አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
. #ኀሠሣ ስጋ

እልፍ ከሲታዎች ቀጥነው የሞገጉ
"ስጋችን የት የሄደ ?" ብለው ሲፈልጉ
አሥሠው አሥሠው በምድር በሠማይ
አገኙት ቦርጭ ሆኖ በአንድ ሠው ገላ ላይ።
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

....የመከራ ቋት መሆኗ እያማረራት መፈጠሯን እስከመጥላትና ሞቷን እስከመመኘት ብትደርስም፤ ምሬቷን በልቧ አምቃ፣ መጨረሻውን እሱ የፈጠራት አምላኳ እንዲያሳምረው መፀለይዋን አላቋረጠችም፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ እግዚአብሔር አይደለም፡፡ በፈጠራት ነፍስ ላይ
የሚወስነው አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ መቼ እንደሚወስዳት የሚያውቀው እሱ ብቻ ስለሆነ ፤ ዶክተር ባይከዳኝ እንደማትድን ገልጾ ተስፋ ቢያስቆረጣትም፤ ማን ያውቃል? ፈጣሪ በተአምር ሕይወቷን አትርፎላት፣ ሊተዛዘቡ ይበቁ ይሆናል፡፡ ይህንን ስታስብ፤ ሞቱ ተብለው ደረት የተመታላቸው፤ አበቃላቸው ተብለው ሳጥን የተዘጋጀላቸው፣
በአምላክ ረቂቅ ሥራ ህይወት ዘርተው፤ ለረጅም ዕድሜ ባለፀጋነት የበቁ እንዳሉ ሲታወሳት፣ እንኳንስ ተስፋ ያላት እናቷን፤ ከፈለገ ሬሣ የሚቀሰቅሰው አምላክ፤ በህይወት ሊያቆይላት እንደሚችል በመተማመን፤ የዶክተርን ድንፋታ እየናቀችው፤ እናቷን አሳክማ ለማዳን ትግሏን በጠንካራ መንፈስ ለመቀጠል ወሰነች፡፡

ከዚህ ከእናቷ ህመም በተጨማሪ ደግሞ በተፈጠረው ችግር ምክንያት የሷና የሻምበል ፍቅር ገና በለጋነቱ እንዳይጨናገፍ ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሏታል፡፡
በተለይ የዚያን ዕለት ያየችው ህልም ፍርሃት፤ ፍርሃት፣እንዲላት ዋነኛ ምክንያት ሆኖባታል፡፡
ነገ እሁድ ነው፡፡ ዕሁድ ዕለት እሷና ሻምበል ብሩክ የሚገናኙበት፣ ፍቅር የሚጨዋወቱበት፣ የወደፊት የትዳር ህይወታቸውን እየቀየሱ የሚወያዩበት፤ በአጠቃላይ ሁለቱም በናፍቆት የሚጠብቁትና በሻምበል ብሩክ ቤት በደስታ ውለው የሚያድሩበት ቀን ነው፡፡
ቅዳሜ በጠዋት ተነስታ፤ ለእናቷ አጥሚት አዘጋጅታ፧ ምሣ በሣህን ይዛ፤ ወደ ሆስፒታል ሄደች፡፡ እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት ድረስ ከቆየች በኋላ አንዱዓለምን እናቱ ዘንድ እንዲቆይ አደረገችና፤ ወደዚያች
ችግሯንም ሆነ ደስታዋን እኩል ወደምትካፈልላት ጓደኛዋ ወደ አዜብ
ሄደች፡፡

ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ትናንትና መገናኘታቸውን፣ ከዚያም ቤቱ ይዟት መሄዱን፣ ከዚያም ራሷን ለመፈተሽ ያደረገችውን ሙከራ፣ ከዚያም ዶክተር ባይከዳኝ ሙልጭ አድርጐ ስድቦ ያባረራት መሆኑን አወራችላትና፤ በመጨረሻም ላይ ዐይኖቿ በእንባ ተሞልተው እናቷ መጨረሻ ደረጃ ላይ በደረሰ.... የካንሰር በሽታ መታመሟንና፤
እንደማትድን የገለፀላት መሆኑን፤ አስረዳቻት፡፡
አዜብ እቅፍ አድርጋ አጽናናቻት፡፡ አቤት እንደዛ እቅፍ አድርጋ ስታጽናናት የተሰማት ስሜት! መዋለድ ብቻውን ምን ዋጋ አለው?አንዳንዱ ተዋልዶም ተመልሶ እንደጠላት ይፈላለጋል፡፡ እንደዚህ ያለው
ጓደኝነት ግን ከመዋለድም በላይ ዋጋ ያለው ነው፡፡ መዋለድ ሳይሆን መዋደድ ነው ተብሉ የለ ወትሮውኑ? ፡፡

ዶክተር ባይከዳኝ ሀኪም እንጂ እግዚአብሔር አይደለም፡፡ ስለማሚ ህይወት የሚያውቀው አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ደግሞ ታያለሽ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ድነው ከዚያ ሆስፒታል ባይወጡ አዜብ ምን አለች ትይኛለሽ ?” እሷን ለማጽናናት ስትል .
ከእግዜሩ መልዕክት ደርሶኛል ለማለት ትንሽ ነበር የቀራት። ትህትናም ትህትናም
ያለችው ይሄንኑ ነበር፡፡ ድሮውንም የእናቷን ነገር ለፈጣሪ ነበር የሰጠችው፡፡ ልቧ ተጽናና፡፡ ወደ ሌላው ዋና ርእሰ ጉዳይ ተሸጋገሩ፡፡
“የተፈጠረውን ሁሉ ፍርጥርጥ አድርጐ እውነቱን መናገር ይሻላል ወይስ ሌላ መንገድ አለው?” ስትል አዜብን አማከረቻት፡፡
“እውነቱን መናገር ባልከፋ ነበር፡፡ ምን ያህል አምኖሽ ይቀበለዋል የሚለው ነው ችግሩ። አላየሽም ዶክተር እንኳን የሆነውን? እሱስ ልጃገረድ ነኝ ስትይው ከከረምሽ በኋላ ያለመሆንሽን ሲያውቅ ምን ይሰማዋል?ስትዘል የኖረች አይልሽም?” መልሳ ጠየቀቻት፡፡ ትህትና
የዶክተር ሁኔታ መጣባት፡፡ አውሬ ነበር የሆነው፡፡ የሻምበልም ከዚህ ሊለይ እንደማይችል ገመተችና ፈራች ::
"እሱስ እውነትሽን ነው አዜቢና፤ ታዲያ ምን አባቴ ማድረግ ይሻለኛል? ጨነቀኝኮ! እንደነገርኩሽ ህልሜም ጥሩ አልነበረም፡፡ ወይኔ ብሩኬ.... የልቤን እንዴት አድርጌ ባሳየሁት?” ተከዘች፡፡
አዜብ ጉዳዩን ከብዙ አቅጣጫ ተመለከተችው፤ መረመረችው፡፡የሆነውን ሁሉ መናገር፤ ወይንም ሌላ ዘዴ መፈለግ.... በመጨረሻ ላይ የመጣላትን ዘዴ ልትነግራት ካለች በኋላ በቅድሚያ ልታሳምናት ፈለገች፡፡
“ ትሁት የእድልሽን ሳትሞክሪ ከወዲሁ ቶሎ ብሎ እጅ መስጠቱ የሚያዋጣ አልመሰለኝም፡፡ ቀድመሽ እንደዚህ ሆንኩ ብለሽ ተናግረሽ፤አልፈልግሽም ካለ እንዳይቆጭሽ ፡፡ አሪፍ ከሆንሽ በአንድ ጊዜ ልታሳኪው ትችያለሽ፡፡ ካልተሳካልሽ ደግሞ ሁለተኛውን እድል ትጠቀሚያለሽ፡፡
የተፈጠረውን ሁሉ በዝርዝር ታስረጂዋለሽ እርግጠኛ ስለሚያፈቅርሽ ችግርሽ ይገባዋል :: ስለዚህ በቅድሚያ አማራጩን ብትጠቀሚ” አለቻት፡፡ ትህትና አማራጩን ለመስማት ጓጓች፡፡
“ፔሬድሽ መጥቷል?”
“አልመጣም”
ጥያቄውን ለምን እንዳቀረበችላት ለማወቅ
ቸኩላለች፡፡
“መቼ ነው የሚመጣው?”
"እሮብ ወይም ሀሙስ ብዬ እገምታለሁ”
“በቃ እሁድ ዕለት አትሂጂ፡፡ ለእሮብ ወይም ለሀሙስ ቅጠሪው። የዚያን ዕለት አብረሽው እደሪና፤ እሪ ብለሽ አልቅሽ”
ትህትና በጥፊ እንደተመታ ሰው ክው ብላ ደነገጠች፡፡
“ውይ አዜቢና ይሄስ የማይሆን ነው” ተቃወመች፡፡
“ወደድሽም፤ ጠላሽም፤ ያለው አማራጭ እሱ ብቻ ነው ትሁት”
“እንዴት ሊሆን ይችላል? እንዳታለልኩት ካወቀ ደግሞ የባሰ ነው የሚሆነው” በትካዜ ተውጣ፡፡
“ሊያውቅ አይችልም፡፡ ስንቶቹ ናቸው እንደዚህ የሚሽውዱት ዋናው ያንቺ ቅልጥፍና ነው”
በዚህ ጉዳይ ላይ በሰፊው ከተነጋገሩ በኋላ፤ ያለው አማራጭ ይሄና ይሄ ብቻ መሆኑን አሳመነቻት፡፡
ሳምንቱን ሙሉ ከሻምበል ብሩክ ጋር ስልክ ሲደዋወሉ ነበር ያሳለፉት፡፡ ይሁን እንጂ እሷ በእውነተኛ ፍቅር ...
“ብሩኬ " ስትለው፤ እሱ ደግሞ በአንደበቱ “ሀይ ትሁት”ቢላትም፧ በልቡ “አስመሳይ!” ሲላት ነው የከረመው ::
ይሄንን አስመሳይነቷን፤ ሌብነቷን፤ ደርሶበት ቁርጡን እስከሚያውቀው ድረስ በተቻለው መጠን የድሮውን ሻምበል ብሩክን ለመምሰል ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ልቡ ቢሻክርም፤ እንደበቱን ለማለሳለስ
እየታገለ ነው የከረመው ::
ቅዳሜ ዕለት ስልክ ደወለችለትና ከአዜብ ጋር በተመካከሩት መሠረት የእሁድ ፕሮግራማቸውን ወደ እሮብና ወደ ሀሙስ እንዲሸጋገር አሳወቀችው፡፡
“ምነው ምን ተፈጠረ ትሁት?” አላት በመገረም፡፡
“ማዘር ብሶባታል እሁድ እለት ሆስፒታል ነው የማድረው”
“ይሄኔ ከዚያ ጅል ዶክተርሽ ጋር ለማደር ነው” የሚል ስሜት ተሰማውና ቅናት ቅጥል ቢያደርገውም፤ ቻል አድርጐ
“ልምጣ እንዴ?ችግር አለ እንዴ ?” አላት ለማግደርደር ያህል፡፡
“አትድከም ብሩኬ ከቻልክ እሁድ ብቅ በል” አለችው፡፡
ሻምበል ከሶስት ቀናት በፊት ሆስፒታል
ሄዶ ጠይቋታል፡፡ አሁን ብሶባታል ብላ የምትነግረውን ዓይነት አልነበረባትም፡፡ እንዲያውም እየተሳሳቁ፤ እየተጨዋወቱ! ነው የዋሉት፡፡
እሮብ ወይም ሀሙስ ደግሞ ያልተለመደ ቀጠሮ ነው፡፡
“ይሁን እስቲ!” አለና ንዴቱን በልቡ አምቆ፡፡
“ምንም ችግር የለውም ትሁት፡፡ ዋናው የማዘር ጤንነት ነው፡፡ግን እሮብ ወይ ሀሙስ ከምትይኝ ወይ እሮብን፤ ወይ ሀሙስን፤ ለምን አልመረጥሽም? ማለቴ እንድጠብቅሽ?”
“ችግር የለውም ብሩኬ፡፡ ትክክለኛውን ቀን ደውዬ እነግርሃለሁ”
“ይሁን እንዳልሽ” በሃሣቧ የተስማማ በመምሰል አንጀቱ እያረረ እሁድ አልደርስልህ ብሎት በተስፋ ሲጠባበቅ፤ አሁን ደግሞ ይኸውና እሁድ ሲደርስ ተጨማሪ ሶስት ወይም አራት ቀን ጨምራበት ቁጭ አለች፡፡ ይህንን ሁሉ ችሎ፣ እሁድ እለት እዚያው ሆስፒታል ሄዶ፤እናቷን ጠይቆ፤ ልክ
👍2
እንደ ድሮአቸው በፍቅር ስሜት ሲጫወት አረፈደ፡፡
ደቂቃዎች እንደ ሰዓት፣ ሰዓታት እንደቀናት፣ቀናት ደግሞ የዓመታትን ያህል
የረዘሙ መስለው ቢታዩትም፤ እንደተለመደው እያንዳንዱ ቀን የተፈቀደለትን የጊዜ ርዝመት ጠብቆ እሮብ ዕለት መድረሱ አይቀርምና፤ ደረሰ፡፡
ትህትና የምትጠብቀው እንግዳም በዚሁ ቀን መጣ፡፡ ይህንኑ ሁኔታ ለአዜብ ከነገረቻት በኋላ በጉዳዩ ላይ በስፋት ተወያዩበት፡፡ በመጨረሻም...
“መልካም ዕድል” ብላ ታክሲ አሳፍራ በፍቅር ሸኘቻት፡፡
ለሻምበል ብሩክ ዛሬ የምትመጣ መሆኑን ደውላ ስትነግረው ልቡ ዘለለች፡፡ ወደደችም፤ ጠላችም፤ ዛሬ አንደ ድሮው በቀጠሮ ተንከባክቦ የሚያስቀምጠው የአደራ እቃ አይኖርም፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ ቀድሞት ከሆነ ጉዳዩ እዚያ ላይ ያበቃል፡፡የሱና የትህትና የእህል ውሃ ጉዳይ እዚያ ላይ ያከትማል፡፡ የፍቅራቸው ምዕራፍም ይዘጋል፡፡ ቆንጆዋ ትህትና፣ ድምጸ መረዋዋ ትህትና፣
የመልካም ፀባይ እመቤት የሆነችው ትህትና፤ አጭበርብራው ከሆነ እሱ
ምን ግዜም ለፍቅር አልታደለምና፤ በድጋሚ ልቡ ደም እያለቀሰ ሊለያት
ጨክኖ ተዘጋጅቷል።
ልጃገረድ መሆን ያለመሆንዋ ጥርጣሬው ዛሬውኑ እንዲያከትም ለማረጋገጥ ቸኩሏል፡፡ ለማንኛውም ዛሬ ሁሉ ነገር ይለያል!ስልክ ደውላ እንደምትመጣ ስትነግረው በግዜ እቤቱ ገብቶ
ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ ተዘገጃጅቶ ነበር የጠበቃት፡፡
ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከሩብ ሲሆን በሩን ቆረቆረች፡፡ ሻምበል ብሩክ በሳቅ እየተፍለቀለቀ ሄዶ በሁለመናው አቅፎ ተቀበላት፡፡ እዚያ ሰርቪስ ቤት ውስጥ ሆነው ወንድሞቹ ያዩዋታል፡፡ ከሱ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው ወደ ዋናው ቤት ሲያመሩ፤ ዓይኖቿን ወደ ሰርቪስ ቤቶቹ
ስትወረውር የእጮኛዋ ወንድሞች እጆቻቸውን ሲያውለበልቡላት አየች፡፡
እሷም እጆቿን አውለብልባ ሰላምታ ሰጠቻቸውና፤ ከሻምበል ብሩክ ጋር ተያይዘው ገቡ፡፡መቼም ልቧ ደም ሳይሆን ፍርሃትን ብቻ ነበር የሚረጨው....
ዛሬ የመጨረሻው ወሣኝ ቀን ነው፡፡ ከሻምበል ብሩክ ጋር ፍቅራቸው ወይ እንደ አዲስ ይለመልማል፤ ወይ እንደ ህልሟ ደርቆና፤፡ደቆ፤ በለጋነቱ ይቀጫል፡፡ ጨዋታው ደራ እንደወትሮው ሁሉ፤
ሁለቱም በፍቅር እየተላፉ፣ እየተዝናኑ፣ ከሙዚቃው ጋር አብረው እየዘፈኑ፣ ይሄንን ቀዝቃዛ ቢራ መጐንጨታቸውን ቀጠሉ፡፡
ሻምበል ብሩክ ብቻ ሳይሆን እሷ እራሷ ሞቅ እንዲላት በጣም ፈልጋለች፡፡ ሞቅ ካላት ደፋር እንደምትሆን፣ የአዜብን ምክር ያለችግር መፈፀም እንደምትችል ስለተሰማት፤ በላይ በላዩ ታንቆረቁረው ጀመር። ሻምበል ብሩክም እሰይ የኔ ሸጋ"እያለ ደጋግማ እንድትጠጣ ሞራል ሰጣት፡፡ሞቅ ካላት እቅዱን በቀላሉ ተግባራዊ ለማድረግ ይቀለዋልና፡እስክትሟሟቅለት ድረስ፤ እያያሳሳቀ፤ ያስጎነጫት ጀመር፡፡
እስከ ምሽቱ አምስት ሰዓት ድረስ መኝታ ትዝ ያለው የለም፡፡
ለመሆን የፈለገችውን የሆነችውና፤ ሻምበል የተመኘውን ሆና ለመገኘት የወሰደባት ሶስት ጠርሙስ ቢራ ብቻ ነበር፡፡ ሞቅ ማለት ብቻ ሳይሆን ከዚያ አልፋ ቁጭ አለች፡፡ ሰከረች ማለት
ይቻላል፡፡ ለድፍረት ብላ የጀመረችው መጠጥ እራሷን አንድትስት አደረጋት፡፡
ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ሆና ካያት ቀን ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በጭንቀትና በጥርጣሬ ተውጦ ሰንብቷልና ቁርጡ የሚለይበት ሰዓት በመድረሱ ሻምበል ከፍተኛ ጉጉት አድሮበታል፡፡
በዚህ ሁኔታ ከቆዩ በኋላ ፤ እየተሣሣቁ፤ እየተላፉ፤ እየተጓተቱ፤ወደ መኝታ ክፍላቸው ገቡ....
ትህትና ስታለች፡፡ ሻምበል ብሩክ ሞቅ አለው እንጂ አልሰከረም፡፡ እሷ ግን በስካሩ ምክንያት እፏ መኮለታተፍ ጀምሯል። እንደ እምቦሳ ጥጃ እየቦረቀች ትስመዋለች፡፡ እሱም ከዚያ በላይ መጠበቅ አልቻለም፡፡ ተጣደፈ፡፡ ከዚያም ልብሶቻቸውን አወላልቀው አልጋቸው ላይ ወጡ...ጉዱ ሊለይ... ድብብቆሹ... ሊጋለጥ.... የትያትሩ ምዕራፍ ሊገለጥ...
ሰኮንዶች ቀሩ፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ የሆነ ብዥ፤ ብዥ ፤ የሚል ስሜት ተሰማት፡፡ ልቧ አታሞውን ደለቀ፡፡ አዜብ ደብዝዛ ታየቻች፡፡ ምክሯ፤ ውይይታቸው፤ ትንሽ በትንሹ ትዝ ሊላት ሞከረ፡፡ ሻምበል ብሩክም ልቡ ድው፤ ድው፤ አለ፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ አካሉን ከአካሏ አስጠግቶ ጨዋታ ሊጀምር ሲል፤ እርጥበት ተሰማው፡፡ ቀስ ብሎ በጣቶቹ ምንነቱን ለማረጋገጥ ዳብሶ ተመለከተ፡፡ ግራ ገባው፡፡
“ግን ለምን በዚህ ሰዓት?” እራሱን ጠየቀ፡፡
“እሁድን አሳልፋ እሮብን ለምን መረጠች? እርግዝናን በመፍራት ወይስ? ቢሆንም ቢሆንም...ይለያል፡፡ ዛሬ የመጨረሻው ቀን ይሆናል፡፡”

