#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
በድንገት የተከሰተው አደጋ ክፉኛ ስላስደነገጠው ሻምበል ብሩክ ቀን እረፍት፤ ሌት እንቅልፍ፤ የሚባል ነገር አጥቶ እንደዚሁ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ከረመ፡፡ ለዚሁ ጉዳይ ሲልም ከመስሪያ ቤቱ የአስራ አምስት ቀን ፈቃድ ወሰደ፡፡ በዚህ ፈቃድ በወሰደበት ጊዜው
ውስጥ ደግሞ ብዙ መሯሯጥ ይጠበቅበታል፡፡መጀመሪያ ሆስፒታል የተኛች እናቷን ማረጋጋት አለበት :: ከዚያም ለወንድሟ በቂና አሳማኝ ምክንያት መስጠት ይጠበቅበታል ይህንን ሁሉ ሲያደርግ በሀሳብ የምትረዳውና ! አብራው የምትሯሯጠው! አዜብ ብቻ ነች፡፡ አዜብ ስለደረሰው አደጋ የትህትና አክስት እንዲያውቁት ፈልጋ ነበር፡፡
"አይሆንም ትርፉ ማስደንገጥ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ እነሱ ካወቁ ወሬው መዛመቱና፤ እናትዋ ጆሮ መድረሱ የማይቀር ስለሚሆን፤ በሚስጥር ቢያዝ ይሻላል” በማለት የተከራከረው ሻምበል
ነው፡፡ሻምበል ለእናቷ የሚሰጠው ምክንያት አሳማኝ እንዲሆን ሀሳብ
ሲያወጣና፧ ሲያወርድ፤ አዜብም እንደዚሁ ያሳምናታል ብላ ያሰበችውን ምክንያት ስትደረድር፤ ቆዩና ሁለቱም ይሆናል ባሉት ሃሳብ ላይ በጋራ ከተስማሙ በኋላ፤ ይህንኑ ሊያስረዳ ወደ የካቲት አስራ
ሁለት ሆስፒታል አቀና፡፡ ትህትና ከእናትዋ ጋር በአይነ ስጋ ከተገናኙ ሶስት ቀን ሆኗቸዋል፡፡ አንዱአለምም ድምጹ ከጠፋ ሳምንት አልፎታል፡፡በነገሩ እናት ግራ ተጋብታለች፡፡
"ልጆቼን ምን ነካብኝ?" በሚል ጭንቀት ተውጣለች፡፡ትናንትና ሆስፒታል መጥታ ያስተዳደረቻት ሰራተኛዋ ነበረች፡፡ ትህትና ከቤት ያለማደሯን ብቻ ነው የነገረቻት፡፡ በሽታዋን ማዳመጡን ትታ ልጆችዋን
እያብሰለሰለች፤ በሀሳብ እንደተዋጠች ነበር ሻምበል ብሩክ የደረሰው፡፡ብሩክን ስታየው በደስታ ልቧ ቀጥ አለች ::
"ትህትናዬስ ብሩኬ?" ከኪሱ አውጥቶ ይሰጣት ይመስል በጉጉት አይን አይኑን እያየች ጠየቀቸው፡፡ ሻምበል ብሩክ እንደማፈር ብሎ ሳቅ አለና፤ ተቅለሰለሰ፡፡ ለዘዴው...
“ምነው ብሩኬ በደህና ነው?" ከሁኔታው የከፋ ችግር እንደሌለ ተረድታለች፡፡
“ምንም ችግር የለም እማማ፡፡ ምን የኛ የወጣቶች ነገር...
የሚያሰጋ ነገር ያለመኖሩን ከሁኔታው ብትገነዘብም ምክንያቱን ለማወቅ
ቸኮለች፡፡
"ምንድነው እሱ ታዲያ?
ትህትና ምንም እንኳ እጮኛዬ ብትሆንም፤ ከትዳር በፊት እርግዝና ማለት፤ ትንሽ ያልተለመደ ስለሆነ... አንጠልጥሎ ተወው። ነገሩ ገባት
ከዚያ በላይ ልታስጨንቀው አልፈለገችም እሱ ግን ቀጠለ "ከጋብቻ በፊት ልጅ መውለድ የቤተሰብን ክብር መንካት ነው የሚል እምነት አላት፡፡ ተመካከርንና ማህጸኗ እንዲጠረግላት አደረግን፡፡ አሁን
ራስ ደስታ ሆስፒታል ትንሸ እረፍት ትውለድ ስላሉኝ አስተኝቻታለሁ።"አለና አጭር ድራማውን አጠናቀቀ፡፡ እናት የልጇን አቋም በእርግጥ ታውቀዋለች፡፡
አባቷ ያሳደጋትም በዚያ እምነት ጸንታ
እንድትኖር ነውና፤ በወሰደችው እርምጃ የተቃወሞ ድምጽ አላሰማችም፡፡
ነገሩን ውስጥ ውስጡን ስታብላላ ቆየችና......
“ሻምበል አደራህን! ትሁቴ ህጻን ልጅ ናት።እንደታላቅ ወንድም ተንከባከባት፡፡ እሷ ምኑንም የማታውቅ አንድ ፍሬ
ልጅ ናት፡፡ ለመጠንቀቁም ቢሆን አንተ ትሻላለህ፡፡ እሷ ምኑን ታውቀዋለች ብለህ
ነው?" የአሁኑ ስህተት እንዳይደገምና፤ በሌላ ጊዜ ተጨማሪ ጉዳት
እንዳይደርስባት፤ ሻምበል ሃላፊነቱን እንዲወጣ በማሳሰብ፤ አደራዋን
አጠበቀች፡፡ እሱም ትህትና ከሆስፒታል እንደወጣች ይዟት እንደሚመጣ
ቃል ገባላት፡፡ በመጠኑም ቢሆን ልቧ ትንሽ እረፍት አገኘ፡፡
“የአንዱአለሜ ወሬስ ? ምነው ጭልጥ ብሎ ጠፋ?" አከታትላ ጠየቀችው፡፡
“እኔ ራሴ ካገኘሁት ሳምንት ሆኖኛል እማማ፡፡ ለፈተናው ዝግጅት ሸፍቷል፡፡ ዘንድሮ አንደኛ ካልወጣሁ ሰው አይደለሁም ሲል የፎከረውን ለመፈፀም ቆርጦ መነሳቱን ትህትና ነግራኛለች። ምንም አያስቡ፤ ፈተናውን እንደጨረሰ እንዲመጣ እነግረዋለሁ።” ምክንያቱ
ብዙ ባይዋጥላትም የሻምበልን የማፅናኛ ቃል ከማዳመጥ በስተቀር አማራጭ አልነበራትም፡፡ዝም አለች፡፡ ከዚያም ሻምበል በግማሽ ልቡ ሆኖ፤ የሆነ ያልሆነውን፤ ሲያወራት ከቆየ በኋላ፤ ተሰናብቷት ወደ ትህትና ሩጫውን ቀጠለ....
ትህትና የቀዶ ህክምና ከተደረገላት በኋላ በአንደኛ ማእረግ እንድትተኛ ያደረገው ሻምበል ብሩክ ነው፡፡ ሻምበል አስፈላጊውን ክፍያ በመፈጸም ንጽህናው በተጠበቀና፤ ተጨማሪ በሽተኛ በሌለበት
አንደኛ ማእረግ ውስጥ እንድትተኛ የፈለገበት ዋናው ምክንያት፤
በሚተኙ በሽተኞች ስቃይ ተጨማሪ የአእምሮ መረበሽ ሊደርስባት ይችላል በሚል ፍራቻ ነው፡፡
ለቀዶ ጥገናው የተወጋችው ማደንዘዣ ስራውን በማጠናቀቁ ለአስቸኳይ ህክምናው በተሰጣት በሀያ አራት ሰአት ውስጥ ከሰመመናዊ እንቅልፉ ነቃችና አይኗን ገለጥ አደረገችው፡፡ ጣሪያውን ተመለከተች፡፡ ዙሪያዋን ቃኘች
የት እንዳለች፤ ምን እንደሆነች፤ በፍጹም
አታውቀውም፡፡ የተወጋችው የእንቅልፍ
መርፌ ፤ በጥይት የቆሰለው ሰውነቷና
እንደ ጉድ የፈሰሰው ደሟ መላ
አካሏን ድቅቅ አድርጐታል፡፡ከግራ ጆሮዋ ጀምሮ ፊቷ በአጠቃላይ በፋሻ ተሸፍኗል፡፡በክንዷ ላይ የተሰካውን ግሉኮስ ተመለከተችው፡፡ ጠብ ጠብ... እያለ
ይወርዳል። እንደገና አይኗን ጨፈነች፡፡ትንሽ ቆየችና መልሳ ገለጠችው::
እንደገና በሀሳብ ባህር ውስጥ ገባች፡፡ ምን ነበር የሆነው ? የት ነው ያለችው? እዚህ ለምን መጣች? እሷ ማን ነች? ቆይ .. ቆ ይ.. ምን ነበር የሆነው ? የሆነ
ነገር ብዥ ፧ ብዥ አለባት እንዴ ?..
መርካቶ ውስጥ እንደሻውን... ከዚያ በኋላ እራሷን... እንዴ?
ምንድነው ነገሩ? እሷ ሞታለች አይደለም እንዴ? በሰማይ ቤት ነው ወይንስ በምድር ላይ ያለችው? በዚያች በተሰናበተቻት ምድር ላይ? በፍጹም ሊሆን አይችልም! እንቆቅልሹም ሊገባት አልቻለም፡፡ ከዚያም ፊት ለፊትዋ የተቀመጡትን ሰዎች ትኩር ብላ ተመለከተቻቸው፡፡
ብዥ ፤ ብ ዥ ፤አሉባት አላወቀቻቸውም :: እነሱ በሀዘን ተውጠው አይን አይኗን ይመለከቷታል፡፡ እንደገና ትኩር ብላ ከመታሸግ በተረፈው በቀኝ አይኗ አየቻቸው፡፡ አሁንም አላወቀቻቸውም፡፡ እንቅስቃሴ የላትም፡፡እዚያ ከፊት ለፊቷ ሆነው በሀዘን ኩርምት ጭብጥ ብለው የተቀመጡትን ሰዎች በድጋሜ በጥንቃቄ ተመለከተቻቸው፡፡ የሆነ ምስል መጣላት፡፡
የምታውቀው ምስል በርቀት የምታውቀው ምስል.. አዎን
ታውቃቸዋለች እንጂ !! እንዴ..? በሚገባ ታውቃቸዋለች :: ቀስ ብላ በለሆሳስ ተጣራች "ብ..ሩ. ኬ..... አ . ዜ. ቢ . ና
እህህህ....." በዚህ ጊዜ አዜብ ቀስ ብላ ተነሳችና ሄዳ አጠገቧ ቆመች፡፡ ብሩክም አዜብን ተከትሎ ወደ አልጋው ተጠጋ፡፡ሻምበል እንደዚያ ሆና ሊያያት አልቻለም :: እንባው አመለጠውና ቀስ ብሎ ጉንጮቹን
እያቋረጠ ፈሰሰ፡፡
“እ ማ ዬ...ደ ህ...ና. ነች? ..አ.ን.ዱ.ዬስ..?"
"ሁለቱም በጣም ደህና ናቸው፡፡ ስለ እነሱ ምንም አታስቢ፡፡ እኛ አለን፡፡ አሁን ዋናው ማሰብ ያለብሽ ስለራስሽ ጤንነት ብቻ ነው እሺ?” አዜብ ነበረች፡፡
“እ..ሺ በደከመ ድምጽ፡፡
“ትሁት አዜብ የምትልሽን ስሚያት፡፡ስለ እማማ ምንም የሚያስጨንቅሽ ነገር የለም፡፡እሳቸው አንቺ ስለጠፋሽባቸው ነው ትንሽ ያሰቡት እንጂ በጣም ደህና ናቸው፡፡ ቶሎ ድነሽ ሄደሽ እንዲያዩሽ
በሃሳብና በጭንቀት ራስሽን መጉዳት የለብሽም፡፡ እሺ? አንዱ አለምም ድኗል ማለት ይቻላል፡፡ሰሞኑን መጥቶ ይጠይቅሻል እሺ?” ጉንጮቿን
እየዳበሰ፡፡
እሺ” አለች በድጋሜ፡፡ በዚያው ድክምክም ባለ ድምጿ። አሉኝ የምትላቸውና የምትተማመንባቸው ሁለቱ ጓደኞቿ፤ ደራሾቿ ፤ በዚህ በክፉ ቀን እንኳ ከጐኗ

👍1
ሳይለዩ ፤ አጠገቧ ቆመው ተስፋ
ሲሰጧት፤ እናቷን የማየት ጉጉት፣ ወንድሟን በድጋሜ የማግኘትን
ፍላጎት፤ እንደገና የመኖርን ተስፋ፤ እነዚያ ዳግመኛ ላትመኛቸው የተሰናበተቻቸውን ነገሮች በድጋሜ ለማግኘት፤ ልቧ እንደ አዲስ ተመኘ፡፡
በዚሁ መካከል መርፌ የምትወጋበት ሰአት ስለደረሰ፣ ነርሷ መድሀኒት የያዘውን ጋሪ እየገፋች ወደ ክፍሉ ስትገባ፤ አዜብና ብሩክ ክፍሉን ለቀው ወጡ፡፡ ደግነቱ ሁለቱም ወንድምና እህት የተኙት እዚያው ጥቁር አንበሳ በመሆኑ፤ ለአስታማሚዎቻቸው ሩጫን ቀንሶላቸዋል..... አንዱ አለምን የምትንከባከበው አዜብ ነች፡፡ በተለይ ለዚህ ያበቃሁት እኔ ነኝ የሚል የጥፋተኝነት ስሜት ስለተሰማት፤ ይህንን
ስሜትዋን ለማስወገድ የማታዘጋጅለት የምግብ አይነት አልነበረም፡፡
እዚያ የካቲት አስራ ሁለት ሆስፒታል እየሄደች ከእናቷ ጋር ከመፋጠጥ
እዚሁ ሁለቱን ለመንከባከብ፤ ብሩክ ደግሞ ከሰራተኛዋ ጋር ሆኖ ወይዘሮ ሃመልማልን እንዲንከባከብ፤ ክፍፍሉን ያደረገችው እሷ ናት፡፡ሰራተኛዋ ጥሩ፧ ጥሩ፧ ምግብ እንድታደርስላት በማድረግ በኩል ግን ወደ ኋላ አላለችም፡፡ አንዱአለም አሁን እየዳነ ነው፡፡ በተለይ ሻምበል እዚያ ሆሰፒታል መጥቶ ከጠየቀው በኋላ ደስተኛነቱ በእጥፉ
ጨምሯል፡፡ ትህትና ራስ ደስታ ሆስፒታል ገብታ የጠፋችበትን ምክንያት አዜብ ከነገረችው በኋላ ፧ ሻምበልም ለጥቂት ቀናት የጠፋው በዚሁ ችግር ምክንያት መሆኑን ገመተ ። እህቱ በመጥፋቷ
ብትናፍቀውም፤ እሷን ተክታ አዜብ የምታደርግለት እንክብክቤ ከፍተኛ
በመሆኑም ተፅናንቷል፡፡ አዜብ ለደረሰበት አደጋ ዋና ምክንያት ራሷን አድርጋ ስለቆጠረች ቶሎ ድኖ እንዲወጣ የማታደርገው ጥረት አልነበረም፡፡ ቆንጆ ምግብ አዘጋጅታ ትመጣና፤ እዚያ እጎኑ እቅፉ ስር ገብታ ስታጎርሰው ፤ ከዚያም አፉ ላይ የሚቀረውን ምግብ
ልታፀዳዳለት ከንፈሮቹን እብስ ፤ እብስ ስታደርጋቸው፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሄዳ ከአንገቱ ቀና በማድረግ፤ በክንዷ ላይ ጣል ታደርገውና አጥሚት ስታጠጣው ፤ ከዚያም ራቁት ክንዷ ራቁት ክንዱን
ሲያሞቀው፡፡ ከዚያም ስውነቱን ሲግል ! በዚያ የግለት ስሜት የተነሳ ደግሞ ከዚያ በፊት ስለሷ አንድም ጊዜ ተሰምቶት የማያውቅ ፆታዊ ንዝረት ሲነዝረው፤ በተለይ ደግሞ አስተያየቷ ... አይን አይኑን
በስስት እያየች፤ ስልምልም፤ ስልምልም... ስትልበት፡፡ ይሄ ሁኔታ በየጊዜው እየተደጋገመ ሲመጣ ፤ ለሷ የተለየ
ስሜት እያሳደረ መጣ፡፡ ትኩር ብሎ ሲመለከታት ይቆይና ለራሱ ግርም ይለው ጀመር አዜብ እንደዚህ ቆንጆ ነበረች እንዴ ? በማለት ራሱን ደጋግሞ ጠየቀ፡፡
እንዴት አይነት ተአምር ነው ? ግን አዜብ እንደዚህ ታምር ነበረ? ለምንድነው እስከዛሬ ድረስ እንደዚህ ቆንጆ መሆንዋን ያላየሁት? አቤት ስትስቅ ደግሞ እንዴት ያምርባታል? ጥርሶችዋ እንደዚህ ያምሩ ነበረ? እስከዛሬ ድረስ እንዴት አላየኋቸውም? የታላቅ እህቴ ጓደኛ ስለሆነች እንደ እህቴ ቆጥሪያት አላየኋትም ነበር ማለት ነው ? ጓደኛዋ ብትሆን ታዲያ ምን ነበረበት? ጓደኝነታቸው የበለጠ ይዳብራል እንጂ፤ ይቀንሳል እንዴ? ራሱን በጥያቄ ያዋክብ ጀመር፡፡ አዜብም እንደዚያ አጠገቡ ሆና
ስታጫውተው ፣ ስታሳስቀው፤ ስትደባብስው፤ ስታጐርሰው፤ በክንዷ ላይ
ጣል አድርጋ፤ እህል ውሃ ስታቀማምሰው፤ ጠረን ለጠረን ሲለዋወጡ፡ ሲለማመዱ
ቀስ በቀስ እሷም ስለ አንዱአለም በልቧ ጥያቄዎችን በማነሳሳት እራሷን መጠየቅ ጀመረች፡፡ እንዴት እስከዛሬ ድረስ የዚህ
አይነት ስሜት ሳይሰማኝ ቀረ? በማለት ተገረመች .ስንቱን የምታተረማምሰዋ ሴትዮ አንዱአለምን የመሰለ ውብ ልጅ ለመቅመስ እንዴት እንዳልቀደመች ደነቃት :: የጓደኛዬ ወንድም ስለሆነ ነው ወይንስ
እንደዚህ እንደአሁኑ አይነት አጋጣሚ ተፈጥሮ ተቀራርበን፡ ተጠጋግተን፡
ጠረን ለጠረን መለዋወጥ ባለመቻላችን? አንዱ አለም እኮ የሚፈቀር ልጅ
ነው፡፡ ወይ ጉድ? ..ይህንን የውስጥ ፍላጐታቸውን በአንደበታቸው
አያውጡት እንጂ አንዳንድ ድርጊታቸው ስለሚመሰክር ልብ ለልብ እየተግባቡ መጡ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በድንገት አይኖቻቸው ሲጋጩ ድንግጥ የማለት፡ የልባቸው ምት የመጨመር፡ የስሜት መለዋወጥ፣ ይሄና ይሄንን የመሳሰሉ ክስተቶች ተደጋገሙ፡፡ በዚያን እለት አንዱ
አለም ከጐኑ ያለው በሽተኛ መተኛቱን ሲያረጋግጥ፤ የሚያጎርሰው : የሚዳብሰው፡ የቀኝ እጇን መዳፍ ወደ ደረደቱ አስጠጋና ገልብጦ ውስጡን በስሱ ከዳሰስ በኋላ ፤ ቀስ ብሎ ሳመው :: በዚ ጊዜ ቀልጣፋዋ ልጅ ጊዜ አላጠፋችም፡፡ ከሱ ይህንን ያክል ፍንጭ
ካገኘች በቂ ነው :: እሷም ቀስ አለችና የውስጥ መዳፉን ሳም አደረገችለት፡፡ ከዚያም ወደ ደረቱ ትንሽ ሳብ ሲያደርጋት የገፈተሯትን ያህል ሄዳ ደረቱ ላይ ቀስ ብላ ወደቀችና ፤ ሰው ሳይመጣ ፤ ከንፈሩን
ሳም አደረገችው፡፡ እሱም ሳማት፡፡ መሳም ብቻ ሳይሆን በደንብ አድርጉ መጠጣት፡፡ ጣፈጠችው፡፡ ጣፈጣት፡፡ ፍቅር ተጀመረች፡፡ ከዚያ በኋላማ መነፋፈቅ፡ መቅበጥበጥ : ሲገናኙ ምኑ ይጠየቃል ? ትንሽ ሲለያዩ ፍዝዝ እያሉ መተያየት፡ መደባበስ ሆነ ስራቸው፡፡ ትህትና ከጊዜ ወደ ጊዜ ጤናዋ እየተሻሻለ መጣ :: አዜብና ሻምበል ብሩክ ከላይ እታች በማለት የሚደረገውን ሁሉ እያደረጉ ናቸው፡፡ የእንደሻው ወላጆች
እነሱ ለትህትና ህይወት " እንደዚያ ሲሯሯጡ ፤ ደግሞ የልጃቸውን ህይወት ለማትረፍ ከላይ እታች እየተሯሯጡ ብቻም
ሳይሆን፤ እየተራወጡ፤ ናቸው፡፡ የእንደሻው ጉዳት ከባድ ነበር፡፡ በተለይ....
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ

