አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

የገዳሙ ምዕራብ ክፍል በጥቅጥቅ ደኖች የተሞላ ሲሆን፣ምዕመኑ በየዛፉ ስር ተጠልለው በአርምሞ ፀሎት ያደርጋሉ፡፡ ፀበል ይጠጣሉ። ደቡባዊው ክፍሉ ደግሞ፣ ከፍተኛ ተራራ ላይ ያለ ሲሆን፣
ወደታች ያለው የሚያሰፈራ መጨረሻው ማይታይ ጥልቅ ገደል ነው።
ለገዳሙ እንደአጥር ያገለግላል፡፡ እዚህ አካባቢ የበቀሉ ትላልቅ ዛፎች ቅርንጫፍ ከግቢው አልፎ ወደ ገደሉ ይዘናፈላሉ፡፡ በዚህ አቅጣጫ ገደላማና በረሃማ ስለሆነ፣የሰው ዘር ዝር ብሎበት ሚያውቅ
አይመስልም፡፡ ገና ሳየው፣ በውስጤ እራሴን ማጠፋበት ትክክለኛው ቦታ
እንደሆነ ተሰማኝ፡፡ ጠጋ ብዬ ለወራት የተዘጋጀሁበትን ሰው ሳያየኝ የምፈፅምበትን ዛፍ መምረጥ ጀመርኩ። ውስጤ ምንም አይነት ፍርሃት እየተሰማኝ አይደለም፡፡ አሁን ውስጤ የሚፈልገውን ቦታ አግኝቷል፡፡
ስህተት ላለመፍጠር፣ የግቢውን እንቅስቃሴ በደንብ ማወቅ፣ ተስማሚ
ሰዓት ለመምረጥ፣ አብዛኛውን ጊዜ እዛ አካባቢ ያሉ ዛፎች ስር ቁጭ ብዬ ሰው ጭር የሚልበትን አመቺ ሁኔታ እያጠናሁ፣ የገዛሁትን ፎጣ ለአሰብኩት አላማ እንዲመቸኝ በመቀስ እየቆረጥኩ በሚገባ
አስተካክዬዋለሁ፡፡ ከወራት በኋላ፣ የመጨረሻው መጨረሻ ደርሷል፡፡
ሰዎች እንዳይጠራጠሩኝ ምእመኑ ሚያደርጉትን ሁሉ እፈፅማለሁ፡፡ ሁሌ ሰርክ አስራ አንድ ሰአት ጀምሮ የግቢው ዋና አስተባባሪና ሰባኪ፣ ትምህርት ይሰጣል፡፡ እረጅም ቀጠን ያለ፣ ጥሩ
ተናጋሪ ጎልማሳ ነው፡፡ በስብከቱ ሰዓት ከፕሮግራሙ የሚቀር አንድም ሰው የለም፡፡ ትክክለኛው ሰዓት እንደሆነ እርግጠኛ ሆንኩ፡፡ አንድ ቀን፣የመጨረሻ ከኔ ጋር የቀሩትን የትምህርት ማስረጃዬን ጨምሮ፣ ማስራጃ ሊሆኑ ሚችሉትን፣ እንዳይገኙ ቆፍሬ ስቀብር ዋልኩ፡፡ ማታ ምዕመኑ ለጉባዔ ሲሄድ እኔ የተለመደው ቦታዬ ቁጭ ብዬ የእቅዴን መጨረሻ
ለመፈፀም አደፈጥኩ፡፡ እንደጠበኩት ፀጥ ረጭ አለ፡፡ ተነስቼ ያስተካከልኩትን ፎጣ ቼክ አድርጌ፣ ወደ መረጥኩት ዛፍ ሄድኩ፡፡ ድንገት ኬት እንደመጣ ያላስተዋልኩት አስተባባሪ፤

“እንዴት አመሸህ?” አለኝ፡፡

“እግዚአብሄር ይመስገን!” በንዴት መለስኩ፡፡

“የምሽት ጉባኤ ተጀምሯል እኮ፣ አትሄድም እንዴ?”

“እየሄድኩ ነው፡፡” ኬት ነው የመጣው ባካቹ ኮቴ ቢስ፡፡ ሄጄ የተለመደውን ስብከት ተከታተልኩ፡፡

ከጉባኤ ስመለስ መልካሙን አገኘሁት፡፡ ከገባንበት ቀን ጀምሮ ባገኘኝ ቁጥር ያወራኛል፡፡ የገባሁ ቀን ስለ ላጨኝ የተወሰነ ገንዘብ ሰጥቼዋለሁ፡፡ ሊቀርበኝ ይሞክራል፡፡ ለሻወር ውሃ ላምጣልህ ይለኛል፡፡ሲያመጣ የተወሰነ ነገር እሰጠዋለሁ፡፡ በዛ አምኖኝ ነው መሰል፣ ስለ ገዳሙ ጥሩም መጥፎም የሚሰማውን ይነግረኛል፡፡ የገዳሙ አባት
ከፍተኛ ሀይል እንዳላቸው፣ እርሳቸው ሲመጡ፣ በግቢ ውስጥ ሰይጣን
ያለበት ሁሉ እንደሚጫኽ፣ ከከፍተኛ የባለስልጣን ሚስቶች ጀምሮ የውጪ ሃገር ዜጎች እዚህ እንደሚመጡ ይነግረኛል፡፡ ወራትን የቆዩ ምዕመናን አስተባባሪ ሆነው እንደሚሾሙ፣ ግን አንዳንዶች ያልሆነ ወሬ ስለሚያወሩ መባረር እንደሚያሰጋቸው ያጫውተኛል፡፡ ቢወጡ መሄጂያ፣መጠጊያ ስለሌላቸው እዛ መሆንን እንደመረጡ፣ ተሸሎኝ ወደ መኖሪያዬ ስመለስ እንድጠይቀው፣ እዚህ ኑሮ ከባድ እንደሆነ፣ ከቤት ውጪ ሌላ
ደሞዝ እንደሌላቸው፣ እንደኔ ያሉ አንዳንድ ምዕመናን በሚያደርጉላቸው ድጎማ እንደሚኖሩ አጫወተኝ፡፡

አብዛኛው በገዳሙ የሚገኙት ምዕመናን ወጣት ናቸው፡፡ አማካኝ ዕድሜ ቢስላ ከሰላሳዎቹ መጀመሪያ አይዘልም፡፡ አብዛኞቹ ለሳምንታትና ለወራት ሚቆዩ ናቸው። ባገኘሁት አጋጣሚ ብዙኃኑ ሰው የመጣበት ምክንያት፣ ሰይጣን አለብኝ ብሎ በመጨነቅ፣ በህይወት አለመቃናት
የተከሰተ ጭንቀትና ሌሎች ዓለማዊ ምክንያቶች ናቸው፡፡ በገዳሙ ሁለተኛ ሳምንት እንዳለፈኝ፣ አይታወቅምኮ እኔም ስይጣን አሞኝ ይሆናል ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ሰው እንዴት በሀገር ሰላም እራሴን ላጥፋ ብሎ፣ ይሄን ሁሉ ሀገር አቋርጦ ይመጣል? ለማንኛውም፣ ፀሎት
መድሃኒት ነው ብዬ፣ ለሱባኤ ዋሻ ገባሁ፡፡

የዋሻው አስተባባሪ መነኩሲት፣ ስለዋሻው ህግና ደንብ ትነግረኛለች፤ አፍጥጬ አያታለሁ፡፡ እጅግ ዘመናዊ የምትመስል፣ ሴት ናት፡፡ ጥርት ያለው የፊቷ ቆዳ፣ የገዳማዊ ሴት ሳይሆን፣ ሜክ አፕ
የተቀባች፣ ኑሮ የደላት፣ የከተማ ልጅ ፊት ይመስላል፡፡ ከተሸፈነችበት ነጭ ነጠላ፣ አልፎ ሚታየው ንፁህ፣ ሉጫና ደማቅ ጥቁር ፀጉሯን ሳይ መሀል አዲስ አበባ እንጂ፣ ገዳም ውስጥ ያለሁ አልመሰልህ አለኝ፡፡እያወራች ስታየኝ በሃዘኔታ የምትመለከተኝ መሰለኝ፡፡ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ስንት ጊዜ እንደምፀለይ፣ እንደሚሰገድ፣ እግዚኦ ሲባል እንዴት
ጣት እንደሚቆጠር፣ የለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ፀሎት በእርሷ እየተመራን እንደምንፀልይ አስረዳችኝ፡፡

እኔ ይህች ለጋ ሴት እዚህ ምን ትሰራለች እያልኩ በመገረም አያታለሁ፡፡ አይደለም ስግደት፣ ፆም ባለፈበት አልፋ ምታውቅ
አልመስልህ አለኝ፡፡ እኔ እዚህ ከመጣሁ፣ በሁለት ሳምንት ብቻ ብዙ እንደከሳው ታውቆኛል፡፡ የሱሪዬን ቀበቶ ቀዳዳ ሁለቴ ቀይሬያለሁ፡፡በዋሻው ሚቆየው ሦስት፣ ሰባት፣ አስራ አራት እና ሃያ አንድ ቀን ነው፡፡በሱባኤው ጊዜ፣ ለምትፀልይበት ጉዳይ አርሴማ በአምሳል ተገልጣ
መፍትሄ ትስጥሃለች አለችኝ፡፡ እንደታዘዝኩት መፀለይኩ፣ መሰገድ
ጀመርኩ፡፡ በጣም ከባድ ነው፡፡ እረሃብ አጠወለገኝ፤ ስግደቱ አወላለቀኝ፡፡
የለሊቱ ቅዝቃዜ ይጠዘጥዛል፡፡ መሬቱ በጣም የቆረቁራል፡፡ እንቅልፍ ማይታሰብ ነው፡፡ እዚህ አንዱ ቀን በጣም እረጅም ነው፡፡ ከሦስት ቀን በፊት መውጣት ቢቻል፣ ሲነጋ ውልቅ እል ነበር፡፡ በዛ ላይ ፣ትንሽ ሸለብ ሲያደርገኝ፣ ሰይጣን ክፋቱ መነኩሲቱን እያመጣብኝ ይፈትነኛል፡፡
ሦስቱን ቀን እንደምንም ጨረስኩኝ፡፡ ልወጣ ስል እንዳገባቤ መነኩሲቷ፣
አናገረችኝ::

“እንዴት ነበር ሱባኤህ?

ጥሩ ነበር አልከትና ከዋሻው ወጥቼ ወደ አዳራሼ ተመለስኩኝ፡፡ማታ እንቅልፍ አልወሰደኝም፡፡ አሁን ሁሉም ነገር ታክቶኛል። ባለፈው ያ አስተባባሪ ነው ከመንገዴ ያቆመኝ፡፡ አሁን መሳሳት የለብኝም፡፡
የባለፈውን ስህተት ላለመድገም ለሊቱን እያቀድኩ እስኪነጋልኝ ቸኮልኩኝ፡፡ እንቅልፍ በዐይኔ ሳይዞር ነጋ፡፡ አስር ሰዓት አካባቢ ሲሆን፣ ሙሉ ትጥቄን ይዤ ወጣሁ፡፡ ያቀድኩትን ለመፈፀም ገመዱን አስተካክዬ ዛፉ ላይ ካስርኩ ቦሃላ፣ እስኪጨልም ለመደበቂያነት ወዳሰብኩት
የሚያስፈራው ተራራ ጀርባ ቀስ ብዬ ለመውረድ ስል፣ አፈሩ እየተናደ ቁልቁል ሲዖል ወደ ሚመስለው ጥልቅ ገደል ይዞኝ መውረድ ጀመርኩኝ፡፡


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
#ሰመመን


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...መብራቱን ላጥፋው ? ” አላት ፡ በጣም በደከመ “ እንዳሻህ ” በማለት ዐይነት ትከሻዋን ነቀነቀች ስሜትና ወበቅ ስሳፈኗት መተንፈስ አልቻለችም ሁለቱም በድካም ሰመመናዊ እንቅልፍ አሸለባቸው
ለማ በሰመመን በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲው ተጓዘ ።

ያ ራስ ሆቴል ተቀምጠው ያያቸው ሰውዩ ይመስለዋል በስብሰባ መሐል “ አጀንዳ ይያዝልኝ ” እያለ ደጋማም እጁን ያወጣል

“ እሺ አጀንዳህ ምንድነው? ” ይለዋል የስብሰባው ሊቀ መንበር ከልጃገረድ ተማሪዎቻቸው ጋር ስለሚቀብጡ መምህራን ጉዳይ ነው ” ይላል ሰውዬው ፥ መላ ሰውነቱን በብስጭት እያወራጨ

ለማ ፊቱ ቀልቶ ፡ በራው ላብ አንቸፍፎ ያጋለጠው ይመስለዋል "

እንድ ተማሪ ደግሞ እጁን አውጥቶ ለሰውዬው ድጋፍ ይሰጣል " ይህ ወጣት ለማ ክፍል ውስጥ በጣም የሚያደንቀውም የሚፈራውም ጠንካራ ተማሪ መሰለው ።

አዎ ! እንዲያውም ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ አጀንዳ ነው ይላል ተማሪው ገንፍሎ ።

እሺ " በል አጀንዳህን አብራራ።” ይላል ሊቀ መንበሩ ።

“ በጣም የሚያሳዝን ተግበር ነው ” ይላል ሰውዬው "
በጣም የሚያንገበግብ ነው እንጂ ፣ ” ይላል ተማሪው ተደርቦ።

“በሥነ ሥርዓት ተናገሩ” ይላል ሊቀ መንበሩ በቁጣ ሰውየው ብቻ ንግግሩን ይቀጥላል ።

“በውነቱ በዩኒቨርስቲያችን ውስጥ እንዲህ ዐይነት ድርጊት ሲፈጸም ያሳዝናል ። የዩኒቨርስቲዉን ሥርዓት ማበላሸት ነው ። አንድ መምህር የሚያስተምራትን ተማሪ አውጥቶአት ግሪል ጋብዞአት ከሲኒማ ኢትዮጵያ በስተጀርባ ከሚገኝ አንድ ስውር መኝታ ቤት ይዞአት ሲገባ እኔ ራሴ በዐይኔ በብሌኔ አይቻለሁ ። ሊቀ መንበር ፥ ይህን ጉዳይ ከግላዊ ነጻነት አኳያ አይተው እንዳያይዘጉት አደራ እላለሁ ።መታየት ያለበት በዩኒቨርስቲዉ ውስጥ ከሚያስከትለው የአሠራር ብልሽት አኳያ ነው እጅ ወዳጁ ላይ ሊሰነዘር አይደፍርም " ደካማ ተማሪውን እቅፎ መምህርያም ዐይኑ እያየ ፈተናውን አይጥላትም ። እንዲህ ከቀጠለ ደግሞ ዩኒቨርስቲዉ ውስጥ የሚያስፈልገው ጭንቅላት መሆኑ ቀርቶ ወሲብ ሊሆን ነው ።

ለማ " ላቡ በጀርባው ሲንቆረቆር እየተስማሙ ብቸኛ ላለመሆን በዐይኑ ሚስተር ራህማንን ፍለጋ አዳራሹን ያማትራል ሚስተር ራህማን የሉም ።

ተጨማሪ ያልተጠቀሰ ነጥብ እያል ተማሪዉ ጣቱን ያወጣል " ሊቀ መንበሩ እንዲናገር ይፈቅድለታል

“ አዎ ! በተጨማሪም ጒዳዩ መታየት ያለበት ከዩኒቨርስቲው የአሠራር ስልት ጋር ነው ።ዩኒቨርስቲው የተማሪዎችን የፈተና ወረቀት አርሞ ማርክ የሚሰጠው በስኬል ሲስተም ነው ። ስለሆነም አንድ መምህር የሚወዳትን ደካማ ተማሪ ከውድቀት ለማዳን የአንድ ጎበዝ ተማሪውን ዕድል እንደሚያበላሽ ፡ ምናልባት ባይጥለው እንኳ ይፈጃውን እንደሚቀንስበት አብሮ መታየት አለበት “ ”

“እሺ " እንግዲያ ! ቤቱ ይነጋገርበት” ይላል ሊቀመንበሩ ። በአዳራሹ ውስጥ ታላቅ ማዕበል የተነሣ ይመስል ሁሉም ጸጥ ረጭ ይላል “ የለማ ነፍስ በማዕበሉ ክፉኛ የተንገላታች ያህል ድምፅ የሌለው ጩኸት ትጮሀለች " ውስጥ ውስጡን ብቻዋን ትንፈራገጣለች ።

ከረዥም ጸጥታና እርስ በርስ መፋጠጥ በኋላ ፥ ከተሰበሰቡት ተሳታፊዎች አንዱ ተነሥቶ "

“ አጀንዳ ያስያዙት ግለሰብ ጥፋተኛውን ሊጠቁም ይችላሉ ? ” ሲል ይጠይቃል
በሚገባ ነዋ ! ያው መሐላችሁ ለማ
ካብት ይደመር እያለ በጣቱ ያመለክታል

“ማ? ! ” ብሎ ለማ ሲባርቅ፡ በእርግጥ ድምፅ ስላወጣ ከሰመመናዌ እንቅልፍ
ባንኖ ቤተልሔምንም አባነናት

“ውይ ምን ነካህ ?” አለች ቤተልሔም በድምፁ ደንግጣ።

“ እ ? ምንም ። ቅዠት ነው ” አላት : ሥራ ሥሮች በጭንቀት ተገታትረው ፊቱን አጨፍግጎ ።

በጭንቀት በተጨናበሰው ስሜቱ ሲያያት አጠገቡ የተኛችው ኮረዳ ሰይጣን መሰለችው ። እሷን ያቀፈበት እጁ
ዘግነነው ፤ቀስ ብሎ ክንዱን ከአንገቷ ሥር አወጣው ።

ቤተልሔም ደንግጣ " ዐይኖቿን በሚያስፈራው የለማ ፊት ላይ አንከባለለቻቸው።

“ በዚህች ደቂቃ የዐይኖቿ ውበት አልታየውም " ሁለተኛ እኔ ከማስተምርበት ክፍል አንዳትቀሪ እሺ?” አላት በመቆጣትም በማባበልም ዐይነት ምናልባት ሊያስጠረጥራቸው ከሚችሉት መንገዶች አንዱን መጥረጉ ነበር።

ቤተልሔም ምንም አልመለሰችለትም ። ለማ ዐይን ውስጥ ቀንዳቸውን አሹለው በተጠንቀቅ የቆሙ ሰይጣኖች
ተመለከተች የሴትነት ኃይሏን የተሸከሙት ዐይኖቿ እኒህን ሰይጣኖች ማሸነፍ አለባቸው ። እናም ስይጣናቱን በቆሙበት ብቸኛ መሣሪያዎቿ ዐይኖቿን ዐይኑ ላይ ማንከባለሏን ቀጠለች ። እንዲያ ሲንከባለሉ የሚታዩ እንጂ የሚያዩ አይመስሉም የዐይኖቻቸው ፍልሚያ የሁለቱንም ምላስ አሳስረው....
=========

“ ...ኧረ መላ በሉ ወዳጅ ዘመዶቼ
ዐይን አፋር ሆኛለሁ ዐይን አፋር አይቼ
ሰሳምታ አልሰጠኋት አሳነጋገርኳት
በዐይን ብቻ እያየሁ ሦስት ወር ወደድኳት

አቤል መተከዣውን ሙዚቃ በለሆሳስ እያዜመ መኝታው ላይ ጋደም እንዳለ በዐይኑ ማፍቀር የጀመረበትን ጊዜ
ርቀት ይለካ ጀመር ። ለወጉ ያህል ዐይኑን መጽሐፍ ላይ ሰክሷል ፤ ነገር ግን በፊደላት ፈንታ በርካታ የትዕግሥት
ምስሎች ነበሩ መጽሐፉ ውስጥ የሚነበቡለት ሳያስበው እርሳስ ከኪሱ አውጥቶ ስሌት ጀመረ ።

“ሦስት ወር ዐሥራ ሁለት ሳምንት ፥ ዘጠና ቀን ሁለት ሺህ አንድ መቶ ስድሳ ሰዓት አንድ መቶ ሃያ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ደቂቃ ፤ ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ሴኮንዶች ... እንዴት በዚህ ሁሉ ጊዜ አንዲት ቃል እንኳ ሳልተነፍስላት እቆያለህ ? እንዴት ይህን ያህል ጊዜ በዐይን ፍቅር ብቻ እንገላታለሁ ? ! አንድ ወንድ እንዴት ይህን ያህል ጊዜ ልቡን ለሴት ልጅ ይሰጣል?” እያለ ሲያስብ
ድንገት ሳምሶን ጉልቤው ” የመኝታ ክፍሉን በር ከፍቶ ዘው አለ።

ከፀሐይ ላይ ስለ መጣ በስፖርት የዳበረው ጡንቻው ያብለጨልጭ ነበር አብዛኛውን ጊዜ በካኒቴራ ወይም
ጉርድ ሸሚዝ ነው የሚውለን ።

ተነሥ ደብዳቤ መጥቶልሃል ። ሰምህ ተለጥፎአል አለው አቤልን አስገምጋሚ ድምፅ አለው ። ልማድ ሆኖበት ረጋ ብሎ መናገር አይችልም ። ሳይቆጣም የተቆጣ
ይመስላል ። አቤልን ይወደዋል ። አቤል ግን ኣጸፋውን አይመልስለትም ሁሌ ዝምነው “ ይህንን ጸባዩንም ቢሆን ሳምሶን ጉልቤው የመኝታ ክፍል ጓደኛው እንደ መሆኑ መጠን ይረዳለታል ።

አቤልን ሁለት የዩኒቨርስቲዉ ወጣቶች በዐይን ፍቅረኝነቱ ሲያሙት ሰምቶ ካልተደባደብኩ ብሎ በግድ ነበር
የተገላገለው ። ፈጽሞ ጥቃቱን አይወድም

