አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

ጊዜ መደፊት አይገፈትርም።ጊዜ ለሰው ጭንቀትም ሆነ ደስታ ደንታ የለውም።
የራሱን ሥርዓት ጠብቆ የሚጓዘው፤ያለፈ ጊዜ አይመለስም ፤የወደፊቱ ደግሞ እንደ
ፈለግጉት ፈጥኖ አይመጣም። ሰው በጊዜ ቁጥጥር ሥር ነው እንጂ ጊዜ በሰው ቁጥጥር ስር አይደሉም ሰዓት ሰው ሠራሽ ነገር ነው ፤ ሞላውን በማዞር ካለበት ሰዓት ወይም ደቂቃ ማስቀደም ይቻላል ። የቀን መቁጠሪያም ሰው ሠራሽ
ነገር ነው ፤አንዱን ወር አልፎ ሌላውን ወር ማየት ይቻላል ።ቀንን ገፍቶ ማስመሸት፣ ወይም ምሽት ጎፍቶ ማንጋት ግን
የማይቻል ነው ።

አቤል ቢቸግረው እንዲህ አይነት የጊዜ ምርምር ውስጥ ገባ ። ችግሩ ነው ምርምሩን የጋበዘው ቀኑ አልመሽልህ "
ሌሊቱ አልነጋልህ እያለው ተቸገረ ለሌላው ተማሪ የዕረፍት ጊዜ ለእሱ ግን የመጨረሻው ደረጃ የጭንቀት ጊዜ
ሆኖበታል ። ቀንም ይተኛል ፡ ማታም ይታኛል ። ነገር ግን እንቅልፍ አይወስደውም ። እንዲሁ አልጋው ላይ እየተገላበጠ በሐሳብ መብከንከን ሆነ ። ጊዚ ከመቼውም ይልቅ የኋሊት እየተጎተተ የሚያቃስት መስለው ።

ሳምሶን ለዕረፍቱ ወደ ቤቱ ስለ ሔደ መኝታ ክፍላቸው ውስጥ የቀሩት አቤል ፡ እስክንድርና "ድብርት ” ብቻ ነበሩ ። “ ድብርት ” ፈተና ካለቀ በኋላ ያሳየው ለውጥ ቢኖር አልጋ ማንጠፉ ብቻ ነው ። በተረፈ እንደ ጥንቱ “ድብርት ጥናቱም ቢቀር ያው አልጋውን በጋቢ ጋርዶ በራሱ ሕልም ውስጥ መኖሩን አልተወም ። ወደ ውጭ ቢወጣ ብቻውን ነው ።

እስክንድር የዕረፍት ጊዜ ጓደኛው መጽሐፍ ነው ።የአማርኛና የእንግሊዝኛ ልብወለድ መጽሐፎችን እየተዋሰ
ሲያነብ ስለሚውል፥ ቀኑ በፍጥነት ነው የሚገሰግስለት ማንበብ ስልቸት ሲለው፡ወደ መዝናኛው ክበብ እየሔደ ቼዝ
ይጫወታል ። መቼም ከሱ ቦታ ሰው ቢጠፋ ሚስተር ሆርስ አይጠፋም ።

እስክንድር በዚህ ሁኔታ የዕረፍቱን ጊዜ ቢያሳልፍም ከአቤል ጋር አብሮ መጨነቁ አልቀረለትም ። ዐቅሙ በሚፈቅደው መጠን አቤልን ለማዝናናት የማያደርገው ሙከራ የለም ። ከአነበባቸው መጽሐፎች ውስጥ ጥሩ የሚላቸውን መርጦ ይሰጠዋል ። አቤል ግን ነጻ ኣዕምሮ ስለሌለው፥ አንዱንም ከነጣዕሙ አንብቦት አያውቅም ። ጀምሮ ሳይጨርሰው ይቀራል ። ወይም በግል ሐሳቡ ውስጥ እየዋዠቀ ገጹን
በመቁጠር ብቻ ይጨርሰዋል ። እስክንድር ወደ ቼዝ መጫወቻው ቦታ ሲሔድ አቤል አብሮት እንዲሔድ ለማድረግ ቢሞክርም እሺ አላለውም ፡ ከሚስተር ሆርስ ጋር ከተጣላ ወዲህ የመዝናኛ ክበቡን ረግጦት አያውቅም ።
አቤል ወደ ውጭ ብቅ እያለ ከሰዎች ቢቀላቀል ፡ ጊዜውን መዝናኛ ቦታዎች እየሔደ ቢያሳልፍና በአንዳንድ እን
ቅስቃሴዎች ቢሳተፍ፡ ጭንቀቱ እንደሚቀልለት እስክንድር
ቢረዳም ፡ ይህን ለማድረግ ሁኔታዎች አልተመቻቹለትም አብዛኛው መዝናኛ ገንዘብ ይጠይቃል ። ይህን ማሟላት
አይችሉም ። ገንዘብ በማይጠይቅበት መዝናኛ ቦታ ለመዋል ደግሞ የአቤል ሙሉ ፈቃደኝነት አይገኝም ። ሌላ ቀርቶ
ከእስክንድር ጋር ከሚያወራበት ጊዜ ይልቅ፡ ብቻውን ተደብሮ ውስጥ ውስጡን ነገር ሲያብሰለስል የሚውልበት ጊዜ
ይበልጣል ።

ትዕግሥት በተለያየ መልክ በሕልሙ እየመጣች ትታየዋለች ። አንዴ ይጣላሉ ፤አንዴ ጥላው በመሔዷ የተሰማውን ቅሬታ ይገልጽላታል ፤ አንዳንዴ ደግሞ ደብረ ዘይት ድረስ ሔዶ ሲገናኛት ያድራል ቀን ያሰበውን ማታ በሕልሙ ይደግመዋል አንዳንዴ በቅዠት ይወራጫል ።
ከትዕግሥት ናፍቆት ጋር ተደርቦ የወላጆቹ በተለይም የእናቱ ሁኔታ ፊቱ ላይ እየተደቀነበት መጨነቁ አልቀረም ።
ያስብ ያስብና ሁሉም ነገር ፍቺ የሌለው እንቆቅልሽ ይሆንበታል ። ሆኖም እንቆቅልሽ ነው ብሎ አይተወውም ።

ተመልሶ በዚያው ሐሳብ ዙሪያ ይሽከረከራል ፡ በሐሳብ ከመብከንከኑ ጋር የምግብ ፍላጎቱም እየቀነሰ ስለመጣ
በጣም ከስቶ ነበር ። ግን ለዚህ ደንታ አልነበረውም ። አካሉ መንምኖ ነፍሱ ብቻ ከውስጥ ሚን ሚን እስክትል ይጠብቃታል

ብርቅነሽ ትዝ ስትለው የደስታ ብርሃን ትፈነጥቃለች ።ስለ እሷ ማሰብ ደስ ይለዋል። አብሯት ካደረ ጀምሮ የመውደድ ስሜት ተቀርጾበታል ። የፍቅሩን ዐይነት ግን በግል ለይቶ ማወቅ አልቻለም ። ትዕግሥትን ይወዳታል ፡ ብርቅነሽን ይወዳታል ። የመወደዱ ዐይነት ይለያያል ሲያስቡት ደስ የሚልና ሲያስቡት የሚያስቃይ ፍቅር ! ስለ ብርቅነሽ ማሰብ ያስደስተዋል ፤ አያሠቃየውም ፤ ጭንቅላቱን አይበጠብጠውም ። ስለ ትዕግሥት ማሰብ ግን ያሰቃየዋል፥
ይበጠብጠዋል ፤ ያስለቅሰዋል ። እንዲያም ሆኖ ፍቅሩ ለምታሠቃየው ለትዕግሥት ያደላል ። ሙሉ ልቡን ያሳረፈው በትዕግሥት ላይ ነው ። ቀርቦ ምስጢሩን ካካፈላት ፥ ገላዋን ካቀፈውና ትኩሳቷን ሲቀበል ካደራት ሴት ይልቅ ከዐይኑ ላላለፈች ሴት ፍቅሩ ማመዘኑ ለምን እንደያነ ሊገባው አልቻለም ። “ የፍቅር ምስጢሩ ምንድነው ? ሲል አሰበ "
ፍቅር የሚወደው ሥቃይን ይሆን እንዴ ? ?

አንድ ቀን ብርቅነሽን ሲያስታውስ ከውስጡ “ሔደህ እያት ” የሚል አንዳች ግፊት መጣበት። ለእስክንድር ሳያማክረው ተደብቆ ብቻውን ሔደ ። ለምን እንደሚሔድና ቢያገኛት ምን እንደሚላት አላሰበበትም ። ገብቶ ለመጫወትም ቢሆን ፥ የሚጠጣ! ለማዘዝ በኪሱ ገንዘብ የለም ። እናም ቡና ቤቱ አጠገብ ሲደርስ ቀጥ ብሎ ቆመ።

የቡና ቤቱ በር ክፍት ነው ። ነገር ግን ድምፅ አይሰማበትም። እንደዚያ ዕለቱ ምሽት ሙዚቃና የሰው ቻቻታ የለበትም ። ከዝንቦች እምታ በቀር ጸጥ ረጭ ብሏል ።
መግባት አልደፈረም ። እየተንጎራደደ ሰው ብቅ እስኪል ይጠብቅ ጀመር ። ጥቂት እንደ ቆየ ፥ አንዲት ሴት የከሰል
ምድጃ ይዛ ከውስጥ ብቅ አለች ። አለባበሷ ግድ የለሽ ነው ።
ሻሿን የገርዳሳ አስራለች ።

አቤል ሲያያት ክው አለ ። የዋህነቷንና ጥሬነቷን አይታ የቡና ቤቷ ባለቤት ማታ ማታ እንደ አሻሻጭ ቀን ደግሞ እንደ ገረድ ነው የምትጠቀምባት ፡ ከሰሉ እንዲቀጣጠልላት ምድጃውን ወደ ንፋስ አድርጋ ቀና ስትል አየችው ቶሎ አልለየችም። ያው እንደ መንገደኛ ነበር የተመለከተችው ። ስታየው ተደናግጦ ጀርባውን ሰጥቷት ወደ ኋላው ሊመለስ ፈልጎ ነበር ። ግን ዐይኑን ከማሸሹ በፊት የምታውቀው ወንድ መሆኑን ለይታ ጥርሷን ብልጭ አረገችለት እሷን ፍለጋ ያልመጣ ለመምሰል እጁን ኪሱ ከትቶ በግዴለሽ አረማመድ ተጠጋት ስሜቱን ለመሸፈን በከንቱ ደከመ እንጂ በድንጋጤ ፊቱ ቀልቶ ግንባሩን አልቦት ነበር።

ውይ ! አንተ ነህ እንዴ ? በሞትኩት ! ምነው ጠፋህ ? ” አለች ከልብ በሆነ አነጋግር ።

ምንም ሳይመልስላት ስሜቱን በፈግግታ ብልጭታ ለመሸፈን እየሞከረ ጨበጣት

ሙት እውነቴን እኮ ነው ጠፋህ ? ቆይ እስኪ ስንት ቀን ሆነን አዎ ሳምንት አልፎሃል ። እኔ ከዛሬ ነገ ትመጣለህህ እያልኩ በልቤ ሳስብህ ነበር አለችው።

“ እነቷን ይሆን እንዴ ? ” ሲል አሰበ ግን አሁንም ከመቅለስለስና ራሰን ከማከክ ሌላ ምንም አልመለሰም ። ድምጿ የእውነት ቅላጼ ነበረው የተናገረችው የልቧን ነው ፤ ለአቤል አንድ ጥሩ የሆነ ስሜት አድሮበታል ። ሴት ያልለመደ መሆኑና የተማረ መሆኑ ፥ በስሜቷ ውስጥ እንዲቀረጽ አድርጎታል እናም እንዳለችው አብራው ካደረችበት ሌሊት በኋላ ዐልፎ ዐልፎ በልቧ ታስበው ነበር ። የተሰማራችበት ሙያ ሆነና በወሲብ ተገናኙ እንጂ ፥ እሷ ለሱ ያደረባት ስሜት ሐሳቧንና ችግሯን እንደምታዋየው
እሱም በዕውቀቱ እንደሚረዳት የቅርብ ዘመዷ ወይም ታናሽ ወንድሟ ዐይነት ነበር

“ በል እሺ ግባ ! በር ላይ አትቁም አለችው ከእሱ አንዳችም ቃል ባለመስማቷ እያዘነች ።

“አአይ ልሒድ ፤ድንገት ሳልፍ'ኮ ነው
👍2
አላት ፡በአንድ በኩል እንደ መግደርደር ያለ ፡ በሌላ በኩል ደግሞ የኪሱን ባዶነት እያሰበ ።

"ግባ እባክህ፥ ትንሽ ተጫውተህ ትሔዳለህ ” አለችና ጎተት አደረገችው ።

በባዶ እምነትና ኩራት የተገነባ ግትር ሰውነቱን አቅልላ መጎተቷ ውስጡን ደስ እሰኘው ራሱን አቅልሎ መቅረብ አይችልም ። ንጹሕ ልብ ያለው ሰው አቅልሎ ሲቀበለውግን ይወዳል። በልቡ “ የሚቀጥለውስ ዶረጃ ምን ይሆን ? ?
እያለ ያለማመንታት ወደ ውስጥ ዘለቀ።

ምንም ሰው የለም እንዴ ? ”አላት ፥ ቅርቡ ባጋጠመው ወንበር ላይ እየተቀመጠ ።

“ውይ በቀን ምን ገበያ አለ ብለህ ነው ? ያው ማታ ነው ሞቅ የሚለው ” አለችው አጠገቡ እየተቀመጠች ።

አጠገቡ ስትቀመጥ ጊዜ፥ ልቡ ናድናድ ይል ጀመር። ለሰውነቷ መቅረቡን ቢወደውም ከእሷ ካልመጣ በቀር እሱ
ደፍሮ መጠጋጋት ወይም መተሻሸት አልቻለም ። እንጂ ያውም በዚያን ሌሊት ራሱ ደፍሮ ክንፉን ዘርግቶ ይህችን
ሴት አቅፎ ማደሩን ዛሬ ተጠራጠረ ማድረግ በማይችሉት ነገር ላይ ለመገፋፋት መጠጥ መልካም ቅመም ሳይኖረው አይቀርም ብሎ ገመተ።

“ እሺ ። እስቲ በል ተጫወታ” አለችው ቀጠለችና ሣቅ እያለች ።

እሺታውን ለመግለጽ የሚዋትቱት ዐይኖቹ ከጥርሷ ጉራማይሌ ንቅሳት ላይ ዐረፉ ። የሣቋ ምንጭ ምን እንደሆን ማወቅ አልቻለም ። ምናልባት አብሬኣት ያደርኩባትን ሌሊት አስታውሳ ይሆን እንዴ ?” በሚል ጥርጣሬ በአንዴ
ፊቱን ላብ አሰመጠው ።

አሁን ዕረፍት ላይ ናችሁ አይደል ? አለችው ስሜቱን ሳታጤን።

“ አዎ ብቻ ዕረፍቱ ወደ ማለቁ ነው ። ”

“ ጨካኝ ነህ ግን አንተ ዕረፍት ሆነህ ይህን ያህል ቀን ሳትመጣ ? ! ”

ጭካኔ አይደለም አላት ፥ ድምፁ ከመድከሙ የተነሣ የራሱ መሆኑ እያጠራጠረው ።

ታዲያ ምንድነው ? ”

ምን እንደሚላት ግራ ገባው ፍርሀት ፥ የኪስ መድረቅ ? ወይስ ጭራሹን ያለ መፈለግ ?

ለመልሱ ሲጨነቅ አይታ ሐሳቧ ቶሎ ሌላ ነገር ላይ ሮጠ ።

ያቺ ልጅ እንዴት ናት ? ”

የቷ ? ” አለ ፡ የማይፈልገው ጥያቄ መሆኑን ገምቶ ዐይኑን እያፈጠጠ ።
ያቺ ዩኒቨርስቲ ያለችው ! ያንን ሌሊት ያጫወትከኝ ” አለችው ደንታ ባጣ ቀላል ስሜት "

ከሌላ ሰው ስለ ትዕግሥት አንዳችም ጥያቄ ሆነ ጨዋታ ሲነሣበት አይወድም ። የብርቅነሽ አጠያየቅ ግን፥ ለጊዜው
ቢያስደነግጠውም ድንጋጤው ጭንቅላቱ ውስጥ አልቆየም ።ምክንያቱም የብርቅነሽ አጠያቀቅና አቀራረብ እንደ ምሁራኑ ከፍተኛ አትኩሮት ያለውና የሰው ስሜት የሚያጤን ዐይነት አልነበረም ። ነገሮችን ሁሉ ቀላል አድርጋ በቀላል
አነጋገር ነው የምታቀርባቸው ። መልስ ብታጎኝ አገኘች ባታገኝም ወደ ሌላ ጨዋታ ትሸጋገራለች እንጂ ፥ ሥራዬ
ብላ የሰወ ስሜት በማጥናት ወይም ነገር በማውጣጣት አትጨነቅም ።

"ግቢ ውስጥ የለችም ፤ በዕረፍቱ ወጥታለች”አላት ደፋር ጥያቄዋ አደፋፍሮት ፥ ድንጋጤው ተግ ብሎለትና
ነገሩን ማቅለሏ እሱም አቅልሎ እንዲያየው ገፋፍቶት ።

ውይ ፡ ሠፈሯ የት ነው ?” አለችው ።
“ደብረ ዘይት ” ሲላት፡ጉሮሮው ላይ አንዳች ነገር እየተናነቀው ነበር ።
“ ውይ ! ከአዲስ አበባ ውጭ ? ” አለችው ከልቧ አዝና ። ትዕግሥትን ሳያያት ማደር እንደማይችል አጫውቷት ስለ ነበር፥ ርቃው ስትከርም ምን ያህል እንደሚሠቃይ በመገመት አዘነችለት ። ከእሱ መልስ ሳትጠብቅ ቀጥላ ፡

“ ስትሔድ ምን አለችህ ? ” አለችው ።
ምንም ።

ምንም አልተባባላችሁ ? አሃ ፡ በቃ ተነጋግራችሁ አታውቁም ?

በአሉታ ራሱን ነቀነቀ ።

“ ውይ ! ምን ዐይነት ፍቅር ነው ? ” አለች

“ ጭፍን ፍቅር ነዋ ! ” አላት በብሽቀት ። የሆነ ነገር ዐይኑን ለበለበው ። የገዛ ልቡ ከበደው ። በዚህ አርዕስት ላይ ቀጥሎ ከብርቅነሽ ጋር መጫወት እንደማይችል ገመት ።ይህን ያህልም ግልጽ የሆነው ለእሷ ብቻ ነው። እሷም ከዚያ በላይ ልትጠይቀው አልቻለችም ። ቃላት መለዋወጥ ቀርቶ በሙሉ ዐይን ተያይተው ከማያውቁ ፍቅረኞች ምን መረጃ
ይገኛል ? አብዛኛውን ድፍን ሁኔታ አብረው ያደሩ ዕለት አጫውቷታል ። እና ዝም ብላ ዐይን ዐይኑን ስታየው ስሜቱ የተጋባባት ትመስል ነበር ።

እንዲህ እየተጫወቱ ትንሽ እንደ ቆዩ የቡና ቤቷ ባለቤት ከጓዳ ብቅ አለች ። ከቀኑ አምስት ሰዓት ተኩል አካባቢ ቢሆንም እሷ ገና በሌሊት ልብሷ ነበረች ። ፊቷ ሲያዩት ይከብዳል ። በዚያ ላይ ገና ከመኝታዋ መነሣቷ ስለሆነ ፊቷ ላይ
የተጋደመው ሰምበር መልክ አሳጥቶአታል በሒና የቀላው ጸጉሯ ትንሽ ባያደምቃት ኖሮ፡ ጭራ ትመስል ነበር። አቤል
ያን ምሽት ያያት ሴት መሆኗን ተጠራጠረ ያኔ ታምር ነበር ። " የቡና ቤት ሴቶች ውበታቸው ማታ ማታ ብቻ ነው ማለት ነው ? ” ሲል አሰበ ።

ባለቤቷ ናቸው እንዴ ? ” ሲል ብርቅነሽን ።
ሹክ ብሎ ጠየቃት።

“ አዎ ” አለችና ብርቅነሽ እየሣቀች ፡ “ ብቻ አንቱ ስትላት እንዳትሰማህ ፡ አትወድም ” አለችው ፥ እሷም እንዲሱ ሹክ ብላ ።

« እኛህን የሚያክሉ ሴትዮ አንቺ ማለት ነወር ነው ብዬ ነው።

“ ሆሆይ ! እሷ ስትስነብት ልጃገረድ ነኝ ሳትል ኣትቀረም እንደገና ሣቋን አፍና ።

ባለቤትየዋ እየቀረበች ስትመጣ ጨዋታችውን አቋረጡ።

“ ከሰሉ አልተቀጣጠለም እንዴ ?” ስትል ብርቅነሽን በተቆፋጠነ ድምፅ ጠየቀቻት ቡና ማፍያቸው ሰዓት ነበር።

“ ውይ ፡ እረ እስካሁን ይቀጣጠላል ” አለችና ብርቅነሽ ተስፈንጥራ ብድግ አለች ከሰሉ እንዲቀጣጠል ውጭ ማድረጓን ዘንግታው ነበር ።

ሻሽሽ ሊወድቅ ነው ? ” አላት አቤል ፡ ከጸጉሯ ላይ ሲንሸራተት አይቶ ።

“ ኬሬዳሽ ! ” አለችና ጭራሹን ፈትታ ጣለችው ።በልቡ “ የዋህ ፍጡር እያለ ከተቀመጠበት ተነሥቶ ወደ ውጭ ተከተላት።

“ ምነው ተጫወት እንጂ፡ እኔ “ኮ ከሰሉን ላገባ ነው ።”

“ ተጫወትኩ ኮ ልሒድ” አላት ወደ ፊቱ እየተራመደ።

“ እሺ በል ማታ ትመጣለህ ?”

