አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ተጨማልቆ እንደሆነ የማጣራት ስራዬ ላይ ትኩረት አድርጌ መስራት እፈልጋለሁ፡፡ አንቺ አለቃ ስለሆንሽ የአትኩሮት አቅጣጫዬን ልትመርጪልኝ ትችያለሽ፡፡ ደግሞስ ከፋይ ሁሌም ትክክል ነው አይደል የሚባለው?” አላት፡፡

ኒኪ የመጨረሻው ገለፃው ትንሽ ፈገግ አሰኛት፡፡

“ምነው የሚያስቅ ነገር አለ?”

“የለም ኧረ...” ብላ ኒኪ ፊቷ ላይ ፈገግታዋ እንዳለ “በቃ መልካም ሰው
ነህ ዴሪክ፡፡ በጉዳዩ ላይ በጣም በጥሩ ሁኔታ ነው ስራህን የሰራኸው ለዚያውም በሚገርም ጉልበት፡፡ በነገርከኝ ነገሮች አናቴን አዙረኸዋል፡፡ ያም ሆኖ ግን አመሰግናለሁ፡፡ በዛ ላይ ደግሞ አምንሃለሁ፡፡” አለችው፡፡

ዊሊያምስ ከሴት ምስጋናን ከሰማ ብዙ ጊዜ ሆኖት ነበር፡፡

“እኔም አመሰግንሻለሁ” አላት እያፈረ እና “ይህንን ጥሩ ሰው ነህ ያልሺውን ነገር ግን ለፈታኋት ሚስቴ በደብዳቤ ፅፈሽ ብትነግሪልኝ በሚቀጥለው ወር ሥራዬን በነፃ ነበር የምሰራልሽ፤ የእውነቴን አይደለም፡፡ ገንዘብ ያስፈልገኛል” ብሎ ዊሊያምስ ገለፈጠና “የሆኑ የምሸፍናቸው ወጪዎች ነበሩብኝ..” ኒኪ የቼክ ደብተሯን አውጥታ አንደኛው ወረቀት ላይ መፃፍ ጀመረች። እርግጥ ነው ብዙ እየጠየቃት መሆኑን ታውቃለች፡፡ ግን ጆንስን እና ጉድማን በሁለት ሳምንት ውስጥ ያልሰሩትን ስራ እሱ በአራት
ቀናት ውስጥ ሰርቶ አሳይቷታል፡፡ ምንም እንኳን ያቀረበላት ብዙ መረጃዎች
የተንጠለጠሉ እና ያልተቋጩ ሀሳቦች ቢሆኑም ማለት ነው፡፡

“በዚህ ሳምንት ትኩረትህን በባሌ ላይ ስለደረሰበት የመኪና አደጋ ላይ
አድርገህ እንደትሰራ እፈልጋለሁ፡፡” ብላ ቼኩን ከደብተሩ ላይ ቀደደችና እጁ
ላይ አስቀመጠችለት፡፡ በመቀጠልም “ስለ ሌንካ በጣም ብዙ ነገሮችን ማወቅ
እፈልጋለሁ፡፡” አለችው፡፡

ዊሊያምስም “እርግጠኛ ነሽ ይሄን ነገር ነው ቅድሚያ ሰጥተሽ ማወቅ የምትፈልጊው?” ብሎ ጠየቃት፡፡

“አዎን ለዚህ ጉዳይ ነው ቅድሚያ የምሰጠው” ኒኪ መለሰች። ህይወትሽ
አደጋ ላይ እንዳለ አስበሸው ታውቂያለሽ?” ብሎ ዊሊያምስም ምክንያታዊነቱን በማስቀደምም “ይሄ የአደንዛዥ ዕፅ ስራ የብዙ ሚሊዮኖች ዶላር ሥራ ነው። ቢዝነሱን የሚጋሩት ስዎች ደግሞ በጣም ሰው በላ እብዶች ናቸው፡፡ ስለ ሉዊስ ሮድሪጌዝ ብቻ አይደለም እዚህ ጋር የማወራሽ፡፡ በዚህ ቢዝነስ ውስጥ የተሳተፉ ሩሲያውያን፣ ሜክሲካውያን እና ቻይናውያን ሁሉ የቢዝነሳቸው ጠላት የሆነ ሰውን ከማስወገድ ወደ ኋላ የማይሉ ሰዎች ናቸው፡፡”

እኔ እንዴት ነው ጠላታቸው ልሆን የምችለው?” ብላ ኒኪ ጠየቀች፡፡

“እሱን እንዴት እንደሆነ እስከ አሁን አልደረስኩበትም፡፡ በዚህ ሳምንት
ግን ልደርስበት እችላለሁ። ምናልባት እነዚህ ነፍሰ በላዎች አንቺንም እንደ
ሌሎቹ ገዳዮቻቸው ቆራርጠው ገድለው ካልጣሉሽ በስተቀር ማለቴ ነው፡፡
ንግግሬ ካስቀየመሽ ይቅርታ”

“ችግር የለውም” አለችው እና ኒኪ በመቀጠልም “ስላሰብክልኝ አመሰግንሃለሁ ዴሪክ። የእውነት አመሰግናለሁ፡፡ ህይወቴ አደጋ ላይ ቢሆን
እና ነገ እንኳን ቢገድሉኝ ፤ስለ ባለቤቴ ማወቅ ያለብኝን ነገሮችን ሁሉ ዛሬ
ላይ አውቄ ነው መሞት የምፈልገው፡፡ ስለ እዚህች ሌንካ ስለምትባል ሴት
ማን ናት እሷ? ይሄን መመለስ ከባድ አይመስለኝም ላንተ?” አለችው፡፡

“እንግዲህ አለቃው አሁንም አንቺ ነሽ” ብሎ ዊሊያምስ መለሰላት።

አብረው ከቢሮው ወጥተው ወደ መኪናዎቻቸው አመሩ። ኒኪ መኪናዋን
አስነስታ ስትሄድ በመስኮት የመኪና መስታወት እያያት ምን ያህል
የምትገርም ሴት ናት አለ ለራሱ፡፡ ደስ ብላዋለች በተለይ ደግሞ “ጥሩ ሰው
ነህ' ስላለችው በጣም ደስ ብላዋለች፡፡ ምክንያቱም የለበጣ ሳይሆን ከልቧ ነው
ይህንን ነገር የነገረችው እና ልቡ ተነክቷል።

ወደ ቤቱ መኪናውን እያሸከረከረ ሲሄድም ለራሱ ጮክ ብሎ “ዴሪክ አንተ ጥሩ ሰው ነህ፡፡ በእውነት አንተ ጥሩ ሰው ነህ” እያለ ነበር “አዎን እኔ ጥሩ ሰው ነኝ፡፡”

እሱ ከዶውግ ጀርባ ስላለችው ውሽማው ሚስጥር ፈልፍሎ ማወቅ ይችላል፡፡ ኒኪ ልክ ናት፡፡ ይሄ ነገር እንዴት ለእሱ ከባድ ሊሆን ይችላል?
ይህንን ሁለቱን ሰዎች የገደለውንም ሰው ያገኘዋል፡፡ ከዚህ ግድያ በስተጀርባ
ያሉትን እና ኒኪንም የሚያስፈራሩ ሰዎችን ማንነት በቅርቡ ያገኛቸዋል፡፡
ቫላንቲና እና ዊሊ ባደን እዚህ ውስጥ ሊኖሩ ይችላሉ! ሮድሪጌዝማ ዋነኛው
ተሳታፊ ነው፡፡ ልክ የቻርሎቴ ክላንሲ ጉዳይ ላይ ዋነኛ ተሳታፊ እንደሆነው
ሁሉ እዚህ ላይም አለበት ብሎ ዊሊያም ያስባል፡፡ በመጨረሻም ይሄንን
የዞምቢ ግድያ ወንጀልን በደንብ አድርጎ ይፈታዋል፡፡ ከዚያም የዚህቺን ቆንጆ
ደንበኛውን ልብ እርፍ እንዲል ያደርጋል፡፡

ስለከፈለችው አይደለም ይህን የሚሰራላት፤ ነገር ግን እሱ ጥሩ ሰው
ስለሆነ ነው ይህንን የሚያደርግላት፡፡...

💫ይቀጥላል💫
አትሮኖስ pinned «#የፍቅር_ሰመመን ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ሰባት ፡ ፡ #ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን ፡ ፡ #ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው ድርጅት የእገታ ማስለቀቂያውን የገንዘብ ክፍያ ከታጋች ቤተሰብ ተቀብለው እና ድርሻቸውን ቆርጠው ለአጋቾች እንደሚሰጡ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ አንደኛው የቢዝነስ አካሄድ ነው፡፡ ሌላኛው ነገር ደግሞ ራሳቸው የወሮበላ ቡድኖቹ አብረዋቸው የሚሰሩ ሰዎቻቸውን ወደ አሜሪካ ከገቡ በኋላ በአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች…»
#ያምራል

በጥሩ ቀን አይደል----- ፌሽታ በሞላበት፣
በሃቅ የሚመዘን---- መልካም ጓደኝነት፡፡
ወዳጄ ...
በሞላልህ ጊዜ -----ፍለጋ ብትወጣ፣
እንዳትጠራጠር ----ጓደኛ ያልሆነን ነው
አስሰህ የምታጣ፡፡
ይልቅስ ...
በእቶን እሳት መሃል---- እየተራመዱ፣
ሰዎች እስኪሞቱ----- ካየህ ሲረዳዱ፣
ጭላጭ የኮዳ ውሃ -----እየተካፈሉ፣
ላንተ ትሁን ላንተ -----ካየህ ሲባባሉ፣
በፈንጂ የታጠረ መሬትን ለመርገጥ-- እየተቻኮሉ፣
እኔ ልቅደም ብለው----በወሳኟ ሰዓት ሞትን ሲቀበሉ፣
ለሃገር ሲፋለሙ ----በጠላት ተኩስ ቆስለው፣
በትከሻቸው ግን----አንድም የተሰዋ
አንድም የተጎዳ …………ጓዳቸውን አዝለው
ካየህ እስከ ህይወት ጥግ
ለጓደኝነት ክብር ----ውድ ዋጋ ሲከፍሉ፣
ማን ናችሁ በላቸው
እኛ ወታደሮች ነን---- ስለ ሃገር ቆመን
ስለ ፍቅር የምናልፍ -----ሲሉ ይመልሳሉ፡፡
ከዚያ ግን ትላለህ ...
በበረሃ ንዳድ----ያውም በጦርነት፣
ሺዎች እንደ አንድ ሆነው ---በተሰለፉበት፣
ጠብታ የኮዳ ውሃ ----በሚካፈሉበት፣
ፍቅር አፍ አውጥቶ -----በሚናገርበት፣
በወታደር መሃል ------ያምራል ጓደኝነት፡፡

🔘ሻለቃ/ጋዜጠኛወይን ሐረግ በቀለ🔘
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አርባ_አራት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

....ናትናኤል ባለበት እንደቆመ በእልህ የሚርገበውን ካልቨርትን ሲመለከት የፈጸመው ስህተት ወለል ብሎ ታየው፡፡

“እጇን እየጠመዘዙ ሲያስጮኋት መፈረካከስ ጀመርክ.. እዬዬዋን
ስትሰማ ስለሰጡህ ቃልኪዳን መስበክ አማረህ… ናትናኤል የሚወዱት ሰው
አደጋ ላይ ሲወድቅ ምን እንደሚሰማ አውቀዋለሁ፡፡ እንዳንተ ለደቂቃዎች
ሳይሆን ለቀናት ለሳምንታት አብሮኝ ከርሟል። ይህ ብቻ አይደለም፤
የሚወዱትን ማጣት ምን ምን እንደሚልም ቀምሼዋለሁ። አሁን ድንገት
ወጣ ብለህ የፍቅረኛህን ለቅሶ አዳምጠህ ስለመጣህ ካንተ ጋር በአንድ ሲባጎ ተሸብቤ ወደ መቃብራ እንድነዳ ትጠይቀኛለህ? !ኦ ! ኢየሱስ!”

ናትናኤል ድምፅ ሳያሰማ ባለበት እንደቆመ ቆየ።

“ኣብረኸኝ ትጠፋለህ ወይስ እጅህን ትሰጣለህ? ” አለ ካልቨርት የሴት
ነጠላ ጫማውን ኣጥልቆ ሰፊ የሴት ቦርሳውን ዚፕ ከመዝጋቱ በፊት ድንገት
ቀና ብሎ እየተመለከተው፡፡

አብሬህ እጠፋለሁ፡፡” አለ ናትናኤል ጥርሱን ነክሶ እንባውን እየታገለ፡፡

“ትረፍ ሲልህ ጥሩ መንገድ መርጠሃል” አለ ካልቨርት ከስፊው ቦርሳው ውስጥ አንድ ትንሽ ሽጉጥ አውጥቶ እየፈተሽ፡፡ “እጅህን ልትሰጥ ብትወስን ኖሮ እዚሁ ጨርሼህ ልሄድ ነበር የወሰንኩት፡፡ መቼም አይኔ እያየ እየመራህ እንድታሲዘኝ ልተውህ አልችልም፡፡ በል ቶሎ እንውጣ፡፡” አለ ካልቨርት ሽጉጡን ፈትሾ አቀባብሎ መጠበቂያውን ብቻ ባለበት ትቶ መልሶ
ቦርሳው ውስጥ እየከተተው፡፡

ካልቨርት የሴት ልብስ ለብሶ በላዩ ላይ ድሪያውን ተከናንቦ ናትናኤል ደግሞ ከወገቡ በታች ሽርጡን እንዳሸረጠ በነጭ ሸሚዝ ከትንሿ ክፍል ተከታትለው ወጡ፡፡

“ወዴት ልትሄዱ ነው?” አሉ የየምሥራች እናት ድምፅ ሰምተው ከጓዳ ብቅ እያሉ፡፡
“ሰላም ነው፡፡ወደ አዲስ አበባ ነው የምንሄደው በላቸው፡፡” አለ
ካልቨርት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈጠን ብሎ፡፡ “እና ስላደረጉልኝ ሁሉ በደንብ
አመስግንልኝ፡፡”

ናትናኤል ካልቨርት ያለውን በአማርኛ ተርጉሞ ለሴትየዋ ተናገረ፡፡

“ውዴታዲያ ብትሄዱስ በዓመት በዓል ነው እንዴ! ምነው ዋል አደር ብትሉ፡፡” አሉ የተከፉ የሚመስሉት ሴትዮ ካልቨርት ለብሶት የመጣውን የሴት ልብስ ድጋሚ ለብሶ ሲያዩ ምስጢሩ እያጓጓቸው፡፡

“ብንሄድ ይሻላል፡፡ የምሥራች ትጠብቀናላች:: ዛሬ ከሰዓት መግባት
አለብን፡፡”

“በአውሮፕላን ነው የምትሄዱ?” አሉ ሴትየዋ፡፡
“አዎ፡፡” አላቸው ናትናኤል፡፡
“ውይ አፈር በበላሁ! ደብዳቤ እንኳን ሳልጥፍ!” ኣሉ ሴትየዋ
እጃቸውን ሽርጣቸው ሳይ እየጠራረጉ “ማነሽ እመ… እመቤት ወረቀት
ወዲህ በይ ...ቶሎ...”
“አይ… ” አቋረጣቸው ናትናኤል እንዳያዘገይዋቸው ሰግቶ፡፡ “ሰሞኑን
ከቻልኩ ተመልሼ እመጣለሁ ከምሥራች ጋር፡፡ መልዕክት ግን እነግሮለታለሁ፡፡ አሁን ቶሎ መሄድ አለብን፡፡”

ሊወጡ ሲሉ ካልቨርት ከቦርሳው ውስጥ በርካታ ገንዘብ አውጥቶ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ምሥጋና እየደረደረ ለሴትየዋ ዘረጋላቸው፡፡

“በቁልቢው! ኧረ እኔ'ቴ! እዚህም ሆኖ የተቀበልኩት'ኮ ሁሉን ላሟላበት አቅም ስለሌለኝ እንጂ. ደግሞ የምን ክፍያ አመጣችሁብኝ? የልጄ ባልንጀሮች ልጆቼም አይደላችሁ? ግድ የለም 'እግዜር ይስጥህ የኔ ልጅ በልልኝ በኣ
አፉ በቋንቋው፡፡” አሉ ሴትየዋ ፊታቸውን ወደ ናትናኤል መልሰው፡፡

የምሥራች እናት ቤት ወጥተው ብዙም ሳይርቁ ከአንድ አነስተኛ ቡና ቤት ገቡና ጥግ ላይ ጨለምለም ያለ ቦታ መርጠው ተቀመጡ፡፡

“አዲስ አበባ ነው ለመሄድ ያሰብኩት::” አለ ካልቨርት ቦታ ይዘው እንደተቀመጡ፡፡ “በዚህ ሰዓት ተመልሰው እመህላችን ይገባሉ ብለው አይጠረጥሩንም:: ወደዚያው ማምራታችንን በትክክል እስካልደረሱበት ደግሞ ሠላም ልናገኝ የምንችለው አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ነው፡፡”

“ታዲያ ለምን ለየምሥራች እናት እውነቱን እንድነግራቸው ነገርከኝ?” አለ ናትናኤል፡፡

“አውቄ ነው:: ተባራሪ የሚሄድበትን፤ የሚሽሽበትን በትክክል አይናገርም። ሴትየዋ ቢያወሩም ዋጋ የሚሰጠው የለም፡፡ ይልቅ እንዴት አድርገን ወደ አዲስ አበባ መሄድ እንደምንችል ነው ያልተገለፀልኝ፡፡”

“ሦስት አማራጭ ነው ያለን አውሮፕላን- ባቡር መኪና፡፡”

“አውሮፕላኑን እርሳው:: ባቡር አንድ አማራጭ ነው:: ቢሆንም በጣቢያዎች ላይ ሰዎች ሊኖሩአቸው ይችላል፡፡ አውቶቡስ ጣቢያዎችም ተመሳሳይ ናቸው”

“እያቆራረጥን መጓዝ እንችላለን፡፡” አለ ናትናኤል ዝም ብለው ተቀምጠው ያዘዙትን ሻይ ሲጠጡ ከቆዩ በኋላ፡፡

“እንዴት?”
“ለጊዜው ክድሬዳዋ ብእግርም ቢሆን መውጣት.… ከዛ በኋላ የጭነት
መኪናዎችና የቤት መኪናዎች እየተከራየን እያቆራረጥን መጓዝ
እንችላለን፡፡”

“በእግር እስከየት ድረስ እንሄዳለን?” አለ ካልቨርት ትክሻው ላይ ካነገበው ከሰፊው የሴት ባርሳው ውስጥ አነስተኛ የአገር ጎብኚ ካርታ አውጥቶ እመሃል ካለው ጠረጴዛ ላይ እየዘረጋ፡፡ «እዚህ ነው ያለነው፡፡ አለ ካልቨርት የሌባ ጣቱን ድሬዳዋ ላይ ተክሎ፡፡ «እዚህ ነው መድረስ ያለብን፡፡ጣቱን ከድሬዳዋ አንስቶ አዲስ አበባ ላይ ጫነው፡፡

