አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)


......ከተደጋጋሚ ጥዝ የሚል አስፈሪ ድምፅና መንቀጥቀጥ በኋላ ጄሶው ተፈልቅቆ ወጣ፡፡ እጄን እንድዘረጋውና እንዳጥፈው አዘዘችኝ፡፡ የቀደመውን ያህል አይታጠፍም አይዘረጋም፡፡ ዶክተሯ እጄ
ላይ የቀረውን ጥጥና ቆሻሻ በአልኮል እያፀዳችልኝ፡፡

“ጥሩ ነው፡፡ በየቀኑ ለተወሰኑ ደቂቃዎች እንደዚህ እያደረክ ካለማመድከው፣ ወደ ቀድሞው ቦታ ይመለሳል፤” አለችኝ፣ በእጆቿ እጄን እጥፍ ዘርጋ እያደረገች እያሳየችኝ፡፡

“እሱን ሃላፊነት እኔ እወስዳለሁ፡፡ አመሰግናለሁ ዶክ፤” አላት ዶክተር ሄኖክ ፈገግ ብሎ፡፡ ወደኔ ዞር አለና፣
“እንኳን ደስ አለህ ያቤዝ! አሁን ህክምናህን ጨርሰሃል፡፡” አለኝ
እጄን ይዞ እየወጣ፡፡ ምንም
አልመለስኩም፡፡ አሁን ከሆስፒታል ውጣ
ከተባልኩ የት እንደምሄድ፣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ሃሳብ በአንዴ በድን አደረገኝ፡፡ እጄን እንደያዘኝ የሆስፒታሉን ዋና በር አልፈን ወጣን፡፡ዝምታዬን ሊሰብር፣

“ሆስፒታላችንን እንዴት አየኸው?” አለኝ፡፡
“አሪፍ ነው፡፡” በአጭሩ መለስኩ፡፡ የት እንደምሄድ፣ በምን ገንዘብ እንደምሄድ ጨንቆኛል፡፡ ለዚህም ዶክተርን ማስቸገር እንደሌለብኝ እያሰብኩ ነው፡፡ የሆስፒታሉ በር አካባቢ ወደ ቆሙ ታክሲዎች ሄድን፡፡
ፒያሳ፣ አራዳ እያሉ ይጣራሉ፡፡ ሁሉም ሃገር ፒያሳ አለ ማለት ነው?
ከዚህ በፊት የት ነበር የሰማሁት? አዎ፣ ደሴ፡፡ ስለ ፒያሳ ማሰብ ጀመርኩ። ከሚያስጨንቀኝ ሃሳቤ ፒያሳ ነፃ አወጣችኝ፡፡ ዶክተር አንዱ ታክሲ ውስጥ ይዞኝ ገባ፡፡ ታክሲው የት እንደጠራ አልሰማሁም፡፡ ከቀልቤ አልነበርኩም፡፡ የጎንደርን ፒያሳ ምን እንደምትመስል ለማየት ጓጓው::የተወሰነ እንደሄድን፣ የታክሲው እረዳት፣

“አስራ ስምንት ወራጅ አለ?” ብሎ ጠየቀ፡፡

“አዎ፡፡ ና እዚህ ነን፤” ብሎኝ ዶክተር መውረድ ጀመረ።ተከተልኩት፡፡ ከታክሲው ወርደን ትንሽ እንደተጓዝን፣
“አሁን የምንሄደው ወደኔ ቤት ነው :: ወደ ቤተሰብም ለመሄድ ሆነ ስራ ለመጀመር ተረጋግተህ እስክትወስን እኔ ጋር ትሆናለህ፡፡ ካሁን በኋላ እንደ ሃኪምህ ሳይሆን፣ እንደ ወንድምህ፣ እንደ ጓደኛህ ልታስበኝ ትችላለህ፡፡ ምንም ነገር አታስብ፤ ምትፈልገው ነገር ካለ ምንም
ሳትጨነቅ ልትጠይቀኝ ትችላለህ፡፡”

“አመሰግናለሁ ዶክተር፡፡ መቼም የማልከፍለው ውለታህ አለብኝ፡፡ የት እንደምሄድ በጣም ጨንቆኝ ነበር፡፡”
ትልቅ የብረት በር ያለው ግቢ ጋር ስንደርስ፣ ዶክተር በሩን በቁልፍ ከፍቶ ገባን፡፡ ሰፊ ንፁህ ግቢ፣ መሃል ላይ የቆመ ትልቅ ቪላ፣ ዙሪያውን የተደረደሩ ስርቪስ ቤቶች፣ ዶክተር ቪላውን አልፎ ጥግ ላይ
ያለች ሰርቪስ ክፍል ከፍቶ ገባ፡፡

“ግባ፡፡ እንግዲህ የወንደ ላጤ ቤቴ ይቺ ናት፡፡ ብቻዬን ነው ምኖረው፡፡ ካሁን በኋላ እንጋራታለን፡፡ አንድ ቁልፍ እንካ፡፡”

“ደስ ትላለች፡፡” አልኩኝ ወደ ውስጥ ገብቼ ዙሪያውን እየቃኘሁ፡፡መለስተኛ አንድ ክፍል ቤት፣ መሃል ላይ በመጋረጃ ተከፍላለች።ከመጋረጃው ጀርባ አልጋ እንደሆነ ገመትኩ፡፡ ቴሌቪዥን፣ በመፅሃፍት የተሞላ የመፅሃፍት መደርደሪያ፣ ዱካዎች፣ እቤት እንደሚያበስል የሚናገሩ እቃዎች፡፡ ዶክተር አንዲህ እንደሚኖር ገምቼም አላውቅም፡፡እኔ ከዚህ በጣም የተሻለ ንሮ ነበረኝ፡፡

“ቁጭ በል እንጂ፤ ቆመህ ቀረህ እኮ...” አለኝ ዶክተር ወደ ዱካዎች እያመለከተኝ፡፡ አንዱን ስቤ ተቀመጥኩ፡፡ወዲያው ዶክተር
ምግብ ማብሰል ጀመረ፡፡ አንዳንድ ነገር እያቀበልኩት ቆንጆ ሽሮ ወጥ ሰርቶ ምሳ በላን፡፡ በጣም ይጣፍጣል፡፡ የቤት ምግብ ናፍቆኝ ነበር፡፡ እቃ በማጠብ የቤተኝነት ስሜት እንደተሰማኝ ለማሳየት ሞከርኩ። ስንጨርስ ፒያሳ ወስዶ ከተማውን አሳየኝ፡፡ ፑል ተጫወትን፤ ሲመሻሽ ከፒያሳ
ወደቤት ወክ እያደረግን ተመለስን፡፡ ስንመለስ መንገዱ ቁልቁለት ስለሆነ
ነው መሰለኝ፣ ቅርብ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡

ህይወት እንዲህ ቀጠለች፡፡ የኪስ ገንዘብ ይሰጠኛል፡፡ እርሱ ወደ ስራ ሲሄድ ከተማ ወጣ ብዬ ሻይ ቡና እላለሁ፡፡ እረፍት ሲሆን ከተማ ወጥተን ሻይ ቡና ብለን ፑል ተጫውተን እንመለሳለን፡፡ ስራ ከዋለ፣
ከስራ ሲመጣ ወክ እያደረግን እንጨዋወታለን፡፡ ዶክተር የሰጠኝ ፍቅር
አሁንም የሚፈልጉኝ ሰዎች እንዳሉ ተሰማኝ፡፡ እንድነቃቃና መኖር እንዳለብኝ እንዳስብ አድርጎኛል፡፡ በጣም ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነው::ስራ መጀመር እንዳለብኝ እያሰብኩ ነው፡፡ እርሱ ስራ ሲሄድ፣ በብዛት
ከተደረደሩት የስነ አዕምሮ መፅሃፍት እያነሳሁ፣ ስለ ባይፖላር ለመረዳት በብዛት በቤቱ ከደረደራቸው የስነ አዕምሮ መፅሃፍት እየመረጥኩ ሳነብብ እውላለሁ፡፡

#ህመም_አልባው_በሽታ

ዶክተር የባይ ፖላር በሽታ አለበህ ካለኝ ቀን ጀምሮ፣ ስለ ባይፖላር የማወቅ ፍላጎቴ ጨምሯል፡፡ መድሃኒት ከጀመርኩኝ በኋላ እያየሁ ያለሁት ለውጥ ጥሩ ስሜት ፈጥሮልኛል፣ ከቀደመው ስሜቴ
ጋር ሳነፃፅረው፣ አሁን የተለየ የተረጋጋሁ ይመስለኛል። አለምን የማይበትን መነፅር የቀየርኩ ያህል ልዩነት ይሰማኛል፡፡ ባይ ፖላር ግን ምን ማለት ነው...? እብድ ማለት ነው...? ወፈፌ...? ቀውስ ማለት
ይሆን...? ሆ...ሆ... ኧረ በጭራሽ...! እኔማ ቀውስ አይደለሁም፡፡
እንትና ቀውሱ፣ እንትና እብዱ፣ ያ ሾጡ፣ ቅብርጥሱ፣ ምናምን ሲሉ እሰማለሁ፡፡ ህመሞች ይሁኑ ስድቦች አይገቡኝም፡፡ እኔን ማንም እንዲህ ሲለኝ አልሰማሁም፡፡ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ሆኖ ይሆን እንዴ?
ኖ.ኖ. እብድማ ብዙ ግዜ ተብዬ አውቃለሁ፡፡ እና ባይፖላር እብድ
ማለት ነው? ስለበሽታዬ ለማወቅ በየቀኑ አሰላስላለሁ። ዶክተር እንዳለው፣ ታምሜ ከነበር ይኼ በሽታ ህመም አልባ በሽታ ነው፡፡ ዶክተር ስራ ሲሄድ፣ እቤት ያለውን ስራ ጨርስና፣ ከተደረደሩት የስነ አዕምሮ
መፅሃፍት፣ እየቀያየርኩ አነበብኩኝ፡፡ አብዛኞቹ በሽታዎች ተመሳሳይ ሆኑብኝ፡፡ አንዱን ከአንዱ መለየት ቸገረኝ፡፡ ዶክተርን ማብራሪያ እንዲሰጠኝ ሚመቸውን ቀን መጠበቅ ጀመርኩ፡፡

አንድ ቀን ዶክተር አዳር ስርቶ ጥዋት መጣ፡፡ ከሰዐት ምሳ በልተን ፀሃዩ በረድ ሲል እንደተለመደው ወክ ልናደርግ ከቤት ወጣን፡፡በአባ ሳሙኤል አድርገን ቁልቁል ወደ እየሱስ መውረድ ጀመርን፡፡ ዛሬ
ለቀናት ያጠራቀምኳቸውን ጥያቄዎች ላዘንብበት ተዘጋጀሁ፡፡ ከግቢ
ወጥተን ትንሽ እንደተጓዝን፤

“ዶክ ጥያቄ ልጠይቅህ ፈልጌ ነበር”

“ጣድያ ምን ችግር አለው፣ ጠይቀኛ፡፡”

“ዶክ ባይፖላር አለብህ ካልከኝ ጀምሮ ስለበሽታው ለማወቅ ብዙ ሞክሬያለሁ፡፡ ብዙ አነበብኩ፤ ግን አልገባኝም፡፡ አስረዳኝ?”

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
#ሰመመን


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

ከተማሪ ጋር መውጣትም፡“ ለለውጥ ያህል ይመስላል ። እስክንድርም ስሜቱን የሚያነቃቃ ልብስ ባለመልበሷ በልቡ በሽቋል ።

በል እሺ ጨዋታ አምጣ ” አለችው በመጓዝ ላይ እንዳሉ ። ለተወሰኑ ሴኮንዶች በሁለቱም ዘንድ ጸጥታ ሰፍኖ ነበር።

“ ታዲያስ ' ትምህርት እንዴት ነው ? ” አላት ፡ የጨዋታ አርዕስት እንዴት እንደሚጀመር ግራ ገብቶት እባክህ ሌላ ጨዋታ አምጣ የትምህርት ወሬ ራስ
ምታት ሆኖብኛል!” አለችው ።

ምነው ?
“አስጠላኛ ! ሰው ስንት ዓመት ይማራል ?”

ዕድሜውን ሙሉ ነዋ !” አላትና ፈገግ ብሎ፥ “ግን ኮ ትምህርት የሚጠላ ነገር አይደለም ። ካልቪስ በሕይወት ውስጥ እንደ ትምህርት ጣፋጭ ነገር የለም ። የዘመኑ እኛነታችን ራሱ የትምህርት ውጤት ነው ። በሕይወት ላይ ትምህርት ያላስከተለው ለውጥ ምን አለ ?እስኪ ከምንራመድበት አስፋልት ጀምረሽ አካባቢሽንና ዐለምን በዓይነ ሕሊናሽ ዳስሺው ዕድገቱና ሥልጣኔው ሁሉ የትምህርት ውጤት ነው ። የሰው ልጅ በትምህርት ኃይል መልሶ እስከ መፍጠር የደረሰበት ሰዓት ነው ፡ እና ትምህርት
የሚጠላ ነገር አይደለም ” አላት ' ዮናታን “ ትምህርት የሚገላገሉት ዕዳ አይደለም ” ያሉትን እያስታወሰ ።
“ በእርግጥ እኛ አብዛኛውን ጊዜ ትምህርትን የምንመለከተው ጨርሰን ከመገላገሉ አንጻር ነው ። ይህ ጠባብና
ደካማ አመለካከት ይመስለኛል ። ትምህርት ሕይወት ነው ።አያልቅም ። እኛ እንድንጠላው : ከግልግል እንድንቆጥረው
የሚያረጉን ነገሮች የትምህርት መስክ አመራረጣችንና የትምህርት አሰጣጡ ሁኔታዎች ናቸው የትምህርት መስክ
ጠብቦ መታየት የለበትም ። እያንዳንዷ የሕይወት እንቅስቃሴ የምትበለፅገውና የምታድገው በትምህርት ነው ። ”

ተወኝ ባክህ ! ይልቅ የናንተ ትዕግሥት ይገርመኛል ።

ዩኒቨርስቲ አራት ዓመት መቆየታችሁ ። ”

“ ምነው ? እንዴት ? ”

“ በጭንቀትና በወጥረት ግቢ አራት ዓመት ሙሉ ? ትዕግሥታችሁ ይገርመኛል

ምን ታረጊዋለሽ ! የህልውና ትግል ነው ። ሁሉም የማይረሳኝ የውጥረትና የጭንቀት ጊዜ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ በነበርንበት ጊዜ ያሳለፍነው ነው ። የገናን ማዕበል እስክገናልፍ ድረስ ካምፓስ ውጭ ብቅ ብለን አናውቅም ነበር ። ዕውቀቱ ሳያንሳቸው ጭንቀቱ ብቻ የሚጥላቸው ልጆች ነበሩ ። በተለይ እኔ አጠገብ ይተኛ የነበረ ልጅ እስካሁን ትዝ ይለኛል ። ሴሚስተሩን ሁሉ ልብሱን አወልቆ መኝታ ውስጥ ገብቶ አያውቅም ። መጽሐፍ ወይም ደብተር እንደ ያዘ " ልብሱን ሳያወልቅ ፥ አልጋው ላይ ጋደም ይልና ማንበብ ይጀምራል ። እንቅልፍ እያንገላጀው ያነባል ፤
ጥቂት ቆይቶ ደብተሩን እንደያዘ ዐይኑን ይከድናል ። ደሞ ትንሽ ድምፅ ሲሰማ ይባንናል ። ያሳዝነኛል ። “ ለምን አትተኛም? ከፈለግክ እኔ ሌሊት እቀሰቅስህና ታጠናለህ ። ኣሁን ተኛ እለዋለሁ ። “አይ ደህና ነኝ” ይልና ዐይኑን በጣቶቹ ደባብሶ ማንበብ ይቀጥላል ። አፍታም ሳይቆይ እንደ ጎና ያንቀላፋል ። እንዲህ እንዳለ ያነጋታል እንጂ ፥ ጨክኖ
ልብሱን አውልቆ ቀደንበ አይተኛም ። ታዲያ የሚያጠናው።ነገር እንደማይገባው ይሰማኝ ነበር ። በዚያ ላይ እንደዚያ
ሆኖ አድሮ ጠዋት “ሌክቸር' መቀበል አይችልም ። መጨረሻ ያው የገና ማዕቀል ጠርጎ ከዩኒቨርስቲ አባረረው ። እሱስ ተገላገለ እንጅ ተባረረ አልልም ። ትንሽ ቆይቶ ያብድ ነበር ።
የሚያሳዝነኝ ግን አምስቱን የትምህርት ዐይነት“ፍላት ነው የወጣው

“ ውይ ምስኪን ! ” ብላ ማርታ ከንፈርዋን መጠጠች ።
“ አዎ ! ታዲያ እንዲህ ዐይነቱ ችግር ከምን የመጣ ይመስልሻል ? ተማሪው ስለ ትምህርት ያለው ደካማ አመለካከት፥ የትምህርት አሰጣጡና የተማሪው መመዘኛ ሥርዓት ፥እንዲሁም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ኋላ ቀርነት ተደራርበው የፈጠሩት ችግር ነው እንጂ ፥ ዩኒቨርስቲ በመሠረቱ የጭንቀትና የውጥረት ቦታ መሆን የለበትም ። ይልቁንም የጥበብና የምርምር ቦታ ነው

“ለማንኛውም ” ብል ፥ መናገር የፈለገችውን ሳትጨርስ አቋረጣት ።

“ አዎ ! ለማንኛውም አሁን ያለው ምርጫ በተሰጠን የትምህርት ክልልና መመዘኛ ውስጥ ተወዳድሮ ማለፍ ነው ። ፈትናም” ኮ ተቃርቦአል ።ቢበዛ ሦስት ሳምንት ነው
የቀረወ ። በርትተሽ ማጥናት ነው ። ”

ማን ይፈራል ሞት ! ” አለችው ።
እንዴት ? ”

ማለቴ ፥ እኔ መጨነቅ አልፈልግም ። ደግሞም ኢትዮጵያ ውስጥ እንደማልቆይ ዐውቃለሁ ።

እስክንድር በልቡ ፥ “ ይህ በእንክብካቤ የተያዘ ሰውነትሽ እንደምንስ ጭንቀት ይችላል ? ” እያለ “ የት ትሔጂያለሽ ? ” ሲል ጠየቃት ።

ውጭ ሀገር ነው ።

ሰባ ደረጃ ስለደረሱ ደረጃውን ሲወርዱ ማርታ የእስክንድርን ክንድ እንደ መደገፊያ አርጋ ያዝ አረገችው ።የእጅዋ ሙቀት በክንዱ አልፎ መላ ሰውነቱን ሲያዳርሰው
“ምነው ክንዴን ለቀሽ ወገቤን ወይም አንገቴን ብትደገፊ አለ በሐሳቡ።

ስኮላርሺፕ ልትጠይቂ አስበሻል እንዴ ? ”
“ ኖ ! ዋው ! ብቻ በሆነ መንገድ እሔዳለሁ ። ”

የት ? አሜሪካ ?” እላት በምጹት አነጋገር እሷን ከመሰሉ ሴቶች የሌላ አገር ስም አይጠበቅም ብሎ ነው ።

እንዳሾፈባት አልገባትም ። “ አዎ ! አሜሪካን አገር ወንድሞቼ አሉ ። እንግሊዝ አገርም የአክስቴ ልጆች አሉ ።እኔ ግን የአሜሪካኑ ይሻላል ብዬ በዚያ በኩል እየሞከርኩ ነው ” አለችው »

ቤተሰብሽ ሁሉ ውጭ ሀገር ናቸው ? ” ሲል ሸርደድ አረጋትና “ ለካ ቅድም እኔን ፈረንጅ ነህ ያልሺኝ አንቺ ፈረንጅነት ስለሚሰማሽ ነው ” አላት ።

“ ማሾፍህ ነው ? ”

እንደ በሸቀች ገባውና ፡ “ ማርትዬ ሙች ፥ ማሾፌ አይደለም የምሬን ነው ” አላት ።

“ደግሞ እንድታቆላምጠኝ የፈቀደልህ ማነው ? ማንም ወንድ ሳያስፈቅደኝ ሊያቆላምጠኝ አይችልም ።”

“ ውበትሽ እንዳቆላምጥሽ ቢያስገድደኝስ ? ”
“ውበቴንም ለማድነቅ ቢሆን ፈቃድ ያስፈልጋል ።
“ በተለይ ሴቶች ! ” አላትና ክንዱን የያዘችበትን እጅዋን ጭብጭ አርጎ «ወደ ጎኑ አስጠጋት ።

“ሂድ ደረቅ ! ”
"የት ልሒድ ” ርጥብ !”
ሁሉንም “ ደረቅ ” ማለት ስለሚቀናት እሱ ደግሞ "ርጥብ ” እያለ ያበሽቃታል

ደረጃውን ወርደው ወደ ግራ ከታጠፉ በኋላ ። “ ከቤተሰቦችሽ ጋር ነው የምትኖሪው ? ” ሲል ጠየቃት ።

ለምን ጠየቀኝ ብላ አልተመራመረችም ፤ወይም አልተደናገጠችም ።
“ ዳዲ የለም ። ወንድሞቼም እንደ ነገርኩህ ውጭ ናቸው ። እኔና እናቴ ብቻ ነን እዚህ ያለነው ።

“ እባትሽ የት ሔዱ? ”አላት በኀዘኔታ ዐይነት ።

“ ሔቨን” አለችው፥ መሞታቸውን ብቻ ሳይሆን መጽደቃቸውንም ለማስገንዘብ ።

እስክንድር አንዴ " ሥነ ልቦና ትምህርት ክፍለ ጊዝ መምህሩ በነገራቸው ቀልድ ውስጥ በምድር ላይ ለድሀ የመጸመተው አምስት ሳንቲም ተመልሰለት ከገነት በር የተባረረረው ሰው ትዝ አለውና • “ የማርታ አባት በምድር ላይ ብዙ ገንዘብ መጽውተው ነበር ማለት ነው” ሲል በልቡ ቀለደ

ግን ምን ሆነው ሞቱ ? ”
“ምን ያደርግልሃል?” አለችና አመንትታ ዝም አለች።

እስክንድር ምክንያቱን መናገር እንዳልፈለገች ገባውና ምናልባት የአብዮቱ ባቡር ጨፍልቆአቸው ይሆናል ብሎ ዝም አለ ። ለጥቂት ሴኮንዶች ሁለቱም ዝም ተባባሉ ።

አደራሽን ማርታ! ፈረንጅ ሀገር ስትሔጂ ነጭ እንዳታግቢ አላት እስክንድር ጥቂት ሲያስብ ቆይቶ ።

ለምን ? ምነው ?”

