አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#በራ_የመስቀል_ደመራ

የአደይ ችቦ እየፋመ እየጋመ
ኢዮሃ እያስገመገመ እየተመመ
የመስቀል ደመራ
በራ።
በራ የአዲስ ዘመን ችቦ
በመስከረም ላብል እብቦ
ከዋከብቱን ፈነጠቀ
ርችቱን አንጸባረቀ
ተኳለ አዲስ ደመቀ
መለኩን በቀለም እዝርእት በጥበብ አጥለቀለቀ
ሸለቆው ተንቆጠቆጠ፥ ተራራው አሸበረቀ
ኢዮሃ ኢዮሃ አበባዬ! ምድር ሕይወት አፈለቀ።
ነጋ፥ የእዲስ ዘመን ችቦ
ፈካ፥ ፀደይ አርብቦ
ሌሊቱ እንደጎሕ ቀደደ፥ ጨለማው እንደ ቀን ጠራ
እንደውቅያኖስ ዕፅዋት እንደጠፈር ኮከብ ደራ
ምድር ሥጋጃ ለበሰ፥ የጌጥ አልባሳት ተቀባ
ሰማይ በእልልታ እስተጋባ
እዮሃ መስከረም ጠባ።
ነጋ የአዲስ ዘመን ችቦ፥ ምድር ሕይወት አፈለቀች
የምሥራች እዝርእቷን፥ እዲስ ቡቃያ ወለደች
የአደይ አበባን ለገሠች
ለአዲለ ዘመን አዲስ ብርሃን፥ አዲስ መስከረም ገበየች።
ነጋ፥ የአዲስ ዘመን ችቦ
ፈካ፡ ፀደይ እረብቦ
በራ፥
የመስቀል ደመራ።

መስከረም - ፲፱፻፳፫ - መስቀል አደባባይ

🔘ፀጋዬ ገብረመድህንን🔘
የመስቀል ለት ማታ

ከደመራው ጀርባ ከችቦው ብልጭታ፤ 
ከመዘምራን ጋር ዝማሬ ተጫውታ፡፡
ከተካነችው ልጅ የሚያምር ፈገግታ፤
ካፈቀርኳት ቆንጆ የመስቀል ለት ማታ፡፡
ደመራው ሲለኮስ እሳት ተቀጣጥሎ፤
በሀሳብ ከወሰደኝ ፍቅሯ ልቤን ሰቅሎ፡፡
የመስቀል ወፍ ሆና ልቤን የሰጠኋት፤
በሐበሻ ቀሚስ ዘንጣ ያየኋት፤
የመውደዴ ረሀብ የፍቅሬ ጥማት ናት፡፡

ወረብ ስትወርብ ከበሮ ስትመታ፤
ፍቅር ካስያዘችኝ የመስቀል ለት ማታ፤
አለብኝ ቀጠሮ ላግኛት ላንድ አፍታ፤
ታዳምጠው ስሜቴን የልቤን ትርታ፡፡
በእምነት ግንባሯ ላይ መስቀል አሰርታ፤
ከሄደችው ወጣት ትናንትና ማታ፤
አለብኝ ቀጠሮ የመስቀል ለት ማታ፡፡ 
         
🔘ቢንያም ደምሴ🔘
#ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር

ያሳለፍነዉ ሁሉ
አሁን ትዝታ እንጂ
ዉስጡ ህይወት የለም እያልሽ ላገሩ
ታወሪያለሽ አሉ


(እኔ ግን ልንገርሽ)
የሁለታችን ፍቅር
ምን እንደሚመስል. . .
እንዴት እንደነበር
በሶስት ምስክር
1
አሁን በቀደም ለት
የሆነ ቦታ ላይ
ድምጻችን ከፍ አርገን የሳቅንበት ቦታ
ፒያሳ አደባባይ
ድንገት
በቀደም ለት
በዛ ቦታ ስሄድ
ከሰባት ወር በፊት
ስቀሽ የነበረዉ
ያንቺ ሳቅ ተሰማኝ
መራመድ አቃተኝ
የሚገርምሽ ነገር
ያለፈ ነዉ ያልሺዉ
ትዝታ ነዉ ያልሽዉ
ፍቅርሽና ሳቅሽ
ከሰባት ወር ኋላ እንደ ወንዝ ፍሳሽ
ይሰማል ልንገርሽ

(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
የወንዝ ዉሀ ሳቅሽ
ያለፈ ትዝታ ምናምን ነዉ ብሎ
ማንም ተራ ዘፋኝ የሚሸነግልሽ
(ይልቅ እኔን ስሚኝ)

ወደየትም ሳይሆን
ወዴትም ተመለሽ
የትም ሳትደርሺ
ጊዜን እንዳቆምነዉ
እንኳን ጊዜ ቀርቶ ሰዓት እንዳልሄደ
ደቂቃ እንዳልሄደ
አስረጂ ሊሆንሽ
ምስክር ሊሆንሽ
ከምንም አቅጣጫ. . . የትም ሳትመለሽ
አደባባይ መሀል
ከቡና ጠረን ጋር
እንደወንዝ የሚፈስ
ሳቅሽን ትሰሚያለሽ

2
ትዝ ይልሽ እንደሆን
ካንቺ መኖሪያ ቤት
(የመጣሁኝ ጊዜ)
የመራራቅ ናፍቆት
አስክሮን ቸኩለን
ሰማያት ለመዝለቅ
ከመሬት ላይ ወድቀን
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ከሴት ወዝሽ ጋራ
የጡትሽ ስር ሽቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ምወደዉን ሸሚዝ
ለመልበስ እርም አልኩኝ
ለብሼዉ እንዳልሄድ
ከበደኝ ጨነቀኝ
ያንቺን ጠረን ማጠብ. . .
ነፍስ የማጥፋት ያህል
ሀጥያት መስሎ ታየኝ
(የሚገርምሽ ነገር)
እስከ ዛሬ ድረስ
በመስኮቱ ዘልቆ. . .በበሬ
የሚወጣዉ የማለዳዉ ነፋስ
በሽቶሽ ጠረን ነዉ መንደሩን የሚብስ

3
ታስታዉሽ እንደሆን
የሆነ ቅዳሜ
የሆነ ዉብ ሆቴል
ደግሞም አትረሺዉም. . .ፍጻሜ ምሳ ነዉ
ይኼ እንኳን ትዝ ይላል
እና. . .
እኔና አንቺ ብቻ
የተቀመጥንበት ወንበር ጠረጴዛዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ. . .
እዛዉ ቤት ዳግመኛ ተመልሼ ባየዉ
የሚገርምሽ ነገር
ጻፊዉን ባላዉቅም
#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
የሚል ጽሁፍ ሰቅለዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ
አንድ ለብቻዬ ካንድ አንቺ ናፍቆት ጋር
ነበር ለምትይዉ ለሁለታችን ፍቅር
(ምስክር ሊሆኑን)
ያኔ ሁለታችን የጠጣነዉ ወይን
ከወይንም. . . Two Ocean
እኔ የጨለጥኩት
አንቺ ያጋመስሽዉ
እኛ ያስተረፍነዉ
እስከዛሬ ድረስ
ያተረፍነዉ ማዕድ. . .
ጠርሙስና ጽዋዉ
በክብር ተቀምጧል
ማንም ሳያነሳዉ. . .ያኔ እንደነበረዉ
(ታዲያ ምን ማለት ነዉ)



ፒያሳ አደባባይ
የወንዝ ዉሃ ሳቅሽ
ከቡና ጠረን ጋ
ከኔ መኖሪያ ቤት. . .
የምወደዉ ሸሚዝ ላይ
የሽቶ መአዛሽ
ከሴት ላቦትሽ ጋር
ደግሞም
እዚያ ዉብ ሆቴል ስር
ያስተረፍነዉ . . .
ማዕድ ጠርሙስና ጽዋ
አንጀት ከሚበላ
ከቆንጆ ጥቅስ ጋር
‘’#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር::’’

ነበርን እስካሁን
በመሆን እያየሽ
ሳቅሽ ፈሶ ሳያልቅ
ከምወደዉ ሸሚዝ
የሽቶ መዓዛሽ ዉብ ጠረኑ ሳይለቅ
ማዕድ ሳይነሳ ጽዋዉ ሳይታጠብ
ሦሥቱን ምስክሮች በዓይንሽ ፊት እያየሽ
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
ያሳለፍነዉ ሁሉ
"አሁን ትዝታ እንጂ .....
ዉስጡ ህይወት የለም"
ብለሽ ለመንደሩ
ላገሩ ማዉራትሽ
እዉነት ለምንድን ነዉ?




ኤፍሬም ስዩም
(ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር)
😱1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

...“ናትናኤል የቆርቆሮውን የአጥር በር ገፋ አድርጎ ሲገባ ያጋጠመው ሰፊ ግቢ ነበር፡፡ በግራና በቀኝ አያሌ መኪኖች ተደርድረዋል፡፡ የሆቴሉ ህንፃ ውስጥ ገብተው መስተናገድ ያልፈለጉ ደንበኞች ያማራቸውን እዚያው ከየመኪናዎቻቸው ውስጥ አዘው ይጋበዛሉ፡፡ ፍጥነቱን ሳይቀንስ ወደፊት በሆቴሉ ዋና በር እቅጣጫ ገሰገሰ፡፡

ግቢው በጨለማ ቢዋጥም ከፊት ለፊት የሆቴሉ አዳራሽ ብርሃን እውጭ በረንዳው ላይ የምሽቱን እየር እየተነፊሱ የሚጋበዙ እንግዶችን ያሳያል፡፡

በዋናው በር መግባት አደገኛ ነው፡፡ ያለጥርጥር እሱን የሚጠብቅ ድንገት የሚወነጨፍ ወጥመድ ሊኖር ይችላል፡፡

ወደቀኝ እጥፍ ብሎ በሆቴል ቤቱ በስተቀኝ ወደጓሮ ዞረ፡፡

ጭስ፡፡ እዚያና እዚህ ተፍ ተፍ የሚሉ የወጥ ቤት ሴቶች፡፡ማናቸውም ቀና ብለው አላዩትም:: በጨለማው ውስጥ ዘና ብሎ ከኋለኛው በር ደጃፍ ወጣ ብላ ወደቆመች ሴት ጠጋ አለ፡፡

“ታዲያስ!” አላት እንደቤተኛ ተዝናንቶ::
“አለን!” አለች በጨለማው ውስጥ ፊቱን ለማየት እየሞከረች፡፡
“የምሥራችን ምን ነካት ዛሬ?” አለ ጎንበስ ብሎ የእግር ሹራብን ሳብ ሳብ እያደረገ ፊቱን እንዳታየው:: ጨለማው ፊቱን እንደሚከልልለት ቢረዳም መንፈሱ አልረጋጋልህ አለው፡፡

“እንዴት ምን ሆኑ?” አለች ሴትየዋ የእመቤቷ ስም ሲነሳ፡፡
“አላየኋትም፡፡” አለ ፊቱን ወደ ማዕድ ማዘጋጃው ቤት መልሶ፡፡
“ኧረ አሉ፡፡ ከዋናወ ቤት ናቸው ኮ፡፡”
“ከዋናው አዳራሽ?” አለ ለጥቂት ሴኮንዶች ፊቱን መለስ አድርጎ
አይቷት ወዲያው ዞር ብሎ እየተንጠራራ፡፡ ሴትየዋ የምታወቀው ሰው የዘነጋችው ደንበኛ ይሆናል ብላ እንድትጠራጠር አለቅጥ እየተዝናናባት፡፡
“ዋናው አዳራሽማ ገብቼ ነበር፡፡ የለችም፡፡ ክፍል ጨርሳችኋል እንዴ?” አላት
አከታትሎ፡፡

“አልጨረስንም፡፡ ልያዝሎት? ” አለችው::
“አዎ፡፡” ከኪሱ ገንዘብ አውጥቶ ሰጣት፡፡
ሴትየዋ ወደ ውስጥ ስትገባ እያፏጨ እየተንጎራደደ ጠበቃት፡፡
ከወዲያ ወዲሀ የሚሯሯጠትን ብቅ ጥልቅ እያሉ እንግዶቻቸውን የሚያስተናግዱትን ሴቶች እየተመለከተ ቆየ::
“አዛሉ! ሁለት ጥብስ አንድ ክትፎ ሶስት ፍርፍር ቶሎ በይ!” አለች አንድ ሴት ከጀርባው ካለ መስኮት ብቅ ብላ፡፡ “ዓለም! ዓለምነሽ! ለሦስት ቁጥር ሰዎች አምቦ ውሃ ወሰጂላቸው እንጂ!” ወደ ውስጥ የገባችው ሴት መልሳ በዛው መስኮት ብቅ ብላ ተጣራች፡፡

“መጣሁ መጣሁ! እዚህም'ኮ ስራ ነው:: ጭቅጭቅ?” ዓለምነሽ እያልጎመጎመች ከማዕድ ቤቱ ወጥታ የአምቦ ውሃ ጨብጣ ወደ ዋናው ቤት ሮጠች፡፡

“ይኽው ሰባት ቁጥርን ያዝኩሎት፡፡” አለችው ቁልፉንና መልስ ገንዘብ የያዘችበትን እጇን ወደፊት ዘርግታ፡፡
ቁልፉን ብቻ ተቀብሎ “ተይው” አላት መልሱን ልትሰጠው ስትከጅል፡፡
“እግዜር ይስጥልኝ፡፡" አለች በጨለማው ውስጥ ፈገግታ ደርባ፡፡
“ምስር ከአዲስ ደንበኞች ጋር ነች መሰለኝ? እኛን ረሳችንሳ፡፡” አለ
የተከራየውን ክፍል ቁልፍ፡ ሌባ ጣቱ ላይ እያሽከረከረ፡፡
“አይ..ከነጋሼ ኪዳኔ ጋር ናቸው...ጓዳ፡፡”
“ኪዳኔ የኛ?” አላት በጭፍን፡፡
“አዎ፡፡” አለችው:: ቤተኛ ነው ብላ እንደደመደመች ግልጽ ሆነለት::
“አይ እነሱስ .. ከሆነ ችግር የለም፡፡ አንድ ሰው ይፈልግሻል በያት፡ክፍሌ ውስጥ ነኝ፡፡” ለመመለስ ጊዜ ሳይሰጣት ፊቱን መልሶ መደዳ ወደተሰሩት የመኝታ ቤቶች አመራ…4..5.6..7 ቁልፉን ከቶ በሩን ከፈተና ወደ ውስጥ ገባ፡፡ በሩን ከዘጋው በኋላ መብራቱን አበራው፡፡

የክፍሉን አብዛኛ ቦታ የያዘው ቀይ ጨርቅ የለበሰ አንድ ሰፊ አልጋ በሁለት ኮመዲኖዎችና ቁምሳጥን ታጅቦ መሃል ላይ ተንጋሏል፡፡ አነስተኛ የፊት መታጠቢያ ሳህን ከነፊት መስታወቱ በስተቀኝ ይታያል፡፡ ከክፍሉ ጀርባ ከአልጋው ራስጌ አንድ የተዘጋ የእንጨት መስኮት አላ:: ናትናኤል ክፍሉን ካጠና በኋላ ወደፊት ራመድ እልና በኮርኒሱ መሃል
የተንጠለጠለችውን አምፖል አላላት፡፡ ጨለማ፡፡

አልጋው ላይ ተቀምጦ መጠባበቅ ያዝ፡፡ ልቡ እየተነሳ ሲፈርጥ ደረቱን ሲነርተው እራሱን ኣሳፈረው፡፡ለሳምንታት አንድ በአንድ ሲያስኬደው የቆየው ዕቅድ ቀላል ሆኖ እንዳልታየው ሁሉ ሰዓቱ ሲደርስ በላብ ይዘፈቅ ጀመር፡፡ …ምንድነው የሚላት? ካልቨርት ያላትን ነው መድገም ያለበት፡፡የካልቨርት ቢጤ ምስኪን ተባራሪ ነው መሆን ያለበት፡፡ ያኔ ነው ካልቨርትን
ባየችበት አይኗ ልታየው የምትችለው፡፡ ባታምነውስ? ብትጮኽስ? ኡ! ኡ!
ብትልስ? ወይ አባብላ የተስማማች መስላ ብታስያዘውስ?. አንዱ ክፍሉ
ውስጥ ከገባች በኋሳ መውጣት የለባትም፡፡ መጀመሪያ መውጣት ያለበት እሱ ነው፡፡ ግን ብትጮህ ምን ያደርጋታል? አፏን አፍኖ ይዞ ማስፈራራት?
አጥፍቷል፡፡ ጩቤ ቢይዝ ጥሩ ነበር፡፡ ቀደም ብሎ ያላሰበው ያልጠረጠረው
ሁኔታ ሲከሰትላት ደንገጥ አለ፡፡ ለጥቂት ደቂቃዎች አሰላሰለና ድንገት አፈፍ
ብሎ ተነስቶ በሩን ከፍቶ ወደ ማዕድ ቤት ሮጥ ብሎ ሄደ፡፡

“እዛሉ! ዓለምነሽ! ማናችሁ... ምነው ዛሬ ችላ አላችሁን?” ጭንቅላቱን በማዕድ ቤቱ ጠባብ መስኮት ገባ እድርጎ ታጣራ፡፡ ከውስጥ የክፍሉ ብርሃን ሴቶቹን ቁልጭ አድርጎ ቢያሳየውም ከውጭ የቆመው
የእርሱ ፊት ግን በጨለማው ውስጥ እንደተዋጠ ነበር፡፡

“አቤት...ምንድነው?” አለች ኣዛለች ትሁን ዓለምነሽ ያልለያት ሴት በግራዋ መጥበሻ በቀኟ ሳህን እንደያዘች ፊቷን ወደ እርሱ መልሳ፡፡

“ስንቴ ነው የምንልክባችሁ? ቢላ ቢላ! ቢላ! በይ አሁን አንድ ስጪኝ!” አለ እጁን ዘርግቶ እያራገበ::

ዞር ብላ ከጠረጴዛው ላይ የተቀመጠ የገበታ ቢላ አንስታ አቀበለችው ቢላውን ከተቀበላት በኋላ ፊቱን መልሶ እየተጣደፈ ወደ ተከራየው ክፍል ሲመለስ ከጀርባው ድምጽ ተሰማው፡፡ የክፍሉን በር ከፍቶ እንደያዘ ዞር ብሎ ተመለከተ፡፡

“ማን ነው? ብለዋል እትዬ…ማን ልበላቸው ስሞትን?” አለች የላካት
ልጅ ስሙን ባለማስታወሷ እያፈረች፡፡
“ይሻላል? ህ ህ! ሀ! ሀ!” ልጅቷ ላይ አንቧረቀባት፡፡ “ብላ ብላ ደግሞ ማነው ትለኝ ጀመር? እንደምትያት መታወቂያ ወረቀቴን ብልክ አይሻልም ወይ? ብሏል በያት” ጊዜ ሳይሰጣት ወደ ክፍሉ ገባ፡፡ “ማነሽ…ደሞ
ሻማና ክብሪት ይሽልኝ ተመለሽ፡ አምፖላችሁ ተቃጥሏል፡፡ እንደው ነው'ኮ
እዚህ የምንመጣ፡፡ የናንተ አስተናጋጅነት ድሮ ቀረ::” በሩን ዘጋው፡፡

አለቅጥ መዝናናቱ ልጅቷን ግራ እንደማያጋባትና እመቤቷ በቅርብ
የሚያውቁት ሰው ነው ብላ እንድታስብ እንደሚያደርጋት ገብቶታል፡፡ ክፍሉ
ውስጥ ከገባ በኋላ ቢላ የጨበጠ ቀኝ እጁን ኪሱ ውስጥ ከትቶ አልጋው ላይ
ተቀመጠና ጨሰማው ላይ ኣፈጠጠ፡፡
ቢላውን የጨበጠበት እጁ በላብ ሲጠመቅ አውጥቶ ሱሪው ላይ
ሞዥቀው፡፡ መፍራት የለበትም ቀፍፁም! አሳዳጆቹ ፍርሀት የሚገባቸው ፤
ርህራሄ የሚውጣቸው አይደሉም። አንገቱን አርደው ቱቦ ውስጥ ሊጥሉት
የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ፍርሀት አይበጀውም:: ፍርሀት አያዋጣውም፡፡

ምንድነው የሚላት? ሊያስፈራራት አይገባም፡፡ እሰም እንደ ካልቨርት ተባራሪ መሆኑን ነው ሊያሳምናት የሚገባው፡፡ ያን ጊዜ ነው የምታምነው! ካልቨርትን ባየችበት እይኗ የምታየው:: እንቢ ካለች ግን በራሷ ቢላዋ ያባብላታል፡፡

ያለበት ክፍል በር ወደ ውስጥ ተከፈተ፡፡
“እንዴ! ምነው ጨለማ ውስጥ ?!” ለሴት ጎርነን ያለ ድምፅ፡፡

“አምፖልሽ ተቃጥሏል ምስርዬ፡፡ ሻማ በያት ልጅቷን፡፡” አለ ናትናኤል በጭለማ ውስጥ እንደተቀመጠ ተዝናንቶ፡፡ ልቡ ትቼህ ልብረር ልብረር አለው፡፡

“ማነህ?” አለ ያው ጎርነን ያለ የሴት ድምፅ ጥርጣሬ የገባው በሚመስል ቃና

“እስቲ ሻማው ይምጣና
👍1
እንተያያለን፡፡” ቢላውን ጨምቆ ያዘው፡፡ ክፍሉ ውስጥ ከመግባቷ በፊት ሻማውን መለኮስ የለባትም! ማን መሆኑን መለየት የለባትም! አትለየውማ! አታውቀውማ!
“ማነሽ ብርክቲ እስቲ ከአንደኛው ክፍል አንድ አምፖል አምጪ፡፡” ከበር የቆመችው ሴት የካልቨርት ወዳጅ ያለበትን ክፍል መዝጊያ ከፈት ኣድርጋ እንደቆመች ስትናገር ተሰማው::

“ይኸው ሻማ አምጥቻለሁ::” አለ የሌላ ሴት ድምፅ፡፡

· “በይ አምጪው ሻማውን፡፡ ሂጃና ከአንዱ ባዶ ክፍል ደህና አምፖል አውልቀሽ አምጪ፡፡” አለች ከበር የቆመችው ሴት።

“ያሁን ይሁን፤ ሻማ ካለ ይበቃል፡፡” አለ ናትናኤል ጮክ ብሉ፡፡

ከበር የነበረችው ሴት የያዘችውን በር ገፋ አድርጋ ወደ ውስጥ ገባችና የክብሪቱን ሳጥን ከፍታ ክብሪት ማውጣት ጀመረች፡፡

“ከበሩ ዞር በይ! ንፋስ ያጠፋብሻል፡፡” አለና ድንገት ብድግ ብሎ ከጀርባዋ ያለውን መዝጊያ ዘጋው፡፡ ቆለፈው፡፡
“አምጪው" ብሎ ሻማውንና
ክብሪቱን ከእጇ ቀማት፡፡

"አንዴ! ቆይ ልለኩሰው እንጂ!” ሴትየዋ በጨለማው ውስጥ ግራ ተጋብታ ቆመች፡፡

ናትናኤል ተንጠራርቶ . ፡ እጁን አወናልጨፈና በክፍሉ መሃል
የተንጠለጠለችውን ሲገባ ያሳላትን አምፖል ሲያገኝ መልሶ አጠበቃት፡፡

ክፍላ በብርሃን ተሞላ፡:

ድንገት በብርሃን በተጥለቀለቀው ክፍል ውስጥ ለሴኮንዶች አይኖቻቸውን እያጨናበሱ ተፋጠጡ፡፡ ከጠበቃት በላይ ወጣት ነች:: ከሰላሳ አትበልጥም:: ለሴት በጣም ረጅም ነች፡፡ ከታች እስከላይ ሙልት ብሎ የጋባው ቀይ ገላዋ ደህና እንደተያወ ጮኾ ይናገራል፡፡

“ማነህ? “ አፈጠጠች፡፡

“አታውቀኝም እላውቅሽም:: የምረዳሽ የምትረጂኝ ነገር ስላለ ብቻ ነው አንቺ ጋ የመጣሁት::”አለ ጀርባውን ለበሩ ሰጥቶ እንደቆመ ፊት ለፊት እየተመለከታት፡፡

“ምንድነው የምረዳህ?” አንድ እርምጃ ወደ ኋላ አፈገፈገች፡፡

“አትፍሪ፤ አንቺን የሚያስጋሽ ነገር የለም:: ስሚኝ...” ካልቨርት ያላትን ነው መድገም ያለበት ካልቨረት ያላትን! “ስሚኝ” አለ ድጋሚ ምራቁን ውጦ፡፡”ሊገድሉኝ የሚያባርሩኝ ሰዎች አሉ፡፡ መሽሽግ አለብኝ፤ ከኋላዬ እንደ እብድ ውሻ የሚያሯሩጡኝ ሰዎች ኣሉ፡፡ መደበቅ አለብኝ፤ መሽሽ አለበኝ፡፡ ግን ደግም መሽሽ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ አንድ ቀን
እያንዳንዳችንን ከያለንበት ከየተደበቅንበት ፈልፍለው ያወውናል፡፡ እያረዱ በየስርቻ ይጥሉናል ለአንዳፍታ ትክ ብሎ ተመለከታት “ይህ ከመሆኑ በፊት ልናቆማቸው ይገባል፡፡ ልንገታቸው ይገባል፡፡ ልንገታቸው የምንችለው ደግሞ እኛ ተባራሪዎቹ በአንድነት ስንጋፈጣቸው ብቻ ነው:: በየአቅጣጫው ተበታትነን በመደበቅ አይደለም::” ንግግሩን አቋርጦ በዝምታ ተመለከታት:: ፍርሃት: ፊቷን አስምጦታል፡፡ ቢሆንም የተናገረው ሁሉ
እንቆቅልሽ እንዳልሆነባት ግልፅ ነበር፡፡ ፊቷ ላይ የሚያንዣብበው ፍርሃት
እንጂ መደናገር አልነበረም::

“እና... እኔ ምንድነው የምረዳህ?“ .
“ከካልቨርት ጋር ሆኜ እነዚህን አውሬዎች ልጋፈጣቸው ነው የምፈልገው፡፡ ከካልቨርት ጋር ብታገናኝኝ...”

