#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
..... “የኔ ልጅ” አሉ ቀረብ ብለው ቆመው የነበሩ ነጭ “ጥምጥም የጠመጠሙ ቄስ፡፡ “እዚህ ላይ የሚጣፈውን ትጥፊልኝ… አላወቅበት ብዬ
እንዳላዟዙረው ሰጋሁ::” የያዙትን የታሸገ ፖስታ ወደ ልጅቷ ፊት አስጠጉት፡፡ ሲናገሩ ድምጻቸው ይንቀጠቀጣል፡፡ ወረቀቱን ሲያቀበሏት ምርኩዛቸው አምልጧቸው ወደቁ፡፡
“ምንድነው የፈለጉት?” እለች ልጅቷ ቄሱ ሲደነጋገሩባት ግራ ተጋብታ፡፡
“የኔ ልጅ ይህን ቦስጣ ልልከው ፈልጌ ነበር፡፡ ታዲያ ከይህና ከይህ የሚጣፈውን እንዳላበላሽ አሉ ቄሱ ያሽጉትን ፖስታ እያገላበጠ፡፡ “እምን ከምን እንደሚሰፍር አላውቅት ብዬ ትጥፈልኝ፡፡” ለሳምንታት
የሸመደዱትን ተረተሩላት።
“የሚልኩለትን ሰው አድራሻ ያውቁታል?” አለች ልጅቷ ፖስታውን ልትቀበል እጁን እየዘረጋች::
“እንዴታ ቄስ ገብረክርስቶስ ጋ”
“አይደለም… አይደለም… ማለቴ ሙሉ አድራሻውን” አለች ልጅቷ ፈገግ ብላ፡፡
“እነግርሻለሁ፡፡ ብቻ እንቺ ከሥፍራ ከስፍራው ጣፊልኝ::”
ልጅቷ ወረቀቱን ከተቀበለቻቸው በኋላ ወረቀቱ ላይ አቀርቅራ የሚነግራትን ለመፃፍ ትጠባበቅ ጀመር።
“ቄስ ገበዝ ገብረክርስቶስ በይማ::”
ልጅቷ በፖስታ ከረጢቱ ጀርባ ላይ ቄሱ ያሏትን ማስፈር ጀመረች፡፡ ቄሱ ጠጋ ብለው ከጠረጴዛው ላይ ተደራርበው የተቀመጡትን የመታወቂያ ወረቀቶች ሰብሰብ ስብራብ አደረጓቸው፡፡
“እንዲያ ደብረሊባኖስ ገዳም በይ አዎ..ደብረ…” ቄሱ ከጠረጴዛው ላይ የሰበሰቧቸውን አራት መታወቂያች አጋብሰወ ከጋቢያቸው ስር ከኪሳቸው ውስጥ ጨመሯቸው። “ሸዋ... በይበት... እንዲያ ተባረኪ!” አሉ ድምጻቸው እየተንቀጠቀጠ፡፡
“የእርሶስ አድራሻ? ” አለች ልጅ:: ቀና ብላ እየተመለከተቻቸው፡፡እኔማ ምን አድራሻ አለኝ? መንገደኛም አደለሁ?” አሏት ቄሱ
ፖስታቸውን ተቀብለው ለመሄድ እየተጣደፉ፡፡
“ቢሆንም ስሞትን እንኳን ልጻፈው፡፡”
“ልክ! ልክ! ቄስ ዘነበ ዘነበ ወልደሰማያት በይልኝ፡፡ አንዲያ ዘነበ፡፡” አሉ ድንገት የተቻኮሉት ቄስ፡፡
የፈለጉትን አድራሻ በታሸገው ፖስታ ላይ ጽፋ እንደጨረሰች ቄስ መርቀዋት ፈጠን ብለው ከፖስታ ቤቱ አዳራሽ ወጡ፡፡ ገልመጥ አላሉም፡፡መንገዱን ተሻግረው ታክሲ ውስጥ ገብተው ወደ ክፍለሃገር አውቶብስ መሳፈሪያ ሲያምሩ ነበር ምርኩዛቸውን ረስተው መምጣታቸው
የታወሳቸው፡፡ ክው አሉ፡፡ ለመመለስ ግን አልደፈሩም::
ናትናኤል የገጠር አውቶቡስ መሳፈሪያ ደርሶ እንደወረደ ወደ ተከራየው ወደ ዘውዲቱ ቤት አልሄደም፡፡ ወደ አንድ ሱቅ ገባና ስልክ ጠይቆ ርብቃ መሥሪያ ቤት ደወለ፡፡
ሃሎ ምህረት?”
“ናትናኤል!” አለች ምህረት ገና ድምፁን ስትለየው፡፡
“እንደምንድነሽ ምህረት ደህና ነሽ?”
“አንተ! ምን እንዲህ አጠፋህ? በጤናህ ነው?”
“አለሁ እለሁ፡፡ ምህረት እባክሽ ርብቃን ትጠሪልኝ…”
“የለችም፡፡ ለመሆኑ አዲስ አበባ ነው ያለኸው?”
“ስራ ኣልገባችም?” አለ ጥያቄዋን ችላ ብሎ፡፡
አዎ ከትላንት ጀምራ አልገባችም፡፡ ቤቷ ደውዬ ነበር የሚያነሳ የለም:: ደጋግሜ ሞክሬ ነበር፡፡”
ናትናኤል ምህረትን ተሰናብቶ ስልኩን ዘግቶ ወደ ዘውዲቱ ቤት መንገድ ጀመረ፡፡ ሃሳብ ገባው፡፡ አሟት ይሆን? እንዴት ሁለት ቀን በተከታታይ ከሥራ ትቀራለች.… በጤና ብትሆን? ቤቷ ሊደውል አሰበና ፈራ ስልኳ ተጠልፎ እንደሆንስ ድጋሚ አደጋ ላይ ሊጥላት አይገባም:: ቆያይቶ ሰሞኑን እዚያው ምህረት ቢሮ ደውሎ ቢያነጋግራት ይሻላል፡፡
ናትናኤል ዘውዲቱ ቤት ሲደርስ በሩ እንደተቆለፈ ነበር፡፡ ዘውዲቱ የለችም ማለት ነው፡፡ የሰጠችውን ተለዋጭ ቁልፍ አውጥቶ በሩን ከፍቶ ገባና ከውስጥ ቆለፈው:: ወዲያ ጋቢውን ወርውሮ ጥምጥሙን አውልቆ ጥሎ ከኪሱ ውስጥ ከፖስታ ቤት የሰረቃቸውን አራት የመታወቂያ ወረቀቶች አወጣና ተራ በተራ እየከፈተ አነበባቸው፡፡
ሻለቃ ብርሃኑ ገብረማርያም አቶ ጀማል አብዱልከሪም ዶክተር አለሙ ገዛኸኝ ሲስተር ሠናይት አሽኔ፡፡ ሀሳብ ገባው የትኛውን ሊያቀስ እንደሚችል ግራ ገባው::
ምርጫ አልነበረውም፡፡ዶክተር አለሙ ገዛኸኝ የሚለውን መታወቂያ ነጥሎ አንስቶ በጥንቃቄ ፎቶግራፉን ነቀለና ቀን ከተነሳቸው ፎቶግራፎች መሃል አንዱን ተካበት፡፡ ወዲያው ቶሎ ብሎ ከመሬት አንስቶት ወደ ቤት ገባና ጭቃውን በጨርቅ ያፀዳ ጀመር፡፡ የመታወቂያ ወረቀቱን በጥንቃቄ ጠራረገው፧ አፀዳው፡፡እንደ በፊቱ ንፁህ ባይሆንም..መቼስ.….አለሙ ገዛኸኝ የሚለው ይነበባል፡፡ያንን ነበር የሚፈልገው:: 'ዶክተር የሚለው አስፈላጊ አልነበረም፡፡ ለተቀሩት መታወቂያዎች ደግሞ ሰኑን ሌሎች ፎቶግራፎች ይነሳላቸዋል፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በሩ..የመኝታ ቤቷ በር ወደ ውስጥ ሲገፋ ጠረጴዛውን ደገፉ እንዳለች ቀረች፡፡በሩ ተከፍቶ የሰው ቅርጽ ታያት፡፡ ሰውየው ወደ ውስጥ ገብቶ በሩን ዘጋው፡፡ ከጀርባው ባለው መስኮት የሚገባው ስስ የጨረቃ
ብርሃን ቀጠን ረዘም ካለው ሰውነቱ ላይ ሲያርፍ ሰው ሳይሆን ህይወት ያለው ጥላ መሰላት፡፡ ግራ ጉንጩን ከላይ እስከታች የገመሰው ኣስጠሊታ ጠባሳ የአካሉ አንድ ክፍል እንዳልሆነ ሁሉ በጨረቃዋ ብርሃን ውስጥ ጎልቶ ታያት፡፡ አተኩራ ትናንሽ አይኖቹን ተመለከተቻቸው፡፡ ሰውነቷ ይንቀጠቀጥ ጀመር፡፡ ሆዷ ውስጥ ያለው ሽል የተላወሰ መሰላት ሊያስመልሳት እንደፈለገ ሁሉ አንጀቷ ሲመናተቀል ለራሱ ነፍስ የዘራ ይመስል ሲቋጠር ሲፈታ.. ሳይታወቃት ወደፊት ዘላ ጉብ አለችበት፡፡
“ገደላችሁት! ገደላችሁት አይደል?
አታለላችሁኝ!” አውቃ አስባ ሳይሆን ከውስጥ የሚነዳትና የሚጋልባት ዛር እንዳለ ሁሉ ዘላ ፀጉሩን ጨመደደችው፡፡ ፊቱን በጥፍሮቿ ገባችበት::
“ርብቃ!” ጥፍሮቿን አሹላ አይኖቹን ልትጓጉጠው ስታሻቅብ ባለ በሌለ ሃይሉ እራሱን እየተከላከለ ጮኸ፡፡ “ርብቃ! አልገደልነውም! ማንም አልደረሰበትም... እሱን ለመግደልም አላሰብንም... ርብቃ አዳምጪኝ!” ሁለት እጆቿን ወደኋላ ጠምዝዞ ደረቷን ደረቱ ላይ ለጥፎ አገጯን በቀኝ እጁ ግጥም አድርጎ ይዞ ጮኸባት፡፡
“ውሽታም! ውሸታም! አታላችሁኛል፤ ገድላችሁታል.…ቱፍ” ፊቱን በምራቅ አለበሰችው::
“አልሞተም አለ፡፡ ስላመለጠን ነው ወደ አንቺ የመጣነው:: ርብቃ ረጋ በይ!”
ለአንድ አፍታ ረጋ ያለች መሰሰች፡፡ቀና እንዳለች ቁና ቁና እየተነፈሰች አፈጠጠችበት:: ድንገት ፡ እጆቿን መንጭቃ ከእቅፉ ወጣች፡፡ ከፊቱ ተጋርጦ አይኖቿን አጉረጠረጠችበት፡፡
“ልትገድሉት ነበር የጠራችሁት፥ ጓደኛውን እንደገደላችሁት እሱንም ልትገድሉት ነበር፡፡ አትዋሽ! አሁን ደግሞ ወር ሙሉ እናገኘዋለን ታገሽ ስትለኝ ቆይተህ አመለጠን ትለኛለህ! ”
“ርብቃ እመኝኝ፡፡ እሱን የመግደል ሃሳብ አልነበረንም፡፡ አስፈላጊም አልነበረም:: ምንም አያውቅም፡፡ በድንግዝግዝ ጨረቃ ብቻውን እንደሚሮጥ እብድ ነው::” አለ ሰውየው ከኪሱ ወስጥ መሃረብ አውጥቶ ፊቱ ላይ የትዝረበረበውን ምራቅ እየጠረገ፡፡
“ጓደኛውን አልገደላችሁትም? አትዋሽ!”
“ገድለነዋል፡፡ አስፈላጊም ነበር መሞቱ:: ምሥጢሩን ከሞላ ጎደል ደርሶበታል፡፡ በማንኛውም ሰዓት ሊያወጣው ይችል ነበር፡፡ ኣደገኛ ሰው ነበር፡፡
“እሱን የገደላችሁት ሌሊት ናትናኤልን ጠርታችሁታል:: ልትገድሉት ነበር፡፡ አትዋሽ!” ከሥሯ ያለውን ወለል በእግሯ ደቃችው፡፡
“ርብቃ እመኝኝ፡፡ የዛን ቀን ጓደኛው አደገኛ የሆነ እርምጃ ወሰደ፡፡ገደልነው:: ምንም ምርጫ አልነበረም... እርግጥ በጥድፊያ ውስጥ ነበርን የዛን ማታ ሁለቱም እንዲገደሉ ነበር የተላለፈው ትዕዛዝ፡፡ እንደ አጋጣሚ ያንቺ ሰውዬ አመለጠ.. ትራፊክ ፖሊስ

👍2
ይዞት፡ በማግስቱ ግን ሁኔታው ሲረጋጋ የሞቱ ትዕዛዝ ተነስቶ የሃያ አራት ሰዓት ክትትል እንዲደረግበት
ነበር የተወሰነው፡፡“
“…ሰዎቻችን መሥሪያ ቤቱ ሲገባ አይተውታል፡፡ ግን ከሰዓት በኋላ
እንደደወለለሽና አምባሳደር ቲያትር ውስጥ በስውር ሊያገኝሽ እንደሚፈልግ
ባሳወቅሽን ጊዜ ሰዎች ተመድበው ትያትር ቤት ድረስ ተከታትለውሽ ነበር ግን አንቺ ራስሽ ከመታጠብያ ቤት ከወጣሽ በኋላ እንደተሰወርሽበት ነበር ሪፖርት ያደረገው ከዛ በኋላ ልናገኘው አልቻልንም
“ብታገኘት ምን ልታደርጉት? ልታርዱት፤ ልትገድሉት?”
“ረጋ በይ፡፡ ማንም ሊገድለው የሚፈልግ የለም፡፡”
“ታዲያ ለምን ፈለጋችሁት?” ፊቷን አስግጋ ቀረበችው፡፡ “ተናገር ምን ልታደርጉት ፈለጋችሁት? ሁሉን ዘርዝረህ ንገረኝ ናትናኤል ከመጥፋቱ በፊት አንድ የተሰወረ ዲፕሎማት እንደሚፈልግ ነግሮኛል፡፡ ምን ማለት ነው? ማነው እሱ?
"ሃገርኩሽ! ለሞት የሚያደርሰው ነገር የለም ፤ በቃ፡፡ ምንም አያውቅም የተሰባበሩ ጥቃቅን ጥያቄዎች ይዞ ነው ከወዲያ ወዲህ የሚሮጠው:: እርግጥ ጓደኛው ስለታገደለ ፈርቶ ይሆናል... ግን ባጭሩ እሱን መግደል አስፈላጊ አይደለም:: በቁጥጥር ስር ልናቆየው ነው የምንፈልገው... እስከጊዜው:: ከዚህ ውጪ ዝርዝር ነገሮችን ልነግርሽ አልችልም፡፡ አንቺም ታውቂያለሽ እያንዳንዳችን ማወቅ የሚባን እንደየደረጃችንና እንደአስፈላጊነቱ
ማወቅ የሚገባንን ብቻ ነው::”
“ልታስሩት!…የፊጥኝ አስራችሁ እየገረፋችሁ እያንገላታችሁ ልትገድሉት” አይኖቿን አጥብባ በጥላቻ ተመለከተችው፡፡ ለዚህ ነው
የፈለጋችሁት እንግዳው!”
“ዓላማ አለን! አስፈላጊ ከሆን ደግሞ ሌሎችን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን የገዛ ሕይወታችንን አሳልፈን ልንሰጥለት የተዘጋጀንለት ዓላማ አለን!”
“ዓላማ ቢስ ናችሁ አታላችሁኛል! ሁላችን ተታለናል፡፡ ምንም ቁንጅና የለንም፡፡ ቆንጆዎች አይደላችሁም! ነፍሰ ገዳዮች ናችሁ!”
“ቆንጆ ማለት ደካማ ማለት አይደለም.… ቆንጆ ማለት አቅም የለሽ ማለት አይደለም… ራሱን የማይከላክል ቁንጅና የቀትር ፀሃይ ሲወጣ ይረግፋል…ቆንጆዎች ነን… ጠንካሮችም ነን፡፡”
በምን ተለያችሁ ከቀድሞዎቹ?..በምን“ ታለያችሁ ከከዳተኞቹ?... ሥልጣን ላይ ከተሰገሰጉት እሾሆች በምን ተለያችሁ? እናንተም እንደነሱ ትኮሰኩሳላችሁ፤ እናንተም እንደነሱ ትናደፋላችሁ፤ እናንተም እንደነሱ እሾህ ናችሁ! ምኑ ላይ ነው ቁንጅናችሁ?”
“ቁልቋልም ጽጌረዳም እሾህ አላቸው.…ሁለቱም ይናደፋሉ:… ጽጌረዳ ግን ቆንጆ ነው ጽጌረዳዎች ነን… ጥቋቁር ጽጌረዳዎች... ጠላቶቻችንን ሊቀጥፉን የሚመጡትን እንደ ጽጌረዳ እንናደፋለን... ለሚያደንቀን ግን ውብ ነን ለሚያሽቱን ጥዑም ነን፡፡”
ፊቷን መልሳ አልጋዋ ላይ ቁጭ አለች፡፡
“ቆንጆ ማለት ደካማ ማለት አይደለም…ራሱን የማያከላከል ቁንጅና...” የሚለው የማርቆስ ንግግር ጆሮዋ ላይ ደወለባት፡፡ እነዚህ ምን ቆንጆዎች ናቸው?…በግድያ የሚያምኑ በአፈና የሰለጠኑ የቀትር
ጅቦች ምናቸው ይታመናል? የሠላም ፀሮች!.…ጥላቻዋ ገኖ ይታያት ጀመር፡፡
መቼ ነበር. አዎ ሶስና ለልደት የጋበዘቻቸው ዕለት…. ናትናኤልንና እሷን
“የአፍሪካ ጥያቄ የፖለቲካ ጥያቄ ነው፤ የአፍሪካ ነፃነት የሚገኘው በተዋህዶ
እንቅስቃሴ አፍሪካ አንድ ስትሆን ነው” ባለችው ጊዜ ናትናኤል ምን ነበር
ያላት?ለማስታወስ ሞከረች፡፡ “በአገሮች መካከል ኢኮኖሚያዊ ትብብርና ጥንካሬ መቅደም አለበት፡፡ የፖለቲካው ውህደት ከዚያ በኋላ ነው የሚመጣው... ለአፍሪካ እድገት ቅንጅት ያለው እንቅስቃሴ መኖር አስፈላጊም ሲሆን ሂደቱ ዲሞክራሲያዊ መሆን አለበት፡፡ በዕቅድ የሚመራ ዲሞክራሲ በትምህርትና በልምድ ሊዳብር ይገባል…” ሲል ናትናኤል የተናገራት ትዝ አላት፡፡ ርብቃ አንዳች አዲስ ነገር ህሊናዎ ጓዳ ውልብ አለባት። ይህ ምን ማለት ነው? ናትናኤል ዲሞክራሲያዊ ህብረት ሲል ምን ማለቱ ነበር? አዎን ግልጽ ነው እነዚህ ራሳቸውን “ቆንጆ” ያሉት ሰዎች የሚከተሉት መስመር ይሄ አይደለም፡፡ “እነሱ የሚያምኑት በኃይል ነው:: ዲሞክራሲ ማለት ለነሱ ዝም ብሎ ለአፍሪካ መቆርቆር ነው.. አፍሪካ አንድ ትሁን ሲሉ በኃይል እንጠቀም ማለታቸው መሆኑ በእኩይ ተግባራቸው ይታያል…አይሆንም
አይሆንም ልክ አይደሉም ወይ ናትናኤል...ናቲ ናቲ… ልክ ነህ.. ናቲ…” በእጆቿ ራሷን ቀብራ በሃሳብ ጭልጥ ካለችበት ስትመለስ የግንዛቤዋ
የቀስ በቀስ ሂደት መከለት ስሜቷን ነካው፡፡ ጩሂ ጩሂ አሰኛት፡፡
“ረጋ ብለሽ ኣዳምጪኝ እንዳልኩሽ ልንጎዳው አንፈልግም… ግን ደግሞ በደመነፍስ ያለዕውቀት ጥፋት ለማድረስ ሲሯሯጥ ዝም ብለን ልንመለከተው ኣይገባም… የያዝነውን ዓላማ ስላልተረዳ ብቻ ጠላታችን ሆኗል..
“አስሬ ይሆናል የነገርኳችሁ..በየሳምንቱ በምጽፈው ሪፖርት ላይ.. ይመልመል ብቁ ነው ይመልመል ብያችኋለሁ!” “ርብቃ ያንን አላውቅም… ውሳኔ የሚሰጡ ሌሎች ናቸው… ዋናው ነገር አሁን ባለማወቅ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል…ንገሪኝ..የት ነው ያለው?”
“አላውቅም፤እየፈለግነው ነው የምትለኝ ውሸት ነበር ማለት ነው?እየደወልኩ ጠፋ ስልህ አላመንክኝም ማለት ነው?”
“ውሸትሽን ነው፡፡”
“አላውቅም አልኩሀ ኣላውቅም! ውሸቴን አይደለም፡፡”
“አስታውሽ.…ከናትናኤል ጋር ያገናኘሽ የእኛ ዓላማ ነው:: አንቺ ግን አላማሽን ረስተሽ ለስጋ ፍላጎትሽ ተሽነፍሽ…” አይኖቹን አሳንሶ በንቀት ቁልቁል ተመለከታት፡፡ “የት ነው ያለው...ንገሪኝ፡፡”
“ዓላማችሁ ነፍስ መቅጠፍ መሆኑን ባውቅ ኖሮ፤ አላማችሁ ሕይወት ማጨለም መሆኑን ባውቅ ኖሮ አላማዬ ብዬ አልይዘውም ነበር:”
“ምንድን ነበር የጠበቅሽው? ፌሽታ? ጭፈራ?..አትሞኝ.… ከግባችን ለመድረስ የግድ ደም መፍሰስ ካለበት ይፈሳል…ምርጫ የለንም።” አጠገቧ አልጋዋ ላይ ተቀምጦ ትከሻዋን በሁለት እጆቹ ይዞ ትክ ብሎ ተመለከታት
“...አስታውሽ የጋናው ነቢይ ያለውን፡፡ ደህንነታችን አንድነታችን ነ ከዚያ ውጪ ደህንነት የለንም፡፡ በዚህ ሰዓት ከዓላማሽ ማፈግፈግ አትችይም ክህደት ነው፡፡”
ቀና ብላ አትኩራ ተመለከተችው፡፡
“…እመኚኝ አንጎዳውም… ጊዜው ደርሷል… ያኔ ነፃ ይሆናል፡፡ ለትንሽ ጊዜ አንድ ቦታ ሰውረን እናስቀምጠዋለን… ምንም አናደርገውም…የት ነው ያለው?”
ነገርኩህ'ኮ እኔ ራሴ የት እንዳለ አላውቅም::”
““እደውልልሻለሁ ማለቱን
አስታውቀሽ ነበር፡፡”
“አዎ። ብሎኝ ነበር ግን አልደወለልኝም፡፡”
“ለምን? እንዴት አልደወለም? ምሥጢሩን እውጥተሻል ማለት ነው፡፡”
“ባወጣሁት በነገርኩት ደስ ባለኝ ነበር!” አለችው በጥላቻ እየተመለከተችው፡፡
“እርጉዝ ነሽ? ድንገት ጠየቃት፡፡ ቃናው ጥያቄ ሳይሆን ትዝብት መሰላት
ደነገጠች፡፡ እንዴት ደረሱበት?
“ያ የግል ጉዳዬ ነው።” አለች በትቻላት ድፍረቷን አሰባስባ ኣፍጥጣ
እየተመለከተችው፡፡
“የመጨረሻ ዕድል እሰጥሻለሁ፡፡የት ነው ያለው?”
“ኣላውቅም!”
ድንገት ከትከሻው እንደ ወስፈንጠር ተለጠጠባት። ከአልጋው ላይ
ተፈናጥሮ ተነሳ።ጥርሱን ሲነክስ ጉንጩ ላይ የተጋደመው ጠባሳ በጨረቃዋ
ብርሃን ጎልቶ ወጣ፡፡ ራመድ ብሎ ወደ መስኮቱ ሄደና መጋረጃውን ሰብሰብ
አድርጎ ከአፓርታማው አጥር ውጭ ወደቆመችው ሲትሮይን ቁልቁል
ተመለከተ፡፡ ወዲያው ከግራ የደረት ኪሱ የቅርብ ርቀት መገናኛ ሬዲዮ …
አውጥቶ ተጫነው-
“ቆንጆዎቹ…ቆንጆዎቹ… ዜሮ አራት መቀጠል ትችላለህ።” ፊቱን መልሶ ቀጨለማው ውስጥ አፍጥጦ ተመለከታት፡፡
“ከዳተኛ ነሽ ባንዲ…” አለ ቅዝቅዝ ብሎ፡፡
ከተቀመጠችበት ሳትንቀሳቀስ በፍርሃት ተመለከተችው።
“…ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ ከዚች ክፍል