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
#ሰመመን


#ክፍል_አርባ_አምስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

አቤል ካምፓሱን በለቀቀ ማግሥት ሳምሶንም ጓዙን ይዞ ስለ ወጣ እስክንድር ፊቱን ወደ ዩኒቨርስቲው ማዞር አስጠልቶት ሦስት ቀን ያህል መኖሪያ ቤቱ ነበር የሰነበተው ። እዚያም ሆኖ የአቤልን ጉዳይ ለማስፈጸም ወዲያ ወዲህ
ማለቱ አልቀረም ። ብርቅነሽን አነጋግሮአት አቤል ያካፈላትን ምስጢር ለቢልልኝ እንድትነግራቸው አድርጓል ። መጀመሪያ ብርቅነሽ ፍርድ ቤት የመቅረብ ያህል ቆጥራው እምቢ ብላ አስቸግራው ነበር ። በብዙ ውትወታና ማሳመን ነው ወደ ቢልልኝ የወሰዳት ። ከእሷም ሌላ አቤል ቀድሞ በርቀት ካስተዋወቀው ሰዎች መሐል ለሥነ ልቡናው ምርምር ጥቂት
ይረዳሉ ብሎ የገመታቸውን ከቢልልኝ ጋር በመመካከር አነጋግሮአቸዋል ። እሱም እንደ ዮናታን በጓደኛው በአቤል ጉዳይ ውስጥ እጁን ማስገባቱና አንዳንድ ጠቃሚ ውጤቶች ማስገኘቱ አስደስቶት የበለጠ እንዲገፋበት እያደረገው
ነበር ።

በአራተኛው ቀን ወደ ካምፓስ ሲገባ ሁለት ሴቶች በጥብቅ ሲፈልጉት እንደ ሰነበቱ ድብርት ነገረው ። ቶሎ ሐሳቡ ውስጥ የመጣችበት ማርታ ነበረች ።

” ምን ዐይነት ሴቶች ? ” አለው ፡ ለማወቅ ቸኩሎ።

“ አንዷ ወፍራም ቀይ ፡ አንዷ መጠነኛ ወይም ሁለቱም አጭሮች ” ካለው በኋላ ፥ የነገሩትን ስም አስታውሶ ።ድብርት“ ቤተልሔምና ትዕግሥት የሚባሉ” አለው
“ አሃ ! ” አለ እስክንድር ። የተፈለገበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለመገመት ጊዜ አልወሰደበትም ። ነገር ግን በጣም የጓጓው ስለ አቤል የሚቀርብለት ጥያቄ ከትዕግሥት ከራሷ አፍ ይወጣ እንደሆን ለመስማት ነበር ።
ሁለቱም በምሳ ሰዓት ወደ መመገቢያው አዳራሽ ሊገቡ ሲሉ አገኛቸው ።
በእግር በፈረስ ስትፈለግ የት ነው እንዲህ የጠፋኸው ? ” አለችው ቤተልሔም ።

በመኪና ብትፈልጉ ፡ ታገኙኝ ነበር ! ” ሁለቱም ሴቶች በቀልዱ ሣቁ ።

“ ማርታኮ ፡ ሔደች ! ” አለችው ቤተልሔም ሣቋን ገታ አድርጋ

“ የት?” አላት የደመ ነፍሱን ።

“ ወድቃ ፡ ትላንት ሻንጣዋን ይዛ ግቢውን ለቀቀች ። ”

"እና? እና እኔ ታዲያ እኔ ምኗ መሰልኳት የማርታን መርዶ የጨዋታ መክፈቻ የምታደርግልኝ ”አለ እስክንድር በልቡ ።

“ በራሷ ጥፋት ነው ” አለች ቤተልሔም ፡ ከእስክንድር መልስ ስታጣ ።

“ እንዴት ? ”

"ጸባይ የላትም ። ጸባይ ቢኖራት ኖሮ ህእ ! ” አለችው ፥ እንደ ሕፃን ልጅ ለምቦጭዋን ጥላ ።

“ ጸባይ ወይስ ጭንቅላት ?” እለ እስክንድር በሐሳቡ ።ምን ለማለት እንደ ፈለገች ገብቶታል ። ወዲያው ትዝ ያለው
ማርታ ለማን አጥላልታ ያወራችለት ነገር ነበር ።

“ ያንተስ ጓደኞች ?” አለችው ትዕግሥት በድንገት ።ስለ አቤል ለማወቅ ካላት ጉጉት የተነሣ፥ ሌላውን ጨዋታ
ለስማት ትዕግሥት አጥታ ነበር ።

“ ሳምሶን ወድቆ ተባረረ” አላትና አቋረጠ
ቤተልሔም የሳምሶንን ስም ሲጠራ እሱ ራሱ አጠገቧ የቆመ ያህል ሽምቅቅ አለች ከፍርሀቷ ብዛት ተደብቃው ከርማ ግቢውን ለቅቆ መሔዱን ካረጋገጠች በኋላ ነበር
ከመኝታ ክፍሏ መውጣት የጀመረችው ።

እስክንድር የሳምሶንን መባረር ብቻ ተናግሮ ስለ አቤል ምንም ነገር ሳያነሣ ያቋረጠው ሆነ ብሎ ነበር ። ትዕግሥት
ደፍራ ትጠይቀው እንደሆን ሊፈትናት ፈልጎ ነበር ትዕግሥት ዐይን ዐይኑን አየችው የምትፈልገውን እንዲነግራት በዐይኗ ለመነችው ። ነገር ግን ከእስክንድር አፍ ጠብ ያለ ነገር ኣልነበረም ።

“አቤልስ ? ” አለችው ደፍራ ። ድምጿ ግን ድክምክም ብሎ ነበር።

እስክንድር ደስ አለው ። ትዕግሥት ለመጀመሪያ ጊዜ የአቤልን ስም በጓደኛው ፊት መጥራቷ በእርግጥም ትልቅ ለውጥ ነበር ። ደስታዊው ስላስደነገጠው ቶሎ መልስ አልሰጣትም ። እሱም ድምፅ እንደ እሷው እንዳይደካክም መጠ ንቀቅ ነበረበት ።

“ አበል እንኳ አልወደቀም ። ግን እሱም ካምፓሱን ለቅቆ ወጥቶአል ” አላት ።

እስክንድር ይህን ሲናገር ከትዕግሥት ፊት ላይ የጠበቀውን ለውጥ አልተመለከተም አቤል ግቢውን መልቀቁ ያስደነግጣታል ብሎ ነበር ። ነገር ግን ትዕግሥትም ሆነች
ቤተልሔም ለነዚህ ዜና እንግዳ አልነበሩም ። አቤል በዮናታን መኪና ሻንጣውን ጭኖ የወጣ ዕለት ነበር ያዩት ተማሪዎች ወሬውን ቀምመው ሲያራቡ ነው የሰነበቱት ። እና አሁን የትዕግሥት ጉጉት የአቤል መውደቅ ትክክለኛ መሆኑን
ማረጋገጥ ብቻ ነበር ።

“ ታዲያ ካልወደቀ ለምን ካምፓሱን ለቅቆ ወጣ ? " አለችወ ትዕግሥት በጥርጣሬ ።

“ በሌላ ምክንያት ነው ”አላትና እስክንድር ለአመላለስ ተቸግሮ ፡ “ ሰፊ ነው ነገሩ ፣ በቁም ጨዋታ የሚያልቅ አይደለም ” አለ።
አላመነችውም ፊቷ ላይ ጥርጣሬ አነበበ የተከፋው ገጽታዋ አቤል ወድቋል ብላ እንደ ደመደመች ይናገራል ።ይህ እስክንድርን ብዙ አላስጨነቀውም ጊዜውን ጠብቆ ሁሉን ነገር እንድታውቀው ይደረጋል ። ዋናው ነገር በሩ መከፈቱ ነውጅ የአቤልን ስም እንስታ በግልጽ መጫወት ጀምራለች።

"ግን ምን ይሆን ' ወይስ ማን ይህን ያደፋፈራት ?? ሲል አሰበ ።

ከደስታው የተነሣ ምሳውን በሚበላበት ጊዜ ጉዳይ እንዳለበት ሰው እየተጣደፈ ቶሎ ቶሎ ነበር የጎረሰው ምግቡን ቶሎ ጨርሶ ያንን ሰው የበዛበት አዳራሽ ለቅቆ ወጥቶ ብቻውን ከሐሳቡ ጋር እየተሣሣቀ ለመፈንደቅ ካልሆነ በስተቀር ፡ ሌላ የሚሔድበት ቦታ አልነበረውም ።

መኝታ ክፍሉ ገብቶ እንደ ወትሮው አጭር የቀን እንቅልፍ ለመተኛት ቢሞክርም አልሆነለትም ከውጭ ይዞት የገባው ደስታ ጠፍቶ ትካዜ ተጫጫነው ። ከክፍሉ ውስጥ አቤልንና ሳምሶንን ማጣቱ ቅር ቅር አሰኘው ወና ቤት ውስጥ የገባ ይመስል ሰውነቱን ቀፈፈው ። ለሚቀጥሉት አራት ወራት በዚህ ክፍል ውስጥ የሚያሳልፈው ሕይወት
በጣም ብቸኛ ሆኖ ታየው ። በእርግጥ አጠንቡ ድብርት አለ ግን ድምፁ ከማይሰማ ሰው ጋር እንዴት ይኖራል ?

ሳምሶን "ጉልቤው" መኝታ ክፍሉን ምን ያህል ያደምቀው እንደ ነበር የገባው አሁን ነው » እየፈሳም ሆነ እየዘለለ ወይም ድብርትን እያበሽቀ ክፍሉን ሕይወት ይሰጠው ነበር ። መቼም መለያየት ክፉ ነው» ፤ እንደዚያ የሚያበሽቀው ድብርት እንኳ ሳምሶን ሲባረር ተገላገልኩ አላለም
ከልቡ ነበር ያዘነላት እስክንድር እንደ ተጋደመ ስለ ሳምሶን ሲያስብ የተለያዩበት ቀን ትዝ አለው ። በሰላም አልነበረም የተለያዩት ።

ሳምሶን ሰው ሳያየው ተደብቆ ካምፓሱን ለመልቀቅ ከለሊቱ አስራ አንድ ሰዓት አካባቢ ዕቃውን ሲያሰነዳዳ እስክንድር ድንገት ከእንቅልፉ ባነነ ። ሆኖም አዝማሚያው ስለገባው እስከ መጨረሻው ልመልከት ብሎ ፊቱን ከአንሶላው ውስጥ ሳያወጣ ጭጭ ብሎ ያዳምጥ ጀመር። ሻንጣውን አዘገጃጅቶ ጨርሶ ሲወጣ በሩጋ ሲደርስ ከአንሶላው ውስጥ አሾልቆ ተመለከተውና ፡ “ ሳምሶን ! ” ብሎ በኃይለ ቃል ጠራው።

"ምነው ? ! ”አለ ሳምሶን ዘወር ብሎ ከቁጣ ባልተናነሰ ድምፅ ስለተነቃበት ተናዶ ነበር።

"ምን ሆነሃል ? ”

"መሄዴ ነው"

“ ታዲያ እንዲህ ነው እንዴ የሚኬደው ? ምነው ሳምሶን ? የተወሰነ ጊዜም ቢሆን በጓደኝነት አሳልፈናል ። ቻው ብለኸን በሰላም ሸኝተንህ ፥ ብንለያይ ምናለበት ? መውደቅ በአንተ አልተጀመረ ! ” አለው እስክንድር ፥ ሆድ ብሶት ።

“ ሸኝ አልፈልግም ! ያው ሰፈር እንገናኛለን” ! ብሉ ጥሎት ሔደ ።

ሰው ለምን ድክመቱን ለመሸፈን ሲል እውሬ ይሆናል?” አለ እስክንድር በልቡ ። በሳምሶን አልበሸቀበትም " እንዲያውም ፡ “ በዚህ በንዴቱ ሰዓት ምግብ ቢቀርብለት
እንደ ቀድሞው ይበላ ይሆን ? ” ብሎ አስቦ ሣቅ አለ ። “ ጥርሳሞች ! ” ሲል በሐሳቡ ታየው ።ሰው
👍1
የሚገናኝበት አጋጣሚና የሚለያይበት ሁኔታ ሲመዛዘን መለያየቱ ይከብዳል እስንድር የዩኒቨርስቲ ሕይወቱን በሐሳብ ሲዳስስ ግሲው አስተዋውቅት ጊዜ ያለያየም ብዙ ተማሪዎች ታወሱት ። በተቀራረበ የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚገኙበት ግቢ በመሆኑ'አብዛኛውን ጊዜ የጋራ የሆኑ ስሜቶች ይንጸባረቃሉ ። ይህ ሳይሆን አይቀርም በትምህርት ዓመታት ላለፈው የጋራ ኑሮ ጣዕም የሚሰጠው
ለጊዜው ሆዱን ያባባው ሳምሶንና አቤል ግቢዉን መልቀቃችው ነው ። ነገር ግን ከአራት ወራት በኋላ እሱም ራሱ ግቢዉን ይለቃል ። አብረውት የነበሩት ሁሉ በተለያየ የሥራ መስክ ተበታትነው በየፊናቸው የግል ጎጆአቸውን መቀየሰ
ይጀምራሉ ። የዩኒቨርስቲ የጋራ ሕይወት የሩቅ ትዝታ ሆኖ ይቀራል ።

ለክፉም ለደጉም አሁን ከእስክንድር አጠገብ ያለው ሰው ድብርት ነው አብሮት ሴሚስተሩን ሊያስልፍ የሚችል ሰው እሱው ነው ። እናም የግዱን እንዲጫወት ይጎተጉተው ጀመር ።

“ እንዴት ነው ? ውጤትህን ለወላጆችህ ነገርካቸው ?” ሲል ጠየቀው ።

“ ለማን እነግራለሁ ብለህ ነው ? ” እለ ድብርት ኀዘን በተቀላቀለበት ድምፅ ።

"እንዴት ? ”

“አባቴ ቢሰማም ግድ የለኝም ። እሱም ግድ የለው አለው ድብርት ። ምን ስሜቱን ፈንቅሎ እንዳናገረው ገረመው ።

"ታዲያ ለእናትህ አትነግራቸውም ? ”

“ እኔ እናት የለኝም ፡ የእናት ጣዕም አላውቅም ” አለው ምርር ብሎ ።

እስክንድር ከተጋደመበት ቀና አለ ። ወሬው ጆሮውን ብቻ ሳይሆን መላ ሰውነቱን አነቃቃው ።

ምነው ? ለምን ? ” አለው እስክንድርም እዝን ብሎ ወዲያውም የምስጢሩን ካዝና ለመበርሰር ጓጉቶ ።

ድብርት ፡ ቶሎ አልመለሰለትም ። ሲያመነታ ቆየ ።ሁሉን በሆዱ ይዞ እንደ ቆየ ሁሉ፥ አሁንም የቀረችዋን አንዲት ሴሚስተር እንደ ታፈነ መጨረስ ፈለገ ። ነገር ግን የእስክንድር አጣያየቅ ከበደው

“ ወይ ቀድሞውኑ ጫፍ ባላስያዝኩት ኖሮ !” አለ በልቡ ። በአፉ ባይናገረውም በልቡ ለእስክንድር ፍቅርና ክብር ነበረው እንደ ሌሎቹ ስለማይተናኮለው ብቻም ሳይሆን ከአብዛኛዉ ድርጊቱ የሚያይበት ብስለት፣ፍቅር አሳድሮበታል።

"ማለቴ ፥ እናትህ" በቅርብ የሉም እንዴ ? ”አለው እስክንድር እንደገና ሀዘኔታ አዝሎ በሚያውጣጣ የአነጋግር ስልት »

“ በልጅኔቴ ነው እናቴ የሞተችው”አለ ድብርት እሷ ስትሞት ነፍስ አላውቅም ነበር ለዚህ ነው ጣዕሙን አላውቅም ያልኩት።

እስክንድር ከንፈሩን መጠጠ ሌላ ማስተዛዘኛ መንገድ አልነበረውም ።

ደኅና አባት ቢኖረኝ ኖሮ እንኳ የእናቴ ሞት ያን ያህል ባልጎዳኝ ነበር ” አለው ድብርት የእስክንድርን ማዘን አይቶ ።

"አባትህ ..."

“ አባቴ አረመኔ ነው !! »

እስክንድር ቃላቱ ሰቅጥጦት ጭጭ አለ ። አጠገቡ የሚያወራው ሰው።የድሮው ድብርት ሊመስለው አልቻለጭም ።
ልሣኑ መከፈቱ ብቻ ሳይሆን የአነጋገር ስልቱም ነው የተቀየረበት ። ታፍኖ ቆይቶ የፈነዳ ነገር ነው የሆነበት ። “ ቁስል
መጥፎ ነው ! ዲዳንም ያናግራል ” አለ በልቡ ። በዚህም ረገድ መኝታ ክፍሉ ወስጥ ሁለቱ ብቻ መቅረታቸውን
ወደደው ብቻቸውን ባይሆኑ ኖሮ እንዲህ ምስጢሩን አያወራለትም ነበር ።

“ ከእናቴ የተወለድነው እኔና አንዲት እኅቴ ነን ።አባቴ ለሁለታችንም አስተዳደግ ደንታ አልነበረውም ።በጥረታችን ነው ያደግነው ማለት እችላለው እኔ እንደምንም ተፍጨርጭሬ ዩኒቨርስቲ ገባሁ። እኅቴ ከአሥራ ሁለተኛ ክፍል ወድቃ አሁን የአውራ መንገድ አውታታ ሆናለች ። ”

« አባትህ ከእናትህ ሞት በኋላ ሌላ ሚስት አላገቡም ማለት ነው ?

“ ምን ያገባል ? ! እሱ ሁሏም ሚስቱ ነች እኛን በገረድ ነው ያሳደገን ። ለዚያውም ደሞ ” አለና ድብርት ሊቀጥል ያሰበውን ነግር ለራሱም አስጠልቶት አቋረጠ ።

በአባታቸው ግድየለሽነት ሳቢያ ድብርትና እኅቱ በቤት ሠራተኞችም እየተሰቃዩ ነበር ያደጉት ገረዶች ሲለዋወጡባቸው ነበር የኖሩት ። የሚቀጠሩት የቤት ሠራተኞች
እና ድብርትን ለመጀመሪያ ኋዜ በደንብ ይመግቧቸዋል ።ውለው ሲያድሩ ግን የአባታቸውን ፍቅረ ቢስነት ይመለከቱና
እነሱም ቸል ይሏቸዋል አባታቸው ሰክረው ሲመጡ ቤት ውስጥ የተገኘውን ሠራተኛ ፥ “ እግርሽን ታጠቢ ! ከእኔ ጋር ነው የምትተኚው ” ይሏታል ። ከዚያ በኋላ በቃ ! ሠራተኛዋ የቤት እመቤት ትሆንና ልጆቹን ቁልቁል ማየት ትጀምራለች ከእነሱ ይልቅ እሷ ተሰሚነት ይኖራታል
በተለይ ድብርት አባቱ ፊት ምንም ቃል እንዲተነፍስ አይፈቀድለትም ነበር።

ለልጆቹ የሚያዝኑ አንዳንድ ደግ ሠራተኞች ቢገቡም ብዙ አይቆዩም የተለመደው" እግርሽን ታጠቢ" ሲከተል ሰራተኛም በወር ውስጥ ፡ “አረገዝኩ ” ትላለች ።ይኽኔ የድብርት አባት ጓዝሽን ጠቅልይና ውጭ ! ” ብለው ያባርሯታል ። አብዮቱ ከፈነዳ ወዲህ እንደዚያ መቀጠል ስሳልቻሉ በተለይ አንዲት ሠራተኛችው በቀበሉ ማኅበር ከሳ ስላስቀታቻቸው ፡ ገረድ መቅጠሩን እርም ብለው ትተውታል
ልጆቹ ራሳቸው አብስለው እንዲበሉ ተገደዱ።

ታዲያ ድብርትና እኅቱ በልጅነታቸው በሠራተኛ ተጨቁነው ሲርባቸው
ይመካከሩና ሠራተኛዋ ሳታይ መሶብ
ከፍተው ይበላሉ ። ነገሩ ተነቅቶባቸው አባታቸውጋ ሲደርስ ድብርት ድርቅ ብሎ ይክዳል ። እህቱ ትፈራና እውነቱን
ታወጣለች ከዚያ በኋላ በድብርት ላይ የሚወርደው የዱላ ውርጅብኝ አያድርስ ! ጭንቅላቱን ከመሬት ጋር አጣብቀው
ይቀጠቅጡታል " ይረግጡታል አመታታቸው የአባት ዐይነት አልነበረም ። ግን ገና ለገና እመታለሁ ብሎ ራብ
ሲሞረሙረው መሶብ ከፍቶ መብላቱን አልተወም ጭራሽ ጋግርታም እየሆነ ሄደ
አባቱ ፊት ቀርቦ ሲጠይቁት አፉን ዘግቶ ድርቅ ፡ ድፍን ሲልባቸው እሳቸውንም ያስፈራችው ጀመር ። ይህ ጸባይ እያደገበት ሔዶ በቤት ብቻ ሊወሰን
አልቻለም ። ውጭ ባለው ማኅበራዊ ግንኙነት ድብርት ሆኖ ቀሩ ።
" ግን አባትህ ጤነኛ ናቸው ? ” ሲል እስክንድር በመገረም ጠየቀው ።

