አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
በቂ መረጃ አላቸው።
“ ትዕግሥትን ነው እንዴ ? ምስኪን ፍጥረት! እሷ'ኮ ምንም አታውቅ ። ከነድንግሏ እንደምትገኝ እኔ በዐሥር ጣቴ
እፈርርማለሁ።

“ በምን አወቅክ ? የፈተንካት አትመስልም ? ! ”

“ ኧረ ግፍ አትናገሩ! እሷ ከቀለም ሌላ ምንም አታውቅ ዐይነ - ውሃዋም ያስታውቃል አትን እባክህ ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር ፈስ ተምራ ትመጣለች እንደሚባለው ነው ። ከእነ ማርታ ጋር ውላ ደሞ ጤነኛ ትሁን እንዴ ሲል ጠርጣሪው ክፍል መከላከያውን ይኑረድራል ።

እነ "ሳተላይት ” እዚህ ላይ ትክክለኛውን መረጃ በመስጠት ሙግቱን ያስረዳሉ ።

“ እሷስ ገና ጥሬ ናት ። ምን ያረጋል ! ጥሬነቷ ነው ያንን ጂኒየስ ልጅ ያሳበደው

"ማንን ? ”

"አቤልን ነዋ ! ”

ምስኪኖች ! የእነሱ ነገር በጣም ይገርማል ? ኮ በዓይን ከመተያየት በስተቀር ተቀራርበው፦ ተነጋግረው አያውቁም

የዐይን ፍቅር ነዋ ! ዐይኑካ ! ”

“ ግን በምን ጣለበት? ሌላ ሴትኮ ቀና ብሎ አያይም ።

የዐይን ፍቅር ላይ የጣለው ጭምትነቱ ሳይሆን እይቀርም”ኮ ! ” በማለት የራሱን አስተያየት አከል የሚያደርግም አይጠፋም.....

«ምን ዋጋ አለው ! ጮማ ጭንቅላት ይዞ አሁን በሷ ምክንያት መቀነሱ ነው።እንዴ ኮ አዳራሹ ውስጥ ከነ ምግቡ የወደቀው እሷን እሷን ሲያይ ነው ! ”

"ትቀልዳለህ ? ይህን ያህል ? ”

አንተ ደሞ ለዚህ ለቀላሉ ጉዳይ ነው እንዴ ? ዕብዶች ሀኪም ቤት ድረስ ግብቷል “ኮ ! ”

በእሷው ምክንያት ?” ይላል ፡ ቀድሞ ነገሩን የሰማውም አብሮ ። ያልሰማው ጓጉቶ ነው ፤ የሰማው ደግሞ የሌላውን የፍቅር ሥቃይ ደጋግሞ መስማቱ ስለ ሚጥመው ነው።

“ ታዲያስ ! እንዲያውም እንደ ሰማሁት ከሆነ ዘንድሮ ትምህርቱን ጨርሶ የሚመረቅ አይመስልም ። ”

“ ያሳዝናል ! ” ሲል አብዛኛው ከንፈሩን ይመጣል ።

"ምን ያሳዝናል ፥ ያናድዳል እንጂ ! ዲዳ እይደል ።ቀርቦ አያናግራትም እምቢ ብትለውም ሴት አልጠፋ ባገሩ ! ” የሚል ተሟጋች ከመሐል ብቅ ይላል ።

“ እንደሱ አትበል እባክህ አያድርስ ነው ! ፍቅር መልኩ ብዙ ስለሆነ መፍረድ አትችልም " "

ግማሹ በሀዘኔታ ግማሹ በቀልድ የጦፈ ክርክር ያካሒዳል። አጋጣሚ ሆኖ እስክንድር ጨዋታቸው መሀል ካለ ኮቴውን ሳያሰማ ቀስ ብሎ ሹልክ ይላል የአቤልን ክፉ መስማት አይፈልግም ። እሱ ለአቤል ያለውን ቅርበትና ጓደኝነት ብዙዎቹ ስለሚያውቁ፡ በጨዋታው ላይ የበኩሉን መረጃ እንዲሰጣቸው ዐይን ዐይኑን ሲያዩት ነው የሚሾልከው።

ሳምሶን ጉልቤው በዕረፍቱ ጊዜ ካምፓስ ውስጥ አለመኖሩ ነው እንጂ፥ በአቤል ጉዳይ ከስንቱ ጋር በተጣላ ነበር።
በግቢው የአቤልና የትዕግሥት የዐይን ፍቅር የጨዋታ ማድመቂያ ሆኗል ። የሚወራው እውነትም ቢሆን ሳምሶን
የአቤልን ስሜት የሚጎዳ ነገር እንዲነሣ አይፈልግም ።

💥ይቀጥላል💥
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

ሻምበል ብሩክና ትህትና ድንበሩ ከተዋወቁ ዛሬ ልክ አንድ ወራቸው፡፡ የፍቅራቸው ወርሃዊ ልደት ውል የሚበጅበት ቀን በመሣሣም ደረጃ የቆየው ፍቅር ዛሬ ወደ አካላዊ ውህደት ሊሸጋገር እቅድ ተይዞለታል። ሻምበል ብሩክም ሆነ ትህትና የዛሬውን ቀን በልዩ ጉጉት ነው የጠበቁት።

እሁድ ዕለት አሥመራ መንገድ በሚገኘው በሻምበል ብሩክ ቤት ለማደር የወሰነችበት ቀን ነበር፡፡ ወደ ዶክተር ባይከዳኝ ቀጠሮ ስትሄድ የሚሰማት ስሜት ከቀጠሮው በስተጀርባ ባለው ምክንያት አስገዳጅነት እንጂ በፍቅር አስገዳጅነት አልነበረም፡፡
ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር የምትፈጽማቸው ግንኙነቶች እውነተኛ ስሜቷን የምትገልጽባቸው ሳይሆኑ፤ በተላበሰችው ጭምብል እውነተኛ ማንነቷን ደብቃ፤ በመድረክ ላይ ትያትር የምትሰራ ተዋናይ ሆና ነው የምትውለው፡፡ በሻምበል ብሩክ ፍቅር ግን ሰውነቷ እንደሻማ እየቀለጠ፣
ልቧ በዕልልታ እየጨፈረች፤ ሁለንተናዋን አሳልፋ የምትሰጠው በደስታ ስሜት ሰክራ ነው፡፡ በተለይ የመጀመሪያዋ በሆነው የወንድ ልጅ ፍቅር የተረታችለት ሰው፤ እንደዘመኑ ወጣቶች በአንድ ነገር ላይ ብቻ ትኩረት የሚሰጥ ሳይሆን በሷ ቦታ ሆኖ ሁሉን ነገር የሚያስብላትና፤
የሚያጽናናት፤ ሆኖ በመገኘቱ ፈጣሪዋን ታመሰግናለች፡፡
ብቻ አንዳንድ ጊዜ የሰው ልጅ ሥጋ ለባሽ ፍጡር ነውና፣ ሰው ተላላና ደካማ ፍጡር ነውና፤ ሰው ሰው ነውና፤ ይህ ሁሉ ፍቅር ድንገት ብን ብሎ ጠፍቶ፣ ሻምበል ብሩክም ተለውጦ፣ እንዳይከዳት ልቧ
መጠርጠሩ አልቀረም፡፡
እንደዚያ ታስብና ደግሞ አስተሳሰቧ ትክክል ባለመሆኑ እራሷን ወቅሳ “ብሩኬ አይለወጥም”
በማለት መልሳ መጽናናትን ታሳድራለች፡፡ በዛሬው ዕለት ሻምበል ብሩክ ቤት ለማደር ቀጠሮውን በልቧ የወሰደችው በከፍተኛ ደስታ ነው። ምናልባት የዛሬው አዳር ደግሞ ያንን ተንከባክባ ያቆየችውን የልጃገረድነት ወግ፣ ብር አምባሯን የምትፈተሽበት ወቅት ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚያ በኋላ “ዞር በይ” ቢላትስ? ልቧ
በመጠራጠርና፤ ባለመጠራጠር፤ስሜት መሀል ገብቶ ሲዋዥቅ ከዋለ በኋላ
አንድ ነገር አሰበች።

ለሻምበል ብሩክ ልጃገረድ መሆኗን ገልጻለት፤ እንደ ወጉ፤ እንደ ሥርዐቱ፤ በጫጉላ ቤት ብር አምባሯን ልትሰጠው ያላትን ምኞች የሱን ስሜትና ፍላጐት ከተረዳች በኋላ ካሳወቀችውና በአጠቃላይ ስለማንኛውም ነገር አብረው በጋራ መወሰን እንደሚችሉ ገምታ፤ በዚሁ ሃሳብ ፀናች።
“እማይዬ ዛሬ አዜቢና ጋ ነው የማድረው ፓርቲ አዘጋጅታለች' በማለት እናቷን ዋሸቻት።
“ባርቲ ደግሞ ምንድነው ትሁቴ?” እናት በመጠራጠር ስሜት፡፡
“ያው ነዋ! ጓደኞቿ ተሰባስበን ስንጫወት ማደር ማለት ነዋ!” እየሳቀች፡፡
አደራሽን የኔ እራስሽን ጠብቂ!!” እናቷ ዐይን ዐይኖቿን እያየቻት።የውጭ አዳር የተሰማው ገና ዛሬ ነው፡፡
“ምንም ችግር የለም:: ማሚ ሙች!” ጉንጫን ሳመቻት፡፡ እናቷ በልቧ
ዝግጅቷን አሰበችው፡፡ በጠዋት ተነስቶ መተጣጠቡ፣ ቀኑን ሙሉ ሲመረጥ የተዋለው ልብስ፣ ሦስት ጊዜ አውልቃ ቀይራለች። መስተዋቱ ሥራ አልፈታም፡፡ መኳኳሉ ሁሉ ያልተለመደ ነበር።
በልቧ ወደ ሻምበል ብሩክ እንደምትሄድ ብታውቀውም የሰጠቻትን ምክንያት ይሁን ብላ ተቀበለቻት፡፡
ዛሬ ሻምበል ብሩክ ጋ የምታድር መሆኗን ለአንዱአለም ስለነገረችው በጊዜ ወደቤት እንዲገባ ተስማምተዋል። በዚህ ላይ የቤት ሰራተኛዋ እታፈራሁ ታክላበት እናቷን በመንከባከብ በኩል ኃላፊነቱን
ስለሚወስዱ የሚያስጨንቃት ነገር አልነበረም፡፡ ሁሉንም አጥብቃ አደራ
ብላ፤ ከቤት የወጣችው ከቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ ነበር።
ሻምበል ብሩክ ዛሬ ሽር ጉድ ሲል አርፍዷል። አልጋው ቦታ ሲመረጥለት፤ ሲንከራተት፤ የቤቱ ቁሳቁሶች በሙሉ በአዲስ መልክ አንዴ በጭንቅላታቸው፧ አንዴ በእግራቸው፤ ሲቆሙ፤ ቦታ ሲመረጥላቸው ነው የተዋለው፡፡
በዛሬው የቤት ዝግጅት ላይ ሠራተኛዋ ብቻ ሳትሆን ሁለቱም ታናናሽ ወንድሞቹ አብረውት ቤቱን ሲያተራምሱት ነው የዋሉት፡፡
በመጨረሻ ላይ ግን ከዚያ በፊት ያልታየበት ዓይነት ሥርዓትና መልክ ይዞ ሲያይ ሻምበል ብሩክ ተደነቀ፡፡
በእርግጥም ይህ ሁሉ የሆነው በትህትና ምክንያት መሆኑን ሲያስብ፤ የትዳር ውጥኑ አግባብ መሆኑን አመነ። በዚያ በቤቱ ሥርዓት ተማርኮ ወደሌላ ሃሳብ ውስጥ ገባ፡፡
ባለፋቸው መጥፎ ጊዜያቶች ውስጥ የተጐዳ ልቡ፣ በትህትና የወደፊት የትዳር እመቤቱ አማካይነት ሊታደስና፤ ሲታነጽ፤ ታየው።
እናም የትዳር መዓዛ በርቀት ሸተተው፡፡ ይህ በርቀት የሚሸተው የትዳር መዓዛ ቀርቦ እንዲያውደው ተመኘ፡፡
ትህትና እስከምትመጣለት የቀጠሮው ሰዓት እስከሚደርስ ድረስ ተንቆራጠጠ።
ዛሬ የሚነግራት ትልቅ ጉዳይ አለው። እሷም እንደሱ በጉዳዩ
ላይ ፈቃደኛ ከሆነች ጉዳዩ የምሥራች ይሆናል። እሷን የፈለጋት ጊዜያዊ
ፍቅረኛ እንድትሆነው ሳይሆን፤ ዘላቂ የትዳር ጓደኛው እንድትሆን ነው::
ይህ እሱ የጓጓለትን በፀጋ ከተቀበለችለት ደስታው እጥፍ ድርብ ይሆናል፡፡
“ትሁት.. ትሁት.. ትሁት.. ስሟን ደጋገመው። በልቡ፡፡

ልክ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ታላቋ እንግዳ የዱር ጽጌረዳ መስላ አምራና፤ ደምቃ ከች! አለች፡፡ ቤቱን ከዚህ ቀደም አንድ ሁለት ጊዜ አይታዋለች፡፡ የዛሬውን ልዩ የሚያደርገው ለማደር ወስና የመጣችበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡
ሻምበል ብሩክ ከደጅ ወጥቶ እየተጠባበቃት ነበር። በሁለመናው
አቅፎ ተቀበላት፡፡
ከዚያም አጥሩን ዘልቀው እየተሳሳቁ፣ እጅ ለእኛ ተያይዘው ወደ ቤት ገቡ፡፡
የሻምበል ብሩክ ሁለት ታናናሽ ወንድሞቹ ሰላምታ አቅርበውላት ትንሽ ከተጫወቱ በኋላ የግል ነፃነት ሊሰጧቸው ወጡ።
ዛሬ የሻምበል ብሩክ ቤት ልዩ ሆናለች:: ትህትናም ከዚያ በፊት ያየቸው ቤት መሆኑ እስከሚያጠራጠራት ድረስ የቤት ዕቃዎቹ አቀማመጥ አስደንቋታል፡፡
ሻምበል ብሩክ የትዳር ምኞቱን ሊገልጽላት ሲያሰላስል፤ እሷ ደግሞ ሌላ የምትገልጽለት እጹብ ድንቅ የሆነ የምስራች ነበራት። ሻምበል ብሩክ በፍቅር ቢወድቅላትም፤ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ያልገመተውን ገፀ በረከት ልታቀርብለት ማሰቧን ቢያውቅ ኖሮ ምንኛ ደስተኛ ይሆን ነበር?፣
ቀለል ያለ እራት ከበሉ በኋላ ይሄንን የቀዘቀዘ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራቸውን
መኮምኮም ቀጠሉ። ዛሬ ቢራው አልመረራትም። የፍቅር ስኳር
ተጨምሮበት ነው መሰል፤ ከምትወደው ሰው ጋር በፍቅር እየቀለጡ፤ ሲኮመኩሙት ማር ሆነና ቁጭ አለ፡፡ ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ሆና ስትጠጣው የግራዋ ጭማቂ ያህል ነበር የሚመራት። አሁን ግን ጣፈጣት፡፡
አንዱን ቢራ ጨረስችና በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለተኛውን የቢራ ጠርሙስ ጨበጠች፡፡ ሻምበል ብሩክ የወደፊት የትዳር ጓደኛው ከምትሆን ቆንጆ ጋር እያሳለፈ ባለው ጊዜ እጅግ ከመደሰቱም በላይ ከረጅም ዓመታት በፊት እጮኛው ከነበረችው በድሏ ጋር ያሳልፉ የነበረውን ዓይነት ልዩ ስሜት አጫረበትና፤ ጨዋታውን በሰፊው ቀጠለ። እየተቃቀፉ መላላሱ ፤ መሳሳሙ፤ ሁሉ ለጉድ ነበር፡፡
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ሲሆን ወደ መኝታ ክፍላቸው መሄድ ፈለጉ።
የመኝታ ክፍሏ በንጽህና የተጠበቀች ናት። እንደገቡ በነጭ ስስ የመጋረጃ ጨርቅ የተሸፈነውን ባለመስታወት መስኮት ሲገልጡት ፍንትው ብላ ደምቃ የወጣችው ጨረቃ ብርሃኗን ወደመኝታ ክፍላቸው ውስጥ አዘለቀችላቸው...

ያንን የጨረቃ ውበት ሲያስተውሉ፤ መብራቱን አጠፉት በዚያች ክፍል
ውስጥ ጨረቃና ፍቅር ነገሱ ከዚያም ልብሳቸውን እንደለበሱ አልጋቸው ላይ ጋደም ብለው መላፋታቸውን ቀጠሉ....
የትህትና ሁኔታ የተለየ ነበር ከዚያ በፊት ለወንድ ልጅ የነበራት ስሜት ምን እንደ ነበረና አሁን ምን እየሆነች እንዳለች
ስታስበው
👍2🔥21
አንዳንድ ጊዜ ያበደች ይመስላታል። አንዳንዴ ደግሞ ሻምበል
ብሩክን ከማግኘቷ በፊት ጤነኛ መሆኗ ያጠራጥራታል፡፡ ፍቅር ማለት እንደዚህ አቅል የሚያስት፧ እንደዚህ የሚያስፈነድቅ ስሜት መሆኑ ይገርማታል።
አንዴ በቀኝ ክንዱ፣ አንዴ በግራ ክንዱ ላይ እየተገላበጠች፤ ቅብጥ ሲያደርጋት ደግሞ እዚያ ስፊ ደረቱ ላይ እየተንከባለለች፤ የደረቱን ጸጉር
እያፍተለተለች፤ ስትስመው፣ ሲስማት፤ ስታሸው፣ ሲያሻት፤ እንዲሁ በስሜት ሲጋጋሉ፤ በመቆየታቸው ገላቸው ከሚገባው በላይ ሞቀና ወደ መፍላት ደረጃ ላይ ደረሰ። ትህትና ቁና ቁና መተንፈስ ጀመረች፡፡
ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ስትሆን በሚሰማት የጣዕር ዓይነት የመቃተትና
የማቃሰት ስሜት ሳይሆን፤ በጣፋጭ ስሜት፤ እራስን አሳልፎ ለመስጠት
በመፈለግ ስሜት፤ መወራጨቷን ቀጠለች፡፡
ሻምበል ብሩክ የትዳሩን ሁኔታ አሁን ልግለጽላት ወይንስ ሲነጋ? እያለ ሲያመነታ ቆየ፡፡ ግን አልነገራትም።
ጨረቃዋ በክዋክብቱ ታጅባ፤ ከዋክብቶቹ እየደነሱ ጨረቃን ሞሽረው ሰማዩን ብሩህ ባደረጉበት ምሽት፧ እነሱ ደግሞ ይህ ሁሉ
ትርዒት ወለል ብሎ በሚታይበት የመኝታ ክፍላቸው ውስጥ በጀርባቸው ተንጋለው አዲሱ ፍቅራቸውን እየሞሸሩ፤ በስሜት መንኩራኩር ተሳፍረው፤ ያቺ ውብ ጨረቃ ወደ ታደመችበት ህዋ፤ መጠቁ....
በአንድ መግነጢሳዊ ኃይል ምድሪቱን ለቀው፤ በሀሳብ ክንፋቸው እየከነፉ፤
በህዋው ላይ ሲናኙ፤ ደስታቸው ገደቡን ስቶ የሚሆኑትን አጡ፡፡ ይህ የደስታ ስሜት ዑደት ከሷ ወደሱ፤ ከሱ ወደሷ ፤ እየተቀባበለ፤ እየተቀጣጠለ፤ በስሜት ክብሪት ተጭረው በፍቅር እየነደዱ ፤ እጆቿ አዛዥ ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው ስልጣን የሱን ልብስ ማውለቅ ሲጀምሩ፤ የእሱም እንደዚሁ የሷን ማወላለቁን ቀጠሉ፡፡ ለሁሉ ነገር ጥንቃቄ እወስዳለሁ ያላችው ሴትዮ፡-
“ጥንቃቄ ገደል ይግባ !!" ያለች መሰለች። ከዚህ በላይ ንግግር የለ፣ ውይይት የለ! ብቻ ሁለቱም በፍጥነት ከላያቸው ላይ የነበረውን ደንቃራ አስወግደው፤ለአንድ ወር በናፍቆት የተጠማ ገላቸው እርስ በርሱ ተፋጭቶ በመካከላቸው የሚፈጠረውን መብረቃዊ ብልጭታ ሊሟሟቁ ተጣድፈው ፤ ልብሶቻቸውን በፍጥነት አወላለቁ.....
የሷ ጣቶች በእሱ ሰውነት ላይ ሲርመሰመሱ፤ የሱም ጣቶች በሷ ለስላሳ
ገላ ተረታ ተሸነፈና አንዳቸው በሌላው አካል ውስጥ ቀስ በቀስ እየሰመጡ፣ በስሜት እየቀለጡ፣ በመንፈስም በአካልም እየተቆራኙ ሄዱ......
የሁለቱም ገላ ከሚገባው በላይ በስሜት ግሎ ነበረና ከጧፍ እንደተሰራ ሁሉ ፤ ተቀጣጥሎ ወደ ፈሳሽ ነጠብጣብነት የተቀየረ እስከሚመስላቸው ድረስ በወሲብ ፍላጐት ነደደ...ከዚያም በከፍተኛ የረሃብ ስሜት እርስ በርሳቸው ተሻምተው አንዳቸው በሌላው ውስጥ ጠፉ....

