ለሁ አላት ። ፈገግ ብላ በእሺታ ራሷን ነቀነቀች ።
እስክንድር በልቡ እየቦረቀ ትዕግሥትን መኝታ ክፍሏ ድረስ ሸኛት ። ምን ዐይነት ደብዳቤ እንደምትጽፍ ለማወቅ ልቡ ክፉኛ ጓጓ ። “ በፖስታ ታሽገው ይሆን ? ” አለ አቤል ጋ ከማድረሱ በፊት ለማንበብ አስቦ ።
ትዕግሥትን ሸኝቶ ሲመለስ ከሩቅ ስሙን የምትጠራ ሴት ሰማ ። ከመኝታ ክፍሏ መስኮት በኩል አይታው የጠራችው ቤተልሔም ነበረች ። ዘወር ብሎ ሽቅብ አያትና ለሰላምታ የጠራችው መስሎት እጁን አውለበለበ “ ቆየኝ ፡ እፈልግሃለሁ ! ” አለችው ።
ለምን ይሆን የፈለገችኝ ? ” ብሎ አሰበ ። መከረኛ ልቡ ያለ ምክንያት ሲነጥር ትሰማው ።
ፎቁን ወርዳ ድክ ድክ እያለች አጠገቡ እስክትደርስ ቆሞ ጠበቃት ።
“ ኡ ... ፍ ! ያደክማል ” አለች አጠገቡ ስትደርስ ተራራ የወጣች ያህል ቶሎ ቶሎ እየተነፈሰች በነጠላ ጫማ ስለ ነበረች፡ከእጥረቷ ጋር በማይጣጥመው ውፍረቷ ይብሱን ቁልቁል ተቀብራበት አጭር በርሜል መሰለችው ። በገጽታዋ ላይ መጠነኛ ለውጥ አስተዋል ። የተከፋች ትመስላለች የምትለውን ለመስማት ቸኮለ
አንተ ሲፈልጉህ አትገኝም" አለችው "
“ ይኸው አለው” አለ እስንድር ፍርጥም ብሎ ።
" አትቁልድ እባክህ !
“ ቀለድኩ እንዴ ? ” አለ እስክንድር በልቡ አኳኋኗ ግራ ገብቶት አኳኋኗ ሁሉ ያኮረፈች ሚስት ዐይነት ሆነበት
በዝምታ ትንሽ ቆየች ፡ ስትንደረደር እንደ መጣችው ያሰበችን በአንዴ መዘርገፍ አልቻለችም ። እጀማመሩ ቸገራት
“ እስቲ ሻይ ጋብዘኝ ?
“ ፍራንክ አለኝ ብለሽ ነው ? ! እያለ ኪሱን ዳበሰ ።
ተአምር ይፈጥር ይመስል ፥ አታዋርደኝ ኪሴ ! ” አለ ። ግን ኪሱ ባዶ መሆኑን አላጣውም።
ከሌለህ፣ ግድ የለም ፤ እኔ ልጋብዝህ
አለችው ! ጭንቀቱ ታውቋት ።
"አዎ ይሻላል ” አላት ፡ መደናገጡን ለመሸሸግ እየሞከረ « የለኝም ማለት ለምን እንደሚያሳፍረው ወይም እንደሚያስደነግጠው ለራሱም ይገርመዋል።
ግቢ ውስጥ ወደ ሚገኘው ሻይ ቤት ሄደው ትንሸ ከቆዩ በኋላ ፡ ቤትልሔም ሻይዋን ፉት እያለች ፥ ጨዋታዋን ጀመረች
“ባገኘሁህ ቁጥር እነግርሃለሁ እያልኩ” አለችና አቋረጠች ።
"ምን አላት?"
"ጓደኛዬ እንድትሆን"
የሐፍረት ሣቅ ሣቀች “ ስሜቱን ለማጥናት ዐይኖቿን ፊተ ላይ ተከለች።
ከእስክንድር አፍ ጥያቄም ሆነ መልስ አልወጣም የሚያባብሉ ዐይኖቿን ማየት አፍሮ እንገቱን ሰበረ ። የተቆጣ እንዳይመስል ግድ ፈገግ አለ ። ምን ማለት እንደ ፈለገች በውል ሊገባው አልቻለም ።
“ አየህ እስክንድር እኔ እዚህ ግቢ ውስጥ ስሜ ጠፍቷል ። ኃጢያቴ አልገባኝም ። አንተ አስተዋይ ሰው ነህ በግቢው ውስጥም ጥሩ ስም አለህ ” አለችው በአንዴ ልውጥ ብላ ፥ ጭራሽ ድምጿ ወደ ለቅሶ እያደላ ።
“እና እስክንድር የተበላሸ ስም አዳሽ ነው እንዴ ? ? አለ በልቡ ። ግልጽነቷ ግን አስገረመው ። ምርጫ ሲኖረኝ ነው ራሳችንን የምንደብቅው ። ምርጫ ማጣት ሰውን ምን ያህል ግልጽ እንደሚያደርገው ትረዳ።
“አባባልሽ በደንብ አልገባኝም ”” ኣላት አፍ አፉን ስታየው የሚናገረው ጠፍቶት
መቼም እኔ እዚህ ግቢ ውስጥ በለማ እንደምታማ ታውቃለህ ” ?
“ አሃ ! አዎ ፡ ዐልፎ ዐልፎ አንዳንድ ወሬ እሰማለሁ።አላት ፡ አጠያየቋ የሚያውቀውን ለመካድ አስቸግሮት
እንዴት እንደምትቀጥል ተቸግረች ።
“ ለመሆኑ ፥ ከአስተማሪ ጋር መውጣት ወንጀል ነው እንዴ ? "ስትል እሱኑ ጠየቀችው
“ እንደዚያ ሳይሆን፥ ግንኙነቱ ከጥቅም ጋር ስለተያያዝ ነው ። እ! እንደምታውቂው ፡ እዚህ ግቢ ውስጥ የማርክ ነገር የተማሪዉ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው ። እንኳንስ በሌላ ግንኙነት በጭንቅላትም መብለጥ አይወድም ። እና የጥላቻው
ምንጭ ይኸ ይመስለኛል ” ሲል ፊቷ ክፉኛ ተለዋወጠ።
“ እምልሽ ፥ እኔ ተማሪዉ ሲያወራ የሰማሁትን ነው ? አለ ፡ እንዳያስቀይማት ፈርቶ ።
“ ምቀኝነት ነው ! ” አለች ፥ ሳግ እየተናነቃት ።
“እኔ ማንም ተማሪ በዚህ መንገድ ይተረጉምብኛል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ለማንኛውም አሁን ከለማ ጋር ግኑኝነታችን ተቋርጧል።.......
💥ይቀጥላል💥

#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ትህትና ዛሬ ትንሽ ደሟ መለስ ብሎ ስትመለከት እናቷ ደስ አላት፡፡ ሰሞኑን ጥውልግልግ ብላ አስደንግጣት ነበር፡፡ ዛሬ ግን ሰውነቷን ተጣጥባ፣ ፊቷን ተቀባብታ፣ ምርጥ ለብሳ፣ ትህትናን መስላ ስታያት፤“ተመስገን” አለች በልቧ።
ያንን ምሽት እንደ አስታማሚ ልጅ ሳይሆን፤ እንደ ጥሩ አፍቃሪ ባል ፡ እቅፍ አድርጋት አደረች። ናፍቆቷን ሙሉውን ሌሊት አቅፋት በመተኛት ተወጣች፡፡
አሁን ሁሉንም ጣጣዋን ጨርሳለች፡፡ ዕቅዷን ልትፈጽም ሰዓቱ እየደረሰ ነው፡፡ በሌሊት ተነስታ ልብሷን ለባብሳ ጨረሰችና፣ ከፔርሙስ ትንሽ አጥሚት ቀድታ ካጠጣቻት በኋላ፤ “ወደ ቤት ልሂድ እማ!” ብላ ለመሄደ ተነሳች፡፡
ደግማ፤ ደጋግማ፤ ጉንጮቿን አገላብጣ ሳመቻትና፤ ወጣች፡፡ስትወጣ መንፈሷ ሁሉ ጠንካራ ነበር፡፡ ፍርሀት ጓዙን ጠቅልሎ ነው የሄደው፡፡ ቤት ደርሳ ያንን ትናንትና በፍቅር ስታሽሞነሙነው የዋለችውን የአባቷን ቅርስ ሸፋፍና፤ በቦርሳዋ ይዛ፤ ወደ መርካቶ ገሰገሰች፡፡
እዚያ እፍልሚያው ቦታ ስትደርስ ከታክሲ ወረደችና ራቅ ብላ ዓይኖቿን በሱቁ ላይ ተክላ ትጠባበቅ ጀመር፡፡
ልቧ ድው! ድው፤ ይላል፡፡ እልህና ሲቃ ይተናነቋታል፡፡ እንዷ ደቂቃ አቤት ርዝመቷ! አውሬው ወጥመዱ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ በንቃት መጠባበቋን ቀጠለች፡፡
አንዳንድ ሱቆች መከፈት ጀምረዋል፡፡ እምብዛም ሰው አይታይም፡፡ መርካቶ ትንሽ ሞቅ ሲል እንደዚያ እንደማይተራመስ ሁሉ አሁን ያለው ሁኔታ የሚያስገርም ነው፡፡
ነጠላዋን ተሸፋፍና፣ መንገደኛ መስላ፧ አንድ ጥግ ላይ ተቀመጠችና፤ ግዳይዋን መጠባበቁን ተያያዘችው፡፡ በእርግጥም ስለቸኮለች ነው መሰል በጣም ቀድማ ነበር የመጣችው፡፡
ገንዘብ በገፍ እየገባለት የመጣው ጎረምሳ በንግዱ ላይ ትኩረቱን እየጣለ ሄዶ ነበር፡፡ አበራን ወደዚያ ካባረረ በኋላ ትርፉን ለግሉ ማግበስበስ ጀምሯል።
ገንዘብ ሲቀምሱት ይጣፍጣል፡፡ በላይ በላዩ ያስመኛል። እህል ሲጠግቡት ያስገሳል፡፡ሲበዛም ያስጠላል፡፡ ገንዘብ የሚጠግብ ሆድ ግን የለም፡፡ ግሳትም የለው፡፡ በላይ በላዩ ጨምሩልኝ፣ ጨምሩልኝ፣ የሚያሰኝ፣ እየበሉት የሚርብ ነገር ቢኖር ገንዘብ ነው፡፡
እንደሻው የራሱ የሆነውን፤ እንደፈለገው የሚያዝበትን ገንዘብ ሲያገኝ፤ እንደጠላት ገንዘብ ማውደም ሳይሆን፣ ቀስ በቀስ ሱቁን በማደራጀት ሀብታም መሆን ስለፈለገ፣ ቆጣቢና ትጉህ ሠራተኛ ሆኗል።
ዛሬ ከሌሎቹ ሁሉ ቀደም ብሎ ገበያ ሊሻማ መጣና የሱቁን በር ከፈተ፡፡ ሙሉ ጂንስ ለብሷል፡፡ ከላይ ጥቁር ክብ ባርኔጣ አድርጓል፡፡
አንገቱ ላይ አጠር ያለች ወፍራም ሻርፕ ጠምጥሞ ነበር፡፡
የሱቁን በር ከፍቶ ወደ ውስጥ መዝለቁን ስታይ ትህትና ተዘጋጀች፡፡ እሷም ጂንስ ሱሪ ነው የለበሰችው፡፡
ቀስ ብላ ቀኝ እጇን ወደ ቦርሳዋ ሰደደችና፣ ማጥበቂያውን አላላች፡፡ ሽጉጡ ላግዳጁ ዝግጁ ሆነ፡፡ አሁንም ቀስ ብላ ጨበጠቸው፡፡ እጇ የተንቀጠቀጠ መሰላት፡፡
“አይዞሽ ትህትና ጠንከር በይ” አለች ለራሷ፡፡ “የመጨረሻው ሰዓት የድል ሰዓት ደርሷል፡፡ የመጨረሻውን የድል ሰዓት ባትወጪው አበቃልሽ!” አለችና ራሷን አደፋፈረች፡፡
ይህ የመጨረሻው መክሸፍ የሌለበት እርምጃ ነው፡፡ በእውነትም ጠንከር አለች፡፡ ልቧ በትክክል መምታት ጀመረ፡፡ ሰውነቷ መራራ ደም ሲረጭ ተሰማት፡፡ የቀድሞ ባህሪዋ ከውስጧ ጥርግርግ ብሎ ወጣና፤ አዲስ የቆራጥነት፣ የደፋርነትና፤ የጭካኔ ባህሪይ ተላበሰች፡፡
“አምላኬ በደሌን አንተ ይቅር በለኝ፡፡ ነፍሴን ተቀበላት!” አለችና የሽጉጡን ምላጭ እንደያዘች እየተንደረደረች ወደ ሱቁ ሩጫዋን ቀጠለች፡፡
ሱቁ በር ላይ ስትደርስ እንደሻው በሚያየው ነገር ተደናግጦ፣ ዐይኖቹ ተበልጥጠው፣ አፉ ተከፍቶ እንደቀረ ትንፋሽ ከማውጣቱ በፊት
ሽጉጡን ላጥ አድርጋ አወጣችው፡፡
ንግግር የለ፣ ግርግር የለ፣ ፋታ ሳትሰጠው በቀጥታ እርምጃውን ወሰደች፡፡
ዷ! ዷ! ዷ! ዷ! አምስት የቆጠረች መሰላት፡፡ አራንቱን ጥይቶች ካንጣጣችበት በኋላ፣ ተንገዳግዶ መውደቁን ስታረጋግጥ፧ ሽጉጡን
ወደራሷ አዙራ አፍዋ ውስጥ አስገባቸው፡፡
ሰው መሯሯጥ ጀመረ፡፡ ለሚተራመሰው ሰው ቦታ ሳትሰጥ፤
እርምጃዋን በራሷ ላይ ወሰደች፡፡ ምላጩን ሳበቸው፡፡ ዷ! ዷ!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሰማዩ የተባዘተ ጥጥ በመሰለው ደመና ተዥጐርጉሯል።
ጨረሯን የፈነጠቀችው ፀሐይ ያንን የደመና ቁልል እየናደችው ስትመጣ፤
ሰዓሊው በሸራ ላይ በብሩሹ የፈነጠቀው ንድፍ እየመሰለ ሄደ፡፡ ከዚያም ሙሉ ለሙሉ ደመናው ተገፈፈና፤ ጥርት ያለ ሰማይ ታየ፡፡
የሰው ልጅ የውስጥ ስሜቱ ሲጐዳ፣ ሲከፋው፣ ሲጨንቀው፤ ልክ ሰማዩ በደመና እንደሚያኮርፈው ሁሉ፤ ይህንን መጥፎ የውስጥ ስሜቱን በጨፈገገ ገጽታው ይገልጸዋል፡፡ በሆነ ባልሆነው ሆደ ባሻነት ያጠቃዋል፡፡
እነሆ ልቡ ከአምስት ዓመታት በላይ ከፍቅር ተገልሎ የቆየው ሻምበል ብሩክ ትህትናን ካገኘበት እለት ጀምሮ መንፈሱ ታድሶ!
የወደፊት የትዳር ህይወቱን በቅርብ ርቀት አሻግሮ መመልከት ሲጀምር፤ በእንጭጩ ተቀጨ፡፡
ትህትና ፍቅሯን ብቻ ሳይሆን፤ ያንን ደስተኛነቱን ጭምር በልቡ ውስጥ ገድላበት ነው የሄደችው፡፡
ድምጿን ለመስማት ይፈልጋል፣ ወዲያውኑ ደግሞ ከነመፈጠሯ እንዲረሳት ይመኛል፡፡ ትናፍቀዋለች፤ የሠራችው በደል ፊቱ ላይ ድቅን
ይልበታል፡፡ በቅናት ይቃጠላል፡፡ ወዲያውኑ ደግሞ ብሩኬ.... ብሩኬ....
ብሩኬ.... የሚለው ያ ለስላሳ ድምጿ፣ ያ ለስላሳ ሰውነቷ ያ ለስላሳ ባህሪዋ፤ ይታወሰዋል፡፡
በፊት የነበረችው ትህትና እንዴት የምትወደድ ልጅ ነበረች? ለምን ፈጣሪ አሳይቶ ነሳው? ምነው እሱ ለፍቅር አልታደለ? ሁል ጊዜ መጨነቅ?
“ምነው የዚያን ዕለት ባልተገናኘን ኖሮ” የሚል ሃሣብ መጣበት፡፡ ሆኖም በመገናኘታቸው አንድ መልካም ሥራ መስራቱ ያስደስተዋል፡፡
አጋር ያልነበራት እናቷን መርዳት መቻሉ እርካታን ይሰጠዋል።
ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም፡፡ እንዲሉ፣ እሷ ትበድለው እንጂ፤ እሱ ከበደል ይልቅ መልካም ሥራን የሠራ ተበዳይ መሆኑ ሲታወሰው፤ “ይሁን እስቲ ሁሉ ነገር ከፈጣሪ ይገኛል” ይልና
ይጽናናል፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ የሰሞኑ ሁኔታው የተለየ ነበር፡፡ ናፍቆቷ ነፍሱን ሊያወጣው ደርሷል፡፡
በውስጡ ፍቅርና ጥላቻ ነግሰውበታል፡፡ እንዳይጠላት ይወዳታል፣ እንዳይወዳት ደግሞ የሠራችው ሥራ...እንዳንድ ጊዜ ያ አለቃቀሷ፤ እዚያ እላዩ ላይ ተጠምጥማ እየተንሰቀሰቀች የተናገረችው ንግግር፣ ትዝ ይለውና፤ “ምን ነበረበት ይቅር ብላት ኖሮ? ግብዝ ነኝ” በማለት እራሱን
ይኮንናል፡፡ ወዲያው ደግሞ የሻክረና ጥርጣሬ የገባው ልብ ተመልሶ ልብ
ላይሆን፡፡ የነቃ ብርሌ ተመልሶ ዕቃ ላይሆን፣ አጉል ሙጥኝ አለማለቱን
ይወደውና..
እንኳንም በጊዜ አቋረጥን” የሚል ስሜት ይሰማዋል፡፡በጠዋቱ መ/ቤቱ እንደደረሰ ወደ ቢሮ ከመግባቱ በፊት ጫማውን
ሊያስጠርግ ሄደ፡፡ሰማዩን አየው፡፡ ከቤት ሲወጣ በደመና የተሸፈነ ነበር፡፡ አሁን
ግን ጥርት ብሏል፡፡ የሱ ስሜት ግን እንደሰማዩ አልጠራም፡፡ ፊቱ ጨፍግጓል፡፡ ጫማውን አስጠርጐ ወደ መሥሪያ ቤቱ ግቢ ሲዘልቅ......
“እንደምን አደርክ ሻምበል መልዕክት አለህ” አዳሪው ፖሊስ ከኪሱ ውስጥ ያስቀመጠውን ፖስታ አቀበለው፡፡
ሻምበል ፖስታውን ተቀብሎ ተመለከተው፡፡ የላኪው ሥም
የለበትም፡፡
የአደራ ደብዳቤነቱን እንጂ ከማን እንደተላከ አይገልጽም፡፡
“ማን ነው የሰጠህ?” ሲል ፖሊሱን ጠየቀው፡፡ ስሟን እንዳልነገረችው ገለፀለት፡፡ በቀጥታ ወደ ቢሮው ሄደ፡፡
የቢሮውን መስኮት ከፈተው፡፡ ንፁህ አየር ገባ፡፡ ከዚያም

