#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
.....ናትናኤል ጊዜ ሳያጠፋ ታክሲ ተሣፍሮ ወደ ለገሃር ሄደ፡፡ ደጋግሞ ደውሎ ነበር ስልኩ የተነሳለት፡፡ቀደም ብሎ የመሥሪያ ቤቷ ጓደኛዋ ምህረትጋ ደወሎ ርብቃን አቅርቢልኝ ሲላት: እሁንም ወደ ስራ
ገበታዋ አለመመሰሏን ስትነግረው አለቅጥ ተጨነቀ፤ከራሱ ጋር ክርክር
ገጠመ፡፡ እንደታመመችና ቤቷ ደውሎ ከቻለም ሄዶ ቢያያት እንደሚሻል
ምህረት ስትነግረው መንፈሱ ሸፈተበት፡፡ ልቡ ላይ እንደጦር የተሸነቀረበት
ግን ሌላ ነበር
“በጣም አሟታል እንዴ?” አላት ምህረትን ቅንድቦቹን አጠጋግቶ፡፡ “ምንድነው በሽታዋ ማለቴ…”
“እንዴት ነው ነገሩ..ኣላወቅህም ማለት ነው? ወይስ…ናትናኤል ርብቃ'ኮ እርጉዝ ነች፡፡”
ድንገት እንደመሽ ሁሉ ጭልምልም አለበት ፤ ጭንቅላቱ እንደ ድንጋይ ከበደው፤ ማጅራቱን ጨምድዶ ያዘው፡፡ አንድ ቃል ብቻ ይደጋግም ጀመር “ፈጣሪዬ! . ፈጣሪዬ! ፈጣሪዬ! ስልኩን ከዘጋ በኋላ በቆመበት ተገትሮ ቀረ፡፡ እንደህፃን ልጅ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ፈለገ፡፡ “ርብቃ ... ርብቃ!” ራሱን መቆጣጠር ተሳነው “ገደል ይግባ!” ሁሉ ነገር ገደል ይግባ!” የሚንቀጠቀጥ እጁን ኪሱ ከቶ ከአንድ ቡና ቤት ገብቶ ተቀመጠ፡፡ ለሰዓታት ከራሱ ጋር ተወራጨ፡፡ በመጨረሻ ከቡና ቤቱ ወጥቶ የህዝብ ስልክ ይፈልግ ጀመር፡፡
ስልኩ ቢጠራም የሚያነሳው ሰው አልነበረም፡፡ በሚንቀጠቀጥ ቀኝ
እጁ የስልኩን እጀታ ጨምድዶ ይዞ ተጠባበቀ:: ርብቃ'ኮ እርጉዝ ነች ስልኩ
ይጠራል፤ የማያነሳ የለም፡፡ ቀጥታ እቤቷ ድረስ ብሄድስ? አሰበ፡፡ መሄድ የለብኝም:: እሷንም ቢሆን ለባሱ አደጋ ማጋለጥ ነው የሚሆነው፡፡ ደጋግሞ ደውሎ ነበር ስልኩ የተነሳለት
“ሀሎ” አለ ስልኩ እንደተነሳ ቀድሞ፡፡ ድምፅ ተጠባበቀ፡፡ ግን ምንም
አልነበረም:: መልሶ “ሃሎ አለ የሚንቀጠቀጥ ድምፁን ማረጋጋት
እየታገለ፡፡
“ናቲ..ናናቲ” ድምጿን ከመቅጽፅት ለየው፡፡ ቢሆንም በጣም የደከመ ድምጽ ነበር፡፡
“ርብቃ! ደህና ነሽ…?”
“ናቲ...ናቲ አቃጠሉኝ..ና…” .
“ናትናኤል ነኝ ርብቃ… ጮክ በይ አይሰማኝም፡: ርብቃ መሥሪያ
ቤትሽ ደውዬ ነበር፡፡ ርብቃ… እ?… አይሰማም፡፡” ድምጿ እየደከመበት ሄደ፡፡
ሌላ ሰው ስልኩን እንደተቀበላት ተረዳ፡፡
“ሀሎ፡፡” አለ ለስለስ ያለ የወንድ ድምፅ፡፡
“ሃሎ.… እባኮት ርብቃን ነበር፡፡”
“ማን ልበል? ” .
“ሀሎ..እባኮት ርብቃን ያቅርቡልኝ::” ናትናኤል ረጋ ብሎ ጠየቀ፡፡
“ይቅርታ፡፡ትንሽ አሟታል፡፡ በስልክ መቅረብ አትችልም::
የምነግርልዎት መልዕክት ካለ.….”
"እሷኑ ለማነጋገር ስለምፈልግ ነበር፡፡” ናትናኤል ጠንከር አለ፡፡
“ይቅርታ… ስትነጋገር ስለሚደክማት ነው፡፡ መልዕክት ካሎት ልንገርሎት፡፡ ታናሽ ወንድሟ ነኝ ብስራት ነኝ፡፡”
ናትናኤል ለማስታወስ ሞከረ፡፡ ቤተሰቦቿን ብዙም አልቀረባቸውም፤ ቢሆንም ከብስራት ጋር ከአንድ ሁለት ሦስት ጊዜ ተገናኝተዋል፡፡ ብስራት ገና ሃያ ዓመት ያልሞላው ወጣት ወንድሟ ነው::
“እንደምንዋልክ ብስራት፡፡ ናትናኤል ነኝ፤
ታስታውሰኛለህ? የርብቃ..እ… ”
“እዎ እዎ አስታውስሃለሁ፡፡ እንደምንድነህ? ደህና ነህ? ምነው
ጠፋህ? ርብቃ በጣም አስባለች፡፡ ለምን ብቅ አትልም? ”
“እ..” ናትናኤል አመነታ፡፡ “ምን መሰለህ ብስራት መምጣት እንኳን አልችልም፡፡ ግን እሷ እንዴት ነች?”
“አሟታል…በጣም ነው የታመመችው ሐኪም ቤት እያመላለስናት ነው::”
“ምን አሉ ሐኪሞቹ? ማለቴ ምንድነው?” ናትናኤል በልቡ የሚንቀዋለለውን ለመጠየቅ ጭንቅ አለው::
“አላወቁላትም፡፡ ግን ምግብ አይበላላትም፤ ስትበላም አይረጋላትም፡፡
ሰውነቷ ላይ ግን ችግር የለባትም፡፡ 'ጭንቀት ነው' ነው የሚሉት ሐኪሞች፡፡
ምን እንደሚያስጨንቃት ግን ሊገባን ኣልቻለም፡፡ በጣም ደክማለች::
ናትናኤል መጥተህ ብታያት ጥሩ ነበር:: በእንቅልፍ ልቧ ሁሉ ስምህን
ትጠራላች፤ ከቀን ወደቀን እየባሰባት ነው፡፡” ናትናኤል በረጅሙ ተነፈሰ፡፡ እጁን ግንባሩ ላይ ጫነ፡፡ ከራሱ ጋር ክርክር ገጠመ:: የፈለገው ይምጣ ሄዶ ያያታል፡፡ መቼም በቤቷ አካባቢ ሊያንዣብቡ ይችሉ ይሆናል፡፡ ግን ምርጫ የለውም:: ሹልክ ብሎ ገብቶ ሹልክ ብሎ ይወጣል ወሰነ::
“ብስራት መደወሌን ለማንም አትናገር ዛሬ ማታ መጥቼ አያታለሁ እሺ? ልክ ከምሽቱ አስራ ሁለት ተኩል ሲሆን ውጭ በሩጋ ጠብቀኝ” ናትናኤል ስልኩን ከዘጋ በኋላ በግራው ያንጠለጠለውን ትንሽ የሽራ
ሻንጣ ይዞ እዚያው ለገሃር ኣቅራቢያ ወዳለ አነስተኛ ቡና ቤት ተመልሶ ገባ፡፡
ጥግ ወዳለ ወንበር ሄዶ ሰውነቱን ለማርገብ፣ ለማረጋጋት በዝምታ
ተቀመጠ፡፡ በግራሶና ዘይት የተጨማለቀ ሰማያዊ ቱታ ለብሷል። ጭንቅላቱ
ላይ ያጠለቀው ዙሪያው እንደጠወለገ ቅጠል የተልፈሰፈሰው ባርኔጣ በግንባሩ
ላይ ኣዝምሞ ፊቱን ሸፍኖታል፡፡ ከደረት ኪሱ ሲጋራ አውጥቶ ከሚንቀጠቀጥ እጁ ጋር እየታገለ ከለኮሳት በኋላ ክብሪቱን እያጠፋ ሲጋራዋን ምጥጥ አደረጋት፡: “ርብቃ... ርብቃ.… ምነው አጠገብሽ መሆን ብችል!”
“ምን ልታዘዝ::” አለችው ሰማያዊ ሽርጥ ወገቧ ላይ ሸብ ያደረጎች አስተናጋጅ የለበሰውን ቆሻሻ ቱታ ስታይ ድምጿን ቆጥብን አድርጋ::
“ቡና፡፡” አላት ቀና ብሎ አያቷት የዋጠውን የሲጋራ ጭስ ቀረጁሙ እየለቀቀ፡፡
“ሂሣብ በቅድሚያ ነው የሚከፈለው፡፡” አለች ሁለት እጆቿን በጎንና ጎን የሽርጥ ክሶች ውስጥ እየወሸቀች፡፡
ከቀኝ ኪሱ ውስጥ ሣንቲሞች አውጥቶ ጠረጴዛው ላይ በተን እደረገላት፡፡ ሃሳቡ ግን ሌላ ቦታ ነበር፡፡ ርብቃ ለምን ደበቀችው? «ወይስ ወሯ ገና ነው ማለት ነው ሊሆን አይችልም:: ደብቃው ነው፡፡ ግን ለምን.… ለምን?
የሚወደው ገጿ መጥቶ ፊቱ ላይ ድቅን አለበት፡፡ ርብቃ'ኮ እርጉዝ ነች የምህረት ድምፅ እቃጨለበት፤ አሟታል ምግብ አይበላላትም ብትበላም አይረጋላትም “ጭንቀት ነው" ነው የሚሉት ሐኪሞቹ….
የብስራት ድምፅ ደወለበት...
“አምላከኔ ምን ዓይነት ጉድ ወስጥ ነው የከተትከኝ ኣለ እምላከ ከፊት ለፊቱ ባለ ወንበር ላይ የተቀመጠ ይመስል ፊት ለፊት አፍጥጦ፡፡
ምንድነው ሊያደርግ የሚችለው? ቀጥ ብሎ ፖሊስጋ ሄዶ እጁን መስጠት፡፡ ቢገሉትስ? ይግደሉት፡፡ ከዚህ በላይ ስቃይ መሸከም አይችልም ግን ለፖሊሶችስ ምን ሆንኩ ብሎ እጁን ይሰጣል? ሁሉን ነዋ!.. የሆነውን
ሁሉ ዘርዝሮ ማውጣት ነዋ! ግን ማን ያዳምጠዋል? ማን ያምነዋል? ፍጹም!
ፖሊስ ወጥመድ ነው! እጁን መስጠት ማለት ሞቱን ማፋጠን ማለት ነው፡፡
ለማን ይበጃል መሞቱ? ለርብቃ? ስልጁ? የአብርሃም መሞት ማንን ጠቀመ?
መረጋጋት ነው ያለበት፡፡ ካሁን ወዲያ ወደኋላ ማለት አይችልም፤ መረጋጋት
ነው ያለበት፡፡
ከቁጥጥር ውጭ በሚንቀጠቀጥ ቀኝ እጁ የያዛትን ያለቀች ሲጋራ ለመጨረሻ ጊዜ መጠጣትና ከፊት ለፊቱ ጠረጴዛ ላደ በተቀመጠው የሲጋራ መተርኮሻ ውስጥ ደፈጠጣት፡፡ መረጋጋት…. መረጋጋት ነው ያለበት...
የቡና ቤቱ አስተናጋጅ ያዘዛትን ቡና አምጥታ እፊቱ ደነቀረችለት::
አንስቶ ፉት ኣላው፡፡ ስኳር አልነበረውም:: ክፉኛ መረረው፡፡ ቢሆንም ስኳር
አልጠየቃትም፡፡ ድጋሚ ፉት ኣለው፡፡ ትኩስ ቡና በጉሮሮው አልፎ በሆዱ
ሲተራመስ ስንዝር በስንዝር ተከታትለው:: ሆዱ ጩርርርር ሲል ተሰማው:: ትላንት ምሳ የበላ ነው፡፡ ቢሆንም ምግብ አላሰኘውም:: ከቡናው ድጋሚ ፉት አለለት፡፡ ሰውነቱን ማዝናናት አለበት፤ ማረጋጋት አለበት፡፡በተቀመጠበት ወንበር ላይ በደኋላ ጋለል ብሎ ዓያኖቹን ጨፈናቸው፡፡ ቀኝ እጁ ከደረት ኪሱ ገብቶ ሲጋራና ክብሪት ይዞ ተመለሰ፡፡ ርብቃ ለምን ደበቀችው? በቃ በቃ... ስለርብቃ

👍2
ማስብ የለበትም:: አለበለዚያ ያብዳል!
አለበለዚያ አእምሮወን ይስታል፡፡
አእምሮውን ወደኋላ አጠንጥኖ የደረሰበትን ያጋጠመውን ድጋሚ መረመረው...
ከትላንት ወዲያ ማታ ዓይኑ ስር ከተፈጸመው ግድያ በኋላ
ሰውነቱን አረጋግቶ መቆየት አልቻለም:: አንዱ እንደቆሰለች ሚዳቆ ቅጠል
በተንኮሻኮሸና ወፍ በረረች ቁጥር መበርገግ ብቻ ሆነ::
“ሩጥ!” ስትለው አሁንም ጥርት ብሎ ይሰማዋል፡፡ “ሩጥ!” እንዴት እንደ ሮጠ ትዝ አይለውም፡፡ ወደ ዋናው የመኪና መንገድ ከገባም በኋላ ሩጫውን አልገታም ነበር፡፡ በመጨረሻ ፍርሃቱ ታግሶለት ሳይሆን ልቡ ልፍረስ ሲለው… አፉ ደም ደም ሲሰው ፥ ድካም ጎሮሮውን ይዞ ሊፈጠርቀው ሲጀምር! ጥጋት ይዞ ቆመና ቁና ቁና እየተነፈሰ አይኖቹን በጨለማው ውስጥ በመጣበት አቅጣጫ አፈጠጣቸው::
ሊያፍነው ቢሞክርም ከሚጨስ ሳንባው እየተጣደፈ በአፍ በአፍንጫው የሚሽቀዳደም የገዛ ትንፋሹ ድምፅ አስጋው፡፡ ከወዲያ ማዶ ትንፋሹን ሰምተው እንዳይመጡ የፈራ ይመስል እጁን አፉ ላይ ጭኖ ቆመ፡፡
ድምፅ የለም፡፡ ዘግይቶ ነበር እርቆ መሄዱንና ዙሪያውም ማንም እንደሌለ የተረዳው ነፍሱ መለስ ያለችለት፡፡ ሲፈራ ሲቸር ከተደበቀበት ጥጋት እየተገላመጠ ወጥቶ በመኪና መንገዱ ጥግ ጥግ እየተራመደ ራቅ ብለው ወደሚታዩ የመሸታ ቤቶች ኣመራ፡፡ በዚያ ሰዓት ርቆ ለመሄድ መሞከር እንዴሌለበት ተረድቷል፡፡ እዚሁ አፍንጫቸው ስር ነው መደበቅ ያለብኝ ብሎ አሰበ፡፡ እይጠረጥሩኝም። እዚሁ ይቆያል ብለው አይገምቱም፡፡አለበለዚያ ርቄ ለመሄድ ከሞከርኩ ወዲህ ወዲያ ስል ያገኙኛል፡፡ ቶሎ አንድ ቦታ ይዤ መርጋት አለብኝ! እመሃላቸው ቢሆንም ማድፈጥ መቻል
አለብኝ፡፡
ትዝ ይለዋል… “እባክሽ የእኔ እህት አልጋ አለ? ” አላት ወደ አንድ አነስተኛ ሆቴል ገባ ብሎ፡፡
ሴትየዋ መልስ ሳትሰጠው አይኖቿን ኣፍ፡ጥጣ መላ ሰውነቱን ትመለከተው ጀመር፡ ጎንበስ ብሎ የገዛ ሰውነቱን ሲመለከት በረገገ፡፡ ከፊት ለፊት ነጭ ሸሚዙ እጆቹ፣ . ክንዱ ሁሉ በደም ተበክሏል፡፡ ለራሱ
እስኪያስደነግጠው ድረስ ክፉኛ በደም ተጨማልቋል፡፡
እ.. ሰዎች ተደባድበው ስገላግል ነው:: እ…አልጋ አላችሁ?”
መልስ ሳትሰጠው ጭንቅላቷን ብቻ ነቀነቀችበት:: ፊቷ ላይ የሚንቀዋለሰውን ያልተቆነጠጠ ፍርሃት ሲመለከት ተስፋ ቆረጠ.. ሌሊቱን ቆሞ ሲያድር አልጋ እንደማታከራየው ገባው:: ለእርዳታ ሳትጮኽ ኡ! ኡ! ብላ ሳታስይዘው ቶሎ ብሎ ወጣና በፍጥነት በጨለማው ውስጥ ተሰወረ::
ድጋሚ ሌላ ሆቴል ከመግባቱ በፊት የኮቱን ቁልፍ ግጥም አድርጎ
ቆልፎ፣ ኮሌታውን ቀልብሶ እጆቹን ከሱሪው ኪስ ውስጥ ወሽቃቸው:: ወደ
ሆቴሉ ሲገባ የፊተኛው አዳራሽ ባዶ ነበር፡፡ ደንበኞች ወጥተው የአዳራሹን
መስኮቶች የምትዘጋጋ አስተናጋጅ ተመለከተ፡፡ፈገግታ አስቀደመና ኣልጋ
ጠየቃት::
“ስድስት ብር፡፡” አለች ስታየው ኮስተርተር ብላ መስኮቶቹን መዘጋጋቷን ሳታቋርጥ፡፡
በደም የተጨማለቁ እጆቹን ከሱሪው - ኪስ ውስጥ እንዴት እንደሚያወጣ ግራ ተጋባ፡፡ በአዳራሹ ውስጥ ያለው ብርሃን ደብዛዛ ቢሆንም እጆቹ የተነከሩበትን ደም ሳትመለከት ልጅቱ የሚሰማት ስሜት አልጋ እንደሚያስከለክለው እርግጠኛ ነበር፡፡
“መጀመሪያ ክፍሉን ልየዋ፡፡” አላት በተቻለው ራሱን ለመግዛት
እየጣረ::
'ተከተለኝ ለማለት ጭንቅላቷን መታ አደረገችና ፊቷን መልሳ ወደ ጓዳ ገባች፡፡ ተከተላት:: ከሚከራየት ክፍል ሲደርሱ በሩን ከፍታ፣ መብራቱን አብርታ ፈቀቅ አለችለት፡፡ ወደ ክፍሉ ገባና ቀልጠፍ ብሎ መብራቱን አጠፋው:: ወዲያው የገንዘብ ቦርሳውን አውጥቶ ከመተላለፊያው በሚመጣው ስስ ብርሃን የአስር ብር ኖት አውጥቶ ሰጣት፡፡
“መልሱን ያዥው እ… መታጠቢያ ቤት ይኖራል?”
ያው!” አለች ከአስር ብሩ የሚመላሶው አራት ብር የእርሷ መሆኑን ስታውቅ ፈገግ ብላ፡፡
መታጠቢያ ቤት ገብቶ በደም የተበከላ ልብሱንና ሰውነቱን አጣጥቦ ወደተከራየ ክፍል ተመለሰ፡፡ አልጋው ላይ በጀርባው ተንጋሎ አይኖቹን ከደነ፡፡ እንቅልፍ ግን አልጎበኘውም፡፡ ሰውነቱ ሊረጋጋለት አልቻለም፡፡
ምንድነው ነገሩ የተዘበራረቀበትን ሁኔታ ትርጉም ሊሰጠው ተጣጣረ:: ሴትዮዋ ከየት መጣች? ሰካራሟ ማነች? ያለጥርጥር የካልቨርትን አድራሻ ትፈልጋለች፡፡ ለዚህም ነው የምሥራችን የገደለቻት:: ግን እሱን ለምን ተወችው? ሠውነቱው በቻ ሳይሆን ሕይወቱን ለማትረፍ የሌላ ስው ሕይወት ለምን አጠፋች? እሷ ማነች? በአውሬው ውስጥ ለውስጥ አለመግባባትና መከፋፈል አለ ማለት ነው? አንደኛው ወገን ሊያጠፋው
ሲፈልግ የተቀረው ወገን ሞቱን አይሻም ማለት ነው? ግን ለምን? የእርሱ
መኖር ማንን ይጠቅማል? እንዴት? የምሥራች መሞትስ ምን ይጨምራል?
ሴትየዋ ማነች? ሰውየውስ? ሰውየው በምሥራች ሞት ለምን ተደናገጠ?
እርሱንስ ለምን ሊገለው ሞከረ? ሴትየዋ ከጀርባው ባትቀድመው ጨርሶት
ነበር'ኮ!”
የምሥራችን ሳይሆን የእርሱን መጥፋትና መሞት የሚሻ ወገን አሉ ማለት ነወ፡፡ ያለ ጥርጥር ይህኛው ወገን ነው ከብርሃምን የገደለው:: ግን እነማን ናቸው? ምንድነው የሚፈልጉት? ግልፅ ነው:: ሁሉም የሚፈልጉት ካልቨርትን ነው፡፡ የካልቨርትን አድራሻ የምታውቅ የምሥራች ብቻ ነበረች፡፡ ሊያስፈራራት ቢላውን ሲያወጣባት ምንድን ነበር ያላችው የምሥራች?'
“አትነካኝም! ጫፌን ብትነካኝ ዮሴፍ ምን እንደሚያደርግ ታውቃላችሁ! ያወጣዋል ምሥጢራችሁን ያውጣዋል! "
አዎ…እንደጠረጠረው ካልቨርት ይዞት የተሸሸገው ምሥጢር ኣለ፡፡አውሬው የምሥጢሩን መጠበቅ ለማረጋገጥ ሲል ካልቨርትን እጁ ማስገባት ቢፈልግም የምሥራችን ለመተናኮል ያልደፈረው ካልቨርት ምሥጢሩን በይፋ ለማውጣት እንዳይሰቀለው በመፍራት መሆን አለበት፡፡ አወሬው የካልቨርት አባራሪ ይምሰል እንጅ እስረኛውም ነው፡፡ ምክንያቱም ካልቨርት የአውሬውን ምሥጢር በመዳፉ አድርጓል፡፡ የአብርሃም አደራ ታወሰው
«ካልቨርትን አግኝ... ካልቨርትን» አብርሃም ትክክል ነው፡፡ ቁልፉ ያለው
ከዚያ ነው፡፡ ካልቨርት የያዘውን ምሥጢር በጁ ያገባ ሁሉ የአውሬኑን እፍንጫ መሰነግ ይችላል፡፡ ግን ምንድነው ምሥጢሩ? የት ነው ካልቨርት...?
የምሥራች ነበረች ኣድራሻውን የምታውቅ፡፡ ሞታለች፡፡ ሌላ ማን አለ? እርሱ ራሱ ! ነግራዋለች፡፡ አዎ… የካልቨርትን ኣድራሻ ነግራዋለች፡፡ እሱ ብቻ ነው የካልቨርትን አድራሻ የሚያውቅ
“እ…እማዬጋ..ድራዳዋ::"
እማዬጋ... ድሬዳዋ.. የት ናቸው እማዬ? እናቷ? ድሬዳዋ ድሬዳዋ የት?
ናትናኤል በተከራየው የሆቴል ክፍል ወስጥ በጀርባወ አልጋው ላይ እንደተንጋለሉ ዓይኖቹን ኮርኒሱ ላይ ተክሎ ቀረ፡፡
በድሬዳዋ እየተዘዋወረ “የምሥራች እናት እያለ አይፈልግ! ስማቸውን እንኳን አያውቅም፡፡ የምሥራች ይልማ:: እርግጥ የምሥራችን አባት ስም ያውቃል አቶ ይልማ... አስር አለቃ ይልማ ቄስ ይልማ
ፈጣሪ ይወቅ! አባቷን ካገኘ ግን እናቷን አገኘ ማለት ነው:: አብረው አይኖሩ
እንደሆንስ? ቢሆንም የእናቷን አድራሻ ሳያውቁ አይቀሩም ግን አባቷንስ ቢሆን “አቶ ይልማ” እያለ በድሬዳዋ ከተማ ቢዞር አባቷን እንዴት ማግኘት ይችላል? የአባታቸውን ስም ቢያውቅ ጥሩ ነበር፡፡ ያንን እንኳን ማግኘት ይችላል፡፡ እ… ተመልሶ ወደ ሆቴሏ ሄዶ የንግድ ፈቃዷ ላይ ማንበብ ይችላል፡፡ የአባቷና የአያቷ ስም ይኖራል፡፡ ግን ከአሁን ወዲያ ወደዚያ
አቅሪቢያ መሄድ በገዛ እጁ መንጠልጠል ነው:: ሰው ቢልክስ? ማንን?
አንዱን የሠፈር ስራፈት ጎረምሳ አምስት ብር ቢያሳየው ሄዶ ያነብለታል
በዚህ ከደገኛ ሰዓት የላከው ወጣት የንግድ ፈቃዷን ተጠግቶ ፊደል ሲቆጥር
“ምንድነው የምትሰራው?” ብለው