ከዚያም ሻምበል ብሩክ በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች መካከል በሚደረገው ውህደት ላይ ለመድረስ መንቀሳቀስ ሲጀምር፤ ትህትና ሉጋሙን ጥሶ እንደፈለግሁ ልጋልብ ከሚላት ስሜቷ ጋር መታገል ጀመረች፡፡ እንደሰንጋ ፈረስ ሽምጥ በመጋለብ ላይ የነበረው ስሜቷን እንደምንም ታግላ ሉጋሙን ያዘችውና...
“ብሩኬ .....እኔኮ.... ልጃገረ.....ድ ነኝ ” ስትል እያቃሰተች ሹክ አለችው፡፡
ሻምበል ብሩክ የሰማውን ማመን አቅቶትና ጆሮውን ተጠራጥሮ..
“ምን አልሽኝ ትሁት?” ሲል በድጋሚ ጠየቃት፡፡ አንገቱን በአንገቷ ውስጥ
እንደቀበረ።
“ገርል ነኝ” አለችው ደገመችና ፍስስ... ባለ ድምጽ።
ሻምበል በደስታ ብዛት የሚይዝ የሚጨብጠው ጠፍቶት እቅፍ
አድርጉ እንደ ሎሚ መጠጣት...
ይህ ሹክ ያለችለትን የምስራች ምንም እንኳን ቢያምናትም፤ እንደ ቶማስ ሀቁን ዳብሶ ለመረዳት ፈለገና፤ በሹክሹክታ ተነጋገሩ።
ከዚያም ተግባቡና በጥንታዊ አነጋገር ክራር በሚባለው ጨዋታ ለመጠቀም ተስማሙ፡፡
ከዚያም አካሉን ከአካሏ ቀስ በቀስ እያዋሀደ፤ እያለማመደ፤ ለስለስ ባለ ሁኔታ ክራሩን መምታት ቀጠለ፡፡ የዚያ የክራር ቅኝት ስሜት ለሁለቱም ልባቸውን ሰርስሮ የሚገባ፣ በጆሮ የሚደመጥ ሳይሆን በቀሪ የስሜት ህዋሳቶቻቸው የሚደመጥ፣ በሠራ አካላቸው የሚንቆረቆር፣ ውብ ጣዕመ ዜማ ያለው ሆኖ ተሰማቸው፡፡
ትህትና በዚያ በሰማችው የክራር ቅኝት እጅግ ረክታ፡
ሁለመናዋን ለቅኝቱ አሳልፋ ሰጠች፡፡ እናም በዚያ ቅኝት ውስጥ ትዝታን፤
በዚያ ቅኝት ውስጥ አንቺ ሆዬ ለኔን ! በዚያ ቅኝት ውስጥ አምባሰልን፣
ቢዘያ ቅኝት ውስጥ ባቲን ተጫወቱ፡፡
በእርግጥም የተዋጣለት ጨዋታ ነበረ፡፡ እዚያ እላይ ከስሜት ንረት ጥግ! ደርሰው ሲመለሱ ሁለቱም ቁና ቁና እየተነፈሱ ቆዩና እንደገና ተቃቅፈው ፤ እንደገና ተቆላልፈው፣ እንደገና ሊጫወቱ በስሜት ጭልጥ ብለው ነጎዱ.....
ሻምበል ብሩክ በፍቅር የተረታላት ልጅ ጣፋጭና ከሱ በፊት ያልቀመሳት
ልጃገረድ ሆና በማግኘቱ ደሰስታው ገደብ
አልነበረውም፡፡ የፍቅር አምላክ እምባውን ሊያብስለት ፈልጎ ትህትናን እንደሰጠው አምኖ በዚህ ባጋጠመው ዕድል ረክቶ ፈጣሪውን አመሰገነ፡፡የሁለት ተፈላላጊዎች ውህደት.
ትህትና በደስታ ብዛት የወሰደችው ሁለት ቢራ ሙቀትና ድፍረት ሰጥቷታል።ከፍቅር ጨዋታው መልስ በሻምበል ብሩክ ደረት ላይ እየተንከባለለች ስትፈነድቅ ፤የውስጥ ስሜቷን አምቃ መያዝ ተሳናትና፤
ደስታዋ ገደቡን ጣሰና፤ በዚያ አፍ በሚያስከፍት ማራኪና ተስረቅራቂ
ድምጿ ታንቆረቁረው ጀመር...
ምንም ሳላስበው ውጥን ሳይኖረኝ
የሚያስለቅስ ፍቅር በድንገት ያዘኝ፡፡
ጤና አእምሮ እያለኝ የሚያስብልኝ
የሚያስብልኝ።
እንዲሁ ቁጭ ብዬ አለቅሳለሁኝ
አለቅሳለሁኝ፡፡
ለካስ ፍቅር ሰውን እንዲህ ያደርግ ኖሯል
እንዲህ ያደርግ ኖሯል፡፡
በዚህ አስተያየት ስንት ሰው ተጎድቷል
ስንት ሰው ተጎድቷል፡፡
እያንሰቀሰቀ የሚያስለቅሰኝ የሚያስለቅሰኝ
ፍቅር እንደሆነ ጠቢብ ነገረኝ
ጠቢብ ነገረኝ
በረጅሙ የብዙነሽ በቀለን ዘፈን ትለቀው ጀመር። ከዘፈኑ ጋር በስሜት ተመስጣ፤ በሃሳብ ጭልጥ ብላ፣ በደስታ ሰክራ መስረቅረቋን ቀጠለች፡፡
ሻምበል ብሩክ በአድናቆት ፈዝዞና ደንዝዞ ያንን ልብ የሚሰረስር ድምጽ እያዳመጠ በስሜት አብሯት ጭልጥ ብሎ ሄደ...
ድንበሩን ያለፈ ደስታ አንጎል ያዞራልና፤ ሻምበል ብሩክ አንጎሉ ዞረ።
በመልክና በፀባይ የታደለችውን ወጣት የሱ እንዲያደርግለት ሲመኝ፤ ከነሙሉ ክብሯ አገኛት፡፡ ከዚያም አልፎ ደግሞ ይኸውና በዚያ በሚያደነዝዝ ድምጿ የፍቅር ዘፈን ስታንቆረቁርለት፤ ተደንቆ ይህችን ዕንቁ የሰጠውን አምላክ መላልሶ በልቡ እያመሰገነ፤ እሷ፣ ስትዘፍን፤ እሱ
ሲሰማት፣ እሷ ስትስረቀረቅ፤ እሱ በደስታ ሲቦርቅ፤እንቅልፍ በዐይናቸው ሳይዞር ሰማይና ምድር ተላቀቁ.....
የሻምበል ብሩክ ወንድሞች የሚያድሩት ከዋናው የመኖሪያ ቤት ራቅ ብሎ በተሰራው ሰርቪስ ውስጥ ነው፡፡ ሰራተኛዋ እራታቸውን ካቀረበችላቸው በኋላ ሲያጠኑና ቼዝ ሲጫወቱ ስላመሹ እንቅልፍ ጥሎአቸዋል። እዚያ እላይኛው ቤት በሻምበል ብሩክ የመኝታ ክፍል
ውስጥ የቀለጠውን ጉድ አልሰሙም::

ጠዋት ሲነጋ ሻምበል ብሩክ የጋብቻ ጥያቄውን አቀረበላት፡፡እሷም ፈቃደኛነቷን ከንፈሩን በመሳም አረጋገጠችለት። ከዚያች ቀን ጀምሮ እጮኛው ልትሆን ቃል ከገባችለት በኋላ አይን አይኑን በፍቅር እያየች..
“ለዚያን ዕለት ብለህ ነው የማርከው አይደል ብሩኬ?” እንደ መቅበጥ እያለች እየሳቀ ጠየቀችው፡፡

“ምኑን ትሁት?”ያለችው ቢገባውም አውቆ ያልገባው በመምሰል እሱም እየሳቀ ጠየቃት፡፡
“የወርቅ አምባሩን ነዋ!” ሄዳ እላዩ ላይ ወድቃ ሳመችው። እንደዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዐይን አውጣ ሆንኩ አይደለም እንዴ? እያለች ድርጊቷ ለራሷ ቢገርማትም፤ ለሻምበል ብሩክ ግን ከዚያም በላይ ብትሆንለት ፈቃዷ ነበር፡፡
አይሻልም ትሁት?” አላት እሱም እየሳማት፡፡
👍3
“በጣም እንጂ ብሩኬ አርቆ አስተዋይ ነህ” አለችው።
“እኔ የዘመኑ ጋብቻ ያስቀኛል?” አላት፡፡
“እንዴት?” ስትል ጠየቀችው። አይኖቿን ከአይኖቹ ላይ ሳትነቅል፡፡
“እዚያ ጫጉላ ቤት የሚገቡት ለምን ይመስልሻል?”
“ለምንድነው? እኔ አላውቅም” እየሳቀች፡፡
“ዋናው ቁም ነገሩን ገና ድሮ ይሸኙትና፧ እዚያ ጫጉላ ቤት ውስጥ ገብተው 'ወይኔ ዛሬ ቢኖር ኖሮ? እያሉ ተቃቅፈው ለመላቀስ ነው” አለና እራሱ ስቆ እሷንም በሳቅ ገደላት።
“ከሁሉ የበለጠ የሚያሳዝነኝ ደግሞ ሚዜ ነው።የሚዜ ጣጣው ብዙ ነው፡፡ ልጃገረድ ሆና ካልተገኘች ፤ ጣትን ቆርጦ ማድማት ይጠበቅበታል፡፡
በሰርጉ ማግስት ደግሞ የውሸት አበባ ይዞ ወደ ወላጆች መሄድም አለ ፡፡
አቤት የሚዜ ጣጣው! እኛም ሚዜዎቻችንን ከምናስቃያቸውና ብር
አምባር ሰበረልዎ እየተባለ ሲዘፈን ከምንሳቀቅ እስከዛው ድረስ ብናቆየው
አይሻልም ትሁት? ”
“በጣም ደስ ይለኛል ብሩኬ፡፡ የኔም እምነትና ፍላጐት ይሄው ነው፡፡አሁን
አንተ ስለሚዜዎችና ስለ ጫጉላ ቤት ስታወራኝ ግን አንድ ነገር ትዝ አለኝ
አለችና ከመናገሯ በፊት በሳቅ ፍርስ አለች፡፡ ሻምበል ብሩክም
ምንነቱን ሳያውቅ አብሯት ሲስቅ ቆየና ምንድነው እሱ ሲል ጠየቃት
ለመስማት ቸኩሎ..
እርጉዝ ሆነው ጋብቻ የሚፈጽሙትስ? እዚያ ጫጉላ ቤት ውስጥ ምንድነው የሚሰሩት? ስትለው እቅፍ አድርጓት ከጣራ በላይ ሲስቅ ቆየና ልብሳቸውን ለባብሰው ጨረሱ፡፡ ከዚያም ቁርሳቸውን አብረው ከበሉ በኋላ መጀመሪያ እሷን እቤቷ ድረስ ሸኝቷት ወደ ስራው ሄደ።


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሶስት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና ሻምበል ብሩክና ትህትና ድንበሩ ከተዋወቁ ዛሬ ልክ አንድ ወራቸው፡፡ የፍቅራቸው ወርሃዊ ልደት ውል የሚበጅበት ቀን በመሣሣም ደረጃ የቆየው ፍቅር ዛሬ ወደ አካላዊ ውህደት ሊሸጋገር እቅድ ተይዞለታል። ሻምበል ብሩክም ሆነ ትህትና የዛሬውን ቀን በልዩ ጉጉት ነው የጠበቁት። እሁድ ዕለት አሥመራ መንገድ በሚገኘው በሻምበል ብሩክ…»
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ በዛሬው ዕለት ከመሰል የሥራ ባልደረቦቹ ጋር ከፍተኛ የቀዶ ጥገና ሕክምና አጋጥሞት ነበር የዋለው፡፡ የቀዶ ጥገናው የተደረገላት ሴት በማኅፀን ዕጢ
በሽታ የምትሰቃይ ነበረች፡፡የሆድ ዕቃዋ ተከፍቶ ተከፈፍቶ የተገመተውና፤ በተግባር የታየው የሰማይና ምድር ያህል
ልዩነት ነቀረው።

በማህፀኗ ላይ ለአራት ሰአት የተደረገው የቀዶ ሕክምና ከሁለት ኪሎ ግራም በላይ ዕጢ እንዲወጣላት አስቻለ፡፡ ዶክተር ሰውነቱ በሥራ ደክሞ ስለዛለ በቂ ዕረፍት ለመውሰድ በጊዜ ወደ ቤቱ ገብቶ አልጋው ላይ ጋደም ለማለት ፈልጓል፡፡
ከድካሙ ቀለል እንዲለው ፤ በቀዝቃዛ ውሃ ገላውን ሙልጭ አድርጉ ከታጠበ በኋላ፤ የጥጥ ፒጃማውን እንደለበሰ ነበረ የተኛው፡፡በዚሁ መሀል ትህትና ገርበብ ያለውን የመኝታ ክፍሉን በር ከፍታ ገባች::
በዛሬው ዕለት ያለወትሮዋ የተርከፈከፈችው ሽቶ ቀድሟት ገባና
ክፍሉን በመዓዛው አወደው:: የዱር ጽጌረዳ፣ ጣፋጭ መዓዛ፤ እሷም
የጽጌረዳ አበባ መስላለች። ወትሮ ከሚያውቃት ትህትና በእጥፍ አምራ
ተውባለች፡፡ ኮቴዋን ሳታሰማ ወደሱ ትመጣለች፡፡
ቁልቁል ትመለከተዋለች፡፡ ገርበብ ባሉት ዐይኖቹ ሰረቅ አድርጎ አያት፡፡ በልቡ ውበቷን አደነቀ። ቀጭን ሳቋ ጆሮውን ሰረሰረው፡፡ ዐይኖቹን ገለጥ አድርጉ በሚያየው ነገር ተደንቆ፤ ሽቅብ ተመለከታት፡፡ እሷም በፈገግታ ተሞልታ እየተፍለቀለች ጐንበስ ብላ ጉንጬን ሳመችው፡፡
ከበላዩ ቆሞ፤ ውብ ፈገግታን የሚለግስ፤ በኋላም በአካል የሚዳስስ፤ መልአክ መስላ ታየችው፡፡
የዛሬው አመጣጧ ድንገተኛ ሆኖበታል። የተቀጣጠሩት ለዛሬ አልነበረም፡፡ እንዴት ቀድማ መጣች? ገረመው። ከቀጠሮ በፊት መምጣቷ ምናልባትም በፍቅሩ ወጥመድ እየወደቀችለት ለመሆኗ ፍንጭ ስለሰጠው የደስታ ስሜት የሠራ አካላቱን አዳረሰው፡፡
“የደብረዘይቱ የሽርሽር ውጤት እየታየ ነው” አለ በልቡ፡፡ የሚገርመው ደግሞ አንጀቱን ለመብላት ያላደረገችው ጥረት የለም፡፡ የለበሰችው ስስ ተካፋች ጃኬት እኒያ ገና ከሩቅ ሲያያቸው ውሃ
የሚሆንላቸው! ጡቶቿን፤ አጋልጦ ያሳያል። በዚህ ላይ እኒያን ውብ ባትና ጭኖቿን፣ በግልጽ የሚያሳይ አጭር ቀሚስ ነው የለበሰችው፡፡

“በቃ በፍቅር ወድቃልኛለች ማለት ነው”
በስሜት እንደሰከረ ፍዝዝ ባሉት ዐይኖቹ ይመለከታት ጀመር። ጭውው አለበት፡፡ ሽውው የሚል ነፋስ ሲነፍስ፣ የፍቅር አማልክት በያሬዳዊ የሙዚቃ ቅኝት
ስለፍቅር ሲያዜሙ ፧ ተሰማው፡፡ ድብት የሚያደርግ የድካም ስሜት..ድቅቅ
ያለ ሰውነት በደስታ የሰከረ ቀልብና ልብ፡፡
አሁንም ከት ብላ ሳቀች። አሳሳቋ እንደ ገደል ማሚቶ አስተጋባ፡፡ ሁኔታዋ ሁሉ ግርም ብሉት፤ አፉን ከፍቶ ይመለከታት ጀመር፡፡ ዐይን አፋራ፣ ቅልስልሷ ፤ ትህትና መሆኗን ተጠራጠረ፡፡ ፍቅር ያንን ሁሉ
የእፍረት ማቅ አሽቀንጥራ እንድትጥል አድርጓታል ማለት ነው? ፍቅር እውር ነው ወይስ እውር ያደርጋል? በትክክል እውር እንደሚያደርግ ከሷ እንደዚህ የውቦች ቁንጮ ሆናለት፤ ከቀጠሮአቸው በፊት ሹልክ ብላ ስትመጣለት ምን ይባላል? ማመን አልቻለም፡፡
ዐይኖቹን አሸት አሸት አድርጉ ሁለት እጆቹን ወደላይ ዘረጋና
“ትሁትዬ” አላት በደከመ ድምጽ።
ቀስ በቀስ ያ ሰውነቱ እየጋለ መሄድ ጀምሮ ነበር፡፡ በተለይ የዘረጋላት እጆቹን ወደዚያ ውርውር አድርጋ..
“ከቀጠሮ በፊት ስለመጣሁ መዘነጥህ ነው?” ብላ ከተሰቀለው መስታወት
ውስጥ ፊቷን ለማየት ዘወር ስትል፤ አጭሩ ቀሚስ እላይ ድረስ ዘልቆ እኒያ የሚያማምሩ ጭንና ባቶቿን ወለል አድርጉ ሲያሳየው አልቻለም፡፡ቀስ በቀስ እንደ ካውያ እየጋለ በመሄድ ላይ የነበረው ሰውነቱ የሚያደርገውን ያሳጣው ጀመር፡፡
በተለይ የምትሽኮረመም ሴት ይወዳል። እንዲያ ግፍትር አድርጋው ስትሽኮረመም፧ እልህ ያዘው። በዚህ ላይ ባቶቿ ኑ ብሉኝ! ኑ ብሉኝ! እያሉ ይጋብዛሉ። በዚያ ባዶ ቤት ውስጥ፤ በዚያ ሰፊ የሞዝቦልድ አልጋ ላይ እየተንከባበሉ፤ ያንን ባለፈው ጊዜ ተልፈስፍሶ ያመለጠውን ሲሳይ ዳግም እንዳያመልጠው ሊሞክር ቸኩሎ ተነሳና...
“ከቀጠሮ በፊት መምጣትሽ ምን ያህል ልቤን እንዳስደሰተው ከፍተሽ ባየሽው የኔ ቆንጆ?” በጀርባዋ በኩል ሄዶ፤ በሁለት እጆቹ እቅፍ አድርጓት፤ አንገቱን በአንገቷ ውስጥ ቀበረና! ጡቶቿን ያሻሻቸው
ጀመር..
ቀስ በቀስ እየሞቀች ስትሄድ ግለቷ ተሰማው። ከዚያም አፏ እንደተከፈተ ዘወር ስትልለት፤ በተከፈተው አፉ ቀለባት፡፡ ከዚያም እጆቹ ወገቧ ላይ ሲጠመጠሙ፤ እጆቿ ደግሞ በአንገቱ ዙሪያ እንደ ድር
ተጠንጥነው፤ ሰስሜት ተዋህደው ነጐዱ.....
እኒያ ውብ አይኖቿ ስልምልም ብለው ጠፉ፡፡ ከዚያም ቀስ ብለው እየተደነቃቀፉ፤ እየተደጋገፉ፤ ወደ አልጋው ሄዱና ወደቁ፡፡ ዛሬ ትህትና እንደዚያን ዕለቱ ዐይኖቿ በእንባ አልተሞሉም፡፡ ይልቁንም በደስታ እየተፍለቀለቀች፤ በፍቅር፤ ለፍቅር፤ ስትል ሁለመናዋን በግልጽ እየሰጠችው ነው፡፡
ዶክተር በዛሬው ዕለት ብር አምባር ለመስበር በእርግጠኝነት መንፈስ ተሞልቷል፡፡ በደብረ ዘይቱን የሽርሽር ወቅት በተለይም በሆራ ራስ መኝታ ክፍል ውስጥ ሲልፈሰፈስ ያመለጠው
እንዳያመልጠው በመስጋት፤ ኃይሉን የአንበሳ፤ አድርጎ ትግሉን ቀጠለ፡፡
የታጠቀችው የውስጥ ሱሪ ከዚህ በፊት የሚያውቀው ነጩ ባለወንፊቱ ነበር፡፡ በስሜት ደርተው ሲታገሉ፣ በፍቅር ስሜት ተውጣ የሆነ ነገር እያቃሰተች በጆሮው ሹክ አለችው፡፡ “አስገ...ው...ባ..ው..ው."

በዚህ ጊዜ ዶክተር በሲቃ ስሜት ተውጦ ካሰበበት ለመድረስ ጥድፊያውን ቀጠለ፡፡
እሷ ለሚሆነው ነገር ሙሉ ለሙሉ እራሷን ዝግጁ አድርጋ ሲመለከት፤ ደስታው እጥፍ ድርብ ሆነ፡፡ ዶክተር ላብ በላብ ሆኗል።ትህትናም በላብ ተነክራለች። ከረጅም ጊዜ ትግል በኋላ ...
“ዋ!!.......ይ!! !” ብላ ጮኸችና የዶክተር ባይከዳኝን ሰውነት በጥፍሮቿ ግጥም አድርጋ ይዛ አለቀሰች፡፡ ዶክተር ስለተቧጠጠ ገላው ደንታም ሳይሰጠው በድል አድራጊነት እርካታ ተውጦ ግዳዩን ለማየት ተጣደፈ፡፡
በእርግጥም ድል አድርጓል፡፡ በዚያው ስሜቱ እስከሚረካ ድረስ ቆየ። ከዚያም ተዘርራ ተመለከታት፡፡ ይህ ውስጥ ለውስጥ ያደርገው የነበረው ስሜታዊ ትግል፤ ቀስ በቀስ በውስጡ ሲሯሯጥ ከቆየ በኋላ፤ አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ፤ ወደ ገሀዳዊው ዓለም ተለወጠ፡፡
በዚህ ለውጥ ሰዓት ከእግር ጥፍሩ፤ እስከራስ ጠጉሩ ድረስ የነዘረው ንዝረት አባነነውና፤ በላብ እንደተዘፈቀ ከገባበት የቅዠት ዓለም ወጣ! እግዜኦ! ዶክተር በዚያን ሰዓት የተሰማውን የስሜት ስብራት በቃላት ማስቀመጥ ይከብዳል።
ያ ሁሉ ዓለም፣ ያ ሁሉ ደስታ፤ እንዲህ እንደዋዛ እንደጉም በንኖ ጠፋና፤ የሱን ስሜት እንዳይሽር አድርጎ አቁስሎት በፀፀት ጉድቶት አለፈ፡፡ ያ ሁሉ የድል አድራጊነት ስሜት በቅጽበት ቦታውን ለሽንፈት ለቀቀና፤ በዶክተር ባይከዳኝ ልብ ውስጥ ሀዘን ጥቁር ደመናውን አጥልቶበት ሄደ...
“ቡል ሺት! ” አለና ትራሱን በቡጢ ጠልዞ የሆነውን ነገር እንደ አዲስ አስተዋለ፡፡ በቅዝቃዜው ስሜት ተጠራጥሮ ሲዳብስ፤ ፒጃማውን ረጥቦ አገኘው፡፡ ከዚህ በኋላ ሁኔታዎችን ቀስ ብሎ ይመረምር ጀመር።
በቀላሉ የሚልፈሰፈሰው አካሉ አሳድሮበት የነበረው ሥነ ልቡናዊ ተጽዕኖ
ለጥቂት ጊዜ እራሱ በፈጠረው ትንሽ የቅዠት ደሴት ውስጥ ጠፍቶ፤ነበር
ጊዜያዊ የተስፋ ጮራ በልቡ ውስጥ እንደፈነጥቅበት፤ እሱም ጓደኞቹ
ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ እንደሚችል፤ አረጋግጦለት ነበር።.....

