አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
575 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
መልኩ ሁሉ ጠፍቷል እኮ ወላጅ እናት ለልጃቸው ያላቸውን ተቆርቋሪነት ጭምር ገለፁ፡፡
ነገሮች አስቀድመው የተመቻቹላቸው አባት ጊዜ ሳያጠፉ ወደ ውሳኔ
ሃሳብ አመሩ..
“እንግዲያውስ እሱ በትምህርቱ እንዲበረታ ፤ ንግዱን በተመለከተ ደግሞ
አበራ ሃላፊነቱን እንዲወስድ እናዳርግና ስራውን እናስቀጥላ፡ ገና ለገና የወለድነው ልጃችን ነው በሚል ምክንያት ብቻ በማይሆን መንገድ መጓዙን ብንቀጥል ተያይዞ ገደል እንዳይሆንብን፡፡"
“እውነትህን ነው አበራ እኮ ባንወልደው እንጂ ያው ልጃችን ማለት አይደል? ደግሞስ የእህት ልጅ ማለት ከራስ ልጅ በምን ይለያል? እኔም የምለው ይሄንኑ ነው፡፡ ለዚህ ጉዳይ ጊዜ ባትሰጠው ይሻላል፡፡” በማለት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጭምር አሳሰቡ፡፡ እናት የልጃቸው ነገር ሲያሳስባቸው እንጂ የቀድሞ ፍላጐታቸው የአቶ በቀለ የታላቅ እህታቸው ልጅ የሆነው አበራ በሃላፊነት ቦታ ይቅርና ከዚያ ሱቅ አካባቢ
እንዲደርስ አይፈልጉም ነበር፡፡ ጊዜው ተለዋወጠና፤ ሁኔታው አስገደደና፤
አበራ ለሱቁ ስራ አስኪያጅነት ተፈለገ፡፡
እንግዲያውስ የዚያ የተሾመ ልጅ ስራ አስገባልኝ ያለቻትንም ልጅ ታምጣትና ታግዛቸው፡፡ከሷ ጋር ያው ስድስት መሆናቸው ነው፡፡ ትንሽ ይበዛሉ ቢበዙም ይሁን ይረዳዳሉ፡፡" አሉ አቶ በቀለ ወጪው ትንሽ እያሳሰባቸው፡፡
በዚህ ውይይት ባልና ሚስት በሃሳብ በመግባባታቸው፤ እንደሻው ከሱቅ
እንዲባረር ሲወሰን ፤ የትህትናም የስራ እድል በር በዚህ አጋጣሚ ተከፈተ ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንደሻው ሙሉ ለሙሉ ሃላፊነቱን ለአበራ እንዲያስረክብ ሲደረግ፤ አበራ ሳያስበው የገበያ
አዳራሹ ባለሙሉ ስልጣን ስራ አስኪያጅ ሆኖ ቁጭ አለ፡፡
እንደሻው ያንን ከባድ የወላጆቹን ውሳኔ የሰማ እለት፤ እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ነበር የነጋበት፡፡ስውነቱ በንዴት ተቃጠለ ::ተንገበገበ፡፡ አባትና እናቱ ከገንዘብ ባህር ውስጥ በጭካኔ አውጥተው የወረወሩት አሳ መሆኑ ተሰማው፡፡ እርምጃው በሱ ላይ በመጨከን ሳይሆን እሱንና ገንዘብን ለማቆራረጥ የተደረገ መሆኑን ልቡ ቢያውቀውም፤ ይህንን በቀላሉ አምኖ መቀበል አልቻለም፡፡አሁን እሱና ገንዘብ ሊለያዩ የማይችሉ ፍቅረኛሞች ሆነዋል፡፡ አንዳቸው ያለ ሌላው መኖር ፈጽሞ
የማይታሰብ ነው :: ወላጆቹ የሚያወሩት ትምህርት ምናምን ለሱ ጊዜው ያለፈበት ሞኝነት ነው፡፡ ስለዚህ ከወዳጁ ከገንዘብ ጋር ተመልሰው ፍቅራቸውን ለመቀጠል ያለውን አማራጭ በሀሳቡ ሊዳስስ፤
ሲያውጠነጥን ቆይቶ ያገኘው አንድ አማራጭ ብቻ ነው፡፡ ያንን አባቱ
ቢለምኑት አሻፈረኝ ያለውን ንግድ በግሉ መጀመር በቃ! ።ጊዜው ተለወጠና! ሲለመን ፤ ሲሽሞነሞን፤ እምቢ ያለው ሰውዬ፣ በተገላቢጦሽ አባቱ እግር ላይ ሊወድቅ ወሰነ፡፡ ገንዘብ ዋናው የወላጆቹ አላማ እሱንና ገንዘብን ለማለያየት
መሆኑን ቀድሞ ስለተገነዘበ፤ ንግድ ፈቃዱን ብቻ እንዲሰጡት ለመለመን
ቆረጠ፡፡ ይህንን ሃሳቡን ለማሳካት ግን መጀመሪያ ከአበራ ጋር በሰፊው
ሊወያይበትና አበራን አግባብቶ ንግዱን በጋራ በማጧጧፍ፤ በትንሽ ጊዜ የብዙ ገንዘብ ጌታ ለመሆን እቅድ ነደፈ :: በዚሁ
መሰረት አበራን ከአንድ መጠጥ ቤት ቀጠረው፡፡የዚያን እለት ምሽት እንደሻው የአበራን ይሁንታ ያለማወላወል ለማግኘት እንዲያስችለው ሞቅ ያለ ግብዣ ካደረገለት በሁዋላ..
"ስማ አበራ የትልቅ ሰው ትልቅ አሽከር፧ ወይስ የራስህ ትንሽ ጌታ መሆን?" ሲል ያልጠበቀውን የመጀመሪያውን ጥያቄ አቀረበለት፡፡ አበራ አልገባውም፡፡ ቀጠለ እንደሻው፡፡ "ማለቴ እንደምታውቀው ሽሜው አፈር ግጠህ፤ የልጅነት መልክህ እስከሚለቅ ድረስ እንደምትሰራለት
ቢያውቅም፤ የራሱን የመሸበት ጥቅም ከማስቀደም ባለፈ ታዳጊነቴን አይቶ እድገቴን ይመኝልኛል ብለህ ተስፋ የምትጥልበት ሰው እንዳልሆነ
ከእኔ ሁኔታ ሳትገነዘብ የቀረህ አይመስለኝም"
“እና ምን ይሁን?" አበራ በመገረም፡፡ በስራ አስኪያጅነቱ የቀናበት ነው
የመሰለው ::
“እንደሱ አትበል አበራ፡፡ የምናወራው ስለአባቴ፤ ወይንም ደግሞ ስለአጎትህ ቢሆንም አንተም ስጋዬ መሆንህን መርሳት የለብህም፡፡ ይህንን
የማጫውትህ ደግሞ የሃሜት ሱስ ኖሮብኝ ሳይሆን የኔንም ያንተንም
የወደፊት ህይወታችንን በሚመለከት ጉዳይ ስምምነት ላይ እንድንደርስ
ብዬ ነው፡፡"
“ምንድነው እሱ ?
“አሸከርነትህን በስራ አስኪያጅነት ስም በጸጋ ትቀበለዋለህ?"
“በትክክል እቀበለዋለሁ"
“አሽከርነቱንስ ልትቀጥልበት ትፈልጋለህ?"
“አማራጭ እስከሌለኝ ድረስ አዎን"
"አማራጭ ካገኘህስ ?"
“አስብበታለሁ"
“እንግዲያውስ አማራጩን ልንገርህ አበራ ሁኔታውን ለመስማት ጓጓ፡፡
“በስሜ ንግድ ፍቃድ ማውጣቱን ታውቃለህ አይደል ?"
“አዎን አውቃሁ"
“እሉን ካወቅክ በአሁኑ ወቅት አዲስ የንግድ ፍቃድ
እንደማይቻል የምታጣው አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ የንግድ ፈቃዱ ለአገር ውሰጥ ገቢ ከሚመለስ እኔና አንተ በጋራ በዚያ የንግድ ፈቃድ ምን ልንሰራበት እንደምንችል መገመትም ይሳንሃል የሚል እምነት የለኝም"

"እንዴት አድርገን?"ከፊቱ ግርታ ይታይበት ነበር።
"አይዞህ ! አንተ የስራ አስኪያጅነት ሹመትህን ሳትለቅ እንድትቀጥል
ይደረጋል።ሌላውን ጉዳይ የምጨርሰው እኔ እሆናለሁ፡፡አሁን ከአንተ የምፈለገው ለመነሻ የሚሆነንን ትንሽ ገንዘብ እንድታዘጋጅ ብቻ ነው፡፡
ሌላውን ደግሞ ቀስ በቀስ ከሽሜው ስልቻ ፤ ወደ ራሳችን ስልቻ እናንቆረቁረዋለን እመነኝ በአጭር ጊዜ ውስጥ በራሳችን ቪላ ቤት እየኖርን፤ የራሳችንን መኪና የምናሽከረክርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡"
ጀርባውን ቸብ ፤ ቸ ብ፤ አደረገው፡፡ አበራ ላለፉት አስር አመታት ከዚህም፤ ከዚያም፤ ያጠረቃቀማትን ሳንቲም በባንከ የማስቀመጥ ባህል ያዳበረ ጠንቃቃ ልጅ ነው፡፡ የሚበላው ፤ የሚጠጣው፤ የሚለብሰው፤ የሚኖረው በአጎቱ ቤት ስለሆነ ብዙ ወጪ አልነበረበትም :: እንደሻውም ይህንን ስለሚያውቅ ነው ልቡን ያንጠለጠለው፡፡ በዚህ በእንደሻው
ንግግርና በሚጠጣው ቢራ አበራ በደስታ ሰክሮ፤ በጋራ በሚከፍቱት የንግድ ድርጅት የሚመጣው ርዝቅ ከወዲሁ ታየውና፤ ምንም ሳያቅማማ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ፧ ስምምነቱን ገለጸለት፡፡ ከዚያ በሁዋላ የሆነው ምን ይጠየቃል? አንገት ፤ ለአንገት፤ ተቃቅፈው ለጤናችን እያሉ ዋንጫዎቻቸውን ደጋግመው አጋጩ፡፡ እንደሻው የአበራን ይሁንታ ካገኘ
በሁዋላ የቀረው አባቱን ማነጋገር ብቻ ነበር፡፡ አንድ ምሽት ላይ አባቱ በመኝታ ክፍላቸው ውስጥ ሆነው፤ ዳዊታቸውን በመድገም ላይ ሳሉ መጣ፡፡ እስከሚጨርሱ ድረስ ጠበቃቸው፡፡ ከዚያም ዳዊታቸውን ደግመው
ሲያበቁ ቀና ብለው እንደሻውን አዩት፡፡
"እህ ጎረምሳው ?" ወደ እርሱ እየቀረቡ፡፡ ጭንቅላቱን በአክብሮት እንደማከክ

አለና... ".... እ .. እ ላነጋግርህ ፈልጌ ነበር አባባ "አላቸው፡፡
“በጄ " አሉት፡፡

“የንግድ ፈቃዴን እንድትሰጠኝ ነበር፡፡ ል .. ል .ልስራበት "በእፍረት ስሜት ትንሽ ተንተባተበ፡፡

"ለአገር ውስጥ ገቢ ልመልሰው ነው፡፡ስትለመን አሻፈረኝ አላልክም? አንተ
እንደሆንክ ሰው የምትሆን አይደለህም፡፡ “አሉት ወደ ጎን እየተመለከቱትና
ይህ አዲስ ሃሰብ የመጣበት ሁኔታ እየገረማቸው፡፡
ግድ የለም አባባ፡፡ አንተ የንግድ ፍቃዱን ብቻ ስጠኝ፡፡ ገንዘብ ያለው ሰው አግኝቻለሁ፡፡ በጋራ ለመስራት “አላቸው እየተለማመጠ፡፡
“ይሄኔ ከአንተ ቢጤ እብድ ጋር ያደረግከው ምክር ነው"
አባባ ሙት እንደሱ አይደለም፡፡ አንተም ማስቸግርህ ሌላ ነገር የለም፡፡
ፍቃዱን ብቻ ስጠኝና ልስራበት፡፡"
የንግድ ፈቃዱን ሊመልሱ የወሰኑት በንዴት እንጂ ! አዲስ የንግድ ፈቃድ
ማውጣት በተከለከለበት በዚያን ሰአት መመለሱ ጉዳት እንጂ ጥቅም እንደ
👍2
ሌለው አጥተውት አደለም..

Join Join Join 👇👇👇

https://xn--r1a.website/joinchat/UbOx5WgaYwc4UVnb


💫ይቀጥላል💫

በየቀኑ ሳይቆራረጥ እንዲደርሳችሁ የበዛ Like 👍 እንዲሁመሸ የበዛ #Share እፈልጋለው።

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አራት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና ....ሰማያዊ ሰማይ ጥርት ያለ ብሩህ ቀን ነው፡፡ የክረምቱ ወራት ሊገባ ተቃርቧል፡፡ በዛሬው እለት በትህትና ህይወት ላይ ሁለት ክስተቶች ተከስተዋል፡፡ አንደኛው የሚያስደነግጥ፤ ሁለተኛው የሚያስደስት ትህትና እንደወትሮው በዚያ ቋት ጠብ የማይል የእንጀራ ሽያጭ ስራ ተጠምዳለች። ከትናንት ወዲያ ማታ ያቦካችውን ሊጥ አብሲት ጥላ…»
#የዘንድሮ_ትዳር

ወንዶች ብር ሲያጡ
ሴቶች ልብ እያጡ
ፍቅር ሳይገባቸው እየተጃጃሉ
ትዳር ትዳር ብለው ዘለው ይጋባሉ
ትናንት የተጋቡት ዛሬ እየተጣሉ

ወንዱ ብር ሲያገኝ አይምሮ እየሸጠ
ሴትን እንደ ሸቀጥ እየለዋወጠ
ሴቶች በተራቸው ልብ አገኙ ሲባል
ገንዘብ ያምራቸዋል ሀብታም የሆነ ባል
አንዱ አንዱን ሲፋልግ አንዱን እየሸሸ
የዘንድሮ ትዳር ነግቶም አላመሽ
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....እንደሌለው አጥተውት አልነበረም፡፡ ሰው እሆናለሁ ብሎ በራሱ ጊዜ ለምኖ ሲመጣ ደግሞ አይሆንም ማለቱ ሌላ ችግር መፍጠር መሆኑን አመዛዘኑና..
“ምን ቸገረኝ፡፡ ልብህ ልብ ሲገዛ ፤ ወደፊት ከዚህ የበለጠ ይቆጭህ ይሆናል እንዲህ አደረገኝ ብለህ እንድታማርርብኝ እድል
አልሰጥህም፡፡ አመለጥክም ሰመጥክም፤ ከእንግዲህ ውሳኔው ያለው ባንተው እጅ ነው፡፡ ከአሁን በሁዋላ አንተ ህጻን ልጅ አይደለህም፡፡
ትምህርቱ ይቅርብኝ ማለትህ እንደሆነና፤
የተቋረጠ ሱስህን ለመቀጠል ያቀድከው እቅድ እንደሆነ አውቄዋለሁ፡፡እውነት ልብ ገዝተህ፣ ተጸጽተህ ፤ ራስህን ለመቻል አስበህ፤ ያቀድከው እቅድ እንዳልሆነ
እያወቅሁም ቢሆን፤ ፈቃዱ ያውልህ
አሉና ሳጥን ከፍተው ካስቀመጡበት ቦታ አወጡና፤ እጁ ላይ ጣሉለት፡፡ እንደሻው አላመነም፡፡እንደሚሰጡት ባይጠራጠርም እንደዚህ በፍጥነት እጄ ላይ ያስቀምጥልኛል ብሎ አላሰበም ነበር :: ከወገቡ ለጥ ብሎ እጅ ነስቶ
አመስግኖ ተቀበለ፡፡
ግድየለህም አባባ እሰራበታለሁ :: እለወጥበታለሁ" ቃል ገባላቸው።
ከዚህ በሁዋላ ነበር እንግዲህ እንደሻው እዚያው መርካቶ ውስጥ አንድ ግንባር ክፍል ተከራይተው፤ ከአበራ ጋር የሽርክና ንግድ የጀመሩት፡፡እንደዋዛ የተጀመረው ንግድ ቀስ በቀስ እየደረጀ ሲሄድ፤ አበራና
እንደሻውም ሽርክናቸው የበለጠ እየጠበቀና፤ እያደገ መጣ፡፡አበራ
አብዛኛውን ጊዜውን በአጉቱ የጫማ መሸጫ ሱቅ ውስጥ ሲያሳልፍ፤
እንደሻው ደግሞ የጋራ በሆነው የንግድ ቤታቸው የበላይነቱን እያሳየ ሄደ፡፡

