አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ቀመጠ ።አቤል ገና በአንድ ቢራ መፍዘዝ ጀምሮአል ። ዝምታው እንግዳ ነገር ባይሆንም” ፥
ከዚያ በላይ ጥልቅ ተመስጦ ውስጥ እንደ ገባ ያስታውቅ ነበር ። በአዳራሹ ውስጥ የሚንቻቻውን ጠጪ ትክ ብሎ ይመለከታል ። በዐይኑ ይመልከት እንጂ ልቡ ከዚያ አልነበረም ።

እስክንድርና ሳምሶን ቢራ እስኪደክሙ ድረስ ምላሳቸው አልተፍታታም ። ሆኖም የአቤል ሁኔታ በግምት ስለ ገባቸው ከተመስጦው ሊያነቃቁት ሞክሩ ።

“ አቤል ፥ ተጫወት እንጂ ! ” አለወ• ሳምሶን " ፍቅር ባዘለ ድምፅ ። ሳምሶን ከማንም ጋር በሰላም እንኳ ቢነጋገር ፥ የድምፅ ቅላጼ ቁጣ ያለበት ይመስላል ። አቤል ላይ ሲሆን ምን እንደሚያሳሳው ለራሱም ይገርመዋል ።

“ እሺ ጨዋታ ሕምጣ በል ” አለ አቤል ስሜቱን ወደ እነሱ ለመሰብሰብ እየሞከረ

ድብርትን ለምን ይዘኸው አልመጣህም ? ” ሲል እስክንድር በድንገት ሳምሶንን ጠየቀው ። ጨዋታ ለመክፈትም
ከሳምሶን ጋር ለመለካከፍም ያቀረበው ጥያቄ ነበር ።

« እሺ አይለኝም እንጂ ይዤው እመጣ ነበር ” አለ ሳምሶን ከልቡ መኝታ ክፍል ውስጥ ቢለክፈውም ቅሉ፡ በሳምሶን ልብ ውስጥ የመረረ ተንኮል ወይም መጥፎ ስሜት አልነበረም።

« ሆሆይ ! ኧረ እሱ አንገቱን ቢያርዱትም ከሰው ጋር አይመጣም ” አለ አቤል ጸባዩን ስለሚያውቅ ።

ሌለ ድብርት ከሳምሶን የበለጠ የሚያውቁት ብዙ ጊዜ አብረውት የኖሩት አቤልና እስክንድር ናቸው ሦስት ዓመት
ያህል አንድ መኝታ ቤት ውስጥ ሲኖሩ ፥ አንዳችም ከድብርት ጋር የሚጋሩት ትውስታ የለም ። ከግቢው አይወጣም ።
ከወጣም ብቻውን ነው ። ከሰው ጋር ተቀራርቦ ተጫውቶ የሚጣጣም አይመስለውም ። የእሱ ሕይወት እንቅልፍን ትመስላለች ። የሕይወትነት መዓዛ የላትም ። በዚህ ምክንያት
እስክንድር ድብርትላ ከውስጡ ወይም ከውጭው አካሉ አንድ የተደበቀ የጎደለው ክፍል ይኖራል የሚል ጥርጣሬ አለ ።

« እኔ ማየት የምጓጓው እሱ የሚይዛትን የሴት ጓደኛ ነው አለ እስክንድር ።

አንዲት የሱ ቢጤ ድብርት አለችውኮ! አለ ሳምሶን ብዙ ቀን ግቢው ውስጥ አብረው አይቻቸዋለሁ።

"እኛ ግቢ ውስጥ ? ” አለ እስክንድር ተደንቆ

“ ስነግርህ ! ” አለው ሳምሶን “ እንዲያውም፤ድብርት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሥቅ ያየሁት ከእሷ ጋር ሆኖ ነው ። ወሬአቸው ሁሉ በክሹክታ ዐይነት ፡ አለ አይደል ብቻ በዐይንህ ብታያቸው ፍቅር መሆኑ ይገባሃል......

💥ይቀጥላል💥
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

#ፖሊስ_ጣቢያ

የጣቢያው የምርመራ ሹም ሻምበል ብሩክ በላይ በእለታዊ የስራ ጉዳዩ ላይ ተጠምዶ፤ አንገቱን እንዳቀረቀረ ነበር፡፡ የቢሮው በር በቀስታ ተቆርቁሮ በዝግታ ሲከፈት፤ ልብ አላለም ፡፡እሱ በያዘው
አስደናቂ የወንጀል ሪፖርት ተመስጦ በሃሳብ ጭልጥ ብሎ ሄዶ ነበር፡፡ደመ ነፍሱ፤ በሩን ከፍቶ የገባው ከስራ ባልደረቦቹ አንዱ እንደሆነ ነበር
የነገረው፡፡በሩን ቆርቁሮ የገባው እንግዳ ግን ፤ እንደወትሮው ከስራ ባልደረቦቹ
አንዱ አልነበረም፡፡ ባለጉዳይ ነው፡፡ እሱ እንደዚያ አንገቱን አቀርቅሮ የቀረበለትን ፋይል ሲመረምር፤ ከፊት ለፊቱ እጆቹን አጣምሮ የቆመው እንግዳ ደግሞ፤ በድንጋጤ ተውጦ፤ የሱን ሁኔታ ይመረምር ነበር፡፡ዘንካታ ቁመናው ልቡን እንደመሰጠው ፤ መልኩ የሞዛርት ትዝታን
አመጣበት፡፡በተለይ ተጠቅልሎ ሄዶ ከግንባሩ ላይ ሲደርስ ክንብል ያለው
ዞማ ጸጉሩ ልዩ ውበትን አጎናጽፎት ተመለከተ፡፡ ሻምበል ብሩክ የደንብ
ልብሱ አብሮት እንደተፈጠረ ሁሉ እጅግ የሚያምርበት ግርማ ሞገስ ያለው ወጣት መኮንን ነው፡፡ ያ የገባ እንግዳ እሱ ራሱ በሌላ እንግዳ በሆነ የስሜት ሉጋም ተሸምቅቆ ልቡ በሃይል እየመታ፤ ትንፋሹ ቁርጥ፤ ቁርጥ፤እያለበት “እህህ እህህ ...."በማለት ጉሮሮውን ሳለና ድምጽ
አሰማ :: ሻምበል ብሩክ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀና ያለው በዚያ የእንግዳው ቀስቃሽ ድምጽ ምክንያት ነበር፡፡እንደዋዛ ቀና ያለው አንገቱ ዳግም ላለማጎንበስ ምሎ የተገዘተ ይመስል በዚያው ቀረ፡፡ባየው ነገር ተደናግጦና አይኖቹን ማመን ተስኖት እስከሚያስታውቅበት ድረስ ልቡ ዘለላች፡፡እዚህ ጋ ጎደለሽ የማትባል፤ አምላክ እጁን ታጥቦ የሰራት የምታስብል፧
የውበት እመቤት እጆችዋን ወደ ኋላ አጣምራ አንገትዋን አቀርቅራ ከፊት ለፊቱ ቆማ ተመለከተ፡፡ ሻምበል ብሩክ ልጅቷን አተኩሮ በማየት ፈዝዞና “ምን ልርዳሽ?" ብሎ መጠየቅ ግዴታው መሆኑን ዘንግቶት፤ የመጣችበትን ምክንያት ሳይጠይቅ፤ ለረጅም ደቂቃዎች በመዘግየቱ፤ እፍረት ቢጤ ቢሰማውም፤ እሷም ከዚያ በፊት በማንኛውም ወንድ ላይ ተሰምቷት በማያውቅ እንግዳ ስሜት ተሸብባ መቅረቷን ሲያውቅ ኖሮ፤
የእፍረት ስሜቱ ትንሽ በቀነስለት ነበር፡፡ እሱ ምን እንደዚያ እንዳፈዘዘው
ውስጡን ሲጠይቅ፤ ትህትናም “ለምን ደነገጥኩ ግን? የሚል ጥያቄ ለራሷ አቅርባ ነበር፡፡ልቧ የደነገጠበትን የመኮንኑ ተክለ ቁመናና ውበት ወደዚያ ተወት አድርጋ እራሷን ብትዋሽም ከዚያ የበለጠው ዋነኛ ምክንያቷ ግን፤ እንደዚያ ከነ ማእረግ ልብሱ አምሮና ተውቦ ስታየው፣ልቧ በደስታ የሚሞላበትን፤ እጅግ በጣም የምትወደውን፤ የአባቷን ትክለ ቁመና ስላስታወሳት መሆኑ ሳይታወቃት አልቀረም፡፡በትንሽነቷ ጊዜ አባቷ ያንን የምትወድለትን የማእረግ ልብሱን ለብሶ ስታየው፤ ትንሷ ልቧ
በደስታ እየዘለለች ፤እሷም እንደ አባቷ እንዲያምርባት፣ በዚያ በትንሽ ሰውነቷ ላይ ያንን ትልቅ ኮት ትደነቅር ፧ ሱሪው ውስጥ ትገባና እየተጎተተች ስትዘንጥ ፤ አባቷ በሳቅ ሲፈነዳ “አያምርብኝም አባዬ
"ስትለው፡፡
"እንዴታ ትህትናዬ በጣም እንጂ! አንቺም ስታድጊ እንደኔ ወታደር ትሆኝና ፤ ዩኒፎርምሽን ለብሰሽ፤ እንደዚህ ታጥቀሽ ፤ እንዴት እንደሚያምርብሽ ይታየኛል፡፡" ሲላት ቶሎ አድጋ፤ ያንን ዩኒፎርም
ለብሳ የምር የምትዘንጥበትን ጊዜ ስትናፍቅ፤ እያደገች ስትመጣ ደግሞ
ያንን ከጎኑ ሻጥ የሚያደርገውን ሽጉጥ ትቀበለውና፤ እሷም ጎኗ ላይ ሻጥ አድርጋ ስትንጎራደድ፤ ልዩ ደስታን ይሰጣት ነበር፡፡አባቷ ያንን ሽጉጥ ጥይቶቹን ከውስጡ ያወጣና ስለ አተኳኮሱ፧ ስለ አጠቃቀሙ ፤
እያሳያት፤ ባዶውን ሲሰጣት ታነጣጥርበትና ምላጩን ሳብ
ስታደርገው ፤ እሱም የውሸት ወደ ኋላ ሲወድቅላት፤ ከዚያም ትመጣና
ከሞተበት እንዲነሳ ስትኮረኩረው፡፡ከዚያም በሳቅ እየተፍለቀለቀ እቅፍ
አድርጎ ወደ ላይ አንስቶ ሲስማት፤ ይህ ሁሉ የነበረው ሁኔታ ..እሱ ታስቧት
ይሆን? ወይንስ ወንድሟን እንዲፈታላት መልአክ አድርጋ በሀሳቧ የሳለችው ሰው ነው ? እሷም አልገባትም ::
በህይወት እያለ ይሰማት የነበረው ስሜት አፈር ከለበሰ ይሄውና አመታት መቆጠር ጀምረዋል፡፡ አሁን ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ያ ስሜት ፊት ለፊቷ በምታየው መኮንን ምክንያት በትዝታነቱ ተቀስቅሶባት
የገባችበትን ምክንያት እስከምትዘነጋው ድረስ አፈዘዛትና ቆማ ቀረች፡፡
ሻምበል ብሩክ የገባበት ሁኔታ ቀስ በቀስ አልፎለት፤ ስሜቱን መግዛት ሲጀምር።
ፊት ለፊቱ የቆመች ልጅ ምን እንደምትፈልግ መጠየቅ እንደሚገባው
ሲታሰበው፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊቱን ፈካ፤ ጥርሶቹን ብልጭ አደረጋቸው፡፡ እግዚኦ ! ጥርሶቹ እንዴት ነው የሚያምሩት? ስሜቷ እንደገና ተለዋወጠና ልቧ ትር ትር አለባት
አይኖቿ እንደዚያ ፍጥጥ ብለው ሲመለከቱት ሻምበልም ምን ልታዘዝ የኔ እመቤት?" የሱም ስሜት አብሯት እየተለዋወጠበት፡፡
"ወንድሜ ታስሮብኝ ነው የመጣሁት " ትንፋሽዋ እየተደነቃቀፈ፡፡
“እሺ ወንበሩ ላይ አረፍ በይና ንገሪኝ እስቲ በእጁ ወንበሩን እያመለከታት፡፡
ሻምበል ብሩክ ስሜቱ ለሁለት ተከፍሏል ፡አይኖቹ ከፊት ለፊቱ የሚታየውን ድንቅ ውበት በማድነቅ ስራቸውን ሲሰሩ ፤ ጆሮዎቹ ደግሞ የአቤቱታውን ምክንያት ለማዳመጥ ተከፍተዋል፡፡ ትህትናም አፏ
ስለአጋጠማት ችግር ሲያወራ፤ ልቧ ፊት ለፊቷ በተቀመጠው መኮንን ውብ ትክለ ቁመና ተማርኮ ከውስጥ እየሟሸሸባት ነበር፡፡
የእለት ሁኔታ መዝጋቢው ለእርስዎ እንዳመለክት ነግረውኝ ነው የመጣሁት”
“በምን ጉዳይ ነው የታሰረው? ማነው ስሙ? " አከታትሎ ጠየቃት፡፡
“አንዱአለም ድንበሩ ነው ስሙ"
"በዚያ በዲፕሎማት መኪና ላይ ስርቆሽ ከፈጸሙት ውስጥ ነው?"
“ኸረ እሱ ሌባ አይደለም" ፈርጠም ብላ፡፡
"ቆይኝ አንድ ጊዜ "አለና የቀረበለትን ሪፖርት ለማውጣት የጠረጴዛውን
መሳቢያ ከፈተ፡፡ በዚያ በስርቆት ወንጀል ላይ የተሳተፉት ሶስት ሰዎች ሲሆኑ የአንዱአለም ስም የለበትም፡፡
ልክ ነሽ፡፡ በዋናው ስርቆት ላይ አልነበረም
"ለምን ታሰረ ታዲያ?" በልቧ" ዋና ስርቆትና ሁለተኛ ስርቆት የሚባል
ነገር አለ እንዴ? እያለች ነበር፡፡
“ምን መሰለሽ? በስርቆቱ ላይ ባይኖርበትም ከሌቦቹ ጋራ በአንድ ላይ
ሆነው የተሰረቀውን ገንዘብ ሲያጠፉ ከተገኙ ሰዎች ጋር አብሮ ተገኝቶ ነው የተያዘው" በማለት ስለሁኔታው አስረዳት፡፡
ታዲያ አሁን አይለቀቅም?" በልምምጥ መልክ አይኖቿን በአይኖቹ ላይ
አንከራተተቻቸው፡፡
ያንተ ያለህ !እንዴት ነው አይኖቿ የሚያምሩት? አይኖቿን ለመሸሽ
አይኖቹ ወዲያና ወዲህ ተሯሯጡ :: የሚሄዱበት አጥተው ማምለጥ
ሲሳናቸው ደግሞ ተመልሰው መጡ፡፡ በአይኖቿ ባህር ውስጥ ሰጥመው በተዘረጋላቸው መረብ እንደ አሳ ሊዋጡ.......
“ስምሽ ማነው የኔ እመቤት?" ::
"ትህትና ድንበሩ" እየተቅለሰለሰች፡፡
“አንዱአለም ታላቅሽ ነው ወይስ ታናሽሽ?"
"ታናሼ ነው "
ሻምበል ብሩክ በስርቆቱ ወንጀል ላይ የተሳተፉት ዋነኞቹ ወንጀለኞች በእስር ቤት እንዲቆዩና፤ ሌሎቹ በዋስትና እንዲለቀቁ እሱና ሻለቃ ለሜሳ ቀደም ብለው ተወያይተው መመሪያ የሰጡበት ጉዳይ ነው፡፡የ ፶ አለቃ ውብሸት በመመሪያው መሰረት ሊያስተናግዳት ሲችል ለምን ወደ እሱ እንደላካት? ግራ ቢገባውም ልቡ አንድ ነገር ጠረጠረና በራሱ ግምት ትንሽ ፈገግ አለ፡፡
ይህቺን እንኮይ አንድ በላት ማለቱ ይሆን?"
"አንቺ ዋስ ሆነሽ ልታስፈቺው ነው የመጣሽው?"

“አዎን፡፡ ከፈቀዱልሽ ትችያለሽ ብለውኛል"
"ማነው እንደሱ ያለሽ?"
"መርማሪው"
ትህትና? ደግሞም አንቱ አትበይኝ አንተ እያልሽ አስረጂኝ”
"ስንት አመትሽ ነው
አስራ ሰባት "
ሻምበል ብሩክ ፈገግ አለና ...
"ዋስ ለመሆን እኮ እድሜሽ ቢያንስ አስራ ስምንት መሙላት አለበት::ስለዚህ እናትሽ ወይንም አባትሽ መጥተው ዋስ ሊሆኑት ይችላሉ፡፡
ከተናገራት በኋላ ሻምበል ብሩክ በፍጹም
እሺ?" አላት፡፡ ይህንን ከተናገራት በኋላ ሻምበል ብሩክ በፍፁም ያልጠበቀው ሁኔታ ገጠመው ፡፡ አይኖቿ በአንድ ጊዜ በእንባ ተሞልተው አይኖቿ ውስጥ
ይንከባለሉ ጀመር፡፡ከእነዚያ ለማየት እንኳ ከሚያሳሱ እኒያን የመሰሉ ውብ አይኖች
እምባዋ እንደጉድ ፈሰሰ፡፡ ሻምበል
በእንባ ሲሟሽሹ ዝም ብሎ ማየት ተስኖት ተርበተበተ፡፡
“ምን ሆነሻል ትህትና?ወንድምሽ እንደሆነ ዛሬውኑ ይፈታልሻል፡፡ ምን ሆነሽ ነው እንደዚህ የምትሆኚው?" ሲል በድንጋጤ ተውጦ ጠየቃት፡፡
"አባት የለኝም :: እናቴም ከአልጋ ላይ መነሳት የማትችል በሽተኛ ነች፡፡
እነሱ ዋስ ሊሆኑት አይችሉም፡፡ የኔ እድሜ አስራ ስምንት ሊሞላው አምስት ወር ብቻ ነው የቀረው፡፡ እባክዎት እኔ ዋስ ልሁነውና ይፈታ?"
ተለማመጠችው፡፡ ሻምበል ብሩክ ይህንን አሳዛኝ ታሪክ ከዚህች ቆንጆ ትንሽ ልጅ አንደበት ሲሰማ ከልቡ አዘነላት፡፡ ያንን ውበት ያለወላጅ እንክብካቤ በፍጹም ያልጠበቀው ስለነበረ በፈጸመው ስህተት
ተጸጸተ፡፡ትህትና ከልቡ እንዳዘነላት ሲገባት ታሪኳን በግልፅ ነገረችው፡፡ አባቷ ወታደር የነበረ መሆኑን፤ በምስራቅ ጦር ግንባር
መውደቁን ፤ ከዚያም እናቷ በበሽታ ምክንያት አልጋ ላይ መዋልዋንና
የቤተሰብ ሃላፊነት ሸክሙ እሷ ላይ የወደቀ መሆኑን ፤አንድም ሳታስቀር
ዘረዘረችለት፡፡ ያንን በቀላሉ ለማንም የማታወራውን ሚስጥሯን አንዱ አለምን ያስፈታልኛል በሚል እምነት ብቻ ሳይሆን፤ ለእራሷም እንግዳ በሆነ ስሜት ምንም ሳትደብቅ አወጋችው በይበልጥ የተደፋፈረችው ደግሞ ሻምበል ታሪኩን ለመስማት ያሳየውን ፈቃደኝነት በመጠቀም ጭምር ነበር። ወደ ቢሮው ሌላ ባለጉዳይ እንዳይገባ ለስራ ባልደረቦቹ ትእዛዝ በመስጠት በዝርዝር እንድታስረዳው ስላደፋፈራት ተረጋግታ፤
የወንድሟ ያክል ምንም ሳትፈራው! በዝርዝር ነገረችው፡፡ ሻምበል የምትናገረውን በጸጥታ ካዳመጠ በኋላ...
“አይዞሽ ትህትና ለወንድምሽ እኔ ራሴ ዋስ እሆነዋለሁ። አታስቢ፡፡በተረፈው ግን ሰፋ ያለ ጊዜ ወስድን እንወያያለን፡፡ አይዞሽ ! እሺ?"አጽናናት፡፡ ደስ አላት ፡፡ሄዳ ብትስመው ምንኛ በወደደች? ገና እንዳየችው ልቧ ያለምክንያት እንዳልደነገጠባት አወቀች፡፡ ምስጋናዋን ከመቀመጫዋ ብድግ በማለት በአንገቷ ለመግለጽ ስትሞክር...
"ግድየለም ቁጭ በይ" አለና ትከሻዋን ያዝ አድርጐ ወደ ወንበሩ መለሳት፡፡ ከዚያም መርማሪ ፖሊሱን ጠርቶ፤ በሱ ዋስትና አንዱአለም እንዲለቀቅ አደረገ፡፡ ከዚያም የስልክ ቁጥር እንዳላት ቢጠይቃት
ስልክ ያለው ጎረቤት እንኳ እንደሌላት ነገረችውና ተሳስቀው ፤ የራሱን የቢሮውንና የመኖሪያ ቤቱን ስልክ ቁጥሮች ጽፎ እንድትደውልለት"
አደራ" ብሎ ከወንድሟ ጋር አያይዞ አሰናበታቸው፡፡ ትህትናም በአንድ
ድንጋይ ሁለት ወፍ እየገደለች መሆንዋንና ያንን እንደገባች የፈዘዘችለትን ሰው እንደዚህ በአጭሩ ዘመድ ማድረግ በመቻሏ እየተገረመች ሳለ፤ በተጨማሪ ስልኩን ሊሰጣት ፈቃደኛ መሆኑን ስታረጋግጥ ደግሞ የበለጠ ልቧ በደስታ ዘለለች፡፡ ሆኖም ልቧ ከውሰጥ መጨፈሯ እንዳይታወቅባት ጥንቃቄ ሳይጎድላት ሻምበል የስልክ ቁጥሩን ጽፎበት የሰጣትን ወረቀት ቀስ ብላ ተቀብላ ወደ ጡት ማስያዣዋ ከላከችው በኋላ ምስጋናዋን ያለገደብ አቅርባ፤ ወንድሟን ይዛና፤ በፍቅር ተይዛ፤ ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ አንዱ አለም ከዚያ ሲኦል ከሚመስል እስር ቤት ባስፈታችው እህቱ ተመካባት፡፡ ከዚያ ባለፈ ደግሞ ሻምበል
ብሩክ የከፈለለትን ዋጋ በዝርዘር ከትህትና ሲሰማ፤ ሻምበል ብሩክን
አከበረው፡፡ ወደደው፡፡ ትህትና በለስ ቀንቷት ወንድሟን አስፈትታ መመለሷ በእጅጉ ቢያስደስታትም፤ ከሻምበል ብሩክ ጋር እንደዚህ በአጭሩ መለያየቷ ግን ቅር አሰኛት፡፡"ምንድነው እንደዚያ የሚያደርገኝ?'ብላ እራሷን ስትጠይቅ፡፡