“ እ ? ”

"ማታ ና ! ”

እሺ ብሎ ተሰናበታት ። ደስ ብሎት ዋለ ። እናም « አንዲህ ደስታ የምትሰጠኝ ከሆነ ለምን ደጋግሜ አላያትም ?”
የሚል ሐሳብ አደረበት። ብርቅነሽ ጋ መሔዱን ለእስክንድር አልነገረውም ። ድብርትን ፈልጎ አንድ ብር እንዲያበድረው
ጠየቀው ። ድብርት ምን ጊዜም ገንዘብ አያጣም ። ለክፉ ቀን በሚል እምነት እንደሚቀብር አቤል ያውቃል ። ከዚያ
በፊት ጠይቆት ስለማያውቅ፥ ድብርት ገርሞት እንድ ብር አወጣና ሰጠው ። ከሳጥኑ ውስጥ ከስር ፥ ከመጽሐፍ ሽፋን
ብሩን መዝዞ ሲያወጣ ሲያየው አቤል ገረመው ። « የሰውን እጅ ብቻ ሳይሆን የራሱንም እጅ ሳይጠረር አይቀርም
አለ በሐሳቡ።

አቤል ኮካ ኮላውን ይዞ ማታ ወደ ብርቅነኝ ዘንድ አመራ ። ካምፓስ ውስጥም ሆነ ውጪ እስክንድር እንዳያየው መንገድ እየመረጠ ነበር የሄደው።

እቡና ቤቱ ሲደርስ የተለመደች ፍርሀቱ መጣችበትና ቆሞ ትንሽ አመነታ። ቡና ቤቱ ጢም ብሎ ሞልቶ፥ ቻቻታው
ደርቶ ነበር ። ቀስ ብሎ ወደ በሩ ተጠጋ ። አንገቱን ውስጥ ገባ ሲያድርግላ ዐይኑ አነጣጥሮ ብርቅነሽ ላይ ዐረፈ ። የሆነ ነገር ፊቱ ላይ ብልጭ እለበት ። ራሱን መቆጣጠር ያቃተው ይመስል- በሩን ደገፍ ብሎ ቆመ ብርቅነሽ ባንኮኒው አጠገብ አንድ ወንድ ጭን ላይ ተቀምጣ ቢራ ትጠልለች። ከት ከት እያለች ከልቧ ትሥቃለች " ትጫወታለች የዋህ ልቧን ለማንም ከፍታ ትሰጣለች ወንድየው በአንድ እጁ ወገቧን ደግፎ በአንደኛው ጡቶቿን እያሻሸ አብሯት ይሥቃል ፤ ይጠጣል ፤ ይጫወታል ።

አቤል እንዳያት እንድታየው አልፈለገም ። ለምን ከማንም ጋር ትሥቃለች? ለምን ከማንም ጋር ትጫወታለች ?ለምን ለማንም ልቧን ትከፍታለች
? ሳታየው ቀስ ብሎ ወደ ኋላው ተመለሰ ።

ወደ መንገዱ ሲያቀና በሐሳሱ የቡና ቤቱ ሰው ሁሉ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ግባ እኔጂ ምነው ተመለስክ? የቀናህባት ሴት አለች እንዴ ? ቡና ቤት እኮ ነው የመጣህው የሚለው መሰለው።

የገዛ ስሜቱን እንደሚሸሽ ሁሉ ፊቱን ወደ ስድስት ኪሎ አቅንቶ መንገዱን ጀመረ ። በሐሳቡ ውስጥ ገንዘብ ከፍተኛውን ቦታ ይዞ አብሮት ገሰገሰ ። ገንዘብ ፈለገ ። ገንዝብ ፈጥኖ ለማግኘት ጓጓ ። ገንዘብ የነገሮች ሁሉ ማሰሪያ ነው አለ በልቡ ።

💥ይቀጥላል💥
#የቀን_ቅዠት

ደመ ግቡ ፣ ቀይ ሴት
የመልኬ ገጽ ፣ ፍኩ ሐሤት
በእይታ አፍታ ፣
በብልጭታ ፍጥነት . . .
ከዐጸዴ መጥታ ፣

ድንግዝግዝ ፍዝ ቀን ፣ በፈገግታ ጠርቶ
ወጀብን የሚያቆም . . .
የሰመመን ዓለም ከቤቴ ተገኝቶ።

ጀንበርን ሸሽጋ ፣ ጨረቃዋን ጋርዳ
በድንገት መሽጋ ከዕልፍኜ ጓዳ።
በሻማ ተስላ . . .
ሸማ ተሸልማ ፣ ተገልጣ በ'ኔ ዐይን
አበባ ታቅፋ ፣ ጽዋ ሙሉ ወይን ፣
(. . . ከዕቅፌ ገባች . . )
ማእዱን ተቋደስን ያብሮነትን መባ
በቅጽበት ደመኩኝ ፣ በቅጽበት ተውባ
ድንገት ተሰለበች !
እኛነት ለለበች።(ዋሸች,አታለለች)

( ምን ነበረ የኾነው . . . ?)
በቀን በጠራራ ሳልም የነበርኩት ?
በክፍልፋይ ሰከንድ እያየው የዋልኩት ?
እኮ ምን ነበረ? ...
ልፈታው ቸገረኝ !
ቅኔው ግራ ገባኝ ተመሳጥሮ ሕልሜ
ተሠፋኹ ፣ ተቋጠርኩ ፤ በቀን ሐሳብ ቀኔ።

ለማላውቃት ውብ ሴት . . .
ፀምን ሕልሟ ብኾንም ፣ ሕልም ብትኾን ለ'ኔ፤
ያልታኖረ ሕይወት . . .
የሐምሌ ፀሐይ ነው የክረምት ምናኔ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
#ሐዘን_እና_ዘፈን

ማሞና ማሚቱ . . .
የሚገዙት ቆሎ ጠፋና ባ'ገሩ ፣
ፍቅራቸው ቀነሰ ፤
ጭራሽ ተባብሶ መቃቃር ጀመሩ።

ቆሎ ሻጫ እሜቴ ከገበያ ጠፍታ
የምትሠፍረውን ገብስ ከጎተራ 0ጥታ፣
መደቧ ተራቁቷል ፤ የስፍር ቁናዋ
የገብስ ዘር ጠፍቶ ከትልቅ ማሳዋ።

ቆሎ ቆርጣሚ ሰው ሥንቁ ጥራጥሬ
“ለምን? እኽል ጠፋ ካ'ገሬው ገበሬ”
እያለ 'ሚጠይቅ . .
“በየምልክቱ ገብስ እየለጠፉ
እኮ ለምንድነው? ከማሳው ያጠፉ
ብሎ የሚጠይቅ . . .

ሰበበኛ ቀዬ ፤
ገብሱን እየጠጣ ገብስ ቆሎ 'ሚያልም
ፈጭቶ ከመጋገር በጥሬ የሚልም።
ከእንክርዳዶች መኻል እኽልን ያለየ
“ገብስ ነው!” ይልኻል ፣ ገለባ እያሳየ
ገለባ ሕይወቱን ሰፍሮ እየመዘነ
በሥጋ ውቂያ ላይ ፣ ትልሙ ተበተነ።

የተበተነው ሕልም .
ዘፈን ይዞ መጣ ግልብ ኾኖ ነፋሱ ፣
ማሞ ዳቦ ናፍቆ . . .
የሚቀምሰው ቢያጣ ቢቆም እስትንፋሱ ፣
የጓዳቸውም ሐቅ . .
በሰነፍ ቆሎ ዕጣ ወድቆ ከመቅደሱ።

(. . . አዜሙ ዘፈኑ . . . )
ዘፈን ነው መፍትሔ? . . .

በተቃርኖ ስሌት ሲኾን ሱሪ ባ'ንገት
ዳቦ የበላና . . .
ቆሎ የሚናፍቅ ሲወድቅ በድንገት
በድንገቴ ሐሳብ የድንገቴ ኹነት
የዳቦ እሥረኛ ቆሎ ዕላሚ ኑረት !
መሠረት የሌለው ቤቱ ዐጥር አልባ ፣
በገል ምንነቱ . . .
ማዕበል ተማምኖ የሚዋዥቅ ጀልባ፡፡

የ'ንእሜቴ ጎጆ . .
እንዲኽ ባ'ንድ ጊዜ ገብስ ጠፋ ሲሉ
የ'ነማሞ ፍቅር መፍረስ ነው ሽመሉ።
በጥሬ ሕይወቱ . .
ቆሎ ቆርጣሚ ሰው ፣ ዳቦ እየናፈቀ
ከሥጋ መደብ ላይ በሆዱ ወደቀ
ከግብሩ ሲራራቅ ዘፈኑ ደመቀ።

‹‹ማሞና ማሚቱ ገዙ ዳቦ ቆሎ
ሮጠው ወደቁ ተነሡ በቶሎ!››

በየወደቁበት እየተዋወቁ
በየቦረቁበት እየተዋደቁ
በየዘገኑበት እየተሣለቁ ፣
የጓዳቸውም ሐቅ .
ከግዙፉ ማሳ መደቡ ተለቀ ፤
ዳቦቆሎ ኾኖ . . .
የጥንዶች ቅኔ በዘፈን ዐለቀ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

“ጤና ይስጥልኝ ወይዘሪት እንዳሻው በቀለ.... እባላለሁ እራሱን በሚገባ አስተዋወቀ። እሷም ስሟን ሰጠችው። ፈርጣማ ወጠምሻ ነው።

“ምን ያህል ጊዜ ሆነሽ ሥራ ከጀመርሽ?” ድዱን እየገለፈጠ
“እንድ ሳምንት ሆኖኛል” በር በሩን እያየች::
“በስመአብ ይህንን ያክል ቀን ስትቆዪ ያለመምጣቴ ደደብ ያሰኘኛል”
“ለምን? ይኸው አሁን ተዋወቅን አይደል? ምን ልዩነት አለው?”
“ተይ እንጂ! ጊዜ እኮ የውጤት አብራክ ነው” ትንሽ እየተውረገረገ።
“እንዴት ማለት?”
“ከአንድ ውጤት ላይ ለመድረስ ድርጊት የሚወሰነው በጊዜ ውስጥ ነው
ማለቴ ነው” ሊፈላሰፍባት ሞከረ፡፡
“አልገባኝም?”::
እንደሻው በልቡ “ተይ እንጂ ቆንጂት? አንድ ሳምንት እኮ ለጥብስ የምትበቂበት ጊዜ ነበር፡፡ አሁን ግን ገና ጥሬ ነሽ፡፡ አንድ
ተጨማሪ የማብሰያ ሳምንት ሳትወስጅብኝ አትቀሪም” አለ፡፡
“ማለቴ ይሄኔ በደንብ ተዋውቀን፣ ተግባብተን፤ ሞቅ ያልን ጓደኛሞች መሆን የምንችልበት ጊዜ ነበር ማለቴ ነው”
ወደ ወ/ሮ አረጋሽ በቆረጣ ተመለከተ።
ወ/ሮ አረጋሽ በዕድሜ ጠና ያለች በዚህ ሱቅ ውስጥ ለረጅም አመታት ተቀጥራ ያገለገለች ቅጥር ሠራተኛ ናት።
ልክ እሱ እሷን ሲያይ፤ እሷም ቀስ ብላ በቆረጣ አየችውና ጠቀሰቸው፡፡
“በኔ ተማመኝ አሁን ነው የማቀላጥፋት በሚል ስሜት
ከንፈሩን ወደ ጎን አጣሞ የግራ ዐይኑን ጨፈን አደረገው። ተግባቡ።
እንደ እውነቱ ከሆነ እንደሻው እዚህም እዚያም እያለ ከሚልከሰከስ፤ ይህችን የመሰለች ልጅ መቀላጠፍ ብቻ ሳይሆን ቢያገባት የወ/ሮ አረጋሽ ምኞች ነበር፡፡ በዚህ የተጀመረው ትውውቅ ቀጠለ፡፡ አበራ በዚያን ዕለት አልነበረም፡፡ እንደሻው ድሮ ወደዚያ ሱቅ ዝር እንደማይል ሁሉ ትህትናን ካየ በኋላ ያንን የጫማ ሱቅ እንደ ቤተ ክርስቲያን ሳይሳለም ወደራሱ
ሱቅ መሄድ አቆመ፡፡
ምንም እንኳን እግሩ እስከሚቀጥንድረስ ቢመላለስም መጀመሪያ አይቷት እንደገመተው ግን አልሆነችለትም፡፡
“እንደሻው በዚህ በኩል ያለህ ሃሳብ ቢለወጥና ጥሩ ወንድሜ ሆነህ ጓደኝነታችን ቢቀጥል ደስታውን አልችለውም:: ከማንም አንሰህ
ሳይሆን፤ የግሌ በሆነ ምክንያት ብቻ ጥያቄህን ለመቀበል ስለማልችል
እባክህን ይቅርታ አድርግልኝ?” ብላ ለመነችው። -
“ምንድነው የግል ችግርሽ?” ሲል ደጋግሞ ጠየቃት፡፡
“እጮኛ አለኝ” ስትል ቁርጡን ነገረችው፡፡

እንደሻው ግን እንኳን እጮኛ ባሏ ቢሆን ደንታ የሌለው አጥር ዘላይ መሆኑን
አላወቀችም ብትለምነው ብትማፀነው
እሷን ካልቀመሰ እንደሚሞት ሁሉ እሺ ካላለችው፤ ከስራ እንድትባረር ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይል እየገለጸ፤ ያስፈራራት፤ ጀመር፡፡
ይህ ጊዜያዊ ስሜቱ ቀስ በቀስ እንደሚለወጥና፤ ልመናዋን እንደሚቀበላት ተማምና፤በምታገኘው ጊዜ ሁላ በጸባይ ትቀርበው ነበር።

እንደሻው እንዳስበው ሳይሳካለት መቅረቱን ሲያውቅ አማላጅ አድርጐ የላካት ወ/ሮ አረጋሽ ትህትናን ለብቻዋ ጠራቻትና...ትሁት በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል አይነት ሆንሽብኝ እኮ!
ምንም ትንሽ ልጅ ብትሆኝ አመለካከትሽ ብስል መሆኑን ከተረዳሁት ውዬ አድሬአለሁ። አሁን ግን ሳይሽ ልጅነትሽ የለቀቀሽ አልመስል አለኝ፡፡
ሰማሽ የኔ ልጅ? ዕድል እጅ ላይ የምትወድቀው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
እንደገባችም ካልተጠቀሙባትና አንዴ ካለፈች ደግሞ በፀፀት ትጎዳለች እንጂ
ተመልሳ አትገኝም። በዚህ በቁንጅና ወቅት በዚህ በልጅነት ጊዜ ችላ
የተባለ እድል ደግሞ በእኛ ዕድሜ ላይ ከደረሱ በኋላ ና! ብለው ቢለምኑት፤ ቢጣሩት፤ ተመልሶ አይመጣም፡፡እንደታኘከ የሸንኮራ አገዳ መመጠጥና የትም ተጥሎ መቅረት ነው ትርፉ። ልብሽ ልብ ይበል!፡፡ ዛሬ የደነደነው ልብሽ ነግ ደም እንዳያለቅስ?። እግዚአብሔር ከዚህ የሀብት ባህር ውስጥ አምጥቶ ሲጥልሽ፤ በየወሩ አፍንጫዬ ላይ የሚወረወርልኝ
ሳንቲም ይበልጥብኛል ብለሽ ይህንን ሁሉ ሀብት ንብረት ብትገፊ፧
ዕድልሽ የተገፋ ነው የሚሆነው :: እወቂበት፡፡ የዚህ ቤት የሽማግሌው
አጠቃላይ ንብረት ወራሽ እንደሻው መሆኑን አትዘንጊ!! የጠየቀሽን
አድርገሽ ልጥፍ፤ ጥብቅ፧ ነው ልጄ ዋእ...!”
ያልደሰኮረችላት ዲስኩር አልነበረም፡፡ ትህትና ወይ ንቅንቅ!
“አመሰግናለሁ እትዬ አረጋሽ፡፡ ያለሽ ቀና አመለካከት፣ ምክርሽም ሁሉ ለኔ ጥሩ በመመኘት፣ እኔ ጥሩ ደረጃ ላይ እንድደርስ በማስብ እስከሆነ
ድረስ ከልቤ ነው የማመሰግንሽ :: እንደሻው ቢበዛብኝ እንጂ አንሶኝ
እንዳልሆነ አምናለሁ፡፡ በሁሉም ረገድ ከኔ የበለጠች ማግኘት የሚችል ሲሆን እኔ ግን ለሱ የማልገባ እዚህ ግቢ የማልባል መናጢ ደሀ መሆኔንም አልዘነጋሁትም፡፡ ይህንን ሁሉ ደግሞ ለሱ ነግሬዋለሁ። እትዬ አረጋሽ የማፈቅረው ጓደኛ አለኝ፡፡ በሱ ላይ ደርቤ ማፍቀር አልችልም፡፡
እባክሽን ይቅርታ እንዲያደርግልኝና ሀሳቡን እንዲለውጥ ለምኝልኝ?”
በማለት እግሯ ላይ ወድቃ እያለቀሰች ለመነቻት፡፡
ወ/ሮ አረጋሽ በልጅቷ ንግግር ልቧ ቢነካም፤ ጉልበተኛው እንደሻው ያጋጨኛል ብላ ስለፈራች! የአደራ መልዕክቱን ለእንደሻው ሳታደርስላት ቀረች፡፡

የወይዘሮ አረጋሽ አማላጅነት
በቀጠሮ እየተጓተተ ውጤት የማይታይበት ሆኖ በመገኘቱ እንደሻው ተናደደና አበራን አማከረው::
“ይህቺ ጭንጋፍ አሮጊት ያነጋገረቻት አልመሰለኝም፡፡በንዴት መንጋጭላዋን ከማውለቄ በፊት ምን አለበት ብትገላግለኝ?!” ሲል ለአበራ ጥያቄ አቀረበለት፡፡
“እንዴት ማለት?”
“ትህትናን በጣም አፍቅሬአታለሁ፡፡ በተደጋጋሚ አነጋግሬአታላሁ፡፡ፈቀደኛ አልሆነችም፡፡ እሺ ብትላት ብዬ አበራሽን አማላጅነት ልኬባት ነበር፡፡ ለሷም እሺ ያለቻት አልመሰለኝም፡፡ አንተ አለቃዋ ስለሆንክ ልትፈራህ ትችላለች፡፡ በእውነት ነው የምልህ አበራ የወደድኳት፡፡ በቀላሉ አገኛታለሁ ብዬ ነበር የገመትኩት፡፡ እንደገመትኩት አልሆነም፡፡ ልታግባባልኝ የምትችለው የመጨረሻው ሰው አንተ ብቻ ነህ፡፡” ለመነው፡፡ እንደሻው እንደተስገበገበባት ከሁኔታው ተገነዘበ፡፡
አበራና እንደሻው ፍቅራቸው በከፈቱት ንግድ ምክንያት እየጠበቀ የሄደ
ሽሪኮች ስለሆኑ እምቢ ሊለው አልፈለገም።

“አይዞሽ! እንደሻው ሁሉንም ነገር ለኔ ተይው! እኔ እጨርሰዋለሁ! በኔ ተማመኝ!” ጀርባውን ቸብ፤ ቸብ፤ በማድረግ ተስፋ በተስፋ አደረገው። አበራ ሙሉ በሙሉ ተማምኖ የእሺታ ቃሏን ለመቀበል ብቻ ያነጋገራት
“ልሸኝሽ በማለት በመኪና ውስጥ ካስገባት በኋላ ነበር፡፡

ስሚ ትህትና!” ፊት ለፊት እየተመለከተና መሪውን እያስተካከለ።
“አቤት ጋሽ አበራ” አንድ የሚነግራት ነገር እንዳለ በመጠራጠር ስሜት ወደጐን እያየችው፡፡
“እንደሻው አነጋግሮሽ ነበር መሰለኝ” መሪውን በእጁ እየመታ።
“ስለምኑ?”
“ያው ነዋ!! እንደሚወድሽ” ፍርጥ አደረገው፡፡ ምን ዙሪያ ጥምጥም
መሄድ ያስፈልጋል?።
ትንሽ እንደማፈር አለችና በኃይል መምታት የጀመረው ልቧ ሲረጋጋላት፡-
“አነጋገርኳት አለ እንዴ?” አለችው፡፡
“ከዚያም አልፎ አረጋሽንም እንደላከብሽ ሳይደብቅ አጫውቶኛል” እየሳቀ።

አዎን እንደሱ ነው”ውጭ ውጭውን በመስታወቱ አሻግራ እየተመለከተች፡፡
“ታዲያ ምን መልስ ሰጠሽው?”
“ያው እንደነገረህ ነዋ ጋሽ አበራ?” የሰጠችውን መልስ እያወቀ
እንደሚጠይቃት ገብቷታል።
" መልሱ ያንቺ መሆኑ አጠራጥሮኝ ነው እኮ የምጠይቅሽ?” የአለቅነት ስሜቱ እየታገለው ነበር፡፡በዚህ ላይ ደግሞ ስራውን ምን ያህል እንደምትፈልገውና ችግረኛ መሆኗን በሚገባ ያውቃል፡፡