ስም የለሽ ካፊቴሪያ በር ላይ ስለደረሱ እሷን አስቀድሟት ገቡና ጥግ ቦታ መርጠው ተቀመጡ ። ብዙ ሰው አልነበረም ። ሞቅ ያለ የፈረንጅ መዚቃ ቤቱን ያናጋዋል ።
👍2
አሳላፊው መጥቶ " “ ምን ልታዘዝ ? ” ሲል ከፊታቸው ቆመ ። እስክንድር ማርታ እንድታዝ ቅድሚያ ስጣት ።

ከጭማቂ ዘር ምን አላችሁ ? ” ስትል አሳሳፊውን ጠየቀችው

“ ለምን ሌላ ነገር አትጠጪም ? ቢራ ምናምን ? ” አላት እስክንድር ለማግደርደር ያህል

“እኔ የፍራፍሪ ጭማቂ ነው የምፈልገው ” አለችና

ወደ አሳላፊው ተመለከተች "

"ፓፓዬና ብርቱካን ”አለ አሳላፊው ።
“ ለኔ የብርቱካን ጭማቂ” አለች ማርታ"
“ በል እሺ፡ ለኔም እንደዚያው” አለ እስክንድር አሳላፊው ከሔደ በኋላ እስክንድር ፡ “ የሚበላስ ነገር "
ሳንድዊች ምናምን ?” ሲል አግደረደራት

“ ምንም አልፈልግም ” ካላችው በኋላ ልቧ ተንጠልጥሎ ከቀረው ጨዋታቸው ላይ ተሰቅሎ ስለ ነበር፡ “ይልቅ ቅድም የውጪ ዜጋ እንዳታቢ ያልከኝ ለምንድን ነው?" ስትል ጠየቀችው ።

ለምን መሰለሽ ” አላትና እንዴት እንደሚገልጽላት በመቸገር ዐይነት ትንሽ ከቆየ በኋላ ኑሮሽ ጤናማ የሚሆን አይመስለኝም ” አላት።

“ እንዴት ? ”

አየሽ ! አንቺና የውጪው ዜጋ የተወለዳችሁበት ያደጋችሁበትና የኖራችሁበት አካባቢ የተለያየ ነው ። ባህላችሁ ይለያያል ። በምግብ ዓይነት ወይም ባአመጋገብ ሥርዓት ፥ በአለባበስ ሁኔታ በጨዋታ ዐይነቶች ፡ በመዝናኛ
ስፍራ አመራረጥ ፥ በእንግዳ አቀባበል ፡ በልጆች አስተዳደግ ከሁሉም በላይ ደግሞ አስተሳሰብና ማኅበራዊ ኑሮ አመ
ለካከት ልትለያዩ ትችላላችሁ ። ትዳር ማለት ደግሞ እኒህን ነገሮች መጋራት ነው እና በባህልም ሆነ በሥነ ልቡናዊ
አመለካከት ብቻ የተራራቁ ጥንዶች ትዳር የሚያምር አይመስለኝም ። ”

“ አባባልህ ልክ ልሆን ይችላል ነገር ግን ማንም ሰው በጋራ የሚፈልገው ነገር አለ ያም ያማረ ፥ የሠለጠነና የበለጸገ ኑሮ ነው የጋራ መሰረታችንን ወይም
ግባችንን ጥሩ ኑሮ አድርገን አንዳችን ከአንዳችን መማር እንችላለን።"

ሁለቱም የቀረበላቸውን የብርቱካን ጭማቂ ተጎነጩ ።አሳላፊው ሌላ የሚታዘዛቸው እንዳለ ለማረጋጥጥ ጥቂት ከቆመ በኋላ ተመልሶ ሔደ ።

“ ምን መሰለሽ ማርታ ነገሩ እንዲህ እንደምታስቢው ቀላል አይሆንም ” ሲል እስክንድር ቀጠለ አየሽ የአሁኑ አንቺነትሽ ክረዥም ዓመት አኗኗርሽና አካባቢሽ
የተገነባ ነው ። ይህን ግንባታ ማደሳ ወይም መለወጥ በጣም ከባድ ነው ። ሊሆንም ቢችል እንኳ ከባድ ትግል ጠንካራመንፈስና ብልህ ጭንቅላት ይጠይቃል።

እባክህ ተው ዋናው ነገር ፍቅር ነው። በሁለቱም መሐል መፈቃቀር ካለ ይህ ችግር አይፈጠርም ። ”....

💥ይቀጥላል💥
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)


...“በጣም ጎበዝ ያቤዝ፡፡ ስለ አለብህ የጤና ችግር ለማውቅ መፈለግ በጣም ጉብዝና ነው፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጥቅም አለው፡፡ ባይፖላር ዲስኦርደር ማለት፣ ሰዎች ሁለት የስሜት ዋልታዎች መፈራረቅን ተከትሎ፣ተደጋጋሚ የሚመጣ የባህሪ መለዋወጥ ሲያጋጥማቸው ነው።
መለዋወጦቹም፧ በስሜት ከፍታዎች እና በስሜት ዝቅታዎች መካከል የሚከሰት ነው:: በመሆኑም ይህ ችግር ያለበት ሰው፣ ባለበት የስሜት ከፍታ ወይም ዝቅታ መሰረት አሰተሳሰቡ፣ ውሳኔ አሰጣጡ፣ በነገሮች ላይ የሚኖረው ፍላጎት፣ ድርጊቶችን ለማድረግ የሚኖረው ሀይልና ጉልበት፣ በአጠቃላይ የህይወት አመለካከቱና አረዳዱ በሰዐቱ እንዳለው
የስሜት ሁኔታ የተለያየ ነው፡፡ በተጨማሪም፣ የዚህ ችግር ተጠቂ የሆኑ
ሰዎች ውስጣዊ ለውጦች ሊኖራቸው፣ አካባቢያቸው የተለወጠ ስለሚመስላቸው የሚሰጡት ምላሽ የተሳሳተ ሊሆን ይችላል፡፡

የዚህ ችግር ተጠቂዎች የስሜት ከፍታ ሲኖራቸው ማኒያ ወይም ሃይፖማኒያ ይባላል፡፡ ማኒያ ከሃይፖማኒያ ተመሳሳይ ምልክት ቢኖረውም፣ ማኒያ በህመም ደረጃው ከበድ ያለ በሽታ ነው፡፡ ይህ
የባህሪዎች መለዋወጥ፣ ችግሩ ያለባቸውን ሰዎች በስራ፣ በትምህርት፣
በማህበራዊ እንቅስቃሴያቸው እና ግንኙነቶቻቸው ላይ ችግሮች
ማወቅ እንዲከሰቱ ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ የስሜት ከፍታ ላይ ሲሆኑ፤ በፊት
ብዙም ትኩረት ማይሰጡትን ጉዳይ የማየት፣ የመስማትና የማወቅ ፍላጎት መጨመርን ያሳያሉ፤ ከነበራቸው ማህበራዊ መግባባት የጨመረ
የመቀራረብና የመግባባት ባህሪ ያሳያሉ፣ የማይጨበጡ፣ ወይም

ቶሎቶሎ ሚቀያየሩ አዳዲስ ሀሳቦችንና ንድፎችን በማምጣት ያወራሉ፤አንድ ቦታና አንድ ሃሳብ ላይ በጥልቀት ማስብ ስለሚያስጨንቃቸው ቶሎ ከሃሳብ ወደ ሃሳብ ይቀያይራሉ፣ በጥቃቅን ነገሮች አክርረው ይጨቃጨቃሉ፣ ነገሮቹ ከነርሱ ህይወት ጋር ጠቃሚ ግንኙነት ባይኖራቸውም፣ ስለሚሰሟቸው ነገር ከፍተኛ የማወቅ ፍፈላጎት ያሳያሉ፤ ለነገሮች ከተገቢው በላይ ይናደዳሉ፣ ይበሳጨሉ፣ ከብሰጭት ስሜት መውጣት ይቸገራሉ፣ የተጋነነ በራስ የመተማመን ስሜት ይኖራቸዋል፤ የሚያመጧቸውን ሀሳቦች ፍፁም አድርገው ያስባሉ፡፡
ትችትና አስተያየት መቀበል ይከብዳቸዋል እንደሚተገብሯቸው እርግጠኛ መሆን፡፡ የእንቅልፍ ፍላጎት መቀነስ፤ በፊት ከሚተኙበት ሰዓት ዘግይቶ መተኛትና ባልተለመደ ንቁ መሆን፤ ያልተለመደ
ወሬኛነት፤ ከማይግባቧቸውና ከማያቋቸው ሰዎች ጋር ጭምር
ያልተለመደ የማውራት ፍላጎት፤ ነገሮችን አብዝቶ ማቅለል፤ ደካማ ውሳኔ መስጠት ያስከትላል፡፡ የመሳስሉትን ምልክቶች የሚያሳዩ ሰዎች ሃይፖማኒያ ይባላል፡፡”

“ስለዚህ ዶክ፣ አንድ ሰው የተዘረዘሩት ምልክቶች በሙሉ ሊኖርበት ነው ይሄ ችግሩ አለበት ሚባለው?”

“ኖኖ! እንደዛ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ከላይ ከዘረዘርኳቸው ውስጥ፣ ሶስቱን ወይም ከዚያ በላይ ምልክቶች ካሳየና በሃኪም
ከተረጋገጠ ሃይፖማኒያ አለበት ልንል እንችላለን፡፡” በውስጤ አሰላሰልኩ፡፡ እነዚህ ስሜቶች ሶስቱ ሳይሆን ሁሉም ግዜ ጠብቀው፣እብደቴ ሲነሳ በደስታ ማስተናግዳቸው ሲሜቶች ናቸው፡፡

“ዶክ ከእነዚህ ስሜቶች አብዛኞቹ በተደጋጋ እኔን ሲስሙኝ ኖረዋል። ታዲያ ሃይፖማንያ ሳይሆን ለምን ባይፖላር አለብህ አልከኝ?”

ትክክል ነህ ያቤዝ፡፡ አንተ እነዚህ ስሜቶች ሲሰሙህ እንደከረሙ ነግረኸኛል፡፡ ነገር ግን፣ ሃይፖማንያ ሚባሉት እነዚህን
ስሜቶች ብቻ ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ አንተ ግን፣ እነዚህ ስሜቶች ብቻ አይደሉም ሲሰሙህ የነበረው፡፡ ሌላም ስሜቶች ነበሩህ፡፡”

“ሌላ ስሜትም ስትለኝ፣ ሌላ ምን አይነት ስሜት?"

“አንተ የሃይፖኒያ ስሜቶች ብቻ ሳይሆን የነበረህ፣ ግዜን ጠብቆ ሚፈራረቅ የስሜት ዝቅታ ወይም የዲፕረሽን ምልክቶችም ነበሩህ፡፡”

“የስሜት ዝቅታ /የዲፕረሽን/ ምልክቶችስ ምን ምን ናቸው?"

“የዲፕረሽን ምልክቶች የምንላቸው፤ ከፍተኛ ብስጭት፣ማህበራዊ መነጠል፣ ብቸኝነት ማብዛት፤ ከፍተኛ ምክንያት የለሽ የድካም ስሜት፧ የጡንቻ መዛል፤ ቁርጥማት፣ የጀርባ ህመም፤ የመረበሽ
ስሜት ፣ በስራ፣ በትምህርትና ቤተሰባዊ ሃላፊነቶች ከተገቢው በላይ መጨነቅ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ፣ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የመዝናናት የፍላጎት ማጣት፣ እንዲሁም፣ የጥፋተኝነት ስሜቶች፣ ዋጋቢስ እና ተገቢ ያልሆነ ራስን መቅጣት፣ በራስ የመተማመን ስሜት መቀነስ፣ ደካማ እና የቀነሰ ትኩረት፣ አፍራሽ እና መጥፎ ሃሳቦችን በተደጋጋሚ ማሰብ፣ ራስን የማጥፋት አስተሳሰብ እና ራስን የመጉዳት ወይም ራስን የመግደል ሙከራዎች እና የመሳሰሉት ምልክቶች ካሉበት፤ የዲፕረሽን ችግር አለበት ይባላል”

እነዚህ የበሽታ ምልክቶች ከሆኑማ
ታምሜያለሁ፣ሲፈራረቁብኝ ኖረዋል፡፡ ነገር ግን፣ ብዙ ሰው እንደዛ ሚሰማው
ይመስለኛል፡፡ ሃኒ በአምሮዬ ውልብ አለች፡፡ ትበሳጭ ነበር፤ ትናደድ ነበር፤ ብቻዋን መደበቅ ፈልጋ ስትመጣ ነው የተገናኘነው፣ እራሷን አጥፍታለች። እና ሃኒም እንደኔ የዲፕረሽን ታማሚ ነበረች ማለት ነው?፣ እራሷን ለማጥፋት ያደረሳት ይህ ህመም አልባ በሽታ ነበር ማለት ነው?

“እና ዲፕረሽን አሁን ከጠቀስካቸው ምልክት ሶስቱን ማሳየት ማለት ነው?”

“አይደለም፡፡ ዲፕረሽን እንደ ሃይፖ ማንያ በሶስት ምልክት ብቻ አይደለም፡፡ ከእነዚህ ምልክቶች መካከል አምስቱን ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑት አንድ ስው ደጋግሞ ሲኖረውና የእለት ተለት ህይወቱን እንዳይመራ ተፅእኖ ሊኖራቸው ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህን በሽታዎች
ሃኪም ሳያማክሩ ምልክት በመቁጠር ብቻ እንዲህ ነኝ እንዲያ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ግን ምልክቶቹ ከተደጋገሙና ከቆዩ ሃኪም ማማከር አስፈላጊ ነው፡፡”

“እነዚህም ምልክቶች እኮ በደንብ እንደነበሩኝ ነግሬሃለው ዶክተር፡፡ ታድያ ለምን ዲፕረሽንም አለብህ አላልከኝም? ህይወቴን እዚህ ያደረሱት እኮ አሁን የጠቀስካቸው ምልክቶች ሲስሙኝ ነው። ያማል፣ያላምጣል፣ ያመነዥካል፣ ሞት እንደ ጣፋጭ መድሃኒት ይናፍቃ፡ ዶክ፣
ስለዚህ እኔ ያለብኝ ችግር እንደውም ዲፕረሽን ነው፡፡”

“አየህ ያቤዝ፣ ቅድም ለዛ ነበር ሃኪም ሳያማክሩ ምልክቶችን ቆጥሮ ይሄ ነው፣ ያ ነው ያለብኝ፣ ማለት አይቻልም ያልኩህ፡፡ አንተ የሃይፖማንያም የዲፕረሽንም ምልክቶች እየተቀያየሩብህ አሳይተሃል፡፡
አንድ ስው የሃይፖማንያ ምልክት ብቻ ካለው፣ በሃኪም ከተረጋገጠ በኋላ ሃይፖማንያ አለበት ይባላል፤ የድባቴ ምልክቶች ብቻ ካሉበት፣ በሃኪም ከተረጋገጠ በኋላ የድባቴ ችግር አለበት ይባላል፤ የሁለቱ በሽታዎች ምልክት እየተፈራረቁ ከተሰሙት ደግሞ፣ በሃኪም ከተረጋገጠ በኋላ የባይፖላር ችግር አለበት ይባላል፡፡”

አሁን ለቀናት ሳነብ አልገለጥልህ ያለኝ ተገለጠልኝ፡፡ አይኔ በራ፡፡ዶክተር እያወራ ነው፡፡ “ባይፖላር ዲስኦርደር የዕድሜ ልክ ሁኔታ ቢሆንም፣ሕክምና በመከታተል የስሜት መለዋወጥን እና ሌሎች
ምልክቶችን በመቆጣጠርና መሰናክሎችን በማስቀረት በህይወት ስኬታማ መሆን ይቻላል፡፡ ባይፖላር
ዲስኦርደር በስነ ልቦና ምክር (ሳይኮቴራፒ)እና በመድኃኒቶች ይታከማል፡፡

በግማሽ ልቤ ነው ማዳምጠው፡፡ እኔ ወደ ውስጤ ተወሽቄያለሁ።ወደኋላ ተመልሼ በሃሳብ እየተብሰለሰልኩ ነው፡፡ ዶክተር እውነቱን ነው::ቅድም የጠቀሳቸው ስሜቶች ብዙ ግዜ ተፈራርቀውብኛል። ባይፖላር ዲስኦርደር፣ በጋና ክረምት የሚመሰሉ ስሜቶች መፈራረቅን ተከትሎ
የሚመጣ የባህሪ መለዋወጥ ነው፡፡ በጋ፣ ብርሀን ነው ፧ ተስፋ ነው ፤ በጋ ሙቀት ነው ፤ ሀይል ነው፤ መቦረቅ ነው፡፡ ክረምት ግን፣ ብርድ ነው ፤መሸሸግ፣ መኮራመት ነው፡፡ አዎ! የኔ
👍3😁1
ችግር ባይፖላር ነው፡፡

ለካ በጋ ስሆን ነበር፣ ሁሉን የማወቅ፣ ሰውና አካባቢዬን የመቅረብ ፍላጎቴረ ከፍተኛ የሚሆነው። ሃይልና ጉልበቴ ስርቼ
ማይደክመኝ፡፡ አላስተዋልኩም ነበር እንጂ፣ በውስጤ ክረምትና በጋ
ሲፈራረቁብኝ ኖረዋል፡፡ ክረምት፣ ብርድ ነው ፤ መሸሽግ፣ መኮራመት ነው፡፡ ክረምት ጭለማ፣ ፍርሀት ነው፡፡ አካባቢዬ የሚጨልምብኝ፣ ሁሉ ነገር ሚያስፈራኝና ሚያስጨንቀኝ፣ በሚረባ በማይረባው የምበሳጨውና የምነጫነጨው፣ መደበቅ መሸሸግ ምርጫዬ የሚሆነው፣ ሃይሌ ተሟጦ ሁሉ ነገር የሚስላቸኝ፣ ሁሉ ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ እየሆነብኝ ስራዬን
ምቀያይረው፣ ለካ ውስጤ ክረምት ሲሆን፣ ሲደምን፣ ሲጨልም ነበር፡፡
ለካ ታምሜ ነው፡፡ ህመም አልባ በሽታ፡፡

ወይኔ...! ሃኒም ታማ ነበር ማለት ነው፡፡ ለዛ ነው ክቡር ህይወቷን እንደቀልድ ያጠፋችው! እርሷን ታማለች ብሉ መገመት
ይከብዳል፡፡ እጅግ በጣም ውብና ማራኪ ነበረች፡፡ በዛ ላይ ገና አንድ ፍሬ ልጅ፡ እንደሷ ስንቶች ይሆኑ የአካላዊ ምቾታቸው የአዕምሯዊ በሽታቸውን የጋረደባቸው? ከቤተሰብ ጋር ካላት አለመግባባትና ብስጭት ውጪ ህመም ሚባል ነገር በፍፁም ያላት አትመስልም ነበር፡፡ አሁን ግን፣ ከምልክቶች አብዛኛውን እንደነበራት አስተዋልኩኝ፡፡ በእርግጥም
ብስጭቷ፣ መከፋቷ፣ ደስታ ማጣቷና እራሷን ማጥፋቷ ከቤተሰብ አለመግባባት ብቻ በፍፁም ሊሆን አይችልም፡፡ እርሷን የመሰለች ልጅ ብዙ ሌላ አማራጭ ማየት ነበረባት፡፡ ግን እንዴት እንደዛ አይነት
የተመቻት ምትመስልን ልጅ ታማ ነበር ብሎ መጠርጠር ይቻላል? ግን ግንዛቤው ቢኖረን ኖሮ፣ ንዴትና ብስጭቷ፣ ከቤተሰብ መሸሽ ምልክት ነበሩ፡፡ ለነገሩ እራሴንስ መታመሜን ያወኩት ገና አሁን አይደል።
እሷም እንደኔ ያዝ ለቀቅ ያደርጋት ነበር? እንደኔው ባይፖላር ትሆን ወይስ ድባቴ ብቻ? በውስጤ ለሃኒ ዳግመኛ አነባሁ፡፡ እርሷን ጠርጥሬ አላውቅም፡፡

ይገርማል! እንደታመሙ ሳያውቁ መታመምም አለ ለካ፡፡ ምንም ህመም የሌለው በሽታ፡፡ በግልፍተኝነት ያሳለፍኳቸው ደካማ ውሳኔዎች በአዕምሮዬ እንደፈጣን የፊልም ትዕይንት ውልብ፣ ውልብ እያሉ ያልፉብኛል፡፡ እንደኔ ባለ ስሜት ስንቶች እየተሰቃዩ ይሆን? አፍሶ መበተን የሰለቻቸው፣ ዘርቶ ማጨድ ሚቸግራቸው ስንቶች ይሆኑ?
ድንገት በአእምሮዬ ኤፍሬም ውልብ አለብኝ፡፡ ኤፍሬም መቼም ከውስጤ
አይወጣም፡፡ መንገድ ላይ ብቻውን ሚያወራ፣ የተጎሳቆለ ባየሁ ቁጥር
እርሱ ትዝ ይለኛል፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች አዕምሮዬ ስለሱ ያስባል፣ይተክዛል፣ ልቦናዬን ሃዘን ይጫጫነዋል፡፡ የኤፍሬምስ ችግር ምን ይሆን...? ሳሚ ወፈፌ ሲለው መዝገብ ቤታችን ቀውስ ብለውታል፣
ልዩነቱ ምንድን ነው? ማንኛቸው ነበሩ ትክክል? ስለ ሌሎች የአዕምሮ
ችግሮች የማወቅ ፍላጎቴ ጨመረ፡፡ ዶክተር ወደ እራሴ ተመልሼ
እያብሰለሰልኩ እንደሆነ ተረድቶ፣ ላለማቋረጥ ዝም ብሎ በእርጋታ ወክ
ያደርጋል። ስለሌሎች ህመሞች እንዲነግረኝ ፈለኩኝ፡፡ ኤፍሬምን
ማግኘት ፈለኩ፡፡ ሳናውቀው እርቀን ሄደናል፡፡ ዞብልን አልፈን ቸቸላ ሆስፒታል ልንደርስ ምንም አልቀረን፡፡

“እርቀን መጣን፡፡ እንመለስ?”

