አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
በኋላ ልብሶቿን ቀያየረች። የዛሬው ደስታ እውነተኛ ደስታ እንዲሆን፣ ቆንጆ እራት መስራት እንዳለባት ወሰነች፡፡
“አንዱዬ ተነስ ሥጋ ገዝተን እንምጣ” አለችው። አንዱ ዓለምም በደስታ ብድግ አለና ተያይዘው ወጡ፡፡
መደዳውን ከሚታዩት ልኳንዳ ቤቶች መካከል ከየትኛው እንደሚገዙ ለመወሰን ሲያማትሩ...
"ነይ ቆንጂት ምርጥ የሀረር ሰንጋ ነው” አላት አንድ ነጭ ካፖርት የለበሰ ወጣት የሉካንዳ ሠራተኛ የተሰቀለውን ስጋ በቢላዋ እየነካካ፡፡
መደዳውን የተሰቀሉት ብልቶች በሙሉ ሦስት መቶ ሻማ መብራት እላያቸው ላይ ነዶባቸው ያብለጨልጫሉ፡፡ አንዳንድ ሥጋ ቤቶች ሥጋውን ሆነ ብለው ቅባት ይለቀልቁታል፡፡ እንዲያብለጨልጭ...
እንዲያብረቀርቅ... ዐይን እንዲስብ፡፡ በቁም የትኛው ጥሩ ከብት እንደነበረ
የሚያውቀው አራጁ እንጂ ትህትናም ሆነች ወንድሟ በዚህ ረገድ ልምዱ
አልነበራቸውም፡፡ ወደ ጠራቸው ልኳንዳ ቤት ጎራ አሉ፡፡
“ልክ እንዳንቺ ቆንጆ ሥጋ ነው” አላት፡፡ መቼም ለገበያ ሲባል የማይሰጥ ምሳሌ የለም::
ሰውና ሥጋን እንዴት አመሳሰልከው እባክህ?” አለው አንዱአለም በቀልድ መልክ፡፡
“ልክ እንደናንተ ለዐይን ደስ የሚል፤ ሲበሉት ደግሞ ኬክ የሆነ ሥጋ ነው ማለቴ ነው” አለና ትንሽ ፈገግ በማለት እነሱንም ገበያውንም አንቆለጳጰሰ፡፡
“በል እስቲ ከሱ ከሽንጡ ሁለት ኪሎ” አለችው። በእውነትም ጥሩ ሥጋ ደህና አድርጐ ሳይሽቅባቸው ሰጣቸው፡፡ የዛሬው ቀን በእውነትም ልዩ ነው፡፡ የሥጋ ዘር ካዩ ድፍን አሥራ አምስት ቀናቸው
ነበር፡፡
ያንን ሥጋ በልዩ ልዩ ዓይነት ሠራችው። እጅ የሚያስቆረጥም አድርጋ እየተጨዋወቱ ፤እየተጎራረሱ፤ ከተመገቡ በኋላ ሊተኙ አካባቢ...
“ብሩኬ ይዘሽው ነይ ብሎኛል እኮ!” አለችው ለአንዱዓለም፡፡
“ብሩኬ” የሚለው ቁልምጫ ምን ማለት እንደሆነ ወዲያውኑ ገባው::
እንደ እውነቱ ከሆነ ትህትና ሻምበል ብሩክን ብታገባው የሚል ስሜት ካደረበት ውሎ አድሯል፡፡ ያንን ሲኦል የሆነ እስር ቤት ደግሞ አድሮበት ቢሆን ኖሮ ምን አይነት የሞራል ውድቀት ይደርስበት
እንደነበረ ሲያስበው ይዘገንነዋል፡፡ እነዚያ ቢወረወሩ ሰው የሚፈነክቱ እንደ ጥጥ ያባዘቱት ተባዮች ደም እንባ አስለቅሰውታል። ክርፋቱ አይረሳውም ፡፡ከዚህ ሁሉ ነጻ ያወጣው ሻምበል ብሩክ ነው፡፡ ግርማ ሞገሱ የሚያኮራው፣ ደስ የሚል፤ ሳቂታውና፤ ተጫዋቹ ሻምበል ብሩክን ልቡ ስለወደደው፤ እህቱ ብታገባውና፤ የቤተሰብነት ዝምድናን ቢመሰርቱ ደስታው ወደር አልነበረውም::
ሻምበል ብሩክና ትህትና በጣይቱ ሆቴል ሆነው ሲጨዋወቱ
ያልተወያዩበት ርዕስ አለ ማለት አይቻልም፡፡ በተለይ ስለጓደኛዋ አዜብና
ስለአንዱ ዓለም ስታጫውተው በሚቀጥለው ፕሮግራማቸው ላይ
ሁለቱንም ይዛቸው እንድትመጣና የምሳ ግብዣ እንደሚያደርግላቸው ነግሯታል፡፡
ከሻምበል ብሩክ ጋር የፍቅር ሀሁ መጀመሯን፤ ከዚያም በላይ እዚያ አጥራቸው አጠገብ ምን እንዳደረጉ ሁሉ ለአዜብ ልትነግራት ቸኩላ ነበር።
መቼ ነው ይዘሽው ነይ ያለሽ?” አላት አንዱዓለም በጉጉት፡፡
የዛሬ ሣምንት የትም እንዳትሄድ እሺ? የምሳ ግብዣ አለህ” አለችው፡፡ አንዱዓለም በጣም ተደሰተ፡፡ ቀጠሮው ናፈቀው፡፡ ከዚያም እሱ ወደ ድንክ አልጋው ሲሄድ እሷ ደግሞ ወደ እኗቷ አልጋ ሄደች፡፡
ጠዋት ወደ ሥራ ከመሄዷ በፊት ለአዜብ ስልክ ደወለችላት፡፡
“ልነግርሽ አልችልም በቃ ሆነ!” በሳቅ እየተፍነከነከች፡፡
ትሁቲና አትይኝም!” አዜብ በነገሩ ተደንቃ ጠየቀቻት፡፡
“አዜቢና ሙች! ልክ እንዳልነው”
“ውይ ታድለሽ ትሁት” የበለጠ አደነቀችላት። ስለነበረው ሁኔታ ጫፍ
ጫፉን ነገረቻት፡፡
ትህትና አንድ አጋር በማግኘቷ፣ የኑሮ ቀንበር ያጎበጠው ወገቧን ቀና
የሚያደርግላት፤ ስታዝን፤ ስትተክዝ፤ አለሁልሽ የሚላት አለኝታ በማግኘቷ አዜብ ደስታውን አልቻለችም።
“አዜቢና ሳምንት የምሳ ግብዣ አለሽ ! አስተዋውቂኝ ብሎኛል፡፡ ሌላውን
ደግሞ ሀሙስ ዕለት እቤት መጥቼ አጫውትሻለሁ። ቻዎ!”
እሽ ትሁት በናፍቆት እጠብቅሻለሁ፡፡ ቻዎ!” ያንን እስከ ዛሬ ድረስ ለማንም ተሸንፎ የማያውቀውን የጓደኛዋን ልብ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሸነፍና መማረክ የቻለውን ሰው ለማየት ጓጓች....
በሥራ ላይ ከቆየች በኋላ የምሳ ሰዓት ሊደርስ አካባቢ አበራን አስፈቅዳ ወጣችና ለሻምበል ብሩክ ስልክ ደወለችለት፡፡ በስልክ ተጨዋወቱ፡፡ በቃ ፍቅር ሥሯን እየሰደደች መጣች፡፡ ድምጹን ካልሰማች
ቅር ቅር ይላት ጀመር፡፡ በየደቂቃው ብትሰማው ምንኛ ደስ ባላት? እሱም
ሳምንቱን ሙሉ ሲደዋወሉ ከቆዩ በኋላ ክፉኛ ተነፋፍቀው፤ የቀጠሮአቸው ቀን ደረሰላቸው፡፡ አዜብና አንዱአለም የዛሬው የክብር እንግዶች በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት አብረዋት ሄዱ።
ቀጠሮአቸው በጥሬ ሥጋና ጎድን ጥብስ ዝግጅቱ በታወቀው በመተባበር ሆቴል ነበር። በዚያን ዕለት ሻምበል ብሩክ ሱፍ ለብሷል፡፡ ክራቫትም አስሮ ነበር። አቦ እንዴት ነበር ያማረበት? ትህትና ስታየው
የበለጠ በደስታ ሰከረች። የደንብ ልብሱ ብቻ መስሏት ነበር፡፡ ይሄኛው ደግሞ ጭራሽ ልዩ ሆነባት፡፡ ሄዳ እቅፉ ውስጥ ስትወድቅ በከንፈሩ ተቀበላት።
ፍቅራቸው ገደብ አጣና፤ በጓደኛዋና በወንድሟ ፊት ሳማት፡፡
ደንታም አልሰጣቸው፡፡ አዜብና አንዱአለም ትንሽ እንደማፈር ብለው ማዶ
ማዶውን አዩ።
ባልሳሳት አዜብ ነሽ” ቀልጠፍ ብሎ እጁን እየዘረጋላት፡፡
አልተሳሳትክም አዜብም ሳቅ እያለች።
“አንዱ ዓለም ጋር እንኳ በሚገባ እንተዋወቃለን” እቅፍ አደረገው።
አንዱዓለም ደስ አለው። ብቻ ሻምበል ብሩክ ሳቂታና ተጫዋች ስለሆነ
የሰውን ልብ በቀላሉ የመማረክ ችሎታ አለው፡፡
የሀረር ሰው ለሳቅና ጨዋታ የታደለ መሆኑ ይነግርለታል፡፡ለዚህ ነው መስል፤ ሻምበል የዚህ ዓይነት ባህሪ ይንፀባረቅበታል።
አይከብድም፡፡ አዜብም አንዱዓለምም በሱ ሁኔታ ነፃነት ተሰማቸው።አዜብ በዝና ከምታውቀው የበለጠ የምታየው ሻምበል ብሩክ ማረካት፡፡
“እንዴት ዓይነት እድል ነው የገጠማት?” በጓደኛዋ ጥሩ ዕድል ቀናች፡፡
ለምን እንደቀናች ግን እሷም አልገባትም። የምትወዳት ጓደኛዋ ናትና።
ብሩክ ወዲያውኑ “አዜቢና” እያለ መጫወት ጀመረ፡፡ የቁልምጫን ስም በአንድ ቀን መጥራት ይከብዳል፡፡ ለብሩክ ግን ይህ ቀላሉ ነው፡፡
ሁሉም ነገር በሚያስደስት ሁኔታ ቀጠለ፡፡ ጨዋታና ሳቁ ደራ። ፍቅር በፍቅር ሆኑ።
ትህትና ይህንን የመሰለ ጠንበለል የሰጣት አምላክ ችግሯን አይቶ ሊክሳት መሆኑን አመነች። በዚህ መሃል አንዱአለም እስር ቤት የገባበት ምክንያት በርዕስነት ተከፈተና መወያየት ሲጀምሩ.

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_አርባ ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና ከዚያም ትንሿ ልቧ ከውስጥ... በደስታ!! እየዘለለች እየጨፈረች...እሷ ደግሞ ከላይ....እየተሸኮረመመች... እየተቅለሰለሰች ...እየተፍለቀለቀች .... ቀረበችው፡፡ ከቀኑ አስራ ሁለት ሰዓት ሆኖ ነበር:: በፍቅር መረታቷ ሌላው ችግር ቢሆንም፤ ሻምበል የምትወደው ታናሽ ወንድሟን ዋስ ሆኖ ያስፈታላት ባለውለታዋ ጭምር ነው::…»
Forwarded from አትሮኖስ (፲፬)
👉 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉​​ ግለ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ማግባት ይችላልን?
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

በእነዚህ ትምህርቶች ዙርያ እየተማማርን እንገኛለን እርሶም እውቀቱ እንዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን መስፈንጠርያ ይንኩ👇



https://xn--r1a.website/joinchat/9UhoYGd7ODFhMmM0
https://xn--r1a.website/joinchat/9UhoYGd7ODFhMmM0
1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በትክክል_ገና


ውድ አንባብያን ከላይ በለቀቅናቸው ሁለት ክፍሎች ላይ ማለትም 39, እና 40 ያልነው በስተት ነው ክፍል19 እና 20 ናቸው ስለተፈጠረው ስተት ይቅርታ እየጠየቅን በቀጣዩ ክፍሎች ላይ እናስተካክላለን..የቁጥር ስተት ብቻ ነው እንጂ የክፍል መቆራረጥ የለውም። መልካም ንባብ።
=========================
....“እኔና አንተ ሌላ ቀጠሮ ይኖረናል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ አድርገን
እንወያያለን እሺ?” አለው፡፡ አንዱ አለም በደስታ ተቀበለው። ርዕሱ ተቀየረ፡፡

ምሳው አብቅቶ የሚጠጣ ነገር ሲታዘዝ፤
አንዱአለም ቢራ፤ አዜብና ትህትና ደግሞ ጭማቂ፤ አዘዙ፡፡ በወንድሟና በጓደኛዋ ፊት በመሆኑ እንጂ ከሻምበል ጋር ብቻ ብትሆን ኖሮ በዛሬው የፌሽታ ቀን ቢራ ትጠጣ ነበር፡፡ እድሜ ለዶክተር ባይከዳኝ ቢራ አለማምዷታል፡፡
ሻምበል ብሩክ ለትህትና የሆነ ነገር በጆሮዋ ሹክ አላት::
እንዲያ ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብሎ ፤ በግራ ክንዱ ትከሻዋን እቅፍ አድርጎ፤አዜብ ስትመለከት በድጋሜ ቀናች፡፡ እንደዚህ ያፈቀረችው እና ያፈቀራት ሰው አጋጥሟት አያውቅም፡፡ የሷ ጓደኞች የሳምንት ግፋ ካለ የአንድ ወር ብቻ ናቸው፡፡ ችግሩ ከማን እንደሆነ እራሷን እየጠየቀች እስከዛሬ ድረስ መልስ ያላገኘችለት ጉዳይ ነው፡፡ አብዛኞቹ “አዜቢና አዜቢና” እያሉ
እያቆላመጡ ይጠጓትና፤ ከአንድ ቀን ግብዣ በኋላ በሁለተኛው ቀጠሮ
ላይ ጨርቅ ተጋፍፈው፤ በዚያው እብስ ብለው ይጠፋሉ፡፡ እንደውነቱ ከሆነ እሷም ወረተኛ ነች፡፡ በተለይ መኪና ላለው ወንድ ልቧ ይደነግጣል። ለሚያዝናና፤ ለሚያንሸረሽር፤ ልቧ ክፍት ነው። እግረኛው ብዙም አይስባትም፡፡

