኖ መከተል ያለበት ድምዕ መሰማት የለበትም… የአፖርትመንቱ ነዋሪዎች ከየክፍሎቻቸው . ብቅ ማለት የለባቸውም፡፡ ከራሱ ጋር ሙግት ያዘ፡፡

የበሩ እጀታ ወደታች አዝምሞ በሩ በቀጭኑ ተከፈተ፡፡

“ምንድነው?" አለ የወንድ ድምፅ፡፡
“ናትናኤል ነው የላከኝ፡፡” አለች ህፃን ልጅ የተሸከመችው ሴት በተነገረችወ መሰረት::
“ማን?” አለ ሰውየው በቀጭኑ ከፍቶ የያዘውን በር ይበልጥ ከፈት አድርጎ ጭማሪ ለመስማት ወጣ እያለ።

ያን ጊዜ በስተግራ ግድግዳው ላይ ተለጥፎ የነበረው ካልቨርት ወደቀኝ እንደ ወስፈንጥር ተወንጭፎ የያዘውን የብረት ቱቦ በሰውየ መሃል
አናት ላይ አሳረፈው:: በሩን በትከሻው በርግዶት ገባ፡፡ ናትናኤል በድንጋጤ
በድን የሆነችውን ሴት ወደፊት ገፍቶ በበሩ አግድም በተዘረረው ሰው ላይ
ተሻገረና የሴትዮዋን ክንድ እንደጨመደደ : ወደ ወስጥ ተንደረደረ፡፡
መጀመሪያ ሲንቀሳቀስ ባየው ነገር ላይ ሽጉጡን ደግኖ ጮኸ።

“እንዳትነቃነቅ!” አላ ናትናኤል ከሳሎኑ መስኮት በስተግራ ፎቴ ላይ
የተቀመጠው ሰው ላይ አፍጥጦ፡፡

ማርቆስ ጆሮ ያለው አልመሰለም:: ያለማወላወል ከተቀመጠበት
ወንበር ላይ ወደቀኝ ተወርወር መሬቱ ላይ አንዱ ተንከባለለና ለአይን ለመከታል በሚያስቸግር ፍጥነት የድምፅ ማፈኛ የተገጠመለትን ሽጉጡን አውጥቶ ተኮሰ፡፡ የታፈነውን የጥይት ድምፅ ተከትሎ ናትናኤል ሚዛኑ ከዳው:: የግራ ጉልበቱ በገዛ ክብደቱ ስር ዋለለሰት:: ቁመቱ መሉ ተዘረጋ፡፡ በስተቀኝ ሸብረክ ብሎ የነበረው ካልቨርት እንደ ነብር ተወርውሮ በርከክ
ያለው ማርቆስ ተጨማሪ ጥይት ከመትፋቱ በፊት ተከመረበት::

ካልቨርት በግራ እጁ ከስሩ የተኛውን የማርቆስን ቀኝ እጅ ይዞ ከወለሉ ጋር ሲያጋጨው ሽጉጠ ከማርቆስ እጅ አፈትልኮ በበሩ ኣቅጣጫ ተፈናጠረ፡፡
ማርቆስ ተስፋ አልቆረጠም፡፡የቀኝ ጉልበቱን እንደ መብረቅ ወርውሮ
በካልቨርት ጉልበቶች መሃል ኣጋጨው:: ካልቨርት ለአፍታ ሊቆጣጠረው
የማይችለው ስቃይ እስከ ጎሮሮው ተናነቀው፡፡ እጆቹን ግን ከማርቆስ ኣንገት .
ላይ አላነሳም፡፡ ማርቆስ ለሁለተኛ ጊዜ ጉልበቱን አወናጭፎ ሲሰድ ካልቨርት
በጉልበቶቹ መሃል የተሰማው ስቃይ የሚያየውን ሁሉ አጨለመበት፡፡
ማርቆስ ገልብጦት ተነሳ፡፡