“እዎ..ይኽውልህ አንደኛው መንገድ በሐረር አቅጣጫ አድርጎ አለማያ ከመድረሱ በፊት ወደ ግራ ታጥፎ አሰበ ተፈሪ ይገባና ከዚያ ወዲያ በሚኤሶ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ይደርሳል፡፡ የተለመደው መንገድ ይህ ይመስለኛል፡፡”

“ይመስለኛል? አታውቀውም እንዴ?” አለ ካልቨርት ደንገጥ ብሎ፡፡

“እውነቱን ለመናገር አላውቀውም.. የመጀመሪያ ጊዜዬ ነው ድሬዳዋ ስመጣ፡፡”

“በእየሱስ! ከኔ አትሻልማ!” አለ ካልቨርት ወደኋላ ወንበሩ ላይ ተደግፎ፡፡

“አታስብ አማርኛ እስከተናገርኩ ድረስ የትም ይዤህ መሄድ እችላለሁ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ፡፡ ይኸውልህ... ሌላው አማራጭ ደግሞ ከሞላ ጎደል ከባበር ሃዲዱ ጋር ጎን ለጎን የሚሄደው የየረር ጎታ መስመር ነው፡፡ ይታይሃል በዚህ እድርጎ.” . ናትናኤል ወደ አዲስ አበባ ሊያመሩ
የሚችሉባቸውን ሁለት የመኪና መንገዶች አንድ በአንድ ለካልቨርት አሳየው፡፡

እኔ ሁለተኛውን እመርጣለሁ፡፡ እንዴልከው ብዙም የማይዘወትር ከሆነ አለ ካልቨርት፡፡

“ጥሩ፡፡ ግን ከዚያ በፊት ልብሶቻችንን መቀየር አለብን። ቤት ስንመጣ የምሥራች እናት እይተውናል፡፡አዳኞቻችን ከጠነከሩባቸው ፈርተው
ሊናገሩ ይችላሉ፡፡”

መዝድ ከመጀመራቸው በፊት ናትናኤል ከአንድ የልብስና የጫማ ሱቅ ገብቶ ለካልቨርት የሚሆን ሽርጥናጫማ፣ ለሁለቱም ደግሞ የእስላም ቆቦች ገዝቶ ተመለሰ፡፡ ከአንድ ቡና ቤት መጸዳጃ ቤት ውሰጥ ካልቨርት የለበሰውን የሴት ልብስ በአዲሱ ሼርጥ ከቀየረ በኋላ የወንድ ጫማውን ተጫምቶ መኪና ፍለጋ ወጡ።

“ጎን ለጎን ባንሄድ ጥሩ ነው። የሚፈልጉት ሁለት ሰዎችን ስለሆነ ዓይናቸው ጥንድ መንገደኞች ላይ ይበልጥ ጠንቃቃ ይሆናል፡፡አንተ ከፊት ከፊቴ ሂድ፡ እኔ በቅርብ ርቀት እከተልሃለሁ።” አለ ካልቨርት፡፡

"እንጠፋፋለና።”

“አንጠፋፋም፡፡ ብቻ አተ ከጀርባህ መኖሬን ለማረጋገጥ አትገላመጥ፡፡ ኣማርኛ የምትናገር አንተ ስለሆንክ በተቻለ መኪናውን ቶሉ ለማግኘት ብቻ ሞክር፡፡ እኔ እከተልሃለሁ። አታስብ፡፡ ለአት እዲስ ነው እንጂ እኔ የኖርኩበት ዓለም ነው ድብብቆሽ፡፡” አላ ካልቨርት፡፡
«እ..ናትናኤል ሊይዙን ቢችሉም ቀድመው የሚይዙት አንዳችንን ነው…አንተን ከያዙህ ዕሩቅ ስለማይህ ችግር የለውም! አመልጣለሁ፡፡ እኔን ከያዙኝ ግን የጥይት ድምፅ ስትሰማ ሳትገላመጥ ሳትደናገጥ ለማምለጥ ሞክር፡፡አንተንም ከያዙህ የምመክርህ የገዛ ሕይወትህን እንድታጠፋ ነው፡፡ አለበለዚያ
የሚከተለውን ለመሸከም መምረጥህ ነው፡፡”

“መሣሪያ እኮ
👍2
የለኝም።” አለ ናትናኤል መሣሪያ ቢኖረውም የዚህን ዓይነት ዕብደት እንደማይፈጽም እየተማመነ።

“እንዴት አለ ካልቨርት በመደነቅ ፊት እየተመለከተው።በእየሱስ ያንን ሁሉ ያስለፈለፍከኝ ባዶ እጅህን ነው ማለት ነው»ካልቨርት ናትናኤል ላይ አፍጥጦ ቀና ፈገግ አለ፡፡ አትሙት ብሎ የፈጠረው ሞኝ ዝንጀሮ አንተን እየሁ።”
ብዙም ሳይቸገሩ በዱርዬዎች እርዳታ ከድሬዳዋ ተነስቶ ቢኬ የሚገባ አሮጌ የቤት ዕቃ የጫነ አነስተኛ የጭነት መኪና አግኝተው ሂሣብ ተስማምተው ተሳፈሩ። መንገዱ ተዘግቷል እያለ የሚነጫነጨው ሹፌር ሂሳቡን አለቅጥ ቢቆልለውም ካልቨርት ተሽቀዳድሞ ይሁን ስላለ ከጀርባ መኪናው ላይ ወጥተው ጉዞ ጀመሩ፡፡

“አስፋልት መንገዱን ዘግተውታል። ዙሪያ ጥምጥም በአቧራው በሜዳው አሳብሬ ነው የምወስዳችሁ! እንደውም በእርካሽ ነው ያገኛችሁኝ አቦ!” እያለ እየተነጫነጨ ሹፌሩ ከመሪው ኋላ ገብቶ ከመነቃነቃቸው በፊት በብብቱ ከያዘው ቱባ ጫት ሁለት ዘለላ መዝዝ ወረወረላቸው፡፡ የጭነት መኪናው ከጀርባ የጫነው የሳሎን ፎቴዎች፣ ጠረጴዛዎች፣ ትናንሽ ሳጥኖች አንዱ በኣንዱ ላይ ተነባብረው ትከምረዋል፡፡ እዚያ ውስጥ ናትናኤልና ካልቨርት በትይዩ በተቀመጡ ሁለት የሳሎን ፎቴዎች ላይ ተቀምጠው
አስፋልቱን ትተው ሹፌሩ ብቻ በሚያውቀው አቅጣጫ ሜዳ ለሜዳ
በአቧራው ላይ እየጋለቡ ተዘጋ የተባለውን ኬላ አሳብረው ጋለቡ፡፡

የጭነት መኪናው ያረጀ ብቻ ሳይሆን በአያያዝ ጉድለት ይሁን ወይ
እንደ ወፍ ክንፍ አውጥቶ ሊበር በማዳዳው የሹፌሩ ኣነዳድ ብቻ ክፉኛ
ወላልቋል። በእያንዳንዱ ኩርባ ላይ የሚያሰማው ኳኳታ በእያንዳንዱ ጉድባ
ላይ የሚለቀው ጓጓታ ከእሁን አሁን ተፈረካክሶ በበረሃው መሃል ተቆለለ
ያስብላል፡፡

ከጋቢናው በስተኋላ ባለው መስኮት ውስጥ ጀርባው የሚታያቸው ሹፌር ልጅ እግር አይደለም:: የከሳ ሰውነቱ በጫትና በመጠጥ እንደተጎዳ ያስታውቃል፡፡፡ አኳኋኑና አነዳዱ ፤ በየሰበሰበ በየኩርባው ከአፉ የሚወጣ ስድብና ጩኸቱ ግን ወጠምሻ ጎረምሳን ያስንቃል። ጀርባውን ፈትቶ ከጎኑ ካለው ወንበር ላይ ከበተነው ጫት አሁንም አሁንም እያነሳ ኣፉን ያጭቃል፡፡ መንገዱን ዘጉ የተባሉትን ወታደሮች ያሳደባል፤ አባቶቻቸውን ይራገማል፤ እናቶቻቸውን ያፈቅራል…ሌላም ሌላም ነገር ያደርጋል…ወደፊት ይከንፋል.…

ትንሽ እንደሄዱ ካልቨርት ከቦርሳው ውስጥ ትንሹን የአገር ጎብኚ
ካርታ አውጥቶ ዘረጋና

“እሁን የት ድረስ ነው ይህ ሰው የሚያደርሰን?” አለ ባጎነበሰት
ዓይኖቹን ብቻ አቅንቶ ናትናኤልን በግንባሩ እየተመለከተ::

“ይኸውልህ።” አላ ናትናኤል ካርታው ላይ ያለችውን ጸቢኬኝ ከተማ በትንሽ ጣቱ ነካ አድርጎ::

“ከዋናው መንገድ ተገንጥሎ ይወጣል ይሄ ከተማ?” አለ ካልቨርት በካርታው ላይ ኣፍጥጦ::

“መሆኑ ነው መሰለኝ፡፡”

"ከዚያ በምን ሙቀጠል እንችላለን?” ካልቨርት ግንባሩን ከስክሶ
ጠየቀ፡፡

ናትናኤል ሰዓቱን ተመለከተ፡፡ «እንጃ ካልቨርት፡፡ ይመሻል፡፡ እዛው ማደር ሳይኖርብን አይቀርም፡፡ አሁን ዘጠኝ ተኩል ሆኗል፡፡ አስራ ኣንድ...አስራ ሁለት ላይ ብንደርስ ነው፡፡ በዛ ሰዓት ወደ አዲስ አበባ የሚያመራ መኪና ማግኘት አስቸጋሪ ነው የሚሆንብን፡፡»

ለአንድ አፍታ ካልቨርት ሃሳብ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡ ናትናኤል ጓደኛውን ምን እንደሚያስብ ባይረዳም ዝም ላለማለት ያህል፡

“እሁን አዲስ አበባ ስንደርስ ምንድነው የምናደርገው?” አለ፡፡
“በመጀመሪያ እዚያ እንድረስ፡፡ በነገራችን ላይ ይሀች ሀኬ ወዳልካት ከተማ ከመታጠፋችን በፊት ንገረኝ::" እለ ካልቨርት፡፡

“እሺ እነግርሃለሁ፡፡ መቼም ባላውቃትም ክፉኛ ወደ ቀኝ ከታጠፈ እሷ መሆን አለባት፡፡ ከዛ ቀድሞ ሌላ የሚገነጠል መንገድ የለም ካርታ'ው ላይ፡፡” አለ ናትናኤል በተቀመጠበት ፎቴ ላይ ለጠጥ ብሎ፡፡ “አዲስ ኣበባ ስንደርስ ምን ማድረግ እንዳለብን ብንነጋገር ግን ጥሩ ይመስለኛል፡፡ ቀድሞ ማቀድ ኮመሽቀዳደምና ከመደናበር ያድናል ካለፈው ልምዴ እንዳየሁት፡፡”

“ምንም ዕቅድ አያስፈልግም።” አለ ካልቨርት ፊቱን በዙሪያቸው
ወደተንጣለው በረሃ መልሶ፡፡

“እንዴት?”
“ምንም የምናደርገው ነገር የለማ።”
“ምንም ካልሰራን ለምን ወደዚያ እንሄዳለን?”
“ናትናኤል” አለ ካልቨርት በተሰላቸ ድምፅ፡፡ “ምን ለማድረግ ነበር
የምታስበው… አዲስ አበባ ውስጥ ተደብቀን ለመቆየት ይበልጥ አመቺ ስለሆነ ብቻ ነው ወደዚያ የምንሄደው፡፡ በቃ፡፡”
“ርብቃስ! የኔስ ፍቅረኛ፡፡ እጃቸው ውስጥ መሆኗን እያወቅሁ የገዛ አንገቴን ለማዳን ስል ድምጹን እንዳጠፋሁ እንድቆይ ነው የምትመክረኝ?"
ናትናኤል በስልክ የሰማው ማስጠንቀቂያ አንድ በአንድ ታወሰው። :
“ስለዚህ ምን ልታደርግ አሰብክ?”
“ኣስፈራራቸዋለኋ! እንዲለቋት፡፡” አለ ብስጭት ብሎ፡፡
“በምን ነው የምታስፈራራቸው?” አለ ካልቨርት ለመጀመሪያ ጊዜ ፈገግ ብሎ፡፡


💫ይቀጥላል💫
👍2
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው


ኒኪ ከዊሊያምስ ቢሮ ወጥታ ጥቂት መቶ ሜትሮችን መኪናዋን ካሽከረከረች በኋላ ከኋላዋ ብልጭ ብልጭ የሚል የመኪና መብራትን የሚያሳያት መኪና እንዳለ ለማየት ቻለች፡፡ ያው የሎስ አንጀለስ መንገድ የተጨናነቀ ስለሆነ ምናልባትም የቀደመችው ሹፌር ንዴቱን ለማሳየት
በመብራት እየሰደባት እንደሆነ በመገመት ላይ እያለች ግን የፖሊስ ሳይረን
ድምጽ ስለሰማች መኪናዋን ጥግ አስይዛ ከመንገዱ ዳር በንዴት አቆመች እና
መስታወቱን ዝቅ አድርጋ “ፖሊስ ምን ያጠፋሁት ነገር አለ... እንዴ! አንተ
ነህ እንዴ?” አለችው በመስኮቱ ስር ቀና ብላ ከመኪናዋ በር አጠገብ የቆመውን መርማሪ ፖሊስ ጉድማንን ስትመለከት፡፡ የጉድማን ቆንጆ ፊትም በፈገግታ እንደ በራ “ከዴሪክ ዊሊያምስ ቢሮ ወጥተሽ መንገድ ከጀመርሽ ጀምሮ እንድታይኝ ያላደረግኩት ጥረት አልነበረም፡፡”

ኒኪም በስጨት ብላ “ስለ ዊሊያም ደግሞ እንዴት አወቅክ? ስትከታተለኝ
ነበር እንዴ?” ብላ ጠየቀች “አትበሳጪ” ብሏት ጉድማን በማስከተልም “ስራዬ
እኮ ነው፡፡ ማለቴ አንዱ የስራ እድል ነው፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ አንቺ እራስሽን
አላማ ያደረጉ የግድያዎች ሙከራዎች የተደረጉብሽ ሰው ስለሆንሽ እንደ
አንድ መርማሪ አንቺን መከታተሌ ክፋት የለውም እላለሁ።” አላትና በሰማያዊ አይኖቹ ሰርስሮ ሲመለከታት አፈረችና “ይቅርታ” ብላ ተንተባተበች፡፡ “በመቀጠልም ልወነጅልህ ፈልጌ አይደለም፡፡ አንተ ስራህን እየሰራህ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ግን በድንገት ስላገኘሁህ ተገርሜ ነው።”

“አሁን ወዴት እየሄድሽ ነው?”
“ወደ ቤት”
“እራት በልተሻል?”
የሚለው ጥያቄው ትንሽ የነፃነት ስሜት ሰጣትና እስከ አሁን አልበላሁም” ብላ መለሰችለት፡፡

“መልካም ተከተይኝ” ብሎ ጉድማን የእሷን ሀሳብ ሳይጠይቅ በመወሰን
“የሆነ የግሪኮች ምግብ ቤት ከዚህ በትንሽ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የምትወጂው ይመስለኛል፡፡ በዚያ ላይ እናወራለን” ሲላት ኒኪ አብራው ለመሄድ ስታመነታ በማየቱ “ስለ አዲሱ ወዳጅሽ ስለ ሚ/ር ዊሊያምስ እናወራለን፡፡ ስለ እሱም ልታውቂያቸው የሚገቡ አንዳንድ ነገሮች አሉ፡፡” አላት፡፡

ከአስር ደቂቃ በኋላ ከግሪኮቹ ሬስቶራንት ውስጥ ከጉድማን ፊት ለፊት ዘና ብላ ተቀምጣ ራሷን አገኘችው፡፡ የጉድማን የሸሚዙ የላይኞቹ ሁለት ቁልፎች ተከፍተዋል፡፡ እጅጌውን ስለጠቀለለው ጡንቻማ እጁ ይታያል፡፡ቆዳው ለስላሳ እና ልጥፍ ያለ ነው፡፡ ፈገግ ሲል ደግሞ ነጫጭ ጥርሶቹ በግልፅ ይታያሉ፡፡ እርግጥ ነው ጉድማን ምንም አይነት እሷን የማማለል ድርጊቶችን በግልፅ ባያሳይም ባለፈው ማታ አብረው እየጠጡ በነበሩበት ሰዓት ላይ ለጥቂት ነው አብራው ከማደር የተረፈችው፡፡

“እስቲ ሀሳብሽን ሰብስቢ” አላት እና ጉድማን ውሃ እና አፒታይዘር
ለአስተናጋጁ አዝዞ ከጨረሰ በኋላም “አንዲት ሴት ላይ የራሴን ተፅዕኖ
በማድረግ ልወነጅል አልፈልግም” አላት የውስጧን ሀሳብ ያነበበ ይመስላል፡፡

ይህንን ሲላት የወሲብ ውጥረት በመሀከላቸው ተፈጠረ፡፡ ነገር ግን
ይህንን ስሜቷን ሆነ ብላ ችላ አለችው፡፡ ህይወቷ በፍቅር የተነሳ ተዘበራርቆባታል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ውስጧ ያለው የፍቅር ስሜት ሦስት አራተኛው ጉልበቷ ከእኔ ቤታ ማን ጋር ይገኛል፡፡ ከዚህም በላይ ደግሞ የባሏን ሀዘን አልጨረሰችም፡፡ እናም ለወሲብ ዝግጁ አይደለችም፡፡

“እሺ ስለዴሪክ ዊሊያምስ ምንድነው ማወቅ ያሉብኝ ነገሮች?” ብላ
ጠየቀችው፡፡

“እሱ የሴራ ፅንስ ሀሳቦችን እና ሁሌም የራሱን ካርድ ይዞ የሚጫወት ሰው ከመሆኑ በተጨማሪ ማለትሽ ነው?” ጉድማን ጠየቃት፡፡
“ዊሊያምስ ጥሩ ሰው ነው ደስ ብሎኛል” አለችው ኒኪ፡፡
“ብለሽ ነው?” ብሎ ጉድ ማን በቀልድ ስሜት ውስጥ በመሆን
“ለምን?” ብሎ ጠየቃት፡፡
“እውነተኛ ሰው ነው...”
“እውነተኛ ሰው ነው ...” ብሎ ጉድማን የእሷን ቃል ደገመው እና በቃሉ
እየተደመመ “መልካም ይሄን እንግዲህ እኔ በዚህ መልኩ ነው የማስቀምጠው፡፡ የእኛ ዲፓርትመንት በሚገለፅበት መልኩ
በእርግጥ እውነተኛ ያስመስለዋል፡፡”

“ለምን ይመስልሀል ግን?” ብላ ኒኪ ጠየቀችው፡፡ ዴሪክ ስለ ኤል.ኤ.ፒ.ዲ
መጥፎ ነገሮችን ሊያወራ የቻለበትን ምክንያት ከጉድማን ለማወቅ ፈለገች::