ድንግልናን መግሰስ በማይችል አካላዊ ብቃቱ ለዘመናት አዝኖ እንዳልኖረ ሁሉ፤ በዚህች ቅጽበት፤
2👍2🔥1
በቅዠት ዓለም፤ ከቆንጆዬዋ ከትህትና ድንበሩ ጋር በፈፀመው ግንኙነት፤ ጥንካሬውን በማረጋገጡ፤ ልቡ በደስታ ሞቆ ነበር። ምን ያደርጋል? በነበር ቀረ እንጂ....
ዶክተር አንጀቱ ተቃጠለ፡፡ አልቅስ፤ አልቅስ የሚል ስሜት ተሰማው፡፡ የዛሬው ቅዠት ከትህትና ጋር በእሱ መኖሪያ ቤት ለመገናኘት የያዙት ቀጠሮ ቶሎ አልደርስልህ ብሎት ከመጣደፍና ከመጨነቅ የመነጨ መሆኑን፣ቀንም ሆነ ሌሊት እሷን በማስብ የተፈጠረ መሆኑን፤
ሲያውቅ አዘነ። እንዲወስንበት አሳልፋ በሰጠችው ገላ ላይ መወሰን አቅቶት ሲንደፋደፍ፤ እድሉን ለሌላ አሳልፎ እንዳይሰጠው በልቡ ውስጥ ከፍተኛ ስጋት አደረበት። የሚያደርገውን አሳጣው፡፡በዚህ ሁኔታ ስሜቱ በእጅጉ ተነክቶ ሲያሰላስል፤ ድሮ እዚያ ገጠር ውስጥ እረኞች እያሉ ጓደኞቹ የሚሳሳቁበት ትዝ አለው:: ያንን ሀፍረተ
ሥጋ መሸፈን የማይችል ጥብቆ ለብሰው ከጓደኞቹ ጋር እየተጫወቱ በእረኝነት ሲውሉ፡-
“ባይከዳኝ ለአህዮች ሲታደል ነው እንዴ የተሰለፈው?” እያሉ የሚሳሳቁበት ትዝ አለው፡፡ እንደዚያ ሲሉት ድሮ ሁሉንም ነገር በሳቅ ነበር የሚያሳልፈው። አሁን ግን አንጀቱ እየተቃጠለ፤ በምሬት ነው
የሚያስታውሰው፡፡ በተለይ በተለይ ከእንስሳት ሁሉ አህዮች ፍቅር ሲሰሩ
ማየት ያስደስተው ነበር፡
“ለምን ይሆን?” ሲል እራሱን ጠየቀና ...
እውነት እንዳሉት የአህያ ጂን ይኖርብኝ ይሆን እንዴ?” በማለት ለራሱ ባቀረበው ጥያቄ ቢስቅም፤ አንጀቱ ግን እርር፤ ድብን፤ ከማለት አልዳነላትም:: የምሬት ሳቅ ሳቀ፡፡ ዶክተር እዚያ ገጠር ውስጥ በተፈጠረ አንድ ምክንያት ይኸውና
እስከዛሬ ድረስ ድመት ሲያይ እንደበረገገ ይኖራል። አሁን ደግሞ ልጃገረድ
የሚለውን ሲሰማ በጥላቻ መበርገግ እንዳይጀምር እያሰጋው መጥቷል።
ድመት የጠላበት ምክንያት ነበረው፡፡ እንደዚህ እንደዛሬው በአካልና በአእምሮ ጎልምሶ ከፍተኛ የሙያ ድርሻ በሆነው በህክምና ዶክተርነት ሙያ ላይ ከመሰማራቱ በፊት በአካልም በአእምሮም ጥሬ በነበረበት፤ ክፉውንና ደጉን በውል ለይቶ በማያውቅበት፤የልጅነት ጊዜ የተፈጠረ ነው፡፡እንደወትሮው ሁሉ ጥጆች በመጠበቅ ላይ እያለ፤ መልኩ የቀይ
ቡሬ የሆነ የደስ ደስ ያለው ድመት ይመጣና ይተሻሽው ጀመር። ትንሹ
ባይከዳኝ ያንን ብቸኝነቱን ሊያስረሳለት ጫካ ድረስ የመጣለትን ድመት ማሻሸቱን ቀጠለ ማሻሸቱን ቀጠለ፡፡ ድመቱም ሲታከከው ፤ እሱም ሲደባብሰው ፣ ቀስ በቀስ ተላመዱና ፍጹም የሆነ ወዳጅነት መሠረቱ፡፡
በተለይ ድመቱ ጭራውን እየቆላ....
" ሚያው እያለ በጀርባው ተንጋሎ፤ ትናንሽ የፊት እግሮቹን ወደ ላይ ሰቅሉ፤ አንገቱን እንደ እስክስታ ወራጅ ወዲያና ወዲህ እየሰበረ የእንፉቅቅ ይሽከረከር ጀመር፡፡
ባይከዳኝም እዚያ ጥጆች የሚጠብቅበት ቦታ ድረስ መጥቶ ምንም እንኳ በቋንቋ ባይግባቡም በለስላሳ ሰውነቱ
የሚያጫውተውን እንስሳ ወደደውና! ትንሿ ልቡ በፍቅር ወደቀች::

አሁን አሁን ጓደኞቹ “ድመት!” እያሉ የሚያስደነብሩትና የሚሳሳቁበት፤ የዚያን ዕለት ከዚያ የዱር ድመት ጋር በፈጠረው አጉል ጓደኝነት በድንጋጤ የተመታችው ትንሿ ልቡ ጥላቻ እንዳደረባት በማደጓ
ምክንያት ነው። ከድመቱ ጋር ያ ሁሉ የጓደኝነት ጨዋታ በሰላም ሲካሄድ
ከቆየ በኋላ፤ ከዚያ በፊት አብረው እንዳልነበሩ ሁሉ፣ እንደዚያ እየተሻሹ
ሲጨዋወቱ እንዳልቆዩ ሁሉ፤ ያ ድመት ትንሹ ባይከዳኝን ከድቶት ጥሎት ሊሄድ ሲል ፀቡ ተፈጠረ።
በነብርና በድመት መካከል ያለውን አንድነትም ሆነ ልዩነት የማያውቀው ባይከዳኝ፤ ድመቱ ጥሎት እንዳይሄድ ፍቅሩን መግለጹ ነበር፡፡ ድርጊቱ ሁሉ አሳዛኝ የሆነው ግን ከዚያ በኋላ ነው።“ውርርር..ይልና ባይከዳኝ የድመቱን ጭራውን ይዞ ይጐትተዋል። በሱ ቤት ገና እቤቱ ወስዶ፧ ወተት ሰጥቶት፤ ማታ
ማታም እቅፍ አድርጎት እየተኛ፤ ዘላቂ ጓደኛ ሊያደርገው ነበር ሀሳቡ።
ያ ጭራውን የተያዘ ድመት ወዲያውኑ ሰውነቱ ተቆጥቶ ያብጥና ለስላሳ ባህሪው በውስጥ ነብርማ ባህሪው ከመቅጽበት እንደተለወጠ፤ ዘወር ይላል። ዐይኖቹ ቀልተው ያስፈራሩ ነበር። ከዚያ በኋላ የሆነውን ባይከዳኝ ማስታወስ አልቻለም። ብቻ የሆኑ ሹል ነገሮች ከግንባሩ ጀምሮ
እስከ እምብርቱ ድረስ በስጋው ውስጥ ዘልቀው ሲሄዱ ይሰማዋል።
በመጨረሻም በፈላጊዎች የተገኘው፤ መላ ሰውነቱ በደም አበላ ተነክሮና፤ እራሱን ስቶ ነበር። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ይኸውና እሰከአሁን ድረስ ድመት እንደጠላ ይኖራል። ዶክተር እመኝታው ላይ ሆኖ በተፈጠረው ሁኔታ እየተገረመ የሕይወት ታሪኩን ወደኋላ አጠንጥኖ
በዚያ በገጠር ውስጥ ስለነበረው ሕይወቱ ሲያስብ ቆየና፤ በብስጭት
ተነስቶ ልብሱን ለባብሶ፤ ሲጃራውን አቀጣጥሎ፤ አንድ ሲጃራ ካጨስ
በኋላ፤ ይህንን መጥፎ ስሜቱን እንዲያስወግድለት፤ መጠጥ ለመጠጣት፤መኪናውን አቁሞ፤ በእግሩ ቀስ እያለ፤ ወደ ደንበኛው ወደ አብርሃም
ግሮሰሪ አመራ...

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
#ሰመመን


#ክፍል_አርባ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ


....እስክንድር በግቢው ውስጥ በሚካሔዱት የመዝናኛ ቀልዶች ተረቦችና ጨዋታዎች በተሳተፈ ቁጥር አንድ
የሚገርመው ነገር አለ ። አብዛኛው ወሬ ስለ ሴትና ወንድ ግንኙነት ወይም ስለ ፍቅር ነው ። “ ሌላ ወሬ አጥተን ነው
ወይስ ዕድሜአችን ነው በዚህ አርዕስት ዙሪያ የሚያሽከረክረን ? ወይስ ደግሞ የጋራ ስሜታችንን የሚነካ ጉዳይ ይህ
ብቻ ሆኖ ነው ?” ሲል ያስባል ። ነገር ግን ከአቻው ጋር በተገናኘ ቁጥር ዞሮ ዞሮ አመርቂ አርዕስት ሴት ሆናለች ፤ እና
የዕድሜን ኃይል ግለት ይታዘባል ትኩስ 'አፍላ የሚያቅበጠብጥ ዕድሜ።

የዕረፍቱ የጨዋታ ምሽቶች ከፍቅር እልፍ ያሉ እንደ ሆን በግቢው ውስጥ ከሚታዩት ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ያርፋሉ የፍቅር ጉድጓድ እንደሚሰረስሩት “ሮይተሮች ” ሁሉ በዩኒቨርስቲው ውስጥ ፀረ መጤ ሃይማኖት አቋም ይዘው እያንዳንዷን እንቅስቃሴ እየተከታተሉ የሚ
ተርቡም አሉ ። በየዕለቱ በየትኛው ድርጅት ውስጥ ማን እንደ ተመለመለ ወሬው አያመልጣቸውም ሌላው ቀርቶ
የትኛው የሃይማኖት ድርጅት በግቢው ውስጥ የአባላት ብዛት እንዳለው የሚያውቁና በአሀዝ የሚያቀርቡ አሉ ።

ሰሞኑን “ ሁለተኛው አምላክ ዘ" ታላቅ ኪሳራ ደርሶበታል ” ሲል አንዱ ይጀምራል

“ እንዴት ? ”

“ በፈተና ሰሞን የመለመላቸው አባላት አብዛኛዎቹ ፈተና ካለቀ በኋላ ርግፍ አርገው ትተውታል። ከመብላታቸው በፊት መጸለይ አቁመዋል ። አስረጅ ”

“ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በሃይማኖት አባልነት የተመለመሉት የሚታወቁት፡ምግብ ኣዳራሽ ውስጥ ከመመገባቸው
በፊት አቀርቅረው ሲጸልዩ ነው ። ጸሎቱን ሲያቆሙ ኮንትራታቸውን መጨረሳቸው ይታወቃል

“ አትለኝም ማን ማን ተወ በናትህ ? ”

የሚታወቁትን በስም የማይታወቁትን በመልክ ጥቆማ ይካሔዳል ።

“ ምነው ውጤት እስኪቀበሉ እንኳ ቢቆዩ ፈተና ላይ “ የረዳቸው ” አምላክ የአራሚውንም መምህር እጅ በማሳሳት እንዲረዳቸው ። ”

"ቸኮሉዋ ! ምን ያርጉ በዕረፍት ጊዜያቸው በሃይማኖቱ ከቀጠሉበት ሴቶቹ መደነስ ወንዶቹም መጠጣት ሊያመልጣቸው ሆነ ለማን ጀቴ ብለው !”

“ አሥቂኝ ነው ” ይላል አንዱ ቀልደኛ ከመሐል።

“ እንዴት ?” ሲል ሁሉም ጆሮውን ይቀስራል ።

“ ከአምላካቸው ጋር ድብብቆሽ ጨዋታ ነው ” ኮ የተያያዙት ። ፈተና ሲደርስ ይሰግዱለታል ። ከፈተና ከወጡ በኋላ ይዘጉታል ። ዋ ብቻ አንድ ቀን ያመረረ ዕለት !”

ቀልዱ ሲኮረኩራቸው መሣቅ እየፈለጉ በልባቸው አፍነው የሚያሳልፉ አሉ። ሲሥቁበት አምላክ እንዳያያቸው
የፈሩ ይመስላሉ ። አንዳንዱ በዚህ አርዕስት ላይ ሲያሾፍ ፡ ሲቀልድ ፥ ሲተርክ አንዳንዱ ደግሞ ገለልተኛ ሆኖ መስማቱን ይመርጣል ። ጨዋታውን ማዳመጥ ይወዳል ፤ ግን በሃይማኖታዊ ድርጅቶችም ሆነ በአምላክ ላይ አንዳችም
ተቃርኖ አያነሣም ። “ ከአፍ የወጣ እንጂ በጆሮ የገባ አያረክስም” ከሚል ግምት ላይ የደረሰ ይመስላል ።አፌን በዳቦ
ነው ነገሩ ።

እንዲህ ዐይነቶቹ የጨዋታ ምሽቶች በብዙ ተማሪዎች አእምሮ ተቀርጸው የሚቆዩ ናቸው ። በሴቶችም መኝታ ክፍል ቢሆን ሐሜቱና ተረቡ ቢበዛ እንጅ አያንስም ። ወንዶችን በማብጠልጠል አስተማሪዎችን በመቦጨቅና ራስን በመካብ ሴቶቹን የሚያህል የለም ። “ እገሌ “ኮ እንድወጣለት ጠይቆኝ ዘጋሁት ያ ባላገር ” የብዙዎቹ የጋራ ፈሊጥ ይመስላል ። የሚገርመው ደግሞ ሴቶቹ ሲዋሹ እርስ
በርሳቸው ይቻቻላሉ ። እንደ ወንዶቹ “ረገጣ” እና “ስጥ እንግዲህ ” እየተባባሉ ቅስም አይሰባበሩም ።

ቀልድ እየፈጠሩና ወሬ እያጠናቀሩ ተማሪውን የሚያዝናኑትን ያህል በየአስተማሪው ቢሮ እየተሹለከለኩ የፈተና ውጤት ከመነገሩ በፊት መርዶ የሚያረዱ አንዳንድ ተማሪዎችም አሉ ። እነዚህን ማንም አይወዳቸውም የዩኒቨርስቲ ሕይወታቸው ዕድሜ የሚኖረው ለአስተማሪዎች ወሬ በማመላለስ ነው እየተባሉ ይታማሉ ። ማርክ ቀድም የመስማት ሱስ አለባቸው ። የራሳቸውን ሳይሆን የሌሎቹንም የመስማት ሱስ ነው የያዛቸው ። እወደድ ባይ ወይም ለተራ ወሬ ጆሮውን የሰጠ መምህር የሦስት ልጆችን ማርክ ይነግራቸዋል ።እነሱ ደግሞ አባዝተውት የሃምሳ ልጆችን ውጤት እንደ ሰሙ አርገው ወሬውን ይዘራሉ መምህሩ ወደቀ ካላቸው እነሱ “ ተሰበረ ” ብለው በግቢው ውስጥ ሽብር ይፈጥራሉ ።

ዘንድሮ ይህን ያህል ፍሬሽ ይባረራል ” ብለው በአፋቸው ሙሉ ሲናገሩ የሬጂስተራሩን ቢሮ የያዙት ይመስላሉ ።

“ የእንትን አስተማሪ ከዚያ ሁሉ ተማሪ መሐል ሁለት “A” ብቻ ነው የሰጠወ” ሲሉ የመምህሩ የቅርብ ጓደኛ ይመስቀሉ

ከመልካም ዜና ይልቅ የዝቅተኛና የውድቀት ማርክ ሽብር መፍጠር ነው የሚቀናቸው ። ሌላውን አስበርግጎ ወይ
እነሱ የወሬ ሱሳቸውን ካልተወጡ አይሆንላቸውም ።

እቅጩ የሚታወቀው ግን ጊዜው ደርሶ ማንኛውም ተማሪ የራሱ ውጤት በራሱ እጅ ከደረሰው በኋላ ነው፡አቤል ከሁሉም፦ ርቋል ጥሩውንም መጥፎውንም አይሰማም ። “ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው” እንዲሉ በሱ ላይ የሚወራበትን አያውቅም። ነገር ግን ተማሪው ሁሉ በሽታወን ያወቀበት እየመሰለው ከሁሉም ሸሽቶአል ። ጓደኛው ብቸኝነቱ ነው » አጫዋቹ የቀን ቅዠቱ ፥ የሌሊት
ሕልሙ ነው ። ሌላው ክፍል ተማሪው ተሰብስቦ እያወራ እየቀለደና እየተጫወተ ሲሣሣቅ፥ አቤል ከብቸኝነቱ ጋር
ይሟገታል ። ትዕግሥትን ያልማል ፤ በል ሲለውም ይረግማታል ። የመልካሙ ተበጀን ዘፈን ያዜማል ። ብርቅነሽን ያስባል ከራሱ ጋር ይሥቃል ። ከራሱ ጋር እየተጣላ ያለቅሳል።

በዚህ ዓይነት የሚገፉ ዐሥራ አምስት የዕረፍት ቀናት የዐሥራ አምስት ዓመት ያህል ቢረዝሙም ማለቃቸው አይቀርም ያልቃሉ ። የሚጠበቀውም ቀን መድረሱ
አይቀርም ይደርሳል ።

ትዕግሥት የፈተና ውጤት ሊሰጥ እንድ ቀን ሲቀረው ከደብረ ዘይት አዲስ አበባ ገባች ። ወደ ዩኒቨርስቲዉ መኝታ ክፍሏ ስታመራ፥ አንዳች ነገር የኋሊት ይጎትታት ነበር። ከዘመዶቿ ጋር ከርማ መለያየቷ ተጫጭኖዋታል "በዚያ ላይ ማርታና ቤተልሔምገና ስላልመጡ ብቻዋን ነበረች።

አቤልን ለማየት ቆርጣ ነበር የመጣችው ። ተለይታው በከረመችበት የዕረፍት ጊዜ ውስጥ ሲናፍቃት ነበር ። ግን ለምን ? መናፈቁን ነው እሷ ያልወደደችው ። ትዕግሥትም እንደ አቤል ለፍቅር እንግዳ ናት ። በልጅነቷ ጭቃ እያቦካች
ጎጆ ሠርታ፡ “ባልናሚስት” የተጫወተችበትን ጊዜ ወይም
ከትምህርት ቤት ጓደኞቿ ጋር የተጫወተችባቸውን ጊዜያት ታስታውስ እንደሆን ነው እንጂ ሌላ የፍቅር ትዝታ የላትም፡ አሁን ዕድሜዋ ይገፋፋታል " የወንድ ልጅ ክንድ ተደግፋ
በነፋሻማ ስፍራዎች መወዝወዝ ያምራታል አፍ ለአፍ ገጥማ ምስጢር የምታወራው አቻ ወንድ ያምራታል የወንድ ልጅ ከንፈር ጣዕም መቅመስ የሚያሰኛት ዕድሜ ላይ
ነች። ነገር ግን በዚህ ፋንታ የመጀመሪያ ፍቅሯ ከዐይን የማያልፍ ሆነ ። አቤል ቀርቦ ምስጢሯን አይካፈላትም ።የፍቅር ትኩሳቷን አይጋራትም ፡ የደረቀ ከንፈሯን አያረጥብላትም ፡ ወንዶች ላይ ለሚቅበዘበዝ ዐይኗ ገደብ አይገዛላትም። እሷነቷን ቀርቦ አያውቅላትም ። በሩቅ እየተያዩ መነፋፈቅ ብቻ

ትዕግሥት ይህን ሁሉ አመዛዝና ነበር አቤልን ቀና ብላ ለማየት የወሰነችው ። ትርጉም የሌለው ፍቅር ሆነባት ።
ከመጐዳቱና ከማንገብገቡ በቀር ጥቅሙ አልታይ አላት ።እንዳሰበችው የመጣች ዕለት ጨክና ሳታየው ዋለች። ከደብረ
ዘይት ያመጣችው የአገልግል ምግብ ስለ ነበር ወደ ምግብ አዳራሽም ብቅ ሳትል ዋለች ። ሐሳቧ ሴሚስተሩን በሙሉ
ከእርሱ ርቃ ለመቀጠል ነበር ። ግን ያን ዕለቱኑ ወደ ምሽት ላይ ከቁጥጥሯ በላይ
👍1
የሆነ ውስጣዊ ኃይል እንድትወጣ ገፋፋት " ዐይኗ ውጭውን ማየት ፈለገ ጋቢ ደርባ ወጣች
አቤል ራቱን በልቶ የሚገጣጠሙበትን መንግድ አስልታ ነበር የሔደችው።ሆኖም አቤል ወደ መመገብያው አዳራሽ
የገባው መጨረሻ ላይ ስለ ነበር እንዳሰበችው ቶሎ አላገኘችውም ዐይኗ ተርቦ ለግማሽ ሰዓት ያህል በምግብ
አዳራሹና በወንዶች መኝታ ክፍሎችና መሐል ከተንጎራደደች በኋላ ጨረፍታውን አየች ። አቤል አፉን እየጠራረገ
ከምግብ አዳራሹ ወጣ ። እሱን ስታይ የልቧ ትርታ መጨመሩ ራሷን በራሷ ትዝብት ላይ ጣላት ፡ ካየችው በኋላ ለመሄድ ብታስብም እግሯ አልተንቀሳቀሰም ። ማየት ብቻ ሳይሆን
መታየትንም ፈልጋ ነብር ።

ድፍን ባይልም መጨላለም ጀምሮ ስለ ነበር እቤል ትእግሥትን ከሩቅ አልለያትም ቀረብ ሲል ነው በጋቢ ውስጥ የተደበቀ ውበቷ የታየው ። እሷ መሆኗን ዐይኑ
እንዳረጋገጠ፥ እየተራመደ ብርክ ሲይዘው ታወቀው ። ሊቀርባት የፈራ ይመስል እርምጃውን ቀነሰ ። እሷም ቆማ አልጠበ
ቀችውም ። እንዲያያት ካረጋገጠች በኋላ ዞራ ወደ መኝታ ክፍሏ ተራመደች ። እግሯ እንጂ ልቧ አቤልን መሸሽ አልፈለገም ነበር ።አድራጎቷ እሷኑ መልሶ አሣቃት። ልታየው ፈልጋ ወጥታ ሲያያት መሸሿ ምን ይባላል ? ! ፍቅረኞች ተለያይተው ከርመው ሲተያዩ አንግት ለአንገት ተቃቅፈው እየተሳሳሙ ፍቅራቸውን ይወጣሉ እንጂ ይደባበቃሉ ?
ከዚች ደቂቃ ጀምሮ ልቧ አቤልን ብቻ መወንጀሉን አቆመ ። የአቤል ሕመም እንደ ተጋባባት ተሰማት ። ታዘብኩህ ! ” አለችው ልቧን በልቧ ።

እቤል በእይታው ቅጽበት ውስጥ ፊቷ ዐይኑ ውስጥ ተቀረጸበት ። የወፈረች መሰለው ። ዕረፍቱ ተሰማምቷት
ነበር ማለት ነው ? ደግሞም ስታየው ፈገግ ብላለት በፈገግታዋ የሚጎደጉድ ጉንጮቿን ያየ መሰለው « ሁሌም ስሜቱ
የፈጠረው ምስል ይሆናል እንጂ ፥ ባያት ቅጽበት ውስጥ ይህን ያህል ለማጤን የተረጋጋ መንፈስ አልነበረውም ።
በደንብ ያየው ጀርባዋን ነው ። ጋቢዋ ከዐይኑ እስኪጠፋ ድረስ ተከተላት ።
ካያት ደቂቃ ጀምሮ ልቡ መሠቃየቱ አልቀረም ። ነገር ግን የዚህ ምሽቱ ሥቃይ ከወትሮው የተለየ ሆኖ ተሰማው።