አዜብ ትህትናን ይዛ ከተንጣለለው የጫማ መሸጫ አዳራሽ የደረሰችው ሳትቀድምም ሳታረፍድም በሰአቱ ነበር፡፡
አቶ በቀለ የፈዘዙ አይኖቻቸውን ቦግ አድርገው ትህትናን ከላይ እስከ
ታች ሲቃኙ ቆዩ፡፡ ለምን እንደሆነ ባያውቁትም ይህቺ ልጅ የወለዷት ልጃቸው መስላ ታየቻቸው፡፡ከአይነ ውሀዋ ገራገርነቷን፤ ከቆንጆ መልኳ ውስጥ ደግሞ ታማኝነቷን፤ ያነበቡ መሰላቸው። አበራም እንደዚሁ በአድናቆት ይመለከታት ነበር፡፡ በቤቱ ውስጥ ያሉት ሰራተኞች በሙሉ አይኖቻቸው ያረፉት በሷ ላይ ነበር።
"እንደምነሽ የኔ ልጅ?" እጃቸውን ለሰላምታ ዘረጉላት : ከአዜብ በፊት
የጨበጡት እሷን ነበር፡፡
“እሷ ናት ጓደኛሽ?" እንደ አዲስ ወደ አዜብ ፊታቸውን መለስ አድርገው
ጠየቋት፡፡
"አዎን እሷ ናት አባባ "አዜብ ቀልጠፍ ብላ መልስ ሰጠቻቸው፡፡
"ስምሽ ማነው የኔ ልጅ ?"
"ትህትና"
"እውነትም ትህትና " አሉ መልኳ እንደስሟ ሆኖባቸው፡፡
"ትህትና ማን?"
"ትህትና ድንበሩ"መሬት መሬቱን እያየች
የአባትዋን ስም ተናገረች፡፡
አቶ በቀለ በአዲሱ ስራ አስኪያጅ ጥንካሬና በዚህች ውብ ልጅ ገዳምነት
ንግዳቸው የተሟሟቀ እንደሚሆን
የመተማመን ስሜት አሳድረዋል፡፡
ትንሽ ስለ ታሪኳ ከጠያየቋት በሁዋላ..
አበራ በል እንግዲህ እሷም በሽያጩ ስራ እንድታግዛችሁ የመጣች፥የአዜብ ጓደኛ ነች፡፡የወር ደመወዟን ለጊዜው ሰማንያ ብር እንከፍላታለን።
እንደሁኔታዋ እየታየ ደግሞ ወደፊት በገንዘብ ያዥነት ቦታ ላይ በእድገት እናሰራታለን" ሲሉ መመሪያ ሰጡት።እግረ
መንገዳቸውን ለእድገትዋም ስትል በርትታ እንድትሰራ ማሳሰባቸው
ነበር፡፡አበራም ትእዛዛቸውን መቀበሉን በእሺታ ከአንገቱ ጎንበስ በማለት
ሲያረጋግጥ፤ ሽማግሌው ቀጠል አደረጉና..
“ይሄውልሽ የኔ ልጅ ከእንግዲህ የምትሰሪው ከእነሱ ጋር ነው፡፡ አበራ
ደግሞ የዚህ ድርጅት ሀላፊ ነው ::ማንኛውንም የድርጅቱን ስራ
የምትሰሪው እሱ በሚሰጥሽ ትእዛዝ መሰረት ነው" በማለት ሌባ ጣታቸውን ወደ አበራ እያመለከቱ ገለፁላት፡፡ ትህትና በደስታ ስሜት ተውጣ አንገቷን እንዳቀረቀረች ሽማግሌው የሚሰጧትን መመሪያ ሁሉ"እሺ እሺ" በማለት እየተቀበለች ነበር፡፡ያልገመተችው ሲሳይ ነውና በደስታ ስሜት ሰክራ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
“በይ እንግዲህ ስራውን ነገ ትጀምሪያለሽ አበራ አንተ ደግሞ ደመወዟን ከዛሬ ጀምረህ ታስብላታለህ ፡፡ውሉን አዘጋጅተህ የለም?" አሉት፡፡አበራም ውሉ መዘጋጀቱን ጭንቅላቱን በመነቅነቅ ካረጋገጠላቸው
በኋላ ፤ ሁሉም ተቀጣሪዎች የሚዋዋሉበትን የቅጥር ፎርም አቀረበ በዉሉ ላይ የቀጣሪና ተቀጣሪ ስም የደሞዝ መጠንና ፤የዋስ ስም በውሉ ላይ
ሰፍሮበታል በዋስትናው በኩል የተማመኑት በአዜብ ቢሆንም ለደንቡ
ያክል ዋስ በሚለው ቦታ ላይ አዜብ እንድትፈርምበት ሲደረግ፤ ቀጣሪና
ተቀጣሪ በሚለው ርእስ ስር
ታዲያ ቀጣሪ አቶ በቀለ ሞላና ተቀጣሪ ትህትና ድንበሩ ፊርማቸውን በማኖር የቅጥር ውሉ ተጠናቀቀ፡፡አቶ በቀለም
በሉ አትቁሙ ማነሽ የኔ ልጅ ?ትህትና ነገ በጊዜ እንድትመጪ አሉና አሰናበቷቸው፡፡
“አባባ በጣም ነው የማመሰግነው፡፡ ነገ በጠዋት ትመጣለች፡፡ ደህና ይዋሉ”
አለችና አዜብ እጆችዋን ለሰላምታ ዘርግታ እዚያ የነበሩትን ሁሉንም ስትሰነባበት፣ ትህትናም ተከትላት እንደዚያው ካደረገች በኋላ ተያይዘው ወጡ፡፡ከዚያ ሲወጡ የትህትና አይኖች እንባ አቅርረው ነበር፡፡እንደዚህ ሰው አስቸግራ ስራ ያስቀጠረቻት ጓደኛዋን አገላብጣ
ሳመቻትና፤ እግዚአብሄር ያውቃል፡፡ የበሽተኛዋ እናቴ አምላክ ሳይቀርበኝ
አልቀረም፡፡ስትል በልቧ ተጽናናች፡፡ በሁኔታው ሁለቱም በጣም ተደስተው ስለነበረ እያወሩ ሳያሰስቡት ከቤት ደረሱ፡፡ እንደገቡ ትህትና ሳመቻት፡፡ ሁሉም ተሳሳሙ ወዲያውም የደስ ደሱን ከአዜብ ጋር እናቷን አቅፋ ስራ መያዟን አበሰረቻት እንደ አዲስ አዜብንም አቅፋ ሳመቻት ሁሉም ተሳሳሙ ወድያውም ከአዜብ ጋር እየተጋገዙ፤ ከሰል አቀጣጥለው፤ ቡና አፍልተው፣ ቤቱን ሲያጫጭሱት ተዝናንተው የነበሩ ዝንቦችና ትንኞች ድራሻቸው ጠፋ፡፡
አንዳንዱ ቀን በደስታ አስክሮ ያውላል አንዳንዱ ቀን በሃዘን አጨማዶ ያውላል አንዳንዱ ቀን ደግሞ በሀዘንና በደስታ መካከል እያዋዠቀ፤ ደስታው ደስታ፤ ሀዘኑም ሃዘን፤ እንዳይሆን ግራ ሲያጋባ
ያውላል፡፡ ትህትናን ዛሬ ያጋጠማት ይሄው ነበር ፡፡የዚያን ያክል ጊዜ በስራ ፍላጋ ስትንከራተት ቆይታ እነሆ ዛሬ ታላቅ የምስራች በሰማችበት የደስታዋ ቀን፤ ሌላ ዱብ እዳ አጋጠማት፡፡የቤቱ በር ተቆረቆረ ትህትና ወጣች የሆነ ጸጉሩ የተንጨፈረረ ጨበሪያም ወጣት ቆሟል ልጁን በፍርሀት ተውጣ ቆማ ተመለከተችው፡፡እሷ አታውቀውም እንጂ እሱ ያውቃታል፡፡
“አንዱ አለም ልኮኝ ነው " አላት ትናንትና ውጭ ሲያድር አልፎ አልፎ እንደተለመደው ከጓደኞቹ ጋር ሲጫወት መሽቶበት ነው ብላ ገምታ ነበር
“ምን ብሎ ላከህ ?! የት ነው ያለው?!'ልቧ የሆነ ነገር እየተጠራጠረ ፍርሀት ፍርሃት እያላት ነበር፡፡
"ለእህቴ ንገርልኝ ብሎ"
“ምኑን ?!" አሁን ፍርሃቷ ወደ ድንጋጤ እየተቀየረ ነበር።
"መታሰሬን ንገርልኝ ብሎ"
"ለምን ታሰረ?!” ጮኸችበት፡፡
“እኔ እንጃ፡፡ ፖሊስ ጣቢያ አስረውታል፡፡” የት እንደታሰረ ካረጋገጠች በሁዋላ እንባዋን እያፈሰሰች፤ እያለቀሰች ተመለሰች፡፡በሩ ጋር ስትደርስ ግን በድንገት ቀጥ ብላ ቆመች እናትዋን በዚያ ሁኔታ ማስደንገጥ እንደሌለባት ታወሳት፡፡በበሽታ ላይ ድንጋጤ ሲጨመር ምን ሊፈጠር እንደሚችል ገመተችና ስሜትዋን ተቆጣጠረች ትንፋሿን ዋጥ
አደረገችና ድምጿ እንዳይርገበገብባት ተጠንቅቃ አዜብን ጠራቻት አዜብ
መጣች የሆነውን ሁሉ ለአዜብ ነገረቻት ስለሁኔታው ከተመካከሩ
በሁዋላ ከሱቅ እቃ ለመግዛት የምትሄድ አስመስለው እናቷን በማታለል አዜብ ቤት እንድትቆይ ካደረጉ በሁዋላ እሷ ወጣችና ወደ ፖሊስ ጣቢያ በረረች፡፡ ስትሮጥ ነፍሷን አታውቀውም ነበር፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍3
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...የከተማው ዋና ዋና መንገዶች በዩኒቨርስቲው ተማሪዎች መወረር ጀምረዋል ። የአራት ኪሎና እካባቢዋ ቡና
ቤት አሳላፊዎች፥ ለተማሪ ሻይ ቡና በማቅረብ ተዋክበዋል ። የተማሪዉ አንሶላዎች'ልብሶች በየሥርቻው ተወርውረው የከረሙ የእግር ሹራቦች ከውሃ በመታረቅ ላይ ናቸው ሕሜት ፥ ውረፋ ፡ ዘለፋና ቀልድ ጊዚአቸውን
ጠብቀው ተመልሰዋል በሴሚስተሩ ውስጥ በዩኒቨርስቲው የተደረገች አንዳች ነገር ሳትቀር እየተነሳች መብጠልጠያዋ ጊዜ ነው።

ይህ ሁሉ ፈተና ማለቁን የሚያበሥር ነው የፈተና ውጤት ቀርቦ ማዕበሉ ማንን ጠርጎ ማንን እንደ ተወ እስኪታወቅ ድረስ ለሁለት ሳምንቱ የዕረፍት ቀናት አብዛኛው ተማሪ ከዚህ ክልል አይወጣም ።

እቤልና እስክንድርም የመጨረሻውን ፈተና እንደ ተፈተኑ ግቢውን ለቀው ወጥተዋል ። የተዝረከረኩ ዕቃዎች
ለማስተካከል እንኳ፥ ወደ መኝታ ክፍላቸው አልተመለሱም።ተያይዘው በቀጥታ ወደ እስክንድር እናት ቤት ተክለ ሃይማኖት አካባቢ ሔዱ። አቤል ለአውደ አመትና አልፎ አልፎም ለዕረፍት እነ እስክንድር ቤት መሔድ የጀመረው ገና የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ሳለ ከእስክንድር ጋር እንደተዋወቁ ነው።አንዳንዴ አብረው ይሔዱና የተገኘውን ቀማምሰው ተጫውተው ይመለሳሉ ። ዘንድሮ ግን አቤል ቤታቸው ሳይሔድ ቆይቷል ።

የጠፋው ሰው እንደ ምን አላችሁ ልጆቼ ?
እሁና እናትየዋ ፥ ሁለቱን አቅፈው ሳሙዋቸው ።

“ አቤል ፣ ምነው እንዲህ ጠፋህ ልጄ ?”
ምን እባክዎን ፥ ጥናት በዝቶ ነው
“ ቢሆንስ ታዲያ ፥ አንዳንዴ መቼስ እናት ቤት ብቁ ተብሎ የተገኘውን ቀማምሶ ይኬዳል ። አሀን ፈተና ጨረሳችሁ አይደለም ? ”
“ አዎ መቼስ"

“ እንግዲህ አንድ ፈተና ነዋ የቀራችሁ ? የፊታችን ሰኔ መመረቂያችሁ አይደለም ?

አቤል ዝም አለ ። እስክንድር ስሜቱ ስለ ገባው ቶሎ ብሎ ጣልቃ ገባ ።

“ አዎ ! አይዞሽ ደርሰናል ” አላቸው « እጁ ላይ ሲጋራ መኖሩን ያዩት ይሄኔ ነበር ።

« ይኼንን ሲጋራህን ምናለ ብትተወው እስክንድር ? አቤል ጓደኛህን አትመክረውም ? ! ”

ብዙ ዓመት የተናገሩት ነገር ነው ። ሆኖም ዐይናቸው ባየ ቁጥር ዝም ማለት አይችልም ። አቤል ከመቅለስለስ ልላ
ምንም አልመለሰም።

“አይዞሽ ፡ በቅርቡ አቆማለሁ” አላቸው እስክንድር ራሱ ። እሳቸው ሣቁ ሁሌም
የሚላቸው ነገር ስለሆነ።

ማዘር ሙች አቆማለሁ ። አራት ወር ያህል
ብቻ ታገሽኝ ብቻ አላቸው።

ከልቡ ለማቆም ቆርጦ ነበር እናትየው ግን ጊዜው ደርሶ እስካሳዩ ድረስ ሊያምኑት አይችሉም ።

“ምግብ አቀረቡላቸው ከበላሉ በኋላ ሲጫወቱ ቆይተው ሲመሻሽ እስክንድርና አቤል ሊሔዱ ሲሉ፡-

ዛሬ ለምን ከዚሁ ስትጫወቱ አታድሩም ” እሉ እናትየዋ ።

“ አአይ እንሔዳለን ። እዚያው ካምፓችን ይሻለናል አለ እስክንድር እሳቸው በሚናገሩት አይነት ፣

እስክንድር በዕረፍቱ ሰሞን አቤልን ጥሎ ቤት መክረም አልፈለገም። አብረው እንዳይሆኑ ደግሞ ቤቱ አይበቃም።
ሁለት መኝታ ብቻ ነው ያለው “ አንዱ የናትየዋ ነው " በአንዱ መኝታ ላይ ከታናሽ ወንድሙ ጋር ሦስት ሆነው ተጨናንቀው መክረሙን ኣልፈለገም ። በዚያ ላይ እናትየዋ ለእነሱ የሚያቀርቡትን ምግብ ጣፈጠ አልጣፈጠልኝ ብለው ሲጨነቁ እንዲከርሙ አይፈልግም " ከአሁን በፊትም ቢሆን ትልቁ የክረምት ዕረፍት ላይ ካልሆነ የገናወን ዕረፍት ቤቱ አሳልፎ አያውቅም ። እዚያው ዩኒቨርስቲ
ውስጥ የሚከርመው ። እናትየውም ይህንኑ ስለሚያውቁ ብዙም አላግደረደሩት "

ተሰናብተዋቸው ከውጭው በር እንደ ደረሱ። እናትየው እስክንድርን ወደ ኋላ አስቀሩትና አንድ ነገር እጁ ውስጥ
ሽጉጥ አደረጉለት።

“ ምንድነው እሱ ? ” አላቸው ፡ ምን እንደሆን ልቡ እያወቀ።

“ ያዘው ለዚያ ለምናምንቴ ለሱስህ ይሆንሃል አሉት ። የዐሥር ብር ኖት ነበር ።
እኔ ከሌላ ቦታ አላጣም እባክሽ ። ይሄ ለራስሽ ይሁንሽ ” አላቸው ።ለመግደርደር ያህል ሳይሆን ከልቡ ነበር ።
ምን ጊዜም ከእናቱ ገንዘብ ሲወስድ ልቡ ያዝናል ። እንደ ሲጋራ ሱሰኝነቱ አይቅበዘበዝም ።

ያዘው ግድ የለህም” ። እኔ አለኝ ። አንድ አረርባ ብር የመንደር ዕቁብ ነበረችኝ ፤እሷ ወጥታልኝ ነው ” አሉት ።

አመስግኖ ብሯን ኪሱ ከተተ ወዲያው ማርታ በሀሳቡ መጣችበት ግን በዐሥር ብር ምን ሊኮን ?

“ አቤል ፡ በል እንግዲህ ብቅ እያላችሁ ጠይቁኝ ። አሁን ዕረፍት ናችሁ ” አሉት እናትየዋ « አቤልን ቅር እንዳይለው

ከእናቱ ተለይተው ከሔዱ በኋላ እስክንድር ስለ ድህነትና የእናት አንጀት ተቃራኒ ሁኔታ እያብሰለሰለ ነበር
ድህነት እጅዋን ሊያስራት ይሞክራል ፤ እናት እጅን ለልጅዋ ለመዘርጋት ትፍጨረጨራለች ፡፡ ምኞቷና አድራጎቷ እኩል አይሆንም “ በፍቅር ወደ ልጅዋ ስትንጠራራ
ድህንት ጨምድዶ ይይዛታል ግን ያም ሆኖ እትረታም አትሽንፍም እንደ ምንም ተፍጨርጭራ የልጅዋን እጅ
ትነካለች።

“ አሁን ወዴት ነን ?” አለ አቤል " ትንሽ እንደተጓዙ

“ አንድ ቤት ጎራ ብለን ደርቆ የከረመ ጉሮሮአችንን እናርጥብ እንጂ ! ” አለ እስክንድር ።

አቤል ገንዘብ መቆጠብ የማይችለው የእስክንድር እጅ አስግርምት ሳቀ ። ከእናቱ የተቀበላትን ገንዘብ ለማጥፋት
እንደ ቸኮለ ገባው።

“ ይልቅ ቦታ ምረጥ የት ይሻለናል ? ” አለው እስክንድር

“ ወደ ሠፈራችን አቅራቢያ አይሻልም ? ” አለ አቤል ።መቼም ከዩኒቨርስቲው አካባቢ ርቆ መቆየት አይሆንለትምና።

“ ስድስት ኪሎ ደኅና ቡና ቤት የለማ ! ከጠጣን አይቅር ትንሽ ትርምስ ብጤ ያለበት ይሻለናል ። የጠርሙስ ካካታ ! ”

" አራት ኪሎ እንሒዳ! በዚያው ወደ ካምፓስ ለመግባት ይቀርበናል ”

በዚሁ ተስማምተው ወዶ አራት ኪሎ እመሩ ።

እዚያ ሲደርሱ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ገደማ ሆኖ ነበር እስክንድር ቻቻታ ያለበትን ቦታ መምረጥ ስለፈለገ ከቡና ቤት ቡና ቤት ሲዘዋወሩ በብዛት የሚያገጥማቸው የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበር ። ተማሪው ታስሮ እንደተፋታ ሆኖአል ንኮኒ ትተደግፎ የሚጠጣው የሴት አሳላፊዎችን ዳሌ የሚዳብሰው በቡድን ተቀምጦ እየጠባ የሚንቻቻው ተሜ ነው። ከወላጅ ከዘመድ የተላከ ከወዲያ ወዲህ ተጠራቅሞ ተቀብሮ የቆየ ገንዘብ መውጫው ዕለት ነዉ። በፈተና ማግሥት ሰክሮ መጥቶ ግቢው ውስጥ መደንፋት ፡ የማይጠጡ ተማሪዎችን መረበሽ ። ወይም ሰክሮ በየበረንዳው አድሮ
ጠዋት “ ጀብድ ” አርጎ ማውራት በዩኒቨርስቲ ውስጥ እየተለመደ የመጣ ይመስላል በተለይ ይህ ሁኔታ አይሎ
የሚታየው ከገጠር በወጡ ተማሪዎች ላይ ነው ። የአዲስ አበባው ተማሪ የቡና ቤቱን ትርምስ ከማዘውተር “ የኖርንበት ነው ” በማለት ዐይነት ቆጠብ ይላል ። ገንዘቡንም ቢሆን ከገጠረ እንደ መጡት አጠራቅሞ ማቆየት አይችልም ። አንዳንዱ እንደ ቱሪስት አስጐብኝ ገጠሬዎቹን ይዞ የከተማውን
ምርጥ ቡና ቤቶች በማስተዋወቅ የጋራ “ ጀብድ ” ይፈጽማል

እስክንድር አንድ ሞቅ ያለ ቡና ቤት አግኝተዉ ገቡ አንድ አንድ ቢራ ይዘው ቁጭ ከማለታቸው ፡ ሳምሶን ጉልቤው ዝንጥ ብሎ መጣ ሁሉም አራት ኪሎ መጠጣት የመረጡት ማታ ወደ መኝታ ቤታቸው ለመግባት እንዲቀርባቸው ይመስላል ።

ሳምሶን እስክንድርና አቤልን ሲያገኛቸው ደስ አለው ።በተለይ አቤልን መጋበዝ፤ ይፈልግ ነበር ።ጠዋት የለበሰውን
ቀያይሮ አፍላ ጉልበቱን ወጣጥሮ በሚያሳይ መሉ ጅንስ ሽክ ብሎአል ።

"ከመቼው ተሠየማችሁ ? አላቸው ፡ አጠግባቸው ለመቀመጥ መንበር እየሳበ

“ አንተም ደህና ጊዜ ደርሰሃል ፤ ቁጭ በል አለው እስክንድር።

ሳምሶንም ቢራ አዝዞ
👍1
ቀመጠ ።አቤል ገና በአንድ ቢራ መፍዘዝ ጀምሮአል ። ዝምታው እንግዳ ነገር ባይሆንም” ፥
ከዚያ በላይ ጥልቅ ተመስጦ ውስጥ እንደ ገባ ያስታውቅ ነበር ። በአዳራሹ ውስጥ የሚንቻቻውን ጠጪ ትክ ብሎ ይመለከታል ። በዐይኑ ይመልከት እንጂ ልቡ ከዚያ አልነበረም ።

እስክንድርና ሳምሶን ቢራ እስኪደክሙ ድረስ ምላሳቸው አልተፍታታም ። ሆኖም የአቤል ሁኔታ በግምት ስለ ገባቸው ከተመስጦው ሊያነቃቁት ሞክሩ ።

“ አቤል ፥ ተጫወት እንጂ ! ” አለወ• ሳምሶን " ፍቅር ባዘለ ድምፅ ። ሳምሶን ከማንም ጋር በሰላም እንኳ ቢነጋገር ፥ የድምፅ ቅላጼ ቁጣ ያለበት ይመስላል ። አቤል ላይ ሲሆን ምን እንደሚያሳሳው ለራሱም ይገርመዋል ።

“ እሺ ጨዋታ ሕምጣ በል ” አለ አቤል ስሜቱን ወደ እነሱ ለመሰብሰብ እየሞከረ

ድብርትን ለምን ይዘኸው አልመጣህም ? ” ሲል እስክንድር በድንገት ሳምሶንን ጠየቀው ። ጨዋታ ለመክፈትም
ከሳምሶን ጋር ለመለካከፍም ያቀረበው ጥያቄ ነበር ።

« እሺ አይለኝም እንጂ ይዤው እመጣ ነበር ” አለ ሳምሶን ከልቡ መኝታ ክፍል ውስጥ ቢለክፈውም ቅሉ፡ በሳምሶን ልብ ውስጥ የመረረ ተንኮል ወይም መጥፎ ስሜት አልነበረም።

« ሆሆይ ! ኧረ እሱ አንገቱን ቢያርዱትም ከሰው ጋር አይመጣም ” አለ አቤል ጸባዩን ስለሚያውቅ ።

ሌለ ድብርት ከሳምሶን የበለጠ የሚያውቁት ብዙ ጊዜ አብረውት የኖሩት አቤልና እስክንድር ናቸው ሦስት ዓመት
ያህል አንድ መኝታ ቤት ውስጥ ሲኖሩ ፥ አንዳችም ከድብርት ጋር የሚጋሩት ትውስታ የለም ። ከግቢው አይወጣም ።
ከወጣም ብቻውን ነው ። ከሰው ጋር ተቀራርቦ ተጫውቶ የሚጣጣም አይመስለውም ። የእሱ ሕይወት እንቅልፍን ትመስላለች ። የሕይወትነት መዓዛ የላትም ። በዚህ ምክንያት
እስክንድር ድብርትላ ከውስጡ ወይም ከውጭው አካሉ አንድ የተደበቀ የጎደለው ክፍል ይኖራል የሚል ጥርጣሬ አለ ።

« እኔ ማየት የምጓጓው እሱ የሚይዛትን የሴት ጓደኛ ነው አለ እስክንድር ።

አንዲት የሱ ቢጤ ድብርት አለችውኮ! አለ ሳምሶን ብዙ ቀን ግቢው ውስጥ አብረው አይቻቸዋለሁ።

"እኛ ግቢ ውስጥ ? ” አለ እስክንድር ተደንቆ

“ ስነግርህ ! ” አለው ሳምሶን “ እንዲያውም፤ድብርት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሥቅ ያየሁት ከእሷ ጋር ሆኖ ነው ። ወሬአቸው ሁሉ በክሹክታ ዐይነት ፡ አለ አይደል ብቻ በዐይንህ ብታያቸው ፍቅር መሆኑ ይገባሃል......