“ እውነትክን ነው ? ” አለው አቤል ፡ የደብዳቤውን መምጣት በመጠራጠር ። የደብዳቤ መምጣት ማንንም ስለሚያጓጓ ተማሪዎች አንዳንዱን ሳይመጣለት “ መጥቶልሃል ” እያሉ ልብ መስቀል የተለመደ ነበር ።

“ እውነቴን ነው ይልቅ የፖስታ ማደያው ቢሮ ሳይዘጋ ቶሎ ሒድ” አለውና ሳምሶን በአክብሮት ዘሎ አልጋው ላይ መጣ ። መኝታው ላይ በርጋታ ወጥቶ አያውቅም ።
የአልጋውን የጠርዝ ብረት ተመርኩዞ ሽቅብ ካልዘለለ አይሆንለትም ። ድብርትን ከሚያበሽቁት ነገሮች አንዱ
ሳምሶን መኝታው ላይ ሲወጣ የሚሰማው የአልጋው መንገጫገጭ ነው ።ተኝቶም ከሆነ ያባንነዋል ።

አቤል በነጠላ ጫማ በፍጥነት እርምጃ የመኝታ ቤቱን ደረጃ ወርዶ በሐሳቡ ማን ይሆን የጻፈልኝ ? ” እያለ በጉጉት ከደብዳቤ መቀበያው ቢሮ ደረሰ ።

“ የላኪው አድራሻ ” በሚለው በኩል የተጻፈው የእናቱ ስም ነበር ። የአራተኛ ዓመት ትምህርቱን ከጀመረ ከቤተሰቡ ደብዳቤ መጥቶለት አያውቅም ነበር እሱም ልኮ አያውቅም ደብዳቤውን
👍2
ለማንበብ ተቻኩሎ በመጣበት ፍጥነት ተመልሶ ገና ከምኝታ ክፍሉ በር ላይ ሲደርስ እሽጉን ቀደደው

“ እ ከየት ነው ? ” አለው ሳምሶን 'አ አልጋው ላይ እንደ ተንጋለለ።

“ ከቤተሰቦቼ ነው ”አለውና አቤል ከመኝታው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብሎ ያነብ ጀመር ።

“ እንደምን አለህ ልጄ ? ይህ ጽሑፍ የእኔ የናት። መሆኑን አትጠራጠር ” ይላል የደብዳቤው መግቢያ አቤል በእርግጥ የእናቱ ጽሕፈት መሆኑን ሊያምን አልቻ
ለም ። ነገር ግን ከቤተሰቡ ውስጥ እንደዚያ ዐይነት የእጅ ጽሑፍ ያለው ሌላ ሰው እንደሌለ ገመተ ። በቅርቡ ከማይምነት የተላቀቀ ጣት እንዳረፈበት በፊደል አጣጣሉ በመጫን የተጐዳው ወረቀት ያስታውቃል ።አቤል የሁለተኛ ዓመት ትምህርቱን እንደ ጨረሰ ወላጆቹን ሊጠይቃቸው ሔዶ በነበረበት ጊዜ ፥ እናቱ መሠረተ ትምህርት መጀመራቸውን
ነግረውት ነበር ። ሆኖም ይህን ያህል አርኪ ውጤት ያሳያሉ ብሎ አልገመተም ነበር ። ሕፃናት ማንበብና መጻፍ ቢችሉ
በዕድሜያቸው ምክንያት አያስደንቅም ። የወላጆቹ ከማይምነት መላቀቅ ግን ባህላችን ሆኖ ከደማችን እስኪዋሃድ
ድረስ ለጊዜው ያስደንቀናል ።

ተአምር ነው !” አለ አቤል በልቡ በዐይነ ሕሊናው በእጃቸው ብዕር ይዘው ከወረቀት ላይ ቃላት የሚያሰፍሩ
እናቱን እየተመለከተ ። መንፈሱ በደስታ ተወራጨ ። ጥሩ ነገር ማየት ጥሩ ሕልም ያሳልማል ። አቤልም ለአፍታ ያህል
በልቡ ትምህርቱን ጨርሶ ለኅብረተሰቡ ሊያበረክት የሚችለውን የተቀደሰ ተግባር አሰበ ። ለብልጽግናና ለተቀደሱ ግቦች ሀገሪቱ የምትጠብቀው የጋራ እጅ ብሐሳቡ ታየው ።እናም አንዳች የደስታና የተስፋ ስሜት ሰውነቱረን ወረረው
ነገር ግን ደብዳቤውን ዘልቆ ሊያነብ በቅጽበት ስሜቱ ተለዋወጠ ።

ቁትጽፍልን ይህን ያህል ለመቆየት እንደምን አስቻለህ ልጄ ? ደብዳቤም እኮ ተስፋ ነው ። አደራህን የምልህ ነገር ልጄ መመረቂያህ ቀን ሲደርስ እንድትነግረኝ
ነው ። እንዲያው እንደ ምንም ብዬ እመጣለሁ ። ቆብህን የምትጭንበትን ያንን ወርቅ ቀን አጠገብህ ሆኜ እልል
እያልኩ ማየት አለብኝ። አሁንማ ዓመቱን አጋምሰኸዋል፡ትንሽ ነው የቀረህ ። አባትህ ጤናም የለው ። ሁለቱንም አህዮች ሽጦአቸው ውሎው ከቤት ሆኗል መንቀሳቀስ አልቻለም ።በአሁኑ ጊዜ የእሱ ጓደኞች በጋራ ተደራጅተው ያርሳሉ ።
እንዴት የሞቀ ቤት አላቸው መሰለህ ! አርሶ ለባላባት መገበር ከቀረ ወዲህ የገበሬው ቤት ሙሉ ነው ። ምን ይሆናል !
አባትን ለዚህ አልታደለም ። ያ አስሙ በየጊዜው እየተነሳበት ያሠቃየዋል ። ቤተሰቡንደግፋ የያዘችው ያቺ አንድ
ላም ናት ። የሷንም ወተት ለተከራይዎቹ ማድረስ እንዴት ችግር መሰለህ ! ቤት ውስጥ የሚላክ ትንሽ ልጅ የለ ! እንዲያ መዋተት ነው ። ብቻ ግድ የለም ። ይኸው መውደቂያችኝ ላይ አምላክ አንተን አድርሶልናል ። እንግዲህ ምርኩዛችን
ነህ ። እጅህን እየጠበቅን ነው ልጄ !...

አቤል ደብዳቤውን ጨርሶ ማንበብ አልቻለም ። ደብዳቤው ላይ የሰፈሩት የሰቆቃው ጥሪ ፊደሎች እንባ ባቀረሩት
ዐይኖቹ ጎልተይን ብዥ ብዥና እያሉ ታዩት ወላጆቹ ዘንድሮ ይመረቅናል ብለው ማሰባቸውና በአንጻሩ እሱ በዚ ዓመት
ትምህርቱን እንደማይጨርስ አድርጎ መገመቱ ግላዊ የአእምሮ ግጭት ውስጥ ከተተው ። ነገሮች ተምታቱበት ድህነት ! ... ድህነት ! ... ድህነት ! ... ፍቅር ... የዐይን ፍቅር ! ...ትምህርት !... ትምህርት !

“ ድሀ ማፍቀር አይችልም ማለት ነውን ? ” ሲል ራሱን በራሱ ጠየቀ ። " አዎን አይችልም ፡ እንደምን ይችላል !
ከድህነቱ ለመፈወስ ይፍጨረጨራል ወይስ ፍቅሩን ያስታምማል ? ... እኔ ግን ድህነቴን የማላውቅ ዕውር ነኝ ። ለድህነቱ መፍትሔ ሳላገኝ ፍቅር ጀመርኩ እና አሁን የወላጆቼ የሰቆቃ ጥሪ በጠበጠኝ ። ... ግን ይታየኛል ።ለሁለቱም አልሆንም ። ከድህነቴም አልፈወስ ፥ ለፍቅርም አልበቃ ! . . . አዎ ! ለሁሉም አልሆንም ! ” እያለ በሐሳቡ ተወራጨ።

ድህኔትና የዐይን ፍቅር በእሱ የተነሣ ከፊት ለፊቱ ቆመው ፍልሚያ የገጠሙ መሰለው ። ድህነት የተበጣጠሰ ጥብቆ ለብሶ ተባዮች በሰውነቱ ላይ ፈልተው ፡ የተንጨባረረ ጸጉሩን እየፎከተ “ አድነኝ ” እያለ የተጠጋው መሰለው ። በአንጻሩ ደግሞ ፍቅር የተጐሳቆለና የከሳ ሰው
ነቱን አኮራምቶ የተራቡ ዐይኖቹን እያስለመለመ አስታመኝ ” ብሎ የተጠጋው መሰለው ።

ጥጋበኛ ድሀ ! ” ሲል አቤል ራሱን ሰደበ ። ዐይኑ ላይ የተራቀመው እንባ እስካሁን ጠብ አላለም ። ያሳለፈው ረዥም የድህነት ዘመን ታየው።

💥ይቀጥላል💥
👍1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

#የመጨረሻው_መጨረሻ

ድንገት ስነቃ እራሴን አልጋ ላይ በጀርባዬ ተዘርሬ አገኘሁት፡፡ከፍተኛ ህመም ይሰማኛል፡፡ እራሴ አካባቢ፣ በቀኝ በኩል ሰውነቴን፣ፊቴን ይጠዘጥዘኛል፡፡ ዐይኖቼን ለመክፈት ሞከርኩ፡፡ የቀኝ ዐይኔን
ህመም ተሰማኝ፡፡ አልከፈት አለኝ፡፡ ዐይኔ ምን እንደሆነ ለመዳበስ፣ የቀኝ እጄን ለማንሳት ስሞክር፣ እ...ህ... ከፍተኛ ህመም፡፡ ማንቀሳቀስም፣ ማንሳትም አልቻልኩም፡፡ እጄስ ምን ሆኖ ነው...? ወደ እጄ ዞር ስል፣አንገቴ ከሆነ ነገር ጋር ታስሯል፡፡ ምን ሆኜ ነው..? የት ነው ያለሁት..? ማን ነው እዚህ ያመጣኝ...? በግራ እጄ ላይ የግልኮስ ገመድ
ተንጠልጥሎ አየሁ፡፡ ሆስፒታል ነው ያለሁት። የት ሆስፒታል ነው ያለሁት?፣ ምን ሆኜ ነው...? ለማስታወስ ሞከርኩ፡፡ ብዙ ጥያቄዎች በፍጥነት በጭንቅላቴ ተመላለሱብኝ፡፡ በበር በኩል፣ በርቀት አንድ ነጭ ገዋን የለበሰ ሰው ሲገባ አየሁ፡፡ እንዲስማኝ፣ አ...ብዬ አቃሰትኩ፡፡
እንደገመትኩት ድምፄን ሰምቶ ነው መሰል፣ በቀጥታ ወደ እኔ መጣ፡፡

“ኦ...ነቃህ?፣ በጣም ደስ ይላል፡፡ እንዴት ነህ?፣ ምን ይሰማሃል?” አለኝ፡፡

“ደህና ነኝ፡፡ ትንሽ እራሴ አካባቢ...” በደከመ ድምፅ፡፡

“ቆይ መጣሁ፡፡” ብሎኝ ሄደና፣ ብዙም ሳይቆይ የታካሚ ካርድ ይዞ ተመለሰ፡፡

የግራ እጄን ይዞ የልብ ምቴን ቆጠረ፡፡ በደም መለኪያ የደም ግፊቴን ለካ፡፡ ዐይኖቼን ከፍቶ አያቸው፡፡ ደረቴን በማዳመጫ አዳመጠ፡፡እግሮቼን አንቀሳቅስ እያለኝ፣ እግሮቼን በሹል ነገር እየወጋኝ፣ በሙሉ ስውነቴን መረመረኝ፡፡

“የት እንዳለህ አውቀሃል?” ጠየቀኝ፡፡

“ሆሰፒታል ነኝ መሰለኝ..."

“በጣም ጥሩ። እኔን ታውቀኛለህ?”

“አላውቅህም፡፡ ግን ዶክተር ትመስለኛለህ፡፡”

“እሺ፤ አሁን ስንት ሰዐት ይመስልሃል?”

“ሰዓቱን አላውቅም፡፡”

“በግምት፣ ጥዋት ከሰዓት ወይስ ምሽት ይመስልሃል?”

“መገመት ይከብደኛል።” አጠገቤ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጠና መፃፍ ጀመረ፡፡ ለደቂቃዎች ከፃፈ በኋላ፣ “አይዞህ፡፡ ትንሽ አደጋ ደርሶብህ ነው፡፡ አሁን ደህና ነህ፤
ተርፈሃል፡፡ እራስህና እጅህ አካባቢ ትንሽ ጉዳት ደርሶብሃል፡፡ ግን እድለኛ ነህ... ተረፈሃል ለህመምህ ማስታገሻ እንሰጥሃለን አይዞህ ብሎኝ ማስታገሻ መርፌ እንድወጋ አደረገ፡፡ ከብዙ ህመም ቦሃላ መልሶ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡

ጥዋት ከእንቅልፌ ስነሳ፣ እረጅም እንቅልፍ እንደተኛው ተሰማኝ፡፡ ቀጣዮቹም ቀናት እጅግ በጣም ከባድ ነበሩ። ያለፈውን፣ የተፈጠረውን፣ መቀበልም መቋቋም አልቻልኩም፡፡ እራሴን በቁሜ
ቦርቡሬ፣ ገዝግዤ ጨርሼዋለሁ፡፡ ዳግመኛ እንዳልነሳ እንዳላንሰራራ
አድርጌ ቀብሬዋለሁ፡፡ አሁን ለኔ መኖር ከቀደመው የባሰ ሲኦል ነው፡፡ አሁን መሞት በጣም ያስፈልገኛል፡፡ ተሰምቶኝ ማያውቅ ጭንቀት እየተሰማኝ መጥቷል፡፡ . ትንሽ ድምፅ ይረብሸኛል። እንቅልፍ አይወስደኝም፡፡ ነገርግን፣ እንኳን እራሴን ላጠፋ፣ እራሴን ማንቀሳቀስ
ማልችል እንደሆንኩ ሳስብ እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ ጭንቅላቴ
ሊፈነዳ ይደርሳል፡፡ በእንዲህ ባለ ሁኔታ ቀናቶች አለፉ፡፡ ዶክተሮች መጥተው ይከታተሉኛል፤ መድሀኒት ያዙልኛል። ጥዋት ጥዋት፣ የፊቴ ቁስል ይጠረግልኛል፡፡

አንድ ቀን እንደተለመደው ዶክተሮች ከጎበኙኝ ቦሃላ ሌላ እስፔሻሊስት ዶክተር መጥቶ እንደሚያየኝ ነግረውኝ ሄዱ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ሚከታተለኝ ወጣት ዶክተር እንደርሱ ነጭ ገዋን ከለበሰ ወጣት ጋር
ተመልሶ መጣ፡፡ አዲሱ ዶክተር ካርዴን ተቀብሎ አገላብጦ አነበበው፡፡

“ማን ነው እዚህ ያመጣው?” አዲሱ ዶክተር ጠየቀ፡፡

“አምስት ቀን ሆነው፡፡ ገዳም አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ናቸው አምጥተውት የሄዱት።”

ዝም አልኩኝ፡፡ በራሴ አፈርኩ፤ ዐይኔን ጨፈንኩ፡፡ አዲሱ ዶክተር፣ እኔን ሳያናግረኝ በእጁ ግራ እጄን እያሻሸ፣ ከስራ ባልደረባው ጋር ያወራል፡፡ በእጁ እንቅስቃሴ፣ ልስላሴና ሙቀት፣ በውስጡ እያዘነልኝ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡

“ዶ/ር ሄኖክ እባላለሁ፡፡ ሄኖክ ብለህ ልትጠራኝ ትችላለህ፡፡ የስነ-አዕምሮ ህክምና ክፍል፣ የመጨረሻ አመት የድህረ ምረቃ ሃኪም ነኝ፡፡አንተስ ስምህን ትነግረኛለህ?” ፊቱ፣ ድምፁ፣ ሁሉ ነገሩ ላይ ሃዘኔታና ርህራሄ የሚነበብ መሰለኝ፡፡

“ያቤዝ እባላለሁ፡፡”

“ያቤዝ ማን?”

“ያቤዝ አለማየሁ፡፡”

“እድሜ ?”

“ሠላሳ አራት፡፡”

“እራስህን ልታጠፋ ሞክረህ እንደነበር፣ ምታስታውሰው ነገር አለ?”

ዝም አልኩ፡፡ ጭንቅላቴ ይወቅረኝ ጀመር፡፡

“ደህና ነህ ያቤዝ?”

“ደህና ነኝ ዶክተር።”

“እሺ ያቤዝ፣ ለህክምናህ ስለሚረዳኝ የሆነውን ነገር ልትነግረኝ ትችላለህ?፡፡ ልትነግረኝ ምትፈልገውን፣ ግን ትክክለኛውን ብቻ ንገረኝ፡፡ እያንዳንዱ የምትነግረኝ መረጃ ካንተ ፍቃድ ውጪ፣ ለማንኛም ሶስተኛ ወገን በፍፁም አይደርስም፡፡ ለቤተሰብህም ቢሆን እንኳን፡፡ መናገር የማትፈልጋቸው ነገሮች ካሉ እለፋቸው፣ እንዳትዋሸኝ፡፡››
“እሺ!” አልኩት በደከመ ድምፅ፡፡ ውስጤ በጣም እየተረበሸ ነው፡፡ምን ብዬ ነው የምነግረው? ከየት ነው የምጀምረው? የተፈጠረውን ወደ ኋላ ሳስበው፣ እንባ እየተናነቀኝ መጣ፡፡

“ያቤዝ እየጠበኩህ ነው፡፡ የሆነውን፣ የተፈጠረውን ንገረኝ፡፡እራስህን ልታጠፋ ለምን ሞከርክ?”

ማልቀስ ጀመርኩኝ፡፡ ዶክተር ሊያባብለኝ ሞከረ፡፡ ውስጤ ጭራሽ ገነፈለ፡፡ “እኔ ከሞትኩ ቆይቻለሁ፡፡ በቁሜ የአርባና ሰማንያ ተዝካሬን አውጥቻለሁ፡፡ ሀብትና ንብረቴን ነፍስ ይማር ብዬ በትኜዋለሁ፡፡ለወራት ስንከራተት የከረምኩት፣ አስክሬኔን የምቀብርበት ምቹ ቦታ ፍለጋ ነበር እንጂ፣ ላለመሞት አልነበረም፡፡ እንዴት ተረፍኩኝ...? ለምን..? እኔ
መኖር አልፈልግም...!” እየጮኸኩ ተንሰቀሰኩ፡፡ ቢያባብሉኝም፣ ማቆም
አልቻልኩም፡፡ እንባዬ የፊቴን ቁስል እየለበለበኝ ይወርዳል፡፡ ዶክተሮቹ
ከወንበራቸው ሲነሱ፣ ኮቴ ሲበዛ፣ ግርግር ሲፈጠር፣ እጄ ላይ በተቀጠለው ግሉኮስ፣ መድሃኒት ሲስጠኝ ይሰማኛል፡፡ የማለቅስበት ሃይል እየከዳኝ፣ ሳላስበው እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡

ከዛች ቀን ጀምሮ የዶክተር ሄኖክ ክትትል በጣም የተለየ ነበረ፡፡እንደቤተሰብ ብዙ ሰዓታት ከኔ ጋር ያሳልፋል። ጥሩ ተቀራርበናል፤የሚሰማኝን የህመም ስሜት እነግረዋለሁ፡፡ መድሃኒት ያዝልኛል፡፡
ያዘዘልኝ መድሃኒቶች፣ ጥሩ እንቅልፍ እንድተኛ እያገዙኝ ነው፡፡እኔ ሳልፈልጋቸው ወደ ጭንቅላቴ እንደፈለጉ ሚፈነጩብኝ፣ እነዛ ተላምጠው ማያልቁ አስጨናቂና ተስፋቢስ ሃሳቦች እንደ ሀምሌ ዝናብ
እኝኝ ማለታቸውን አየቀነሱልኝ ነው፡፡ ዶ/ር ሄኖክ በተለየ አቅርቦት ይንከባከበኛል፡፡ እንደታካሚው ሳይሆን፣ እንደታላቅ ወንድም፣ እንደቤተሰብ፣ በሁሉም ነገር እያገዘኝ ነው፡፡ ከሁሉም ታካሚዎች ቀድሞ እኔን ይጎበኘኛል የሚያስታምመኝ ቤተሰብ ስለሌለ ይሁን አዛኝ ተፈጥሮ
ኖሮት ባላውቅም፣ ካወቀኝ ጀምሮ ከኔ አልተለየም፡፡ የህክምና ወጪዬንም
እየሸፈነ እንደሆነ አውቂያለሁ፡፡ አልፎ አልፎ ምግብ ከውጪ ያስመጣልኛል፤ አብዛኛውን ግዜ ስራውን ሲጨርስ፣ በተለየ ርህራሄና ፍቅር ያጫውተኛል፤ ያበረታታኛል፡፡ ተስፋንና ጥንካሬን በውስጤ ይረጨል፡፡ ቀናቶች ሲያልፉ፣ እየተሻለኝ መጥቷል፡፡ የፊቴና የእጄ
ቁስሎች ለውጥ አላቸው፡፡ ህመሞቼ እየቀነሱ፣ ለውጥ እያመጣሁ፣ የሞተው፣ የተቀበረው ተስፋዬ ዳግም ያቆጠቁጥ ጀመር፡፡