“ በግድ በመጠጥ ኃይል ራሴን ሳሳብደው ካላለ• ጤነኛ ነው ! ” አለ ድብርት በምሬት ድምፅ።

እስክንድር ዘልቆ ሊጠይቀው አልፈለግም ድብርት በአባቱ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ እንዳለው ካወቀ በኋላ፥ ለሚጠይቀው ሁሉ ጤናኝ መልስ እንደማይሰጠው ገመተ እስክንድር የድብርትን አባት ጸባይ ሊያይ የሞከረው በተለየ መልክ ነበር ። ድብርት ለኣሁኑ ጸባዩ ምክንያት የሆነው ያን ዐይነት ሥር ካለው አባቱም ያንን ዐይነት ጸባይ ያበጁበት ሥር ያለው ምክንያት ይኖራቸው ይሆን የሚል ጥርጣሬ አደረበት ምናልባት የሚስታቸው መሞት አእምሮአቸውን ረብሾት ነካ አድርጎኣቸው ይሆናል የሚል ሐሳብ ገባው ። ነገር ግን ፥ “ ኧረ ባክህ እስክንድር ፥ ምንስ ቢሆን ይህን ያህል
በወለዳቸው ልጆች ላይ አውሬ የሚሆን አባት ? ” ሲል የኅሊና ሙግት ገጠመው
በአንጻሩ የራሱ ሟች አባቱ በሐሳቡ መጡበት እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ከእስክንድር ጋር በፍቅር ነበር የንሩት ግና ከልጅነቱ ጀምሮ ከአባቱ ጋር ገበታ ቀርቦ ፥ የሔዱበት እየተከተላቸውም ነው ያደገው በተለይ ወንድ ሆኖ በመፈጠሩ ይኮሩበት ነበር ። ስለዚህ ጠጅ ቤትም ፡ ዕድርና እቁብ ቦታም ቢሔዱ እያስከተሉት ፥ ነጻ ስሜት እንዲኖረው አድርገው ነው ያሳደጉት ። እንዲያውም እናትየዋ ፥ “ ልጄን አባለክብኝ ” ሲሉ ዘወትር ጸብ ነበር አሁን የድብርትን አባት ታሪክ ከሰማ በኋላ አባቱን ይበልጥ በልቡ አመሰገናቸው።

“ አይዞህ ለማንኛውም አሁን አንተ ራስህን ከምትችልበት ደረጃ ላይ ደርሰሃል ” ሲል አጽናናወን ።

“ ነገሩ ነው እንጂ ፥ እሱማ የት ይቀራል ? ” በማለት ድብርትም ራሱን ነቀነቀ ።
እስክንድር
ተክዞ ቀረ ። በየቤቱ ስንት ድብቅ ልብ አለ! በማለት ተገረመ ። ሁላችንም ብንሆን በጉልምስናችን ዘመን
የምናሳየው ጸባይ ራሱን የቻለ መሠረት አለው ግማሹን ከወላጆቻችን ደም ፥ ግማሹን ደግሞ ከምንኖርበት ኣካባቢ
ይዘን የመጣነው ጸባይ ነው አሁን ያምናንጸባርቀው እና ማርታም በቅናት ቅንድቧ የሚርገበገብበትና ለሐሜት ጆሮዋ የሚቆምበት ሳምሶንም የምግብ ፍቅርና የጉልበተኝነት ጸባይ የሚታይበት ሁሌም ከበስተጀርባው ለማንነቱ ሳቢያና ምክንያት አለው ። በዚህ ዓለም ላይ ከአካባቢው ነጻ ሆኖ የሚኖር ሰው ማን አለ ?

የድብርትን ታሪክ ከሰማበት ደቂቃ ጀምሮ እስክንድር በዚህ በቅጽል ስሙ መጥራቱን አቆመ ። የቅጽል ስሙ ራሱ መጥፎ ሥነ ልቡናዊ ተጽዕኖ እንዳለው ገምቶ አሥራት በሚለው ትክክለኛ ስሙ ይጠራው ጀመረ።

የእስንድር ስሜት እሥራትን ለማስደሰት ቸኮለ ይህን የተደበቀ ልቡን ከፍቶ ያጫወተውን ሰው ፍቅሩን በምን መንገድ ሊገልጽለት ይችላል ? የመጋበዝ ሐሳብ መጣበት ግን ምን ? ያው መጠጥ ነዋ ከአካባቢው የወረሰው ልማድ ሆኖበት ሰውን ማስደሰት ሲያስብ መጠጥ መጋበዝ ነው የሚታየው ነግር ግን ሐሳቡን አስቦ በእደ ኅሊናው
ኪሱን ቢዳብስ " ቤሳ ቤስቲን አልነበረውም ።

💥ይቀጥላል💥
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....መጨረሻውን ለማየት፤ እንደድሮው በስስት ሳይሆን፤ በውስጡ የነበረውን
ጥርጣሬ ለማስወገድ፤ በተቻኮለ ስሜት ወደ አካሏ በኃይል ዘለቀ.....
በዚያን ጊዜ ከድንጋጤው ብዛት የተነሣ መብረቅ እንደመታውአው ክው ብሎ ቀረ፡፡ ውስጡ የነበረው ጥቃት ደም በስሪንጅ ተመጦ! በምትኩ በረዶ የጨመሩበትን
ያህል ደሙ ቀዝቅዞ፤ ወደ በረዶነት
አብጦ የተነረተው ስሜቱ ሙሽሽ ብሎ ሲወርድ ፤ እሷ ደግሞ እንድ ስህተት መፈጸሟን ተረድታ በነቃችበት ያበቃለት ምዕራፍ ላይ “እሪ!” ብላ ጩኸቷን ስታቀልጠው፤ አንድ ሆነ፡፡ነገሩ ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ ሆኖ ነበር፡፡ ሻምበል ብሩክ በሃሣብ ጭልጥ ብሎ ከገባበት ሰመመን እሪታዋ አስደነገጠውና...
“ምን ሆነሻል?” በማለት በተሰበረ አንደበቱ ጠየቃት፡፡
“ወይኔ ብሩኬ! ጉድ አደረከኝ አይደል?!” ፍራሹ ላይ በደረቷ ድፍት ብላ አለቀሰች፡፡
ሻምበል ብሩክ እንደዚያ ሆና ሲያያት አቤት የተሰማው ስሜት!
አቤት የተቃጠለው መቃጠል!! በአንድ ጥይት ቢያስቀራት ምንኛ ልቡ በወደደ...?
“ምን አደረኩሽ?” አላት፡፡ አእምሮው ከዘመተበት ሳይመለስ ጣራ፤ ጣራውን፤ በድን ሆኖ እየተመለከተ፡፡
“ደግሞ ምን አደረኩሽ ትላለህ?” እዬዬ ብላ አለቀሰች፡፡ ያንን የአዞ እንባዋን ስታወርደው፤ ተገርሞ ፍዝዝ ብሎ እንደትንግርት ያስተውላት ጀመር.... እንደዚያ የሚወዳትና የሚያፈቅራት ልጅ ገላ አባጨጓሬ መስሎ እስከሚታየው ድረስ ኮሰኮሰችው፡፡በደረቱ የሚሳብ እባብ
ሆና ታየችው፡፡ ጠላት፡፡ ከጥላቻ ሁሉ በላይ የሆነ ጥላቻ በልቡ ነግሶ....
“ምን ነበርኩ ለማለት ነው?” አላት ንቀትና ምሬት በሚንፀባረቅበት አንደበት፡፡
“አታየውም እንዴ ያደረከኝን?” በዚህ ጊዜ ሻምበል ሣቁን መቆጣጠር አልቻልም፡፡ በሳቅ ፈነዳ!!፡፡ እሱ እንደዚያ በሣቅ ሲፈነዳ ደንግጣ፣ ........
“ምን ያስቅሃል?” አለችው፡፡
የሌባ ዐይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ፤ ሁኔታዋን ሲመለከተው ፤ የእስከዛሬው ፍቅር ሁሉ የውሸት መሆኑን፣ የለየላት አስመሳይ ትያትረኛ መሆኗን፣ የዚያን ዕለት እንደዚያ ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛ እየቦረቀች የገባችው፣ እኔ እኮ ልጃገረድ ነኝ እያለች ያታለለችው፡፡
ለመጀመሪያ ቀን የተገናኙ ዕለት እዚያ እነሱ መኖሪያ ቤት እጥሩ ጥግ
በአየር ላይ እየተንሳፈፈች እንደጥሩ ተዋናይ ፀጉሯን አየር ላይ እየነሰነሰች ትስመው የነበረው፤ በተለይ ለዚያን እለቱ ብለህ ነው የማርከው አይደል? ብላ ያፌዘችበት፡፡ይሄ ሁሉ ሲታሰበው፤ የማስመሰል ችሎታዋ ከከፍተኛ ልምድ የመነጨ መሆኑን ተገነዘበ ። የመጠጥ
ልምዷም ከዚሁ ጩሉሌነቷ የመነጨ መሆኑን ሲያውቅ፤ የእስከዛሬው
የዋህነቱ፣ በቀላሉ መታለሉ፤ ይሄ ሁሉ ታስቦት ጥላቻው ከልክ አለፈና ቋቅ እስከምትለው ድረስ አስጠላችው፡፡ከዚያም ከአልጋው ላይ ብድግ ብሎ፤ የምሽት ልብሱን ለባብሶ፤ የመኝታ ክፍሉን ከውጭ ቆለፈና፤ ወደ ሳሎን ሄዶ ሶፋው ላይ ጋደም አለ፡፡

ሻምበል ብሩክ እዚያ ሶፋ ላይ ተኝቶ በሃሣብ ወደኋላ ጭልጥ. ብሎ ሄዶ በዕድሏን እያሰባት እንባው ኮለል እያለ በጉንጮቹ ላይ ወረደ::
እግዚአብሔር ለምን እያሳየ እንደሚነሳው ግራ ገብቶት
“መጨረሻዬ ምን ይሆን?” በሚል ጭንቀት ተዋጠ፡፡የሰው ልጅ ውስጣዊ ገመናውና፤ውጫዊ ባህሪው ያለመጣጣሙ ሚስጥር ገረመው፡፡
ትህትና ካያት ዕለት ጀምሮ ከልቡ የወደዳት ልጅ ነበረች፡፡በኋላም ዐይኑ ጉድ እስካየበት ቀን ድረስ ሙሉ እምነት ነበረ የጣለባት፡፡
“አይ ሰው? ሰውን ለማመን እንዴት ይቻላል? እራስንም ማመን አይቻልም፡፡ ቀበሮ ለሰው ሞት አነሰው ነበር ያለችው?" ከዚህ በፊት በአንድ ግድግዳ ላይ ተጽፎ ያነበበውን ጥቅስ አስታወሰ፡፡
“ሰው እኮ......"
ይላል፡፡ የማይሞላ የክፋት ጉድጓድ ነው
ማለቱ ይሆን? ሲል አሰበ፡፡ በዚህ ስሜት ተውጦ እንቅልፍ የሚባል ነገር በዐይኑ አልዞር ብሉት እንዲችው ሲገላበጥ ነጋለት ::
ትህትና ደግሞ እዚያ መኝታ ክፍል ውስጥ ስካሯ ሁሉ ጠፍቶ በእንባ እየተንፈቀፈች የቡኮ እቃ መስላለች፡፡
“ለምን ተፈጠርኩ? ለምን እግዚአብሔር በዚህ ሁሉ ቅጣት ይቀጣኛል? ምን አደረኩት?” እያለች አምርራ እያለቀሰች፤ ስትጨነቅ፤የሆነ ሰይጣናዊ መንፈስ ተጠጋትና በጀሮዋ መጥቶ የሆነ ነገር ሹክ
አላት፡፡
ትህትና... ትህትና.... ምን እያደረግሽ ነው? ምን ትጠብቂያለሽ? ለምን ከዚህ ሁሉ ስቃይ አትገላገይም? የወዲያኛውን
የሰላም ዓለም ለምን ፈራሽው? አባትሽ የሄደበት ዓለም አይደለም እንዴ?
ይህንን የመሰለ አእምሮሽ ሊሸከም የማይችለውን ስቃይ አስወግደሽ፤
ለምን እስከወዲያኛው በእፎይታ አትተኝም? ተስፋሽ ምኑ ላይ ነው?
እናትሽ እንደማትድን ዶክተር ቁርጡን ነግሮሻል እኮ!
ሻምበልንም ይኸውና አጥተሽዋል፡፡ ለምን ወደ አባትሽ ዘንድ አትሄጅም?
ሂጅ ወደሱ...ሂጂ. ሂጂ ሂጂ . ሂጅ” አላት፡፡
ከዚያም በቀጭን ገመድ ላይ በድን አካሏ ተንጠልጥሎ በንፋሱ ሃይል ወዲያና፤ ወዲህ፤ ሲወዛወዝ ታያት ...የዚህችን አለም ጣጣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተገላግላ እፎይ.... ስትል ታያት፡፡ ከዚያም አላፊ አግዳሚው የተንጠለጠለ በድን አካሏን ከቦ አዬ ጉድ! ሲባባልባት፤ ምነው ገና በልጅነቷ ምን አግጥሟት ይሆን እየተባለ ሲነጋገርባት ታያት፡ የፈለገው ይምጣ !! በመሞቷ ቆረጠች፡፡ ከዚህ በላይ መከራን የምትቋቋምበት አቅም ፈጽሞ የላትም አሁን ለሷ የሚያስፈልጋት
እረፍት ብቻ ነው፡፡ ቆማም ቢሆን ሞታለች፡፡የትኛው አለም ከእንግዲህ
ያጓጓታል? እናትዋ፤ ሻምበል ብሩክ፤ አባትዋ ፤ የሌሉበት ባዶ አለም?
መፍትሄው መገላገል ብቻ ነው! ስትል ደመደመች፡፡ በዚህ ውሳኔዋ መካከል ግን ሌላ ሃሰብ መጥቶ ድንቅር አለባት፡፡ ለምን ትህትና? ለምን? እናትሽ እኮ ተስፋዋ ገና አላበቃም፡፡ ሞትሽን ስትሰማ አንድ ቀን
እንደማታድር አታውቂም? ወንድምሽ አንዱአለም ገና ታዳጊ ልጅ እኮ ነው ። ለምን ለሱሰ አታስቢለትም? ካላንቺ ማን አለው? እየተሰቃየሽም የምትከፍይው የመስዋእትነት ዋጋ ስለሆነ ቻል ብታደርጊውስ ? እያለ ይሟገታት ጀመር፡፡ እናቷና የምታፈቅረው ወንድሟ መጡባት፡፡ይህ ድርጊት ሲፈጸም ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ታሰባት። በሞቷ ልትቀጣቸው ቀፈፋት፡፡ ሰውነቷን ውርር አደረጋት፡፡
ይሄንን ሹክ ያላትን እርኩስ መንፈስ ሸሸችው፡፡ ፈራች፡፡
“ምነው ከአዜብ ጋር እንደዚህ ያለውን ምክር ባልተማከርኩ ኖሮ? ምነው እውነቱን በነገርኩት ኖሮ? ” እያለች ስትፀፀት፤ ስታለቅስ መንጋቱ አይቀርምና ለሁለቱም ያ ሌሊት በስቃይ ነጋላቸው፡፡
ሻምበል በማለዳ ተነሣና ልብሱን ለባብሶ፤ የመኝታ ቤቱን በር ከፍቶ፤ ቀስ ብሎ ገባ፡፡ በእንባ ምክንያት ተበላሽቶ ያደረው ፊቷን
ሲመለከት ከልቡ አዘነላት፡፡ ቀስ ብሉ ሄዶ ኣልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠና...
“ግን ለምን እንደዚህ ትሁት ?” አላት ልቡ አሁንም በሃዘን እንደተነካ፡፡
እንደዚያ ቅስሙ ስብር ብሎ ስትመለከተው አልቻለችም፡፡ እንጀቷ ተላወሰና፧ ሄዳ እላዩ ላይ ተጠምጥማ፤ እንደ አዲስ ጧ! ብላ ትንሰቀሰቅ ጀመር፡፡ ሻምበል በረጅሙ ተንፍሶ፤ አተኩሮ አያት፡፡ አለቃቀሷ በብሶት የታፈነና ሳግ የተቀላቀለበት ነበረ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ሻምበል ብሩክ በሁኔታዋ እጅግ አዝኖላት ነበር፡፡ ከዚያም በኋላ ብድግ አለችና
እያለቀሰች የሆነውን ሁሉ ትነግረው ጀመር፡፡ የምትነግረውን ታሪክ
አዳምጦ ካበቃ በሁዋላ፡፡
“ተይው በቃ ትሁት! ቁርጡን ለማወቅ እንጂ የሆነውን ሁሉ በዐይኔ በብረቱ አይቼዋለሁ፡፡ ተይው አትጨነቂ” አላት፡፡
ምን እንዳየ ገርሟት እስከሚነግራት ድረስ አይን አይኑን እያየች በጉጉት ጠበቀችው፡፡
ከዚያም እሷ አሁን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተፈጠረ ብላ ከምትነግረው የእንደሻው ልብ ወለድ ታሪክ ቀደም ብሎ ሁሉንም
ነገር የደረሰበት መሆኑን ! በአይኑ በብረቱ ተመልክቶ ያረጋገጠው ሀቅ መሆኑን፤ ቀኑን፣ ሰዓቱን፤ ቦታውን፤ ይተነትንላት ጀመር። ከብሔራዊ መኖሪያ ቤቱ ድረስ
ትያትር እስከ ሽሮ ሜዳ የዶክተር ባይከዳኝ ተከታትሉ ሄዶ ያረጋገጠውን እውነት ዘረዘረላት፡፡
“አዬ ጉድ!!” አለች፡፡ ይሄንን ደግሞ እንዴት አድርጋ ይሆን የምታሳምነው? ዶክተር ባይከዳኝ ማለት ጥርስ የሌለው አንበሳ መሆኑን፧ ምንም ያላደረጋት መሆኑን ብትነግረው ደግሞ፤ የበለጠ በሳቅ ሊፈነዳ ነው፡፡
“ይሄንን የልጅ ጨዋታሽን ወደዚያ አድርጊው!” ሊላት ነው:: የበለጠ ሊጠላት ነው ።የመታመኗ ጉዳይ፣ የእህል ውሃቸው ነገር ያከተመለት መሆኑ ታወቃት፡፡
“ትህትና አንቺ ገና ትንሽ ልጅ ነሽ፡፡ በአንቺ ዕድሜ ደግሞ እንደዚህ ዓይነቱ ነገር ለምን ይፈጠራል የሚል ጥያቄ ፈጽሞ የለኝም::
ቀድሞውንም ፍቅሬ ከአንቺ እንጂ ከሌላው አልነበረም፡፡ እንደዚያ ሆኖ
ከተገኘም እሰየው ብዬ ነበር፡፡ ከሁሉ የበለጠ አእምሮዬን ያቆሰለው
ልጃገረድ ሆነሽ ያለመገኘትሽ ሳይሆን፤ ልጃገረድ ያለመሆንሽን ልብሽ
እያወቀው፤ ስላፈቀርኩሽ ብቻ፤ ፖሊስ መሆኔን ጭምር ዘንግተሽ፤ እንደ
ህጻን ልጅ ልታታልይኝ ያደረግሽው ሙከራ ነው፡፡ ትህትና በጣም አዝናለሁ፡፡ በድርጊትሽ ልቤ ዳግም ተመልሶ ላይድን ነው የቆሰለው፡፡እውነቴን ነው የምልሽ ይህንን ሳስብ ሁልግዜም ልቤ እንደደማ
ይኖራል :: የቆሰለ ልቤ እንዲድን፤ ከዚህ ህመም እንዲገላገል፤ ከተፈለገ ደግሞ ከአሁን በኋላ መነካካት አያስፈልግም፡፡ ቁስሉ ሊድንና ሊደርቅ የሚችለው እኔና አንቺ የጀመርነውን እዚህ ላይ አቁመን፤ በወንድምነትና በእህትነት መቀጠል ስንችል ብቻ ነው፡፡ በእውነት ነው የምልሽ፤ ልቤ ተሰብሯል፡፡ ከዚህ በኋላ በእኔና ባንቺ መካከል የሚኖረው ግንኙነት
የወንድምና የእህትነት ግንኙነት ብቻ ነው፡፡ አንቺ ማለት ከእንግዲህ
በኋላ ትንሿ እህቴ ማለት ነሽ፡፡ እናትሽ ድነው እስከሚወጡ ድረስ በምችለው አቅሜ ሁሉ ከጐንሽ አልለይም :: ትህትና ከእንግዲህ በኋላ ብሩክ ማለት ታላቅ ወንድምሽ ማለት መሆኑን አምነሽ መቀበል ይኖርብሻል፡፡ የፍቅር ግንኙነታችንም በዚሁ አብቅቷል። ለሁለታችንም መልካም ዕድል ይግጠመን፡፡ ተጽናኚ እኔም አጽናናለሁ” ሲል የመጨረሻውን መርዶ አረዳት፡፡ ምንም የምትለው አልነበራትም፡፡
ደንዝዛና ፈዝዛ ስታዳምጠው ከቆየች በኋላ፤ አእምሮዋን ሳት ያደረገች
መሰለች፡፡ “እ?... እ?... እ?....እሺ” አለችና አይኖቿ ማረፊያ አጥተው ይንቀዠቀዡ ጀመር፡፡ ከዚያም ተመልሰው እንደገና፤ አይን፤ አይኑን መመልከት ቀጠሉ፡፡እፍረት፣ፀፀት፤ፍቅር፤ ተደበላለቁባት፡፡ ግጥምጥሞሹ ደነቃት፡፡ በእድለቢስነቷ አዘነች፡፡ ከዚያም በሃሣብ ጭልጥ ብላ ሄደች.....