“ደከመህ? እሺ” ብሎ ዞረ፡፡ ዶክተር እረጅም ወክ ይወዳል።...


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ሰመመን


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ (MD)

...“ችግሩ ግን ፍቅሩ፥ ራቡ ትክክለኛ ምንጭ የለውም ፤እንዲሁም በስሜት እሳት ይጀምራል ። አብዛኛውን ጊዜ ደግም እንዲህ ዐይነቱ፡ ብቻ ቁሳቁሳዊ ይሆናል ። የረዥም ጊዜ መጠናናትና መፋቀርም የለም : በስሜት እሳት የተጀመረ ሚክስድ ማሬጅ” ደግሞ ዘላቂነት የለውም።ዓመት አብረው
ከቆዩ በኋላ፥ የስሜት እሳቱ (አንቺ ፍቅር የምትይው) ይቀዘቅዝና ለኑሮ ቦታውን ይለቃል። በዚያ ሰዓት በስሜት እሳት ተሸፍኖ የቆየው፡ በሁለቱ መሐል ያለው የአስተሳሰብ የአስተዳደግ እና የአኗኗር ልዩነት ብቅ ማለት ይጀምራል። ይልቁንስ
ይህን ዐይነቱ ጋብቻ ዘላቂነት ሲኖረው ያየሁት በጥብቅ ኃይማኖት በተሳሰሩ ሰዎች ላይ ነው ። ይህ የእምነት ጉዳይ ነው ።በአንድ ሃይማኖት ተከታይነት ተዋውቀው የተጋቡ አንድ ኢትዮጵያዊና እንዲት አሜሪካዊት ለረዥም ዓመት የሚያስቀና ትዳር እንደ ነበራቸው አስታውሳለሁ ።እንዲያውም መዉለድ ማቆም በፈለጉበት ወቅት ብልቱን በቀዶ ሕክምና ያስመከነው ኢትዮጵያዊው ወንድ ነበር ። ይህም የሚያሳየን ከነሱ ውጭ ከሆነ መለኮታዊ ኃይል ተጫኝነት ተሳስረው መኖ ተሳስረው መኖራቸውን ነው እንጂ የአካባቢ የአስተሳሰብና የባህል ልዩነት አስወግደዋል ማለት አይደለም ። ”

“ ድንቄም ” እንደ ማለት ያህል ከንፈሯን አጣማ ብርጭቆውን እነሣች ። የጨዋታቸው አርዕስት ቢለወጥ በወደደች ነበር ። እስክንድር ግን አርዕስቱን ሊለውጥላት አልቻለም ። እንዲህ ዐይነት ክርክር ሲነኝ ደስ ይለዋል፤ መላ ህዋሳቶቹ ይግላሉ። ሐሳቡና ነጥብ አመታቱ እያደገ ፥ እየጠነከረና እየተወሳሰበ ሲሔድ ለራሱም ይገርመዋል ከዕድገቱ ፡ ከኣካባቢውና ከትምህርት ቤቱ ብዙ ዕውቀት መቅሰሙን የሚያወቀው በእንዲህ ዐይነቱ የግለት ወቅት ነው ።

“ደግሞም የዚህ ዐይነት፡ የተደቀለ ጋብቻ ችግሩ በባልና ሚስቱ ላይ ብቻ አይቀርም ” ሲል ቀጠለ ፣ ይብሱን ችግሩ የሚነሳው በዊ ወልዷቸው ልጆች ላይ ነው ። ልጆቹ
እያደጉ ሲመጡ ራሳቸውን ከየትኛውም ወገን እንደሚያስቀምጡ ይቸገራሉ ። የሥነ ልቡና ጠበብቶች ይህንን ችግር
አይደንቲቲ ክራይሲስ ? ይሉታል ። ልብ ብለሽ እንሆነ አብዛኛውን ጊዜ ለሌብነት ለአልኮል ሱሰኝነት ፡ ለሲሰኝነትና ለመሳሰሉት ርካሽ ተግባራት የሚጋለጡት ከእንዲህ ዐይነት ቤተሰብ የወጡት ወደ እኛ ክልስ የምንላቸው ናቸው ። ስለ ራሳቸው የሚኖራቸው የተዘበራረቀና የተበላሸ ስሜት ይመስለኛል፡ ወደዚህ አድራጎት የሚመራቸው ”

ማርታ ክርክሯን መሸሽ አልቻለችም ። ዝም ብላ በከፊል ሙዚቃ በከፊል እሱን ስታዳምጥ ትቆይና በነገር ወጋ ሲያደርጋት ወይም አነጋገሩ አልጥምሽ ሲላት አንድ ቃል ጣል ታደርጋለች "

ልጆቹ እንዴት ራሳቸውን የሚያስቀምጡበት ቦታ ይጠፋቸዋል ? ከሁለት የተለያዩ ዜጎች ቢወለዱም የሚኖሩበትን አካባቢ መስለው ማደግ ይችላሉ ” ስትል ተገታተረችው።

አይችሉም ! ” አላት በስሜት ጭንቅላቱን እየነቀነቀ ። “ የሚኖሩበት አካባቢ የእናታቸው ወይም የአባታቸው እንጂ የሁለቱም አይደለም ። ሰለዚህ ከእንደዚ
ዐይነት ቤተሰብ የተወለደ ልጅ ( ለምሳሌ እናቱ አበሻ አባቱ፡ ፈንጅ ቢሆኑና ኑሮው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሆን በሙሉ ልቡ የኢትዮጵያውያንን አኗኗርና ባህል መቀበል
ያዳግተዋል።ግማሽ ፈረንጅነት ይሰማዋል ” ካለ በኋላ " እስክንድር ትንሽ ሲያስብ ቆየና ፡ “ እንደሚመስለኝ ይህ ችግር በታዳጊና በበለጸጉ አህጉረሮች መሐከል ያለው የልዩነት ችግር ነጸብራቅ ነው " ፍርንጅና የዕድገት የሥልጣኔ የበላይነት ምልክት ተደርጎ ስለሚወሰድ ክልሱ ልጅም ይህ ተጽዕኖ ከራሱ ጋር እንዲጣላ ያደርገዋል ብቻ ምን ልበልሽ አሁን ባለንበት የተራራቀ የኑሮና የአስተሳሰብ ደረጃ (ሚክስድ ሜሬጅ) በጣም አስቸጋሪ ነው ” አላት ።

“ሊቅ ነህ ” አለችው ማርታ' በልቧ እንደ ማድነቅ በአፉ እንደ ማሽሟጠጥ አድርጋ
“ ሊቅነት አይደለም ” አላት እስክንድር ኪሱን እየዳበሰ “ “ አንቺም ብትሆኝ መጽሐፍ አንብበሽ ልታገኚ
የምትችይው ይውቀት ነው ።

ኪሱን የዳበሰው ሲጋራ ፍለጋ ነበር የክርክር ስሜቱ ሲግል ከንፈሩ እየደረቀ መጣ ። ሲጋራ ትዝ አለው ። ከምሳ
በኋላ ሲጋራ ላለማጨስ ምሎ አፉ ላይ የቀረችውንም መስበሩን እንደ ቅዠት ወይም እንደ እንቅልፍ ልብ ውሳኔ ወስዶት አሁን ከኪሱ አንድ ብር አወጣና አሳላፊውን ሲጋራ እንዲያመጣላት አዘዘው ። የያዛት ገንዘብ ከቀረበላቸው
ጭማቂ እንደምትተርፍ በልቡ አስልቷታል

“ በነገራችን ላይ ፡ በስሜታዊ ብርገጋ ተነሣሥተው ነጭ እያገቡ ወደ ውጭ ሀገር የሚሔዱ አበሻ ሴቶች ዕጣቸው
ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ ? ?” ሲል ጠየቃት ።

“ ምንድነው ልትለኝ ነው ? ” አለችው ግንባሯን አኮማትራ ።

“ መጨረሻቸው ሽርሙጥና ነው ” አላት ድርቅ ብሎ ። “ አብዛኛውን ጊዜ ቅድም ባልኩሽ ምክንያቶች ስለ ማይሰማሙ። በመጨረሻ እዚያው ሽርሙጥና ይጀምራሉ ።ከአፍሪካ አግብቶ የወሰዳትን ሴት በጥንቃቄ የሚይዝ ነጭ በሐይማኖቱ ያደረ ወይም ሕይወቱን ለሥራና ለምርምር የሰጠ ጥቂት ሰው ብቻ ነው ።

የማርታ ፊት ተለዋወጠ ። በአነጋገሩ እንደ ተከፋች ገባው።

“ ምን ማለቴ መሰለሽ ? ” አለና እጅዋን ይዞ ሊያረጋጋት ሞከረ ።

እጄን ልቀቅና ማለት የፈለግከውን ተናገር ” አለችው ፡ ስልቱን ባጣ ድምፅ ።

“ ምን መሰለሽ ማርታ ! አንድ ልንክድ የማንችለው ነገር አለ ። ሰዎች ስንባል ብዙ ጊዜ ለጊዜያዊና እሳታዊ ስሜታችን ተገዥዎች ነን ። በሆነ እሳታዊ ስሜት ወይም ግንፍልተኝነት ተነሣሥቶ እናት ሀገርን ጥሎ መኮብለል ጉዳቱ የሚሰማው ቆይቶ ነው ። እስካሁን ድረስ በነጮች ሃገር ደልቶት የሚኖር ኢትዮጵያዊ አላየሁም ፤አልሰማሁም ።
አብዛኛው እዚህ ትውልድ ሀገሩ ውስጥ የሚንቀውን ሥራ ፡እንደ ቤት ማጽዳት ፥ መስታወት መወልወል ፥ መኪና ማጠብ
ሽንት ቤት ማጽዳትና የመሳሰለውን እየሠራ ነው የሚኖረው ።
ጥቂት ኢትዮጵያውያን በቂ ገንዘብና ቁሳቁስ ቢኖራቸውም ነጻነቱና ክብሩ ስለሌላቸው ሰላም አያገኙም ። በገንዘባቸውን ብዛት ህሊናቸውን የሚመክቱበት የአልኮልና የሺሽ ግንብ
ሰርተው ከዚያ ውስጥ እየዋኙ ይኖሩታል መኖር ከተባለ።

ማርታ የተዘበራረቀ ስሜት ተሰማት ። ዘመዶቿ ከውጭ ሐገር በሚልኩላት ደብዳቤ ደስተኞች እንዳልሆኑ ታውቃለች
ስለዚህ እስክንድር የተናገረውን ናቅ አርጋ ልታልፈው አልቻለችም ። በሌላ በኩል ደግሞ ፡ የእሷ ስሜትና ፍላጎት የምንጊዜም ውጭ ነው ፤ ፈረንጅ ሀገር ነው ። ይህ ሰሜት ስላየለባት ሐቁን ልትቀበል አልፈለገችም ።

። ይብላኝ ለምታገባት ፤ እኔ እንደዚህ አኞ አትመስለኝም ነበር ” አለችው ።

“ እንዴት ? ” አላት እስክንድር ፥ ተገርሞ ።

እንደዚህ ለጭቅጭቅና ለመግት ሽንጥህን ገትረህ የምትቆም አይነት ሰው አትመስለኝም ነበር ።

በርግጥ እንዳለችውም ። እንዳሁኑ ሰፊ አጋጣሚ አግኝተው ተጨዋውተው ስለሚያውቁ። እስክንድርን የምትገምተው
እንደ ማድየለሽና " ለኑሮወም ለሀገሩም ደንታ የሌለው ሰው አድርጋ ነበር ። አሁን ኢትጵያዊነቱ እንዲህ ሽንጡን ገትሮ መቆሙ አስገርሞታል ።

ጭቅጭቅኮ አይደለም ” አላት እስክንድር የራሱ ያልሆነ ፈገግታ እያሳያት ። “ ይልቅስ ሳናስበው ብዙ ትምህርት የተለዋወጥን ይመስለኛል ። ”

አሳላፊው ሲጋራውን አምጥቶ ሰጠው ። እስክንድር በመጀመሪያ ማርታን ጋብዞአት፡ቀጥሎ ለራሱ ከፓኮው ውስጥ ይልቅ ይህን ሲጋራ የሚያስተውህ ወዳጅ ብታገኝ ጥሩ ነበር” ስትል ለከፍ አረገችው

ያንችስ ምን ይላል ? ” አላት ፥ ክብሪት እየጫረ
“ እኔ እኮ እላጨስም ። ከሚያጨስ ወንድ ጋር
👍5🔥1
ወይም ጨዋታ ቦታ ስሆን፥ እንዲሁ አጨሳለሁ እንጂ ሱሰኛ አይደለሁም
አለችው ።

እስክንድር አጫጫሷን አመንላት ሙሉውን ጭስ ነው ወደ ውጭ የምታወጣው።

“ የሚገርምሽ ፥ ሁለት በቅርብ ማጨስ የጀመሩ ጓዶኞቼን መክሬ አስትቼለሁ ። ብዙ ዓት ስላጨስኩትል በግል ሕይወትም ሆነ በማኅበራዊ ግኑኙነት ውስጥ የሚያስከትለውን ችግር በሚያሳምን ሁኔታ አቀርባለሁ መጥፎነቱን እሰብካለሁ እኔ ራሴ ግን ማቆም አቃተኝ ። ”

ጠንቋይ ለራሱ አያቅም ይባል የለ? ” ስትል አፌዘችበት።

"ግድ የለም ። ጥሩ ሚስቴ ሳገባ ማጨሴን አቆማለሁ የሚል ተስፋ አለኝ ።

"አንተ ያልተውከውን እሷ እንዴት ታስተውሃለች? ”

“ ታስተወኛለች ። ጠንካራና ጥሩ ሴት ከሆነች እንኳን ሲጋራ መተው ሌላም ታስደርገኛለች» ሴቶች ምን ያህል
ኃይለኛ እንደሆኑ ዐውቃለሁ።

" እንዴት ? ” አለችው ።

ፊቷ በደስታ ሲፈካ ተመለከተ መልሱን በጉጉት እንድመትጠብቅ ገባው ። ሊያኩራራት አልፈለገም።

"እንዴት እንደሆነ አልነግርሽም ” አላትና " በልቡ ለምንድነው ሰዎች ኃያል መባል ደስ የሚለን ? ሌሎችን ማንበርከክ በቁጥጥራችን ሥር ማዋል እንዲሰግዱልን ማድረግ የምንፈልገው ለምንድነው ? የበላይ ሆኖ የመገኘት
ስሜት ለምን ያጠቃናል ? ” እያለ ሲያስብ ቆይታ በባሎቻቸው ላይ ኃያል መሆን የሚችሉት ሁሉም ሴቶች አይደሉም ። ጥቂት ጠንካሮችና ልበሙሉዎች ናቸው አላት።

በመልሱ ባለመርካቷ ቀደም ብላ ዐይኖን ከእሱ ለማሸሸ ያህያ ከማዶ ካለው ባዶ ግድግዳ ላይ ተከለች።

ሰማሽኝ ማርቲና ? ” አላት በቀልድም በቁልምጫም ዐይነት

“ ደረቅ ! ”

"ርጥብ"!

እስክንድር ለአፍታ ያህል ዐይኑን ከዐይኗ ሳይነቅል ቆየ። ከአፉ በሚወጣው የሲጋራ ጢስ ቀለበት እየሰራ ሲወረውር በሰፊው ቀለበት ውስጥ ጠበባ ቀለበት ሰርቶ ሲያሾልክ የማርታ ጆሮ ሙዚቃውን እየቀዳ ልቧን ሲያወራው ።በዐይኗ እስክንድርን የጢስ ቀለበቶች ተከትላ ጭልጥ ብላ ስትሔድ፡ ቀለበቶቹ እየሰፉ፥ እየተምዘዝዘጉ ሄደው ሲበታተኑ እንደገና ዐይኗን ወደ እስክንድር አፍ መልሳ ሌሎች
ቀለበቶች ስትጠብቅ ደስ ሲል !

ማርታ ምርምሩና ክርህሩ ቀርቶ እንዲህ እንዲህን አይነት ጨዋታ ቢጫወቱ ደስ እንደሚላት እስክንድር ያውቃል የወጡትም ለዚሁ ነበር ታድያ ለምድን ነው የማይዋጥላትን ክረርክር እያቀረብኩ ማደርቃት ? ሲል አሰበ ገንዘብ በማጣቴ
ከእሷ ጋር ሌላ ዐይነት ጨዋታ መጫወት ባለመቻሌ ያረብኩት ማካካሻ ይሆን? ጎበዝ ነው ብላ እንድትወደኝ ይሆን ? ወይስ በእርግጥ የምርምርና የክርክር
ጥማት ይዞኝ ነው? ” እያለ ሲያስብ የሷው ጥያቄ አባነነው።

“ እውነት እስክንድር ሚስት ታገባለህ ? ”

ምን ማለትሽ ነው ? ” አላት በአጠያየቋ ተገርሞ
እንዴት አላገባም ። ? ”

ማለት ፡ በቃ እንዲያ ግዴለሽ ዐይነት ትመስላለህ ። የትዳር ስሜት ያለህ አትመስልም ። ”

ምን ለማለት እንደ ፈለገች ስለ ገባው ፡ “ ላለባበሱ ብዙ አለመጨነቁ ሲጋራ ማጨስ ወይን ሌላ ምንድን ነው ከቁም ነገረኝነት አምባ ያገለለኝ የመሰለሽ ? ወይም ደግም ሙሉ ሰው ለመሆን ጥሩ ዜጋ ለብባል የሚያስፈልጉ ሌሎች
መመዘኛዎች ካሉ ብትገልጪልኝ ? ” አላት ፌዝ በተቀላቀለበት አነጋገር ።

💥ይቀጥላል💥
👍4
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

...ሳናውቀው እርቀን ሄደናል፡፡ ዞብልን አልፈን ቸቸላ ሆስፒታል ልንደርስ ምንም አልቀረን፡፡

“እርቀን መጣን፡፡ እንመለስ?”