💥ይቀጥላል💥
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

#ፖሊስ_ጣቢያ

የጣቢያው የምርመራ ሹም ሻምበል ብሩክ በላይ በእለታዊ የስራ ጉዳዩ ላይ ተጠምዶ፤ አንገቱን እንዳቀረቀረ ነበር፡፡ የቢሮው በር በቀስታ ተቆርቁሮ በዝግታ ሲከፈት፤ ልብ አላለም ፡፡እሱ በያዘው
አስደናቂ የወንጀል ሪፖርት ተመስጦ በሃሳብ ጭልጥ ብሎ ሄዶ ነበር፡፡ደመ ነፍሱ፤ በሩን ከፍቶ የገባው ከስራ ባልደረቦቹ አንዱ እንደሆነ ነበር
የነገረው፡፡በሩን ቆርቁሮ የገባው እንግዳ ግን ፤ እንደወትሮው ከስራ ባልደረቦቹ
አንዱ አልነበረም፡፡ ባለጉዳይ ነው፡፡ እሱ እንደዚያ አንገቱን አቀርቅሮ የቀረበለትን ፋይል ሲመረምር፤ ከፊት ለፊቱ እጆቹን አጣምሮ የቆመው እንግዳ ደግሞ፤ በድንጋጤ ተውጦ፤ የሱን ሁኔታ ይመረምር ነበር፡፡ዘንካታ ቁመናው ልቡን እንደመሰጠው ፤ መልኩ የሞዛርት ትዝታን
አመጣበት፡፡በተለይ ተጠቅልሎ ሄዶ ከግንባሩ ላይ ሲደርስ ክንብል ያለው
ዞማ ጸጉሩ ልዩ ውበትን አጎናጽፎት ተመለከተ፡፡ ሻምበል ብሩክ የደንብ
ልብሱ አብሮት እንደተፈጠረ ሁሉ እጅግ የሚያምርበት ግርማ ሞገስ ያለው ወጣት መኮንን ነው፡፡ ያ የገባ እንግዳ እሱ ራሱ በሌላ እንግዳ በሆነ የስሜት ሉጋም ተሸምቅቆ ልቡ በሃይል እየመታ፤ ትንፋሹ ቁርጥ፤ ቁርጥ፤እያለበት “እህህ እህህ ...."በማለት ጉሮሮውን ሳለና ድምጽ
አሰማ :: ሻምበል ብሩክ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀና ያለው በዚያ የእንግዳው ቀስቃሽ ድምጽ ምክንያት ነበር፡፡እንደዋዛ ቀና ያለው አንገቱ ዳግም ላለማጎንበስ ምሎ የተገዘተ ይመስል በዚያው ቀረ፡፡ባየው ነገር ተደናግጦና አይኖቹን ማመን ተስኖት እስከሚያስታውቅበት ድረስ ልቡ ዘለላች፡፡እዚህ ጋ ጎደለሽ የማትባል፤ አምላክ እጁን ታጥቦ የሰራት የምታስብል፧
የውበት እመቤት እጆችዋን ወደ ኋላ አጣምራ አንገትዋን አቀርቅራ ከፊት ለፊቱ ቆማ ተመለከተ፡፡ ሻምበል ብሩክ ልጅቷን አተኩሮ በማየት ፈዝዞና “ምን ልርዳሽ?" ብሎ መጠየቅ ግዴታው መሆኑን ዘንግቶት፤ የመጣችበትን ምክንያት ሳይጠይቅ፤ ለረጅም ደቂቃዎች በመዘግየቱ፤ እፍረት ቢጤ ቢሰማውም፤ እሷም ከዚያ በፊት በማንኛውም ወንድ ላይ ተሰምቷት በማያውቅ እንግዳ ስሜት ተሸብባ መቅረቷን ሲያውቅ ኖሮ፤
የእፍረት ስሜቱ ትንሽ በቀነስለት ነበር፡፡ እሱ ምን እንደዚያ እንዳፈዘዘው
ውስጡን ሲጠይቅ፤ ትህትናም “ለምን ደነገጥኩ ግን? የሚል ጥያቄ ለራሷ አቅርባ ነበር፡፡ልቧ የደነገጠበትን የመኮንኑ ተክለ ቁመናና ውበት ወደዚያ ተወት አድርጋ እራሷን ብትዋሽም ከዚያ የበለጠው ዋነኛ ምክንያቷ ግን፤ እንደዚያ ከነ ማእረግ ልብሱ አምሮና ተውቦ ስታየው፣ልቧ በደስታ የሚሞላበትን፤ እጅግ በጣም የምትወደውን፤ የአባቷን ትክለ ቁመና ስላስታወሳት መሆኑ ሳይታወቃት አልቀረም፡፡በትንሽነቷ ጊዜ አባቷ ያንን የምትወድለትን የማእረግ ልብሱን ለብሶ ስታየው፤ ትንሷ ልቧ
በደስታ እየዘለለች ፤እሷም እንደ አባቷ እንዲያምርባት፣ በዚያ በትንሽ ሰውነቷ ላይ ያንን ትልቅ ኮት ትደነቅር ፧ ሱሪው ውስጥ ትገባና እየተጎተተች ስትዘንጥ ፤ አባቷ በሳቅ ሲፈነዳ “አያምርብኝም አባዬ
"ስትለው፡፡
"እንዴታ ትህትናዬ በጣም እንጂ! አንቺም ስታድጊ እንደኔ ወታደር ትሆኝና ፤ ዩኒፎርምሽን ለብሰሽ፤ እንደዚህ ታጥቀሽ ፤ እንዴት እንደሚያምርብሽ ይታየኛል፡፡" ሲላት ቶሎ አድጋ፤ ያንን ዩኒፎርም
ለብሳ የምር የምትዘንጥበትን ጊዜ ስትናፍቅ፤ እያደገች ስትመጣ ደግሞ
ያንን ከጎኑ ሻጥ የሚያደርገውን ሽጉጥ ትቀበለውና፤ እሷም ጎኗ ላይ ሻጥ አድርጋ ስትንጎራደድ፤ ልዩ ደስታን ይሰጣት ነበር፡፡አባቷ ያንን ሽጉጥ ጥይቶቹን ከውስጡ ያወጣና ስለ አተኳኮሱ፧ ስለ አጠቃቀሙ ፤
እያሳያት፤ ባዶውን ሲሰጣት ታነጣጥርበትና ምላጩን ሳብ
ስታደርገው ፤ እሱም የውሸት ወደ ኋላ ሲወድቅላት፤ ከዚያም ትመጣና
ከሞተበት እንዲነሳ ስትኮረኩረው፡፡ከዚያም በሳቅ እየተፍለቀለቀ እቅፍ
አድርጎ ወደ ላይ አንስቶ ሲስማት፤ ይህ ሁሉ የነበረው ሁኔታ ..እሱ ታስቧት
ይሆን? ወይንስ ወንድሟን እንዲፈታላት መልአክ አድርጋ በሀሳቧ የሳለችው ሰው ነው ? እሷም አልገባትም ::
በህይወት እያለ ይሰማት የነበረው ስሜት አፈር ከለበሰ ይሄውና አመታት መቆጠር ጀምረዋል፡፡ አሁን ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ያ ስሜት ፊት ለፊቷ በምታየው መኮንን ምክንያት በትዝታነቱ ተቀስቅሶባት
የገባችበትን ምክንያት እስከምትዘነጋው ድረስ አፈዘዛትና ቆማ ቀረች፡፡
ሻምበል ብሩክ የገባበት ሁኔታ ቀስ በቀስ አልፎለት፤ ስሜቱን መግዛት ሲጀምር።
ፊት ለፊቱ የቆመች ልጅ ምን እንደምትፈልግ መጠየቅ እንደሚገባው
ሲታሰበው፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊቱን ፈካ፤ ጥርሶቹን ብልጭ አደረጋቸው፡፡ እግዚኦ ! ጥርሶቹ እንዴት ነው የሚያምሩት? ስሜቷ እንደገና ተለዋወጠና ልቧ ትር ትር አለባት
አይኖቿ እንደዚያ ፍጥጥ ብለው ሲመለከቱት ሻምበልም ምን ልታዘዝ የኔ እመቤት?" የሱም ስሜት አብሯት እየተለዋወጠበት፡፡
"ወንድሜ ታስሮብኝ ነው የመጣሁት " ትንፋሽዋ እየተደነቃቀፈ፡፡
“እሺ ወንበሩ ላይ አረፍ በይና ንገሪኝ እስቲ በእጁ ወንበሩን እያመለከታት፡፡
ሻምበል ብሩክ ስሜቱ ለሁለት ተከፍሏል ፡አይኖቹ ከፊት ለፊቱ የሚታየውን ድንቅ ውበት በማድነቅ ስራቸውን ሲሰሩ ፤ ጆሮዎቹ ደግሞ የአቤቱታውን ምክንያት ለማዳመጥ ተከፍተዋል፡፡ ትህትናም አፏ
ስለአጋጠማት ችግር ሲያወራ፤ ልቧ ፊት ለፊቷ በተቀመጠው መኮንን ውብ ትክለ ቁመና ተማርኮ ከውስጥ እየሟሸሸባት ነበር፡፡
የእለት ሁኔታ መዝጋቢው ለእርስዎ እንዳመለክት ነግረውኝ ነው የመጣሁት”
“በምን ጉዳይ ነው የታሰረው? ማነው ስሙ? " አከታትሎ ጠየቃት፡፡
“አንዱአለም ድንበሩ ነው ስሙ"
"በዚያ በዲፕሎማት መኪና ላይ ስርቆሽ ከፈጸሙት ውስጥ ነው?"
“ኸረ እሱ ሌባ አይደለም" ፈርጠም ብላ፡፡
"ቆይኝ አንድ ጊዜ "አለና የቀረበለትን ሪፖርት ለማውጣት የጠረጴዛውን
መሳቢያ ከፈተ፡፡ በዚያ በስርቆት ወንጀል ላይ የተሳተፉት ሶስት ሰዎች ሲሆኑ የአንዱአለም ስም የለበትም፡፡
ልክ ነሽ፡፡ በዋናው ስርቆት ላይ አልነበረም
"ለምን ታሰረ ታዲያ?" በልቧ" ዋና ስርቆትና ሁለተኛ ስርቆት የሚባል
ነገር አለ እንዴ? እያለች ነበር፡፡
“ምን መሰለሽ? በስርቆቱ ላይ ባይኖርበትም ከሌቦቹ ጋራ በአንድ ላይ
ሆነው የተሰረቀውን ገንዘብ ሲያጠፉ ከተገኙ ሰዎች ጋር አብሮ ተገኝቶ ነው የተያዘው" በማለት ስለሁኔታው አስረዳት፡፡
ታዲያ አሁን አይለቀቅም?" በልምምጥ መልክ አይኖቿን በአይኖቹ ላይ
አንከራተተቻቸው፡፡
ያንተ ያለህ !እንዴት ነው አይኖቿ የሚያምሩት? አይኖቿን ለመሸሽ
አይኖቹ ወዲያና ወዲህ ተሯሯጡ :: የሚሄዱበት አጥተው ማምለጥ
ሲሳናቸው ደግሞ ተመልሰው መጡ፡፡ በአይኖቿ ባህር ውስጥ ሰጥመው በተዘረጋላቸው መረብ እንደ አሳ ሊዋጡ.......
“ስምሽ ማነው የኔ እመቤት?" ::
"ትህትና ድንበሩ" እየተቅለሰለሰች፡፡
“አንዱአለም ታላቅሽ ነው ወይስ ታናሽሽ?"
"ታናሼ ነው "
ሻምበል ብሩክ በስርቆቱ ወንጀል ላይ የተሳተፉት ዋነኞቹ ወንጀለኞች በእስር ቤት እንዲቆዩና፤ ሌሎቹ በዋስትና እንዲለቀቁ እሱና ሻለቃ ለሜሳ ቀደም ብለው ተወያይተው መመሪያ የሰጡበት ጉዳይ ነው፡፡የ ፶ አለቃ ውብሸት በመመሪያው መሰረት ሊያስተናግዳት ሲችል ለምን ወደ እሱ እንደላካት? ግራ ቢገባውም ልቡ አንድ ነገር ጠረጠረና በራሱ ግምት ትንሽ ፈገግ አለ፡፡
ይህቺን እንኮይ አንድ በላት ማለቱ ይሆን?"
"አንቺ ዋስ ሆነሽ ልታስፈቺው ነው የመጣሽው?"

“አዎን፡፡ ከፈቀዱልሽ ትችያለሽ ብለውኛል"
"ማነው እንደሱ ያለሽ?"
"መርማሪው"
ትህትና? ደግሞም አንቱ አትበይኝ አንተ እያልሽ አስረጂኝ”
"ስንት አመትሽ ነው
አስራ ሰባት "
ሻምበል ብሩክ ፈገግ አለና ...
"ዋስ ለመሆን እኮ እድሜሽ ቢያንስ አስራ ስምንት መሙላት አለበት::ስለዚህ እናትሽ ወይንም አባትሽ መጥተው ዋስ ሊሆኑት ይችላሉ፡፡
ከተናገራት በኋላ ሻምበል ብሩክ በፍጹም
እሺ?" አላት፡፡ ይህንን ከተናገራት በኋላ ሻምበል ብሩክ በፍፁም ያልጠበቀው ሁኔታ ገጠመው ፡፡ አይኖቿ በአንድ ጊዜ በእንባ ተሞልተው አይኖቿ ውስጥ
ይንከባለሉ ጀመር፡፡ከእነዚያ ለማየት እንኳ ከሚያሳሱ እኒያን የመሰሉ ውብ አይኖች
እምባዋ እንደጉድ ፈሰሰ፡፡ ሻምበል
በእንባ ሲሟሽሹ ዝም ብሎ ማየት ተስኖት ተርበተበተ፡፡
“ምን ሆነሻል ትህትና?ወንድምሽ እንደሆነ ዛሬውኑ ይፈታልሻል፡፡ ምን ሆነሽ ነው እንደዚህ የምትሆኚው?" ሲል በድንጋጤ ተውጦ ጠየቃት፡፡
"አባት የለኝም :: እናቴም ከአልጋ ላይ መነሳት የማትችል በሽተኛ ነች፡፡
እነሱ ዋስ ሊሆኑት አይችሉም፡፡ የኔ እድሜ አስራ ስምንት ሊሞላው አምስት ወር ብቻ ነው የቀረው፡፡ እባክዎት እኔ ዋስ ልሁነውና ይፈታ?"
ተለማመጠችው፡፡ ሻምበል ብሩክ ይህንን አሳዛኝ ታሪክ ከዚህች ቆንጆ ትንሽ ልጅ አንደበት ሲሰማ ከልቡ አዘነላት፡፡ ያንን ውበት ያለወላጅ እንክብካቤ በፍጹም ያልጠበቀው ስለነበረ በፈጸመው ስህተት
ተጸጸተ፡፡ትህትና ከልቡ እንዳዘነላት ሲገባት ታሪኳን በግልፅ ነገረችው፡፡ አባቷ ወታደር የነበረ መሆኑን፤ በምስራቅ ጦር ግንባር
መውደቁን ፤ ከዚያም እናቷ በበሽታ ምክንያት አልጋ ላይ መዋልዋንና
የቤተሰብ ሃላፊነት ሸክሙ እሷ ላይ የወደቀ መሆኑን ፤አንድም ሳታስቀር
ዘረዘረችለት፡፡ ያንን በቀላሉ ለማንም የማታወራውን ሚስጥሯን አንዱ አለምን ያስፈታልኛል በሚል እምነት ብቻ ሳይሆን፤ ለእራሷም እንግዳ በሆነ ስሜት ምንም ሳትደብቅ አወጋችው በይበልጥ የተደፋፈረችው ደግሞ ሻምበል ታሪኩን ለመስማት ያሳየውን ፈቃደኝነት በመጠቀም ጭምር ነበር። ወደ ቢሮው ሌላ ባለጉዳይ እንዳይገባ ለስራ ባልደረቦቹ ትእዛዝ በመስጠት በዝርዝር እንድታስረዳው ስላደፋፈራት ተረጋግታ፤
የወንድሟ ያክል ምንም ሳትፈራው! በዝርዝር ነገረችው፡፡ ሻምበል የምትናገረውን በጸጥታ ካዳመጠ በኋላ...
“አይዞሽ ትህትና ለወንድምሽ እኔ ራሴ ዋስ እሆነዋለሁ። አታስቢ፡፡በተረፈው ግን ሰፋ ያለ ጊዜ ወስድን እንወያያለን፡፡ አይዞሽ ! እሺ?"አጽናናት፡፡ ደስ አላት ፡፡ሄዳ ብትስመው ምንኛ በወደደች? ገና እንዳየችው ልቧ ያለምክንያት እንዳልደነገጠባት አወቀች፡፡ ምስጋናዋን ከመቀመጫዋ ብድግ በማለት በአንገቷ ለመግለጽ ስትሞክር...
"ግድየለም ቁጭ በይ" አለና ትከሻዋን ያዝ አድርጐ ወደ ወንበሩ መለሳት፡፡ ከዚያም መርማሪ ፖሊሱን ጠርቶ፤ በሱ ዋስትና አንዱአለም እንዲለቀቅ አደረገ፡፡ ከዚያም የስልክ ቁጥር እንዳላት ቢጠይቃት
ስልክ ያለው ጎረቤት እንኳ እንደሌላት ነገረችውና ተሳስቀው ፤ የራሱን የቢሮውንና የመኖሪያ ቤቱን ስልክ ቁጥሮች ጽፎ እንድትደውልለት"
አደራ" ብሎ ከወንድሟ ጋር አያይዞ አሰናበታቸው፡፡ ትህትናም በአንድ
ድንጋይ ሁለት ወፍ እየገደለች መሆንዋንና ያንን እንደገባች የፈዘዘችለትን ሰው እንደዚህ በአጭሩ ዘመድ ማድረግ በመቻሏ እየተገረመች ሳለ፤ በተጨማሪ ስልኩን ሊሰጣት ፈቃደኛ መሆኑን ስታረጋግጥ ደግሞ የበለጠ ልቧ በደስታ ዘለለች፡፡ ሆኖም ልቧ ከውሰጥ መጨፈሯ እንዳይታወቅባት ጥንቃቄ ሳይጎድላት ሻምበል የስልክ ቁጥሩን ጽፎበት የሰጣትን ወረቀት ቀስ ብላ ተቀብላ ወደ ጡት ማስያዣዋ ከላከችው በኋላ ምስጋናዋን ያለገደብ አቅርባ፤ ወንድሟን ይዛና፤ በፍቅር ተይዛ፤ ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ አንዱ አለም ከዚያ ሲኦል ከሚመስል እስር ቤት ባስፈታችው እህቱ ተመካባት፡፡ ከዚያ ባለፈ ደግሞ ሻምበል
ብሩክ የከፈለለትን ዋጋ በዝርዘር ከትህትና ሲሰማ፤ ሻምበል ብሩክን
አከበረው፡፡ ወደደው፡፡ ትህትና በለስ ቀንቷት ወንድሟን አስፈትታ መመለሷ በእጅጉ ቢያስደስታትም፤ ከሻምበል ብሩክ ጋር እንደዚህ በአጭሩ መለያየቷ ግን ቅር አሰኛት፡፡"ምንድነው እንደዚያ የሚያደርገኝ?'ብላ እራሷን ስትጠይቅ፡፡