“አዜቢና ከቦይ ፍሬንዷ ጋር ለምን አልመጣችም?” በማለት ነበር ሹክ ያላት፡፡ ትህትና ሣቅ አለችና...
“ በሚቀጥለው” አለችው፡፡ የሚያወሩት ስለእሷ እንደሆነ ጠርጥራ አዜብ
ትህትናን ጠቀሰቻት፡፡ እሷም መልሳ ጠቀሳቻት። ተጠቃቀሱ። አዜብ
ስለእሷ የምታውቀውን ያህል እሷም ስለአዜብ ታውቃለች፡፡
የሆቴል ልብስ የለበሱት አስተናጋጆች በጎደለ ለመሙላት ሽር ጉድ ይላሉ፡፡ ሻምበል ብሩክ እናቷን ለመጠየቅ መፈለጉን ገልጾ ያሳወቃት ወደ ማምሻው ላይ ነበር፡፡ ሻምበል ይህንን ያልጠበቀችውን እጅግ አስደሳች
የሆነ ሀሳብ ሲያቀርብላት በደስታ ተውጣ ቀና ብላ አየችው:: ፈገግ አለና
ወደ ጎን ተመለከታት፡፡
“ተያይዘን ወደ ቤት” አላት፡፡ ለዚህ ንግግሩ ካሳ ከንፈሩን መሳም ነበር፡፡ምን ያደርጋል? አይመችም።እያማራት፤ ተወችው::
"አይመሽብሽም አዜቢና" አለቻት ጓደኛዋን፡፡
“አይመሽብኝም" አለች ቶሎ ልትለያቸው ስላልፈለገች። በሻምበል ብሩክ ሀሳብ አዜብና አንዱአለም እጅግ ተደሰቱ፡፡ አንዱ አለም እስር ቤት ገብቶ ያደረ ዕለት ትደነግጣለች ብላ ከደበቀቻት በኋላ ሻምበል ብሩክ የተባለ ሰው ዋስ ሆኖ ያስፈታው መሆኑን ለእናቷ የነገረቻት፤ አንዱ አለም በሽተኛን ለመጠየቅ
ተፈትቶ እቤት ሲገባ ነበር፡፡ ከዚያን ቀን በኋላ ግን ስለ ሻምበል ብሩክ
ያልተወራበት ቀን አለ ለማለት ያስቸግራል።
በሆነው ባልሆነው የሻምበል ብሩክ ሥም እንደ ዳዊት ሲደገም እናቷ ጠርጥራለች፡፡ በዚህ ምክንያት ወ/ሮ አመልማል ሻምበል ብሩክን በመልክ ባይሆንም በዝና አውቃዋለች ማለት ይቻላል።
በሽተኛን ለመጠየቅ
ተፈትቶ እቤት ሲገባ ነበር፡፡ ከዚያን ቀን በኋላ ግን ስለ ሻምበል ብሩክ
ያልተወራበት ቀን አለ ለማለት ያስቸግራል።
በሆነው ባልሆነው የሻምበል ብሩክ ሥም እንደ ዳዊት ሲደገም እናቷ ጠርጥራለች፡፡ በዚህ ምክንያት ወ/ሮ አመልማል ሻምበል ብሩክን በመልክ ባይሆንም በዝና አውቃዋለች ማለት ይቻላል።በሽተኛን ለመጠየቅ በሚል ሰበብ ሻምበል ብሩክ ለእናቷ ያልገዛው ነገር የለም። ሥጋው፣ አትክልቱ፣ ለስላሳው፣ ኬኩ ይህንን ሁሉ ገዝተው ተሸክመው እቤት ሲደርሱ ሠራተኛዋ መጥታ በሩን ከፈተችላቸው፡፡ ልጅቷ በሻምበል ብሩክ ላይ ዐይኖቿ ተተክለው ቀሩ፡፡ግርማ ሞገሱ ያስፈራል። ከዚያም ትህትና ቀደም ብላ ወደቤት ገባችና ቤቱን ትንሽ ለማዘጋጀት ጥረት አደረገች። ጠንቃቃና ጽዳት ጠባቂ
ስለሆነች መዝረክረክ አይታይም ነበርና ብዙም አልተቸገረችም፡፡
እማዬ እንግዳ መጥቷል” ብላ ለእናቷ ሹክ ስትላት ማን መጣ ትሁቴ?” ደንግጣ ከተኛችበት ቀና ለማለት ተንደፋደፈች።
ብርድ ልብሱን እያለባበሰቻት፡፡
ወዲያው ሦስቱም ተከታትለው ገቡና ከእንግዳ ማረፊያው ከሶፋ ወንበሩ ላይ አረፍ አሉ። ቤቱ ንጹህና ቅልል ያለ ነበር፡፡ ሻምበል ዙሪያ ገባውን ተመለከተ፡፡ በትልቅ መስታወት ውስጥ ከነግርማ ሞገሱ የሚያየው ፎቶ የአባቷ እንደሆነ ገመተ፡፡ በቤቱ ንጽህናና አያያዝ ልቡ
ተማርኮ...
“የኔና የትሁት ጎጆም እንደዚችው ...” ሲል አሰበ። ትህትና ከደስታዋ ብዛት የምታደርገውን አታውቅም፡፡ የምትይዝ የምትጨብጠው ጥፍት ብሎባታል፡፡

“ሻምበል ብሩክ ነው አይዞሽ” ::
“ብሩኬ ና ወደዚህ” መጣችና እጁን ሳብ አድርጋ ካስነሳችው በኋላ ወደ እናቷ የምኝታ ክፍል ይዛው ገባች፡፡
ወ/ሮ አመልማል ሻምበል ብሩክን እንዳየችው ወደደችው። በቃ ልቧ ያለማመንታት አማችነቱን ተቀበለው። ልጅዋ ፍርጥ አድርጋ ባትነግራትም፤ እሷም ኮረዳ ሆና ባሳለፈችበት ዘመን ውስጥ የድብቅ ፍቅር ምልክቶች ምን ምን እንደሆኑ ቀምሳዋለችና፤ ልጅዋ በሻምበል ብሩክ መረታቷን በቀላሉ እንዳወቀች፤ ከወደደችው ሰው ጋር በወግ
በማዕረግ በትዳር እንድትኖር ምኞቷ ሆነ፡፡
ከዚህ ሁሉ የበለጠው ደግሞ፤ ይዛ የመጣችው ሰው ልብ የሚያስደነግጥ ለግላጋ ወጣት መሆኑን ስትመለከት፤ በደስታ ፈነጠዘች፡፡

“ጤና ይስጥልኝ እናቴ” ሄዶ ጉንጮቿን በተኛችበት ሳማት፡፡
ወ/ሮ አመልማል በዚያን ሰዓት የተሰማትን ስሜት መግለጽ አስቸጋሪ ነው። የሆነ ስሜት የሆነ የደስታ ሲቃ ተናነቃት፡፡

ለመጀመሪያ ቀን የምታየው ጠንበለል ወጣት፤ እሷን እዚያ ለረጅም ጊዜ ከአልጋ ያልተነሳችውን ገመምተኛ፤ ልክ እንደ እናቱ ሄዶ እቅፍ ድግፍ አድርጎ ሲስማት፤ ከልጆቿ አንዱ እንጂ፤ ፍጹም ባዳ ነው
ብሎ ማመን አቃታት፡፡
ይህ ለሷ ከብዶ ታያት እንጂ ፤ ለሻምበል ብሩክ ተወዳጅነትን ካተረፉለት መልካም ባህሪዎቹ አንዱ ነበር፡፡ ሰውን ትንሽ ትልቅ በማለት የማይንቅ፤ የታሰረ የታመመ መጠየቅ የሚወድ ሰው ነው። እሷም
ጉንጬን ሳመችው። እነሱን ስትመለከት የትህትና ልብ በደስታ ዘለለች::አቤት የተሰማት ደስታ!
“አይ ብሩኬ ምን ዓይነት ወርቅ ሰው ነህ?” ብሩክን በልቧ አደነቀችው::
ሻምበል ብሩክ ከዚህ በፊት የኖረ ዘመድ መስሎ ቁጭ አለ::
የመጣለትን ወንበር ትቶ እዚያ አልጋው ጫፍ ላይ አጠገቧ ቁጭ ብሎ
ራሱን ካስተዋወቀ በኋላ፤ ስለበሽታዋ፤ ስለኑሮዋ ስለወደፊቱም ፤ እያነሳሳ ሲያጨዋውታት፤ ከላይዋ ላይ የተገፈፈላት ያህል ተሰማትና፤ በሻምበል ብሩክ ሁለንተና ተመስጣ ጨዋታ ቀጠለች።

አዜብ ስለመሸባት ተሰናብታቸው ወደ ቤቷ የሄደችው የግዷን ነበር ማለት ይቻላል። የሻምበል ብሩክን ሁኔታ ያየ እንግዳ ነው ብሉ ለመናገር ይቸግራል፡፡ በአንድ ጊዜ ቤተኛ ሆኖ ቁጭ አለ። በዚህ ሁኔታ
ሲጨዋወቱ ካመሹ በኋላ ተሰናብቶ ሲወጣ፤ ከወንድሟ ጋር ሆነው
ሸኙት፡፡ ከዚያች ቀን በኋላ ሻምበል ብሩክ ቤታቸው ቤቱ ሆነ።
ከተቀጠረች ሁለተኛ ሳምንቷን ይዛለች፡፡ በእርግጥም ማለፊያ የገቢ ምንጭነቷና ገዳምነቷ ከወዲሁ እየታየ ነው፡፡ ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ የደንበኞች ቁጥር እየጨመረ ነው።
እዚያ ለገበያ ገብቶ በመጀመሪያ እሷን እንደ ሽንኩርት በዓይኑ ሳይልጣት ወደ መጣበት ጉዳይ የሚመለስ መቼም ጥቂቱ ነው። የዕድሜ አቻዎቿ ብቻም ሳይሆኑ የአሮጊቱ የሽማግሌው
👍21
ዐይን ከላይዋ ቶሎ አይነቀልም።

እሷም ይህንን በዐይን የመላጡን አደጋ እየተለማመደችው ስለሄደች አሁን አሁን ሲያይዋት ማቀርቀርን እየተወች መጥታለች፡፡ሊያሻት ሊተሻሻት የሚፈልገውን በፀባይ የመሸኘት ልምዱንም አዳብራለች::

“ይብላኝ እዚያ ቡና ቤት ውስጥ ተቀጥረው ለሚሰሩ” እያለች ሁሉንም በፀባይ ታስተናግዳለች፡፡ ከዚህ ሁሉ ውስጥ ግን አንድ ሰው ብቻ በቀላሉ በፈገግታ ግብዣ የሚሽኝላት አልሆነም :: ከዚያም አልፎ በግል ህይወቷ ውስጥ እስከመግባት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጾ አስፈራርቷታል።
ይህ የማትጋፋው ባላንጣ፤ በቤቱ ውስጥ የፈላጭ ቆራጭነት መብት አለኝ የሚለውና፤ በአባቱ ሀብት ስለሚመካ ከሥራ ያስወጣናል እያሉ ሰራተኞች የሚፈሩት እንደሻው ነበር።
“ምን የመሰለች ልጅ መለሰችህ ዛሬ ሽሜው የቀጠረው” ብሎ አበራ የነገረው እለት እንደዋዛ ነበር ያዳመጠው። የዚያን ያክል ትሆናለች ብሎ መገመት ቀርቶ አላለመውም። ትህትናን ያያት ሥራ በጀመረች በሣምንቷ ነበር።
ገና የሱቋን በር አልፎ ወደ ውስጥ እንደገባ፤ ያዩት እስከሚያፍሩበት ድረስ በቆመበት ቦታ አፉን ከፍቶ ቀረ፡፡ በሃሳቡ
እንደአውራ ዶሮ ሲከመርባት... ከዚያም በጭኖቿ መካከል ያለውን ሚስጥር ሲፈትሽ... ታየው። ምራቁን ዋጠ፡፡
“በደቂቃ ለጥብስ አደርሳታለሁ” አለ በልቡ፡፡ ለሚያዩት ሠራተኞች ደንታም ሳይሰጠው፤ በቀጥታ ደረቱን ነፍቶ ወደ ትህትና ሄደ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አንድ ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና ውድ አንባብያን ከላይ በለቀቅናቸው ሁለት ክፍሎች ላይ ማለትም 39, እና 40 ያልነው በስተት ነው ክፍል19 እና 20 ናቸው ስለተፈጠረው ስተት ይቅርታ እየጠየቅን በቀጣዩ ክፍሎች ላይ እናስተካክላለን..የቁጥር ስተት ብቻ ነው እንጂ የክፍል መቆራረጥ የለውም። መልካም ንባብ። ========================= ....“እኔና…»
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

ጊዜ መደፊት አይገፈትርም።ጊዜ ለሰው ጭንቀትም ሆነ ደስታ ደንታ የለውም።
የራሱን ሥርዓት ጠብቆ የሚጓዘው፤ያለፈ ጊዜ አይመለስም ፤የወደፊቱ ደግሞ እንደ
ፈለግጉት ፈጥኖ አይመጣም። ሰው በጊዜ ቁጥጥር ሥር ነው እንጂ ጊዜ በሰው ቁጥጥር ስር አይደሉም ሰዓት ሰው ሠራሽ ነገር ነው ፤ ሞላውን በማዞር ካለበት ሰዓት ወይም ደቂቃ ማስቀደም ይቻላል ። የቀን መቁጠሪያም ሰው ሠራሽ
ነገር ነው ፤አንዱን ወር አልፎ ሌላውን ወር ማየት ይቻላል ።ቀንን ገፍቶ ማስመሸት፣ ወይም ምሽት ጎፍቶ ማንጋት ግን
የማይቻል ነው ።

አቤል ቢቸግረው እንዲህ አይነት የጊዜ ምርምር ውስጥ ገባ ። ችግሩ ነው ምርምሩን የጋበዘው ቀኑ አልመሽልህ "
ሌሊቱ አልነጋልህ እያለው ተቸገረ ለሌላው ተማሪ የዕረፍት ጊዜ ለእሱ ግን የመጨረሻው ደረጃ የጭንቀት ጊዜ
ሆኖበታል ። ቀንም ይተኛል ፡ ማታም ይታኛል ። ነገር ግን እንቅልፍ አይወስደውም ። እንዲሁ አልጋው ላይ እየተገላበጠ በሐሳብ መብከንከን ሆነ ። ጊዚ ከመቼውም ይልቅ የኋሊት እየተጎተተ የሚያቃስት መስለው ።

ሳምሶን ለዕረፍቱ ወደ ቤቱ ስለ ሔደ መኝታ ክፍላቸው ውስጥ የቀሩት አቤል ፡ እስክንድርና "ድብርት ” ብቻ ነበሩ ። “ ድብርት ” ፈተና ካለቀ በኋላ ያሳየው ለውጥ ቢኖር አልጋ ማንጠፉ ብቻ ነው ። በተረፈ እንደ ጥንቱ “ድብርት ጥናቱም ቢቀር ያው አልጋውን በጋቢ ጋርዶ በራሱ ሕልም ውስጥ መኖሩን አልተወም ። ወደ ውጭ ቢወጣ ብቻውን ነው ።

እስክንድር የዕረፍት ጊዜ ጓደኛው መጽሐፍ ነው ።የአማርኛና የእንግሊዝኛ ልብወለድ መጽሐፎችን እየተዋሰ
ሲያነብ ስለሚውል፥ ቀኑ በፍጥነት ነው የሚገሰግስለት ማንበብ ስልቸት ሲለው፡ወደ መዝናኛው ክበብ እየሔደ ቼዝ
ይጫወታል ። መቼም ከሱ ቦታ ሰው ቢጠፋ ሚስተር ሆርስ አይጠፋም ።

እስክንድር በዚህ ሁኔታ የዕረፍቱን ጊዜ ቢያሳልፍም ከአቤል ጋር አብሮ መጨነቁ አልቀረለትም ። ዐቅሙ በሚፈቅደው መጠን አቤልን ለማዝናናት የማያደርገው ሙከራ የለም ። ከአነበባቸው መጽሐፎች ውስጥ ጥሩ የሚላቸውን መርጦ ይሰጠዋል ። አቤል ግን ነጻ ኣዕምሮ ስለሌለው፥ አንዱንም ከነጣዕሙ አንብቦት አያውቅም ። ጀምሮ ሳይጨርሰው ይቀራል ። ወይም በግል ሐሳቡ ውስጥ እየዋዠቀ ገጹን
በመቁጠር ብቻ ይጨርሰዋል ። እስክንድር ወደ ቼዝ መጫወቻው ቦታ ሲሔድ አቤል አብሮት እንዲሔድ ለማድረግ ቢሞክርም እሺ አላለውም ፡ ከሚስተር ሆርስ ጋር ከተጣላ ወዲህ የመዝናኛ ክበቡን ረግጦት አያውቅም ።
አቤል ወደ ውጭ ብቅ እያለ ከሰዎች ቢቀላቀል ፡ ጊዜውን መዝናኛ ቦታዎች እየሔደ ቢያሳልፍና በአንዳንድ እን
ቅስቃሴዎች ቢሳተፍ፡ ጭንቀቱ እንደሚቀልለት እስክንድር
ቢረዳም ፡ ይህን ለማድረግ ሁኔታዎች አልተመቻቹለትም አብዛኛው መዝናኛ ገንዘብ ይጠይቃል ። ይህን ማሟላት
አይችሉም ። ገንዘብ በማይጠይቅበት መዝናኛ ቦታ ለመዋል ደግሞ የአቤል ሙሉ ፈቃደኝነት አይገኝም ። ሌላ ቀርቶ
ከእስክንድር ጋር ከሚያወራበት ጊዜ ይልቅ፡ ብቻውን ተደብሮ ውስጥ ውስጡን ነገር ሲያብሰለስል የሚውልበት ጊዜ
ይበልጣል ።

ትዕግሥት በተለያየ መልክ በሕልሙ እየመጣች ትታየዋለች ። አንዴ ይጣላሉ ፤አንዴ ጥላው በመሔዷ የተሰማውን ቅሬታ ይገልጽላታል ፤ አንዳንዴ ደግሞ ደብረ ዘይት ድረስ ሔዶ ሲገናኛት ያድራል ቀን ያሰበውን ማታ በሕልሙ ይደግመዋል አንዳንዴ በቅዠት ይወራጫል ።
ከትዕግሥት ናፍቆት ጋር ተደርቦ የወላጆቹ በተለይም የእናቱ ሁኔታ ፊቱ ላይ እየተደቀነበት መጨነቁ አልቀረም ።
ያስብ ያስብና ሁሉም ነገር ፍቺ የሌለው እንቆቅልሽ ይሆንበታል ። ሆኖም እንቆቅልሽ ነው ብሎ አይተወውም ።

ተመልሶ በዚያው ሐሳብ ዙሪያ ይሽከረከራል ፡ በሐሳብ ከመብከንከኑ ጋር የምግብ ፍላጎቱም እየቀነሰ ስለመጣ
በጣም ከስቶ ነበር ። ግን ለዚህ ደንታ አልነበረውም ። አካሉ መንምኖ ነፍሱ ብቻ ከውስጥ ሚን ሚን እስክትል ይጠብቃታል

ብርቅነሽ ትዝ ስትለው የደስታ ብርሃን ትፈነጥቃለች ።ስለ እሷ ማሰብ ደስ ይለዋል። አብሯት ካደረ ጀምሮ የመውደድ ስሜት ተቀርጾበታል ። የፍቅሩን ዐይነት ግን በግል ለይቶ ማወቅ አልቻለም ። ትዕግሥትን ይወዳታል ፡ ብርቅነሽን ይወዳታል ። የመወደዱ ዐይነት ይለያያል ሲያስቡት ደስ የሚልና ሲያስቡት የሚያስቃይ ፍቅር ! ስለ ብርቅነሽ ማሰብ ያስደስተዋል ፤ አያሠቃየውም ፤ ጭንቅላቱን አይበጠብጠውም ። ስለ ትዕግሥት ማሰብ ግን ያሰቃየዋል፥
ይበጠብጠዋል ፤ ያስለቅሰዋል ። እንዲያም ሆኖ ፍቅሩ ለምታሠቃየው ለትዕግሥት ያደላል ። ሙሉ ልቡን ያሳረፈው በትዕግሥት ላይ ነው ። ቀርቦ ምስጢሩን ካካፈላት ፥ ገላዋን ካቀፈውና ትኩሳቷን ሲቀበል ካደራት ሴት ይልቅ ከዐይኑ ላላለፈች ሴት ፍቅሩ ማመዘኑ ለምን እንደያነ ሊገባው አልቻለም ። “ የፍቅር ምስጢሩ ምንድነው ? ሲል አሰበ "
ፍቅር የሚወደው ሥቃይን ይሆን እንዴ ? ?