👍1
መለዮውን አውልቆ፤ ጠረጴዛው ላይ ካኖረው በኋላ፤
የዚህን እንግዳ የሆነ ደብዳቤ ይዘት ለማወቅ ጓጉቶ፤ ፓስታውን ቀደደው፡፡
“እንደምን አደርክ ሻምበል ገብተሃል እንዴ?” የጣቢያው አዛዥ ወደ ቢሮአችው ሲሄዱ እግረ መንገዳቸውን ሰላምታ ሰጥተውት አለፉ፡፡
እግዚአብሔር ይመስግን ሻለቃ ደህና አደሩ?” አፀፋውን ቆሞ ሰላምታ ከሰጠ በኋላ ወደ ደብዳቤው ተመለሰ፡፡
ሻምበል ብሩክ ደብዳቤውን ማንበብ ሲጀምር ሰውነቱ እየተለዋወጠ ሄደ፡፡ ቀስ በቀስ ልቡ ታርዶ እንደተጣለ ዶሮ ትንደፋደፍ ጀመር፡፡ በመደናገርና በድንጋጤ ስሜት እንደተዋጠ ንባቡን ቀጠለ፡፡ ወደ ዝርዝሩ በገባ ቁጥር ደርዘን ፍርሃትና ጥርጣሬ እየተጫነው ሄደ።
ይህ ጭንቀቱ በግንባሩ ላይ ላብ ችፍ፤ ችፍ፤ ያስደርገው ጀመር፡፡ ከዚያም የሆነ ቦታ ላይ ሲደርስ ወረቀቱን አጥፎ ዐይኖቹን ጨፈነና..
“እፎ ይ ይ ይ ......” ሲል በረጅሙ ተነፈሰ፡፡ ልቡ ትር ትር ትር አለች፡፡ “ወይኔ ብሩክ ምን ተአምር ነው የማየው? ወይኔ የበላይ ልጅ፤ ነፍሰ ገዳይ ልሆን ነው ማለት ነው?
እውነት ትህትና ጨክና እራሷን በራሷ ልታጠፋ ነው ማለት ነው?”
እናቷ ሆስፒታል ውስጥ እያለቀሰች ታየችው፡፡ ወንድሟ አንዱአለም ፊቱ ላይ ድቅን አለበት፡፡
“አንተ ነፍስ ገዳይ እህቴን ገደልካት” ብሎ ጣቱን ሲቀስርበት ታየው። ዝቅ እያለ ሄደ። ኸረ በፈጣሪ? አገር ጥላ ኮበለለች? ትህትና እራሷን አታጠፋም! ባይሆን ወደ አንድ የማይታወቅ ቦታ ሄዳለች ማለት
እንደሻው? እንደሻው? የዚያን ጊዜ አንገቱ ላይ ተጠምጥማ እያለቀሰች የነገረችው ትዝ አለው፡፡ ልክ ነበር ማለት ነው? ትህትና አልዋሸችኝም ነበር ማለት ነው?
ወይኔ ብሩክ ጥይት ተኩሼ ባልገድላትም ገዳይዋ እኔው ነኝ፡፡ ወረደ ልክ ነው፡፡ ወደ መጨረሻው ሲቃረብ በጭንቅላቱ ወስጥ የሆነ ነገር የፈነዳ መሰለው፡፡ አይኖቹን
ጨፈነና ትንሽ ቆይቶ ገለጣቸው፡ አልቀረለትም :: የጠረጠረው ሆኖ አገኘው፡፡
ስሜቱ ተናወጠ፡፡ አእምሮው በጭንቀት ሊፈርስ ተቃረበ፡፡ ዐይኖቹን አሁንም ጨፈነ፡፡ እንደገና ገለጣቸው፡፡ እንደገና ጨፈናቸው...
እንደገና በመጨረሻው ብዥ ብዥ ብዥ... የሚል ነገር ታየው፡፡ አስፈሪው የስንብት ቃል! ሲያነበው እያንዳንዱ ፊደል ጦር ሆኖ አእምሮውን አየሰቀሳቀ፤ እየወጋ፤ አቆሰለው፡፡ የዚያች የንፁህ ልጅ
የስንብት ቃል......
“እወድሃለሁ ብሩኬ፡፡ የመጀመሪያም የመጨረሻም ፍቅሬ አንተ ነበርክ፡፡ ደህና ሁንልኝ....”
“ሁሉ ነገር አልቋል መርካቶ
“ወይኔ ብሩክ!” እንደ እብድ ወንበሩን ወደዚያ አሸቀንጥሮ ወደ አለቃው ቢሮ ሮጠ፡፡
“እባክዎትን ሻለቃ አንድ ጊዜ የመኪና ቁልፍ ይስጡኝ?” ሰውነቱ
ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡
ሻለቃ ሁኔታውን ሲያዩ ደነገጡ፡፡ያልተለመደ ሆኔታ ይታይበት
ነበር፡፡ “ምን ሆነሃል ሻምበል? አይዞህ ረጋ በል” ከወንበራቸው ተነስተው፡፡ ድምፁም ልክ እንደሰውነቱ ይንቀጠቀጥ ነበር።
የሱን ሀኔታ ሲያዩ ሻለቃ ሃሣባቸውን አስተካከሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ መኪና ይዞ ቢሄድ አደጋ እንዳይደርስበት ስለፈሩ የአሥር አለቃ ዓለማየሁን ጠርተው ......
“እንካ ቁልፍ፡፡ ሻምበልን የሚፈልገው ቦታ አድርሰው፡፡ ረጋ ብላችሁ ሂዱ ታዲያ! " ሲሉ ትዕዛዝ ሰጡት፡፡ ከዚያም ወደ መርካቶ ይከንፉ ጀመር፡፡
ሻምበል ብሩክ ሩጫው ከንቱ ... ጥረቱ ዜሮ የምትወደው ጓደኛው ትህትና... ጀንበሯ ጠለቀች? ወይስ?
እየበረሩ መርካቶ ገበያ አዳራሽ አጠገብ በህዝብ የተጨናነቀ ስፍራ ደረሱ::
“ቱፍ! ቱፍ! በሞትኩት እኔን! እኔን!
ወይኔ ምን ብታደርገው ነው? ያቺን አበባ የመሰለች ልጅ?.....”
“አቤት! አቤት! እንዴት ያለው አሳዛኝ ታሪክ ነው? አሁን ይሄ የሰይጣን እንጂ ፤ የሰው ሥራ ይሉታል? የጋኔን ስራ እንጂ! ያንተ ያለህ ድብን አድርጓት ለራሱም ጠጣው አቤት! አቤት!”
ግማሹ ከንፈሩን ይመጣል፣ ገሚሱ ደረቱን ይደልቃል፡፡ ወደ ስማይ ወደ ፈጣሪ እያንጋጠጠ....
“ወንድ ነው! እኔ በበኩሌ አደንቀዋለሁ!! አንጀቱን አሳርራው ይሆናል ዋጋዋን የሰጣት! በቁሙ ተቃጥሎ ከሚሞት፤
አቃጥሏት መገላገሉ በጀው”፡፡ የጉርምስና ስሜት ከሚታይባቸው መካከል
የሚሰነዘር.... እንደዚያ ሰው ተሰብስቦ የሚንጫጫበትን እየሰነጠቀች አንዲት የፓሊስ ሠሌዳ ቁጥር ያላት ቮልስ ዋገን መሀል ገብታ ቆመች፡፡ ሻምበል ብሩክ ፊቱ ጥላሸት መስሎ፣ ዐይኖቹ በድንጋጤ
እንደተጐለጐሉ፤ ከመኪናው ላይ ዱብ ብሎ ወረደ፡፡ አብዛኞቹ በፍርሃት
ገለል ገለል አሉ፡፡ የሚታፈሱ ነው የመሰላቸው፡፡
“ምን የተፈጠረ ነገር አለ? ምንድ ነው!” አንዱን ጐረምሣ ቢጤ አፋጠጠው፡፡
ለሱ አልታወቀውም እንጂ ልጁን እንደ ነፍሰ ገዳይ ኮሌታውን ጨምድዶ ይዞት ነበር፡፡
“ተጋደሉ በጥይት ወንፊት አደረጋት” አንገቱን ለማስለቀቅ እየሞከረ፡፡
“ማን ነው ማንን ወንፊት ያደረገው?” ተገላቢጦሹ ግራ ገባው።
“አትቀባጥር! ቀባጣሪ! ለወሬ ከመሽቀዳደምህ በፊት አጣራ!
ወሬኛ!” አለና አንዱ ጎረምሣ ልጁን ወደዚያ ገፍትሮ ወደ ሻምበል ብሩክ
ጠጋ አለ፡፡
“ጌታዬ እሷ ናት የመታችው፡፡ ደጋግማ ከተኮሰችበት በኋላ ለራሷ ጠጣች፡፡ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ ይህን በዐይኔ በብረቱ ነው ያየሁት” አለና ምስክርነቱን ሰጠ፡፡
“ሞታለች?” ሻምበል ስውነቱ በብርክ እየተንቀጠቀጠ፡፡ ትሙት ትኑር አላውቅም፡፡ ከዚህ ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ ግን ሁለቱም በህይወት ነበሩ፡፡ የሚተርፉ ግን አይመስለኝም፡፡”
“የት ሆስፒታል ነው የተወሰዱት? ና እስቲ ግባ” ልጁን መኪና ውስጥ አስገባው፡፡ሁለቱም ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተነገረውና፤ ተያይዘው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በረሩ፡፡ሻምበል ብሩክ ነፍሱን አያውቅም፡፡ ሆስፒታል ደርሰው ወዲያና ወዲህ እየተራወጡ ስለ ሁኔታው ጠየቁ፡፡
አንዲት ነጭ ካፖርት የለበሰች ነርስ የሆነውን ቀስ ብላ አስረዳችው፡፡ ሁለቱም ጉዳተኞች በህይወት እንደሚገኙና በድንገተኛ ህክምና ክፍል እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ረጋ ብላ ገለፀችለት፡፡
“እውነትሽን ነው? አልሞተችም?” በሁለት እጆቹ ትከሻዋን ይዞ በጉጉት ጠየቃት፡፡
ይመኑኝ በተለይ እሷ ለህይወቷ የሚያሰጋ ጉዳት እንዳልደረሰባት ሀኪሞቹ ሲናገሩ በጆሮዬ ሰምቻለሁ፡፡” . ነፍሱን ትንሽ
መለስ አደረገችለት፡፡
“ምን እናድርግ አሁን ሲስተር? ደም የሚጠየቅ ከሆነ እባክሽን አጣሪልኝና
ደም ልስጥ፡፡ ሌላም የሚያስፈልገውን እርዳታ ሁሉ አሳውቂኝ፡፡ ሲስተር ትልቅ ባለውለታዬ ትሆኛለሽ፡፡ ተባበሪኝ” ተማፀናት፡፡
“ግድ የለዎትም አይረበሹ፡፡ የሚሆነውን ሁሉ በዶክተሮች ትዕዛዝ መሠረት እንፈጽማለን፡፡ እስከዚያው ይምጡ” አለችና ወስዳ አንድ ክፍል ውስጥ አረፍ እንዲል አደረገችው፡፡
ሁኔታው ስላሳዘናት ነው ትንሽ እረፍት እንዲወስድና፤ እራሱን እንዲያረጋጋ፤ የፈለገችው፡፡
ሻምበል ብሩክ አምላክ ነፍስ ገዳይ እንዳያደርገው በልቡ ፀሎት እያደረሰ፣ የሚሆነውን ሁሉ በሲስተር ማን አህሎች በኩል ለመሰማት በጉጉት መጠባበቁን ቀጠለ፡፡
“መኪናውን ይዘህ ሂድ” አለና ሾፌሩን ሸኘው፡፡ ለልጁ አምስት ብር አስጨብጦ ሁለቱንም ላክና፤ እሱ እዚያ ሆኖ ውጤቱን ይጠባበቅ ጀመር፡፡ አሁን ትንሽ ነፍሱ መለስ ስትልለት፤ አንድ ነገር ትዝ አለው፡፡
ለአዜብ እንዲደውልላት አደራ ብላው ነበር፡፡ የስልክ ቁጥሩን ከደብዳቤው ላይ አነበበና ለአዜብ ደወለላት፡፡ ዝም ብሎ በደፈናው ችግር መድረሱን ገልጾ፤
ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በአስቸኳይ እንድትመጣ ነገራት፡፡
አዜብ ይህንን ስትሰማ ክው ብላ ደንገጠች፡፡ አንዱአለም የሞተ መሰላት፡፡ ነፍሷን ሳታውቀው፤ ፀጉሯን እንኳን ሳታበጥር፤ እየከነፈች መጣች፡፡ ሻምበል ብሩክ በሩ ላይ ሆኖ

👍2
እየጠበቃት ነበር፡፡
“አንዱዓለም ሞተ?! ሞተ ሻምበል?!” ሰውነቷ ተረብሿል። እዚያ እሱቁ ድረስ ወስዳ እንደሻውን ያሳየችው እሷ ነች፡፡ ጦሱ የሷ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ሲሞት እሷ እንደገደለችው እየተርበተበተች ፤ ሻምበልን አፋጠጠችው፡፡
የተፈጠረው ተአምር ግን ከግምቷ ውጭ
ነበር፡፡ጭራሽ ይሆናል ብላ ልትገምተው የማትችለው አስደንጋጭ ሁኔታ! ሻምበል
እንዴት እንደሚገልጽላት ጨንቆት ዐይኖቹ ፈጠው ቀሩ...
“አንዱዓለም ምንም አልሆነም፡፡ አዜብ ሌላ ነገር ነው ትህትና እንደሻውን በጥይት ከመታችው በኋላ፣ እራሷን
“እናስ ከዛስ? እራሷን ምን?!!!...ጮኸች፡፡
“አራሷንም በጥይት ጐድታለች..
ኡይይ! ሞታለች በለኝ እንጂ ሻምበል! ጓደኛዬ ሞታለች በለኝ እንጂ!ትሁትዬ፣ ያልታደለችው ጓደኛዬ ሞታለች፡፡ ትሁት ሞታለች፣እንደሰው ሳይደላት እንደተቃጠለች ሞተች፡፡ እንዳለቀሰች ቀረች ጓደኛዬ ትሁትዬ? የት ነው ያለሽው? የኔ እመቤት! ጓዱ .... ጓደኛዬ እንደ እብደ ሆና እየጮኽች ወደ ግቢው ውስጥ ሩጫ ጀመረች፡፡
ሻምበል ተከትሏት ሮጠና፤ በግድ አጇን ይዞ አስቀራት፡፡ ወዴት ልትሄድ እንደነበረ እግዜር ይወቀው፡፡ እዚያ እመሬት ላይ ወድቃ በእንባ እየታጠበች አለቀሰች፡፡ የማትለው፤ የማትናገረው፤ ነገር የለም፡፡ ትህትና በህይወቷ አንድም ቀን ሳይደላት፤ እንደተሰቃየች፣እንደተቸገረች፣እንደተንከራተተች፤ መሞቷን፣ የሷ ደስታ ከሻምበል ጋር ያሳለፈችው አጭር ወቅት ብቻ መሆኑን፣ እየለፈለፈች አለቀሰች፡፡
ሻምበል አልቻለም፡፡አንጀቱ ከውስጥ ተንሰፈሰፈ፡፡ ድምፁን ውጦ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡ በአንድ በኩል እሱ እራሱ አልቃሽ፤ በአንድ በኩል ገላጋይ ሆነ፡፡
“እባክሽ ዝም በይ አዜብ፡፡ ደህና መሆኗን አረጋግጫለሁ፡፡
ለህይወቷ እንደማያሰጋት ተነግሮኛል። እባክሽ ዝም በይ” እንደዚያ ሆና በምሬት ስታለቅስ፤ በትህትና ላይ የደረሰው
የህይወት ፈተና፣ ስቃይዋ፣ እራሷን እስከማጥፋት የሚያደርስ መከራ
መሸክሟ፣ ንፁህነቷ፤ በሃሣብ ታየው፡፡
በተለይ እላዩ ላይ ጥምጥም ብላ፤ ስቅስቅ ብላ! ያለቀሰችው፣ እፊቱ ላይ ድቀን ቢልበት ... ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡፡
አዜብ ትንሽ ቀዝቀዝ ስትል፤ ስለሁኔታው ከሀኪሞች አንደበት እንድትስማ! ወደ ሲስተር ማን አህሎሽ ዘንድ ይዟት ሄደ።
ሁሉንም አዜብ ትነግርሃለች ብላው ነበር፡፡ስለሁሉም ሁኔታ ዝርዝሩን ከአዜብ ሊሰማ፤ ደብዳቤውን ሰጣት፡፡ አዜብ ያንን ደብዳቤ እያለቀሰች አንብባ ከጨረሰች በኋላ፤ የሆነውን ሁሉ፤ አንድም ሳታስቀር እውነታውን ተረከችለት....
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ

#ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ
፡
፡
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ
....ለማንኛውም አሁን ከለማ ጋር ግንኙነታችን ተቋርጧል።
"በቃ?"
" አዎ " ከእንግዲህ በዚህ አይነት የምንቀጥል አይመስለኝም ። በእሱ የተነሣ ነው ፡ እንዲህ ስሜ የጠፋው ። ”
ሁለቱም ዝም አሉ። እስክንድር ለሁኔታው ያልተዘጋጀበት ሆኖ ነው ለአፋጣኝ ጥያቄም ሆና መልስ የተቸገረው።
ቤተልሄም ግን በዝምታው መርከብ ተሳፍራ ወደ ኋላዋ ከለማ ጋር የተጣሉበት ቀን ደርሳ ነበር።
የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት ተጀምሮ ልማ ምንም ኮርስ እንደማያስተምራት ካረጋግጠች በኋላ ፥ ቤተልሔም ሸርተት ለማለት ትጀምራለች ። ጭራሹን ለአንድ ሳምንት ያህል ትሰወርበታለች።ለማ ልቡ ይጠረጥርና በዚያው ሳምንት ግቢ ውስጥ ፈልጎ ካገኛት በኋላ ፥ ቤቱ ድረስ እንድትመጣ ነብር ሆኖ ይቀጥራታል ።
"ምን ሆነሽ ነው እንዲህ የጠፋሽው!" እንደ ብራቅ ጮህባት።
"ስላልተመቸኝ ነው"
"ይህው ነው መልስሽ?" አላት በሽቆ።
ዐይኗን ሰብራ ዝም አለች ። አኳኋኑ አስፈራት ። ገላጋይ በሌለበት ባዶ ቤት ውስጥ የያዛት እንደሆን ማን ይደርስላታል ? ሽንቷ ወጠራት ።
"ምን መሰለህ ለማ" አለችው እንባ በተናነቀው ድምፅ ዬኒቨርስቲዉ ውስጥ ስሜን እያጠፉ ነው ። ከአንተ ጋር ባለኝ ግንኙነት ክፉኛ ታምቻለሁ ። ሰላም ይሉኝ የነበሩ ተማሪዎች ሁሉ ዘግተውኛል !
"እና ? ”
“ እና ለአንተም ስም ሆነ ለእኔ ይህን ግንኙነታችንን ብናቋርጠው ይሻላል ብዬ ነው። እኔ እዚያ ግቢ ውስጥ መኖር
እልቻልኩም ፡ ሰውነቴ አለቀ” አለችው ፡ ለቅሶ እየቃጣት
እንዲሁ ነች ። እስክንድርን ጠርታ ፥ “ ጓደኛዬ ሁን ” እንዳለችው መሆኑ ነው ። ብልጠቷ ስልት የለውም ። ይህ ስልት ያጣው ብልጠቷ ለማን አብከነከነው ።
“ ስሚ ! ” አላት ። መቀጠል አልቻለም ። ጉሮሮው ላይ የሆነ ነገር ተናነቀው ። ከወጣትነት ባለፈ ዕድሜው የእልህ ዕንባ እንዳያነባ ፈራ ። እናም ከምላሱ ይልቅ እጁን ማንቀሳቀስ መረጠ ። የራስጌ ኮመዲኖውን ከፍቶ አንድ ወረቀት አወጣና ሰጣት ።
ምንድነው ? አለችው ።
አንብቢው ! አላት ፡ ዐይኑን አፍጥጦ ።
በዚሁ ሳምንት ውስጥ ቢሮው ወስጥ በድብቅ ተጥሎ ያገኘው ወረቀት ነበር ። ቤተልሔም ተቀብው ማንበብ ጀመረች።
ጽሑፉ በቅጡ አልተቀነባበረም ። በግጥም ይጀምርና
ምሁር ሰማ ዘቀጠ ...
ኅሊናውን ለሴት ሽጠ ...
ካለ በኋላ ፥ በስድ ንባብ ይቀጥላል ። ቃላቱ ተስፋ መቁረጥን ያመለክታሉ ። በለማ ላይ የተደረደሩ ተራ ስድቦች ነበሩ ።
በመሐል ደግሞ
... ወሲብ አንጎል ሆኖ ሲያስመርቅ እያየሁ ፡ የእኔ ጥናት ከንቱ እንዲያው ተሠቃየሁ አወይ እኔ ፡ አወይ እኔ ! ሴት አለ መሆኔ !...” ይልና፡ ተመልሶ ስድቡን ይቀጥላል ።
አንብባ ጨርሳ ቀና ስትል፥ የምትናገረውን ለመስማት ዐይን ዐይኗን ተመለከታት ። ለእሷ ሲል የተጋፈጣቸው ችግሮች በውስጧ ኅዘን እንዲፈጥሩባት ነበር ሃሳቡ ። እንዲህ ዐይነት ነገሮችን ሥራዬ ብሎ ነው የሚነግራት ። አንዴም በመጀመሪያው ሴሚስተር አንድ ጓደኛው መቼም የቅርቤ ነው ብሎ ሊመክረው ፥ “ ለማ እዚህ ግቢ ውስጥ በአንዲት
ልጅ ምክንያት ስምህ እየተበከለ ነው ” ብሎ ሲጀምር' ለማ በሽቆ ፡ “ ስለዚህ ጉዳይ ምንም አታንሣብኝ ። ተፈጥሮን
ተመክሮ አይመልሰውም ! ማንም የፈለገውን ሊል ይችላል” ብሎ ዘግቶታል ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ መምህራንም
እየታዘቡት መሆናቸውን ሊነግረው ነበር ጓደኛዉ የፈለገው ነገር ግን ለማ የሚበገር ሰው አልሆነም።
በወቅቱ ይህንንም ለቤተልሔም አጯውቷታል ።በአንቺ የተነሳ ያየሁት አበሳ" አይነት መሆኑ ነው። ታዲያ ያኔ ቤተልሄም አዝና ከንፈሯን መጥጣለት
ነበር ።
"አበሻ ነገር መፈትፈት ልማዱ ነው ! አትጨነቅ ” በማለትም አበረታታዋለች ። አሁን ግን ግጥሙን አንብባ የዚያን ዐይነት መልስ አልሰጠችውም ፡፡ እንዲያውም ለአፍራሽ ሐሳቧ መንገድ የጠረገላት ነው የመሰላት......
እና ፥ ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ ወዴት ነው። ሸርተት የምትይው ? አላት አፍጥጦ።
“ እኔስ የፈራሁት ይህንኑ አይደል ? ” አለችና ጽሑፉ ክፉኛ እንደ ቆረቆራት ሁሉ ዐይኗን አሸች ። ዕንባው ደግሞ ራሱ ካልፈቀደ እንደ ፈለጉት አይመጣ ! ዐይኗን ምራቅ እንዳትቀባ ለማ አጠገቧ ቆሟል።
መጀመሪያ ለምን ነበር የቀረብሽው ? ” አላት እስክንድር።
" ፈራሁኛ ! ”
"ምን ? "
"ማትስ እንዳልወድቅ ። እኔ የቁጥር ዘር ጠላቴ ነው ።
ፍቅር ብቻ ሳይሆን እልህ ጭምር ነበር የያዘው ። አስተያየቱ አላማራትም ጡንቻው ላይ አባብጠው የተጋደሙት
ሥሮች አሰፈሯት ። ከተቀመጠችበት ቀስ ብላ ተነችና ወደ በሩ አምራች ።
የት ልትሔጂ ነው ? ” አለና ፥ አጠገቡ የነበረውን አምቦ ውሃ ጠርሙስ አንስቶ ግንባሯ ላይ አነጣጠረ።
“ውይ ለማ ! ” ብላ ጮሃ ጣውላው ላይ ቁጭ አለች ።
“ ሸርሙጣ ! ” አላት አጠገቧ ደርሶ ቁልቁል እየተመለከታት
የሚለማመጡና የተቆጡ ዐይኖች ሽቅብና ቁልቁል ተፋጠጡ ። ለማ ደፍሮ እጁን ሊያሳርፍባት አልቻለም ። አቅፎ
ለማባበልም ልቡ ያን ያህል አላላም ።
"ስሚ ፤ በሦስት ቀን ውስጥ አስበሽበት መልሱን ንገሪኝ። የሦስት ቀን ዕድሜ ሰጥቼሻለሁ ! ” አላት እንዳፈጠጠ ።
ቤተልሄም ከጣውላው ላይ ቶሎ አልተነሳችም” በድንጋጤ ከጭኗ ሥር ሽንት ጠብ ያለ ስለ መስላት እንዳይታይባት ፈራች ። ነገር ግን ሰውነቷን ዐልፎ ጣውላው ላይ
የደረሰ አልነበረም...
ያን ዕለት እንደ ምንም ከክፍሉ ከወጣች በኋላ መንገድ ላይ በጕዳዩ እሰበችበት ። የይህሆን ጨዋታ ነው ። የለማ ኮንትራት አልቋል ። አብራው ከቀጠለች ለሚቀጥሉት ዓላማዎቿ ዕንቅፋት ይሆንባታል ። ከአንድ ወንድ ጋር ብዙ መታየት ሴሎች የጥቅም መንገድን ወመዝጋት ነው ። ጥቅሙን የሚያሳድድ ሰው በአንድ ነገር ላይ መርጋት አይችልም ትርፉን ከኪሳራው እያሰላ በሚያዋጣው መንገድ መንቀሳቀስ አለበት ... እና ለማ እስኪረሳት ድረስ ከዐይኑ ለመሰወር ወሰነች። ከዚህ ውሳኔ በኋላ ስሟን ለማደስ በግቢው ውስጥ አብራው
የምትታይ ተማሪ ስታስብ ፥ እስክንድር በሐሳብዋ ብቅ አለ ። ብዙ ተማሪዎች ከዘጓት በኋላ እሱ ሳይለወጥ እንደ
ወትሮ ሰላም ይላት ስለ ነበር ነው የታሰባት......
እስክንድር በሆዱ ሣቀ። የግልጽ ሰው ሳይሆን የብልጥ አንበሳ ምስል ከፊቱ የቆመ መሰለው ለጥቅም የቆመች
አንበሳ ! ሣር ባየችበት ሁሉ የምታጎነብስ በግ ፤ ግን ደግሞ እንስሳ ለማዳ ነው ያበላውን ያጠጣውን ፥ የቀረበውን ቶሎ
ያፈቅራል ።
«ግን ታዲያ አብራችሁ ስትቆዩ ከለማ ጋር ፍቅር አልያዘሽም ? ” ሲል ጠየቃት ።
“ ኤጭ ! ” አለች በንቀት
"እሺ ፤ እሱስ ፍቅር ቢይዘው ኖሮ ? ”
“ እእይ እኔ አስቀድሜ ነግሬዋለሁ" አለች ግንባሯን አኮማትራ
"ምን ብለሽ ?
“ አሜሪካ የመሔድ ሐሳብ እንዳለኝ እጮኛዬ እየጠበቀኝ ነው።
ሣቁ እንዳያመልጠው እየሞከረ ፥ ዋና ይዘሽ በትርፍ እየተጫወትሽ ነዋ ! ” አላት
ፈገግ ብላ ዝም አለች ።
“የእኔም ጓደኝነትስ ምሽን እስካሳደርስሽ ድረስ ነዋ!”አላት ድንገት ግልፍ ብሎት ።
ወይኔ ! ካንተ ጋር እኮ እንዲሁ ጓደኝነት ነው ” አለችው ፥ ድንገተኛ ቁጣው አስደንግጧት ።
“ እንዲሁ ጓደኝነት ብሎ ነገር ምንድነው?” ሲል አሰበ። ሐሳቡ ከውስጥ ጥቀርሻ እየለበሰ ሲመጣ ተሰማው ። የአሁኗ
ቤተልሔም ሳትሆን ነገ የምትይዘው ቦታና የምትፈጽመው ተግባር ነው የታየው በዚህ ዐይነት ብላሽ ጥበብ ከዩኒቨርስቲ የምትረቅ ሴት ፥ በሥራ ዓለም ስትሠማራም መሰሎቿን ታፈራና ትመለምል እንደሆን እንጂ ያስተማራትን ሕዝብ

👍4
ምን ያህል ትረዳለች ? ”
አንቺና መሰሎችሽ ተመርቃችሁ በምትይዙት ቦታም የኅብረተሰቡ በሽታ ነው የምትሆኑት ! ሊላት ፈለገ ። ግን
በምላሱ እንዲህ አምርሮ ሊያስቀይማት አልደፈረም ። “ ይልቅስ ለምን ቀርቤያት ከጥፋቷ እንድትማር አላደርጋትም ?
ሴት ልጅ ውበቷንና ገላዋን ለፍቅር እንጂ ለጥቅም መሸጥ የለባትም ፡ ካለዚያ ውሎ ሲያድር እንደ ዕቃ መቆጠር ይመጣል ብዬ ለምን አልመክራትም ? እንዲህ ዐይነቱ ከንቱ ብልጠት ከቤተልሔም ጋር አብሯት አልተወለደ ፤ ከኖረችበት አካባቢ የቀሠመችው በሽታ ነው እንጂ " እኔ ከማግለል ማስተማሩ አይሻልም ? ” የሚል የኅሊና ሙግት ገጠመው ።
ከሐሳቡ በስተጀርባ የችኮላ ስሜት ወጥሮት ነበር ።ወዴት ለመሔድ እንደ ቸኮለ አልገባውም። የሚሔድበትም
ጉዳይ አልነበረውም ።ከትዕግሥት ጋር የተያያዘ ስሜት ነበር የወጠረው ። እሷ ለአል ደብዳቤ ልትጽፍለት መሆኑን
ለቅርቡ ሰው አጫውቶ ተንፍሶ እንዲወጣለት ይፈልጋል ግን ለማን ? ለአሥራት ? ለቢልልኝ? ለዮናታን ?...
"ምነው ዝም አልክ ? ” አለችው ቤተልሄም ዝምታው አስከፍቶአት።
"እእይ ፤ እንዲሁ ነው" አለና "ግድየለሽም
ግኝኙነታችን እንደ ጥንቱ ቢቀጥል ይሻላል ” አላት እያመነታ።
አኩርፋ ለመሄድ ተነሣች።
“ እፎይ ትሒድልኝ ”አለ እስንድር በልቡ...

እሠይ ስሞ አገኘኹ፤
በሰው አፍ ተገኘኹ፡፡
"እሱ"... መባል ያዘ፤ መከረኛው ስሜ፤
መነከስ ጀመርኩኝ ፤ ጨረስኩኝ ተስሜ፡፡
ሰየሙልሽ፤
መዘኑልሽ፤
ሰፈሩልሽ፤
መተሩልሽ፤
መከሩልሽ፤
መከሩብሽ፤
"ከሴት ሴት አይቶ ፣ አይመኝም ደሞ
ሌላ ሴት ያስባል ፤ካንቺ ጋር ተጋድሞ።"
ይሉሻል!
“ከአንድ ግጥሙ ፣ እንኳን አበልጦ አያይሽም፤
ካልመሽበት በቀር ፣ ካንቺ አያመሽሞ።"
ይሉሻል!
የኔ ዓለሞ ሐቅ ነው!
ትልቅ ውሸት ሳይኮን ፣ ቅንጣት ውሸት የለው።
የኔ ዓላሞ ሐቅ ነው!
አሙልሽ አይደል ፣ የኔን ብሽቀት ላንቺ ፣ እያደማመቁ?
የሚያመትን እኔን...
አንቺ እንደፈጠርሽው፣መች እነ'ሱ አወቁ።?
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
በሰው አፍ ተገኘኹ፡፡
"እሱ"... መባል ያዘ፤ መከረኛው ስሜ፤
መነከስ ጀመርኩኝ ፤ ጨረስኩኝ ተስሜ፡፡
ሰየሙልሽ፤
መዘኑልሽ፤
ሰፈሩልሽ፤
መተሩልሽ፤
መከሩልሽ፤
መከሩብሽ፤
"ከሴት ሴት አይቶ ፣ አይመኝም ደሞ
ሌላ ሴት ያስባል ፤ካንቺ ጋር ተጋድሞ።"
ይሉሻል!
“ከአንድ ግጥሙ ፣ እንኳን አበልጦ አያይሽም፤
ካልመሽበት በቀር ፣ ካንቺ አያመሽሞ።"
ይሉሻል!
የኔ ዓለሞ ሐቅ ነው!
ትልቅ ውሸት ሳይኮን ፣ ቅንጣት ውሸት የለው።
የኔ ዓላሞ ሐቅ ነው!
አሙልሽ አይደል ፣ የኔን ብሽቀት ላንቺ ፣ እያደማመቁ?
የሚያመትን እኔን...
አንቺ እንደፈጠርሽው፣መች እነ'ሱ አወቁ።?
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
በድንገት የተከሰተው አደጋ ክፉኛ ስላስደነገጠው ሻምበል ብሩክ ቀን እረፍት፤ ሌት እንቅልፍ፤ የሚባል ነገር አጥቶ እንደዚሁ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ከረመ፡፡ ለዚሁ ጉዳይ ሲልም ከመስሪያ ቤቱ የአስራ አምስት ቀን ፈቃድ ወሰደ፡፡ በዚህ ፈቃድ በወሰደበት ጊዜው
ውስጥ ደግሞ ብዙ መሯሯጥ ይጠበቅበታል፡፡መጀመሪያ ሆስፒታል የተኛች እናቷን ማረጋጋት አለበት :: ከዚያም ለወንድሟ በቂና አሳማኝ ምክንያት መስጠት ይጠበቅበታል ይህንን ሁሉ ሲያደርግ በሀሳብ የምትረዳውና ! አብራው የምትሯሯጠው! አዜብ ብቻ ነች፡፡ አዜብ ስለደረሰው አደጋ የትህትና አክስት እንዲያውቁት ፈልጋ ነበር፡፡
"አይሆንም ትርፉ ማስደንገጥ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ እነሱ ካወቁ ወሬው መዛመቱና፤ እናትዋ ጆሮ መድረሱ የማይቀር ስለሚሆን፤ በሚስጥር ቢያዝ ይሻላል” በማለት የተከራከረው ሻምበል
ነው፡፡ሻምበል ለእናቷ የሚሰጠው ምክንያት አሳማኝ እንዲሆን ሀሳብ
ሲያወጣና፧ ሲያወርድ፤ አዜብም እንደዚሁ ያሳምናታል ብላ ያሰበችውን ምክንያት ስትደረድር፤ ቆዩና ሁለቱም ይሆናል ባሉት ሃሳብ ላይ በጋራ ከተስማሙ በኋላ፤ ይህንኑ ሊያስረዳ ወደ የካቲት አስራ
ሁለት ሆስፒታል አቀና፡፡ ትህትና ከእናትዋ ጋር በአይነ ስጋ ከተገናኙ ሶስት ቀን ሆኗቸዋል፡፡ አንዱአለምም ድምጹ ከጠፋ ሳምንት አልፎታል፡፡በነገሩ እናት ግራ ተጋብታለች፡፡
"ልጆቼን ምን ነካብኝ?" በሚል ጭንቀት ተውጣለች፡፡ትናንትና ሆስፒታል መጥታ ያስተዳደረቻት ሰራተኛዋ ነበረች፡፡ ትህትና ከቤት ያለማደሯን ብቻ ነው የነገረቻት፡፡ በሽታዋን ማዳመጡን ትታ ልጆችዋን
እያብሰለሰለች፤ በሀሳብ እንደተዋጠች ነበር ሻምበል ብሩክ የደረሰው፡፡ብሩክን ስታየው በደስታ ልቧ ቀጥ አለች ::
"ትህትናዬስ ብሩኬ?" ከኪሱ አውጥቶ ይሰጣት ይመስል በጉጉት አይን አይኑን እያየች ጠየቀቸው፡፡ ሻምበል ብሩክ እንደማፈር ብሎ ሳቅ አለና፤ ተቅለሰለሰ፡፡ ለዘዴው...
“ምነው ብሩኬ በደህና ነው?" ከሁኔታው የከፋ ችግር እንደሌለ ተረድታለች፡፡
“ምንም ችግር የለም እማማ፡፡ ምን የኛ የወጣቶች ነገር...
የሚያሰጋ ነገር ያለመኖሩን ከሁኔታው ብትገነዘብም ምክንያቱን ለማወቅ
ቸኮለች፡፡
"ምንድነው እሱ ታዲያ?
ትህትና ምንም እንኳ እጮኛዬ ብትሆንም፤ ከትዳር በፊት እርግዝና ማለት፤ ትንሽ ያልተለመደ ስለሆነ... አንጠልጥሎ ተወው። ነገሩ ገባት
ከዚያ በላይ ልታስጨንቀው አልፈለገችም እሱ ግን ቀጠለ "ከጋብቻ በፊት ልጅ መውለድ የቤተሰብን ክብር መንካት ነው የሚል እምነት አላት፡፡ ተመካከርንና ማህጸኗ እንዲጠረግላት አደረግን፡፡ አሁን
ራስ ደስታ ሆስፒታል ትንሸ እረፍት ትውለድ ስላሉኝ አስተኝቻታለሁ።"አለና አጭር ድራማውን አጠናቀቀ፡፡ እናት የልጇን አቋም በእርግጥ ታውቀዋለች፡፡
አባቷ ያሳደጋትም በዚያ እምነት ጸንታ
እንድትኖር ነውና፤ በወሰደችው እርምጃ የተቃወሞ ድምጽ አላሰማችም፡፡
ነገሩን ውስጥ ውስጡን ስታብላላ ቆየችና......
“ሻምበል አደራህን! ትሁቴ ህጻን ልጅ ናት።እንደታላቅ ወንድም ተንከባከባት፡፡ እሷ ምኑንም የማታውቅ አንድ ፍሬ
ልጅ ናት፡፡ ለመጠንቀቁም ቢሆን አንተ ትሻላለህ፡፡ እሷ ምኑን ታውቀዋለች ብለህ
ነው?" የአሁኑ ስህተት እንዳይደገምና፤ በሌላ ጊዜ ተጨማሪ ጉዳት
እንዳይደርስባት፤ ሻምበል ሃላፊነቱን እንዲወጣ በማሳሰብ፤ አደራዋን
አጠበቀች፡፡ እሱም ትህትና ከሆስፒታል እንደወጣች ይዟት እንደሚመጣ
ቃል ገባላት፡፡ በመጠኑም ቢሆን ልቧ ትንሽ እረፍት አገኘ፡፡
“የአንዱአለሜ ወሬስ ? ምነው ጭልጥ ብሎ ጠፋ?" አከታትላ ጠየቀችው፡፡
“እኔ ራሴ ካገኘሁት ሳምንት ሆኖኛል እማማ፡፡ ለፈተናው ዝግጅት ሸፍቷል፡፡ ዘንድሮ አንደኛ ካልወጣሁ ሰው አይደለሁም ሲል የፎከረውን ለመፈፀም ቆርጦ መነሳቱን ትህትና ነግራኛለች። ምንም አያስቡ፤ ፈተናውን እንደጨረሰ እንዲመጣ እነግረዋለሁ።” ምክንያቱ
ብዙ ባይዋጥላትም የሻምበልን የማፅናኛ ቃል ከማዳመጥ በስተቀር አማራጭ አልነበራትም፡፡ዝም አለች፡፡ ከዚያም ሻምበል በግማሽ ልቡ ሆኖ፤ የሆነ ያልሆነውን፤ ሲያወራት ከቆየ በኋላ፤ ተሰናብቷት ወደ ትህትና ሩጫውን ቀጠለ....
ትህትና የቀዶ ህክምና ከተደረገላት በኋላ በአንደኛ ማእረግ እንድትተኛ ያደረገው ሻምበል ብሩክ ነው፡፡ ሻምበል አስፈላጊውን ክፍያ በመፈጸም ንጽህናው በተጠበቀና፤ ተጨማሪ በሽተኛ በሌለበት
አንደኛ ማእረግ ውስጥ እንድትተኛ የፈለገበት ዋናው ምክንያት፤
በሚተኙ በሽተኞች ስቃይ ተጨማሪ የአእምሮ መረበሽ ሊደርስባት ይችላል በሚል ፍራቻ ነው፡፡
ለቀዶ ጥገናው የተወጋችው ማደንዘዣ ስራውን በማጠናቀቁ ለአስቸኳይ ህክምናው በተሰጣት በሀያ አራት ሰአት ውስጥ ከሰመመናዊ እንቅልፉ ነቃችና አይኗን ገለጥ አደረገችው፡፡ ጣሪያውን ተመለከተች፡፡ ዙሪያዋን ቃኘች
የት እንዳለች፤ ምን እንደሆነች፤ በፍጹም
አታውቀውም፡፡ የተወጋችው የእንቅልፍ
መርፌ ፤ በጥይት የቆሰለው ሰውነቷና
እንደ ጉድ የፈሰሰው ደሟ መላ
አካሏን ድቅቅ አድርጐታል፡፡ከግራ ጆሮዋ ጀምሮ ፊቷ በአጠቃላይ በፋሻ ተሸፍኗል፡፡በክንዷ ላይ የተሰካውን ግሉኮስ ተመለከተችው፡፡ ጠብ ጠብ... እያለ
ይወርዳል። እንደገና አይኗን ጨፈነች፡፡ትንሽ ቆየችና መልሳ ገለጠችው::
እንደገና በሀሳብ ባህር ውስጥ ገባች፡፡ ምን ነበር የሆነው ? የት ነው ያለችው? እዚህ ለምን መጣች? እሷ ማን ነች? ቆይ .. ቆ ይ.. ምን ነበር የሆነው ? የሆነ
ነገር ብዥ ፧ ብዥ አለባት እንዴ ?..
መርካቶ ውስጥ እንደሻውን... ከዚያ በኋላ እራሷን... እንዴ?
ምንድነው ነገሩ? እሷ ሞታለች አይደለም እንዴ? በሰማይ ቤት ነው ወይንስ በምድር ላይ ያለችው? በዚያች በተሰናበተቻት ምድር ላይ? በፍጹም ሊሆን አይችልም! እንቆቅልሹም ሊገባት አልቻለም፡፡ ከዚያም ፊት ለፊትዋ የተቀመጡትን ሰዎች ትኩር ብላ ተመለከተቻቸው፡፡
ብዥ ፤ ብ ዥ ፤አሉባት አላወቀቻቸውም :: እነሱ በሀዘን ተውጠው አይን አይኗን ይመለከቷታል፡፡ እንደገና ትኩር ብላ ከመታሸግ በተረፈው በቀኝ አይኗ አየቻቸው፡፡ አሁንም አላወቀቻቸውም፡፡ እንቅስቃሴ የላትም፡፡እዚያ ከፊት ለፊቷ ሆነው በሀዘን ኩርምት ጭብጥ ብለው የተቀመጡትን ሰዎች በድጋሜ በጥንቃቄ ተመለከተቻቸው፡፡ የሆነ ምስል መጣላት፡፡
የምታውቀው ምስል በርቀት የምታውቀው ምስል.. አዎን
ታውቃቸዋለች እንጂ !! እንዴ..? በሚገባ ታውቃቸዋለች :: ቀስ ብላ በለሆሳስ ተጣራች "ብ..ሩ. ኬ..... አ . ዜ. ቢ . ና
እህህህ....." በዚህ ጊዜ አዜብ ቀስ ብላ ተነሳችና ሄዳ አጠገቧ ቆመች፡፡ ብሩክም አዜብን ተከትሎ ወደ አልጋው ተጠጋ፡፡ሻምበል እንደዚያ ሆና ሊያያት አልቻለም :: እንባው አመለጠውና ቀስ ብሎ ጉንጮቹን
እያቋረጠ ፈሰሰ፡፡
“እ ማ ዬ...ደ ህ...ና. ነች? ..አ.ን.ዱ.ዬስ..?"
"ሁለቱም በጣም ደህና ናቸው፡፡ ስለ እነሱ ምንም አታስቢ፡፡ እኛ አለን፡፡ አሁን ዋናው ማሰብ ያለብሽ ስለራስሽ ጤንነት ብቻ ነው እሺ?” አዜብ ነበረች፡፡
“እ..ሺ በደከመ ድምጽ፡፡
“ትሁት አዜብ የምትልሽን ስሚያት፡፡ስለ እማማ ምንም የሚያስጨንቅሽ ነገር የለም፡፡እሳቸው አንቺ ስለጠፋሽባቸው ነው ትንሽ ያሰቡት እንጂ በጣም ደህና ናቸው፡፡ ቶሎ ድነሽ ሄደሽ እንዲያዩሽ
በሃሳብና በጭንቀት ራስሽን መጉዳት የለብሽም፡፡ እሺ? አንዱ አለምም ድኗል ማለት ይቻላል፡፡ሰሞኑን መጥቶ ይጠይቅሻል እሺ?” ጉንጮቿን
እየዳበሰ፡፡
እሺ” አለች በድጋሜ፡፡ በዚያው ድክምክም ባለ ድምጿ። አሉኝ የምትላቸውና የምትተማመንባቸው ሁለቱ ጓደኞቿ፤ ደራሾቿ ፤ በዚህ በክፉ ቀን እንኳ ከጐኗ