“እንጃልሽ ! ይላታል የገዛ ስሜቷ፡፡ የዚያን አይነት ስሜት ከዚያ ቀን በፊት በፍጹም ተሰምቷት አያውቅም ነበርና ግራ ተጋባች፡፡ ያም ሆነ ይህ ለተቃራኒ ጾታ
ፍቅር ስሜቷ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሸነፈ መሆኑ ግን ትንሽ በትንሹ ሳይገለጥላት አልቀረም፡፡አሳሳቁ ፤ አለባበሱ ግርማ
ሞገሱ፤ ትህትናው፤ የጸጉሩ ውበት፤ በተለይ ያቺ ከፊቱ ላይ ክንብል
ያለችው ዞማ ጠጉሩ፤ በዚህ ሁሉ ላይ ደግሞ ወንድሟን ከእስር ቤት ያስፈታላት ባለውለታዋ መሆኑ፤ ይሄ ሁሉ ነገሩ በዛባትና፤ ሻምበል ብሩክን አከበረችው፡፡ አፈቀረችው፡፡ በዚህ መሃል አንድ ሃሳብ መጣባት
"ሚስት ትኖረው ይሆን?" የሚል፡፡ ወየው ጉዴ፡፡ የቀለበት ጣቱን አላየሁትም እኮ፡፡ ለምን ጣቱን ሳላይ ቀረሁ ?ምን አይነቷነኝ ግን? በፍጹም አይኖረውም፡፡ ገና ወጣት ነው :: ከዚህ በፊትስ አያገባም ከራሷ ህሊና ጋር ተሟገተች :: የጣት ቀለበቱን ባለማየቷ ተናደደች፡፡መናደድ ብቻም ሳይሆን ሄደሽ ተመልሰሽ አረጋግጭና
እወቂው የሚል ስሜትም ገፋፍቷት ነበር፡፡ እንደምንም ብላ ቻለችው እንጂ

ከአንድም ሁለት ጊዜ ለመገናኘት ይዘውት የነበረውን ፕሮግራም እየሰረዘች ፤ የማትፈልገው መሆኑን ለመግለጽ ጥረት ብታደርግም፤ዶክተር ባይከዳኝ ፍቅሩ በገፍ፤ ስሜቱ በእጥፍ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ ሊሄድ አልቻለም፡፡ ሁሌም የዚያ የደብረዘይቱ ጉዞ ስኬታማነት፣ በዚያ
የመኝታ ክፍል ውስጥ የተሰማው የእርካታ ስሜት፤ እየታወሰው፣ እንዲያ በወሲብ ግለት ነዶ ራቁት ሰውነቷን በጉጉት ሲመለከታት የነበረው ሁኔታ፤ ያ የልጅነት ውብ ገላዋ ፣ያ የማይጠገብ ጣፋጭ
መአዛዋ፤ እነዚያ በከንፈር ውስጥ ቀልጠው የሚጠፉ የሚመስሉት
እንጆሪ ከንፈሮቿ ፤ ከዚያም ሁሉ በላይ ደግሞ ማንነቱን የሚፈትሽበት ድንግልናዋ፤ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው፤ ተባዝተው፤ በሀሳቡ እየተግተለተሉ ይመጡበትና፤ እሷን ለማግኘት በሲቃ ስሜት ያወራጩታል፡፡

ትህትና በተላይ ሻምበል ብሩክን ካየችውና ልቧ ከደነገጠላት በኋላ
ዶክተር ባይከዳኝ በጣም ነበር ያስጠላት ቢሆንም ግን የዚያ የእናቷ ጉዳይ በመካከላቸው አላና፤ በአስቸኳይ ልትገላገለው አልቻለችም፡፡ሻምበል
ብሩክን ካወቀችው ዛሬ አምስተኛ ቀኑ ነው፡፡ አምስት ቀን ሙሉ ስልከ አልደወለችለትም፡፡ ቶሎ ብትደውልለት የሚንቃት፤ የሚጠላት፤ እየመሰላት ናፍቆቷን በልቧ አምቃ ቆየች፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ አዜብም የምትመክራት ትንሽ ኮራ እንድትል ነው፡፡ ወንድ ልጅ ፊት ከሰጡት
ጥጋቡ ኣይቻልም እያለች፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ ለዛሬ ራት በራሱ መኖሪያ ቤት ነበር፡፡ ዶክተር ፍጹም ቅዠት ነው ተብሎ ሊታመን በማይችል ሁኔታ በህልሙ ተለይቷት ባያውቅም፤ ከደብረ ዘይት ሽርሸር በኋላ በአካል ያገኛት ገና
አሁን ነው፡፡
ትህትና ሥራ እንደጀመረች እናቷን የምትጠብቅላትና፤ እንጀራ የምትጋግር ልጅ እግር ሠራተኛ ከዚያችው ከምታገኘው ደመወዝ ላይ እንደአቅሚቲ ስለቀጠረች፤ ወጣ ገባ፤ ለማለት ዕድል አግኝታለች፡፡......


ይቀጥላል

በየቀኑ ሳይቆራረጥ እንዲደርሳችሁ የበዛ Like 👍 እንዲሁም የበዛ #Share እፈልጋለው።

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...“ እንዲያው ምን ምን ይላት ይሆን?እኔ እሱ ለሴት ልጅ የሚያወራውን ነገር ለመስማት እጓጓለሁ " ግን አንተ ባል
ከው ዐይነት አገጣጥሞኝ አያውቅም ። ”

“አጅሬ ምኑ ሞኝ ነው ላንተ የሚታየው ?!እሷን ሲያገኛት ቦታው ጭር የሚልበትን ጊዜ ጠብቆ ነው ።

“ ወይ ጉድ ! መቼም ፍቅር የማያሸንፈው ልብ የለም ”አለ እስክንድር በልቡ ። ስለ ድብርት የበለጠ ለማወቅ ጓጉቶ ነበር ። ሆኖም ጨዋታው በተዘዋዋሪም ቢሆን አንዳንድ የአቤልን ድርጊቶች እንደሚንካ ስለ ገመተ አርዕስቱን ለመለወጥ ፈለገ ሳምሶንም ይህንን ሁሉ ልብ ሳይል እንደ መጣለት ነበር የሚጫወተው ። እስክንድር ግን የአቤል ስሜት
እየተለዋወጠ እንደ መጣ በሥርቆት ከገጽታው ላይ አንብቦአል ድብርት የሴት ጓደኛውን ለማግኘት ጭር ያለ ጊዜ
መጠበቁ የአቤልን ስሜት ክፉኛ ነክቶታል እሱም ትዕግሥትን ለማየት የሚጠቀምባቸውን ጊዜያቶች ያውቃል ።

ስማኝ ላምሶን ! ግን ለምንድነው አንተ ብዙ ጊዜ ድብርትን የምትለክፈው ? ” በማለት እስክንድር አርዕስቱን አሸጋገረው
“ ለተንኮል አይደለም ። ግን የሚነፋነፍ ሰው መልከፍ እንዲሁ ደስ ይለኛል ። እንዴት ብዬ ላስረዳህ ? ለምሳሌ
ቀርቦ መናከስ የማይደፍር ውሻ በሩቁ እያፈገፈገ ሲጮህብህ እልሁን ለማስጨራረስ በዱላ እንደምትተናኮለው ዐይነት ነው ። ብቻ እንዲሁ ስለክፈው ደስ ይለኛል እንጂ ለድብርት መጥፎ አመለካከት የለኝም ለየት ያለ ተፈጥሮ ስላለው ያስገርመኛል ” አለና አሳላፊዋን ለመጥራት ጠረጴዛውን ጠበጠበ።

“ አቤት ! ምን ልታዘዝ? ” እያለች አንገቷ በንቅሳት የተዥጎረጎረ ሴት ከፊታቸው መጥታ ቆመች ።

“ ቢራ ድገሚን ሦስት ቢራ ! ” አላት ሳምሶን በዚያው ቁጡ ድምፁ

“ እኔ ይብቃኝ ! ” አለ አቤል "

“ አትቀልድ እባክህ ። አንቺ እኔ የማዝሽን አምጪ!” አለና ሳምሶን አሳላፊዋ ላይ ጮኸባት ።

"ጥርስሽን እንዳያወልቅ ” አለና እስክንድር በልቡ ሳቀ ።

“ እኔኮ ያንተም ተፈጥሮ ያስገርመኛል ” አለው እስክንድር ሳምሶንን
“ እንዴት ?”
“ አሁን ሚስተር ሆርስ ከአቤል ጋር ከታረቀ በኋላ ለምን ትዝትበታለህ ?”

“ አዎ ! የማታውቀው ነገር አለ እስክንድር እየዛትክ የምትተው ከሆነ ዛቻው ሲደጋገም ሰው ይንቅሃል ።ወንድ ከሆንክ አንዴ ማቅመስ አለብህ ። እንዲያውም አንተን ብዬ ነው እንጂ እሱን ልጅ አንድቀን ብሰብረው ደስይለኛል ። ከፈለገ የገዛ ጥርሱን ከመሬት አሰለቅመዋለሁ ።

“ጡንቻህን ፈትነኝ እያለ ያስቸግሃል መሰለኝ” አለና እስክንድር እየሣቀ ከእሱ መልስ ሳይጠብቅ ፡ “ ብቻ ያለንበትንም ጊዜ አትዘንጋ : ሀያኛው ክፍለ ዘመን ላይ ነን ” አለው ።

“ እና ? ” የብሽቀት ድምፅ ነበር ።

“ እናማ ስፖርተኝነትህን እወድልሃለሁ ። ይህችን በጡንቻ መመካትህን ግን ...

“ እንግዲህ አትልከፈኝ ፡ ልጠጣበት ! ” አለና ቢራውን ተጎነጨ

ሳምሶን ሌላ ሰው እንዲህ ቢናገረውም ካልተደባደበ በዋዛ እይላቀቁም ነበር ። ለእስክንድር ያለው ክብር ግን ብዙ ዓመት ከቆየ የልጅነት የአስተሳሰብ ተጽዕኖ የመጣ ነው ። የሠፈር ልጆች እንደ መሆናቸው መጠን ሳምሶን ስለ እስክንድር ብዙ ነገር ያውቃል ። እሱ ገና ልጅነቱን ሳይጨርስ እስክንድር በሠፈራቸው ውስጥ ስመ ጥር ጎረምሳ
ነበር ። እንዲህ እንዳሁኑ ከመስከኑ በፊት እናቱ በእስክንድር ያላዩት አበሳ የለም ። ከለውጡ በፊት ጸብ አሽትቶ ነበር
የሚፈልገው ። እስር ቤትን ቤቱ አድርጎት ነበር ። አንዴ ጸበኞቹ በቡድን ሆነው ከደበደቡት በኋላ ሆዱ ላይ በጩቤ
ወግተውት ለጥቂት ነው ከምት የተረፈው ከለውጡ በኋላ ደግሞ በወቅቱ በተፈጠሩት የፖለቲካ ድርጅቶች ሳቢያ
ያልቀመሰው፡ አበሳ የለም ። ችኩል ነበር ። ሰው አይገራውም ፣ ያየሁት አይለፈኝ የሚል ስሜት ያሸንፈዋል ።
የጀብደኝነት ስሜት ያጠቃዋል ። ትኩስ ኃያልነቱ፡ መንፈሱን ያቅበጠብጠዋል ። አሁን ግን በዕድሜም በብስለትም ሰክኖ
እንኳን ለራሰ ሌሎችንም ይመክራል ። ከአፍላነት ቅብጥብጥነት ጊዜው ይዞ የመጣውና አሁንም ያልተወው ነገር ቢኖር
የሲጋራ ሱስ ብቻ ነው። ይህ ሁሉ ሁኔታ በሳምሶን ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም። በፀጉሩ ኪንኪነት እየለከፈው ከእስክንድር ጋር መቃለድ የጀመረው እንኳ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው።

አቤል እባክህ ተጫወት ይሄንን ተወው
አለ ሳምሶን እስክንድርን በመንቀፍ አይነት

“ እየሰማኋችሁ “ኮ ነው ? ” አለ አቤል በጨዋታቸው ውስጥ የቆየ ለመምሰል ጥርሱን በውሸት ብልጭ አደረገ።

ሐሳቡ በከፌል ወደ እነ ትእግስት ዘምቶ ነበረ። ፈተና ከጨረሰች በኋሳ ወዴት ትሔድ ይሆን ? አርፎ መተኛት ወይስ
ዙረት መውጣት ? እያለ ሲያሰላስል ነው የቆየው።ሁለተኛውን ጠርሙስ ቢራ ግማሽ አድርሶታል ። ከቻቻታው ጋር
ቢራው ሞቅ አድርጎት ውስጥ ውስጡን እየሰከረ መምጣቱ ይሰማው ነበር። የመጠጣት ልምድ ስለሌለው ጭንቅላቱ ቶሎ መረታት ጀምሯል ። ድፍረትም ተሰማው ማንንም ያለመፍራት ሃይነት ስሜት !

“ ለምን ሙዚቃውን አይቀይሩልንም ? ” ሲል ድምፁን አሰማ ። የእንግሊዝኛ ሙዚቃ ነበር አዳራሹን የሚነቀንቀው፤“ ማስቀየር እንችላለን ። የማን ክር ይደረግ ? ” አሉ እስክንድርና ሳምሶን በአንድ ድምፅ አቤል ከዝምታ ወደ
ተሳትፎ መምጣቱ ደስ አሰኝቶአቸው ነበር

•የ... የመልካሙ ተበጀ ክር ቢሆን
ይሻላል” አለ አቤል በተሰባበረ ድምፅ

እስክንድርም ሆነ ሳምሶን በፍጥነት የጠረጠሩት ነገር አልነበረም ። አሳላፊዋን ጠርተው ክሩ እንዲቀየር አዘዟዋት።

ባለቤትየዋ እሷ የመረጠችው ዘፈን ካልሆን እሺ አትልም ግን ልሞክርላችሁ ” አለች አሳላፊዋ ።

“ ንገሪያት ! ለምን እሺ አትልም ? ” አለና ሳምሶን አፈጠጠበት እሷ ዘፈኑን ልታዝዝ ስትሔድ አቤል ቀድሞ በልቡ
ያንጐራጉር ጀመር።

አረ መላ ምቱ ወዳጅ ዘመዶቼ
ዐይናፋር ሆኛለሁ ፡ ዐይናፋር አይቼ
ሰሳምታ አልሰጠኋት አላነጋገርኳት
በዐይን ብቻ እያየሁ አንድ ዓመት ወደድኳት።

ልቡ ይህን እያዜመ፥ ጆሮው የሚሰማው ግን ሌላ ሙዚቃ ነበር ቢጠብቅ ፥ ቢጠብቅ የተለወጠ ነገር የለም ጥቂት
ቆይታ አሳላፊዋ ተመልሳ መጣች።

የመልካሙ ክር የለም ብላለች ባለቤትየዋ ! ”

አቤል በሽቆ “ ገደል ግቢ በያት ! ” ከማለቱ ዐይኑ እንባ አቀረረ ። የሰው ስሜት የማይጠበቅበት ዓለም ! ባለቡና ቤቶች ፍቅረኛውን የሚያስታውስበትን ዘፈን አይከፍቱለትም "መምህራን ትምህርት ምን ያህል እንዳስጠላው አይረዱለትም ። ወላጆቹ ልጃቸው ከድህነት ቀንበር እንዲያላቅቃቸው
ይመኛሉ እንጂ እሱ ያለበትን ችግር አያውቁለትም ። ጓደኞቹ ብቸኝነቱን አይፈቅዱለትም ።

“ እሷ ከሙዚቃዋ ጋር ገደል ትግባ ! አንቺ ቢራ ድግሚን ” አላት ሳምሶን በሽቆ ።

“ኧረ ይብቃን ! ሰዓቱም መሽቷል የካምፓስ ፖሊሶች አያስገቡንም ” አለ እንክንርድ ኪሱን እየዳበሰ ።

አምጪልን እባክሽ እንጠጣው ዛሬ ካምፓስ ማን ይገባል? ” አለ ሳምሶን በሞቅታ ስሜት ።

“በይ እንግዲያው አንቺንም እንጋብዝሽ የምትጠጪውን ነገር ይዘሽ ነይ ” አላትና እስክንድር ፡ ወደ ሳምሶን ዘወር ብሎ ፥ “ ከጠጣን አይቀር መሐላችን አንዲት አንስታይ ስትኖር ይሻላል” አለው ። ከሳምሶን ሁኔታ ገንዘብ እንደያዘ
ገምቶ ነበር "

እቤል ምንም አስተያየት አልሰጠም ። የያዘውን ቢራም አልጨረሰም ። ከዚያ በላይ መጠጣት አልፈለገም ። ሆኖም
አልተከላከለም ። ሕይወትን የመሰልቸት ዐይነት ነበር የሚሰማው ። ለምንም ነገር ያለመጨነቅ ። ስካር ማለት ይሄ ይሆን እንዴ?
👍1
ስለ መጠጣት ስላለመጠጣት ፥ ካምፓስ ስለ መግባት ስላለመግባቱ አቤል ደንታ የለውም ። “ እነሱ ይከራከሩበት

ጠርሙስ ውስጥ የቀረውን ቢራ አንሥቶ ጅው አደረገው ጉሮሮው ላይ እየተናነቀው ለምን በግድ እንደሚጠጣ መመራመር አልፈለገም ። ብዥ አለበት ቻቻታ ! ትርምስ ብዥዥ ዥ... ራስን የሚረሱበት ዓለም ።

ድፍረት ድፍረት አለው ። እልህ ተናነቀን ማንን እንደሚደፍር ፥ በማን ላይ እልሁን እንደሚወጣ ግን አያውቅም።
“ ስማ እስክንድር ! ” አለው ሣቅ እየተናነቀው ወደ እስክንድር ፊት ተጠግቶ “ እኔ ትዕግሥትን እወዳታለሁ ።
እሷ ግን አይገባትም ። እ -አይገባትም ። ”

እስክንድርና ሳምሶን ተደናገጡ ድንገተኛ አርዕስት ሆነባቸው። አቤል ግን አርዕስቱን በልቡ ከጀመረው ቆይቷል
ያም ሲሆን ጉዳዩም ሁለቱም አላጡትም

"ከወደድካት ይገባታል እንጂ አቤል ለምን አይገባትም ችግሩ ሁለታችሁም ተቀራርባችሁ ያለመነጋገራችሁ ነው" አለ እስክንድር ፈራ ተባ በሚል ድምፅ።

ከአሁን በፊት በግልጽ ተነጋግረውበት የሚያውቁት ጉዳይ መነሣቱ በእስክንድር ላይ ሁለት ስሜት አሳደረበት።

በአንድ በኩል እውነቷን ከአቤል ለመስማት ሲጓጓ ስለ ከረመ ደስ ብሎታል በሌላ በኩል ደግሞ አቤል ምስጢሬ
ብሎ የያዘዉን ነገር በስካሩ ጊዜ ማውጣቱ ሲውል ሲያድር ትዝብት ላይ የሚጥለው መሰለው ። በመጨረሻ ግን ነገሩን እሱ ጀምረው እንጂ እኔ አልጀመርኩት ” ብሎ ተጽናና ።

የምትወደኝ ከሆነ ለምን ዝም ትለኛለች ? አየህ እስክንድር እኔ'ኮ ትዕግሥትን ሳላያት ውዬ ማደር አልችልም ። ምርኮኛዋ ነኝ ። ምርኮኛዋ ስለሆንኩ እፈራታለሁ ።
ላናግራት አልደፍርም እሷ ለምን ዝም ትለኛለች? የራሱ ጉዳይ ብላ ኢይደለም ? ! ”

ሲናገር እንባውን ወደ ውስጥ ለመግታት እየታገለ ነበር ።እከክንድርና ሳምሶንም ልባቸው አዘነ ።

ትዕግሥትም ለእንተ የግዴለሽነት ስሜት ያላት አይመስለኝም ።” አለው እስክንድር ፡ “ ተገናኝታችሁ መነጋገር ስላልቻላችሁ ነው እንጂ ፡ እኔ እንደሚገባኝ እሷም
ያንተኑ ያህል ትወድሃለች ። ”

“ እሺ ይሁን ። እሷ ምናልባት ትወደኝ ይሆናል ። ነገር ግን በመሃላችን ምቀኞች አሉ ። ጓደኞቿ ናቸው የሚመክሯት ። በተለይ ያቺ ማርታ ! ”

“ እሷም ለአንተ መጥፎ ስሜት የላትም ፡፡ አቤል ሙት እልሃለሁ ። እኔ በቅርብ ዐውቃታለሁ ” አለው እስክንድር ።

"ዋናው ችግር ምንድን ነው? ለምን እኛ አንረዳውም ? » አለ ሳምሶን ከልቡ ተቆርቁሮ።

«ለመረዳት ቦዘንን ብለህ ነው ችግሩ የቀላል ከባድ ሆነና ነው እንጂ!” አለው እክንድር ቀስ ብሎ ።

“ ምን መሰላችሁ እኔ በእሷ ያልሆንኩት ነገር የለም ።እ....ብቻ -- እኔ ብቻ ነኝ ስለ ራሴ የማውቀው ” እያለ ከተቀመጠበት
ተነሣ ። ወንበሩን ሲለቅ ትንሽ ተንገዳገደ።

“ ወዴት ትሔድ ” አለው እስክንድር
"ወዶ ሽንት ቤት"በየት በኩል ነው ?