“ካልቨርት የት እንዳለ አላውቅም::¨ አቋረጠችው ፡፡ ሮጣ ከክፍሉ
ልትወጣ እንዳስቀች ሁሉ ከጀርባው ያለውን በር አሻግራ ተመለከተች፡፡

"ትክክል ነሽ፡፡ መደበቅሽ ትክክል ነው፡፡ ምክንያቱም የሚያሳድዱን አውሪዎች እኛን እጃቸው ለማስገባት የማይፈጥሩት ዘዴ የማይሞክሩት መንገድ የለም:: ግን እመኝኝ:: እኔም እንደ ካልቨርት ተባራሪ ነኝ:: እኔም እንደ ካልቨርት ታዳኝ ነኝ:: እርጂኝ፡፡ ሪሴንም ካልቨርትንም ልረዳ
እችላለሁ:: ልናቆማቸው እንችላለን፤ ልንገታቸው እንችላለን፡፡ ግን ካልቨርትን
ማግኘት አለብኝ፡፡ ብቻዬን መደጨለማው መውጣት አልችልም:: ረዳት እፈልጋለሁ:: ካልቨርትን እፈልጋለሁ

“ነገርኩህ፡ ስለካልቨርት የማውቀው ነገር የለም፡፡”

ያሉበት ክፍል በር ድንገት ተንኳኳ፡፡

“ማነው? አለ ናትናኤል ፊቱን ወደ መዝጊያሁ መልሶ::

መልስ የለም:: በሩ ድጋሚ ተንኳኳ፡፡ ናትናኤል ደነገጠ፡፡ በገዛ እጁ እንደ አይጥ ሮጦ ወጥመዳቸው ውስጥ እንደገባላቸው ተረዳ፡፡ ዞር ብሎ የካልቨርትን ወዳጅ ተመለከታት።

“እዚህም አሉ?" አላት በደፈናው:: ምን ለማለት እንደፈለገ ግን ለራሱ ግልፅ አልነበረም::

ለአንድ አፍታ ካቅማማች በኋላ በአዎንታ ጭንቅላቷን ነቀነቀችለት፡፡

ሰውነቱ ሲግል ተሰማሁ፡፡ ልበ ያንን ደረቱን ይነርተው ጀመር፡፡አፉ ክው ብሎ ደረቀ፡፡ ወደ በሩ ተጠጋ፡፡

“ማነው?” አለ ድጋሚ ፍርሃቱን ክድምፁ ላይ ለመደምሰስ እየጣረ፡፡
“አምፖሉን አምጥቻለሁ” አለ የሴት ድምፅ
ሰውነቱ ሲረጋጋ ውሃ እንደፈሰሰበት ሁሉ ከላይ እስከታች ሰውነቱን ቀዘቀዘው::

“ተይው… ላልቶ ነበር አምፖሉ፤ አጥብቄዋለሁ::” አላት ወደ ቀሩ
ጠጋ ብሎ፡፡

ፊቱን መልሶ ቆመ፡፡ ግንባሩ ላይ ችፍፍ ያለውን ቀዝቃዛ ላብ በክንዱ ሞዠቀ:: ትክ ብላ የምትመለከተውን የካልቨርትን ወዳጅ አያኖች ሲያይ ፍርሃቱን ክፊቱ ላይ እንዳነበበችው ተረዳ:: ምናልባት በካልቨርት ፊት ላይ ያነበበችው ፍርሃት ታውሷት ይሆናል፡፡ ብሎ አሰበ፡፡

“ለምንድነው የሚያባርሩህ?” አለችው፡፡ እርጋታዋ አስደነቀው::
“ካልቨርት አልነገረሽም?“ አላት አልፏት ሄዶ አልጋው ጫፍ ላይ እየተቀመጠ።

“አልነገረኝም:: ሊነግረኝ የሚችለው ነገር እንዳልሆነ ስላስረዳኝ አስጨንቄ አልያዝኩትም::”

“ትክክል ነው ያደረገው:: ቢነግርሽም ዋጋ አይኖረውም፡-“አለ ምሥጢሩን እንደሚያውቅ ሁሉ አይኖቹን በባዶው ግድግዳ ላይ ተክሎ

“ለምንድነው ለፖሊስ የማታስታውቁት?” ለመጀመሪያ ጊዜ ድምጿ ውስጥ ጭንቀት አቃጨለ፡፡ “እስከመቼ ተደብቃችሁ ትኖራላችሁ?”

“ከፖሊስ በላይ ናቸው::"
“ነግርኛል፡፡ ይህንንና ሌላም ነግሮኛል ዮሴፍ፡፡ ግን ቢሆንም ያላችሁን ሁሉ በድብብቆሽ ልታሳልፉት አትችሉም! "

“ትክክል ነሽ እኔም የምለው ይሄን ኑ:፡፡ ተባራሪዎች እኔና ካልቨርት ብቻ አይደለንም:: ሌሎችም አሉ:: ግን እስከመቸ ተደብቀን እንዘልቃለን? ለዚህ ነው የሚመጣውን ሁሉ ተጋፍጠን መቆም አለብን የምለው ምናልባት ጥቂቶቻችን ሕይወታችንን እናጣ ይሆናል፡፡ ግን ይህ
ምንም አይደለም፡፡ የተቀሩት ንፁህ ኣየር ተንፍሰው ይኖራሉ፡፡”


“ታዲያ ለምን…?”

“ለዚህ ነው፡፡” አቋረጣት “ለዚህ ነው ካልቨርትን የምፈልገው ሌሎቹንም እየዞርኩ የምፈልገው ጥቂቶቹን አግኝቻቸዋለሁ አብዛኛዎቹ ግን
አብረውኝ ሊቆሙ ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ እንደ ቱሃን መሸሽጉን እንደ አይጥ
መሽሎክሎኩን ነው የመረጡት::”

ለጥቂት ሴኮንዶች ዝም አለ
ዓይኖቿን ሳትሰብር ትክ ብላ ተመለከተችው፡፡ ለአንድ አፍታ ፊቷ
ላይ ሃዘኔታ ያነበበ መሰለው፡፡

“ካልቨርት የት ነው ያለው? እርጅኝ::” ድምፁን ለስለስ አድርጎ ጠየቃት፡፡

ድንገት ከየት መጣ ሳይለው ጥርጣሬ ፊቷን ሸፈነው
“አላውቅም፡፡”

ተስፋ እንደቆረጠ ሁሉ ትንፋሹን በረጅሙ ለቅቆ ወደ ወለሉ አቀረቀረ፡፡

“እየው::” መጥታ አጠገቡ አልጋው ላይ ተቀመጠች፡፡ “ምናልባት እወነትህን ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ዮሴፍ ሊረዱት የሚፈልጉ ወገኖች እንደሌሉና አድራሻውን ለማንም መናገር እንደሌለብኝ አስጠንቅቆኛል፡፡”

“እውነቱን ነው ማንም ሊረዳው የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ እኔም
እራሴ ካልቨርትን ለመርዳት ስል አይደለም ከሞቀ ቤቴ በሌሊት የጠፋሁት:: ትሰማኛለሽ? ! ለነፍሰ፣ ለገዛ ሕያወቴ ፈርቼ ነው:: ግን የኔ፤ የካልቨርትና
የሌሎቹም ሕይወት የሚተርፈው ከተደበቅንበት ወጥተን አሳጁጆቻችንን
ስንገታቸው ብቻ ነው:: እንደ ሰጎን ጭንቅላታችንን አሸዋ ውስጥ ቀብረን
ስለቆምን አይደለም:: እመኚኝ ያገኙናል
👍1
እመኘኝ፡፡ አንድ በአንድ እያረዱ
ይጥሉናል፡፡ ካልቨርት የት ነው ያለው?

"ጥሩ ጊዜ ስጠኝ በመጀመሪያ እሱ ምን እንደሚል መልዕክት ልኬ ማወቅ አለብኝ፡፡ ስምህ ማነው? ማን ልበለው?” አለች ክንዱን ያዝ አድርጋ ትክ ብላ እየተመለከተችው::

“ጊዜ የለኝም! ጊዜ የለኝም! ከኋላዩ እያለከለኩ የሚሮጡት ተኩላዎች የሚፈልጉት ነፍሴን ነው! ጉሮሮዬን! ነው ይገባሻል?! አንቺ ከካልቨርት
ጋር እስክትመካከሪ ልጠብቅ አልችልም!” በንዴት ተንቀጠቀጠ፡፡
ያቅርታ ፤ ምንም ላደርግልህ አልችልም:: ከተቀመጠችበት ተነሳች

“ያቅርታ አትጠያቂኝ:: የእኔን ነፍስ ብቻ አይደለም ስጋት ላይ የጣልሽው የካልቨርትንም ነወ፡፡ እመኚኝ ያገኙታል፡፡ የጊዜ ጉዳያ ነው፤ ያገኙታል፡፡ ዓያንሽ ፊት አርደው ይጥሉታል፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት
እርጅን፤ የት ነው ያለው ካልቨርት? ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ ቢላው! ቢላህ!
ልምምጥ ካልገባት የራሷ ቢላዋ ጠልቋት ይገባል፡፡ ቢላውን ከኪሱ ውስጥ
አውጥቶ ያዘው::

አይኖቿ ቢላው ላይ ሲያርፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊቷ ገረጣ፡፡
“ምን ልታደርግ ነው?.
“ምን የማደርግ ይመስልሻል? ጓደኛዬ እንዴት እንደተገደለ ልተርክልሽ? ከሞቀ ቤቴ ወጥቼ እንደቀረሁ!! ላዋይሽ? የገዛ ፊቴን እንደ እስስት እየቀያየርኩ እንዳበደ ውሻ እንዴት እንደምሮጥና እንደምክክለፈለፍ ላወጋሽ?” በላውን እንደያዘ ተጠጋት፡፡

"አትነካኝም!“ አለች የማይታይ ከለላ እንዳላት ሁሉ ከቆመችበት ሳትንቀሳቀስ፡፡ “ጫፌን ብትነካኝ ዮሴፍ ምን እንደሚያደርግ ታውቃላችሁ”

“ካልቨርት እንደ እኔ ተባራሪ ሚዳቆ ነው:: ምን ሊያደርግ ይችላል?” ቢላውን ወደፊት ገፋ አድርጎ ተጠጋት::

“ያወጣዋል!” ጮኸችበት:: “ምሥጢራችሁን ሁሉ ያወጣዋል፡፡
ደግሞ ነግሯችኋል፡፡ አትነኩኝም!” ፍርሃትና ጥርጣሬ ድምጿን ይነዝረው፣
እንደ በገና ክር ያርገበግበው ጀመር፡፡

“እኔ ምን የምፈልግ ይመስልሻል ታዲያ? ያንን ነው የምፈልገው፤ምሥጢሩ መውጣቱን ነው'ኮ የምፈልገው! ገባሽ?!” አምባረቀባት፡፡ካልቨርት የጠፋው የተሸሽገው የኔን ምሥጢር ይዞ አይደለም፡፡ ምሥጢሩን ቢያወጣው በሰላም እቤቴ እመለሳለሁ፡፡” ቢላውን እንደያዘ ቀረባት:: ሌይዛት ግራ እጁን ሲሰድ በድንጋጤ ወደኋላ ስታፈገፍግ ቀይ የአልጋ ልብስ በለበሰው አልጋ ላይ ወደቀች:: ለአንድ አፍታ ጮኸች፡፡

በሩ ተንኳኳ፡፡

ናትናኤል ፊቱን መለስ አድርጎ አዳመጠ፡፡ ድጋሚ. ተንኳኳ፡፡ ናትናኤል ግራ እጇን ለቀም አድርጎ ድምፅ እንዳታሰማ ቢላውን አንገቷ ስር ሸጉጦ በምልክት አስፈራራት::
“'ማነው?' በያ፡፡” አላት ወደ ጆሮዋ ተጠግቶ፡፡
•ማነው?" አለች የምሥራች በሚንቀጠቀጥ ድምጿ፡፡
መልስ የለም፡፡ በሩ ተንኳኳ፡፡

“ማነው?“ አለች የምሥራች ጮክ ብላ፡፡ ድምጿ ፍርሃቷንና ጭንቀቷን በክፋሉ ውስጥ አስተጋባው፡፡
መልስ የለም:: በሩ ተንኳኳ፡፡
ናትናኤል ወደ ጆርዋ ተጠግቶ ሹክ አላት፡፡

“ቆያ መጣሁ... አንዴ ጠብቂኝ!” አለች የምሥራች ጮክ ብላ፡፡

ናትናኤል ዘሎ አልጋው ላይ ወጣና በራስጌ ያለውን መስኮት በቀስታ ከፈተው:: ጨለማ፡፡ አሁንም ገፋ አድርጎ ጭንቅላቱን ብቅ አደረገና ተመለከተ:: ጭር ያለ ጓሮ፡፡ ዞር አለና የምሥራችን ክንድ እፈፍ አድርጎ
“ዝለይ” አላት በሹክሹክታ::
“የት ነው የምዘለው?” በፍርሃት የረዘመ ፊቷን ቀና አድርጋ አፈጠጠችበት::

“ለማድረግ የማልፈልገውን ነገር እንዳደርግ አታስገድጃኝ::” አለ
የያዘውን ቢላ ጫፍ: ወደ እምብርቷ አስጠግቶ፡፡ “ጥያቄ እልፈልግም፥
ዝለይ:”

እሷ በመጀመሪያ፤ እሱ ተከትሏት በመስኮቱ ዘለው ወጡ፡፡

“የት ነው የምትወስደኝ?” በግራው ክንዱን ይዞ እየጎተተ በቀኙ
በያዘው ቢላ ወገቧን እየነካካ እየገፋት፣ ሲያዋክባት እሪ በይ እሪ በይ አላት፡፡ ነገር ግን አፉን ብትከፍት በቀኙ የያዘውን ረጅም ቢላ ሽንጧ ላይ እንደሚሰካው ሲሰማት ዝም ማለቱን መረጠች፡፡

ዝም ብለሽ ነይ፧ በአጥሩ ላይ እንዘላለን፡፡“ አላት በቢላው ጫፍ ወገቧን እየነካካ ወደ ጓሮው የቆርቆሮ አጥር እየገፋት፡፡

“አልችልም!” አለች ድንገት መጋኛ እንደመታት ድርቅ ብላ ቆማ፡፡

"ጥሩ... እኔ ከመዝለሌ በፊት ቢላሽን ሆድሽ ውስጥ እጨምርልሻለሁ፡፡” ፊቱን ወደፊቷ ኣስጠግቶ በጥርሶቹ መሃል ተናገራት፡፡
“አልችልም ነው'ኮ የምልህ! እንዴት ነው በአጥሩ የምዘለው” አለች በፍርሃት እየተንቀጠቀጠች በልመና ድምፅ። የስርቆሽ በር አለ፡ በዚያ አስወጣሃለሁ። እኔን ተወኝ፡፡ አልናገርም፡፡”

“የታለ የስርቆሽ በር?” ናትናኤል አብርሃም የነገረው ትዝ አለው ካዛንቺስ ከወዳጁ ቤት የሴት ልብስ ለብሶ ድሪያ ተከናንቦ በስርቆሽ በር ሲወጣ እየው… “የታል” አላት ደግሞ፡፡

ሳትናገር ወደ ግራ እጥፍ ብላ ዙሪያውን በቆርቆሮ ከታጠረው ግቢ በአንደኛው መዓዘን ከጓሮ ወዳለች ትንሽ በር ወሰደችው።

“ልቀቀኝ!” ይዟት ከግቢው ሊወጣ ሲል ክንዷን ለማስለቀቅ እየታገለች ጮኸች፡፡

የቢላውን ጫፍ ትከሻዎ ላይ ተከለና የለበሰችውን ቀሚስ ሰጡቶቿ
መሃል ቁልቁል ቀረደደው፡፡ በድንጋጤ በድን ሆነች፡፡

ድጋሚ ድምፅሽን አሰሚና ይህን ቢላ
ዓይንሽ ውስጥ እጨምረዋለሁ። ተጠንቀቂ፡፡ እርቄ ከመሄዴ በፊት አልለቅሽም፡፡ ካሁን በኋላ
እንዳትታይኝ” በጭለማው ውስጥ አፈጠጠባት፡፡

ድንገት ከጀርባቸው የሰው ዱካ ተሰማቸው፡፡

ክንዷን እንደያዘ በስርቆሽ በሩ ወጣና እየጎተታት ቀን ባጠናት ከዋናው መንገድ ተገንጥላ ወደ ሠፈር ውስጥ በምትገባው ቁልቁለት ተንደረደረ፡፡

መንገዱ ጭር ብሏል፡፡ በግራና በቀኝ የተደረደሩት ትናንሽ መሽታ ቤቶች በሮቻቸውን ገርበብ ገርበብ እንዳደረጉ ደንበኞቻቸውን ያስተናግዳሉ።
ክንዷን እንደያዛት ሮጠ፡፡

ከጀርባቸው የቆርቆሮ ኳኳታ ተሰማ፡፡

“ቁም!”

ወደ ግራ እጥፍ ብሎ በኮረኮንች መንገድ ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ያደረገችው ረጅም ጫማ ቢያስቸግራትም እየተወለካከፈች አብራው ሮጠች፡፡ ከግቢው ከወጡ በኋላ ለራሱም ግልፅ ባልሆነለት ሁኔታ የተለየ ስጋት የያዛት ይመስል! እሷም እንደሱው ተባራሪ እንደሆነች ሁሉ አብራው ተጣደፈች::

💫ይቀጥላል💫
👍2
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

...ካርተር በርክሌይም ቢሆን ሀብታም ነው ይህንን አታውቅ ይሆናል።ዊሊ ባደን እኮ በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላርን ለ ኤል.ኤ.ፒዲ የበጎ ሥራ አገልግሎት እንዲውል አስቦ ይለግሰናል።
የካርተር በርክሌይም ባንክ እስከ አሁን ድረስ ከሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለግሶናል።” አለው፡፡

ይሄኔም ጆንሰን ኮስተር ብሎ “ይህንን እንኳን አላውቅም ነበር ጌታዬ”
አለ ጉድማን “እኔም ብሆን ይህንን አላውቅም ነበር” ብሎ መለሰ፡፡

“ታዲያ እነርሱ ይህንን የመሰለ የበጎ እርዳታ ልገሳን ለእኛ በማድረጋቸው
ለእነርሱ የተለየ ነገር ይገባቸዋል ጌታዬ?” ብሎ ጆንሰን ጠየቀ፡፡

“ደግሞ በዚህ አይነት ድምፀት እንድታናግረኝ አልፈቅድልህም” ብሎ
ብሩዲ ኮስተር አለ እና “አዎን እነርሱ ይህንን ነገር ለእኛ በማድረጋቸው
የሆነ ነገር ከእኛ የፖሊስ ዲፓርትመንት ይጠብቃሉ። በእርግጥም ደግሞ
እነርሱ እነዚህን ነገሮችን በበጎ ፈቃድ ሥም ለእኛ ሲያደርጉ በምላሹ የእኛን
ዲፓርትመንት ጊዜ ግንዛቤ እና ክብርን ይጠብቃሉ፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ እነዚህ
ሰዎች ወንጀለኞች ወይንም ደግሞ በግድያው ወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች
አይደሉም። ዶክተር ሮበርትስም ቢሆን ማስረጃህን ሳታቀርብ እንደ ወንጀለኛ
ወይንም እንደ ተጠርጣሪ ልታያት አትችልም” ብሎ ብሩዲ ተናገረው።

ይህን የሰማው ጆንሰንም በቁጣ ፈነዳ እና “ሁሉም የዘረዘርካቸው ሰዎች በሙሉ ወንጀለኛ ሊሆኑ የማይችሉበት ምክንያት የለም።”

“ኒኪ ሮበርትስ ባሏ ከትዳሯ ውጪ ስላለው ግንኙነት ዋሽታናለች።ካርተር በርክሌይም ቢሆን ዛሬ ሆነ ብሎ የፖሊስ ጊዜን አባክኗል። በግድያ ወንጀል ላይ በሚደረግ የምርመራ ሂደት ሲዋሸኝ ነው የዋለው። ባደንም ቢሆን እኔ ባናገርኩት ወቅት ላይ ጠበቃው የሰጠው ስክሪፕት ዝንፍ ሳይል ነበር ይመልስልኝ የነበረው:: ስለዚህ ይሄ ሰውም ወንጀለኛ ላይሆን
የሚችልበት አንዱም ምክንያት አይታየኝም!”