ተፋጠጡ፡፡ ፊት ለፊት ሸብረክ ሸብረክ ብለው ተፋጠጠ፡፡የመጨረሻ ምት በአንደኛው ላይ አርፎ ዓለም ከማለፉ በፊት ተፋጠጡ፡፡ ካልቨርት የሚንቀጠቀጡ ጉልበቶቹ ቢያስቸግሩትም እንደ ግስላ ጥርሰን
ገጥሞ ካፈጠጠበት ሰው ጋር እስከመጨረሻው ለመጓዝ ቆረጠ፡፡ ቢሆንም የባላጋራወን ፍጥነት ሊቋቋመውና ሊስተካከለው አልቻለም፡፡ የመጀመሪያው ግራ ቡጢ ቀኝ አገጩ ላይ አርፎ ሳያነሳ ሌላ ቡጢ ልቡን ሲደቁሰው
ወደኋሳ ተወርውሮ ባለቋሚ የሳሎኑ መብራት ላይ ተዘረገፈ::
የካልቨርትን ሁኔታ የተመለከተው ማርቆስ እሱን ትቶ ሽጉጡ ወደተፈናጠረበት እቅጣጫ መለስ ሲል የገዛ መሣሪያውን ጠላቱ ናትናኤል እጅ ውስጥ አየው፡፡ ለአንድ አፍታ ባለበት ረጋ፡፡

“ትንሽ ተነቃነቅ…እዘረጋሃለሁ፡፡” አለ ናትናኤል : መሬት ላይ እንደወደቀ የድምፅ ማፈኛ የተገጠመለትን የማርቆስን ሽንጥ በራሱ በማርቆስ ላይ ደግኖ::

ማርቆስ ለአንድ አፍታ የመሽነፍና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ፊቱን ያለበሰው መሰለ፡፡ ወዲያው የጋለበው አጋንንት በል እንዳለው ሁሉ ወደ ግራ ተወርውሮ ቀኝ እግሩን ናትናኤል አገጭ ላይ አሳረፈው። የታፈነ የጥይት ድምፅ ተሰማ፡፡በጀርባው የተንጋለለወን ናትናኤልን ቁልቁል ሲመለከት የቆየው ማርቆስ በደም የቀላ ደረቱን እንደጨበጠ እያጉተመተመ ወደመሬት አዘቀጠ... “ባንዳ!... ባንዳ!”

“አይዞህ ተርፈሀል፡፡” “ አለ ካልቨርት የናትናኤልን ክንድ ይዞ ሊያነሳው እየታገለ። “በርታ ቶሎ ከዚህ መውጣት አለብን፡፡ ድምፅ አሰምተናል፡፡ አንተ ሂድ፡፡ እኔ ይዣት እመጣለሁ ርብቃን፡፡” ናትናኤል
ተነስቶ በፍርሃት የምትንቀጠቀጠውን ሴት ተደግፎ በአንድ እግሩ እንደቆመ
ካልቨርት ፊቱን መልሶ በስተግራ ወዳለው የመኝታ ቤት በር ሮጠ፡፡

ናትናኤል የተነደለ ጉልበቱን በግራው እንደጨበጠ ህፃን ልጇን የታቀፈችውን ሴት ተደግፎ ከክፍሉ ወጣና ቀጥሎ ወዳለው ክፍል ተጎተተ::

ካልቨርት የመኝታ ቤቷን መዝጊያ ክፍቶ ሲጎባ አልጋዋ ላይ ተኝታ አገኛት፡፡ ሆዷ ገፍቷል ከኣልጋዋ ላይ አፈፍ አድርጎ አንስቷት እየጎተተ ከመኝታ ክፍሏ አወጣት፡፡ ማን መሆኑን ለማስረዳት ጊዜ አልነበረውም፡፡ወደደችውም ጠላችወም እንደ ህፃን ልጅ እየጎተተ ወሰዳት፡፡ "ቶሎ መውጣት አለበት. ቶሎ...