መውጣት አትችይም…ሰውዬሽን..አታስቢ እናገኘዋለን፡፡ እንዳገኘነው እናስወግደዋለን፡፡” ወደ መኝታ ቤቷ በር ራመድ ብሎ በሩን ከውስጥ ቀረቀረው፡፡
“ምን ልታደርጉኝ ነው? አኔንም ልትገድሉኝ አሰባችሁ እንዴ?” አለችወ ፍርሃቷን ለመሽፈን እየታገለች።
“አስፈላጊ አይደለም፡፡ አንቺም ታውቂዋለሽ፡፡ አስፈላጊ መግደል ብቻ ሳይሆን በደስታ የገዛ ሕይወታችንን
እንሰዋለን ከአሁን ወድያ በዓለም ላይ ማንም አይመልሰንም! ማንም አይቋቋመንም! ተንቀን፤ ተጠልተን፤ ተዋርደን፤ ለባርነት መለያ ሆነን ኖረናል፡፡ ተግዘናል፤ ተሸጠናል፤ ተለውጠናል፡፡ አሁን ግን ያበቃል፡፡ ደህንነታችንን፤ ለይስሙላ
ያልሆነ አውነተኛ ነፃነታችንን በእንድነታችን እናገኘዋለን ቅርብ ነው ጊዜው…”
ወንበር ስቦ ተቀመጠ፡፡
አልጋዋ ላይ እንደተቀመጠች በጨለማው ውስጥ ኣፈጠጠችበት፡፡ያለፈው ሁሉ እንደቅዠት እየተዘበራረቀና እየተደራረበ መጣባት…
💫ይቀጥላል💫

#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
...ለምንድነው እሷ የሌሎችን ፈጠራ የምትነግረን?” ብሎ ጉድማን እጆቹን
እያወናጨፈ “ ለምን?” ብሎ ጠየቀው፡፡
ጆንሰንም ትከሻውን ሰብቆ “ምናልባት ትኩረት ለማግኘት ፈልጋ!”
እኮ ያንተን ትኩረት? ላስቀይምህ አይደለም ኒኪ፤ ግን እሷ አንተ ላይ
ምንም አይነት ፍላጎት የላትም”
“አላውቅም ሉው። ምናልባት ያንተን ትኩረት ፈልጋ ይሆናል” አለ እና ማክ በንዴት ስሜት ውስጥ እንደሆነም “ምናልባት እሷን ባገኘናት ቁጥር
የምላስህን በምኞት ማለክለክ እና ሱሪህ ላይ ድንኳን የሚሰራውን ብልትህን
በቅርበት ማየት ፈልጋ ይሆናላ።” ብሎ መለሰለት፡፡
ጉድማንም ራሱን በሀዘኔታ ነቀነቀና በውስጡ እንዴ ይሄ ሰው? ምናልባት ገና የሦስተኛ ክፍል ተማሪ ይሆን?' አለ በሆዱ፡፡
በዚህ የጆንሰን ሙግት የደከመው ጉድማንም ከባልደረባው ጋር ከዚህ
በላይ ቢከራከር ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ስላወቀ የምርመራ ክፍሉ
ውስጥ ዝም ብሎ ቁጭ አለ። የባልደረባውን ዝምታ ውይይታቸው እንዳበቃ እንደሚያሳየው ምልክት በመቁጠርም ጆንስን “በብራንዶን ግሮልሽ ላይ የተለየ መረጃን አግኝተሃል?” ብሎ ጠየቀው፡፡
“ምንም የሚጠቅም ነገር አላገኘሁም” ብሎ ጉድማን በመቀጠልም “ራሄል
ኬስሊ የተባለችውን ለቫለንቲና የብራንዶን ግሮልሽን ብዙ አደንዛዥ ዕፅ በመውሰዱ ምክንያት መሞቱን የሚገልፅ ደብዳቤን የፃፈችውን ልጅ ተከታትዬ ለማግኘት ችዬ ነበር”
“እና?”
“ኡፍ” ብሎ ጉድማን በረዥሙ ተነፈሰ እና “ከስምንት ሳምንት በፊት በብዛት ዕፅ በመውሰዷ ምክንያት በሃያ ሁለት ዓመቷ ህይወቷ አልፏል። ቤተሰቦቿም ሳንድያጎ አቅራብያ ነው የቀበሯት።” አለው፡፡
ጆንሰንም በሰማው ነገር ተናድዶ “እነዚህ ልጆች ላይ ምንድነው እየተከሰተ ያለው?” ብሎ በቁጣ ጠየቀ፡፡
“በእርግጥ ያሳዝናል” አለው ጉድማን፡፡
ጆንስን ወደ ቅድሙ ስሜቱ በድንገት በመመለስ “እንዴት እንደሆነ ባይገባኝም
“ኒኪ ሮበርትስ በሁለቱ ግድያዎች ላይ እጇ እንዳለበት ይሰማኛል።” ብሎ
እርግጠኛ ነኝ፡፡ በቃ እውነቱን ለማጣራት በጣም ማረጋገጫው ከእጃችን እያመለጠን ያለ ነው የሚመስለኝ፡፡” አለው ጆንሰን፡፡
ጉድማን ባልደረባው ጆንሰን ልንደርስበት ጥቂት ርቀት ብቻ ነው የቀረኝ የሚለው አነጋገሩን ምንም አይሰማውም። ከዚያ ይልቅ ባልደረባው ዶክተር ኒኪ
ሮበርትስን እና ማዋረዱን ቢተው እሷ
የምትሰጣቸውን መረጃዎች (ለምሳሌ የቀዩ መኪና ሹፌርን ነገር የመሳሰሉ
ጥሬ መረጃዎችን በደንብ ልትገልፃቸው እንደምትችል ይሰማዋል።
እንግዲያውስ ብራንዶን ግሮልሽ የእውነትም ሞቶ ከሆነ የሚቀራቸው ብቸኛ የግድያ ወንጀሉ ተጠርጣሪ የጥቁሯ ላንድክሩዘር ሹፌር ይሆናል ማለት
ነው።
“እሺ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ?” አላት ሀዶን ፊቱ በፈገግታ እንደተሞላ
ከጠረጴዛው ባሻገር የምትገኘውን ኒኪ ሮበርትስን እየተመለከተ፡፡ የትሬይን
ሞት ሊያረዳት ቤቷ ከመጣ በኋላ ተገናኝተው አያውቁም። ዛሬ ላይ ደግሞ
ያኔ የትሬይን ሞት ሲያረዳት ይታይባት የነበረው የሀዘን እና የባዶነት ስሜት
አሁን አይታይባትም።
“ጠይቀኝ” አለችው ኒኪ፡፡
ሀዶንም አይኑን እሷ ፊት ላይ እንደተከለ “የሜየር ሌመን ማለት ምን ማለት ነው?
ኒኪ በሀዶን ጥያቄ ሳቀች። የሚገኙት ሎስ አንጀለስ ቬነስ ውስጥ አቦት
ኬንሌይ መንደር ዳር ምርጥ ምግብ ከሚቀርብበት አዲስ ትንሽዬ ምግብ ቤት
ውስጥ ነው።
ሀዶን በመቀጠልም “እዚህ የምግብ ሜኖዎች ላይ የማያቸው የምግብ
ዝርዝሮች አዳዲስ እና አስደንጋጭ ናቸው። የድሮዎቹ የምግብ ስያሜዎች
የት ጠፉ?”
“ኧረ አሉ” ኒኪ በእንፋሎት የተጠበሰውን ሶሪትን በቢላዋ በስሱ ቆርጣ እና በሹካ ወደ አፏ እየላከች “ከዚህ ስድስት ብሎኮች አለፍ ብሎ ከሚገኘው ኤል ፓሎ ከሚባለው ምግብ ቤት ውስጥ ታገኛቸዋለህ፡፡ ያውም ከዚህ በአስር
እጥፍ ባነሱ ዋጋዎች፡፡ ግን ያው እንደዚህ አይነት ረከስ ያሉ ምግብ ቤቶች
መመገብ ያንተ ስታይል አይደለም ብዬ ነው እዚህ ይዤህ የመጣሁት” ብላ
ነገረችው፡፡
ሀዶን ልክ እንደ በፊቱ ከዶውግ የመኪና አደጋ በፊት ኒኪ እንደዚህ ዘና ብላ ስትተርበው በማየቱ ደስ አለው:: ከባሏ ዶውግ ሞት በኋላ ውስጧ ግማሹ ሀዘን፣ ግማሹ ደግሞ ንዴት እንደሆነ ይሰማዋል። በተለይ ደግሞ ባሏ
በሞተበት ጊዜ ላይ ባወቀችው የእሱ ሚስጥር ባሏን እንደማታውቀው አይነት
ስሜት እንደሚስማት ይገምታል።
“ዲዘርት እንዲቀርብልሽ ትፈልጊያለሽ?” ብሎ ሀዶን ቀዩን የክሬይ ዓሳን
(ከሜይር ሌመን ጋር) በልቶ እየጨረሰ “ወይስ እንሂድ?” ብሎ ጠየቃት፡፡
“ብንሄድ ይሻላል።” ምክንያቱም አሁን ሀቸኮሌት የመብላት ስሜት ውስጥ
አልገኝም።” ብላ መለሰችለት።
እሱ እና ባሏ ዶውግ ባለፉት ስምንት ዓመታት ሊከፍቱት ያስቡት ወደ
ነበረው የቬኒስ ክሊኒክ አመሩ። ዶውግ ሙሉ ጉልበቱን ለዚህ በሎስ አንጀለስ
ቬነስ ውስጥ ሊከፍቱት ባሰቡት የበጎ ፈቃድ ክሊኒክ ያለመሰሰት እውቀቱንና
ጉልበቱን ሲያውል እና የተለያዩ ዕቅዶችን ሲያወጣ ነበር፡፡ እዚህኛው
የከተማው ክፍል ውስጥ የሪል ስቴት ዋጋ እየጨመረ ስለመጣም አካባቢው
የቤት አልባ ሰዎች እና የአዕእምሮ በሽተኞች መናሃሪያ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ከእነዚህ ነዋሪዎች አብዛኛዎቹም ለብዙ ጊዜ የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚ እና
ሱሰኞች ናቸው። ዶውግ የክሊኒኩ ህንፃን በተቻለ አቅም በርካሽ ዋጋ ከገዛ
በኋላ ብዙዎቹን የአካባቢው አርቲስቶች፣ አርክቴክቶች እና ኮንትራክተሮች
በነፃ አገልግሎት ህንፃውን በደንብ አድርገው እንዲያድሱት አድርጎታል።
አሁን ላይ ሀዶን ነው ቦታውን በበላይነት የሚያስተዳድረው። ክሊኒኩ
ከጥቂት ወራት በፊት ቢከፈትም ሁልጊዜም ከክሊኒኩ እርዳታን የሚፈልጉ
ታካሚዎች ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምረው ሰልፍ በመያዝ መጠበቃቸው የተለመደ ሆኗል።
ሀዶንም ክሊኒኩን እንድትጎበኝለት እና ምሳም አብረው እንዲበሉ ቀጠሮ፦
አስይዟት የነበረው ትሬይ ከመሞቱ በፊት ነበር። ስለዚህ ቀጠሮውን በማክበሯ ሁለቱም ተደስተው ነበር፡፡ ኒኪ ሀዶን ዶፍ መልካም እና የዋህ ሰው እንደሆነ ታውቃለች፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ከሟቹ ባሏ ጋር ያላቸውን በደስታ የተሞላ ግንኙነት የሚያሳስባት ብቸኛው ሰው ነው ብላ ስለምታምን ነው በቀጥታ ከፖሊስ ጣቢያው ምሳ ለመብላት ወደ ተቀጣጠሩበት ቦታ የመጣችው፡፡ ማክሰኞ ማታ ላይ ስለተሞከረባት በመኪና ተገጭቶ የመገደል ሙከራን ልታካፍለው አልፈለገችም፡፡ ምክንያቱም አንዴ እሷ ይህን ጉዳይ አንስታ ለሀዶን ከነገረችው እሷን ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ ሙከራዎችን እንደሚያደርግ በማሰብ ነው። ለዚህ ደግሞ ሀዶን ጊዜ እንደሌለው ከማንም በላይ ታውቃለች፤ በተለይ ደግሞ በቬነስ ክሊኒክ እና በሴዳርስ ሆስፒታል የሚያደርጋቸው ሰዎችን የማከሙ ነገር በጣም ብዙ ጊዜ እንዳይኖረው ነው ያደረገው። ስለዚህም አጠገቧ ሆኖ ሊጠብቃት እንደማይችል ስለምታውቅ ለእሱ ነገሩን በመንገር ማስጨነቅ አትፈልግም፡፡
ከሬስቶራንቱ ወጥተው ክሊኒኩ ወደሚገኝበት የስድስት ብሎክ ርቀት
ሲጓዙ ከበሉበት ሬስቶራንት አጠገብ ያሉት ውድ ውድ የድሮ ዕቃ መሸጫ እና ውድ ልብሶች መሸጫ ሱቆች 1920 ላይ ወደ ተሰሩት የጎጆ ኢንዱስትሪ ማምረቻ ህንፃነት እየተቀየሩ መጡ፡፡ በሰንሰለት የተዘጉ የህንፃ በሮች ሥር የበቀሉ አረሞች አሉ። ወደፊት እየተራመዱ ባሉበት ሰዓትም መንገዱ ዳር
ላይ የወዳደቁ የድሮ ጋሪዎች አሮጌ ጫማዎች፣ የተበላሹ ሳይክሎች
ወዳድቀው ይታያሉ። በዚህ አይነት ስድስት ብሎኮችን ተራምደው
እንደጨረሱ ኮርነር ላይ አንድ ሙሉውን ነጭ ቀለም የተቀባ በእንጨት
የተሰራ ክሊኒክ ጋ ደረሱ፡፡

👍1
የክሊኒኩ በር ላይም “የሮበርትስ እና ዶፎ ክሊኒክ
ሁላችሁም እንኳን በሰላም ወደ እዚህ መጣችሁ” የሚል ፅሁፍም ተፅፎበታል።
“ይሄው ደረስን” ብሎ ሀዶን ወደ ኒኪ ዞረ እና “እንዴት አገኘሺው? መቼስ በህይወት ቢኖር እና ቢመለከተው የሚወደው ይመስለኛል” አላት። ይህንን የሰማችው ኒኪም ስሜቷን ተቆጣጠረች እና “አዎን በእውነቱ ይወደው ነበር” አለችው፡፡
ወደ ህንፃው ውስጥ እንደገቡም ውጪ ያለው በተስፋ የተሞላ የነጭ ህንፃ ስሜት ልክ እንደ አረፋ ፊኛ ፈነዳባት። ወንድ እና ሴቶች አብዛኛዎቹ ወንዶች ናቸው፡፡ የክሊኒኩ ኮሪደር ላይ ቁጭ ብለው ወይንም ደግሞ አጎንብሰው ጉልበቶቻቸውን እንደያዙ አቀርቅረው በሚያሳዝን የስቃይ ስሜት ውስጥ ሆነው ይታያሉ፡፡ አንዳንዶቹ ታካሚዎች ከፕላስቲክ በተሰራው ከግድግዳው ጋር በተጣበቀ ወንበር ላይ ተቀምጠዋል። በሌሎቹ ሁለቱ በሽተኞች ወረፋ ይዘው በሚገኙት ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ደግሞ በተለያዩ የሱስ ደረጃዎች ውስጥ የሚገኙ ሱሰኞችና ህክምና እንዲደረግላቸው እየጮሁ ወይም እያጓሩ ነርሶቹን የሚያስቸግሩ ናቸው።
በእንደዚህ ሁኔታ ከሚያስቸግሩት ወንዶች መሀል ግን የኒኪ አይንን የሳቡ ሁለት ጎረምሶች ነበሩ። ፊታቸው እና ሰውነታቸው በጣም ከመክሳቱም በላይ የቆዳቸው ቀለም ሙሉ በሙሉ አረንጓዴ ስለሆነ በጣም ያስፈሩ ነበር።ከፊታቸው፣ ከእጃቸው እና ከክንዳቸው ላይም ልክ ከግድግዳ ላይ እየተፋቅ የሚወድቅ አይነት ቆዳ ነው ያላቸው:: የልጆቹ ፊት ላይም ፍፁም ተስፋ መቁረጥ የሚታይበት ሲሆን የህክምና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ነበሩ።
“ሄሮይን ነው አይደል? ብላ ኒኪ በሀዶን ጆሮ ሹክ አለችው እና “ምስኪን
ሲያሳዝኑ። ደማቸው እኮ የተመረዘ ነው የሚመስሉት” አለችው፡፡
ህዶንም ለጥያቄዋ መልስ ከመስጠቱ በፊት ወደ ቢሮው አስገባት እና በሩን ዘግቶ እንድትቀመጥ አደረጋት፡፡
“ሄሮይን አይደለም” ብሎ ለኒኪ ነገራት፡፡ እናም “ግን ከእሱ ጋር ተመሳሳይነት ያለው የዴይስሞርፊን ዴሪቬቲቭ ነው። ስሙ ኮሮኮዳይል ወይም ደግሞ በሩስያኛ ክሮክዲል ይባላል፡፡ ይህንን ዕፅ ወደዚህ የሚያስገቡት ደግሞ ሩሲያውያን ናቸው።”
“ስያሜው የወጣለት የቆዳን ቀለም ልክ እንደ አዞ ቆዳ ቀለም
ስለሚለውጠው ነው?” ብላ ኒኪ ጥያቄዋን አቀረበች። ሀዶንም በአዎንታ ራሱን ነቅንቆ “በጣም በሚያሳቅቅ ሁኔታ ነው ተጠቃሚውን የሚጎዳው። ዶውግ
ስለዚህ የዕፅ አይነት ነግሮሽ አያውቅም?”
ኒኪም ራሷን በአሉታ ወዝውዛ “አይመስለኝም” አለችው፡፡
“ይሄ አደንዛዥ ዕፅ አሁን ላይ ሎስ አንጀለስ ውስጥ አዲስ አደንዛዥ ዕፅ
ነው።” ብሎ ይበልጥ እያብራራላት “ሩስያውያንና ሜክሲካውያን እዚህ
ከሚገኘው የአደንዛዥ ዕፅ ቢዝነስ ገፍተው ሊያስወጧቸው ይፈልጋሉ።
ወይም ደግሞ ከሩስያውያን ጋር በከፍተኛ ፉክክር ውስጥ ይገኛሉ። በሁለቱ
አደንዛዥ ዕፅ አቅራቢዎች ፉክክር የተነሳ ግን በጣም እየተጎዱ ያሉት እንደነዚህ ያሉት ልጆች ናቸው፡፡ እናም ክሮክ የተባለው አደንዛዥ ዕፅ አሁን ላይ የአደንዛዥ ዕፅ አቅራቢዎች ዋነኛው ትውልዱን መግደያ መሳሪያቸው
ነው።”
“ችግር የሚሆነው ደግሞ ለምን መሰለሽ? አደንዛዥ ዕፁ በጣም በቀላሉ
በቤት ውስጥ መዘጋጀት የሚችል መሆኑ ነው፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ እነዚህ
አደንዛዥ ዕፆች ውስጥ የተለያዩ ብዙ ነገሮች ይገኛሉ ማለት ነው። የግድግዳ
ቀለሞች ሀይድሮክሎሪክ አሲድ እና ሌሎችም ንጥረ ነገሮች ይገኙበታል። ይህ
አደንዛዥ ዕፅ ሩስያ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ሲጠቀሙበት ነበር። አሁን ላይ
ደግሞ እዚህ እንደ አዲስ ሥር እየያዘላቸው ነው::”
“እንደዚህ አይነት በዕፅ የተጎዱ ብዙ ህፃናት አይተህ ታውቃለህ?” ኒኪ አረንጓዴ ቆዳ ያላቸው ጎረምሳዎች ፊት ከውስጧ ስለቀረባት ጥያቄን አቀረበችለት።
“አዎን በየሳምንቱ እንደዚህ አይነት ልጆች ይገጥሙናል” ብሎ ሀዶን መለሰላት እና በማስከተልም “ያው ቅድም እንደነገርኩሽ ነገሩ የንግድ ጦርነት ነው፡፡ ሩሲያውያኖቹ ይህንን በውስጡ ብዙ ንጥረ ነገር ያለውን አደንዛዥ እፅን ለተጠቃሚዎች ያቀርባሉ፡፡ አሁን ላይ ደግሞ ሜክሲካውያኑ ምርጥ
ንፁህ እና ከሩሲያኖች የተሻለ ክሮክን በማቅረብ የንግድ ፉክክሩን እያጦዙት
ነው፡፡ በእርግጥም ሚክሲካውያኑ የሚያቀርቡት ምርት ከሩስያኖቹ ጋር
ሲነፃፀር ዋጋው ውድ ቢሆንም አሁንም ቢሆን በቀላሉ የሚገኝ እና ርካሽ
ነው።”
“የማግዝህ ነገር ይኖራልን?” ብላ ኒኪ በቅንነት ጥያቄዋን አቀረበች::
ሀዶንም ለእሱ ሀሳብ የእርዳታ እጇን ለመዘርጋት በቅንነት ስለጠየቀችው
ልቡ ተነካ እና “አመሰግናለሁ የኔ ውድ” ብሎ እጇን ጨምቆ ያዘው እና በእውነት ጥያቄሽን ስላቀረብሽልኝ ደስ ብሎኛል። ግን አንቺ በጣም በብዙ ነገሮች ውስጥ ያለፍሽ ስለሆነ እና መረጋጋትሽንም የሚጠበቅ በመሆኑ አሁን ላይ እገዛሽ አያስፈልገኝም::” አላት።
“ዶውግ አንቺን ብዙ ጊዜ ሊንከባከብሽ ይፈልግ ነበር። እኔም ብሆን አንቺን ልንከባከብሽ ብችል ደስ ይለኛል፡፡ በተለይ ደግሞ አሁን ላይ ባለሽበት ስሜት ውስጥ በመሆንሽ ትሬይ እና ፍላንገን የተባለችው ታካሚሽ ላይ በደረሱት ነገሮች ጥሩ ስሜት ውስጥ እንዳልሆንሽ አውቃለሁ። በነገራችን ላይ ፖሊሶች በጉዳዩ (በወንጀሉ) ዙሪያ ያገኙት አዲስ ነገር አለ?” ብሎ ጠየቃት፡፡ ኒኪም “የለም” ብላ ድምጿ በቁጣ እንደተሞላ መለሰችለት፡፡ ፊቷ ላይ የነበረው የደስታ ስሜትም ጠፋ። ምናልባትም ባልጠበቀችው ጊዜ የሟች
ባሏ ሥም በመጠቀሱ ሊሆን ይችላል ፊቷ ሊኮሳተር እና የተረበሽ ስሜት
ሊታይበት የቻለው ሲል አሰበ፡፡
“ይቅርታ” ብሎ ሀዶን ተናገረ እና በመቀጠልም “አንቺን ለማበሳጨት
አስቤ አልነበረም” አላት፡፡
“ኧረ አላበሳጨኸኝም” ኒኪ ሊፈስ የቀረበውን እምባዋን እንዳይወርድ
እየታገለች “አሁን እኔ በጣም ደህና ነኝ” ብላ መለሰችለት።
ከዚያ በኋላም ክሊኒኩን በሚጎበኙበት ጊዜ ላይ ያገኘቻቸው የክሊኒኩ
ሰራተኞች እያቀፏት እና እየጨበጧት በባሏ ዶውግ ሞት የተሰማቸውን
የሀዘን ስሜት ይገልፁላት ጀመር፡፡ ለሰላሳ ደቂቃ ያህል ክሊኒኩን ጎብኝታ ከጨረሰች በኋላ ስትሰናበተው ኒክን አቀፈችው::
“ቅድም ስለሆንኩት ነገር ይቅርታ” አለች እና “ዶውግ እኔን ይንከባከበኝ ስለነበረው ነገር ስታወራኝ እኔን ስለደበቀኝ ነገሮች ማሰብ በመጀመሬ የተነሳ ነው እንደዚያ የሆንኩብህ፡፡ ሁሉንም ሚስጥሮቹን። ያው ለእኔ በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነበር ታውቃለህ መቼስ?” አለችው። “ይገባኛል” አላት እና ደፎ እቅፍ አድርጎ ወደ እራሱ አስጠጋት፡፡ በመቀጠልም
“እኔን ይቅርታ ማለት አይጠበቅብሽም፡፡ በቃ ለራስሽ ብቻ ትኩረት ለመስጠት ሞክሪ ኒኪ። ወደ ኋላ ሳይሆን የወደፊቱን ህይወትሽን ተመልከቺ።” አላት።
ኒኪ ፈገግ ብላ “እሺ ዶ/ር ዶፎ እስቲ እንዳልከኝ ለማድረግ እሞክራለሁ”
ተሰናብታው መኪናዋን አስነስታ ስትወጣ ሀዶን የብሎኩ ጥግ እስከምትደርስ እና ታጥፋ ከአይኑ እስከምትሰወር ድረስ ቆሞ ይመለከታት ጀመር። በቆመበትም ጠንክራ ያለፈውን ህይወቷን እንድትረሳ እና ወደፊት እንድትቀጥል ፀሎቱን አደረሰ። ምክንያቱም ለሁለቱም ከዚያ የተሻለ ነገር የለም።
ዶክተር ሀዶን ዶፎ አንድ አንድ በሮች አንድ ጊዜ ከተዘጉ በኋላ
እንደማይከፈቱ ከማንም በተሻለ ያውቃል። ሟቹ ጓደኛው ዶውግ ሮበርትስ ደግሞ እሷ ከምታውቀው በላይ
ይጠብቃት እና ይንከባከባት ነበር።
✨ይቀጥላል✨