“ይህንን አሁን መስማት አልፈልግም” ብሎ የፖሊስ አዛዡ ብሩዲ እጁን
አነሳ እና “ጆንሰን ለጋሾታችንን ማበሳጨትህን አቁም። ደግሞ ምስክር ሊሆኑ የሚችሉ ዐሰዎቻችንንም አታበሻቅጥ፡፡ አንተም ብትሆን ጉድማን
መልመጥመጥህን አቁም፡፡ ለማንኛውም ሁለታችሁም የግሮልሽን ሬሳን
በፍጥነት አግኙ ወይንም ደግሞ ስለመኪና አደጋው የተጨበጠ ነገር አግኙ
ያለበለዚያ ግን ሁለታችሁንም ከዚህ ምርመራ ላይ ላነሳችሁ እገደዳለሁ።”
አላቸው፡፡
ከአለቃቸው ቢሮ ወጥተው በሩን እንደዘጉም ጉድማን በፍጥነት
እየተራመደ ከጆንሰን ፊት ፊት መቅደም ጀመረ።ሀሀሀሀሀ
“እውነቴን ነው እኮ! ይልቅ ነገሮችን በግልፅ እንዳታይ እየከለከለችህ
ነው። ስለዚህ ባሏ ከትዳሯ ውጪ ስላለው ያልተገባ ግንኙነት ጠይቃት
አለው ጆንሰን ጉድማንን እየተከተለው።
ጉድማንም ከፊት ለፊቱ የሚገኘውን ሁለት በር ገፍቶ ወደ መኪና
ማቆሚያው ቦታ ቶሉ ቶሎ እየተራመደ መሸሽ ጀመረ።
“ጠይቃት!” አለው እና ጆንሰን ጉድማንን እየተከተለም
“ትላንትና ማታ አብራችሁ ነበራችሁ አይደል?” አለው።
ጉድማንን ጆንሰን ሊሆን ይችላል ብሎ ያሰበው ነገር እና እሱን ለማናገር
የተጠቀመበት ዘዴ ይሆናል ብሎ አሰበ እና መልስ ሳይመልስለት ወደ
መኪናው ገባ፡፡
“ስለ ባሏ ውሽማ አንድም ነገር አልነገረችህም አይደል? ሰውዬ እሷ
እየተጠቀመችብህ እና እየተጫወተችብህ ነው። ስለዚህ አይንህን ክፈት
እባክህን” አለው፡፡
ጉድማንም መኪናውን አስነስቶ በፍጥነት እያሽከረከረ ከጆንሰን ሲሽሽ
ጆንሰን በመጨረሻ ላይ የተናገረው ነገር ጆሮ ውስጥ እየደወለበት ነበር።

ጉድማን ከፖሊስ ጣቢያው የሆኑ ያህል ብሎክ ከራቀ በኋላ መኪናውን
አቆመ እና ሦስት ጥልቅ ረዥም አየርን ወደ ውስጡ ሳበ፡፡

በአለቃቸው ብሩዲ ቢሮ ውስጥ እያሉ ጆንሰን ስለ ኒኪ ሮበርትስ የተናገረው ነገር ብዙም አላሸበረውም ነበር። ምክንያቱም እሱ ለእሷ ያለው አመለካከት ጆንስን ስለ እሷ ከተናገረው የተለየ በመሆኑ ነው።
መኪናው ውስጥ እንደተቀመጠም ሚክ በኒኪ ሮበትስ ላይ ስላቀረባቸው
ውንጀላዎች ተመስጦ ላለማሰብ ፈለገ። ማለትም ኒኪ ሮበርትስ ባሏ ከትዳሩ
ውጪ ስላለው ግንኙነት በፊት ላይ አስቀድማ በማወቋ የተነሳ የመኪና
አደጋው እንዲደርስ፣ ባሏም ከነ ውሽማው እንዲሞት ማድረጓን እንደዚሁም
ደግሞ ይህንን ብልህ አዕምሮዋን ተጠቅማ የሊዛ ፍላንገን እና የትሬይ
ሬይሞንድን ግድያዎችን ፈጽማለች ብሎ ጆንሰን ያቀረበውን ነገር በተመስጦ
ማስብ አልፈለገም፡፡

በመጨረሻ ላይ ጉድማን ኒኪ ሊዛን እና ትሬይን እንዳልገደለች አመነ፡፡ባሏን እና ውሽማውን መግደሏ ግን ሊሆን ይችላል? ይህንን አምኖ መቀበል አልፈለገም። ያም ቢሆን ግን ጆንሰን በእዚህኛው ጉዳይ ላይ የተለየ እውነታን ለማቅረብ ሞክሯል። ብቻ አሁን ላይ የተቆራረጡ ሀሳቦችን መሰብሰብ እንዳቃተው ያምናል።

“ማን ናት የዶውግ ሮበርት ውሽማ?

ለምንድነው የእሷ ሥም እና ማንነት በወቅቱ በአደጋው ጊዜ ላይ
ያልተገለፀው? ስለ አደጋው የቀረበው ሪፖርት የት ሄደ?

ደግሞ ኒኪ ትላንትና ማታ ነፃ ሆነን በግልፅ እያወራን በነበረበት ጊዜ
ላይ ለምንድነው ባሏ ከትዳሩ ውጪ ስለነበረው ግንኙነት ልትነግረኝ
ያልቻለችው? የሚሉ ጥያቄዎችን በውስጡ እያስተናገደ እያለ ጆንሰን
“እየተጫወተችብህ ነው አይንህን ክፈት እባክህን!” ብሎ ቅድም የተናገረው
ነገር በጆሮው አንቃጨለበት፡፡

ኒኪ ሮበርትስ በእውነት እየተጫወተችበት ነውን?

በዚህ ሀሳብ ውስጥ እያለ ነበር ጉድማን ስልኩን አውጥቶ ወደ ኒኪ ስልክ
የደወለው፡፡

በደበዘዘው ብርሃን በዲስኒ የኮንሰርት አዳራሽ ውስጥ ቁጭ ያለችው ኒኪ
ስልኳ ሲጠራ ስልኳን ከቦርሳዋ ውስጥ አወጣች እና ተመለከተችው።
የጉድማንን ሥም ከስክሪኑ ላይ ስለተመለከተች ስልኩን መለሰች እና ስልኳን አጥፍታ ቦርሳዋ ውስጥ ከተተችው። ቦርሳውን ለኮንስርቱ ብላ ነው
የገዛችው፡፡ ለምሽቱ የኮንሰርት ዝግጅት አስባም ያገዛችው ረዥም ቀሚስ
ሰውነቷ ላይ ልክክ ብሎባታል። ቀሚሱ እሷ ላይ ልክክ በማለቱ ደግሞ
ኮንሰርቱን ለመታደም አዳራሽ ውስጥ ያሉትን የወንዶች አይን ስቦላታል፡፡
ከወንዶች ጋር ያሉት ሴቶችም እሷን በቅናት አይን ነው የሚመለከቷት፡፡

አኔ ቤታማንም የሁለት ሰዓቱን የሙዚቃ ኮንስርት ዝግጅትን በቫዮሊኗ
እየተጫወተች አድምቃዋለች:: አኔ ቫዩሊኗን በሚገርም ችሎታ እና ብቃት
ስትጫወት ኒኪን እና አዳራሹ ውስጥ ኮንሰርቱ ላይ የታደሙትን ሰዎች ሁሉ
ስሜት በደንብ ነበር ይዛ የቆየችው።

ደግሞም የአኔን ድንቅ የሙዚቃ ችሎታን ያ ራስ ወዳዱ ባሏ ይፋ እንዳታወጣው በእንስሳ ማጎሪያ ክፍል ውስጥ ዘግቶ ለብቻው ሊያስቀምጣት መፈለጉ ደግሞ በእውነትም ኪሳራ ነበር ማለት ይቻላል። ኒኪ አኔ ቤታማን ቫዩሊኗን እጅግ በጣም ተመስጣ ስትጫወት በመመልከቷ ስሜቷ
በማታውቀው ሁኔታ ተነካባት እና አይኗ በእምባ ተሞላ። የእምባዋ መምጣት ሙዚቃውን አኔ ቤታማን በድንቅ ሁኔታ እየተጫወተች ስለሆነ ወይንም ደግሞ እሷን ገጥመዋት ከነበሩት የሀዘን ስሜቶች የተነሳ እንደሆነ እርግጠኛ አልነበረችም፡፡

ትላንትና ማታ ከጉድማን ጋር ያሳለፈችው ምሽት የሆነ መጨረሻ ላይ የደረሰች ያህል ነበር እንዲሰማት ያደረገው። በእውነትም ደግሞ አስገራሚ ሞኝ ሆኖ ነበር ማለት ይቻላል። በግድያው ወንጀል ላይ ምርመራውን ከሚያደርግ ፖሊስ ጋር ለመተኛት እስከምትፈልግና ሞቅ እስከሚላት ድረስ መጠጣቷ ትክክል አልነበረም፡፡ ለመርማሪው ፖሊስ የተሰማት ከፍተኛ የሆነ አካላዊ ስበት ደግሞ ለረዥም ጊዜ ሳይሰማት የቆየ ስሜቷ ስለነበር ገርሟታል። ምንድነው
ችግሬ? ምን ሆኛለሁ?” ብላ አሰበች እና በመቀጠልም እኔ እኮ እንደዚህ አይነት ሰው አልነበርኩም፡፡ እንዴ በደንብ ከማላውቀው ሰው ጋር አብሬ እየጠጣሁ ሰክሬ ነበር። በዚህም ራሴን አደጋ ውስጥ ጥዬ ነበር ብላ አሰበች፡፡

ግን ደግሞ እኮ ባለፉት ወራቶች ከዚህ በፊት የማታደርጋቸውን ነገሮች ስታደርግ አልነበር? ለምሳሌ ያህል ታካሚዋን ለማስገረም አንድ ሺ ዶላር አውጥታ ምርጥ ቀሚስ ገዝታለች። ለዚያውም አግብታ እና ባሏን ጥላ የመጣችን ሴት ለማማለል አስባ። ኒኪ ከዚህች ታካሚዋ ለመነጠል ትፈልጋለች፡፡ ነገር ግን ከታካሚዋ ጋር አብራ መሆኗ በሟች ባሏ ላይ የሚሰማትን ከፍተኛ የሆነ ንዴትን ለማስወገድ ተጠቅማበታለች።

“ምስኪን ዶውግላስ። ግን እኮ ዶውግላስ አሁን በህይወት የለም። ግን አልረሳችውም፡፡”

መቼም ቢሆን ባሏን ዶውግን ልትረሳው አትችልም፡፡

አኔ የቫዮሊኑን ዘንግ በዝግታ ስታወርድ እና ኮንዳክተሩም የኮንሰርቱ ማብቃትን ሲያሳውቅ አንድ ሆነ፡፡ ሙዚቃው ካበቃ ከጥቂት ሰከንዶች በኋላም አዳራሹ ውስጥ የነበሩት ታዳሚዎች የአድናቆት ጭብጨባቸውን እያሰሙ ከተቀመጡበት ወንበሮች ላይ ተነሱ። ታዳሚዎቹ በፉጨት እና በጭብጨባ አድናቆታቸውን እየገለፁ እያሉም የአዳራሹ መብራት በራ። ትላንትና

በጠጣችው መጠጥ ከደረሰባት የዞረ ድምር እና የአዳራሹ ታዳሚዎች
በሚያሰሙት ከፍተኛ ድምፅ እና በአዳራሹ ድንገተኛ መብራት ራሷን ትንሽ
ዘወር ሲያደርጋትና አኔ ከመድረኩ ላይ ቆማ የቫዩሊን መጫወቻ ዘንጓን ይዛ
ስታያት በጣም ትንሽዬ እና የምትሰበር ነበር የመሰለቻት። የአኔ ነጭ ፊት
ከለበሰችው ቀለል ያለ ግራጫማ ቀሚስ ጋር ተዋህዷል።

የኔ ጥበቃ ያስፈልጋታል ብላ ኒኪ አሰበች፡፡ “የእኔ ሙያዊ እገዛ
ያስፈልጋታል። እንድትወድቅ ልተዋት አይገባም፡፡ እጇን ይዤ ላሻግራት
ይገባል አለች ለራሷ።

ኒኪ አኔ የሰጠቻትን የይለፍ ወረቀት እያሳየች አለፈች እና ከመድረኩ ጀርባ ደረሰች። አኔ የመልበሻ ክፍሉ ውስጥ ስትገባ ኒኪን እየጠበቀቻት ነበር፡፡

“ሄሎ” ብላ አኔ ኒኪን እያፈረች አቀፈቻት። የአኔ ማፈር ኒኪን ኮንሰርቱ ላይ እና ከመድረኩ ጀርባም እንድትገኝ አጥብቃ ለምና ያላስመጣቻት ስለሚመስል፣ ኒኪ ትንሽ ቅር አላት፡፡ “ዋው መጣሽልኝ፡፡ አደረግሽው!” አለቻት አኔ።

“እንዴታ እመጣለሁ ብዬሽ አልነበር?” ብላ ኒኪ አኔን አቀፈቻት፡፡

“እንዴት ነበር?” ብላ አኔ ኒኪን በጉጉት ተሞልታ አስተያየቷን ጠየቀቻት፡፡

“በሚገርም ብቃት ነበር ቫዮሊንሽን የተጫወትሽው፡፡ ሁላችንንም አዳራሹ
ውስጥ የታደምነው ሰዎችን ነው በስሜት የናጥሽው።”

“በእውነት? ከምርሽ ነው?”

“ከእውነትም በላይ እሺ” ብላ ኒኪ መለሰች፡፡

አንድ አንዴ ኒኪ አኔ የምትጫወትባት እና እንደ አንድ ታካሚም ለእሷ ብቻ ደንታ እንዲኖራት የምትፈልግ ይመስላታል፡፡ ያ ሁሉ ሰው ተነስቶ ሲያጨበጭብላት ሙዚቃውን በጥሩ ሁኔታ እንደሰራችው መቼም መገመት አያቅታትም አይደል? ለማንኛውም እርግጠኛነቱን ከኒኪ ስለምትፈልገው ኒኪ ትንሽ በውስጧ ኮራች።
“አኔ ያንቺን አይነት ችሎታ ያላቸውም ሰዎች ማግኘት ቀላል አይደለም።
ባይገርምሽ እኔ ያንቺን ያህል ሽራፊ ችሎታ ቢኖረኝ ኖሮ በደስታ ሰክሬ
እሞት ነበር” አለቻት ኒኪ፡፡

አኔም ፈገግ አለች እና “አታሹፊ ካንቺ በላይ በሙያው የተሳካለት ሰው
አለ እንዴ ደግሞ፡፡ በነገራችን ላይ ዛሬ ምሽት ደግሞ እጅግ በጣም
አምሮብሻል። በጣም ቆንጆ ሆነሻል” አለቻት፡፡

አኔ ስለ ቁንጅናዋ የሰጠቻት አስተያየት የጠበቀችው ስላልነበር ጉንጫ በእፍረት ቀላባት እና “አመሰግናለሁ። አንቺም ብትሆኚ አምሮብሻል” አለቻት።

የበሩ መንኳኳት ወሬያቸውን አቋረጣቸው። ኒኪ በሩ አጠገብ ስለነበረች በሩን ከፈተችው፡፡ በሩ እንደተከፈተም አንድ ወጣት ልጅ በተሸከመው ውብ
ነጭ አበባ ብዛት እየተንገዳገደ ወደ ውስጥ ገባ። ምናልባት የአበባው ክብደት
ከወጣቱ ልጅ ክብደት እኩል ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከመቶ በላይ የሚሆኑት
የአበባው ግንዶች እግራቸው ላይ ታስረዋል።

“ወይዘሪት ቤታማን ይሄ አበባ ላንቺ ነው።” አለ እና የአበባውን ማስቀመጫ ወለሉ ላይ አስቀመጠ እና ካርድ አውጥቶ “እንኳን ደስ አለሽ” ብሎ ሰጣት፡፡

“በእግዚአብሔር ሥም!” ብላ ጮኸች አኔ ከእሷ በቁመት የሚበልጠውን
አበባ እየተመለከተች።

“ይሄ ሁሉ አበባ ምን ያደርግልኛል? እባክሽን ከነዚህ አበቦች የቻልሺውን
ያህል ወደ ቤትሽ ወይንም ለቢሮሽ ውሰጂ” ብላ አኔ ወደ ኒኪ ዞራ ጠየቀቻት
እና ካርዱን ገልጣ ከውስጥ ያለውን ማንበብ ጀመረች። ኒኪ አኔ ካርዱን
ስታነብ ፊቷ ላይ የሚታየውን ለውጥ በቴራፒስት አይኗ መከታተል ጀመረች። አኔ እጇን ልቧ ላይ ጭና የታችኛው ከንፈሯን በጭንቀት ነክሳለች። ፊቷ ላይም ሀዘን እና ፍቅር የሚታይበትንም ፈገግታን ከፊቷ ላይ ተመለከተች።

ኒኪ ልቧን እየከበዳት “አበባዎቹን የላካቸው እሱ ነው አይደል?”
አለቻት፡፡

አኔም በአዎንታ ራሷን ነቅንቃ በረዥሙ ተነፈሰች “አዎ አበባዎችን የላከልኝ ባሌ ነው፡፡ እዚህ ተገኝቶ ሙዚቃዬን ስሠራ ቢመለከተኝ ደስ ይለው እንደነበር ግን እንዳልቻለ፣ እንደዚሁም ደግሞ የእኔን ሙዚቃ በየቀኑ በህልሙ እንደሚያይ እና በልቡም ይዞት እንደሚዞር ነው የፃፈልኝ” አለቻት፡፡

ኒኪም በቁጣ ተሞልታ እያየቻት “ይሄ በእውነት የሚያሳፍር ነው።መቼም እሱ ያንቺን ሙዚቃ በልቡ ይዞት ዞሮ አያውቅም፤ ምክንያቱም ከፍቃድሽ ውጪ ልክ እንደ እስረኛ ከቤቱ ሳትወጪ እና በየትኛውም መድረክ ላይ ሙዚቃ እንዳትጫወቺ ከልክሎሽ አልነበር? ለዚያውም ለስድስት ዓመት ሙሉ?”

“አውቃለሁ” አለች እና አኔ አበባዎቹ ላይ አይኗን ተክላ “እዚህ ምን ይላል መሰለሽ ይሄው ከእሱ የራቅኩበትን ቀናት በአበቦቹ ቁጥር ልክ ቆጥሮ ነው የላከልኝ። ይህ ደስ አይልም ታዲያ?” አለቻት።

ኒኪ በሰማችው ነገር በጣም ተናደደች። “እንዴት ነው አንዲት ሴት አንድ
ወንድ እንደዚህ እንዲጫወትባት እና እንዲቆጣጠራት የምትፈቅድለት?' ብላ
ስታስብ ደግሞ ይበልጥ ተበሳጨች እና

“ድንቄም ደስታ! ስለ እግዚአብሔር ብለሽ አኔ ለማደግ ሞክሪ! ይሄ እኮ የሆነ የዕቃቃ ጨዋታ አይደለም። እየተጫወትሽ ያለሽው እኮ በወደፊት ህይወትሽ ላይ ነው።” ብላ ጮኸችባት፡፡

አኔም ፊቷ በንዴት ተለዋወጠ። አንድም ቀን ቢሆን በኒኪ ላይ ንዴቷን አሳይታ አታውቅም እና ኒኪ የአኔ ንዴት ግድቡን አፍርሶ እንደሚወጣ ጎርፍ ሲሆንባት ተመለከተች።

“ልክ ነሽ ይህ የእኔ ህይወት ነው፡፡ የእኔ ብቻ ያንቺ ያልሆነ! ስለ እዚህ ተይኝ!”

አኔ እኔ እኮ ስለ አንቺ ደንታ አለኝ” ብላ “እንደ ቴራፒስት...”

አቁሚ!” ብላ አኔ ጮኸችባት እና በመቀጠልም “ይሄ የቴራፒስትነት
ጉዳይ አይደለም። ምን እየተሰማሽ እንደሆነ ሁለታችንም እናውቃለን እኮ”
አለቻት።

ኒኪ አኔ ከተናገረች በኋላም ወደ እሷ እየተመለከተች ፈዝዛ ቀረች::
ለአፍታ ያህል ጊዜም ሁለቱ ዝም ብለው ቆዩ። በመጨረሻም አኔ ነገሩን
ለማለዘብ በማሰብ መናገር ጀመረች፡፡

“ይሄውልሽ ስለ ምክርሽ አመሰግናለሁ። አንቺ እንደምታስቢልኝ አውቃለሁ። ስላደረግሽልኝ ሙያዊ እገዛም በጣም አመሰግናለሁ። በዚህም ህይወቴን ለውጠሽልኛል” አለቻት እና በመቀጠልም “ግን ባሌን ሁልጊዜም ልትጠይው አይገባም። ማለቴ ጥሩ ነገር ሲያደርግልኝ እንኳን እያየሽ ለእሱ ያለሽ ጥላቻ ያው ነው።”

“ይሄ እኮ ጥሩ ነገር አይደለም። እውነታውን እወቂ! ይሄ ሌላኛው አንቺን
የመቆጣጠሪያው መንገዱ እና የማስገደጃ መንገዱ ነው፡፡ በነገራችን ላይ እሱ ባልሽ ሳይሆን ጥለሺው የመጣሽው ሰው ነው። ይቅርታ አኔ ቆም ብለሽ
ራስሽን መጠየቅ ይኖርብሻል ለምንድነው
👍3
እንደዚህ መታወር የፈለግሺው?” ብላ በንዴት ጠየቀቻት።

“እንዴት ነው መታወር የፈለግሺው ነው ያልሺኝ? አንቺስ?” ብላ አኔ መለሰችላት እና እምባዋ እንዳይወርድ እየታገለች “አንቺስ ምን ያህል ታውረሽ እንደነበር ረሳሽው እንዴ? ህም? ባልሽ ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት እንዳለው እያወቅሽ እንኳን ታውረሽ አልነበር እንዴ?” አለቻት።

ኒኪ ይህንን ስትሰማ ወድያውኑ ፊቷ ገረጣ። ዓለም ሁሉ የታፈነ ነገር
ሆነባት፡፡ ይህንን ወሬያቸውንም የሚያወሩት ወይ ውሃ ውስጥ ሆነው
አልያም ደግሞ በህልሟም መሰላት “ይህንን ደግሞ ከየት ልታውቅ ቻልሽ?
ማን ነው ይህን የነገረሽ?”

“አሁን ከዚህ መሄድ አለብሽ” ብላ አኔ ቁርጥ ባለ ድምፅ መለሰችላት።
ኒኪም አኔ ነገሩን ከየት እንደሰማች እንደማትነግራት ገባት። አሁን ሁለቱም
መስመር አልፈዋል፤ ከዚህ በኋላ ወደ ኋላ መመለስ የለም፡፡

የሆነ ሰው አሲድን ወደ ጉሮሮዋ፣ ወደ ደረቷ፣ ከዚያም ወደ ታች ወደ
ሆዷ እየጨመረባት እንዳለ አይነት ስሜት እየተሰማት እሺ እሄዳለሁ” ብላ
ወደ በሩ ተራመደች እና በሩ ጋ ስትደርስ ወደ አኔ ዞር ብላ “ ይገድልሻል
ታውቂያለሽ አይደል? ወደ እሱ ከተመለስሽ አንድ ቀን ይገድልሻል፡፡ እንደ
እሱ አይነት ወንዶች ሁሌም እንደዚህ ናቸው:: መግደል ወይም መገደል ነው
አላማቸው።” ብላ በሩን በሀይል ጠርቅማባት ወጣች።......