“ምንም አያጠራጥርም ጋሼ አበራ፡፡ በእርግጥ እንደሻው የሚጠላ ወይንም
ለኔ የሚያንስ ልጅ ሆኖ አይደለም። እንደኔ ያለች ደሃ እሱን
👍1🔥1
የመሰለ ልጅ ማግኘቷ ሎተሪ ቢሆንም ዕድሉን እንዳልጠቀምበት ከሱ በፊት የተዋወቅሁት እጮኛ ስለአለኝ ብቻ ነው” ሀቁን ነገረችው::
አበራ ትንሽ ፀጥ ካለ በኋላ...
እስቲ አስቢበት! ቶሎ ቸኩሎ መወሰን ይከብዳል፡፡ ቀምሰሽ ያላጣጣምሽውን ምግብ አይጣፍጥም ብትይ ተሳስተሻለል አማራጩን ቀምሰሽ ቀምሰሽ ለማጣጣምና፤ የጣፈጠሽን መርጠሽ ለመብላት ሞክሪ!” አላት፡፡
“ጋሽ አበራ እኔ ለአንድ ወንድ፤ አንድ ወንድ ደግሞ ለእኔ ለአንዷ ሴት ብቻ እስከተፈጠርን ድረስ፤ የተገኘውን ወንድ ሁሉ እየቀመስኩ ማጣጣም የምችል አይመስለኝም” ስትል መለሰችለት፡፡
“ኦሆሆ! ይህቺ መልኳ ልስልስ፤ አነጋገሯ መርዝ፤ የሆነች ልጅ የዋዛ አደለችም ለካ አለ በልቡ።
ሳያሳምናት ፧ሳታሳምነው፧ ለእንደሻው በሙሉ ልብ የገባለትን የተስፋ ቃል ሳያሳካ፤ ታክሲ የምትይዝበት ቦታ ደረሰች፡፡
“በጣም አመሰግናለሁ ጋሼ አበራ፡፡ ደህና እደር ብላው ከመኪናው ወረደች።

አስቢበት ትህትና” አላትና ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡ ከአቋሟ ንቅንቅ እንደማትል የታወቀው፤ በተደጋጋሚ የተደረገው ሙከራ ከሽፎ ከተረጋገጠ በኋላ ነው።እንደሻው ይህንን ቁርጡን እያወቀ ሲመጣ በንዴት ጥርሱን ነክሶ፡-
“እሰራላታለሁ!!” አለና ፎከረ።.....
።።።።።።።።።።።።።።።

#Share እያደረጋቹ አደለም አንድ Poat 4 እና 5 ሰው ነው #Share እያደረገ ያለው እናም በጣም ትንሽ ነው ለሌላው እንዲደርስ ሁላችሁም #Share እያደረጋችሁ

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሁለት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና “ጤና ይስጥልኝ ወይዘሪት እንዳሻው በቀለ.... እባላለሁ እራሱን በሚገባ አስተዋወቀ። እሷም ስሟን ሰጠችው። ፈርጣማ ወጠምሻ ነው። “ምን ያህል ጊዜ ሆነሽ ሥራ ከጀመርሽ?” ድዱን እየገለፈጠ “እንድ ሳምንት ሆኖኛል” በር በሩን እያየች:: “በስመአብ ይህንን ያክል ቀን ስትቆዪ ያለመምጣቴ ደደብ ያሰኘኛል” “ለምን? ይኸው አሁን…»
#ሰመመን


#ክፍል_አርባ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ


የዕረፍቱ ጊዜ ለአቤል ብቻ ሳይህን ለአብዛኛው ተማሪ ረዥም ነበር " በጥናት መወጠር የለምደ አእምሮ ሥራ ሲፈታ ደቂቃዋም ትረገማለች ። የአዲስ አበባም ተማሪዎች እንኳ አብዛኛዎቹ ወደየ ዘመዶቻቸው መጥተው ሰንብተዋል። ከየክፍለ ሀገሩ የመጡ ተማሪዎች ግን መሄጃም ሆነ ጊዜ ማሳለፊያ በማጣት ቦዝነው ነው የሰነበቱት ቀን ቀን ሁሌም ተደብረው ይውላሉ " ጫዋታና ቀልድ የሚኖረው ማታ ማታ በየመኝታቸው ሲሰፍሩ ነው " በአብዛኛው መኝታ ክፍል ተደጋጋሚ የጨዋታ አርዕስቶች ሆነው የሚቀርቡት የአቤልና የትዕግሥት የዐይን ፍቅር • የለማና የቤተልሔም ጉዳይ ፡ ወይም ሌሎችን የተደረሰባቸው አዲስ
ፍቅረኞችን ማጋለጥ የመሳሰሉት ናቸው ።

የግቢውን የፍቅር ታሪክ መሰለልን መዝናኛችው አድርገው የያዙ አንዳንድ ተማሪዎች አሉ ። ወሬአቸውን የሚያደምቁት የፍቅረኞቹ ጓደኛ በመምሰል ቀርበው ምስጢራቸውን እየሰረሰሩ ነው ። በዚሁ ተግባራቸው፡“ ሳተላይት”” “ ሮይተር” ፡ “ ቢቢሲ” የሚል የቅጽል ስም የወጣላቸው ተማሪዎች ነበሩ ። ወሬ አጠናቅረው መጥተው በግቢው ያሰራጫሉ ። ምሽት ላይ እነሱ ሲመጡ! ሁሉም ወሬ ለመስማት ከተኛበት ብድግ ብድግ ይላል ።

“ ያልሰማህ ስማ ! የሰማህ ላልሰማ አሰማ ! አዲስ ዜና በዚህ በዝግ ጊዜ ውስጥ አንድ መምህር ከአንዲት ተማሪው ጋር በዋቢ ሸበሌ ሆቴል የዳንስ ምሽት ላይ መታየቱ፥ ከታመኑ የዜና ምንጮች ደርሶናል።

• ደሞ ማን ይሆን ? ” እያለ ተሜ ከመኝታው ውስጥ በአንሶላው ብቻ እየወጣ ' በጆሮው ሳይሆን በመላ ሰውነቱ
የሚያዳምጥ ይመስል' ወሬው ወደ ነፈሰበት ይጠጋል ምን ጊዜም የሚሞቀው « እነ “ ሮይተር ” እነ “ ሳተላይት” ያሉበት መኝታ ክፍል ነው ። ብዙ ተማሪ ክፍሉን ትቶ እነሱ ያሉበት ድረስ እየመጣ ያመሻል ።

« ማነው እሱ በናትህ፣"

"ለማን ታውቁታላችሁ ? ሁለተኛ ዓመቶችን የሚያስተምር ራሰ በራ ሰውዬ።

“ እ" ዐወኩት ። ከማን ጋር ነው የታየው ? ” ይላል " የሚያውቀው።

ለማን የማያውቀው ደግሞ ፣ በእዝነ
ልቦናው ለማን ፍለጋ ይጓዛል።

"በተልሔም ከምትባል ቀይ ወፍራም የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ጋር ፡ ..".

“ውይ እሷንማ ሲያወጣት ቆይቶ የለም እንዴ? " ይላል ከአሁን በፊት ቀድሞ ወሬውን የሰማ።

"ሒ.....ድ?" ይላል ለወሬው እንግዳ የሆነ ሁሉ በአድናቆት

“ ኧረ እንዲያውም ሊጋቡ ነው ” ሲል ቤተልሔም ጣት ላይ የጌጥ ቀለበት ያየው ደግም ነገሩን ያጋንናል ።

“ ስጥ እንዲህ ! ” ይላሉ ፡ ውሸቱ አልዋጥ ያላቸው።

“ ተወው እስኪ ያውራ ፡ እጅሬ መቼም መስጠት ልማዱ ነው።

ውሸት ፈጥረው የወሬ ማጣፈጫ እያደረጉ በማቅረብ የተካኑ ተማሪዎች አሉ ። “ ስጥ እንግዲህ ” የጨዋታቸው»
አርዕስት ሲሆን እነሱ ደግሞ “ አባ መስጠት ” በመባል ይታወቃሉ ።

ውሸቱ ከፍ ያለ እንደህነ "ርግጫ ” ይባላል ። ዋሻዎቹ “ ረጋጮች” ሲባሉ፥ የፕሮግራማቸው ስም ደግሞ

“ረግጣ” ነው ። ማኅበራዊ ኑሮን የሚጠሉ ጥቂት መሠሪዎች ካልሆኑ በስተቀር ። የአብዛኛው ተማሪ የሮይተሩም የረጋጩም - ተግባር የዩኒቨርስቲውን የዕረፍት ጊዚ ሕይወት ለማጣፈጥ ነው። »

“ እባካችሁ ጨዋታውን ወደ ቀልድ እትቀይሩት ይላል ለወሬው የጓጓ ፥ አምርሮ ።

"በቃ " ይኸው ነው ለማ ቤተልሔምን እወጣት

“ “A” ያለምንም መጨነቅ በእጅዋ ገባ ማለት ነው ።ከቻለ ደግሞ ከራሱ ትምህርት ዐልፎ ሌሎቹም ጓደኞቹ እንዲረዷት ይለምንላታል ፡

“ እናታቸውን ! እነዚህ ሴቶች ጨረሱን ” ኮ ! ጭንቅላት ሲያጡ በወሲብ ዩኒቨርስቲን ሊወጡ ! ” ሲል ፥ ሁሉም
በብሽቀት ጥርሱን እያንቀጫቀዉ በጅምላ ሴቶቹን ይራገማል።

“ ለካ ለዚህ ነው ” ይላል " እርዕስቱ እንዳይቋረጥ የሚፈልገህ ለአርዕስቱ እንደገና ሕይወት ለመስጠት ቅመም እያዘጋጀ

“ ምኑ ? ብዙ ጆሮዎች ሰልተው ይቆማሉ "

"ሰሞኑን ለማ ከሚስተር ራህማን ጋር ግንባር ፈጥሮት የሚታየው !!

"ራህማን ? ”

"ሚስተር ራህማን እኝያ ህንዳዊው ። ”

“ እ ! እ ! ” ሞቅ ያለ ሣቅ ።

“ ለማ የቅርብ ጓደኞቸ ሆኗል ። ለሻይ ሲወጡም አንድ ላይ ነው።

“ የዓላማ አንድነት ነዋ ያስተሳሰራችው ።

“ እሳቸው”ኮ ሐኪም ሳያይዝላቸው አይቀርም ። በሴት ቀልድ አያውቁም ፤ በተለይ ወፍራም ሴት ሲወዱ ! ”

“ ብቻ አንድ ቀን ሴት ጭን ውስጥ ትንፋሻቸው ቆሞ እንዳይገኙ ” ይላል የበሸቀው ክፍል እያፈዘ »

ጨዋታው ይቀጥልና ከመምህራን ተመልሶ ወድ ግል መበሻሸቅ ያመራል ። እርስ በርስ መጋለጥ ይመጣል ። አንዱ
የሌላውን ምስጢር ለመጎልጎል በነገር ጎሸም ያረጋል "ነገሩ የሚነካው ቁስለኛ ካለ በወዲሁ ማኩረፍ ይጀምራል ።
ሆኖም እነ “ ሮይተር ” የማንም ኩርፊያ አያግዳቸውም ።

“ ነገርን ነገር ያነሣዋል ” ሲሉ ይጀምራሉ

“ ደሞ ምን ልታመጡ ነው ? ”

የቤተልሔምን ጓደኛ ሊያወጣ የሞከረም ከመሃከላችንም አይጠፋም ኮ ! ”

ማንን ? ያቺን ማርታን እንዳይሆን ? ! ”
“ እህህሳ ! ማርታ ዐይኗ ስለማያርፍ ሳይሆን አይቀርም ፤ ብዙ ተማሪዎች ዐይናቸውን ጥለውባታል ፡ በግቢው ውስጥ ከብዙ ሴቶች መሃል ተለይታ ትታወቃለች ። ጠይቀው ሊያወጧት የሞከሩ ወይም የሚፈልጓት ከእስክንድር ሌላ ብዙ ናቸው በአለባበሷ ደምቃ ከመታየቷ ሌላ ምን ጊዜም ዐይኗ አያርፍም ። ስትበላ የአዳራሹን ወንድ እየቃኘች ነው ። ስታጠናም መጻሕፍት ቤት የተቀመጠ ፍጥረት አይቀራትም ። ወንዶችን ብቻ ሳይሆን ሴቶችንም ሥራዬ ብላ ነው የምታየው ፡ ሴቶችን የምታየው ግን በጤናማ ዐይን አይደለም ። ዘወር ብላ እንደ ሽንኩርት ትልጣቸዋለች ። በተለይ ደመቅ ያለች ሴት ማርታ ዐይን ውስጥ ከገባች አለቀላት !
ውሸት ፈጥራ ስሟን ታጠፋለች ። !

“ ውይ ! ያቺን ሞጥሟጣ ነው እንዴ ?” ሲል ቁስል ያለበት ማጥላላት ይጀምራል
“ሞጥሟጣነቷን በምን ዐወቅክ ? ” በማለት ፡ ሳታላይቶቹ ያፈጣሉ "

“ደሞ ምን ልታመጡ ነው ? እዚያው በጸበላችሁ ! ”
ቁስለኞ ማኩረፍ ይጀምራል ።

“ አንተ ምን አስኮረፈህ ? አንድ ቀን ብቻ ነው የጠየቅካት እና “F” ኮመኩህ ተመለስክ ። ይሄ ደሞ አያሳፍርም ።"

ጠይቆ ሲሳካ “A” እንደማግኘት ሲቆጠር ፡ ሳይሳካ ሲቀር ደግሞ "F" መኮምኮም ይባላል ።

“ አይ አጅሬ ! መኮምኮም አይሰለቸው ! ” በማለት ከፊሉ ያደንቃል "

“ ስጡ እንግዲህ ! አባ መስጠቶች መስጠት አይሰለቻችሁ።

“ ምኑ ላይ ነው ውሸቱ ?”

“ መዋሽት ብቻ ነዉ እንዴ ደኅና አርጎ መርገጥ ነው እንጂ ። ምን ታረጉ ? ! ዝም ብለው የሚረገጡላችሁ እገኛችሁ ርግጡዋቸው !”

አስረጅ ! ” በማለት ከመሐል ነገሩን አጠናካሪ ይናገራል።

"ደም አንተ ምን ልትል ነው ? ”

“ አጅሬ አንድ ቀን" እነማርታ የሚያጠኑበት ኣካባቢ ያለ ሥራው ሲያንዣብብ አግኝቼዋለሁ ፡ ”
አጥቂ ሲበዛበት ቁስለኛው የሚያመልጥበትን ዘዴ ያሰላሰላል ኩርፊያ አያዋጣም ። ቁጣም አያዋጣም ። የዚህ
ዐይነት አዝማሚያ ከታየ ተማሪዎቹ የባሰ ያሳብዳሉ ። ያለው ምርጫ ቀስ ብሎ ቀዘዴ አርዕስት ማስለወጥ ነው ።

“ ይልቅ የሚገርመው የዚያች የእነ ማርታ ጓደኛ ነገር ነው " ያ የአራተኛ ዓመት የማዕረግ ተማሪ የሚወዳት ! ”
ሲል እንደ ምንም ወደ ሌላ አርዕስት ይሸጋገራል ።

የቤተልሔም እና የማርታ ነገር ከተነሣ የትዕግሥትም አይቀርም » ብዙ ጊዜ አብረው ስለሚታዩ ነው ። አቤል ከሚስተር ሆርስ ጋር ተጣልቶ የአዕምሮ መታከሚያ ሆስፒታል ከተወሰደ ጊዜ ጀምሮ እነ “ ሮይተር ” ስለዚህ ጉዳይ
👍21
በቂ መረጃ አላቸው።
“ ትዕግሥትን ነው እንዴ ? ምስኪን ፍጥረት! እሷ'ኮ ምንም አታውቅ ። ከነድንግሏ እንደምትገኝ እኔ በዐሥር ጣቴ
እፈርርማለሁ።

“ በምን አወቅክ ? የፈተንካት አትመስልም ? ! ”

“ ኧረ ግፍ አትናገሩ! እሷ ከቀለም ሌላ ምንም አታውቅ ዐይነ - ውሃዋም ያስታውቃል አትን እባክህ ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር ፈስ ተምራ ትመጣለች እንደሚባለው ነው ። ከእነ ማርታ ጋር ውላ ደሞ ጤነኛ ትሁን እንዴ ሲል ጠርጣሪው ክፍል መከላከያውን ይኑረድራል ።

እነ "ሳተላይት ” እዚህ ላይ ትክክለኛውን መረጃ በመስጠት ሙግቱን ያስረዳሉ ።

“ እሷስ ገና ጥሬ ናት ። ምን ያረጋል ! ጥሬነቷ ነው ያንን ጂኒየስ ልጅ ያሳበደው

"ማንን ? ”

"አቤልን ነዋ ! ”

ምስኪኖች ! የእነሱ ነገር በጣም ይገርማል ? ኮ በዓይን ከመተያየት በስተቀር ተቀራርበው፦ ተነጋግረው አያውቁም

የዐይን ፍቅር ነዋ ! ዐይኑካ ! ”

“ ግን በምን ጣለበት? ሌላ ሴትኮ ቀና ብሎ አያይም ።

የዐይን ፍቅር ላይ የጣለው ጭምትነቱ ሳይሆን እይቀርም”ኮ ! ” በማለት የራሱን አስተያየት አከል የሚያደርግም አይጠፋም.....

«ምን ዋጋ አለው ! ጮማ ጭንቅላት ይዞ አሁን በሷ ምክንያት መቀነሱ ነው።እንዴ ኮ አዳራሹ ውስጥ ከነ ምግቡ የወደቀው እሷን እሷን ሲያይ ነው ! ”

"ትቀልዳለህ ? ይህን ያህል ? ”

አንተ ደሞ ለዚህ ለቀላሉ ጉዳይ ነው እንዴ ? ዕብዶች ሀኪም ቤት ድረስ ግብቷል “ኮ ! ”

በእሷው ምክንያት ?” ይላል ፡ ቀድሞ ነገሩን የሰማውም አብሮ ። ያልሰማው ጓጉቶ ነው ፤ የሰማው ደግሞ የሌላውን የፍቅር ሥቃይ ደጋግሞ መስማቱ ስለ ሚጥመው ነው።

“ ታዲያስ ! እንዲያውም እንደ ሰማሁት ከሆነ ዘንድሮ ትምህርቱን ጨርሶ የሚመረቅ አይመስልም ። ”

“ ያሳዝናል ! ” ሲል አብዛኛው ከንፈሩን ይመጣል ።

"ምን ያሳዝናል ፥ ያናድዳል እንጂ ! ዲዳ እይደል ።ቀርቦ አያናግራትም እምቢ ብትለውም ሴት አልጠፋ ባገሩ ! ” የሚል ተሟጋች ከመሐል ብቅ ይላል ።

“ እንደሱ አትበል እባክህ አያድርስ ነው ! ፍቅር መልኩ ብዙ ስለሆነ መፍረድ አትችልም " "

ግማሹ በሀዘኔታ ግማሹ በቀልድ የጦፈ ክርክር ያካሒዳል። አጋጣሚ ሆኖ እስክንድር ጨዋታቸው መሀል ካለ ኮቴውን ሳያሰማ ቀስ ብሎ ሹልክ ይላል የአቤልን ክፉ መስማት አይፈልግም ። እሱ ለአቤል ያለውን ቅርበትና ጓደኝነት ብዙዎቹ ስለሚያውቁ፡ በጨዋታው ላይ የበኩሉን መረጃ እንዲሰጣቸው ዐይን ዐይኑን ሲያዩት ነው የሚሾልከው።

ሳምሶን ጉልቤው በዕረፍቱ ጊዜ ካምፓስ ውስጥ አለመኖሩ ነው እንጂ፥ በአቤል ጉዳይ ከስንቱ ጋር በተጣላ ነበር።
በግቢው የአቤልና የትዕግሥት የዐይን ፍቅር የጨዋታ ማድመቂያ ሆኗል ። የሚወራው እውነትም ቢሆን ሳምሶን
የአቤልን ስሜት የሚጎዳ ነገር እንዲነሣ አይፈልግም ።

💥ይቀጥላል💥
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

ሻምበል ብሩክና ትህትና ድንበሩ ከተዋወቁ ዛሬ ልክ አንድ ወራቸው፡፡ የፍቅራቸው ወርሃዊ ልደት ውል የሚበጅበት ቀን በመሣሣም ደረጃ የቆየው ፍቅር ዛሬ ወደ አካላዊ ውህደት ሊሸጋገር እቅድ ተይዞለታል። ሻምበል ብሩክም ሆነ ትህትና የዛሬውን ቀን በልዩ ጉጉት ነው የጠበቁት።