ሥቃዪ ውስጥ ደስታም ነበረበት በዚህ ሰአት ብቻዋን ምን አንጎራደዳት? ያውም በወንዶች ቤት አካባቢ ሲል ራሱን ጠየቀ።
ሆን ብላ ልታየው ፈልጋ መምጣቷን
ለአፍታም አልተጠራጠረም ። የስነበተ ናፍቆቷን በዓይኗ ተወጥታ መሄዷን ልቡ ነግረው እናም ለዐይን ፍቅሩ የመሸነፏ ወይም የመድከሟ አዝማሚያ ሆኖ ታየው ይህ ነበር በሥቃዩ ውስጥ ደስታን የፈጠረለት።

ያጋጠመውን ሁኔታ ለሌላ ሰው ለማጫወት ወይም በደስታና ሥቃይ መሀል የሚዋልል ስሜቱን ለማዋየት
ፈለገ ማታ ለእስክንድር ሊያጫውተው ከጀል አደረገና እስካሁን ያልነበረውን ግልጽነት መጀመሩ አስቸጋሪ ሆንበት ስለዚህ ስሜቱን አፍኖ አልጋ ላይ ወጣ።

በማግሥቱ ጠዋት አንድም ከግቢ የወጣ ተማሪ አልነበረም ። ሁሉም የፈተናውን ውጤት በመጠባበቅ በማስታወቂያ ሰሌዳ አካበቢ ያንዣብባል ። እንደ ተለመደው የብዙ ተማሪ ልብ በድንጋጤ ወንጠሩ አልቀረም ለፈተና ሲቀርቡ ድንጋጤ ! ለውጤት ሲቀርቡ ድንጋጤ

የእያንዳንዱ ተማሪ ምኞትና ጭንቀት ሲታይ ተአምር እንጂ የሥራውን ውጤት የሚጠብቅ አይመስልም ።

አቤልና እስክንድርም ወደ ትርምሱ ሊቀላቀሉ ሲሔዱ ከሳምሶን ጉልቤው ጋር መንገድ ላይ ተገናኙ ከውጭ እንደ ወጣ ማስታወቂያ ሰሌዳው አካባቢ ስላጣቸው
እነሱኑ ፍለጋ ወደ መኝታ ክፍላቸው እየገሰገሰ ነበር።

“ እንዴት ነው ? በጠዋት ከተፍ ! ” አለው እስክንድር ፡ ሰላምታ ሲለዋወጡ።

“ እንዴ ! ቶሉ መርዶአችንን እንስማ እንጂ ! ”አላቸው ፥ እጃቸውን አጥብቆ ጨብጦ እየወዘወዘ። እስክንድርም ሆነ አቤል በዘዴ እጃቸውን ከሳምሶን ለማላቀቅ አየሞከሩ ነበር ። እሱ በፍቅር ስለሚይዛቸው አይታወቀውም እንጂ እጁ ያማል ። ሲጨብጥ የዱላ ያህል ነው የሚሰነዝረው አጥብቆ ከያዘም በኋላ አይለቅም ። እሱን ላለመጨበጥ ከሩቅ
ሰላም እያሉ የሚሸሹት ተማሪዎች ብዙ ናቸው።
ገና በጠዋቱ አልቦታል ። መላጣው ራሱ ቅቤ የቀለጠበት መስሏል ። የደረቱ ቅርጽና የክንዱ ጡንቻ እንዲታይ
ለት ጥብቅ ያለ ጉርድ ሸሚዝ ነበር የለበሰው ውጤቱን ለማወቅ ከመጠን በላይ ቸኩሎ ነበር ።

“ ዕረፍቱ ተስማምቶሃል ጃል ” አለው እስክንድር ! ወደ ትርምሱ ሲያመሩ "
“ መጠርጠሩስ ! ከቤቴ ሌላ አንዴ አክስቴ ቤት አንዴ አጎቴ ቤት እያልኩ ስገነባ ነው የከረምኩት ። አቤል በአንተስ በኩል ዕረፍቱ እንዴት ነበር ? ”

አቤል አልሰማውም ። ወደ ትርምሱ እየቀረቡ በሔዱ ቁጥር ከትርምሱ ውስጥ ትዕግሥትን ለይቶ ለማውጣት ልጃገረዶቹ ላይ በዐይኑ እየተንቀዋለለ ነበር ።

“ ምን አልክ ? ” አለው ሳምሶንን ' ጥያቄው ወደሱ መሆኑን በደመ ነፍስ ተረድቶ ዕረፍቱ እንዴት ነበር ።

“ ደኅና ነበር ፡ ” አለው ፡ ከጥያቄው ለመገላገል ብሎ።

“ ብርቅነሽ ጋ ከዚያ ወዲህ ሔደህ ታውቃለህ ? ”

ጥያቄው አስደነገጠው ። እሱ ለተጠየቀው ከሌላ ሰው መልስ ይፈልግ ይመስል የእስክንድርን ዐይን ዐይን ተመለከተ ሳምሶንም እሱን ተከትሎ እስክንድርን ተመለከት "

እስክንድር ዐይናቸውን ለመሸሽ ማዶ ማዶ ይመለከት ጀመር ። የብርቅነሽ ስም ሲጠራ ንቅሳቷ ታየው ። ጨዋታዋ
ታወሰው ። የዋህ ንጹሕ ሴት ! “ኬሬዳሽን !” አለ በልቡ የሦስቱም ዐይን በየሔደበት ሲያርፍ ያደናገጣቸው
ጥያቄ ሳይመለስ ቀረ ።

“ ምን ታያለህ ? ” አለው ሳምሶን እስክንድርን
“ አንተስ ምን ታያለህ ?”
ሁለቱም እርስ በርስ ተነቃቁና ተሣሣቁ የአበል ዐይን እነሱ ያዩትን ቢያይም ምንም አልተናገረም።

“እንዴት ደምቃለች ጃል! ” አለ እስክንድር ነጀሩን ግላጭ አውጥቶ ።

ህም ! ” ሲል ሳምሶንም አድናቆቱን ገለጸ

የሦስቱም ዐይን ያረፈው ማርታ ላይ ነበር ቦግ ብሎ የቀላው የከንፈር ቀለሟና በጸጉር ሥራ ጥበብ ቡናማ የሆነውን
ጸጉሯ አድምቀዋታል ። ልብሷ ሰው ሳይሆን አሻንጉሊት አስመስሏታል ። ሁለመናዋ ከሩቅ ዐይን ይስባል ። እሷን
ካዩ በኋላ ነው ትዕግሥትና ቤተልሔም አጠገቧ መኖራቸውን የለዩት ። የአቤል ዐይን ወደ ትዕግሥት ሲሻገር ፡ የሁለቱ ግን ማርታ ላይ እንደ ተተከለ ነበር ።

ቤተልሔምና ማርታ በጠዋት ነው የመጡት ። እንደ መጡ ወደ መኝታ ቤቷ ሔደው ከትዕግሥት ጋር ከተገናኙ
በኋላ ቁርሷን እንኳ በደንብ ሳትበላ እያዋከቡ ነው ወደ ማስታወቂያ ሰሌዳው አካባቢ ያመጧት ፡ ሦስቱም ውጤታቸውን ለመስማት በጣም ጓጉተዋል ።

የቆመበት ቦታ ሞቅ ያለ የግል ጨዋታ ይዘው ስለ ነበር እነ አቤልን አላዩአዋቸውም ። ማርታ በእጅዋም በአፉም ታወራለች ። በዕረፍቱ ጊዜ ስንት ወንድ እንዳወጣች ፡ ስንት ሆቴል እንዳዳረች ትዘረዝራለች ። የሷ ወሬ እንዲ
ደነቅላት ብቻ ስለምትፈልግ ፥ ሌሎች እንዲያመሩ ፋታ አትሰጥም ። ትዕግሥት አድማጭ ነች ። ቤተልሔም ምንም
አትተነፍስም ፡ - ውጭ ባይበርድም ውስጧን እያንቀጠቀጣት ነበር ። ውጤት የማወቅ ሰዓት በመሆኗ እንደ ልማዷ በፍርሀት እየተርበደበደች ማርታ የምታወራትን አንዱንም አልሰማች ።

“ እግዚአብሔርዬ ፥ አንተ ታውቃለህ ! ” አለች አንድ ሰወዬ ወረቀቶች ከመለጠፍያ ጋር ይዞ ወደ ማስታወቂያው ሰሌዴ ሲጠጋ አይታ ።

ሰውዬውን ተከትለው ሁሉም ወደ ሰሎዳው ግር ብለው ተጠጉ ። የፈተናው ውጤት በየትምህርት ዓመታቸው በተለያዩ ሰሌዳዎች ላይ ተለጠፈ። ተማሪ አንዱ በአንዱ ላይ እየተንጠራራ ከሰሌዳው ላይ የመለያ ቁጥሩን መጸለግ ጀመረ።.......

💥ይቀጥላል💥
👍21
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

ቀናት ገሠገሡ። ሳምንታት አለፉ። አሮጌው ሄደ፡፡ አዲሱ መጣ፡፡ የጊዜ
ዑደት ሕግ ሥርዓቱን ጠብቆ በአንድ አቅጣጫ ወደፊት ያመራል።
ህይወት ግን በዝብርቅርቅና በውጣ ውረድ ቀለበት ውስጥ እየተዟዟረች
ትህትና ድንበሩና ሻምበል ብሩክ በላይ በከንፈር ማህተም ያፀደቁትን ቃል
ኪዳን ጠብቀዋው ስለወደፊቱ የትዳር ህይወታቸው በሰፊው መወያየቱን
ከጊዜ ጋር ትራመዳለች::
ቀጥለዋል።
ሻምበል ብሩክ በቤተሰቡ ልብ ውስጥ ዘልቆ ከገባና ዝምድናውን ካጠናከረ በኋላ ያ ቤት ድሮ የትህትና አባት መቶ አለቃ ድንበሩ እያለ የነበረውን የህይወት ሙቀት ቀስ በቀስ መላበስ ጀምሯል፡፡
ይህ አባት አከል የወደፊት የትዳር ጓደኛዋ፤ ወድቆባት የነበረውን የህይወት ሸክም አቀለለላት፤ “አለሁልሽ” እያላት ነው፡፡ ለእናቷ የተጠየቀውን ገንዘብ ከፍሎ ሆስፒታል ተመልሳ እንድትገባ ያደረገ
ዕለት...
“ ለምን ሌላ ሆስፒታል አናስተኛትም ብሩኬ?” ስትለው፡፡
“የመጀመሪያው ሆስፒታል ምን አለን ትሁት?” አላት፡፡
“እሱማ ምንም አላለን፤ አማራጭ እስካለን ድረስ ለምን ሆስፒታል አንቀይርም ለማለት ፈልጌ ነው እንጂ” አለችው መልሳ።
“እንደኔ፤ እንደኔ፤ መጀመሪያ ሲከታተላቸው የቆየው ዶክተር
ቢያክማቸው ውጤቱ ያማረ ይሆናል ባይ ነኝ፡፡ አዲስ ዶክተር ማለት አዲስ ህክምናን ሀ ብሎ እንደመጀመር ነው የሚሆነው፡፡ ይሁን ካልሽም እሺ” አላት ዐይን ዐይኖቿን በፍቅር እያየ።
ከዶክተር ባይከዳኝ ሙሉ ለሙሉ ለመራቅ እንጂ፤ በህክምናው በኩል ተደናቂ ሀኪም መሆኑን ዘንግታው አልነበረም፡፡ ሻምበል ብሩክም ልክ አዜብ እንዳለቻት ሁሉ ህክምናውን የመጀመሪያው ሀኪም
እንዲቀጥል ሀሳብ ሲያቀርብላት ጥያቄዋን አነሳች፡፡
በዚህ ሰዓት ሆስፒታል በመቀየር ከምታገኘው ጥቅም ይልቅ የእናቷን ጤንነት ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲከታተል በቆየው ዶክተር ህክምናውን መቀጠሉ የሚያስገኘው ጥቅም አመዝኖ ታያትና...
“እንግዲያውስ ይሁን” በማለት ተስማማች። ዕድሜ ለሱ። ዛሬ የሰላምና የንፁህ አየር እየተነፈሰች የወደፊት የትዳር ህይወቷን ትልም በመንደፍ ላይ ነች ፤ እናቷ ተገቢውን ህክምና እንድታገኝ የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው። በሻምበል ብሩክ ከፍተኛ ምክርና ጥረት አንዱአለም
ችላ ብሎት የነበረው ትምህርቱን በሚገባ መከታተል ጀምሯል።
ይህ ውጣ ውረድ የበዛበት ህይወቷን ለማስተካከል እንድትችል ማካካሻ ያገኘችበት መልካም እድል
ሊሆንላት፤ የዶክተር ባይከዳኝና
የእንደሻው ጥላ ደግሞ በሄደችበት እየተከተላት፤ ሀሳቧን ጠቅለል አድርጋ
እንዳትተኛ እንቅፋት ከመሆን አልቀረላትም፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ በፍቅሯ እንደተቃጠለ ነው። እንዲያውም እስከመጨረሻው የሱ ሆና እድትቀር የነበረው ምኞቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሳካት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ልዩ ልዩ ስጦታዎች ያበረክትላት ጀምሯል። የዶክተር ባይከዳኝ ጥርስ የሌለው አንበሳነት፤ በህይወቷ ላይ ችግር የማያስከትል በመሆኑ እናቷ ሙሉ ለሙሉ ከበሽታዋ ድና እስከምትወጣ የተለመደውን ከልብ ያልመነጨ ፍቅር እያቀመሰችው ለመቆየት ወስናለች።
ይህንን የወሰነችው ደግሞ ብቻዋን አልነበረም፡፡ ከአዜብ ጋር በደንብ አድርገው ከተወያዩበትና ከተማመኑ በኋላ ነው።
“አዜቢና ለምን ቁርጡን አልነግረውም?” በማለት ስሜቷን ለጓደኛዋ ስትገልጽላት።
“ምን ብለሽ ትሁት?” ስትል ጠየቀቻት።
“በቃ እጮኛ እንዳለኝና እንዲተወኝ ብጠይቀውስ?”
“ሞኝ ሆንሽ እንዴ ትሁት? እንደሱ ብለሽ ብትነግሪው የሚያምንሽ ይመስልሻል? ጠልተሽው የደረብሽበት ነው የሚመስለው፡፡
በዚህ ላይ ይሄ ሁሉ የስጦታ ግርግር ፍቅር መሆኑን አትርሺ!!
ምን ቸገረሽ ለትንሽ ጊዜ ብትታገሺ? ፍቅር የያዘው ሰው ፍቅሩን ለሌላ አሳልፎ መስጠት ስለማይፈልግ ሌላ አፈቀርኩ ብለሽ ብትነግሪው ጥሩ አይመጣም፡፡ ያፈቀረ ብዙ ነገር ከማድረግም ወደኋላ አይልም፡፡ አቅሙን እንደሆነ የምታውቂው ነው፡፡ ጉዳት እስካላስከተለብሽ ድረስ ማሚ ድነው እስከሚወጡ እየሸወድሽው ብትቆዪ ምናለበት? በዚህ ላይ ታዋቂ ሀኪም ነው” ስትል አማከረቻት።
እሱን በአሁኑ ሰዓት ማጣት ጉዳት እንጂ ጥቅም ስለሌለው ከሻምበል ብሩክ ጋር ጋብቻቸውን እስከሚፈጽሙ ድረስ ግንኙነታቸው እንደነበረ እንዲቀጥል ተስማሙ።
በተቻላት መጠን ግን ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማርገብ ጥረት እንድታደርግ፤ ቀስ በቀስ የግንኙነት ገመዱን ለማላላት እየቀጠሩ መጥፋት፤ ሲገናኙ መለማመጥና ምክንያት እየሰጡ
በአጭር ጊዜ ውስጥ ላለመገናኘት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ በዚህ
ውስጥ እንዲጠቃለሉ በስፋት ተማከሩበት። በዚሁ መሠረት ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ለረጅም ጊዜ ሳይገናኙ
ቀሩ። ለረጅም ጊዜ ያለመገናኘታቸው ደግሞ እንደግምታቸው ተስፋ የመቁረጥና የመረሳሳትን አዝማሚያ ከማሳየት ይልቅ ' ዶክተር በናፍቆት
ተጠብሶና፤ በፍቅር ተቃጥሎ፤ እንዲጠብቃት አደረገው፡፡ሻምበል ብሩክ አስፈላጊውን ክፍያ ሁሉ ፈጽሞ እናቷን
ሆስፒታል ባስገባችበት ዕለት ተገናኙ። እናቷ በገንዘብ እጥረት ምክንያት
ከሆስፒታል እንድትወጣ ሲደረግ! ስለገንዘብ ከሆነ አለሁልሽ ብሏት
ነበር፡፡ በክፍያ ችግር ምክንያት መሆኑን ልትገልጽለትና በሽንፈት እጇን
ስላልፈለገች... “ለገንዘቡ አይደለም ዶክተር፤ እናቴ ከሆስፒታል ወጥታ በቤት ውስጥ ለመታከም ስለፈለገች ነው
” በማለት ነበር መልስ የሰጠችው::
አሁን እናቷን ሆስፒታል መልሳ ማስተኛቷን ሲያውቅ ቶሎ ቶሎ ለመገናኘት እድል ይፈጥርለታልና በጣም ተደሰተ፡፡ እሷ ግን ይህንን አልወደደችውም።ሻምበል ብሩክ ግንኙነታቸውን እንዳይደርስበት ሰጋች።
ሆኖም እሱን ከማንኛውም ጥርጣሬ ነፃ የምታደርግበት የራሷ ማረጋገጫ
አላትና፧ ተጽናናች። ሁሌም ለእሷ ንፁህ የመሆን ማህተሙ አብሯት እስካለ ድረስ ዶክተር ባይከዳኝ የእናቷ ሀኪም ከመሆኑ ባሻገር ሌላ ጉዳይ ይኖራቸዋል ብሎ እንደማይገምት ተማምና፤ ከዶክተር ጋር ያላትን ቀዝቃዛ ግንኙነት ቀጠለች።
ይህ ሁኔታ በዚሁ ቀጥሎ ሳለ፤ አንድ ቀን ሻምበል ብሩክ በፖሊስ መምሪያ የተካሄደውን ስብሰባ ተካፍሎ፤ ምሳውን ከበላ በኋላ፤ ወደ ቢሮው ለመመለስ የያዛትን የመንግስት መኪና በሚያሽከረክርበት ወቅት አዲስ ነገር ተፈጠረ።
ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ሆኗል።
ብሔራዊ ቲያትር አካባቢ ነው። የትራፊክ መብራት ይዞትእንደቆመ፤ በስተቀኝ በኩል ከፊት ለፊቱ ቀደም ብላ የቆመችውን ነጭ
ኦፔል መኪና እንደዋዛ በዐይኖቹ ገረፍ አደረጋት።
በዚያች መኪና ውስጥ እንደዋዛ ያየው ነገር የትኩረት ስሜቱን ሳበውና፤ መኪናውን ቀስ ብሎ ትንሽ ወደፊት በማንቀሳቀስ ተጠጋ፡፡ፍጹም ሊሆን የማይችል ነገር ነው። አእምሮው ሊጠረጥረው የማይችለውን
ነገር በማየቱ፤ አይኖቹን ተጠራጠረ። የሚያየውን እውነታ ህሊናው በቀላሉ ሊቀበልለት ስላልቻለ፤ ቀይ መብራት በርቶ
መኪኖች ሲለቀቀቁ እንኳ አልታወቀውም ነበር። የሚያየው ነገር እውነት መሆኑን፤ አይኖቹ የሚያሳዩት የሌለ ነገር ሳይሆን፤ ያለውን ሀቅ መሆኑን፤ ሲረዳ ግን፤ ጭንቅላቱ በከባድ ነገር እንደተመታ ሁሉ፤ ክው ብሎ ደርቆ ቀረ።
በሚያየው ነገር ምክንያት ሰውነቱን ማተኮስ ስለጀመረው! የመኪናውን የበር መስታወት ወደታች ዝቅ አድርጎ ንፋስ አስገባ፡፡ በዚያች መኪና ውስጥ ያለቸው ትህትና ድንበሩ መሆኗን
ሲያረጋግጥ፤
መኪናውን የሚያሽከረክረውን ሰው ማንነት ለመለየት ፈለገና አተኩሮ
ተመለከተው፡፡ ያውቀዋል። ዶክተር ባይከዳኝ ነው።ጉድ ፈላ! ስራውን ትቶ የዚህን ተአምር ማብቂያ ሊከታተል
ወሰነ። መብራቱ አረንጓዴ በርቶ ሲለቀቁ ነጫን ኦፔል መኪና ተከትሎ ያሽከረክር ጀመር ክትትሉ እንዳይታወቅበት
🔥2👍1
በጥንቃቄና በርቀት እየነዳ አደኑን ቀጠለ፡፡
ሻምበል በጭንቅላቱ ውስጥ የማይመላለስበት የጥያቄ አይነት
አልነበረም። አታላይ ናት ማለት ነው? እሱ ዶክተር እኔ ወታደር በመሆኔ ወደሱ መገልበጧ ነው ማለት ነው? የእናቷ ሀኪም ስለሆነ ነው ወይንስ ከኔ በፊት ይተዋወቁ ነበረ ማለት ነው? ከኔ በፊት ከሆነስ እስከዛሬ ድረስ እንዴት ልጃገረድ ልትሆን ቻለች? ልጃገረድ ነኝ እያለች
ስትጫወትብኝ ነው? ወይስ ከኔ በኋላ እየተቀላጠፋት ይሆን? ዘመድ
እንዳይባል ስለዚህ ጉዳይ ምንም የነገረችኝ ነገር የለም። ምን ሊሆን
ይችላል? አቅጣጫዬ ወዴት ነው? እርምጃዬስ? ራሱን የማይጠይቀው
ጥያቄ አልነበረም::
እንደዚህ በሃሳብ ተጨንቆ ሲከተላቸው፤ ወደ ስድስት ኪሎ አቀኑ። እሱም አብሮ አቀና፡፡ ከዚያም ዶክተር ባይከዳኝ ሽሮ ሜዳ ሲደርስ፤ ዋናውን መንገድ ለቀቀና ወደ መኖሪያ ቤቱ ታጥፎ ይዟት በመግባት የመኪና ጥሩምባ ሲያሰማ፤ ሠራተኛዋ የአጥሩን በር ከፈተች።
ትህትናን ምሳ ጋብዟት እየተመለሱ ነበር፡፡
ሻምበል ከመኪናው ወርዶ ቀስ ብሎ ወደ አጥሩ በመጠጋት በቀዳዳ አጮልቆ ይመለከት ጀመር። ከመኪና ወርደው እጅ ለእጅ ተያይዘው በደስታ እንደሲካካ ዶሮ እያስካካች፤ አብራው ስትገባ ተመለከተ፡፡
በፍጹም ፍቅራቸው የቅርብ ጊዜ እንዳልሆነ ገመተ።
“ወይኔ ብሩክ?” አለ። የውጩን በር የከፈተችውን የቤት ሠራተኛ አያት፡፡ ከትህትና ጋር ተሳሳሙ::
“ይህችን ይወዳል ብሩክ?! ቤተኛ አይደለችም እንዴ?' አጭር ቀሚስ ነበረ የለበሰችው፡፡ እንደ እምቦሳ ጥጃ እየቦረቀች ገባች::
“ወይኔ ብሩክ? ወይኔ ሰውየው!” አንጀቱ ጨሰ፡፡ የሰራ አካላቱ ተቃጠለ፡፡ እስከመቼ ድረስ የበይ ተመልካች ለመሆን? በቃ ስታታልለኝ ነው የከረመችው ማለት ነው! ይህችን ብሎ ልጃገረድ! አስመሳይ! መሰሪ! ግድ የለም ጉዱ ይለያል! የውሸት ልጃገረድነቱ ታሪክ በቅርብ ጊዜ ውስጥ
ገሀድ ይወጣል! በዚያን ሰዓት ግን እሷን እያድርገኝ አልለቃትም!
በህይወቴ ላይ ተጫውታብኛለች፡፡ የዋህ ልቤ ላይ መርዟን ነስንሳበታለች።
ጅል በሬ አድርጋኛለች፡፡ እኔ ግን በሬ አይደለሁም!!
ያ ሁሉ የውሸት ዘፈን፤ ያ የመጀመሪያ ምሽት፣ አብረው ሲዝናኑ ያደሩበት ሌሊት፤ እንደኮሶ በሚመር ትዝታ እፊቱ ላይ ድቅን
አለበት። አቤት አታላይነት? አቤት ስትችልበት? ደግሞ ጠዋት ላይ ምን
ነበር ያለችው? ለሠርጋችን ዕለት ብለህ ነው የተውከው?' አጭበርባሪ
ሸርሙጣ!! አልምራትም አይማረኝ !። አለና ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ደሙ እየተንተከተከ፤ ከመኪናው ውስጥ ተመልሶ ገባና፤ በሃይል አላትሞ በሩን ዘግቶ፤ ሞተሩን አስነሳ፡፡ከዚያ በፊት ሻምበል ብሩክን የሚያውቀው ሰው አሁን ቢያየው እሱ ነው ብሎ ለማመን ይቸገራል፡፡ የቆሰለ አውሬ ሆኗል፡፡ ፊቱም ሳምባ መስሏል ዐይኑም ደም ጎርሰዋል። በአጠቃላይ ያስፈራራል። ያ ሳቂታውና ተጫዋቹ ሻምበል ብሩክ ሳይሆን ተቃራኒውን ሆኗል፡፡ በቀጥታ መኪናዋን ይዞ ወደ መሥሪያ ቤት ከመሄድ ይልቅ፤
ወደ ኮተቤ መስመር ተፈተለከና እዚያ ዳገቱ ላይ ካለው ኮረብታማ ስፍራ
ላይ ከተሰራ አንድ ሆቴል ገብቶ ለዚያ ለንዴቱ ማስታገሻ እንዲሆነው ውስኪ አዘዘ።
እንደዚያ ካልሆነ በስተቀር አእምሮው በንዴት አብጦ የሚፈነዳ ስለመሰለው ለዚህ ሁሉ ማስታገሻ ይሆናል ብሎ የገመተውን ውስኪ ደብል ደብሉን ይገለብጠው ጀመር።እውነትም ያ ውስኪ ቀስ በቀስ የስቃይ ስሜቱን ያስወገደለት
መሰለው። ሞቅ እያለው ሲመጣ፤ ያንን የሚያሳብድ ድርጊት እንደዋዛ እያሰበ እራሱን ማረጋጋት ቀጠለ፡፡ እዚያ ባንኮኒው ውስጥ የቆመች ድንቡሽቡሽ ቆንጆ በሳቅ ስትፍለቀለቅለት፤ ትኩር ብሎ ሲመለከታት ከቆየ በኋላ ጠራት።
መቼም መቀመጫዋ የአንድ ሰው ብቻ ነው ማለት ያስቸግራል፡፡ እያገላበጠችው መጣች፡፡
“ተጋበዥ” አላት:: ሃሳቡን ሳይቀይር ቶሎ ብላ የአልኮልጠርሙሶች ወደ ተደረደሩበት መደርደሪያ ሄዳ ውስኪ ቀድታ መጣችና አጠገቡ ቁጭ ካለች በኋላ ትሽኮረመም ጀመር፡፡
ከወዲያ ጥግ ሁለት ሰዎች እየጠጡ ይጨዋወታሉ እነሱን ዞር ብሎም አላያቸው:: የዚያች አጠገቡ የተቀመጠች አስተናጋጅ የጭኖቿ ውፍረት እንዲህ ቀላል አልነበረም፡፡ አጭሩ ቀሚስ ወለል አድርጎ የተጋጠሙ ጭኖቿን ያስጎበኛል።
ልጃገረድ ነኝ ባይዋ እስካታለለችው ቀን ድረስ ከሴት ልጅ ገላ ለብዙ ጊዜ ርቆ ነበር፡፡ ያቺ አጭበርባሪ! ያቺ ሸርሙጣ ፤ያንን ስሜቱን፣ ያንን የተዳፈነ ፍላጐቱን ቀስቅሳ፤ ውሸቷን ያንተው ነኝ እያለች
ስታታልለው፤ ስትጫወትበት፤ ቆይታለችና ያ የተዳፈነ የወሲብ እሳት እንዲነድ፤ እንዲንቦገቦግ፣ እዚህ አጠገቡ የተቀመጠች የቀይ ዳማ እኒያን ጋባዥ ጭኖቿን በሰፊው ስታስጎበኘው፤ ከሞቅታው ጋር ተደፋፍሮ:ጣቶቹን ወደ ጭኖቿ መሀል አሳረፈና ለስላሳ ገላዋን ነካካት፡፡
ያ ለስላሳ ገላዋ ከኤሌክትሪክ አስተላላፊ ገመድ እንደተሰራ ሁሉ ፧የሚነዝር ሙቀቷን በፍጥነት ወደ እንደ ኤሌክትሪክ የሚነዝር ሙቀቷን በፍጥነት ወደ ቀሪ አካሉ
ሲያስተላልፍለት፤ የሱም አካል በፍጥነት ሞቀና አብሯት ሊጫወት ፈለገ።