እስክንድር በምልክት አሳየው ። በዚያ ሁሉ ጠጪ መሐል ሁለት እጁን እኪሱ አድርጎ ፡ ሁሉንም በንቀት ዐይን እየተመለከተ ነበር ወደ ሽንት ቤቱ የሔደው ።.......

💥ይቀጥላል💥
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

.....ቀኑ እሁድ ነው፡፡ ለዛሬው ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ለሚኖራት ግንኙነት
በቂ ዝግጅት አድርጋለች፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ እንደዚያን ዕለት አምሮና ተውቦ ፒጃማውን ለብሶ ከሳሎኑ ሶፋ ወንበር ላይ ጋደም ብሎ እየጠበቃት ነበር፡፡

ለምን እንደሆነ እሱ እራሱ አንዳንዴ ግራ ቢገባውም፤ ልቡ እንደዚያ በፍቅሯ እየተቃጠለ፣ በስሜት እየነደደላት፤ እሷ ፊት ግን ኮራ ለማለት ይሞክራል፡፡

በእርግጥ ይሄ ኮራ ማለቱ ጠቀመው እንጂ አልጎዳውም፡፡ ሴት ልጅ
ጠንካራ ሰውነት ብቻ ሳይሆን፤ ደንዳና - የወንድ ልጅ ልብ እንደሚያሸንፋት ሳይንሱን ሳያገኘው አልቀረም፡፡

እንደዚያ ኮራ፤ ጀነን፤ ሲል የዶክተርነት ሙያው ፈጣሪ አከል አምልኮን በልቧ ያሳድርባትና፤ እያከበረችው፤ እሱ ያዘዛትን እንድትፈጽም ያስገድዳታል፡፡

የዛሬዋ ትህትና ልክ የዚያን ዕለት ስታቃዠው የዋለችው ትህትና ሆና
መጣችለት፡፡ የለበሰችው አጭር ቀሚስ ነው፡፡ ከላይ ጣል ያደረገችው ተካፋች ሸሚዝና አጠር ሳሳ ያለ ነጭ ኮት ነበር፡፡ እድሜ ለአዜብ ወጣ የምትልባቸውን ልብሶች የምትዋሰው ከሷ ነው፡፡ በአጠቃላይ እንደ ደብረ ዘይቱ ጉዞ የመስክ ሠራተኛ መስላ ሳይሆን የወንድ ጓደኛዋን ስሜት ለመማረክ የተዘጋጀች አፍቃሪ መስላለች፡፡

ዶክተር ባይከዳኝ በወሲብ ላይ ምን ያክል ደካማ እንደሆነ ተገንዝባዋለች፡፡የዛሬ ሁኔታዋም አቅሙን ለመፈተን፤ ጠንካራ
ሆኖ ከተገኘች የሚቀጥለውን ውሳኔ ለመወሰን፤ እንደዚያ እንደ ደብረዘይቱ የሚልፈሰፈስ ከሆነ ደግሞ እንዲህ እንደዋዛ ለሚያልፍ ነገር ላለመቀያየምና ችግር ውስጥ ከመግባት ይልቅ እሱን ደስ እያሰኘች ለመቆየት ወስና ነበር፡፡
ለዚህ ሁሉ እንዲረዳት ደግሞ አዜብ የሚያስፈልጋትን ቲዎሪ አስጠንታታለች፡፡

በዚህ ዓይነቱ ግንኙነት ወቅት መፀነስ ሊኖር እንደሚችል አውቃ እንድትጠንቀቅ፤ የመከላከያ መድኃኒቱን አምጥታላታለች። ትህትና አዲሱን ሥራዋን ከጀመረች ዛሬ አምስተኛ ቀኗ ነው፡፡ መንፈሷም አካሏም ነቃ ያለው እንደሰው ሥራ በመያዟ ፤ እቤት ከመዋል ይልቅ በሥራ ተጠምዳ መዋል በመጀመሯ ሳይሆን አይቀርም፡፡
ዛሬም ከሠራተኛዋ ከእታፈራሁ ጋር እየተረዳዳች እናቷን የምትጠብቅላት አዜብ ስትሆን፤ ቶሎ ካልተመለሰች ወደ ቤቷ እንድትሄድ ተስማምተው ነው የተለያዩት፡፡
የቤቱ በር ተቆረቆረ፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ ሊከፍት ወጣ፡፡ በጉጉት ተውጦ
ይጠባበቃት ስለነበረ በደስታ ስሜት ተውጦ ቀና አለና ከንፈሯን ሳማት፡፡
እሷም በናፍቆት ስትጨነቅ እንደቆየች ሁሉ ግጥም አድርጋ ከንፈሩን ሳመችለት፡፡
እንደዚህ አድርጋ ነፍሱን ታስደስትለት እንጂ! ያለበለዚያማ.. ከዚያም እጅ ለእጅ እንደተያያዙ፤ ወደ ውስጥ ዘለቁ፡፡ በቤት ያለችው የቤት ሠራተኛው የትነበርሽ ብቻ ነች፡፡ የዛሬ እንግዳውን የቤት ሠራተኛው አይታ እንድታደንቅለት በዚያውም እሱንም በምርጫው እንድታደንቀው ስለቸኮለ ጠራት፡፡

“ተዋወቂያት ትህትና ትባላለች” በእጁ ወደ ትህትና እያመለከተ፡፡ የቤት ሠራተኛዋ በሁለት እጆችዋ እየጨበጠቻት ስሟን ነገረቻት፡፡ በዕውነቱ በልጅቷ ውበት ተደነቃ..
“ይህችን አንድ ፍሬ ቆንጆ ልጅ ከየት አገኛት?” ብላ እራሷን ጠየቀች።

“ትህትና አንድ ሰዓት ያህል ዘግይተሽ በረሀብ እንደቀጣሽኝ ታውቂያለሽ?” አለና ሰዓቱን ተመለከተ :: በእርግጥም በስድስት ሰዓት ከቀጠረችው በኋላ የመጣችው ሰባት ሰዓት ላይ ነበር፡፡
እስካሁን አልበላህም ዶክተር?” ጠየቀችው በመገረም፡፡የምበላ ይመስልሻል ? ”
“ ምናለበት ? ”
መገመትም የለብሽ ” አለና ከሷ ውጭ እህል እንደማይዋጥለት ሰው ሆነ፡፡

ወዲያውኑ ሠራተኛዋ የእጅ ውሀ አምጥታ ካስታጠበቻቸው በኋላ የተዘጋጀው ምሣ ቀረበ፡፡ በእውነቱ ብፌ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ ድግስ ደገስ እንጂ ምሳ ጋበዘ አይባልም፡፡ በምሳው ዓይነትና ብዛት ተገርማ “ ይህ ሁሉ ለምን?” ስትል በልቧ እያወራች ከዶክተር
ባይከዳኝ ጋር መጐራረሳቸውን ቀጠሉ፡፡ በእውነቱ ግሩም የምሣ ዝግጅት
እንደተደረገላት ልቧ አምኖ ተቀብሎታል፡፡
ምሳው እንዳበቃ አንድ ጠርሙስ ሄግ ዊስኪ ከመለኪያዎችና ከበረዶ ጋር የትነበርሽ ይዛ ቀረበች፡፡ መለኪያው ሁለት ነው፡፡
ዶክተር አንዱን እሱ ፊት፤ አንዱን እሷ ፊት አደረገ፡፡
“ ምን ልትሆን?! "በቀልድ መልክ መለኪያውን ገፋ አደረገችው፡፡
“የዚያን ዕለት በሰው ሀገር፤ በሰው ቤት፤ ስለነበርን ነው ያላስቸገርኩሽ፡፡ዛሬ ግን በራሳችን አገር፤ በራሳችን ቤት፤ ውስጥ መጠጣት መጫወት አለብሽ” አላት፡፡ ደብረ ዘይትን ውጭ አገር አስመስሎ፡፡

“ ዶክተር ሙት አልሞክረውም፡፡ ይሄማ መቅበጥ ነው”

ሰው በቤቱ ከሚወደው ጋር ሆኖ ካልቀበጠ የት ይቀብጣል ታደያ?”
ጉሽም አደረጋት።
“ከምሳው ጋር እንዴት ይሄዳል መሰለሽ ትሁት?” በቃ እሱን አልጠጣም፡፡ ባይሆን እንደዚያን ዕለቱ ትንሽ ቢራ ልቅመስ”
ቢራ ከፍቶ በብርጭቆ ቀዳላት፡፡ ከዚያም ከሶፋው ላይ ተቀምጠው መጨዋወት፤ መተሻሸት፤ መላፋታቸውን ቀጠሉ፡፡
ዶክተር በጭኖቿ ውበት ተረትቶ፤ በስሜት ሰክሮ፤ አንዳንድ ጊዜ ጣቶቹ ድንበር እየዘለሉ ይጓዙ ነበር፡፡
ትህትና ቀስ በቀስ ሞቅ እያላት ሄደ፡፡ በተለይ ለውሃ ሽንት ወደ ሽንት ቤት ስትሄድ፤ በቢራው ውስጥ ውስኪ የጨመረበት መሆኑን ሳታውቅ
የምትጐነጨው ዊስኪ የተደባለቀበት ቢራ ቶሎ እንድትግል አድርጓታል፡፡
ከዚያም መሣሣም ጀመሩ፡፡ የትነበርሽ በጉደለው ለመሙላት ተፈልጋም እንደሁ ለመታየት፤ ብቅ ብትል ፤ የትህትና አንገት
እንደቀጭኔ አንገት ወደ ላይ ተመዞ፤ የዶክተር ባይከዳኝ አንገት ደግሞ
ቁልቁል ተሰብሮ፤ እንደ ጉድ ከንፈር፤ ለከንፈር፤ ተሳስመው ሳይሆን
ተጉራርሰው ደረሰች፡፡

"ያንተ ያለህ!” አለችና ባየችው ነገር ደንግጣ ዳግም ተመልሳ ላትመጣ
ሮጣ ወጣች፡፡ የሰማትም ያያትም አልነበረም፡፡ የሁለቱም የስሜቶቻቸው
ሕዋሳቶች ደንቁረው፤ በአንድ ነገር ላይ ብቻ ስለተጠመዱ፤ ቦንብ ቢፈነዳ
እንኳ የሚሰሙ አይመስሉም ነበር፡፡
ትህትና እንደዚያ ግልጽ ሆናለት፣ በፍቅር ስሜት ተውጣ፤ እጆቿ አንገቱ ላይ ተጠምጥመው! እኒያ ብስል እንጆሪ የመሰሉ ከንፈሮቿን ስታቋድሰው፤ ደስታ ፈንቅሎት፤ የበለጠ በፍቅር ተረታላት፡፡
ምንም እንኳን በቢራው ውስጥ የደባለቀበት ውስኪ ሞቅ እንዳደረጋት
ቢረዳም! እንደዚያ በስሜት ሰክራ፤ ሁለመናዬን በፍቅር እየዳሰሰች ፤
እራሷን አሳልፋ ትሰጠኛለች ብሎ አልገመተም ነበር፡፡

ቀስ በቀስ እየተሸነፈች ሄደች :: ዛሬ በተራዋ አዛዥ ስትሆን፤ዶክተር ባይከዳኝ ደግሞ ታዛዥ ፤ ሆነ ። የተገላቢጦሽ !!
አውልቀው ከላይ ያለውን! " በትዕዛዝ መልክ፡፡ ከመቅጽበት ፒጃማውን
አውልቆ ወዲያ ጣለው ባሰበችው ነገር ላይ ቶሎ ለመድረስ ቁና ቁሩ እየተነፈሰች የራሷንም እንደዚያው አደረገች፡፡
ከዚያም በገባችበት የቅዠት ዓለም ውስጥ ሆና የምትሠራው ሁሉ ለዶክተር ባይከዳኝ እንግዳ ነገር ነበር፡፡ እሷ እንደዚያ ሁለመናዋን ግልጽ አድርጋለት በስሜት የጋለችው ፤ እንደዚያ ሰውነቷ አተኩሶ መቃተት የጀመረችው፤ እንደዚያ በሁለመናዋ ተጠምጥማበት አትልቀቀኝ ያላችው፡ እሱን መስሎት፤ ከደስታ ብዛት የሚሆነውን አጣ፡፡ ምን ዋጋ አለው?
እሷ ግን በዚያን ሰዓት አካሏ እንጂ መንፈሷ፤ ልቧና፤ ቀልቧ ፤ ሁሉ
ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር አልነበረም፡፡
እሷ በዚያች ሰዓት አቅፋ እንደዚያ በስሜት የሰከረችለት ሰው ፧ሁለመናዋን ግልጽ ያደረገችለት ሰው፤ ከአምስት ቀን በፊት ያየችው፤በኋላም ልቧንም ቀልቧንም ወስዶባት የሄደው፤ በድንጋጤ አፏን ከፍታ የቀረችለት፤ በአጠቃላይ በፍቅር የተረታችለት፤ ሻምበል ብሩክን እያሰበች
👍2
ነበር፡፡
በእያንዳንዷ ደቂቃ የምታደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ ለየት ያለና፤ ከዚያ
በፊት ተሰምቷት የማያውቅ ስሜት ነበር፡፡
በሕይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ በወሲብ ስሜት ተቃጥላ ፤ ተቀራኒዋን ተጠምታ የታየችበት ቀን ቢኖር ዛሬ ነው፡፡
ለወንድ ልጅ እንደዚህ ዓይነት ስሜት ተሰምቷት አያውቅም፡፡ ዶክተር
ባይከዳኝ አካሏ እንጂ ልቧ በብዙ ኪሎ ሜትር ከሱ ውጭ መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ ምንኛ ልቡ በሀዘን ይጐዳ ነበር? ይሄንን ደግሞ እሱ እራሱ የሚያደርገው ነው፡፡

በወሲብ የሚወዳት ጨው አላት የሚላት የቡና ቤት ፍቅረኛው ሣራን መቼም አይረሳት፡፡ ከሌላ ሴት ጋር እየተዳራ፤ በስሜቱ የሚያጣጥመው ሣራን ነበር፡፡ በእርግጥም እሷን ሲያስብ አብሯት ከሚጫወተው ሴት ጋር ይጣጣማል፡፡ በአካል እዚህ በሃሳብ ግን እዚያ ::
ዶክተር ከሱ ጋር ያለች መስሎት፤ በምትሰጠው ትዕዛዝ መሠረት
በፍጥነት ተንቀሳቀሰ፡፡ ከዚያም ሁለቱም ከስሜት ንረት ጥግ እዚያ እጣራው ላይ ሲደርሱ በሁሉም ረገድ ዝግጁ የሆነው
እንደማግኔት ተፈላለገና፤ ወደ ጓዳው
ለመግባት እንኳን ፋታ አሳጥቷቸው፤ በተጋደሙበት ሶፋ ላይ ጨዋታ ጀመሩ፡፡

ዶክተር በዚህ በዛሬው አጋጣሚ ተደስቶ ያንን ድል ሊቀዳጅ አሞቱን ኮስተር አድርጎ ትግል ገጠሙ፡፡ ትህትና እያቃሰተችና፤ እየቃተተች ሙሉ በሙሉ መረታቷን አረጋገጠችለት፡፡
ዶክተር በሁኔታዋ ተመስጦ፤ በደስታ እየፈነደቀና የሠራ አካላቱ የሚያመነጨው ሙቀት፣ ከሷ ሙቀትና ትኩስ ትንፋሽ ጋር ተዋህዶ በላብ እየተጠመቁ፤ ትግሉን ቢቀጥልም፤ አስቀድማ ደካማነቱን የጠረጠረችው ሰው ዛሬም ዳግማዊ
ውድቀቱን አረጋገጠላት፡፡ በመከራ የጋለው ሰውነቱ ሟሽሾ፧ ልክ እንደ ደብረ ዘይቱ ሁሉ ተልፈስፍሶ፤ እላይዋ ላይ በደረቱ ተዘረረ፡፡ በዚያን ሰዓት ቀልቧና ልቧ ከዘመተበት ዓለም ተመልሶ፤ ከላይዋ
የተጋደመውን ከባድ ሰው አተኩራ ብትመለከተው ፤ በፍቅር የተነደፈችለት ሻምበል ብሩክ ያለመሆኑን አወቀች፡፡ዶክተር ባይከዳኝ ልቧ ብዙም ያልደነገበጠበት ዶክተር ባይከዳኝ የሆነውን አየች፡፡ በቃ ዶክተር ጥርሱ ያለቀበት አንበሳ መሆኑን አረጋገጠችለት፡፡ ከዚያ በኋላ ቀስ ብላ እየሳቀች ተነሳችና የረጠበውን ሰውነቷንና፤ ላቧን፤ አደራርቃ
ልብሷን ለባበሰች፡፡ ዶክተርን ቁልቁል ተመለከተችው :: ተዘርሯል፡፡ተዘርግቷል ፡፡ በጥይት ተመቶ የወደቀ ነው የሚመስለው

“ምስኪን” አለችው በልቧ፡፡ ከዚያም ቀስ በቀስ የሆነውን ለማስታወስ ሞከረች፡፡ ሰክራ ነበር፡፡ የሰከረችው ግን በአንድ ቢራ ነው ወይስ ? በዚያ ቢራ ውስጥ ውስኪ ቀላቅሎበት እንደሆነ ጠርጥራ፤ በጠርሙሱ ውስጥ ያለውን ጭላጭ ቀመሰችው፡፡ የጣዕም ልዩነት እንዳለው ተረዳች፡፡
ዶክተር እንድትሰክር ብሉ ውስኪ እንደጨመረበት አወቀች፡፡ በፈጸመችው ድርጊት አፈረች፡፡ አሁን ነፍሷን እያወቀች፤ ሞቅታው እየተሸረጠላት ነበር፡፡ ሄዳ ፊቷን በቀዝቃዛ ውሀ ሙልጭ አድርጋ ታጥባ
መጣችና ዶክተር ባይከዳኝን ቀሰቀሰችው ዓይኖቹን የግድ ከፈታቸው ሙትት ብለው ቦዘዋል፡፡

"ልሂድ ዶክተር?” አለችው፡፡
“ልትሄጂ ነው?” አላት :: አይኖቹን በግድ ከፍቶ ሽቅብ እያስተዋላት፡፡
"አዎን” አለችው፡፡
“መቼ ትደውይልኛለሽ?”
“ስሞኑን”
"እሺ ትሁት.. ቻው...” የደቀቀ ሰውነቱን ከሶፋው ላይ እንዳጋደመ በሩን
ከፍታ ወጣች፡፡
ከቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት ሆኖ ነበር፡፡ እንደዚያ የሚንሰፈሰፍላት ልጅ እንደዋዛ ወጥታ ስትሄድ በስልምልም ዐይኖቹ ሸኛትና እዚያው በተጋደመበት ቀረ፡፡

የትነበርሽ እንግዳዋ መውጣቷን ስታረጋግጥ ቀስ ብላ ወደ ሳሎኑ
መጣችና ዶክተር ባይከዳኝን አየችው፡፡ ተዝለፍልፎ እሶፋው ላይ ወድቋል፡፡ ከውስኪው የበለጠ የደከመው በትግሉና ከትግሉ በኋላ በተፈጠረው ሁኔታ ነበር፡፡
“ጋንዲያ ”ስትል በልቧ ሰድባው ተመልሳ ወጣች።የትነበርሽ በልቧ የሰደበችው እንደዚያ በሁለት እጆቹ ታቅፎ ያስገባትን
ልጅ ጉዳዩን ከጨረሰ በኋላ ያለመሸኘቱ አናዷት ነበር፡፡

“የውሻ ልጅ ነኝ” አለ ዶክተር እራሱን በራሱ፡፡ ዛሬ ትራሱን በቡጢ ሳይሆን በጥርሱ ነክሶ ቀረ፡፡ አልቅስ፤ አልቅስ፤ አለው፡፡ ግን አላለቀሰም፡፡ያ ዕድል ዛሬም አመለጠው :: በሀሣብ ቅዠት ነጎደ :: በስሜት ስብራት አካላቱ በሀዘን ተኮማትሮ፤ በዊስኪው ጡዘት አእምሮው ዞሮ፡የሚሆነው አሳጣው፡፡ የሚፈጥረው ተአምር አልነበረምና፤ ውስጥ ውስጡን አንጀቱ እየጨሰ፤ ትህትናን አሰባት...
መሄዴ ነው ስትለው እንደዋዛ ተወት ያደረጋት፤ በገዛ ደካማነቱ አዝኖ
መሆኑን ተረድታዋለች፡፡ ይሄ ግን ለሷ ጥሩ አጋጣሚ ስለነበረ ቀስ ብላ፧ሹልክ ብላ፤ ወጥታ ሄደች፡፡ የሄደችው በቀጥታ ወደ አዜብ ዘንድ ነበር፡፡
አዜብ ጋ ለመሄድ ያደፋፈራት ምክንያት አላት፡፡ አዎን ከዚህ በላይ መጠበቅ አትችልም፡፡ አምስት ቀናት፤ አምስት ሌሊቶች፤ በሰዓትና፧ በደቂቃ፤ ሲባዙ የትየለሌ ናቸው :: እነዚህ አምስት ቀናት፤ ለሷ መቋቋም ከምትችለው በላይ የናፍቆት ዘመናት ሆነውባታል፡፡
ስለዚህ ዛሬ እነ አዜብ ቤት ሄዳ፤ ከአዜብ ጋር ሆነው፤ ስልኩን አዜብ መኝታ ክፍል ወዳለው ሶኬት ያዞሩና፤ ይደውላሉ፡፡ ከዚያም ታነጋግረዋልች፡፡ አዜብ የወንድ ጓደኞቿን በመኝታ ክፍሏ ውስጥ ባለው
ስልክ ስትቀጥራቸው፤ ስታጫውታቸው፤ ስትሞላቀቅባቸው፧ አይታለችና
ከሻምበል ብሩክ ጋር እንደልቧ ለመነጋገር፤ የአዜብ የመኝታ ክፍል
ታያት፡፡
እንደዛሬው ወኔ ያገኘችበት ቀን የለም፡፡ የመጠጡ ወኔ ሙሉ በሙሉ አልከዳትም በቃ ዛሬ ለሻምበል ብሩክ የተሰማትን ሁሉ ትገልጽለታለች።
እቢሮው ሳይሆን እቤቱ ትደውልለታለች፡፡ በዚያን ሰዓት አዜብም ወደ ቤቷ እንደምትመለስ ገምታ በቀጥታ ታክሲ ተሳፈረችና ወደ መርካቶ በረረች......