እሁድ ዕለት አሥመራ መንገድ በሚገኘው በሻምበል ብሩክ ቤት ለማደር የወሰነችበት ቀን ነበር፡፡ ወደ ዶክተር ባይከዳኝ ቀጠሮ ስትሄድ የሚሰማት ስሜት ከቀጠሮው በስተጀርባ ባለው ምክንያት አስገዳጅነት እንጂ በፍቅር አስገዳጅነት አልነበረም፡፡
ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር የምትፈጽማቸው ግንኙነቶች እውነተኛ ስሜቷን የምትገልጽባቸው ሳይሆኑ፤ በተላበሰችው ጭምብል እውነተኛ ማንነቷን ደብቃ፤ በመድረክ ላይ ትያትር የምትሰራ ተዋናይ ሆና ነው የምትውለው፡፡ በሻምበል ብሩክ ፍቅር ግን ሰውነቷ እንደሻማ እየቀለጠ፣
ልቧ በዕልልታ እየጨፈረች፤ ሁለንተናዋን አሳልፋ የምትሰጠው በደስታ ስሜት ሰክራ ነው፡፡ በተለይ የመጀመሪያዋ በሆነው የወንድ ልጅ ፍቅር የተረታችለት ሰው፤ እንደዘመኑ ወጣቶች በአንድ ነገር ላይ ብቻ ትኩረት የሚሰጥ ሳይሆን በሷ ቦታ ሆኖ ሁሉን ነገር የሚያስብላትና፤
የሚያጽናናት፤ ሆኖ በመገኘቱ ፈጣሪዋን ታመሰግናለች፡፡
ብቻ አንዳንድ ጊዜ የሰው ልጅ ሥጋ ለባሽ ፍጡር ነውና፣ ሰው ተላላና ደካማ ፍጡር ነውና፤ ሰው ሰው ነውና፤ ይህ ሁሉ ፍቅር ድንገት ብን ብሎ ጠፍቶ፣ ሻምበል ብሩክም ተለውጦ፣ እንዳይከዳት ልቧ
መጠርጠሩ አልቀረም፡፡
እንደዚያ ታስብና ደግሞ አስተሳሰቧ ትክክል ባለመሆኑ እራሷን ወቅሳ “ብሩኬ አይለወጥም”
በማለት መልሳ መጽናናትን ታሳድራለች፡፡ በዛሬው ዕለት ሻምበል ብሩክ ቤት ለማደር ቀጠሮውን በልቧ የወሰደችው በከፍተኛ ደስታ ነው። ምናልባት የዛሬው አዳር ደግሞ ያንን ተንከባክባ ያቆየችውን የልጃገረድነት ወግ፣ ብር አምባሯን የምትፈተሽበት ወቅት ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚያ በኋላ “ዞር በይ” ቢላትስ? ልቧ
በመጠራጠርና፤ ባለመጠራጠር፤ስሜት መሀል ገብቶ ሲዋዥቅ ከዋለ በኋላ
አንድ ነገር አሰበች።

ለሻምበል ብሩክ ልጃገረድ መሆኗን ገልጻለት፤ እንደ ወጉ፤ እንደ ሥርዐቱ፤ በጫጉላ ቤት ብር አምባሯን ልትሰጠው ያላትን ምኞች የሱን ስሜትና ፍላጐት ከተረዳች በኋላ ካሳወቀችውና በአጠቃላይ ስለማንኛውም ነገር አብረው በጋራ መወሰን እንደሚችሉ ገምታ፤ በዚሁ ሃሳብ ፀናች።
“እማይዬ ዛሬ አዜቢና ጋ ነው የማድረው ፓርቲ አዘጋጅታለች' በማለት እናቷን ዋሸቻት።
“ባርቲ ደግሞ ምንድነው ትሁቴ?” እናት በመጠራጠር ስሜት፡፡
“ያው ነዋ! ጓደኞቿ ተሰባስበን ስንጫወት ማደር ማለት ነዋ!” እየሳቀች፡፡
አደራሽን የኔ እራስሽን ጠብቂ!!” እናቷ ዐይን ዐይኖቿን እያየቻት።የውጭ አዳር የተሰማው ገና ዛሬ ነው፡፡
“ምንም ችግር የለም:: ማሚ ሙች!” ጉንጫን ሳመቻት፡፡ እናቷ በልቧ
ዝግጅቷን አሰበችው፡፡ በጠዋት ተነስቶ መተጣጠቡ፣ ቀኑን ሙሉ ሲመረጥ የተዋለው ልብስ፣ ሦስት ጊዜ አውልቃ ቀይራለች። መስተዋቱ ሥራ አልፈታም፡፡ መኳኳሉ ሁሉ ያልተለመደ ነበር።
በልቧ ወደ ሻምበል ብሩክ እንደምትሄድ ብታውቀውም የሰጠቻትን ምክንያት ይሁን ብላ ተቀበለቻት፡፡
ዛሬ ሻምበል ብሩክ ጋ የምታድር መሆኗን ለአንዱአለም ስለነገረችው በጊዜ ወደቤት እንዲገባ ተስማምተዋል። በዚህ ላይ የቤት ሰራተኛዋ እታፈራሁ ታክላበት እናቷን በመንከባከብ በኩል ኃላፊነቱን
ስለሚወስዱ የሚያስጨንቃት ነገር አልነበረም፡፡ ሁሉንም አጥብቃ አደራ
ብላ፤ ከቤት የወጣችው ከቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ ነበር።
ሻምበል ብሩክ ዛሬ ሽር ጉድ ሲል አርፍዷል። አልጋው ቦታ ሲመረጥለት፤ ሲንከራተት፤ የቤቱ ቁሳቁሶች በሙሉ በአዲስ መልክ አንዴ በጭንቅላታቸው፧ አንዴ በእግራቸው፤ ሲቆሙ፤ ቦታ ሲመረጥላቸው ነው የተዋለው፡፡
በዛሬው የቤት ዝግጅት ላይ ሠራተኛዋ ብቻ ሳትሆን ሁለቱም ታናናሽ ወንድሞቹ አብረውት ቤቱን ሲያተራምሱት ነው የዋሉት፡፡
በመጨረሻ ላይ ግን ከዚያ በፊት ያልታየበት ዓይነት ሥርዓትና መልክ ይዞ ሲያይ ሻምበል ብሩክ ተደነቀ፡፡
በእርግጥም ይህ ሁሉ የሆነው በትህትና ምክንያት መሆኑን ሲያስብ፤ የትዳር ውጥኑ አግባብ መሆኑን አመነ። በዚያ በቤቱ ሥርዓት ተማርኮ ወደሌላ ሃሳብ ውስጥ ገባ፡፡
ባለፋቸው መጥፎ ጊዜያቶች ውስጥ የተጐዳ ልቡ፣ በትህትና የወደፊት የትዳር እመቤቱ አማካይነት ሊታደስና፤ ሲታነጽ፤ ታየው።
እናም የትዳር መዓዛ በርቀት ሸተተው፡፡ ይህ በርቀት የሚሸተው የትዳር መዓዛ ቀርቦ እንዲያውደው ተመኘ፡፡
ትህትና እስከምትመጣለት የቀጠሮው ሰዓት እስከሚደርስ ድረስ ተንቆራጠጠ።
ዛሬ የሚነግራት ትልቅ ጉዳይ አለው። እሷም እንደሱ በጉዳዩ
ላይ ፈቃደኛ ከሆነች ጉዳዩ የምሥራች ይሆናል። እሷን የፈለጋት ጊዜያዊ
ፍቅረኛ እንድትሆነው ሳይሆን፤ ዘላቂ የትዳር ጓደኛው እንድትሆን ነው::
ይህ እሱ የጓጓለትን በፀጋ ከተቀበለችለት ደስታው እጥፍ ድርብ ይሆናል፡፡
“ትሁት.. ትሁት.. ትሁት.. ስሟን ደጋገመው። በልቡ፡፡

ልክ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ታላቋ እንግዳ የዱር ጽጌረዳ መስላ አምራና፤ ደምቃ ከች! አለች፡፡ ቤቱን ከዚህ ቀደም አንድ ሁለት ጊዜ አይታዋለች፡፡ የዛሬውን ልዩ የሚያደርገው ለማደር ወስና የመጣችበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡
ሻምበል ብሩክ ከደጅ ወጥቶ እየተጠባበቃት ነበር። በሁለመናው
አቅፎ ተቀበላት፡፡
ከዚያም አጥሩን ዘልቀው እየተሳሳቁ፣ እጅ ለእኛ ተያይዘው ወደ ቤት ገቡ፡፡
የሻምበል ብሩክ ሁለት ታናናሽ ወንድሞቹ ሰላምታ አቅርበውላት ትንሽ ከተጫወቱ በኋላ የግል ነፃነት ሊሰጧቸው ወጡ።
ዛሬ የሻምበል ብሩክ ቤት ልዩ ሆናለች:: ትህትናም ከዚያ በፊት ያየቸው ቤት መሆኑ እስከሚያጠራጠራት ድረስ የቤት ዕቃዎቹ አቀማመጥ አስደንቋታል፡፡
ሻምበል ብሩክ የትዳር ምኞቱን ሊገልጽላት ሲያሰላስል፤ እሷ ደግሞ ሌላ የምትገልጽለት እጹብ ድንቅ የሆነ የምስራች ነበራት። ሻምበል ብሩክ በፍቅር ቢወድቅላትም፤ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ያልገመተውን ገፀ በረከት ልታቀርብለት ማሰቧን ቢያውቅ ኖሮ ምንኛ ደስተኛ ይሆን ነበር?፣
ቀለል ያለ እራት ከበሉ በኋላ ይሄንን የቀዘቀዘ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራቸውን
መኮምኮም ቀጠሉ። ዛሬ ቢራው አልመረራትም። የፍቅር ስኳር
ተጨምሮበት ነው መሰል፤ ከምትወደው ሰው ጋር በፍቅር እየቀለጡ፤ ሲኮመኩሙት ማር ሆነና ቁጭ አለ፡፡ ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ሆና ስትጠጣው የግራዋ ጭማቂ ያህል ነበር የሚመራት። አሁን ግን ጣፈጣት፡፡
አንዱን ቢራ ጨረስችና በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለተኛውን የቢራ ጠርሙስ ጨበጠች፡፡ ሻምበል ብሩክ የወደፊት የትዳር ጓደኛው ከምትሆን ቆንጆ ጋር እያሳለፈ ባለው ጊዜ እጅግ ከመደሰቱም በላይ ከረጅም ዓመታት በፊት እጮኛው ከነበረችው በድሏ ጋር ያሳልፉ የነበረውን ዓይነት ልዩ ስሜት አጫረበትና፤ ጨዋታውን በሰፊው ቀጠለ። እየተቃቀፉ መላላሱ ፤ መሳሳሙ፤ ሁሉ ለጉድ ነበር፡፡
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ሲሆን ወደ መኝታ ክፍላቸው መሄድ ፈለጉ።
የመኝታ ክፍሏ በንጽህና የተጠበቀች ናት። እንደገቡ በነጭ ስስ የመጋረጃ ጨርቅ የተሸፈነውን ባለመስታወት መስኮት ሲገልጡት ፍንትው ብላ ደምቃ የወጣችው ጨረቃ ብርሃኗን ወደመኝታ ክፍላቸው ውስጥ አዘለቀችላቸው...

ያንን የጨረቃ ውበት ሲያስተውሉ፤ መብራቱን አጠፉት በዚያች ክፍል
ውስጥ ጨረቃና ፍቅር ነገሱ ከዚያም ልብሳቸውን እንደለበሱ አልጋቸው ላይ ጋደም ብለው መላፋታቸውን ቀጠሉ....
የትህትና ሁኔታ የተለየ ነበር ከዚያ በፊት ለወንድ ልጅ የነበራት ስሜት ምን እንደ ነበረና አሁን ምን እየሆነች እንዳለች
ስታስበው
👍2🔥21
አንዳንድ ጊዜ ያበደች ይመስላታል። አንዳንዴ ደግሞ ሻምበል
ብሩክን ከማግኘቷ በፊት ጤነኛ መሆኗ ያጠራጥራታል፡፡ ፍቅር ማለት እንደዚህ አቅል የሚያስት፧ እንደዚህ የሚያስፈነድቅ ስሜት መሆኑ ይገርማታል።
አንዴ በቀኝ ክንዱ፣ አንዴ በግራ ክንዱ ላይ እየተገላበጠች፤ ቅብጥ ሲያደርጋት ደግሞ እዚያ ስፊ ደረቱ ላይ እየተንከባለለች፤ የደረቱን ጸጉር
እያፍተለተለች፤ ስትስመው፣ ሲስማት፤ ስታሸው፣ ሲያሻት፤ እንዲሁ በስሜት ሲጋጋሉ፤ በመቆየታቸው ገላቸው ከሚገባው በላይ ሞቀና ወደ መፍላት ደረጃ ላይ ደረሰ። ትህትና ቁና ቁና መተንፈስ ጀመረች፡፡
ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ስትሆን በሚሰማት የጣዕር ዓይነት የመቃተትና
የማቃሰት ስሜት ሳይሆን፤ በጣፋጭ ስሜት፤ እራስን አሳልፎ ለመስጠት
በመፈለግ ስሜት፤ መወራጨቷን ቀጠለች፡፡
ሻምበል ብሩክ የትዳሩን ሁኔታ አሁን ልግለጽላት ወይንስ ሲነጋ? እያለ ሲያመነታ ቆየ፡፡ ግን አልነገራትም።
ጨረቃዋ በክዋክብቱ ታጅባ፤ ከዋክብቶቹ እየደነሱ ጨረቃን ሞሽረው ሰማዩን ብሩህ ባደረጉበት ምሽት፧ እነሱ ደግሞ ይህ ሁሉ
ትርዒት ወለል ብሎ በሚታይበት የመኝታ ክፍላቸው ውስጥ በጀርባቸው ተንጋለው አዲሱ ፍቅራቸውን እየሞሸሩ፤ በስሜት መንኩራኩር ተሳፍረው፤ ያቺ ውብ ጨረቃ ወደ ታደመችበት ህዋ፤ መጠቁ....
በአንድ መግነጢሳዊ ኃይል ምድሪቱን ለቀው፤ በሀሳብ ክንፋቸው እየከነፉ፤
በህዋው ላይ ሲናኙ፤ ደስታቸው ገደቡን ስቶ የሚሆኑትን አጡ፡፡ ይህ የደስታ ስሜት ዑደት ከሷ ወደሱ፤ ከሱ ወደሷ ፤ እየተቀባበለ፤ እየተቀጣጠለ፤ በስሜት ክብሪት ተጭረው በፍቅር እየነደዱ ፤ እጆቿ አዛዥ ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው ስልጣን የሱን ልብስ ማውለቅ ሲጀምሩ፤ የእሱም እንደዚሁ የሷን ማወላለቁን ቀጠሉ፡፡ ለሁሉ ነገር ጥንቃቄ እወስዳለሁ ያላችው ሴትዮ፡-
“ጥንቃቄ ገደል ይግባ !!" ያለች መሰለች። ከዚህ በላይ ንግግር የለ፣ ውይይት የለ! ብቻ ሁለቱም በፍጥነት ከላያቸው ላይ የነበረውን ደንቃራ አስወግደው፤ለአንድ ወር በናፍቆት የተጠማ ገላቸው እርስ በርሱ ተፋጭቶ በመካከላቸው የሚፈጠረውን መብረቃዊ ብልጭታ ሊሟሟቁ ተጣድፈው ፤ ልብሶቻቸውን በፍጥነት አወላለቁ.....
የሷ ጣቶች በእሱ ሰውነት ላይ ሲርመሰመሱ፤ የሱም ጣቶች በሷ ለስላሳ
ገላ ተረታ ተሸነፈና አንዳቸው በሌላው አካል ውስጥ ቀስ በቀስ እየሰመጡ፣ በስሜት እየቀለጡ፣ በመንፈስም በአካልም እየተቆራኙ ሄዱ......
የሁለቱም ገላ ከሚገባው በላይ በስሜት ግሎ ነበረና ከጧፍ እንደተሰራ ሁሉ ፤ ተቀጣጥሎ ወደ ፈሳሽ ነጠብጣብነት የተቀየረ እስከሚመስላቸው ድረስ በወሲብ ፍላጐት ነደደ...ከዚያም በከፍተኛ የረሃብ ስሜት እርስ በርሳቸው ተሻምተው አንዳቸው በሌላው ውስጥ ጠፉ....

ከዚያም ሻምበል ብሩክ በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች መካከል በሚደረገው ውህደት ላይ ለመድረስ መንቀሳቀስ ሲጀምር፤ ትህትና ሉጋሙን ጥሶ እንደፈለግሁ ልጋልብ ከሚላት ስሜቷ ጋር መታገል ጀመረች፡፡ እንደሰንጋ ፈረስ ሽምጥ በመጋለብ ላይ የነበረው ስሜቷን እንደምንም ታግላ ሉጋሙን ያዘችውና...
“ብሩኬ .....እኔኮ.... ልጃገረ.....ድ ነኝ ” ስትል እያቃሰተች ሹክ አለችው፡፡
ሻምበል ብሩክ የሰማውን ማመን አቅቶትና ጆሮውን ተጠራጥሮ..
“ምን አልሽኝ ትሁት?” ሲል በድጋሚ ጠየቃት፡፡ አንገቱን በአንገቷ ውስጥ
እንደቀበረ።
“ገርል ነኝ” አለችው ደገመችና ፍስስ... ባለ ድምጽ።
ሻምበል በደስታ ብዛት የሚይዝ የሚጨብጠው ጠፍቶት እቅፍ
አድርጉ እንደ ሎሚ መጠጣት...
ይህ ሹክ ያለችለትን የምስራች ምንም እንኳን ቢያምናትም፤ እንደ ቶማስ ሀቁን ዳብሶ ለመረዳት ፈለገና፤ በሹክሹክታ ተነጋገሩ።
ከዚያም ተግባቡና በጥንታዊ አነጋገር ክራር በሚባለው ጨዋታ ለመጠቀም ተስማሙ፡፡
ከዚያም አካሉን ከአካሏ ቀስ በቀስ እያዋሀደ፤ እያለማመደ፤ ለስለስ ባለ ሁኔታ ክራሩን መምታት ቀጠለ፡፡ የዚያ የክራር ቅኝት ስሜት ለሁለቱም ልባቸውን ሰርስሮ የሚገባ፣ በጆሮ የሚደመጥ ሳይሆን በቀሪ የስሜት ህዋሳቶቻቸው የሚደመጥ፣ በሠራ አካላቸው የሚንቆረቆር፣ ውብ ጣዕመ ዜማ ያለው ሆኖ ተሰማቸው፡፡
ትህትና በዚያ በሰማችው የክራር ቅኝት እጅግ ረክታ፡
ሁለመናዋን ለቅኝቱ አሳልፋ ሰጠች፡፡ እናም በዚያ ቅኝት ውስጥ ትዝታን፤
በዚያ ቅኝት ውስጥ አንቺ ሆዬ ለኔን ! በዚያ ቅኝት ውስጥ አምባሰልን፣
ቢዘያ ቅኝት ውስጥ ባቲን ተጫወቱ፡፡
በእርግጥም የተዋጣለት ጨዋታ ነበረ፡፡ እዚያ እላይ ከስሜት ንረት ጥግ! ደርሰው ሲመለሱ ሁለቱም ቁና ቁና እየተነፈሱ ቆዩና እንደገና ተቃቅፈው ፤ እንደገና ተቆላልፈው፣ እንደገና ሊጫወቱ በስሜት ጭልጥ ብለው ነጎዱ.....
ሻምበል ብሩክ በፍቅር የተረታላት ልጅ ጣፋጭና ከሱ በፊት ያልቀመሳት
ልጃገረድ ሆና በማግኘቱ ደሰስታው ገደብ
አልነበረውም፡፡ የፍቅር አምላክ እምባውን ሊያብስለት ፈልጎ ትህትናን እንደሰጠው አምኖ በዚህ ባጋጠመው ዕድል ረክቶ ፈጣሪውን አመሰገነ፡፡የሁለት ተፈላላጊዎች ውህደት.
ትህትና በደስታ ብዛት የወሰደችው ሁለት ቢራ ሙቀትና ድፍረት ሰጥቷታል።ከፍቅር ጨዋታው መልስ በሻምበል ብሩክ ደረት ላይ እየተንከባለለች ስትፈነድቅ ፤የውስጥ ስሜቷን አምቃ መያዝ ተሳናትና፤
ደስታዋ ገደቡን ጣሰና፤ በዚያ አፍ በሚያስከፍት ማራኪና ተስረቅራቂ
ድምጿ ታንቆረቁረው ጀመር...
ምንም ሳላስበው ውጥን ሳይኖረኝ
የሚያስለቅስ ፍቅር በድንገት ያዘኝ፡፡
ጤና አእምሮ እያለኝ የሚያስብልኝ
የሚያስብልኝ።
እንዲሁ ቁጭ ብዬ አለቅሳለሁኝ
አለቅሳለሁኝ፡፡
ለካስ ፍቅር ሰውን እንዲህ ያደርግ ኖሯል
እንዲህ ያደርግ ኖሯል፡፡
በዚህ አስተያየት ስንት ሰው ተጎድቷል
ስንት ሰው ተጎድቷል፡፡
እያንሰቀሰቀ የሚያስለቅሰኝ የሚያስለቅሰኝ
ፍቅር እንደሆነ ጠቢብ ነገረኝ
ጠቢብ ነገረኝ
በረጅሙ የብዙነሽ በቀለን ዘፈን ትለቀው ጀመር። ከዘፈኑ ጋር በስሜት ተመስጣ፤ በሃሳብ ጭልጥ ብላ፣ በደስታ ሰክራ መስረቅረቋን ቀጠለች፡፡
ሻምበል ብሩክ በአድናቆት ፈዝዞና ደንዝዞ ያንን ልብ የሚሰረስር ድምጽ እያዳመጠ በስሜት አብሯት ጭልጥ ብሎ ሄደ...
ድንበሩን ያለፈ ደስታ አንጎል ያዞራልና፤ ሻምበል ብሩክ አንጎሉ ዞረ።
በመልክና በፀባይ የታደለችውን ወጣት የሱ እንዲያደርግለት ሲመኝ፤ ከነሙሉ ክብሯ አገኛት፡፡ ከዚያም አልፎ ደግሞ ይኸውና በዚያ በሚያደነዝዝ ድምጿ የፍቅር ዘፈን ስታንቆረቁርለት፤ ተደንቆ ይህችን ዕንቁ የሰጠውን አምላክ መላልሶ በልቡ እያመሰገነ፤ እሷ፣ ስትዘፍን፤ እሱ
ሲሰማት፣ እሷ ስትስረቀረቅ፤ እሱ በደስታ ሲቦርቅ፤እንቅልፍ በዐይናቸው ሳይዞር ሰማይና ምድር ተላቀቁ.....
የሻምበል ብሩክ ወንድሞች የሚያድሩት ከዋናው የመኖሪያ ቤት ራቅ ብሎ በተሰራው ሰርቪስ ውስጥ ነው፡፡ ሰራተኛዋ እራታቸውን ካቀረበችላቸው በኋላ ሲያጠኑና ቼዝ ሲጫወቱ ስላመሹ እንቅልፍ ጥሎአቸዋል። እዚያ እላይኛው ቤት በሻምበል ብሩክ የመኝታ ክፍል
ውስጥ የቀለጠውን ጉድ አልሰሙም::