#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
....ሶስና ነበረች የመለመለቻት…አንድ በአንድ ይታወሳታል... ጓደኛዋ ሶስና ነበረች የመለመለቻት፡፡
ርብቃ ሶስናን የምታውቃት በዩኒቨርስቲ ዓመቶቿ ነው፡፡ ሁለቱም የቋንቋ ተማሪዎች ነበሩ፡፡ ከትምህርት ዓለም ተሰናብተው ወደ ሥራ ዓለም ሲሸጋገሩ ሶስና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ርብቃ ደግሞ በማስታወቂያ ሚኒስቴር ሥራ ያዙ፡፡
የሥራ ቦታቸው መለያየት ሊለያያቸው የሚችል ቢሆንም አልተራራቁም፡፡ ቢያንስ በሣምንት አንዴ እየተገናኙ አብረው ጊዜያቸውን ያሳልፉ ነበር፡፡ በመጨረሻም የለያያቸው ሶስና በአንደኛ ፀሃፊ የሥራ መደብ ካይሮ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መሄዷ ነበር፡፡
ባለፈው ዓመት መጨረሻ ገደማ ላይ ነበር፡፡ ከሥራ ሰዓት በኋላ ዘወትር እንደሚያደርጉት ቀጠሮ ተሰጣጥተው ተገናኝተው ሲጫወቱ አመሹ፡፡ ወደ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ ሶስና ድንገት ተነስታ ቀጠሮ እንዳላት ስትነግራት ርብቃ አዲስ ነገር ሆነባት።
“በዚህ ሰዓት?” አለች መምሽቱን ተመልክታ፡፡
አዎ ርብቅዬ... ማታ ማታ ነው የምንገናኘው።”
“ማነው ባክሽ?” አለች ርብቃ እየተሽኮረመመች፡፡
“ኦ! ወንድ መስሎሽ ነው እንዴ አይደለም ጓደኞቼ ናቸው፡፡”
“እኔ የማላውቃቸው ጓደኞች! ሂ! ሂ! ሂ!” ርብቃ ሳቀች ጓደኛዋ የደበቀቻት ምሥጢር እንዳለ በማመን፡፡
“ርብቃ ሙች እንዳስብሽው አይደለም፡፡ ምን መሰለሽ በእርግጥ አታውቂያቸውም፡፡ እኔም ቅርብ ጊዜ ነው የተዋወቅኋቸው.. እና አልፎ አልፎ ተገናኝተን በተለያዩ አርዕስቶች ላይ እንነጋገራለን፡፡”
“ምን ልትፈጥሩ?” “ አለች ርብቃ ጓደኛዋ የምትለው መላቅጡ ሲጠፋት፡፡
“የተሻለ ዓለም!” አለች ሶስና ጓደኛዋ ትኩር ብላ እየተመለከተቻት ምን መሰለሽ .. ” አለች የርብቃን መደናገር ስታይ፡፡ “በአንድ ርዕስ ላይ ስትከራከሪ የተለያዩ ሃሳቦችን ታገኝያለሽ፡፡ ጭንቅላትሽ ይሰፋል አስተሳሰብሽም ይዳብራል፡፡”
“እና ለመከራከር ተቀጣጥራችሁ ትገናኛላችሁ ማለት ነው?”
“አዎ አንድ ርዕስ እንመርጥና እንዘጋጅበታለን፡፡ ለምሳሌ ስነጽሁፍ …ወይ…ኋላቀርነት ወይ አፍሪካ በቃ እንድ ርዕስ ከዛ በርዕሱ ላይ እያንዳንዳችን እንዘጋጅና ተገናኝተን የሰበሰብነውን
እንለዋወጣለን! እንከራከራለን፡፡” .
“ጥሩ ነው ሃሳቡ፡፡” አለች ርብቃ ቦርሳዋን እያነሳች:: “በይ ከሄድሽ ቶሎ እንሂድ፡፡ እንዳይመሽብሽ፡፡”
“ለምን አብረን አንሄድም?”
“የት?!” አለች ርብቃ ጓደኛዋ ላይ አፍጥጣ፡፡
“አሁን ያልኩሽ ቦታ ነዋ::”
“አበድሽ እንዴ? ደግሞ እኔ ምንድነኝ? አንቺኮ ጓደኞችሽ ስለሆነ…”
“አይደለም. አይደለም:: ባይገርምሽ አብዛኛዎቻችን የተዋወቅነው
እዛው ነው:: እየሽ እያንዳንዱ አባል ብስለት አለው የሚለውን ሰው መጋበዝ
ይችላል፡፡እና ተጋባዥ እንድ ፕሮግራም ይካፈልና ከጣመው አባል ይሆናል፡፡”
“ሌላ ጊዜ።” አለች ርብቃ የጓደኛዋን ክንድ ይዛ ከነበሩበት ቡና ቤት እየወጡ፡፡
ለምን? ነይና እይው፡፡ ምንም መናገር አያስፈልግሽም፡፡ ዝም ብለሽ ተቀምጠሽ እኛ ስንወያይ ታዳምጫለሽ፡፡ እንዳልኩሽ ፕሮግራሙ የሚጠቅምሽ ከመሰለሽ… እያየሽ ትቀጥያለሽ፡፡ ማን ያውቃል ብዙ ነገር ታስተምሪን ይሆናል፡፡ ጋዜጠኛ መሆንሽን ሲያውቁማ ወጥረው ነው የሚይዙሽ፡፡” ሶስና ገፋፋቻት፡፡
“ጋዜጠኛ ለፍላፊ ነው ለማለት ነው ብሽቅ!” አለች ርብቃ ጓደኛዋ
የወትሮውን ብሽሽቅ የጀመረች መስሏት፡፡
“አይደለም... አየሽ ጋዜጠኞች በተለያዩ አርዕስቶች ላይ ስለምትስሩ ከተራው ሰው የተሻለና ሰፋ ያለ እውቀት ይኖራችኋል፡፡ ይህ ደግሞ የሚያከራክር አይደለም፡፡ የኛ ጋዜጠኞች ደግሞ ዋዛዎች አይደላችሁም፡፡
“እ…እ”
“ሙች ሙች ከምሬ ነው:: ሌላውን ብንተወው እንኳን… ለየግላችሁ ያላችሁ ዕውቀት የሚናቅ አይመስለኝም:: ብቻ እስቲ ነይና እይው።”
“እረ በናትሽ ሳይጠሩኝ ሰተት ብዬ ቤታቸው ስሄድ ምን ይለኛል?
“በደስታ የሚፈነድቁት ርብቃ ሙች! አዲስ ሰው በመጣ ጊዜ ምን ያህል እንደምንደሰት ብታውቂ… አዲስ አስተያየት፤ አዲስ አመለካከት ማለት ነው!”
“ግን ታመሹ እንደሆነ?”
“ምንም ችግር የለም። መኪና የሚይዙ ስላሉ ሁላችንን በየቤታችን የሚጥሉን እነሱ ናቸው፡፡ እሱ አያሳስብሽ…እሺ በቃ እንሂድ… እሺ?” ውጥር አድርጋ ያዘቻት፡፡
“ግን… እንጄ.…” እያለች ነበር ርብቃ ለመሄድ የተስማማችው::
ታክሲ ተሳፍረው በንፋስ ስልክ መስመር ወደ ጎተራ አቅጣጫ አመሩ፡፡ መሃል ላይ ሶስና “እዚህጋ ይበቃናል፡፡” ብላ ታክሲውን አስቁማ ሲወርዱ ሊጨልም ዳድቶት ነበር፡፡ አንድ ሰዓት ከአሥር፡፡
“አርፍደናል፤ከአንድ ሰዓት በፊት መገኘት ነበረብን፡፡” አለች ሶስና ከዋናው መንገድ በስተግራ ተገንጥሎ ሽቅብ ወደሚወጣ መንገድ እያመራች።
ጎን ለጎን እየተራመዱ በዝምታ ቀጠሉ። ከአንድ ግራጫ ቀለም ከተቀባ
የብረት በር አጠገብ ሲደርሱ ሶስና ጠጋ ብላ መጥሪያውን ተጫነችው።
አራት ማዕዘን ቅርፅ ያላት ትንሽ የስርቆሽ በር ተከፈተችና አንድ ሰው አጮልቆ ተመለከታቸው። ሶስና ምንም ሳትናገር ጠጋ ብላ ፊቷን አሳየችው፡፡ የስርቆሽ በር ተዘጋችና ዋናው የብረት በር ተከፈተላቸው፡፡ ገቡ፡፡
ርብቃ ከማታውቀው ቤት ሳትጠራ በመምጣቷ እፍረት ቢሰማትም
ውስጥ ገብታ ጉዷን እስክታየው ቸኮለች። ከፊት ለፊት ያለው ቤት ትልቅ ሳይሆን ቀልብጭ ብሎ በጥሩ ሁኔታ የተያዘ ይመስላል፡፡ ምናልባት በቅርብ
ጊዜ የተሰራ ስለሆነም ሊሆን ይችላል፡፡ ከፊት ለፊት የሚታዩት ሁለት
መስኮቶች ተዘግተዋል፤በግቢው ውስጥ ከጥግ እስከጥግ እንደምንጣፍ
የተነጠፈው አስፋልት መሐል የሚታይ የአትክልት ዘር የለም፡፡ ቤቱ
ሕይወት ያለበት አይመስልም፡፡
የገዛ ቤቷ እንደሆነ ሁሉ ሶስና ነይ፡፡ አይዞሽ አትፍሪ” እያለች የዋናውን ቤት የፊት በር ከፍታ ገቡ፡፡ ከውስጥ የተቀበሳቸው ጨለማ ነበር፡፡
በጠባቧ መተላለፈያ ውስጥ ባለው ደብዘዝ ያለ ብርሃን ሦስት የተዘጉ በሮች
ይታያሉ፡፡ ስልክ የተቀመጠበት ትንሽ ጠረጴዛና ወንበር ጥግ ይዘዋል፡፡
በተረፈ ምንም የለም:: ድንገት የታፈነ የሚመስል ድምፅ በስተቀኝ በኩል
ካለው በር ጀርባ መጣ፡፡ ሰዎች የሚነጋገሩ ይመስላል በለሆሳስ፡፡
ነይ እንጅ…” አለች ሶስና በስተቀኝ ወዳለው በር እያመራች፡፡ ርብቃ
ከተል አለቻት፡፡
ከውስጥ የተቀበላቸው ክፍል ከመተላለፊያው የተሻለ ብርሃን ያለበት
ቢሆንም እዚያም ያለው ጨለማ ለአይን የሚከብድ ነበር፡፡ እራቅ ካለ ማዕዘን
የቆመው ባለ ረጅም ቋሚ መብራት ድብዝዝ ያለ ብርሃን ይተፋል፡፡ ከቋሚ
መብራቱ ቀይ ጨርቅ የሚፈሰው ብርሃን ቤቱን ፍም አስመስሎታል፡፡
“ይቅርታ ስላረፈድን፡፡ አንደምን ዋላችሁ።” አለች ሶስና በደፈናው፡፡
በሳሎኑ ክፍሉ ውስጥ ሰዎች ተቀምጠዋል፡፡ ወዲያ ማዶ የተዳፈነው
ቀይ ብርሃን አጠቃላይ ቁመናቸውን እንጅ ገፅታቸውን ጥርት አድርጎ አያሳይም።
“ዛሬ አዲስ እንግዳ ይዤ ነው የመጣሁት።” አለች ሶስና የርብቃን
እጅ ይዛ ወደ ሳሎኑ እየተጠጋች፡፡
ማናቸውም ድምፅ አላሰሙም፡፡ በተቀመጡበት “ጭንቅላታቸውን
እያነቃነቁ ስምምነታቸውን ሲገልፁ ርብቃ በጨለማ ውስጥ ሸንጎ የተቀመጡ
አማልክት መሰሏት።
ሶስና ከማናቸውም ጋር አላስተዋወቀቻትም::የርብቃን ስም አልተ
ናገረችም፡፡ አንድ ፎቴ ላይ እንድትቀመጥ ካመለከተቻት በኋላ ከወደጥግ ካለ
ጠረጴዛ ላይ ወደ ተቀመጠች አነስተኛ ማቀዝቀዣ ሄዳ ከፈተቻት፡፡ ለአንድ
አፍታ ከማቀዝቀዣዋ ውስጥ የወጣው ብርሃን በሳሉን ክፍል ውስጥ ሲናኝ
ርብቃ ከፊት ለፊቷ የተቀመጡትን ሦስት ሰዎች ተመለከተቻቸው… ሁለቱ
ወንዶች ሲሆኑ በስተቀኝ ዳር ያለችው ሴት ነች… በስተግራዋ

የተቀመጡትን ሰዎች ግን ለመመልከት አልቻለችም፡፡ የማቀዝቀዣዋ ብርሃን ከጀርባቸው
ነበር፡፡
ወዲያው ሶስና ማቀዝቀዣዋን ስትዘጋ ክፍሉ በቀድሞው ጨለማ ውስጥ ሰመጠ፡፡ ሶስና ከማቀዝቀዣዋ ውስጥ ያወጣቻቸውን ሁለት የኮካኮላ
ጠርሙሶች ይዛ ከጠረጴዛው ላይ ከተደረደሩት ብርጭቆዎች መሃል ሁለቱን
አንስታ ይዛ ተመለሰችና ርብቃ ጎን ተቀመጠች፡፡ጠርሙሶቹን ከፍታ ከቀዳች
በኋላ ቀና አለች፡፡
“ይቅርታ…አቋረጥናችሁ…?”
ችግር የለም። ገና ስንጀምር ነው የደረሳችሁት።” አለ ፊት ለፊት
የተቀመጠው ዕው፡፡ ድምፁ ረጋ ለዘብ ያለ ነው፡፡ ወዲያው በስተግራ
ወደተቀመጠው ሰው ዞር አለና “እሺ ቀጥል፡፡” አለ፡፡
“አዎ… እና …እንዳልኩት ሁላችንም ባርያዎች ነን…” አለ በስተግራ
የተቀመጠው ሰው በዙሪያው የተኮለኮሉትን ሁሉ በተራ እየተመለከተ
“ባርያ!” አለ ድጋሚ ጮክ ብሎ፡፡ “የካሊፎርኒያው ነጭ የስነልቦና ሊቅ
አርዘር ጆንሰኝ እንዳለው በዝቅተኛ የአእምሮ የዕድገት ደረጃ ላይ በሰውና
በዝንጀሮ መሃል የምንገኝ ፍጡሮች ነን እኛ አፍሪካውያን፡፡ ይህንን ባንቀበል
ደግሞ ተጨማሪ ድንቁርና ይሆንብናል፡፡ ማለቴ ባርነታችንን፡፡ እዚህ ላይ
ባርያ ስል ማስተዋል የጎደለው ለራሱ ሊቆም የማይችል አሳፋሪ ዝርክርክ
ተቀጥላ ፍጡር ማለቴ እንጅ ምናልባት አንዳንዶቻችሁ እንደምታስቡት
ጥቁርና ለንቦጫም ማለቴ አይደለም፡፡ በፍጹም! እስቲ አዲስ የመጣችውን
ልጅ አንድ እንቆቅልሽ ልጠይቃት…” አለ ሰውየው ድንገት ወደ ርብቃ ፊቱን
መልሶ፡፡ “አስቢው! ይታይሽ የገዛ ከርሱን ሊሞላበት ከውጭ የሚጠብቅ ፡
የገዛ ገላውን ሊሸፍንበት ከውጭ የሚጠብቅ፤ በባዕድ ዳንኪራ እየረገጠ እርስ በርሱ የሚናከስ ዝንጀሮ ማነው? ንገሪኝ አለዛ አገር ስጪኝ!” ጮኹባት።
ርብቃ ተማታባት።
“አለቀ!” አለ ኣለመናገሯ ስምምነት እንደሆነ ሁሉ። “አፍሪካዊ ነው
ባርያ!”
ለአንድ አፍታ በክፍሉ ውስጥ ፀጥታ ነገሠ።
“እንቆቅልሽ ለእኔ ቀርቦ ቢሆን ኖሮ 'አፍሪካዊ' ሳይሆን ኋላቀር ህዝብ እለው ነበር መልሱን፡፡” አለ በስተግራ ከተቀመጠት ሰዎች ሁለተኛው፡፡ “በዓለማችን ኋላቀር የሆንን ህዝቦች ደግሞ አፍሪካውያን ብቻ ነን ለማለት ያስቸግራል፡፡”
ደቂቃዎች እየተሽቀዳደሙ በነጎዱ ቁጥር ክርክሩ እየጦፈ የተናጋሪዎች እልህ እየጋመ ሲመጣ ርብቃ በዝምታ አንድም ሳይቀራት ተከታተለቻቸው፡፡ ዝግጅቱ ኣልቆ ሲበተኑ ሶስና አብረው እንዲያድሩ ስለጠየቀቻት ከተሰብሳቢዎቹ መሃል አንደኛው ሁለቱንም በመኪናው ሶስና ቤት ድረስ አድርሷቸው ተሰናብቷቸው ተመለሰ፡፡
ሶስና የቤቷን በር ከፍታ እስኪገቡ አልተነጋገሩም ነበር፡፡
“ሶስና...ግን ያ ሰውዬኮ እውነቱን ነው፡፡ መጀመሪያ ሲናገር በጣም ነበር ያበሸቀኝ::ማለቴ… ባርያ ነን ሲል፡፡ ግን በኋላ ባስበው የጨፈነኝ አጉል ኩራት መሆኑ ገባኝ፡፡” አለች ርብቃ ወደ ውስጥ እንደገቡ፡፡
“እንዴት?” አለቻት ሶስና ትኩር ብላ እያጠናቻት፡፡
“አስቢው እስቲ፡፡ እውነቱንኮ ነው፡፡ ባርያ ማለት ልዩ ፍጠር ማለት አይደለም:: የራሱን መብት ማስጠበቅ የማይችል ማለት ነው፡፡ እስቲ የትኛው አፍሪካዊ ኣገር ነው በሁለት እግሮቼ ቆሜአለሁ ብሎ አፉን ሞልቶ የሚናገር? ታዲያ በሁለት እግሩ መቆም ያልቻለ ህፃን ሲሰጡት ከመቀበል ሲከለክሉት ከመነጫነጭ አልፎ በየት አገር ነው መብቱን የሚያስጠብቅ? አንቺ እማምላክን ዛሬም ባርያዎች ነን!” የተናገረችው ለራሷ የቀፈፋት ይመስል ርብቃ እጇን አፏ ላይ ጫነችው፡፡
ከዛን ቀን ጀምሮ በየሳምንቱ ሁለት ሁለት ቀን እዚያው ቤት እየተመላለሰች ለአራት ወራት ዝግጅቱን ስትካፈል ቆየች። መረቡ እንደ ሸረሪት ድር ከተበተባት ኣጥማጆቿ እንዳቀዱት አፍሪካዊነቷ ነፍስ ዘርቶ
እንደ ሽል ሆዷ ውስጥ መገለባበጥና መራገጥ ከጀመረ ሰኋላ ነበር ሁኔታው
የተገለፀላት፡፡
ለአራት ወራት እብረዋት ተቀምጠው ሲከራከሩና ሲፋተጉ የነበሩ ሁሉ ይሰሩት የነበረው ቲያትር መሆኑን የተገነዘበችው እጅግ ዘግይታ ነበር፡፡ ሁሉም የያዙት አቋም አንድ ነበር፡፡ወክለው የሚከራከሩት ወግነው የሚፋተጉት ግን የእሷኑ ህሊና ግራና ቀኝ ነበር፡፡ ሳታውቀው ሳትገነዘበው
መረባቸው ውስጥ ገባች፡፡ አይኖቿ በሩላት፡፡ እሷም እንደ ኣጥማጆቿ ሌሉች
አይናቸው ያልበራላቸውና ኣይናቸው የሞጨሞጩ እስቀያሚዎች ሲመጡ
“ባርያ! ባርያዎች ነን!” እያለች እልህ ዘራች፤ቁጭት አበቀለች፤አፍሪካዊነት አጨደች፣ቆንጆዎች አመረተች።
ስብሰባውን መካፈል በጀመረች በስባተኛው ወር ነበር በህቡዕ
ድርጅቱ ውስጥ በአፍሪካዊነቷ ልታገለግል በመሉ ልብ ቃል የገባችው::
መጀመሪያ ቀን በተለበለበችባት ጨለማ ክፍል ወስጥ በክፍሉ ውስጥ የእሷው ብጤ አዲስ ተጠማቂዎች ተሰብስበዋል
ስምንት፡፡ ሌሎች የማታውቃቸው እንግዶችም በሥነሥርዓቱ ላይ ተገኝተው
ነበር፡፡ ክፍሉ ውስጥ በአጠቃላይ ያለው ሰው ሃያ ይደርሳል፡፡ አብዛኞቹ በእርሷ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ መሃል ፎቴው ላይ ቦታ የተለቀቀላቸው አራት ሰዎች ግን በዕድሜ የገፉ ነበሩ፡፡
ሰዎቹ የተገኙት ዝግጅቱን ለመምራትና አዲስ አባላቱን ለመቀበል ነበር፡፡ ርብቃ በደብዛዛዋ ብርሃን ውስጥ ተመለከተቻቸው፡፡ ሦስቱን ሰዎች
በፍጹም አታውቃቸውም…. በግራ በኩል ጥግ ላይ የተቀመጡትን አንደኛውን
ሰው ግን ለይታ ስማቸውን ባትጠራም ከዚህ በፊት መልካቸውን ማየቷ ትዝ
ያላታል፡፡ ቢሆንም የት እንደሆነ ልታስታውስ እልቻለችም::
ዝግጅቱ እንደተጀመረ ከአራቱ አዛውንት አንደኛው ንግግር አደረጉ፡፡
“ከሰላሳ ዓመታት በፊት በ1963 አዲስ አበባ ላይ ከየአቅጣጫው የተሰበሰበው የጥቂት ነፃ አፍሪካ አገሮች መሪዎች ስብሰባ ላይ ተገኝቼ ነበር፡፡ያኔ እኔም እንደ እናንተ ገና ትኩስ ጎልማሳ ነበርኩ::” አሉ ከተቀሩት ሦስት አዛውንት በዕድሜ ላቅ ያሉ የሚመስሉት የመሃለኛው:: ደብዛዛው ቀይ ብርሃን በትልምና በደረጃ በተከፋፈለው ፊታቸው ላይ ሲያርፍ የቀለጠ ነሃስ አስመስሏቸዋል፡፡ ቀዩ ብርሃን ሊነካው ዝገት የሚመስለውን ሽበት የበዛበት ፀጉራቸውን ..እንደ ጧፍ የሚንቀለቀለውን አይናቸውን በእምቢተኝነት ቀጥና ቀና ያለ ትከሻቸውን ስትመለከት ርብቃ ሃውልት መስሏት፤ቅርስ፡፡
“ያኔ…” ቀጠሉ ፊታቸው የሃዘን ፈገግታ ለብሶ፡፡“ያኔ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ የተስፋ ጸዳል ይንቀለቀል ነበር…ያኔ …ጠንካራ አፍሪካን ገንብተን ከሌላው የሰው ዘር ጋር ትከሻ ለትከሻ ልንቆም እርግጠኞች ነበርን፡፡ ከሰላሳ
ዓመታት በፊት…ድሮ፡፡ በስብሰባው ላይ የአፍሪካ አባት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ
የተናገሩት ምን ጊዜም ከአእምሮዬ አይጠፋም፡፡ አንድነታችን ከጊዜ ጋር
የምንቀዳጀው ነው፡፡ በቀን ተቀን በምናደርገው እንቅስቃሴ ጠንካራ
መሠረት ከጣልን ግንበኛውና መሣሪያው ከሰጠ… ጠንካራ ቤት እንገነባለን፡፡ ነበር ያሉት፡፡ ሰላሳ አመታት አለፉ። ያ ቤት አሁንም አልቆመም።ይብሱን የተጣለው መሠረት ይሰነጣጠቅ ጀመር! የግንበኛው አላዋቂነት ይሆን ወይስ ግንበኞች በዙ? ልባም ሠራተኛ ጠፋ? ወይስ በጣሽ ቀጣዩ ሂያጅ መጪው ፈላጭ ቆራጩ በረከተ? ”
የክፍሉ ፀጥታ ከመቃብር ከበደ።....