ይቀጥላል
🔥1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

...ከሩቅ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ በርሜሎች ሲመለከት ክንዷን ይዞ ወደዚያው ጎተታት፡፡አካባቢውን ባለበሰው የቆሻሻ ክምር ላይ ተሻግረሁ ከበርሜሎቹ ጀርባ ዞረው ሸብረክ ሸብረክ አሉ፡፡በስተግሪ ራቅ ብሎ መደዳውን ከተኮለኮሉት የመሸታ ቤቶች የሚወጣው ደብዛዛ ብርሃን አካባቢውን በድቅድቁ ጨለማ ከመዋጥ አድኖታል ወዲያ ማዶ አንድ የጭነት መኪና ቆሟል፡፡ በስተቀኝ የውሾች ጥል በጨለማ ውስጥ አስተጋባ፡፡ድምፃቸውን አጥፍተው ተጠባበቁ፡፡

ናትናኤል ቀና ሲል በጨለማው ውስጥ አንድ ነገር ውልብ ሲል ተመለከተ፡፡ ዓይኖቹን በሰፊው ከፍቶ በጨለማው ላይ አፈጠጠ፡፡ ድምፅ ተሰማው... እየቀረበች ስትመጣ ሲለያት በእፎይታ ትንፋሽን ለቀቀ።ሰካራም ሴት ነበረች:: እንደመንገዳገድ ትልና ወደፊት ትራመዳለች፡፡ ትንሽ ታንጎራጉርና ደግሞ ወደፊት ተራመዳለች፡፡ ብዙም ሳይቆይ ከሰካራሟ ጀርባ የሌሎች ሰዎች ሩጫ ተሰማ፡፡ ናትናኤል ከበርሜሎቹ ጀርባ ሳይወጣ ጭንቅላቱን ብቻ አቅንቶ ተመለከተ::

ሦስት ሰዎች እየተሯሯጡ በኮረኮንቹ መንገድ መጡ፡፡ በኮረኮንቾ
መንገድ ላይ እየተወለካከፉ ሲሮጡ ናትናኤል አዳኞቹ እንደሆኑ ገባው::
ሰካራሟ ሴትጋ እንደደረሱ ከሦስቱ አንደኛው የያዘውን ባትሪ መለስ አድርጎ
ፊቷ ላይ ቦግ እደረገባት፡፡
“ትዝታ እ.. እባላለሁ፡፡” አለች ሰካራሟ ኣይኖቿን ባትሪው ብርሃን በክንዷ ከልላ “ሀ! ሀ! ሀ! ከፈለግህ ደሞ እቤት እንሂድና::ባትሪውን ያበራባት ሰው ትቷት ከጓደኞቹ ጋር ወደፊት ቀጠለ።
ሦስቱ ሰዎች ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያዎቹ ሲደርሱ ትንሽ ሲቀራቸው ቆም አሉና ተነጋገሩ፡፡ ወዲያው ሁለቱ በስተቀኝ ታጥፈው በጨለማው ውስጥ ሲሰወሩ ባትሪ የያዘው ሰው በበርሜሎቹ ኣቅጣጫ አመራ፡፡
ናትናኤል አብራው የተደበቀችውን የካልቨርትን ወዳጅ ጠረጠራት፡፡
ብትጮህስ? ብትጣራና ብታሲዘውስ? እዚሁ ቆሻሻ መጣያ በርሜል : ስር
ደፍተውት ሊሄዱ አይደል? ፈጠን ብሎ ቀኝ እጁን በትከሻዋ አሳልፎ አፏን
አፈናትና በግራ እጁ የያዘውን የቢላ ጫፍ አንገቷ ስር ሽጎጠው፡፡

“ትንፍሽ እንዳትይ… ፊቱን ከማዞሩ በፊት ይሄ ቢላ ማጅራትሽ ነው የሚደርሰው፡፡” አላት ዓይኖቹን በበርሜሎቹ አቅጣጫ ቀሮጠው ሰው ላይ ተክሎ፡፡

ሳትነቃነቅ አይኖቿን ብቻ ኣቅንታ በጭንቀት ተመለከተችው::እንገቷ ስር የተሸጎጠው የቢላ : ስሎት ለስላሳ ቆዳዋን እንደ ምላጭ ሲሰነጥቀው ተሰማት::
ሰውየው ወደ በርሜሎቹ እየተጠጋ በመጣ ቁጥር በደመነፍስ ያወቀና የተረዳ ይመስል ፍጥነቱን ቀንሶ የባትሪውን ብርሃን እንደ ነብር ጅራት ከወዲያ ወዲህ እያላጋ ዙሪያውን እየፈትሽ በዝግታ ይራመድ ጀመር፡፡ እየቀረባቸው ሲመጣ ናትናኤል በበርሜሎቹ አናት ላይ ተመለከተው።በግራው ባትሪውን እንደጨበጠ በስተቀኝ የኮት ኪሱ ውስጥ የጨመረውን እጁን ሲመለከት ስውየው መሣሪያ እንደያዘ ናትናኤል ተረዳ፡፡ በየምሥራች አፍ ላይ የጫነውን የቀኝ እጁን ጠበቅ አደረገና በግራው የያዘውን ቢላ ከአንገቷ ስር አውጥቶ ይዞ ተዘጋጀ፡፡ ተጠባበቀ፡፡ ከበርሜሎቹ ዙሪያ
የፈሰሰው ቆሻሻ ላይ ሲረግጥ የአዳኙ ኮቴ ኮሽታ ተሰማው። ሲጠጋውና
ሲቀርበው ሲደርስበት ተወርውሮ ቢላውን ሊሰካበት ተዘጋጀ፡፡ ሰውየው
ድንገት ቆም አለ፡፡ ያመነታ መስለ ባትሪውን ዞር አድርጎ በበርሜሎቹ ላይ
እበራ፡፡ የባትሪውን ብርሃን በዙሪያው አወናጨፈው፡፡ ወዲያው ፊቱን መልሶ
በኮረኮንቹ መንገድ ወደፊት ቀጠለ፡፡

ሰውየው ከራቀ ወዲያ ነበር ናትናኤል ለመተንፈስ የደፈረው።የምሥራችን አፍ ለቀቀና ቀና አደረጋት፡፡

“አይዞሽ አትፍሪ፤ ልጎዳሽ አልፈልግም:: እመኚኝ፡፡ ከዚህ በላይ ምን ማረጋገጫ ነው የምትፈልጊው?” አለ ትከሻዋን በሁለት እጆቹ ይዞ እየነቀነቀ፡፡ “በይ ተነሺ… ሳንቻኮል በእርጋታ እየተራመድን ወደ ዋናው መንገድ እንውጣለን፡፡ ለመሮጥ ወይ ለመጮህ ብትሞክሪ ግን ምርጫ አይኖረኝም::”

“አልሮጥም::” አለች ፊቷን መልሳ በፍርሃት እየተመለከተችው::

ናትናኤል የምሥራችን ክንድ እንደያዘ ቁጢጥ ካለበት ብድግ ሲል እንቅስቃሴ ታየው፡፡ ተመልሶ ሸብረክ አለና እንዳጎነበሰ አሻግሮ ተመለከተ፡፡
እየተንገዳገደች ቆም ራመድ እንደገና ቆም እያለች በኮረኮንቹ መንገድ
ተመልሳ ትመጣለች ሰካራሟ፡፡

“ተነሽ…” አለ ናትናኤል የምሥራችን ክንድ እየጎተተ፡፡ “ሰካሪሟ ከተደበቁበት የቆሻሻ ማጠራቀሚያ በርሜሎች ስር ወጥተው ፈጠን ብለው በዋናው መንገድ አቅጣጫ አመሩ፡፡

“ታዲያስ!” አለቻቸው ከፊት ለፊታቸው እየተወለካከፈች፣ እየተንገዳገደች የምትመጣው ሰካራም::“እስቲ ወንድም ብር ግፋ፡፡” አለችው ናትናኤልን ስትመለከት እጇን ወደፊት ዘርግታ፡፡

“ዞር በይ!” አላ ናትናኤል አልፏት ለመሄድ እየሞከረ:: ድንገት በዘረጋችው መዳፏ ውስጥ የጨበጠችውን ሲመለከት ግን መላ አካላቱን ደነዘዘው፡፡ : የምሥራች ከፊቷ የተደቀነውን ስታይ እንዳትጮህ የፈራች ይመስል የገባ አፏን በገዛ መዳፏ ግጥም አድርጋ ዘጋችው፡፡

“የማይሆን ነገር አትሞክር፡፡” ኣለች ሰካራሟ የያዘችውን ሽጉጥ ወደ
ሆዱ ገፋ አድርጋ፡፡ “ተነቃነቅ..ዘረግፍሃለሁ፡፡” ድንገት ፊቷን ወደ የምሥራች መለሰችው፡፡ “አንድ ዕድል እሰጥሻለሁ፤ ካልቨርት የት ነው?”
የሽጉጧን አፈሙዝ መለስ አድርጋ የምሥራች ላይ ደቀነችው፡ “ንገሪኝ ጊዜ
አትውሰጂ!”

“እኔ ኣላውቅም፡፡”
በእጁ የጨበጠው የምሥራች ክንድ ሲንቀጠቀጥ ተሰማው:: “ተኩሼ ሳልቀረድድሽ ንገሪኝ:: ካልቨርት የት ነው?' ሴትየዋ አፏን ሳትከፍት በጥርሶቿ መሃል ተናገረች፡፡

“አላውቅምኮ፡፡” የምሥራች ድምፅ እንደ ወፍ ትንፋሽ ሳሳ፡፡ፍርሃት ያንቀጠቅጣት ጀመር፡፡

ሴትየዋ አላመነቻም፡፡ ወደኋላ ጥቂት እርምጃዎች አፈገፈገች፡፡ ናትናኤል ያልጠበቀው ድምፅ ቡፍ አለ፡፡ የምሥራች እጁ ላይ ተልፈሰፈሰችበት... ለቀቃት። ዝልፍልፍ ብላ በስተቀኙ ተዘረጋች፡፡ ከፊት
ለፊቱ ሽጉጧን ደግናበት ከቆመችው ሴት ጋር ተፋጠጠ፡፡ ትንፋሹን ይዞ ጠበቃት፡፡ አእምሮው እርስበርሱ ተጣላበት፡፡ ሊፈነዳ ያሰበ ይመስል ማጅራቱ ሲወጠር ተሰማው:: ዘሎ ይነቃት? ወይስ መጨረሻውን በቆመበት ይቀበል?
ድንገት ፈገግ ያለች መሰለው.. ፈገግ አለች ሴትየዋ፡፡ ከኋላው የሩጫ ድምፅ
ተሰማው፡፡ ከፊት ለፊቱ ቆማ የነበረችው ሴት በፍጥነት የሽጉጧን አፈሙ
ወደ መሬት መለሰችና ከትከሻው ላይ አሻግራ በጨለማው ላይ አፈጠጠች

“ሩጥ!” አለችው በሹክሹክታ ወደጎን ትታው የሩጫው ድምፅ ወደመጣበት እየተራመደች፡፡ “ተዋትና ሩጥ፤” አለችው ድጋሚ ፊቷን መልሳ፡፡ የምሥራችን እየጎተተ ወደ ጥግ ሲሸሸግ ስታየው፡፡ “እሷን ተውና ሩጥ!”

ናትናኤል ሳይመልስላት የምሥራችን ብብቶቿ ውስጥ ገብቶ እየጎተታት ወደ ጥግ ሽሽግ አለ፡፡ መሬቱ ላይ ተንበርክኮ የምሥራችን ጭንቅላት ቀና አደረገና ትንፋሿን አዳመጠ፡፡ አለች፡፡ የምሥራች... የምሥራች...” ድምፁን ቀንሶ ተጣራ፡፡
እያኖቿን በትግል ፡ ገልጣ ተመለከተችው.. እየሞተች ነው...
እየቀዘቀዘች ነው… እያበቃች ነው... ሊያድናት እንደማይችል ተረዳ፡፡
“የምስራች ንገሪኝ ካልቨርት የት ነው ንገሪኝ! ሁላችንን ሳይጨርሱን በፊት ንገሪኝ?”
“ካልቨርት ዮ....ሴፍ” ከጉሮሮዋ የሚወጣው ድምፅ ሻከረበት፡፡
“አዎ ዮሴፍ ዮሴፍ፡ ካልቨርት የት ነው ያለው?”
ከወዲያ የሚሰማው የሩጫ ድምፅ እየቀረበው መጣ አንድ ሴት
ስታንጎራጉር ይሰማል.. በጨለማው ውስጥ..
ዮ....ሴፍ...” የምሥራች ድምፅ በጭንቀት እየተበጣጠሰ ተንጠባጠበ፡፡
“አዎ.... አዎ የት ነው?”

የሩጫው ድምፅ ቀረበ፡፡ ናትናኤል ጭንቅላቱን መልሶ ከጀርባው ተመለከተ፡፡ ሰካራሟ መሀል
👍1
ኮረኮንቹ ላይ እየተንገዳገደች ወደፊት ራመድ ትልና እንደገና ቆም ብላ ታንጎራጉራለች..

“ንገሪኝ የምሥራች ካልቨርት የት ነው?”
“ዮሴፍ… እ… እማዬጋ” አየር ለመሳብ ስትታገል ደረቷ ሽቅብ ተስቀለ፡፡

“የት... የት?”
“እእማዬጋ ድሬዳዋ” የጀመረችውን ከመጨረሷ በፊት ሰውነቷ ተዝለፍልፎ ክንዱ ላይ ወደቀች፡፡ ናትናኤል ቀና ሊያደርጋት ሞከረ። አብቅታለች። ሰውነቱ ከቁጥጥሩ ውጭ ሆነበት ከተንበረከከበት ብድግ ብሎ ለመሮጥ ተዘጋጀ፡፡ ከወዲያ እየሮጠ የሚመጣው ሰው ሰካራሟጋ ሲደርስ በጨለማው ውስጥ ታየው፡፡ አዳኙ ወደ ሴትየዋ እንደደረሰ በግራው የያዘወን ባትሪ ፊቷ ላይ ቦግ አደረገውና ወዲያው ወደጎን ገፍተር አድርጓት አለፈ... ከመቅፅበት ባትሪውን ወደጎን መለስ አድርጎ ናትናኤል ላይ ሲተክለው ናትናኤል ቁጢጥ ካለበት መነሳት ተሳነው፡፡

አዳኙ ቀኝ እጁን ከኪሱ መንጭቆ አውጥቶ ሽጉጡን ደግኖ ይዞ
ተጠጋው፡፡

“አገኘሁህ!” አለ ወደ ውጭ ተንፍሶ ወዲያው ከናትናኤል ጎን የተዘረጋውን የምሥራችን ሰውነት ሲመለከት አይኖቹ ከየጉድጓዶቻቸው ወጡ፡፡ “ገደልካት?!” አለ የሚያየውን ማመን አቅቶት ኣፉን በድንጋጤ ከፍቶ::

“እኔ አይደለሁም! እኔ አይደለሁም!” አለ ናትናኤል ጭንቅላቱን በጭንቀት እያርገፈገፈ::

ሰውየው በጥላቻ ቁልቁል ተመልክተው:: “ከሃዲ! ያንተ ዓይነቶቹ ውሾች ናቸው ለባርነት የዳረጉን ዝርክርክ!” ሽጉጡን አንስቶ አነጣጠረበት፡፡

ናትናኤል ጉሮሮው እንደኮረት ሲወጠርበት ልሳኑ ሲከዳው… ሁለት እጆቹን ወደፊት ዘርግቶ አውለበለባቸው:: አርፈህ በሰላም ኑር…እንደ እሳት እራት ወደ ፍሙ… ተጠንቀቅ…የሽጉጡን አፈሙዝ ተመለከተው… እንደ አጋንንት ከፊቱ ተደቅኖ ሲያየው ሰውነቱ ፈሰስ... አይኖቹን ጨፈናቸው…
ርብቃ! …ቡፍ! ሲተኮስ ተሰማው፡፡ የትጋ እንደተመታ አልታወቀውም። እላዩ ላይ ወደቀበት፡፡ ዓይኖቹን ገልጦ ግራ ተጋቡ፡፡ አዳኙ እላዩ ላይ ተዘርግፎበታል። ዓይኖቹ ከየጎሬአቸው ወጥተው ተጎልጉለዋል፡፡ በጭንቅ የገጠመው ጥርሱና ከጉሮሮው የሚወጣው ሲር ሲር የሚለው ድምፅ:..
ባንድ ወገን ከአፉ ቡልቅ ብሎ የወጣ ደም ደረቱ ላይ ሲረጭ... ናትናኤል
ሰውየውን ከላዩ ገፍትሮ አገለለው፡፡ ቁጢጥ ባለበት ጥይት የበሳው ገላውን
አዳመጠ፡፡ የለም፡፡ ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡

ራቅ ብላ በቀኟ ያንጠለጠለችውን የሽጉጥ አፈሙዝ ወደ መሬቱ መልሳ : ቆማለች፡፡ ፈገግ አለችለት፡፡ ጀርባውን ለግድግዳው እንደሰጠ ተመልከታት፡፡

“ሩጥ፡፡” አለችው ፈገግ ብላ።
ሮጠ፡፡
ሮጠ ናትናኤል፡፡ በኮረኮንቹ እድርጎ ቁልቁል በመጣበት ቀጭን መንገድ ሽቅብ በረረ፡፡ ከኋላው የተከተለው አጋንንት እንዳለ ሁሉ በጨለማው
ውስጥ እጆቹን ወደፊት ዘርግቶ በነነ፡፡ በአካባቢው ድምፅ አልነበረም::
ጠባቧን የኮረኮንች መንገድ ጨርሶ ከመውጣቱ በፊት ብቻ ከጀርባው ሳቅ
አጀበው:: የሴት ሳቅ የሰካራም ሳቅ

ሃ...ሃ...ሃ. …ሃ...ሂ....ሂ... ሂ!”.....

💫ይቀጥላል💫
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

.....አኔም በሩ ከተዘጋ በኋላ ይዛው የነበረውን እምባዋን ለቅቃ እየተንሰቀሰቀች ማልቀስ ጀመረች::

ወደ ታችኛው የከተማው ክፍል በ10ኛው ጓዳና ላይ መኪናዋን የምታሽከረክረው ኒኪ ሆዷ ድረስ ዘልቆ የሚሰማ የንዴት እና የሀዘን ስሜት ውስጥ ትገኛለች። አለ
አይደል በደም ሥሯ ደም ሳይሆን እርጎ
የሚዘዋወርባት ይመስል ሁለመናዋን የሚስማት የሚቆመጥጥ ነገር ብቻ
ነው። አንዴ ለእሷ ታዝናለች፤ ደግሞ የተዋረደች ይመስላታል፡፡ ደግሞ
ንዴት እና ፀፀት ተቀላቅሎ ይሰማታል።

ስለ አኔ ባል ለአኔ የነገረቻት ነገር ትክክል ነው። ባሏ ምንም ያህል ለጋስ እና አማላይ ቢሆንም ያው ደካማን የሚያጠቃ በጥባጭ ነገር ነው። በጥባጭ
ሰው ደግሞ መቼም አይለወጥም። ይህንን ነገር ለአኔ ብትነግራት አሁን ላይ
እንደማትሰማት ይገባታል። ምክንያቱም ከአሁን በኋላ አኔ ኒኪን እንደ ሀኪሟ አይደለም የምታያት። አኔ ኒኪን እንዴት ነው የምታያት? ብላ ራሷን ጠየቀች፡፡ “እንደ ጓደኛዋ? ምናልባት እንደ ፍቅረኛዋ? ምናልባት ከባሏ ልትነጥላት ቆርጣ እንደተነሳች ሴት?”

አኔን በዚህ መልኩ ማናገር አልነበረባትም።

ይሄው አኔ በግልፅ ባይሆንም ኒኪ ቀድማ ብዙ ስለቀረበቻት ይህንን ተናግራት አይደል “አንቺ እንደ ቴራፒስት አይደለም ለእኔ ደንታ ያለሽ፡፡ ይሄንን ደግሞ ሁለታችንም እናውቀዋለን!” ብላታለች። ግን የዶውግን ከትዳር ውጪ ስላለው ግንኙነት እንዴት ልታውቅ ቻለች? አኔ እንዴት ስለ እዚህ ጉዳይ ማወቅ ቻለች? ይህንን ጉዳይ የሚያውቁት ደግሞ ጓደኛዋ ግሬቸን እና ዶፎ ናቸው፡፡ እነርሱ ደግሞ በፍፁም ይህንን ነገር ለማንም እንደማያወሩት ታውቃለች፡፡

የሚሰማት የሚያስጠላ ስሜት ሲጨምር በመኪናው መስኮት ወደ ውጪ ተመለከተች፡፡ አራት ቤት አልባ የሆኑ ሰዎች ከቲያትር ቤቱ መግቢያ በር
ላይ ተደርድረው ቁጭ ብለዋል፡፡ ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ባዶ እና ተስፋ አልባ
ስሜት ውስጥ ሆኖ ወደ እሷ አይኑን ጎልጉሎ ይመለከታታል። በሱስ ናውዟል፤ ያስታውቃል፡፡ የሆነ የሀዘኔታ ስሜት እንዲሰማት ጠበቀች። የለም፡፡ ይሄንን ስሜቷን ያቺ ሸርሙጣ የሟች ባሏ ሩሲያዊቷ ውሽማ አጥፍታባታለች፡፡

የሆነ ልቧ ውስጥ ያለውን ያቺን የዋህዋን
ኒኪን ይህቺ ሴት ገድላባታለች። ወይንም ይሄ ነገሯ አልሞተም፤ በቃ ነዳጅ ምናምን አልቆበት ነው። ምናልባት አንድ ቀን የፍቅር እና ለሰዎች ያላት የመልካም ስሜቷ ነዳጇ መልሶ ሙሉ ሲሆን የሀዘኔታ ስሜቷን መልሳ ታገኘው ይሆናል።

ምናልባት!