ጠዋት ሲነጋ ሻምበል ብሩክ የጋብቻ ጥያቄውን አቀረበላት፡፡እሷም ፈቃደኛነቷን ከንፈሩን በመሳም አረጋገጠችለት። ከዚያች ቀን ጀምሮ እጮኛው ልትሆን ቃል ከገባችለት በኋላ አይን አይኑን በፍቅር እያየች..
“ለዚያን ዕለት ብለህ ነው የማርከው አይደል ብሩኬ?” እንደ መቅበጥ እያለች እየሳቀ ጠየቀችው፡፡

“ምኑን ትሁት?”ያለችው ቢገባውም አውቆ ያልገባው በመምሰል እሱም እየሳቀ ጠየቃት፡፡
“የወርቅ አምባሩን ነዋ!” ሄዳ እላዩ ላይ ወድቃ ሳመችው። እንደዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዐይን አውጣ ሆንኩ አይደለም እንዴ? እያለች ድርጊቷ ለራሷ ቢገርማትም፤ ለሻምበል ብሩክ ግን ከዚያም በላይ ብትሆንለት ፈቃዷ ነበር፡፡
አይሻልም ትሁት?” አላት እሱም እየሳማት፡፡
👍3
“በጣም እንጂ ብሩኬ አርቆ አስተዋይ ነህ” አለችው።
“እኔ የዘመኑ ጋብቻ ያስቀኛል?” አላት፡፡
“እንዴት?” ስትል ጠየቀችው። አይኖቿን ከአይኖቹ ላይ ሳትነቅል፡፡
“እዚያ ጫጉላ ቤት የሚገቡት ለምን ይመስልሻል?”
“ለምንድነው? እኔ አላውቅም” እየሳቀች፡፡
“ዋናው ቁም ነገሩን ገና ድሮ ይሸኙትና፧ እዚያ ጫጉላ ቤት ውስጥ ገብተው 'ወይኔ ዛሬ ቢኖር ኖሮ? እያሉ ተቃቅፈው ለመላቀስ ነው” አለና እራሱ ስቆ እሷንም በሳቅ ገደላት።
“ከሁሉ የበለጠ የሚያሳዝነኝ ደግሞ ሚዜ ነው።የሚዜ ጣጣው ብዙ ነው፡፡ ልጃገረድ ሆና ካልተገኘች ፤ ጣትን ቆርጦ ማድማት ይጠበቅበታል፡፡
በሰርጉ ማግስት ደግሞ የውሸት አበባ ይዞ ወደ ወላጆች መሄድም አለ ፡፡
አቤት የሚዜ ጣጣው! እኛም ሚዜዎቻችንን ከምናስቃያቸውና ብር
አምባር ሰበረልዎ እየተባለ ሲዘፈን ከምንሳቀቅ እስከዛው ድረስ ብናቆየው
አይሻልም ትሁት? ”
“በጣም ደስ ይለኛል ብሩኬ፡፡ የኔም እምነትና ፍላጐት ይሄው ነው፡፡አሁን
አንተ ስለሚዜዎችና ስለ ጫጉላ ቤት ስታወራኝ ግን አንድ ነገር ትዝ አለኝ
አለችና ከመናገሯ በፊት በሳቅ ፍርስ አለች፡፡ ሻምበል ብሩክም
ምንነቱን ሳያውቅ አብሯት ሲስቅ ቆየና ምንድነው እሱ ሲል ጠየቃት
ለመስማት ቸኩሎ..
እርጉዝ ሆነው ጋብቻ የሚፈጽሙትስ? እዚያ ጫጉላ ቤት ውስጥ ምንድነው የሚሰሩት? ስትለው እቅፍ አድርጓት ከጣራ በላይ ሲስቅ ቆየና ልብሳቸውን ለባብሰው ጨረሱ፡፡ ከዚያም ቁርሳቸውን አብረው ከበሉ በኋላ መጀመሪያ እሷን እቤቷ ድረስ ሸኝቷት ወደ ስራው ሄደ።


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሶስት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና ሻምበል ብሩክና ትህትና ድንበሩ ከተዋወቁ ዛሬ ልክ አንድ ወራቸው፡፡ የፍቅራቸው ወርሃዊ ልደት ውል የሚበጅበት ቀን በመሣሣም ደረጃ የቆየው ፍቅር ዛሬ ወደ አካላዊ ውህደት ሊሸጋገር እቅድ ተይዞለታል። ሻምበል ብሩክም ሆነ ትህትና የዛሬውን ቀን በልዩ ጉጉት ነው የጠበቁት። እሁድ ዕለት አሥመራ መንገድ በሚገኘው በሻምበል ብሩክ…»
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ በዛሬው ዕለት ከመሰል የሥራ ባልደረቦቹ ጋር ከፍተኛ የቀዶ ጥገና ሕክምና አጋጥሞት ነበር የዋለው፡፡ የቀዶ ጥገናው የተደረገላት ሴት በማኅፀን ዕጢ
በሽታ የምትሰቃይ ነበረች፡፡የሆድ ዕቃዋ ተከፍቶ ተከፈፍቶ የተገመተውና፤ በተግባር የታየው የሰማይና ምድር ያህል
ልዩነት ነቀረው።

በማህፀኗ ላይ ለአራት ሰአት የተደረገው የቀዶ ሕክምና ከሁለት ኪሎ ግራም በላይ ዕጢ እንዲወጣላት አስቻለ፡፡ ዶክተር ሰውነቱ በሥራ ደክሞ ስለዛለ በቂ ዕረፍት ለመውሰድ በጊዜ ወደ ቤቱ ገብቶ አልጋው ላይ ጋደም ለማለት ፈልጓል፡፡
ከድካሙ ቀለል እንዲለው ፤ በቀዝቃዛ ውሃ ገላውን ሙልጭ አድርጉ ከታጠበ በኋላ፤ የጥጥ ፒጃማውን እንደለበሰ ነበረ የተኛው፡፡በዚሁ መሀል ትህትና ገርበብ ያለውን የመኝታ ክፍሉን በር ከፍታ ገባች::
በዛሬው ዕለት ያለወትሮዋ የተርከፈከፈችው ሽቶ ቀድሟት ገባና
ክፍሉን በመዓዛው አወደው:: የዱር ጽጌረዳ፣ ጣፋጭ መዓዛ፤ እሷም
የጽጌረዳ አበባ መስላለች። ወትሮ ከሚያውቃት ትህትና በእጥፍ አምራ
ተውባለች፡፡ ኮቴዋን ሳታሰማ ወደሱ ትመጣለች፡፡
ቁልቁል ትመለከተዋለች፡፡ ገርበብ ባሉት ዐይኖቹ ሰረቅ አድርጎ አያት፡፡ በልቡ ውበቷን አደነቀ። ቀጭን ሳቋ ጆሮውን ሰረሰረው፡፡ ዐይኖቹን ገለጥ አድርጉ በሚያየው ነገር ተደንቆ፤ ሽቅብ ተመለከታት፡፡ እሷም በፈገግታ ተሞልታ እየተፍለቀለች ጐንበስ ብላ ጉንጬን ሳመችው፡፡
ከበላዩ ቆሞ፤ ውብ ፈገግታን የሚለግስ፤ በኋላም በአካል የሚዳስስ፤ መልአክ መስላ ታየችው፡፡
የዛሬው አመጣጧ ድንገተኛ ሆኖበታል። የተቀጣጠሩት ለዛሬ አልነበረም፡፡ እንዴት ቀድማ መጣች? ገረመው። ከቀጠሮ በፊት መምጣቷ ምናልባትም በፍቅሩ ወጥመድ እየወደቀችለት ለመሆኗ ፍንጭ ስለሰጠው የደስታ ስሜት የሠራ አካላቱን አዳረሰው፡፡
“የደብረዘይቱ የሽርሽር ውጤት እየታየ ነው” አለ በልቡ፡፡ የሚገርመው ደግሞ አንጀቱን ለመብላት ያላደረገችው ጥረት የለም፡፡ የለበሰችው ስስ ተካፋች ጃኬት እኒያ ገና ከሩቅ ሲያያቸው ውሃ
የሚሆንላቸው! ጡቶቿን፤ አጋልጦ ያሳያል። በዚህ ላይ እኒያን ውብ ባትና ጭኖቿን፣ በግልጽ የሚያሳይ አጭር ቀሚስ ነው የለበሰችው፡፡

“በቃ በፍቅር ወድቃልኛለች ማለት ነው”
በስሜት እንደሰከረ ፍዝዝ ባሉት ዐይኖቹ ይመለከታት ጀመር። ጭውው አለበት፡፡ ሽውው የሚል ነፋስ ሲነፍስ፣ የፍቅር አማልክት በያሬዳዊ የሙዚቃ ቅኝት
ስለፍቅር ሲያዜሙ ፧ ተሰማው፡፡ ድብት የሚያደርግ የድካም ስሜት..ድቅቅ
ያለ ሰውነት በደስታ የሰከረ ቀልብና ልብ፡፡
አሁንም ከት ብላ ሳቀች። አሳሳቋ እንደ ገደል ማሚቶ አስተጋባ፡፡ ሁኔታዋ ሁሉ ግርም ብሉት፤ አፉን ከፍቶ ይመለከታት ጀመር፡፡ ዐይን አፋራ፣ ቅልስልሷ ፤ ትህትና መሆኗን ተጠራጠረ፡፡ ፍቅር ያንን ሁሉ
የእፍረት ማቅ አሽቀንጥራ እንድትጥል አድርጓታል ማለት ነው? ፍቅር እውር ነው ወይስ እውር ያደርጋል? በትክክል እውር እንደሚያደርግ ከሷ እንደዚህ የውቦች ቁንጮ ሆናለት፤ ከቀጠሮአቸው በፊት ሹልክ ብላ ስትመጣለት ምን ይባላል? ማመን አልቻለም፡፡
ዐይኖቹን አሸት አሸት አድርጉ ሁለት እጆቹን ወደላይ ዘረጋና
“ትሁትዬ” አላት በደከመ ድምጽ።
ቀስ በቀስ ያ ሰውነቱ እየጋለ መሄድ ጀምሮ ነበር፡፡ በተለይ የዘረጋላት እጆቹን ወደዚያ ውርውር አድርጋ..
“ከቀጠሮ በፊት ስለመጣሁ መዘነጥህ ነው?” ብላ ከተሰቀለው መስታወት
ውስጥ ፊቷን ለማየት ዘወር ስትል፤ አጭሩ ቀሚስ እላይ ድረስ ዘልቆ እኒያ የሚያማምሩ ጭንና ባቶቿን ወለል አድርጉ ሲያሳየው አልቻለም፡፡ቀስ በቀስ እንደ ካውያ እየጋለ በመሄድ ላይ የነበረው ሰውነቱ የሚያደርገውን ያሳጣው ጀመር፡፡
በተለይ የምትሽኮረመም ሴት ይወዳል። እንዲያ ግፍትር አድርጋው ስትሽኮረመም፧ እልህ ያዘው። በዚህ ላይ ባቶቿ ኑ ብሉኝ! ኑ ብሉኝ! እያሉ ይጋብዛሉ። በዚያ ባዶ ቤት ውስጥ፤ በዚያ ሰፊ የሞዝቦልድ አልጋ ላይ እየተንከባበሉ፤ ያንን ባለፈው ጊዜ ተልፈስፍሶ ያመለጠውን ሲሳይ ዳግም እንዳያመልጠው ሊሞክር ቸኩሎ ተነሳና...
“ከቀጠሮ በፊት መምጣትሽ ምን ያህል ልቤን እንዳስደሰተው ከፍተሽ ባየሽው የኔ ቆንጆ?” በጀርባዋ በኩል ሄዶ፤ በሁለት እጆቹ እቅፍ አድርጓት፤ አንገቱን በአንገቷ ውስጥ ቀበረና! ጡቶቿን ያሻሻቸው
ጀመር..
ቀስ በቀስ እየሞቀች ስትሄድ ግለቷ ተሰማው። ከዚያም አፏ እንደተከፈተ ዘወር ስትልለት፤ በተከፈተው አፉ ቀለባት፡፡ ከዚያም እጆቹ ወገቧ ላይ ሲጠመጠሙ፤ እጆቿ ደግሞ በአንገቱ ዙሪያ እንደ ድር
ተጠንጥነው፤ ሰስሜት ተዋህደው ነጐዱ.....
እኒያ ውብ አይኖቿ ስልምልም ብለው ጠፉ፡፡ ከዚያም ቀስ ብለው እየተደነቃቀፉ፤ እየተደጋገፉ፤ ወደ አልጋው ሄዱና ወደቁ፡፡ ዛሬ ትህትና እንደዚያን ዕለቱ ዐይኖቿ በእንባ አልተሞሉም፡፡ ይልቁንም በደስታ እየተፍለቀለቀች፤ በፍቅር፤ ለፍቅር፤ ስትል ሁለመናዋን በግልጽ እየሰጠችው ነው፡፡
ዶክተር በዛሬው ዕለት ብር አምባር ለመስበር በእርግጠኝነት መንፈስ ተሞልቷል፡፡ በደብረ ዘይቱን የሽርሽር ወቅት በተለይም በሆራ ራስ መኝታ ክፍል ውስጥ ሲልፈሰፈስ ያመለጠው
እንዳያመልጠው በመስጋት፤ ኃይሉን የአንበሳ፤ አድርጎ ትግሉን ቀጠለ፡፡
የታጠቀችው የውስጥ ሱሪ ከዚህ በፊት የሚያውቀው ነጩ ባለወንፊቱ ነበር፡፡ በስሜት ደርተው ሲታገሉ፣ በፍቅር ስሜት ተውጣ የሆነ ነገር እያቃሰተች በጆሮው ሹክ አለችው፡፡ “አስገ...ው...ባ..ው..ው."

በዚህ ጊዜ ዶክተር በሲቃ ስሜት ተውጦ ካሰበበት ለመድረስ ጥድፊያውን ቀጠለ፡፡
እሷ ለሚሆነው ነገር ሙሉ ለሙሉ እራሷን ዝግጁ አድርጋ ሲመለከት፤ ደስታው እጥፍ ድርብ ሆነ፡፡ ዶክተር ላብ በላብ ሆኗል።ትህትናም በላብ ተነክራለች። ከረጅም ጊዜ ትግል በኋላ ...
“ዋ!!.......ይ!! !” ብላ ጮኸችና የዶክተር ባይከዳኝን ሰውነት በጥፍሮቿ ግጥም አድርጋ ይዛ አለቀሰች፡፡ ዶክተር ስለተቧጠጠ ገላው ደንታም ሳይሰጠው በድል አድራጊነት እርካታ ተውጦ ግዳዩን ለማየት ተጣደፈ፡፡
በእርግጥም ድል አድርጓል፡፡ በዚያው ስሜቱ እስከሚረካ ድረስ ቆየ። ከዚያም ተዘርራ ተመለከታት፡፡ ይህ ውስጥ ለውስጥ ያደርገው የነበረው ስሜታዊ ትግል፤ ቀስ በቀስ በውስጡ ሲሯሯጥ ከቆየ በኋላ፤ አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ፤ ወደ ገሀዳዊው ዓለም ተለወጠ፡፡
በዚህ ለውጥ ሰዓት ከእግር ጥፍሩ፤ እስከራስ ጠጉሩ ድረስ የነዘረው ንዝረት አባነነውና፤ በላብ እንደተዘፈቀ ከገባበት የቅዠት ዓለም ወጣ! እግዜኦ! ዶክተር በዚያን ሰዓት የተሰማውን የስሜት ስብራት በቃላት ማስቀመጥ ይከብዳል።
ያ ሁሉ ዓለም፣ ያ ሁሉ ደስታ፤ እንዲህ እንደዋዛ እንደጉም በንኖ ጠፋና፤ የሱን ስሜት እንዳይሽር አድርጎ አቁስሎት በፀፀት ጉድቶት አለፈ፡፡ ያ ሁሉ የድል አድራጊነት ስሜት በቅጽበት ቦታውን ለሽንፈት ለቀቀና፤ በዶክተር ባይከዳኝ ልብ ውስጥ ሀዘን ጥቁር ደመናውን አጥልቶበት ሄደ...
“ቡል ሺት! ” አለና ትራሱን በቡጢ ጠልዞ የሆነውን ነገር እንደ አዲስ አስተዋለ፡፡ በቅዝቃዜው ስሜት ተጠራጥሮ ሲዳብስ፤ ፒጃማውን ረጥቦ አገኘው፡፡ ከዚህ በኋላ ሁኔታዎችን ቀስ ብሎ ይመረምር ጀመር።
በቀላሉ የሚልፈሰፈሰው አካሉ አሳድሮበት የነበረው ሥነ ልቡናዊ ተጽዕኖ
ለጥቂት ጊዜ እራሱ በፈጠረው ትንሽ የቅዠት ደሴት ውስጥ ጠፍቶ፤ነበር
ጊዜያዊ የተስፋ ጮራ በልቡ ውስጥ እንደፈነጥቅበት፤ እሱም ጓደኞቹ
ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ እንደሚችል፤ አረጋግጦለት ነበር።.....

ድንግልናን መግሰስ በማይችል አካላዊ ብቃቱ ለዘመናት አዝኖ እንዳልኖረ ሁሉ፤ በዚህች ቅጽበት፤
2👍2🔥1
በቅዠት ዓለም፤ ከቆንጆዬዋ ከትህትና ድንበሩ ጋር በፈፀመው ግንኙነት፤ ጥንካሬውን በማረጋገጡ፤ ልቡ በደስታ ሞቆ ነበር። ምን ያደርጋል? በነበር ቀረ እንጂ....
ዶክተር አንጀቱ ተቃጠለ፡፡ አልቅስ፤ አልቅስ የሚል ስሜት ተሰማው፡፡ የዛሬው ቅዠት ከትህትና ጋር በእሱ መኖሪያ ቤት ለመገናኘት የያዙት ቀጠሮ ቶሎ አልደርስልህ ብሎት ከመጣደፍና ከመጨነቅ የመነጨ መሆኑን፣ቀንም ሆነ ሌሊት እሷን በማስብ የተፈጠረ መሆኑን፤
ሲያውቅ አዘነ። እንዲወስንበት አሳልፋ በሰጠችው ገላ ላይ መወሰን አቅቶት ሲንደፋደፍ፤ እድሉን ለሌላ አሳልፎ እንዳይሰጠው በልቡ ውስጥ ከፍተኛ ስጋት አደረበት። የሚያደርገውን አሳጣው፡፡በዚህ ሁኔታ ስሜቱ በእጅጉ ተነክቶ ሲያሰላስል፤ ድሮ እዚያ ገጠር ውስጥ እረኞች እያሉ ጓደኞቹ የሚሳሳቁበት ትዝ አለው:: ያንን ሀፍረተ
ሥጋ መሸፈን የማይችል ጥብቆ ለብሰው ከጓደኞቹ ጋር እየተጫወቱ በእረኝነት ሲውሉ፡-
“ባይከዳኝ ለአህዮች ሲታደል ነው እንዴ የተሰለፈው?” እያሉ የሚሳሳቁበት ትዝ አለው፡፡ እንደዚያ ሲሉት ድሮ ሁሉንም ነገር በሳቅ ነበር የሚያሳልፈው። አሁን ግን አንጀቱ እየተቃጠለ፤ በምሬት ነው
የሚያስታውሰው፡፡ በተለይ በተለይ ከእንስሳት ሁሉ አህዮች ፍቅር ሲሰሩ
ማየት ያስደስተው ነበር፡
“ለምን ይሆን?” ሲል እራሱን ጠየቀና ...
እውነት እንዳሉት የአህያ ጂን ይኖርብኝ ይሆን እንዴ?” በማለት ለራሱ ባቀረበው ጥያቄ ቢስቅም፤ አንጀቱ ግን እርር፤ ድብን፤ ከማለት አልዳነላትም:: የምሬት ሳቅ ሳቀ፡፡ ዶክተር እዚያ ገጠር ውስጥ በተፈጠረ አንድ ምክንያት ይኸውና
እስከዛሬ ድረስ ድመት ሲያይ እንደበረገገ ይኖራል። አሁን ደግሞ ልጃገረድ
የሚለውን ሲሰማ በጥላቻ መበርገግ እንዳይጀምር እያሰጋው መጥቷል።
ድመት የጠላበት ምክንያት ነበረው፡፡ እንደዚህ እንደዛሬው በአካልና በአእምሮ ጎልምሶ ከፍተኛ የሙያ ድርሻ በሆነው በህክምና ዶክተርነት ሙያ ላይ ከመሰማራቱ በፊት በአካልም በአእምሮም ጥሬ በነበረበት፤ ክፉውንና ደጉን በውል ለይቶ በማያውቅበት፤የልጅነት ጊዜ የተፈጠረ ነው፡፡እንደወትሮው ሁሉ ጥጆች በመጠበቅ ላይ እያለ፤ መልኩ የቀይ
ቡሬ የሆነ የደስ ደስ ያለው ድመት ይመጣና ይተሻሽው ጀመር። ትንሹ
ባይከዳኝ ያንን ብቸኝነቱን ሊያስረሳለት ጫካ ድረስ የመጣለትን ድመት ማሻሸቱን ቀጠለ ማሻሸቱን ቀጠለ፡፡ ድመቱም ሲታከከው ፤ እሱም ሲደባብሰው ፣ ቀስ በቀስ ተላመዱና ፍጹም የሆነ ወዳጅነት መሠረቱ፡፡
በተለይ ድመቱ ጭራውን እየቆላ....
" ሚያው እያለ በጀርባው ተንጋሎ፤ ትናንሽ የፊት እግሮቹን ወደ ላይ ሰቅሉ፤ አንገቱን እንደ እስክስታ ወራጅ ወዲያና ወዲህ እየሰበረ የእንፉቅቅ ይሽከረከር ጀመር፡፡
ባይከዳኝም እዚያ ጥጆች የሚጠብቅበት ቦታ ድረስ መጥቶ ምንም እንኳ በቋንቋ ባይግባቡም በለስላሳ ሰውነቱ
የሚያጫውተውን እንስሳ ወደደውና! ትንሿ ልቡ በፍቅር ወደቀች::