👍1
ቢይዘትስ? . “ምራ” ቢሉትስ?
አስከትሏቸው ከተፍ ቢልስ? አ! አ! አ አይሆንም፡፡ ሌላ ምርጫ መኖር
አለበት፡፡ የንግድ ፈቃድ ግብር... አገር ውስጥ ገቢ... አዎ እዚያም የአያቷ
ስም ይኖራል፡፡ ግን አገር ውስጥ ገቢ የሚያውቀውና ፋይሏን አውጥቶ
የሚያይለት ወይ የሚያሳየው የለውም፡፡ ሂዶ ፋይሏን ቢጠይቅ ደግሞ
ጥርጣሬ መፍጠር ነው:: “ለምን ፈለግኸው? ምንድነህ አንተ?” ቢሉት ምን ሊመልስ? አ! አ! አይሆንም፡፡ ሌላ ምርጫ ሌላ መፍጠን ኣለበት!
መቅደም አለበት! ቶሎ ወዴ ድሬዳዋ ቶሎ ወደ ካልቨርት... ቶሎ ወደ ምሥጢሩ… ቶሎ ቶሎ ! የአባቷ ሙሉ ስም ማነው? ይልማ... ይልማ ማን?........
💫ይቀጥላል💫

#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....ዴሪክ ዊሊያምስ ከሀይ ሆፕ ካፌው ወጥቶ ስምንት ብሎክ ወደሚቀርበው ሴንተሊና ውስጥ ወደሚገኘው ቢሮው ለመሄድ መኪናውን ሲያሽከረክር ከጠዋቱ አራት ሰዓት አልፎ ነበር። ቢሮው 12 ጫማ በ 8 ጫማ ስፋት ያለው ሆኖ መስኮት አልባ ነው፡፡ ነገር ግን ኪራዩ በጣም ርካሽ ስለሆነ እና የዋይፋይ ኢንተርኔቱ ጥሩ ስለሆነ ቢሮው ተስማምቶታል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ከፎቁ ሥር የሚገኙት ወዳጆቹ የብረት ጎማ ስላላቸው ደምበኞቹ አስቸጋሪ በሚሆኑበት ጊዜ አስፈላጊውን እገዛ ያደርጉለታል፡፡
የአሁኗ ደንበኛው ያን ያክል አስቸጋሪ አይደለችም፡፡ ለሦስት ሰዓታት ያህል ቁጭ ብላ ስታወራው ዴሪክ ሦስት ነገሮች ለመገንዘብ ችሏል፡፡
የመጀመሪያው ነጥብ በትክክል እጁ ላይ ያለውን ካርዶችን በአግባቡ የሚጫወትበት ከሆነ በሥራው በጣም ብዙ ገንዘብ ያገኝበታል፡፡
ሁለተኛው ነገር ደግሞ ዕድሉ ከሆነ እና ከተሳካለት የድሮ ጠላቶቹ የሆኑትን የሎስ አንጀለስ ፖሊስ ዲፓርትመንት መበቀል ያስችለዋል::
ሦስተኛው ነገር ደግሞ ይሄ ጉዳይ ራሱን አደጋ ውስጥ ሊከተው የሚችል ነገር መሆኑ ነው።
ከሦስቱ ጉዳዩች በዋነኝነት የሳበው ነገር ቢኖር የሦስተኛው ጉዳይ ነው:: በጣም ከረዥም ጊዜ በኋላ ራሱ ላይ አደጋን የሚፈጥር ጉዳይ ሊገጥመው ነው። ትዳር ከመመስረቱ በፊት እንደዚህ ያሉ አደገኛ ጉዳዮች ላይ ነበር ይሰራ የነበረው። እናም ዛሬ ዶክተር ኒኪ ሮበርትስ
ጉዳይዋን እንዲመረምርላት ስታናግረው የድሮው ማንነቱን ምን ያህል እንደናፈቀው
ነበር የተረዳው።
ማታ ላይ የጠጣው መጠጥ እና ጠዋት ላይ የበላው ቁርስ ሆዱ ውስጥ ቁጭ ስላለበት፣ እንዲፈጭለት ሁለት የአልካ ሲልትዘርን በትልቅ ብርጭቆ ውስጥ በሚገኝ የቧምቧ ውሃ ላይ ጨምሮ ጭልጥ አድርጎ ጠጣው። ከዴስኩ
ውስጥም የድሮ የማስታዋሻ ደብተር አውጥቶ መፃፍ ጀመረ፡፡ እንደ
ሁልጊዜም ሁሉ ሠረዝ ሠረዝ እያደረገ ከማንኛውም ደምበኛው የመጀመሪያ
ስብሰባ ካደረገ በኋላ በዚህ መልኩ ይፅፋል።
ወዲያውንም ገፆችን እየሞላ ማስታወሻውን መያዝ ጀመረ።
ኒኪ ሮበርትስ የምታስገርም ሴት ናት። በተለይ ደግሞ ለፖሊሶች ያልነገራቻቸውን ሚስጥሮቿን ለእሱ መንገሯ ጉዳይዋን ከፖሊሶቹ ቀድሞ ሊቋጭላት ያስችለዋል። እሷ እንዲፈታላት የፈለገችውን ነገር ለሁለት ከፍሎ ምርመራ መጀመሩ
ገቢውን ስለሚጨምርለት የተደራደራት። እሷም በእሱ ሀሳብ ሙሉ በሙሉ ተስማምታ ሌሎች ሰዎችን
በዚህ መልኩ ነበር ከሚያስከፍለው በእጥፍ ሂሳብ ሲጠይቃት ጭምር ያለማንገራገር ለዚያውም ከነ ቦነሱ ነበር ቼክ የፃፈችለት።
“ባልሽ ከትዳር ውጪ ስላለው የፍቅር ግንኙነት ለማወቅ ትፈልጊያለሽ አይደል? ማለትም ሴትየዋ ማን እንደሆነች፣ እንዴት እንደተገናኙ እና ከእሷ ጋር የተያያዙትን ነገሮች ሁሉ ማወቅ እፈልጋለሁ ብለሻል?” ብሎ ጠየቃት።
“ልክ ነው” ብላ መለሰችለት ኒኪ
“መልካም እሱ የመጀመሪያው ጉዳይሽ ነው። ሌላኛው ደግሞ ግድያዎቹን
በተመለከተ እና አንቺ ላይ የግድያ ማስፈራሪያ እየተደረገብሽ ስላለ ጉዳይ
ነው። ከእነዚህ ግድያዎች በስተጀርባ ያለውን ሰው ልታውቂ ትፈልጊያለሽ።
ይሄ ደግሞ እኔ የኤል.ኤ.ፒ.ዲ ሥራን እንድሠራላቸው ትፈልጊያለሽ ማለት
ነው?”
“በትክክል”
“ይሄ ደግሞ ሁለተኛው ጉዳይሽ ነው” ብሎ ለእያንዳንዱ ጉዳዮቿ ዋጋ አውጥቶ ሲጠይቃት ኒኪ የወር ወጪውን በእጥፍ ዋጋ ነበር ቼኳ ላይ ፅፋ የሰጠችው። በዚህም የተነሳ ይህቺን ሴት በእውነቱ ሳይወዳት አይቀርም፡፡
ቢሮው ገብቶ ስለ ሁለቱ ጉዳዮች ሲያስብ የመጀመሪያው ባሏ ውሽማ ጉዳይ ገንዘብን የሚያልብበት ጉዳዩ እንደ ሆነ ገባው:: ምክንያቱም የኤል.ኤፒዲ ፖሊሶች ስለ ዶውግ ውሽማ ማንነት የሚያጣሩበት አንድም ምክንያት የላቸውም እና እሱ ጉዳዩን እስከፈለገው ጊዜ ድረስ በመጎተት የማያቋርጥ የገቢ ምንጩ ማድረግ ይችላል። በምዕራባዊ ሎስ አንጀለስ ውስጥ በዝሙት ዙሪያ ያሉ ጉዳዮች በሙሉ በጣም ምርጥ የገቢ ምንጭ የሚያስገኙለት ጉዳዮቹ ናቸው እና አምላኩን ያመሰግናል።
በግድያዎቹ ዙሪያ ላይ የሚያደርገው የግል ምርመራ ግን ያን ያህል የብዙ ጊዜው አስተማማኝ የገቢ ምንጩ ላይሆን ይችላል። ምክንያቱም
ምናልባት ይህንን ወር እንኳን ሳይጨርስ ኤል.ኤ.ፒ.ዲ የሊዛ ፍላንገን እና
የትሬቨን ሬይሞንድን ገዳዮችን ይዘው ለፍርድ ማቅረብ ይችላሉ። ምናልባት
ፖሊሶቹ በፍጥነት ጉዳዩን እንዳይቋጩ የሚያደርጋቸው ነገሮች ቢኖሩ
ዶክተሯን በመኪና ገጭቶ ሊያመልጥ የሞከረውን ገዳይ መከታተል ችላ
ማለታቸው አንደኛው ነው፡፡ ሁለተኛው ነገር ደግሞ ኒኪ በፖሊሶቹ ላይ
ሙሉ እምነት ስለሌላቸው የግድያ ማስፈራሪያ የኢ-ሜይል መልዕክቷን
እንኳን አምጥታ ለእሱ (ላዊሊያምስ) ማስረከቧ ነው።
ይሄ ደግሞ ሌላ ምርጥ ምልክት ነው፡፡ በጣም ብዙ መረጃዎችን በጉዳዩ
ዙሪያ መሰብሰብ እስከቻለ ድረስ ከኤል.ኤ.ፒ.ዲ ቀድሞ ምርመራውን በድል ማጠናቀቅ የሚችልበትን ዕድል ይፈጥርለታል፡፡
ከባሏ ውሽማ ይልቅ የሊዛ እና የትሬይ ግድያዎች ጉዳይ እሱን በደንብ የሳበው ሌላኛው ነገር ነው:: እንደ ሁሉም የሎስ አንጀለስ ነዋሪ ሁሉ ዴሪክም ቢሆን የግድያዎቹን ዜናዎች በደንብ ይከታተል ነበር፡፡ የኒኪ ሮበርትስ ታካሚ የሆነችው ቆንጆዋ ሞዴል ሊዛ ፍላንገን በአሰቃቂ ሁኔታ ሰውነቷ ተቆራርጦ እና ልቧ ላይ በጩቤ ተወግታ ህይወቷ አልፏል። ሊዛ
ትሬይ ሊዛ አፍሪካ አሜሪካዊው
ከተገደለች ከሦስት ቀናት በኋላም
በተገደለችበት በተመሳሳይ ሁኔታ ለመገደል በቅቷል። በመጀመሪያ ላይ በሊዛ ጥፍር ውስጥ የተገኘው የሞተ ሰው ህዋስን በማስመልከት ዞምቢው ነፍሰ ገዳይ በሚል ርዕስ በየማህበራዊ ገፆች ላይ ሲሰራጭ የነበረው ዜና
በመጨረሻ ላይም በዋነኛ የሚዲያ ተቋማት ላይ በዜና መልክ ቀርቦም
ተመልክቶታል፡፡ ሰዎች በእውነተኛው ዓለም ላይ እንደዚህ አይነት ነገር አለ
ብለው ማመናቸውን በወቅቱ ዴሪክን አስቆት ነበር፡፡ ያም ቢሆን ግን እስከ
አሁን ድረስ ጉዳዩን አወሳስቦታል።
“እና እስከ አሁን ድረስ ኤል.ኤ.ፒ.ዲ በግድያው ጠርጥሮ የያዘው አንድም
ሰው የለማ?” ብሎ ዴሪክ ኒኪን ጠየቋት ነበር፡፡
“እስከ አሁን ድረስ የለም። እንዲያውም አንደኛው ጆንሰን የተባለው መርማሪ ፖሊስ እኔን እንደ ገዳይ ሁሉ ይጠረጥረኛል፡፡ ባገኘኝ እና ባወራኝ
ቁጥርም እኔን የሚያወራኝ ልክ እንደ ወንጀለኛ ነው::”
“ይሄንን ባያደርግ አይገርመኝም፡፡ ሁሉም ፖሊሶች ባለጌዎች ናቸው፡፡” ብሎ ዴሪክ መለሰላት፡፡
“ሁሉም እንኳን አይደሉም ብላ ኒኪ አሰበች፡፡ ይህን ሀሳቧን ግን ለዊሊያምስ አልነገረችውም። በመቀጠልም ዊሊያምስን ያስገረመ አንድ ነገር
እንደደበቀቻቸው ነገረችው።
“ብራንዶን ግሮልሽ የሚባል ልጅ አውቅ እንደሆነ ጠይቀውኝ ነበር። ነገር
ግን አላውቅም ብዬ ነው የመለስኩላቸው፡፡ ልጁን አውቀው ነበር። ባለቤቱ እኔ ህክምና እንዳደርግለት ወደ እኔ ቢሮ ይዞት መጥቶ ነበር::”
“ለምንድነው ስለ እዚህ ልጅ የጠየቁሽ? አንቺስ ለምን ዋሸሻቸው?” ብሎ
ዊሊያምስ ጠየቃት፡፡
ኒኪም ትከሻዋን ሰበቀች እና “ለምን እንደጠየቁኝ አላውቅም። ምናልባት
ግን ልጁ ከግድያዎች ጋር የተያያዘ ነገር አለው ብለው እንደሚያስቡ ገምቻለሁ። ይሄውልህ ይሄ ብራንዶን የተባለ ልጅ እንደዚህ አይነት ነገርን የማድረግ አቅም የለውም፡፡ ልጁ በጣም ጨዋ እና መልካም ልጅ ነበር::" ብላ ፈገግ በማለት
አሁን ላይ ሳስበው ግን ልጁን አላውቀውም ብዬ የዋሸሁለት ከእነርሱ
ልከላከለው አስቤ ይመስለኛል”
“ፖሊሶቹ መዋሸትሽን ቢደርሱበት መረጃን በመደበቅ

👍7
በሚል ወንጀል ሊከሱሽ እንደሚችሉ ታውቂያለሽ?” ብሎ ተኮሳትሮ ጠየቃት፡፡
“አውቃለው ግን ደንታ የለኝም” ብላ ኒኪ ኮስተር ብላ መልሳለት በመቀጠልም
“ምን መሰለህ እውነታው ሚ/ር ዊሊያምስ? ፖሊሶቹን አላምናቸውም”
አለችው። ይህንን ከእሷ የሰማው ዴሪክ ዊሊያምስም ተነስቶ ቢጨብጣት እና
እኔም አላምናቸውም ቢላት ደስ ባለው ነበር፡፡
“እኔን ግን ታምኚኛለሽ አይደል?” ፈገግ ብሎ ጠየቃት፡፡
“ባላምንብህ ለምን ብዬ ነው የጠየቅከውን ሳልከራከርህ የምከፍልህ” ብላ ኒኪ በፈገግታ መለሰችለት፡፡
“ልክ ነሽ” ብሎ ዊሊያምስ ፈገግ አለ እና “እሺ ይሄንን ብራንዶን የተባለ ልጅን ለመጨረሻ ጊዜ ያገኘሺው መቼ ነው?” ብሎ ጠየቃት፡፡
“ሁ ረዥም ጊዜ አልፎታል ካገኘሁት፡፡ ዓመት አይሆነውም ብለህ ነው? አዎን ከቦስተን ደውሎልኝ ነበር፡፡ አደንዛዥ ዕፅን በድጋሚ መጠቀም ጀምሮ ነበር። በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ነበር ወደ እኔ የደወለው” ብላ ኒኪ መለሰችለት፡፡
“ብራንዶን ሞቷል ብለሽ ታስቢያለሽ?” ብሎ ዊሊያምስ ጠየቃት፡፡
ኒኪም ትከሻዋን ከሰበቀች በኋላ “ሊሞት ይችላል። ግን ስለ እሱ እርግጠኛ ሆኜ ልነግርህ አልችልም”
“እሺ አሁን ደግሞ በግድያው ዙሪያ ላይ ምርመራውን ስለሚያደርጉት
ፖሊሶች ንገሪኝ እስቲ?” አላት፡፡
ኒኪ በረዥሙ አየር ስባ ከተቀመጠች በኋላ መርማሪ ፖሊስ ሚክ ጆንስን ለእሷ ጥሩ አመለካከት እንደሌለው እና እሷንም እንደወንጀለኛ እየቆጠራት እንደሆነ ከነገረችው በኋላ “ባይገርምህ እኔን ገጭቶ ለማምለጥ ሙከራ ስላደረገው ላንድክሩዘር መኪና እና ስላዳነኝ ቀዩ የስፖርት መኪና ሹፌር ሁሉ ፈጥሬ እያወራሁት እንዳለ አምኖ ነው በቁጣ እየወነጀለ ያወራኝ፡፡ ባልደረባው መርማሪ ፖሊስ ሉው ጉድማን ግን ምክንያታዊ ሰው ይመስለኛል” ብላ የጉድማንን ስም ስትጠራ የኒኪ ፊት በፈገግታ ሲፈካ ዴሪክ
ዊሊያምስ ተመለከተ፡፡ “ብቻ እሱ ይለያል” አለችው፡፡
“እሱ በምን መልኩ ነው ይለያል ብለሽ ለመናገር የቻልሽው?”
“እያንዳንዱ ነገሩ። ትሁት ነው፤ ጠንካራ ሠራተኛ ነው፤ የተማረ እና ግልፅ ነገር ነው” ብላ ኒኪ መለሰችላት። እንደዚህ ሆኖም ግን እኮ የምርመራ ጉዳያቸውን ከጫፍ አላደረሰም” ብሎ ዊሊያምስ አሳሰባት፡፡
“ይሆናል” ብላ ኒኪ ቅር እያላት ዊሊያምስ ባነሳው ሀሳብ ተስማማች እና “እርግጥ ነው መዘግየት ይታይበታል፡፡ እሱ እንደነገረኝ ከሆነ ሊዛ ፍላንገን ሊገድል የመጣው ነፍሰ ገዳይ በስህተት እኔን መስላው ነው ሊገድላት የቻለው። ምክንያቱም በወቅቱ እሷ የእኔን የዝናብ ኮት አድርጋ ነበር። ምንም እንኳን እንደ እሷ በጣም ቆንጆ ባልሆንም ቁመታችን
ተመሳሳይ ስለነበረ ነፍሰ ገዳዩ እኔኸ መስዬው እሷን እንደገደላት ግምቱን
አስቀምጦልኛል።”
“ሊያስኬድ ይችላል” ብሎም ዴሪክፀ ዊሊያምስ መለሰላት።
በመቀጠልም ኒኪ ከመኝታ ክፍሏ ውስጥ ስለተሰረቀው ፎቶግራፍ ነገረችው። አስከትላም ጥቁር ላንድሮቨር ገጭቶ ሊገድላት ሞክሮ እንዳመለጠ እንዲሁም ደግሞ ኢ ሜይል የተላከላትን የግድያ ማስፈራሪያ ኮፒ ሰጠችው።
ዴሪክ ዊሊያምስ ጆንሰን የተባለው መርማሪ ፖሊስ እሷ ላይ በደረሱ ነገሮች
ላይ ለምን አትኩሮት እንዳልሰጠበት ሊገባው አልቻለም። በተለይ ደግሞ
የተደረገባትን የግድያ ሙከራ እና ምርመራ የሚያደርግበትን ሁለት የግድያ
ጉዳዮችን ለምን ማያያዝ እንዳልፈለገ ግልፅ ሊሆንለት አልቻለም። ምናልባት
ባልደረባው ጉድማን የማያውቀው ነገርን ጆንሰን ያውቅ ይሆን እንዴ? እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎቹን በማስታወሻ ደብተሩ ላይ ከትቦ አስቀመጠ።
በመቀጠልም ኒኪ ዋነኛ ጉዳይ ነው ብላ ያሰበችውን የባሏን ውሽማ (ጣውንቷን) ጉዳይ መናገር ስትጀምር በጥሞና ማዳመጥ ጀመረ::
ኒኪ ስለ ጣውንቷ እየነገረችው ያለችው ነገር ሆድ የሚቆርጥ ቢሆንም እሱ ግን እሷ አንድ የደበቀችኝ ነገር አለ ብሎ ስላመነ ሆዱን ሊቆርጠው አልቻለም። አልያም ደግሞ ኒኪ ስለ ነገሩ ብዙ አታውቅም ብሎ እያሰበ ነበር
ሲያዳምጣት የነበረው።
ኒኪ እንደነገረችው ከሆነ ስለ ባሏ እና ስለ ጣውንቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማወቅ የበቃችው ባሏ 405ኛው ጎዳና ላይ የመኪና አደጋ ደርሶበት ከተደወለላት በኋላ ነበር። እዚያም ስትደርስ ባሏ ዶውግ መኪናው ውስጥ ብቻውን እንዳልነበር ተረዳች።
“አብራው ያለችውን ሴት አውቃት እንደሆነ ጠየቁኝ፡፡ እኔም ሴትየዋን ማን እንደሆነች እንደማላውቅ መለስኩላቸው። በወቅቱ እኔ ያሰብኩት እሷ ታካሚው ወይንም ደግሞ የሥራ ባልደረባው ሆና ምናልባት በአጋጣሚ ሊፍት የሰጣት ሴት አድርጌ ነበር ያሰብኳት። ከጥቂት ቀናት ኋላ ግን
እውነቱን ለማወቅ በቃሁ። ጉዳዩን የሰማሁት ሁለት ፖሊሶች ሲያወሩ
በነበሩበት ጊዜ ላይ ነበር። ዶውግ ይሰራበት የነበረ ሆስፒታል ውስጥ
ከዶውግ ጋር አብረው የሚሠሩ ሰዎችን በሚጠይቁባት ጊዜ ሴትየዋ የዶውግ
ፍቅረኛ እንደሆነች ተናገሩ። ጉዳዩን ስሰማ መጀመሪያ አላመንኩኝም ነበር፡፡
ደግሞም እስከ አሁን ነገሩ ምንም አይነት ስሜት ሳይሰጠኝ ነው የቆየብኝ።
ለማንኛውም በጉዳዩ ዙሪያ ጓደኛውን ሀዶንን ስጠይቀው ግን የሰማሁት ነገር
እውነት እንደሆነ አመነልኝ። በጣም ነበር ልቤ የተሰበረው። ስለ ጉዳዩ
በዝርዝር እንዲነግረኝ ሀዶንን ብለምነውም ከዚህ በላይ ምንም እንደማያውቅ መለሰልኝ።” አለችው ኒኪ፡፡
“እና አመንሽው?”
“አንተ በእኔ ቦታ ብትሆን ታምነው ነበር?” ብላ ኒኪ ጠየቀችው እና በመቀጠልም
“እሱ እና ዶውግ የልብ ጓደኛማቾች ናቸው:: ምናልባት ለእኔ ጉዳዩን በዝርዝር መግለፅ ያልፈለገው እኔ በጣም እንዳልጎዳ ወይንም ደግሞ የጓደኛውን ሚስጥር ለመጠበቅ አስቦ ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ። ሀዶን እንደፈለገ አስቦ ጉዳዩን ቢደብቀኝም ግን እኔ በጉዳዩ ላይ መልስ እፈልጋለሁ። ሚ/ር ዊሊያምስ ስለ ጣውንቴ የማውቀው ነገር ቢኖር ሩሲያዊ መሆኗን እና ስሟም ላንከ እንደሚባል ብቻ ነው።”
“ስለ እሷ ምን ምን ነገሮችን ለማወቅ ነው የምትፈልጊው?” ብሎ ዊሊያምስ ጠየቃት፡፡
“ሁሉንም ነገሮች” ብላ ኒኪ አይኗ በቁጣ በራ እና “ስለ እሷ እያንዳንዱን ነገሮች ማወቅ እፈልጋለሁ:: ማን እንደሆነች፣ ለምን ያህል ጊዜ አብረው እንደቆዩ፣ እንዴት እንደተገናኙ፣ የት እንደተገናኙ ሁሉ ማወቅ እፈልጋለሁ።
በየምን ያህል ጊዜያቶች ርቀትስ አብረው ይተኙ እንደነበር፣ የት ቦታ አብረው ይተኙ እንደነበር እና ለምን እሱ እንደዚህ ሊያደርግ እንደቻለም ጭምር ማወቅ እፈልጋለሁ:: ለምን ግን? አየህ እኛ በህይወታችን ደስተኞች ነበርን። ሌላ ሰው እኮ አያስፈልገውም ነበር! እውነት ፍቅራችን ሌሎችን የሚያስቀና ነበር እኮ!” ብላ ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ከፍተኛ የንዴት ስሜት ውስጥ ሆና ስታወራው ዴሪክ ዊሊያምስ ዝም ብሎ ያስተውላት ጀመረ።
ስለ ሊዛ እና ትሬይ በመኪና ተገጭታ እንድትሞት ስለተሞከረባት ሁኔታ እና ስለመርማሪ ፖሊሶቹ ስታወራው ራሷን ገዝታ ምንም የስሜት ለውጥ ሳታሳይ ነበር፡፡ ስለ ሟች ባሏ እና ውሽማው
ስታወራው ግን የተረጋጋው ስሜቷ ሙሉ በሙሉ ተለወጠ። የማይበርድ
ሀዘን፣ መከዳት ስሜት እና በጣም ሀይለኛ የንዴት ስሜት ውስጥ ሆና ነበር
ያወራችው።
ይህቺ ሴት ሁለት አይነት ገፅታ ነው ያላት አለ በሃሳቡ፡፡
የመጀመሪያዋ ኒኪ ስሜቶቿን መቆጣጠር የምትችለዋ ናት፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በፍፁም ስሜቷን መቆጣጠር የማትችለዋ ኒኪ ናት።
አንደኛዋ ኒኪ በተጨባጩ እውነተኛው ዓለም ውስጥ የምትኖረዋ ስትሆን
ሌላኛዋ ግን በቅዠት ዓለም ውስጥ ጥገኛ የሆነችዋ ኒኪ ናት፡፡
አንደኛዋ ኒኪ እውነት የምትናገረዋ ስትሆን ሌላኛዋ ኒኪ ግን ሰዎችን
እና እራሷን ጭምር የምትዋሸዋ ናት።
ሌላው