ሳይለዩ ፤ አጠገቧ ቆመው ተስፋ
ሲሰጧት፤ እናቷን የማየት ጉጉት፣ ወንድሟን በድጋሜ የማግኘትን
ፍላጎት፤ እንደገና የመኖርን ተስፋ፤ እነዚያ ዳግመኛ ላትመኛቸው የተሰናበተቻቸውን ነገሮች በድጋሜ ለማግኘት፤ ልቧ እንደ አዲስ ተመኘ፡፡
በዚሁ መካከል መርፌ የምትወጋበት ሰአት ስለደረሰ፣ ነርሷ መድሀኒት የያዘውን ጋሪ እየገፋች ወደ ክፍሉ ስትገባ፤ አዜብና ብሩክ ክፍሉን ለቀው ወጡ፡፡ ደግነቱ ሁለቱም ወንድምና እህት የተኙት እዚያው ጥቁር አንበሳ በመሆኑ፤ ለአስታማሚዎቻቸው ሩጫን ቀንሶላቸዋል..... አንዱ አለምን የምትንከባከበው አዜብ ነች፡፡ በተለይ ለዚህ ያበቃሁት እኔ ነኝ የሚል የጥፋተኝነት ስሜት ስለተሰማት፤ ይህንን
ስሜትዋን ለማስወገድ የማታዘጋጅለት የምግብ አይነት አልነበረም፡፡
እዚያ የካቲት አስራ ሁለት ሆስፒታል እየሄደች ከእናቷ ጋር ከመፋጠጥ
እዚሁ ሁለቱን ለመንከባከብ፤ ብሩክ ደግሞ ከሰራተኛዋ ጋር ሆኖ ወይዘሮ ሃመልማልን እንዲንከባከብ፤ ክፍፍሉን ያደረገችው እሷ ናት፡፡ሰራተኛዋ ጥሩ፧ ጥሩ፧ ምግብ እንድታደርስላት በማድረግ በኩል ግን ወደ ኋላ አላለችም፡፡ አንዱአለም አሁን እየዳነ ነው፡፡ በተለይ ሻምበል እዚያ ሆሰፒታል መጥቶ ከጠየቀው በኋላ ደስተኛነቱ በእጥፉ
ጨምሯል፡፡ ትህትና ራስ ደስታ ሆስፒታል ገብታ የጠፋችበትን ምክንያት አዜብ ከነገረችው በኋላ ፧ ሻምበልም ለጥቂት ቀናት የጠፋው በዚሁ ችግር ምክንያት መሆኑን ገመተ ። እህቱ በመጥፋቷ
ብትናፍቀውም፤ እሷን ተክታ አዜብ የምታደርግለት እንክብክቤ ከፍተኛ
በመሆኑም ተፅናንቷል፡፡ አዜብ ለደረሰበት አደጋ ዋና ምክንያት ራሷን አድርጋ ስለቆጠረች ቶሎ ድኖ እንዲወጣ የማታደርገው ጥረት አልነበረም፡፡ ቆንጆ ምግብ አዘጋጅታ ትመጣና፤ እዚያ እጎኑ እቅፉ ስር ገብታ ስታጎርሰው ፤ ከዚያም አፉ ላይ የሚቀረውን ምግብ
ልታፀዳዳለት ከንፈሮቹን እብስ ፤ እብስ ስታደርጋቸው፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሄዳ ከአንገቱ ቀና በማድረግ፤ በክንዷ ላይ ጣል ታደርገውና አጥሚት ስታጠጣው ፤ ከዚያም ራቁት ክንዷ ራቁት ክንዱን
ሲያሞቀው፡፡ ከዚያም ስውነቱን ሲግል ! በዚያ የግለት ስሜት የተነሳ ደግሞ ከዚያ በፊት ስለሷ አንድም ጊዜ ተሰምቶት የማያውቅ ፆታዊ ንዝረት ሲነዝረው፤ በተለይ ደግሞ አስተያየቷ ... አይን አይኑን
በስስት እያየች፤ ስልምልም፤ ስልምልም... ስትልበት፡፡ ይሄ ሁኔታ በየጊዜው እየተደጋገመ ሲመጣ ፤ ለሷ የተለየ
ስሜት እያሳደረ መጣ፡፡ ትኩር ብሎ ሲመለከታት ይቆይና ለራሱ ግርም ይለው ጀመር አዜብ እንደዚህ ቆንጆ ነበረች እንዴ ? በማለት ራሱን ደጋግሞ ጠየቀ፡፡
እንዴት አይነት ተአምር ነው ? ግን አዜብ እንደዚህ ታምር ነበረ? ለምንድነው እስከዛሬ ድረስ እንደዚህ ቆንጆ መሆንዋን ያላየሁት? አቤት ስትስቅ ደግሞ እንዴት ያምርባታል? ጥርሶችዋ እንደዚህ ያምሩ ነበረ? እስከዛሬ ድረስ እንዴት አላየኋቸውም? የታላቅ እህቴ ጓደኛ ስለሆነች እንደ እህቴ ቆጥሪያት አላየኋትም ነበር ማለት ነው ? ጓደኛዋ ብትሆን ታዲያ ምን ነበረበት? ጓደኝነታቸው የበለጠ ይዳብራል እንጂ፤ ይቀንሳል እንዴ? ራሱን በጥያቄ ያዋክብ ጀመር፡፡ አዜብም እንደዚያ አጠገቡ ሆና
ስታጫውተው ፣ ስታሳስቀው፤ ስትደባብስው፤ ስታጐርሰው፤ በክንዷ ላይ
ጣል አድርጋ፤ እህል ውሃ ስታቀማምሰው፤ ጠረን ለጠረን ሲለዋወጡ፡ ሲለማመዱ
ቀስ በቀስ እሷም ስለ አንዱአለም በልቧ ጥያቄዎችን በማነሳሳት እራሷን መጠየቅ ጀመረች፡፡ እንዴት እስከዛሬ ድረስ የዚህ
አይነት ስሜት ሳይሰማኝ ቀረ? በማለት ተገረመች .ስንቱን የምታተረማምሰዋ ሴትዮ አንዱአለምን የመሰለ ውብ ልጅ ለመቅመስ እንዴት እንዳልቀደመች ደነቃት :: የጓደኛዬ ወንድም ስለሆነ ነው ወይንስ
እንደዚህ እንደአሁኑ አይነት አጋጣሚ ተፈጥሮ ተቀራርበን፡ ተጠጋግተን፡
ጠረን ለጠረን መለዋወጥ ባለመቻላችን? አንዱ አለም እኮ የሚፈቀር ልጅ
ነው፡፡ ወይ ጉድ? ..ይህንን የውስጥ ፍላጐታቸውን በአንደበታቸው
አያውጡት እንጂ አንዳንድ ድርጊታቸው ስለሚመሰክር ልብ ለልብ እየተግባቡ መጡ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በድንገት አይኖቻቸው ሲጋጩ ድንግጥ የማለት፡ የልባቸው ምት የመጨመር፡ የስሜት መለዋወጥ፣ ይሄና ይሄንን የመሳሰሉ ክስተቶች ተደጋገሙ፡፡ በዚያን እለት አንዱ
አለም ከጐኑ ያለው በሽተኛ መተኛቱን ሲያረጋግጥ፤ የሚያጎርሰው : የሚዳብሰው፡ የቀኝ እጇን መዳፍ ወደ ደረደቱ አስጠጋና ገልብጦ ውስጡን በስሱ ከዳሰስ በኋላ ፤ ቀስ ብሎ ሳመው :: በዚ ጊዜ ቀልጣፋዋ ልጅ ጊዜ አላጠፋችም፡፡ ከሱ ይህንን ያክል ፍንጭ
ካገኘች በቂ ነው :: እሷም ቀስ አለችና የውስጥ መዳፉን ሳም አደረገችለት፡፡ ከዚያም ወደ ደረቱ ትንሽ ሳብ ሲያደርጋት የገፈተሯትን ያህል ሄዳ ደረቱ ላይ ቀስ ብላ ወደቀችና ፤ ሰው ሳይመጣ ፤ ከንፈሩን
ሳም አደረገችው፡፡ እሱም ሳማት፡፡ መሳም ብቻ ሳይሆን በደንብ አድርጉ መጠጣት፡፡ ጣፈጠችው፡፡ ጣፈጣት፡፡ ፍቅር ተጀመረች፡፡ ከዚያ በኋላማ መነፋፈቅ፡ መቅበጥበጥ : ሲገናኙ ምኑ ይጠየቃል ? ትንሽ ሲለያዩ ፍዝዝ እያሉ መተያየት፡ መደባበስ ሆነ ስራቸው፡፡ ትህትና ከጊዜ ወደ ጊዜ ጤናዋ እየተሻሻለ መጣ :: አዜብና ሻምበል ብሩክ ከላይ እታች በማለት የሚደረገውን ሁሉ እያደረጉ ናቸው፡፡ የእንደሻው ወላጆች
እነሱ ለትህትና ህይወት " እንደዚያ ሲሯሯጡ ፤ ደግሞ የልጃቸውን ህይወት ለማትረፍ ከላይ እታች እየተሯሯጡ ብቻም
ሳይሆን፤ እየተራወጡ፤ ናቸው፡፡ የእንደሻው ጉዳት ከባድ ነበር፡፡ በተለይ....