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
#ሰመመን


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

....ቢልልኝና ረዳቶቻቸው በስብሰባው አዳራሽ ቀድሞው ቦታቸውን ይዘዋል ። ከዩኒቨርስቲው አስተዳደርና ትምህርት
ክፍል በአቤል ላይ የተካሔዶውን የሳይኮሉጄ ጥናት እንዲያዳምጡ
የተጋብዙ፥ እንግዶች እየተንጠባጠቡ ገቡ

ዮናታን ፈገግታ በፈገግታ ሆነው አዳራሹ መግቢያ በር ላይ ከእስክንድር ጋር ቆመው ለእንግዶቻቸው ሞቅ ያለ ሰላምታ በመስጠት ላይ ይገኛሉ። እስክንድር ከዮናታ ግዙፍ ቁመና ስር ግብቶ አንድ ፍሬ ልጅ ይመስላል። እንግዶቻቸውን
አስገብተው ከጨረሱ በኋላ እነሱም ገብተው ተቀመጡ።

ቢልልኝ ንግግሩን ለመክፈት ተነስተው ጎሮሮአቸውን ሲሰሉ አዳራሹ ጸጥ አለ ።

“ እንግዶቻችን ፡ እንኳን ደኅና መጣችሁ የዛሬው አርዕስታችን በዐይን ፍቅር የተለከፈ ወይም የተጠመደ አንድ ወጣት ነው ። የሥነ ልቦና ጥናት ክፍላችን በዚህ
ወጣት ችግር ላይ አቅሙ በፈቀደ መጠን ጥናት አድርጎ ውጤቱን ይዞ ቀርቧል ። ”

እንግዶቹ መሐል ጥናቱ የተካደበት ወጣት ማን እንደሆነ የሚያቁ ስለነበሩ፥ በስሜታቸው ውስጥ ወጣቱን የማወቅ ጉጉት ያዛቸው ። አቶ መአምርና ዶክተር አጥናፉ እንዲሁም ሌሎች ከአሁን በፊት ዮናታን የአቤልን ጐዳይ ያናገሯቸው ሰዎች ቸል ያሉት ጉዳይ አድጎ እዚህ መድረሱ ሳያስደንቃቸውም ሳያሳፍራቸዉም አልቃረም የአንድ
ተማሪ የዓይን ፍቅር ችግር፡ ክብደት ተሰጥቶት ይህን ያህል መጠናቱ አስገርሞአቸው አዳራሹ ወስጥ እንዲያው ለትዝብት የተቀመጡም አልጠፉም

በመጀመሪያ ለዚህ ተማሪ ግላዊ ችግር አትክሮትና ክብደት ሰጥተውት ሳይታክቱ ጥረት በማድረግ ለደከመለት
ለፍልስፍና መምህር ዮናታን ምስጋና እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ ። ”

”ሞቅ ያለም” ባይሆን ድጋፉን የሚገልጽ መጠነኛ ጭባ ጨባ ሲሰማ ፥ ዮናታንም ሳያስቡት ለራሳቸው እያጨበጨቡ
ነበር ።

ዮናታን በዕውቀቱ የሚተማመኑበት ጎበዝ ተማርያቸው ሲደክም ወይም ሲሰንፍ እያዩ ቸል ቢሉት ኖሮ የአቤል ውስጣዊ ችግር ተዳፍኖ ውጤቱ ከዩኒቨርስቲው መባረር ነበር በዚህም ሆነ በሌላ ተመሳሳይ ችግር ከአሁን በፊት በርካተታ ጎበዝ ተማሪዎች በአጭር እንደ ቀሩ ጥርጥር የለውም።

በመደበኛ ተማሪነት ወደ ዩኒቨርስቲያችን ከሚገቡት መሐል አብዛኛዎቹ ወጣቶች ናቸው ። ጥሩውንና ገንቢውን ነገር በፍጥነት እንደሚቀበሉ ሁሉ ፥ ለአደጋና ለአፍራሽ ነገሮችም በቀላሉ ይጋለጣሉ። ቀዩኒቨርስቲያችን በተካሔው የሳይኮሎጂ ጥናት ወሠረት የተማሪዎች ዋነኛ ችግር፥
ሦስት ናቸው ። አንደኛ ፡ ወላጆቻቸው ችግረኞች በሆኑ ተማሪዎች ላይ የሚታየው የኢኮኖሚ ችግር ነው ። ይኸው ችግራቸው እያስገደዳቸው የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን እያቋረጡ የወጡ ተማሪዎች አልጠፉም ። ሁለተኛ ፡ የማርክ ወይም የደረጃ ችግር ነው ። ማንኛውም ተማሪ አነስተኛ ውጤት ማግኘት አይፈልግም ። ነገር ግን ፉክክር እስካለ ድረስ መበላለጥ አለ ። ይህን ሐቅ መቀበል አቅቷቸው ፥ ወይም ለጥናት
የሚያደርጉት ጥረትና የሚያገኙት ውጤት አልገጣጠም እያላቸው ከራሳቸው ጋር የሚጣሉም ሞልተዋል ። ሦስተኛ
በሁለቱ ትርጉም ጾታዎች ግንኙነት ላይ የሚታየው ችግር ወይም በድፍን ፍቅር ” እየተባለ የሚጠራው ነው ።

ዛሬ ይዘን የቀረብነው በዚ በሦስተኛው ችግር የተጠመደ ወጣት አርዕስት ነው። ወደ ወጣቱ ጉዳይ ከመግባታችን በፊት ፍቅር የሚለውን ቃል ለማተት እንገደዳለን
እዚህ ላይ የማተኩረው በሁለቱ፡ ጾታዎች መካከል ዕድሜን ተከትሎ የሚመጣው ፍቅር ላይ ነው ።

“ ፍቅር በልባችን ውስጥ ታላቅ ቦታና ክብደት ያለው :ከልባችን ወጭ ግን የሚገባውን ክብደትትና አትኩሮት የነፈግነው ጉዳይ ነው ብል ማጋነን አይመስለኝም » አንድ ፈላስፋ እንዳለው ፥ ዓለምን የሚያንቀሳቅሷት ፍቅርና ረሃብ
ናቸው አንጋፋው ሳይኮሎጂስት ፎሮይድ የፍቅርን ክብደት ሲገልጽ ጥሳቻ ማለት ሞት ነው ፍቅር ደግሞ ከጥላቻ የጠነከረ ነው እናም ፍቅር ከሞት ይጠነክራል ማለት ነው” ይለዋል ። በመሠረቱ ጤናማ የሆነና ጤናማ ያልሆነ የፍቅር ዐይነት አለ ሌላው የሥነ ልቡና ጥናት ሊቅ ሆርኒ
እንደሚለው ጤናማ ያልሆነው የፍቅር ፍላጎት ጠንክሮ ሊገለጽ የሚችለው ለፍቅር ባለን ከመጠን ያለፈ ግምት ነው ።

“ ለመሆኑ ፍቅር ምንድን ነው ? ከባድ ጥያቄ ነው። አብዛኛዎቻችን ፡ፍቅር ዕውር ነው” እንላለን ። ነገር ግን ፍቅር ዕውር አይደለም። ፍቅርን በግድ ዕውር የምናደርገው እኛው ነን ። ወይም በፍቅር ላይ ዕውራኑ እኛ ነን ለማለት እደፍራለሁ ። ይህም ራሱን የቻለ ምክንያት አለን ። የባህል ኋላ ቀርነታችን ፍቅርና ወሲብን ውስጥ ውስጡን እንድናደርጋቸው እንጂ በአደባባይ እንዳንወያይባቸውም። ስለሚያፍነን ?ወይም ከልጅነታችንና ከዝቅተኛ ክፍል ጀምሮ በትምህርት
መልክ ስለማይሰጥ ይመስለኛል ዕውር የሚሆንብን ። አሁንም ሌላው ሳይኮሎጂስት አንግያል እንዲህ ይላል ። “እውነተኛ ፍቅር ዕውር አይደለም ፤ እንዲያውም ዐይናማ ነው ሌሎች የማያዩትን ያያል ። ”

“በርካታ የሥነ ልቡና ጥናት ሊቃውንት ለፍቅር በቅርጽ የተለያየ በይዘቱ ግን የተቀራረበ ትርጓሜ ሰጥተውታል ።
ይሁንና አብዛኛዎቹ “ ፍቅር መተሳሰር ነው በሚለው የተስማሙ ይመስላል ። ሆርኒ እንደሚለው ፍቅር ራስን በግብታዊነት ለሌላው የመስጠት ችሎታ ነው ። ከአብዛኛው የቀን ተቀን ገጠመኛችን እንደምንረዳው ፍቅር የመላማመድም
ውጤት ነው ።

ይህ እንግዲህ በጥቅሉ ለፍቅር ያለን ግምት ነው ።ወደ ዋናው አርዕስተ
ነገራችን ስንመጣ ፥ አቤል የተጠመደው
በዐይን ፍቅር ሆኖ እናገኘዋለን ።

ከተሳታፊዎቹ መሐል አንድ ሰው እጁን ሲያወጣ አይተው ቢልልኝ ንግግራቸውን አቋረጡ ሰውየው ይቅርታ ጠይቆ ጥያቄውን ቀጠለ “ የዐይን ፍቅር የሚለው አርዕስት እንግዳ ነው የሆነብኝ ። ደሞም ለፍቅር ከተሰጠው ሐተታ ጋር የሚጋጭ መስለኝ ። እና በመጀመሪያ ይህንን ሊያብራሪልኝ ቢችሉ።

ጠያቂዉ እጅ ነሥቶ ተቀመጠ ቢልልኝ ቀጠሉ "

“ወደያዚያ ልመጣ ነበር ። በእርግጥም የዓይን ፍቅር ለብዝዎቻችን እንግዳ አርዕስት እንደሚሆን እገምታለሁ ።
በሌላ ስያሜ ፤አስቸጋሪ በመሆኑ ነው በዚሁ ሰም መጥራት የተገደድነው። ወይነቱ የደመ ነፍስ ፍቅር ነው ። አንድን
ነገር አይቶ መወደድ ስሜት ልብ ሲደንግጥ ማንኛውም ዐይነት ፍቅር የሚጀምረው ከዐይንኮ ነው ያላዩት
ሀገር አይናፍቅም ” ይባል የለ ! አይተው ሳያልሙ መላመድ ሆነ መተባበር አይኖርም የሚወዱት ነገር ዓይን ውስጥ ከተቀረጸ በኋላ ነው መተሳሰሩ የሚቀጥለው ። ነገር ግን አይቶ በመውደድ ስሜት ልብ የደነገለጠለት ሰው ተቀራርቦ በአካልና በመንፈስ መተሳሰሩ ቀርቶ በዐይን ልማድ ላይ
ብቻ ሲወሰን ፥ ከዐይን ፍቅር የተሻለ ስያሜ እናገኝለትም።

ይህ ዐይነቱ ሁኔታ” ነው በአቤልና በወደዳት ኮረዳ መሐል የታየው በጥናታችን እንደደረስንበት
አቤል ትዕግሥት አዳነ የምትባለዋን የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ አይቶ ልቡ ውስጥ ከቀረጻት ጀምሮ እነሆ ለአራት ወራት ያህል ያለ አንዳች የተቀራረበ ግንኙነት በዐይኑ ብቻ ወዶአታል ።
በቅርቡ ለውጡን ከተከታተሉት ሰዎች መረዳት እንደቻልነው አቤል ትዕግስትን ቀርቦ ባያነጋግራትም ፥ ቀጥተኛ
የአፍቃሪ ስሜት ይታይበት ነበረ ። በቂ ያለመብላት እንቅልፍ ማጣት ትምህርቱን መጥላትና ብቸኛ መሆን በዐይን ፍቅር ከተጠመደ ወዲህ ያሳያቸው የጸባይ ለውጦች ናቸወ፡፡ ልጅቷን ሳያያት ውሎ መደር፤ አይችልም ። ነገር ግን ይህን እይታውንም ሆነ ውስጣዊ መውደዱን ሰው እንዳያውቅበት በመጠንቀቅ ብቻውን ተሰቃያቷል ። ደረጃው ይለይ እንጂ ትዕግሥት ራሷም ከቀን በኋላ የዐይን
👍1
ፍቅር እንደያዛት ደርሰንበታል ።ሁለቱም እንደ አፍላ ፍቅረኞች ይነፋፈቃሉ ፤ ተፈላልገው ይተያያሉ ፤ ነገር ግን መነጋገር
ቀርቶ ሰላምታ አይለዋወጡም ።

በአዳራሹ ውስጥ ማጉረምረም ተሰማ ። ጉርምርምታው መደነቅንም ፥ ሣቅንም የያዘ ነበር ። የአቤልና የትዕግሥት
ግንኙነት ለብዙዎቹ እንቆቅልሽ ሆነባቸው በአንጻሩ የሁኔታውን እሙንነት ተረድቶ የግል ቁስሉን የነኩትን ያህል እየተስማሙ ጸጥ ብሎ የሚያዳምጥም ነበር ።

የእኛ ጥናት የሚያተኩረው የሁኔታውን ምንጭ አጥንቶ መፍትሄ ከመፈለጉ ላይ ነው አቤል በመጣበት መንገድ ሌሎች
ተማሪዎች እንዳይመጡ በገንቢ ሁኔታ
ምንጩን ከማድረቅ ላይ ነው ። በዚህም መሠረት አንዳንድ አስፈላጊ ጥያቄዎችን አንሥተን እንድንመረምር ተገደናል ።
አቤል ከዐይን ፍቅር ወደ ተግባራዊ ፍቅር ለመሸጋገር ለምን አልቻለም ? የትዕግሥት መልክ ወይም ቁመና እንዴት
ሳበው ? መውደዱን ከሰው በመደበቅ ለምን ይሠቃያል ? የሚሉትንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ተመርኩዘን ጥናቱን አካሔድን ። እንደሚታወቀው ፣ የሳይኮሎጂ ጥናት ሁለገብ ነው ። አንድና ሁለት ሰው ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ አካባቢው በመተባበር የሚሠራው ሥራ ነው ። በመሆኑም አቤል በዩኒቨርስቲ ሕይወቱ በቅርብ የሚያውቁትንና ጎንደር ውስጥ እሱ ባደገበት አካባቢ የሚኖሩትን ሰዎች በማፈላለግ አንዳንድ መረጃዎች ለማግኘት ችለናል ። በተለይም ደግሞ
አቤል አንድ ቀን ብቻ አብሮአት ካደረው ሴትኛ አዳሪ ብዙ ፍንጮች አግኝተናል ።

እስክንድር በሐሳቡ ብርቅነሽ ድቅን አለችበት ። አቤል ምስጢሬ ብሎ ያጫወታትን ሁሉ ፥ “ውይ ፥ ምስኪን የሆነ
ልጅ ! ምንም አያውቅም'ኮ ! ” እያለች ; ከንፈሯን እየመጠጠች ለቢልልኝ ስትዘከዝክላቸው ታየችው ። « ለመሆኑ ፡
ክብረ ንጽሕናውን መውሰዷንስ ነግራቸው ይሆን ? ” ሲል አሰበ ።

“ የአቤልን የአካዳሚክ ሕይወት ስናጠና በትዕግሥት መልክ እስከ ተማረከባት ጊዜ ድረስ በጣም ጎበዝ ተማሪ ሆኖ እናገኘዋለን ። ከትምህርቱ ውጪ ብዙ ማኅበራዊ ግንኙነት የለውም ። ከመረጃዎቻችን መገምገም እንደ ቻልነውም ከትዕግሥት በፊት ሴት ወዶ አያውቅም ። ይህ ማኅበራዊ ልምድ ማጣት አቤል በያዘው የዐይን ፍቅር አጥብቆ እንዲሠቃይ ካረጉት ምክንያቶች አንዱ ነው የሚል ግምት አለን ። የአቤል ችግሩ የወደዳትን ልጅ እንዴት ብሎ
መቅረብና ማነጋግር እንደሚችል አለማወቁ ነው ።

ከጓደኞቹ ወይም የቅርቡ ከሆኑ ሰዎች ለችግሩ ዘዴ እንዳያገኝ ደግሞ የልቡን አፍረጥርጦ ስሰዎች ማማከሩን
አልታደለውም ። ግልጽ የሆነ ጸባይ የለውም ። በራሱ ላይ ከፍ ያለ
መተማመን ስላለው ማንኛውንም ችግር በግሉ የሚወጣው የተሳሳተ እምነት ያሳደረበት በአካዳሚክ ሕይወቱ የተደነቀ
ጭንቅላት መያዙ ነው ። ነገር ግን የአካዳሚ ጉብዝናና ማኅበራዊ ችግርን የመቋቋም ችሎታ የተለያዩ ነገሮች ናቸው
እንዲያውም በማኅበረሰብ ውስጥ የሚገጥሙዋቸውን ቀላል ችግሮች መቋቋም አቅቷቸው ፥ ከራሳችን ጋር ከሚጣሉት ውስጥ አብዛኞቹ በአካዳሚክ ሕይወታቸው የተደነቀ ጭንቅላት ያላቸው ናቸው ።

ፍቅር ማኅበራዊ ነው ። በተለይ በስሜት
አድጎና ዕድሜውን ጠብቆ ለሚከሰተው የሁለቱ ጾታዎች ፍቅር የተዘጋጀ ሥፍራ በውስጣችን አለ ። ይህ ስፍራ በአንድ ወቅት የግድ ፍቅር ሊሰፍርበት ይገባል ። አለዚያ ርካታ አይኖርም ። ይህን ስሜት ጨቁኖና በግል አፍኖ ውስጥ
ውስጡን መሠቃየት ተርፉ የአቤል ዐይነት መድኃኒት አልባ በሽታ ነው ።

“አቤል ፍቅሩን አፍኖ መታየቱ፡ አካባቢው የፈጠረበት በሽታ ነው ። ተወልዶ ያደገው የሴትና የወንድ ፍቅር በምስጢር እንጂ በግልጽ ማድረግ በሚያስነውርበት አካባቢ ነወ : በአቤል እምነት ስላፈቀራት ሴት በግልጽ ማውራት አሳፋሪ የሆነበት ይህ የባህል ተጽዕኖ በአእምሮው ውስጥ
ተቀርጾ ስላደገ ነው ። ደረጃው አድጎ አቤልን ለስሥቃይ ከመዳረጉ በስተቀር ይህ ዐይነቱ ሕመም በብዙዎቻችን ስጥ
ያለ ነው ። አብዛኛዎቻችን ለወደድነው ሰው ቀጥተኛና ግልጽ አይደለንም ።