“እንጃልሽ ! ይላታል የገዛ ስሜቷ፡፡ የዚያን አይነት ስሜት ከዚያ ቀን በፊት በፍጹም ተሰምቷት አያውቅም ነበርና ግራ ተጋባች፡፡ ያም ሆነ ይህ ለተቃራኒ ጾታ
ፍቅር ስሜቷ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሸነፈ መሆኑ ግን ትንሽ በትንሹ ሳይገለጥላት አልቀረም፡፡አሳሳቁ ፤ አለባበሱ ግርማ
ሞገሱ፤ ትህትናው፤ የጸጉሩ ውበት፤ በተለይ ያቺ ከፊቱ ላይ ክንብል
ያለችው ዞማ ጠጉሩ፤ በዚህ ሁሉ ላይ ደግሞ ወንድሟን ከእስር ቤት ያስፈታላት ባለውለታዋ መሆኑ፤ ይሄ ሁሉ ነገሩ በዛባትና፤ ሻምበል ብሩክን አከበረችው፡፡ አፈቀረችው፡፡ በዚህ መሃል አንድ ሃሳብ መጣባት
"ሚስት ትኖረው ይሆን?" የሚል፡፡ ወየው ጉዴ፡፡ የቀለበት ጣቱን አላየሁትም እኮ፡፡ ለምን ጣቱን ሳላይ ቀረሁ ?ምን አይነቷነኝ ግን? በፍጹም አይኖረውም፡፡ ገና ወጣት ነው :: ከዚህ በፊትስ አያገባም ከራሷ ህሊና ጋር ተሟገተች :: የጣት ቀለበቱን ባለማየቷ ተናደደች፡፡መናደድ ብቻም ሳይሆን ሄደሽ ተመልሰሽ አረጋግጭና
እወቂው የሚል ስሜትም ገፋፍቷት ነበር፡፡ እንደምንም ብላ ቻለችው እንጂ

ከአንድም ሁለት ጊዜ ለመገናኘት ይዘውት የነበረውን ፕሮግራም እየሰረዘች ፤ የማትፈልገው መሆኑን ለመግለጽ ጥረት ብታደርግም፤ዶክተር ባይከዳኝ ፍቅሩ በገፍ፤ ስሜቱ በእጥፍ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ ሊሄድ አልቻለም፡፡ ሁሌም የዚያ የደብረዘይቱ ጉዞ ስኬታማነት፣ በዚያ
የመኝታ ክፍል ውስጥ የተሰማው የእርካታ ስሜት፤ እየታወሰው፣ እንዲያ በወሲብ ግለት ነዶ ራቁት ሰውነቷን በጉጉት ሲመለከታት የነበረው ሁኔታ፤ ያ የልጅነት ውብ ገላዋ ፣ያ የማይጠገብ ጣፋጭ
መአዛዋ፤ እነዚያ በከንፈር ውስጥ ቀልጠው የሚጠፉ የሚመስሉት
እንጆሪ ከንፈሮቿ ፤ ከዚያም ሁሉ በላይ ደግሞ ማንነቱን የሚፈትሽበት ድንግልናዋ፤ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው፤ ተባዝተው፤ በሀሳቡ እየተግተለተሉ ይመጡበትና፤ እሷን ለማግኘት በሲቃ ስሜት ያወራጩታል፡፡

ትህትና በተላይ ሻምበል ብሩክን ካየችውና ልቧ ከደነገጠላት በኋላ
ዶክተር ባይከዳኝ በጣም ነበር ያስጠላት ቢሆንም ግን የዚያ የእናቷ ጉዳይ በመካከላቸው አላና፤ በአስቸኳይ ልትገላገለው አልቻለችም፡፡ሻምበል
ብሩክን ካወቀችው ዛሬ አምስተኛ ቀኑ ነው፡፡ አምስት ቀን ሙሉ ስልከ አልደወለችለትም፡፡ ቶሎ ብትደውልለት የሚንቃት፤ የሚጠላት፤ እየመሰላት ናፍቆቷን በልቧ አምቃ ቆየች፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ አዜብም የምትመክራት ትንሽ ኮራ እንድትል ነው፡፡ ወንድ ልጅ ፊት ከሰጡት
ጥጋቡ ኣይቻልም እያለች፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ ለዛሬ ራት በራሱ መኖሪያ ቤት ነበር፡፡ ዶክተር ፍጹም ቅዠት ነው ተብሎ ሊታመን በማይችል ሁኔታ በህልሙ ተለይቷት ባያውቅም፤ ከደብረ ዘይት ሽርሸር በኋላ በአካል ያገኛት ገና
አሁን ነው፡፡
ትህትና ሥራ እንደጀመረች እናቷን የምትጠብቅላትና፤ እንጀራ የምትጋግር ልጅ እግር ሠራተኛ ከዚያችው ከምታገኘው ደመወዝ ላይ እንደአቅሚቲ ስለቀጠረች፤ ወጣ ገባ፤ ለማለት ዕድል አግኝታለች፡፡......


ይቀጥላል

በየቀኑ ሳይቆራረጥ እንዲደርሳችሁ የበዛ Like 👍 እንዲሁም የበዛ #Share እፈልጋለው።

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...“ እንዲያው ምን ምን ይላት ይሆን?እኔ እሱ ለሴት ልጅ የሚያወራውን ነገር ለመስማት እጓጓለሁ " ግን አንተ ባል
ከው ዐይነት አገጣጥሞኝ አያውቅም ። ”

“አጅሬ ምኑ ሞኝ ነው ላንተ የሚታየው ?!እሷን ሲያገኛት ቦታው ጭር የሚልበትን ጊዜ ጠብቆ ነው ።

“ ወይ ጉድ ! መቼም ፍቅር የማያሸንፈው ልብ የለም ”አለ እስክንድር በልቡ ። ስለ ድብርት የበለጠ ለማወቅ ጓጉቶ ነበር ። ሆኖም ጨዋታው በተዘዋዋሪም ቢሆን አንዳንድ የአቤልን ድርጊቶች እንደሚንካ ስለ ገመተ አርዕስቱን ለመለወጥ ፈለገ ሳምሶንም ይህንን ሁሉ ልብ ሳይል እንደ መጣለት ነበር የሚጫወተው ። እስክንድር ግን የአቤል ስሜት
እየተለዋወጠ እንደ መጣ በሥርቆት ከገጽታው ላይ አንብቦአል ድብርት የሴት ጓደኛውን ለማግኘት ጭር ያለ ጊዜ
መጠበቁ የአቤልን ስሜት ክፉኛ ነክቶታል እሱም ትዕግሥትን ለማየት የሚጠቀምባቸውን ጊዜያቶች ያውቃል ።

ስማኝ ላምሶን ! ግን ለምንድነው አንተ ብዙ ጊዜ ድብርትን የምትለክፈው ? ” በማለት እስክንድር አርዕስቱን አሸጋገረው
“ ለተንኮል አይደለም ። ግን የሚነፋነፍ ሰው መልከፍ እንዲሁ ደስ ይለኛል ። እንዴት ብዬ ላስረዳህ ? ለምሳሌ
ቀርቦ መናከስ የማይደፍር ውሻ በሩቁ እያፈገፈገ ሲጮህብህ እልሁን ለማስጨራረስ በዱላ እንደምትተናኮለው ዐይነት ነው ። ብቻ እንዲሁ ስለክፈው ደስ ይለኛል እንጂ ለድብርት መጥፎ አመለካከት የለኝም ለየት ያለ ተፈጥሮ ስላለው ያስገርመኛል ” አለና አሳላፊዋን ለመጥራት ጠረጴዛውን ጠበጠበ።

“ አቤት ! ምን ልታዘዝ? ” እያለች አንገቷ በንቅሳት የተዥጎረጎረ ሴት ከፊታቸው መጥታ ቆመች ።

“ ቢራ ድገሚን ሦስት ቢራ ! ” አላት ሳምሶን በዚያው ቁጡ ድምፁ

“ እኔ ይብቃኝ ! ” አለ አቤል "

“ አትቀልድ እባክህ ። አንቺ እኔ የማዝሽን አምጪ!” አለና ሳምሶን አሳላፊዋ ላይ ጮኸባት ።

"ጥርስሽን እንዳያወልቅ ” አለና እስክንድር በልቡ ሳቀ ።

“ እኔኮ ያንተም ተፈጥሮ ያስገርመኛል ” አለው እስክንድር ሳምሶንን
“ እንዴት ?”
“ አሁን ሚስተር ሆርስ ከአቤል ጋር ከታረቀ በኋላ ለምን ትዝትበታለህ ?”

“ አዎ ! የማታውቀው ነገር አለ እስክንድር እየዛትክ የምትተው ከሆነ ዛቻው ሲደጋገም ሰው ይንቅሃል ።ወንድ ከሆንክ አንዴ ማቅመስ አለብህ ። እንዲያውም አንተን ብዬ ነው እንጂ እሱን ልጅ አንድቀን ብሰብረው ደስይለኛል ። ከፈለገ የገዛ ጥርሱን ከመሬት አሰለቅመዋለሁ ።

“ጡንቻህን ፈትነኝ እያለ ያስቸግሃል መሰለኝ” አለና እስክንድር እየሣቀ ከእሱ መልስ ሳይጠብቅ ፡ “ ብቻ ያለንበትንም ጊዜ አትዘንጋ : ሀያኛው ክፍለ ዘመን ላይ ነን ” አለው ።

“ እና ? ” የብሽቀት ድምፅ ነበር ።

“ እናማ ስፖርተኝነትህን እወድልሃለሁ ። ይህችን በጡንቻ መመካትህን ግን ...

“ እንግዲህ አትልከፈኝ ፡ ልጠጣበት ! ” አለና ቢራውን ተጎነጨ

ሳምሶን ሌላ ሰው እንዲህ ቢናገረውም ካልተደባደበ በዋዛ እይላቀቁም ነበር ። ለእስክንድር ያለው ክብር ግን ብዙ ዓመት ከቆየ የልጅነት የአስተሳሰብ ተጽዕኖ የመጣ ነው ። የሠፈር ልጆች እንደ መሆናቸው መጠን ሳምሶን ስለ እስክንድር ብዙ ነገር ያውቃል ። እሱ ገና ልጅነቱን ሳይጨርስ እስክንድር በሠፈራቸው ውስጥ ስመ ጥር ጎረምሳ
ነበር ። እንዲህ እንዳሁኑ ከመስከኑ በፊት እናቱ በእስክንድር ያላዩት አበሳ የለም ። ከለውጡ በፊት ጸብ አሽትቶ ነበር
የሚፈልገው ። እስር ቤትን ቤቱ አድርጎት ነበር ። አንዴ ጸበኞቹ በቡድን ሆነው ከደበደቡት በኋላ ሆዱ ላይ በጩቤ
ወግተውት ለጥቂት ነው ከምት የተረፈው ከለውጡ በኋላ ደግሞ በወቅቱ በተፈጠሩት የፖለቲካ ድርጅቶች ሳቢያ
ያልቀመሰው፡ አበሳ የለም ። ችኩል ነበር ። ሰው አይገራውም ፣ ያየሁት አይለፈኝ የሚል ስሜት ያሸንፈዋል ።
የጀብደኝነት ስሜት ያጠቃዋል ። ትኩስ ኃያልነቱ፡ መንፈሱን ያቅበጠብጠዋል ። አሁን ግን በዕድሜም በብስለትም ሰክኖ
እንኳን ለራሰ ሌሎችንም ይመክራል ። ከአፍላነት ቅብጥብጥነት ጊዜው ይዞ የመጣውና አሁንም ያልተወው ነገር ቢኖር
የሲጋራ ሱስ ብቻ ነው። ይህ ሁሉ ሁኔታ በሳምሶን ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም። በፀጉሩ ኪንኪነት እየለከፈው ከእስክንድር ጋር መቃለድ የጀመረው እንኳ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው።

አቤል እባክህ ተጫወት ይሄንን ተወው
አለ ሳምሶን እስክንድርን በመንቀፍ አይነት

“ እየሰማኋችሁ “ኮ ነው ? ” አለ አቤል በጨዋታቸው ውስጥ የቆየ ለመምሰል ጥርሱን በውሸት ብልጭ አደረገ።

ሐሳቡ በከፌል ወደ እነ ትእግስት ዘምቶ ነበረ። ፈተና ከጨረሰች በኋሳ ወዴት ትሔድ ይሆን ? አርፎ መተኛት ወይስ
ዙረት መውጣት ? እያለ ሲያሰላስል ነው የቆየው።ሁለተኛውን ጠርሙስ ቢራ ግማሽ አድርሶታል ። ከቻቻታው ጋር
ቢራው ሞቅ አድርጎት ውስጥ ውስጡን እየሰከረ መምጣቱ ይሰማው ነበር። የመጠጣት ልምድ ስለሌለው ጭንቅላቱ ቶሎ መረታት ጀምሯል ። ድፍረትም ተሰማው ማንንም ያለመፍራት ሃይነት ስሜት !

“ ለምን ሙዚቃውን አይቀይሩልንም ? ” ሲል ድምፁን አሰማ ። የእንግሊዝኛ ሙዚቃ ነበር አዳራሹን የሚነቀንቀው፤“ ማስቀየር እንችላለን ። የማን ክር ይደረግ ? ” አሉ እስክንድርና ሳምሶን በአንድ ድምፅ አቤል ከዝምታ ወደ
ተሳትፎ መምጣቱ ደስ አሰኝቶአቸው ነበር

•የ... የመልካሙ ተበጀ ክር ቢሆን
ይሻላል” አለ አቤል በተሰባበረ ድምፅ

እስክንድርም ሆነ ሳምሶን በፍጥነት የጠረጠሩት ነገር አልነበረም ። አሳላፊዋን ጠርተው ክሩ እንዲቀየር አዘዟዋት።

ባለቤትየዋ እሷ የመረጠችው ዘፈን ካልሆን እሺ አትልም ግን ልሞክርላችሁ ” አለች አሳላፊዋ ።

“ ንገሪያት ! ለምን እሺ አትልም ? ” አለና ሳምሶን አፈጠጠበት እሷ ዘፈኑን ልታዝዝ ስትሔድ አቤል ቀድሞ በልቡ
ያንጐራጉር ጀመር።

አረ መላ ምቱ ወዳጅ ዘመዶቼ
ዐይናፋር ሆኛለሁ ፡ ዐይናፋር አይቼ
ሰሳምታ አልሰጠኋት አላነጋገርኳት
በዐይን ብቻ እያየሁ አንድ ዓመት ወደድኳት።

ልቡ ይህን እያዜመ፥ ጆሮው የሚሰማው ግን ሌላ ሙዚቃ ነበር ቢጠብቅ ፥ ቢጠብቅ የተለወጠ ነገር የለም ጥቂት
ቆይታ አሳላፊዋ ተመልሳ መጣች።

የመልካሙ ክር የለም ብላለች ባለቤትየዋ ! ”

አቤል በሽቆ “ ገደል ግቢ በያት ! ” ከማለቱ ዐይኑ እንባ አቀረረ ። የሰው ስሜት የማይጠበቅበት ዓለም ! ባለቡና ቤቶች ፍቅረኛውን የሚያስታውስበትን ዘፈን አይከፍቱለትም "መምህራን ትምህርት ምን ያህል እንዳስጠላው አይረዱለትም ። ወላጆቹ ልጃቸው ከድህነት ቀንበር እንዲያላቅቃቸው
ይመኛሉ እንጂ እሱ ያለበትን ችግር አያውቁለትም ። ጓደኞቹ ብቸኝነቱን አይፈቅዱለትም ።

“ እሷ ከሙዚቃዋ ጋር ገደል ትግባ ! አንቺ ቢራ ድግሚን ” አላት ሳምሶን በሽቆ ።

“ኧረ ይብቃን ! ሰዓቱም መሽቷል የካምፓስ ፖሊሶች አያስገቡንም ” አለ እንክንርድ ኪሱን እየዳበሰ ።

አምጪልን እባክሽ እንጠጣው ዛሬ ካምፓስ ማን ይገባል? ” አለ ሳምሶን በሞቅታ ስሜት ።

“በይ እንግዲያው አንቺንም እንጋብዝሽ የምትጠጪውን ነገር ይዘሽ ነይ ” አላትና እስክንድር ፡ ወደ ሳምሶን ዘወር ብሎ ፥ “ ከጠጣን አይቀር መሐላችን አንዲት አንስታይ ስትኖር ይሻላል” አለው ። ከሳምሶን ሁኔታ ገንዘብ እንደያዘ
ገምቶ ነበር "

እቤል ምንም አስተያየት አልሰጠም ። የያዘውን ቢራም አልጨረሰም ። ከዚያ በላይ መጠጣት አልፈለገም ። ሆኖም
አልተከላከለም ። ሕይወትን የመሰልቸት ዐይነት ነበር የሚሰማው ። ለምንም ነገር ያለመጨነቅ ። ስካር ማለት ይሄ ይሆን እንዴ?
👍1
ስለ መጠጣት ስላለመጠጣት ፥ ካምፓስ ስለ መግባት ስላለመግባቱ አቤል ደንታ የለውም ። “ እነሱ ይከራከሩበት

ጠርሙስ ውስጥ የቀረውን ቢራ አንሥቶ ጅው አደረገው ጉሮሮው ላይ እየተናነቀው ለምን በግድ እንደሚጠጣ መመራመር አልፈለገም ። ብዥ አለበት ቻቻታ ! ትርምስ ብዥዥ ዥ... ራስን የሚረሱበት ዓለም ።

ድፍረት ድፍረት አለው ። እልህ ተናነቀን ማንን እንደሚደፍር ፥ በማን ላይ እልሁን እንደሚወጣ ግን አያውቅም።
“ ስማ እስክንድር ! ” አለው ሣቅ እየተናነቀው ወደ እስክንድር ፊት ተጠግቶ “ እኔ ትዕግሥትን እወዳታለሁ ።
እሷ ግን አይገባትም ። እ -አይገባትም ። ”

እስክንድርና ሳምሶን ተደናገጡ ድንገተኛ አርዕስት ሆነባቸው። አቤል ግን አርዕስቱን በልቡ ከጀመረው ቆይቷል
ያም ሲሆን ጉዳዩም ሁለቱም አላጡትም

"ከወደድካት ይገባታል እንጂ አቤል ለምን አይገባትም ችግሩ ሁለታችሁም ተቀራርባችሁ ያለመነጋገራችሁ ነው" አለ እስክንድር ፈራ ተባ በሚል ድምፅ።

ከአሁን በፊት በግልጽ ተነጋግረውበት የሚያውቁት ጉዳይ መነሣቱ በእስክንድር ላይ ሁለት ስሜት አሳደረበት።

በአንድ በኩል እውነቷን ከአቤል ለመስማት ሲጓጓ ስለ ከረመ ደስ ብሎታል በሌላ በኩል ደግሞ አቤል ምስጢሬ
ብሎ የያዘዉን ነገር በስካሩ ጊዜ ማውጣቱ ሲውል ሲያድር ትዝብት ላይ የሚጥለው መሰለው ። በመጨረሻ ግን ነገሩን እሱ ጀምረው እንጂ እኔ አልጀመርኩት ” ብሎ ተጽናና ።

የምትወደኝ ከሆነ ለምን ዝም ትለኛለች ? አየህ እስክንድር እኔ'ኮ ትዕግሥትን ሳላያት ውዬ ማደር አልችልም ። ምርኮኛዋ ነኝ ። ምርኮኛዋ ስለሆንኩ እፈራታለሁ ።
ላናግራት አልደፍርም እሷ ለምን ዝም ትለኛለች? የራሱ ጉዳይ ብላ ኢይደለም ? ! ”

ሲናገር እንባውን ወደ ውስጥ ለመግታት እየታገለ ነበር ።እከክንድርና ሳምሶንም ልባቸው አዘነ ።

ትዕግሥትም ለእንተ የግዴለሽነት ስሜት ያላት አይመስለኝም ።” አለው እስክንድር ፡ “ ተገናኝታችሁ መነጋገር ስላልቻላችሁ ነው እንጂ ፡ እኔ እንደሚገባኝ እሷም
ያንተኑ ያህል ትወድሃለች ። ”

“ እሺ ይሁን ። እሷ ምናልባት ትወደኝ ይሆናል ። ነገር ግን በመሃላችን ምቀኞች አሉ ። ጓደኞቿ ናቸው የሚመክሯት ። በተለይ ያቺ ማርታ ! ”

“ እሷም ለአንተ መጥፎ ስሜት የላትም ፡፡ አቤል ሙት እልሃለሁ ። እኔ በቅርብ ዐውቃታለሁ ” አለው እስክንድር ።

"ዋናው ችግር ምንድን ነው? ለምን እኛ አንረዳውም ? » አለ ሳምሶን ከልቡ ተቆርቁሮ።

«ለመረዳት ቦዘንን ብለህ ነው ችግሩ የቀላል ከባድ ሆነና ነው እንጂ!” አለው እክንድር ቀስ ብሎ ።

“ ምን መሰላችሁ እኔ በእሷ ያልሆንኩት ነገር የለም ።እ....ብቻ -- እኔ ብቻ ነኝ ስለ ራሴ የማውቀው ” እያለ ከተቀመጠበት
ተነሣ ። ወንበሩን ሲለቅ ትንሽ ተንገዳገደ።

“ ወዴት ትሔድ ” አለው እስክንድር
"ወዶ ሽንት ቤት"በየት በኩል ነው ?

እስክንድር በምልክት አሳየው ። በዚያ ሁሉ ጠጪ መሐል ሁለት እጁን እኪሱ አድርጎ ፡ ሁሉንም በንቀት ዐይን እየተመለከተ ነበር ወደ ሽንት ቤቱ የሔደው ።.......