እጄን ሁለት ጊዜ ራጅ ተነሳሁ፡፡የተሰበረው አጥንቴ ጥሩ ሆኖ ጠግኗል፡፡ የታሰረልኝ ጄሶ ሊፈታልኝ ቀጠሮ ተሰጠኝ፡፡ የፊቴ ቁስል ህመሙ ጠፍቷል፡፡ በእጆቼ ዳበስኩት፤ ይሻክራል፡፡ ፊቴ ላይ ትልቅ
የማይሽር
👍41
ጠባሳ ጥሎ እንደሚያልፍ ታወቀኝ፡፡ ሀኪሞች አሁን ብዙ አይጎበኙኝም፡፡ ግሉኮሱ ከተነቀለልኝ ቆየ፣ አሁን የምወጋው መርፌ የለም፡፡ የምውጣቸው ክኒኞችም፣ ዶ/ር ሄኖክ ያዘዘልኝ ናቸው:: በቅርብ ከሆስፒታል ውጣ መባሌ ማይቀር ነው፡፡ የት ነው ምሄደው? በምን ገንዘብ ነው ምሄደው? ለማን መደወል እችላለሁ? የማንም ስልክ
የለኝም፡፡ ዱካዬን ሳጠፋ፣ ስልኬን ሰባብሬ ቀፎውን ጥዬዋለሁ፡፡ በአካል ካልሄድኩኝ፣ ምንም የመገናኛ መንገድ የለኝም፡፡ ልሂድ ብልስ ማን ጋር ነው ምሄደው? ምንስ ብዬ ነው? እንዴትስ እንዲህ እንደሆንኩኝ ምን
ብዬ አስረዳለሁ...? ዶክተር ድንገት አጠገቤ ቁጭ ሲል ከሄድኩበት ሃሳብ
ተመለስኩ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አምስት ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD) #የመጨረሻው_መጨረሻ ድንገት ስነቃ እራሴን አልጋ ላይ በጀርባዬ ተዘርሬ አገኘሁት፡፡ከፍተኛ ህመም ይሰማኛል፡፡ እራሴ አካባቢ፣ በቀኝ በኩል ሰውነቴን፣ፊቴን ይጠዘጥዘኛል፡፡ ዐይኖቼን ለመክፈት ሞከርኩ፡፡ የቀኝ ዐይኔን ህመም ተሰማኝ፡፡ አልከፈት አለኝ፡፡ ዐይኔ ምን እንደሆነ ለመዳበስ፣ የቀኝ እጄን ለማንሳት ስሞክር፣ እ...ህ...…»
#ሰመመን


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

አቤል ለወላጆቹ አንድ ነው ። እናትና አባቱ ከተጋቡ በኋላ ብዙ ዓመት ቆይቶ ነው የተወለደው ። ለብዙ ዓመት ልጅ በማጣታቸው ምክንያት በቤተሰብ ውስጥ ሰላም እንዳል ነበረ ሲወራ ይሰማል ። አባቱ በእናቱ ላይ አንዲት መሸታ
ነጋዴ ወሽመዋል እየተባሉ ይታሙ ነበር ። ይህን ያደረጉት ሚስታቸው ስለ መከኑ ፡ ልጅ ፍለጋ ነው የሚል ማስተባበያም ነበር ለማንኛውም የአቤል መወለድ በቤተሰቡ
ውስጥ መጠነኛ ሰላም አወረደ ።

አባቱ አቶ ሙሉዬ ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩት በአህዮቻቸው ጭነት በማመላለስ ነበር ።አቤል ነፍስ ካወቀ
በኋላ እንኳ የአገልግሎት ዘመናቸውን ጨርሰው የሞቱ ሦስት አህዮች ያስታውሳል ። አንዳንዴ እንደ እንስሳ ሳይሆን እንዴ ሰው የቤተሰቡን ድህነት ተረድተው ለመርዳት የቆመ ይመስለው ነበር ።

አብዛኛውን ጊዜ አባቱ፡ የሚሰሩት በወፍጮ ቤት አካባቢ ነበር ። እህል በአህዮቻቸው ጭነው ወደ ወፍጮ ቤት
ያደርሳሉ ። ወይም ደግሞ የተፈጨውን ወደየቤቱ ይመልሳሉ ። ሙሉዬ በዚህ ሁኔታ ከሚያገኙት ገንዘብ ውስጥ
ከፊሉ የሚቀረው ወይዘሮ ይንጡ በዝናሽ ጠጅ ቤት ውስጥ ነበር ።አህዮቻቸውን “ ቶሽ ! ” በማለት ሲደርቅ የሚውል ጉሮሮአቸውን በመሸታ ጠጅ ሳያርሱ ወደ ቤታቸው ገብተው አያውቁም ። ጠጥተው ገብተው በሰሳም አይተኙም ። የድህነታቸውን እልህ የሚወጡት በሚስታቸው ላይ ነበር ። ይጨቃጨቃሉ አብዛኛውን ጊዜ እህል አስፈጭተው ከሚያደርሱበት ቤት ስለሚጐራርሱ የቤታቸውን ምግብ አይበሉም ። የቤታቸውን አስተዳደር ቸል የሚሉትም በዚሁ ምክንያት ነበር ። ይህም በመሆኑ የአቤል እናት አርፈው አልተቀመጡም ። ከገበያ ትናንሽ ሸቀጦችን እያመጡ
ይቸረችሩ ነበር ። እኒህን ሁኔታዎች በማየት አቤል ገና በልጅነቱ ፍቅሩ ወደ እናቱ አጋደለ ።

አቶ ሙሉዬ ከአህዮቻቸው ጋር ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ ስለሚውሉ፥ ማታ ቤት ሲገቡ የቦት ጫማቸው ሽታ አያስቀምጥም ነበር አቤል ዩኒቨርስቲ ከገባ በኋላ በጋራ የመኝታ ቤት ኑሮ ውስጥ የካልሲ ሽታ ሲነሣ የአባቱ ቦት ጫማ ትዝ ይለዋል እሱም ከፍ ካለ በኋላ አብሮአቸው በየወፍጮ እየዞረ መጫኛ አስተሳሰር ተምሮ ነበር ። የአባቱ ምኞት
አቤል ፈለጋቸውን ተከትሎ አህዮቹን እየጫነ በምትካቸው ቤተሰቡን እንዲያስተዳድር ነበር ። ከዚህ መሀይማዊ ፈለግ ያዳነው ጎረቤታቸው የሆነ አንድ መምህር ነው ። አባቱን
አቶ ሙሉዬን እንደ ምንም ጎትጓቶ አቤል ትምህርት እንዲጀምር አደረገ የጨለማ ጉዞ የጀመረችውን ሕይወት መንጥቆ የብርሃን መንገድ እንድትይዝ አደረጋት ። ይህ መምህር ወደ ሌላ ክፍለ ሀገር ተቀይሮ እስከሔደበት ጊዜ ድረስ ለአ
ምስት ዓመት ያህል ማንኛውንም የትምህርት ቁሳቁስ በመግዛት አቤልን ረድቶታል ።

ቤታቸው ከከተማው ወጣ ስለሚል አቤል ትምህርቱን የተከታተለው ብዙ መንገድ አቋርጦ አቶ ባርካ ድረስ እየ
መጣ ነበር ። አብረውት ከአንድ ሰፈር የሚመሳሰሱ ሌሎች ተማሪዎች ስለ ነበሩ የአህዮቹ ወሬ በክፍል ጓደኞቹ በቀላሉ ይሰራጭና "የአህያ ጫኝው ልጅ” እያሉ ያበሽቁታል።ትምህርት ቤት አርፍዶ የደረሰ እንደሆነ “ ለምን አህዮቻችሁን አትጋልብም ? ” ብለው ይተርቡታል ። በነ አቤል አህዬች ላይ የማይነገር ምሳሌ አልነበረም ። ነገሩ የልጅነት ዘመን የቀልድ ቅንብር ነበር ። ነገር ግን ይህ ቀልድ ምን
ሥነ ልቡናዊ ጉዳትና መደባዊ ተጽዕኖ እንደ ነበረው አቤል መረዳት የጀመረው እየበሰለ ከመጣ በኋላ ነው ። የብዙዎቹ
መራራ ቀልዶች ጠባሳ አእምሮው ውስጥ ቀርቷል።

አቤል እያደገ በመጣ ቁጥር ድህነት ምን እንደሆነ የበለጠ እየተሰማው መጣ ። ድህነትን ጠላው ፤ረገመው ። ድህነት የመሠረታዊ ፍላጐቶች ገደብ መሆኑ ገባው ።ድህነት የበታችነት መሆኑን ተገነዘበ ። ድህነት የሕይወት እግር ብረት መሆኑን ተረዳ። ድህነት ግማሽ ህይወት
መሆኑን ዐወቀ ። እናም ከዚህ እግር ብረት ማምለጫው ብቸኛ መንገድ ትምህርት ታየው ። የሚደነቅ ግሩም ተማሪ ወጣው
በአንደኛ ደረጃ ትምህርቱ ሁለት የተለያዩ ክፍሎች በድርብ ዐለፈ " ይሁን እንጂ ሕይወቱን ለትምህርት ብቻ ስለሰጠ
መማኅበራዊ ግንኙነቱ የላላ ነበር ። ከአካዳሚክ ሌላ በትምይርት ቤት ውስጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አይሳተፍም
ይህም ነው የእሱንና የቤተሰቡን ድህነት ከማኅበራዊ ሥርዓቱ ነጥሎ እንዲመለከት አድርጐት የነበረው ።

በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለ የኢትዮጵያ አብዮት ፈነዳ የለውጥ እሳት ተቀጣጠለ አቤልም በደመ ነፍስ ይህ አብዮት በጋራ ለኅብረተሰቡ በግል ደግሞ ለወሳጆቹ ድህነት መፍትሔ መሆኑን ተረዳ ። መሬት ለአራሹ ሆነ ። የነአቤልም መንደር ከከተማው ወጣ ያለ በመሆኑ አባቱ በማኅበር ተደራጅተው እንዲያርሱ ለኣባልነት ተጠይቀው ነበር ። ነገር
ግን አቶ ሙሉዬ ከአህዮቻቸው ጋር የተቆራኘ የረዥም ጊዜ |ሕይወታቸውን መክዳት አልፈለጉም ። እናም ተደራጅቶ
በማረስ ፈንታ ያንኑ የጭነት ሥራቸውን ቀጠሉ ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዕድሜ መግፋትና መድከም የአህዮቹ ቁጥር
እየቀነሰ መጣ ። የመጨረሻው ዜና ሁለቱን አህዮቻቸውን ሸጠው ከቤት መዋላቸው ሆነ ።

አቤል ከሐሳብ ጉዞው ሲመለስ በአካባቢው ያለው ነገር ሁሉ አስጠላው ። የተቀመጠበት አልጋ ቁልቁል የሚሰምጥ
የተደረበው አልጋ ከላዩ ላይ የሚደረመስበት መሰለው ወንበሩ ላይ ተበታትነው የተቀመጡትን የትምህርት ቁሳቁሶችና በታይፕ የተባዙ ወረቀቶችን ማየት አልፈለገም ደብዳቤውን እንዳንጠለጠለ ክፍሉን ለቅቆ ወጣ ።

በምግብ አዳራሽ ውስጥ በትዕግሥት ፊት ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ ፍጹም የመንፈስ ጤንነት አልነበረውም ። ትምህርቱን ሳምንት ያህል ኣቋርጦ ነው የጀመረው ። ሰው አስ ጠልቶታል ። ማንንም ባያይ ፡ ከሁሉም ተነጥሎ ብቻውን ቢውል ይመርጣል ። ምንም ቢሆን ግን ትዕግሥትን በሆነ አጋጣሚ ሳያያት : በልቡ የመልካሙን የዐይን ፍቅር ዜማ ሳያዜምላት አይውልም ። ከጥናት ጋር ፈጽሞ ተራርቀዋል የምግብ ፍላጎቱ እጅግ ቀንሶአል ። የተማሪውን ዐይን ስለ ሚፈራ ሁሉም በልተው ከጨረሱ በኋላ መጨረሻ ላይ ነው ገብቶ የሚበላው ። አብዛኛውን ጊዜ ሳምሶን “ ጥቅሙን
ያውቃላ !”አቤል ምግቡን ለኮፍ ለኮፍ አድርጎ ሲተው “አይ ያንተ ነገር!” ይልና የአቤልን ሰሀን ወደርሱ ይስባል ።
አቤል ሳይበላም ሳምሶን ሲበላ በማየት ይደሰታል ። አጠቀላለሉና አጎራረሱ ! ለምግብ ያለው ትልቅ ፍቅር ያስደንቀዋል
ሆኖም ሳምሶን የአቤልን እስከ መጨረሻ ቆይቶ መግባት አልወደደም ። ምግቡ ይቀዘቅዛል ። አንዳንዴም ሲያልቅና ጎደሎ ጭልፋ ሲጨልፍለት ይችላል ። ያም ሲሆን ጥቅሙን ከጉዳቱ በማመዛዘን ዘግይቶ አብሮት ይገባል ።

የአቤል ሕይወት በመንፈስ ጭንቀት ብትወጣጠርም በእስክንድርና ጓደኞቹ ብርታት መጥፎ ሁኔታ ላይ ከመውደቅ
ተጠብቃ ልትቆይ ችላለች ። የአሁኑ ደብዳቤ ደግሞ ያንኑ የላላ መንፈሱን የባሰ የሚረብሽ ሆነበት ፡ ስለ ምግብ
ማሰብ ከተወ ስንብቷል ። በደመ ነፍስ ሆኖአል የሚንቀሳቀሰው።

የመኝታ ክፍሉን ለቅቆ እንደ ወጣ እግሩ ያለምንም ዓላማ ወደ ኮሪደሩ መስኮት መራው ።ዘወትር ጠዋት ትዕግሥትን በዓይኑ የሚሳለምበት የሕይወቱ መስኮት! ሁለቱንም መስታወት ውለል አድርጎ ከፈተው ። መስኮቱ ሰፊ በመሆኑ
አቤል ሰውነቱን ከወገቡ በላይ ወደ ውጭ አውጥቶ ቁልቁል ተመለከተ ። ትዕግሥት በዚህ ሰዓት አትኖርም " የሚያልፍ
የሚያገድምም ማንም ሰው የለም። አካባቢው ጭር ብሎአል ።አቤል ጭር ያለውን አካባቢ ተመርኩዞ የሆነ ሰይጠናዊ ስሜት ሰፈረበት ምድራዊውን ሥቃይና ጭንቀት ለመገላገል ያለ ዓላማና ግብ በመዋዥቅ ላይ ያለችውን ሕይወቱን
ዕረፍት ለመስጠት ፥ በድህነት የማቀቀች በዐይን ፍቅር የተጠመደች ሕይወቱን ለማሳረፍ ከቆመበት ሦስተኛ ፎቅ
ቁልቁል የመፈጥፈጥ ሐሳብ መጣበት ። ሁሉ ነገር መራራ መስሎ ታየው የቤተስቡ ድህነት ጥንትም የሚያውቀው ጉዳይ ቢሆንም ከራሱ ጋር በሚጣላበት ሰዓት ተጨማሪ ሰቆቃው ሆኖ በመቅረቡ በጠበጠው ። ከሁሉም ነገር መገላገል
ግልግል ... ግልማል የ ከጥቂት ሴኮንዶች በኋላ ነፍሱ የምታገኘው ጸጥታ ታየው ።

አዎ ይታየኛል ! ለሁለቱም አልሆንም ። ከድህነቴም አልፈወሰ ፥ ለፍቅርም አልበቃ ! ለማንኛቸውም አልሆንም
አለ እንዶ ገና በሐሳቡ ።

ሕይወቱ የትጋ ፍጻሜዋን እንደምታገኝ ለመገመት ሞከረ ፎቁን አልፋ ሳትጨርስ በአየር ላይ ወይስ መሬት

ከተፈጠፈ በኋላ ፥ በይኖቹ እንደ ገና እንባ አቀረሩ ። እንባውን ለመዋጥ ጥርሱን ነከሰ ። ግንባሩን አኮማተረ ። “ሕይወት
መራራ ሆና ሳለ ፡ ልንለያት ስንል ምን ያስለቅሰናል ? ” ሲል አሰበ። ከሦስት ፎቅ ወድቆ መሬት የተከሰከሰ ጭንቅላት ፥
የተፈረካከሰ አጥንትና የተበጣጠሰ ሥጋ በሐሳቡ ታየው ።ሬሣውን ከበው የሚንጪጩት ሰዎች ድምፅ ሰቀጠጠወ
በዐይን ፍቅር ራሱን የገደው የአቤል ርካሽ ዝና ከዩኒቨርስቲው አልፎ በአካባቢው ሁሉ ሲወራ መምህራን ምሳሌ
ሲሰጡት ፥ አንዳንዶች ሲያዝኑለት ፥ አንዳንዶች ሲሥቁበት ቁልጭ ብሎ ታየው ያቺ ትዕማሥት እንዴት ትሆን ይሆን ?

“ ምን እያደረግክ ነው ፥ አቤል ? ” የሚል ድምፅ ድንገት ከኋላው ሲሰማ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ እንደ ተያዘ ሰው ክው አለ ። የእስክንድር ማንደፍሮ ድምፅ
መሆኑን ግን ለይቶታል።

“ እ" ምንም ። እንዲያው ነው ” አለውቀስ ብሎ ፊቱን አዙሮ።

እስክንድር ፡ አቤል እጅ ላይ ደብዳቤ ባየ ጊዜ አንዳች ጥርጣሬ ገባው።ደብዳቤው ውስጥ አቤልን ያስደሰተው ወይም ያስከፋፈው ነገር እንዳለ በንቁ አእምሮው ገምተ።ሊፈስ የደረሰ እንባውን ለመግታት በመታገል ደም የመሰሉት አይኖቹን ባየ ጊዜ ደግሞ የተስፋ ስሜት እንዳለው
አወቀ።

“ ደብዳቤው ከየት ነው የመጣልህ ? ” አለው ። ቁልቁል ተወርውሮ እንዳያመልጠው የፈራ ይመስል ቀስ ብሎ እየተጠጋው።

"ከቤት ነው"....... አለና አቤል ሊቀጥል የፈለገውን ነገር መልሶ ዋጠው ። ጥቂት ሲያሰላስል ቆየና እንደ ገና ፡ “ “ እኔ እምልህ፣ እስክንድር" አለው

“ አቤት ? ” አለ እስክንድር በደከሙ ድምፅ ።

“ ይህችን መራራ ሕይወት ለምን እንወዳታለን ? ”

“ ጣዕሟ ከምሬቷ ውስጥ ነው የሚገኘው” አለው ።

እስክንድር በልቡ የአቤልን ስሜት እያጠና
“ ሲበዛስ ? መራራነቷ ሲበዛስ ? ”

እስክንድር የአቤል ሁኔታ አላማረውም " ፊቱ እየተለዋወጠ እንባውን የሚታግለው ዐይኑ ይብሱን ደም እየመሰለ ሲሔድ ፥ የግንባሩ ሥራሥሮች እየተግተረተሩ ሲሔዱ ተመለከተ ቀስ ብሎ ግራ ክንዱን ያዘውና ' “ ና ቆይ ። ስለ ሕይወት ቢት ውስጥ ሆነን እንጫወታለን ” አለው ።

“ መኝታ ቤቱ አስጠልቶኛል” አለ አቤል በምሬት ።

“ እነዚያ መግባት አልፈለገም ”

“ ግድ የለም ፥ ከእኔ ጋር ስትሆን ትወደዋለህ ። ይልቅ ና እንግባ ” አለና ጎተት አደረገው » አቤል በልቡ፡ “ይህን
ሰው የሕይወቴ ዘብ ያደረገው ማነው ?” አለ ። አደጋ ላይ ባለበት ሰዓት መድረሱ በእርግጥም አስገርሞት ነበር ።

እነሱ ወደ መኝታ ክፍላቸው ሲገቡና ሳምሶን ጉልቤው ? ሲወጣ በር ላይ ተገጣጠሙ ።

ታዲያስ ” አለው እስክንድር " ለመጨበጥ እየፈራ ።ሳምሶን ሲጨብጥ እጅ እስኪያም አጥብቆ ካልያዘ ወይም
ካልነቀነቀ አይሆንለትም ።

ምን እባክህ ! ልተኛ ነበር እንቅልፍ እንቢ አለኝ ይቺ ስልቻዬ ስለ ጎደለች ነዉ መሰለኝ ” አለው። ወደ ሆዱ እያሳየ ።

ታዲያ አሁን ወዴት ነዉኑ ? ”

ወደ ራት ነዋ ! ”

እንዴ ሰዓት” ኮ ገና ነው አለ እስክንደድር
በልቡ እየሣቀ ።

ቢሆንም እዚያው ሔዶ ቀድሞ ሰልፍ መያዝ ይሻላል እባክህ ” አለውና ጥሎአቸው ሔደ ።

ወደ ውስጥ ሲገቡ ድብርት እየተነጫጨጨ ነበር የቆያቸው»

“ ስማ አንተ እስክንድርያ ይህንን ሰው ብታስታግሱት ይሻላል " እኔ አህያ አይደለሁም ። እሱ የማኅበራዊ ኑሮ
ትርጉም አይገባው ”

“ ማንነው አሁ ? ” አለ እስክንድር ' ማን መሆኑን ልቡ እያወቀ "

“ ይሄ ሳምሶን ነዋ አስደንግጦኝ ይሔዳል እንዴ? አበዛው እኮ”

“ ምን አጣላችሁ ? ”

“ እንጃለት ! ለራት እንሰለፍ አለኝ ። ገና ነው እቆያለሁ ስለው ፥ “በይ እንግዲህ! ቀለምሽን ጠጭ ” ብሎ እግሬ ላይ ረግጦኝ ሔደ ። እኔ የናንተ ጓደኛ ነው ብዬ ነው እንጂ እከሰዋለሁ

« ግድ የለም እንመክረዋለን ” አለው እስክንድር ሣቁን ለመግታት እየታገለ ። የድብርት ተፈጥሮ ያስቀዋል ።ተደበሮ ሰው የሚደብረውን ያህል ፥ አንዴ መልጎምጎም ከጀመረም መቆሚያ የለውም ። ካልነኩት ግን አይነካም ።

ምከሩት ይሄ ማኅበራዊ ኑሮ ነው " ተከባብሮ መኖር ይሻላል ” አለ ፥ እንደ ሕፃን ልጅ ትከሻውን እየነቀነቀ።
አቤልም ጎምዛዛ ሣቅ ሳቀ ።

💥ይቀጥላል💥
👍2
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

ብዬ አስረዳለሁ...? ዶክተር ድንገት አጠገቤ ቁጭ ሲል ከሄድኩበት ሃሳብ
ተመለስኩ፡፡

“እንዴት አደርክ ያቤዝ?” አለኝ፡፡

“እንዴት አደርክ ዶ/ር፡፡”

“ምነው በሀሳብ ነጉደሀል? ምን እያሰብክ ነው?”