ጉድማን አንዴ ከመጠጡ ተጎነጨና “እሱ እኛ ሙሰኞች፣ ሰነፎች እና ደደቦች እንደሆንን አድርጎ ሊነግርሽ ይችላል፡፡” አላት እና “እውነቱ ግን ሌላ ነው፡፡ የራሱ መራር መሆን ነው እንደዚህ እንዲያስብ ያደረገው:: ወጣት እያለ የፖሊስ ሀይሉን ለመቀላቀል ማመልከቻ አስገብቶ ነበር፤ ለዚያውም ለብዙ ጊዜ፡፡ ግን ሊቀጥሩት ፍቃደኛ አልነበሩም።”

“በምን ምክንያት?” ብላ ኒኪ ጠየቀችው እና “ንገሪኝ ካልከኝ እሱ ለምርመራ ሥራ የተፈጠረ ሰው ነው” አለችው፡፡

“ስለ እሱ እንኳን የማውቀው ጉዳይ የለም፡፡ ግን ምናልባት መጥፎ ባህሪ
ስላለው? በጣም ችኩል እና በስሜት የሚገፋፋ ስለሆነም ይሆናል? ብቻ
ባጠቃላይ ዴሪክ ዊሊያምስ ለቡድን ሥራ የሚሆን ሰው አይደለም፡፡ ነገሮችን
ሁሉ ከራሱ ጋር የሚያያዝ ሰው ነው፡፡ ስለሆነም ብዙውን ጊዜ ለዲፓርትመንቱ የጭቃ እሾህ ሆኖ ነው የቆየው፡፡ ባይገርምሽ የፀረ አደንዛዥ ዕፅ
ቡድን ቢሮ ውስጥ ፎቶው ቦርድ ላይ በስፒል ተሰቅሏል፡፡ምክንያቱም በጣም ብዙ ጉዳዮቻቸው ውስጥ ጣልቃ እየገባ እነርሱ መርምረው ነገሮችን እንዳይደርሱባቸው ሲያደርግ የነበረ ሰው ነው” አላት፡፡

ኒኪ ግራ ተጋብታለች:: ጉድማን ጥሩ ግልፅ ሰው መሆኑ ብታምንም
ዴሪክ ዊሊያምስ ጨለምተኛ እና የተጣመመ አመለካከት ያለው ሰው ነው
እያለ ነው የሚነግራት፡፡ ይህ ደግሞ እሷ ስለዊሊያምስ ከምታውቀው በጣም
የተለየ ነው የሆነባት፡፡

“እሱን በዚህ መልኩ መፈረጁ ምቾት ላይሰጥሽ ይችላል። ስለ እኛ ዲፓርትመንት የነገረሽ ነገሮች በሙሉ የጥላቻ እና የቂም በቀል ናቸው፡፡ ግን
አንድ ነገር ልንገርሽ እሱ ገንዘብን በተመለከተ ደምሽን ነው የሚመጥሽ፡፡
ይሄ የአንቺ ጉዳይ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ግን እስኪ እስከአሁን ስንት ነው
ያስከፈለሽ?” ብሎ ጉድማን ጠየቃት፡፡

ኒኪ ለዴሪክ የከፈለችውን በግማሹ አሳንሳ ለጉድማን ብትነግረውም
በጣም ብዙ እየከፈለችው እንደሆነ ነገራት፡፡

“ይሄውልሽ ቆንጆ ጉዳዩ ያንቺ ቢሆንም ሰውዬው እስስት አይነት ነገር ስለሆነ ለእሱ የምትነግሪያቸው ነግሮች ላይ ጥንቃቂ አድርጊ፡፡” አላት እና
በኒኪ ውስጥ ትንሽም ቢሆን ዴሪክ ዊሊያምስን ለመጠራጠር የሚያስችል
የጥርጣሬ ዘርን በመዝራቱ ደስ እያለው የሚያወሩትን ርዕስ ቀየረ፡፡ “ይልቅ
አንድ ነገር ልጠይቅሽ ፈልጌ ነበር” አላት፡፡
“እሺ” አለችው፡፡

“ብራንዶ ግሮልሽ” ብሎ ስሙን ሞቅ አድርጎ ጠራና “አውቃለሁ እሱን
አክመሽ እንደማታውቂ ነግረሽናል፡፡ ግን እሱ በጣም የሄሮይን ዕፅ ተጠቃሚ
ስለሆነ ምናልባት ለህክምና የባለቤትሽ ክሊኒክ መጥቶ ሊሆን አይችልም
ብለሽ ታስቢያለሽ?”

“መጥቶ ታክሞ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ዶውግ እና ዶፎ እንደርሱ
አይነት ችግር ውስጥ የሚገኙ በጣም ብዙ ሰዎችን ሲያክሙ ነበር፡፡” ብላ መለሰችለት ኒኪ።

ግን ስለ ታካሚዎቻቸው ማንነት መረጃዎችን ያስቀምጣሉ አይደል?"

የአንዳንዶቹን አዎን” ብላ ኒኪ ትንሽ አመነታች እና በመቀጠልም የእነርሱ አሠራር ከእኔ ይለያል፡፡ እዚያ ለህክምና የሚመጡ ሰዎች ቤት አልባ ሰዎች፣ ምንም አይነት የመታወቂያ ወረቀት የሌላቸው ሰዎች፣ ምንም አይነት የኑሮ ዋስትና እና ጡረታ የሌላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ከእነዚህ አይነት ሰዎች ውስጥ ማግኘት ከገለባ ውስጥ
👍1
መርፌ እንደመፈለግ ነው የሚሆነው”

“ጆንሰንን በዚህ ጉዳይ ላይ ስጋ ወይንም አጥንት ነክሶ እንደተቀመጠ ውሻ ቁጠሪው” አላት እና ጉድማን በመቀጠልም “እሱ በግሮልሽ እና በባልሽ
ወይንም በግሮልሽ እና ባንቺ በኩል የሆነ አይነት ግንኙነት እንዳለ ካወቀ ነገሩ መጥፎ ነው የሚሆንብሽ” ብሎ ጉድማን አስጠነቀቃት

“እንዴ እኔ ባለቤቴ ሲያክማቸው የነበሩ ሱሰኞችን ሁሉ ማስታወስ ይጠበቅብኛል እንዴ?” ብላ አፈጠጠችበት

“ልክ ብለሻል” ብሎ ጉድማን ፈገግ አለ እና በአይኑ አጫወታት፡፡ ኒኪ
የወሬያቸው አካሄድ አልገባ ብሏታል ወሬያቸው በሙሉ ያልተለመደ የቴኒስ
ጨዋታ ነው የሆነባት፤ ማለትም በማማለል እና በጣም ቁምነገር በሆነ ወሬ መሀል የሚመላለስ ነው የሆነባት፡፡ ታዲያ ይህን ሰው ልታምነው ትችላለች?

“በነገራችን ላይ ለምንድነው እናንተ ስለ ብራንዶን ግሮልሽ ለማወቅ ይህን ያህል ፍላጎት ያደረባችሁ?” ብላ ጠየቀችው። ጉድማንም ለጥቂት ሰከንዶች ሊያያት ቆየና “የእሱን ዲ.ኤን.ኤ በሁለቱም ሟቾች ሬሳ ላይ አግኝተናል” አላት እና “አሁን ደግሞ መናገሩ ያንቺ ተራ ነው” አላት

“የኔ ተራ ምን?”

“እንዴ ምን ሆነሻል ኒኪ፡፡ ስለ ብራንዶን ግሮልሽ የምታውቂው ነገር ካለ እንድትነግሪን እንፈልጋለን፡፡ ምንም እንኳን እኛ ሞቷል ብለን ብናምንም ማለት ነው፡፡” አላት እና እሷ አሁንም ዝም ስላለች ማስረዳቱን ቀጠለ
“የዞምቢ ገዳይ እየተባለ የሚወራው ዝባዝንኬ በዚህ ምክንያት ነው::
የተገደሉት ሰዎች ላይ የተገኙት ዲ.ን.ኤ ዎች የሞተ ሰው ህዋስ እንደሆነ
በምርመራ አረጋግጠናል፡፡ ማለትም ከብራንዶ ሬሳ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ አንች
እሱን ለመከላከል ብለሽ ስለእሱ የምታወቂውን ነገር ከደበቅሺን
የምትተባበሪው ፖሊስን ሳይሆን ነፍስ ገዳዮቹን ይሆናል ማለት ነው” አላት
በቁጣ ድምፅ፡፡

“በመጀመሪያ እኔ የማንንም ነፍስ ገዳይ እየተከላከልኩኝ አይደለም፡፡ ስለ
እዚህ ያንተ አጋር የሆነው ጆንሰን መርፌውን ከገላባው መሀል እንደፈለገ
ፈልፍሎ (ቆፍሮ) ማግኘት ይችላል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ እኔ ፍርድ ቤት
ውስጥ እንዴት አድርጌ ራሴን መከላከል እንደምችል ንገረው፡፡ እሺ ብዙ ጊዜ
በባለሞያ ምስክርነት ፍርድ ቤት ቀርቤያለሁና እንደዚህ በቀላሉ የምበረግግ ፈሪ ሰው አይደለሁም” አለችው፡፡

“በእርግጥ አንቺ እንደማትፈሪ አውቃለሁ” አላት ጉድማን፡፡

“ይቅርታ በአንተ ላይ ችግር የለብኝም” ብላ ኒኪ ነገሩን መቀጠል እንዳለባት እና ስለብራንዶን የተናገረችውን ውሸት በድጋሚ ተመልሳ ማመን እንደሌለባት በመወሰን “ብዙውን ጊዜ የባለሙያ ምስክርነቴን በእነዚህ የዊሊያም ፎቶ ላይ ስፒል ሰክተው የግድግዳ ሰሌዳቸው ላይ በሰቀሉት ፖሊሶች ላይ የምስክርነት ቃሌን ሰጥቻለሁ እናም አብዛኞቹ በሙስና
የተጨማለቁ መሆናቸውን በእነዚያ ጊዚያቶች ላይ ለማወቅ ችያለሁ እና
ዊሊያም እውነቱን ነው”

“ጥቂቶቹ ምናልባት ሊሆኑ ይችላሉ” ብሎ ጉድማን አመነላት እና በአዕምሮው የሆነ ነገር መጣለት፡፡

“እኔ የባለሙያ ምስክር ነበርኩኝ...”

“እኔ የባለሙያ ምስክር ሆኜ በፖሊሶች ላይ መስክሬያለሁ፡፡”

“ፍርድ ቤት ውጥ የአንተ የስራ ባልደረባዎች እርስ በእርስ ለመጠባበቅ
ብለው ነጭ ውሸት ሲዋሹ ተመልክቻለሁ፡፡” ብላ ስለ ብራንዶን የዋሸችውን ነገር ረስታ ነገሩን አጋለችው፡፡

“ዶውግ ስለ ፖሊሶች ተቆጥረው የማያልቁ አስፈሪ ነገሮችን ነግሮኛል።
ማለትም በተጠርጣሪው ቤት ውስጥ መረጃዎችን ማስቀመጥን የአጭር ጊዜ
እና አነስተኛ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ነፃ ፍርድ እንዲሰጥ በማድረግ በጣም ትላልቆቹ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ነፃ
እንዲወጡ

እንደሚያደርጉም ጭምር ነግሮኛል፡፡ ስለዚህ በእናንተ ላይ የተደበላለቀ
ስሜት ያለው ዴሪክ ዊሊያምስ ብቻ እንዳልሆነ እወቅ” አለችው፡፡

“እሺ እሺ” ብሎ ጉድማ እጁን አነሳ እና “አሁን ገባኝ ግን እኔ ጠላትሽ
እንዳልሆንኩኝ አስታውሺ እሺ”

“እሱን አውቃለሁ” አለችና እና ኒኪ ረጋ በማለት “አንተ ጠላቴ ነህ ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡ ዴሪክን የቀጠርኩት አንዳንድ መልሶችን ለማወቅ ብዬ ነው፡፡ እናም ደግሞ እንደተጠርጣሪ መታየቱ ስለሰለቸኝ ነው፡፡” ጉድማን ቢሉን ሙሉውን ከፈለና መኪናዋ ድረስ ሸኛት፤ “ይሄንን ነፍሰ ገዳይ እስክንይዘው ድረስ እባክሽን ጥንቃቄ አድርጊ”

“እሺ እጠነቀቃለሁ” አለችው፡፡

“ዴሪክ ዊሊያምስ ገንዘብሽን ነው የሚፈልገው፤ እኔ ደግሞ ያንቺን
ገንዘብ አልፈልግም፡፡ ስለዚህም ከሁለታችን የትኛችንን ማመን እንዳለብሽ
ስታስቢ ይህን አስታውሺ” አላት፡፡ መኪናውን አስነስታ ስትሄድ ቃላቶቹ
ጆሮዋ ላይ እየደወሉ ቆዩ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ካሊፎርኒያ ስቴት ውስጥ ማዴራ ተብሎ በሚጠራው ገጠራማ ቦታ ላይ የቾውቺላ ከተማን በተመለከተ ዊኪፔዲያ ላይ የተገለፁት ሁለት ነገሮች ብቻ
ስለከተማዋ እንድናውቅ ፍላጎትን ያሳድራሉ፡፡ የመጀመሪያው የከተማው
'ቾውቺላ የተባለው ሥም ነው። ከቀድሞዎቹ የአሜሪካ ጎሳዎች መሀከል
ነባር ተብሎ የሚጠራ ጎሳ አባላት እዚህ ቦታ ላይ ይኖሩ ነበር፡፡ በእነርሱ ቋንቋ ደግሞ 'ቾውቺላ' ማለት 'ገዳዮቹ ማለት ነው፡፡ ይህንን የእነርሱን ጎሳ አደገኝነት ለመግለፅ ስያሜውን ለዚህች ከተማ ሰጥተው ይኖሩባት ስለነበረ ነው፡፡ ሁለተኛው ነገር ደግሞ የባሊስቴት ማረሚያ ቤት (እስር ቤት) ስለሚገኝበት ነው፡፡ ይህ እስር ቤት በፊት ላይ የሴቶች እስር ቤት የነበረ ሲሆን፣ አሁን ላይ ግን ወደ አንድ ሺ የሚጠጉ ወንድ እስረኞችም በዚህ ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡

መካከለኛ ጥበቃ ከሚደረግባቸው ውስጥ የሚመደበው እስር ቤት አጥሩ
በከባድ ኮንክሪት ከመሰራቱም በላይ ከአጥሩ ላይ ያለው ጥቅልል እና እሾሃማ
የኤሌክትሪክ ሽቦውን ለሚመለከቱ የእስረኛ ጠባቂዎች ሀይለኛ ጥበቃ'
የሚደረግባቸው እስር ቤቶች ምን ይመስሉ ይሆን? የሚል ጥያቄን
ራሳቸውን እንዲጠይቁ ያደርጋቸዋል፡፡
ጄሪ ኮቫክ የእስር ቤቱን የውጪ ክፍል ካየ ስድስት ዓመት አልፎታል።
ወደዚህ እስር ቤት የተላለፈው በጣም በእስረኞች ከተጨናነቀው ሄልሆል
ከሚባለው በሎስ አንጀለስ ካውንቲ ከሚገኘው እስር ቤት ነው፡፡ ለዚህ እና
ለሌሎቹም ነገሮች ውድ ጓደኛውን ሚክ ጆንሰንን ሳያመሰግነው አያልፍም፡፡
የጄሪ ጠበቃዎች ተስፋ በሌላቸው የይግባኝ ጥያቄዎች ጊዜውን እንዳያጠፋ
ከተለያዩ ይግባኝ ከሚያሰጡት ህጎች ጋር አቀናጅቶ፣ ከአንድም ሁለቴ ይግባኝ
መክረውት ነበር፡፡ ነገር ግን ጓደኛው ሚክ ጆንሰን የይግባኝ ደብዳቤውን እንዲጠይቅ አድርጎታል፡፡ ምንም እንኳን ውጤቱ እንደጠበቁት ባይሆንም፡፡
ስለዚህ ምናልባት እሱ ከዚህ እስር ቤት ሊወጣ የሚችለው በሞት እና ሬሳው
በሳጥን ተከትቶ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡

ወደ እስረኛ መጠየቂያው ክፍል ውስጥ ለህፃናት ጠያቂዎች መጫወቻ
እንዲሆን በደማቅ ቀለም ከተቀባው የግድግዳው ክፍል አጠገብ ከሚገኙት
አንደኛው ወንበር ላይ ጄሪ ተቀመጠና ጠያቂውን ይጠብቅ ጀመር፡፡ ምናልባት
ዛሬ ልጁ ይሳካላት እና መጥታ አያታለሁ ብሎ ተስፋ አድርጓል፡፡ ልጁን
ጁሊን ካያት ስድስት ወር አልፎታል፡፡ እርግጥ አሁን ላይ እሷ የምትንከባከባቸው ሶስት ሕፃናት እና እሱን የማይወደው ባል አላት፡፡
በተጨማሪም ደግሞ ከሎስ አንጀለስ ቾውቺላ ድረስ በመኪና የአራት ሰዓት
መንገድ ስለሆነ ብዙም ተስፋ አታድርግ ብሎ ለራሱ እየነገረ ሳላ ብቻውን
ሊጠይቀው የመጣውን ሚኪ ጆንሰን የመጠየቂያው ክፍል ውስጥ ሲገባ
ተመለከተና ልጁ አብራው ስላልመጣች የተሰማውን ቅሬታ በውስጡ ያዘው፡፡

ጄሪ አጠገብ ከሚገኝ አንድ ወንበር ላይ ሚኪ ተቀመጠ እና ወደ እስር ቤቱ እንዲያስገባ
የተፈቀዱለትን የዓሣ ማጥመጃ መፅሄት፣ የሱዱኮ መጫወቻ መለማመጃ መፅሀፍ እና መገጣጠሚያ ለህመሙም የሚጠቅመው የባህላዊ መድሀኒት ስጠው፡፡ “ሰውዬው እንዴት ነህ? አምሮብሃል ደግሞ” አለው፡፡

“አመሰግናለሁ፡፡ አዎን ጥሩ ነኝ” አለው፡፡

አሁን የሚባባሉት ነገር ውሸት እንደሆነ ሁለቱም ያውቃሉ፡፡ ምክንያቱም
ያኔ ገና ጀማሪ ፖሊስ ሆነው የተገናኙ ጊዜ ጄሪ ኮቫክ በጣም መልከ መልካም
፣ ረዥም እና ከኮረዳ እስከ አሮጊት ድረስ የሚማልሉበት ወንድ ነበር፡፡
ይህም ሆኖ ሳለ ግን ጄሪ ከአንድ ሴት ጋር የሚረጋ ወንድ ሆኖ ለሚስቱ ሜሪያን እና ለልጁ ጁሊ ታማኝ እና የሙሉ ጊዜ አፍቃሪ ሆኖ ነበር የቆየው።