💥ይቀጥላል💥
👍2
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...ድሮ የሰማችው የንፁሁ የአቢላዛር ታሪክ ትዝ አላት፡፡ኤቢላዛር በሀሰት ውንጀላ በአባቱ ዘንድ እምነት ያጣና፤ባልሰራው ወንጀል፡ ከባድ ስቃይና ቅጣት የደረሰበት እናቱ በህጻንነቱ የሞተችበት ወጣት ነበር፡፡አቢላዛር በቁንጅናው ምክንያት በሕይወቱ ላይ ታላቅ ስቃይና
መከራ ደርሶበታል፡፡የአቢላዛር አባት ባትሮሊዮ ሕጻን ልጁን እናትም አባትም ሆኖ አሳደገው፡፡ አቢላዛር ዕድሜው ለአቅመ አዳም ሲደርስ አባቱ ባትሮሊዮ
ሚስት ለማግባት ፈለገ፡፡ሚስት ቢያገባ ለእሱም፤ ለልጁም፤ ረዳት - እንደምትሆን
በመገመት በዕድሜዋ ወጣት የሆነችውን ውቧ ጉቲኤራን አገባት፡፡ጉቲኤራ በቁንጅናዋ እዚህ ጉደለሽ የማትባል ብትሆንም፤ በራሷ ቁንጅና ላይ የነበራት ኩራት ወደታች የወረደው ፤ የባሏን ልጅ አቢላዛርን ያየችው ዕለት ነበር፡፡ በዚያን ዕለት በፍቅር የተነደፈ ልቧን ሐኪምም፤
ፀበልም፤ ማንም እንደማያድነው አወቀች፡፡ መድሃኒቱ አንድ ነው፡፡ እሱም
አቢላዘር ብቻ! ስሜቷን አምቃ እየተሰቃየች፣ በአንድ ወገን የእንጀራ ልጂ
የመሆኑ ጉዳይ ቢያስጨንቃትም፤ ፍቅሯን መቋቋም አልቻለችምና፤የእንጀራ ልጅነቱን ጉዳይ ችላ በማለት፤በፍቅር ልታጠምደው ቆርጣ ተነሳች፡፡
ጉቲኤራ በፍቅር የተረታችለት መሆኑን እንዴት አድርጋ እንደምትገልጽለት ጨንቋት ውስጥ ውስጡን ስትሰቃይ ኖረች።ቀስ በቀስ ውስጥ ውስጡን የሚያብሰለስላት፣ የሚያብከነክናት፤
የፍቅር መጋዝ፤ በአካሏም ላይ ለውጥ እያስከተለ ሄደ፡፡
አፏን ከፍታ ፍዝዝ፣ ድንዘዝ፣ ብላ የምትቀርበት ጊዜ ጥቂት አልነበረም፡፡ ይህ ሁኔታ ለአቢላዛር በፍፁም አልተገለጠለትም ነበር፡፡በእርግጥ አቢላዛር ማንም በቀላሉ አይቶት የሚያልፈው ልጅ አይደለም፡፡ ያጓጓል፡፡ በዚሁ መሀል ለጉቲኤራ አንድ አጋጣሚ ተፈጠረላት። በጣም አስደሳች አጋጣሚ፡፡
ባሏ ባትሪሊዮ ግመሎቹን በሙሉ እየነዳ
የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ለማምጣት ድንበር ጥሶ የሚሄድበት ቀን ደረሰ፡፡
ባትሮሊዮ ቢያንስ ከሁለት ወራት በፊት አይመጣም፡፡ በቃ በዚህ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ የሚያለቅሰው ልቧ ፈውስ ሊያገኝ ነው፡፡ እሺ አለም እንቢ፤ በውድም ይሁን በግድ፤ አቢላዛርን ማግኘት አለባት፡፡ እንቢ ቢል ልታስገድደው ወሰነች፡፡
አቢላዛር እናትም አባትም ሆኖ ላሳደገው ለአባቱ ያለው ፍቅር የተለየና በአለም ላይ ከሚያፈቅራቸው ነገሮች ሁሉ በላይ ነው፡፡
የአባቱ የጉዞው ቀን ደረሰ፡፡ አቢላዛር አባቱን በፍቅር ተሰነባበተው፡፡ ጉቲኤራ ደግሞ በቶሎ አይመልስህ ብላ ሸኘችው፡፡ ከዚያም ባትሮሊዮ በሄደ በሳምንቱ ጉቲኤራ ተቅበጠበጠች፡፡ ከዚህ በላይ ብትቆይ የምትፈነዳ መሰላት፡፡ከዚህ በላይ መቆየት መታገስ አቃታት፡፡ አቢላዛር
ደግሞ እስከአሁን ድረስ ቅንጣት ታክል ችግሯን አልተረዳላትም፡፡
በሣምንቱ መጨረሻ፤ ያ ምሽት፤ እንደወትሮው ሁሉ፤ አቢላዛር የመኝታ ክፍሉን በር ቀርቅሮ የተኛበት ምሽት ነበር፡፡ ጉቲኤራ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት አካባቢ ሲሆን የውስጥ ሱሪዋን ብቻ እንደለበሰች ወደ መኝታ ክፍሉ መጣች፡፡
“አቢላዛር! አቢላዛር ድረስልኝ! እባክህ በሩን ቶሎ ክፈትልኝ!”
እያለቀሰች በሩን በሃይል መታቸው፡፡
አቢላዛር በዚያን ሰዓት በሆነ ቅዠት ላይ ነበረ፡፡ በሩ በሃይል ተንኳኳ፡፡ ተንጓጓ፡፡ በዚህ ጊዜ ከእንቅልፉ ባኖ ቢያዳምጥ፤ የእንጀራ እናቱ በእንባ ሲቃ በታፈነ ድምጽ ስትጣራ ሰማ፡፡ በሁኔታው በጣም
ተደናገጠና በሩን ከፈተው፡፡
የሚያየውን ነገር ማመን አቅቶት፤ አሁንም በህልሙ እንዳይሆን ተጠራጠራና፧ አይኖቹን አሻሽ፡፡ በርግጥም በህልሙ አልነበረም፡፡ በውኑ ነው፡፡

የጉቲኤራ ራቁት ገላ፣ ያገጠገጡ ጡቶቿ፤ ባለጥንድ አፈሙዝ ድግን መትረየስ መስለው፤ ከፊት ለፊቱ ተወድረዋል፡፡
ዓይኖቿ በማያቋርጥ የእንባ ምንጭ ይዋኛሉ፡፡
“ምን ሆንሽ ጐቲኤራ?” ደንግጦ ጠየቃት፡፡
“አነቁኝ፡፡ መጡብኝ ሊበሉኝ ነው” ወተወተች፡፡
“እነማናቸው? ማን አባቱ ነው ሊበላሽ የመጣው?”
በእንጀራ እናቱ ላይ እጁን የሰነዘረውን ጠላቱን ሊተናነቀው አይኖቹ በንዴት ቀልተው ጠየቃት፡፡
“ግዴለም ቆይ ቁጭ በል፡፡ አሁን ሄደዋል፡፡”
“ጅል፤ ነገር የማይገባህ ደደብ” አለችው በልቧ፡፡ እኒያ የቆሙ ጡቶቿ ያ ውብና ማራኪ ራቁት ሰውነቷ የማይታየው እውር አናደዳት፡፡
“ሰይጣኖች ናቸው፡፡ ሰዎች አይደሉም፡፡ ይኸውልህ እዚህ ላይ ነው በጣም የትጫኑኝ፡፡ ተመልከት እዚህ ጋ” የቀኝ እጁን ይዛ ጡቶቿ መካከል አስቀመጠችው፡፡
አቢላዛር በየዋህነት እዚያ ጡቶቿ ሥር የሚሰማትን ህመም እንዲወገድላት አሻሻት፡፡
በዚያን ሰዓት ጉቲኤራ ጦፋ በሃሣቧ ከዚያ በኋላ በሚፈጠረው
ትርኢትና፤ በትርኢቱ ውስጥ የሚስማትን የእርካታ ስሜት እያጣጣመችው ነበር፡፡
“በቃ እዚሁ እሆናለሁ ከአሁን በኋላ እዚያ ዳፍንታም ክፍል አልመለስም” አለችውና ሄዳ እሱ አልጋ ላይ ቁጭ አለች፡፡
“ብርድ ይመታሻል ልብስ ልበስ” ብሎ የራሱን ሸሚዝ እላይዋ ላይ ጣል ቢያደርገው ፤ ወደዚያ ውርውር አድርጋ...
“ይልቁን እሱን በደንብ አድርገህ እሽልኝ፡፡ ያለበለዚያ ያመኛል
በታዘዘው መሠረት እዚያ ጡቶቿ
ሥር፧ሰይጣኖቹ ያሳመሟትን ቦታ፤ ለማዳን ማሻሸት ቀጠለ፡፡ጉቲኤራ ደግሞ እንደዚያ
ጡቶቿን ሲያሻሽላት የምትሆነውን አጣች፡፡ እንደሰም ቀልጣ መፍሰስ ጀመረች።
ሙሉውን ሌሊት በእንባ እየታጠበች ብትለምነው ንዴቱ እየባሰበት እንጂ ሃሣቡን የመለወጥ አዝማሚያ ሳያሳይ ቀረ። በዚህ ሁኔታ በተደጋጋሚ ፈተነችው፡፡ አቢላዘር ግን ወይ ንቅንቅ! አለ፡፡
በመጨረሻም እንዳልተሳካላት ቁርጧን ስታውቅ፤ ልትበቀለው ቆርጣ ተነሳች፡፡
ሴራዋን ስትጎነጉን ሰነበተች፡፡ ባሏ ከሁለት ወር በኋላ ሲመጣ፣በናፍቆት ከመቀበል ይልቅ፤ እሳት ጎርሳ፤ እሳት ለብሳ፤ ተቀበለችው:: የሁለት ወር ሙሉ ናፍቆት አቃጥሎት ሲስማት አመናጨቀችው፡፡
“የጋብቻ ውላችንን አፍርስልኝ” ስትል ጮኽችበት ባትሮሊዮ በነገሩ ተደናግጦ ምክንያቱን ቢጠይቃት...
“ምንም እንኳን ባልወልደው፤ ልጅህ ፤ ልጄ ይሆናል ብዬ ነበር እዚህ ጣጣ ውስጥ የገባሁት፡፡ እሱ ግን ለሚስትነት ፈለገኝ” ብላ ከፍላጐቷ ውጭ አስገድዶ በግብረ ሥጋ የተገናኛት መሆኑን እያለቀሰች ነገረችው፡፡
ባትሮሊዮ እንደ አይኑ ብሌን የሚያየው አንድዬ ልጁ፣ እናትም አባትም ሆኖ ተሰቃይቶ፣ በሽንት ተጨማልቆ ያሳደገው የሚወደው ልጁ ተመልሶ እጁን ስለነከሰው ፤ ሀዘኑ ጣራውን አለፈና፤ ለዚህ ወደር ለሌለው ጥፋቱ ቅጣቱን ሲያውጠነጥንለት ዋለ፡፡በመጨረሻ የመጣላት ሃሣብ መግደል ቢሆንም፧ መግደል ብቻውን አላረካህ አለው፡፡ ከዚያ በላይ በቁሙ እያለ እንዲቀጣ ፈለገ፡፡
እንደዚያ በጥጋብ እንዲያነጠንጥ፤ እንደዚያ ያለውን አፀያፊ ሥራ እንዲሠራ፤ የገፋፋውን ችግሩን ከላዩ ላይ ሊያስወግድለት ወሰነና፤ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ላይ የመኝታ ቤቱን በር አስከፍቶት ገባ፡፡
አቢላዘር ከእንቅልፉ ባንኖና፤ በሁኔታው ተደናግጦ፡
“ምነው አባባ?” ሲል ጠየቀው፡፡
“ዝም በል!! የምትታዘዘውን ብቻ ትፈጽማለህ!!” ሲል ጠንካራ ትዕዛዝ ሰጠው፡፡አባቱ እሳት ለብሶ፤ እሳት ጉርሶ፤ ሲያይ ልጁ በአባቱ አዲስ ፀባይ ተደናግጦና፤ ግራ ተጋብቶ፤ የታዘዘውን ሁሉ በአክብሮት ይፈጽም ጀመር፡፡ራቁቱን አስቁሞ እጁንም እግሩንም አሰረው፡፡ ያለተቃውሞ
በአባቱ ትዕዛዝ መሠረት እጁንም፤ እግሩንም፤ ለገመድ ሰጠ፡፡
“በሽንትህ ተጨማልቄ፤ ያለ እናት ያሳደግኩህ አባትህ መሆኔን አውቀህ ፤ ቤቴን ትዳሬን አክብረህ ስለቆየኸኝ ፤የረጅም ዘመን ድካሜን ዋጋ ለመክፈል እንቅልፍ አጥተህ ስለጠበቅከኝ፤ ይህንን የዋልክልኝን ከፍተኛ የልጅነት ውለታህን ተቀብዬ፤ እኔም የአባትነት ውለታዬን
🔥21👍1
በዚህ ልከፍልህ እገደዳለሁ፡፡” በማለት እንዲናገር ፋታ እንኳን ሳይስጠው! ከመቅጽበት ደብቆ የያዘውን ስለት በማውጣት ዐይኖቹ ላይ አወናጨፈና፤ እጁን ወደታች ሰንዝሮ ቢመትረው፣ ውድና ትንሿ አካሉ ከቀሪ አካሉ በመለየት መሬት ላይ ወድቃ ተንፈራፈረች፡፡ አቢላዛር
ባልሰራው ሀጢአት ወንድነቱን ተነጠቀ....
ትህትናም ይህንን የአቢላዛር ታሪክ ከራሷ የህይወት ገጠመኝ አዛምዳ፤በሀሳብ
ባህር ውስጥ ስትዳክር ቆየች፡፡ ንፁህነቷን
የሚያውቅላት አጥታ፤ የልቧን፤ የውስጧን የሚረዳላት አጥታ፤እሱ እንደዚያ በሀዘን ቅስሙ ተሰብሮ በምሬት ሲናገር፤ የሷም ቅስም አብሮት ተስብሮ ልቧ ከውስጥ ደም እያነባ መሆኑን ሳያውቅላት ቀርቶ ብሩክ ንግግሩን ጨረሰ፡፡ በምትወደው ሰው ዘንድ እንደዚያ ያለች ባለጌ ሆና
በመታየቷ እያዘነች፤ ከአልጋው ላይ ወረደችና ያበጠ ፊቷን ተጣጥባ፣
ልብሷን ለባብሳ፤ ጨረሰች፡፡ሁለቱም ምንም አይነት የምግብ ስሜት አልነበራቸውም፡፡ለወትሮው ጠዋት ሲነሱ ከሻምበል ቤት ከፍ ብላ ካለችው ግሮሰሪ
ገብተው፤ ጭማቂ ጠጥተው፤ ተጨዋውተው፤ ተሳስቀው፤ ነበር
የሚለያዩት፡፡ ዛሬ ግን እጅ ለእጅ ተያይዘው ከቤት ወጡ :: በልብ ግን
ተለያይተው....
የሱ ፍላጐት መጀመሪያ እሷን በታክሲ ከሸኛት በኋላ ለመሄድ ነበር፡፡
“ቆይ መጀመሪያ አንተ ሂድ፡፡ ሥራ ይረፍድብሃል፡፡ እኔ ቀስ ብዬ እደርሳለሁ” አለችው በሻከረው ድምጿ፡፡ ከዚያም ታክሲ አስቁሞ...
“በይ ትሁት እንዳትጠፊ፡፡ የማዘርን ሁኔታ እየደወልሽ ንገሪኝ፡፡ አንዱዓለምና አዜብን ሰላም በይልኝ እሺ? ቻው በማለት
ከተሰናበታት በኋላ እጁን በታክሲው የበር መስታወት ውስጥ አውለበለበላት፡፡
ዓይኖቿ ቅዝዝ ብለው፤ ታክሲው ከዓይኗ እስኪሰወር ድረስ በቆመችበት ቀረች፡፡ እንባዋ ፈስሶ ተንጠፍጥፎ አልቋል፡፡ አሁን
የምታፈሰው እንባ የላትም፡፡ ቆሽቷ እርር ድብን እያለ፣ ደም እያለቀስ፣ የመጨረሻውን ስንብት እሷም እጆቿን በማውለብለብ ተሰናብታው፤ በትካዜ ነብዛና፤ በባዶነት ስሜት ተውጣ፤ ወደሰፈሯ በሚያደርሳት ታክሲ ውስጥ ገባች፡፡...

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_አንድ ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና ...ድሮ የሰማችው የንፁሁ የአቢላዛር ታሪክ ትዝ አላት፡፡ኤቢላዛር በሀሰት ውንጀላ በአባቱ ዘንድ እምነት ያጣና፤ባልሰራው ወንጀል፡ ከባድ ስቃይና ቅጣት የደረሰበት እናቱ በህጻንነቱ የሞተችበት ወጣት ነበር፡፡አቢላዛር በቁንጅናው ምክንያት በሕይወቱ ላይ ታላቅ ስቃይና መከራ ደርሶበታል፡፡የአቢላዛር አባት ባትሮሊዮ ሕጻን ልጁን…»
#ሰመመን


#ክፍል_አርባ_ሰባት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

“ሕመሙ በአቤል ላይ ሊጠነክርበት የቻለው ፍቅሩ ከዐይን ባለማለፉ ነው የሚል ግምት አለን ። የዐይን ፍቅር
የሚጠነክርበት ምክንያት የወጭውን ወይም ያጓጓውን ክፍል ብቻ ስለሚወድ ነው ። ተቀራርቦ ውስጣዊ ገጽታዎችን የሚተያዩበት አፍላ ፍቅር የሕመም ኃይሉ ሊቀንስ ይችላል ፤ ምክንያቱም በሰዎች መልክም ሆነ ባህርይ ፍጹምነት የለምና ነው ። ለዐይን ፍቅር አቤል የመጀመሪያ ሰው ኣይደለም ። ችግራቸው አድጎ እንዲህ አደባባይ ባይወጣም የዚህ
በሽታ ምርኮኞች ጥቂት አይደሉም ። መልካሙ ተበጀ
“ ሰላምታ ኣልሰጠኋት # አላነጋገርኳት ፥ በዐይን ብቻ እያየሁ አንድ ዓመት ወደድኳት ”” እያለ የሚጫወተው ዘፈን
በብዙ ሰዎች መወደዱና በዘፈን ምርጫ ፕሮግራም በተደጋጋ መቅረቡ ችግሩ በጥቂት ሰዎች ብቻ ያልተወሰነ መሆኑን
ያስገነዝበናል ።

ቢልልኝ ንግግራቸውን አቋርጠው ለጥያቄ ፋታ ሰጡ ።ነገር ግን ሁሉም በተመሳሳይ ከማዳመጥ በቀር ለጥያቄ እጁን
ያወጣ አልተገኘም ።

“ መልካም ! ” ሲሉ ቀጠሉ ቢልልኝ ፣ “ የእቤል ፍቅር ከዐይን ያላለፈበትንና ስሜቱን ደብቆ በግሉ የሚሰቃይባቸውን ምክንያቶች በመጠኑ አይተናል ። እስቲ ደግሞ የትዕግሥት መልክ ወይም ቁመና አቤልን እንዴት ሳበው ?ወይም ትዕግሥት አቤል ዓይን ወሰጥ እንዴት ልትገባ
ቻለች ? የሚለውን ነጥብ እናያለን ። ለዚህ ጥናት እንዲረዳን የትዕግሥትን ፎቶግራፍ ወስደን ከአቤል የሕይወት ታሪክ ጋር ለማስተያየት ሞክረን ነበር ። ሆኖም ፥ በአገራችን የሥነ ልቡና ጥናት አሁን ካለበት ዝቅተኛ ደረጃና የኢኮኖሚ
ችግር አንጻር አቤል ከጎንደር ሕይወቱ ጀምሮ የተቀራረባቸው ዋና ዋና የሴት ምስሎች ማግኘት አስቸጋሪ ሆኖብናል ። በጎንደር ዉስጥ አንድ ዋርካ ሥር አዘውትረው ን ይገናኙ የነበሩ ሁለት ፍቅረኞች በአቤል የልጅነት ጭንቅላት
ውስጥ ከፍተኛውን ቦታ ይዘው ይገኛሉ ። ምናልባትም የልጅቷ መልክ ወይም ቁመና ከአሁኗ ትዕግሥት ጋር የሚመሳ
ሰልበት አለ የሚል ግምት አለን ።
አቤል አንድ ቀን አብሯት ላደረው ሴትኛ አዳሪ እንዳጫወቻት

(ይህን ስታነቡ የተሰማቹ ስሜት እኔንም ተሰምቶኛል ግን በጊዜው ችግር አልነበረውም መሰለኝ)

ከሆኔ ፥ ትዕግሥትን ከዱሮ ጀምሮ የሚያውቃት ይመስለዋል ። ነገር ግን አቤልና ትዕግሥት በተለያየ ክፍለ ሀገር ስላደጉ፡የቆየ ትውውቅ ሊኖራቸው አይችልም ።ቁም ነገሩ፡የእሷን የመሰለ መልክ ከልጅነቱ ጀምሮ ሳያስበው
ጭንቅላቱ ውስጥ ተቀርጾበታል ማስት ነው ። ፎሮይድ እንደሚለው ፍቅር የሚጀምረው በልጅነት ነው ። በልጅነታ
ችን የምናፈቅረውና የምንፈልገው ሰው በጭንቅላታችን ውስጥ ተደብቆ እድጎ ነው- በጉልምስናችን ጊዜ ምርጫችን
የሚሆነው ። የመልክ ወይም የውበት ማነጻጸሪያችንም የሚመሠረተው ባደግንበት አካባቢ ዓይን ነው ። በሀገራችን በተዘዋዋሪም ቢሆን ይህን ሐቅ የሚያንጸባርቁ አንዳንድ አባባሎች አሉ ። ለምሳሌም ፥ ባልና ሚስት ከአንድ ዉሃ ይቀዳሉ ” ሲባል በሁለቱም ውስጥ ተቀርጾ ያደገና ተግናኙ በኋላ የዳበረ ተመሳሳይ ስሜትና ምርጫ መኖሩን ያሳያል ። ሌላው ደግሞ ፡ የ እናትህን የመሰለች እስክታገኝ ሚስት አታገባም ” የሚለውም አነጋገር የሚያሳየን የውበት ማነጻጸሪያዎቻችን ከልጅነት ጀምሮ ጭንቅላታችን ውስጥ የሚቀረጹት ወላጆቻችን ወይም ሌሎች በአካባቢው
በቅርብ የምናገኛቸው ሰዎች መሆናቸውን ነው ።