ለዚህ በንዴት ለሚቃጠለው ገላው መድሃኒት እንዲሆንለትና እፎይታ ለማግኘት፣ ትህትናም ሆነች ይህች አጠገቡ ያለችው አስተናጋጅ ልዩነት እንደሌላቸው ሲሰማው ጠጋ አላትና፡-
“አልጋ አለ?” ሲል ጠየቃት። እሷም በደስታ ፈንድቃ፡-
“ሞልቷል” አለችው እየተፍለቀለቀች፡፡ ከዚያም ወደ ጓሮ ወጥታ አልጋ የሚያከራየውን ልጅ አልጋ ጠይቃው ተመለሰችና ወደ ሻምበል ብሩክ ጆሮ ጠጋ ብላ...
“ስምንት ቁጥር ገብተህ ጠብቀኝ” አለችው። ሻምበል ከዚያ ግለቱ ሊቀዘቅዝ በፍጥነት ወደ ቁጥር 8 የመኝታ ክፍል ገባ፡፡ ተዘገጃጅታ ብትመጣ፣ ሻምበል ሙሉ እርቃኑን ሆኖ በጉጉት እየጠበቃት መሆኑን ስትመለከት አፈጣጠኑ፣ ገርሟት የመጣባትን ሳቅ ዋጠችና ስሜት የለሹን
ለገበያ የሚውለው ሸቀጥ ገላዋን ልታቋድሰው ሄደችለት።
ውሸቷን በፍቅር የተረታችለት አስመስላ እያቃሰተች ስትስለመለም፤እውነቷን መስሎት፤ በደስታ ተያይዘው ነጎዱ። ከዚያም በረጅም እፎይታ ተነፈሰና ሰውነቱ ቀዝቀዝ አለ።
ያ ጣፋጭ የፍቅር ህይወት ከዚህ ቀን ጀምሮ በሻምበል ብሩክ ልብ ውስጥ ጥቀርሻ ለበሰ፡፡በዚህ ዕለት ሻምበል ብሩክ ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ እቤት ሲገባ
ወንድሞቹም ሆኑ የቤት ሠራተኛዋ ተደናግጠው ነበር። ሲጋት ያደረው
አልኮል ጠዋት እሳቱን ስለለቀቀበት፤ ሠራተኛዋ እንጀራ በሽሮ ፈትፍታ ከሰጠችው በኋላ በዚያው ጋደም ብሎ ትናንትና የሆነውን ሁሉ መለስ ብሎ ሲያስተውል፣ በሠራው ስራ ያፍርበት ጀመር።
ምንም ቢሆን የዚያን ያህል መሳሳት እንዳልነበረበትና ከዝሙት አዳሪ ጋር መዳራቱ ይቅር የማይባል ስህተት መሆኑን በማመን ተፀጽቶ እራሱን ወቀሰ፡፡
“ፖሊስ ነኝ የሠራሁት ስራ ግን የፖሊስ ስራ አይደለም፡፡ ፖሊስ ችኩል መሆን የለበትም። የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል። ለማንኛውም ነገር ፍንጩ ጠቃሚ ቢሆንም፤ ከሀቁ ላይ ለመድረስ ግን እርጋታ እርጋታ እርጋታ ያስፈልጋል አለ ለራሱ፡ እርጋታ ናፈቀችው፡፡ እሷም ምነው ዘነጋኸኝ ሻምበል ብሩክ? ብላ እጆቿን ዘርግታ በርቀት ጠራቸው.....

ንዱቱ ከበረደለት በኋላ ነገሮችን በእርጋታ ለመመርመር፤ በይሆናል ብቻ ስህተት ላይ ላለመውደቅ፤ መጠንቀቅ እንዳለበት
በማመን፤ በዶክተር ባይከዳኝና በትህትና መካከል ያለውን የግንኙነት ደረጃ በትክክል ለማወቅ፣ የድሮ ፀባዩን ሳይለውጥ፤ በዘዴ ሊጠቀም እንደሚገባው ተረድቶ፣ ሚስጥሩን በስውር ለመከታተልና ሀቁን ፈልፍሎ
ለማውጣት ለራሱ ቃል ገባ፡፡

#Share #Share #Share #Share

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
1👍1
#ሰመመን


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ


ተማሪ አንዱ በአንዱ ላይ እየተንጠራራ ከሰሌዳው ላይ የመለያ ቁጥሩን መፈለግ
ጀመረ።

እነ እስክንድር ግርግሩ መሀል ሲደርሱ እነ ማርታ ውጤታቸውን ለማየት ስለ ተበታተኑ ተሰወሩባቸው ። የአንደኛና የሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች ውጤት ብቻ ነበር የወጣው ።

የአራተኛ ዓመቶች ውጤት አልደረሰም እንዴ ? ”
አለው እስክንድር ውጤቱን የለጠፈውን ሰውዬ ሲመለስ አግኝቶት።

"ከሰዓት በኋላ ” ብሎት ሰውዬው እየተደፈ ሐደ ።

“ እስቲ እኔም ጉዴን ልመልከት ”አለ ሳምሶን አስደንጋጭ ድምፁ ስልት አጥቶ እየተንቀጠ።

“ ቆይ ምን አስቸኮለህ ? ግርግሩ ተግ ይበልልህ! ” አለው እስክንድር ።

ሳምሶን አረ ባክህ ! ” ብሎት " ተማሪውን እየገፈታተረ ወደ ልለተኛ ዓመቶች የውጤት ሰሌዳ አመራ።

እቤልና እስክንድር ከግርግሩ መሀል ወጥተው ብቻ ቸውን ቆመው ቀሩ አንዳች ነገር ተጫጭኗቸዋል አይነጋገረም።

ግርግሩን አትረው ይመለከቱ ጀመር » ማንኛውም ነገር ውስጡ ሲሆኑበትና ከውጭ ሲታዘቡት የተለያየ ገፅታ አለው የፈተና ውጤት ግዜ እንዲህ ከሩቅ ሆነው ሲያዩት አሳዛኝ ትርኢት ይታይበታል ውጤቱ የድካም ውጤት ሳይሆን የብሔራዊ ሎተሪ እጣ ይመስላል አንዳንዱ እየሳቀ ሄዶ ውጤቱን አይቶ ሲመለስ ፊቱ ኮሶ ይመስላል በፍርሃት
እየተንቀጠለጠ ሔዶ እየቦረቀ የሚመለስም አለ ውጤቱ አስደንግጦት የቆመበት ዘፍ የሚልም አይታጣም አብዛኛው ተማሪ ስለ ራሱ የነበረው ግምትና አሁን ያገኘው ውጤት እየተራራቀበት ፊቱን አጨማዶ ሲመለስ ነው የሚታየው።
እኔስ ከየትኛው ዐይነት እሆን ? ” ሲል እስክንድር ራሱን ጠየቀ ። የውጤት ጊዜን ሁኔታ እንዲህ በሩቅ ታዝቦ አያውቅም ነበር ።

አንዲት ልጃገረድ በጓደኞቿ ተደግፋ እያለቀሰች በኣጠገባቸው ስታልፍ አይተው የአቤልም የእስክንድርም ልብ
አብሮ አለቀሰ።
አይዞሽ ፡ ዩኒቨርስቲ የሕይወት መጨረሻ አይደለም ” አላት እስክንድር ቀስ ብሎ።

ቀና ብላ አላየችውም ጓደኞቿ ግን ያሾፈባት መስሏቸው ዞረው ገላመጡት ። ግልምጫ ከዐፈር የሚደባልቅ ቢሆን የማይተዋወቁት ሰው ግልጫ ኦሆሆ ! ቶሎ ብሎ ዐይኑን ከአይናቸን አሸሸ ።

ዘወር ሲል ሚስተር ሆርስ ከሶስት ልጆች ጋር ሆኖ ቅልጥሙን እጥፍ እያረገ ፌቱ ፈክቶ ሲያልፍ አየው ።

“ እንዴት ነው ውጤት? ፊትህ ሁሉ ጥርስ ሆኖአል” አለው በሩቁ ከአኳኋኑ ማለፉን ተረድቶ

“ አልሞትንም ፤ ተርፈናል ። የዩኒቨርስቲ ሕይወታችንን አራዝመናል።

« እንኳን ደስ ያለህ ! ” አለውና ፥ “ በቀላሉ የሚደሰት ተፈጥሮ ጥሩ ነው ” አለ በልቡ በድንግት የአቤል ድምፅ አስደነገጠው።

“ ያቻት ትዕግስት"

አቤል ከርቀት ትዕግሥትንና ማርታን ሲያይ ሳያስበው ነው ስሟ ያመለጠው ። በድንጋጤ ስሟን ከመጥራቱ ሌላ
የሚጨምርበት ነገር አልነበረም ።

“ እህ ?” አለው እስክንድርም ደንግጦ "

አቤል ምንም አልመለሰም ። ፊቱ በቅጽበት ተለዋውጦ ከሰል መሰለ ከንፈሩ ተጣብቆ አልላቀቅ አለው ዐይኑ
ፈዞ ቀረ።

እስክንድርም መልስ አልጠበቀም ፥ የአቤልን ዐይን ተከትሎ ትዕግሥትንና ማርታን ተመለከታቸው ውጤታቸውን
አይተው በመመለስ ላይ ነበሩ ። ፊታቸው ዳምኗል ።በኀዘን ተውጠው አንዳችም ቃል ሳይለዋወጡ መሬት መሬት እያዩ ነው የሚሔዱት ። ለእነ አቤል ደግሞ የባሰ
ዳምነውና ተክዘው ታዩአቸው ።

ትዕግሥትና ማርታ እነ አቤልን ሲያዩዋቸውመንገዱቸውን አሳብረው በሌላ በኩል ሔዱ። በማርታ ግፊት ነበር
ይህ የተደረገው። ማንም ሳያያት ወደ መኝታ ክፍሏ መሔድ ነው የፈለገችው ።

አቤል መቆም ኣልቻለም ። ወገቡ የተቀነጠሰ መሰለው። ትዕግሥት ወድቃለች ማለት ነው ? ከዩኒቨርስቲው ልትባረርና ሊያጣት? ስለ ራሱ ውጤት አንዴም አላሰበ መለየት የሞት ያህል ሆኖ ታየው ።

ቃላት መተንፈስ ፈለገ ግን ከንፈሮቹ አልላቀቅ አሉት እርዳታ በሚጠይቅ አመለካከት እስክንድርን አየው ። ከተረታ ወይም ከደከመ ልብ ብቻ ነው የዚያን
ዐይነት እይታ የሚመነጨው።

“ ምን ልርዳህ ? ” አለው እስክንድር ' ሁኔታው ስለ ገባው።

አቤል ምንም ሳይመልስለት ፡ በሚስለመለም ዐይኖቹ እያየው ቀስ ብሎ አጠገቡ ያገኘው ነገር ላይ ቁጭ አለ።

እስክንድር በሐሳቡ አሁን ምን በወቅንና ነው ? ” አለ ። “ ምናልባት እነዚህ ልጆች ሳይወድቁ በዝቅተኛ ማርክ ብቻ እንደሆነስ የተከዙት ? ለምን ተከትዬአቸው ሔጂ አልጠይቃቸውም ? እነሱ ቢሸሹኝ ተናደው ይሆናል። እኔ
ግን ሔጄ ጠይቄአቸው ወድቀውም ከሆነ ማጽናናት አለብኝ ካለዚያ የመተዋወቅ ትርጕሙ ምንድን ነው ? ” አለና አቤልን የተቀመጠበት ትቶት ሔደ ።

ከሁለቱም ከማዘኑ ሌላ የእንድም ቀን የጫዋታ ትዝታ ቢሆን መጥፎ ነውና ከማርታ ጋር የመለያየቱ ነገር እሱንም ቅር ብሎት ነበር ።

ፈጥኖ ሔደ። ሲደርስባቸው ቀድማ ያየችው ትዕግሥት ነበረች ። በደካማ ፈገግታ ሰላምታ ሰጠችው ። ማርታም
እሷን ተከትላ ዘወር ስትል አየችው ። ሰላምታ ልትሰጠው ብትፈልግም ፈገግ ማለት አልቻለችም ።

እስክንድር አጠገባቸው ከደረሰ በኋላ ስለ ውጤታቸው መጠየቅ ፈርቶ ከንፈሩ ይንቀጠቀጥ ጀመር ።

“ እንዴት ነው ? ” አላቸው ፡ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ፥ አንዴ ወደ ማርታ አንዴ ወደ ትዕግሥት እየተመለከተ ።

“ ዩኒቨርስቲያችሁን ለቀቅኩላችሁ እናንተው ኑሩበት!” አለችው ማርታ ቀድማ መንፈሷ ቢደክምም ምላሷ አልሞትም ነበር ።

“ ምነው ? ውጤቱ መጥፎ ነው እንዴ ? ”
ኤጭ ! ”
ከንፈሩን መጠጠና ወደ ትዕግሥት ዞሮ ' “ የአንቺስ ውጤት እንዴት ነው ? ” ሲል ጠየቃት ።

ጥሩ ነው ። በመካከለኛ ውጤት አልፌአለሁ ” አለችው በፈገግታ ።

“ እንኳን ደስ ያለሽ ! ዋናው ማለፍሽ ነው!!” አለና እሱም ፈገግ ብሎ እንደገና ጨበጣት ።

ማርታ ሁለቱንም በቅናት አስተያየት ላጠቻቸው "ዐይን የሚገድል ቢሆን ሁለቱም የቆሙበት ክው ብለው ቀርተው ነበር ።

እስክንድር ደስታና ኀዘን መሐል ገብቶ ወደ የትኛዋ 'እንደሚሆን ግራ ገባው ። “ ግማሽ ፊትን አጥቁሮ፡ ግማሽ ፊትን ማሣቅ ቢቻል እንዴት ጥሩ ነበር !” አለ በልቡ ።

ማርታን ፊት ለፊት ሊያያት አልደፈረም ። ቀስ ብሎ በስርቆሽ ተመለከታት የጠወለገች አበባ መስላለች ለካ ውበት የስሜት ነጸብራቅ ነው?” አለ በሐሳቡ ። ስሜቷ ከውስጥ ሲንድ ፡ሲቃጠል ሲብከነከን ታየው ድርብ የከንፈር ቀለሟ በመጠውለጉ ፊቷ ላይ ጎልቶ ምናምን
የላሰች አይጥ አስመስሏታል ። ቅንድቧ ብቻ እንደ ወትሮው ይርገበገባል ።

እስክንድር የቅንድቧን መርገብገብ አይቶ ወሬ እንደምትፈልግ ዐወቀ ። ግን ምን ዐይነት ወሬ ? በእሷ መውደቅ ምክንያት ተማሪውንና አስተማሪውን ማማት መቦጨቅ ? አይዞሽ ማርታ ዩኒቨርስቲ የሕይወት መጨረሻ አይደለም ” አላትና ፡ አንድ ቀን ያጫወተችውን አስታውሶ : “ ደሞም ከዚህ ወጥተሽ ስኮላርሽፕ መጠበቅ ትችያለሽ ” አላት ።

“እኔ ማርታ ጉዳዬም አይደል ! ብቻ እንኳን ዩኒቨርስቲ የምትሉትን አየሁላችሁ !
እስክንድር በልቡ “ እኛ ደሞ ምን አደረግንሽ ? " ብሎ ጭጭ።

“ የማትስ አስተማንሪኮ ነው ጉድ ያረገኝ ” አለች ትንሽ ቆየችና።

“ እሱ "F" ባይሰጠኝ ኖሮ ሌላ ትምህርት አልጎዳኝም ነበር።

“ ማነው እሱ? ” አላት ያስተዛዘናት መስሎት

“አቶ ኃይሉ የሚሉት አንድ ሽማግሌ አለ " ላውጣሽ ብሎኝ ስለ ዘጋሁት ቁጭቱን ተወጣብኝ ”

“ ያሳዝናል ! ” አለ እስክንድር ፡ ውሸቷ ኮርኩሮት በህዱ እየሳቀ።

ደሞ ከእሱ ጋር ልውጣ እንዴ? ቅሌታም ሽማግሌ ! ”፥

እስክንድር እንደገና ከንፈሩን
1
መጥጦ ዝም አለ ። ማርታ በሸቀች ዝምታውን አልወደደችም ወሬዋን እያዳነቀ
ከእሷ ጋር አብሮ መምህሩን ያለመወንጀሉ ነው ያናደዳት።እስክንድር ደግሞ ይህን ለማድረግ ኅሊናው አልፈቀደለትም” ። የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ በነበረበት ጊዜ፡አቶ ኃይሉን 101 ሒሳብ አስተምረውታል ። እናም እንዲህ በቀላሉ የሚልከሰከሱ ሰው እንዳልሆኑ ያውቃል ። እንዲያውም ለእምነታቸውና ለሥራቸው የቆሙ ስለሆኑ አንዳንድ ሰዎች “ግትር
የሚል ስም ሰጥተዋቸዋል ።

ቶሎ ቶሎ እንዲድ እባክሽ ! ” አለችና ማርታ ትእግስሥትን አመናጨቀቻት።

“ እሺ ” አለችና ትዕግሥት እየተከተለቻት ፥ “ የእናንተስ ውጤት እንዴት ነው ? ” አለችው እስክንድርን ። የአቤልን ውጤት ለማወቅ ጓጉታ ስለ ነበር ነው ደፍራ የጠየቀችው።

“ የእኛ ገና ከሰዓት በኋላ ነው ” አላት ።

“ እሺ በል ቤተልሔምን ካገኘኘት ወደ መኝታ ክፍል መሔዳችንን ንገራት ” አለችው በእሽታ ራሱን ነቀነቀ ፡ እነሱ ከአጠገኑ ሲሔዱ እሱ ወደ ኋላ መመለስ አልቻለም ቆሞ ተመለከታቸው ።ለማርታ ከልብ አዘነላት ተዋውቆ መለያየት እንዴት
አሳዛኝ ነገር ነው ! ያቺ አብረው ያሳለፏት አንዲት ቀን ትዝታ አልችው ባይሳካም ከእሷ ጋር ተባብረው ለመርዳት ሞክረው ነበር ። ሐሜት መውደዷና ቀናተኛነቷ ፊቱ ላይ መጡበት። አንድ ቦታ የማያርፉት ዐይኖቿ ሲቁለጨለጩ በሐሳቡ ታየው እንድ ቀን ፡ "ያ ነገር እለህ እንዴ ? ” ያለችው ታወሰው እሷን ለማውጣት ብር አጥቶ ድህነቱን የረገመባቸው ቀናት ታመሱት ።

“ ወይኔ እስክንድር ! ” አለና ከኪሱ የማስታወሻ ደብተሩን አወጣ የማርታ ስልክ ቁጥር እውስጡ መኖሩን ካረ
ጋግጠ በኋላ መልሶ ኪሱ ከተተው
መደ አቤል ሲመለስ ከቤተልሔም ጋር መንገድ ላይ ተገናኙ ።
ብቻዋን ትፍነከነካለች ዐይኗም ጥርሷም ጉንጯም ሁለመናዋም ይሥቃል። ዐይኗ መልካም ዜና ለማብሠር የሚያውቀውን ሰው ፍለጋ ይንቀለቀላል ውጤቷን መጠበቅ አስፈላጊ አልነበረም "

“ እንኩዋን ደስ ያለሽ !” አላት እየሳቀ
“ በአምላክህ ! የናንተስ ገና ነው ? ”
"ገና ፡ ከሰዓት"

ጨበጣት ። እጅዋ ብብቷ ጡቷ ሁለመናዋ ላብ ያመነጫል ። ከመቼውም የበለጠ ወፍራ ታየችው።

“ ማርታና ትዕግሥት ወደ መኝታ ቤት ሒደናል ብለውሻል ” አላት ፡ ሲጨብጣት የራሰውን እጁን ለማድረቅ ቀስ ብሎ ሱሪው ላይ እየጠረገ

“ እነሱን ፍለጋ ኮ ነው የምሔደው ። እንዴት ሆነው ይሆን ?