“ደከመህ? እሺ” ብሎ ዞረ፡፡ ዶክተር እረጅም ወክ ይወዳል።

“ዶክ አሁን እንደገባኝ፣ የአዕምሮ በሽታ ከምጠብቀው በላይ በብዛት፣ በዙሪያችን ያለና ብዙ ምስቅልቅሎችን እያስከተለ ያለ፣ ግን በማህበረሰቡ ዘንድ ብዙም ግንዛቤ የሌለው በሽታ ይመስለኛል፡፡”

“እውነት ብለሃል ያቤዝ፡፡ አሁን ስለ በሽታው በደንብ እየተረዳህ ነው፡፡ እንደዚህ ያሉ ብዙ በሽታዎች እንዳሉ ብታውቅ ደግሞ የችግሩ ግዝፈት በደንብ ይታይሃል፡፡”

“ቅድም እንዳልኩህ አልገባኝም እንጂ፣ እቤትህ ያሉትን መፅሃፍት ለማንበብ ሞክሪያለሁ፡፡ ለምሳሌ፤ ስለ ፓራኖይድ፣ ኦብሴሽን፣ዚኮኒያ ምናምን ለማንበብ ሞክሬ ነበር” አልኩኝ በዛው ስለነሱ
እንዲነግረኝ፡፡

“ምነድን ዚኮኒያ ካካካካ...” ዶክተር ለመጀመሪያ ግዜ ከልቡ ሲስቅ
አየሁት፡፡ የበሽታውን ስም ስጠራ እንደተሳሳትኩ ገባኝ፡፡ ዶክተር ሲስቅ
ስላየሁት ግን፣ በመሳሳቴ ደስ አለኝ፡፡

“ዚኮኒያ ... እንደዛ ነገር ያነበብኩ መሰለኝ፡፡” አውቄ ደገምኩለት፡፡
እየተንከተከተ ሳቀ፡፡ ዶክተርን እወደዋለሁ እሱ ለኔ ህይወቴን ያዳነልኝ ጠባቂ መላዕኬ ነው፡፡ ህይወቱን ሙሉ ደስተኛ ቢሆንልኝ ምኞቴ ነው። እሱ ግን ስሜቱ በብዛት የረጋ ነው፡፡ ቶሎ አይደሰትም፣ አይናደድም፡፡ዛሬ በኔ ምክንያት ደስ ስላለው ከልቤ ደስ አለኝ፡፡ ስጦታ የሰጠሁት ያህል ተሰማኝ፡፡ ስቆ ሲጨርስ፤

“ገባኝ፣ ስኪዞፍሬኒያ ለማለት ነው፡፡ የህክምና ቃላቶች ትንሽ ይከብዳሉ፡፡ እንደውም አንተ ጎበዝ ነህ፡፡ ሌሎቹን በትክክል ጠርተሃቸዋል፡፡ እሺ ለማንኛውም እነግርሃለው፡፡ ፓራኖይድ የባህርይ መዛባት ችግር ተብለው ከሚጠሩ ሁኔታዎች አንዱ ነው። ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ከመጠን ያለፈ ተጠራጣሪ ናቸው፡፡ ሰው በተፈጥሮው
ይጠራጠራል፡፡ እንደ ችግር ምንቆጥረው ግን፣ ያለ ምንም ተጨባጭ ምክንያት ሲጠራጠርና፣ እያንዳንዱ ድርጊታቸው በሌሎች እንጠቃለን ከሚል ከፍተኛና የማያቋርጥ ስጋት፣ አለማመንና ጥርጣሬ የመነጨ ሲሆን ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ከማንኛውም ሰው ጋር የሚያደርጉት
ግንኙነትና ድርጊታቸው፣ በጥርጣሬ አስተሳሰቦች የተቃኙ ስለሆነ፣
በማህበራዊ ግንኙነትም ሆነ በስራቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጠርባቸዋል፡፡

ይህ ችግር ብዙውን ጊዜ በልጅነት ወይም በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚጀምር ሲሆን፣ ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ የተለመደ ነው::ፓራኖይድ ያለባቸው ሰዎች ሁልጊዜ ሌሎች ሰዎች እነርሱን ዝቅ ሊያደርጓቸው፣ ሊጎዷቸው ወይም ሊያስፈራሯቸው እንደሚሞክሩ
ስለሚያስቡ ድርጊታቸው ሁሉ እራሳቸውን በመከላከል የተቃኘ ነው::እነዚህ መሠረተ ቢስ እምነቶች፣ እንዲሁም የማመካኘትና ሌሎችን ያለማመን ባህሪ፣ የቤተሰባዊም ሆነ የስራ ግንኙነቶችን በከፍተኛ ሁኔታ
ይስተጓጉላል፡፡ በመሆኑም የፍቅር ህይወታቸው፣ የትዳርና የቤተሰብ
ህይወታቸውን ጨምሮ ማንኛውም ከሰዎች ጋር ለሚያደርጉት ግንኙነት
ከፍተኛ መሰናክል ይሆንባቸዋል፡፡

አነዚህ ግለሰቦች ከሚያሳዩዋቸው ምልክቶቹም መሃከል፤ሌሎችን ሁል ግዜ መጠራጠር በጣም የሚቀርቧቸውንና ሃኪማቸውን ጨምሮ፣ ሌሎች እነሱን በማታለል ወይም በመበዝበዝ እንደሚጠቀሙ ማሰብና ማመን፤ የግል መረጃዎቻቸው እኔን ለመጉዳት ይውላል በሚል ፍራቻ ለሌሎች መደበቅ፣ ለሰዎች ይቅርታ ማድረግ መቸገር፤ ቂም መያዝ፣ ቁጡና ትችትን በአግባቡ መቀበል መቸገር፤ የሚሰጧቸው አስተያየቶችና የማሻሻያ ሃሳቦች ውስጥ የተደበቁ ትርጉሞችን መፈለግ፣

የሰውነት እንቅስቃሴዎችን እንደማይታዩ የጥቃት፣ የንቀት ወይም የማስፈራራት ምልክት አድርጎ መረዳት፣ በአፀፋው ለመመለስ መፍጠን፤ እንዲሁም በቁጣ ምላሽ መስጠት፤ የማያቋረጥ ምክንያት
አልባ ጥርጣሬዎችን ማብዛት፣ ይህም ፍቅረኛቸውን ወይም የትዳር ጓደኛቸውን በጥርጣሬ ማሰብ፤ ክህደትን ለምከላከል ነገሮችን ሁሉ በጥርጣሬ መመልከት፤ ሁልጊዜ እራሳቸውን ትክክል እንደሆኑ ማመንና በግጭቶች ውስጥ የራሳቸውን ድክመት ወይም አስተዋፅኦ ማየት
አለመቻል፤ አብዛኛውን ግዜ ተቃዋሚዎች ዘና ማለት የሚቸገሩ፣ግትር እና ተከራካሪ ናቸው፡፡ የፓራኖይድ /የምናባዊ/ ጥርጣሬዎችን መለያ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፤

አጠራጣሪውን አስተሳሰብ የሚጋራ ሌላ ሰው ከሌለ፤
ለጥርጣሬ መነሻ ትክክለኛ ማስረጃ ሳይኖር ሲቀር፤
ማስረጃ ባለው ጉዳይ ላይ አልፎ የሚነሳ የጥርጣሬ ሃሳብ፤
ስለጉዳዩ ማሰብ ማቆም የሚከብድ ከሆነ፤
ከሌሎች ማረጋገጫ ተሰጥቶም በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬ ከቀጠለ፤

ጥርጣሬው ከማስረጃ ይልቅ፣ በስሜቶች እና አሻሚ ክስተቶች ላይ የተመሰረቱ ሲሆኑ ይህ ጥርጣሬ ጤነኛ ያልሆነ የፓራኖይድ ምልክት ሊሆን ስለሚችል ሃኪምን ማማከር ከከፋ ችግር ይከላከላል፡፡

ይህ ችግር ብዙ ሰዎች በሕይወታቸው በመለስተኛ ደረጃ ሊያጋጥማቸው የሚችል ሲሆን የከፋ ጉዳት አያስከትልም ነገር ግን፣በሌላው ጫፍ ሲከሰት በጣም ከባድ ችግርን ሰለሚያመጣ፣ ህክምና
መፈለግ የግድ ነው፡፡” ዶክተር እያወራልኝ ግርማ ትዝ አለኝ፣ በፍቅረኞቻቸው ላይ በአልተጨበጠ ቅናት አሲድ መድፋትና ሌሎች የጭካኔ ወንጀሎችን ሚፈፅሙ ሰዎች በአዕምሮዬ ተመላለሱ፡፡

“ሌላው ደግሞ ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር /ኢኮዲ/የምንለው ነው፡፡ ኦ.ኮ.ዲ. ከመጠን ያለፈ አስጨናቂ የጥርጣሬ ሃሳቦች መከሰትና ጥርጣሬውን ለማረጋገጥ ወይም ለማስተካከል ተመሳሳይ ድርጊቶችን በተደጋጋሚ ለመፈፀም የሚስገድድ ባህሪ ነው፡፡ ግለሰቡ ድርጊቶቹን የሚፈፅመው ወደ አእምሮው ሊቆጣጠረው ከሚችለው በላይ
በተደጋጋሚ እየመጡ በሚያስጨንቁት ሃሳቦች፣ ምስሎች ወይም ፍላጎቶች ምክንያት ነው:: ሃሳቦቹ አስጨናቂ ናቸው፡፡ ነገር ግን፣በሰውየው አዕምሮ የሚመነጩ እንጂ፣ በነባራዊው አለም የማይከናወኑ
ወይም የሌሉ ናችዉ:: በተጨማሪም፣ እነዚህ ሰዎች እራሳቸውን እንደታዋቂ ወይም ከፍተኛ ደረጃ እንዳላቸው ይሰማቸዋል።

ኦ.ኮ.ዲ. ምልክቶች በአብዛኛውን ጊዜ በትንሹና ቀስ በቀስ ስለሚጀምሩ፣ ችግሩ ላለበት ሰው፣ የተለመዱ ባህሪዎች ሊመስሉ ይችላሉ:: ድርጊቶቹን ሲፈፅሙ የተወሰነ እፎይታ ይሰማቸዋል፡፡ ነገር
ግን፣ እፎይታው ለትንሽ ጊዜያት ብቻ የሚቆይ ስለሆነ የድርጊቶች
ድግግሞሽ ይቀጥላል። ተደጋጋሚና አስገዳጅ ድርጊቶች በሌሎች ሰዎች
በተለየ ሁኔታ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፤ በማህበረሰቡ እንደጥዩፍ ሊቆጠሩ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ፣ ለግለሰቡ የግዴታ ተግባሮችን ለመቆጣጠር በጣም ከባድ ናቸው፡፡ ምክንያቱም፣ ግለሰቦቹ በተደጋጋሚ እየደጋገሙ ማይታወቃቸው ስለሆነ ነው:: ለምሳሌ፣ ሰው ከጨበጡ ወይም እቃ ከነኩ በኋላ እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ ሰውን ለመጨበጥ በመፍራት
ሰላምታን በሌላ መልኩ መስጠት፣ የበር መቆለፍን በተደጋጋሚ ማረጋገጥ፣ ልዩ ቃላትን ወይም ጸሎቶችን መደጋገም፣ ደጋግሞ መቁጠር በጣም በተደጋጋሚ የዝግጅት አቀራረቦችን መፈተሽ ናቸው፡፡
እነዚህን ድርጊቶች እንዲፈፅሙ የሚያደርጓቸው ምክንያቶች ፣በጀርሞችን ወይም በቆሻሻ መበከልን በከፍተኛ ደረጃ መፍራት፣ ከመጠን ያለፈ ጥርጣሬ ወይም ስህተት የመስራት ፍርሃት እያደረጉት ላለው ነገር ትክክለኛነት ከሌሎች የማያቋርጥ ማበረታቻና ማረጋገጫ መፈለግና ለስርዐት የበዛና የተጋነነ ቦታ መስጠት ናቸው፡፡

አንዳንዶቹ ድርጊቶች ሰዎቹ ላይ በቀጥታ ጉዳት ባይኖራቸውም፣አላስፈላጊ ግዜንና ጉልበትን በመውሰድ፣ በሌሉ ጉዳዮች ላይ በመጨነቅ ውጤታማነትን በእጅጉ ይጎዳሉ፡፡ በመሆኑም ይህ ችግር አላስፈላጊ ግዜንና ጉልበት
👍3
በመጠቀም ገቢን በማሳጣትና የህይወት ጥራትን
በመቀነስ ላይ ከሚገኙት እጅግ አስከፊ ከሆኑት አስር በሽታዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የኦ.ኮ.ዲ. ከባድነት ከሰው ወደ ሰው የተለያየ ሲሆን፣ ይህ ችግር ለተደጋጋሚ የቤተሰብ እና የጋብቻ አለመግባባትና ፍቺ አንዱ ምክንያት ነው፡፡ በመሆኑም፣ በማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ ትልቅ አሉታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል፡፡

“ዶክተር ግን አሁን የነገርከኝ በሽታዎች ሁሉ ምክንያታቸው ምንድነው?”

“ጥሩ ጥያቄ ነው ያቤዝ፡፡ እንደ እድል፣ የአዕምሮ በሽታዎች መንስኤ እስካሁን በትክክል ይሄ ነው ለማለት አልተቻለም፡፡ ነገር ግን፣ተፈጥሮ፣ አካባቢ እና በአዕምሮ ውስጥ ያሉ ንጥረ ቅመሞች ማነስና መብዛት የየራሳቸው አስተዋፅዖ አላቸው፡፡ በተለይ ሴሮቶኒን የተባለ ንጥረ ቅመም፡፡”

“ዶክ ይሄ ሴሮቶኒን የተባለውን ቃል ከዚህ በፊት ሰምቼዋለሁ።” “የት?፣ ከዚህ በፊት ሃኪም አማክረህ ታውቃለህ ወይም የጤና
ባለሙያ ጓደኛ ነበረህ?”

“ሃኪም አማክሬ ላውቅም፡፡ የጤና ባለሙያ ጓደኛም የለኝም፡፡ ግን የሆነ ቦታ ሰምቼዋለሁ::”

ይህን ቃል የት ነው የሰማሁት?፣ የት ነው የማውቀው..?፣ በደንብ እርግጠኛ ነኝ:: ይኼን ቃል ከዚህ በፊት የሆነ ሰው ሲለው
ሰምቻለው፡፡ ሳሚ. አይደለም፡፡ ሃብትሽ... አይመስለኝም፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...እንዲዚያ ሳይሆን አለ አይደል ! እንዲያው ዝም ብዬ ሳይህ በቃ...

"እንዲያው ዝም ብለሽ ስታዪኝ ? ” ሲል ቃሏን ደገመና “ ታዲያ ምኑን ነው የወደድሽው ? ” አላት ።

“ ሒድ ደረቅ ! ”
"ርጥብ!"

ሸፋፍና ልታልፈታ ብትሞክርም እስንድርን እንድትወደው ወይም እንድትቀርበው ያደረጋት ነገር ለራሷም ግልጽ ሆኖ አይታይቃትም በቁመናው አልተማረከችም ።ጸጉሩ በእሷ ዐይንና አስተሳሰብ የሚጠላ “ ኪንኪ” ነው።
በአለባበሱ ብዙም ደንታ የለው ። አስተሳሰብና ዕውቀቱን ለመታዘብ
ከዚህ ቀን በፊት ዕድል አላጋጠማትም ። ታድያ ምኑን ነው የምትወደው ? የአቤል ጓደኛ በመያኑ ? በዲግሪ ለመመረቅ የደረሰ ተማሪ በመሆኑ ? ወይስ ካያት ቀን
ጀምሮ ወዲያውኑ በፍቅር እግሯ ሥር ስላልወደቀላት የእልህ ፍቅር ይዞአት ? ... በተምታታ ሐሳብ ጭልጥ ብላ ሔደች።
ከሚንቋት ወንዶች ጋር የእልህ ፍቅር ስለሚይዛት ይህን አዛማማያ ትፈራዋለች ነገር ግን እስካሁን ከእስክንድር
ጋር ያላቸው ግንኝነት ከዚያ የሚያደርስ ባለመሆኑ በእልህ ፍቅር ልትደምድመው አልቻለችም ።

"ስሚ እኝጂ ማርታ ”አላት እስክንድር ፡ ከፓኮው ሌላ ሲጋራ እየመዘዘ ፤ “ አንድ ነገር እጠይቅሻለው ብዬ ባገኘሁሽ ቁጥር እረሳዋለሁ ። ”

“ ምንድን ነው ? ” አለችው የወሬ ህዋሳቶቿ መነቃቃታቸው በጎጽታዋ ላይ እየተነበበ ።

“ያቺ አጠር ወፈር ያለች ቀይ ልጅ ፡ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ፡ ጓደኛሽ ነች አይደል ? ” አላት ስሟን እንደማ
ያውቅ ሁሉ ።

“ እ ቤቴ ? ”
“ አዎ" ቤተልሔም ። እሷ ልጅ “ሊክቸረሯን” አውርዳዋለች የሚል ወሬ ሰምቼ...

የማርታ የነገር መቀበያ አንቴናዎች ሽቅብ ተቀሰሩ በቅናት የተውጣጥረው ሰውነቷ ተቁነጠነጠ በጆሮዎቿ ብቻ ሳይሆን በመላ ሰውነቷ እንደምታዳምጥ ሁሉ ፊቷን እስክንድር ፊት ደቅነችው የሐሜት ወሬ ሲጀመር ለመስማት ካላት ጉጉት የተነሳ ቅንድቦቿ ይርገበገባሉ።

ማን ነገረህ ? አቤት ወንዶች እኛን ትሳደባላችሁ እንጂ እናንተኮ የባሰ ወሬኞች ናችሁ ! ”

እንደዚያ ሳይሆን ፡ በጨዋታ መሐል ተነሥቶ አንድ ጓደኛችን ነው የነግረን " ሳምሶን ጉልቤውን ታውቂዋለሽ ?

አዎ ያ ብዙ ጊዜ አብሯችሁ የሚሄደው ስፖርተኛው ልጅ ... ዐውቀዋለሁ ”

እሱ ነው የነገረኝ ። ቤተልሔም ጋር አንድ ዲፓርትመንት ስለሆኑ ሁኔታውን ያውቃል ወሬው ከዲፓርቲመንቱ ተማሪዎች ጆሮ ደርሷል

የወለጋ ልጅ ነዉ አይደል ? ” አለችው ብምጹታዊ አነጋገር።

እኔ እንጃ ! እኔ የማውቀው። በኢትዮጵያዊነቱ ነው።ለማ ካብት ይመር ይባላል ።

“ አዎ የወለጋ ልጅ ነው ሲሉ ሰምቻለሁ ብታይ ወድዋት ሊሞት ነው አብዶላታል

እሱን ተይው መቼም ሴቶች ቆዳችሁን ማዋደድ ታወቁበታላችሁ ተወደድን እንጂ ወደድን አትሉም።

“ሒድ ደረቅ ፥ እኔ የታዘብኩትን ነው የምነግርህ እንዲያውም ካላገባሁሽ እያለ ያደርቃታል ።

ታድያ ለምን አታገባውም ? አግኝታው ነው? ዘንድሮ እኮ ባል ወድ ነው ” አላት እስክንድር ትንሽ ላሳርራት ብሎ።

ሒድ ጉረኛ ! ሚስት ለማግኘት ገና ካሁኑ የበለጠ ደጅ የምትጠኑበት ዘመን ይመጣና ” ብላ የብሽቀቷን ከተናገረች በኋላ ቤቴ እንደሆን ለጊዜው ነው እንጂ አታገባውም" አለችው።

« ምነው ለምን ? ”
ውጭ ሃይገር የመሄድ ሐሳብ አላት
“ እ 'ፈረንጅ ነዋ የምታገባው ? ” አለና ቀለዶባት "
በሸቀችና አፍንጫንና ከንፈሯን አገናኝታ “
እኝኝዋ አለችው ።

እስክንድር ሳቀና “ በድን ሥጋችሁ ነው እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ልባችሁና ነፍሳችህ አውሮፓ ጎብቷል አይ የኛ ዘመናውያን ! ” አለ በልቡ ።

“እኔ እንደ ሰማሁት ከሆነ ለማ በቤተልሄም ምክንያት ከተማሪዎቹ ጋር ግጭት ውስጥ ገብቷል ይባላል ” አላት ።

የምን ግጭት ? ” ስትል ግንባሯን አኮማትራ ጠየቀች መልሱ ቀጥተኛ አልነበረም ። ፍርሀት የማያስከትለው ግጭት ይመስለኛል ”አላት

"አልገባኝም"

“ምን መሰለሽ ሳምሶን እንደ ነግረኝ ከሆነ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለማ በተማሪዎቹ ላይ የሚያሳየው ጸባይ ተለዋውጧል ቀድሞ ክፍሉ ውስጥ ገብቶ አስተምሮ ከመውጣት በስተቀር፥ ከተማሪው ጋር ምንም ዐይንት ግጭት አልነበረም አሁን ግን ቀጡነት ይታይበታል ለተማሪዎቹ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ ቀና አደለም ጥያቄ የሚጠይቁትን ለማወቅ ሳይሆን ለተንኮል ይመስለዋል ከተማሪው
ጋር እንደ አይጥና ድመት መተያየት ጀምሮአል ። እንደሚመስለኝ ከሆነ የዚህ ሁሉ ምንጩ ተማሪዎቹ እሱ ከቤተልሔም ጋር ያለውን ግንኙነት ያወቁበት እየመሰለው የሚፈጥረው ጭንቀት ነው ። አትኩረው የሚያዩት ተማሪዎች ሁሉ
የሚያሙት ሊመስለው ይችላል ። ደግሞ ያሙት” ይሆናል ።የጸባዪ መለውወጥና የግንባሩ መኮማተር፥ ለፍርሀቱ የሚያቀርባቸው መከላከያዎች ናቸው ብቻ አኳኋኑ ውስጣዊ ሰላም ማጣቱን ያሳያሉ።

ማርታ እኔ ምን አገባኝ ? ” የማለት ያህል አንገቷን ቅንጥስ ትከሻዋን ንቅንቅ አርጋ ዝም አለች።

“ ይገርምሻል በፊት ግሩም መምህር ነበር አሉ ። ታዲያ ምን ይሆናል ! ሴቶች የገባችሁበት ነገር ምን ግዜም ቢሆን
ሰላም አያገኝ ” አላት በፊቱም ባይገልጸው በልቡ እርር ብሎ።

ምን? ” አለችሁ እሰም ተቆጥታ።

ምንም አልመለሰላትም ። ቁጣዋን ለማብረድ ዝም አላት።

ተማሪው ትምህርቱን ትቶ እንዲያው ነገር መፈትፈት ይወዳል ” አለችው በንቀት አነጋገር ።

“ ነገር መፈትፈት አይደለም ። ተማሪውን የሚመለከት ጉዳይ ነው ለብዙዎቹ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲው ከዕውቁት
ይልቅ ለማርክ መፋለሚያ ቦታ ሆኗል ። በዛ ላይ ሴትነትና ውበት ጣልቃ ገብተው ሲበጠብጡ ምነው አያናድድ ! ”

ፊቷ ላይ ክፉኛ መከፋት አነበበ ።

እምልሽ ...,, ብሎ መናገር የፈለገውን ሳይጨርስ አቋረጠችው።

አሁን አንተ አስተማሪ ብትሆንና ከምታስተምራቸው መሀል አንዲት ልጅ ብትወድ አጋጣሚውን ከመጠቀም ትቆጠባለህ ? ”

እስክንድር ጥያቄው ድንገተኛ የሆነበትን ያህል፥ ክህ ብሎ ለጥቂት ሴኮንዶች አሰበ ፈዛዛ ሣቅ ሥቆ ፥ በልቡ ምን አስደነገጠህ እስክንድር ? ራስህን ትጠራጠረዋለህ እንዴ ?” እያለ “ አይመስለኝም ። ማርክ የነገሠበት ሥርዓተ ትምህርት እስካልቀረ ድረስ ፡ እንዲህ ተማሪዎች የሚከፋፍልና የሚያማርር ድርጊት የምፈጽም አይመስለኝም ” አላት ።