💫ይቀጥላል💫

በየቀኑ ሳይቆራረጥ እንዲደርሳችሁ የበዛ Like 👍 እንዲሁም የበዛ #Share እፈልጋለው።

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሰባት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና .....ቀኑ እሁድ ነው፡፡ ለዛሬው ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ለሚኖራት ግንኙነት በቂ ዝግጅት አድርጋለች፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ እንደዚያን ዕለት አምሮና ተውቦ ፒጃማውን ለብሶ ከሳሎኑ ሶፋ ወንበር ላይ ጋደም ብሎ እየጠበቃት ነበር፡፡ ለምን እንደሆነ እሱ እራሱ አንዳንዴ ግራ ቢገባውም፤ ልቡ እንደዚያ በፍቅሯ እየተቃጠለ፣ በስሜት…»
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት
;
;
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ


እስክንድር በምልክት አሳየው ። በዚያ ሁሉ ጠጪ መሐል ሁለት እጁን እኪሱ አድርጎ ፡ ሁሉንም በንቀት ዐይን እየተመለከተ ነበር ወደ ሽንት ቤቱ የሔደው ።

“ ቢራዋ ሥራዋን እየሠራች ነው ” አለ እስክንድር የአቤል አረማመድ እያየ ።

“ ግን ምን ይሻለዋል ?” አለ ሳምሶን " በአቤል ሁኔታ በማዘን ' “ አሁን በማዕረግ የሚመረቅ ይመስልሃል ? ” እስክንድር ገርሞት ሣቀ ። የሳምሶን ጥያቄ ግን ከቅን
መንፈስ የመነጨ ነበር ። አቤል የሚወደውም የሚያከብረውም በማዕረግ ተማሪነቱ ነው ። የአቤል የማዕረግ ተማሪነት በዩኒቨርስቲው ውስጥ በብዙ ተማሪዎች ዘንድ ይታወቃል
እንደ እስክንድር ጠጋ ብለው የማያውቁት አሁንም የዓመቱ የፕሬዚዳንት የከፍተኛ የማዕረግ ሽልማት ከአቤል እጅ አይወጣም የሚል ግምት አላቸው ። ሳምሶንም የመኝታ ክፍል ጓደኛው ቢሆንም ቅሉ በትምህርት ያን ያህል መድከሙን አያውቅም ነበር ።

“ እውነቴን ኮ ነው ። ምን ያሥቅሃል ?”

ማዕረጉ ቀርቶ በዚህ ዓመት መመረቁ ራሱ ነው እኔን የሚያጠራጥረኝ” አለው እስክንድር " በኀዘን ስሜት ፊቱ
ተለዋውጦ።

“ ያሳዝናል ! ግን ምን ታረገዋለህ! ” አለና ሳምሶን "ቢራውን ከጠርሙሱ ውስጥ እየጨለጠ ፥ “ በነገራችን ላይ መውደቂያችንን እናዘጋጅ እንጂ ! መቼም ዛሬ ወደ ካምፓስ አንገባም” አለው ።

እስክንድር የሳምሶን ሐሳብ ገባሁ ፤አንድ ሴሚስተር ሙሉ ታፍኖ የቆየ ስሜቴ ተነሣ ነገር ግን ኪሱ አስተ ማማኝ አልነበረም ።

“ እኔጋ በቂ ገንዘብ የለማ ! ” አለው ልመና በተቀላቀለበት ድምፅ ከልብ ተዝናንቶ ።

አቤልም እሺ የሚል አይመስለኝም ። ከአሁን በፊት ውጭ እድሮ አያውቅም ።
“ ምን ትቀልዳለህ ? ጭራሽ ? እምልህ ...”
“ አዎ ፡ ከእኔ ጋር ስንተዋወቅ ይኸው አራት ዓመት አለን አንድ ቀንም ኣድርጎት አያውቅም ።

እንግዲያው ዛሬ ድንግሉን ማስወሰድ አለብን ? ”አለ ሳምሶን ተንኮልም የፍቅር ስሜትም እየተሰማው ።

“ እዩዬ ! ተው እባክህ ! ” አለ እስክንድር ' በተዘበራረቀ ስሜት ።

“ ምናለበት ? አንተ ደሞ ! እንዲያውም ሴት ከቀመሰ የዐይኑ ፍቅር ይለቀው ይሆናል ። ገንዘብ እንደሆን እኔ ይዣለሁ ብዬሃለሁ ።

እስክንድር የሳምሶን ሁኔታ ራሱ እንግዳ ሆነበት ። ሳምሶን አብዛኛውን ጊዜ በኪሱ በርካታ ገንዘብ ይይዛል ። ወላጆቹ ደኅና ገቢ አላቸው ። አባቱ በአንድ ኢንተርናሽናል ድርጅት ውስጥ በጥሩ ደመወዝ ይሠራሉ ። በእናቱ ስም ደግሞ
መስጊድ አካባቢ የሰዓት መሸጫ ሱቅ አላቸው ። ወላጆቹ ለሳምሰን በወር ተቆራጭ ካደረጉለት ሃምሳ ብር ሌላ
ሊጠይቃቸው ብቅ ባለ ቁጥር አንድ ወይም ሁለት ባለ አሥር ኖት ሳያሽጉት አይመለስም ። ታዲያ ሳምሶን ይህን ሁሉ ገንዘብ ሲይዝ " ለመጠጥ ማጥፋት አይወድም። የሱ ገንዘብ የሚያልቀው በምግብ ነው ። መብላት ፡ ስፖርት መሥራት ግንባታ ብቻ ! በዩኒቨርስቲው አቅራቢያ ካሉት ምግብ ቤት ባለቤቶች ውስጥ እሱን የማያዉቅ የለም ። ዛሬ ገንዘቡን ለመጠጥና ለሴት ለማውጣት መዘጋጀቱ ነው እስክንድርን ያስገረመ።

“ እንዴት ነው ? ዛሬ ግንባታው ቀርቶ ለማፍረስ ነው መሰል የታጠቅከው ” አለው እስክንድር እየሣቀ ።

“አንዳንዴ ያስፈልጋል እባክህ ! ”
አሳላፊዋ አራት ጠርሙስ ቢራ ይዛ መጣች አንዱ ለራስዋ መሆኑ ነው ።

ቢራ እዚሁ ጓዳ መጥመቅ ጀመራችሁ እንዴ ? "
አላት እስክንድር ፡ ከታዘዘች መዘግየቷን ለመጠቆም ።

“ ቆየሁ እንዴ?አንድ ሰካራም ይዞ ሲነተርከኝ ነው” አለች ፥ ቢራውን እየከፈተች ።

“ አንቺው መጠጥ አቅርበሽለት አንቺው፡ሰካራም ትይዋለሽ ? በይ ነይ በይ ” አለና ሳምሶን ፡ ዳሌዋ ላይ ቸብ አደረጋት ቸብታው ጠንከር ያለ ስለ ነበር ዳሌዋን ለበለባት።

“ እንደዬ ! ታዲያ ዱላው ምንድነው ? ” አለች ተቆጥታ ዳሌዋን በእጅዋ እያሻሸች

ዝም በይና ቁጭ በይ ! ከፈለግኩ ጥርስሽን ነው የማረግፈው አላት ሳምሶን እንደ ልማዱ ።

እስክንድር ነገሩ ማየሉን ሲያይ ተደናገጠ

“ ኧረ እባክህ ! የማነህ ሒድና የሚስትህን ጥርስ አውልቅ " የእኔን የብርቅነሽን አይደለም። ስለ ቢራው እንደሆን ኬረዳሽ ! ” ብላው የከፈተችውን ቢራ ጥላ ተነሣች ብርቅነሽ አምርራ ልትሔድ ስትል'እስክንድር እጅዋን
ይዞ አባብሎ አስቀመጣት ።

“ አንቺ ደሞ እረፊ እንግዲህ ። እሱ ለጠዋታ ያህል ነው የነካሽ
እየተመናቀረች ከሳምሶን ርቃ እስክንድር ጎን ተቀምጠች ። ሳምሶንም ጥርሱን እያንቀጫቀጨባት ነበር ። በማይ
ረባ ነገር ተለካክፈው የጎሪጥ መተያየታቸው እስክንድርን
አስገረመው ።

“ ሁለታችሁም ዕረፉ ፡ ይሄ ቡና ቤት ነው በሰላም ጠጥተን መጫወት ነው የምንፈልገው ”አላቸው : ከግንባሩ ኮስተር ብሎ ፥ ግን በሆዱ እየሣቀ ።

የእስክንድር ሐሳብ እነሱጋ ረግቶ አልቆየም ። በድንገት አንድ ሐሳብ አእምሮውን ወጋው ።አቤል ወደ ሽንት
ቤት ከሔደ ቆይቷል ፤ግን አልተመለሰም ። እስክንድር ልቡ መጥፎ ነገር ጠረጠረና ድንገት ከተቀመጠበት ተነሣ ።

ምነው ?” አለው ሳምሶንም ፡ በሁኔታው ተደናግጦ ።

“ ምንም አይደለም ፥ መጣሁ ” ብሎ እስክንድር ወደ ሽንት ቤቱ ሄደ ። አቅለሽልሾት ይሆናል በሚል ግምት ሳምሶን ነገሩን ቸል አለው ።

እስክንድር ከመጸዳጃ ቤቱ አጠገብ ሲደርስ አቤል እጁን በኪሱ እንዳደረገ ግድግዳ ተደግፎ ቆሞ ነፋስ ሲቀበል አገኘው። ዐይኑ በርበሬ መስሏል ።አላፊ አግዳሚውን በንቀት ዐይን ነው የሚመለከተው።

ቴክሱ ምነው ? ”አለው እስክንድር ፥ ደህና መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ"

“ ወረፋ ሆኖብኝ ነው እባክህ ! ”

“ የሽንት ወረፋ ? በል እንግዲህ ጠብቅ ። ምን ታረገዋለህ ? ” ብሎት እስንድርን ወደ መጣበት ተመለሰ ።አቤል አንድ አደጋ ደርሶቀታል የሚል ሥጋት ስለ ነበር፡ በሰላም በማግኘቱ ልቡ ተረጋጋ ። ምንጊዜም አያምነውም አንድ ቀን በራሱ ላይ የሞት ቅጣት ይፈርዳል የሚል ፍራቻ አለው።

ወደ መቀመጫው ሲምለስ ብርቅነሽና ሳምሶን ተስማተው ጎን ለጎን ተቀምጠው ሲያወሩ አገኛቸው ።

ታረቃችሁ እንዴ ? ”

“ ዱሮስ መች ተጣላን ? አንተ ደሞ ” አለችና ብርቅነሽ ጠየቀችው፡ ፡

ቀድሞውንም ጸበኞች የሚገባበዙት መሐላቸው ገላጋይ ሲኖር ነው ። ብቻቸውን ሲሆኑ አንደኛው ዐቅሙን
ዐውቆ ወይም ጥቅሙን ከጉዳቱ አመዛዝኖ ጸባዩን ያሳምራል ? አለ እስክንድር በልቡ ።

“ ያንን ነገር “ኮ ለብርቅነሽ ነገርኳት” አለው ሳምሶን' ዓይኑን እስክንድር ላይ ተክሎ "

የቱን ነግር ? ”

የአቤልን ነዋ ! በቃ እሷ ይዛው ትደር ።

ሳምሶን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መሆናቸውን አጫውቷት ከዚያው ቡና ቤት መኝታ እንድትይዝ ገንዘብም
ሰጥቷታል ።

“ አንተ ዛሬ የልጁን ድንግል ለማስወሰድ ታጥቀህ ተነሥተሃል ማለት ነው? ” አለ እስክንድር ጉጉቱ አስገርሞት እየሣቀ ።

“መሆን አለበት ብዬሃለሁ ። አድቬንቸር ነው
“ አንቺስ ? በነገሩ ተስማማሽ ? ” አላት እስክንድር ፊቱን ወደ ብርቅነሽ መልሶ።

ውይ በደስታ ነዋ ! እንዲያም ድንግል ወንድ ደርሶኝ አያውቅም ። ዕድሌ ሆኖ የተፈተነ ብቻ ነው የሚደርሰኝ።

ስትናገር ሣቅ ሃቅ ስለምትል የቀልዷን ይመስላል እንጂ ብርቅነሽ የምትናገረው የልቧን ነበር ። ወሲብ ጀማሪ ደርሷት
አያውቅም ። የልጅነት ባሏም ቢሆን ሁለተኛ ሚስቱ ነበረች ።ቡና ቤቱ ውስጥ የሥራ ጓደኞቾ፥ “ ዛሬ የአንዱን ጀማሪ ድንግል ወሰድን ” እያሉ ሲያወሩ ትቀናለች በዚህ ወሬ የተካነችው የቡና ቤቱ ባለቤት ነች የጥንት ዝናዋን ስታወራ ይሄ አርዕስት
👍1
ከመሐል ይጠፋም ። የቀትር ቡናዋን እያፈላች በሸርሙጦች ተከባ ውቃቢዋን ስትለማመን ንግግር መክፈቻዎ ይኽው ነው ።

አይ ዘመን ስንቱ አለፈ ቡና ቤቱ እንዲህ እንዳሁኑ ሳይደራጅ ሠራተኛ ሠፈር ትንሽ ኪዮስክ ከፍቼ ነበር የጀመርኩት ታዲያ ያኔ ስንቱን ባላገር ገራሁት መሰላችሁ ! መቼም የሰው ነጭ ነው ያየሁበት ። ፍቅር በድርያ የሚያዝ ቢሆን ቀልጬ እቀር ነበር። እበስኩ ! ዕረፍት ሳላገኝ ነበር የምውለው ። ታዲያ በጥም ትዝ የሚሉኝ ገና ልጅነታቸውን ያልጨረሱ ተማሪዎች ናቸው በምሽት ተሰርቀው ብቅ ይሉና ድንግላቸውን አስረክበው ይመለሳሉ ። ምን የመሰሉ ሎጋዎች ነበሩ ! ”

አንዴ ከጀመረች ማቆሚያ የላትም ። ዐይኗ ዕንባ እስኪያቅር ድረስ የጥንት ኑሮዋ ውስጥ ሰምጣ ትቀራለች ። በዚህ
ጊዜ ብርቅሽ በልቧ ትቀናለች ።

ምነው ፈዘዝሽ?” አላት እስክንድር በሐሳብ ጭልጥ ብላ መሔዷን እያየ ።

መፍዘዝ ሆሆይ ! እንኳን ፈዘን ቀልጥፈንም አልሆነልን” ስትል አቤል ተመልሶ መጥቶ አጠገባቸው ተቀመጠ ።

ኖር ብላናል ” አለችው ፡ ሞቅ ካለ ፈገግታ ጋር ።

ስትሥቅ ድዷ ይታያል ። የላይኛው ድዷን ጉራማይሌ ተነቅሳዋለች ። አንገቷ ንቅሳት ድዷ ንቅሳት አቤል ያሤሩበትን አላወቀም የተከፈተለትን ሦስተኛ ቢራ ልጠጣው
ወይስ አልጠጣው በሚል ስሜት ዝም ብሎ ተመለከተው ።

“ ይሄ ነገር ቢበቃኝስ ?” ሲላቸው ፥ ምላሱ ትንሽ ትንሽ መተሳሰር ጀምሯል ።

“ እረ ጠጣ ! ምን እንዳይልህ ? ዕረፍታችሁ አይደለም እንዴ ? ” አለችው ብርቅነሽ ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ዐይን
ልዐይን ተያዩ ።

“ ስሚ ብርቅነሽ ' ይህ ሁሉ ንቅሳት ምንድነው ?”አላት እስክንድር፡ ጣልቃ ገብቶ ። ለለከፋ መሆኑ ገብቷታል ።

ጌጥ ነዋ ! ምን አገባህ አንተ ደግሞ ? ”

“ ማለቴ ' አዲስ አበባ ስትገቢ ልታጠፊው አልሞከርሽም ? ”

ውይ ፥ ለምን ብዬ ! ቁምጥና መሰለህ ? ”

“ እሱን ተይው የሚቻል ቢሆን ኖሮ ሴቶች ንቅሳታችሁን ለማጥፋት የማትገቡበት ጉድጓድ አልነበረም ። ለመሆኑ ከሀገርሽ ከወጣሽ ስንት ጊዜ ሆነሽ ?

💥ይቀጥላል💥
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

.....በሐረርጌ ክፍለ ሀገር፤ በሀረር ከተማ ነዋሪ የሆኑት ፊታውራሪ በላይ እንግዳ፤ ከመጀመሪያ የህግ ባለቤታቸው ከወ/ሮ አይኔአበባ ጥሩነህ ከወለዷቸው ስምንት ልጆች ውስጥ፣ ብሩክ በላይ አራተኛ ልጅ ነው።
ፊውታራሪ በላይ፤ ልጃቸው ብሩክ ! በእናቱ ማህፀን ውስጥ እንዳለ፤
በወዳጅነት አብረዋቸው ደስታንና ችግርን ካሳለፉት ከባላምበራስ ትኩነህ
መብራቱ ጋር ከጓደኝነትም በላይ ወዳጅነታቸውን በጋብቻ ትስስር
ሊያሳድጉት ፈለጉና፤“ልጅህ ሴት ከሆነች ለወንድ ልጄ፤ ወንድ ከሆነ ለሴት ልጄ” በማለት ቃል ተገባቡ፡፡

ሁለቱ ጓደኛሞች፤ በእርጉዝ ሚስቶቻቸው ማኀፀን ውስጥ ባሉት ጽንሶች ሊቆራኙ በገቡት ቃል ኪዳን መሠረት፤ እንደ አጋጣሚ ሆኖ የፈታውራሪ በላይ ልጅ ወንድ ሆኖ ሲወለድ፤ የባላምባራስ ትኩነህ ልጅ ደግሞ ሴት ሆነች፡፡

በሁለቱ ሕፃናት መካከል የነበረው የዕድሜ ልዩነት ሁለት ወር ብቻ ነበር፡፡ በዚህም ብሩክ ታላቅ ለመሆን በቅቷል፡፡ በዚያን ዕለት ወንድ ተወልዶ ቢሆን ኖሮ፤ ያ ሁሉ የወላጆች ምኞት ከንቱ ሆኖ ይቀር ነበር፡፡ያ የረጅም ጊዜ ምኞታቸው ምኞት ብቻ ሆኖ ባለመቅረቱ፤ ሴቷ ልጅ
የተወለደች ዕለት የሠርግ ያክል ድግስ በሁለቱም ቤት ተደግሶ ይህችን
ዕድለኛ ልጅ በዕድሏ ብለው ሰየሟት፡፡

በዕድሏ ትኩነህና፤ ብሩክ በላይ፤ በቤተሰባቸው ፍቃድ አንዳቸው ለሌላው
የትዳር ዋልታ መሆናቸውን ሳያውቁ፤ በዚያ በወርቃማ የልጅነት ጊዜ ውሀ እየተራጩ ፤ጭቃ እያቦኩ፤ አብረው አደጉ፡፡ ብሩክና በዕድሏ በአካል እየጐለመሱ፤ በአእምሮ እየበሰሉ፤ ሲመጡ ወላጆቻቸው በትዳር እንዲተሳሰሩ የተስማሙባቸው ወደፊት ባልና ሚስትነት የታጩ መሆናቸውን ቀስ በቀስ እየተረዱ ሲመጡ፤ ለጥቂት
ጊዜም ቢሆን የመተፋፈርና፤ የመሽኮርመም፤ ፀባይ ቢያሳዩም፤ ቀስ በቀስ ይህንን እያስወገዱ፤ በተቃራኒ ጾታዎች መካከል በሚፈጠረው የግንኙነት መስመር መጓዝ ጀመሩ፡፡

ቀስ በቀስ የልጅነት ነጻ ፍቅራቸውን በጾታዊ ፍቅር እያጐለመሱት መጡ፡፡በተለይ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ አብረው እየተማሩ፤አብረው እየዋሉ፤ ማምሸት ሲጀምሩ፣ ቀስ ብለው ጊዜውን ጠብቀው ሊሆን የሚችለውን፤ ከወዲሁ ቸኩለው ጀመሩት፡፡ .