ወይም ደግሞ ጨርሶም ላይመጣ ይችላል።

የመንገዱ እግረኛ ማቋረጫ ላይም አንዲት በመሀከለኛ ዕድሜ ላይ
የምትገኝ ሌላ ሴትን ተመለከተች፡፡ ይህቺ ሴትም ያኔ ዶፎ ቬኒስ ውስጥ የሚገኘውን ክሊኒክ ሲያስጎበኛት እንዳየቻቸው ሁለቱ ጎረምሶች አጥንቷ ገጥጦ ወጥቷል፡፡ መልካም አረንጓዴ ነው። ዶፎ ክሮክዳይል ይባላል። አዲስ የመጣ አደንዛዥ ዕፅ ነው ብሎ የነገራትን ነገር አስታወሰች፡፡

ያኔ ክሊኒኩ ውስጥ ላየቻቸው ሁለቱ ጎረምሶች ሀዘኔታ ተሰምቷት ነበር፡፡
አሁን ግን ይሄው ባዶ ናት፤ ምንም ነገር አይሰማትም። ምናልባት ከአኔ ጋር
ስታወራ የተቀበለችው ውርደት ይህንን ውስጧ የቀረውን እንጥፍጣፊ
የሀዘኔታ ስሜትን አጥፍቶባት ይሆን?
ምንም ነገር ማሰብ አቆመች እና ዝም ብላ ወደ ቤቷ አቅጣጫ መኪናዋን
ማሽከርከር ጀመረች። ቤቷ ስትደርስ ደጃፏ ላይ ሁለት ፖሊሶች የፖሊስ
መኪና ውስጥ ተቀምጠው አገኘቻቸው። ፖሊሶቹ ትላንትና ማታ መርማሪ
ፖሊስ ጉድማን የእሷን እምቢታ ሳይቀበል ቀርቶ እንዲጠብቋት የመደበላት
ፖሊሶች ናቸው፡፡

ትላንትና ማታ የእሱ መኪና ውስጥ ቁጭ ብለው እጁን ታፋዋ ላይ አድርጎ “ጥበቃ ያስፈልግሻል” ብሏት ነበር።

“ምንም አይነት ጥበቃ አልፈልግም”

“ኒኪ ጥበቃውን አንቺ ስለፈለግሽው ሳይሆን የምመድብልሽ ሥራዬ
ስለሆነ ነው እሺ” ብሎ ሲናገራት ውስጧን ደስ የሚል ነገር ተሰምቷት
ነበር።

“እኔ ያንተን ጥበቃ ባልፈልግስ?” ብላው ነበር። የእሷን እጅ የት አድርጋ ፀታወራው እንደነበር አስታውሳም።
እንደርሱ ከሆነማ እተውሻለሁ ዶክተር” ብሏት ነበር ጉድማን ማዕረጓን ልክ እንደ ስድብ የተጠቀመበት።

የፖሊሶቹ ቤቷ አጠገብ መገኘት ጉድማን ትላንትና ማታ እሷን ለማማለል ሳይሆን ስለ ጥበቃ ያወራው ነገር የእውነቱን መሆኑን እንድትረዳ አደረጋት። ግትርነት የምትወዳቸው የወንዶች ፀባይ ነው መሰለኝ ግትር ወንዶች ደስ ይሏታል። ምንም እንኳን መጨረሻቸው ባልጠበቀችው መልኩ ቢያበቃም ባሏ ዶውግም እንደዚያ ነበር።

አይኗ በእምባ ሲሞላ ኒኪ ተናደደች እና እምባዋን ውጣ፣ መኪናዋንም አቁማ ወደ ቤቷ ገባች። የቤቷን መብራት አብርታ እና ጫማዋን ወርውራ አውልቃ ወደ ማብሰያ ክፍሏ አመራች። አዲስ የገዛችውን ቦርሳዋን ከማብሰያው ክፍል ባልኮኒ ላይ አስቀመጠች። የማታው የዞረ ድምር እስከ አሁን ባይለቃትም ፍሪጂ ውስጥ ያስቀመጠችውን ቨርጅን ሜሪ መጠጥ
ብርጭቆዋን ሞላች። የባልኮኒው ወንበር ላይ ቁጭ እንዳለችም ላፕቶፕዋን
ከፈተች እና ኢ ሜይሏን ተመለከተች፡፡
ምናልባት አኔ ኢ ሜይል ልካ ከሆነ ብላ ነበር ለፕቶፕዋን የከፈተችው።

ከአኔ ግን ምንም የተላከ ኢ ሜይል አላገኘችም።

ሌላ የተላከላት ኢ ሜይል ስለበነረም ከፈተችው። የማታውቀው ኢ ሜይሉን የላከላት ግለሰብ 'ትላንትና ማታ አይቼሻለሁ! በሚል ርዕስ ሥር
ትላንትና ማታ ከጉድማን ጋር አብረው የነበሩበት የዳን ታና ሬስቶራንት ፎቶ
ለጥፏል። ከሆቴሉ ሥር ያለው ሁለተኛው ፎቶ ደግሞ የእሷን ከአንገት በላይ
ያላ ፎቶን ከአንዲት ራቁቷን ከምትወዛወዝ የካርቶን ቪዲዩ ላይ በፎቶ ሾን አያይዞታል። ከፎቶውም በታች “አንቺ ሸርሙጣ እገድልሻለሁ!” የሚል
ማስፈራሪያ ተፅፎበታል።

ኒኪ ይህንን ካየች በኋላ ድንገተኛ ድንጋጤ እና ፍርሃት ወረራት፡፡
በመቀጠልም ድንዝዝ ያለ ስሜት ውስጥ ገብታ ቁጭ አለች።

ስሜቷ ደንዝዞ ብትቀመጥም ጎበዙ አዕምሮዋ የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለበት ይወተውታት ጀመረ። ይሄ ቀልድ አይደለም። ይሄ የግድያ ዛቻ ነው፡፡ ለዚያውም የእሷን እያንዳንዱን እንቅስቃሴዎቿን ከሚያውቅ ሰው
ትላንትና ማታ ዳና ሬስቶራንት ውስጥ ከማን ጋር እንደነበረች ሁሉ
ከሚያውቅ ሰው ነው ማስፈራሪያው የተላከላት። ስለዚህ ነገሩን ለፖሊስ
ማሳወቅ ይኖርባታል። አሊያም ደግሞ ለጉድማን ልትነግረው ይገባል።

ግን ደግሞ ትንሽ አመነታች፡ ለመልከመልካሙ መርማሪ ፖሊስ
ጉድማን ነገሩን ማሳወቅ እሱን ይበልጥ ወደ እሷ ህይወት እንዲገባ ማድረግ
አይሆንምን?

ልጠብቅሽ ነው በሚል ሀሳብ ከእሷ ጋር እንዲጣበቅ ምክንያት ማቀበል
አይሆንም?

ግማሽ እሷነቷ ለመርማሪው ነገሩን አሳውቂ ሲላት፣ ግማሽ እና ብልሁ
ሌላኛው እሷነቷ ግን ይህ ትክክል እንዳልሆነ ነገራት።

ጉድማን መልካም ሰው ነው፤ ችግሩን ለመፍታት አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ ያደርጋል። ግን ደግሞ ባልደረባው የሰይጣን ቁራጩ ጆንሰን አብሮት
የሚሰራ አጋሩ እስከሆነ ድረስ ሁለቱም የግድ የእሷን ጉዳይ ይመለከቱታል
ማለት ነው። ይሄ የእሱ አጋርነት ደግሞ የሊዛን እና የትሬይን ገዳይ እንዲሁም ደግሞ እሷን ጭምር በመኪና ሊገድላት የሞከረ ሰውን ይዞ ለፍርድ ማቅረብ ያቃተው እንደሆነ እያየችው ነው።

ለማንኛውም ህይወቷ አደጋ ላይ ነው፣ ኒኪ ጥበቃ ያስፈልጋታል።ከጥበቃው በላይ ደግሞ መልስ ትፈልጋለች፡፡ የምትፈልገው መልስ ደግሞ ስለ ግድያዎቹ ብቻ አይደለም። የዶውግን ክህደት ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ
በዋናነት የእሷን ህይወትን መርዞባት እስከ አሁን ድረስ ውስጧን ለሚያደማት
👍21
ጥያቄ መልስ ትፈልጋለች።

የጎግልን መክፈቻ ተጭና ከፈተች። ከዚያም ከመፈለጊያው መስመር
ውስጥ ምዕራብ ሎስ አንጀለስ ውስጥ የሚገኝ የግል መርማሪ የሚል ፅሁፍ
ፃፈች እና ፈልግ የሚለውን ቦታ ተጫነች፣ ሁለተኛው ዕቅዷን ማካሄድ ያለባት አሁን ነው::
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።፣፣፣
“እሺ አንድርያ ላጤ ምን ማለት እንደሆነ ታውቂያለሽ?”

አላት ዴሪክ ዊሊያምስ አይ ሆፕ ካፌ ውስጥ ሆኖ አስተናጋጇን እየተመለከታት፡፡

“ዴሪክ አሁን እኮ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ነው።” አለችው ድካም ውስጥ የምትገኘው አስተናጋጅ ኩባያውን በቡና እየሞላችለት፡፡ “ይሄ ከእነዚያ የብልግና ቀልዶችህ አንዱ ከሆነ እኔ ጥሩ ስሜት ውስጥ ስላልሆንኩኝ ልሰማህ አልፈልግም::”

“የብልግና ቀልድ አይደለም። ምናለ አንድ አንዴ እንኳን ዘና ብለሽ ብታወሪኝ አንድሪያ?” አላት ዴሪክ፡፡

አስተናጋጇም ቅንድቧን ቋጥራ “ዴሪክ እስቲ ግድግዳዎቹን በደንብ ተመልከታቸው እና ስታስተናግዱ የአስተናጋጁን ፈገግታን ይጨምራል
የሚል ማሳሰቢያ ተለጥፏል?” ብላ ስትመልስለት ዴሪክ ከት ብሎ ቅርፅ
አልባው ሰውነቱ እስኪንዘፈዘፍ ድረስ ሳቀ፡፡ አንድሪያ የሚፈልጋት አይነት
ሴት ናት። ብቸኛ አስተናጋጅ ሆና በሰዓት ስምንት ዶላር እየተከፈላት የምትሠራ ቀልደኛ ሴት።

“ላጤ ማለት አንድን ስህተት ዳግመኛ የማይሰራ ሰው ነው:: አያስቅም
ውዴ? እመኚኝ፡፡ ሌላ ደግሞ ቀልድ አለኝ” አላት፡፡

አንድሪያም ፈገግ ብላ ሁለት ሜኖዎችን ጠረጴዛ ላይ እያስቀመጠች
ተመለከተችው፡፡

“ፍርድ ቤት ለልጅ ማሳደጊያ ብሎ የሚቆርጠው ገንዘብ ምን ይባላል?”
ብሎ ሲጠይቃት ከአጠገቡ ሄደች፡፡

“ይሄ ደግሞ ተንደላቅቆ በሰው ገንዘብ መኖር ማለት ነው” አላት።

የመጨረሻው ቀልድ ለዴሪክ ዊሊያምስ የራሱን ህይወት የሚገልጽ ነበር፡፡ የቀድሞ ሚስቱ ፍርድ ቤት ገትራው ነበርና። “እኔ የግል መርማሪ ነኝ የተከበሩ ዳኛ” ብሎ የመጨረሻው የፍርድ ቀን ቀርቦ በነበረበት ጊዜ ላይ “እኔ ጠበቃ አይደለሁም ወይንም ደግሞ የኢንቨስትመንት ባንከርም አይደለሁም ወይም ደግሞ ሳንፍራንሲስኮ ውስጥ የምኖር የኮምፒውተር ባለሙያም አይደለሁም፡፡ የኢንተርኔት ካምፓኒውን ፓሎ አልቶ' ብዬ እንኳን መፃፍ የማልችል ሰው ነኝ” ነበር ያለው፡፡

“ይህን በመስማቴ አዝናለሁ።” አለችው ሴቷ ዳኛ፡፡ የሆነች የሴቶች መብት አቀንቃኝ ነገር ናት ግን እስር ቤት እንዴት እንደሚፃፍ እንደምታውቅ እርግጠኛ ነኝ። ስለዚህ ተገቢውን የልጅህን ማሳደጊያ ብርዐለሚስትህ ሶላኔ የማትከፍል ከሆነ እስር ቤት ነው የሚጠብቅህ” ብላ
ሚስ ሶላኔ። ስሟን ደግሞ ከመቼው ቀየረችው? ምን የራሷን ብቻ ፍቺውን ከፈፀመች በኋላ የወንድ ልጃቸው ስም ላይም የራሷን ስም ከትታበት በፍርድ ቤት ስሙን ቀይራለታለች። ሀንተር ሶላኔ ዊሊያምስ ብላዋለች። አሁን ምን ይሉታል ለአንድ የስምንት ዓመት ወንድ ልጅ ይህንን ስም መስጠት? እንዴ ገና ከአሁኑ የሴት ስም ሰጥታው ልጁን ግብረ
ስዶማዊ ልታደርገው ነው? ለማንኛውም ከፍቺያቸው በኋላ ልጁን ሀንተርን
ብዙ ጊዜ አግኝቶት አያውቅም። ይህንን አስመልክታም “ከእሱ ጋር አንድም
ጊዜ ቢሆን አብረኸው አሳልፈህ አታውቅም ዴሪክ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ ህጉ ምን እንደሚል ላንተ አልነግርህም!” እያለችም ታስፈራራው ነበር።

“ሚስተር ዊሊያምስ?” የሚል ድንገተኛ ድምፅ ሲሰማ ደንብሮ ተነሳ። እጁ ላይ ይዞት የነበረውን ቡና የለበሰው ሸሚዝ ላይ ተደፋበት፡፡ “ማን…” ብሎ እየተራገመ በቡናው ምክንያት ሰውነቱ ላይ የተጣበቀውን ሸሚዝ ከገላው ላይ እያስለቀቀ ወደ ጎን ሲመለከት አንድሪያ ድምጿን አጥፍታ ስትስቅ ተመለከታት፡

“በእግዚአብሔር ስም! በጣም ይቅርታ” አለችው አጠገቡ የቆመችው ባለ
ቢጫ ፀጉር ቆንጆ ሴት የኔ ጥፋት ነው”

አይደለም አንቺ ምንም ጥፋት የለብሽም” ብሎ በሶፍት ሸሚዙን እየጠረገ “የሆነ ነገርን እያሰብኩኝ ነበር፡፡ የሆነ ቅዥት ነገር። ባልሳሳት ዶክተር ሮበርትስ ነሽ?”

ኒኪ ብለህ ልትጠራኝ ትችላለህ። በጠዋት ልታገኘኝ ስለተስማማህልኝ አመሰግናለሁ፡፡” አለችው እና እጇን ለሰላምታ ዘረጋችለት። ዴሪክ ቀና ብሎ
ሲመለከታት የዞምቢው ግድያ በሚል ርዕስ በቴሌቪዥን ላይ ካያት በላይ
ውብ ናት፡፡ ዶክተር ሮበርትስ እኩለ ለሊት ላይ ነበር የደወለችለት። ስልኩን ካላነሳም የድምፅ መልዕክት ልትተውለት አስባ ነበር የደወለችለት፡፡ ነገር ግን ዊሊያምስ ስልኩን አነሳ እና አወራት። በግሏ ልታውቅ የምትፈልጋቸው ነገሮች ስላሉ የግል መርማሪ እንደምትፈልግና ጠዋት ላይ መገናኘት ይችሉ እንደሆነም ጠየቀችው፡፡ ጠዋት ላይ ሊያገኛት ግድ የሆነበት ምክንያት ገንዘብ ስለሚያስፈልገው ብቻ አይደለም፡፡ የድምጿ ቅላፄ እውነተኛ የተስፋ መቁረጥ ስሜት የሚታይበት መሆኑን ስለተረዳና በዚህ ስሜት ውስጥ
የሚገኙ ደምበኞቹ ያለማንገራገር የተጠየቁትን ገንዘብ ለመክፈል ያላቸውን
ዝግጁነት በማወቁ ጭምር ነው፡፡

ይቀጥላል
👍21🔥1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ



#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


....በጥፊ ጆሮ ግንዷን እናጋው፡፡
ለጥቂት ደቂቃዎች ያለችበት ጠፋት፤ዘሪያዋ ጨለማ ለበሰ፡፡ እዛው
አፓርትመንት ክፍሏ ውስጥ እጆቿንና እግርቿን ከአልጋዋ ጋር በአንሶላ
ጨርቅ ጥፍር አድርገው አስረው እንዳትጮህ አፏ ውስጥ ጨርቅ ጎስጉሰው ለጉመው አጋድመዋታል፡፡

“ንገሪኝ!” አለ ድጋሚ ሊያጣፋት እየተንጠራራ “የት ነው ያለው?
ትነግሪኛለሽ አትነግሪኝም?”
ጭንቅላቷን በጭንቀት አርገፈገፈችው:: ከተለጎመው አፏ ጀርባ ጉሮሮዋ . “የት እንዳለ አላውቅም:: እውነቴን ነው!” አለች:: ድምፅ ግን አላወጣችም፡፡

ውልብ አለባት ድጋሚ፡፡ ጆሮዋ ላይ ሌላ ጥፊ ደወለ፡፡
“ንገሪኝ!”

ዱላው እየጨመረ በመጣ ቁጥር እልኋና ቁጣዋ እንዴት ተደፈርኩ ባያነቷ እንደጨው እየሟመ ለማይታክተው እንባዋ እስረከበዋታል፡፡ ፀጉሯ
ሲጨመደድ ተሰማት::

“ንገሪኝ! የት ነው ያለው?”
ድጋሚ በጥፊ አይኖቿን ከደናቸው፡፡
“ንገሪኝ!”

ተከትሎ ምን እንደተናገረ አልሰማችውም:: ጆሮዋ ላይ የሚደውለውን ስቃይ ተከትሎ ዙሪያዋ ፅልመት ተከናነበ፡፡ አይኖቿን ድጋሚ ስትገልጣቸው ሰውነቷን ክፉኛ ቀዘቀዛት፡፡ለሶስተኛ ጊዜ ውሃ አፍስሰውባታል፡፡
አልጋዋ በየደቂቃው ህሊናዋን በሳተች ቁጥር በሚቸለስባት ቀዝቃዛ ውሃ
ረስርሳል:: የለበሰችው ስስ ቀሚስ እላይዋ ላይ ተጣብቋል፡፡

ዓይኖቿን ግርብብ አድርጋ ተመሰከተቻቸው፡፡ ሶስቱም በአልጋዋ
ዙሪያ ቆመው ቁልቁል ይመለከቷታል፡፡ ሁለቱን አታቃቸውም፡፡ ሶስተኛው
ግን ያው የህዋሷ መሪ ማርቆስ ነበር፡፡ በጠባሳ የተገመሰ ፊቱን ቁልቁል
አንዘርቦ ይመለከታታል፡፡ ደጉን የተወያየችው የገዛ ጓደኛዋ አልመስልሽ
አላት፡፡ አይኖቿን ጭምቅ አድርጋ ጨፈነቻቸው፡፡ በተንጋለለችበት እንባዋ
የገዛ አይኖቿን እንደጨው እየለበለበ ፈሰሰ፡፡

“ከሃዲ!” አለ ሰስተግራዋ የቆመ ሌሊቱን ሲጠፈጥፋት ያደረው ሰው ድንገት ፊቱን መልሶ የመኝታ ክፍሏን በር ከፍቶ እየወጣ፡፡

በክፍሉ ውስጥ የቀሩት ሁለት ሰዎች ለጥቂት ደቂቃዎች ያለ እንቅስቃሴ ቁልቁል ሲመለከቷት ቆዩ፡፡ ወዲያው ማርቆስ ጠጋ ብሎ አፏ የተለጎመበትን ጨርቅ መፍታት ጀመረ፡፡ ሽቅብ ፊቱን ስትመለከተው ከዓመት በላይ የምታውቀው አብራው የቀለደችና የሳቀች ያው የድሮው የህዋሷ መሪ ማርቆስ መሆኑን ማመን አቃታት፡፡

“ምን ማድረግህ ነው?” አለ ከበስተግርጌ የቆመው ጺማም ሰውዬ ማርቆስ አፏ የተለጎመበትን ጨርቅ ሲፈታላት ሲያይ እየተቁነጠነጠ።

ማርቆስ ለሰውየው መልስ ሳይሰጠው አፏን ሞልቶ ተርፎ የነበረውን ቡትቶ ጨርቅ ጎትቶ አወጣላት፡፡ ተበርግዶ የቆየ መንጋጋዋ የራሷ መንጋጋ እንዳልሆነ ሁሉ አልገጥምልሽ አላት፡፡ ደርቆ የቆየ ጉርሮዋ የገዛ ምራቋን አልውጥልሽ አላት፡፡ እንባዋ ብቻ ጉንጮቿን እየተለተለ መውረዱን
ቀጠለ፡፡

“ርብቃ …ለምን ለእኛም ለራስሽም አስቸጋሪ ትሆኛለሽ?” ማርቆስ
ቁልቁል እየተመላከተ ተማፀናት፡፡ “ርብቃ ልለምንሽ የት እንዳለ ንገሪንና
ይህ ሁሉ ያብቃ፡፡” ተለማመጣት፡፡

ለምን አይገባቸውም?! ናትናኤል የት እንደለ ኣላውቅም ስትላቸው ለምን አያምኗትም?! እንዴት አድርጋ ነው እውነቱን እውነት ነው የምትላቸው?

“የት እንዳለ አላውቅም፡፡” ልትል ፈለገችና ጉሮዋ አልታዘዝሽ አላት፡፡ በጀርባዋ በተንጋለለችበት ጭንቅላቷን ነቀነቀች፡፡
“ርብቃ ጊዜ በወሰድሽ ቁጥር ሁኔታው ለራስሽ እየከፋ ነው የሚሄደው፡፡ የምትጋፈጫቸው ሰዎች ትዕግሥታቸው ያለቀና ቁጣቸው ወደ ዕልህ የተቀየረ ራሳቸውን መቆጣጠር የማይችሉ ናቸው:: ርብቃ እነዚህ ሰዎች ሊያደርጉት የሚገፋፉትን ደግሞ ማንም አይወደውም፡፡ አንቺ ሴት ነሽ፡፡ እነዚህን ሰዎች የሚቋቋም የመንፈስ ጠንካራነት የለሽም:: በቀላሉ እንደቀርከሃ ሊሰባብሩሽ ይችላሉ፡፡ በቀላሉ! እባክሽን ንገሪኝ፡፡፡ ናትናኤል የት ነው?” የሌሊት ሁኔታዋን መቋቋም አቅቶት ሲቁነጠነጥ ያደረው
ማርቆስ የባሰ ከመምጣቱ በፊት ሊያሳምናት ታገለ፡፡

አ....አላውቅም፡፡” አለችው እንባዋን እያስተናገደች::
“ጥሩ፡፡ መስሪያ ቤትሽ ደውሉ ሲያጣሽና ስራ ከገባሽ ውሰሽ ማደርሽን ሲረዳ እንዴት እዚህ አልደወለም?”
“ፈርቶ ይሆናል... እኔ ምን አውቃለሁ፡፡” እውነተኛነቷን ይገልፅላት ይመስል ድምጿን አለሰለሰችው::

“ምን? ማንን ነው የሚፈራው?”
“እናንተን፡፡” አለች በለቅሶ መሃል፡፡

“አየሽ ይህ ማለት አንቺ ከእኛ ጋር ግንኙነት እንዳለሽ አውቋል ወይም በፊትም ያውቅ ነበር ማለት ነው፡፡ ይህን ሊያውቅ የሚችለው ደግሞ አንቺ....”

አልነገርኩትም!” አለች አቅጣጫውን ስትረዳ አቋርጣው፡፡ “እኔ አልነገርኩትም፡፡እኔ በእርሱ ላይ መረጃ ስስበስብ መቆየቴንም ጭራሽ አያውቅም፡፡ ግን እዚህ ሲመጣ ልታገኙት እንደምትችሉ ጠርጥሮ ይሆናል፡፡”
ለምን ድጋሚ መሥሪያ ቤትሽ ስልክ አልደወለም? ባለፈው ጊዜ ሲደውል ጓደኛሽ ቢሮ ከገባሽ ዉስሽ ማደርሽን እንድትነግረው አድርገናል፡፡እዚህ መደወል ወይ መምጣት ነበረበት፡፡ አልመጣም፧ አልደወለም:: መሥሪያ
ቤትሽም መልሶ አልደወለም:: ለምን?”

“አላውቅም::” እለች በማስተዛዘን፡፡

“ውሽት አውቋል… ሁሉንም ተረድቶታል:: ለዚህ ነው ሊገናኝሽ ያልሞከረ፡፡ ባያውቅ ኖር..”