አንድ ቀን ብርቅነሽን ሲያስታውስ ከውስጡ “ሔደህ እያት ” የሚል አንዳች ግፊት መጣበት። ለእስክንድር ሳያማክረው ተደብቆ ብቻውን ሔደ ። ለምን እንደሚሔድና ቢያገኛት ምን እንደሚላት አላሰበበትም ። ገብቶ ለመጫወትም ቢሆን ፥ የሚጠጣ! ለማዘዝ በኪሱ ገንዘብ የለም ። እናም ቡና ቤቱ አጠገብ ሲደርስ ቀጥ ብሎ ቆመ።

የቡና ቤቱ በር ክፍት ነው ። ነገር ግን ድምፅ አይሰማበትም። እንደዚያ ዕለቱ ምሽት ሙዚቃና የሰው ቻቻታ የለበትም ። ከዝንቦች እምታ በቀር ጸጥ ረጭ ብሏል ።
መግባት አልደፈረም ። እየተንጎራደደ ሰው ብቅ እስኪል ይጠብቅ ጀመር ። ጥቂት እንደ ቆየ ፥ አንዲት ሴት የከሰል
ምድጃ ይዛ ከውስጥ ብቅ አለች ። አለባበሷ ግድ የለሽ ነው ።
ሻሿን የገርዳሳ አስራለች ።

አቤል ሲያያት ክው አለ ። የዋህነቷንና ጥሬነቷን አይታ የቡና ቤቷ ባለቤት ማታ ማታ እንደ አሻሻጭ ቀን ደግሞ እንደ ገረድ ነው የምትጠቀምባት ፡ ከሰሉ እንዲቀጣጠልላት ምድጃውን ወደ ንፋስ አድርጋ ቀና ስትል አየችው ቶሎ አልለየችም። ያው እንደ መንገደኛ ነበር የተመለከተችው ። ስታየው ተደናግጦ ጀርባውን ሰጥቷት ወደ ኋላው ሊመለስ ፈልጎ ነበር ። ግን ዐይኑን ከማሸሹ በፊት የምታውቀው ወንድ መሆኑን ለይታ ጥርሷን ብልጭ አረገችለት እሷን ፍለጋ ያልመጣ ለመምሰል እጁን ኪሱ ከትቶ በግዴለሽ አረማመድ ተጠጋት ስሜቱን ለመሸፈን በከንቱ ደከመ እንጂ በድንጋጤ ፊቱ ቀልቶ ግንባሩን አልቦት ነበር።

ውይ ! አንተ ነህ እንዴ ? በሞትኩት ! ምነው ጠፋህ ? ” አለች ከልብ በሆነ አነጋግር ።

ምንም ሳይመልስላት ስሜቱን በፈግግታ ብልጭታ ለመሸፈን እየሞከረ ጨበጣት

ሙት እውነቴን እኮ ነው ጠፋህ ? ቆይ እስኪ ስንት ቀን ሆነን አዎ ሳምንት አልፎሃል ። እኔ ከዛሬ ነገ ትመጣለህህ እያልኩ በልቤ ሳስብህ ነበር አለችው።

“ እነቷን ይሆን እንዴ ? ” ሲል አሰበ ግን አሁንም ከመቅለስለስና ራሰን ከማከክ ሌላ ምንም አልመለሰም ። ድምጿ የእውነት ቅላጼ ነበረው የተናገረችው የልቧን ነው ፤ ለአቤል አንድ ጥሩ የሆነ ስሜት አድሮበታል ። ሴት ያልለመደ መሆኑና የተማረ መሆኑ ፥ በስሜቷ ውስጥ እንዲቀረጽ አድርጎታል እናም እንዳለችው አብራው ካደረችበት ሌሊት በኋላ ዐልፎ ዐልፎ በልቧ ታስበው ነበር ። የተሰማራችበት ሙያ ሆነና በወሲብ ተገናኙ እንጂ ፥ እሷ ለሱ ያደረባት ስሜት ሐሳቧንና ችግሯን እንደምታዋየው
እሱም በዕውቀቱ እንደሚረዳት የቅርብ ዘመዷ ወይም ታናሽ ወንድሟ ዐይነት ነበር

“ በል እሺ ግባ ! በር ላይ አትቁም አለችው ከእሱ አንዳችም ቃል ባለመስማቷ እያዘነች ።

“አአይ ልሒድ ፤ድንገት ሳልፍ'ኮ ነው
👍2
አላት ፡በአንድ በኩል እንደ መግደርደር ያለ ፡ በሌላ በኩል ደግሞ የኪሱን ባዶነት እያሰበ ።

"ግባ እባክህ፥ ትንሽ ተጫውተህ ትሔዳለህ ” አለችና ጎተት አደረገችው ።

በባዶ እምነትና ኩራት የተገነባ ግትር ሰውነቱን አቅልላ መጎተቷ ውስጡን ደስ እሰኘው ራሱን አቅልሎ መቅረብ አይችልም ። ንጹሕ ልብ ያለው ሰው አቅልሎ ሲቀበለውግን ይወዳል። በልቡ “ የሚቀጥለውስ ዶረጃ ምን ይሆን ? ?
እያለ ያለማመንታት ወደ ውስጥ ዘለቀ።

ምንም ሰው የለም እንዴ ? ”አላት ፥ ቅርቡ ባጋጠመው ወንበር ላይ እየተቀመጠ ።

“ውይ በቀን ምን ገበያ አለ ብለህ ነው ? ያው ማታ ነው ሞቅ የሚለው ” አለችው አጠገቡ እየተቀመጠች ።

አጠገቡ ስትቀመጥ ጊዜ፥ ልቡ ናድናድ ይል ጀመር። ለሰውነቷ መቅረቡን ቢወደውም ከእሷ ካልመጣ በቀር እሱ
ደፍሮ መጠጋጋት ወይም መተሻሸት አልቻለም ። እንጂ ያውም በዚያን ሌሊት ራሱ ደፍሮ ክንፉን ዘርግቶ ይህችን
ሴት አቅፎ ማደሩን ዛሬ ተጠራጠረ ማድረግ በማይችሉት ነገር ላይ ለመገፋፋት መጠጥ መልካም ቅመም ሳይኖረው አይቀርም ብሎ ገመተ።

“ እሺ ። እስቲ በል ተጫወታ” አለችው ቀጠለችና ሣቅ እያለች ።

እሺታውን ለመግለጽ የሚዋትቱት ዐይኖቹ ከጥርሷ ጉራማይሌ ንቅሳት ላይ ዐረፉ ። የሣቋ ምንጭ ምን እንደሆን ማወቅ አልቻለም ። ምናልባት አብሬኣት ያደርኩባትን ሌሊት አስታውሳ ይሆን እንዴ ?” በሚል ጥርጣሬ በአንዴ
ፊቱን ላብ አሰመጠው ።

አሁን ዕረፍት ላይ ናችሁ አይደል ? አለችው ስሜቱን ሳታጤን።

“ አዎ ብቻ ዕረፍቱ ወደ ማለቁ ነው ። ”

“ ጨካኝ ነህ ግን አንተ ዕረፍት ሆነህ ይህን ያህል ቀን ሳትመጣ ? ! ”

ጭካኔ አይደለም አላት ፥ ድምፁ ከመድከሙ የተነሣ የራሱ መሆኑ እያጠራጠረው ።

ታዲያ ምንድነው ? ”

ምን እንደሚላት ግራ ገባው ፍርሀት ፥ የኪስ መድረቅ ? ወይስ ጭራሹን ያለ መፈለግ ?

ለመልሱ ሲጨነቅ አይታ ሐሳቧ ቶሎ ሌላ ነገር ላይ ሮጠ ።

ያቺ ልጅ እንዴት ናት ? ”

የቷ ? ” አለ ፡ የማይፈልገው ጥያቄ መሆኑን ገምቶ ዐይኑን እያፈጠጠ ።
ያቺ ዩኒቨርስቲ ያለችው ! ያንን ሌሊት ያጫወትከኝ ” አለችው ደንታ ባጣ ቀላል ስሜት "

ከሌላ ሰው ስለ ትዕግሥት አንዳችም ጥያቄ ሆነ ጨዋታ ሲነሣበት አይወድም ። የብርቅነሽ አጠያየቅ ግን፥ ለጊዜው
ቢያስደነግጠውም ድንጋጤው ጭንቅላቱ ውስጥ አልቆየም ።ምክንያቱም የብርቅነሽ አጠያቀቅና አቀራረብ እንደ ምሁራኑ ከፍተኛ አትኩሮት ያለውና የሰው ስሜት የሚያጤን ዐይነት አልነበረም ። ነገሮችን ሁሉ ቀላል አድርጋ በቀላል
አነጋገር ነው የምታቀርባቸው ። መልስ ብታጎኝ አገኘች ባታገኝም ወደ ሌላ ጨዋታ ትሸጋገራለች እንጂ ፥ ሥራዬ
ብላ የሰወ ስሜት በማጥናት ወይም ነገር በማውጣጣት አትጨነቅም ።

"ግቢ ውስጥ የለችም ፤ በዕረፍቱ ወጥታለች”አላት ደፋር ጥያቄዋ አደፋፍሮት ፥ ድንጋጤው ተግ ብሎለትና
ነገሩን ማቅለሏ እሱም አቅልሎ እንዲያየው ገፋፍቶት ።

ውይ ፡ ሠፈሯ የት ነው ?” አለችው ።
“ደብረ ዘይት ” ሲላት፡ጉሮሮው ላይ አንዳች ነገር እየተናነቀው ነበር ።
“ ውይ ! ከአዲስ አበባ ውጭ ? ” አለችው ከልቧ አዝና ። ትዕግሥትን ሳያያት ማደር እንደማይችል አጫውቷት ስለ ነበር፥ ርቃው ስትከርም ምን ያህል እንደሚሠቃይ በመገመት አዘነችለት ። ከእሱ መልስ ሳትጠብቅ ቀጥላ ፡

“ ስትሔድ ምን አለችህ ? ” አለችው ።
ምንም ።

ምንም አልተባባላችሁ ? አሃ ፡ በቃ ተነጋግራችሁ አታውቁም ?

በአሉታ ራሱን ነቀነቀ ።

“ ውይ ! ምን ዐይነት ፍቅር ነው ? ” አለች

“ ጭፍን ፍቅር ነዋ ! ” አላት በብሽቀት ። የሆነ ነገር ዐይኑን ለበለበው ። የገዛ ልቡ ከበደው ። በዚህ አርዕስት ላይ ቀጥሎ ከብርቅነሽ ጋር መጫወት እንደማይችል ገመት ።ይህን ያህልም ግልጽ የሆነው ለእሷ ብቻ ነው። እሷም ከዚያ በላይ ልትጠይቀው አልቻለችም ። ቃላት መለዋወጥ ቀርቶ በሙሉ ዐይን ተያይተው ከማያውቁ ፍቅረኞች ምን መረጃ
ይገኛል ? አብዛኛውን ድፍን ሁኔታ አብረው ያደሩ ዕለት አጫውቷታል ። እና ዝም ብላ ዐይን ዐይኑን ስታየው ስሜቱ የተጋባባት ትመስል ነበር ።

እንዲህ እየተጫወቱ ትንሽ እንደ ቆዩ የቡና ቤቷ ባለቤት ከጓዳ ብቅ አለች ። ከቀኑ አምስት ሰዓት ተኩል አካባቢ ቢሆንም እሷ ገና በሌሊት ልብሷ ነበረች ። ፊቷ ሲያዩት ይከብዳል ። በዚያ ላይ ገና ከመኝታዋ መነሣቷ ስለሆነ ፊቷ ላይ
የተጋደመው ሰምበር መልክ አሳጥቶአታል በሒና የቀላው ጸጉሯ ትንሽ ባያደምቃት ኖሮ፡ ጭራ ትመስል ነበር። አቤል
ያን ምሽት ያያት ሴት መሆኗን ተጠራጠረ ያኔ ታምር ነበር ። " የቡና ቤት ሴቶች ውበታቸው ማታ ማታ ብቻ ነው ማለት ነው ? ” ሲል አሰበ ።

ባለቤቷ ናቸው እንዴ ? ” ሲል ብርቅነሽን ።
ሹክ ብሎ ጠየቃት።

“ አዎ ” አለችና ብርቅነሽ እየሣቀች ፡ “ ብቻ አንቱ ስትላት እንዳትሰማህ ፡ አትወድም ” አለችው ፥ እሷም እንዲሱ ሹክ ብላ ።

« እኛህን የሚያክሉ ሴትዮ አንቺ ማለት ነወር ነው ብዬ ነው።

“ ሆሆይ ! እሷ ስትስነብት ልጃገረድ ነኝ ሳትል ኣትቀረም እንደገና ሣቋን አፍና ።

ባለቤትየዋ እየቀረበች ስትመጣ ጨዋታችውን አቋረጡ።

“ ከሰሉ አልተቀጣጠለም እንዴ ?” ስትል ብርቅነሽን በተቆፋጠነ ድምፅ ጠየቀቻት ቡና ማፍያቸው ሰዓት ነበር።

“ ውይ ፡ እረ እስካሁን ይቀጣጠላል ” አለችና ብርቅነሽ ተስፈንጥራ ብድግ አለች ከሰሉ እንዲቀጣጠል ውጭ ማድረጓን ዘንግታው ነበር ።

ሻሽሽ ሊወድቅ ነው ? ” አላት አቤል ፡ ከጸጉሯ ላይ ሲንሸራተት አይቶ ።

“ ኬሬዳሽ ! ” አለችና ጭራሹን ፈትታ ጣለችው ።በልቡ “ የዋህ ፍጡር እያለ ከተቀመጠበት ተነሥቶ ወደ ውጭ ተከተላት።

“ ምነው ተጫወት እንጂ፡ እኔ “ኮ ከሰሉን ላገባ ነው ።”

“ ተጫወትኩ ኮ ልሒድ” አላት ወደ ፊቱ እየተራመደ።

“ እሺ በል ማታ ትመጣለህ ?”