“ ጉረኛ” አለችው ፡ ከቀድሞው ቀዝቀዝ ባለ ስሜት “ ጉራህ ከቁመትህ ይበልጣል

"ማንም ሰው ቢሆን ለራስ ከፍ ያለ ግምት ይኖረዋል እና ተሳስቼ ይሆናል” ።

ሲናገር ድምፁንም ሆነ እሱነቱን ለምን እንዳዝናናው አልገባውም ። የሆነ ጽላላዊ ስሜት ተጫጫነው ።በአንጻሩ ደግሞ የማርታ ገጽታ እየደመቀ ሲሔድ ተመለከተ። « ምን እንዲህ እስቦረቃት ? በሙዚቃው ይሆን ? ወይም ድምፁ መሳሳቱን ሰምታ የተረታሁላት መስሏት ይሆን ? ” አለ በልቡ ።ሐሜትና ሙዚቃ የማርታን ሕዋሳቶች ምንኛ እንደሚያነቃቁ ገመተ።

የሸሚዟን የደረት ቁልፍ ፈትታ፡ጡቶቿን ለእስንድር ዐይን አጋለጠቻቸው ። ከተቀመጠችበት ባትነሳም ባለችበት
ትከሻዋን እየሰበቀች ከሙዚቃው ጋር አብራ ታዜም ጀመር ።
“ እታዎን ” የተጫወቱት "ሺ ኢዝ ኦል ” የሚል የእንግሊዝኛ ሙዚቃ ነበር ።

"ሙዚቃ ትወጃለሽ ? ” እላት እስክንድር ዐይኑን ከጠጡቶቿ ሳይ ለመንቀል እየታገለ።

“ ሙዚቃ የሚጠላ አለ እንዴ ? ሕይወት የሌለው ፍጡር ካልሆነ በስተቀር ” አለችው ! እንቅስቃሴዋን ሳትገታ ።
ማለቴ ፥ የመውደድ ደረጃ ሊለያይ ይችላል ። ”።

“ እኔ ግን ይገርምሃል ሙዚቃ እንደ ነፍሴ ነው
👍1
የምወደው ። በተለይ በዚች ሙዚቃ ትልቅ ትዝታ አለኝ ።

"ክብደቱ ምን ያህል ይሆን? '' ሲል ቀለደባት።

"ደረቅ ! ” አለችና ፣ “ የራሴ የሆነ ትዝታ ነው ብላ የትከሻ እንቅስቃሴ ሳታቆም ዐይኗን በጠረጴዛው ባዶነት ላይ ተክላ ጭልጥ ብላ ትዝታዋ ውስጥ ገባች።

ከአንድ ዓመት በፊት ነበር ። ማርታ አንድ ወንድ ጓደኛዋ ቤት ስትሔድ ጓደኛዋ ከጥቂት ጓደኞቹ ጋር ያዘጋጀው ፓርቲ
ላይ ደረሰች ። በአጋጣሚ የተዘጋጀ የጓዳ ፓርቲ በመሆኑ በቂ ቅንብር ስላልነበረው ሴቶች አልነበሩበትም ። ስምንት
ያህል የመንደሩ የሚቀራረቡ ወንዶች ብቻ ራሳቸውን ለማዝናናት ያን ዕለቱኑ ያወጠኑት ፕሮግራም ነበር ። ማርታን

💥ይቀጥላል💥
🔥1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሰላሳ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)


በመጨረሻም ስኪዞፍሬኒያ ፤” ብሎ ቀጠለ፡፡ እኔ እሱን በግማሽ ልቤ እያዳመጥኩት ይህን ቃል የት እንደስማሁት ለማስታወስ፣የአዕምሮዬን ጓዳ እበረብራለሁ፡፡ “ይህ በሽታ ከቀደሙት ሁሉ ከባዱ ሲሆን፣ ሰዎች የእውነታውን አለም በቋሚነት በተሳሳተ መንገድ የሚረዱበትና የሚተረጉሙበት የአዕምሮ ችግር ነው። ስኪዞፍሬንያ
ያለባቸው ሰዎች በጣም ያልተለመደ አስተሳሰብ እና ባህሪ ያሳያሉ፡፡
የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን መተግበር አይችሉም፡፡ በመሆኑምከሌሎች የአእምሮ ችግሮች በላይ ማህበረሰቡ ይሄ ችግር ያለባቸውን ሰዎች በቀላሉ ይለያል፡፡ ችግሩ ግን በማህበረሰባችን ያለው በጣም አናሳና የተሳሳተ የአዕምሮ ችግሮች ግንዛቤ እነዚህ ሰዎችን ወደ ህክምና ከማምጣት ይልቅ ወደ ሌሎች ቦታዎች መውሰድና ማግለል ሚያበረታታ
ነው፡፡ ነገር ግን፣ ይህም ችግር ህክምና ያለው ሲሆን፣ በተለይ ደግሞ ከባድ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ህክምና መጀመር ምልክቶችን ለመቆጣጠር እና ከባድ ችግሮች እንዳይከሰቱ ለማድረግ ይረዳል፡፡

ምልክቶቹም፤ የግል ንፅህናንዉን ችላ ማልት፤ ስሜት የጎደለው የሚመስል ምላሽ መስጠት፤ የዓይን ለዓይን ግንኙነት አለማድረግ፣በንግግር ወቅት ስሜት አልባ የፊት ገፅታዎች ማሳየት፣ በማኅበራዊ
ኑሮ ደስታን ማጣት፤ ማኅበራዊ ግንኙነት መሻከር፤ በነባራዊው ቦታ የሌሉ ነገሮችን ማየት ወይም መስማትና ለነሱ ምላሽ መስጠት፤ ከፍተኛ ብስጭት፣ ያልተለመደ ሃይለኝነትና ለፀብ መጋበዝ፤ ያልተደራጀ
አስተሳሰብና ንግግር፣ የሚሰጡት መልስ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የማይገናኝ መሆን፤ በንግግር የማይታወቁ፣ ትርጉም የለሽ ቃላትን አሰባስቦ መናገር፣ ያልተለመደ የልጆች ከሚመስል ሞኝነት እስከ ለመረዳት የሚከብድ ብስጭት፤ ምክንያት የለሽ ፈጣን እንቅስቃሴዎችን
ማሳየት፣ በስራም ሆነ በተለያየ ቦታዎች መመሪያዎችን መቃወም፣ያልተለመደ ወይም ተገቢ ያልሆነ አቀማመጥ ወይም አቋቋም ማሳየት፣የእብሪት ስሜቶችና ለመታዘዝ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ባህሪያትን ማሳየት የመሳሰሉት ናቸው፡፡” ብሎኝ ጨረሰ፡፡

“አስታወስኩት!” ሳይታወቀኝ ጮኸኩኝ፡፡
“ምኑን ያቤዝ?” አለኝ ዶክተር ደንገጥ ብሎ፡፡ “ሴሮቶኒን ያለኝን ሰው፡፡ የሆነ ፈረንጅ ነበር፡፡ ጫት ያነቃቃል ስለው፣ ውስጡ ሴሮቶኒን አለው ወይ ያለኝ፡፡ አላውቅም ምናልባት ፈረንጁ ዶክተር ይሆናል።”

“አይ ያቤዝ ላይሆንም ይችላል፡፡ ጤና ከመሰረታዊ እውቀቶች አንዱ ነው። ሁሉም ሰው ስለ ጤና እውቀት ሊኖረው ይገባል። ስለ መኪናችን ስለ ኮምፑተር ለማወቅ የምንጥረውን ያክል፣ ዶክተሩን
ለመተካት ሳይሆን እራሳችንን ከከፋ ጉዳት ለመከላከል፣ ሃኪማችን
የሚለንን በአግባቡ ለመረዳት ሁሉም ሰው ስለ ህክምና መሰረታዊ እውቀት ሊኖረው ይገባል፡፡ ያደጉት ሃገራት ማህበረሰቡ እንደዛ ነው ለዛ ሊሆን ያልከው ሰው ያወቀው፡፡ እንዳልኩህ እኛ ሃገር ብዙ ሰው

ከሙያው በተጨማሪ፣ ስላለው መኪና፣ ስለ ቤቱ፣ ስለ ኮምፑተር ከባለሙያው ጎን ለጎን የተወሰነ እውቀት አለው፡፡ ነገር ግን፣ መሰረታዊ ስለሆነው ጤናው ግን ለጤና ባለሙያዎች ብቻ ተቶ ተቀምጧል።
እንደዚህ ስል ግን፣ አንተንና እንዳንተ ያሉትን ስለ በሽታቸው ለማወቅ ብዙ ጥረት ሚያደርጉም እንዳሉ አልዘነጋም፡፡ ግን ጥቂት ናቸው።መስተካከል ያለበት ይመስለኛል፡፡”

“ትክክል ብለሃል ዶክ፡፡ መኪናም ቤትም ጤና ሲኖር ነው፡፡ ግን እኔ ምልህ ዶክተር ”

“ወዬ ያቤዝ”

“እነዚህ ያስረዳኸኝን በሽታዎች ማህበረሰባችን ያውቃቸዋል? መጥቶስ ይታከማል?”

“በቂ መረጃ አለ ብዬ ለማለት ይከብደኛል፡፡ በሃገራችን እነዚህ
ችግሮች ያለባቸው ሰዎች በሚሊዬን የሚቆጠሩ እንደሆነ ይገመታል፡፡ ነገር ግን ህክምና ፈልገው ሚመጡት በጣም ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ አብዛኞች፣ ሲያፍሱ ሲበትኑ፣ ወደፊት እንዳይጓዙ መሰናክል ሆኗቸው፣ እታገሉ በየመስሪያ ቤቱ አሉ። ገሚሶቹ ደግሞ፣ ከእምነት ጋር አያይዘውት በህይወት ያጋጠማቸው መሰናክል፤ በሽታ ሳይሆን መንፈስ አድርገው ሌላ አማራጮችን ፍለጋ እተንከራተቱ ናቸው፡፡ በጣም የሚያሳዝነኝ ግን፣ ስለ በሽታውና በሽታው ባለባቸው
ሰዎች ላይ ያለው አሉታዊ አመለካከት ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች አክመን ደግፈን ውጤታማ ማድረግ ሲገባን፣ እያንጓጠጥናቸው ምናባብስባቸውን
ሳይ፣ እስከመቼ እያልኩ ልቤ ይደማል፡፡” አለኝ በትካዜ መሬት መሬቱን እያየ፣ በእግሮቹ ጠጠሮችን እንደ ኳስ እየመታና እያንከባለለ፡፡

ለአይን ያዝ ሲያደርግ ወደቤት ደረስን፡፡ የዶክተር ቁጭት፣ እንደ ኤሌክትሪክ ነዝሮኝ ወደኔም ሲተላለፍ ተሰማኝ፡፡ እቤት ገብተንም ሁለታችንም በሃሳብ ሄድን፡፡ አዎ ይሄን በሽታ እኔም ሁሉ ነገሬን ወስዶብኛል፡፡ ስራዬን፣ ያፈራሁትን ሃብት ንብረቴን እንደ ሰላቢና እንደ ድግምት ለፍቼ ያመጣሁትን አመድ አድርጎብኛል፡፡ እድሜዬን ነጥቆኛል፣ ነብሴን ሊቀማኝ ሲል በተአምር ነው የተረፍኩት፡፡ ከሁሉም
በላይ ግን፣ ግማሽ ህይወቴን፣ የምወዳትን ሃኒን ቀምቶኛል። አሁን እኔ
ታምሜ እንደነበር ማን ይጠረጥራል?፣ በቅርበት የሚያቀኝ ሳሚ እንደታመምኩ መች አወቀ?፣ እናቴስ መች አወቀች? እንደኔ፣ እንደ ሃኒ፣ እንደ ኤፍሬምና ሌሎች ዶክተር በነገረኝና ባልነገረኝ በሽታዎች
ሚስቃዩ ሚሊዮኖችን አሰብኩ፡፡ ካሁን ቦሃላ፣ እኔም ይህን በሽታ በምችለው ሁሉ ልታገለው ይገባኛልና ልዋጋው ይገባል፡፡ በዝምታ ሆነን እንደተለመደው እየተጋገዝን እራት ሰርተን በላን፡፡ የተጓዝነው ረጅም የእግር ጉዞ አድክሞናል ስለነበር፣ እራት እንደበላን ቶሎ ተኛን፡፡

በሚቀጥሉት ቀናቶች ቶሎ ወደ ሃገሬ ለመመለስና ህይወቴን እንደገና እንዴት መጀመር እንደምችል ማሰብ ጀመርኩ፡፡
በየመሃሉ የአእምሮ ጤና ጉዳይ በከፍተኛ እልህ አስባለሁ።አነባለሁ። ኤፍሬም ይህ ችግር ገጥሞት ሊሆን ይችላል ለማለት
የሚያበቃኝ እውቀት ማግኘት አልቻልኩም ነገር ግን፣ ባነበብኳቸው
በሽታዎች ሁሉ ትንሽ ቁጥር የማይባሉ ሰዎችን ከጓደኞቼም ከቤተሰቤም ጭምር፣ እከሌ የዚህ ችግር ይኖርበት/ባት ይሆን እንዴ ብዬ አስቤያለሁ።
እከሌ እንዲህ የሚቸገረው በዚህ ጉዳይ ቢሆንስ፣ እያልኩ አሰላስያለሁ፡፡እንደኔ ብዙ ሰዎች ሳያውቁት በነዚህ ችግሮች እየተፈተኑ እንደሆነ ዶከተር የነገረኝ እውነቱን ነው፡፡ እንደ ሃገር የሚያጋጥሙን
ምክንያቶች አንዱ ቢሆንስ ብዬም አሰብኩ፤

አለመግባባትና የፀብ በየመስሪያ ቤትና በየቤተሰቡ(እንደ ሃኒ) የፀብ መክረር ምክንያትስ ቢሆን..፡፡

እንዴት ግን መንግስትን ጨምሮ ሌሎች አጋር አካላት በዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው ሰፊ ስራ መስራት አልቻሉም?፣ ስንቶች የመስራት አቅም እያላቸው፣ ትንሽ ታክመው ውጤታማ መሆን ሚችሉ፣ እንደኤፍሬም ወደ ረመጡ ተገፍተዋል?፣ ስንቶች በዚህ ምክንያት እየተሰናከሉ ሲወድቁ፣ ሌላ ምክንያት ላይ ጣታቸውን
እየቀሰሩ፣ ምርታማ እድሜያቸውን እያባከኑ አሉ?፣ ማን ያውቃል፤ ብዙዎች ይህ ችግር እስከነመኖሩም መረጃው የላቸው ይሆናል፣ ስንቶች ይሆኑ የአዕምሮ ችግር ሲባል ጨርቅ መጣል ብቻ ሚመስላቸው?፣ስንቶች ይሆኑ ይህ በሽታ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ
እንደሚያስከትል ሚረዱ?፣ ስንቶች ይሆኑ ችግሩ እንዳለባቸው ሚገነዘቡ፣ የህልማቸው መሰናክል እንደሆነ ያወቁ፤ ታክመው ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ የተረዱ፣ ስንቶች ናቸው? ማሰላሰል ጀመርኩኝ፡፡

ሰው አዕምሮው ጤነኛ ካልሆነ፣ ሌላው አካሉ ምን ያህል ጤነኛ ቢሆን፣ ምን ሊሆነው፣ ምን ሊበጀው?

“ጭንቅላት አይክዳህ ...” ነበር ያለኝ ያ ጓደኛዬ?...

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
😁1
ነገ የመጨረሻውን ክፍል ይዤ እመጣለው አስተያየታችሁን እንደተለመደው አድርሱኝ ሌላ ምርጥ ድርሰት እየተዘጋጀ ነው እናንተም ለሌሎች እንዲደርስ #Share እያደረጋቹ ሃሳብ አስተያየት እርስ በእርስም በዚ #Group @dertogadaa እየተወያያቹ

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...ማርታን መልካም እግር ጣላት የአንዲት ሴት ከመሐከላቸው መግኘት ሁሉንም አስደስታቸው ።

በመጀመሪያ ከእያንዳንዳቸው ጋር ተራ በተራ እየተነሣች ስትደንስ ቆየች ። ለዳንስ ያላት ሰሜት ከምንም የላቀ ነው።ወፍጮ ሲያስፈጫት አውለው ዳንስ ላይ ቢያቀርቧት ሌሊቱን ሙሉ ስትነካው ታድራለች ። በዕለቱም ጨዋታ እየሞቀና የጎረምሶቹ ሰውነት እየጋለ በሔደ ጊዜ፥ ተራ መጠበቁ ቀርቶ ሁሉም አንድ ላይ እየተነሡ ይጨፍሩ ጀመር ።ማርታም መሐላቸው ገብታ ሁሉንም ማጫወት ቀጠለች ላባቸው ፊታቸውን እያጠበ ከአንገታቸው ሊቀነጠሱ እየደረሱ ከመወገባቸው እየተሸበረኩ ፡ ከእግራቸው እየተብረከረኩ ዙሪያዋን ከበው ሲደንሱ ደንሱ ማርታ የላዕላይነት ስሜት ተሰማት በሴትነቷ ተኩራራች ። ነገር ግን ኮርታ
ከመደነስ አልተቆጠበችም ። ይብሱን ፥ ከወገቧ በላይ በጡት መያዣ ብቻ ዕርቃኗን ሆና እስከ በቃት ተፍነከነከች ።
ቦረቀች ፤ ተወዛወዘች ።

ሺ ኢዝ ኦል ” የሚለውን ሙዚቃ ስድስት ጊዜ ደጋግመው ደነሱበት ። እሷን ከመሐከላቸው እንዳረጓት እያንዳዳቸው
የሙዚውን ስልት በመጠበቅ ጣታቸውን ወደ ማርታ እየጠቆሙ" ሺ ኢዝ ዲስኮ ” አሏት ። ከሙዚቃው ጋር እያንዳንዳዱን የዲስኮን ቃላት በተናጠል ይሉና በአንድነት “ ኦ ኦ ኦ... ኦ ” የሚለውን ድምፅ ሲደጋግሙ ፥ አንገቷን አቅንታ ይብሱን ቁልቁል እየተሽከረከረች ትፍነከነካለች ።

ማርታ በርካታ የዳንስ ቀኖችም ሆኑ ምሽቶች አሳልፋለች ከሁሉም ይልቅ በዚህ ቀላል የዳንስ ቀን "ዲስኮ" ጭንቅላቷ ውስጥ ተቀርጾ የቀረው ፥ ምንም ሴት ባልነበረበት አዳራሽ እሷ "ዲስኮ ሌዲ” ሆና በወንዶች መሐል እንደ ጣኦት ተከባ ያሳለፈችው ዕለት ስለሆነ ነው ። ከዚያን ዕለት ጀምሮ ለሴትነቷ ልዩ ግምት ሰጥታዋለች ።

“ዳንስ ትወጃለሽ ? ” አላት እስክንድር ፡ ክትዝታ ባሕር ውስጥ መግባቷን ሳያጤን "የትከሻዋን መነቃነቅ ብቻ እየተመለከተ ።

«ፐ ነፍሴ ነው ! ” አለችና የሚቀጥለውን የእስክንድር ቃል በመጠባበቅ ከእንገቷ ቀና አለች።

"ጥሩ ነው ”አላትና ዝም አለ ።
“ አንተስ ?"

“ እኔም እወዳለሁ ። በውጭ ሀገር ሙዚቃዎች እደንሳለሁ ። የበለጠ ደስ የሚለኝ ግን በሐገር ባህል ሙዚቃዎች
ስጫወት ነው ” አላት ።

ኤፍ ! ” ብላ ፊቷን መደዛ አዞረችና “ አቤት አቤት እንዲያው ቁና ሙሉ ጉራ ! ” አለችው።

"ጉራ አይደለም ከምደንሰው የበለጠ እክክስታ እወርዳለሁ አብዛኛውን ዐይነት የሐገር ባህል ጨዋታ እጫወታለሁ ። በ “ትዝታ” አንጐራጉራለሁ ጉብልዬን
አዜማለሁ ! “ እየዬው ድማው ” ን እተክዝበታለሁ " አንቺ ግን እስክስታ መውረድ ቀርቶ የሐግርኛውን ዘፈን ግጥም አንድ ቤት መምታት መቻልሽን እጠራጠራለሁ አላት ፊቱ ላይ የፌዝ ሣቅ ብልጭ ድርግም እያለ ።

ማወቅም ሆነ መቻል አልፈልግም ” አለችው ፥ በግድየለሽነት ትከሻዋን እየሰበቀች ።

“ ይሄንን ነው ” ኮ የምልሽ " አንቺ የማታዉቂዉ አንቺ ነትሽን ነው ። እኔ ግን እኔነቴን ሳላውቅ «መኖር አልችልም
የሀገሬ ባህልና ጨዋታዎች የእኔነቴ ክፍሎች ናቸው ። አንዳንዴ ለብዙ ጊዜ አከታትዬ በውጭ ሀገር ሙዚቃ የደነስኩ
እንደሆን ከራሴ ጋር ጸብ እጀምራለሁ መሠረቴ የተናጋ ይመስለኛል " ባዶነት ይሰማኛል ። ባህሌን ንቂ ለውጪ ባህል የተንበረከክሁ ይመስለኛል ።

የንቀት ሳቅ ሳቀችና “ሐቀኛ ኢትዮጵያዊ ነህ ” አለችው።

አንቺ ግን ሁለቱንም አይደለሽም ” አላት እያሾፈ "ማለቴ ፡ አውሮፓዊትም ኢትዮጵያዊትም አይደለሽም
የንግግሩ ክብደት አልተሰማትም "
“ እስቲ እናንተው ሁኑበት” ብላ ቀለደችና “እውነት ግን ከልብህ ነው እንዲህ ሀገር ወዳድ ሆነህ የምትከራከረው ? ” አለችው

“ ከአንጀቴ ነው” አላት ወደ ኋላው ለጥ ብሎ ራሷን ነቀነቀች ፥ግን የውጭው ሙዚቃ የዐገር ባህሉ ምን አሰኘህ ?ሁሉም መዝናኛ እስከሆነ ድረስ በቃ።

"አዎ ሁሉም መዝናኛ ነው ለውጭው እየተገዙ የራስን ናቅ ማድረግ ግን ራስን መርሳት ይመስለኛል ።ከውጭ የምንቀበለውን ያህል የራሳችንንም ባህል ወደ ውጭ ብናንጸባርቅ ምንኛ ባማረብን በሀገርና በውጭ መካከል የባህል ልውውጥ መኖር እንዳለበት አምናለሁ ። ከአንድ ጎን ብቻ ሲመጣ ወይም ሲንጸባረቅ ግን ፡ የባህል ተጽዕኖ ይሆናል። በምዕራባውያን ሙዚቃ ረግድ እኛ የተያያዝነው ይህን ይመስላል ።

“ ኧረ በናትህ ! አርዕስት ቀይር እስክንድር
ምን ሞዛዛ ነህ ! ልታደርቀኝ ነው እንዴ ያወጣኸኝ ? ” አለችው ከልቧ በሽቃ።

“ ኧረ ላዝናናሽ ነው ማርትዬ ! ይልቅ ጭማቂውን ድገሚ አላት ልቧን ሊያሟሽሸው ።

“ በቃኝ ፤ይልቅ እንሒድ ! ”

ቆይ እንጂ ተጫወቺ! የት እንሔዳለን ? አይዞሽ አንድ ቀን እንጨፍራለን።

"መቼ ? ” አለችው ዕለቱን በናፍቆት በመጠበቅ ዐይነት

“ መቼ ? መቼ ? ” እያለ ቃሏን በልቡ ደጋገመና ግድየለሽም አንድ ቀን አላት።

“እኮ አንድ ቀን መቼ? ” ስትል የገዛ ሐሳቡ አፋጠጠውም።
• እጅ አጠረኝ ፥ ኮረንቲ ብስብ የሚባባሉት የልጅነት ጨዋታ ታወሰው ። ምናልባት በሐሳቡ የሚገምተው የመመረቂያው ጊዜ በሚቀርብበት አካባቢ ነው ፣ ያኔ አጎቱ ለምርቃቱ ሥነ ሥርዓት ልብስ ማሰፍያ ብሎ ገንንዘብ እንደሚልክለት ይተማመናል ። እና ምናልባት ያኔ ግን ከዚያ በፊት ይቺ ልጅ ከዩኒቨርስቲው ወድቃ ብትባረርስ ? ነገሩ ሁሉ ከንቱ ዝማሬ መሆኑ አይደለም ?