“ለወራትኮ ማሰብ አቁሜ ነበር ዶክተር፡፡ አሁን ማሰብ ስጀምር፣ ውዝፍ ሀሳብ ሁሉ ይመጣብኛል። ምን ማላስበው ነገር አለ?”

“ብዙ አትጨነቅ፡፡ ሁሉም በጊዜው፣ ቀስ በቀስ ይፈታል፡፡ ዋናው በርታ በርታ ማለት ነው፡፡” እሱ ሲያወራኝ የመረጋጋት ስሜት
ይሰማኛል፡፡

ቀጠል አደረገናም “ያቤዝ፣ አሁን ቁስሎችህ እየሻሩ ነው፡፡ ነገር ግን ስለመሰረታዊ ችግርህ እስከዛሬ በደንብ አላወራንም፡፡ ባለፈው ስጠይቅህ በጣም ስለተረበሽክ፣ እንዲያግዝህ ስሜት ማረጋጊያና ጭንቀት መቀነሻ መድሃኒትቶችን እንድትወስድ እያደረኩ ነው የቆየሁት፡፡ ካልረበሸህ፣ ባለፈው እንደጠየኩህ፣ ለምን እራስህን ለማጥፋት
ደግሜም ያልጠየኩህ እስክትረጋጋ ብዬ ነው፡፡ አሁን ለውጥ አለህ ካልረበሸህ ባለፈው እን።ጠየቁህ ለምን ራስህን ለማጥፋት እንደሞከርክ እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ፡፡” ብሎ ዐይን ዐይኔን ይመለከተኝ ጀመረ፡፡

እውነቱን ነው፡፡ ለውጥ አለኝ፡፡ አሁን ሁሉን ነገር፣ ቀስ በቀስ ለምጄዋለሁ፡፡ እንባ አልተናነቀኝም፡፡ ነገርግን፣ ከየት እንደምጀምርለት ግራ ገብቶኛል፡፡ መቼም፣ ዝም ብዬ ከሞቀ ህይወቴ፣ እራሴን ላጥፋ ብዬ አልተነሳሁም፡፡ እንኳን እራስን ማጥፋት፣ በቃኝ ብሎ መመነን ብዙ ታስቦነት፣ ታኝኮና ተላምጦ ነው ሚወሰነው፡፡ ከየት ጀምሬ ልንገረው?፣
እንዴት እዚህ ውሳኔ ላይ ደረስኩ፣ እንዴት ላስረዳው?

“ያቤዝ እየጠበኩህ ነው፡፡”

“እሺ ዶክተር፡፡ ከየት እንደምጀምር ግራ ገብቶኝ ነውኮ፡፡ ታሪኩ ረጅም ነው፡፡”

“ችግር የለውም፤ ደስ ካለህ ጀምረው፡፡ ደስ ያለህን፣ ትዝ ያለህን ንገረኝ፡፡ ብቻ እውነቱን ንገረኝ፡፡ ከዛ ውስጥ እኔ የሚጠቅመኝን እወስዳለሁ፡፡”

“እሺ፡፡ እኔ በማኔጅመንት ሁለት ዲግሪ አለኝ፡፡ አስር አመታት አካባቢ በስራ ላይ ቆይቻለሁ፡፡ ህይወቴ መጥፎ ሚባል አልነበረም።ውስጤ ግን፣ ወቅት እየጠበቀ ደስታ ቢስ፣ ተስፋ ቢስ ይሆናል።ህይወትን በየመሀሉ በጥቁር መነፅር ብቻ እመለከታታለሁ። ጨለምተኛ
እሆናለሁ፡፡ የመኖር ፍላጎቴ ባዶና ገለባ ይሆንብኛል፡፡ አንዳንዴ ድግሞ፣ ህይወት ዳግመኛ ውብና አጓጊ ትሆንብኛለች፡፡ የማያቸው ነገሮች ሁሉ ያጓጉኛል፡፡ እነሱን ለማግኘት ከፍ ያለ ፍላጎትና ሃይል ይኖረኛል። ደርስባቸዋለሁ እንደጓጓሁ ስደርስባቸው፣ ሳገኛቸውና ሳቃቸው
ለተወሰነ ግዜ ደስተኛ እሆናለሁ፡፡ ከቆይታ በኋላ ግን፣ ደስታውና እርካታው መልሶ ይጠፋል። ሁሉም ማስመሰል፣ ከንቱና ባዶ ሆኖ ይመለስብኛል። አዕምሮዬ ከጥሩ ነገር ይልቅ፣ መጥፎና አስጨናቂ
ነገሮች ላይ አመዝኖ እንዳስብ ያደርጋል፡፡ እንዲህ ሲሰማኝ ስራዬን ደጋግሜ ለቅቂያለሁ፡፡ አዕምሮዬ ሚያስጨንቅ ሃሳብ ያላምጣል፣ ያመነዥካል። ያስጨንቀኛል፡፡ ሞቼ መገላገል እስክመርጥ፡፡

መጀመሪያ አካባቢ እነዚህን ስሜቶች ያዝ ለቀቅ ነበር ሚያደርጉኝ፡፡ ዛሬ ደስታ ነገ ድብርት፣ ዛሬ ብርሀን ነገ ጨለማ፣ እንደዛ
ነበር፡፡ ቀስ በቀስ ከሁሉም ነገር ላይ መጥፎውን መመልከት ጀመርኩ፡፡
ቤተሰብና ጓደኝነት ከንቱ መስለው ይታዩኝ ጀመር፡፡ ሰዎችን ሸሸሁ። ስራዬ አስጠላኝ፡፡ ለቅቄ ብቸኝነቴን መረጥኩኝ፡፡ ሁሉም አርቴፊሻል የማስመሰል፣ የውሸት ኑሮ ሆነብኝ፡፡ ይህን መጥፎ ስሜት ለመሸሽ
ወደ ሱስ ገባሁኝ፡፡ ለግዜው ከጭንቀቴ፣ ከድብርቴ ቀለል እንዲለኝ አገዘኝ፡፡
በየእለቱ በሚባል ሁኔታ መቃም ጀመርኩኝ ሲመሽ መጠጣት፡፡ ጓደኞቼ
በሙሉ የሚቅሙና ሚጠጡ ሆኑ፡፡

አዎ ወራቶች አለፉ ዳግም ህይወቴ አሰልቺ ሆነችብኝ ደስታ ቢስ ሆንኩኝ፡፡ ለእዚህ አሰልቺ ህይወት ስትወጣ ስትወርድ መኖር የለብህም፣ የሚል ሀሳብ በጭንቅላቴ እንደ ሀምሌ ዝናብ ቀንና ለሊት ይዘንብብኝ ጀመር፡፡ ልቆጣጠረው አልቻልኩም፡፡ አመንኩኝ፡፡ በየቀኑ
እየቃምኩ፣ ከቤተሰቦቼ ደብዛዬን አጥፍቼ፣ እንዴት እራሴን ማጥፋት እንዳለብኝ አሰብኩ፤ እቅድ አወጣሁ፡፡ ስለዚህም፣ ከምኖርበት ራቅ ያለ ቦታ፣ የጠረፍ ከተማ፣ የተሻለ እንደሆነ አሰብኩኝ፡፡ መተማን መረጥኩ፡፡ወደ መተማ ስጓዝ አንድ ገዳም አየሁ፡፡ ጥቅጥቅ ጫካው ትክክለኛ ቦታው
እዚህ ነው ብዬ ወሰንኩ፡፡ ከዛም ያሰብኩትን ሞክርኩ፡፡” ሳበቃ ቀና ብዬ
ዶ/ርን አየሁት፡፡ አይኖቹ በእንባ ተሞልተዋል፡፡

“አይዞህ ያቤዝ! አይዞህ! አሁን ተርፈሃል፡፡ ህይወት ዳግመኛ የመኖር እድልን ሰጥታሀለች፡፡ ብዙዎች አንተ የሆንከውን የሆኑ ይህን እድል አያገኙም፡፡ እድለኛ ነህ፡፡ ጎበዝ ልጅም ነህ፡፡ ባይፖላር የተባለ
የአዕምሮ ህመም አለብህ፡፡ የነገርከኝ፣ በአንተ ላይ የሆነው አብዛኛው ነገር ሁሉ፣ ካለብህ የአዕምሮ በሽታ የተነሳ ነው።”

“በሽታ ነው ያልከኝ ዶ/ር? እኔኮ ምንም አይነት የህመም ስሜት ኖሮኝ አያውቅም፡፡”

“አይደለም ያቤዝ፡፡ ባይፖላር የተባለ የአዕምሮ በሽታ አለብህ፡፡የነዚህ በሽታዎች የህመም ምልክቶች እንደ ሌሎች በሽታዎች ትኩሳት፣እራስ ምታትና ቁረጠት የመሳሰሉት አይደሉም፡፡ ለዛም ነው የህመም ስሜት የለኝም ያልከኝ እንጂ፣ የህመም ምልክቶችማ በተደጋጋሚ ነበረህ፡፡ ከመጠን ያለፈ የባህሪ መለዋወጥ፣ ስለ አንድ ጉዳይ ከመጠን ባለፈ ሁኔታ ማሰብና መጨነቅ፣ አብዝቶ ብቸኝነትን መምረጥ፣ እራስን
የማጥፋት ሃሳቦች ሁሉ የህመም ምልክቶች ናቸው።” ዝም ብዬ ወደ
ራሴ ማሰብ ጀመርኩ፡፡

“ያቤዝ አውቃለሁ ስራህን አጥተሃል፣
ንብረቶችህን አጥፍተሀል፤ ከቤተሰቦችህንና ከጓደኜችህ እርቀህ ተሰውረሃል፡፡ ቢሆንም ግን፣ አንተ በጣም እድለኛ ነህ፡፡ በማህበረሰባችን ባለው የግንዛቤ እጥረት ምክንያት መፍትሄ ብለህ የመረጥካቸው ሁሉ፣ ለግዜው ቀለል ያደረጉልህ ቢመስልህም፣ በመሰረቱ ችግሩን የሚያባብሱ ነበሩ። ሰዎች ሲጨነቁ፣ ሲከፉቸውም ሆነ ሲደሰቱ የአልኮል መጠጦችን መጠቀም
መጥፎ ማህበራዊ ልማድ ነው፡፡ እነዚህ ሱሶች በተደጋጋሚ የሚከሰት የስሜት መረበሽ ሲኖር ግዜያዊ መፍትሄ ቢመስሉም፣ ሲቆዩ ወደ ተባባሰና ወደከፋ ስነ አዕምሯዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ይዳርጋሉ፡፡

ስለዚህም ካሁን በኋላ የጀመርኩልህን መድሀኒቶችን መውሰድ፣ ክትትልም በደንብ ማድረግ አለብህ፡፡ አንተ ገና በጣም ወጣት ነህ፡፡ በዚህ እድሜ ገና ትምህርት ቤት ያሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ህይወትን እንደገና መጀመር ትችላለህ፡፡ ሁሉንም ነገር ያጠፋህ ቢመስልህም፣ በጣም ብዙ ያልጠፉ ነገሮችም አሉህ፡፡ ለምሳሌ፤ ትምህርትህ፣ ጥሩ የስራ ልምድህ አሁንም በጣም ተፈላጊ ናቸው፡፡ እንደገና መኖር አለብህ። አንተ ለቤተሰቦችህ፣ ለጓደኞችህ፣ ለማህበረሰብህና ለሀገርህ ታስፈልጋለህ፡፡ሰሞኑን ህክምናህን ጨርሰህ ትወጣለህ በርታ በርታ በል ፤ " ብሎኝ ወጣ፡፡

ትነሽ ቆይቶ ተመልሶ መጣና፣ ከዛሬ ጀመሮ አንደኛው መድሃኒት በሌላ
እንደተቀየረልኝ ነግሮኝ፣ አዲሱን መድሃኒት ሰጥቶኝ ወደ ቢሮው ሄደ::

እኔ ስለነገረኝ በሽታ ሳብሰለስል ውዬ አደርኩ፡፡ መድሃኒት ከተቀየረልኝ በኋላ፣ የበለጠ የተረጋጋ ስሜት እየተሰማኝ ነው፡፡ ምሽት ምሽት ከዶክተር ጋር የሆስፒታል ግቢ ውስጥ እየተንቀሳቀስን ንፋስ
መውሰድን ልምድ አድርገነዋል፡፡ ስለ ባይፖላር በሽታ በደንብ የማወቅ
ፍላጎቴ ጨመረ፡፡ ነገር ግን፣ ስለበሽታው መረጃ ለማግኘት ስልክ ወይም መፅሃፍ በእጄ ላይ የለም፡፡ አንድ ጥዋት ዶክተር ወደ መኝታ ክፍል መጥቶ፣

“ታዲያስ ያቤዝ፣ እንዴት ነህ?”
“ደህና ነኝ ዶክ፣ እንዴት ነህ አንተስ?”
“ደህና ነኝ
👍2
ዛሬ የእጅህ ጄሶ ይፈታል። ተነስ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል እንሂድ፡፡” ተከትዬው ሄድኩ፡፡ ቀዶ ጥገና ክፍል ያለችው ወጣት ዶክተር ጋር ሰላም ከተባባሉና እኔን ካስተዋወቀኝ በኋላ፣ ሚያስፈራ ድምፅ ባለው የኤሌክትሪክ መጋዝ እጄ ላይ ያለውን ጀሶ ለመቁረጥ
ዶክተሯ ትታገል ጀመር፡፡ መጋዙ ጄሶውን አልፎ እጄን እንዳይቆርጠኝ ተሳቅቄያለሁ፡፡ ዶክተሯ ፊቴ ላይ የሚታየውን የፍርሃት ስሜት አይታ፣

“እንዴ! እንዲህማ አትፍራ፡፡ እጅህ ጋር አይደርስም፡፡ ምንም አያደርግህም፤” አለችኝ ፈገግ ብላ፡፡ እጅ እጄን እያየሁ ፈገግ ለማለት ሞከርኩ፡፡ ከተደጋጋሚ ጥዝ የሚል አስፈሪ ድምፅና መንቀጥቀጥ በኋላ ጄሶው ተፈልቅቆ ወጣ፡፡ እጄን እንድዘረጋውና እንዳጥፈው
አዘዘችኝ፡፡ የቀደመውን ያህል አይታጠፍም አይዘረጋም፡፡ ዶክተሯ እጄ
ላይ የቀረውን ጥጥና ቆሻሻ በአልኮል እያፀዳችልኝ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስድስት ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD) ብዬ አስረዳለሁ...? ዶክተር ድንገት አጠገቤ ቁጭ ሲል ከሄድኩበት ሃሳብ ተመለስኩ፡፡ “እንዴት አደርክ ያቤዝ?” አለኝ፡፡ “እንዴት አደርክ ዶ/ር፡፡” “ምነው በሀሳብ ነጉደሀል? ምን እያሰብክ ነው?” “ለወራትኮ ማሰብ አቁሜ ነበር ዶክተር፡፡ አሁን ማሰብ ስጀምር፣ ውዝፍ ሀሳብ ሁሉ ይመጣብኛል። ምን ማላስበው ነገር…»
#ሰመመን


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

እስክንድር ከነጋ ያጨሰውን ሲጋራ ብዛት ቆጠረ ። እኩለ ቀን ከመሆኑ በፊት አሥራ አንድ አጭሷል ። ብር ልመና በገባበት ቢሮ ሲጋራ እየሰጡ ይሸኙታል ። ዊንስተን
ከሚያጨሰው ዊንስተን ፥ ኒያላ ከሚያጨሰው ኒያላ ፥ቪንሰን ከሚያጨሰው ቪንሰን ፥ ከባለሮዝማኖች ሮዝማን እየተቀበለ ሲያጨስ ይውላል ። ለወትሮው እስከ ምሳ ሰአት ድረስ
ባለው ጊዜ ውስጥ ከሁለት ሲጋራ በላይ አያጨስም” ነበር ።በዚህ ዕለት ግን በየጓዶኞቹ ቢሮ ገብቶ የመጣበትን ዓላማ ባልተሳካለት ቁጥር “ ለማካካሻ ” ሲጋራውን ሲለኩስ ቁጥሩን ዐሥራ አንድ እደረሰው ።

ትርፉ መቃጠል ነው ! ”አለና ከምሳ በኋላ በማጨስ ላይ ያለውን ዐሥራ ሁለተኛ ሲጋራ ግማሽ ወገቡ ላይ ቆርጦ ጣለው ኪሱ ውስጥ ሌላ ሲጋራ አልነበረም ። ነገር ግን አድራጎቱ ከንቱ ፉከራ መሆኑን ልቡ ያውቁዋል ። ሲጋራ ለመተው በርካታ ጊዜ ዝቷል ። በርካታ ጊዜ ምሏል። በርካታ ጊዜ ኪሱ ውስጥ የቀሩ ሲጋራዎችን ሰብሯል ። ሙከራዎቹንም የሚያከናውነው አልኮል ሲጠጣ ወይም በልቶ ሲያበቃ ማለትም በከፍኛ የጥማት ጊዜያቶቹ ነው ።ነገር ግን ውሎ አድሮ ፥ አሳሳች ጋባዥ ሲጋብዘው እምቢ ብሎ እጁን መሰብሰብ ያቅተዋል ። በዚህ በኩል ራሱን ገምታ በቅቶታል ። ለሃያ ስድስት ዓመት ወጣት ስምንት ዓመት ያህል
በሲጋራ ሳንባን ማቃጠል ፥ ምን ያህል ሕይወት ላይ መቀለድ እንደሆነ ይገባዋል ለራሱም በጣም የሚገርመው ግን
ብዙ ሲቸገር ለሲጋራ ማጨስ ወይም ሲጋራ ገባዥ፣ አለማጣቱ ነው ሱስ ምርኮኞቿ እንዳይክዷት ጾም ጸሎት እያደረገች ወይም ለአማልክት እየሰጊደች የምትደብቃቸው ይመስላል እስክንድር አሁን ስለ ሱስ ለመመራመር ጊዜ የለውም ። ከማርታ ጋር የተቃጠረበት ሰዓት ስለተቃረበ ሽሚዙን ቀይሮ
ከርዳዳ ጸጉሩን እየታገለ ያበጥር ጀመር ። ቶሎ ስለማያድግ ማበጠሪያውን ማስገባት ብዙም አያስቸግረውም ።
ነገር ግን ጊዜ የሚያጠፋበት ሲያበጥረው በሁሉም በኩል ተስተካክሎ አለ መቆሙ ነው። የማበጠሪያው ጣቶች በአንድ
በኩል ገብተው ከፊሉን ጸጉር ሲያስተካክሉት በሌላ በኩል ያለውን ያጎደጉዱታል ። አንዴ ተስተካክሎ ከቆመ በኋላ ግን ቀኑን ሙሉ የሚነቀንቀው የለም ሳምሶን ቤት ውስጥ አለመኖሩ ነው እንጂ፥ እስክንድር ጸጉሩን በሚያበጥርበት ጊዜ ትንሽ መለካከፍ ልማዳቸው ነበር ።

አንተ ጸጉርህን ስታበጥር እንኳንስ የተኛ ሰው ሬሳ ትቀሰቅሳለህ ”ይለዋል ሳምሶን ፡ የእስክንድርን ጸጉር ድምፅ በማጋነን ።

“ ምን ታረገዋለህ ! የንጹሕ አፍሪካዊ ጻጉ ነው ! እኮራበታለሁ ” ሲል እስክንድር ይመልሳል ።

“ የንጹሕ አፍሪካዊ ምልክት ጸጉር ሆነ እንዴ ? ”
“ ሌሎችም መመዘኛዎች አሉ ። ይህም ግን ከመመዘኛዎቹ ኣንዱ ነው ። ”
ኪንኪ ጸጉር የሌለው ንጹሕ ኣፍሪካዊ አይደለም ያለው ማነው እባክህ ?”