ይሄ እንግዲህ ከዛሬ አስራ አምስት ዓመት በፊት የነበረ ታሪካቸው ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላ ሚኪ እና ሌሎቹ ባልደረባዎቹ እየወፈሩ እና እየተመለጡ ሲመጡ፣ ጄሪ ግን ልክ በርሃ ላይ እንደሚገኝ ዛፍ ነው የሆነው፡፡ ቆዳው እንደ ማብሰያ ወረቀት የደረቀ እና የተሰነጣጠቀ ሆነ፡፡ አይኖቹ ቀይ እናዐየአይኑ ዙሪያም የተጨማደደ ሆነ፡፡ በቃ ያረጀ ሰው ሆነ፡፡

ጄሪ አርባ አምስት ዓመት ሲሞላው የመከራ መአት ከሰማያዊው አካል
ይዘንብበት ጀመር፡፡ በመጀመሪያ ማሪያኔ ታመመች፣ በታመመች በጣም በጥቂት ወራት ውስጥ ማንም ይሆናል ብሎ ባልጠበቀበት ወቅት ላይ በሽታዋ ወደማይቀረው ዓለም ይዟት ሄደ፡፡ በእነዚያ ጄሪ ሚስቱን በሞት
በተነጠቀበት ጊዜ ላይ ጄሪ የሆናቸውን ነገሮችን ሚክ መቼም ቢሆን አይረሳቸውም፡፡ ጓደኛው ጄሪ እንደቆሰለ ውሻ አንገቱን ደፍቶ ቅስስ እያለ ከመራመዱም በላይ እስከ ዛሬ ድረስ ሚክ ካያቸው ሀዘኖች ሁሉ የላቀ ጥልቅ
ሀዘንን ነበር ጄሪ ያስተናገደው፡፡

በጊዜው ጄሪ ፈቃድ ወስዶ ሀዘኑን ከብቸኛ ልጁ ጁሊ ጋር ሊወጣ ይገባው ነበር፡፡ ነገር ግን ያኔ ነገሮች የተለዩ ነበሩ፡፡ ሙሉ በሙሉ በአይሪሽ ፖሊሶች በተያዘው የፀረ አደንዛዥ ዕፅ የመከላከያ ቡድን ውስጥ ነበር በቅርቡ የተዛወረው!! የእነዚህ ቡድን አባት ቤታቸው ውስጥ መሽገው እነርሱ
ከአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ጋር ቅልጥ ያለ ጦርነት ውስጥ ነበሩ። ይህንን
ጦርነታቸውን ደግሞ የአንድ ፖሊስ ሚስት ገና በ42 ዓመቷ በካንሰር ስለሞተች ብለው አያቋርጡም፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ጄሪ ስራውን ማቋረጥ አልፈለገም፡፡ ለሚክ ያኔ ሲነግረው ሀዘኑን ለመርሳት መስራት እንዳለበት እንዲሁም ደግሞ አሁን ለጁሊ እኔ ብቻ ነኝ ያለኋት እና “እሷን በደንብ ለማሳደግ ገንዘቡን እፈልገዋለሁ” እንዳለውም አይረሳም፡፡

መርማሪ ፖሊስ ጆንሰን የመስክ ሥራ ተሰጥቶት በኤል ኤ ጓዳዎች ላይ
ስራዎችን መስራት ጀመረ፡፡ በመጀመሪያዎቹ የስራ ጊዜያት ላይ ጥሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ሀዘኑ ወደ ተስፋ መቁረጡ ሲሻገር ከዚያም የሚስቱን ሞት አምኖ መቀበል ሲያቅተው ከዚያም ከፍተኛ ንዴት ውስጥ እየገባ ሲመጣ የእሱም ባህሪ አብሮት እየተለወጠ ሄደ፡፡ በጣም በቀላሉ ይናደዳል፡፡ በመኪና ማቆሚያ ስፍራ በተነሳ ጭቅጭቅም በቦክስ የጀማሪ ፖሊስን አፍንጫን ሰበረ፡፡ ፀባቸው ወደ ቢሮ ሳይሄድ ጄሪ ይቅርታ ብሎት ታረቁ፡፡ ነገር ግን መስክ ላይ በየቀኑ ከሚያገኛቸው የዕፅ ተጠቃሚዎች እና አዘዋዋሪዎች እና ሴተኛ አዳሪዎች
እና ለፀረ ዕፅ ቡድን መረጃ የሚያቀብሉ ጠቃሚ ስዎቻቸው ጋር እየተጣላ
የተለየ ሰው ሆነ፡፡ ደረቅ ጥል የማያሰለቸው እና ጥል የሚፈልግ ሰው ሆነ፡፡......

ይቀጥላል
👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አርባ_አምስት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


....ደውዬ አነጋግራቸዋለሁ። እስካልለቀቋትና በሰላም እስካልተዋት
ድረስ ዕቅዳቸውን እንደማወጣ አስጠነቅቃቸዋለሁ፡፡”

“እንበልና ሊለቋት ባይስማሙስ?”
“አዝረከርከዋለኋ ጉዳዩን! እየተለቀመ ይጎባታል፡፡” ናትናኤል ንዴት ወረረው::

“አየህ... እዚህ ላይ ነው የማንስማማው:: ልንገርህ... ይህን ምስጢር ልታወጣ ብትሞክር ቀድሜ የምቀነጥስህ እኔ ነኝ፡፡” አለ ካልቨርት ሽጉጥ የከተተበትን ኪሱን በቀኝ እጁ መታ መታ እያደረገ፡፡

“ምን ለማለት ነው?” አለ ናትናኤል ዓይኖቹን አጥብቦ፡፡

“ሰምተኸኛል፡፡ ባጭሩ ምስጢሩን ለማውጣት ብትሞክር ቀድሜ
እገድልሃለሁ፡፡ ናትናኤል ኣንድ ተስፋ ቢኖረን... አንድ ጭላንጭል ቢታየን
እሱንም ልታጨልመው ስትሞክር ዝም ብዬ አልመለከትህም::” ቆፍጠን አለ
ካልቨርት፡፡

“ተስፋ… ተስፋ አትበልብኝ ሰባቴ…” ናትናኤል የተሰማውን ንዴት መደበቅ አልቻለም የነፍሰ ገዳዮች ጥርቅም...““ የወንበዴዎች ሆያሆዬ አይደለም ተስፋ
የሚፈነጥቅብኝ ተስፋ አይደለም፡፡ የሚታየኝ..እልቂት ነው ጥፋት ውድቀት፡፡”

“ታዲያ ለምኑ ፈራህ? ለአፍሪካዊ እልቂትና ፍጅት፣ ጥፋትና ዉድቀት ከመቼ ወዲህ ባዳ ሆነበት? በዘርና በጎሳ፣ በፖለቲካና በሃያማኖት ሰበብ የገዛ ወንድሙን በየጫካው በጥይት እየጠዘጠዘ እየቆላ ላለ አዳኝ ታዳኝ ሕዝብ እልቂትና ፍጅት እዲስ ናቸው? የገዛ መንጋጋው ሊያላምጠው የሌለው የገዛ ጨጓራው ሊሰለቅጠው የሌለው ነጋ ጠባ ከኣውሮፓ ኣራጣ አበዳሪዎች ጓዳ ለማይጠፋ ድሀ ህዝብ ወድቀት ብርቅ ሆነ? ለምነ ፈራህ ..ምን እንዳይመጣ ሰጋህ? ከዜሮ በታች ቁጥር አለ? ከአፍሪካ በታች ገሃነም አለ? ብንሻውም እንኳን ከዚህ በታች የምንወርድበት የምናዘቅጥበት ስፍራ የለም አትስጋ፡፡”

“አንዱ የተፋጀ ዝንተ ዓለም ቢፋጅ… አንዴ የወደቀ ዘለአለም ቢወድቅ ምን ገዶኝ ማለትህ ነው?" አለ ናትናኤል በሃሳሱ የመጣችበት ግን ዘውዲቱ ነበረች… ተጎድቸ ያላቀልኝ ሸርሙጣ… ምኔ ይጎዳል?

“አላልኩም፡፡ ለደዌአቸው መድሃኒቱ እዚያው እመህላቸው አፍሪካ ውስጥ መሆኑን መቀበል ተስኗቸወ ከባዕድ ጋር እየተመሳጠሩ ከመጤ ጋር እየተሻረኩ የገዛ ወንድሞቻቸውን ዕልቂት የሚያራቡ አፍሪካውያን ናቸው፡፡ አፍሪካ አንድ መሆን አለባት።”

“እንድነት'ኮ በዘፈቀደ በአየር ላይ አይመስረትም፡፡” አለ ናትናኤል
ስሜቱን ለማስረዳት ተቸግሮ። “እኔ'ኮ ውህደትን አልተቃወምኩም፡፡ ግን
ፖለቲካዊ አንድነት የኤኮኖሚያዊና የማህበራዊ ዕድገት ጥንቅር ውጤት
ነው፡፡ ከዚያ ውጭኮ ውህደት ጭፍን ውህደት ዲሞክራሲን ችላ ማለት ብቻ
ሳይሆን ኢሳይንሳዊ ነው፡፡”

“ፐ! ኢሳይንሳዊ ሳይንሳዊ ቅራቅንቦ! በአፍሪካ ውስጥ ከነፃነት ወዲህ ስንት ሳይንሳዊ ፖሊሲዎችና ሳይንሳዊ ዕቅዶች በወረቀት እንደሰፈሩ አንድ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቅ፡፡ የየትኛው አፍሪካዊ አገር ኤኮኖሚ ሲያብብ ሲፈካ… የየትኛው አፍሪካዊ አገር ማህበራዊ ኑሮ ሲለመልምና ሲምነሸነሽ ታየ? በላ ንገረኝ!”

“ታዲያ እኮ የዚህ ምክንያቱ ዲሞክራሲያዊ ሂደት ስለሌለ ነው፡፡
ዲሞክራሲና ሠላም በሌለበት ዕድገት የለም…” አለ ናትናኤል፡፡

“ውህደት ነው መልሱ!” ዕልህ ያጨናነቀው የካልቨርት ድምፅ
አቋረጠው:: “ልክ እንዳንተ በርካታ አፍሪካውያን ከፖለቲካ ውህደት በፊት
ኤኮኖሚያዊ ግንባታ ሊቀድም እንደሚገባና የፖለቲካን ውህደት ወደፊት
ልንቀዳጀው የምንችል ግብ አድርገው ያቀርቡታል፡፡ ነገር ግን ማስተዋል
የሚገባን የምንጓጓለት ኤኮኖሚያዊ ጥንካሬ ሊፈጠር የሚችለው ሙሉ
ፈቃደኝነት የተሞላበት መደጋገፍና መረዳዳት በአፍሪካ አገሮች መሃከል
ሲሰፍን ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ መደጋገፍና መረዳዳት በቅድሚያ
የሚጠይቀው ነገር አለ የጋራ ፖለቲካዊ መድረክ፡፡”

“አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ…” አለ ናትናኤል አቋርጦት፡፡ “አፍሪካውያንን፤ ምንድነው ሊያስተሳስረን የሚችል? የአፍሪካ አንድነትና በሥነ ስርዓቱ የተደከመበት ዓላማ ነው፡፡ አልሆነም እንጂ፡፡”

“ከባድ ጥያቄ!” ካልቨርት ጭንቅላቱን ወደኋላ ጥሎ የማሾፍ ሳቅ ሳቀ። “ምንድነው የውህደታችን መሠረት? በእየሱስ ምን እንድልህ ትፈልጋለህ? የሴንጎር ኒግሪትዩድ? የሴኩትሬ አፍሪካዊ ብሄረተኝነት?የንክሩማን የቅኝ ግዛት እስክ ቁስል ጠባሳ? አይደለም፡፡ ለእኔ ባዶ ሆዳችን ነው አንድ የሚያደርገን! የመሰንበትና ያለመሰንበት ጥያቄ ነው
የሚያስተባብረን፡፡ ተነጣጥለን ልንሞላው ያልቻልነውን ከርሳችንን .. ለየብቻ
ቆመን ልናረጋግጠው ያቃተንን ሰላምና ደህንነታችንን እጅ ለእጅ ተያይዘን
ልንጋፈጠው ይገባል! በእኔና በአንተ እግር ላይ የወደቀን ቋጥኝ ለማንሳት የእኔና ያንተን የዝምድና ግንድ መቁጠርና መመርመር አያሻንም።

በመጀመሪያ እግሮቻችን ከመጨፍለቃቸው ፡ በፊት ተረዳድተን ቋጥኙን ከላያችን ማንሳት አለብን፡፡ አለቀ፡፡ የአፍሪካ ውህደት የተደከመበት ነው ላልከው... እርሳው:: ለእኔ አይዋጥልኝም:: በቆንጆ ቆንጆ ከተሞች ቆንጆ ቆንጆ ህንፃዎች እየገነቡ የአፍሪካ ድርጅት'፤ 'የአፍሪካ… ኮሚሽን የአፍሪካ...
ኢንስቲትዩት እያሉ ስም ማውጣት ትንሽ ትንሽ እየሰሩ ብዙ ብዙ የሚከፈላቸውና በሽንጠ ረጃጅም ቆንጆ ቆንጆ የአውሮፓ መኪናዎቻቸው ቆንጆ . ቆንጆ ኮረዶችን እየጫነ መዞር ሥራቸው የሆነ : ውድ ውድ
ኤክስፐርቶችን ማሰባሰብ አፍሪካን አንድ አያደርጋትም::”

“እኔኮ ሊገባኝ ያልቻለው…" ናትናኤል የጀመረውን ሳይጨርስ ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም አሉ፡፡ “እሺ ሆነ እንበል፡፡ እንዲያው ድንገት አፍሪካ አንድ ሆናለች ብለህ በመገናኛ መስመሮች ስትለፈልፍ፡ ሌላውን ተወው አፍሪካውያን እራሳቸው ምን ይላሉ? ፍጹም ያላሰበበትና በማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህብረት ያላለፉብት ወንድማማችነታቸውን አጠናክረው በሚገባ ያልተዋወቁበት… ድንገተኛ ዱብ ዕዳ ሲመጣባቸው ምን ይላሉ?

“ምን ይላሉ?” ካልቨርት መልሶ ጠየቀ፡፡ “አየህ… ኣንተ በተላያዩ የአፍሪካ አገሮች ያለውን ህዝብ የፖለቲካ አመለካከት አልተረዳህም:: አፍሪካ ውስጥ ፖለቲካ ግለሰብአዊ ነው፡፡ ግለሰቦች ፖለቲካን ይፈጥሩታል እንጂ የፖለቲካ አመለካከት ግለሰቦችን አይቀርጽም ምክንያቱም ፖለቲካ ራስን መጠበቂያ መሣሪያ ነው
አፍሪካ ውስጥ ጥያቄው የትኛው የፖለቲካ መስመር ለእድገት ይበጃል
አይደለም:: ጥያቄው የትኛው የፖለቲካ መስመር ሥልጣን ላይ ያሰነብተኛል ነው ለዚህ ነው ፖለቲካ ግለሰብአዊ ነው
የምልህ፡ ነፃ አፍሪካ አንድ ብትሆን አፍሪካውያን የሚሉት 'አፍሪካ አንድ
ሆነች ነው:: በቃ::”

ያሉባት መኪና ድንገት ፍጥነቷን አብርዳ ከኋላዋ የአቧራ ቁልል አንስታ፡፡ ወደ ቀኝ ስትታጠፍ፡ ቤኬ መገንጠያ ላይ ደርሰናል ብለው አሰቡ፡፡ ለአንድ አፍታ ተያዩ፡፡ ወዲያው ካልቨርት ወደጎን አዝምሞ ከሹፌሩ ጀርባ ያለችውን ትንሽ መስኮት እየደበደበ ሹፌሩ መኪናዋን እንዲያቆም በምልክት ይወተውተው ጀመር፡፡

“ምንድነው? ምንድነው የምታደርገው?” አለ ናትናኤል የካልቨርት ፈሊጥ አልገባህ ሲለው፡፡

“አቁም በለው፡፡ እቃ ጥለሃል በለው::” አለ ካልሸርት ፊቱን ወደ ናትናኤል መልሶ፡፡

ናትናኤል ወደ መስኮቱ ተጠግቶ ለሹፌሩ ዕቃ መጣሉን በምልክት ሲያስረዳው ሹፌሩ መኪናውን አብርዶ ጥግ አስያዛት፡፡

“ምን ሆናችኋል?” ጮኸ ሹፌሩ ጭንቅላቱን ጠምዝዞ፡፡
“ምንድነው የፈለከው? አለ ናትናኤል በተራው ፊቱን ወደ ካልቨርት መልሶ::

"መጣሁ፡፡” አለ ካልቨርት:: ከጭነት መኪናዋ ጀርባ ዘሎ ወረደና ወደ ሹፌሩ ሄደ፡፡ የሽፌሩን በር ከፍቶ ያለሃተታ የሹፌሩን ክንድ ጨመደደና ጎትቶ አወረደው፡፡ የሚነጫነጨው
👍2
ሹፌር እግሮች መሬት እንደነኩ ካልቨርት
የቀኝ እጁን አንስቶ አንገቱ ስር ቢለው ጫትና መጠጥ የሽረሽሩት ሹፌር
ወርዶ እግሩ ስር ተቆለለ፡፡

“ምን ማድረግህ ነው? አብደሃል እንዴ?” ናትናኤል ከተቀመጠበት ወንበር ጋር እንደተጣበቅ ሁሉ ካለበት ሳይንቀሳቐስ ጮኸ፡፡

ካልቨርት የናትናኤልን ጩኸት ችላ ብሎ በእርጋታ የሾፌሩን እጆች ወደኋላ አዙሮ ግጥም አድርጎ አስረና አፉን በጨርቅ ጎስጉሶ ሲጨርስ ብብትና ብብቱ ውስጥ ገብቶ እያንዘላዘለ ከጭነት መኪናው ጀርባ በዕቃዎች መሃል የተጠቀለለ ምንጣፍ ገልጦ ከውስጥ አጋደመው፡፡

“ውረድና ከፊት ግባ፡፡” አለ ካልቨርት ምንም እንዳልተፈጸመ ሁሉ ናትናኤልን እየተመለከተ፡፡ ወዲያው ፊቱን አዙሮ ሹፌር በር በኩል ገባና መሪውን ጨበጠ፡፡

ናትናኤል ሁኔታውን ሲያይ በፍጥነት ከመኪናው ጀርባ ዘሎ ወረደና ከጎን ያለውን የጋቢና በር ከፍቶ ከካልቨርት ጎን ጋቢናው ውስጥ ገባ፡፡አብሮት የሚሸሸው ሰው ባህርይ ቀስ በቀስ እየተገለፀለት ሲመጣ ናትናኤል ስጋት ገባው፡፡

“ምንድነው የሠራኽው? ምን አደረገህ ሰውየው?” አለ ናትናኤል ድንጋጤ ፊቱን አገርጥቶት፡፡

“ናትናኤል ለሁሉ ነገር ጊዜ ኣለው:: ለግብረገብም ጊዜ አለው፡፡ ገና
ለገና መሪውን ስለያዘ የፈለገበት ሲወስደን እንደሰንጋ በሬ ከጀርባው ተቆልዬ
የምሄድበት ምክንያት የለም:: መሄድ የምፈልገው ወደ አዲስ አበባ ነው፡፡
የአዲስ አበበ አቅጣጫ ደግሞ በዚህ አይደለም፡፡”

-ካልቨርት ያለ ጥድፊያ የጭነት መኪናዋን እሽክርክሮ ተገንጥለው ወደ መጡበት መንገድ ተመለሰና ከዋናው መንገድ ሲደርስ ወደ ቀኝ ታጥፎ የመኪናውን ኣፍንጫ ወደ አዲስ አበባ መለሰው፡፡ ከኪሱ ውስጥ ያችነ ትንሽ የመንገደኛ ካርታ አወጣና ከመሃላቸው ዘረጋት፡፡

“ስለሚቀጥለው ከተማ ንገረኝ፡፡ ርቀቱን፣ ፀባዩን የምታውቀውን ሁሉ:፡” አለ ካልቨርት ቁርጥ ባለ ድምፅ፡፡ ሰውየው ሰካራሙ ካልቨርት ድንገት ቆፍጣና ወታደር ሲሆንበት ናትናኤል ግራ ተጋባ፡፡

“እ...አፍደም ይላል. አላውቀውም፡፡” አላ
የሚናገረው ግራ ገብቶት::

“ስለእየሱስ ብለህ ርቀቱን ንገረኝ! የያዝከው'ኮ ካርታ ነው!” አለ
ካልቨርት በስጨት ብሎ፡፡

እ..አርባ አርባ አምስት ኪሎ ሜትር ይሆናል፡” አለ ናትናኤል ከበኩ መገንጠያ እስክ አፍደም ያለውን ርቀት ለመገመት እየሞከረ፡፡
“የሚቀጥለው ከተማ ከነርቀቱ?”
“ሚኤሶ፡፡ ርቀቱ... እጥፍ ይሆናል… ዘጠና
መቶ…”

ካልቨርት ስዓቱን ተመለክተ:: አስራ ኣንድ ከሃያ ይላል፡፡

የሚቀጥለውስ ከተማ?”
“እንጃ፡፡ እይነበብም:: አንድ ነገር አፍስሰህበታል፡፡”
“ተወው አረቄ ይሆናል የሚቀጥለውስ ከተማ ከነርቀቱ ?