💥ይቀጥላል💥
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

.....ቀኑ እሁድ ነው፡፡ ለዛሬው ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ለሚኖራት ግንኙነት
በቂ ዝግጅት አድርጋለች፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ እንደዚያን ዕለት አምሮና ተውቦ ፒጃማውን ለብሶ ከሳሎኑ ሶፋ ወንበር ላይ ጋደም ብሎ እየጠበቃት ነበር፡፡

ለምን እንደሆነ እሱ እራሱ አንዳንዴ ግራ ቢገባውም፤ ልቡ እንደዚያ በፍቅሯ እየተቃጠለ፣ በስሜት እየነደደላት፤ እሷ ፊት ግን ኮራ ለማለት ይሞክራል፡፡

በእርግጥ ይሄ ኮራ ማለቱ ጠቀመው እንጂ አልጎዳውም፡፡ ሴት ልጅ
ጠንካራ ሰውነት ብቻ ሳይሆን፤ ደንዳና - የወንድ ልጅ ልብ እንደሚያሸንፋት ሳይንሱን ሳያገኘው አልቀረም፡፡

እንደዚያ ኮራ፤ ጀነን፤ ሲል የዶክተርነት ሙያው ፈጣሪ አከል አምልኮን በልቧ ያሳድርባትና፤ እያከበረችው፤ እሱ ያዘዛትን እንድትፈጽም ያስገድዳታል፡፡

የዛሬዋ ትህትና ልክ የዚያን ዕለት ስታቃዠው የዋለችው ትህትና ሆና
መጣችለት፡፡ የለበሰችው አጭር ቀሚስ ነው፡፡ ከላይ ጣል ያደረገችው ተካፋች ሸሚዝና አጠር ሳሳ ያለ ነጭ ኮት ነበር፡፡ እድሜ ለአዜብ ወጣ የምትልባቸውን ልብሶች የምትዋሰው ከሷ ነው፡፡ በአጠቃላይ እንደ ደብረ ዘይቱ ጉዞ የመስክ ሠራተኛ መስላ ሳይሆን የወንድ ጓደኛዋን ስሜት ለመማረክ የተዘጋጀች አፍቃሪ መስላለች፡፡

ዶክተር ባይከዳኝ በወሲብ ላይ ምን ያክል ደካማ እንደሆነ ተገንዝባዋለች፡፡የዛሬ ሁኔታዋም አቅሙን ለመፈተን፤ ጠንካራ
ሆኖ ከተገኘች የሚቀጥለውን ውሳኔ ለመወሰን፤ እንደዚያ እንደ ደብረዘይቱ የሚልፈሰፈስ ከሆነ ደግሞ እንዲህ እንደዋዛ ለሚያልፍ ነገር ላለመቀያየምና ችግር ውስጥ ከመግባት ይልቅ እሱን ደስ እያሰኘች ለመቆየት ወስና ነበር፡፡
ለዚህ ሁሉ እንዲረዳት ደግሞ አዜብ የሚያስፈልጋትን ቲዎሪ አስጠንታታለች፡፡

በዚህ ዓይነቱ ግንኙነት ወቅት መፀነስ ሊኖር እንደሚችል አውቃ እንድትጠንቀቅ፤ የመከላከያ መድኃኒቱን አምጥታላታለች። ትህትና አዲሱን ሥራዋን ከጀመረች ዛሬ አምስተኛ ቀኗ ነው፡፡ መንፈሷም አካሏም ነቃ ያለው እንደሰው ሥራ በመያዟ ፤ እቤት ከመዋል ይልቅ በሥራ ተጠምዳ መዋል በመጀመሯ ሳይሆን አይቀርም፡፡
ዛሬም ከሠራተኛዋ ከእታፈራሁ ጋር እየተረዳዳች እናቷን የምትጠብቅላት አዜብ ስትሆን፤ ቶሎ ካልተመለሰች ወደ ቤቷ እንድትሄድ ተስማምተው ነው የተለያዩት፡፡
የቤቱ በር ተቆረቆረ፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ ሊከፍት ወጣ፡፡ በጉጉት ተውጦ
ይጠባበቃት ስለነበረ በደስታ ስሜት ተውጦ ቀና አለና ከንፈሯን ሳማት፡፡
እሷም በናፍቆት ስትጨነቅ እንደቆየች ሁሉ ግጥም አድርጋ ከንፈሩን ሳመችለት፡፡
እንደዚህ አድርጋ ነፍሱን ታስደስትለት እንጂ! ያለበለዚያማ.. ከዚያም እጅ ለእጅ እንደተያያዙ፤ ወደ ውስጥ ዘለቁ፡፡ በቤት ያለችው የቤት ሠራተኛው የትነበርሽ ብቻ ነች፡፡ የዛሬ እንግዳውን የቤት ሠራተኛው አይታ እንድታደንቅለት በዚያውም እሱንም በምርጫው እንድታደንቀው ስለቸኮለ ጠራት፡፡

“ተዋወቂያት ትህትና ትባላለች” በእጁ ወደ ትህትና እያመለከተ፡፡ የቤት ሠራተኛዋ በሁለት እጆችዋ እየጨበጠቻት ስሟን ነገረቻት፡፡ በዕውነቱ በልጅቷ ውበት ተደነቃ..
“ይህችን አንድ ፍሬ ቆንጆ ልጅ ከየት አገኛት?” ብላ እራሷን ጠየቀች።

“ትህትና አንድ ሰዓት ያህል ዘግይተሽ በረሀብ እንደቀጣሽኝ ታውቂያለሽ?” አለና ሰዓቱን ተመለከተ :: በእርግጥም በስድስት ሰዓት ከቀጠረችው በኋላ የመጣችው ሰባት ሰዓት ላይ ነበር፡፡
እስካሁን አልበላህም ዶክተር?” ጠየቀችው በመገረም፡፡የምበላ ይመስልሻል ? ”
“ ምናለበት ? ”
መገመትም የለብሽ ” አለና ከሷ ውጭ እህል እንደማይዋጥለት ሰው ሆነ፡፡

ወዲያውኑ ሠራተኛዋ የእጅ ውሀ አምጥታ ካስታጠበቻቸው በኋላ የተዘጋጀው ምሣ ቀረበ፡፡ በእውነቱ ብፌ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ ድግስ ደገስ እንጂ ምሳ ጋበዘ አይባልም፡፡ በምሳው ዓይነትና ብዛት ተገርማ “ ይህ ሁሉ ለምን?” ስትል በልቧ እያወራች ከዶክተር
ባይከዳኝ ጋር መጐራረሳቸውን ቀጠሉ፡፡ በእውነቱ ግሩም የምሣ ዝግጅት
እንደተደረገላት ልቧ አምኖ ተቀብሎታል፡፡
ምሳው እንዳበቃ አንድ ጠርሙስ ሄግ ዊስኪ ከመለኪያዎችና ከበረዶ ጋር የትነበርሽ ይዛ ቀረበች፡፡ መለኪያው ሁለት ነው፡፡
ዶክተር አንዱን እሱ ፊት፤ አንዱን እሷ ፊት አደረገ፡፡
“ ምን ልትሆን?! "በቀልድ መልክ መለኪያውን ገፋ አደረገችው፡፡
“የዚያን ዕለት በሰው ሀገር፤ በሰው ቤት፤ ስለነበርን ነው ያላስቸገርኩሽ፡፡ዛሬ ግን በራሳችን አገር፤ በራሳችን ቤት፤ ውስጥ መጠጣት መጫወት አለብሽ” አላት፡፡ ደብረ ዘይትን ውጭ አገር አስመስሎ፡፡

“ ዶክተር ሙት አልሞክረውም፡፡ ይሄማ መቅበጥ ነው”

ሰው በቤቱ ከሚወደው ጋር ሆኖ ካልቀበጠ የት ይቀብጣል ታደያ?”
ጉሽም አደረጋት።
“ከምሳው ጋር እንዴት ይሄዳል መሰለሽ ትሁት?” በቃ እሱን አልጠጣም፡፡ ባይሆን እንደዚያን ዕለቱ ትንሽ ቢራ ልቅመስ”
ቢራ ከፍቶ በብርጭቆ ቀዳላት፡፡ ከዚያም ከሶፋው ላይ ተቀምጠው መጨዋወት፤ መተሻሸት፤ መላፋታቸውን ቀጠሉ፡፡
ዶክተር በጭኖቿ ውበት ተረትቶ፤ በስሜት ሰክሮ፤ አንዳንድ ጊዜ ጣቶቹ ድንበር እየዘለሉ ይጓዙ ነበር፡፡
ትህትና ቀስ በቀስ ሞቅ እያላት ሄደ፡፡ በተለይ ለውሃ ሽንት ወደ ሽንት ቤት ስትሄድ፤ በቢራው ውስጥ ውስኪ የጨመረበት መሆኑን ሳታውቅ
የምትጐነጨው ዊስኪ የተደባለቀበት ቢራ ቶሎ እንድትግል አድርጓታል፡፡
ከዚያም መሣሣም ጀመሩ፡፡ የትነበርሽ በጉደለው ለመሙላት ተፈልጋም እንደሁ ለመታየት፤ ብቅ ብትል ፤ የትህትና አንገት
እንደቀጭኔ አንገት ወደ ላይ ተመዞ፤ የዶክተር ባይከዳኝ አንገት ደግሞ
ቁልቁል ተሰብሮ፤ እንደ ጉድ ከንፈር፤ ለከንፈር፤ ተሳስመው ሳይሆን
ተጉራርሰው ደረሰች፡፡

"ያንተ ያለህ!” አለችና ባየችው ነገር ደንግጣ ዳግም ተመልሳ ላትመጣ
ሮጣ ወጣች፡፡ የሰማትም ያያትም አልነበረም፡፡ የሁለቱም የስሜቶቻቸው
ሕዋሳቶች ደንቁረው፤ በአንድ ነገር ላይ ብቻ ስለተጠመዱ፤ ቦንብ ቢፈነዳ
እንኳ የሚሰሙ አይመስሉም ነበር፡፡
ትህትና እንደዚያ ግልጽ ሆናለት፣ በፍቅር ስሜት ተውጣ፤ እጆቿ አንገቱ ላይ ተጠምጥመው! እኒያ ብስል እንጆሪ የመሰሉ ከንፈሮቿን ስታቋድሰው፤ ደስታ ፈንቅሎት፤ የበለጠ በፍቅር ተረታላት፡፡
ምንም እንኳን በቢራው ውስጥ የደባለቀበት ውስኪ ሞቅ እንዳደረጋት
ቢረዳም! እንደዚያ በስሜት ሰክራ፤ ሁለመናዬን በፍቅር እየዳሰሰች ፤
እራሷን አሳልፋ ትሰጠኛለች ብሎ አልገመተም ነበር፡፡

ቀስ በቀስ እየተሸነፈች ሄደች :: ዛሬ በተራዋ አዛዥ ስትሆን፤ዶክተር ባይከዳኝ ደግሞ ታዛዥ ፤ ሆነ ። የተገላቢጦሽ !!
አውልቀው ከላይ ያለውን! " በትዕዛዝ መልክ፡፡ ከመቅጽበት ፒጃማውን
አውልቆ ወዲያ ጣለው ባሰበችው ነገር ላይ ቶሎ ለመድረስ ቁና ቁሩ እየተነፈሰች የራሷንም እንደዚያው አደረገች፡፡
ከዚያም በገባችበት የቅዠት ዓለም ውስጥ ሆና የምትሠራው ሁሉ ለዶክተር ባይከዳኝ እንግዳ ነገር ነበር፡፡ እሷ እንደዚያ ሁለመናዋን ግልጽ አድርጋለት በስሜት የጋለችው ፤ እንደዚያ ሰውነቷ አተኩሶ መቃተት የጀመረችው፤ እንደዚያ በሁለመናዋ ተጠምጥማበት አትልቀቀኝ ያላችው፡ እሱን መስሎት፤ ከደስታ ብዛት የሚሆነውን አጣ፡፡ ምን ዋጋ አለው?
እሷ ግን በዚያን ሰዓት አካሏ እንጂ መንፈሷ፤ ልቧና፤ ቀልቧ ፤ ሁሉ
ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር አልነበረም፡፡
እሷ በዚያች ሰዓት አቅፋ እንደዚያ በስሜት የሰከረችለት ሰው ፧ሁለመናዋን ግልጽ ያደረገችለት ሰው፤ ከአምስት ቀን በፊት ያየችው፤በኋላም ልቧንም ቀልቧንም ወስዶባት የሄደው፤ በድንጋጤ አፏን ከፍታ የቀረችለት፤ በአጠቃላይ በፍቅር የተረታችለት፤ ሻምበል ብሩክን እያሰበች
👍2
ነበር፡፡
በእያንዳንዷ ደቂቃ የምታደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ ለየት ያለና፤ ከዚያ
በፊት ተሰምቷት የማያውቅ ስሜት ነበር፡፡
በሕይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ በወሲብ ስሜት ተቃጥላ ፤ ተቀራኒዋን ተጠምታ የታየችበት ቀን ቢኖር ዛሬ ነው፡፡
ለወንድ ልጅ እንደዚህ ዓይነት ስሜት ተሰምቷት አያውቅም፡፡ ዶክተር
ባይከዳኝ አካሏ እንጂ ልቧ በብዙ ኪሎ ሜትር ከሱ ውጭ መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ ምንኛ ልቡ በሀዘን ይጐዳ ነበር? ይሄንን ደግሞ እሱ እራሱ የሚያደርገው ነው፡፡

በወሲብ የሚወዳት ጨው አላት የሚላት የቡና ቤት ፍቅረኛው ሣራን መቼም አይረሳት፡፡ ከሌላ ሴት ጋር እየተዳራ፤ በስሜቱ የሚያጣጥመው ሣራን ነበር፡፡ በእርግጥም እሷን ሲያስብ አብሯት ከሚጫወተው ሴት ጋር ይጣጣማል፡፡ በአካል እዚህ በሃሳብ ግን እዚያ ::
ዶክተር ከሱ ጋር ያለች መስሎት፤ በምትሰጠው ትዕዛዝ መሠረት
በፍጥነት ተንቀሳቀሰ፡፡ ከዚያም ሁለቱም ከስሜት ንረት ጥግ እዚያ እጣራው ላይ ሲደርሱ በሁሉም ረገድ ዝግጁ የሆነው
እንደማግኔት ተፈላለገና፤ ወደ ጓዳው
ለመግባት እንኳን ፋታ አሳጥቷቸው፤ በተጋደሙበት ሶፋ ላይ ጨዋታ ጀመሩ፡፡

ዶክተር በዚህ በዛሬው አጋጣሚ ተደስቶ ያንን ድል ሊቀዳጅ አሞቱን ኮስተር አድርጎ ትግል ገጠሙ፡፡ ትህትና እያቃሰተችና፤ እየቃተተች ሙሉ በሙሉ መረታቷን አረጋገጠችለት፡፡
ዶክተር በሁኔታዋ ተመስጦ፤ በደስታ እየፈነደቀና የሠራ አካላቱ የሚያመነጨው ሙቀት፣ ከሷ ሙቀትና ትኩስ ትንፋሽ ጋር ተዋህዶ በላብ እየተጠመቁ፤ ትግሉን ቢቀጥልም፤ አስቀድማ ደካማነቱን የጠረጠረችው ሰው ዛሬም ዳግማዊ
ውድቀቱን አረጋገጠላት፡፡ በመከራ የጋለው ሰውነቱ ሟሽሾ፧ ልክ እንደ ደብረ ዘይቱ ሁሉ ተልፈስፍሶ፤ እላይዋ ላይ በደረቱ ተዘረረ፡፡ በዚያን ሰዓት ቀልቧና ልቧ ከዘመተበት ዓለም ተመልሶ፤ ከላይዋ
የተጋደመውን ከባድ ሰው አተኩራ ብትመለከተው ፤ በፍቅር የተነደፈችለት ሻምበል ብሩክ ያለመሆኑን አወቀች፡፡ዶክተር ባይከዳኝ ልቧ ብዙም ያልደነገበጠበት ዶክተር ባይከዳኝ የሆነውን አየች፡፡ በቃ ዶክተር ጥርሱ ያለቀበት አንበሳ መሆኑን አረጋገጠችለት፡፡ ከዚያ በኋላ ቀስ ብላ እየሳቀች ተነሳችና የረጠበውን ሰውነቷንና፤ ላቧን፤ አደራርቃ
ልብሷን ለባበሰች፡፡ ዶክተርን ቁልቁል ተመለከተችው :: ተዘርሯል፡፡ተዘርግቷል ፡፡ በጥይት ተመቶ የወደቀ ነው የሚመስለው

“ምስኪን” አለችው በልቧ፡፡ ከዚያም ቀስ በቀስ የሆነውን ለማስታወስ ሞከረች፡፡ ሰክራ ነበር፡፡ የሰከረችው ግን በአንድ ቢራ ነው ወይስ ? በዚያ ቢራ ውስጥ ውስኪ ቀላቅሎበት እንደሆነ ጠርጥራ፤ በጠርሙሱ ውስጥ ያለውን ጭላጭ ቀመሰችው፡፡ የጣዕም ልዩነት እንዳለው ተረዳች፡፡
ዶክተር እንድትሰክር ብሉ ውስኪ እንደጨመረበት አወቀች፡፡ በፈጸመችው ድርጊት አፈረች፡፡ አሁን ነፍሷን እያወቀች፤ ሞቅታው እየተሸረጠላት ነበር፡፡ ሄዳ ፊቷን በቀዝቃዛ ውሀ ሙልጭ አድርጋ ታጥባ
መጣችና ዶክተር ባይከዳኝን ቀሰቀሰችው ዓይኖቹን የግድ ከፈታቸው ሙትት ብለው ቦዘዋል፡፡

"ልሂድ ዶክተር?” አለችው፡፡
“ልትሄጂ ነው?” አላት :: አይኖቹን በግድ ከፍቶ ሽቅብ እያስተዋላት፡፡
"አዎን” አለችው፡፡
“መቼ ትደውይልኛለሽ?”
“ስሞኑን”
"እሺ ትሁት.. ቻው...” የደቀቀ ሰውነቱን ከሶፋው ላይ እንዳጋደመ በሩን
ከፍታ ወጣች፡፡
ከቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት ሆኖ ነበር፡፡ እንደዚያ የሚንሰፈሰፍላት ልጅ እንደዋዛ ወጥታ ስትሄድ በስልምልም ዐይኖቹ ሸኛትና እዚያው በተጋደመበት ቀረ፡፡

የትነበርሽ እንግዳዋ መውጣቷን ስታረጋግጥ ቀስ ብላ ወደ ሳሎኑ
መጣችና ዶክተር ባይከዳኝን አየችው፡፡ ተዝለፍልፎ እሶፋው ላይ ወድቋል፡፡ ከውስኪው የበለጠ የደከመው በትግሉና ከትግሉ በኋላ በተፈጠረው ሁኔታ ነበር፡፡
“ጋንዲያ ”ስትል በልቧ ሰድባው ተመልሳ ወጣች።የትነበርሽ በልቧ የሰደበችው እንደዚያ በሁለት እጆቹ ታቅፎ ያስገባትን
ልጅ ጉዳዩን ከጨረሰ በኋላ ያለመሸኘቱ አናዷት ነበር፡፡

“የውሻ ልጅ ነኝ” አለ ዶክተር እራሱን በራሱ፡፡ ዛሬ ትራሱን በቡጢ ሳይሆን በጥርሱ ነክሶ ቀረ፡፡ አልቅስ፤ አልቅስ፤ አለው፡፡ ግን አላለቀሰም፡፡ያ ዕድል ዛሬም አመለጠው :: በሀሣብ ቅዠት ነጎደ :: በስሜት ስብራት አካላቱ በሀዘን ተኮማትሮ፤ በዊስኪው ጡዘት አእምሮው ዞሮ፡የሚሆነው አሳጣው፡፡ የሚፈጥረው ተአምር አልነበረምና፤ ውስጥ ውስጡን አንጀቱ እየጨሰ፤ ትህትናን አሰባት...
መሄዴ ነው ስትለው እንደዋዛ ተወት ያደረጋት፤ በገዛ ደካማነቱ አዝኖ
መሆኑን ተረድታዋለች፡፡ ይሄ ግን ለሷ ጥሩ አጋጣሚ ስለነበረ ቀስ ብላ፧ሹልክ ብላ፤ ወጥታ ሄደች፡፡ የሄደችው በቀጥታ ወደ አዜብ ዘንድ ነበር፡፡
አዜብ ጋ ለመሄድ ያደፋፈራት ምክንያት አላት፡፡ አዎን ከዚህ በላይ መጠበቅ አትችልም፡፡ አምስት ቀናት፤ አምስት ሌሊቶች፤ በሰዓትና፧ በደቂቃ፤ ሲባዙ የትየለሌ ናቸው :: እነዚህ አምስት ቀናት፤ ለሷ መቋቋም ከምትችለው በላይ የናፍቆት ዘመናት ሆነውባታል፡፡
ስለዚህ ዛሬ እነ አዜብ ቤት ሄዳ፤ ከአዜብ ጋር ሆነው፤ ስልኩን አዜብ መኝታ ክፍል ወዳለው ሶኬት ያዞሩና፤ ይደውላሉ፡፡ ከዚያም ታነጋግረዋልች፡፡ አዜብ የወንድ ጓደኞቿን በመኝታ ክፍሏ ውስጥ ባለው
ስልክ ስትቀጥራቸው፤ ስታጫውታቸው፤ ስትሞላቀቅባቸው፧ አይታለችና
ከሻምበል ብሩክ ጋር እንደልቧ ለመነጋገር፤ የአዜብ የመኝታ ክፍል
ታያት፡፡
እንደዛሬው ወኔ ያገኘችበት ቀን የለም፡፡ የመጠጡ ወኔ ሙሉ በሙሉ አልከዳትም በቃ ዛሬ ለሻምበል ብሩክ የተሰማትን ሁሉ ትገልጽለታለች።
እቢሮው ሳይሆን እቤቱ ትደውልለታለች፡፡ በዚያን ሰዓት አዜብም ወደ ቤቷ እንደምትመለስ ገምታ በቀጥታ ታክሲ ተሳፈረችና ወደ መርካቶ በረረች......