“ እኔ በበኩሌ ባለ ሉጫ ጸጉሮቹ የዘር ሥራቸው ያጠራጥረኛል ። እንዲያውም አንተ ጸጉርህን የምትላጨው ይህን
ለመደበቅ ይመስለኛል” ይለዋል። ሳምሶንን ለማብሸቅ ሆነ ብሎ የሚያቀርበው መከላከያ ነው ። ሳምሶን ሉጫ ጸጉር ቢኖረውም ሁሌ መላጣ ነው የስፖርተኝነት ምልክት አድርጎ ስለሚወስደው ጸጉሩን አያሳድግም ።

እስክንድር ተሞሻሽሮ ከመኝታ ክፍሉ ወጣ መንገድ ላይ ማንንም ማግኘት አልፈለገም ። አቤልና ሳምሶን ለምሳ
የገቡት መጨረሻ ላይ ስለሆነ ፥ መመለሻቸው መቃረቡ ገመተ ስለዚህ እንዳያገኙት ከወትሮው በተለየ መንገድ
ታጥፎ ሔደ ። ከማርታ ጋር የተቃጠሩት ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ከሚያስወጣው ከዩኒቨርስቲው ዋና በር አካባቢ ነበር ።

በመንገድ ላይ ሆኖ ፡ ከተገናኙ በኋላ የት እንደሚወስዳት ያሰላስል ጀመር ። ምንም ያቀደው ነገር የለውም ።መገናኘት ብቻ ! በጠዋት ተነሥቶ አልተሳካለትም መጨረሻ የሔደበት ጓደኛው ብቻ አምስት ብር ሰጠው ። እሷውም ኪሱ መኖሯን ካረጋገጠ በኋላ ፡ አሁን በዚች አምስት ብር
ምን ይደረግባታል ? ” ሲል አሰበ ፡ “ እንኳንስ ሴት ለማውጣት ወንድ ጓደኞችም ቡና ለመጋበዝ አትበቃም ። ኪሱ በደረቁበት ጊዜ ከማርታ ጋር መተዋወቁ አበሸቀው ።

አሁን ገንዘብ ሊያገኝ የሚችልበት ምንም ምንጭ የለውም ። አባቱ ሞተዋል ። ከእናቱ ምንም ሳንቲም አይጠብቅም ። የምትደርሳቸው ግማሽ የጡረታ አበል እንዴት ከወር እስከ ወር እንደምታደርሳቸው ሲያስብ ይገርመዋል በዚያ ላይ አብሮአቸው የሚኖር የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የሆነ ታናሽ ወንድሙ አለ ። ትንሽም የሚረዳቸው ጅማ የሚኖር መጠነኛ ግሮሰሪ ያለው አጎቱ ነው ። እስክንድር በክረምቱ ወራት
ሊጠይቀው ሔዶ ሦስት መቶ ብር ሰጥቶት ነበር። ሲቀበለው የዓመት ድርጎው መሆኑን ያውቃል ። ነገር ግን ሁለት ወር ያህል እንኳ አላቆየውም የክረምቱን ዕረፍት ጨርሶ ትምህርት ሲጀምር ሰማንያ ብር ብቻ ነበር ፥ ይዞ የገባው ።

(አንባብያን በደጉ ዘመን ነው አሁን ላይ 300 ብር ዋጋዋ ይታወቃል😄)

እሷኑም ወዲያው አጠናቀቃት ። ኪሱ ገንዘብ ማቆየት አይችልም ። ቶሎ ብትንትን አርጎ አጠናቆ ፥ ከዚያ በኋላ ጫማውና ቀለም ሳይተያዩ የልብስ ማጠቢያ ሳሙና እየተበደረ ሲጋራ እየወጋ ዓመቷን ያሳልፋታል ። ያለቦታው ያቃጠለው ገንዘብ የሚያንገበግበው እንዲህ እንደ አሁኑ ዐይነት የበሰለ
እንጆሪ ቀርቦለት የሚቀጥፍበት እጅ ሲያጥረው ነው ። ድህነቱንና ሲያገኝም ብኩንነቱን እያነጻጸረ እንዲሁ እየተገረመ
ይኖራል ።

ከማርታ ጋር ያላቸው ግንኙነት አቤል ምግብ አዳራሽ ውስጥ ከወደቀበት አጋጣሚ ጀምሮ እየዳበረ መጥቶአል ።
ከሰላምታ መሰጣጠት አልፈው ቆመው ማውራት ወይም በቀልድ ተጎሻሽሞ ማለፍ ከጀመሩ ሰንብተዋል ። ባያት ቁጥር
ድርብ ሚና የምጫወትባት ሴት ” ብሎ መፎከሩ አልቀረም ። ነገር ግን እስካሁን እንኳን ድርብ ፥ አንዱንም ሚና መጫወት አልቻለም ። አንድ አቤልን እረዳዋለሁ ብሎ ያሰበበት መንገድ ነበር። ሆኖም ትዕግሥት ለማርታ የልቧን አውጥታ ስለማታጫውታት፡ ከማርታ በቂ መረጃ ማግኘት አልቻለም ። በሌላ በኩል ደግሞ የእስክንድር ልብ ማርታን ለወሲብ ቢከጅላትም : የወንድነት ስሜቱ የሴትነት ገላዋን እያየ ቢጓጓላትም ኪሱ ባዶ መሆኑ ስሜቱን ለመግታት ይገደዳል ። እሷ ግን ኪሱን አሳየችለትም ። ወይም ስሜቱን
እንዲገታ አልፈቀደችለትም ። ባገኘችው ቁጥር ወንድነቱን ትፈታተነዋለች ።

አንድ ቀን ዝንጥ ብላ ከግቢ ስትወጣ አገኛትና ፡ “ ፖ! ዛሬ ወደ ካምፓስ የምትመለሺ አትመስይም ” ሲላት ፤

መጠርጠሩስ “ማን ይሆን የታደለ ፥ አንቺን መሳይ ጽጌረዳ የሚቀጥፍ ? ” ሲላት በምፀታዊ አንጋገር ፤

“ ዕድል ሳይሆን ልብ ይጠይቃል ! ” አለችው ።

እኔ እስኔንድር ልብ «የለኝም ማለት ነው ? ! ” ብሎ በልቡ ኪሱን ሲዳብስ ሳንቲም እንኳ አልነበረውም ። እልህም
የወንድነት ስሜትም ወጥረው ስለ ያዙት በማግሥቱ ጠዋት ተነሥቶ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ በንበረበት ጊዜ ሃያ ስምንት ብር የገዛውን አንድ መጽሐፍ ይዞ ወደ አሮጌ የመጻሕፍት ተራ ሔደ። ሲሆን ሃያ ካልሆነም ዐሥራ አምስት ብር ያወጣልኛል ብሎ የገመተውን መጽሐፍ ፥ “ ስድስት ብር እንግዛህ ” ብለው ወገቡን ቆመጡት በሽቆ መጽሐፉን ይዞ ወደ ቤቱ ተመለሰ ። ልብ ይጠይቃል ያለችውን እያስታወሰ። “ እጅ ከቶ ልብ ብቻውን ምን ያረጋል” አለ በሐሳቡ ። የወንድነት እልሁም ሆነ የስሜት እሳቱ በገንዘብ እጥረት ተዳፍኖ ከረመ ።
በቅርቡ ደግሞ " ከትዕግሥት ጋር ሆነው ወደሚያጠኑበነ ዋርካ ሲሔዱ እሱ ከዋናው ቤትጻሕፍቼ ወጥቶ ሲመጣ ተገናኙና ወዴት ነው የምትሄው ? ” ሲሉ
ጠየቁት "
👍1
ወደ ሽንት ቤት ” አላቸው ።

ማርታ ትዕግሥትን አስቀድማ ወደ ኋላ ቀረት አለችና ፤
ያ ነገር አለህ እንዴ ? ” አለችው ።
“ምኑ?” ብሎ ሊጠይቃት ሲል እያስካካች ስለ ሔደች እሱም ገባውና ብቻውን እየሣቀ ሔደ ።

ነገር ግን በሣቁ ውስጥ አንዳች ስሜት ተናነቀው። ያቺን ዕለት ሳያድር ምሽቱን መኝታ ቤቷ ድረስ ሔዶ ማርታን አስጠራትና ፥ “ በይ እሺ ፡ መቼ ይመችሻል ? ” አላት ።

ጣራ በሚሰነጥቅ ድምፅ እያስካካች ፥ “ ለምኑ ? አለችው።

እሱም በልቡ “ ምናባቷ ታሾፋለች ” እያለ አብረን ስንጫወት ለመዋል ነዋ ! አላት ።
የእልህ ስሜት እንደ ያዘው ስለ ገባት ብዙ ልትቀልድ አልፈለገችም ። “ያው ቅዳሜ ከሰዓት ይሻላል ! ” አለችው ።

ቀጥሯት ሲመለስ • “ አሳያታለሁ !” እያለ በልቡ ይዝት ነበር ። ነገር ግን እጅ እንደሚያስፈልግ ልቡ አላጣውም ።
እናም ሰሞኑን ገንዘብ የሚገኝበትን መንገድ ሲያሰላስል ቆይቶ የመጨረሻ ውሳኔ ሠራተኛ ጓደኞቹን ማስቸግር
ሆነ ። ከእነሱም የተገኘችው አምስት ብር ብቻ ሆነች ።

እስክንድር ይህን እያሰበ በአንጻሩም ፥ እንዲህ፥ አይነት ጭንቀት ውስጥ ከገባሁማ አቤልን መርዳቴ ቀርቶ እኔም
ሌላው አቤል መሆኔ ነው ” እያለ ከኅሊናው ጋር አየተሟገተ ድህነትን እየረገመ ትምህርቱን ጨርሶ የሚመረቅበትን ጊዜ በልቡ እየመተረ ከቀጠሮው ቦታ ሲደርስ ማርታ
ቁድማ ቆማ አገኛት።

ቀድማው በመገኘቷ እንደ መገረም እንደ መደናገጥም ብሎ “ ዘገየሁ እንዴ ? ” አለና ጨበጣት ።

“ አይ ! እኔ ትንሽ ቀደም ብዬ ነው ። ፈረንጅ ነህ ? አለችው ።

“ ቀጠሮ አክባሪነትን ለፈረንጆች ብቻ ማን ሰጣቸው ?”

ሥልጣኔያቸው ነዋ ! ቀጠሮ ማክበር ” ኮ የስልጣነሰ ምልክት ነው ። ”

“ታዲያ ሥልጣኔ በስመ ፈረንጅ መች ሆነልሽ ? ከአህያ የማይሻል ፈረንጅ ሞልቷልኮ እኔ አበሻ ነኝ ጥቁር ነኝ"
ፈረንጅ አይደለሁም ” አላት ።

“ ክብር አይወድልህም ” አለችው ፡ ንግግሩን ናቅ አርጋ ።

“ ፈረንጅ መባል ለኔ ክብር ሳይሆን ስድብ ነው ። ማርትዬ ሙች እልሻለሁ ስድብ ነው እኔነቴ ክብር ያጣ ይመስለኛል ። ጥቁርነቴ መሠረተ ቢስ ወይም ማረግ ቢስ ሆኖ የተቆጠረ ይመስለኛል ። ”

“ ማርትዬ ” በመባሏ ደስ አላት ፤እንኳን ወንድ ሴቶችም እንዲህ አቆላምጠው ሲጠሯት ትወዳለች ።

“ጉረኛ ! ” አለችው በግድየለሽነት አነጋገር “ ይልቅ አሁን በየት በኩል እንሒድ ? ”

“ እ ! በየት በኩል እንሒድ?” ሲል እስክንድር ቃሏን ስልት ባጣ ድምፅ ደገመና ፥ “ ሲኒማ ልጋብዝሽ እንዴ?”
አላት በልቡ የገንዘቡን አቅም እያሰላሰለ ።

“አይ ዛሬ ቅዳሜ ነው ፤ ሰው ይበዛል ” አለች»

እንግዲያው በዚህ በኩል እንሒድና አንድ ቤት ቁጭ ብለን እንጫወታለን !”አላትና' አስፋልቱን ተሻግረው ወደ ሰባ ደረጃ የሚወስደውን መንገድ ያዘ ። ወዲያው ሐሳቡ ውስጥ የመጣችለት ሰባ ደረጃን ወርዶ በስተግራ በኩል የም ትገኝ አንዲት ስም የለሽ ካፊቴሪያ ነበረች ።

የማርታ አለባበስ አልማረከውም ። የሰውነቷን ቅርጽ ከፋፍሎ ዳሌዋን እያነጠረ የወንድነት ስሜት የሚያግል
ወይም የጡቶቿን መግቢያ እያሳየ ልብ የሚሰልብ ልብስ አልለበሰችም ። ለለውጥ ያህል ጂንስ ሱሪ ከቀላልና አነስተኛ ታኮ ጫማ ጋር አድርጋ ከላይ እጄ ጉርድ ሸሚዝ ለብሳለች ።

ኤለባበሷም ከተማሪ ጋር መውጣትም፡“ ያህል ይመስላል ። እስክንድርም ስሜቱን የሚያነቃቃ ልብስ ባለመልበሷ በልቡ በሽቋል ።

በል እሺ ጨዋታ አምጣ ” አለችው በመጓዝ ላይ እንዳሉ ። ለተወሰኑ ሴኮንዶች በሁለቱም ዘንድ ጸጥታ ሰፍኖ ነበር...

💥ይቀጥላል💥
👍2
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)


......ከተደጋጋሚ ጥዝ የሚል አስፈሪ ድምፅና መንቀጥቀጥ በኋላ ጄሶው ተፈልቅቆ ወጣ፡፡ እጄን እንድዘረጋውና እንዳጥፈው አዘዘችኝ፡፡ የቀደመውን ያህል አይታጠፍም አይዘረጋም፡፡ ዶክተሯ እጄ
ላይ የቀረውን ጥጥና ቆሻሻ በአልኮል እያፀዳችልኝ፡፡

“ጥሩ ነው፡፡ በየቀኑ ለተወሰኑ ደቂቃዎች እንደዚህ እያደረክ ካለማመድከው፣ ወደ ቀድሞው ቦታ ይመለሳል፤” አለችኝ፣ በእጆቿ እጄን እጥፍ ዘርጋ እያደረገች እያሳየችኝ፡፡

“እሱን ሃላፊነት እኔ እወስዳለሁ፡፡ አመሰግናለሁ ዶክ፤” አላት ዶክተር ሄኖክ ፈገግ ብሎ፡፡ ወደኔ ዞር አለና፣
“እንኳን ደስ አለህ ያቤዝ! አሁን ህክምናህን ጨርሰሃል፡፡” አለኝ
እጄን ይዞ እየወጣ፡፡ ምንም
አልመለስኩም፡፡ አሁን ከሆስፒታል ውጣ
ከተባልኩ የት እንደምሄድ፣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ሃሳብ በአንዴ በድን አደረገኝ፡፡ እጄን እንደያዘኝ የሆስፒታሉን ዋና በር አልፈን ወጣን፡፡ዝምታዬን ሊሰብር፣

“ሆስፒታላችንን እንዴት አየኸው?” አለኝ፡፡
“አሪፍ ነው፡፡” በአጭሩ መለስኩ፡፡ የት እንደምሄድ፣ በምን ገንዘብ እንደምሄድ ጨንቆኛል፡፡ ለዚህም ዶክተርን ማስቸገር እንደሌለብኝ እያሰብኩ ነው፡፡ የሆስፒታሉ በር አካባቢ ወደ ቆሙ ታክሲዎች ሄድን፡፡
ፒያሳ፣ አራዳ እያሉ ይጣራሉ፡፡ ሁሉም ሃገር ፒያሳ አለ ማለት ነው?
ከዚህ በፊት የት ነበር የሰማሁት? አዎ፣ ደሴ፡፡ ስለ ፒያሳ ማሰብ ጀመርኩ። ከሚያስጨንቀኝ ሃሳቤ ፒያሳ ነፃ አወጣችኝ፡፡ ዶክተር አንዱ ታክሲ ውስጥ ይዞኝ ገባ፡፡ ታክሲው የት እንደጠራ አልሰማሁም፡፡ ከቀልቤ አልነበርኩም፡፡ የጎንደርን ፒያሳ ምን እንደምትመስል ለማየት ጓጓው::የተወሰነ እንደሄድን፣ የታክሲው እረዳት፣

“አስራ ስምንት ወራጅ አለ?” ብሎ ጠየቀ፡፡

“አዎ፡፡ ና እዚህ ነን፤” ብሎኝ ዶክተር መውረድ ጀመረ።ተከተልኩት፡፡ ከታክሲው ወርደን ትንሽ እንደተጓዝን፣
“አሁን የምንሄደው ወደኔ ቤት ነው :: ወደ ቤተሰብም ለመሄድ ሆነ ስራ ለመጀመር ተረጋግተህ እስክትወስን እኔ ጋር ትሆናለህ፡፡ ካሁን በኋላ እንደ ሃኪምህ ሳይሆን፣ እንደ ወንድምህ፣ እንደ ጓደኛህ ልታስበኝ ትችላለህ፡፡ ምንም ነገር አታስብ፤ ምትፈልገው ነገር ካለ ምንም
ሳትጨነቅ ልትጠይቀኝ ትችላለህ፡፡”

“አመሰግናለሁ ዶክተር፡፡ መቼም የማልከፍለው ውለታህ አለብኝ፡፡ የት እንደምሄድ በጣም ጨንቆኝ ነበር፡፡”
ትልቅ የብረት በር ያለው ግቢ ጋር ስንደርስ፣ ዶክተር በሩን በቁልፍ ከፍቶ ገባን፡፡ ሰፊ ንፁህ ግቢ፣ መሃል ላይ የቆመ ትልቅ ቪላ፣ ዙሪያውን የተደረደሩ ስርቪስ ቤቶች፣ ዶክተር ቪላውን አልፎ ጥግ ላይ
ያለች ሰርቪስ ክፍል ከፍቶ ገባ፡፡

“ግባ፡፡ እንግዲህ የወንደ ላጤ ቤቴ ይቺ ናት፡፡ ብቻዬን ነው ምኖረው፡፡ ካሁን በኋላ እንጋራታለን፡፡ አንድ ቁልፍ እንካ፡፡”

“ደስ ትላለች፡፡” አልኩኝ ወደ ውስጥ ገብቼ ዙሪያውን እየቃኘሁ፡፡መለስተኛ አንድ ክፍል ቤት፣ መሃል ላይ በመጋረጃ ተከፍላለች።ከመጋረጃው ጀርባ አልጋ እንደሆነ ገመትኩ፡፡ ቴሌቪዥን፣ በመፅሃፍት የተሞላ የመፅሃፍት መደርደሪያ፣ ዱካዎች፣ እቤት እንደሚያበስል የሚናገሩ እቃዎች፡፡ ዶክተር አንዲህ እንደሚኖር ገምቼም አላውቅም፡፡እኔ ከዚህ በጣም የተሻለ ንሮ ነበረኝ፡፡

“ቁጭ በል እንጂ፤ ቆመህ ቀረህ እኮ...” አለኝ ዶክተር ወደ ዱካዎች እያመለከተኝ፡፡ አንዱን ስቤ ተቀመጥኩ፡፡ወዲያው ዶክተር
ምግብ ማብሰል ጀመረ፡፡ አንዳንድ ነገር እያቀበልኩት ቆንጆ ሽሮ ወጥ ሰርቶ ምሳ በላን፡፡ በጣም ይጣፍጣል፡፡ የቤት ምግብ ናፍቆኝ ነበር፡፡ እቃ በማጠብ የቤተኝነት ስሜት እንደተሰማኝ ለማሳየት ሞከርኩ። ስንጨርስ ፒያሳ ወስዶ ከተማውን አሳየኝ፡፡ ፑል ተጫወትን፤ ሲመሻሽ ከፒያሳ
ወደቤት ወክ እያደረግን ተመለስን፡፡ ስንመለስ መንገዱ ቁልቁለት ስለሆነ
ነው መሰለኝ፣ ቅርብ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡

ህይወት እንዲህ ቀጠለች፡፡ የኪስ ገንዘብ ይሰጠኛል፡፡ እርሱ ወደ ስራ ሲሄድ ከተማ ወጣ ብዬ ሻይ ቡና እላለሁ፡፡ እረፍት ሲሆን ከተማ ወጥተን ሻይ ቡና ብለን ፑል ተጫውተን እንመለሳለን፡፡ ስራ ከዋለ፣
ከስራ ሲመጣ ወክ እያደረግን እንጨዋወታለን፡፡ ዶክተር የሰጠኝ ፍቅር
አሁንም የሚፈልጉኝ ሰዎች እንዳሉ ተሰማኝ፡፡ እንድነቃቃና መኖር እንዳለብኝ እንዳስብ አድርጎኛል፡፡ በጣም ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነው::ስራ መጀመር እንዳለብኝ እያሰብኩ ነው፡፡ እርሱ ስራ ሲሄድ፣ በብዛት
ከተደረደሩት የስነ አዕምሮ መፅሃፍት እያነሳሁ፣ ስለ ባይፖላር ለመረዳት በብዛት በቤቱ ከደረደራቸው የስነ አዕምሮ መፅሃፍት እየመረጥኩ ሳነብብ እውላለሁ፡፡

#ህመም_አልባው_በሽታ

ዶክተር የባይ ፖላር በሽታ አለበህ ካለኝ ቀን ጀምሮ፣ ስለ ባይፖላር የማወቅ ፍላጎቴ ጨምሯል፡፡ መድሃኒት ከጀመርኩኝ በኋላ እያየሁ ያለሁት ለውጥ ጥሩ ስሜት ፈጥሮልኛል፣ ከቀደመው ስሜቴ
ጋር ሳነፃፅረው፣ አሁን የተለየ የተረጋጋሁ ይመስለኛል። አለምን የማይበትን መነፅር የቀየርኩ ያህል ልዩነት ይሰማኛል፡፡ ባይ ፖላር ግን ምን ማለት ነው...? እብድ ማለት ነው...? ወፈፌ...? ቀውስ ማለት
ይሆን...? ሆ...ሆ... ኧረ በጭራሽ...! እኔማ ቀውስ አይደለሁም፡፡
እንትና ቀውሱ፣ እንትና እብዱ፣ ያ ሾጡ፣ ቅብርጥሱ፣ ምናምን ሲሉ እሰማለሁ፡፡ ህመሞች ይሁኑ ስድቦች አይገቡኝም፡፡ እኔን ማንም እንዲህ ሲለኝ አልሰማሁም፡፡ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ሆኖ ይሆን እንዴ?
ኖ.ኖ. እብድማ ብዙ ግዜ ተብዬ አውቃለሁ፡፡ እና ባይፖላር እብድ
ማለት ነው? ስለበሽታዬ ለማወቅ በየቀኑ አሰላስላለሁ። ዶክተር እንዳለው፣ ታምሜ ከነበር ይኼ በሽታ ህመም አልባ በሽታ ነው፡፡ ዶክተር ስራ ሲሄድ፣ እቤት ያለውን ስራ ጨርስና፣ ከተደረደሩት የስነ አዕምሮ
መፅሃፍት፣ እየቀያየርኩ አነበብኩኝ፡፡ አብዛኞቹ በሽታዎች ተመሳሳይ ሆኑብኝ፡፡ አንዱን ከአንዱ መለየት ቸገረኝ፡፡ ዶክተርን ማብራሪያ እንዲሰጠኝ ሚመቸውን ቀን መጠበቅ ጀመርኩ፡፡

አንድ ቀን ዶክተር አዳር ስርቶ ጥዋት መጣ፡፡ ከሰዐት ምሳ በልተን ፀሃዩ በረድ ሲል እንደተለመደው ወክ ልናደርግ ከቤት ወጣን፡፡በአባ ሳሙኤል አድርገን ቁልቁል ወደ እየሱስ መውረድ ጀመርን፡፡ ዛሬ
ለቀናት ያጠራቀምኳቸውን ጥያቄዎች ላዘንብበት ተዘጋጀሁ፡፡ ከግቢ
ወጥተን ትንሽ እንደተጓዝን፤

“ዶክ ጥያቄ ልጠይቅህ ፈልጌ ነበር”

“ጣድያ ምን ችግር አለው፣ ጠይቀኛ፡፡”

“ዶክ ባይፖላር አለብህ ካልከኝ ጀምሮ ስለበሽታው ለማወቅ ብዙ ሞክሬያለሁ፡፡ ብዙ አነበብኩ፤ ግን አልገባኝም፡፡ አስረዳኝ?”