“ እ ? ”

"ማታ ና ! ”

እሺ ብሎ ተሰናበታት ። ደስ ብሎት ዋለ ። እናም « አንዲህ ደስታ የምትሰጠኝ ከሆነ ለምን ደጋግሜ አላያትም ?”
የሚል ሐሳብ አደረበት። ብርቅነሽ ጋ መሔዱን ለእስክንድር አልነገረውም ። ድብርትን ፈልጎ አንድ ብር እንዲያበድረው
ጠየቀው ። ድብርት ምን ጊዜም ገንዘብ አያጣም ። ለክፉ ቀን በሚል እምነት እንደሚቀብር አቤል ያውቃል ። ከዚያ
በፊት ጠይቆት ስለማያውቅ፥ ድብርት ገርሞት እንድ ብር አወጣና ሰጠው ። ከሳጥኑ ውስጥ ከስር ፥ ከመጽሐፍ ሽፋን
ብሩን መዝዞ ሲያወጣ ሲያየው አቤል ገረመው ። « የሰውን እጅ ብቻ ሳይሆን የራሱንም እጅ ሳይጠረር አይቀርም
አለ በሐሳቡ።

አቤል ኮካ ኮላውን ይዞ ማታ ወደ ብርቅነኝ ዘንድ አመራ ። ካምፓስ ውስጥም ሆነ ውጪ እስክንድር እንዳያየው መንገድ እየመረጠ ነበር የሄደው።

እቡና ቤቱ ሲደርስ የተለመደች ፍርሀቱ መጣችበትና ቆሞ ትንሽ አመነታ። ቡና ቤቱ ጢም ብሎ ሞልቶ፥ ቻቻታው
ደርቶ ነበር ። ቀስ ብሎ ወደ በሩ ተጠጋ ። አንገቱን ውስጥ ገባ ሲያድርግላ ዐይኑ አነጣጥሮ ብርቅነሽ ላይ ዐረፈ ። የሆነ ነገር ፊቱ ላይ ብልጭ እለበት ። ራሱን መቆጣጠር ያቃተው ይመስል- በሩን ደገፍ ብሎ ቆመ ብርቅነሽ ባንኮኒው አጠገብ አንድ ወንድ ጭን ላይ ተቀምጣ ቢራ ትጠልለች። ከት ከት እያለች ከልቧ ትሥቃለች " ትጫወታለች የዋህ ልቧን ለማንም ከፍታ ትሰጣለች ወንድየው በአንድ እጁ ወገቧን ደግፎ በአንደኛው ጡቶቿን እያሻሸ አብሯት ይሥቃል ፤ ይጠጣል ፤ ይጫወታል ።

አቤል እንዳያት እንድታየው አልፈለገም ። ለምን ከማንም ጋር ትሥቃለች? ለምን ከማንም ጋር ትጫወታለች ?ለምን ለማንም ልቧን ትከፍታለች
? ሳታየው ቀስ ብሎ ወደ ኋላው ተመለሰ ።

ወደ መንገዱ ሲያቀና በሐሳሱ የቡና ቤቱ ሰው ሁሉ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ግባ እኔጂ ምነው ተመለስክ? የቀናህባት ሴት አለች እንዴ ? ቡና ቤት እኮ ነው የመጣህው የሚለው መሰለው።

የገዛ ስሜቱን እንደሚሸሽ ሁሉ ፊቱን ወደ ስድስት ኪሎ አቅንቶ መንገዱን ጀመረ ። በሐሳቡ ውስጥ ገንዘብ ከፍተኛውን ቦታ ይዞ አብሮት ገሰገሰ ። ገንዘብ ፈለገ ። ገንዝብ ፈጥኖ ለማግኘት ጓጓ ። ገንዘብ የነገሮች ሁሉ ማሰሪያ ነው አለ በልቡ ።

💥ይቀጥላል💥
#የቀን_ቅዠት

ደመ ግቡ ፣ ቀይ ሴት
የመልኬ ገጽ ፣ ፍኩ ሐሤት
በእይታ አፍታ ፣
በብልጭታ ፍጥነት . . .
ከዐጸዴ መጥታ ፣

ድንግዝግዝ ፍዝ ቀን ፣ በፈገግታ ጠርቶ
ወጀብን የሚያቆም . . .
የሰመመን ዓለም ከቤቴ ተገኝቶ።

ጀንበርን ሸሽጋ ፣ ጨረቃዋን ጋርዳ
በድንገት መሽጋ ከዕልፍኜ ጓዳ።
በሻማ ተስላ . . .
ሸማ ተሸልማ ፣ ተገልጣ በ'ኔ ዐይን
አበባ ታቅፋ ፣ ጽዋ ሙሉ ወይን ፣
(. . . ከዕቅፌ ገባች . . )
ማእዱን ተቋደስን ያብሮነትን መባ
በቅጽበት ደመኩኝ ፣ በቅጽበት ተውባ
ድንገት ተሰለበች !
እኛነት ለለበች።(ዋሸች,አታለለች)

( ምን ነበረ የኾነው . . . ?)
በቀን በጠራራ ሳልም የነበርኩት ?
በክፍልፋይ ሰከንድ እያየው የዋልኩት ?
እኮ ምን ነበረ? ...
ልፈታው ቸገረኝ !
ቅኔው ግራ ገባኝ ተመሳጥሮ ሕልሜ
ተሠፋኹ ፣ ተቋጠርኩ ፤ በቀን ሐሳብ ቀኔ።

ለማላውቃት ውብ ሴት . . .
ፀምን ሕልሟ ብኾንም ፣ ሕልም ብትኾን ለ'ኔ፤
ያልታኖረ ሕይወት . . .
የሐምሌ ፀሐይ ነው የክረምት ምናኔ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
#ሐዘን_እና_ዘፈን

ማሞና ማሚቱ . . .
የሚገዙት ቆሎ ጠፋና ባ'ገሩ ፣
ፍቅራቸው ቀነሰ ፤
ጭራሽ ተባብሶ መቃቃር ጀመሩ።

ቆሎ ሻጫ እሜቴ ከገበያ ጠፍታ
የምትሠፍረውን ገብስ ከጎተራ 0ጥታ፣
መደቧ ተራቁቷል ፤ የስፍር ቁናዋ
የገብስ ዘር ጠፍቶ ከትልቅ ማሳዋ።

ቆሎ ቆርጣሚ ሰው ሥንቁ ጥራጥሬ
“ለምን? እኽል ጠፋ ካ'ገሬው ገበሬ”
እያለ 'ሚጠይቅ . .
“በየምልክቱ ገብስ እየለጠፉ
እኮ ለምንድነው? ከማሳው ያጠፉ
ብሎ የሚጠይቅ . . .

ሰበበኛ ቀዬ ፤
ገብሱን እየጠጣ ገብስ ቆሎ 'ሚያልም
ፈጭቶ ከመጋገር በጥሬ የሚልም።
ከእንክርዳዶች መኻል እኽልን ያለየ
“ገብስ ነው!” ይልኻል ፣ ገለባ እያሳየ
ገለባ ሕይወቱን ሰፍሮ እየመዘነ
በሥጋ ውቂያ ላይ ፣ ትልሙ ተበተነ።

የተበተነው ሕልም .
ዘፈን ይዞ መጣ ግልብ ኾኖ ነፋሱ ፣
ማሞ ዳቦ ናፍቆ . . .
የሚቀምሰው ቢያጣ ቢቆም እስትንፋሱ ፣
የጓዳቸውም ሐቅ . .
በሰነፍ ቆሎ ዕጣ ወድቆ ከመቅደሱ።

(. . . አዜሙ ዘፈኑ . . . )
ዘፈን ነው መፍትሔ? . . .

በተቃርኖ ስሌት ሲኾን ሱሪ ባ'ንገት
ዳቦ የበላና . . .
ቆሎ የሚናፍቅ ሲወድቅ በድንገት
በድንገቴ ሐሳብ የድንገቴ ኹነት
የዳቦ እሥረኛ ቆሎ ዕላሚ ኑረት !
መሠረት የሌለው ቤቱ ዐጥር አልባ ፣
በገል ምንነቱ . . .
ማዕበል ተማምኖ የሚዋዥቅ ጀልባ፡፡

የ'ንእሜቴ ጎጆ . .
እንዲኽ ባ'ንድ ጊዜ ገብስ ጠፋ ሲሉ
የ'ነማሞ ፍቅር መፍረስ ነው ሽመሉ።
በጥሬ ሕይወቱ . .
ቆሎ ቆርጣሚ ሰው ፣ ዳቦ እየናፈቀ
ከሥጋ መደብ ላይ በሆዱ ወደቀ
ከግብሩ ሲራራቅ ዘፈኑ ደመቀ።

‹‹ማሞና ማሚቱ ገዙ ዳቦ ቆሎ
ሮጠው ወደቁ ተነሡ በቶሎ!››

በየወደቁበት እየተዋወቁ
በየቦረቁበት እየተዋደቁ
በየዘገኑበት እየተሣለቁ ፣
የጓዳቸውም ሐቅ .
ከግዙፉ ማሳ መደቡ ተለቀ ፤
ዳቦቆሎ ኾኖ . . .
የጥንዶች ቅኔ በዘፈን ዐለቀ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

“ጤና ይስጥልኝ ወይዘሪት እንዳሻው በቀለ.... እባላለሁ እራሱን በሚገባ አስተዋወቀ። እሷም ስሟን ሰጠችው። ፈርጣማ ወጠምሻ ነው።

“ምን ያህል ጊዜ ሆነሽ ሥራ ከጀመርሽ?” ድዱን እየገለፈጠ
“እንድ ሳምንት ሆኖኛል” በር በሩን እያየች::
“በስመአብ ይህንን ያክል ቀን ስትቆዪ ያለመምጣቴ ደደብ ያሰኘኛል”
“ለምን? ይኸው አሁን ተዋወቅን አይደል? ምን ልዩነት አለው?”
“ተይ እንጂ! ጊዜ እኮ የውጤት አብራክ ነው” ትንሽ እየተውረገረገ።
“እንዴት ማለት?”
“ከአንድ ውጤት ላይ ለመድረስ ድርጊት የሚወሰነው በጊዜ ውስጥ ነው
ማለቴ ነው” ሊፈላሰፍባት ሞከረ፡፡
“አልገባኝም?”::
እንደሻው በልቡ “ተይ እንጂ ቆንጂት? አንድ ሳምንት እኮ ለጥብስ የምትበቂበት ጊዜ ነበር፡፡ አሁን ግን ገና ጥሬ ነሽ፡፡ አንድ
ተጨማሪ የማብሰያ ሳምንት ሳትወስጅብኝ አትቀሪም” አለ፡፡
“ማለቴ ይሄኔ በደንብ ተዋውቀን፣ ተግባብተን፤ ሞቅ ያልን ጓደኛሞች መሆን የምንችልበት ጊዜ ነበር ማለቴ ነው”
ወደ ወ/ሮ አረጋሽ በቆረጣ ተመለከተ።
ወ/ሮ አረጋሽ በዕድሜ ጠና ያለች በዚህ ሱቅ ውስጥ ለረጅም አመታት ተቀጥራ ያገለገለች ቅጥር ሠራተኛ ናት።
ልክ እሱ እሷን ሲያይ፤ እሷም ቀስ ብላ በቆረጣ አየችውና ጠቀሰቸው፡፡
“በኔ ተማመኝ አሁን ነው የማቀላጥፋት በሚል ስሜት
ከንፈሩን ወደ ጎን አጣሞ የግራ ዐይኑን ጨፈን አደረገው። ተግባቡ።
እንደ እውነቱ ከሆነ እንደሻው እዚህም እዚያም እያለ ከሚልከሰከስ፤ ይህችን የመሰለች ልጅ መቀላጠፍ ብቻ ሳይሆን ቢያገባት የወ/ሮ አረጋሽ ምኞች ነበር፡፡ በዚህ የተጀመረው ትውውቅ ቀጠለ፡፡ አበራ በዚያን ዕለት አልነበረም፡፡ እንደሻው ድሮ ወደዚያ ሱቅ ዝር እንደማይል ሁሉ ትህትናን ካየ በኋላ ያንን የጫማ ሱቅ እንደ ቤተ ክርስቲያን ሳይሳለም ወደራሱ
ሱቅ መሄድ አቆመ፡፡
ምንም እንኳን እግሩ እስከሚቀጥንድረስ ቢመላለስም መጀመሪያ አይቷት እንደገመተው ግን አልሆነችለትም፡፡
“እንደሻው በዚህ በኩል ያለህ ሃሳብ ቢለወጥና ጥሩ ወንድሜ ሆነህ ጓደኝነታችን ቢቀጥል ደስታውን አልችለውም:: ከማንም አንሰህ
ሳይሆን፤ የግሌ በሆነ ምክንያት ብቻ ጥያቄህን ለመቀበል ስለማልችል
እባክህን ይቅርታ አድርግልኝ?” ብላ ለመነችው። -
“ምንድነው የግል ችግርሽ?” ሲል ደጋግሞ ጠየቃት፡፡
“እጮኛ አለኝ” ስትል ቁርጡን ነገረችው፡፡

እንደሻው ግን እንኳን እጮኛ ባሏ ቢሆን ደንታ የሌለው አጥር ዘላይ መሆኑን
አላወቀችም ብትለምነው ብትማፀነው
እሷን ካልቀመሰ እንደሚሞት ሁሉ እሺ ካላለችው፤ ከስራ እንድትባረር ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይል እየገለጸ፤ ያስፈራራት፤ ጀመር፡፡
ይህ ጊዜያዊ ስሜቱ ቀስ በቀስ እንደሚለወጥና፤ ልመናዋን እንደሚቀበላት ተማምና፤በምታገኘው ጊዜ ሁላ በጸባይ ትቀርበው ነበር።

እንደሻው እንዳስበው ሳይሳካለት መቅረቱን ሲያውቅ አማላጅ አድርጐ የላካት ወ/ሮ አረጋሽ ትህትናን ለብቻዋ ጠራቻትና...ትሁት በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል አይነት ሆንሽብኝ እኮ!
ምንም ትንሽ ልጅ ብትሆኝ አመለካከትሽ ብስል መሆኑን ከተረዳሁት ውዬ አድሬአለሁ። አሁን ግን ሳይሽ ልጅነትሽ የለቀቀሽ አልመስል አለኝ፡፡
ሰማሽ የኔ ልጅ? ዕድል እጅ ላይ የምትወድቀው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
እንደገባችም ካልተጠቀሙባትና አንዴ ካለፈች ደግሞ በፀፀት ትጎዳለች እንጂ
ተመልሳ አትገኝም። በዚህ በቁንጅና ወቅት በዚህ በልጅነት ጊዜ ችላ
የተባለ እድል ደግሞ በእኛ ዕድሜ ላይ ከደረሱ በኋላ ና! ብለው ቢለምኑት፤ ቢጣሩት፤ ተመልሶ አይመጣም፡፡እንደታኘከ የሸንኮራ አገዳ መመጠጥና የትም ተጥሎ መቅረት ነው ትርፉ። ልብሽ ልብ ይበል!፡፡ ዛሬ የደነደነው ልብሽ ነግ ደም እንዳያለቅስ?። እግዚአብሔር ከዚህ የሀብት ባህር ውስጥ አምጥቶ ሲጥልሽ፤ በየወሩ አፍንጫዬ ላይ የሚወረወርልኝ
ሳንቲም ይበልጥብኛል ብለሽ ይህንን ሁሉ ሀብት ንብረት ብትገፊ፧
ዕድልሽ የተገፋ ነው የሚሆነው :: እወቂበት፡፡ የዚህ ቤት የሽማግሌው
አጠቃላይ ንብረት ወራሽ እንደሻው መሆኑን አትዘንጊ!! የጠየቀሽን
አድርገሽ ልጥፍ፤ ጥብቅ፧ ነው ልጄ ዋእ...!”
ያልደሰኮረችላት ዲስኩር አልነበረም፡፡ ትህትና ወይ ንቅንቅ!
“አመሰግናለሁ እትዬ አረጋሽ፡፡ ያለሽ ቀና አመለካከት፣ ምክርሽም ሁሉ ለኔ ጥሩ በመመኘት፣ እኔ ጥሩ ደረጃ ላይ እንድደርስ በማስብ እስከሆነ
ድረስ ከልቤ ነው የማመሰግንሽ :: እንደሻው ቢበዛብኝ እንጂ አንሶኝ
እንዳልሆነ አምናለሁ፡፡ በሁሉም ረገድ ከኔ የበለጠች ማግኘት የሚችል ሲሆን እኔ ግን ለሱ የማልገባ እዚህ ግቢ የማልባል መናጢ ደሀ መሆኔንም አልዘነጋሁትም፡፡ ይህንን ሁሉ ደግሞ ለሱ ነግሬዋለሁ። እትዬ አረጋሽ የማፈቅረው ጓደኛ አለኝ፡፡ በሱ ላይ ደርቤ ማፍቀር አልችልም፡፡
እባክሽን ይቅርታ እንዲያደርግልኝና ሀሳቡን እንዲለውጥ ለምኝልኝ?”
በማለት እግሯ ላይ ወድቃ እያለቀሰች ለመነቻት፡፡
ወ/ሮ አረጋሽ በልጅቷ ንግግር ልቧ ቢነካም፤ ጉልበተኛው እንደሻው ያጋጨኛል ብላ ስለፈራች! የአደራ መልዕክቱን ለእንደሻው ሳታደርስላት ቀረች፡፡