👍2😁1
#ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ
...ማሰብና መጀመር የተለያዩ ሆነውበት ተቸግሯል አቤል ። ሐሳቡ በጣም ይመጥቅበታል ።ሊጽፍ ያሰበው ነገር መጽሐፍ ይሆንበታል ። ለሐሳቡ ወግ የሚያግኝለትም አይመስለው ። ወረቀቱን ይዞ ቁጭ ሲል ግን ከብዕሩ ጠብ የሚል ነገር ይጠፋል ። ባዶ ወረቀት ላይ ማን ፎር ሂምሰልፍ” ከሚል አርዕስት ጋር መፋጠጥ ብቻ !
“ችግሩ ከቋንቋው ይሆን ? ” ሲል አሰበ ። በሰው ቋንቋ ከምቸገር ሓሳቤን እንደ ልቤ ላንቆረቁርበት በምችለው በራሴ ቋንቋ ለምን አልፅፍም?።
ባዶውን ወረቀት ከአጠገቡ አገለለና መጽሐፍ ገለጠ ለጽሑፉ የሚጠቅመውትን መጽሐፎች መርጦ አውጥቶ ጠረጴዛው ላይ ከምሯል ። መጻፍ ከመጀመሩ በፊት በዚህ አርዕስት
ጐዳይ ላይ የተጻፉ ብዙ መጽሐፎች ማንበብ እንዳለበት ስለ ተረዳ፡ ሰሞኑን እያነበበ ነበር። ችግሩ ግን አለ ከሚያነበው መጽሐፍ ላይ ብዙ ሰዓት መቆየት አለ መቻሉ ነው ከመጽሐፉ ውስጥ ጠቃሚ ሐሳብ ሲያገኝ የእሱ ሐሳብ ቀድሞ ይሐጥቅና ጻፍ ጻፍ ይለዋል
አሁንም ከተቀመጠበት ተነሥቶ ትንሽ ተንጎራደደ ። ከመንጐራደዱ ጋርም የሚጽፈው ነገር ብልጭ አለለት
ሰው ከራሱ ጋር የሚጣላው ለምንድነው ? በግል ምኞትና ግብ አእምሮው ተወጥሮ ሲጨነቅ ነው ። ነገር ግን የሰው ልጅ የመጨረሻ ግቡ እኛ እንጂ እኔ መሆን የለበትም ከራሱ ጋር ሊታረቅ የሚችለው በዚህ እምነት ተጠምቆ ከግሉ ይልቅ ለማኅበራዊ ችግር ክብደት ሲሰጥና ደስታውን ከኅብረተሰቡ ጣፋጭ ሕይወት ውስጥ ለማግኘት ሲሞክር ነው ። ሰው በመጀመሪያ ለሕያውነቱ ከፍተኛ ግምት መስጠትና ማድነቅ አለበት ። ይህን ካመነ ደግም ማናቸውም በውስጡ የሚከሠቱ ነገሮች የሕያውነቱ ነጸብራቆች ስለሆኑ
እንዳመጣጣቸው ተቀብሎ መፍታት እንጂ ለችግሮች ምረታት የለበትም ። ሰው በትግሉ በተጸጥሮ ላይ ፍጹም የበላይነቱን መቀዳጀት አለበት ።
እቤል መጻፍ የፈለገውን መቋጠሪያ ሐሳብ ያገኝ መሰለው ደስ ደስ አለው። በአንጻሩ ግን ከውስጡ አዘናጊ ስሜት ይታግለው ነበር ። " አይ አቤል ፤ አሁንስ ጅል ሆንክ አዲስ ሐሳብ ያፈለቅክ መስሎህ ነው ? ስንት ፈላስፋዎች ብለውት ብለውት የበቃውን ነገር እንዴት እንደ አዲስ ታነሳዋለህ ? እባክህ ይልቅ ያልተሳበ አዲስ ነገር ፈልግ ።ለዚያውስ በዚህ ዓለም ላይ ምን ያልተባለ ነገር አለ ?”
አቤል የራሱ ስሜት አስጠላው ለምንድነው ስሜቱን ገንቢውን ትቶ አፍራሹ ላይ የሚሮጠው? አዲሱ ሰው ሁሉን ነገር “ ተብሏል” እያለ ራሱን የሚያዘናጋ ከሆነና እጁን አጣምሮ ከተቀመጠ ነገር ተበላሸ ከአሁን በፊትም ማንም ቢሆን ፍጹም አዲስ ነግር ይዞ አልተሄዶም ። ሁሉም እውቀቱን የቀመረው በተከሠረት ወይም በተባለ ነገር ላይ እየቆመ ነው።እና አቤል አቤልሽ ! ይልቅ ደፍረህ ጀምር የአቅምህን ሞክር ፤ ጫር ! ” አለና እንደገና ቁጭ አለ።
እንዴት እንደሚጀምረው ቁልጭ ብሎ ታየው " ሰፊ አርዕስት ነው የያዘው ፤ስለዚህ በንዑስ ርዕስ ከፋፍሎ እያንዳንዷን ንዑስ ክፍል በጽሑፍ ማስረጃና በሕይወት ገጠመኝ
አስደግፎ ማስኬድ ! ሰውነቱን አንዳች የደስታ ስሜት ወረረው ። ሐሳቡ ካለበት መጥቆ ሲሮጥ ንዑስ ርዕሱ ልጓም ሆኖ
ያዘለት ። ሰው የራሱ ወዳጅ የሚሆንበትን ሐሳብ ከመደርደሩ በፊት ከራሱ ጋር የሚጣላባቸውን ሁኔታዎች ለመደርደር ተገደደ ። እዚህ ላይ ለመድረስ ደግሞ፥ ሰው በተፈጥሮ ይዟቸው የሚወጣውንና ከአካባቢው የሚቀስማቸውን ዐብይት ጸባያት ይዞ መነሣት ነበረበት ። የጅማሬ ሐሳቡን በዚህ ንዑስ ርዕስ ሥር አጠቃልሎ ፥ “ በዚህ ዓለም ላይ ታላቅና
ክቡር ፍጡር ነው” ሲል ጀመረ ።
በተመስጦ እየጻፈና ደጋፊ ሐሳቦች ፍለጋ መጽሐፎች እያገላበጠ ትንሽ እንደ ቆየ ፡ ሞኒካ ሻይ ይዛለት መጣች።
የአምስት ሰዓት ሻይ ነበር ። ጊዜው ከምኔው እንደ ሮጠ ገረመው
“ ጽሑፉን ጀመርኩት “ ኮ ” አላት ፡ ገና እየገባች ሳለች ።
“ ዳስ ኢስት ሸን ” አለችው ሞኒካ • ፈገግ ብላ ደስታዋን በመግለጽ ።
አቤል ይህንኑ “ ጀመርኩት ” የሚለውን ቃል ለዮናታንም ለመንገር ተቻኮለ ። እንዲያመጡለት የጠየቃቸውን የቀድሞ የተበላሹ የጥናት ጽሑፎቹን ባመጡለት ጊዜ ፥ የገባላቸው ቃል ትዝ አለው ። ወረቀቶቹን ተቀብሎ ፊታቸው በክ
ብሪት ካቃጠለ በኋላ ፥ አሁን ከፊትዎ የቆመው አዲሱ አቤል ነው ። አዲስ ጽሑፍ አዘጋጅቶ ያሳይዎታል ” ብሏ
ቸው ነበር ። አሁን ዮናታን የሚመጡበት የምሳ ሰዓት ራቀበት።
ሞኒካ አሁን እቤል ያለበትን ጥሩ ስሜት ካረጋገጠች በኋላ፥ ወደ መኝታ ክፍሏ ሔዳ አንድ ጉርድ ፎቶግራፍና የታሸገ
ኢንቬሎፕ ይዛ ተመለሰች ።
“ ይህችን ልጅ ታውቃታለህ ? ” አለችው ፥ ፎቶውን ዐይኑ ሥር አቅርባ ።ፉት ብሎ የነበረውን ሻይ ቶሎ መዋጥ አቃተው
የልብ ትርታ የሚቀሰቅስ ምስል ! አስደንግጦ የሚያስደስት ምስል ! “ ማወቅ ብቻ ነው!? አምልኬባታለሁ እንጂ!” ሊላት ፈለገ። የሞኒካ ቶሎ መልስ መፈለግ ግን፥ አቤል ነገሩን አመዛዝኖ እንዲናገር ጊዜ አልሰጠውም ።
አዎ ! አላት ፥ ሌላውን ስሜቱን ዋጥ አድርጎ
“ የት ? ”
“ ዩኒቨርስቲ ውስጥ አንድ ሴሚስተር ሙሉ በዐይን ፍቅር የማቀቅኩላት ናት” አላት ቃናው በተለወጠ ድምፅ ።
“ ከዚህ ፎቶዋ ጋር ደብዳቤ ልካልሃለች ” አለችና የታሸገውን ፖስታ ሰጠችው። ፈጥኖ ተቀበላት ። ነገር ግን ፈጥኖ መቅደድ አልቻለም ። አንዳች ነገር እጁን የያዘው ይመስል ተንቀጠቀጠ ።
በሚያነብበት ጊዜ ነጻ እንዲሆን በማሰብ ሞኒካ ክፍሉን ለቅቃለት ወጣች ። ደብዳቤዉንና ፎቶዉን ከእስክንድር
ከተቀበሰች ሁለት ቀን አልፎአል ።ለአቤል ወድያውኑ ያልሰጠችው እንዲህ ጥሩ ስሜት እስኪታይበት በመጠበቅ ነበር።
አቤል ደብዳቤዉን ግልጾ ማንበብ ጀመረ፡-
አቤል፥ ስምህን ደብዳቤ ላይ ለመጀሪያ ጊዜ ስጽፈው የተሰማኝን ስሜት ልገልጽልህ አልችልም ። የምወደውንና
የምፈልጎውን ቃል መጥራት ለምን እንደሚያስፈራኝ ሊገባኝ አልቻለም ። የዚህን ደብዳቤ ረቂቅ ብታየው ትግረማለህ ። ስርዝ፤ ድልዝዝ ብቻ ነው። ከስሜቴ ጋር ክፉኛ መታገሌን በዚህ መገመት ትችላለህ ።
ይህን ደብዳቤ እንድጽፍልህ ያደፋፈረኝ እስክንድር ነው ። ጥሩ ጓደኛ ነው ያለህ እሱ ባይገፋፋኝ ኖሮ እንዲሁ ስሜቴን አምቄ ውስጥ ውስጤን እሠቃያለሁ እንጂ ከቶም አልሞክረውም ነበር ። አንተ በእኔ የተነሣ የተቀበልከውን ስቃይ ስሰማ ለብቻዬ ተደብቄ ስቅስቅ ብዬ ነው ያለቀስኩት ፤ግን ጥፋተኛው ማን ነው ? አየህ አቤል ! እኔ መቼም ሴት ነኝ ፤ደፍሬ መጥቼ እንዳነጋግርህ የአካባቢ ተጽዕኖ
አለብኝ ። አንተ ግን በሩቅ ከምትሠቃይ ቀርበህ ! ብታነጋረኝና እወድሻለሁ ብትለኝ ምን ነበረበት ።
“ሕመምህ ጠልቆ የተሰማኝ አሁን ነው ። ለካስ ፍቅር ተገጣጥሞ ካልሰመረ ሥቃይ ነው። በካምፓስ ውስጥ አንተን በዐይኔ ካጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ያለሁበትን ሁኔታ ልገልጽልህ አልችልም ። አንተን ለማየት እናፍቃለሁ ፣ ብቸኝነት ያሰቃየኛል ፥ አካባቢዩ ያስጠላኛል ፤ጥናት ያንገሸግሸኛል ፣ሁሉ ነገር ከብዶና መርሮ ይታየኛል ። እውነቴን ነው የምልህ
የተፈጥሮ ክሥተት ባይሆን ኖሮ፡ አፍላ ፍቅር ፈጽሞ እያስመኝም
“ በመጀመሪያው ሴሚስተር ከትምህርቴ እንዳልሰናከል እፈራ ስለ ነበር፡ ፍቅርህን ክፉኛ ተቃውሜዋለሁ›
አሁን የተረዳሁት ነገር ቢኖር ግን ፥ ፍቅር ታግለው የሚጥሉት ነገር አለመሆኑን ነው ። ገና መጀመሪያ የዩኒቨርስቲውን ግቢ ስረግጥ ካየኸኝ ጀምሮ በዐይን እንደምትከተለኝ ያልተረዳሁልህ እንዳይመስልህ እያንዳንዷ እይታ ከንግግር የበለጠ ተሰምታኛለች። እንዲያውም አንዳንዴ ቃላት

❤1👍1🥰1
መግለጽ የማይችሉትን ዐይን እንደሚናገር ተረድቻለሁ ።በተለይ ፥ ታስታውስ እንደሆነ እንድ ቀን እኔ ፡ ማርታና ቤተልሔም ከካምፓስ ወጥተን ስንሔድ ምን ያህል በቅናት ስሜት እንደ ተመለከትከኝ መቼም አልረሳውም ። አንተ ሌላ ቦታ የምንሔድ መስሉህ ሊሆን ይችላል ። ነገር ግን የሒድነው ሰርግ ቤት ተጠርተን ነበር። ታዲያ ያኔ የዋልኩት ውሎ ውሎ አይበለው ! በቅናት የተከተለኝ ዐይን ዐይኔ ውስጥ ቀርቶ ፥ ቀኑን ሙሉ ሲለበልበኝ ነው የዋለው ...
ይህን ሁሉ የምጽፈው የቆየ ቁስልህን ለመቀስቀስ አይደለም ። በአንድ በኩል ደብዳቤው በእርግጥ ከእኔ ከት ዕግሥት የተላከልህ መሆኑን እንድታምንበት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ስሜትህ ያልገባኝ ወይም ሥቃይህንን ያልተረዳሁልህ እንዳይመስልህ ነው ።
“ከላይ እንደ ገለጽኩልህ፡ችግሩን በመፍራት ፍቅርህን ታግዬ የማሸንፈው አልሆንኩም ። ብሞክረውም አንተን መርሳት ፍጹም የማይቻል ሙከራ ሆነብኝ። ምክንያቱም በአካባቢዬ ሴቶች ስለ አንተ ሲያወሩ በሰማሁ ቁጥር ስሜቴ ይቀሰቀሳል። ስምህን የሚያውቁት፡ “ ያ ጎበዙ ተማሪ” በሚል ቅጽል ነው የሚጠሩህ ። ይህ ቃል በእኔ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ነው ያሳደረብኝ ። በጉብዝናው በሚደነቅ ተማሪ መፈቀር ደስ ያሰኛል። ግን ደግሞ ግንኙነታችን ከዐይን አለ ማለፉን ሳመዛዝን ያበሽቀኛል ። ያ ሁሉ ዐልፎአል ። አሁን ስሜቴን አፍረጥርጨ ያወጣሁልህ ይመስለኛል ። አንተም ግልጽ ሁንልኝ ። ፍቅርን ሕመም ያደረግነው እኛው ነን ፤እባክህ ጐንለጐን ቁጭ ብለን አንተ በእኔ ፥ እኔ ባንተ እንደሰት ። ትምህርትህ በእኔ ምክንያት በመቋረጡ አዝናለሁ ። የምረዳህም
ሆን የምክስህ ነገር ቢኖር፡ ከወዲሁ ሙሉ ፈቃደኝነቴን እገልጽልሃለሁ ። በእኔ ግምት ካሳው ፍቅር ነው ፍቅሬን ሰጥቼህ ፍቅርህን ከመቀበል ሌላ ምን መፍትሔ ይኖራል ?
ያንተው ትዕግሥት አዳነ ”
አቤል ደብዳቤውን ሁለቴ አንብቦ በዝግታ አጠፈው ።እውስጡ ያነበበው የፍቅር ቃላትን ብቻ ሳይሆን እንባም ጭምር ነው ትዕግሥት ፊቷ በእንባ ሳይታጠብ ይህን
ደብዳቤ ጻፈች ማለት ዘበት ነው ። ጽሑፉን ያነበበ ሳይሆን ድምጿን የሰማ መሰለው ። ግን በእርግጥ ትዕግሥት እንዲህ ግልጽ ሆና የውስጧን የምትናገር ሴት ትሆን ? ማነው ጥፋተኛው ? ” የሚለው ቃል ታወሰውና፡ “እውነት ማነው?” ሲል አሰበ ። እሷንም ራሱንም ጥፋተኛ ማድረግ አልቻለም ። አንዲት የፍቅር ቃል እወድሻለሁ ብትለኝ ” ያለችው አንጀቱን በላው ። ነገር ግን ቃሏ አንድ መሆኗ ሳይሆን ክብደቷ ነው ለትዕግሥት ያልገባት ። ይህችን በፍቅረኛ ፊት መተንፈስ መቻል ምንኛ መታደል ነው !
ስለ እስክንድር አሰበ ። ለደብዳቤዉ መጻፍ ያደረገው ጥረት አስገረመው ። ከአሁን በፊትም እሱን ለመርዳት ያዶረገውን ሙከራ ሁሉ ታወሰው ። ከራሱ ጋር ተጣልቶ በሰይጣናዊ ግፊት ፎቅ ላይ በቆመበት ጊዜ የደረሰለት ዕለት ትዝ
አለው ። “ እባክህ ችግርህን ንገረኝና ልረዳልህ ብቻህን አትጨነቅ” በማለት አቤልን የወተወተበትም ጊዜ ነበር።
እና አሁን ጥረቱ ፍሬ አስገኘ ።
“ አንብበህ ጨረስክ ? ” አለችው ሞኒካ • ተመልሳ መጥታ ። ዐይኑ ዕንባ አቅርሮ ተመለከተች ። አቤል በትዕግሥት የፍቅር ቃላት ልቡ ተነክቶ የፍቅር ዕንባ ሲያነባ ከአሁን በፊት በእሷ ምክንያት የደረሰበት ቁስል እየሻረለት ነበር ።
አዎ ጨረስኩ ” ኣላት ዝግ ባለ ድምፅ ዐይን ዐይኗን እያየ።
"እንዴት ነው ? ?
ድንቅ ነው ፤ ሸጋ ነው ! ”
እኔም መልስ መጸፍ ይኖርብኛል ” አላት ጸጉሩን እያሻሸ።
እዚሁ ድረስ ትመጣልሃልች ደብዳቤ መጻፍም አያስፈልግህ ” አለችው ሞኒካ ፈገግ እንዳለች ።
"መቼ ?
"እሑድ ጠዋት"።
የያዘውን ቀን አሰበ ።ሐሙስ ነው ለእሑድ ገና ሁለት ቀንና ሦስት ሌሊት ይቀረዋል ። እንዴት ይደርስ ይሆን ?የትዕግሥትን ፎቶግራፍ ከጠረጴዛው ላይ አንሥቶ እንደገና ተመለከተው ።
አቤል በዚህ ሐሳብ ውስጥ በመዋዠቅ ላይ እንዳለ የምሳ ሰዓት ደርሶ ዮናታን መጡ ።ከምሳቸዩ በፊት ወደ ጥናት ክፍሉ ወስዶ ያስተናገዳቸው አቤል ነበር ።
“ ጽሑፉን ” ኮ ጀመርኩት! ” አላቸው ፡ በደስታና በኵራት ድምፅ ።ግሩም ! ” አሉት ዮናታን ፡ ጠረጴዛው ላይ ያሉትን
ቁሳቁሶች እያዩ ። የትዕግሥት ፎቶግራፍ ከመጽሐፉና ከወረቀቶቹ ጐልቶ ታያቸው ። ሊጠይቁት አሰቡና ስሜታቸውን ቆንጠጥ አደረጉ ።አሁንም እንደ ድሮው ይደብቃቸው ይሆን ?
እሷም ልትመጣ ነው ፤ ደብዳቤዋ ደርሶኛል አላቸው : ዐይናቸውን ተከትሉ ስሜታቸው ያረፈበትን በመገመት ።
ግሩም ! ሥራና ፍቅር ተገጣጠሙ በለኛ ! ” አሉት ደስታ ፈንቅሎአቸው ።
ዐይናቸው ከፎቶግራፉ ወደ ጥናት ጽሓፉ ሲሸጋገር ደግሞ ከወረቀቱ አናት ላይ ፡ “ በዚህ ዓለም ላይ ታላቅና ክቡር ፍጡር ሰው ነው የሚለው መንደርደሪያ ደምቆ
ተመለከቱ ።
“ ፍጹም ጤናማ አመለካከት ነው ፤ጤናማ ኅብረተሰብ የጨዋማ ግለሰቦች ውጤት ነው ብለው አሰቡ ።
“በጅማሬህ በጣም ተደስቼአለሁ ። ቀጥልበት ታላቅ ሥራ ሠርተህ ታላቅ ሰው የምትሆንበትን ጊዜ በተስፋ እጠብቃለሁ አሉት ።
ፈገግ እያለ ዐይን ዐይናቸውን ተመለከታቸው ያ መነጽሩን ዐልፎ ዐይናቸው ውስጥ ፍቅር ይነበባል ።
የመጨረሻ ዐረፍተ ነገራቸው ጭንቅላቱ ውስጥ ደወለበት።...
💥ይቀጥላል💥