#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....ሎው ጉድማን ስታር ተብሎ ከሚጠራው የሎስ አንጀለስ መንገድ ላይ መኪናውን ሲያስገባ ፀሐይ መጥለቅ ጀምራ ነበር። የሴንቸሪ ሲቲ ትልቅ ፎቅ
ደግሞ በሎስ አንጀለስ ሐምራዊ ብርቱካናማ የምሽት ፀሐይ የሆነ ህልም
ውስጥ የሚገኝ ፎቅ መስሎ ቆሟል።
በመንገዱ ዳር እና ዳር የሚገኙት
የዘንባባ ዛፎችም በሞቃታማው ንፋስ ልክ እንደሰከረ ሰው ይወዛወዛሉ።
የፖሊስ ባጁን እንደያዘም የህንፃው እንግዳ ተቀባይ ዴስክ አጠገብ
በመድረስ “መርማሪ ፖሊስ ሉው ጉድማን የግድያ ወንጀል ምርመራ ፖሊስ
ነኝ፡፡ ክፍል ቁጥር 706 ን ለማየት ነው የመጣሁት እና ቁልፉን ትሰጪኝ”
አላት ላላቲኖዋ እንግዳ ተቀባይ ፈገግ እያለ፡፡ ልክ እንደሁልጊዜው የፍርድ
ቤት ማዘዣ ወረቀት ሳይዝ እንደሚያደርገው ማለት ነው፡፡
ልጅቷም የአፀፋ ፈገግታዋን ለግሳው እና በውስጧም ኮሌምቢያ ውስጥ ከምታውቃቸው ፖሊሶች የተሻለ መልካም ፀባይ እንዳለው እያሰበችም “ አለኝ፡፡ ግን አያስፈልግህም፡፡ ዶክተር ሮበርትስ ቢሮዋ ከገባች አንድ ሰዓት አልፏታል። አሁንም ቢሮዋ ውስጥ ትገኛለች፡፡ በግራ በኩል ያለውን አሳንስር መጠቀም ትችላለህ አለችው።
"አመሰግናለሁ” አላት መብሸቁን ለመደበቅ ፈገግ እያለ፡ ጉድማን የኒኪ
ቢሮ ውስጥ ብቻውን በመግባት ቢሮዋን መበርበር ነበር የፈለገው፡፡ በዚህ
ሰዓት ምን ትሰራለች? ብሎ ራሱን ጠየቀ፡፡ ግን ቢሮዋ ውስጥ እሷ መኖሯ ጥሩ ነው ብሎም አሰበ፡፡ ምክንያቱም ቀን ላይ ባልደረባው ጆንሰን እሷን ስላበሸቃት ብዙ ልትነግራቸው የምትፈልጋቸውን ነገሮች መናገር ትታ ነበር::ምናልባት አሁን እሱ ብቻውን ስለሆነ ይበልጥ ግልፅ ሆና ልታወራኝ ትችላለች ብሎ አሰበ እና ተረጋጋ።
በአሳንሰሩ ሰባተኛው ፎቅ ድረስ ወጣና በኮሪደሩ ላይ እየተራመደ የዶክተር ኒኪ ሮበርትስ ቢሮ ጋ ሲደርስ ቆመ፡፡ በሩ ገርበብ ብሎ ስለተከፈተም ወደ ውስጥ መሰስ ብሎ ገባ፡፡ ኒኪ ጀርባዋን ሰጥታ በወረቀት መክተፊያው ማሽን ውስጥ ወረቀቶችን እያስገባች ወረቀቶችን እየከተፈች ነበር፡፡ እግሯ ሥር ካስቀመጠችው ካርቶን ውስጥ ዶክመንቶችን እያነሳች ወደ ማሽኑ እየከተተች እና እየከተፈች ልትጨርስ ስትል
“እንዴት ነሽ?” የሚል ሰላምታን ስጣት፡፡
ኒኪም ድምፁን ስትሰማ በከፍተኛ ድንጋጤ ቀለሙ የተለወጠውን ፊቷን
ወደ እሱ በማዞር ፍርሃት በተሞላ አይን ተመለከተችው፡፡
“በእግዚአብሔር! በፍርሃት ነፍሴ ልትወጣ ነበር!” አለችው፡፡
“ይቅርታ” አላት እና እጇ ላይ የቀረውን ለማሽኑ ልታጎርሰው ያዘዘችውን
ፋይል በጉጉት እየተመለከተ
“ምንድነው የያዝሽው?” አላት፡፡
“ምንም አይደለም። ፅዳት እያካሄድኩኝ ነው::” አለችው እና ወረቀቱን ወደ ማሽኑ አፍ ከተተችው:: ማሽኑም ወረቀቱን እየሸረካከተ በዚያኛው ጎን
በኩል ሲተፋው ኒኪ “አታስብ ጠቃሚ የሆኑ የታካሚዎቼ ፋይሎች አይደሉም። ባልደረባህ መጥቶ ይህንን ሲያይ ይበልጥ የማያምንበት ነገር እንዳገኘ እንዳያስብ እና ይበልጥ እንደ ወንጀለኛ
ሌላ እኔን እንዳይመለከተኝ ደግሞ”
“እውነቱን ስለነገርሺኝ አመሰግናለሁ::” ብሎ ፈገግ አለ። ደግሞስ እንዲ
ዶክተር ኒኪ ያሉ ቆንጆ ሴቶች ፊት ሥርዓት ያለው ፖሊስ ሆኖ መተወን እንዴት ያቅተዋል?
“እና ቅዳሜ ምሽት እዚህ ምን እግር ጣለህ መርማሪ ፖሊስ ጉድማን?”
ብላ ማሽኑን እያጠፈች ጠየቀችው።
“ጠዋት ላይ ስለተፈጠረው ነገር ይቅርታ ልጠይቅሽ ነው የመጣሁት” አላት እና ውሸቱን በመቀጠልም መርማሪ
ፖሊስ ጆንሰን አንቺን እንደዚያ መናገር
አልነበረበትም።” አላት።
“መልካም” አለች እና ኒኪ በመቀጠልም “ግን እኮ ለጥፋቱ ይቅርታ መጠየቅ ያለበት እሱ እንጂ አንተ መሆን አልነበረብህም። አይመስልህም?”
ጉድማንም ትከሻውን ሰብቆ “እኔ እና እሱ ባልደረቦች አይደለንም። በዚያ
ላይ ደግሞ ለጥፋቱ ይቅርታ መጠየቅ አንደኛው የእሱ ችግር ነው እና እኔ
ልጠይቅለት ብዬ ነው” አላት።
ኒኪም ሳቀች እና “አሁን ገባኝ” አለችው። መርማሪ ፖሊስ ጉድማን ለማውራት ቀለል የሚል ሰው ስለሆነ ደስ ብሏታል “መቼስ እየዋሸሁ እንዳልሆነ ይገባሃል ብዬ አስባለሁ።” ብላ በማስከተልም “ባለፈው ምሽት እኔ የምኖርበትን ቦታ የሚያውቅ ሰው መኖርያ ሰፈሬ ድረስ መጥቶ በመኪና ገጭቶ ሊገድለኝ ነበር” አለችው፡፡
አምንሻለሁ” አላት እና ጉድማን በማስከተልም “ጆንሰንም ቢሆን
ያምንሻል። ምክንያቱም የምርመራ ቴክኒሽያኖችን ብዙ ብዙ ማስረጃዎችን
ከአካባቢው ላይ ሰብስበዋል”
“እውነትህን ነው?” ብላ ኒኪ የመገረም ፊት እያሳየች “ታዲያ ለምንድን ነው እኔን የቀን ቅዠተኛ እያለ የሚወነጅለኝ? እኔ ምን አድርጌ ነው?”
“እሱን እንኳን አላውቅም” ብሎ ለሰኮንዶች ያክል ዝም ብሎ ቆየ፡፡
ከዚያም “ምናልባት እኔ እና አንቺ ሆነን እሱ አንቺን ለምን እንደዚህ
እንደሚመለከትሽ ኋላ ላይ እንደርስበታለን፡፡ መጠጥ ልጋብዝሽ ዶ/ር
ሮበርትስ?”
ሎስ አንጀለስ ውስጥ ብዙ ሰው ወደማይበዛበት ጎዳና ታናስ ወደ ተባለ
ባር ይዟት ሄደ:: ኒኪ ጃክ ዳንኤልን አዘዘች እና ሲቀዳላት ብርጭቆውን
( ጉድማን አስተናጋጁ ሙሉውን ጠርሙስ ጠረጴዛው ላይ ትቶት እንዲሄድ
ሙሉውን መጠጥ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠችው። በዚህም የተበረታታው
በምልክት ነገረው እና ትቶላቸው ሄደ፡፡
“ባለፈው ምሽት ላይ እኔን መኪና ገጭቶ ሊገድለኝ የነበረው ሰው ሊዛን እና ትሬይን የገደለው ሰው ነው ብለህ ታስባለህ?” ብላ በቀጥታ ጠየቀችው።
“ምናልባት እራሱ ወይንም እነርሱን ከገደለው ሰው ጋር ግንኙነት ያለው ሰው ነው ብዬ አስባለሁ ብሎ ጉድማን
መጠጡን ተጎንጭቶ ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ገዳዩ አላማ ያደረገው አንቺን ነው ብዬ ነው የማምነው።” አላት፡፡
ኒኪ ለሊዛ ፍላንገን ባዋሰቻት የዝናብ ኮቷ የተነሳ ኒኪን መስላቸው በስህተት እንደገደሏት ጭምር ግምቱን ነገራት፡፡ በዚያ ላይ ባለፈው ማክሰኞ የተሞከረባት ግድያ የሚያመለክተው ኒኪ ከሊዛ እና ከትሬይ ጋር ባላት ግንኙነት ምክንያት ግድያዎቹ እንደተከወኑ ጭምር አስረዳት፡፡
“ልክ ነህ እንበል እሺ” ብላ ኒኪ በእርጋታ መለሰችለት እና “እሺ እነዚህ ሰዎች እኔን ለመግደል እየተከታተሉኝ ነው ልበል። ግን እነዚህ ሰዎች እኔን ለመግደል ለምንድነው የሚፈልጉት? ምንድነው ምክንያታቸው?”
“አሁን ላይ አንቺን ለመግደል ምክንያታቸው ምን እንደሆነ አላውቅም”
ብሎ ጉድማን በመቀጠልም “ግን ሊዛን እና ትሬይን የገደሉት ሰዎች ሁለቱንም ሰዎች አሰቃይተዋቸው ነው። ሰዎቹ ደግሞ ሰዎችን የሚያሰቃዩት
የሆነ መረጃን እንዲሰጧቸው ስለሚፈልጉ ነው። አይመስልሽም?” ብሎ
ጠየቃት፡፡
ኒኪም ለአፍታ ያህል ስታስብ ቆይታ “እኔም እንደዚያ አስቤው ነበር።
ግን ደግሞ ገዳዮቹ በሰዎች ስቃይ የሚደሰቱ ሳዲስቶች ቢሆኑስ?” ብላ
ጠየቀችው፡፡
ጉድማንም መጠጡ ያለበት ብርጭቆ ላይ እንዳፈጠጠ ይህም ሊሆን
ይችላል ብሎ አሰበ፡፡
“የሞቱት ሰዎች ላይ የሌለ የሞተ ሰው ህዋስ ተገኝቷል የሚባለው ነገር
እውነት ነው?” ብላ ኒኪ ጠየቀችው፡፡
ጉድማንም በጥያቄዋ በጣም ደንግጦ “ይህንን ደግሞ ማነው የነገረሽ?”
“ከኢንተርኔት ላይ አንብቤው ነው” ብላ ኒኪ በመቀጠልም “የዞምቢ ገዳይ በሚል ርዕስ ዙሪያ በኢንተርኔት ላይ ሰዎች ዜናውን እየተቀባበሉት ነው” አለችው፡፡
ጉድማንም በሰማው ነገር በጣም በሸቀ። ይህን የመሰለ መረቅ መረጃቸው ከእነርሱ አፈትልኮ ከወጣ በኋላ ደግሞ ነገሩ እየሰፋ ይሄድ እና የአሽሙር ጋዜጣ ገፆች ላይ ይወጣል ብሎ አሰበ፡፡
“እውነት ነው ነገሩ” ብላ ኒኪ ተጭና ጠየቀችው፡፡

“የሊዛ እና የትሬይ ገዳይ ዞምቢ ነው ተብሎ የሚወራው ነገር ውሸት ነው።” ብሎ ጉድማን ነገሩን ሊዘጋባት ሞከረ፡፡
“እና የሞተ ሰው ህዋስ በሟቾቹ ላይ አልተገኘም?”
“ስለ ምርመራው ዝርዝር ልነግርሽ አልችልም። ግን ይሄ ስለ ዞምቢ
የሚወራው ነገር የማይረባ ነው፡፡ ይልቅ እኔን ለምን መግደል ይፈልጋሉ?
የሚለው ጥያቄሽ ጥሩ ነው፡፡ ስለ ሳዲስትነት የተናገርሽው ነገር እንዳለ ሆኖ
እኔ ግን የማምነው ከግድያዎቹ ጀርባ የሚገኝ አንድ ሰው አንቺ የሆነ ነገር
እንደምታውቂ ያውቃል ብዬ እገምታለሁ። ይሄን ነገር ደግሞ ምናልባትም ትሬይ እና ሊዛ ያውቁታል ብለው ገዳዮቹ ያስባሉ። ይሄ ነገር ምን እንደሆነ አሁን ላይ እኔ ለማወቅ አልችልም። ምናልባት ስለታካሚዎችሽ ሊሆን ይችላል? የሆነ ሰው ተደብቆ እና ሚስጥር ሆኖ እንዲቆይለት የፈለገው ሚስጥር ሊሆን ይችላል? ወይንም ደግሞ ሟቹ ባለቤትሽ ያከመው እና ያዳነው ሰው ሚስጥር ሊሆን ይችላል... ግን ግምቴ” ብሎ ጉድማን ከመጠጡ በድጋሚ ተጎነጨ እና “ይህንን ገዳዮቹ እንዳይወጣባቸው የፈለጉትን ሚስጥር አንቺ እንደምታውቂ ነው::”
ኒኪም ግራ በተጋባ ፊት ጉድማንን እየተመለከተችው “ተሳስተሃል!
በእውነት ስለ እዚህ ስለምታወራው ነገር እኔ ምንም አላውቅም። ነገሩን ባውቅ እና ብረዳ ኖሮ ለእናንተ አልነግራችሁም ነበር እንዴ? እኔ እኮ ስለ ትሬይ በተለየ መንገድ ቢሆንም ስለ ሊዛ ደንታ አለኝ”
“ደንታ አለሽ?” ብሎ ቅንድቡን ቋጥሮ ጉድማን ጠየቃት፡፡
“አዎን ደንታ አለኝ።” ብላ ኒኪ በማስከተልም “ሙያዬ ለእሷ ደንታ
እንዲኖረኝ ያስገድደኛል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ስለ እራሴም ቢሆን ደንታ
አለኝ፡፡ እኔ መገደል የምፈልግ ይመስልሃል? ቤቴ ደጃፍ ላይስ በመኪና
ተደፍጥጬ መሞት የምፈልግ ይመስልሃል? እመነኝ ይህ ነፍሰ ገዳይ
ቢያዝንልኝ ከማንም በላይ ልቤ ያርፋል፡፡ ገባህ መርማሪ ፖሊስ ጉድማን”
“ሎው ብለሽ ጥሪኝ” ብሎ ጉድማን ለሁለቱም መጠጥ ቀዳና “እንዴ አንቺ
በገዳዮቹ ለመጎዳት ፈልገሽ እንዳልሆነ እኮ ይገባኛል፡፡ ይሄ ሊያስገድልሽ
የሚያስችለውን ነገርንም በግልፅ ታውቂያለሽ ማለቴ አይደለም፡፡ ግን በድብቁ የአዕምሮ ክፍልሽ ውስጥ ይሄ ነገር ተደብቆ ተቀምጧል። የዚህን እንቆቅልሽ መፍቺያ ቁልፍ ከአንቺ ጋር ይገኛል እና ቁልፉን ስታገኚው ነገሩ ሙሉ
በሙሉ ይፈታል ማለት ነው።” አላት፡፡
ብርጭቆውን አንስቶ መጠጡን ሲጎነጭ ኒኪም ብርጭቆዋን አንስታ መጠጧን ተጎነጨች። የሆነ የሞቅታ ስሜት እየተሰማት ነው። የተነጋገሩት
ነገር ሞቅታን ይልቀቅባት ወይንም ደግሞ መጠጡ እርግጠኛ አይደለችም::በዚያ ላይ ደግሞ እሱ ይሁን ወይንም እሷ ከሁለት አንዳቸው እጁን ቀድሞ
ሰድዶ ጣቶቻቸው ተቆላለፉ። ጣቶቻቸው ሲቆላለፉ ወደ ብልቷ አካባቢ ሞቅ
አላት። በተለይ ደግሞ ቀና ብላ ስታየው ከንፈሩን ምጥጥ አድርገሽ ሳሚው
ሳሚው የሚል ስሜት መጣባት። ይሄው ከብዙ ወራት በኋላ የወሲብ ስሜቷ
በጤነኛ መልኩ ስለተቀሰቀሰባት ደስ ብሏታል። ምክንያቱም ለአኔ ቤታማን
የሚሰማት ስሜት ሁሌም ግራ ይገባት ነበር።
እሱም ቢሆን ለእሷ የሆነ ነገር እንደተሰማው አይኑ ውስጥ
ያስታውቅበታል። ድምፁም ቢሆን ይሄንን ጥያቄ ሲጠይቃት ትንሽ ሻከር
ብሎበት ነበር።
“ለምንድንነው ሳይኮሎጂስት ለመሆን የፈልግሽው?” ብሎ ጠየቃት።
ይህንን ጥያቄ ከእሱ የምትጠብቀው ጥያቄ ስለነበርም ፈገግ አለች እና
“ምናልባት ተመሳሳይ እና አሰልቺ ሥራን የሚሠራ ባለሙያን መሆን ስላልፈለኩኝ ይሆናል፤ አለ አይደል የህግ ባለሙያ ወይንም አካውንታንት ከመሆን ይሄንን መረጥኩኝ። የመድህኒት ነገሮች ደስ አይሉኝም። ደም ማየት በጣም ስለምፈራ ደግሞ የቀዶ ጥገና ሀኪም መሆን አልችልም”
“እንደዚህ ድንጉጥ ነገር ነሽ እንዴ?” ብሎ እያሾፈ ጠየቃት፡፡
“እንደዚያ ነገር” አለች እና ትንሽ አፍራ “አንተ ለምን ፖሊስነትን መረጥክ?”
“ኸ” አላት እና ጉድማን ወንበሩን ደገፍ አለ እና ስሜቱ እና ፊቱ ላይ የሚታየው ነገር ትንሽ ከተለወጠ በኋላ “መልካም እንግዲህ... ይመስለኛል ወንጀለኛ እና መጥፎ ሰዎችን ከድርጊታቸው ለማስቆም በማሰብ መሰለኝ ፖሊስ የሆንኩት፡፡ የሆነ የደነዘ መልስ መለስኩልሽ መሰለኝ?”
ኧረ መልስህ በፍፁም የደነዝ መልስ አይደለም” አለችው።
“ህፃን እያለሁ የሆኑ ሰዎች አባቴን አታለውት ሀብቱን እንዲያጣ
አደረጉት” አላት እና ጉድማን ቀጥሎም “የሆነ የማይሆን የውሸት ድርድር
ውስጥ እንዲገባ ካደረጉት በኋላ ሁሉንም ነገሮቹን እንዲያጣ አደረጉት።
መኖሪያ ቤታችን እና ትዳሩንም እንዲያጣ አደረጉት፡፡ እነዚህን ሰዎች
እጠላቸዋለሁ።”
“ይገባኛል የምትለው” ብላ ኒኪ ራሷን በአዎንታ ከፍ ዝቅ ካደረገች በኋላም ወደ እሱ ዘንበል አለች። መጠጡ ምላሱን ትንሽ ያዝ ቢያደርገውም እየተናገረ ያለው በስካር መንፈስ እንዳልሆነ፣ ትክክለኛውን የሚሰማውን ስሜቱን መሆኑን ለማየት ችላለች “እሺ አባትህ በድጋሚ አግብቶ ኑሮውን መኖር ጀመረ?” ብላ ጠየቀችው::
ጉድማንም በጥያቄዋ የምሬት ሳቁን ሳቀ እና “የአሥር ዓመቴን ባከበርኩኝ በሳምንቱ ጋራዦችን ውስጥ በጋዝ አፍኖ ራሱን አጠፋ።በሚቀጥለው ቀንም ቤታችን እና መኪናችን ለጨረታ ቀረበ።” አላት፡፡
ኒኪም በሰማችው ነገር ልቧ ተነክቶ “በጣም ይቅርታ ሉው።በእግዚአብሔር ሥም ወደ ኋላ መልሼ አሳዘንኩህ።” አለችው፡፡
ፊቱንም በእፍረት በእጁ ሸፍኖ ከዚህ ጨዋታ ለመውጣት በሚያሳብቅ
ስሜት ውስጥ ሆኖ “ችግር የለውም አትጨነቂ፡፡ ነገሩ በእርግጥ በጣም
አሳዛኝ ነገር ቢሆንም ፖሊስ ለመሆን ያነሳሳኝን ገጠመኝ ሰጥቶኛል። ፖሊስ
መሆን ብቻ ሳይሆን ገጠመኙ ያስተማረኝ ገንዘብ ምን ያህል አስፈላጊ ነገር
እንደሆነም ጭምር ነው። ማንም ሰው እኔን እንዲቆጣጠር እንዳልፈቅድም
አድርጎኛል። የእኔ ህይወት አለቃ እኔ ነኝ አይደል?”
ምንም እንኳን መጨረሻ የተናገረው ነገር እውነት እንደሆነ እርግጠኛ ባትሆንም ኒኪ ራሷን በማስማማት ነቀነቀችለት፡፡
“ሊዛ ከመሞቷ ከወራቶች በፊት የገጠሙሽ የተለዩ እንግዳ የሆኑ ነገሮች
እንዳሉ ማስታወስ ትችያለሽ?” ብሎ ጠየቃት ጉድማን ወሬያቸውን ወደ እሱ
ጉዳይ ለመመለስ በማሰብ፡፡
ኒኪም አይኗን ጨፍና እጁንም ጨመቀች፡፡ ወደ እሱ በጣም ያቀረባትም
መሰላት፡፡ ምክንያቱም የልጅነት ሚስጥሩን ሳይደብቅ አምኖ ነግሮኛል ብላ ታምናለች።
“ሊዛ ላይ ወይንስ እኔ ላይ?” ብላ ጠየቀችው፡፡
"ሁለታችሁም ላይ''
መልካም” ብላ ኒኪ ምራቋን ዋጠች እና “ሊዛ ለዊሊ ባደን ግንኙነታቸው
ማብቃት እንዳለበት ነግራው ነበር። ይሄ ያልተለመደ ነገር ነው?”
ጉድማንም “እሺ የአንቺን ንገሪኝ?” አላት፡፡
ኒኪም አይኗን ገለጠች እና አይኑን ትክ ብላ እያየችው
“እኔን ከገጠሙኝ በጣም አስገራሚ ነገሮች ውስጥ አንዱ ደግሞ ባለቤቴን
በሞት ማጣቴ ነው” አለችው፡፡
ጉድማንም ጣቶቿን ወደ ከንፈሩ ወስዶ ሳማቸው፡፡
ከባሩ ኋላ ተቀምጦ ኒኪ እና
ጉድማን እጅ ለእጅ ተያይዘው
የሚያደርጉትን ነገር የሚከታተል አንድ ሰው አለ።
ይህቺ ሴት ይህንን ሰው በምትፈልገው መልኩ እየቃኘችው ነው ብሎ ጉድማን የኒኪን ፀጉር እየዳበሰ እና አፉ ለመሳም ሲከፈት የተመለከተው ሰውዬ በውስጡ አሰበ፡፡ በመቀጠልም ምንም አይነት አሳዛኝ ታሪክ ነግራው ቢሆንም ያሰበችው ተሳክቶላታል አለ ሰውዬው አሁንም በሃሳቡ፡፡ ሁለቱንም እየተመለከተ፡፡ በእውነቱ ይህቺ ሴት ይህንን ሰው በጣም እያሞኘችው ነው ጉድማን ለመጠጡ ሲከፍል የተመለከተው ሰውዬም ቢራውን ጨለጠ፡፡
ዶ/ር ሮበርትስ እና ጉድማንም ልክ እንደ አፍላ ወጣቶች እጅ ለእጅ ተያይዘው በሳንታ ሞኒካ ጎዳና ላይ ሲራመዱ ተመለከተ።

👍1🔥1
ተመልካች ብቻ ሆኖ መቅረት እና ምንም ነገር ማድረግ አለመቻሉ ጭንቀትን ፈጠረበት።
ሰውዬው ራሱን የድርጊት ሰው አድርጎ ነው የሚያስበው። ግን ያለፉት ጥቂት ሳምንታት ነገሮችን በትዕግስት ተሞልቶ መከወን ጥሩ ነገር እንደሆነ ትምህርት ወስዷል። ደግሞስ ከዚህ በኋላ ለነገሮች ሁሉ ዘገምተኛ ሆኖ መቆየት እንደማይችል ስለሚያውቅ ትንሽ ተፅናና።
ከዚህ በኋላ መመልከት ብቻ ሳይሆን ማድረግም ይችላል፡፡ ለዚያውም
በጣም በቅርቡ...