አልታገለችውም፡፡ በግድየለሽነት ተጎተተችለት፡፡ እያነከሰች ተሳበችለት:: ገርበብ ያሉ ዓይኖቿ አጥርተው የሚያዩ አይመስሉም:: ወደፊት መጥቶ ግንባሯ ላይ የተበተነው ጥቁር ጸጉራ የተጎሳቆላ ፊቷን ሊሸፍነው አልቻለም:: ስስ ብጫ ቀሚስ እንዳጠለቀች ባዶ እግሯን ተጎተተችለት፡፡ከመኝታ ቤቷ ወጥተው ሳሎኑን ኣልፈው ከመተላለፊያው ሲደርሱ ድምፅ የሰማ አንድ የአፓርትመንቱ ነዋሪ በሩን ከፍቶ ብቅ አለ። ወዲያው
የካልቨርትን ደም የጎረሱ ዓይኖች ሲመለከት ከፍቶ የያዘውን መዝጊያ
ጠረቀመው፡፡ ካልቨርት የርብቃን እጅ እንደያዝ ቀጥሎ ካለው ክፍል ውስጥ
ገባና በሩን ዘግቶ በጀርባው ተደግፎት ቆመ:: ያ ዕብድ አገጩ ላይ ያሳረፈበት
ቡጢ መሃል አናቱ ድረስ የተሰነጠቀ ይመስል ሲነዝረው ተሰማው፡፡

ርብቃ አዲስ የገባችበትን ክፍል እስክትለማመደው ድረስ ለአፍታ
ፈዘዝ ያለች መሰለች፡፡ ወዲያው ከፊት ለፊቷ ባለው የሳሉን ፎቴ ላይ ብደም
ተበክሉ የተንጋለሰው ናትናኤል መሆኑን ስትገነዘብ ራሷን መቆጣጠር ተሳናት፡፡ ተንደርድራ ሄዳ ተጠመጠመችበት።
ማንም ማንንም ለማባበል ብታርታት አልነበረውም፡፡ ድንጋጤ ሲያልፍ መረጋጋት ሲተካ ካልቨርት የርብቃን ክንድ ይዞ በትግል ከናትናኤል ላይ አነሳት፡፡ ናትናኤል : በጀርባው እንደተንጋለለ ከፊቱ ቆማ ሳግ የሚተናነቃትን እርጉዝ ሴት በጭንቀት ይመለከታቅ ጀመር…ይቅርታ ለመጠየቅ…ይቅርታ ለመለመን ግን ሃይል ኣልነበረውም፡፡ዓይኖቹ ብቻ በጭንቅ ግራ
በመጋባት ተንቀዋለሉ።
“ያንተ ልጅ ነው…ናትናኤል ሳልነግርህ ቀርቼ ነው… አርግዤልሃለሁ ናትናኤል” ርብቃ ፎቴው ስር ተንበርክካ የሚተናነቃትን ሳግ እየታገለች ልታስረዳው ታገለች:: በጭንቅ የትወጠረውን ፊቱን ስትመለከት
እርግዝናዋ ግራ ያጋባው መሰላት፡፡ ናትናኤል ያንተ ነው ወተወተች፡፡
ካልቨርት የናትናኤልን ሁኔታ ሲመለከት ርብቃን ጎትቶ ከተንበረከከችበት
👍1
አነሳትና ህፃን ልጇን እንዳቀፈች እራቅ ብላ ወደቆመችው ሴት ፊቱን መለሰ..

“ይዘሻት ውስጥ ግቢ ቁስሉን ልይለት፡፡” .
ሴትየዋ የርብቃን ክንድ በትግል እየጎተተች ወደ መኝታ ክፍሏ
ይዛት ገባች::

ካልቨርት ቀልጠፍ ብሎ ከናትናኤል ጎን ብርከክ አለና ቱታ ሱሪውን ቀድዶ ቁስሉን ገለጠው፡፡ በጥይት የተነደለውን የጉልበቱን ሎሚ ስቡን ሲመለከት ሳይታወቀው ዓይኖቹን ጨፈነ፡፡

“ሎሚዬን ኣግኝቶኛል፡፡ ኣይደል? ጉልበቴን አግኝቶኛል፡፡” አለ ናትናኤል በጀርባው እንደተንጋለለ ዓይኖቹን ጣሪያ ላይ እንደሰካ ጥርስን ነክሶ ስቃዩን ለመቻል እየታገለ፡፡