“ እኔ እንጃ : በደንብ አልጠየቅኳቸውም ” አላት ፡ ነገሩን ለማሳጠር ብሎ " አቤልጋ ደርሶ የትዕግሥትን መልካም ዜና ለማብሠር ቸኩሎ ነበር ።

ከነበረበት ቦታ እንደ ተቀመጠ አገኘው

“ ስማ አቤል ፡ ትዕግሥት ዐልፋለች ” አለው "

አቤል ጆሮውን ማመን አቃተው፤ ከተቀመጠበት እንደ አክሮባት ዘሎ ተነሣ።

“ እ? ምን አልክ ? ”

“ ትዕግሥት አልፋለች ። ማርታ ነች የወደቀችው ። ”

የአቤል ገጽታ ላይ የነበረው የትካዜ ደመና ተበታትኖ ጠፋ ። ከደመናው ውስጥ ፀሐይ ብቅ አለች ።

የትዕግሥት ማለፍ ብቻ ሳይሆን የማርታም መውደቅ የአቤልን ደስታ ድርብ እንዳደረገለት እስክንድር ገመተ "

" ግን ለምንድን ነው የምንጠላውን ሰው ክፉ እንዲደርስበት የምንመኘው አለ በሐሳቡ ። ሆኖም ለማሰብ ፋታ አላገኘም ሳምሶን ጉልቤው ውጤቱን አይቶ ሲመለስ አየው።

አረማመዱ አላማረውም ። ፊቱ ከበደው አኩርፎ ከቤት የወጣ ሕፃን ልጅ መስሏል የሚለውን ለመስማት እስክንድርና አቤል ቸኮሉ።

“ ወደቅኩኮ ! ” አላቸው አጠገባቸው ከመድረሱ
“ እ ? ! ” አሉት ሁለቱም ተደናግጠው ።
እስክንድርና እቤል እንዴት እንደሚያጽናኑት ግራ ገብቷቸው ተፋጠው ቀሩ " አሁንም ግማሽ ደስታ ግማሽ
ሀዘን ! ይህች የተዘበራረቀች ዓለም !

“ አየህ አንድ ዓመት ነው የምታቃጥለው አለው እስክንድር ክንዱን ይዞ መንገድ ከጀመሩ በኋላ ፤ “ በሚቀጥለው ዓመት እንደገና ገብተህ መቀጠል ትችላለህ”

“ ነገሩ ነው እንጂ የሚያበሽቀው ! ” አለ ሳምሶን ጥርሱን ነክሶ ።

“ ደሞ አንተ ማንን ልትወነጅል ይሆን ? ” አለ እስክንድር በልቡ በራሴ ድክመት ነው የወደቅኩት የሚል ተማሪ ማን ይሆን ? ”

ትንሽ እንደ ሔዱ ሳምሶን ድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ ቤተልሔም ወደ መምህራን ቢሮ ስታልፍ በርቀት አይቷት ነበር ።
እሱ ውጤቱን ሊያይ ሲሔድ እሷ በውጤቷ ተደስታ ስትቦርቅ አይቷታል። ያኔ ምንም አላላት አሁን መውደቁን ካወቀ
በኋላ ግን በእሷ ማለፍ ተናደደ ። እና ከሩቅ ሲያያት ከንፈሩን ነከሰባት።

ቤተልሔም ወደ መኝታ ክፍል ከመሔዷ በፊት ለለማ ደስታዋን ልታበሥረው እየሔደች ነበር ። አንኳኩታ እንደገባች ከቢሮው ተቀምጦ አገኘችው ".....

💥ይቀጥላል💥
1
#ሐቅ_ዕንቅ

ሐመልማል ወጋገን ፣ ጎጆዬ ላይ ውላ
የሐሤት ወይን ጠጅ ፣ በጽዋዬ ሞላ።
ደስታ በአክናፉ ዕቅፎና ደግፎ
0ጸዴን አፈካው! ተርፎ ተትረፍርፎ።

ከዐጸዱ ኋላ...
የጎረቤት ጎጆ ፣ ከል ጽልመት ለብሶ
እንባውን ይረጫል ሐዘን ቤቱ ደርሶ።
ውሾች ይጮኻሉ ፣ ሽቅብ ወደ ሰማይ
እንባዬ ይጎርፋል ፣ ከፊቴ ጉንጮች ላይ
የልቤ ሐዘን ነው? ወይስ የደስታ እንባ?
ጥርሴ በሣቅ ፈክቶ ፣ ሆዴ እሚባባ ?!

ከጎረቤቴ ደጅ . .
የ'ኔው ጥቁር ውሻ ፣
ያላዝናል ሽቅብ ዐንገቱን ቀስሮ ፤
በኅቡእ ምሳሌ . . .
ከእግዜር ሊማከር የጊዜን ቀጠሮ።
( ይመስላል . . .!)

መስሎኝም አልቀረ ፤
ሥጋዬ ተረሳ . . .
የምናቤ ምስል በ'ውን ተቀየረ።
. ኼድኩኝ . . .
ከጎረቤቴ ደጅ ሞቴን አገኘኹኝ ፤
በሕልሜ ታጅቤ ነፍሴን አስነሣኹኝ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

#አውጉስታ

ቅዱስ ገብርኤል የሚከበርበት የዓመቱ በአል ደረሰ፡፡ ይህንን በዓል የእንደሻው ወላጆች የሚያከብሩት ሐረርጌ ቁልቢ ገብርኤል በመሄድ ነው። ለዓመቱ ገብርኤል የተሳሉትን ስለት ይዘው፣ ትንሹ ልጃቸው ሲሳይን አስከትለው፤ ለመሄድ የባቡር ትኬት ቀደም ብሎ ተቆርጧል።
ገብርኤል የሚከበርበት ቀን እንደ ነገ ሆኖ፤ ትህትና ሥራዋን በምታከናውንበት ወቅት ደግሞ አንድ ደስ የሚል ዜና ሰማች፡፡ ትናንትና ሻምበል ብሩክን በስልክ ስታነጋግረው የድሮው ሻምበል ብሩክ ሳይሆን ትንሽ የመቀዝቀዝና፤ የመለወጥ ስሜት ስላየችበት ብስጭትጭት ብላ
ነበር የዋለችው። ይህንን ብስጭቷን ሲያካክስላት ነው መሰል የደስደስ
ያለው ወሬ ከአበራ ሰማች፡፡
የምስራች!” አላት አበራ እየፈነደቀ።
“ምስር ብላ” አለችው የምሥራቹ ናፍቋት፡፡
“ጋሼን ምን እንዳስነካሻቸው አላውቅም፡፡ለማንም ያላደረጉትን ነው ላንቺ እያደረጉ ያሉት፡፡የገቡልሽን ቃላቸውን ጠብቀዋል፡፡ ከነገ ጀምሮ ደመወዝሽ አንድ መቶ ብር ሆኖ በገንዘብ ያዥነት እንድትሰሪ ተወስኗል”
በደስታ ብዛት ሄዳ አበራን እቅፍ አደረገችው። እሱም እቅፍ አደረጋት።

“ዛሬ እቤት ይዘሀት ትምጣና አዲስ ውል ትፈርም ብለውኝ ነበር። ዛሬ ሥራ ስለሚበዛ ለነገ ይሻላል ብያቸዋለሁ” አላት ድምጹን ዝቅ አድርጎ፡፡
ትህትና በእርግጥም በሥራዋ ቀልጣፋና ደከመኝን የማታውቅ ልጅ መሆኗን ማንም ይመሰክርላታል።
“ለማንም እንዳትናገሪ ታዲያ! በተለይ ይህቺ አሮጊት ከሰማች ታብዳለች” :: ይህቺ አሮጊት የሚለው ወ/ሮ አረጋሽን ነው። በእርግጥም ወይዘሮ አረጋሽ በዚህ የጫማ መሸጫ አዳራሽ ውስጥ ዘጠኝ ዓመት ሙሉ ሰርታ ደመወዟ አሁንም ዘጠና ብር ብቻ ነበር፡፡
“ጋሼ አበራ ሙት ለማንም አልናገርም” ቃል ገባችለት፡፡ በዚሁ መሠረት ተደስታ ውላ፤ ተደስታ አደረች፡፡ ትንሽ ቅር ያላት ሻምበል ብሩክ በስልክ ስታነጋግረው ከወትሮው የቀዘቀዘበት ምክንያት ግራ
ስላጋባት ነበር።ምክንያቱን ለማወቅ
ሄዳ እስከምታገኘውና የሳምንቱ
"መጨረሻ እስከሚደርስ ድረስ ከመቸኮሏ በስተቀር ሁሉም ነገር ሰላም ነው፡፡ እናቷ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለችው። አንዱዓለም ጠንካራ ተማሪ ሆኗል። ይኸውና እሷ ደግሞ ዛሬ ዕድገት የማግኘቷን ዜና ሰማች፡፡ ይህንን የዕድገት ውሏን ለመፈረም አቶ በቀለ ከመኖሪያ
ቤታቸው ድረስ እንድትመጣ በሥራ አስኪያጁ በአበራ በኩል የላኩባትን
መልዕክት ተቀብላ ለመሄድ ተዘጋጀች፡፡
በማግሥቱ ሥራ እንደገቡ አበራ ወደ
ወ/ሮ አረጋሽ ጠጋ ብሎ ከትህትና ጋር አንድ ግዜ ወደ ፋብሪካ ደርሰን እንመጣለን” አለና ምክንያቱን አሳውቆ ትህትናን ጠራትና መኪና ውስጥ አስገባት፡፡ ሞቅ ባለ ፍጥነት ከአውጉስታ ፋብሪካ በስተጀርባ ወደሚገኘው ወደ አቶ በቀላ መኖርያ ቤት በረሩ።
ከዚያ ደርሰው የመኪና ጥሩንባ ሲያሰሙ፤ አንዲት ጠቆር ያለች ልጅ እግር የቤት ሠራተኛ የአጥሩን ብረት በር ወለል አድርጋ ከፈተችው፡፡
ቤቱ በዚያ ሰፊ ቦታ ላይ በግርማ ሞገስ ጉብ ብሎ ሲታይ ይማርካል። በልዩ ልዩ አበቦችና ዛፎች አጊጧል። ከትልቁ ቪላ ፊት ለፊት በሰፊው ተንጣሎ የሚታየው የወይን ዛፍ ቀዝቃዛ ጥላን አጐናጽፎት
ምድረ ገነት አስመስሎታል።
በግቢው ውስጥ የማይታይ የአበባ ዓይነት የለም፡፡ ትህትና በአጠቃላይ የቤቱ ውበት ተማርካለች፡፡ ከዚያም ተያይዘው ከመኪናው ወረዱ።
የወጣ ሰው የለም፡፡ አበራ “ቆይ ጠብቂኝ” አለና በጓሮ በኩል ዞረ።እሷ በፊት ለፊቱ በር ቆማ እየጠበቀችው ነበር፡፡
የቤት ሠራተኛዋ አንድ ጊዜ ብቅ ብላ ትህትናን ሰረቅ አድርጋ አየቻትና ተመልሳ ገባች።
“ነይ ትህትና በዚህ በኩል”፡፡ በፊት ለፊቱ ሳይሆን በጓሮው በር አስገባት፡፡
እዚያ ፈቅ ብሎ በተሠራ የውሻ ቤት ውስጥ የታሰረው ትንሽ የፈረንጅ ውሻ ቡፍ ቡፍ አለ። ትህትና ውሻውን ስታየው ግንባሩ ፍጥጥ ብሎ ወደ ውጭ የወጣ ከመሆኑም በላይ ፤ የሆነ የምታውቀው ሰው መልክ አስታወሳትና፤ ትንሽ ሳቅ ብላ አበራን ተከተለችው::

ቁጭ በይ ወንበር ጋበዛት፡፡ ሄዳ ወንበሩ ላይ ተቀመጠች።
“እስከዚያው ምን ይምጣልሽ?” ፊቱ ጥርስ በጥርስ እንደሆነ።
“ጋሽአበራ ምንም አያስፈልግኝም” እሷም በፈገግታ እንደተዋጠች፡፡
ዕድገትን ለመሰለ ፀጋ መጥቶ ባይበላ፤ ባይጠጣስ? ልቧ ያለው በውሉ ሁኔታ ላይ ነበር። በዚህ ላይ የቤቱ ውበት አስደንቋት ዙሪያ ገባውን እየቃኘች ነበር፡፡
“እንደሱ አይባልም፡፡ ምንም ቢሆን እኮ ለቤቱ እንግዳ ነሽ፡፡
እንዳይለምድብሽ፡፡ ለስላሳ ይምጣልሽ?”
“ይሁን እሺ ጋሽ አበራ፡፡”
ትህትና እዛ ክፍል ውስጥ ሆና በዚያች የምታምር ክፍል ውስጥ የተሰቀለውንም፤ የተንጠለጠለውንም፤ በዐይኖቿ እየቃኘች አቶ በቀላ ብቅ ብለው ውሉን እስከሚያስፈርሟት ድረስ በናፍቆት ስትጠባበቅ፤ በግራ በኩል ውስጥ ለውስጥ የተሠራው ባለመስታወት በር ንቅናቄ አሳየ።
እስከዚያን ጊዜ ድረስ አንዳችም ጥርጣሬ ያልተሰማት ልጅ ልቧ እንደመዝለል አለባትና ዐይኖቿ በበሩ ላይ ተተክለው እንደቀሩ፤ ፒጃማ የለበሰ ወጣት ብቅ!!..... አለ፡፡
ያንን ሰው ስትመለከት፤ እጅግ ከመደንገጧ የተነሳ አፏ ተከፍቶ ቀረ። ከዚያም ነፍሷን ስትገዛ “ዋይ!” ብላ እሪታዋን ልታቀልጠው ስትል፡-
“ፀጥ በይ!! ያለበለዚያ!!” አለና ደብቆ የያዘውን እህል ውሃ የማያሰኝ ጩቤ መዘዘው። ዐይኖቿ ተጎልጉለው ወጡ
በድንጋጤ ደምስሮቿ በግንባሯ ላይ ተገታተሩ፡፡ ትንፋሽ ሳታወጣ ፀጥ አለች፡፡
ከዚያም ሁኔታዎች በእንደሻው ፍላጐት መስመር ያለችግር ይቀላጠፉ ጀመር።
ጠጋ አላትና በግራ በኩል በቃሪያ ጥፊ ቢያላጋት ዐይኖቿ በእጥፉ ተጎልጉለው ከመውጣታቸውና ፊቷ ሳምባ ከመምሰሉ በስተቀር ቃል አልተነፈሰችም።የሚያርዳት ነው የመሰላት፡፡
“የምትታዘዥውን የማታደርጊ ከሆነ ይሄ!” አለና በጡቶቿ ሥር ጩቤውን አሳርፎ “ወደ ውስጥ እንዲዘልቅልሽ ይደረጋል!” አላት በጭካኔ ስሜት።
“ተነሽ!!” አለና አንቧረቀባት።
ሹክክ ብላ ተነሳች። ከኋላ በኩል ዞሮ ያንን ዞማ ፀጉሯን ጨመደደና፤ የገባበትን በር በእርግጫ በረገደው፡፡ ከዚያም ወደ ውስጥ ሲገፈትራት፤ ተንገዳግዳ የገባችበት ክፍል ጨለማ ዋጣት...
እዚያ ጨለማ ውስጥ ሆና የገባችበትን ሲኦል ለማየት ዐይኖቿን ስትገልጥ፧ ሄዶ ማብሪያና ማጥፊያውን ቢጫነው፤ እዚያ ክፍል ውስጥ ከዳር እስከዳር የተንጣለለ ሞዝቮልድ አልጋ ተነጥፎ አየች። ይህንን
የምታተኩርበት ስሜትም፤ ጊዜም፤ አልነበራትም፡፡ ማንስ ጊዜ ሰጥቷት?
እንደዚያ ሲለምናት፤ ሲያስለምናት ከርሞ፤ እንቢ ስለአለችው፤ በቀየሰው ዘዴ የገባችለትን ወጣት ሊሰቀላት ቆርጦ ተነስቷል።
“አውልቂ!! አለና ጮኸባት፡፡
ጩቤውን እንደያዘው ነው፡፡ እየተንፈቀፈቀች ዝም ብላ ቆማ
ዐይን ፤ ዐይኑን፤ ታየው ጀመር፡፡ እንባዋን አይቶ የሚያዝንላት መሰላት፡፡
እንባዋ እንደጎርፍ ፈሰሰ፡፡ አቤት በዚያን ሰዓት የተሰማት ስሜት!? ሻምበል ብሩክ መጣባት፡፡
“እውነት ልታደርጊው ትሁትዬ?” የሚላት መሰላት፡፡
“ተይ! ተይ! ትሁት!” በአካል የቀረባት መሰላት። ስቅስቅ ብላ አለቀሰች
“አውልቂ!” አለና እንደገና አንቧረቀባት። በዚህ ጊዜ በእልህና ተውጣ፤ : እንደቆሰለ
አውሬ እየጓጎረች፤ ልታንቀው በሲቃ
ተንደረደረችበት፡፡
እንደሻው አመጣጧን አይቶ ካፈገፈገ በኋላ እዚያ ከመንጋጋዋ በታች የሆነ ደም ስሯ ላይ ክፉኛ ቢመታት፤ ሄዳ በአፍ ጢሟ ተደፋች፡፡
ከዚያም ያንን ሲቋምጥለት የነበረው ገላዋን እርቃኑን ለማየት ተጣድፎ
ልብሶቿን በፍጥነት አወላለቃቸው፡፡ እራሷን ስታ ነበር፡፡ ሙሉ በሙሉ
ልብሷን ካወለቀ በኋላ ወስዶ አልጋው ላይ ዘረራት.... ከዚያም ያንን
👍3
ካልቀመሰው፤ በስተቀር የሚሞት ይመስል የጓጓለት፤
የተንሰፈሰፈለት፣ ገላዋን ሊሻማው በጥድፊያ እላይዋ ላይ ሰፈረ....
እንደሻው በፍጹም ሊያምነው የማይችል ነገር አጋጠመው፡፡
ሊሆን አይችልም!! ጭንጫ ነች መሰለኝ” አለና ትግሉን ቀጠለ፡፡ በኃይል ተጫናት፡፡ በዚያን ሰዓት የስቃይ ስሜት ተሰምቷት
ዐይኖቿን ትንሽ ገለጥ አድርጋ የሰፈረባትን አውሬ ተመለከተችለው፡፡
የት እንዳለች ለማስታወስ ሞከረች፡፡ አልመጣልሽ አላት፡፡ብዥዥ አለባት፡፡ በሕልም ዓለም ያለች መሰላት፡፡ ደሟ እንደጉድ ፈሰሰ።እንደሻው በደስታ ቦረቀ....
ያጋጠመው ዕድል ከዚህ ቀደም የነበረውን ልምድ በአንድ ነጥብ
ያሳድግለታል፡፡ ከዚህ ቀደም የሁለት ልጆገረዶች ድንግልና ወስዷል፡፡
የዛሬዋ ስትጨመርበት ሶስት መሆናቸው ነው፡፡እሷ ቀስ በቀስ ነፍሷን እያወቀች ስትመጣና የሚሰማትን የስቃይ
ስሜት በጥርሶቿ ነክሳ ስታለቅስ፣እንደሻው ደግሞ ያንን የማይጠገብ ገላዋን በቀላሉ ሊለቀው ባለመፈለግ፤ ደጋግም ስሜቱን እስከሚያረካ ድረስ ቆየባት፡፡ ለሱ ቀላል ነገር፡፡ ለሷ ሕይወት ግን አደጋ.... ለሱ ትንሽ ነገር፡፡ለሷ ሕይወት ግን ታላቅ ውድቀት፡፡ ለእንዳሻው ትልቅ ደስታ፣ ለሷ ግን ታላቅ ስቃይና የዘለዓለም ፀፀት....
እሱ ከአሁን በኋላ ዳግም ላያስታውሳት ይችላል፡፡ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ የፈፀመው ድርጊት ግን እስከወዲያኛው ሲከተላት ይኖራል፡፡
ለህፃናት መጫወቻ ለወፊቱ ግን የነፍስ ጉዳይ ነው....
እንደሻው ጉዳዩን ሲጨርስ ሄዶ እራሱን አፀዳዳ፡፡ ትህትና ግን ዳግም እንደማትነሳ ሆና፤ እራሷን ስታ፤ እዚያ በደም ተጨማልቃ፤ ተዘርራለች፡፡ እንደሻውም ሆነ አበራ ልጃረገድ ትሆናለች ብለው በፍጹም
አልጠረጠሩም ነበር፡፡
ሠራተኛዋ በተሰጣት ማስጠንቀቂያ መሠረት ወደዚያ አካባቢ ድርሽ አላለችም፡፡ እንደሻው ያንን እልሁን ተወጣ፡፡ ያውም ለሱ እጅግ በሚያስደስት ሁኔታ ድንግልናዋን ወሰደ፡፡ ከዚያም ልብሱን ለባበስና መጥቶ አያት፡፡ ግንባሯ በላብ ተዘፍቆ፤ ዐይኖቿ ተከድነው ትጋድማለች፡፡ጉንበስ ብሎ አያት፡፡ አሁን ደሙ አስጠላው። ከዚያም ለሷ ሳይሆን
የአልጋው መበላሽት አበሳጭቶት የቻለውን ያህል አፀዳና፣ ብርድ ልብስ
እላይዋ ላይ ጣል አድርጐ ወጥቶ ከዋናው ቤት ሄደና አበራ መኪናውን
ይዞ በአስቸኳይ እንዲመጣ በስልክ ነገረው፡፡
አበራም መኪናውን ይዞ እያበረረ መጣ፡፡
ከገመትነው በላይ ድል ነው የተቀዳጀነው! ቢሆንም ግን ተጐድታለች” አለው :: አበራ ደነገጠና..
“ምን ሆና ተጐዳች?” ሲል ጠየቀው፡፡ ዐይኖቹ እንደፈጠጡ፡፡
“ገርል ነበረች” እየሳቀ፡፡ አትለኝም?!!” በድንጋጤ አመዱ ቡን ብሎ እንደሻውን አፍጥጦ ተመለከተው፡፡
“ አበራ ሙት እውነቴን ነው፡፡ አሁን ምን ይሻላል ትላለህ?”አበራ በጣም አዘነ፡፡
እንደሱ መሆኑን ባውቅ ኖሮ እጄን አላስገባም ነበር፡፡” አለው፡፡
አሁን ግን እጅህ ገብቶበታል፡፡ መላውን በጋራ እንፈልግ?”
ለአበራ ድንጋጤ ቦታ አልሰጠውም፡፡
አበራ በፀፀት እንደተዋጠ፤ ከእንደሻው ኋላ እየተከተለ ትህትና ወደተኛችበት መኝታ ክፍል ገቡ፡፡ አሁንም ነፍሷን አላወቀችም፡፡ የደረሰባት ዱላና በአሰቃቂ ሁኔታ የተፈጸመባት የግብረ ሥጋ ግንኙነት
ከአካሏም በላይ መንፈሷን ላይሽር አቁስሎት ስለሄደ፤ እራሷን ስታ
ተኝታለች፡፡
አበራ ቀስ ብሎ ብርድ ልብሱን ገልጦ አያት፡፡ በሆነው ነገር ዘገነነው :: ለሴት መድሀኒቱ ሴት ነውና፤ ለሠራተኛዋ
ኃላፊነቱን እንስጣት በማለት ተስማሙ፡፡
እንድታጸዳዳት አዘዟት፡፡ ሠራተኛዋም ሴት መሆኗን እስከምትጠላ ድረስ
ከዚያም ጠርተው በዚያች ውብና አሳዛኝ ልጅ ላይ የተፈጸመው ግፍ አስለቀሳት፡፡ ከዚያም በኋላ አበራና እንደሻው ተያይዘው ሲወጡ፤ እሷ ትህትናን ማስታመሙን ቀጠለች....