“ ጀርመናዊው ፈላስፋ ሾፐንሀወር የፍቅረኛ ምርጫን በሚመለከት እንዲህ ብሎ ነበር “ ለፍቅር ምክንያት ከሚሆነው ነገር ዘጠኝ አሥረኛው በአፍቃሪው ወስጥ ያለ ነው። አንድ አሥረኛው ምናልባት በተፈቃሪው ላይ ይኖር ይህናል ። ” ይህም የሚያሳየን አንድ ሰው አፍቅሮ የሚመርጠው ራሱኑ ወይም በውስጡ ያለውን ስሜት እንጂ ከውጭ
አለመሆኑን ነው ። ለማንኛውም ይህ የአፈቃቀር ሁኔታ ለእኛ እንጂ ለአቤል ችግር የለውም ።

ዐይን አይከለከልም : አቤል አይቷል ። መውደድ አይከለከልም ፡ ያያትን ወዷል ። ነገር ግን ፥ ፍቅሩ በዐይን በመወሰኑ ማስደሰቱ ቀርቶ ትርፉ ሕመም ሆኖበታል
እና አሁን እንዴት እንርዳው ነው ጥያቄው ዮናታን አቤልን ለመርዳት በግላቸው ብዙ ጥረዋል ። ከትዕግሥት ጋር አሁን ያለበት ሁኔታ ጤናማ መልክ እንዲይዝ ለማድረግ
ከተቻለ እኛም ከመርዳት ወደኋላ አንልም ሆኖም በትምህርቱ ረገድ ለሚኖረው ችግር የአካዳሚክ ኮሚሽኑን ርዳታ
እንጠብቃለን አቤል በልጅቷ ፍቅር ከተጠመደበት ጊዜ ጀምሮ ፡ “ ትምህርቱ ላይ በጤናማ አዕምሮ ላለመቀመጡ
በርካታ ማስረጃዎች አሉ ምግብ አዳራሽ ውስጥ ከተማሪው መሐል ወድቆ ታሟል፤ በአእምሮ ንክነት ሳይኪያትሪስት ድረስ ተወስዶ ታክሟል " እኚህንና የመሳሰሉትን ማስረጃዎች በመደገፍ አቤል በዚህ ሴሚስተር የተከታትላቸው ኮርሶች ተሰርዘውለት በሚቀጥለው ዓመት እንደገና እንዲጀምራቸው የአካዳሚክ፦ ኮሚሽኑን ፈቃድ እንጠይቃለን ።

“ በእኛ በኩል ያለው ዝግጅት ይኸው ነው አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ካለ መድረኩን ለሌሉች እለቃለሁ ። ”

ቢልልኝ ጨርሰው ከተቀመጡ በኋላ ፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ያህል ከጎን ለጎን መወያየት ያለፈ ጥያቄ አልነበረም
ዮናታን ተነሥተው አሁን አቤል ያለበትን ሁኔታና ከእሳቸው ጋር ለተወሰነ ጊዜ እንዲኖር መወሰናቸውን ለስብሰባው
ገለጹ " ይህ ሁኔታ የብዙዎቹን ስሜት ለእርዳታ ገፋፍቶ ነበር ዮናታንን ተከትሎ አንድ ሌላ ሰው ለመናገር ተነሣ ።

“ ትንሽ ነገር እንድናገር ይፈቀድልኝ " በእውነት ይህ ጉዳይ አትኩሮት ተሰጥቶት ለዚህ መድረክ መቅረቡ ደስ ያሰኛል እኔ እስከማውቀው ድረስ ጎበዝ ተማሪዎቻችን
በፍቅርም ሆነ በሌላ ማኅበራዊ ችግር እየተደናቀፉ ትምህርታቸውን ሲያቋርጡ እስካሁን ዩኒቨርስቲያችን ብዙም
ትኩረት አልሰጣቸውም ። አንድ ተማሪ ያፈቀራት ልጅ ገድሎ ጓደኛውንም ለመግደል ሲፈልግ ሌላው ሲያብድ
የሥነ ልቡና ጥናት መሰሉችም ሆኑ ዩኒቨርስቲው በቸልታ ነው የተመለከቱት ። ወይም ድርጊቶች ከተከናወኑ በኋላ
ዜናውን ከማድነቁ ላይ ነው የተተኮረው ። ለመሆኑ ፡ ጎበዝ ተማሪያችን በትምህርቱ ሲደክምና ደረጃው ሲቀንስ ያገኘውን ሰጥተን ባወጣ ያውጣህ ከማለት በቀር ተማሪውን በግል ጠርተን ለማጤን ወይም ችግሩን ለማማከር የሞከርን ስንቶቻችን ነን ? ይህ ለማንም መምህር የሚከብድ ርዳታ አይደለም ። ! የሚያሳዝን ቸልተኝነት ያለብን ይመስለኛል አሁን ግን መልካም አጀማመር ነው የታየው ። እንግፋበት እላለሁ ። እኔም ማንኛውንም ዐቅሜ የሚፈቅደውን ርዳታ ለማድረግ ከጎናችሁ እቆማለሁ ። ”

ሰውየው ከኋላ ስለነበር፡ ዮናታን ዘወር ብለው በአድናቆት ተመለከቱት ። እንግዳ አልነበረም ። እዚያው ግቢ የታሪክ መምህር ነው ። “ ወይ ልብ ለልብ አለመተዋወቅ ! አሉ ዮናታን በሐሳባቸው

ቢልልኝ የሰውየው ሐሳብ የግድ እንዲናገሩ ገፋፋቸው ። መልካም ነው ። ድጋፍህን ተቀብለናል ። ሆኖም እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት የእኛ ዓላማ የሚያተኩረው ግለሰቦችን በማስታመም ላይ ሳይሆን ችግራቸውን ወስደን አጠቃላይ መፍትሔ ከመፈለጉ ላይ ነው ። ይህ ደግሞ በዩኒቨርስቲያችን ውስጥ ብቻ ሳይሆን ፥ ከዚህ ውጭም መጠናትና መታሰብ ያለበት ነገር ነው ። የዩኒቨርስቲው አባላት ከማኅበረሰቡ የወጡ ናቸው ። ችግሩንም ይዘው የሚመጡት ከማኅበረሰቡ ነው ። ለምሳሌ ፥ በየአካባቢውና በየትምህርት ቤቱ ፍቅር በማኅበራዊ ኑሮ ክፍልነቱ ግልጽ ተደርጎ ትምህርት ቢሰጥበት ፡ ሁለቱም ጾታዎች መፋቀሪያ ጊዜያቸው ላይ ሲደርሱ እንዲህ ዐይነት ችግር አይገጥማቸውም ግልጽና ጤናማ ዜጋ ለማፍራት ከአካባቢው ከሥር ከመሠረቱ ነው
መኮትኮት ያለበት ። እናም ኋላቀር አስተሳሰብ ከፈጠረብን ችግር ለመላቀቅ የሁላችንም ጥሪ የሚያተኩረው።
የባህል አብዮት ላይ ነው።

ስብሰባው እንዳለቀ ዮናታን የቸኮሉት ይህን መልካም ዜና ለሚስታቸው ለማብሠር ነበር ። ስብሰባው በጥሩ ሁኔታ
ማለቁ ብቻ ሳይሆን ፥ ከስብሰባው ውጭ በዮናታን ጥረት የተደነቁ ሰዎች አቤልን ለመርዳት ያላቸውን በጎ ፈቃድ ሲገልጹላቸው ደስታቸው ገደብ አጣ ። የአቤልን የትምህርት ጉብዝና ያውቁ የነበሩ ሰዎች፡አቤል ዮናታን ቤት መሆኑ ከተገለጸላቸው በኋላ ትምህርቱን እንደገና እስኪጀምር ድረስ እንደ የዐቅማቸው ገንዘብ በማዋጣት እንደሚተባበሯቸው ነው- የነገሩዋቸው ።

“ ይኸኛውን ርምጃችንን በጥሩ ሁኔታ ተወጥተነዋል ” አሉት ዮናታን እስክንድርን “ የሚቀጥለው ጉዳይ
አቤልን ከትዕግሥት ጋር ማገናኘቱ ወይም ማለያየቱ ነው "
አንድም በጥሩ መንፈስ ልቡ ውስጥ እንድትታሰብ ማድረግ ካልሆነም ከልቡ ውስጥ ፈንቅሎ ማውጣት ! ”

እስክንድር ራሱ ይህን ጉዳይ እያሰበበት ነበር " ስብሰባው እንዳለቀ ፡ ዮናታን ሁኔታውን ለሚስታቸው ለማብሰር ስሜታቸው ሲቻኮል • የእሱ ስሜት ደግሞ ዘሎ ያረፈው ትዕግሥት ላይ ነበር ።አፍ አውጥታ ስለአቤል ከጠየቀችው
ጊዜ ጀምሮ እኒህ የዐይን ፍቅረኞች የሚቀራረቡት የተስፋ ጭላንጭል በልቡ ውስጥ እየፈነጠቀ ነበር ። እናም ለትዕግሥት ስለ አቤል ለማጫወት ወይም እሷ ስለ አቤል ያላትን ጥልቅ ስሜት ለመስማት አጋጣሚ ነበር የሚጠብቀው "

“ አቤልና ትዕግሥትን ማገናኘት ነው እንጂ' ማለያየቱ ምን ሲደረግ ይታሰባል ? ” አላቸው እስክንድር ፈገግ ብሎ
“ ለሕይወቱ እንቅፋት ከሆነችበት አራርቆ እንዲረሳት ማድረጉ ይመረጣል ብዬ ነዋ ! ” አሉ ዮናታን ግራ በተጋባ ስሜት "

እዬዬ ! ልቡ ውስጥ ገብታ ካደገች በኋላ መፈንቀሉ አስቸጋሪ ነው። ለጊዜው ርቆአት ሊረሳት ቢሞክርም ወደ ዩኒቨርስቲ በሚመለስበት ጊዜ ሲያያት ቁስሉ የሚቀሰቀስበት ይመስለኛል ። የአፍላ ፍቅርን ዛፍ ሥሩ መቁረጥ የሚቻል አይመስለኝም " ታዲያ ምን ይሻላል ? ” አሉት ዮናታን በተጨነቀ
ስሜት ።ሁለቱን አገናኝተን የ ፍቅራቸው ከዐይን ተሻግሮ በቅርብ እንዲተሳሰሩ ማድረግ ነዋ ! ”
• ከተቻለማ ጥሩውም መንገድ እሱ ነበር
“አይጠራጠሩ ! ” ሲላቸው ፡ የተማመነበት ነገር ምን አንደሆነ ለራሱም በደንብ ግልጽ ሆኖ አልታወቀውም ነበር ።

💥ይቀጥላል💥
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


እቅዳቸው በአሳዛኝ ሁኔታ መክሸፉን፤ መክሸፍ ብቻም ሳይሆን የሷና የሻምበል ብሩክ ፍቅር እስከ ወዲያኛው ዳግም ላይጠገን እንክትክት ብሎ መሰባበሩን ስትሰማ አዜብ ክፉኛ ደነገጠች፡፡ ምን
የማይሆን ምክር መክሬ ጉድ ያደረኳት፤ በሚል ጸጸት ተቃጠለች፡፡ ለዚህ
ችግር መንስኤው እሷ እንደሆነች
ሁሉ “እኔ ነኝ ጉድ ያደረኩሽ ትሁትዬ፡፡ እኔ ነኝ ጥፋተኛዋ፡፡ ድሮውንም ቢሆን አንቺ አይሆንም ብላሽ ነበር። አጉል የማይሆን ምክር መክሬ እዚህ ጣጣ ውስጥ የከተትኩሽ እኔ ነኝ፡፡በደሉ የኔ ነው፡፡ ወይኔ ጓደኛዬ... እዬዬ እያለች አብራት
ስታለቅስ ዋለች፡፡

እየዋለ እያደረ ግን ለትህትና ህይወት መበላሽት ዋናው ምክንያት እሷ ያለመሆንዋን፤ ትህትና ለተደጋጋሚ ፈተና የተጋለጠችው በሷ ምክንያት ሳይሆን በሌላ ሰው ጦስ መሆኑን፤እያመነች መጣች፡፡የወንጀል ድርጊቱ እንደተፈፀመባት ወዲያውኑ ህጋዊ እርምጃ ማስወሰድ ሲችሉ፤ እንደሻው የአዜብ ወላጆች የክርስትና ልጅ ነው፤ አባቱም ለትህትና ባለውለታ ናቸው፤ በሚል ሰበብ ጉዳዩን አዳፍነው፤ አለባብሰው ማለፋቸው ተገቢ ያለመሆኑ እየተገለጠላት መጣ፡፡ በዚያን ሰአት በደም ተጨማልቃ የጠበቀቻት ትህትና ታየቻት፡፡ ከዚያም ከዶክተር ባይከዳኝና
አሁን ደግሞ ከሻምበል ብሩክ ጋር ለነበራት ግንኙነት ዋናው የጸቡ
መንስኤ የእንደሻው ጦስ መሆኑ ያለጥርጥር ታወቃት፡፡ እንደሻው በሰላም
እንቅልፉን ይለጥጣል፡፡ ትህትና ግን በየቀኑ ታነባለች፡፡ በዚህ ላይ አንድም
ቀን እንኳን የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶት ይቅርታ ጠይቆ አያውቅም፡፡ስለዚህ የእጁን ማግኘት አለበት ብላ ወሰነች፡፡ በእንደሻው ምክንያት ትህትና ክብረ ንጽህናዋን፣ ሥራዋን፤ እጮኛዋን፤ አጥታለች። ግዴለም! ስትል በልቧ ዛተች፡፡

አንዱ አለም በሁኔታው ግራ ተጋብቶ.. “እታለም ሥራውን ተውሽው እንዴ?” ብሎ የጠየቃት እለት “ትንሽ ዕረፍት ወስጄ ነው
አልተውኩትም” ብላ ዋሽታው ነበር፡፡ በኋላ ግን በውሸቷ መቀጠል አልቻለችም፡፡ ሥራው ያልተስማማት በመሆኑ ያቋረጠችው መሆኑን
ገለፀችለት፡፡
“አይዞሽ ቆንጆ የቢሮ ሥራ ነው የምትይዥው፡፡ የምን ጫማ
መሸጥ ነው”? ሲል ሞራል ሰጣት፡፡
ከሥራው የበለጠ እንዱዓለምን ያሳሰበው እህቱ ይሄንን ሰሞን ሙሉ ለሙሉ መለወጧን፣ በሆነ ባልሆነ ማልቀስ ማብዛቷን፣ ሲጠሯት ቶሎ ያለመስማቷን፣ ፍዝዝ ማለቷን፣ እህል እምብዛም ያለመድፈሯን፣ እንዳትሞት ያህል ብቻ አፏ ላይ ጣል , አድርጋ በቃኝ ማለትን
ማዘውተሯን፣ ሰውነቷ እየጠወለገ መሄዱን፣ በአጠቃላይ ሻምበል ብሩክን
ካገኘች በኋላ ደስተኛ መሆን የጀመረችው ልጅ ሰሞኑን በሚገርም ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ተለውጣ በማስተዋሉ ነው፡፡

በዚህ ላይ ደግሞ እንደታላቅ ወንድሙ የሚያየው “አንዱዓለም እስቲ እንካ ይህችን ለደብተር መግዣ፣ ለፀጉርህ መስተካከያ አይዞህ በርትተህ ተማር” እያለ የሚንከባከበው የእህቱ እኛ የሻምበል ብሩክ ድምፁ እየጠፋ ነው፡፡ ነገሩ አሳሰበው፡፡ አጠራጠረው፡፡
ይሄ ሁኔታ ከሳምንት በላይ አስቆጠረ፡፡ አንዱዓለም ጥርጣሬው እየጨመረ መጣ፡፡ እህቱ ምንም ነገር ልትነግረው ፈቃደኛ አልሆነችም፡፡ መላው ቢጠፋው አዜብን ሊያማክራት ፈለገ፡፡
አዜብ አንጀቷ እየተቃጠለ፤ የዚህ ሁሉ በደል ምንጭ የሆነው እንደሻው የሚቀጣበት መንገድ ጨንቋት ውስጥ ውስጡን በንዴት ስትንጨረጨር ነው የከረመችው፡፡
አንዱዓለም ስለእህቱ ሁኔታ ሲጠይቃት፤ ተደስታ አንድም ሳታስቀር እንደሻው የፈፀመባትን ወንጀል ዘከዘከችለት፡፡ በእህቱ ላይ የተፈፀመውን ወንጀል ሲሰማ አንዱአለም በንዴት ተንዘፈዘፈ። ከዚያም
በላይ እንደ እብድ አድርጎት ነበር፡፡ ከዚያም ያንን ግፈኛ ሊበቀለው
የሚገኝበትን ቦታ ጠየቃት፡፡
አዜብ አላመነታችም፡፡ “አሳይሀለሁ” አለችው፡፡ ለዚሁ ጉዳይ ተቀጣጠሩና፤ እንደሻው የሚገኝበትን ሱቅ ልታሳየው ይዛው ሄደች፡፡
ትህትና ይህንን ሁሉ አታውቅም፡፡ ወንድሟ ከሰው ጋር ተጣልቶ አደጋ እንዳይደርስበት ስለምትሰጋ፤ በፍፁም እንዳይሰማ አዜብን አደራ ብላት ነበር፡፡ አዜብ ግን እሺ አልነግረውም ብትላትም፤ እሱ ቀድሞ ባይጠይቃት ኖሮ ቀድማ ልትነግረው ተዘጋጅታ ነበር፡፡
በሷ እምነት እንደሻው ለፈፀመው ግፍ ተጠያቂ መሆን አለበት፡፡ ለወንጀሉ በቂ ቅጣቱን ማግኘት አለበት፡፡ አለበለዚያም በአፏ አላወጣችውም እንጂ ፤ በሱ ምክንያት ከባድ ችግር ላይ የወደቀች ልጅ
በመሆኗና ክብረ ንጽህናዋን የደፈረው እሱ በመሆኑ ወደደም ጠላም
ሊያገባት ይገባል ነው እምነቷ፡፡
የዚያን ዕለት አንዱዓለም እንቅልፍ በዐይኑ ሳይዞርለት ነጋ:: አንጅቱ እያረረ አደረና፤ በማግስቱ ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ሲሆን ብቻውን ወደዚያ ሱቅ ሄደ፡፡
ከሱቁ ሲደርስ እንደሻው ሲጃራውን እያቦነነ አገኘው፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ሲጃራውን ምጉ ቁራጩን በእግሩ ደፈጠጠና የመጣለትን ቁርስ ሊበላ
ሻይ በመቅዳት ላይ እንዳለ፤ ዐይኖቹ እንደ በርበሬ ቀልተው፤ ፊቱ ሳምባ እንደመሰለ፤ በንዴት መላ ሰውነቱ የሚንቀጠቀጥ ወጣት በሩ ላይ ገጭ አለበት፡፡
አንዱአለም የሰራ አካላቱን እንደ ኤሌክትሪክ የሚነዝር የጥላቻ
ስሜት ወሮት ተንደርድሮ ሄደና ያንን የሻይ ማንቆርቆሪያ አንስቶ ፊቱ ላይ ቸለሰበት፡፡ እንደሻው በዚያ ትኩሳ ሻይ ተቀቀለ፡፡ በድንጋጤ ከባንኮኒው ላይ ዘሎ ወጣና ግብ ግብ ተያያዙ፡፡

አንዱዓለም በእህልና፤ በቁጭት፤ ሰይጣናዊ ጉልበት ተላብሷል፡፡
እንደሻው ግን በብርክ ስለተዋጠ ሊቋቋመው አልቻለም፡፡ እየደጋገመ ፊቱን
እንደተርብ ጠዘጠዘው፡፡ ከዚያም ትንሽ በትንሹ ከድንጋጤው ተመልሶ
አንዱዓለምን ሊያንቀው ሲዘጋጅ ጐረቤትም መንገደኛም መሀል ገባና
ገላገላቸው፡፡
አንዱዓለም እየጮኸ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ይሳደብ ጀመር፡፡
“አንተ የውሻ ልጅ!! በዚህ ብቻ የምለቅህ እንዳይመስልህ...!”
አለው፡፡ እንደሻው እየተርበተበተና በድንጋጤ ዐይኖቹ እንደተበለጠው
ይህንን ሰይጣን ማን ላከብኝ በሚል ስሜት ግራ ተጋብቶ ይመለከተዋል፡፡
አበራ በሃሣቡ ድቅን አለ፡፡ “በቃ አበራ የላከው ሰው መሆን አለበት” አለ በልቡ፡፡