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
#ሰመመን


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

ከተማሪ ጋር መውጣትም፡“ ለለውጥ ያህል ይመስላል ። እስክንድርም ስሜቱን የሚያነቃቃ ልብስ ባለመልበሷ በልቡ በሽቋል ።

በል እሺ ጨዋታ አምጣ ” አለችው በመጓዝ ላይ እንዳሉ ። ለተወሰኑ ሴኮንዶች በሁለቱም ዘንድ ጸጥታ ሰፍኖ ነበር።

“ ታዲያስ ' ትምህርት እንዴት ነው ? ” አላት ፡ የጨዋታ አርዕስት እንዴት እንደሚጀመር ግራ ገብቶት እባክህ ሌላ ጨዋታ አምጣ የትምህርት ወሬ ራስ
ምታት ሆኖብኛል!” አለችው ።

ምነው ?
“አስጠላኛ ! ሰው ስንት ዓመት ይማራል ?”

ዕድሜውን ሙሉ ነዋ !” አላትና ፈገግ ብሎ፥ “ግን ኮ ትምህርት የሚጠላ ነገር አይደለም ። ካልቪስ በሕይወት ውስጥ እንደ ትምህርት ጣፋጭ ነገር የለም ። የዘመኑ እኛነታችን ራሱ የትምህርት ውጤት ነው ። በሕይወት ላይ ትምህርት ያላስከተለው ለውጥ ምን አለ ?እስኪ ከምንራመድበት አስፋልት ጀምረሽ አካባቢሽንና ዐለምን በዓይነ ሕሊናሽ ዳስሺው ዕድገቱና ሥልጣኔው ሁሉ የትምህርት ውጤት ነው ። የሰው ልጅ በትምህርት ኃይል መልሶ እስከ መፍጠር የደረሰበት ሰዓት ነው ፡ እና ትምህርት
የሚጠላ ነገር አይደለም ” አላት ' ዮናታን “ ትምህርት የሚገላገሉት ዕዳ አይደለም ” ያሉትን እያስታወሰ ።
“ በእርግጥ እኛ አብዛኛውን ጊዜ ትምህርትን የምንመለከተው ጨርሰን ከመገላገሉ አንጻር ነው ። ይህ ጠባብና
ደካማ አመለካከት ይመስለኛል ። ትምህርት ሕይወት ነው ።አያልቅም ። እኛ እንድንጠላው : ከግልግል እንድንቆጥረው
የሚያረጉን ነገሮች የትምህርት መስክ አመራረጣችንና የትምህርት አሰጣጡ ሁኔታዎች ናቸው የትምህርት መስክ
ጠብቦ መታየት የለበትም ። እያንዳንዷ የሕይወት እንቅስቃሴ የምትበለፅገውና የምታድገው በትምህርት ነው ። ”

ተወኝ ባክህ ! ይልቅ የናንተ ትዕግሥት ይገርመኛል ።

ዩኒቨርስቲ አራት ዓመት መቆየታችሁ ። ”

“ ምነው ? እንዴት ? ”

“ በጭንቀትና በወጥረት ግቢ አራት ዓመት ሙሉ ? ትዕግሥታችሁ ይገርመኛል

ምን ታረጊዋለሽ ! የህልውና ትግል ነው ። ሁሉም የማይረሳኝ የውጥረትና የጭንቀት ጊዜ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ በነበርንበት ጊዜ ያሳለፍነው ነው ። የገናን ማዕበል እስክገናልፍ ድረስ ካምፓስ ውጭ ብቅ ብለን አናውቅም ነበር ። ዕውቀቱ ሳያንሳቸው ጭንቀቱ ብቻ የሚጥላቸው ልጆች ነበሩ ። በተለይ እኔ አጠገብ ይተኛ የነበረ ልጅ እስካሁን ትዝ ይለኛል ። ሴሚስተሩን ሁሉ ልብሱን አወልቆ መኝታ ውስጥ ገብቶ አያውቅም ። መጽሐፍ ወይም ደብተር እንደ ያዘ " ልብሱን ሳያወልቅ ፥ አልጋው ላይ ጋደም ይልና ማንበብ ይጀምራል ። እንቅልፍ እያንገላጀው ያነባል ፤
ጥቂት ቆይቶ ደብተሩን እንደያዘ ዐይኑን ይከድናል ። ደሞ ትንሽ ድምፅ ሲሰማ ይባንናል ። ያሳዝነኛል ። “ ለምን አትተኛም? ከፈለግክ እኔ ሌሊት እቀሰቅስህና ታጠናለህ ። ኣሁን ተኛ እለዋለሁ ። “አይ ደህና ነኝ” ይልና ዐይኑን በጣቶቹ ደባብሶ ማንበብ ይቀጥላል ። አፍታም ሳይቆይ እንደ ጎና ያንቀላፋል ። እንዲህ እንዳለ ያነጋታል እንጂ ፥ ጨክኖ
ልብሱን አውልቆ ቀደንበ አይተኛም ። ታዲያ የሚያጠናው።ነገር እንደማይገባው ይሰማኝ ነበር ። በዚያ ላይ እንደዚያ
ሆኖ አድሮ ጠዋት “ሌክቸር' መቀበል አይችልም ። መጨረሻ ያው የገና ማዕቀል ጠርጎ ከዩኒቨርስቲ አባረረው ። እሱስ ተገላገለ እንጅ ተባረረ አልልም ። ትንሽ ቆይቶ ያብድ ነበር ።
የሚያሳዝነኝ ግን አምስቱን የትምህርት ዐይነት“ፍላት ነው የወጣው

“ ውይ ምስኪን ! ” ብላ ማርታ ከንፈርዋን መጠጠች ።
“ አዎ ! ታዲያ እንዲህ ዐይነቱ ችግር ከምን የመጣ ይመስልሻል ? ተማሪው ስለ ትምህርት ያለው ደካማ አመለካከት፥ የትምህርት አሰጣጡና የተማሪው መመዘኛ ሥርዓት ፥እንዲሁም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ኋላ ቀርነት ተደራርበው የፈጠሩት ችግር ነው እንጂ ፥ ዩኒቨርስቲ በመሠረቱ የጭንቀትና የውጥረት ቦታ መሆን የለበትም ። ይልቁንም የጥበብና የምርምር ቦታ ነው

“ለማንኛውም ” ብል ፥ መናገር የፈለገችውን ሳትጨርስ አቋረጣት ።

“ አዎ ! ለማንኛውም አሁን ያለው ምርጫ በተሰጠን የትምህርት ክልልና መመዘኛ ውስጥ ተወዳድሮ ማለፍ ነው ። ፈትናም” ኮ ተቃርቦአል ።ቢበዛ ሦስት ሳምንት ነው
የቀረወ ። በርትተሽ ማጥናት ነው ። ”

ማን ይፈራል ሞት ! ” አለችው ።
እንዴት ? ”

ማለቴ ፥ እኔ መጨነቅ አልፈልግም ። ደግሞም ኢትዮጵያ ውስጥ እንደማልቆይ ዐውቃለሁ ።

እስክንድር በልቡ ፥ “ ይህ በእንክብካቤ የተያዘ ሰውነትሽ እንደምንስ ጭንቀት ይችላል ? ” እያለ “ የት ትሔጂያለሽ ? ” ሲል ጠየቃት ።

ውጭ ሀገር ነው ።

ሰባ ደረጃ ስለደረሱ ደረጃውን ሲወርዱ ማርታ የእስክንድርን ክንድ እንደ መደገፊያ አርጋ ያዝ አረገችው ።የእጅዋ ሙቀት በክንዱ አልፎ መላ ሰውነቱን ሲያዳርሰው
“ምነው ክንዴን ለቀሽ ወገቤን ወይም አንገቴን ብትደገፊ አለ በሐሳቡ።

ስኮላርሺፕ ልትጠይቂ አስበሻል እንዴ ? ”
“ ኖ ! ዋው ! ብቻ በሆነ መንገድ እሔዳለሁ ። ”

የት ? አሜሪካ ?” እላት በምጹት አነጋገር እሷን ከመሰሉ ሴቶች የሌላ አገር ስም አይጠበቅም ብሎ ነው ።

እንዳሾፈባት አልገባትም ። “ አዎ ! አሜሪካን አገር ወንድሞቼ አሉ ። እንግሊዝ አገርም የአክስቴ ልጆች አሉ ።እኔ ግን የአሜሪካኑ ይሻላል ብዬ በዚያ በኩል እየሞከርኩ ነው ” አለችው »

ቤተሰብሽ ሁሉ ውጭ ሀገር ናቸው ? ” ሲል ሸርደድ አረጋትና “ ለካ ቅድም እኔን ፈረንጅ ነህ ያልሺኝ አንቺ ፈረንጅነት ስለሚሰማሽ ነው ” አላት ።

“ ማሾፍህ ነው ? ”

እንደ በሸቀች ገባውና ፡ “ ማርትዬ ሙች ፥ ማሾፌ አይደለም የምሬን ነው ” አላት ።

“ደግሞ እንድታቆላምጠኝ የፈቀደልህ ማነው ? ማንም ወንድ ሳያስፈቅደኝ ሊያቆላምጠኝ አይችልም ።”

“ ውበትሽ እንዳቆላምጥሽ ቢያስገድደኝስ ? ”
“ውበቴንም ለማድነቅ ቢሆን ፈቃድ ያስፈልጋል ።
“ በተለይ ሴቶች ! ” አላትና ክንዱን የያዘችበትን እጅዋን ጭብጭ አርጎ «ወደ ጎኑ አስጠጋት ።

“ሂድ ደረቅ ! ”
"የት ልሒድ ” ርጥብ !”
ሁሉንም “ ደረቅ ” ማለት ስለሚቀናት እሱ ደግሞ "ርጥብ ” እያለ ያበሽቃታል

ደረጃውን ወርደው ወደ ግራ ከታጠፉ በኋላ ። “ ከቤተሰቦችሽ ጋር ነው የምትኖሪው ? ” ሲል ጠየቃት ።

ለምን ጠየቀኝ ብላ አልተመራመረችም ፤ወይም አልተደናገጠችም ።
“ ዳዲ የለም ። ወንድሞቼም እንደ ነገርኩህ ውጭ ናቸው ። እኔና እናቴ ብቻ ነን እዚህ ያለነው ።

“ እባትሽ የት ሔዱ? ”አላት በኀዘኔታ ዐይነት ።

“ ሔቨን” አለችው፥ መሞታቸውን ብቻ ሳይሆን መጽደቃቸውንም ለማስገንዘብ ።

እስክንድር አንዴ " ሥነ ልቦና ትምህርት ክፍለ ጊዝ መምህሩ በነገራቸው ቀልድ ውስጥ በምድር ላይ ለድሀ የመጸመተው አምስት ሳንቲም ተመልሰለት ከገነት በር የተባረረረው ሰው ትዝ አለውና • “ የማርታ አባት በምድር ላይ ብዙ ገንዘብ መጽውተው ነበር ማለት ነው” ሲል በልቡ ቀለደ

ግን ምን ሆነው ሞቱ ? ”
“ምን ያደርግልሃል?” አለችና አመንትታ ዝም አለች።

እስክንድር ምክንያቱን መናገር እንዳልፈለገች ገባውና ምናልባት የአብዮቱ ባቡር ጨፍልቆአቸው ይሆናል ብሎ ዝም አለ ። ለጥቂት ሴኮንዶች ሁለቱም ዝም ተባባሉ ።

አደራሽን ማርታ! ፈረንጅ ሀገር ስትሔጂ ነጭ እንዳታግቢ አላት እስክንድር ጥቂት ሲያስብ ቆይቶ ።

ለምን ? ምነው ?”

ስም የለሽ ካፊቴሪያ በር ላይ ስለደረሱ እሷን አስቀድሟት ገቡና ጥግ ቦታ መርጠው ተቀመጡ ። ብዙ ሰው አልነበረም ። ሞቅ ያለ የፈረንጅ መዚቃ ቤቱን ያናጋዋል ።
👍2
አሳላፊው መጥቶ " “ ምን ልታዘዝ ? ” ሲል ከፊታቸው ቆመ ። እስክንድር ማርታ እንድታዝ ቅድሚያ ስጣት ።

ከጭማቂ ዘር ምን አላችሁ ? ” ስትል አሳሳፊውን ጠየቀችው

“ ለምን ሌላ ነገር አትጠጪም ? ቢራ ምናምን ? ” አላት እስክንድር ለማግደርደር ያህል

“እኔ የፍራፍሪ ጭማቂ ነው የምፈልገው ” አለችና

ወደ አሳላፊው ተመለከተች "

"ፓፓዬና ብርቱካን ”አለ አሳላፊው ።
“ ለኔ የብርቱካን ጭማቂ” አለች ማርታ"
“ በል እሺ፡ ለኔም እንደዚያው” አለ እስክንድር አሳላፊው ከሔደ በኋላ እስክንድር ፡ “ የሚበላስ ነገር "
ሳንድዊች ምናምን ?” ሲል አግደረደራት

“ ምንም አልፈልግም ” ካላችው በኋላ ልቧ ተንጠልጥሎ ከቀረው ጨዋታቸው ላይ ተሰቅሎ ስለ ነበር፡ “ይልቅ ቅድም የውጪ ዜጋ እንዳታቢ ያልከኝ ለምንድን ነው?" ስትል ጠየቀችው ።

ለምን መሰለሽ ” አላትና እንዴት እንደሚገልጽላት በመቸገር ዐይነት ትንሽ ከቆየ በኋላ ኑሮሽ ጤናማ የሚሆን አይመስለኝም ” አላት።

“ እንዴት ? ”

አየሽ ! አንቺና የውጪው ዜጋ የተወለዳችሁበት ያደጋችሁበትና የኖራችሁበት አካባቢ የተለያየ ነው ። ባህላችሁ ይለያያል ። በምግብ ዓይነት ወይም ባአመጋገብ ሥርዓት ፥ በአለባበስ ሁኔታ በጨዋታ ዐይነቶች ፡ በመዝናኛ
ስፍራ አመራረጥ ፥ በእንግዳ አቀባበል ፡ በልጆች አስተዳደግ ከሁሉም በላይ ደግሞ አስተሳሰብና ማኅበራዊ ኑሮ አመ
ለካከት ልትለያዩ ትችላላችሁ ። ትዳር ማለት ደግሞ እኒህን ነገሮች መጋራት ነው እና በባህልም ሆነ በሥነ ልቡናዊ
አመለካከት ብቻ የተራራቁ ጥንዶች ትዳር የሚያምር አይመስለኝም ። ”

“ አባባልህ ልክ ልሆን ይችላል ነገር ግን ማንም ሰው በጋራ የሚፈልገው ነገር አለ ያም ያማረ ፥ የሠለጠነና የበለጸገ ኑሮ ነው የጋራ መሰረታችንን ወይም
ግባችንን ጥሩ ኑሮ አድርገን አንዳችን ከአንዳችን መማር እንችላለን።"

ሁለቱም የቀረበላቸውን የብርቱካን ጭማቂ ተጎነጩ ።አሳላፊው ሌላ የሚታዘዛቸው እንዳለ ለማረጋጥጥ ጥቂት ከቆመ በኋላ ተመልሶ ሔደ ።

“ ምን መሰለሽ ማርታ ነገሩ እንዲህ እንደምታስቢው ቀላል አይሆንም ” ሲል እስክንድር ቀጠለ አየሽ የአሁኑ አንቺነትሽ ክረዥም ዓመት አኗኗርሽና አካባቢሽ
የተገነባ ነው ። ይህን ግንባታ ማደሳ ወይም መለወጥ በጣም ከባድ ነው ። ሊሆንም ቢችል እንኳ ከባድ ትግል ጠንካራመንፈስና ብልህ ጭንቅላት ይጠይቃል።

እባክህ ተው ዋናው ነገር ፍቅር ነው። በሁለቱም መሐል መፈቃቀር ካለ ይህ ችግር አይፈጠርም ። ”....

💥ይቀጥላል💥
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)


...“በጣም ጎበዝ ያቤዝ፡፡ ስለ አለብህ የጤና ችግር ለማውቅ መፈለግ በጣም ጉብዝና ነው፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጥቅም አለው፡፡ ባይፖላር ዲስኦርደር ማለት፣ ሰዎች ሁለት የስሜት ዋልታዎች መፈራረቅን ተከትሎ፣ተደጋጋሚ የሚመጣ የባህሪ መለዋወጥ ሲያጋጥማቸው ነው።
መለዋወጦቹም፧ በስሜት ከፍታዎች እና በስሜት ዝቅታዎች መካከል የሚከሰት ነው:: በመሆኑም ይህ ችግር ያለበት ሰው፣ ባለበት የስሜት ከፍታ ወይም ዝቅታ መሰረት አሰተሳሰቡ፣ ውሳኔ አሰጣጡ፣ በነገሮች ላይ የሚኖረው ፍላጎት፣ ድርጊቶችን ለማድረግ የሚኖረው ሀይልና ጉልበት፣ በአጠቃላይ የህይወት አመለካከቱና አረዳዱ በሰዐቱ እንዳለው
የስሜት ሁኔታ የተለያየ ነው፡፡ በተጨማሪም፣ የዚህ ችግር ተጠቂ የሆኑ
ሰዎች ውስጣዊ ለውጦች ሊኖራቸው፣ አካባቢያቸው የተለወጠ ስለሚመስላቸው የሚሰጡት ምላሽ የተሳሳተ ሊሆን ይችላል፡፡

የዚህ ችግር ተጠቂዎች የስሜት ከፍታ ሲኖራቸው ማኒያ ወይም ሃይፖማኒያ ይባላል፡፡ ማኒያ ከሃይፖማኒያ ተመሳሳይ ምልክት ቢኖረውም፣ ማኒያ በህመም ደረጃው ከበድ ያለ በሽታ ነው፡፡ ይህ
የባህሪዎች መለዋወጥ፣ ችግሩ ያለባቸውን ሰዎች በስራ፣ በትምህርት፣
በማህበራዊ እንቅስቃሴያቸው እና ግንኙነቶቻቸው ላይ ችግሮች
ማወቅ እንዲከሰቱ ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ የስሜት ከፍታ ላይ ሲሆኑ፤ በፊት
ብዙም ትኩረት ማይሰጡትን ጉዳይ የማየት፣ የመስማትና የማወቅ ፍላጎት መጨመርን ያሳያሉ፤ ከነበራቸው ማህበራዊ መግባባት የጨመረ
የመቀራረብና የመግባባት ባህሪ ያሳያሉ፣ የማይጨበጡ፣ ወይም

ቶሎቶሎ ሚቀያየሩ አዳዲስ ሀሳቦችንና ንድፎችን በማምጣት ያወራሉ፤አንድ ቦታና አንድ ሃሳብ ላይ በጥልቀት ማስብ ስለሚያስጨንቃቸው ቶሎ ከሃሳብ ወደ ሃሳብ ይቀያይራሉ፣ በጥቃቅን ነገሮች አክርረው ይጨቃጨቃሉ፣ ነገሮቹ ከነርሱ ህይወት ጋር ጠቃሚ ግንኙነት ባይኖራቸውም፣ ስለሚሰሟቸው ነገር ከፍተኛ የማወቅ ፍፈላጎት ያሳያሉ፤ ለነገሮች ከተገቢው በላይ ይናደዳሉ፣ ይበሳጨሉ፣ ከብሰጭት ስሜት መውጣት ይቸገራሉ፣ የተጋነነ በራስ የመተማመን ስሜት ይኖራቸዋል፤ የሚያመጧቸውን ሀሳቦች ፍፁም አድርገው ያስባሉ፡፡
ትችትና አስተያየት መቀበል ይከብዳቸዋል እንደሚተገብሯቸው እርግጠኛ መሆን፡፡ የእንቅልፍ ፍላጎት መቀነስ፤ በፊት ከሚተኙበት ሰዓት ዘግይቶ መተኛትና ባልተለመደ ንቁ መሆን፤ ያልተለመደ
ወሬኛነት፤ ከማይግባቧቸውና ከማያቋቸው ሰዎች ጋር ጭምር
ያልተለመደ የማውራት ፍላጎት፤ ነገሮችን አብዝቶ ማቅለል፤ ደካማ ውሳኔ መስጠት ያስከትላል፡፡ የመሳስሉትን ምልክቶች የሚያሳዩ ሰዎች ሃይፖማኒያ ይባላል፡፡”

“ስለዚህ ዶክ፣ አንድ ሰው የተዘረዘሩት ምልክቶች በሙሉ ሊኖርበት ነው ይሄ ችግሩ አለበት ሚባለው?”