ከረጅም ጊዜ በኋላ ትህትና ነቅታ እራሷን አወቀች፡፡ከዚያም ሁሉንም ነገር እንደሷው በፆታ ከምትመሳስላት የቤት ሠራተኛ ጋር
ተወጡት፡፡ በዚህ ሁኔታ ወደቤቷ መሄድ እንደማትችል ሲያውቁ ከእንደሻው ጋር ሌላ መላ ፈለጉ፡፡ በመጨረሻም እንደሻው ባመጣው ሀሳብ ላይ ተስማሙ፡፡ እሱም ሁኔታውን ለአዜብ ማሳወቅ ነበር፡፡

“በል እንደገባህበት ተወጣው፡፡ እኔ የለሁበትም አለና አበራ እያዘነና፤ እየተጸጸተ፤ ወደ ሥራው ሄደ፡፡ እንደሻው ከአበራ ላይ መኪናውን ተቀብሎ ወደ አዜብ በረረ፡፡ ከዚያም የሆነውን ሁሉ ለአዜብ ነገራት፡፡አዜብ በምትወዳት ጓደኛዋ ላይ በተፈጸመው ህገ ወጥ ድርጊት ተበሳጭታ፤ አብራው ለመሄድ ፈቃደኛ ባትሆንም፤ ቅድሚያ ጉዳት
የደረሰባት ጓደኛዋን መርዳት ነውና...
ሌላው በሌላ ጊዜ ይሆናል” በማለት በዚህ አቋሟ ፀናች፡፡ ለምናልባቱ
ብላም የራሷን ልብስ በቦርሣ ይዛ ከመኪናው ውስጥ ገባች፡፡
እዚያ እስከሚደርሱ ድረስ ቃል አልተነጋገሩም፡፡ አዜብ እንደደረሰች
አለባብሳት፤ ይዛት ወደ ቤቷ ሄደች፡፡ ከቤት እንደደረሰችም በራሷ የመኝታ ክፍል ውስጥ አስገብታ ሙሉ ቀን አስታመመቻትና በሁለተኛው ቀን
መንፈሷ ባይድንም አካሏ ድኖ ከአልጋ ተነሳች፡፡
የአዜብ ቤተሰቦች የመጀመሪያ ልጃቸው በሆነችው በአዜብ ላይ ያላቸው ቁጥጥር አነስተኛ በመሆኑ፤ በተቻላት ሁሉ ጓደኛዋን ለመርዳት እድል ፈጥሮላታል፡፡ በተለይ ለአካለ መጠን የደረሰች ሴት ልጅን በሆነ
ባልሆነው አጥብቀን እንያዝሽ ማለቱ በጐረቤታቸው በወይዘሮ እርጉ ላይ
የደረሰውን አደጋ ዓይነት መጋበዝ እንዳይሆን ስለፈሩ ቁጥጥሩ የላላ
ነበር፡፡
የወይዘሮ እርጉ ልጅ በስንት ሰዓት ወጣሽ ? በስንት ሰአት ገባሽ? ይህ ለምን ሆነ? ያ ለምን አልተደረገም? እያሉ እናቷ ሲቆጣጠሯት፤ እናቷን ለመጉዳት ብላ የአረም መርዝ ጠጥታ ነው የሞተችው :: በዚህ አጋጣሚ አዜብ ነጻነቷን አስከብራ የፈለጋትን በፈለጋት መንገድ ስታደርግ ሥራዬ ብሎ እምብዛም የሚከታተላት አልነበረም፡፡.....

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስድስት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና #አውጉስታ ቅዱስ ገብርኤል የሚከበርበት የዓመቱ በአል ደረሰ፡፡ ይህንን በዓል የእንደሻው ወላጆች የሚያከብሩት ሐረርጌ ቁልቢ ገብርኤል በመሄድ ነው። ለዓመቱ ገብርኤል የተሳሉትን ስለት ይዘው፣ ትንሹ ልጃቸው ሲሳይን አስከትለው፤ ለመሄድ የባቡር ትኬት ቀደም ብሎ ተቆርጧል። ገብርኤል የሚከበርበት ቀን እንደ ነገ ሆኖ፤ ትህትና…»
#ሰመመን


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

.....“እህ • ውጤት እንዴት ነው ?” አለ ገና ሲያያት "
“ ኮንግራጁሌሽን ! አልፌአለሁ” አለችው በተቀመጠበት ልታቅፈው እየተንደረደረች
“ ወዳጅ ዘመድ ይኑር በይ ” አላት እርዳታውን ለመጠቀምም ።
“ ይኑር ! ” ብላ አንገቱ ላይ ተጠመጠመችና ጉንጬን ሳመችው

"ምን ምን ደኅና አገኘሽ ? ” ሲል ጠየቃት

“ ሒሳብ “ 203 ” ጎጆ ሠርቻለሁ

በዩኒቨርስቲ ውስጥ “F ያገኙበትን ትምህርት ባንዲራ ሰቅያለሁ” ሲባል “ A ? ያገኙበትን ትምህርት ደግሞ ፡ “ ጎጆ ሠርቻለሁ” ማለት የተለመደ ቋንቋ ሆኖአል

“ እሱማ የኔው ነው ” አላት እንደገና ባለውለታነቱን ለመጠቆም

“ እኮ ! ” አለችው እየቦረቀች ።

ታዲያ ጎጆውን የሰራው ማነው ? እኔ ነኝ ወይስ አንቺ ? ”

“ አንተ!” ብላው እንደገና ልትስመው ከንፈሯን ስታስጠጋው በሩ በድንገት ብርግድ አለ ። ሁለቱም እንደ ተቃቀፉ
ክው ብለው ቀሩ የገባው ሳምሶን ጉልቤው ነበር ። አውሬ መስሎ
ታያቸው

ሁኔታቸው የፊልም ትርኢት መሰለ ። እነሱ ዱብ ዕዳ እንደ ወረደባቸው ፍቅረኞቹ በጭንቀት ተቃቅፈው ሳምሶን ቆሞ በፍቅረኞቹ ላይ ሽጉጡን የደገነ ፥ " ቴክስ” ይመስል ነበር።

“ ምን ፈለግክ ? ” አለው ለማ ድንጋጤው ከበረደለት በኋላ በትዕቢት ድምፅ ። ሳምሶን ለእሱ አልመለሰለትም ።

“ አንቺ ሸርሙጣ!” አላት ቤተልሔም ላይ አፍጥጦ። እናንተ አስተማሪ እያወረዳችሁ ትኖራላችሁ ፤ እኛ ግን እንባረራለን ! ”

“ ወይኔ ! ” ብላ ቤተልሔም ለማ ሥር ሽጉጥ አለች። ሊውጣት የመጣ ነው የመሰላት ። ዐይኖቹ ውስጥ የሚንቀ
ለቀለው የንዴት እሳት አስፈራት። ሽንቷ አምልጧት ጭርር ሲል ተሰማትና ጭንና ጭኗን አጋጠመች ።

ለማና ሳምሶን ተፋጠጡ ። የአንበሳና የነብር ፍጥጫ መሰለ ። በጉልበቱ የሚተማመነው ሳምሶን ለማ ፊት እንደ
ቆመ ጡንቻውን ለመሰንዘር ምን እንዳገደው ለማሰብ ሞከረ፡ ሕግ ! የሰዎችን የስሜት ፈረስ ለጉሞ ሲይዝ ታየው ።

“ እንዴዬ ! አሁን ምንድነው የፈለግከው ? ” አለው "ከተቀመጠበት ለመነሣት እያሰላ

“ ምን አገባህ ! ” ብሎ ሳምሶን ሌላ መናገር ፈርቶ እንዳፈጠጠ'ያላየው ሰው ከኋላ መጥቶ በድንገት ትከሻውን
ጨመደደው ።

“ምን ማድረግህ ነው ሳምሶን ? ” አለው እስክንድር ትከሻውን እንደ ጨመደደ ከቢሮው ሊያስወጣው እየታገለ ።
ከእሱና ከአቤል ተለይቶአቸው መምጣቱ ከንክኖት ነበር እስክንድር እየሮጠ የደረሰበት ።

“ ልቀቀኝ ! ” አለው ሳምሶን መጋበዙ እልሁን አግሎበት ።

እስክንድር በግድ እየጎተት ከቢሮው ካወጣው በኋላ
“ ዕረፍ ሳምሶን ” አለው ፡ “ ነገሮችን ለማመዛዘን ሞክር ።ለማ ቤተልሔምን ይጠቅማት ይሆናል እንጂ አንተን አይ
ጎዳህም ። ምክንያቱም ቀድሞ የምትዋደዱበት ወይም የምትጣሉበት ምንም ግንኙነት አልነበራችሁም

“ እንጃልህ ! ” አለና እሱም ላይ አፈጠጠበት ። “ ወቼ ጉድ ! ዛሬስ ለእኔም አይመለስ ” አለና ቀስ ብሎ እያባበለሀው ይዞት ሔደ ።

እስክንድርና አቤል ፥ ሳምሶንን እያባበሉ ወደ መኝታ ክፍሉ ከወሰዱት በኋላ ስለ ራሳቸው ለማሰብ ተገደዱ። የሌላውን የፈተና ውጤት የሰማው ጆሮአቸው የራሳቸውን ለመስማት ተጣደፈ ። መውደቅና ማለፍ ሁለቱ ተቃራኒ ነገሮች
እስካሉ ድረስ ፥ መከሠታቸው የግድ ቢሆንም ፡ የማንም አእምሮ በቀላሉ አይቀበላቸውም ። ከሰዓት በኋላው ለእነአቤል በጣም ራቀባቸው ። በተለይ አቤል የትዕግሥትን ማለፍ ከሰማ በኋላ የራሱን ውጤት ለማወቅ ለምን እንደሚጓጓ ሊገባው አልቻለም ። ምናልባት ተአምር ይወርድ ይሆን ?
ሁለቱም፥ ውጤት ከሰማው ተማሪ ጋር መቀላቀል አልፈለጉም ። ግን ጆሮአቸውን በጥጥ አይደፍነት ነገር! ባለፉ ባገደሙበት ቦታ ተማሪው በቡድን ቆሞ አንዱን ሲያነሣ አንዱን ሲጥል መስማት እሰለቻቸው ። አንዱ በአንዱ ሲቀና ወይም ደግሞ መምህሩን ሲወነጅል ነው የሚሰማው ።

በዚህ ዓለም ላይ ማን ይሆን ለኅሊናው ሐቀኛ የሆነ ፍጡር ! ሁሌም የራሱን ማንነት ደብቆ ሌላውን ሲወነጅል
ነው የሚገኘው ሁሉም ። ተማሪው አስተማሪውን በማርክ አሰጣጥ ይወነጅላል።ሠራተኛ አለቃውን ይወነጅላል።አለቃም ድክመቱን በበታች ሠራተኛ ላይ ይለጥፋል ። ለዚህ ምንጩ
ምን ይሆን ? የአስተዳደጋችንና የአኗኗራችን ኋላቀርነት የፈጠረብን ችግር ይሆን እንዴ ? ምናለበት አንዱ ሌላውን ከመወንጀሉ በፊት ፡ « ለመሆኑ እኔ ማን ነኝ ? ” ብሎ ራሱን መጠየቅ ቢችል ? አንዱ ከሌላዉ ጋር የሚኖረው የግንኙነት መሠረት ሥራና የሀገር ፅድት ሆኖ ሳለ ፥ እርስ በርስ መቦጫጨቅ ቢቀር ምናለበት ? ማንም ከምድር በላይ ወይም
ከምድር በታች ላይኖር ለመበላለጥ በምናደርገው ቅናት የበዛበት ፉክቻና ግላዊ ርኩቻ የጋራችን የሆነችውን ምድር
ባንጎዳት ምናለበት ? እስክንድር በሸቀ ።

ከቀትር በኋላ፥ከነእስክንድርና ከአቤል ቀድሞ ውጤቱን የተመለከተው "ድብርት ” ነበር ።

“ ውጤት ወጥቷል ” አላቸው ፡ የራሱን አይቶ ወደ መኝታ ክፍሉ ከተመለሰ በኋላ ደስታ አፍኖት ሲያልጎመጉም ጥርሱን አሳይቶ አልሣቀም ።

"ያንተ እንዴት ነው ? ” አሉት ።
"ግሩም ነው !
“ ስንት ጎጆ ሠራህ ? ” አለው እስክንድር
ሦስቱን ጣቶቹን አሳያቸው ።

“ የጉልበት ዋጋ ነው !” አለ እስክንድር በልቡ የድብርት ” አጠናን ምንጊዜም የጉልበት ሥራ ያህል በመታገልና
ብዙ ሰዓት በማጥናት ስለሆነ፡በጉልበቱ ዩኒቨርስቲ መቆየቱን ሁሉም ያውቅለታል "

ወዲያው እስክንድርና አቤል ተያይዘው ወደ ሰሌዳው ሔዱ። የሦስተኛና የአራተኛ ዓመት ተማሪዎች ቁጥር ያን ያህል ብዛት ስለ ሌለው በቀላሉ ወደ ሰሌዳው ተጠግተው ተመለከቱ ። እስክንድር በጥሩ ውጤት ዐልፏል ። የአቤል
ውጤት ግን አልወጣም ። አቤል ራሱን ማመን አቅቶት የመታወቂያ ወረቀቱን
ከኪሱ አውጥቶ የመለያ ቁጥሩን ተመለከተ ። ያ ቁጥር ሰሌዳው ላይ የለም ማለፍም ሆነ መውደቅ የግድ ሰሌዳ ላይ
መውጣት አለበት ። እና የአቤል ከዚህ ከሁለቱ ውጭ ምን ሊሆን ይችላል ?
የእስክንድር ማለፍ ሲያስደስታቸው፡ በሌላ በኩል ደግሞ የአቤል ጉዳይ ሁለቱንም ግራ አጋባቸው ። እስክንድር
ልቡ ፈራ ። ስሜቱ መጥፎ ነገር ጠረጠረ ። ለማንኛውም ተያይዘው ውጤቱ ወደ ተዘጋጀበት ቢሮ ሒዱ ።

“ አቤት ! ምን ነበር ? " አለቻቸው ጸሐፊዋ ፡ የምታንቀጭቅጨውን ታይፕ አቋርጣ ። “ የእሱ ውጤት አልወጣም ። እና ... ብሎ እስክንድር ወደ አቤል እያመለከተ
ንግግሩን ሳይጨርስ አቋረጠችው ።

« ስሙ ማን ነው ? ”
“ አቤል ። የፍልስፍና ትምህርት ክፍል

“አሃ ! አቤል ሙሉዬ ፡ ያንተ ውጤት አልደረሰንም እስኪ ዮናታንን ሒደህ አነጋግራቸው አለችና ሥራዎን
ቀጠለች ።

“ውጤቱ ዮናታን ጋር ምን ያደርጋል?” አለ አቤል በልቡ።ዮናታንን ማየት አልፈለገም ነበር ። በዝጉ ውስጥ ሲሸሻቸው ነው የከረመው። ምክራቸውን አለመስማቱና ሕክምናውን ያለ መቀጠሉ እያሳፈሩት ከእሳቸው ለመራቅ ምክሮ ነበር።

የግዱን ከእስክንድር ጋር ሆኖ ወደ ዮናታን ቢሮ ሔደ።ዮናታን የሉም ። ቢሮኣቸው ተቆልፎአል ።

“ ምን ይሻላል ? ” አለ የእስክንድርን ዐይን ዐይን እያየ

“ ምን ይሻላል ? ” ብሎ እስክንድርም ቃሉን በትካዜ ድምፅ ከደገመ በኋላ ፥ “ እንግዲህ ነገ መጥተን እንጠይቃቸዋለን " መቼም ከአሁን በኋላ አይገቡም ” አለው እያስተዛዘነ።

ነገ እንዴት ይነጋ ይሆን ? የጭንቅ ምሽት ፤የመከራ ሕልም ሌሊት ።

በማግሥቱ ጠዋት አቤልና እስክንድር ዮናታንን ቀድመው ነበር፡ ከቢሮአቸው የደረሱት ።አቤል ዐይናቸውን ማየት
👍21
ቢያስፈራውም አልቀረለትም ። ለሰላምታ እጁን ሲዘረጋላቸው፡አንገቱን ደፍቶ መሬት መሬት እያየ ነበር ።

“ እህሳ ፡ ምነው እንዲህ ጠፋችሁ ? በዕረፍታችሁ ጊዜ ጭራሹን ሸፍታችሁ ከረማችሁ !” አሉ ዮናታን ።

“ምን ... እንዲያው ፡ ባናስብበት ነው ” አለ እስክንድር ፡ መልሱ ጠፍቶት እየተንገዳገደ ። ከአቤል ለመስማት
ዐይን ዐይኑን ተመለከቱት ፡ አቤል የመጣበትን ጉዳይ አዘግይቶ ለመልካም ማኅበራዊ ግንኙነት ሲልህ ላይ ላዩን ማውራት የማይችል ፍጡር ነው ። የመጣው ስለ ፈተናው ውጤት ስማወቅ ነው ፤የሚፈልገውም አንዲት የዮናታንን ቃል ነው ።

ሦስቱም ከልባቸው ጋር ድብብቆሽ ሲጫወቱ ቆዩ ።ዋናውን አርዕስት የሚጀምረው ጠፋ ።
“ ውጤትህ እንዴት ነው ? ” አሉት ዮናታን " እስክንድርን ። ለመንደርደሪያ ያህል እንጂ የእስክንድርን ውጤት ካወቁት ቆይተጋል ።

"ጥሩ ነው አላቸው ።

“ እ ... የአቤል ውጤት እንኳ አልደረሰውም መሰለኝ ” ሲሉ በዝግታ ፡ ወደ ዋናው ጉዳይ ገቡ ።

አቤልና እስክንድር በአዎንታ ራሳቸውን ነቀነቁ ።

አዎ ... እ ... ውጤቱ እንኳ ደኅና ነበር። ነገር ግን እኛ ኣቤልን በደኅና ውጤት ሳይሆን በማዕረግ ማስመረቅ ስለምንፈልግ ነው ውጤቱ ከመሰጠቱ በፊት የፍልስፍናው ትምህርት ክፍል በእሱ ጉዳይ ላይ መነጋገር ይፈልጋል ። ለዚህ ነው፡ ውጤቱ የዘገየው” አሉ፡ ወደ እስክንድር እየተመለከቱ፤ እግረ መንገዳቸውንም በስርቆሽ እይታ የአቤልን ስሜት እያጠኑ ። የአቤልን ስሜት ላለመጉዳት የፈጠሩት ውሸት ነው እንጂ ውጤቱስ ደህና አልነበረም ።

ዮናታን የተማሪዎቻቸውን የፈተና ወረቀቶች በሚያርሙበት ጊዜ፡በመጀመሪያ የተመለከቱት የአቤልን ነበር
አንድም የጠለቀ መልስ የሰጠበትጥያቄ የለም ። የእያንዳንዱን መልስ ጨረፍ ጨረፍ አድርጎታል ። መልሱን የማያውቀውንም ጥያቄ ባዶውን ትቶታል ዮናታንም ለማየት ያህል ተመለከቱት እንጂ ለአቤል ወረቀት ደረጃ ለመስጠት አልነበረም ። በዮናታን የአሠራር ዘዴ ውስጥ የመጨረሻ ፈተና የወሳኝነት ቦታ የለውም ። ለተማሪዎቻቸው የውጤት ደረጃ የሚፈስበት በመጨረሻው ፈተና ሳይሆን ሲሚስተሩን ሙሉ ተማሪው ባሳየው የትምህርት እንቅስቃሴ ነው ። እናም “ ምን መደረግ አለበት ? ” ሲሉ አሰቡ ። በዚያውም ሌልቹ መምህራን በአቤል ምን ዓይነት ውጤት እንደ ሰጡት ስለጓጉ ሔደው ጠየቁ አቤል ከሚወስዳቸው አምስት ኮርሶች ውስጥ ከዮናታን በስተቀር የአራቱ መምህራን ውጤት ተሰጥቶባቸው ነበር ።
በሁለቱ የትምህርት ዓይነት "D” በሁለቱ ደግሞ “F” ሰጥተውታል ። " D" የሰጡት መምህራንም ምናልባት በመመረቂያው ዓመት አናጨናግፈውም ከሚል ርኅራኄ
የመነጨ ሳይሆን አልቀረም ። ዮናታን ይህን ውጤት ባዩበት ጊዜ የቆሙበት አንቀጠቀጣቸው ። “ በሰው ሕይወት መፍረድ እንዴት ቀላል ነው ?” ሲሉ አሰቡ እናም ወዲያው ቢልልኝ ጋር ለመነጋገር ወደ ቢሮአቸው ሔዱ ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኤቤልን ጉዳይ በመከታትል የሥነ - ልቡናው መምህር ቢልልኝ በጥብቅ እየረዷቸው ነበር ።