“አዋሽ፡፡ ርቀቱ እንጃ:: ሩቅ ነው፡፡” አለ ናትናኤል መገሙቱ ቢያስቸግረው
ካርታ እንዴት መነበብ እንዳለበት የሚያውቀው ነገር የለም፡፡

“አምጣ፡፡” አለ ካልቨርት መኪናውን ጥግ አስደዞ:: ካርታውን ከናትናኤል እጅ ተቀብሎ ሲያጠናው ቆየና ቀና አለ

“ዛሬ ሌሊቱን አዋሽ ደርሰን እናድራለን፡፡ በጠዋት ተነስተን በሌላ ተሽከርካሪ እንቀጥላለን፡፡”
“ነዳጅስ ይበቃናል? ”
“እሱን የሚያውቅ እንድ ዲያብሎስ ብቻ ነው::”

ቀኑ እየሸሽ ምሽቱ እየደመቀ ሲመጣ ዝምታ ተጫናቸው:: የሚጓዙበት አሮጌ የሴት ዕቃ የጫነች አሮጌ መኪና ከምታሰማው ኳኳታ በስተቀር ጋቢናው ውስጥ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ ጨለማው ሊጋርዳቸው ሲዳዳው ካልቨርት
አንዱ ይህን አንዴ ያንን ሲጫን ከቆየ በኋላ የመኪናውን የፊት መብራት አበራው፡፡የበራው ግን የግራው ወገን አንድ መብራት ብቻ ነበር፡፡ ፍጥነታቸ
ውን ቀንስው ወደፊት ቀጠሉ::
በመንገዳቸው ላይ ትናንሽና ከፍ ከፍ ያሉ ጥቂት ከተሞት ቢያጋጥሟቸውም ጉዟቸውን ያለማቋረጥ ቀጠሉ፡፡ ምሽቱ ከገፋ በኋላ አንድ ከፍ ያለች ከተማ ኢጋጠመቻቸው፡፡

“መኢሶ የሚሏች መሆን አለባት ይሀች፡፡” እለ ናትናኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ፀጥታውን አደፍርሶ፡፡

ከተማዋን አልፈው ድጋሚ ጭልጥ ባለው በረሃ ውስጥ ሰመጡ፡፡ከከተማው ብዙም ሳይርቁ ከጀርባቸው ድምፅ ይሰማቸው ጀመር፡፡

“ምንድነው” አለ ናትናኤል ፊቱን ወደኋላ መልሶ፡፡

ካልርት በፍጥነት መኪናዎን ጥግ እስይዞ በሩን ከፍ ዘሎ ወረደና ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ተመልሶ መጣ፡፡
“ምንድነው?” አለ ናትናኤል
“ሰውየው ነው፡፡”
ነቅቶ ነው አለ ናትናኤል ካልቨርት ሹፌሩን ማለቱ እንደሆ ስለገባው
አዎ፡፡”
“ምን አደረከው?” አለ ናትናኤል ሃሳብ ገብቶት።

“አስተኝቼው መጣሁ”

ሌሊቱ ከተጋመሰ በኋላ ካሉበት መንገድ በስተቀኝ ተገንጥሉ የሚሄደውን የአሰብን መንገድ ሲያዩ ከፊታቸው የተንጣለለችው አነስተኛ ከተማ የአዋሽ ከተማ እንደሆነች ገምቱ።

ወደ ከተማዋ እየተጠጉ ሲመጡ በግራና በቀኝ ያለው በረሃ ድንገት በትናንሽ ቤቶች የተሞላ መሰለ፡፡ ወደ ከተማዋ ዘልቀው ከመግባታቸው በፊት ካልቨርት መኪናቸውን ጥግ አስያዝና በሮቻቸውን እየከፈቱ ወረዱ፡፡ጊዜው እጅግ በመግፋቱ ይሆናል በአካባቢው የሚዘዋወር ሰው አይታይም ከተማዋን መሃል ለመሃል ሰንጥቆ የሚያልፈውን መገድ ይዘው ወደ ትንሿ ከተማ እምብርት በእግራቸው ቀጠሉ፡፡

አልፎ አልፎ ከተዘጉ በሮችና መስኮቶች የሚያመልጥ የብርሃን ጭላንጭል ይታያል፡፡ ልብሳቸውን የሚያርገበግበው ደረቅ ቀዝቃቅ የሌሊት ንፋስ ፊት ፊታቸውን ሲላቸው አይኖቻቸው እምባ አቀረዘዙ።

“በዚህ ሰዓት ማደሪያ ማፈላለግ ኣትኩሮት መሳብ ይመስሉኛል፡፡” አለ ካልቨርት በትክሻው ያነገበውን ቦርሳ አወርዶ ደሪት ደረቱን የሚሰውን ንፋስ ይከላከልለት ይመስል ደረቱ ላይ ለጥፎ ይዞ፡፡
“አዎ…እነዛ የጭነት መኪናዎች ይታዩሃል?” አለ ናትናኤል አገጩን
ማዶ በጨለማው ውስጥ ጭነታቸውን ጋራ አሳክለው ሽራቸውን ተጀቡነው
ወደተደረደሩ ከባድ የጭነት መኪናዎች አሹሎ “…ከነሱ ውስጥ ጠዋት ወደ
አዲስ አበባ የሚነቃነቅ ኣይጠፋም፡፡ አንዳንዶቹን አነጋግረን ከተስማማን
አሁኑኑ እንሳፈርና በጠዋት ጉዞ መጀመር እንችላለን፡፡”

በፊት ወዳዩአቸው የጭነት መኪናዎች እንደቀረቡ ናትናኤል ወደ አንደኛው የጭነት መኪና ተጠግቶ በመወጣጫው ላይ ተንጠላጠለና ፊቱን በጎን መስተዋቱ ላይ ለጥፎ ወደ ጋቢናው ውስጥ ተመለከተ፡፡ አንድ ሰው ጋቢ ተጀቡኖ ከመሪው ጎን ባለው ወንበር ላይ ተኝቶኣል፡፡ መስኮቱን በዝግታ
አንኳኳ፡፡ ሰውየው ባንኖ ተነስቶ እያመነታ መስኮቱን ዝቅ አደረገና
“ምንድነው?” አለ በእንቅልፍ ልቡ ጋቢውን ከጭንቅላቱ ላይ እየገፈፈ፡፡

“ይቅርታ ረበሽኩህ፡፡ ባክህ መንገድ ላይ መኪና ተሰብሮብን ነው::ዛሬ ጠዋት ወደ አዲስ አበባ ለመነሳት ነበር ያሰብነው፡፡ ጠዋት ወደዛው ትነሱ እንደሆነ የምታደርስልኝ ፖስታ ነበር።” አለ ናትናኤል፡፡

“ወደ አዲስ አቦ እይደለም የምንሄደው፤ ሚሌ ነው፡፡” አለ ሰውየው ናትናኤል ከመናሩ ፊት መስኮቱን እየዘጋበት፡፡

ናትናኤል ታስፋ ሳይቆርጥ ከመኪና መኪና እየቀያየረ መጠየቁን ቀጠለ፡፡ አራተኛው መኪና ውስጥ ያገኘው አውታንቲ ወደ አዲስ አበባ የሚሄድ መሆኑን ሲነግረው መጣሁ ደብዳቤውን ይዤ ብሎት ወደ ካልቨርት
ተመለስ፡፡

ለአውታንቲው ሳይነግሩት ድምፅ ሳያሰሙ ወደ አዲስ አበባ ከሚሄደው የጭነት ጀርባ ላይ እየተንጠላጠሉ ወጥተው ከጭነቱ የፊት ጫፍ ሸራ ገልጠው ገብተው ተደበቁ፡፡ የለበሱት አቧራማ ሽራ ከጨካኙ ንፋስ ቢያተርፋቸውም ሰውነታቸው ተረጋግቶ ለማረፍና እንቅልፍ ለማሰብ አልቻሉም፡፡

ማለዳ ላይ የተደበቁበት የጭነት መኪና የአዋሽን ከተማ ለቆ እያጓራ እያገሳ አቧራውን እያቦነነ ወደ አዲስ አበባ ለመክነፍ የመጀመሪያ ባይሆንም
የኋላ ኋላ የቀደሙትን መኪናዎች ተከትሎ ረጅሙን በረሃማ መንገድ በጠዋቱ ተያያዘው፡፡

አልፎ አልፎ ብቻ
👍1
የተሸፋፈኑበትን ሸራ ገሰጥ እያደረጉ ከፊት ለፊታቸው እየተሽቀዳደመ ወደ መኪና ሆድ ስር የሚገባውን የአስፋልት መንገድ እያዩ ቆዩ፡፡ ሲረፋፍድ ፀሃይዋ እየጋለች እየጠነከረች ስትመጣ ከስራቸው ስር የሚፍለቀለቀው ሙቀት ሰውነታቸውን እሳት እንደገላመጠው ጎማ አልፈሰፈሰው፡፡ ከሽራው ውስጥ ለመውጣት ግን አልደፈሩም።

አልቻልኩም ሙቀቱን፡፡ አለ ናትናኤል ሽራውን ገለጥ አድርጎ ይዞ በተቻለ መጠን ከፊት የሚከንፈውን ንፋስ ወደ ሸራው ስር ለማስገባት እየሞከረ::

ለመተኛት ሞክር::

ወለጪቲን እንዳለፉ የተሳፈሩበት መኪና ድንገት ፍጥነቱን ቀንሶ ጥግ ሲይዝ ሁሉቱም በጥያቄ ተያዩ፡፡ ወዲያው የሌላ መኪና ድምፅ ተስማቸው:: የተሳፈሩት ከጭነቱ በላይ ስለሆነ እታች ክጭነት መኪናው ጎን ለጎን የሚሄደው መኪና አልታያቸውም። ወዲያው ያሉበት መኪና ጥግ ይዞ እንደቆመ አንድ ጥቁር ሬንጅር ሮቨር አለፍ ብሎ ከፊት ቆመ።

"እነሱ ናቸው"አለ ካልቨርት በጥድፊያ ሸራውን መልሶ በጭላንጭል ቁልቁል እየተመለከተ፡፡

ጥግ ይዛ የቆመችው ሬንጅሮቨር የፊትና የኋላ በሮች ተከፍተው አራት ሰዎች ወረዱ በእጃቸው አጫጭር አውቶማቲክ ጠመንጃዎች ይዘዋል የያዟቸውን መሳርያዎች ለመድበቅ ሙከራ ሳያደርጉ ወደፊት ደግነው ይዘው በፍጥነት ወደ ጭነት መኪናለሁ ተጠጉና በግማሽ ክብ ቅርፅ ፈንጠር ፈንጠር ብለው ቆሙ::

“እርግጠኛ ነህ? እነሱ ናቸው? አንሾካሾክ ናትናኤል ከሸራው ስር።

ዝም በል! አለ ካልቨርት ሸሪውን በግራ እጁ በስሱ ከፈት አድርጎ እንደያዘ ቀኝ እጁን በሽራው ስር ቁልቁል ሰድዶ ሽጉጡን ከኪሱ ውስጥ እያወጣ

ከሬንጅሮቨር ከወረዱት ሰዎች መሃል ሦስቱ ግራና ቀኝ በተን ብለው ሲቆሙ አራተኛው አውቶማቲክ ጠመንጃውን ወደፊት እንደደገነ ወደ ከባድ መኪናው ሹፌር ተጠግቶ እንዲወርድ ምልክት ሰጠው:: ሹፌሩና ረዳቱ ያለክርክር ከጭነት መኪናው ወረዱ፡፡

እንዳትነቃነቅ” ራቅ ብሎ የቆመው ሰው ሹፌሩ ላየ ጮኸበት::

ሹፌሩና ረዳቱ ከመኪናው ስር በመሆናቸው ከዓይን ቢከለሉም
ካልቨርት አራቱን አዲስ መጤዎች በጥንቃቄ ይከታተላቸው ጀመር።

የጫናችሁት ሰው አለ?” አለ አራተኛው ስው በቁጠ ድምፅ የያዘውን አውቶማቲክ መሣሪያ አፈሙዝ በከባድ መኪናው ሹፌር አቅጣጫ ደግኖ፡፡

“የለም፡፡ ሁለታችን ብቻ ነን፡፡” የሹፌሩ ድምፅ ከበስተግራ ተሰማ፡፡

“ጭነታችሁን ገልጠን አንድ በአንድ እንፈትሻለን፡፡ ሰው ብናገኝ ወየውላችሁ፡፡ የምንከታተለው ከፍተኛ ወንጀለኞችን ነው:: እውነቱን ንገረኝ::” አለ መሣሪያውን የያዘው ሰው አየተቁነጠነጠ፡፡ “ፖሊሶች ነን የምንከታተለው የመንግሥት ወንጀለኞችን ነው::"

“እንደፈለጋችሁ ፈትሹ፤ ሁለታችን ብቻ ነን፡፡” አለ ትርፍ ሰው እንዳልጫነ ለራሱ እርግጠኛ የሆነው ሹፌር በሚንቀጠቀጥ ድምፅ:: ......


💫ይቀጥላል💫
👍1
እስቲ እኛም እንጨክን፤
አስቲ አኛሞ እንጀግን፤
ይብቃን እንባባል፤
የምን ሚስት ፣የምን ባል፤
የተዘራው ቢያሽት፣ አርመን ሳንጨርስ
መዝፈን ያልታደልን ፣ #ክርፓ ሶሮሪንስ።
ብኩን...
አንቺን መደለሌን፣
ሠርክ መበደሌን ፣ የሞደጋግመው፣
በደል አስጨክኖሽ ፣ እንድትጠዪኝ ነው።
እስቲ አኛም እንጨክን፤
እስቲ እኛም እንጀግን፤
ይቅርብሽ ብዬ እንጂ ፣ የማልዘረዝረው፣
ላንቺ ስል እኮ ነው ፣ የማመነዝረው።
ስሕተት ስመ ብሩክ ፣ኹለት ግብር ያቅፋል፤
ተሳሳችን ጸጸት፣
ተበዳይን ምጸት ፣ወልዶ ያስታቅፋል።
ታቀፍኩት፤
ታዘልከት፤
ታመምኩት፤
መበደል ዕድሉ
ራስን በመጣል
እንኳን ትታኝ ሄደች ፣ ብሎ ማጃጃሉ፤
መጃጃል አይደል ፣ የመኖር ዐመሉ?

#ክርፖ_ሶሮሪ
በኮንሶ ባህል የለፉበትን የእርሻ ማሳቸውን ሲያርሙ ከድካሙ የሚበረቱበት ህብረ ዝማሬ ነው።

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
........መፅናኛ ለሰካራምች.......
ጌትነት እንየው


በቀን እንግድነት - ከአለም እልፍኝ ገብቶ
ባይተዋር ሲሆኑ የሚመስል ጠፍቶ
ህሊናን ሲሸብብ ፣ የሰው ተንኮል ደርቶ
መንፈስን ሲደፍቅ ፣ የሰው ግፉ ምልቶ
ንፁህ ልብ ሲያፍን ፣ ክፋቱ ከርፍቶ
ሚዛንን ሲስቱ ፣ በቀን ሰው ተገፍቶ
ይሄን ጊዜ ሰውን፦
ባይጠሉትም ፈርቶ
ባይፈሩትም ሰግቶ
ከምላሱ ሸሽቶ
ይህንን የቀን ሰው ፣ ከቀን ጋራ ትቶ
ምሽት ተከናንቦ ፣ መሸታ ቤት ገብቶ
ብርሌ አንደቅድቆ ፣ መለኪያ ለግቶ
ለግቶ ለግቶ
ጨልጦ ጠጥቶ
ቢሰደቡም ሰምቶ
ቢመቱም ተመቶ
ቢገደሉም ሞቶ
ብቻ እርሱ ፈጣሪ፦
"ይቅር" እንዲላቸው ፣ ለማርያም ልጅ ሰቶ
ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ ፣ ጨርቅ ሆኖ ቡትቶ
እንደ ህፃን ድሆ ፣ ተማደሪያ ገብቶ
ቢቻል በር ዘግቶ
ካልተቻለም ትቶ
ቀበቶ ሳይፈቱ፦
ጫማ ሳያወልቁ ፣ ታልጋ ተዘርግቶ
ከሞት ከፍ የሚል ፣ እንቅልፍ አንቀላፍቶ
ተ...ኝ...ቶ ተ....ኝ....ቶ
አሁንም ተኝቶ
ሌቱ አልቆ ቀን ሲሆን ፣ ማለዳ ነቅቶ
ማታ በጠጅ ጠርቶ
ማታ በጠጅ ነፅቶ
እራስን ካገኙት
ጠዋት እንደ ክፃን ሁሉንም እረስቶ
ንጡህ ወደኔ ይቅረቡ
ብሎ እንዳላላቸው ጌታ በመዝገቡ
የየዋህነት ገፅ የፍቅር ድርሳኑ
አርጎ እንደፃፋቸው ህፃናት ከሆኑ
ምናለ ቢጠጡ
ምናለ ቢሰክሩ
በቀን ያደፈትን በምሽት ካጠሩ
#ውርሰ-ውበት



ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...