👍2🔥1
በጣም ያስገረመው ነገር ቢኖር ህይወቷ አደጋ ላይ ሆኖ ሰዎች ሊገድሏት እያሳደዷት ባሉበት ወቅት ላይ ሆና ስለ ባሏ ውሽማ ማወቅን ቅድሚያ ሰጥታ መንቀሳቀሷ ነው። የሆነ ያልነገረችኝ ነገር ይኖር ይሆን? ስለ ጣውንቷ ሌንካ የደበቀችው ነገር አለ? ምናልባትም ስለ ጣውንቷ ሌንካ ለማወቅ ያላት የቀን ተቀን እና የማያቋርጠው ጥያቄዋ ይሆን ሞትን እንኳን እንዳትፈራ ያደረጋት? አለ አይደል በባሏ ህይወት ማለፍ መሰቃየቷ
ሳያንሳት በእሱ መከዳቷ ህይወትን እንድትፀየፈው አድርጓት ይሆናል።
ከዚያን ጊዜ በኋላ እንግዲህ ኒኪ ሮበርትሰን ምንም ነገር አያስፈራትምን?
ዊሊያምስ ከህይወት ተሞክሮ አንድ ነገር ተምሯል። እሱም “በህይወት ምንም ነገር ካልቀራቸው ሰዎች የበለጠ በጣም አደገኛ እና አስፈሪ ሰዎች ያለመኖራቸውን ነው::”
ቢሮው ውስጥ ቁጭ ብሎ ስለ ኒኪ ማስታወሻ እየፃፈ አንድ ሰዓት ያህል
አሳለፈ። አሁን ከረፋዱ አምስት ተኩል ነው የምሳ ሰዓት ደርሷል። ያም ቢሆን ግን ዴሪክ ዊሊያምስ መቼም ለሆዱ ቅድሚያ ሰጥቶ አያውቅም እና የምሳ ሰዓትን ችላ አለው:: ስለሆነም ኒኪ ሮበርትስ የሰጠችውን የታሸገ ኤንቨሎፕ ከፍቶ መረጃዎችን መመልከት ጀመረ፡፡
ጠዋት ቁርስ ላይ ከነገረችው መረጃዎች ውስጥ የትኞቹን እዚህ ኤንቨሎፕ ውስጥ ማካተት አለማካተቷንም ለማወቅ ጓጓ። ስለ ብራንዶን የነገረችው ነገር እዚህ ውስጥ የለም፡፡ ስለዚህ ኒኪ እሱን ከፖሊሶቹ በላይ እንዳመነችው ገባው። ይህም ቢሆን ግን ማንኛዎቹም የእሱ ደምበኞች ሙሉ አንድም እውነታቸውን
ሳያስቀሩ ነግረውት እንደማያውቁ ከበፊት
ተሞክሮዎቹ ይረዳል።
ከኤንቨሎፑ ውስጥ አንደኛውን ወረቀት ስቦ ሲያወጣም ልቡ ላይ የሆነ
ስሜት ተሰማው። የተሰማው ነገር ጭንቀት፣ የምግብ አለመፈጨት ስሜት
ወይንም ደግሞ ቃር አልነበረም። አዎን እሱ አሁን ላይ የሚሰማው የደስታ
ስሜት ብቻ ነው። በአንድ ሌሊት ዕድሉ የተለወጠም መሰለው፡፡ አዲስ የምርመራ ጉዳይ እና አዲስ ተግዳሮትን ለማግኘት በቅቷል።
የድሮው ዴሪክ ዊሊያምስ ተመልሷል፡፡
ለረዥም ጊዜ በዝምታ ውስጥ ሆኖ የኒኪን ፋይሎች ከኤንቨሎፕ ውስጥ
እያወጣ አነበባቸው። ደግሞም ደጋግሞም አነበባቸው። ደቂቃዎች ወደ
ስዓቶች ተለወጡ። እሱ ከሚፈልገው ቦታ የጉዳዩን ምርመራ ሀ ብሎ መጀመር ይችላል።
መጨረሻ ላይ ግን ኒኪ በፅሁፍም ሆነ በቃል ከገለፀቻቸው ነገሮች ውስጥ
አንድ ስም ወደ አዕምሮው መጣ፡፡ እነዚህ ሁለት ግድያዎች የተፈፀሙበት ሂደት እና ሌሎች ነገሮችም ከዚህ በፊት ወዳከናወነው የግል ምርመራ ጉዳይ
ወደ ኋላ መለሰው።
አዕምሮውም በግምት ወደ ዛሬ አሥር ዓመት ጉዳይ መለሰው።......
✨ይቀጥላል✨

🔥1
#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
....ናትናኤል ለጥያቄው መልስ ሲያገኝ ይበልጥ ተበሳጨ፡፡ ለዚህ ቀላል ጥያቄ፣ ለዚህ ቀላል መልስ ይህን ያህል ከተቸገረ እንግዲያው ማስተዋል ቀንሷል ማለት ነው ከሚገባው በላይ ተወናብዷል ማለት ነው፡፡ ፈርቷል ማለት ነው፡፡
እራሱን ገሰጸወ፡፡
ረጋ ማለት አለበት፡፡ አለበለዚያ በማይረባ ስህተት እራሱን አጋልጦ ይሰጣል፡፡
ስሟን እስካወቀ፤ የስልክ ቁጥሯን እስካወቀ፤ የአባቷንና የአያቷን ስም ከማንኛውም የስልክ ደብተር ላይ በቀላሉ ያገኘዋል፡፡
ሌሊቱን በሙሉ በሃሳብ ሲታመስ ሳያሸልበው ፀሐይ ሥፍራዋን
ተረከበች::
ናትናኤል ከአልጋው ተነስቶ ማታ አለቅልቆና በእርጥብ መሃረቡ
ጠራርጎ ከግርጌ ካለ ወንበር ላይ ያሰጣቸውን ሸሚዙንና ኮቱን አንስቶ
ለባበሰና ወደ መታጠቢያ ቤት ገባ፡፡ በተቻለው መጠን ረጋ ብሎ ተጣጥቦ
ያለፈውን ሌሊት አሻራ ሙልጭ አድርጎ ካፀዳ በኋላ ወደ ሆቴሉ አዳራሽ ብቅ
አለ፡፡
ጥግ ላይ ተቀምጦ ሁለት ስኒ ቡና ጠጣና ፈጠን ብሎ ከሆቴሉ ወጣ፡፡ ሌላቱን ያለእንቅልፍ ቢያሳልፈውም የድካም ስሜት አልተሰማውም፡፡ምናልባት ድንጋጤው ይሆናል፧ ምናልባት ፍርሃት፣ ምናልባት ሥጋት፡፡
ደሙ በሰውነቱ ውስጥ ሲሽቀዳደምና ሲራወጥ ለራሱ ይሰማዋል፡፡ መፍጠኝና
መሮጥ አለበት!
ታክሲ ተሳፈረና ወደ መርካቶ ሸሸ፡፡
መርካቶ ባህር ነው ውቅያኖስ፤ መርካቶ ጫካ ነው ደን፡፡መርካቶ ቤቱ ነው የዘውድዬ፡፡
መሀል መርካቶ ከታክሲ እንደወረደ ወደ አንድ ቡና ቤት ገባ፡፡ገንዘብ ተቀባይዋን ተጠግቶ ሠላምታ ከሰጣት በኋሳ የስልክ ማውጫ ጠየቃት፡፡
“ጩኒ ቁልፍ፡፡” አለች ረጅም ወንበር ላይ የተቀመጠችው ወጣት ሴት ወደኋላ ዞራ፡፡
“ በእድሜ የሚመጣጠናት ወንድ ልጅ በቀጭን ሰንሰለት ውስጥ የተሰገሰጉ አስር የሚሆን ቁልፎች አቀበላት፡፡ ከቁልፎቹ ውስጥ አንዷን መርጣ አወጣችና አጠገቧ ያለ መሳቢያ ስባ የስልኩን ደብተር አውጥታ
አቀበለችው::
"እግዜር ይስጥልኝ” አላት ማውጫውን ተቀብሏት እየከፈተው፡፡
'የምሥራች ይልማ መጀመሪያ የምሥራችን ስም ፈለገ፡፡ በርካታ የምሥራች ይልማዎች የተደረደሩትን ገፅ እንዳገኘ የስልክ ቁጥሯን ፈለገው:: ቁጥሩን እንዳገኘ ወደኋላ ተመልሶ በትይዩ የተፃፈውን የምሥራችን ስም እስከ አያቷ ስም አነበበው የምሥራች ይልማ ገዛኽኝ::
“እቶ ይልማ ገዛኸኝ ድጋሚ የስልክ ማውጫውን እያገለባበጠ
ይፈልግ ጀመር አቶ ያልማ ገዛኸኝ... ይ.… ይ. ይ.. ያልማ አዳሙ... ይልማ መብራቱ
ይልማ ገብረማርያም…ያልማ ገዛኽኝ
የስልክ ቁጥሩን በወረቀት ላይ ገለበጠና የቡና ቤቱን ገንዘብ ተቀባይ አመስግኖ ወጣ፡፡ እዚያው አካባቢ የሕዝብ ስልክ ፈልጎ ኣቶ ይልማ ገዛኸኝ መኖሪያ ቤት ደወለ፡፡“
ከቤት” አለው ቀጠን ያለ የሴት ድምፅ፡፡
“እባኮት አቶ ይልማን ነበር”
“ሥራ ናቸው” አለች ሴትየዋ በተሰላቸ ድምዕ::
“እባኮት ችግር ገጥሞኝ ነው የሥራ ቦታቸውን ስልክ ቢሰጡኝ፡፡
“የሱቁን ነው?”
“አዎ ላገኛቸው የምችልበትን ቦታ፡፡”
ነገረችው:: ቀልጠፍ ብሎ ቁጥሩን ጻፍ ጻፍ አደረገና አመስግኗት ስልኩን ዘጋ:: ወዲያው የሰጠችውን ቁጥር ደወለ፡፡
ሃሎ” አለ ውፍረት የደፈነወ፣ ስጋ የዘጋው፣ እርስ በእርስ የሚተሻሽ ድምፅ::
“እባኮት አቶ ያልማ ይኖራሉ?”
“ነኝ:: ማን ልበል?”
“እንደምን ዋላ፡፡ የምሥራች ነበረች የላከችኝ..." ናትናኤል የሰውየውን ስሜት ለማጥናት ለአንድ አፍታ ዝም አለ፡፡
“ማን አሉኝ?” አለ ሰውየው መልሰው፡፡
“የምሥራች… የምሥራች ይልማ፡፡”
“ከየት ነው? ማንን ነው የሚፈልጉት?” ሰውየው ግራ የተጋቡ መሰሉ፡፡
“የምሥራች... የምሥራች የእርሶ ልጅ::”
“የማን ልጅ? ” ሰውየው ያበልጥ ተደነጋገራቸው፡፡
““ካዛንቺስ ሆቴል ያላት የእርሶ ልጅ::የምሥራች ይልማ ባለሆቴሏ...
“የምን ሆቴል ነው የሚሉኝ?”
ይቐርታ ጠይቋቸው ስልኩን ዘጋ፡፡
ሌላ ይልማ ገዛኽኝ በአዲስ አበባ ስልክ ማውጫ ደብተር ውስጥ የተመዘገበ የለም፡፡ ያለው አማራጭ ወደ ድሬዳዋ መንጎድ ብቻ ነው፡፡ድሬዳዋን አያውቃትም:: እዚያም ሄዶ መቸገሩ የማይቀር ነው፡፡ ግን የተሻለ
ምርጫ የለም::
መፍጠን አለበት፡፡ ምንም ጠባብ ቢሆን በተከፈተለት በር ሁሉ መሮጥ አለበት፡፡
ወደ ካልቨርት መጠጋት አለበት::
ዝግጅቱን ለማጠናቀቅ ወደ ባቡር ጣቢያ ሄዶ በማግስቱ ምሽት ላይ ወደ ድሬዳዋ በሚሄድ ባቡር ላይ የሁለተኛ ማዕረግ ትኬት ከቆረጠ በኋላ አውቶቡስ ተራ ወደ ዘውዲቱ ቤት ወደ ጎሬው በረረ፡፡
ምሳውን ከዘውዲቱ ጋር ከበላ በኋላ አሰዓት ወደ ገበያ ወጣ፡፡መርካቶ የዘመን መለወጫ በዓልን መስከረም አንድን ለመቀበል በሚዘገጃጅ ገብያተኛ ተጣባለች፡፡
ወደ ድሬዳዋ ሲሄድ ሊለብስ ያሰበውን ጀለቢያና ሽርጥ ነጠላ ጫማ እንዲሁም አንድ አነስተኛ የሸራ ሻንጣ ገዛ፡፡ አዲስ አበባ እስካለ ድረስ ደግሞ አጥልቆት የሚዘዋወረውን ወራጅ የጋራዥ ቱታና ፊቱን ጥሩ እድርጋ የምትሸፍንለት አንድ የተልፈሰፈሰች ባርኔጣ ጨመረ፡፡መንገድ ላይ ከኣንድ ጋራዥ ገባ ብሎ ለዘበኛወ ሁለት ብር ሰጠና በትንሽ ቆርቆሮ የተቃጠለ ዘያት ይዞ ወደ ጎሬው ሲመለስ ከእንድ ሱቅ ጎብቶ አንድ ጥሩ ሽቶና የሴት
ነጠላ ጫማ ሾመተ:: ከዘውዲቱ ቤት ሲደርስ ባይመሽም ቀኑ ገፍቶ ነበር።
ልብሱን አወላልቆ ዘወዲቱ እልጋ ወስጥ ገብቶ ጥቅልል አለ፡፡ የዘውዲቱን ቤት ተከራይቶ ከገባ ጀምር ለመጀመሪያ ጊዜ ዘውዲቱ፡ አብሯት የሚያድር ደንበኛ አጥታ እንድትመጣ ተመኘ፡፡
ያን ሌሊት በውዲቱ ቀንቷት ደንበኛ አገኘች አልተመለሰችም፡፡አልጋዊ ላይ ብቻዉን ሲገላበጥ ሲያቃዠው አደረ፡፡አንዱን ቅዠት ሳያገባድድ ሌላ ቅዠት እያቋረጠው ያባረረው ውሻ ሳያዘው ጭልጥ ካለ ገደል እየገባ ከገደሉ ወለል ደርሶ አናቱ እንደ እንቁላል ሳይፈርጥ አየር ላይ ጭልፊቶች
ገላውን እየገመጡ አይኖቹን እየጓጎጡት ሲወራጭ አደረ፡፡
ጠዋት በሩ ሲከፈት በርግጎ ሲነሳ ጭንቅላቱን በፋስ ሲወቅረው ተሰማው እራስ ምታት ነፍስ ዘርቶ፡፡
“እንደምን አደርክ?” አለችው ዘውዲቱ ወደ ውስጥ ገብታ በሩን እየዘጋች፡፡ እስካሁን አልተነሳህም? ሁለት ሰዓት አልፏልኮ::” የያዘችውን የላስቲክ ከረጢት ወንበር ላይ ጣል ኣድርጋ ኣልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ አለችና ኩንታል ስትሸከም እንዳደረች “
ኡፍ.....ፍ፡!” አለች፡፡ “እንዴ ለምን እራትህን ሳትበላ አደርክ?” አለች ሳይከፈት ያደረውን የምግብ ሳህን ከራስጌ ስታይ ዞራ እየተመለከተችው::
“አላየሁትም ነበር፡፡” አላት ናትናኤል እራቁት ደረቱን እያከከ ዞር ከራስጌ የተቀመጠውን ሳህን እየተመለከተ::
“እና ጾምን አደርክ ማለት ነው? ደግሞ ከትላንት ወዲያ የት ነበር ያደርከው?” ጥያቄ አከታተለችበት፡፡
ሳይመልስላት ከአልጋው ተነስቶ ከወገቡ በላይ ለመለቃለቅ በሩን ከፍቶ ወጣ፡፡ ሰወነቱን ተለቃልቆ ሲመለስ ዘውዲቱ ከራስጌ ያደረውን ሳህን ከፍታ በግራ እጇ ይዛ እየተንጎራደደች በላይ በላዩ ስትጎርስ አገኛት::
“ቡዳ የሆነ ሰውዬ ራቴን ሳያበላኝ ቤቱ ወስዶ እንደቅሪላ ሲያለፋኝ አደረ::” አለች እየሳቀች፡፡ “ላጉርስህ? ”
ራሱን ነቀነቀ፡፡ ናትናኤል ምግብ አላሰኘውም፡፡
“ምን ሆነሃል? ቤት ደህና አይደሉም እንዴ? ”
“ደህና ናቸው እነሱስ...” የጀመረውን አንጠልጥሎ ተወው፡፡
“ታዲያ ምን ሆነሃል? "
“ሰውየው ተያዘ::”
የቱ ሰውዬ?” መንጎራደዷን አቁማ በተቀመጠበት ቁልቁል ተመለከተችው፡፡
“አለቃዬ። የመሥሪያ ቤታችንን ገንዘህ ያጠፋው፡፡”
“አትለኝም!” የያዘችውን የምግብ ሳህን ከራስጌ አስቀምጣ በወጥ የተጨማለቀ እጇን አንከርፋ ኣልጋው ላይ ከጎኑ