የዮናታን ተረብሾ መሔድ ቢልልኝንም ቢረብሻቸውም የዚያኑ ያህል የሚጽናኑበት ነገር በልባቸው ይዘው ነበር በአቤል ጉዳይ ላይ ከሥራ ረዳቶቻቸው ጋር ባካሔዱት ጥናት ብዙ መረጃዎች ማግኘታቸው ልባዊ ደስታ ሰጥቶአቸዋል ።
ሆኖም ጥናታቸው ውጤት ላይ ከመድረሱ በፊት፡አቤል ከዩኒቨርስቲው መባረሩ ሌላው አሳሳቢ ነገር ነበር ። ዮናታንና
ቢቢልልኝ በጉዳዩ ላይ ከተወያዩ በኋላ፡አንድ መደምደሚያ ላይ ደረሱ ። የነበረው ምርጫ ዮናታን ለአቤል ወረቀት ውጤት
ሳይሰጡ መተው ነበር ። የአምስቱም ኮርሶች ውጤት ካልተሟላ፡ጠቅላላ ውጤቱ ተጠናቅሮ ለተማሪው ሊቀርብ አይችልም ። ዮናታን ይህን ሲያደርጉ በፍልስፍናው ትምህርት ክፍል ለሚነሳው ክርክርም ሆነ በግል ለማፂጠየቁት ማንኛ
ውንም ኃላፊነት ወስደው ነበር ። ምናልባትም እንዲህ ዐይነቱን ኃላፊነት እንዳይፈሩ ያደረጋቸው ንጹሕ እምነታቸው
ሊሆን ይችላል ።

“ ታዲያ እንዴት ይሻላል ? ” አላቸው እስክንድር ተጨንቆ ።

“ ምንም ችግር የለውም ። ጉዳዩ በጥቂት ቀናት ውስጥ ውጤት ያገኛል ” አሉ ዮናታ፥ቢልልኝ የሰጣቸውን መተማመኛ ተመርኩዘው ።

አቤል መተንፈስ ፈለገ ። የዮናታንን ስሜት ሳይጎዳ መናገር የፈለጋቸው ቃላት፥ ከልቡ ሳይሆን ከመሬት ውስጥ የሚፈልቁ ይመስል፥ መሬት መሬቱን ተመለከተ

“ እርስዎ ሊረዱኝ ደክመዋል ። እና አሁን ባልፍም ብወድቅም ምንም አይደለም ” አላቸው ፡ በዐይኑ እያስተዛዘነ።

“ ግን አንተ የምትወድቅ ተማሪ አይደለህም ” አሉት ። እሳቸውም ; የልባቸወ ኀዘን ፊታቸው ላይ እየተነበበ
“ ለማንኛውም አትጨነቅ ። ቅድም እንዳልኩህ በጥቂት ቀናት ውስጥ ውጤትህን ታገኛለህ ። ”

• ጥቂት ቀናት ?እስከ መቼ ? ምነው የእኔ ብቻ እንዲህ አከራካሪ ሆነ ? መውደቅ ወይም ማለፍ ከሁለቱ አንዱ ነው ድርሻዬ ካላጠኑ ማለፍ እንደማይቻል ዐውቃለሁ ።
ምነው አሁን ከመውደቁ አፋፍ ላይ ስደርስ ልቤ ተንቀጠቀጠ ? ለምንስ ሰው ኣስቸግራለሁ ? እያለ በሐሳብ እየዋዠቀ ዮናታንን በጥያቄ ዐይን ተመለከታቸው ።

“ መውደቅ ” ከሚለው ቃል ጋር ትዕግሥት በሐሳበ መጣችበት ። ምን ይሰማት ይሆን ?

“ እንግድያው እንሒድና ውጤቱ እስኪደርስ እንጠብቃ ? ” አለ እስክንድር ዝምታፀኑ አላምር ብሎት ወደ
አቤል እየተመለከተ

ዮናታን እስክንድርን በግል ለማነጋገር ፈልገው እንዴት ምልክት እንደሚሰጡት ተቸግረው ነበር " በመጨረሻ አቤልና እስክንድር ሊሔዱ ሲሉ ነገሩት »

“ እስክንድር ፡ ስለ ውጤትህ ለብቻህ ላነጋግርህ እፈ ልጋለሁ ።

እስክንድር ግራ ገባው ውጤቱ በእጁ ግብቷል " እና ምን የሚያስፈልግ ነገር አለ ? ወይስ በእጁ ከገባው ውጤት
ውስጥ የሚለወጥ ነገር አለ ?
“ታዲያ መቼ ልምጣ ? ” አላቸው በሩን ይዞ ቆሞ ።

በተመቸህ ጊዜ " እኔ አሁንም ቢሆን እስከ ስድስት ሰዓት ቢሮዪ ነኝ ። ”

ነገሩን ለማወቅ ስለ ተቻኮለ ፥ አቤልን ወደ መኝታ ቤቱ ሸኝቶ ወዲያውኑ ተመለሰ ።

“ የፈለግኩህ ስለ አቤል ጉዳይ ላነጋግርህ ነው ” ሲሉ ጀመሩ ዮናታን “ ትምህርቱን ሊቀጥል አይችልም ።
ማቋረጥ አለበት ። ውጤቱም ጥሩ አይደለም ። ግን ውጤቱን ሰጥቶ ዩኒቨርስቲዉን እንዲለቅ ማድረግ ለእንደሱ ዐይነት ጎበዝ ተማሪ ሞራሉን ክፉኛ መጉዳት ይሆናል ። በዚያ ሁኔታ
ከወጣ ሁለተኛ ፊቱን ወደ ትምህርት ዓለም አይመልስም።

“አዎ ። እና ትምህርቱን በዘዴ እንዲያቋርጥ ማድረግ ፣።ነው። ሰለ ደረሰበት ችግር ወይም ስለ ወደቀበት የዐይን ፍቅር በአሁኑ ጊዜ አስፈላጊው ጥናት ተገባድዷል ። ለዚህ ተብሎ
የተቀናጀ የበጎ ፈቃደኞች ስብስብ በቅርቡ ጉዳዩን አጥንቶ ጨርሶ ይነግረናል ። በዚህ ጉዳይ አቶ ቢልልኝ በጣም ነው
የተባበሩኝ ። ቢልልኝ ፡ ከሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል ታውቃቸዋለህ ? ”

“ አዎን ። እኔንም ጠርተው ስለ አቤል የማውቀውን ያህል እንድነግራቸው ጠይቀውኛል ። ”

“ የእሳቸው ጥረትና ትብብር አጽናንቶኛል ምኞቴ ከንቱ ሆኖ አልቀረም ። ምናልባትም ለአቤል ጉዳይ ይህን
ያህል አትኩሮት መስጠቱ የሌሎች ተማሪዎችንም ግላዊ ችግር መፍትሔ የሚያስገኝ ይሆናል ። እንደ አቤል ያልባሰ
ባችሁ ሕመምተኞች ውስጥ ውስጡን ካሉ ማለቴ ነው ”ዮናታን ንግግራቸውን አቋርጠው መነጽራቸውን ያለምክንያት ከጠረጴዛው ላይ አነሡ ። የመነጽሩን ጠርዝ በጣታቸው እየነካኩ ቀጠሉ ።

“ እና አሁን ከአንተ የምፈልገው ትብብር በሁለት ነገር ሳይ ነው

“ እሺ!”
“ አንደኛ ከግቢም ሆነ ከውጪ ለአቤል በሀገር ልጅነት ወይም በዝምድና ወይም በጓደኝነት የሚቀርበው
ሰው ካለ፥ ለሥነ ልቡና ጥናቱ ስለሚረዳ እንድትጠቁመን
ነው ። በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንኳ ከእሱ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብሎ የተገመተውን ከአንተ ጀምሮ የጥናት ቡድኑ ያነጋገረ ይመስለኛል ።በተለይ ከውጭ የምታውቀው ካለ ይመረጣል

እስክንድር አሰበ ። ግን ወዲያውኑ በሐሳቡ የመጣለት ሰው አልነበረም ።

“ ሁለተኛ , የጥናት ቡድኑ ውጤቱን እስኪነግረን ወይም የትምህርት ክፍሉ ለኣቤል ችግር መፍትሔ እስኪያገኝለት ድረስ፥ የመኝታ ክፍል ጓደኛው እንደ መሆንህ መጠን አቤል ራሱን እንዳይጎዳ በማጽናናት እንድትረዳው አደራ
ጥለንብሃል

“ አቤልን እንዴት ማጽናናት ይቻላል ? ” ሲል አሰበ እስክንድር ።

“ ግን ሁለተኛው ነገር ከባድ ነው ኣላቸው ተስፋ ባጣ ድምፅ ።

"ግድ የለም ። ማለቴ ፡ አንት በሚቻልህ መጠን በቅርቡ ሁን ። ብቻውን አትተወው በተረፈ ብቸኛ የማይሆንበትን የተሻለ ዘዴ እኔ በዚሁ ሰሞን ውስጥ እፈልግለታለሁ አሉ። አንዳች የተማመኑበት ነገር በልባቸው እንደ ያዙ ኮራ ብለው ።

እስክንድር ትዕዛዛቸውን በደስታ ተቀበለ ። ደስ አለው ።ከዮናታን ተለይቶ ከሔደ በኋላ፥መንገድ ላይ ብቻውን ከሐሳቡ
ጋር ይሣሣቅ ነበር ። ያስደሰተው አቤል በሚረዳበት ጥረት እሱም መግባቱ ነው ። ዮናታን በጠየቁት መህረት ከዩኒቨርስቲ ውጭ አቤልን የሚቀርብ ሰው አሰበ ዘመዶቼ ብሎ አቤል ያስተዋወቀው አንዳንድ ሰዎች በሐሳቡ መጡበት ።
ነገር ግን አቤል ብዙ አይቅርባቸውም ። ያን ያህል አይጠያየቁም ። እና፥ ታዲያ ምን ያህል ይጠቅማሉ ?
አንዲት ሴት ትዝ አለችው ። ብርቅነሽ ! የአንድ ቀን አዳር ትውውቅ ቢሆንም፡ከአቤል ጋር ከሌለች የተሻለ ግንኙነታቸው ለአቤል በሕይወቱ ውስጥ አዲስ አይነት ግንኙነት ነውና ።

💥ይቀጥላል💥
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....መንፈሷ ላይድን ቆስሎ፧ ሃሣቧ እዚህም እዚያም እየባከነ፤በተኛችበት ሆና በእንባ እየታጠበች ሁለት ቀን በጓደኛዋ ቤት ካሳለፈች በኋላ፤ ተነሣች፡፡
አካሏ ጠንካራ ቢመስልም፤ መንፈሷ ግን ደካማና የተረበሽ ነበር።በዚህች በሁለት ቀን ውስጥ ከዚህ ዓለም የተገለለች ዓይነት ሰሜት ይስማታል፡፡
የእናቷ፡ የወንድሟና፤ የሻምበል ብሩክ ሁኔታ ከፊቷ ድቅን ይልባታል፡፡
እናቷን ለሁለት ቀን ሳታያት በመቅረቷ ሁለት ዓመት የተለያቻት ያህል በናፍቆት ተቃጥላለች፡፡
“እንዴት ሆና ይሆን?” እያለች ሌሊቱን ስትጨነቅ ነው ያደረችው፡፡እናቷን በህልሟ አይታታለች፡፡ በዚያው ጐን ለጐን የሻምበል ብሩክ ጉዳይ አለ፡፡ ዛሬ እሁድ ስለሆነ ሻምበል ብሩክ እየጠበቃት ነው፡፡ ስለዚህ እሱን ማግኘት አለባት፡፡ ካላየችው ጤነኛ የምትሆን አልመሰላትም፡፡ልቧ ከውስጥ ደም ቢያለቅስም፤ ጥርሶቿ ግን እውነተኛ ስሜቷን በመደበቃቸው፤አዜብ ተጽናናች፡፡
“በቃ እንሂድ”አለቻት ለአዜብ ልብሷን ለባብሳ እንደጨረሰች፡፡
እሺ ትሁት፡፡ መጣሁ ጠብቂኝ” አለችና ሄዳ የታክሲ ገንዘብ ይዛ መጣች፡፡ ከቤት ሲወጡ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡ ዕለቱ እሁድ ነው :: ተያይዘው በታክሲ ወደ የካቲት አስራ ሁለት ሆስፒታል በረሩ...
በዚህ ቀን ሻምበል ብሩክ ከአሁን አሁን ትመጣለች በማለት በጉጉት እየተጠባበቃት ነበር፡፡ ትዕግስት መራራ ነች ፍሬዋ ግን ጣፋጭ ነው የሚለውን ብሂል በሃሣቡ እያውጠነጠነ ፣ትዕግስት አልባ በመሆን ስህተት እንዳይፈጽም ከራሱ ጋር እየተሟገተ ይገኛል፡፡
ከዚህ በፊት ከትዕግስት ውጭ በመሆን ከሱ የማይጠበቅ ድርጊት በመፈጸሙ ተፀፅቶ፤ ለራሱ የገባውን ቃል ዘነጋና፤ ባለፈው ስልክ የደወለችለት ዕለት፤ በድጋሚ ስህተት ፈጸመ፡፡በዚያን ሰዓት ትህትና በሁኔታው ተደናግጣ...
ምን ሆነሃል ብሩኬ?“ ነበር ያለችው፡፡ በአነጋገሩ የድሮው ሻምበል ብሩክ መሆኑ ፍጹም አጠራጥሯት፡፡
ሻምበል ብሩክ እንደበረዶ ቀዝቅዞ ነበር ያነጋገራት :: ይህንን ስህተት መፈጸሙን ያወቀው ግን ስልኩን ከዘጋ በኋላ ነው፡፡
ስልኩን አንስቶ ሲያነጋግራትና፤ሲሰናበታት በነበረው ሁኔታ ተደናግጣ ተደናግጣ “ምን ሆነብኝ?“ በማለት ተጨንቃ፤ ምን እንዳጋጠመው ለማወቅ ፤ እሁድ
አልደርስልሽ አላት፡፡ ሻምበል ብሩክም ስልኩን ከዘጋ በኋላ ምን ያደርግ እንደነበር ሲረዳ ተደናገጠና፤ የሚይዝ የሚጨብጠው ጠፋው፡፡
“ ምን ዐይነት እራሴን መቆጣጠር የማልችል ደደብ ነኝ?” ሲል በራሱ አማረረ
"እሺ አሁን ምን ይሻላል?“ በሚል ጭንቀት ተውጦ ለፈፀመው ስህተት ምክንያት ሲፈልግ አንድ ሃሣብ መጣለት፡፡
ሻምበል ስሜቱ በሁለት ተቃራኒዎች መካከል መዋዠቅ ጀምሯል፡፡ወደር የሌለው ፍቅር በአንድ በኩል፤ የጥላቻ ስሜት በሌላ በኩልእንደከበሮ ወጥረው ይሞግቱታል፡፡
በቃላት ሊገልጸው በማይችለው ሁኔታ ያፈቅራታል፡፡ የዚያን ዕለቱ ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር እጅ ለእጅ ተቆላልፋ ወደ ቤቱ ይዟት ሲገባ የነበረው ሁኔታዋ
ከፊቱ ላይ ድቅን ሲልበት ደግሞ፤ ከአንጀቱ ይጠላታል፡፡
ለማንኛውም ይህ ፍቅሩ ጥላቻውን የሚያጠፋበት፣አሊያም ጥላቻው
ፍቅሩን ከውስጡ ጠራርጉ የሚያስወግድበት፤ እውነተኛው ሰዓት
እስከሚደርስ ድረስ በትዕግስት ለመቆየትና የዚያ የውሽት ልጃገረድነት
ጭምብል ወልቆ እውነተኛው ማንነቷ የሚረጋገጥበትን ጊዜ በጉጉት
መጠባበቁን መረጠ፡፡
በሱ እምነትና ግምት ያ ቀን እሁድ እለት እንዲሆን ወስኗል፡፡ሻምበል እሁድ ዕለት ደርሶለት ይሄ ጥርጣሬና ጥላቻው አንድም የሚወገድበት፤አሊያም ከትህትና ጋር የሚቆራረጥበት ዕለት በመሆኑ የአሁኑ እሁድ ከምንግዜውም የበለጠ ናፈቀው፡፡
ትህትና ደግሞ በበኩሏ ሻምበል ብሩክ እንደዚያ ቅዝቅዝ ብሎና ተለውጦ በስልክ ሲያነጋግራት ተረብሻ፣የመገናኛቸው ዕለት ደርሶላት ሄዳ ምን እንደሆነ እስከምትጠይቀው ድረስ ቸኩላ፤ እሁድን እየተጠባበቀች ነበር፡፡
ሁለት ልቦች በየግል ምክንያቶቻቸውን አምቀው፤ ሰዓቱን በመጠባበቅ ላይ ቢሆኑም፤ ሰዎች በፈለጉት መንገድ ሳይሆን፤ ጊዜ በራሱ ህግና ስርዓት የሚመራ ነውና፤ እሁድ የራሱን አዲስ ክስተት ይዞ ብቅ አለ፡፡
ሰው በጊዜ ቢያቅድም ጊዜ የሰው ተጐታች አይደለምና የታቀደ ሁሉ
አይሳካም :: በተገላቢጦሽ ደግሞ ሰው የጊዜ ተጉታች ነውና፤ አንዳንድ የሰዎች ዕቅድ ጊዜው ካልፈቀደ በዕቅድነቱ ይቀርና ጊዜ የራሱን አዲስ ክስተት ይዞ ይመጣል፡፡
ትህትና ድንበሩ በአበራና በአለሌው እንደሻው አማካይነት በተቀነባበረ ሴራ፤ በአካሏ ላይ ጉዳት ስለደረሰባትና ፤በቀሪ ህይወቷ ላይ ጥቁር ነጥብ የሚጥል ወንጀል ስለተለፈፀመባት፤ በናፍቆት የተጠባበቀችው እሁድ ቢመጣም ያ ቀን ከደረሰባት ዱላና አስገዳጅ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ጉዳት ያገገመችበት ቀን ሆኖ ዋለ፡፡
እንደዚያ የምታፈቅረው ጓደኛዋ ናፍቋት፤ እናቷን ለሁለት ቀናት ያህል ስትለያት የምታደርገው ጠፍቷት፤ በእንባ እየታጠበች በዚያች በሁለት ቀን ውስጥ ወዟ ምጥጥ ብሎ፤ አካሏ ጠውልጉና ውበቷ ተገፍፎ ስትታይ፤ ትህትና ነች ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነበር፡፡ውበት የስሜት
ነጸብራቅ የመሆኑ እውነታ ከፊቷ ይነበብ ነበር፡፡
ለዚያውም አዜብ ከአጠገቧ ሳትለይ በማንኛውም ረገድ ባታፅናናትና
ባትንከባከባት ኖሮ፤ ጉዳቷ ከዚህም የከፋ ይሆን ነበር፡፡ከዚህ ሁሉ በኋላ በሁለተኛው ቀን ላይ ሰውነቷን ተጣጥባ፤ በቅባት ፊቷን አባብሳ፤ የአዜብን ምርጥ ቀሚስ ለብሳ ፤ ሰው መስላ ተነሣች፡፡
ሞራሏ እንዳይነካና ያለፈውን እንድትረሣ አዜብ ያላደረገችላት ጥረት አልነበረም፡፡ ትህትናም ጓደኛዋን ለማስደሰት ያህል ብቻ ልቧ ከውስጥ ደም እያለቀስ፤ ከላይ ከላይ ፈገግታ እያሳየቻት ተነሳች፡፡
በተለይም በዚያን ዕለት ጨረቃዋ በመኝታ ክፍላቸው ውስጥ ብርሃኗን ስትፈነጥቅ፤ ከሻምበል ብሩክ ጋር ባሳለፈችው አስደሳች ምሽት የተናገረችው ትዝ ይላትና እረፍት ይነሳታል፡፡ ያንን የሚያሰቃይ ስሜቷን ውጣ በፍጹም ጤነኛና ደሰተኛ መስላ ልብሷን ለባብሳ እንደጨረሰች...
"እንሂድ አዜቢና” አለቻት፡፡
እናቷ ይህችን ሁለት ቀን ልጇ ሳትመጣ በመቅረቷ እዚያ ሆስፒታል ውስጥ በእንባ እየታጠበች አንዱአለምን ካልወለድካት እያለች ስታስጨንቀው፤ በሁለተኛው ቀን ላይ የት እንዳለች ቁርጡን ነገራት፡፡
አንዱዓለም እህቱ የት እንዳለች የሰማው ከአዜብ ነው፡፡
• ትሁት ሻምበል ጋ ነች፡፡ ሁለት ቀን እዚያ ስለምትቆይ አንተ ከእናትህ እንዳትለይ አደራህን” ብላ በሚስጥር ስለነገረችው፤ አንዱአለም ዜናውን በደስታ ተቀብሎ ለደቂቃ ከእናቱ እንደማይለይ በገባላት ቃል መሠረት ከዚያ አካባቢ ውልፍት ሳይል ነው የቆየው፡፡
ትህትና በዚህች በሁለት ቀን ውስጥ ሁለት ዓመት እንደተለያቻች ሁሉ ናፍቃት፤ ሆስፒታል ስትደርስ እየሮጠች ሄዳ እናቷ ላይ ድፍት ብላ አለቀሰች፡፡ አዜብ የጓደኛዋን ሁኔታ ስትመለከት አንጀቷ ተላወሰ፡፡አልቻለችም፡፡ አብራት አለቀሰች፡፡
እናቷም ልጇ ላይ ጥምጥም ብላ በስስት እያገላበጠች ሣመቻትና..
በጤናሽ ነው ትሁቴ? አለሽልኝ የኔ እናት? ” ዐይን ዐይኖቿን በጉጉት እያየች፡፡
“ደህና ነኝ እማይዬ አንቺስ እንዴት ነሽ?” እናቷን እያሻሸች በዐይኗ አንዱአለምን ስትፈልግ እሱም የሆነ ነገር ሊነግራት ፈልጐ ምልክት ሲሰጣት አየችና ልትስመው ሄደች.....
“ሻምበል ጋ እንደነበርሽ ነግሬአታለሁ” አላት ድምፁን ዝቅ አድርጉ፡፡
ትንሽ ሣቅ ብላ......
“እሺ" አለችው::
ከዚያም በኋላ ከእናቷ አጠገብ የተኙትን በሽተኛ አዛውንት ጤንነታቸውን ጠይቀው፣ እናቷን ከበው ተቀመጡ፡፡ እናቷ የልጇን
ዐይን፤ዐይን፤በስስት ስትመለከት ሆዷ ቡጭ ቡጭ
👍1