በዕድሏ እዚህ ጐደለሽ የማትባል ቆንጆ ልጅ ነበረች፡፡ ምንም እንኳን የወደፊት ሚስቱ እንድትሆን በቤተሰብ መልካም ፈቃድ የተቸረችው ቢሆንም፤ የሱ፤ የግሉ፤ ብቻ መሆኗን ለማረጋገጥ ብሩክ ቀስ በቀስ እያባበለ የፍቅር ጭውውት አስጀመራት፡፡
በዕድሏ ቀስ በቀስ ከብሩክ የበለጠ በፍቅር ወደቀች፡፡ ብሩክን የምትወድበት ቃልም አልነበራትም፡፡ በአጠቃላይ ነፍሷ እስከምትወጣ ድረስ ትወደዋለች፡፡ ይወዳታል፡፡

ይህ ለሁለቱም ፍቅረኛሞች ኦቦል የሆነ ፍቅር ቀስ በቀስ ሥር እየሰደደ የሚያስቀኑ እየሆኑ ሄዱ፡፡በዚህ መሀል ነበረ እንግዲህ አብዮቱ የፈነዳው፡፡ በዚያን ጊዜ በፊታውራሪ በላይ ቤት በአሽከርነት ተቀጥሮ ይሠራ የነበረው አደፍርስ፤
በአብዮት ጥበቃ አባልነት በቀበሌ ውስጥ ከተመረጠና፤በኋላም የቀበሌው የአብዮት ጥበቃ ኃላፊ ከሆነ በኋላ፤ ያንን ለዘመናት ውስጡን ሲበላው የቆየውን የፊታውራሪን ልጅ በዕድሏን የማግኘት ሕልሙን ሊያሳካ
ቆርጦ ተነሳ፡፡

በመጀመሪያ አባቷን መሣሪያ ደብቀዋል በሚል ምክንያት ካሳስራቸው በኋላ “በሕዝብና በአብዮቱ ላይ ደባ የፈጸመ አድሃሪ ስለሆነ መረሸን አለበት” የሚል አቋም ያዘ፡፡
ለዚህ ጥቆማው ሚስጥሩን ያውቃሉ በሚል ሽፋን ካሳሰራቸው ጠቅላላ
ቤተሰቦች መካከል በዕድሏ እንዷ ነበረች፡፡

“አባትሽን ወይንስ ብሩክን?” ሲል ለህሊና የከበደ ጥያቄ አቀረበላት ።ከዱላው ብዛት የተነሳ ከሁለቱ አንዳቸውን ከመምረጧ በፊት ሁለቱንም ነበር መልሷ፡፡በመጨረሻ ላይ ግን ሰውነቷ በዱላ ብዛት ተተልትሎ
አባቷንም፤ ብሩክንም፤ እራሷንም እንዳታጣ ስለሰጋችና የሁለቱንም
ህይወት ለማትረፍ ስትል፤ ያቀረበላትን ጥያቄ! እንደኮሶ እየመራራት ለመቀበል ተገደደች፡፡

ከዚያም ብሩክ በፀረ አብዮተኛነት ስም ወህኒ ቤት እንዲገባ ካደረገ በኋላ፤
አደፍርስ ድል ያለ ድግስ ደግሶ በሠርግ አገባት፡፡
ብሩክ ከአባቱ ጋር እሥር ቤት ውስጥ እንዳለ፤ አደፍርስ እና በዕድሏ
መጋባታቸውን ሲሰማ እራሱን ጠላ፡፡
መፈጠሩን አማረረ፡፡ በእንባ እየታጠበ ፤ አንጀቱ እየከሰለ! የሚወዳት የሚያፈቅራት ከጭቃ ማቡካት ጀምሮ በልቡ ውስጥ የጠነሰሳት ፍቅረኛውን መነጠቁን አመነ፡፡
ለስድስት ወራት ያህል በዚህ ሁኔታ በእሥር ቤት እንዲቆይ ከተደረገ
በኋላ ተሳትፎው በንባብ ደረጃ ብቻ ስለሆነ “ማሪኝ አብዮቴ” የሚል
መዝሙር ዘምረው በምህረት እንዲለቀቁ ከተደረጉት ወጣቶች መካከል አንዱ ለመሆን በቃ፡፡

የአደፍርስ ምኞት እንዲገደል ነበር፡፡ ሳይሆንላት ቀረ፡፡

“ብሩክ ምን ለመሆን ነው የምትፈልገው? “ ሲሉት አባቱ..
“ዶክተር፧ ኢንጂነር፣ አውሮፕላን ነጂ፣ሳይንቲስት ” ጥሩ ጥሩውን ሁሉ
ለመሆን የሚመኘው፤ በትምህርቱ ጠንካራ የነበረው ልጅ ሞራሉ ተነካ፡፡
ደስታን አጣት :: ከዚያም አሥራ ሁለተኛ ክፍልን እንደጨረሰ በቀጥታ በፖሊስ መኮንኖች ማሰልጠኛ ኮሌጅ ገባ፡፡
በማሰልጠኛው ውስጥ ባስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ልዩ ሽልማትን ለማግኘት የበቃ ጠንካራ ተማሪም ነበር፡፡ ትኩረቱን ሁሉ በማስልጠኛው በሚሰጠው ትምህርት ላይ አደረገ፡፡ በዕድሏን አጥቷታል ፤ስለፍቅር የምትዘፍን ልቡ በዚያ ምትክ ለዘመናት የሀዘን እንጉርጉሮ ስታንጐራጉር ኖራለች፤ ስለፍቅር መስማት ይጓጉ የነበሩ ጆሮዎቹ ያንን ሲሸሹ ኖረዋል
በለጋነቱ በውስጡ የደረቀች የፍቅር አበባ ሁሉን እንዲጠላ አድርጋዋለችና እልሁን የሚወጣው ጠንክሮ በመስራት ብቻ ሆነ፡፡

የሚያዳምጠው ማንኛውም የፍቅር ዘፈን ስንኝ ለሱ መሪር የሀዘን ስሜቱን እያጫረበት በዕድሏን በዓይነ ህሊናው የእንባ ጭጋግ ከጋረዳቸው ዐይኖቹ ባሻገር በትዝታና በሰቀቀን እያሰባት፤ ረጅሙን ጊዜ በብቸኝነትና በሃዘን አሳለፈው፡፡

በዕድሏ የሶስት ልጆች እናት ስትሆን፤ እሱ ግን ይኸውና እስከ ዛሬ ድረስ የትዳርን ነገር ሳይመኘው፤ ሳያስበው በአደፍርስ ላይም የቂም በቀል እጁን ሳይሰነዝር፤ የራሱን ዓለም በራሱ ውስጥ ፈጥሮ በመኖር ላይ ይገኛል፡፡

ሻምበል ብሩክ በመ/ቤቱ ውስጥ ተወዳጅና ተሰሚነት ያለው ወጣት መኮንን ነው።በአጭር ግዚው ውስጥ የሹመት ባለ ዕድል ለመሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማታው መርሃ ግብር፤ በማኔጅመንት ለዲግሪ በመማር ላይ ይገኛል፡፡

ሻምበል የቤት ሠራተኛ ቀጥሮ ሁለት ታናናሽ ወንድሞቹን በማስተማር ላይ ሲሆን፤ በትዳር ላይ የነበረው ምኞት ገና በአፍላው ከተጨናገፈ አስቦትም፤ አልሞትም አያውቅም፡፡ እሱ
አይጨነቅበት፤ እንጂ የትዳር አምላክ እራሱ ለሱ ሲጨነቅለት፤ ሲጠበብለት፤ ቆይቶ የሚሆነውን ሊሰጠው ፤ በሀዘን የተሰበረ ልቡን ሊጠግንለት፤ ተቃርቧል፡፡

በቢሮው ውስጥ ወንድሟን ልታስፈታ ለአቤቱታ የገባችውን ወጣት ሲያይ፤ እንደዚያ በድንጋጤ ደንዝዞና፤ ፈዝዞ፧ የቀረው ያለምክንያት አልነበረም፡፡
ያች ወጣት፤ ያች ውብ ልጃገረድ፤ ሞቶ አፈር የለበዕ ስሜቱን የቀሰቀሰችበትን፤ የሻረ የልቡን የውስጥ ቁስል የነካካችበት፤ ያለምክንያት አልነበረም፡፡ በዚያች ቅጽበት ሻምበል ብሩክ የልጅነት እጮኛው፤ ከሁሉም በላይ የሚያፈቅራት ጓደኛው፤ በዕድሏ እራሷ የመጣች ነበር የመሰለው
በጣም ነው በመልክ የሚቀራረቡት፡፡

ሁለመናው ተረብሾ፤ ያችን ወጣት ለማነጋገር አንደበት ልሳኑ የተዘጋው፤ በዚህ ምክንያት ነበር በተለይ ዓይኖቿ ቁርጥ በዕድሏን ናቸው ለወንድሟ ዋስ ሊሆንላት ቃል ሲገባላት ያቺ ወጣት በኑሮ
ውጣ ውረድ ምክንያት የደረሰባትን
👍3
ችግር፤ አባቷን በጦርነት ምክንያት
ማጣቷን፤ እናቷ በሕመም ስቃይ የአልጋ ቁራኛ መሆኗን፤ የምትወደው ወንድሟ ደግሞ ፀባዩ እየተለወጠ ሄዶ እስከመታሰር የደረሰበትን ምክንያት፤ በዚያች አጭር ጊዜ ውስጥ አጫወተችው።

በዚያን ጊዜ ልቡ አዘነላት ከሀዘኔታውም ውስጥ አብሯት በስሜት አለቀሰ ፡፡ ለምን የዚያን ቀን ምሽት በሕልሙ መጣችበት? እንጃ ! ሻምበል ብሩክ በዕድሏን በትህትና ውስጥ ስላየ ትህትና የበለጠ ናፈቀችው፡፡
ከአሁን አሁን ስልክ ትደውላለች ብሉ ጆሮዎቹን በቤቱም፤ በቢሮውም፤
ስልክ ላይ ጥሎ ሲያዳምጥ ዋለ፡፡ አልደወለችም፡፡ በሁለተኛውም፤ በሶስተኛውም ፤ በአራተኛውም ቀን ሳትደውል ቀረች፡፡ ተጨነቀ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ እየናፈቀችው ነው፡፡

ለሴት ልጅ የነበረው የቀዘቀዘ ስሜት በዚህች ወጣት ምክንያት ለምን ተቀሰቀሰ? ትህትና.....ትህትና...ትህትና...
በሀሳብ ታየችው፡፡ስታለቅስ፤ አቤት አይኖቿ ሲያሳዝኑ፤ ስትናገር ልሳኗ የሚጣፍጥ፤ቅልስልስ ስትል፤ እንዴት ያምርባታል!፡፡ ከዚያም ዐይኖቻቸው በድንገት ሲጋጩ ከድንጋጤዋ ውስጥ ዘልቆ ከዐይኖቿ ውስጥ ያነበበው ስሜት
እንዴት ነበር?፡፡ በጣም ደስ የሚል ፤ ልዩ ስሜት ነበር፡፡ ቃላት ሊገልጹት የማይችሉት ስሜት.....
ይህ ሁሉ በሀሳቡ እየተመላለሰ፤ ሻምበል ብሩክ ትህትናን በመናፈቅ የሚሆነውነ አጣ፡፡ ዋስ ሆኖ ወንድሟን አስፈታላት እንጂ ከወንጀሉ ነፃ ሆኖ አልተሰናበተም፡፡ ጉዳዩ ያላለቀ በመሆኑ መፈለግም ሊኖር
ይችላል፡፡ታዲያ ምነው ድምጿን አጠፋች? ሁኔታው ግራ አጋብቶት ከረመ፡፡

ሻምበል ብሩክ በሥራ ላይ አምሽቶ መግባቱ ነው፡፡ ከምሽቱ አንድ ሰዓት
ተኩል ሲሆን ከቤት ደረሰ፡፡ ከዚያም ከታናናሽ ወንድሞቹ ጋር ቼዝ እየተጫወተ ሳለ የቤቱ ስልከ የጥሪ ድምጽ ሰጠ :: የአሥራ አራት ዓመት ዕድሜ ያለው ትንሽ ወንድሙ ፀጋዬ ሄዶ ስልኩን አነሳ፡፡
“ ሀሎ" አለ ፀጋዬ፡፡

“ሀሎ” አለው ከወዲያ ማዶ ያለው ቆንጆ የሴት ድምጽ፡፡
“ማን ልበል ?" ፀጋዬ አዲስ በሰማው ድምጽ ግራ ተጋብቶ፡፡
“ሻምበል ብሩክ ቤት ነው?"
አዎን”
ይኖራሉ ? ”
"አሉ” አላት፡፡
“እባክህ አቅርብልኝ ?"

ጋሼ ስልክ ይፈልግሀል” አለውና ስልኩን አስቀምጦ ተመለሰ፡፡ ሻምበል ብሩክ በልቡ ምን አለበት እሷ ብትሆን? ወይኔ ብሩክ እባክህን እሷን አድርግልኝ” እያለ፤ እሷን እንዲያደርግለት እየተመኘ፤ ወደ ስልኩ ሄደና አነሳው፡፡

“ሀሎ "አለ ልቡ እየዘዘለች፡፡
“ሻምበል ብሩክ ነህ”
“አዎን ነኝ ማን ልበል?፡፡ ተመስገን አምላኬ፡፡ አዎን አሷው ናት!”

" ትህትና እባላለሁ፡፡ ካልረሳኸኝ” ሻምበል ብሩክ ብቻውን ቢሆን ኖሮ በደስታ ይጨፍር ነበር፡፡ ምን ያደርጋል? እዚያ ወዲያ ወንድሞቹ አሉ።ያዩታል፡፡ የሚይዝ የሚጨብጠው ጠፍቶት ተቁነጠነጠ፡፡

"ትህትና ምነው እስከዛሬ ድረስ ሳትደውይልኝ?”
"አልተመቸኝም ነበር ሻምበል”
“ በጣም እንደናፈቅሽኝስ ይገባሻል?"
እንዴት ማወቅ እችላላሁ ሻምበል?" በልቧግን“ እኔም ተቃጥዬልሃለሁ” እያለች ነበር፡፡

እኔ እንጃ ብቻ ስንገናኝ ብነግርሽ ይሻላል፡፡ ሰሞኑን ጆሮዬ ከኔ ጋር ሳይሆን ከስልኮቹ ጋር ነበር የከረመው፡፡ ለማንኛውም ከስልክ ይልቅ በአካል ተገናኝቶ መጫወቱ አይሻልም? ሲላት....
“ አዎን እንደሱ ይሻላል” አለችው ቶሎ ብላ፡፡

“ እናትሽ ተሻላቸው ትህትና? አንዱ አለምስ ፀባዩን አሻሻለ?”

“ እማዬ እየተሻላት ነው፡፡ ደህና ነች :: አንዱዓለሜ እንዴት ተለውጧል መሰለህ? በዚያች እሥር ቤታችሁ ውስጥ ምን እንዳቀመሳችሁት እንጃ፡፡” እየሳቀች፡፡

እስቲ ስለሁሉም ለመጫወት መቼ እንገናኝ ታዲያ? እኔ እንዳልደውልልሽ እኮ ስልክ የለኝም ስላልሽ ነው እንጂ ይሄን ያህል አልጨክንም ነበር” በማለት አንጀቷን ሊበላው ሲሞክር.....

“ ሻምበል እኔንም እንደጨካኝ አትቁጠረኝ፡፡ ያለመመቸት ጉዳይ ነው፡፡”
በልቧ ግን ነገ አይመቸኝም ካለ ጉድ ፈላ! ከዚህ በላይስ መቆየት አልችልም” እያለች ነበር፡፡

ዛሬ መሽቷል እንጂ ዛሬ ብንገናኝ ደስ ይለኝ ነበር” ሳታስበው አመለጣት፡፡

ሻምበል ጆሮውን ማመን አቃተው፡፡
“ ለምን ነገ አንገናኝም ታዲያ?” አላት በጉጉት፡፡ደስ ይለኛል” እንዲህ በድፍረት ስሜቷን ሳትደብቅ እንድትናገር
የገፋፋት የቀመሰችው አልኮል መሆኑን አላወቀም፡፡ የሚገናኙበትን

ሰዓትና ቦታ ተቀጣጥረው! ትንሽ ተሳስቀው በናፍቆት ተሰነባብተው ፤
ስልኩ ተዘጋ፡፡
ሁለቱም ልባቸው በናፍቆት ተሸብሮ፤ የዛሬው ምሽት ከድንጋይ እየከበዳቸው ተለያዩ፡፡ እውነትም ያ ምሽት በዕድሜአቸው ሙሉ ከሚያውቋቸው ምሽቶች በጣም ረጅሙ ምሽት ነበር፡፡
እንደዚያ ከሻምበል ብሩክ ጋር በስልክ ስትጨዋወት አዜብ ከፊት ለፊቷ
ቁጭ ብላ በዐይኖቿም፤በእጆቿም፤ በጥርሶቿም ጭምር አመራር
እየሰጠቻት ነበር፡፡
ስልኩ ከተዘጋ በኋላ ሻምበል ብሩክ ከአምስት ቀን በፊት ወዳያት ወደ
ትህትና ሲዘምት፤ እሷም ከአምስት ቀናት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ልቧን ውሃ ወዳደረገው መልክ መልካም ወጣት በሀሳብ ከነፈች.....
ሁለቱም በስሜት እየተፈላለጉ በመንፈስ እየተደባበሱ... አካላቸውን በየአልጋቸው ላይ አሳረፋ፡፡ ትህትና እንደዚሁ እየቃዠች፤ የነገው ቀጠሮ እንደናፈቃት፤ እናቷን እቅፍ አድርጋ! ተኛች፡፡
ሻምበል ብሩክ ግን እንቅልፍ እምቢ ስላለው መጽሐፍ ማንበብ ፈለገና
ያንን ከዚህ በፊት አላነብም ብሎ ያስቀመጠውን የፍቅር መጽሐፍ ለማንበብ ጉጉት አድሮበት “ሀ ”ብሎ ገጹን ገለጠ....

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስምንት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና .....በሐረርጌ ክፍለ ሀገር፤ በሀረር ከተማ ነዋሪ የሆኑት ፊታውራሪ በላይ እንግዳ፤ ከመጀመሪያ የህግ ባለቤታቸው ከወ/ሮ አይኔአበባ ጥሩነህ ከወለዷቸው ስምንት ልጆች ውስጥ፣ ብሩክ በላይ አራተኛ ልጅ ነው። ፊውታራሪ በላይ፤ ልጃቸው ብሩክ ! በእናቱ ማህፀን ውስጥ እንዳለ፤ በወዳጅነት አብረዋቸው ደስታንና ችግርን ካሳለፉት…»
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

....“ ምናገባህ ? ሞዛዛ ?" ስትለው ድምጿ የብሽቀት ቅላጺ ነበረው ።

“እውነት ብርቄ ፥ ምን ያህል ጊዜ ሆነሽ?” አላት ሳምሶን?

"አራት ዓመት!”

"የአራት ዓመት የሥራ ልምድ ! ከሌሎቹ አንጻር ሲታይ ትንሽ ነው ” እላት ሳምሶን "

“ መላጣ ! ” አለችው ፡ ጭንቅላቱን በዐይኗ ቂጥ እያየችው ።

“ በአራት ዓመት ውስጥ ስምሽን ለመለወጥ አልሞክርሽም ? ”አላት እስክንድር ሲቀልድባት ፡ “ እዲስ የከተማ
ስም እንደ ራሄል ኤደን ማርታ ፡ ዓለም ከተሜ ለመሆን እ ? ”

“ሒድ'ደረቅ ! ”

ሒድ፡ደረቅ !ሒድ፡ደረቅ!ደረቅ ማርታ በቅናት ቅንድቧን እያርገበገበች ከፊቱ ድቅን አለችበት ። በሐሳቡ ቁመናዋን ቃኘ በሞቅታ መንፈስ እንደገና አለማት ፡ ኪሱ ባዶ ማለም ብቻ ! ማነጣጠር ብቻ !

"ሒድ ፡ ደረቅ የሴቶች የጋራ ፈሊጽ ” አለ በልቡ ።

የብርቅነሽ ጥሬነት አስገረመው ፡ ስትጫወት የባላገር ለዛ አላት ። ንቅሳቷ ባላገርነቷን ይመሰክራል የባላገር ስሟን
አልለወጠችም " እምብዛም የከተሜ ጭምብል አላጠለቀችም ግን ከሀገርሽ ለምን ወጣሽ ? ” አላት በድንገት ።

“ ሆሆይ !ጋዜጠኛ ነህ እንዴ ?”