የወይዘሮ አረጋሽ አማላጅነት
በቀጠሮ እየተጓተተ ውጤት የማይታይበት ሆኖ በመገኘቱ እንደሻው ተናደደና አበራን አማከረው::
“ይህቺ ጭንጋፍ አሮጊት ያነጋገረቻት አልመሰለኝም፡፡በንዴት መንጋጭላዋን ከማውለቄ በፊት ምን አለበት ብትገላግለኝ?!” ሲል ለአበራ ጥያቄ አቀረበለት፡፡
“እንዴት ማለት?”
“ትህትናን በጣም አፍቅሬአታለሁ፡፡ በተደጋጋሚ አነጋግሬአታላሁ፡፡ፈቀደኛ አልሆነችም፡፡ እሺ ብትላት ብዬ አበራሽን አማላጅነት ልኬባት ነበር፡፡ ለሷም እሺ ያለቻት አልመሰለኝም፡፡ አንተ አለቃዋ ስለሆንክ ልትፈራህ ትችላለች፡፡ በእውነት ነው የምልህ አበራ የወደድኳት፡፡ በቀላሉ አገኛታለሁ ብዬ ነበር የገመትኩት፡፡ እንደገመትኩት አልሆነም፡፡ ልታግባባልኝ የምትችለው የመጨረሻው ሰው አንተ ብቻ ነህ፡፡” ለመነው፡፡ እንደሻው እንደተስገበገበባት ከሁኔታው ተገነዘበ፡፡
አበራና እንደሻው ፍቅራቸው በከፈቱት ንግድ ምክንያት እየጠበቀ የሄደ
ሽሪኮች ስለሆኑ እምቢ ሊለው አልፈለገም።

“አይዞሽ! እንደሻው ሁሉንም ነገር ለኔ ተይው! እኔ እጨርሰዋለሁ! በኔ ተማመኝ!” ጀርባውን ቸብ፤ ቸብ፤ በማድረግ ተስፋ በተስፋ አደረገው። አበራ ሙሉ በሙሉ ተማምኖ የእሺታ ቃሏን ለመቀበል ብቻ ያነጋገራት
“ልሸኝሽ በማለት በመኪና ውስጥ ካስገባት በኋላ ነበር፡፡

ስሚ ትህትና!” ፊት ለፊት እየተመለከተና መሪውን እያስተካከለ።
“አቤት ጋሽ አበራ” አንድ የሚነግራት ነገር እንዳለ በመጠራጠር ስሜት ወደጐን እያየችው፡፡
“እንደሻው አነጋግሮሽ ነበር መሰለኝ” መሪውን በእጁ እየመታ።
“ስለምኑ?”
“ያው ነዋ!! እንደሚወድሽ” ፍርጥ አደረገው፡፡ ምን ዙሪያ ጥምጥም
መሄድ ያስፈልጋል?።
ትንሽ እንደማፈር አለችና በኃይል መምታት የጀመረው ልቧ ሲረጋጋላት፡-
“አነጋገርኳት አለ እንዴ?” አለችው፡፡
“ከዚያም አልፎ አረጋሽንም እንደላከብሽ ሳይደብቅ አጫውቶኛል” እየሳቀ።

አዎን እንደሱ ነው”ውጭ ውጭውን በመስታወቱ አሻግራ እየተመለከተች፡፡
“ታዲያ ምን መልስ ሰጠሽው?”
“ያው እንደነገረህ ነዋ ጋሽ አበራ?” የሰጠችውን መልስ እያወቀ
እንደሚጠይቃት ገብቷታል።
" መልሱ ያንቺ መሆኑ አጠራጥሮኝ ነው እኮ የምጠይቅሽ?” የአለቅነት ስሜቱ እየታገለው ነበር፡፡በዚህ ላይ ደግሞ ስራውን ምን ያህል እንደምትፈልገውና ችግረኛ መሆኗን በሚገባ ያውቃል፡፡

“ምንም አያጠራጥርም ጋሼ አበራ፡፡ በእርግጥ እንደሻው የሚጠላ ወይንም
ለኔ የሚያንስ ልጅ ሆኖ አይደለም። እንደኔ ያለች ደሃ እሱን
👍1🔥1
የመሰለ ልጅ ማግኘቷ ሎተሪ ቢሆንም ዕድሉን እንዳልጠቀምበት ከሱ በፊት የተዋወቅሁት እጮኛ ስለአለኝ ብቻ ነው” ሀቁን ነገረችው::
አበራ ትንሽ ፀጥ ካለ በኋላ...
እስቲ አስቢበት! ቶሎ ቸኩሎ መወሰን ይከብዳል፡፡ ቀምሰሽ ያላጣጣምሽውን ምግብ አይጣፍጥም ብትይ ተሳስተሻለል አማራጩን ቀምሰሽ ቀምሰሽ ለማጣጣምና፤ የጣፈጠሽን መርጠሽ ለመብላት ሞክሪ!” አላት፡፡
“ጋሽ አበራ እኔ ለአንድ ወንድ፤ አንድ ወንድ ደግሞ ለእኔ ለአንዷ ሴት ብቻ እስከተፈጠርን ድረስ፤ የተገኘውን ወንድ ሁሉ እየቀመስኩ ማጣጣም የምችል አይመስለኝም” ስትል መለሰችለት፡፡
“ኦሆሆ! ይህቺ መልኳ ልስልስ፤ አነጋገሯ መርዝ፤ የሆነች ልጅ የዋዛ አደለችም ለካ አለ በልቡ።
ሳያሳምናት ፧ሳታሳምነው፧ ለእንደሻው በሙሉ ልብ የገባለትን የተስፋ ቃል ሳያሳካ፤ ታክሲ የምትይዝበት ቦታ ደረሰች፡፡
“በጣም አመሰግናለሁ ጋሼ አበራ፡፡ ደህና እደር ብላው ከመኪናው ወረደች።

አስቢበት ትህትና” አላትና ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡ ከአቋሟ ንቅንቅ እንደማትል የታወቀው፤ በተደጋጋሚ የተደረገው ሙከራ ከሽፎ ከተረጋገጠ በኋላ ነው።እንደሻው ይህንን ቁርጡን እያወቀ ሲመጣ በንዴት ጥርሱን ነክሶ፡-
“እሰራላታለሁ!!” አለና ፎከረ።.....
።።።።።።።።።።።።።።።

#Share እያደረጋቹ አደለም አንድ Poat 4 እና 5 ሰው ነው #Share እያደረገ ያለው እናም በጣም ትንሽ ነው ለሌላው እንዲደርስ ሁላችሁም #Share እያደረጋችሁ

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሁለት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና “ጤና ይስጥልኝ ወይዘሪት እንዳሻው በቀለ.... እባላለሁ እራሱን በሚገባ አስተዋወቀ። እሷም ስሟን ሰጠችው። ፈርጣማ ወጠምሻ ነው። “ምን ያህል ጊዜ ሆነሽ ሥራ ከጀመርሽ?” ድዱን እየገለፈጠ “እንድ ሳምንት ሆኖኛል” በር በሩን እያየች:: “በስመአብ ይህንን ያክል ቀን ስትቆዪ ያለመምጣቴ ደደብ ያሰኘኛል” “ለምን? ይኸው አሁን…»
#ሰመመን


#ክፍል_አርባ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ


የዕረፍቱ ጊዜ ለአቤል ብቻ ሳይህን ለአብዛኛው ተማሪ ረዥም ነበር " በጥናት መወጠር የለምደ አእምሮ ሥራ ሲፈታ ደቂቃዋም ትረገማለች ። የአዲስ አበባም ተማሪዎች እንኳ አብዛኛዎቹ ወደየ ዘመዶቻቸው መጥተው ሰንብተዋል። ከየክፍለ ሀገሩ የመጡ ተማሪዎች ግን መሄጃም ሆነ ጊዜ ማሳለፊያ በማጣት ቦዝነው ነው የሰነበቱት ቀን ቀን ሁሌም ተደብረው ይውላሉ " ጫዋታና ቀልድ የሚኖረው ማታ ማታ በየመኝታቸው ሲሰፍሩ ነው " በአብዛኛው መኝታ ክፍል ተደጋጋሚ የጨዋታ አርዕስቶች ሆነው የሚቀርቡት የአቤልና የትዕግሥት የዐይን ፍቅር • የለማና የቤተልሔም ጉዳይ ፡ ወይም ሌሎችን የተደረሰባቸው አዲስ
ፍቅረኞችን ማጋለጥ የመሳሰሉት ናቸው ።

የግቢውን የፍቅር ታሪክ መሰለልን መዝናኛችው አድርገው የያዙ አንዳንድ ተማሪዎች አሉ ። ወሬአቸውን የሚያደምቁት የፍቅረኞቹ ጓደኛ በመምሰል ቀርበው ምስጢራቸውን እየሰረሰሩ ነው ። በዚሁ ተግባራቸው፡“ ሳተላይት”” “ ሮይተር” ፡ “ ቢቢሲ” የሚል የቅጽል ስም የወጣላቸው ተማሪዎች ነበሩ ። ወሬ አጠናቅረው መጥተው በግቢው ያሰራጫሉ ። ምሽት ላይ እነሱ ሲመጡ! ሁሉም ወሬ ለመስማት ከተኛበት ብድግ ብድግ ይላል ።

“ ያልሰማህ ስማ ! የሰማህ ላልሰማ አሰማ ! አዲስ ዜና በዚህ በዝግ ጊዜ ውስጥ አንድ መምህር ከአንዲት ተማሪው ጋር በዋቢ ሸበሌ ሆቴል የዳንስ ምሽት ላይ መታየቱ፥ ከታመኑ የዜና ምንጮች ደርሶናል።

• ደሞ ማን ይሆን ? ” እያለ ተሜ ከመኝታው ውስጥ በአንሶላው ብቻ እየወጣ ' በጆሮው ሳይሆን በመላ ሰውነቱ
የሚያዳምጥ ይመስል' ወሬው ወደ ነፈሰበት ይጠጋል ምን ጊዜም የሚሞቀው « እነ “ ሮይተር ” እነ “ ሳተላይት” ያሉበት መኝታ ክፍል ነው ። ብዙ ተማሪ ክፍሉን ትቶ እነሱ ያሉበት ድረስ እየመጣ ያመሻል ።

« ማነው እሱ በናትህ፣"

"ለማን ታውቁታላችሁ ? ሁለተኛ ዓመቶችን የሚያስተምር ራሰ በራ ሰውዬ።

“ እ" ዐወኩት ። ከማን ጋር ነው የታየው ? ” ይላል " የሚያውቀው።

ለማን የማያውቀው ደግሞ ፣ በእዝነ
ልቦናው ለማን ፍለጋ ይጓዛል።

"በተልሔም ከምትባል ቀይ ወፍራም የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ጋር ፡ ..".

“ውይ እሷንማ ሲያወጣት ቆይቶ የለም እንዴ? " ይላል ከአሁን በፊት ቀድሞ ወሬውን የሰማ።

"ሒ.....ድ?" ይላል ለወሬው እንግዳ የሆነ ሁሉ በአድናቆት

“ ኧረ እንዲያውም ሊጋቡ ነው ” ሲል ቤተልሔም ጣት ላይ የጌጥ ቀለበት ያየው ደግም ነገሩን ያጋንናል ።

“ ስጥ እንዲህ ! ” ይላሉ ፡ ውሸቱ አልዋጥ ያላቸው።

“ ተወው እስኪ ያውራ ፡ እጅሬ መቼም መስጠት ልማዱ ነው።

ውሸት ፈጥረው የወሬ ማጣፈጫ እያደረጉ በማቅረብ የተካኑ ተማሪዎች አሉ ። “ ስጥ እንግዲህ ” የጨዋታቸው»
አርዕስት ሲሆን እነሱ ደግሞ “ አባ መስጠት ” በመባል ይታወቃሉ ።

ውሸቱ ከፍ ያለ እንደህነ "ርግጫ ” ይባላል ። ዋሻዎቹ “ ረጋጮች” ሲባሉ፥ የፕሮግራማቸው ስም ደግሞ

“ረግጣ” ነው ። ማኅበራዊ ኑሮን የሚጠሉ ጥቂት መሠሪዎች ካልሆኑ በስተቀር ። የአብዛኛው ተማሪ የሮይተሩም የረጋጩም - ተግባር የዩኒቨርስቲውን የዕረፍት ጊዚ ሕይወት ለማጣፈጥ ነው። »

“ እባካችሁ ጨዋታውን ወደ ቀልድ እትቀይሩት ይላል ለወሬው የጓጓ ፥ አምርሮ ።

"በቃ " ይኸው ነው ለማ ቤተልሔምን እወጣት

“ “A” ያለምንም መጨነቅ በእጅዋ ገባ ማለት ነው ።ከቻለ ደግሞ ከራሱ ትምህርት ዐልፎ ሌሎቹም ጓደኞቹ እንዲረዷት ይለምንላታል ፡

“ እናታቸውን ! እነዚህ ሴቶች ጨረሱን ” ኮ ! ጭንቅላት ሲያጡ በወሲብ ዩኒቨርስቲን ሊወጡ ! ” ሲል ፥ ሁሉም
በብሽቀት ጥርሱን እያንቀጫቀዉ በጅምላ ሴቶቹን ይራገማል።

“ ለካ ለዚህ ነው ” ይላል " እርዕስቱ እንዳይቋረጥ የሚፈልገህ ለአርዕስቱ እንደገና ሕይወት ለመስጠት ቅመም እያዘጋጀ

“ ምኑ ? ብዙ ጆሮዎች ሰልተው ይቆማሉ "

"ሰሞኑን ለማ ከሚስተር ራህማን ጋር ግንባር ፈጥሮት የሚታየው !!

"ራህማን ? ”

"ሚስተር ራህማን እኝያ ህንዳዊው ። ”

“ እ ! እ ! ” ሞቅ ያለ ሣቅ ።

“ ለማ የቅርብ ጓደኞቸ ሆኗል ። ለሻይ ሲወጡም አንድ ላይ ነው።

“ የዓላማ አንድነት ነዋ ያስተሳሰራችው ።

“ እሳቸው”ኮ ሐኪም ሳያይዝላቸው አይቀርም ። በሴት ቀልድ አያውቁም ፤ በተለይ ወፍራም ሴት ሲወዱ ! ”

“ ብቻ አንድ ቀን ሴት ጭን ውስጥ ትንፋሻቸው ቆሞ እንዳይገኙ ” ይላል የበሸቀው ክፍል እያፈዘ »

ጨዋታው ይቀጥልና ከመምህራን ተመልሶ ወድ ግል መበሻሸቅ ያመራል ። እርስ በርስ መጋለጥ ይመጣል ። አንዱ
የሌላውን ምስጢር ለመጎልጎል በነገር ጎሸም ያረጋል "ነገሩ የሚነካው ቁስለኛ ካለ በወዲሁ ማኩረፍ ይጀምራል ።
ሆኖም እነ “ ሮይተር ” የማንም ኩርፊያ አያግዳቸውም ።

“ ነገርን ነገር ያነሣዋል ” ሲሉ ይጀምራሉ

“ ደሞ ምን ልታመጡ ነው ? ”

የቤተልሔምን ጓደኛ ሊያወጣ የሞከረም ከመሃከላችንም አይጠፋም ኮ ! ”

ማንን ? ያቺን ማርታን እንዳይሆን ? ! ”
“ እህህሳ ! ማርታ ዐይኗ ስለማያርፍ ሳይሆን አይቀርም ፤ ብዙ ተማሪዎች ዐይናቸውን ጥለውባታል ፡ በግቢው ውስጥ ከብዙ ሴቶች መሃል ተለይታ ትታወቃለች ። ጠይቀው ሊያወጧት የሞከሩ ወይም የሚፈልጓት ከእስክንድር ሌላ ብዙ ናቸው በአለባበሷ ደምቃ ከመታየቷ ሌላ ምን ጊዜም ዐይኗ አያርፍም ። ስትበላ የአዳራሹን ወንድ እየቃኘች ነው ። ስታጠናም መጻሕፍት ቤት የተቀመጠ ፍጥረት አይቀራትም ። ወንዶችን ብቻ ሳይሆን ሴቶችንም ሥራዬ ብላ ነው የምታየው ፡ ሴቶችን የምታየው ግን በጤናማ ዐይን አይደለም ። ዘወር ብላ እንደ ሽንኩርት ትልጣቸዋለች ። በተለይ ደመቅ ያለች ሴት ማርታ ዐይን ውስጥ ከገባች አለቀላት !
ውሸት ፈጥራ ስሟን ታጠፋለች ። !