በፈረሶች ፀጉር ለሚዋቡ ሴቶች
ውርስ ተይላቸው
አብሮሽ አይቀበር ውበት ይሁናቸው


ብዙ ኩል ቀላቅለው አሳር ለሚበሉ
ስራ አቅልይላቸው አይንሽን ይትከሉ


ለቁንጅና ድጋፍ አፍንጫ ጆሯቸው
ለጌጥ ለሚበሱ
ያንቺን አውርሻቸው ውብ ጌጥ ነው በራሱ


ሳቃቸው እንዲያምር
ተነቅሰው በመፋቅ አሳር ለሚበሉት
ጥርስሽን ስጫቸው ወስደው ያስተክሉት


ሁሉንም አካልሽን ከአፈር መበስበስ መቀበር አድኚ
ቆመሽ ብቻ አይደለም ሞተሽ ውበት ሁኚ


ፀባይሽ ግን ውዴ...

እኔ ያልቻልኩትን አፈሩ ከቻለው
አደራ አታውርሺ
ፀባይሽ ቢወረስ ትርፉ መቃጠል ነው


ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...

ውበትን ለሚሹ ሴቶች አውርሻቸው
እኔም ያንቺ አፍቃሪ....

እኔም ያንቺ አፍቃሪ
ውርስሽን ልካፈል እነሱን ላግባቸው
💔 ትዝታ እና ሻማ🔥

ከሰሙ ክምር ላይ አንድ ክር ይታያል
እሱን ባየው ቁጥር...
የክሩ አቀማመጥ ያንቺን ይመስለኛል


ብርሐንና ጥላ እሳትና ቅኔ
በጨለማ መሀል የምራመድ እኔ
ልፈታ እጥራለው
ላስር እጓጓለው
በትንሿ ቤቴ..
ከሻማችን በላይ መብራቱ ምንድነው?


በቤቴ ታሪክ ውስጥ በቤቴ ብራና በጉልህ የሰፈረ
``ሻማ ሂወቴ ነው`` የሚል ቃል ነበረ
ሻማ ሂወቴ ነው ክሩ ደግሞ አንቺ
በርግጥ ቅኔ አደለም ቢሆንም ግን በርቺ
ባንቺው ስለሚያምር አንቺው ቃሌን ፍቺ
ይላል ብራናዬ!
የቤቴ አንድ ገፅ አንዱ ምዕራፌ
ያኖርኩትኝ ለሷ በሻማዬ ፅፌ
(እንዴት ነው የፃፍኩት...)


ያው እንደምታውቂው
የዚ መብራት ነገር አይታመንም ብዬ ሻማ ገዝቻለው
ግን ከገዛው ወድያ ሻማ ነው ወዳጄ መብራቱን ትቻለው
ሁሌ ማታ ማታ እሱን እያበራው
ሳበራ ሳጠፋ ብዙ ሳምንት ቆየው
ከላታት ባንቺ ቀን ባንቺ ተከፍቼ
ቤቴ ተቀምጬ ሻማዬን አብርቼ
አንቺን እያሰብኩኝ ሻማውን እያየው
ቁጥሩን ባላውቀውም ብዙ ሰዐት ቆየው
ሻማዬ ሲበራ ሻማዬ ሲያልቅብኝ
ካይምሮዬ ሰፈር አንቺን ለኮሰብኝ
ፍቅርሽ ፍቅር ነበር ያውም ሰማያዊ
መዳፍሽ የመለአክ ሁሉን ቻይ ቤዛዊ
ትዝታሽ ግን ውዴ
ትዝታሽ ግን ውዴ እንደ ሻማዬ ክር
እያቀለጠኝ ነው ሰም አድርጎኝ ፍቅር
ሰም መሆን ክፋቱ
ወይ ሰው መሆን ከንቱ
ሲያቀልጠው ይኖራል የትዝታ እሳቱ


ካይምሮዬ ሰፈር የነደደው እሳት
ሰም ነበረች እና ልቤን አቀለጣት
ለነገሩ ትቅለጥ ድሮም የኔ አይደለች
ነዳ የምታነደኝ ክሬ ግን እሷ ነች
እኔ ምስኪን ሻማ ባልሞላ ኑሮዬ
እሳት ፍም ትዝታን ተሸክሜ ችዬ
አለው እኖራለው እድሜ ለሷ ብዬ
ትዝታና ሻማን በሳት አቃጥዬ!
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው


.....በመጨረሻም የሚፈልገውን ጥል እንዳሰበው አገኘው፡፡ ኬስሌ ጀምስ፡፡
ይህ ኬስሊ ጀምስ የተባለ ወጣት ዋት መንደር ውስጥ የተወለደ የወረደ
ህይወት ያለው ሴት አቃጣሪና በትርፍ ጊዜውም የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ
ሲሆን አውቆ የተሳሳተ መረጃ ሰጠውና የመጀመሪያውን ትልቁን የወንጀል
ምርመራ ጉዳዩን አሳጣው፡፡ ከፍርድ ቤት ከወጣ በኋላ ጄሪ በቀጥታ ጄምስን
ፍለጋ ጄምስ ወደሚገኝበት ቤት አመራ፡፡ ጄምስንም መኪናው ውስጥ አገኘው፡፡ ከመኪናው ጎትቶ አውርዶት ሰው ሁሉ እያየው እስኪበቃው ድረስ ቀጠቀጠው፡፡ ልጁ ለሶስት ሳምንት ያህል በፅኑ ህሙማን ክፍል ከቆየ በኋላ እንደምንም ብሎ ህይወቱ ተረፈ::፡ ነገር ግን ዕድሜውን በሙሉ በተሽከርካሪ
ወንበር ላይ እንደሚያሳልፍ እንዲሁም ደግሞ መሰረታዊ የሆኑ የተፈጥሮ
ግዴታዎቹን እንኳን ለመወጣት የግድ አጋዥ የሚያስፈልገው ሰው ሆነ::

ጄሪ በሰው መግደል የሙከራ ወንጀል ተከስሶ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ሁሉም
በፍርድ ቤቱ የሚገኙ ወንዶች ጄሪ በስራው ላይ እያለ ጄምስን ሊይዘው ሲል
ስለተቃወመውና እንደዚሁም ደግሞ መሳሪያ ሊመዝበት ስለነበረ ጄሪ ራሱን
ለመከላከል ሲል ያደረገው ነገር ነው ብለው መሰከሩለት፡፡ ነገር ግን የኬስሊ
ጄምስ እናት ፍርድ ቤት ቀርባ እየተንሰቀሰቀች እና እየጮኸች እህቶቹም ያኔ በፖሊስ እስኪሞት ድረስ የተደበደበው የመጨረሻ ዝቃጭ ወንድማቸውን
የወደፊቱን ብሩህ ህይወቱን እንደተነጠቀበት አድርገው አራገቡት፡፡

ሚክ ጆንስን የፍርድ ሂደቱን በየቀኑ ሲከታተል ነበር፡፡ ችሎቱን በማስኬድ ላይ የምትገኘውን ሊብራል (ነፃ አሳቢ፣ ለዘብተኛ) ጨጓራ የምትልጠው ሴት ዳኛ የጄምስ ቤተሰብ የሚናገረውን እያንዳንዱን ቃላት በውስጧ ስትይዝ እየታዘባት ነበር፡፡ በተለይ ደግሞ የጄምስ ቤተሰቦች ስለዚህ የማይረባ ልጃቸው የሌለውን የውሽት ነገሮች እያወሩ የጄሪን ጥሩ ሥም እንዲጨቀይ ስላደረጉ በንዴት ጨጓራው ይላጥ ነበር፡፡ ግን ምንም ማድረግ አይችልምና ዝም አለ፡፡ ጄሪ የግድ የዳኛውን ልብ የሚያሳዝን ታሪክ መፍጠር ያስፈልገዋል፡፡

የመጀመሪያው በሚስቱ ሞት የተነሳ ከፍተኛ ሀዘን ደርሶበት ስለነበር
የአዕምሮ አለመረጋጋት ስለደረሰበት ነው የሚል የመከላከያ ሀሳብን አቅርቦ
ጠበቃው ተከራከረለት፡፡ በመቀጠል ትንሿ ልጁን ጁሊን አቅርቦ ጁሊ እንዴት
አባቷን እንደምትወድ እና እናቷ ከሞተች ጀምሮ ቤተሰቡ በጣም እንደተጎዳ
ጭምር ተናገረች፡፡ የጄሪ የቀድሞ የትቤት እና የእግር ኳስ ክለቡ ጓደኞቹም
ለጄሪ መሰከሩለት፡፡ ምን ይሄ ብቻ የአካባቢው ፖስተርም ፍርድ ቤት ቀርቦ
ስለ ጄሪ መልካም ባህሪ እና ሃይማኖተኝነት ጭምር የምስክርነት ቃሉን
ሰጠ፡፡
ነገር ግን ይህቺ ሸርሙጣ ኒኪ ሮበርትስ የተባለችው ሴት የምስክርነት ሳጥን ውስጥ ገብታ የምስክርነት ቃሏን ስትሰጥ የጄሪ የመከራ ህይወት ተጀመረ፡፡ ዶክተር ሮበርትስ ከፍተኛ ሀዘን በሀዘንተኛው ላይ ስለሚያሳድረው የስነ ልቦና ችግር የባለሙያ ምስክር ሆና ነበር የቀረበችው፡፡ ከፍተኛ የሆነ ሀዘን ላይ ያለ ሰው ጄሪ ያደረገውን ነገር ያደርጋል? ከፍተኛ ሀዘን
ልንቆጣጠረው የማንችለውን የአመፃ ስሜትን በሰዎች ላይ ያሳድራል? ጄሪ
ከቫክ በጣም ከፍተኛ ሀዘን ውጥ ስለነበረ ሀዘኑም አዕምሮውን ኬስሊ ላይ
ጥቃት ሲሰራም በትክክለኛ አዕምሮው አልነበረም? የሚሉ የባለሙያ መልስ
የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች ለዶክተር ሮበርትስ ቀርቦላት ነበር፡፡ እሷ ግን
መልሶቹን ስትመልስ

“አያደርግም፡፡”

“አያሳድርም፡፡”

“እንደዚህ የሚባል ነገር የለም፡፡”

የሚሉ መልሶችን ሰጠች

ዶክተር ሮበርትስ በሰጠችው ሙያዊ ምስክርነት ውስጥ አንድም የጄሪን
ነገር ያካተተ ሚዛናዊ አስተያየት አላከለችም፡፡ በእሷ ሙያዊ አስተያየት
ደግሞ ጄሪ ምንም አይነት የአዕምሮ ችግር እንደሌለበት አስረዳች፡፡
ጥቃቱንም ሲፈፅም በድንገት ሳይሆን አቅዶበት ነው አለች፡፡ ምናልባትም ጄሪ
ባለው የዘረኝነት እና የራስ ወዳድነት ምክንያት ጥቃቱን ሲፈፅም ከሀዘን
ይልቅ የሀይለኝነት ስሜቱን ለማንፀባረቅ ስላሰበ ነው ብላ ሁሉ ነገሩን በጄሪ
ላይ ደፈደፈችበት፡፡ ሚክ ጆንሰን ይህቺ ቀጭን ዶክተር ተብዬ ባለሙያ ስለ
ጄሪም ሆነ በሥራ ላይ ስላሉ ፖሊሶች ምን ያህል አደጋን ከእንደነዚህ ኬስሊ
ጄምስን ከመሳሰሉ ሰዎች እንደሚቀበሉ አታውቅም እና እርር እያለ የእሷን
ምስክርነት ቁጭ ብሎ ሰማት፡፡

በመጨረሻም ጄሪ ኮቫክ ከፍተኛ ወንጀለኛ ሆኖ ተገኘና ይህቺ ለዘብተኛ
ዳኛ የሃያ አምስት ዓመት የእስር ፍርድን ፈረደችበት፡፡ ለሁለት ጊዜ ያህል
ይግባኝ ቢልም በእነዚህ ሁለቱ የይግባኝ ጊዜዎችም ይህቺ የተረገመች ኒኪ
ሮበርትስ የተባለች ሴት በፍቃደኝነት እየቀረበች ከጄሪ በተቃራኒ ሆና
ምስክርነቷን ሰጠች፡፡ በቃ እንዲሁ እንደቀልድ በኒኪ ሮበርትስ የተነሳ ሚክ
ጆንስን ጓደኛው ጄሪ ኮቫክ ቀሪ ዕድሜውን በእስር ቤት እንዲያሳልፍ
አስፈረደችበት፡፡
ወደ ድሮ ጓደኛው ዞሮ ፈገግ እያለም ለራሱ እንኳ የማይሰማውን በጎነትን ጓደኛው እንዳያጣ አስቦለት ሦስተኛውን ይግባኝ እንዳመለከተለት ነገረው፡፡

“ጥሩ ነገር የምናገኝ ይመስልሃል?” ብሎ ጄሪ ጠየቀው፡፡

“ይመስለኛል” ግን የአሁኑ ይግባኛችን ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡
ለሚቀጥሉት ስድስት ሳምንታትም ከፍርድ ቤት ምንም አይነት ምላሽ ላናገኝ እንችላለን” አለው ሚክ፡፡

“አታስብ እስር ቤት ውጥ ስትሆን እኮ የሚኖርህ ብቸኛ ነገር ጊዜ ብቻ
ነው። ይልቅ አንተ በመርማሪነት ስለያዝነው ጉዳይ ንገረኝ እስቲ? በጩቤ
ተወግተው ነው ሰዎቹ የተገደሉት ብለኸኝ ነበር አይደል?” ብሎ ጄሪ
ጠየቀው፡፡

“አዎን” ብሎ ጆንሰን ትንሽ ተንተባተበና “በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ይመስለኛል፡፡ ትንሽ መፍጠን ባንችልም ወደ መቋጫው እየቀረብን ሳይሆን አይቀርም”

ዶክተር ኒኪ ሮበርትስ ከዚህ የዞምቢ ግድያ ጋር ስላላት ግንኙነት ላጄሪ
ሊነግረው አልፈለገም ወይም ደግሞ ስለ ዝርዝር ነገሩ ሊያጫውተው ፈቃደኛ
አልሆነም፡፡ ሚክ ጆንሰን ኒኪ በባሏ የመኪና አደጋ ግድያ ላይ እጂ እንዳለበት
ሙሉ በሙሉ ያምናል፡፡ ያህንን ማረጋገጥ ግን ይጠበቅበታል፡፡ ከተሳካለት
በመረጃ አስደግፎ እሷን ፍርድ ቤት ያስቀርብና በጄሪ ላይ የሰጠችው
የምስክርነት ቃል ተቀባይነት እንዳያገኝ በማድረግ ጄሪን ያስለቅቀዋል፡፡
ወይም ደግሞ እሱ ላይ መስክራ ቀሪ ዕድሜውን በእስር ቤት እንዲያሳልፍ
ያስፈረደችበት ሴት፣ ልክ እንደ እሱ እስር ቤት ቀሪ እድሜዋን እንድታሳልፍ
ሲያደርግ ያሳውቀዋል፡፡ አሁን ግን ይህንን ሀሳቡን ላጄሪ ቢነግረው ያልሆነ
ተስፋ ያድርበትና ምናልባት ጉዳዩ እንዳስበው ባይሳካለት ይጎዳል ብሎ
በማስብ ሳይነግረው ቀረ፡፡

በቀረው የጥየቃ ሰዓታቸው ሁለቱ ሰዎች ብዙ ሳያወሩ ቁጭ ብለው ቆዩ፡፡ ሚክ በሚቀጥለው ወር መጥቶ እንደሚጠይቀው እና ጁሊ ልጁንም
አብራው እንድትሄድ እንደሚጠይቃት ቃል ገብቶለት ተሰናብቶት ወጣ፡፡ ሚክ
ጆንሰን ምንም እንኳን ልጅ ባይኖረውም የጓደኛው ብቸኛ ልጁ ጁሊ ኮቫክ
በአባቷ እንደዚህ መሆን ምንኛ እንደሚጎዳት ይገባዋል፡፡ በእርግጥም በድጋሜ ኒኪ ሮበርትስ ከጄሪ የነጠቀችው ሌላኛው ነገር ደግሞ ሴት ልጁን ነው፡፡።
ጁሊ አባቷ ጄሪ ኮቫክ ላይ የሃያ አምስት ዓመት የእስር ፍርድ ሲፈረድበት የ13 ዓመት ልጅ ነበረች፡፡ በዚህ ምክንያት በመካከላቸው ሊኖር የሚገባው የአባት እና የልጅ ግንኙነት ተበጠሰና ለመራራቅ በቁ፡፡

ያቺ ሸርሙጣ ዶክተር ጄሪ ኮቫክን ሁሉ ነገሩን ነው ያሳጣችው፡፡

ጆንሰን ወደ ሎስአንጀለስ እየተመለሰ እያለ መሀል ላይ
የመኪናው አየር ማቀዝቀዣ አልሰራም አለው፡፡ ሁሉንም የመኪናውን መስኮቶች ቢከፍትም
ሙቀቱ ልብሱን በላብ እንዳራሰው ነበር መኪናውን ሲያሽከረክር የነበረው፡፡
መሪ አጥብቆ እንዳይዝ እያስቸገረው በነበረበት ጊዜ ላይ ነው እንግዲህ አጋሩ
ጉድማን ወደ እሱ የደወለው፡፡ ስልኩን ሲያነሳም ልክ ፀሐይ እንዳቃጠለው
ውሻ እያለከለከ ነበር፡፡

“ምድነው?” ብሎ ጆንሰን በቁጣ ተሞልቶ ስልኩን አነሳ።

“የት ነው ያለኸው?” ብሎም ጉድማንም በቁጣ መለሰለት፡፡

“እየነዳሁ ነው”

“በኢየሱስ ምድነው ይሄ ሁሉ ማወጣጣት?” አለና ጆንሰን በመቀጠልም
“ማወቅ አለብኝ ካልክ ከቫሊ ስቴት እስር ቤት ወደ ሎስ አንጀለስ እየመጣሁ ነው።

“ጓደኛህ መርማሪ ፖሊስ ጄሪ ኮቫክን ጠይቀህ በመመለስ ላይ ነዋ
ያለኸው?” ብሎ ጉድማን ሸረደደውና በመቀጠልም “የሚገርም አጋጣሚ ነው
ባክህ የኮቫክን የችሎት ውሳኔ እና የምስክሮቹን ቃል እያነበብኩኝ ነበር።
ታዲያ በዚህ ሪፖርት ላይ የባለሙያ ምስክርነትን የሰጠችው ሰው ማን
እንደሆነች ገምት እስቲ?” አለው እና ጉድማን አሸናፊ በሆነ የኮራ ድምፅ
“ትላንትና ማታ ከኒኪ ሮበርትስ ጋር አብረን እራት በልተን ነበር” አለው፡፡

“እሱንማ አውቃለሁ” ብሎ ጆንሰን በምሬት በተሞላ ድምፅ መለሰለት።
“እናማ ማታ ላይ ስለ ፍርድ ቤት ተሞክሮዋ አንስታ አንዳንድ ነገር
አውርታኝ ነበር” ብሎ ጉድማን አውቆ ነገሩን ለማክረር በሚል ስሜት “ከእሷ
ከተለየሁ በኋላ በእሷ ዙሪያ ምርምራዎችን ሳደርግ ምን ባገኝ ጥሩ ነው? ሁለታችሁ ለካ የጋራ ታሪክ ነበራችሁ፡፡”

“እሺ እሺ አሁን ማሾመርህን ትተህ በቀጥታ ወደ ጉዳይህ ለምን
አትገባም?” አለው ጆንሰን፡፡

“ምንድነው ያልነገርከኝ?” ብሎ ጆንሰን ጠየቀ፡፡

“ምንም የሚነገር ነገር የለንም ነው ያልከኝ? ኧረ ባክህ? ለዚህ ነበር ለካ
የምትጠላት አይደል? ምክንያቱም የልብ ጓደኛህ ላይ የምስክርነት ቃሏን
ስለሰጠች ነው አይደል?”