“ኖኖ! እንደዛ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ከላይ ከዘረዘርኳቸው ውስጥ፣ ሶስቱን ወይም ከዚያ በላይ ምልክቶች ካሳየና በሃኪም
ከተረጋገጠ ሃይፖማኒያ አለበት ልንል እንችላለን፡፡” በውስጤ አሰላሰልኩ፡፡ እነዚህ ስሜቶች ሶስቱ ሳይሆን ሁሉም ግዜ ጠብቀው፣እብደቴ ሲነሳ በደስታ ማስተናግዳቸው ሲሜቶች ናቸው፡፡

“ዶክ ከእነዚህ ስሜቶች አብዛኞቹ በተደጋጋ እኔን ሲስሙኝ ኖረዋል። ታዲያ ሃይፖማንያ ሳይሆን ለምን ባይፖላር አለብህ አልከኝ?”

ትክክል ነህ ያቤዝ፡፡ አንተ እነዚህ ስሜቶች ሲሰሙህ እንደከረሙ ነግረኸኛል፡፡ ነገር ግን፣ ሃይፖማንያ ሚባሉት እነዚህን
ስሜቶች ብቻ ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ አንተ ግን፣ እነዚህ ስሜቶች ብቻ አይደሉም ሲሰሙህ የነበረው፡፡ ሌላም ስሜቶች ነበሩህ፡፡”

“ሌላ ስሜትም ስትለኝ፣ ሌላ ምን አይነት ስሜት?"

“አንተ የሃይፖኒያ ስሜቶች ብቻ ሳይሆን የነበረህ፣ ግዜን ጠብቆ ሚፈራረቅ የስሜት ዝቅታ ወይም የዲፕረሽን ምልክቶችም ነበሩህ፡፡”

“የስሜት ዝቅታ /የዲፕረሽን/ ምልክቶችስ ምን ምን ናቸው?"

“የዲፕረሽን ምልክቶች የምንላቸው፤ ከፍተኛ ብስጭት፣ማህበራዊ መነጠል፣ ብቸኝነት ማብዛት፤ ከፍተኛ ምክንያት የለሽ የድካም ስሜት፧ የጡንቻ መዛል፤ ቁርጥማት፣ የጀርባ ህመም፤ የመረበሽ
ስሜት ፣ በስራ፣ በትምህርትና ቤተሰባዊ ሃላፊነቶች ከተገቢው በላይ መጨነቅ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ፣ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የመዝናናት የፍላጎት ማጣት፣ እንዲሁም፣ የጥፋተኝነት ስሜቶች፣ ዋጋቢስ እና ተገቢ ያልሆነ ራስን መቅጣት፣ በራስ የመተማመን ስሜት መቀነስ፣ ደካማ እና የቀነሰ ትኩረት፣ አፍራሽ እና መጥፎ ሃሳቦችን በተደጋጋሚ ማሰብ፣ ራስን የማጥፋት አስተሳሰብ እና ራስን የመጉዳት ወይም ራስን የመግደል ሙከራዎች እና የመሳሰሉት ምልክቶች ካሉበት፤ የዲፕረሽን ችግር አለበት ይባላል”

እነዚህ የበሽታ ምልክቶች ከሆኑማ
ታምሜያለሁ፣ሲፈራረቁብኝ ኖረዋል፡፡ ነገር ግን፣ ብዙ ሰው እንደዛ ሚሰማው
ይመስለኛል፡፡ ሃኒ በአምሮዬ ውልብ አለች፡፡ ትበሳጭ ነበር፤ ትናደድ ነበር፤ ብቻዋን መደበቅ ፈልጋ ስትመጣ ነው የተገናኘነው፣ እራሷን አጥፍታለች። እና ሃኒም እንደኔ የዲፕረሽን ታማሚ ነበረች ማለት ነው?፣ እራሷን ለማጥፋት ያደረሳት ይህ ህመም አልባ በሽታ ነበር ማለት ነው?

“እና ዲፕረሽን አሁን ከጠቀስካቸው ምልክት ሶስቱን ማሳየት ማለት ነው?”

“አይደለም፡፡ ዲፕረሽን እንደ ሃይፖ ማንያ በሶስት ምልክት ብቻ አይደለም፡፡ ከእነዚህ ምልክቶች መካከል አምስቱን ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑት አንድ ስው ደጋግሞ ሲኖረውና የእለት ተለት ህይወቱን እንዳይመራ ተፅእኖ ሊኖራቸው ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህን በሽታዎች
ሃኪም ሳያማክሩ ምልክት በመቁጠር ብቻ እንዲህ ነኝ እንዲያ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ግን ምልክቶቹ ከተደጋገሙና ከቆዩ ሃኪም ማማከር አስፈላጊ ነው፡፡”

“እነዚህም ምልክቶች እኮ በደንብ እንደነበሩኝ ነግሬሃለው ዶክተር፡፡ ታድያ ለምን ዲፕረሽንም አለብህ አላልከኝም? ህይወቴን እዚህ ያደረሱት እኮ አሁን የጠቀስካቸው ምልክቶች ሲስሙኝ ነው። ያማል፣ያላምጣል፣ ያመነዥካል፣ ሞት እንደ ጣፋጭ መድሃኒት ይናፍቃ፡ ዶክ፣
ስለዚህ እኔ ያለብኝ ችግር እንደውም ዲፕረሽን ነው፡፡”

“አየህ ያቤዝ፣ ቅድም ለዛ ነበር ሃኪም ሳያማክሩ ምልክቶችን ቆጥሮ ይሄ ነው፣ ያ ነው ያለብኝ፣ ማለት አይቻልም ያልኩህ፡፡ አንተ የሃይፖማንያም የዲፕረሽንም ምልክቶች እየተቀያየሩብህ አሳይተሃል፡፡
አንድ ስው የሃይፖማንያ ምልክት ብቻ ካለው፣ በሃኪም ከተረጋገጠ በኋላ ሃይፖማንያ አለበት ይባላል፤ የድባቴ ምልክቶች ብቻ ካሉበት፣ በሃኪም ከተረጋገጠ በኋላ የድባቴ ችግር አለበት ይባላል፤ የሁለቱ በሽታዎች ምልክት እየተፈራረቁ ከተሰሙት ደግሞ፣ በሃኪም ከተረጋገጠ በኋላ የባይፖላር ችግር አለበት ይባላል፡፡”

አሁን ለቀናት ሳነብ አልገለጥልህ ያለኝ ተገለጠልኝ፡፡ አይኔ በራ፡፡ዶክተር እያወራ ነው፡፡ “ባይፖላር ዲስኦርደር የዕድሜ ልክ ሁኔታ ቢሆንም፣ሕክምና በመከታተል የስሜት መለዋወጥን እና ሌሎች
ምልክቶችን በመቆጣጠርና መሰናክሎችን በማስቀረት በህይወት ስኬታማ መሆን ይቻላል፡፡ ባይፖላር
ዲስኦርደር በስነ ልቦና ምክር (ሳይኮቴራፒ)እና በመድኃኒቶች ይታከማል፡፡

በግማሽ ልቤ ነው ማዳምጠው፡፡ እኔ ወደ ውስጤ ተወሽቄያለሁ።ወደኋላ ተመልሼ በሃሳብ እየተብሰለሰልኩ ነው፡፡ ዶክተር እውነቱን ነው::ቅድም የጠቀሳቸው ስሜቶች ብዙ ግዜ ተፈራርቀውብኛል። ባይፖላር ዲስኦርደር፣ በጋና ክረምት የሚመሰሉ ስሜቶች መፈራረቅን ተከትሎ
የሚመጣ የባህሪ መለዋወጥ ነው፡፡ በጋ፣ ብርሀን ነው ፧ ተስፋ ነው ፤ በጋ ሙቀት ነው ፤ ሀይል ነው፤ መቦረቅ ነው፡፡ ክረምት ግን፣ ብርድ ነው ፤መሸሸግ፣ መኮራመት ነው፡፡ አዎ! የኔ
👍3😁1
ችግር ባይፖላር ነው፡፡

ለካ በጋ ስሆን ነበር፣ ሁሉን የማወቅ፣ ሰውና አካባቢዬን የመቅረብ ፍላጎቴረ ከፍተኛ የሚሆነው። ሃይልና ጉልበቴ ስርቼ
ማይደክመኝ፡፡ አላስተዋልኩም ነበር እንጂ፣ በውስጤ ክረምትና በጋ
ሲፈራረቁብኝ ኖረዋል፡፡ ክረምት፣ ብርድ ነው ፤ መሸሽግ፣ መኮራመት ነው፡፡ ክረምት ጭለማ፣ ፍርሀት ነው፡፡ አካባቢዬ የሚጨልምብኝ፣ ሁሉ ነገር ሚያስፈራኝና ሚያስጨንቀኝ፣ በሚረባ በማይረባው የምበሳጨውና የምነጫነጨው፣ መደበቅ መሸሸግ ምርጫዬ የሚሆነው፣ ሃይሌ ተሟጦ ሁሉ ነገር የሚስላቸኝ፣ ሁሉ ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ እየሆነብኝ ስራዬን
ምቀያይረው፣ ለካ ውስጤ ክረምት ሲሆን፣ ሲደምን፣ ሲጨልም ነበር፡፡
ለካ ታምሜ ነው፡፡ ህመም አልባ በሽታ፡፡

ወይኔ...! ሃኒም ታማ ነበር ማለት ነው፡፡ ለዛ ነው ክቡር ህይወቷን እንደቀልድ ያጠፋችው! እርሷን ታማለች ብሉ መገመት
ይከብዳል፡፡ እጅግ በጣም ውብና ማራኪ ነበረች፡፡ በዛ ላይ ገና አንድ ፍሬ ልጅ፡ እንደሷ ስንቶች ይሆኑ የአካላዊ ምቾታቸው የአዕምሯዊ በሽታቸውን የጋረደባቸው? ከቤተሰብ ጋር ካላት አለመግባባትና ብስጭት ውጪ ህመም ሚባል ነገር በፍፁም ያላት አትመስልም ነበር፡፡ አሁን ግን፣ ከምልክቶች አብዛኛውን እንደነበራት አስተዋልኩኝ፡፡ በእርግጥም
ብስጭቷ፣ መከፋቷ፣ ደስታ ማጣቷና እራሷን ማጥፋቷ ከቤተሰብ አለመግባባት ብቻ በፍፁም ሊሆን አይችልም፡፡ እርሷን የመሰለች ልጅ ብዙ ሌላ አማራጭ ማየት ነበረባት፡፡ ግን እንዴት እንደዛ አይነት
የተመቻት ምትመስልን ልጅ ታማ ነበር ብሎ መጠርጠር ይቻላል? ግን ግንዛቤው ቢኖረን ኖሮ፣ ንዴትና ብስጭቷ፣ ከቤተሰብ መሸሽ ምልክት ነበሩ፡፡ ለነገሩ እራሴንስ መታመሜን ያወኩት ገና አሁን አይደል።
እሷም እንደኔ ያዝ ለቀቅ ያደርጋት ነበር? እንደኔው ባይፖላር ትሆን ወይስ ድባቴ ብቻ? በውስጤ ለሃኒ ዳግመኛ አነባሁ፡፡ እርሷን ጠርጥሬ አላውቅም፡፡

ይገርማል! እንደታመሙ ሳያውቁ መታመምም አለ ለካ፡፡ ምንም ህመም የሌለው በሽታ፡፡ በግልፍተኝነት ያሳለፍኳቸው ደካማ ውሳኔዎች በአዕምሮዬ እንደፈጣን የፊልም ትዕይንት ውልብ፣ ውልብ እያሉ ያልፉብኛል፡፡ እንደኔ ባለ ስሜት ስንቶች እየተሰቃዩ ይሆን? አፍሶ መበተን የሰለቻቸው፣ ዘርቶ ማጨድ ሚቸግራቸው ስንቶች ይሆኑ?
ድንገት በአእምሮዬ ኤፍሬም ውልብ አለብኝ፡፡ ኤፍሬም መቼም ከውስጤ
አይወጣም፡፡ መንገድ ላይ ብቻውን ሚያወራ፣ የተጎሳቆለ ባየሁ ቁጥር
እርሱ ትዝ ይለኛል፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች አዕምሮዬ ስለሱ ያስባል፣ይተክዛል፣ ልቦናዬን ሃዘን ይጫጫነዋል፡፡ የኤፍሬምስ ችግር ምን ይሆን...? ሳሚ ወፈፌ ሲለው መዝገብ ቤታችን ቀውስ ብለውታል፣
ልዩነቱ ምንድን ነው? ማንኛቸው ነበሩ ትክክል? ስለ ሌሎች የአዕምሮ
ችግሮች የማወቅ ፍላጎቴ ጨመረ፡፡ ዶክተር ወደ እራሴ ተመልሼ
እያብሰለሰልኩ እንደሆነ ተረድቶ፣ ላለማቋረጥ ዝም ብሎ በእርጋታ ወክ
ያደርጋል። ስለሌሎች ህመሞች እንዲነግረኝ ፈለኩኝ፡፡ ኤፍሬምን
ማግኘት ፈለኩ፡፡ ሳናውቀው እርቀን ሄደናል፡፡ ዞብልን አልፈን ቸቸላ ሆስፒታል ልንደርስ ምንም አልቀረን፡፡

“እርቀን መጣን፡፡ እንመለስ?”

“ደከመህ? እሺ” ብሎ ዞረ፡፡ ዶክተር እረጅም ወክ ይወዳል።...


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ሰመመን


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ (MD)

...“ችግሩ ግን ፍቅሩ፥ ራቡ ትክክለኛ ምንጭ የለውም ፤እንዲሁም በስሜት እሳት ይጀምራል ። አብዛኛውን ጊዜ ደግም እንዲህ ዐይነቱ፡ ብቻ ቁሳቁሳዊ ይሆናል ። የረዥም ጊዜ መጠናናትና መፋቀርም የለም : በስሜት እሳት የተጀመረ ሚክስድ ማሬጅ” ደግሞ ዘላቂነት የለውም።ዓመት አብረው
ከቆዩ በኋላ፥ የስሜት እሳቱ (አንቺ ፍቅር የምትይው) ይቀዘቅዝና ለኑሮ ቦታውን ይለቃል። በዚያ ሰዓት በስሜት እሳት ተሸፍኖ የቆየው፡ በሁለቱ መሐል ያለው የአስተሳሰብ የአስተዳደግ እና የአኗኗር ልዩነት ብቅ ማለት ይጀምራል። ይልቁንስ
ይህን ዐይነቱ ጋብቻ ዘላቂነት ሲኖረው ያየሁት በጥብቅ ኃይማኖት በተሳሰሩ ሰዎች ላይ ነው ። ይህ የእምነት ጉዳይ ነው ።በአንድ ሃይማኖት ተከታይነት ተዋውቀው የተጋቡ አንድ ኢትዮጵያዊና እንዲት አሜሪካዊት ለረዥም ዓመት የሚያስቀና ትዳር እንደ ነበራቸው አስታውሳለሁ ።እንዲያውም መዉለድ ማቆም በፈለጉበት ወቅት ብልቱን በቀዶ ሕክምና ያስመከነው ኢትዮጵያዊው ወንድ ነበር ። ይህም የሚያሳየን ከነሱ ውጭ ከሆነ መለኮታዊ ኃይል ተጫኝነት ተሳስረው መኖ ተሳስረው መኖራቸውን ነው እንጂ የአካባቢ የአስተሳሰብና የባህል ልዩነት አስወግደዋል ማለት አይደለም ። ”

“ ድንቄም ” እንደ ማለት ያህል ከንፈሯን አጣማ ብርጭቆውን እነሣች ። የጨዋታቸው አርዕስት ቢለወጥ በወደደች ነበር ። እስክንድር ግን አርዕስቱን ሊለውጥላት አልቻለም ። እንዲህ ዐይነት ክርክር ሲነኝ ደስ ይለዋል፤ መላ ህዋሳቶቹ ይግላሉ። ሐሳቡና ነጥብ አመታቱ እያደገ ፥ እየጠነከረና እየተወሳሰበ ሲሔድ ለራሱም ይገርመዋል ከዕድገቱ ፡ ከኣካባቢውና ከትምህርት ቤቱ ብዙ ዕውቀት መቅሰሙን የሚያወቀው በእንዲህ ዐይነቱ የግለት ወቅት ነው ።

“ደግሞም የዚህ ዐይነት፡ የተደቀለ ጋብቻ ችግሩ በባልና ሚስቱ ላይ ብቻ አይቀርም ” ሲል ቀጠለ ፣ ይብሱን ችግሩ የሚነሳው በዊ ወልዷቸው ልጆች ላይ ነው ። ልጆቹ
እያደጉ ሲመጡ ራሳቸውን ከየትኛውም ወገን እንደሚያስቀምጡ ይቸገራሉ ። የሥነ ልቡና ጠበብቶች ይህንን ችግር
አይደንቲቲ ክራይሲስ ? ይሉታል ። ልብ ብለሽ እንሆነ አብዛኛውን ጊዜ ለሌብነት ለአልኮል ሱሰኝነት ፡ ለሲሰኝነትና ለመሳሰሉት ርካሽ ተግባራት የሚጋለጡት ከእንዲህ ዐይነት ቤተሰብ የወጡት ወደ እኛ ክልስ የምንላቸው ናቸው ። ስለ ራሳቸው የሚኖራቸው የተዘበራረቀና የተበላሸ ስሜት ይመስለኛል፡ ወደዚህ አድራጎት የሚመራቸው ”

ማርታ ክርክሯን መሸሽ አልቻለችም ። ዝም ብላ በከፊል ሙዚቃ በከፊል እሱን ስታዳምጥ ትቆይና በነገር ወጋ ሲያደርጋት ወይም አነጋገሩ አልጥምሽ ሲላት አንድ ቃል ጣል ታደርጋለች "

ልጆቹ እንዴት ራሳቸውን የሚያስቀምጡበት ቦታ ይጠፋቸዋል ? ከሁለት የተለያዩ ዜጎች ቢወለዱም የሚኖሩበትን አካባቢ መስለው ማደግ ይችላሉ ” ስትል ተገታተረችው።

አይችሉም ! ” አላት በስሜት ጭንቅላቱን እየነቀነቀ ። “ የሚኖሩበት አካባቢ የእናታቸው ወይም የአባታቸው እንጂ የሁለቱም አይደለም ። ሰለዚህ ከእንደዚ
ዐይነት ቤተሰብ የተወለደ ልጅ ( ለምሳሌ እናቱ አበሻ አባቱ፡ ፈንጅ ቢሆኑና ኑሮው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሆን በሙሉ ልቡ የኢትዮጵያውያንን አኗኗርና ባህል መቀበል
ያዳግተዋል።ግማሽ ፈረንጅነት ይሰማዋል ” ካለ በኋላ " እስክንድር ትንሽ ሲያስብ ቆየና ፡ “ እንደሚመስለኝ ይህ ችግር በታዳጊና በበለጸጉ አህጉረሮች መሐከል ያለው የልዩነት ችግር ነጸብራቅ ነው " ፍርንጅና የዕድገት የሥልጣኔ የበላይነት ምልክት ተደርጎ ስለሚወሰድ ክልሱ ልጅም ይህ ተጽዕኖ ከራሱ ጋር እንዲጣላ ያደርገዋል ብቻ ምን ልበልሽ አሁን ባለንበት የተራራቀ የኑሮና የአስተሳሰብ ደረጃ (ሚክስድ ሜሬጅ) በጣም አስቸጋሪ ነው ” አላት ።

“ሊቅ ነህ ” አለችው ማርታ' በልቧ እንደ ማድነቅ በአፉ እንደ ማሽሟጠጥ አድርጋ
“ ሊቅነት አይደለም ” አላት እስክንድር ኪሱን እየዳበሰ “ “ አንቺም ብትሆኝ መጽሐፍ አንብበሽ ልታገኚ
የምትችይው ይውቀት ነው ።

ኪሱን የዳበሰው ሲጋራ ፍለጋ ነበር የክርክር ስሜቱ ሲግል ከንፈሩ እየደረቀ መጣ ። ሲጋራ ትዝ አለው ። ከምሳ
በኋላ ሲጋራ ላለማጨስ ምሎ አፉ ላይ የቀረችውንም መስበሩን እንደ ቅዠት ወይም እንደ እንቅልፍ ልብ ውሳኔ ወስዶት አሁን ከኪሱ አንድ ብር አወጣና አሳላፊውን ሲጋራ እንዲያመጣላት አዘዘው ። የያዛት ገንዘብ ከቀረበላቸው
ጭማቂ እንደምትተርፍ በልቡ አስልቷታል

“ በነገራችን ላይ ፡ በስሜታዊ ብርገጋ ተነሣሥተው ነጭ እያገቡ ወደ ውጭ ሀገር የሚሔዱ አበሻ ሴቶች ዕጣቸው
ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ ? ?” ሲል ጠየቃት ።

“ ምንድነው ልትለኝ ነው ? ” አለችው ግንባሯን አኮማትራ ።

“ መጨረሻቸው ሽርሙጥና ነው ” አላት ድርቅ ብሎ ። “ አብዛኛውን ጊዜ ቅድም ባልኩሽ ምክንያቶች ስለ ማይሰማሙ። በመጨረሻ እዚያው ሽርሙጥና ይጀምራሉ ።ከአፍሪካ አግብቶ የወሰዳትን ሴት በጥንቃቄ የሚይዝ ነጭ በሐይማኖቱ ያደረ ወይም ሕይወቱን ለሥራና ለምርምር የሰጠ ጥቂት ሰው ብቻ ነው ።