መቼም አንዳንድ ግዜ ፍቅር እንደ አጀማመሩ አያልቅም፡፡
በተለይ በጥቅም ላይ የተመሰረተ ፍቅር ዕድሜው አጭር ነው፡፡ ከአበራ ጋር ንግዱን የጀመሩ ሰሞን ፍቅራቸው ሌላ ነበር። እየዋለ እያደር ሱቃቸው ሲደረጅ፣ ጠቀም ያለ ገንዘብ መምጣት ሲጀምር፣ እንደሻው ተስገበገበና፤ ሞቅ ባለው የሽርክና ፍቅራቸው ላይ ቀዝቃዛ
ውሃ ቸለሰበት፡፡
የዚያን ዕለት አበራን የተናገረው ንግግር ትዝ አለው፡፡ “አበራ እስከዛሬ ድረስ የወሰድከው ሳይታሰብ፤ ያዋጣኸውን ገንዘብ በጥሬው እመልስልሃለሁ፡፡ ግድ የለም እኔ ልጐዳ” በማለት ነበር በድንጋጤ ያስበረገገው፡፡
“እና ሱቁን የግልህ ብቻ ልታደርገው?” አበራ በንዴት እየተንቀጠቀጠ፡፡
“የንግድ ፈቃዱ የግሌ መሰለኝ፡፡እዚህ የምፍጨረጨረውም በግሌ
አንተም ከዚህ በላይ ልትጐዳኝ የምትፈልግ መሆኑን እያየኽው
አይመስለኝም” ቁርጡን ነገረው፡፡
“እሺ እንደሻው እግዚአብሔር ለሁላችንም የሥራችንን ይስጠን፡፡ አንተ ግን ሰው አይደለህም! እባብ ነህ! ያንተ ነገር በቃኝ!ሥጋዬም አይደለህ፡፡ በቃኝ! በቃኝ!” እያለ እየተማረረ እየተንቀጠቀጠ
ከሱቁ ወጥቶ የሄደው ትዝ አለው፡፡ በዚሁ ሀሳብ መሀል ግን...
የትህትና ወንድም መሆኔን እወቅ!” ለሠራኸው ሥራ በዚህ ብቻ የምንላቀቅ እንዳይመስልህ! እስከመጨረሻው እፋረድሃለሁ!!” በማለት ፎከረበት፡፡

በዚህ ጊዜ እንደሻው አመዱ ቡን አለ፡፡ እሱ እንደሆነ ትህትናን ከነመፈጠሯ ነበር የረሳት፡፡ አሁን ግን ጉድ ሊፈላ ነው፡፡ የሚበቀል ወንድም አላት ለካ !!
👍3
ይህ ወጣት እንደማይምረው አወቀ፡፡ የሰራው ሥራ ትዝ አለው። ትህትና መጣችበት፡፡ ልጁን አየው፡፡
“እንዴት ነው የሚመሳሰሉት?” በሃሣቡ፡፡
“አበቃልኝ እንደሻው!! ምን ይሻለኛል?” በዚህ በጭንቀት ውስጥ አንድ ሃሣብ ብልጭ አለለት፡፡ ጋርጠው! ፊቱ መጥቶ ተጋረጠ፡፡ ከአሁን በኋላ ፋታ ሲሰጠው፤ አድፍጦ የሚገድለው መሰለው፡፡ ስለዚህ?
“ሳይቀድመኝ ልቅደመው” ሲል ወሰነ፡፡ ገላጋዩ ሲተራመስ ቀስ ብሎ የሚላላክለትን ጩሎ ጠራው፡፡ ጩሎው መጣ፡፡
“ጋርጠውን በአስቸኳይ ይፈልግሃል በለው” ልጁ እንደተላከው መልዕክቱን ሊያደርስ እየበረረ ሄደ፡፡ የሰው ግርግር ሳይቀንስ፤ አንዱዓለም ከአካባቢው ሳይርቅ፤ ጋርጠው ከች አለ፡፡
“እንዳይሞት እንዳይድን አድርገህ!!” ሃምሳ ብር አስጨበጠው፡፡
“እንዳልከው!!” ሃምሣ ብሩን ላጥ አድርጐ ኪሱ እየከተተ፡፡
ከዚያም ገላጋይ መስሎ ተቀላቀለና አንዱዓለምን በሥውር መከታተሉን
ቀጠለ፡፡

ግርግሩ ከበረደ በኋላ አንዱዓለም በእልህና በቁጭት እንደተዋጠ
ወደ አምባሳደር ሲኒማ ቤት ጉዞ ጀመረ፡፡ ከኋላው ጋርጠውን የመሰለ ጅብ እንዳስከተለ አላወቀም፡፡
የጋርጠው ሰውነት የሚያስፈራ ነው፡፡ በሬ
የዋጠ ነው የሚመሰለው፡፡ የሰው ዝሆን....
አንዱዓለም እስከ ምሽቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ድረስ እዚያ ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ ከጓደኞቹ ጋር ሲጫወት ካመሸ በኋላ ወደ ቤቱ ሊሄድ ተሰናበታቸው፡፡ ጋርጠው በንቃት ይከታተለዋል፡፡ “ኦርማ ጋራዥ አካባቢ ሲደርስ፤ በዚያ በጨለማ ውስጥ፤ መልኩ እራሱ እንደጨለማው የጨለመ
ግዙፍ ሰው ከየት መጣ ሳይባል፤ በከፍተኛ ምት ማጅራቱን አደቀቀው፡፡

አንዱዓለም ህሊናውን ከመሳቱ በፊት
“እንደሻውን መድፈር ማለት ሞት ማለት መሆኑን እወቅ!”
የሚል አስፈሪ ድምጽ መስማቱና ከዚያም መኪና ገጭቶት መሄዱን ነው የሚያስታውሰው፡፡
ጭውው.... አለበት፡፡ የሆነ ጥቁር ነገር ጋረደው፡፡ ከዚያ በኋላ የሆነውን አያውቅም፡፡ ጋርጠው የተሰጠውን ግዴታ በሚገባ ከተወጣ በኋላ በፍጥነት ከአካባቢው ተሰወረ፡፡ በዚያን ሰዓት ከመንገድ ዳር ቱቦ ውስጥ ሆኖ በቃተተ ድምጽ
“ድረሱልኝ!” የሚል የጣዕር ጩኸት የሚያሰማ ሰው ድምጽ የሰሙ ሁለት
መንገደኞች ጠጋ ብለው ቢመለከቱ፤ እዚያ የቆሻሻ መውረጃ ቦይ ውስጥ
በአፍ በአፍንጫው ደም የሚፈሰው ወጣት ተመለከቱ፡፡
በሁኔታው ደንግጠው የእርዳታ ድምጽ ሲያስተጋቡ፤ ሰዎች ከግራና ከቀኝ ብቅ ብቅ እያሉ ወደዚያ ይሮጡ ጀመር፡፡ ትርምሱ ሌላ ሆነ፡፡ ለእርዳታ ከመጣው ሰው መካከል እንዲት ሴት የተመታውን ልጅ ማንነት አጣራችና እሪታዋን አቀለጠችው....
“ወይኔ አንዱዬ.... ወይኔ ....” ያዙኝ ልቀቁኝ አለች። የሂሩት ጓደኛ ሜርኩሪ ነበረች፡፡ ከዚያም እሩጫ በሩጫ ሆነ፡፡ ወዲያውም የፖሊስ አንቡላንስ መኪና ደረሰና የተመታውን ጉዳተኛ ይዞ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በረረ፡፡
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሪከቨሪ ክፍል ገብቶ፤ አስቸኳይ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ተደረገለት፡፡ ስለደረሰው አደጋ እንዲነግሯት ሜርኩሪ ለሂሩት ሰው ልካባት ስለነበረ በጠዋቱ ከች ብላለች ። የአንዱአለም የወንድና የሴት ጓደኞቹ በጠዋቱ ተሰባስበው ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ በሁኔታው የተደናገጡ ይመስላሉ። እንደዚያ ተሰባስበው ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ እያሉ፤ ብዙ ደም ስለፈሰሰው ደም
የሚያስፈልገው መሆኑ ተገለጸላቸው፡፡ በዚህ ጊዜ እርስ በርሳቸው ይተያዩ
ጀመር፡፡
“እኔ አለሁ” የሚል ጠፋ፡፡ ወሬ ለማዳመቅ እንጂ ትንሽ መስዋዕትነት ከፍሎ ፤ ትልቁን የስው ልጅ ህይወት ለማዳን “ አለሁ”
የሚል ታጣ፡፡ ሂሩት እንደዚያ እየጮኽች ስትመጣ፤ ደም ሳይሆን ነፍሷን
የምትሰጥ ነበር የምትመስለው፡፡ድምጧ ጠፋ፡፡
“ለምን እህቱን አንጠራትም?” አለ ትህትናን የሚያውቃት ጓደኛው የሁሉንም ጭንቀት ተመልክቶ ::
“በጣም ጥሩ ነው እንዲያውም የእህቱ ደም ይሻለዋል” ደም ለመስጠት ያልፈለገ ሌላ ጓደኛው፡፡የራሱን ደም መስጠት ባንችል እንኳን እህቱን በጠዋቱ ጠርተን
ከምናስደነግጣት ለምን
አንገዛም?” አለች ሜርኩሪ ያመጣችውን አዲስ ሃሳብ እንደሚቀበሉ በመተማመን፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ሁለት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና እቅዳቸው በአሳዛኝ ሁኔታ መክሸፉን፤ መክሸፍ ብቻም ሳይሆን የሷና የሻምበል ብሩክ ፍቅር እስከ ወዲያኛው ዳግም ላይጠገን እንክትክት ብሎ መሰባበሩን ስትሰማ አዜብ ክፉኛ ደነገጠች፡፡ ምን የማይሆን ምክር መክሬ ጉድ ያደረኳት፤ በሚል ጸጸት ተቃጠለች፡፡ ለዚህ ችግር መንስኤው እሷ እንደሆነች ሁሉ “እኔ ነኝ ጉድ ያደረኩሽ ትሁትዬ፡፡…»
#ሰመመን


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...ዮናታን ቤታችው ሲደርሱ፥ ሞኒካ የስብሰባውን ሁኔታ ለመስማት ጓጉታ በሕንፃው መናፈሻ በኩል ቁልቁል እየተመለከተች መምጫቸውን በመጠባበቅ ላይ ነበረች ።

“ እንዴት ነው ? ” አለቻቸው ፡ ከፊቷ ላይ የማይጠፋ ፈገግታዋን ብልጭ አድርጋ "

“ ደስ የሚያሰኝ ስብሰባ ነበር " በብዙ ሰዎች ላይ ቀና ስሜት አሳድረናል” አሏት፡እጅዋን ይዘው ወደ ውስጥ እየገቡ ጥናቱንም ቢልልኝ በጥሩ መልክ አቅርበውታል የጥናቱን ጽሑፍ ከእሳቸው ተውሼ ሰሞኑን አመጣልሻለሁ”

ሞኒካ ስብሰባው ላይ ለመገኘትና በአቤል ላይ የተካሔደውን ጥናት ለማዳመጥ ከፍተኛ ጉጉት ነበራት ጥናቱ የቀረበው በአማርኛ ስለ ነበር በደንብ የማትሰማው ቋንቋ ሆኖባት ነው የቀረችው።

“ አካዳሚክ ኮሚሽኑስ ምን አለ ? ” ስትል ጠየቀቻቸው "

“ የእነሱ መደበኛ ስብሰባ ገና ከአራት ቀን በኋላ ነው ።ሆኖም ስብሰባችን ላይ የነበሩት የኮሚሽኑ አባላት በግል ተስፋ ሰጥተውኛል ። እና ጥሩ ውጤት እጠብቃለሁ ።

ዮናታን ከሚስታቸው ጋር እያወሩ ልባቸው አቤልን ለማየት ጓጉቶ ነበር • ሳሎን ውስጥ ሲያጡት የት እንዳላ
ለማወቅ ሞኒካን መጠየቅ አላስፈለጋቸው? በቀጥታ ወደ መጻሕፍት ክፍላቸው ሔዱ ። በሩን በዝግታ ከፍተው
ሲገቡ'አቤል በሚያነበው መጽሐፍ ክፉኛ ተመስጦ አገኙት ።
ሊረብሹት አልፈለጉም ። በሩን በዝግታ ዘግተው ለመመለስ ቢያስቡም እጃቸው የበሩን እጀታ መጎተት አልቻለም ለአቤል አንዳች ነገር ሊነግሩት ፈለጉ ። ቀን ምን እንደሚነግሩት ወይም ደስታቸውን እንዴት እንደሚገልጹለት አያውቁም ነበር። አቤል በእሱ ጉዳይ ስብሰባ መካሔዱን አያ
ውቅም ። ጉዳዩ ክብደት ተሰጥቶት አደባባይ መቅረቡ በአንድ በኩል ሊያስደስተው ቢችልም በሌላ በኩል ደግሞ የሚደብቀው የዐይን ፍቅር መጋለጡ ስሜቱን ሊጎዳው ስለሚችል፥ ይህን በማመዛዘን ዮናታን ሆነ ብለው ነበር ያልነገሩት አሁንም ይህን ሊነግሩት አልፈለጉም። እንዲሁ ብቻ በፈገግታ የደስታ ስሜታቸውን ሊያስተላልፉለት አሰቡ ።

ወደ ውስጥ የጫማቸው ድምፅ አቤልን ከተመሰጠበት አባነነውና ካቀረቀረበት መጽሐፍ ቀና አለ ። ፈገግታቸውን
ሲያይ ፡ ምን አገኙ ይሆን ? ብሎ አልተደነቀም ። ንባብ ላይ ተቀምጦ በማግኘታቸው የተደሰቱበት መሰለው ።
“ እንደምን ውለሃል ? ” አሉት ፡ እንዲህ የሳበው መጽሐፍ ምን እንደሆነ ለማወቅ ዐይናቸውን ወደ ርዕሱ እየወረወሩ
ደኅና ፡ ሲገቡ አልሰማሁዎትምኮ ” አላቸው ፡ የደረሰበት ገጽ እንዳይጠፋው ማዕዘኑ ላይ እያጠፈ ።

የሚያነበው “ ማን አገንስት ሄምሰልፍ ! ” “ ሰው ራሱን ሲጻረር ! የሚለው የዶክተር ሜኔንገር መጽሐፍ ነበር " ዮናታን ይህን አርዕስት ሲያዩ ደነገጡ ። ካልጠፋ
መጽሐፍ ይኽን ለምን መረጠው ? የሚል ጥርጣሬ አደረባቸው፤ፈገግታቸው በአንድ አፍታ ጠፋ ። ፈጥነው ሊጠይቁት ግን አልደፈሩም ። ከውጭ ይዘውት የመጡት የደስታ ስሜት ከውስጥ ጥቀርሻ ሲለብስ ተሰማቸው ።

“ ወደ ውጭ ወጣ ብለን እንናፈስ ? ዛሬ ንባብ ላይ ብዙ የቆየህ ይመስለኛል ” አሉት ' ስሜቱ በመጥፎ ነገር ተወጥሮ ከሆነም ወጣ ብሎ መናፈሱ ይሻለዋል በሚል ግምት ።

“ በደስታ!” አላቸው ከተቀመጠበት እየተንጠራራ ።

አመላለሱም ሆነ የፊቱ ብርሃን ከውስጡ መጥፎ ስሜት የወጠረው ሰው አይመስልም ። ዮናታን በግምታቸው ግራ
ተጋቡ ።

ሊብሊንግ ፡ ሽርጥሽን አውልቂና ወጣ እንበል ”አሏት ሚስታቸውን ወደ ሳሎኑ ተመልሰው ።

ሞኒካ ቤት ውስጥ ከሆነች ከወገቧ ነጭ ሽርጥ አይጠፋም።

“ አቤልስ ይመጣል ? ”አለቻቸው ፈቃደኛነቱን ለማረጋግጥ ።

“ አዎ ፡ እወጣለሁ ብሏል ” አሏትና " ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብለው ፥ የዛሬ ውሎው እንዴት ነው ? ” አሏት ፡

የመጽሐፉ አርዕስት እየከነከናቸው ነበር
“ ደኅና ነው የዋለው ። እንዲያውም ንባብ ከመጀመሩ በፊት እሱ ባደገበት አካባቢ ያለውን የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት ሲያጫውተኝ ነበር ” አለቻቸው ሽርጧን እየፈታች ።

ዮናታን ውጭ ወለው ቤት ሲገቡ ስለ አቤል ሁኔታ መጠየቅ ልማዳቸው ነበር ። አቤልም ዮናታን ቤት መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ ያሳየው ለውጥ ቀላል አልነበረም » እብሯቸው ሲኖር ሳምንት ሆኖታል ። ከእራሱ ጋር መታረቅ ጀምሯል ለውጡ የሞኒካ የድካም ውጤት ነው
ማለት ይቻላል ።

ለመጀመሪያው ሁለት ቀን አቤል ራሱን ገዝቶ ቤት ውስጥ መቀመጡ በጣም አስቸግሮት ነበር " ትዕግሥት በሐሳቡ
እየመጣችበት ብረር ብረር ይለው ነበር ። ሲጠላው የነበረው ዩኒቨርስቲ ይናፍቀዋል ትንሽም ቀለል የሚለው እስክንድር መጥቶ አጫውቶት ሲሔድ ነበር ።

ዮናታንና ሚስታቸውም ይህን ችግሩን ሳይረዱለት አልቀሩም ። ሐሳቡን ከትዕግሥትም ሆነ ከሌላ መጥፎ
ስሜት ለማዘናጋት የተጠቀሙበት ዘዴ መንፈሱ ለሥራ መወጠር ነበር ለቀን ተቀን እንቅስቃሴው ፕሮግራም
አውጥተውለታል ። ሞኒካ ምግብ በምታበስልበት ሰዓት አብሯት ሆኖ የምግብ አሠራሯን እያጠና በአንዳንድ
ማኅበራዊ አርዕስቶች ላይ ይወያያሉ በቀን የተወሰነ ሰዓት እሷ ጀርመንኛ ታስተምረዋሶች ። እሱም በፈንታው
ለተወሰነ ሰዓት አማርኛ ያስተምራታል ። ይህ አቤል ከመምጣቱ በፊት የዮናታን ሥራ ነበር ። ስለዚህ ማታ ማታ ሞኒካ ቀን የተማረቻቸውን አንዳንድ አዳዲስ የአማርኛ ቃላት ስትናገር፥ ዮናታን ወደ አቤል እየመተለከቱ ፥ ጥሩ ረዳት አገኘሁ እንዲያው ከኔ የተሻለ ዘዴ ሳይኖርህ አይቀርም ” በማለት ይክቡታል ። በመጀመሪያ ለንባብ የተመደበለት የተወሰነ ሰዓት ነበረው ውሎ ሲያድር ወደ ንባቡ ፍቅር ሲመለስ ግን፡ለንባብ ከተቀመጠበት ስፍራ የሚነሣው .
በቀስቃሽ ሆነ ። ከንባብ ውጭ ለመዝናናት ያህል በቤት ውስጥ የሚያገኛቸውን የጀርመን ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሥዕላዊ መግለጌ የያዙ መጻሕፍት ማገላበጠት በመንፈስ
ውስጥ የጥሩ ሕይወት ስሜት ያሳድርበት ነበር ። የሀገር ውስጥና የውጭ ሙዚቃ በሙሉ ጆሮው ሰምቶ ለማድነቅ
የቻለው በዚህ ሳምንት ውስጥ ነው ። ትርጉሙም ሆነ ጣዕሙ ሲገባው ያልቻለውና ዮናታን የሚያደንቁትና በተመስጦ ያሚያዳምጡት፡የእነ ቫግነርና ቤትሆቭን ክላሲካል ሙዚቃ ነው "
ቤት ውስጥ ሙዚቃ ማዳመጡ ቢያስደሰተውም አንዳንዴ ትካዜ ስለሚጫነው ፥ ለመቆጠብ ወይም ብቸኝነት በማያጠቃው ሰዓት ብቻ ለማዳመጥ ተግዶ ነበር ።

ቀን በዚህ ዐይነት ውሎ ወደ ማታ ላይ ሦስቱም ነፋስ ለመቀበል ወደ ከተማው ጸጥታማ ቦታዎች ብቅ ይላሉ ።
አሰልሠው ሲኒማ ይገባሉ ። ይህን የመሰለው የሕይወት እንቅስቃሴ አቤልን ከብቸኝነት ስሜቱ በማዘናጋት ሐሳቡ
አንድ ነገር ላይ ብቻ በማተኮር እንዳይሠቃይ ከፋፍሎታል ። ያም ሆኖ ትዕግሥትን እያሰበ ሳይጨነቅ አያድርም
ግን ጭንቀቱ እንደ ቀድሞው አልነበረም ፡ በሥራ በተወጠረ አእምሮ ወይም ደክሞ እንቅልፍ በፈለገ ጭንቅላት ስለሆነ የሚያስባት ፥ ያን ያህል አይረበሽም ።