👍2😁1
#ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ
...ማሰብና መጀመር የተለያዩ ሆነውበት ተቸግሯል አቤል ። ሐሳቡ በጣም ይመጥቅበታል ።ሊጽፍ ያሰበው ነገር መጽሐፍ ይሆንበታል ። ለሐሳቡ ወግ የሚያግኝለትም አይመስለው ። ወረቀቱን ይዞ ቁጭ ሲል ግን ከብዕሩ ጠብ የሚል ነገር ይጠፋል ። ባዶ ወረቀት ላይ ማን ፎር ሂምሰልፍ” ከሚል አርዕስት ጋር መፋጠጥ ብቻ !
“ችግሩ ከቋንቋው ይሆን ? ” ሲል አሰበ ። በሰው ቋንቋ ከምቸገር ሓሳቤን እንደ ልቤ ላንቆረቁርበት በምችለው በራሴ ቋንቋ ለምን አልፅፍም?።
ባዶውን ወረቀት ከአጠገቡ አገለለና መጽሐፍ ገለጠ ለጽሑፉ የሚጠቅመውትን መጽሐፎች መርጦ አውጥቶ ጠረጴዛው ላይ ከምሯል ። መጻፍ ከመጀመሩ በፊት በዚህ አርዕስት
ጐዳይ ላይ የተጻፉ ብዙ መጽሐፎች ማንበብ እንዳለበት ስለ ተረዳ፡ ሰሞኑን እያነበበ ነበር። ችግሩ ግን አለ ከሚያነበው መጽሐፍ ላይ ብዙ ሰዓት መቆየት አለ መቻሉ ነው ከመጽሐፉ ውስጥ ጠቃሚ ሐሳብ ሲያገኝ የእሱ ሐሳብ ቀድሞ ይሐጥቅና ጻፍ ጻፍ ይለዋል
አሁንም ከተቀመጠበት ተነሥቶ ትንሽ ተንጎራደደ ። ከመንጐራደዱ ጋርም የሚጽፈው ነገር ብልጭ አለለት
ሰው ከራሱ ጋር የሚጣላው ለምንድነው ? በግል ምኞትና ግብ አእምሮው ተወጥሮ ሲጨነቅ ነው ። ነገር ግን የሰው ልጅ የመጨረሻ ግቡ እኛ እንጂ እኔ መሆን የለበትም ከራሱ ጋር ሊታረቅ የሚችለው በዚህ እምነት ተጠምቆ ከግሉ ይልቅ ለማኅበራዊ ችግር ክብደት ሲሰጥና ደስታውን ከኅብረተሰቡ ጣፋጭ ሕይወት ውስጥ ለማግኘት ሲሞክር ነው ። ሰው በመጀመሪያ ለሕያውነቱ ከፍተኛ ግምት መስጠትና ማድነቅ አለበት ። ይህን ካመነ ደግም ማናቸውም በውስጡ የሚከሠቱ ነገሮች የሕያውነቱ ነጸብራቆች ስለሆኑ
እንዳመጣጣቸው ተቀብሎ መፍታት እንጂ ለችግሮች ምረታት የለበትም ። ሰው በትግሉ በተጸጥሮ ላይ ፍጹም የበላይነቱን መቀዳጀት አለበት ።
እቤል መጻፍ የፈለገውን መቋጠሪያ ሐሳብ ያገኝ መሰለው ደስ ደስ አለው። በአንጻሩ ግን ከውስጡ አዘናጊ ስሜት ይታግለው ነበር ። " አይ አቤል ፤ አሁንስ ጅል ሆንክ አዲስ ሐሳብ ያፈለቅክ መስሎህ ነው ? ስንት ፈላስፋዎች ብለውት ብለውት የበቃውን ነገር እንዴት እንደ አዲስ ታነሳዋለህ ? እባክህ ይልቅ ያልተሳበ አዲስ ነገር ፈልግ ።ለዚያውስ በዚህ ዓለም ላይ ምን ያልተባለ ነገር አለ ?”
አቤል የራሱ ስሜት አስጠላው ለምንድነው ስሜቱን ገንቢውን ትቶ አፍራሹ ላይ የሚሮጠው? አዲሱ ሰው ሁሉን ነገር “ ተብሏል” እያለ ራሱን የሚያዘናጋ ከሆነና እጁን አጣምሮ ከተቀመጠ ነገር ተበላሸ ከአሁን በፊትም ማንም ቢሆን ፍጹም አዲስ ነግር ይዞ አልተሄዶም ። ሁሉም እውቀቱን የቀመረው በተከሠረት ወይም በተባለ ነገር ላይ እየቆመ ነው።እና አቤል አቤልሽ ! ይልቅ ደፍረህ ጀምር የአቅምህን ሞክር ፤ ጫር ! ” አለና እንደገና ቁጭ አለ።
እንዴት እንደሚጀምረው ቁልጭ ብሎ ታየው " ሰፊ አርዕስት ነው የያዘው ፤ስለዚህ በንዑስ ርዕስ ከፋፍሎ እያንዳንዷን ንዑስ ክፍል በጽሑፍ ማስረጃና በሕይወት ገጠመኝ
አስደግፎ ማስኬድ ! ሰውነቱን አንዳች የደስታ ስሜት ወረረው ። ሐሳቡ ካለበት መጥቆ ሲሮጥ ንዑስ ርዕሱ ልጓም ሆኖ
ያዘለት ። ሰው የራሱ ወዳጅ የሚሆንበትን ሐሳብ ከመደርደሩ በፊት ከራሱ ጋር የሚጣላባቸውን ሁኔታዎች ለመደርደር ተገደደ ። እዚህ ላይ ለመድረስ ደግሞ፥ ሰው በተፈጥሮ ይዟቸው የሚወጣውንና ከአካባቢው የሚቀስማቸውን ዐብይት ጸባያት ይዞ መነሣት ነበረበት ። የጅማሬ ሐሳቡን በዚህ ንዑስ ርዕስ ሥር አጠቃልሎ ፥ “ በዚህ ዓለም ላይ ታላቅና
ክቡር ፍጡር ነው” ሲል ጀመረ ።
በተመስጦ እየጻፈና ደጋፊ ሐሳቦች ፍለጋ መጽሐፎች እያገላበጠ ትንሽ እንደ ቆየ ፡ ሞኒካ ሻይ ይዛለት መጣች።
የአምስት ሰዓት ሻይ ነበር ። ጊዜው ከምኔው እንደ ሮጠ ገረመው
“ ጽሑፉን ጀመርኩት “ ኮ ” አላት ፡ ገና እየገባች ሳለች ።
“ ዳስ ኢስት ሸን ” አለችው ሞኒካ • ፈገግ ብላ ደስታዋን በመግለጽ ።
አቤል ይህንኑ “ ጀመርኩት ” የሚለውን ቃል ለዮናታንም ለመንገር ተቻኮለ ። እንዲያመጡለት የጠየቃቸውን የቀድሞ የተበላሹ የጥናት ጽሑፎቹን ባመጡለት ጊዜ ፥ የገባላቸው ቃል ትዝ አለው ። ወረቀቶቹን ተቀብሎ ፊታቸው በክ
ብሪት ካቃጠለ በኋላ ፥ አሁን ከፊትዎ የቆመው አዲሱ አቤል ነው ። አዲስ ጽሑፍ አዘጋጅቶ ያሳይዎታል ” ብሏ
ቸው ነበር ። አሁን ዮናታን የሚመጡበት የምሳ ሰዓት ራቀበት።
ሞኒካ አሁን እቤል ያለበትን ጥሩ ስሜት ካረጋገጠች በኋላ፥ ወደ መኝታ ክፍሏ ሔዳ አንድ ጉርድ ፎቶግራፍና የታሸገ
ኢንቬሎፕ ይዛ ተመለሰች ።
“ ይህችን ልጅ ታውቃታለህ ? ” አለችው ፥ ፎቶውን ዐይኑ ሥር አቅርባ ።ፉት ብሎ የነበረውን ሻይ ቶሎ መዋጥ አቃተው
የልብ ትርታ የሚቀሰቅስ ምስል ! አስደንግጦ የሚያስደስት ምስል ! “ ማወቅ ብቻ ነው!? አምልኬባታለሁ እንጂ!” ሊላት ፈለገ። የሞኒካ ቶሎ መልስ መፈለግ ግን፥ አቤል ነገሩን አመዛዝኖ እንዲናገር ጊዜ አልሰጠውም ።
አዎ ! አላት ፥ ሌላውን ስሜቱን ዋጥ አድርጎ
“ የት ? ”
“ ዩኒቨርስቲ ውስጥ አንድ ሴሚስተር ሙሉ በዐይን ፍቅር የማቀቅኩላት ናት” አላት ቃናው በተለወጠ ድምፅ ።
“ ከዚህ ፎቶዋ ጋር ደብዳቤ ልካልሃለች ” አለችና የታሸገውን ፖስታ ሰጠችው። ፈጥኖ ተቀበላት ። ነገር ግን ፈጥኖ መቅደድ አልቻለም ። አንዳች ነገር እጁን የያዘው ይመስል ተንቀጠቀጠ ።
በሚያነብበት ጊዜ ነጻ እንዲሆን በማሰብ ሞኒካ ክፍሉን ለቅቃለት ወጣች ። ደብዳቤዉንና ፎቶዉን ከእስክንድር
ከተቀበሰች ሁለት ቀን አልፎአል ።ለአቤል ወድያውኑ ያልሰጠችው እንዲህ ጥሩ ስሜት እስኪታይበት በመጠበቅ ነበር።
አቤል ደብዳቤዉን ግልጾ ማንበብ ጀመረ፡-
አቤል፥ ስምህን ደብዳቤ ላይ ለመጀሪያ ጊዜ ስጽፈው የተሰማኝን ስሜት ልገልጽልህ አልችልም ። የምወደውንና
የምፈልጎውን ቃል መጥራት ለምን እንደሚያስፈራኝ ሊገባኝ አልቻለም ። የዚህን ደብዳቤ ረቂቅ ብታየው ትግረማለህ ። ስርዝ፤ ድልዝዝ ብቻ ነው። ከስሜቴ ጋር ክፉኛ መታገሌን በዚህ መገመት ትችላለህ ።
ይህን ደብዳቤ እንድጽፍልህ ያደፋፈረኝ እስክንድር ነው ። ጥሩ ጓደኛ ነው ያለህ እሱ ባይገፋፋኝ ኖሮ እንዲሁ ስሜቴን አምቄ ውስጥ ውስጤን እሠቃያለሁ እንጂ ከቶም አልሞክረውም ነበር ። አንተ በእኔ የተነሣ የተቀበልከውን ስቃይ ስሰማ ለብቻዬ ተደብቄ ስቅስቅ ብዬ ነው ያለቀስኩት ፤ግን ጥፋተኛው ማን ነው ? አየህ አቤል ! እኔ መቼም ሴት ነኝ ፤ደፍሬ መጥቼ እንዳነጋግርህ የአካባቢ ተጽዕኖ
አለብኝ ። አንተ ግን በሩቅ ከምትሠቃይ ቀርበህ ! ብታነጋረኝና እወድሻለሁ ብትለኝ ምን ነበረበት ።
“ሕመምህ ጠልቆ የተሰማኝ አሁን ነው ። ለካስ ፍቅር ተገጣጥሞ ካልሰመረ ሥቃይ ነው። በካምፓስ ውስጥ አንተን በዐይኔ ካጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ያለሁበትን ሁኔታ ልገልጽልህ አልችልም ። አንተን ለማየት እናፍቃለሁ ፣ ብቸኝነት ያሰቃየኛል ፥ አካባቢዩ ያስጠላኛል ፤ጥናት ያንገሸግሸኛል ፣ሁሉ ነገር ከብዶና መርሮ ይታየኛል ። እውነቴን ነው የምልህ
የተፈጥሮ ክሥተት ባይሆን ኖሮ፡ አፍላ ፍቅር ፈጽሞ እያስመኝም
“ በመጀመሪያው ሴሚስተር ከትምህርቴ እንዳልሰናከል እፈራ ስለ ነበር፡ ፍቅርህን ክፉኛ ተቃውሜዋለሁ›
አሁን የተረዳሁት ነገር ቢኖር ግን ፥ ፍቅር ታግለው የሚጥሉት ነገር አለመሆኑን ነው ። ገና መጀመሪያ የዩኒቨርስቲውን ግቢ ስረግጥ ካየኸኝ ጀምሮ በዐይን እንደምትከተለኝ ያልተረዳሁልህ እንዳይመስልህ እያንዳንዷ እይታ ከንግግር የበለጠ ተሰምታኛለች። እንዲያውም አንዳንዴ ቃላት

❤1👍1🥰1
መግለጽ የማይችሉትን ዐይን እንደሚናገር ተረድቻለሁ ።በተለይ ፥ ታስታውስ እንደሆነ እንድ ቀን እኔ ፡ ማርታና ቤተልሔም ከካምፓስ ወጥተን ስንሔድ ምን ያህል በቅናት ስሜት እንደ ተመለከትከኝ መቼም አልረሳውም ። አንተ ሌላ ቦታ የምንሔድ መስሉህ ሊሆን ይችላል ። ነገር ግን የሒድነው ሰርግ ቤት ተጠርተን ነበር። ታዲያ ያኔ የዋልኩት ውሎ ውሎ አይበለው ! በቅናት የተከተለኝ ዐይን ዐይኔ ውስጥ ቀርቶ ፥ ቀኑን ሙሉ ሲለበልበኝ ነው የዋለው ...
ይህን ሁሉ የምጽፈው የቆየ ቁስልህን ለመቀስቀስ አይደለም ። በአንድ በኩል ደብዳቤው በእርግጥ ከእኔ ከት ዕግሥት የተላከልህ መሆኑን እንድታምንበት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ስሜትህ ያልገባኝ ወይም ሥቃይህንን ያልተረዳሁልህ እንዳይመስልህ ነው ።
“ከላይ እንደ ገለጽኩልህ፡ችግሩን በመፍራት ፍቅርህን ታግዬ የማሸንፈው አልሆንኩም ። ብሞክረውም አንተን መርሳት ፍጹም የማይቻል ሙከራ ሆነብኝ። ምክንያቱም በአካባቢዬ ሴቶች ስለ አንተ ሲያወሩ በሰማሁ ቁጥር ስሜቴ ይቀሰቀሳል። ስምህን የሚያውቁት፡ “ ያ ጎበዙ ተማሪ” በሚል ቅጽል ነው የሚጠሩህ ። ይህ ቃል በእኔ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ነው ያሳደረብኝ ። በጉብዝናው በሚደነቅ ተማሪ መፈቀር ደስ ያሰኛል። ግን ደግሞ ግንኙነታችን ከዐይን አለ ማለፉን ሳመዛዝን ያበሽቀኛል ። ያ ሁሉ ዐልፎአል ። አሁን ስሜቴን አፍረጥርጨ ያወጣሁልህ ይመስለኛል ። አንተም ግልጽ ሁንልኝ ። ፍቅርን ሕመም ያደረግነው እኛው ነን ፤እባክህ ጐንለጐን ቁጭ ብለን አንተ በእኔ ፥ እኔ ባንተ እንደሰት ። ትምህርትህ በእኔ ምክንያት በመቋረጡ አዝናለሁ ። የምረዳህም
ሆን የምክስህ ነገር ቢኖር፡ ከወዲሁ ሙሉ ፈቃደኝነቴን እገልጽልሃለሁ ። በእኔ ግምት ካሳው ፍቅር ነው ፍቅሬን ሰጥቼህ ፍቅርህን ከመቀበል ሌላ ምን መፍትሔ ይኖራል ?
ያንተው ትዕግሥት አዳነ ”
አቤል ደብዳቤውን ሁለቴ አንብቦ በዝግታ አጠፈው ።እውስጡ ያነበበው የፍቅር ቃላትን ብቻ ሳይሆን እንባም ጭምር ነው ትዕግሥት ፊቷ በእንባ ሳይታጠብ ይህን
ደብዳቤ ጻፈች ማለት ዘበት ነው ። ጽሑፉን ያነበበ ሳይሆን ድምጿን የሰማ መሰለው ። ግን በእርግጥ ትዕግሥት እንዲህ ግልጽ ሆና የውስጧን የምትናገር ሴት ትሆን ? ማነው ጥፋተኛው ? ” የሚለው ቃል ታወሰውና፡ “እውነት ማነው?” ሲል አሰበ ። እሷንም ራሱንም ጥፋተኛ ማድረግ አልቻለም ። አንዲት የፍቅር ቃል እወድሻለሁ ብትለኝ ” ያለችው አንጀቱን በላው ። ነገር ግን ቃሏ አንድ መሆኗ ሳይሆን ክብደቷ ነው ለትዕግሥት ያልገባት ። ይህችን በፍቅረኛ ፊት መተንፈስ መቻል ምንኛ መታደል ነው !
ስለ እስክንድር አሰበ ። ለደብዳቤዉ መጻፍ ያደረገው ጥረት አስገረመው ። ከአሁን በፊትም እሱን ለመርዳት ያዶረገውን ሙከራ ሁሉ ታወሰው ። ከራሱ ጋር ተጣልቶ በሰይጣናዊ ግፊት ፎቅ ላይ በቆመበት ጊዜ የደረሰለት ዕለት ትዝ
አለው ። “ እባክህ ችግርህን ንገረኝና ልረዳልህ ብቻህን አትጨነቅ” በማለት አቤልን የወተወተበትም ጊዜ ነበር።
እና አሁን ጥረቱ ፍሬ አስገኘ ።
“ አንብበህ ጨረስክ ? ” አለችው ሞኒካ • ተመልሳ መጥታ ። ዐይኑ ዕንባ አቅርሮ ተመለከተች ። አቤል በትዕግሥት የፍቅር ቃላት ልቡ ተነክቶ የፍቅር ዕንባ ሲያነባ ከአሁን በፊት በእሷ ምክንያት የደረሰበት ቁስል እየሻረለት ነበር ።
አዎ ጨረስኩ ” ኣላት ዝግ ባለ ድምፅ ዐይን ዐይኗን እያየ።
"እንዴት ነው ? ?
ድንቅ ነው ፤ ሸጋ ነው ! ”
እኔም መልስ መጸፍ ይኖርብኛል ” አላት ጸጉሩን እያሻሸ።
እዚሁ ድረስ ትመጣልሃልች ደብዳቤ መጻፍም አያስፈልግህ ” አለችው ሞኒካ ፈገግ እንዳለች ።
"መቼ ?
"እሑድ ጠዋት"።
የያዘውን ቀን አሰበ ።ሐሙስ ነው ለእሑድ ገና ሁለት ቀንና ሦስት ሌሊት ይቀረዋል ። እንዴት ይደርስ ይሆን ?የትዕግሥትን ፎቶግራፍ ከጠረጴዛው ላይ አንሥቶ እንደገና ተመለከተው ።
አቤል በዚህ ሐሳብ ውስጥ በመዋዠቅ ላይ እንዳለ የምሳ ሰዓት ደርሶ ዮናታን መጡ ።ከምሳቸዩ በፊት ወደ ጥናት ክፍሉ ወስዶ ያስተናገዳቸው አቤል ነበር ።
“ ጽሑፉን ” ኮ ጀመርኩት! ” አላቸው ፡ በደስታና በኵራት ድምፅ ።ግሩም ! ” አሉት ዮናታን ፡ ጠረጴዛው ላይ ያሉትን
ቁሳቁሶች እያዩ ። የትዕግሥት ፎቶግራፍ ከመጽሐፉና ከወረቀቶቹ ጐልቶ ታያቸው ። ሊጠይቁት አሰቡና ስሜታቸውን ቆንጠጥ አደረጉ ።አሁንም እንደ ድሮው ይደብቃቸው ይሆን ?
እሷም ልትመጣ ነው ፤ ደብዳቤዋ ደርሶኛል አላቸው : ዐይናቸውን ተከትሉ ስሜታቸው ያረፈበትን በመገመት ።
ግሩም ! ሥራና ፍቅር ተገጣጠሙ በለኛ ! ” አሉት ደስታ ፈንቅሎአቸው ።
ዐይናቸው ከፎቶግራፉ ወደ ጥናት ጽሓፉ ሲሸጋገር ደግሞ ከወረቀቱ አናት ላይ ፡ “ በዚህ ዓለም ላይ ታላቅና ክቡር ፍጡር ሰው ነው የሚለው መንደርደሪያ ደምቆ
ተመለከቱ ።
“ ፍጹም ጤናማ አመለካከት ነው ፤ጤናማ ኅብረተሰብ የጨዋማ ግለሰቦች ውጤት ነው ብለው አሰቡ ።
“በጅማሬህ በጣም ተደስቼአለሁ ። ቀጥልበት ታላቅ ሥራ ሠርተህ ታላቅ ሰው የምትሆንበትን ጊዜ በተስፋ እጠብቃለሁ አሉት ።
ፈገግ እያለ ዐይን ዐይናቸውን ተመለከታቸው ያ መነጽሩን ዐልፎ ዐይናቸው ውስጥ ፍቅር ይነበባል ።
የመጨረሻ ዐረፍተ ነገራቸው ጭንቅላቱ ውስጥ ደወለበት።...