የማርታ ፊት ተለዋወጠ ። በአነጋገሩ እንደ ተከፋች ገባው።

“ ምን ማለቴ መሰለሽ ? ” አለና እጅዋን ይዞ ሊያረጋጋት ሞከረ ።

እጄን ልቀቅና ማለት የፈለግከውን ተናገር ” አለችው ፡ ስልቱን ባጣ ድምፅ ።

“ ምን መሰለሽ ማርታ ! አንድ ልንክድ የማንችለው ነገር አለ ። ሰዎች ስንባል ብዙ ጊዜ ለጊዜያዊና እሳታዊ ስሜታችን ተገዥዎች ነን ። በሆነ እሳታዊ ስሜት ወይም ግንፍልተኝነት ተነሣሥቶ እናት ሀገርን ጥሎ መኮብለል ጉዳቱ የሚሰማው ቆይቶ ነው ። እስካሁን ድረስ በነጮች ሃገር ደልቶት የሚኖር ኢትዮጵያዊ አላየሁም ፤አልሰማሁም ።
አብዛኛው እዚህ ትውልድ ሀገሩ ውስጥ የሚንቀውን ሥራ ፡እንደ ቤት ማጽዳት ፥ መስታወት መወልወል ፥ መኪና ማጠብ
ሽንት ቤት ማጽዳትና የመሳሰለውን እየሠራ ነው የሚኖረው ።
ጥቂት ኢትዮጵያውያን በቂ ገንዘብና ቁሳቁስ ቢኖራቸውም ነጻነቱና ክብሩ ስለሌላቸው ሰላም አያገኙም ። በገንዘባቸውን ብዛት ህሊናቸውን የሚመክቱበት የአልኮልና የሺሽ ግንብ
ሰርተው ከዚያ ውስጥ እየዋኙ ይኖሩታል መኖር ከተባለ።

ማርታ የተዘበራረቀ ስሜት ተሰማት ። ዘመዶቿ ከውጭ ሐገር በሚልኩላት ደብዳቤ ደስተኞች እንዳልሆኑ ታውቃለች
ስለዚህ እስክንድር የተናገረውን ናቅ አርጋ ልታልፈው አልቻለችም ። በሌላ በኩል ደግሞ ፡ የእሷ ስሜትና ፍላጎት የምንጊዜም ውጭ ነው ፤ ፈረንጅ ሀገር ነው ። ይህ ሰሜት ስላየለባት ሐቁን ልትቀበል አልፈለገችም ።

። ይብላኝ ለምታገባት ፤ እኔ እንደዚህ አኞ አትመስለኝም ነበር ” አለችው ።

“ እንዴት ? ” አላት እስክንድር ፥ ተገርሞ ።

እንደዚህ ለጭቅጭቅና ለመግት ሽንጥህን ገትረህ የምትቆም አይነት ሰው አትመስለኝም ነበር ።

በርግጥ እንዳለችውም ። እንዳሁኑ ሰፊ አጋጣሚ አግኝተው ተጨዋውተው ስለሚያውቁ። እስክንድርን የምትገምተው
እንደ ማድየለሽና " ለኑሮወም ለሀገሩም ደንታ የሌለው ሰው አድርጋ ነበር ። አሁን ኢትጵያዊነቱ እንዲህ ሽንጡን ገትሮ መቆሙ አስገርሞታል ።

ጭቅጭቅኮ አይደለም ” አላት እስክንድር የራሱ ያልሆነ ፈገግታ እያሳያት ። “ ይልቅስ ሳናስበው ብዙ ትምህርት የተለዋወጥን ይመስለኛል ። ”

አሳላፊው ሲጋራውን አምጥቶ ሰጠው ። እስክንድር በመጀመሪያ ማርታን ጋብዞአት፡ቀጥሎ ለራሱ ከፓኮው ውስጥ ይልቅ ይህን ሲጋራ የሚያስተውህ ወዳጅ ብታገኝ ጥሩ ነበር” ስትል ለከፍ አረገችው

ያንችስ ምን ይላል ? ” አላት ፥ ክብሪት እየጫረ
“ እኔ እኮ እላጨስም ። ከሚያጨስ ወንድ ጋር
👍5🔥1
ወይም ጨዋታ ቦታ ስሆን፥ እንዲሁ አጨሳለሁ እንጂ ሱሰኛ አይደለሁም
አለችው ።

እስክንድር አጫጫሷን አመንላት ሙሉውን ጭስ ነው ወደ ውጭ የምታወጣው።

“ የሚገርምሽ ፥ ሁለት በቅርብ ማጨስ የጀመሩ ጓዶኞቼን መክሬ አስትቼለሁ ። ብዙ ዓት ስላጨስኩትል በግል ሕይወትም ሆነ በማኅበራዊ ግኑኙነት ውስጥ የሚያስከትለውን ችግር በሚያሳምን ሁኔታ አቀርባለሁ መጥፎነቱን እሰብካለሁ እኔ ራሴ ግን ማቆም አቃተኝ ። ”

ጠንቋይ ለራሱ አያቅም ይባል የለ? ” ስትል አፌዘችበት።

"ግድ የለም ። ጥሩ ሚስቴ ሳገባ ማጨሴን አቆማለሁ የሚል ተስፋ አለኝ ።

"አንተ ያልተውከውን እሷ እንዴት ታስተውሃለች? ”

“ ታስተወኛለች ። ጠንካራና ጥሩ ሴት ከሆነች እንኳን ሲጋራ መተው ሌላም ታስደርገኛለች» ሴቶች ምን ያህል
ኃይለኛ እንደሆኑ ዐውቃለሁ።

" እንዴት ? ” አለችው ።

ፊቷ በደስታ ሲፈካ ተመለከተ መልሱን በጉጉት እንድመትጠብቅ ገባው ። ሊያኩራራት አልፈለገም።

"እንዴት እንደሆነ አልነግርሽም ” አላትና " በልቡ ለምንድነው ሰዎች ኃያል መባል ደስ የሚለን ? ሌሎችን ማንበርከክ በቁጥጥራችን ሥር ማዋል እንዲሰግዱልን ማድረግ የምንፈልገው ለምንድነው ? የበላይ ሆኖ የመገኘት
ስሜት ለምን ያጠቃናል ? ” እያለ ሲያስብ ቆይታ በባሎቻቸው ላይ ኃያል መሆን የሚችሉት ሁሉም ሴቶች አይደሉም ። ጥቂት ጠንካሮችና ልበሙሉዎች ናቸው አላት።

በመልሱ ባለመርካቷ ቀደም ብላ ዐይኖን ከእሱ ለማሸሸ ያህያ ከማዶ ካለው ባዶ ግድግዳ ላይ ተከለች።

ሰማሽኝ ማርቲና ? ” አላት በቀልድም በቁልምጫም ዐይነት

“ ደረቅ ! ”

"ርጥብ"!

እስክንድር ለአፍታ ያህል ዐይኑን ከዐይኗ ሳይነቅል ቆየ። ከአፉ በሚወጣው የሲጋራ ጢስ ቀለበት እየሰራ ሲወረውር በሰፊው ቀለበት ውስጥ ጠበባ ቀለበት ሰርቶ ሲያሾልክ የማርታ ጆሮ ሙዚቃውን እየቀዳ ልቧን ሲያወራው ።በዐይኗ እስክንድርን የጢስ ቀለበቶች ተከትላ ጭልጥ ብላ ስትሔድ፡ ቀለበቶቹ እየሰፉ፥ እየተምዘዝዘጉ ሄደው ሲበታተኑ እንደገና ዐይኗን ወደ እስክንድር አፍ መልሳ ሌሎች
ቀለበቶች ስትጠብቅ ደስ ሲል !

ማርታ ምርምሩና ክርህሩ ቀርቶ እንዲህ እንዲህን አይነት ጨዋታ ቢጫወቱ ደስ እንደሚላት እስክንድር ያውቃል የወጡትም ለዚሁ ነበር ታድያ ለምድን ነው የማይዋጥላትን ክረርክር እያቀረብኩ ማደርቃት ? ሲል አሰበ ገንዘብ በማጣቴ
ከእሷ ጋር ሌላ ዐይነት ጨዋታ መጫወት ባለመቻሌ ያረብኩት ማካካሻ ይሆን? ጎበዝ ነው ብላ እንድትወደኝ ይሆን ? ወይስ በእርግጥ የምርምርና የክርክር
ጥማት ይዞኝ ነው? ” እያለ ሲያስብ የሷው ጥያቄ አባነነው።

“ እውነት እስክንድር ሚስት ታገባለህ ? ”

ምን ማለትሽ ነው ? ” አላት በአጠያየቋ ተገርሞ
እንዴት አላገባም ። ? ”

ማለት ፡ በቃ እንዲያ ግዴለሽ ዐይነት ትመስላለህ ። የትዳር ስሜት ያለህ አትመስልም ። ”

ምን ለማለት እንደ ፈለገች ስለ ገባው ፡ “ ላለባበሱ ብዙ አለመጨነቁ ሲጋራ ማጨስ ወይን ሌላ ምንድን ነው ከቁም ነገረኝነት አምባ ያገለለኝ የመሰለሽ ? ወይም ደግም ሙሉ ሰው ለመሆን ጥሩ ዜጋ ለብባል የሚያስፈልጉ ሌሎች
መመዘኛዎች ካሉ ብትገልጪልኝ ? ” አላት ፌዝ በተቀላቀለበት አነጋገር ።

💥ይቀጥላል💥
👍4
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

...ሳናውቀው እርቀን ሄደናል፡፡ ዞብልን አልፈን ቸቸላ ሆስፒታል ልንደርስ ምንም አልቀረን፡፡

“እርቀን መጣን፡፡ እንመለስ?”

“ደከመህ? እሺ” ብሎ ዞረ፡፡ ዶክተር እረጅም ወክ ይወዳል።

“ዶክ አሁን እንደገባኝ፣ የአዕምሮ በሽታ ከምጠብቀው በላይ በብዛት፣ በዙሪያችን ያለና ብዙ ምስቅልቅሎችን እያስከተለ ያለ፣ ግን በማህበረሰቡ ዘንድ ብዙም ግንዛቤ የሌለው በሽታ ይመስለኛል፡፡”

“እውነት ብለሃል ያቤዝ፡፡ አሁን ስለ በሽታው በደንብ እየተረዳህ ነው፡፡ እንደዚህ ያሉ ብዙ በሽታዎች እንዳሉ ብታውቅ ደግሞ የችግሩ ግዝፈት በደንብ ይታይሃል፡፡”

“ቅድም እንዳልኩህ አልገባኝም እንጂ፣ እቤትህ ያሉትን መፅሃፍት ለማንበብ ሞክሪያለሁ፡፡ ለምሳሌ፤ ስለ ፓራኖይድ፣ ኦብሴሽን፣ዚኮኒያ ምናምን ለማንበብ ሞክሬ ነበር” አልኩኝ በዛው ስለነሱ
እንዲነግረኝ፡፡

“ምነድን ዚኮኒያ ካካካካ...” ዶክተር ለመጀመሪያ ግዜ ከልቡ ሲስቅ
አየሁት፡፡ የበሽታውን ስም ስጠራ እንደተሳሳትኩ ገባኝ፡፡ ዶክተር ሲስቅ
ስላየሁት ግን፣ በመሳሳቴ ደስ አለኝ፡፡

“ዚኮኒያ ... እንደዛ ነገር ያነበብኩ መሰለኝ፡፡” አውቄ ደገምኩለት፡፡
እየተንከተከተ ሳቀ፡፡ ዶክተርን እወደዋለሁ እሱ ለኔ ህይወቴን ያዳነልኝ ጠባቂ መላዕኬ ነው፡፡ ህይወቱን ሙሉ ደስተኛ ቢሆንልኝ ምኞቴ ነው። እሱ ግን ስሜቱ በብዛት የረጋ ነው፡፡ ቶሎ አይደሰትም፣ አይናደድም፡፡ዛሬ በኔ ምክንያት ደስ ስላለው ከልቤ ደስ አለኝ፡፡ ስጦታ የሰጠሁት ያህል ተሰማኝ፡፡ ስቆ ሲጨርስ፤

“ገባኝ፣ ስኪዞፍሬኒያ ለማለት ነው፡፡ የህክምና ቃላቶች ትንሽ ይከብዳሉ፡፡ እንደውም አንተ ጎበዝ ነህ፡፡ ሌሎቹን በትክክል ጠርተሃቸዋል፡፡ እሺ ለማንኛውም እነግርሃለው፡፡ ፓራኖይድ የባህርይ መዛባት ችግር ተብለው ከሚጠሩ ሁኔታዎች አንዱ ነው። ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ከመጠን ያለፈ ተጠራጣሪ ናቸው፡፡ ሰው በተፈጥሮው
ይጠራጠራል፡፡ እንደ ችግር ምንቆጥረው ግን፣ ያለ ምንም ተጨባጭ ምክንያት ሲጠራጠርና፣ እያንዳንዱ ድርጊታቸው በሌሎች እንጠቃለን ከሚል ከፍተኛና የማያቋርጥ ስጋት፣ አለማመንና ጥርጣሬ የመነጨ ሲሆን ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ከማንኛውም ሰው ጋር የሚያደርጉት
ግንኙነትና ድርጊታቸው፣ በጥርጣሬ አስተሳሰቦች የተቃኙ ስለሆነ፣
በማህበራዊ ግንኙነትም ሆነ በስራቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጠርባቸዋል፡፡

ይህ ችግር ብዙውን ጊዜ በልጅነት ወይም በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚጀምር ሲሆን፣ ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ የተለመደ ነው::ፓራኖይድ ያለባቸው ሰዎች ሁልጊዜ ሌሎች ሰዎች እነርሱን ዝቅ ሊያደርጓቸው፣ ሊጎዷቸው ወይም ሊያስፈራሯቸው እንደሚሞክሩ
ስለሚያስቡ ድርጊታቸው ሁሉ እራሳቸውን በመከላከል የተቃኘ ነው::እነዚህ መሠረተ ቢስ እምነቶች፣ እንዲሁም የማመካኘትና ሌሎችን ያለማመን ባህሪ፣ የቤተሰባዊም ሆነ የስራ ግንኙነቶችን በከፍተኛ ሁኔታ
ይስተጓጉላል፡፡ በመሆኑም የፍቅር ህይወታቸው፣ የትዳርና የቤተሰብ
ህይወታቸውን ጨምሮ ማንኛውም ከሰዎች ጋር ለሚያደርጉት ግንኙነት
ከፍተኛ መሰናክል ይሆንባቸዋል፡፡

አነዚህ ግለሰቦች ከሚያሳዩዋቸው ምልክቶቹም መሃከል፤ሌሎችን ሁል ግዜ መጠራጠር በጣም የሚቀርቧቸውንና ሃኪማቸውን ጨምሮ፣ ሌሎች እነሱን በማታለል ወይም በመበዝበዝ እንደሚጠቀሙ ማሰብና ማመን፤ የግል መረጃዎቻቸው እኔን ለመጉዳት ይውላል በሚል ፍራቻ ለሌሎች መደበቅ፣ ለሰዎች ይቅርታ ማድረግ መቸገር፤ ቂም መያዝ፣ ቁጡና ትችትን በአግባቡ መቀበል መቸገር፤ የሚሰጧቸው አስተያየቶችና የማሻሻያ ሃሳቦች ውስጥ የተደበቁ ትርጉሞችን መፈለግ፣

የሰውነት እንቅስቃሴዎችን እንደማይታዩ የጥቃት፣ የንቀት ወይም የማስፈራራት ምልክት አድርጎ መረዳት፣ በአፀፋው ለመመለስ መፍጠን፤ እንዲሁም በቁጣ ምላሽ መስጠት፤ የማያቋረጥ ምክንያት
አልባ ጥርጣሬዎችን ማብዛት፣ ይህም ፍቅረኛቸውን ወይም የትዳር ጓደኛቸውን በጥርጣሬ ማሰብ፤ ክህደትን ለምከላከል ነገሮችን ሁሉ በጥርጣሬ መመልከት፤ ሁልጊዜ እራሳቸውን ትክክል እንደሆኑ ማመንና በግጭቶች ውስጥ የራሳቸውን ድክመት ወይም አስተዋፅኦ ማየት
አለመቻል፤ አብዛኛውን ግዜ ተቃዋሚዎች ዘና ማለት የሚቸገሩ፣ግትር እና ተከራካሪ ናቸው፡፡ የፓራኖይድ /የምናባዊ/ ጥርጣሬዎችን መለያ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፤

አጠራጣሪውን አስተሳሰብ የሚጋራ ሌላ ሰው ከሌለ፤
ለጥርጣሬ መነሻ ትክክለኛ ማስረጃ ሳይኖር ሲቀር፤
ማስረጃ ባለው ጉዳይ ላይ አልፎ የሚነሳ የጥርጣሬ ሃሳብ፤
ስለጉዳዩ ማሰብ ማቆም የሚከብድ ከሆነ፤
ከሌሎች ማረጋገጫ ተሰጥቶም በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬ ከቀጠለ፤

ጥርጣሬው ከማስረጃ ይልቅ፣ በስሜቶች እና አሻሚ ክስተቶች ላይ የተመሰረቱ ሲሆኑ ይህ ጥርጣሬ ጤነኛ ያልሆነ የፓራኖይድ ምልክት ሊሆን ስለሚችል ሃኪምን ማማከር ከከፋ ችግር ይከላከላል፡፡

ይህ ችግር ብዙ ሰዎች በሕይወታቸው በመለስተኛ ደረጃ ሊያጋጥማቸው የሚችል ሲሆን የከፋ ጉዳት አያስከትልም ነገር ግን፣በሌላው ጫፍ ሲከሰት በጣም ከባድ ችግርን ሰለሚያመጣ፣ ህክምና
መፈለግ የግድ ነው፡፡” ዶክተር እያወራልኝ ግርማ ትዝ አለኝ፣ በፍቅረኞቻቸው ላይ በአልተጨበጠ ቅናት አሲድ መድፋትና ሌሎች የጭካኔ ወንጀሎችን ሚፈፅሙ ሰዎች በአዕምሮዬ ተመላለሱ፡፡

“ሌላው ደግሞ ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር /ኢኮዲ/የምንለው ነው፡፡ ኦ.ኮ.ዲ. ከመጠን ያለፈ አስጨናቂ የጥርጣሬ ሃሳቦች መከሰትና ጥርጣሬውን ለማረጋገጥ ወይም ለማስተካከል ተመሳሳይ ድርጊቶችን በተደጋጋሚ ለመፈፀም የሚስገድድ ባህሪ ነው፡፡ ግለሰቡ ድርጊቶቹን የሚፈፅመው ወደ አእምሮው ሊቆጣጠረው ከሚችለው በላይ
በተደጋጋሚ እየመጡ በሚያስጨንቁት ሃሳቦች፣ ምስሎች ወይም ፍላጎቶች ምክንያት ነው:: ሃሳቦቹ አስጨናቂ ናቸው፡፡ ነገር ግን፣በሰውየው አዕምሮ የሚመነጩ እንጂ፣ በነባራዊው አለም የማይከናወኑ
ወይም የሌሉ ናችዉ:: በተጨማሪም፣ እነዚህ ሰዎች እራሳቸውን እንደታዋቂ ወይም ከፍተኛ ደረጃ እንዳላቸው ይሰማቸዋል።

ኦ.ኮ.ዲ. ምልክቶች በአብዛኛውን ጊዜ በትንሹና ቀስ በቀስ ስለሚጀምሩ፣ ችግሩ ላለበት ሰው፣ የተለመዱ ባህሪዎች ሊመስሉ ይችላሉ:: ድርጊቶቹን ሲፈፅሙ የተወሰነ እፎይታ ይሰማቸዋል፡፡ ነገር
ግን፣ እፎይታው ለትንሽ ጊዜያት ብቻ የሚቆይ ስለሆነ የድርጊቶች
ድግግሞሽ ይቀጥላል። ተደጋጋሚና አስገዳጅ ድርጊቶች በሌሎች ሰዎች
በተለየ ሁኔታ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፤ በማህበረሰቡ እንደጥዩፍ ሊቆጠሩ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ፣ ለግለሰቡ የግዴታ ተግባሮችን ለመቆጣጠር በጣም ከባድ ናቸው፡፡ ምክንያቱም፣ ግለሰቦቹ በተደጋጋሚ እየደጋገሙ ማይታወቃቸው ስለሆነ ነው:: ለምሳሌ፣ ሰው ከጨበጡ ወይም እቃ ከነኩ በኋላ እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ ሰውን ለመጨበጥ በመፍራት
ሰላምታን በሌላ መልኩ መስጠት፣ የበር መቆለፍን በተደጋጋሚ ማረጋገጥ፣ ልዩ ቃላትን ወይም ጸሎቶችን መደጋገም፣ ደጋግሞ መቁጠር በጣም በተደጋጋሚ የዝግጅት አቀራረቦችን መፈተሽ ናቸው፡፡
እነዚህን ድርጊቶች እንዲፈፅሙ የሚያደርጓቸው ምክንያቶች ፣በጀርሞችን ወይም በቆሻሻ መበከልን በከፍተኛ ደረጃ መፍራት፣ ከመጠን ያለፈ ጥርጣሬ ወይም ስህተት የመስራት ፍርሃት እያደረጉት ላለው ነገር ትክክለኛነት ከሌሎች የማያቋርጥ ማበረታቻና ማረጋገጫ መፈለግና ለስርዐት የበዛና የተጋነነ ቦታ መስጠት ናቸው፡፡

አንዳንዶቹ ድርጊቶች ሰዎቹ ላይ በቀጥታ ጉዳት ባይኖራቸውም፣አላስፈላጊ ግዜንና ጉልበትን በመውሰድ፣ በሌሉ ጉዳዮች ላይ በመጨነቅ ውጤታማነትን በእጅጉ ይጎዳሉ፡፡ በመሆኑም ይህ ችግር አላስፈላጊ ግዜንና ጉልበት
👍3