አሁን አሁን ጓደኞቹ “ድመት!” እያሉ የሚያስደነብሩትና የሚሳሳቁበት፤ የዚያን ዕለት ከዚያ የዱር ድመት ጋር በፈጠረው አጉል ጓደኝነት በድንጋጤ የተመታችው ትንሿ ልቡ ጥላቻ እንዳደረባት በማደጓ
ምክንያት ነው። ከድመቱ ጋር ያ ሁሉ የጓደኝነት ጨዋታ በሰላም ሲካሄድ
ከቆየ በኋላ፤ ከዚያ በፊት አብረው እንዳልነበሩ ሁሉ፣ እንደዚያ እየተሻሹ
ሲጨዋወቱ እንዳልቆዩ ሁሉ፤ ያ ድመት ትንሹ ባይከዳኝን ከድቶት ጥሎት ሊሄድ ሲል ፀቡ ተፈጠረ።
በነብርና በድመት መካከል ያለውን አንድነትም ሆነ ልዩነት የማያውቀው ባይከዳኝ፤ ድመቱ ጥሎት እንዳይሄድ ፍቅሩን መግለጹ ነበር፡፡ ድርጊቱ ሁሉ አሳዛኝ የሆነው ግን ከዚያ በኋላ ነው።“ውርርር..ይልና ባይከዳኝ የድመቱን ጭራውን ይዞ ይጐትተዋል። በሱ ቤት ገና እቤቱ ወስዶ፧ ወተት ሰጥቶት፤ ማታ
ማታም እቅፍ አድርጎት እየተኛ፤ ዘላቂ ጓደኛ ሊያደርገው ነበር ሀሳቡ።
ያ ጭራውን የተያዘ ድመት ወዲያውኑ ሰውነቱ ተቆጥቶ ያብጥና ለስላሳ ባህሪው በውስጥ ነብርማ ባህሪው ከመቅጽበት እንደተለወጠ፤ ዘወር ይላል። ዐይኖቹ ቀልተው ያስፈራሩ ነበር። ከዚያ በኋላ የሆነውን ባይከዳኝ ማስታወስ አልቻለም። ብቻ የሆኑ ሹል ነገሮች ከግንባሩ ጀምሮ
እስከ እምብርቱ ድረስ በስጋው ውስጥ ዘልቀው ሲሄዱ ይሰማዋል።
በመጨረሻም በፈላጊዎች የተገኘው፤ መላ ሰውነቱ በደም አበላ ተነክሮና፤ እራሱን ስቶ ነበር። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ይኸውና እሰከአሁን ድረስ ድመት እንደጠላ ይኖራል። ዶክተር እመኝታው ላይ ሆኖ በተፈጠረው ሁኔታ እየተገረመ የሕይወት ታሪኩን ወደኋላ አጠንጥኖ
በዚያ በገጠር ውስጥ ስለነበረው ሕይወቱ ሲያስብ ቆየና፤ በብስጭት
ተነስቶ ልብሱን ለባብሶ፤ ሲጃራውን አቀጣጥሎ፤ አንድ ሲጃራ ካጨስ
በኋላ፤ ይህንን መጥፎ ስሜቱን እንዲያስወግድለት፤ መጠጥ ለመጠጣት፤መኪናውን አቁሞ፤ በእግሩ ቀስ እያለ፤ ወደ ደንበኛው ወደ አብርሃም
ግሮሰሪ አመራ...

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
#ሰመመን


#ክፍል_አርባ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ


....እስክንድር በግቢው ውስጥ በሚካሔዱት የመዝናኛ ቀልዶች ተረቦችና ጨዋታዎች በተሳተፈ ቁጥር አንድ
የሚገርመው ነገር አለ ። አብዛኛው ወሬ ስለ ሴትና ወንድ ግንኙነት ወይም ስለ ፍቅር ነው ። “ ሌላ ወሬ አጥተን ነው
ወይስ ዕድሜአችን ነው በዚህ አርዕስት ዙሪያ የሚያሽከረክረን ? ወይስ ደግሞ የጋራ ስሜታችንን የሚነካ ጉዳይ ይህ
ብቻ ሆኖ ነው ?” ሲል ያስባል ። ነገር ግን ከአቻው ጋር በተገናኘ ቁጥር ዞሮ ዞሮ አመርቂ አርዕስት ሴት ሆናለች ፤ እና
የዕድሜን ኃይል ግለት ይታዘባል ትኩስ 'አፍላ የሚያቅበጠብጥ ዕድሜ።

የዕረፍቱ የጨዋታ ምሽቶች ከፍቅር እልፍ ያሉ እንደ ሆን በግቢው ውስጥ ከሚታዩት ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ያርፋሉ የፍቅር ጉድጓድ እንደሚሰረስሩት “ሮይተሮች ” ሁሉ በዩኒቨርስቲው ውስጥ ፀረ መጤ ሃይማኖት አቋም ይዘው እያንዳንዷን እንቅስቃሴ እየተከታተሉ የሚ
ተርቡም አሉ ። በየዕለቱ በየትኛው ድርጅት ውስጥ ማን እንደ ተመለመለ ወሬው አያመልጣቸውም ሌላው ቀርቶ
የትኛው የሃይማኖት ድርጅት በግቢው ውስጥ የአባላት ብዛት እንዳለው የሚያውቁና በአሀዝ የሚያቀርቡ አሉ ።

ሰሞኑን “ ሁለተኛው አምላክ ዘ" ታላቅ ኪሳራ ደርሶበታል ” ሲል አንዱ ይጀምራል

“ እንዴት ? ”

“ በፈተና ሰሞን የመለመላቸው አባላት አብዛኛዎቹ ፈተና ካለቀ በኋላ ርግፍ አርገው ትተውታል። ከመብላታቸው በፊት መጸለይ አቁመዋል ። አስረጅ ”

“ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በሃይማኖት አባልነት የተመለመሉት የሚታወቁት፡ምግብ ኣዳራሽ ውስጥ ከመመገባቸው
በፊት አቀርቅረው ሲጸልዩ ነው ። ጸሎቱን ሲያቆሙ ኮንትራታቸውን መጨረሳቸው ይታወቃል

“ አትለኝም ማን ማን ተወ በናትህ ? ”

የሚታወቁትን በስም የማይታወቁትን በመልክ ጥቆማ ይካሔዳል ።

“ ምነው ውጤት እስኪቀበሉ እንኳ ቢቆዩ ፈተና ላይ “ የረዳቸው ” አምላክ የአራሚውንም መምህር እጅ በማሳሳት እንዲረዳቸው ። ”

"ቸኮሉዋ ! ምን ያርጉ በዕረፍት ጊዜያቸው በሃይማኖቱ ከቀጠሉበት ሴቶቹ መደነስ ወንዶቹም መጠጣት ሊያመልጣቸው ሆነ ለማን ጀቴ ብለው !”

“ አሥቂኝ ነው ” ይላል አንዱ ቀልደኛ ከመሐል።

“ እንዴት ?” ሲል ሁሉም ጆሮውን ይቀስራል ።

“ ከአምላካቸው ጋር ድብብቆሽ ጨዋታ ነው ” ኮ የተያያዙት ። ፈተና ሲደርስ ይሰግዱለታል ። ከፈተና ከወጡ በኋላ ይዘጉታል ። ዋ ብቻ አንድ ቀን ያመረረ ዕለት !”

ቀልዱ ሲኮረኩራቸው መሣቅ እየፈለጉ በልባቸው አፍነው የሚያሳልፉ አሉ። ሲሥቁበት አምላክ እንዳያያቸው
የፈሩ ይመስላሉ ። አንዳንዱ በዚህ አርዕስት ላይ ሲያሾፍ ፡ ሲቀልድ ፥ ሲተርክ አንዳንዱ ደግሞ ገለልተኛ ሆኖ መስማቱን ይመርጣል ። ጨዋታውን ማዳመጥ ይወዳል ፤ ግን በሃይማኖታዊ ድርጅቶችም ሆነ በአምላክ ላይ አንዳችም
ተቃርኖ አያነሣም ። “ ከአፍ የወጣ እንጂ በጆሮ የገባ አያረክስም” ከሚል ግምት ላይ የደረሰ ይመስላል ።አፌን በዳቦ
ነው ነገሩ ።

እንዲህ ዐይነቶቹ የጨዋታ ምሽቶች በብዙ ተማሪዎች አእምሮ ተቀርጸው የሚቆዩ ናቸው ። በሴቶችም መኝታ ክፍል ቢሆን ሐሜቱና ተረቡ ቢበዛ እንጅ አያንስም ። ወንዶችን በማብጠልጠል አስተማሪዎችን በመቦጨቅና ራስን በመካብ ሴቶቹን የሚያህል የለም ። “ እገሌ “ኮ እንድወጣለት ጠይቆኝ ዘጋሁት ያ ባላገር ” የብዙዎቹ የጋራ ፈሊጥ ይመስላል ። የሚገርመው ደግሞ ሴቶቹ ሲዋሹ እርስ
በርሳቸው ይቻቻላሉ ። እንደ ወንዶቹ “ረገጣ” እና “ስጥ እንግዲህ ” እየተባባሉ ቅስም አይሰባበሩም ።

ቀልድ እየፈጠሩና ወሬ እያጠናቀሩ ተማሪውን የሚያዝናኑትን ያህል በየአስተማሪው ቢሮ እየተሹለከለኩ የፈተና ውጤት ከመነገሩ በፊት መርዶ የሚያረዱ አንዳንድ ተማሪዎችም አሉ ። እነዚህን ማንም አይወዳቸውም የዩኒቨርስቲ ሕይወታቸው ዕድሜ የሚኖረው ለአስተማሪዎች ወሬ በማመላለስ ነው እየተባሉ ይታማሉ ። ማርክ ቀድም የመስማት ሱስ አለባቸው ። የራሳቸውን ሳይሆን የሌሎቹንም የመስማት ሱስ ነው የያዛቸው ። እወደድ ባይ ወይም ለተራ ወሬ ጆሮውን የሰጠ መምህር የሦስት ልጆችን ማርክ ይነግራቸዋል ።እነሱ ደግሞ አባዝተውት የሃምሳ ልጆችን ውጤት እንደ ሰሙ አርገው ወሬውን ይዘራሉ መምህሩ ወደቀ ካላቸው እነሱ “ ተሰበረ ” ብለው በግቢው ውስጥ ሽብር ይፈጥራሉ ።

ዘንድሮ ይህን ያህል ፍሬሽ ይባረራል ” ብለው በአፋቸው ሙሉ ሲናገሩ የሬጂስተራሩን ቢሮ የያዙት ይመስላሉ ።

“ የእንትን አስተማሪ ከዚያ ሁሉ ተማሪ መሐል ሁለት “A” ብቻ ነው የሰጠወ” ሲሉ የመምህሩ የቅርብ ጓደኛ ይመስቀሉ

ከመልካም ዜና ይልቅ የዝቅተኛና የውድቀት ማርክ ሽብር መፍጠር ነው የሚቀናቸው ። ሌላውን አስበርግጎ ወይ
እነሱ የወሬ ሱሳቸውን ካልተወጡ አይሆንላቸውም ።

እቅጩ የሚታወቀው ግን ጊዜው ደርሶ ማንኛውም ተማሪ የራሱ ውጤት በራሱ እጅ ከደረሰው በኋላ ነው፡አቤል ከሁሉም፦ ርቋል ጥሩውንም መጥፎውንም አይሰማም ። “ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው” እንዲሉ በሱ ላይ የሚወራበትን አያውቅም። ነገር ግን ተማሪው ሁሉ በሽታወን ያወቀበት እየመሰለው ከሁሉም ሸሽቶአል ። ጓደኛው ብቸኝነቱ ነው » አጫዋቹ የቀን ቅዠቱ ፥ የሌሊት
ሕልሙ ነው ። ሌላው ክፍል ተማሪው ተሰብስቦ እያወራ እየቀለደና እየተጫወተ ሲሣሣቅ፥ አቤል ከብቸኝነቱ ጋር
ይሟገታል ። ትዕግሥትን ያልማል ፤ በል ሲለውም ይረግማታል ። የመልካሙ ተበጀን ዘፈን ያዜማል ። ብርቅነሽን ያስባል ከራሱ ጋር ይሥቃል ። ከራሱ ጋር እየተጣላ ያለቅሳል።

በዚህ ዓይነት የሚገፉ ዐሥራ አምስት የዕረፍት ቀናት የዐሥራ አምስት ዓመት ያህል ቢረዝሙም ማለቃቸው አይቀርም ያልቃሉ ። የሚጠበቀውም ቀን መድረሱ
አይቀርም ይደርሳል ።

ትዕግሥት የፈተና ውጤት ሊሰጥ እንድ ቀን ሲቀረው ከደብረ ዘይት አዲስ አበባ ገባች ። ወደ ዩኒቨርስቲዉ መኝታ ክፍሏ ስታመራ፥ አንዳች ነገር የኋሊት ይጎትታት ነበር። ከዘመዶቿ ጋር ከርማ መለያየቷ ተጫጭኖዋታል "በዚያ ላይ ማርታና ቤተልሔምገና ስላልመጡ ብቻዋን ነበረች።

አቤልን ለማየት ቆርጣ ነበር የመጣችው ። ተለይታው በከረመችበት የዕረፍት ጊዜ ውስጥ ሲናፍቃት ነበር ። ግን ለምን ? መናፈቁን ነው እሷ ያልወደደችው ። ትዕግሥትም እንደ አቤል ለፍቅር እንግዳ ናት ። በልጅነቷ ጭቃ እያቦካች
ጎጆ ሠርታ፡ “ባልናሚስት” የተጫወተችበትን ጊዜ ወይም
ከትምህርት ቤት ጓደኞቿ ጋር የተጫወተችባቸውን ጊዜያት ታስታውስ እንደሆን ነው እንጂ ሌላ የፍቅር ትዝታ የላትም፡ አሁን ዕድሜዋ ይገፋፋታል " የወንድ ልጅ ክንድ ተደግፋ
በነፋሻማ ስፍራዎች መወዝወዝ ያምራታል አፍ ለአፍ ገጥማ ምስጢር የምታወራው አቻ ወንድ ያምራታል የወንድ ልጅ ከንፈር ጣዕም መቅመስ የሚያሰኛት ዕድሜ ላይ
ነች። ነገር ግን በዚህ ፋንታ የመጀመሪያ ፍቅሯ ከዐይን የማያልፍ ሆነ ። አቤል ቀርቦ ምስጢሯን አይካፈላትም ።የፍቅር ትኩሳቷን አይጋራትም ፡ የደረቀ ከንፈሯን አያረጥብላትም ፡ ወንዶች ላይ ለሚቅበዘበዝ ዐይኗ ገደብ አይገዛላትም። እሷነቷን ቀርቦ አያውቅላትም ። በሩቅ እየተያዩ መነፋፈቅ ብቻ

ትዕግሥት ይህን ሁሉ አመዛዝና ነበር አቤልን ቀና ብላ ለማየት የወሰነችው ። ትርጉም የሌለው ፍቅር ሆነባት ።
ከመጐዳቱና ከማንገብገቡ በቀር ጥቅሙ አልታይ አላት ።እንዳሰበችው የመጣች ዕለት ጨክና ሳታየው ዋለች። ከደብረ
ዘይት ያመጣችው የአገልግል ምግብ ስለ ነበር ወደ ምግብ አዳራሽም ብቅ ሳትል ዋለች ። ሐሳቧ ሴሚስተሩን በሙሉ
ከእርሱ ርቃ ለመቀጠል ነበር ። ግን ያን ዕለቱኑ ወደ ምሽት ላይ ከቁጥጥሯ በላይ
👍1
የሆነ ውስጣዊ ኃይል እንድትወጣ ገፋፋት " ዐይኗ ውጭውን ማየት ፈለገ ጋቢ ደርባ ወጣች
አቤል ራቱን በልቶ የሚገጣጠሙበትን መንግድ አስልታ ነበር የሔደችው።ሆኖም አቤል ወደ መመገብያው አዳራሽ
የገባው መጨረሻ ላይ ስለ ነበር እንዳሰበችው ቶሎ አላገኘችውም ዐይኗ ተርቦ ለግማሽ ሰዓት ያህል በምግብ
አዳራሹና በወንዶች መኝታ ክፍሎችና መሐል ከተንጎራደደች በኋላ ጨረፍታውን አየች ። አቤል አፉን እየጠራረገ
ከምግብ አዳራሹ ወጣ ። እሱን ስታይ የልቧ ትርታ መጨመሩ ራሷን በራሷ ትዝብት ላይ ጣላት ፡ ካየችው በኋላ ለመሄድ ብታስብም እግሯ አልተንቀሳቀሰም ። ማየት ብቻ ሳይሆን
መታየትንም ፈልጋ ነብር ።

ድፍን ባይልም መጨላለም ጀምሮ ስለ ነበር እቤል ትእግሥትን ከሩቅ አልለያትም ቀረብ ሲል ነው በጋቢ ውስጥ የተደበቀ ውበቷ የታየው ። እሷ መሆኗን ዐይኑ
እንዳረጋገጠ፥ እየተራመደ ብርክ ሲይዘው ታወቀው ። ሊቀርባት የፈራ ይመስል እርምጃውን ቀነሰ ። እሷም ቆማ አልጠበ
ቀችውም ። እንዲያያት ካረጋገጠች በኋላ ዞራ ወደ መኝታ ክፍሏ ተራመደች ። እግሯ እንጂ ልቧ አቤልን መሸሽ አልፈለገም ነበር ።አድራጎቷ እሷኑ መልሶ አሣቃት። ልታየው ፈልጋ ወጥታ ሲያያት መሸሿ ምን ይባላል ? ! ፍቅረኞች ተለያይተው ከርመው ሲተያዩ አንግት ለአንገት ተቃቅፈው እየተሳሳሙ ፍቅራቸውን ይወጣሉ እንጂ ይደባበቃሉ ?
ከዚች ደቂቃ ጀምሮ ልቧ አቤልን ብቻ መወንጀሉን አቆመ ። የአቤል ሕመም እንደ ተጋባባት ተሰማት ። ታዘብኩህ ! ” አለችው ልቧን በልቧ ።

እቤል በእይታው ቅጽበት ውስጥ ፊቷ ዐይኑ ውስጥ ተቀረጸበት ። የወፈረች መሰለው ። ዕረፍቱ ተሰማምቷት
ነበር ማለት ነው ? ደግሞም ስታየው ፈገግ ብላለት በፈገግታዋ የሚጎደጉድ ጉንጮቿን ያየ መሰለው « ሁሌም ስሜቱ
የፈጠረው ምስል ይሆናል እንጂ ፥ ባያት ቅጽበት ውስጥ ይህን ያህል ለማጤን የተረጋጋ መንፈስ አልነበረውም ።
በደንብ ያየው ጀርባዋን ነው ። ጋቢዋ ከዐይኑ እስኪጠፋ ድረስ ተከተላት ።
ካያት ደቂቃ ጀምሮ ልቡ መሠቃየቱ አልቀረም ። ነገር ግን የዚህ ምሽቱ ሥቃይ ከወትሮው የተለየ ሆኖ ተሰማው።


ሥቃዪ ውስጥ ደስታም ነበረበት በዚህ ሰአት ብቻዋን ምን አንጎራደዳት? ያውም በወንዶች ቤት አካባቢ ሲል ራሱን ጠየቀ።
ሆን ብላ ልታየው ፈልጋ መምጣቷን
ለአፍታም አልተጠራጠረም ። የስነበተ ናፍቆቷን በዓይኗ ተወጥታ መሄዷን ልቡ ነግረው እናም ለዐይን ፍቅሩ የመሸነፏ ወይም የመድከሟ አዝማሚያ ሆኖ ታየው ይህ ነበር በሥቃዩ ውስጥ ደስታን የፈጠረለት።

ያጋጠመውን ሁኔታ ለሌላ ሰው ለማጫወት ወይም በደስታና ሥቃይ መሀል የሚዋልል ስሜቱን ለማዋየት
ፈለገ ማታ ለእስክንድር ሊያጫውተው ከጀል አደረገና እስካሁን ያልነበረውን ግልጽነት መጀመሩ አስቸጋሪ ሆንበት ስለዚህ ስሜቱን አፍኖ አልጋ ላይ ወጣ።

በማግሥቱ ጠዋት አንድም ከግቢ የወጣ ተማሪ አልነበረም ። ሁሉም የፈተናውን ውጤት በመጠባበቅ በማስታወቂያ ሰሌዳ አካበቢ ያንዣብባል ። እንደ ተለመደው የብዙ ተማሪ ልብ በድንጋጤ ወንጠሩ አልቀረም ለፈተና ሲቀርቡ ድንጋጤ ! ለውጤት ሲቀርቡ ድንጋጤ