#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
እነሱ ለትህትና ሕይወት እንደዚያ ሲሯሯጡ ደግሞ የእንደሻው ወላጆች ደግሞ የልጃቸውን ህይወት ለማትረፍ ከላይ ከተች እየተሯሯጡም ብቻ ሳይሆን እየተራወጡ ናቸው። የእንደሻው ጉዳት ከባድ ነበር። በተለይ አንዷ ጥይት የራስ ቅሉን በስታው ስላለፈች፤ የአእምሮ ቀውስ
እንዳያስከትልበት፤ ከፍተኛ ስጋት አለ፡፡
በተፈጠረው አደጋ ምክንያት የእንደሻው ወላጆችና የአዜብ ወላጆችም ግንኙነት አቋርጠዋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ...
"ያቺን የተረገመች ልጅ አምጥታ ልጃችንን ልታስገድለው የነበረችው አዜብ ነች በሚል ሲሆን፤ ፀቡን ከአዜብ ጋር ብቻ ሳይሆን ከቤተሰቦቿ ጭምር አድርገውታል :: እነሱ እንደዚያ ብለው ይናገሩ እንጂ ፤ የአዜብ ወላጆች ሁኔታው ሊፈጠር የቻለው አለሌው ልጃቸው
በፈፀመው ተደጋጋሚ አስነዋሪ ድርጊት ሳቢያ መሆኑን ሲያውቁ የክርስትና ልጃችን ነው በሚል ምክንያት ብቻ ፤ በትህትና ላይ ሊፈርዱባት
አልደፈሩም....
"ሁሉንም ስራው ያውጣው በማለት መጨረሻውን ለማየት እየተጠባበቁ ናቸው፡፡ ትህትና ጤናዋ በከፍተኛ ፍጥነት እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም፤ ጐን ለጐን በነፍስ ማጥፋት ሙከራ ወንጀል በአቃቤ ህግ ክስ ተመሰረተባት፡፡ አዜብና ብሩክ ይህንን እንዳወቁ ቀጣዩ ትኩረታቸው
በምን ላይ መሆን እንዳለበት በስፋት ተመካከሩ፡፡ ከዚያም አንዳንድ
በመከላከያነት ይጠቅማሉ ያሏቸውን ማስረጃዎች ለማሰባሰብ ፤ ሁለቱም
በየፊናቸው ሩጫ ጀመሩ፡፡ ለዚህ ጉዳይ አበራ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገመቱ :: ምክንያቱም አበራ በእንደሻው ክህደት የደረሰበትና፤ በትህትና ላይ ስለተፈፀመው ወንጀል በሚገባ የሚያውቅ የአይን ምስክር ስለነበረ ነው፡፡ አበራ በእንደሻው ስለተፈፀመበት ክህደት ለአገሩ ሁሉ ሲያወራ ለአዜብም አጫውቷት ነበር ፡፡
ከዝምድና ይልቅ ገንዘብን አስበልጦ አስር
አመት ሙሉ ያጠራቀምኩትን ገንዘቤን ወስዶ ከከበረበት በኋላ ከዳኝ፡፡ በጋራ
እናድግበታለን ብሎ የገባውን ቃሉን አፍርሶ አባረረኝ " በማለት በምሬት ነበር የገለፀላት፡፡ ታዲያ ያ ሁሉ በደል የተፈፀመበት ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ እውነቱንና የሚያውቀውን ከመናገር ወደኋላ ሊል ይችላል? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ በፍፁም ወደኋላ አይልም ስትል ተማመነች፡፡ምክንያቱም እሱ እንደዚያ በንዴት እየተንቀጠቀጠ
ሲነግራት...
“አይዞህ አበራ ተወው፡፡ አንተ ጤና ሁን እንጂ ፤ገንዘብ አላፊ ጠፊ ነው፡፡ በክህደት የተገኘ ገንዘብ ደግሞ የትም አያደርስም፡፡
ከሰራህ ከካደህ ሰው በላይ መሆን ትችላለህ :: አይዞህ! እግዚአብሄር ላንተ ያለውን ምንግዜም አታጣውም " በማለት ትልቅ የማፅነኛ ቃል ለግሳው ነበር፡፡ ያንን
የሰጠችውን የተስፋ ቃል እንኳ አስታውሶ እሺ ይላት ይሆን? ወይንስ እሱም እንደወላጆቹ ተደርቦ ከእውነት ጀርባ ይቆም ይሆን? ልቧ ተጠራጠረ፡፡ ለማንኛውም አለችና ስልክ ደወለችለት :: ስልኩን አነሳና እሷ መሆንዋን ሲያውቅ የሞቀ ሰላምታ አቀረበላት፡፡ ትንሽ እፎይ አለች በልቧ፡፡ለጉዳይ እንደምትፈልገው
ስትገልፅለት፤ በደስታ ተቀብሎ የሚገናኙበትን ቦታ ተቀጣጥረው
ተሰነባበቱ፡፡ በማግስቱ በቀጠሮው ቦታ ቀድሞ የደረሰው እሱ ነበር።
የተፈለገበትን ጉዳይ ስትነግረው...
"ተይ እንጂ አዜብ እቤት ድረስ የወሰድኳት እኮ እኔ ነኝ፡፡በወንጀለኛነት አያስጠይቅህም ነው የምትይኝ?" ሲል በጥርጣሬ ጠየቃት።
"ስለሱ ከሻምበል ጋር በደንብ ተነጋግረንበታል፡፡ አንተን በወንጀል
ተባባሪነት እንዳያስጠይቅህ በቂ ምክንያት ማቅረብ ይቻላል፡፡”
"ለምሳሌ ምን?"
"አበራ ሙት ምንም አትፍራ! በዚህ ጉዳይ አንተ በጥፋተኛነት እንድትጠየቅ የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር ፧ አንተ ይዘሃት የሄድከው ወደ ቀጣሪዋ ቤት እንጂ፤ ወንጀል
ወደሚፈጸምበት ጫካ ውስጥ አይደለም፡ቀጣሪዋ ቤት አደረስካት ማለት፤ እንደሻው ደብድቦና፤ አስገድዶ፧ ክብረ ንፅህናዋን እንዲደፍራት አደረክ ማለት አይደለም :: የቀጣሪዋን ቤት የወንጀል መፈፀሚያ ዋሻ ያደረገው ወንጀለኛ ብቻ ነው ለዚህ ተጠያቂ የሚሆነው፡፡ አይዞህ ምንም የሚያስፈራ ነገር የለውም፡ አበራን ለማሳመን ብሎ ብሩክ ያስጠናትን ደሰኮረችለት፡፡ አበራ ልቡ ትንሽ ተለሳለሰ፡፡
"በሌላ በኩል ብታየው ደግሞ የቀጣሪዋ ባለቤት ልጅ የቅጥር ውል እንድትፈርም ይዘሃት ና ብሎ አዘዘህ :: አንተም ይህን ነገርካት። እሷም እሺ ብላ ሳታስገድዳት በፈቃደኝነት አብራህ ሄደች። ከዚያም አንተ በሌለህበት እንደሻው ወንጀል ፈፅሞባት ደረስክ፡፡ በቃ፡፡ ይህ አይደለም
ታሪኩ? አንተን የሚያስጠይቅህ ምኑ ነው ታዲያ?" ስትል የማደፋፈሪያ
ሀሳብ አዥጐደጐደችለት፡፡
በልቡ ያሳደረው ጥርጣሬ ሙሉ ለሙሉ ባይጠፋለትም፤ በአዜብ አቀራረብ ተስማማ፡፡ እንዳለችውም እሱን በቀጥታ ተጠያቂ ሊያደርገው የሚችል ጭብጥ እንደሌለ ተሰማው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ
ያቺ ምስኪን እንጀራ ፈላጊ ልጅ ፤ በደም ተጨማልቃ ወድቃ ያያት እለት የተሰማው ስሜት ፊቱ ላይ ድቅን አለበት፡፡ በተፈፀመባት ወንጀል ከልቡ አዝኖ ነበር፡፡ በዚህ ላይ ያ ግፈኛ ከሃዲ ከሱቁ ካባረረው በኋላ አሁን አሁን በርካታ ካፒታል በማንቀሳቀስ በቅናት እያቃጠለው
ነው፡፡ በጥይት መቃጠሉን የሰማ እለት " እሰይ የእጁን ነው ያገኘው"ነበር ያለው፡፡ አሁን ደግሞ እሱ ተጠያቂ በማይሆንበት ሁኔታ ለምን ያየውን ከመመስከር ወደ ኋላ ማለት እንደሌለበት ተገነዘበ ፡፡ያየኽውን እውነት መሰከርክ ብሎ የሚፈርድበት ዘመድ እንደማይኖርና፤ ቢኖርም መፅሀፍ ቅዱስ ይዞ በሚፈፅመው መሃላ በውሸት መስክሮ ነፍሱን ማስኮነን እንደሌለበት ተሰማው። እንደሻውን ሊበቀል
የሚችልበትን ይህንን መልካም አጋጣሚ ሊጠቀምበት ወሰነ : እንቢ ቢልስ የት ሊደርስ ? በተለይ አዜብ እየነገረችው
ያለው ፣ ባለስልጣን ፖሊስ ከአዜብ በስተጀርባ መኖሩን ነው፡፡ በተለይ "ሻምበል ጋር በደንብ ተነጋግረንበታል"
ስትለው ምን እያለች እንደሆነ
ገብቶታል፡፡አልመሰክርም ቢል በተባባሪ ወንጀለኛነት ተፈርጆ፣ ለፍርድ እንደሚቀርብ እየነገረችው ነው፡፡ ይሄንን ጭምር አስቦ፤ ልቡ ስለፈራ፤ ያየውን ሁሉ በዝርዝር ሊያስረዳና፤ ለትህትና ድንበሩ የመከላከያ ምስክር ሊሆን ቃል ገባላት፡፡ ቃል መግባት ብቻም ሳይሆን ተጨማሪ ማስረጃ ጠቆማት..
"እኔ ብቻ ሳልሆን በዚያን እለት ሁኔታውን የተመለከተችው የቤት ሰራተኛዋ ወርቅ ያንጥፉም ያየችውን ሁሉ እውነቱን ሳትደብቅ እንድትመሰክር እናደርጋለን :: ደግሞም ትመሰክራለች፡፡ አትጠራጠሪ!
በትህትና ሁኔታ በጣም ነው ያዘነችው፡፡እሷም ስመ እግዚአብሄርን ጠርታ
ያየችውን ሁሉ ትመሰክራለች፡፡ አይዞሽ ! " አላት፡፡ አዜብ ከጠበቀችው በላይ ተባባሪ ሆኖ ስለኣገኘችው፤ በደስታ እቅፍ አደረገችው፡፡ በዚሁ መሰረት አበራና ወርቅ ያንጥፉ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው፤ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተደረገ፡፡ ቀኑን፡ ሰአቱን፡ የድርጊቱን አፈፃፀም፡ ዝርዝር ሁኔታውን፤ በሙሉ በአንድ አይነትና ፤ ተመሳሳይ በሆነ ቃል
መሰከሩ። ያም ብቻ ሳይሆን አንዱአለምን ጋርጠው በሚል ቅፅል ስሙ በሚታወቀው ወሮበላ እንዳይሞት፤ እንዳይድን፤ አደርጐ ያስደበደበው
መሆኑን፤ ራሱ እንደሻው በኩራት ሲናገር መስማቱን፧ ጭምር ገለፀ፡፡
በእርግጥም እንደሻው ያንን ለአበራ የተናገረው፤ ይሄ ይመጣብኛል ብሎ ሳይሆን፤ አንተም አርፈህ የማትቀመጥና ወሬ አበዛለሁ የምትል ከሆነ፤ አስወቅጥሀለሁ፤ የሚል ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ነበር፡፡ ሆኖም በዚህ አጋጣሚ እንደሻውን የደበደበው ጉልበተኛ
ስለታወቀ፤ ወዲያውኑ ታድኖ እንዲያዝ ሲደረግ ፤ አበራ ማንነቱን በማሳየትና የሚገኝበትን

👍2❤1
ቦታ በመጠቆም ፤ ለፖሊስ ሙሉ ተባባሪነቱን አሳየ፡፡ በተለይ ሻምበል ብሩክ "አይዞህ ስለማንኛውም ነገር ፍጹም ስጋት አይሰማህ! ከጐንህ አለሁ! "በማለት ሞራል ስለሰጠው ፤ ተኩራራ።
ጋርጠው በፖሊስ ተይዞ፤ አንድ ሁለት ጊዜ በቃሪያ ጥፊ ሲወለወል፤ ያልተጠየቀውን ጭምር ይለፈልፍ ጀመር፡፡ ከዚያም ቃሉ ተመዝግቦ በማስረጃነት እንዲያዝ ተደረገ፡፡
አንዱ አለም ድንበሩ ሆስፒታል በገባ በሶስተኛ ሳምንቱ ሙሉ ለሙሉ ዳነ፡፡ ሆስፒታል በተኛበት ጊዜ በተለይ አዜብ
ባደረገችለት ከፍተኛ እንክብካቤ ወፍሮ፤ ቀልቶና አምሮበት ሲታይ ሆስፒታል የከረመ በሽተኛ ሳይሆን ጫጉላ ቤት የከረመ ሙሽራ መስሎ ቁጭ አለ፡፡ ሙሉ
ጤንነቱ ተረጋግጦ ከሆስፒታል እንዲወጣ
ከተደረገ በኋላ ግን፤ ስለእህቱ
በየእለቱ የሚነገርውን ልብ ወለድ
ሳይሆን፤ እውነተኛውን ታሪክ ሰማ... ሻምበል ብሩክና አዜብ ከዚህ በፊት እንዳይሰማ የፈለጉበት ዋነኛው ምክንያት ከህመሙ ሳያገግም፤በድጋሜ ሌላ ችግር እንዳይፈጥር ስለሰጉ ነበር፡፡ አሁን ድኖ ከተነሳ በኋላ ግን ሁሉንም ነገር እንዲያውቅ አደረጉ፡፡ የሚወዳት አንድና
ብቸኛ እህቱ የደረሰባትን አደጋ፤ አይኖቹ በእንባ ጭጋግ ተሞልተው እየዋኙና፧ መላ ሰውነቱ በከፍተኛ ሀዘንና ድንጋጤ ተኮራምቶ፤ ሰማ... የወንድሟ ደም ሜዳ ላይ ፈስሶ እንዳይቀር፤ አለኝታነቷን
ልታረጋግጥለት፤ የሱን የደም ዋጋ ፤ ከራሷ የህይወት ዋጋ ፤ አስበልጣ እንደሞተችለት ፤ትልቁንና የመጨረሻውን ለሰው ልጅ ውድ የሆነው ህይወቷን አሳልፋ እንደሰጠችለት፤ አይዞህ አንዱዬ ደምህ እንደዚህ ሜዳ ላይ ፈሰሶ አይቀርም ብላ የሰጠችውን ቃሏን አክብራ ሄዳ፤ ደሟን እንደጎርፍ እንዳፈሰሰችለት፤ መስማት አይቀርምና ሁሉንም
ነገር ሰማ... ይህንን ሁሉ ሰምቶ ካበቃ በሁዋላ ህይወቷን ያተረፈለት አምላኩን አመሰገነ : ይህች እሱንና፤ እናቱን፤ ለመርዳት ከአቅሟ በላይ የሆነውን ከባድ ሃላፊነት ተሸክማ፤ ቀና ደፋ ስትል የኖረችና፤ ከምንም፧ ከማንም፤ በላይ የሚያፈቅራት እህቱን ከእንግዲህ በኋላ ዳግም ለሌላ አደጋ እንዳትጋለጥ፤ ዳግም እንዳትንከራተት፤ ሸክሙን ሙሉ ለሙሉ ራሱ ሊሸከምላት ፤ ከአሁን በኋላ እኔ አለሁልሽ ሊላት፤ ቁርጥ ውሳኔ ላይ ደረሰ... በዚህ ሰአት የጉርምስናው ስሜት ጥርግርግ ብሎ ወጥቶ ሄደና፤ በምትኩ አዲስና የቤተሰብ ሃላፊነት ሸክምን ለመሸከም ቆርጦ የተነሳሳ ሰው ስሜት፤ ሙሉ ለሙሉ በውስጡ ነገሰ፡፡ ከዚያም
ይህንን ሃሳቡን ለማሳካት ከሚረዳው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ደረሰ፡፡
ከዚያም ትህትና ወደተኛችበት ክፍል
በሻምበል ብሩክና በአዜብ መሪነት ወደ ሶስተኛ ፎቅ ወጡ፡፡ይህ ወቅት ትህትና ከፍተኛ ለውጥ ያሳየችበትና ሀኪሞች በቅርብ ቀን እንደምትወጣ ያረጋገጡበት
ወቅት ነበር፡፡
ትህትና አንዱአለምን ስታየው ከደስታ ብዛት የምትሆነውን ነበር ያጣችው፡፡ ሁለቱንም እጆቿን ወደ ላይ ዘረጋችለት፡፡ሄዶ በእቅፏ ውስጥ ወደቀና፤ አለቀሰ፡፡እሷ ደግሞ በተራዋ አባበለችው፡፡እሱ ሆስፒታል ተኝቶ እሷ ስታለቅስ ! እሱ ያባብላት ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ተራው የሱ
ሆነና፤ ናፍቆት ጭምር ሆዱን ስለአባባው አቅፏት አነባ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ አዜብና ብሩከ ሁለቱ እንደዚያ ሆነው ሲመለከቱ ልባቸው የሚረጨው ደም ብቻ ሳይሆን ሀዘንን ጭምር ነበር ማለት ይቻላል፡፡
አንዱ አለም ከዚያች ቀን ጀምሮ እህቱን
የማስታመም ሙሉ ሃላፊነቱን ወሰደና ፤ ለሻምበል ብሩክና፤ ለአዜብ ትንሽ እረፍት
ስጣቸው፡፡ አንዱአለም ከሻምበል ብሩክና
ከአዜብ በስተቀር ምንም መመኪያ የሌላት እህቱ በአልጋ ላይ ውላና፤ እናቱም የአልጋ ቁራኛ ሆና ሳለ፤ እሱ ደግሞ ተጨማሪ ሆኖ፤ ለዚህ መብቃቱ ሲታሰበው እጅግ ይዘገንነው ነበር፡፡
በዚህ አስከፊ ጊዜ ሻምበል ብሩክና አዜብ ባይኖሩስ ?” ብሎ ሲያስብ ደግሞ፤ የሚሰማው ስሜት ከዚያ የባሰ ነው፡፡ ሻምበል ብሩክ አንድ ሰሞን ጥፍት እንዳለ ቢቀር ኖሮ ዛሬ ቤተሰቡ ምን ሁኔታ
ሊያጋጥመው ይችል እንደነበረ ሲያስበው፤ የአእምሮ ሰላም ይነሳው
ጀመር፡፡ ስለዚህ ያንን ውሳኔውን በአስቸኳይ ተግባራዊ በማድረግ
የእናትና እህቱ አስተማማኝ አለኝታነቱን ማረጋገጥ አለበት፡፡ ወቅቱ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ወጣቶችን በባህረኛነት ለመመልመል ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ የሚገኝበት የጦርነት ወቅት ነበር፡፡ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም፤ በባህር ሃይሉ ውስጥ ለመቀጠርና፤ እሱ መስዋእትነትን
ከፍሎ፤ እነሱን የሚወዳቸውን እህቱንና እናቱን በመርዳት አለኝታነቱን ሊያስመሰክር፤ ያለማወላወል ቆርጦ ተነሳ፡፡ እናቱ ሶስት ሳምንት ሙሉ ጠፍቶ የከረመ ልጇን ያየችው እለት ከደስታ ብዛት እዬዬ ብላ ነው ያለቀሰችው፡፡ በተለይ ለሁለት ቀን ልትለያት የማትችለዋን ሴት ልጇን ሁለት ሳምንት ሙሉ ስትጠፋ በህይወት አገኛታለሁ አላለችም ነበር።
በማህፀኗ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት ወይንም ደግሞ ሊነግሩኝ ያልፈለጉት ሌላ ከፍተኛ ችግር አጋጥሟት ይሆናል እንጂ ፤
ልጄ እንዴት ይሄንን ያክል ጨክና ትጠፋለች በሚል ስጋት ተወጥራ
ነበር፡፡ ሻምበል ቀኑ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የሱም ሰበብ ቁጥሩ እየበዛ
ሄዶ፤ አሁን አሁን እያፈረ መጥቷል፡፡ ሁሌም ለተጨማሪ ቀናት በሆስፒታል እንድትቆይ መወሰኑን ነው የሚነግራት፡፡ እንደዚያ እያለ እየዋሸ ጊዜ ይግዛ እንጂ እንዴት ጥይት ጠጥታ ተኝታለች ብሎ
ይንገራት? አንዱ አለም እናቱ እንደዚያ ፊቷ በትኩስ እንባ ተላልጦ ፤
ገርጥቶና፤ ከሰል መስላ ፤ ሲያገኛት ደንግጦ..
"ምነው እማዬ ፊትሽ ምን ሆኖ ነው እንደዚህ የተላላጠው? -
በማለት እያባበለ ጠየቃት። ለጠየቃት ጥያቄ መልስ ሳትሰጠው አቅፍ አድርጋ በስስት እያገላበጠች ከሳመችው በኋላ
"እህትህስ አንዱአለሜ? ትህትናዬስ የት ነው ያለችው ? ልጄስ የት ነች? ነፍሷ አለ? ለመሆኑ በአይንህ አይተሃታል? አንተስ ምነው ከእንባዋ ጋር እየታገለች የጥያቄውን መአት አዥጐደጐደችበት።
"እማዬ ስለ እታለም ምንም ሀሳብ አይግባሽ፡፡ ጋሽ ብሩክ እንደነገረሽ ነው፡፡ሀኪሞቹ ትንሽ ትቆይ ብለው ስላዘዙ ብቻ ነው፡፡ በጣም ደህና ነች፡፡ የከፋ ነገር ቢኖር ካንቺ ይደበቃል እንዴ ?”
በመለመንና፤ እንደ አቅሚቲ ቆጣ በማለት፤ እራሷን በማይሆን ሀሳብ
እንዳትጐዳ መከራት :: እንደዚያ ቆጣ ብሎ ሲናገራት፤ ትኩር ብላ ታየው ጀመር
በጣም አምሮበታል፡፡ እሷ ግን ግምቷ እንደዚያ አልነበረም፡፡ የሆነ ነገር ሆኗል የሚል ስጋት ነበር ልቧን ሲንጠው
የከረመው፡፡ እንደ እናቴ ሳይሆን እንደሚስቴ አውለኝ የሚለው አባባል
ትዝ አላት ::ስለ ትህትናም እሷ ክፉ ክፉውን ታስብ እንጂ፤ እንደ ወንድሟ አምሮባት ልትመጣ እንደምትችል ማሰብንስ ማን ከለከላት?።ይህንን ስታስብ ከልጇ ቁጣ በስተጀርባ መልካም ነገር ታሰባትና.......
ይሁን እሺ" ስትል ትንሽ ተስፋን በልቧ አሳደራ፤ ተፅናናች፡፡ አንዱ አለም ከእነዚያ ዱርዬ ጓደኞቹ ሙሉ በሙሉ ግንኙነቱን አቋረጠ፡፡
ሰሞኑን አዜብ አንድ የሚያምር ጂንስ ሱሪና፧ ቆንጆ ሸሚዝ፤ ገዝታለት እሱን ለብሶ፤ ከዚያ ውፍረትና ቅላቱ ጋር ሌላ ሆኗል።በዚያ ላይ ደግሞ በጣም ከሚያከብረውና ከሚወደው ሻምበል ብሩክ ጋር ስለማይለያዩ ፧ አንዳንድ ቀን ሻምበል ቤት እየሄደ ማደር ጀምሯል፡፡
አሁን የትህትና ተንከባካቢዎች ቁጥራቸው ከሁለት ወደ ሶስት ከፍ
ብሏል፡፡ አዜብ፡ ሻምበል ብሩክ፡
ትህትናና፤አንዱአለም በፈተና
የተፈተኑና፤ የተሰናሰሉ ጓደኛሞች ግንኙነታቸውና ፍቅራቸው እየተጠናከረ ሄዶ፤ ህይወት በራሱ ባቡር አሳፍሮና፤ አቅጣጫውን ቀይሶ፣ አስተሳስሮ ይዟቸው ወደፊት እየተወነጨፈነው ነው። በጭንቀት የእህል ፍላጐቱ ቀንሶና፤ እንቅልፍ የሚባል ነገር ከድቶት የከረመው
ሻምበል ብሩክ ትህትና በቅርብ