አቤል ከብርቅነሽ ቀጥሎ በሕይወቱ የገጠመችው ግልጽ ሴት ሞኒካ ነች ። በአንድ ምሽት ዕድሜም ቢሆን
የብርቅነሽ ትሑትና ግልጽ ተፈጥሮ በልቡ ተቀርጿል ። ምናልባትም የብርቅነሽ ግልጽነት ከማይምነቷ ጋር የተያያዘ
የልብ ክፍትነትና የጥሬነት ውጤት ሊሆን ይችላል ። የሞኒካ ግልጽነት ግን ምሁራዊ ጥልቅ ትርጉምና ድምቀት አለው ። ከአኳኋኗ መረዳት እንደሚቻለው “የምንፈጽመው ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር የህልውናችን ነጸብራቅ ነው ፤ ስለሆነም
እኛነታችንን ደብቀን መሠቃየት የለብንም ፤ መጥፎ የምንለውን አምቀን ጥሩ የምንለውን ብቻ የምንተነፍስ ከሆነ
ውስጣችን ገምቶ ደማችን ይደፈርሳል የምትል ትመስላለች አቤል በቀላሉ ነው የተግባባት
👍4
አንዳንዴ በንጹሕ ጨዋታዋ ሲመሰጥ ! ስሜቱን ደብቆ የሚወጣጠር ተፈጥሮውን
ይረግማል። እያደር ራሱን መደበቅ ከማይችልበት ደረጃ እየደረሰ ነበር " የእሷ ግልጽነትና ማብቂያ የሌለው ጣፋጭ
መስተንግዶ ሳይወድ በግድ ልቡን እየከፈትበት መጥቷል "

በተለይ አንድ ቀን ሞኒካ ከዮናታን ጋር ስላላት ግንኙነት ግልጽ ሆና ያጫወተችው ነገር ጭንቅላቱ ውስጥ ተቀርጾ ቀርቷል ። ዮናታን ለንባብም ሆነ ለጥናት ሥራ ቤታቸው ውስጥ አንዴ ከተቀመጡ ወጣ ብሎ የመዝናናቱ ነገር አይታያቸውም ። የሕይወታቸውን አብዛኛውን ክፍል ለኣካዳሚክ ጥረት ስለሰጡ ደስታ የሚሰጣቸው ከጠረጴዛ ትጣብቆ መዋሉ ነበር ። ሞኒካ ደግሞ መጫወት ትፈልጋለች መዝናናት ትፈልጋለች ! ለውጥ ያምራታል ይህ ልዩነት ለተወሰነ ዓመታት አብሮአቸው ቆይቷል ። ከዚህ በላይ የከ
በደው ልዩነት ደግሞ በግብረሥጋ ግንኙነት ረገድ ያለው ነበር " የዮናታን የጠነከረ የአካዳሚክ ሕይወትና የዕድሜ
ያቸው መግፋት የወሲብ ፍላጎታቸውን ስለሚያዳክምባቸው ጥማታቸው ከሞኒካ ጋር እኩል አይሆንም " ቀዝቃዛ ይሆኑባታል ። አንዴ ሞኒካ መኝታዋ ውስጥ ገብታ ዮናታንን በመጠበቅ ብዙ ቆየች • በመጨረሻም በሽታ ዕርቃኗን ከመኝታዋ ወጥታ ወደ መጻሕፍት ክፍሉ ሔደች ። ዮናታን መጽሐፍ ላይ እንዳቀረቀሩ ነበሩ ስሜቷ ተወጣጥሮ ቢያሠቃያትም ኅሊናዋን ስላልሳተች፡እንዳትረብሻቸው ፈርታ ወደኋላ
ተመለሰች “ ነገር ግን ብሽቀቱ ልቧ ውስጥ እንደ ተቀበረ ስለ ነበር ሳሎኑ ጠረጴዛ ላይ ያገኘችውን የዕብነ በረድ የሲጋራ መተርኮሻ በደመ ነፍስ አንሥታ ስትወረውር የብፌውን መስታወት ከሰከሰችው ደገመችና ብፈው ወስጥ
የነበሩትን ስኒዎች አንከታከትቻቸው "

ዮናታን ደንግጠው ከጥናት ክፍቸው እየሮጡ ሲደርሱ ሚስታቸው ዕርቃኗን ተገትራ ፡ የመስታወቱ ድቃቂ መሪት
ተዘርግፎ ተመለከቱ ጸጉሯ ተበታትኖ ፡ ነጭ ፊቷ ፍም መስሎ ሲያዩዋት ልዩ ፍጥረት መሰለቻቸው " ምን ሆንሽብኝ ሊበሊንግ ? ” አሏት ። ዐይኗን ከማፍጠጥ ሌላ ፈጥና አልመለሰችላቸውም ። የማይጠገብ ትሕትናዋን ያህል ' የተናደደች እንደሆን አያድርስ ነው • የቤት ዕቃ አይተርፋትም “ በብሽቀት ጊዜ ሰው እንዳታስቀይም ወይም እንዳትጎዳ የስሜት እሳትን የምታበርዳው ዕቃ በመሰባበር ነው ። ያን ዕለት ችግሯን ለዮናታን ፍርጥርጥ አድርጋ ነገረቻቸው ። ከዚያ ጊዜ በኋላ፥ ዮናታን የምሽት የንባብ ጊዜያችውን ቀይረው እሷን ቀድመው መኝታ ውስጥ እየገቡ ይጠ
ብቋት ጀመር ።

አቤል ይህን ከእሷው አፍ መስማቱ፡ ነው ያስደነቀው ።ድርጊቷን ስትነግረው በልጅነቱ ሴት አያቱ ሴት ልጅ ካልተገረዘች ዕቃ ትሰብራለች ” የሚሉት ፈሊጣቸው ነበር ትዝ ያለው ሞኒካ ለአቤል ሌሎችም ነግሮች በግል ባጫወተችው ቁጥር በዚህ ጥቂት ቀናት ውስጥ ስሜቱ በቀላሉ ታዛዥ እየሆነ መጣ ። አቤል በሞኒካ የሚደነቅበት ሌላዉ ነገር ደግሞ የቤት ውስጥ እንቅስቃሴዊ ነው ። ዐርፋ አትቀመጥም ። ደስታዋ የሚመነጨው ከሥራና ሰውን ከማስደሰት ይመስላል።

ሞኒካ ከሀገሯ እንደ መጣች ለሁለት ዓመት ያህል በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በነርስነት ሠርታለች። ነግር ግን ከጊዜ
በኋላ የመድኃኒት ሽታ ለጤንነቷ ስላልተስማማት ፥ ይኸን ስራዋን ለማቆም ተገደደች። ያ ሲቀር የቤት አስተዳደር ሥራ
ኮስተር ብላ ያዘች ።ለእሷ ትልቁ ሥራዋ ምግብ ማብሰል አይደለም ። ለቤቷ ሕይወት ለመስጠት ነው የምትደክመው
ለዐይን እንዳይሰለች ትጥራለች ። ጥልፍ የመሳሰሉት የእጅ ሥራዎቿ አንድ ግድግዳ ላይ ከተወሰነ ጊዜ በላይ ኣይቆዩም ።
ይለዋወጣሉ ። የቤት ውስጥ የአበባ ተክሎቿን መከርከምና ውሃ ማጠጣት ሕፃን ልጅ አቅፎ እንደሚጫወት ነው የሚያስደስታት ። ከአልጋ ጀምሮ የቤት ዕቃዎች አቀማመጥ በተለያየ ጊዜ ትለዋውጣለች ። የመኖሪያ ቤት ዕቃዎች አቀማመጥ መቀያየር በነዋሪው ላይ ምን ያህል መንፈስ የማደስ ኃይል
እንዳለው ታውቃለች ። ዐይን በቀላሉ ይወዳል ፤ ዐይን በቀላሉ ይጠላል ፤ ዐይን በቀላሉ ይታለላል ። ዐይን ከረካ፡ የውስጥ
ስሜት በጥላቻ አይደፈርስም ። መኖሪያ ቤቱ የሚስብ ከሆነ ልብ ወደ ውጭ አይኮበልልም ። ይህን መመሪያዋ አድርጋ
የያዘች ትመስላለች ሞኒካ ። ቤቱን አዘገጃጅታ ስትጨርስ መጽሐፍ ታነባለች የየወቅቱን የውጭ መጽሔቶች እያነበበች ለዮናታን ሥራ የሚጠቅም አርዕስት ስታገኝ መርጣ ታስቀምጥላቸዋለች ። ጀርመን ካሉት ዘመዶችዋ ጋር ደብዳቤ
መጻጻፍ የሚያስደስታት ጊዜ ማሳለፊያዋ ነው ። አከታትላ ስትጽፍ አቤል እየገረመው ምን እንደምትጽፍ ለማወቅ
ይጓጓል ።

ይህ ሁሉ የሞኒካ ሁኔታ በአቤል ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳረፈበት የአስተሳሰብ ተጽዕኖ ቀላል እንዳልሆነ
ዮናታን በሚገባ ይከታተላሉ ። ሕይወትን ከመናቅና ከመጥላት ሕይወትን ወደ ማድነቅ እየተሸጋገረ መሆኑን ከኣንዳንድ ድርጊቶቹና ጨዋታዎቹ ለማወቅ ችለዋል (ዛሬም ትንሽ ያስደነገጣቸው ይዞ ያገኙት ከወትሮው ለየት ያለ ዐይነት መጽሐፍ ነው

“ መሔድ እንችላለን” አላቸው አቤል ከመኝታ ክፍሉ ወደ ሳሎን ብቅ ብሎ ጸጉሩን ሲያበጣጥር ነበር የቆየው ።
ዮናታንና ሚስታቸው ተሰናድተው እሱን በመጠበቅ ላይ ስለ ነበሩ፥ ወዲያው ተያይዘው ወጡ ። አቤል ፊት ላይ ከወትሮው ለየት ያለ ይነበብ ነበር ። ምን ተሰምቶት ይሆን ?ዮናታንና ሞኒካ ስሜቱን መጋራት ፈለጉ። ሆኖም ደረጃውን ለመውረድ አሳንሰሩ ውስጥ እስኪገቡ ድረስ ምንም ቃል አልተነፈሱም ።

የዛሬው ንባብህ እንዴት ነበር ? ሲሉ ዮናታን ፈገግ ብለው ጠየቁት ።ጥሩ ነበር እንዲያውም ... ” ብሎ አቋረጠ ።
የሚቀጥለውን ለመስማት ቢጠብቁትም መልሶ ዋጠው፡፡ መደበቅ ፈልጎ ሳይሆን እንዴት እንደሚነግራቸው ተቸግሮ
ነበር ።

ያንን ይዘኸው የነበርከውን መጽሐፍ እንዴት ወደድከው ? ” ሲሉ ዮናታን ደግመው ጠየቁት ።

“ እንዳጋጣሚ መጽሐፍ ስመርጥ ነው ያገኘሁት ። ገና “ማን አጌንስት ሄምሰልፍ” ( የ ሰው ራሱን ሲጻረር ) የሚ
ለውን አርዕስት ሐሳቤ ውስጥ ማን ፎር ሄሳምሰልፍ (ሰው ራሱን ሲያፈቅር ) በሚል አርዕስት የመጻፍ ስሜት
አደረብኝ ። እንዴት እንደሆን እንጃ ! ላሳስበው ስሜቴን ቀሰቀሰብኝ ። ስለዚህ " ሰው ለራሱ ወዳጅ የሚሆንበትን ሁኔታ
ለመጻፍ በመጀመሪያ ሰው ለራሱ ጠላት የሆነባቸውን ሁኔታዎችና ምክንያቶች ማወቅ ይጠቅማል ብዬ ነው-እሱን
በማንበብ ላይ ያለሁት ። እና እንዲያውም ከማንበብ ወደ መጻፍ ልሸጋገር ሳይሆን አይቀርም ።

ዮናታን ደስ አላቸው ። ከአቤል ጋር የሚያወሩት በአማርኛ ስለ ነበረ ለሞኒካ ተረጐሙላት ።

“ በእርግጥ ? ” አለች በእንግሊዝኛ ፡ የእሷም ደስታ ገደብ አጥቶ ዐይኖችዋን እያቁለጨለጨች ።

በእርግጥ ! በማለት አቤል ጨዋታው ውስጥ እሷም እንድትሳተፍ በእንግሊዝኛ ቀጠለ። “ በዚህ አርዕስት የመጻፍ ሐሳብ ጭንቅላቴን ወጥሮ ይዞታል ። አሁን ገና ሳልጀምረው ችግር የሆነብኝ የጊዜ ጉዳይ ነው መሠረት የሚሆኑኝን መጽሐፎች አንብቤ ለመጻፍ ብዙ ጊዜ ያስፈልጋል ።
እና ጊዜ የሚያንሰኝ መሰለኝ ። ”

ከአሳንሰሩ ወጥተው ወደ መኪናቸው አመሩ ።

“ ገድየለህም እስቲ ጀምረው ” አሉ ዮናታን ፥ የጊዜው ነገር አይቸግርም ። መቼም ይኸን ሴሚስተር ትምህርት
ህን ማቋረጥህ የታወቀ ነው ። ስለዚህ እስከ አዲሱ ዓመት ድረስ ስድስት ወር ያህል ነጻ ጊዜ ይኖርሃል ።
በሰበቡ ትምህርቱን የማቋረጡን ውሳኔም መናገራቸው ነበር ። አቤል ግን ይህንን ቀድሞም አላጣውም ። የሁለተኛው ሴሚስተር ትምህርት እንደ ተጀመረ ያውቃል ። የናታን ቤታቸው ያመጡት አንዴ ቢሮአቸው ጠርተውት ፡ “ ትምህርትህን ማቋረጥ አለብህ ” ያሉትን ነገር ተግባራዊ ለማድረግ
👍3
መሆኑ እየገባው መጥቷል ። ሆኖም ጥረታቸው ሁሌ ለእሱ ጥቅም መሆኑን በማወቁ ውሳኔአቸውን ለመቀበል በቅቷል ። ለወላጆቹ ደብዳቤ ሲጽፍ እጁን ይዞ ያስቸገረው
“ ትምህርቴን ለጊዜው አቋርጨአለሁ የሚለው ዐረፍተ ነገር ነበር ። ሲውል ሲያድር ግን ነገሩን አቅልሎ እንዲመለከ
ተው ተገዷል ።
ዐውቃለሁ ። ግን ስድስት ወሩም የሚበቃ አይመስለኝም ። አእምሮዬ የጀመረውን ሐሳብ ሳስበው ብዙ ነው ? አላቸው ።

አይዞህ ኣንተ ጽሑፉን ከጀመርክ ጊዜን ወደኋላ የሚጎትት ነገር እንፈጥራለን ” አሉት ዮናታን ፣ ደስታው ለቀልድ ጋብዞአቸው ።

አቤል ፈገግ አለ ። ጤናማና ልባዊ ፈገግታ! የሞኒካም ፊት እንደዚያው ነበር
ዛሬ ለለውጥ ያህል ኳስ ጨዋታ ብንመለከትስ ? ”አሉ ዮናታን መኪና ውስጥ ከገቡ በኋላ የሚስታቸውንና
የአቤልን ፈቃደኝነት በሚጠይቅ ድምፅ ።

ሁለቱም በፈገግታ ፈቃደኝነታቸውን ግለጹላቸው ። ዮናታንና ሞኒካ ዐልፎ ዐልፎ ኳስ ጨዋታ መመልከት ይወዳሉ ።

“ ወድያውም ፎቶግራፋችን ደርሶ እንዶሆን እግረ መንግዳችንን እንጠይቅ ” አለች ሞኒካ ።

ሦስቱ አንድ ላይ ፎቶ ተነሥተው ፊልሙን ለማሳጠብ ሰጥተው ነበር ። አቤልም ይህንኑ ፎቶ ለመሳክ በማሰብ ለወላጆቹ የጻፈውን ደብዳቤ ገና አልሰደደውም ።

ፎቶው ቤት ሲጠይቁ ደርሶላቸው አገኙት ፡ ግሩም ሆኖ ነው የታጠበው። አቤልን ከመሐላቸው አቁመው ባልና ሚስቶቹ፤ ትከሻውን አቅፈው ነበር የተነሱት ። በስተጀርባቸው የአትክልት ስፍራ ስለ ነበረ ለፎቶው ልዩ ድምቀት ሰጥቶታል ። አቤል ፎቶውን ሲመለከት በሐሳቡ የመጠበት
እናቱ ነበሩ ። “ ትደሰት ይሆን ? ወይስ ልጄን ቀሙኝ ብላ ትቀና ይሆን ? ” ሲል አሰበ ።

ነገ ጠዋት ከደብዳቤው ጋር ወደ ወላጆቼ እልከዋለሁ፡ አላቸው ፍርጥም ብሎ ።

ጥሩ አሉና ዮናታን ፥ ቦርሳቸውን አውጥተው ሰማንያ ብር ቆጥረው ፥ ይህንንም ጨምረህ ላክላቸው
አሉት ።

"ምንድን ነው" አላቸው ተደናግጦ።

"ገንዘብ ነፃ ! ” አለችው ሞኒካ ። ሰሞኑን ዮናታንና ሞኒካ ተመካክረው ያሰቡበት ነገር ነበር ።

አቤልን መቀበል ከበደው።

ሥራ ስትይዝ የምትከፍለው ዕዳ ነው ! አይዞህ ” አሉና ዮናታን ቀለዱበተት።

አቤል ምንም አልመለሰም ። ዝምታን መረጠ ። ደስታ ገደቡን ሲያልፍ ቃላ መግለጽ እንደማይቻል ገባው !
እነሱም ‹እሱ ዝምታ እንደ ጋባቸው ሁሉ ጸጥ አሉ ቮልሳቸው ብቻ ማቃሰቷን እላቋረጠችም ።

አቢል ጭንቅላት ውስጥ በይነታ የታጀበ የተላያየ ሐሳብጨ ተፈራረቀበት ። ነገር ግን የአንዱን ጭራ መያዝ አልቻለም ከመኪናዋ ፍጥነት ጋር የሐሳብ ግልቢያ ብቻ !

“ ጋሽ ዮናታን ፤ ነገ ቢሮ ሲገቡ ከዚ በፊት የሰጠዎትን የጥናት ፅሁፍ ወረቀቶች ያምጡልኝ ”አላቸው ሲያስብ ቆይቶ በድንንት ።

“ ለምን ፈለግካቸው? እንደ ገና አርመህ ልትሠራቸው ነው? ”አሉት ዮናታንም አጠያየቁ ጤናማ መልክ እንዳለው በመገመት።

“ ብቻ ያምጡልኝ” አላቸው ሙያ በልብ ነው የሚል ኩራት በያዘ ድምፅ። ”

እሺ በደስታ ! ”አሉትና ዮናታን ትንሽ ቆይተው ሌላስ ከዩኒቨርስቲ የምትፈልገው ነገር የለም ? » ሲሉ ጠየቁት ።

ምን ?” አላቸወ መልሶ ። ነገሩ ቶሎ አልገባውም ። ከኋላ ስለ ተቀመጠ፥ ዮናታን በመስታወት ውስጥ ፊቱን እያዩት ነበር።

ከፈለግክ ትዕግሥትም ትመጣልሃለች” አሉት በአዝጋሚ ድምፅ ። ፊቱን በመጠኑ ሲለወጥ በመስታወት ውስጥ ተመልከቱት ።

“ ምን ታረግልኛለች ? ! እሷ ጠላቴ ነች ። እሷን ማየት ካቋረጥኩ ጀምሮ አእምሮዬ በደንብ መሥራት ጀምሯል አላቸው በሻከረ ድምፅ ።

ዮናታን አመነቱ ። እውነት ሰላም ካገኘ እሷ ብትቀርበትስ ? ብለው አሰቡ ወዲያው ግን ከእስክንድር ጋር የተወያዩት ነገር ሐሳባቸውን አፈረሰባቸው ።

ትዕግሥት ፍቅር እንጂ ጠላትህ አይደለችም ። ጠላትህ ስለ ፍቅር ጠልቀህ እንዳታውቅ ጨቁኖ ያሳደገህ
አካባቢህ ነው ” አሉት ፥ የቢልልኝ ድምፅ ጆሮአቸው ። ውስጥ እየደወለ ።

አቤል መጥፎም ጥሩም አልመለሰም ። አንገቱን እቀርቅሮ እንደገና ፎቶአቸውን ይመለከት ጀመር ።

💥ይቀጥላል💥
👍3