የእያንዳንዱ ተማሪ ምኞትና ጭንቀት ሲታይ ተአምር እንጂ የሥራውን ውጤት የሚጠብቅ አይመስልም ።

አቤልና እስክንድርም ወደ ትርምሱ ሊቀላቀሉ ሲሔዱ ከሳምሶን ጉልቤው ጋር መንገድ ላይ ተገናኙ ከውጭ እንደ ወጣ ማስታወቂያ ሰሌዳው አካባቢ ስላጣቸው
እነሱኑ ፍለጋ ወደ መኝታ ክፍላቸው እየገሰገሰ ነበር።

“ እንዴት ነው ? በጠዋት ከተፍ ! ” አለው እስክንድር ፡ ሰላምታ ሲለዋወጡ።

“ እንዴ ! ቶሉ መርዶአችንን እንስማ እንጂ ! ”አላቸው ፥ እጃቸውን አጥብቆ ጨብጦ እየወዘወዘ። እስክንድርም ሆነ አቤል በዘዴ እጃቸውን ከሳምሶን ለማላቀቅ አየሞከሩ ነበር ። እሱ በፍቅር ስለሚይዛቸው አይታወቀውም እንጂ እጁ ያማል ። ሲጨብጥ የዱላ ያህል ነው የሚሰነዝረው አጥብቆ ከያዘም በኋላ አይለቅም ። እሱን ላለመጨበጥ ከሩቅ
ሰላም እያሉ የሚሸሹት ተማሪዎች ብዙ ናቸው።
ገና በጠዋቱ አልቦታል ። መላጣው ራሱ ቅቤ የቀለጠበት መስሏል ። የደረቱ ቅርጽና የክንዱ ጡንቻ እንዲታይ
ለት ጥብቅ ያለ ጉርድ ሸሚዝ ነበር የለበሰው ውጤቱን ለማወቅ ከመጠን በላይ ቸኩሎ ነበር ።

“ ዕረፍቱ ተስማምቶሃል ጃል ” አለው እስክንድር ! ወደ ትርምሱ ሲያመሩ "
“ መጠርጠሩስ ! ከቤቴ ሌላ አንዴ አክስቴ ቤት አንዴ አጎቴ ቤት እያልኩ ስገነባ ነው የከረምኩት ። አቤል በአንተስ በኩል ዕረፍቱ እንዴት ነበር ? ”

አቤል አልሰማውም ። ወደ ትርምሱ እየቀረቡ በሔዱ ቁጥር ከትርምሱ ውስጥ ትዕግሥትን ለይቶ ለማውጣት ልጃገረዶቹ ላይ በዐይኑ እየተንቀዋለለ ነበር ።

“ ምን አልክ ? ” አለው ሳምሶንን ' ጥያቄው ወደሱ መሆኑን በደመ ነፍስ ተረድቶ ዕረፍቱ እንዴት ነበር ።

“ ደኅና ነበር ፡ ” አለው ፡ ከጥያቄው ለመገላገል ብሎ።

“ ብርቅነሽ ጋ ከዚያ ወዲህ ሔደህ ታውቃለህ ? ”

ጥያቄው አስደነገጠው ። እሱ ለተጠየቀው ከሌላ ሰው መልስ ይፈልግ ይመስል የእስክንድርን ዐይን ዐይን ተመለከተ ሳምሶንም እሱን ተከትሎ እስክንድርን ተመለከት "

እስክንድር ዐይናቸውን ለመሸሽ ማዶ ማዶ ይመለከት ጀመር ። የብርቅነሽ ስም ሲጠራ ንቅሳቷ ታየው ። ጨዋታዋ
ታወሰው ። የዋህ ንጹሕ ሴት ! “ኬሬዳሽን !” አለ በልቡ የሦስቱም ዐይን በየሔደበት ሲያርፍ ያደናገጣቸው
ጥያቄ ሳይመለስ ቀረ ።

“ ምን ታያለህ ? ” አለው ሳምሶን እስክንድርን
“ አንተስ ምን ታያለህ ?”
ሁለቱም እርስ በርስ ተነቃቁና ተሣሣቁ የአበል ዐይን እነሱ ያዩትን ቢያይም ምንም አልተናገረም።

“እንዴት ደምቃለች ጃል! ” አለ እስክንድር ነጀሩን ግላጭ አውጥቶ ።

ህም ! ” ሲል ሳምሶንም አድናቆቱን ገለጸ

የሦስቱም ዐይን ያረፈው ማርታ ላይ ነበር ቦግ ብሎ የቀላው የከንፈር ቀለሟና በጸጉር ሥራ ጥበብ ቡናማ የሆነውን
ጸጉሯ አድምቀዋታል ። ልብሷ ሰው ሳይሆን አሻንጉሊት አስመስሏታል ። ሁለመናዋ ከሩቅ ዐይን ይስባል ። እሷን
ካዩ በኋላ ነው ትዕግሥትና ቤተልሔም አጠገቧ መኖራቸውን የለዩት ። የአቤል ዐይን ወደ ትዕግሥት ሲሻገር ፡ የሁለቱ ግን ማርታ ላይ እንደ ተተከለ ነበር ።

ቤተልሔምና ማርታ በጠዋት ነው የመጡት ። እንደ መጡ ወደ መኝታ ቤቷ ሔደው ከትዕግሥት ጋር ከተገናኙ
በኋላ ቁርሷን እንኳ በደንብ ሳትበላ እያዋከቡ ነው ወደ ማስታወቂያ ሰሌዳው አካባቢ ያመጧት ፡ ሦስቱም ውጤታቸውን ለመስማት በጣም ጓጉተዋል ።

የቆመበት ቦታ ሞቅ ያለ የግል ጨዋታ ይዘው ስለ ነበር እነ አቤልን አላዩአዋቸውም ። ማርታ በእጅዋም በአፉም ታወራለች ። በዕረፍቱ ጊዜ ስንት ወንድ እንዳወጣች ፡ ስንት ሆቴል እንዳዳረች ትዘረዝራለች ። የሷ ወሬ እንዲ
ደነቅላት ብቻ ስለምትፈልግ ፥ ሌሎች እንዲያመሩ ፋታ አትሰጥም ። ትዕግሥት አድማጭ ነች ። ቤተልሔም ምንም
አትተነፍስም ፡ - ውጭ ባይበርድም ውስጧን እያንቀጠቀጣት ነበር ። ውጤት የማወቅ ሰዓት በመሆኗ እንደ ልማዷ በፍርሀት እየተርበደበደች ማርታ የምታወራትን አንዱንም አልሰማች ።

“ እግዚአብሔርዬ ፥ አንተ ታውቃለህ ! ” አለች አንድ ሰወዬ ወረቀቶች ከመለጠፍያ ጋር ይዞ ወደ ማስታወቂያው ሰሌዴ ሲጠጋ አይታ ።

ሰውዬውን ተከትለው ሁሉም ወደ ሰሎዳው ግር ብለው ተጠጉ ። የፈተናው ውጤት በየትምህርት ዓመታቸው በተለያዩ ሰሌዳዎች ላይ ተለጠፈ። ተማሪ አንዱ በአንዱ ላይ እየተንጠራራ ከሰሌዳው ላይ የመለያ ቁጥሩን መጸለግ ጀመረ።.......

💥ይቀጥላል💥
👍21
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

ቀናት ገሠገሡ። ሳምንታት አለፉ። አሮጌው ሄደ፡፡ አዲሱ መጣ፡፡ የጊዜ
ዑደት ሕግ ሥርዓቱን ጠብቆ በአንድ አቅጣጫ ወደፊት ያመራል።
ህይወት ግን በዝብርቅርቅና በውጣ ውረድ ቀለበት ውስጥ እየተዟዟረች
ትህትና ድንበሩና ሻምበል ብሩክ በላይ በከንፈር ማህተም ያፀደቁትን ቃል
ኪዳን ጠብቀዋው ስለወደፊቱ የትዳር ህይወታቸው በሰፊው መወያየቱን
ከጊዜ ጋር ትራመዳለች::
ቀጥለዋል።
ሻምበል ብሩክ በቤተሰቡ ልብ ውስጥ ዘልቆ ከገባና ዝምድናውን ካጠናከረ በኋላ ያ ቤት ድሮ የትህትና አባት መቶ አለቃ ድንበሩ እያለ የነበረውን የህይወት ሙቀት ቀስ በቀስ መላበስ ጀምሯል፡፡
ይህ አባት አከል የወደፊት የትዳር ጓደኛዋ፤ ወድቆባት የነበረውን የህይወት ሸክም አቀለለላት፤ “አለሁልሽ” እያላት ነው፡፡ ለእናቷ የተጠየቀውን ገንዘብ ከፍሎ ሆስፒታል ተመልሳ እንድትገባ ያደረገ
ዕለት...
“ ለምን ሌላ ሆስፒታል አናስተኛትም ብሩኬ?” ስትለው፡፡
“የመጀመሪያው ሆስፒታል ምን አለን ትሁት?” አላት፡፡
“እሱማ ምንም አላለን፤ አማራጭ እስካለን ድረስ ለምን ሆስፒታል አንቀይርም ለማለት ፈልጌ ነው እንጂ” አለችው መልሳ።
“እንደኔ፤ እንደኔ፤ መጀመሪያ ሲከታተላቸው የቆየው ዶክተር
ቢያክማቸው ውጤቱ ያማረ ይሆናል ባይ ነኝ፡፡ አዲስ ዶክተር ማለት አዲስ ህክምናን ሀ ብሎ እንደመጀመር ነው የሚሆነው፡፡ ይሁን ካልሽም እሺ” አላት ዐይን ዐይኖቿን በፍቅር እያየ።
ከዶክተር ባይከዳኝ ሙሉ ለሙሉ ለመራቅ እንጂ፤ በህክምናው በኩል ተደናቂ ሀኪም መሆኑን ዘንግታው አልነበረም፡፡ ሻምበል ብሩክም ልክ አዜብ እንዳለቻት ሁሉ ህክምናውን የመጀመሪያው ሀኪም
እንዲቀጥል ሀሳብ ሲያቀርብላት ጥያቄዋን አነሳች፡፡
በዚህ ሰዓት ሆስፒታል በመቀየር ከምታገኘው ጥቅም ይልቅ የእናቷን ጤንነት ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲከታተል በቆየው ዶክተር ህክምናውን መቀጠሉ የሚያስገኘው ጥቅም አመዝኖ ታያትና...
“እንግዲያውስ ይሁን” በማለት ተስማማች። ዕድሜ ለሱ። ዛሬ የሰላምና የንፁህ አየር እየተነፈሰች የወደፊት የትዳር ህይወቷን ትልም በመንደፍ ላይ ነች ፤ እናቷ ተገቢውን ህክምና እንድታገኝ የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው። በሻምበል ብሩክ ከፍተኛ ምክርና ጥረት አንዱአለም
ችላ ብሎት የነበረው ትምህርቱን በሚገባ መከታተል ጀምሯል።
ይህ ውጣ ውረድ የበዛበት ህይወቷን ለማስተካከል እንድትችል ማካካሻ ያገኘችበት መልካም እድል
ሊሆንላት፤ የዶክተር ባይከዳኝና
የእንደሻው ጥላ ደግሞ በሄደችበት እየተከተላት፤ ሀሳቧን ጠቅለል አድርጋ
እንዳትተኛ እንቅፋት ከመሆን አልቀረላትም፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ በፍቅሯ እንደተቃጠለ ነው። እንዲያውም እስከመጨረሻው የሱ ሆና እድትቀር የነበረው ምኞቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሳካት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ልዩ ልዩ ስጦታዎች ያበረክትላት ጀምሯል። የዶክተር ባይከዳኝ ጥርስ የሌለው አንበሳነት፤ በህይወቷ ላይ ችግር የማያስከትል በመሆኑ እናቷ ሙሉ ለሙሉ ከበሽታዋ ድና እስከምትወጣ የተለመደውን ከልብ ያልመነጨ ፍቅር እያቀመሰችው ለመቆየት ወስናለች።
ይህንን የወሰነችው ደግሞ ብቻዋን አልነበረም፡፡ ከአዜብ ጋር በደንብ አድርገው ከተወያዩበትና ከተማመኑ በኋላ ነው።
“አዜቢና ለምን ቁርጡን አልነግረውም?” በማለት ስሜቷን ለጓደኛዋ ስትገልጽላት።
“ምን ብለሽ ትሁት?” ስትል ጠየቀቻት።
“በቃ እጮኛ እንዳለኝና እንዲተወኝ ብጠይቀውስ?”
“ሞኝ ሆንሽ እንዴ ትሁት? እንደሱ ብለሽ ብትነግሪው የሚያምንሽ ይመስልሻል? ጠልተሽው የደረብሽበት ነው የሚመስለው፡፡
በዚህ ላይ ይሄ ሁሉ የስጦታ ግርግር ፍቅር መሆኑን አትርሺ!!
ምን ቸገረሽ ለትንሽ ጊዜ ብትታገሺ? ፍቅር የያዘው ሰው ፍቅሩን ለሌላ አሳልፎ መስጠት ስለማይፈልግ ሌላ አፈቀርኩ ብለሽ ብትነግሪው ጥሩ አይመጣም፡፡ ያፈቀረ ብዙ ነገር ከማድረግም ወደኋላ አይልም፡፡ አቅሙን እንደሆነ የምታውቂው ነው፡፡ ጉዳት እስካላስከተለብሽ ድረስ ማሚ ድነው እስከሚወጡ እየሸወድሽው ብትቆዪ ምናለበት? በዚህ ላይ ታዋቂ ሀኪም ነው” ስትል አማከረቻት።
እሱን በአሁኑ ሰዓት ማጣት ጉዳት እንጂ ጥቅም ስለሌለው ከሻምበል ብሩክ ጋር ጋብቻቸውን እስከሚፈጽሙ ድረስ ግንኙነታቸው እንደነበረ እንዲቀጥል ተስማሙ።
በተቻላት መጠን ግን ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማርገብ ጥረት እንድታደርግ፤ ቀስ በቀስ የግንኙነት ገመዱን ለማላላት እየቀጠሩ መጥፋት፤ ሲገናኙ መለማመጥና ምክንያት እየሰጡ
በአጭር ጊዜ ውስጥ ላለመገናኘት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ በዚህ
ውስጥ እንዲጠቃለሉ በስፋት ተማከሩበት። በዚሁ መሠረት ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ለረጅም ጊዜ ሳይገናኙ
ቀሩ። ለረጅም ጊዜ ያለመገናኘታቸው ደግሞ እንደግምታቸው ተስፋ የመቁረጥና የመረሳሳትን አዝማሚያ ከማሳየት ይልቅ ' ዶክተር በናፍቆት
ተጠብሶና፤ በፍቅር ተቃጥሎ፤ እንዲጠብቃት አደረገው፡፡ሻምበል ብሩክ አስፈላጊውን ክፍያ ሁሉ ፈጽሞ እናቷን
ሆስፒታል ባስገባችበት ዕለት ተገናኙ። እናቷ በገንዘብ እጥረት ምክንያት
ከሆስፒታል እንድትወጣ ሲደረግ! ስለገንዘብ ከሆነ አለሁልሽ ብሏት
ነበር፡፡ በክፍያ ችግር ምክንያት መሆኑን ልትገልጽለትና በሽንፈት እጇን
ስላልፈለገች... “ለገንዘቡ አይደለም ዶክተር፤ እናቴ ከሆስፒታል ወጥታ በቤት ውስጥ ለመታከም ስለፈለገች ነው
” በማለት ነበር መልስ የሰጠችው::
አሁን እናቷን ሆስፒታል መልሳ ማስተኛቷን ሲያውቅ ቶሎ ቶሎ ለመገናኘት እድል ይፈጥርለታልና በጣም ተደሰተ፡፡ እሷ ግን ይህንን አልወደደችውም።ሻምበል ብሩክ ግንኙነታቸውን እንዳይደርስበት ሰጋች።
ሆኖም እሱን ከማንኛውም ጥርጣሬ ነፃ የምታደርግበት የራሷ ማረጋገጫ
አላትና፧ ተጽናናች። ሁሌም ለእሷ ንፁህ የመሆን ማህተሙ አብሯት እስካለ ድረስ ዶክተር ባይከዳኝ የእናቷ ሀኪም ከመሆኑ ባሻገር ሌላ ጉዳይ ይኖራቸዋል ብሎ እንደማይገምት ተማምና፤ ከዶክተር ጋር ያላትን ቀዝቃዛ ግንኙነት ቀጠለች።
ይህ ሁኔታ በዚሁ ቀጥሎ ሳለ፤ አንድ ቀን ሻምበል ብሩክ በፖሊስ መምሪያ የተካሄደውን ስብሰባ ተካፍሎ፤ ምሳውን ከበላ በኋላ፤ ወደ ቢሮው ለመመለስ የያዛትን የመንግስት መኪና በሚያሽከረክርበት ወቅት አዲስ ነገር ተፈጠረ።
ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ሆኗል።
ብሔራዊ ቲያትር አካባቢ ነው። የትራፊክ መብራት ይዞትእንደቆመ፤ በስተቀኝ በኩል ከፊት ለፊቱ ቀደም ብላ የቆመችውን ነጭ
ኦፔል መኪና እንደዋዛ በዐይኖቹ ገረፍ አደረጋት።
በዚያች መኪና ውስጥ እንደዋዛ ያየው ነገር የትኩረት ስሜቱን ሳበውና፤ መኪናውን ቀስ ብሎ ትንሽ ወደፊት በማንቀሳቀስ ተጠጋ፡፡ፍጹም ሊሆን የማይችል ነገር ነው። አእምሮው ሊጠረጥረው የማይችለውን
ነገር በማየቱ፤ አይኖቹን ተጠራጠረ። የሚያየውን እውነታ ህሊናው በቀላሉ ሊቀበልለት ስላልቻለ፤ ቀይ መብራት በርቶ
መኪኖች ሲለቀቀቁ እንኳ አልታወቀውም ነበር። የሚያየው ነገር እውነት መሆኑን፤ አይኖቹ የሚያሳዩት የሌለ ነገር ሳይሆን፤ ያለውን ሀቅ መሆኑን፤ ሲረዳ ግን፤ ጭንቅላቱ በከባድ ነገር እንደተመታ ሁሉ፤ ክው ብሎ ደርቆ ቀረ።
በሚያየው ነገር ምክንያት ሰውነቱን ማተኮስ ስለጀመረው! የመኪናውን የበር መስታወት ወደታች ዝቅ አድርጎ ንፋስ አስገባ፡፡ በዚያች መኪና ውስጥ ያለቸው ትህትና ድንበሩ መሆኗን
ሲያረጋግጥ፤
መኪናውን የሚያሽከረክረውን ሰው ማንነት ለመለየት ፈለገና አተኩሮ
ተመለከተው፡፡ ያውቀዋል። ዶክተር ባይከዳኝ ነው።ጉድ ፈላ! ስራውን ትቶ የዚህን ተአምር ማብቂያ ሊከታተል
ወሰነ። መብራቱ አረንጓዴ በርቶ ሲለቀቁ ነጫን ኦፔል መኪና ተከትሎ ያሽከረክር ጀመር ክትትሉ እንዳይታወቅበት
🔥2👍1
በጥንቃቄና በርቀት እየነዳ አደኑን ቀጠለ፡፡
ሻምበል በጭንቅላቱ ውስጥ የማይመላለስበት የጥያቄ አይነት
አልነበረም። አታላይ ናት ማለት ነው? እሱ ዶክተር እኔ ወታደር በመሆኔ ወደሱ መገልበጧ ነው ማለት ነው? የእናቷ ሀኪም ስለሆነ ነው ወይንስ ከኔ በፊት ይተዋወቁ ነበረ ማለት ነው? ከኔ በፊት ከሆነስ እስከዛሬ ድረስ እንዴት ልጃገረድ ልትሆን ቻለች? ልጃገረድ ነኝ እያለች
ስትጫወትብኝ ነው? ወይስ ከኔ በኋላ እየተቀላጠፋት ይሆን? ዘመድ
እንዳይባል ስለዚህ ጉዳይ ምንም የነገረችኝ ነገር የለም። ምን ሊሆን
ይችላል? አቅጣጫዬ ወዴት ነው? እርምጃዬስ? ራሱን የማይጠይቀው
ጥያቄ አልነበረም::
እንደዚህ በሃሳብ ተጨንቆ ሲከተላቸው፤ ወደ ስድስት ኪሎ አቀኑ። እሱም አብሮ አቀና፡፡ ከዚያም ዶክተር ባይከዳኝ ሽሮ ሜዳ ሲደርስ፤ ዋናውን መንገድ ለቀቀና ወደ መኖሪያ ቤቱ ታጥፎ ይዟት በመግባት የመኪና ጥሩምባ ሲያሰማ፤ ሠራተኛዋ የአጥሩን በር ከፈተች።
ትህትናን ምሳ ጋብዟት እየተመለሱ ነበር፡፡
ሻምበል ከመኪናው ወርዶ ቀስ ብሎ ወደ አጥሩ በመጠጋት በቀዳዳ አጮልቆ ይመለከት ጀመር። ከመኪና ወርደው እጅ ለእጅ ተያይዘው በደስታ እንደሲካካ ዶሮ እያስካካች፤ አብራው ስትገባ ተመለከተ፡፡
በፍጹም ፍቅራቸው የቅርብ ጊዜ እንዳልሆነ ገመተ።
“ወይኔ ብሩክ?” አለ። የውጩን በር የከፈተችውን የቤት ሠራተኛ አያት፡፡ ከትህትና ጋር ተሳሳሙ::
“ይህችን ይወዳል ብሩክ?! ቤተኛ አይደለችም እንዴ?' አጭር ቀሚስ ነበረ የለበሰችው፡፡ እንደ እምቦሳ ጥጃ እየቦረቀች ገባች::
“ወይኔ ብሩክ? ወይኔ ሰውየው!” አንጀቱ ጨሰ፡፡ የሰራ አካላቱ ተቃጠለ፡፡ እስከመቼ ድረስ የበይ ተመልካች ለመሆን? በቃ ስታታልለኝ ነው የከረመችው ማለት ነው! ይህችን ብሎ ልጃገረድ! አስመሳይ! መሰሪ! ግድ የለም ጉዱ ይለያል! የውሸት ልጃገረድነቱ ታሪክ በቅርብ ጊዜ ውስጥ
ገሀድ ይወጣል! በዚያን ሰዓት ግን እሷን እያድርገኝ አልለቃትም!
በህይወቴ ላይ ተጫውታብኛለች፡፡ የዋህ ልቤ ላይ መርዟን ነስንሳበታለች።
ጅል በሬ አድርጋኛለች፡፡ እኔ ግን በሬ አይደለሁም!!
ያ ሁሉ የውሸት ዘፈን፤ ያ የመጀመሪያ ምሽት፣ አብረው ሲዝናኑ ያደሩበት ሌሊት፤ እንደኮሶ በሚመር ትዝታ እፊቱ ላይ ድቅን
አለበት። አቤት አታላይነት? አቤት ስትችልበት? ደግሞ ጠዋት ላይ ምን
ነበር ያለችው? ለሠርጋችን ዕለት ብለህ ነው የተውከው?' አጭበርባሪ
ሸርሙጣ!! አልምራትም አይማረኝ !። አለና ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ደሙ እየተንተከተከ፤ ከመኪናው ውስጥ ተመልሶ ገባና፤ በሃይል አላትሞ በሩን ዘግቶ፤ ሞተሩን አስነሳ፡፡ከዚያ በፊት ሻምበል ብሩክን የሚያውቀው ሰው አሁን ቢያየው እሱ ነው ብሎ ለማመን ይቸገራል፡፡ የቆሰለ አውሬ ሆኗል፡፡ ፊቱም ሳምባ መስሏል ዐይኑም ደም ጎርሰዋል። በአጠቃላይ ያስፈራራል። ያ ሳቂታውና ተጫዋቹ ሻምበል ብሩክ ሳይሆን ተቃራኒውን ሆኗል፡፡ በቀጥታ መኪናዋን ይዞ ወደ መሥሪያ ቤት ከመሄድ ይልቅ፤
ወደ ኮተቤ መስመር ተፈተለከና እዚያ ዳገቱ ላይ ካለው ኮረብታማ ስፍራ
ላይ ከተሰራ አንድ ሆቴል ገብቶ ለዚያ ለንዴቱ ማስታገሻ እንዲሆነው ውስኪ አዘዘ።
እንደዚያ ካልሆነ በስተቀር አእምሮው በንዴት አብጦ የሚፈነዳ ስለመሰለው ለዚህ ሁሉ ማስታገሻ ይሆናል ብሎ የገመተውን ውስኪ ደብል ደብሉን ይገለብጠው ጀመር።እውነትም ያ ውስኪ ቀስ በቀስ የስቃይ ስሜቱን ያስወገደለት
መሰለው። ሞቅ እያለው ሲመጣ፤ ያንን የሚያሳብድ ድርጊት እንደዋዛ እያሰበ እራሱን ማረጋጋት ቀጠለ፡፡ እዚያ ባንኮኒው ውስጥ የቆመች ድንቡሽቡሽ ቆንጆ በሳቅ ስትፍለቀለቅለት፤ ትኩር ብሎ ሲመለከታት ከቆየ በኋላ ጠራት።
መቼም መቀመጫዋ የአንድ ሰው ብቻ ነው ማለት ያስቸግራል፡፡ እያገላበጠችው መጣች፡፡
“ተጋበዥ” አላት:: ሃሳቡን ሳይቀይር ቶሎ ብላ የአልኮልጠርሙሶች ወደ ተደረደሩበት መደርደሪያ ሄዳ ውስኪ ቀድታ መጣችና አጠገቡ ቁጭ ካለች በኋላ ትሽኮረመም ጀመር፡፡
ከወዲያ ጥግ ሁለት ሰዎች እየጠጡ ይጨዋወታሉ እነሱን ዞር ብሎም አላያቸው:: የዚያች አጠገቡ የተቀመጠች አስተናጋጅ የጭኖቿ ውፍረት እንዲህ ቀላል አልነበረም፡፡ አጭሩ ቀሚስ ወለል አድርጎ የተጋጠሙ ጭኖቿን ያስጎበኛል።
ልጃገረድ ነኝ ባይዋ እስካታለለችው ቀን ድረስ ከሴት ልጅ ገላ ለብዙ ጊዜ ርቆ ነበር፡፡ ያቺ አጭበርባሪ! ያቺ ሸርሙጣ ፤ያንን ስሜቱን፣ ያንን የተዳፈነ ፍላጐቱን ቀስቅሳ፤ ውሸቷን ያንተው ነኝ እያለች
ስታታልለው፤ ስትጫወትበት፤ ቆይታለችና ያ የተዳፈነ የወሲብ እሳት እንዲነድ፤ እንዲንቦገቦግ፣ እዚህ አጠገቡ የተቀመጠች የቀይ ዳማ እኒያን ጋባዥ ጭኖቿን በሰፊው ስታስጎበኘው፤ ከሞቅታው ጋር ተደፋፍሮ:ጣቶቹን ወደ ጭኖቿ መሀል አሳረፈና ለስላሳ ገላዋን ነካካት፡፡
ያ ለስላሳ ገላዋ ከኤሌክትሪክ አስተላላፊ ገመድ እንደተሰራ ሁሉ ፧የሚነዝር ሙቀቷን በፍጥነት ወደ እንደ ኤሌክትሪክ የሚነዝር ሙቀቷን በፍጥነት ወደ ቀሪ አካሉ
ሲያስተላልፍለት፤ የሱም አካል በፍጥነት ሞቀና አብሯት ሊጫወት ፈለገ።