“ ስማ አንተ እስክንድር ! ” ስትል ማርታ ከሐሳቡ አባነነችው ። “ ይሄ አቤል ለምንድን ነው ሲያየኝ ግንባሩን የሚያኮማትረው ?

ይሉኝታ ይዞአት ነው እንጂ ከእስክንድር ጋር ከተናኙባት ደቂቃ ጀምራ ከአሁን አሁን ላንሳው እያለች ስታሰላስለው የቆየችው አርዕስት ነው ።

“ ይኮማተርብሻል እንዴ ? ” አላት እስክንድር • ሁኔታውን እንደማያውቅ ሁሉ

ኧረ ብታይ እንደ ጠላቱ ነው የሚያየኝ ! ”
«« ምን እሱ እኮ ከማንም ጋር ቢሆን ያን ያህል አይጫወትም ” አላትና ሐሳቡን ቆርጦ ለመሆኑ ትዕግሥት ደህና ናት ? ” ሲል ጠየቃት ።

“ ደህና ነች ፥ እሷም ብታያት የተዘጋች ናት ፈጽሞ የውስጥ ስሜቷን አትናገርም ። እኔ መቼም በመኝታ ክፍል የቅርቧ ነኝ ብዬ ብዙ ላደርግላት ሞከርኩ " እሷ ግን ግልጽ
አይደለችም ። ከአቤል ጋር ፍቅር እንደ ጀመረች ያወቅኩት ከስንት ማውጣጣት በኋላ መሰለህ ! ”

እስክንድር ለተወሰኑ ሴኮንዶች በትካዜ ዝም ብሎ ቆየ ። ምን እንደሚናገር ግራ ገብቶታል ። የአርዕስቱ መነሣት
ቢያስደስተውም መፍትሔ የሌለው ድግግሞሽ ጨዋታ መሆኑ ሰሜቱን ከፋፍሎታል ።አቤልን ለመርዳት በምን መንገድ ይቻላል ? ሁለቱም ስሜታቸውን ለሰው የማያካፍሉ የርስ በርስም ልሳናቸው ዐይናቸው ብቻ !

እጅግ ያስገርሙኛል ” አለችው ማርታ የእስክንድር ንዘምታ ጨዋታውን እንዳያቆመው ፤ ፍቅር በረከሰበት ዘመን ደግሞ ይህን ያህል መጨነቅ ሊያውም ነ በአይን ፍቅር ! ምን ከረፈፎቹ ናቸው ! ”

ከረፈፍነት አይደለም ! አያድርስ ነው በፍቅር ጀግንነት የለም ” አላት አምርሮ ።

“ ምነው ደርሶብሃል እንዴ ? "

እስክንድርም ምንም አልመለሰላትም ። ጥቂት እያሰበ ቆይቶ ይልቅስ ልንረዳቸው የምንችልበትን መንገድ ብንፈልግ ጥሩ ነበር አላት።

“ እንዴት ” አለችው የሱን ስሜት በማየት ለነገሩ አትኩሮት ሰጥታው ። “ እምልህ የልባቸውን እስካላወቅን ድረስ እንዴት መርዳት ይቻላል ? ”

“ አዎ ችገሩ” ኮ እሱ ነው አለና መፍትሔ
ከጣራው ላይ የሚወርድ ይመስል ጣራ ጣራውን እያየ “ ምን መሰለሽ ፥ እስካሁን አቤልን
👍1🔥1
ለመረዳት የሚታጎሉት ዮናታን ብቻ ናቸው

“ ዮናታን ? ” ስትል ግራ በተጋባ ስሜት ኣቋረጠችው “ የፍልስፍና መምህር ። እኝያ ረዥም ቀይ ጸገራቸው ትንሽ ግባ ያለ ሰውዬ ! ብዙ ጊዜ እንኳ ብቻቸውን ነው የሚሔዱት።

“ እ ... አወኳቸው"

እንዴት ህይነት ግሩም ሰወ መሰሉሽ ። ታዲያ ምን ይሆናል ፥ ብቻቸውን ነው የሚፍጨረጨሩት ። አቤልን ለማዳን ሌላ በቅጡ የሚረዳቸው ሰው አላገኙም ። እኔን አንዳንድ እየጠሩ ስለ ሁኔታው ይጠይቁኛል ።ነገር ግን በቂ መረጃና
ድጋፍ ልሰጣቸው አልቻልኩም አቤል ታፍኖ መሞት የሚፈልግ ልጅ ነው ፡ ”

“ እውነት ፡ ምን ዐይነት ተፈጥሮ ነው ? ” አለችው ክፉኛ እንደ ተገረመችበት በሚገልጽ ስሜት ።

“ ተፈጥሮ አይደለም ከአካባቢው የወረሰ፡ በሽታ ነው ። ፍቅር ምስጢር ተደርጎ በሚወሰድበት አካባቢ እስካደገ ድረስ ፡ እና እሱም ያንኑ ስሜት ነው የሚያንፀባርቀው በዚህ ላይ ደሞ እኔ እንደሚመስለኝ ፡ አቤል ለፍቅር ጥሬ
ነው ይህችኑ ትንሽ ዕድሜውን ሁሉ በመሉ ደብተሩ ላይ ነው ያሳለፋው የሱን የባላገር ንጹሕ ስሜት ከእኛ የከተማ
የትርምስ ሕይወት ጋር ልናወዳድረው አንችልም ካለ በኋላ ነገሩን ለማዛመድ አሰላሰለና “ ሁለታችን ይልቅ አሁን እሱን ለመርዳት ብንችል ጥሩ ነበር "" አላት ።

እንዴት ? አለችው በጉጉትና ሞራል በተሞላበት ስሜት " እንደ ማንኛውም ሕያው ሌላውን የመርዳት ጉጉት
ተሰማት ። ገና ምኑንም ሳትጀምረው ደስ ደስ አላት ። “ የሚቻል ከሆነ በደስታ ! ” አለችው። "

"አዎ እንዴት መሰለሽ እኔና አንቺ ዘዴ ሁለቱን አገናኝተን ለማነጋግር ብንችል ። ”

"እንዴት ? ” አለችው እንደገና ተቻኩላ።

“ እኔና አንቺ እንድ የሆነ ቦታ እንቀጣጠርና አንቺ ትእግስትን ፥ እኔ ደግሞ አቤልን እዚያ ቦታ በዘዴ ይዘናቸው ለመምጣት እንሞክበር ። በአጋጣሚ እንጂ በቀጠሮ የተገናኘን አናስመስለውም " ።

« እሺ መች ? "

“ነገ ነዋ ! ምን ጊዜ መስጠት ያስፈልገዋል ? ” አላት እስክንድርም ራሱ ተቻኩሎ ስሜቱ በደስታ እየተቁነጠነጠ »

በስንት ሰዓት?

“ ከቀትር በኋላ ወደ አሥር ሰዓት አካባቢ “ ዝም ብሎ አፉ ላይ የመጣለት የሰዓት ምርማ ምርጫ ነበር።

“ የት ቦታ ? ” አለችው ።

“ የት ይሻላል ? እ ... እዚያ አንቺና ትግሥት የምታጠኑበት ዋርካ ሥር እያጠናችሁ ጠብቁን ፤ እኔ እንደ
እሱን ይዤ እመጣለሁ።

በደስታ !

እስክንድር ከዚች ደቂቃ ጀምሮ ሐሳቡ ተቁነጠነጠ ከማርታ ጋር ካፊቴሪያው ውስጥ ጥቂት ሲጫወቱ ቆይተው
ሔዱ። ከአቤል አርዕስት በኋላ ማርታ የምታወራለትን አንዱንም ከልቡ አላዳመጠም ። አቤልና ትፅግሥትን ለማገናኘት ታላቅ ጥበብ የተከፈተለት መሰለው ። ነገ ... እሁድ
... ከአንድ ሌሊት በኋላ ... አቤት ርቀቱ! ሐሳቡ በርሮ እሑድ ላይ ዐረፈ ። እዚያች ዋርካ ሥር ትዕግሥትና ማርታ የሚያጠኑ መስለው ሲጠብቋቸው ... እሱ አቤልን አጅቦ ከተፍ ሲል ... ተማሪ ሙሽሮች ከነሚዜዎቻቸው...
ግን አቤል እምቢዮ አልሔድም ቢልስ ? ወይም ደግሞ ትዕግሥትን ሲያያት የኋሊት ቢበረግግስ ? . .

💥ይቀጥላል💥
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ (የመጨረሻ ክፍል)


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

#ድህረ_ታሪክ

አራት አመት አለፈኝ፡፡ የህክምና ክትትል አደርጋለሁ፡፡ እድሜ ለነ ሃብትሽ፣ አደራ የሰጠኋቸውን የዶሮ እርባታ በቅንነትና በታማኝነት ሰርተው ከነ ፍሬው ጠበቁኝ፡፡ መልሼ ለመቋቋም በቃሁኝ፡፡ ለዶክተር
ለህክምናዬ ያወጣውን ግማሹን ቢሸፍን እንኳ ብዬ የተወሰነ ገንዘብ ላኩለት፡፡ አሁን ውስጤ በጣም የተረጋጋ ስሜት ይሰማኛል። የግል ስራዬን አስፋፍቼ ንሮዬን አዲስ አበባ አድርጌያለሁ፡፡ ነገሮች እንደበፊቱ ቶሎ አይረብሹኝም እንደውም፣ አሁን የሰዎችን ህመም አዳማጭና
መካሪ ሆኛለሁ፡፡ አንዳንዴማ፣ እንደ ዶክተርም ሊቃጣኝ ይሞክራል፡፡ሰዎች
በማይረባው ነገር ተረብሸው፣
ስራቸውን መስራት እስኪያቅታቸው፣ የማትረባዋን ነገር አግዝፈው ሲያኝኩ፣ ሲያብሰለስሉ ሳይ፣ ሰዎች ሁሉ ተደራጅተው ሊያጠቁኝ ነው ብለው እያሰቡ ሲጨነቁ ሳይ፣ ወደራሳቸው ማየት ሲያቅታቸው፣ ወላፈኑ እየለበለባቸዉ
ሲመስለኝ፣ ከነበልባሉ፣ ከእረመጡ ውስጥ ገብተው ሳይቃጠሉ፣ መፍትሄ
እንዲያገኙ ሃኪም እንዲያማክሩ እመክራለሁ፡፡

አሁን ዐይኔ በርቶልኛል፡፡ በአጠገቤና በአካባቢዬ በጣም ብዙ ሰዎች ላይ ምልክቱን አያለሁ፡፡ በተቻለኝ መጠን ልረዳቸው አዳምጣቸዋለሁ፡፡ አሁን ግን፣ ይሄ ብቻ በቂ እንዳልሆነ እየተሰማኝ ነው።
ቁጭ ብዬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰላስልኩ ነው፡፡ ከጎረቤት የተከፈተው የዳንኤል አምደሚካኤል መዝሙር ይሰማኛል፡፡ አብሬ ማንጎራጎር ጀመርኩ፡፡

“ዐይኔ በርቶልኛል፣ ሁሉን አይቻለሁ፡፡

ከዚህ የበለጠ ምን እፈልጋለሁ..::

እናገራለሁኝ...፣ አልታክትም ሁሌ..
.
ስለዚህ ሳወራ..አ..ሃ..ሃ፣ ከቶ አልደክምም እኔ።”

ከዶ/ር ሄኖክ ጋር እየተደዋወልን እንጠያየቃለን፡፡ በእድሜም ስለምንቀራረብ ነው መሰለኝ፣ ግንኙነታችን ጠብቋል፡፡ ከሳምንት በፊት፣
ደውሎልኝ ወደ አዲስ አበባ እንደተዘዋወረና ሊመጣ እንደሆነ ሲነግረኝ በጣም ደስ አለኝ፡፡ ውለታው የሚመለስ ባይሆንም፣ ለሱ ያለኝን ክብርና ፍቅር የምገልጥበት አጋጣሚ እንዳገኘሁ ተሰማኝ፡፡ ሲመጣ እኔ ጋር
እንዲያርፍ ተቀበልኩት፡፡ ተከራይቼ ምኖርበት፣ ሳር ቤት መቻሬ ኮንዶሚኒየም ወሰድኩት::


“ዶክ ተዋወቃት ባለቤቴ ናት፡፡”

“እንኳን ደህና መጣህ፡፡ ግባ፡፡ ማሂ እባላለሁ፡፡” አለችው ባለቤቴ
እየጨበጠችው፡፡

“እንኳን ደህና ቆየሽኝ፡፡ ሄኖክ፡፡ እንዴት ነሽ?"

“ዶክ ይህንንም ጎረምሳ ተዋወቀው፡፡ ልጄ ነው፡፡”

‹‹እንዴ! ከመቼው ይሄን አደረስክ?” ልጄን እየሳመው በመገረም ጠየቀኝ፡፡

ሁሌም ከአምናችን ይዘን ምንሻገረው ጥሩም መጥፎም ነገር ይኖራል፡፡ አንድ ጥሩ ነገር ቤቢ ነው፡፡ ይህ ትልቅ የፊቴ ጠባሳ ደግሞ ሌላው፡፡” ማሂ በፈገግታ ታስተናግደናለች፡፡

ዶክተርን ከማሂ ጋር ሆነን በምንችለው አቅም በደንብ አስተናገድነው፡፡ በህይወቴ ባሳየሁት ለውጥ በጣም ደስተኛ እንደሆነ
ደጋግሞ ነገረኝ፡፡ ለሳምንት የራሱን ቤት እስኪያመቻች ከኛ ጋር ቆየ፡፡ደስ የሚል ግዜን አሳለፍን፡፡ ቤት አፈላለኩለት፣ እቃዎችን አጋዛሁት፣ባገኘሁት አጋጣሚ ያለኝን ፍቅርና ክብር ለማሳየት ሞከርኩ፡፡ ያለኝን ትርፍ ሰዓት አብረን እናሳልፋለን፡፡ ወክ እናደርጋለን፣ ሃሳብ እንለዋወጣለን፡፡ ነገ ወደ ተከራየው አዲሱ ቤት ይገባል፡፡ ዛሬ የሰፈራችንን የመጨረሻውን ወክ ልናደርግ ወጣን፡፡

“ያቤዝ...”

“ወዬ ዶክ፡፡”

“ሰሞኑን አንተ ላይ ባየኋቸው ለውጦች ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩ ስነግርህ ቆይቻለው፡፡ ዛሬ ግን፣ እንደ አዲስ ሙሉ የህይወት ታሪክህን እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ።”

“ማለት? አልገባኝም ዶክ፡፡”

“በቃ ህይወትህን፣ ከልጅነትህ ጀምረህ እንድትተርክልኝ እፈልጋለሁ።”

“እንዴ! ለምን?”

“ለምን እንደሆነ ባላውቅም፣ ካየሁህ፣ ካገኘሁህ ቀን ጀምሮ ስላንተ በጥልቀት ማወቅ ፈልጌያለሁ፡፡ ስላንተ ብዙ አስባለሁ፤ እገምታለሁ፡፡ እስከዛሬ ግዜው እንዳልነበር ይሰማኝ ነበር፡፡ ሰሞኑን ግን፣
ከመቼውም ግዜ በላይ ደስተኛና የተረጋጋህ እንደሆንክ አይቻለው፡፡
ስለዚህ ብትነግረኝና ብሰማኸ ደስ ይለኛል፡፡

“ዶክ፣ አንተን ይህን ያህል ካስደሰትህ፣ እንኳን ይሄን ሌላም
አደርግልሃለው፡፡ መቼም ከፍዬው ማልጨርሰው ውለታህ አለብኝ፡፡”

“ኧረ በፍፁም! እንደዛ ሁለተኛ እንዳትለኝ፡፡ እኔ ምንም አላደረኩልህም፡፡ አንተ ጎበዝና ጠንክራ ሰው ስለሆንክ ነው፡፡”

“እሺ እንዳልክ፡፡ ብቻ ግን ውለታህን ለመመለስ ያብቃኝ፡፡”

“አሁን የጠየኩህን፣ ታሪክህን ንገረኝ፡፡”

“እሺ! ያቤዝ እባላለሁ፡፡ ሰላሳ ስምንት አመቴ ነው። በልጅነቴ ዝምተኛም፣ አስቸጋሪም ልጅ ነበርኩ፡፡ ደግሞም ጎበዝ ተማሪ፡፡.” ከመቻሬ ኮንዶሚኒየም ወጥተን የጦር ሀይሎች አጥርን ታከን ቁልቁል
የካርል አደባባይን እየወረድን ነው፡፡ ዶ/ር ሄኖክ ዝም ብሎ ያዳምጠኛል፡፡ገብርኤልን አልፈን፣ በቶታል ማዞሪያ ቁልቁል ወደ መካኒሳ እየወረድን፣ከልጅነት እስከ ዩኒቨርስቲ፣ ከመመረቅ እስከ ከፍተኛ ሀላፊነት፣ ደስታና ሃዘን መውጣትና መውረዶች፣ ከእሱ ጋር እስከተዋወቅንበት ያለውን የማስታውሰውን ያህል ነገርኩት፡፡ በየመሀሉ የሚሰማኝን የጥፋተኝነትና
የቁጭት ስሜቶች ከፊቴ እንዳያነብብኝ፣ ቀና ብዬ ሳላየው በተመስጦ ተረኩለት፡፡ ስጨርስ ዝም አልኩኝ፡፡

“እንዙር፡፡” አለኝ፡፡ እርቀን ሄደናል፡፡ እሺ ሳልለው ዝም ብዬ ዞረኩኝ፡፡ ምንም እያወራ አይደለም፡፡

“በቃ ይኸው ነው፡፡ ከዛ ህይወቴን አንተ ቀጠልከው:: አሁን ደስተኛ ነኝ፡፡ ቀድሜ ህክምና ብጀምር ብዙ ጉዳቶቼን ማስቀረት እችል ነበር፡፡ ግን፣ ባለፈ ክረምት ቤት አይሰራም፡፡ እንዴት እንደምመልስው ባላውቅም፣ ውለታህ በህይወት ዘመኔ ሁሉ አልረሳውም፡፡”

“የምን ውለታ ነው ምትለው ያቤዝ፣ መልስህ እንዲህ ደስተኛና ስኬታማ ሆነህ በማየቴ ብቻ፣ በምንም ከፍዬ ማላገኘው ደስታ ነው::ታሪክህ ደግሞ ከጠበኩት በላይ ይገርማል፡፡ መፅሀፍ እየተረክልኝ
እስኪመስለኝ፣ ተመስጬ ነበር ያዳመጥኩህ፡፡”

“እንዴት..?”