ተቀመጠችና አይን አይኑን ትመለክታው ጀመር፡፡ “ውሸትክን ነው!”
ናትናኤል ከዘውዲቱ የሚለይበት ሰዓት እንደደረሰ የተገነዘበው ከአንድ ቀን በፊት ነበር፡፡ የምሥራች “እማዬ ጋ... ድሬዳዋ” ካለችው ወዲያ:: ዘወዲቱን ሊሰናበታት ደግሞ ምክንያት መስጠት አለበት፡፡ ቢሆንም ችግሩ ሁሉ እንደተፈታ አድርጎ መቅረብ የለበትም፡፡ መጪው አይታወቅም፡፡ ማን ያውቃል.. ተመልሶ ወደ አዲስ ኣበባ መምጣትና መሸሸግ ያስፈልገው ይሆናል፡፡ ያን ጊዜ የት ይገባል? ዞሮ መግቢያው መሽሽጊያው ነች ዘወዲቱ፡፡
“አዎ ተያዝ ዘውድዬ እየተመረመረ ነው አሉ፡፡ ግን ገና ነው! ያመነ አይመስለኝም፡፡
እሺ...አለች ለተጨማሪ ወሬ ጓጉታ ድዷ ውስጥ የገባ ምግብ በምላሷ እየጠረገች፡፡
ግን መጥፎ ወሬ ሰማሁ…“
“ምን?'' ቅንድቦቿን አጠበበቻቸው::
“ፖሊሶች አዲስ ኣበባ ውስጥ መደበቄን ደርሰውበታል አሉ፡፡ ያየኝ ሰው ሳይመራብኝ አልቀረም::”
ገብርኤልን.…” ደነገጠች:: “እንዴት አወቅህ? ።
“በየዘመዶቼና በየጓደኞቹ ቤት እየዞሩ ሲያጠያይቁ ነው እሉ የሰነበቱት፡፡” አላት ሃሳብ እንደገባው ሁሉ አይኖቹን ቡዝዝ አድርጎ ለምጻም ግድግዳዋ ላይ ተክሎ፡፡
“አይዞህ፡፡ እዚህ ሊያገኙህ አይችሉም፤ ከቤት ያለመውጣት ነው... ድምፅህን ካጠፋህ…” ታረጋጋው ጀመረች::
“አይ ዘውድዬ…. እኔም ተይዤ ለኣንቺም መዘዝ ከምሆን ከአዲስ አበባ ብወጣ ይሻላል:: እማዬጋ ልሄድ ነው ያሰብኩት::”
“የት ናቸው እናትህ?"- .
“ደብረብርሃን፡፡”
ከሰዓት በኋላ ጀለቢያውን ነጠላ ጫማውን ሌሎቹንም እቃዎቹን
በሸራው ቦርሳ ውስጥ ቀርቅቦ፤ በተቃወለ ጥቁር ዘይት የተጨማለቀ ቱታውን አጥልቆ፣ ልፍስፍስ ባርኔጣውን አድርጎ ተሰናበታት፡፡
“ልክ አይደለሀም፡፡ ይሄን ያህል ጊዜ አብረን ቆይተን ዘመን መለወጫ ሁለት ቀን ሲቀረው ትተኸኝ ትሄዳለህ? በፍጹም ልክ አይደለም፡፡ ምናለበት
ሁለት ቀን ቆይተህ እንቁጣጣሽን አብረን ብናሳልፍ ተለማመጠችው::
“አይሆንም ዘዉድዩ:: ከደረሱብኝ መጥፎ ነው::" አለ ጊዜ ማጥፋት እንደማይገባው ለራሱ እየመከረ፡፡ ዘውድዬ ይሄን ለአንቺ ነው የገዛሁት፡፡” አላት ሽቶውንና ነጠላ ጫማውን እየሰጣት፡፡ “ብድር መመለሴ አይደለም፤ ብድርሽን የምመልሰው ጥሩ ቀን ሲመጣ ነው፡፡ ይሄን ለዘመን መለወጫ ነው የገዛሁልሽ፡፡”
የዘውዲቱ ዓይኖች በእንባ ተሞሉ፡፡ ለስላሳነት ሲያይባት የመጀመሪያ ጊዜው ነበር፡፡ ሁሌ ተናጋሪ ሁሌ ግድ የለሽ ነበረች ዘውዲቱ፡፡አይኖቿ ውስጥ ያቆረዘዘውን እንባ ሲመለከት እሷም ለስላሳ፣ እሷም ሙቅ እንደሆነች ተረዳ፡፡
ዘላ አንገቱ ላይ ተጠመጠመችበት፡፡
ከዘውዲቱ ቤት ሲወጣ ዘጠኝ ሰዓት አልሞላም ነበር፡፡ ወደ ድሬዳዋ የሚጓዘው ባቡር ምሽት ላይ ይነሳል፡፡ ወደ ድሬዳዋ ከመሄዱ በፊት ግን ርብቃ መሥሪያ ቤት ለመደወል ወሰነ::
ርብቃ መሥሪያ ቤት ሲደውል ምህረትን ሲያገኝ ግን ያልጠበቀው ዱብ ዕዳ ጭንቅላቱን መታው የሱ ርብቃ አርግዛለች…የሱ ርብቃ ልጁን በሆዷ ተሸክማ ብቻዋን ትጨነቃለች.… የሱ ርብቃ…
ናትናኤል ወደኋላ ጋለል ካለበት ወንበር ላይ ቀና ኣለና ተቀመጠ፡፡ሰዓቱን ተመለከተ አስራ ኣንድ ተኩል ሊል ነው፡፡ የርብቃን ወንድም በአስራ ሁለት ተኩል ነው የቀጠረው፡፡ አንድ ሰዓት አለው ማለት ነው::
ከተቀመጠበት ተነስቶ ከቡና ቤቱ ወጣ፡፡ ሰማዩ ላይ ያዘበዘበው እርጉዝ ደመና ሌሊቱን ሀይለኛ ዝናብ ሊጥል እንዳሰበ ያስታውቃል፡፡ ለገሃር ታክሲ ይዞ በቸርችል ጎዳና ሽቅብ ወደ ፒያሳ ወደ ርብቃ አፓርታማ አመራ።
መጠንቀቅ አለበት፡፡ በቤቷ አካባቢ የሚያንዣብቡ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ሲገባና ሲወጣ መታየት የለበትም፡፡ አለበለዚያ እሮጦ ከእጃቸው እንደገባላቸው ነው የሚቆጠር፡፡ መጠንቀቅ አለበት፡፡ ቀጥታ ወደ ክፍሏ
ማምራት የለበትም። መሰለል… ዙሪያውን ማጥናትና መጠንቀቅ አለበለዚያ
ለሷም ተጨማሪ ችግር ነው የሚፈጥርባት፡
ርብቃ አፓርትመንት ከመድረሱ በፊት እራቅ ብሎ ከታክሲ ወረደና የስራ ሻንጣውን ትከሻው ላይ አንግቦ ጭንቅላቱ ላይ የደፋትን የጨርቅ ቆብ ወደ ታች ወደ ግንባሩ እየጎተተ በመንገዱ ቁልቁል በእርጋታ ወረደ፡፡ ሰዓቱ ገና ቢሆንም ከዳር እስከ ዳር ያንዣበበው ጥቁር ደመና አካባቢውን የመሸ አስመስሎታል፡፡ ሰዓቱን ተመለከተ፡፡ በአንድ ሰዓት አካባቢ ባቡር ጣቢያ መገኘት ይኖርበታል፡፡
ሃምሳ ደቂቃዎች አሉት… ብዙ መቆየት የለበትም ርብቃ ጋ ቶሎ አይቷት መውጣት አለበት። መጨከን አለበት… መጨከን መጨከን፡፡.....

#ክፍል_ሀያ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....ከዘጠኝ ዓመታት በፊት
ዴሪክ ዊልያምስ ሙሉ መስታወት በሆነው የቢሮ በር አሻግሮ ከእንግዳ
ማረፊያ ክፍል ውስጥ የተቀመጡትን ባል እና ሚስቶችን እየተመለከታቸው
ነው፡፡
ቢሮው ትልቅ እና ውድ በሆኑ እቃዎች የተሞላ ነው፡፡ የእንግዳ ማረፊያ ክፍሉም ቢሆን ኮርኒሱ ከፍ ብሎ የተሰራ ከመሆኑም በላይ በጥሩ የዲዛይን ባለሙያ እና በደንብ ባጌጡ ሶፋዎች የተሞላ ነው፡፡
ጠረጴዛዎቹ ላይም ላይፍ ስታይል መፅሄቶች ሞልተውታል፡፡ ይህ እንዲሆን ያደረገችው ደግሞ የዴሪክ ዊልያምስ አዲሱ ሚስቱ ሎርያን ነች፡፡
“ማሬ ገንዘብ ለማግኘት እኮ ገንዘብ ማውጣት ይኖርብናል” የሚለው
ምክርዋ ዋነኛው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ “ሰዎችን መጀመሪያ ባገኘሃቸው
ጊዜ ነው ልታስደስታቸው የምትችለው ሌላ እድል የለህም” የሚለው ነው።
ዴሪክ የሎርያንን ምክር ተግባራዊ ያደርግ የነበረው ስለምወዳት ነው ብሎ
ያስባል ወይንም ደግሞ ምርጥ ጡቶችና ያበደ መቀመጫ ስላላት እና ሌሎች
ሰዎችን ትታ እሱን በመምረጥዋ ሊሆን ይችላል ብሎ አንዳንዴ ይፈላሰፋል።
ለማንኛውም ይሄ “ገንዘብ ለማግኘት እኮ ገንዘብ ማውጣት ይኖርብናል የሚለው ፍልስፍና ሲሰራ ተመልክቷል። ምክንያቱም አዲሱ ቢሮው ከተሰራ
በኋላ የእሱ ተፈላጊነት በስልሳ ፐርሰንት ጨምሯል። ገቢውም ቢሆን በሶስት
እጥፍ ለማደግ ችሏል፡፡ ምናልባትም ይሄ
ሊሆን የቻለው ሰዎች ለሚያገኙት
አገልግሎት ብዙ ገንዘብ ሲያወጡ ነገሩ እንደሚከናወንላቸው ስለሚያምኑ ሊሆን ይችላል፡፡ ማንም ሰው ደግሞ እርካሽ የሆነ አገልግሎት አይፈልግም ብላ ሚስቱ የምትነግረው ነገር ትክክል ስለሆነም ሊሆን ይችላል፡፡
የዛሬዎቹ ጥንዶች ግን ለዴሪክ አገልግሎት የከፈሉት ክፍያ ትንሽ
ከመሆኑም በላይ ከዚህ በፊትም ለሰራላቸው የተለያዩ ምርመራዎች
ያልከፈሉት ብዙ ዕዳዎች አለባቸው፡፡ ለምን እንደሆነ አያውቀውም ብቻ
ለእነርሱ ከልብ የመነጨ የሃዘኔታ ስሜት ይሰማዋል። ለምንስ ዛሬ ሊያገኙት
እንደመጡ ሲያስብ ደግሞ ልቡን ፍርሃት ፍርሃት ብሎታል። እነሱ ግን እጅ
ለእጅ ተያይዘው እና ጣቶቻቸውን አቆላልፈው ጎን ለጎን ተቀምጠዋል።
ሰውዬው ተከር ክላንሲ ይባላል፡፡ ጥቅጥቅ ያለ በደንብ የተገነባ ሰውነት
አለው፡፡ ደንዳና አንገቱን ጥብቅ አድርጎ በሸሚዙ ስለቆለፈው የታነቀ ይመስላል፡፡ ካኪ ሱሪ እና ጂንስ ሱሪ ለብሷል፡፡ ወግ አጥባቂ ነገርም ስለሆነ ምናልባት ልብሱን ሲያወልቅ ሰውነቱ ላይ የሪፐብሊካን ፓርቲ ምልክት የሆነውን ዝሆን ተነቅሶት ሊሆን ይችላል፡፡ ሁሉ ነገሩን በጥንቃቄ እና
በስርአቱ የሚከውን ሰው መሆኑን ፊቱን በማየት ብቻ ማወቅ ይቻላል። ያም
ቢሆን ግን የደረሰበት ከፍተኛ ሀዘን እና ውስጣዊ ሀዘኑን ከፊቱ ላይ ማንበብ
ይቻላል። ዕድሜው በአርባዎቹ አጋማሽ ላይ ቢገኝም ሲታይ ግን የስልሳ
አመት ሽማግሌ ነበር የሚመስለው፡፡ አንድ ልጅን በሞት ማጣትን የሚመስል
ከባድ ሀዘን አይገኝም፡፡ ነገር ግን ይህቺን አንድ ልጅህን ጠፍታ ሳትገኝ መቅረትዋ በወላጅ የዋህ ልብም የጠፋችው ልጅ የሆነ ቀን ላይ ተገኝታ ወደ ቤትዋ በመመለስ የወላጆችዋን ስቃይ እንዲያበቃ ታደርጋለች ብሎ መጠበቅን
የመሰለ እጅግ በጣም ስሜትን የሚጎዳ ነገር እንደሌለ ዴሪክ ዊልያምስ በደንብ
ይገባዋል፡፡
ባለቤቱ ሜሪ ግን በጥሩ ሁኔታ ላይ የምትገኝ ትመስላለች። እርግጥ ነው
እሷም ብትሆን ይደክማታል፤ ያም ሆኖ ግን የልጅዋን ዕጣ ፈንታ ከባሏ በታቃራኒ መልኩ ተቀብላ ነገረ አለሙን ሁሉ ረስታ የተቀመጠች ሴት ሆናለች፡፡ ለዚህም ሊሆን ይችላል በውስጧ የሚገኘውን ስቃይዋን ፊቷ ላይ ማንበብ የማይቻለው፡፡ ይሄ ጥሩ ነው፤ ቢያንስ ከሁለቱ አንዱ እውነታውን ተቀብለውታል ብሎ ዊልያምስ አሰበ፡፡
ለሶስት ሳምንት ያህል ሜክሲኮ ሲቲ ውስጥ ዊሊያምስ የክላንሲን ልጅ
ቻርሎቴን ለመፈለግ ሲኳትን ነበር፡፡
ከመጥፋትዋ በፊት ያሉትን የቻርሎቴ
ውሎዎችን አና ያገኘቻቸውን ሰዎች በማግኘትም ዱካዋን ለመፈለግ ጥረት
ሲያደርግ ቆየ፡፡ ቆንጅየዋ ቻርሎቴ ክላንሲ ረጅም ናት፤ በተለይ ደግሞ ከሃገሬው የሜክሲኮ ሴቶች አንጻር በቀላሉ በምትኖርበት አካባቢ የምትለይ
ቢሆንም ከጠፋችበት ምሽት በኋላ ማንም ሰው አይቷት እንደማያውቅ ነበር
የነገሩት፡፡
በመጀመሪያ ጊዜ ባል እና ሚስቱ የቻርሎቴ ወላጆች ስለ ቻርሎቴ የፍለጋ
ሁኔታ በደንብ አልነገሩትም ነበር፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አባቷ ተከር አላንሲ የውጭ ሀገር ፖሊሶች በተለይ ደግሞ የሜክሲኮ ፖሊሶች በሙሉ የማይረቡ ናቸው ብሎ ስለሚያምን ነበር፡፡ ስለዚህም በፍለጋው ላይ ምናልባትም ኤፍ.ቢ.አይ እና በሜክሲኮ የአሜሪካ ቆንስላ በጉዳዩ ላይ ቢገቡበት ልጁ የምትገኝ መስሎት ነበር፡፡ ነገር ግን በሚገርም ሁኔታ ከሜክሲኮ ፖሊሶች በባሰ መልኩ የልጁን ጉዳይ ችላ ስላሉት ንዴቱን በዚህ
መልኩ ነበር የገለጸለት፡፡
“ስለ ቻርሊ እኮ ምንም ደንታ የላቸውም” ብሎ በመጮህ ነበር ተከር ክላንሲ በሁሉም ነገር ተስፋ ቆርጦ እሱን ለመቅጠር በመጣ ጊዜ የተናገረው
እሷ የአሜሪካ ዜግነት ያላት ሴት አይደለችም እንዴ? ታዲያ ለምንድነው
በየጥሻው ውስጥ የማይፈልጓት?”
ዊልያምስ የተከር ክላንሲ ንዴት ይገባዋል ግን ደግሞ በኤፍ.ቢ.አይ እና በቆንጽላው ጽ/ቤት አልተገረመም፡፡ “አሳዛኙ ነገር ግን ምን መሰላችሁ ቻርሎቴን በደንብ ሊፈልጓት የሚችሉት እሷ የሀብታም ልጅ ወይንም የባለስልጣን ልጅ ብትሆን ነበር፡፡ ስለሆነም የኤፍ ቢ አይ ሰዎች እሷን ለመፈለግ ጊዜያቸውን እና ሀብታቸውን ማውጣት አይፈልጉም፡፡ እሷ
ለመጨረሻ ጊዜ ወደ እናንተ ስትደውልላችሁ እድሜዋ ከ18 አመት በላይ ነበር፡፡ ብዙ ልጆች ደግሞ በዚህ እድሜያቸው ላይ ለወላጆቻቸው ሳይናገሩ
ከሆነ ሰው ጋር ሊጠፉ ይችላሉ፡፡”
ቻርሊ በፍፁም እንደዚህ ያለ ነገር አታደርግም” አለ ተከር ክላንሲ፡፡በዚያ ላይ ደግሞ ለአመታት ያህል በእኛ ላይ ጨክና ሳታናግረን አትተወንም፡፡” ሲል ሚስቱም ቀጠል አድርጋ “ሚስተር ዊልያምስ የሆነ ነገር ልጃችን ላይ እንደደረሰባት ይታወቀናል” ብላ እምባዋን ታግላ አስቀረችው እና ወይዘሮ ባደን እንደነገረችንኸውን ሜክሲኮ ውስጥ በየአመቱ ቱሪስቶች እና ሌሎች ሰዎች እንደሚታገቱ ነው፡፡”
“ምን አልሽኝ?” ብሎ ዊልያምስ ጠየቀ፡፡
“ቫለንቲና ባደን ናት፡፡ የዊሊ ባደን ሚስት ናት፡፡ የጠፉ ሰዎችን የሚያፈላልጉ የበጎ አድራጎት ድርጅት የከፈተች ናት።ከማንም በላይ ቻርሎቴን ለመፈለግ እገዛ አድርጋልናለች አለው ተከር ክላንሲ፡፡”
ይህንን ሲሰማ በድንገት አንድ ነገር ትዝ አለው ተከር፡፡ የሆነ ማታ ላይ ሁለት ታላላቅ ክለቦች እየተጫወቱ በነበሩበት የእራት ሰዓት ላይ ልጆቻቸውን እንዲያፈላልጉላቸው ሲማጸኑ እንደነበር አስታወሰ፡፡ ያኔ በዚህ የእረፍት ሰዓት ላይ ለሚተላለፉ ማንኛውም ነገሮች በጣም ውድ የሆነ ዋጋ ለቲቪ ጣቢያዎች ተከፍሎ ነው፡፡ ስለዚህም ይህንን የማስታውቂያ ክፍያ የከፈለችው
የዊሊ ባደን ሚስት ቫለንቲና ባደን መሆንዋን ተረዳ፡፡
“በፍፁም ወደዚያ እንድትሄድ ልፈቅድላት አይገባኝም ነበር፡፡” አለ ተከር ክላንሲ በቁጭት፡፡
“ምን መሰለህ ሚስ ባደን በእገታ የተወሰዱ ሰዎችን በማፈላለግና
ለአጋቾቹ የማስለቀቂያ ክፍያ እየከፈለች ታጋቾችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር
እንደምታገኛኝ ነው የምናውቀው፡፡ ይሄው እንግዲህ ስለልጃችን ግን አንድም
ሰው እስካሁን ድረስ የደወለልን የለም፡፡ ይሄ ነገር ጥሩ ይሁን መጥፎ ሊገባን
አልቻለም” አለችው ሜሪ ክላንሲ፡፡
መጥፎ ነው እንጂ ብሎ አሰበ ዊልያምስ ደግሞም ይህቺ ቫለንቲና
ባደን ለቻርሎቴ

ወላጆች ቻርሎቴን በህይወት የማግኘታቸው እድል ከመቶ
አንድ እንደሆነ ነግራታለች። ከአሜሪካ በደቡብ አዋሳኝ ላይ ያለውን የኑሮ
ሁኔታ መካከለኛ ገቢ ያላቸው የአሜሪካ ወላጆች አይረዱትም፡፡ በዚያ ላይ
ደግሞ ቻርሎቴ ወጣት እና በቀላሉ ሰው አይን ውስጥ የምትገባ ልጅ ስለነበረች እሷን በህይወት ዳግመኛ ማየት በጣም ጠባብ ነው፡፡
ለማንኛውም የቻርሎቴ ወላጆች ዴሪክ ዊልያምስ ቻርሎቴን እንዲፈልግ ቀጠሩት፡፡ እሱም ደግሞ በጣም በምርጥ ሁኔታ እና ያለውን አቅምም እስከመጨረሻው በመጠቀም ቻርሎቴን የመፈለግ ስራውን አከናውኖ ነበር፡፡
ዊሊያምስ የቻርሎቴ ወላጆች ከቀጠሩት ከአራት ቀናት በኋላ ሜክሲኮ
ሲቲ የገባው ቻርሎቴን ቀጥረው የሚያሰሯት ሰዎች የመኖሪያ አድራሻን እና
ቻርሎቴ ወደ ቤተሰቦችዋ ስትደውል አንድ ጊዜ የምታነሳላቸውን የጓደኛዋን የመጀመሪያ ስም ብቻ ይዞ እና ደግሞም አንዳንድ ፎቶዎችን እና ሜክሲኮ ውስጥ ስትጠቀምበት የነበረውን የስልክ ቁጥሯን ብቻ ነበር፡፡ በነገሩ ላይ ትንሽ ተስፋ እንዳለው እያወቀ ወደ ሜክሲኮ ሊመጣ የቻለበት ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ሚስቱ ሎርያን አስር ሺህ ዶላር እኮ ቀልድ አይደለም ስላለችው ነበር እዚህ ጉዳይ ውስጥ የገባው፡፡
ሜክሲኮን ዊልያምስ ያገኛት ከጠበቀው በላይ ህግ የማይከበርበት ቦታ ሆና ነበር። በቃ ሜክሲኮ ሲቲ ማለት በህገ አራዊት የምትመራ የምእራቡ ዓለም ክፍል ሆና ነበር፡፡ ከተማውን ካየ በኋላ የቻርሎቴ ቤተሰቦች ልጃቸውን አምነው ወደዚች ከተማ መላካቸው በጤናቸው እንዳልሆነ ድምዳሜ ላይ ሊደርስ ቻለ። በየቀኑ በከተማ ውስጥ የሚደረጉት ወንጀሎች የከፉ ናቸው።የአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎች እና አጋች ሽፍቶችም በጠራራ እገታዎቻቸውን እና የእፅ ንግዳቸውን የሚያደርጉባት ከተማ ናት፡፡ እነዚህን ለመጠበቅ በጀግንነት የፖሊስነት ስራቸውን የሚሰሩ ሰዎች በተቃራኒ
የወንጀል ድርጊቶችን ጠንክረው የሚዋጉ እና የህብረተሰቡን ደህንነት ሀይሎች ቤተሰቦቻቸው እና ዘመድ አዝማዶቻቸው ላይ ሳይቀር ስቃይ ይደርስባቸዋል፡፡ በእነዚህ የወንጀል ቡድኖች ተቀጥረው የሚሰሩ ፖሊሶች ደግሞ ህብረተሰቡን ሣይሆን የእነዚህን ወንጀለኞችን ቤተሰብ የሚጠብቁ ናቸው። ብቻ የሀገሪቷ ባላስልጣኖችም ቢሆኑ ከላይ እስከታች በሙስና የተጨማለቁ ናቸው።
ቻርሎቴን ቀጥረው ሲያሰሯት የነበሩት የኢንክሪቶ ቤተሰቦች ለዘመናት ያህል በዚህ ከተማ ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ ሲሆን ምንም የሀዘኔታ ምልክት በማይታይበት ድምጽ “እንደዚህ ያሉ ነገሮች እዚህ ከተማ ውስጥ ሲፈፀሙ ደግሞ አዲስ አይደለም፡፡ ማን ሊገድላት እንዲሚችል ትገምታለህ፡፡ ፀረ አሜሪካዊ አቋም ባላቸው ሰዎች ወይንስ ቤተሰቦችዋ ሀብታሞች ናቸው ብለው በገመቱና የእገታ ማስለቀቂያ ገንዘብን ለመጠየቅ ባሰቡ ሰዎች ግን ያው እንደምታውቀው እስከ አሁን ድረስ ምንም አይነት ጥያቄ ከቤተሰቦችዋ አልመጣም፡፡” አሉት፡፡
ይሄኔ ጥቁር ፀጉር ያላት ቆንጅዬ የጁሃን ሚስት የሆነችው አንጀሊና ኢንክሪቶ ጣልቃ ገባችና “ሚስተር ዊልያምስ በእኛ ከተማ ውስጥ የወሮበላ ቡድኖች ያለምንም ምክንያት ነው አንድን ሰው እንደፈለጉ የሚያደርጉት።ለዚህም ብለን ነበር ቻርሊን ብቻዋን መኪና እንዳታሽከረክር አስጠንቅቀናት
የነበረው፡፡ ይህም ሆኖ ግን እሷ ልትስማን ፈቃደኛ አልነበረችም።”
“እና እሷ ይህን ስታደርግ ልታስቆሟት አልሞከራችሁም ነበር? ማታስ ላይ የእናንተን መኪና ይዛ ስትወጣ አይሆንም ለምንድን ነው ያላላችኋት?” ብሎ ዊልያምስ በንዴት ተሞልቶ ጠየቃቸው፡፡
“እኛ እኮ ቻርሎትን የቀጠርናት ልጃችንን እንድትቆጣጠር ብለን ነው” ብሎ ጁሃን ሞገተ፡፡ እና በመቀጠልም “ስለዚህ እሷ በግል ጊዜዋ የምታደርጋቸውን ነገሮች አድርጊ ወይም አታድርጊ እያልን ልንቆጣጠራት አንችልም፡፡”
በዚያ ላይ ደግሞ ቆንጆ እንደመሆኗ መጠን ምናልባትም እኛን የማትሰማበት ከሰዎች ጋር የወሲብ ግንኙነት ይኖራትም ይሆናል፡፡” አለችው አንጀሊና፡፡
“እናንተ የምታውቁት የወንድ ጓደኛ ነበራት?” ብሎ ሲጠይቃቸው ሁለቱም በአሉታ ራሳቸውን ወዝውዘው አናውቅም ብለው መለሱ፡፡......