👍2
ጊዜ ውስጥ ድና ከሆስፒታሉ እንደምትወጣ ከሰማበት እለት ጀምሮ፤ በደስታ ሰሞኑን ያንን ሲናፍቀው የከረመ እንቅልፉን መለጠጥ ጀምሯል፡፡ በድንጋጤው ብዛትና በእንቅልፍ እጦት ሰውነቱ ላይ ይታይ የነበረው ለውጥም እየተሻሻለ መምጣቱ በግልፅ መታየት ጀምሯል፡፡ ሳቅና ጨዋታ የድሮ ወዳጆቹ ሸሸንህ
እንጂ፤ መቼ ከዳንህ? በማለት፤ ከተደበቁበት ተመልሰው መጥተው
በሰፊው እየጐበኙት ስለሆነ፤ በትካዜ ተኮራምቶ” ከከረመው ሻምበል ብሩክ
ውስጥ፤ የድሮው ሳቂታውና፤ ተጫዋቹ
ሻምበል ብሩክ መታየት ጀምሯል፡፡ይህንን ለውጥ እንኳን እሱ፤ የቅርብ አለቃው ሻለቃ ለሜሳ በሚገባ አጤነው በለውጡ ተደስቷል። አሁን ሻምበልን የሚያሳስበው ትህትና ከሆስፒታል ስትወጣ ስለሚጠብቃት ክስ ነው፡፡ በመሆኑም ከአበራ ጋር በየጊዜው ስልክ ይደዋወላሉ፡፡አበራ ለዚህ ጉዳይ በጣም ጠቃሚ ሰው መሆኑን ከተረዳ ጊዜ ጀምሮ..
"አይዞህ እኔ አለሁልህ" በማለት
ከመመስከር ወደ ኋላ እንዳይል፤ አጥብቆ እያደፋፈረው ነው፡፡ አበራ በማያውቀውና ባልሰራው ወንጀል ደግሞ በዚያን የሰው ልጅ ምንም ከየመንገዱ ላይ እየታፈስ በሚታሰርበት፡ በሚገረፍበትና፤ በሚገደልበት ቀውጢ ወቅት፤ ሻምበል ብሩክን የመሰለ ባለማእረግ ዘመድ ማግኘቱ ለራሱ እድል ስለሆነ፤ የእንደሻው
ወላጆች የፈለጉትን ይበሉ እንጂ እንደሻውን ከመበቀል ባሻገር፤ ከዚያ ጉድ ለማምለጥ ጭምር፤ ሻምበል በሚለው መንገድ የሚያውቀውን ሁሉ ለመመስከር ቆርጦ ተነስቷል። በዚህም መሰረት አበራ ለፖሊስ በሰጠው ቃል እንደሻው በትህትና ላይ ስለፈፀመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ያለ ምንም ፍርሃት በዝርዝር
ሲያስረዳ፤ ፍርድ ቤት ቀርቦ ይህንን የእውነት ቃሉን ያለምንም ማወላወል እንደሚመሰክር አረጋገጠ፡፡ አበራ ከዚህ ውሳኔ ላይ ሲደርስ በልጃችን ላይ የመሰከርክ ከሀዲ ብለው ወላጆቹ ምናልባት ቢያባርሩኝ የሚለው ፍርሃቱን ለመቀነስ፤ በታማኝነት ሲሰራ የኖረው ልጅ ከሱቁ ገንዘብ ላይ ድርሻውን ማነሳሳት ጀምሯል፡፡ ቀናት ተቆጠሩ፡፡ ጊዜው
ወደፊት ገሰገሰ፡፡ በዚህ መካከል አንዱአለም በውሳኔው መሰረት ለባህር
ሃይል አባልነት ተመዝግቦ ፈተናውን ያለፈው በጥሩ ውጤት ነበር፡፡ ይህንን ሁኔታ አዜብ ካወቀች ችግር እንደምትፈጥርበት ስላወቀ፤
ደበቃት፡፡ ከአላማው እንዳያደናቅፉት ጉዳዩን ለሻምበል ብሩክ ጭምር ድብቅ እንዲሆን አደረገ፡፡ የሻምበል ምኞት በትምህርቱ ጠንክሮ ጥሩ ውጤት እንዲያመጣና ዩኒቨርስቲ እንዲገባ ነበር። "አለሁልህ” እያለ በሁሉም ረገድ ከጐኑ የቆመውም አንዱ አለም ያለውን ጥሩ ጭንቅላት ተጠቅሞ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደደርስ ከነበረው ፅኑ ፍላጎት በመነጨ ነበር፡፡
እሱ ግን ሃሳቡን ሙሉ ለሙሉ በሻምበል ብሩክ ላይ ለመጣል ካለመፈለጉም በተጨማሪ ለቤተሰቦቹ ያለውን አለኝታነት
ለማረጋገጥ ጭምር በጥልቀት አስቦበት የወሰነው የመጨረሻ ውሳኔ ስለሆነ፤ ይህን ውሳኔውን ማንም እንዳያሰናክልበት ከባድ የግል ሚስጥሩ አድርጐ ያዘው፡፡
ሻምበል ብሩክ እናቱን እያሳከመ ነው
ሻምበል ብሩክ ትህትናን እያሳከመ ነው፡፡ ሻምበል ብሩክ የራሱን ትናንሽ
ወንድሞቹን እያስተማረ ነው፡፡ ሻምበል በዚህ ላይ ለሱም ጠዋትና ማታ ለሻይ እያለ ኪሱን መዳበሱ አልቀረም ፡፡ በዚህ ላይ ሻምበል የራሱን ህይወት ይመራል፡፡ እና ሻምበል ይሄንን ሁሉ እንዴት መሸከም ይችላል? በዚህ ላይ የወታደር ደሞዝ ምን ያክል ነው ? እሱ ከበደኝ አቃተኝ
ብሎ እስከሚናገር መጠበቅ ያስፈልጋል? ሽክምነትስ እስከመቼ ??
እነዚህና፤ እነዚህን፤ የመሳሰሉ ጥያቄዎችን እያነሳ እራሱን ሲጠይቅ
ውሳኔው ይዋል ይደር የማይባል መሆኑን አመነበት :: ስለዚህ ይሄንን የሻምበል ብሩክን ከባድ ሸክም ለማቃለል... እናትና እህቱን አይዟችሁ እኔ አለሁላችሁ ለማለት... ህሊናውን ከወቀሳ ነፃ ለማድረግ... የተገኘውን አማራጭ በመጠቀም የኢትዮጵያ ባህር ሃይል አባል መሆን!! ዩኒፎርሙ ታየው፡፡ መለዮው መጣበት፡፡ በመርከብ ላይ...በቀይ ባህር
ላይ..ቀዘፈ...... በሃሳብ ከነፈ...

#ክፍል_ሃምሳ_ሁለቴ
፡
፡
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ
...የጠዋት ፀሐይ የማንንም ፈቃድ ሳትጠይቅ ፈገግ ብላ በዝግታ ወደ ጥናት ክፍሉ ገባች ። ፈገግታዋ ሙቀት እንጂ
ድምፅ ስለ ሌለው ፥ አቤል ቶሎ አላያትም እያዘገመች የተቀመጠበት ወንበር ላይ ደርሳ ግራ ጐኑን ስትሞቀው ነቃ ከእንቅልፉ ሳይሆን በተመስጦ ይሠራው ከነበረው ጽሑፍ ላይ እና ብዕሩን ወረቀቱ ላይ ወርውሮ በተቀመጠበት ተንጠራራ ። ሰውነቱን አፍታታ ።
እጁ ላይ ሰዓት የለም ። ነገር ግን፥ከንጋቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ መሆኑን ለመገመት አልተቸገረም” ። ከተቀመጠበት
ሳይነቃነቅ ሦስት ሰዓት ያህል መቆየቱ አላስገረመውም ። ከሌሊቱ ዐሥር ሰዓት ከእንቅልፉ እየነቃ እስከ ንጋት ድረስ
መሥራት፡ሰሞኑን ልማድ እያደረገው መጥቷል ። በንጹሕ አእምሮ ስለሚሠራ፥ ፍሬያማ ውጤትም አግኝቶበታል ።
ዮናታን ይህንኑ በመመልከት ለማንቃት እንዲረዳው የሳሎ ኑን ባለደወል የጠረጴዛ ሰዓት መኝታ ክፍሉ ውስጥ አድርገውለታል ። ቀን ቀን ለጥናት ጽሑፉ የሚረዱትን መጽሐፎች ሲያገላብጥ ውሎ በዚች በለሊቷ ሰአት መጻፉ ጥሩ መንገድ
ሆኖለታል።
ተንጠራርቶ ሲያበቃ ከተቀመጠበት ተነሣ ወደ በረንዳ መናፈሻ ብቅ ብሎ ፀሐይዋን ሙሉ በሙሉ ሊሞቃት ፈለግ ። የሰንበት ፀሐይ ! ጭለማው ገልጦ የእሑድ ፀሐይ ብቅ ካለች ከውጭ የሚመጣ ሰው አለ ስለዚህ የእሑድ እንግዳውን ለመቀበል ጸጉሩን ማበጣጠር ልብሱን መቀየር ነበረበት።
ጸጉሩን ሲያበጥር ልቡ ድቤ መምታት ጀመረ ። ዕረፍ ብለው አያሳርፉት ነገር ! የልብን ከበሮ አይቆጠሩት ነገር !
የገዛ ልቡ አናደደው ። ድንገት የበሩን ደወል የሰማ መሰለው ተሳስቷል ። ናፍቆት የፈጠረ ደውል ካልሆነ በስተቀር ፡ በክፍሉ ውስጥ የተሰማ ድምፅ የለም ። የሹካ ማንከያና የስሐን ድምፅ ግን በርግጥ ከሌላኛዉ ክፍል ይሰማል ።
ያቺ ሞኒካ ስትንደፋደፍ ነው ። መቼም እሷ ጠዋት መተኛት አትወድ።
ወደ በረንዳው መናፈሻ ወጥቶ ከፎቁ ቁልቁል ተመለከተ ። የዮናታን መኪና እቦታዋ የለችም ። ጠዋት ሲነሡ
ስለሰማ፡የት እንደሔዱ አላጣውም። በአስፋልቱ ሳይ ከሚሠሩ መኪናዎች መሐል ነጥሎ የሚለያት ይመስል ዐይኑን ወደ ሩቅ ወረወረ ። የቤት መኪናዎች እምብዛም የሉም ። ታክሲዎች ናቸው ሽቅብ ቁልቁል ውር ውር የሚሉት ።
ቆሞ መጠበቁ ሰለቸው ። የቆመበት ጊዜ ከዐሥራ አምስት ደቂቃ ባይበልጥም ለእሱ የዓመት ያህል ረዘመበት
“ምን ሆነው እንዲህ ቆዩ ? ” አለ በሐሳቡ፡ አልሔድም ብላቸው ይሆን ? ወይስ የሙሽራ ልብስ አልብሰው ሊያመጧት
ይሆን ? ?
ትዕግሥቱ አልቆ ወደ ውስጥ ተመለሰና ሞኒካ ጋ ሔደ።ወጥ ቤት ውስጥ ምግብ እያበሰለች ነበር ። የቡታ ጋዙን ሦስቱም ምድጃ ድስት ተጥዶበታል ። ሰርግ ሰርግ ሸተተው ፤ የወጡ ሽታ ራብ ለቀቀበት ። ቁሌቱ ገና ይንተሸተሻል ። የበሰለው ደግሞ ክዳኑን ሽቅብ እየገፈተረ ይንተከ
ተካል ። ሞኒካ ፊት ላይ ክፉኛ መቻኮል አነበበ ።
“ ምን ልርዳሽ ? ” አላት ። እሷም ፈገግ ብላ " ከምድጃው ላይ አንዱን ድስት አውርዳ ፥ ቡና በማንቆርቆሪያ
እንዲጥድላት ነገረችው ፡ሁለቱም የሥራ ድርሻቸው ላይ አትኩረው እግረ መንግዳቸውን ስለ ጽሑፍ ሥራው ሁኔታ መጨዋወት ላይ እንዳሉ ድንገት ደወሉ ተንቃጨለ።
አቤል ሲሰማው በላብ ተጠምቀ ፣ጭንቅ አለው ፤የልቡ ትርታ ፍጥነቱን ጨመረ ። ምን ሰው ያስደነግጣሉ ! ቀስ ብለው አይደውሉም እንዴ ? ” የቡና ማንቆርቆሪያ ክዳን እንደ ወደቀበት ያስተዋለው ቆየት ብሎ ትንሽ ከተረጋጋ በኋላ ነው።
ሞነካ ዋናውን በር ከፍታ እንግዶቿን ስትቀበል አቤል ወጥ ቤት ውስጥ እንደ ቆመ ጆሮውን ላከ። የተነባበረ የጫማ ድምፅ ። የማን የማን ይሆን ? የዮናታን ፡ የእስክንድር ፡ የሚሰማው የወንዶች ድምፅ ብቻ ሆነበት ። የልቡ ምት ስላስፈራው ደረቱን በእጁ ደገፈ ። ወዲያው ግን ሞኒካ ራሷን በእንግሊዝኛ ስታስተዋውቅ ስለ ሰማ አዲስ ሰው
መምጣቱን ገመት ።
ያላበውን እጁን አጠገቡ ያገኘው ነገር ላይ ጠራረገ ።ግንባሩን ፡ ጉንጩን ዐይኑን በእጁ አሻሸ እንደ ቆመ ጸጉሩን አበጣጠረ ። የሸሚዝ ኮሌታውን እያስተካከለ በረዥሙ ተነፈሰ ጭንቀት የሚያባርር፥ ፍርሐት የሚያስወግድ አተነፋፈስ : እና ርምጃውን በልቡ እየቆጠረ ወደ ሳሎን ገባ ።
ከአጭር ጠይም ሴት ልጅ ጋር ዐይን ለዐይን ተገጣጠሙ ። የሁሉም ፊት በፈገግታ ደምቆአል " ፈገግታው ሁሉ ለአቤል ጐልቶ የታየው የትዕግሥት ነው " በጉንጭ መሰርጐድ የታጀበ ፈገግታ ! ይህን ፈገግታዋን ለመጀመሪያ ጊዜ ካየው አንሥቶ ከአምስት ወር ራብ በኋላ ማየቱ ነው ። የሚወደውን የጉንጯን ስርጉድ ቀርቦ ሲያይ የመጀመሪያው ጊዜው መሆኑ ነው ። ማንን ቀድሞ መጨበጥ እንዳለበት ግራ ገብቶት ሲርበተበት አብራው የቆየችውን
ሞኒካንም እንደ አዲስ ጨበጣት ።
ለእስክንድር ያለዉን ስሜት ቆንጥጦ መያዝ አልቻለም ። ስሜቱ ፈንቅሎት ጉንጩን ጥብቅ አድርጐ ሳመውና
ይህ ሁሉ የአንተ ጥረት ያስገኘው ፍሬ ነው አስው ። ፊቱን በቅጽበት ወዶ ዮናታን መል። እና ደግሞ የርስዎ ? ” አላቸው ። ፍቅሩን በዓይኑ ከመግለጽ ቀቀር ተንጠራርቶ ሊስማቸው አልደፈረም ። ሦስተኛ ባለውለታውን ሲያመሰግን ዘወር ሲል ከአጠገቡ አጣት ። ሞኒካ ድስት ሲገነፍል ሰምታ እየሮጠች ወደ ወጥ ቤቱ ተመልሳ ነበር ።
ትዕግሥት በነጭ የሀገር ልብስ ነው የመጣችው።አቤል ይህንኑ ለብሳ የተመለከተቀትን እሑድ ወዲያው አላስታወሰም " ቆይቶ ቆይቶ ነው ከእነ ማርታ ጋር ሰርግ ቤት ስትሄድ ልብሳው እንደ ነበር ያስታወሰው። ሰላምታውንና ምስጋናውን ጨርሶ ሲቀመጥም ልቡ እልተረጋጋም ነበር ።ይበልጥ የትርታውን ፍጥነትና አስጭናቂነት ጨመረ
ዘሎ ዘሎ አንዴ ቀጥ እንዳይል ፈራ።
ትዕግሥት ማለት እሷ ነች ። ታዲያ የተመኙትን ሲያገኙ መንቀጥቀጥ ነው ? ደብዳቤዉ ያሳደረበት ስሜትና ሲገናኙ የደረሰው ሁኔታ ባለመገጣጠሙ በልቡ በሸቀ። ያ ሁሉ የፍቅር ቃላት ጋጋታ ምን ዋጠው ? ይኖራል ! ጸጥታውን የሚሰብርለት ድምፅ አጥቶ ነው እንጄ በሁለቱም ውስጥ አለ ።
አቤል ኤቼዳች ቃል መተንፈስ ፈልጎ ምላሱን ተጠራጠረው " ምናልባት የተሳሰረበት እንደሆንስ ? ከፍቅር
እመቤቱ ፊት የተቀመጠው ገላው የሚንቀጠቀጥ ጀርክ የሚመታ መሠለው።
በድንገት ዐይኑ የእጁ ጠባሳ ላይ ዐረፈ ምግብ አዳራሹ ውስጥ የወደቀ ጊዜ የወጡ ፍንጣቂ ያተረፈለት ጠባሳ ።
መጥፎ ስሜት አልተናነቀውም መጥፎ የልብ ጠባሳ ነበር እንጂ የእጅ ጠባሰ ምንም አይደለም ። የልቡን ቁስል ደብዳቤዋ ባመነጨበት እንባ ካጠበው ሰንብቷል ።
ተጫወቺ የሚል ቃል እንደ ምንም ከአፉ
ገፍትሮ አወጣ ።
ትዕግት በእሺታ ፈገግ አለች ፈገግታዋ ጠዋት ከሥራው ላይ ካባነነችው ፀሐይ ይበልጥ ደምቆ ታየው።
ሳያስቡት የዝምታው ባሕር ዮናታን እስክንድርም ውጧቸው ነበር ። ከተቀመጡ ጀምሮ ቃል አልተነፈሱም
ታዛቢ ባይሆኑም ታዛቢ መሰለዋል ። ወጥ ቤት ውስጥ የሚንተሽተሽው ምግብ ሽታ የእስክንድርን አንጀት እያላወሰው ነበር። በአፉ ምራቅ ሲሞላ ተሰማው።
"በመጀመሪያ የመኝታና የጥናት ክፍሎችህን ለትእግስት አሰጎብኛት ! አሉ ዮናታን በቤቱ ውስጥ እንቅስቃሴና ድምፅ ለመፍጠር በማሰብ።
አቤል ከትዕግሥት ጋር ተነሣ" ዮናታንና እስክንድርን በዝግታ ከኋላቸው ተከተሏቸው ።
“ ፍቅራቸው በጥሩ መልክ ይቀጥል ይሆን ? ” አለ እስክንድር በሹክሹክታ ድምፅ ፥ ወደ ዮናታን ጆሮ ጠጋ ብሎ ።
ቢቀጥል መልካም ነው ። ባይቀጥልም አቤልን እንዳለፈው አይጐዳውም ። ተቀራርበው ቃላት ከተለዋወጡ
ዐይኑን መግለጥ ይችላል አሉ ዮናታንም በሹክሹክታ በአቤልና

👍2🥰2
ትእግስት መሐከል የጫማቸው ድምፅ ካልሆነ በስተቀር የቃላት ልውውጥ አልተሰማም ። የመኝታ
ክፍሉን ጎብኝታ ወደ ጥናት ክፍሉ ስትገባ ግን ትዕግሥት ተነፈሰች ።
“ በጣም ትልቅ ይቅርታ ! ” አለችው ፡ ዐይኗ ዕንባ እቅርሮ ።
“ ምነው ለምን ? ” አላት ፥ ዕንባዋ የቀሰቀሰበትን ስሜት ከጉሮሮው ወደ ውስጥ ለመዋጥ እየታገለ ።
"ትምህርትህ በእኔ ምክንያት በመቋረጡ ይቅርታ አድርግልኝ !! »
“ ታዲያ አንቺ ምን አጠፋሽ ? ” አለና አቤል አሁንም ጉሮሮው ላይ የሚተናነቀውን ነገር በምራቁ አወራርዶ
“ ይልቅ እዚሁ ቤት የጥናት ጽሑፍ ማዘጋጀት ጀምሬአለሁ ። ለሥራው የሚረዱኝ መጽሐፎችና ሐሳቦች በማፈላለግ ትረ ጂኛለሽ ? ” አላት ።
ፈቃደኝነቷን ለመግለጽ ራሷን መነቅነቅ ወይም ቃላት መናገር አላስፈለገም ።
“ እና ትምህርቴንም በአዲስ ዓመት ፥ በአዲስ ልቦና ፥ በአዲስ ተስፋ እቀጥላለሁ ።
ቃላት አንሰዋቸው ዐይን ለዐይን ሲተያይ አልተፋፈሩም ። ዐይኗ ብሌን ውስጥ ምስሉን ሲመለከት እሷም ዐይኑ ብሌን ወስጥ ምስሏን እየተመለከተች ነበር ።
ትዕግሥት ከአቤል ዐይን ዳርቻ ላይ ዐይን አር አየች ልትጠርግለት ብትሞክርም እጅዋ ይንቀጠቀጥ ይሆን? እንደ
ምንም ደፍራ እጅዋን ዘርግታ በጣቷ አነሣችለት ።
ምንድን ነው ? ” አላት ከንፈሩ እየተንቀጠቀጠ
“ ጉድፍ” አለችው የእሷም ከንፈር እየተንቀጠቀጠ ።
ዐይኑን የነካው እጅዋን ጥብቅ አድርጎ ሳመው ።
ዮናታንና እስክንድር በደስታ ፈዘው ቀሩ። እውን ሳይሆን የፊልም ትርኢት የሚያዩ ነበር የመሰላቸው ። በተለይ
እስክንድር ራሱን መቆጣጠር አቅቶት እንደ ሕፃን ፈንደቅ ፈንደቅ የሚል ስሜት ታገለው። ደስታ በሣቅ ሣቅም በጥርስ
የሚገለጽ ነገር ባይሆን ኖሮ መላ ሰውነቱ እየሣቅ ነበር ።
ለአፍታ ያህል ጓደኞቻቸው ፊቱ ላይ ድቅን አሉበት ። ማርታ የነገር ቅንድቧን እያርገበገበች ፡ ድብርት በጋቢው
ተጀቡኖ እየተልጐመጐመ ፥ ሚስተር ሆርስ ቼሱን ታቅፎ ቅልጥሙን እንደ ዘረጋ ቤተልሔም በፈተና ሰዓት ወደ
ሽንት ቤት እየሮጠች ፡ ሳምሶን ጉልቤው ጡንቻውን ወጣጥሮ ለአቤል ሊማታለት እየተጋበዝ - ሁሉም በእስክንድር
ሐሳብ ውስጥ ተሰለፈ ። “ ምነው አንዳፍታ መጥተው ይህን ትርኢት ለማየት በታደሉ ! ” አለ በልቡ ።
አቤል የትዕግሥትን እጅ ስሞ አልለቀቀውም እንደገና ወደ ደረቱ እስጠግቶ ጥብቅ አርጐ ያዘው ። እጇ
እንደ ኤሌትሪክ ሽቦ የአቤልን ልብ ትርታ እየተቀበለ ወደ እሷ ያስታሳልፍ ጀመር ። ትርታው ነዝሯት አላፈገፈገችም ። ይልቁንም መላ ሰውነቷን በዝግታ ወደ አቤል አካል አስጠጋችው ። ትንፋሻቸው ተገጣጠመ ። ሁልቱ እንደ አንድ ሰው !
“ እ --- እ --- እፀድሻለሁ ። ”
አስቸግራው የኖረቺውን አንዲት ቃል ተነፈሳት ።
💥ተፈፀመ 💥
ሰመመን ይሄን ይመስላል ብዙዎቻችሁ ድሮ አንብባችሁት አልፋችሁ ይሆናል አሁን በዚህ ቻናል ሲለቀቅም ገና ያነበበው ሊኖርም ይችላል የሁላችሁንም አስተያየት እፈልጋለው በ @atronosebot አድርሱኝ