“አዎ፡፡” አለ ካልቨርት ቁርጥ ባለ ድምፅ:: ናትናኤል ያለጥርጥር የዕድሜ ልክ ሽባ መሆኑ ውስጡን እየረበሸው፡፡ “አይህ ዋናው ህይወትህ መትረፉ ነው፡፡”

ካልቨርት ከተሰረገደው ቁስል የሚያገዥውን ደም ለማቆም ይታገል .
ጀመር። ከናትናኤል እግር ላይ ቀድዶ ያነሳውን ቱታ ለሁለት ተርትሮ ቀስሉን ግጥም አድርጎ አሰረው:: እግሩን ወደላይ ሰቅሎ ያዘለት፡፡ በቁስሉ ላይ የታሰረው ካኪ ደም እየጠጣ ደም እየጠገበ ሲቀላም ደሙ ቀስ በቀስ መፍሰሱን አቆመ::

ካልቨርት የናትናኤልን እግር ቀና አድርጎ አስደግፎ ወደ መደርደሪያው ሄደና አንድ የወስኪ ጠርሙስ ይዞ ተመለሰ፡፡ ናትናኤል ጎን ወንበር ላይ ተቀምጦ የውስኪውን ጠርሙስ ክዳን ከፍቶ በአፉ ሙሉ ተጎነጨለት፡፡
የአገጩን ስቃይ ሊቋቋመው አልቻለም፡፡ አገጩን ብሎ ከመሬት የደባለቀው
ሰው ናትናኤል በተኮሰው ጥይት የተበሳ ደረቱን አፍኖ ሲወድቅ ያለው የተናገረው መጣበት “ባንዳ!”፡፡ ራሱን ጠላ ካልቨርት፡፡ ድንገት የመኝታ ቤቱ በር ሲከፈት ካልቨርት ድጋሚ ሊጎነጭለት ያነሳውን ጠርሙስ መለስ አድርጎ ፊቱን አዞረ፡፡

“ኧረ አመማት!” አለች የህፃኗ እናት እየተርበተበተች::
“ምን?” አሉ ካልቨርት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሴትየዋ የተናገረችው አማርኛ አልገባህ ሲለው:: .
“ርብቃ…” አለች ሴትየዋ በእንግሊዝኛ መልሳ፡፡ “አመማት፡፡”
“ምነው?” አሉ ካልቨርት ከተቀመጠበት ደንግጦ እየታነሳ፡፡
“እንጃ ምጥ መሠለኝ፡፡"አለች ሴትየዋ በፍርሃት፡፡
“በእየሱስ! እርግጠኛ ነሽ?”
“መሰለኝ... ሁኔታዋ እንደዛ ነው፡፡” -
“ልትረጃት አትችይም?”
“እኔ ኣላውቅበትም፡፡” የሴትየዋ ገፅ በፍርሃት ዋኘ፡፡
ከመኝታ ቤታ የስቃይ ጩኸት ተስማቸው
“እዚህ ምድር ቤት አንድ አሮጊት አሉ… ግሮሰሪ ያላቸው.…
ልጥራቸው?” አለች ሴትየዋ የካልቨርትን ግራ መጋባት ስትመለከት ጠንከር
ለማለት እየሞከረች፡፡