💫ይቀጥላል💫

በየቀኑ ሳይቆራረጥ እንዲደርሳችሁ የበዛ Like 👍 እንዲሁም የበዛ #Share እፈልጋለው።

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሰባት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና .....ቀኑ እሁድ ነው፡፡ ለዛሬው ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ለሚኖራት ግንኙነት በቂ ዝግጅት አድርጋለች፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ እንደዚያን ዕለት አምሮና ተውቦ ፒጃማውን ለብሶ ከሳሎኑ ሶፋ ወንበር ላይ ጋደም ብሎ እየጠበቃት ነበር፡፡ ለምን እንደሆነ እሱ እራሱ አንዳንዴ ግራ ቢገባውም፤ ልቡ እንደዚያ በፍቅሯ እየተቃጠለ፣ በስሜት…»
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት
;
;
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ


እስክንድር በምልክት አሳየው ። በዚያ ሁሉ ጠጪ መሐል ሁለት እጁን እኪሱ አድርጎ ፡ ሁሉንም በንቀት ዐይን እየተመለከተ ነበር ወደ ሽንት ቤቱ የሔደው ።

“ ቢራዋ ሥራዋን እየሠራች ነው ” አለ እስክንድር የአቤል አረማመድ እያየ ።

“ ግን ምን ይሻለዋል ?” አለ ሳምሶን " በአቤል ሁኔታ በማዘን ' “ አሁን በማዕረግ የሚመረቅ ይመስልሃል ? ” እስክንድር ገርሞት ሣቀ ። የሳምሶን ጥያቄ ግን ከቅን
መንፈስ የመነጨ ነበር ። አቤል የሚወደውም የሚያከብረውም በማዕረግ ተማሪነቱ ነው ። የአቤል የማዕረግ ተማሪነት በዩኒቨርስቲው ውስጥ በብዙ ተማሪዎች ዘንድ ይታወቃል
እንደ እስክንድር ጠጋ ብለው የማያውቁት አሁንም የዓመቱ የፕሬዚዳንት የከፍተኛ የማዕረግ ሽልማት ከአቤል እጅ አይወጣም የሚል ግምት አላቸው ። ሳምሶንም የመኝታ ክፍል ጓደኛው ቢሆንም ቅሉ በትምህርት ያን ያህል መድከሙን አያውቅም ነበር ።

“ እውነቴን ኮ ነው ። ምን ያሥቅሃል ?”

ማዕረጉ ቀርቶ በዚህ ዓመት መመረቁ ራሱ ነው እኔን የሚያጠራጥረኝ” አለው እስክንድር " በኀዘን ስሜት ፊቱ
ተለዋውጦ።

“ ያሳዝናል ! ግን ምን ታረገዋለህ! ” አለና ሳምሶን "ቢራውን ከጠርሙሱ ውስጥ እየጨለጠ ፥ “ በነገራችን ላይ መውደቂያችንን እናዘጋጅ እንጂ ! መቼም ዛሬ ወደ ካምፓስ አንገባም” አለው ።

እስክንድር የሳምሶን ሐሳብ ገባሁ ፤አንድ ሴሚስተር ሙሉ ታፍኖ የቆየ ስሜቴ ተነሣ ነገር ግን ኪሱ አስተ ማማኝ አልነበረም ።

“ እኔጋ በቂ ገንዘብ የለማ ! ” አለው ልመና በተቀላቀለበት ድምፅ ከልብ ተዝናንቶ ።

አቤልም እሺ የሚል አይመስለኝም ። ከአሁን በፊት ውጭ እድሮ አያውቅም ።
“ ምን ትቀልዳለህ ? ጭራሽ ? እምልህ ...”
“ አዎ ፡ ከእኔ ጋር ስንተዋወቅ ይኸው አራት ዓመት አለን አንድ ቀንም ኣድርጎት አያውቅም ።

እንግዲያው ዛሬ ድንግሉን ማስወሰድ አለብን ? ”አለ ሳምሶን ተንኮልም የፍቅር ስሜትም እየተሰማው ።

“ እዩዬ ! ተው እባክህ ! ” አለ እስክንድር ' በተዘበራረቀ ስሜት ።

“ ምናለበት ? አንተ ደሞ ! እንዲያውም ሴት ከቀመሰ የዐይኑ ፍቅር ይለቀው ይሆናል ። ገንዘብ እንደሆን እኔ ይዣለሁ ብዬሃለሁ ።

እስክንድር የሳምሶን ሁኔታ ራሱ እንግዳ ሆነበት ። ሳምሶን አብዛኛውን ጊዜ በኪሱ በርካታ ገንዘብ ይይዛል ። ወላጆቹ ደኅና ገቢ አላቸው ። አባቱ በአንድ ኢንተርናሽናል ድርጅት ውስጥ በጥሩ ደመወዝ ይሠራሉ ። በእናቱ ስም ደግሞ
መስጊድ አካባቢ የሰዓት መሸጫ ሱቅ አላቸው ። ወላጆቹ ለሳምሰን በወር ተቆራጭ ካደረጉለት ሃምሳ ብር ሌላ
ሊጠይቃቸው ብቅ ባለ ቁጥር አንድ ወይም ሁለት ባለ አሥር ኖት ሳያሽጉት አይመለስም ። ታዲያ ሳምሶን ይህን ሁሉ ገንዘብ ሲይዝ " ለመጠጥ ማጥፋት አይወድም። የሱ ገንዘብ የሚያልቀው በምግብ ነው ። መብላት ፡ ስፖርት መሥራት ግንባታ ብቻ ! በዩኒቨርስቲው አቅራቢያ ካሉት ምግብ ቤት ባለቤቶች ውስጥ እሱን የማያዉቅ የለም ። ዛሬ ገንዘቡን ለመጠጥና ለሴት ለማውጣት መዘጋጀቱ ነው እስክንድርን ያስገረመ።

“ እንዴት ነው ? ዛሬ ግንባታው ቀርቶ ለማፍረስ ነው መሰል የታጠቅከው ” አለው እስክንድር እየሣቀ ።

“አንዳንዴ ያስፈልጋል እባክህ ! ”
አሳላፊዋ አራት ጠርሙስ ቢራ ይዛ መጣች አንዱ ለራስዋ መሆኑ ነው ።

ቢራ እዚሁ ጓዳ መጥመቅ ጀመራችሁ እንዴ ? "
አላት እስክንድር ፡ ከታዘዘች መዘግየቷን ለመጠቆም ።

“ ቆየሁ እንዴ?አንድ ሰካራም ይዞ ሲነተርከኝ ነው” አለች ፥ ቢራውን እየከፈተች ።

“ አንቺው መጠጥ አቅርበሽለት አንቺው፡ሰካራም ትይዋለሽ ? በይ ነይ በይ ” አለና ሳምሶን ፡ ዳሌዋ ላይ ቸብ አደረጋት ቸብታው ጠንከር ያለ ስለ ነበር ዳሌዋን ለበለባት።

“ እንደዬ ! ታዲያ ዱላው ምንድነው ? ” አለች ተቆጥታ ዳሌዋን በእጅዋ እያሻሸች

ዝም በይና ቁጭ በይ ! ከፈለግኩ ጥርስሽን ነው የማረግፈው አላት ሳምሶን እንደ ልማዱ ።

እስክንድር ነገሩ ማየሉን ሲያይ ተደናገጠ

“ ኧረ እባክህ ! የማነህ ሒድና የሚስትህን ጥርስ አውልቅ " የእኔን የብርቅነሽን አይደለም። ስለ ቢራው እንደሆን ኬረዳሽ ! ” ብላው የከፈተችውን ቢራ ጥላ ተነሣች ብርቅነሽ አምርራ ልትሔድ ስትል'እስክንድር እጅዋን
ይዞ አባብሎ አስቀመጣት ።

“ አንቺ ደሞ እረፊ እንግዲህ ። እሱ ለጠዋታ ያህል ነው የነካሽ
እየተመናቀረች ከሳምሶን ርቃ እስክንድር ጎን ተቀምጠች ። ሳምሶንም ጥርሱን እያንቀጫቀጨባት ነበር ። በማይ
ረባ ነገር ተለካክፈው የጎሪጥ መተያየታቸው እስክንድርን
አስገረመው ።

“ ሁለታችሁም ዕረፉ ፡ ይሄ ቡና ቤት ነው በሰላም ጠጥተን መጫወት ነው የምንፈልገው ”አላቸው : ከግንባሩ ኮስተር ብሎ ፥ ግን በሆዱ እየሣቀ ።

የእስክንድር ሐሳብ እነሱጋ ረግቶ አልቆየም ። በድንገት አንድ ሐሳብ አእምሮውን ወጋው ።አቤል ወደ ሽንት
ቤት ከሔደ ቆይቷል ፤ግን አልተመለሰም ። እስክንድር ልቡ መጥፎ ነገር ጠረጠረና ድንገት ከተቀመጠበት ተነሣ ።

ምነው ?” አለው ሳምሶንም ፡ በሁኔታው ተደናግጦ ።

“ ምንም አይደለም ፥ መጣሁ ” ብሎ እስክንድር ወደ ሽንት ቤቱ ሄደ ። አቅለሽልሾት ይሆናል በሚል ግምት ሳምሶን ነገሩን ቸል አለው ።

እስክንድር ከመጸዳጃ ቤቱ አጠገብ ሲደርስ አቤል እጁን በኪሱ እንዳደረገ ግድግዳ ተደግፎ ቆሞ ነፋስ ሲቀበል አገኘው። ዐይኑ በርበሬ መስሏል ።አላፊ አግዳሚውን በንቀት ዐይን ነው የሚመለከተው።

ቴክሱ ምነው ? ”አለው እስክንድር ፥ ደህና መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ"

“ ወረፋ ሆኖብኝ ነው እባክህ ! ”

“ የሽንት ወረፋ ? በል እንግዲህ ጠብቅ ። ምን ታረገዋለህ ? ” ብሎት እስንድርን ወደ መጣበት ተመለሰ ።አቤል አንድ አደጋ ደርሶቀታል የሚል ሥጋት ስለ ነበር፡ በሰላም በማግኘቱ ልቡ ተረጋጋ ። ምንጊዜም አያምነውም አንድ ቀን በራሱ ላይ የሞት ቅጣት ይፈርዳል የሚል ፍራቻ አለው።

ወደ መቀመጫው ሲምለስ ብርቅነሽና ሳምሶን ተስማተው ጎን ለጎን ተቀምጠው ሲያወሩ አገኛቸው ።

ታረቃችሁ እንዴ ? ”

“ ዱሮስ መች ተጣላን ? አንተ ደሞ ” አለችና ብርቅነሽ ጠየቀችው፡ ፡

ቀድሞውንም ጸበኞች የሚገባበዙት መሐላቸው ገላጋይ ሲኖር ነው ። ብቻቸውን ሲሆኑ አንደኛው ዐቅሙን
ዐውቆ ወይም ጥቅሙን ከጉዳቱ አመዛዝኖ ጸባዩን ያሳምራል ? አለ እስክንድር በልቡ ።

“ ያንን ነገር “ኮ ለብርቅነሽ ነገርኳት” አለው ሳምሶን' ዓይኑን እስክንድር ላይ ተክሎ "

የቱን ነግር ? ”

የአቤልን ነዋ ! በቃ እሷ ይዛው ትደር ።

ሳምሶን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መሆናቸውን አጫውቷት ከዚያው ቡና ቤት መኝታ እንድትይዝ ገንዘብም
ሰጥቷታል ።

“ አንተ ዛሬ የልጁን ድንግል ለማስወሰድ ታጥቀህ ተነሥተሃል ማለት ነው? ” አለ እስክንድር ጉጉቱ አስገርሞት እየሣቀ ።

“መሆን አለበት ብዬሃለሁ ። አድቬንቸር ነው
“ አንቺስ ? በነገሩ ተስማማሽ ? ” አላት እስክንድር ፊቱን ወደ ብርቅነሽ መልሶ።

ውይ በደስታ ነዋ ! እንዲያም ድንግል ወንድ ደርሶኝ አያውቅም ። ዕድሌ ሆኖ የተፈተነ ብቻ ነው የሚደርሰኝ።

ስትናገር ሣቅ ሃቅ ስለምትል የቀልዷን ይመስላል እንጂ ብርቅነሽ የምትናገረው የልቧን ነበር ። ወሲብ ጀማሪ ደርሷት
አያውቅም ። የልጅነት ባሏም ቢሆን ሁለተኛ ሚስቱ ነበረች ።ቡና ቤቱ ውስጥ የሥራ ጓደኞቾ፥ “ ዛሬ የአንዱን ጀማሪ ድንግል ወሰድን ” እያሉ ሲያወሩ ትቀናለች በዚህ ወሬ የተካነችው የቡና ቤቱ ባለቤት ነች የጥንት ዝናዋን ስታወራ ይሄ አርዕስት
👍1
ከመሐል ይጠፋም ። የቀትር ቡናዋን እያፈላች በሸርሙጦች ተከባ ውቃቢዋን ስትለማመን ንግግር መክፈቻዎ ይኽው ነው ።

አይ ዘመን ስንቱ አለፈ ቡና ቤቱ እንዲህ እንዳሁኑ ሳይደራጅ ሠራተኛ ሠፈር ትንሽ ኪዮስክ ከፍቼ ነበር የጀመርኩት ታዲያ ያኔ ስንቱን ባላገር ገራሁት መሰላችሁ ! መቼም የሰው ነጭ ነው ያየሁበት ። ፍቅር በድርያ የሚያዝ ቢሆን ቀልጬ እቀር ነበር። እበስኩ ! ዕረፍት ሳላገኝ ነበር የምውለው ። ታዲያ በጥም ትዝ የሚሉኝ ገና ልጅነታቸውን ያልጨረሱ ተማሪዎች ናቸው በምሽት ተሰርቀው ብቅ ይሉና ድንግላቸውን አስረክበው ይመለሳሉ ። ምን የመሰሉ ሎጋዎች ነበሩ ! ”

አንዴ ከጀመረች ማቆሚያ የላትም ። ዐይኗ ዕንባ እስኪያቅር ድረስ የጥንት ኑሮዋ ውስጥ ሰምጣ ትቀራለች ። በዚህ
ጊዜ ብርቅሽ በልቧ ትቀናለች ።

ምነው ፈዘዝሽ?” አላት እስክንድር በሐሳብ ጭልጥ ብላ መሔዷን እያየ ።

መፍዘዝ ሆሆይ ! እንኳን ፈዘን ቀልጥፈንም አልሆነልን” ስትል አቤል ተመልሶ መጥቶ አጠገባቸው ተቀመጠ ።

ኖር ብላናል ” አለችው ፡ ሞቅ ካለ ፈገግታ ጋር ።

ስትሥቅ ድዷ ይታያል ። የላይኛው ድዷን ጉራማይሌ ተነቅሳዋለች ። አንገቷ ንቅሳት ድዷ ንቅሳት አቤል ያሤሩበትን አላወቀም የተከፈተለትን ሦስተኛ ቢራ ልጠጣው
ወይስ አልጠጣው በሚል ስሜት ዝም ብሎ ተመለከተው ።

“ ይሄ ነገር ቢበቃኝስ ?” ሲላቸው ፥ ምላሱ ትንሽ ትንሽ መተሳሰር ጀምሯል ።

“ እረ ጠጣ ! ምን እንዳይልህ ? ዕረፍታችሁ አይደለም እንዴ ? ” አለችው ብርቅነሽ ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ዐይን
ልዐይን ተያዩ ።

“ ስሚ ብርቅነሽ ' ይህ ሁሉ ንቅሳት ምንድነው ?”አላት እስክንድር፡ ጣልቃ ገብቶ ። ለለከፋ መሆኑ ገብቷታል ።

ጌጥ ነዋ ! ምን አገባህ አንተ ደግሞ ? ”

“ ማለቴ ' አዲስ አበባ ስትገቢ ልታጠፊው አልሞከርሽም ? ”

ውይ ፥ ለምን ብዬ ! ቁምጥና መሰለህ ? ”

“ እሱን ተይው የሚቻል ቢሆን ኖሮ ሴቶች ንቅሳታችሁን ለማጥፋት የማትገቡበት ጉድጓድ አልነበረም ። ለመሆኑ ከሀገርሽ ከወጣሽ ስንት ጊዜ ሆነሽ ?

💥ይቀጥላል💥
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

.....በሐረርጌ ክፍለ ሀገር፤ በሀረር ከተማ ነዋሪ የሆኑት ፊታውራሪ በላይ እንግዳ፤ ከመጀመሪያ የህግ ባለቤታቸው ከወ/ሮ አይኔአበባ ጥሩነህ ከወለዷቸው ስምንት ልጆች ውስጥ፣ ብሩክ በላይ አራተኛ ልጅ ነው።
ፊውታራሪ በላይ፤ ልጃቸው ብሩክ ! በእናቱ ማህፀን ውስጥ እንዳለ፤
በወዳጅነት አብረዋቸው ደስታንና ችግርን ካሳለፉት ከባላምበራስ ትኩነህ
መብራቱ ጋር ከጓደኝነትም በላይ ወዳጅነታቸውን በጋብቻ ትስስር
ሊያሳድጉት ፈለጉና፤“ልጅህ ሴት ከሆነች ለወንድ ልጄ፤ ወንድ ከሆነ ለሴት ልጄ” በማለት ቃል ተገባቡ፡፡

ሁለቱ ጓደኛሞች፤ በእርጉዝ ሚስቶቻቸው ማኀፀን ውስጥ ባሉት ጽንሶች ሊቆራኙ በገቡት ቃል ኪዳን መሠረት፤ እንደ አጋጣሚ ሆኖ የፈታውራሪ በላይ ልጅ ወንድ ሆኖ ሲወለድ፤ የባላምባራስ ትኩነህ ልጅ ደግሞ ሴት ሆነች፡፡

በሁለቱ ሕፃናት መካከል የነበረው የዕድሜ ልዩነት ሁለት ወር ብቻ ነበር፡፡ በዚህም ብሩክ ታላቅ ለመሆን በቅቷል፡፡ በዚያን ዕለት ወንድ ተወልዶ ቢሆን ኖሮ፤ ያ ሁሉ የወላጆች ምኞት ከንቱ ሆኖ ይቀር ነበር፡፡ያ የረጅም ጊዜ ምኞታቸው ምኞት ብቻ ሆኖ ባለመቅረቱ፤ ሴቷ ልጅ
የተወለደች ዕለት የሠርግ ያክል ድግስ በሁለቱም ቤት ተደግሶ ይህችን
ዕድለኛ ልጅ በዕድሏ ብለው ሰየሟት፡፡

በዕድሏ ትኩነህና፤ ብሩክ በላይ፤ በቤተሰባቸው ፍቃድ አንዳቸው ለሌላው
የትዳር ዋልታ መሆናቸውን ሳያውቁ፤ በዚያ በወርቃማ የልጅነት ጊዜ ውሀ እየተራጩ ፤ጭቃ እያቦኩ፤ አብረው አደጉ፡፡ ብሩክና በዕድሏ በአካል እየጐለመሱ፤ በአእምሮ እየበሰሉ፤ ሲመጡ ወላጆቻቸው በትዳር እንዲተሳሰሩ የተስማሙባቸው ወደፊት ባልና ሚስትነት የታጩ መሆናቸውን ቀስ በቀስ እየተረዱ ሲመጡ፤ ለጥቂት
ጊዜም ቢሆን የመተፋፈርና፤ የመሽኮርመም፤ ፀባይ ቢያሳዩም፤ ቀስ በቀስ ይህንን እያስወገዱ፤ በተቃራኒ ጾታዎች መካከል በሚፈጠረው የግንኙነት መስመር መጓዝ ጀመሩ፡፡

ቀስ በቀስ የልጅነት ነጻ ፍቅራቸውን በጾታዊ ፍቅር እያጐለመሱት መጡ፡፡በተለይ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ አብረው እየተማሩ፤አብረው እየዋሉ፤ ማምሸት ሲጀምሩ፣ ቀስ ብለው ጊዜውን ጠብቀው ሊሆን የሚችለውን፤ ከወዲሁ ቸኩለው ጀመሩት፡፡ .