ባልሆን ፥ ይህን ሥራ ምን አስመረጠሽ ፡ ማለቴ ነው ። ””

“ ዋ ! ወድጄን መሰለህ ? ግድ ሆኖብኝ እንጂ ” ከማለቷ ፊቷ የኀዘን ጭጋግ ለበሰ

“ ምነው ?እንዴ? ” አላት እስክንድር ስሜቷን ተከትሎ ስሜቱ እየዳመነ።

“ ባልተቤቴ ነው ለነዚ ያበቃኝ ! በሱ ምክንያት ነው ሀገሬን ለቅቄ የወጣሁት እያለች የታሪኳ ዳር ዳር ጨረፈችው
በፍቅር ለቀረባት ሁሉ ታሪኳን ታወራለች
ልስ ልስ ሆኖ ለቀረባት የአንጀቷን ትዘከዝካለች የተማረ መስሎ ለታያት ችግሯን አፍረጥርጣ ትናገራለች ። መፍትሔ ይገኝልኛል ብላ አይደለም :: የውስጧን ተንፍሳ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን የመንፈስ እረፍት ታገኛለች።

«« እባክሽ አታጓጊን ፣ በደንብ አጫውቺን" አላት እስክንድር ታሪኳን ለመስማት ተጣድፎ።

“ አያችሁ እናንተ ዕድለኞች ናችሁ : ከደኅና ቤተሰብ በመወለዳችሁ ወይም ከተማ በማደጋችሁ ለመማር በቅታችሆል እኔ የቀለም ትምህርት የለኝም ማንበብና መፃፍ እንኳ የቻልኩት አሁን የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ ከተጀመረ ወዲህ ነው።
የድሀ ገበሬ ልጅ ነኝ ። ያውም በእንጀራ
እናት ያደግኩ !ህም እቴ! ታድያ በአሥራ አራት ዓመቴ ተዳርኩ ። ባሌ ገበሬ ነበር ። እኔ ሁለተኛ ሚስቱ ነኝ ።የመጀመሪያ ሚስቱ ከተጋቡ መንፈቅ እንኳ ሳይሞላቸው ሞታበት ነበር ። ወላጆቼም ሲድሩኝ ይህን ያቃሉ በእድሜ በሰል ያለ ነው ። ጸባዩም ጥሩ ነው ለትዳሩ ታታሪ ነው ” ተባለና ተሰጠሁ ።

“ ጎጆአችንን እያሞቅን ፡ የባላባቶችን ግልምጫና ዱላ በጋራ እየተቀበልን መኖር ጀመርን ፡ ምን ይሆናል ። እግዜር ለትንኮሉ ማሕፀኔን ድፍን እደረገው። ዓመት ጠበቅን ሁለት ዓመት ጠበቅን ልጅ የለም ። በእኔና በባልተቤቴ መሐል ቅሬታ መጣ ያም ሆኖ አልተቃቃርንም ። ድህነት ያስተሳስረን ነበር ። እሱ ከገበሬዎቹ ጋር ውጭ ደክሞ ውሎ ሲመጣ ከቤት ያለሁ
ረዳቱ እኔው ነበርኩ በባላባት ጅራፍ ጀርባው ቆስሎ ሲመጣ አንጀቴ እየተንሰፈሰፈ የማለቅስላት እኔ ነበርኩ ዋ! እቴ ምን ያደርጋል!

እንዲህ እንዲህ እያልን አምስት ዓመት ያህል እንደኖርን አብዮቱ ፈነዳ ። ለውጥ መጣ ። ደክመን ለባላበት መገበሩ ቀረ። እፎይ አለን ። ቤታችን ሙሉ ሆነ እውነቴን ነው ደህና ነገር መብላት መልበስም ጀመርን ። ምን ይሆናል ። ከድህና
ኑሮ ጋር ተያይዞ ነገር መጣ ባልተቤቴ ሌላ ሴት ጋር በስርቆት መሔድ ጀምሯል የሚል ወሬ ሰማሁ ። ስውል ሳድር እኔም
ነገሩን ደረስኩበት። እንዲያውም አንድ ልጅ እንደ ወለደችለት አረጋገጥኩ ። ቀናሁ ! ቅናት አንገበገበኝ ። በሐሳብ
ተብከነከንኩ። ጨስኩ ።ቤት ውስጥ !
መቀመጥ አቃተኝ ብዙም ሳልቆይ ጓዝ ምንጓዝ ሳልል በርሬ ወጥቼ አዲስ አበባ ገበኋት !

“ እዚህ ስደርስ ደግሞ ያዘጋጀሁት ማረፊያ የለኝ ፥ እንደሁ ሜዳ ቀረሁ ። ትንሽ ቀን ሰንብቼ በደላላ አማካይነት
ግርድና ተቀጠርኩ። ስድስት ወር እንደ ሰራሁ ግርድናን እርም ብዬ ተውኩት። አባስኩ እቴ ! የሰው ቤት ሹሮ ሲያልቅ
እኔ ላይ ማፍጠጥ ። ዕቃ ሲጠፉ እኔን መወንጀል ። ምነው ከዚህ ሁሉ ሥጋዬን ሸጨ ባድር አልኩና ሽርሙጥና ጀመርኩ
እላችኋለሁ ።

ብርቅነሽ ስትናገር ታላቅ ማዕበል ተነሥቶ ባሕር ውስጥ የከታቸውን ያኸል ሥስቱም ጸጥ ብለው ነበር ። አሳዘነቻቸው። ምስኪን ጥሬ ፍጥረት ! በመጠጥ ሞቅታ ኃይል ለሁሉ ነገር ግዴለሽ ሆኖ የቆየው አቤል እንኳ፥ ከብርቅነሽ አፍ የድህነት ድምፅ ሲሰማ ቸል ማለት አልቻለም ። ሕዋሳቱ በኀዘን ስሜት ተወራጩ ::

ግን ዝዎም ብለሽ ከምትኮበልይ ፥ ሰላምን በአካባቢሽ በሚገኘው የሴቶች ወይም የገበሬ ማኅበር አመልክተሽ መፍ
ትሔ ኣትፈልጊም ነበር ? ” እላት እስክንድር ፡ ከማዘኑ የተነሣ የሚናገረው ጠፍቶት ።

ዋ እቴ ! ቤት ከፈረሰ ወዲያ ሁሉስ ምን ሊበጅ ? አየህ ፡ ቅናት ከመጣ ቤት ፈረሰ ማለት ነው። ለሁሉም እኔ ለማንም አላማከርኩ ። የሚያለቅሱ ልጆች የሉኝ ' ነጠላ ሰው ምናለበት አልኩና ብር ብዬ አዲስ አበባ ፣ ”

ታዲያ ባልሽ ሊፈልግሽ አልመጣም ” አላትአቤል በሁኔታዋ ስሜቱ ተነክቶ ።

“ ውእእይ • ሥራ አጥቶ ! እንዲያውም ከዚያ ሀገር ለንፀግድ የሚመላለሱ ሰዎች እዚሁ ቡና ቤት አግኝቼ ሲነግሩኝ' ውሽማውን ጠቅልሎ ይዟል አሉኝ • እዩዬ ! ” ብላ ሳትጨርስ ጥሬ ሰማች «

“ ብርቅነሽ ? ! አንቺን'ኮ ነው ? ” የቡና ቤት ባለቢቷ ድምፅ ነበር
“ እመት ! ወይ ጕዱ ዛሬ ! ” እያለች ብርቅነሽ ከተቀመጠችበት ተነሣች

“ እንድዩ ! ሰው ሲገባ አትታዘዥም እንዴ! ምን ይጎልትሻል ? ”

ብርቅነሽ የውስጧን ተንፍሳ ቃጠሎዎን አብርዳ ተነሣች ፡ እስክንድር ተከዘ ቃጠሉዋ ወደ እሱ ተላለፈበት ኀዘኗ ጠልቆ ወጋው ። ቅናት ተፈጥሮአዊ ነው ሀብታምና ድሀ አይልም ። የወደደ ሁሌ ለወደደው ነገር ይቀናል ። ለቀናበት ነገር ይሠዋል ። ብርቅነሽ የቅናትን እሳት ሸሽታ ኮበለለች ። ከቅናት ሸሽታ ሴትኛ አዳሪ ሆነች "

እስክንድር ሐሳቡ ከግላዊነት ወደነማኅበራዊነት መጠቀ ለእሱ ሲጋራ መግዣ መስጠት ያቃታቸው ደሀ እናቱ ላይ ሆኑ፡ሕዝቧን በሰፊው ማስተማር ' በቂ ኢንዱስትሪ ከፍታ እነብርቅነሽን ማሠማራት ያልቻለች ረሀብን ለማጥፋት
ማይምነትን ለማጥፋት ርካሽ ልምዶችን ለማስወገድ በባህል ለማደግና የቴክኖሎጂ ውጤት ተጠቃሚ ለመሆን የልጆቿን እጅ የምትማጠን እናት ሀገር፡እጆቿን ዘርግታ በሐሳቡ ታየችው
ከሐሳቡ ፋታ አግኝቶ እሱነቱን ወዳለበት ሲመልስ ምሶን ዐይኑን አፍጥጦ ተመለከተ ።አስተያየቱ አላማረውም ። በልቡ ምርምርህን እዚያው ዩኒቨርስቲው ውስጥ አድርገው ፥ ይሄ መጠጥ ቤት ነው የሚለው መሰለው "
እና እስክንድር ብርጭቆውን አነሣ መጠጣት ! ለጊዜውም ቢሆን ራስንም አካባቢንም ለመርሳት ህሊናን ለማዘናጋት
መጠጣት!

“ ስማ እንጂ እስክንድር እየመሸ ኮ ነው ! ” አለው ሳምሶን ዐይኑን አጉረጥርጦ "

“ እ ? እሺ • እንሒድ እንዴ ? ”

ሁለቱም ብርጭቆአቸውን አጋብተው ብርቅነሽ እስክትመለስ ጠበቁ አቤል ሶስተኛው ቢራ ላይ በግማሽ ተሸንፏል።

የብርቅነሽም ልብ ከእነሱው ጨዋታ ጋር ቀርቶ ስለ ነበር የታዘዘችውን በፍጥነት አቀራርባ ተመለሰች "

“ መሔዳችን ነው እንግዲህ ” አላት እስክንድር ለመነሣት እየተንጠራራ ።

“ ተጫወቱ እንጂ 'ምነው ? ” አለች' አቤል አጠገብ እየተቀመጠች ።

“ እንሒድ እባክሽ ! ገና መውደቂያችንንም አላዘጋጋጀን ” አላትና “ አንቺም ከሦስታችን አንዳችንን ይዘሽ ማደር አለብሽ ” አላት ።

ከሦስታችሁ በዕድሜ ልጅ የሆነውን ነው የምፈልገው ።

“ እንዴት ታውቂያለሽ? ግንባራችን ላይ አልተጻፈ!”

ውይ በደንብ ያስታውቃል አሁን ለምሳሌ እሱ በዕድሜ ልጅ ነው ” አለች አቤልን እንደ ማቀፍ ክንዷን ትከሻው ላይ ጣል አድርጋ ። “ ሳምሶንም ሰውነቱ ፋፋ
እንጂ ጢም እንኳ የለውም ። ባንዴ የተመዘዘ ሰውነት መሆኑ ያስታውቃል ።
እናትሽን ! ” አላት ሳምሶን ሣቅ አፍኖት ።
“ በይ ቀጥዪ እኔስ ?” አላት እስክንድር

“ አንተ እንኳ ጠንዝተሃል ፡ ታስታውቃለህ ” አለችው እየሣቀች።

“ ያጠንዛሽ ! ” አለ እስክንድር ፥ በልቡ እየሳቀ ወደ አቢል ጆሮ ተጠግቶ ፥
ከእንግዲህ የካምፓስ ፖሊሶች አያስገቡንም።መሽቷል።እዚሁ ከብርቅነሽ ጋር ማደርህ ነው” አለው ።

አቤል በቋንቋ መልስ መስጠት አልቻለም በእሺታ ቅንድቡን ሽቅብ ቀልሶ ፈቃደኛነቱን ገለጸ። ፍላጎቱ አለው ።
ግን እንዴት ይሆናል ? ያለ ገንዘብ ይታደራል እንዴ ?

አይዞህ " ችግር የለም ” አለው ሳምሶን ግር እንዳለው አይቶ ።

አቤል በአልኮል የደከሙ ዕይኖቹን እንደገና አስለምልሞ በእሺታ ግንባሩን ነቀነቀ።

የአቤል የደከመ ገጽታ እስክንድር ላይ አንዳች የሀዘን ስሜት ፈጠረበት ። ለእምነቱ ግትር የነበረው አቤል ክፉኛ እየተረታ መምጣቱን ገመተ። እነሆ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሴት ጋር ውጭ ለማደር ፈቃደኛ ሆነ ።.ሴት ልጅ ክንዷን
ትከሻው ላይ ስታደርግ ወይም ስታቅፈው ተቃውሞ አላሳየም ። በዚች ቡና ቤት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ትዕግሥት ከአፉ አውጥቶ ተናገረ ። በእምነት ግትርነት ተወጣጥሮ የቆየ እሱነቱ ሳላ : ይህ መጠጡ የፈጠረው የአካል ድካም ብቻ አይደለም ፤ የመንፈስ መድከም ነው መንፈስ ሲደክም ደግሞ አካልም ይዝላል ምላስም ይተሳሰራል ሰውነት ከአድራጊነት ወደ ተመልካችነት ወይም ታዛቢነት ይሸጋገራል ።

እስክንድር በልቡ ይህን እያሰበ '' ታዲያ አቤል ጓደኛዬ መንፈሱ ሲደክም፡ በማበረታታትና የቀድሞ እምነቱን
በመጠበቅ ፈንታ' ሲሸሸው ወደ ቆየው ተግባር መጨመሩ ትክክል ነው ? ” ሲል ራሱን ጠየቀ ።


ያስፈልጋል : አንዳንዴ ራስን መርሳት ያስፈልጋል ሁልጊዜ ራስን አስታውሶ እንደ ምን ይቻላል? አቤልም ዛሬ ራሱን ይርሳ ! እርሱነቱን በተለየ ገጽታው ይመልከተው ።
ሕይወት ዥጉርጉር ናት ” እያለ ሲያስብ ፡ አልኮል የማይበግረው ኅሊናው ጦሩን መዝዞ ተነሣበት ። እስክንድርም
ጋሻ ይሆነው ዘንድ የቢራ ጠርሙሱን አነሣ ። ነገር ግን ጨርሱ ባዶ ነበር ።

“ እንሂድ እንጂ መኝታ ከያዝን በኋ ከፈለግክ ሌላ ጋር እንጠጣለን አለው ሳምሶን በቁጣ ድምፅ።

ወዲያው ሂሳቡን ክፍሎ ተነሣና ብርቅነሽን ጠቀሳት ። እስከ ውጭ በር ተከተለችው ። ገንዘብ በእጅዋ ሲያስጨብጣት “ ዋ ! ልጁ ምንም አያቅም ብለሽ
እንዳትፈነግይው ” ሲል አስጠነቀቃት ።

“ እኔ ብርቅነሽ ? ሥራዬም አይድል ። ይልቅ ቻው ! ”ብላው ገባች።

እስክንድር ከአቤል ጋር ጠዋት ጆሊ ባር ለመግናኘት ቀጠሮ ሰቶት ወጣ።

ሳምሶን ብቻ ዛሬ በረንዳ እንዳናድር
አለው እስክድር በስሥጋት ።

"ግድ የለህም፥ ገና ሰዓት አለን አለ ሳምሶን ፥ ፊት ለፊት እየቀደመ።

ሁለቱ ከሔዱ በኋላ'አቤልና ብርቅነሽ ተፋጠው ቁጭ ሆነ ከመሐከላቸው ቃል የሚተነፍስ ጠፋ ። ብርቅነሽ ዐልፎ ዐልፎ “ ተጫወት እንጂ ” እያለች ብትጎተጉተውም አቤል ምላሱ ሊፍታታለት አልቻሉም ። ወንድ ሴት
ልጅን ምን እያለ ማጫወት እንዳለበት ገና አላወቀም ።

ወይም መኝታ ክፍልህን ላሳይህ ? ዐረፍ የምትል ከሆነ አለችው ።

“ ብቻዬን ? አላት ድምፁ በመጠጡም በፍርሀትም ተወላግዶ

“አይይ እኔም እመጣለሁ ነገር ግን ከአምስት ሰዓት ተኩል በፊት ሥራ ለመፃቆም ባለበትየዋ አትፈቅድልኝም
እስከዚያ ድረስ እንተ ገብተህ ዐረፍ በል ” አለችው እየሣቀች።

“እሺ በይ አሳዪኝ ። ”

ከቡና ቤቱ በስተጀርባ ከሚገኝ አንድ ክፍል ውስጥ አስገብታው ተመለሰች "
አቤል ቶሎ ልብሱን አላወለቀም አልጋው ላይ ተቀምጦ ጣራ ግድግዳውን ይመለከት ጀመር ። አልጋው ገና
ቁጭ ሲልበት እሮሮውን አሰማ እየተንቃቃ አቃሰተ ። ለዕረፍት ሳይሆን ለድሪያ የተዘጋጀ አልጋ ። ክፍሉ የቤት መልክ አልነበረውም ሆኖም አቤል ይህን ሁሉ ለማጤን አልቻለም ። እግሩን ሳያወጣ በጎኑ አልጋው ላይ ጋደም ሲል ሰማይ ምድሩ ብዥዥ አለበት ። የሚሽከረከር ወሰለው ዐይኑን ዘጋ ። አሁን ደግሞ ክፍሉ ሳይሆን የገዛ ጭንቅላቱ የሚሽከረከር መሰለው ። ብርቅነሽ በሐሳቡ መጥታ ዕርቃኗን ከፊቱ
ቆማ ብዥታውን አበረደችለት ሰውነቱ በወሲብ ግለት ተወማበጠረ ። ቸኮለ ዐይኑን ሲገልጥ ግን ከፊቱ የቆመ ነገር
አልነበረም " ወና ቤት ! ወናነቱ ያስፈራል ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ጥንድ የመሆን ተስፋ በልቡ ባይቀረጽ ኖሮ አቤል ወናውን ክፍል ሸሽቶ በፈረጠጠ ነበር ።

ወናነቱን ላለማየት ወይም ቀድሞ ያየውን እርቃን ደግሞ ለማየት እንደገና ዐይኑን ጨፈነ " የብርቅነሽ ዕርቃን በድጋሚ ሊታየው አልቻለም በምትኩ የሌላ ድምፅ በጆሮው ውስጥ አስተጋባ "
ብር አምባር ሰበረልዎ !
ብር አምባር ሰበረልዎ !
ሸጋው ልጅዎ ! ”

የእስክንድር እና የሳምሶን ድምፅ መሰለው ፡ ጆሮው የሰማ የመሰለውን በዐይኑ ለማረጋገጥ ዐይኑን ገለጠ አሁንም ምንም ነገር የለም ። ዐይኑን እየጨፈነና እየገለጠ ከቅዠቱ ጋር በመጫወት ላይ እንዳለ እንቅልፍ አሸለበው ።

የክፍሉ በር ሲበረድ ከእንቅልፉ ባነነ ብርቅነሽ ነበረች የደም ሰንበር በተጋደመባቸው ዐይኖቹ ውስጥ
ግዙፍ ሆና ታየችው ። ንቅሳቷ ባለበት የሚርገበገብ መሰለው።

"አልተኛህም እንዴ ? ”
"እ ? ”
“ አልተኛህም ወይ ? ”
ገና ከመግባቷ ተወርውራ አጠገቡ ቁጭ አለች « ዘለለና አቀፋት ። ቶሎ ልብሱን አወለቀ፡ ጭኑና ጭኗ ስለ ተጠጋ
ክፉኛ ሞቀው ።

“ አንዴ ቀና በል ፤ የኔ ሸጋ ”

“ እ ? ”

“ አንዴ ቀና በልልኝና በሩን ቆልፌ ልብሳችንን እናውልቅ
ቁና ቁና እየተነፈሰ ቀና አለ " የሴት ልጅ ገላ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጠጋቱ በወሲብ ስሜት የልቡ ትርታ ክፉኛ
ይነጥርበት ጀመር ።......

💥ይቀጥላል💥
👍1
#አሃ . . .!