“ሊረዷት ይችላሉ?”
““እንጂ… ብቻ አሮጊት ናቸው፡፡ ከኛ የሚሻሉ ይመስለኛል፡፡”
ድጋሚ የርብቃ ጩኽት በተከፈተው በር አምባረቀ፡፡
“ሂጅ ሂጅ….ቶሎ በይ አምጫቸው፡፡” እለ ካልቨርት ወደ በሩ እየገፋት::
የህፃኗ እናት እንደወጣች በሩን ቆለፈና ፊቱን መልሶ በጀርባው የተንጋለሰውን ናትናኤልን ተመለከተው፡፡ ዓይኖቹን ጨፍኖ ተጋድሟል፡፡
ወዲያው አላስችልህ ሲለው የተቆራረጠ የማቃሰት ድምፅ ወደሚሰማበት
የመኝታ ቤት ተጠጋ።
ርብቃ አልጋው ላይ በጀርባዋ እንደተንጋለለች ሁለት እጆቿን
ወደኋላ ልካ የተኛችበትን አልጋ የራስጌ እንጨት ይዛ ታቃስታለች በጆሮ ግንዶቿ የሚንቆረቆረውን ላብ ሲመለከት ካልቨርት ጥፋ ጥፋ አለው፡፡ብዙም ሳትቆይ የሀፃኗ እናት ባለግሮስሪዋን ሴት አስከትላ መጥታ በሩን ስታንኳኳ ካልቨርት በድን መስሎ ከቆመበት የመኝታ ቤት በር ሮጥ ብሎ ከፈተላቸው፡፡እንደገባ በሩን መልሶ ቆለፈው፡፡ ሴቶቹ ተከታትለው ወደመኝታ
ቤት ሲያመሩ በዓይኑ ተከተላቸው ባይገባውም፤ ምን እንደተባባሉ ባይረዳም ሴቶቹ በጥድፊያ እያወሩ እየተነጋገሩ ወደ መኝታ ቤቷ ሲገቡ እፎይታ ተሰማው።

ተጠባበቀ፡፡ ደቂቃዎች እየተከታተሉ አለፉ:: ከመኝታ ሴት የገቡት ሴቶች ማንም ብቅ አላሉም። እንቅስቃሴ ሲሰማው ፊቱን መለሰ፡፡ ... ናትናኤል
ነበር፡፡

“አይዞህ ድነሃል…” አለ ካልቨርት ወደ ናትናኤል እየተጠጋ “…አምልጠናል፡፡”

ካልቨርት ናትናኤል ጎን በርከክ ብሎ ትከሻውን ጨበጥ ጨበጥ እያደረገ ኣበረታታው፡፡ ናትናኤል ራሱን መቆጣጠር እንደቻለ ካልቨርት በርከክ ብሎ ከነበረበት ተነሳ፡፡ ሬዲዮኑን ከፈተና ናትናኤል ላይ አፈጠጠ፡፡ የናትናኤል ፊት ከሬድዮኑ ጋር ይቋጠር ይፈታ ጀመር፡፡ ካልቨርት ኣንዴ
የሚለፈልፈውን ሬዲዮ አንዴ ናትናኤልን እየተመለከተ ተጠባበቀ፤ ትዕግስት
አጣ፡፡

“ምንድነው የማለው? ለእኔም ተርጉምልኝ እንጂ!” እስ ካልቨርት ናትናኤል ላይ እንዳፈጠጠ፡፡

“አልገባኝም…” አለ ናትናኤል ካልቨርት ዝም እንዲል አንድ እጁን ብድግ አድርጎ ምልክት እየሰጠው::
“እንዴት? ምን ማለት ነው አልገባኝም?”
ትዕግሥት አጣ ካልቨርት::

ለአንድ አፍታ ናትናኤል ቀና ብሎ አይኖቹን ካልቨርት ላይ ተከለ፡፡ ወዲያው ግራ በመጋባት ስሜት ፊቱን መልሶ በሬድዮው ላይ አፈጠጠ፡፡

“ስለ እየሱስ ብለህ ምን እንደሚል ተርጉምልኝ!” አለ ካልቨርት
በስጨት ብሎ፡፡
“እየተመለሱ ነው፡፡”
“እነማ?” አለ ካልቨርት ግራ ተጋብቶ “ንገረኝ እንጂ” አለ ናትናኤል
ጆሮውን በሬድዮው ላይ ሸክቶ ዝም ሲል፡፡
“መሪዎቹ የአፍሪካ መሪዎች::” አለ ናትናኤል፡፡
“የት ነው የሚመለሱት?”
የአፍሪካ አንድነት ስብሰባ ዛሬ ምሽቱን በሦስት ሰዓት ይጀመራል ተብሎ ሲጠበቅ ስብሰባውን ለመካፈል ወደ ኣዲስ አበባ የገቡ የአፍሪካ መሪዎች ከስብሰባው መክፈቻ ቀደም ብለው ወደየአገሮቻቸው እየተመለሱ ነው ነው የሚለው ራድዮነ፡፡” አለ ናትናኤል ግራ የተጋቡ ዓይኖቹን
ካልቨርት ላይ አፍጥጦ፡፡