በዕድሏ እዚህ ጐደለሽ የማትባል ቆንጆ ልጅ ነበረች፡፡ ምንም እንኳን የወደፊት ሚስቱ እንድትሆን በቤተሰብ መልካም ፈቃድ የተቸረችው ቢሆንም፤ የሱ፤ የግሉ፤ ብቻ መሆኗን ለማረጋገጥ ብሩክ ቀስ በቀስ እያባበለ የፍቅር ጭውውት አስጀመራት፡፡
በዕድሏ ቀስ በቀስ ከብሩክ የበለጠ በፍቅር ወደቀች፡፡ ብሩክን የምትወድበት ቃልም አልነበራትም፡፡ በአጠቃላይ ነፍሷ እስከምትወጣ ድረስ ትወደዋለች፡፡ ይወዳታል፡፡

ይህ ለሁለቱም ፍቅረኛሞች ኦቦል የሆነ ፍቅር ቀስ በቀስ ሥር እየሰደደ የሚያስቀኑ እየሆኑ ሄዱ፡፡በዚህ መሀል ነበረ እንግዲህ አብዮቱ የፈነዳው፡፡ በዚያን ጊዜ በፊታውራሪ በላይ ቤት በአሽከርነት ተቀጥሮ ይሠራ የነበረው አደፍርስ፤
በአብዮት ጥበቃ አባልነት በቀበሌ ውስጥ ከተመረጠና፤በኋላም የቀበሌው የአብዮት ጥበቃ ኃላፊ ከሆነ በኋላ፤ ያንን ለዘመናት ውስጡን ሲበላው የቆየውን የፊታውራሪን ልጅ በዕድሏን የማግኘት ሕልሙን ሊያሳካ
ቆርጦ ተነሳ፡፡

በመጀመሪያ አባቷን መሣሪያ ደብቀዋል በሚል ምክንያት ካሳስራቸው በኋላ “በሕዝብና በአብዮቱ ላይ ደባ የፈጸመ አድሃሪ ስለሆነ መረሸን አለበት” የሚል አቋም ያዘ፡፡
ለዚህ ጥቆማው ሚስጥሩን ያውቃሉ በሚል ሽፋን ካሳሰራቸው ጠቅላላ
ቤተሰቦች መካከል በዕድሏ እንዷ ነበረች፡፡

“አባትሽን ወይንስ ብሩክን?” ሲል ለህሊና የከበደ ጥያቄ አቀረበላት ።ከዱላው ብዛት የተነሳ ከሁለቱ አንዳቸውን ከመምረጧ በፊት ሁለቱንም ነበር መልሷ፡፡በመጨረሻ ላይ ግን ሰውነቷ በዱላ ብዛት ተተልትሎ
አባቷንም፤ ብሩክንም፤ እራሷንም እንዳታጣ ስለሰጋችና የሁለቱንም
ህይወት ለማትረፍ ስትል፤ ያቀረበላትን ጥያቄ! እንደኮሶ እየመራራት ለመቀበል ተገደደች፡፡

ከዚያም ብሩክ በፀረ አብዮተኛነት ስም ወህኒ ቤት እንዲገባ ካደረገ በኋላ፤
አደፍርስ ድል ያለ ድግስ ደግሶ በሠርግ አገባት፡፡
ብሩክ ከአባቱ ጋር እሥር ቤት ውስጥ እንዳለ፤ አደፍርስ እና በዕድሏ
መጋባታቸውን ሲሰማ እራሱን ጠላ፡፡
መፈጠሩን አማረረ፡፡ በእንባ እየታጠበ ፤ አንጀቱ እየከሰለ! የሚወዳት የሚያፈቅራት ከጭቃ ማቡካት ጀምሮ በልቡ ውስጥ የጠነሰሳት ፍቅረኛውን መነጠቁን አመነ፡፡
ለስድስት ወራት ያህል በዚህ ሁኔታ በእሥር ቤት እንዲቆይ ከተደረገ
በኋላ ተሳትፎው በንባብ ደረጃ ብቻ ስለሆነ “ማሪኝ አብዮቴ” የሚል
መዝሙር ዘምረው በምህረት እንዲለቀቁ ከተደረጉት ወጣቶች መካከል አንዱ ለመሆን በቃ፡፡

የአደፍርስ ምኞት እንዲገደል ነበር፡፡ ሳይሆንላት ቀረ፡፡

“ብሩክ ምን ለመሆን ነው የምትፈልገው? “ ሲሉት አባቱ..
“ዶክተር፧ ኢንጂነር፣ አውሮፕላን ነጂ፣ሳይንቲስት ” ጥሩ ጥሩውን ሁሉ
ለመሆን የሚመኘው፤ በትምህርቱ ጠንካራ የነበረው ልጅ ሞራሉ ተነካ፡፡
ደስታን አጣት :: ከዚያም አሥራ ሁለተኛ ክፍልን እንደጨረሰ በቀጥታ በፖሊስ መኮንኖች ማሰልጠኛ ኮሌጅ ገባ፡፡
በማሰልጠኛው ውስጥ ባስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ልዩ ሽልማትን ለማግኘት የበቃ ጠንካራ ተማሪም ነበር፡፡ ትኩረቱን ሁሉ በማስልጠኛው በሚሰጠው ትምህርት ላይ አደረገ፡፡ በዕድሏን አጥቷታል ፤ስለፍቅር የምትዘፍን ልቡ በዚያ ምትክ ለዘመናት የሀዘን እንጉርጉሮ ስታንጐራጉር ኖራለች፤ ስለፍቅር መስማት ይጓጉ የነበሩ ጆሮዎቹ ያንን ሲሸሹ ኖረዋል
በለጋነቱ በውስጡ የደረቀች የፍቅር አበባ ሁሉን እንዲጠላ አድርጋዋለችና እልሁን የሚወጣው ጠንክሮ በመስራት ብቻ ሆነ፡፡

የሚያዳምጠው ማንኛውም የፍቅር ዘፈን ስንኝ ለሱ መሪር የሀዘን ስሜቱን እያጫረበት በዕድሏን በዓይነ ህሊናው የእንባ ጭጋግ ከጋረዳቸው ዐይኖቹ ባሻገር በትዝታና በሰቀቀን እያሰባት፤ ረጅሙን ጊዜ በብቸኝነትና በሃዘን አሳለፈው፡፡

በዕድሏ የሶስት ልጆች እናት ስትሆን፤ እሱ ግን ይኸውና እስከ ዛሬ ድረስ የትዳርን ነገር ሳይመኘው፤ ሳያስበው በአደፍርስ ላይም የቂም በቀል እጁን ሳይሰነዝር፤ የራሱን ዓለም በራሱ ውስጥ ፈጥሮ በመኖር ላይ ይገኛል፡፡

ሻምበል ብሩክ በመ/ቤቱ ውስጥ ተወዳጅና ተሰሚነት ያለው ወጣት መኮንን ነው።በአጭር ግዚው ውስጥ የሹመት ባለ ዕድል ለመሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማታው መርሃ ግብር፤ በማኔጅመንት ለዲግሪ በመማር ላይ ይገኛል፡፡

ሻምበል የቤት ሠራተኛ ቀጥሮ ሁለት ታናናሽ ወንድሞቹን በማስተማር ላይ ሲሆን፤ በትዳር ላይ የነበረው ምኞት ገና በአፍላው ከተጨናገፈ አስቦትም፤ አልሞትም አያውቅም፡፡ እሱ
አይጨነቅበት፤ እንጂ የትዳር አምላክ እራሱ ለሱ ሲጨነቅለት፤ ሲጠበብለት፤ ቆይቶ የሚሆነውን ሊሰጠው ፤ በሀዘን የተሰበረ ልቡን ሊጠግንለት፤ ተቃርቧል፡፡

በቢሮው ውስጥ ወንድሟን ልታስፈታ ለአቤቱታ የገባችውን ወጣት ሲያይ፤ እንደዚያ በድንጋጤ ደንዝዞና፤ ፈዝዞ፧ የቀረው ያለምክንያት አልነበረም፡፡
ያች ወጣት፤ ያች ውብ ልጃገረድ፤ ሞቶ አፈር የለበዕ ስሜቱን የቀሰቀሰችበትን፤ የሻረ የልቡን የውስጥ ቁስል የነካካችበት፤ ያለምክንያት አልነበረም፡፡ በዚያች ቅጽበት ሻምበል ብሩክ የልጅነት እጮኛው፤ ከሁሉም በላይ የሚያፈቅራት ጓደኛው፤ በዕድሏ እራሷ የመጣች ነበር የመሰለው
በጣም ነው በመልክ የሚቀራረቡት፡፡

ሁለመናው ተረብሾ፤ ያችን ወጣት ለማነጋገር አንደበት ልሳኑ የተዘጋው፤ በዚህ ምክንያት ነበር በተለይ ዓይኖቿ ቁርጥ በዕድሏን ናቸው ለወንድሟ ዋስ ሊሆንላት ቃል ሲገባላት ያቺ ወጣት በኑሮ
ውጣ ውረድ ምክንያት የደረሰባትን
👍3
ችግር፤ አባቷን በጦርነት ምክንያት
ማጣቷን፤ እናቷ በሕመም ስቃይ የአልጋ ቁራኛ መሆኗን፤ የምትወደው ወንድሟ ደግሞ ፀባዩ እየተለወጠ ሄዶ እስከመታሰር የደረሰበትን ምክንያት፤ በዚያች አጭር ጊዜ ውስጥ አጫወተችው።

በዚያን ጊዜ ልቡ አዘነላት ከሀዘኔታውም ውስጥ አብሯት በስሜት አለቀሰ ፡፡ ለምን የዚያን ቀን ምሽት በሕልሙ መጣችበት? እንጃ ! ሻምበል ብሩክ በዕድሏን በትህትና ውስጥ ስላየ ትህትና የበለጠ ናፈቀችው፡፡
ከአሁን አሁን ስልክ ትደውላለች ብሉ ጆሮዎቹን በቤቱም፤ በቢሮውም፤
ስልክ ላይ ጥሎ ሲያዳምጥ ዋለ፡፡ አልደወለችም፡፡ በሁለተኛውም፤ በሶስተኛውም ፤ በአራተኛውም ቀን ሳትደውል ቀረች፡፡ ተጨነቀ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ እየናፈቀችው ነው፡፡

ለሴት ልጅ የነበረው የቀዘቀዘ ስሜት በዚህች ወጣት ምክንያት ለምን ተቀሰቀሰ? ትህትና.....ትህትና...ትህትና...
በሀሳብ ታየችው፡፡ስታለቅስ፤ አቤት አይኖቿ ሲያሳዝኑ፤ ስትናገር ልሳኗ የሚጣፍጥ፤ቅልስልስ ስትል፤ እንዴት ያምርባታል!፡፡ ከዚያም ዐይኖቻቸው በድንገት ሲጋጩ ከድንጋጤዋ ውስጥ ዘልቆ ከዐይኖቿ ውስጥ ያነበበው ስሜት
እንዴት ነበር?፡፡ በጣም ደስ የሚል ፤ ልዩ ስሜት ነበር፡፡ ቃላት ሊገልጹት የማይችሉት ስሜት.....
ይህ ሁሉ በሀሳቡ እየተመላለሰ፤ ሻምበል ብሩክ ትህትናን በመናፈቅ የሚሆነውነ አጣ፡፡ ዋስ ሆኖ ወንድሟን አስፈታላት እንጂ ከወንጀሉ ነፃ ሆኖ አልተሰናበተም፡፡ ጉዳዩ ያላለቀ በመሆኑ መፈለግም ሊኖር
ይችላል፡፡ታዲያ ምነው ድምጿን አጠፋች? ሁኔታው ግራ አጋብቶት ከረመ፡፡

ሻምበል ብሩክ በሥራ ላይ አምሽቶ መግባቱ ነው፡፡ ከምሽቱ አንድ ሰዓት
ተኩል ሲሆን ከቤት ደረሰ፡፡ ከዚያም ከታናናሽ ወንድሞቹ ጋር ቼዝ እየተጫወተ ሳለ የቤቱ ስልከ የጥሪ ድምጽ ሰጠ :: የአሥራ አራት ዓመት ዕድሜ ያለው ትንሽ ወንድሙ ፀጋዬ ሄዶ ስልኩን አነሳ፡፡
“ ሀሎ" አለ ፀጋዬ፡፡

“ሀሎ” አለው ከወዲያ ማዶ ያለው ቆንጆ የሴት ድምጽ፡፡
“ማን ልበል ?" ፀጋዬ አዲስ በሰማው ድምጽ ግራ ተጋብቶ፡፡
“ሻምበል ብሩክ ቤት ነው?"
አዎን”
ይኖራሉ ? ”
"አሉ” አላት፡፡
“እባክህ አቅርብልኝ ?"

ጋሼ ስልክ ይፈልግሀል” አለውና ስልኩን አስቀምጦ ተመለሰ፡፡ ሻምበል ብሩክ በልቡ ምን አለበት እሷ ብትሆን? ወይኔ ብሩክ እባክህን እሷን አድርግልኝ” እያለ፤ እሷን እንዲያደርግለት እየተመኘ፤ ወደ ስልኩ ሄደና አነሳው፡፡

“ሀሎ "አለ ልቡ እየዘዘለች፡፡
“ሻምበል ብሩክ ነህ”
“አዎን ነኝ ማን ልበል?፡፡ ተመስገን አምላኬ፡፡ አዎን አሷው ናት!”

" ትህትና እባላለሁ፡፡ ካልረሳኸኝ” ሻምበል ብሩክ ብቻውን ቢሆን ኖሮ በደስታ ይጨፍር ነበር፡፡ ምን ያደርጋል? እዚያ ወዲያ ወንድሞቹ አሉ።ያዩታል፡፡ የሚይዝ የሚጨብጠው ጠፍቶት ተቁነጠነጠ፡፡

"ትህትና ምነው እስከዛሬ ድረስ ሳትደውይልኝ?”
"አልተመቸኝም ነበር ሻምበል”
“ በጣም እንደናፈቅሽኝስ ይገባሻል?"
እንዴት ማወቅ እችላላሁ ሻምበል?" በልቧግን“ እኔም ተቃጥዬልሃለሁ” እያለች ነበር፡፡

እኔ እንጃ ብቻ ስንገናኝ ብነግርሽ ይሻላል፡፡ ሰሞኑን ጆሮዬ ከኔ ጋር ሳይሆን ከስልኮቹ ጋር ነበር የከረመው፡፡ ለማንኛውም ከስልክ ይልቅ በአካል ተገናኝቶ መጫወቱ አይሻልም? ሲላት....
“ አዎን እንደሱ ይሻላል” አለችው ቶሎ ብላ፡፡

“ እናትሽ ተሻላቸው ትህትና? አንዱ አለምስ ፀባዩን አሻሻለ?”

“ እማዬ እየተሻላት ነው፡፡ ደህና ነች :: አንዱዓለሜ እንዴት ተለውጧል መሰለህ? በዚያች እሥር ቤታችሁ ውስጥ ምን እንዳቀመሳችሁት እንጃ፡፡” እየሳቀች፡፡

እስቲ ስለሁሉም ለመጫወት መቼ እንገናኝ ታዲያ? እኔ እንዳልደውልልሽ እኮ ስልክ የለኝም ስላልሽ ነው እንጂ ይሄን ያህል አልጨክንም ነበር” በማለት አንጀቷን ሊበላው ሲሞክር.....

“ ሻምበል እኔንም እንደጨካኝ አትቁጠረኝ፡፡ ያለመመቸት ጉዳይ ነው፡፡”
በልቧ ግን ነገ አይመቸኝም ካለ ጉድ ፈላ! ከዚህ በላይስ መቆየት አልችልም” እያለች ነበር፡፡

ዛሬ መሽቷል እንጂ ዛሬ ብንገናኝ ደስ ይለኝ ነበር” ሳታስበው አመለጣት፡፡

ሻምበል ጆሮውን ማመን አቃተው፡፡
“ ለምን ነገ አንገናኝም ታዲያ?” አላት በጉጉት፡፡ደስ ይለኛል” እንዲህ በድፍረት ስሜቷን ሳትደብቅ እንድትናገር
የገፋፋት የቀመሰችው አልኮል መሆኑን አላወቀም፡፡ የሚገናኙበትን

ሰዓትና ቦታ ተቀጣጥረው! ትንሽ ተሳስቀው በናፍቆት ተሰነባብተው ፤
ስልኩ ተዘጋ፡፡
ሁለቱም ልባቸው በናፍቆት ተሸብሮ፤ የዛሬው ምሽት ከድንጋይ እየከበዳቸው ተለያዩ፡፡ እውነትም ያ ምሽት በዕድሜአቸው ሙሉ ከሚያውቋቸው ምሽቶች በጣም ረጅሙ ምሽት ነበር፡፡
እንደዚያ ከሻምበል ብሩክ ጋር በስልክ ስትጨዋወት አዜብ ከፊት ለፊቷ
ቁጭ ብላ በዐይኖቿም፤በእጆቿም፤ በጥርሶቿም ጭምር አመራር
እየሰጠቻት ነበር፡፡
ስልኩ ከተዘጋ በኋላ ሻምበል ብሩክ ከአምስት ቀን በፊት ወዳያት ወደ
ትህትና ሲዘምት፤ እሷም ከአምስት ቀናት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ልቧን ውሃ ወዳደረገው መልክ መልካም ወጣት በሀሳብ ከነፈች.....
ሁለቱም በስሜት እየተፈላለጉ በመንፈስ እየተደባበሱ... አካላቸውን በየአልጋቸው ላይ አሳረፋ፡፡ ትህትና እንደዚሁ እየቃዠች፤ የነገው ቀጠሮ እንደናፈቃት፤ እናቷን እቅፍ አድርጋ! ተኛች፡፡
ሻምበል ብሩክ ግን እንቅልፍ እምቢ ስላለው መጽሐፍ ማንበብ ፈለገና
ያንን ከዚህ በፊት አላነብም ብሎ ያስቀመጠውን የፍቅር መጽሐፍ ለማንበብ ጉጉት አድሮበት “ሀ ”ብሎ ገጹን ገለጠ....

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
አትሮኖስ pinned «#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስምንት ፡ ፡ #ድርሰት_በትክክል_ገና .....በሐረርጌ ክፍለ ሀገር፤ በሀረር ከተማ ነዋሪ የሆኑት ፊታውራሪ በላይ እንግዳ፤ ከመጀመሪያ የህግ ባለቤታቸው ከወ/ሮ አይኔአበባ ጥሩነህ ከወለዷቸው ስምንት ልጆች ውስጥ፣ ብሩክ በላይ አራተኛ ልጅ ነው። ፊውታራሪ በላይ፤ ልጃቸው ብሩክ ! በእናቱ ማህፀን ውስጥ እንዳለ፤ በወዳጅነት አብረዋቸው ደስታንና ችግርን ካሳለፉት…»
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

....“ ምናገባህ ? ሞዛዛ ?" ስትለው ድምጿ የብሽቀት ቅላጺ ነበረው ።

“እውነት ብርቄ ፥ ምን ያህል ጊዜ ሆነሽ?” አላት ሳምሶን?

"አራት ዓመት!”

"የአራት ዓመት የሥራ ልምድ ! ከሌሎቹ አንጻር ሲታይ ትንሽ ነው ” እላት ሳምሶን "

“ መላጣ ! ” አለችው ፡ ጭንቅላቱን በዐይኗ ቂጥ እያየችው ።

“ በአራት ዓመት ውስጥ ስምሽን ለመለወጥ አልሞክርሽም ? ”አላት እስክንድር ሲቀልድባት ፡ “ እዲስ የከተማ
ስም እንደ ራሄል ኤደን ማርታ ፡ ዓለም ከተሜ ለመሆን እ ? ”

“ሒድ'ደረቅ ! ”

ሒድ፡ደረቅ !ሒድ፡ደረቅ!ደረቅ ማርታ በቅናት ቅንድቧን እያርገበገበች ከፊቱ ድቅን አለችበት ። በሐሳቡ ቁመናዋን ቃኘ በሞቅታ መንፈስ እንደገና አለማት ፡ ኪሱ ባዶ ማለም ብቻ ! ማነጣጠር ብቻ !