“አይደለም” አለው እና ጆንሰን በዝግታ “እሷን የምጠላት ትፋታም ሸርሙጣ ስለሆነች ነው፡፡ እናም ደግሞ ሦስት ንፁሀን ሰዎችን ለመግደል ቅንብር የፈፀመች ሰው ነች ብዬ ስለማምን ነው” አለው፡፡

“ሚክ ከዚህ የምርምራ ጉዳይ ላይ ራስህን በፈቃደኝነት ልታነሳ ይገባሃል!” ጉድማን በንዴት ተሞልቶ ጮኸበት፡፡

“ለምን ብዬ?”

“ምክንያቱም አንተ ለእሷ ጥሩ አመለካከት የለህም”

“ኧረ ነው እንዴ? እሺ አንተስ ባክህ?” ብሎ ጆንሰን ራሱን ለመከላከል
እየሞከረም በመጀመሪያው ቀን ጀምሮ አንተ እሷን ወደ አልጋ ለመውሰድ
ስትቋምጥ ነበር፡፡ ትላንትና ማታ ከእሷ ጋር ራት በልትሃል እኮ በኢየሱስ
ስም! ታዲያ ይህ ነገርህ አንተንስ ለእሷ የተዛባ አመለካከት እንዲኖርህ
አያደርግህምን?”

“አያደርገኝም! ለማንኛውም ከእሷ ጋር ለመወሰብ ሳይሆን እንድትቀርበኝ
እና እንድታምነኝ ስል ነው እሺ” አለው ጉድማን፡፡

ጆንሰን ጉድማንን እያንቋሸሽ ቢስቅም ውስጡ ግን ተረብሾበታል።ጉድማን የኮቫክን፣ የእኔን እና የዶክተር ኒኪን ግንኙነት ይደርስበታል ብሎ አልገመተም ነበር፡፡ ስለዚህ ከአሁኑ በኋላ ስለ ኒኪ ሮበርትስ ሲያወራ በጣም መጠንቀቅ እንዳለበትም አሰበ፡፡

“ትላንትና ማታ በጣም እንድትቀርብህ አላደረግካትም፡፡ ብትቀርባት ኖሮ
ግን ስለ ግሮልሽ ጉዳይ የዋሸችውን ውሽት ታምንልህ ነበር አይደል?” ብሎ
ጆንስን ጉድማንን ጠየቀው፡፡ ምክንያቱም የጉድማን ደካማ ጎን ይህ እንደሆነ
እና በዶ/ር ሮበርትስ ላይም ያለውን እምነት የሚሸረሽርበት ጉዳይ እንደሆነ
ያውቃል፡፡

“እሱ ላይ በደንብ እየስራሁኝ ነው” ብሎ ጉድማን አመነለትና
“ለማንኛውም አሁን ለምነግርህ ነገር ተዘጋጅ፡፡ ኒኪ ሮበርትስ በአንተ ላይ
የአፀፋ ምላሿን ጀምራለች፡፡”

“የአፀፋ ምላሽ?” ብሎ ጆንሰን አሾፈበትና “እንደዚህ አይነት ያሉ ትላልቅ ቃላቶችን ሀርቫርድ እያላችሁ ያስተምሯችሁ ነበር እንዴ?”

“ሚክ እሷ የግል መርማሪ ዴሪክ ዊሊያምስን ቀጥራዋለች” ብሎ ጉድማን
ጉዳዩን አፈረጠለት፡፡

ይህን ሲሰማ ጆንሰን ከፊት ለፊቱ ይመጣ የነበረን መኪናን ከመግጨት የተረፈው ለጥቂት ነበር፡፡ እንደምንም ብሎ መሪውን ጠምዝዞ እና ፍሬን ይዞ መኪናውን አቆመ። ከዚያም ፀያፍ ስድቦችን ይሳደብ ጀመር፡፡

ጆንሰን ልክ በሀይለኛ ነፋስ ውስጥ እንደሚሄድ ሰው ሁሉ በሀይል
እየተነፈሰ “እያሾፍክብኝ ባልሆነ? የምርህን ነው ግን?”

የውሽቴን ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር፡፡” ብሎ ጉድማን ተነፈሰ እና “ትናንት ወደ እሱ ቢሮ ስትሄድ ተከትያት ነበር”

“ይሄ ድቡልቡል ዲቃላ...” ብሎ ጆንሰን ስድቡን ሲመርጥ ጉድማን በውስጡ ሁለታችሁም ያው አይደላችሁም እንዴ?” ብሎ ነገሩን በመቀጠል ሚኪ እንደነገረችኝ ከሆነ የቀጠረችው የሆኑ የምትፈልጋቸውን መልሶችን
ለማወቅ ስለፈለገች እና እኛ ደግሞ ምንም አይነት መልሶችን ልንሰጣት
ስላልቻልን፣ በተጨማሪም ደግሞ እንደ ተጠርጣሪ መታየቷም በጣም
ስላበሳጫት እንደሆነ ነው ያስረዳችኝ፡፡” አለው፡፡

“በጣም ብዙ መልሶችን እኮ ሰጥተናት ነበር ብሎ ጆንሰን አሰበ እና ንገር
ግን ሁሉም መልሶች ወደ እሷ ስለሚያመለክቱ አልወደደቻቸውም አእምሮው አሁን በሰማው አዲስ መረጃ እየታመሰ ራሱን እነዚህን ጥያቄዎችን ይጠይቅ ጀመር፡፡ “ዶክተር ሮበርትስ ለምንድነው ዴሪክ ዊሊያምስን የቀጠረችው?ጆንስን እውነቱን ከሆነ እና ኒኪ ደግሞ ከግድያዎቹ በስተጀርባ የምትገኝ ከሆነ የግል መርማሪን መቅጠር ምንም ፋይዳ የለውም፡፡ ማለትም እሱ በእኛ ላይ የማይረቡ ቆሻሻ ነገሮችን ቆፍሮ እንዲያወጣ ካደረገች በኋላ የእኛ የምርመራ ውጤት እንዲጣል፣ እሷም አንድያውን ከወንጀሏ ነፃ እንድትወጣ ያስችላታል” ብሎ ለራሱ ግምቱን አስቀመጠ፡፡

ይህንን ግምቱን ለጉድማን ሊያሳውቀው በግማሹ ቢፈልግም፣ አጋሩ ጉድማን እሱ በኒኪ ላይ የተዛባ አቋም ነው ብሎ እንደሚያምን ስለሚያውቅ ሊነግረው አይችልም፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ምንም የማይፈራውን ዊሊያምስን ተጠቅማ ምርመራቸውን ስታበላሽባቸው እጁን አጣምሮ ሊመለከታት አይችልም፡፡

“ልናስቆመው ይገባል” አለው ጆንስን፡፡

“በመጨረሻ የምንስማማበት አንድ ነገር አገኘን” አለና

“ግን እንዴት እናስቁመው ነው ጥያቄው”

ሁለቱም ለአፍታ ያህል ዝም ብለው ከቆዩ በኋላ ጆንስን “ከሁለት አንዳችን ልናገኘው ይገባል” አለው፡፡

“አንዳችን ብቻ አይሆንም” ብሎ ጉድማን በመቀጠልም “ሁለታችንም ነን
በጋራ ልናገኘው የሚገባን፡፡ እዚህ ከተመለስክ በኋላ እናወራበታለን አለ፡፡
ጉድማን ስልኩን ከዘጋ በኋላም የኮቫክን የችሎት ውሳኔ የያዘ ወረቀት ወደ ፋይሉ መለሰ፡፡

እንግዲህ በድጋሚ ጄንሰን ና እሱ አጋር ሊሆኑ ነው፡፡ ግን የማይተማመኑ አጋሮች ናቸው፡፡ በትክክለኛው መንገድ ለመሄድ ሊወስደው የሚገባው ጥቂቱ እርምጃውም ነው፡፡ የአባቱን ወዳጆችህን አቅርባቸው፣ ጠላቶችህን ደግሞ በጣም አቅርባቸው” የሚለውን ምክር አስታወሰ፡፡ ሎው ጉድማን ይህንን የአባቱን ምክር ሁሌም እየተገበረ ነበር ሲኖር የነበረው፡፡
እነዚህን መሰል ምክሮችን ለመተግበር በመቻሉም ነው እስካሁን ድረስ
በሕይወት መቆየት የቻለው፡፡

ይቀጥላል
👍21
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


....“ጥሩ እንዳትነቃነቅ::" አለ አራተኛው ሰው መሣሪያውን ደግኖ እንደያዘ ወደ ጭነት መኪናው እየተጠጋ፡፡ በእርጋታ ወደፊት እየተራመደ በዓይነ ጭነቱን ያዳብስ ጀመር፡

እራቅ ብለው ሁኔታውን በዝምታ ይከታተሉ የነበሩት ሦስት ሰዎች የመሃሉ ድንገት ተጣራና ጭንቅላቱን ወደኋላ መታ አደረገ፡፡ ወዲያው ወደ ጭነት መኪናው የተጠጋው አራተኛው ሰው ፊቱን መልሶ ወደ ጓደኞቹ ሮጥ ብሎ ተመለስና ሰብሰብ ብለው ይነጋገሩ ጀመር፡፡
“ጠዋት ምንያህል መኪናዎች ቀድመዋችሁ ወደ አዲስ አበባ
ተነስተዋል?” አለ አራተኛው ሰው ፊቱን ወደ ጭነት መኪናው ሹፌር
መልሶ ድምፁን ከፍ አድርጎ፡፡

“አንድ ሶስት አራት ይሆናሉ፡፡” አለ ከጭነት መኪናው ወርዶ የቆመው ሹፌር፡፡

ወዲያው አራቱ ሰዎች ሮጥ ሮጥ እያሉ ሬንጅሮቨራቸው ውስጥ ገቡና በአዲስ አበባ አቅጣጫ በረሩ፡፡
“ኡፍ .…ፍ!!” አለ ካልቨርት ጭንቅላቱን በተኛበት ጆንያ ላይ ጥሎ፡፡
“ሄዱ? ” አሉ ናትናኤል ሽራውን እንደተከናነበ በሹክሹክታ፡፡
“አዎ፡፡ ያለቀልን መስሎኝ ነበር::”

የጭነት መኪናው ሹፌር መኪናው ውስጥ ገብቶ ሲንቀሳቀሱ በተቻላቸው መጠን መንፈሳቸውን አረጋግተው መመካከር ያዙ፡፡

“ያላጥርጥር በየከተሞቹ ኬላዎች ላይ ይጠብቁናል፡፡ በተለይ ወደ አዲስ አበባ እየቀረብን ስንመጣ አስቸጋሪ ነው የሚሆንብን፡፡” እለ ናትናኤል፡፡
“አዎ፡፡ : ካአሁን ወዲያ ወደየትኛውም ከተማ መግባት የለብንም፡፡ ወደ ከተሞች ስንቀርብ እየወረድን ከጀርባ በግማሽ ክብ ቅርፅ በእግር ማለፍ ነው ያለን አማራጭ፡፡”

“ከናዝሬት ወዲያ ያለውን አካባቢ አውቀዋለሁ! መንገዱን በሩቅ
እይታ እስከተከተልን ድረስ ችግር አይገጥመንም::አለ ናትናኤል፡፡
ናዝሬት ከተማ ሲደርሱ እንድ አምስት ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው ከተደበቁበት ሸራ ውስጥ ብቅ ብቅ እያሉ ከኋላና ከፊት ሌላ ተሽከርካሪ አለመኖሩን ካረጋገጡ በኋላ በጭነት፡ ላይ እየዳሁ ወደ መኪናወ ኋላ ተጠጉ፡፡
ሸራው የተጠፈረባቸውን ወፋፍራሃም ገመዶች የሙጢኝ ጨምድደው ይዘው
ቁልቁል ተንጠለጠሉ፡፡

“ተጠንቀቅ፡፡ አስፋልቱ ላይ ኣንዳታርፍ፡፡ በሁለት እግሮችህ ለማረፍና ለመቆም አትሞክር፤ ከዘለልክ በኋላ ጭንቅላትህን ቀብረህ ተንከባለል፡፡ እኔ ስዘል ተመልከት፡፡” አለ ካልቨርት በወጣትነት ዘመኑ በአገሩ ውስጥ ያሳለፋቸውን የኮማንዶ ህይቱን እያስታወሰ፡፡ "

በሰላሳ ሜትር ርቀት ልዩነት ሁለቱም የተንጠላጠሉባቸውን ገመዶች እየለቀቁ ከጭነት መኪናው ላይ ተፈናጠሩ፡፡ ካልቨርት አልተጎዳም፤ ናትናኤል ግን ግራ ክንዱ ክፉኛ ተገሸለጠ፡፡

“አስፋልቱ ላይ አትረፍ፡ እያልኩህ እንዲያውም ተርፈሃል፡፡ወደጎን
ባትንከባለል ኖሮ ይሄ አስፋልት ጭንቅላትህን ነበር የሚፈረክስልሀ፡፡” አለ
ካልቨርት እየሮጠ መጥቶ ናትናኤልን ደግፎ እያነሳው፡፡

አውራ መንገዱን እየራቁ፤ እየሸሹ የናዝሬትን ከተማ በስተቀኝ
ጀርባዋ ዞሯት::

"መንገዱ ወደቀኝ የሚታጠፍ፡ ስለሆነ ከዚህ በኋላ በቀጥታ መስመር ብንሄድ ወይም በሃያ አምስት ኪሎ ሜትር ላይ በዱከምና በሞጆ መሃል መንገድ ላይ ብቅ እንላለን፡፡ አለ ካልቨርት ካርታውን አውጥተው ሲያጠኑት ከቆዩ በኋላ፡፡

እንዳለው ከሦስት ሰዓት ተኩል የእግር ጉዞ በኋላ በሞጆ ከተማ አልፈው ከአውራ ጎዳናው ጋር ተገናኙ:: ብዙም ሳይቆዩ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ የገጠር አውቶቡስ አስቁመው ተሳፈሩ፡፡

“አዲስ ፈለጥ!“ ይላሉ አውቶብሱ ውስጥ ከሹፌሩ ጀርባ የተቀመጡ አዛውንት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፡፡ “ከአውቶብሱ ገብቶ
መፈተሽ የአባት... “ቆብህን አውልቅ፤ ክንብንብህን አውርድ ብሎ ነገር
ምንድነው? ወቸጉድ!”

“የሚፈልጉት ሰው አለ መሰለኝ::” አለ ባሻገር የተቀመጠ ልጅ እግር፡፡

ታድያ ቢኖርስ ባለፍንበት ከተማ ሁሉ እየቆምን ቆብና ክንብንባችንን መገፈፍ የአባት ነው?ልማድ ነው? ወይ ፈጣሪ?” ሽማግሌው ተቆጠ፡፡

“ምንድነው?” አላቸው ናትናኤል ከጎኑ የተቀመጡትን ሴትዮ::

“እንጃ! ባለፍንበት ከተማ ሁሉ መሣሪያ ደግነው እንደ ሽፍታ ሲበረብሩን ቆዩ፡፡” አሉት ሴትየዋ መደነቃቸውን፣ መገረማቸውን ለማሳየት እጃቸውን አፋቸው ላይ ጣል አድርገው፡፡

“እነማን ናቸው?” ናትናኤል ግራ የተጋባ መስሎ ጠየቃቸው፡፡

“ምኑን አወቄው ብቻ ከወለንጭቲ የጀመሩ ሰባቴ እያስቆሙ ሁለት
ሁለት፥ሦስት ሦስት እየሆኑ እንዲህ እንዲህ እያደረጋቸው ሲበረብሩን ዋሉ፡፡
ሆ! እንደ አነሳሳችንኮ ገና ቅድም ታዲስ አበባ ደርስን ነበር ጊዮርጊስ ይይላቸው”

ናትናኤል ዞር ብሎ ካልቨርትን ሹክ አለው::

ደብረዞይት ሊደርሱ ትንሽ ሲቀራቸው ተጠቃቀሱና መጀመሪያ ካልቨርት እራቅ ብሎ ደግሞ ናትናኤል ተከታትላው ወረዱ፡፡

“ምንድነው?” አለ ካልቨርት አውቶቡሱ ውስጥ የተባለውን ሁሉ አጣርቶ ለመረዳት ጓጉቶ፡፡

ናትናኤል አውቶቡሱ ውስጥ የሰማውን ሁሉ ዘርዝሮ ነገረው፡፡

“ከአሁን ወዲያ መኪና ላይ መውጣት የለብንም::” አለ ካልቨርት፡፡
“ታዲያ እንዴት አናደርጋለን?”
“አሁን ሁለታችንም የተዳከምን ይመስለኛል፡፡ ለጊዜው ከመንገድ
ፈቀቅ ብለን እንረፍና ከጨለመ ወዲያ ሌሊቱን መንገዱን ተከትለን በእግራችን እንቀጥላለን፡፡ ከበረታንና ሰሰዓት አምስት ኪሎ ሜትር ብንጓዝ እንኳን ከምሽቱ አንድ እስከ ጠዋቱ አንድ ሰዓት ስልሳ ኪሎ ሜትር ሽፈንን ማለት ነው:: ፀሐይ ስለማይበረታብን የምንሸነፍ፡ አይመስለኝም፡፡”
ከመንገዱ በስተቀኝ እርቀው ገብተው
ለብቻዋ በቆመች የግራር ዛፍ ስር በደረታቸው ተደፍተው ለማረፍ
ሞከሩ::እየጠለቀች ያለችው ፀሐይ እንደጌጥ ብታብረቀርቅም ሙቀቷ እየከዳት መጣ፡፡ አውላላ ሜዳ ላይ ብቻውን እየተመላለሰ የሚጋልበው ቀዝቃዛ ነፋስ ሰውነታቸውን ጠዘጠዘው፤ ምግብ ሳያገኝ ሁለተኛ ቀኑን የያዘው
ሰውነታቸውም ከፊት የተደቀነውን መንገድ ቁጭ አድርጎ ተዳከመ፡፡ ቢሆንም ፀሐይ ልትሸሽግ ሲዳዳት ከተኙበት ተነስተው የመንገዱን ጥግ ይዘው በአዲስ አበባ አቅጣጫ ጉዞአቸውን በእግር ተያያዙት፡፡