#ክፍል_ሰላሳ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
....እንደ ድንጋይ ከተጫናት ሰመመን ውስጥ ቀስ በቀስ እየወጣች ስትመጣ… እላይዋ ላይ ተጭኖ የያዛት ድቅድቅ ጨለማ እንደ ጭስ እየሳሳ እየበነነ ለቋት ሲጠፋ በመጀመሪያ የተቀበላት በእግሮቿ መሃል የሚነዝራት የደነዘዘ ስቃይ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ ጭንቅላቷ እየጠራ ሲመጣም አይኖቿን ለመክፈት አልደፈረችም፡፡ ሌላ ዱላ፣ ሌላ ስቃይ ሌላ የጋለ ሽቦ የሚችል
አካል አልነበራትም። በክፍሉ ውስጥ ብቻዋን ትሁን አትሁን እርግጠኛ
አልነበረችም፡፡ አይኖቿን ለመክፈት ግን አልደፈረችም፡፡
እጆቿ ግራና ቀኝ ተወጥረው ከታሰሩሰት ተፈተው በድን እንደሆኑ ሁሉ በግራና በቀኝ ተዘርረዋል፡፡ በተኛችበት ልብስ ደርበውላታል፡፡ እግሮቿ ግን አሁንም ግራና ቀኝ ሁለት ቦታ ተወጥረው እንደታሰሩ ናቸው፡፡ ቁስሏን ለማዳመጥ ሞከረች፡፡ በጭኖቿ መሃል የሚሰማትን ስቃይ ለማዳመጥ ዝም አለች የተዳፈነ... የደነዘ… የደበዘዘ ስቃይ፡፡ ግራ ክንዷ ላይ ህመም ተሰማት:: ለመነቃነቅ ግን አልደፈረችም፡፡ በአይነ ህሊናዋ ሁኔታውን
ለመቅረፅ ሞከረች። መቼ ነበር በጋለ ሽቦ ጭኖቿ መሃል ሰውነቷን ያቃጠሏት? ዛሬ? ትላንት? ዛሬ ምንድነው? ቀን ነው ሌሊት? ሰዓታትና ቀናት ትርጉም ካጡባት ቆይተዋል፡፡
ድምፅ የሰማች መስላት። ዓይኖቿን እንደከደነች ጆሮዎቿን ኣስልታ ተጠባበቀች፡፡ የበር ድምፅ ተሰማት… የሚከፈት የበር የሚያሰማው ድምፅ..
“አልተነሳችም፡፡” አለ አንድ ድምፅ በሹክሹክታ፡፡
“ኮለኔል” አለ አንድ ድምፅ በሹክሹክታ “ዙርያውን አጥረነዋል።በርም ላይ አንድ ሰው አቁመን እየተጠባበቅን ነው::”
“መጣሁ” ሲል ተሰማት ማርቆስ፡፡
ሁለት የእግር ኮቴዎች በግራና በቀኟ ተስሟት…በስተቀኝ ኣንድ መዳፍ ግንባሯ ላይ አረፈ::
“ከነቃች የመርፌ ማደንዘዣውን ስጣትስቃይ ሊኖርባት ይችላል።” የማርቆስ ድምፅ ነበር።
“ካስቸገረችኝስ ልምታት?” አለ በስተግራዋ የቆመ ሌላ ሰው፡፡
“ረጋ ብለህ አባብለህ ውጋት። ለምን ትመታታለህ? ደግሞ አታስቸግርህም.. ከተወራጨችብህ ግን ግሉኮሱን ንቀልላት፡፡” አለ እጁን ግንባሯ ላይ የጫነው ማርቆስ በጣቶቹ ፀጉሯን ወደኋላ እያበጠረ፡፡ “ጠዋት እቀየርልሃለሁ፡፡”
ኮቴ ተሰማት፡፡ ተከታትለው ሲወጡ ሰማች። በሩ ሲዘጋ በክፍሉ ውስጥ ፀጥታ ሲነግስ ስትፈራ ስትቸር አይኖቿን ገለጠቻቸው::መኝታ ክፍሏ ውስጥ ብቻዋን አስተኝተዋታል፡፡ በቢጫው የብርድ ልብሷ ከአንገቷ እስከ
እግሯ ጫፍ ድረስ ሸፍነዋታል፡፡ በተንጋለለችበት ዙሪያዋን ተመለከተች፡፡
ግራ ክንዷ ላይ የሚሰማት ህመም ከራስጌዋ ከተንጠለጠለው የግሉኮስ
ከረጢት ጋር የተያያዘው መርፌ ክንዷን ጠልቆ የገባበት ላይ መሆኑን ተረዳች። የክፍሉ መጋረጃ ተዘግቷል፡፡ በጥግና ጥግ የታየው ሰማይ ጨልሟል... መሽቷል፡፡ ሰመነቃነቅ ስትሞክር ግራና ቀኝ የታሰሩት እግሮቿ መሃል የተዳፈነው ስቃይ እንደ ጦር ወጋት፡፡ ከስሱ የብርድ ልብስ በታች ያለው እራቁት ሰውነቷ ተንሰፈሰፈ፡፡
ድምፅ ተሰማት የመኝታ ቤቷ በር ተከፈተ፡፡ ቶሎ ዓይኖቿን ጨፈነቻቸው፡፡ : እንደነቃች ማወቅ የለባቸውም፡፡ ዝም ብላ መተኛት ነው ያለባት፡፡ መረበሽ የለባትም! አለበለዚያ ይመቷታል፡፡ ዝም ብላ መተኛት። በሩ ሲዘጋ ተሰማት: የእግር ኮቴ እየቀረባት መጣ. አንድ በላብ የረጠበ እጅ
እራቁት ትከሻዋ ላይ ሲያርፍ ተሰማት… ትንፋሼ እላይ እታች የሚል ትንፋሽ እላይዋ ላይ የነበረው ስስ የብርድልብስ ፡ ተገፈፈ፡ መረበሽ የለባትም… መንቃቷን ማወቅ የለባቸውም... አለበለዚያ ድጋሚ
ያስቃይዋታል. , ትከሻዋ ላይ ያረፈው በላብ የራሰ መዳፍ ወደታች ወደ
ደረቷ ተንሸራተት…. እልተንቀሳቀሰችም ጡቶቿ ሲዳስሱ ተሰማት እላይ እታች የሚል ትንፋሽ… ፍርሃት ወረራ ግራ ክንዷ ላይ የተሰካውን መርፌ አስሮ የያዘው ፕላስተር ተላጠ.. ክንዷ ላይ የተሰካው መርፌ ተነቀለ መንቃቷን ማወቅ የለባቸውም… አለበለዚያ ይመቷታል... እላይ እታች የሚለው ትንፋሽ ቀረባት፡፡ ብርድ ልብሷ ወደታች ተጎተተ ፍርሃቷ
እየጨመረ መጣ እላይ እታች የሚለው ትንፋሽ ወደ አንገቷ ስር ሲጠጋ ተሰማት.. ብርድ ልብሱ ከላይዋ ላይ ተንሸራቶ ወደ መሬት ወደቀ፡፡ ራሷን መቆጣጠር አቃታት… አይኖቿን ገለጠቻቸው፡፡
ጺማሙ ሰውዬ ነበር፡፡ እላይዋ ላይ እንዳንገርበበ ድንገት አይኖቿን ስትገልጥ ደንገጥ አለ፡፡ ወዲያው ፈገግ አለላት... የሸሚዙን ቁልፎች መፍታት ጀመረ… ፈገግ አለላት ድጋሚ… ሸሚዙን ከላዩ ላይ ወርውሮ ተጠጋት… እጆቹን ጡቶቿ ላይ ጫናቅው ድንገት ተወራጨች፡፡ ሙቅ
እርጥብ እጆቹን ከላይዋ ላይ ገፍትራ ተሸማቀቀች ፈገግ አለላት፡፡ አልጋዋ
ላይ የተንጋለለውን እራቁት ገላዋን ከላይ እስከታች በተራሱ ኣይኖቹ ዳሰሰው፡፡ ምራቁን ሲውጥ ትልቅ ማንቁርቱ እላይ እታች ሲመላለስ በፍርሃት ተንቀጠቀጠች፡፡ ድንገት ዘሉ አፏን በመዳፉ ኣፈናት… ታገለችው…
እጆቿን እያፈራረቀች እንደብረት የደደሩ ሁለት ክንዶቹን ደበደበቻቸው
ቧጠጠቻቸው... ያለብዙ ችግር እፏ ውስጥ ጨርቅ ጎስጉሶ ለጎማት
ትንፍስ ትንፍስ እያለ ቁልቁል ተመለከታት፡፡ አይኖቹ የሚያርፉበት
ቦታ ያጠ ይመስላል፡፡ መላ ሰውነቷ ላይ ተንቀዠቀዡ።
ሱሪውን ማውለቅ ጀመሬ በተንጋለለችበት በምሬት… ጭንቅላቷን አወራጨችው… እንባዋ ደረሰላት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ቢሮው ትዕግስቱ አልቋል፡፡” አለ ከቴልአቪቭ የገባው ይሁዳ አሚ
የብርቱካን ጭማቂውን ተጎንጭቶ ብርጭቆውን ካስቀመጠ ሰኋላ ረጅም
ጺሙን እየዳሰሰ፡፡
የአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴልኝ የመዋኛ ስፍራ በስተቀኛቸው አድርገው ተቀምጠዋል፡፡ በርካታ እንግዶች በመዋኛ ልብሶቻቸው ወዲያ ወዲህ ይላሉ፡፡ የተቀሩት በደረትና በጀርባቸው እየተገላበጡ ጭል ጭል የምትለውን ለስላሳ የጳጉሜ ፀሐይ ይሻማሉ፡፡
ይሁዳ አሚ በሆቴሉ ውስጥ ከያዘው የመኝታ ክፍል ወጥቶ ከቀጠሮኣቸው ስፍራ የደረሰው ልክ በሰዓቱ ነበር። ከቀጠሮው ሰዓት ቀደም ብሎ የደረሰው አሃሮን የእንግዳውን ፀባይ ስለሚያውቅ የብርቱካን ጭማቂ አዝዞ ከፊት ለፊቱ አስቀምጦ ይጠባበቅ ጀመር፡፡ አሚ የሌሊት ልብሱን ሳይቀይር በላዩ ላይ ወፍራም የጠዋት ልብሱን ደርቦ ወገቡ ላይ ቀበቶውን ሽብ አድርጎ ከጥጥ የተሰራ ወፍራም የእግር ሹራብና የቤት ነጠላ ጫማዐእንዳደረገ ወደ መዋኛው ስፍራ የሚወስደውን ደረጃ በእርጋታ ወርዶ ወደዐአሃሮን አመራ፡፡
“እንኳን ደህና መጣህ፡፡” አለ አሃሮን ተነስቶ እንደቆመ የአሚን እጅ
ጠበቅ አድርጎ እየጨበጠ፡፡
“እንኳን ደህና ጠበቅኸኝ።” አለ አሚ ነጫጭ ውብ ጥርሶቹን ለአንድ አፍታ ብልጭ አድርጎ የጓደኛውን እጅ እየወዘወዘ፡፡
አሚ “ ኪዶን” በሚል ስያሜ በሚታወቀው የሞሳድ ገዳይና አፋኝ
ክፍል ውስጥ ለአስራ ሰባት ዓመታት የሰራና አትግደል እና አትዋሽ
ከሚሉት ከሙሴ ትዕዛዛት በስተቀር በተቅሩት በስምንቱ ትዕዛዛት ላይ ፌዝ
የማያውቅ ጥብቅ ሃይማኖተኛ አይሁዳዊ ነው። በሌሊት ልብሱ ላይ የደረበው
ወፍራም የጠዋት ልብስና ቡፍ ካለ ጥጥ መሳይ የቤት ጫማው ጋር ሲያዩት
ጺማሙ ሰው በቤት ውስጥ ተቀምጦ የሳጠራ ዘንቢሉችን ሲሰራ የሚውል
የዋህ በሬ ይመስላል፡፡
“የብርቱካን ጭማቂ፡፡” አለ አሚ ፈገግ ብሉ ከጎኑ የቆመውን የሆቴሉን አስተናጋጅ እየተመለከተ፡፡
የአልኮል መጠጥ ፍጹም የማይቀምስና የአሳማ ስጋ አፉ የማይገባ ጥብቅ ሃይማኖተኛ የሆነው አሚ በመስከረም 5 1972 በሙኒክ ሃያኛው ኦሎምፒክ ዝግጅት ላይ የብላክ ሴፕቴምበር ቡድን የእሥራኤል ስፖርተኞችን ሰፈር በመውረር አስራ አንድ ተጨዋቾችን ከገደለ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር ጎልዳሜይርን የብቀላ ትዕዛዝ

ዳር ለማድረስ ሞሳድ ኦፕሬሽኑን እንዲመራለት የመረጠው ከፍተኛ ችሎታ ያለው የመረጃ ሰው ነው ይህንን ከፍተኛ ኃላፊነት የተቀበለው አሚ በአንድ ወቅት በያሲር አራፋት ፋታህ ድርጅት ውስጥ የስለላ ኃላፊ የነበረውንና በኋላም ሞሳድ
የሙኒኩ ሽብር ጠንሳሽ ነው ያለውን ዩሱፍ ናደር ወይም እሱ ዬሴፍንና በቀጥታ የሙኒኩን እልቂት አቀናጅቷል ብሎ የጠረጠረውን ዓሊ ሃሰን ሣሌም ወይም ሞሳዶች በሰጡት የቅጽል ስም 'ቀዩን ልዑል' ጨምሮ ከሰላሳ አምስት በላይ የሚሆኑ ቀንደኛ ሽብርተኞችን በኪዶን አፈሙዞችና ፈንጅዎች በያሉበት ሲለቅማቸው የገዛ አለቆቹ ሳይቀሩ በመደነቅ ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡
በጥቅምት 1972 በሮም የፒኤልኦ ተወካይ በነበረው አብዱልዋይል
ዝቦይተር ግድያ የተጀመረው የሞሳድ የአሸባሪዎች አደን በምሥራቅና
በምዕራብ አውሮፖ እንዲሁም በመካከለኛው ምሥራቅ ለወራት ሽብር ሲነዛ ቆየ፡፡
ከዚያ ሽብር ወዲያ አሚ በሞሳድ ውስጥ እንዴሚካቢር ሁሉ በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙ ሽብርተኛ ቡድኖች ተጠላ፡፡
“ቢሮው ትዕግሥቱ አልቋል” አለ አሚ የቀረበለትን የብርቱካን ጭማቂ እያነሳ፡፡
“ባለኝ ሃይል ሁሉ እየተነቃነቅሁ ነው፡፡” አለ አሃሮን አሚን ለመምሰል ቀደም ብሎ ያዘውን የብርቱካን ጭማቂ ገፋ እያደረገ፡
“ወንድሜ” አለ አሚ ጺሙን ወደታች እየላገ “ከአሁን በኋላ በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ለመሰብሰብ የምናደርገው ጥረት ብቻውን መልስ እንደማይሆን ቢሮው አምኗል።”
“ይሁዳ” አሊ አሃሮን ፈገግ ብሉ “አንተ እንደምትመጣና እንድቀበልህ መልዕክት ሲደርሰኝ ምን እንደሚከተል መገመት
አላስቸገረኝም፡፡” አለ አሃሮን በሞሳድ ገዳይና አፋኝ ቡድን አባል የሆነውን
ሰው እየተመለከተ።
“ጥሩ ገምተሃል እግዳው።” አለ አሚ ፈገግ ብሎ “ለማንኛውም ዝርዝር ዕቅዱን እሰጥሃለሁ። መኝታ ቤቴ ሻንጣዬ ውስጥ አለ። ለጊዜው ዋና ነጥቡን ከፈለግህ በአጭሩ ላስረዳህ እችላለሁ፡፡”
"ቀጥል፡፡” አለ አሃሮን በወንበሩ ላይ እየተመቻቸ፡፡
“አሃሮን አሚ ለአንድ አፍታ ዞር ዞር ብሎ አካባቢውን ካጠና በኋላ ሁለት ሳምንታት በአፍሪካ አደገኛ የጦር መሣሪዎች
ሲንቀሳቅሱ ሰንብተዋል፡፡ መነሻው በእርግጠኝነት ከዚህ ነው ማለት ባይቻልም ወይ ከጆሃንስበርግ አለዛም ከካይሮ ሳይሆን አይቀርም የሚል
ግምት አለ፡፡”
“አደገኛ የጦር መሣሪያ ስትል?” አለ አሃሮን ድምፁን ቀንሶ
“እጃችን የገቡት ማስረጃዎች ጥቂት ፎቶግራፎችና ግማሽ በግማሽ
የተቃጠለ ጥራዝ ነው፡፡ እነዚህ ማስረጃዎች እንዴት እንደተገኙ ግን ለእኔ
ግልጽ አይደለም፡፡ የሆነው ሆኖ ወደተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የተጓዙት
መሣሪያዎች በርካታና ዓይነታቸውም የተለያየ ቢሆንም አስገራሚ ሆኖ
የተገኘው ግን በስሪቱ የሶቭየት ህብረት ከሆነው የስትሬላ ሚሳይል ጋር
ተመሳሳይ ሆኖ ከትከሻ ላይ የሚወነጨፍ ሚሳይል ነው” አለ አሚ፡፡
“ምኑ ላይ ነው አስገራሚነቱ?” አለ አሃሮን፡፡
“ጥራዙ ውስጥ ያሉ ያልተሟሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት መሆን እነዚህ ሚሳይሎች የኒውክሊየር አረር የሚገጠምላቸው ናቸው። ይህ ምን
ማለት እንደሆነ ይገባሃል፡፡” አለ አሚ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በጥልቀት ተንፍሶ
በዝምታ የሚያዳምጠውን አሃሮንን እየተመለከተ ቀጠለ፡፡ “እሰፈሪው ነጥብ
ግን የአፍሪካ አገሮች አደገኛ የጦር መሣሪያዎችን መቀባበላቸው አይደለም::
ዋናው ነጥብ ከእነዚህ መሣሪያዎች ውስጥ የተወሰኑት ከአፍሪካ ውጪ
ወደአልታወቁ ሥፍራዎች ተወስደዋል የሚል የመረጃ ፍንጭ መገኘቱ ነው፡፡
ይህ ደግሞ የኒውክሊየር አረር የተገጠመላቸውና ከሰው ትከሻ ላይ
ሊወነጨፉ የሚችሉ ሚሳይሎችን በአጥፍተህ ጥፋ የሽብር ፈጠራ ጥቅም
ላይ ሊያውላቸው የደፈረ አንድ ወገን አላ ማለት ነው:: ውጤቱን አንተ እራስህ ልታሰላው ትችላለህ፡፡”
“በገዛ ደጃፍህ ቆመህ ዓለም ስትጠፋ ታያለህ ማለት ነው፡፡” አለ አሃሮን የኒውክሊየር ሽብር ፈጠራ ምን ገጽታ ሊኖረው እንደሚችል ለማሰብ
እየሞከረ።
“ምናልባት እያንዳንዱ የአውሮፓ የአሜሪካና የእስያ ታላላቅ ከተማ
በኒውክሊየር አረሮች ይመታል፡፡አስጠሊታው ጉዳይ ግን ማንኛውም
መንግሥት በየትኛውም አገር ወይም ቡድን ላይ የምላሽ ጥቃት መሰንዘር
እንዳለበት ሊያውቅ አይችልም፡፡ ምክንያቱም ጥቃቱ የሚፈጸመው እዚያው
ከውስጥ ሰርገው በሚገቡ ያበዱ ሽብርተኞች ይሆናል፡፡”
የፈጣሪ ያለህ! ታዲያ ያንተ እዚህ መምጣት…” አሃሮን የጀመረውን ጥያቄ ሳይጨርስ በመሃል አቋረጠ፡፡
“አሃሮን” አለ አሚ አይኖቹን ከመዋኛው ሥፍራ ዙሪያ ቀሚራወጡ ህፃናት ላይ ተክሎ “እኔ ወደእዚህ የመጣሁት የዚህ ሁሉ ምሥጢር ጭንቅላት አዲስ አበባ ውስጥ ስለሆነ ነው፡፡ እነዚህ አደገኛ መሣሪያዎች ከአንዱ የአፍሪካ አገር ወደሌላው እንዲጓጓዙ የተሰጠው ትዕዛዝ በትክክል በማን እንደሆነ ለማረጋገጥ ሲያዳግተንም ትዕዛዙን ያስተላለፈው አካል እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ለመገኘቱ እርግጠኛ ሆነናል፡፡”
“ይህ ነገር ፍጹም ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን ያስፈራል፡፡” አለ አሃሮን የተሰማውን መደናገጥ ለመደበቅ ሳይሞክር፡፡
“ትክክል ነህ:: ቴልኣቪቭም ካ
ከተመሳሳይ ድምዳሜ ላይ የደረሰ
ይመስለኛል፡፡”
“እና የሚቀጥለው ምንድነው ምንድነው መፍትሄው…?
“እኔና አንተ ቀድመን አዲስ አበባ ውስጥ እሳት እናቀጣጥሳለን፡፡”
አለ አሚ፡፡
“አልገባኝም፡፡”
“አሃሮን ከሚቀጥሉት ቀናት ጀምረን በጭፍን በእጃችን የገባውን ማንኛውንም ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣንና የአፍሪካ ዲፕሎማት እንገድላለን፤ እናፍናለን፡፡ ይህ በተለያዩ የአፍሪካ ከተማዎች በአንድ ሰዓት ይጀመራል፡፡ ኦፕሬሽኑን የሚመሪው ሌላ ሥራ አቁመው እዚህ ላይ ብቻ
ሃያ አራት ሰዓት ሚሰሩ የበላይ ባለሥልጣናት የተደራጀ ቡድን ከቴልአቪቭ ነው:: እኔ የአዲስ አበባውን ሽብር ልመራ ነው የመጣሁት:: ረዳቶቹ
በሚቀጥሉት አራት ቀናት ገብተው ይጠናቀቃሉ፡፡”
“ጭፍን ሽብር ወዴት ያደርስናል?”
“አየህ.… ለወራት ብንታገልም ወደ ምስጢሩ ሰብረን ማለፍ አልቻልንም፡፡ ይህ የሚያሳየው ደግሞ ምሥጢሩ የሚጠበቀው እጅግ ከፍተኛ የድርጅት ብቃት ባለው አካል መሆኑን ነው:: ስለዚህ እኛ በጭፍን የምናካሂደው ሽብር በዚህ ድርጅት ሠንሠለት ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡ሆኖም ዋናው ጥቃት ይህ አይደለም። ዋነኛ ዓላማችን በድርጅቱና በመላው አፍሪካ ውስጥ ሽብር መንዛትና የእርስ በርስ አለመተማመንን መዝራት
ከዚያም ተከትሎ በሚመጣው መፍረክረክና ግርግር ወደ ምሥጢሩ
የሚያደርሰንን ቀዳዳ መፈለግ ነው። አየህ ግድያውንና አፈናውን የምናካሄደው እኛ መሆናችንን እስካልደረሱበት የድርጅቱ አባላት የእራሳቸውን አንድነት መጠራጠርና እርስ በእርስ መፈራራት ይጀምራሉ፡፡”
“እና እርስ በእርስ ቢፈራሩስ?”
“በአጭር ጊዜ ውስጥ ድርጅቱ አፈናውንና ግድያውን እስካልተቆጣጠረው ድረስ እያንዳንዱ አባል የገዛ እራሱን ነፍስ ለማዳን ሽሽትና ማፈንገጥ ውስጥ ይገባል፤ክህደት ይከተላል::”
“ጥሩ፡፡ ግን የኔ ድርሻ ምንድነው?” አለ አሃሮን፡፡
“እርዱን እኔ አካሂዳለሁ፡፡ አንተ በግርግሩ ውስጥ ወደ ምሥጢሩ የሚያመራውን ቀዳዳ ትፈልጋለህ፡፡”
“መቼ ነው የሚጀመረው ያንተ እርድ?” አላ አሃሮን ፈገግ ብሎ፡፡
ከሶስት ቀናት በኋላ፡፡”
“ጥሩ” እለ አሃሮን በረጅሙ ተንፍሶ፡፡ ትንሽ ካመነታ በኋላ ቀጠለ
“ግን ምናልባት ከዚያ በፊት ምሥጢሩን አገኘዋለሁ የሚል ግምት አለኝ፡፡”
“እንዴት?” አለ አሚ ለመጀመሪያ ጊዜ እርጋታው እየጠፋ፡፡
“አሚ” አለ አሃሮን ግንባሩን አሻሽና “ምሥጢሩን በእርግጥ ያውቃል ብለን የምንገምተው አንድ የአፍሪካ ዲፕሎማት አለ፡፡ ለጊዜው ተሰውሮብናል፡፡ ቢሆንም ይህን ዲፕሎማት እያደነ