“በህይወትህ የባይፖላር ምልክቶችን በተደጋጋሚና በተለያየ ጊዜ ተፈራርቀውብሃል፡፡በማህበረሰባችን የስነ አዕምሮ የግንዛቤ እጥረት ሰፊ ስለሆነ እንጂ፣ ይሄን ሁሉ ቀውስ ሳታሳልፍ በቀላሉ መቆጣጠር ይቻል ነበር፤” ብሎ ትክዝ አለ፡፡

“እውነትህን ነው፡፡ አሁን፣ እኔም የቀድሞ እኔን ካሁኑ ጋር ሳነፃፅረው እንደዛ ይሰማኛል፡፡ ግን ምን ማድረግ ይቻላል፡፡ ለበጎ ነው ብሎ ከማለፍ ውጪ፡፡”

“ማድረግማ መቻል አለብን፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣በሃገራችን ከአራት ሰዎች አንዱ የሆነ አይነት የአዕምሮ ችግር አለበት፡፡በዚህ ሰዐት እንዳንተ ብዙ ሴ ሰዎች፣ በስራቸው፣ በማህበራዊ ህይወታቸው ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ባለው የመረጃ እጥረትና የተዛባ አመለካከት፣ ብዙ ሰዎች ችግሩ እንዳለባቸው አይገነዘቡም፣ ችግሩም ህክምና እንዳለው አያውቁም፣ ማህበረሰባችን በዚህ ጉዳይ ሃኪም ማናገር ይፈራል፡፡ በዚህ ምክንያት ስንቶች፣ ከሚገባቸው ስኬት በታች ሆነው፣መድረስ ካለባቸው ከፍታ በታች ወርደው፣ በሚገፉት ህይወት
የሚሰማቸውን ቁጭትና ህመም ሳይ፣ ማድረግ ያለብኝን እያደረኩ እንዳልሆነ ይሰማኛል። በጣም አዝናለሁ፡፡ የችግሩን መጠንና ስፋት ስመለከት ደግሞ፣ ነብሴን ትጨነቃለች። የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ይሰማኛል፤” አለኝ አሁንም በትካዜ ውስጥ ሆኖ፡፡ እነዛ አስጨናቂና አስፈሪ፣ ላቆማቸው የማልችላቸው የባዶነት፣የተስፋ ቢስነት፣ ሀሳቦች ትዝ አሉኝ፡፡ አሁን የሉም፡፡ ጠፍተዋል።
ውስጤ ስላምና የተረጋጋ ነው፡፡ አሁን፣ ለእኔ አለም ጨለማ
👍2🥰2🔥1
ሳትሆን ብርሃን ናት፡፡ ዶክተር በነዛ አይነት አስጨናቂ ስሜቶች ሚሰቃዩ ብዙ ሰዎች ጥናቶች እንደሚያሳዩ እየነገረኝ ነው፡፡ እኔም በአካባቢዬ ይህን ታዝቢያለሁ፡፡

“ያቤዝ፣ አንድ ነገር ላስቸግርህ?”

ቅድም ነገርኩህ እኮ ዶክ፡፡ ላንተ ያልከኝን እስከቻልኩት በደስታ ነው ማደርገው፡፡” በወጣንበት መንገድ ተመልሰን ወደ ግቢያችን እየገባን ነው፡፡

“ታሪክህን እንፃፈው...?”

“ምን?” ደነገጥኩ፡፡ ያላሰብኩት ጥያቄ ነው፡፡ ፈራሁ፡፡

“አይዞህ። ስምህን ሁሉ ነገርህን እንለውጠዋለን፡፡ ህይወትህ ለብዙ ሰዎች መማሪያ መሆን የሚችል ነው፡፡ ስንቶች ይህ ችግር እንዳለባቸው ሳያውቁ፣ እንዳንተ ስራቸውን አጥተዋል፣ መግባባት
አቅቷቸው ከማህበረሰቡ ተገልለዋል፣ ተጣልተዋል፣ ትዳራቸውን በትነዋል፡፡ ህክምናው ያለ ማይመስላቸው፣ እየተሰቃዩ መጨረሻቸውን ሚጠባበቁ ብዙዎች ናቸው፡፡ አንተምኮ በእድል ነበር
የመጣኸው፡፡ ሌሎች እንዳንተ እንዳይሰቃዩ ማድረግ አለብን፡፡”
ቤተስብና በውስጤ ኤፍሬም መጣብኝ፡፡ ውስጤ ተላወሰ፡፡ አቅም ነበረው፡፡
በወላፈኑ ሲቃጠል ማንም አልተረዳውም ሳናውቅ፣ ጭራሽ ወደ ነበልባሉ፣ ወደ ረመጡ ገፋተነዋል፡፡ እሱን አዳማ ሄጄ አፈላልጌው አላገኘሁትም፡፡ ቢያንስ ሌላ ኤፍሬሞችን ማህበረሰቡ ሊያድን ይገባል፡፡በሃሳቡ ተስማማሁ፡፡

“ዶ/ር አንተ ይጠቅማል ካልክ፣ እሺ እንፃፈው፡፡ አሁን የምኖርለት ምክንያት ገብቶኛል፡፡ እንዳንተ ሌሎች እንዲኖሩ ለማድረ ነው፡፡” ዶክተር እሺ ምለው አልመሰለውም ነበር፡፡ አላመነም፡፡ በደስታ
ተጠመጠመብኝ፡፡ አብዝቶና ደጋግሞ አመሰገነኝ፡፡ ፊቱ ላይ አይቼበት
ማላውቀው የደስታ ፀዳል ተመለከትኩ፡፡ እቤት ገብተን እራት ከበላን ቦሃላ ሁሉ ደስታው አለቀቀውም፡፡ ሶፋው ላይ ቁጭ ብለን ቲቪ ስናይ ቆይተን፣

“ያቤዝ ማለት፣ ምን ማለት ነበር?” አለኝ ዶክተር፡፡ ማሂ ታዳምጠናለች፡፡

“በችግር የተወለደ፣ ግን ለችግሩ መፍትሄ የሚሆን፡”

እውነትም ያቤዝ ነህ፡፡አመሰግንሃለው!"

ተፈፀመ

ድርሰቱ በዚህ ሁኔታ ተፈፅሟል አስተያያት ሐሳብ ካለ አድርሱኝ

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍3
#ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_ሦስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

እሑድ ጠዋት እስክንድር ማንደፍሮ ከእንቅልፉ ሲነቃ ከሳምሶን ጉልቤው ” በስተቀር ቀድሞት የተነሣ አልነበረም ። ሳምሶን እንደ ልማዱ በጠዋት ተነሥቶ ስፖርት በመሥራት ላይ ነበር ። እስክንድር እንደ ነቃ ዐይኑን በጣቶቹ
ጠራርጎ ሳምሶንን አጨልቆ ተመለከተው ላቡ በግንባሩ ላይ እየወረደ ፡ መሬቱ ላይ ተንጋሎ አንገቱን በእጁ እየደገፈ ከወጓቡ በመነሣትና በመተኛት የሆድ ጂምናስቲክ ይሠራል።ሳምሶን ለስፖርት ያለው ፍቅር እስክንድርን ሁሌም ያስደንቀዋል ። ጠዋት ጠዋት ቀድሞ ተነሥቶ ሰውነቱን ሳያፍታታ ምንም ቢሆን ወደ ውጭ አይወጣም ፡

እስክንድር በሳምሶን እንቅስቃሴ ተነቃቅቶ ስፖርት ለጤንነት ! ” አለና ከመኝታው ውስጥ ተፈናጥሮ ወጣ ። ድካም ስለ “
ተጫጫነው ከአልጋው ለመነሣት የፈጠረው ዘዴ ነበር ። ልብሱን ለባብሶ ከጨረሰ በኋላ ክፍሉ ውስጥ ይንጎራደድ ጀመር ።

“ ምነው ዛሬ በሌሊት ? ”አለው ሳምሶን ፥ በእሑድ ቀን የእስክንድር ማልዶ መነሣት እንግዳ ገር ሆኖበት
አንዳንዴ ለውጥ ያስፈልጋል ።

የምን ለውጥ ? ” አለ ሳምሶን " ጂምናስቲኩን ጨርሶ ዱብ ዱብ በማለት ሰውነቱን እያዝናና ።

“ አንዳንድ ሰንበቶችን ማልዶ የመነሳት ለውጥ አለውና እስክንድር ወደ መስኮቱ ሄዶ ከፈተው።

የጠዋት ፀሐይ ሣር ቅጠሉን ልዩ ድምቀት ሰጥታዋለች።ከእሑድነቱ ሌላ ፥ ጠዋት እንደ መሆኑ መጠን በግቢው ውስጥ የሚንቀሳቀስ ተማሪ ኣልነበረም ለአታክልቱ ከፀሐይ ብርሃን ጋር ውበትና ድምቀት የሰጠው ጸጥታውም ጭምር መስሎ ታየው " የሰዎች ንቅናቄና የሞተሮች ድምፅ የአታክልትን ውበት ውጦ እንደሚውል ተሰማው ። ተፈጥሮን ከመቼውም ይልቅ ፥ ጠዋትና ማታ ጸጥታ ጠብቀን የምናደንቀው በዚህ ሳይሆን ይቀራል ? በዚህ ዓለም ሳይ ድምፅ
የሌለው ተፍጨርጭሮ ድምፁን ያላሰማ ፥ ለመደነቅም ሆነ ለመደነቅም ሆነ ለመታወስ ዕድል አይገጥመውም እያለ ባልተጨበጠ ሐሳብ ሲመራምር ቆይቶ ፥ ለማንኛውም ዛሬ ግሩም ቀን ይምስላል የተስፋ ቀን ነው ” አለ በልቡ ።

አበልና “ ድብርት ” ገና እንደ ተኙ ናቸው ። የአቤል እንቅልፍ እንኳ ያጠራጥራል ። እንኳንስ ድምፅ እየሰማ ሊያንቀላፋ በጸጥታውም ጊዜ በትግል ነው የሚተኛው “ድብርት” ግን ከየቀን ብዛት የሳምሶንን የጠዋት እስፖርት ጆሮው ስለ ለመደለት መባነኑን ትቷል ።

እስክንድር ፊቱን ለመታጠብ የመኝታ ክፍሉን ለቆ ወጣ ለምን ማለዳ እንደ ተነሣ ራሱን በጠየቀ ጊዜ ተጨባጭ
መልስ አጣ አቤል በሌሊት ተነሥቶ እንዳያመልጠኝ ፈርቼ ይሆን ? ” ሲል ራሱን ጠየቀ የቀትር በኋላውን ቀጠሮ ለአቤል የሚነግርበትን ዘዴ ከማታ ጀምሮ ሲያሰላስል ነበር ያደረው ። ከማርታ ጋር የጠነሰሱትን ሴራ በግልጽ ሊነግረው አይችልም” ። ስውር ጥበብ በመፈለግ ከባድ የአንጎል ጃምናስቲክ ሠራ ለራሱ ጥበብ ገና ሳይከሰትለት ሐሳቦ
ሮጦ እነትግስ ክፍል ግባ ። ለመሆኑ ማርታስ ትዕግሥትን የማታለሉ ጥበብ ሰምሮላት ይሆን ? ” ሲል እሲበ።

ፊቱን ታጥቦ ሲመለስ ቁርስ ደርሶል ፡ቁርስ ቁርስ እያለ አቤልና ድብርትን ? አስነሣቸው ። “ድብርት ፊቱን እንዳጨፈገገ ከብርድ ልብሱ ውስጥ በወጣ ጊዜ እስክንድር ስሜቱ ገብቶት በሆዱ እየሣቅ ማበጠሪያ ይፈልግ
ጀመር በአፉ ባይቆጣም ውስጥ ውስጡን እየተነፋነፈ መሆኑ ገባው በልቡ ምን እያለ እየረገመኝ ይሆን? እያለ ማበጠሪያውን እንሥቶ ወደ መስኮቱ ተጠጋ ። ሁሉም በመስኮቱ መስታወት እያዩ ነው ፥ ጸጉራቸውን የሚያበጥሩት

ጸጉሩን ማበጠር ሲጀምር፥ ጥርጣሬ ስሜት ወደ ሳምሶን ዘወር አለ ። ሳምሶምም የሚጥልበትን የተረብ ቃል እያዘጋጀ ያየው ስለ ነበር። ዐይን ለዐይን ተገጣጠሙ የዓይኖቻቸው ግጭት ከቋንቋ ይበልጥ ስላግባባቸው ሁለቱም ተሳስቀው ዐይኖቻውን መለሱ ።

ዛሬ አንድ ቃል እንዳትናገረኝ ” አለው እስክንድር በሥጋት ስሜት ።

“ ማ ተናግረህ ? ” አለው ሳምሶን ፡ የመነቃቃት ሣቅ እየሳቀ ። “ እኛ እንደሆን ሁላችንም ተነሥተናል ጎረቤት ክፍሎችን እንዳትቀሰቅስ ቀስ ብለህ አበጥር።

ዕረፍ ብዬሃለሁ አንተ መላጣ

“ እምልህ በኋላ ወቀሳው ለኛእ ንዳይተርፍ ብዬ ነው።”እስክንድር እንደ ወትሮው ቀልዶ ሊያልፍ አልፈለገም

ስማ ሳምሶን እውነት ይህን ከኪንኪ ጸጐሬን ከልቤ እንደምኮራበት ታውቃለህ ? ” አለው ።

ወደህ ነው ? የተፈጠረልህ አይለወጥ ነገር ! ”

“ እንዴ ስለ ተፈጠረልኝ ሳይሆን በከንኪነቴ እኮራበታለሁ ነው የምልህ ! ”

ይሁንልህ ! ” አለው ሳምሶን በማብሸቅ ዐይነት።አቤልና ድብርት” ልብሳቸውን ለብሰው ፊታቸውን ሊታጠቡ ወጡ ።

“ ለመሆኑ አጭር ኪንኪ ጸጉር መጥፎ ፥ ረዥም ሉጫ ጸጉር ቆንጆ አድርጎ መመዘኛ ያወጣው ምን እንደሆነ ታውቃለህ ? ” አለው እስክንድር አምርሮ

እንጃ እኔ መመዘኛዉ ሲወጣ አልተወለድኩም።

“ አትቀልድ ” አለው እስክንድር የምናገረው።

አትቀልድ አለው እስክንድቁም የምናገረው ቁም ነገር ነው ። አሁን የምንጠቀምበትን የጥሩና መጥፎ ጸጉር
መመዝኛ ያወጣሁት ረዥም ጸጉር ያላቸው። ነጮቹ ናቸው አየህ ነጮች የእኛን የአፍሪካውያንን የዕድገት ኋላ ቀርነት በመመርዝ ክፉኛ ተፅኖአቸውን
በው መመርኮዝ ክፉኛ ተጽዕኖአቸውን አሳርፈውብናል በሚቻላቸው አጋጣሚ ሁሉ በባህላችን ፡ በአኗኗሯችን በአፈጣጠራችን አፊዘዋል። በኋላ ቀርነታችን ተሣልቀዋል ። የዝንጆሮነት ዘመናችሁን አልጨረሳችሁም ” ሊሉን ሞክረዋል ። የሚገርመው የእነሱ ጥረት ሳይሆን የእኛ ለእነሱ እምነትና ፍላጎት መስገድ ነው ። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ የእነሱ ተጽዕኖ ከአባቶቻችንና ከአያቶቻችን ይልቅ በእኛ በተማርነው ትውልድ ላይ ይበልጥ መንጸባረቁ ነው ። ኧረ ! ማይማኑ አያቶቻችን ለሀገራቸው ! ለባህላቸውና ለእምነታቸው ጠንካሮች ነበሩ ። እኛ ነን እንጂ ለውጪ ባህልና እምነት ልፍስፍስ የሆነው ! ”

ረጋ ብሎ የጀመረውን ንግግሩን ውስጣዊ እምነቱ እያጋለው ድምፀቱ ሲጨምርና ፊቱ ሲለዋወጥ ቢመለከትም ሳምሶን የሚረታለት አልሆነም ።

“ ይህ ሁሉ ፍልስፍና አሁን ለኪንኪ ጸጉርህ ማሳመሪያ ነው ? በል እሺ ይሁንልህ ፤ጥሩ ነው ። ”

እስክንድር አሁንም ለቀልድ ቦታ አልሰጠውም ።

ነጮች ለራሳቸው በሚያመቻቸው የነሱን ፍላጎት በሚጠብቅና የነሱን ባህል በሚያንጸባርቅ ሁኔታ ያወጡት መመዘኛም ሆነ መመሪያ ለአፍሪካውያን አይሠራም ። ይህ ከባህል ወረራው አንዱ ክፍል ነው ። አፍሪካውያኖች የራሳችን የሆነ የውበት መመዘኛ ሊኖረን ይገባል ። ደግሞም አለን ። ጥቁረታችን የጸጉራችን እጥረትና ከርዳዳነት ለኛ ውበት ነው ። ”

“ በል እንግዲህ ሁለተኛ ስላ ፀጉር አላነሣም ” አለ ሳምሶን ግማሽ የመሸነፍ ግማሽ የማሾፍ ስሜት እያሳየ ።

“ ምናለበት ? በተከራከርክ ቁጥር ብዙ ትማራለህ ። አለና እስክንድር ጸጉሩን ችምችም አርጎ ካበጠረ በኋላ ተመልከት ባለሉጫና ረዥም ጸጉሮቹ እንዲህ ማድረግ አይችሉም ” አለው ።

ሳምሶን ሥቆ ዝም አለ ።

አራቱም ተጣጥበውና ተበጣጥረው ከጨረሱ በኋላ ለቁርስ ወደ ምግብ እዳራሽ ሔዱ።እስክንድር አሁንም የሚያሰላስለው ። ለሰዓት በኋላው ቀጠሮ አቤኔን የሚያታልልበትን መንገድ ነበር መመገቢያ አዳራሽ ውስጥ ከገቡ በኋላ
ድብርት ከነሱ ተነጥሎ ለብቻው ጥግ ሔዶ ተቀመጠ ።ሦስቴም ነገሩ ስለ ገባችው ተሣሣቁ ። ምንጊዜም ሳምሶን
ያለበት ቦታ መቀመጥ አይወድም ። ይወርፈዋል ። ሥራዬ ብሎ ያበሽቀዋል ። መኝታም ከእሱ ሥር የሚተኛው የግድ
ሆኖበት ነው።

“ ልሒድና አጠገቡ ልቀመጥ ? ” አላቸው ሳምሶን ተንኮል
👍4
እያሰበ ።“ ተው እባክህ ይህንን ልጅ አታናዶው አለው። እስክንድር "በድብርት ተፈጥሮ ከልቡ እያዘነ ።

ሳምሶን ዳቦውን ቶሎ ቶሎ ገምጦ ጨርሶ የአቤልን እጅ እጁን እያየ ፥ በቃኝ የሚልበትን ጊዜ በመጠባበቅ ሻዩን
ይምጥ ጀመር ። አቤልን ሲጠብቅ እስክንድር ቀድሞ ዳቦውን ምንም ያህል ሳይበላ አቆመ ። አቤልም ወዲያው ተከትሎት እጁን በእጁ ጠራረገ ።

“ ብሉ እንጂ ” አላቸው ሳምሶን የተረፋቸውን የዳቦ ጉማጅ እየተመለከተ ።

“ በቃን እባክህ ምን ይሔ ደረቅ ቂጣ አሉ ሁለቱም ፊታቸውን አክፍተው

አይ የናንተ ነገር አለና ሳምሶን የዳቦዎቹን ቁራሾች አፈፍ አደረገ ። አድራጎቱ ተደጋጋሚ ስለሆነ ሁለቱም አትኩሮት አልሰጡትም ።

መብላት አሁን በወጣትነት ጊዜ ነው ። በኋሳ ለራሳችሁ ሳይሆን ለልጆቻችሁን የምታበሉትን ነገር ነው የምታስቡት ” አላቸው ዳቦውን እየገማመጠ ።

ልክ ነህ በርታ ” አለና እስክንድር ፊቱን ወደ አቤል መልሶ “ ታዲያስ ዛሬ የት ነው የምትውለው ? ”ሲል ጠየቀ።

"የት ይኬዳል ፤ እዚሁ ግቢ ነዋ አለው አቤል “ ምን መሄጃ አለን ? ”

ታዲያስ" ! አለ አቤል ፡ አጠያየቁ እንግዳ ሆኖበት ።
የምትወስደኝ ቦታ ካለ ...

አይ ፤ እንዲያው ነገሩን ማለቴ ነው እንጂ እሱማ የት ይኬዳል ? እኔም እዚህ ነው የምውለው ብንችል አንዳንድ
ጥናቶቻችንን እንሸፍናለን።

" እንሞክራለን ። ”

እስክንድር አቤል ግቢ እንደሚውል ካረጋገጠ በኋላ እፎይ አንድ ደረጃ አለቀ የሚቀጥለውን ደረጃ ለማቅረብ
ደግሞ ምን ጥበብ ይከሰትኝ ይሆን ? ” አለ በልቡ ።

«እሁድ ጠዋት እስክንድርም ሆነ አቤል እንዲያው ከመፅሀፍ ጋር በመተያየት ነበር ያሳለፉት ። ሁለቱም መጽሐፎቻቸወን እንደ ከፈቱ። በየግል ሕልሞቻቸው ይጋልባሉ ።አልፎ አልፎ ጥያቄ ሲጠያየቁ እንኳን ከልብ የሆነ መደማመጥ አልነበረም። አቤል የዘወትር ቅዠቱ ላይ ነው እስክንድር ደግሞ የቀትር በኋላ ጥንስሱን ሲያሰላስል ዋለ ።

ዘጠኝ ሰአት ተኩል አካባቢ እስክንድር መጽሐፉን ዘግቶ ማማጥ ጀመረ።

“ ሲጋራ ጠማኝ ፡ እስቲ ውጭ ወጥቼ ገዝቼ ልምጣ አለ ወደ አቤል እየተመለከተ እሱንም ይዞ ከክፍል ለመውጣት የፈጠረው ዘዴ ነበር።

አቤል ምንም አስተያየት አልሰጠም።

አብረን ሄደን ገዝተን እንመለስ 'አለው እስክንድር በጥያቄ ሳይሆን በውሳኔ ድምፅ።

አቤል ሳያመነታ ተነሥቶ አብረው ወጡ " የሚሔድበት እያጣ ነው እንጂ ሲሔድ ቢውል ደስ ይለዋል ። መኝታ ክፍሉ ውስጥ ሆኖ ሲያጠና የፊጥኝ አስረው በግድ ደብተር አስይዘው የሚያስጠኑት መስሎ ነው የሚሰማው “....