“ ውይ ! ያቺን ሞጥሟጣ ነው እንዴ ?” ሲል ቁስል ያለበት ማጥላላት ይጀምራል
“ሞጥሟጣነቷን በምን ዐወቅክ ? ” በማለት ፡ ሳታላይቶቹ ያፈጣሉ "

“ደሞ ምን ልታመጡ ነው ? እዚያው በጸበላችሁ ! ”
ቁስለኞ ማኩረፍ ይጀምራል ።

“ አንተ ምን አስኮረፈህ ? አንድ ቀን ብቻ ነው የጠየቅካት እና “F” ኮመኩህ ተመለስክ ። ይሄ ደሞ አያሳፍርም ።"

ጠይቆ ሲሳካ “A” እንደማግኘት ሲቆጠር ፡ ሳይሳካ ሲቀር ደግሞ "F" መኮምኮም ይባላል ።

“ አይ አጅሬ ! መኮምኮም አይሰለቸው ! ” በማለት ከፊሉ ያደንቃል "

“ ስጡ እንግዲህ ! አባ መስጠቶች መስጠት አይሰለቻችሁ።

“ ምኑ ላይ ነው ውሸቱ ?”

“ መዋሽት ብቻ ነዉ እንዴ ደኅና አርጎ መርገጥ ነው እንጂ ። ምን ታረጉ ? ! ዝም ብለው የሚረገጡላችሁ እገኛችሁ ርግጡዋቸው !”

አስረጅ ! ” በማለት ከመሐል ነገሩን አጠናካሪ ይናገራል።

"ደም አንተ ምን ልትል ነው ? ”

“ አጅሬ አንድ ቀን" እነማርታ የሚያጠኑበት ኣካባቢ ያለ ሥራው ሲያንዣብብ አግኝቼዋለሁ ፡ ”
አጥቂ ሲበዛበት ቁስለኛው የሚያመልጥበትን ዘዴ ያሰላሰላል ኩርፊያ አያዋጣም ። ቁጣም አያዋጣም ። የዚህ
ዐይነት አዝማሚያ ከታየ ተማሪዎቹ የባሰ ያሳብዳሉ ። ያለው ምርጫ ቀስ ብሎ ቀዘዴ አርዕስት ማስለወጥ ነው ።

“ ይልቅ የሚገርመው የዚያች የእነ ማርታ ጓደኛ ነገር ነው " ያ የአራተኛ ዓመት የማዕረግ ተማሪ የሚወዳት ! ”
ሲል እንደ ምንም ወደ ሌላ አርዕስት ይሸጋገራል ።

የቤተልሔም እና የማርታ ነገር ከተነሣ የትዕግሥትም አይቀርም » ብዙ ጊዜ አብረው ስለሚታዩ ነው ። አቤል ከሚስተር ሆርስ ጋር ተጣልቶ የአዕምሮ መታከሚያ ሆስፒታል ከተወሰደ ጊዜ ጀምሮ እነ “ ሮይተር ” ስለዚህ ጉዳይ
👍21
በቂ መረጃ አላቸው።
“ ትዕግሥትን ነው እንዴ ? ምስኪን ፍጥረት! እሷ'ኮ ምንም አታውቅ ። ከነድንግሏ እንደምትገኝ እኔ በዐሥር ጣቴ
እፈርርማለሁ።

“ በምን አወቅክ ? የፈተንካት አትመስልም ? ! ”

“ ኧረ ግፍ አትናገሩ! እሷ ከቀለም ሌላ ምንም አታውቅ ዐይነ - ውሃዋም ያስታውቃል አትን እባክህ ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር ፈስ ተምራ ትመጣለች እንደሚባለው ነው ። ከእነ ማርታ ጋር ውላ ደሞ ጤነኛ ትሁን እንዴ ሲል ጠርጣሪው ክፍል መከላከያውን ይኑረድራል ።

እነ "ሳተላይት ” እዚህ ላይ ትክክለኛውን መረጃ በመስጠት ሙግቱን ያስረዳሉ ።

“ እሷስ ገና ጥሬ ናት ። ምን ያረጋል ! ጥሬነቷ ነው ያንን ጂኒየስ ልጅ ያሳበደው

"ማንን ? ”

"አቤልን ነዋ ! ”

ምስኪኖች ! የእነሱ ነገር በጣም ይገርማል ? ኮ በዓይን ከመተያየት በስተቀር ተቀራርበው፦ ተነጋግረው አያውቁም

የዐይን ፍቅር ነዋ ! ዐይኑካ ! ”

“ ግን በምን ጣለበት? ሌላ ሴትኮ ቀና ብሎ አያይም ።

የዐይን ፍቅር ላይ የጣለው ጭምትነቱ ሳይሆን እይቀርም”ኮ ! ” በማለት የራሱን አስተያየት አከል የሚያደርግም አይጠፋም.....

«ምን ዋጋ አለው ! ጮማ ጭንቅላት ይዞ አሁን በሷ ምክንያት መቀነሱ ነው።እንዴ ኮ አዳራሹ ውስጥ ከነ ምግቡ የወደቀው እሷን እሷን ሲያይ ነው ! ”

"ትቀልዳለህ ? ይህን ያህል ? ”

አንተ ደሞ ለዚህ ለቀላሉ ጉዳይ ነው እንዴ ? ዕብዶች ሀኪም ቤት ድረስ ግብቷል “ኮ ! ”

በእሷው ምክንያት ?” ይላል ፡ ቀድሞ ነገሩን የሰማውም አብሮ ። ያልሰማው ጓጉቶ ነው ፤ የሰማው ደግሞ የሌላውን የፍቅር ሥቃይ ደጋግሞ መስማቱ ስለ ሚጥመው ነው።

“ ታዲያስ ! እንዲያውም እንደ ሰማሁት ከሆነ ዘንድሮ ትምህርቱን ጨርሶ የሚመረቅ አይመስልም ። ”

“ ያሳዝናል ! ” ሲል አብዛኛው ከንፈሩን ይመጣል ።

"ምን ያሳዝናል ፥ ያናድዳል እንጂ ! ዲዳ እይደል ።ቀርቦ አያናግራትም እምቢ ብትለውም ሴት አልጠፋ ባገሩ ! ” የሚል ተሟጋች ከመሐል ብቅ ይላል ።

“ እንደሱ አትበል እባክህ አያድርስ ነው ! ፍቅር መልኩ ብዙ ስለሆነ መፍረድ አትችልም " "

ግማሹ በሀዘኔታ ግማሹ በቀልድ የጦፈ ክርክር ያካሒዳል። አጋጣሚ ሆኖ እስክንድር ጨዋታቸው መሀል ካለ ኮቴውን ሳያሰማ ቀስ ብሎ ሹልክ ይላል የአቤልን ክፉ መስማት አይፈልግም ። እሱ ለአቤል ያለውን ቅርበትና ጓደኝነት ብዙዎቹ ስለሚያውቁ፡ በጨዋታው ላይ የበኩሉን መረጃ እንዲሰጣቸው ዐይን ዐይኑን ሲያዩት ነው የሚሾልከው።

ሳምሶን ጉልቤው በዕረፍቱ ጊዜ ካምፓስ ውስጥ አለመኖሩ ነው እንጂ፥ በአቤል ጉዳይ ከስንቱ ጋር በተጣላ ነበር።
በግቢው የአቤልና የትዕግሥት የዐይን ፍቅር የጨዋታ ማድመቂያ ሆኗል ። የሚወራው እውነትም ቢሆን ሳምሶን
የአቤልን ስሜት የሚጎዳ ነገር እንዲነሣ አይፈልግም ።

💥ይቀጥላል💥
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

ሻምበል ብሩክና ትህትና ድንበሩ ከተዋወቁ ዛሬ ልክ አንድ ወራቸው፡፡ የፍቅራቸው ወርሃዊ ልደት ውል የሚበጅበት ቀን በመሣሣም ደረጃ የቆየው ፍቅር ዛሬ ወደ አካላዊ ውህደት ሊሸጋገር እቅድ ተይዞለታል። ሻምበል ብሩክም ሆነ ትህትና የዛሬውን ቀን በልዩ ጉጉት ነው የጠበቁት።

እሁድ ዕለት አሥመራ መንገድ በሚገኘው በሻምበል ብሩክ ቤት ለማደር የወሰነችበት ቀን ነበር፡፡ ወደ ዶክተር ባይከዳኝ ቀጠሮ ስትሄድ የሚሰማት ስሜት ከቀጠሮው በስተጀርባ ባለው ምክንያት አስገዳጅነት እንጂ በፍቅር አስገዳጅነት አልነበረም፡፡
ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር የምትፈጽማቸው ግንኙነቶች እውነተኛ ስሜቷን የምትገልጽባቸው ሳይሆኑ፤ በተላበሰችው ጭምብል እውነተኛ ማንነቷን ደብቃ፤ በመድረክ ላይ ትያትር የምትሰራ ተዋናይ ሆና ነው የምትውለው፡፡ በሻምበል ብሩክ ፍቅር ግን ሰውነቷ እንደሻማ እየቀለጠ፣
ልቧ በዕልልታ እየጨፈረች፤ ሁለንተናዋን አሳልፋ የምትሰጠው በደስታ ስሜት ሰክራ ነው፡፡ በተለይ የመጀመሪያዋ በሆነው የወንድ ልጅ ፍቅር የተረታችለት ሰው፤ እንደዘመኑ ወጣቶች በአንድ ነገር ላይ ብቻ ትኩረት የሚሰጥ ሳይሆን በሷ ቦታ ሆኖ ሁሉን ነገር የሚያስብላትና፤
የሚያጽናናት፤ ሆኖ በመገኘቱ ፈጣሪዋን ታመሰግናለች፡፡
ብቻ አንዳንድ ጊዜ የሰው ልጅ ሥጋ ለባሽ ፍጡር ነውና፣ ሰው ተላላና ደካማ ፍጡር ነውና፤ ሰው ሰው ነውና፤ ይህ ሁሉ ፍቅር ድንገት ብን ብሎ ጠፍቶ፣ ሻምበል ብሩክም ተለውጦ፣ እንዳይከዳት ልቧ
መጠርጠሩ አልቀረም፡፡
እንደዚያ ታስብና ደግሞ አስተሳሰቧ ትክክል ባለመሆኑ እራሷን ወቅሳ “ብሩኬ አይለወጥም”
በማለት መልሳ መጽናናትን ታሳድራለች፡፡ በዛሬው ዕለት ሻምበል ብሩክ ቤት ለማደር ቀጠሮውን በልቧ የወሰደችው በከፍተኛ ደስታ ነው። ምናልባት የዛሬው አዳር ደግሞ ያንን ተንከባክባ ያቆየችውን የልጃገረድነት ወግ፣ ብር አምባሯን የምትፈተሽበት ወቅት ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚያ በኋላ “ዞር በይ” ቢላትስ? ልቧ
በመጠራጠርና፤ ባለመጠራጠር፤ስሜት መሀል ገብቶ ሲዋዥቅ ከዋለ በኋላ
አንድ ነገር አሰበች።

ለሻምበል ብሩክ ልጃገረድ መሆኗን ገልጻለት፤ እንደ ወጉ፤ እንደ ሥርዐቱ፤ በጫጉላ ቤት ብር አምባሯን ልትሰጠው ያላትን ምኞች የሱን ስሜትና ፍላጐት ከተረዳች በኋላ ካሳወቀችውና በአጠቃላይ ስለማንኛውም ነገር አብረው በጋራ መወሰን እንደሚችሉ ገምታ፤ በዚሁ ሃሳብ ፀናች።
“እማይዬ ዛሬ አዜቢና ጋ ነው የማድረው ፓርቲ አዘጋጅታለች' በማለት እናቷን ዋሸቻት።
“ባርቲ ደግሞ ምንድነው ትሁቴ?” እናት በመጠራጠር ስሜት፡፡
“ያው ነዋ! ጓደኞቿ ተሰባስበን ስንጫወት ማደር ማለት ነዋ!” እየሳቀች፡፡
አደራሽን የኔ እራስሽን ጠብቂ!!” እናቷ ዐይን ዐይኖቿን እያየቻት።የውጭ አዳር የተሰማው ገና ዛሬ ነው፡፡
“ምንም ችግር የለም:: ማሚ ሙች!” ጉንጫን ሳመቻት፡፡ እናቷ በልቧ
ዝግጅቷን አሰበችው፡፡ በጠዋት ተነስቶ መተጣጠቡ፣ ቀኑን ሙሉ ሲመረጥ የተዋለው ልብስ፣ ሦስት ጊዜ አውልቃ ቀይራለች። መስተዋቱ ሥራ አልፈታም፡፡ መኳኳሉ ሁሉ ያልተለመደ ነበር።
በልቧ ወደ ሻምበል ብሩክ እንደምትሄድ ብታውቀውም የሰጠቻትን ምክንያት ይሁን ብላ ተቀበለቻት፡፡
ዛሬ ሻምበል ብሩክ ጋ የምታድር መሆኗን ለአንዱአለም ስለነገረችው በጊዜ ወደቤት እንዲገባ ተስማምተዋል። በዚህ ላይ የቤት ሰራተኛዋ እታፈራሁ ታክላበት እናቷን በመንከባከብ በኩል ኃላፊነቱን
ስለሚወስዱ የሚያስጨንቃት ነገር አልነበረም፡፡ ሁሉንም አጥብቃ አደራ
ብላ፤ ከቤት የወጣችው ከቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ ነበር።
ሻምበል ብሩክ ዛሬ ሽር ጉድ ሲል አርፍዷል። አልጋው ቦታ ሲመረጥለት፤ ሲንከራተት፤ የቤቱ ቁሳቁሶች በሙሉ በአዲስ መልክ አንዴ በጭንቅላታቸው፧ አንዴ በእግራቸው፤ ሲቆሙ፤ ቦታ ሲመረጥላቸው ነው የተዋለው፡፡
በዛሬው የቤት ዝግጅት ላይ ሠራተኛዋ ብቻ ሳትሆን ሁለቱም ታናናሽ ወንድሞቹ አብረውት ቤቱን ሲያተራምሱት ነው የዋሉት፡፡
በመጨረሻ ላይ ግን ከዚያ በፊት ያልታየበት ዓይነት ሥርዓትና መልክ ይዞ ሲያይ ሻምበል ብሩክ ተደነቀ፡፡
በእርግጥም ይህ ሁሉ የሆነው በትህትና ምክንያት መሆኑን ሲያስብ፤ የትዳር ውጥኑ አግባብ መሆኑን አመነ። በዚያ በቤቱ ሥርዓት ተማርኮ ወደሌላ ሃሳብ ውስጥ ገባ፡፡
ባለፋቸው መጥፎ ጊዜያቶች ውስጥ የተጐዳ ልቡ፣ በትህትና የወደፊት የትዳር እመቤቱ አማካይነት ሊታደስና፤ ሲታነጽ፤ ታየው።
እናም የትዳር መዓዛ በርቀት ሸተተው፡፡ ይህ በርቀት የሚሸተው የትዳር መዓዛ ቀርቦ እንዲያውደው ተመኘ፡፡
ትህትና እስከምትመጣለት የቀጠሮው ሰዓት እስከሚደርስ ድረስ ተንቆራጠጠ።
ዛሬ የሚነግራት ትልቅ ጉዳይ አለው። እሷም እንደሱ በጉዳዩ
ላይ ፈቃደኛ ከሆነች ጉዳዩ የምሥራች ይሆናል። እሷን የፈለጋት ጊዜያዊ
ፍቅረኛ እንድትሆነው ሳይሆን፤ ዘላቂ የትዳር ጓደኛው እንድትሆን ነው::
ይህ እሱ የጓጓለትን በፀጋ ከተቀበለችለት ደስታው እጥፍ ድርብ ይሆናል፡፡
“ትሁት.. ትሁት.. ትሁት.. ስሟን ደጋገመው። በልቡ፡፡