#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
እነሱ ለትህትና ሕይወት እንደዚያ ሲሯሯጡ ደግሞ የእንደሻው ወላጆች ደግሞ የልጃቸውን ህይወት ለማትረፍ ከላይ ከተች እየተሯሯጡም ብቻ ሳይሆን እየተራወጡ ናቸው። የእንደሻው ጉዳት ከባድ ነበር። በተለይ አንዷ ጥይት የራስ ቅሉን በስታው ስላለፈች፤ የአእምሮ ቀውስ
እንዳያስከትልበት፤ ከፍተኛ ስጋት አለ፡፡
በተፈጠረው አደጋ ምክንያት የእንደሻው ወላጆችና የአዜብ ወላጆችም ግንኙነት አቋርጠዋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ...
"ያቺን የተረገመች ልጅ አምጥታ ልጃችንን ልታስገድለው የነበረችው አዜብ ነች በሚል ሲሆን፤ ፀቡን ከአዜብ ጋር ብቻ ሳይሆን ከቤተሰቦቿ ጭምር አድርገውታል :: እነሱ እንደዚያ ብለው ይናገሩ እንጂ ፤ የአዜብ ወላጆች ሁኔታው ሊፈጠር የቻለው አለሌው ልጃቸው
በፈፀመው ተደጋጋሚ አስነዋሪ ድርጊት ሳቢያ መሆኑን ሲያውቁ የክርስትና ልጃችን ነው በሚል ምክንያት ብቻ ፤ በትህትና ላይ ሊፈርዱባት
አልደፈሩም....
"ሁሉንም ስራው ያውጣው በማለት መጨረሻውን ለማየት እየተጠባበቁ ናቸው፡፡ ትህትና ጤናዋ በከፍተኛ ፍጥነት እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም፤ ጐን ለጐን በነፍስ ማጥፋት ሙከራ ወንጀል በአቃቤ ህግ ክስ ተመሰረተባት፡፡ አዜብና ብሩክ ይህንን እንዳወቁ ቀጣዩ ትኩረታቸው
በምን ላይ መሆን እንዳለበት በስፋት ተመካከሩ፡፡ ከዚያም አንዳንድ
በመከላከያነት ይጠቅማሉ ያሏቸውን ማስረጃዎች ለማሰባሰብ ፤ ሁለቱም
በየፊናቸው ሩጫ ጀመሩ፡፡ ለዚህ ጉዳይ አበራ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገመቱ :: ምክንያቱም አበራ በእንደሻው ክህደት የደረሰበትና፤ በትህትና ላይ ስለተፈፀመው ወንጀል በሚገባ የሚያውቅ የአይን ምስክር ስለነበረ ነው፡፡ አበራ በእንደሻው ስለተፈፀመበት ክህደት ለአገሩ ሁሉ ሲያወራ ለአዜብም አጫውቷት ነበር ፡፡
ከዝምድና ይልቅ ገንዘብን አስበልጦ አስር
አመት ሙሉ ያጠራቀምኩትን ገንዘቤን ወስዶ ከከበረበት በኋላ ከዳኝ፡፡ በጋራ
እናድግበታለን ብሎ የገባውን ቃሉን አፍርሶ አባረረኝ " በማለት በምሬት ነበር የገለፀላት፡፡ ታዲያ ያ ሁሉ በደል የተፈፀመበት ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ እውነቱንና የሚያውቀውን ከመናገር ወደኋላ ሊል ይችላል? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ በፍፁም ወደኋላ አይልም ስትል ተማመነች፡፡ምክንያቱም እሱ እንደዚያ በንዴት እየተንቀጠቀጠ
ሲነግራት...
“አይዞህ አበራ ተወው፡፡ አንተ ጤና ሁን እንጂ ፤ገንዘብ አላፊ ጠፊ ነው፡፡ በክህደት የተገኘ ገንዘብ ደግሞ የትም አያደርስም፡፡
ከሰራህ ከካደህ ሰው በላይ መሆን ትችላለህ :: አይዞህ! እግዚአብሄር ላንተ ያለውን ምንግዜም አታጣውም " በማለት ትልቅ የማፅነኛ ቃል ለግሳው ነበር፡፡ ያንን
የሰጠችውን የተስፋ ቃል እንኳ አስታውሶ እሺ ይላት ይሆን? ወይንስ እሱም እንደወላጆቹ ተደርቦ ከእውነት ጀርባ ይቆም ይሆን? ልቧ ተጠራጠረ፡፡ ለማንኛውም አለችና ስልክ ደወለችለት :: ስልኩን አነሳና እሷ መሆንዋን ሲያውቅ የሞቀ ሰላምታ አቀረበላት፡፡ ትንሽ እፎይ አለች በልቧ፡፡ለጉዳይ እንደምትፈልገው
ስትገልፅለት፤ በደስታ ተቀብሎ የሚገናኙበትን ቦታ ተቀጣጥረው
ተሰነባበቱ፡፡ በማግስቱ በቀጠሮው ቦታ ቀድሞ የደረሰው እሱ ነበር።
የተፈለገበትን ጉዳይ ስትነግረው...
"ተይ እንጂ አዜብ እቤት ድረስ የወሰድኳት እኮ እኔ ነኝ፡፡በወንጀለኛነት አያስጠይቅህም ነው የምትይኝ?" ሲል በጥርጣሬ ጠየቃት።
"ስለሱ ከሻምበል ጋር በደንብ ተነጋግረንበታል፡፡ አንተን በወንጀል
ተባባሪነት እንዳያስጠይቅህ በቂ ምክንያት ማቅረብ ይቻላል፡፡”
"ለምሳሌ ምን?"
"አበራ ሙት ምንም አትፍራ! በዚህ ጉዳይ አንተ በጥፋተኛነት እንድትጠየቅ የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር ፧ አንተ ይዘሃት የሄድከው ወደ ቀጣሪዋ ቤት እንጂ፤ ወንጀል
ወደሚፈጸምበት ጫካ ውስጥ አይደለም፡ቀጣሪዋ ቤት አደረስካት ማለት፤ እንደሻው ደብድቦና፤ አስገድዶ፧ ክብረ ንፅህናዋን እንዲደፍራት አደረክ ማለት አይደለም :: የቀጣሪዋን ቤት የወንጀል መፈፀሚያ ዋሻ ያደረገው ወንጀለኛ ብቻ ነው ለዚህ ተጠያቂ የሚሆነው፡፡ አይዞህ ምንም የሚያስፈራ ነገር የለውም፡ አበራን ለማሳመን ብሎ ብሩክ ያስጠናትን ደሰኮረችለት፡፡ አበራ ልቡ ትንሽ ተለሳለሰ፡፡
"በሌላ በኩል ብታየው ደግሞ የቀጣሪዋ ባለቤት ልጅ የቅጥር ውል እንድትፈርም ይዘሃት ና ብሎ አዘዘህ :: አንተም ይህን ነገርካት። እሷም እሺ ብላ ሳታስገድዳት በፈቃደኝነት አብራህ ሄደች። ከዚያም አንተ በሌለህበት እንደሻው ወንጀል ፈፅሞባት ደረስክ፡፡ በቃ፡፡ ይህ አይደለም
ታሪኩ? አንተን የሚያስጠይቅህ ምኑ ነው ታዲያ?" ስትል የማደፋፈሪያ
ሀሳብ አዥጐደጐደችለት፡፡
በልቡ ያሳደረው ጥርጣሬ ሙሉ ለሙሉ ባይጠፋለትም፤ በአዜብ አቀራረብ ተስማማ፡፡ እንዳለችውም እሱን በቀጥታ ተጠያቂ ሊያደርገው የሚችል ጭብጥ እንደሌለ ተሰማው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ
ያቺ ምስኪን እንጀራ ፈላጊ ልጅ ፤ በደም ተጨማልቃ ወድቃ ያያት እለት የተሰማው ስሜት ፊቱ ላይ ድቅን አለበት፡፡ በተፈፀመባት ወንጀል ከልቡ አዝኖ ነበር፡፡ በዚህ ላይ ያ ግፈኛ ከሃዲ ከሱቁ ካባረረው በኋላ አሁን አሁን በርካታ ካፒታል በማንቀሳቀስ በቅናት እያቃጠለው
ነው፡፡ በጥይት መቃጠሉን የሰማ እለት " እሰይ የእጁን ነው ያገኘው"ነበር ያለው፡፡ አሁን ደግሞ እሱ ተጠያቂ በማይሆንበት ሁኔታ ለምን ያየውን ከመመስከር ወደ ኋላ ማለት እንደሌለበት ተገነዘበ ፡፡ያየኽውን እውነት መሰከርክ ብሎ የሚፈርድበት ዘመድ እንደማይኖርና፤ ቢኖርም መፅሀፍ ቅዱስ ይዞ በሚፈፅመው መሃላ በውሸት መስክሮ ነፍሱን ማስኮነን እንደሌለበት ተሰማው። እንደሻውን ሊበቀል
የሚችልበትን ይህንን መልካም አጋጣሚ ሊጠቀምበት ወሰነ : እንቢ ቢልስ የት ሊደርስ ? በተለይ አዜብ እየነገረችው
ያለው ፣ ባለስልጣን ፖሊስ ከአዜብ በስተጀርባ መኖሩን ነው፡፡ በተለይ "ሻምበል ጋር በደንብ ተነጋግረንበታል"
ስትለው ምን እያለች እንደሆነ
ገብቶታል፡፡አልመሰክርም ቢል በተባባሪ ወንጀለኛነት ተፈርጆ፣ ለፍርድ እንደሚቀርብ እየነገረችው ነው፡፡ ይሄንን ጭምር አስቦ፤ ልቡ ስለፈራ፤ ያየውን ሁሉ በዝርዝር ሊያስረዳና፤ ለትህትና ድንበሩ የመከላከያ ምስክር ሊሆን ቃል ገባላት፡፡ ቃል መግባት ብቻም ሳይሆን ተጨማሪ ማስረጃ ጠቆማት..
"እኔ ብቻ ሳልሆን በዚያን እለት ሁኔታውን የተመለከተችው የቤት ሰራተኛዋ ወርቅ ያንጥፉም ያየችውን ሁሉ እውነቱን ሳትደብቅ እንድትመሰክር እናደርጋለን :: ደግሞም ትመሰክራለች፡፡ አትጠራጠሪ!
በትህትና ሁኔታ በጣም ነው ያዘነችው፡፡እሷም ስመ እግዚአብሄርን ጠርታ
ያየችውን ሁሉ ትመሰክራለች፡፡ አይዞሽ ! " አላት፡፡ አዜብ ከጠበቀችው በላይ ተባባሪ ሆኖ ስለኣገኘችው፤ በደስታ እቅፍ አደረገችው፡፡ በዚሁ መሰረት አበራና ወርቅ ያንጥፉ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው፤ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተደረገ፡፡ ቀኑን፡ ሰአቱን፡ የድርጊቱን አፈፃፀም፡ ዝርዝር ሁኔታውን፤ በሙሉ በአንድ አይነትና ፤ ተመሳሳይ በሆነ ቃል
መሰከሩ። ያም ብቻ ሳይሆን አንዱአለምን ጋርጠው በሚል ቅፅል ስሙ በሚታወቀው ወሮበላ እንዳይሞት፤ እንዳይድን፤ አደርጐ ያስደበደበው
መሆኑን፤ ራሱ እንደሻው በኩራት ሲናገር መስማቱን፧ ጭምር ገለፀ፡፡
በእርግጥም እንደሻው ያንን ለአበራ የተናገረው፤ ይሄ ይመጣብኛል ብሎ ሳይሆን፤ አንተም አርፈህ የማትቀመጥና ወሬ አበዛለሁ የምትል ከሆነ፤ አስወቅጥሀለሁ፤ የሚል ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ነበር፡፡ ሆኖም በዚህ አጋጣሚ እንደሻውን የደበደበው ጉልበተኛ
ስለታወቀ፤ ወዲያውኑ ታድኖ እንዲያዝ ሲደረግ ፤ አበራ ማንነቱን በማሳየትና የሚገኝበትን

👍2❤1
ቦታ በመጠቆም ፤ ለፖሊስ ሙሉ ተባባሪነቱን አሳየ፡፡ በተለይ ሻምበል ብሩክ "አይዞህ ስለማንኛውም ነገር ፍጹም ስጋት አይሰማህ! ከጐንህ አለሁ! "በማለት ሞራል ስለሰጠው ፤ ተኩራራ።
ጋርጠው በፖሊስ ተይዞ፤ አንድ ሁለት ጊዜ በቃሪያ ጥፊ ሲወለወል፤ ያልተጠየቀውን ጭምር ይለፈልፍ ጀመር፡፡ ከዚያም ቃሉ ተመዝግቦ በማስረጃነት እንዲያዝ ተደረገ፡፡
አንዱ አለም ድንበሩ ሆስፒታል በገባ በሶስተኛ ሳምንቱ ሙሉ ለሙሉ ዳነ፡፡ ሆስፒታል በተኛበት ጊዜ በተለይ አዜብ
ባደረገችለት ከፍተኛ እንክብካቤ ወፍሮ፤ ቀልቶና አምሮበት ሲታይ ሆስፒታል የከረመ በሽተኛ ሳይሆን ጫጉላ ቤት የከረመ ሙሽራ መስሎ ቁጭ አለ፡፡ ሙሉ
ጤንነቱ ተረጋግጦ ከሆስፒታል እንዲወጣ
ከተደረገ በኋላ ግን፤ ስለእህቱ
በየእለቱ የሚነገርውን ልብ ወለድ
ሳይሆን፤ እውነተኛውን ታሪክ ሰማ... ሻምበል ብሩክና አዜብ ከዚህ በፊት እንዳይሰማ የፈለጉበት ዋነኛው ምክንያት ከህመሙ ሳያገግም፤በድጋሜ ሌላ ችግር እንዳይፈጥር ስለሰጉ ነበር፡፡ አሁን ድኖ ከተነሳ በኋላ ግን ሁሉንም ነገር እንዲያውቅ አደረጉ፡፡ የሚወዳት አንድና
ብቸኛ እህቱ የደረሰባትን አደጋ፤ አይኖቹ በእንባ ጭጋግ ተሞልተው እየዋኙና፧ መላ ሰውነቱ በከፍተኛ ሀዘንና ድንጋጤ ተኮራምቶ፤ ሰማ... የወንድሟ ደም ሜዳ ላይ ፈስሶ እንዳይቀር፤ አለኝታነቷን
ልታረጋግጥለት፤ የሱን የደም ዋጋ ፤ ከራሷ የህይወት ዋጋ ፤ አስበልጣ እንደሞተችለት ፤ትልቁንና የመጨረሻውን ለሰው ልጅ ውድ የሆነው ህይወቷን አሳልፋ እንደሰጠችለት፤ አይዞህ አንዱዬ ደምህ እንደዚህ ሜዳ ላይ ፈሰሶ አይቀርም ብላ የሰጠችውን ቃሏን አክብራ ሄዳ፤ ደሟን እንደጎርፍ እንዳፈሰሰችለት፤ መስማት አይቀርምና ሁሉንም
ነገር ሰማ... ይህንን ሁሉ ሰምቶ ካበቃ በሁዋላ ህይወቷን ያተረፈለት አምላኩን አመሰገነ : ይህች እሱንና፤ እናቱን፤ ለመርዳት ከአቅሟ በላይ የሆነውን ከባድ ሃላፊነት ተሸክማ፤ ቀና ደፋ ስትል የኖረችና፤ ከምንም፧ ከማንም፤ በላይ የሚያፈቅራት እህቱን ከእንግዲህ በኋላ ዳግም ለሌላ አደጋ እንዳትጋለጥ፤ ዳግም እንዳትንከራተት፤ ሸክሙን ሙሉ ለሙሉ ራሱ ሊሸከምላት ፤ ከአሁን በኋላ እኔ አለሁልሽ ሊላት፤ ቁርጥ ውሳኔ ላይ ደረሰ... በዚህ ሰአት የጉርምስናው ስሜት ጥርግርግ ብሎ ወጥቶ ሄደና፤ በምትኩ አዲስና የቤተሰብ ሃላፊነት ሸክምን ለመሸከም ቆርጦ የተነሳሳ ሰው ስሜት፤ ሙሉ ለሙሉ በውስጡ ነገሰ፡፡ ከዚያም
ይህንን ሃሳቡን ለማሳካት ከሚረዳው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ደረሰ፡፡
ከዚያም ትህትና ወደተኛችበት ክፍል
በሻምበል ብሩክና በአዜብ መሪነት ወደ ሶስተኛ ፎቅ ወጡ፡፡ይህ ወቅት ትህትና ከፍተኛ ለውጥ ያሳየችበትና ሀኪሞች በቅርብ ቀን እንደምትወጣ ያረጋገጡበት
ወቅት ነበር፡፡
ትህትና አንዱአለምን ስታየው ከደስታ ብዛት የምትሆነውን ነበር ያጣችው፡፡ ሁለቱንም እጆቿን ወደ ላይ ዘረጋችለት፡፡ሄዶ በእቅፏ ውስጥ ወደቀና፤ አለቀሰ፡፡እሷ ደግሞ በተራዋ አባበለችው፡፡እሱ ሆስፒታል ተኝቶ እሷ ስታለቅስ ! እሱ ያባብላት ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ተራው የሱ
ሆነና፤ ናፍቆት ጭምር ሆዱን ስለአባባው አቅፏት አነባ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ አዜብና ብሩከ ሁለቱ እንደዚያ ሆነው ሲመለከቱ ልባቸው የሚረጨው ደም ብቻ ሳይሆን ሀዘንን ጭምር ነበር ማለት ይቻላል፡፡
አንዱ አለም ከዚያች ቀን ጀምሮ እህቱን
የማስታመም ሙሉ ሃላፊነቱን ወሰደና ፤ ለሻምበል ብሩክና፤ ለአዜብ ትንሽ እረፍት
ስጣቸው፡፡ አንዱአለም ከሻምበል ብሩክና
ከአዜብ በስተቀር ምንም መመኪያ የሌላት እህቱ በአልጋ ላይ ውላና፤ እናቱም የአልጋ ቁራኛ ሆና ሳለ፤ እሱ ደግሞ ተጨማሪ ሆኖ፤ ለዚህ መብቃቱ ሲታሰበው እጅግ ይዘገንነው ነበር፡፡
በዚህ አስከፊ ጊዜ ሻምበል ብሩክና አዜብ ባይኖሩስ ?” ብሎ ሲያስብ ደግሞ፤ የሚሰማው ስሜት ከዚያ የባሰ ነው፡፡ ሻምበል ብሩክ አንድ ሰሞን ጥፍት እንዳለ ቢቀር ኖሮ ዛሬ ቤተሰቡ ምን ሁኔታ
ሊያጋጥመው ይችል እንደነበረ ሲያስበው፤ የአእምሮ ሰላም ይነሳው
ጀመር፡፡ ስለዚህ ያንን ውሳኔውን በአስቸኳይ ተግባራዊ በማድረግ
የእናትና እህቱ አስተማማኝ አለኝታነቱን ማረጋገጥ አለበት፡፡ ወቅቱ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ወጣቶችን በባህረኛነት ለመመልመል ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ የሚገኝበት የጦርነት ወቅት ነበር፡፡ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም፤ በባህር ሃይሉ ውስጥ ለመቀጠርና፤ እሱ መስዋእትነትን
ከፍሎ፤ እነሱን የሚወዳቸውን እህቱንና እናቱን በመርዳት አለኝታነቱን ሊያስመሰክር፤ ያለማወላወል ቆርጦ ተነሳ፡፡ እናቱ ሶስት ሳምንት ሙሉ ጠፍቶ የከረመ ልጇን ያየችው እለት ከደስታ ብዛት እዬዬ ብላ ነው ያለቀሰችው፡፡ በተለይ ለሁለት ቀን ልትለያት የማትችለዋን ሴት ልጇን ሁለት ሳምንት ሙሉ ስትጠፋ በህይወት አገኛታለሁ አላለችም ነበር።
በማህፀኗ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት ወይንም ደግሞ ሊነግሩኝ ያልፈለጉት ሌላ ከፍተኛ ችግር አጋጥሟት ይሆናል እንጂ ፤
ልጄ እንዴት ይሄንን ያክል ጨክና ትጠፋለች በሚል ስጋት ተወጥራ
ነበር፡፡ ሻምበል ቀኑ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የሱም ሰበብ ቁጥሩ እየበዛ
ሄዶ፤ አሁን አሁን እያፈረ መጥቷል፡፡ ሁሌም ለተጨማሪ ቀናት በሆስፒታል እንድትቆይ መወሰኑን ነው የሚነግራት፡፡ እንደዚያ እያለ እየዋሸ ጊዜ ይግዛ እንጂ እንዴት ጥይት ጠጥታ ተኝታለች ብሎ
ይንገራት? አንዱ አለም እናቱ እንደዚያ ፊቷ በትኩስ እንባ ተላልጦ ፤
ገርጥቶና፤ ከሰል መስላ ፤ ሲያገኛት ደንግጦ..
"ምነው እማዬ ፊትሽ ምን ሆኖ ነው እንደዚህ የተላላጠው? -
በማለት እያባበለ ጠየቃት። ለጠየቃት ጥያቄ መልስ ሳትሰጠው አቅፍ አድርጋ በስስት እያገላበጠች ከሳመችው በኋላ
"እህትህስ አንዱአለሜ? ትህትናዬስ የት ነው ያለችው ? ልጄስ የት ነች? ነፍሷ አለ? ለመሆኑ በአይንህ አይተሃታል? አንተስ ምነው ከእንባዋ ጋር እየታገለች የጥያቄውን መአት አዥጐደጐደችበት።
"እማዬ ስለ እታለም ምንም ሀሳብ አይግባሽ፡፡ ጋሽ ብሩክ እንደነገረሽ ነው፡፡ሀኪሞቹ ትንሽ ትቆይ ብለው ስላዘዙ ብቻ ነው፡፡ በጣም ደህና ነች፡፡ የከፋ ነገር ቢኖር ካንቺ ይደበቃል እንዴ ?”
በመለመንና፤ እንደ አቅሚቲ ቆጣ በማለት፤ እራሷን በማይሆን ሀሳብ
እንዳትጐዳ መከራት :: እንደዚያ ቆጣ ብሎ ሲናገራት፤ ትኩር ብላ ታየው ጀመር
በጣም አምሮበታል፡፡ እሷ ግን ግምቷ እንደዚያ አልነበረም፡፡ የሆነ ነገር ሆኗል የሚል ስጋት ነበር ልቧን ሲንጠው
የከረመው፡፡ እንደ እናቴ ሳይሆን እንደሚስቴ አውለኝ የሚለው አባባል
ትዝ አላት ::ስለ ትህትናም እሷ ክፉ ክፉውን ታስብ እንጂ፤ እንደ ወንድሟ አምሮባት ልትመጣ እንደምትችል ማሰብንስ ማን ከለከላት?።ይህንን ስታስብ ከልጇ ቁጣ በስተጀርባ መልካም ነገር ታሰባትና.......
ይሁን እሺ" ስትል ትንሽ ተስፋን በልቧ አሳደራ፤ ተፅናናች፡፡ አንዱ አለም ከእነዚያ ዱርዬ ጓደኞቹ ሙሉ በሙሉ ግንኙነቱን አቋረጠ፡፡
ሰሞኑን አዜብ አንድ የሚያምር ጂንስ ሱሪና፧ ቆንጆ ሸሚዝ፤ ገዝታለት እሱን ለብሶ፤ ከዚያ ውፍረትና ቅላቱ ጋር ሌላ ሆኗል።በዚያ ላይ ደግሞ በጣም ከሚያከብረውና ከሚወደው ሻምበል ብሩክ ጋር ስለማይለያዩ ፧ አንዳንድ ቀን ሻምበል ቤት እየሄደ ማደር ጀምሯል፡፡
አሁን የትህትና ተንከባካቢዎች ቁጥራቸው ከሁለት ወደ ሶስት ከፍ
ብሏል፡፡ አዜብ፡ ሻምበል ብሩክ፡
ትህትናና፤አንዱአለም በፈተና
የተፈተኑና፤ የተሰናሰሉ ጓደኛሞች ግንኙነታቸውና ፍቅራቸው እየተጠናከረ ሄዶ፤ ህይወት በራሱ ባቡር አሳፍሮና፤ አቅጣጫውን ቀይሶ፣ አስተሳስሮ ይዟቸው ወደፊት እየተወነጨፈነው ነው። በጭንቀት የእህል ፍላጐቱ ቀንሶና፤ እንቅልፍ የሚባል ነገር ከድቶት የከረመው
ሻምበል ብሩክ ትህትና በቅርብ