💥ይቀጥላል💥
#ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

ወደ ውጭ በር ሲሄድ እስክንድር በልቡ የቀጠሮውን ሰዓት ከእነሱ መድረስ ጋር ለማቀናጀት እያሰላ ነበር ። ቀድመው ከሚመለሱ ዘግየት ብለው ቢደርሱ ከነትዕግሥት ጋር ለመገናኘት ለነደፈው እቅድ አማራጭ መስሎ ስለ ታየው
ዝግ በማለት አቤልንም ከእርምጃው ይጎትተው ነበር ።

ራቅ ወዳለ ሱቅ ሒደው ሲጋራውን ገዝተው ሲመለሱ እስክንድር ዋናውን መንገድ ትቶ በመጻሕፍት ቤቱ ጀርባ
በዋርካው በኩል የሚያስኬደውን መንገድ ያዘ እስክንድር ይህን መንገድ ለምን እንደ መረጠ አቤል ግራ ገብቶት ተከተለው ለመመላለሻ የተቀየሰ መንገድ እይደለም እንዲሁ ብቻ ሰልቸት ያለው ተማሪ መንገድ ማቋረጥ ሲፈለሸግ ይሔድበታል።

ምነው? ለምን በዋናው መንገድ አንሔድም ? ”አለው አቤል ፥ በጥርጣሬ ስሜት ። ሆኖም ርምጃውን አልገታም ።

እስክንድር ከፊት ከፊቱ ስለ ቀደመ ቆሞ ለማነጋገር አልቻለዎም ዋናው መንገድ አንድ መገናኘት የማልፈልገው ሰው። ሲመጣ አይቼ ነው አላው እስክንድር ነ ውሸቱን።

ቤት መጻሕፍቱን አልፈው ወደ ዋርካው አካባቢ ብቅ ሲሉ ፥ የእስክንድር ልብ ክፉኛ መምታት ጀመረ ። አቤል ምንም ዐይነት ጥያቄ እንዳይጠይቀው ለማድረግ ይመስል ግንባሩን አኮማተረው ። እዚህ ላይ ነው ዋናው ችግር አለ በሐሳቡ የመጨረሻው ደረጃ ውጤት እንዳይከሽፍበት እየፈራ።

ትዕግሥትና ማርታ ከዋርካው ሥር ተቀምጠው ሲያጠኑ አያቸው ፣ ትዕግሥት ዐይኗንም ፡ ስሜቷንም ደብተሯ
ላይ እንደ ተከለች ነች ። ማርታ ግን የእነ አቤልን መምጣት በመጠባበቅ ዐይኗን እያቁለጨለጨች ነች ።

አቤል ሁለቱን በተመለከተ ጊዜ ሕዋሳቶቹ በጥርጣሬና በድንጋጤ ተነቃነቁ ። “ የእስክንድር መንገድ መረጣ ያለ ምክንያት አይደለም ሲል አሰበ ። ነገር ግን እነ ትዕግሥትን ከማየት በስተቀር በውል የተከሠተለት አንዳችም ነገር
አልነበረም ።
እስክንድር ከማርታ ጋር በሩቅ ፈገግታ ከተለዋወጠ በኋላ ወደ አቤል መለስ ብሎ ሄደን ሰላም” እንበላቸው ።በሩቅ ሰላም መባሉ ቅር ሊያሰኛቸው ይችላል ” አለው ።

ለአቤል ሁኔታው አላማረውም ። ወደ ዋርካው መሄድ አልፈለገ። ተቀራርቦ ሰላምታ መለዋወጡ ለሱ ያልተለመደ ነገር ነው። ግን እስክንድር ፋታ አልሰጠውም ። እነ ትዕግሥት ጋ ለመሔድ አቤል እንደሚያመነታ ስለ ገባው ቀድሞ ጉዞ ጀምሮአል ።አቤል ተነጥሎት እንዳይቀር ይሉኝታ ይዞት ተከተለው ።

አጠገባቸው እንደ ደረሱ ተጨባበጡ ። አቤል ከትዕግሥት ፊት እንዲህ ሲቀርብ የመጀመሪያ ጊዜው ነው ። የእጆቿን ሙቀት መቀበል አልቻለም ።አጋጣሚውን ተጠቅሞ የትዕግሥትን ወበት በቅርበት ለማጥናት ከቶም አልሞከረም ተደናግጦ የተቋጠረ ፊቱን ሳይፈታ ዝም ብሎ ቆመ ።
በፍቅር የነደደ ልቡን ለማሳየት ፊቱን ከማጨማደድ ሌላ ችሎታ አልነበረውም እንዲህ ፊቱን ካላስከፋባት ካላጨማደደባትና ካላጠቆረባት በስተቀር ውስጥ ውስጡን በፍቅሯ ነዶ መክሰሉን እንደ ምን ልትረዳለት ትችላለች ? ...

ትዕግሥት ራሷ ስትጨብጠው ተደናግጣ በድን እጅዋን ነው የዘረጋችለት ። የሷው መርበትበት የፍቅር ድንጋጤ መሆኑ ይታወቃል የአቤል መኮማተር የነዲድ ፍቅሩ ነጸብራቅ መሆኑን ግን ልትረዳለት አልቻለችም። ከተቀመጠችበት ቦታ አንሥቶ የሚያፈርጣት ይመስል ይብሱን ተረበሸች ። ማርታን በልቧ ረገመቻት ። እሷ ነች ደኅና ከሚያጠኑበት መኝታ ክፍል አውጥታ እዚህ ያመጣቻት ። መኝታ
ክፍል ውስጥ ማርታ ራሷ ወሬ ጀምራ በዘዴ የክፍሉን ሴቶች ካንጫጫችና ካራበሸች በኋላ ትዕግሥትን “እባክሽ
ዋርካው ሥር ሔደን እናጥና እዚህ ቤት ሰላም የለም ” ብላ ገፋፍታ አስወጣቻት ። ነገሩ ሥውር ሤራ እንደ ነበረው ትዕግሥት የገባት አሁን ከአቤል ጋር ሲፋጠጡ ነው

ሁለቱ ፍቅረኞች ብቻ ሳይሆኑ እስክንድርና ማርታም ተደናግጠው የሚናገሩትን አጥተዋል ። መጨባበጡንስ
ተጨባበጡ ። ከዚያስ ምን ይቀጥል ? ምን አርዕስት ይከፈት ?

ድምፃቸውን እንዲያጠፉ የታዘዙ የዋርካው ምርኮኞች ይመስል ሁሉም ጭጭ ! እስክንድር የአቤልን ቁጡ ፊት
ተመልክቶ በልቡ ምን ያህል እንደሚረግመው ገመተ።

“ እንሔድ ! ” አለ አቤል እስክንድር ላይ እንደ መልምጎም እየቃጣው ።

እንዴት ! ተጫውቱ እንጂ አለች ማርታ ወደ አቤል ሳይሆን ወደ እስክንድር እየተመለከተች ።

እስክንድር መልስዓም ባይሰጥ በድጋፍና በልምምጥ ስሜት ዐይኑን እያቁለጨለጨ አቤልን አየው ። አቤል ግን በመጥፎ ስሜት ዐይኑን ማርታ ላይ ተክሎ ነበር ። ቅንድቧ ለምን እንደሚርገበገብ ሊገባው አልቻለም ። ዐይኗ ዳርቻ ላይ የአይን አር በማየቱ ደስ አለው ። ከውበትዋ ይልቅ መጥፎ
ጎኗን ማየት ነበር የሚያስደስተው ። እያያት መቆየት አልፈለገም ። ለአንዳቸውም መልስ ሳይሰጥ ከአጠገባቸው ሔደ።

እስክንድር ፈራ ተባ እያለ በቀስታ ተከተለው ።
ምን ዝጋታው ነው ! ” አለች ማርታ በሽቃ

ትዕግሥት ሰምታ እንዳልሰማች ጭጭ አለች ከውስጥ የሚተናነቃትን እንባ በመታገል ላይ ነበረች ።

ከረፈፍ ! ” ትል ማርታ ደገመች ።

“ ስሚኝ ማርታ እኔ እዚህ የመጣሁት ለትምህርት ነው ። ሌላ ነገር አልፈልግም ለትምህርት ነው በቃ ! ” አለቻት ትዕግሥት ስቅስቅ እያለች ።

ታዲያ እኔ ምን ሁኝ አልኩሽ ? ” ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ቁጣም ጭምር ነበር ።

እንጃ " በቃ ! እኔ ትምህርት ብቻ ነው የምፈልገው !”
ዝጋታሞች ! ” አለች ማርታ በልቧ " ሁለቱንም ፍቅረኞች ደርባ ።

ትዕግሥት ትመስለዋለች ስታጠና እንደ ነበረችው ረዥም ቀሚሷን ለብሳ በነጠላ ጫማ አጭር ቁመቷ ይብሱን ተጋልጦ በፈገግታ ጉንጮቿን እያሠረጎደች አቤል መኝታ ቤት ድረስ በምሽት ከተፍ !

“ ምነው አቤል ? ሰው ለምን ታስቸግራለህ ? እኔንስ ለምን በፍቅር ታሰቃየኛለህ ? ለምን ግልጽ አትሆንልኝም ?? ማፍቀር'ኮ ነውር አይደለም ” ስትለው ...

አቤል ግልጽነቷ እየገፋፋውና የተከዘው ገጽታዋ እያሳዘነው “ እኔ ምን አደረግኩሽ ታዲያ ? ደግሞ ተበዳይ አንቺ ሆንሽ እንዴ ? እኔ ምን ያህል እንደ ተቃጠልኩ ውስጡን ገልጠሽ ባየሽው ! ” አላት "

አትዋሸኝ አቤል ! እውነቱን ንገረኝ ስታየኝ
ግንባርህን የምታኮማትርብኝ ዘግተኸኝ የምታልፈው ለምንድነው ? ፍቅር ነው ጥላቻ ?”

“ የጥላቻ ነገር ለምን ታነሻለሽ ? በእኔና በአንቺ መሐል ጥላቻን ምን አመጣው ? የማደርገው ሁሉ የፍቅር ነው ።በመጥፎ አትተርጉሚብኝ እባክሽ ! ፍቅር ነው።

ታዲያ እንዲህ በዕዉር ፍቅር እንዴት እንዘልቀዋለን አቤል ? ሁለታችንም ውጥረት ላይ ያለን ተማሪዎች ነን። እኔን የገና ማዕበል እየጠበቀኝ ነው። አንተም
መመረቂያ ዓመትህ ነው ፡፡ ግልጽ ካልሆንን እኮ ሁኔታችን ለሁለታችንም ግብ መሰናክል ነው ። "

ከግልጽነቷ ይልቅ የድምጿ ድምቀትና የአነጋገሯ ቀጥተኛነት እየገረመውና በእርግጥ ትእግስት መሆኗን እየተጠ
ጠራጠረ ወይም ደግሞ ትዕግሥት እሱ ከማያውቀው የውስጥ ውበት እንዳላት አርጎ እየገመተ ፥ “ልክ ነሽ የኔ እመቤት ። ሁለታችንም ወጥረት ላይ ነን ። ይህንንስ ካነሳሽ ብዙ የማጫውታት ነገር አለ ። እስቲ ቁጭ በይ የኔ ፍቅር ”
ብሎ የአልጋውን ጠርዝ ሲያመለክታት ...

“አልቀመጥም ፤ እኔ የመጣሁት ከአንተ አንዲት ቃል ለመስማት ብቻ ነው። የምትወደኝ ከሆነ አንዲት ቃል ተንፍስልኝ ” ስትለው ...

የድምጿ ማየልና የገጽታዋ በንዴት መክሰል የቀድሞው ትዕግሥትነቷን ስለ ለወጠበት ፥ “ቀድማኝ አበደች እንዴ ? ”
እያለ ፥ በሀዘን በተደቆሰ ድምፅ ፥ “ አይዞሽ " እንኳን አንድ ቀርቶ ሺህ ቃል እልልሻለሁ ። ብቻ አትጩሂ ።
1
ድምፅሽን ቀንሰሽ አነጋግሪኝ ” ከማለቱ ከአፉ ነጥቃ

አልችልም ። ቀስ ማለት አልችልም ቀስም ዝምም ብዬ ቆይቻል አሁን ግን መናገር አለብኝ ! ” ሳያስበው ወደ አልጋው ሔዳ አጠገቡ ተጠግታ ቁጭ !

አቤል በደስታ ይሁን በድንጋጤ ተረብሾ : ቃልም ሳይተነፍስ ጭጭ ?

በል እንጂ ተናገር ፥ ካንተ ኣንዲት የፍቅር ቃል እፈልጋለው።

“ እሺ ምን ልበልሽ ? ”

“ ከልቤ እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ ፥ በለኝ

ለእንቺ ያለኝን ፍቅር በአንዲት ቃል ብቻ ከመተንፈስ በበርካታ መረጃዎች ላሳይሽ እችላለሁ ብሎ የሸሚዙን ክናድ ገልጦ የእጁን ጠቅሳ ያሳያታል ።

ምን የሆንከው ነው እሱ ? ”

“ በአንቺው ነው ። በአንቺው ነው ! ” ይላታል " የፍቅር እልህ ጉሮሮውን እየተናነቀው ፤ “ እዚያ ምግብ አዳራሽ ውስጥ አንቺን ስመልከት የወደቅኩኝ ጊዜ የተደፋብኝ የትኩስ ወጥ ጠባሳ ነው “

ለመጀመሪያ ጊዜ ያየባት የገጽታ መለዋወጥና የድምፅ ግለት በርዶ ፥ በኀዘን ከንፈሯን ስትመጥለት በማየቱ ደስ
ይለዋል ። ስታዝን ሆዱን ታባባዋለች ።

ይህ ብቻ አይደለም ። አንድ ቀን ደግሞ ይልና ሁኔታውን መናገር ዘግንኖት ዐይኖቹ እንባ ያቀራሉ ። ወንድ ሆኖ ማልቀሱ ትዕግሥትን ቢያፍራትም ዕንባውን ለመግታት ከዐቅሙ በላይ ሆኖበት ይለቀዋል ።

እሷም ስሜቱን ተከትላ እያለቀሰች ፥ “ እሺ ንገረኝ !አንድ ቀን ምን ሆንክ ? ” ትለዋለች

አዎ ! አንድ ቀን በአንቺ ምክንያት ሕይወቴን በገዛ እጄ ላጠፋት ነበር ፡ ካለንበት ሦስተኛ ፎቅ ዘልዬ ልፈጠፈጥ
ነበር።

ትዕግሥት ጮካ ፊቷን ጉያዋ ውስጥ ትደብቀዋለች ።በዝግታ ክንዷን ይዞ። ቀና ያደርጋትና ፡ “ አይዞሽ ።ለማንኛውም ተረፍያለሁ። ግን በዚያ ሁኔታ ብሞት ኖሮ
አንቺ ምን ትሆኝ ነበር ? ” ብሎ ሲጠይቃት ፡

“ ለአንዲት ደቂቃም እዚህ ግቢ አልቀመጥም ነበር ።ወይም ራሴን እገድላለሁ» ወይም አካባቢሎን ጥዬ እኮበልላለሁ ትለዋለች።

እኮበልላለሁ በማለቷ አቤል ይከፋና ለአፍታ ያህል ዝም ይላል ። እሱ ከሞተ እሷም መሞት አለባት ፡ ኮብልላ ማንጋ
ልትደርስ ነው ? የማን ልትሆን ነው ?

ግን እኔ ምን እድርጌህ ነው ራስህን ለማጥፋት የተነሳህው?

አገጣጣሚው ነው ። በእንቺ ፍቅር በምሠቃይበት ከልጅነቴ ጀምሮ የማውቀውን የወላጆቼን ድህነት መባባስና መጨረሻ ደረጃ ላይ መድረስ የሚያረዳ ደብዳቤ ደረሰኝ ። ይሄኔ ለአንቺም ለወላጆቼም መሆን ያልቻለው
እኔነቴ አስጠላኝና ራሴን ለማጥፋት ወሰንኩ ።
እንደገና ከንፈሯን መጥማት ታዲያ እንዲህ የምትወደኝ ከሆነ ለምን ስታየኝ ትሸሻለህ ? ለምን ፊትህን ታጨማድድድብኛለህ ?

ሁሉንም ያደረግኩት ስለምወድሽ ነው አልኩሽኮ ። ከሩቅ የሚያመልኩት ነገር ቀርበው ሲያዩት ያስፈራል ። አንቺንም
ቀርቤ ነነጋግርሽ ያስፈራኝ ይኸው የፍቅር አምልኮቴ ይመስለኛል ። ፊቴን ማኮሳትሬም ልቤ ውስጥ የጋመ ፍቅርሽን ለመከላከል ያደረግኩት ሙከራ ይሆናል እንጂ ተንኮል የለበትም ። እባክሽ በሌላ አትተርጉሚብኝ ፍቅሬ ።

በመልሱ ጥንካሬ ተገርማ ዐይኖቿን እያስለመለመች ለመሆኑ እኔ በምገባበትና በምወጣበት ሰዓት ወይም በማንጠናበት ቦታ ከአንተ ጋር የምንገጣጠመው እንዴት ነው ?
እኔ የማልፍበትን ወይም የማጠናበትን ቦታ የሚነግርህ ስው አለ እንዴ ? ” ብላ ትጠይቄዋለች ።

“ እኔንም በጣም የሚያስገርመኝ ነገር ነው ።ለማያውቅ ሰው የእኔና የአንቺ በየመንገድ መገጣጠም ሆነ ተብሎ የተጠነሰሰ ይመስላል ። ነግር ግን አብዛኛወኑን ጊዜ የማገኝሽ እንዲያው በአጋጣሚ ነው ። የፍቅር አምላክ የሚያቅደው ግንኙነት ፎን፡ ማለቱ ይሻላል መሰለኝ ። ብቻ ፍቅረኛች ባይናጋሩም ቃላት ባይለዋወጡም ልብ ለልብ የሚጎናኙበትና ሐሳብ ለሐሳብ የሚለዋወጡበት ተአምራዊ ጥበብ ያላቸው ይመስለኛል ። ወይም ደግሞ የሥነ ልቡና ጥናት ሊቃውንት ሳይኪክ ፓወር የሚሉት ረቂቅ መገናኛ ለፍቅረኞች መሰላል ሆኖ ሳያገለግል አይቀርም ”

በትንታኔው እየተማረከች ፊቷን ትከሻው ላይ ደገፍ ታደርጋለች ። በልጅነቱ ያያቸው ዋርካ ሥር የሚገናኙት ፍቅረኞች ትዝ ይሉታል ። “ እነሱስ ከዚህ የበለጠ ምን እደረጉ ? ወንድየው ሴቲቱን ከጎኑ ኣስቀምጦ የልቡን የስሜቱን የውስጡን አሟጦ ከማውራት ሌላ ምን ይሰራል ?
ሴቲቱ በወሬው ቃጠሎ እየተንቃቃች በወንድየው ደረት ላይ ከመቅለጥ ሌላ ምን ፈየደች ? ” እያለ ያስባል ።
ትዕግሥት በጣም ስለ ተጠጋችው ፡ የሰውነቷ ሙቀት ልብሱን ዐልፎ እየተሰማው የወሲብ ስሜቱን ይቀሰቅስበታል ። ፊቷ ትከሻውን ተደግፎ ጸጒሯ አንገቱን ይኮሰኩሰዋል ፊቷን ከትከሻው ላይ ሳታነሳ ከአንገቷ ቀና ብላ ዐይኖቿን ዐይኖቹ ላይ ስታስለመልማቸው ስሜቷ ይግባውና ሲስማት ይፈልጋል ነገር ግን በፍራቻ አንድም የሰውነቱ
ክፍል መንቀሳቀስ ያቅተዋል ። አንዳች ነገር ከሙቀት ስሜት ጋር ተቀላቅሎ ሰውነቱን ይወርረዋል ።

በዘዴና በጥንቃቄ ሳይሆን ፥ ፍርሀቱ በፈጠረበት የአውሬ ስሜት ተገፍቶ ፥ ሳታስበው ከንፈሩን ከንፈሯ ላይ ይከድ
ንባትና ፥ ደስ የሚል ሙቀት ይሰማዋል ። በውቀቱ ኃይል የአፍላ ፍቅር ወዘና ከንፈራቸው ላይ የሚንጠባጠብ እየመሰለው ፥ አንዳቸው በአንዳቸው ከንፈር ላይ የቀለጡ ሆኖነው ተሰማው።

ለአፍታ ያህል ቀና ብሎ አይቷት ፥ ተመልሶ ጉንጯን ከንፈሯን ፡ አንገቷን ሲስም ጸጉሯን ትከሻዋን ጡቷን ሲያሻሽ

“ ዕረፍ ፤ ቨርጂን ነኝ ” የሚል ደካማ ድምፅ ይሰማዋል

“ እሺ ቢልም ? እጁ መዳሰሱን ሊያቋርጥ አልቻለም ።

እረረፍ ኮ ነው የምልህ ! ” ብላ አንቧርቃበት ፥ ከአጠገቡ እመር ብላ ትነሣለች።

። ምነው ትዕግሥቴ ? ”

ሒድ ! ስድ ! ወንዶች ስትባሉ ይሔው ናችሁ ዘላችሁ እዚያ ላይ ነው ። እኔ ዘማዊት አይደለሁም እያለች ለመልስ ዕድል ሳትሰጠው እየሮጠች ስትወጣ

ቆይ እንጂ ትዕግሥት እኔኮ፡ መጥፎ ነገር አላሰብኩም ። ቆዪኝ እባክሽ ፤ በሕይወቴ ፈርደሽ አትሒጂ ፤ እኔ ያላንቺ ፍቅር መኖር አልችልም እያለ በሩጫ ሲከተላት
ከእንቅልፉ ባነነ • ••...

ቢነቃም ዐይኑን መግለጥ አልፈልገም። ያ ሁሉ ፍሥሐ ውሸት ነወ ማለት ነው? እንቅልፍ ዐይን መጨፈን ብቻ በሆነና ከትእግስት ጋር ካገናኘው ሕልሙ ላለመንቃት ዕድሜ ልኩን ዐይኑን በጨፈነ ምን ነበረበት.....

💥ይቀጥላል💥
👍7