#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
....የክፍሉ ፀጥታ ክመቃብር ከበደ፡፡
“በዛን ወቅት መንገዱን አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ
በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ ነበር፡፡” ሰውየው ቀጠሉ… “የከማሪካው ልጅ!
የጋናው ነብይ ንክሩማ 'ዋ! ነበር ያለው ዋ! ከፊታችን የተጋረጠውን የአፍሪካ ችግር ተባብረን በአንድነት ከመጋፈጥ ወደኋላ ብንልና ተበታትነን ብንቆም በድጋሚ በሌላ የቅኝ ግዛት ስር ወድቀን ለከፋ ምሬትና ሰቆቃ መከተል መሣሪያ እስክንሆን ድረስ እርስ ሰርሳችን ስንጎነታተልና
ስንቦጫጨቅ እንቆያለን፡፡ ነበር ያለው፡፡”
“ተሳስቶ ኖራል ያ ሰው? ተሳስቶ ኖራል ያ ነብይ? ”
ሽማግሌው መልስ ይፈልጉ ይመስል በክፍሏ ውስጥ የተሰበሰቡትን
ሁሉ በተራ ተመለከቷቸው፡፡ ተጠባበቁ፡፡ መልስ አላገኙም፡፡
“ዛሬ ምን እያደረግን ይሆን?!ያ ሰው እንዳለው እርስ በርሳችን እየተጎናታልን አይደለም? ዛሬ ምን እያደረግን ይሆን? . እርስ በርሳችን እየተቦጫጨቅን አይደለም? ያኔ ክዋሜ ንክሩማን ተቃውመው የቆሙ የሪጅናል ውሀደት አቀንቃኞች የጥንቃቄና የእርጋታ መነኮሳት የት ገቡ? ዛሬ ምን ይላሉ? ምነው ድምፃቸው ጠፋ? በከፋ የቅኝ ግዛት ስር! በረሃብና በድንቁርና ስር በእንብርክክ የሚድኸው የዛሬው የአፍሪካ ህዝብ ተጠየቁ ቢላቸው ያ ሰው ተሳስቶ ነበርን? ቢላቸው ምን ይሆን መልሳቸው?”
አዛውንቱ ለአፍታ አቀርቅረው ቆዩ፡፡ መልሰው ቀና ሲሉ ፊታቸው
እልህና ቁጭት ለብሶ ነበር፡፡
“ለወቀሳ ጊዜ የለንም፤ለቁጭት ጊዜ የለንም ለምሬት ጊዜ የለንም ፤ሰላሳ ዓመት አምጠናል፡፡ እንወልዳለን ቆንጆ ቆንጆ ልጆች፡፡ ዛሬ እዚህ የተሰበሰባችሁ ሁሉ እዋላጆች ናችሁ፡፡ አዲስ የመጣችሁትን እንኳን ጨለማው ተገፈፈላችሁ እላለሁ፡፡ በተረፈ ከፊት የምንጋፈጠውን ሁሉ በሙሉ ልብ ልትቋቋሙት ቃል ትገባላችሁ፡፡”
ርብቃ የገባችው ቃል ምን ያህል አስፈሪና ጥልቅ እንደሆነ እየሰረፀባት የመጣው ጊዜ ከሄደ በኋላ ነበር፡፡
“ብዙ አወራሁ” አሉ ሽማግሌው : ዝግጅቱ አልቆ ሊሄዱ ሲነሱ
“ስለአፍሪካችን ሲነሳ ብዙ ዝም ማለት ይቀናኛል፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆን እኩዮቼ
ሁሉ በዕድሜያችን ያየነው ልሳን የሚያደርቅ ነው፡፡ ዛሬ ግን ሃላፊነቴን
መወጣት ነበረብኝ፡፡ ብዙ አወራሁ:: ይበቃል፡፡”
ተነሱ፡፡
በክፍሉ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ተነስተው ቆሙ:: ሰውየው በክፍሉ ውስጥ ያሉትን ወጣቶች በተራ ጨብጠው ሲያበቁ አብረዋቸው ከመጡት በዕድሜ ከሚቀርቧቸው ሰዎች ጋር ተከታትለው ወደ በሩ አመሩ፡፡ ከክፍሉ ከመውጣታቸው በፊት ቆም አሉና በክፍሉ ውስጥ ሰብሰብ ብለው በአክብሮት የሚመለከቷቸው ወጣቶች ላይ አተኮሩ…
“ተጠንቀቁ!” አሉ አዛውንቱ ፈገግ ብለው፡፡ “እዚህ ያወራነውን ጮክ ብላችሁ አታውሩ። አፍሪካችን ተኝታለች። እንዳትባንን፡፡”
ርብቃ ወዲያው የተሰጣት ትዕዛዝ ወይም ኃላፊነት አልነበረም፡፡
“ጊዜው ሲደርስ ስትፈለጊ ትጠሪያለሽ፡” ተብላ ቆየች፡፡ ቢሆንም በወር አንዴ እሷ የምትገኝበት ህቡዕ ህዋስ በሚያደርገው ስብሰባ ላይ እየተገኘች ስለአፍሪካ ሁለገብ ችግር የሚደረጉትን ውይይቶች ስትካፈል ቆየች፡፡
ከሁለት ወር በኋላ ነበር የመጀመሪያው ትዕዛዝ በምሥጢር የተላሰፈላት፡፡ በሬድዮ “የአፍሪካ ምጣኔ ሃብት” በሚል ርዕስ ሣምንታዊ ኘሮግራም እንድታዘጋጅ ተነገራት፡፡ በመጀመሪያ ሃሳዑን ለአለቃዋ እንዴት እንደምታቀርብ ቸግሯት ነበር፡፡ ነገር ግን በማግስቱ አለቃዋ እራሳቸው
እቢሮኣቸው ድረስ አስጠርተዋት ማክሰኞ ማታ የሚቀርበው የሙዚቃ ክፍለ
ጊዜ ስለሚቋረጥ በምትኩ ሊቀርቡ የሚችሉ ፕሮግራሞች ሰብስሲና
እንነጋገርባቸዋለን፡፡” አሏት፡፡
ደነገጠች፡፡ ነገሩ ገባት፡፡ አባል የሆነችበት ህቡዕ ድርጅት ምን ያህል ውስጥ ለውስጥ ስር የሰደደ እንደሆነ ተገነዘበች፡፡
“እ...የአፍሪካ ምጣኔ ሃብት
ላይ… ” አለች ሳታውቀው፡፡
“ግሩም” አሉ አለቃዋ ፈገግ ብለው ከመቀመጫው እየተነሱ እየጨበጧት፡፡ “በርቺ፡፡ ማንኛውም ችግር ሲገጥምሽ ቀጥታ እኔጋ ነይ፡፡ አይዞሽ፡፡”
ከአለቃዋ ቢሮ ስትወጣ ጉልበቶቿ እየተብረከረኩ ነበር፡፡ ሃላፊነቱ
ከወፍጮ ከብዶ ታያት፡፡
ሁለተኛው ትዕዛዝ ከሁለት ወራት በኋላ ተከተለ፡፡
“እና ምንድነው ማለት ነው የማደርገው?”
ባጭሩ በፈለግሽው መንገድ በእህትነትም ፡ ሆነ በሌላ ታጠምጅዋለሽ እንዳልኩሽ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በአፍሪካ ጉዳይ ቢሮ ውስጥ ሁለተኛውን ወንበር የያዘ ሰው ነው::እያንዳንዱን ነገር ለማግኘት እንፈልጋለን፡፡በተቻለሽ እለቢው... እ..ቤቱ ይዟቸው የሚመጡ ወረቀቶችን አጥኚ፡፡ ያገኘሽውን ሁሉ፡፡ ከዚህ በተረፈ…በየጊዜው ተጨማሪ መመሪያ ይተላለፍንልሻል።” የህቡዕ ህዋሷ መሪ ነበር ማርቆስ፡፡
“እንዴት ነው ሰውየውን የማገኘው? ማለቴ
የሚቀጥለው ቅዳሜ ሶስና የልደት በዓሌ ነው ብላ ትጠራሻለች ግብዣው ላይ ትገኛለሽ አብረው ስለሚሰሩ እሱንም ትጠራዋለች፡፡ ታስተዋወቅሻለች። ከዚያ በኋላ እኔና አንቺ እየተረዳዳን እንቀጥላለን፡፡” ትከሻዋን ቸብ አድርጎ ተነሳ “በነገራችን ላይ የሰውዬሽ የምሥጢር ስም "ዱርዬወ" ነው:: ገባሽ? '
ዱርዬው ” አለ ማርቆስ በጠባሳ የተገመሰ ፊቱን በቀኙ ፈተግ አድርጎ “ተግባባን?”
“ገባኝ፡፡”
እንደተባለችው ሶስና በልደት በአሏ ላይ አስተዋወቀቻቸው፡፡ ናትናኤልን “ዱርየው”ን የህዋሷ መሪ ማርቆስ እንዳላት መረቧን ዘርግታ ፍቅረኛዋ አደረገችው፡፡ ሰርስራ ሕይወቱ ውስጥ ገባች፡፡ ምስጢሯን ነግራው
ምረሥጠርህን አለችው:: ያገኘችውን ሁሉ አሳልፋ ሰጠች፡፡ ጊዜ ሲሄድ እሷው ያዘጋችው መረብ እሷኑ ተቀተባት፧ አደናቀፋት፤ ወደደችው፡፡ሆኖም ሳታቋርጥ ቡድኑ መረጃዎችን ስታቀብል ቆየች፡፡ ይህ ብዙም አላሳሰባትም:: ምክንያቱም ናትናኤል ለአፍሪካ የነበረው ግለት ከማናቸውም የደበዘዘ አልነበረም፡፡ ለዚህም ነበር ላህዋሷ መሪ በሳምንት አንዴ በምታቀርበው ዘገባ ላይ ዱርዬው' በህቡዕ ድርጅቱ ውስጥ ቢመለመል ጉዳት እንደማያስከትል ደጋግማ ያመለከተችው፡፡ ለምን እንደፈሩት ባይገባትም ምክሯን ሊጠቀሙበት አልወደዱም፡፡ ቢሆንም እንደዚህ ዓይነት ነገር ውስጥ ይገባል ብላ ጠርጥራም አታውቅ፡፡ ናትናኤልን እንደ ወንጀለኛ ማሳደድ! መጀመሪያ ነገር ነፍስ ማጥፋትንስ ምን አመጣው? ጓደኝየውንስ ለምን ገደሉት? ፈጣሪዬ የት ገብቶ ይሆን የተሰወረው? እውነት ቢያገኙት አይጎዱትም ይሆን? እንዴት ልታምናቸው ትችላለች? ቢገድሉትስ? ቢቀር
ይሻላል፡፡ እንዲይዙት ብትረዳቸውና አይኖቿ ስር አንድ ነገር ቢያደርጉትስ?
ገብሬልዬ፤ ግን ደግሞ ራሳቸው ፈልገው ቢያገኙትስ? ዘገነናት፡፡ ዘገነናት
ያለፈው ትዝታ ሁሉ መጣባት::እና ቀና ብላ ተመለከተችው በሩ አጠገብ ካለ ወንበር ላይ ተቀምጦ እያከታተለ በላይ በላዩ ሲጋራ የሚያጨሰውን ሰው፡፡ በትዝብት መልሶ ተመለከታት:: ባንዳ!' ያላት መሰላት ድጋሚ።
“ማርቆስ” አለችው አይኖቿ ላይ እንባዋ አቆርዝዞ፤ “ማርቆስ ግን ምን አደረጋችሁ? ናትናኤል'ኮ ምንም አያውቅም፡፡ ማርቆስ እውነቴን ነው፣ ምንም አያውቅም:: እመነኝ አብረን ብዙ ሰርተናል፡፡ አውቅሃለሁ ታውቀኛለህ:: አልዋሽህም:: ምንም አያውቅም ናትናኤል፡፡”
“ነገርኩሽኮ:: ምንም እንደማያውቅ እኛም ደርሰንበታል፡፡ ግን ሊደርስበት ወደማይገባ ቁልፍ እያነፈነፈ እየተጠጋ ነው።ሊያገኘው ይችላል። ሰውዬሽ ቀላል ሰው አይደለም፡፡ ምሥጢሩን ካገኘ ደግሞ ዕቅዱ ሁሉ እጁ ገባ ማለት ነው፡፡ያ ደግሞ ለእኔና ለአንቺ ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም
ለአፍሪካ…ውድቀት ነው ብጥብጥ ነው…ሁከት ነው፡፡ማንም ይቅርታ አያደርግልንም፡፡አንድ በአንድ በየአገሩ እየታደንን በየአገሩ

👍3
እየተመነጠርን እንንጠለጠላለን ሲጋራውን ምጥጥ አድርጎ ከተቀመጠበት ተነሳና መተርኮሻው ላይዐደፈጠጠው፡፡ “ያ ከመሆኑ በፊት እጃችን መግባት አለበት፡፡ አፍሪካ በደም ከመዘፈቋ በፊት፧ በሺህ የሚቆጠሩ ንፁህ ልጆቿ ከመታረዳቸው በፊት ናትናኤል መያዝ አለበት፡፡”
“ይመልመል ስላችሁ ቢመለመል ይህ ሁሉ አይመጣም ነበር።
ናትናኤል የአፍሪካን ችግር ከማንኛችንም እኩል የተረዳ ሰው ነው በራሳችሁ ጥፋት…በገዛ ራሳችሁ ዳተኝነት ዛሬ በማያውቀው ምሥጢር ታሳድዱታላችሁ፡፡ ያኔ ቢመለመል ኖሮ እንዳልኳችሁ ቢመለመል ኖሮ…”
“ርብቃ ንገረኝ ካልሽ እነግርሻለ ናትናኤል ያልተመለመለበት ምክንያት አለው ወኔ ቢስ ነው፡፡ፈሪ ነው ማለቴ አይደለም፡፡ ያንን አላውቅም።ግን ስልብ ነው!ለስልሷል ቦቅቡቋል፤ በነጮች ቅራቅንቦ ላሽቋል፡፡ርብቃ እመኝኝ በርካታ የናትናኤል ብጤ የትማሩ አፍሪካውያን የአፍሪካን
ችግር ሳይረዱት ስለቀሩ አይምሰልሽ ዋጋ ቢስ የሚሆኑት፡፡ የራሳቸው ሚዛን
ስለሌላቸው በነጮች መስሪያ በነጮች ሚዛን ስለታወሩ ነው...
“ጆሞ ኬንያታ እንዳለው ከዘመናት በፊት ነጮች ክርስትናን እየሰበኩና ስለሰማያዊው መንግሥት እያወሱ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያሉ በግራ ወንጌል እንግበው በቀኝ ጠመንጃ ጨብጠው ገቡ የምድሩን ተውት'አሉ፡፡ ዋናው የሰማዩ ነው አሉ፡፡ ቀኙኝ ሲያጉኗችሁ ግራውን ስጡ አሉ፡፡ አመንናቸው፤ተንበርክከን ጭንቅላታችንን
ደፋን፡፡ አልፍተውን አላሽቀውን ሲጨርሱ በተርታ ኣሰልፈው ለባርነት ሽጡን! ለዘመናት እንደ በግና ፍየል ጥጃና ግመል ወይፈንና ግመል ላትና ሻኛችንን ደንደስና ፍርምባችንን እያማረጠ ሽጡን ሽመቱን፡፡
“ዛሬ ደግሞ የተገላቢጦሽ ስለዲሞክራሲና ስሰሰው ልጅ መብት
ሊሰብኩልን ተነሱ፡፡ ያለፈው ሁሉ ተረሳና የዕሩን ሁሉ ተዘነጋና ስለበጎውና
ስለትክክለኛው መንገድ ሰባኪዎቹ ዛሬም እነሱው ሆነ፡፡ ቃል ኪዳናቸውን
ሰብረው ወንጌልን በሰበኩበት አፋቸው . ገበያ አውጥተው : : በዋጋ
እንዳልተከራከሩብን ዛሬ ድጋሚ ቅዱስ መስለው ረኲሳችሁ አሉን፤ የሰው
መብት አፍሪካ ውስጥ ተረገጡ አሉ፡፡ አፍሪካ ውስጥ ዲሞክራሲ
ድምጥማጠ ጠፋ አሉ፡፡ እነ አምኔስቲ ኢንተርናሽናል የዛሬዎቹ ሚሽነሪዎች
ሆኑ፡፡ በግራ ዲሞክራሲን በቀኝ ብድርና ዕርዳታ አንግበው ድጋሚ መጡ፤
የዲሞክራሲን መንገድ አዘጋጁ ፖለቲካውንም አቅኑ አሉ:: 'ኤኮኖሚውን
ተውት፤ ተደጋግፎና ተረዳድቶ ስለመስራቱ ስለማደጉና ስለመበልፀጉ
አትጨነቁ አሉ፤ ስለኋላቀርነታችሁ አትመራመሩ አሉ፤ መጀመሪያ
ዲሞክራሲ አሉ መጀመሪያ የሰው ልጅ መብት፤ መጀመሪያ የራስን ዕድል
በራስ መወሰን አሉ...
“የሚያሳዝነው ግን የእኛ ድጋሚ መታለል ነው?” ድጋሚዐእየተንበረከክን ድጋሚ ጭንቅላታችንን እየደፋን መሆናችን ነው::
“ቴዎድሮስ ከአንድ ምዕተ ዓመት በፊት ያለውን ታስታውሻለሽ በመጀመሪያ የሃይማኖት ሰባኪዎችን ትልክላችሁ፡፡ ቀጥሎ እነሱን የሚጠብቅ ቆንሲል፡፡ ቆንሲሉን ለመጠበቅ ደግሞ ወታደሮቻችሁን፡፡ በመጨረሻ አገራችንን ትወስዳላችሁ ነበር ያለው፡፡ ርብቃ የዛሬም ስልታቸው የተለየ አይምሰልሽ፡፡ ዲሞክራሲን ይሰብኩናል፡፡ ቀጥሎ እሱኑ ማጠናከሪያ ብድርና ዕርዳታ ያጎርፋልናል፡፡ ብድርና እርዳታውን ወጤታማ ለማድረግ ተብሎ ደግሞ በኤኮኖሚያችን ገብተው መሪ ቀያሽ፤ ደጋፊ ኣማካሪ፤ፈላጭ ቆራጭ
ይሆናሉ፡፡ በመጨረሻ አድቅቀውን እላቁጠውን ሲያበቁ ተረጅ ተደጋፊ ለማኝ
ተመዕዋች ያደርጉናል፡፡እምቢ ካልንና ተንኮል ሽራቸውን ቀድመን ካወቅንባቸዉ እርስ በርስ በዘርና በሃይማኖት እያጎናተሉና እያስታጠቁ እያራገቡ ያጨፋጭፉናል ! ሳንወድ በግድ ያንበረክኩናል፧ አንገታችንን ያስደፉናል፡፡ ሃቅና ሀስቱን አማተው አገለባብጠው: እኛነ፡ እራሳችንን ያስወቅሉናል፧
ሳናውቅ ሳንጠረጥር ነጭ አምላኪ ያደርጉናል፡፡ የነሱ ጨቋኝነት ወደ ጎን
ተብሎ እኛኑ ጨቋኝና ተጨቋኝ ብለው ያለያዩናል፡፡
“አፍሪካውያን ለሁለተኛ ጊዜ በነጮች ተበልጠናል፡፡ ለዘመኑ ሃይማኖት ለዲሞክራሲ ለዘመኑ ሚሽነሪዎች በነጭ ጋዜጠኞች ተበልጠናል፡፡ለዘመኑ የኤኮኖሚ ጦረኞች ለአይ.ኤም. ኤፍ.! ለዓለም ባንክና ለሌሎች ተንበርክከናል፤ አንገታችንን ደፍተናል፡፡ ዳግማዊ ሞት ሞተናል፧ ዳግማዊ ትንሳኤ ያሻናል፡፡
“ሬሳው የሚሸትና የሚከረፋው ሬሳው ያልተማረውና ያላወቀው ምስኪን አፍሪካዊ አይምሰልሽ፡፡ በተማርነውና አወቅን ሰለጠንን ባልነው ይብሳል ድሮም ጥቁር... ድሮም አፍሪካ.. ብሎ ነገር የሚጀምረው አወቅሁ ባይ ስልጣን አፍሪካዊ ይብሳል፡፡ ሳንጠረጥር ሳናውቅ ሳንሰማ ሰልበውናል፡፡”
“ለዚህ ነው ናትናኤል ሊመለመል አይችልም ያልኩሽ፡፡ ወኔ የለውም ስልብ ነው ያልኩሽ፡፡ አብሮን ሊሰለፍ የሚችል ለዘመኑ ሃይማኖት ያልተንበረከክ፣ አንገቱን ያልደፋ ኩሩ አፍሪካዊ ብቻ ነው መጀመሪያ አፍሪካ፤ መጀመሪያ የተባበረች አንድ አፍሪካ፤ መከፈል ያለበት ሁሉ ይከፈል ግን አንድ አፍሪካ የሚል መሆን አለበት፡፡ ተግባባን?” ማርቆስ በውስጡ
ያመቀውን ሁሉ የተነፈሰና የቀለለው ይመስል ተመቻችቶ ተቀምጦ ሲጋራ
ፍለጋ ኪሱ ገባ፡፡”
“አልገባኝም…” አለች ርብቃ አፍንጥጣ እየተመለከተችው “ምኑ ላይ ነው የናትናኤል ወኔ ቢስነት ታዲያ? ዲሞክራሲ ምኑ ላይ ነው ችግር የፈጠረው? ዲሞክራሲ በአፍሪካ መስፈኑ ምኑ ላይ ነው ጉዳት የሚሆነው፤ በዘመኑ ሃያማኖት እያልክ የምትኮንነው?”
“አየሽ አንቺም ሳታውቂው መተብተብሽን? ርብቃ ከዘመናት በፊት ነጮች ለአፍሪካውያን የሰበኩት ክርስትና አጥፊና ጎጅ ሆኖ ይመስልሻል የማታ ማታ ለባርነት የተዳረግን? አይደለም፡፡ ክርስትና ሃስትና ማወናበጃ፣ ክርስትና ማታለያ ሆኖ አልነበረም፡፡ እውነቱ ግን ነጮች ክርስትናን ወንጌልን መሣሪያ አድርገው፣ መሽፋፈኛ አድርጎ ሊያዘናጉን መቻላቸው
ነው፡፡ ወንጌልን እንስበክ ብለው ገብተው ውስጥ ገመናችንን ሊሰልሉ፣ሊያውቁ፣ ሊያጠኑንና ሊለያዩን በመቻላቸው ነው ፤ . ቀበሮ ሲሆኑ በግ መስለው በመምጣታቸው ነበር፡፡ ርብቃ ዛሬም ዲሞክራሲ ማታለያ አጥፊና
ጎጅ ሆኖ አይደለም:: ምሥጢሩ ግን በዲሞክራሲ ሰበብ እርስ በርሳችን
እየለያዩ እያቧጨቁ ማፋጀታቸው ነው፡፡ ለያይተው በታትነው አዳክመው
ድጋሚ ሌሽጡን ሊሸምቱን መነሳታቸው ነው፡፡ ከዘመናት በፊት ክርስትናን
እንደተጠቀሙበት ዛሬ ዲሞክራሲን ማንሳታቸው ነው፡፡”
“እና ምን ማድረግ አለብን?”
“መጀመሪያ አፍሪካ ማለት አለብን፡፡ መጀመሪያ አንድነታችን ማለት አለብን፡፡ ያ ብቻ ነው ጥንካሬያችን፡፡ ያ ብቻ ነው ብርታታችን፡፡ ያን ጊዜ አፍሪካ አንድ ስትሆን እንደዛሬው የሃምሳ አገሮች ሹክሹክታ ሳይሆን የአንድ አፍሪካ ድምፅ ያስገመግማል፡፡ ያን ጊዜ ዓለም ያዳምጠናል፡፡ ያን ጊዜ ብርታታችንን ይገነዘቡታል፡፡ አፍሪካችን ገና የምትለማ ነች ይህን አንሱ ያንን አፍርሱ ስላሉን ሳይሆን የሚበጀንን እንገነባለን የማይጠቅመንን እናፈርሳለን፤ አፍሪካችን ሰፊ ገበያ ነች ይህን በዚህ ሽጡ ስላሉን ሳይሆን በሚያዋጣን እንሸጣለን፤ ይህን በዚያ ግዜ ስላሉን ሳይሆን በሚስማማን
እንሸምታለን፡፡ አፍሪካ ድንግል ናት፤ ጥሬ ሃብት የእኛ ነው፤ከፋኝ ሲሉ እናበላልጣቸዋለን፧ አቃረን ቢሉ እናማርጣቸዋለን፡፡
“ያን ጊዜ ዛሬ የተላለቁብን ዛሬ የተዛባበቱብን የገላችንን ቀለም
አይተው አድፍ ፤ ኋላቀርነታችንን ገላምጠው ዝንጀሮ ያሉን ሁሉ
ወዳጅነታችንን ይመኙታል፤ ወንድማማችነቱን ያከብሩታል፡፡ አይ ቢሉ
አሻፈረን ቢሉ ሊገፉትና ሊገድቡት የማይደፍሩት ጎርፍ ሊዝቁት ሊጨርሱት የማይሞክሩት የባህር አሸዋ ጥቁር ሕዝብ ከፊታቸው እንደተጋረጠ ይገነዘባሉ ያኔ ነው ዲሞክራሲ ያኔ ነው የሰው ልጅ መብት ያኔ ነው የራስን