ልክ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ታላቋ እንግዳ የዱር ጽጌረዳ መስላ አምራና፤ ደምቃ ከች! አለች፡፡ ቤቱን ከዚህ ቀደም አንድ ሁለት ጊዜ አይታዋለች፡፡ የዛሬውን ልዩ የሚያደርገው ለማደር ወስና የመጣችበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡
ሻምበል ብሩክ ከደጅ ወጥቶ እየተጠባበቃት ነበር። በሁለመናው
አቅፎ ተቀበላት፡፡
ከዚያም አጥሩን ዘልቀው እየተሳሳቁ፣ እጅ ለእኛ ተያይዘው ወደ ቤት ገቡ፡፡
የሻምበል ብሩክ ሁለት ታናናሽ ወንድሞቹ ሰላምታ አቅርበውላት ትንሽ ከተጫወቱ በኋላ የግል ነፃነት ሊሰጧቸው ወጡ።
ዛሬ የሻምበል ብሩክ ቤት ልዩ ሆናለች:: ትህትናም ከዚያ በፊት ያየቸው ቤት መሆኑ እስከሚያጠራጠራት ድረስ የቤት ዕቃዎቹ አቀማመጥ አስደንቋታል፡፡
ሻምበል ብሩክ የትዳር ምኞቱን ሊገልጽላት ሲያሰላስል፤ እሷ ደግሞ ሌላ የምትገልጽለት እጹብ ድንቅ የሆነ የምስራች ነበራት። ሻምበል ብሩክ በፍቅር ቢወድቅላትም፤ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ያልገመተውን ገፀ በረከት ልታቀርብለት ማሰቧን ቢያውቅ ኖሮ ምንኛ ደስተኛ ይሆን ነበር?፣
ቀለል ያለ እራት ከበሉ በኋላ ይሄንን የቀዘቀዘ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራቸውን
መኮምኮም ቀጠሉ። ዛሬ ቢራው አልመረራትም። የፍቅር ስኳር
ተጨምሮበት ነው መሰል፤ ከምትወደው ሰው ጋር በፍቅር እየቀለጡ፤ ሲኮመኩሙት ማር ሆነና ቁጭ አለ፡፡ ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ሆና ስትጠጣው የግራዋ ጭማቂ ያህል ነበር የሚመራት። አሁን ግን ጣፈጣት፡፡
አንዱን ቢራ ጨረስችና በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለተኛውን የቢራ ጠርሙስ ጨበጠች፡፡ ሻምበል ብሩክ የወደፊት የትዳር ጓደኛው ከምትሆን ቆንጆ ጋር እያሳለፈ ባለው ጊዜ እጅግ ከመደሰቱም በላይ ከረጅም ዓመታት በፊት እጮኛው ከነበረችው በድሏ ጋር ያሳልፉ የነበረውን ዓይነት ልዩ ስሜት አጫረበትና፤ ጨዋታውን በሰፊው ቀጠለ። እየተቃቀፉ መላላሱ ፤ መሳሳሙ፤ ሁሉ ለጉድ ነበር፡፡
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ሲሆን ወደ መኝታ ክፍላቸው መሄድ ፈለጉ።
የመኝታ ክፍሏ በንጽህና የተጠበቀች ናት። እንደገቡ በነጭ ስስ የመጋረጃ ጨርቅ የተሸፈነውን ባለመስታወት መስኮት ሲገልጡት ፍንትው ብላ ደምቃ የወጣችው ጨረቃ ብርሃኗን ወደመኝታ ክፍላቸው ውስጥ አዘለቀችላቸው...

ያንን የጨረቃ ውበት ሲያስተውሉ፤ መብራቱን አጠፉት በዚያች ክፍል
ውስጥ ጨረቃና ፍቅር ነገሱ ከዚያም ልብሳቸውን እንደለበሱ አልጋቸው ላይ ጋደም ብለው መላፋታቸውን ቀጠሉ....
የትህትና ሁኔታ የተለየ ነበር ከዚያ በፊት ለወንድ ልጅ የነበራት ስሜት ምን እንደ ነበረና አሁን ምን እየሆነች እንዳለች
ስታስበው
👍2🔥21
አንዳንድ ጊዜ ያበደች ይመስላታል። አንዳንዴ ደግሞ ሻምበል
ብሩክን ከማግኘቷ በፊት ጤነኛ መሆኗ ያጠራጥራታል፡፡ ፍቅር ማለት እንደዚህ አቅል የሚያስት፧ እንደዚህ የሚያስፈነድቅ ስሜት መሆኑ ይገርማታል።
አንዴ በቀኝ ክንዱ፣ አንዴ በግራ ክንዱ ላይ እየተገላበጠች፤ ቅብጥ ሲያደርጋት ደግሞ እዚያ ስፊ ደረቱ ላይ እየተንከባለለች፤ የደረቱን ጸጉር
እያፍተለተለች፤ ስትስመው፣ ሲስማት፤ ስታሸው፣ ሲያሻት፤ እንዲሁ በስሜት ሲጋጋሉ፤ በመቆየታቸው ገላቸው ከሚገባው በላይ ሞቀና ወደ መፍላት ደረጃ ላይ ደረሰ። ትህትና ቁና ቁና መተንፈስ ጀመረች፡፡
ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ስትሆን በሚሰማት የጣዕር ዓይነት የመቃተትና
የማቃሰት ስሜት ሳይሆን፤ በጣፋጭ ስሜት፤ እራስን አሳልፎ ለመስጠት
በመፈለግ ስሜት፤ መወራጨቷን ቀጠለች፡፡
ሻምበል ብሩክ የትዳሩን ሁኔታ አሁን ልግለጽላት ወይንስ ሲነጋ? እያለ ሲያመነታ ቆየ፡፡ ግን አልነገራትም።
ጨረቃዋ በክዋክብቱ ታጅባ፤ ከዋክብቶቹ እየደነሱ ጨረቃን ሞሽረው ሰማዩን ብሩህ ባደረጉበት ምሽት፧ እነሱ ደግሞ ይህ ሁሉ
ትርዒት ወለል ብሎ በሚታይበት የመኝታ ክፍላቸው ውስጥ በጀርባቸው ተንጋለው አዲሱ ፍቅራቸውን እየሞሸሩ፤ በስሜት መንኩራኩር ተሳፍረው፤ ያቺ ውብ ጨረቃ ወደ ታደመችበት ህዋ፤ መጠቁ....
በአንድ መግነጢሳዊ ኃይል ምድሪቱን ለቀው፤ በሀሳብ ክንፋቸው እየከነፉ፤
በህዋው ላይ ሲናኙ፤ ደስታቸው ገደቡን ስቶ የሚሆኑትን አጡ፡፡ ይህ የደስታ ስሜት ዑደት ከሷ ወደሱ፤ ከሱ ወደሷ ፤ እየተቀባበለ፤ እየተቀጣጠለ፤ በስሜት ክብሪት ተጭረው በፍቅር እየነደዱ ፤ እጆቿ አዛዥ ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው ስልጣን የሱን ልብስ ማውለቅ ሲጀምሩ፤ የእሱም እንደዚሁ የሷን ማወላለቁን ቀጠሉ፡፡ ለሁሉ ነገር ጥንቃቄ እወስዳለሁ ያላችው ሴትዮ፡-
“ጥንቃቄ ገደል ይግባ !!" ያለች መሰለች። ከዚህ በላይ ንግግር የለ፣ ውይይት የለ! ብቻ ሁለቱም በፍጥነት ከላያቸው ላይ የነበረውን ደንቃራ አስወግደው፤ለአንድ ወር በናፍቆት የተጠማ ገላቸው እርስ በርሱ ተፋጭቶ በመካከላቸው የሚፈጠረውን መብረቃዊ ብልጭታ ሊሟሟቁ ተጣድፈው ፤ ልብሶቻቸውን በፍጥነት አወላለቁ.....
የሷ ጣቶች በእሱ ሰውነት ላይ ሲርመሰመሱ፤ የሱም ጣቶች በሷ ለስላሳ
ገላ ተረታ ተሸነፈና አንዳቸው በሌላው አካል ውስጥ ቀስ በቀስ እየሰመጡ፣ በስሜት እየቀለጡ፣ በመንፈስም በአካልም እየተቆራኙ ሄዱ......
የሁለቱም ገላ ከሚገባው በላይ በስሜት ግሎ ነበረና ከጧፍ እንደተሰራ ሁሉ ፤ ተቀጣጥሎ ወደ ፈሳሽ ነጠብጣብነት የተቀየረ እስከሚመስላቸው ድረስ በወሲብ ፍላጐት ነደደ...ከዚያም በከፍተኛ የረሃብ ስሜት እርስ በርሳቸው ተሻምተው አንዳቸው በሌላው ውስጥ ጠፉ....

ከዚያም ሻምበል ብሩክ በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች መካከል በሚደረገው ውህደት ላይ ለመድረስ መንቀሳቀስ ሲጀምር፤ ትህትና ሉጋሙን ጥሶ እንደፈለግሁ ልጋልብ ከሚላት ስሜቷ ጋር መታገል ጀመረች፡፡ እንደሰንጋ ፈረስ ሽምጥ በመጋለብ ላይ የነበረው ስሜቷን እንደምንም ታግላ ሉጋሙን ያዘችውና...
“ብሩኬ .....እኔኮ.... ልጃገረ.....ድ ነኝ ” ስትል እያቃሰተች ሹክ አለችው፡፡
ሻምበል ብሩክ የሰማውን ማመን አቅቶትና ጆሮውን ተጠራጥሮ..
“ምን አልሽኝ ትሁት?” ሲል በድጋሚ ጠየቃት፡፡ አንገቱን በአንገቷ ውስጥ
እንደቀበረ።
“ገርል ነኝ” አለችው ደገመችና ፍስስ... ባለ ድምጽ።
ሻምበል በደስታ ብዛት የሚይዝ የሚጨብጠው ጠፍቶት እቅፍ
አድርጉ እንደ ሎሚ መጠጣት...
ይህ ሹክ ያለችለትን የምስራች ምንም እንኳን ቢያምናትም፤ እንደ ቶማስ ሀቁን ዳብሶ ለመረዳት ፈለገና፤ በሹክሹክታ ተነጋገሩ።
ከዚያም ተግባቡና በጥንታዊ አነጋገር ክራር በሚባለው ጨዋታ ለመጠቀም ተስማሙ፡፡
ከዚያም አካሉን ከአካሏ ቀስ በቀስ እያዋሀደ፤ እያለማመደ፤ ለስለስ ባለ ሁኔታ ክራሩን መምታት ቀጠለ፡፡ የዚያ የክራር ቅኝት ስሜት ለሁለቱም ልባቸውን ሰርስሮ የሚገባ፣ በጆሮ የሚደመጥ ሳይሆን በቀሪ የስሜት ህዋሳቶቻቸው የሚደመጥ፣ በሠራ አካላቸው የሚንቆረቆር፣ ውብ ጣዕመ ዜማ ያለው ሆኖ ተሰማቸው፡፡
ትህትና በዚያ በሰማችው የክራር ቅኝት እጅግ ረክታ፡
ሁለመናዋን ለቅኝቱ አሳልፋ ሰጠች፡፡ እናም በዚያ ቅኝት ውስጥ ትዝታን፤
በዚያ ቅኝት ውስጥ አንቺ ሆዬ ለኔን ! በዚያ ቅኝት ውስጥ አምባሰልን፣
ቢዘያ ቅኝት ውስጥ ባቲን ተጫወቱ፡፡
በእርግጥም የተዋጣለት ጨዋታ ነበረ፡፡ እዚያ እላይ ከስሜት ንረት ጥግ! ደርሰው ሲመለሱ ሁለቱም ቁና ቁና እየተነፈሱ ቆዩና እንደገና ተቃቅፈው ፤ እንደገና ተቆላልፈው፣ እንደገና ሊጫወቱ በስሜት ጭልጥ ብለው ነጎዱ.....
ሻምበል ብሩክ በፍቅር የተረታላት ልጅ ጣፋጭና ከሱ በፊት ያልቀመሳት
ልጃገረድ ሆና በማግኘቱ ደሰስታው ገደብ
አልነበረውም፡፡ የፍቅር አምላክ እምባውን ሊያብስለት ፈልጎ ትህትናን እንደሰጠው አምኖ በዚህ ባጋጠመው ዕድል ረክቶ ፈጣሪውን አመሰገነ፡፡የሁለት ተፈላላጊዎች ውህደት.
ትህትና በደስታ ብዛት የወሰደችው ሁለት ቢራ ሙቀትና ድፍረት ሰጥቷታል።ከፍቅር ጨዋታው መልስ በሻምበል ብሩክ ደረት ላይ እየተንከባለለች ስትፈነድቅ ፤የውስጥ ስሜቷን አምቃ መያዝ ተሳናትና፤
ደስታዋ ገደቡን ጣሰና፤ በዚያ አፍ በሚያስከፍት ማራኪና ተስረቅራቂ
ድምጿ ታንቆረቁረው ጀመር...
ምንም ሳላስበው ውጥን ሳይኖረኝ
የሚያስለቅስ ፍቅር በድንገት ያዘኝ፡፡
ጤና አእምሮ እያለኝ የሚያስብልኝ
የሚያስብልኝ።
እንዲሁ ቁጭ ብዬ አለቅሳለሁኝ
አለቅሳለሁኝ፡፡
ለካስ ፍቅር ሰውን እንዲህ ያደርግ ኖሯል
እንዲህ ያደርግ ኖሯል፡፡
በዚህ አስተያየት ስንት ሰው ተጎድቷል
ስንት ሰው ተጎድቷል፡፡
እያንሰቀሰቀ የሚያስለቅሰኝ የሚያስለቅሰኝ
ፍቅር እንደሆነ ጠቢብ ነገረኝ
ጠቢብ ነገረኝ
በረጅሙ የብዙነሽ በቀለን ዘፈን ትለቀው ጀመር። ከዘፈኑ ጋር በስሜት ተመስጣ፤ በሃሳብ ጭልጥ ብላ፣ በደስታ ሰክራ መስረቅረቋን ቀጠለች፡፡
ሻምበል ብሩክ በአድናቆት ፈዝዞና ደንዝዞ ያንን ልብ የሚሰረስር ድምጽ እያዳመጠ በስሜት አብሯት ጭልጥ ብሎ ሄደ...
ድንበሩን ያለፈ ደስታ አንጎል ያዞራልና፤ ሻምበል ብሩክ አንጎሉ ዞረ።
በመልክና በፀባይ የታደለችውን ወጣት የሱ እንዲያደርግለት ሲመኝ፤ ከነሙሉ ክብሯ አገኛት፡፡ ከዚያም አልፎ ደግሞ ይኸውና በዚያ በሚያደነዝዝ ድምጿ የፍቅር ዘፈን ስታንቆረቁርለት፤ ተደንቆ ይህችን ዕንቁ የሰጠውን አምላክ መላልሶ በልቡ እያመሰገነ፤ እሷ፣ ስትዘፍን፤ እሱ
ሲሰማት፣ እሷ ስትስረቀረቅ፤ እሱ በደስታ ሲቦርቅ፤እንቅልፍ በዐይናቸው ሳይዞር ሰማይና ምድር ተላቀቁ.....
የሻምበል ብሩክ ወንድሞች የሚያድሩት ከዋናው የመኖሪያ ቤት ራቅ ብሎ በተሰራው ሰርቪስ ውስጥ ነው፡፡ ሰራተኛዋ እራታቸውን ካቀረበችላቸው በኋላ ሲያጠኑና ቼዝ ሲጫወቱ ስላመሹ እንቅልፍ ጥሎአቸዋል። እዚያ እላይኛው ቤት በሻምበል ብሩክ የመኝታ ክፍል
ውስጥ የቀለጠውን ጉድ አልሰሙም::

ጠዋት ሲነጋ ሻምበል ብሩክ የጋብቻ ጥያቄውን አቀረበላት፡፡እሷም ፈቃደኛነቷን ከንፈሩን በመሳም አረጋገጠችለት። ከዚያች ቀን ጀምሮ እጮኛው ልትሆን ቃል ከገባችለት በኋላ አይን አይኑን በፍቅር እያየች..
“ለዚያን ዕለት ብለህ ነው የማርከው አይደል ብሩኬ?” እንደ መቅበጥ እያለች እየሳቀ ጠየቀችው፡፡