ለዚህ በንዴት ለሚቃጠለው ገላው መድሃኒት እንዲሆንለትና እፎይታ ለማግኘት፣ ትህትናም ሆነች ይህች አጠገቡ ያለችው አስተናጋጅ ልዩነት እንደሌላቸው ሲሰማው ጠጋ አላትና፡-
“አልጋ አለ?” ሲል ጠየቃት። እሷም በደስታ ፈንድቃ፡-
“ሞልቷል” አለችው እየተፍለቀለቀች፡፡ ከዚያም ወደ ጓሮ ወጥታ አልጋ የሚያከራየውን ልጅ አልጋ ጠይቃው ተመለሰችና ወደ ሻምበል ብሩክ ጆሮ ጠጋ ብላ...
“ስምንት ቁጥር ገብተህ ጠብቀኝ” አለችው። ሻምበል ከዚያ ግለቱ ሊቀዘቅዝ በፍጥነት ወደ ቁጥር 8 የመኝታ ክፍል ገባ፡፡ ተዘገጃጅታ ብትመጣ፣ ሻምበል ሙሉ እርቃኑን ሆኖ በጉጉት እየጠበቃት መሆኑን ስትመለከት አፈጣጠኑ፣ ገርሟት የመጣባትን ሳቅ ዋጠችና ስሜት የለሹን
ለገበያ የሚውለው ሸቀጥ ገላዋን ልታቋድሰው ሄደችለት።
ውሸቷን በፍቅር የተረታችለት አስመስላ እያቃሰተች ስትስለመለም፤እውነቷን መስሎት፤ በደስታ ተያይዘው ነጎዱ። ከዚያም በረጅም እፎይታ ተነፈሰና ሰውነቱ ቀዝቀዝ አለ።
ያ ጣፋጭ የፍቅር ህይወት ከዚህ ቀን ጀምሮ በሻምበል ብሩክ ልብ ውስጥ ጥቀርሻ ለበሰ፡፡በዚህ ዕለት ሻምበል ብሩክ ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ እቤት ሲገባ
ወንድሞቹም ሆኑ የቤት ሠራተኛዋ ተደናግጠው ነበር። ሲጋት ያደረው
አልኮል ጠዋት እሳቱን ስለለቀቀበት፤ ሠራተኛዋ እንጀራ በሽሮ ፈትፍታ ከሰጠችው በኋላ በዚያው ጋደም ብሎ ትናንትና የሆነውን ሁሉ መለስ ብሎ ሲያስተውል፣ በሠራው ስራ ያፍርበት ጀመር።
ምንም ቢሆን የዚያን ያህል መሳሳት እንዳልነበረበትና ከዝሙት አዳሪ ጋር መዳራቱ ይቅር የማይባል ስህተት መሆኑን በማመን ተፀጽቶ እራሱን ወቀሰ፡፡
“ፖሊስ ነኝ የሠራሁት ስራ ግን የፖሊስ ስራ አይደለም፡፡ ፖሊስ ችኩል መሆን የለበትም። የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል። ለማንኛውም ነገር ፍንጩ ጠቃሚ ቢሆንም፤ ከሀቁ ላይ ለመድረስ ግን እርጋታ እርጋታ እርጋታ ያስፈልጋል አለ ለራሱ፡ እርጋታ ናፈቀችው፡፡ እሷም ምነው ዘነጋኸኝ ሻምበል ብሩክ? ብላ እጆቿን ዘርግታ በርቀት ጠራቸው.....

ንዱቱ ከበረደለት በኋላ ነገሮችን በእርጋታ ለመመርመር፤ በይሆናል ብቻ ስህተት ላይ ላለመውደቅ፤ መጠንቀቅ እንዳለበት
በማመን፤ በዶክተር ባይከዳኝና በትህትና መካከል ያለውን የግንኙነት ደረጃ በትክክል ለማወቅ፣ የድሮ ፀባዩን ሳይለውጥ፤ በዘዴ ሊጠቀም እንደሚገባው ተረድቶ፣ ሚስጥሩን በስውር ለመከታተልና ሀቁን ፈልፍሎ
ለማውጣት ለራሱ ቃል ገባ፡፡

#Share #Share #Share #Share

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
1👍1
#ሰመመን


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ


ተማሪ አንዱ በአንዱ ላይ እየተንጠራራ ከሰሌዳው ላይ የመለያ ቁጥሩን መፈለግ
ጀመረ።

እነ እስክንድር ግርግሩ መሀል ሲደርሱ እነ ማርታ ውጤታቸውን ለማየት ስለ ተበታተኑ ተሰወሩባቸው ። የአንደኛና የሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች ውጤት ብቻ ነበር የወጣው ።

የአራተኛ ዓመቶች ውጤት አልደረሰም እንዴ ? ”
አለው እስክንድር ውጤቱን የለጠፈውን ሰውዬ ሲመለስ አግኝቶት።

"ከሰዓት በኋላ ” ብሎት ሰውዬው እየተደፈ ሐደ ።

“ እስቲ እኔም ጉዴን ልመልከት ”አለ ሳምሶን አስደንጋጭ ድምፁ ስልት አጥቶ እየተንቀጠ።

“ ቆይ ምን አስቸኮለህ ? ግርግሩ ተግ ይበልልህ! ” አለው እስክንድር ።

ሳምሶን አረ ባክህ ! ” ብሎት " ተማሪውን እየገፈታተረ ወደ ልለተኛ ዓመቶች የውጤት ሰሌዳ አመራ።

እቤልና እስክንድር ከግርግሩ መሀል ወጥተው ብቻ ቸውን ቆመው ቀሩ አንዳች ነገር ተጫጭኗቸዋል አይነጋገረም።

ግርግሩን አትረው ይመለከቱ ጀመር » ማንኛውም ነገር ውስጡ ሲሆኑበትና ከውጭ ሲታዘቡት የተለያየ ገፅታ አለው የፈተና ውጤት ግዜ እንዲህ ከሩቅ ሆነው ሲያዩት አሳዛኝ ትርኢት ይታይበታል ውጤቱ የድካም ውጤት ሳይሆን የብሔራዊ ሎተሪ እጣ ይመስላል አንዳንዱ እየሳቀ ሄዶ ውጤቱን አይቶ ሲመለስ ፊቱ ኮሶ ይመስላል በፍርሃት
እየተንቀጠለጠ ሔዶ እየቦረቀ የሚመለስም አለ ውጤቱ አስደንግጦት የቆመበት ዘፍ የሚልም አይታጣም አብዛኛው ተማሪ ስለ ራሱ የነበረው ግምትና አሁን ያገኘው ውጤት እየተራራቀበት ፊቱን አጨማዶ ሲመለስ ነው የሚታየው።
እኔስ ከየትኛው ዐይነት እሆን ? ” ሲል እስክንድር ራሱን ጠየቀ ። የውጤት ጊዜን ሁኔታ እንዲህ በሩቅ ታዝቦ አያውቅም ነበር ።

አንዲት ልጃገረድ በጓደኞቿ ተደግፋ እያለቀሰች በኣጠገባቸው ስታልፍ አይተው የአቤልም የእስክንድርም ልብ
አብሮ አለቀሰ።
አይዞሽ ፡ ዩኒቨርስቲ የሕይወት መጨረሻ አይደለም ” አላት እስክንድር ቀስ ብሎ።

ቀና ብላ አላየችውም ጓደኞቿ ግን ያሾፈባት መስሏቸው ዞረው ገላመጡት ። ግልምጫ ከዐፈር የሚደባልቅ ቢሆን የማይተዋወቁት ሰው ግልጫ ኦሆሆ ! ቶሎ ብሎ ዐይኑን ከአይናቸን አሸሸ ።

ዘወር ሲል ሚስተር ሆርስ ከሶስት ልጆች ጋር ሆኖ ቅልጥሙን እጥፍ እያረገ ፌቱ ፈክቶ ሲያልፍ አየው ።

“ እንዴት ነው ውጤት? ፊትህ ሁሉ ጥርስ ሆኖአል” አለው በሩቁ ከአኳኋኑ ማለፉን ተረድቶ

“ አልሞትንም ፤ ተርፈናል ። የዩኒቨርስቲ ሕይወታችንን አራዝመናል።

« እንኳን ደስ ያለህ ! ” አለውና ፥ “ በቀላሉ የሚደሰት ተፈጥሮ ጥሩ ነው ” አለ በልቡ በድንግት የአቤል ድምፅ አስደነገጠው።

“ ያቻት ትዕግስት"

አቤል ከርቀት ትዕግሥትንና ማርታን ሲያይ ሳያስበው ነው ስሟ ያመለጠው ። በድንጋጤ ስሟን ከመጥራቱ ሌላ
የሚጨምርበት ነገር አልነበረም ።

“ እህ ?” አለው እስክንድርም ደንግጦ "

አቤል ምንም አልመለሰም ። ፊቱ በቅጽበት ተለዋውጦ ከሰል መሰለ ከንፈሩ ተጣብቆ አልላቀቅ አለው ዐይኑ
ፈዞ ቀረ።

እስክንድርም መልስ አልጠበቀም ፥ የአቤልን ዐይን ተከትሎ ትዕግሥትንና ማርታን ተመለከታቸው ውጤታቸውን
አይተው በመመለስ ላይ ነበሩ ። ፊታቸው ዳምኗል ።በኀዘን ተውጠው አንዳችም ቃል ሳይለዋወጡ መሬት መሬት እያዩ ነው የሚሔዱት ። ለእነ አቤል ደግሞ የባሰ
ዳምነውና ተክዘው ታዩአቸው ።

ትዕግሥትና ማርታ እነ አቤልን ሲያዩዋቸውመንገዱቸውን አሳብረው በሌላ በኩል ሔዱ። በማርታ ግፊት ነበር
ይህ የተደረገው። ማንም ሳያያት ወደ መኝታ ክፍሏ መሔድ ነው የፈለገችው ።

አቤል መቆም ኣልቻለም ። ወገቡ የተቀነጠሰ መሰለው። ትዕግሥት ወድቃለች ማለት ነው ? ከዩኒቨርስቲው ልትባረርና ሊያጣት? ስለ ራሱ ውጤት አንዴም አላሰበ መለየት የሞት ያህል ሆኖ ታየው ።

ቃላት መተንፈስ ፈለገ ግን ከንፈሮቹ አልላቀቅ አሉት እርዳታ በሚጠይቅ አመለካከት እስክንድርን አየው ። ከተረታ ወይም ከደከመ ልብ ብቻ ነው የዚያን
ዐይነት እይታ የሚመነጨው።

“ ምን ልርዳህ ? ” አለው እስክንድር ' ሁኔታው ስለ ገባው።

አቤል ምንም ሳይመልስለት ፡ በሚስለመለም ዐይኖቹ እያየው ቀስ ብሎ አጠገቡ ያገኘው ነገር ላይ ቁጭ አለ።

እስክንድር በሐሳቡ አሁን ምን በወቅንና ነው ? ” አለ ። “ ምናልባት እነዚህ ልጆች ሳይወድቁ በዝቅተኛ ማርክ ብቻ እንደሆነስ የተከዙት ? ለምን ተከትዬአቸው ሔጂ አልጠይቃቸውም ? እነሱ ቢሸሹኝ ተናደው ይሆናል። እኔ
ግን ሔጄ ጠይቄአቸው ወድቀውም ከሆነ ማጽናናት አለብኝ ካለዚያ የመተዋወቅ ትርጕሙ ምንድን ነው ? ” አለና አቤልን የተቀመጠበት ትቶት ሔደ ።

ከሁለቱም ከማዘኑ ሌላ የእንድም ቀን የጫዋታ ትዝታ ቢሆን መጥፎ ነውና ከማርታ ጋር የመለያየቱ ነገር እሱንም ቅር ብሎት ነበር ።

ፈጥኖ ሔደ። ሲደርስባቸው ቀድማ ያየችው ትዕግሥት ነበረች ። በደካማ ፈገግታ ሰላምታ ሰጠችው ። ማርታም
እሷን ተከትላ ዘወር ስትል አየችው ። ሰላምታ ልትሰጠው ብትፈልግም ፈገግ ማለት አልቻለችም ።

እስክንድር አጠገባቸው ከደረሰ በኋላ ስለ ውጤታቸው መጠየቅ ፈርቶ ከንፈሩ ይንቀጠቀጥ ጀመር ።

“ እንዴት ነው ? ” አላቸው ፡ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ፥ አንዴ ወደ ማርታ አንዴ ወደ ትዕግሥት እየተመለከተ ።

“ ዩኒቨርስቲያችሁን ለቀቅኩላችሁ እናንተው ኑሩበት!” አለችው ማርታ ቀድማ መንፈሷ ቢደክምም ምላሷ አልሞትም ነበር ።

“ ምነው ? ውጤቱ መጥፎ ነው እንዴ ? ”
ኤጭ ! ”
ከንፈሩን መጠጠና ወደ ትዕግሥት ዞሮ ' “ የአንቺስ ውጤት እንዴት ነው ? ” ሲል ጠየቃት ።

ጥሩ ነው ። በመካከለኛ ውጤት አልፌአለሁ ” አለችው በፈገግታ ።

“ እንኳን ደስ ያለሽ ! ዋናው ማለፍሽ ነው!!” አለና እሱም ፈገግ ብሎ እንደገና ጨበጣት ።

ማርታ ሁለቱንም በቅናት አስተያየት ላጠቻቸው "ዐይን የሚገድል ቢሆን ሁለቱም የቆሙበት ክው ብለው ቀርተው ነበር ።

እስክንድር ደስታና ኀዘን መሐል ገብቶ ወደ የትኛዋ 'እንደሚሆን ግራ ገባው ። “ ግማሽ ፊትን አጥቁሮ፡ ግማሽ ፊትን ማሣቅ ቢቻል እንዴት ጥሩ ነበር !” አለ በልቡ ።

ማርታን ፊት ለፊት ሊያያት አልደፈረም ። ቀስ ብሎ በስርቆሽ ተመለከታት የጠወለገች አበባ መስላለች ለካ ውበት የስሜት ነጸብራቅ ነው?” አለ በሐሳቡ ። ስሜቷ ከውስጥ ሲንድ ፡ሲቃጠል ሲብከነከን ታየው ድርብ የከንፈር ቀለሟ በመጠውለጉ ፊቷ ላይ ጎልቶ ምናምን
የላሰች አይጥ አስመስሏታል ። ቅንድቧ ብቻ እንደ ወትሮው ይርገበገባል ።

እስክንድር የቅንድቧን መርገብገብ አይቶ ወሬ እንደምትፈልግ ዐወቀ ። ግን ምን ዐይነት ወሬ ? በእሷ መውደቅ ምክንያት ተማሪውንና አስተማሪውን ማማት መቦጨቅ ? አይዞሽ ማርታ ዩኒቨርስቲ የሕይወት መጨረሻ አይደለም ” አላትና ፡ አንድ ቀን ያጫወተችውን አስታውሶ : “ ደሞም ከዚህ ወጥተሽ ስኮላርሽፕ መጠበቅ ትችያለሽ ” አላት ።

“እኔ ማርታ ጉዳዬም አይደል ! ብቻ እንኳን ዩኒቨርስቲ የምትሉትን አየሁላችሁ !
እስክንድር በልቡ “ እኛ ደሞ ምን አደረግንሽ ? " ብሎ ጭጭ።

“ የማትስ አስተማንሪኮ ነው ጉድ ያረገኝ ” አለች ትንሽ ቆየችና።

“ እሱ "F" ባይሰጠኝ ኖሮ ሌላ ትምህርት አልጎዳኝም ነበር።

“ ማነው እሱ? ” አላት ያስተዛዘናት መስሎት

“አቶ ኃይሉ የሚሉት አንድ ሽማግሌ አለ " ላውጣሽ ብሎኝ ስለ ዘጋሁት ቁጭቱን ተወጣብኝ ”

“ ያሳዝናል ! ” አለ እስክንድር ፡ ውሸቷ ኮርኩሮት በህዱ እየሳቀ።

ደሞ ከእሱ ጋር ልውጣ እንዴ? ቅሌታም ሽማግሌ ! ”፥

እስክንድር እንደገና ከንፈሩን
1