#የእናቴ_መዳፍ
እኔና እናቴ . . .
ከ'ለታት ባ'ንድ ቀን
ከትንሽ ቤታችን
ከትልቅ ልቧ ጋር ፤
ዐይን ዐይኔን እያየች
በሥሥት ፣ በፍቅር
ኾኜ ከእግሯቿ ሥር።
ትላንቷን ዐሰበች ፤ ትዝታ ትላንቷን
አምና ጨቅላነቴን ፣ አምና ጉብሊቷን።
ውብ ለጋ ነበረች ...!
ፍጹም ድንቅ ረቂቅ
የነፍሴ ሥንቅ ሐቅ
የቁንጅና ዕንቍ ፣ መግነጢሰ ውበት
የቀይ ዳማ ቅኔ ፣ የምናብ ሠገነት።
እምዬ ...
ትላንት . . .
ስንቱ ጎበዝ ፣ ደጅ ጠንቶ
ስጦታ ሸክፎ ፣ ዐሪቲውን ገዝቶ፣
ስንቱን ቆነጃጂት ፣ ኩራት እንዳልናደ
እንቢታዊ መልሱን ፣
ያ'ይኾንም ምላሹን ፣ ይዞ ነው የኼደ።
እማምዬ ጀንበር ፣ ደማቅ ፀሓይቱ
የማትጠልቀዋ ፣ እመት አዛኝይቱ
ዐይን ዐይኔን እያየች ፣
ትንንሽ እጆቼን . . .
በእጆቿ ወዘና በቅቤ እያሰላች
እውነትና ምኞት እያሰናሰለች
የመዳፌን መሥመር ማንበቧን ቀጠለች።
ነገኽ እውነት አለው! አንተ ማለት ተስፋ
ረዥሙ ጒዞኽ . . .
ባ'ምላክ እናት ያለ ፣ ታቅፎ ባ'ክናፏ።
ዕንቅፋት ያልበዛው መንገድኽ የቀና
እንደ እጅኽ ለስልሶ ፣ ያርብብ ያ'ንተ ዳና!
( ... አለች ... )
( ... እጇን ያዝኩ ላነበው ... )
የእናቴ መዳፍ .
መንገዱ የበዛ ፣ ሻካራ ሽንትርትር
ምን? ብዬ ላንብበው !
ቍራጭ መሥመር ትርትር።
ከጣቶቿ ግርጌ . .
ፈለግ ነግሦበታል!
ግቻ ሠርቶባታል!
ቀንድ መሰለብኝ የሚያሳሳው ጥፍሯ
ልስላሴው ጠፍቶ . . .
በየአንጓው ሥፍር ፣ እዥ ይዟል መሥመሯ።
( . . የእምዬ መዳፍ . . )
መጻተኛ ኾንኩኝ ልቤ ተሰበረ !
መዳፏ ነገረኝ ውስጤም ተሸበረ!
እናቴ አልማዝ . . .!
መጋቤ ብርሃን ፣ ልትከስም እንደ ሻማ ፤
እመት አዛኚቷ . . .!
ደርቃና ጠውልጋ ፣ ልትረግፍ እንዳ'በባ።
ውብ ጸዳል ዐይኖቿ፣ ፀሓይ የነበሩ
ሞጭሙጨው አነሱ ...
ከ'ርጅና ተጋብተው ፣ ለጊዜ ተዳሩ።
የሐዘን እንባዬ ፣ ፊቴን አረጠበው
ዝሎ! ተሸብሽቦ ፣ ገጼን ዳዋ ዋጠው!)
ዘንግቼው ነበረ! ፣ ፍጻሜ ዘመኑን ፣ እንደነሰነሰ
የድካሟ ካባ ፣ በእናቴ መዳፍ ላይ ፣ እንደተፀነሰ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
እኔና እናቴ . . .
ከ'ለታት ባ'ንድ ቀን
ከትንሽ ቤታችን
ከትልቅ ልቧ ጋር ፤
ዐይን ዐይኔን እያየች
በሥሥት ፣ በፍቅር
ኾኜ ከእግሯቿ ሥር።
ትላንቷን ዐሰበች ፤ ትዝታ ትላንቷን
አምና ጨቅላነቴን ፣ አምና ጉብሊቷን።
ውብ ለጋ ነበረች ...!
ፍጹም ድንቅ ረቂቅ
የነፍሴ ሥንቅ ሐቅ
የቁንጅና ዕንቍ ፣ መግነጢሰ ውበት
የቀይ ዳማ ቅኔ ፣ የምናብ ሠገነት።
እምዬ ...
ትላንት . . .
ስንቱ ጎበዝ ፣ ደጅ ጠንቶ
ስጦታ ሸክፎ ፣ ዐሪቲውን ገዝቶ፣
ስንቱን ቆነጃጂት ፣ ኩራት እንዳልናደ
እንቢታዊ መልሱን ፣
ያ'ይኾንም ምላሹን ፣ ይዞ ነው የኼደ።
እማምዬ ጀንበር ፣ ደማቅ ፀሓይቱ
የማትጠልቀዋ ፣ እመት አዛኝይቱ
ዐይን ዐይኔን እያየች ፣
ትንንሽ እጆቼን . . .
በእጆቿ ወዘና በቅቤ እያሰላች
እውነትና ምኞት እያሰናሰለች
የመዳፌን መሥመር ማንበቧን ቀጠለች።
ነገኽ እውነት አለው! አንተ ማለት ተስፋ
ረዥሙ ጒዞኽ . . .
ባ'ምላክ እናት ያለ ፣ ታቅፎ ባ'ክናፏ።
ዕንቅፋት ያልበዛው መንገድኽ የቀና
እንደ እጅኽ ለስልሶ ፣ ያርብብ ያ'ንተ ዳና!
( ... አለች ... )
( ... እጇን ያዝኩ ላነበው ... )
የእናቴ መዳፍ .
መንገዱ የበዛ ፣ ሻካራ ሽንትርትር
ምን? ብዬ ላንብበው !
ቍራጭ መሥመር ትርትር።
ከጣቶቿ ግርጌ . .
ፈለግ ነግሦበታል!
ግቻ ሠርቶባታል!
ቀንድ መሰለብኝ የሚያሳሳው ጥፍሯ
ልስላሴው ጠፍቶ . . .
በየአንጓው ሥፍር ፣ እዥ ይዟል መሥመሯ።
( . . የእምዬ መዳፍ . . )
መጻተኛ ኾንኩኝ ልቤ ተሰበረ !
መዳፏ ነገረኝ ውስጤም ተሸበረ!
እናቴ አልማዝ . . .!
መጋቤ ብርሃን ፣ ልትከስም እንደ ሻማ ፤
እመት አዛኚቷ . . .!
ደርቃና ጠውልጋ ፣ ልትረግፍ እንዳ'በባ።
ውብ ጸዳል ዐይኖቿ፣ ፀሓይ የነበሩ
ሞጭሙጨው አነሱ ...
ከ'ርጅና ተጋብተው ፣ ለጊዜ ተዳሩ።
የሐዘን እንባዬ ፣ ፊቴን አረጠበው
ዝሎ! ተሸብሽቦ ፣ ገጼን ዳዋ ዋጠው!)
ዘንግቼው ነበረ! ፣ ፍጻሜ ዘመኑን ፣ እንደነሰነሰ
የድካሟ ካባ ፣ በእናቴ መዳፍ ላይ ፣ እንደተፀነሰ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
መርማሪ ፖሊስ ሚክ ጆንሰን ካርተር በርክሌ ውድ ሽሚዙን በደንብ ማኒኩየር በተሰራው ጣቶቹ በደንብ አድርጎ አስተካከለው:: የዶክተር ሮበርትስ
ታካሚ የሆነው የኢንቨስትመንት ባንከሩ ካርተር በርክሌ ሁሉ ነገሩ ውዷ ነው፡፡ ምርጥ መኖሪያ ቤት፣ ምርጥ ምርጥ የቪንቴጅ ጃንዋር ስፖርት መኪኖች እና ሁሉም ቁጭ ያሉበት በምርጥ ሁኔታ ፈርኒሽድ የተደረገው የቤት ውስጥ ቢሮው እራሱ በጣም ውድ ነው፡፡ እንኳን እቃዎቹ ሲያወራ የሚጠቀምባቸው ቃላቶች ሁሉ በጣም የተመረጡ ናቸው፡፡
እዚህ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው እያወሩ እያሉ ካርተር ትላንትና ማታ መኝታ ቤቱ ውስጥ የሆነ ሰው ሊያስፈራራው በማሰብ የሞተ አይጥ አስቀምጦ እንደነበር እየነገረው ነበር። የሞተ አይጥን ማስቀመጣቸው የማፍያዎች ማስፈራሪያ ስልት እንደሆነ ጭምር እያስረዳው ነበር፡፡
“ይሄን ነገር ያደረጉት በእርግጥም እኔን ሊያስፈራሩ አስበው ነው፡፡ደግሞም ተሳክቶላቸዋል። ባይገርምህ መርማሪ ፖሊስ ጆንሰን እናንተ ወደ እኔ ባትመጡ እንኳን እኔ እራሴ ጉዳዩን ለማመልከት ወደ እናንተ መምጣቴ አይቀርም ነበር።
ጆንሰንም ራሱን በአዎንታ በመነቅነቅ የቤቱን ዙሪያ ሲመለከት ዕቃዎቹ
በደንብ ከመወልወልም በላይ የመፅሀፍ መደርደሪያው ሼልፍም ራስን
በመገንባት ላይ እና በፋይናንስ ዙሪያ በተፃፉ መፅሀፍት በሥርዓት
ተጠቅጥቀዋል። አሁን ላይ ካርተር በርክሌይን እየተመለከተው ያለው ጆንሰን
ዶክተር ሮበርትስ ስለ ካርተር ከማስታወሻዋ ላይ ከፃፈችው ነገር ጋር
በመስማማቱ ተናደደ፡፡
ጆንሰን ካርተርን አስመልክታ ኒኪ የፃፈችውን ሲያነብ “መቀወሱ
ያልተረጋገጠ በከንቱ ስሜት ውስጥ የሚናውዝ የሜክሲኮ ወንጀለኞች
ሊገድሉት እንደሚያሳድዱት የሚናገር (ለዚህ ምንም ማረጋገጫ የሌለው)
ለረዥም ጊዜ በጭንቀት ውስጥ የኖረ። ምናልባት በልጅነቱ በደረሰበት ስቃይ
ምክንያት ሊሆን ይችላል? (ወይንም ደግሞ ሜክሲኮ ውስጥ በጉርምስናው
ዘመን ኖሯልና ምናልባት እዚያ የሆነ ነገር ተከስቶ ይሆን?) ውስጡ ያላደገ
ቋሚ የሆነ ፆታዊ ግንኙነት የሌለው እና በግንኙነት አብረውት ያሉ ሰዎችንም በጣም አድርጎ የሚቆጣጠር ነው።” ይላል ማስታወሻው፡፡
ዶክተር ሮበርትስ ካርተር በርክሌን የገለፀችበት መንገድ በሙሉ የተቀበለው ቢሆንም አንድ ነገር ረስታለች እሱም “የሰዎች አትኩሮትን (ታይታን) የሚፈልግ ባህሪ ያለው መሆኑ ነው። ይህንን ደግሞ በእሱ ላይ ያላየችው እሷም የዚህ ልክፍት ስላለባት ነው ብሎ አሰበ፡፡ ለዚህም ነው
ካርተር ከዚህ በፊት በተካሄዱት ግድያዎች ውስጥ ዋነኛ ተፈላጊ ሰው መሆኑን ለማሳየት ያጫወተውን የአይጥ ታሪክ ፈጥሮ ለጆንሰን የተናገረው።
ይሄ ቀሽም ሰው ራሱን እንደተፈላጊ ሰው ያያል ወይንም ደግሞ የሆነ እሱ ስለግድያው የሚያውቀውን ነገር እንዳላውጣጣው እያዘናጋኝ ነው
ብሎም አሰበ፡፡
“ቤትህ ውስጥ ጠባቂዎች አሉህ መሰለኝ?” ብሎ ቅድም ወደ ቤቱ ሲገባ
የተመለከታቸውን ብዙም ስልጠና እንደሌላቸው የሚያስታውቁትን የጥበቃ
ሰዎቹን አልፎ እንደገባ አስታውሶ ካርተርን ጠየቀው። ቤቱ ውስጥ ሲገባ ከጠባቂዎቹ ሌላም የሲ.ሲ.ቲቪ
ካሜራዎችንም አይቶዐካሜራዎችንም በየቦታው ገጥመሃል አይደል እንዴ?”
“አዎን ቤቱ ጥበቃ ስለሚያስፈልገው በጠባቂዎችም፣ በካሜራም ነው
የሚጠበቀው። ግን ዋናው መኝታ ቤቴ ውስጥ ካሜራ አልገጠምኩኝም” ብሎ
መለሰለት፡፡
ጆንሰንም “ለምን ዋናው መኝታ ቤትህ ውስጥ ካሜራ አላስገጠምክም?
ብሎ ጠየቀው፡፡
ባንከሩም እንዴት ይሄ አይገባህም በሚል ሀሳብ ይመስል የጎረምሳ ፈገግታ ከለገሰው በኋላ “እዚህ ጋር የተማረ ሰው ግምት ይኖርሃል ብዬ አስባለሁ። ጠባቂዎቼ ከሁሉም ካሜራዎች በቀጥታ መረጃዎች ይደርሳቸዋል።እኔ ደግሞ በግሌ የማደርጋቸውን ነገሮች ማንም እንዲያውቅብኝ አልፈልግም። ለዚያም ስል ነው በዋናው መኝታ ክፍሌ ውስጥ ካሜራ ያላስገጠምኩት፡፡ በሁሉም ወደ ቤቴ በሚያስገቡ በሮች ላይ ካሜራ
ተገጥሞባቸዋል። እሱ ላይ ብቻ ሳይሆን ፎቅ ላይም ካሜራዎችን
አስገጥሜያለሁ። ስለ እዚህ ወደ እዚህ ቤት የሚገባም ሆነ የሚወጣ ሰው
በካሜራው መታየት ይችላል” ብሎ መለሰ፡፡
“መልካም” አለና ጆንሰን በመቀጠልም “የሞተውን አይጥ መኝታ ቤትህ
ተቀምጦ ካገኘህ በኋላ መቼስ ካሜራዎቹ የቀረፁትን ቪዲዩዎች ተመልክተሀቸዋል አይደል?” ብሎ ጠየቀው፡፡
“አዎን አይቻቸዋለሁ”
“ግን ማንም ሰው አላየህም?”
ቤቴ ውስጥ ከሚሰሩ ሰዎች በስተቀር አንድም ሰውን አላየሁም። ይሄ ታዲያ አይገርምም?” ብሎ የሸሚዙን ኮሌታ በሀይል ጎተተው።
“እና እንዴት ነው ይሄ አንተ የማፍያዎች የማስፈራሪያ መንገድ ነው ብለህ ያሰብከውን የሞተውን አይጥ መኝታ ቤትህ ድረስ ሊያስቀምጡ የቻሉት?” ብሎ ጆንሰን ጠየቀ፡፡
ካርተርም ፊቱ ላይ ግራ የመጋባት ፊት እያሳየው “እኔ ይሄንን በምን አውቃለሁ? መርማሪ ፖሊሱ እንግዲህ አንተ ነህ አይደል? አንተው ንገረኝ
እንጂ” ብሎ መለስ፡፡
“እና ቪድዮው ላይ አዲስ ሰው እስካላየህ ድረስ ቤት ውስጥ የሚሰራ
ሰው ነው አይጡን መኝታ ቤትህ ያስቀመጠው ማለት ነው፡፡ አይመስልህም?”ብሎ ጠየቀው እኔ ጋር አለ ብሎ ባልጠበቀው የራሱ ትዕግስት ጭምር እየተገረመ፡፡
“ይሄማ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም እኔ እነዚህን ሰዎች ስቀጥር
የበፊት ህይወታቸውን በሚገባ አስጠንቼ እና ተጠንቅቄ ነው፡፡ ስለሆነም
አሁን አንተ የተናገርከው ነገር ሊሆን አይችልም...”
ብሎ ያሰበውን ነገር ተናግሮ ሳይጨርስ ጆንሰን አቋረጠው እና ምናልባት አይጡን ልታሳየኝ ትችላለህ? ስለዚህ አይጡን አንስቼ ምርመራ እንዲደረግበት ማድረግ እችላለሁ” አለው ከወንበሩ ላይ ተነሳ፡፡
“አይጡን ላሳይህ አልችልም” ብሎ መለሰለት፡፡ ጆንሰንም የካርተርን
መልስ ሲሰማ ዶክተር ሮበርትስ “ዝም ብሎ የቅዠት ሀሳብ የሚፈጥር ብላ
የተናገረችው ነገር ትክክል እንደሆነ አወቀ።
ለምንድነው አይጡን የማታሳየኝ?” ብሎ ኮስተር ብሎ ጠየቀው እና ለእንደዚህ አይነት ሰው ዶክተር ሮበርትስ እንዴት በየቀኑ የቴራፒስት ህክምና ልትሰጥ እንደምትችል ራሱን ጠየቀ፡፡ እንደዚህ አይነቶቹ ቴራፒስቶች አፍንጫቸው መመታት የለበትም ታዲያ?
“ትላንትና ማታ ነው አይጡን ያገኘሁት እሱን ደግሞ ነግሬሀለሁ አይደል?” ብሎ ካርተር ክርክሩን በመቀጠል “ቤቴን የምታፀዳው ሴት ደግሞ እስከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ድረስ አልመጣችም ነበር፡፡ እሷ እስክትመጣ ድረስ ደግሞ አይጡን ክፍሌ ውስጥ ልተወው አልችልም፡፡ ምክንያቱም አይጡ ምን አይነት በሽታ ይዞ እንደመጣ ማንም አያውቅም፡፡” ብሎ መለሰለት።
“እና መረጃ የሚሆነንን ነገር ነው የጣልከው?”
“መጣል ነበረብኝ”
“አይጡን ከክፍልህ ስታስወግድ ያየህ ሰው አለ?”
የለም ያው እንዳልኩህ በጣም መሽቶ ነበር” ብሎ ሲመልስለት የጆንሰን
ትዕግስት ተሟጥጦ ስላለቀ አሁንም ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ተነሳ፡፡
የታለ ቆሻሻ የምትጥልበት የቆሻሻ ማስቀመጫህ? ምናልባት አይጡ
እዚያው ቆሻሻ መጣያው ውስጥ ይኖር ይሆናል ይሄኔ” አለው ጆንሰን
ይህንን የጆንሰን ጥያቄ ሲሰማ ቢያንስ ካርተር ማፈር ነበረበት፤ ግን እሱ
ይበልጥ ድርቅ ብሎ “አሁን ላይ በእርግጠኝነት ባዶ ነው የሚሆኑት። ቆሻሻ የሚሰበስቡ ሰዎች ዛሬ በጠዋት ነው ያለወትሮ የመጡት። ያንን አስቢ
አይጡን ሌላ ቦታ ማስቀመጥ ነበረብኝ፡፡ ወይም በጣም ነው ያጠፋሁት.”ጆንሰን ወደ ዋናው የፖሊስ ማዘዣ ጣቢያ ለመመለስ መኪናውን በተጨናነቀ መንገድ ላይ ሲያሽከረክር ከአንድ ሰዓት በላይ ፈጅቶበታል ጣቢያውም የደረሰው በሚያስጠላ