“ምኑን ትሁት?”ያለችው ቢገባውም አውቆ ያልገባው በመምሰል እሱም እየሳቀ ጠየቃት፡፡
“የወርቅ አምባሩን ነዋ!” ሄዳ እላዩ ላይ ወድቃ ሳመችው። እንደዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዐይን አውጣ ሆንኩ አይደለም እንዴ? እያለች ድርጊቷ ለራሷ ቢገርማትም፤ ለሻምበል ብሩክ ግን ከዚያም በላይ ብትሆንለት ፈቃዷ ነበር፡፡
አይሻልም ትሁት?” አላት እሱም እየሳማት፡፡
👍3
“በጣም እንጂ ብሩኬ አርቆ አስተዋይ ነህ” አለችው።
“እኔ የዘመኑ ጋብቻ ያስቀኛል?” አላት፡፡
“እንዴት?” ስትል ጠየቀችው። አይኖቿን ከአይኖቹ ላይ ሳትነቅል፡፡
“እዚያ ጫጉላ ቤት የሚገቡት ለምን ይመስልሻል?”
“ለምንድነው? እኔ አላውቅም” እየሳቀች፡፡
“ዋናው ቁም ነገሩን ገና ድሮ ይሸኙትና፧ እዚያ ጫጉላ ቤት ውስጥ ገብተው 'ወይኔ ዛሬ ቢኖር ኖሮ? እያሉ ተቃቅፈው ለመላቀስ ነው” አለና እራሱ ስቆ እሷንም በሳቅ ገደላት።
“ከሁሉ የበለጠ የሚያሳዝነኝ ደግሞ ሚዜ ነው።የሚዜ ጣጣው ብዙ ነው፡፡ ልጃገረድ ሆና ካልተገኘች ፤ ጣትን ቆርጦ ማድማት ይጠበቅበታል፡፡
በሰርጉ ማግስት ደግሞ የውሸት አበባ ይዞ ወደ ወላጆች መሄድም አለ ፡፡
አቤት የሚዜ ጣጣው! እኛም ሚዜዎቻችንን ከምናስቃያቸውና ብር
አምባር ሰበረልዎ እየተባለ ሲዘፈን ከምንሳቀቅ እስከዛው ድረስ ብናቆየው
አይሻልም ትሁት? ”
“በጣም ደስ ይለኛል ብሩኬ፡፡ የኔም እምነትና ፍላጐት ይሄው ነው፡፡አሁን
አንተ ስለሚዜዎችና ስለ ጫጉላ ቤት ስታወራኝ ግን አንድ ነገር ትዝ አለኝ
አለችና ከመናገሯ በፊት በሳቅ ፍርስ አለች፡፡ ሻምበል ብሩክም
ምንነቱን ሳያውቅ አብሯት ሲስቅ ቆየና ምንድነው እሱ ሲል ጠየቃት
ለመስማት ቸኩሎ..
እርጉዝ ሆነው ጋብቻ የሚፈጽሙትስ? እዚያ ጫጉላ ቤት ውስጥ ምንድነው የሚሰሩት? ስትለው እቅፍ አድርጓት ከጣራ በላይ ሲስቅ ቆየና ልብሳቸውን ለባብሰው ጨረሱ፡፡ ከዚያም ቁርሳቸውን አብረው ከበሉ በኋላ መጀመሪያ እሷን እቤቷ ድረስ ሸኝቷት ወደ ስራው ሄደ።


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሶስት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና ሻምበል ብሩክና ትህትና ድንበሩ ከተዋወቁ ዛሬ ልክ አንድ ወራቸው፡፡ የፍቅራቸው ወርሃዊ ልደት ውል የሚበጅበት ቀን በመሣሣም ደረጃ የቆየው ፍቅር ዛሬ ወደ አካላዊ ውህደት ሊሸጋገር እቅድ ተይዞለታል። ሻምበል ብሩክም ሆነ ትህትና የዛሬውን ቀን በልዩ ጉጉት ነው የጠበቁት። እሁድ ዕለት አሥመራ መንገድ በሚገኘው በሻምበል ብሩክ…»
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ በዛሬው ዕለት ከመሰል የሥራ ባልደረቦቹ ጋር ከፍተኛ የቀዶ ጥገና ሕክምና አጋጥሞት ነበር የዋለው፡፡ የቀዶ ጥገናው የተደረገላት ሴት በማኅፀን ዕጢ
በሽታ የምትሰቃይ ነበረች፡፡የሆድ ዕቃዋ ተከፍቶ ተከፈፍቶ የተገመተውና፤ በተግባር የታየው የሰማይና ምድር ያህል
ልዩነት ነቀረው።

በማህፀኗ ላይ ለአራት ሰአት የተደረገው የቀዶ ሕክምና ከሁለት ኪሎ ግራም በላይ ዕጢ እንዲወጣላት አስቻለ፡፡ ዶክተር ሰውነቱ በሥራ ደክሞ ስለዛለ በቂ ዕረፍት ለመውሰድ በጊዜ ወደ ቤቱ ገብቶ አልጋው ላይ ጋደም ለማለት ፈልጓል፡፡
ከድካሙ ቀለል እንዲለው ፤ በቀዝቃዛ ውሃ ገላውን ሙልጭ አድርጉ ከታጠበ በኋላ፤ የጥጥ ፒጃማውን እንደለበሰ ነበረ የተኛው፡፡በዚሁ መሀል ትህትና ገርበብ ያለውን የመኝታ ክፍሉን በር ከፍታ ገባች::
በዛሬው ዕለት ያለወትሮዋ የተርከፈከፈችው ሽቶ ቀድሟት ገባና
ክፍሉን በመዓዛው አወደው:: የዱር ጽጌረዳ፣ ጣፋጭ መዓዛ፤ እሷም
የጽጌረዳ አበባ መስላለች። ወትሮ ከሚያውቃት ትህትና በእጥፍ አምራ
ተውባለች፡፡ ኮቴዋን ሳታሰማ ወደሱ ትመጣለች፡፡
ቁልቁል ትመለከተዋለች፡፡ ገርበብ ባሉት ዐይኖቹ ሰረቅ አድርጎ አያት፡፡ በልቡ ውበቷን አደነቀ። ቀጭን ሳቋ ጆሮውን ሰረሰረው፡፡ ዐይኖቹን ገለጥ አድርጉ በሚያየው ነገር ተደንቆ፤ ሽቅብ ተመለከታት፡፡ እሷም በፈገግታ ተሞልታ እየተፍለቀለች ጐንበስ ብላ ጉንጬን ሳመችው፡፡
ከበላዩ ቆሞ፤ ውብ ፈገግታን የሚለግስ፤ በኋላም በአካል የሚዳስስ፤ መልአክ መስላ ታየችው፡፡
የዛሬው አመጣጧ ድንገተኛ ሆኖበታል። የተቀጣጠሩት ለዛሬ አልነበረም፡፡ እንዴት ቀድማ መጣች? ገረመው። ከቀጠሮ በፊት መምጣቷ ምናልባትም በፍቅሩ ወጥመድ እየወደቀችለት ለመሆኗ ፍንጭ ስለሰጠው የደስታ ስሜት የሠራ አካላቱን አዳረሰው፡፡
“የደብረዘይቱ የሽርሽር ውጤት እየታየ ነው” አለ በልቡ፡፡ የሚገርመው ደግሞ አንጀቱን ለመብላት ያላደረገችው ጥረት የለም፡፡ የለበሰችው ስስ ተካፋች ጃኬት እኒያ ገና ከሩቅ ሲያያቸው ውሃ
የሚሆንላቸው! ጡቶቿን፤ አጋልጦ ያሳያል። በዚህ ላይ እኒያን ውብ ባትና ጭኖቿን፣ በግልጽ የሚያሳይ አጭር ቀሚስ ነው የለበሰችው፡፡

“በቃ በፍቅር ወድቃልኛለች ማለት ነው”
በስሜት እንደሰከረ ፍዝዝ ባሉት ዐይኖቹ ይመለከታት ጀመር። ጭውው አለበት፡፡ ሽውው የሚል ነፋስ ሲነፍስ፣ የፍቅር አማልክት በያሬዳዊ የሙዚቃ ቅኝት
ስለፍቅር ሲያዜሙ ፧ ተሰማው፡፡ ድብት የሚያደርግ የድካም ስሜት..ድቅቅ
ያለ ሰውነት በደስታ የሰከረ ቀልብና ልብ፡፡
አሁንም ከት ብላ ሳቀች። አሳሳቋ እንደ ገደል ማሚቶ አስተጋባ፡፡ ሁኔታዋ ሁሉ ግርም ብሉት፤ አፉን ከፍቶ ይመለከታት ጀመር፡፡ ዐይን አፋራ፣ ቅልስልሷ ፤ ትህትና መሆኗን ተጠራጠረ፡፡ ፍቅር ያንን ሁሉ
የእፍረት ማቅ አሽቀንጥራ እንድትጥል አድርጓታል ማለት ነው? ፍቅር እውር ነው ወይስ እውር ያደርጋል? በትክክል እውር እንደሚያደርግ ከሷ እንደዚህ የውቦች ቁንጮ ሆናለት፤ ከቀጠሮአቸው በፊት ሹልክ ብላ ስትመጣለት ምን ይባላል? ማመን አልቻለም፡፡
ዐይኖቹን አሸት አሸት አድርጉ ሁለት እጆቹን ወደላይ ዘረጋና
“ትሁትዬ” አላት በደከመ ድምጽ።
ቀስ በቀስ ያ ሰውነቱ እየጋለ መሄድ ጀምሮ ነበር፡፡ በተለይ የዘረጋላት እጆቹን ወደዚያ ውርውር አድርጋ..
“ከቀጠሮ በፊት ስለመጣሁ መዘነጥህ ነው?” ብላ ከተሰቀለው መስታወት
ውስጥ ፊቷን ለማየት ዘወር ስትል፤ አጭሩ ቀሚስ እላይ ድረስ ዘልቆ እኒያ የሚያማምሩ ጭንና ባቶቿን ወለል አድርጉ ሲያሳየው አልቻለም፡፡ቀስ በቀስ እንደ ካውያ እየጋለ በመሄድ ላይ የነበረው ሰውነቱ የሚያደርገውን ያሳጣው ጀመር፡፡
በተለይ የምትሽኮረመም ሴት ይወዳል። እንዲያ ግፍትር አድርጋው ስትሽኮረመም፧ እልህ ያዘው። በዚህ ላይ ባቶቿ ኑ ብሉኝ! ኑ ብሉኝ! እያሉ ይጋብዛሉ። በዚያ ባዶ ቤት ውስጥ፤ በዚያ ሰፊ የሞዝቦልድ አልጋ ላይ እየተንከባበሉ፤ ያንን ባለፈው ጊዜ ተልፈስፍሶ ያመለጠውን ሲሳይ ዳግም እንዳያመልጠው ሊሞክር ቸኩሎ ተነሳና...
“ከቀጠሮ በፊት መምጣትሽ ምን ያህል ልቤን እንዳስደሰተው ከፍተሽ ባየሽው የኔ ቆንጆ?” በጀርባዋ በኩል ሄዶ፤ በሁለት እጆቹ እቅፍ አድርጓት፤ አንገቱን በአንገቷ ውስጥ ቀበረና! ጡቶቿን ያሻሻቸው
ጀመር..
ቀስ በቀስ እየሞቀች ስትሄድ ግለቷ ተሰማው። ከዚያም አፏ እንደተከፈተ ዘወር ስትልለት፤ በተከፈተው አፉ ቀለባት፡፡ ከዚያም እጆቹ ወገቧ ላይ ሲጠመጠሙ፤ እጆቿ ደግሞ በአንገቱ ዙሪያ እንደ ድር
ተጠንጥነው፤ ሰስሜት ተዋህደው ነጐዱ.....
እኒያ ውብ አይኖቿ ስልምልም ብለው ጠፉ፡፡ ከዚያም ቀስ ብለው እየተደነቃቀፉ፤ እየተደጋገፉ፤ ወደ አልጋው ሄዱና ወደቁ፡፡ ዛሬ ትህትና እንደዚያን ዕለቱ ዐይኖቿ በእንባ አልተሞሉም፡፡ ይልቁንም በደስታ እየተፍለቀለቀች፤ በፍቅር፤ ለፍቅር፤ ስትል ሁለመናዋን በግልጽ እየሰጠችው ነው፡፡
ዶክተር በዛሬው ዕለት ብር አምባር ለመስበር በእርግጠኝነት መንፈስ ተሞልቷል፡፡ በደብረ ዘይቱን የሽርሽር ወቅት በተለይም በሆራ ራስ መኝታ ክፍል ውስጥ ሲልፈሰፈስ ያመለጠው
እንዳያመልጠው በመስጋት፤ ኃይሉን የአንበሳ፤ አድርጎ ትግሉን ቀጠለ፡፡
የታጠቀችው የውስጥ ሱሪ ከዚህ በፊት የሚያውቀው ነጩ ባለወንፊቱ ነበር፡፡ በስሜት ደርተው ሲታገሉ፣ በፍቅር ስሜት ተውጣ የሆነ ነገር እያቃሰተች በጆሮው ሹክ አለችው፡፡ “አስገ...ው...ባ..ው..ው."

በዚህ ጊዜ ዶክተር በሲቃ ስሜት ተውጦ ካሰበበት ለመድረስ ጥድፊያውን ቀጠለ፡፡
እሷ ለሚሆነው ነገር ሙሉ ለሙሉ እራሷን ዝግጁ አድርጋ ሲመለከት፤ ደስታው እጥፍ ድርብ ሆነ፡፡ ዶክተር ላብ በላብ ሆኗል።ትህትናም በላብ ተነክራለች። ከረጅም ጊዜ ትግል በኋላ ...
“ዋ!!.......ይ!! !” ብላ ጮኸችና የዶክተር ባይከዳኝን ሰውነት በጥፍሮቿ ግጥም አድርጋ ይዛ አለቀሰች፡፡ ዶክተር ስለተቧጠጠ ገላው ደንታም ሳይሰጠው በድል አድራጊነት እርካታ ተውጦ ግዳዩን ለማየት ተጣደፈ፡፡
በእርግጥም ድል አድርጓል፡፡ በዚያው ስሜቱ እስከሚረካ ድረስ ቆየ። ከዚያም ተዘርራ ተመለከታት፡፡ ይህ ውስጥ ለውስጥ ያደርገው የነበረው ስሜታዊ ትግል፤ ቀስ በቀስ በውስጡ ሲሯሯጥ ከቆየ በኋላ፤ አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ፤ ወደ ገሀዳዊው ዓለም ተለወጠ፡፡
በዚህ ለውጥ ሰዓት ከእግር ጥፍሩ፤ እስከራስ ጠጉሩ ድረስ የነዘረው ንዝረት አባነነውና፤ በላብ እንደተዘፈቀ ከገባበት የቅዠት ዓለም ወጣ! እግዜኦ! ዶክተር በዚያን ሰዓት የተሰማውን የስሜት ስብራት በቃላት ማስቀመጥ ይከብዳል።
ያ ሁሉ ዓለም፣ ያ ሁሉ ደስታ፤ እንዲህ እንደዋዛ እንደጉም በንኖ ጠፋና፤ የሱን ስሜት እንዳይሽር አድርጎ አቁስሎት በፀፀት ጉድቶት አለፈ፡፡ ያ ሁሉ የድል አድራጊነት ስሜት በቅጽበት ቦታውን ለሽንፈት ለቀቀና፤ በዶክተር ባይከዳኝ ልብ ውስጥ ሀዘን ጥቁር ደመናውን አጥልቶበት ሄደ...
“ቡል ሺት! ” አለና ትራሱን በቡጢ ጠልዞ የሆነውን ነገር እንደ አዲስ አስተዋለ፡፡ በቅዝቃዜው ስሜት ተጠራጥሮ ሲዳብስ፤ ፒጃማውን ረጥቦ አገኘው፡፡ ከዚህ በኋላ ሁኔታዎችን ቀስ ብሎ ይመረምር ጀመር።
በቀላሉ የሚልፈሰፈሰው አካሉ አሳድሮበት የነበረው ሥነ ልቡናዊ ተጽዕኖ
ለጥቂት ጊዜ እራሱ በፈጠረው ትንሽ የቅዠት ደሴት ውስጥ ጠፍቶ፤ነበር
ጊዜያዊ የተስፋ ጮራ በልቡ ውስጥ እንደፈነጥቅበት፤ እሱም ጓደኞቹ
ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ እንደሚችል፤ አረጋግጦለት ነበር።.....

ድንግልናን መግሰስ በማይችል አካላዊ ብቃቱ ለዘመናት አዝኖ እንዳልኖረ ሁሉ፤ በዚህች ቅጽበት፤
2👍2🔥1