ጊዜ ውስጥ ድና ከሆስፒታሉ እንደምትወጣ ከሰማበት እለት ጀምሮ፤ በደስታ ሰሞኑን ያንን ሲናፍቀው የከረመ እንቅልፉን መለጠጥ ጀምሯል፡፡ በድንጋጤው ብዛትና በእንቅልፍ እጦት ሰውነቱ ላይ ይታይ የነበረው ለውጥም እየተሻሻለ መምጣቱ በግልፅ መታየት ጀምሯል፡፡ ሳቅና ጨዋታ የድሮ ወዳጆቹ ሸሸንህ
እንጂ፤ መቼ ከዳንህ? በማለት፤ ከተደበቁበት ተመልሰው መጥተው
በሰፊው እየጐበኙት ስለሆነ፤ በትካዜ ተኮራምቶ” ከከረመው ሻምበል ብሩክ
ውስጥ፤ የድሮው ሳቂታውና፤ ተጫዋቹ
ሻምበል ብሩክ መታየት ጀምሯል፡፡ይህንን ለውጥ እንኳን እሱ፤ የቅርብ አለቃው ሻለቃ ለሜሳ በሚገባ አጤነው በለውጡ ተደስቷል። አሁን ሻምበልን የሚያሳስበው ትህትና ከሆስፒታል ስትወጣ ስለሚጠብቃት ክስ ነው፡፡ በመሆኑም ከአበራ ጋር በየጊዜው ስልክ ይደዋወላሉ፡፡አበራ ለዚህ ጉዳይ በጣም ጠቃሚ ሰው መሆኑን ከተረዳ ጊዜ ጀምሮ..
"አይዞህ እኔ አለሁልህ" በማለት
ከመመስከር ወደ ኋላ እንዳይል፤ አጥብቆ እያደፋፈረው ነው፡፡ አበራ በማያውቀውና ባልሰራው ወንጀል ደግሞ በዚያን የሰው ልጅ ምንም ከየመንገዱ ላይ እየታፈስ በሚታሰርበት፡ በሚገረፍበትና፤ በሚገደልበት ቀውጢ ወቅት፤ ሻምበል ብሩክን የመሰለ ባለማእረግ ዘመድ ማግኘቱ ለራሱ እድል ስለሆነ፤ የእንደሻው
ወላጆች የፈለጉትን ይበሉ እንጂ እንደሻውን ከመበቀል ባሻገር፤ ከዚያ ጉድ ለማምለጥ ጭምር፤ ሻምበል በሚለው መንገድ የሚያውቀውን ሁሉ ለመመስከር ቆርጦ ተነስቷል። በዚህም መሰረት አበራ ለፖሊስ በሰጠው ቃል እንደሻው በትህትና ላይ ስለፈፀመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ያለ ምንም ፍርሃት በዝርዝር
ሲያስረዳ፤ ፍርድ ቤት ቀርቦ ይህንን የእውነት ቃሉን ያለምንም ማወላወል እንደሚመሰክር አረጋገጠ፡፡ አበራ ከዚህ ውሳኔ ላይ ሲደርስ በልጃችን ላይ የመሰከርክ ከሀዲ ብለው ወላጆቹ ምናልባት ቢያባርሩኝ የሚለው ፍርሃቱን ለመቀነስ፤ በታማኝነት ሲሰራ የኖረው ልጅ ከሱቁ ገንዘብ ላይ ድርሻውን ማነሳሳት ጀምሯል፡፡ ቀናት ተቆጠሩ፡፡ ጊዜው
ወደፊት ገሰገሰ፡፡ በዚህ መካከል አንዱአለም በውሳኔው መሰረት ለባህር
ሃይል አባልነት ተመዝግቦ ፈተናውን ያለፈው በጥሩ ውጤት ነበር፡፡ ይህንን ሁኔታ አዜብ ካወቀች ችግር እንደምትፈጥርበት ስላወቀ፤
ደበቃት፡፡ ከአላማው እንዳያደናቅፉት ጉዳዩን ለሻምበል ብሩክ ጭምር ድብቅ እንዲሆን አደረገ፡፡ የሻምበል ምኞት በትምህርቱ ጠንክሮ ጥሩ ውጤት እንዲያመጣና ዩኒቨርስቲ እንዲገባ ነበር። "አለሁልህ” እያለ በሁሉም ረገድ ከጐኑ የቆመውም አንዱ አለም ያለውን ጥሩ ጭንቅላት ተጠቅሞ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደደርስ ከነበረው ፅኑ ፍላጎት በመነጨ ነበር፡፡
እሱ ግን ሃሳቡን ሙሉ ለሙሉ በሻምበል ብሩክ ላይ ለመጣል ካለመፈለጉም በተጨማሪ ለቤተሰቦቹ ያለውን አለኝታነት
ለማረጋገጥ ጭምር በጥልቀት አስቦበት የወሰነው የመጨረሻ ውሳኔ ስለሆነ፤ ይህን ውሳኔውን ማንም እንዳያሰናክልበት ከባድ የግል ሚስጥሩ አድርጐ ያዘው፡፡
ሻምበል ብሩክ እናቱን እያሳከመ ነው
ሻምበል ብሩክ ትህትናን እያሳከመ ነው፡፡ ሻምበል ብሩክ የራሱን ትናንሽ
ወንድሞቹን እያስተማረ ነው፡፡ ሻምበል በዚህ ላይ ለሱም ጠዋትና ማታ ለሻይ እያለ ኪሱን መዳበሱ አልቀረም ፡፡ በዚህ ላይ ሻምበል የራሱን ህይወት ይመራል፡፡ እና ሻምበል ይሄንን ሁሉ እንዴት መሸከም ይችላል? በዚህ ላይ የወታደር ደሞዝ ምን ያክል ነው ? እሱ ከበደኝ አቃተኝ
ብሎ እስከሚናገር መጠበቅ ያስፈልጋል? ሽክምነትስ እስከመቼ ??
እነዚህና፤ እነዚህን፤ የመሳሰሉ ጥያቄዎችን እያነሳ እራሱን ሲጠይቅ
ውሳኔው ይዋል ይደር የማይባል መሆኑን አመነበት :: ስለዚህ ይሄንን የሻምበል ብሩክን ከባድ ሸክም ለማቃለል... እናትና እህቱን አይዟችሁ እኔ አለሁላችሁ ለማለት... ህሊናውን ከወቀሳ ነፃ ለማድረግ... የተገኘውን አማራጭ በመጠቀም የኢትዮጵያ ባህር ሃይል አባል መሆን!! ዩኒፎርሙ ታየው፡፡ መለዮው መጣበት፡፡ በመርከብ ላይ...በቀይ ባህር
ላይ..ቀዘፈ...... በሃሳብ ከነፈ...

#ክፍል_ሃምሳ_ሁለቴ
፡
፡
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ
...የጠዋት ፀሐይ የማንንም ፈቃድ ሳትጠይቅ ፈገግ ብላ በዝግታ ወደ ጥናት ክፍሉ ገባች ። ፈገግታዋ ሙቀት እንጂ
ድምፅ ስለ ሌለው ፥ አቤል ቶሎ አላያትም እያዘገመች የተቀመጠበት ወንበር ላይ ደርሳ ግራ ጐኑን ስትሞቀው ነቃ ከእንቅልፉ ሳይሆን በተመስጦ ይሠራው ከነበረው ጽሑፍ ላይ እና ብዕሩን ወረቀቱ ላይ ወርውሮ በተቀመጠበት ተንጠራራ ። ሰውነቱን አፍታታ ።
እጁ ላይ ሰዓት የለም ። ነገር ግን፥ከንጋቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ መሆኑን ለመገመት አልተቸገረም” ። ከተቀመጠበት
ሳይነቃነቅ ሦስት ሰዓት ያህል መቆየቱ አላስገረመውም ። ከሌሊቱ ዐሥር ሰዓት ከእንቅልፉ እየነቃ እስከ ንጋት ድረስ
መሥራት፡ሰሞኑን ልማድ እያደረገው መጥቷል ። በንጹሕ አእምሮ ስለሚሠራ፥ ፍሬያማ ውጤትም አግኝቶበታል ።
ዮናታን ይህንኑ በመመልከት ለማንቃት እንዲረዳው የሳሎ ኑን ባለደወል የጠረጴዛ ሰዓት መኝታ ክፍሉ ውስጥ አድርገውለታል ። ቀን ቀን ለጥናት ጽሑፉ የሚረዱትን መጽሐፎች ሲያገላብጥ ውሎ በዚች በለሊቷ ሰአት መጻፉ ጥሩ መንገድ
ሆኖለታል።
ተንጠራርቶ ሲያበቃ ከተቀመጠበት ተነሣ ወደ በረንዳ መናፈሻ ብቅ ብሎ ፀሐይዋን ሙሉ በሙሉ ሊሞቃት ፈለግ ። የሰንበት ፀሐይ ! ጭለማው ገልጦ የእሑድ ፀሐይ ብቅ ካለች ከውጭ የሚመጣ ሰው አለ ስለዚህ የእሑድ እንግዳውን ለመቀበል ጸጉሩን ማበጣጠር ልብሱን መቀየር ነበረበት።
ጸጉሩን ሲያበጥር ልቡ ድቤ መምታት ጀመረ ። ዕረፍ ብለው አያሳርፉት ነገር ! የልብን ከበሮ አይቆጠሩት ነገር !
የገዛ ልቡ አናደደው ። ድንገት የበሩን ደወል የሰማ መሰለው ተሳስቷል ። ናፍቆት የፈጠረ ደውል ካልሆነ በስተቀር ፡ በክፍሉ ውስጥ የተሰማ ድምፅ የለም ። የሹካ ማንከያና የስሐን ድምፅ ግን በርግጥ ከሌላኛዉ ክፍል ይሰማል ።
ያቺ ሞኒካ ስትንደፋደፍ ነው ። መቼም እሷ ጠዋት መተኛት አትወድ።
ወደ በረንዳው መናፈሻ ወጥቶ ከፎቁ ቁልቁል ተመለከተ ። የዮናታን መኪና እቦታዋ የለችም ። ጠዋት ሲነሡ
ስለሰማ፡የት እንደሔዱ አላጣውም። በአስፋልቱ ሳይ ከሚሠሩ መኪናዎች መሐል ነጥሎ የሚለያት ይመስል ዐይኑን ወደ ሩቅ ወረወረ ። የቤት መኪናዎች እምብዛም የሉም ። ታክሲዎች ናቸው ሽቅብ ቁልቁል ውር ውር የሚሉት ።
ቆሞ መጠበቁ ሰለቸው ። የቆመበት ጊዜ ከዐሥራ አምስት ደቂቃ ባይበልጥም ለእሱ የዓመት ያህል ረዘመበት
“ምን ሆነው እንዲህ ቆዩ ? ” አለ በሐሳቡ፡ አልሔድም ብላቸው ይሆን ? ወይስ የሙሽራ ልብስ አልብሰው ሊያመጧት
ይሆን ? ?
ትዕግሥቱ አልቆ ወደ ውስጥ ተመለሰና ሞኒካ ጋ ሔደ።ወጥ ቤት ውስጥ ምግብ እያበሰለች ነበር ። የቡታ ጋዙን ሦስቱም ምድጃ ድስት ተጥዶበታል ። ሰርግ ሰርግ ሸተተው ፤ የወጡ ሽታ ራብ ለቀቀበት ። ቁሌቱ ገና ይንተሸተሻል ። የበሰለው ደግሞ ክዳኑን ሽቅብ እየገፈተረ ይንተከ
ተካል ። ሞኒካ ፊት ላይ ክፉኛ መቻኮል አነበበ ።
“ ምን ልርዳሽ ? ” አላት ። እሷም ፈገግ ብላ " ከምድጃው ላይ አንዱን ድስት አውርዳ ፥ ቡና በማንቆርቆሪያ
እንዲጥድላት ነገረችው ፡ሁለቱም የሥራ ድርሻቸው ላይ አትኩረው እግረ መንግዳቸውን ስለ ጽሑፍ ሥራው ሁኔታ መጨዋወት ላይ እንዳሉ ድንገት ደወሉ ተንቃጨለ።
አቤል ሲሰማው በላብ ተጠምቀ ፣ጭንቅ አለው ፤የልቡ ትርታ ፍጥነቱን ጨመረ ። ምን ሰው ያስደነግጣሉ ! ቀስ ብለው አይደውሉም እንዴ ? ” የቡና ማንቆርቆሪያ ክዳን እንደ ወደቀበት ያስተዋለው ቆየት ብሎ ትንሽ ከተረጋጋ በኋላ ነው።
ሞነካ ዋናውን በር ከፍታ እንግዶቿን ስትቀበል አቤል ወጥ ቤት ውስጥ እንደ ቆመ ጆሮውን ላከ። የተነባበረ የጫማ ድምፅ ። የማን የማን ይሆን ? የዮናታን ፡ የእስክንድር ፡ የሚሰማው የወንዶች ድምፅ ብቻ ሆነበት ። የልቡ ምት ስላስፈራው ደረቱን በእጁ ደገፈ ። ወዲያው ግን ሞኒካ ራሷን በእንግሊዝኛ ስታስተዋውቅ ስለ ሰማ አዲስ ሰው
መምጣቱን ገመት ።
ያላበውን እጁን አጠገቡ ያገኘው ነገር ላይ ጠራረገ ።ግንባሩን ፡ ጉንጩን ዐይኑን በእጁ አሻሸ እንደ ቆመ ጸጉሩን አበጣጠረ ። የሸሚዝ ኮሌታውን እያስተካከለ በረዥሙ ተነፈሰ ጭንቀት የሚያባርር፥ ፍርሐት የሚያስወግድ አተነፋፈስ : እና ርምጃውን በልቡ እየቆጠረ ወደ ሳሎን ገባ ።
ከአጭር ጠይም ሴት ልጅ ጋር ዐይን ለዐይን ተገጣጠሙ ። የሁሉም ፊት በፈገግታ ደምቆአል " ፈገግታው ሁሉ ለአቤል ጐልቶ የታየው የትዕግሥት ነው " በጉንጭ መሰርጐድ የታጀበ ፈገግታ ! ይህን ፈገግታዋን ለመጀመሪያ ጊዜ ካየው አንሥቶ ከአምስት ወር ራብ በኋላ ማየቱ ነው ። የሚወደውን የጉንጯን ስርጉድ ቀርቦ ሲያይ የመጀመሪያው ጊዜው መሆኑ ነው ። ማንን ቀድሞ መጨበጥ እንዳለበት ግራ ገብቶት ሲርበተበት አብራው የቆየችውን
ሞኒካንም እንደ አዲስ ጨበጣት ።
ለእስክንድር ያለዉን ስሜት ቆንጥጦ መያዝ አልቻለም ። ስሜቱ ፈንቅሎት ጉንጩን ጥብቅ አድርጐ ሳመውና
ይህ ሁሉ የአንተ ጥረት ያስገኘው ፍሬ ነው አስው ። ፊቱን በቅጽበት ወዶ ዮናታን መል። እና ደግሞ የርስዎ ? ” አላቸው ። ፍቅሩን በዓይኑ ከመግለጽ ቀቀር ተንጠራርቶ ሊስማቸው አልደፈረም ። ሦስተኛ ባለውለታውን ሲያመሰግን ዘወር ሲል ከአጠገቡ አጣት ። ሞኒካ ድስት ሲገነፍል ሰምታ እየሮጠች ወደ ወጥ ቤቱ ተመልሳ ነበር ።
ትዕግሥት በነጭ የሀገር ልብስ ነው የመጣችው።አቤል ይህንኑ ለብሳ የተመለከተቀትን እሑድ ወዲያው አላስታወሰም " ቆይቶ ቆይቶ ነው ከእነ ማርታ ጋር ሰርግ ቤት ስትሄድ ልብሳው እንደ ነበር ያስታወሰው። ሰላምታውንና ምስጋናውን ጨርሶ ሲቀመጥም ልቡ እልተረጋጋም ነበር ።ይበልጥ የትርታውን ፍጥነትና አስጭናቂነት ጨመረ
ዘሎ ዘሎ አንዴ ቀጥ እንዳይል ፈራ።
ትዕግሥት ማለት እሷ ነች ። ታዲያ የተመኙትን ሲያገኙ መንቀጥቀጥ ነው ? ደብዳቤዉ ያሳደረበት ስሜትና ሲገናኙ የደረሰው ሁኔታ ባለመገጣጠሙ በልቡ በሸቀ። ያ ሁሉ የፍቅር ቃላት ጋጋታ ምን ዋጠው ? ይኖራል ! ጸጥታውን የሚሰብርለት ድምፅ አጥቶ ነው እንጄ በሁለቱም ውስጥ አለ ።
አቤል ኤቼዳች ቃል መተንፈስ ፈልጎ ምላሱን ተጠራጠረው " ምናልባት የተሳሰረበት እንደሆንስ ? ከፍቅር
እመቤቱ ፊት የተቀመጠው ገላው የሚንቀጠቀጥ ጀርክ የሚመታ መሠለው።
በድንገት ዐይኑ የእጁ ጠባሳ ላይ ዐረፈ ምግብ አዳራሹ ውስጥ የወደቀ ጊዜ የወጡ ፍንጣቂ ያተረፈለት ጠባሳ ።
መጥፎ ስሜት አልተናነቀውም መጥፎ የልብ ጠባሳ ነበር እንጂ የእጅ ጠባሰ ምንም አይደለም ። የልቡን ቁስል ደብዳቤዋ ባመነጨበት እንባ ካጠበው ሰንብቷል ።
ተጫወቺ የሚል ቃል እንደ ምንም ከአፉ
ገፍትሮ አወጣ ።
ትዕግት በእሺታ ፈገግ አለች ፈገግታዋ ጠዋት ከሥራው ላይ ካባነነችው ፀሐይ ይበልጥ ደምቆ ታየው።
ሳያስቡት የዝምታው ባሕር ዮናታን እስክንድርም ውጧቸው ነበር ። ከተቀመጡ ጀምሮ ቃል አልተነፈሱም
ታዛቢ ባይሆኑም ታዛቢ መሰለዋል ። ወጥ ቤት ውስጥ የሚንተሽተሽው ምግብ ሽታ የእስክንድርን አንጀት እያላወሰው ነበር። በአፉ ምራቅ ሲሞላ ተሰማው።
"በመጀመሪያ የመኝታና የጥናት ክፍሎችህን ለትእግስት አሰጎብኛት ! አሉ ዮናታን በቤቱ ውስጥ እንቅስቃሴና ድምፅ ለመፍጠር በማሰብ።
አቤል ከትዕግሥት ጋር ተነሣ" ዮናታንና እስክንድርን በዝግታ ከኋላቸው ተከተሏቸው ።
“ ፍቅራቸው በጥሩ መልክ ይቀጥል ይሆን ? ” አለ እስክንድር በሹክሹክታ ድምፅ ፥ ወደ ዮናታን ጆሮ ጠጋ ብሎ ።
ቢቀጥል መልካም ነው ። ባይቀጥልም አቤልን እንዳለፈው አይጐዳውም ። ተቀራርበው ቃላት ከተለዋወጡ
ዐይኑን መግለጥ ይችላል አሉ ዮናታንም በሹክሹክታ በአቤልና