ስሜት ውስጥ ሆኖ ነበር፡፡ ምክንያቱም ካርተርን ያገኘው በዶክተሯ ማስታወሻ ላይ እንደተገለፀው ያልተረጋጋ
አዕምሮ ያለው ሰው ሆኖ ነው። በዚያ ላይ ደግሞ ካርተር ሊዛን አይቷት አያውቅም፡፡ ከትሬይም ጋር የቀረበ ግንኙነት የላቸውም፤ እናም ደግሞ የተጠርጣሪያቸውን ብራንዶን ግሮልሽ የሚል ስምን ለአንድም ቀን ቢሆን
ሰምቶት እንደማያውቅ ነው የተገነዘበው፡፡ ብቻ በአጠቃላይ ባንከሩ ከዚህ
ወንጀል ጋር የተያያዘ አንድም ነገር እንደሌለው ለመረዳት በመቻሉ ካርተርን
ማግኘቱ ውድ ጊዜውን እንዳጠፋበት ብቻ ነው ያወቀው፡፡
የዋናው ማዘዣ ጣቢያ ህንፃ ውስጥ ገና እንደገባም ነበር ዋናው አዛዥ ሊያናግራቸው እንደሚፈልጓቸው ጉድማን የነገረው።
“እኮ ኣሁን?”
“አዎን አሁኑኑ” ብሎ ጉድማን የእጁን ሰዓት ከተመለከተ በኋላም
“እንዲያውም በማርፈድህ ተናድዶብሃል”
“እንዴ እኔ እንዴት ነው ያረፈድኩት?” ብሎ ጆንሰን ተቃወመው እና
“አሁን አይደል እንዴ ሊሰበስበን የጠራን? እኔ ጠዋት 1፡30 ላይ ቢሮገብቼ ነበር በክርስቶስ! እንዲያውም አንተ የት ነበርክ ያኔ?”
“ይቅርታ” ብሎ ጉድማን አጉረመረመ እና በመቀጠልም “ማታ የሆነ ነገር
ገጥሞኝ ስለነበር አርፍጄ ነው የተኛሁት።”
ጠዋት ላይ ጉድማን አልጋው ላይ ተኝቶ እያለ የትላንት ማታውን ከኒኪ ሮበርትስ ጋር ያሳለፈውን ምሽት እያሰበ ከዞረ ድምሩ ጋር ሲታገል ነበር።
ለስላሳ እና ሙቅ ገላዋን እንደፈለገው እያደረገ እንዲያድር ፈቅዳለት ነበር
እኮ፡፡ ግን ምርመራዬን ያበላሽብኛል ብሎ ነው ከእሷ ጋር ማደሩን የተወው።
“ጉድማን! ጆንሰን! ዛሬ የላችሁም እንዴ” ብሎ ዋናው የጣቢያ አዛዥ ብሩዲ እንደብራቅ ሲጮህ ድምፁ በገደል ማሚቶ እያተስተጋባ አዳራዃን
አልፎ የጉድማንን ጆሮ ሰነጠቀው።
“አቤት ጌታዬ!” ብለው የአዛዡ ቢሮ ውስጥ ገብተው ወንበር ስበው
ተቀመጡ።
“እሺ! እስቲ ስለምርምራችሁ አሳውቁኝ” አላቸው ብሩዲ፡፡
ብሩዲ ግዙፍ ሲሆን ዕድሜው በስልሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ይገኛል፡፡
በጣም በቶሎ የሚናደድ ከመሆኑም በላይ ሁልጊዜም ጨፍጋጋ ስሜት
የሚታይበት ሰው ነው፡፡
“ሁለት ተቆራርጠው የተገደሉ ሰዎች አሉን፡፡ ሰዎቹን የገደለውን ሰው
ወይንም ቢያንስ ተጠርጣሪው እንኳን አልተያዘም፡፡ አንዲት የታወቀች
ሳይካትሪስትም የግድያ ሙከራ ተደርጎበታል፡፡ ከተገደሉት መካከል አንዷ
ደግሞ የእሷ ታካሚና የቢሊየነር ቅምጥ የነበረችው ሴት ናት፡፡ ይህንን ነገር
ሚዲያዎች እንደ ጉድ እያራገቡት ይገኛሉ።” አላቸው በቁጣ ተሞልቶ
ሁለቱም ላይ እያፈጠጠ።
“አዎን ጌታዬ” አለ ጉድማን መሬት መሬቱን እያየ፡፡
“ግን ደግሞ ነገሩ እየባሰ እንጂ እየቀዘቀዘ አልሄደም።” አለ እና በቁጣ ጦዘ፡፡ ቀጠለናም “ደግሞ በኢንተርኔት ዞምቢው ገዳይ በሚል ርዕስ የገዳዩን ሰው ዜና እያራገቡት ይገኛሉ። እሱ እሺ ይሁን ዛሬ ደግሞ ጭራሽ ኤን.ቢ.ሲ 4 የቴሌቭዥን ጣቢያ ስለዚህ ዞምቢ ገዳይ የሚባል የማይረባ ነገር ጠዋት ላይ ሲዘግብ ነበር፡፡ ምንድነው በመስራት ላይ ያላችሁት?” ብሎ አሁንም
በቁጣ ስሜት ውስጥ እንደሆነ ጠየቃቸው፡፡
“ምናልባት ጉዳዩ ያፈተለከው ከሬሳ ምርመራው ሆስፒታል ሊሆን
ይችላል” ብሎ ጆንሰን መለሰ፡፡
“ዜናው ከየትም ቦታ አፈትልኮ ቢወጣ እኔ ግድ አለኝ ታዲያ?!” ብሎ ብሩዲ ይበልጥ በቁጣ ነበልባል እየነደደ ጠየቃቸው፡፡
ጆንሰንም በመቀጠል “የሬሳ መርማሪዋ ጄኔ ፎይሌ የተፋቀ የቆዳ ህዋስን
በመጀመሪያዋ ሟች ጥፍር ውስጥ አገኘች፡፡ ይህ ህዋስም በሁለተኛው ሟች
ላይ ከተገኘው የፀጉር ዲኤንኤ ጋር አንድ አይነት ሆነ፡፡ የቆዳ ህዋሱም ሆነ
ፀጉሩ የአንድ ብራንዶን ግሮልሽ የሚባል ከቤቱ የጠፋ ሰው መሆኑም ተረጋግጧል። ይህ ነገር ነው አፈትልኮ የወጣው እና በየኢንተርኔቶች ላይ
የተሰራጨው” ብሎ ጆንሰን አብራራ፡፡
ቺፍ ብሩዲም በረዥሙ ተነፈሰና “እና አሁን አንተ የምትነግረኝ ያለኸው
ዋነኛው በግድያው ላይ ተጠርጣሪ የሆነው ግለሰብ እንደሞተ ነው ማለት
ነው?” ይሄኔም ጉድማን ጣልቃ ገብቶ
“ብራንዶን ግሮልሽን ዋነኛ ተጠርጣሪያችን አድርገን አልያዝነውም። እሱ አደንዛዥ ዕፅ በብዛት በመውሰድ የተነሳ የዛሬ ስምንት ወር ህይወቱ አልፏል። ግድያዎቹን የፈፀመው ወንጀለኛም በሆነ መልኩ የብራንዶንን
ዲ.ኤን.ኤ በገደላቸው ሰዎች ላይ ሲያስቀምጥ ነበር፡፡ ይህንንም የሚያደርገው ብራንዶን ግሮልሽ እንደሞተ ስለሚታወቅ በግድያዎች ላይ ምርመራ
እንዳይደረግ ለማድረግ ነው” ብሎ ጉድማን አብራራ፡፡
“ይህ አንደኛው ቲዎሪያችን ነው” ብሎ ጆንሰን አልጎመጎመ::
“እሺ ሌላኛው ግምታችሁስ?” ብሎ ብሩዲ ጠየቃቸው፡፡
ብሩዲም አይኑን ከእነርሱ ላይ ሳይነቅል “ይሄኛው ግምታችሁ መቼስ ዞምቢ ምናምን የሚባል ነገር የለውም?”
“የለውም ጌታዬ” ብሎ ጆንሰን ጉሮሮውን ካጠራ በኋላ “ይሄኛው ግምታችን የሚያነጣጥረው ራሷን ዶክተር ኒኪ ሮበርትስን ማእከል በማድረግ ነው” ብሎ ሲናገር ጉድማን አይኑን በቁጣ ቢያጉረጠርጥበትም ጆንሰን ግን
ችላ ብሎት ነገሩን ማብራራቱን ቀጠለ፡፡
“መርማሪ ፖሊስ ጉድማን እና እኔ ለአራት ቀናት ያህል በታካሚዎቿ ላይ የፃፈቻቸውን ማስታወሻዎች ስናገላብጥ እና አንድ አንድ ታካሚዎቿንም ለማናገር ችለን ነበር። ሁለታችንም ግድያው የደረሰባቸው ግለሰቦች ከዶክተሯ ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል። እንዲያውም ጉድማን እራሷ ዶክተሯ የገዳዩ ዋነኛ ዒላማ እንደነበረች ያምናል” ብሎ ተናገረ፡፡
ዋና አዛዥ ብሩዲም አይኑን አጥብቦ ጆንሰንን እየተመለከተው “ግን አንተ
በዚህ ጉዳይ ላይ አትስማማም?” ብሎ ጠየቀው፡፡
“አዎን በባልደረባዬ ሀሳብ አልስማማም ጌታዬ! ምክንያቱም ዶክተሯ በመጀመሪያዋ ሟች በሊዛ ፍላንገን ላይ የፃፈቻቸው ማስታወሻዎች ጤናማ
አይደሉም። ሊዛ ፍላንገን ከባለትዳር ጋር ያላትን ወሲባዊ ግኑኝነት እንደማትወደው፣ ከቢሊየነሩ ያረገዘችውን ልጅ በማስወረዷም በጣም
እንደተበሳጨችባት እና ሊዛ የምትወስደውን ዕፅም ወዳው እየወሰደችው መሆኑን በሚገልፅ መልኩ ነበር ነበር ማስታወሻዎቹን የፃፈፈችው እኔ
እንደማምነው አንድ በስነ ልቦና ህክምና ላይ የተሰማራ ባለሙያ በሽተኞቹን
ማከም እንጂ ስለ በሽተኞቹ ፍርድ መስጠት አይጠበቅበትም ብዬ አስባለሁ።
በሟቿ ላይ የተፃፉት ማስታወሻዎች በሙሉ በበሽታዋ ላይ ፍርድን የሚሰጥ
ሆነው ከመገኘታቸውም በላይ በጣም በንዴት የተሞሉ አስተያየቶች ነበሩ።”
ብሎ ጆንሰን ተናግሮ ጨረሰ፡፡....

#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
....ታክሲው ውስጥ የሚጮኸው ሙዚቃ ጭንቅላቱን በጠበጠው፡፡ማታ እንቅልፍ አልወስድህ ብሎት ሲጨነቅ ነበር ያደረው::
“ምንድነው የሆንከው? ለምን አትነግረኝም?” አለች ዘውዲቱ
ከሆቴል ገዝታ ካመጣችው ምግብ እያጎረሰችው፡፡ “ምስኪን አሁንስ ሚስትህ
ናፈቀችሁ መሰለኝ::
ያጎረሰችውን እያላመጠ ዝም አላት:: ወሬ አላሰኘውም:: ምግቡም እንዳያስከፋት ብሎ ነው እንጅ ቢቀርበት በወደደ፡፡
እራት በልተው ተጣጥበው መብራቱን አጥፍተው አልጋ ላይ ከወጡ በኋላ ናትናኤል በጀርባው እንደተንጋለለ አያኖቹን ጣሪያው ላይ ተክሎ ቀረ፡፡
ምን ሆና ይሆን? እንዴት ሁለት ቀን ሙሉ ስራ ሳትገባ ትቀራለች በጤናዋ ባትሆን ነው እንጅ:: ደግሞ ምህረት እቤቷ: ደወዬ
የሚያነሳ አጣሁ ማለቷ ምን ማለቷ ነው? ቤቷን ዘግታ የት ትሄዳለች? ምናልባት አሟት ወላጆቿጋ ሄዳ ይሆን እንዴ? የወላጆቿን ቤት ደግሞ አያውቀውም ! ጉለሌ እንደሆኑ ነግራዋለች፡፡ ግን በደፈናው ጉለሌ ተብሎ አይኬድ፡፡ ቤቷ ሄዶ ይሞክር ይሆን?
ሌሊቱን ሲጨነቅ አደረ፡፡ አሁን ደግሞ ታክሲው ውስጥ ያለው ሙዚቃ አይሉት ጩኽት
“ሲጋራ ፋብሪካ ነው ያሉኝ?” አለው ባለታክሲው፡፡
“እ? አዎ የኔ ልጅ፡፡ ከዚህ ይበቃኛል፡፡” ናትናኤል የታክሲውን በር ከፍቶ ወረደ፡፡
“አባ ገንዘበስ?!” ባለታክሲው የመኪናውን ጥሩንባ ተጭኖ ጮኹ፡፡
“ይቅርታ! ይቅርታ!” አለ ናትናኤል ከሄደበት ተመልሶ ከጋቢው ስር
ከደረት ኪሱ ገንብ እያወጣ “ይቅርታ የኔ ልጅ፡፡ ሃሳብ ገብቶኝ ተዘንግቶኝ
ነው::” ገንዘቡን ለባለታክሲው አቀበለው
ዘውዲቱ የገዛችላት ላስቲክ ቦት ጫማ መንገደኛ ቢያስመስለውም እላይ ከፈፉ እግሩን ከርክሮት ክፉኛ አቁስሎታል። በተራመደ ቁጥር የጫማው ክፈፍ ቁስሉን ሲነካበትና ሲፈትግበት ይለበልበዋል፡፡
ከመንገዱ ባሻገር የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ህንፃ ብቻውን ተገትሯል ... ሥራ ፈት፡፡ ናትናኤል ይህንን ፎቅ ሲመለከት ምንም ትርጉም አይሰጠውም በፎቁ ቅርፅ ውስጥ መልዕክት ካለ አንድ የሚል መሆን አለበት ቀጥ ያለ ፎቅ እንድ፡፡
ናትናኤል አይኖቹን ከፎቁ ላይ ነቅሎ ሃሳቡን አሰባሰሰ፡፡ ለጥያቄው መፍትሄ የሚያገኝለት ካልቨርትን ቢያገኝ ብቻ እንደሆነ ከተረዳ ቆይቷል፡፡
ካልቨርትን : እግኝቶ የአውሬውን ማንነት ይፋ እስካላወጣ ድረስ የተደበቀውንና የተሸሸገውን ምሥጢር እስካላዝረከረከው ድረስ አንድ ቀን ከአንዱ ጥግ ነው የሚደፉት፡፡አብርሃምን እንደደፉት፡፡
ይህ ከመሆኑ በፊት ካልቨርትን ማግኘት አለበት፡፡ ግን ካልቨርትን ለማግኘት ከየት ሀ ብሎ እንደሚጀምር እንቆቅልሽ ሆነበት::
መረጃ የውስኪ ጠርሙስ ሾፌር ቤላ
መጠጥ ቤት…ሴት ሞሳድ ኤም አይ
ስድስት…ካዛንቺስ ወዳጁ ቤት… የሴት ልብስ ለብሶ ተሰወረ::
ቁልፉ የግድ እዚህ ውስጥ መሆን አለበት መፍትሄው እዚህ ውስጥ ከሌለ ካልቨርትን ሊያገኘው አይችልም:: ምክንያቱም እሱ የሚያውቀው ይህን ብቻ ነው አብርሃም የነገረውን፡፡
ያለጥርጥር ካልቨርት እንዲሰወር የካዛንቺሷ ወዳጁ ረድታዋለች፡፡ በመጨረሻ የታየው ከእሷ ቤት ሲወጣ ነው፡፡ ምናልባት የት እንደሚገኝም
ታውቅ ይሆናል፡፡ በተቻለው መንገድ ሴትየዋን ማግኘት አለበት:: ካልቨርትን
ለረዳው እንደሚፈልግ ሊያሳምናት ይገባል፡፡ ትጠረጥረው ይሆናል፡፡ ግን
ሊያሳምናት ከቻለና ካልቨርት ያለበትን ቦታ ከነገረችው ድብብቆሹ አበቃ ማለት ነው፡፡ ያን ጊዜ ያለጥርጥር አውሬውን መረቡ ውስጥ ይከተዋል፡፡
ካልቨርት የሚያውቀው ነገር እንደሌለስ? ማወቅ አለበት ምንም የማያውቅ ከሆነ ለምን ተሸሽገ? ያውቃል፡፡ ለሕይወቱ የሚያሰጋው ምሥጢር ይዟል፡፡ ያንን ምስጢር ማግኘት አለበት፡፡ ካልቨርትን ለማግኘት ደግሞ መጀመሪያ የካዛንቺሷን ሴት አግኝቶ ማሳመን፤ ማግባባት ማሽነፍ፡፡፡ እሷ ብቻ ነች ዕድሉ፡፡
ግን አውሬው ለምን ሴትየዋን አቆያት? ያለጥርጥር ወደ ካልቨርት
የምትመሪ መንገድ ነች:: ይህንን ደግሞ አውሬው ሳያውቀው የሚቀር አያደለም:: ታዲያ ለምን አሰነበታት? ለምን አስገድዶም በሆን የካልቨርትን
እድራሻ አላወጣጣትም? ወያም ለማንኛውም ወገን ምሥጢሩን የካልቨርትን አድራሻ እንዳትጠቁም ለምን እንደ አብርሃም አሳስወገዳትም?
ምናልባት ሴትየዋ ራሷ ወጥመድ እንደሆነችስ? የካልቨርትን አድራሻ የሚያነፈንፍ፡ አይጥ ወደ ካዛንቺስ እንዲመጣና ከወጥመድ እንዲገባ
የተንጠለጠለች የሥጋ ቁራጭ እንደሆነችስ? ካዛንቺስ ከመድረሱ እንገቱን ቆርጠው ቢጥሉትስ?'፡ ናትናኤል ሰጋ:ዠ ኣብርሃም ያለው ትዝ አለው
“… ሁለቱን የክትትል ሰዎች ባሰማራን በሶስተኛው ቀን አንደኛው ሰዋችን በስለት ታርዶ እዛው ካዛንቺስ ቱቦ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ.…”
ህ! “እዛው ካዛንቺስ” ወጥመድ
ያለጥርጥር ካዛንቺስ ወጥመድ ተጠምዶለታል፡፡ ቢሆንም ምርጫ
የለውም፡፡ ወደ ካልቨርት ሊቀርብ የሚችለው የካዛንቺሏን ሴት ሲያገኝ ብቻ
ነው:: የግድ ካዛንቺስ መሄድ አለበት፡፡
'ካዛንቺስ፡፡ ካዛንቺስ ምኑጋ? ካዛንቺስ ስንት አውራ መንገዶች አሉ?… ካዛንቺስ ስንት መጠጥ ቤቶች አሉ? የትኛዋ ነች የካልቨርት ወዳጅ? “የፈጣሪ ያለህ!' የካዛንቺስ ስፋቱና የቀሚስ ለባሹ ብዛት ታየው::
ሌላ ጥያቄ! እንዴት ሊያገኛት ይችላል? ማን ሊመራው ይችላል? አብርሃም ምንድነው ያለው.…?
የቅብብሎሹን ሠንሠለት መስበር ነው
ካልቨርት የሰረቀውን መረጃ…በውስኪ ጠርሙሶች…በሾፌርነት ለማያገለግል ኢትዮጵያዊ ያቀብላል..ሹፌሩ ቤላ መጠጥ ቤት ላላት.…”
ሹፌሩ ሹፌሩ ሌላ መጠጥ ቤት ያላትን ሴት ያውቃታል ማለት ነው፡፡ የካዛንቺሷንስ? ሊያውቃት ይችላል? ምናልባት ካልቨርት የሚቀርበው ከሆነ ሊያውቃት ያችላል፡፡ ያለው ምርጫ ሾፌሩ ነው:: ሾፌሩን አአግኝቶ የካዛንቺሷን ሴት እድራሻ እንዲሰጠው መጠየቅ::
ሾፌሩ የኛ ሰወ ነው በእሱ በኩል ነው
መረጃውን የምናገኘው...” ነበር ያለው
አብርሃም::
ሌላ ወጥመድ፡፡ ሾፌሩም አደገኛ ነው፡፡ ካዛንቺስ ያለችውን የካልቨርትን ወዳጅ ሆቴል ኣሳየኝ።” ሲለው መቼም መጠራጠሩ አይቀርም፡፡
“እሺ ና” ብሎ ገመድ አንገቱ ቢያስገባለትስ? መሬት ለመሬት እያንሻተተና እየጎተተ ቢያስይዘውስ? እርግጥ ያለው ምርጫ ወደ ካዛንቺሷ እመቤት የሚደርሰው ብቸኛ መንገድ የላይቤርያው ኤምባሲ ሾፌር ብቻ ነው:: ለይቶ የሚያውቀው አድራሻ የእርሱን ብቻ ነዋ! ቢሆንም ሰውየውን በአካል
መገናኘት የለበትም፡፡አንድ ዘዴ መፍጠር አለበት፡፡ ናትናኤል ለበርካታ ቀናቶች ሲያወጣ ሲያወርድ መልስ ሲሻለት የቆየው ጥያቄ ይህ ነበር፡፡መልሱን
አግኝቷል። አቅዶ ወጥኖ ጨርሷል፡፡ ትከሻው ላይ አላርፍልህ ያለውን ጋቢ
እያስተካከለ ከመንገድ ወዳለ ትንሽ ቁርስ ቤት ገባ፡፡
“የኔ ልጅ እባክሽ ስልክ ታስደውይኝ…እከፍላለሁ::ችግር አጋጥሞኝ ነው ልጅ ታማብኝ፡፡” አላቸው እናቱ የሚሆኑትን የቁርስ ቤቷን ባለቤት ጠጋ ብሎ። ያቀደውን ደረጃ በደረጃ ይፈጽም ጀመር፡፡
ሴትየዋ ስልክ ማስደወሉን ባይወዱትም ከቄስ ጋር! ከእግዚኣብሄር ሰው ጋር ክፉ መነጋገሩን አልፈለጉትም፡፡ ከባልኮኒው ስር አንድ ሰማያዊ ስልክ አውጥተው ቄሱ ፊት ቆለሉትና “ያው” ብለው ፊታቸውን አዙረው ሄዱ፡፡ · ደረታቸው ላይ የተቆለለው የጡት ተራራ የዘውዲቱን ጋራ
ያስንቃል፡፡
ናትናኤል ሴትየዋ ዞር እንዳሉለት የስልኩን መነጋገሪያ አንስቶ በመጀመሪያ ወደ ማዞሪያ ደውሎ የላይቤርያ ኤምባሲን የስልክ ቁጥር ከጠየቀና ካገኘ በኋላ ወደ ኤምባሲው ደወለ። በላይቤርያው ኤምባሲ ውስጥ ከአንድ በላይ ሾፌር ሊኖር ይችላል የትኛውን አቅርቡልኝ ሊል ነው? ብቻ ማናቸውም ቢሆኑ የካልቨርት

👍3❤2🥰1
ስም ሲጠራ ከትክክለኛው ሰው ጋር ያገናኙት ይሆናል፡፡ ያለው ምርጫ መሞከር ብቻ ነው:: አብርሃም “ሾፌር” ነው አልው እንጂ በስም ለይቶ አልነገረውም፡፡ 'ወይኔ! አብርሃም በኖረ ኖሮ አብረው ስንት ነገር በሰሩሳምንታት ሳይሆን በቀናት ውስጥ እጃቸው
ውስጥ ባስገቡት ነበር ካልቨርትን
“ሃሎ ላይቤርያ ኤምባሲ ” አለ ቀጭን የሴት ድምፅ፡፡
“ሃሎ... የእኔ እመቤት እባክሽ ከእናንተ ዘንድ መኪና የሚሾፍር ልጅ ነበረ…ዘመድ ከአገር ቤት መልዕክት አስይዞ ከእደራ ጋር ቢልከኝ ነው...ባክሽ እስጠሪልኝ፡፡”
“ማንን ነው የሚፈልጉት?ስሙ ማነው?”
“ሹፌር ..የኔ ልጅ …ሹፌር ነው፡፡”
“ስሙን ይንገሩኝ፡፡” መንጨቅጨቅ አደረገችው፡፡
“የኔ ልጅ ተዘነጋኝ ከአገር ቤት…”
“ስዩምን ነው?” አለች ልጅቷ በስጨት ባለ ድምፅ አቋርጣው፡፡
እዎ አዎ የኔ ልጅ እሱን ነው፡” ምርጫ አልነበረውም።
“አንድ ጊዜ ይጠብቁ፡፡”
ግንባሩ ላይ ቸፈፍ ያለውን ላቡን ጠረገና ተዘጋጀ፡፡ አሁን እንደቂስ ሳይሆን እንደ ወታደር ማውራት አለበት፡፡ ፈጣንና ቁርጥ ያለ መልክት፡፡ እንዳቀደው ለቀናት የተለማመደውን ዲስኩር ሊያወርደው ተዘጋጀ፡፡
“እቤት::” አለ በአፍንጫው የሚናገር የሚመስል ሰው::
ሃሎ ስማኝ ስዩም፡፡ ተጠንቅቀህ አዳምጠኝ::” አላ ናትናኤል ቆፍጠን ባለ ድምፅ:: “ካልቨርት ነው የላከኝ… ትሰማኛለህ?” ናትናኤል ለአንድ አፍታ ከወዲያ ያለው ሰው የሚያሰማው ድምፅ እንዳለ ተጠባበቀ፡፡
“እየሰማሁ ነው፡፡” አለ ሰውየው ፈጠን ብሎ፡፡
ሹፌሩ መሆን አለበት! ሌላ ሰው ቢሆን በፍጥነት ከሁኔታው ጋር ራሱን ለማዛመድ ይቸገር ነበር፡፡ ናትናኤል ደስ አለው፡፡
“ስዩም አሁኑኑ ከኤምባሲው ወጥተህ ከሲጋራ ፋብሪካ በላይ ካለች ትንሽ የቁርስ ቤት ድረስ እንድትመጣ፡፡ ቢጫ ቀለም የተቀባች የቁርስ ቤት ነች … ኮትህን አውልቀህ ቀትከሻህ ላይ አንጠልጥለው፡፡ ከአሥር ደቂቃ በላይ አልጠብቅህም፡፡”
ናትናኤል ስልኩን ሰውየው ጆሮ ላይ ጠረቀመውና የቁርስ ቤቷን የስልክ ቁጥር ኣንብቦ በጭንቅላቱ ይዞ ወደ ባለቤቲቱ ገ
ዞረ፡፡
“ተባረኪ የኔ ልጅ፡፡ እንጀራሽ ፡ከፍ ይበል:: የአያት የቅድመ እያቶችሽን ስም የምታስጠሪ ያርግሽ፡” ምርቃቱን አዥጎደጎደው፡፡ ወዲያው ጋቢውን እየገለበ “ስንት ነው ሂሣቡ .. የኔ ልጅ የደወልከብት?” እያለ ይፍተለተል ጀመር፡፡
“ግድየለም አባቴ ምርቃቶ ይበልጣል::” አሉ ሴትየዋ ከምርቃቱ እንዲጨምር የፈለጉ ይመስል፡፡ .
“ተባረኪ፡፡ ቤትሽ አይጓደል፡፡ ልጅሽን ጧሪ ቀባሪ ያድርግሽ…”ከምርቃቱ ሳያሳንስ ጋቢውን አስተካክሎ ከቁርስ ቤቷ ወጣና በፍጥነት መንገዱን ተሻግሮ ከሌላ ቡና ቤት በራፍ ላይ ቆም ብለው ይጠባበቅ ጀመር፡፡.....