🥰4👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
#ከሁለት_ወራት_በኋላ
እንደሻው በቀለንና ራሷን በጥይት አቁስላ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ህክምናዋን ስትከታተል ከቆየች በኋላ በሁለተኛው ወሯ ሙሉ ለሙሉ ዳነች፡፡
በዚያ ጥይት ምክንያት ከላይኛው መንጋጋ ጥርሶቿ ላይ ሁለቱን አጥታለች፡፡ የግራ ጆሮዋ በመስማት በኩል ትንሽ ቅር ቢለውም ሙሉ ለሙሉ አልደነቆረም፡፡
ጥይቶቹ በተከታታይ ሾልከው የወጡበት ቀዳዳ መጠነኛ ጠባሳን ጥሉባት አለፈ እንጂ፤ ውበቷን እምብዛም የሚፈታተነው አልነበረም፡፡
ከዚህ ሁሉ ሥቃይ በኋላ ግን እቤቷ ገብታ አላረፈችም፡፡ ወንጀለኛ ናትና በቀጥታ በማረፊያ ቤት እንድትቆይ ተደረገ፡፡
የወንጀል ክሱ በዐቃቤ ህግ ከሳሽነት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡
ከሳሽ ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ ወይዘሪት ትህትና ድንበሩ የክሱ ምክንያት ሰው የመግደል ሙከራ ወንጀል ዐቃቤ ህጉ ተከሳሽ ሆን ብላ ተዘጋጅታ ወጣት እንደሻው በቀለ ከሚሰራበት የንግድ ሱቅ ድረስ በመሄድ በአራት ጥይቶች ያቆሰለችው መሆኑንና እራሷንም ለመግደል ሙከራ ማድረጓን ከገለፀ በኋላ፤ የወንጀለኛ መቅጫ ህግና አንቀጽ ጠቅሶ አስፈላጊው ቅጣት እንዲወሰንባት
የተመሰረተ ክስ መሆኑን በማተት አቀረበ፡፡
ትህትና ድንበሩ ተከሳሽ ሆና ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት በቀረበችበት ዕለት፤ ታናሽ ወንድሟ በችሎቱ ላይ በመገኘት ክሱን
አብሯት አዳመጠ፡፡
ፍርድ ቤቱ ለተከሳሽ የሚከተለውን ጥያቄ አቀረበላት፡፡
ስምሽ?”
“ትህትና ድንበሩ”
“ዕድሜሽ?”
"አሥራ ሰባት ዓመት”
“አድራሻ?”
“አዲስ አበባ
“ሥራሽ?”
“ሥራ ፈላጊ”
“ወላጆችሽ በህይወት አሉ?”
“አባቴ ሞቷል እናቴም የአልጋ ቁራኛ ነች”
ይህንንና መሰል ጥያቄዎችን ከተጠየቀች በኋላ “የክሱ ቻርጅ ደርሶሻል?” የሚል ጥያቄ ቀረበላት፡፡
“አዎን ደርሶኛል”
ከዚያም የመሐል ዳኛው መነጽራቸውን ዝቅ አድርገው በግንባራቸው ዐይዋትና........
“ወይዘሪት ትህትና ለተመስረተብሽ ክስ እራስሽ ትከራከሪያለሽ ወይስ?
ጠበቃ ታቆሚያለሽ?” የሚል ጥያቄ አቀረቡላት፡፡
ቀስ ብላ ሻምበል ብሩክን አየችው፡፡ የመከራትን አስታወሰች፡፡
“ድሃ ስለሆንኩ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ?” የሚል መልስ ሰጠች፡፡
ይህንን መልስ ስትሰጥ በተቻላት መጠን ድምጿ እንዲሰማ ጮክ ብላ ነበር፡፡
ፍርድ ቤቱ በጥብቅና ሙያው የታወቀው አቶ ምንውዬለት ተዘራ ለተከሳሽ ጠበቃ እንዲሆንላት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ አቶ ምንውዬለትም ትእዛዙን በደስታ ተቀበለ፡፡
ይህ ከሆነ በኋላ ተከሳሽ የተከሰሰችበት ወንጀል በንባብ እንዲሰማ ተደረገ፡፡
“በተመሰረተብሽ ወንጀል ጥፋተኛ ነሽ አይደለሽም?” ተብላ ተጠየቀች፡፡
በዚህ ጊዜ ጠበቃው አቶ ምንውዬለት ጥቁር ካባውን እንደለበሰ
ብድግ ብሎ ቆመ፡፡
“ጥፋተኛ አይደለችም ክቡር ፍርድ ቤቱ” ሲል መልስ ሰጠ፡፡ ዳኛው መልሱን ከመዘገቡ በኋላ፤ ጠበቃው “ክቡር ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ የዋስ መብቷ ተጠብቆ እንድትከራከር ይፍቀድልኝ” ሲል ጥያቄ አቀረበ፡፡
ፍርድ ቤቱ ግን ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ፤ ተከሳሽ በማረፊያ
ቤት ቆይታ እንድትከራከር በመወሰንና፤ ዐቃቤ ህጉ አሉኝ የሚላቸውን ማስረጃዎች እንዲያቀርብ ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱ አበቃ፡፡
ትህትና እዚያ የተከሳሽ ሳጥን ውስጥ
ቆማ ስትቁለጨለጭ፣እንዳንድ ጊዜ በፍርሃት ተውጣ ሰውነቷ ሲንቀጠቀጥ፣
ድምጿ ሲርገበገብ፣ ሲያልባት፡ እያየች አዜብ እንባ እየተናነቃት ነበር፡፡ ሆኖም አልቅሳ ልትረብሻት አልፈለገችም፡፡ ይልቁንም ሳቅ ፈገግ እያለች ሞራል ልትሰጣት ሞከረች፡፡
እውነትም እንደዚያ ሰውነቷ በፍርሃት ሲሸበርባት፣ ልቧ ድው ድው ሲል፣ ሻምበል ብሩክን፣ ወንድሟንና አዜብን ቀስ ብላ ታያቸዋለች፡፡ እነሱ ፈገግ ይሉና በ“አይዞሽ” ምልክት ሲያበረታቷት “አይዞኝ” በሚል ስሜት እራሷን ስታጠናክር ከቆየች በኋላ ችሎቱ ሲያበቃ በአጃቢ ፓላስ ታጅባ ወጣች፡፡
ከዚያም በአንዱአለም ጠያቂነት አብረው ምሣ ይበሉ ዘንድ ሻምበል ብሩክ አጃቢ ፓሊሱን አነጋገረውና አብረው ምሣ ለመብላት ፈቃድ ስለ አገኙ ፤ እዚያው አካባቢ በሚገኝ ወደ አንድ ሆቴል ገቡ፡፡
አንዱአለም የዛሬውን ምሣ ለመጋበዝ የፈለገበት ምክንያት ነበረው፡፡ የሚፈለገው ምግብና መጠጥ ታዘዘ፡፡
ከባህር ኃይሉ የተሰጠው የኪስ ገንዘብ ስለነበረው ምሣ የጋበዘው እሱ ነበር፡፡ አንዱአለምን ብሎ ጋባዥ በመገኘቱ እየተሳሳቁ፣እየተጨዋወቱ፣ ግብዣውን በደስታ ተቀበሉት፡፡ አጃቢ ፓሊሱ በሻምበል ብሩክ ላይ እምነት ስለጣላ እስረኛዋ ታመልጣላች የሚል ሥጋት አላደረበትም፡፡ እንደዚሁ እየተጨዋወቱ ከቆዩ በኋላ.......
“አንድ ጊዜ” አለና አንዱአለም ትንፋሹን ሰብሰብ፣ ምራቁን ዋጥ አደረገ፡፡
አራቱም በፀጥታ ይመለከቱት ጀመር፡፡ ከወትሮው ለየት ያለ ስሜት ይታይበታል፡፡ እነሱ ከተቀመጡበት አካባቢ ትንሽ ራቅ ብለው በርከት ያሉ እየተጨዋወቱ የሚሳሳቁ ሰዎች ድምጽ ብቻ ይሰማል፡፡
“ይህቺ የምሣ ግብዣ በአንድ በኩል እታለም ለመጀመሪያ ጊዜ
ፍርድ ቤት በቀረበችበት ቀን ተገኝቼ እውነተኛ ፍትህን አግኝታ በነፃ
እንድትለቀቅ መልካም ምኞቴን የምገልጽበት ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ
ለራሴ መሸኛ በማድረግ በግል ውሣኔዬ መሠረት ለነገው ጉዞዬ መቃናት
እንድትመርቁኝና፤ የወጪ እንድላችሁ በማሰብ የተደረገች ግብዣ ነች”
አለ፡፡ ስለምን እንደሚያወራ ቶሎ ማወቅ አልቻሉም :: “የምን ጉዞ? የምን መሸኛ?. “ምንድነው የምትለው አንዱዬ?” በድንጋጤና በጥርጣሬ ተውጣ አዜብ ጠየቀችው፡፡ “ ሁሉንም ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቄአለሁ፡፡
ከአንድ ሣምንት በፊት በኢትዮጵያ ባህር ኃይል ውስጥ ተቀጥሬ ለስልጠና
መሄዱ ነው” ሲል ቁርጡን ነገራቸው፡፡ በዚያ ጨዋታ መካከል ይህንን መርዶ አምጥቶ ሲጥልባቸው ልባቸው ክፉኛ አዘነ፡፡ በተለይ ትህትና የተሰማትን ስሜት መግለጽ ያስቸግራል፡፡ ጭውው አለባት፡፡ ግማሽ አካሏ፣ የምትወደው ታናሽ ወንድሟ ምንም እንኳን እስረኛ ብትሆንም በየጊዜው እየመጣላት ዐይኖቹን ስታየው
የምትጽናናበት አለኝታዋ ነበር፤ በሁኔታው መሪር ሀዘን ተሰምቷት አለቀሰች፡፡
አዜብም እንደዚያው፡ ሻምበል ብሩክም ክፉኛ ነበር የደነገጠው፡፡
ይህ ትንሽ ልጅ የዚህ ዐይነት ከባድ ውሣኔ ላይ ይደርሳል ብሎ ጭራሽ አልገመተም ነበር፡፡ የሱ ፍላጐት አንዱአለም በትምህርቱ ጠንክሮ ዩኒቨርስቲ
እንዲገባ እንጂ እንደዚህ በመሀሉ አቋርጦ ወደ ጦር ሜዳ እንዲሄድ አልነበረም፡፡ ከረጅም ፀጥታ በኋላ......
“እንደሱ ይሻላል አልክ አንዱአለም?” አለው ሻምበል በትካዜ አንደበት።
ትህትና እና አዜብ በእንባ ይንፈቀፈቃሉ፡፡ አጃቢ ፓሊሱ ግራ ተጋብቶ ሁሉንም በዐይኑ ይቃኛል፡፡
“በቃ ብንሄድስ” የሚል ፍላጉት አድሮበታል፡፡ ሞትም ቢሆን በተሰማበት ቅጽበት በድንጋጤ ያደርቃል እንጂ፤ ቀስ በቀስ መለመዱ አይቀርምና፤
ውስጥ ውስጡን እየተቃጠሉ፤ እንባቸውን እየጠራረጉ፤ዐይን፤ ዐይኑን፧ ይመለከቱት ጀመር፡፡ ውሣኔው የፀና፣ ጉዳዩ ያበቃለት መሆኑን ቁርጥ አድርጉ ነገራቸው፡፡
እስከዛሬ ድረስ የቆየው እህቱ ፍርድ ቤት ስትቆምና የተከሰሰችበት ወንጀል ሲሰማ አብሯት ለመገኘት ፍቃድ በመውሰድ መሆኑን፣ ነገ በጠዋት በዋናው መሥሪያ ቤት ተገኝቶ ወደ ማሰልጠኛው ጉዞ የሚጀምርከ መሆኑን፣ለሻምበል ሲያስረዳው ለትህትና እና ለአዜብ ደግሞ የመርዶ ያህል ካረዳቸው በኋላ በአጃቢ ፓሊሱ አሳሳቢነት ተነስተው ወጡ፡፡
“እሺ አሥር አለቃ ስለተባበርከኝ በጣም ነው የማመሰግንህ አለው ሻምበል የአጃቢ ፓሊሱን ትከሻ ቸብ ቸብ እያደረገ፡፡
“እሺ ጌታዬ አኔም የርስዎ ነገር ሆኖብኝ እንጂ፤ ህግ መጋፋቴን አልዘነጋሁትም” አሥር አለቃ ጥላዬ እግረ መንገዱን ውለታውን