በመጸው ሰማይ ሥር
በቀለም ሸብርቃ
ካ'ዋፋቱም ልቃ
የመስቀል ወፍ ታየች ፤
ወረኃ መስከረም
ለምልማና ደምቃ
ከምድር ማሕፀን
ዐደይ በቅላ ፈካች።

አካል ላባዎቿ .
ከጥዑም ድምጿ ጋር
ከደመናው በላይ
በሰማዩ በራ ፤
ሕብር ፣ ሕብረ ቀለም . .
ከአድማስ ጥግ ላይ
ውብ ቀስተ ደመና
በቃል ኪዳን ሠራ።
ማራኪ ገጽታ ፣
ጤዛ ጠብታዎች
አበባ አካሏ ላይ
እንዳሸበረቁ ፤
ቢራቢሮ ፣ ንቦች
ነፍሳቶች በሙሉ
ከዐደይ ላይ ቀስመው
ሕይወትን ሰረቁ።

ግና . . .
የመስቀል ወፍ ውበት ፣ ድምጿ ቢስረቀረቅ
ዐደይ አበባዋም ፣ ምድሩ ላይ ብትደምቅ
በምን ጥበብሽ ነው . . . ?
ያ'ነኚኽን ውበት፣ ጸጋሽ የሚደብቅ።

ምን ዐይነት ኃይል ነው?
መስህብ ጸጋሽ ኹሉ ፣
አንዳች ምስጢር አለው።

አሃ. . .!
ለካ . . !
ይህ ኹሉ የታየው
አንቺ ስላለሽ ነው።

እኔን የገረመኝ . . .!
ዐደይም ስትረግፍ ፣
የመስቀል ወፍ ስታልፍ
ከመጸው ጋር ዕብራ ፤
ፀሓይም ስትጠልቅ ፣
ጨረቃም ስትጎድል
ዝናቡም ሲያባራ ፤
ጊዜ በቀመሩ
ኹሉን አፈራርቆ
በኃይሉ ሲመራ ፤
ምን ምስጢር ኖሮት ነው . . .?
የቁንጅናሽ ጮራ
በዘላለም ስፍር
ኹሌም የሚበራ።
አሃ . . .!
ለካ . . .!
እንኳንና ኅዋው
ውበትም ራሱ
ካ'ንቺ ነው 'ሚሠራ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
#ሚሊዮን ፀሐዮች ሚሊዮን ጨለሞች


ጨረቃ ብቅ አለች ፀሐይ ስትከስም
ያው እንደ ወትሮ ነው
የምሽት የንጋት ፈረቃው አይፈርስም!

የኔ ግን ይለያል
ልቦናየ ቢማስ
ሚሊዮን ፀሐዮች ሚሊዮን ጨለሞች!
ሺ ሰማይ ሺህ አድማስ
ተገልጦ ይታያል።

ስንቴ በጽልመቴ ዙርያየን አዳፈንሁ
ስንቴ በጨረሬ የምድርን ዐይን ወጋሁ
ባንድ ቀን ውስጥ ብቻ
ስንት ጊዜ መሽቼ ስንት ጊዜ ነጋሁ!

በዕውቀቱ ስዩም
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በትክክል_ገና


....መያዣ መጨበጫ በሌለው ቋጥኝ ላይ ተንጠልጥያለሁ፡፡ የሙጥኝ ብዬ የተጣበቅሁት ድንጋይ ቅቤ እንደተቀባ አሎሎ እያሙለጨለጨ ያሰቃየኛል፡፡ ነፍስና ስጋዬ በጭንቀት ተወጥረው
ይሟገታሉ። ቀና ብዬ ተመለከትኩ፡፡ ወደ ተራራው አናት ለመውጣት የማደርገው ጉዞ ሊደረስበት ይቅርና፤ ከቶም የማይታሰብ ሆኖ አገኘሁት..እንደ ብረት ምጣድ ክብ ሆኖ፤ በአናቴ ላይ ሊወድቅ የተዘጋጀ የሚመስል፤ ግዙፍ አለታማ ድንጋይ አየሁ፡፡ የመሹለኪያ አማራጩን
በፍርሃት ተውጬ አማተርኩ፡፡ አሞራ አይደለሁ በክንፌ አልበር ነገር
ሰው መሆኔን የጠላሁት የዚያን ጊዜ ነው፡፡

ከዚህ በላይ ሽቅብ የመውጣቱ ጉዳይ ተስፋ አስቆራጭ ሆነብኝ::በመጣሁበት መንገድ ለመመለስ ፈለግሁ፡፡ ያለኝ የመጨረሻው አማራጭ እሱ ብቻ ነበር፡፡ ምን ያደርጋል? በወጣሁበት መንገድ የመውረድ ምኞቴም እንደ በረዶ በውስጤ የቀዘቀዘው ጎንበስ ብዬ ቁልቁል ስለመከት ነው፡፡ እንዴት አድርጌ፤ እንደምንስ ብርታቱንና ኃይሉን አግኝቼ፤ የዚያን ያህል ሽቅብ ልወጣ እንደቻልኩ ሳስበው፤ ለራሴ ደነቀኝ፡፡
ማርታዬ፤ የኔዋ ውብ ማርታ፤ ዐይኖቿ እንደንጋት ኮከብ የሚያበሩት ማርታ፤ ከበረዶ የሚነፃፀሩ ውብ ነጫጭ ጥርሶቿ ልብን የሚፈለቅቁት የኔዋ ቆንጆ ፤ በእኒያ አለንጋ መሳይ ጣቶቿ ስትደባብሰኝ
ቀለበቷን ለመሆን የሚያስመኘኝ ፍቅርኛዬ ነበረች፤ ኃይሉን በውስጤ የፈጠረችው::

እነዚያ ውብ ከናፍሮቿ የግማሽ ጨረቃን ቅርጽ ይዘው ፈገግ ስትል፤ ልቤ ያለመወርወርያ ገርበብ እንዳለ መዝጊያ፧ ብርግድ የሚልላት ማርታዬ ነበረች ኃይሉንና ብርታቱን ሰጥታ እዚያ ቋጥኝ ላይ በቅዠት ያስወጣችኝ፡፡ የዛሬው አዳሬን አያድርግብኝና፤ ለወትሮው መንፈሴን በሚያስደስት በልዩ ምናባዊ ዓለም ውስጥ የሚያስዋኘኝ ጣፋጭ መዓዛዋ አሁንም ድረስ ያውደኛል፡፡ እያንዳንዳቸው ጥቃቅን ህዋሳቶቼ ከፍቅር
ድርና ማግ እንደተሰሩ ሁሉ፤ መላ አካላዊ ተፈጥሮዬም ወደር የማይገኝለት የማርታዬ የፍቅር ጥልፍና የሽመና ጥበብ ውጤት ሆኖ ይሰማኛል። ጣፋጭ አንደበቷ፣ ዜማዋ፣ ለዛዋ ...ቃናዋ ... ዛሬም ህያው
ነው ለኔ፡፡

ፍቅር የህይወት ቅመም መሆኑን ከማንም ባላነሰ የተረዳሁ ይመስለኛል፡፡ በእነዚያ
ባልታደልኩባቸው ጊዜያቶች ውስጥ
የህይወትን ለዛ ቢስ ጣዕም እስከሚበቃኝ ድረስ አጣጥሜዋለሁ። የህይወቴ ቅመም በድንገት ስትለየኝ ህይወቴ ባዶ ሆነች፡፡ አዎን ጭውው... ያለ መጋዘን በውስጡ ወደል ወደል አይጦች የሚሯሯጡበት
መጋዘን... በኔም ባዶ ህይወት ውስጥ ጭንቀትና ብስጭት እንደልባቸው ይሯሯጡበታል እሷን ባስታወስኩኝ ቁጥር አካሌ እሳት ውስጥ እንደወደቀ ሙዳ ሥጋ ጭብጥ ኩርምት እርር ድብን ይላል፡፡

ፍቅር የራስ መውደድ ነፀብራቅ ነው የሚሉ ካሉ ተሳስተዋል፡፡እኔ እሷን የማያት ከራሴ አስበልጬ ነው። እራሴንም በሷ ውስጥ አልወደድኩም፡፡ እንደዚህ ዓይነቶቹ በፍቅር አበድን! አንቺ ከሌለሽ፤ አንተ ከሌለህ ፤ እየተባባሉ ሲሸነጋገሉ ከቆዩ በኋላ፤ እንደኛው በአጋጣሚ ከተለየ
በማግስቱ ሁሉንም ነገር እንዳልነበረ ረስተውት፤ ከአዲስ ፍቅረኛ ጋር አዲስ ዓለም ለሚቀጩት ወረተኞች ሊሆን ይችላል ፡፡ በገቡት ቃል ኪዳን ፀንተው፤ በመንፈስ አብረው ቆይተው፤ እስከ ወዲያኛው የአካል ግብአተ መሬት ድረስ ፍቅረኞቻቸውን የሚከተሉ መኖራቸውን አልዘነጋውም።
ማርታዬ ለኔ በውስጤ በቅላ፤ አድጋና ጎምርታ ለፍሬ የበቃች የህይወቴ መሠረት ነች:: ፍቅራችን በድቡሽት ላይ የተገነባ ቤት ዓይነት አልነበረም፡፡ ሲቀር የሚቀርም አይደለም፡፡ በልቤ ውስጥ ተተክላ ሥሮቿን ከራስ ጠጉሬ እስከ እግር ጥፍሬ ዘርግታ አድጋና አብባ የምትገኘው
ማርታ ፍቅሬን በቀላሉ ከልቤ ውስጥ ነቅዬ ልጥላት አልቻልኩም።
ከእንግዲህ በኋላ ማርታን ከኔ ልብ ውስጥ ነቅሎ ከማውጣት ይልቅ ነፍሴን ከህያው አካሌ ውስጥ ነቅሎ ማስወጣቱ ይቀላል። ማርታ ከአቅሜ በላይ በቤተሰብ ተፅዕኖ ዐይኖቿ እንደ ጅረት ውሃ ያለማቋረጥ እምባቸውን እየረጩ ብትለየኝም በሷ አልፈረድኩባትም።
እሷ እኮ ለኔ ልዩ ሰው ነበረች፡፡ ልዩ የምትሆንባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉኝ፡፡ ከህይወት ታሪኬ አጀማመርና ሂደት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው:: የማርትዬ እንባ አሁን ድረስ ሲፈስ ይታየኛል፡፡ ከዚያም
በኋላ ሰው አትሆንም። በሀዘን የቆሰለው ልቧ በቀላሉ የሚድን አይሆንም፡፡ ህመሟ ጠልቆ ይጠዘጥዘኛል፡፡ እንባዋ እንደ እንፋሎት ያቃጥለኛል፡፡ ለምን ትሉኝ ይሆናል፡፡
“ይዘኸኝ ጥፋ ሲራኬ እንሂድ... እንሽሽ” እያለች ፍርሀቷን ስትገልጽልኝ ችላ እያልኳት፤ እንደፈራችው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተለያይተን
በመቅረታችን ነው፡፡በደለኛነት ማቆሚያ ወደሌለው የአድማስ ጫፍ ያስሮጠኛል።
እንደጉም ወደማይጨበጥ ዓለም ይወሰደኛል። ወደማልደርስበት አዲስ
ዓለም... እሮጣለሁ፡፡ ፀፀት አእምሮዬን ይገዘግዘዋል። ከእንባ ጭጋግ ባሻገር እጆች ይውለበለቡልኛል፡፡ ነጫጭ ጥርሶች እንደተገሸለጠ የመስኖ በቆሎ እሸት ተውበው ልቤን ያማልሉታል። የብር ጉልላት የመሰሉ ዓይኖች እየተንከባለሉ ሆዴን ያባቡታል። ልደርስባቸው እሮጣለሁ::በጣም እሮጣለሁ፡፡ መቆሚያ የሌለው መድረሻ የሌለው ...የማይጨበጥ ከንቱ ሩጫ....

በድን አይደለሁ ትኩስ ደም በውስጤ ይዘዋወራል። ከአጥንትና ከጅማት የተዋቀረው አካሌ ለኔነቴ መገለጫ ብቸኛው ህያው ምስክር ቢሆንም ውስጤ ግን በህልም ዓለም የሚመራ ዓይነት ሆኗል። አስባለሁ፣አሸታለሁ፣ አዳምጣለሁ፣ እቀምሳለሁ፣ በስሜት ህዋሳቶቼ የማሸታት ቆንጂዬዋን ውብ ጠረን ያላት ማርታዬን ነው፡፡ የዚህችን
ማለቂያና ማብቂያ፤ የሌላት ብልጭልጭ ዓለም ቅጭልጭልታና ጩኸት የማዳመጫ ጆሮ የለኝም፡፡ ለጆሮ ሳይሆን ለልብ የሚሰማ ጣፋጭ ድምጽ
በውስጤ ያንሾካሹካል ::
ሰመመን ወስዶ ዳር በሌለው ሰፊና ውብ ዓለም ውስጥ ያዝናናኛል፡፡ ከሳሽና ተከሳሽ በዳይና ተበዳይ፣ አባራሪና ተባራሪ፣ አጥፊና ጠፊ፣ ወደሌለበት ወደ አንድ ልዩ ዓለም... አዳምጣለሁ፡፡ ኮሽታ አይሰማም፡፡ ህይወት ፀጥ እረጭ ብላለች፡፡ ሁሉም በሰላም የራሱን
ህይወት ይመራል፡፡ በአዲሱ ዓለም፡፡ ያለረብሻ፣ ያለስቃይ፣ ያለረሀብ ያለሀዘን፣ ያለከሳሽ ተከሳሽ፣ ያለተቃራኒ በአንድ አቅጣጫ ብቻ ... ነጣቂና ተነጣቂ በሌለበት በአዲሱ ዓለም... ድህነት ሀብታምነት በሌለበት ውብ ዓለም ህይወት ትጓዛለች፡፡
ዐይኖቼ ፈጠዋል ቁምነገሩ ዐይን ከሆነ እኔም ማለፊያ ትላልቅ ዐይኖች ነበሩኝ፡፡ ከሰው ልጅ ውጫዊ ባህሪ በስተጀርባ የአውሬነት ፀባዩን ማየት የማይችሉ ዐይኖች። በጥርጣሬ ያልተሞሉ ፈዛዛ ዐይኖች፡፡ እንደ ነብር ዐይኖች እየተንቀዠቀዡ አካባቢያቸውን በጥርጣሬ የማይቃኙ ዐይኖች፡፡
ሻምበል ብሩክ መጽሐፉን ከደነና አርዕስቱን ተመለከተው፡፡ እንደገና ጀርባውን ገልብጦ የደራሲውን ፎቶግራፍ በጥንቃቄ አየው።እንደገናም የራሱን ህይወት በመጽሀፉ ታሪክ ውስጥ አየው። በዕድሏን በማርታ፤ ውስጥ ሲራክን ደግሞ ዐራሱ ውስጥ፡፡ የራሱ የህይወት ታሪክ ቅንጭብጭብታ በድርሰቱ ውስጥ ተጠቃቅሶ ስላገኘው ያለዕረፍት አንብቦ ለመጨረስ ጉጉት አደረበት። የማርታ መጨረሻዋ ናፈቀው፡፡ የባለታሪኩ የሲራክ የህይወት አቅጣጫ ወዴት እንደሚያመራ ለማወቅ ልቡ ተንጠለጠለች...
ዐይኖቹ እንባ እንደቋጠሩ በዕድሏን አሰባት፡፡ የልጅነት ፍቅራቸው ታወሰው፡፡ የአደፍርስ ምስል ከፊቱ ድቅን አለ። ፍቅሩን የነጠቀው ነጣቂ፡፡በዚህም ምክንያት ለረጅም ጊዜ ስሜቱ ቆስሏል፡፡ ልቡ ደምቷል። ፍቅርን ሸሽቷት ኖሯል፡፡ ፍቅር ግን እሱ ሲሸሻትም እሷ አልሽሸችውም። ይኸውም እንደ አዲስ መንፈሱን የሚንጥ፤ የተቀበረ ስሜቱን
👍3
የተቀሰቀሰበት፤ የፍቅር ጥንስስ፤ በድሏን በምትመስል ቆንጆ ልጅ በትህትና ድንበሩ ውስጥ ቀስ በቀስ ልቡን እየሸረሸረው ነው...አሁን እንደባለ ታሪኩ ሲራክ እራሱን አይኮንንም፡፡ ዕረፍት አጥቶ ሰሀሳብ የባከነበት የመከራ ጊዜ ማክተም አለበት፡፡ ያንን አላነብም ብሎ ትራስ አድርጉት የቆየውን አስደናቂ መጽሀፍ እንቅልፉን አጥቶ እስከ እኩለ ለሊት ድረስ አነበበ ስለንባብ የነበረው አመለካከት ተቀየረ፡፡በአንባቢ የሚታወቀውና የአራተኛ አመት የማኔጅመንት ተማሪ የሆነው ጓደኛው አቤል የተናገረውን አስታወሰ ፡፡ ፊደል ከቆጠረ በኋላ መጽሃፍ የማያነብ ሰው አረምና ሙጃ አብቅሎ ከሚንቀሳቀስ እዳሪ መሬት ተለይቶ አይታይም። ጥበብ የህይወት ማእድ ነች፡፡ የቀይ ወጥና
የአልጫ ብፌ ጠግቦ በቁንጣን ከመታመም ይልቅ የጥበብን ማእድ በገፍ
ለነፍሱ የሚጋብዝ ብልህ ነው፡፡ ሰእል፤ ስነጽሁፍ፤ ትያትር፤ ሲኒማ፤
ሙዚቃ የጥበብ ማእድ ብፌዎች ናቸው፡፡ ከጥበብ ማእድ ደጋግሞ የሚመገብ እያደር ይራባል እንጂ በቁንጣን አይታመምም :: በተለይ ስነጽሁፍን ለማድነቅ የተፈጥሮ አይንና ጆሮ ብቻ ሳይሆኑ ቢያንስ ፊደል መቁጠርን የሚጠይቅ ፤በስክሪንና በመድረክ ስፋት ልክ ሳይሆን በጭንቅላትህ አድማስ ልክ አለምን የምትቃኝበት መድረክ በመሆኑ
ስነጽሁፍን ልታፈቅር ይገባል ” ይለው ነበር ሁል ጊዜ፡፡
“እውነቱን ነው!!” አለ፡፡ ከመጽሃፍት ራሱን ያገለለባቸውን ጊዚያት በጸጸት አስታወሰና መጽህፉን ከከደነ በኋላ....
“አንተ ታውቃለህ አምላኬ” ብሎ ብርድ ልብሱ ውስጥ ገብቶ ተጠቀለለ...

በእቴጌ ጣይቱ ስም የተሰየመው ሆቴል በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት አንጋፋና ነባር ሆቴሎች መካከል አንዱ ነው። ጥንት አራዳ አሁን ደግሞ ፒያሳ ተብሎ በሚጠራው የከተማዋ እምብርት ላይ የሚገኝ ትልቅ ሆቴል....
ሻምበል ብሩክና ትህትና የተቀጣጠሩት በዚሁ ሆቴል ሲሆን ከሆቴሉ ግቢ ተርፎ አውቶሞቢሎች ደጁን አጥለቅልቀውት ይታያል።
ሻምበል ብሩክ ከቀጠሮው አምስት ደቂቃ ቀደም ብሎ በመምጣት እየተጠባበቃት ነው የትናንትናው ቀጠሮ የተለዋወጡበት ምሽት በምጥ ነግቶ፤ ቀሪውን አሥራ ሁለት ስዓት ደግም በሥራ ቦታቸው ላይ
ስላሳለፉት በአካል እስከሚናኙ ድረስ ተነፋፍቀው ነበርና፤ በርቀት ተያይተው ተሳሳቁ፡፡.......

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍3
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

....በማግሥቱ ጠዋት ከቀጠሮው ሰዓት ቀድሞ ጆሊ ባር የተገኘው እስክንድር ነበር። ያደረበት ቤት ስላልተስማማው
በሌሊት ነበር ሾልኮ የወጣው ። የቤቱ አለ መስማማት ብቻ ሳይሆን የሰው ዐይን ፍራቻም ነው “ አላሁ አክብር” ሳይል ያስወጣው ። የገዛ ኅሊናው ዐይን ሲያለቅስ እንባውን አድርቆ ሲልከሰከስ እያደረ ' የሌሎችን ዐይን ለምን እንደ
ሚፈራ ሁሌም ይገርመዋል ። ባደረበት ቤት አንግቶ፡ ተዝናንቶ ቆይቶ አያውቅም ።

ይህን ልምድ ከየት ይሆን የቀዳነው ? ” ሲል አሰበ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በትምህርት ወራት ቀለም ላይ ተደፍቶ
መክረም ፡ በዕረፍት ሳምንታት ደግሞ ኪስ እስከ ተቻለ ድረስ በአልኮል ማበድና በየበረንዳው ማደር ፈሊጥ እየሆነ መምጣቱ ነበር ያሳሰበው ። በዛሬው ዕለት እንኳ እንደ እሱው የሰው ዐይን እየፈሩ ከያደሩበት በረንዳ በሌሊት እየተሾለኩ " ጸጉራቸው እንደ ተንጨፈረረ ወደ ካምፓስ ቢሮ ያያቸው ተማሪዎች ቁጥር ትንሽ አልነበረም ።

ሁኔታው በትምህርት ተጨንቆ የከረመን አዕምሮ የማዝናናት አዝማሚያ ይመስላል” ሲል ሐሳቡን ቀጠለ
“ ታዲያ ከሰው ዐይንም ; ከዛ ኅሊናም የማይሸሹበት ሌላ መዝናኛ መፍጠር አይቻልም ወይ ? ተማሪው ከተባበረ ከፈተና በኋላ ባለው የዕረፍት ጊዜ ውስጥ እንደየዓቅሙ ገንዘብ አዋጥቶ ' የሙዚቃና ሌሎች የተለያዩ ትርኢቶችን እንዲሁም አዝናኝና አነቃቂ ውድድሮችን ማዘጋጀት፥ በቡድን ሆኖ ከከተማ ወጣ እያሉ ብርቅና ድንቅ ቦታዎችን መጐብኘትና የመሳሰሉት ልምዶች ቢዳብሩ ጤናማ መዝናኛ ይሆኑ
ነበር ። ታዲያ ይህን በጐ ተግባር ለማስተባበር የግንባሩን ቦታ ማን ይውሰድ ? ?