“ውሸቴን አይደለም!” አቋረጠችው “እመኑኝ ናትናኤል ምንም የሚያውቀው ነገር የለም ናት…”

“ያውቃል! ያውቃል! ምንም የማያውቅ ሰው በጭካኔ የሁለት ሰው ነፍስ አጥፍቶ አይሰወርም፡፡ ትሰሚኛለሽ? የፈጸመው ወንጀል ምንም የማያውቅ ሰው የሚፈጽመው አይደለም!” ትከሻዋን በሁለት እጆቹ ይዞ ነቅነቃት፡፡

“ናትናኤል ሰው ፡ አይገድልም...ውሸት
ነው፡፡” ለራሷ ፡ ነበር የተናገረችው፡፡

“ርብቃ…. ሰዎቻችን ያውቁታል፡፡ ለይተው ስላወቁትም ነው የተከታሉት፡፡ ይገባሻል? የካልቨርትን አድራሻ ከሴትየዋ ማግኘት ስላልቻለ ምናልባትም አድራሻውን አስገድዶ ካውጣጣት በኋላ ነው ደረቷን በጥይት የበሳው፤ ገድሏት የሄደው፡፡
አስታውሽ እሷን ብቻ አይደለም ያጠፋው!
የኛንም ሰው ነው:: ርብቃ… እባብ ነው ሰውዬሽ፡፡ ሁላችንንም አታሎናል፡፡
ምንም የማያውቅ የዋህ መስሎ አታሎናል፡፡ አንቺንም አታሎሻል፡፡ አብረን
ልናቆመው ይገባናል፡፡ ንገሪኝ፤ የት ነው የተሸሸገው?”

“አላውቀውም አልኩህ፡፡”
ገፁ በንዴት ተኮማተረ፡፡

“ርብቃ” አይኖቹን አጥብቦ ተመለከታት፡፡ “በአንድ ወቅት ከጎናችን መቆምሽን አንዘነጋውም፤ ያ የሩቅ ትዝታ አይደለም፤ ግን ደግሞ መረባችን በከዳተኞች ምላጭ ሲበጣጠስና ውጥናችን በባንዳዎች ራስ ወዳድነት እርቃኑን ወጥቶ እያንዳንዳችን ለስደትና ለሞት ስንዳረግ በዝምታ መመልከት አንችልም፡፡ ይህ እንዳይሆን ደግሞ የምንጠላውንም ነገር ቢሆን ለማድረግ እንገደዳለን፡፡ ርብቃ ትሰሚኛለሽ? መንፈስሽ መኮሳሽት ካለበት እናኮላሽዋለን፤ሰውነትሽ መዋረድ ካለበት እናዋርደዋለን! ህሊናሽ መጨቅየት ካለበት እናጨቅየዋለን… የማታ ማታ የጠየቅንሽን ሁሉ ታወጪዋለሽ፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት አስተውይ፡፡ ናትናኤል አታሎሻል! የስጋ ፍላጎትሽን ተጠቅሞ
ምስጢራችንን ከቀዳ በኋላ አጋልጦሽ ተሰውሯል፡፡ የት ነው ያለው?
ናትናኤል የት ነው?”

“አላውቅም'ኮ” እንባዋ ገና ድሮ በቀደደው ቦይ ያንቆረቆር ጀመር፡፡

የመኝታ ቤቷ በር ተከፍቶ ሦስት ሰዎች ተከታትለው ገቡ፡፡ ሁለቱን አይታቸው አታወቅም አንደኛው ግን ከትላንት ጀምሮ ሲቀጠቅጣት የቆየ ነው ከፊት ቀደም ያለው ሰው በእድሜ ጠና ያለ ይመስላል፡፡ ወደፊት ራመድ ብሎ ወደ አልጋዋ ግርጌ ከተጠጋ በኋላ በክፍሉ ውስጥ ለተሰበሰቡት ሰዎች እንዲፈቷት ምልክት ሰጣቸውና ከማርቆስ ጋር በሹክሹክታ ይነጋገር ጀመር
1👍1
ተከትለውት የገቡት ሰዎች ፈጠን ብለው እጆቿንና እግሮቿን ፈተው ለሁለት ብብትና ብብቷ ውስጥ ገብተው ከአልጋው ላይ አነሷትና ጥግ ወዳለ ወንበር ተሸክመው ወሰዷት፡፡ እግሮቿ በገዛ ክብደቷ ስር እንደ
ሰንበሌጥ ተልፈሰፈሱባት:: ወንበሩ ላይ ካስቀመጧት በኋላ ከአልጋዋ ግርጌ
የቆመው ሰው ወንበር ስቦ ከፊት ለፊቷ ተቀመጠ፡፡ ዕድሜው ገፋ ያለ
መሆኑን ከጆሮ ግንዶቹና ሪሁ ላይ ጣልጣል ያደረገበት ሽበት ያሳጣል፡፡
የለበሰው ሙሉ ልብስ፣ ያጠለቀው ጫማና የጸመ አከረካክም... የጠገበ ነጋዴ አስመስሎታል፡፡

በውሃ የበሰበሰውን ልብሷን ሲመለክት አይኖቹን ከላይዋ ላይ ሳያነሳ
“ልብስ ደርቡላት::” አለ፡፡ቀልጠፍ ባለ ሁኔታ ከቁም ሳጥኗ ውስጥ
አውጥተው በጋቢ ጠቀለሏት፡፡
“በዚህ ኣይነት ሁኔታ መገናኘታችን በእውነት ያሳዝነኛል፡፡” በተቀመጠበት ወደፊት ዘመም ብሎ ተናገራት፡፡“ድርሻሽን በሚያኮራ ሁኔታ ስትወጪ ቆይተሻል፡፡ እያንዳንዳችን በተለያዩ ምክንያቶች ለስሀተት እንዳረጋለን፡፡ ይህ
ቢያሳዝንም ሊያስቆጣን አይገባም ወደፊት ጎንበስ ብሎ ጉልበቶቿን
እየተመተመ አበረታታት፡ “የሥራ ድርሻዬን መናገሬ ከደንቡ ውጪ ቢሆንም
ሁኔታው የሚጠይቅው በመሆኑ አልደብቅሽም፡፡ በንቅናቄው ውስጥ የመረጃ ክፍል በምሥራቅ አፍሪካ የምድብ ለ መሪ ነኝ፡፡ ብርጋድየር ጀኔራል አብይ ሰናይ እባላለሁ::ምን አይነት አስጊ ሁኔታ ላይ እንዳለን ላስረዳሽ አልሞክርም፡፡ ምክንያቱም በሚገባ ትረጅዋለሽ፡፡ ስለሁኔታው ገለፃ እንደተደረገልሽ ተነግሮኛል፡፡ አልደግመውም፡፡ እንድትረጂኝ ነው የምጠይቅሽ…ቆይ ቆይ” አለ ሰውየው ርብቃ ልታቋርጠው ስትል ቀኝ እጁን ወደፊት ዘርግቶ፡፡ “አስጨርሽኝ፡፡ እንደተነገረሽ ናትናኤል የካልቨርትን ወዳጅ ገድሏታል፡፡
ስለካልቨርት ማንነት በቂ እውቀት እንዳለሽም ነግረውኛል፡፡ ስለዚህ ካልቨርት ስለወዳጁ መገደል ፍንጭ ከደረሰው እርሱ ራሱ እንደዛተው ምሥጢራችንን በቀጥታ በውጪ የስለላ ድርጅቶች አሰበለዚያም ለጋዜጠኞች ነው አሳልፎ የሚሰጠው:: ይህ ምን እንደሚያስከትል ከእኔ እኩል ትረጅዋለሽ፡፡ እርግጥ የሴትየዋን እሬሳ ለጊዜው ሰውረነዋል፡፡በቤቷም ውስጥ ያሉ ሴቶች
ስለሁኔታው እንዳይረዱና እንዳያወሩ የሚቻለው ሁሉ እየተደረገ ነው፡፡ ነገር
ግን አሁንም አንድ እጃችን ያልገባ ውል አለ፡፡ናትናኤል የሴትየዋ ግድያ
በእኛ እንደተፈጸመ አድርጎ ለካልቨርት ሊያስተላልፍ ከቻለ ወይንም የካልቨ
ርትን አድራሻ ደርሶበት ከተገናኘውና ምሥጢሩን ከተረዳ ውጤቱ ለሁላ
ችንም ጥፋት ነው:: እመኝኝ በአሁኗ ሰዓት ናትናኤል ከካልቨርት የበለጠ አደገኛ ነው፤ ሊያጠፋን ይችላል፡፡ እጅግ አደገኛ ሰው ነው፡፡”

“እኔኮ…” አለች ርብቃ እንባዋ በዓኗኗ ሲሞላ ልትውጠው እየታገለች።

“ይገባኛል... ይገባኛል ስሁኔታሽ ተነግሮኛል፡፡” አለ ሰውየው ለአንድ አፍታ ዓይኖቹን ወደ ሆዷ ዝቅ አድርጎ፡፡ «እርግጥ ስህተት ቢሆንም አንዴ ተፈጽሟል። ያረገዝሽው ልጅ የእርሱ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሕይወቱን ለአደጋ አሳልፈሽ መስጠቱ የከቀደሽ፤ ይገባኛል፡፡ ወደእዚህ የመጣሁት መሃል ላይ የምንስማማበትን መስመር ለመፍጠር ነው፡፡ አንቺ የት እንዳለ ትነግሪኛለሽ፡፡ አለበለዚያም አጥምጄ እንድይዘው ትረጂኛለሽ፡፡ እኔ ደግሞ በሕይወቱም ላይ ሆነ በአካል ማንኛውም ዓይነት አደጋ እንደማይደርስበት ቃል እገባልሻሁ፡፡ እጃችን እንደገባ እዚህ እናመጣዋለን ወይም አንቺን እርሱን ወደምናቆይበት ስፍራ ፡ እንወስድሻለን፡፡ ለጊዜው ብቻ በቁጥጥር ስር እናቆየዋለን፡፡ ዕቅዳችንን ከውጤት ልናደርስ የቀረን አጭር ጊዜ ነው፡፡ከስድስት ቀን በኋላ አደገኛነቱ ያከትማል፡፡ ሁለታችሁም ነፃ ናችሁ፤ ቃል
እገባልሻለሁ:: ትስማሚያለሽ?” ጎንበስ ብሎ ጉልበቷን በወዳጅነት ስሜት ያዝ!
አደረገው፡፡

“የት እንደተደበቀ አላውቅም...
የት ብዬ ልናገር? "

“ግድ የለም ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ዘጠኝ ሰዓት ላይ መሥሪያ ቤትሽ ጓደኛሽጋ ደውሎ ነበር:: ስላንቺ ማሰቡንም ነግሯታል፡፡ ትንሽ መታመምሽንና ቤትሽ ስልክ ደውሎ ቢያነጋግርሽ እንደሚሻል እንድትነግረው አድርገናል፡፡ በማንኛውም ሰዓት እዚህ ሊደወል ይችላል፡፡ በሚደውልበት ሰዓት በጠና መታመምሽንና እንዲያይሽ መፈለግሽን እስተዛዝነሽ ትነግሪዋለሽ፡፡ በተቻለ መጠን ወጥመዳችን ውስጥ እንዲገባ ታባብያዋለሽ፡፡” ክንዷን ያዝ አድርጎ ተናገሪ- ::

ርብቃ በረጅሙ ተነፈሰች፡፡ ጭንቅላቷ እርስ በእርሱ ይጨቃጨቅ ይከራከር ጀመር... ይገድሉታል እውነት ከሆነ «ሰው ገደለ» ያሉት እውነት ከሆነ አይተውትም.. ሲያታልሏት ነው ሊያግባቧት ነው መስማማት የለባትም…እምቢ ብትል የሚከተላትን ስታስብ አይኖቿ በእንባ ተዘፈቁ፡፡ ያስቃይዋታል.ይደበድቧታል… ያንገላቷታል...
“ጊዜ የለንም... በማንኛውም ደቂቃ ሊደውል ይችላል፡፡ እመኚኝ እጄ እንዲገባ እርጅኝ፣ ቃሌን እጠብቃለሁ፡፡”

“አልችልም::” አለችው እንባዋ በጉንጮቿ እየወረደ፡፡
“ቃሌን ማንም ሊሽረው አይችልም! እመኚኝ፡፡ የምነግርሽ እውነት ነው፡፡ አንዲት ፀጉሩ ከላዩ እትወድቅም፡፡”

“አላምንም ሁላችሁንም ኣላምንም፡፡ ጓደኛውን ገድላችሁታል፡፡ አይደለም? እሱንም አትተውትም፡፡” ድምጿ በጭንቅ ቃተተ፡፡

ከቃሌ በላይ ልሰጥሽ የምችለው ማስተማመኛ የለኝም..ቃሌ ደግሞ
እውነት ነው::”
“አላምንም! ውሸት ነው! ውሽት ነው! ውሸት ነወ፡!…” እንዳትሸነፍ፡
የፈራች ይመስል አይኖቿን ጨፍና ጭንቅላቷን ቀኝና ግራ አላጋችው::

“ስለምንሽ ካልረዳሽኝ አስገድጄሽ የምፈልገውን : እንድትፈጽሚ
ማድረግ እችላለሁ።” ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፁ ውስጥ የነበረ ልስላሴ
ሲቆረፍድ ተሰማት፡፡

“አልችልም! ልትገድሉኝ ትችላላችሁ፡፡አይኔ እያየ ለሞቱ አልጠራውም... ግደለኝ!” ሰውነቷን ነዘራት::

“አልገድልሽም፡፡ ያ ፍጹም ስህተት ነው አለ ሰውየው ከተቀመጠበት በእርጋታ እየተነሳ፡፡

ከጀርባው ለቆሙት ሰዎች ምልክት ከሰጣቸው በኋላ ሰእርጋታ ወደ
መስኮቱ ተጠግቶ ውጭ ወጪውን ይመለከት ጀመር፡፡ ከወንበሯ ላይ
ለሁለት ተሸክመው አንስተው ኣልጋዋ ላይ አጋደሟት፡፡ በፍጥነት አፏን ፈልቅቀው ቡትቶ ጨርቅ ጠቅጥቀው ለጎሟት፡፡ኣንዴ ብቻ “ማርቆስ!” አለች በጭንቀት…ያ የምታውቀው የሚያውቃት የህዋሷ መሪ ያግዝላት፣ ያድናት ይመስል፡፡ ከቆመበት አልተነቃነቃም::በጭንቅ የሚውጠው
ማንቁርቱን እላይ እታች ሲያመላልሰው የተጨነቀላት፣ ያዘነላት መሰላት፡፡
ተስፋ አደረገች፡፡ ትክ ብሎ ሲመለከታት ኣይኖቹ እንባ ያቆረዘዙ፡ መሰላት::
ተስፋ አደረገች፡፡ ማርቆስ ግን ከአልጋዋ በስተቀኝ ፈንጠር ብሎ እንደቆመ
ቀረ፡፡ አፏ ሲለጎም ልሳኗ ሲከዳት በአይኖችዋ ተማፀነች::: ዓይኖቹን
ከአይኖቿ ነቅሎ ትንፋሹን እላይ እታች እያመላለሰ ቆሞ ቀረ፡፡ ተስፋ ቆረጠች:: ለማይቀረው ዱላና ስቃይ ተዘጋጅታ ተጋደመች፡፡ ተጠባበቀች….
ኣልጋዎ ላይ ያጋደሟት ሰዎች እጆቿኝ ግራና ቀኝ ከአልጋው ጠርዝ ጋር
ጠፍረው ካሰሯት በኋላ የለበሰችውን ውሃ የበሰበሰ ስስ ቀሚስ ክላይዋ ላይ
እንደ ወረቀት እየቀዳደዱ ያነሱት ጀመር፡፡ ድንገት ሴትነቷ ገንፍሏት ወጣ፡፡
እግሮቿን እያፈራገጠች ወገቧን እየሰበቀች ቀሚሷን እላይዋ ላይ ለማስቀረት
ታገለች… ቀሚሷን ግን ኣላተረፈችውም፡፡ እግሮቿን ግራና ቀኝ በርግደው
ከአልጋው ጠርዞች ጋር ጠፈሯቸው...

የተሰማትን ህፍረት፣ የተሰማትን ውርደት ያጥብላት ይመስል እንባዋ ያለማቋረጥ በዓይኗ ጎንና ጎን ተዥጎደጎደ፡፡ ሃሞቷ ሆዷ ውስጥ የፈሰሰ ይመስል ሰውነቷ በመራራ ተሞላ፡፡ግራና ቀኝ ተበርግደው የታሰሩ
እግሮቿን ከታሰሩበት ገመድ ጋር እያፋተገች ሰውነቷን፣ ሴትነቷን፣
ለመሽፈን፣ ለመደበቅ፣
👍1👎1
ለመሽሽግ ታገለች፡፡ ገመዶቹ ግን አልተሸነፉላትም….

“ስልክ በማደወል ስዓት በጠና መታመምሽን አስተዛዝነሽ ትነግሪዋ
ለሽ…” ፊቱን ሳይመልስ በመስኮቱ ውጭ ውጭውን እየተመለከት በእርጋታ
ተናገራት:: መጥቶ እንዲያይሽም ትጎፋፊዋለሽ፡፡የመረጥሽውን መንገድ
ተጣቀሚ ተለማመጪው፤ለምኝው፤ አልቅሽ፡፡ መምጣት አለበት።ያንን ብቻ
አስታውሽ፡፡ ይህ ደግሞ የእኔ ብቻ ሳይሆን የአንቺም ፍላጎት ነው፡፡ ምክንያቱም ሳይመጣ ቢቀር ለሚቀጥሉት በርካታ ቀናት መጥፎ ነገር ታያለሽ፡፡እመኚኝ፡፡ ከዚያ በኋላ ቀሪ ሕይወት ቢኖርሽ እንኳን ልትኖሪው ፈቃደኛ አትሆኝም፡፡” ፊቱን መልሶ ቆመና ትክ ብሎ ተመለከታት፡፡ ወዲያው ከአልጋዋ በስተቀኝ ከቆሙት ሁለት ሰዎች ለኣንደኛው ምልክት ሰጠው፡፡

በስተቀኟ የቆመውን ሰው ከደረበው ጥቁር ቆዳ ጃኬት የውስጥ ኪስ
ውስጥ እስክሪብቶ የምትመስል ዕቃ አውጥቶ በአንደኛው ጫፉ በከል ክንድ
እስክታክል ድረስ መዘዛት፡፡ከቀኝ ኪሱ ውስጥ አነስተኛ የሲጋራ መለኮሻ
አውጥቶ ከለኮሰው ሰኋላ የመዘዛትን ቀጭን ሽቦ ጫፍ በእሳቱ ላይ
እሳረፋት፡፡ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ቀጭኗ ሽቦ በቁመቷ: ሙሉ ከጫፍ
እስከጫፍ ግላ ፍም መሰለች፡፡ጠጣር ብረት መሆኗ ቀርቶ ፈሳሽ እሳት
እስክትመስል ድረስ ተንቀለቀለች፡፡ በዙሪያዋ ቀይ ብርሃን እስኪያንገርብብ
ጋመች፡፡

ሰውየው ቀጭኗ ሽቦ ፍም መምስሏን ሲመለከት የሲጋራ መለኮሻውን አጥፍቶ የጋለችውን ሽቦ ወደፊት ይዞ ወደ እግሮቿ መሃል ቀረበ፡፡ ጉልበቶቿ መሃል ገባ፡፡

ተወራጨች፡፡ ከቆመችው ሽቦ ለመሽሽ በተቻላት ሰውነቷን ከአልጋው ጋር አጣበቀችው:: ሽቦዋ ግን በቀስታ በጭንና ጭኖቿ መሃል ወደ
ሰውነቷ እየቀረበቻት መጣች… ጭንቅላቷን አርገፈገፈችው…ቃተተች…

“እመኚኝ የምናደርውን አትወጅውም ያህንንም ውሸት ነው ትያለሽ? ቃሌን እስካልፈጸምሽ ድረስ የሚከተለውን አትወጀውም፡፡” ጀርባውን ለመስኮቱ እንደሰጠ አሻግሮ ተመለከታት፡፡

በፍርሃት ተርበተበተች፡፡ በእርጋታ እየተራመደ : ወደ አልጋዋ ተጠጋ። ቀኝ እጁን እራቁት ትከሻዋ ላይ ጭኖ እንደ ህፃን ልጅ በሃዘኔታ ቁልቁል ተመለከታት፡፡

ባልኩሽ ሃሳብ ትስማሚያለሽ፣ ሲደውል ረጋ ብሰሽ ታነጋግሪዋለሽ፡፡መፍራት የለበትም፣ ቢሆንም በመጠኑ መደንገጥ አለበት:: መታመምሽንና ሊያይሽ እንደምትፈልጌ አስተዛዝነሽ ታስረጅዋለሽ፡ ታባብይዋለሽ፡፡”

ሰውነቷን ሳታነቃንቅ ዓይኖቿን ብቻ በፍርሃት እያቁለጨለጨች ሽቅብ ተመለከተችው፡፡

ወደፊት ጎንበስ ብሎ ከማጅራቷ የተቋጠረውን ጨርቅ ፈትቶ አፏ
ውስጥ የታጎስጎስውን ቡትቶ እወጣላት፡፡
“አይዞሽ ጥርጣሬ አይግባሽ፡፡ ልንጎዳሽ አንሻም:: ዛሬም ነገም ባልንጀሮችሽ ነን፡፡ ለአንድ ዓላማ የቆምን ነን፡፡ ያንን ሰይጣን ያንን ነፍስ ገዳይ ብቻ እጄ አግቢልኝ፡፡”

“ሠይጣን አንተ ነህ!” ድንገት ዛር ፈለቀባት፡፡ “ነፍሰ ገዳይ አንተ ነህ! እንኳን እጅህ ላገባልህ አጠገቡ አትደርስም ቱፍ! አፏ ውስጥ በተጠራቀመው መራራ ምራቅ ፊቱን ሸፈነችው:: በጥፊ ሲያግላት ያለችበት ተዘበራረቀባት፡፡ እግሮቿ መሃል ሲቡ ተሰማት:: ሽቦዋ.. ሽቦዋ፡፡.....

💫ይቀጥላል💫
#ሌሎች_እንዲያነቡትና_እንድማሩበት_አስተማሪ_ሆኖ_ካገኛችሁ_ሼር_ያድርጉ

#ስንት _ዓመት_ተማርን?