“ሊሆን አይችልም!” አለ ካልቨርት “ተሳስተሃል... አንዲያ ሊል አይችልም!”
“የሰማሁትን ነው'ኮ የምነግርህ” አለ ናትናኤል ራሱን የተጠራጠ ይመስል ትከሻውን ሰብቆ፡፡ “ሦስት የአፍሪካ መሪዎች መዲናዋን ለቀው ወደ አገሮቻቸው ተመልሰዋል. ቆይ ቆይ” አለ ናትናኤል አትኩሮቱን ወደ ሬድዮው መልሶ::

“ምንድነው… ምንድነው የሚለው?” አለ ካልቨርት ናትናኤል ጎን ቁጢጥ እያለ፡፡

“የኢትዮጵያ መንግሥት የስብስባው መክፈቻ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ዛሬ ምሽቱን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ባለሥልጣናትን መጠየቁን ውስጥ አዋቂዎች ሊጋዜጠኞች ገለፁ ነው የሚለው፡፡” አለ ናትናኤል ከፊት ለፊቱ ቁጢጥ ያለውን ካልቨርትን እየተመለከተ፡፡

“ሊያከሽፉት ነው!” አለ ካልቨርት በስጨት ብሎ “ከሃዲዎች!..
ምስጢሩ ወጥቷል፡፡”
ድሮም እብደት ነበር፡፡” አለ ናትናኤል በለሆሳስ፡፡ “አበቃላት!”
“ምናልባት…”
“ምን ማለት ነው ምናልባት?”
“ለጊዜው የጊዜው እብደት አብቅቶለት ይሆናል፡፡ ለአፍሪካ ችግር መልስ እስካላገኘን ድረስ ግን ሌላ እብደት ጊዜውን ጠብቆ እንደሚፈነዳ
አትጠራጠር፡፡” አለ ካልቨርት ዓይኖቹን ቦዝዝ አድርጎ፡፡

ከተዘጋው የመኝታ ቤት ጀርባ ጩኸት ተሰማቸው፡፡ በድንጋጤ ተፋጠጡ፡፡ የህፃኗ እናት በሩን ከፍታ ብቅ አለች፡፡ ካልቨርት በፍርሃትና በጥያቄ መልክ አፈጠጠባት፡:

“ደህና ነች...ምጥ ነው፡፡ አለጊዜው ነው የመጣው፡፡ ሰባት ወሩ ነው አለችን፡፡ ግን ምንም አትልም፡፡” አለች የህፃኗ እናት ተረጋግታ፡፡ ናትናኤል የሚሰማውን የሚያየውን ሁሉ መሸከም አቃተው፡፡ ድንገት የመኪና ፍሬን በፍጥነት ሲያዝ ያሰማው ሲጥታ ከውጭ ተሰማቸው:: ካልቨርት ቶሎ ብድግ ብሎ ወደ መስኮቱ ተጠጋና መጋረጃውን በስሱ ገለጥ አድርጎ ወደ ውጭ ተመለከተ፡፡ውጭው ቢጨልምም ከአፓርታማው አጥር ግቢ መግቢያ ላይ ከደረሰችው መኪና ውስጥ ሦስት ሰዎች በጥድፊያ ወጥተው
ሽማግሌውን በረኛ ወደጎን ገፍትረው 'እየሮጡ ወደ አፓርርትመንቱ ሲጠጉ
ታየው:: ካልቨርት ፈጠን ብሎ ፊቱን መለሰና የህፃኗን እናት ርብቃ
👍2
​​ወዳለችበት ክፍል እንድትገባና ድምፃቸውን እንዲያጠፉ ነገራት፡፡ ሴትየዋ
ወደ መኝታ ክፍሏ ስታመራ ካልቨርት በፍጥነት ወደ ዋናው በር ሄዶ
መዝጊያው መቆለፉን ኣረጋገጠ፡፡ ወዲያው መብራቱን አጥፍቶ በስሷ
የጨረቃ ብርሃን እየተመራ ወደ ናትናኤል ተጠጋ፡፡