ያለ እንድ ኢትዮጵያዊ አድራሻውን አግኝቶታል የሚል ጥርጣሬ አለኝ፡፡ ይህን ኢትጵያዊ ስከታተል ቆይቼ በመጨረሻው ጭራውን ይዣለሁ።”
“ጀህን 'ኢትዮጵያዊ' የምትለውን አፍነኸዋል ማለት ነው?
“ኣላፈንኩትም፡፡ ከጀርባ እየተከታተልኩኝ ነው፡፡ ወደምፈልገው ዲፕሎማት እንደሚመራኝ እርግጠኝ ነኝ፡፡ ትላንት ማታ ይኽው ሰው ራሱን ቀያይሮ በሃሰት ስም ወደ ድሬዳዋ ከተማ ለመሄድ የባቡር ትኬት ሲያስቆርጥ ልጆቼ አገኙት::”
“እሺ፡፡” አለ አሚ አይኖቹን አጥብቦ ተጨማሪ ለመስማት እየተጠባበቀ፡፡
“ባቡሩ ዛሬ ማታ ይነሳል፡፡ ልጆቼን እንዲከተሉትና የላይቤርያውን
ዲፕሉማት ፈልገው እንዲያፍኑ አዘጋጅቻቸዋለሁ፡፡”
“በቂ ሃይል አለህ?”
ያከበቂ በላይ፡፡” አለ አሃሮን በመተማመን፡፡ “ስምንት ሰዎችን የያዘ
ቡድን ከኢትዮጵያዊው ጋር በአንድ ባቡር ለመሄድ ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡”
“ከዚህ ሁሉ በኋላ የፈለከውን ዲፕሎማት ሳታገኘው ብትቀርስ?”
“ያንተ እርድ ይቀጥላል” አለ አሃሮን ፈገግ ብሎ፡፡.....

#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
. “እሷን ብሎ እዚህ እናንተ ጋር አይመጣም ነበር?”
“ማንም አይመጣም” ብላ አንጀሊና መለሰች እና ቀጥላም “ብዙውን ጊዜ
አንዲት ጓደኛ ነበረቻት ምናልባትም ብዙውን ጊዜ ከእሷ ጋር ታሳልፍ የነበረው ከልጆቻችን ጋር ነበር ኮሎኒያ ጀሃሬዝ ውስጥ የምትኖር አንዲት ጓደኛ ነበረቻት
ምንአልባትም ብዙውን ጊዜ ከእሷ ጋር ታሳልፍ ይሆናል በቃ ከማንም ጋር አይቻት አላውቅም
የልጅትዋ ስም ፍሬድሪክ ነው?” ብሎ ዊልያምስ ጠየቃት፡፡
“አዎን ልክ ነው ስሟ ፍሬድሪክ ነው፡፡” አለችው አንጀሊና ፈገግ ብላ
“የአባቷን ስም አታውቂም?” ብሎ ዊልያምስ ሲጠይቅ አንጀሊና ኢንክሪቶ
ራስዋን በአሉታ ነቀነቀች
“እኔ አውቀዋለሁ” የሚል የህፃን ድምፅ ድንገት ተሰማ፡፡ ህፃኑም ሙሉ ነጭ የሜዳ ቴኒስ ልብሱን እንደለበሰ ከእነርሱ ጋር ተቀላቀለ
“ዚዳን ነው የአባቷ ስም ኮከብ የእግር ኳስ ተጫዋች ስለሆነ ስሙን
አልረሳሁትም”
“አመሰግናለሁ ግን ስምህን ማን ልበል?” ብሎ ዊልያምስ ጠየቀው
“አንቶኒዮ እባላለሁ” ብሎ ከመለስ በኋላ በአዋቂ ወሬ ውስጥ እያወራ ስለሆነ
ደስ አለው፡፡ ወላጆቹ ግን ልጁ ከዊልያምስ ጋር ሲያወራ ማየታቸው
እንደረበሻቸው ከፊታቸው ላይ ይነበብ ነበር፡፡
“ከቻርሎቴ ጋር ሆናችሁ ፍሬድሪክን አግኝታችኋት ታውቃላችሁ አንቶኒዮ?” ብሎ ዊልያምስ ልጁን ጠየቀው
“አዎን ብዙ ጊዜ እናውቃለን”
“የት ነበር የምታገኟት?”
የምናገኛት፡፡ እዚያ ሁሉም ሴቶች ናቸው ግን የውሃ ላይ ሸርተቴ ስላለው
“በመናፈሻው ውስጥ እና እሷ በምትኖርበት ቤት እየሄድን ነበር
...” ብሎ ሊቀጥል ሲል እናቱ አንጀሊና አቋርጣው
“በጣም ነው የምናመሰግነው የኔ ውድ” ብላ ከባልዋ ጋር በአይን እየተነጋገሩ “አሁን ወደ ቴኒስ ጨዋታህ መመለስ ትችላለህ አለችው፡፡”
ዊልያምስ የልጁን እጅ ይዞ “ቤትዋ የት እንደሆነ ታውቃለህ?” ብሎ ጠየቀው።
ይሄኔ አባቱ ጁሃን እንክሪቶ “የሜዳ ቴኒስ የስልጠና ሰአቱ ይረፍድበታል እባክህን ሚስተር ዊልያምስ ልጁ ከአንተ ስራ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ አክብረንም ስላገኘንህ ይሄን ያህልም ልትጫነን አይገባም” አለው።
“ከእኔ ስራ ጋር ይገናኛል እንጂ” ብሎ ዊልያምስ በቁርጠኛ ድምፁም
“ሲኞር ኢንክሪቶ እኔ የልጅቷን ቤት ማወቅ እፈልጋለሁ፤ ምክንያቱም ይቺ ፍሬድሪክ ዚዳን ብቻ ልትሆን ትችላለች በቻርሎቴ ላይ ምን እንደደረስ ልታውቅ የምትችለው፡፡ ምስኪኖቹ የቻርሎቴ ቤተሰቦች በአሁኑ ሰአት ምን
እየተሰማቸው እንደሆነ አስበው እስቲ? የጠፋው ልጅህ ቢሆን ምን ይሰማህ
ነበር?” ብሎ ልሂድ ወይስ ልቅር እያለ ወደሚያመነታው ልጁ ወደ አንቶኒዮ
አመለከተው፡፡
ይሄኔም የልጁ አባት ተረጋጋ፡፡ “እና አንቶኒዮ የልጅትዋ ቤት የት እንደሆነ ታውቃለህ?” ብሎ በእርጋታ ጠየቀው፡፡
“አዎን አውቀዋለሁ!” ብሎ አንቶኒዮ ፈገግ አለ፡፡ “እና እኔ ነገሮቹን አልረሳም፡፡ ከፈለግክ አሁን ቤቷ ልወስድክ እችላለሁ፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡
ፍሬድሪኩ ዚዳን ሃያዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ ወጣት ሴት ናት፡፡ፀጉሯ አመድማ ቡኒ እና አጭር ነው፡፡ ፊቷም ሞላ ብሎ ነጣ ያለ ስለሆነ በአርባዎቹ ዕድሜዋ ላይ የምትገኝ ሴት ያስመስላታል፡፡ የለበሰችው ልብስ
ግን ይህንን ነገሯን የሚሸፍንላት አይነት ነው፡፡ የበሩን ደውል ሰምታ ለዊልያምስ ስትከፍትለት ዊልያምስ በጣም አጭር ቀሚሷን፣ ነጭ ቲሸርት እና ከቦዲዋ ስር የሚታየውን የጡት ማስያዣዋን ተመለከተ፡፡ ዊልያምስም የመጣበትን ምክንያት ሲያሳውቃት ፍሬድሪኩ ቤትዋ እንዲገባ በትህትና ጠየቀችው፡፡
“ከበጎ አድራጎት ሀላፊዋ ሴትዮ ውጪ አንተ ብቻ ነህ ስለ ቻርሎቴ ለመጠየቅ እዚህ ድረስ የመጣኸው” ብላው እንዲቀመጥ ሶፋው ላይ ያሉትን
ጨርቆች ወደ አንድ ጎን ሰበሰበችለት።
“የትኛዋ ሴትዮ?”
“የአፈላላጊ ድርጅቱ ሀላፊን ለማለት ነው” ብላ ፍሬድሪኩ ግልፅ አደረገችለት እና በመቀጠልም “እዚህ ካሉት ፖሊሶች በበለጠ መልኩ ቻርሎቴን ፈልጎ ለማግኘት በየቦታው ፎቶዎቿን በመለጠፍ ፍለጋቸውን ሲያደርጉ ነበሩ።”
ይሄ ጥሩ ነገር ሳይሆን አይቀርም ብሎ ዊልያምስ በውስጡ አሰበ፡፡
“ምክንያቱም ከተከር እና ሜሪ ክላንሲ እንደተረዳው ቫለንቲና ባደን እና የበጎ
አድራጎት ድርጅት በቅርቡ ብቻ እንዳገኟቸው ነው፡፡ ለዚያውም በቴሌቪዥን ቀርበው ስለጠፋችው ልጃቸው እንዲናገሩ ለማድረግ ነው ያገኟቸው።
ቫለንቲና ባደን ገና ቻርሎቴ ከጠፋችበት ጊዜ ጀምሮ በቻርሎቴ ጉዳይ ፍላጎት ኖሯት ትንቀሳቀስ እንደነበር ስላወቀ ጥሩ ነገር አልተሰማውም። ነገሩ ጥሩ ቢሆን ኖሮ ለቻርሎቴ ወላጆች የቻርሎቴን ጓደኛ ፍሬድሪኩን አግኝታ እንዳነጋገረቻት ተነግራቸው ነበር፡፡
የአሜሪካ ፖሊስ በቻርሎቴ መጥፋት ጉዳይ ላይ ምርመራ እንደሚያደርጉ በወቅቱ ተነግሮኝ ነበር፡፡ ነገር ግን እስካሁን ድረስ አንድም ፖሊስ እኔን አላገኘኝም" አለችው ፍሬድሪኩ፡፡
እንግሊዘኛዋን የምትናገረው በፈረንሳይኛ ዘይቤ (ቅላፄ) መሆኑን ያስተዋለው ዊልያምስ ስለ እዚህ ጉዳይ ሲጠይቃት “ልጅ እያለሁ ከቤተሰቤ ነበር የእንግሊዘኛ ቋንቋ የተማርኩት። አሁን ላይ ደግሞ እስፓኒሽ እና ጣልያንኛ በደንብ መናገር
እችላለሁ፡፡ ስለዚህም ይመስለኛል እዚህ ሀገር ቀለል ብሎኝ የምኖረው።
ቻርሊ ግን እስፓኒሽ ብዙም ስለማትችል ሰዎች ያገልሏት ነበር፡፡ ለስራው አዲስ እና ልጅ ስለነበረች እኔ እንድተረጉምላት ትጠይቀኝ ነበር።በእግዚአብሔር በጣም ነበር የምታሳዝነው፡፡
“እዚህ ለወራት ያህል ለእንክሪቶ ቤተሰብ እየሰራች ስትኖር እንዴት ትኖር እንደነበር ማወቅ እፈልጋለሁ” ብሎ ዊልያምስ ሲጠይቃት ፍሬድሪኩም ወደ እሱ ዘንበል ብላ በጉጉት እየተመለከተችው “እሺ ስለ እሷ ምንድነው ማወቅ የፈለከው?” ብላ ጠየቀችው፡፡
እሷ ትሰራበት የነበረውን ቤተሰብ ቻርሎቴ የወንድ ጓደኛ የላትም ነው ያሉኝ፡፡ ይህ እውነት ነው?”
“እነርሱ ስላላዩ ፍቅረኛ የላትም ቢሉ ችግር የለውም!!!”
“ነገር ግን ቻርሊ ከሆነ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት ነበራት፡፡” ይሄንን ነገር ደግሞ ለፖሊሶች ነግሬያቸው ነበር፡፡የጠፋችውም ያን ምሽት እሱን
ልታገኝ ሄዳ ሳለ ነው ብዬ ብነግራቸውም በዚህ ጉዳይ ላይ ግን ፖሊሶቹ ምንም አይነት ፍላጎት ሲያሳዩ አላየሁም” አለችው።
“እኔ ስለ እሱ በጣም ማወቅ እፈልጋለሁ” አላት እና ዊልያምስ በመቀጠልም “በአካል አግኝተው ታውቂያለሽ? ስሙንስ ታውቂዋለሽ?” ብሎ ጠየቃት፡፡ ፍሬድሪኩም ራስዋን በአሉታ ነቀነቀች፡፡
“አላውቀውም በቃ ሰውዬው ሚስጥር ነበር፡፡ ቻርሊ ሁሌም ስለእሱ ሳታወራኝ ያደረችበት ቀን የለም፡፡ ፍቅረኛዋ ባለ ትዳር ነው፡፡ በእድሜም ከእሷ በጣም ይበልጣታል፡፡ ስለዚህ ሰውዬውን ልታገናኘኝም ሆነ ስለ እሱ ማንነት ልትነግረኝ አልቻለችም” ብላ ስትነግረው ዊልያምስ በጣም በጉጉት እያዳመጣት ነበር፡፡
“ሜክሲኳዊ ነው ወይስ አሜሪካዊ?”
“ስለ ዜግነቱ ስታወራ ሰምቼ አላውቅም፤ ግን የዚህ ሀገር ሰው ይመስለኛል ወይም ግምቴ ስህተት ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ለብዙ ጊዜያት ወደ ሌሎች ሀገሮች በስራ ምክንያት የሚንቀሳቀስ ይመስለኛል፡፡ ማለቴ ብዙውን ጊዜ ከተማ ውስጥ አይገኝም ነበር፡፡ ባይገርምህ እሱ ወደ ውጪ ሀገር ለስራ በሚወጣባቸው ጊዜያት ልክ ሙጭሊቷ እንደጠፋባት እናት ድመት ነበር ያደርጋት የነበረው።
ዊልያምስ ማስታወሻ እየወሰደ “እንዴት እንደተገናኙ ታውቂያለሽ?” ብሎ
ፍሬድሪኩም ዝም ብላ ለጥቂት ሰከንዶች ስታስብ ቆየችና በመቀጠልም
“ከእሱ ጋር የተገናኙት

ተቀጥራ ከምትሰራበት ቤት ውስጥ ይመስለኛል፡፡
የእሷ አሰሪ ከዚህ ሰውዬ ጋር አብረው የሆነ ስራ ይሰራሉ፡፡”
“ሌላ የምታውቂው ነገር የለም? ማለቴ ሰውዬው ምን እንደሚሰራ አልነገረችሽም? ስለትዳሩስ ወይንም ደግሞ ስለ አስተዳደጉ አላጫወተችሽም? ወይም ሌላ ሰውዬውን ፈልጌ እንዳገኘው የሚያስችለኝ ነገር አልነገረችሽም?” ብሎ ጠየቃት፡፡
“ያለ አይመስለኝም፡፡” ብላ ፍሬድሪኩ የታችኛውን ከንፈሯን ነከሰች እና
“ምንም እያገዝኩህ አይደለም መሰለኝ? ይመስለኛል ሰውዬው ፋይናንስ ላይ
ነው የሚሰራው፡፡ በጣም ብዙ ገንዘብ የሚያስገኝ ስራን መሰለኝ ይሰራ
የነበረው፡፡ ያው እንደነገርኩህ ሰውዬው ባለ ትዳር እንደነበረ አውቃለሁ ነገር
ግን ከዚያ የዘለለ ስለ ሰውዬው ብዙ አላውቅም፡፡ ብዙ ጊዜ እሷ ስለ ሰውዬው
የምታወራኝ በአልጋ ላይ ጫወታ ጎበዝ እንደሆነ እና ስለሚገዛላት ስጦታዎች
ነበር፡፡”
“ምን አይነት ስጦታዎች?”
ፍሬድሪኩ ትልቅ ቡናማ አይንዋን እያበራች “አልማዝ እና የአንድ ሺህ
ዶላር ጫማ ገዝቶላት ነበር፡፡ ስጦታዎቹ ውድ እና ምርጥ ነበሩ፡፡ ብቻ ምን
ልበልህ እሷ እሱን እንደጣኦት ነበር ታመልከው የነበረው፡፡ እንደ እሷ
አነጋገር ከሆነ ፍቅሩ በሁለቱም በኩል እንደነበር ነው የገባኝ፡፡”
“እሷ በጠፋችበት ጊዜ ላይ አብረው ነበሩ? ማለቴ ተጣልተው ነበር?
ወይንስ ግንኙነታቸውን አቋርጠው ነበር?” ብሎ ጠየቃት፡፡
ፍሬድሪኩም በአሉታ እራሷን ወዝውዛ “በፍፁም አልተጣሉም አብረው ነበሩ፡፡ እንዲያውም ያኔ ፍቅራቸው በጣም የደራበት ወቅት ላይ ነበር፡፡የጠፋችበት ምሽት ላይ ለመገናኘት ተቀጣጥረው ስለነበር በጣም ደስ ብሏት ነበር፡፡ ትዝ ይለኛል አንተ የተቀመጥክበት ቦታ ላይ ተቀምጣ ቀጣዩን ህይወቷን እንዴት ከዚህ ሰው ጋር በደስታ እንደምታሳልፍም ስትነግረኝ ነበር፡፡”
እስከአሁን ድረስ ቻርሎቴ ሞታለች ብሎ ነበር ያስብ የነበረው፡፡ አሁን ግን ጓደኛዋ ስለ ቻርሎቴ የፍቅር ህይወት ስትነግረው ምናልባት የሆነ የተስፋ ጭላንጭል ስለታየው “ምናልባት ከሰውዬው ጋር አብረው ኮብልለው ይሆን? ምናልባትም ከዚህ ሰውዬ ጋር የሆነ ሀገር ውስጥ ከሚገኝ የባህር ዳርቻ ላይ አብረው እየኖሩ ይመስልሻል?” ብሎ ጠየቃት፡፡
“አንዳንድ ጊዜ እኔም እንደዚያ አስባለሁ።” ብላ ፍሬድሪኩ በመቀጠል
“እንደዚያ ቢሆን በጣም ነበር ደስ የሚለኝ፡፡ ግን አይመስለኝም፡፡ አንተስ ይመስልሃል? ትዳር ያለው፣ ሀይለኛ እና ቤተሰብ ያለው ሀብታም ሰው እንደዚህ በቀላሉ ጠፍቶ ሊቆይ አይችልም፡፡ እንደዛ ቢሆን እንኳ ቻርሊ ለቤተሰቧ ስላለችበት ሁኔታ የማታሳውቅ መጥፎ ልጅ አይደለችም፡፡” ብላ ሃሳቧን ገለፀችለት፡፡
ዊልያምም ፍሬድሪኩን ስላደረገችለት ትብብር አመሰገናት እና የቢዝነስ
ካርዱንም እየሰጣት “ለሚቀጥሉት 10 ቀናት ያህል ሒልተን ሆቴል ነው
የምቆየው፡፡ አዲስ የተለየ ነገር ካስታወስሽ ካርዱ ላይ ባለው ስልክ ቁጥር ልትደውይልኝ ትችያለሽ፡፡” ብሎ ተሰናበታት፡፡
ከዚያ በኋላ ነገሮች በፍጥነት ማለፍ ጀመሩ፡፡ ወደ ኢንክሪቶ ቤተሰብም
በድጋሚ ተመልሶ ባለትዳር የሆነ ከጁሃን ኢንክሪቶ ጋር ቢዝነስ አብሮ የሚሰራ ጎልማሳ ቤታቸው መጥቶ ያውቅ እንደሆነ ቢጠይቃቸውም አጥጋቢ መልስ ሳይሰጡት ቆዩ፡፡ እንደ እድል ሆኖ ግን የኢንክሪቶ ቤተሰብ ሰራተኛ የሆነ አንድ ሰውዬ ጥሩ መረጃን ሰጥቶት ነበር፡፡ ይህንን የቤቱን ሰራተኛ ዊልያምስ ውጪ አግኝቶት የሜክሲኮ ፔንሶዎችን በጉቦ መልክ ሰጥቶት እና የአሜሪካን ውስኪንም ጋብዞት ስለተለየው ጠቃሚ መረጃን አቀብሎት ነበር፡፡ ይሄ ሰራተኛ እንደተናገረው ከሆነ የሆነ መልከመልካም አሜሪካዊ ጎልማሳ ሰው ወደ ኢንክሪቶ ቤት ብዙ ጊዜ ይመጣ እንደነበር፣ እንዲሁም ደግሞ ከቻርሎቴ ጋርም ሲያወራ እንደተመለከተ አጫወተው፡፡
“እንደምትወደው ያስታውቃል፤ እርስ በእርስ ይዋደዱ ነበር” ብሎ ሌላኛው የእንክሪቶ ቤተሰብ አትክልተኛ በወላቃ ጥርሱ እየሳቀም
“ሁኔታቸውን በማየት ማወቅ ይቻላል፡፡” አለው፡፡
ለማንኛውም ይሄ አሜሪካዊ ወይም የባንክ ሰራተኛ አሊያም ደግሞ ጠበቃ የተባለው ሰው ሳይሆን አይቀርም ለጁሃን እንክሪቶን ያስተዋወቀው።”ሉዊስ ሮድሪጌዝ የተባለ ሜክሲኳዊ ሀብታም እና ቸር ሰው እንደሆነም ጭምር ሌሎች የቤቱ ሰራተኞች ለዊሊያምስ ነገሩት፡፡
አትክልተኛው በመቀጠል “ሮድሪጌዝአ በጣም ምርጥ ሰው ነው” ብሎ
ሌሎች የቤት ሰራተኞች ስለ ኢንክሪቶ ቤተሰብና ስለ ሰውዬው ሲያወሩ
በሚገልጹበት ድምፀት እንደተሞላ “ሮድሪጌዝ ከድሀ ቤተሰብ ነው የተገኘው፡፡
ግን እንደ ኢንክሪቶ ቤተሰብ ሳይሆን አሁንም ቢሆን እሱ ለድሃ ሰዎች ያስባል፡፡ ግን በእሱ ዙሪያ ስለሚገኙት ማለትም ስለ አሜሪካዊው የባንክ ሰራተኛ ጉዳይ ምንም የማውቀው ነገር የለም፡፡” ብሎ መልሶለት ነበር፡፡
ዊልያምስ ፍሬድሪኩን ካገኛት ከጥቂት ቀናት በኋላ በጣም በጥሩ ስሜት
ውስጥ ሁኖ ወደ ሚስቱ ደወለና....