❖አሁን የምንሰራው ስራ ለሥጋዊ ኑሮ የሚሆን የሚጠቅም ነው በዚች ምድር ላይ ሳለን እንዳይርበን እንዳይጠማን እንዳይበርድን ኑሮአችን ለማመቻቸት እንወጣለን እንወርዳለለን🤔
👉✥ከሕፃንነታችን ጀምሮ እንማራለን
ሶስት ዓመት ጊዜ ወስደን መዋእለ ሕፃናት ተምረናል
👉 አስራ ሁለት ዓመት ጊዜ ሰጥተን 12 ክፍል ጨርሰናል(አቋርጠንም ያለን ልንኖር እንችላለን
👉 አምስት ዓመት በላይ ጊዜ ሰጥተን በድግሪ በማስተር ተመርቀናል
👉ባጠቃላይ የሥጋ ሥራ ለመያዝ ከሃያ ዓመት በላይ ተምረናል
🤔እንደዚህም ተምረን ስራ አጥተን በስራ ፍለጋ ደክመናል ወንድሜ(እህቴ) ሆይ አሁን ከ20 ዓመት በላይ የተማርነው ትምህርት ለስንት ዓመት ያሰራናል ?
🤔ጡረታ እስክንወጣ ነው ከዛ በሇላ የተማርነው ትምህርት አያገለግለንም
ከ20 ዓመት በላይ ስንማር የፈተፈተነው ጊዜ እናስብ ጭንቀቱን ድካሙን እንቅልፍ ማጣቱን
ከትምህርት ቤት ለመድረስ የእግር ጉዞውን ሁሉ አንርሳ ያ ሁሉ ደክመን የተማርከው ስንሞት አይጠቅመንም 🙊
🤔ሥጋችን መቃብር ሲገባ ምድራዊ እውቀታችን አብሮ ይቀበራል
👉በህይወት እያለን ጡረታ የምንወጣው መስራት አትችሉም ተብለን ነው
👉🤔ከ20 ዓመት በላይ በተማርነው ትምህርት ብንሰራበት 30 ዓመት ቢሆን ነው ያም እድሜ ከታደለህ ነው።
👉🤔ወንድሜ(እህቴ) ሆይ እስቲ ልጠይቃችሁ
ለሥጋችን ስራ ለመስራት ከ20 ዓመት በላይ ተምረናል
#ለነፍሳችን ስንት ዓመት ተማርን?
👉ለነፍሳችን የተማርነው ትምህርት ጡረታ የለውም
በሥጋ የተማርነው የመንግሥት ስራ ያስይዘናል
👉በነፍስ የተማርነው የእግዚአብሔር ስራ ያስይዘናል
የነፍስ ትምህርት ምን ይመስለናል ቃለ እግዚአብሔር ነው
#የእግዚአብሔርን ቃል በወር ስንት ሰዓት ተምረናል ?
👉✥በዓመት ስንት ቀን ይሆናል የተማርንበትም ጊዜ እስቲ እንደምረው?
✥ባጠቃላይ የተማርንበት ጊዜ እስክንሞትስ ስንት ዓመት ይሆናል?
👉✥ መቼም የሥጋውን የተምህርት ጊዜ አያክልም
✥በነፍስ የተማርነው ትምህርት ስንት ዓመት እንደሚያሰራልን እናውቃለን ?
✥ቁጥር የማይደርስበት ጊዜ ነው
ዘመናት አልፈነው እንሰራበታለን ለዘላለም ጡረታ አያወጣንም
👉✥እኛ ግን ይሄን ረስተናል ቀኑን ሙሉ ለሥጋችን እንሮጣለን ለነፍሳችን የምንማርበት ጌዜ አጥተናል በሚያልፈው ነገር እራሳችንን ቢዚ አድርገናል ::
👉✥ሁለት ሰኣት ቁጭ ብለን የተለያዩ ፊልም እናያለን 30 ደቂቃ ቁጭ ብለን ወንጌል መማር ይሰለቸናል::
👉✥ሁለት ሰአት ቆመን እያጨበጨብን ኳስ እንደግፋለን 2 ሰአት ቆመን ቅዳሴ ማስቀደስ አቅቶን በዕለተ ሰነበት ተኝተን እናረፍዳለህን
👉✥ልብ ወለድ ዝሙታዊ የሆኑ መጻፎችን በየቀኑ እናነባለን የእግዚአብሔር እስትንፋስ የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍን ለማንበብ ይሰለቸናል
👉✥ለዘፈን የከፈትነውን አፋችንን ለምስጋና ይዘጋል
👉✥ለሀሜት የሚፈጥነው አፋችን ለጸሎት ይዘገያል
👉✥ለእስፓርት የጠነከረው ጉልበታችን ለስግደት ይዝላል
👉✥ለስርቆት የሚላከው እጃችን ለምጽዋት አይታዘዝም
👉✥ወደጭፈራ ቤት የሚገሰግሰው እግራችን ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይተሰሰራል
👉✥ሀሜት የሚሰማው ጆሮአችን ወንጌል ለመስማት ይደነቁራል
👉✥የዝሙት ሸቶ የሚያሸተው አፍንጫችን የመቅደሱን እጣን ሽታ ይፀየፈዋል
👉✥ጫት የለመደው አፋችን ሥጋውን እና ደሙን ረስቶአል
👉✥አልኮል የለመደው አፋችን ፀበሉን ተፀይፎታል
👉✥ ቂም የሚቋጥረው ልባችን ፍቅርን ረስቷል
🤔✥ስናጣ እግዚአብሔርን እንቀርበዋለን ስናገኝ ግን እንርቀዋለን
🤔👉ስንጨነቅ አምላካችንን እንጠራዋለን ስንደሰት እንረሳዋለን
🤔✥ወንድሜ(እህቴ) ሆይ በህይወታችን አንቀልድባት
👉✥ከእኛ በፊት የነበሩት ተዋቂው አዋቂው ሁሉ የት አሉ? 👉✥መቃብር ውስጥ አይደሉምን ?
✟✥✟ይህንን አስበን ከፈጣሪያችን ጋር የሚያገናኝ ስራ እንስራ
✟✥✟ በአዲስ ዓመት አዲስ እቅድ ያስፈልገናል
✟✥✟ወደቤተ ክርስቲያን ሄደን ዘወትር ወንጌል እንማር
✟✥✟ ለማስቀደስ ለመፆም ለመስገድ እንትጋ
✟✥✟ ለንስሐ እንዘጋጅ ቅድሚያ ለነፍሳችን ሁሉን ነገር እናድርግ
❖አንደበታችን ለጸሎት ይትጋ
❖እጅአችን ለምጽዋት ይዘርጋ
❖ልባችን ለምህረት ይነሳሳ
❖ሥጋውን እና ደሙን ለመቀበል እንወስን

👉👉✥ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከአካፈልኩ በኁላ ቻነላችንን ይቀላቀሉ
@Z_TEWODROS
ሌሎችም እንድማሩበት
#ሸር ያድርጉ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔም ጸልዩ!
✥"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን

#ሌሎች_እንዲያነቡትና_እንድማሩበት_አስተማሪ_ሆኖ_ካገኛችሁ_ሼር_ያድርጉ!
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥•
@Z_TEWODROS •✥•💚
💛 •✥•
@Z_TEWODROS •✥•💛
💖 •✥•
@Z_TEWODROS •✥• 💖
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

.... የቢሊየነሩ ዊሊ ባደን ውሽማ የነበረችው ሊዛ ፍላንግ ከዚህች ከዶክተር ሮበርትስ ጋ ህክምና ትወስድ እንደነበረ
ለማወቅ ያገዙት እነዚያ የግድያ ዜናውን የሚያራግቡት ሚዲያዎች ነበሩ።
ለሃያ ደቂቃ ያህል ጎግል ላይ ስለ ዶክተር ኤኮላስ ሮበርትስ የሰበሰበው መረጃ
ዶክተሯ በምዕራብ ሎስ አንጀለስ ውስጥ የምትኖር፣ በሙያዋ የምትከበር እና
ባለፈው ዓመትም ባሏ ዶክተር ዶውግላስን በሞት ያጣች ሴት እንደሆነች
ለማወቅ ችሏል፡፡ ይሄ ደግሞ እሷን የተጠየቀችውን መክፈል የምትችል ሰው
ያደርጋታል። በዚያ ላይ ደግሞ እስር ቤት እንዳይገባም ያቺ የተረገመች ዳኛ
የወሰነችለትን የልጁን ተቆራጭ ገንዘብ ማቋረጥ የለበትም፡፡ እናም ጥሩ
ገንዘብ ያስፈልገዋል። እንግዲህ ዕድሉን ቡናውን ሽሚዙ ላይ በመድፋቱ የተነሳ ያበላሸ አይመስለውም፡፡ ኒኪ እሱን ደንጋጣ ነው ብላ ካሰበችው ችግር
ሊፈጠርበት ይችላል፡፡

ለማንኛውም ኒኪ ሮበርትስ በራሷ ሀሳብ ውስጥ ስለነበረች ሊሆን ይችላል
እሱ እንደፈራው ቡና የደፋበትን ሁኔታ አላስተዋለችም፡፡ አጠገቡ ከሚገኝ
አንድ ወንበር ላይ ቁጭ አለች እና ከቦርሳዋ ውስጥ አንድ ኤንቨሎፕ
አውጥታ ሰጠችው።

“ከየት መጀመር እንዳለብኝ እርግጠኛ አይደለሁም። ስለዚህም ኢንቨሎፕ
ውስጥ ትናንሽ ማስታወሻዎችን ትቼልሀለሁ።” ብላ በመቀጠልም “ሚስተር ዊሊያምስ ያንተን እርዳታ እፈልጋለሁ። ያው ትላንትና ማታ እንደነገርኩህ ፖሊሶች ነፍሰ ገዳዩን ለመያዝ ምንም አይነት የተሻለ ነገር ሲያደርጉ አልታየኝም::” አለችው፡፡

“ዶክተር ሮበርትስ ኒኪ ይህንን የፖሊሶቹን የማይረባ ሥራ ለብዙ ጊዜ ሰምቼያለሁ” አላት እና ወደ እሷ አንገቱን አስግጎ በመጠጋትም “ኢንቨሎፕ ውስጥ ያለውን ነገር በኋላ ላየው እችላለሁ፡፡ ለአሁኑ ግን አንቺ ራስሽ ለምን ያለውን ነገር አትነግሪኝም?” አላት እና ዝም ብሎ ይመለከታት ጀመር።

ኒኪ ሁለመናውን መገምገም ጀመረች፡፡ ወፍራም፣ ፈዛዛ ቢጫ ቀለም ያለው ፊት፡፡ ዘገም ያለ የአካላዊ እንቅስቃሴን የሚያደርግ ሰው ነው።በውስጧም ምናልባት እሱ ሰካራም ምናልባትም ፈት እና ገንዘብ የሚያጥረው ሰው ነው ብላ ደመደመች። በእርግጥ ይህንን ግምቷን
ለማስቀመጥ የግድ አልበርት አንስታይንን መሆን አይጠበቅባትም።ምክንያቱም ማንም በከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ፕሮፌሽናል ሰው የቁርስ ላይ ቀጠሮውን እዚህ ርካሽ ከሆነው አይ ሆፕ ውስጥ እንደማይዝ መቼስ ይታወቃል አይደል?

ማታ ላይ ስለ ዴሪክ ዊሊያምስ የቀድሞ ደምበኞቹ ስለ እሱ ለማግኘት የማይፈነቅለው ነገር የለም። በዚህም የተነሳ ከአንድም ሁለት ጊዜ ከነገሮች በላይ (ከህግ በላይ) በጣም ገፍቶ በመሄድ የሚፈልገውን መረጃ
ፍርድ ቤት ቀርቧል። ይህንን አደጋን የመጋፈጥ እና ነገሮችን በጣም ገፍቶ
በመሄድ የሚሰራ ሰው እንደሆነ ስለምታውቅ ነበር ኒኪ እሱን የፈለገችው።
ወደ እሱ ደውላ ቀጠሮ የያዘችበት ዋነኛ ምክንያቷም የግል መርማሪውን ደፋርነት በማንበቧ ነው።

“እንደ ነገርኩህ እኔ ከየት መጀመር እንዳለብኝ አላውቅም” አለችው፡፡

“መጀመሪያ ነው ብለሽ ካሰብሽው ነገር ለምን አትጀምሪም?” አላት እና ዊሊያምስ ባልኮኒው ጋር ወደምትገኘው አስተናጋጅ አንድሪያን ዞሮ “የኔ ቆንጆ ቁርሴን የተጠበሰ እንቁላል ከጎኑ ደግሞ ፓንኬክ አድርጊልኝ፡፡ ለጓደኛዬ ደግሞ?” ብሎ ኒኪን ተመለከታት፡፡

“እኔ ቡና ብቻ ነው የምወስደው”

“ለእሷም እንቁላል ጥብስ ይሁንላት” አላት እና ዊሊያምስ በግርምት ወደምታየው ኒኪ ፊቱን መልሶ “የእኔ እመቤት መብላት ይኖርብሻል። ሰዎች
በኑሯቸው ዙሪያ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ደውለው እኔን ካገኙ እና ጭንቀታቸውን ካረገፉ ምን ይቀራቸዋል? ስለዚህ አንቺ ምን ማድረግ አለብሽ መሰለሽ? በቃ በደንብ መብላት እና ሀሳብሽን ለእኔ ጥለሽ መተኛት ነው የሚኖርብሽ” አላት፡፡

ዴሪክ ዊሊያምስ በቅንነት ሀሳቡን ስለነገራትም ነው መሰል ኒኪ ተበረታታች እና ማውራት ጀመረች፡፡ “መልካም እንግዲህ... ከመጀመሪያው ጀምረሽ ንገሪኝ ብለኸኛል አይደል? ለእኔ እውነተኛው የመጀመሪያው ነገር
ምን መሰለህ? ሟቹ ባለቤቴ ከትዳሩ ውጪ የፍቅር ግንኙነት ነበረው” ብላ
ነገሯን ጀመረች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ቫላንቲና ባደን የጂ 6 አውሮፕላኗ ጎማዎች ሜክሲኮ ካቦ ውስጥ
ከሚገኘው የሳን ሉካን አየር ማረፊያ ወለል ሲነኩ አምላኳ በሰላም ስላስገባት
የምስጋና ፀሎትን በውስጧ አደረገች፡፡

ቫለንቲና ብዙ ነገሮችን የምትፈራ ሴት አይደለችም። እህቷ ከ 50 ዓመት
በፊት ከጠፋችበት ጊዜ ጀምሮ በደንብ እስካሰበችባቸው ጊዜ ድረስ ያለፈቃዷ
ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ነገሮች በጣም ጥቂት እንደሆኑ ለማወቅ ችላለች።
ወዳጆቿ በአውሮፕላን የመጓዝ ፍርሃቷ የመነጨው ነገሩን መቆጣጠር
እንደማትችል ከማመኗ የተነሳ እንደሆነ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።ምናልባት ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ። ምክንያቱም ከበፊት ጀምሮ ቫለንቲና በትዳሯ፣ በቤተሰቧ፣ በምትሰራቸው ቢዝነሶቿ እና ከሰዎች ጋር ያሏትን ግንኙነቶች በሙሉ እሷ ሙሉ በሙሉ ስትቆጣጠራቸው ነው የኖረችው።

የሎስ አንጀለስ ቆይታዋ ስኬታማ ነበር። ሳይጠብቋት በድንገት ወደ በጎ
አድራጎት ድርጅቶቿ ቢሮዎች ጎራ ብላ ነበር። ቢሮዎቹ ውስጥ ገብታም
የድርጅቱን የተሳኩ የፍለጋ ሥራዎችን እንዲሁም ደግሞ የስድስት ወሩን
የተዘበራረቀ የባንክ ሂሳብ ሪፓርትን እንዲያሳዩአት ጠይቃ ለማየት ችላለች።
የአሜሪካ ውስጥ የገቢዎች ቢሮ የድርጅቱን ከውጪ የሚገቡለትን ገቢዎች
ምንጭ ማነፍነፍ ከጀመረ ወዲህ ቫለንቲና ራሷ ናት እነዚህ አይነት ነገሮችን
የምትቆጣጠረው። በድርጅቱ ውስጥ የሚሰሩ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው
እውነተኛው የሥራ አካሄዳቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁት እና ሥራቸው
ሚስጥሩ ተጠብቆ መስራት እንዳለበት የሚገነዘቡት። ዊሊ ባሏ ደግሞ ሰነፍ
ስለሆነ እሷ የምትሰራቸው ሥራዎች ላይ አትኩሮት ሰጥቶ አያውቅም።ባለፈው ጊዜ ዊሊ ለኤል.ኤ ፖሊስ ክፍያ በመፈፀም ይደረግባቸው የነበረው
ምርመራ እንዲቋረጥ አድርጓል። የአሁኑ የአሜሪካ የውስጥ ገቢዎች አካሄድ
ግን ይለያል እና ቫለንቲና መጠንቀቅ እንደሚኖርባት ታውቃለች።

በዚያ ላይ ደግሞ እሷ በድንገት ቢሯቸው ውስጥ ገብታ እሷን ንግስታቸውን ለማስደስት የሚራኮቱትን ሰራተኞችን መመልከት ደስ ይላታል፡፡ የበጎ አድራጎት ሥራዎችም ልክ እንደ ሌሎች ለትርፍ የሚሠሩ ድርጅቶች ሁሉ የራሳቸው የሆነ መለኪያ እንዳላቸው፣ መለኪያዎቹም
ድርጅቱ የሚያስመዘግባቸው በጎ ውጤቶች መሆኑን ለሰራተኞቿ በየጊዜው
ነው የምትነግራቸው።

ለባለፉት አሥራ አምስት ዓመታትም በጣም በጣት ከሚቆጠሩት የፍለጋ
ሥራዎቻቸው በስተቀር ሁሉም በጥሩ ሁኔታ እንደተጠናቀቁ ስታስረዳቸው
በኩራት ነበር። ሬቼ ላምብ የተባለ ድክ ድክ የሚል ህፃን ቱርክ ውስጥ
ቤተሰቦቹ ለመዝናናት በሄዱበት ጊዜ ላይ ጠፍቶ አልተገኘም። የቻርሎቴ
ክላንሲ መጥፋት፣ የዚህች ወጣት ያለመገኘት ደግሞ ራሷን ቫለንቲናን
ጭምር ያሳዝናታል፡፡ ምክንያቱም ልጅቷ የጠፋችው ልክ እንደ ቫለንቲና መንታ እህት ሜክሲኮ ውስጥ ስለነበረ ቫለንቲና ልቧ ተነክቶ ነበር። ምንም እንኳን ውጤታቸው ፍሬ አልባ ቢሆንባቸውም፤ ከሌሎች የማፈላለግ ሂደቶች
በተለየ መልኩ በየሚድያዎቹ ላይ ስለ ክላንሲ እንዲነገር አድርጋ ነበር
ድርጅቷ በሁሉም የፍለጋ ሥራዎቻቸው ላይ መቋጫን ሳያበጁ ፍለጋውን
አያቋርጡም። ለምሳሌ ያህል የብራንዶን ግሮልሽን ፍለጋ የሚመስሉ አይነት
ሥራዎቻቸው ላይ የፈላጊ ቤተሰብን ልብ የሚሰብር አሳዛኝ ነገርንም መናገር
(ማሳወቅ)
👍2🔥1🥰1
) ይችላሉ። ለማንኛውም ድርጅቱ እንደዚህ አይነት ስኬቶችን
የመጎናፀፍ ምክንያቶች ቫለንቲና ሳታቋርጥ ስራተኞቿን በመሸለሟ እና
በመቅጣቷ የመጡ ስኬቶች ነበሩ።

የዚህ ሳምንት አሰራር ግን ቅጣትን መሰረት ያደረገ ነበር። ቢሮ ውስጥ
በቆየችባቸው የአንድ ሰአት ጊዜዋ ውስጥ አካውንታንቱ እና ረዳቶቹን ስታሸብር ነበር።

“ሥራዎች በአግባቡ እንዲከናወኑ ከፈለግክ ሥራውን አንተ ራስህ ስራው ብላ ቴሪ ኤንጀልስ የተባለውን የኤል.ኤ ኦፊስ ማናጀርን ወረፈችው።

“የባለፉት ስድስት ወራት ፋይሎች በሙሉ የማይረቡ እና ያልተደራጁ ናቸው። እዚህ በምቆይበት ጊዜ ላይም እኔው ራሴ አደራጃቸዋለሁ።በሚቀጥለው ጊዜ ግን እንደዚህ አይነት ጉዳይ ቢገጥመኝ ቦታህን ትለቃለህ”

የገንዘብ ነክ ጉዳዮች ላይ ያሏትን ሥራዎች ከጨረሰች በኋላ ቢሮው
ውስጥ ያልተገኙ ሠራተኞች ላይ ቅጣቶችን ወስና ከቢሮዋ ወጣች። ሌሎች ልትሠራቸው ያሰበቻቸውን ሥራዎችንም ሎስ አንጀለስ ውስጥ በቆየችባቸው ጊዜያት ላይ በደንብ አጠናቅቃ ወደ ሜክሲኮ ካቦ ተመለሰች። ሎስ አንጀለስ በቆየችባቸው ጊዜያት ላይ እሷን ቫለንቲና ባደንን ማንም ሰው ሊያሞኛት እንደማይችል ተገቢውን ትምህርት ለሁሉም ሰዎች ሰጥታ ወደ ካቦ ስለተመለሰች፤ ቆይታዋ ስኬታማ እንደሆነ ገምታ ጥሩ ስሜት ተሰማት።
ዊሊ ባደን በየጊዜው ወደ እሷ እየደወለ አሁን ላይ አብሮት እየሰራው በሚገኘው ሰው ላይ ያለውን ፍራቻ በመንገር ሲነዘንዛት ብቻ ትንሽ ምቾት አጥታ ነበር፡፡ አሁን ላይ የሚያስፈልጋቸው ነገር ቢኖር ሚድያዎች ስለ ሊዛ ፍላንገን እና ስለ ዊሊ የፍቅር ግንኙነት እንዲሁም ደግሞ ስለዚያች የተረገመች ሳይኮሎጂስት
ዶክተር ሮበርትስ የሚያወሩትን ነገሮች
እንዲያቆሙ ማድረግ ብቻ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ነገሮች ወደ ቀድሞ ሰላማዊ ሁኔታቸው ይመለሳሉ። .

“እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን መጣሽልኝ” አላት ዊሊ ባደን ለቫለንቲና፡፡ ዊሊ ባደን ራሱ አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ ሊቀበላት በመምጣቱ ትንሽ ገርሟታል። የታርማክ መኪናቸው ሹፌር የቫለንቲናን ቦርሳዎች ተቀብሏት መኪናው ውስጥ ካስገባ በኋላ መኪናውን መሾፈር ጀመረ።
ይሄኔም ዊሊ ባደን “ሁለት ቀን ሙሉ ስደውልለት እኮ ስልኩን አያነሳም!”
ብሎ ፍርሃት በወረረው ድምፅም “
ሰማሺኝ? ሁለት ቀን ሙሉ ስልክ
አያነሳም፡፡ በጣም ሳይናደድብኝ አልቀረም!” አላት፡፡

“ማን ነው የተናደደው?” ብላ ቫለንቲና ጠየቀችው፡፡

“ስለማን ነው እያወራሁኝ ያለሁት?” ብሎ በንዴት ጠየቃት፡፡

“ሮዲሪጉዜን ነው?” ብላ ቫለንቲና በረዥሙ ተነፈሰች።

“አዎ ሮዲሪጉዜ ነዋ!” ብሎ በፍርሃት ድምፀት ውስጥ ሆኖ “እሱ ጋር
ሥራ መሥራት አልነበረብንም፡፡ ይሄ የማይረባ ድርድር...” ብሎ

“ብዙ የሥራ ዕድልን እና ሀብትን ይዞልን ይመጣል።” ብላ ቫለንቲና እሱ ሊናገር ባላሰበው መልኩ መለሰችለት እና ክንዱን ጭምቅ አድርጋ በመያዝ “ዊሊ መረጋጋት ይኖርብሃል። በዚህ ጊዜ ላይ ፍራቻን ማሳየት የለብህም። እንደ ሮዲሪጉዜ ያሉ ሰዎች የሌሎች ሰዎችን ድክመት ልክ ሻርክ ደምን በሚያሸትበት ሁኔታ ነው የሚያሽቱት። ከእንደ እሱ አይነት ሰዎች ጋር እንዳደግኩኝ ነግሬሀለሁ አይደል? እዚህ ነገሮች በተለየ መልኩ ነው
የሚከወኑት።” አለችው፡፡

“እሱንማ አውቃለው” በማለት ዊሊ መለሰላት።

“እንግዲያውስ ይህንን ካወቅክ በዚህ መልኩ ነው መንቀሳቀስ የሚገባህ”
ብላ ቫለንቲና ተናገረች እና በማስከተልም “አንተ የድርሻህን ተወጥተሃል ይገባዋል ብለህ ያሰብከውንም ድርድር አቅርበህለታል በዚህ ነገርህ ከተናደደ
ግን በጣም መጥፎ ነገር ነው።”

“በጣም መጥፎ ነው ያልሽው?” ብሎ ዊሊ በድንጋጤ ድምፅ ጮክ ብሎ
ተናግሮ አፉን በእጁ ይዞ ቆየ “በጣም መጥፎ ነው ያልሽው ቫለንቲና? እሱ
እኔ ላይ ሊያደርግ የሚችላቸውን ነገሮች አስበሻቸዋል? በቃ ይገድለኛል።” አላት ቫለንቲናም ረጋ ብላ ጭንቅላቷን ከወንበሩ መደገፊያ ላይ አስደግፋ አይኗን ዘግታ ለጥቂት ጊዜ ዝም አለች፡፡

“አንተ እነዚህን ሜክሲኮያውያንን አታቃቸውም። ከዚህ በፊት ከሮዲሪጉዜ
ጋር በጠፉ ሰዎች ዙሪያ ለወራት ያህል አብረን ስንሰራ እንደነበር ነግሬሃለሁ
አይደል?”