እያዘስመዘገበ....አንዱአለም ከእህቱ ጋር ተቃቅፈው፤ ተሳስመው ፤ ሲሰነባበቱ ግን አልቻልም፡፡ ሆዱ ባባና አቅፏት አለቀሰ፡፡
በመጨረሻም ትህትና ወደ እሥር ቤት ጉዞዋን ስትቀጥል፤ እሱ ደግሞ ዝግጅቱን ሊያጠናቅቅ ወደ ባህር ኃይል መሥሪያ ቤት ለመሄድ ሻምበል ብሩክን ተሰናበተና ከአዜብ ጋር ሆነው ታክሲ ውስጥ ገቡ......
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
በመጨረሻም ትህትና ወደ እሥር ቤት ጉዞዋን ስትቀጥል፤ እሱ ደግሞ ዝግጅቱን ሊያጠናቅቅ ወደ ባህር ኃይል መሥሪያ ቤት ለመሄድ ሻምበል ብሩክን ተሰናበተና ከአዜብ ጋር ሆነው ታክሲ ውስጥ ገቡ......
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ላንቺው_ነው
💚 💛 ❤️
የጎደለው አንዳች የለም
የሚያሳንሰው . . . ከሰው ግብር፣
ለራሱ መኖርን አስንቆ
በቀን ሃሩር የሚያንገላታ
በሌ'ቱ ቁር የሚያሳድር፡፡
ቀና ሲል የሰማይ አድማስ
ደረቅ ቁጥቋጦ ሲያዘቀዝቅ፣
ቆምኩ ሲል የጋለ መሬት
ቢራመድ ከቆንጥር መናጠቅ
ምን ቢፈተን በተፈጥሮ
ጥርሱን ነክሶ ያሸነፈ ፣
በብርሃንሽ ላይ ያጠላውን
ጨለማሽን የገፈፈ፡፡
ሰላም ውለሽ እንድታድሪ
ከእንቅልፉ ጋር የተፋታ፣
ስለ ክብርሽ የመነነ
ስለ እረፍትሽ ያጣ ፋታ፡፡
ድንበርሽን ባጥንቱ አጥሮ፣
ሰንደቅሽን በደሙ ያቆመ
ከምትክ የለሽ ህይወቱ እንኳ፣
ህልውናሽን ያስቀደመ
ላንቺው ነው እምዬ እናቴ፣
ላንቺው ነው አንቺ እናት ሃገር
ለሰንደቅሽ ከፍታ ሲል፣
የወደቀልሽ ወታደር፡፡
ላንቺው ነው........!
በእረፍት የለሽ ኑሮ መሃል፣
ያንቺን ነገ እየሳለ
በረሃውን አለሙ አድርጎ፣
ከተፈጥሮ ጋር የታገለ
በተጋፈጣት ተራራ፣
በወረደባት ቁልቁለት
በተሻገራት ወንዝ ይሁን፣
በፈተነችው ተዳፋት፣
በተጓዘባት ሸለቆ
ባቆራረጣት ተረተር፣
በእያንዳንዷ ስንዝር መሬት
በረገጣት ቅንጣት አፈር፣
ያንቺን ክብር የሚመጥን
ላብ ከፍሎበታል ወታደር፡፡
ምንም ገፁ ቢጎሰቁል
ቢሻክር ደድሮ መዳፉ፣
ምንም አንጀቱ ቢታጠፍ
በውሃ ጥም----- ቢደርቅ አፉ፣
በጉዞ ብዛት ቢዝሉ
እረፍት አያውቄ እግሮቹ፣
በእንቅልፍ እጦት ቢዳከሙ
ቢደበዝዙ አይኖቹ
በማይታየው ውስጡ ግን
ባላየነው ልቡ ላይ፣
ሃገሬ አንቺ ነግሰሻል
ደምቀሻል ከፀሃይ በላይ፡፡
ላንቺው ነው........!
ላንቺው እንጂ መኖር የሚሻ
በበረሃው ሃሩር ነድዶ፣
ስለ ክብርሽ እንጂ የሚሞት
ስጋ አጥንቱን በእሳት ማግዶ
ወታደርኮ ሃቅ ነው ለገባው ቃል የታመነ፣
ቤት ንብረቴን - ልጄን ሳይል
ሃገር አፍቅሮ የመነነ፡፡
በጀግንነት ጠላት ጥሎ
ሲሰዋ እንኳን በጦር ስፍራ፣
በስስት እያያት ያሸልባል
የሃገሩን ውብ ባንዲራ፡፡
የጀግናችን የፍቅር ጥግ
ታውቂያለሽ እናት ሃገሬ፣
በአንቺ ነው አፉን የፈታ
ዜማው ነሽ ህብረ ዝማሬ፡፡
ማንም ሊደፍረው ባልተቻለው
ፀንቶ ባቆመው ድንበርሽ ላይ፣
የወታደር አፅም አለበት
በሃቅ ሚዛን ብቻ የሚታይ፡፡
ከአፈርሽ ጋር ተቀላቅሎ
ሉአላዊ ክብርሽ የፀናበት፣
በነፃነት ዱካሽ መሃል
የወታደር ደም አለበት፡፡
ላንቺው ነው!
🔘በሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
💚 💛 ❤️
የጎደለው አንዳች የለም
የሚያሳንሰው . . . ከሰው ግብር፣
ለራሱ መኖርን አስንቆ
በቀን ሃሩር የሚያንገላታ
በሌ'ቱ ቁር የሚያሳድር፡፡
ቀና ሲል የሰማይ አድማስ
ደረቅ ቁጥቋጦ ሲያዘቀዝቅ፣
ቆምኩ ሲል የጋለ መሬት
ቢራመድ ከቆንጥር መናጠቅ
ምን ቢፈተን በተፈጥሮ
ጥርሱን ነክሶ ያሸነፈ ፣
በብርሃንሽ ላይ ያጠላውን
ጨለማሽን የገፈፈ፡፡
ሰላም ውለሽ እንድታድሪ
ከእንቅልፉ ጋር የተፋታ፣
ስለ ክብርሽ የመነነ
ስለ እረፍትሽ ያጣ ፋታ፡፡
ድንበርሽን ባጥንቱ አጥሮ፣
ሰንደቅሽን በደሙ ያቆመ
ከምትክ የለሽ ህይወቱ እንኳ፣
ህልውናሽን ያስቀደመ
ላንቺው ነው እምዬ እናቴ፣
ላንቺው ነው አንቺ እናት ሃገር
ለሰንደቅሽ ከፍታ ሲል፣
የወደቀልሽ ወታደር፡፡
ላንቺው ነው........!
በእረፍት የለሽ ኑሮ መሃል፣
ያንቺን ነገ እየሳለ
በረሃውን አለሙ አድርጎ፣
ከተፈጥሮ ጋር የታገለ
በተጋፈጣት ተራራ፣
በወረደባት ቁልቁለት
በተሻገራት ወንዝ ይሁን፣
በፈተነችው ተዳፋት፣
በተጓዘባት ሸለቆ
ባቆራረጣት ተረተር፣
በእያንዳንዷ ስንዝር መሬት
በረገጣት ቅንጣት አፈር፣
ያንቺን ክብር የሚመጥን
ላብ ከፍሎበታል ወታደር፡፡
ምንም ገፁ ቢጎሰቁል
ቢሻክር ደድሮ መዳፉ፣
ምንም አንጀቱ ቢታጠፍ
በውሃ ጥም----- ቢደርቅ አፉ፣
በጉዞ ብዛት ቢዝሉ
እረፍት አያውቄ እግሮቹ፣
በእንቅልፍ እጦት ቢዳከሙ
ቢደበዝዙ አይኖቹ
በማይታየው ውስጡ ግን
ባላየነው ልቡ ላይ፣
ሃገሬ አንቺ ነግሰሻል
ደምቀሻል ከፀሃይ በላይ፡፡
ላንቺው ነው........!
ላንቺው እንጂ መኖር የሚሻ
በበረሃው ሃሩር ነድዶ፣
ስለ ክብርሽ እንጂ የሚሞት
ስጋ አጥንቱን በእሳት ማግዶ
ወታደርኮ ሃቅ ነው ለገባው ቃል የታመነ፣
ቤት ንብረቴን - ልጄን ሳይል
ሃገር አፍቅሮ የመነነ፡፡
በጀግንነት ጠላት ጥሎ
ሲሰዋ እንኳን በጦር ስፍራ፣
በስስት እያያት ያሸልባል
የሃገሩን ውብ ባንዲራ፡፡
የጀግናችን የፍቅር ጥግ
ታውቂያለሽ እናት ሃገሬ፣
በአንቺ ነው አፉን የፈታ
ዜማው ነሽ ህብረ ዝማሬ፡፡
ማንም ሊደፍረው ባልተቻለው
ፀንቶ ባቆመው ድንበርሽ ላይ፣
የወታደር አፅም አለበት
በሃቅ ሚዛን ብቻ የሚታይ፡፡
ከአፈርሽ ጋር ተቀላቅሎ
ሉአላዊ ክብርሽ የፀናበት፣
በነፃነት ዱካሽ መሃል
የወታደር ደም አለበት፡፡
ላንቺው ነው!
🔘በሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....ቀጠሮው ደረሰ፡፡ ትህትና ድንበሩ ለተመሠረተባት ክስ መልስ የምትሰጥበት ቀን... ጠበቃዋ አቶ ምንውየለት ተዘራ በመልሱ ላይ ተከሳሽ ሆን ብላ ተሰናድታ ሳይሆንእንደሻው በቀለ በእሷና በወንድሟ
ላይ በፈጸመውና ባስፈጸመው ተደጋጋሚ ወንጀል ምክንያት ህሊናዋ ስለቆሰለ፤ ንብረትነቱ የወላጅ አባቷ የነበረውን ከቤት የተቀመጠ መሣሪያ በድንገት ይዛ በመውጣት፤ በደም ፍላት ተነሳስታ፤ ድርጊቱን መፈጸሟን፣ ወጣት እንደሻው በቀለ በፈጸመባት አስገዳጅ የግብረ ሥጋ
ግንኙነት ምክንያት፤ ክብረ ንጽህናዋ በመደፈሩ፤ ለትዳር ከወጠነችው እጮኛዋ ጋር ከመጣላቷም በላይ፤ ታናሽ ወንድሟ አንዱዓለም ድንበሩ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ምክንያት፤ በእንደሻው በቀለ አማካይነት በገንዘብ በተገዛ ወሮበላ ተደብድቦ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን፤ እነዚህ
ተደራራቢ ጥቃቶች፤ ወንጀሉን እንድትፈጽም ያነሳሷት ድርጊቶች
ከመሆናቸው በተጨማሪ፤ ወጣቷ በዕለቱ ወጣት እንደሻውን ለማጥቃት ብቻ ሳይሆን በራሷ ህይወት ላይ የወሰደችው ቅጽበታዊ ሙከራ ሁሉ፤ የነበረባትን የአእምሮ ጭንቀት ደረጃ በግልጽ የሚያሳይ በመሆኑ፧ ክቡር ፍርድ ቤቱ የዕድሜዋን ሁኔታ፤ የደረሰባትን የሞራል መገደድ፣ የቤተሰብ ኃላፊነት ደረጃዋንና ከዚህ በፊት የነበራትን መልካም ስነ ምግባር፧ ከግምት ውስጥ በማስገባት በነፃ እንዲያሰናብታት ሲል በመጠየቅ መልስ ሰጠ፡፡
ለዚህም መልስ የመልስ መልስ እሰጣለሁ በማለት ዐቃቤ ህጉ ስለጠየቀ፤
የመልስ መልሱን እንዲሰጥ ተደረገ፡፡
ከዚህ በኋላ በፓሊስ የቀረበው የምርመራ መዝገብ፣ የሀኪም ማስረጃና፤ በእግዚቢትነት የተያዘው ኮልት ሽጉጥ ለፍርድ ቤቱ ቀረቡ፡፡ ዐቃቤ ህጉ በሰጠው የመልስ መልስ ላይ ተከሳሽም ሆነች
ወንድሟ ተፈጽሞብናል የሚሉት ወንጀል ቢኖር፤ በወቅቱ ጉዳዩን ለህግ አቅርበው ፍትህን መጠየቅ ሲችሉ፤ ይህንን ሳያደርጉ ቀርተው፤ ተከሳሽ ከተመሰረተባት የክስ ጭብጥ፤ ምክንያትና ውጤት ጋር፤ግንኙነት የሌለውን ሀተታ በመልስ ውስጥ በመዘርዘር፤ በነፃ እንድትለቀቅ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን፤ ወንጀልን ማካካስ የማይቻል
በመሆኑም በመልሱ ላይ የቀረበው የወንጀል ማካካሻ ጥያቄ ውድቅ
እንዲደረግ ጥያቄ በማቅረብና ፤ ተከሳሽ እራሷን ለማጥፋት ያደረገችው ሙከራም ህጋዊ ድጋፍ የሌለው ህገውጥ ድርጊት ከመሆን አልፎ ከጥፋትዋ ነፃ እንድትወጣ በቂና አሳማኝ ምክንያት ሊሆን የማይችል
ስለሆነ፤ ክቡር ፍርድ ቤቱ በተከሳሽዋ ላይ የጥፋተኛነት ውሳኔ
በዚህም መሰረት
ቃለ መሀላ
እንዲሰጥልኝ በማለት ስለተከራከረ ፤ ለተፈጸመው ወንጀል ያውቁልኛል
የሚላቸውን ምስክሮች እንዲያቀርብ ተደረገ በምስክርነት ያቀረባቸው ሶስት ምስክሮች ፍ/ቤት ቀርበው እንዲፈጽሙ ከተደረገ በኋላ ፤ ወንጀሉ የተፈጸመበትን ቦታ፣ ቀንና ሰዓት ጠቅሰው ተከሳሽ እንደሻው በቀለን በአራት ጥይቶች ደጋግማ ማቁሰሏን በማረጋገጥ፤ ተመሳሳይነት ባለው ቃል መሰከሩ፡፡
የዐቃቤ ህጉ ምስክሮች ተሰምተው እንዳበቁ በተከሳሽ ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች ከበድ ያሉ ሆነው በመገኘታቸው፤ ፍ/ቤቱ ተከሳሽን
እንድትከላከል ትዕዛዝ ሰጠ፡፡በዚህ ጊዜ የተከሳሽ የመከላከያ ምስክሮች ሆነው የቀረቡት
1ኛ ወ/ት አዜብ ተሾመ
2ኛ ወ/ት ወርቅ ያንጥፉ አደራ
3ኛ. አቶ አበራ ፈይሳ
አስፈላጊውን ቃለ መሀላ ከፈጸሙ በኋላ፤ ተከሳሽ በአስተዳደግ፤ በተማረችበት ትምህርት ቤት፤ በሥራ ቦታዋ ላይም ሆነ በመኖሪያዋ አካባቢ የነበራትን ሥነ ምግባር፣ ከዚህ በፊት ተከሳ ያልተቀጣች ጨዋ ወጣት መሆኗንና፤ ወጣት እንደሻው በቀለ ድምጽ በሌለው መሣሪያ አስገድዶ ክብረ ንጽህናዋን ለመድፈሩ፤ እያንዳንዳቸው የሚያውቁትንና
ያዩትን ዘርዝረው መሰከሩ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እራሱ ሻምበል ብሩክ ፍርድ ቤት ቀርቦ ከእጮኛው ከትህትና ድንበሩ ጋር ወጥነውት የነበረው የትዳር ዕቅድ፤
ከተፈጸመባት አስገዳጅ የክብረ ንጽህና መደፈር ጋር ተያይዞ በተፈጠረ
ያለመግባባት ምክንያት መበላሸቱን አስረዳ፡፡
ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክርና የቀረቡትን ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ
“ተከሳሽ በማያጠራጥር ሁኔታ ድርጊቱን የፈጸመች ሆና ስለአገኘናት በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 27/524.ለ/ መሠረት ጥፋተኛ ነች ብለናል”
ሲል የጥፋተኛነት ውሣኔውን ሰጠ፡፡
ጥፋተኛነትዋ ተረጋግጦ ውሣኔ ከተሰጠ በኋላ፤ ቀሪው በቅጣት ውሣኔው ላይ የሚካሄድ ክርክር ነው፡፡በዚህ መሠረት ተከሳሽዋ ለፈፀመችው ወንጀል የቅጣት ውሣኔውን ለመስጠት እንዲያስችል ዐቃቤ ህጉ የቅጣት ማቅለያ ወይንም የማክበጃ ሃሣብ ካለው እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ስለጠየቀ፤ ተከሳሽ ትህትና ድንበሩ በቀልን በልቧ በማሳደር፤ በቂ ዝግጅት በማድረግና፤ የጦር መሣሪያ በመያዝ፤ ከሥራ ቦታው ድረስ ሄዳ ወጣት እንደሻው በቀለን በአራት ጥይቶች ደጋግማ ህይወቱን ለማጥፋት ሙከራ ማድረጓ በበቂ ማስረጃ የተረጋገጠባት በመሆኑ፡ ለዚህ ለፈጸመችው ወንጀል ተመጣጣኝ ቅጣት እንድታገኝ የወንጀለኛ መቅጫ ህግና አንቀጽ ጠቅሶ ጠየቀ፡፡
የተከሳሽ ጠበቃም እንደዚሁ ስለህጉና፤ ስለጉዳዩ፤ በማብራራት ቅጣቱ እንዲቀልላት አስተያየቱን አቀረበ፡፡
በዚህ የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ላይ በወጣት እንደሻው በቀላ ወላጆች ቤት ውስጥ ተቀጥረው የሚያገለግሉት በተለይ የወጣት እንደሻው የሥጋ ዘመድ የሆነው አቶ አበራ ፈይሣ የዝምድና ደረጃው ሳያግደው በሃቅ እንደመሰከረውና፤ በቤት ሠራተኛነት ተቀጥራ የምታገለግለው ወይዘሪት ወርቅ ያንጥፉ አደራ በዐይኗ ባየችው ድርጊት ላይ በሰጠችው የምስክርነት ቃል በተረጋገጠው መሠረት፤ እንደሻው በቀለ ሃይል ተጠቅሞ፤ በተከሳሿ ላይ የሞራል ተቃራኒ የሆነ፤ የወደፊት የትዳር ህይወቷን ያበላሸና፤ ከምትኖርበት ማህበረሰብ ባህልና እምነት አንፃር ዝቅተኛ ግምት የሚያሰጣትን ወንጀል የፈጸመባት በመሆኑ፤ ከዚሁ ወንጀል ጋር በተያያዘም ጋርጠው መራን በገንዘብ በመግዛት በወንድሟ ላይ የድብደባ ወንጀል በማስፈጸም ያደረሰባት ድርብ፤ ድርብርብ ጥቃት ለጋ አእምሮዋን የነካና፤ ለወንጀል ያነሳሳት ድርጊት መሆኑን :: ወጣቷ
በምትኖርበትም ሆነ በተማረችበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፍጹም ጨዋና
ዕላማዊ ዜጋ መሆኗ የተመሰከረላት ከመሆኑ በተጨማሪ፧ ወላጅ አባቷ
ለግዳጅ ተጠርቶ በጦር ሜዳ ላይ በመሞቱ ምክንያት፧ በለጋ እድሜዋ
ከራሷ ጭምር ሶስት ቤተሰብ የማስተዳደር ሃላፊነት የተሸከመች ወጣት
በመሆንዋ ክቡር ፍርድ ቤቱ.....
ሀ. ተከሳሽ ወንጀሉን ለመፈጸም የተነሳሳችበትን ሁኔታ
ለ. የተከሳሽን የዕድሜ ሁኔታ
ሐ. ተከሳሽ ወንጀሉን ስትፈጽም የነበረችበትን ሁኔታ
መ. የተከሳሽን የቤተሰብ ኃላፊነት ደረጃ
ሠ. ተከሳሽ ከዚህ በፊት በማናቸውም ወንጀል ተከሳ ቅጣት ያልተፈፀመባትና፤ ለወደፊቱ ያላትን የሥነ ምግባር ታራሚነት ከግምት ውስጥ በማስገባት እስከዛሬ ድረስ በማረሚያ ቤት የቆየችበት ጊዜ በቂ
ሆኖ ቅጣቱ እንዲቀልላት በማለት አስተያየቱን ሰጠ፡፡
ከዚህ በኋላ የሚቀረው ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ የቅጣት ውሣኔ የሚሰጥበትን ዕለት በጉጉትና በናፍቆት መጠባበቅ ብቻ ሆነ
አንዱአለም በአሁኑ ሰዓት ምጽዋ በባህር ኃይል ውስጥ በስልጠና ላይ ይገኛል፡፡ ለኪስ የሚሰጠውን አነስተኛ ገንዘብ የሚልከው ለእህቱ ነው፡፡ እህቱ በማንኛውም ረገድ እንድትበረታ፣ መታሰር ማለት በህይወት ውስጥ ከሚገጥሙ የኑሮ ውጣ ውረዶች አንዱ እንጂ ከህብረተሰቡ መገለል ማለት ያለመሆኑን እየገለጸ “አይዞሽ” እያለ በማጽናናትና፤ ስለሱ እንዳታስብ በቀይ ባህር ዳርቻ፣ በመርከብ ላይ፣ ብቻውንና ከጓደኞቹ ጋር
ሆኖ የተነሣቸውን ፎቶ ግራፎች ለሷና

👍4
ለእናቱ በመላክ፡ ናፍቆታቸውን
እንዲወጡ እያደረገ ነው፡፡
“አይዞሽ እማምዬ ልጦርሽ ደርሻለሁ፡፡ አሁን ትልቅ ሰው ሆኜልሻለሁ፡፡ እንደድሮው ትንሽ ልጅ አይደለሁም፡፡ በቅርቡ ድነሽ መጥተሽ እንደምትጠይቂኝ ተስፋ አደርጋለሁ” ከሚል የማበረታቻና
የናፍቆት ደብዳቤ ጋር...
ለእናትና ለእህቱ የዚህ ዓይነት ደብዳቤ ሲያዘጋጅ ለአዜብ ተሾመ የሚልክላት ደብዳቤ ደግሞ ለየት ይላል፡፡ በጦር የተወጋ ልብ ያለበት ስዕል
በአበባ የተጌጠ ስዕል..... የቀለበት ስዕል የሚሳሳሙ ፍቅረኛሞች ያሉበት ፓስት ካርድ..... ስለ ፍቅር የተጠቃቀሱ ጥቅሶች.. ስለወደፊት የትዳር ህይወታቸው መልካም ምኞት ..... የማይፃፃፉት ነገር የለም፡፡
አዜብም በፍቅርና፤ በናፍቆት፤ ሙትት ብላለች፡፡ ትንሽ ገጽ ፍቅሯን የሚገልጽላት ስለማይመስላት፤ አምስት ስድስት ገጽ አይበቃትም፡፡ሁለቱ ፍቅረኛሞች በየልባቸው ውስጥ የተተከለው የፍቅር ችግኝ እያደገና እያበበ በመሄዱ ትዳርን እንዲጠነስሱት መሠረት እየጣለ
በመሄድ ላይ ነው፡፡ እሱ ከእሷ፤ እሷም ከእሱ ሌላ ለፍቅር የተፈጠረ የለም እስከሚያስኛቸው ድረስ ተዋደዱ፡፡ በፍቅር ድር ተተብትበው..በፍቅር ሰንሰለት ተቆራኝተው... ርቀት ሳያግዳቸው፤
በመንፈስ ሳይለያዩ፧ አንድ አምሳል፤ አንድ አካል፤ ሆነው፤ በትዳር ለመኖር ምኞታቸው ገደብ አልነበረውም፡፡
ፍርድ ቤቱ ለረጅም ጊዜ ሲያከራክር ከቆየ በኋላ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጠ፡፡ በዚሁ መሰረት የቀጠሮው ቀን ተገልጾ ለአንዱአለም ደብዳቤ ተጻፈለት፡፡ እህቱ የተከሰሰችበት አንድ ዓመት ሙሉ
ያከራከረው ክስ የሚቋጭበት ዕለት መወሰኑን የሚገልፀው ዳብዳቤ
እንደደረሰው ልቡ ተንጠለጠለች፡፡ ምንም እንኳን በአካል ርቋት ቢገኝም፤ በሃሣብ ከሷ ሳይለያት በመንፈስ ሲጨነቅና ሲጠበብ ቆይቷልና፤ አዲስ አበባ ሄዶ ከአጠገቧ ተገኝቶ የክሱ ምዕራፍ የሚዘጋበትን የፍርድ ውሣኔ ሊሰማ ከፍተኛ ጉጉት ስለአደረሰት ጉዳዩን ለጓደኞቹ አሳወቃቸው፡፡
ምን ያክል ይጨነቅና ይጠበብ እንደነበረ የሚያውቁት ጓደኞቹም ምኞቱ እንዲሳካለት ተረባረቡ፡፡ የጠየቀው ፍቃድ እንዲሰጠው በማስተባበርና ለመጓጓዣ የሚሆን ገንዘብ በማዋጣት፤ ከጐኑ ቆሙ፡፡ ከዚያም የአውሮፕላን ቲኬት ቆርጠው......
“አድባር ትከተልህ መልካም ዜና ለመስማት ያብቃህ” ብለው
መርቀው ሸኙት፡፡አንዱአለም በዚህ አጋጣሚ የእናቱን፣ የሻምበል ብሩክ እና
የአዲስ አበባን ናፍቆት ሊወጣ፤ ከፍቅረኛው ከአዜብ ተሾመ ጋር በአካል
ተገናኝተው ፤ አድማስ የጋረደው የፍቅራቸውን ግርዶሽ ወዲያ ገላልጠው ፤
የናፍቆታቸውን ጥም ሊቆርጡ፤ በመታደሉ ጭምር ጉዞው በአንድ ድንጋይ ሶስት ወፍ ሆኖለት በደስታ ተውጦ አውሮፕላን ላይ ወጣ፡፡.....