#ክፍል_ሰላሳ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
....አፓርትመንቷ ጋ ከመድረሱ በፊት ወደ ግራ እጥፍ ብሎ ከአንድ ትንሽ ሻይ ቤት ገባና በሩ አጠገብ ካለ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሻይ አዘዘ፡፡ ጥንቃቄ ያስፈልጋል እርጋታ፡፡ ባሻገር የሚታየው የአፓርትመንቱ ቅጥር ግቢ አለቅጥ ጭር ብሏል፡፡ የወትሮው ግርግር ወጪና ገቢ አይታይም፡፡ ከአፓርትመንቱ ስር መኪናዎች በስርኣት ተደርድረው ቆመዋል፡፡ ለወትሮው ሲሯሯጠ የሚታዩ ሲጫወቱ የሚገኙ የአፓርትመንቱ ነዋሪዎች ልጆች በግቢው አይታዩም፡፡በር ላይ ብቻ እኛው የድሮው ሽማግሌ ዘበኛ አፈርማ ካፖርታቸውን ደርበው ከዘበኛዋ ቤት ደጃፍ ላይ ቁጭ ብለው ያንጎላጃሉ፡፡
ይህ ነው ብሎ ምክንያት ሳይሰጠውም ፍርሃት ገባው፡፡ ፀጥታ ተራ ነገር አይደለም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሙሉ ፀጥታ አደጋ ከመድረሱ በፊት የሚያንዣብብ ማዘናጊያና አደጋው ከደረሰ በኋላ ድንጋጤን ደርቦ የሚንጠለጠል ግግርት ነው፡፡ ጥፍሩን መቆረጣጠም ጀመረ። ጭንቅላቱ ግራና ቀኝ ቆሞ ይሟገት ጀመር፡፡
ሰዓቱን ተመለከተ አሥራ ሁለት ከሃያ፡፡
ዝም ብዬ ነውኮ ይልቅ ብሎ ገብቼ እይቻት ብወጣ ይሻላል...ግን በአካባቢው የአውሬው አይን ቢኖርስ ስገባ ቢያየኝስ?ወዲያው ቢከቡኝስ ታዲያ እስከመቼ እዚህ ተቀምጨ እቆያለሁ?! ስልክ ደውዩ
ወንድሟን «ውጣ» ብለውስ ከአፓርትመንቱ እራቅ እንዲል ነግሬው
ባነጋግረውስ ምን ዋጋ አለው? ገብቼ ካላየኋትማ ለምንስ መጣሁ? ብገባ
ይሻላል... አዎ አይቻት ቶሉ እወጣለሁ… በአካባቢው ካሉ ግን ያለጥርጥር
እንደ ጅግራ ነው ክንፌን ብለው የሚጥሉኝ…ምን ዘዴ መፍጠር ይሻላል?
ጭንቅላቱን አፋጨው፡፡ አካባቢው እየጨለመ መጣ፡፡ የመንገድ
መብራቶች ቦግ ቦግ ቢሉም ደቂቃዎች በሄዱ ቁጥር ይበልጥ የሚደምቀውን
ጨለማ መታገል ማሸነፍ መግፈፍ እያቃታቸው መጠ፡፡ ናትናኤል ያለበትን
ክፍል ቃኘው፡፡ ትንሿ የሻይ ቤት ንጽህና የሌላት ናት፡፡ . በውስጧ የተሰበሰቡትም ሰዎች እሱው?እንዳጠለቀው በህይት የተጨማለቀ የጋራዥ ቱታ ቆሻሻ ልብስ የለበሱ ቀዝቅተኛ ኑሮ የሚገፉ፤ የሚጎትቱ እንደሆነ “ ያስታውቃሉ፡፡ ሰዓቱን ድጋሚ ተመለከተ፡፡ አስራ ሁለት ተኩል፡፡
በተቀመጠበት እንዳለ አሻግሮ የአፓርትመቱን መግቢያ በር ቃኘው፡፡ በሩቅ በድንግዝግዝ አንድ ሰው ይታየዋል፡፡ የበሩን አንድ ወገን መቃን ተደግፎ ቆሟል ሰውየወ:: ናትናኤል አትካር ተመለከተው፤ ካፖርት ለብሶ
አንገተዬውን ቀልብሶ የቆመውን ሰው ግን ሊለየው አልቻለም፡፡
'ብስራት ይሆን? መሆን አለበት። አሰበ፡፡
ተነስቶ ወደ አፓርትመንቱ መሄድ ግን ፈራ፡፡ ድጋሚ ዞር አለና እሱ ከተቀመጠበት ስፍራ ፈንጠር ብሎ ሁለት ክንዶቹን ጠረጴዛ ላይ ተክሎ
ጉንጭጮቹን በሁለት መዳፎቹ ደግፎ የተቀመጠ ጎረምሳ ላይ አተኮረ፡፡ አንድ
ዘዴ መጣለት:: ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ ወጣቱ ተጠጋ፡፡
“ሰላም...ልቀመጥ?” አለ ከወጣቱ ጠረጴዛ ዙሪያ ከተደረደሩት ሦስት
ወንበሮች አንዱን ያዝ ኣድርጎ፡፡
ወጣቱ ጉንጮቹን ዘሁለት መዳፎቹ ውስጥ ሳያወጣ አይኑን ብቻ
አቅንቶ ተመለከተው::
“ተቀመጥ:: አለ ወጣቱ ግድ እንደሌለው ለማሳየት ትከሻውን ከፍ ዝቅ አድርጎ፡፡
“እንድ የምትሰራልኝ ስራ ነበር፡፡ በቂ ገንዘብ እከፍልሃለሁ፡፡” አለ ናትናኤል ከኪሱ ቦርሳወን አውጥቶ ሁለት የአስር ብር ኖቶች እየመዘዘ፡፡
ከፊት ለፊቱ የተቀመጠው ወጣት ቀያዮቹን ኖቶች ሲመለከት ጉንጮቹን ለቀቅ አደረገና ቀና አለ፡፡ የደረበው ረጅም አሮጌ ኮት አንገትዬው ነትቧል፤ ከውስጥ ሸሚዞ በሽቅጧል፡፡
“ትስማማለህ?”
“ምንድነው የምሰራልህ? የሚደበደብ ሰው ከሆነ እርሳው፡፡” አለ ወጣቱ አገጩ ላይ ችፍርግ ብሎ የበቀለውን የቆሽሽ ጺም እያከከ፡፡
“አይደለም፡፡” አለ ናትናኤል ወደፊት ጠጋ ብሎ “እየው ያ ፎቅ ይታይሃል? በሩ ላይ የቆመው ሰውዬ ይታይሃል?”
ወጣቱ በ'አዎንታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ፡፡
“…ቀጥ ብለህ ወደ ሰውየው ትሄድና አጠገቡ ልትደርስ ጥቂት
እርምጃዎች ሲቀርህ ናትናኤል ይፈልግሃል። ተከተለኝ በለውና ድንገት
ፊትህን መልሰህ እየሮጥክ ከግቢው ወጥተህ ትመጣለህ፡፡”
“እናስ.. ከዛ በኋላስ?”
“በቃ::”
“እንዴት በቃ? እለ ወጣቱ ፊቱ ጥርጣሬ ለብሶ:: “እዛች ደርሼ ስለተመለስኩ ነው ይህን የምትሰጠኝ?” ወጣቱ፡፡ ዓይኖቹን በሁለቱ፡ የአስር ብር ኖቶች ላይ አነጣጠራቸው፡፡
“አዎ::"
“ምንም ሳልሰራ?”
“አዎ፡፡”
“አትቀልድ፡፡ ነገር አለው፡፡” አለ ጎረምሳው ወደ አንድ ወገን እየሳቀ፡፡
“ምንም ነገር የለውም፡፡”
ወጣቱ ኣይኖቸን አጥብቦ ናትናኤልን ሊያጠናው ሞከረ::
“ለምን እራስህ አትሄድም?"
“ትፈልጋለህ አትፈልግም?” አለ ናትናኤል ሁለቱን የአስር ብር ኖቶች ወደፊት እየገፋ::
ወጣቱ፡ ከራሱ ጋር ክርክር የገጠመ መሰለ፡፡ ናትናኤል ድንገት ትቶት ሲነሳ ፈጠን ብሎ አብሮት ተነሳ፡፡
“እሺ አምጣ፡፡ ፀጥ ብዬ ገብቼ ናትናኤል ያጠራሃል ብዬው ፀጥ ብዬ መወጣት ነው… እይደል?”
“እየሮጥክ ነው የምትወጣው፤ ፀጥ ብለህ አያደለም:: ልክ ከሰውየው እንደምትሸሽ ዓይነት እየሮጥክ፡፡” ናትናኤል ቆፍጠን አለ ሃያ ብር
የያዘውን ቀኝ እጁን ወደኋላ ሰብስቦ፡፡
“እሺ ኣምጣ…. እሮጣለሁ፡፡” አለ ወጣቱ እጁን ወደ ብሩ ዘርግቶ፡፡
“ደርስህ ስትመለስ…. መሮጥሀን ካየሁ በኋላ፡፡” ናትናኤል ፈርጠም አላ::
“እሺ ግማሹን ስጠኝ::”
“ደርሰህ ስትመለስ መሉው ያንተ ነው፡፡”
ወጣቱ ከሻይ ቤቷ ወጥቶ ወደ አፓርትመንቱ ሲያመራ ናትናኤል
ተከትሎት ወጣና የመኪና መንገዱን ተሻግሮ ከለላ ይዞ የሚሆነውን
ይከታተል ጀመር፡፡
የሚጠባበቁት ሰዎች ካሉ ወደ አፓርትመንቱ ሲገባ ሊይዘት ወጥመድ ያጠመዱ ካሉ። ወጥመዳቸው በወጣቱ ላይ እንደሚወነጨፍ እርግጠኛ ነበር፡፡
ወጣቱ የአፓርትመንቱን የአጥር ግቢ በር አልፎ ሲገባ ሽማግሌው ዘበኛ ከእንቅልፋቸው አልነቁም:: ወጣቱ እጆቹን የኮት ከሶቹ ውስጥ ከትቶ በእርጋታ አፓርትመንቱ በር ላይ ወደቆመው ሰው አመራ፡፡ ሰውዬውጋ ለመድረስ በግምት አአስር እርምጃዎች ሲቀሩት ድንገት ቆም አለና ናትናኤል እንዳዘዘው መልዕክቱን ተንፍሶ ፊቱን መልሶ ሮጥ ከማለቱ፡ ግራና ቀኝ ቆመው የነበሩ መኪናዎች በሮች እየተበረገዱ አራት ሰዎች ዱብ ዱብ አሉ፡፡
ናትናኤል አይኖቹን አፍጥጦ ቀረ፡፡ በሁኔታው የተደናገጠው ወጣት
ለማምለጥ ቢሞክርም ከአጥር ግቢው በር ከመድረሱ በፊት ይዘው እፍስፍጥ
አድርገው ከአንደኛዋ መኪና ውስጥ ከተቱት፡፡
ለደቂቃዎች ናትናኤል ካለበት ሳይንቀሳቀስ ተጠባበቀ፡፡ ወዲያው
የመኪናዋ በር ተከፈተና በሁለት በኩል የወጣቱን ክንዶች የልጨመደዱ ሁለት
ሰዎችና ሌሎች ተጨጨማሪ ሶስት ሰዎች ወደ አፓርትመንቱ፡ ግቢ በር ያጣደፉ ጀመር፡፡ ከአፓርትመንቱ፡ ግቢ ሲወጡ ናትናኤል ወደ ኋላ አፈገፈገና ጥሩ ከለላ ይዞ በሩቁ በአይኑ ያስተውላቸው ጀመር::
አምስቱ ሰዎች ወጣቱን ከበው ወደ ሻይ ቤቷ ተጣደፉ፡፡ ከሻይ ቤቷ ደጃፍ፡ እንደደረሱ ሀለቱ ልጁን አስቀድመን ከተል ብለው ሲገቡ ሁለቱ፡፡ በሻይ ቤቷ ጓሮ ዞሩ፡፡ የተቀረው አምስተኛው እፊት ለፊት ጀርባውን ግድግዳው ላያ ለጥፎ ቀኝ እጁን ከኮቱ፡ ስር ብብቱ ስር ከቶ ቆመ::
ናትናኤል ሰውየው ከኮቱ ስር የጨበጠው ምን እንደሆነ ሲረዳ አብርሃም ታወሰው፡፡ ሻይ ቤቷ ውስጥ የቡት ሰዎች ከውስጥ ሲያጡት ወጥተው አካበቢውን ሊያስሱ እንደሚችሉ ሲረዳ ፈጠን ብሎ ከተደበቀበት ወጣና ሽቅብ በሩጫ ተፈተለኩ ታክሲ ተራ ደርሶ ለገሃር ብሎ ታክሲው ወንበር ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሁሉ ሁለት ሦስቴ እየተገላመጠ ተመለከተ፡፡ ከጀርባው የተከተለው ሰው ግን አልነበረም፡፡ ወደኋላ መመለስ

አይችልም፡፡ ካሁን በኋላ ያለው ምርጫ መጨከን ብቻ ነው፡፡ መቁረጥ:: ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለርብቃም አደገኛ ነው አውቀዋል! ስልኳን ጠልፈውታል ማለት
ነው! ለዚህ ነው በሯ : ላይ : ተዘጋጅተው የጠበቁት፡፡ ቢሄድ'ኮ ኖሮ ባይጠረጥርና እሱ ራሱ ሄዶ ቢሆን ኖሮኮ... "
ናትናኤል ሰውነቱን ሁሉ ዘገነነው፡፡ የአብርሃም ዓይኖች ታወሱት.…የምሥራች እሬሳ ተደቀነበት። አማተበ፡፡ምንም ምርጫ የለውም:: መቼም ርብቃ ታዝናላች…. ግን ሁኔታውን እንዴት ሊያስረዳት ይችላል? «ቤትሽን
ከበው ይጠብቁኛል» አይላት ነገር ለእሷም አደገኛ ነው:: ስለነገሩ የምታውቅ
ነው የሚያስመስልባት:: ለጊዜው ትቀየመው፡፡ ኣንድ ቀን ያስረዳታል፡፡ ከስር
ከመሰረቱ ይተርክላታል፤ ታምነዋለች፣ እርግጠኛ ነው ታምነዋለች::
የተሳፈረበት ታክሲ ባቡር ጣቢያ ደርሶ ክታክሲው ሲወርድ ዙሪያው
ጨለማ ለብሶ ነበር፡፡ ሳያመነታ ወደ አንድ ቡና ቤት ኣመራና መታ ጠቢያ .
ቤት ጠይቆ ገባ፡፡
ቀልጠፍ ብሎ በዘይትና በአቧራ የተጨማለቀ ቱታውን ከላዩ ላይ
ኣውልቆ፣ እጆቹን ተጣጥቦ ከጨርቅ ባርኔጣው ስር የተደፈጠጠ ፀጉሩን
አበጣጥሮ ሲጨርስ የገዛ ልብሱን ለበሰና ከሸራ ሻንጣው ወስጥ ትቶ በሸሚዙ ላይ ነጭ ጀለቢያውን ኣጠለቀ፡፡ መደረቢያውን በኣንገቱ አጠለቀና በለፈስፋሳ የጨርቅ ቆቡ ፋንታ ሽርጡን ጠምዘዝ አድርጎ ጭንቅላቱ ላያ ጠምጠመው:: ያደረገውን የቆዳ ጫማ በነጠላ ጫማ ቀየረው፡፡ በሻንጣው ይዞት ሲዞር ከዋለው በእንስት ቅጠል ከተጠቀለለው ጠባላጋ የጫት ቅጠል አንድ ዘለላ መዝዞ ጥቂት ቅጠሎች ቀነጣጠበና በመዳፉ ኣድቦልበሎ ከኣፉ ጨመረው፡፡ ያለቀውን ቱታ እዛው መታጠቢያ ቤቱ ውስጥ ትቶ ሻንጣውን በቀኝ ትከሻው አንጠልጥሎ ዙርባ ጫቱን በግራ ብብቱ ሽጉጦ ከቡና ቤቱ ወጣ፡፡ በኪሱ ያለው መታወቂያ ነጭ ሽሚዝ ለብሶ፣ የእስላም ቆብ ደፍቶ
የተነሳው ፎቶግራፉ የተለጠፈበት ነው::
ጀማል አብዱልከሪም ይላል ስሙ፡፡
ወደ ባቡር ጣቢያው ስያመራ ኣድቦልበሉ አፉ በውስጥ የከተተው ጫት በምራቁ እየራሰ ጣዕም ማፍለቅ ሲጀምር እሬት የጎረስ መስለው፡፡ምራቁን እንትፍ አለና የተጨማደደ ፊቱን ለመፍታት እየታገለ ጉንጬን ቡጢ አሳክሎ ሰልፍ ከያዝወ ባቡር ተሳፋሪ ኋላ ስፍራውን ያዘ፡፡
ሸኝው፣ ተጓዡ፣ ህፃኑ፥ ሽማግሌው፤ ሌባው፣ ነጋዴው፣ ዘንቢሉ፣ ሻንጣው፣ ትከሻው፣ ዳሌው እርስ በርሱ ያጋፋል፡፡ በባቡር ሄዶ ስለማያውቅ ይሆናል ዙሪያውን ተለማምዶ የግድ የለሽነት ገፅታ ለመላበስ ተቸገረ፡፡በገፉት ቁጥር ገድገድ እያለ፣ እግሩ ስር በገባ ቀጥር እየተደናቀፈ፣ ትኬቱን አሳይቶ ከባቡሩ ገብቶ ቦታውን ያዘ፡፡ ጀርባው ተከትለውት ከገቡት ሰዎች መሃል ዓይኖቹ በአንድ ሴተ ላይ አረፉ፡፡ ሴትዬዋ አጠገቧ ካለ ጎልማሳ ጋር እየተጫወተች አልፋ ከጀርባው በሁለተኛው ረድፍ ተቀመጠች:: ለአንድ
አፍታ ዞር ብሎ ተመለከታት፡፡ ፊቷን ያውቀዋል... ግራ ግንባሯ ላይ
ያለውን የሽታ ምልክት ከዚህ በፊት አይቶታል፡፡ ማነች? ድንገት ሴትየዋ
ዞር ስትል ዓይን ለዓይን ተጋጩ፡፡ ደንገጥ ብላ ዓይኖቿን ሰበረች፡፡ ናትናኤል
ግራ ገባው፡፡ ማነች? ያውቃታል…ማነች?
ባቡሩ ጡሩምባውን አምባረቀው:: ከአንድ ሰዓት ተኩል ቆይታ በኋላ ባቡሩ ተንቀሳቀሰ፡፡ ናትናኤል ከጀርባው የተቀመጠችው ሴት ማንነት
ከነከነው፡፡
ባቡሩ ከጣቢያው ተነስቶ የአዲስ አበባን መሃል ሰንጥቆ ውልቅ ሲል ከቤቶች በርና መስኮት የሚወጣ ብርሃን ታየው::: በምሽቱ ቀዝቃዛ አየር የሚሯሯጡ ህፃናት..በየመንገዱ ንፋስ የሚቀበሉ ወጣቶች ቆመው የሚያወጉ አዛውንቶች፡፡ ባቡሩ ጥሩምባውን አሰማ... ቱ..! ...ቱ! ! .
መኪናዎች በሰልፍ ቆመው ባቡሩን ሲያሳልፉ የጎተራ መንገድ ውልብ አለበት፡፡ ችምችም ያሉ ቤቶች… ከባቡሩ ጎንጎን የሚሮጡ ህፃናት እጃቸውን
ኦውለበለቡለት፡፡ፈገግ አለ፡፡የስልክ እንጨት…ሜዳ ሜዳ ባዶ ሜዳ ጨለማ
ሆዱ ባባበት… ሊያቅለሸልሸው ፈለገ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ አፉ ውስጥ ያለውን የጫት ጭማቂ ዋጥ አደረገና ፊቱን ኮሶ አስመሰለ፡፡ አእምሮው አላርፍ ሊለው ድጋሚ ፊቱን ጠምዘዝ አድርጎ ከጀርባ ያለችውን ሴት ተመለከታት፡፡ ድጋሚ ዓይን ለዓይን ሲጋጩ አሁንም ቀድማ ዓይኖቿን
ሰበረች፡፡ መስሎኝ ነው ወደስ አውቃታለሁ ፊቱን መልሶ ተቀመጠ፡፡ ባቡሩ ናዝሬት ከመድረሱ በፊት አዲስ አበባ ላይ ካንገርበበው ጥቁር ደመና ስር
አፈትልኮ ሲወጣ አካባቢው በጨረቃዋ ብርሃን ወገግ አለ፡፡ ናትናኤል በሩቁ
ተራሮችና ኮረብታዎቹ.. ጣት ጣት የሚያካክሉት ዛፎች ውልብ ውልብ
እያሉ ወደ መጠበት ሲጣደፉ ድሮ ህፃን ሆኖ አባቱ ያሉት ትዝ አለውና ፈገግ አለ
አንድ ጊዜ ድሮ በደብረዘይት መንገድ ሲሄዱ ነው፡፡ እናቱና አባቱ ከፊት እሱ ደግሞ ከኋላ ተቀምጦ ነበር፡፡ “ከተቀመጠበት ድንገት ተነስቶ
ከፊት ከተቀመጡት እናትና አባቱ ትከሻ መሃል ገባ አለና “አባዬ ዛፉ መሬቱ
ሁሉም ወዲያ ሄዱልህ!” አለ ወደ ጀርባው እያመለከተ ሌሎች ያሳዩት ጉድ ያገኘ መስሎት አደጋ ከመድረሱ በፊት ለማስጠንቀቅ፡፡
“ሀ! ሀ!ሀ! ሳቁበት አባቱ፡ የመኪናውን መሪ በግራ እጃቸው እንደያዙ ፊታቸዉን መለስ አድርገው በቀኝ እጃቸው ጉንጩን ቆንጠር ቆንጠር እያደረጉ፡፡ “አይ ናትናኤል... እኛ ወደ ደብረዘይት ስንሄድ
ደብረዘይት: ወደ እኛ መንገድ ጀምሯል አትለኝም? ህ! ህ! !“ እናቱም ተደርበው ሳቁበት::
“ያዝ፡፡:” የሚል ድምፅ ሰምቶ ከሃሣቡ ነቃ::
ናትናኤል ፊቱን መልሶ ተመለከተ::
ባቡሩ ውስጥ የተሳፈረች ወጣት ሴት በእፍኟ ዳቦ ቆሎ ዘግና ዘረጋችለት፡፡ ቀይ ነች:: የእንቁላል ቅርጽ ያለው ፊቷ… ጎላ ጎላ ያሉ ኣይኖቿ ጎረድ ያለው አፍንጫዋ... ትናንሽ ከናፍሯ የህፃን ገጽታ ስጥተዋታል፡፡ የአደሬ የባሀል
ልብስ ለብሳለች፡፡ ሳቅ ስትል ከላይ በስተቀኝ የወርቅ ጥርሷ ብልጭ አለለት::
“ያዝ .…ዳቦ ቆሎ፡፡” አለችው እጇን ወደፊት ሰደድ አድርጋ፡፡ ድምጿ
ለሴትም ቢሆን ቀጠን ያለ ነው::
“አላህ ይስጥልኝ::¨ አላት እየተቀበላት፡፡
“የት ነው የምትሄድ?”
“ድሬዳዋ::”
“እኔም እዚያው ነኝ፡፡ ከዚያ ነው የምትኖረው?
“እ..እመላለሳለሁ…ነጋዴ ነኝ::
“ኮንትሮባንድ?“ አለች የተናገረችው ሥራ ህጋዊ የዕለት ተዕለት ተግባር እንደሆነ ሁሉ ተዝናንታ::
“አያ..ሱቅ አለኝ፡፡ ለሱ ነው::
“አትለኝም!
“ወላሂ፡፡”
የወርቅ ጥርሷን ብልጭ አደረገችለት።
“የሐረር ልጅ ነህ? "
“ወሎ፡፡“
“አትለኝም! እናቴ ወለዩ ነች፡፡” የወርቅ ጥርስ፡፡ “የአገሬ ልጅ ነህ ለካ!”
ፈገግ ኣለ ናትናኤል፡፡ ከያዘችው የዳቦ ቆሎ ጭማሪ ወግና አስታቀፈችው::
“ይጣፍጣል፡፡” አላት ኣይኑን ጨፍኖ፧ ኣፉ ወስጥ የነበረውን የጫት ቅጠል እንዳለ ከዋጠ ሰኋላ በምትኮ ዳቦ ቆሎ እየቃመበት፡፡
“ይኸውልህ ጥሎብኝ ባለሙያ ነኝ፡፡” ተሽኮረመመችለት፡፡
“በቃ እህቴን ታስተምሪልኛለሻ፡፡” ሳቀ፡፡
“የት? አዲስ አበባ ነች ድሬ?"
“ደሴ ናት::?''
“ሚስትህን አይሻልም? ሰርታ እንድታበላህ?”
“አይ ሚስትስ ገና እያፈላለግሁኝ ነው፡፡” አለ ፈገግ ብሎ፡፡
“አሄሄ... !"
“ወላሂ!”
“እንግዳው አንደኛህን ባለሞያዋን አፈላልገህ ብታገባ አይሻልም?”
የወርቅ ጥርስ፡፡ “ሲቲና እባላለሁ::”
“ናት…እ.. ጀማል... ጀማል አብዱልከሪም፡፡”
ፈገግ አልችለት ድጋሚ፡፡
የሌሊቱን አብዛኛውን ክፍል ከሲቲና ጋር ሲጫወት አሳለፈው፡፡
ቀልዷ ለዛዋ በተለይ ሴታሴትነቷ አለቅጥ ሳበው፡፡
አሰቦትን እንዳለፉ ሲቲና ደከመኝ ትንሽ ልረፍ፡ ብሳ ድሪ ነጠላዋን ፊቷ ላይ ጣል አድርጋ ትከሻው ላይ ደገፍ አለች የተቀረውን ጉዞ አለፍ አለፍ እያለ ፊቱን እየመለሰ በስሱ ድሪ ነጠላ ውስጥ አልፎ