#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....ዋናው አዛዥ ብሩዲም ወደ ጉድማን ዞሮ “አንተም ማስታወሻዎቹን
አንብበህ ጨርሰሃል አይደል? እሺ በጆንሰን ሀሳብ ትስማማለህ?”
ጉድማንም የእግሮቹን ንብብሮሽ ስላልተመቸው ቀያየራቸው እና ዶክተር
ሮበርትስ ስለ በሽተኞቿ በማስታወሻዎቿ ላይ የፃፈቻቸውን ነገሮች በውስጡ
መከለስ ጀመረ።
ዶክተር ሮበርትስ ማስታወሻዎቹን ሌላ ሰው ያነባቸዋል ስላልገመተች ስለ በሽተኞቿ የተሰማትን ነገሮች ሁሉ ነው ማስታወሻዋ ላይ ያሰፈረችው። ይህንን ደግሞ ያደረገችው ምናልባት በሚቀጥለው የህክምና ጊዜያቸው ላይ በሽተኞቿን ስታገኛቸው ከግለሰባዊ ባህርያቸው በመነሳት ልትረዳቸው በማሰብ እንደሆነም ያምናል። ግን እዚህ ላይ ጆንሰን ለዶክተሯ ያለው ጥላቻ ወደዚህ አይነት ማጠቃለያ ላይ እንዲደርስ ሊያደርገው እንደሚችል እንዴት አላሰበውም? ይህንን በውስጡ ሲያውጠነጥን ቆየ እና
“መልካም ማስታወሻዎቹ ላይ ስለ ታካሚዎቿ ስነ ባህሪ ግምገማን (ፍርድን)
አካሂዳለች ብዬ አምናለሁ” ብሎ መለሰ፡፡
ይሄኔም ጆንሰን የሹፈት ሳቅ ሳቀበት እና ግምገማ አልክ? ሮበርትስ እኮ ይህቺ ሊዛ ፍላንገን የተባለችን ሴት ትጠላታለች። በማስታወሻዋ ላይ ሊዛ ፍላንገን የምትገልፃት ለድርጊቷ መጠየቅ እንዳለባት ማለትም በሌሎች ሴቶች (ሚስቶች) ላይ ለፈጠረችው ስቃይ መጠየቅ እንዳለባት ነው የማስታወሻዋ ዋነኛ ሀሳብ” አለ፡፡
“ዋነኛው ሀሳብ ደግሞ ምንድነው?” ብሎ አዛዡ ግራ ተጋብቶ ጠየቀው።
ሚኪ ሮበርትስ ውሽማ በሚሆኑ ሴቶች ላይ ሁሉ ቂም አላት” አለ ጆንስን፡፡
“እንዴ ይሄ እኮ ሃጢአቱን እሷ ላይ ማብዛት ነው።” ብሎ ጉድማን
ጣልቃ ገባ ።
“ይመስልሀል? እኔ ግን አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም ማስታወሻዋን
ካነበብኩኝ በኋላ ለምንድነው በሊዛ ፍላንገን ላይ ይህን ይህል ቅሬታ
ያደረባት? ብዬ ራሴን ጠየቅኩኝ” ብሎ ጆንሰን ማብራሪያውን በመቀጠልም
“በመጨረሻም ነገሩ ከሟች ባሏ ጋር በተገናኘ እንደሆነ ለማወቅ በቃሁ”
“ባሏ ሞቶ አይደል እንዴ?” ብሎ አዛዥ ብሩዲ ጉንጩን እያሸ ጠየቀ::
“ልክ ነው ባሏ ሞቷል። ዶክተር ዳግላስ ሮበርትስ ባለፈው ዓመት በ 405 ኛው ጎዳና ላይ የአደጋው ምክንያት ባልታወቀ የመኪና አደጋ ህይወቱን አጥቷል። ግን በወቅቱ መኪናው ውስጥ ከእሱ ጎን ማን እንደነበር እስቲ ገምቱ” አላቸው፡፡ ሁለቱም አዛዥ ብሩዲ እና ጉድማን ግምታቸውን ለማስቀመጥ በጥሩ ስሜት ውስጥ ስላልሆኑ ምላሹን እንዲሰጣቸው
እያፈጠጡበት ዝም አሉ።
“ውሽማው አብራው ነበረች!” ብሎ ጉድማን በመቀጠልም “የሆነች
ሩሲያዊ ሴትን ከጎኑ አስቀምጦ መኪናውን ሲያሽከረክር ነበር አደጋው የደረሰው። በአደጋው ሁለቱም ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ያን ዕለት ነበር ዶክተር ኒኪ ሮበርትስ ባሏ ከትዳር ውጪ ያለውን ግንኙነት ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቀችው እንግዲህ”
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደጋው ከነደደ መኪና ውስጥ የሁለት ሰዎችን ሬሳ ሲያወጡ እሷ ምን ሊሰማት እንደሚችል አስቡት እስቲ! የውስጥ ህመሙን? ውርደቱን? ሁሉም ሰው እና እናንተም ጭምር ሁለቱ ምን ያህል የሚቀናበት ትዳር እንዳላቸው ታምኑ አልነበር?” ብሎ ጆንሰን ጉድማንን አገኘሁህ በሚል ስሜት ተመለከተው፡፡
ኒኪም ማታ ላይ ስለ ባሏ በግልፅ ነግራዋለች፡፡ ስለ ባሏ የተናገረችበት
መንገድ ግን ሀዘን እና ንዴት የተቀላቀለበት እንደሆነም በወቅቱ ተረድቶ
ነበር። ያም ቢሆን ግን ስለ ባሏ ውሽማ ምንም አይነት ነገር እንዳልነገረችው
አስታወሰ። በተጨማሪ ደግሞ ኒኪን ያገባ ወንድ ምንጎድሎበት ነው ሌላ ውሽማ የሚይዘው? ዊሊ ባደን ቫለንቲና ስላረጀችበት ሊሆን ይችላል ሌላ
ወጣት ሴት የወሸመው፡፡ ስለዚህም ጆንሰን ሆን ብሎ ነገሩን እንደፈጠረ
ገመተ፡፡
“ይህንን አንተ እንዴት አወቅክ?” ብሎ በቁጣ ድምፅ ጠየቀው፡፡
“በኢንተርኔት ላይ ተገልፆ ነበር፡፡” ብሎ ጆንሰን መለስ እና በመቀጠልም
“ወዲያው አደጋው እንደደረሰ ሳይሆን ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ነው። ታዲያ ዜናው ላይ የተገለፀው:: ከዶክተር ዳግላስ አጠገብ አንዲት ሴት ብቻ
ነበረች ብሎ ነው የዘገበው፡፡ እኔ ግን የዶውግን እና የኒኪን የቅርብ ጓደኞቻቸውን አግኝቼ በመጠየቅ እውነቱን ለማረጋገጥ በቃሁ። ይሄንን አስቀያሚ ሚስጥሯንም ደብቃናለች። ይህ ሚስጥሯም ነው እንግዲህ ከፍተኛ
ንዴት ውስጥ የሚከታት...”
“እሺ ባሏ እንደፈለገ እየማገጠ ነበር እንበል። ታዲያ ይህ ነገር ከሁለቱ
ግድያዎች ጋር ምን ያገናኘዋል?” ብሎ ብሩዲ ጆንሰንን ጠየቀው፡፡
“ጌታዬ እኔ በዚህ ዙሪያ ስላሉ ነገሮች በትንሹም ቢሆን ምርመራዎቼን
ለማድረግ ሞክሬ ነበር። ከሁለት ቀናት በፊት ስለ አደጋው የተደረገውን
ሪፖርትንም ለማየት ሞክሬ ነበር። በዚህም ስለ ዶክተር ዳግላስ እና ስለ
ሩስያዊት ውሽማው ለማወቅ የበኩሌን ጥረት ሳደርግ ነበር።”
ይሄኔም ጉድማን ከተቀመጠበት ፍንጥር ብሎ ተነሳ እና “ይሄን ነገር እኮ
አልነገርከኝም!” ብሎ በመጮጮህ ተቃውሞውን አሰማ፡፡
እንዴ አንተ ሥራ በዝቶብህ ነበር እኮ ታስታውሳለህ?” ብሎ ጆንሰን መለሰለት እና “በዚያ ላይ ደግሞ አንተው ራስህ እንዳወራህልኝ ግልፅ አልነበርክም። ለማንኛውም አታስብ ስለ አደጋው የቀረበ ሪፖርት አንድም የተመዘገበ ነገር አላገኘሁም”
“ምን ማለትህ ነው?” ብሎ ነገሩ እንቆቅልሽ የሆነበት አዛዥ ብሩዲ
ጥያቄውን አቀረበ፡፡
“አዎን ሲስተሙ ላይ አደጋው የተመዘገበ አንድም ሪፖርት የለም ወይንም አደጋው ጨርሶ አልተመዘገበም ወይንም ደግሞ የተመዘገበውን የሆነ ሰው ሰርዞታል” ብሎ ሲናገር አዛዥ ብሩዲ በስልቸታ ፊት ሲያየው ጊዜ ጆንስን ማብራሪያውን ቀጠለ። “ወደ ነጥቤ እየመጣሁ ነው አንዴ ታገሱኝ።ይሄ ደግሞ ነገሩን ይበልጥ እንድመረምረው ምክንያት ሆነኝ። አደጋው እንደደረሰ እንኳን እኔ ማንም ሰው ያውቀዋል። አደጋው በየጋዜጦቹ ላይ
በጊዜው ሲፃፍ ነበር፡፡ በተለይ ደግሞ ኤል.ኤ.ታይምስ ዶክተር ዳግላስ ምን
ያህል ትሁት እና ጨዋ ሰው እንደሆነ፣ ባሏ የሞተባትንም ዶክተር ኒኪንም
ምን ያህል የተጎዳች ቆንጆ መልከ መልካም አድርጎ ነበር ሲፅፍላቸው
ማንኛውም ጋዜጣ ወይንም መፅሄት ግን አብራው ስለሞተችው ሩስያዊት
አልገለፁም፡፡ የሩስያዊቷ ጉዳይ የወጣው ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ነበር።
ለማንኛውም ዶክተር ግላስ ቴስላ መኪናዋን የገዛበትን የመኪና መሸጫ
ቦታን ፈልጌ አገኘሁት:: እዚያም ደርሼ ከአደጋው በኋላ የመኪናውን
የኮምፒውተር ሲስተም የመረመረውን ኢንጅነር አግኝቼው ነበር። እሱ
እንደነገረኝም ከአደጋው በፊት የመኪናው የኮምፒውተር ሲስተም ተበላሽቶ
ነበር።
“ተበላሽቶ ነበር ማለት?”
“በሪሞት ኮንትሮል ሀክ ተደርጎ ነበር” አለ እና ጆንሰን ማብራሪያውን በመቀጠልም “በነገሩ በጣም እርግጠኛ ባይሆንም የመኪናው የኮምፒውተር ሲስተም ኮድ ተዛብቶ ስለነበረ ይሄ የኮድ መዛባት ደግሞ መኪናው የሆነ ፍጥነት ካለፈ በኋላ የፍጥነትና እና የፍሬን ሲስተሙ ተናብበው እንዳይሰሩ እንደሚያደርጋቸው ገምቶ ነበር፡፡ ይህንን ነገርም በወቅቱ ለአለቃው አመልክቶ ነበር። አለቃውም ነገሩን ለፖሊስ ሪፖርት እንዲያደርግም
አሳስቦት ነበር”
“እናስ ጉዳዩን ለፖሊስ አመለከተ አለቃው?” ብሩዲ ጠየቀ፡፡
“ቅድም እንደነገርኳችሁ ስለ አደጋው ሪፖርት የተመዘገበ ነገር የለም::
ስለዚህ የኢንጅነሩ አለቃ ጉዳዩን ለፖሊስ ያመልክት አያመልክት ለማወቅ አልቻልኩም፡፡ የኢንጅነር ዴመን አለቃም ባለፈው ፋሲካ በልብ በሽታ ህይወቱ አልፏል” አላቸው
ጆንስን ይህንን ከተናገረ በኋላ ጉድማን እና የፖሊስ አዛዥ ብሩዲ

ለአፍታ ያህል ዝም ብለው ቆዩ፡፡
“እሺ እስቲ ስለ አንተው ሀሳብ ጉዳይ ጨርስልና” አለው ብሩዱ፡፡
“የእኔ ፅንሰ ሀሳብማ ምን መሰለህ አለቃ? ኒኪ ሮበርትስ አዕምሮዋ የተነካ ወንጀለኛ ነገር ናት ብዬ አስባለሁ። ከአደጋው በፊት ባሏ ዶክተር ዳግላስ ከትዳሩ ውጪ እያማገጠ እንደሆነ በሆነ መልኩ አውቃ ነበር። በተለይ ደግሞ እሷ ለማርገዝ የሚያስችላትን ህክምና እያደረገች ባለችበት ሰዓት ይህንን ማወቋ እንደ ቀውስ አደረጋት። ስለዚህም የመኪናውን ሲስተም ለሚያበላሽላት አንድ ሰው በመክፈል ሲስተሙን አበላሸላት። በቃ እሱን እና ውሽማውን በመኪና አደጋ እንደሞቱ አድርጋ አስወገደቻቸው።”
“ኧረ ስለ ክርስቶስ ብለህ ይህ ሊሆን አይችልም!” ብሎ ጉድማን በንዴት
አይን ጆንስንን ተመለከተው፡፡ ጆንሰን ግን ማብራራቱን ቀጠለ፡፡
“ባሏን እና ውሽማውን የማስገደል እቅድ እንደ ህልም ነበር የተሳካላት እና ማንም አልጠረጠራትም፡፡ ከግድያው በኋላ የባሏ ንዴት አልበረደላትም እና ይሄንን ንዴት ማስወገድ ይገባታል። ስለዚህ ለውሽማዎች እና የሰውን ትዳር በሚያበላሹ ሰዎች ላይ ሁሉ ቂም ይዛ ቆየች። ሊዛ ፍላንገንም ከውሽሞች ምድብ ስለምትመደብ ውስጧ ያለውን ንዴቷን ለመወጣት የሆነ ሰውን ቀጥራ ሊዛ ፍላንገን አስገደለቻት።
“ምናልባትም ጉድማን እንደጠቆመው ግድያውን ማን እንደፈፀመው
እንዳይታወቅ የብራንዶን ግሮልሽ የሞተ ህዋስን ሟች ላይ እንዲገኝ አድርገው ይሆናል”
እኔን እዚህ ግምት ውስጥ አትክተተኝ ብሎ ጉድማን ጮኸና በመቀጠልም “ይሄ በፍፁም የማይረባ ሀሳብ ነው! ሚክ በኒኪ ሮበርትስ ይህንን አድርጋለች የሚያስብልህ አንድም ማስረጃ የለህም እኮ!”
“በዚህ እንኳን አልስማማም። አየህ እዚህ ላይ የሆነ የክህደት ነገር ይሸተኛል። ኒኪ ለሊዛ ፍላንገን መውደድ እንዳላት ስትነግረን ነበር፡፡ ነገር ግን ስለ ሊዛ የፃፈችው ነገር የሚያሳየው ተቃራኒውን ነው:: ባሏንም አሁንም አፈቅረዋለሁ ብትልም ብዙዎች የሚያውቋት ሰዎች አሁንም ቢሆን በእሱ ከትዳር ውጪ መማገጥ ከፍተኛ ንዴት ውስጥ እንደምትገኝ ነው የመሰከሩልኝ፡፡ ኒኪ ሮበርትስ በጣም ብልህ ሰው ስለሆነች ሰዎችን በቀላሉ አምኛለሁ ብላ ታስባለች፡፡ እኔ ግን እሷን የማስባት እንደ አንድ የወጣላትዐውሽታም እና ነፍሰ ገዳይ ነው:: እስከ አጥንቴ ድረስ ነው እሷ እነዚህ ሁለት ግድያዎች ውስጥ እጇ እንዳለበት የሚሰማኝ!” አለ፡፡
“ኧረ ባክህ! ገና ከመጀመሪያው ጀምሮ ነው ለእሷ መጥፎ ስሜት እንዳለህ ስመለከት የነበረው!” ብሎ ጉድማን በንዴት ተናገረው፡፡
“አንተ ደግሞ በአካል ካገኘሃት ጀምሮ ልትተኛት ትፈልግ ስለነበረ ይሄ ለእሷ ያለህ ስሜት እንዳታመዛዝን አዕምሮህን ደፍኖብሃል።” አለው ጆንሰን።
እሺ በቃ!” ብሎ የፖሊስ አዛዡ ብሩዲ ጣልቃ ገባ እና “ሁለታችሁም
ሥርዓት ያዙ! እሺ ጆንሰን የትሬይ ግድያስ? እሱ እና እሷ ይቀራረቡ
አልነበረ እንዴ?” ብሎ ጠየቀ፡፡
ከላይ ሲታዩ የሚቀራረቡ ይመስሉ ይሆናል፡፡ ግን በውስጣቸው ያለውን
ማን ማወቅ ይችላል? ምናልባት ትሬይ የዶውግን ከትዳር ውጪ የመማገጥን
ሁኔታ አስቀድሞ ያውቅ ነበር:: የባሏን ከሌላ ሴት ጋር ያለውን ግንኙነትም
ደብቆ ሳያሳውቃት ቀርቷል:: ወይንም ደግሞ እሷ ከ ዶውግ የመኪና አደጋ
ጀርባ እንዳለች ሊያውቅ ይችላል። ወይንም ደግሞ እሷ ሊዛ ፍላንገን መግደሏን በደንብ አውቋል ትሬይ ደግሞ ለሊዛ ፍላንገን የተለየ ስሜት ቢኖረውስ? በነገሩ ዙሪያ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ አሁን ላይ የለኝም ጌታዬ”ብሎ ጆንሰን አመነ እና “ያው ነገሩ በፅንስ ሀሳብ ላይ የተመሰረተ ግምት ነው::”
“መልካም” አለ እና ሁለቱን የእጁን መዳፎች ጠረጴዛው ላይ በማስቀመጥ ውይይታቸው እንደ አበቃ አሳወቀ እና “መልካም እንግዲህ ፅንሰ ሀሳብህን እቀበልሃለሁ፤ ግን ሀሳብህ ያልተቋጨ እና ገና ክፍት መሆኑን እወቅ”
ይሄኔም ጉድማን ተቃውሞውን ለማሰማት በማለት “አለቃ!” ብሎ ሊቀጥል ሲል አቋረጠው እና “ልክ ያንተንም የሆነ ወንጀለኛ ሰው የብራንዶን ግሮልሽን ሬሳ ሰርቆ ግድያውን ማን እንደፈፀመው እንዳታውቅ እያደረገ ነው የሚለውን ሀሳብህን እንደተቀበልኩት ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም ሀሳባችሁን የሚያረጋግጥ ተጨባጭ ማስረጃ እንድታቀርቡልኝ
በተጨማሪም በግድያው ተጠርጥሮ የሚገኝ ሰውን አስራችሁ እንድታሳዩኝ
እፈልጋለሁ።” አላቸው አለቃ ብሩዲ፡፡
“እሺ ጌታዬ” ብሎ ጆንሰን መታዘዙን ለማሳየት አንሾካሾከ፡፡
ብሩዲም ኮስተር ብሎ “ሚክ ለተናገርካቸው ነገሮች በሙሉ ማስረጃ
ማቅረብ ይኖርብሃል፡፡ ስለዚህም ከዚህ በኋላ ኒኪ ሮበርትስን እና ታካሚዎቿ
ላይ በማይገባ መልኩ ጥቃት ማድረስህን ማቆም ይኖርብሃል”
“እኮ እኔ ነኝ ያልተገባ ጥቃት በማድረስ ላይ ያለሁት?” ብሎ ጆንሰን ጠየቀ፡፡
“በአንተ ዙሪያ ደግሞ አራት ሰዎች በሥርዓቱ ቢሮ ድረስ መጥተው
ቅሬታዎች ቀርበውብሃል፡፡ አንዱ ከዶክተር ሮበርትስ፣ አንዱ ከትሬየቨን ሬይሞንድ እናት፣ አንዱ ከካርተር በርክሌይ እና አንዱ ደግሞ ከዊሊ ባደን የቀረቡብህ ቅሬታዎች ናቸው፡፡ ሁሉም ቅሬታዎች ደግሞ አንተን ባለጌ ጠብ ፈላጊ...” ብሎ ብሩዲ ሳይጨርስ ጉድማን የባልደረባው ፊት መልክ ከነጭነት ወደ ሃምራዊነት ወደሚያደላ ቀይነት ሲለወጥ ተመለከተ። ያም ቢሆን ግን ጆንሰን እንደምንም የንዴት ስሜቱን ውጦ ነበር ለአለቃቸው መልስ የሰጠው፡፡
“ከይቅርታ ጋር ጌታዬ! ኒኪ ሮበርትስ አዕምሮዋ የተነካ ወንጀለኛ ናት።
ካርተር በርክሌይ ደግሞ በትክክል የተመሰከረለት በቀን ቅዥት ውስጥ
የሚገኝ የስነልቦና ችግር ያለበት ሰው ነው እና ደግሞ ዊሊ ባደንም ቢሆን የሆነ የድሮ አራዳ፣ የአሁን ዘመን ደግሞ ፋራ ነው...” ብሎ ጆንሰን ሊቀጥል ሲል ብሩዲ አቋረጠው “መርማሪ ፖሊስ ጆንሰን ዊሊ ባደን እኮ ቅልጥጥ ያለ ሀብታም መሆኑንም የዘነጋህ መሰለኝ አለው እና ወንበሩ ላይ ለጠጥ በማለት.....