#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳንኤል
#ቅድመ_ታሪክ
እሪ! እሪ! ይላል አምቡላንሱ። ከፊቱ ያለውን እያተራመሰ፤እየደረማመሰ በጭለማው ውስጥ እንደ ቀስት ወደፊት
ይወነጨፋል፡፡ ቦግ..እልም ቦግ...እልም የሚሉትና የሚንቀለቀሉት ቀያይ የአደጋ መብራቶቹ የሚተፉት ቀይ ብርሃን በጨረቃ የለሹ ምሽት እየተወራጨ በዝናቡ ጎርፍ በተዘፈቀው አስፋልት ላይ ሲያርፍ ዙሪያው የደም ኩሬ ይመስላል። እሪ! እሪ! እሪ! ይላል አምቡላንሱ፤ በደሙ ኩሬ ውስጥ እየተንቦራጨቀ እሪ! እንደ መብረቅ ሲወረወር በሩቅ ያዳመጡት
አሽከርካሪዎች ጥግ ጥግ ይይዛሉ፡፡ እግረኞች ከመኪናው መንገድ ይሸሻሉ
በሩቅ ቆመው በምሽት ከር ሰበርግጎ እንደወጣ ጎሽ አፍጥጠው ይመለከቱታል። ከእራት ኪሎ አቅጣጫ የመጣው አምቡላንስ መሃል ለመሃል
ተርትሯት ሲገባ ካዛንቺስ ተሸበረች።
መንገድ ዳር የቆመችው የዲፕሎማቲክ መለያ ታርጋ የለጠፈችው መኪና ፈንጂ እንደተጠመደባት ሁሉ በቅ በሕዝብ ተከባለች፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በየመኪናዎቻቸው አናት ላይ የተገጠመላቸውን ሰማያዊ መብራት "ብልጭ ድርግም ብልጭ ድርግም እያደረጉ የደረሱት ፖሊሶች ሕዝቡን ለመብተን ይጥራሉ፡፡ ከዚህ ሲበትኑት ከወዲያ ይጠራቀማል፡፡የደንብ ልብስ የለበሱ ሁለት የፖሊስ መኮንኖች ከመኪናዋ ጎን እንደቆሙ የአምቡላንሱን ድምዕ ሲሰሙ ተቁነጠነጡ፡፡ ጠና ያለው ወደ መኪናዋ ተጠጋ፡፡ በመሪው በኩል ያለው በር ተከፍቷል፤ መስታወቱ ኣስፋልቱ ላይ ረግፏል፡፡ በሹፌሩ መቀመጫ ላይ የተቀመጠው የሞሮኮው ወታደራዊ አታሼ
ወደኋላ ተንጋሎ ዐይኖቹን ገርበብ አድርጓቸዋል፡፡ በስተግራ ከማጅራቱ ስር
ጥይቱ ከገባበት ጠባብ ቀዳዳ በቀጭኑ የሚንቆረቆረው ደም ግራ ትከሻውን
አበስብሶታል፡፡ ፖሊሱ ጠጋ ብሎ አጠናው፤ ግራ እጁን አንስቶ የልቡን ምት
አዳመጠ፡፡ አለ፡፡ አልሞተም፡፡ ደም የምትረጭ ልቡ የቀራትን እንጥፍጣፊ
እየጨመቀች ትር ትር ትላለች፡፡
የአምቡላንስ አዩዬ እያቀረበ መጣ፡፡ ፖሊሱ ትከሻው ሲነካ ተሰማው፡፡ ቀና ብሎ ተመለከተ፡፡ ከጀርባው ከቆመው ጓደኛው ጋር ተያዩ፡፡በመላ ተነጋገሩ፡፡ የአምቡላንሱ ድምዕ ቀረበ፡፡ ትርትር ትላለች ልቡ፡፡ ዋይ!
ዋይ! ይላል ኣምቡላንሱ። ፖሊሶቹ ተያዩ፡፡ የተሰጣቸው ትዕዛን ቁርጥ ያለ ነው:: ጠና ያለው ፖሊስ እጁን ሰደደና ከመሪው ጀርባ ጋላል ያለውን ቁስለኛ አፍና አፍንጫ ጥርቅም አድርጎ አፈነው፡፡ ትርትር አለች ልቡ:: ትንሽ ተፈራገጠ። ትር ትር ወዲያው ዝም አለ፡፡ ቀና አዕ ፖለሱ፦ ለመጀመሪያ
ጊዜ እርጋታ እየታየበት፡፡
#ቆንጆዎቹ_ገና_አልተወለዱም።
ኤኬ አርማህ
..አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና… እሁድ ሐምሌ 21.99… ማለዳ ያነባል. በርኖሱን ደርቦ፤ አንገቱን ቀልሶ እንባውን ያወርዳል ሰማዩ፡፡ ምድርን ከምድር ሲያይ፤ሲያዝን ሲተክዝ ሲባባ፤ ሲመረው... ሰማዩ ከሰማይ ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል። እረፍ አልኩ ስል በርኖሱ ይተክዛል፡፡ ዳግም ሆዱ ሲርድ... አንጀቱ ሲላወስ ሆድ ዕቃው
ሲታሰስ መንፈሱ ሲታመስ አሄሄ!… እህህ! ነፍሱ ስታቃስት ዳግም ይጀምራል ሊያለቅሰው፣ ሊያነባ…. ሰማዩ ማለዲ
ክረምቱ ጨክኗል ዓለም ምድር… ማማ..ከል ለብሳለች...ትንፋሿ ዳምኗል.. ጥላሸት? ….. እንፋሎት? ጭጋግ ነው! ባዘቶ!...
በአፓርትመንቱ ሶስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በጉም በተሸፈነው የመኝታ ቤት መስኮት ቁልቁል የሚታየው ድብዝዝ ያለ ትርኢት አላጠግብህ ቢለው እጁቹን በመጋረጃ ውስጥ አሾልኮ ቀዝቃዛውን መስታወት በመዳፉ ወለወለው፡፡ ጨካኙ ቅዝቃዜ እንደመርፌ ጠቅ አደረገው እጁን ግን አልሰበሰበም፡፡
ከመንገዱ ባሻገር ያለው መናፈሻ ጭር እንዳለ ነው... ቢሆንም.…እየነጋ ነው. ሌላ ቀን አዲስ ቀን
ባዶ እግሩን ምንጣፉ ላይ እንደቆመ ራቁት ደረቱን አከክ አከክ አደረገና ሰዓቱን ተመለከተ፡፡
እንድ ሊሆን ነው አንድ አንድ ቀን፡፡
ፊቱን ወደ አልጋው መልሶ ቆመ ፡፡ እንደ ሁሌው እግሮቿን ዘና አድርጋ እጆቿን እዚያና እዚያ አመናቅራ በጀርባዋ ተንጋላ ተኝታለች፡፡ከላይዋ ላይ ተንሸራቶ አንድ ጠርዙ ከመሬት ሌላው ጠርዝ ከአልጋው መሃል የደረሰው የብርድ ልብስ ክፉኛ አጋልጧታል፡፡ የተመነቃቀረውንና የተበታተነውን አልጋ ሲመለከት ሰውነቱ ተፍታታበት፡፡
ቶሎ ብሎ ዓይኖቹን ክተጋለጠው ሰውነቷ ላይ ነቀላና ወደ መታጠቢያ ቤት አመራ፡፡
ሰውነቱን በሙቅ ውሃ ተጣጥቦ በሰፊ ፎጣ ኣካላቱን እያደራረቀ ወደ መኝታ ቤቱ ተመለሰ። ፈገግ አለ ሲመለከታት። ከእንቅልፏ ተነስታ ሰፊው አልጋ መሃል ተቀምጣለች፤ እንቅልፍ ያሳበጠው ትኩስ ፊቷ ወደ ቀድሞ ቅርጹ አልተመለሰም። ቦዛዝ ያሉ ጥቋቁር ዓይኖቿ ገና ማየት የጀመሩ አይመስሉም፡፡ ብትንትን ብሎ ትከሻና ደረቷ ላይ የተዘራው ፀጉሯ የደነበሩ መንታ ሚዳቆዎች የሚመሳስሉ ራቁት ጡቶቿን መሸፈን መሸሸግ አቅቶት
ግራ ተጋብቷል፡፡
“እንዴት አደርሽ እንዳትለኝ፡፡” አለች እንቅልፍ ባጎረነነው ድምጿ ተሽቀዳድማ፡፡
ለምን?” ፈገግ አለ፡፡
“ደህና አልልህማ! እብደት ነበር'ኮ… ናቲ ሙት እብደት ነው፡፡አንዳንደሰ ሰው መሆንህን ያጠራጥረኛል። አውሬ! " አለች ድንገት በሁለት እጆቿ ጭንቅላቷን ያዝ አድርጋ።
“አዳም ካደረገው የተለየ ምን ሳደርግ ተገኘሁ?” አለ ናትናኤል እየሳቀ፡፡ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጦ ጎተት አደረጋት። ተጎተተችለት፡፡እጆቹን በብብቶቿ አሳልፎ አቅፎ ያዛት:: ሳመችው።
“አዳም እንዳንተ ከቀበጠ ሄዋን ብትጮህም የሚደርስላት የለም ብሎ
ነው፡፡ አንተ ግን ድገመኝና አስይዝሃለው…ጎረቤቶችህን ነው የምቀሰቅስልህ፡፡”
“ሀ! ሀ ! ሀ! ጎረቤቶቼ ከእኔ ተሽለው? ርብቃ፤ ሁሉም በየጓዳው አውሬ ነው፡፡ ፊት ከሰጡት ሁሉም አንድ ነው። ፊጥ ካለበት አይወርድም፡፡”እጆቹ በአንሶላው መሀል ዋኝተው አልፈው ጭኖቿ መሃል ገቡ፡፡
“እረፍ! እየው ደሞ ጀመረህ.. ቆይ! ናቲ!”
ሳይታወቀው ተመልሶ ገባበት፡፡ ስህተት:: ዛሬ ኣልጋ ላይ መዋል የለበትም፡፡በፍጹም! ምን ማድረጉ ነው ታዲያ? ድንገት ከአልጋው ላይ ተፈናጥሮ ተነሳ፡፡ ሳይታወቀው ፕሮግራሙን አበላሽቶ ነበር። ከርብቃ ጋር አንዴ ጨዋታ ከጀመረ! ልፊያ ከቀመሰ ቀኑ እንደማይበቃው ያቀዋል።አሽትቶ፣ ልሶ፧ ገምጦ፣ አኝኮ፤ ውጦ አያጠግባትም፡፡ ድጋሚ እንደ አዲስ
ሊያሸታት ይጀምራል፡፡ ሳይወድ በግድ ራሱን ተቆጣጥሮ ፊቱን መለስና ማበጠሪያውን አንስቶ , ፀጉሩን ያበጥር - ጀመር፡፡ : እናቷን! ይቺ ልጅ ሳይታወቀኝ መዳፏ ውስጥ ልትከተኝ ነው. አሰበ።
“ለምን ተነሳህ ግን በጠዋት?" በጀርባዋ “ክተንጋለለችበት ሳትነሳ ሽቅብ እያየች ጠየቀችው::
“ቀጠሮ” በመስታወቱ ውስጥ እየተመለከታት::
“በእሁድ!”
“አዎን ርብቃ፡፡” አለ በለሆሳስ፡፡
“ምንድንነበር ያልከኝ?…አበዛኸው! ናትናኤል ሙት አበዛኸው አሁንስ የቤትህ ቁሳቁስ መሰልኩህ መሰለኝ…” አለች እንደተከፋ ሕፃን እግሮቿን አመናጭራ ከአልጋ እየወረደች፡፡ “…በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ መገናኘታችን በዛና በእሁድም ቀጠሮ ተይዝ ጀመር…አልታወቀህም እንጂ በጣም ነው የተዘባነንከው፡፡” ከእልጋው ግርጌ የተቀመጠውን ነጭ የጠዋት ልብስ ኣንስታ ሳትደርበው መሬት ለመሬት እየጎተተችው እራቁቷን የመታጠቢያ ቤቱን በር በርግዳ ገባችና ከውስጥ ጠረቀመችው፡፡ደቂቃም ሳትቆይ ጮሃ ስትሳደብ ተስማው-“አንተ ብሽቅ!... እርኩስ!…”፡፡ ብቻዋን ትጮሀለች፡፡ ፈገግ አለ የጥርስ ሳሙና የተቀባውን የሽንት ቤት መቀመጫ አስታውሶ ስትናደድ!
ስትቆጣ፤ ግስላ ስትሆን ይበልጥ ታምረዋለች፡፡ተራ ህይወታቸው ብቻ
አይደለም፥ ፍቅራቸውም ትግል ነው! ንክሻ ፤ ቡጭሪያ እሷም ብትሆን ጠዋት ጠዋት ትነጫነጭ

👍3
እንጂ ያአፈቃቀር ዘዬውን ተላምዳዋለች፡፡ጠዋት 'አውሬ ብትለውም ማታ አትፈራው ሲነጋ 'ጭራቅ ብትለውም ሲመሽ አትሸሸውም ..እላይዋ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ አልነቀል ሲላት፤እንደ ቅንቅን ፡ በሰራ አካሏ ሲፍለከለላ እንደ አልቅት
ደሟን ሲመገምግ እንደምያሌ አካሏን ሲሰረስር ! እንደምስጥ በአጥንቷ
ሲያስኬዳት ያላንተ…ትለዋለች… ሌላ ፀሐይ ስትወጣ ደግሞ ሌላ ነገ ሲተካ... አውሬ 'ሰው በላ፡፡
ቅርፅ ባለው መስታወት ፊት ቆሞ ክራባቱን ያስር ጀመር፡፡ከፊቱ፡ የተቆለለውን ቀን እንዴት እንደሚንደው እርግጠኛ አይደለም::በትክክል የት መሔድ እንዳለበት ለራሱም ግልፅ አልሆነለትም፡፡ እውነቱን ለመናገር እርሱ ሱም ቢሆን ምን ለመስማት እንደጠበቀ አያውቅም፡፡ጥያቄውን ማቅረቡ ራሱ እስቸጋሪ ነው፡፡ ቢሆንም ለጥርጣሬው አንድ መልስ እስካላገኘ ድረስ ለጥያቄው የሚያቀርበው ያልተሟላ ብቻ ሳይሆን ባዶ ቀፎ እንደሚሆን ተሰምቶታል ፡፡ የትም ይሂድ የት ብቻ ለጥርጣሬው በቂ መልስ
ማግኘት አለበት::ለዚህ ነው እሁድን
ሲሰዋ ደሟን ሊያፈስ የቆረጠው::
ጥርጣሬውን ያገነነበት የላይቤርያው ወታደራዊ አታሼ የገባበት መጥፋት
ነወ፡ በአንድ ሳምንት ሶስተኛ ጥያቄ፡፡ ሊሆን የማይችል ተራ አጋጣሚ፡፡
ስውየው ቀደም ሲልም በዚህ የስራ መደብ ላይ ለስድስት ዓመታት ሲሰራ
እንደቆየና ለኣዲስ ኣበባም እንግዳ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ ታዲያ ድንገት
መስርን ምን አመጣው? የላያብኤርያ ኤምባሲ ባለሥልጣኖችስ ያሳዩት
ለዘብተኝነት እንዴት ጤነኛ ሊሆን ይችላል?የወታደራዊ አታሺውን መጥፋት
ችላ ማለቱ ለነገሮች ተገቢ አትኩሮት አለመስጠት መስሎ ታየው::
በመጀመሪያ ደረጃ በሳምንቱ መጀመሪያ በአዲስ አበባ የተከሰተው የጊኒና የሞሮኮ ወታደራዊ አታሼዎች ግድያ የምን ውጤት ነበረ? የወታደራዊ አታሼዎቹ ሬሳ በተለያዩ ቦታዎች የተጣለበትን ቢሆንም በተመሳሳይ ሁኔታ በየመኪናዎቻቸው ውስጥ ነበር የተገኘው፡፡ ለሁለቱም ሰዎች ሞት ምክንያት የሆኑት ጥይቶች ከአንድ ሽጉጥ ለመተኮሳቸው የቀረበው ሪፖርት በዝርዝር ያስቀመጠው ጉዳይ ነው፡፡ በሬሳዎቹም ላይ የተገኙት ቁስሎችና ሌሎችም የአካባቢና የቴክኒክ, ማስረጃዎች የሚያመለክቱት በሁለቱ ሰዎች ላይ የተፈፀሙት ግድያዎች በተመሳሳይ መሳሪያ፧ በተመሳሳይ ርቀት፤ በተመሳሳይ ማዕዘን ምናልባትም በአንድ ሰው መሆኑን ነው፡፡ ያ ሰው ማነው? መልስ ሊያገኝ የቻለ ጥያቄ አይደለም:: ሳምንቱ ከመገባደዱ በፊት ደግሞ ሌላ ሁኔታ ተፈጠረ የላይቤርያው ወታደራዊ አታሼ ድንገት የገባበት ጠፋ፡፡
ታዲያ ይህን እንዴት 'ተራ አጋጣሚ ብሎ ማለፍ ይቻላል?የእርግጥ የሰዎቹ አሟሟት በየተራ ነው፡፡ ነገር ግን የናትናኤልን ጭንቅላት እረፍት የነሳው የወታደራዊ አታሼዎቹ ሞትና መሰወር ምናልባት ባለፉት ጥቂት ወራት አዲስ አበባ ከሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ኤምባሲዎች ያልተለመደ እንቅስቃሴ ጋር
ዝምድና አለው ብሎ መጠርጠሩ ብቻ አልነበረም:: ባለፉት ወራት በተለያዩ የአፍሪካ አገሮችና በአውሮፓም ያጋጠሙ ድንገተኛ አደጋዎች ያለወትሮ በርካታ ብቻ ሳይሆኑ ምክንያተ ቢስም ነበሩ፡፡
ቢሮው ውስጥ ቁጭ ብሎ ደጋግሞ ካነበባቸው የውጭ ዘገባዎች ጥቂቶቹ
ታወሱት::
ጅብራልተር:- መጋቢት ሃይታንጂየር ከምትባል የሞሮኮ የወደብ ከተማ
ተነስታ ካዲስክ ወደምትባል
የስፔይን የወደብ ከተማ በመጓዝ
ላይ የነበረች አንድ የሞተር ጀልባ የገባበት ጠፋ፡፡ የታመነ የወሬ ምንጮች በጀልባዋ ላይ ሞሮኮው የውጭ ጉዳይ
ሚኒስትር በምስጢር ተሳፍረው ነበር ይላሉ፡የሞሮኮ መንግሥት ጉዳዩን በተመለከተ ያለው የለም… (ዘ ኤዲፕንደንት)
ካሜሩን:- ሚያዝያ ሁለት የአገሪቱን ኤታማዦር ሹምና የአገር አስተዳደር ሚኒስትሩን አሳፍራ ከያውንዴ ወደ ዱዋላ ትበር የነበረች የካሜሩን የጦር ሄሊኮፕተር በአየር ላይ እንዳለች ስትቃጠል በውስጧ በካሜሩን የእሥራኤል አምሳደርን ጨምሮ ስድስት ባለሥልጣኖች አለቁ… (ካሜሩን ትሪቡን)
ያውንዴ:- ሚያዝያ ስምንት የካሜሩን የአየር ሃይል አዛዥ ከዋና ከተማዋ , ወጣ ብሎ በሚገኝ የገጠር ቤታቸው ውስጥ ራሳቸውን ገደሉ ተባለ፡፡ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት የጄነራሉ ቤት ለአራት ቀናት በልዩ ኮማንዶ ሃይል ተከቦ የቆየ ሲሆን የባለሥልጣኑ ስልክም ተቆርጦ ነበር… (ዴይሊ ቴሌግራፍ)
ኔፕልስ:- ግንቦት አስር-ከአልጀርስ ተነስተው ወደ ጣሊያን ያልተጠበቀ .
በረራ ያደረጉት የአልጄሪያ · መከላከያ ሚኒስትር ኔፕልስ አውሮፕላን ማረፊያ ባረፉ ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ህይወታ
ቸው ባልታወቀ አሸባሪ ጥይት አለፈች…(እልሞጃሂድ)
አጋጣሚ? ይህ ሁሉ ተራ አጋጣሚ?አዲስ አበባ ውስጥ የሚፈፀመው ግድያና መሰወርስ? ይህም አጋጣሚ? ከአራት ወር በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ ይህ ሁሉ አጋጣሚ?…
በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ነበር ኣለቃው ወደ ቢሮአቸው ያስጠሩት፡፡
“ደውለው ፈልገውህ ነበር።” ብላው ነበር ፀሃፊው ያን ዕለት ጠዋት አርፍዶ ቢሮው ሲገባ፡፡ ማን? አላላትም፡፡ እሱ በሚሰራበት ሁለተኛ ፎቅ ላይ
'አንቱ' ፤ እርስዎ ! 'እርሳቸው እየተባለ የሚነገርላቸው የሱ ኣለቃ ብቻ ናቸው፡፡የተረፈው በዕድሜም በሥልጣንም ተቀራራቢ ነው 'አንተ አንዳንዴም 'አንቺ ነው የሚባባለው፡
“ይሄ ጭን ይገጠም ሳምሪ።” አላት ናትናኤል ወደ ቢሮው በር ሲያመራ ፈርከክ ያደረገቻቸውን ጭኖቿን እየተመሰከተ፥
• “ተወው ባክህ እሱ የከፈተውን ሳይዘጋው አያድርም ተብሏል።” አለች ሳምራዊት ፈረግ ብላ፡፡
“አዲስ የመጣ ሪፖርት አለ?” አላት እየሳቀ የቢሮውን በር ከፍቶ
ከመግባ ፣በፊት፡፡ሁለት፡” አለችው የታች ከንፈሯን በምላሷ አርጥባ፡፡ ልማዷ ነው።
ሳምራዊት ቆንጅዬ ልጅ ነች፡፡ የምትፈልገውንና የምትመኘውን
ትዳር እንዴት ሳታገኝ እንደዘገየች ሁሌ ይገርመዋል፡፡ ምናልባት በጣም ስለምትጓጓና ስሜቷንም ስለማትደብቅ ይሆናል፡፡ ናትናኤል ገና ከጠዋቱ ነው
የሸሻት፡፡ ሌላ ወሬ የላትማ! ባል ጋብቻ ትዳር፡፡ሸሽት። ጎመን በጤና።
ቢሮው ገብቶ ከወንበሩ ላይ ከመቀመጡ በፊት ጠረጴዛው ላይ የተቀመጡትን ሁለት ; ወረቀቶች አንስቶ ዋጣቸው፡፡ የጠበቀው ነበር አንደኛው ወረቀት ስለ ልጄርያ ወታደራዊ አታሼ፤ሁለተኛው ደግሞ ስለሞዛቢክ ወታደራዊ አታሼ የቀረበ ሪፖርት፡፡ ሁሉቱም ሰዎች ወደ
አገራቸው ሄደዋል - የሰሞኑ ተደጋጋሚ ዜና፡፡
ወረቀቶቹን በነበሩቀት አስቀምጦ ለአፍታ ዓይኖቹን ቡዝዝ አድርጎ ቆመ። 'ምን ማለት ነው? ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ከሰላሳ የሚበልጡ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ኤምባሲዎች የሚሰሩ ወታደራዊ እታሼዎች እየተጠሩ ወደየ አገሮቻቸው ሄደዋል፡፡ ጥቂቶቹ ሲመለሱ የተቀሩት ሌሎች ተተክተዋል። ይሁን እንጂ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ለነዚህ ሁሉ ወታደራዊ አታሼዎች መጠራት ከሚወክሏቸው መንግሥታትም ሆነ ከሌላ አካል የተሰጠ ምክንያታዊ ፍንጭ የለም፡፡
💫ይቀጥላል💫