#ክፍል_ሰላሳ
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
...ዊልያምስ ፍሬድሪኩን ካገኛት ከጥቂት ቀናት በኋላ በጣም በጥሩ ስሜት
ውስጥ ሁኖ ወደ ሚስቱ ደወለና
“ማሬ የክላንሲ ቤተሰቦቼን እኔ ለቀጣይ አንድ ሳምንት ያህል እዚሁ ሜክሲኮ ውስጥ ሊያቆየኝ የሚያስችለኝን ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍሉኝ ጠይቋቸው ተስማምተዋል፡፡ ምክንያቱም ስለ ቻርሎቴ ልደርስበት ትንሽ የቀረኝ ነገር አለ፡፡
ይኸውልሽ ውዴ እዚህ ጋር ማን ይመስልሻል እየዋሸ የሚገኘው፡፡”
እኔ ምን አውቃለሁ ዴሪክ አንተው ንገረኝ እንጂ?” ብላ ጠየቀችው፡፡
“ቫለንቲና ባደን ናት፡፡ አየሽ ይቺ ሴትዮ ለወራት ያህል ቻርሎቴን ስትፈልግ እንደነበር ነገር ግን ይህንን ፍለጋዋን ለቻርሎቴ ቤተሰብ አላሳወቀችም ለምን? የሆነ የተደበቀ ነገር ያለ ይመስለኛል” አላት እና በዚያ ላይ ደግሞ ደጋግሞ ለቫለንቲና ባደን ስደውል ስልክ አታነሳም፡፡”
“እሺ ይሁን ግን አንድ ሳምንት ብቻ ነው መቆየት ያለብህ፤ ምክንያቱም
ሰዎች እየደወሉ የሚሰጡንን ስራዎችን እየመለስኩ ነው፡፡” አለችው
ቻርሎቴ፡፡
“እንዴ ውዴ ይህም እኮ ስራ ነው” አላት፡፡
“ለአንድ ሥራ እንደዚህ ጊዜ ወስደህ መስራትህ ሌሎች ስራዎቻችንን
እየመለሰብን ነው፡፡ ምን ሆነሃል? ሊወለድ የተቃረበ ልጅና ቤተሰብ እንዳለህ
የዘነጋህ መሰለኝ፡፡” ብላ ተነጫንጫ ስልኩን ዘጋችበት፡፡
በሎሬን እየተናደደ ዊልያምስ ስልኩን ዘጋ፡፡
እሱ ሉዊስን አገኘ ማለት የቻርሎቴን ባለትዳር የሆነ ጓደኛን አገኘ ማለት
ነው፡፡ ለዚህም ቻርሎቴ ማታ ላይ ይህንን ባለ ትዳር ፍቅረኛዋን ለማግኘት
ከሄደች በኋላ የተከሰተውን ነገር በመፍታት ኤፍ.ቢ.አይ እና የሜክሲኮ
ፖሊሶች ያላደረጉትን ነገር ማሳካት ይችላል። በዚህም ይበልጥ ዝነኛ
ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ተከር ክላንሲ እና ሜሪ ክላንሲ ስለጠፋችው ልጃቸው
በቴሌቪዥን ጣቢያዎች ይናገሩ ስለነበር ይህንን ሚስጥር መፍታት ቢችል
የአለም ቁጥር አንድ የግል ወንጀል መርማሪ መሆን የሚያስችለውን እድል
ይሰጠዋል።
ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ቻርሎቴ ለደረሰባት በደል ፍርድ ማግኘት አለባት ብሎ ያምናል፡፡ አንዳንዴ “እኔ፣ ወላጆቿ እና ፍሬድሪኩ ብቻ ነን እንዴ ስለ
ቻርሎቴ መጥፋት ግድ ያለን?” ብሎ ዊልያምስ ያስባል፡፡ ይህንን እያሰበ እያለም ስልኩ ጮኸ።
ቫለንቲና ባደን ሁኚ... ብሎ እያሰበ ስልኩን ሲያይም፣ ፍሬድሪኩ ነበረች የደወለችው፡፡ ደግሞም እንደተደሰተች ያስታውቃል፡፡
“የሆነ የረሳሁት ነገር ትዝ አለኝ፡፡” አለችው፡፡
“ጎበዝ ልጅ” ብሎ ዊልያምስ እስክሪብቶ እና የማስታወሻ ደብተሩን አዘጋጀ፡፡
“የሆነ ቀን ላይ ቻርሎቴን በመኪና ሲወስዳት አይቼ ነበር፡፡ መኪናዋ ትዝ
አለችኝ፡፡ የመኪናዋን ሹፌር ባላየውም እሷ ግን ለቀጠሮ የተዘጋጀች ስለነበር
መሰለኝ ሽክ ብላ ለብሳለች...
“ምን አይነት መኪና ነበር?” ብሎ ጠየቃት እና መኪናው እዚህ ከተማ ውስጥ ያልተለመደ መኪና እንዲሆን ተመኘ፡፡
“ጃጓር ነበር መኪናው፡፡ የመኪናው ቀለሙም ጥቁር አረንጓዴ ሲሆን
የውድድር መኪና ነው የሚባለው፡፡ “
ዊልያምስም ይህንን ሲሰማ አጠገቧ ቢሆን ኖሮ ዘሎ ይስማት ነበር፡፡
“እዚህ ከተማ ውስጥ ብዙ እንደነዚህ አይነት መኪኖች የሉም አይደል?
ሜክሲኮ ሲቲ ውስጥ እንደዚህ ያሉ መኪኖች ትንሽ ናቸው አይደል?” ብላ
ፍሬድሪኩ ጠየቀችው፡፡
በጣም ጥቂት ናቸው እንጂ ብሎ ለራሱ ተናገረ፡፡
ይሄ ሳምንት በጣም የተጨነቀበት ጊዜ ነበር፡፡ የቻርሎቴ ወላጆች በተጨማሪ ሶስት ሺህ ዶላር ላኩለት። የሒልተን ሆቴል ቆይታውንም ለአንድ ሳምንት ያህል አራዘመ:: ነገሮቹን ግን እሱ እንዳሰበው በቶሎ ሊጨርስ አልቻለም፡፡ እዚህ ከተማ ውስጥ እንዴት ሰው ስራ ሰርቶ ሊሳካለት
እንደሚችልም ገረመው፡፡ ታዲያ እንዴት ነው ሉዊስ ሮድሪጌዝ እንደዚህ ባለ
ከተማ ውስጥ ሰርቶ እንደዚህ ስኬታማ ለመሆን የበቃው? ብሎ እስኪናገር
ድረስ ዴሪክ ዊልያምስ እንዳሰበው መራመድ አልቻለም፡፡
ዊልያምስን ካስጨነቁት ነገሮች አንደኛው ሉዊስ ሮድሪጌዝ እራሱ ነው ከተማው ላይ እንደፈለገ ቸርነቱን የሚያሳይ ሰው ቢሆንም እሱን በአካል ማግኘት ግን በጣም የማይታሰብ ነገር ነው የሆነበት።
የቢሮ ፀሃፊዎቹን ሄዶ ሲያናግራቸው ሁሌም የሚመልሱለት “ሮድሪጌዝ ቢሮ ውስጥ የለም” የሚል ነበር፡፡ በስልክ ሲደውል እና በአካልም ሊያገኘው
ቢሞክርም አልተሳካለትም፡፡ የሚልካቸው ኢሜሎችን በማያውቃቸው ሰዎች
ይመልሱለታል፡፡ የስልክ ቁጥሮችን ሲደውል ደግሞ መኖር እስኪያስጠላው ድረስ ቀጠሮዎቹ በየጊዜው ይሰረዙበታል፡፡
ዊልያምስ የሮድሪጌዝ ቢሮ በር ላይ ቆሞ እየጠበቀው ሮድሪጌዝን ሊያናግረው ሙከራ ቢያደርግም እስከ አፍንጫቸው የታጠቁት የግል ጠባቂዎቹ በፍፁም ወደሚፈልገው ሰው ሊያቀርቡት አልቻሉም፡፡ ወደ መኖሪያ ቤቱም ቀርቦ ሰውዬውን ለማግኘት የሚያደርገው ሙከራ ደግሞ ከቤቱ የማይደፈር አጥር እና ወታደሮች ምክንያት አልፎ ወደ ውስጥዐመግባት እንዳይችል አደረጉት፡፡
በመጨረሻም ሉዊስ ሮድሪጌዝን እንዲመረምርለት የሆነ ሰው ለመቅጠር
ቢፈልግም ሁሉም ከተማ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በሙሉ ቢሊኒየሩን በጣም
ቸር ለጋስ እና የደሃ አባት ነው ብለው እንደሚያምኑት ብቻ ነበር የሚናገሩት፡፡
“እኔም የጎዳና ልጅ ነኝ እና የጎዳና ኑሮን በደንብ ነው ጠንቅቄ የማውቀው” ብሎ ባለፈው አመት ጆርዳና የተባለ መፅሄት ላይ የሰጠውን ቃለመጠይቅን
ዊልያምስ ለደርዘን ጊዜ አንብቦታል፡፡ “አንዳንድ ሰዎች እኔ ለፖሊሶች የማደርገውን የገንዘብ ድጋፍን አይወዱትም፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን
እኛ ፖሊስ ያስፈልገናል፣ ከአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ጋር ፊት ለፊት እየተዋጉ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ነገር ማንም ሰው ጦርነት ነው ማለት አይችልም፡፡
“ለዚያም ነው እኔ ከአደንዛዥ እፅ ሱስ ለማገገም ለሚረዱ የህክምና ማዕከላት ድጋፍ የማደርገው፡፡ ታናሽ እህቴን ያጣሁት በአደንዛዥ እፅ ምክንያት ነው፡፡ ለዚያም ነው ከዕፁ ሱስ ራሳቸውን ለጎዱ ሰዎች ስራን የምሰጣቸው፡፡ እኔ ፖለቲከኛ አይደለሁም፡፡ እኔ ለሰዎች ሃዘን ብቻ ነው
ያለኝ፡፡” የሚል ቃለ ምልልስ ነበር፡፡
ዊልያምስ ከቃለ መጠይቁ የተረዳው ነገር ቢኖር ሰውዬው ልታይ ልታይ የሚል፣ ይሄው እኔ እነዚህን ሁሉ በጎ ነገሮችን አድርጌያለሁ ብሎ ለሰዎች ለመናገር በሚመስል መልኩ ነው፡፡ እርግጥ ነው የአደንዛዥ ዕፁን ለመከላከል ብዙ ገንዘቦችን በልገሳ መልክ አበርክቷል፡፡ ሴቶችን በተመለከተ ደግሞዐሰውዬው ሀይለኛ አማላይ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ዝናውን ስለሚጨምርለት ማንም ሴት ከእሱ ጋር ለመተኛት እንዳታመነታ እንደሚያደርጋት በወሬ ወሬ ሰምቷል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ የሜክሲኮ ሲቲ ደሀ ነዋሪዎች እንደ አምላክ ያመልኩታል፡፡
ረቡዕ እለት በለስ ቀናው እና ሉዊስ ሮድሪጌዝን በአካል አገኘው “እኔ
ከአሜሪካ ድረስ መጥታ ስለጠፋች አንዲት ወጣት አሜሪካዊ ጉዳይ ላይ
ምርመራ የማደርግ ሰው ነኝ፡” ብሎ ሲጠጋው የግሉ ጠባቂ በፍጥነት
ከለለው:: “ጌታዬ ይቅርታ አንድ ደቂቃ ብቻ ስጡኝ፡፡ ከእርሶ ጋር ስራ አብሮ
ከሚሰራ ሰው ጋር ልጅቷ ግኑኝነት እንዳላት ሰምቼ ነበር ስሟም ቻርሎቴ ክላንሴ ይባላል አለው።
የግል ጠባቂው ዊልያምስን መትቶ ከመሬት ሊዘርረው ሲል ሮድሪጌዝ
እጁን አነሳ፡፡ ይሄኔም ጠባቂው በሪሞት እንደቆመ ሮቦት ሁሉ ቀጥ ብሎ
ቆመ::
ቻርሎቴ ቻርሎቴ” ብሎ ዊሊያምስን እየተመለከተ “የእህቴ ስም ነው፡፡
አንተ ከእኔ ጋር ስራ የሚሰራ ሰውን ሰው ማግኘት እፈልጋለሁ ነው እፈልጋለው ያልከኝ?” ብሎ ሮድሪጌዝ ጠየቀ፡፡
አዎን ልክ ነህ ጌታዬ፤ አሜሪካዊ ነው የፋይናንስ

❤1👍1
ሰራተኛ ወይም ደግሞ
ጠበቃ ነገር ነው፡፡ የሚያሽከረክረው መኪናም ጥቁር አረንጓዴ ጃግዋር
የስፖርት መኪና ነው፡፡”
ሮድሪጌዝም ኮስተር ብሎ “ምንም ሊመጣልኝ አልቻለም አየህ እኔ ከብዙ
አሜሪካውያን ጋር ስራ እሰራለሁ፡፡ሚ/ር...
“ዊልያምስ፣ ዴሪክ ዊልያምስ እባላለሁ” ብሎት ተጨባበጡ፡፡
“ለምን ማታ ወደ 12 ሰአት ላይ ኮሎንያ ዴል ቫሌ ላይ ከሚገኘው ቢሮዬ
አትመጣም? እስከዛ ድረስ ለፀሃፊዬ እነግራትና ነገሮችን አመቻችታ
እንድትጠብቅህ አደርጋለሁ፡፡ ደግሞም
አሜሪካዊ ሰው አስታውሳ ትነግርህም ይሆናል፡፡” አለው፡፡
“በእውነት ልትተባበረኝ ፈቃደኛ ስለሆንክ በጣም ነው የማመሰግነው”ብሎ ታላቅ ትህትናውን አሳየው፡፡ ከብዙ ሙከራዎች በኋላ እንግዲህ የሚፈልገውን ነገር ሊያሳካ ነው “እሺ እመጣለሁ” ብሎ ሉዊስ ሮድሪጌዝን ተሰናብቶት ሄደ፡፡
12 ሰአት ሊሆን ትንሽ ደቂቃ እንደቀረው ዊልያምስ ኮሎኒያ ዴል ቫሌ ላይ ከሚገኘው ምድር ላይ ከሚገኘው የሉዊስ ሮድሪጌዝ ቢሮ ደረሰ፡፡ እንግዳ ተቀባይዋ ጋ የቀረበው ዊልያምስ የገረጣ ከላይነን ጨርቅ የተሰፋ ሙሉ ልብሱን አድርጎ ነበር፡፡
እዚህ መሆን በራሱ በጣም ደስ የሚል ስሜትን ይሰጣል፡፡ አሁን ይሄው
እንግዲህ በመጨረሻ ጉዳዬን ልቋጨው ነው፡፡
ዊልያምስ ይህ የቻርሎቴ ፍቅረኛ በእሷ መጥፋት እጁ አለበት ብሎ ያምናል። አሁን ቻርሎቴ ሞታለች ብሎ ደምድሟል፡፡ ስለሆነም የሰውዬው ማንነት ካወቀ በኋላ ሰውዬው ላይ ክሱን መመስረት ይችላል፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ለምስኪኖቹ የቻርሎቴ ቤተሶች"ስለ ታሮሎ እውነተኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ነገርን ማሳወቅ ይቻላል፡፡የሚያሳውቃቸው ነገር የልጃቸውን ሞት ቢሆን እንኳ ልባቸውን የሚያሳርፋቸውን ነገር የግድ ማድረግ
ይኖርበታል።
“ሉዊስ ሮድሪጌዝ ጋር ቀጠሮ ነበረኝ” አላትና ካርዱን አንስቶ አቀበላትና እየጠበቀኝ መሰለኝ አላት።
ልጅትዋም ፈገግ አለች እና የስልኩን እጀታ አንስታ ለጥቂት ጊዜ በእስፓንሽ ቋንቋ ስታወራ ቆይታ ስልኩን ዘጋች፡፡
“እርግጠኛ ነህ ቀጠሮህ ዛሬ ነው ሚስተር ዊሊያምስ?” ብላ በትህትና
ጠየቀችው፡፡ እና “ይቅርታ በሚ/ር ሮድሪጌዝ የቀጠሮ ካላንደር ላይ ስምህ የለም....
ይህንን ሲሰማ ዊልያምስ ሰውነቱ ሽምቅቅ አለበት፡፡
እርግጠኛ ነኝ ዛሬ ጠዋት ላይ አግኝቼው ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ሊያገኘኝ ቀጠሮ ይዘን ነበር፡፡ እኔ...” ሀሳቡን ተናግሮ ሳይጨርስ ሁለት የታጠቁ ፖሊሶች ጎን ለጎን ወደ እሱ መጡና
“ዴሪክ ዊልያምስ አንተ ነህ አለው?” ከሁለት አንደኛው ፖሊስ፡፡
“አዎን” ብሎ ስሙን እንዴት አውቀው ሊጠሩት እንደቻሉ ተገርሞ
ይመለከታቸው ጀመር፡፡
“ሚ/ር ዊልያምስ በቁጥጥር ስር ውለሃል” ብለውት በፍጥነት እጁን
ጠምዝዘው ይዘው እና ቀበቶውን ወደ ላይ ስበው እየጎተቱ በገባበት በር
መንገድ ላይ አወጡት፡፡
“በቁጥጥር ስር ምን አጥፍቼ?” ብሎ መንገድ ላይ እሱን እየተመለከቱ
በሚገኙት መንገደኞች አስተያየት እያፈረ ፖሊሶቹን ጠየቀ “ተሳስታችሁ
እንዳይሆን” አላቸው፡፡
“ቪዛ ሳይኖርህ ሜክሲኮ ውስጥ በመገኘትህ ነው” ብሎ አንደኛው
ሲመልስለት ሌላኛው በክርኑ የዊሊያምስን ጎድን አጥንት በሃይል ወቀረው፡፡
“ወደ ሀገርህ በቶሎ እንድንመልስህ ትእዛዝ ተሰጥቶናል” አለው፡፡
“አስገድዳችሁ እንድትመልሱኝ ምን?” ብሎ ዊሊያምስ በንዴት “የማይረባ
ነገር ነው እያወራችሁ ያላችሁት፤ እኔ በቱሪስትነት ነው ወደ ሜክሲኮ
የገባሁት እና ቪዛ አያስፈልገኝም” ብሎ ሲናገር መንጋጋው ላይ ያረፈው ሃይለኛ ቦክስ ወሬውን እንዳይጨርስ አደረገው፡፡ ሁለተኛው ቦክስ ደግሞ አፍንጫው ላይ በማረፉ አፍንጫው ሲሰበር ተሰማው፡፡ በፊቱ ላይም ደሙ እንደ ጎርፍ ይወርድ ጀመር፡፡ ከድብደባው ይልቅ ድንጋጤው በርትቶበት ስለነበር ፈዞ ቆመ:: ወዲያውንም ጎትተውት ከአንድ መኪና ኋላ ወንበር ወረወሩትና ድብደባውን ቀጠሉበት፡፡
አውሮፕላን ውስጥ ሲገባ ያስታውሳል፤ ነገር ግን ከሜክሲኮ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ አውሮፕላኑ ይነሳ አይነሳ የሚያስታውሰው ነገር የለም ይሰማው የነበረውን ከፍተኛ የህመም ስሜት
ያስታውሳል ከአጠገቡም አንድ ነጭ ጋዋን ያደረገ ሰው ሲሪንጁን አውጥቶ ታፋው ላይ በመርፌው ሲወጋው ትዝ ይለዋል አውሮፕላኑ የሎስ አንጀለስ አየር
ማረፊያን ምድር ሲነካ እና በድጋሚ ሲነቃ ግን ከአጠገቡ ማንንም ሰው ስላላገኘ ምናልባትም በቅዠት ውስጥ ሆኜ ነው፡፡ ሰውዬውን ያየሁ የመሰለኝ አለ ለራሱ፡፡...

👍1🔥1