👍2🥰2
ትእግስት መሐከል የጫማቸው ድምፅ ካልሆነ በስተቀር የቃላት ልውውጥ አልተሰማም ። የመኝታ
ክፍሉን ጎብኝታ ወደ ጥናት ክፍሉ ስትገባ ግን ትዕግሥት ተነፈሰች ።
“ በጣም ትልቅ ይቅርታ ! ” አለችው ፡ ዐይኗ ዕንባ እቅርሮ ።
“ ምነው ለምን ? ” አላት ፥ ዕንባዋ የቀሰቀሰበትን ስሜት ከጉሮሮው ወደ ውስጥ ለመዋጥ እየታገለ ።
"ትምህርትህ በእኔ ምክንያት በመቋረጡ ይቅርታ አድርግልኝ !! »
“ ታዲያ አንቺ ምን አጠፋሽ ? ” አለና አቤል አሁንም ጉሮሮው ላይ የሚተናነቀውን ነገር በምራቁ አወራርዶ
“ ይልቅ እዚሁ ቤት የጥናት ጽሑፍ ማዘጋጀት ጀምሬአለሁ ። ለሥራው የሚረዱኝ መጽሐፎችና ሐሳቦች በማፈላለግ ትረ ጂኛለሽ ? ” አላት ።
ፈቃደኝነቷን ለመግለጽ ራሷን መነቅነቅ ወይም ቃላት መናገር አላስፈለገም ።
“ እና ትምህርቴንም በአዲስ ዓመት ፥ በአዲስ ልቦና ፥ በአዲስ ተስፋ እቀጥላለሁ ።
ቃላት አንሰዋቸው ዐይን ለዐይን ሲተያይ አልተፋፈሩም ። ዐይኗ ብሌን ውስጥ ምስሉን ሲመለከት እሷም ዐይኑ ብሌን ወስጥ ምስሏን እየተመለከተች ነበር ።
ትዕግሥት ከአቤል ዐይን ዳርቻ ላይ ዐይን አር አየች ልትጠርግለት ብትሞክርም እጅዋ ይንቀጠቀጥ ይሆን? እንደ
ምንም ደፍራ እጅዋን ዘርግታ በጣቷ አነሣችለት ።
ምንድን ነው ? ” አላት ከንፈሩ እየተንቀጠቀጠ
“ ጉድፍ” አለችው የእሷም ከንፈር እየተንቀጠቀጠ ።
ዐይኑን የነካው እጅዋን ጥብቅ አድርጎ ሳመው ።
ዮናታንና እስክንድር በደስታ ፈዘው ቀሩ። እውን ሳይሆን የፊልም ትርኢት የሚያዩ ነበር የመሰላቸው ። በተለይ
እስክንድር ራሱን መቆጣጠር አቅቶት እንደ ሕፃን ፈንደቅ ፈንደቅ የሚል ስሜት ታገለው። ደስታ በሣቅ ሣቅም በጥርስ
የሚገለጽ ነገር ባይሆን ኖሮ መላ ሰውነቱ እየሣቅ ነበር ።
ለአፍታ ያህል ጓደኞቻቸው ፊቱ ላይ ድቅን አሉበት ። ማርታ የነገር ቅንድቧን እያርገበገበች ፡ ድብርት በጋቢው
ተጀቡኖ እየተልጐመጐመ ፥ ሚስተር ሆርስ ቼሱን ታቅፎ ቅልጥሙን እንደ ዘረጋ ቤተልሔም በፈተና ሰዓት ወደ
ሽንት ቤት እየሮጠች ፡ ሳምሶን ጉልቤው ጡንቻውን ወጣጥሮ ለአቤል ሊማታለት እየተጋበዝ - ሁሉም በእስክንድር
ሐሳብ ውስጥ ተሰለፈ ። “ ምነው አንዳፍታ መጥተው ይህን ትርኢት ለማየት በታደሉ ! ” አለ በልቡ ።
አቤል የትዕግሥትን እጅ ስሞ አልለቀቀውም እንደገና ወደ ደረቱ እስጠግቶ ጥብቅ አርጐ ያዘው ። እጇ
እንደ ኤሌትሪክ ሽቦ የአቤልን ልብ ትርታ እየተቀበለ ወደ እሷ ያስታሳልፍ ጀመር ። ትርታው ነዝሯት አላፈገፈገችም ። ይልቁንም መላ ሰውነቷን በዝግታ ወደ አቤል አካል አስጠጋችው ። ትንፋሻቸው ተገጣጠመ ። ሁልቱ እንደ አንድ ሰው !
“ እ --- እ --- እፀድሻለሁ ። ”
አስቸግራው የኖረቺውን አንዲት ቃል ተነፈሳት ።
💥ተፈፀመ 💥
ሰመመን ይሄን ይመስላል ብዙዎቻችሁ ድሮ አንብባችሁት አልፋችሁ ይሆናል አሁን በዚህ ቻናል ሲለቀቅም ገና ያነበበው ሊኖርም ይችላል የሁላችሁንም አስተያየት እፈልጋለው በ @atronosebot አድርሱኝ

🥰4👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
#ከሁለት_ወራት_በኋላ
እንደሻው በቀለንና ራሷን በጥይት አቁስላ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ህክምናዋን ስትከታተል ከቆየች በኋላ በሁለተኛው ወሯ ሙሉ ለሙሉ ዳነች፡፡
በዚያ ጥይት ምክንያት ከላይኛው መንጋጋ ጥርሶቿ ላይ ሁለቱን አጥታለች፡፡ የግራ ጆሮዋ በመስማት በኩል ትንሽ ቅር ቢለውም ሙሉ ለሙሉ አልደነቆረም፡፡
ጥይቶቹ በተከታታይ ሾልከው የወጡበት ቀዳዳ መጠነኛ ጠባሳን ጥሉባት አለፈ እንጂ፤ ውበቷን እምብዛም የሚፈታተነው አልነበረም፡፡
ከዚህ ሁሉ ሥቃይ በኋላ ግን እቤቷ ገብታ አላረፈችም፡፡ ወንጀለኛ ናትና በቀጥታ በማረፊያ ቤት እንድትቆይ ተደረገ፡፡
የወንጀል ክሱ በዐቃቤ ህግ ከሳሽነት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡
ከሳሽ ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ ወይዘሪት ትህትና ድንበሩ የክሱ ምክንያት ሰው የመግደል ሙከራ ወንጀል ዐቃቤ ህጉ ተከሳሽ ሆን ብላ ተዘጋጅታ ወጣት እንደሻው በቀለ ከሚሰራበት የንግድ ሱቅ ድረስ በመሄድ በአራት ጥይቶች ያቆሰለችው መሆኑንና እራሷንም ለመግደል ሙከራ ማድረጓን ከገለፀ በኋላ፤ የወንጀለኛ መቅጫ ህግና አንቀጽ ጠቅሶ አስፈላጊው ቅጣት እንዲወሰንባት
የተመሰረተ ክስ መሆኑን በማተት አቀረበ፡፡
ትህትና ድንበሩ ተከሳሽ ሆና ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት በቀረበችበት ዕለት፤ ታናሽ ወንድሟ በችሎቱ ላይ በመገኘት ክሱን
አብሯት አዳመጠ፡፡
ፍርድ ቤቱ ለተከሳሽ የሚከተለውን ጥያቄ አቀረበላት፡፡
ስምሽ?”
“ትህትና ድንበሩ”
“ዕድሜሽ?”
"አሥራ ሰባት ዓመት”
“አድራሻ?”
“አዲስ አበባ
“ሥራሽ?”
“ሥራ ፈላጊ”
“ወላጆችሽ በህይወት አሉ?”
“አባቴ ሞቷል እናቴም የአልጋ ቁራኛ ነች”
ይህንንና መሰል ጥያቄዎችን ከተጠየቀች በኋላ “የክሱ ቻርጅ ደርሶሻል?” የሚል ጥያቄ ቀረበላት፡፡
“አዎን ደርሶኛል”
ከዚያም የመሐል ዳኛው መነጽራቸውን ዝቅ አድርገው በግንባራቸው ዐይዋትና........
“ወይዘሪት ትህትና ለተመስረተብሽ ክስ እራስሽ ትከራከሪያለሽ ወይስ?
ጠበቃ ታቆሚያለሽ?” የሚል ጥያቄ አቀረቡላት፡፡
ቀስ ብላ ሻምበል ብሩክን አየችው፡፡ የመከራትን አስታወሰች፡፡
“ድሃ ስለሆንኩ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ?” የሚል መልስ ሰጠች፡፡
ይህንን መልስ ስትሰጥ በተቻላት መጠን ድምጿ እንዲሰማ ጮክ ብላ ነበር፡፡
ፍርድ ቤቱ በጥብቅና ሙያው የታወቀው አቶ ምንውዬለት ተዘራ ለተከሳሽ ጠበቃ እንዲሆንላት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ አቶ ምንውዬለትም ትእዛዙን በደስታ ተቀበለ፡፡
ይህ ከሆነ በኋላ ተከሳሽ የተከሰሰችበት ወንጀል በንባብ እንዲሰማ ተደረገ፡፡
“በተመሰረተብሽ ወንጀል ጥፋተኛ ነሽ አይደለሽም?” ተብላ ተጠየቀች፡፡
በዚህ ጊዜ ጠበቃው አቶ ምንውዬለት ጥቁር ካባውን እንደለበሰ
ብድግ ብሎ ቆመ፡፡
“ጥፋተኛ አይደለችም ክቡር ፍርድ ቤቱ” ሲል መልስ ሰጠ፡፡ ዳኛው መልሱን ከመዘገቡ በኋላ፤ ጠበቃው “ክቡር ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ የዋስ መብቷ ተጠብቆ እንድትከራከር ይፍቀድልኝ” ሲል ጥያቄ አቀረበ፡፡
ፍርድ ቤቱ ግን ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ፤ ተከሳሽ በማረፊያ
ቤት ቆይታ እንድትከራከር በመወሰንና፤ ዐቃቤ ህጉ አሉኝ የሚላቸውን ማስረጃዎች እንዲያቀርብ ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱ አበቃ፡፡
ትህትና እዚያ የተከሳሽ ሳጥን ውስጥ
ቆማ ስትቁለጨለጭ፣እንዳንድ ጊዜ በፍርሃት ተውጣ ሰውነቷ ሲንቀጠቀጥ፣
ድምጿ ሲርገበገብ፣ ሲያልባት፡ እያየች አዜብ እንባ እየተናነቃት ነበር፡፡ ሆኖም አልቅሳ ልትረብሻት አልፈለገችም፡፡ ይልቁንም ሳቅ ፈገግ እያለች ሞራል ልትሰጣት ሞከረች፡፡
እውነትም እንደዚያ ሰውነቷ በፍርሃት ሲሸበርባት፣ ልቧ ድው ድው ሲል፣ ሻምበል ብሩክን፣ ወንድሟንና አዜብን ቀስ ብላ ታያቸዋለች፡፡ እነሱ ፈገግ ይሉና በ“አይዞሽ” ምልክት ሲያበረታቷት “አይዞኝ” በሚል ስሜት እራሷን ስታጠናክር ከቆየች በኋላ ችሎቱ ሲያበቃ በአጃቢ ፓላስ ታጅባ ወጣች፡፡
ከዚያም በአንዱአለም ጠያቂነት አብረው ምሣ ይበሉ ዘንድ ሻምበል ብሩክ አጃቢ ፓሊሱን አነጋገረውና አብረው ምሣ ለመብላት ፈቃድ ስለ አገኙ ፤ እዚያው አካባቢ በሚገኝ ወደ አንድ ሆቴል ገቡ፡፡
አንዱአለም የዛሬውን ምሣ ለመጋበዝ የፈለገበት ምክንያት ነበረው፡፡ የሚፈለገው ምግብና መጠጥ ታዘዘ፡፡
ከባህር ኃይሉ የተሰጠው የኪስ ገንዘብ ስለነበረው ምሣ የጋበዘው እሱ ነበር፡፡ አንዱአለምን ብሎ ጋባዥ በመገኘቱ እየተሳሳቁ፣እየተጨዋወቱ፣ ግብዣውን በደስታ ተቀበሉት፡፡ አጃቢ ፓሊሱ በሻምበል ብሩክ ላይ እምነት ስለጣላ እስረኛዋ ታመልጣላች የሚል ሥጋት አላደረበትም፡፡ እንደዚሁ እየተጨዋወቱ ከቆዩ በኋላ.......
“አንድ ጊዜ” አለና አንዱአለም ትንፋሹን ሰብሰብ፣ ምራቁን ዋጥ አደረገ፡፡
አራቱም በፀጥታ ይመለከቱት ጀመር፡፡ ከወትሮው ለየት ያለ ስሜት ይታይበታል፡፡ እነሱ ከተቀመጡበት አካባቢ ትንሽ ራቅ ብለው በርከት ያሉ እየተጨዋወቱ የሚሳሳቁ ሰዎች ድምጽ ብቻ ይሰማል፡፡
“ይህቺ የምሣ ግብዣ በአንድ በኩል እታለም ለመጀመሪያ ጊዜ
ፍርድ ቤት በቀረበችበት ቀን ተገኝቼ እውነተኛ ፍትህን አግኝታ በነፃ
እንድትለቀቅ መልካም ምኞቴን የምገልጽበት ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ
ለራሴ መሸኛ በማድረግ በግል ውሣኔዬ መሠረት ለነገው ጉዞዬ መቃናት
እንድትመርቁኝና፤ የወጪ እንድላችሁ በማሰብ የተደረገች ግብዣ ነች”
አለ፡፡ ስለምን እንደሚያወራ ቶሎ ማወቅ አልቻሉም :: “የምን ጉዞ? የምን መሸኛ?. “ምንድነው የምትለው አንዱዬ?” በድንጋጤና በጥርጣሬ ተውጣ አዜብ ጠየቀችው፡፡ “ ሁሉንም ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቄአለሁ፡፡
ከአንድ ሣምንት በፊት በኢትዮጵያ ባህር ኃይል ውስጥ ተቀጥሬ ለስልጠና
መሄዱ ነው” ሲል ቁርጡን ነገራቸው፡፡ በዚያ ጨዋታ መካከል ይህንን መርዶ አምጥቶ ሲጥልባቸው ልባቸው ክፉኛ አዘነ፡፡ በተለይ ትህትና የተሰማትን ስሜት መግለጽ ያስቸግራል፡፡ ጭውው አለባት፡፡ ግማሽ አካሏ፣ የምትወደው ታናሽ ወንድሟ ምንም እንኳን እስረኛ ብትሆንም በየጊዜው እየመጣላት ዐይኖቹን ስታየው
የምትጽናናበት አለኝታዋ ነበር፤ በሁኔታው መሪር ሀዘን ተሰምቷት አለቀሰች፡፡
አዜብም እንደዚያው፡ ሻምበል ብሩክም ክፉኛ ነበር የደነገጠው፡፡
ይህ ትንሽ ልጅ የዚህ ዐይነት ከባድ ውሣኔ ላይ ይደርሳል ብሎ ጭራሽ አልገመተም ነበር፡፡ የሱ ፍላጐት አንዱአለም በትምህርቱ ጠንክሮ ዩኒቨርስቲ
እንዲገባ እንጂ እንደዚህ በመሀሉ አቋርጦ ወደ ጦር ሜዳ እንዲሄድ አልነበረም፡፡ ከረጅም ፀጥታ በኋላ......
“እንደሱ ይሻላል አልክ አንዱአለም?” አለው ሻምበል በትካዜ አንደበት።
ትህትና እና አዜብ በእንባ ይንፈቀፈቃሉ፡፡ አጃቢ ፓሊሱ ግራ ተጋብቶ ሁሉንም በዐይኑ ይቃኛል፡፡
“በቃ ብንሄድስ” የሚል ፍላጉት አድሮበታል፡፡ ሞትም ቢሆን በተሰማበት ቅጽበት በድንጋጤ ያደርቃል እንጂ፤ ቀስ በቀስ መለመዱ አይቀርምና፤
ውስጥ ውስጡን እየተቃጠሉ፤ እንባቸውን እየጠራረጉ፤ዐይን፤ ዐይኑን፧ ይመለከቱት ጀመር፡፡ ውሣኔው የፀና፣ ጉዳዩ ያበቃለት መሆኑን ቁርጥ አድርጉ ነገራቸው፡፡
እስከዛሬ ድረስ የቆየው እህቱ ፍርድ ቤት ስትቆምና የተከሰሰችበት ወንጀል ሲሰማ አብሯት ለመገኘት ፍቃድ በመውሰድ መሆኑን፣ ነገ በጠዋት በዋናው መሥሪያ ቤት ተገኝቶ ወደ ማሰልጠኛው ጉዞ የሚጀምርከ መሆኑን፣ለሻምበል ሲያስረዳው ለትህትና እና ለአዜብ ደግሞ የመርዶ ያህል ካረዳቸው በኋላ በአጃቢ ፓሊሱ አሳሳቢነት ተነስተው ወጡ፡፡
“እሺ አሥር አለቃ ስለተባበርከኝ በጣም ነው የማመሰግንህ አለው ሻምበል የአጃቢ ፓሊሱን ትከሻ ቸብ ቸብ እያደረገ፡፡
“እሺ ጌታዬ አኔም የርስዎ ነገር ሆኖብኝ እንጂ፤ ህግ መጋፋቴን አልዘነጋሁትም” አሥር አለቃ ጥላዬ እግረ መንገዱን ውለታውን

እያዘስመዘገበ....አንዱአለም ከእህቱ ጋር ተቃቅፈው፤ ተሳስመው ፤ ሲሰነባበቱ ግን አልቻልም፡፡ ሆዱ ባባና አቅፏት አለቀሰ፡፡
በመጨረሻም ትህትና ወደ እሥር ቤት ጉዞዋን ስትቀጥል፤ እሱ ደግሞ ዝግጅቱን ሊያጠናቅቅ ወደ ባህር ኃይል መሥሪያ ቤት ለመሄድ ሻምበል ብሩክን ተሰናበተና ከአዜብ ጋር ሆነው ታክሲ ውስጥ ገቡ......