#ክፍል_አርባ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
በዚያን ታሪካዊ ቀን አንዱአለም ብቻ ሳይሆን ያንን የመሰለ ክፉ ንግግር ተናግሮ አእምሮዋን ያቆሰለው ዶክተር ባይከዳኝም የፍርድ ውሳኔው በሚሰጥበት ዕለት እንዲገኝ ስለፈለገች ... አዜብ ልትጠይቃት
ወህኒ ቤት ሄዳ በተገናኙበት እለት.....
“አዜቢና እግዚአብሔር ከሞት ካተረፈኝና፤
ለዚህ ካበቃኝ፤ ዶክተር ባይከዳኝም በዚያን እለት ፍ/ቤት ተገኝቶ ሸርሙጣ ያለመሆኔን ቢያውቀው ደስ ይለኝ ነበር፡፡ አለቻት፡፡ ይህንን ስትናገር አዜብ ትኩር
ብላ ስታያት ቆየችና ፈገግ አለች :: የአዜብ የፈገግታ ምንጭ ለጊዜው ባይታወቃትም እሷን ተከትላ እሷም ፈገግ አለች፡፡
እንዲገኝ አደርገዋለሁ” አለቻት፡፡ በእርግጠኛነት፡፡ አዜብ እንደዚያ ፈገግ ያለችውና እንደሚገኝም እርግጠኛ የሆነችው ልትሰራው ያሰበችው ተንኮል ፍጻሜው መድረሱን በማወቋ ነበር፡፡ ሁል ጊዜም የሚከነክናት ነገር በዶክተርና በሻምበል መካከል የነበረው ልዩነት ነበር።
ትህትና ልጃገረድ ያለመሆንዋን ሲያውቅ ፤ ሻምበል ፍቅሩን ያቋረጠበት ሁኔታና፤ የዶክተር ሁኔታ፤ ፍጹም የተለያየ ነበር፡፡ሻምበል አባብሎና አጽናንቶ፤ነው የሸኛት፡፡ ዶክተር ግን አዋርዶ፡ ሞራሏን ነክቶና፡ የጭካኔ ንግግር ተናግሮ ነው ያባረራት፡፡ ለዚህ ድርጊቱ ደግሞ መቀጣት አለበት
ብላ ታስብ ስለነበረ ፤ በዚያን እሷና ብሩክ ብቻ በሚያውቁት እለት ተገኝቶ እንዲቀጣ ፈለገች፡፡
በማግስቱ የካቲት አሥራ ሁለት ሆስፒታል የደረሰችው ከቀኑ አምስት ሰዓት ሲሆን ነበር፡፡ ምሽቱን ስትቀምም ያደረችውን መልእክት ይዛ፡፡ እዚያ እንደደረሰች፤ የዶክተር ባይከዳኝን የምርመራ ክፍል ጠይቃ የሚያሳያት ሰው አገኘችና ወደዚያው አመራች፡፡
ዶክተር የመጨረሻውን በሽተኛ እየመረመረ ነበር፡፡ ቀስ ብላ በሩን ከፍታ ወደ ውስጥ ተመለከተች፡፡ አጠገቡ የነበረችው ነርስ ፈጠን ብላ መጣችና.....
“ምን ፈለግሽ?” አለቻት አንገቷን ወጣ አድርጋ፡፡
“ለግል ጉዳይ ዶክተር ባይከዳኝ ዘንድ ነው የመጣሁት፡፡” ስትላት ሲስተሯ ከላይ እስከታች ተመለከተቻትና “በሽተኛ እየመረመረ ስለሆነ ጠብቂ” ብላ በሩን መልሳ ዘጋችውና ሰው የሚፈልገው መሆኑን ነገረችው ::
ዶክተር ምርመራውን ከጨረሰ በኋላ፤ እንድታስገባት ለሲስተሯ ነገራትና፤ በሩን ከፍታ እንድትገባ በምልክት ጠራቻት ከዚያም አዜብ በሳቅ እየተፍለቀለቀች ፤ እራሷን አስተዋወቀችው፡፡ ዶክተርም
እንድትቀመጥ ጋበዛት፡፡ ሁኔታዋ ግር አሰኝቶታል።
“ለትንሽ ደቂቃ ብቻህን ላነጋግርህ ፈልጌ ነበር ዶክተር” አለችው፡፡
በዚህ ጊዜ ሲስተሯ የዶክተርን የስንብት ቃል ሳትጠብቅ ሹልክ ብላ ወጣች፡፡
“የትህትና ጓደኛ ነኝ” አለችው፡፡ ለምን እንደሆነ ባያውቀውም የትህትናን ስም ሲሰማ ልቡ ዘለለች፡፡ ከዚያም አንዲት የተጣጠፈችና የተቀደደች ፖስታ ከኪሷ አውጥታ፤ አቀበለችው፡፡ በፖስታው ላይ
ያለውን አድራሻ ተመለከተ፡፡ ለዶክተር ባይከዳኝ ሙሉሰው የካቲት አስራ
ሁለት ሆስፒታል ይላል ፡፡ዶክተር ነገሩ ግራ አጋብቶት፤ አይን አይኗን እያየ፤ ደብዳቤውን ተቀበላትና በልቡ የምን መልእክት ይሆን የይቅርታ ወይንስ የስድብ? ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡ ከወዲሁ መገመት አልቻለም፡፡
መልሱን የሚያገኘው ከደብዳቤው ብቻ ነው፡፡ በጉጉት ተውጦ ደብዳቤውን
ገልጦ ማንበቡን ቀጠለ፡፡ እያንዳንዷ ቃላት ተመርጣ የተጻፈች ስለነበረ፡፡ ወደ ውስጥ በዘለቀ ቁጥር የልብ ምቱ እየጨመረ ሄደ፡፡ አዜብ ራሷ ያዘጋጀችው ቀኑ ያልተጻፈበት ደብዳቤ ነው፡፡ ደብዳቤው ልክ ትህትና ለሻምበል ብሩክ የጻፈችለትን አይነት ይዘት ነበረው፡፡ እጅግ የምታፈቅረው የምትወደውና፤ የምታከብረው፤ ባለውለታዋ መሆኑን ይገልጻል ፡፡በፍቅር ስላሳለፉት ጊዜያት ጣፋጭነትም ያወራል፡፡ የመለያየታቸው ምክንያት በመቃቃር ወይንም ደግሞ በመጠላላት ሳይሆን፤ በድንገት በተፈጠረ
ችግር ምክንያት መሆኑን ያስረዳል፡፡ የጸባቸው መንሰኤ በሆነውና የምትወደውን ሰው እንድታጣ ክብረ ንጽህናዋን በደፈረው ወንጀለኛ ላይ
እርምጃ ወስዳ ለመሞት መወሰኗን ካወራ በኋላ፤ እስከ ወዲያኛው አፍቃሪ እህትህ ትህትና ድንበሩ በሚል ይደመድማል፡፡ ምንድነው
ተአምሩ? ዶክተር ግራ ተጋብቶና፤ ፊቱ ላይ ቸፍ ያለውን ላቡን እየጠራረገ፤ በአዜብ ላይ አይኖቹን አፈጠጠ...
“አይዞህ ህይወቷ ተርፏል” ስትል አረጋጋችው፡፡ ዶክተር ከድንጋጤ ሳይመለስ ቡዝዝ ባሉት አይኖቹ ሲመለከታት ከቆየ በኋላ ስለሆነው ነገር እንደ አዲስ ጠየቃት፡፡ ከደብዳቤው የተረፈውን በቃሏ ተረከችለት፡፡ ትህትና ደብዳቤውን አሽጋ በጐረቤት በኩል የላከችላት መሆኑን፡ ደብዳቤው ተቀዶ ከተነበበና፧ እጅግ ከዘገየ በኋላ፤ እንደቀላል ነገር እንዲደርሳት መደረጉን፡አሁን ትህትና ለፍርድ ቀርባ ፍርዷን
እየተጠባበቀች መሆኑንና፤ ድርጊቱ የተፈጸመበትንም ጊዜ በግማሽ
አሳጥራ በቁጭት ስትነግረው ፤ አመናት፡፡አሁን ለዶክተር ቁም ነገሩ የጊዜው ጉዳይ አይደለም፡፡ ለሱ ዋናው ቁም ነገር እውነቱን ማወቁ ብቻ ነው፡፡
ዶክተር ለመጨረሻ ጊዜ ከትህትና ጋር የተለዋወጡት መራራ ቃላት ታወሱት፡፡
ካንተ በኋላ የተዋወቅሁት ፍቅረኛዬ በክብር የወሰደው ነው” የሚለው አጥንት የሚሰብረው ንግግሯ ታሰበው፡፡አሁን ደግሞ አዜብ የምትነግረውና የላከችለት ደብዳቤ የሚያወራው ታሪክ ከዚህ የተለየ
ነው፡፡ የትኛው ይሆን እውነቱ? በእርግጥም ትህትና በግድ የተፈጸመባት
ወንጀል ነበር ወይንስ የታሰረችበት ሌላ ምክንያት ይኖር ይሆን?
በአጠቃላይ እውነቱን ለማወቅ፣ የክሱን መንስኤ፣ የወንጀሉን አፈጻጸምና ድርጊት ለማረጋገጥና፤ ትህትና ለፍርድ ቀርባ ውሣኔ በሚሰጥበት እለት እዚያ አጠገቧ ተገኝቶ እውነታውን ለማየት፤ ልቡ ተንጠለጠለች፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ምንም እንኳን ከተለያዩ አንድ አመት ቢሞላቸውም ሙሉ ለሙሉ ከልቡ አልጠፋችም ነበረና፤ ሄዶ ዐይኖቿን በማየት፤ የአንድ ዓመት ናፍቆቱን ለመወጣት ቸኮለ፡፡
“አልቀርም እመጣለሁ” በማለት ፍርዱ የሚሰጥበትን ቀን በማስታወሻ ደብተሩ ላይ መዝግቦ ከያዘው በኋላ ስለእናቷ ጤንነት ጠየቃት። በዘውዲቱ ሆስፒታል በተመላላሽነት በመታከምና በተሻለ
የጤንነት ደረጃ ላይ የምትገኘ መሆኗን ነገረችው፡፡አዜብ ተሰናብታው
ከወጣች በሁዋላ፤ ዶክተር በሃሰብ ፈረሱ ላይ ተጭኖ ሽምጥ ይጋልብ ጀመር፡፡ ምንድነው ይሄ ተአምር? እውነት ትህትና ድንግልናዋን ያጣችው ተደፍራ ነበር ማለት ነው? አላታለለችኝም ነበር ማለት ነው? ይሄ ሆኖ ከተገኘ በቀላሉ ሊወጣው ከማይችለው የህሊና ጸጸት ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ሲያስበው፤ ዘገነነው፡፡ ነገሩ እውነት እንዳይሆን ተመኘ፡፡ ያሳለፉት ጊዜ ትዝታው እንደ አዲስ ተቀሰቀሰበት፡፡ የዚያ
የደብረዘይቱ የማይረሳ ትዝታ መጣበት፡፡ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ እየተላፉ
እሱ በፈለገው መንገድ አንድም ቀን ተቃውሞ ሳታሰማ፤ እሱን ደስ እንዲለው ታደርግ የነበረው ጥረት፤ ጠጥታ የማታውቀውን መጠጥ እንኳ ለሱ ስትል ታደርገው እንደነበረ፡ ድንግልናዋንም በፍቅር አሳልፋ ስትሰጠው የነበረው ሁኔታዋ : ድቅን አለበት፡፡ ከራሱ ደካማነት እንጂ ከእሷ ምንም የጐደለበት ነገር አልነበረም፡፡ ያቺ ለስላሳ :ያቺ ቅልስልስ፡
ያች ስትስቅ ስትናገር፤ አፍ የምታስከፍት ትንሽ ልጅ፡ ለሱ ሁሉንም ነገር ሆናለት ነበር፡፡ እሱ ግን እንደዚያ አልሆነላትም፡፡ ቅስሟን ሰብሮ፤ ሞራሏን ነክቶ ነበር፤ እንደውሻ ከቤቱ ያባረራት፡፡ ያውም እንደዚያ የምትንሰፈሰፍላት እናቷን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደምትሞት የቁም መርዶ አርድቶ ነው ያባረራት፡፡ እሷ ግን ይሄውና ለሱ ስትል ህይወቷን
እስከማጥፋት የሚደርስ እርምጃ ወስዳ፤ ፍቅሯን እየገለጸችለት ነው ነገሩ እውነት

ሆኖ ከተገኘ፤ እጅግ ከባድ ፀፀት ብቻም ሳይሆን ለደረሰባት አሰቃቂ አደጋ ጭምር ተጠያቂው እሱ መሆኑንን ጭምር አእምሮው ሹክ አለው....
በዚያን የፍርድ ውሳኔው በሚሰማበት ዕለት ሻምበል ብሩክ አዜብና አንዱአለም ፀአዳ ለብሰው አምረውና ደምቀው ውሣኔውን ሊሰሙ ወደ ፍርድ ቤት ሄዱ፡፡ እናቷ ወይዘሮ አመልማል በአካል አብራቸው መሄዱ ቢያቅታትም ልቧ ተከትሏቸዋል፡፡ በተለይ ሻምበል ብሩክ ሙሉ ጥቁር ሱፍ፣ ነጭ ሸሚዝና ፍንጥቅጥቅ ውሃ ሰማያዊ ክራቫት አስሮ
ሙሽራ መስሏል፡፡ ምን አስቦ ይሆን?.....
የወንጀል ችሎት... የፍትሐብሔር ችሎት... የሥራ ክርክር ልዩ ልዩ ችሎቶች በሚመረመሩበት በህግ የሚፈተሽበት
በአንቀጽ በሚተነተንበት ጠበቆች ወገባቸውን ጠበቅ አድርገው በሚሟገቱበት፡ ዳኞች በጥቁር ካባቸውን
ተጐናጽፈው፤ በግርማ ሞገስ ተሰይመው ፍርድ ወደ ሚሰጡበት አምባ.....ግማሹ ሲስቅ፣ ግማሹ ወደሚያለቅስበት፡
የፍትህ አደባባይ፤የተፈረደለት ሲፈነድቅ፤ የተፈረደበት አንገቱን ወደሚያቀረቅርበት፤ ወደ ፍርድ ቤት ሄዱ፡፡
ሶስቱ ዳኞች ካባቸውን ደርበው ከፍ ብሎ በተዘጋጀው መድረክ ላይ በግርማ ሞገስ ተሰይመዋል፡፡
በችሎቱ ውስጥ ታዳሚው ግጥም ብሎ ሞልቷል፡፡ ሞልቶ ተርፎም ከደጅ ድረስ ቆሟል። አንዳንዱ ልማድ ያለው እንጂ ጉዳይ ያለው ሆኖ አይደለም፡፡ እዚያ ፍርድ ቤት ሆነው የፍርድ ቤቱን ስርዓትና ደንብ
መመልከት፣ የህግ አንቀጾችን ማጥናት፣ የጠበቆችን የክርክር ስልት መከታተል፡ አንደሱስ የሆነባቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ከእነዚህ መካከል አንድ ታዳሚ ግን የፍርድ ቤቱን ደጃፍ የረገጠው ገና ዛሬ ነው፡፡
ሁለመናው አቆብቁቦ፤ በሰው መግደል ሙከራ ወንጀል ተከሳ የታሰረች ወጣት
ወደ ፍርድ ቤቱ አዳራሽ የምትገባበትን ጊዜ በናፍቆት እየተጠበባበቀ ይገኛል፡፡ ደጅ ደጁን አስር ጊዜ ያያል ።ከዚያም ያ
በናፍቆት ሲጠባበቀው የቆየው ስም ተጠራ :፡ልቡ ድው፧ ድው፤ አለችበት፡፡ አይኖቹ ወደ በሩ ተወረወሩ፡፡ ከዚያም ያቺ ወጣት በአጃቢ ፖሊስ አማካኝነት ታጅባ ወደ ፍርድ ቤቱ አዳራሽ ስትዘልቅ ተመለከተ ::
አይኖቹን ማመን አቃተው፡፡ ልክ ነው፡፡ ራሷ ናት፡፡ በግራ ጆሮዋ ላይ ጠባሳ
ተጋድሞባታል፡፡ መልኳም ትንሽ ተጐሳቁሏል፡፡ አንጀቱ ተርገፈገፈ፡፡
እንባው አመለጠው፡፡ እሱ እንደዚያ
በጉጉት ተውጦ ሁኔታዎችን ሲከታተል፤ አዜብ ደግሞ ተደብቃ የሱን ሁኔታ ትከታተል ነበር :: ተንኮሏ ስለሰራላት በጣም ተደስታ ነበር፡፡ የት አባቱ! ለሰራው
ግፍ አያንሰውም እያለች ነበር፡፡ በልቧ፡፡ በኋላ ላይ ግን ይህንን ሃሳቧን የሚፈታተን ድርጊት ስትመለከት ልቧ አዘነ፡፡ እንባ ከፊቱ ኮለል እያለ ሲወርድ ተመልክታ፤ የሆነ ስሜት፤ የመጸጸት ስሜት፤ ተሰማት :: ከዚያም ተከሳሿ በተከሳሽ መቆሚያ ሳጥን ውስጥ ሆና የፍርድ
ውሳኔው መሰማት ጀመረ፡፡
ረዘም ቀላ ያሉትና ፀጉራቸውን ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት የመሐል ዳኛ የዳጎሰ አረንጓዴ ፋይል አወጡ፡፡ በዛሬው ችሎት ላይ እንደሻው በቀለ ተገኝቷል በወላጆቹ ታጅቦ ከወዲያ ማዶ ሆኖ ከወዲህ ማዶ
የተቀመጡት እነ ሻምበል ብሩክን በቀሉት ዐይኖቹ ይገረምማቸዋል።
ከዚያም ዳኛው መነጽራቸውን አውልቀው ወለወሉና ፋይሉን ገለጡ፡፡
ከሳሽ፣ ዐቃቤ ህግ
ተከሳሽ፣ ወይዘሪት ትህትና ድንበሩ
የክሱ ምክንያት ሰው የመግደል ሙከራ ወንጀል
ተከሳሽ ትህትና ድንበሩ፤ የጦር መሣሪያ በመያዝ፤ ወጣት እንደሻው በቀለ ከሚሰራበት የግል የንግድ ሱቅ ድረስ በመሄድ፤ በአራት ጥይቶች ተኩሳ በማቁሰል፤ የመግደል ሙከራ በማድረጓ የተመሰረተ ክስ ሲሆን፤ ለክሱ መልስና የመልስ መልስ ተሰጥቶበታል፡፡ ከሳሽ የሆስፒታል ማስረጃ፣ የፓሊስ ሪፓርትና፤ ወንጀሉ የተፈጸመበትን የጦር መሣሪያ፧
በኤግዚቢትነት ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡ ምስክሮች ቀርበው ተሰምተዋል።
ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ፤ ተከሳሽ ጥፋተኛ ሆና በማግኘቷ
የጥፋተኛነት ውሣኔ ሰጥቷል፡፡
ተከሳሽ በተመሰረተባት ክስ መሠረት የቅጣት ውሣኔ ለመስጠት እንዲያስችል፤ ዐቃቤ ህግና የተከሳሽ ጠበቃ፤ የቅጣት ማቅለያ፤ ወይንም የቅጣት ማክበጃ፤ ሃሣባቸውን እንዲያቀርቡ ተደርጐ፤ በሁሉቱም ወገን የቀረበው የመፋረጃ ሃሣብ በፍርድ ቤቱ ተመዝግቧል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ የቀረበውን የግራ ቀኙን የመፋረጃ ሃሣብ በመመርመርና፤ የወንጀለኛ መቅጫ ህጐችን መሠረት በማድረግ፤ ከዚህ የሚከተለውን የፍርድ ውሣኔ ሰጥቷል፡፡
#ፍርድ
ተከሳሽ በፈጸመችው ወንጀል ጥፋተኛ ሆና ብትገኝም፤ ወንጀሉን ለመፈጸም የተነሳሳችበትን የሞራል ተቃራኒ ድርጊት፤ የተከሳሽን የቀድሞ ስነምግባር ሁኔታ፤ የቤተሰብ ሃላፊነት ደረጃን፤ የተከሳሿን የዕድሜ ሁኔታ፤ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ እንደዚሁም፧ ተከሳሽ ከዚህ በፊት በማንኛውም የወንጀል ድርጊት ውስጥ ተሳትፋ ያልተቀጣችና፤ ለወደፊቱ
ከዚህ ጥፋት ተምራ መልካም ዜጋ ልትሆን የምትችል ታዳጊ ወጣት መሆኗን በማገናዘብ፤ እጇ ከተያዘበት ዕለት ጀምሮ ለሶስት ዓመት በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ቆይታ እንድትታረም ወስነን፤ ፋይሉን ዘግተን፤ ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል፡፡
ፊርማ
የመሀል ዳኛ
ጸጥ አርጋቸው ተፈራ
በውሣኔው ቅር የተሰኘ ወገን ይግባኝ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ውሣኔውን ለመስማት ሁሉም ፀጥ ብሏል፡፡ እያንዳንዷ እንቅስቃሴና
ኮሽታዋ ሁሉ፤ ጎልታ ትሰማ ነበር፡፡ ልብ ድው፤ ድው! ሲል ይደመጣል፡፡ ትንፋሽ በአጭር በአጭሩ....ይሮጣል፡፡ ዶክተር ባይከዳኝም የፍርዱ ውሳኔ እስከሚነበብ ድረስ የልቡ ምት ፍጥነቱን ጨምሮ ነበር፡፡
በዚያች ሰዓት ለትህትና እና ከጉኗ ለተሰለፉት ወገኖቿ የዓለም እንቅስቃሴ የቆመ መስሏቸው ነበር። እንደ እውነቱ ከሆነ ውሣኔው ከገመቱት በጣም ያነሰ ነበር የፍርድ ውሳኔዋን ሰምታ ከተከሳሽ
መቆሚያ ሣጥን እንደወረደች፣ ፓሊሱ ከፊት አስቀድሟት ወጣ፡፡ አዜብ
ሻምበል ብሩክና ወንድሟ ፓሊሱን ተከትለው አጀቧት፡፡ ከዚያም ሄደው
አቀፏትና......
“አይዞሽ አንዱን ጨርስሻል፡፡ የቀረችሽ ሁለት ዓመት ብቻ ናት፡፡
ሁለት ዓመት ማለት ሁለት ቀን ነች” በማለት ሞራል ሰጧት፡፡
እዚያ የተሰበሰበው ህዝብ የእነሱን ሁኔታ እያየ... አይዞሽ? አይዞሽ! አይዞሽ!” በማለት የማያቋርጥ የማበረታቻ ድጋፍ እየሰጣት ነበር፡፡ ተደጋጋሚ በደል የተፈጸመባት ወጣት በመሆኗ፤ አብዛኞቹ እንደ ወንጀለኛ በክፉ አይናቸው ሊያይዋት አልፈለጉም፡፡ዶክተር ባይከዳኝም
ከፍርድ ውሳኔው ዝርዝር በተጨማሪ አጠገቡ ተቀምጦ ከነበረው ታዳሚ
አንደበት፧ ልክ አዜብ በነገረችው መሰረት፤ የወንጀሉን ታሪክ ሰምቷል፡፡ በጉልበቱ ድንግልናዋን በወሰደው ሰው ላይ አደጋ አድርሳ በራሷም ላይ ጉዳት ማድረሷን፤ እንደሻውን ጠቁሞ በማሳየት ጭምር
አረጋግጦለታል፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ ይህንን ሁሉ ካረጋገጠ በኋላ፤ እንደፈራው አልቀረም፡፡ ከባድ ጸጸት አደረበት፡፡ በዚያን ዕለት መጥፎ ስድብ በሰደባት ዕለት የነበረችው ትህትና ታወሰችውና ራሱን ወቀሰ፡፡ ትህትና በአጃቢ ፖሊሱ ታጅባ ከችሎቱ እንደወጣች፤ ፖሊሱ ከፊትዋ ቀደመና፤ ፈጠን ፈጠን፤ እያለ አስከተላት፡፡ ከሁዋላ፤ ከሁዋላው፤ ተከተለችው :: ከዚያም
እዚያ በጣም ትልቅና በጥላው ምክንያት ቀዝቃዛ አየር ከሚነፍስበት የግራር ዛፍ አጠገብ ሲደርስ ቆም አለ ፡፡ ሻምበልም ወደ አጃቢ ፖሊሱ ጠጋ አለና ጀርባውን ቸብ፤ ቸብ፤ በማድረግ ፈገግ አለ፡፡ ፖሊሱም ሰፊ ፈገግታውን ለገሰው፡፡ መልካም... ይሁንልህ ማለቱ ይሆን? :: ከዚያም ሻምበል ብሩክ ለዚህች ለዛሬዋ አስገራሚ እለት የተዘጋጀበትን፡ አስቀድሞ
ፍቃድ ያገኘበትን፡ እቅዱን ሊያጠናቅቅ፤ ወደ ትህትና ተጠጋ፡፡ ፖሊሱም በአክብሮት ፈንጠር ብሎ ቆመና ቦታውን ለሻምበል

ለቀቀ :: ፖሊሱ የሕግ ነገር ሆኖበት ነው እንጂ፤ የዛሬን እንኳን ሊለቅለት በወደደ ነበር፡፡ ትህትና የተሰበሰበውን ታማትራለች፡፡ምንም የመደናገጥና የመረበሽ ስሜት አይታይባትም፡፡ ይልቁንም በፈገግታ ተሞልታ፤ የሻምበል ብሩክን ሁኔታ እየተከታተለች ፤ ነበር፡፡ ምን ሊያደርግ ነው? በሚል ስሜት ሰው ሁሉ ሻምበል ብሩክን ያስተውለዋል፡፡ ምን ለማድረግ
እንደፈለገ እሷም ማወቅ አልቻለችም ነበር፡፡.....