"ሒድ ፡ ደረቅ የሴቶች የጋራ ፈሊጽ ” አለ በልቡ ።

የብርቅነሽ ጥሬነት አስገረመው ፡ ስትጫወት የባላገር ለዛ አላት ። ንቅሳቷ ባላገርነቷን ይመሰክራል የባላገር ስሟን
አልለወጠችም " እምብዛም የከተሜ ጭምብል አላጠለቀችም ግን ከሀገርሽ ለምን ወጣሽ ? ” አላት በድንገት ።

“ ሆሆይ !ጋዜጠኛ ነህ እንዴ ?”

ባልሆን ፥ ይህን ሥራ ምን አስመረጠሽ ፡ ማለቴ ነው ። ””

“ ዋ ! ወድጄን መሰለህ ? ግድ ሆኖብኝ እንጂ ” ከማለቷ ፊቷ የኀዘን ጭጋግ ለበሰ

“ ምነው ?እንዴ? ” አላት እስክንድር ስሜቷን ተከትሎ ስሜቱ እየዳመነ።

“ ባልተቤቴ ነው ለነዚ ያበቃኝ ! በሱ ምክንያት ነው ሀገሬን ለቅቄ የወጣሁት እያለች የታሪኳ ዳር ዳር ጨረፈችው
በፍቅር ለቀረባት ሁሉ ታሪኳን ታወራለች
ልስ ልስ ሆኖ ለቀረባት የአንጀቷን ትዘከዝካለች የተማረ መስሎ ለታያት ችግሯን አፍረጥርጣ ትናገራለች ። መፍትሔ ይገኝልኛል ብላ አይደለም :: የውስጧን ተንፍሳ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን የመንፈስ እረፍት ታገኛለች።

«« እባክሽ አታጓጊን ፣ በደንብ አጫውቺን" አላት እስክንድር ታሪኳን ለመስማት ተጣድፎ።

“ አያችሁ እናንተ ዕድለኞች ናችሁ : ከደኅና ቤተሰብ በመወለዳችሁ ወይም ከተማ በማደጋችሁ ለመማር በቅታችሆል እኔ የቀለም ትምህርት የለኝም ማንበብና መፃፍ እንኳ የቻልኩት አሁን የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ ከተጀመረ ወዲህ ነው።
የድሀ ገበሬ ልጅ ነኝ ። ያውም በእንጀራ
እናት ያደግኩ !ህም እቴ! ታድያ በአሥራ አራት ዓመቴ ተዳርኩ ። ባሌ ገበሬ ነበር ። እኔ ሁለተኛ ሚስቱ ነኝ ።የመጀመሪያ ሚስቱ ከተጋቡ መንፈቅ እንኳ ሳይሞላቸው ሞታበት ነበር ። ወላጆቼም ሲድሩኝ ይህን ያቃሉ በእድሜ በሰል ያለ ነው ። ጸባዩም ጥሩ ነው ለትዳሩ ታታሪ ነው ” ተባለና ተሰጠሁ ።

“ ጎጆአችንን እያሞቅን ፡ የባላባቶችን ግልምጫና ዱላ በጋራ እየተቀበልን መኖር ጀመርን ፡ ምን ይሆናል ። እግዜር ለትንኮሉ ማሕፀኔን ድፍን እደረገው። ዓመት ጠበቅን ሁለት ዓመት ጠበቅን ልጅ የለም ። በእኔና በባልተቤቴ መሐል ቅሬታ መጣ ያም ሆኖ አልተቃቃርንም ። ድህነት ያስተሳስረን ነበር ። እሱ ከገበሬዎቹ ጋር ውጭ ደክሞ ውሎ ሲመጣ ከቤት ያለሁ
ረዳቱ እኔው ነበርኩ በባላባት ጅራፍ ጀርባው ቆስሎ ሲመጣ አንጀቴ እየተንሰፈሰፈ የማለቅስላት እኔ ነበርኩ ዋ! እቴ ምን ያደርጋል!

እንዲህ እንዲህ እያልን አምስት ዓመት ያህል እንደኖርን አብዮቱ ፈነዳ ። ለውጥ መጣ ። ደክመን ለባላበት መገበሩ ቀረ። እፎይ አለን ። ቤታችን ሙሉ ሆነ እውነቴን ነው ደህና ነገር መብላት መልበስም ጀመርን ። ምን ይሆናል ። ከድህና
ኑሮ ጋር ተያይዞ ነገር መጣ ባልተቤቴ ሌላ ሴት ጋር በስርቆት መሔድ ጀምሯል የሚል ወሬ ሰማሁ ። ስውል ሳድር እኔም
ነገሩን ደረስኩበት። እንዲያውም አንድ ልጅ እንደ ወለደችለት አረጋገጥኩ ። ቀናሁ ! ቅናት አንገበገበኝ ። በሐሳብ
ተብከነከንኩ። ጨስኩ ።ቤት ውስጥ !
መቀመጥ አቃተኝ ብዙም ሳልቆይ ጓዝ ምንጓዝ ሳልል በርሬ ወጥቼ አዲስ አበባ ገበኋት !

“ እዚህ ስደርስ ደግሞ ያዘጋጀሁት ማረፊያ የለኝ ፥ እንደሁ ሜዳ ቀረሁ ። ትንሽ ቀን ሰንብቼ በደላላ አማካይነት
ግርድና ተቀጠርኩ። ስድስት ወር እንደ ሰራሁ ግርድናን እርም ብዬ ተውኩት። አባስኩ እቴ ! የሰው ቤት ሹሮ ሲያልቅ
እኔ ላይ ማፍጠጥ ። ዕቃ ሲጠፉ እኔን መወንጀል ። ምነው ከዚህ ሁሉ ሥጋዬን ሸጨ ባድር አልኩና ሽርሙጥና ጀመርኩ
እላችኋለሁ ።

ብርቅነሽ ስትናገር ታላቅ ማዕበል ተነሥቶ ባሕር ውስጥ የከታቸውን ያኸል ሥስቱም ጸጥ ብለው ነበር ። አሳዘነቻቸው። ምስኪን ጥሬ ፍጥረት ! በመጠጥ ሞቅታ ኃይል ለሁሉ ነገር ግዴለሽ ሆኖ የቆየው አቤል እንኳ፥ ከብርቅነሽ አፍ የድህነት ድምፅ ሲሰማ ቸል ማለት አልቻለም ። ሕዋሳቱ በኀዘን ስሜት ተወራጩ ::

ግን ዝዎም ብለሽ ከምትኮበልይ ፥ ሰላምን በአካባቢሽ በሚገኘው የሴቶች ወይም የገበሬ ማኅበር አመልክተሽ መፍ
ትሔ ኣትፈልጊም ነበር ? ” እላት እስክንድር ፡ ከማዘኑ የተነሣ የሚናገረው ጠፍቶት ።

ዋ እቴ ! ቤት ከፈረሰ ወዲያ ሁሉስ ምን ሊበጅ ? አየህ ፡ ቅናት ከመጣ ቤት ፈረሰ ማለት ነው። ለሁሉም እኔ ለማንም አላማከርኩ ። የሚያለቅሱ ልጆች የሉኝ ' ነጠላ ሰው ምናለበት አልኩና ብር ብዬ አዲስ አበባ ፣ ”

ታዲያ ባልሽ ሊፈልግሽ አልመጣም ” አላትአቤል በሁኔታዋ ስሜቱ ተነክቶ ።

“ ውእእይ • ሥራ አጥቶ ! እንዲያውም ከዚያ ሀገር ለንፀግድ የሚመላለሱ ሰዎች እዚሁ ቡና ቤት አግኝቼ ሲነግሩኝ' ውሽማውን ጠቅልሎ ይዟል አሉኝ • እዩዬ ! ” ብላ ሳትጨርስ ጥሬ ሰማች «

“ ብርቅነሽ ? ! አንቺን'ኮ ነው ? ” የቡና ቤት ባለቢቷ ድምፅ ነበር
“ እመት ! ወይ ጕዱ ዛሬ ! ” እያለች ብርቅነሽ ከተቀመጠችበት ተነሣች

“ እንድዩ ! ሰው ሲገባ አትታዘዥም እንዴ! ምን ይጎልትሻል ? ”

ብርቅነሽ የውስጧን ተንፍሳ ቃጠሎዎን አብርዳ ተነሣች ፡ እስክንድር ተከዘ ቃጠሉዋ ወደ እሱ ተላለፈበት ኀዘኗ ጠልቆ ወጋው ። ቅናት ተፈጥሮአዊ ነው ሀብታምና ድሀ አይልም ። የወደደ ሁሌ ለወደደው ነገር ይቀናል ። ለቀናበት ነገር ይሠዋል ። ብርቅነሽ የቅናትን እሳት ሸሽታ ኮበለለች ። ከቅናት ሸሽታ ሴትኛ አዳሪ ሆነች "

እስክንድር ሐሳቡ ከግላዊነት ወደነማኅበራዊነት መጠቀ ለእሱ ሲጋራ መግዣ መስጠት ያቃታቸው ደሀ እናቱ ላይ ሆኑ፡ሕዝቧን በሰፊው ማስተማር ' በቂ ኢንዱስትሪ ከፍታ እነብርቅነሽን ማሠማራት ያልቻለች ረሀብን ለማጥፋት
ማይምነትን ለማጥፋት ርካሽ ልምዶችን ለማስወገድ በባህል ለማደግና የቴክኖሎጂ ውጤት ተጠቃሚ ለመሆን የልጆቿን እጅ የምትማጠን እናት ሀገር፡እጆቿን ዘርግታ በሐሳቡ ታየችው
ከሐሳቡ ፋታ አግኝቶ እሱነቱን ወዳለበት ሲመልስ ምሶን ዐይኑን አፍጥጦ ተመለከተ ።አስተያየቱ አላማረውም ። በልቡ ምርምርህን እዚያው ዩኒቨርስቲው ውስጥ አድርገው ፥ ይሄ መጠጥ ቤት ነው የሚለው መሰለው "
እና እስክንድር ብርጭቆውን አነሣ መጠጣት ! ለጊዜውም ቢሆን ራስንም አካባቢንም ለመርሳት ህሊናን ለማዘናጋት
መጠጣት!

“ ስማ እንጂ እስክንድር እየመሸ ኮ ነው ! ” አለው ሳምሶን ዐይኑን አጉረጥርጦ "

“ እ ? እሺ • እንሒድ እንዴ ? ”

ሁለቱም ብርጭቆአቸውን አጋብተው ብርቅነሽ እስክትመለስ ጠበቁ አቤል ሶስተኛው ቢራ ላይ በግማሽ ተሸንፏል።

የብርቅነሽም ልብ ከእነሱው ጨዋታ ጋር ቀርቶ ስለ ነበር የታዘዘችውን በፍጥነት አቀራርባ ተመለሰች "

“ መሔዳችን ነው እንግዲህ ” አላት እስክንድር ለመነሣት እየተንጠራራ ።

“ ተጫወቱ እንጂ 'ምነው ? ” አለች' አቤል አጠገብ እየተቀመጠች ።

“ እንሒድ እባክሽ ! ገና መውደቂያችንንም አላዘጋጋጀን ” አላትና “ አንቺም ከሦስታችን አንዳችንን ይዘሽ ማደር አለብሽ ” አላት ።

ከሦስታችሁ በዕድሜ ልጅ የሆነውን ነው የምፈልገው ።

“ እንዴት ታውቂያለሽ? ግንባራችን ላይ አልተጻፈ!”

ውይ በደንብ ያስታውቃል አሁን ለምሳሌ እሱ በዕድሜ ልጅ ነው ” አለች አቤልን እንደ ማቀፍ ክንዷን ትከሻው ላይ ጣል አድርጋ ። “ ሳምሶንም ሰውነቱ ፋፋ
እንጂ ጢም እንኳ የለውም ። ባንዴ የተመዘዘ ሰውነት መሆኑ ያስታውቃል ።
እናትሽን ! ” አላት ሳምሶን ሣቅ አፍኖት ።
“ በይ ቀጥዪ እኔስ ?” አላት እስክንድር

“ አንተ እንኳ ጠንዝተሃል ፡ ታስታውቃለህ ” አለችው እየሣቀች።

“ ያጠንዛሽ ! ” አለ እስክንድር ፥ በልቡ እየሳቀ ወደ አቢል ጆሮ ተጠግቶ ፥
ከእንግዲህ የካምፓስ ፖሊሶች አያስገቡንም።መሽቷል።እዚሁ ከብርቅነሽ ጋር ማደርህ ነው” አለው ።

አቤል በቋንቋ መልስ መስጠት አልቻለም በእሺታ ቅንድቡን ሽቅብ ቀልሶ ፈቃደኛነቱን ገለጸ። ፍላጎቱ አለው ።
ግን እንዴት ይሆናል ? ያለ ገንዘብ ይታደራል እንዴ ?

አይዞህ " ችግር የለም ” አለው ሳምሶን ግር እንዳለው አይቶ ።

አቤል በአልኮል የደከሙ ዕይኖቹን እንደገና አስለምልሞ በእሺታ ግንባሩን ነቀነቀ።

የአቤል የደከመ ገጽታ እስክንድር ላይ አንዳች የሀዘን ስሜት ፈጠረበት ። ለእምነቱ ግትር የነበረው አቤል ክፉኛ እየተረታ መምጣቱን ገመተ። እነሆ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሴት ጋር ውጭ ለማደር ፈቃደኛ ሆነ ።.ሴት ልጅ ክንዷን
ትከሻው ላይ ስታደርግ ወይም ስታቅፈው ተቃውሞ አላሳየም ። በዚች ቡና ቤት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ትዕግሥት ከአፉ አውጥቶ ተናገረ ። በእምነት ግትርነት ተወጣጥሮ የቆየ እሱነቱ ሳላ : ይህ መጠጡ የፈጠረው የአካል ድካም ብቻ አይደለም ፤ የመንፈስ መድከም ነው መንፈስ ሲደክም ደግሞ አካልም ይዝላል ምላስም ይተሳሰራል ሰውነት ከአድራጊነት ወደ ተመልካችነት ወይም ታዛቢነት ይሸጋገራል ።

እስክንድር በልቡ ይህን እያሰበ '' ታዲያ አቤል ጓደኛዬ መንፈሱ ሲደክም፡ በማበረታታትና የቀድሞ እምነቱን
በመጠበቅ ፈንታ' ሲሸሸው ወደ ቆየው ተግባር መጨመሩ ትክክል ነው ? ” ሲል ራሱን ጠየቀ ።


ያስፈልጋል : አንዳንዴ ራስን መርሳት ያስፈልጋል ሁልጊዜ ራስን አስታውሶ እንደ ምን ይቻላል? አቤልም ዛሬ ራሱን ይርሳ ! እርሱነቱን በተለየ ገጽታው ይመልከተው ።
ሕይወት ዥጉርጉር ናት ” እያለ ሲያስብ ፡ አልኮል የማይበግረው ኅሊናው ጦሩን መዝዞ ተነሣበት ። እስክንድርም
ጋሻ ይሆነው ዘንድ የቢራ ጠርሙሱን አነሣ ። ነገር ግን ጨርሱ ባዶ ነበር ።

“ እንሂድ እንጂ መኝታ ከያዝን በኋ ከፈለግክ ሌላ ጋር እንጠጣለን አለው ሳምሶን በቁጣ ድምፅ።

ወዲያው ሂሳቡን ክፍሎ ተነሣና ብርቅነሽን ጠቀሳት ። እስከ ውጭ በር ተከተለችው ። ገንዘብ በእጅዋ ሲያስጨብጣት “ ዋ ! ልጁ ምንም አያቅም ብለሽ
እንዳትፈነግይው ” ሲል አስጠነቀቃት ።

“ እኔ ብርቅነሽ ? ሥራዬም አይድል ። ይልቅ ቻው ! ”ብላው ገባች።

እስክንድር ከአቤል ጋር ጠዋት ጆሊ ባር ለመግናኘት ቀጠሮ ሰቶት ወጣ።

ሳምሶን ብቻ ዛሬ በረንዳ እንዳናድር
አለው እስክድር በስሥጋት ።

"ግድ የለህም፥ ገና ሰዓት አለን አለ ሳምሶን ፥ ፊት ለፊት እየቀደመ።

ሁለቱ ከሔዱ በኋላ'አቤልና ብርቅነሽ ተፋጠው ቁጭ ሆነ ከመሐከላቸው ቃል የሚተነፍስ ጠፋ ። ብርቅነሽ ዐልፎ ዐልፎ “ ተጫወት እንጂ ” እያለች ብትጎተጉተውም አቤል ምላሱ ሊፍታታለት አልቻሉም ። ወንድ ሴት
ልጅን ምን እያለ ማጫወት እንዳለበት ገና አላወቀም ።

ወይም መኝታ ክፍልህን ላሳይህ ? ዐረፍ የምትል ከሆነ አለችው ።

“ ብቻዬን ? አላት ድምፁ በመጠጡም በፍርሀትም ተወላግዶ

“አይይ እኔም እመጣለሁ ነገር ግን ከአምስት ሰዓት ተኩል በፊት ሥራ ለመፃቆም ባለበትየዋ አትፈቅድልኝም
እስከዚያ ድረስ እንተ ገብተህ ዐረፍ በል ” አለችው እየሣቀች።

“እሺ በይ አሳዪኝ ። ”

ከቡና ቤቱ በስተጀርባ ከሚገኝ አንድ ክፍል ውስጥ አስገብታው ተመለሰች "
አቤል ቶሎ ልብሱን አላወለቀም አልጋው ላይ ተቀምጦ ጣራ ግድግዳውን ይመለከት ጀመር ። አልጋው ገና
ቁጭ ሲልበት እሮሮውን አሰማ እየተንቃቃ አቃሰተ ። ለዕረፍት ሳይሆን ለድሪያ የተዘጋጀ አልጋ ። ክፍሉ የቤት መልክ አልነበረውም ሆኖም አቤል ይህን ሁሉ ለማጤን አልቻለም ። እግሩን ሳያወጣ በጎኑ አልጋው ላይ ጋደም ሲል ሰማይ ምድሩ ብዥዥ አለበት ። የሚሽከረከር ወሰለው ዐይኑን ዘጋ ። አሁን ደግሞ ክፍሉ ሳይሆን የገዛ ጭንቅላቱ የሚሽከረከር መሰለው ። ብርቅነሽ በሐሳቡ መጥታ ዕርቃኗን ከፊቱ
ቆማ ብዥታውን አበረደችለት ሰውነቱ በወሲብ ግለት ተወማበጠረ ። ቸኮለ ዐይኑን ሲገልጥ ግን ከፊቱ የቆመ ነገር
አልነበረም " ወና ቤት ! ወናነቱ ያስፈራል ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ጥንድ የመሆን ተስፋ በልቡ ባይቀረጽ ኖሮ አቤል ወናውን ክፍል ሸሽቶ በፈረጠጠ ነበር ።

ወናነቱን ላለማየት ወይም ቀድሞ ያየውን እርቃን ደግሞ ለማየት እንደገና ዐይኑን ጨፈነ " የብርቅነሽ ዕርቃን በድጋሚ ሊታየው አልቻለም በምትኩ የሌላ ድምፅ በጆሮው ውስጥ አስተጋባ "
ብር አምባር ሰበረልዎ !
ብር አምባር ሰበረልዎ !
ሸጋው ልጅዎ ! ”

የእስክንድር እና የሳምሶን ድምፅ መሰለው ፡ ጆሮው የሰማ የመሰለውን በዐይኑ ለማረጋገጥ ዐይኑን ገለጠ አሁንም ምንም ነገር የለም ። ዐይኑን እየጨፈነና እየገለጠ ከቅዠቱ ጋር በመጫወት ላይ እንዳለ እንቅልፍ አሸለበው ።

የክፍሉ በር ሲበረድ ከእንቅልፉ ባነነ ብርቅነሽ ነበረች የደም ሰንበር በተጋደመባቸው ዐይኖቹ ውስጥ
ግዙፍ ሆና ታየችው ። ንቅሳቷ ባለበት የሚርገበገብ መሰለው።

"አልተኛህም እንዴ ? ”
"እ ? ”
“ አልተኛህም ወይ ? ”
ገና ከመግባቷ ተወርውራ አጠገቡ ቁጭ አለች « ዘለለና አቀፋት ። ቶሎ ልብሱን አወለቀ፡ ጭኑና ጭኗ ስለ ተጠጋ
ክፉኛ ሞቀው ።

“ አንዴ ቀና በል ፤ የኔ ሸጋ ”

“ እ ? ”

“ አንዴ ቀና በልልኝና በሩን ቆልፌ ልብሳችንን እናውልቅ
ቁና ቁና እየተነፈሰ ቀና አለ " የሴት ልጅ ገላ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጠጋቱ በወሲብ ስሜት የልቡ ትርታ ክፉኛ
ይነጥርበት ጀመር ።......

💥ይቀጥላል💥
👍1