በራሱ ሣቀና ሲጋራ ለመፈለግ ኪሱን ይደባብስ ጀምር ትላንት ማታ ሌላ፡ ዛሬ ጠዋት ሌላ መሆኑ ነው ያሣቀውም
የአንድ ሰው ሁለት ልክ ? አለ በልቡ።

ሣቁ ከፊቱ ላይ ሳይጠፋ ሳምሶን ጉልቤው ደረሰ። ፊቱን ጭፍግግ አድርጐታል • እሱነቱ አስጠልቶት ራሱን የሚጥልበት ቦታ ያጣ ሰው ይመስላል "

“ ታድያስ ? ” አለው እስክንድር ፈገግ እያል ።

ሳምሶን አፉ መናገር እንዳቃተው ሁሉ “ መቼም አልሞትኩም ! ” በማለት ዐይነት አፍንጫውን አጣሞ አንገቱን ወደ ግራ አዘነበለ እጆቹን ኪሶቹ ውስጥ እንደ
ከተተ ሊቀመጥ ሲል ሱሪው የመተርተር ድምፅ አሰማ።

“ እናትክን ! ” አለው ሱሪውን ።

ጥርሳም እንዳትለው ሱሪው ጥርስ የለው አለና እስክንድር ቀለደበት ።

ሳምሶን ፈገግም አላለም "ቢኮረኩሩትም የሚሥቅ አይመስልም

“ ምነው ደበረህ ?” አለው እስክንድር ሣቁን እየዋጠ ።
“ ምን እባክህ ነጭ ናጫ ሴት ነች የገጠመችኝ፡እንዲሁ ስንበጣበጥ ነው ያደርነው "

አይዞህ አንድ ነን ። እኔም ቀዝቃዛ አሮጌት ይዤ ነው ያደርኩት መጠጥ ምን የማይሠራው አለ? ብቻ አትፍረድባቸው ። የእንጀራ ጉዳይ ሆኖባቸው ነው እንጂ ሰልችቶቸዋል "

“ ጥርሳሞች ! ” አላቸው ሳምሶን በልቡ ። ከእስክንድር ጋር መከራከርም መጫወትም አልፈለገም ። መላ ሰውነቱ
ደክሞአል " ለመፍታታት ያህል እንኳ የጠዋት ስፖርት አልሠራም። ሕይወትን የመሰላቸት ስሜት ተሰማው ፡ ፊቱን
በመስታወት ባያየውም በስሜቱ ጠውልጎ ታየው ። የጠጣበትን ቡና ቤት ያጠጣውን ገንዘብና አብሯት ያደረችውን ሴት በልቡ እየረገመ ጠረጴዛውን በቡጢ ደበደበ "

“አቤት!ምን ልታዘዝ?” ሲልአሳላፊው ከተፍ አለ ።
"አንድ ጠርውስ ቀዝቃዛ አምቦ ውሃ ”
“ አዎ ጎሽ ፡ የተቃጠለ አንጀት ለማራስ” አለ እስክንድር ተደርቦ ።

አምቦ ውሃው ቀርቦላቸው እየጠጡ በመጫወት ላይ ሳሉ አቤልን በውጭው መስተዋት በኩል አዩት። ከኋላው
የሚያባርሩትን ያህል በፍጥነት ነበር ወደ እነሱ የሚገሰግሰው ። የእስክንድርና የሳምሶን የተደበረ ስሜት አቤልን
ሲያዩ ተነቃቃ ። ወሬውን ለመስማት አጠገባቸው እስኪደርስ ተቻኮሉ። እሱም ከውጭ ሲያያቸው ዐይናቸውን አፍሮ
በሆዱ አቀርቅሮ ነበር የተጠጋቸው» ማታ በቅዠት መልክ የሰማውን “ ብር አምባር ሰበረልዎ ” አሁን ለቱ ሰበውን የሚሉት መሰስው ።

“ እህሳ ? ሌሊቱ እንዴት ነበር ? ” አለው ሳምሶን' ቀድሞ ሊጨብጠው እጁን እየዘረጋ።

ጥሩ ነበር” አለ አቤል ሁለቱንም ከጨበጣቸው በኋላ ጠርሙሱ ውስጥ የተረፈውን አምቦ ውሃ በብርጭቆ
እየቀዳ ። ጠጥቶ እንደ ጨረሰ በእርካታ ተንፍሶ፡ “እንሒድ እባካችሁ ” አላቸው ።

"ቁጭ በልና ተጫወት እንጂ ” አለው ሳምሶን ለወሬው ጓጉቶ ። አቤል ግን መቀመጥ አልፈለገም ። ወደ ካምፓስ ለመሔድ ቸኩሎአል ። በዩኒቨርስቲም ግቢ ውስጥ አንዳች ነገር ጥሎ ያደረ ይመስል ልቡ ተሰቅሎአል ። እስክንድርም ይህን ስሜቱን ስለ ተረዳለት ለመሔድ ተነሣ።

ወደ ስድስት ኪሎ ሲጓዙም ሳምሶን ከእቤል የመስማት “ጥማቱ እንደ ቀጠለ ነበር ። በዝምታ ትንሽ እንደ ተራመዱ "

“ ታዲያስ ፡ እንዴት ነበር ? ” ሲል ይጠይቀዋል የሴት ተግባሩን አስጐልጉሎ ለማናዘዝ በሚጥር ጥልቅ ስሜት ።

“ ደኅና ነበር ይላል አቤል ነገሩን ቸል ብሎ ለማሳጠር በሚጥር ስሜት ። ሳምሶን በዚህ መልስ አይረካም

"ብርቅነሽ እንዴት ነች ? ” ሲል ደግሞ ሊያወጣጣ ይሞክራል ።

“ ብርቅነሽ ጥሩ ሴት ነች” ሲል አቤል ነገሩን በአጭሩ ይደመድመዋል ።

አቤል ከብርቅነሽ ጋር ምን ዐይነት የመጀመሪያ ሌሊት እንዳሳለፈ ለመስማት ሳምሶን ብቻ ሳይሆን እስክንድርም
ጓጉቶ ነበር ። የብርቅነሽ ጥሬነት ፡ ግልጽነትና ጣፋጭነት ሳያስቡት በሁሉም ልብ ውስጥ ግልጽ ያልሆነ የፍቅር
ስሜት አሳድሮባቸው ነበር። ያም ሆነ ይህ፡ አቤል እንደ ጠበቁት በሰፊው የሚያወራላቸው አልሆነም ። ጓደኛሞች እንዲህ ዐይነት ሌሊት አሳልፈው ጠዋት ሲገናኙ ስለ አዳራቸው ሁኔታ ወይም አብረዋት ስላደሩት ሴት ማውራት
የተለመደ ቢሆንም ፥ ለአቤል እንግዳ ነገር ነበር ። ስለ አዳሩ እንዳይናዘዝ የፍረትና የቁጥብነት ስሜት ኅሊናውን
ጨምድዶ ያዘው ።

ብርቅነሽ የትዕግሥትን ቦታ ባትወስድም በአቤል ልብ ውስጥ የተወሰነ ዳርቻ ይዛ ነው ያደረችው ። ለወሲብ የመጀመሪያ ሴቱ በመሆንዋ ብቻም አይደለም ። እስዋም ራስዋ ሁኔታውን በማየትና ሳምሶን የነገራትን በማገናዘብ
ለአቤል ቀና ስሜት ስለ ነበራት በባነነ ቁጥር አብራው ስትባንን ነው ያደረችው ። የልቧን አጫውታው የልቡን ምስጢር ወስዳለች ። ግልጽነቷና ፍቅራዊ መስተንግዶዋ አስገድዶት አቤልም ስለ ትዕግሥት ሲያጫውታት ነው ያደረው።
የትዕግሥትን ጉዳይ ለብርቅነሽ ግልጽ ማውጣቴ የቆረቆረው ጠዋት ከተለያት በኋላ ነው ። በግትርነት ተወጥሮ የነበረው መንፈሱ እየላላ መምጣቱ ለራሱም ተሰማው ። ምስጥሬ ብሎ ደብቆ የያዘውን የትዕግሥትን ነገር በመጀመሪያ ለሐኪሙ ፡ በትላንቱ ምሽት በመጠጥ ኃይል ለእስክንድር ሌሊቱን ደግሞ ለብርቅነሽ መናዘዙን ሲያስታውስ የመንፈሱ መላላት ታወቀው ።

ሳምሶንም ሆነ እስክንድር የጓጉትን ያህል ሳያወራቸው ከዩኒቨርስቲው በር ደረሱ ። ግቢው ጭር ብሎአል ።ለወትሮው ቢሆን ይህ ሰዓት ወደ ትምህርት ክፍል መግቢያ ጊዜ በመሆኑ መራወጥ ይታይበት ነበር።ዛሬ ግን ገና ከእንቅልፉ ያልተነሣም ኘለ ። የሚነቃነቅ ተማሪ አይታይም ።

እነ አቤል ግቢ ውስጥ ከገቡ በኋላ፥ወደ መኝታ ቤታቹኑ የሚወስደውን ጠምዛዛ መንገድ ሲይዙ አራት ልጃገረዶች
ከሩቅ ተመለከቱ ። ልጃገረዶቹ ሻንጣ ሻንጣቸውን ይዘው ከግቢው በመውጣት ላይ ነበሩ ። ሦስቱ፡ ልጃገረዶች እነማን
እንደሆኑ ሦስቱም ወንዶች ከመቅጽበት ለዩኣቸው ትዕግሥት፡ ማርታና ቤተልሔም ነበሩ ። ሁሉም ያላወቋት አንዷ ልጃገረድ የቤቴልሔም የመኝታ ክፍል ጓደኛ ነበረች
አቤል ደነገጠ
👍1
በአንዴ ገጽታው ተለዋወጠ ። ሻንጣ ይዘው ወዴት ነው ? ማርታና ቤተልሄምስ ይሒዱ ግልግል
ነው ። ትዕግሥት ግን እኔን ጥላ ወዴት ነው የምትሔደው? ወደ ቤታ ወደ ደብረ ዘይት ? አይደረግም ? ” ሲል አሰበ ።
ልቡ የድንጋጤ ታምቡር ይመታ ጀመር ።

እስክንድር የአቤልን ሁኔታ ለማጤን ጊዜ አልወሰደበትም ። እነሱን ከነሻንጣቸው ሲያይ፥ ፈጥኖ የአበልን ገጽታ ነው የተመለከተወ ምን ስሜት ሊሰማው እንደሚችል ጠንቅቆ ያውቃል ። ከልጃገረዶቹ ጋር ፊት ለፊት ያገጣጠማቸውን አጋጣሚ በልቡ ረገመ ትንሽ ብንቆይ ወይም ትንሽ ብንቀድም ኖሮ፥ መንገደ ላይ አንገናኝም ነበር የሚል
ከንቱ ጸጸት ተሰማው ።የአገጣጣሚውን መጥፎ ጎን እምብዛም ያላጤነው ሳምሶን ከልጃገረዶቹ አጠገብ ሲደርሱ ነዉ ነጻ
በሆነ ስሜት • “ ታዲያስ? በጠዋት ወዴት ነው? ” አላቸው። ቤተልሔምን ብሎ ነው እንጂ ከትዕግሥትና ማርታ ጋር ንግግር የለውም ፡

“ እናንተስ በጠዋት ከየት ነው ? ” አለች ቤተልሄም ሁሉንም በተራ እየጨበጠች ።

ማርታ ምላሷ አምልጧት በረንዳ አድረው ይሆናል ! ” ልትል አስባ ለትንሽ መለሰችው። አቤል መሐላቸው ማየቷ ነው ያሳፈራት ። ከእነሱ ጋር ደርባ ልትተቸው አልደፈረችም ።

ለተጠየቁት ጥያቄ ከሁለቱም ወገን መልስ የሰጠ የለም ። ነገሩን አደባብሰው የመጨባበጡን ሥነ-ሥርዓት
ያካሒዱ ጀመር። የእስክንድርና የአቤል ሰላምታ አለዋወጥ ዘዴ የተሞላበት ነበር።እስክንድር በመጀመሪያ ቤተልሔምንና ትዕግሥትን ጨብጦ ማርታን መጨረሻ ያደረገበት ምክንያት አለው ከጨበጣት በኋላ እጁን እጅዋ ውስጥ ለማቆየት ፈልጎ ነው ። አቤልም ለተመሳሳይ ምክንያት ትዕግሥትን መጨረሻ ጨበጣት ። ነገር ግን እንኳንስ እጅዋን ይዞ ሊቆይ ቀርቶ አንድ አፍታ ዘርግቶ ለመመልሱም ተንቀጥቅጦ
ነበር ። ቀና ብሎ ፊቷን ሳያይ ፈንጠር ብሎ ቆመ እዚህ አካባቢ ትዕግሥትን በተመሳሳይ ሁኔታ ሲያገኛት ሁለተኛ
ጊዜው መሆኑ ነው። አንዴም እንዲሁ ማርታና ቤተልሔም ይዘዋት ወደ ሠርግ ሲሔዱ አጋጥመውት የረገማቸው እዚሁ
መውጫ ላይ ነበር ። እና የሁኔታዎች መደጋገም አስደነቀው። እንደ ተቀጣጠረ ሰው መውጪያና መግቢያ ላይ መገናኘቱ
አስገረመው " የ እውነትም የፍቅር አምላክ ይኖር ይሆን እንዴ ?” ሲል አሰበ “ ወይንስ ደግሞ ሳይኮሎጂስቶች ቴሌፓዚ. ” እና “ ክሪቮያንስ ” የሚሉት የርቀት ግንኙነት በእርግጥ ለፍቅረኞች ሥሠራ ይሆን ? ”

ይህን ጠልቆ ለማሰብ ጊዜ አላገኘም ። አሁን እንገብጋቢው ጥያቄ የትዕግሥት መሔድ ነው የ አስር ወይም አሥራ አምስት ቀን ተለይታው ልትከርም ? እንዴት ይሆናል ? ያን ሁሉ ቀን ዐይኑ ምን እየተመገበ ይኖራል ?

ቀስ ብሎ አንገቱን አዙሮ ሰርቆ ተመለከታት ። አጠገቧ እንዳይቆም የተከለከለ ይመስል ከጨበጣት በኋላ ፈንጠር ብሎ ለሁሉም ጀርባውን ሰጥቶአችው ነበር የቆሞው ።
አቋቋሙም ሳምሶንና እስክንድር ከሴቶቹሰ ጋር ያወሩ ስለ ነበር እስኪጨርሱ በመጠበቅ ዐይነት ነው ። ሰርቆ ሲያያትና ሰርቃ ስታየው ፥ ድንገት ዐይናቸው ተገጣጠመ። የሁለቱም ልብ ዘለለ። እሱ ቀድሞ አይኑን ሰበረ የሚሆነውን ለማየት ድርቅ ብላ አየችው አስተያየቷ ብሽቀትና የመንፈስ መብከንከን ያዘለ ይመስላል ።

ትዕግሥት ራሷ ፡ ከአቤል ጋር ባላት ድፍን ግንኙነት እየበገነች መምጣት ከጀመረች ሰንብታለች ። ሰውን ለሁኔታዎች ተገዥ የሚያደርገው መላመድ መሆኑን ተገንዝባለች ። የአቤልን የዐይን ፍቅር ብትሽሸውም አልሆንላትም ።እሱ ተደብቆ ሳያያት ማደር እንደማይቻለው ሁሉ ፡
እሷም ሳታየው መዋል እንዳቃታት እየተረዳች መጥታለች።የሚያበግናት የፍቅሩ መልከ ቢስነት ነው ። መተያየትን
ፈልገው ፥ ሲተያዩ መተፋፈር ፤መገናኘትን ፈልገው ፡ ሲገናኙ መኮሰታተር እየተዋደዱ መራራቅ ፤ የዚህ አስጨናቂ ሁኔታ መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ብታወጣው ብታርደው ፥ ብታሰላስለው ልትደርስበት አልቻለችም ።ሁለቱ የያዙት የማይገናኝ ቀጥታ መንገድ መስሎ ታያት

ከዚህ በተጨማሪ የትዕግሥትን ልብ ያቃጠለው የአካባቢው ወሬ ነው ። ባለፈች ባገደመች ቁጥር ከተማሪው
ሹክሹክታ መሐል የአቤል ስም ጆሮዋ ውስጥ ጥልቅ ይላል ገና ፈተና ከማለቁ ምሽቱን በሴቶች መኝታ ቤት ውስጥ
ከሞላ ጎደል ሐሜቱ ያተኩረው በእሷና በአቤል ሁኔታ ላይ ነበር ። ሰምታ እንዳልሰማች ጆሮዋን በመድፈን ኣካባቢውን መጋተር አልቻለችም ። ፈተና ባለቀ ማግሥት ግቢውን ለቅቃ ለመውጣት የተገደደችውም በዚሁ ምክንያት ነው ።ለተወሰኑ ቀናትም ቢሆን ፥ ከአቤል ዐይን መራቁ ለእሷም ከብዷታል ሆኖም ማርታና ቤተልሔም ለዕረፍት ግቢውን ስለሚለቁ ብቸኝነት እንዳያጠቃት ፈርታ ነው አብራቸው ግቢውን ለመልቀቅ የወሰነችው።

ትዕግሥት ምነው ፈዘዝሽ ? ” አላት እስክንድር ከማርታ ጋር የያዘውን ጨዋታ አቋርጦ። ከጨበጣት ጀምሮ እጅዋን ሳይለቅ እያዋራት ነበር ። ሳምሶን ጨዋታ አጥቶ “ ታዲያስ ? ” ብሎ እየጠየቀ ፥ “ "እና ” ተብሎ እየተመለሰለት ፥ለወጉ ያህል አብሯቸው እንደ ቆመ ነበር።

ትዕግሥት እስክንድር ለጠየቃት ጥያቄ መልስ ሳትሰጠው ዝም ብላ ተመለአተችው። አስተያየቷ ጤናማ አልነበረም ። የሦስቱንም ወንዶች የደከመ አካልና የጠወለገ ፊት በማየት ውጭ አድረው መምጣታቸውን ለመገመት ችላለች። ግን ውጭ የት ? እና ምን ሲያደርጉ ? ቅናት ተሰማት ። እስክንድር አቤልን እንዳበለገው አድርጋ በመገመት በጥላቻ አየችው። አቤል በማርታ ላይ ያለውን አይነት መጥፎ ስሜት ትዕግስት በእክንድር ላይ ማሳየት ጀመረች።

እስክንድር ይህን የትዕግሥትን ውስጣዊ ለውጥ ሳያጤን ፥ “ ማርታና ቤተልሔም እንኳ ከካምፓስ ቢወጡም እዚሁ ከተማ ናቸው ፤ አንቺ ግን የት ልትሔጂ ነው ? ”
ብሎ ጠየቃት ።

አቤል የዚህን መልስ ለመስማት ጆሮውን አሰላ ።

ትዕግሥት የእስክንድርን ጥያቄ ለመመለስ ተገደደች ። “ እኔም ወደ ሀገሬ ወደ ደብረ ዘይት ነዋ ! ዕረፍቱን ከወላጆቼ ጋር ላሳልፍ ብዬ ነው ።

የአቤል ልብ እንደገና ተንፈራገጠ ። ወደ ወላጆቿ ዘንድ ለመሔድ መነሣቷን ገና ሻንጣዋን ሲያይ የገመተ ቢሆንም ፡ ከእሷው አፍ መስማቱ የባሰ ልቡን ረበሸው ።ሆዱን አንቦጫቦጨው ። ደብረ ዘይት ከአዲስ አበባ ስንት ኪሎ ሜትር ይሆን ? በስም እንጂ አቤል ቦታውን አያውቀውም ። እና ቆሞ ሲያሰላስል ትዕግሥትን ሳያይ የሚከርመው
ዐሥራ አምስት ቀን ዐሥራ አምስት ዓመት መስሎ ታየው።

“ እንሒድ እባካችሁ ! ” የሚለው የሳምሶን ድምፅ አቤልን ከሐሳቡ እስክንድርንም ከወሬው አቋረጣቸው ።ሆዱን ስለ ሞረሞረው፥ ከሴቶቹ ለመለየት ቸኩሎ ነበር ።

አቤል የሳምሶንን ድምዕ ተከትሎ መራመድ ጀመረ ።ሴቶቹ ለስንብት ዐይናቸውን አቁለጨለጩ ። እስክንድር
ግን የያዘዉን የማርታን እጅ መልቀቅ አልፈለገም ነበር ።

“ እሺ እንግዲህ ! ታዲያ ዕረፍቱን የት ትገኝያለሽ ? ” አላት የግዱን እጅዋን እየለቀቀ ።

“ ደውልልኛ ! ” አለችና ስልክ ቁጥሯን ነገረችው ።ከእሱ ጋር ስታወራ ወደ አቢል እያየች ነበር ። አቤል ሲናገር ወይም ሲጫወት መስማት ትፈልጋለች ። ይህ ጅንን ፥ ኩሩ ሰው ሲተነፍስ ምን እንደሚመስል መስማት ትመኛለች ።
ለምን እንደማያናግራት አይገባትም ። አጠገቧ አንድም ቃል ተንፍሶ አያውቅም ሲጨበጣትም እጁን እየዘገነነው ነው ። ልክ እንደ አባቱ ገዳይ ነው የሚያያት ።

አሁንም ሳይሰናበታቸው ሔደ ። እስክንድርና ሳምሶን ልጃገረዶቹን ተሰነባብተው ሲከተሉት ኮቴአቸውንና ድምፃቸውን ሰማ ። ከትዕግሥት ጋር ጀርባ ተሰጣጥተው ተለያዩ እሷ ወደ ውጭ እሱ ወደ ግቢ ። ዝም ብሎ ወደፊት ለመቀጠል አልቻለም ። ዘወር ብሎ ሊመለከ
👍1