“እነሱ ናቸው::” አለ ካልቨርት ስማቸውን መጥራት እንደፈራ ሁሉ በሹክሹክታ፡፡
በጨለማው ውስጥ ኣንዳቸው የአንዳቸውን ትንፋሽ እያዳመጡ
ተጠባበቁ፡፡ ከተቆላፈው በር ጀርባ በመተላለፊያው ላይ የእግር ኮቴዎች
ተሰማቸው፡፡ተከትሎም ከጎን ያለው ክፍል ሰር ተበርግዶ ሰዎች ተከታትለው
ሲገቡ ኣዳመጡ፡፡ ካልቨርትና ናትናኤል በጨለማው ውስጥ በፍርሃት
ተያዩ፡፡

የርብቃ ጩኽት ድንገት አስተጋባ፡፡

ናትናኤልና ካልቨርት በድንጋጤ ደርቀው ቀሩ፡፡ መተላለፊያው የእግር ኮቴ ተሰማቸው፡፡ ተጠባበቁ፡፡ የመኪና ድምፅ ሲጥጥ! አለ። ካልቨርት በቀስታ ወደ መስኮቱ ተጠጋ፡፡ ቀደም ብለው ከአፓርትመንቱ አጥር ግቢ በር ላይ ከቆሙት ሁለት ተደርበው ከቆሙ ሌሎች ሁለት መኪናዎች የወረዱ ስምንት ስዎች የያዙትን የጦር መሣሪያ ለመሸሸግ እንኳን ሳይሞክሩ ወደፊት እንደደገኑ የአፓርትመንቱን የአጥር በር አልፈው ተከታትለው ገቡ:: ከግቢው መሃል እንደደረሱ ከአፓርትመንቱ ከወጣ አንድ ሰው ጋር ሰብሰብ ብለው ተነጋገሩ፡፡ ወዲያው ሁለቱ ሰዎች ወደ መጡባቸው
መኪናዎች ሲመለሱ የተቀሩት ወደ አፓርትመንቱ ተጣደፉ፡፡ ካልቨርት ወደ
ናትናኤል ተመልሶ ያየውን ሁሉ ለናትናኤል አንሾካሾከለት፡፡

“አፓርትመንቱን የሚፈትሹ ይመስልሃል?”አለ ናትናኤል ጨለማው
ላይ አፍጥጦ፡፡

“ፈጣሪ አያድርገው::”
“ስንት ሰዓት ነው?” ናትናኤል ጠየቀ፡፡
“ሁለት ከሰላሳ፡፡” አለ ካልቨርት ሰዓቱን ወደ አይኑ አስጠግቶ፡፡

የመኝታ ቤቱ በር ተከፈተ:: ከውስጥ የሚወጣው ደብዛዛ ብርሃን የሳሎኑን ጨለማ ወገግ አደረገው የሆፃኗ እናት አንድ ነገር ታቅፋ ተጠጋቻቸው፡፡

“ተገላገለች፡፡” አለች በሚንቀጠቀጥ ድምፅ፡፡

"ባለ ግሮሰሪዋም አርጊት ቀረብ ብለው የህፃኑን ፊት ትኩር ብለው ተመለከቱት
ካልቨርትና ናትናኤል የሚመልሱት ግራ ገብቷቸው በጨርቅ በተጠቀለለው
አዲስ ህይወት ላይ አፈጠጡ፡፡

ወንድ ልጅ ተገላገለች:፡” አለች የህፃኗ እናት ድጋሚ ወንዶቹ ያልሰሟት ይመስል ዝም ሲሏት አሁንም ከወንዶቹ መልስ አላገኘችም። ሁለቱም ቡዝዝ ብለው እሩቅ ሄዱበት።