ያ እኮ ያ የማይረባ የበጎ አድራጎት ሥራ ነው” ብሎ ዊሊ ጮኸባት እና
“ይሄ ግን ይለያል!” አላት።

ቫላንቲናም በውስጧ ይህማ አንተ የምታስበው እና ከላይ የሚታየው
ሥራዬ ነው!' አለች፡፡

“ለማንኛውም እውነታው ምን መሰለህ? አንተ እንዳልከው ሁለታችንንም ሊገድለን ይችላል። እመነኝ ይህንን ግን አያደርገውም፡፡ ዊሊ ሎስ አንጀለስ
ላይ አንተ ታስፈልገዋለህ። ማለቴ ከጠቃሚ ሰዎች ጋር ያለህ ግንኙነት እና
ህጋዊ ድርጅቶችህን ሊጠቀምባቸው ይፈልጋል። ይሄውልህ በአንተ እጅ ላይ
ብዙ ጠቃሚ ካርዶች አሉ። ከአንተ የሚጠበቀው ነገር እነዚህን ካርዶች
በአግባቡ መጫወት ብቻ ነው።” አለችው፡፡

ዊሊ አፉን በመክፈት የሆነ ነገር ሊናገር ሲል ቫላንቲንና አቋረጠችው እና

“አሁን ደክሞኛል ውዴ፡፡ ያለፉት ቀናቶችን በጣም ስሠራ ነበር ያሳለፍኩት። በዚህ ጉዳይ ላይ ልታወራኝ ከፈለግክ ግን ራት ላይ ልታነሳው ትችላለህ።” ብላ አይኗን ከድና መደገፊያው ላይ ራሷን አሳረፈች፡፡

“ሮዲሪጌዜ ጋር አሁን ልደውልለት?” አላት ዊሊ በጭንቀት እንደተዋጠ፡፡
ቫለንቲናም አይኗን ሳትከፍት “ስለ ፈጣሪ ብለህ ዊሊ እስቲ አንድ አንዴ እንኳን ወንድ ወንድ ሽተት እንጂ” ብላ ቀዝቀዝ ባለ ስሜት መለሰችለት።

ይህንን የሰማው ሹፌራቸውም ድምፁን አፍኖ እየሳቀ ወደ ፊት መንዳቱን ቀጠለ።

ይቀጥላል
👍4
#ህመምህ አሞኛል


የጥበብን ቀኝ እጅበቀኙ የዘየረ፣
ነብዩ ሰለሞን “ያማል” ይል ነበረ፡፡
ቆሞ ሲጠብቃት ቀርታበት ወዳጁ፣
አንድ እሷ የምትሞላው፣
ኦና ቢሆን ደጁ፣
ግትልትል መኪናው፣
ታክሲው አውቶብሱ፣
የሰው ግሳንግሱ፣
የሰው አጋሰሱ፣
ላይኑ አልሞላ ብሎት፣
ለተራበች ነፍሱ፣
“ያማል” ይል ነበረ፡፡
በአይኖቹ አንቀልባ በእንባ መቀነቻ፣
ተስፋ እንደቋጠረ፣
ማዶ ማዶ እያየ በተሰበረ ቅስም “ያማል”ይል ነበረ!
እኔ መች ተሰማኝ የጓዴ ህመሙ፣
የታባቴ ገብቶኝ የጥበቃ ጥሙ፣
ዛሬ ግን አወቅኩት...ብቻዬን ባወራው እብድ ይሉኛል ብዬ፣
ህመምን ላለፍካት ህመሜን ላኩልህ ʻባረቄʼ ጠቅልዬ፡፡
እየውልህ ጓዴ...

ያች የነገርኩህ ልጅ የፍቅር እትብቴ፣
ለተስፋዬ ደብር ያኖርኳት ፅላቴ፣
በራችንን ዘግተን ሲንቆረቆር ህልሜ ሲንቆረቆር ህልምህትዝ አይልህም ጓዴ፣
እልፍ ʻዝም በልʼ ያልኩህ


(እ.................................................................ሷ!)
የሰው ሁሉ ዳና ʻየሷ ነውʼ እያልኩኝ፣
ከበሬ ሲርቁ ተስፋ እያስወረድኩኝ፣
የጠበቅኳት ፍቅሬ - መቼ ለታ መጣች፣
ጓዴ ሃሌ ሉ.....ያ የኔ ፀሐይ ወጣች፣
ከምዕራብ አድማስ ብርሃኗን ነዛች፡፡
ተዘግቶ የነበር በሬ ተከፈተ፣
ገድሎኝ የነበረው ብቸኝነት ሞተ፡፡
ሊተን የነበረ የመውደዴ ተስፋ፣
ፀጉሬ ጫፍ ላይ ሲደርስ ተመልሶ ፋፋ፡፡
ጥቋቁር ተራሮች ፍቅሬን የጋረዱ፣
የእግሯን ዳና ሰምተው ከፊቴ ተናዱ፡፡
ጓዴ ሃሌሉ.....ያ
አበቦች ደመቁ፣
የመከኑ ምንጮች ኩል ውሃ አፈለቁ፣
በጠራራ ግንቦት አደይ ምድሩን ሞላ፣
ምን ልበልህ ሌላ...ሃሃሃ ሃሃ ሃሃ እኔ እምልህ ጓዴ፣
“የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ...”ነበረ አይደል ያልከው ?
ከመቅረት የባሰ አመጣጥ እንዳለ አንተ መቸ አወቅከው ?!!
እና የነገርኩህ ልጅ...
መኖሬን ረስታ፣
ደብሬን ክፍቱን ትታ፣
እግዜር የሰማውን የእምነት ቃሏን ክዳ፣
ከበዓድ ተዛምዳከባዕድ ተዋልዳ፣
“አ...ንተ እስካሁን አለህ ?”አትለኝ መሰለህ…ል...ሙትልህ ጓዴ !

እንዲህ ነው ያለችኝ፣
ቁልቁል እያየችኝ፡፡
እንዲህ ናት ቅፅበቷ...
እሷ ከፊቴ አለች፡፡
የጎደፈ እምነቷን፣
በቃል እያጠበች፡፡
ውራጅ ፍቅሯን ገዝቶ፣
ደረቱን የነፋ ʻፈረንጅʼ ጎኗ ቆሟል፣
ከሷና እሱ ኋላ፣
ተራራ ሸንተረር ዛፍ ቅጠሉ ታምሟል..
.ደመናውም ደክሟል...ከደመናው በላይ አፉን በእጁ ይዞ፣
እግዜርም ተደምሟል(ወቸ ጉድ እያለ…)
ፈረንጁ....
እጁን ʻመክሊቴʼ ላይ ጣል አድርጎ ያየኛል፣
ያኔ ያልከው ʻህመምʼ ጎኔን ይወጋኛል፡፡
የምትወዳት ልጅ በሌላ መታቀፍ፣
ከዚህ በላይ ስቃይ ከዚህ በላይ መቅፈፍ...ምናለበት
እሱ...ግዴለም ይቀፋት፣
በፈራረሰ ቤትጭቃው በረገፈ፣
በንፁህ ልቦና በቀን ባልጎደፈ፣
አንዲት አግዳሚ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠን፣
አንድ እርሳስ ተካፍለን አንድ መፅሐፍ ገልጠን፣
የአበበን በሶ - የጫላን ስል ጩቤ፣
እኔ እንጅ የማስታውስ - ልቤ ላይ ከትቤ፣
ፈረንጁ ምን እዳው… ከሀዲን ያስከዳው፡፡
የአየለን ብርታት፣
የጫልቱን እንስራ፣
በቀዳዳው ጣራ፣
ጉንጯ ላይ ያረፈች የምተገርም ጮራ...፡፡
ቆዳዋ ላይ ያሉ ገራገር ስስ ፀጉሮች፣
ጥቁር ሰሌዳ ላይ ተስፋ የሚቃርሙ የልጀነት አይኖች፡፡
አርፈው የማይቆሙ፣
ተወዛዋዥ እግሮች፣
እርሱ መቸ አያቸው...
ከአንጎሉ ጥልቀት በትዝታ መረብ መች አጠመዳቸው፡፡
ምቾት ያደለበው ስጋዋን ይቀፈው፣.
እንደመሲህ ካባ በእምነት የምነካው፣
ሰገባ ቀሚሷን በድፍረት ይግፈፈው…
ከሰማይ የራቁኝ - ጡቶቿ መካከል፣
በእፎይታ ይረፍ-በአርያም ይንሳፈፍ…ልሙትልህ ጓዴ፣
እጎኔ ብትኖርʻእናቷን ጨረቃʼ ያስባለህ ህመምህ፣
በጠራራ ፀሃይ ይነሳብህ ነበር፡፡
እኔ ተነሳብኝ ሾይጧን ወሰወሰኝ፣
እከካም ክህደት የምፎክትበት ጥፍርህን አውሰኝ፡፡
የኔና እሷን ነበር ዛሬ ያላወራው፣
ʻእ ና ቱ ንʼ ...ሸለቆው እ ና ቱ ን ተራራው፡፡
እፊቴ የቆመው... እ ና ቱን ፈረንጁ፣
ወገቧን ያቀፈው እ ና ቱ ን ቀኝ እጁ፡፡

ስማኝማ አንተ ሰው..
.የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ አልነበረ ያልከው…
ከመቅረት የባሰ አመጣጥ እንዳለ አንተ መች አወቅከው፡፡
አይዞን ወዳጄ፣
ያው እንዳንተ ደጃፍ ኦና ሆኗል ደጄ፣
አሁን ናፍቀኸኛል...
እጠብቅው የለኝ ትጠብቀው የ ለህ፣
እንገናኝና ʻአረቄʼ እየጠጣን፣
ግጥም እንፃፍለት፣
ለድህነታችን ጥበቃን ላሳጣን
!!እናቱን ድህነት !!
እናቱን ጥበቃ
!!በቃ!!
👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


.....ናትናኤል ጊዜ ሳያጠፋ ታክሲ ተሣፍሮ ወደ ለገሃር ሄደ፡፡ ደጋግሞ ደውሎ ነበር ስልኩ የተነሳለት፡፡ቀደም ብሎ የመሥሪያ ቤቷ ጓደኛዋ ምህረትጋ ደወሎ ርብቃን አቅርቢልኝ ሲላት: እሁንም ወደ ስራ
ገበታዋ አለመመሰሏን ስትነግረው አለቅጥ ተጨነቀ፤ከራሱ ጋር ክርክር
ገጠመ፡፡ እንደታመመችና ቤቷ ደውሎ ከቻለም ሄዶ ቢያያት እንደሚሻል
ምህረት ስትነግረው መንፈሱ ሸፈተበት፡፡ ልቡ ላይ እንደጦር የተሸነቀረበት
ግን ሌላ ነበር

“በጣም አሟታል እንዴ?” አላት ምህረትን ቅንድቦቹን አጠጋግቶ፡፡ “ምንድነው በሽታዋ ማለቴ…”
“እንዴት ነው ነገሩ..ኣላወቅህም ማለት ነው? ወይስ…ናትናኤል ርብቃ'ኮ እርጉዝ ነች፡፡”
ድንገት እንደመሽ ሁሉ ጭልምልም አለበት ፤ ጭንቅላቱ እንደ ድንጋይ ከበደው፤ ማጅራቱን ጨምድዶ ያዘው፡፡ አንድ ቃል ብቻ ይደጋግም ጀመር “ፈጣሪዬ! . ፈጣሪዬ! ፈጣሪዬ! ስልኩን ከዘጋ በኋላ በቆመበት ተገትሮ ቀረ፡፡ እንደህፃን ልጅ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ፈለገ፡፡ “ርብቃ ... ርብቃ!” ራሱን መቆጣጠር ተሳነው “ገደል ይግባ!” ሁሉ ነገር ገደል ይግባ!” የሚንቀጠቀጥ እጁን ኪሱ ከቶ ከአንድ ቡና ቤት ገብቶ ተቀመጠ፡፡ ለሰዓታት ከራሱ ጋር ተወራጨ፡፡ በመጨረሻ ከቡና ቤቱ ወጥቶ የህዝብ ስልክ ይፈልግ ጀመር፡፡

ስልኩ ቢጠራም የሚያነሳው ሰው አልነበረም፡፡ በሚንቀጠቀጥ ቀኝ
እጁ የስልኩን እጀታ ጨምድዶ ይዞ ተጠባበቀ:: ርብቃ'ኮ እርጉዝ ነች ስልኩ
ይጠራል፤ የማያነሳ የለም፡፡ ቀጥታ እቤቷ ድረስ ብሄድስ? አሰበ፡፡ መሄድ የለብኝም:: እሷንም ቢሆን ለባሱ አደጋ ማጋለጥ ነው የሚሆነው፡፡ ደጋግሞ ደውሎ ነበር ስልኩ የተነሳለት

“ሀሎ” አለ ስልኩ እንደተነሳ ቀድሞ፡፡ ድምፅ ተጠባበቀ፡፡ ግን ምንም
አልነበረም:: መልሶ “ሃሎ አለ የሚንቀጠቀጥ ድምፁን ማረጋጋት
እየታገለ፡፡

“ናቲ..ናናቲ” ድምጿን ከመቅጽፅት ለየው፡፡ ቢሆንም በጣም የደከመ ድምጽ ነበር፡፡
“ርብቃ! ደህና ነሽ…?”
“ናቲ...ናቲ አቃጠሉኝ..ና…” .
“ናትናኤል ነኝ ርብቃ… ጮክ በይ አይሰማኝም፡: ርብቃ መሥሪያ
ቤትሽ ደውዬ ነበር፡፡ ርብቃ… እ?… አይሰማም፡፡” ድምጿ እየደከመበት ሄደ፡፡
ሌላ ሰው ስልኩን እንደተቀበላት ተረዳ፡፡
“ሀሎ፡፡” አለ ለስለስ ያለ የወንድ ድምፅ፡፡
“ሃሎ.… እባኮት ርብቃን ነበር፡፡”
“ማን ልበል? ” .
“ሀሎ..እባኮት ርብቃን ያቅርቡልኝ::” ናትናኤል ረጋ ብሎ ጠየቀ፡፡
“ይቅርታ፡፡ትንሽ አሟታል፡፡ በስልክ መቅረብ አትችልም::
የምነግርልዎት መልዕክት ካለ.….”
"እሷኑ ለማነጋገር ስለምፈልግ ነበር፡፡” ናትናኤል ጠንከር አለ፡፡
“ይቅርታ… ስትነጋገር ስለሚደክማት ነው፡፡ መልዕክት ካሎት ልንገርሎት፡፡ ታናሽ ወንድሟ ነኝ ብስራት ነኝ፡፡”
ናትናኤል ለማስታወስ ሞከረ፡፡ ቤተሰቦቿን ብዙም አልቀረባቸውም፤ ቢሆንም ከብስራት ጋር ከአንድ ሁለት ሦስት ጊዜ ተገናኝተዋል፡፡ ብስራት ገና ሃያ ዓመት ያልሞላው ወጣት ወንድሟ ነው::

“እንደምንዋልክ ብስራት፡፡ ናትናኤል ነኝ፤
ታስታውሰኛለህ? የርብቃ..እ… ”

“እዎ እዎ አስታውስሃለሁ፡፡ እንደምንድነህ? ደህና ነህ? ምነው
ጠፋህ? ርብቃ በጣም አስባለች፡፡ ለምን ብቅ አትልም? ”

“እ..” ናትናኤል አመነታ፡፡ “ምን መሰለህ ብስራት መምጣት እንኳን አልችልም፡፡ ግን እሷ እንዴት ነች?”

“አሟታል…በጣም ነው የታመመችው ሐኪም ቤት እያመላለስናት ነው::”

“ምን አሉ ሐኪሞቹ? ማለቴ ምንድነው?” ናትናኤል በልቡ የሚንቀዋለለውን ለመጠየቅ ጭንቅ አለው::

“አላወቁላትም፡፡ ግን ምግብ አይበላላትም፤ ስትበላም አይረጋላትም፡፡
ሰውነቷ ላይ ግን ችግር የለባትም፡፡ 'ጭንቀት ነው' ነው የሚሉት ሐኪሞች፡፡
ምን እንደሚያስጨንቃት ግን ሊገባን ኣልቻለም፡፡ በጣም ደክማለች::
ናትናኤል መጥተህ ብታያት ጥሩ ነበር:: በእንቅልፍ ልቧ ሁሉ ስምህን
ትጠራላች፤ ከቀን ወደቀን እየባሰባት ነው፡፡” ናትናኤል በረጅሙ ተነፈሰ፡፡ እጁን ግንባሩ ላይ ጫነ፡፡ ከራሱ ጋር ክርክር ገጠመ:: የፈለገው ይምጣ ሄዶ ያያታል፡፡ መቼም በቤቷ አካባቢ ሊያንዣብቡ ይችሉ ይሆናል፡፡ ግን ምርጫ የለውም:: ሹልክ ብሎ ገብቶ ሹልክ ብሎ ይወጣል ወሰነ::

“ብስራት መደወሌን ለማንም አትናገር ዛሬ ማታ መጥቼ አያታለሁ እሺ? ልክ ከምሽቱ አስራ ሁለት ተኩል ሲሆን ውጭ በሩጋ ጠብቀኝ” ናትናኤል ስልኩን ከዘጋ በኋላ በግራው ያንጠለጠለውን ትንሽ የሽራ
ሻንጣ ይዞ እዚያው ለገሃር ኣቅራቢያ ወዳለ አነስተኛ ቡና ቤት ተመልሶ ገባ፡፡
ጥግ ወዳለ ወንበር ሄዶ ሰውነቱን ለማርገብ፣ ለማረጋጋት በዝምታ
ተቀመጠ፡፡ በግራሶና ዘይት የተጨማለቀ ሰማያዊ ቱታ ለብሷል። ጭንቅላቱ
ላይ ያጠለቀው ዙሪያው እንደጠወለገ ቅጠል የተልፈሰፈሰው ባርኔጣ በግንባሩ
ላይ ኣዝምሞ ፊቱን ሸፍኖታል፡፡ ከደረት ኪሱ ሲጋራ አውጥቶ ከሚንቀጠቀጥ እጁ ጋር እየታገለ ከለኮሳት በኋላ ክብሪቱን እያጠፋ ሲጋራዋን ምጥጥ አደረጋት፡: “ርብቃ... ርብቃ.… ምነው አጠገብሽ መሆን ብችል!”

“ምን ልታዘዝ::” አለችው ሰማያዊ ሽርጥ ወገቧ ላይ ሸብ ያደረጎች አስተናጋጅ የለበሰውን ቆሻሻ ቱታ ስታይ ድምጿን ቆጥብን አድርጋ::

“ቡና፡፡” አላት ቀና ብሎ አያቷት የዋጠውን የሲጋራ ጭስ ቀረጁሙ እየለቀቀ፡፡

“ሂሣብ በቅድሚያ ነው የሚከፈለው፡፡” አለች ሁለት እጆቿን በጎንና ጎን የሽርጥ ክሶች ውስጥ እየወሸቀች፡፡

ከቀኝ ኪሱ ውስጥ ሣንቲሞች አውጥቶ ጠረጴዛው ላይ በተን እደረገላት፡፡ ሃሳቡ ግን ሌላ ቦታ ነበር፡፡ ርብቃ ለምን ደበቀችው? «ወይስ ወሯ ገና ነው ማለት ነው ሊሆን አይችልም:: ደብቃው ነው፡፡ ግን ለምን.… ለምን?

የሚወደው ገጿ መጥቶ ፊቱ ላይ ድቅን አለበት፡፡ ርብቃ'ኮ እርጉዝ ነች የምህረት ድምፅ እቃጨለበት፤ አሟታል ምግብ አይበላላትም ብትበላም አይረጋላትም “ጭንቀት ነው" ነው የሚሉት ሐኪሞቹ….
የብስራት ድምፅ ደወለበት...

“አምላከኔ ምን ዓይነት ጉድ ወስጥ ነው የከተትከኝ ኣለ እምላከ ከፊት ለፊቱ ባለ ወንበር ላይ የተቀመጠ ይመስል ፊት ለፊት አፍጥጦ፡፡

ምንድነው ሊያደርግ የሚችለው? ቀጥ ብሎ ፖሊስጋ ሄዶ እጁን መስጠት፡፡ ቢገሉትስ? ይግደሉት፡፡ ከዚህ በላይ ስቃይ መሸከም አይችልም ግን ለፖሊሶችስ ምን ሆንኩ ብሎ እጁን ይሰጣል? ሁሉን ነዋ!.. የሆነውን
ሁሉ ዘርዝሮ ማውጣት ነዋ! ግን ማን ያዳምጠዋል? ማን ያምነዋል? ፍጹም!
ፖሊስ ወጥመድ ነው! እጁን መስጠት ማለት ሞቱን ማፋጠን ማለት ነው፡፡
ለማን ይበጃል መሞቱ? ለርብቃ? ስልጁ? የአብርሃም መሞት ማንን ጠቀመ?
መረጋጋት ነው ያለበት፡፡ ካሁን ወዲያ ወደኋላ ማለት አይችልም፤ መረጋጋት
ነው ያለበት፡፡

ከቁጥጥር ውጭ በሚንቀጠቀጥ ቀኝ እጁ የያዛትን ያለቀች ሲጋራ ለመጨረሻ ጊዜ መጠጣትና ከፊት ለፊቱ ጠረጴዛ ላደ በተቀመጠው የሲጋራ መተርኮሻ ውስጥ ደፈጠጣት፡፡ መረጋጋት…. መረጋጋት ነው ያለበት...

የቡና ቤቱ አስተናጋጅ ያዘዛትን ቡና አምጥታ እፊቱ ደነቀረችለት::
አንስቶ ፉት ኣላው፡፡ ስኳር አልነበረውም:: ክፉኛ መረረው፡፡ ቢሆንም ስኳር
አልጠየቃትም፡፡ ድጋሚ ፉት ኣለው፡፡ ትኩስ ቡና በጉሮሮው አልፎ በሆዱ
ሲተራመስ ስንዝር በስንዝር ተከታትለው:: ሆዱ ጩርርርር ሲል ተሰማው:: ትላንት ምሳ የበላ ነው፡፡ ቢሆንም ምግብ አላሰኘውም:: ከቡናው ድጋሚ ፉት አለለት፡፡ ሰውነቱን ማዝናናት አለበት፤ ማረጋጋት አለበት፡፡በተቀመጠበት ወንበር ላይ በደኋላ ጋለል ብሎ ዓያኖቹን ጨፈናቸው፡፡ ቀኝ እጁ ከደረት ኪሱ ገብቶ ሲጋራና ክብሪት ይዞ ተመለሰ፡፡ ርብቃ ለምን ደበቀችው? በቃ በቃ... ስለርብቃ
👍2