“እርምጃህን አትቀያይር በአንድ ዓይነት ፍጥነት አንድ አይነት ስፋት ተራመድ አለበለዚያ ይደክምሃል፡፡” አለ ካልቨርት እጆቹን እያወናጨፈ፤ “ከጎን ከጎኑ የሚንቶሰቶሰውን ናትናኤልን ዞር ብሎ
ተመልክቶ፡፡

አልፎ አልፎ በሩቁ የመኪና መብራት ሲታያቸው ፈጠን ብለህ ከአውራ መንገዱ እራቅ እያሉ መሬቱ ላይ በደረታቸው አየተኙ እያሳለፉ መንገዳቸውን ያለንግግር ቀጠሉ፡፡ ሁለት ጊዜ ጅቦች ሲያጋጥሟቸውም ሁለቱንም ጌዜ የካልቨርት ሽጉጥ የጥይት ጩኹት አተረፋቸው፡፡

እንዳሰሱት እስከጠዋቱ አንድ ሰዓት ድረስ አልተጓዘም፡፡ ከጠዋቱ አስራ አንድ ሰዓት አካባቢ አቃቂ ከተማ እንደደረስ ያለዕረፍት መቀጠል እንደማይችሉ ስለተረዱ ከመንገዱ ወጥቶ እራቅ ካለ ጫካ ውስጥ ገብተው ካልቨርት እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡ናትናኤል እስካሁን ያሳለፋውን ሁኔታዎች አንድ በአንድ በህሊናው እየመላለሰ ይቃኝ ጀመር፡፡ ርብቃ…
አብርሃም… የቢሮ አለቃው.… ወታደራዊ አታሼዎቹ… ነጭዋ ሲትሮይን
የምሥራች ዘውዲቱ… አዲስ አበባ ድሬዳዋ…ካልቨርት ይህ ሁሉ ውጣ
ውረድ ከርብቃ ስቃይና ከእርግዝናዋ ጋር እየተሰባጠረ ይታየው ጀመር፡፡
ርብቃን ለማዳን ምን ማድረግ አለበት? አወሬዎቹን መጋፈጥ? ከአውሬዎቹ
ጋር መደራደር? ካልቨርት ምስጢሬን ይዤ ልሙት ባይ ነው፡፡ ካልቨርትን እንደገና ማግባባትና ማሳመን ይቻላል? ወይስ የሞተ ፡ ነገር ነው? ለማናቸውም ለካልቨርት ምንም ፍንጭ ማሳየት የለበትም… ማናቸውንም ጉዳይ ከካልቨርት መደበቅ ይኖርበታል፡፡

የተጫናቸው ድካም በዙሪያቸው ከነበረው የማለዳ ውርጭ የከበደ
👍1
ነበር፡፡ ሁለቱም ለበርካታ ሰዓታት ተኝተው አረፈዱ፡፡ በመጀመሪያ ከእንቅልፉ የነቃ ካልቨርት ነበር፡፡

“ረፍዷል... የምንበላው ምናምን ብናገኝ የቀረንን መንገድ ተጠናክረን እንቀጥል ነበር፡፡” አለ ካልቨርት፡፡
ከእንቅልፉ ነቅቶ ፡ እግሮቹን አንፈራጦ ከጀርባው ያለ የዛፍ ግንድ ተደጋግፎ የተቀመጠው ናትናኤል በመዳፉ ፊቱን ሲያሻሽ ቆየና ቀና አለ፡፡

“እስቲ አቃቂ ከተማ ቀስ ብዬ ገብቼ ምናምን እፈልጋለሁ፡፡”

ናትናኤል ከተደበቁበት ጫካ ወጥቶ ሰፊውን ሜዳ አቋርጦ በግራ ጎን በኩል ከተማዋን ለሁለት ከፍሉ ሲገባ የጠበቀውን ያህል ብዙ ችግር
አልገጠመውም::

ከአንድ አነስተኛ ኪዎስክ በሞላላ ላስቲክ ውሃ ይዞ ወደሌላ ሱቅ ተሻገረ፡፡ ከሱቁ ሁለት የላስቲክ ከረጢቶች ገዛና ዳቦ፣ የላስቲክ ወተትና ፍራፍሬዎች አጭቆባቸው በመጣበት መንገድ ከትንሿ ከተማ ሹልክ ብሎ ወጣ፡፡

“ውሃውን ስጠኝ፡፡” እል ካልቨርቱ ናትናኤል ሁለቱን የላስቲክ ከረጢቶች አስቀምጦ ያመጣውን ዕቃ እያወጣ ሲደረድር፡፡

“ብዙ ኣትጠጣ… ቁርጠት እዚሁ እንዳያውለን፡፡”

የውሃውን ላስቲክ ለካልቨርት እያቀበለው::
ዳቦውንና ፍራፍሬውን ተመግበው ወተቱን ጠጥተው ሲያበቁ ውሃውን ይዘው ጉዞአቸውን ቀጠሉ፡፡ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ አዲስ አበባ በሩቁ ታየቻቸው፡፡

• “ከእንግዲህ ነፃ ነን፡፡” አለ ካልቨርት፡፡
“ምን ማለትህ ነው?”
“ከጥቂት ቀናት በኋላ አፍሪካ አንድ ትሆናለች::» አለ ካልቨርት
ፊቱን ወደ አዲስ አበባ አቅጣጫ እንዳቀና ፈገግ እለና:: «ነፃ እንደመሆን
የሚጣፍጥ ምን ነገር አለ።”

“ምንም” አለ ናትናኤል ካልቨርት ሽጉጥ የከተተባትን ሻንጣውን እየተመለከተ፡፡

💫ይቀጥላል💫
#ቅኔ... 💚 💛 ❤️

ከቀስተ ደመና ቀለም ጠቅሶ
አምላክ ወደ ሃበሻ ምድር የላካት፣
ስንቶች ለክብሯ ዘብ ቆመው
ስለ ፍቅሯ የሞቱላት፣
የሺህ ዘመናት ታሪክ
በስፋትና ጥልቀቷ ልክ
ላይፋቅ የደመቀባት፣
የሁላችን የጋራ ክብር
ሰንደቅ አላማ ቅኔ ናት።


💚 💛

🔘ሻለቃ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሃምሳ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


...“አሁን ገና ሰው መሰልክ?” አለ ካልቨርት ፊቱ ፈገግታ ለብሶ፡፡
“አይዞህ አንተም ውሃ ሲገላምጥህ ሰው ትመስላለህ::” ናትናኤል ፀጉሩን በፎጣ እያደራረቅ ወደተከራዩት የሆቴል ክፍል ገብቶ ከኋላው በሩን ዘጋው፡፡
“ህ! ! ህ ለሁሉም ጊዜ አለው::”አለ ካልቨርት ከተቀመጠበት ተነስቶ የሚቀይረውን አዲስ ልብስ ተሸክሞ ወደ መታጠቢያ ቤት እየሄደ፡፡

ካልቨርት ከክፍሉ ወጣ እንዳለ ናትናኤል ፈጠን ብሎ ካልቨርት ከጥግ ያስቀመጠውን ቦርሳ ይፈትሽ ጀመር፡፡ እንደተመኘውና እንዳሰበው፣
እንዳቀደው የካልቨርትን ሽጉጥ ቦርሳው ውስጥ አገኘሁ፡፡ ሽጉጡን ቶሎ ብሎ
ከቦርሳው ውስጥ አወጣና ካርታን አውጥቶ ጥይቱን ቆጠረ፡፡ ሰባት ጥይት
በቂ ነው፡፡ ካርታውን በቦታው መለሰና ሽጉጠን አቀባብሎ መጠበቂያውን
ለቆ በሩን እያየ ካልቨርትን ይጠባበቅ ጀመር፡፡ ምርጫ የለውም... ሌላ
ምንም ምርጫ የለውም!

ባያስማማስ ጭራሽ ባይስማማስ ፍንክች አልል ቢልስ? የራሱ ጉዳደ:: እዚሁ ይጨርሰዋል፡፡ አለዛም ትቶት ይሄዳል፤ ብቻውን ይጋፈጣቸዋል:: የሚላቸውን ካልሰሙትም ጉዳቸውን ያዝረክርክዋል፡፡ ጊዜ የለውም:: ነገ ሳይመሽ ርብቃን እጁ ማድረግ አለበት አለበለዚያ የሚመጣው አይታወቅም...
ናትናኤል ከአልጋው ግርጌ እንደቆመ የርብቃን መጨረሻ ሲያስብ ሊደርስባት የሚችለውን አደጋ ሲያሰላስል ትንፋሽ አጠረው፡፡

የነገዋ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ርብቃን እጁ ማግባት አለበት፡፡አለበለዚያ በግርግርታ አንድ ነገር ሲያደርጓት…. - በማታወቀው ምስጢር የመስዋዕት በግ ቢያደርጓት...እርሱ ነፍሰን ስለወደደ የገዛ ደህንነቱን ስለፈለገ ብቻ ቢያጠፏት ከዚያ ወዲያ ምን ሊሆን ህይወቱ?' ናትናኤል ሽጉጡን ጨምድዶ እንደያዘ በተከራዩት ክፍል ውስጥ ካሉት አልጋዎች በአንደኛው ጫፍ ላይ ቁጭ አለና ካልቨርትን ይጠባበቅ : ጀመር፡፡ የራሱ ጉዳይ! ካልተስማማ ትቶት ይሄዳል፡፡ ሊቃወመው ወይ ሊያቆመው ከሞከረ ግን…. የራሱ ጉዳይ! ሞት ነው የሚጠብቀው፡፡ . ናትናኤል የጨመደደውን ሽጉጥ ወደግራ እጁ አዙሮ በላብ የተጠመቀውን የቀኝ እጁን ሱሪው ላይ ሞዥቀና ሽጉጡን ጨሰጠ፡፡

ብዙም ሳይቆይ ካልቨርት ፎጣውን ትከሻው ላይ ጥሎ መንገድ ላይ
ለብሶት የቆየውን በአቧራና በላብ የተበከለ ሽርጥና ሸሚዝ በጥያፌ በሁለት
ጣቶቹ አንጠልጥሎ የተከራዩትን ክፍል በር ከፍቶ ሲገባ የገጠመውን ትርዒት ማመን አቃተው፡፡

“ካልቨርት ምርጫ የለኝም...
የማይሆን ነገር እንዳደርግ
አታስገድደኝ::'' አለ ናትናኤል ከተቀመጠበት¨ ሳይንቀሳቀስ የያዘውን ሽጉጥ ቀና እያደረገ፡፡

“ምንድነው የምትሰራው? ምን ልትሆን ነው?” አለ ካልቨርት የተሸከመውን ቆሻሻ ልብስ ወለሉ ላይ እየዘረገፈ፡፡

“ከአንተ ምንም እርዳታ አልፈልግም፡፡ ርብቃ ያለችበትን ሁኔታ እያወቅሁ በዝምታ መጠበቅ ግን አልችልም:: አዝናለሁ ካልቨርት… ሽጉጥሀን ስለሰረቅሁ፡፡ ግን ምርጫ ያለኝም:: ይሀንን ካላደረግሁ እስረኛሀ እንደምታደርገኝ ግልጽ ነው፡፡”

“ስማ!” አለ ካልቨርት በንዴት መንፈስ ወደፊት አንድ እርምጃ እየተራመደ።

“አ! አ" ናትናኤል የሽጉጠን አፈሙዝ ካልቨርት ላይ ደግኖ ተነስቶ ቆመ፡፡ “እንዳትጠጋኝ፡፡ ሞኝ ነገር አትፈጽም:: ክፉ ነገር መፈጸም አልፈልግም፡፡ ግን ምርጫ የለኝም... ካስገደድከኝ ደፍቼህ ነው የምወጣው፡፡”

ካልቨርት ተስፋ በመቁረጥ አልጋው ላይ ቁጭ አለና ፊቱን ሁለት መዳፎቹ ውስጥ ቀበረ፡፡

ናትናኤል የምትሰራው ጥፋት ነው... ከአሁን ወዲያ ምንም ልትረዳት አትችልም፡፡ እጃቸው ውስጥ ነች፡፡”

“አስፈራራቸዋለሁ! አንተ የምስራችን እንዳይነኩ እንዳስፈራራሃቸው
አስፈራራቸዋለሁ፡፡”

“እናስ ከዛስ?”
“ይለቋታላ! ”
“ሞኝ አትሁን፡፡ እርግጥ ይለቋት ይሆናል… ግን ከለቀቋት ወዲያ እንደ ወጥመድ ነው የሚጠቀሙባት ምክንያቱም ወይ ሰስልክ ወይ በአካል ልትገናኛት መሞከርህ አይቀርም፡፡ እትጠራጠር ይይዙሃል።”

“ከያዙኝ ይያዙኝ ዝም ብዬ ግን አልቀመጥም”
“ባይስማሙስ? ባይለቋትስ?”
“አወጣዋለሁ ምሥጢራቸውን፡፡”

ካልቨርት ቀና ብሎ በቁጣ ፊት ናትናኤልን ገላመጠው፡፡

“እታደርገውም… የምትጎዳው እነሱን አይደለም አፍሪካን ነው፡፡ ነገሮችን አስፍቶ የሚያይ ጭንቅላት ካለህ የምልህ ይገባሃል፡፡ የዚህን ዓይነት ጥፋት ስታጠፋ ደግሞ በዝምታ አልመለከትህም፡፡”

“ሽጉጡ ያለው በእኔ እጅ ነው፡፡”

“ተኩስ! ፈሪ!” ካልቨርት ከተቀመጠበት ተፈናጥሮ ተነሳ፡፡

“ተጠንቀቅ ካልቨርት ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይመለሳል ብለህ አታስብ እንደዛፍ ነው በቁምህ የምጥልህ፡፡” ናትናኤል ጥርሱን ነክሶ አፈጠጠ፡፡

የናትናኤልን አዝማሚያ ሲመለከት ካልቨርት ራሱን ነቀነቀና ተመልሶ አልጋው ላይ ተቀመጠ፡፡

“እና አሁን ምን ልታደርግ አሰብክ?” አለ ካልቨርት፡፡
“ጠዋት ስልክ ደውዬ እነግራቸዋለሁ፤ አስጠነቅቃቸዋለሁ፡፡ ከዚያ
ወዲያ የራሳቸው ምርጫ ነው፡፡”
“ናትናኤል እስቲ አስበው በቀላሉ ድምፃችንን ብናጠፋ ሁሉ ነገር
ጊዜውን ጠብቆ መድኃኒት ያገኛል እመነኝ ይለቋታል፡፡”

“ባይሳካስ ዕቅዱ ቢከሽፍስ? ጉዳቸውን ልመሰክር ለመደበቅ እንደሚገድሏት አታውቅም። ካልቨርት መፍጠን አለብኝ! አንድ ነገር ብትሆን ለራሴ ይቅርታ አላደርግለትም::"

“ናትናኤል ስሜትህ ያገባኛል… ምናልባት እኔም በአንተ ቦታ ብሆን ተመሳሳይ ስህተት ለመፈጸም እገፋፋ ይሆናል፡፡ ለምን እንዲህ አናደርግም..ጥፋት ማጥፋታችን ካልቀረ አንስተኛ ጥፋት ይሻላል፡፡” ካልቨርት ያሰበውን እቅድ ለናትናኤል በእርጋታ ተነተነለት፡፡

“አይሆንም! ይይዙናል፡፡”

“ይገባናል ሊይዙን ይችላሉ
እንዳልከው በስልክ ልታስፈራራቸው ብትሞክርም መያዝሀ አይቀርም፡፡ የእኔ መንገድ ይሻላል፡፡ሁልጊዜ የተሻለው አስተማማኙ መንገድ ይበልጥ አደገኛና ይበልጥ አስፈሪ! ይበልጥ አስደንጋጭ የሆነው ጤነኛ ሰው በጤነኛ አእምሮ
የማይመርጠው መንገድ ነው አትጠራጠር፡፡”

“ግን ቢይዙንስ?”
“አለቀልና! ምነው ፈራህ እንዴ?” ካልቨርት ፈገግ አለ፡፡ ««ቢያዙኝም ይያዙኝ አላልክም ዋናው ነገር ፍቅረኛህን ከመዳፋቸው ማውጣታችን የእነሱንም ዕቅድ እለማደናቅፋችን ነው... ለዚህ ደግሞ የተሻለው መንገድ የእኔ ነው:: ትስማማለህ?

ናትናኤል በዝምታ ማውጣትና ማውረድ ያዘ፡፡

“እትፍራ፡፡” አለ ካልቨርት ፈገግ ብሎ፡፡
“አልፈራሁም!” በስጨት አለ ናትናኤል፡፡
“እንግዲያው እንስማማ…” ካልቨርት ቀኝ እጁን ዘረጋለት
“እንተማመን ናትናኤል ደግሞ እሱን ሽጉጥ ዞር አድርገው:: ቢባርቅ
ሆዴን ነው የምትዘረግፈው::”
“ካልቨርት ልታታልለኝ ብትሞክር…” አለ ናትናኤል በጥርጣሬ ፊት ካልቨርት የዘረጋለትን እጁን እየተመለከተ፡፡ “ከአሁን በኋላ ሁለቴ ለማሰብ ጊዜ የለኝም:: አንዲት አጉል እንቅስቃሴ ካደረክ አጓጉል ነው የምትሆነው፡፡”

“ቃል እገባልሃለሁ፡፡”አለ ካልቨርት እጁን ወደፊት እንደዘረጋ፡፡

ናትናኤል ሽጉጡን ወደግራው አሻግሮ የተዘረጋውን የካልቨርትን እጅ በቀኙ ጨበጠው፡፡

“ጥሩ አሁን እቅዳችንን አንድ በአንድ ተንትነን እንነጋገርበት ካጠፋን አይቀር፡፡” አለ ካልቨርት ሁለት ወንበሮች አምጥቶ አንዱን ለናትናኤል አቀብሎት በሁለተኛው ላይ እየተፈናጠጠ፡፡

ፊት ለፊት ቁጭ ብለው በማግስቱ ስለሚፈፅሙት ተግባር አንድ በአንድ ተነጋገሩ ተመካከሩ ፤ ተከራከሩ፤ ተስማሙ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሰማዩ ጥርት ብሏል፡፡ ለጋዋ ፀሐይ ከእንቅልፏ እንደነቃች ሁሉ ከረጅሙ የክረምት ጨለማ በኋላ በሰማዩ ላይ ብቻዋን ትምነሸነሽበታለች:: አለፍ አለፍ እያሉ እንደ
👍1