ቆንጆ ልጅ እይደለም?” አለች ከተደናገጡት ወንዶች መልስ ያጣችው ሴት ፊቷን ወደ አሮጊቷ መልሳ በአማርኛ::

“የዛሬ ልጆች ቆንጆዎች ናቸው::” አሉ አሮጊቷ አይኖቻቸውን ከህፃኑ ፊት
ላይ ሳያነቅሉ፡፡

ሴቶቹ፡፡ በአማርኛ ቋንቋ የተመላለሱት ያልገባው ካልቨርት ወደ ናትናኤል ፊቱን መልሶ ጠየቀው::

“ምንድነው ያሉት?

"የዛሬ ልጆች ቆንጆዎች ናቸው ነው ያሉት” አለው ናትናኤል የሚታገለውንና የሚተናነቀውን የደስታ እንባ እየታገለ፡፡

💫 ተፈፀመ 💫

#ቆንጆዎቹ ይህን ይመስላል በደራሲ ሠርቅ-ዳ በ 1988 የተዘጋጀው ቆንጆዎቹ ተወዳጅ መጽሐፍ ከዚህ በፊት ያነበባችሁት ለትውስታ ያላነበባችሁት ደግሞ በክፍል በክፍል ተዘጋጅቶ እንድታነቡት ቀርቦ ዛሬ ተጠናቀቀ ሁሌችሁም አስተያየታችሁን ብታደርሱኝ ደስ ይለኛል።

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍31
እና...

አምርሬያለሁ መሰል ፣ ግድ የለኝሞ ሒጂ፤
መረበሽ ይስፋልሽ ፤ ሌላ ሰው አጥሞጂ፤
አምርሬያለሁ ስልሽ ፣ ለስንብቱ ቃል
ደብዳቤ አትጻፊ ፤ ቻው ማለት ይበቃል፤
ቻው ማለት ይበቃል፤ ለስሞሞ
ለእርምሞ፤
አክ እንትፍ ማለት፣
ሒጂ ልቤን ልየው፣ እስቲ ይለይለት።
ዕንባሽን ጠራርገሽ ፣ሂጂ ይቅናሽ አንቺሞ፤
አወየው ሴትነት
ስንቴ ታለቅሺያለሽ? ለሰርግም ለፍቺሞ።
አንዱ እንኳን ይቅርልሽ
አንዱ እንኳን ይቅርብሽ፤
ሜሪው መንገዱን ፤ ሒጂ ሳይመሽበሽ።
እየሄድሽ!
እግርሽን ከመሬት
ብድግ አድርገሽው፣ብሆንም እንዳልሆን፣
ግን ደሞ አውቃለሁ፤
በዚህ በኩል መሄድ ፣ በዚያ በኩል መምጣት ፣ አንዳንዴ እንደሚኾን።
እግርሽን ከመሬት ፣ብድግ እንደማድረግ፤
መንበርከክ ፤ መለመን ፤ የትንሽ ሰው ማዕረግ፤
አረግ፤
ግድ የለም ብረሪ፤
እስከትሰበሪ፤
ግድ የለም ቅዘፊ
እስከምትጠፊ፤ እስክትቀጠፊ፤
ዐይንሽ ዐይን ይወጣለት ፤ ይቀላውጥ ያማትር፤
ሌላ ልበ ስፊ፣ የኔን ልብ ይተርነር።
ታቀፊ በመዳፍ ፤ታቀፊ በፍርጥሞ፤
እነደ ካህን ጥሞጥሞ።
ዙሪያሽን በመሉ...
ይክበብሽ ተባዓት፤
ሰው ይኹነሽ መዓት፤
አንቺ..
አሜን በይ ከሰዓት፤
ሒጂልኝ ወደዛ በሐዘንሽ ታንቅሽ፤
ግን...
ይሄን ሁሉ ያልኩት
ጤነኛ ሆኜ እንደሁ፣ እይኝ ተደብቀሽ።

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍2